Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

“በሻአቢያም ይሁን በህወሓት/ኢህአዴግ የሚካሄድ የመብት ረገጣ ሁላችንንም ሊያሳስብ ይገባል”–ሸንጎ

$
0
0

ሸንጎ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያወጣው ጽሁፍ

በአንድ ከባቢ የሚኖሩ ሰዎች ድንገት ሰፈራቸው በእሳት ጋይቶ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ፣ምናልባት ብንድን ብለው ወደሌላ አቅጣጫ ካለው ሰፈር ለመጠለል ሲሮጡ፣ ከዛኛውም ሰፈር እንደዚሁ እሳት ተነስቶ ኑሮ፣ ብዙ ሰዎች ወደዚህኛው ሰፈር ሲገሰግሱ መሃል ቦታ ላይ ተገናኙ። ከመካከላቸው አንዱ የእኛ ሰፈር በእሳት ጋይቶ ለመጠለል ወደ እናንተ ሰፈር እየመጣን እናንተ ደግሞ በእጥፍ ቁጥር ወደእኛ እየገሰገሳችሁ ነው፡፡ ለመሆኑ የደረሰብንን ጉዳት ሰምታችሁ እሳቱን ለማጥፋት ነው ወይስ እኛን ከመንገድ ላይ ተቀብላችሁ ልታስተናግዱን ነው ይኸ ሁሉ ሰው የመጣው? ብሎ የወዲያኛውን ሰፈር ኗሪ ጠየቀ። የተጠየቀውም ሰው ግር ብሎት የእሳቱ መነሳት እንዴት ከእናንተ ጆሮ ደረሰ? ለማጥፋት ልትተባበሩን ነው የመጣችሁት? ብሎ በመገረም መልሶ ጠየቀው።

shengo

ሁሉም ግራ ተጋቡና የየራሳቸውን ሰፈር መቃጠል እያነሱ ሲጨቃጨቁ በመገረም የሚያስተውሉ አንዱ አረጋዊ ሰው፤ምነው ወገኖቼ ተደማመጡ እንጂ! ሁለታችሁም እኮ እሳት ያባረራችሁ የእሳት በደለኞች ናችሁ። እንዴት መደማመጥ ይሳናችዃል? አንዳችሁ የሌላውን መቃጠል መረዳት ተስኗችሁ የእኔ ሰፈር ነው የተቃጠለው፣ የአንተ ሰፈር ሰላምና ከእሳት ነጻ ነው፤ መባባል አመጣችሁ? አንዱ የአንዱን መቃጠል መቀበልና ማወቅ እንዴት ይሳነዋል? ሰው ወዶ ቤቱንና ሰፈሩን አይለቅም። እሁለታችሁም ሰፈር እሳት አለ፣የሁለታችሁም ቤት እየጋየ ነው።እሳት እሳት ነው። አንዱን አጥፍቶ ሌላውን አይምርም።እሳት አንዱን የሚያቃጥል ሌላውን የሚያበርድ አይደለም።በሁለታችንም ሰፈር የተነሳውን እሳት የለም ብሎ መካድ ከለኮሰው ጋር ተመሳጥሮ ጉዳትን አለማወቅና አለመቀበል ነው። እሳት ሁላችንንም እያጠፋ ቤት ንብረታችንን እያወደመ ነው። ይልቁንስ አንድ ላይ ሆነን የለኮሰውን እንፈልግና ለሕግ እናቅርብ፤ ለወደፊቱም እሳት እንዳይነሳ ማገዶ ከሚሆን እንጨት የተሻለ ቤት ለመስራትና ከአደጋው ለመገላገል መላ እንምታ በማለት በሳል አስተያየትና ምክር አቀረቡ።

እኛ ኢትዮጵያውያንና ቀደም ኢትዮጵያውያን የአሁኑ ኤርትራውያን ሕዝቦች በምንኖርበት አገር የሰፈኑት አምባገነን ስርዓቶች የሚፈጁ እሳቶች ናቸው። ሁላችንም የሚፈጽሙት ግፍና በደል ሰለባዎች ነን፡፤ሁላችንም በተመሳሳይ አምባገነንና ጸረ ዴሞክራሲያዊ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች በሆኑ፣ ተደጋጋፊ ስርዓቶች ውስጥ  የምንማቅቅ፣ ለስደት የተዳረግን፣ አንድ አይነት ፍላጎት፣ ታሪክ፣ ባህል፣ እምነት መልክ፣ ስም ስነልቦና ያለን ዜጎች ነን።

ሁለቱ አምባገነን ስርዓቶች በሚቆጣጠሩት መሬት ውስጥ ለሚኖረው ሕዝብየሚያቃጥሉእሳቶችናቸው። የእነዚህንስርዓቶችክፋትናበሕዝብ ላይ የሚያደርሱትን በደል መካድና እንደ በጎ አድራጊ መቁጠር፣ወይም አንዱን በማርከስ ሌላውን በማንገስ ወይም በማወደስ ፣የራስን በደል እያጎሉ የሌላውን ሕዝብ ስቃይ እንደሌለ መካድ በሰው ቁስል ላይ እንጨት እንደመክተት ይቆጠራል። ለማይረባ ጥቅም ሲሉ ሌላውን መሰል ሕዝብ አሳልፎ መስጠትና ችግሩን አለመገንዘብ በታሪክ ያስጠይቃል። ከጠላት የበሉት በሶ፣ ይወጣል ደም ጎርሶ እንደሚባለው ፣ሕዝብ ከጠላው ስርዓትና መሪ ጋር አብሮ መቆም ሲገረሰስ አብሮ መጨፍለቅ እንደሚሆን ማሰቡ ብልህነት ነው። ከአንድ ሕዝብ ከጠላው መሪና ስርዓት ጋር ከመሰለፍ ከሕዝብ ጎን ቆሞ በደሉን ቢያውቁለት የተሻለናበድልማግስትየሚያኮራይሆናል። ከማፈርናአንገትከመድፋት ያድናል።

በተመሳሳይ ደረጃም ለጥቂት ጊዜአዊ ጥቅም ሲሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውህወሃትመራሹንአምባገነንስርዓት ዴሞክራቲክአድርጎማቅረብና በኤርትራ መሬት ላይ ላለፉት ሃያ አምስት ዓመት በፈላጭ ቆራጭነት በስልጣን ላይ የተቀመጠውን የሻእብያ መንግሥትና መሪ ዴሞክራትና አርቆ አሳቢ፣ ለሕዝብ ተቆርቋሪ አድርጎ ማቅረብ የሚያስተዛዝብ ጉዳይ ነው።

እነዚህን የሕዝብ የመከራ ምንጭ የሆኑትን አምባገነን ስርዓቶች በህዝብ ላይ የሚያደርሱትን ግፍ መካድ፣ ብሎም ለነሱ ድጋፍ መስጠትና

ያልሆኑትን ናቸው እያሉ መካብ የዓለም ሕዝብ የሚያውቀውን እውነት መካድ ማለት ነው።
ከኢትዮጵያና ከኤርትራ በየቀኑ በቀይባህርና በሜዲትራንያን ባሕር አደጋን ለመጋፈጥና ካሉበት ኑሮ የነጻነት ሞትን መርጠው የሚሰደዱትን እንደ ቅንጡ አገር ጎብኝ በመቁጠር ከአገራቸው የሚያባርራቸው ምክንያት የሆነ መንግሥትና ስርዓት የለም ብሎ ማቅረብ ነው።

በሁለቱም አምባገነኖች የሚረገጡት ሕዝቦች የጋራ ችግር አለባቸው፤ ያም የመልካም ስርዓት አለመኖርና ቀና መሪ አለመኖር ነው። አለዚያማ  እንዴት ሰው አገሩን፣ ወገኑንና ቤተሰቡን ጭምር ጥሎ ለመድረሱ ዋስትና በሌለው መንገድ ወደ ማያውቀው አገር ይሰደዳል?፣ድህነት ነው ቢባልም፣ድህነቱ በምን ምክንያት ተፈጠረ ብሎ መጠየቅ ይገባል። ለዚያ ደግሞ መልሱ ከስርዓቱ ጋር የተያያዘ ሆኖ ይገኛል።

የኢትዮጵያና የአሁኗ ኤርትራ ሕዝብ አብሮ በአንድ አገር ልጅነት ለዘመናት ኖሯል፡፤ወደፊትም መልሶ ሊኖር ይችላል።በሕዝብ የሚመረጥ፣ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ ፣ሕዝብ የሚያቀራርብ ስርዓት እንዲሰፍን፣ አብሮ ለመኖር የሚያስችለውን ፍላጎት እንዲዳብር የሚሻ ዜጋ አሁን ከሕዝቡ ጎን ይቆማል እንጂ ከጨቋኝ ጋር አይሞዳሞድም። ለአምባገነኖች ድጋፍና እውቅናም ሰብሳቢም አሰባሳቢም አይሆንም።

በሁለቱም ሕዝቦች ላይ የተጫኑትን ጨቋኝና አምባገነን አገዛዞች ለውጦ አሳታፊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመመስረት፣ በርግጥም የህዝብን ልዖላዊነት እውን ለማድረግ፣ በሁሉም በኩል ያሉ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች በጋራ በመቆምና በመተባበር የህዝብ ወገንተኛነታቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሸንጎ) አመለካከት በኤርትራና በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩት ዜጎች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች ናቸው፣በስልጣንም ላይ ያሉት አምባገነኖች እንደዚሁ።

ሁለቱም ሕዝብ በማራራቅና በማለያየት ስልጣን ላይ የተቀመጡት አምባገነኖች ዕድሜ ሲያጥር ካለፍላጎታቸው ተገደው የተለያዩት የሚቀራረቡበትና በሰላም
የሚኖሩበት ዕድል ይፈጠራል ብሎ ያምናል።የሁሉንም ችግር ለመፍታት የሚያስችል ስርዓት እንዲመጣ በህብረት መታገል ተገቢ ነው ብሎ ያምናል እንጂ ለትንሽና ጊዜያዊ ጥቅም ሲል ህዝብን አሳልፎ አይሰጥም።

ህወሃትና ኢሕአዴግን የሚደግፉ ኤርትራውያንም ሆኑ ሻብያንና ኢሳያስን የሚደግፉ ኢትዮጵያውያን ማሰብ ከሚገባቸው ነገር ውስጥ አንዱ የህዝብ መሰረታዊ መብት መከበር ከጊዚያዊ የፖለቲካ ድግፍ ማሰባበብ ባለፈ ሁኔታ ሊታይ የሚገባው ክቡር ጉዳይ እንደሆነና በመንገዳገድ ላይ ያለው የነዚህ አምባገነኖች ስርዓት ሲወድቅ ምን ይደርስብኝ ይሆን? የእኔ ተግባር ሕዝብ ሊያራርቅ ወይም ሊያቀራረብ ይችላል ወይ?ብሎ መጠየቅና መንገዳቸውን ማስተካከልና ማረም እንደሚኖርባቸው ነው።

በየቦታው ያሉ አምባገነኖች በህዝብ ጣምራ ትግል ይወገዳሉ!! የአንዱ ጭቁን ሕዝብ በደል ለሌላው ጭቁን ሕዝብ በደሉ፣የአንዱ

ጭቁን ሕዝብ ድልም ለሌላው ጭቁን ሕዝብ ድሉ ነው። በአንድነት፣ለአንድነት!!!

ሽንጎ


የአጥር መፍረስ የሚያስትለው ጦስ –ማስተዋል በለጠ (አዲስ አበባ)

$
0
0

“ቤት ያለ አጥር፣ ጥርስ ያለ ከንፈር (አያምሩም)” ይላል – ቱባው ኢትዮጵያዊ የሥነ ቃል ትውፊታችን፡፡ ግሩም አባባል ነው፡፡ በተለይ ሁለንተናዊ ዕድገታችን እየጫጫ በሚሄድበት የኛይቷን በመሰሉ ሀገራት ከአንድም ባለፈ ሁለትና ሦስት አጥርም ቢኖር ለደኅንነታችን ዋስትና አስተማማኝ ነው፡፡ ቢያንስ ቢያንስ መንግሥት ከሚባለው ህግ አልባ ወምበዴ ውጪ የሚያጠቁንን ተራ ሌቦች ይከላከልልናል፡፡ አጥርን በፊት ለፊት ትርጉሙ ካየነው ማለቴ ነው፡፡

capped_privacy_fenceጥርስንም ካለ ከንፈር ማሰብ አንችልም፡፡ የገጠጡ፣ የወላለቁና የተሰባበሩ ጥርሶች ገመናቸውን የሚከትላቸው ከንፈር ነው፡፡ እናንተም እንደምታውቁት የከንፈር ጥቅም ከዚህም ያልፋል፡፡…

አነሳሴ ስለአጥርና ከንፈር መግለጫ ለመስጠት አይደለም፡፡ ምሣሌያዊ ንግግሩን ተመርኩዤ ግን አንዳንድ ሀገራዊ ጠቃሚ ነጥቦችን ማስታወስ እፈልጋለሁ፡፡ ጊዜ ያለው ለ5 ደቂቃ ያህል አብሮኝ ቢጓዝ  በምድርም ባይሆን በሰማይ ዋጋውን አያጣም፡፡

አንድ ማኅበረሰብ እንደማኅበረሰብ እንዲኖር ብዙ አጥሮች ያስፈልጉታል፡፡ ከተራው ግለሰብ ጀምሮ ሀገር ምድሩን እስከሚሞላው ሕዝብ የሚባል የአንዲት ሀገር ዋና ሀብት ድረስ አንዱ ከሌላው ሳይደርስ፣ ባልተገባ ጠብና ግጭት ምክንያት የመኖሪያ ቀዬና አካባቢ ሳይደፈርስ ሁሉም በሰላም እንዲኖር የተለያዩ አጥሮች አሉ ወይም ሊኖሩ ይገባል፡፡ እነዚያ አጥሮች ከፈረሱ ወይም በቅጡ ካልተበጁ የሚያስከትሉት ጦስ ሀገርን እስከመበተን ሊያደርስ ይችላል፤ ይህም ትንሹ ጦስ ነው፡፡ ከዚያም ባለፈ በሦርያና ከቅርባችንም በሶማሊያ እንደምናየው ያለ ዘላቂ ጭፍጨፋና ዕልቂት የባህል ያህል ተተክሎ ዜጎች ሲንከራተቱ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

አጥሮቹ ምን ምን ናቸው? እንዴትና በማንስ ይገነባሉ? ለምንና በማን ሊፈርሱ ይችላሉ?

አጥሮች በመልክም በይዘትም ይለያያሉ፤ ግንባታቸውም የዘመናት ማኅበረሰባዊ ተራክቦዎችን የሚጠይቅ ሲሆን አስፈላጊነታቸውም አብሮነትን ማስተሳሰር የሚያስችል መጣብቅ መፍጠር ነው፡ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ኖሯቸው ከተገነቡ በአብዛኛው በቀላሉ የመደርመስ ዕድላቸው አነስተኛ ነው፡፡ ነገር ግን አጥሮች ተገንብተው ሲያበቁ እኩል መጠን ያላቸውን ፍጡራን በእኩል ደረጃ የማያስገቡ ወይ የማያስወጡ ከሆኑና ይህ አሠራራቸው በተገልጋዮች ዘንድ ከታወቀ አድሎኣዊ እንደሆኑ ይቆጠርና ህገወጥነት ህጋዊነት ይሆናል፤ አጥሮቹም ምንም እንኳ ተገትረው ቢታዩ ማንም የሚጥሳቸው ውሽልሽል አጥር ይሆናሉ፡፡የሚያከብራቸውም ሆነ የሚፈራቸው አይኖርም፡፡ ኑሯቸው የላንቲካ ዓይነት ይሆንና ‹ከጅ አይሻል ዶማ‹ ወይም ‹የአህያ ባል ከጅብ አያስጥል› እየተባሉ በማኅበረሰቡ ዘንድ ይተቻሉ፡፡ ቀስ እያለም አጥርነታቸው ይቀርና በ“እነማን ነበሩ” መዝገብ ተዛውረው ወደመረሳቱም ሊያዘነብሉ ይችላሉ፡፡ እንዲህ ያለ ሁኔታ ሠለጠነ በሚባለው ዓለም በስፋት ይስተዋላል፡፡ እኛ ሀገር ጥርዥ ብርዥ የሚሉ ሃይማኖትን መሰል ትውፊቶች በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት ወደታሪክነት የመቀየራቸው አዝማሚያ የዚህ ነባራዊ ሁኔታ ውጤት ነው፡፡ …

በሀገራችንም ሆነ በሌላው ዓለም ዜጎች ተከባብረው እንዲኖሩ ለማስቻል ሃይማኖት እንደ አንድ ዋና አጥር ሆኖ ለዘመናት ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሔርን ወይም ፈሪሃ አላህን እያነገሠ ዜጎች ለክራቸው ወይም ለአንድ የሚያምኑበት ልዕለ-ሰብዕ የሆነ ኃይል እንዲገዙና ከሞት በኋላ ሕይወት እንደሚኖር በዚያም ሕይወት ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው በዚህ ምድር የሚከናወነው የጽድቅ ወይም የኩነኔ ተግባር እንደሆነ በማሳመን ሰዎች ተጠንቅቀው እንዲኖሩ ሃይማኖታዊ መጻሕፍቱና ቀሣውስትና ሼሆቹ እምነቶቹን በየምዕመኖቻቸው አእምሮ ያሠርጻሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት አካሄድ ሣይንስን መሰል ምድራዊ የምርምር ተቋማትና ኢ-አማንያን ባይቀበሉትም ሕዝቦችን በፍቅርና በመተዛዘን አስተሳስሮ በማኖር ረገድ ያለው ጉልህ ድርሻ ግን ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ አጥር ፈረሰ ማለት ደግሞ አንድ ልጓም ተበጠሰ ማለት ነውና ሰዎች የለዬላቸው ዐውሬዎች በመሆን አሁን በሀገራችን እያስተዋልነው እንደምንገኘው ያለ ችግር ይፈጠራል፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥም የቀን ጅብነት የዘመኑ ፋሽንና ያልተጻፈ ህግ ይሆናል፡፡ ለሆድ ማደር እንደ መልካም ባህል ይቆጠራል፤ ሞራላዊ ፍጡር መሆን በፋራነት እያስፈረጀ ጅልና ቂል ያሰኛል፡፡ ከተለመደው ብልሹ ሥርዓት ውጪም አድርጎ ለጉዳት ይዳርጋል፡፡

