Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ምሁር ሆድ አደር ሲሆን …! – (ይገረም ዓለሙ)

$
0
0

የተማረ ሆኖ እውነቱን የማይገልጽ ፣
ባለ ጸጋ ሆኖ ገንዘቡን የማይሰጥ፣
ደሃ ሆኖ መስራት የማይሻ ልቡ፣
ሶስቱም ፍሬ ቢሶች፣
ለምንም አይረቡ።

(ከበደ ሚካኤል የእውቀት ብልጭታ )

ለዚህች ጽሁፍ መነሻ ምክንያት የሆነኝ ጉዳይ በአጭሩ አንዲህ ነው፡፡ አሜሪካና ካናዳ የሚኖሩና አዲስ አበባ ላይ ሆስፒታል ለማቋቋም በሚል የተሰባሰቡ ሁለት መቶ ሀምሳ የሚሆኑ የህክምና ዶክተሮችን አስመልክቶ ከወር በፊት የተሰማው ዜና ነው፡፡ የስብስቡ አመራሮች ዶ/ር ቴዎድሮስ ለአለም የጤና ድርጅት መሪነት ለመመረጥ የሚያደርጉትን ዘመቻ ደግፈው መግለጫ አወጡ፡፡ በዚሁ ሰሞን አባላቱ ሲሰበሰቡ አንድ አባል የተፈጸመው ድርጊት ከስብስቡ ዓላማ ውጪ መሆኑን በመግለጽ አንሰራዋለን ለምንለው ሆስፒታል መሰረት ያልጣልን ሰዎች ለመግለጫ መሮጣችን ተገቢ አይደለም በማለት ተቃውሞአቸውን አሰሙ፡፡በስብሰባው ቦታ ድጋፍ ለመስጠት ያልቻለ ዶ/ር (ምሁር ) ሁሉ ከስብሰባ ሲወጡ ልክ ነህ የእኛን ሀሳብ ነው የገለጽከው ወዘተ በማለት አድናቆቱን ገለጸላቸው፡፡ ይህ ግን ከተፈጸመው ድርጊት ከሰብሳቢዎችም ከተሰጣቸው ምላሽ በላይ ያበሳጫው እንደሆነ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገለጹ ፡፡ አሳዛኝ አሳፋሪ!

በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የሚተላለፍ ሃምሳ ሎሚ የሚባል ፕሮግራም ነበር፡፡አዘጋጆቹ አሜሪካ ሄደው በአርቲስት ዓለም ጸይ ወዳጆ ጣይቱ የባህል ማእከል መድረክ ላይ ተገኝተው የቀረጹትን ልከው አሳዩንና አነርሱ ወደ ሀገር ከመመለሳቸው በፊት ፕሮግራሙ ከኢትዮጵያ ቴሌቭዝን ተሰሰናበተ፡፡አነሳሴ ስለ ፕሮግራሙ የምለው ኖሮኝ ሳይሆን በዛ ፕሮግራም የቀረቡ አንድ ምሁር የተናገሩት ለርእሰ ጉዳዬ መንደርደሪያ ለመጠቀስ አንጂ፡፡
Tewodros Adhanom
ምሁሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር ናቸው፣ የርሳቸውን ስምና የእለቱን ፕሮግራም ርዕስ ባላስታወስም የተናሩት የሚረሳ አይደለም፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ምሁር የሚለው መጠሪያ አይገባንም አሉና ምክንያታቸውን ሲያስረዱ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት እስከ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያም ሆነ ሁለተኛና ሶስተኛ ድግሪ የሚደረስው እያንዳንዱን እርከን ለማለፍ ሲባል ብቻ በሚደረግ ንባብ መሆኑን ገልጸው ከዚህ ያለፈ ለሀገር ለወገን ምን ሰራን በማለት ጠየቁና እኛ ምሁራን ሳይሆን የፊደል ሐዋሪያ ነው መባል ያለብን አሉ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ምሁር የሚለውን የወል መጠሪያ ይዘው ህብረተሰቡም በዚሁ ጥሮ ግሮ በሚገኝ መጠረያ እያከበራቸው በተግባር ግን ለመጠሪያው የማይመጥኑ ለተሰጣቸው ክብር የማይበቁ ሆነው ሲገኙ ያሳዝናል፡፡ በሙያቸው ሕዝብን ማገልገሉ በእውቀታቸው ሀገር መጥቀሙ ቢቀር እውነት ለመናገር ድፍረቱ የጎደላቸው ወይንም ተፈጥሮአቸው ለዛ ያላደላቸው ቢሆኑ እንኳን ምሁርነታቸውን መኖሪያ ብቻ አድርገውት ህይወታቸውን ቢገፉ ጥሩም ባይሆን ባልከፋ ነበር፡፡
ነገር ግን ለሆዳቸው አድረው ሎሌ ሲሆኑ ፤በጥቅም ተሸንፈው ወይ በዘር ወግነው በእውነት ላይ ሲያምጹ፤ አባይ ምስክር ሆነው አደባባይ ሲወጡ፤ ለገዢዎች አጨብጫቢ ሆነው ሲሰለፉ ወዘተ ማየት የመማርን ትርጉም ያሳጣል፡፡ አንዲህ አይነቶቹ ምሁራን ለራሳቸው ከመኖር ባለፈ (በዚህ መልኩ መኖር ኑሮ ከተባለ) ከበደ ሚካኤል አንዳሉት ለምንም የማይረቡ ናቸውና የአዲስ አበባው ዩኒቨርሲትው መምህር ያወጡት መጠሪያም (የፊደል ሐዋሪያ ) ይበዛባቸዋል፡፡ ፊደል መቁጠር ክፉና ደጉን ለመለየት ካላስቻለ፤የህሊናና የሆድን ሚና ካላሳወቀ፤ ምነው ሸዋ ካላስባለና ጎመን በጤና እያሉ ኗሪ ካደረገ ወዘተ ምኑን ፊደል ተቆጠረ ምኑንስ ምሁር ተሆነ?

እናት አባቶቾቻን ብሎም አያት ቅድመ አያቶችችን የትምህርት ቤት ደጃፍ ያረገጡቱ፤ፊደል አይተው የማያውቁት ተማርኩ በሚለና መማሩ ከሆድ አደርነት ባላወጣው ወገን ኋላ ቀር የሚባሉት፤ በእውነት ላይ አያሸምቁም፤አማራጭ በማጣት ካልሆነ በስተቀር ለሆዳቸው ብለው በሎሌነት አያድሩም ፣ቃላቸውን አያብሉም፤አምነታቸውን አይሽሩም፡፡ የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ የሚለው ብሂላቸው ቃል አክባሪነታቸውን የእምነት ጽናታቸውን ያሳያል፡፡ አይገፉት ባላጋራ ገጥሟቸው፣ግዜ ፊቱን አዙሮባቸው ለመኖር ብለው ህሊናቸው ያለፈቀደውን ነገር ሲፈጽሙ ደግሞ፤

ልጅ አሳድግ ብዬ በሀገር እኖር ብዬ፤
ሚስቴን ለሹም ሰጠሁ እህቴ ናት ብዬ በማለት ቁጭታቸውን ይገልጻሉ

ተልፈስፋሽ የሆነ ህሊናውን ገሎ በሆዱ የሚመራ፣ለራሱ ጌታ ሆኖ መኖር እየተቻለው ልበ ሙት ሆኖ በሎሌነት የሚያድር ሲያጋጥማቸው ደግሞ እሱም አይደል ልቡ ነው እውሩ፣
ጥንድ በሬ እያለው ለጌታ ማደሩ ፡ ይሉታል፡፡

የዚህ ጽሁፍ መነሻ ምክንያት የሆኑት ምሁራን ( የፊደል ሐዋርያት) ጥንድ በሬ እያለው ለጌታ ያደረው ገበሬ አይነት ናቸው፡፡ከላይ አንደገለጽኩት ለሀገር ለህዝብ የሚለው ቢቀር በቀሰሙት እውቀት በያዙት ሙያ ሰርተው ለራሳቸው መኖር የሚያቅታቸው አይደሉም፡፡ እንደውም አንዳንዶቹ በድሎት የሚንቀባረሩ፤አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አይቶት አይደለም ሰምቶት የማያውቅ ብር የሚቆጥሩ ናው፡፡ በዚህ ሁኔታ እየኖሩ ግን ለተጨማሪ ጥቅም ሎሌነት ሲያምራቸው፤ መስሎ ለማደር ከእውነትጋር ሲጣሉ፣ በጥቅሉ የምሁር ሆድ አደር ሊያስብላቸው የሚበቃ ተግባር ሲፈጽሙ ማየትና መስማት ያሳዝናል ያሳፍራል፡፡

በተለይ ደግሞ በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ድርብ ዜግነት ወይንም የመኖሪያ ፈቃድ ኖሮአቸው በሙያቸው ስራ ፈጥረው ድርጅት መስረተው የሚኖሩ ከመንግሥት ተሞዳሙደው ሀገር ውስጥ ሊያገኙት ስለሚችሉት ጥቅም በማሰብ ከእውነት ጋር እየተጣሉ በሎሌነት ሲያገለግሉ በሀገር ውስጥ የመንግሥት ጥገኛ ሆኖ የሚኖረውና ከስራ ቢወጣ የእለት ጉርስ የሚቸገረው ወገን ምንም ቢያደርግ ምን እንዴት ይፈረድበታል?

ህሊና የበላይነቱን ወሳኝና አዛዥነቱን ጠብቆ ሆድም ተገቢ ድርሻውን እየከወነ ኖሮ ሰው ከነክብሩ ለህልፈት ሲበቃ ራሱን ብቻ ሳይሆን ባለቤቱን ልጆቹን ቤተሰቡን ወዳጅ ዘመዱን ሁሉ ያኮራል፡፡ የእገሌ ናቸው ያስብላል፡፡ምሁር ተብሎ ለሀገር የሚበጅ ለወገን የሚጠቅም ተግባር መከወን ቢያቅት ልጆች የሚመኩበት ወዳጅ ዘመድ የሚኮራበት መሆን ቢቸግር ከአሳፋሪ ተግባር በመራቅ፣ አኩሪ መሆን ባይቻል አሳፋሪ ላለመሆን መጠንቀቁ የሚገድ አይሆን ነበር፡፡ መማር ምሁር መባል ለዚህ ካላበቃ …
የዛሬን አያድርገውና አበው የተማረ ሰው አያብልም፣ለጥቅም አያድርም፣ሀቅ አያዛንፍም ድሀ አይበድልም፤ለጌታ አያጎበድድም ወዘ ብለው ያምኑ ስለነበር የተማረ ይግደለኝ ይሉ ነበር፡፡ ዛሪስ? ይሄ ስንን ምላሽ ይሰጠን ይሆን!

፡አባባ ገድልህን ለምን ነው የነገርከኝ?
ለትናንት አሻቅለህ ዛሬ አስጠላኸኝ
ብትከፍተው ገለባ
ሕይወት ትግል አልባ፣ ትግሉም ሕይወት አልባ
የተማረ ይግደለኝ ብለህ አጓግተኸኝ
ፊደል ከቆጠረ ቁጥርን ከደመረ ለሆዱ ካደረ
መንጋ መሀል ጣልከኝ
እኔም ተማከርኩልህ” ተመራመርኩልህ
የመብት አቡጊዳ ትግሌን ጀመርኩልህ
መብሌን አትንኳት ብዬ ፎከርኩልህ
ኧረ በሞትኩልህ ይልቅስ ልንገርህ” ሞትክን በተማረ መመኘትክን እርሳው
ጽድቁን ከፈለከው
ፊደል ያልቆጠረው ያገሬ ገበሬ ተኩሶ ይጣልህ፣ ይግደልህ ከማሳው፡፡

(ቼበለው መኩሪያ፣ ማለዳ፣ 1993)

↧

↧

ፌዴሬሽኑ ታዋቂ ዲጄ ሳይሆን አዋቂ ዲጄ ያስፈልገዋል

$
0
0

yehune

ከሔኖክ ዓለማየሁ

ቶሮንቶ በተደረገው ዓመታዊው የኢትዮጵያ ስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል የመዝጊያ ዝግጅት ላይ የታዘብኩት ነው:: ዝግጅቱ ያማረና የደመቀ ሲሆን በርካታ ታዳሚም ነበር:: ሆኖም በዚህ የመዝጊያ ዝግጅት ላይ በተለይም መሃሪ ደገፋው የሙዚቃ ሥራውን ሲያቀርብ ከጀርባ መስቀል የተሸከመ አንበሳ ከኢትዮጵያ ባንዲራ ጋር በስክሪኑ ላይ ዲጄው አድርጎት ታዝቤያለሁ::

ዲጄው ባለማወቅም ይሁን በማወቅ ይህን ማድረጉ አሳፋሪ ቢሆንም የፌዴሬሽኑ ሰዎች ወዲያውኑ ይህ መደረጉ አግባብ አይደለም ብለን ላቀረበነው ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸውና ማስነሳታቸው ያስመሰግናቸዋል::

ይህ መስቀል የያዘውን አንበሳ በሙዚቃ ኮንሰርቱ ላይ ማድረጉ የሚያስቆጣው የ እስልምና እና የሌሎች እምነት ተከታዮችን ብቻ ሳይሆን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞችንም ጭምር ነው:: በቅድሚያ ፌዴሬሽኑ ከሃይማኖት እና ከፖለቲካ እንዲሁም ከዘር የጸዳ በመሆኑ እንዲህ ያለውን ምስል በመዝጊያው ምሽት ላይ ማድረጉ ተገቢ አይደለም:: የሌሎች እምነት ተከታዮችን መብት የሚጋፋ ነው:: በሌላ በኩል ደግሞ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችንም እምነት የሚያረከስ ነው:: ሙዚቃ በኦርቶዶክስ እምነት ሃጢያት በመሆኑ እንዲህ ያለውን ምስል ማቅረቡ ተገቢ አይደለም::

ለዚህም ነው ፌዴሬሽኑ ለወደፊቱ ታዋቂ ዲጄ ሳይሆን አዋቂ ዲጄ በቦታው ማስቀመጥ ያለበት የምለው::

↧

የቴዲ አፍሮን ልደት በማስመልከት አድናቂዎቹ ደም ለገሱ –ከወደቁትን አንሱ አረጋውያንን ምሳ አበሉ

$
0
0

13624672_10206602795140758_1284372011_n

13650537_10206605081157907_1890357747_n 13652430_10206605081277910_5553935_n 13652561_10206605081437914_1833062748_n 13664315_10206605081197908_1927505071_n 13664383_10206605081557917_315955183_n

(ዘ-ሐበሻ) የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) 40ኛ የልደት በዓል በማስመልከት አድናቂዎቹ የደም ልገሳ እና የምሳ ማብላት ፕሮግራም አካሄዱ:: ይህ ተግባር እስከ ልደቱ ሐምሌ 7 እንደሚቀጥል አድናቂዎቹ ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ አመልክተዋል::

“በየትኛውም ስፍራ ጥሩ ሆነህ ተገኝ:: ጥሩ ነገርም አድርግ” የሚለውን የቴዲ አፍሮን ንግግር እንደ መሪ ቃል በማድረግ በአዲስ አበባ ከወደቁትን አንሱ አረጋውያን መርጃ ማህበር ውስጥ ካሉ አረጋውያን ጋር ምሳ የመብላትና የተለያዩ ስጦታዎችን ለአረጋውያኑ በማበርከት የቴዲ አፍሮ 40ኛ ዓመት ልደት በዓል መከበር ጀምሯል::

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች ገንዘብ በማሰባሰብ አረጋውያኑን ለማገዝ መነሳታቸውም ታውቋል::

በተጨማሪም እነዚሁ የቴዲ አፍቃሪዎች የአርቲስቱን 40ኛ ዓመት በማስመልከት በብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በመገኘት ደም መለገሳቸውም ለዘ-ሐበሻ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል::

↧

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከታሰረ 1ሺህ 760 ቀናት ሆኑት

$
0
0

Eskinder-Nega

ስሜነህ ከሚኒሶታ

“አይበገሬው” (The Iron Man) ይሉታል አድናቂዎቹ – ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ:: ከ150 በላይ የትግል ስልቶችን በመጽሐፍና በጋዜጣ ያቀረበ ሰላማዊ የዴሞክራሲና የሰዎች እኩልነት ታጋይ ነው:: የዓለም የጋዜጦችና ዜና አታሚዎች ማኅበር (WAN-IFRA) የ2014 የነጻነት ወርቅ ብዕር ሽልማት ተሸላሚም ነው:: እነ ፔን ኢንተርናሽናልን ጨምሮ ያልሸለመው ተቋም የለም:: የሚጽፋቸው ሃገራዊ ጽሑፎች ለመንግስት መስታወት ሆነው ችግሩን ሊያሳዩት ቢችሉም በመስታወት ራሱን ማየት የማይችለው ‘አስቀያሚው’ መንግስት በአሸባሪነት ከሶት 18 ዓመት ፈርዶበት እስር ቤት ይገኛል:: በስሙ ተመዘገበ ባለ አንድ ፎቅ ቤት እና <<በውርስ ከቤተሰቡ ያገኘው ‘ግራውንድ ፕላስ ቱ’ ቤቱንም ወርሰውበታል::

ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ዛሬ በፌስቡክ ገጿ ላይ እንዳስታወሰችን ከሆነ እስክንድር ነጋ ከታሰረ ዛሬ 1 ሺህ 760 ቀናት ሆነውታል:: እስክንድር በጥንካሬው እስር ቤትም ሆኖ እኛን እያጠነከረን እስካሁን አለ::

ረዥም ዕድሜ ለ እስክንድር ነጋ – የታሰረላት ሃገር ከህወሓት መንግስት እስር ወጥታ ሁላችንም በነጻነት የምንተነፍስባት ሃገር ያድርግልን::

↧

ቴዲ አፍሮ የፊታችን ረቡዕ ከካናዳ ማኒቶባ ግዛት ፕሪምየር ሊሸለም ነው

$
0
0

በመላው ዊኒፔግ (ካናዳ) እና አካባቢዋ ለምትገኙ የሙዚቃ አፍቃሪዎች በሙሉ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ኩራት የሆነው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ ) የትውልዱ ኮከብ ተሸላሚ (Star of the generation) በመባል ከማኒቶባው ፕሪምየር ግሬግ ሴሊንገር  የፊታችን ረቡዕ July 13 ቀን ሽልማቱን ይቀበላል ።

በዚህ ዝግጅት መሳተፍ የምትፈልጉ የቴዲ አፍቃሪዎችና በዌኔፔግ ካናዳ የምትገኙ ወገኖች የተወሰነ ቦታ ስላለ በዚህ ቁጥር 204-990-2376 በመደወል ቦታ ያስይዙ::
teddy afro

↧
↧

የማለዳ ወግ …የበጎው ሰው ፣ የጎልማሳው ህልፈት  …  ! –ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

* ” …በህብረት መኖር አለብን ብሎ የሚመክር የሚዘክር ድንቅ ሰው ነበር  ፣ አቡኬ ”

fe9a5677-cbd6-4801-8a43-62a40a2432b1   በያዝነው ሳምንት … በአብዛኛው የሀበሻ መገናኛ መንደር  ፣ በማህበራዊ ድህረ ገጽ ዋንኛ መድረክ በ Facebook መስኮት አንድ መሪር መርዶ ተሰምቷል  :( የትሁት ፣ አስተዋይና አርቆ አስተዋዩ በጎ ሰው ፣ የጎልማሳው የአቡኬ አሌክስ ህልፈት  !!!  የአቡኬ አሌክስ በድንገት መለየት ጥልቅ ሀዘናን ሁላችንም አንገብግቦናል  :(  “ከሞቱ አሟሟቱ ”  እንዲሉ አቡኬ ባንድ ጀንበር ታይቶ በርቶ ፣ ባንዱ ጀንበር ሳይታሰብ ጠፍቶብናል   :(  እናም በቅርብ ከሚያውቁት ፣ ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ጓደኞች እኩል በስራው በዝና  የምናውቀው በሀዘኑ አዝነን ከፍቶናል  :(

የጎልማሳው በጎ ሰው አቡኬ አሌክስ መረጃዎች የቅርብ ተከታታይ የሆነችው ባለቤቴ በህልፈቱ ጥልቅ ሀዘን የተሰማቸው መካከል አንዷ ናት  ፣ ስለአቡኬ ስትገልጽ እንዲህ ብላኛለች ” አቡኬ ብሩህ አዕምሮ የነበረው ፣ ኢትዮጵያውያንን በዘር በሐይማኖታዊ ሳይለየን በህብረት መኖር አለብን ብሎ የሚመክር የሚዘክር ድንቅ ሰው ነበር  ፣ አቡኬ  !” ብላኛለች … አዎ  !  ሁላችንም በፊስ ቡክ የመረጃ መለዋዎጫ መድረክ ሃሳቡን በነጻነት አንሸራሻሪ ፣ መረጃ አቀባይና ተቀባይ ፣ ሩቅ አሳቢ መልካም ሰው አቡኬ አሌክስን አጥተናል … በእርግጥም ተጎድተናል …

እንደኔ እንደኔ አቡኬ ሲለየን ያመመን ፣ አቡኬ እንደ ተመራማሪ ታዋቂ የሀገር አውራ ሰው መለየት ያስቆጠረን ፣ የብዙሃኑ መሪር ሃዘን የመሆኑ የታየን  እውነታና ሚስጥር አለው  !  ለእኔ የአቡኬ መልካምነት ገኖ መውጣት ውስጠ ምስጥሩ … ጎልማሳው ማህበራዊ መገናኛዎቻችን በመልካም ጎኑ ተጠቃሚ ፣ የሀገርና  የህዝብ የሁለትዮሽ እሴቶታችን መሰረት የሆነው  የህበረታችን አድማቂ  ፣  መረጃዎችን አቅራቢና አስተላላፊ በመሆን ጊዜውን ለቁም ነገርና ለመልካም ስራ ያዋለ አርቆ አሳቢ በመሆኑ ይመስለኛል  !  አቡኬ አሌክስ …

የአቡኬ ሳይታሰብ በድንገት የህይዎት ጉዞ ፈጻሚ የብዙዎቻችን ቅስም ሰባሪ አሳዛኝ ሀዘንና መርዶ ነው ፣  በህልፈቱ ለተጎዱት ለመላ ቤተሰቡ ፣ ለጓደኞቹና ዘመድ አዝማድ አድናቂዎቹ መጽናናትን እመኛለሁ   !

