Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አተት ዳግም በአዲስ አበባ ተከሰተ

$
0
0
file photo

file photo

(ዘ-ሐበሻ) “ውሃ በፈረቃ; ያውም ውሃ የመጣ እንደሆነ የቧንቧ ውሃው የሚፈጸው ጭቃ ነው:: ይህን አፍልቶ ለመጠጣት ደግሞ መብራት/ኤሌክትሪክ የለም” ይላሉ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ:: እንደነዋሪው አስተያየት “ሰው እጁን በየሰዓቱ ለመታጠብ ይቅርና ገላውን እንኳ በሳምንት እና ከዚያም በላይ የሚታጠበው ብዙ በሆነባት አዲስ አበባ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) በሽታ መከሰቱ አይገርምም” ይላሉ::

የአጣዳፊ ተቅማጥና ተውከት በሽታ በአዲስ አበባ ከታየ በኋላ በትናንትናው ዕለት በርካታ የአዲስ አበባ ሆስፒታሎች ውስጥ በርካታ ታካሚዎች በዚህ በሽታ መያዛቸው ቢገለጽም የመንግስት ጤና ጥበቃ ሚኒስተር ግን የታየው ሁለት ህሙማን ላይ ነው ሲል አስተባብሏል;;
የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) በሽታ በተለያዩ በዓይን የማይታዩ ጥቃቅን ተዋህሲያን አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን፣ ከንጽህና መጓደል በተለይም በተበከሉ ምግቦች፣ የመጠጥ ውሃና በሌሎች መተላለፊያ መንገዶች ከሰው ወደ ሰው በከፍተኛ ፍጥነት የሚተላለፍ ነው በሽታ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ::
በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ መብራትና ውሃ በፈረቃ ሕዝቡ ስለሚያገኝ በቅጡ ንጽህናውን ለመጠበቅ እንደሚቸገር የሚገልጹት ነዋሪዎች የአተት ዳግም መከሰት ነዋሪውን እጅግ እንዳሰጋው ገልጸዋል::


“ሳልሰማ ከሰደበኝ የነገረኝ አሳመመኝ”   ሁለት  (ግዜነው ደም መላሽ)

$
0
0

 

Tesfaye Gebreab
“ከሰጠሁት ጥቆማ በላይ ግን በሁለቱ መጽሃፍት- እነዚያን ጥቆማዎች ለማድረግ በተደረገ እንቅስቃሴም።…… እነዚህ ሁለት መጽሃፍት (የጋዜጠኛው ማስታወሻ እና የደራሲው ማስታወሻ ) ለመጻፍ ችያለሁ።እነዚህ ሁለት መጽሃፍት ያስገኙት የፖለቲካ ፋይዳ በአንድ ባለሙያ ማስጠናት ብቻ በቂ ነው። ያለፈውን ገድል በማንሳት ጉራ መንዛትም ብቻ ግን ዋጋ የለውም።ወደ ሚቀጥለው ተግባር መሸጋገር ያስፈልጋል።”  ይህ ጥቅስ “ጌዜ መስታወቱ”  በሚል እርህስ አለማየሁ መሰለ የተስፋዬ ገአብን ሰላይነት ካጋለጠበትና ከተስፋዬ  ማስታወሻ ላይ በእጅ ፅሁፍ ተከትቦ እባሪ ሆነ ከቀረበ ሰነድ ላይ የወሰድኩት ነው። መልክቱ ተስፋዬ ኤርትራ ውስጥ ላለ አለቃው የላከው ነው። ሙሉውን ከታች ያለውን ሊንክ በመክፈት ማንበብ ይቻላል።

http://www.ethiomedia.com/14store/tesfaye_gebreab_part_two.pdf

ወደኔው ሀሳብ ስመለስ ቁጥር “ሁለት”ን የተጠቀምኩት እርህሱን ከዚህ ቀደም ዘአበሻ ላይ ተመሳሳይ አስተያየት ለመስጠት ተጠቅሜበት ስለነበረ ነው። እ.አ.አ በየካቲቲ  17 /2016 ዓ. ም ገጣሚ በእዉቀቱ ስዩም ከአሜን ባሻገር በሚለውን መፀሐፍ ውስጥ በአባቱ  ከኦሮሞ የዘር ግንድ  እንደሚጋራ መግለፁን ተከትሎ ተስፋዬ ገ/አብ የገጣሚውን ቀደምት ስራዎች ከብሔርተኝኘት አንፃር ያየበትንና የአማራን ሕዝብ የዘለፈበትን ሀሳብ ለመሞገት ነበር። በውቀቱ በመፀሐፋ የግለሰቡን የፈጠራ ድርሰቶቻ ታሪካዊ ማስረጃዎችን እያጣቀሰ አፈር አልብሶአቸው ስለነበር ተስፋዬ ሀሳቦችን ይሞግታል ተብሎ ሲጠበቅ ለገጣሚው ስራዎች ምናባዊ ትርጉም በመስጠት ወደሚቀለውና ወደ ዋናው አጀንዳው ወደ ሆነው አማራን መዝለፍና ማንኮሰስ ቀይሮ ሲውተረተር በማየቴ ነበር ከላይ በተጠቀሰው እርህስ ሀሳቤን የገለፅኩት።

“መጥፎ ቁራኛ ካለመቃብር አይለቅም”  ነውና  ይህ ግለሰብ በምንም አይነት አጀንዳ ላይ ቢሆን የሚያገኘውን  መድረክ  የሚጠቀመው በዋናነት በእሱ አመለካከት የአማራን ስነ ልቦና ይጎዳል ብሎ የሚያምንበትንና በምናቡ የፈጠረውን ሀሳብ ለማስተላለፍ  ነው።ከዚህም ከፍ ሲል ደግሞ  በተግባር እንደምናውቀው በኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ውስጥ ጠላትነት ይፈጥሩ ይሆናል የሚላቸውን በማር የተቀቡ መርዝ ሀሳቦችን ለመርጨት ነው።

ኤርትራዊው ሰላይ ተስፋዬ  ገ/አብ እ. አ.አ ሰኔ 7/ 2016 ዓ.ም በዘሐበሻ ድህረገፅ ላይ “የግንቦት ፖለቲካ”  በሚል አንድ መጣጥፍ ለቋል። የመጣጥፉን መግቢያ ላነበበ ፀሀፊው በእርህሱ እንደገለፀው የግንቦት ወርን ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ጋር ያለውን ትስስር ለመተንተን ከፍ ካለም በገዢው መንግስት ውስጥ ያሉ አንዳንድ መረጃዎችን ለማካፈል የፈለገ ነው  የሚመስለው።  ነገር ግን ይህ የአማራና የኢትዮጵያ ጠላት የሆነ ግለሰብ ከተነሳበት አጀንዳ ጋር አንዳች ግኑኝነት የሌላቸው የተለመዱ ምናባዊ የፈጠራ ወሬዎቹን በመደርደር አጋጣሚውን የአማራን ሕዝብ ለመዝለፍ ተጠቅሞበታል።

የመጀመሪያው ሀሳብ እንዲህ ተብሎ ተቀምሯል።

“ አንድ ጊዜ ሰንገዴ ተብላ የምትታወቅ የኢህዴን ክፍለ ሰራዊት ከOLF ጋር ውጊያ ገጥማ ተሸነፈች። መሪዋ ተፈራ ካሳ የኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ነበር። በዚያን ጊዜ ገና የተዋሃደ ሰራዊት አልተቋቋመም። ሰንገዴ በOLF ተሸንፋ ከተበታተነች በሁዋላ ጄኔራል ሳሞራ በህይወት የተረፉትን ወታደሮችና መሪያቸውን ለግምገማ ሰበሰበ። እንዴት ሽንፈቱ ሊከሰት እንደቻለ ሰፊ ግምገማ ከተደረገ በሁዋላ ሳሞራ በጣም ስለተበሳጨ፣ “ሽንፈት የተከሰተው ተፈራ ካሳ ፈሪ ስለሆነ ነው። ችግሩ ይሄ ነው።” አላ ይለንና  ትንሽ መቀባቢያ ካከለ በኋላ ይወርድና መጨረሻ ላይ  “እውነት ነው የተናገርኩት። ልጨምርላችሁም እችላለሁ። አማራ ራሱ በተፈጥሮው ፈሪ ነው!!” አለ ብሎ ይደመድማል።

እኔ ላነሳው የፈለኩት ቁም ነገር ሳሞራ “አማራ በተፈጥሮ ፈሪ ነው”  ብሏል ወይም አላለም የሚል አይደለም። ሳሞራም ሆነ ድርጅቱ ህውሃት በአማራ ሕዝብ ላይ በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር ለቁጥር የሚታክቱ ግፎችን ፈፅመዋል። የኔ መከራከሪያ ተስፋዬ  በተደጋጋሚ  ይህንን ግለሰብ እየተጠቀመና ያለአንዳች ማጣቃሻ  “ሳሞራ አማራን አርቀን ቀብረነዋል” አለ  ሳሞራ ፣ “አማራ በተፈጥሮው ፈሪ ነው”  አለ   እና መሰል ሌላም ሌላም ድርሰቶችን እየደረሰ አማራ ላይ ቅርሻቱን እንዲተፋ መፍቀዱ ላይ ነው። ማንኛውም ሰው  (የኢትዮጵያ ጠላት መሆኑን ለሕዝብ ይፋ በሆነ በተጨባጭ ማስረጃ የተረጋገጠለትና በእኩይ ስራውም በሁለት ሕዝቦች መካከል ቋሚ የሚባል ሀውልት እንዲተከል ያደረገውን ኤርትራዊ ተስፉየን ጨምሮ)  ሀሳቡን በነፃት የመግለፅ ተፈጥሮአዊ መብት አለው የሚል መከራከሪያ ማቅረብ ይቻላል።በአንድ ነገር ላይ የራሱን አስተያየት መሰንዘር፣ በእድሜው በአካል ያለፈባቸውን  ልምዶቹን ለሌሎች ማካፈል፣ በወቅቱ ያለው ስርሀት እየተገበረ ባለው ፖሊሲዎችም ሆና ባጠቃላይ ስርሀቱን ደግፎም ሆነ ተቃርኖ ሀሳብ መስጠት፣ ዛሬ ከሚስተዋሉት ነባራዊ እውነታዎች ተነስቶ በመሰለውና በተረዳበት መልኩ ነገን መተንበይ፣ እና መሰለ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሀሳብን መወርወር ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ውስጥ  የሚከተቱ ናቸው።  ነገር ግና እንደኔ ግንዛቤ አንድ ግለሰብ እሱ ባልነበረበትና በሌላ አካል የተፈፀመን ድርጊት  ደጋግሞ አያነሳ የልብ ወለድ ድርሰት ሲፅም ፣ እሱ ባልነበረበት ትውልድ ተፈፀሙ የሚላቸውን ምናባዊ ፈጠራዎቹን ያለ አንዳች ማጣቀሻ ይዞ ሲቀርብ አሜን ብለን የምናስተናግድበት ጉዳይ ሁሌም የሚገርመኝ ነገር ነው።

ከላይ ወደ ተተረከው ድርሰት ልመለስ።  በመጀመሪያ በህውሃትና በኦነግ መካከል የተደረገ ጦርነት መኖሩን እኔ የምሰማው ለመጀመሪያ ግዜ መሆኑ ነው። እነዚህን ሁለት ፀረ ኢትዮጵያ ቡድኖች ያዋጋቸውን አጀንዳ አብሮ ቢያስረዳን ለግንዛቤ በጠቀመን ነበር። ህውሃትና ኦነግ ኢትጵጵያን ማፍረሱን በተመለከተ የነበራቸው አቋም አንድ አይነት ነበር። እነዚህ ቡድኖች በህውሃትና በኢህአፓ እንዲሁም በህውሃትና በኢዲዩ መካከል እንደነበረው የአላምም ሆነ በመታገያ ቦታ ሽሚያ ትግል ውስጥ የገቡበት ታሪክ ሰምቸም አንብቤም አላውቅም። ከተሳሳትኩ እታረማለው። እነዚህ ቡድኖች ተመጋጋቢ እንደነበሩና ኦነግ ሆነ ህውሃት የስልጠናና የስንቅ ድጋፍ ይደረግላቸው የነበረው በአባታቸው በሻብያ እንደነበረ እነሱም ደጋግመው የሚተርኩት ጉዳይ ነው። እንደውም ሌንጮ ለታ በቅርቡ እንደተናገረው ኦነግ ከሶማሌዎች በኩል ይደርስበት የነበረውን ጥቃት ለማስቀረት ሻብያዎቹ በአማላጅነት ዚያድባሬን መለመናቸውን ነው።

“ሰንገዴ”  ባብዛኛው ከከዱት ኢህአፓ አባላት የተቋቋመና በኋላም የቀድሞ ድርጅቱን ኢህአፓ እንዲሁም የትግል ወንድሞችን በህውሃት አጋዥነት የደመሰሰ  የኢህድን ሀይል   እንደነበር እውነት ነው። ነገር ግን ይህ የህውሃት ክንፍ ከኦነግ ጋር ስላደረገው ጦርነት የመኖሩ ጉዳይ እንግዳ ታሪክ ይመስላል።ሌላው ተስፋዬ  እንደሚለው ድርጊቲ የተከሰተው “የተዋሃደ ሰራዊት”  ከመቋቋሙ በፊትና ህውሃቶች ገና  ከነ ኢህአፓ ጋር የነበራቸውን ጉዳይ ከመጨረሳቸው በፊት ነው።  በዚህ ወቅት ደግሞ ተስፋዬ  ደብረ ዘይት ጭቃ እያቦካ ነበርና ታሪኩን እሱ በቦታው ተገኝቶ እንደሰማው በማስመሰል መዘገቡ የግለሰቡን የፈጠራ የተለመድ ተንኮል የሚያሳይ ነው።ቦታው ላይ የነበሩና በሕይዎት ያሉ ግለሰቦች ስለሚኖሩ ሊያርሙን ይችላሉ ብዬ እጠብቃለሁ።  ለማንኛውም  የዚህ ሀሳብ አላማ ሁለት ነው። አንደኛው እንደ ሁል ግዜው ሳሞራንም ሆነ ሌላ ምናባዊ የአማራ ሰዳቢ በመሳል አማራን የመስደብ ሱሱን ለመወጣት ነው።  ሁለተኛው ደግሞ በአማራ የተዋቀረውን የህውሃት ክንፍ ኦነግ በትግል መድርክ አሸንፎታል በማለት በሞጋሳ ዜግነት ላገኘበትና ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደ መሳሪያ ለሚጠቀምበት የኦሮሞ ማሕበረሰብን የስነ ልቦና ድጋፍ እያደረገ ለማስመሰል ነው።