ዱሮ በኔ የልጅነት ዘመን ሃይማኖት ትልቅ ዋጋ ነበረው፡፡ ማዕድ ላይ ቀርቦ የጠገበ ሰው ወዳጆቹ ሊያጎርሱት ብለው የልጅ ምሣ የሚያህል ጉርሻ በጃቸው ይዘው ሲንጠራሩ “ገብርኤልን” ብሎ ከማለ አንዲት ግራም የምትመዝን እንጀራ እንኳን አይቀምስም፡፡ ማላ ማላ ነበር፡፡ አሁን ግን አንድ ክርስቲያን ነጋዴ በአንድ መቶ ብር የገዛውን ዕቃ ሊሸጥ ሲያስማማ “ቅዱስ ገብርኤልን በአንድ ሺ ብር ነው ያስገባሁት፣ ሊያውም ላንተ ለደንበኛየ ስል ከአንድ ሺህ አንድ መቶ ብር ሣንቲም አልቀንስም፡፡” ሲል ቅንጣት አያፍርም፡፡ ምክንያቱም አንድ ዋና አጥር ተደርምሷል፤ ለእህል ውኃ ሲባል አንድ ጠንካራ ማተብ ተበጠሰ፤ አንገትም ዞረ ማየቱን ረሳ፡፡ ይህን አጥር ማን ቀድሞ ደረመሰው? ምናልባት አገልጋዮቹ፣ ምናልባት የቅዱስ መንፈስ ተፀራሪ የሆነው የአጋንንት ኃይል፣ ምናልባት በሕይወት ተስፋ የቆረጡ ሰዎች፣ ምናልባት በፈጣሪ ፍርድ ምድራዊ “ቀርፋፋነት” ወይም የዘገዬ መምሰል የተበሳጩ ሰዎች፣ … ብቻ ማንም ቀድሞ ይደርምሰው ዋናው ነገር ግን አጥሩ ፈራርሶ ማኅበረሰባችን በኅሊና ቀውስ እየተሰቃየና በመንፈሣዊ ኪሣራ ተዘፍቆ እምነቱ እየተሸረሸረ ይገኛል፡፡ የሃይማኖት ልጓሙ የተበጠሰበት ማኅበረሰብ ደግሞ ዐይን የለውም፤ እርስ በርስ እንደጅብ ሲበላላ ለጭካኔው ወደር አይገኝለትም፡፡ በአሁኑ ወቅት ቤተ አምልኮዎች ለታይታና ለባህል እንጂ ከእውነት እግዚአብሔርን ስለማምለካቸው አላውቅም – ደግሞም ሃይማኖትና ባህል ተዛንቀው ምኑንም ከምኑ ለመለየት አዳጋች ሆኗል፡፡ ባጭሩ ሁሉ ነገር ተደበላለቋል፡፡ እግዜር ተረስቷል፤ የሥጋ ገበያ ደምቋል፡፡ ገንዘብ ተመልኮ ሰብኣዊነት ረክሶ፣ ዘረኝነት ደርቶ፣ ሆዳምነት ፋፍቶ፣ ያለው ከሌለው ተለይቶ የሚከበር፣ የሌለው ካለው ተለይቶ የሚዋረድ… ሁሉ ነገር ግራ የሚያጋባና የተዘበራረቀ ሁኔታ ጎልቶ የሚታይበት ሀገራዊ ድባብ ነው የሚታየው፡፡ አጥር ሲፈርስ እንዲህ ነው፡፡ ይሉኝታ ይጠፋል፤ የመተሳሰብና የመተዛዘን ምንጭ ይደርቅና በቦሌም ይሁን በባሌ የግል ጥቅምን ማሳደድ ቅድሚያ የሚሰጠው ይሆናል፡፡ ተያይቶ ማደግ፣ በጋራ መበልጸግ በመጽሐፍ የክት ቃልነት እንጂ በእውን አይታሰብም፡፡ በበኩሌ በኔ ዕድሜ መጨረሻችን እንዲህ ይሆናል ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡

ቀደም ሲል አንድ ነጋዴ የሚከብረው በዓመታት ልፋት ነበር፡፡ ላቡን ጠብ አድርጎ በአንዲት ዕቃ ላይ ጥቂት ሣንቲሞችን ብቻ በማትረፍ በከፍተኛ ድካም ያሰበው ጫፍ ይደርሳል፡፡ በዚያም ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ከንግድ ይልቅ መምህርነትና ሌላው የመንግሥት የቢሮ ሥራ ይመረጥ የነበረው፡፡ ዛሬ ግን ሁሉ ነገር ተገለባብጦና ተመሰቃቅሎ ይታያል፡፡ መምህሩ በደመወዙ ከልደታ እስከባታ እንኳን መኖር አቅቶት በቀዳዳ ጫማና በነተበ ሸሚዝ ለመኖር ያህል ሲንጠራወዝ ትናንት ማታ ወደንግድ ዓለም የገባው የ20 ዓመቱ ታዳጊ ወጣት በአንድ አዳር የአየር ባየር ንግድ(ዘረፋ ማለት ነው የሚቀለው) የሚያምር ቪላ ሠርቶ በቪ8 እና በሀመር መኪኖች ሲንደላቀቅ ስናይ አጥሮቻችን ሁሉ ፈራርሰው ሀገር የወንበዴዎችና የወሮበሎች መፈንጪያ መሆኗን እንረዳለን፡፡

የዱሮ ነጋዴ ሃይማኖት ስለነበረው በዚያ ላይ የሀገርና የወገን ፍቅርም ተፈጥሯዊ የፀጋ ሀብቱ ስለነበሩ ይሉኝታና ሀፍረት ያውቅ ነበር፡፡ የአሁኑ ግን ኅሊናውን ለገንዘብ የሸጠና ጫፍ ላይ የሚታየው ገንዘብ ብቻ በመሆኑ እዚያ የሚያጓጓ ጫፍ ለመድረስ የማይፈነቅለው ድንጋም ይሁን ቋጥኝ የሌለው የለዬለት ጅብ ነው፡፡ ከትምህርት ትምህርት የለውም፤ ከዕውቀት ዕውቀት የለውም፤ ከሃይማኖት ሃይማት የለውም፤ ከተሞክሮ ተሞክሮ የለውም፤ ከመንግሥት ሃይ የሚለው መንግሥት ወይም የህግ የበላይነትን የሚያስጠበቅ አካል የለውም፡፡ ምን ይዳኘው? ማን ይውቀሰው? ማን ይክሰሰው? ማን ሥርዓት ያሲዘው? በጥቅምና በዘር ሐረግ ከላይ እስከታች ተያይዞ  ሀብት ማማ ላይ ፊጥ ብሎ የሚታየው አብዛኛው ዜጋ ደንቆሮና ሆዳም ብቻ ነው – አእምሮውን የተነጠቀ፡፡

ከሃይማኖት አጥር ሌላ የባህል፣ የሰብኣዊነት፣ የግብረገብ (ሞራል)፣ የይሉኝታ፣ የወገንተኝነት፣ የዕውቀትና ትምህርት፣ የግንዛቤ ዕድገት፣የጓደኝነትና የወዳጅነት፣ የቤተሰብነት፣ የአብሮ አደግነትና የመሳሰሉ አጥሮችም ነበሩ – የዛሬን አያድርገውና፡፡ በአሁኑ ወቅት እነዚህ አጥሮች ተሰባብረው በዘረኝነትና በተናጠላዊ የሀብት ክምችት አባዜ ብቻ ተለውጠው አዳሜ የግል ሩጫውን ሽምጥ እየጋለበ ይገኛል፤ በዚህ ሩጫውም የሚሊኖችን ኢኮኖሚያዊ ነፍስ እየደፈጠጠ በመኖርና ባለመኖር መካከል ያንጠራውዛቸዋል፡፡ ተቆጣጣሪ የሚባል መንግሥታዊም ሆነ የግል ተቋም ባለመኖሩ አለ ቢባልም ይስሙላ በመሆኑና ሀገር ምድሩ በሙስና በመብከቱ ማንም ማንንም ቆም ብሎ የሚያዳምጥበት ትግስትና ፍላጎት የለውም፡፡ ያለን መንግሥታዊ ቅርጽም ለዚህ ዓይነቱ ቅጥ አምባሩ የጠፋ ሥርዓት-አልበኝነት(አናርኪዝም) የተመቸ ነው፡፡ ሆድ በነገሠበት አእምሮ ወደሆድ ወርዶ ይሸጎጣልና በኩኑ ከማሆሙ የሆድአምላኪዎች መርህ አንድም በዘረፋው ትካተታለህ አለዚያም የኢኮኖሚያዊ ሞትህን ተቀብለህ በድህነት አሣርህን እየበላህ ለመኖር ያህል ብቻ ትኖራለህ፡፡ ና እስቲልህ – ባገሬ ጅልን ሰው “ አንተ ‹ና እስቲለው› አንዴ ናማ ልላክህ” ይባላል –  እኛም እንደዚያው ነን፡፡ ምርጫህ በመኖርና ባለመኖር መካከል ነው፡፡ ምርጫህ የሚንጠለጠለው ለኅሊናህ አድረህ የሚመጣብህን ፍዳ በመቀበል ወይም በተቃራኒው ከነሱ ጋር ወግነህ የልብህን በመሥራት እንደፈለግህ በመሆን መካከል ነው – እየኖርክ መሞት ወይም እየሞትክ መኖር፡፡ ሌላው ምርጫ ጠባብ ነው – ምናልባት ከሀገርህ ወጥተህ መሰደድ፡፡ እሱም የሞት ሞት ነው – ኢትዮጵያህ እንዲህ ናት፡፡ ደናቁርት ወደ ሥልጣን ሲመጡ፣ ከደናቁርትም የሚገዙትን ሕዝብና አገር እንደራስ ሕዝብና አገር የማይቆጥሩ፣ ራሳቸውንም እንደአድሮ ሂያጅ የባዕዳን ቅኝ ገዢዎች የሚያዩ የዕድሜ ልክ ሽፍቶች ባዶ ቤተ መንግሥት ሲገቡ ነገረ ሥራቸው ሁሉ የዝንጀሮና የጃርት ዓይነት ነው የሚሆን፡፡

ማኅበረሰብኣዊ ወግና ባህል መልካም አጥሮች ነበሩ፡፡ ዱሮ ለኅሊናህ ብለህ የምትሠራቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ፡፡ ልጆች ሆነን ትልቅ ሰው የተሸከመውን ዕቃ ተቀብለን እናግዛለን – አጉል ቦታ የቆመ መኪናን ገፍተን ዳር እናሲዛለን ወይም እንዲነሳ እናደርጋለን፤ አቅመ ደካማን በሸክም ወይም ዐይነ ሥውር ከሆነ እየመራን መንገድ እናሻግራለን ፤ ቤትና ሠፈር የጠፋውን ሰው እናመላክታለን – … ይህን ሁሉ ስናደርግ ግን ገንዘብ መስጠትም ሆነ መቀበል አይታሰብም፤ ነውር ነው፡፡ ዛሬ ግን አይደለም ሠፈር ጠቁመህ መስቀል ተሳልመህና “በጥፊ ምቱኝ፤ ይጠቅመኛል” ብለህም ገንዘብ ትጠየቃለህ – ብዙ ገንዘብ ሊያውም፡፡ የኔ ቢጤ (ለማኝ) ባቅሙ ከብርና ከሃምሣ ሣንቲም በታች ብትሰጠው አንዳንዱ ይወረውርልሃል፡፡ የልመና ‹ኤቲክስ›ም ተለውጧል፡፡ ለምን ብትል ብዙ አጥሮች ፈራርሰዋልና፡፡ እነዚህ የፈራረሱ አጥሮች ይዘን ኢትዮጵያን እንደ አዲስ መገንባት ይከብዳል፡፡ ብዙ ሥራ መሠራት ይኖርበታል፡፡ አለበለዚያ ጉዟችን ህልማዊ እንጂ እውናዊ አይሆንም፡፡

ዜጎች የማኅበረሰብ ሸክላና ጡቦች ናቸው፡፡ በሥርዓት ታንጸው ካደጉና በመልካም ግብረ ገባዊ ሰበዞች ተሰፍተው ለወግ ለማዕረግ ከበቁ ሀገርም ትታደላለች፡፡ ወንጀልና ክፋት ይቀንሳሉ፡፡ ጥሩ መንግሥትም ይኖራል – ምክንያቱም መንግሥት ከሰማይ የሚወርድ ሣይሆን ከሕዝቡ የሚወጣ የማኅበረሰቡ ሁለንተናዊ ዕድገት ነፀብራቅ ነውና፤ ጥሩ ሕዝብ ጥሩ መንግሥት ይኖረዋል፤ መጥፎ ሕዝብም መጥፎ መንግሥት ይኖረዋል – ባብዛኛው፡፡ እንደኛ እንዳሁኑ ከሆነ ግን ከሥር መሠረታቸው በቂም በቀልና በጥላቻ ተኮትኩተው፣ ከራሰጌያቸው እስከግርጌያቸው በዘረኝነት የመርዝ ዝልል ተጨመላልቀው ወደ ሥልጣን የሚመጡ ዜጎች ከተፈጠሩ አዲዮስ ሀገርና ሕዝብ፡፡ ለምን ቢባል የመልካም አስተዳደር ባህልና ወግ አጥር ፈርሷልና፡፡ እነመለስና አቦይ ስብሃት ያደጉበት ከባቢያዊ ሁኔታ በፀረ-ኢትዮጵያ አስተሳሰብ በእጅጉ የተበከለ ስለነበር እነዚህ ሰዎች በለስ ቀንቷቸው ከደደቢት እስከ አራት ኪሎ ሲጓዙና ከዚያም በኋላ በነበራቸው ሰፊ ጊዜ ብዙ የወል አጥሮችን አፈራርሰው ባዶ ያገኙትን አልጋ ተደላድለው ተኙበት፡፡ ይህንን ባዶውን ያገኙትን አልጋ ትኋንና ቁንጫ አወረሱትና ሌላ ከነሱ የተሻለ ደህና ዜጋ እንኳን መጥቶ እንዳይተኛበት አጓጉል አደረጉት፡፡ ደህና ሰውም እንዳይፈጠር በጠላቶቻችን ምክር ደህና ደህናውን ከመካከላችን እያወጡ ለመቀጣጫነት ለጭዳ ዳረጉት፡፡ ለጭካኔያቸው ወደር ማጣት ትልቁ ሰበብ ትውልድ ሁሉ ሀገር አለኝ ብሎ እንዳያስብ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ እንዲገባና እንዲደብተው ማድረግ ነው፡፡ የአጥር መፍረስ ጦሱ ብዙ ነው፡፡

የማያልቅ ነገር ነው የያዝኩት፡፡ አውሎ የሚያሳድር ብቻ ሳይሆን የሚያከርም ነው፡፡ ስለዚህ ለምን ሰዎች ዐረመኔ ይሆናሉ? በሚል ድረ-ገፃዊ መዛግብትን ሳገላብጥቨ ያገኘሁትን አንድ ጥሩ እሳቤ ላካፍላችሁና ለአሁኑ ልሰናበት፡፡ ማንበብንም ዕርም ብለው የተው እጅግ ብዙ ዜጎች ስላሉ መጻፍንም ዕርም ብለን ልንተው የደረስን መኖራችንን ግን በዚህ አጋጣሚ ሳልጠቅስ ማለፍ አልፈለግም፡፡ አጥር አፍራሹ የወያኔው ጭፍራ ያዞረብን ሁለንተናዊ አፍዝ አደንግዝ ከሀገራችን የጋራ ጉዳይ  እንድንወጣ ሳያስገድደን አልቀረም፡፡ ከፍ ሲል በጨረፍታ ለመጠቆም እንደሞከርኩት ብዙዎቻችን ጥልቅ እንቅልፍ ላይ ነን፡፡ መድኅናችን ከሰማይ እንዲወርድ የምንጠብቅ ብዙ ተላላዎች አለን፡፡ እንደውነቱ ተመቸኝ ብሎ ሀገርንና ሕዝብን እርግፍ አድርጎ መተው የጤናማነት ምልክት አይመስለኝም፡፡ “ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ”ም ደግ አይደለም፡፡ ሀገርን በደስታዋ ጊዜ ብቻ ሣይሆን በመከራዋ ዘመንም አለሁልሽ ማለት ይገባል፡፡ ይህ የትኋንና የመዥገር ግሪሣ ሲራገፍ – መራገፉ አይቀርምና – ያኔ አደባባይ ወጥቶ የሌለን ነገር በመናገር የድል አጥቢያ አርበኛ ከመሆን ከአሁኑ የተቻለንን ማድረግ ይሻለናል፤ ይገባናልም፡፡ ሀገር አንደበት ስለሌላት አትወቅሰኝም፣ አትከሰኝም አይባልም፡፡ ዋናው ወቃሽና ከሳሽ ደግሞ ኅሊና ነው፡፡ እነዚህ ክፉዎችና ጊንጦች በአሁኑ ሰዓት ምን እየሠሩ እንደሆነ ማወቅና ማሣወቅ አለብን፡፡ ምንም እንኳን ዓለም አቀፉን የክፋት ኃይል በአጠገባቸው ቢያሰልፉም ቀን ማለፉ አይቀርምና ፈጣሪ ፊቱን ሲያዞርልን ልንከሳቸውና ልንወቅሳቸው ከፈለግን አሁን መተኛት የለብንም፤ ለመክሰስና ለመውቀስ ደግሞ አንዳች ማስረጃ በእጃችን መያዝ ይኖርብናል፡፡ የሚሠሩትን ክፋት መዝግበን እናስቀምጥ፡፡ “ምንም ደግ ሥራ ሣይኖራችሁ ጌታ ሆይ የተራቡትን በስምህ መግበናል፤ የታረዙትን በስምህ አልብሰናል፤ የታመሙትን በስምህ ጎብኝተናል… ብትሉ ያኔ አላውቃችሁምና ባባቴ ፊት ‹ዘወር በሉ› እላችኋለሁ” ሲል ክርስቶስ የተናገረውን መልካም ምክር እናስብ፡፡ ኢትዮጵያና ሕዝቧም በዚህ የነናቡከደነፆር ግፈኛ አገዛዝ ሲሰቃዩ ቢያንስ ልንጮኻላቸው ካቻልን በቁማችን እንደሞትን ህል ነው፡፡ እስኪ የድረ ገፆቻችንን ልፋትና ድካም እንኳን ቆም ብለን እናስብ፡፡ እኔማ ኑሯቸውን የተው እስኪመስለኝ ድረስ ሲፈጉ መዋል ማደራቸውን ስረዳ “እንዴ፣ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ለነዚህ ጥቂት የቁርጥ ቀን ልጆች ብቻ ተትታ ቀረች ማለት ነው?” እላለሁ፡፡ እግዜር  ይባርካቸው ልበል በዚህ አጋጣሚ፡፡ ስም መጥራት ብጀምር ስለማልጨርሰው ይቅርብኝ፡፡ በነፃነት ቀን ዋጋቸው  ትልቅ መሆኑን ብመሰክር ግን ደስ ይለኛል፡፡

ዛሬ ስለ ሕወሓት የጭካኔ ተግባር በኢሜል አድራሻየ ኪሩቤል በቀለ የተባለ ታጋያችን የላከልኝን ነገር ሳነብ በኅሊና አልቅሻለሁ፡፡ ወያኔ በአንደበት እንኳን በማይነገር የማሰቃያ ዘዴው ዜጎችን እንዴት አድርጎ እንደሚያሸማቅቅና ተደብቀው እንዲኖሩ እንደሚያደርግ ስንሰማ የመከራችን ክብደት ግዘፍ ነስቶ ይታየናል፡፡ የሞቱስ ሞቱ – ተገላገሉ፡፡ ነገር ግን እንደነ እንትና ያሉ የክፉ ቀን ልጆቻችን ከእሥር ቤት እንደወጡ በስማም የተባለበት ሰይጣን ይመስል አፋቸውን ለጉመው የሚኖሩበት ምክንያት እነዚህ የአጋንንት ውላጆች ምን ቢያደርጓቸው እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ይህን የመሰለ ሰይጣናዊ ኃይል ቤተ መንግሥት አስቀምጦ ሌላው ይቅርና ዘፈን ማዳመጡ ራሱ ነውር ሊሆንብን በተገባ ነበር፡፡ ብሔራዊ ሀዘን መታወጅ ነበረበት፤ እስከነጻነት ድረስ የሚዘልቅ ጥቁር ልብስ መልበስ ነበረብን፤ እነዚህ ወያኔዎች የሚሠሩብን ግፍ ወደር የሌለው ነው፡፡… ብድራታቸውን መከፈላቸው ባይቀርም እያደረሱብን ያለው አእምሯዊ፣ ኅሊናዊና አካላዊ ስብራት ግን መቼም የሚጠገን አይደለም፡፡ (የውሻን ደም በከንቱ የማታስቀር የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ኢትዮጵያን  ከነዚህ የዲያብሎስ ሽንቶች ፈጥነህ ገላግላት፤ ምሕረትህን በቶሎ ላክልን፡፡ አሜን)