ነፍስ ይማር አቡኬ   :(

ነቢዩ ሲራክ
ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓም

↧

ዛሬም ጎንደር አነባች! –ሙሉቀን ተስፋው

$
0
0

13599793_1251874374837173_4740002020126252036_nየፌደራል ፓሊስ የለበሱ የትግራይ ልዩ ኃይሎች በጎንደር ዐማሮች ላይ ተኩስ ከፍተዋል፤ ሰዎችም እየሞቱ ነው። መንገዶች ከታች በምስሉ እንደሚታየው ተዘግተዋል።

ወጣቶች “ዐማራ ነን፤ አንፈራም” እያሉ ከትግሬ ሰራዊት ጋር ደማቸውን እያፈሰሱ ነው።
ወጣቶች ወንድሞቻቸውን የወልቃይት ዐማራዎች አሳልፈው አይሰጡም።

የዐማራን ደም ጠጥቶ የማይረካው የትግሬ ፋሽስት

የትግሬ ፋሽስታዊ ሥርዓት በጎንደር ዐማሮች ላይ ዛሬም ደም እያፈሰሰ ነው፤ ሲፈልግ የአዲስ ዓመት ዋዜማ፣ ሲሻው በየቤቱ እየለቀመ፣ አሊያም በማረሚያ ቤት በሕግ ጥላ ሥር ባሉበት የዐማራን ደም ያፈሳል፡፡ ይህ እብሪትና ፍጹም መታበይ ነው፡፡

የወልቃይትን ዐማሮች በተወለዱበት ቀየ፣ ባባቶቻቸው ርስት እነርሱ መጥተው አባረሯቸው፡፡ ቀያቸውን ለቀው ጎንደር ከተማ ባሉበት ‹‹እስኪ የሚያድናችሁን አያለሁ›› እያሉ በየተጠጉበት መንጥሮ መውሰድ የደረሱበትን የእብሪትና መታበይ መጠን ያሳያል፡፡

ይህ የአንድ አናሳ ቡድን ፋሽስታዊ ሥርዓት በዐማራው ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል ዘርዝረን አንዘልቀውም፡፡ በጎንደር ከተማ ብቻ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ የገደለውን ሰው ብዛት ማንም ቆጥሮ አይዘልቀውም፡፡ ይህ ሥርዓት በ85/86 ዓ.ም. በአዲስ ዓመት ዋዜማ አደባባይ ኢየሱስ ገብቶ ከ60 በላይ ምዕመንን ረፈረፈ፤ የቤተ መቅደስ መጋረጃዎች በደም የጨቀየ የቤተ መቅደስ መወልወያ ሆነ፡፡ የሞተ አስከሬን የከፈን ጨርቅ ሆነ፡፡ በ2006/7 ዓ.ም. ጥረው ግረው የሠሩትን ቤት በገንፎ ቁጭ አካባቢ አፈራረሰ፤ ብዙ ሰዎችንም በጠራራ ፀሐይ ገደለ፡፡ በ2008 ዓ.ም. ማረሚያ ቤት አቃጥሎ በሕግ ጥላ ሥር ያሉ ከ100 የሚልቁ ዐማሮችን በጅምላ ጨረሰ፡፡

ይኸው ዛሬ የማኅበራዊ ሚዲያን ዘግቶ የጎንደር ዐማሮችን ለመጨፍጨፍ በንጹኃን ሰዎች ላይ የጥይት እሩምታ ከፍቷል፡፡ ከፊል የወልቃይት የዐማራ ማንነት አስተባባሪ ከሚቴዎችን አፍኖ ወስዷል፤ ቀሪዎችን ለመውሰድ በመከላከያና በፌደራል ፖሊስ አካባቢው ከቧል፡፡ አንድ የወልቃይት ዐማራ በጥይት ተመቶ ሆስፒታል ገብቷል፡፡ ዛሬም እንደ ትናንቱ በየአደባባዩ ያፈሰሱት ደም ቆሌያቸውን የሚያረካው አልሆነም፡፡

ሞት ለዐማራ ሕዝብ አዲስ አይደለም፤ የፋሽስቱ የትግሬ መንግሥት ሃያ አምስት ዓመት ሲገድለው ኖሯል፡፡ የዐማራ ሕዝብ ለሁሉም እየኖረ ብቻውን ሲሞት ነው ታሪክ የሚያውቀው፡፡ የጎንደር ዐማሮችም የወልቃይት ዐማራ የማንነት ኮሚቴዎችን (ያልተወሰዱትን) አሳልፈው እንደማይሰጧቸው አምናለሁ፡፡ እርግጥ ነው ወያኔዎች ብዙ ሰው ይገድላሉ፤ መቼስ ያልገደሉበት ጊዜ አለና፡፡

ይህ እብሪት በዐማራ ሕዝብ የተባበረ ክንድ የሚተነፍስበት ቀን ሩቅ እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ በጎንደር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ስለራሳቸው መጻኢ እጣ ፈንታ ሲሉ ወገኖቻቸው በዐማራው ላይ የሚያደርሰውን በደል እንዲያቆሙ መናገር አለባቸው፡፡ እስካሁን የተዘረፈው፤ እስካሁን የተገደለው ከበቂም በላይ ነው፡፡ ጥጋብ ከልክ ካለፈ ያቅራል፡፡

ማሳሰቢያ፡ በአካባቢው ያላችሁ ዐማሮች መረጃዎችን በመለዋወጥ እንድትተባበሩ አሳስባለሁ፤ ገለልተኛ ነን የሚሉ የመገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን ይከታተሉት ዘንድም እጠይቃለሁ፡፡

↧

የሕወሓት ንብረት የሆነው ሰላም ባስን የጎንደር ወጣቶች በእሳት አነደዱት

$
0
0

selam bus

(ዘ-ሐበሻ) የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ምንነት ጥያቄ አቅራቢ የኮሚቴ አባላትን ለመያዝ መሞከራቸውና  ማገታቸውን ተከትሎ በተለይም ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ቤት ውስጥ የተኩስ እሩምታ መሰማቱን ተከትሎ ከትግራይ የተላኩ የደህንነት አባላትን ለመቃወም በተነሳ ግጭት በጎንደር ከተማ ሕዝቡ ቁጣውን በመግለጽ በአካባቢው የነበረውንና የሕወሃት ንግድ ድርጅት አካል የሆነውን ሰላም አውቶቡስ በማቃጠል ተቃውሞን እየገለጸ ነው::

ጎንደር ከተማ በተኩስ እሩምታ ስትናጥ መዋሏን ተከትሎ ሕዝቡ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ሲሆን ጎንደርን አቋርጦ የሚሄደው ሰላም ባስ የጫናቸውን ሰዎች በማውረድ አውቶቡሱ በ እሳት እንዲነድ ተደርጓል:: ሰላም ባስ ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ የተማሪዎች አመጽ ጊዜም መቃጠሉ አይዘነጋም::

በጎንደር ውጥረቱ እንዳየለ ነው – ተከታታይ መረጃዎችን ዘ-ሐበሻ ይዛ ትመለሳለች::

↧

የኢትዮጵያ ኦሎምቲክ ኮሚቴ ለህውሃት ሚሊየን ብሮችን አስረከበ

$
0
0

2016-07-16-02-33-17--1818555830

ቶማስ ሰብስቤ

ለዘንድሮ ብራዚል  ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የገቢ ማሰባሰቢያውን እያገባደደ ነው።ጨርሷልም የሚሉ አሉ።በዚህ የማሰባሰቢያ የተገኘው ገቢ ሁለተኛ ከፍተኛ በጀት ግን ወደ ህውሃት ንብረት ዋፋ ነው የሚገባው።

ዋፋ ስንት ብር ያገኛል――ለምን?

ዋፋ የማስታወቂያ እና የገቢ ማሰባሰቢያው በበላይነት ሰለሚሰራ ቢያንስ 15 ሚሊየን ብር ተሰቶታል ተብሏል።ይህን ሰሰማ በወንዶች 10 ሺ እንደው ደከም ሰላልን ዋፋ በዚህ ርቀት ሊሮጥ ይሆን ብያለው።

ጨረታ የሌለው አሸናፊነት!

ማንም አልተወዳደረም ሳይሆን ስራው ያለቀው በቤተሰብ ዋጋ ነው።ምክንያት ካላችሁኝ በፌደራል ወጣቶች እና ሰፖርት ሚኒስቴር ውስጠ ደንብ ላይ እንዲ ይላል «የትኛውም መንግስት የሚሰራቸው የገቢ ማሰባሰቢያ በዋፋ በኩል ይፈፀማል»።ታዲያ ይህ ህግ ካለ ጨረታ ጆከር ነው ብል ምን ያነሰኛል።

ዋፋ እንዴት የህውሃት ልጅ ሆነ የምትሉ ?

ዋፋ ማለት እንደ ቁምሳ ነው።በቀን ሶሰቴ መብላት ያልቻልነው ኢትዮጵያዊያነን  በአንድ ወቅት በዚህ ቀመር በልተናል።ቁርስ አምስት ሰዓት ፣እራት  አስራ አንድ ሰዓት።ለዚም ከቁርስ,,,,,,ቁ ፣ ከምሳ,,,,, ምሳ ወስዶ ቁምሳ እንዳለው በእውቀቱ።ዋፋ እንደዛው ነው። ዋልታ እና ፋና አንዳንድ ፊደል አዋተው ነው።በእናትም በአባትም አንድ ሆንው ዋፋ ያሉት።ከግራ ኪስ ቀኝ ኪስ ማለት ይሄ ነው።እዚህ ላይ ምርመራ ጋዜጠኝነት ሰራለው ብትል አሸባሪ ነህ።

የዋፋን  ጠበቃ ማነው?

እውነት ለመናገር ዋፋ ይህን ብር ሳያውቀዉ በአራት አመት አንዴ የሚመጣለት ህውሃት ጠይቆ ሳይሆን በ ፖለቲካ ሂሳብ ነው።የኦሎምፒክ ኮሚቴው በህውሃት እና ኦፒዲዮ  ስራ አስኪያጆች ይመራል።ሲዝናኑ እንኳን ከዋካ ዋካ ይልቅ ዋፋ ይመጣባቸዋል።

ዘንድሮስ እንደ ለንደን ከአትሌቶቹ በላይ ኮሚቴ ይበዛል ለመሄድ!

አይ ! ይህ እማ ብራዚል እኮ ነው አይበዙም ካላቹ ተሳስታችሃል።ጫወታው የቀን አበል ፤ ጥቅማ ጥቅም ነው።ሮጦ ወርቅ ከሚያመጣው ቁጭ ብሎ የሚያጨበጭ ኮሚቴ አበሉ ይበዛል።ደሞ ሲመጡ የሚሸጥ እቃ ያመጣሉ እና ሜዳሊያ እንዳይረሳ።

የመጀመሪያው የመንግስት ድጋፍ ውሃ እንዳይበላው!

በኦሎምቲክ ታሪክ ለሀገራችን ኮሚቴ መንግስት ድጋፍ አድርጓል ዘንድሮ።ልክ እንደ ኬንያ መድቡልን ብላቹ በዛው ከውጤቱ ጋር እንዳይጠፋ መጠንቀቅ።የታቀደው 4 ወርቅ ፣4 ብር ፣ 4 ነሃስ ሜዳሊያ ብዙ ሰራ ይሻል።

↧
↧

የሕወሓት ስጦታ ለአርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ

$
0
0

hodam

የሕወሓት መንግስትን ግድያ፣ ህዝብን ማዋረድ፣ አንድነትን ማፍረስና ዘረኝነት የምትደግፍ ከሆነ ትግርኛ ባትናገርም የትግርኛ ፕሮግራም እንድታዘጋጅ ገንዘቡም ሚዲያውም ይፈቀድልሃል:: የሕወሃት ደጋፊ ከሆንክ አይደለም ገንዘብ የአሸንዳ በዓል መከበሪያ ቀንም ይቀየርልሃል  ልክ እንደሸዋፈራው ደሳለኝ::

ሸዋፈራው ልክ እንደ ሰራዊት ፍቅሬ ሁሉ ከሕወሓት ባለስልጣናት ጎን የቆመ እንዲሁም በየበዓላቸው እየተገኘ የሚያወድስ በመሆኑ በቀጭን ት ዕዛዝ ገንዘብ እንዲሰራ እንዲህ ያለው ፕሮግራም ይፈቀድለታል:: የሚገርመው የአሸንዳ በዓል የሚከበረው ነሐሴ 15/ 16 ቢሆንም ለሸዋፈራው የተፈቀደው ፕሮግራም ግን ለነሐሴ 8 ነው:: የአሸንዳ በዓልን ለምን ከአንድ ሳምንት በፊት ቀድሞ ማክበር ለምን አስፈለገ? የሚለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ ይህንን ፕሮግራም ከፍተኛ የመንግስት ድርጅቶች ስፖንሰር እንዲያደርጉትም በቀጭኑ ሽቦ ታዟል:: በአጭሩ ሸዋፈራው በአሸንዳ በዓል ዝግጅት ብቻ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ይሰራበታል:: አየህ የሕወሓትን ወንጀል ከደገፍክ የማይፈቀድልህ ነገር የለም:: ለሕሊናቸው ያደሩና ገለልተኛ ሆነው የተቀመጡ ባለሙያ አርቲስቶች ቤታቸው ተቀምጠው ሆዳሞች በአቋራጭ ገንዘቡን ይሰሩታል::

ከኢቢሲ የወጣውን ደብዳቤ ይመልከቱት::

shewaferaw

↧

ከእልቂት እንዲድኑ  ትግሬ ሁሉ ወያኔ አለመሆኑን ያሳዩን –አብርሃም ታዬ

$
0
0

debark carየእናንተ ቤት እየተመረጠ ሲቃጠል፥ የእናንተ ድርጅት እየተነጠለ ጉዳት ሲደርስበት፥ የሰላም ባሳችሁ በየወቅቱ  ሲቃጠል ምንም አይሰማችሁም ትግሬ ወያኔዎች? ኢትዮጵያ ውስጥ ግርግር በተነሳ ቁጥር ለምን የሁሉም ጣት እኛ ላይ ያነጣጥራል ብላቹ ለምን አትገመግሙም። ምርጫ ዘጠና ስባትን ተከትሎ በተነሳው ነውጥ ሆነ የአሁኑ የጎንደር ህዝብ ጥያቄ ላይ የትግሬ  ሆቴል እና ንብረት ኢላማ መሆናቸው ሌላውም ሲነሳ ያንገበግባችኋል።መጽሃፍ እንደሚል በእርጥቡ እንዲህ ከሆነማ በደረቁ እንዴት እንደምትነዱ አስቡት። ዘላለም ስለማትነግሱ የለውጥ አብዮቱ አራት ኪሎ ቤተመንግስት ለመግባት ገና ግማሽ ሃገር ሲቀረው ሙሉ በሙሉ የዘረኝነት ጄኖሳይድ ሰለባ እንደምትሆኑ ግልጽ ነው። ከኢትዮጵያ ህዝብ  አምስት ከመቶ የማይሞላ የቁጥራችሁን ማነስን የባሰ የሚገዳደር ዕልቂት ተጋርጦባችኋል።በየጊዜው ቂም የያዘባቹ  ከዘጠና ፐርሰንት በላይ  የሚሆን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የግፍ ጽዋው ሲሞላ ይበቀላችኋል። ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በሰላም በፍቅር በመከባበር ለመኖር የሚያስችል የእርቅ ድልድይ  መፍጠር ካለባቹ ጊዜው አሁን ነው።

የተገላቢጦሽ  እናንተ ግን  የአናሳ አምባገነን (minority dictatorship )ነታቹ ብሶባችኋል።ከናዚ ጀርመን  የበለጠ የሚዘገንን ሰይጣናዊ በሆነው ዘረኝነት ታውራቹ ዛሬም  አማራ እና ኦሮሞን በማናቆር  በዳኝነት  ስልጣን ለመክረም የማትፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ይልቁንም ተጋሩ የተሰኘው ማህበራችሁ ሳይቀር ያባሳጨው የወደመው ንብረት እንጂ ከሁለቱም ወገን የተቀጠፈው የሰው ህይወት አይደለም በመግለጫቹ  እንዳሳሰባችሁት።

በአገዛዙ ተማረው ተሰደው  በግፈኛው  አይሲስ እና በሜዲትራንያን ባህር ያለቁት ኢትዮጵያውያን   መሆናቸውን የአለም ሚዲያዎች እየዘገቡት እየነገሯችሁ  ዜግነታቸውን ሳናጣራ እንደርስላቸውም በማለታችሁ ስንቶች መንግስት የሌላቸው አስከሬን ሆኑ? ለህወሃቱ ዘፋኝ ኢያሱ በርሄ ወይም ለመለስ ዜናዊ በድን ግን መንገድ ተዘግቶ ከሁለት ሳምንት በላይ ብሄራዊ የ ሃዘን ቀን ታውጆ ነበር። እነዚህ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ሊወክሉ የሚችሉ  ከመቶ በላይ የወገኖች  ደም ከዘረኛው መለስ ዜናዊ ወይ ካንዱ  ዘረኝነትን ሊተክል ከተሰዋ ትግራዋይ ደም በብዙ እጥፍ መከበር ነበረበት።  በጋምቤላ የአኙዋክና የኑዌርን ጎሳ በማጋጨት ለፈጸማችሁት የዘር ጅምላ ጭፍጨፋ የብዙ ሺ ሰዎች  ፍርድ ሳታገኙ የሩዋንዳን ሁቱ እና ቱት ሲን  ኢንተርሃሞይ ዕልቂት ትዘክራላቹ። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላልች ማለት ህወሃት ናት። ጀኖሳይድ ዋች የተባለ ድርጅት እንደዘገበው ኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ ሁሉም አይነት  ድርጊት በዘር ከመከፋፈል classification እስከ ጅምላ ጭፍጨፋ ያሉት ሰባት እርከኖች ተፈጽሞብናል። “Genocide Watch considers Ethiopia to have already reached Stage 7 of the 8 stages of, genocidal massacres, against many of its peoples, including the Anuak, Ogadeni, Oromo, and Omo tribes.”

በደኖ በሃረር በቁማቸው ለተቀበሩት የአማራ ወገኖች እልቂት መንስኤ መፍትሄ ሳታበጁ ከሃያ አምስት  አመት በላይ ተጎልታቹ በፌደራሊዝም ስም ትነግዳላችሁ።

አማራ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው ብሎ ህወሃት እንደተነሳ ሁሉ አማራው እናንተ ላይ የአጸፋ እርምጃ ቢወስድ አይደንቅም። ሆን ተብሎ በሰሜን ጎንደር ያሉ ሴቶች እንዳይወልዱ የሚያመክን መርፌ ለምን ተወጉ? ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ እንዳረጋገጠው የአማራ ህዝብ ብዛት መሆን ካለበት በሶስት ሚሊዮን ያነሰው በዘመናዊ ጀኖሳይድ ሂሳብ ብትገድሉ ኣይደል እንዴ? በጀቱን ለመቀነስ?