ይህ የአማራና የኢትዮጵያ ጠላት የሆነ ግለሰብ በዚሁ መጣጥፉ ላይ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦና ይጎዳልኛል በማለት የተጠቀመበት ሌላው ስልት ደግሞ በአካል የሌለ  የ “አውሮፓውያኑ ሪፖርት” የሚልና በአውሮፖዊያን የተጠና ጥናት እንዳለ ለማስመሰል በመጣር ነው። ኤኔ ባለኝ መጠነኛ መረጃ የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ ካካሄደ በኋላ የአውሮፖ ሕብረት ሪፖርት ያወጣው አንድ ግዜ ብቻ ነው። በዚህ ሪፖርት ውስጥ ገዢውን መንግስ በመክሰስ ከተዘረዘሩት በርካታ ነጥቦች ዉስጥ በ E ውስጥ ከተቀመጠውና አማራን ከትግሬዎቹ ጋር የተቀሩትን ሕዝቦች ላይ ተፅእኖ እያደረሰ ነው ከሚለው የተሳሳተ ሀርግ ውጭ አማራን የተመለከተ ሌላ  እፀፅ የለም።  ሙሉውን ማንበብ ለሚፈልግ ሊንኩ እዚህ ይኛል።http://www.europarl.europa.eu/sides/getDoc.do?pubRef=-//EP//NONSGML+MOTION+P8-RC-2016-0082+0+DOC+PDF+V0//EN

ጠላታችን እንዲህ ብሎ ይጀምራል  “በአዲሳባ በምእራባውያን አገራት ኤምባሲዎች የሚሰሩ ወይም ዲፕሎማቶችን የሚያማክሩ በአብዛኛው የአማራ ልሂቃን መሆናቸው ይታወቃል። በቅርቡ ያየሁዋቸው ሰነዶች እንደጠቆሙኝ የአማካሪዎቹ ምክሮች በአብዛኛው ከኦሮሚያ አመፅ በሁዋላ “ጊዜ ያለፈባቸው” ተብለው ወደ መጋዘን ተልከዋል። አማካሪዎቹ ስለ ኢትዮጵያዊነት እና ስለ ፌደራል ስርአቱ ደካማ ጎን ሲያቀርቡ የነበረው መረጃ ከኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ጋር ያልተስማማ ሆኗል። አማካሪዎቹ ወይም ጥቆማ ሰጪዎቹ የሚያመጡት መረጃ ወደ መጋዘን ከመላኩ በፊት፣ “የውስጥ ፍላጎታቸውን ብቻ የሚያንፀባርቅ፤ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን እውነታ ያላካተተ” ተብሏል።”

በመጀመሪ በህውሃት የአገዛዝ  ዘመን በመንግስ ተቋማትም ሆነ በምእራባውያን አገራት ኤምባሲዎች የሚሰሩና ዲፕሎማቶችን የሚያማክሩ  አማራዎች ናቸው ብሎ ማለት የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁናቴ ከማያውቅ ደንቆሮ ሰው የሚጠቅ ድምዳሜ ነው። ይህንን ማረጋገጥ የሚያስችል አንድም ጥናታዊ ነገር የለም።መንግስታዊ ተቋማትን ትተን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ አለም አቀፍ ድርጅቶች ቅጥርን በተመለከተ እንዴት እየሰሩ እንዳለ በቅርቡ የጀርመን ኢምባሲ በግልፅ ለጥፎት የታየ ጉዳይ ነው።ትግረኛ ቋንቋን እንደ ዋና መስፈርት በግላጭ አስቀምጠው አይተናል። በታሪክም አፍሪካ ዉስጥ መቀመጫቸውን የሚያደርጉ የውጪ ድርጅቶች ከአምባገነን መሪዎች ጋር ሲሞዳሞዱ እንጂ በስርሀቱ ተጠቂ ከሆኑት ማሕበረሰብ ጋር ሲያብሩ አይስተዋልም።

ሌላው ተስፋዬ  በምናብ የበላዩነቱን የሰጣቸው ዲፕሎማቾቹን የሚያማክሩ የአማራ ሊእቃን “ስለ ፌደራል ስርአቱ ደካማ ጎን ሲያቀርቡ የነበረው መረጃ ከኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ጋር ያልተስማማ ሆኗል” ይላል። ስለየትኛዎቹ ደካማ ጎኖች እንደሚያወራ ባለውቅም  ከግለሰቡ ቀደምት ስራዎችና  አማራ አንድነት አቀንቃኝ ነው ከሚለው ብነሳ “የአማራ ሊቅአን ላላቸው የውስጥ ፍላጎታቸውን ብቻ የሚያንፀባርቅ”  ብሉ ለመግለፅ የሞከረው የኢትዮጵያ ሕዝብ  ህሃትና ኦነግ የተከሉትን አድሎአዊና ወጥነት የሌለው፣ መገንጠልንና የአገር መፍረስን የሚደግፍ ፌደራል ስርአት  እንደማይደግፈውና አንድነቱን እንደሚፈልግ ብለው የሰጡትን ሀሳብ ይመስላል።ስለዚህ ሊለን የፈለገውና እሱም ሆነ ለስለላ ያሰማራው መንግስት እንደሚመኙት ከዚህ በተቃራኒ ያለው የኦነግ ሀሳብ በ”አውሮፓውያኑ”  ተቀባይነት አግኝቶል ነው።

በመቀጠልም ወደ ዋናው አላማው ሲወርድ  “በተጨማሪ ሪፖርቱ “የህወሃት አመራር በአማራ ልሂቃን ላይ ያለውን ንቀት” ይጠቁማል። አማሮች በአማራነትም ሆነ በኢትዮጵያዊነት ጠንክረው መደራጀት አለመቻላቸውን፣ ወደፊትም ሊደራጁ ስለመቻላቸው እንደሚያጠራጥር፣ በመንግስት ስራ ላይ ያሉ አማሮች የህወሃት አለቆቻቸውን ንቀት መለማመዳቸውን ፅሁፉ በጥቅሉ ያነሳል። ንቀቱን በተመለከተ ከዚህ በላይ ዝርዝር ነገር አላቀረበም።”

እንግዲህ ይታያችሁ ይህ ግለሰብ “አውሮፓውያኑ”  ኢትዮጵያ ውስጥ ባደረጉት ጥናት መሰረት  “አማሮች በአማራነትም ሆነ በኢትዮጵያዊነት ጠንክረው መደራጀት አለመቻላቸውን፣ ወደፊትም ሊደራጁ አይችሉም”  የሚል ሪፖርት አውጥተዋል ነው የሚለን።ከሪፖርቱ ቀጥታ እንደቀዳው ለማሳየት ደግሞ በትምህርተ ጥቅስ ነው ያስቀመጠው።  ሪፖርቱ ተዘጋጅቶል የሚለን  በቅርቡ ኦሮሚያ ውስጥ ከተፈጠረው ተቃውሞ በኋላ መሆኑ ነው። ይህ ሀሳብ  በአንድ ግለሰብ የወቅቱን የኢትዮጵያን ሁናቴ በማጤንና በአማራው ማሕበረሰብ ዘንድ ተከስቷል የሚለውን  ዝምታ በመታዘብ እንደ ግል አስተያየት ቢሰነዘር ምንም ግምት ባልተሰጠው ነበር። ጉዳዩን  ሀሳብን በነፃነት የመናገር መብት በሚለው ውስጥ አካተን ሀሳቡን በሀሳብና በማስረጃ  በማስደገፍ ወደመሞገት ነበር የሚገባው።። ግለሰቡ ግን የግሉ ሀሳብ ሳይሆን የአውሮፖ ሕብረትን  በሚያህል ግዙፍ አካል ተጠንቶ የቀረበ ሪፖርት አድርጎ በማቅረብ ነው የስነ ልቦና ጦርነቱን የሚያካሄደው። ከዚህ ቀደም የምናውቀው “አንድ አባት እንዲህ አሉኝ” ፣ “ከሌንጮጋ ጅን እየጠጣን ስናወራ እንዲያ ብሎ ነገረኝ”፣ “የኦሮሞ ሕዝብ የልቡን ትርታ ብታዳምጡት እንዲህና እዲያ ነው የሚያስበው”  እና መሰል  የማጭበርበሪያ ስልቶችን ነበር የሚያቀርበው። አሁን እረቀቅ ያለ ስልት መሆኑ ነው የ“አውሮፓውያኑ ሪፖርት” የሚል ደመና ማስቀመጡ።

እኔ በዚህ ሀሳብ ላይ ማንሳት የምፈልገው ስለ አማራ መደራጀት መቻልና አለመቻል ጉዳይ አይደለም።ሲጀመር ይህ ጉዳይ የአማራ ጉዳይ እንዲ የአንድ ኤርትራዊ ሰላይ ሆድ የሚቆሥጥ ጉዳይ አይደለምና ። ሌላው የሞኝ ክርክር ነው የሚሆነው። ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ገናና ስም ከሚያሰጦትን አድዋን ከመሳሰሉ የታሪክ ድርሳናት ጀርባ ማን እንዳለ አሁንም የሕውሃትም ሆነ የኦነግ እራስ ምታት የሚሆናቸው ሕዝብ ማን እንደሆነ ሁሉም በሚገባ የሚያውው ጉዳይ ነው።  ተስፋዬንስ እንዲህ አቅሉን አስቶ የሚያስወተውተው ጉዳይ ምን ሆነና?? እርግጥ ነው የዛሬው ወንድም ወንድሙኑ የገደለበትንና ሀገርን ወደብና ድንበር አልባ እንዲሆን ያስቻለው የታሪክ ክፍል የአማራ የታሪክ ክፍል አይደለም። የሻብያ የህውሃትና የኦነግ ገድል ነው።እርግጥ ነው አማራ እራሱን በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር አድርጎ ሲንገታገት 25 አመታት ማለፋቸውና በዚህም ዋጋ እንደከፈለበት መሬት ላይ ያለ ሀቅ ነው። ይህ ማለት ግን እንደ ተስፋዮ ባሉ ባለጌዎች ኦሮሞን ለማጀገንና የአማራን ስነ ልቦና ለመጫን በአግባቡ ማጣቀሻ ባልቀረበበትን በምናባዊ ሪፖርት እንዲያላግጡበት መድረክ መስጠት አሳዛኝ ነው።

በኔ ትውልድ ከፊት መስመር ከምናውቃቸው ከሻብያ ፣ህውሃትና የኦነግ መሪዎች በተጨማሪ እንደ ግለሰብ በሕዝብ መካከል ከፍተኛ ጥላቻ እንዲፈጠርና ሀገር በማፍረሱ ሂደት ወሳኝ ድንጋይ ያቀበለ ሰው ካለ ይህ ኤርትራዊ ነው። አኖሌን ደርሶ በአካል ሀውልት እንዲተከል ያስቻለ መርዝ። ሌላው ግለሰቡ ኢትዮጵያን በበጎ ጎን የማያየው የሻብያ የስለላ አባል መሆኑ በነ አለማየሁ ምንም ጥርጥር በሌለውና በማያሻማ መልኩ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው።የአማራን ሕዝብ ለመዝለፍ ፣ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን አደጋ ውስጥ ለመክተት እንደትል ሳያንቀላፋ የሚተጋ እኩይ ፍጥረት። እና ይህ ግለሰብ በሰው ዘር ላይ በተፈፀመ ወንጀል በአለም ማሕበረሰብ የተከሰሰች አባት ሀገር ኤርትራ ዜጋ ሆኖ ፤ሕዝቤና ሀገሬ ለሚለው አካል የመፍትሄ ሀሳብ እንደማዋጣት የኛን ሕዝብና ሀገር እንዲያደማ መፍቀድ ይኖርብናል ትላላችሁ ወገን??  ምናለ በአንድ እባብ ደጋግማችሁ ባታስነክሱን??