ቀጥሎ ያለው ጽሑፍ የሚያወራው ሰዎችን በጠላትነት ስለመፈረጅና ከሰው ተራ ስለማውጣት ነው፡፡ አንድ የሰዎች ቡድን አንድን የማኅበረሰብ ክፍል በአንድ ነገር ፈርጆ ዐይንህ ላፈር ካለው በዚያ የማኅበረሰብ ክፍል ላይ የሚፈጽምበትን በደልና ግፍ ሁሉ በሰው ላይ ሳይሆን በዐውሬ ወይም በእንስሳ ላይ እንደሚፈጽመው ይቆጥራል፡፡ ለምሣሌ  አይሁዶች በተለይም የጽዮናዊነትን መርህ አቀንቃኝ የሆኑት ይሁዳዎች ሌላውን የዓለም ሕዝብ “ጎይ” ይሉታል – ሥርዓት ባለው አጠራር “ጀንታይል” ሲሆን ደግሞ ይሉናል፡፡ ይህን ትልቅ ቁጥር ያለውን የዓለም ሕዝብ እንደበሬ ጠምደው ቢያርሱት፣ እንፊሪዳ አርደው ቢበሉት፣ እንደ ታዳኝ ዐውሬ ተኩሰው እየገደሉ ቢዝናኑበት፣ እንደባሪያ ቢሸጡትና ቢለውጡት፣ ሴቶቹን እየቀሙ (እንዳይወልዱ በመጠንቀቅ!) ቢዝናኑባቸው፣ ወዘተ. ለነሱ የተፈቀደና በመጽሐፈ ቶራ ወታልሙዳቸው የጸደቀ የአበው ውርስ ነው፡፡ ወንድሞቼና እህቶቸቼ – አንጎልን የመሰለ አስቸጋሪ ነገር የለም፤ እምነትን የመሰለ ክፉ አባዜ የለም፡፡ አንድን መጥፎ ነገር በሚሊዮኖች አእምሮ ውስጥ እንደጽድቅ ነገር መትከል ይቻላል፡፡ ከዚያም የሰነቀርከው ነገር ፍሬ ሲያፈራ በጭካኔ ተግባራት እየተደሰትክ መኖር ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሰይጣን አዝመራ ነው፡፡

ወያኔዎች  ፍጹም ምሥኪንና ከትግሬ ቀርቶ ከማንም የባዕድ ወገን ጋር ጠብ የሌለውን የዐማራን ሕዝብ በሆነ ነገር ፈርጀው እንዲህ የሚያስጨርሱት ተራው ጀሌ በገባው ነገር ሣይሆን ብልጣብልጦቹና አስተዳደግ የበደላቸው እነመለስ ዓይነቶቹ የሰንበት ፍሬዎች በዘሩት የዐመፃ ዘር ነው፡፡ ይህን የዐመፃ ዘርና ቡቃያ ለመንቀል ሌላ ከዚህ አስተሳሰብ የተሻለ መላ መምታት ይገባል፤ የዳግም መምጣቱ ብሥራት በአሁኑ ወቅት በአድማሳት ውስጥ የሚታየው ክርስቶስ ብቻ ሣይሆን አልበርት አነስታይንም የሚለው ይህንኑ ነው፡፡ ክርስቶስ “ክፉን በክፉ አትቃውሙ” ሲል አነስታይን ደግሞ “አንድን ክፉ ተግባር ለማክሸፍ ያ ክፉ ሥራ በተቃኘበት የአስተሳሰብ መንገድ መጓዝ ሳይሆን ከርሱ በተቃራኒ ማሰብ ያስፈልጋል” ይላል፡፡ በተመሳሳይ መንገድ መጓዙ የመጠፋፋትን ቀጣይነት እንደማረጋገጥ ነውና እንደሕዝብ ስናስብ ከዚህ የአነጋገር ትውፊት ትምህርት ብንቅስም ደስ ይለኛል፡፡ እንደ ጦር ሠራዊት ስናስብ ግን መጽሐፉም “ደም ትነጽሕ በደም” ይላልና በምንም ዓይነት መንገድ ማሸነፍ የማትችለውን የሰይጣን ኃይል ባለ በሌለ ጉልበትህ ብትደመስሰው ጽድቅ እንጂ ኃጢኣት የሌለበት መሆኑን የነሣምሶን ተሞክሮ በጉልኅ ያስረዳል፡፡ ሣምሶን በመቶዎች የሚቆጠሩ ጠላቶቹን በአንዴ በአንድ የአህያ መንጋጋ ይረፈርፋቸው እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ቢበቃኝስ …

THE SPIRIT OF ABSTRACTION

It’s called the spirit of abstraction, a term originally coined by Gabriel Marcel in his essay “The Spirit of Abstraction as a Factor Making for War,” and is defined as the practice of conceiving of people as functions rather than as human beings. In early American history a large segment of the population labeled African Americans as “slaves,” reducing their identity as human beings into an abstract idea only, freeing slave owners to consider slaves their property. Hitler convinced a majority of Germans to conceive of a segment of their population as “Jews,” abstracting their identity as human beings into something he convinced the German people was so inferior he was able to wipe out 6 million of them (not to mention half a million gypsies as well). Americans, in turn, abstracted the Japanese people into “Japs,” a derogatory term that reduced them from human beings with hopes, loves, families, and fears into the “enemy” on whom it was therefore eventually permissible to drop two atomic bombs.

 

ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስንቀርብ ምን አልባት ህክምና የማገኝበት ጥቂት ጭላንጭል ተስፋ ይኖራል የሚል ግምት ነበረኝ

$
0
0

ነገረ ፍርድ ቤት

13339492_1135782779813325_7476937859922073015_n
ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስንቀርብ ምን አልባት ህክምና የማገኝበት ጥቂት ጭላንጭል ተስፋ ይኖራል የሚል ግምት ነበረኝ ፡ ጠበቃዮ አቶ አመሃ መኮንን ህመሜ እያመመዉ ዳኞችን ተማፀነ የህመሜን ብርታት አስረዳ ፡ ዳኞቹ ግን ቀጠሮዉን ለአንድ ወር በማስረዘም ሰኔ 28 ቅረቡ ከማለት አልተቆጠቡም ። የፍርድቤት ቆይታዮ አንድ በጎ ገፅታ ወዳጄ አብርሃ ደስታን አግኝቼ አቅፌ መሳሜ ብቻ ነበር። በርታ አይዞህ አልኩት አይዞህ አለኝ ከዚያ በላይ ማዉራት አልተቻለም ወታደሩ አናጠበን፡ ምን እናረጋለን ወትሮስ መናገር አይደለም ወንጀለኛ ያሰኘን እንደቃላቸዉ ዝም…ተሰነባበትን…

ሀብታሙ  አያሌው

 

የዳያስፖራዎች ቤት ግብዣ |በእውቀቱ ስዩም

$
0
0

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen).
ከዘፋኞች ቡድን ጋር አሜሪካ በገባን ማግስት ዘፋኞች በዶላር ከበሩ፡፡

እኔ አጥብቄ ተቸገርኩ፡፡

በወይዘሮ የሺሻ-ወርቅ ናይት ክለብ ውስጥ፤ ፋሲል ደመወዝ የጣውላ ክላሹን አነግቶ “አረሡት የሁመራን መሬት” ብሎ ዘፍኖ ሁመራን ለመሸመት የሚበቃ የሽልማት ዶላር ይዞ ሲወርድ እኔ ግጥም ለማንበብ ወደ መድረክ እወጣለሁ፡፡

ከዚያ በግጥም ደብተሬና በእኔ መሃል የቆመውን ወፍራም የሺሻ ጭስ ባይበሉባዬ ገለል አድርጌ…

“ዓለማዊ ልቤ ለበሰልሽ ዳባ ምናኔ ተመኘ
በእናቴ ቀብር ላይ የጠፋብኝ እምባ ፊቴ ላይ ተገኘ“
…ብየ ስጀምር አያስጨርሱኝም፡፡

“ምናኔ ደሞ ምንድነው”? ትለኛለች ከጥግ ቁጭ ብላ ሺሻ የምትጠባ ደንበኛ፡፡

ብልጭ ይልብኛል ! ግጥሜን ላንብብ ወይስ አንቺን አማርኛ ላስተምር?

“አቦ ይሄ ልጅ ያስቃል ሲባል አልነበረ እንዴ ? ምንድነው እዚህ ”ቀብር“ ምናምን እያለ የሚያለቃቅስብን ?”ይላል ሌላው የሚወረወር ነገር ባካባቢው እየፈለገ፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከኢትዮጵያ ያስመጣኝ ፕሮሞተር በኔ ተስፋ ቆረጠ፡፡ ጥረህ ግረህ ብላ ብሎ ጥሎኝ ጠፋ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ምግብ አማርጥ የነበርኩት ሰውዬ አሜሪካ ውስጥ ያለ ፈቃዴ በተከታታይ እፆም ጀመር፡፡

ጠዋት የቤቴን በር ስከፍት ከነ ጃንቦ ጆቴ ክፍል መአት ዓይነት የፕላስቲክ አገልግል፤ የሰርዲን ጣሳ፤ ድርብ ሰረዝ የመሰለ በርገር፤ እንዲሁም የቢራ ጠርሙስ እየተጠረገ ሲወጣ አያለሁ፡፡

ሲብስብኝ ማንኛውንም የምሳ ግብዣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል ጀመርኩ፡፡

ዘፋኞቹ ”ተጋባዡ ገጣሚ“ በማለት ይፎትቱኝ ጀመር፡፡

አንድ ቀን ቨርጂንያ አውራ ጎዳና ዳር ቆሜ በጥሞና ሳሰላስል ፊቴ ላይ የሚታየውን ጥልቅ ጥሞና የተመለከተ ሰው ስለ ቀጣይ ያገራችን እጣ ፈንታ እንጂ ስለ ቀጣዩ ምሳ እያሰበ ነው ብሎ አይገምትም፡፡

”ሃይ በእውነቱ“ የሚል የሴት ድምጽ ካሳቤ አባነነኝ ፡፡

አንዲት ያገሬ ልጅ መኪናዋን አቆመችልኝ፡፡

ትንሽ ከተደናነቅን በኋላ ”ለምን ምሳ አብረን አንበላም?“አለቺኝ፡፡

ገና ”ለምን ምሳ… “ የሚለው አርፍተ ነገር ባየር ላይ እያለ መኪናዋን ከፍቼ ከኋላ ወንበር ቁጭ ብያለሁ፡፡

ትንሽ እንደ ሄድን መኪናዋን ካንድ ጥግ አቁማው የሆነ ዐራት ማእዘን ሰውዬ ገብቶ አጠገቧ ተቀመጠ፡፡

ከዚያ ዞር ብሎ “የማን አባቱ ጉቶ ነው” በሚል አይነት ገላመጠኝ ፡፡

ወድያው ግን በድጋሚ ከተመለከተኝ በኋላ
“አጅሬ! አንተነህ እንዴ?ለመሆኑ ወደ ሥነጽሁፍ ዓለም እንዴት ገባህ“ እያለ በባዶ ሆዴ ያደርቀኝ ጀመር፡፡

ቤት ገብተን ልጅት ምሳ ለመሥራት ወደ ጓዳ ገባች፡፡

ሰውየው የፍቅርና የትዳር ታሪኩን ባጭሩ ለሁለት ሰዓት ያህል ተረከልኝ፡፡

አዲሳባ ውስጥ በፍቅር እንደኖሩ፤ ከዚያ እሱ ወደ አሜሪካ እንደተሰደደና እሷን በስንት ውጣውረድ እንዳመጣት ነገረኝ፡፡ በቅጡ አልሰማሁትም፡፡

ከሰውየው ትረካ በላይ ጥርት ብሎ የሚሰማኝ ከጓዳ የሚመጣው የመክተፍያ ድምጽ ነበር፡፡

ልጅቷ በያይነቱ ሠርታ ጨረሰች፡፡ ግን ቶሎ አልቀረበም፡፡

እኔን ራብ እየሞረሞረኝ ባልና ሚስቱ ስለኣቀራረብ ስታይል ይራቀቃሉ፡፡

“ስንግ ቃርያው የሚቀመጠው ከቲማቲሙ በስተቀኝ በኩል ነው በስተግራ በኩል ነው”? በሚለው ዙርያ ለሃያ ደቂቃ ያክል ተከራከሩ፡፡

እኔ ወደ ማእዱ ለመሄድ ትንሽ ሲቀረኝ ማእዱ ከፊቴ ቀረበ፡፡

”ይገርምሃል ለመጀመርያ ጊዜ ሲዲህን የሰማሁት ደሳለኝ ቤት ሆኜ ነው” አለችኝ ከጠረጴዛው ላይ ብርጭቆ የሞላ ውሀ እያስቀመጠች፡፡

”ደሳለኝ? ደሳለኝ ማን ነው?“አለ ሰውየው የህጻን ብርድልብስ የሚያክል እንጀራ ሰሀኔ ላይ እያነጠፈ፡፡

”ደሳለኝ፡፡ ተከራይቶ የሚኖር ልጅ ነበር፤ እኛ ግቢ”
”ኦኬ ምን ልትሠሪ ቤቱ ገባሽ?“ ባሉካ ባረቀ፡፡

”ቲቪ ላይ ነዋ ! የደሳለኝ ብቸኛ ሀብቱ ግዙፍ ቴሌቪዥኑ ነበር፡፡ ይገርምሀል ቤቱ ውስጥ ወንበር እንኳ አልነበረውም” አለች ወደኔ ዞራ፡፡

“ወንበር ከሌለው ታድያ ምን ላይ ተቀምጠሽ ቲቪውን ዓየሽው?” ሰውየው አፈጠጠ፡፡

“እምም አልጋው ጫፍ” አለች ፈገግታዋ እንዳያመልጣት ከንፈሯን እየጨቆነች፡፡

ሰውየው ለመደባደብ ያሟሙቅ ጀመር፡፡

ብድግ ብዬ ”ተው እንጂ! ነውር ኣይደለም እንዴ?” ምናምን እያልኩ በማሃላቸው ገባሁ፡፡

“ነውር ኣይደለም እንዴ? አትሊስት ምሳዬን እስክበላ ድረስ ለምን አትታገስም?“ አልኩ በልቤ፡፡

”አሜሪካ እንዳለህ አትርሳ፡፡ ጫፌን አትነካኝም!“ አለች ከመጤፍ ሳትቆጥረው፡፡

እውነቷን ነው፤ አሜሪካ ውስጥ የሴትን ጫፍ መንካት ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ ወንዶች ንዴታቸውን የሚወጡት ግድግዳ በቴስታ በመምታትና የመኪና ጎማ በካልቾ በመጠለዝ ነው፡፡

ሰውየው በንዴት አረፋ እየደፈቀ ዞር ሲል ከግድግዳ የተሻለ ንዴቱን ማስተንፈሻ ተመለከተ፡፡

ቁልቁል ዐየኝ፡፡

ቀጥሎ የተከሰተው ብዙ ነገር ትዝ አይለኝም፡፡
ብቻ…

“አቦ ወደዛ ዞርበልልኝ” ሲልና የመጥረቢያ ዛቢያ የመሰለውን ክርኑን ወደ አንገቴ ሲሰነዝር ትዝ ይለኛል፡፡

አንገቴ ወደ ቀድሞው ጤንነቱና ውበቱ ለመመለስ ላንድ ሳምንት ያህል የፒትልስ ሹራብ ኰሌታ የመሰለ ጄሶ ድጋፍ ማግኘት ነበረበት፡፡

እና እስከዛሬ ድረስ ”አንገት ከሚሰበር ባይበላስ ቢቀር“ የሚለውን የቴዲ አፍሮ ዘፈን በሰማሁ ቁጥር ይሄ ልጅ የኔን ታሪክ ማን ነግሮት ይሆን ? እላለሁ፡፡
.

የዲሲ ግብረሃይል ለአርቲስቶች ማስጠንቀቂያ ሰጠ |መግለጫውን ይዘናል

$
0
0

Boyycott

(ዘ-ሐበሻ) በሼህ መሀመድ አላሙዲ “የደም ገንዘብ” ይደገፋል የሚባለውንና በሰሜን አሜሪካ ያለውን የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽንና ህዝቡን ለመከፋፈል ተቋቁሟል የሚባለውን ኤኢሳ ዋን (AESA ONE) ለሚተባበሩ አርቲስቶች የዲሲ ግብርሃይል ማስጠንቀቂያ ሰጠ:: ከዚህ ቀደም እነ ሐመልማል አባተ; ሽዋፈራው ደሳለኝ; ደረጀ ደገፋው; ን የመሳሰሉ የስርዓቱ ተላላኪ አርቲስቶች ላይ የማያዳግም ቅጣት የጣለው የዲሲው ግብረሃይል “ኢትዮጵያዊ ክብርና ሞገሳችንን ገፈው ህዝባችንን መቀለጃ የሚያደርጉ አርቲስቶችን ቦይኮት እናደርጋለን” ሲል መግለጫ አውጥቷል::

የደም ገንዘብ አጓጉቷቸው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚቀልዱትን አርቲስቶች ማንነት ተራ በተራ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ እናቀርባለን::

መግለጫው እንደሚከተለው ተስተናግዷል:-

ከዲሲ ግብረ ሀይል የተሰጠ መግለጫ! ሼር በማድረግ እንተባበር!

በኤኢሳ ዋን (AESA ONE) ላይ መሳተፍ በወገናችን እልቂት መቀለድ ነው !!

ኢትዮጵያዊ ክብርና ሞገሳችንን ገፈው ህዝባችንን ጥሪቱን አሟጠው በንቀት እየተጫወቱ ያሉት ቡድኖች የሀገር ውስጡ አልበቃ ብሏቸው እነሆ ላለፋት 4 ዓመታት በውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ ለመበታተን ያደረጉትን ሴራ ህዝባችን አንድ በመሆን በቂ ምላሽ ሰጥቶ አክሽፎታል፤ ሆኖም ዛሬም ለ33 አመታት የቆየውን የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽናችንን ከኢትዮጵያ ህዝብ በግፍ በተዘረፈ የደም ገንዘብ ሊበታትኑት ኢትዮጵያን በኢንቨስትመንት ስም እራቁቷን እያስቀራት ባለው አላሙዲ አማካኝነት ለአምስተኛ ግዜ ቨርጂኒያ አሌክሳንድሪያ ውስጥ በሚገኘው ማውንት ቨርነን ሃይ ስኩል ከጁላይ 3 እስከ ጁላይ 9 የሚካሄድ የመከፋፈያ ዝግጅታቸውን አዘጋጅተዋል።

በዚህ ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈል በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ማንኛውም አገር ወዳድ ባለመካፈል ወገናዊነታችሁን እንድታሳዩ ጥሪአችንን እያስተላለፍን፤ በተጨማሪም አርቲስቶቻችንን ክብር የሰጣችሁ ወገናችሁን ፀረ ኢትዮጵያ በሆነ ዝግጅት ላይ ባለመካፈል አጋርነታችሁን አሳዩ እያልን፤ በዚህ የደም ዝግጅት ላይ የወገናችሁን እልቂት ችላ ብላችሁ በምትሳተፉ አርቲስቶች ላይ ማህበረሰቡ በማናቸውም ዝግጅቶቻችሁ ላይ ማእቀብ (boycott) እንደሚያደርግባችሁ ከወዲሁ ልትረዱት ይገባል ።

ይህንኑ ዝግጅትም በመቃወም በዲሲ እና አካባቢው የሚገኙ ሀገር ወዳዶች የተለያዩ የተቃውሞ ዝግጅቶች ያዘጋጁ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።

የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል!!!