በታሪክ ድንበሩ ከተከዜ ወንዝ  አልፎ ያማያውቀውን የትግራይ ክልል ከሱዳን ጋር ለማዋሰን ስትሉ ብሎም በአፋርም በወሎም በኩል ያልነበራችሁን ይዞታ የመውረር አባዜ ግጭት የፈጠራችሁት እናንተ አይደላችሁ እንዴ? በጎንደር ወልቃት ጠገዴ  አማራነት ላይ ያልነበረ ማንነት ባትፈጥሩ ኖሮ ይኼ ሁሉ  ቀውስ ባልመጣ ነበር።

ለመሆኑ የትኛው የኦሮሚያ ክልል ወይ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ነው በህወሃት ከተሰጠው ሃላፊነት ውጭ ራስ ገዝ የሆነው?  ለጠቅላይ ሚንስትር አማካሪ በትግሬው  መለስ ጊዜ ሳይኖር ከደቡብ ለመጣው ሃይለማርያም ደሳለኝ ሲሆን ግን አራት አማካሪ በአናቱ ማስቀመጥ ስድብ አይሆንም? ተጠቅላይ ምኒስትርነቱን ለማጉላት ለዛውም አለቆቹ ሁሉ ትግሬ። እራሳቹ  እንደምትናገሩት ኦሮሞዎችን የምታስፈራሩበት የምትገለገሉበት ድርጅት  ኦህዴዶች ልባቸው ቢፋቅ ኦነግ ናቸው። በቅርቡ ግምገማቹ   ስጋታችሁን እንደገለጻችሁት  የአማራው ብአዴን ወይ የደቡቡ አሻንጉሊት ድርጅት  ደኢህዴን ውስጥ ግንቦት ሰባቶች  አሉ። እነዚህ ህወሃትን ያዘሉ አንቀልባ ድርጅቶች ማዘል ደክሞአቸው በቃ ሲሉ ማንም የሚያዝንላቹ የለም።  እስካሁንም ያላችሁት በነዚህ ተላላኪ ካድሬዎች ብቻ ነው። አንዳንድ የኦህዴድ፥ የብአዴን ወይም የደቡብ ህዝብ ደኢህዴን  አመራሮች ከአለቃቸው ህወሃት የበለጠ ዘረኝነቱንስ ሲያስፈጽሙ ወገናቸው ላይ የመጨከናቸውን ያህል ትግሬ ሆኖ ህወሃትን ጨክኖ አንቅሮ የሚተፋ አርአያ ሰብ ያስፈልጋል።

በየድርጅቱ ፥በየሰራዊቱ ፥በየህዋሱ ጠርናፊው ህወሃት ብቻ ሲሆን አንድ ቀን በቃኝ የማይሉ ይመስላችኋል? እስቲ አስቡት ከስልሳ የጦር ጄነራሎች 57 ትግሬ፥ ብሎም የቴሌ እና ሌሎች ሲቪክ መስሪያ ቤቶች ጠርናፊ አለቃ ትግሬ ሲሆን አይሰቀጥጣችሁም?  ንግዱንማ ሙሉ በሙሉ  በድፍረት ተቆጣጥራሁታል።

ኢፈርት በተባለ የህወሃት ክንዳቹ  የሃገሪቱ ሃብትን ስትቀራመቱ ያልመሰላችሁን ከገበያ ስታባርሩ ከርማችሁ  በቅርቡ የሆላንድ ካር(Holland car ) ድርጅትን  ከአዲስ አበባ በቀይ ካርድ አባራችሁ  የፈረንሳዩ ፔጆ መኪና በመስፍን ኢንደስትሪያል ስር እንዲመረት ፋብሪካውን መቀሌ ላይ ገነባችሁ። ትግራይ ልትለማ ሌላው የሚደማ ለምንድነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ቲቪ  ከፍተን ስናይ ማስታወቂያው ሁሉ ሲሚንቶ፣ መድሃኒት ፋብሪካ፥ ምግብ እና የተለያዩ ሸቀጦች ወዘተ የተገነቡት ወይ አድራሻቸው ትግራይ ላይ ነው። ብቻውን የበላ ብቻውን እንደሚሞት ማን በነገራችሁ? የሃገሪቱ ሃብት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለሁሉም ተደራሽ ይሁን የሚል እንዴት አንድ ቅን አሳቢ ከመሃላችሁ ይጥፋ?

ለኮሎኔል አታክልቲ ገብረሚካኤል  ልጅ ህክምና ከኢፌዲሪ የብረታብረት ኮርፖሬሽን ኤጀንሲ 14 ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች  ሶስት ሚሊዮን ብር አዋጥተው ባንኮክ ታይላንድ አሳከሙት። ብቸኛው የህዝብ ልጅ ሃብታሙ አያሌው ግን በከፍተኛ ኪንታሮት ታሞም ከሃገር ወጥቶ እንዳይታከም ተከልክሏል። ኢፍትሃዊነት በየፈርጁ ማለት ይኸ ነው። ህወሃት ማለት ኢፍት ሃዊነት ነው።

በእርግጥ ትግሬ ሁሉ አልፎለታል ወይም ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው ባይባልም ትግሬ ሆኖ ተቃዋሚ የሆነ አስር አይሞሉም። እንዘርዝር ሲባል ወያኔ አስሮ ከሚፈታቸው አብርሃ ደስታ ፤ አሰግድ ገብረስላሴ ወይም በስደት ካሉት ገብረመድህን እና አረጋሽ ይጠቀሳሉ።በቃ። ከነዚህ  ውጭ ሰው የለም እንዴ? ህወሃት እየገነባ ካለው ራሱን አጥፊ ዘረኝነት አንጻር ቅን ትግሬዎች ተሰባስባቹ ትግራይን እናድን የሚል ማህበር ወይ ፓርቲ ብትመሰርቱ ጥቅሙ ለራሳችሁ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በጉልህ ከሚጠቀስላችሁ የጣልያን ጊዜ ባንዳነታቹ (የመለስ ዜናዊ አባትንም የጣልያን ተላላኪ እንደነበሩ በመጥቀስም) ወይም ወይም ሞላ አስገዶም ትህዴንን  ስለካደ    አይደለም ካሳ የምትከፍሉት። ይልቅ ከትግራይ ማሕጸን ተወልደው መሰዋዕት የሆኑት የራስ አሉላ አጽም ብሎም ለጣልያን ያደሩ መስለው ለአጼ ምኒልክ መረጃ በማቀበል ለአደዋው ድል  አስተዋጾ ያበረከቱት የባሻ አውአሎም አጽም እንዳይወቅሳችሁ  ነው።ለወያኔ ተብሎ  የተተኮሰ ጥይት ወይ ፍንጣሪ  እናንተንም በማወቅም ይሁን ባለማውቅ   ስለሚመታችሁ አስቡበት።ነግ በኔ በሉ። ለወያኔ የተወረወረ እሳት ትግሬዎችን በሙሉ እንዳያቃጥል መፍትሄውን ራሳቸው አሁኑኑ ይጠቁሙን ትግሬ ሁሉ ወያኔ ላለመሆኑ በተናጥል ወይ በማህበር  አሳዩን።  ጀግኖች በአንድነት የተዋደቁላትን ሃገር እንዳትፈራርስ ማደረግ  የሁሉም ሃላፊነት ነው።

አብርሃም ታዬ  zeabraham@gmail.com

 

↧

“እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል”–ሰቆቃ በማዕከላዊ

$
0
0

TPLF

ሰቆቃ በማዕከላዊ
“እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ
ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም
ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ
አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡”

አበበ ካሴ

እኔ አበበ ካሴ እባላለሁ፡፡ የሰሜን ጎንደር ተወላጅ ነኝ፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤት ከ5 ወር በላይ ታስሬለሁ፡፡ ከዚህ መካከል 4 ወር ከ25 ቀናት በጨለማ ቤት ተቆልፎብኝ ቆይቻለሁ፡፡ ማዕከላዊ በነበርኩበት ወቅት የሁሉም እግርና እጆቼ ጥፍሮች ተነቅለዋል፡፡ አንዳንድ ቀን እጄ ላይ የሆነ
ነገር ስለሚወጉኝ ጥፍሮቼ ሲነቀሉ አላውቅም፡፡ ስነቃ ነው መነቀላቸውን የማውቀው፡፡ ከዛም ቁስሉን እየነካኩ ያሰቃዩኛል፡፡ ማደንዛዣ ለምን እንደሚወጉኝ አላውቅም፡፡ ጥፍሮቼን ሲነቅሉኝ ብቻ ሳይሆን ሌላ ጊዜም ራሴን እንድስት ያደርጉኛል፡፡ እጅና እግሬን አስረው እንደ ፍሪጅ ያለ
እቃ ውስጥ ያለ በረዶ ውስጥ ያስቆሙኛል፡፡ ለብዙ ሰዓት በጣም ቀዝቃዛ የሆነ ቦታ ላይ እስክደነዝዝ ቆሜ እውላለሁ፡፡ እስኪበቃቸው ከደበደቡ በኋላ እጅና እግሬን አስረው ከምርመራ ክፍሉ በታች በሚገኝ ምድር ቤት ክፍል ውስጥ ያለ ጉድጓድ ላይ ጥለውኝ ይሄዳሉ፡፡ ጉድጓዱ ጉንዳንን ጨምሮ ተባዮች ያሉት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እግሬንና እጄን አስረው ዘቅዝቀውኝ ይሄዳሉ፡፡ የመጣው ሁሉ ዝዋዥዌ እንደሚጫወት ህፃን ወዲያና ወዲህ ያደርገኛል፡፡ ገልብጠው አስረው ሲዘቀዝቁኝ በአብዛኛው ራሴን እስታለሁ፡፡ እግርና እጄን ከወንበር ጋር ያስሩኛል፡፡

ከወንዶች በተጨማሪ ሴቶችም ይመረምሩኛል፡፡ ሴቶቹ የሚመረምሩኝ ራቁቴን አርገው ነው፡፡ እነሱም ራቁታቸውን ሆነው ነው የሚመረምሩኝ፡፡ አሁን ለመናገር የማልደፈርው አፀያፊ ነገርም ፈፅመውብኛል፡፡ ይህን አፀያፊ ነገር የሚፈፅሙት አደንዛዥ እፅ እየተጠቀሙ ነው፡፡ ይህን
ሲያደርጉ በአይኔ አይቻቸዋለሁ፡፡ መርማሪዎቹ ሰውነቴን በኤሌክትሪክ አቃጥለውኛል፡፡

ኤሌክትሪኩን የሚሰኩት ደረቴና የውስጥ እግሬ ላይ ነው፡፡ በዚህም የውስጥ እግሬ ተገልብጦ ሌላ ሰውነት አምጥቶ ነበር፡፡ እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡ ይህን ያህል አሰቃይተው ከጥቅም ውጭ ስሆን ቂሊንጦ አምጥተው ጣሉኝ፡፡ 11 ወር ያህል አልጋ ላይ ነበርኩ፡፡ በኤሌክትሪክ ግርፊያው ምክንያት ግራ ሰውነቴ ሽብ ሆኖ ነበር፡፡ ግራ እግሬ መንቀሳቀስ አይችልም ነበር፡፡ በምርኩዝ ነበር የምሄደው፡፡ አሁን እያነከስኩ ነው የምሄደው፡፡

በተለይ ማዕከላዊ ውስጥ ይህን ያህል የሚሰቃዩኝ አንደኛ የሚያግዛችሁ አገር ማን ነው በሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አማራ ክልል ውስጥ እንድትንቀሳቀሱ የሚተባበሯችሁን የብአዴን ባለስልጣናት ስም ተናገር እያሉ ነው፡፡ በሶስተኛ ደረጃ የሚያሰቃዩኝ የት የት ቦታ ነው የሰለጠንከው እያሉ ነው፡፡

እዚህ ቂሊንጦ ከመጣሁ በኋላም ያሰቃዩኛል፡፡ ወጣቶች እንዳይቀርቡኝ ያስፈራሩዋቸዋል፡፡ ማንም ጠርቶ እንዳይጠይቀኝ እየተደረገ ነው፡፡ ጨለማ ክፍል ወስደውም አስረውኝ ያውቃሉ፡፡ እነሱ ደብድበው ከጥቅም ውጭ ካደረጉኝ በኋላ የምደገፍበትን ምርኩዝም ቀምተውኛል፡፡ ‹‹ይህኮ የጦር
መሳሪያ አይደለም፡፡ እንጨት ነው፡፡ ለምን ትቀሙኛላችሁ? ደግሞም እናንተ ናችሁ እንዲህ ያደረጋችሁኝ፡፡›› ብያቸው ነበር፡፡ የሚሰሙ ሰዎች አይደሉም፡፡ የታሰርኩበት ክፍል ውስጥ እንድተኛበት የተሰጠኝ ቦታ ሽንት ቤቱ አጠገብ ነው፡፡ ሽንት እየሸተተኝ ነው የምተኝው፡፡

‹‹ወደ ሌላ ቦታ ቀይሩኝ!›› ስላቸው ‹‹ደግሞ ለአንተ ይህ አንሶህ ነው?›› ይሉኛል፡፡ ያ ሁሉ ድብደባ ደርሶብኝ አልጋ ላይ በነበርኩበት ወቅት ወጣቶቹ ህክምና እንዳገኝ ወደ ሀኪም ቤቱ ወሰዱኝ፡፡ እነሱ ግን ‹‹ለአንተ ህክምና ሳይሆን ጥይት ነበር የሚገባህ›› ብለው መለሱኝ፡፡ እንዲህ እያሉ ለምን እንደማይገድሉኝ ይገርመኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ልጆችዋ ለእልቂት፣ ለስደት፣ ለግድያ እየተዳረጉ ነው፡፡ በአካልም ሆነ በስነ ልቦና ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ዓለም ለሰው ልጅ ምቹ በሆነችት ከዓለም ውጭ ሆነናል፡፡ የመገናር፣ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት በአጠቃላይ ሰው የሚያደርጉንን መብቶች ተነጥቀናል፡፡ ከሰው የማንቆጠርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ገዥዎቻችን ህዝብን እየገደሉና ከሰው በታች አድርገው እየገዙም ቢሆን ግን ዓለምን እያታለሉ ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ሁሉ የሚደረገው የአንድን ቡድን የበላይነት ለማስፈን መሆኑ ነው፡፡ እንዲጠፋ ሆን ተብሎ ጥቃት የሚደርስበት ህዝብም እንዳለ እያየን ነው፡፡ ግን ኢትዮጵያ የ95 ሚሊዮን ህዝን ሀገር ናት፡፡

አሁን ያለው ስርዓት የአንድ ቡድን ስርዓት ነው፡፡ ለእሱ መኖር ደግሞ ሌሎቹን ገድሎ፣ አሰቃይቶ፣ አሳድዶ መኖር ይፈልጋል፡፡ ለስሙ የብሄር ብሄረሰብ መብት እናከብራለን ቢባልም እውነቱ ግን ኢትዮጵያውያን የመናገር፣ የመፃፍ፣ የመደራጀትና ሌሎች መብቶችን ተነፍጎ ከሰውነት ወጥተው ይገኛሉ፡፡ በዓለም ደረጃ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ቋንቋና ዘርን አይለይም፡፡ ይህ የሚደረገው በህወሓት ስርዓት ብቻ ነው፡፡ እኔ በርካታ ሰቆቃ የደረሰብኝ ሰው ስለሆንኩ ስርዓቱ የሚፈፅመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመመስከር እችላለሁ፡፡ እኔን ሰቆቃ ያደረሱብኝ ሰዎች ማንነታቸው መታወቅ ስላለባቸው እንደሚከተለው ስማቸውን እዘረዝራለሁ

1. አቶ አሸነፍ ተስፋሁን ላቀው
2. አቶ አብርሃም አይሸሽም
3. ሙሉጌታ ወርቁ
4. አቶ ደረሱ አያናው
5. የአማራ ክልል ደህንነት ኃላፊ የሆነው አቶ ተሾመ
6. የሰ/ጎ/መ/የታክቲክ ኃላፊ አቶ ሙላ እንየው
7. የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ተክላይ
8. የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ጌትነት
9. አቶ አሰፋ አትንኩት (ምርመራበ ኃላፊ)
10. መቶ አለቃ ተስፋዬ (መርማሪ)
11. ሳጅን ፍሬ ህይወት (መርማሪ)
12. ሳጅን ፅጌ (መርማሪ)
ከላይ የጠቀስኳቸውን በስምና በአካል የማውቃቸው ሲሆኑ ከእነዚህ በተጨማሪ ከደህንነት መስሪያ ቤቱ እየመጡ የሚያሰቃዩን ስማቸውን የማላስታውሳቸውና በመልክም የማውቃቸው የህወሓት ደህንነቶች አሉ፡፡

እዚህ እኛን እንደዚህ ሲያሰቃዩ ሀገሪቱን ገንዘብ መዝብረው የታሰሩ ሰዎች ምንም አይሆኑም፡፡ ተመችቷቸው ነው የሚኖሩት፡፡ ቂሊንጦ ውስጥ ሰው እንዳይቀርበኝም ቢፈልጉም ሰው ግን በጣም ይወደኛል፡፡ አሁን ጥፍሮቼ በቅለዋል፣ መራመድ ችያለሁ፡፡ አንድ ሽህ አመት አይኖርም፡፡ በጣም ብዙ ወገኖቻችን ሞተዋል፡፡ እኔ አለሁ፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ባለስልጣናት እኔ ላይ የደረሰውን ጨምሮ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ በፈፀሙት ወንጀል መጠየቃቸው የማይቀር ነው፡፡ ይህ ሁሉ በደል ደረሰብኝ ስል ዝም ብዬ አይደለም፡፡ ማንኛውም ሰው መጥቶ የተሸማቀቀውን እግሬን፣ ቅጥ ባጣ ድብደባ የተጎዳው ሰውነቴን ማየት ይቻላል፡፡ ጥፍሮቼንም ለመስክርነት ይዤያቸዋለሁ፡፡ እነሱ ነቅለው ጥለው ሲሄዱ እኔ ስነቃ ሰብስቤ አስቀምጣቸዋለሁ፡፡ የተወሰኑትን ለመረጃነት አስቀምጫቸዋለሁ፡፡ ይህን ስል ግን እኔ ላይ የደረሰው ስቃይም የማይጠበቅ ሆኖ አይደለም፡፡ እነዚህ ሰዎች እንኳንስ ግለሰብ ሀገርም ገንጥለዋል፡፡ ከ40 አመት በፊት የነበረው የኢትዮጵያ ካርታ ተሸርፏል፡፡ እንኳን ሰው ሀገርም ለማጥፋት እየሰሩ ነው፡፡ ታሪካቸው፣ አመጣጣቸውም የሚያሳየው ይህን ነው፡፡ ይህን ሁሉ የምለውም መታወቅ ስላለበት ነው፡፡

↧

አለም አቀፍ የመገናኛ ሚዲያዎች የጎንደርን ግጭት በስፊው እየዘገቡ  ይገኛሉ

$
0
0

በሰሜን ኢትዮጵያ ጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰቀሰውን  ግጭት የአለም አቀፍ የመገናኛ ሚዲያዎችን ቀልብ እየሳበ ይገኛል።   በተለያዩ  አቅጣጫዎች እየተስተዋለ የሚገኘውን  የህዝብና የመንግስት ግጭቶች እና መንግስት እየወሰደ  ያለውን  ጥቃት   የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ትኩረታቸውን  ወደ ምስራቅ አፍሪቃ እንዲያደርጉ እያስገደዳችው  ነው።

debark car

የጎንደርን የህዝብ አመጽና የመንግስትን እርምጃ በተመለከተ አልጄዚራ( Al Jazeera)  የጀርመኑ ዶቼ ቬሌ የእንግሊዘኛ ሚዲያ (Deutsche Welle English) እንዲሁም ሶማሌ ላንድ ፕሬስ( Somali land press) በሰፊው  ዘገባ አቅርበውበታል።    በ15072016  አልጄዚራ   በእንግሊዘኛ የዜና ዳሰሳው  በትንሹ የ10 ሰዎች ህይወት በጎንደር በተቀሰቀሰው  ግጭት እንዳለፈ  ዘግቧል ።  የሟቾቹ  ቁጥር ወደ  20 እንደሚደርስ የሰብአዊ  መብት ተከራካሪዎች እየተናገሩ  መሆናቸውንም አልጄዚራ   በዜናው  አስፍሯል።   ይህ ሚዲያ የመንግስት ኮሚንኬሽን ሃላፊ የሆኑት አቶ ጌታቸው  ረዳ  ስለ ጎንደሩ  ግጭት የስጡትን መግለጫም አካትቷል፤   አቶ ጌታቸው  ረዳ በመግለጫው  የኤርተራ መንግስት በጎንደሩ  የህዝብ ዓመጽ  ጀርባ እንደሚገኝበት ገልጸዋል ።  ነገር ግን አልጄዚራ  ይሄንን  ክስ ለማረጋገጥ  እንዳልቻለ  ዘግቧል ።  ከጎንደሩ  ግጭት ተጨማሪም ከ300 በላይ ንጹሃን የኦሮሞ ተወላጆችም  በተመሳሳይ  ሁኔታ በመንግስት ታጣቂዎች  ህይወታቸው  እንዳለፈ  አልጄዚራ በዚሁ  የዜና ስርጭት አካቶ ዘግቧል።

 

 

የጀርመኑ ዶቼ ቬሌ (Deutsch Welle English)  በ15 07 2016 በእንግሊዘኛው  ዜናው  በተመሳሳይ መልኩ  በትንሹ  10 ሰዎች  በጎንደር  ከተማ  በተቀሰቀሰው  ግጭት  መሞታቸውን  ገልጿል ፤  መንግስትም ለዚህ የህዝብ  ዓመጽ በኤርትራ  ተቀማጭነት  አለው  ያለውን ተቃዋሚ  ደርጅትን እንደ  ከሰሰ  የጀርመኑ ዶቼ ቬሌ  በዜናው  ላይ አካቷል።   በተጨማሪም   ዶቼ ቬሌ ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ  የጎንደርን ነዋሪዎችንም  ስለ  ተቀሰቀሰው  ግጭት  ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል።   ይህ ሚዲያ አንድ  የጎንደር ነዋሪ  ስለ ሁኔታው  የሰጠውን አስተያየት እንደዚህ  አስፍሮታል “ማንኛውንም  ለነጻነት  የሚታገልን  ከኤርትራ ጋር እና ከሽብር ጋር ማገናኘት የረከሰ የፖለቲካ  ፕሮፓጋንዳ ነው” “ That is a very cheap political propaganda. Every freedom fighter is linked to Eritrea or terrorism.” ዶቺ ቬሌ በዚሁ  የእንግሊዘኛ ዜና ሽፋኑ  የአሜሪካ መንግስት ወደ ጎንደር ለሚጉዋዙ ዜጉዎቹዋ ከፍተኛ  ጥንቃቄ  እንዲያደርጉ  መግለጫ  መስጠትዋንም  ዘግቧል  ፍቃደኛ  የአይሁድ  ዘር ያለባቸውን ኢትዮጵያውያንንም  የእስራኤል  መንግስት ከጎንደር ከተማ በዚሁ  ግጭት ምክንያት ወደ እስራኤል መውሰዱንም በተጨማሪም ዶቼ ቬሌ  ዘግቧል።