ግዜነው ደም መላሽ

gizdemelash@gmail.com

 

 

 

በዛሬው የአዲስ አበባ ስታዲየም ብጥብጥ ከ50 ሰዎች በላይ ሲቆስሉ አንድ ሰው መሞቱ ተሰማ

$
0
0

addia ababa addis ababa stadium

ተመልካቾች የተጎዳውን ሰላማዊ ተመልካች ይዘው ወደ ህክምና ሲሮጡ

ተመልካቾች የተጎዳውን ሰላማዊ ተመልካች ይዘው ወደ ህክምና ሲሮጡ

 

 

(ዘ-ሐበሻ) “ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ብጥብጥ ነበር:: የቡና ደጋፊዎች የተመልካቹን አጥር በመዝለል ሜዳውን ወረውት ነበር:: ኢትዮጵያ ቡና ከሐዋሳ ከተማ ጋር ባደረጉት በዚህ ጨዋታ ላይ ተመልካቹ ዘሎ ሜዳ ውስጥ በመግባት ዳኞችን ለመደብደብ ሞክረዋል” – ይህ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ ነበር:: መረጃውን ለማጣራት ሞክረን የነበረ ሲሆን በዚህም መሰረት በዛሬው የአዋሳ ከነማ እና የኢትዮጵያ ቡና የአዲስ አበባው ስታዲየም ጨዋታ የ እግር ኳስ ሜዳ ሳይሆን የድንጋይ ድብድብ አውድማ ይመስል ነበር::

ቡና ከአዋሳ ያደረጉት ጨዋታ ሁለተኛው አጋማሽ በከፍተኛ ብጥብጥ ለአንድ ሰዓት ያህል ተቋርጦ 2ኛው አጋማሽ እንዲካሄድ ቢወሰንም ጥቂት እንደተጫወቱ የአዋሳ ከነማ ተጫዋቾች ጥሩ ስሜት አይሰማንም በማለታቸው ጨዋታው ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል::

እንደ አይን እማኞች ገለጻ ለዚህ ብጥብጥ መነሻ የሆነው ከዕረፍት በፊት አዋሳ ከነማ አስቻለው ግርማ ያስቆጠውን ጎል ተከትሎ የቡና ደጋፊዎች ጎሉ ከጨዋታ ውጪ (ኦፍሳይት) ሆና ዳኛው ጎሏን አጽደቀዋል በሚል አጥር ዘለው ወደ ሜዳ በመግባት ዳኞችን ለመደብደብ በመሞክራቸው ነው:: በዚህም የተነሳ የድንጋይ; የውሃ ጠርሙስና የወንበር ውርወራዎች ተደርገዋል:: በስታዲየሙ ጨዋታውን ለመታደም የነበሩ በርካታ ተመልካቾች የተፈነከቱ ሲሆን የአንድ ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ሕይወትም እንደጠፋ ተጠቁሟል::

በስታዲየሙ የነበረውን ብጥብጥ ለማርገብ ፌደራል ፖሊሶች እንዳቃታቸው የሚጠቁሙት የአይን እማኞች ሕዝቡ “አተኩስም ወይ ስራህ አይደለም ወይ” ሲሉ ሲቃወሙ ነበር:: ሆኖም ግን የተነሳውን ብጥብጥ ፌዴራል ፖሊሶች ለማብረድ ባለመቻላቸው ተጨማሪ ልዩ ኃይል እንደመጣ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

በዛሬው የአዲስ አበባ ስታዲየም ግጭት ከ50 በላይ ሰዎች ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ ሲደርስባቸው የአንድ ሰው ሕይወት በድብደባ ጠፍቷል::

ዳግማዊ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (ዳግማዊ መዐሕድ) ባለ 5 ነጥብ መግለጫ አወጣ

$
0
0

all amhara

መግለጫ

ቀን፡ 27-05-2016

የትግራይ ፋሺስቶችና ተባባሪወቻቸው በዐማራው ሕዝብ ላይ የሚያካሒዱትን የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት የግፍ ተግባር እስካላቆሙ ድረስ የዐማራ ሕዝብ ከሽብርተኛ፣ ከነፍሰ ገዳዮችና ከዘራፊ ኃይሎች ራሱን የመከላከልና የማዳን ሰብዓዊና ተፈጠሮዓዊ መብት አለው።

ፋሺስቱ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር ገና ከጅምሩ ጫካ የገባበትን ምክንያት በመዘርዘር በምኒፌስቶውና በተለያዩ ሰነዶቹ እንደመዘገበውና መሪዎቹም በተለያዩ አጋጣሚዎች በአደባብይ እንዳረጋገጡት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊ የሆነውን የዐማራ ነገድና ኢትዮጵያን ማጠፋት ቀዳሚ አጀንዳቸው አድርገው ነው።

በ 17 ዓመታቱ የጫካ ዘመናቸው በተመሳሳይ ጥላቻ የተለከፉ ነሰፍስ ገዳዮችን በመቀፍቀፍና የጥቅም ወዳጅነትና የጋራ ስምምነት በመፍጠር፤ ዐማራውን እየገደሉና እየዘረፉ ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር መብቃታቸውን ኢትዮጵያዊ ቀርቶ ዓለም የሚያወቀው ሐቅ ነው። ለዚሁ የዐማራ ጠላትነት ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚሆነውን ገንዘብና ቁሳቁስ ለማግኘት የዘየዱት፣ ያለምንም ሃፍረት ለኢትዮጵያ የታሪክ ጠላቶች የቆየ ዓላማ አስፈጻሚነት እራሳቸውን በቅጥረኝነት በማሳደር ነው። ይህንንም የተገበሩት በፈጠሩት ቡደናዊና ጎሳዊ የፖለቲካ ቁማር በማጭበርበር፣ ደላላነት፣ ቅጥረኝነት፣ ክህደትና ከፋፋይነት የመሳሰሉትን ማፊያዊ ድርጊቶች በመጠቀም ነው።

AAPO !!እደምናስታውሰው የወረራና የመስፋፈቱን ጦርነት ወደ መሃል አገር ሲለኩሱት በዐማራው መንደሮች ውስጥ በመግባት ከፈፀሟቸው ወንጀሎች ውስጥ ግድያዎች፣ አፈናና እስራት፤ ድብደባና ዝረፊያ፤ መንደር ማቃጠልና የእንሰሳት ሰርቆት የመሳሰሉት የእለት ከእለት ተግባራቸው ነበር።
የየዋሁን የዐማራ አርሶ አደር ወጣት ልጃገረዶች እየመለመሉ ለአረቦች የወሲብ ንግድ አሻግሮ በመሸጥ። ወንዶች ልጆቹን ለጥይት በመዳረግ። አባወራውን ዐማራ ተተኪ ትውልድ በማሳጣት የፈፀሙትን ግፍና ዘግናኝ ድርጊት ታሪክ በማይረሳ ሁኔታ መዝግቦታል።

ዐማራውን በማግለልና ጨርሶ በማጥፈት ላይ የመሰረቱትን የፖለቲካ ፕሮግራም ለመፈፀምና ለማስፈፀም የተጠቀሙበት ሌላው አቢይ ጉዳይ በአገር ውስጥ ተጨማሪ ፀረ-ዐማራ ግለሰቦችን በልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም በመደለል ዐማራውን የሚያጠፉ ቅጥር ነፍሰገዳዮችን ማደራጀት መቻላቸው ነው። የትግራይ ፋሺስቶች በዘመናት ታሪካችን ውስጥ ኢትዮጵያን እንደ አገር እንዳትቀጥል የሚፈልጉትን የታሪክ ጠላቶቻችንን ለማስደሰት የዐማራ ገዳይ ድል አድራጊነትን መፈክር ማሰማታቸውም አልቀረም። ለፈፀሙት ጀብዱ እንዲሆን የተፈቀደላቸው ነገር ቢኖር አሸባሪ ተፈጥሮቸውን በመደበቅ ያለ ተፈጥሮቸው ሰላማዊና አገር የሚመራ መንግስት በማስመሰል ከጌቶቻቸው እውቅናን ሠተዋቸዋል። በማንኛውም መልክ ያላቋረጠ ቁሳዊና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍም ለማግኘት በቅተዋል። አሁንም ይህ ሸፍጥና ተንኮል እንደቀጠለ ነው።
ነገር ግን የትግራይ ፋሺስቶችና አጋሮቻቸው ጨርሶ ሊደብቁት የማይችሉት ነገር ቢኖር ፤ በዘረኝነትና በዝቅተኝነት ስሜት አብደው በዐማራውና በሌሎች ኢትየጵያዊ ነን ባሉ ነገዶችና ማሕበረሰቦች ላይ የሚፈፅሙትን የእለት ከእለት የጥፋት ተግባራቸውን ነው።

በዓለማችን የተፈፀሙትን የሰው ልጅ ከፍተኛ እልቂቶች ከታሪክ ማህደር ስንቃኝ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይሁዶች በአዶልፍ ሒትለር የዘር ማጥፋት ፍጅት ተፈፅሞባቸዋል።

በጣሊያኑ ግራዚያኒ በኢትየጵያውያን ላይ በጭካኔው ወደር ያለተገኘለት ዓለማችንን ያሳዘነ ጭፍጨፋ አድርሷል። ሩዋንዳ ውስጥ የሁቱ ጎሳወች አንድ ሚሊዮን በሚጠጉ ቱሲወች ላይ የሚዘገንን ግድያና ዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመዋል።

የዘመናችን የትገራይ ፋሺስቶችና ተባባሪወቻቸው የዐማራውን ሕዝብ ቁጥር በማመናመን በሂደት ለመጨረስ በፈጸሙት ግልጽና ስወር የዘር ማጥፈት ተግባር፤ በብዙ ሚሊዮን በሚቆጠር የዐማራውን ሕዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲያልቅ አርገዋል።
በ 25 ዓመታት የስልጣን ዘመናቸው ዐማራውን ለይቶ የማጥፋቱ ፕሮግራማቸው ተሳክቶ፤ ዛሬ ከገደሉትና ካስገደሉት የተረፈውን ዐማራ የተባለ ኢትየጵያዊ ሰው፦

  •  በመላው አገሪቱ ውስጥ አገር የሌለው።
  •  ንብረቱንና ሓብቱን ማንም ባለ ጊዜ የሚቀማው።
  •  የተፈጠረበትንና የኖረበትን እርስቱን ተነጥቆ ከትውልድ ቦታው ላይ ማንም የሚያባርረው።
  •  በገዛ አገሩ ሐብት ማፍራት የማይችል።
  •  እንደ ሰው ህይወቱን በሠላም ለማኖር ያልቻለ።
  •  እንደ ዱር አራዊት እየታደነ የሚገደል።
  •  ስልጣንን መከታ በማድረግ ያገኘ ሁሉ በገፍ በእስር ቤቶች ውስጥ የሚያጉረው።
  •  በአሰቃቂ ሁኔታ በግፍ ተገድሎ ከገደል የሚወረወር።
  •  ወልዶ ለመሳምና ለማሳደግ እንዳይበቃ ተፈጠሮዋዊ ትውልድ የመተካት መብቱን የተቀማ።
  •  በልዩ ልዩ ወያኔ ሰራሽ በሽታዎችና ድርቅ በማለቅ ላይ ያለ ሕዝብ ነው።
  •  በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዐማራው የተለየ የፈፅሞ መጥፋት አደጋም

    የገጠመው አሳዛኝ ፍጡር ለመሆን በቅቷል።
    በአጠቃላይ በዚህ መግለጫ ውስጥ የትግራይ ፋሺስቶችና ግብረ አበሮቻቸው በዐማራው ላይ የፈፀሙትንና በመፈፀም ላይ ያሉትን የዘር ማጥፋት ሴራ አጠቃሎ ለማቅረብ እንደማይቻል ብንገነዘብም፤ ለመንደርደሪ ያህል ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት አመላካች ነጥቦችን በመጠቆም ወደ መግለጫችን መሠረታዊ ነጥብ እናመራለን።

    ዳግማዊ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት በአሁኑ ወቅት በዐማራው ሕዝብ ላይ እተፈፀመ ያለውን የፈፅሞ ማጥፋት ወያኔያዊ እብሪት የጥፋትና የዘር ማጥፋት ዘመች በቃህ መባል ስላለበት የሚከተሉትን ነጥቦች ለማመላከት ተገዷል።

  • የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን በፖለቲካ ፕሮግራሙ መሠረት ታላቋን ትገራይን ከዐማራ ቅኝ ገዥነት ነፃ አውጥቷል። ኢትዮጵያን አፍርሷል። ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የማጋጨቱን የቤት ሥራ አጠናቋል። የኢትዮጵያን ሐብትና ንብረት የግልና የወል ይዞታዎችን ጨምሮ ወርሷል። የፈለገውንም ዘርፎ ወደ ትግራይ አጓጉዟል። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የዐማራ መሬት ነው ብሎ በከለለው ቦታ ወራሪ ሰራዊቱና ደህንነቱ ምን እየሠሩ ነው? የሚለው ጥያቄ ወቅታዊና መነሳት ያለበት ጉዳይ ነው። ስለዚህ ትግስቱ ተሟጦ ሕልውናው አደጋ ላይ የወደቀው የዐማራ ሕዝብ በውስጡ ተሰግስገው የሚገሉትንና የሚያስገድሉትን የፋሺስት ትግሬ መሪወች፣ ሰላዮችና ገዳይ እሰኳዶችን በተገኘው የትግል ስልት ሁሉ ተጠቅሞ መንጥሮ የማስወጣት ሙሉ ኃላፊነት ስላለው፤ ይህን ተግባራዊ እንዲያደርገው ዳግማዊ መዐሕድ ጥሪውን ለመላው ዐማራ ሕዝብ ያቀርባል። በማንኛውም መልክ ከሕዝቡ ጎን ለመቆም ዝግጅቱን አጠናቋል።
  • በዐማራው ስም ተደራጅተው ያሉ ኃይሎች በሙሉ ዐማራው ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገበት ተባብሮ መሥራት ምርጫ ሳይሆን አስፈላጊ ነው። በተለይም በተለያዩ የዐማራው የመኖሪያ አካባቢዎች ሕዝቡ ማንነቱን ለማስከበር ያነሳቸውን ጥያቄወች በመደገፍና ከጉኑ በመቆም ዐማራውን ከፈፀሞ መጥፋት ለመታደግ ቆርጦ መነሳት አለበት። የዐማራው ልጆች አንድ መሆን በውጭም በውስጥም ተናቦ ተግባብቶና ተመካክሮ መሥራት።
  • ዐማራው ላነሳቸው አንገብጋቢ ጥያቄወች ሁሉ ምላሽ መስጠት እንደሆነ አድርጎ ዳግማዊ መዐሕድ ይመለከተዋል። ስለዚህ የወልቃይት ጠገዴ ወገናችን የዐማራ ማንነት ጥያቄና በሌሎች አካባቢወች ዐማራው የሚደርገውን የነፃነት፤ የህልውናና የኢትዮጰያዊነት ጥያቄዎች ማጠናከር አስፈላጊና ወቅታዓዊ ስለሆነ ለተግባራዊነቱ የትብብር ጥሪውን ለዐማራው ተወላጆች በሙሉና በዐማራ ስም አለን ለሚሉ ድርጅቶች ሁሉ ያቀርባል። በተለይም የዐማራ ወጣት የወገንህን ደም ያባቶችህ ታረክ ይጣራልና ምላሽ የመስጠት ታሪካዊ ግዴታ ወቅቱ ጥሎብሃል። መንገዱን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ አሳይተውሃልና ሳትቀደም መቅደም ይኖርብሃል።
  • ኢትዮጵያዊነት ለዐማራ ሕዝብ የመጀመሪያ የማንነቱ መግለጫና የህልወናው መሰረቱ በመሆኑ በአገሩ ጉዳይ ላይ አይደራደርም። እየደረሰበት ያለው ፈፅሞ የመጥፋት አደጋም በዚሁ ምክንያት እንደሆነ በማያሻማ ሁኔታ ይታወቃል። በእብሪተኛ ፋሽስት ወራሪ ትግሬዎች በሚደርስበት ግፍ ራሱን ከጥፋት መከላለከል የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ግዴታው በመሆኑ በሚወስዳቸው ራሱን የመከላከል እርምጃዎች ሰብዓዊነት የሚሰማው ሁሉ ከጎኑ ሊቆም ይገባል እንላለን። ይሁንና አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች ርቀው በመሄድ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ የዐማራውን እንቅስቃሴ በጎሰኝነት መስፈርት በመፈረጅ መዓት የሚነዙ መኖራቸውን ተረድተናል። ስለኢትዮጵያዊነትና አንድነት ለዐማራው ሕዝብ ማስተማር ወይም ለመንገር መሞከር ፌይዝ ወይም ድፍረት ነውና ይህ የወረደ ሃሣብ መቆም እንዳለበት ዳግማዊ መዐሕድ አጥብቆ ያሳስባል። ከላይ በመጠኑም ቢሆን ለመጥቀስ እንደሞከርነው በሠፊው መታወቅ ያለበት፤ የዐማራውን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ሚሰጥሩ ፍፁም ኢትዮጵያዊነቱና የአንደነት መሠረት በመሆኑ ነው። ዐማራው የአንድነቱን ኃይሎች ያጠናክራል እንጂ፤ የአንድነቱን ጎራ የሚንድና ጠር አይደለም። በታሪኩም ሆኖም አያወቅም። ወደፊትም አይሆንም።

    ለዚህም በርካታ ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል። ዐማራው በወያኔ የትግሬ ፋሽስቶችና አጋሮቹ በሚፈፀምበት ግፍ ተገዶ፤ እራሱንና አገሩን የማዳን ታሪካዊ ሃላፊነት እንደ ወድቅበት በማየት ዘግይተውም ቢሆን እንደ እሳት አደጋ ተከላካይ የተፈጠረውን መዐሕድና ሌሎች የዐማራው ስብስቦችን ብንመለከት ግባቸው ዐማራውን ከአጠላበት መጠነ ሠፊ አደጋ ማላቀቅና ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። ይዘው የተነሱት ዓርማም ቀደምት ኢትዮጵያዊያን በጋር የተዋደቁላትን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ነው። ቅኝታቸውና መዝሙራቸው ኢትዮጵያ ወይም ሞት ነው። ታዲያ ምኑ ላይ ነው የአንድነት ጎራውን ተቃዋሚ እንደሆኑ ተደርጎ የሚተቹት??? የሚለውን ጥያቄ ዳግማዊ መዐሕድ አጥብቆ እየጠየቀ።

    ይልቁንም በኢትዮጵያ አንድነት ስም ዐማራውንና የኢትዮጵያዊነትን ጥላቻ በኪሳቸው ደብቀው ከሚያዘናጉን ተኩላዎች፣ ታላቁና አርቆ አስተዋዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ መጠንቀቅ እንዳለብለበት ዳግማዊ መዐሕድ አበክሮ ያስገነዝባል።

    የትግሬ ፋሽስቶችና ተባባሪወቻቸው በዐማራው ላይ የሚያካሂዱትን የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ተግባር እስካላቆሙ ድረስ የዐማራ ሕዝብ ከሽብርተኛ ነፍሰ ገዳዮችና ዘራፊ ኃይሎች ራሱን የማዳን ሰባዓዊና ተፈጠሮዓዊ መብት አለው። በዚህ መሰረት ዐማራው በማንኛውም የትግል ስልት ተጠቅሞ ወራሪዎችን ከቀየው ነቅሎ ማስወጣት የመጀመሪያ ተግባሩ ነው።

    ስለዚህ አካባቢን ከትግሬ ፋሽስቶች አገልጋዮችና ቅጥረኞች የማጽዳቱ ተግባር በጥንቃቄና ስልታዊ በሆነ መንግድ በአፋጣኝ እንዲቀጥል ዳግማዊ መዐሕድ ጥሪውን ያቀርባል። በአንፃሩም ኢትዮጵያን እንወዳለን ለአንድነት ቆመናል የሚሉ ወገኖች ደግሞ ከዐማራው ሕዝብ ጎን እንዲቆሙ ያሳስባል።

    ወልቃይት ጠገዴ የዐማራውና የኢትዮጵያ የሕልውና መገለጫ ነው !!

    ዳግማዊ መዐሕድ

ለጠቅላላ እውቀት: ዓለማችንን በሕዝብ ብዛት የሚመሯት 30 ሃገራት ደረጃ

$
0
0

zehabesha facts

ደረጃ  ሐገር           ብዛት
1      ቻይና      1,355,692,544
2    ሕንድ       1,236,344,576
3    አሜሪካ    318,892,096
4    ኢንዶኔዥያ  253,609,648
5    ብራዚል     202,656,784
6   ፓኪስታን    196,174,384
7   ናይጄሪያ      177,155,760
8   ባንግላዴሽ    166,280,704
9   ሩሲያ          142,470,272
10   ጃፓን        127,103,392
11   ሜክሲኮ     120,286,656
12   ፊሊፒንስ   107,668,232
13   ኢትዮጵያ  96,633,456
14   ቬትናም    93,421,832
15   ግብጽ       86,895,096
16   ቱርክ       81,619,392
17   ጀርመን    80,996,688
18   ኢራን      80,840,712
19   ኮንጎ ዴሞክራቲክ 77,433,744
20   ታይላንድ          67,741,400
21   ፈረንሳይ          66,259,012
22   ብሪታንያ          63,742,976
23   ጣሊያን           61,680,120
24   በርማ             55,746,252
25   ታንዛኒያ           49,639,136
26   ደቡብ ኮሪያ        49,039,984
27   ደቡብ አፍሪካ     48,375,644
28   ስፔን               47,737,940
29   ኮሎምቢያ        46,245,296
30   ኬንያ             45,010,056

 

ምንጭ: CIA World Factbook | ሲ አይ ኤ ይህን ደረጃ ያወጣው በ2014 ነው:: ከዚያ በኋላ ያወጣው ደረጃ የለም::

ማሳሰቢያ ለጎንደር ዳባት ሕዝብ –“በመከላከያ ውስጥ የምትገኙ የውስጥ አርበኞች አንድ ነገር አድርጉ”

$
0
0

Dabat

ከሉዑል ዓለሜ

በ 2007 ዓ/ም የተደረገ የህዝብ ቆጠራዎች ሊስት እንደሚያመለክተዉ 145.509 ህዝብ በዳባት ይኖራል ከ1994 ዓ/ም ጀምሮ በ22% ህዝብ መጨመሩን መረጃዉ የሚያመለክት ሲሆን 73,852 ወንዶች 71,657 ሴቶች በዳባት ወረዳ የሚኖራሉ፣ ዳባት በ 1.187.93 ስኳር ኪ/ሜ ስፋት ላይ ትገኛለች በዳባት ወረዳ ዉስጥ 97.7 % ያህሉ ህዝብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ነው 2.4% ደግሞ እስልምና እምነት ተክለታዮች ናቸዉ።

የዳባት ህዝብን ለየት የሚያደርገዉ ነገር ቢኖር አትንኩኝ ባይና ከነኩትም የማይመለስ በመሆኑ ነው፡ ዳባት በሰሞኑ ከትግራይ ነጻ አዉጪዉ ቡድን ጋር በገጠመዉ አለመግባባት ምክንያት በብዛት ዱር ቤቴ ብሏል!

የሰሜኑ ጎንደር አይበገሬ ወረዳ ህዝብ ዳባት በደቡብ በኩል ወገራ የሚያዋስነዉ ሲሆን በምእራብ ታች አርማጭሆ እንዲሁም በሰሜን ምእራብ ጠገዴ እና በሰሜን ምስራቅ ደባርቅን ይዋህዳል ዳባት ክተት ካለበት ወቅት አንስቶ ለወያኔ ልዩ ኃይልና ለመከላከያ ሰራዊት የማይቀመስ በመሆን እንቅልፍ ነስቷል!

በመሆኑም ወያኔ የዳባትን ህዝብ ዙሪያዉን ለመክበብና ለመዉረር ከመከላከያ ሰራዊት በተላለፈ ትእዛዝ መሰረት እየተንቀሳቀሰ ነው በጠገዴና በደባርቅ እንዲሁም ከራስ ዳሽን ተራራ አካባቢ በሶስት አቅጣጫ ዳባትን ለማንበርከክ የወያኔ ሰራዊት ዝግጅቱን በማጠናቀቅ የአሰሳ መመሪያ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

በመሆኑም በማላዉ ዳባትና በዳባት ዙሪያ የሚገኙ የዉስጥ አርበኞች ወረራዉን ለመመከት በመከላከያ ሰራዊቱ ዉስጥ የሚቻላቸዉን እንደሚያደርጉ እያስጠነቀቁ ህዝቡ የበኩሉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አደራቸዉን አስተላልፈዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!


ወያኔ በዳባት ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል

የሙሉነህ ዮሐንስ ዘገባ

*ዳባት ከተማ ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ በታጠቁ ቅልብ የወያኔ ልዩ ሃይልና በፌደራል ሃይል ተወራለች።
*በዛሬው እለት ከፍተኛ ድብደባ ጉዳትና እስር በህዝቡ ላይ እየተፈፀመ ነው።
*በጥይት የቆሰሉ አሉ።
*ብዙ ወጣት ታስሯል…የተወሰኑትን ስም ዝርዝር ይዘናል…
*ትናንት በነበረው ስብሰባ የዳባት ወጣት ግልብጥ ብሎ ወደ አዳራሹ በመግባት መፈክር አሰምቷል በአዳራሹም መፈክር ለጥፏል። 25 አመት ያለ መንግስት ኖረናል አሁንም አንፈልጋችሁም ሂዱልን። ወያኔ ሌባ። ዳባት የጠላት ግንባር ብላችሁ ለስቃይ ዳረጋችሁን።
*ባቅራቢያው ያለችው የደባርቅ ህዝብ በነገው እለት ሰልፍ በመውጣት ለዳባት ህዝብ ድጋፉን እንዲገልፅ ወረቀት ተበትኗል። ውጥረቱ በጣም ተባብሷል።
*የጎንደር ከተማ ህዝብ በቅርብ እየተከታተለው ነው።
የወገኑን ጥቃት አይፈቅድም ጎንደሬ ጥንትም ሆነ ዛሬ።
*የታሰሩና በጥብቅ ክትትል ስር ያሉ የዳባት እንቁ ልጆች የሚከተሉት ናቸው ልንታደጋቸው ይገባል…
መታሰራቸው የታወቀ
1.ታጠቅ በቀለ
2.ጥላሁን አደመ
3.ፍሲል ደጌ ናቸው።
በጥብቅ የሚፈለጉትን የብዙ ወጣቶች ስም ዝርዝር ለደህንነታቸው ስንል አናወጣውም…