የአርበኞች አኩሪ ተግባር በኦስሎ |ግርማ ቢረጋ

$
0
0

በኖርዲክ አባል ሃገራት የአርበኞች ግንቦት 7 የውይይት እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በኦስሎ ከተማ  በደማቅ ሁኔታ መከበሩ ከተለያዮ አባል ሃገራት በመጡ አባላት መካከል የነበረው አና መተሳሰብ ከምንም በላይ የሚያሳይ  አኩሪ ተግባር  ሲሆን የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆኑት የኖርዌይ የአርበኞች ግንቦት7 አባላት በሙሉ ለትግሉ ያላቸውን ቆራጥነት ያሳየ ሲሆን ለድርጅታቸው መሪ ያላቸው ክብርና መሪያቸው ደ/ር  ሙሉዓለም እንዲሁ ለአባላት ያሳዩት የነበረው ክብርና ቀረቤታ ለሌላውም ቢሆን ሊዘነጋ የማይችል ለቆሙለት ድርጅት ሲባል ምን ያህል ለሰው ልጅ ክብር እንደሚገባውና የመተሳሰብ  ስርዓት ከምንም በላይ ወሳኝ መሆኑን ለማስተማር ችለዋል።

Dr Birhanu Nega

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ታሳታፊ የነበሩ የስዊድን አርበኞች ግንቦት 7 አባላት በቦታው በመገኘት ለድርጅቱ ሊቀመንበር አርበኛ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ያደረጉት አቀባበል ከምንም በላይ ለአባላት ኩራት መሆኑ ሊዘነጋ የማይችል ሃቅ ነው ።

ከዚያም ባለፈ መድረኩን በፍፁም ጨዋነት ይመሩት ስለነበሩት ዶ / ር ሙሉዓለም ብዙ ማለት የሚቻል ነበር ይህም ከራሳቸው ልጆች / አባላት / ብዙ አድናቆት ያተረጉና እሳቸውም ለልጆቹ ያላቸውን ክብር ማየት ብቻ በቂ ነው ። በእንግድነት ቀርበው የነበሩትን ፕ/ ር ጌታቸው በጋሻው በጣም ትምህርት አዘል ንግግር ከመቼውም በላይ በሚመስጥ በለሰለሰ አንደበታቸው ታዳሚውን ግንዛቤ አስጨብጠውት ሲያልፉ እንዲሁም የጀግናው አንዳርጋቸው እህት ወ/ሮ ብዙነሽ ፅጌ ባልታሰበ ሁኔታ በቦታው መገኘት ታዳሚውን ሁሉ በደስታ እንዲፈነድቅ ያደረገ ሲሆን እሳቸው በአንዲ ስም አቅርበውት የነበረ ግጥም የአብዛኛውን ተሳታፊ ልብ የነካና ለቀጣዩ ትግል በበለጠ የሚያበረታታ ነበር። ሌላው በድርጅቱ ሊቀመንበር አርበኛ ፕ /ር ብርሃኑ ነጋ የቀረበውን ንግግር እና ከአባላት የሚጠየቁ ጥያቄዎች እና መልስ አባላትን ያስደሰተና ለቀጣዩ የትግል አቅጣጫችን ከምንግዜውም በላይ ስንቅ መሆኑና ትግሉ የደረሰበትን ሁኔታ በግልፅ ያሳየ ነበረ። ባጠቃላይ የዝግጅቱ መርሃ ግብር ለጨረታ በቀረበው ምስል በከፍተኛ ዋጋ 800,162 በወ/ሮ ብዙነሽ ፅጌ አሸናፊነት ተጠናቆ እሳቸው ግን ምስሉን ወንድማቸው አንዳርጋቸው  ለሚወዱት ለኖርዌይ የአርበኞች ግንቦት 7 በስጦታ ሲያስረክቡ የኖርዌይ የአግ 7 ታጋዮች ደግሞ ረጅም ርቀት ተጉዘው ለዝግጅቱ ድምቀት ለሰጡት የስዊድን አርበኞች ወዳጅነትንና ፍቅርን በሚገልፅ አኳኃን አበርክተዋል ።

ድል ከአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች!!!

Ethiofri@gnäll.com

ጁን 2016

ትቸው! ረስቸው! –አስፋ ጫቦ Dallas Texas USA

$
0
0

 

“መድረክ ንጉሳዊ ነው እንዴ ?”በሚል አንድ የኔን ስም ጠቅሶ ግርማ ሰይፉየጻፈው እነሆ:-

አቶ አስፋ ጫቦ በቅርቡ ባሳተመው መፅኃፍ ውስጥ የሸዋ ንግስና ከተመለሰ የእኛም መመለስ አለበት የሚል ስላቅ አቅርቦ ነበር፡፡ ፕሮፌሰር በየነም ቤተሰቦቻቸው በአካባቢው እንዲህ ዓይነት የንግሰና ጥያቄ ከመጠ ከሚጠይቁት ወገን ናቸው ስለሚባል፤ ይህ እስኪመጣ ድረስ መድረክን የንግስና መለማመጃ ያደረጉት መስለኝ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ብዙ ሙከራ አድርገው ያልተሳካላቸውን የአመራር ቦታ ቢቻል ፖለቲካውን ጭምር መተው ለምን ተቸገሩ?

አቶ አሰፋ ጫቦ

አቶ አሰፋ ጫቦ

መጀመሪያ ከት-ከት ብዬ ሳቅኩ::ሁለተኛም አንድ ፤”እዚያ መድረስ ክልክል ነው!” ብዬ የሾህ አጠር ያጠርኩበት መንደር አደረሰኝ።ስለዶክተር በየነ ጴጥሮስ ያለው ነው።ፈርቼ ፤አለሳልሼ ፤በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ የቆመለትን አላማ፤እኔም ጠንሳሽ መሥራች የሆንኩትን ድርጅት፣የደቡብ ኢትዮጵያሕዝቦች ሕብረት አገር እያየ መቃብር ሲያወርደው ዝም አልኩ። ዝም እንኳን አላልኩም። አገር ሳያውቀው ፀሐይ ሳይሞቀው በ email ብዙ አልኩት። መንፈሱ  “አትቅበረን! አትከፋፍለን!አመራጩ መንገድ ይህ ነው!” የሚል ነበር። አሁን በግርማ ምክንያት ለበየነ ጴጥሮስ የላኩለትን መልእክት ሳነበው ገረመኝ። ዛሬየገረመኝ ከ2003 በፊት ጀምሮ የላኩት መልእክት በጣም ብዙ፤ረዣዥምም ነበሩ።ይህ ባይመጣ ኖሮ ለሕይወቴ ታሪክ ያልኩት ነበር።

በየነን  ያውኩት በነሐሴ 1983  አፍሪካ አደራሽ “የስላምና ድሞክርሲ ስብስባ” ሳቢያ ሒልተን ሆቴል የስነበትን ስሞን ነበር። ደቡብ ኢትዮጵያወጣቶች ሕዲያን ጨምሮ የፖለቲካ ዝንባሌ የነበራቸው ባብዛኛው እንተዋወቃለን። በየነ ከዚያ ውስጥ አልነበረምና ሳየው ገረመኝና “አንተ ደግሞ ከየት መጣህ?” ያልኩት በውስጤ ነበር። በዚያ ስብሰባ ሳቢያ የደቡብ ህቦች ህብረት ፈጠርን። የ11 ብሔረሰብ ተውካዮች ተፈራረምንበት። የተፈራርምነው በሒልተን ሆቴል አርማ(Letterrhead)ር ባለበት ወረቀት ነበር። አንድ ቅጅ ለሆቴሉ ማነጀር ሰጠሁ። እኔ የለኝምና አስቀምጦት ከሆነ ታሪካዊም ይመስላል። እኔ ሊቀ መነበር ተስፋዬ ሐቢሶ ዋና ጸሐፊ ሆነን ተመረጥን። በየነ ጵጥሮስ በነጋታው ስራውን ጀመረ።’

beyene_petros

በነጋታው በጥብቅ ፈልግሐለሁ ብሎ ቡና ጋብዞኝ  ተስፋዬ ሐቢሶ ላይ ክሱን  ይደርድር ጀመረና አቋረጥኩት። በሐዲያና ከምባቶች መካከል ያለውን የአካባቢ አለመግባባት በመጠኑም አውቅ ስልነበረ፤ከሁሉም በላይ ተስፋዬ ሐቢሶን የተሻለ የማውቀውም ስለነበረ ክሱን አልተቅበልኩትም። የሆነ ሆኖ ነገሩን ከተስፋዬ ጋር ሳነሳው “በየነ ዋና ጸሀፊ ለመሆን ስለሚፈልግ ይውስደው!” አለኝና አቃለለኝ።ዋና ጸሐፊም ሆነ።

በሕዳር ወር 1984 ወደ አውሮጳና አሜሪካ ለመጓዝ ሲግጅት ላይ እያለሁ ፒያሳ  ቲ- ሩም ምሳ ሊጋብዛኝ እንደሚፍልግ ነገረኝና ተገናኘን።የምትሔድ ከሆነ ስራውን በተሻለ ለማጠናከር  የሊቀመንበርነቱን ስራ በውክልና ስጠኝ”  አለኝ።ወረቀት የዞ ነበርና እዚያው ፈርሜእስከምመለስ ድረስ በየነ ጴጥሮስ ሊቀ መንበር ክሆኖ እንዲስራ” ብዬ ጻፍኩለት።ለዚህ ጉዳይ ምሳ መጋበዝ ድረስ መሔዱ ያኔም አሁንም ይገርመኛል። ምሳ የሚያስጋብዝ ትውውቅ የለንምና ነው።

ከዚያም እኔ በህዳር 1984 ከኢትዮጵያ ወጣሁ። መመለሻ ድልድዬን መለስ ዜናዊ ቦደሰውና በዚሁ ቀረሁ። በየነ ጴጥሮስድርጅት ማፈራረሱን፤መከፋፈሉን፤ማኩረፉን ተያያዘው። ይህንን ስራውን የሚቃወም የሚመስለውን፤የሚጠረጥረውን ሰው ያኮርፋል።ይህንን ወዳጃችንን ዶክተር ማራራ ጉዲናና መጠየቅ ነው። አንዴ ኢድሐቅ ለሚባል የኢሕአፓ ስዎች ያሰባሰቡት ድርጅት ሊቀ መንበረነት በየነ ጋር ተወዳድሮ መረራ ሲያሸንፍ ጊዜ አኮረፈው።ሌሎች ስማቸውን ለጊዜው መጥራት የማልፈለገው ሁለት የደቡብ ኢትዮጵያ ድርጅቶች መሪዎች የነበሩም ማኩረፉን ነግረውኛል። ከኔም ጋር ያለው ግንኙነት የኩርፊያ ያክል ነው። ለዚያውም እኔ ተጠንቅቀ ሸሽቼ እንጅ ተቀናቅኜም አላውቅም። የምሸሸው “አስፋ እንዲህ አለኝ !”የሚል ምክንያት ላለመስጠት ነበር።

መጀመሪያ የበተነው የኛን ድርጅት ኦሞቲክን ነበር።ኦሞቲክ ከድርጅቶ በስነ ሥርአት ጉድለት ያሰናበታቸውን ሁለት ሰዎች፤ ፊታውራሪ መኮንን ዶሪንና ደምሴ ጻራና የምክር ቤት አባል አስደራጋቸው። የሚገርመውኮ ፊታውራሪ መኮንን ወያኔ ሁኖ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስቴር ሆኖ የተሾመው ከኦሞቲክ ከተገለለ ማግስት ነበር። ሌላው በጥር ወር 1984ወደ 2,000 የሚጠጋ አዲስ አበባ ኗሪ የጋሞ ጎፋ ሰው” መኮንንና ደምሴ ከሐዲዎች ናቸው !”ብሎ ሰለማዊ ሰልፍ አድርጎ ማንነታቸውን በአደባባይ ገልጧልኮ።

አሁን ዘመኑን በረሳሁት በየነና መኮንን አሜሪካ ይመጡና እኔ የነበርኩበት ቤት ያርፋሉ። ምንም ምንም እንዳልሆነ አድርጌ አስተናገድኳቸው። የመጡት ፕሬዚዳንት ካርተር አትላንታ ባዘጋጁት የሆነ የእርቅ ስበስባ ላይ ለመገኘት ነበር። የትኛውን ድርጅት ወክሎ እንደመጣ እንኳን እኔ በየነም የሚያስታውሰው አይመስለኝም። ሊቀ መንበር የሆነውን ድርጅት ብዛት ማስታውስ የሚችል አይመስለኝም። ዘመኑም ራቅ ብሏል። የማስታወሰው አቶ ተሾመ ገብረ ማርያምም አብሮ መጥቶ ነበር። ቦስተን ሁኖ ለበየነ ስልክ ሲደውል አንድ ሁለቴ አነጋግሪያለሁ። ካርተርንም በስልክ ያነጋገርኩት በዚያ አጋጣሚ ነበር። ብቻ ብዙ አብረው የመጡ ስልክ ይደውሉልታልና ያነጋግራል። እስማለሁም!!በተመሳስይ ጉዳይ ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ መልስድ ሲስጥ እስማዋለሁ:: ይገርመኛል!!

አንድ ጥዋት ሎስ አንገጄሊስ (Los Angeles) በእግራችን ሽረሸር ስናደርግ “በየነ አንተ ከደቡብ ኢትዮጵያ አትመስለኝም!” አልኩት። ከት ከት ብሎ ስቆ ፤ሳቁ( ትርጉሜ ጭምር ገብቶትና በ አድናቆትም እንደታገርኩት ቆጥሮ ጭምር ይመስለኛል)” እንዴት? ለምን?” አለኝ። “ሁለመናህ !”አልኩት። “አባቴ ፖሊስ ነበሩ።ያደኩትም ጋሞ ጎፋ ነው” አለኝ። አንድምታው ተንኮሉን የተማርኩት ከፖሊሱ አባቴ ነው ለማለት መስለኝ።የጨንቻ ሰዎች” የፖሊስ ዘመድ የቤንዚን አመድ የለውም!” ሲሉም እሰማነበር።እኔ ከደቡብ ኢትዮጵያ አተመስለኝም ስለው የደቡብ ኢትዮጵያ ሰው ይህ አነባባሮ ጠባይ የለውም ለማለት ነበር።

ከብዙበጥቂቱ፣በየነ የጋሞ ልጆችን አበጣበጠ። የጋሞ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት የሚባል ነበርና መሪዎችን አልፎ፤ተቀናናቃኝ ፈጠሮ፣ በነዚያ ተቀናቃኞች አመካይነነት ማባላቱን ጀመረው።ይህ መባላት የጋሞ መሠረታዊ ባሕርይም ስለ አልሆነ እንዴት እንደተሳካላት አሁንም ይገርማኛል። በዚህ ምክንያት ያደርኩት email አሁን ሳነበው ታሪካዊ ስነድ ይመስለኛል። አጥጋቢም ሆነ የሚረባ መልስ አልሰጠኝም። የዚህ የemail ጥሩ ነገሩ በየነ አልደረሰኝም ሊል አይችልም።ከደረሰ ደረሰ  ፤ካልደርሰ ተቀባይ የለውም ብሎ መልሶ ለላኪው ይልክለታል።

ግርማ ስይፉ ስለንጉስና በዝርያ አልጋ መውረሱን ያነሳው ኃይለ ሥላሴን አስታወሰኝ። 1966 ንጉሱ ጃጅተው ነበር :: ያም ሁኖ ስልጣንዋን የሙጥኝ ብለው ያዟት። ከዚያ በኋላ ደርርግ የሆነው የወታደር ስብስብ  ሰላምታ ይሰጥና “እግሌንም እገሌንም ወህኒ ማውረድ እንፈለጋለን!” ሲሉ” ወሰዷቸው!” ነበር። አድሮ” ልጆችዎንም የልጅ ልጆችዎንም !”ሲሏቸው ውሰድዋቸው ሆነ። በመጨረሻም ራሳቸውን አንዲት እዚች ግቢ በማትባል መኪና አስገብተው ወስዷቸው።”ከስልጣን ሞት ነው የሚለየን!” የማለት ጥሩ ምሳሌ ይመስሉኛል።

በኢትዮጵያ ፓለቲካ  ከ1983 ጀምሮ ስማቸው ያልየለተለየ 3 አሉ። በየነ ጴጥሮስ ፤ኃይሉ ሻውል  ፤ይቅርታ ኢንጂኔር ኃይሉ ሻውልና ዶክተር መረራ ጉዲና ናቸው። ኢንጂኔሩ አሁን  በተፈጥሮ ግዴታ ገሸሽ ያለ  ይመስላል። ማራራስለትላንት ስለዛሬ ሰለነገም ይጽፋል። ይናገራል! በፓለትካዉ ቦታ፤በቀጥታ ም በተዘዋዋራም ስፍራ (Relevance) ያለው ይመስለኛል።ጎበዝ !ያለበለዚያኢትዮጵኮ የወጣቶችአገርኮ ነች!!