 

ምንጭ :-

http://www.aljazeera.com/news/2016/07/10-killed-ethnic-protests-northern-ethiopia-160714193323905.html

 

http://www.dw.com/en/ethiopia-riots-in-gonder-claim-casualties/a-19403372

 

በዘርይሁን  ሹመቴ

ከ ጀርመን

 

↧
↧

  አለም አቀፍ የመገናኛ ሚዲያዎች የጎንደርን ግጭት በስፊው እየዘገቡ  ይገኛሉ –በዘርይሁን ሹመቴ

$
0
0

weበሰሜን ኢትዮጵያ ጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰቀሰውን  ግጭት የአለም አቀፍ የመገናኛ ሚዲያዎችን ቀልብ እየሳበ ይገኛል።   በተለያዩ  አቅጣጫዎች እየተስተዋለ የሚገኘውን  የህዝብና የመንግስት ግጭቶች እና መንግስት እየወሰደ  ያለውን  ጥቃት   የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ትኩረታቸውን  ወደ ምስራቅ አፍሪቃ እንዲያደርጉ እያስገደዳችው  ነው።

 

የጎንደርን የህዝብ አመጽና የመንግስትን እርምጃ በተመለከተ አልጄዚራ( Al Jazeera)  የጀርመኑ ዶቼ ቬሌ የእንግሊዘኛ ሚዲያ (Deutsche Welle English) እንዲሁም ሶማሌ ላንድ ፕሬስ( Somali land press) በሰፊው  ዘገባ አቅርበውበታል።    በ15072016  አልጄዚራ   በእንግሊዘኛ የዜና ዳሰሳው  በትንሹ የ10 ሰዎች ህይወት በጎንደር በተቀሰቀሰው  ግጭት እንዳለፈ  ዘግቧል ።  የሟቾቹ  ቁጥር ወደ  20 እንደሚደርስ የሰብአዊ  መብት ተከራካሪዎች እየተናገሩ  መሆናቸውንም አልጄዚራ   በዜናው  አስፍሯል።   ይህ ሚዲያ የመንግስት ኮሚንኬሽን ሃላፊ የሆኑት አቶ ጌታቸው  ረዳ  ስለ ጎንደሩ  ግጭት የስጡትን መግለጫም አካትቷል፤   አቶ ጌታቸው  ረዳ በመግለጫው  የኤርተራ መንግስት በጎንደሩ  የህዝብ ዓመጽ  ጀርባ እንደሚገኝበት ገልጸዋል ።  ነገር ግን አልጄዚራ  ይሄንን  ክስ ለማረጋገጥ  እንዳልቻለ  ዘግቧል ።  ከጎንደሩ  ግጭት ተጨማሪም ከ300 በላይ ንጹሃን የኦሮሞ ተወላጆችም  በተመሳሳይ  ሁኔታ በመንግስት ታጣቂዎች  ህይወታቸው  እንዳለፈ  አልጄዚራ በዚሁ  የዜና ስርጭት አካቶ ዘግቧል።

 

 

የጀርመኑ ዶቼ ቬሌ (Deutsch Welle English)  በ15 07 2016 በእንግሊዘኛው  ዜናው  በተመሳሳይ መልኩ  በትንሹ  10 ሰዎች  በጎንደር  ከተማ  በተቀሰቀሰው  ግጭት  መሞታቸውን  ገልጿል ፤  መንግስትም ለዚህ የህዝብ  ዓመጽ በኤርትራ  ተቀማጭነት  አለው  ያለውን ተቃዋሚ  ደርጅትን እንደ  ከሰሰ  የጀርመኑ ዶቼ ቬሌ  በዜናው  ላይ አካቷል።   በተጨማሪም   ዶቼ ቬሌ ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ  የጎንደርን ነዋሪዎችንም  ስለ  ተቀሰቀሰው  ግጭት  ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል።   ይህ ሚዲያ አንድ  የጎንደር ነዋሪ  ስለ ሁኔታው  የሰጠውን አስተያየት እንደዚህ  አስፍሮታል “ማንኛውንም  ለነጻነት  የሚታገልን  ከኤርትራ ጋር እና ከሽብር ጋር ማገናኘት የረከሰ የፖለቲካ  ፕሮፓጋንዳ ነው” “ That is a very cheap political propaganda. Every freedom fighter is linked to Eritrea or terrorism.” ዶቺ ቬሌ በዚሁ  የእንግሊዘኛ ዜና ሽፋኑ  የአሜሪካ መንግስት ወደ ጎንደር ለሚጉዋዙ ዜጉዎቹዋ ከፍተኛ  ጥንቃቄ  እንዲያደርጉ  መግለጫ  መስጠትዋንም  ዘግቧል  ፍቃደኛ  የአይሁድ  ዘር ያለባቸውን ኢትዮጵያውያንንም  የእስራኤል  መንግስት ከጎንደር ከተማ በዚሁ  ግጭት ምክንያት ወደ እስራኤል መውሰዱንም በተጨማሪም ዶቼ ቬሌ  ዘግቧል።

 

ምንጭ :-

http://www.aljazeera.com/news/2016/07/10-killed-ethnic-protests-northern-ethiopia-160714193323905.html

 

http://www.dw.com/en/ethiopia-riots-in-gonder-claim-casualties/a-19403372

 

በዘርይሁን  ሹመቴ

ከ ጀርመን

 

↧

አትሌት ጣዕሞ ሹምዬና ስንታየሁ መርጋ አበረታች እጽ መጠቀማቸው በምርመራ በመታወቁ የታገዱበት ደብዳቤ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ6 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ላይ አበረታች እጽ ተጠቅመው ሮጠዋል በሚል የጀመረው ምርመራ የመጨረሻ ውጤት ታውቋል:: በዚህም መሰረት 4ቱ አትሌቶች ነጻ ሲባሉ ሁለቱ አትሌቶች ማለትም አትሌት ጣዕሞ ሹምዬና ስንታየሁ መርጋ አበረታች እጽ መጠቀማቸው ተረጋግጧል:: በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የ እገዳ ደብዳቤ አስተላልፏል::
ደብዳቤው ዘ-ሐበሻ እጅ ደርሷል ይመልከቱት::

13734780_10208749728292601_1726520696_n

↧

በጎንደር ሕዝባዊ አመጽ ለመቀስቀሱ መሠረታዊው ምክንያት ወያኔ በሕዝቡ ላይ ለ25 ዓመታት የፈጸመው ግፍ ነው!

$
0
0

Moresh-901.jpgከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ የትግሬ ወያኔ በጎንደር ዐማራ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው በዘር ላይ ያነጣጠረ ጭፍጨፋ፣ ከባለፉት 40 ዓመታት ጀምሮ ሲያደርገው የነበረው ጭፍጨፋና ዐማራን ከምድረገጽ የማጥፋት ዓላማው ተከታይ እንደሆነ ወያኔ የተጓዘበት ጉዞና የቆመለት ዓላማ በግልጽ ያሳያል። የጭፍጨፋው አጀማመርና ሂደት እንዲህ ነው፥ ከሃያ የሚበልጡ የወያኔ ልዩ ኃይል ፖሊሶች፣ ሐምሌ መጀመሪያ 2008 ዓም ላይ የትግሬው ገዥና የወያኔ ሊቀመንበር በሆነው ዐባይ ወልዱ ልዩ ትዕዛዝ ጎንደር ከተማ ገብተው የተለያዩ የስለላ ሥራዎችን ሢሠሩ እንዲቆዩ ተደረገ። የአፋኝ ቡድኑ አባሎች ወደ ጎንደር ከተማ እንዲገቡ የተደገበት ስበብ፣ የዐሥራ ሁለተኛ ክፍል የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን ለመቆጣጠር በሚል ምክንያት እንደሆነና እነርሱም ከሕዝቡ ጋር ባደሩት ግንኙነት ይኸንኑ የ«በሬ ወለደ» ወሬ ሲያዛምቱ እንደነበር ታውቋል።

ሆኖም፣ ዋና ተልዕኮአቸው የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ሕገመንግሥታዊ በሆነ አግባብ መልስ እንዲያገኝ በሕዝቡ የተመረጡትን የኮሚቴ አባላት መኖሪያ ቤቶች፣ መውጫና መግቢያ ሰዓት፣ እንዲሁም የሰዎቹን ማንነት ለይቶ በማወቅ እነርሱን ሕዝብ ሳያውቅና ሳይሰማ አፍኖ ለመውሰድ የሚችሉበትን መንገድ ማጥናት ነበር። በእነርሱ እሳቤ የፈለጉትን የአፈና ሥራ ጥናት አጠናቀው፣ የሕዝቡን ተወካዮች ሕዝቡ ሳያውቅ በሌሊት አፍኖ ለመውሰድ አመች ቀን ሆኖ የመረጡት ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ከእኩለ ሌሊት ላይ እንዲሆን ወሰኑ። በውሣኔአቸው መሠረት እኩለ ሌሊት ላይ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎችን በየቤታቸው በጥንቃቄ እየዞሩ ማፈን ጀመሩ። በዚህ አፈና አንደኛ፥ አቶ አታላይ ዛፌ፣ ሁለተኛ፥ አቶ ጌታቸው አደመ፣ ሦስተኛ፥ አቶ መብራቱ ጌታሁን፣ አራተኛ፥ አቶ አለነ ሻማ የተባሉትን የኮሚቴ አባላት አፍነው ያዙ። እነዚህን አራት «የወልቃይት የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ» አባላት አፍነው ከያዙ በኋላ፣ ለታፋኞቹ የሰጡዋቸው ምክንያት የፌደራል የመንግሥቱ የደኅንነት አባሎች መሆናቸውን ነው። አራቱን ጠንካራ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባሎች ካፈኑ በኋላ ጉዞአቸውን ያደረጉት ሌሊት 10 ሰዓት ላይ የኮሚቴው ሰብሳቢ ወደሆነው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ቤት ነው። ኮሎኔል ደመቀ ወታደር ከመሆኑም በላይ ለበርካታ ዓመታት ከወያኔ ጋር የቆየ በመሆኑ የወያኔን ባሕሪ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ፣ በደረቁ ሌሊት እንደሌባ «ቤትህን ከፍተህ እጅህን ስጥ» ለሚለው ጥያቄ የሰጣቸው መልስ፣ ‹‹ሕጋዊ ሰዎች ከሆናችሁ፣ ጠዋት ሲነጋ በብርሃን እንነጋገር›› የሚል ነበር። አፋኝ ቡድኑ ግን ሕጋዊም ሆነ የፌደራሉ ደሕንነት አባሎችም ባለመሆናቸው፣ ኮሎኑል ደመቀ ለሰጣቸው ትክክለኛና ተገቢ ጥያቄ ተገዥ አልሆኑም። አስገድደው ለመውሰድ በቤተሰቡ ላይ የጥይት ናዳ አወረዱበት። ኮሎኔል ደመቀም ራሱንና ቤተሰቡን ባለው የመከላከል ተፈጥሮአዊና ሕጋዊ መንገድ በመጠቀም በከፈተው የአጸፋ ተኩስ፣ መላው የጎንደር ከተማ ሕዝብ ሁኔታውን እንዲያውቅ የግንኙነት መስመር ከፈተ። የትግሬ ወንበዴዎች ከጎንደር ሕዝብ መሐል ጥያቄ ከማቅረብ ውጭ ምንም ዓይነት ወንጀል የሌለባቸውን ልጆቹን በሌሊት አፍኖ ለመውሰድ የተደረገው ጥረት እጅግ በማስቆጣቱ ሕዝቡ ቀፎው እንደተነካበት ንብ በመትመም በአፋኝ ቡድኑ አባላትና በወያኔ ተባባሪዎች ላይ የቁጣ መግለጫ የሆነ ርምጃ ወሰደ። የከተማዋን እምብርት የንግድ ቦታዎች ዐማራዎችን አፈናቅለው ተቆጣጥረው የነበሩትን የትግሬ ንግድ ቤቶች፣ ሱቆች፣ አውቶቡሶች፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ባንኮችና ወርቅ ቤቶች አጋዩ። «ምንጊዜም በመስተዋት ቤት የሚኖር ሰው ቀድሞ ደንጋይ አይወረውርም» የሚባለውን ዘመን የማይሽረው ወርቃማ አባባል ከምንም ያልቆጠሩት የወያኔ ጀሌዎች፣ በተናጠል ጎንደሬውን፣ በጥቅል ዐማራውን ከመናቅና ከማዋረድ ዘለው፣ አንጡራ ሀብቱን ዘርፈውና ቀምተው፣ ካለርሱነቱ በቀር «ይህ ሀብት አለኝ» የሚለው የሌለው ሕዝብ መሀል፣ ልጆቹን በሌሊት ሰርቀው ለመውሰድ ባደረጉት ሙከራ፣ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት የተወረወሩ ደንጋዮች የመስታውቱን ቤቶች አውድመዋል። የጎንደር ሕዝብ በአመጹ የሚያጣው ምንም ነገር ካለመኖሩም በላይ፣ በአመጹ አትራፊ ይሆናል። የታሠረበትን ሰንሰለት ያወልቃል። ነፃነቱን መልሶ ይላበሳል። ያም ሆኖ፣ የኮሎኔል ደመቀ ቤተ በከባድ መሣሪያ እንዲፈራርስ መደረጉ ታውቋል፡፡

ዐማራውን መጨፍጨፍ የለመደው የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ ሥርዓት፣ በንጹሐኑ የጎንደር ሕዝብ ላይ በከፈተው ተኩስ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀኖች በትግሬ አፋኝ ቡድኖችና በጎንደር ከተማ ሕዝብ መካከል በተደረገው የማጥቃትና የመከላከል ሕጋዊና ሰብአዊ ግብግብ ላለቁት የዐማራ ልጆች፣ ከሁሉም በላይ ለሕዝቡ ነፃነትና መብት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጩሁ የነበሩት እንደ አቶ ሲሣይ ታከለ የመሳሰሉት ጀግኖችን ማጣት፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተሰማው ሐዘን መሪርና ጥልቅ ነው። ይሁን እንጂ፣ ድል ካለመስዋዕትነት የሚታሰብ ባለመሆኑ፣ መስዋዕትነቱ የነፃነታችን ተገቢ ዋጋ እንዲሆን፣ የእነርሱን ፈለግ በመከተል ትግሉን ከዳር ለማድረስ ቃል እንገባለን። መስዋዕትነት፣ የጥቂቶች፣ ድል ደግሞ የብዙኃኑ ነውና፣ የድሉ ተጠቃሚ የሚሆነው ሠፊው የዐማራ ነገድ የጀግኖቻችን አርኣያነት በመከተል፣ ዘረኛው ወያኔን ከሕዝቡ አናት ላይ አምዘግዝገን ለመጠል በጎንደር ሕዝብ፣ ከሁሉም በልይ በወልቃይት ጠገዴ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ሕዝብ የተቀጣጠለውን የለውጥ እሳት ግለቱ እንዳይበርድ፣ ስሜቱ እንዳይቀዘቅዝ፣ የድሉ ጊዜ እንዳይራዘም በያለንበት የጎበዝ አለቃችን በመምረጥ የወያኔን ጉርንቦ አንቆ ለመፈጥረቅ ክንዳችን ልናነሳ ግድ ይለናል።

ይህም በመሆኑ፣ በሰሜን ጎንደር ባሉ የአውራጃና የወረዳ ከተሞች የሕዝባዊ አመፁ በመቀጣጠል ላይ ነው። በዚህም መሠረት፣ ሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓም ከጎንደር ከተማ 100 ኪሎሜትር ላይ የምተገኘው የሰሜን አውራጃ ዋና ከተማ በሆነችው በደባርቅ ከተማ የወያኔ ሰላዮችና አሽቃባጮች በሆኑ ግለሰቦች ንብረት ላይ ሕዝቡ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል። የዐማራው ሕዝብ መብቱንና ማንነቱን ለማስከበር ባደረገው ትግል ወያኔና ወያኔን በሚደግፉ ግለሰቦች ንብረት ላይ ያነጣጠረ ርምጃ መውሰዱ የሚያሳየው ዕውነታ፣ እነዚህ ሰዎች ባልደከሙበት፣ በዘረፉት የሕዝብና የመንግስት ሀብት የናጠጡ መሆናቸው ነው። እርሱ ቁንጣን ሲያስቸግራቸው ሠፊው የዐማራው ሕዝብ በገዛ አጽመ-ርስቱ የበይ ተመልካች ከመሆን አልፎ ማንነቱን በመገፈፉ ነው። ይህ ዓይነቱ ድርጊት እንዳይደገም ከፈለጉ መፍትሔው አንድ ብቻ ነው። ወያኔን እያጋለጡ ከሕዝቡ ጎን መቆም። ይህን በማያደርጉት ላይ ግን ሕዝባዊ አመፁ በስፋት መቀጠሉ አይቀሬ ነው። ንብረቱ ከርሱ ተወስዶ ለሌሎች የተሰጠ ነውና መብቱን በትግሉ ማስከበሩ የታሪክ ሐቅ ነውና ይቀጥላል። በዚህ ረገድ የጋይንት፣ የደብረታቦር፣ የሊቦ፣ የጭልጋ አውራጃ ሕዝብ የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ ትግል ሳይውል ሳያድር ሊቀላቀል ይገባል። በዚያው አንፃር የጎጃም፣ የሸዋ፣ የወሎና የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን ከፋፋይና አጥፊ ቡድን ለማስወገድ የጎንደርን ሕዝብ የእንቢተኝነት ትግል አካል እንዲሆን ጥሪያችን እናቀርባለን።

በወያኔ የሚመራው የፌደራል መንግሥት የወልቃይት ዐማራ ማንነት አስተባባሪ ኮሚቴዎችንና መላውን የዐማራ ሕዝብ ራሱ በተቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን «አሸባሪዎች ናቸው» ብሎ የመፈረጁ ግብ ሕዝቡን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን አመልካች ነው። «ከፌዴራል የጸረ-ሽብር ግብረ ኃይል ተላለፈ» ተብሎ በተነበበው መግለጫ፣ የኮሚቴ አባላቱን «ከኤርትራ ትእዛዝ በመቀበል ሽብር ሊያደርሱ ሲሉ እርምጃ ተወስዷል» ያለ ሲሆን፣ ለተቃውሞ የወጣውን ሕዝብ ደግሞ «የሽብርተኞች ተባባሪዎች» በማለት በግልጽ አገዛዙ በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙሃን አሳውቋል። ይህ በማጭበርበር፣ በክህደትና በውሸት ተወልዶ በውሸት የሚኖርን ዘረኛ የሞሶሎኒ ደቀመዝሙር ቡድን አጥፍቶን ሳይጠፋ፣ ፋታ ሳንሰጥ ሳያጠፋን ቀድመን ለማጥፋት የተባበረ ክንዳችን ልናነሳበት ይገባል። ይህ ዕድል እንዳለፉት ሁሉ እንዳያመልጠን በአግባቡ ልንጠቀምበት እንደሚገባ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያሳስባል።

በጎንደር ከተማ በተካሔደው የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ሕዝብ ሥርዓቱን ተቃውሞ የወጣ መሆኑ ታውቋል። ይኸን ሕዝብ አሸባሪ ብሎ ወያኔ የመፈረጁ ሚስጢር፣ የዐማራውን ሕዝብ በጅምላ ለመጨረስ፣ ብሎም የወልቃይት ጠገዴን የዐማራ ማንነት ጥያቄ ለማዳፈን ካላው ጽኑ ፍላጎት የመነጨ መሆኑን ላፍታ ልንጠራጠር አይገባም። አገዛዙ በዚሁ በ2008 ዓ.ም. በኢትዮ-ሱዳን ድንበር በቋራና መተማ አካባቢ የአገራቸውን ድንበር የሚያስጠብቁ ዐማሮችን በፓርላማ (ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት) ‹‹ሽፍቶች ናቸው›› ማለቱ የታወቀ ነገር ነው። ቀደም ባሉት ዘመናትም ቢሆን በ1985/86 ዓ.ም. የዘመን መለወጫ ዋዜማ በጎንደር በአደባባይ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችን ሲገድል እና ሲያቆስል በተመሳሳይ መልኩ ‹‹ሽፍቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ›› ብሎ እንደነበር የምናስታውሰው በቁጭት ነው።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በተደጋጋሚ ይፋ እንዳደረገው፣ የትግሬ-ወያኔ ሥርዓት የዐማራውን ሕዝብ በተለያየ መልኩ ለመጨረስ የተለያዩ የጅምላ ወንጀሎችን እየለጠፈ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን መግደሉን፤ ማፈናቀሉን፣ ማሰደዱንና ማሰሩን እናውቃለን። ዛሬም በጎንደር ዐማሮች ላይ እየወሰደ ላየው የጥፋት እርምጃ የዚሁ ተከታይ መሆኑን ላፍታ ሳንጠራጠር፣ የአጥፊውን አካል የስለላ፣ የመገናኛ፣ የኢኮኖሚ፣ የኃይል ማመንጫ፣ የወታደራዊና መሰል ተቋሞች ላይ የማያዳግም ርምጃ መወሰድ አለበት። «ጅብ ከሚበላን፣ ጅብ በልቶ መቀደስ» የሚለው የአባቶቻችን አባባል ትክክለኛ ቦታው ይህ ነው እንላለን!