ለትግራይ ህዝብ መጥፎ አስተሳሰብ የትኛው ነው

$
0
0

tigray1) ጀነራል ሳሞራ ዮኑስ ‹‹ የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ ናቸው፡፡ ህወሓት ማለት የትግራይ ህዝብ ማለት ነው፡፡›› ብሏል
2) ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ‹‹የትግራይ ህዝብና ወያኔ (ህወሓት) የተለያዩ ናቸው፡፡ወያኔ (ህወሓት)ም ቢሆን ተጠቃሚና ተጠቃሚ ያልሆነ ተብሎ መከፈል አለበት፡፡›› ብሏል
የትኛው ሓሳብ ነው የሚገልፀን
አንድ ሰው ውስብስብ ነገሮች ለመረዳትና በደምብ አንጥሮ ለማወቅ ቅንነትና እውቀት ሊያስፈልገው ይችላል፡፡ይህ ለመለየት ግን አንዴ ማንበብ(መስማት) ብቻ በቂ ነው፡፡በደርግ ግዜም ቢሆን አንድ አልነበሩም ምክንያቱም ቤተሰቦቻቸው በህወሓት የተገደሉባቸው(የሚረሸኑባቸው) እኮ ነበሩ ግን በጣም ብዙ ሰው ህወሓትን ይደግፍ ነበር፡፡ጭራሽ አሁን ግን ምንም ግኑኝነት የላቸውም ማለት በሚሻልበት ግዜ አንድ ናቸው ማለት ለኔ ምን ታመጣላቹህ ብሎ መናቅ ይመስለኛል፡፡ እስቲ በምንድ ነው አንድ የሚሆኑት በአስተሳሰብ እምነት ወይስ በአኗኗር መቸም በአኗኗር ያለው ልዩነት ግልፅ ነው ልለፈውና ለአስተሳሰብ ቀላል ምሳሌ ልስጥ አሁንም ጭምር እንደመሪያቸው በሚያዩዋቸው በአቶ መለስ ዜናዊ ‹‹መስረቅ እስካልተያዙ ድረስ ስራ ነው›› ተብሏል ጀነራል ሳሞራ ዮኑስ ይቀበሉት ይሆናል የመለስ ራዕይ ተከታይ በመሆናቸው በጀነራል ሳሞራ ዮኑስ እናትና አባት ግን መስረቅ ታየህም አልታየህም ሓራም(የተወገዘ) ነው፡፡በአቶ መለስ ዜናዊ ቤተሰብም ቢሆን መስረቅ ታየህም አልታየህም እጅግ የተወገዘ ነው፡፡ አስተሳሰባችሁ ትንሽዋ ብዛት ቤተሰባቹም አንድ አታረግም ይቅርና የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ ሊያደርገን እንደውም እንደኔ እምነት ተጠቃሚዎቹም ቢሆኑ በሁለት መክፈል አለብን በህጋዊ የተጠቀሙና በህገ ወጥ የተጠቀሙ(ሙሰኞች) ብለን፡፡ ባጭሩ በትግራይ ህዝብና በህወሓት ያለው ግንኙነት በአማራ ህዝብና በኢህደን ያለው ግንኙነት፤በኦሮሞ ህዝብና በኦህዴድ ያለው ግንኙነት፤ በደቡብ ህዝብና በደኢህደን ያለው ግንኙነት ማለት ነው፡፡ለትግራይ

ጞኢቶም ፀጋይ

“እንደ ላስ ቬጋስ እና ሚኒሶታ ሁሉ ዛሬም ልዩ ምሽት በሲያትል ይኖረናል”–ኤፍሬም ታምሩ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ዘመን ከማይሽራቸው አንጋፋ ድምፃውያን መካከል አንዱ የሆነው ድምጻዊ ኤፍሬም ታምሩ በሰሜን አሜሪካ የጀምረውን “አማን ነው ወይ?” የሙዚቃ ጎዞውን ቀጥሎ ዛሬ ምሽት በሲያትል ልዩ የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚያቀርብ ከአዘጋጆቹ አካባቢ የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል::

በላስ ቬጋስ; በሚኒሶታና በኦሃዮ ከተሞች እስካሁን የተሳካ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን እያቀረበ የሚገኘው ኤፍሬም ከሲያትል ቀጥሎ በዋሽንግተን ዲሲ ከዝነኛው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ጋር የሙዚቃ ሥራዎቹን እንደሚያቀርብ ታውቋል:: ኤፍሬም የሰሜን አሜሪካ ጉዞውን እንዳጠናቀቀ ወደ ካናዳ ከዚያም አውሮፓ ይሄዳል::

እንደ ድምፃዊው ምንጮች ገልጻ ኤፍሬም በደቡብ አፍሪካ; በኬንያና በሱዳን የሙዚቃ ሥራዎቹን ለማቅረብ እየተነጋገረ ይገኛል::

ኤፍሬም ታምሩ ዛሬ ምሽት በሲያትል ከ8 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የሙዚቃ ኮንሰርቱን ሲያቀርብ ከአዘጋጆቹ እንደተገለጸው ቀድመው የወጡ ትኬቶች ተሽጠው እያለቁ ነው:: ኤፍሬም ሲያትል እንደደረስ ለአድናቂዎቹ ይህን መል ዕክት አስተላልፏል


በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን በዴዶ ወረዳ በሞሌ ቀበሌ በህዝብ ተቃውሞውን ቀጥሎዋል

$
0
0

በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን በዴዶ ወረዳ በሞሌ ቀበሌ በህዝብ ተቃውሞውን ቀጥሎዋል ። ህዝቡ በተቃውሞው ላይ የመብት ጥያቄዎቹን በመጠየቅ ቀጥሎዋል ። በዚህ ተቃዉሞ ከተሰሙት መፈክሮች የመልካም አስተዳደር ችግር አለብን የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሙስሊም በአል ላይ መደረጉን እንቃወማለን መንግስት ጊዜውን በአስቸኩይ ይቀይርልን ።

መንግስት መብታችንን ያክብርልን እ ናእጁን ከእምነት ያውጣ ሌሎችም ተቃውሞዎችን ሲያሰሙ እንደነበረም ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል ።

#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

13344810_1735651886706007_4387383092289860834_n 13450216_1735651893372673_2225181582845385919_n

በጀርመን አ.ግንቦት 7 የተሳካ ስብሰባ እያደረገ ነው |ሕወሓቶች በር ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ወጥተዋል

$
0
0
አርበኞች ግንቦት 7ን ለመደገፍ አዳራሽ ውስጥ የሚገኘው ህዝብ

አርበኞች ግንቦት 7ን ለመደገፍ አዳራሽ ውስጥ የሚገኘው ህዝብ

አርበኞች ግንቦት 7ን ለመደገፍ አዳራሽ ውስጥ የሚገኘው ህዝብ

አርበኞች ግንቦት 7ን ለመደገፍ አዳራሽ ውስጥ የሚገኘው ህዝብ

(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር በተገኙበት በጀርመን በርሊን ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ሕዝብ አዳራሹን ሞልቶ እየተመለሰና ከውጭ ሆኖ እየተከታተለ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከበርሊን ዘገቡ:: ባልተለመደ መልኩ የሕወሓት ኢምባሲ ሰራተኞችና ለትምህርት ወደዚያው የተላኩ የባለስልጣናት ዘመዶች “አርበኞች ግንቦት 7 የ እናት ጡት ነካሽ ነው” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮችን ይዘው ከአዳራሹ ፊት ለፊት ተቃውሞ እያሰሙ ነው::

አርበኞች ግንቦት 7 የጠራው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ እየተካሄዱ ነው ያሉት እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከውጭ የሕወሓት ሰዎች የትግራይ ክልልን ባንዲራ ይዘው በመቃወም ላይ ናቸው ብለዋል:: ‘የኢትዮጵያ ሕዳሴ በሕዝቦቿ እውን ይሆናል’; “አዲሲቷ ኢትዮጱያልማትን እንጂ ጦርነትን እና ሽብርን አትሻም” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮችን የያዙት እንዚሁ 15 የማይሞሉት ሰልፈኞች አርበኞች ግንቢት 7ን ለመደገፍ በሄደው ሕዝብ ድምፃቸው እንደተዋጠ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች ጠቁመዋል::

የበሊኑን ስብሰባ እንዳለቀ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን::

ግንቦት 7ን ለመቃወም ከውጭ የቆሙት የሕወሓት ኢምባሲ ሰራተኞችን እና የባለስልጣናት ዘመዶች

ግንቦት 7ን ለመቃወም ከውጭ የቆሙት የሕወሓት ኢምባሲ ሰራተኞችን እና የባለስልጣናት ዘመዶች

ግንቦት 7ን ለመቃወም ከውጭ የቆሙት የሕወሓት ኢምባሲ ሰራተኞችን እና የባለስልጣናት ዘመዶች

ግንቦት 7ን ለመቃወም ከውጭ የቆሙት የሕወሓት ኢምባሲ ሰራተኞችን እና የባለስልጣናት ዘመዶች

የ ስብከተ ወንጌል ገበሬው አባ ወልደትንሳኤ አያልነህ በኤጲስ ቆጶስነት ማእረግ ተሾሙ –በታምሩ ገዳ

$
0
0
“ኤጲስ ቆጶስ ሆይ ለማስተማር ትጋ፣የበደለውንም … ወደ ቤ/ክን መልሰው እንጂ…”ፍትሃ ነገስት

“ኤጲስ ቆጶስ ሆይ ለማስተማር ትጋ፣የበደለውንም … ወደ ቤ/ክን መልሰው እንጂ…”ፍትሃ ነገስት

ለሰበከተ ወንጌል መሰፋፋት እና ለሃዋሪያዊ ተልእኮ ሲባል ወደ ሰሜን አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አወሮፓ፣ ምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ፣ አወስትራሊያ ፣ኒውዚላንድ እና የመሳሰሉት አህጉራት እና አገሮች በመጓዝ በመንፈሳዊ ርሃብ እና ጉስቁልና የሚሰቃዩ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮችን በማጸናናት እና በማበረታት የሚታወቁት አባ ወልደትንሳአኤ አያልነህ ለከፈሉት መሰዋትነት እና በመከፈል ላይ ላሉት መንፈሳዊ እና ሃዋሪያዊ አገልገሎት በወጪ አገር የምትገኘው የኢ/አ/ተ/ቤ/ክ ሰሞኑን አዲስ የመንፈሳዊ አባትነት ሹመት እና ሓላፊነት አንደሰጠቻቸው ታወቀ።

ባለፈው እሁድ እ ኤ አ ሰኔ 5/ 20 16 በሎሳንጀለስ ከተማ በምትገኘው እና ኣባ ወልደተንሳኤ አብዛኛውን ጊዜያት በክህነት እና በሰብከተ ወንጌል የሚያገለግሉባት የድንግል ማሪያም የ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተካሄደው የቅዳሴ መረሃ ግብርን ለጥቆ የሰልጣነ ክህነቱ እና የምስራች ዜናው ለምእመናኖች በአውደ ምህረቱ ላይ የተበሰረ ሲሆን በእለቱ በ ስፍራው የነበሩ በርካታ መእመናኖችም እዲሱን የ እባ ወልድትንሳኤን ሹመት የደልዎ ወይም”አባታችን ይገባዎታል” በማለት ደሰታቸውን በእልልታ እና በጭብጨባ ገልጸዋል። ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት እንደተቻለው በ ስላጣነ ክህነት ዋስጥ ከፈተኛ ማረግ የሆነው አባ ወልደተንሳኤ የተሰጣቸውን የ ኤጲስ ቆጶስ ማእረግን እና ሃላፊነትን በመጪው ቅዳሜ ሰኔ 18 /2016 እኤ አ በካሊፎርኒያው ፣ኦክላንድ፣ በሚደረገው ልዩ መንፈሳዊ ፕሮግራም ላይ ታላላቅ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች እና ምእመናኖች ፊት በመቅረብ የሚሾሙ እና ተጥጨማሪ ሃላፊነቶችን የሚቀበሉ ሲሆን ከዚሁም ጋር በተያያዘ ኣባ ወልደትንሳኤ ከአለማቀፍዊ እና ሃዋሪያዊ ተልእኳቸው መልስ አብዛኛውን ጊዜያት የሚያገለግሉበት የሎሳንጀለስ ድንግል ማሪያም ቤተክርስቲያን መእመናኖች እና በርካታ የመንፈስ ልጆቻቸውም በከብረ በአሉ እና ሹመቱ ላይ ለመገኘት በኮንትራት እወቶቡሶች እና በግል መኪኖቻቸው በመጓዝ የክብረ በአሉ ታዳሚዎች እና የበረከቱም ተሳታፊዎች ለመሆን በዝግጅት ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከዚያም በሁዋላ የደንግል ማሪያም ቤተክርስቲያን እና ምእመናኖቿ ለብጹነታቸው ልዩ “የእንኳን ደስ ያሎት እና እንኳን ደስ ያለን የምስጋና መረሃ ግብር ” ከ ባአለ ስሜቱ በሁዋላ በቀጣዩ ሳምንት ማዘጋጀቷ ተገልጿል።

 

ኣባ ወልደተንሳኤ ቤተክርስቲያኒቱ እና ልጆቿ በሚፈልጓቸው ጊዜያት እና ቦታዎች “ደከመኝ ፣ሰለቸኝ” ሳይሉ ፣ ግላዊ ክብር እና ሙገሳን ሳይሹ በተጠሩበት እና የመምህራን እጥረት እና ክፍተት አለ ብለው በሚያምኑባቸው የአለም ዳርቻዎች በመጓዝ ሃዋሪያዊ ተልእኳቸውን ከሚወጡ ታዋቂ የወንጌል ገበሬዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ ቅዱስ መጽሃፍ እንደሚለው ሰጋ ለባሽ ሁሉ ሃጢያተኛ እንደ መሆኑ ሁሉ አንዳንዴ እርሳቸውን ጨምሮ ከካህናቶች በኩል ሰህተቶች ሲፈጸሙ በግንባር ቀደምነት ወጥተው የሚቃወሙ ፣የሚያወግዙ እና ይቅርታን የሚያስቀድሙ ፣በገሃዱ አለምም ቢሆን የህግ ጥሰቶች ሲኖሩ ፣ ደሃዎች እና ደካሞች ሲገፉ ዘር ቀለም ሳይለዩ ሁሉንም ወገኖችን የሚገስጹ መንፈሳዊ አባት ሰለመሆናቸው እንዲሁም ህገ ኦሪትን ከ ሕገ ወንጌል ጋር በማጣቀስ በቀልድ እና በምሳሌ መልክ የምእመናኖችን መንሰፈን እና ልቦችን በእግዜ አብሔር ቃላት የሚያረሰረሱ ታላቅ የወንጌል መምህር /ገበሬ እንደሆኑ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል።