በየነ ጴጥሮስ እላይ በጨረፈታ ለማሳየት ለሞከርኩት ስራው መላውን አለም ደጋግሞ ዞሯልኮ! በዚህ 25 አመት ሙሉ የድርጅቶች መሪነቱ ምን ፈየደ? ምንስ ተናገረ? ምንስ ጻፈ ?የሚል ቢኖር ጉዱ ይፈላ ነበር። የሚል ሰው አለመኖሩ የበጀው መስለኝ። እንዳይኖሩ አድርጎ ይሆን?አሁን ግርማን ላከበት? አንዳንዴ ያኔ ከባንክ ገንዘብ ይዞ ጠፍቶ በኋላ የወያኔ አባል ሁኖ የገንዘብም ምክትል ሚንስቴር እንደሆነው ሰውዬ በየነ  ጴጥሮስም የወያኔ አባል ይሆን? እላለሁ  የኸው ለ25 አመት ያ ሁሉ ሰው ወህኒ ሲወርድ በየነ አለምን ይዞራል።

ዘኃለፈ ስርየት ይባልና ለንስሀ ሞት አብቃኝ !!ተብሎም ይጸለያል

የኢትዮጵያ መንግስት በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሸጠውን የቦንድ ገንዘብ እንዲመልስ ተፈረደበት

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በአባይ ግድብ ሰበብ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች እየተዟዟረ ለኢትዮጵያውያን ቦንድ የሸጠው የኢትዮጵያ መንግስት ገንዘቡን እንዲመለስ ተፈረደበት::

bond abay
የአሜሪካን የቦንድ ሽያጭ የሚቆጣጠረው መስሪያ ቤት (The Securities and Exchange Commission) ዛሬ ባወጣው መግለጫው የኢትዮጵያ መንግስት በአሜሪካን ሃገር እየተዟዟረ የሸጠው ቦንድ ህገወጥና ያልተመዘገበ የሃገሪቱን ሉአላዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው::

በአባይ ቦንድ ሰበብ የኢትዮጵያ መንግስት በአሜሪካ ቦንድ በመሸጥ 5.8 ሚሊዮን ዶላር የሰበሰበ ሲሆን የአሜሪካን የቦንድ ሽያጭ የሚቆጣጠረው መስሪያ ቤት (The Securities and Exchange Commission) ባቀረበው ክስ መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት ገንዘቡን እንዲመልስ ተፈርዷል:: የኢትዮጵያ መንግስት በአሜሪካ የቦንድ ሽያጭ ማድረጉን ማመኑንም ኮሚሽኑ በድረገጹ ያወጣው መረጃ ይጠቁማል::

የኢትዮጵያ መንግስት የአሜሪካንን ህግ ሳያጠና በደመነፍስ በየከተማው ዞሮ የሸጠውን ቦንድ ገንዘብ ከመመለሱም በላይ ቅጣት የተጣለበት መሆኑን ያስታወቀው የኮሚሽኑ መስሪያ ቤት ድረገጽ ከተበደረው ብድር ላይ ተጨምሮ ከነቅጣቱ 6.5 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተስማምቷል::

በኮሚሽኑ ክስ ላይ እንደቀረበው የአዲስ አበባው መንግስት ከ3100 ኢትዮጵያውያን በአባይ ቦንድ ሰበብ ዶላር ሰብስቧል::

ሕወሓት የሚመራው መንግስት በአሜሪካ ቦንድ ለመሸጥ ሲንቀሳቀስ በርካታ ምሁራን ድርጊቱ ሕገወጥ ነው በሚል ሲቃወሙ; የተለያዩ አስተያየቶችንም ሕግ እያጣቀሱ በዘሐበሻ ድረገጽ ላይ ሲጽፉ እንደነበር ይታወሳል:::


ከሃብታሙ አያሌው እስከ በቀለ ገርባ –በእስር ቤት የሚፈጸሙ ሰቆቃዎች |ከሙሉነህ ኢዩኤል

$
0
0

ባለፈው ሳምንት አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች የኦሮሞ ፌዴራልስት ኮንግረስ መሪዎች ከታጎሩበት ጎረኖ “ፍርድ ቤት” ቀርበው ነበር። መቸም ስም አጥቼለት እንጂ “ፍርድ ቤት” ብዬ ስጠራው በጣም እየሰቀጠጠኝ እንደሆነ ይታወቅልኝ። ያለ ስሙ ስም ሰጥቼ “ፍርድ ቤት” ስለው አቶ በቀለና ሌሎች ብዙ ሺዎች የሚያዩትን ፍዳ ያራከስኩባቸው፣ ወያኔንም ስልጣኔ የሚባል ነገር እስከወዲያኛው የማይገባው እጅግ ኋላ ቀር ቡድን እንደሆነ እያወኩ ተቀናቃኞቹን ፍርድ ቤት አቅርቦ እንዲዳኙ እድል የሚሰጥ ስልጡን ቡድን እንዲመስል ያረኩ እየመሰለኝ በጣም እየተሳቀቅኩ ነው። ቢያንስ አቶ በቀለና በዚያ ማሰቃያ ቦታ የተገኙና ወደፊትም የሚገኙ ሁሉ ፍርድ ቤት ቀርበዋል ብዬ እንደማላምን ያውቃሉ ብዬ አስባለሁ። እነርሱም ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና ወያኔ እስካለም ድረስ እንደማይቀርቡ ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ትግላቸው ለምን ሆነና?

bekele gerba

እጅግ አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተው ጉዳይ ግን የእነ አቶ በቀለና ጓዶቻቸው በቁምጣና በእጅጌ ካንቴራ ተገላልጠው መምጣታቸው ነበር። ለዚህ ደግሞ ምክንያት የነበረው የሚለብሱትን የልብስ አይነትና ቀለም ወያኔዎች ካልመረጥንላችሁ በሚል ባነሱት የእብሪት እርምጃ አልበገር ያሉ ታሳሪዎች የሰው ልጆች መሆናቸውንና ለሰው ልጅነት ያላቸውን የተከበረ እይታ ለማሳየት አጋጣሚውን ለመጠቀም መወሰናቸው ነበር። የእነ አቶ በቀለ መልዕክት ከአሳሪዎቻቸው መልዕክት በእጅጉ ይቃረናል። እስቲ ሁለቱን መልዕክቶች ተራ በተራ እንያቸው፤

ታሳሪዎች የ”ፍርድ ቤት” ቀጠሮ እንዳላቸው ስለሚያውቁ አስቀድመው ተዘጋጅተዋል። እነ አቶ በቀለ “ፍርድ ቤት” ሊሄዱ የተነሱት በአጋዚ ጦር በኦሮሚያ ውስጥ ለተገደሉ ከ400 በላይ ለሚቆጠሩ ወንድሞቻቸው ሃዘን ሊቀመጡ እንጂ ፍትህ ፍለጋ አልነበረም። በሃገራችን ባህል ደግሞ ሰው ሀዘን ሲቀመጥ ጥቁር ይለብሳል። እንኳን በግፍ ለተጨፈጨፉ ወንድሞቻቸው ቀርቶ ሰው እድሜ ጠግቦ ለሞተ ዘመዱም ጥቁር ይለብሳል። ለቅሶ ደርሰው የሟች ቤተሰቦችን ማጽናናት ባይችሉ እንኳን ”በፍርድ ቤት” ደጃፍ ተገኝተው ሃዘናቸውን መግለጽ ይፈልጋሉ። ሰው መሆን ይሀው ነው ትርጉሙ።

አሳሪዎች ጥቁር የለበሱ ታሳሪዎችን ሲመለከቱ ደማቸው ፈላ። ወደየመኪኖቻቸው መውሰዱን ለጊዜው ገታ በማድረግ ወደዞኖቻቸው መልሰው ልብስ እንዲቀይሩ ያዛሉ። ወላጆች ለህጻናት አልያም በራሳቸው መምረጥ ለማይችሉ (mentally impaired) ለሆኑ ልጆቻቸው ልብስ ይመርጡላቸዋል። ጌቶች ለታሳሪዎች “ልብሳችሁን ቀይሩ” ሲሏቸው ምን እያሏቸው ነው? ህጻናት ወይም የአካል ጉዳተኛ ስለሆናችሁና መምረጥ ስለማትችሉ እኛ እንምረጥላችሁ እያሏቸው ነው። ለአቶ በቀለ ከራሱ ልብሶች ውስጥ አሳሪዎች መርጠው ቢሰጡት በራሱ ምርጫ የገዛቸውና ሌላ ጊዜ ሲለብሳቸው የነበሩት የራሱ ልብሶች በጣም አስጠሉት። እነርሱ የመረጡለትን ልብስ መልበስ ህጻን ነኝ አልያም የአካል ጉዳተኛ ነኝ ብሎ እንደማመን ሆነበት። “እናንተ የመረጣችሁልኝን የራሴን ልብስ ከምለብስ እራቁቴን ብሄድ ይሻለኛል” አለ። የራሱ ልጆች ያሉት የተከበረ ሰው (adult) መሆኑን አስመሰከረ። ሰው የመሆን ትርጉሙ ለራሱ የሚለብሰውን የሚጠጣውን የሚመራውን መምረጥ መሆኑን አስተማራቸው። እንዳለመታደል ሆኖ አሳሪዎቹ ይሄ ትምህርት ይገባቸዋል ወይ ብዬ እጠይቅና በአንድ ወቅት በእጃቸው ስለነበርኩና እነዚህን ሰዎች ስለማውቃቸው ድንጋይ ላይ ውሃ እንደማፍሰስ ስለሚሆንብኝ በጣም እተክዛለሁ።

በመጨረሻ በእስር ቤት ውስጥ ሰቆቃ ስሚፈጽሙና ስለሚያስፈጽሙ ሰዎች ማንነት ጥቂጥ ልበል። የእስር ቤቱ ዋና ዋና ሰዎች የአንድ አካባቢ ተዎላጆች ናቸው። ዋናው ሃላፊ አብርሃም ወ/አረጋይ ይባላል። ሰውነቱ ሞላ ያለ፤ ምቾት ያንገላታው ሰው መሆኑን ከቆዳው ወዝ በቀላሉ መገመት የሚያስችል አይነት ሰው ነው። ከድንጋይ ማምረቻ ድግሪ ጭኗል እይተባለ ይወራለታል። ድንጋይ የሚፈለጥበት እንጂ እውቀት የማይገበይበት ቦታ ለመሆኑ ከአብርሃም ወ/አረጋይ በላይ ምን ምሳሌ ማቅረብ ይቻላል? አብርሃምን ያገኘ ሁሉ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን ማድነቁ የማይቀር ነው። በምንም አይነት ጉዳይ ላይ ከአብርሃም ጋር ተነጋግሮ መግባባት የማይታሰብ ነው። ድንጋይ ታውቃላችሁ? የሰው ድንጋይ። ለፖለቲካ እስረኞች ያለው ጥላቻ ድግሞ የሚያስፈራ ነው።

በሁለተኛ ደረጃ ያለው ሰው አበበ ዘሚካኤል ይባላል። ቀይ አጭር፤ በአንድ በኩል ከጆሮው ከፍ ብሎ ጭንቅላቱ ላይ ትንሽ እብጠት ያለበት ሰው። እህቱ የቀበሌያችን ሊቀመንበር ነበረች። ከበደች ዘሚካኤል ትባላለች። አበበ በጣም የምትወዱት ክፉ ሰው ነው። እንዴት ክፉ ሰው ይወደዳል ትሉኝ ይሆናል። ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ የምትናገሩት ነገር የሚገባው ሰው ማግኘት መቻል እንዴት ብርቅ ነገር መሰላችሁ! እስር ቤት ውስጥ ያሉ ሃላፊዎች ሁሉ ድንጋይ በሆኑበት ቦታ የምትናገሩት ነገር የሚገባው ብቸኛ ሰው አበበ ይባላል። ርህራሄ የሚባል ነገር መኖሩን ያልሰማ ሰው ነው። አብርሃም በማይኖርበት ጊዜ የእስር ቤቱ ሃላፊ እርሱ ነው። በተጨማሪ ለእስረኞች የሚመጡ መጽሃፍትን አንብቦ እንዲገቡ አልያም እንዳይገቡ የሚወስነው እርሱ ነው።

በሶስተኛ ደረጃ የሚቀመጡት ሶስት ሰዎች ሲሆኑ፤ እነርሱም ሻለቃ አፈወርቅ፣ ጉኡሽና የማነህ ተክሉ ይባላሉ። የአፈወርቅንና የጉኡሽን የአባቶቻቸውን ስም አላውቅም። በዚህ አጋጣሚ የአባቶቻቸውን ስሞች ላስቀዳኝ ወሮታ እከፍላለሁ። ሻለቃ አፈወርቅ ገራ ገር ሰው ነው። በገራገርነቱ ካልሆነ በቀር በእውቀት ከሌሎቹ እምብዛም የሚለይ አይደለም። ምንም እንኳን በተወላጅነት የጌቶቹ አገር ሰው ቢሆንም የደርግ ሻለቃ ስለነበር ሌሎቹን ይፈራቸዋል። እኔ እንዳየሁት ሌሎቹን ስለሚፈራ ነው እንጂ በጎ ነገር ለማድረግ ፍላጎት ያለው ሰው ይመስላል። ከብዙ እስረኞች እንደሰማሁት የጥቅምት 21 1998 የጅምላ ጭፍጨፋ ያስቆመው እርሱ እንደሆነ የመሰክሩለታል፤ ራሱም የዚያን ጎደሎ ቀን የጅምላ ፍጅት ማስቆሙን ይናገራል። በዚህ ጭፍጨፋ የሞቱት 163 እስረኞች ሲሆኑ ስም ዝርዝራቸውን “የቃሊቲው መንግስት” በሚለው የሲሳይ አጌና መጽሃፍ ውስጥ መመልከት ይቻላል። ሻለቃው ለአጣሪ ኮሚሺን ሃላፊዎች በሰጠው ቃል በ30 ደቂዳ ውስጥ 1500 ጥይት መተኮሱን እየተጸጸተ መግለጹን ሰምቻለሁ። ከቃሊቲ የወጣን ቀን በእነ አቶ ሀይሉ ሻውል ዞን የነበሩትን የቅንጅት እስረኞች “አውቀን በድፍረት ሳናውቅ በስህተት የፈጸምነውን በደል ይቅር በሉን” አይነት ሰላምታ ሰጥቶ መሸኘቱን በዚያ ዞን ከነበሩ እስረኞች ሰምቻለሁ።

ጉኡሽ በእድሜ ተለቅ ያለ ሰው ነው። በቤትና በስራ ቦታው መካከል ልዩነት እንዳለው የሚያውቅ አይመስልም። ወይ አልነገሩትም፤ ወይም አልገባውም። ጋቢ ለብሶ እስር ቤት ውስጥ ሲንጎማለል ስታዩት እስረኛ እንጂ ከጌቶቹ ወገን በጭራሽ አይመስላችሁም። “ጌታዬ ይሄ እኮ የሥራ ቦታ ነው፤ ጋቢ ተለብሶ አይዞርም” ብሎ ማን ወንድ ይነግረዋል? አንዳንዴ ደርግ በእነዚህ መሸነፉ በጣም ያስገርማል። አልፎ አልፎ ሲስቅ እንዳየሁት ትዝ ይለኛል።

የማነህ ተክሉ ፊቱ ዝናብ አርግዞ እንድጠቆረ የሃምሌ ወር ዳመና ፊቱ የማይፈታ ሰው ነው። እንደሱ አይነት ጨካኝ ከሰው ያልተፈጠረ አይነት ሰው ነው። ስለዚህ ሰው ባሰብኩ ቁጥር የሚመጡብኝ አንድ ቀን ነው። የሄ ቀን “ፍርድ ቤት” ደጃፍ መኪና ውስጥ ተቀምጠን ወደአዳራሽ እስከሚያስገቡ እየተጠባበቅን ሳላ እኛን ካለንበት መኪና ማዶ ባለ ሌላ መኪና ውስጥ ያለችውን ባለቤቱን ሰላምታ ስለሰጣት እስክንድርን ሊቆጣው ወደ መኪናችን የመጣበት ቀን ነው። በጣም ተናዶ ለመማታት እየቃጣው ሰላምታ መስጠት እንደማይችል ገለጸለት። እስክንድርም የዘጠኝ ወር እርጉዝ የሆነች ባለቤቱን ሰላም በማለቱ እንዲያው ሊያዝንለት እንጂ ሊቆጣው እንደማይገባው በትህትና ሊያስረዳው ሞከረ። ይባስ ብሎ ሰርካለምና እስከንድር እንዳይተያዩ ሴት እስረኞችን የጫነው መኪና እኛ ካለንበት ዞር እንዲል ትዕዛዝ ሰጠ። እስረኞች ሰዎች መሆናቸውን የዘነጋ ሰው ነው። እነ አቶ በቀለና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች በምን አይነት መከራ ውስጥ እንደሚያልፉ እንዲያስታውሰን የአቶ ሃብታሙ አያሊውን ሰቆቃ ልጋብዝዎ፦

በሚሪንዳ ላይ በፌስቡክ እየተጻፈ ያለው ነገር የአላሙዲንን ሞሐ እያሸበረው ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) አንድ ማንነቱ ያልተገለጸ ሰው በፌስቡክ 12 ሰዎች ሚሪንዳ ጠጥተው መሞታቸውን ማሰራጨቱ በአላሙዲን የሚመራውን ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካን እያሸበረው መሆኑ ተሰማ::

በፌስቡክ እየተሰራጨ ያለው መረጃና በድፍን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እየተወራ ያለው በስክሪን ሻት የምታዩት ነው::

Screen Shot 2016-06-09 at 3.30.34 AM

የሞሐ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ ባወጣው መግለጫው “ሰሞኑን በፌስቡክ ድረ-ገጽ አንድ ተራ ጸሐፊ ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃና ምንም የተፈጠረ ነገር ሳይኖር በተጠቃሚው ዘንድ መልካም ስም ያተረፈውንና ተወዳጁን የሚሪንዳ ምርታችንን ስም ለማጉደፍ ወሬ ነዝተዋል:: ይህ የሐሰት መረጃ በሐዋሳ ጤና መምሪያና ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም ችግሩ ተከስቷል በተባለው የዘውዲቱ ሆስፒታል ተገኝተን ባጣራነው መሰረት የሚሪንዳን ምርት በመጠቀም አንድም የታመመ ወይም የሞተ ሰው እንደሌለ አረጋግጠናል” ሲል ገልጿል::

በሚሪንዳ ምርት የተነሳ ተከሰተ ስለተባለው ነገር የተቋማት ሃላፊዎች ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ያስታወቀው የሞሐ ለስላሳ መጠጦች መግለጫ “ይህ የበሬ ወለደ ውሸት እና ተራ አሉባልታ የተለመደና ድርጅታችንን ለመጉዳት ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ ሴራ ነው” ብሎታል::

በፌስቡክ ላይ ሚሪንዳ ሰው ስለመግደሉ አንድ ሰው የጻፈው ጽሁፍ በሞሐ ለስላሳ መጠጦች ውስጥ ከፍተኛ ሽብር የተፈጠረ ሲሆን ድርጅቱ ይህንን ለማስተባበል ከዘውዲቱ ሆሥፒታል “ምንም የሞተ ሰው የለም” የሚል የማረጋገጫ ደብዳቤ አስወጥቶ በትኗል:: ሁለቱንም ደብዳቤዎች ይመልከቷቸው::

pepsi facebook

አገዛዙ አለኝ የሚለውን ህገ መንግስት በተግባር ቀዶ ጥሎታል!!! – ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

blue-party-276x3001.jpgአገዛዙ ራሱ ያፀደቀው ህገ መንግስት አንቀፅ 15 ማንኛውም ሰው በህግ በተደነገገው ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ህይወቱን አያጣም በማለት ቢደነግግም ለአንድ ቀንም እንኳ ህግን አክብሮ የማያወቀው ህወሃት/ኢህአዴግ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ዜጎችን በጠራራ ፀሀይ መግደሉን ዋና ስራው አድርጎታል፡፡ በተመሳሳይ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 21 በጥበቃ ላይ ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰባዊ ክብራቸውን በሚጠብቁ ሁኔታዎች የመያዝ መብት እንዳላቸውና ከትዳር ጓደኞቻቸውና ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ከሃይማኖት አማካሪዎቻቸው ከሃኪሞቻቸውና ከህግ አማካሪዎቻቸው ጋር ለመገናኘትና እንዲጎበኟቸውም ዕድል የማግኘት መብት እንዳላቸው ቢገልፅም አገዛዙ በህገ መንግስቱ የተሰጣቸውን የመፃፍ፣ የመናገርና የመደራጀት መብታቸውን ተግባራዊ በማድረጋቸው ብቻ በየእስር ቤቱ ያጎራቸው ዜጎች በአስከፊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ያለምንም ክስ ከአምስት ወራት በላይ ማዕከላዊ በሚባለው የዜጎች ማሰቃያ ጣቢያ ቆይቷል፡፡
እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አስተባባሪ አቶ አግባው ሰጠኝ እና ከእሱ ጋር በአንድ መዝገብ የተከሰሱ ተከሳሾች በማንነታቸው ብቻ በደል እንደሚደርስባቸው በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤት ቢናገሩም አገዛዙ ከማስተካከል ይልቅ ለምን ተናገራችሁ በማለት በጨለማ ክፍል ወስጥ አሰሯቸው ይገኛል፡፡ አመፅ አነሳስታችኋል በሚል ክስ የቀረበባቸው ምክትል ሊቀመንበሩን አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራሮችና አባላት በቀጠሯቸው እንዳይቀርቡ ከመደረጉም በላይ የእስረኞችን ስነ ልቦና በሚጎዳ ሁኔታ ልብሶቻቸውን ተቀምተው በባዶ እግራቸውና በወስጥ ልብሶቻቸው ፍርድ ቤት ለመቅረብ ተገደዋል፡፡