የጎንደር ዐማሮች ከአገዛዙ ጋር የሚያደርጉት ተጋድሎ፣ በየትኛውም መልኩ ከውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነትም ሆነ ንኪኪ የለውም። ሻዕቢያ ከዐማራው ይልቅ ለወያኔ አሳዳጊ አባቱ ከመሆን አልፎ፣ መሪዎቻቸው በሥጋ ልደት የተቆራኙ መሆናቸው ይታወቃል። በዚህም ምክንያት የዐማራ ሕዝብ ንቅናቄ በራሱ ልጆች፣ ወያኔ በፈጠረው ብሶት የተቀጣጠለ እንጂ፣ እንደወያኔ በውጭ ውሻል የሚዘወር አለመሆኑ ወዳጅም ጠላትም እንዲያውቀው እንሻለን።

ከመላው የዐማራ ሕዝብ ጠንካራ ተቃውሞ የደረሰበት ወያኔ፣ አሁን «ነገሮችን በሽምግልና ለመፍታት» በሚል ማኅበረሰቡን ለማዘናጋት እየሞከረ እንዳለ እየተሰማ ነው። የሥርዓቱ አገልጋይ በሆኑ የሃይማኖት አባቶችና በብአዴን ካድሬዎች የሚደረገው ውይይትና ሽምግልና ፍጹም ተቀባይነት የሌለውና የወልቃይት ጠገዴን የዐማራ ማንነት ጥያቄ አዳፍኖ የሚያስቀር፣ ብሎም የታሠሩ ወገኖቻችንም ሕይዎት አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ መላው የዐማራ ሕዝብ ድርጊቱን በጽኑ በመቃወም፣ በተጀመረው ሕዝባዊ አመጽ ሙሉ መብትና ነፃነቱን እንዲያረጋግጥ ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና የመገናኛ ብዙኃን ለእንቅስቃሴው አስፈላጊውን ትኩረትና በመስጠት ወያኔ በዐማራው ነገድ ላይ የሚያደርሰውን የዘር ጥፋት እንዲያወግዙና ከተጠቂው ወገን እንዲቆሙ ጥሪአችን እናቀርባለን። ለዚህ ዕውነተኛ ጥያቄ ተገቢ መልሱን እንዲያገኝ፣ ከጎኑ አለመቆም ፈጠነም ዘገየም የታሪክ ተወቃሽ ሊያደርግ እንደሚችል መናገር ነቢይ መሆንን አይጠይቅም።

በመጨረሻም በወያኔ ፖሊሶችና ደኅንነቶች በተሰው የዐማራ ታጋዮች ሞረሽ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለዘመዶቻቸው መጽናናትን በመመኘት፣ «ይዋል ይደር እንጂ፣ አህያ የጅብ ናት» እንደሚባለው፣ የወንድሞቻችን ደም ደመ-ከልብ ሆኖ የማይቀር መሆኑን ሞረሽ ወገኔ ያምናል።

 

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ሞት ለወያኔና ለአጫፋሪዎቹ!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

↧

የወልቃይት ተወላጆች ከአዲስ አበባና ካርቱም እየታፈሱ ነው

$
0
0

የወልቃይት ተወላጆች ከአዲስ አበባና ካርቱም እየታፈሱ ነው::

welkaytየጎንደሩ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ የተደናበረው የወያነ አገዛዝ የወልቃይት ተወላጆችን ከአዲስ አበባ እና ካርቱን እያፈሰ በማሰር ላይ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል::ጎንደር ከተማና በአጠቃላይ በአማራ ክልል ሕዝባዊውን አመጽ ተከትሎ በአደባባይ ሰዎች በብዛት ባይታዩም ውስጥ ውስጡን ግን ሰዎች መንቀሳቀስ እንዳቃታቸውና እየታሠሩ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ::

በተለያዩ ሰበቦች የአማራውን ሕዝብ ለማጥቃት ዝግጅት እያደረገ ያለው የወያነእ አገዛዝ በጎንደር የወልቃይት ማነት ጉዳይን የሚመሩ ግለሰቦችን ለመያዝ ሃይል የተቀላቀለበት እርምጃ ለመውሰድ ሲገሰግስ በሕዝብ ሃይል አደጋ ተጥሎበት ከጥቅም ውጪ መሆኑን በዚህ ሰውን የሚወጡ ዘገባዎች መስክረዋል::በዚህ ከፍተኛ እፍረት እና ድንጋጤ የገባው የወያኔው አገዛዝ በሌሎች ክልሎች በሚኖሩ አማሮች ላይ በተለይ የወልቃይት ተወላጆች ላይ የበቀል ዱላውን ለማሳረፍ በአዲስ አበባና በሱዳን ወና ከተማ ካርቱም አፈሳውን ተያይዞታል::በተለይ የወልቃይት ተወላጆች ይበዙበታል በሚባለው ገዳሪፍ እና ካርቱም ውስጥ የፈሰሱት የወያነ የደህንነት አባላት አፈናው አጠናክረው በመቀጠል ላይ ሲሆን የተለያዩ መሳሪያዎች እና ጥይቶችን በመግዛት ወደ ጎንደር ያስገባሉ የተባሉ የወልቃይት ተወላጆች መያዛቸውን ምንጮች ጠቁመዋል::

↧
↧

ለኢህአዴግ የመጨረጫው መጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከወደ ጎንደር ተሰማ –ከተማ  ዋቅጅራ

$
0
0

《ሕዝቤን ልቀቅ ይላል እግዚአብሔር》የሙሴ ማስጠንቀቂያ

《ሕዝብህንም አለቅም እግዚአብሔርንም አላውቅም》የፈርዖን መልስ

ልቦናው የከፋ የፈርዖን ተስፋ

debark carእንደዚህ አይነት እብሪት የሚመጣው ስልጣን የዘላለም የሚመስላቸው እና በመሳሪያቸው ብዛት ተመክተው ሁሌም እራሳቸውን እንደአሸናፊ አድርገው ከሚያስቡ ደካማ እና ስህተታቸውን ከማይቀበሉ ሰዎች ዘንድ ነው። እንደነዚ አይነቶቹ ሰዎች ምንም ልቦናቸው በክፋት እና በትእቢት የተወጠረ  ቢሆንም ቅሉ ቀድሞ ከስህተታቸው እንዲመለሱ እና ሊቀበሩበት የሚችለውን ጉድጓድ መቆፈራቸውን እንዲያቆሙ ቀድሞ በተለያየ መንገድ እና በተለያዩ  አመልካች ሰዎች የማስጠንቀቂያ መልዕክት ይነገራቸዋል።

ሕዝቤን ልቀቅ የሚለው ቃል ለፈርኦን ሲነገረው የልመና ቃል ሳይሆን የማስጠንቀቂያ ቃል ነበረ። የፍራቻ ሳይሆን የትእዛዝ ነበረ። የፈርኦን መልስ ግን ሕዝብህን አለቅም እግዚአብሔርንም አላውቅም የሚል የእብሪት ቃል ነበረ ምላሹ። ይሄንን ቃል ላስተዋለው በሙሴ  እና በፈርዖን መካከል የተደረገውን ሁለት ጎራ እንደሚፈጥር የታወቀ  ነው። በሙሴ ወገን የነበሩት ፈርዖን ፈጽሞ  እንደሚጠፋ ስሙም ታሪክ ብቻ ሆኖ  እንደሚቀር ሲያውቁ….. በፈርዖን ወገን የነበሩ ደግሞ የጀግንነት የአሸናፊነት ያልበገርነት መስሏቸው ፈርዖን ጀግና ነው የጀግና ዘር ብለው ማስጠንቀቂያውን ከመስማት ይልቅ ፈርዖንና ተከታዮቹ  ልቦናቸውን በማደንደን የበለጠ በትእቢት እንዲወጠር አደረጋቸው። ወይ አስተዋይ መሪ አልያም አስተዋይ ህዝብ ከሌለ የጥፋት ማእበሉ በራፋቸው ደርሶ  እብሪነታቸውን አይተውም።

ሙሴም እግዚአብሔር እንደሚያዘው ማድረግ ጀመረ… የመጀመሪያው መቅሰፍት ወደፈርዖንና ወደ ህዝቡ መጣ የዚህን ግዜ ፈርዖን እና ሕዝቡ ተጨነቁ ፈርኦንም ሙሴን አለው…. ሙሴ ይሄ መቅሰፍት ከአገሬ እንዲጠፋ አድርግልኝ እንጂ ህዝብህን እለቃለው አለው። ሙሴም  እንዳለው አደረገለት የመጣው መቅሰፍት እንዲጠፋ  አደረገ። መቅሰፍቱ ከራቀ በኋላ ተመልሶ ሕዝብህን አለቅም በማለት የጭቆና ቀንበሩን መልሶ  ይጭንባቸውዋል። እንዲ እንዲ እያለ ዘጠኝ  የማስጠንቀቂያ መቅሰፍቶች በፈርዖን  እና በሕዝቡ ላይ ይወርድ ጀመረ መቅሰፍቱ ሲመጣ እለቃለው ብሎ ተማጽኖ  ያቀርባል መቅሰፍቱ ሲርቅለት ተመልሶ ጭቆናውን ይቀጥላል አስረኛው መቅሰፍ እና የመጨረሻው መጨረሻ ማስጠንቀቂያ በፈርዖን እና  በሕዝቡ መጣ። በፈርኦን ግዛት ውስጥ የሚኖሩት የበኩር ልጆቻቸውን  የሚገድል መቅሰፍት ተላከባቸው የበኩር ልጆቻቸው በሙሉ በሞት ተመቱ የዚህን ግዜ ፈርዖንና  ህዝቡ ደንግጠው ሙሴን እንዲ አለው ህዝብህን ለቅቄአለው ብሎ ተናገረው ይዘህ ወደ አገርህ ግባ አለው። ሙሴም ህዝቡን ይዞ  ከፈርኦን ግዛት መውጣት ጀመረ። ሙሴም ባህረ  ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ህዝቡን በደረቅ መሬት በመሃሉ መሻገር ሲጀምሩ ፈርዖን ልቡ አንዴ  ደንድኗልና ከለቀቃቸውም በኋላ በመቆጨቱ መልሼ በግዞት መያዝ አለብኝ ብሎ ሰራዊቱን በሙሉ በማዝመት ሙሴን እና እዝቡ ወደግዞቱ ሊመልስ ወደ ኤርትራ  ባህር ደረሰ ሙሴም ባህሩን እንደ ግንብ አቁሞ ህዝቡን እያሻገረ እያለ ሙሴ በከፈለው ባህር ውስጥ ፈርዖንና ሰራዊቱ ገቡ ሙሴም ህዝቡን አሻግሮ  ከጨረሰ  በኋላ ባህሩን ከደነው የፈርዖን ሰራዊት ከነሙሉ ሰራዊቱ ሰጥመው ላይመለሱ ፍጻሜአቸው ሆኗል።

 

 

በፈርዖን ግዛት ውስጥ ወንድ የወለዱ እስራኤላውያን በሙሉ ይገደልባቸው ነበረ ያላለቀሰች እናት ያላዘነ አባት የለም ነበረ። ግፍ ሲበዛ ግፍ አድራጊው መጥፊያውን ያቀርባል ይባላል።

ዛሬም እንደ ፈርዖን ልቦናቸውን ያደነደኑ ሲነገራቸው የማይሰሙ ትዕግስት እንደ ፍራቻ የህዝብም ድምጽ በንቀት የሚመለከቱ በስልጣናቸው እና  በመሳሪያቸው ተመክተው የማስጠንቀቂያ ደውሎችን ረግጠው እና ጨፍልቀው የሚያልፉ የመስጠሚያችሁ ባህር ከፊታቹ እንዳለ ላሳውቃችሁ እወዳለው።

selam bus gonderለኢህአዴግ ብዙ ምልክቶች ተነግረውታል ብዙ ማስጠንቀቂያዎችም ደርሰውታል በማን አለብኝነት እና በመሳሪያ ኃይል አፈንኩኝ ብሎ ያስባል እንጂ…  ከአዲስ አበባ ጀምሮ  የተነሱ የህዝብ የማስጠንቀቂያ ማዕበል መልስ ሳይሰጣቸው ተዳፍነው እንዲቀሩ ተደርጓል። ልብ በሉ ተዳፍኗል እንጂ አልጠፋም። በኦሮሚያም የተነሳው የህዝብ ማእበል አሁንም መልስ ሳይሰጥበት በመሳሪያ  ኃይል እንዲዳፈን ተደርጓል። በጋንቤላም የተነሳው እንዲሁ እንዲዳፈን ተደርጓል። ይሄን ሁሉ ሲያደርግ ግን ኢህአዴግ ፍጹም የበላይ ነኝ ብሎ  ነበረ። የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ እንሻለን …100% ተሸንፈህ 100% አሸነፍኩኝ አትበል… ውሸት ሰለቸን… ነጻነት እንሻለን… አደባባይ የወጣውን ህዝብ የኔ በሚላቸው ታጣቂዎች ህዝቡን በመፍጀት የተነሳውን የህዝብ ማእበል ትክክለኛውን መልስ ሳይሰጥ በኃይል እንዲዳፈን ተደርጓል።

የአዲስ አበባው፣ የሰንዳፋው፣ የጋንቤላው፣ የአንቦው፣ የወለጋው፣ የባህር ዳሩ፣ የወሎው፣ የአሪሲው፣ የሃረሩ፣ የባሌው፣ የሻሸሜኔው እያልን ስንቀጥል ለኢህአዴግ ፈጽሞ ከመጥፋታቸው በፊት የተነገራቸው የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ቢሆኑም ቅሉ ሊጠቀሙበት አልቻሉም። ጭራሽ 5 ሚሊዮን ሆነን 90 ሚሊዮንን አንቀጥቅጠን የምንገዛ ጀግና የጀግና ዘር ነን ገና ቂጥ ቂጣችሁን እያልን 100 አመት እንገዛችኋለን በማለት በህዝባችን ላይ ይዘባበታሉ። ልብ በሉ እሳቱ በሁሉም ኢትዮጵያ  ውስጥ ተዳፍኖ  ነው ያለው።

ለኢህአዴግ የመጨረጫው መጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከወደ ጎንደር ታይቷል።

bus eየመጨረሻ መጨረሻ ማስጠንቀቂያ በጎንደር ህዝብ ተነግሮታል። ይሄ ማስጠንቀቂያ ለኢህአዴግ የመጨረሻ መጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው።ከዚህ ቀደሙ በኢትዮጵያ  ህዝብ ላይ ድምጻቸውን ለማሰማት ወደ አደባባይ የወጡትን በጥይት እየቆሉ የተቀረውን ደግሞ  ቤት ለቤት እየገቡ ያለበደሉ ለእስር እየዳረጉ አሰቃቂ ግፍና በደል በማብዛት ለአመታት አሰቃይተዋል። ማንም እኔን አይነቀንቀኝም ሲልና ሲፎክር የነበረ  ኢህአዴግ የጎንደር ህዝብ በሁለት ቀን   የመጨረሻ መጨረሻቸውን ማስጠንቀቂያ አሳይቷቸዋል። እንደለመዱት ገድዬ  እና አፍኜ እወስዳለው በማለት የመጣውን ጎንደሬዎቹ ገድለውና ማርከው የመጨረሻው መጨረሻህ ደርሷል ሞት ደጃፋችሁ እንደደረሰ ነጻነት ለህዝቡ እንደመጣ እወቁ ብሎ ነግሯቸዋል። ካሁን በኋላ ገላችሁ እና  ማርካችሁ መሄድ ሳይሆን ተገላችሁም ተማርካችሁም የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነትን የሚያውጅበት ቀን ቅርብ ነው ሲሉ የጎንደር ህዝብ አሳይቷቸዋል።

የጎንደሩ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለኢህአዴግ የመጨረሻ መጨረሻ ማስጠንቀቂያ  ደውል ነው። ከዚህ በኋላ  እንደድሮው አፍኜ እቀጥላለው ማለት ወደማይቀረው እና ኢህአዴግ ላይመለስ ወደሚሰጥምበት ባህር ውስጥ መግቧቷ ነው። ካሁን በኋላ ምንም አያመጡም ጀግና የጀግና ዘር እኛ  ነን የምትለዋ ተረት ግዜዋ ያለፈችበት ቀልድ እንደሆነች ተረዱ። በኢትዮጵያ ዙሪያ የተዳፈነው እሳት አመዱን ገለጥ አድርጎ  ይነሳል ያም እሳት የህዝብ ባህር ይባላል የመጨረሻውን የኢህአዴግ የመጨረሻዋ ሞትን የሚያበስራት ኃይን ነው። ይህንን ስል እያስፈራራው አይደለም ወይንም ያለምክንያት አይደለም የሚታይ እና ሊመጣ የተቃረበ እውነት  እንጂ።

ማሳሰቢያ 1:- ከተለያዩ ኢትዮጵያ ምድር  በአማራነቱ ሲፈናቀል ሲገደል ዝም ያለ ሁላ… ከተለያዩ ከኢትዮጵያ ምድር የኦሮሞ ገበሬ መሬቱ ተነጥቆ ሲባረር እና  ሲገደል ዝም ያሉ ሁላ ባእድ እንኳን ሳይቀሩ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ጋንቤላ  ገብተው ህዝባችንን ጨፍጭፈውና  ማርከው ሲወስዱ ዝም ያሉ ሁላ ሌላም ሌላም ግፎች በአገሪቷ ሲፈጸም  ያልተነፈሰ ሰላም ባስ ተቃጠለ ሆቴል ፈረሰ ንግድ ቤት ተቃጠለ እያሉ የሚሊዮኖች የሰው ነፍስ ሲጠፋ እና  የሚሊዮኖች መብት ሲረገጥ ሳይጨንቃቸው ለቁስ የሚያለቃቅሱትን መልስ አትስጧቸው። በተለይ በተለይ ትላልቅ ሚዲያዎች የሚዲያ  አካሎች መስራት ያለባችሁን ትክክለኛውን ስራ  ብቻ  ስሩ። ማልቀስ ካለባቸው ያልቅሱ.. መጮህ ካለባቸው ይጩሁ… መመለስ ካለባቸውም ይመለሱ… ስለነሱ በደልና ችግር መናገር ካለባቸው እራሳቸው መሆን አለባቸው እንጂ እነሱ እንዲ ናቸው እንዲ አያደርጉም ብሎ  ያልሰሩትን እና  ያላሰቡትን መናገር የበለጠ እንዲኮፈሱ ሲለሚያደርጋቸው ቢታሰብበት ጥሩ ነው።

ማሳሰቢያ 2:- ምርጫውን 100% በኦሮሚያ  አሸነፍን ባሉበት ማግስት 100% በአማራ አሸንፍን ባሉበት ማግስት 100% በአዲስ አበባ አሸንፍ ባሉበት ማግስት 100% ከሁሉም አቅጣጫ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። በከፍተኛ የመንግስ የስልጣን ቦታውን የያዛችሁ ኢትዮጵያዊያኖች በእድሜ የሸመገላችሁም አላችሁ ልጅ እና  የልጅ ልጅም ያያችሁ አላችሁ ሌላው ቢቀር ለልጃችሁ እና ለልጅ ልጆቻችሁ ስትሉ ለዚህች አገር ሰላም በእውነት መስራት አይገባችሁምን? እስከ መቼ ሕሊና ተሸጦ ጥቅም ብቻ በመፈለግ ስልጣንን በኃይል ለማቆየት የሚፈጸመውን ግፍ ትክክል ነው ትላላችሁ? አገር ስትጠፋስ እንዴትስ ቆማችሁ ትመለከታላችሁ? ልጆቼ ብላችሁ ለምትጠሯቸው ለአብራካችሁ ክፋይ ጨለማን ለማውረስ ስቃይን ለማስረከብ ስለምን ልቦናችሁ አሰበ? የሰው ክብሩ እውነተኛነቱ እና  አገሩ ነው። እውነትን እና  በነጻነት የሚኖሩባትን አገር ለማውረስ ስለምን መልካም መስራት ተሳናችሁ? ግዜው እየረፈደ ነውና ነጻነት ከሚፈልገው ህዝብ ጋርና ከእውነት ጋር የምትቆሙበት ሰዓት አሁን ነው። ይህንን ሳታደርጉ ብትቀሩ ግን ለሚመጣው ነገር ጥርስ ሟፏጨት ብቻ  ይሆናልና ይታሰብበት።

ማሳሰቢያ 3:- ለአርቲስቶች…  ገጣሚ በግጥሙ ጸሃፊም በጽሁፉ ዘፋኙም  በዘፈኑ ስለ አገር ፍቅር፣ አንድነት፣ ህዝባችን ለይ ስለሚደርሰው ግፍ፣ ወደፊት ስለሚመጣው አደጋ፣ ባጠቃላይ የኢትዮጵያን ህዝብ ስሜት እና በደል  ያለፍራቻ እውነትን በመናገር ህዝባችንን ታስተሳስሩት ዘንድ ትልቅ አቅም አላችሁ። ይሄንን አቅማችሁን ተጠቅማችሁ ከህዝብ ጎን የምትቆሙበት ሰአቱ አሁን ነውና ስለምትወዱት እና  ስለሚወዳችሁ ህዝብ ብላችሁ ስለምትወዷት ኢትዮጵያ  አገራችሁ ብላችሁ ብዕራችሁን አንሱ እና በተሰጣችሁ  ጸጋ በድምጻችሁ ለህዝብ ያላችሁን ፍቅርና ለአገራችሁ ያላችሁን ስሜት አሰሙ። ነገሮች የከፋ ደረጃ ላይ ደርሶ  እንዲ ብልና ባደርግ ተብሎ የሚቆጭበት ግዜ  ሳይመጣ አሁኑኑ ሁሉም  አርቲስት ለአገሩ እና ለህዝቡ ቅድሚያ  ይስጥ። የህዝብ ወዳጅ ማን እንደሆነ የሚለይበት ግዜ ተቃርቧልና ይታሰብበት። ፈሪ አይጸድቅም… ገለባም አይበቅልም… ይባል የለ።

ሳጠቃልለው :- ኢህአዴግ ሆይ የተናገሩትን እያነቁ ማሰር እና መግደል ጋዜጠኞንን እና ጸሃፊዎችን  እያነቁ ማሰርና መግደል አቁሙና የመጨረሻ መጨረሻ የማስጠንቀቂያ ደውሉ በጎንደር ህዝብ ስለተነገራችሁ ቆም ተብሎ ይታሰብ።ይሄ ሳይሆን ቀርቶ አሁንም የተለመደውን የማፈን ስራ  በመስራት ስልጣኔን አስቀጥላለው የሚለውን ተረት ካልተዋችሁ የኢትዮጵያ  ህዝብ የተዳፈነው እሳትን አራግፎ ለነጻነቱ በመነሳት ነጻነቱን የሚያውጅበት ቀን ተቃርቧል እና በህዝብ ባህር ሰጥሞ  ከመጥፋት በፊት ቢታሰብበት መልካም ነው እላለው። አበቃው።

ከተማ  ዋቅጅራ

17.07.2016

Email- waqjirak@yahoo.com

 

 

 

 

↧

ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ – ወልቃይትም ዘውጉን ናፈቀ!