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሃይማኖት እና ስርአት መሰረት የኤጵስ ቆጶስነት ሹመት የሚሰጠው አንድ አገልጋይ ሰለ ሃይማኖቱ፣ስለ እወቀቱ፣ስለ አኗኗሩ፣ስለ መልካም ምግባሩ በ መእመናኖች እና በጳጳስ ሲረጋገጥለት ብቻ እንደሆነ የቤተክርስቲያኒቱ ዋንኛ መተዳደሪያ የሆነው ፍተሃ ነገስት ይደነግጋል።የ አንድ ኤጵስ ቆጶስ ሃላፊነቱም ከ ብዙ በጥቂቱ “ኤጲስ ቆጶስ ሆይ ለማስተማር ትጋ።መጽሃፍትን ሁሉ ለመተርጎም ብትችል ህዝብህን ትምህርት አጥግባቸው።በብዙ ትምህርት ባለጠጎች ይሆኑ ዘንድ ከህጎችህ ብርሃን አብራላቸው።የበደለውን አውግዘህ ብትለየው በውጭ አትተወው ወደ ቤተክርስቲያን መልሰው እንጂ።የጠፋውንም ፈልግ።ስለ ሃጢያቱ ብዛት እድናለሁ ብሎ ተሰፋ የማያደረገውን በሁሉ ጠፍቶ ይቀር ዘንድ አትተወው።እንዲህም ኤጲስ ቆጶስ የሃጡን ሃጢያት ሊሸከም ይገባዋል።” ይላል።

በውጪ አገር የምትገኘው የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ሰሞኑን ለተለያዩ ታላላቅ መንፈሳዊ አገልጋዮቿ ሹመት እና ማእረግ እንደሰጠች የታወቀ ሲሆን ለአብነት ያህል አባ ሳሙኤል ከዲንቨር ፣አባ ጽጌ ከ ሎሳንጀለስ ቅድስት ማሪያም (ስላውስን አጥቢያ)፣አባ ሳሙኢል ከካንዳ፣ አባ ወልደተንሳኤ ከሎሳንጀልስ ድንግል ማሪያም(ሜን ስትሪት አጥቢያ) እና አባ ተሰፋሚካኤል ከብዙ በጥቂቱ ተጠቃሾች ናቸው ።ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በምእራብ አውሮፓ ሎንዶን ከተማ ወስጥ የሚኖሩ አቶ ያእቆብ አድማሱ ለዚህ ጸሃፊ እንደገለጹት “ በርካታ ታላላቅ አባቶች በእድሜ መግፋት እና በጤንነት መታወክ ምክንያት ከመደበኛ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው መስተጓጎላቸው የግድ በመሆኑ እና የቤተክርስቲያኒቱ ሃዋሪይዊት ተልእኮም እየተበራከተ እና እየተስፋፋ በመምጣቱ ሳቢያ ተጨማሪ እና አዳዲስ አገልጋዩችን መሾም እና ክፍተቱን መሙላት ተገቢ እና ለ ነገ የማይባል ጉዳይ ነው።” በማለት አሰታያየታቸውን ሰጥተዋል።

በሎሳንጀለሰ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በድንግል ማሪያም ቤ/ክ ለበረካታ አመታተ የተገለገሉባት እና በመገልገል ላይ የሚገኙት፣ በክርስትና ሰማቸው ቤተማሪያም የተባሉ አንድ ምእመን በበኩላቸው የእባ ወልደትንሳኤ መሾምን በተመለከተ ለዚህ ጸሃፊ በሰጡት አስተያየት ” አኛ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው አባታችን የደል ዎ /ይሁን ብለናል” በማለት ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን ሰለ አጠቃልይ የእምነቱ ተከታዮች በሰጡት የግሌ አሰተያየት ነው ባሉት ”ይህቺ በተከታዮቿ ብዛት ከሩሲያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተከታዮች በመቀጠል በአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምተገኘው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ከተመሰረተች ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ለትምህርት፣ ለፍትህ ፣ ለአንድነት እና ለመሳሰሉት አገራዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ፋና ወጊ በመሆን አስከ ዛሬው ትወልድ ድረስ ያደረሰች ታላቅ ባለውለታ የእምነት ተቋም መሆኗን በማንኛውም ወገን በኩል ለአፈታ እንኳን ሊዘነጋ አይገባም። ክብር ለሚገባው ክብር የመስጠት ባህል ሊለመድ ይገባል። የሃይማኖት አባቶችም ቢሆኑ ዘመን አመጣሹ ልዩነቶቻቸውን እና የመወጋገዝ ዘያቸውን ወደጎን በማድረግ ቤተከርስቲያኒቱ ስርእቷን እና ወጓን ጠበቃ ቀደምት አባቶች ሰለእምነታቸው ሲሉ የከፈሉትን መሰዋእትነትን ወደኋላ መልስ ብለው በመመልከት እና የቆሙበትንም ምድር በማጤን በ21ኛው ክፍለዘመን ውስጥ በሚደረጉ ማንኛውም እንቀሰቃሴዎች ላይ ግንባር ቀደም ሚና ተጫዋች እንድትሆን የማድረግ ታላቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው መገንዘብ ይኖርባቸዋል።” በማለት የታናሽነት ምክራቸውን ሰጠተዋል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

ሰበር ዜና: አክሱም ስታዲየም ፌደራል ፖሊሶች ተፈነከቱ –ሕዝቡ በድንጋይ ተከታከተ (ፎቶዎች ይዘናል)

$
0
0

aksum Tig aksum Tigrai 1 axum tigrai axum

(ዘ-ሐበሻ) በትግራይ አክሱም ስታዲየም ውስጥ በተደረገ የ እግር ኳስ ጨዋታ ደጋፊዎች ባነሱት ሁከት ፖሊሶችና በርካታ የስፖርት ደጋፊዎች ተፈነከቱ::

በአክሱም ስታዲየም የአክሱም ከተማ እና የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ እየደረገ ባለበት ወቅት ደጋፊዎች ባነሱት ሁከት የተነሳ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ ስታዲየሙ ሄልሜት ባጠለቁ ልዩ ኃይሎች መከበቡ ታውቋል::

በኢትዮጵያ ከፍተኛው ሊግ የሚጫወቱት ሁለቱ የትግራይ ክልል ክለቦች ደጋፊዎች ያነሱት ሁከት ላይ ተጫዋቾች ሳይቀሩ መፈንከታቸውና ደጋፊዎች በድንጋይ ሲከታከቱ እንደቆዩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም የቡና ደጋፊዎች ባነሱት ብጥብጥ ስታዲየሙ ላይ እና በሰዎች ላይ ጉዳት ከመድረሱም በላይ አንድ ሰው መሞቱን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

 

ለጠቅላላ ዕውቀት: ጥቂት ስለሰው ልጆች

$
0
0

zehabesha facts

  • የሰው ልጆች ልብ ለአንድ መቶ የመዋኛ ገንዳ የሚበቃ ደም በህይወት ዘመናችን ይረጫል::
  • አንድ እርምጃ ሲራመዱ ምን ያህል ጡንቻዎች እንደሚንቀሳቀሱ ገምተው ያውቃሉ:: 200 ያህል ጡንቻዎች በአንድ ነጠላ ርምጅ ይንቀሳቀሳሉ::
  • በሰው ልጆች አካል ውስጥ ሰባት ነጥብ ስድስት ሳንቲ ሜትር የሚረዝም ሚስማር ሊያሰራ የሚችል የብረት ክምችት አለ::
  • ከወንዶች የልብ ምት ይልቅ የሴቶች ይፈጥናል:: እንዲሁም የሴቶች አይን እርግብግቢትም ከወንዶች ይበልጣል::
  • የሰውልጆች97ሺህኪሎሜትር የሚረዝም የደምስር አላቸው::

    ምንጭ፡- Amazing Facts

ቴዲ አፍሮ 40ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ከወደቁትን አንሱ አረጋውያን ጋር ሊያከብር ነው | Updated

$
0
0
ቴዲ አፍሮ ከቤተሰቡ ጋር

ቴዲ አፍሮ ከቤተሰቡ ጋር

Updated | (ዘ-ሐበሻ) አንድናቂዎቹ “የኢትዮጵያ ሙዚቃ አብዮተኛ; የፍቅር ንጉሥ; የፍቅር መልዕከተኛ ወዘተ…” እያሉ የሚጠሩት ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ አፍቃሪዎቹ አስተባበሪነት እና አዘጋጅነት 40ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ከተቸገሩ አረጋውያን ጋር አብሮ ሊያከብር መሆኑ ተሰማ:: ለዘ-ሐበሻ የደረሱት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ቴዲ አፍሮ እነዚህ አረጋውያንን የሚረዱበት ማዕከልን ይረዳል::

ቴዲ አፍሮ 40ኛ ዓመቱን የሚደፍነው ሐምሌ 7, 2008 ዓ.ም ሲሆን ይህ በዓል የሚከበረው የወደቁትን አንሱ የአረጋውያን ማዕከል ውስጥ እንደሆነና ይህ ተቋም ከሚረዳቸው አረጋውያን ጋር እንደሆነ ታውቋል:: ይህን በዓል ያዘጋጁትና አስተባባሪዎቹም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የቴዲ አፍሮ አፍቃሪዎች ናቸው ተብሏል::

ይህን የልደት በዓል በማስመልከትም ለነዚህ አረጋውያን በቴዲ አድናቂዎች የተዘጋጀ ነገር እንዳለም ተሰምቷል::

ቴዲ አፍሮ 37ኛ ዓመቱን ያከበረው የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች በሚኒሶታ ባዘጋጁት የሙዚቃ ኮንሰርት ቀን መድረክ ላይ እንደነበር ይታወሳል::

በቴዲ አፍሮ ስም አድናቂዎቹ ይህን ያድርጉ እንጂ ቴዲ አፍሮ በተለያዩ ሰብአዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፏል:: ከዚህ ቀደም ካደረጋቸው በርካታ በጎ ተግባሮች መካከል የሰው ሕይወት አጥፍቷል በሚል በአሥር ቀናት ውስጥ በሞት እንዲቀጣ ወይም የነፍስ ዋጋ 700 ሺሕ ብር እንዲከፍል የፍርድ ውሳኔ ተላልፎበት፣ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ሙሉ ክፍያውን (700 ሺሕ ብር) ከፍሎ ያተረፈው ኢትዮጵያዊው አስመሮም ኃይለ ሥላሴ ገብረ ኢየሱስ ይጠቀሳል::

በተጨማሪም ቴዲ አፍሮ ታስሮ ከተፈታ በኋላ ወላጆቻቸውን ላጡ ህፃናት መርጃ የሚውል የሙዚቃ ኮንሰርት በአዲስ አበባ ስታዲየም አዘጋጅቶ ሙሉ ገቢውን ሰጥቷል:: በተጨማሪም ለአበበች ጎበና ህፃናት ማሳደጊያም በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ ሲያደርግ ነበር::

በሌላ በኩል ቴዲ አፍሮ አዲሱን የሙዚቃ አልበሙን እንደጨረሰና ይህም ሥራው ለኢትዮጵያ አዲስ አመት ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል::

 

አቶ አሰፋ ጫቦ -ምነው እስካሁን? –ይገረም አለሙ

$
0
0
አቶ አሰፋ ጫቦ

አቶ አሰፋ ጫቦ

ከአቶ አሰፋ ጫቦ ጋር ያስተዋወቀችን ተወዳጇ ጦቢያ መጽሄት ነበረች፡፡ በጽሁፋቸው አወኳቸውና በይበልጥ በሁለት ነገር ውዴታና አክብሮት በልቤ ታትሞ ቀረ፡፡ አንደኛው ጽሁፋቸው የሚነበብ ብቻ ሳይሆን የሚታይ መሆኑ ነው፡፡ ፊልም የማየት ያህል ነው፡፡ ማዕከላዊ የሚባለውን የግፍ ቦታ ለአጭር ግዜም ቢሆን ገብቼ ከማየቴ በፊት በአይነ ልቦናዬ የቃኘሁት ፤ጨንቻን በእግሬ ሳልረግጣት በፊት ያወቅኋት በአቶ አሰፋ ጽሁፍ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በዛ አባላሽኝ ዘመን ለሆነው ሁሉ ተጠያቂነታችን ይበዛ ያንስ ካልሆነ በስተቀር ማናችንም ነጻ አይደለንምና የድርሻ ድርሻችንን እንውሰድ በማለት (ቃል በቃል አልጠቅሼ ይሆናል) በየጽሁፎቻቸው ይወተውቱ የነበረው ነው፡፡ ያን ማድረግ ተችሎ ቢሆን ዛሬ የደረስንበት የውድቀት ደረጃ ላይ ባልተገኘን ነበር፡፡

ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ አልፎ አልፎ  በድረ-ገጾች ብቅ እያሉ ትውስታቸውን የሚያካፍሉን አቶ አሰፋ ሰሞኑን “ትቼው ረስቼው” በሚል ርዕስ የኢትዮጵያን የተቃውሞ ፖለቲካ ጎራ ርስተ ጉልት ስላደረጉት ኢ/ር ኃይሉ ፕ/ር በየነና ፕ/ር መረራ በጥቅል ትንሽ ግን ጥልቅ መልእክት ያለው ነገር ነገሩን፡፡ ስለ ፕ/ር በየነ ደግሞ ትንሽ ሰፋ አድርገው ትውውቃቸውን፣ የፕ/ር የሥልጣን ጥም ፣ፓርቲ አፍራሽነት ብሎም በወያኔነት መጠርጠር ነገሩን፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ምነው አቶ አሰፋ እስከ ዛሬ ያሰኘኝ፡፡ ፕሮፌሰሩ ይህን ያህል ዓመት በየግል ፓርቲዎችን ሲያብጡ፣ ህብረት በተባለበት ቦታ ሁሉ ፊጢ እያሉ ሲያሽመደምዱ አቶ አሰፋ ነጋሪም ኮርኳሪም ሳያስፈልጋቸው ለውጥ አመጣም አላመጣም ስለ ፕ/ር በየነ የሚያውቁትን በመግለጽ ማንነታቸውን በማጋላጥ የበኩላቸውን ማድረግ ነበረባቸው ብዬ አሰብኩ፡፡ ዛሬም ቢሆን የኢትዮጵያ ጉዳይ  እየባሰ እንጂ እየተሻለ አልሄደምና፣ ፕሮፌሰር በየነም የሁለትና ሶስት ፓርቲዎች ሊቀመንበር ከመሆን አልታቀቡምና፣መድረክን እግር ከወረች አስረውታልና ፤ ከሞት በመለስ ሥልጣን የሚለቁም አይመስሉምና ወዘተ አቶ አሰፋ የሚያውቁትን በተለመደው ግልጽነትዎና ድፍረትዎ ያካፍሉን፡፡