በቂሊንጦ ማጎሪያ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ አመራሮች አግባው ሰጠኝ ፣ዮናታን ተስፋዬ፤ ፍቅረማሪያም አስማማውና ብርሃኑ ተክለያሬድ በአሁኑ ሰዓት በጨለማ ክፍል ውስጥ ታስረው የሚገኙ ሲሆን በቅርብ ዘመዶቻቸውና በጠበቆቻቸው እንዳይጎበኙ ተደርገዋል፡፡ በአጠቃላይ አገዛዙ የራሱን ዜጎች በመግደልና በማሰር በስልጣን ለመቆየት መወሰኑን ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ የፈፀመው ወንጀል ያረጋግጣል፡፡ ስለሆነም ከዚህ አስከፊ አገዛዝ ተላቀን ህዝባዊ አስተዳደር መገንባት የምንችለው ሁላችንም ለመታሰርና ለመሞት ቆርጠን ስንነሳ ብቻ መሆኑን ተገንዝበን ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
ሰኔ 2 ቀን 2008 ዓ.ም

የበእውቀቱ ስዩም፣ የተስፋዬ ገብረአብና የእኛ ኢትዮጵያ

$
0
0

Beweketu Siyum

(ዮሴፍ ወርቁ ደግፌ)

«ነፍጠኞች የሴቶቻችንን ጡት እኛ ከበግ ላይ ጸጉር እንደምንሸልተው እንዲያ ነበር የሚቆርጡት። እነዚህ ሰዎች በግ ሲያርዱ በስመአብ ብለው ይጀምራሉ። የሴቶቻችንን ጡት

ሲቆርጡ ግን በስመአብ አይሉም። ግን ሀይማኖት አለን ይሉናል»
(ተስፋዬ ገብረአብ “የቡርቃ ዝምታ”)

«…ባጠቃላይ በሚኒልክ ተፈጸመ የተባለው ያኖሌ ጡት ቆረጣ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሰነዶች ላይ ያልተመሰረተ ለመሆኑ ይህ በቂ ማስረጃ ይመስለኛል። በአርሲ ታሪክ ዋና ባለሙያ የሆነው ፕሮፌስር አባስ ገነሞ በመጽሀፉ ውስጥ ጡት ቆረጣ መፈጸሙን የሚያሳይ አንድም የታሪክ ሰነድ ማቅረብ አልቻለም»

(በእውቀቱ ስዩም “ከአሜን ባሻገር”) «በፍትህ በኩል ግን ጣሊያን ይሻል ነበር። አማራ ሲመጣ ሰው የገደለ ይገደል የሚል አዋጅ

አመጡና እርስ በራስ መተላለቅ ሆነ»

(ተስፋዬ ገብረአብ “የቡርቃ ዝምታ”)

«የሁላችንም አባቶች የሁላችንም ጌቶች በፈረቃ ግፍ መፈጸማቸው በታሪክ ተመዝግቧል። በዘመናችን የምሬትንና የቂምበቀል ፉከራን ርግፍ አድርገን ትተን በሚያቀራርቡ በሚያስተባብሩ ሀሳቦች ላይ ከተጠመድን ከአባቶቻችን የተሻለ አለም እንደምንፈጥር ጥርጥር የለኝም»

(በእውቀቱ ስዩም “ከአሜን ባሻገር”)

የበእውቀቱ ስዩምን «ከአሜን ባሻገር» አዲስ መጽሀፍ ካነበብኩ በኋላ፥ ጥቂት ዘመናት ወደፊትና ወደኋላ በምናቤ ተንጬ ሳበቃ፥ አንድ ጓደኛዬን የበእውቀቱ ስዩምንና የተስፋዬ ገብረአብን ሥራዎች እንዴት ታነጻጽራቸዋለህ? ብዬ ጠየቅሁት። “በይዘት ነው በቅርጽ?” በማለት ጥያቄዬን በጥያቄ መለሰው። በ«ይዘት» አልኩት።

“ተስፍዬና በእውቀቱ ምንና ምን ናቸው፣
የጆሮ ጉትቻ፣ የአንገት ሀብል ናቸው” (እንደማይል ብጠብቅም)

“ተስፍዬና በእውቀቱ ምንና ምን ናቸው፣
የመርዝና የመድሀኒት ብልቃጥ ናቸው” (ይላል ብዬ ግን አልገመትኩም)

 

ይህች መጣጥፍ በ“መድሀኒት” እና በ“መርዝ” ብልቃጥ ሥራዎች ላይ አጭር ዳሰሳ የምታደርግ ናት። የተስፋዬ ገብረአብ እኩይ ፖለቲካዊ ትርክቶች ትዝታቸው ሳይደበዝዝ፥ ከእድሜው በላይ የበሰለው ወጣቱ ብእረኛ በእውቀቱ ስዩም፣ ለተስፋዬ መርዛማ ጽህፎች ማረከሻ መድሀኒት፣ ታሪክን በማስረጃ እያጣቀሰ ያቀረባት መጽሀፍ «ከአሜን ባሻገርን» ትሰኛለች። ማንኛውም ሰው በቀላሉ ሊያነባት የሚችል እጥር ምጥን ያለች ናት።

በእውቀቱ ስዩም ባለቅኔ ገጣሚና ድንቅ የወግ ጸሀፊ ሲሆን፥ አሁን ደግሞ የታሪክ ተመራማሪ እየሆነ ነው። ተስፋዬ ገብረአብ ጋዜጠኛና አጫጭር መጣጥፍ ጸሀፊ ነው። ተስፋዬ ገብረአብና በእውቀቱ ስዩም በጽሁፎቻቸው ይዘት ብቻ ሳይሆን፥ በጥበባዊ እውቀት (knowledge of wisdom) ደረጃም ቢሆን ሊወዳደሩ የሚችሉ አይደሉም። በእውቀቱ የትየለሌ ይልቃል። ተስፋዬ ገብረአብን ከበእውቀቱ ስዩም የሚለየው ዋና ነገር ደግሞ ከሙያ ስነምግባርና ከሞራል ሀላፊነት ውጭ፥ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጥላቻን ወይም ጠላትነትን ማእከል አድርጎ፥ የኦሮሞን ህዝብ እንደ ፖለቲካ መሳሪያነት በመጠቀም፥ ጥናት ያላደረገበትን ፖለቲካዊ ታሪክ፥ እንደ አፈታሪክ አጋኖ በመጻፍ፥ ህዝቦችን ለማጋጨት የሚጥር፥ እበላ ባይ የአስቤዛ ጸሀፊ መምሰሉ ነው። ይሁንና በ«ጀሚላ እናት» መጽሀፉ ምርቃት ላይ፥ በዋሽንግተን ዲሲ በአንዲት ትንሽ ክፍል ውስጥ በጣም ጥቂት የኦሮሞ ልጆች ብቻ በተገኙበት ባደረገው ንግግር ላይ ተስፋዬ ምኞቱን ከዚህ በታች እንደተጠቀሰው ገልጿል። (የቪዲዮ ክሊፑ ይገኛል) መልካም ምኞት ነው።

«በእውነቱ ቅር ነው የሚለኝ ዛሬ፥ የደስታዬ ቀን ነው አልልም። የልቤን ነው፣ የልብህን ተናገር ካላችሁኝ ደስተኛ ነኝ ልል አልችልም። ምክንያቱም የትግራይ ሰዎችም፥ ኤርትራውያንም፥ አማሮችም፥ ኦሮሞችም፥ አንድ ትልቅ አዳራሽ ውስጥ ተሰብስበው መጽሀፌን ብመርቀው ደስ ይለኛል። ይኼ ባለመሆኑ ቅር ይለኛል። ይሄ እንዲመጣ ነው የምመኘው» (የተስፋዬ ገብረአብ «የጀሚላ እናት» የመጽሀፍ ምርቃት ንግግር)

በእውቀቱ ስዩም የፖለቲካ ታሪክ ተመራማሪነቱን ፍንጭ የሚያሳይ ጠንካራ ብእር ያነሳው እንደ ፕሮፌሰር አስመሮምና እንደ ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረአብ ለመሳሰሉት፥ የኢትዮጵያ መበታተን ለኤርትራ ህልውና የሚበጅ ለሚመስላቸው፥ በጠላትነትና በጥላቻ ስሜት በተዛባ ታሪክ ለጻፉት የፕሮፓጋንዳ ስራ አጻፋ ምላሽ፥ በጥናት የተደገፈች፥ ለማጠቃሻነት (Reference) የምትበቃ «ከአሜን ባሻገር»ን በመጻፍ ነው። በእውቀቱ ስዩም ፖለቲካዊ ታሪክን ያለአድሎ (witout bias) ለመጻፍ ከእድሜው በላይ የሚታትር ብርቱ ጸሀፊ የሆነበት ምክንያት ፖለቲካዊ ወገንተኛነት፤ የ«ዘሬን ያንዘርዝረኝ»፤ ወይም እበላባይነት ችግር ስለሌለበት ይመስለኛል። እርሱም በተዘዋዋሪ ጠቅሶታል። በፕሮፌሰር አስምሮምና በተስፋዬ ገብረአብ መካከል ላለው ልዩነትም፥ ፕሮፌሰር አስምሮም ኤርትራ ተመልሳ በኢትዮጵያ ውስጥ ትካለላለች ከሚል ስጋት (insecurity) ታሪክን

እያወቁ፥ ነገርግን እያጣመሙ የሚጽፉ ምሁር ሲሆኑ፥ ተስፋዬ ደግሞ ያለእውቀት በድፍረት፥ ያለጥናታዊ ማስረጃ አፈታሪክ ላይ ተመስርቶ የሚጽፍ የአስቤዛ ጸሀፊ መሆኑ ነው።

የተስፋዬም ይሁን የበእውቀቱ ጽሁፎች የአስተዳደግ ተጽዕኖ ይታይባቸዋል። በእውቀቱ ስዩም «አምላክ አልባ» (Atheist) መሆኑን በግልጽ እየተናገረ፥ ነገርግን በ«ከአሜን ባሻገር» መጽሀፉ «የሚያስታርቁ ብጹአን ናቸው» (ማቴ.5፥9) የሚለውን የክርስትና መርህ የሚከተል ጸሀፊ ተመስሏል። «አምላክ የለኝም» ቢልም ታሪካዊ እውነታን ግን በማስረጃ በመግለጽ፥ አድልኦ የሌለበት ስራ አቅርቧል። ተስፋዬ ገብረአብ ደግሞ «ክርስቲያን ነኝ» እያለ፥ ነገርግን የክርስትና መርህን ተገላቢጦሽ «በወንድማማች መካከል ጸብን የሚዘራ» (ምሳሌ 6:19) እኩይ ጸሀፊ ሆኖ ይገኛል። ተስፋዬ የክርስትና እምነት ቢኖረውም፥ በአስተዳደጉ ኢትዮጵያን እንዲጠላ የተደረገበት ለመሆኑ ማስረጃው የዘመናት የጥላቻ ምርጊት ወደጠላትነት ተቀይሮበት፥ የጽሁፍ ስራዎቹ በሙሉ ኢትዮጵያን ወደ መበታተን የሚገፋፉት መሆናቸው ነው።

በአንድ ሰው ውስጥ እንዲህ አይነት ተቃርኖ (paradox, self-contradictory) ከአስተዳደግ ተጽእኖ ውጭ በደም /በመወለድ ብቻ/ የሚመጣ አይደለም። መጽሀፍ ቅዱስም አንድ ዛፍ ጣፋጭም መራራም ፍሬ ሊያፈራ አይቻለውም ነው የሚለው። በርግጥ ተስፋዬ ኦሮሚያን እወዳለሁ ይላል። ኦሮሚያን መውደዱ በንጹህ ልብ ከሆነ ምንም ችግር የለበትም። ነገርግን ህዝብን በመሳሪያነት ለመጠቅምና ለእበላ-ባይነት ከሆነ፣ ጊዜውን ጠብቆ ተስፋዬ ክፉ ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ መሆኑ አይቀርም። ተስፋዬ ገብረአብ የአሰፋ ጫቦ ጽሁፍን የሚመስል እንደውሀ የሚፈስ የስነጽሁፍ ስጦታ ነበረው፤ ነገርግን በጽሁፎቹ ይዘት ምክንያት፥ ዛሬ እጅግ በጣም በጥቂት ሰዎች (ጥቂት ኦሮሞዎች ብቻ) ተወስኖ፥ ከአብዛኛው ኦሮሞም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝቦች ተነጥሎ በቅሬታ ውስጥ እንደሚኖር በ«የጀሚላ እናት» መጽሀፍ ምርቃት ላይ ራሱ መናገሩ ከላይ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ደግሞ ተስፋዬ አንድን ብሄር በጠላትነት በማየት እያብጠለጠለ በሚጽፋቸው እኩይ ስራዎቹ በመደሰት፥ ተራ ፖለቲካዊ ድጋፍን መፈለግ፥ የራስን ትልቅነት ባለመረዳትና በራስ ባለመተማመን የሚመጣ ጉድለት ያስመስላል። ይህም ተስፋዬ ገብረአብን የኦሮሞ «መሲህ አዳኝ» አድርጎ የማየት ችግር ነው። ይህንን በማለቴ “ነፍጠኛ ስለሆንክ ነው” ምናልባት የምትሉ ብትኖሩ፤ መግለጽ ካስፈለገ ከጃዋር መሀመድ የበለጠ ኦሮሞ መሆኔን ላረጋግጥ እችላለሁ። (ጃዋር መሀመድ በኢሳት ቲቪ ላይ «በአባቴ 50% እስላም ኦሮሞ ነኝ በእናቴ 50% አማራ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነኝ» ማለቱን ያስታውሷል) የሰው ልጅ መቸም ቢሆን ከአንድ ወይም ከሁለት ከሶስትም ዘር ሊወለድ መቻሉ እውነት ነው። ከዚህኛው ዘር ልወለድ ብሎ ጠይቆም አይወለድም። የሰው ትልቅነት የሚለካው ለዘሩ ከሚያደርገው ተቆርቋሪነት በላይ ለሌሎች በሚያደርገው መልካም ስራ መሆኑን አንዘንጋ። እምነታችንም ይህን ያዘናል።

የበእውቀቱ ስዩም «ከአሜን ባሻገር» መጽሀፍ ይዘትዋ እንደ ርዕስዋ ነው። ዋና ጭብጧ በየዘመኑ የሚሰጠንን ፖለቲካዊ ታሪክ ኪኒን ዝም ብለን አንዋጥ። ሁላችንም በጋራ ላመጣነው በሽታ፥ በጋራ መድሀኒት እንፈልግ፥ በጋራ እንፈወስ ነው። ጸሀፊው በዚህች አነስተኛ መድብል ውስጥ ጠለቅ ያለ ፖለቲካዊና ታሪካዊ ጭብጥ በማንሳት በጥናትም በመደገፍ፥ ብዥታ አለባቸው የሚላቸውን በግልጽ ይሞግታል። አብዛኛዎቻችን ወደዘራችን ባጋደለ ታሪክ አመለካከት በመፍገምገም፣ ሚዛኑን የጠበቀ ፖለቲካዊ እይታ ለመያዝ ተቸግረናል። አካሄዳችን ልከኛ ስላልሆነ ለማንኛችንም አይበጅም። በእውነተኛ የታሪክ ማስረጃ (historical facts) ይዘት እንከራከር፥ እንግባባ፥ የወደፊቱን በማሰብ በይቅርታና በምህረት እንኑር ይላል።

ኑ በስነስርዓት እንወቃቀስ፤ ማንም ከደሙ ንጹህ የለም። ሁሉም የኢትዮጵያ መሪዎች በጉልበት በግፍ የሚገዙ ነፍጠኞች ናቸው። የሩቁን ትተን ከአጼ ዮሀንስ እንኳን ብንጀምር፥ አጼ ዮሀንስ አጼ ቴዎድሮስን ለባእድ የእንግሊዝ ጦር በር ከፍተው ለሞት አሳልፈው በመስጠት ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ከሆኑ በኋላ፥ ኦሮሞንም አማራንም ሌሎችንም አስገብረው የገዙት በነፍጥ እንጂ በዲሞክራሲ አይደለም። አጼ ዮሀንስ ለንግስት ቪክቶሪያ በጻፉት ደብዳቤ የአዘቦ ኦሮሞ ሙስሊሞችን በሀይል መግዛታቸውን ያሰፈሩበት ማስረጃ እንዲህ ይላል።

«ባገሬ ኧዘቦ የሚባል የኦሮሞ እስላም አለ። ከርሱም ሽፍታ ተነሳብኝ፤ ለማጥፋት ዘመትሁ፥ እነርሱንም በእግዚአብሄር ሀይል አጠፋሁኝ»

(በእውቀቱ ስዩም “ከአሜን ባሻገር”)

አጼ ዮሀንስ ጎጃምን ለማስገበር በወረሩበት ጊዜ፥ የጎጃም ባላገሮች ከአጼ ዮሀንስ ጦር እግዚአብሄር እንዲታደጋቸው ተማጽነው ኖሮ፥ እግዜር ግን ባለመድረሱ፥ ንጉሱ በጎጃም ብዙ ጦርና ህዝብ በመጨረሳቸው ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ የወደቀች አንዲት ጎጃሜ የሚከተለውን ስንኝ ቋጥራ ነበር ይለናል «ከአሜን ባሻገር»።

ከሀበሻ ወዲህ ከሀበሻ ወዲያ፥
ሰውን ገረመው እኔንም ገረመኝ፤
ዮሀንስ እግዜርን ገድሎታል መሰለኝ፤ (በእውቀቱ ስዩም “ከአሜን ባሻገር”)

*/ በዚህ አገላለጽ ግን የአጼ ዮሀንስን ታላቅነት እያቃለልሁ አይደለም። ለሀገራቸው ነጻነት አንገታቸውን ለሰይፍ የሰጡ በጀግንነት ከወደቁት የሀገራችን መሪዎች አንዱ መሆናቸውን ማንም አይክድም/

አጼ ሚኒልክም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ደቡብ ኢትዮጵያ በአንድ ማእከላዊ ንጉሰ ነገስት መንግስት ስር እንዲኖር ያስገበሩት፣ በወረራ በነፍጥ እንጂ፣ በሰላማዊ መድረክ በድርድር አልነበረም። በዚያ ስልጣኔ አልባ