$
0
0

 

Amhara
የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ደጋግመው ይናገሩ የነበሩት ስለ በግድ ምስለት ወይም በግድ እኔን መስለህ ኑር  (forced cultural assimilation) ጉዳይ ነበር። እንደ አዲስ መገለጥ ነበር ይህን የሚሰብኩት። ህወሃት ገና ደርግን ስልጣን ላይ ትንሽ ቆይቶ ሳያየው ወደ ጫካ ወሰደኝ የሚለው ጉዳይ ይሄው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በነሱ ቋንቋ “መጨፍለቅ…… መዳጥ” ጉዳይ ነው ይላሉ። ይህ ማለት ቡድኖች ሳይወዱ በግድ አማራውን እንዲመስሉ ተደርጓል በሚል ነው። በነሱ ቋንቋ “አማራይዜሽን” ይሉታል። እንዴው አማራው እንዲህ ባለፉት ስርአቶች ከተመቸው ስለምን ሃይለስላሴን ታገለ? ስለምን የወሎ እናት በነ አሊ ሙሳ ልጆቿን ተቀማች? ስለምን ሸዋ አመፀ? ስለምን ጎጃም ተነሳ…… ስለምን ጎንደር ታገለ…..ለዚህ ጥያቄ ወያኔ መልስ የለውም።

 

እንግዲህ ህወሃት ይህን የአማራ የባህል የበላይነት አጠፋለሁ ሲል እንደሚታወቀው  አብዛኛው ማለት ይቻላል የቡድኖች ባህሎች ሃይማኖታዊ ናቸው ወይም በሃይማኖት ተፅእኖ ስር የወደቁ ናቸውና የአማራን የብዙሃን ሃይማኖት መምታት ፈለገ። በዚህ መሰረት ኦርቶዶክስን መምታት አንዱ ዋና የትግል ስትራተጂው አድርጎ ነበር። ለዚህም ነው እነ አቶ መለስ በተለይም አቶ ስብሃት በግልጽ ቋንቋ አማራንና ኦርቶዶክስን መምታት አለብን ያስባላቸው። በርግጥም እንዳሰቡት ስልጣን ሲይዙ ኦርቶዶክስን ለሁለት ከፈሉና ጳጳስ በጳጳስ ላይ ሾሙ። ለነገሩ ሙስሊሙም አልቀረለት ይሄውና ዛሬ መከራውን ያያል። አማራውንም በተለያየ መንገድ ሲያሰቃዩት አሉ።

 

 

ህወሃት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ስለዚሁ ስለ ባህል ምስለት ጉዳይ ብዙ የሰበከ ሲሆን ወያኔ ደጋግሞ በተለይ ኦሮሞውን በግድ የአማራ ስም ኣውጥተህ ራስህን ያገኘኸው ለዚህ ነው ይል ነበር። በቅርቡ ዶክተር ቴድሮስ የአንድ የአስመራ ዩኒቨርሲቲ ጓደኛቸው ስሙ ገላና የነበረ ኦሮሞ በደረሰበት ጫና ገላነው ተባለ ይሉናል። እውነቱን እግዜር ይወቅ። ግን የራሳቸው የቴድሮስ ስምስ መቼ ትግርኛ ነው። ግሪክ እኮ ነው መነሻው። እንዴው በዚህ ደረጃ ወርዶ መወያየት ቢያሳፍርም ማለቴ ነው። የኔ የራሴ ስም ገለታው ነው። መነሻው ኦሮምኛ ነው። በኦሮምኛ ገለታ ነው ስሜ ማለቴ ነው። ምንም እንኳን ኦሮሞ ባልሆንም እኮራበታለሁ። ለነገሩ እነ ዶክተር ቴድሮስ ህወሃቶች ይህቺን የስም ነገር እያራገቡ የኦሮምያን አንጡራ ሃብት ሲበዘብዙ ቆይተው ዛሬ ይሄውና የኦሮሞ ህዝብ መሬት አንቀጥቅጥ አመጽ ላይ ነው። ዛሬ አለም ታዝቦ ለካ ህወሃትን ጫካ የወሰደው ጉዳይ የብሄሮች ማንነት ጉዳይ ሳይሆን ለኢኮኖሚ ጉዳዮቹ ነው ተብሏል። ለማናቸውም እንግዲህ ወያኔ አገሪቱን በብሄር ፌደራሊዝም ማስተዳደሩን ቀጠለ። ልዩነት በጣም ሲራገብ አንድነት አቅሉን አጣ።

 

በርግጥ የበፊቷ ኢትዮጵያ በሃይል ነበርና የተመሰረተችው የባህል ሚዛኑ ችግር ነበረበትበ ። የቋንቋ አጠቃቀም ጉዳይ የባህል ማንነት ጉዳይ በተሻለ ሲስተም ሊተዳደር ይገባው ነበር። መጀመሪያ ላይ ወያኔ ይህን የብሄር ብሄረሰብ እኩልነት ሲዘምር አማራው ቅር አላለውም። ሁሉም ብሄሮች ደግፈዋል። ምክንያቱም ይህቺ አገር የሁላችን እንደመሆኗ ሁሉም ብሄሮች በእኩልነት ሊኖሩባት ይገባልና ነው። አለበለዚያ አንድ የተባበረች ጠንካራ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ልታምረን አይገባም። ሩቅ ማሰብ አለብን። መሪነት ይሄ ነው። ነገን የማያይ መሪ መሪ አይባልም።

እንግዲህ ወያኔ ወደ ስልጣን ሲመጣ የጎንደር የወሎ የሸዋ ህዝብ እየሰነቀ ነው የሸኘው። በተለይ ጎንደር ብዙ መከራ አይቷልና። በርግጥም በህወሃት ትግል ጊዜ ከታች የነበረው ተራው ታጋይ በእውነት በንጽህና ነበር ይታገሉ የነበሩት። እኔ በግሌ ያኔ ገና አዲስ አበባ ሳይገቡ ካደኩባት ከተማ ውስጥ ቀድመው ገብተው ነበርና የህወሃትን ታጋዮች አይቻለሁ። እነ ሃደራን፣ እነ አበባን፣ እነ ጎይቶምን፣ መቼም አልረሳቸው። በንጽህና ደርግን ታግለዋል።አንድ ተጋዳላይ ባህርዩ ማርኮኝ ስለነበርና ተስፋ መስሎ ስለታየኝ ልብስ ሲያጥብ አይቼ ሱሪህን ካላጠብኩ ሞቼ እገኛለሁ ብየ አጠብኩ። ደስ አለኝ። ያቺን እናቴን እባክሽ ቡና አፍይና ጥሪያቸው እያልኩ ስንት ቀን አብርን ቡና ጠጣን። እሷም እግዜር ይስጣት ጠብ እርግፍ እያለች ታስተናግድልኝ ነበር። አባቴ ዛፍ እንዲሰጥ ለመንኩ። የሚያበስሉበት የቸገራቸው መስሎኝ ነው።  በሽማግሌ ጎኑ እንጨት እየፈለጠ በጎረቤት ሰፍረው የነበሩ ወያኔዎችን አገዘ። እንቢ ሳይለኝ ያልኩትን አደረገልኝ። ወያኔዎቹ ቁምጣቸውንም ይሁን ሱሪያቸውን ዝቅ አድርገው ስለሚታጠቁ የተራቡ እየመሰለኝ ብዙ ቀን ተሳቀኩ። ቤተሰቦቼ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ቢኖራቸውና በእኔ በልጃቸው ስም ለወያኔዎቹ ቢለግሱልኝ ይሰማኝ የነበረው ደስታ ሃያል ነበር። ኋላ ላይ ከዚያች ከኛ ከተማ ወያኔዎች አፈገፈጉና 18ኛው ተራራው የተባለው ጦር ይመስለኛል (እርግጠኛ አይደለሁም) ከተማዋን መልሶ ያዘ።  ጨካኙ ደርግ ጎረቦቶቼን አጎቴን የትምህርት ቤት ርእሰ መምህሬን ጥርግርግ አድርጎ በአንድ ጉድጓድ ረሸናቸው። ከዚያች ትንሽ ከተማ አስር ታዋቂ ሰው ሲጠፋ ሲረሸን ከተማዋ ባዶ የቀረች ያህል ይሰማል። ከወያኔ ጋር ተባብራችኋል አብልታችሁ አጠጥታችኋል ነው ክሱ። በዚህ ጊዜ አንዱ ሊረሸን የነበረው የኔ አባት ነበር። ደርግ እንደገና ከተማዋን ሲቆጣጠር አባቴ ታስሮ ነበር።  ሊገደል ተወስኖ በታምር ተረፈ። ደርግን ድሮም እጠላው ነበር አሁን አውሬ መስሎ ታየኝ። ሁዋላ ላይ ለትምህርት በሚል ወደ ሌላ ከፍ ያለች ከተማ እንድመጣ ተወሰነና መጣሁ። ቤሳቢስቲ ሳይኖረኝ በዚያች ሻል ያለች ከተማ ደረስኩ። እድሜ ለቀይ መስቀል በነሱ እርዳታ ነው በዚያ ትምህርት የጀመርኩት። እንደኔ ላሉ ተፈናቃዮች ቀይመስቀል አባትና እናት ሆኖ አከረመን። ታዲያ በዚያ ከተማ እያለሁ የመጨረሻውን የደርግን ግፍ አይ ዘንድ እግዚአብሄር ፈቅዶ ነበር መሰለኝ ወደ አንድ ፓለቲካ የሌለበት ሃይማኖታዊ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ሄጄ በደርጉ ፓሊሶች ታሰርኩ። መታሰር ብቻ አይደለም ግርፍም ነበር። በመጀመሪያው ቀን ስንያዝ የመጣንበትን ተጠይቀን እኔ የመጣሁባት ከተማ ውስጥ አሁን ወያኔ ስላለ እንደምገደል ገምቼ ነበር። የኔና የጥቂት ሰዎች ጉዳይ ከወያኔ ሰላይነት ጋር ሊያያዝ ነው ማለት ነው። የፓሊስ አዛዡም ይህን ጠቆም አርገው ነበር። ታዲያ ስንገረፍ ትዝ የሚለኝ ሁለት ፓሊሶች አምስታችንን እየተፈራረቁ ይገርፉን ነበር። ለምን እንደሆነ አላውቅም  አንዱ ፓሊስ እኔን ለብቻየ አውጥቶ ይደበድበኝ ጀምር።

 

አንድ የምናገረው አለ አልኩት ጮክ ብየ። በግርፉ መሃል።

 

“ምንድን ነው!” አለኝ። በሚያቧርቅ ድምጽ። ኮፍያው ተጣሟል አልቦታል።

 

ፋታ የሰጠኝ ስለ ወያኔ የምለው ያለ መስሎት ይመስለኛል። እኔ ግን እንዲህ አልኩት

 

አስራ ስምንት አመት አልሞላኝም እኮ! አልኩት።

 

እውነቱን ለመናገር አስራ ስምንት አመት ይሙላኝ አይሙላኝ ይለፈኝ ጠንቅቄ አላውቅም። የልደት ካርድም የለኝም። ስለ እድሜ እኛ አካባቢ ብዙ ትኩረት የለም። ለፓሊሱ ያንን ያልኩበት ዋናው አጀንዳየ ግን አንድም ቢያንስ ድብደባውን እንዲተወኝ….አለ አይደለም እንዲያዝንልኝ ነበር። አሰነዛዘሩ እስክሞት የሚቀጥል መስሎኝ ነው።  መዘየዴ ነበር። ሌላው ደግሞ ለህግ ይገዙ እንደሆን ብየም ነበር። ያ ፓለስ የሳቀው ሳቅ ከህሊናየ አይጠፋም። እስኪችል ደበደበኝ። ይህን በመጠየቄ እጥፍ ዱላ ተቀበልኩ። ያ ፓሊስ በህግ ላይ ነበር የሳቀውና ውስጤ እንደ ብረት ሆነ። በእግሩ ስር ሲወቃኝ ልታገለው እስካስብ ሃይል ተሰማኝ። በቃ ለውጥን ሰብአዊነትን ከልብ ለሃገሬ የተመኘሁላት ያን ቀን ጨለማ እስር ቤት እያለሁ ምሽት ላይ ነበር ልበል። ለወደፊት በዚህ ጭለማ ላይ ሻማ በርታ ብርሃኑ ጨለማውን አስወግዶ በምናብ አየሁ። አብሮኝ ለታሰረው ሹክ አልኩት። ሻማ በርቶ ይህ ጭለማ በብርሃን ተሸንፎ አየሁ አልኩት። በድብደባ የሞተውን እግሩን እያሸ ሲስቅ ይሰማኛል። በነገራችን ላይ በዚያች በትንሽ ጨለማ እስር ቤት ውስጥ ሁለት በእግር ብረት የታሰሩ ወያኔዎችን አገኘሁ። እንዲሁ ስናንሾካሹክ አደርን። ያሳዝናሉ። የሚጠብቃቸው ነገር የፍርድ ሂደት ሳይሆን የሜጀር ጀነራል ከፈለው ይብዛን ወይም ከዛ በታች ያለ አዛዥ የሚሰጠውን የግድያ ትእዛዝ ብቻ ነው። መጨረሻ ላይ እኔ በዋስ ስወጣ እዚህ አካባቢ ዘመድ ካላችሁ ላኩኝ ስንቅ እንዲያመጣላችሁ ብየ ሹክ ብላቸው ምንም ሰው የለንም አሉኝ። በኋላም አብዮታዊ ርምጃ እንደተወሰደባቸው ሰማሁ። ወደ ኋላ እንዳልመልሳችሁ እንጂ በዚያች ባደኩባት ከተማ አንድ የደርግ መኮንን ውሃ በኮዳ እንድቀዳ ያዘኛል። እየሮጥኩ ሄጄ በዚያች በኮዳው ውሃ ይዤ መጣሁ። ስመለስ አንድ ዘግናኝ ነገር ገጠመኝ። ይህ ወታደር የሆነ አንድ ገበሬ ከፊቱ አቁሞ ያናግራል። ያገበሬ ቃል የለውም። በርግጠኝነት በእውቀት ላይ የተደገፈ የወያኔ ደጋፊ አይደለም። ወያኔ አብልቶ አጠጥቶ ቢገኝም። ምክርና ቁጣ ለዚህ ገበሬ ከበቂ በላይ ነው። ወታደሩ የወንበዴ ቅጥረኛ እያለ ያዋርደዋል። እኔ ደግሞ ያቺን ውሃ ሙሉ ኮዳ እንደዘረጋሁ ነው። ጥቂት ከንፈሩን ነከሰና ሽጉጡን ላጥ አርጎ ግንባሩን አለው። ለብዙ ቀን የዚያ የገበሬ ሁኔታ ሲያሳዝነኝ ነበር። ብዙ ሰው ሞቶ አይቻለሁ እንደዛ ገበሬ ያሳዘነኝ የለም።

 

ወደ ወያኔዎቹ ልመለስና በውነት እነዚያ የትግራይ ልጆች ሃቀኞች ነበሩና ማርከውኝ ነበር። ይህን የግል ህይወቴን ሁሉ የማወራችሁ ሌላም ዜጋ ወያኔን እንደኔው ተስፋ አድርጎ አስቦ ነበር ብየ ስላመንኩ ነው። ታዲያ የነዚያን የዋህ ወያኔዎች ሁኔታ አይቼ ተስፋ ብሰንቅም የነሳሞራ፣ የነ ገብሩ፣የነ አባይ ጉዳይ በርግጥ አሳስቦኝ ነበር። አዲስ አበባ ላይ ያቺን ትልቅ ኢትዮጵያን ሊያስተዳድሩ ማሰባቸው በጣም አሳስቦኝ ነበር። ከነበራቸው እውቀት አንጻር ማለቴ ነው። ከነበራቸው ሎጂክ አንጻር ማለቴ ነው። ይሁን እንጂ አሁን ጀነራል የሆነው ሳሞራ እኔ ተልእኮየ ህዝብን ነፃ ማውጣት ነው ከዚያ ወደ ግል ኑሮየ…. ብሎ ነበር። ይሄ ትንሽ ረፍት ሰጥቶኝ ነበር። በርግጥ እነዚህ ታጋዮች ታግለው ታግለው የልጅነት ጊዚያቸውን በረሃ በልቶት ኢትዮጵያ ዝም ብላ አትበትንም። የካሳ ዘመን ልትደግስላቸው እንደሚገባ በሚችሉት ሃገራቸውን ሊያገለግሉ እንደሚገባ አምን ነበር።እኔና ከነዚህ ታጋዮች መሃል አንዱ ለስራ ውድድር ቀርበን ለሱ አፈርማቲቭ አክሽን ተብሎ አድቫንቴጅ ቢሰጠውና እኔ ሌላ እድል ብጠብቅ ቅር አይለኝም ነበር። ይህ ግን አልሆነም። እንደገቡ ምሁር የተባለውን በባትሪ እየፈለጉ ከነሱ በእውቀት ያንሳል የሚሉትን እየፈለጉ ኢትዮጵያን በመልካም አስተዳደር እጦት ይቀጡ ጀመር።

 

እነዚያ ብዙ ንፁህ የህወሃት ታጋዮች መስዋእትነት ከፍለው ለእኩልነት ይታገሉ እንጂ  እነመለስ ከመነሻው በነዚህ ሰዎች ሬሳ ላይ ሌላ አጀንዳ ነበራቸው። ይሄው አጀንዳው ስልጣን ላይ ሲወጡ ታየ።

 

ጎንደር እኮ በደርግ ጊዜ ኢትዮጵያ የሁላችን ነች፣አምባገነንነት ይውደም ባለ ነው ልጆቹን ያጣው። የጎንደር እናት እንዲህ ስትል ሙሾ አውርዳ አልነበር?

 

መላኩ ተፈራ የእግዜር ታናሽ ወንድም

የዛሬን ማርልን ሁለተኛ አልወልድም።

 

በርግጥም የጎንደር ወጣቶች የሞቱትና የተሰደዱት ለብሄሮች እኩልነት ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ነው። ታዲያ እንዲህ በደርግ የተጎዳ ጎንደር ህወሃት ወደ ክልሉ ስትገባ  የብሄርተኝነቱ ስሜት ስላልነበረ እነዚህ ወያኔዎች ወገኖቻችን ናቸውና እስቲ እነሱ ከበረቱልን ይህን ኣረመኔ ደርግ ይጣሉት እኩልነትን ያመጣሉ ከሚል ስንቅ እያቀበለ እየደገፈ ነበር የሸኛቸው። ጎጃም ለወሎ ወሎ ለሸዋ እያቀበላቸው ነው አዲስ አበባ የገቡት። እንዴውም በአንድ ቦታ እንዲህ ተዘፍኖ ነበር። ዘፋኙ ሰው ልጆቹን ሁሉ በግድ ለብሄራዊ ውትድርና ገብሮ የመረረው ገበሬ ነበር።

 

ምንሽር ልገዛ በሬየን ሳስማማ

ወያኔ ደረሰች በነጠላ ጫማ

 

በርግጥ ለውጥ የተራበ ህዝብ ኣንዳንዴ ኣይመዝንምና ስለወያኔ የፓለቲካ ተፈጥሮ ሳይመራመር ደጋግፎ አዲስ አበባ አስገባ። ብዙ ሳይቆይ ወያኔ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ ያንኑ ሲያበላው የነበረውን እጅ መንከስ ጀመረ። እነዚህ ሰዎች ለብሄር እኩልነት ሳይሆን የመጡት ለዘረፋ ነው ተባለ። ከሃያ አመት በኋላ ወጣቱን ስራ ፈት አደረጉት። አምራቹን ተንከራታች ስደተኛ አደረጉትና ሲመረው እንዲህ ሲል ዘመረ። ዝማሬው ያስደነግጣል።

 

ና ና መንግስቱ ናና

ናና መንግየ ናና…….