ስለ ፕ/ር በየነ ብዙ ተጽፏል፣የአቶ አሰፋ ግን ከሁሉ ሚዛን አንደሚደፋ እገምታለሁ፡፡በተጨባጭ ማስረጃ የሚገለጽ  የአይን እማኝነት ነውና፡፡ በፕ/ር በየነ ከተነገሩና ከተደረጉ አያሌ ነገሮች መካከል ሁለቱ ዘወትር ይገርሙኛል፡፡ አንደኛው  በአንድ ግዜ የብሔርም  የሕብረ ብሔርም ፓርቲ ሊቀመንበር መሆናቸውና የምርጫ ቦርድ ምሥክር ወረቀት ማግኘታቸው ነው፡፡ የብሄሩ የሀድያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሲሆን ሕብረ ብሔራዊዎቹ  ብዙ ናቸው፡፡ ሁለተኛው የቅንጅት አመራሮች ከእስር በተፈቱ ሰሞን ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል የጀመረው ደቡብ ህብረት ነው  ከዛ በኋላ ከበሮ በሰው አጅ ሲያዩት ያምር አንደሚባለው ብዙዎች እንገፍ እንገፍ ሲሉ አይተናል፣አንዳንዶችም እየሮጡ ወደ እስር ቤት ሲገቡ ተመልከተናል፡” ( ቃል በቃል አልጠቅሼ ይሆናል ) ያሉት ነው፡፡

አቶ አሰፋ የጠቀሱዋቸው የፕሮፌሰር መረራና የፕ/ር በየነ የአመታት ቁርኝትም የውስጥ አዋቂ ገለጻ የሚሻ ነው፡፡ ምክንያቱም ውጫዊ ሁኔታቸውን በቅርብ ለምናውቅ ሰዎች ሁለቱን እንዲህ ለአመታት በሊቀመንበርነት ቦታ እያፈራረቀ የሚያቆይ ሁኔታ የላቸውም፡፡ የውስጡን ግን አላወቅንም፣ ማወቅም አልቻልንም እናም አቶ አሰፋ የሚያውቁት ካለ ጀባ ቢሉን፡፡ ህብረት በተባለ ቁጥር ሰዉስ ርሳቸውን የሚመርጥበት ምክንያት ምን ይሆን?

ስለሁለቱ ካነሳሁ አይቀር አንድ ትውስታየን ላካፍል ምን አልባት አቶ አሰፋንም ለመኮርኮር ይረዳ ይሆናል፡፡ ትቼው ረስቼው ያሉትን ያካፋሉን የአቶ ግርማ ሰይፉ ጽሁፉ ኮርኩሮቸው እንደሆነ ነግረውን የለ፡፡

ግንቦት 1992 ዓም ነው፤ በኦብኮ አስተባባሪነት በኢተፖድኀ ድጋፍ ስምንት ፓርቲዎች ትብብር ለመፍጠር በኢየሩሳሌም ሆቴል ስብሰባ ተቀምጠዋል፡፡ ህብረቶችን ካለመራሁ የሚሉት ፕ/ር በየነ በዚህ ስብሰባ አልተጋዙም ነበርና ተሰብሳቢዎቹ ገና ከአዳራሽ ሳይወጡ የፖለቲካ ቁማር በማለት አውግዘው የተቃውሞ መግለጫ አወጡ፡፡ መድረኩን ያስተባበረው ኦብኮ (አሁን ኦህኮ ነው)  ሊቀመንበር ፕ/ር መረራ ጉዲና በዚህ ጉዳይ ላይ ጦቢያ መጽሄት ጠይቋቸው (ቁጥር 12/1992) የሰጡት ምላሽ ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ የሚል ነበር፡፡  “…በኢተፖድኀ አመራርና በዶ/ር በየነ መካከል፣ በዶ/ር በየነና በሌሎች የአማራጭ ኃይሎች መሪዎች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት በተከበረ ኢትዮጵያዊ የሽምግልና ባሕል እንዲፈታ ብዙ ጥረን ነበረ፡፡ በተለይ በምርጫ አካባቢ የተቀዋሚ ኃይሎች ኀብረት እጅግ በጣም አስፈላጊ ስለነበር ዶ/ር በየነ እመራቸዋለሁ የሚሉዋቸውን ድርጅቶች  በሙሉ ጋብዘን ነበር፡፡ ኢህአዴግ በሚያዘጋጃቸው ስብሰባዎች የለምንም ጥያቄ አቤት ብለው የሚሄዱት ዶ/ር በየነ እሳቸው የሚመሩት አማራጭ ኃይሎች በጋራ ስብሰባውን ካላዘጋጀ አልገኝም  ብለው የቅንጦት የሆነ የቴክኒክ ቅድመ ሁኔታ አቀረቡ፡፡ እሳቸው የሚመሩት አማራጭ ኃይሎች አዘጋጅ ከሆነ በዛ ያሉ ሌሎች ድርጅቶች ደግሞ የማይገኙ ስለሆኑብንና አማራጭ ስላጣን ስብሰባውን ስንቀጥል ደግሞ ያለ እኔ እንዴት ተሰበሰቡ በማለት ሕዝባዊ ኃላፊነት ከሚሰማው ተቀዋሚ የማይጠበቅ መግለጫ አወጡ፡፡ የሚገርመው ደግሞ እሳቸው የሚመሩት አማራጭ ኃይሎች ጸሐፊ ከእኛ ጋር ተሰብስቦ እያለ ከማን ጋር እንደጻፉና ማኀተሙን ከየት እንዳመጡ ባናውቅም መግለጫቸው ስብሰባ ላይ እያለን ደረሰን፡፡ ዶ/ር በየነ ለደቡብና ለተቀሩት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ምን እንደሚፈልጉ አንድ ቀን እውነቷን እስኪነግሩን ድረስና ተቀዋሚው ኃይል ለእሳቸው ቁመት የሚሆን ኀብረት ፈጥሮ እሳቸው እስኪታረቁን ድረስ ዝርዝር ሁኔታ ውስጥ መግባት ባንፈልግም ዶ/ር በየነ ለማን የፖለቲካ ጠቀሜታና ለምን ተልእኮ ደጋግመው በእኛም ድርጅት ላይ ሆነ በሌሎች ተቀዋሚ ኃይሎች ላይ ድንጋይ እንደሚወረውሩ ግራ እንደገባን ከኢትዮጵያ ሕዝብ መሸሸግ አንፈልግም፡፡ ….የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ ተቀዋሚ ኃይሎችን እየከፋፈለ ነው ለሚለው የዶ/ር በየነ በሬ ወለደ ተረት ሳንጨነቅና እላይ እናድስቀመጥነው ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ ነገ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተቃዋሚው ጎራ ማን የአምስተኛ ረድፍኛ ሚና እየተጫወተ እንዳለ በተግባር ሊታይ ስለሚችል ወደፊትም ጥረታችንን እንቀጥላለን፡፡”

የፕ/ር መረራ ጥያቄ ምላሽ ባያገኝም አምሰተኛ ረድፈኛው ቢያንስ ለህዝብ በይፋ ባይታወቅም ይህ ከተባለ  ወዲህ ሁለቱ በኢዴኃህ ሊቀመንብረነት ወንበር ላይ ተፈራርቀዋል፤ መድረክንም እየተፈራረቁበት ነው፤ ምስጢሩ ምን ይሆን?

በኢትዮጵያ ውስጥ  አዲስ ፓርቲ ለመመስረትም ሆነ ህብረት ለመፍጠር እንቅስቅሴ ሲጀመር በውስጥ ለውስጥ መንገድ ከወያኔ ሰፈር የምትተላለፍ መልእክት አለች፡፡ እገሌን ሊቀመንበር ብታደርጉት ተግባብተን ልንሰራ እንችላልን የምትል፡፡ ወያኔን በቅጡ ለሚያውቅ ይህች ነገር በምክር ብቻ እንደማትቆም ይረዳል፡፡ የሚፈልጉት ሰው ሥልጣኑን እንዲይዝ የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ተሳክቶላቸዋል ያልተሳካላቸውም አለ፡፡

ይህች ነገር አቶ አሰፋ በጽሁፋቸው ማጠቃለያ ላይ

“በየነ ጴጥሮስ እላይ በጨረፈታ ለማሳየት ለሞከርኩት ስራው መላውን አለም ደጋግሞ ዞሯልኮ! በዚህ 25 አመት ሙሉ የድርጅቶች መሪነቱ ምን ፈየደ? ምንስ ተናገረ? ምንስ ጻፈ ?የሚል ቢኖር ጉዱ ይፈላ ነበር። የሚል ሰው አለመኖሩ የበጀው መስለኝ። እንዳይኖሩ አድርጎ ይሆን?አሁን ግርማን ላከበት? አንዳንዴ ያኔ ከባንክ ገንዘብ ይዞ ጠፍቶ በኋላ የወያኔ አባል ሁኖ የገንዘብም ምክትል ሚንስቴር እንደሆነው ሰውዬ በየነ  ጴጥሮስም የወያኔ አባል ይሆን? እላለሁ  የኸው ለ25 አመት ያ ሁሉ ሰው ወህኒ ሲወርድ በየነ አለምን ይዞራል።” በማለት ከገለጹት ጋር ይዛመድ ይሆን! ረዥም እድሜ ከጤና ጋር ለአቶ አሰፋ ጫቦ ተመኘሁ፤ ከይር ያሰማን ፤ፍቅርና ሰላም ይስጠን፤

 

 


በኦሮሚያና ጎንደር የተወሰደው እርምጃ ተገቢና ተመጣጣኝ ነው ብለዉ አረፉት –ግርማ ካሳ

$
0
0

13406942_10209402620733222_1993397166186942191_nየሕወሃቱ አዲሱ ገብረእግዚአብሄር፣ የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ሆኖ፣ የወያኔን ሞቶ በሞቶ መሳቂያ የምርጫ ዉጤት ይፋ ያደረገ ሰው ነው። ከዚያም የሕወሃት ፖሊት ቢሮ ፣ ወደ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሃላፊ እንዲሆን አደረገው።

ለወራት በኦሮሚያና በሰሜን ጎንደር በተደረገው ሕዝባዊና ሰላማዊ ተቃዉሞዎች በሕወሃቶች ፣ በነመሐመድ(ሶሞራ) የነስ የሚታዘዙት ታጣቂዎች ከፍተኛ ኢሰብአዊ የሆነ የጭካኔ ተግባራትን በመፈጸም፣ አሮጊቶች፣ ሕጻናትን ሳይቀሩ መግደላቸው ይታወቃል። በጎንደር እና በኦሮሚያ በግፍ ሕይወታቸው ያለፉት ቢደመሩ፣ የሚታወቁት ብቻ ወደ ስድስት መቶ ይደርሳሉ።

ሆኖም አዲሱ ገብረ እግዚባሄር በፓርላማ፣ አይኑን በጨው አጥቦ፣ በሕዝቡ ላይ የተወሰደው እርምጃ ተመጣጣኝ ነበር ሲል ነው የተናገረው። የወያኔው ፋና እንዲህ ሲል ዘግቧል፡

“ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱም የተወሰደው እርምጃ ከተፈጠረው ሁከት እና ብጥብጥ አንጻር ተመጣጣኝ እንደነበር አረጋግጠናል ነው ያሉት።በኦሮሚያ ክልል አንዳንደ ቦታዎች የነበረውን ግጭት የፀጥታ ሀይሉ ገብቶ በያረጋጋ ኑሮ ሊደርስ የሚችለው ከዚህ የበለጠ ነበር ሲሉም ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።የተከሰተውን ሁከት እና ግጭት ለማሰቆም ክልሎች ለምን በራሳቸዉ ሃይል አልተጠቀሙም የፌደራል የጸጥታ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት የበለጠ ጉዳቱ ከፍ እንዲል አድርጓል የሚለው ትክክል አይደለም ሲሉም አቶ አዲሱ አንስተዋል”

አዲሲ ገብረ እግዚብሄር አጠናን ብሎ ያቀረበው ሪፖርት ፣ እንደ መርጫ ቦርዱ ዉጤት፣ የዉሸት ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በቀጥታ በሕወሃት ፖሊት ቢሮ ተጽፎ የተዘጋጀ ነው። ይህ ሪፖርት ህወሃት ምን ያህል በኦሮሚያና በጎንደር ለሚኖረው ህዝብ ፣ በዚያ ለሞቱትም ዜጎች ቅንጣት ያህል ደንታ እንደሌልውና ምንም እንደማይሰማው ያመላከተ ነው። ጀነራል አያሎም ሲገደል ሕወሃት ገዳዪን ይዞ ለፍርድ አቅርቧል። ሆኖም በኦሮሚያን ቦጎንደር ሰላማዊ ዜጎንች ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ፣ በጠራራ ጸሃይ በጥይት ሲቆሉ ግን፣ ተኩሰው የገደሉ ነፈስ ገዳዮችንና አዛዦቻቸውን ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ ግን ሽልማትና ቡራኬ መስጠቱን፣ “እነርሱ ባይንሮሩ ኖሮ ችግር ይፈጠር ነበር ጥሩ ነው ያደረጉት …” እያሉ ማወደሱን ነው የመረጡት።