ጭለማ ዘመን ቀርቶ ዛሬም በኢትዮጵያ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ድርድር አይሰራም። በ19ኛው ክፍለዘመን በኢትዮጵያ ይቅርና በአውሮፓና በአሜሪካ ግዛት የተስፋፋው በወረራ በሀይል በጠብ-መንጃ ነው። በተለይም ከሚኒልክ መንግስት መስፋፋት ጋር ለሚነሳው ወቀሳ፥ የሚኒልክ ወታደር መሉ በሙሉ አማራ ብቻ በማድረግ ታሪክ ማዛባት ለማንኛችንም አይጠቅምም። የአማራ ጦር ብቻ ይሆን ዘንድም አቅም (የህዝብ ብዛት) አልነበረውም። ስለዚህም አጼ ሚኒልክ በወረራም ሆነ በወዳጅነት (በአምቻ ጋብቻ) ከሸዋ ከኦሮሞና ከጉራጌ ባላባቶች (ያካባቢ ገዢዎች) ጋር ከዋና ዋና የጦር አበጋዞች እንደነ ራስ ጎበና ዳጨ የመሳሰሉ የኦሮሞ ታላላቅ መሪዎችን በፊት አውራሪነት በማዝመት ሀረርን፣ አርሲን፥ ከፋን ወላይታን በማስገበር አንድ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስትና ጦር አቋቁመዋል። በዚህም በአድዋ ጦርነት ለቅኝ ገዥ ያልተንበረከከ፥ መላው የአለም ጥቁር ህዝብ የኮራበት ጦር በመፍጠር አጼ ሚኒልክ ከሀገራቸው አልፎ በአፍሪካውያን ለዘላለም የሚዘከር ስራ ሰርተው አልፈዋል። */የራስ ጎበና ልጅና የአጼ ሚኒልክ ሴት ልጅ ጋብቻ ውጤት የሆነውን የወሰንሰገድ ወዳጆን ፎቶ ማስረጃ ደግፎ ያቀረበ ታሪክ ጸሀፊ ያገኘሁት በእውቀቱ ስዩምን ብቻ ነው/*

«ምኒልክ ቤተመንግስት ውስጥ ወሳኝ የነበሩ ሰዎች ከተለያየ ብሄረሰብ የተገኙ እንደሆኑ ሁሉ በማስገበር ዘመቻ የተሳተፈው ሰራዊትም እንዲሁ ኅብረብሄራዊ መሆኑ እሙን ነው። ይልቁንም ኦሮሞ ያልተሳተፍበት የሚኒልክ ዘመቻ ማግኘት ይከብዳል» (በእውቀቱ ስዩም “ከአሜን ባሻገር”)

እንደ ተሥፋዬ ገብረአብ «በፍትህ በኩል ግን ጣሊያን ይሻል ነበር። አማራ ሲመጣ ሰው የገደለ ይገደል የሚል አዋጅ አመጡና እርስ በራስ መተላለቅ ሆነ» ብሎ ለመናገር እጅግ ይከብዳል ለህሊና ይሰቀጥጣል። ምክንያቱም ሚኒልክ በአድዋ ጦርነት ጣልያንን ድል ባይመታ ኖሮ፥ የቅኝ ተገዢነት ሰለባ በመሆን ዘላለም በበታችነት ስሜት (inferiority complex) እንኖር ነበርና ነው። የኤርትራ ቅኝ መገዛት እንኳን ዝንተ አለም እየቆጨን የሚኖር ነው።

ኦሮሞና የሀገር መሪነት ስልጣን ጥያቄ፦ ኦሮሞ በህዝብ ብዛትም በፖለቲካዊና በኢኮኖሚያዊ ጂኦግራፊም አብላጫ (Majority) ሆኖ ሳለ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የመሪነት ስልጣን አልነበረውም የሚለው ዛሬም ድረስ ውሀ የሚያነሳ ጥያቄ ሆኖ ይገኛል። ቀደም ባሉት የዘውድ መንግስታት የኢትዮጵያ መሪዎች የኦርቶዶክስ እምነታቸው ከፖለቲካ አመራራቸው ጋር እየተቀላቀለባቸው ባሳደረባቸው “በጎ ተጸእኖ” የተነሳ፥ በኦሮሞ ስማቸው በንጉስነት አልተጠሩም እንጂ ኦሮሞ ኢትዮጵያን መርቷል የሚል ወገን ብዙ ነው። ለምሳሌም የወሎው ንጉስ ሙስሊምና ኦሮሞ የነበሩት ራስ አሊ (በኋላ በክርስትና ስማቸው ንጉስ ሚካኤል የተባሉት) ልጅ የሆነው አቤቶ/ልጅ ኢያሱ እንዲሁም ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴን ይጠቀሳሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ከገዳ ባህል የተነሳ የኦሮሞ ንጉስ በኢትዮጵያ የነገሰ ባይኖርም በታሪክ በግልጽ እንደሚታወቀው በየጁ ዳይናስቲ (Yejju Daynasty) በ17ኛው ምዕተ አመት ኦሮሞዎች በገዳ አመራር (Collecetive Leadership) አብዛኛውን የኢትዮጵያ ክፍል የስራ ቋንቋ *ኦሮምኛ በማድረግ እንደመሩ በታሪክ ተጠቅሷል። *ኦሮምኛ በዚህ ዘመን የስራ ቋንቋ እንደነበረ አንዳንድ የውጭ ጽሁፎች ጠቅሰዋል። አቶ ጃዋር መሀመድም እንደ ፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪነት እንደገለጸውም የኦሮሞ ባህል ለአግድሞሽ (Horizontal Leadership) እንጂ ከላይ ወደ ታች በሚወርድ በአንድ ፈላጭ ቆራጭ ሰው ወይም ንጉስ (Vertical Leadership) ለመተዳደር የገዳ ስርአትና ባህሉ አይፈቅድለትም ይላል። ስለዚህም ኦሮሞ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ንጉስ ለመሆን በማንኛውም መመዘኛ አቅም አጥቶ ሳይሆን፥ በባህሉ የተነሳ ለመንገስ አልቻለም ለማለት እንችላለን ማለት ነው። የሰሜን ሰዎች ግን (አማራና ትግሬ) ከኦርቶዶክስ እምነታቸው የተነሳ የቤተክርስቲያን የአደረጃጀት መዋቅርን በመከተል (በአንድ ሊቀ ጳጳስ መመራት) ነገስታቶቹ ሀይማኖትን ከፖለቲካ ጋር በመቀላቀል፥ እየተገለባበጡም ቢሆን በፈረቃ የንጉስ አመራርን እውን አድርገዋል። ኦሮሞም በጋዳ ስርአት (Collective Leadership) ከላይ እንደተጠቀሰው በየጁ ዳይናስቲ አገር መርቷል፥ ብለን መደምደም ሁላችንንም የሚያስማማ ይመስለኛል። በዚህ ከተስማማን የኋላውን/ያለፈውን ለትምህርታችን (ከስህተት ለመማር) እያነሳን የወደፊቱንም በጋራ የምንኖርበትን የሰላምና የእድገት ራዕይ በተነጠል ሳይሆን በአንድነት መተለም ለሁላችንም የሚያዛልቅ ነው።

ነፍጠኛነት፦ «ከአሜን ባሻገር» በታሪካዊ መረጃ ኦሮሞም ነፍጠኛ እንደነበረ ትሞግታለች። ኦሮሞ ነፍጠኛ አልነበረም ብሎ ማመን፥ ታላቁን የኦሮሞን ህዝብ ህዳጣን የማድረግ ያህል ነው። ለምሳሌ ያህል የሲዳሞ፥ የጉራጌ፥ የጌዴኦ፥ የደቡብ-ህዝቦች ነፍጠኞች የአማራ (የክርስትና) ስም ቢይዙም በርካታ ነፍጠኞች ኦሮሞዎች እንደነበሩ ወደ ቦታው ሄዶ ዛሬም ድረስ ያለውን አሻራ ለማረጋገጥ ይቻላል። እነዚ ነፍጠኞች ከታላቁ ጀግና አርበኛ የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ሀገረ ገዥ ከነበሩት ደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶ ጋር ጠብመንጃ አንግተው የሄዱት ኦሮሞዎች ናቸው። በኋላ ላይ በህዝቦች ውህደት (Assimilation) ኦሮሞነት እየቀነሰ በወቅቱ ክርስትና መነሳትና አማርኛ መናገር እንደ ስልጣኔ ስለሚቆጠር፥ ቀስበቀስ ኦሮሞው ክርስቲያን ወይም አማራ ነኝ ማለት ጀመረ። የአሰፋ ጫቦ «የትዝታ ፈለግ» መጽሀፍም የጋሞ ነፍጠኞች ኦሮሞዎች ነበሩ ይላል። በኢህአዴግ መንግስት፥ የጉራጌ ህዝብን ወክለው የፓርላማ አባል የነበሩ ዶ/ር ሀይሌ የተባሉ ሰው (የአባታቸው ስም የተዘነጋኝ) «የጉራጌ ነፍጠኛ እኮ ኦሮሞ ነው፥ ጉራጌ ወደ ሌላ የኢትዮጵያ ክፍል ሄዶ ጥሮ መኖር የጀመረው በኦሮሞ ነፍጠኞች መሬቱ ስለተወሰደበት ነው» በማለት በፓርላማ ውስጥ የተናገሩት በቴሌቪዥን ስርጭት መተላለፉን የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ያስታውሳል። በኢቲቪ ማስረጃው ይገኛል።

ስም የመቀየር ችግር፦ ስም መዋጥ ይለዋል በእውቀቱ። “ከቶሎሳ ወደ ቶማስ” “ከራስ አሊ ወደ ራስ ሚካኤል” “ከተስገራ ወደ ተስፋዬ” ወዘተ የተጀመረው ከገጠሬነት ወደ ከተሜነት በ“መሰልጠን” ሂሳብ እንጂ በዘር ጥላቻ ላይ አይደለም። እንዲሁም በሀይማኖታዊ በጎ ተጽእኖ፥ ይህም በጥምቀት (በክርስትና መነሳት) ስም ነው ይለናል «ከአሜን ባሻገር» መጽሀፍ። በወቅቱ በጥምቀት ወደ ክርስትና መግባትና የክርስትና ስም መያዝ የደህንነት ብቻ ሳይሆን የመሰልጠን ምልክት ተደርጎም ይቆጠር ስለነበረ ግለሰቦች ስማቸውን እስከመቀየር ደርሰዋል እንጂ “ስምህን ቀይር” የሚል አዋጅ አልወጣም ይላል። ኦሮሞውም፥ ደቡቤውም፥ ትግሬውም (አማራውም ቢሆን እርገጣቸው፥ ድፋባቸው፥ ልዋጥህ፥ ክንዴ፥ ጌጤ፥ ብርቄ፥ ማንጠግቦሽ የመሳሰሉትን ስሞች ይዞ) “ስልጣኔ” ፈልጎ ወደ ከተሞች ሲመጣ፥ የከተሜዎች ቀልድ እያስጠላው ስሙን ቀየረ እንጂ ዘርን ማጥላላት አልነበረም። የተስፋዬ ገብረአብ «ጫልቱ እንደ ሄለን» የተጋነነ ትረካ ዋጋ የሚያጣውም ለዚህ ነው።

የዘር ማንዘር ጉዳይ፦ በተለይም የመሪዎቻችን ዘር ተነሳ፥ ለምሳሌ ሀይለ ስላሴ ከኦሮሞነት ወደ አማራነት ራሳቸውን የቀየሩ ንጉስነገስት ናቸው። እናታቸው ከጉራጌ የተገኘች ቆንጆ ሴት፤ አባታቸውም ራስ መኮንን ጉዲሳ ኦሮሞ ናቸው። የሀይለስላሴ ባለቤት እቴጌ መነንም የወሎው ሙስሊም ኦሮሞ ንጉስ አሊ (በኋላ ንጉስ ሚካኤል) የልጅ ልጅ መሆናቸው ይታወቃል። አጼ ሚኒልክም አባታቸው የሸዋ አማራ፤ እናታቸው ብልህ ወላይታ ናት። መንግስቱ ሀይለማርያም ከኦሮሞ ከአማራና ከኮንሶ (ደቡብ) ብሄሮች ተወላጅ ነው። መለስ ዜናዊም ከኤርትራና ከኢትዮጵያ ወላጆች የተገኘ ነው። ኢሳይያስ አፈወርቂም ቢሆን ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ተወላጆች የተወለደ ነው። መሪዎቻችን ከዚህና ከዚያኛው ብሄር ተወለዱ ቢባሉም በሰብዕናቸው (በሰውነታቸው) የሰሩት በጎና ክፉ ስራዎቻቸው እንጂ ዘራቸው ምንም አያደርግልንም።

«እንደው ልፉ ሲለን ነው፥ ዜግነታችን እንጂ ዘራችን አይታወቅም» (በእውቀቱ ስዩም «ከአሜን ባሻገር»)

ፖለቲካዊ ታሪክ፦ ታሪካችን በብዙ ሺ ዘመናት የተሳሰረ፥ ውሉ የተወሳሰበ፥ ስንክሳር ነው። በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ዘመን ብሄራዊ ጭቆና፤ በመንግስቱ ሀይለማርያም ዘመን እርስበርስ ጦርነት፤ በዚህ ላይ የማይረባ የግብርና ፖሊሲ ድርቅና ርሀብ አገሪትዋን አደቀቋት። ዛሬም ያገሪቱ ሩብ ያህል ህዝብ 25 ሚሊዮን ህዝብ ከድህነት ወለል በታች በሞትና በህይወት መካከል ይኖራል፤ ከ10ሚሊዮን በላይ ህዝብ በርሀብ ውስጥ ይገኛል። በዚህ ሂደት መቀጠል ያዋጣል ወይ? የሚያዋጣን ምንድነው? ተቃዋሚዎችን ቀርቶ፥ ኤርትራንም የሚጨምር ውይይት ድርድርና ብሄራዊ እርቅ በማድረግ አብሮ መስራት ያዋጣል። ይህም ባንድ ወገን አሸናፊነት (win/ loss) ሳይሆን፥ ሁሉም ወገኖች በሚያሸንፉበት (win-win) መፍትሄ ሰጥቶ በመቀበል (settling disputes by mutual concession) ነው። መግባባት ከሌለ በሂደት የሚከሰተው ችግር አደገኛ ነው። በተለይም በገቢ ልዩነት

(Economic Inequality) ምክንያት እየተባባብሰ ሄዶ ኢኮኖሚያዊና እና ሰብአዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት አለኝ። ወደብን በተመለከተም ኤርትራና ጅቡቲ ለኢትዮጵያ ከሚያስፈጓት በላይ፥ ኤርትራና ጅቡቲ ኢትዮጵያ እንደምታስፈልጋቸው በተግባር ስለተረጋገጠ፥ አብሮ በመኖር በጋራ ለማደግ፥ መግባባት በስተቀር፥ የሀይል አማራጭ መጠቀም ቀውስ ነው። ከዚህ ጋር የሚያያዝ አንድ የኤርትራ ተወላጅ የሆነ ወንድማችን ያጫወተኝን እውነተኛ አባባል ላካፍላችሁ።

«ኢሳይያስ አፈወርቂ በነጻነት ማግስት ኤርትራን “ሲንጋፖር እናደርጋለን” ብለው ነበር። እውነትም ይኸው ሲንገር-ኤንድ-ፑር (Singer-and-Poor) አደረጉን»

ለዚህ ሁሉ ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ምንጩ እኛው እንደሆንን ሁሉ፥ መፍትሄውም በኛው ዘንድ ብቻ የሚገኝ ነው። በታሪክ ላይ የተጠቀሰችው አልቃሽ እንጉርጉሮ፤

የገደለው ባልሽ፤
የሞተውም ልጅሽ፤ ወንድምሽ ሀዘንሽ ቅጥ አጣ፥
ከቤትሽ አልወጣ፤

ሀዘን በሀዘን ላይ ለተደራረበባት ላንዲት ሴት ብቻ የተሰናኘ ሳይሆን ለእናት ሀገራችን ጭምር ለመሆኑ ታሪካችን ምስክር ነው። ይህ ጥልቅ ሀሳብ ያዘለ መልዕክት ከመካከላችን አንድም ንጹህ እንደሌለ ሁሉም ጥፋተኛ እንደሆነ የሚያሳይና በምህረትና በይቅርታ በጋራ እንድንነሳ የሚያሳስበን ነው። በእውቀቱ ስዩም በ«ከአሜን ባሻገር» መጽሀፍ ያለፈው አለፈ ለመጭው በማሰብ በጋራ በሰላም እንኑር የሚልባት ሶስት መስመር ስንኝ እንዲህ ተቋጥራለች።

አባትህ ለገዛ፥ አያትህ ለነዳ፥
አንተ ምን አግብቶህ ትከፍላለህ እዳ፤

(ተመስገን ተካ) ይልቅ መላ ምታ፤

ማሳረጊያ፦ በዚህ ጽሁፍ አቅራቢ እምነት፥ ኢትዮጵያ እንኳን ልትበታተን ቀርቶ፥ ኤርትራም፥ ሶማሌም፥ ጅቡቲም፥ ሱዳንም፥ ሁሉም የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ሀገሮች፥ አንድነት በልዩነት በሚሆን (Unity with Diversity) እያንዳንዱ አካባቢውን በሚያስተዳድር የእድገት ትስስር በመጓዝ ወደ ታላቅ የምስራቅ አፍሪካ አንድ ሀገርነት መቀየር ይቻላል። “ግሎባላይዜሽን አለምን በሀይል እየገፋ ወደ አንድነት እያመጣን ነው” (የቀድሞ የእንግሊዝ ጠ/ሚር ብሌር) በተለይም ኢትዮጵያ፥ ኤርትራና ጅቡቲ የኢኮኖሚ ውህደት

በመቀጠልም ፖለቲካዊ ውህደት የሚያመጡበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። ለዚህም ራእይን ባለማጥበብ መስራት ይገባል ይቻላልም ብሎ ያምናል። ነገርግን «ኢትዮጵያ ብቻ ወይም ሞት» «ኦሮሚያ ብቻ ወይም ሞት» «ኤርትራ ብቻ ወይም ሞት» «ትግራይ ብቻ ወይም ሞት» «ኦጋዴን ብቻ ወይም ሞት» ወዘተ የሞት መፈክር ሞት እንጂ ዘላቂ ብልጽግናና ሰላም የሚያመጣ አይመስለኝም።