ያሳዝናል።

 

ትናንት ወያኔ ደረሰች በነጠላ ጫማ ይል የነበረ ህዝብ ዛሬ ያንን ያስለቀሰውን መንግስቱን እንደገና ናና መንግስቱ ናና……. እያለ ሲዘፍን እንደማየት የሚያሳዝን ኧረ ለመሆኑ ምን ነገር አለ?  ይህ ህዝብ ወደ ኋላ ያስመኘው ምን ያህል ቢበደል ነው? ምን ያህል ሆድ ቢብሰው….. ምን ያህል ቢመረው ነው? ምን ያህልስ ቢርበው ቢከፋው ነው? የሚለው ነገር እስከ ሃቹ ያስደምማል።

 

ህብረተሰቡን ከምንም በላይ የጎዳው ስነ ልቦናዊው ጉዳይም ነው በርግጥ። በዚያች ሃገር የአንድ ብሄርን የበላይነት ለማምጣት የሚሞክረው ወያኔ ይህ ጉዳይ ለህዝቡ አልተዋጠለትም። ህዝቡ እለት እለት ይህ ስሜት እያበሳጨው እያናደደው ሲመጣ ይታያል። ሃጎስ፣ አበበ፣ ገለታ፣ ሜቶ ጎረቤት ሆነው ሲኖሩ ዛሬ ሃጎስ ህወሃት ስልጣኑን ተቆጣጥሯልና የበላይነት ለማሳየት ቢንጠራራ በርግጥም ሌሎቹን ያሳብዳል። አበበም ሆነ ገለታ ወይም ሜቶ አንዱ ባንዱ ላይ መንጠራራት ካማራቸው ኢትዮጵያ አለቀላት። የብሄር ፓለቲካ ችግር ይሄው ነው እንግዲህ። ወያኔ የዘራውን የዘር ፓለቲካ ሰብል አጨዳ ላይ ነንና ጎበዝ እንጠንቀቅ።

 

ወደ ዋናው ርእሴ ልመለስና እንዴው የኢኮኖሚውን የዴሞክራሲውን ጉዳይ ሁሉ እንተወውና ቢያንስ ይሄ ሞቼለታለሁ የሚለው የብሄሮች ማንነት ጉዳይ እንዴት ነው? ብለን ስንጠይቅ ህወሃት በኣደባባይ ምስለትን ይርገም እንጂ በጓዳው ግን የሆነ ነገር ቀብሮ ይኖራል።   የወልቃይቶች የማንነት ጉዳይ……

 

በመሰረቱ የወልቃይቶች የማንነት ጥያቄ ጉዳይ በመጀመሪያዎቹ ኣመታት አልገነነም ነበር። ለምን? ቢባል ኣንደኛ አማራው ኣብዛኛው አማራ ማለት ነው ከብሄርተኝነት ጋር የተጋጨ ስለነበረና የወያኔን የብሄር ፌደራሊዝም በህሊናው መቀበል ስለተሳነው የወልቃይቱ አማራ የሄደ የሄደ ሳይመስለው እንዲሁ ቆየ። ይህ የብሄር ፌደራሊዝም ሲፈጠርም አማራ አልተካተተም ነበር። የሚሆነውን ሁሉ ዝም ብሎ ከዳር ቆሞ ያይ ነበር። ኋላ ሁኔታው ስላላማረው ላለው መንግስትና ላለው ሲስተም እውቅና (legitimacy) አልሰጠም ነበር። ይህ ሁኔታም የወልቃይትን ጥያቄ አጉልቶ እንዳያይ አድርጎት ቆይቷል። ይሁን እንጂ በመሃል ወልቃይት መጮህ ጀመረ። ጨዋታው በየቤትህ እደር ሆኖ ሃያ ኣምስት ኣመት ሲቆይ ጊዜ ወልቃይት መንጋው ናፈቀው። ትግራይ ወደ መንጋው ሲገባ ሌላውም ማንነትህ ተጠብቋል ተብሎ የብሄር ፓለቲካው ሲጦፍ ወልቃይትም ዘውጉን ናፈቀ። ማንነቱ…… የሚኮራበት…… ያ… አማራነቱ መጣበት…….። እናም በአካባቢው ያሉትን የትግራይ ሰዎች እያየ ይሄው ኣጨፋፈሩ የኔን ኣይመስልም፣ ይሄው በአል ሲካድም እንደኔ ኣይደለም፣ ይሄው ሰርግና ምላሻችን ይለያያል…ያለ ቤቴ ነው ያለሁት….. አለ። ሴቷ የወልቃይት አማራ ደግሞ ልዩነት ፈልጋ የኔ ጸጉርና የሷ ጸጉር ኣያያዝ ኣይመሳሰልም……እንለያያለን……. ወዘተ….. ማለት ተጀመረ። ይህ ነገር በርግጥ ከጥላቻ ኣይደለም። እነዚህ ሁለት ብሄሮች ይጋባሉ። ይሁን እንጂ የፖለቲካው መስመር በየቤትህ እደር ሆኖ የወልቃይቱ ኣማራ ማንነቱ ሳያውቀው እየተነነ የመጣ መሰለውና ደነገጠ። አንድ ትልቅ ክህደት ሊፈጽም መሰለው። በርግጥ ከፍ ሲል እንዳልኩት ሸዋው፣ ጎጃሙ፣ ጎንደሩ፣ ወሎውና በያለበት ያለው ኣማራ ሁኔታውን ዝም ብሎ ማየቱ ያንን የወልቃይት ዘውጉን መዘንጋቱ ሳይሆን እስቲ ወይ ጊዜ ይፈታዋል እስከዚያው ያው ኣገሩ ነው በሚል ነበር። ከሁሉ በላይ ደግሞ ብዙው አማራ ወያኔ የብሄሮችን እኩልነት አመጣበታለሁ ያለውን የልዩነት ፓለቲካ እየረገመ ስለሆነ ያለው የወልቃይቶች የማንነት መጨፍለቅ ጉዳይ ትኩረት ሳያገኝ እንሆ 25 ዓመት ቆየ።  ይሁን እንጂ ኣሁን አሁንስ ወልቃይት ትግራይ ውስጥ ባይተዋርነት ተሰማው……። ለምን ተሰማው? ብንል ከትግራይ ህዝብ ጋር በሚኖረው ኑሮ ሳይሆን ዘረኛ የሆነው ህወሃት የሚያደርስበት ስነ ልቡናዊ ጫና ነው። ዛሬ ዛሬ ግን ወልቃይት ሰሚ ኣገኘ። በርግጥ ትኩር ብለን ካየነው ከማንነት ጋር በተያያዘ በዚህ መንግስት እንደ ወልቃይት የተጎዳ የለም። የዴሞክራሲ መብቶች ችግሮችን ሁላችን የምንጋራ ሆኖ ነገር ግን ወልቃይት በማንነት ጉዳይ በጣም ተጎድቷል።

 

እንዴት? ማለት ጥሩ ነው። በሚከተሉት ምክንያቶች ቀድሞ ከነበረውም የምስለት ግፎች የወልቃይት በጣም ይከፋል።

 

ኣንደኛው ምስለቱ በራሱ ብቻ ሳይሆን የከፋው በግድ መሆኑና ከሁሉ በላይ ደግሞ ይህ በግድ የሆነ ምስለት በብሄር ፖለቲካና ፌደራሊዝም ከባቢ ውስጥ መሆኑ ነው። በኣንድ ሃገር ጥላ ስር ባለ ማንነት ስር የሚደረግ ምስለት በኣንጻራዊነት የሚሻል ሲሆን የብሄር ፖለቲካ በነፈሰበት ኣገር ኣንድ ቡድን ያለ መንጋው ሲገኝ ቢጨንቀው ስለምን ይፈረድበታል? ሆዱ ቢባባና የተረሳ ቢመስለው ስለምን ይፈረድበታል? ኣንዱ የወልቃይትን ስነ ልቡና ያደቀቀው ነገር ጨዋታው በየቤትህ እደር ሆኖ ወልቃይት የሚኮራበት የዘውግ ቤት እያለው ለምን ትግራይ ውስጥ ይሸጉጡኛል የሚለው ነው። ልብ የሚነካ አሳዛኝ ነገር ነው። ማንም ብሄርና ግለሰብ ይህን የወልቃይትን ጉዳይ በሚገባ ሊረዳው ይገባል። ሌላው የወልቃይትን ግፍ የሚያገዝፈው ጉዳይ ደግሞ ይህ በግድ እኔን ምሰል የሚል ነገር  ዛሬ ዘመን ላይ መፈጸሙ ነው። የማንነት ፓለቲካ ተቀባይነት ባይኖረውም ነገር ግን በግድ የመለየት ፖለቲካው ከመጣ በሁዋላ ዜጎች ስለማንነት በሚገባ ያጠናሉ። ማይክሮ የነበሩ ማንነቶችን ሁሉ በማይክሮስኮፕ እያዩ ልዩነትን እየነቀሱ እያወጡ ያገዝፏቸዋል። ልዩነትን ይፈልጋሉ። በዚህ ላይ እውቀታቸው ይጨምራል። ታዲያ እንዲህ በዚህ ዘመን አንድን ቡድን በሃይል መስሎ እንዲኖር ለማድረግ መሞከር የዚያን ማህበረሰብ ስብራት እንዲገዝፍ ያደርገዋል። ከዴሞክራሲያዊ መብቶችም በላይ የወልቃይት ስነ ልቡና ተጎድቷልና ይህን ጉዳት ኢትዮጵያውያን ሊረዱለት ይገባል።

 

የወልቃይት ጥያቄ ንጹህ የማንነት ጥያቄ  ነው። አንድ ነገር መገንዘብ ያለብን ወልቃይት ወደ ዘውጋችን መልሱን ሲል ትግራይ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸው ስለተነካና በዚህ በኩል ኣማራ ክልል ስለሚሻል ኣይደለም። ኣማራ ክልልም ሄድክ ኦሮሚያ ወይም ደቡብ ወይም ሌላ ክልል በአንድም በሌላም መንገድ ገዢው ያው ህወሃት ነው። የወልቃይት ህዝብ ይህንን ያውቃል። ይሁን እንጂ ጥያቄው የዘውግ ጥያቄ ነው። ተመቸውም ኣልተመቸው ወደ ቤቱ መመለስ ይፈልጋል። በቋንቋው በባህሉ እየኖረ በሌላ በኩል ደግሞ ዴሞክራሲ ወደ ሃገሪቱ እንዲመጣ ከሌሎች ብሄሮች ጋር  የወልቃይት ህዝብ የብሄር ፓለቲካንና የከፋፍለህ ግዛውን ስርአት ሊታገል ይፈልጋል። የወልቃይት ህዝብ የሚታገለው ብሄራዊ አንድነቱም ዘውጋዊ ማንነቱም ተጠብቀው ሳይጋጩ የሚያኖርለትን ሲስተም ለማምጣት ነው። ይሄ መታወቅ አለበት። የአንድ ዴሞክራቲክ መንግስት ሃላፊነት እነዚህን ሁለት ዋና ዋና ማንነቶች መጠበቅ ነው።

 

ሌላው የወልቃይትን ጥያቄ ያመረረውና ያከበደው ጉዳይ የህወሃት የፓለቲካ እምነት ነው። በብሄር ፓለቲካ  እምነት መሰረት ራስን በራስ ማስተዳደር የሚባለው ነገር የፍልስፍና መሰረቱ ምንድን ነው? ካልን ዘውጎች በራሳቸው ልጆች ሲመሩ ኣስተዳደሩ ትጋትንና ርህራሄን ይጨምራል፣ ተግባቦት ይጨምራል ከሚል ነው። እኔ በግሌ አላምንበትም።ታዲያ እንግዲህ እንዲህ ኣይነት ኣመለካከት ባለው የፖለቲካ ድርጅት ስር ድንገት የሌላ ዘውግ አባል ሆኖ መገኘት በርግጥም ይጨንቃል። በርግጥም ባይተዋርነት ይሰማል።

 

የጨነቀው የወልቃይት ህዝብ በየማህበራዊ ኣጋጣሚው የሆድ የሆዱን ሹክ ማለቱ ኣይቀርም። እንዴው ለመሆኑ ለምን ፈለጉን……?

ትግርኛ ስለምንሞክር……።

እንዴ? አንዳንድ ክልሎች ቋንቋቸው ኣማርኛ ሆኖ የለም እንዴ?። ኣንድ ቋንቋ መናገር ብቻውን  በአንድ ክልል ውስጥ እንድትሆን ኣያስፈርድብህም። አረብኛ ስለምንናገር ነገ ሱዳን ተነስቶ ይህ አካባቢ የኔ ነበር ምልክቱ ህዝቡ አረብኛ መናገሩ ነው…… ሊል ነው?

 

ወልቃይት እየተደመመ አሁንም ሹክ ይላል…….።

ምን ኣልባትም እነዚህ ሰዎች ይህቺን ኣገር ኣምሰው ኣምሰው ኋላ መውጫ ቀዳዳ ሲጠፋባቸው ወደ መገንጠል ሊያመሩ ይችሉ ይሆን? ከተገነጠሉ ደግሞ የወልቃይት ለም መሬቶች ኣጓጉታቸዋለች ማለት ነው? የሰሊጥና የኑግ ምርት……. ታላቋ ትግራይ የሚያሰኛቸው የዚህ የወልቃይት መጨመር ይሆን?  ይላል ግራ የተጋባ ህዝብ ከዘውጉ ከመንጋው ተገንጥሎ ብዙ ዋጋ እየከፈለ ያለ ወልቃይት………። በነገራችን ላይ ይሄ ታላቋ ትግራይ፣ ታላቋ አማራ፣ታላቋ ኦሮሞ፣ታላቋ ሲዳሞ….. የሚባል ነገር እልም ያለ ቅዥት ነው። የቀን ቅዠት። ትግራይ አይደለችም ኤርትራ የባህር በር ይዛ፣ ለብቻየ ኖሪያለሁ ታሪክ አለኝ ላለችውም የሚበጅ አልሆነም። መገንጠል ማነስ እንጂ ምን ታላቅነት አለው?

 

ወደ ወልቃይት እንመለስና ወልቃይትን ኣሁን ግን ዓለም ይፈርደዋል። ጩኸቱ ከጸባዖት ገብቷል። ስለዚህ ስለ ክልል ጉዳይ ብዙ ሰው ሲጨነቅ እሰማለሁ። የትግራይ ክልል ተከዜ ነው። ከዚያ በመለስ በታሪክ ጎንደር ነው ይላሉ። በርግጥም በዚህ ላይ መቼም መከራከር ኣይቻልም። ይህ ሃቅ ነው። ህወሃት ድንጋዩን ዳቦ ነው ብሎ አፍጦ ስለሚከራከር ከሱ ጋር መከራከር ጊዜ መግደል ነው። ይሁን እንጂ ከህወሃት ቀድሞ ታጋዮች እንዴውም  ይህንን ወልቃይትን ወደ ትግራይ የመከለሉን ስራ የሰሩት ዶክተር ኣረጋዊ በርሄ ራሳቸው እንዲህ ነበር ያለት።

“ወልቃይት ወደ ትግራይ እንዲገባ የተደረገው ወደ ሱዳን መውጫ ለማግኘት ነው”

(ዶክተር አረጋዊ በርሄ)

 

“የትግራይ ወሰን የተከዜ ወንዝ ነው”

(ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም)

“የጎንደር እና ትግራይ ግዛቶች የሚያዋስነው ተከዜ ወንዝ ነው”

(አቶ አሰገደ ገብረስላሴ)

 

” የወልቃይት ህዝብ የዘር ማጥፋት እና ግዛት ማካለል የተጀመረው በ1970ዎች ነው። ህዋሃቶች ወልቃይቶችን ወደ ትግራይ ልትጠቃለሉ ነው ሲሏቸው ህዝቡ እምቢ በማለቱ ከዚያን ጀምሮ የሃይል ርምጃ እየተወሰደ ወልቃይትም በግድ የትግራይ ሆነ”

(አቶ ገብረመድሃን አርእያ)

 

“ወልቃይት ወደ ትግራይ ሲካለል ከሱዳን ጋር ለመገናኘት ስለነበር የህዝብን ፍላጎት አልጠበቀም። በመሆኑም የህዝብ ምርጫ ሊከበር ይገባል”

(አቶ ግደይ ዘርአጽዮን)

 

ከሁሉ በላይ የወልቃይት ህዝብ ሲጠየቅ ይደነቃል። ምስክር በማቅረቡ ራሱ ይገርመዋል። በእንበል ገበያ ሆነን እንድ ሰው አቶ አባይ ፀሃይዬን አንተ ትግሬ አይደለህም የሌላ ብሄር ሰው ነህ ብሎ ቢከራከር አቶ አባይና በውል የሚያውቋቸው ሰዎች ምን ይላሉ? የወልቃይት የአማራነት ጥያቄ በዚህ ደረጃ የሚታይ ነው።  ይሁን እንጂ ህወሃት አንድ ነገር አለው። አንድን የፈጠራ ውሸት ብዙ ጊዜ ደጋግመህ እውነት ነው፣ እውነት ነው፣እውነት ነው….. ካልክ በህዝብ ላይ የሚፈጥረው ስነ ልቡናዊ ጫና አለ አንድም ያሳምናል ቢያንስ ቢያንስ ግን ግራ ያጋባል ይላሉ። ይሄ የማይቀየር የወያኔ የህዝብ ግንኙነት የፍልስፍና መሰረት ነው። በርግጥ ይህ ነገር ሳያዋጣቸው አልቀረም። አይቀይሩትም። የጥንድ ቁጥሩ የእድገት ፕሮፓጋንዳ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እኩልነት ሰፍኗል የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ሰፍኗል…….ፕሮፓጋንዳዎች መሰረት በዚሁ የህዝብ ግንኙነት ፍልስፍና መሰረታቸው ላይ የቆመ ነው።

 

ወልቃይትን ያስጨነቀው ዋና ጉዳይ ወሰኑ ተከዜ ነው ምናምን ሳይሆን የማንነቱ ጉዳይ ነው። ጨዋታው የብሄር ፓለቲካና ፌደራሊዝም በመሆኑና እኔ ደግሞ ያለ ዘውጌ በመገኘቴ ለማንነቴ ችግር ፈጥሯል ነው የሚለው ወልቃይት። ፍትሃዊ ጥያቄ ነው። ወልቃይት እንዴው የዴሞክራሲውንና የልማቱን ጉዳይ ተውትና ስርአቱ ወይም ሲስተሙ ለማንነቴ አደጋ ፈጠረ ነው የሚለው። ትክክለኛ ጥያቄ ነው።

 

የወሰኑ ጉዳያ ብዙ ስሜት ኣይሰጠኝም። ይህ ከማንነት ጋር የተያያዘ ወሰን በአዲስ ኪዳን መፍረሱ ስለማይቀር። የአማራ ህዝብ ወሰኑ ሞያሌ፣ ኢሉባቦር እስከ ኦጋዴን ነው፣ የትግራይ ህዝብ ወሰኑ ተከዜ ሳይሆን ኦጋዴን፣ ሞያሌ፣ ኢሉባቦር ባራቱም ማእዘናት ነው። የኦሮሞ ህዝብ ወሰኑ ሳንጃ ቋራ እስከ ኦጋዴን እስከ ትግራይ ድረስ ነው። የደቡብ ህዝብ ወሰኑ ጠገዴ ኦጋዴን ኣማራ ትግራይ ጫፍ ድረስ ነው። ኣፋሩ፣ ሃረሪው፣ ጋምቤላው፣ ቤንሻንጉል ጉሙዙ፣ ኦጋዴኑ ሁሉ ድንበሩ ባራቱም ማእዘን ነው። ይህ ነው ድንበራችን። አባቶቻችን ያስተማሩን ድንበር የሚባለው ነገር ይሄ ነው። በየቀበሌው የተገኘ ወንዝና ቦይ ሁሉ ድንበር አይባልም። ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃል ወደፊት ድንበር መኖር የለበትም። ሁለት አገር ሆነውም ድንበር አያስፈልጋቸውም። አፍሪካውያን ዛሬ እየተራመዱ ነው። ማንም አፍሪካዊ የትም ሃገር ያለ ቪዛ ሊሄዱ ነው።

 

ኣሁን ያለው የወልቃይት ጥያቄ የማንነት ሲሆን ማንነቱ ዘውጉ ውስጥ ተጠብቆ እንዲኖር ብዙ ማህበረሰባዊ ግንኙነት ለማድረግ ወደሚያስችለው ክልል መሄድ ኣለበት። ማንነቱ ሲነካ የሚወድ የለም። በመሆኑም በኣሁኑ ሰዓት ተነስቶ ሆ ብሎ የሚታገለውን የወልቃይትን ህዝብ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሊደግፉት ይገባል። ለወደፊት ግን ጎበዝ ኣገራችን ኣዲስ ኪዳን ውስጥ መግባት ኣለባት። እነዚህ ሰዎች ለኤፈርት ሃብት ሲሉ አገሪቱን ከባድ ችግር ውስጥ ዘፍቀዋታል።