ከዚህ በታች ያሉት የ74 አመት እናት ናቸው። በአጋዚ የተገደሉ። የ እኝህን እናት ሕይወት በግፍ የቀጠፉትን ነው እንግዲህ አዲሱ ገብረእግዚብሄር “ጥሩ አድርገዋል” የሚሉት።

‎ዩኒሴፍ‬ ታፍነው ከተወሰዱ ሕጻናት ውስጥ 88ቱ ተመለሱ አለ |የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0

ሰኔ 04 ቀን 2008 ዓ.ም. ዜና (June 11, 2016 NEWS)
‪#‎ዩኒሴፍ‬ ታፍነው ከተወሰዱ ሕጻናት መካከል 88 ቱ መመለሳቸውን አስታወቀ
‪#‎በአዲስ‬ አበባ የአተት በሽታ እንደገና አገረሸ ተባለ
‪#‎በሊቢያ‬ የአንድነት መንግስቱን የሚደግፉ ኃይሎች የሲርትን የወደብ አካባቢ ነጻ ያወጡ መሆናቸውን ገለጹ
‪#‎የኡጋንዳ‬ መንግስት በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ያሰማራቸውን ወታደሮች እንደሚያስወጣ ገለጸ
‪#‎ቦኮ‬ ሃራምን ለማጥቃት ናይጄርና ቻድ ተጨማሪ ወታደሮች ወደ ናይጄሪያ እንደሚልኩ ይፋ አደረጉ
‪#‎አልሸባብ‬ ለውጭ ኃይሎች የስለላ ተግባር ያካሂዳሉ ብሎ የወነጀላቸውን አራት ሰዎች መግደሉን ተናገረ

Gambela

  1. ዝርዝር ዜናዎች
    •   ባለፈው ሚያዚያ ወር የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ወደ ጋምቤላ በመግባት ወረራ አካሂደው 216 ሰዎችን መግደላችውና 136 ህጻናትን አፍነው መውሰዳቸው እንዲሁም ከ2000 በላይ የሚሆኑ ከብቶች መንዳታቸው ይታወቃል። የደቡብ ሱዳን መንግስት ባደረገው ድርድር የተወሰኑ ህጻናት ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ መቻላቸውም መዘገቡ ይታወሳል።የተመድ ሕጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ በበኩሉ ሐሙስ ዕለት በሰጠው መግለጫ በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ታፍነው ከተወሰዱ ሕጻናት 88 ቱ መለቀቃቸውን ያስታወቀ ሲሆን አብዛኛዎቹ ከ3 እስከ 5 ዓመት ባለ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ገልጿል። ሕጻናቱ በለጋ ዕድሜያቸው ግድያን በመመልከታቸው የሥነ ልቦና ችግር እንደተፈጠረባቸውና አምስት የሚሆኑ ሕጻናትም በተመጣጠነ የምግብ ዕጥረት ይሰቃዩ እንደነበርም ድርጅቱ ጨምሮ አስታውቋል። ቀደም ብሎ የወያኔ ወታደሮች ህጻናቱን ለማስለቀቅ ድንበር ጥሰው መግባታቸውን ይናገሩ እንጅ አንድም ያስለቀቁት ህጻን እንደሌለ ግልጽ ነው። ቀሪዎቹን 58 ህጻናት ለማስለቀቅ ድርድር መቀጠሉ ሲታወቅ በድርድሩ ለታጣቂዎቹ ስለሚሰጠው ክፍያ ግን የተሰጠ መረጃ የለም።
    •   አተት በመባል የሚታወቀው አጣዳፊ ትውከትና ተቅማጥ የሚያመጣው በሽታ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እንደገና ማገርሸቱ ታውቋል። የወያኔ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ሁለት ብቻ ናቸው በማለት መግለጫ ይስጥ እንጅ የታመሙት ሰዎች ከሁለት በላይ መሆናቸው ይገመታል። የአተት በሽታ ከተራ የጤና ጉድለትና ከእንክብካቤ አለመኖር የተነሳ የሚዛመት መሆኑ ሲታወቅ በተለይም በአዲስ አበባ ውስጥ ባለው የውሃ ዕጥረት ምክንያት የተሟላ ንጽህና የማይቻል በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑ የታወቀ ነው።ንጽህናቸውን ባልጠበቁ ዕቃዎች

የዝናም ውሃን በማጠራቀምና በመጠቀም በሽታው በቀላሉ ሊስፋፋ እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ገልጸው ሁሉም ዜጋ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ይመክራሉ።

  •   በሊቢያ የአንድነቱን መንግስት የሚደግፉ ታጣቂዎችና ሚሊሺያዎች ከተከታታይ ከባድ ውጊያዎች በኋላ የሲርትን ከተማ የወደብ አካባቢ ከአይሲስ ቁጥጥር ያላቀቁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሲርትን ከአይሲስ ቁጥጥር ስር ለማላቀቅ ጦርነት የተከተፈተው ባለፈው ወር መጀመሪያ ላይ ሲሆን ተከታታይ ጦርነተቶች ከመደረጋቸውም በላይ በተለይ ባለፉት ሁለት ቀናት የአይሲስ የእዝ ማዕከል በሆነው በኦጋዲጉ ኮንፈረንስ ሴንተር ላይ የተቀነባበረ የአየርና የምድር ጦር ጥቃት ሲደረግ የቆየ መሆኑ ይታወቃል። የአጥቂው ኃይል ቃል አቀባይ በሰጠው መግለጫ ዋና ዋናዎቹ የአይሲስ መሪዎች አምልጠው ወደ በረሃ የገቡ መሆናቸው ገልጾ በርካታ የአይሲስ ወታደሮች ግን አሁንም በአንዳንድ የከተማዋ ቦታዎች መሽገው የሞት የሽረት ውጊያ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጿል። ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ከአይሲስ ወታደሮች ለማስለቀቅ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተገልጿል።
  •   በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ተቋም ስር በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ተሰማርቶ የነበረውን ጦር ለማስወጣት እቅድ የወሰነ መሆኑን የኡጋንዳ መንግስት አስታውቋል። በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ተሽሽጎ የነበረውን የሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ የተባለውን የአማጽያን ቡድን ለመደምሰስ የተሰማራው የኡጋንዳ ጦር በቁጥር 2500 የሚደርስ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የአማጽያኑ እንቅስቃሴ በመዳከሙና ለኡጋንዳ ጸጥታ አስጊ ባለመሆኑ ጦሩ ወደ አገሩ እንዲመለስ የተወሰነ መሆኑንና ውሳኔውንም ለአፍሪካ ህብረት ማስታወቁን የኡጋንዳ ወታደራዊ ቃል አቀባይ በሰጠው መግለጫ አብራቷል። ሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ የሚባለው የአማጽያን ቡድን መሪ በሰው ዘር ማጥፋትና በጦርነት ወንጀሎች በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት የሚፈለግ ሲሆን በአሁኑ ካፊያ ኪንጊ በተባለውና በሱዳን በደቡብ ሱዳንና በማዕካላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወሰን ላይ በሚገኘው የሱዳን ግዛት ውስጥ ተደብቆ እንደሚኖር ይገመታል። ድርጅቱ በ1970ዎቹ አመታት የኦጋንዳ መንግስትን ለመቃወም የተመሰረተ የጎሳ ቡድን ሲሆን ሕጻናትን አስገድዶ በወታደርነት በማሰልፍና ሴቶችን ለፍትወተ ስጋ ባርያ በማድረግ ወንጀል ሲፈጽም የነበረ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል።
  •   የናይጄርና የቻድ መንግስታት ቦኮ ሃራምን ለመዋጋት ተጨማሪ ወታድሮች ወደ ናይጄሪያ ለመላክ ማቀዳቸውን የናይጀር የመከላከያ ሚኒስትር ገልጸዋል። ሚኒስትሩ ጨምረው እንደገለጹት የሚላኩት ወታደሮች የተለያዩ ተልእኮ የሚፈጽሙ ከመሆናቸው በላይ በሶስቱ አገሮች ወሰን ላይ ወታደራዊ ቁጥጥሩን ለማጥበቅ ይረዳሉ ብለዋል። ምን ያህል ሊሆኑ እንደሚችሉ እና መቸ እንደሚሰማሩ ባይገልጹም የታለመው ግዳጅ ግቡን እስኪመታ ድረስ እንደሚቆዩ ተናግረዋል። በቅርቡ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በናይጀር ውስጥ ተከታታይ ጥቃት ከማድረሳቸውም በላይ ቦሶ በተባለው ወታደራዊ ካምፕ 26 ወታደሮች መግደላቸው ይታወቃል።
  •   በውጭ መንግስታት ተቀጥረው የስለላ ተግባር እያካሄዱ ነው ያላቸውን አራት ሰዎች መግደሉን አልሸባብ በድረገጽ አማካይነት ባስተላለፈው ዜና ገልጿል። እርምጃዎችን የወሰደው በቤይ እና በባኩል የሚገኘው የእስላማዊ ፍርድ ቤት አካል ነው የሚል መረጃም ጨምሮ አሰራጭቷል። ለአሜሪካንና ለኬኒያ መንግስታት ሲስልሉ ነበር የተባሉት ሶስቱ ሰዎች የተገደሉት በጥይት ተደብደበው ሲሆን የአልሸባብ መሪ የነበረበትን ቦታ ለአሜሪካን ወታደራዊ ተቋም በመጠቆም በድሮን ጥቃት እንዲገደል አድርጓል የተባለውና መሀመድ አዳን ኑር ሀሰን በሚል ስም የሚጠራው ግለሰብ በስለት ታርዶ ተገድሏል። በአፍሪካ ህብረትና ሰላም አስከባሪ ጦር እርዳታ የአልሸባ እንቅስቃሴ ተዳክሟል የሚል አስተያየት በተደጋጋሚ የሚሰጥ ቢሆንም በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቡድኑ እንቅስቃሴ አንሰራርቶ እየተጠናከረ መሆኑ ይታያል።፡

Public Meeting with Dr. Berhanu Nega, Dallas , TX, June 25th

$
0
0

9cd1f964-cd9d-4d1c-ab4d-7b4511811806

Public Meeting with Dr. Berhanu Nega, Dallas , TX, June 25th

20 የሚሆኑ የሕወሓት ደጋፊዎች በአውስትራሊያ ኢትዮጵያዊውን የመንግስት ተቃዋሚ ደበደቡ |ቪዲዮ ይዘናል

$
0
0

Feyissa Australia
(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት የሚመራው መንግስት በሜልበርን አውስትራሊያ የጠራውን ሕዝባዊ ሰብሰባ ለመቃወም ከወጡ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ 20 በሚሆኑ የትግራይ ተወላጅ የሕወሓት መንግስት ደጋፊዎች ደበደቡት:: ኒውስ 7 የተሰኘው የአውስትራሊያ የመረጃ ቴሌቭዥን የተጎጂውን ኢትዮጵያዊ ፊት በደም ተለውሶ አሳይቶታል::

ሰሞኑን በአውስትራሊያ የቆዩት የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ; የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድርና የሶማሊያ ክልል አመራሮች የተገኙበትን ይህን ስብሰባ እንዳይካሄድ እንዲሁም በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሰብ አዊ መብት ጥሰት እንዲቆም ከጠየቁት መካከል በፎቶግራፍና ከታች በቭድዮ የምትመለከቱት ወጣት መደብደቡ በዲያስፖራው ውስጥ ያለውን በተለይ የሕወሓት ደጋፊዎች እና የሌሎችን ኢትዮጵያውያን ልዩነት የበለጠ ያሰፋዋል ተብሎ ተሰግቷል::

በሕወሃት ደጋፊዎች በአውስትራሊያ የተደበደበው ወጣት ስሙ ፈይሳ እንደሚሰኝና የትውልድ ክልሉም ኦሮሚያ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመልከታል::

ኢትዮጵያውያኑ ተቃዋሚዎች በሕወሓት መንግስት ወኪሎች ላይ የከረረ ተቃውሟቸውን ከማቅረባቸውም በተጨማሪ የአውስትራሊያ መንግስት ይህንን በሰብ አዊ መብት ጥሰት; በግድያና በ እስራት የሚታወቀውን መንግስት እንዳይተባበርና እንዳይረዳ ጠይቀዋል::

ይህ ሕወሓት የጠራው ስብሰባ በሕዝቡ ብርቱ ተቃውሞ መቋረጡም ታውቋል::

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በዶፍ ዝናብ የተነሳ ተቋርጦ ለነገ ተላለፈ

$
0
0

ethiopia
አጭር መረጃ: ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከጋና አቻው ጋር በኬፕኮስት ስታዲየም የመልስ ጨዋታ ነበራቸው:: ሆኖም ግን በኬፕኮስት በጣለው ዶፍ ዝናብ የተነሳ ጨዋታው ለነገ ተዘዋውሯል::

በጋና ኬፕኮስት ስታዲየም የጣለውን ዶፍ ዝናብ ተከትሎ ሜዳው እጅጉን መጨቅየቱን እና ለነገ እንዲተላለፍ የተወሰነው የጋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የአፍሪካ ፉትቦል ኮንፌዴሬሽን ተወካዮች ሜዳውን ከመረመሩ በኋላ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል::

ወጣት በብሔራዊ ቡድናችን ኢትዮጵያ ላይ በተደረገው የመጀመሪያው ጨዋታ ጋናን 2ለ1 ማሸነፉ ይታወሳል::

መልካም ዕድል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live