 

አገራችን ማህበራዊ ጉዳዮቿንና ይህን የፖለቲካ ጉዳዮቿን ሳይጋጩ የምታስኬድበትን ኣዲስ ስርዓት መከተል ኣለብን። ማህበራዊ ጉዳይን ከፓለቲካ ማላተም አገርን ያፈርሳል። ኢኮኖሚን ይጎዳል። እነዚህ ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ማለትም ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ፣ ማህበራዊ ጉዳይና ፓለቲካዊ ጉዳዮች እንደየ ባህርያቸው በዴሞክራሲ መርሆዎች መተዳደር አለባቸው። በተለይ ኣሁን በዚህ ሁኔታ ውስጥ የቆየች ኣገር ያለባትን ዙሪያ መለስ ችግር የሚፈታላት ኣዲስ ቃል ኪዳን ውስጥ መግባት ብቻ ነው። በዚህ ጽንሰ ሃሳብ ዙሪያ ሌላ ውይይት ለማድረግ ጽሁፍ ተዘጋጅቷል። ለኣሁኑ መብቶቻችንን ለማስከበር ሁላችን በኣንድነት እንነሳ። እንደ አንድ ዜጋ ወንድም በተለይ ወጣቱን እማፀናለሁ።

 

በተለይ ለትግራይ ህዝብ ኣንዲት ነገር መናገር እሻለሁ። በውነት የትግራይ ህዝብ ሆይ ጸጋ በዝቶልሃል። ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ በጣም ሲጠነቀቅልህ ኣያለሁ። ፖለቲካው ወደ ዘር ጥላቻ የሚወስድ ሆኖ እንኳን ኢትዮጵያውያን ወገኖችህ ተጠንቅቀው ወያኔንና ትግራይን ለይተናል እያሉ ሲታገሉ ድፍን ሃያ አራት ኣመት ኣለፈ። ከትግራይ አንድ ተቃዋሚ ወጣት ብቅ ሲል ጭብጨባው ሌላ ነው። ራሱ ወያኔ ለፖለቲካ ትርፉ የሚጠቀምባቸው ሰዎች ትግራይ ለወያኔ እንዳደረ ይናገሩ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ እጅግ ኣክብሮህ ተጠንቅቆልሃል። ወያኔ አለኝ የሚለው ማህበራዊ መሰረት ትግራይ ነው። ታዲያ ለትግራይ ወጣቶች ያለኝ ምክር ምንድነው? ልክ እንደዚህ ኣንተም ይህን ግፈኛ ስርዓት በቀጥታ በመቃወም ኣሳይ። የኦሮሞ ወገኖችህን ጥያቄ ከፍ አድርግ። የወልቃይትን ህዝብ ደግፍ። ይህ ድጋፍህ በሰልፍ ብቻ አይደለም የሚገለፀው። አብሮህ ለሚኖረው ኦሮሞ አብሮህ ለሚኖር አማራ የፍትህ ወገንተኝነትህን አሳይ። ማህበራዊ ሚዲያዎችን በድጋፍ አጨናንቅ። ወያኔ ተቃዋሚውን ለማጃጃል፣ ህብረትን ለማፍረስና ለመጉዳት መጠቀሚያ ሊያደርግህ ሲሞክር እምቢኝ በማለትና ይህን አሳፋሪ የወያኔ የህዝብ ግንኙነት መረብ በመበጠስ አገርህን ታደግ። በተለይ በውጭ አገር የምትኖሩ የትግራይ ልጆች ወንድሞቼና እህቶቼ ወያኔን የሚቃወሙትን የፓለቲካ ሰዎች አክቲቪስቶች ባሉበት ስነ ልቡናቸውን በመጉዳት ህብረታቸውን በማፍረስ በመካከላቸው ፍቅር ጠፍቶ እንዲጣሉ ትግሉ እንዳያድግ ለማድረግ እንደ ታማኝ መሳሪያ ሊጠቀምባችሁ ሲያስብ እምቢኝ በሉ እንዴውም እያጋለጣችሁ ሃገራችሁን ታደጉ። እንዲህ አይነት በባህላችን የሌለ የወያኔ አፍራሽ ስራ በእግዚአብሄር እጅም ያስቀጣል።

 

በቅርቡ ከእንድ ኢትዮጵያዊ ጋር አወጋ ነበር። እንዲህ አለኝ። የትግራይ ሰው እኮ ከ90 በመቶ በላይ ወያኔን ይደግፋል አለኝ። ይህ ሰው ይህን እንዴት ሊል ቻለ ብየ አሰብኩ። ይህን ያስባለው በአካባቢው ካሉ እሱ ከሚያውቃቸው ጥቂት የትግራይ ልጆች ጋር ተወያይቶ ሲደግፉ በማየቱ ሊሆን ይችላል። ወይም አንድ ወያኔ የተወሰኑ የትግራይ ሰዎችን ወደዚህ ሰው እየላከ ትግራይን እንዲጠላ እንዲያጠቃልል አድርገውት ሊሄን ይችላል።  ይህንን የሱን አለም አጠቃሎ ነው ከዘጠና በመቶ በላይ የትግራይ ህዝብ ይደግፋል የሚለኝ።  እኔ ደግሞ ለራሴ ማሰብ ጀመርኩ። ከማውቃቻው ጥቂት የትግራይ ተወላጆች ውስጥ ሁሉም ማለት እችላለሁ ወያኔን ከልብ አይደግፉም ነበር። ከቅርቦቹ ማለቴ እንጂ ድርቅ ያሉ የወያኔ ደጋፊዎችንም አይቻለሁ። በቅርብ በተደጋጋሚ ያየኋቸው ግን ተጠቃሚም አይደሉም አደግፉምም። እንዴውም አንዱ የትግራይ ልጅ ገና በፊት እንዲህ አለኝ።

ገለታው

አቤት

እንደው ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች ሌላ አገር አላቸው ወይ? ሌላ አገር በድብቅ አስቀምጠው ነው ወይ ይህቺን አገራቸውን እንዲህ የሚጎዱት? አለኝ።

አላውቅም ብየ ተደምመን ተለያየን።

ምን ለማለት ነው? ሰው በአካባቢው ያለውን እየቆጠረ ስለሆነ ያለው የትግራይ ልጆች ይህንን ከግንዛቤ ቢያስገቡ ጥሩ ነው። ህወሃትን መደገፍ ከዴሞክራሲ መብት ጋር ስለማይገናኝ ነው ይህን የምለው። አገራችን እውነተኛ መድብለ ፓርቲ ስርአት ውስጥ ስትገባ ያኔ ሰው የፈለገውን ይደግፍ ይባላል። ወያኔ አገር አጥፊ ነው። አይማርም። ሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኔ ደግሞ ትግራይን ይረዳው። እርስ በርስ መረዳት ነው ትልቁ ትግላችን። ወያኔ ምንም እንኳን ማህበራዊ መሰረቴ ትግራይ ነው ቢልም ህወሃት የትግራይ አምባገነናዊ መሪ ነው። የትግራይ ህዝብ በዚህ አምባገነን ስርአት ስር እንዳለ መረዳት ተገቢ ነው። እንዲህ ስናደርግ እርስ በርስ  መተማመን ይጨምራል። ኣይዞን ወገን በያለንበት።አይዞን ወልቃይት። ሁላችን በጋራ ትግላችን ኢትዮጵያችንን ወደ ኣዲስ ኪዳን እናመራና ዘረኝነት ይቆማል። ዴሞክራሲ ያብባል። የተባበረችውን ኢትዮጵያን እንገነባለን። ይህቺ አዲሲቱ ኢትዮጵያ በሁላችን የሁላችን ለሁላችን  ትሆናለች። አማራውም ጎንደር የቀደሰውን ደባርቅ እንደተከተለ ትግሉ ይቀጥል። ኦሮሞው ጥያቄው ሳይመለስ አያርፍም። ደቡቡም ይነሳ! ሁላችን በጋራ እንታገል። የጋራ ትግል የጋራ ድልን ያመጣና ሃገራችንን ወደ ተሻለና የተረጋጋ ስርአት ይመራልናል። ይሄው ነው።

 

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

 

አክባሪ ወንድማችሁ

ገለታው ከሩቅ ምስራቅ

geletawzeleke@gmail.com

 

 

↧

የአማራ የሕልውና ጥሪ  –  ወልቃይት ክብሪታችን ነው! –አንዱዓለም ተፈራ  –  የእስከመቼ አዘጋጅ

$
0
0

እሁድ፣ ሐምሌ ፲ ቀን፤ ፳ ፻ ፰ ዓመተ ምህረት ( 7/17/2016 )

ለጎንደር ኅብረት ማህበር                 ለጎንደር ልማት ማኅበር                 

ለደንበር ኮሚቴ                         ለጠለምት ልጆች ማኅበር                

ለወልቃይት ጉዳይ አስፈፃሚ                     ለሞረሽ ወገኔ                           

ለቤተ አማራ ወጣቶች                   በመላው ዓለም ተበታትናችሁ ለምትገኙ የአማራ ልጆች

ውድ ዘመዶቼ፤

ዘግንኖኝ ዘግንኖኝ፣ ስበግን ከርሜ

አሁን አጥር ዘለልኩ፣ ልቆጠር ነው ቆሜ።

ginbot7-supporters-blame-woyane

 

እያንዳንዱ ድርጅት የተመሠረተበት የየራሱ የሆነ ምክንያት አለው። በየቦታቸውና በየጊዜያቸው መፈጠራቸው፤ ያነገቡት ጉዳይ አስፈላጊ መሆኑን አስምሮበታል። ይህ ተጨባጭ ሀቅ ነው። ዛሬ በጎንደር እየተካሄደ ያለው የሞትና የሽረት ትግል፤ ይሄንን የያንዳንዳችሁን የወደፊት ሂደት፤ የምንነት ጥያቄ  አቅርቦላችኋል። በጎንደር የተነሳው የአማራው የሕልውና ጥያቄ ነው። ይህን የአማራ ወገናችን፤ አማራ ነህ ወይንም አይደለህም ብሎ የነገረው፣ ያስተማረው፣ የቀሰቀሰው የለም። ይልቁንም አማራ ነኝ፣ በአማራነቴ የሚደርስብኝ ውርደት በቃ ብሎ፤ በአማራነታችን አንገታችንን እንድናቀና እኛን አስተምሮናል። የወልቃይትን የምንነት ጥያቄ፤ ወራሪው የትግሬዎች መንግሥት አይመልሰውም። ለሱም የሕልውና ጥያቄ ነው። ለኛም የሕልውና ጥያቄ ነው። እናም የመንግሥቱን ሙሉ ኃይል እንደሚያፈስብን የታወቀ ነው። በውስጥ ያሉት አማራዎች ተነስተዋል። እኛስ ምን እንላለን?

እስከዚች ወር ድረስ፤ እኔ፤ ባደግሁበት የኢትዮጵያ አንድነት ተጎፍኜ፣ በኢትዮጵያዊያን አንድ ሕዝብነት አምኜ፣ በአንድ ብሔርነቷ ተከውኜ፣ ጆሮዬን ቢቆርጡት እንኳን ካለ ኢትዮጵያ አንድነት፤ ፍጹም ሌላ አልሰማም ነበር። የትግሬዎች መንግሥት ለረጅም ጊዜ ያደረገው የዘር ፖለቲካ ሂደት፤ በሕዝባችን የፖለቲካ ግንዛቤ ጥፍሩ ዘልቆ ገብቶ ስለደነደነ፤ በተጨባጩ ሀቅ መገዛት ግድ ሆነብኝ። እየመነመነ የሄደውን የአንድ ኢትዮጵያ ምኞቴ ትግል፤ መረመርኩት። በቦታው ቀፎ ሆኖ ታዬኝ። ተማርኩ። ለሀቁ ተገዛሁ። በዚህ በወራሪው የትግሬዎች ገዢ ቡድን፤ የአማራው የሕልውና ጥያቄ፤ ከሁሉም ነገር በላይ ሆኖ በለጠብኝ። ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ፤ በመላ ኢትዮጵያ ተበታትኖ የሚኖረው የአማራው ወገኔ ብሶትና በደል፤ አሁን ከምችለው በላይ ሆነብኝ። ዘረኛው የትግሬዎች መንግሥት፤ ወሰን በሌለው እብሪት ያካሄደው የመከፋፈል ፖለቲካ፤ የማይቀለበስበት ደረጃ መድረሱ ተሰማኝ። ለአማራው የመኖር ወይንም ያለመኖር፣ የመሞት ወይንም ያለመሞት ትንቅንቅ ሲሆንበት፣ ደንበር መለየት ግድ ሆነብኝ። እናም በአማራነቴ እንድቆም፤ በጎንደር እየተካሄደ ያለው የትግሬዎች ወረራ ገዛኝ። ይህን ምርጫ በመውሰዴ ምንም ዓይነት ቅሬታ የለኝም። ይልቁንም የግዴታ ምርጫዬን ማስተካከሌ ደስታ ሠጥቶኛል። ተምሬበታለሁ።

በጎንደር እየተካሄደ ያለው፤ በትግሬዎችና በአማራዎች መካከል፤ ላጥፋህ አልጠፋም ግብግብ ነው። በቦታው አማራው፤

ሲቆርጡት እያየሁ፣ ሞፈሩን ከበሬ

ጊዜ ይፍታው ብዬ፣ አንጀቴን ቋጥሬ

መግፋት ቀኑን ብይዝ፣ ሀገሬን አክብሬ

ሰይፉን አንገቴ ላይ፣ ወደሩት ወይዛሬ!

ምርጫው እንደጠፋ፣ የታሰረ በሬ

ተገዝግዤ ልሞት፣ በወራሪ ትግሬ

በቃ አለቀ እንግዲህ፣ እሪ በይ ሀገሬ!

በማለት ተነስቷል።

ውድ በአማራው ስም የምትንቀሳቀሱ ግለሰቦችና ስብስቦች፤

እያንዳንዳችሁን ያነሳሳችሁና እንድትሯሯጡ የገፋችሁ ዋናው ምክንያት፤ የአማራው የሕልውና ጉዳይ ነው። ምንም እንኳን በአደረጃጀት ዘይቤም ሆነ በአሰራር ሂደት አንዳችሁን ከሌላችሁ የተለየ የሚያደርጋችሁ ጉዳይ ቢኖርም፤ መሠረታዊ የሆነው ዋናው ጉዳይ፤ የአማራው ሕልውና ነው። አሁን የአማራው ሕልውና በመፈተን ላይ ነው። አማራው የሚጠፋበት ወይንም ራሱን የሚያቀናበት ደውል ተደውሏል። ለዚህ በአንድነት መነሳት የቅድሚያ ግዴታችን ነው። አጀንዳችን በወልቃይት ተነድፏል። እኛ አማራ ነን! ብሏል። አማራነትን ያነገበው የአማራ ጦር ጎንደር ገብቶ፤ የወልቃይትን አጀንዳ ያነገቡትንና ወኪል ተጠሪ የሆኑትን በሰዓቱ ታድጓቸዋል። በርግጥ ወራሪው ጦር የበለጠ የታጠቀና በጦር ትምህርት የሠለጠነ ነው። ይሄንን ለአማራው ጀግና የሚነግረው አያስፈልግም። በመርዝ ጋዝ ሁሉ የታጠቀውን የፋሽስት ጣሊያን ጦር፤ በባዶ እግሩ የተሰለፈና ጥቂት አሮጌ ጠመንጃዎችና ጀሌ ተሰብስቦ ነው ለሀገሩ ሕይወቱን ገብሮ ሀገራችን ያቆየልን።

አሁን የትግሬዎቹ ወራሪ ጦር አማራንና አማራነትን ለማጥፋት ጎንደር ሰፍሯል። መንግሥታዊ መዋቅሩን በመቆጣጠር የትግሬዎችን ጥቅም ለመጠበቅ በከባድ መሳሪያ የታጀበው ጦር፤ በፌዴራል ስም በአማራው ላይ ዘምቷል። አሁን የያንዳንዳችን አጀንዳ ለዚህ አማራን ለማጥፋት ለተነሳ ጦር፤ በጎንደር ዙሪያ የተነሳውን ተቃውሞ ከጎኑ መቆምና ማገዝ ነው። በቦታው ድርጅታዊ መሪነቱን የሚሠጥ አካል አለ። በቦታው በቆራጥነት ሕይወቱን ለመሥጠት ታጥቆ የተነሳ ክፍል አለ። ይህን መሪነት ተቀብለን፤ ጎድሏል የምንለውን በማሟላት እገዛ ማድረግ የኛ ኃላፊንት ነው። ይህ ብቻ ነው ድርጅታችን።

በመካከላችን እኔ እንዲህ ነኝ! አንቺ እንዲያ ነሽ! ብለን የምንወዳደርበት የቅንጦት ጊዜ የለንም። በውጪ ለምንገኝ አማራዎች በሙሉ፤ ጥያቄው አንድ ነው። ከወገናችን ጎን እንቆማለን ወይንስ አንቆምም? ነው። ሽማግሌዎቻችን ሲገናኙ፤ እኔ ልቅደም እኔ ልቅደም የሚሉት፤ ተጎንብሰው አንዳቸው የሌላቸውን ጉልበት ለመሳም ነበር። በመካከላችን አክብሮትና ቅድሚያን ለሌሎች መሥጠት አስተምረውናል። አሁንም ሌሎችን ምሩት እየተባባልን አክብሮት በመካከላችን እናስቀድም።

ውድ በግንቦት ሰባት በአባልነት የምትገኙ የአማራ ልጆች

ውድ በሁለቱ ኢሕአፓዎች በአባልነት የምትገኙ የአማራ ልጆች

ውድ በሸንጎ ውስጥ የምትገኙ የአማራ ልጆች

ውድ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ የምትገኙ የአማራ ልጆች

ድርጅት የሚመሠረተው፤ በድርጅቱ መርኀ-ግብር የተካተቱትን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ ነው። ያንን ከግብ ለማድረስ፤ በሕይወት መገኘት ቅድሚያ ግዴታ ነው። አማራው የሚጠፋበት ወይንም የሚኖርበት አጣብቂኝ ሰዓት ከፊቱ ተጋርጧል። አሁን ቃል ኪሳን ከገባችሁበት የድርጅታችሁ መርኀ-ግብር ይልቅ፤ የአማራው ሕልውና የላቀ ስፍራ አለውና፤ ለዚህ ተገዙ። በፖለቲካ አመለካከታችሁ ምርጫ ኖሯችሁ፤ ድርጅቶችን አወዳደራችሁና አመዛዝናችሁ የወደዳችሁትን ለመከተል፤ ቅንጦቱ አሁን የለም። የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የዘር ፖላቲካ ሥር ሰዶ፤ መሳፋፋት ብቻ ሳይሆን፤ አማራውን ለማጥፋት ሀ ብሎ የተነሳበት ዓላማ፤ አሁን የመጨረሻው ግብግብ ፈጦ ከፊታችን ተጋርጧል። ይህ በአጥር የተለየ ነው። እኔ አጥር ዘልያለሁ። በአጥር ላይ መቆም የለም። እሾሁ ይዋጋል!

ወልቃይት የትግሬዎች መንግሥት መቀበሪያ ነው። ለዚህ የሚደረገው ትግል ቀላል አይደለም። ይህ ትግል ግን ወሳኝ ነው። ሊዳከምና ለበረታ ይችላል። የኛ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው። የትግሬዎች መንግሥት፤ መንግሥታዊ መዋቅሩን በመጠቀምና ዲፕሎማቲካዊ ግንኙነቱን በመሳብ፤ የትግሬዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ የማያደርገው የለም። እናም አሁን ባለው አንጻራዊ ጉልበት፤ ብዙ ጉዳት ሊያደርስና ትግሉን ሊያጨልምብን ይችላል። ዋናው ቁምነገር ግን፤ የማይበርደውን ትግል በምንችለው ሁሉ፤ በአንድነት ተነስተን መርዳት ነው። መርፌ እየተወጋች የመከነችው ዘመዳችን፣ ከአዲግራት የተበላሸና መጣል ያለበት ውዳቂ መድሐኒት የተጋተው ዘመዳችን፤ ለትግሬዎችና ለሱዳን የተሠጠው ለሙ መሬታችን፣ ደንበራችን ተገፍቶ መሐከሉ ዳር የሆነበት መኖሪያችን፤ . . . እስከመቼ! እስከመቼ! እስከመቼ!

በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ መንግሥት የለም። የፌዴራልም የሚባል የለም። ያለው የትግሬዎች መንግሥት ነው። መንግሥታዊ መዋቅሩም የሚያገለግለው የትግሬዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው። እብሪቱ ካራሱ በላይ የዘለቀው ይህ የትግሬዎች ጉድን፤ በምንግሥቱ ስም ሳይሆን በአባይ ወልዱ ትዕዛዝ ነው የትግሬ ጦር ተልኮ ጎንደር ገብቶ የወልቃይት ኮሚቴ አባላትን አፍኖ ለመውሰድ የመጣው!

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የትግሬዎች መንግሥት ነው። ይህ የትግሬዎች መንግሥት ሕጋዊ አይደለም። ይህን የትግሬዎች መንግሥትና የትግሬዎች ጦር መዋጋት ትክክለኛና ግዴታ ነው። ለዚህ ደግሞ የተለያዩ ድርጅቶችና የተለያዩ ጦሮች አያስፈልጉንም። ስለዚህ በአንድነት አማራ ነን ብለን እንነሳ!

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live