ዘላቂ ጥቅም እንጂ ዘላቂ ወዳጅ የለም። «የሶሻሊስት ጎራ» «የካፒታሊስት ጎራ» የሚል አይዶሎጂ ቀርቷል። አሜሪካ የአለምን ህዝብ 5% ብቻ ይዛ 95% አለምን የምታንቀጠቅጠው በኢኮኖሚ የበላይነት ነው። መጽሀፍ ቅዱስም «ላለው ይጨመርለታል፥ ከሌለው ያለውም ይወሰድበታል» ነው የሚለው (መንፈሳዊ ትርጉም ከአለማዊ ትርጉሙ በተቃራኒው ቢሆንም) በኢኮኖሚ በልጦ መገኘት ብቻ ነው በግሎባላይዜሽን ዘመን የሚያዋጣው። የኢኮኖሚ የበላይነት እንጂ የጉልበት ዘመን ላይ አይደለንም። አባይ አይገደብ የምትል ሁሉ ቆም ብለህ አስብ። አንድ ሀገር የሚሆን 25 ሚሊዮን ህዝብ በርሀብ እየተሰቃየ ሳለ፣ አባይ ሲገደብ ከጣና እጥፍ በሚሆን የግድቡ ኩሬ ላይ አሳ በማርባት አንድ ሚሊዮን ህዝብ እንኳን ይመግባል ብሎ ማሰብ እንዴት አይቻልም? ተቃውሞስ ቢሆን ይህ ምን አይነት የአስተሳሰብ ልዩነት ነው? ግድቡ ባለመገደቡ ይበልጥ የሚጎዳው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ገዢው መንግስት አይደለም። የአባይ መገደብ ከከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውም በላይ ምስራቅ አፍሪካን ከጭለማ በብርሀን ሀይል ነጻ በማውጣት በኢኮኖሚ ጥቅም በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላም የማምጣት ፖለቲካዊ ፋይዳው እጅግ ከፍተኛ ነው። የአፍሪካ ቀንድ ህዝብ በአለም ላይ የጎስቋሎች ጎስቋላ ድሀ ሲሆን፥ ምርጫው«ተባብሮ መልማት ወይም እየተበታተነ መጠፋፋት» ብቻ ነው።

ሰዎችን በርግጠኛነት ሊያሸንፍ የሚችለው ሀይል ፍቅር ነው። ለእኛም ችግር መፍትሄው ፍቅር ብቻ ነው። የጥበብ እውቀት (knowledge of wisdom) ያስፈልገናል። በጠብመንጃ የፖለቲካ ስልጣን መነጣጠቅና “በንጉስ ሀይለስላሴ መቃብር ላይ ኮ/ል መንግስቱ ሀይለማርያም” “በኮ/ል መንግስቱ ሀይለማያም መቃብር ላይ ጠሚ/ር መለስ ዜናዊ” “በ…መቃብር ላይ…” አንዱ በአንዱ መቃብር ላይ ቆሞ ስልጣን መጨበጥ መቆም አለበት። ለዚህም የአመለካከት ለውጥ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። ይህም ከእርስበርስ ጥላቻ ነጻ በመውጣት ይጀምራል። አመለካከትን መቃወም እንጂ ሰውን መጥላት መንፈሳዊም ሳይንሳዊም አሰራር አይደለም። አይጠቅምም። መጽሀፍ ቅዱስ የሚወድዱንን መልሰን መውደድ ፍቅር አይደለም ጠላቶቻችንን መውደድ እንጂ ይላል። መውደድ ቢያቅት ጠላት በአለመሆን በአለመግባባትም ቢሆን ተግባብቶ በጋራ መስራት ይቻላል።

ሰውን ጠላት ባለማድረግ ለማሸነፍ ሕንድን ወደ ነጻነት የመሩት ጋንዲና ጥቁር አሜሪካዊው ፓስተር ዶ/ ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጥሩ ሞዴልች ናቸው። ማህተማ ጋንዲ እንግሊዞች በሰጡዋቸው መጽሀፍ ቅዱስ «ጠላትህን እንደራስህ ውደድ» በሚለው መርህ ተመርተው ነው እንግሊዞችንም አለምንም ያሸነፉት። ዶ/ር

ማርቲን ሉተር ኪንግም ለጥቁር አሜሪካውያን ከባርነት ነጻ መውጣት የታገሉበት መንገድ ያለጠላትነት በፍቅር ጥበብ በሰላም መንገድ ብቻ ነው። እኛስ? 2ሺ አመት ሙሉ ክርስቲያን ነን እያልን እርስበርስ መፋለም የምናቆመው መቼ ነው? የምጽአት ቀን መጥቶ እስከሚገላግለን ድረስ ነውን?

ሁለት ክፉ ነገሮች ምዝበራና በእርስበርስ ጥላቻ አገር አጥፊዎች ናቸው። በነዚህ ሁለት ችግሮች የደነደነ ልብ ያላቸው ሰዎች ነጻ መውጣት አለባቸው። ጥላቻን ለማጥፋት፥ «ሀገር እንዳትወረር፥ ከውጭ ከመጣ ወራሪ ጋር ሲፋለሙ በጀግንነት ለወደቁት እንጂ፥ በእርስበርስ ጦርነት፥ ወንድም ወንድሙን በመግደሉ፥ በታሪክ መዘክር እንጂ ሀውልት ሊሰራና አንዱ ብሄር ሌላውን እንደ ጠላት እያየ ሊኖር አይገባም» ያሉት ሰው ማን እንደሆኑ ባላስታውስም፥ ፖሊሲ ሊሆን የሚገባ አባባል ነው። ይህንንም መፈተሽና ማስተካከል ግጭት እንዳይከሰት ለመከላከል ይረዳል። ከሀውልት ይልቅ ብሄራዊ እርቅ ነው የሰላም ቋሚ መሰርቱ። እንደዚሁም ዛሬ በትምህርት (merit) እና በጥረት ማደግ የቀረ ይመስላል። የሚዘርፍ ሁላ “Smart /ስማርት” እንጂ ሌባ አይባልም። በአቋራጭ ሚሊዬነር እየተሆነ ነው። «ከ7 ማስትሬት አንድ የሰበታ መሬት» የሚባልበት «ህጋዊነት»ን በጠ/ሚር ሰብሳቢነት በኢትዮጵያ ቲቪ አየን። የሀገር ሀብት ከድሀ ህዝብ ላይ እየመዘበሩ ከመኖር የሚበልጥ የሞራል ውድቀት የለም። የገቢ ልዩነት (Economic Inequality) በመንግስተ ሰማይና በሲኦል የመኖር ያህል ልዩነት እያመጣ በሀገሪቱ በግልጽ እየታየ ነው። ደላሎች ባለስልጣናትን ከላይ እስከታች በመዋቅር ይዘው “የጅምላና የችርቻሮ አከፋፋይ ኮርፖሬሽኖች” ሆነዋል። ሞራልና ስነምግባር ህዝባዊ እሴቶች እየወደቁ ሙስና ንቅዘት (Corruption) ከላይ እስከታች በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ሀገራዊ ባህል እየሆነ ነው።

በተቃራኒው የትውልድ ሞራል ለመገንባት የሚፍጨረጨሩ ጥቂት ወገኖችን መጥቀስ ይገባል። ለምሳሌ ያህል እንደነ ዶ/ር በላይ አበጋዝ (የህጻናት የልብ ቀዶ ጥገና ሆስፒታል እያለቀሱ ገንዘብ በመለመን ያስገነቡ) ዲ/ን ዳንኤል ክብረት (የበጎ ሰው ሽልማት መስራች/ሰዎችን በመልካም ስራቸው እውቅና የሚሰጥ) ጎዳና የወደቁ ሰዎችን ሰብስቦ የሜቄዶኒያ አረጋውያን የመሰረተው ወጣት ቢኒያም፤ ወዘተ የመሳሰሉት ሰዎች በጎ ጅማሬዎች መተሳሰብና የልብ አንድነት የሚያመጣ ስለሆነ መደገፍ አለበት። ሌሎችንም ለበጎ ስራዎች እጃቸውን እንዲያበረቱ ማነሳሳት ያስፈልጋል። በሙዚቃ እንደነ ቴዲ አፍሮ (“አንድ ላይ ነን ስንል ተለያይተናል”) አብዱ ኪያርም ቢሆን (“እረ እኔስ ሀገሬ”) የመሳሰሉት ለሰላም ለፍቅርና ለአንድነት አቀንቃኞች ይብዙ። ጸሀፍትና ገጣምያን የቲያትርና የኪነጥበብ ሰዎች ለእውነት ለሰላም ለፍቅርና ለህዝቦች አንድነት ይጻፉ፤ የበጎ ሰዎች ስራ ትልቅ እሴት ነው፤ ከፍተኛ ውጤትም አለው። በእውቀቱ ስዩምም በ«ከአሜን ባሻገር» መጽሀፉ የሚያስተራርቅ ሆኗል። አስታራቂነቱ እየዋሸ ሳይሆን፥ ፖለቲካዊ ታሪካችንን እውነታን በማስረጃ በማቅረብ ነው።

የእምነት መሪዎች የት ናችሁ? ከንቅዘት ነጻ የሆነ መልካም ሰብዕና (Sound Mind) ያለውን ትውልድን ኮትኩቶ ማሳደግ፥ ከቤተሰብ ቀጥሎ የናንተ ሀላፊነት እንደሆነ ስለምን ትዘነጉታላችሁ? ከሀይማኖትፖለቲካ በመውጣት ለትውልድ የሚበጅ የሞራል እድገት መስራት የለባችሁምን? ህዝብን ለሰላምና ለፍቅር ማትጋት የለባችሁምን? ነው ወይስ ከመምህሩ ደቀመዝሙሩ የሚሻልበት የመጨረሻው ዘመን ላይ ነን? “እኛን አላላውስ ያለን በአመለካከት ልዩነት አለመቻቻል (Differences by mutual concessions) ሲሆን፤ በጠላትነት የመጠላለፍ «ውሀ ቅዳ ውሀ መልስ» (Zero-sum political game) ጨዋታ ከጥቅም ውጭ ሲያደርገን፤ ስለፍቅር ስለመቻቻል ስለምን አትሰብኩም? ጥላቻ ተጠይውን ብቻ ሳይሆን ጠይውንም የሚጎዳ የስሜት በሽታ ነው። ማንም በማንም ላይ ከፍቅር በስተቀር የጥላቻ እዳ ሳይኖርበት ተቻችሎ ተባብሮ ቢሰራ፥ ሁሉም በሰላም ያድራል” እያላችሁ ስለምን አታስተምሩም?

በመጨረሻም ወጎች፦ ከፖለቲካዊና ታሪካዊ ጽሁፎች በመለስ ያሉት የበእውቀቱ የወግ መጣጥፎች ፈገግ እያስደረጉ በሚያስደምሙ ግላዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ትዝብቶች የተሞሉ በመሆናቸው አንባቢ ራሱን እንዲታዘብና እንዲፈትሽ የሚያደርጉ ናቸው። በዚህ ረገድ በእውቀቱ ስዩም ታዋቂና ተወዳጅ ከነበረው ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም ጋር የሚተካከል ይመስለኛል። እንዲያውም እንደቀልድ እያዋዛ ከሚጽፋቸው ምጸታዊ ኮርኳሪ መልእክቶች አንጻር ለየት ያለ ተሰጥኦ ያለው ነው። ለምሳሌ ያህል በፖለቲከኞቻችን ላይ ወዝ ያላቸው፤ ክብር ነክ ያልሆኑ ወጎች የሚቀልደው በእውቀቱ ስዩም ባንድ ወቅት ጠሚ/ር መለስ ዜናዊን በወግ ጨዋታ መካከል ለስልጣንም Expired Date ይኑረው ማለቱን አስታውሳለሁ። እንዲሁም ዛሬ ላይ «ፖለቲካዊ ሞት ሞተዋል» የሚባሉትና እርሳቸውም የገንዘቡን ምንጭ ሳይጠቅሱ፥ በትውልድ ቀዬአቸው በላሊበላ፥ ባለ5 ኮከብ አለም አቀፍ ቱሪስት ሆቴል ልሰራ ነው የሚሉን፥ የምርጫ-97 ባለረጅም ምላስ ጉምቱ ፖለቲከኛ ኣቶ ልደቱ አያሌውን በተመለከተችው የበእውቀቱ ወግ እንዲህ ትላለች።

“የምርጫ 97 ጦስ ልደቱ አያሌውን በሄደበት ያሳድደዋል። ባንድ ወቅት ልደቱ ከጓደኛው ጋር ምሳ በልቶ ጨርሶ ወደመቀመጫው ይመለሳል። በቦታው የነበረው አንድ ተራቢ ተመጋቢ ብድግ ይልና ወደ ልደቱና ጓደኛው ቀረብ ብሎ፥ «የእጅ መታጠቢያው በየት በኩል ነው?» ይላቸዋል። ልደቱ ተሽቀዳድሞ፥ «በዚህ በኩል» ብሎ በትህትና ይጠቁመዋል። ያን ጊዜ ተራቢው፥ «አንተን አላምንህም፥ እሱን ነው የጠየቅሁት» ብሎ መለሰ”

እግዜአብሄር ማስተዋልን ይስጠን!!
ለአስተያየት ወይም ለትችት፦ danruth2000@gmail.com

የኢትዮጵያ መከላከያ 165 የአልሸባብ ወታደሮችን ገደልኩ ሲል፤ አልሸባብ 43 ገደልኩ አለ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሂራን ዞን አልገን ከተማ የአልሸባብ ጦር እና የኢትዮጵያ ጦር ጦርነት መግጠማቸውን ሁለቱም ካወጡት መረጃ ለመረዳት ተቻለ:: አልሸባብም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ድል ቀናን ባሉበት በዚህ ጦርነት አልሸባብ 43 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገድያለሁ ሲል ዛሬ በመንግስት ሚድያዎች በኩል መግለጫ ያወጣው የኢትዮጵያ መከላከያ ሚ/ር 5 የአልሸባብ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችን ጨምሮ 165 ታጣቂዎችን ደምስሻለሁ ብሏል::

ፎቶ ከፋይል | የአልሸባብ ሚሊሻዎች

ፎቶ ከፋይል | የአልሸባብ ሚሊሻዎች

ለሰላም ማስከበር ሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ካምፕ አካባቢ በአጥፍቶ ጠፊ ተሽከርካሪዎች ጭምር ጥቃት መሰንዘሩ የተነገረለት አልሸባብ በዛሬ ሐሙስ ጥቃቱ ከሞቃዲሾ 300 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሂራን ከተማ ውስጥ በከፈትኩት ጦር የአፍሪካ ሕብረት ጦር አባል የሆኑትን 43 የኢትዮጵያ ወታደሮች ከመግደሌም በላይ በካምፑ ላይ ውርጅብኝ አውርጃለሁ ማለቱን የአልሸባብ የወታደራዊ ኦፕሬሽን ቃል አቀባይ ሸህ አብዲአሲስ አቡ ሙሳብ ገልጸዋል:: እንደ ሼህ አብዲአሲስ ገለጻ ከአልሸባብም በርካታ ወታደሮች መሞታቸውን ለሬውተርስ በሰጡት ቃለምልልስ አምነዋል::

“በጣም ትልቅ ጥቃት ነው የፈጸምነው:: የኢትዮጵያ ጦር የሚገኝበትን ካምፕ ግማሹን አውድመነዋል – መግቢያዎችን አፈራርሰናል” ብለዋል ሼህ አብዲሲስ::

በኢትዮጵያ ወታደራዊ ካምፕ አካባቢ ከፍተኛ ፍንዳታ እንደሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች ሲገልጹ የተኩስ ልውውጡም በጣም ኃይለኛ እንደነበር ተናግረዋል:: አልሸባብ እንዳለው ወደ አፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ጦር ካምፕ ቦምብ የታጠቁ አጥፍቶ ጠፊዎችን ይዞ በመግባት የኢትዮጵያ ወታደሮችን ሊገድል ችሏል::

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስተር ባወጣው መግለጫ “በሂራን ዞን ሀልገን ከተማ እና አካባቢውን በተቆጣጠረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ የማጥቃት ሙከራ ያደረገው አልሻባብ አብዛኛው ሀይሉ ተደምስሷል፡: ሰራዊቱ ቀሪውን እና የተበታተነውን የአልሻባብ ሀይልን የመደምሰስ ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል” ሲል በመንግስታዊ ሚድያዎች መግለጫ አውጥቷል::

መከላከያው ባወጣው መግለጫው “ከተለያዩ ቦታዎች ሀይሉን አሰባስቦ የመጣው እና በአጥፍቶ ጠፊ ተሽከርካሪዎች እና ፈንጂዎች የታገዘው አልሻባብ በአራት አቅጣጫ ማጥቃት ቢጀምርም የኢትዮጵያ መከላከያና የሶማሊያ ስራዊት በወሰዱት የመከላከል እና ፀረ ማጥቃት እርምጃ ተደምስሷል፡፡ በተወሰደው ጠንካራ የማጥቃት እርምጃ አምስት ከፍተኛ የአልሸባብ አመራሮችን ጨምሮ 165 ታጣቂዎቹ ተደምስሰውበታል” ብሏል::

ከመከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ መረዳት እንደተቻለው ከአልሸባብ ተማረከ የተባለው መሳሪያ ዘመናዊና ከሆነ ሃገር የመጣ ሲሆን ይህንን ለማረጋግጥ ስራ እየተሰራ ነው:: በርካታ የአልሸባብ ወታደሮችንም ማርኬያለሁ ብሏል::

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአልሸባብ እና በሰላም አስከባሪው የኢትዮጵያ ጦር መካከል ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል::

Health: የፀጉርዎ ነገር! ሳይንስ ስለፀጉርዎ የሚለውን እንንገርዎት

$
0
0

 

ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም | ለዘሐበሻ

ዘመናዊ ሰዎች የሌሎች ሰዎችን ፀጉር ሲያደንቁ ይስተዋላሉ፡፡ ፀጉራቸውን ለመስተካከል/ለመስራት ሲሯሯጡም እናያለን፡፡ በፀጉር አምሮና ተውቦ ለመገኘት ሁሉም እንደየአቅሙ ሲሟሟት ይታያል፡፡ ግን ለምንድነው ሰዎች ፀጉራቸውን የሚንከባከቡት? ለፀጉር የሚጠፋው ገንዘብና ጊዜ ቀላል ነው? ነጋ ጠባ ፀጉር እያደገ፣ እየተስተካከለ፣ እየተበጠረ የሚኖር መሆኑ አያናድድም? ያለማቋረጥ የሚያድግ ፀጉር ባለቤት በመሆን ረገድ፣ የሰው ልጅ ብቸኛ ፍጡር ነው፡፡ እኮ ለምን?

hair

ከአንድ ሁለት ዓመት ወዲህ ፀጉርን በሚመለከት ሳይንሳዊ አመለካከቶች እየተንፀባረቁ ናቸው፡፡ እንደሚባለው ከሰው በስተቀር ሌሎች ፍጡራን አንዴ ፀጉር ከተላበሱ በኋላ ዕድገቱ ይቆማል፡፡ የእኛ ፀጉር ግን ሲሻው ዕድሜ ልክ ሲያድግ፣ ሲመዘዝ ይባጃል፡፡ ለምንድነው የሰው ፀጉር ያለማቋረጥ ለማደግ የቻለው? በእንክብካቤ ብዛት ወይስ በተፈጥሮ? ለዚህ አስተማማኝ ምላሽ ለመስጠት ይከብድ ይሆናል፡፡

በደንብ የሚታወቀው ሁለት አይነት ፀጉር ያለን መሆኑ፡፡ ዋነኛው የጭንቅላት፣ የቅንድብና የሽፋሽፍት፣ ሌላው በሌሎች የሰራ አካላታችን የሚገኙት ናቸው፡፡ እነዚህም እንደየሰዉ ዕድሜ፣ ፆታና ተፈጥሮ ይብዛ ይነስ እንጂ የብሽሽት፣ የብብትና የጢምንም ጨማምሮ ዘጠኝና አስር አይነት ይሆናሉ፡፡ በትከሻ ላይ ዝቅ ብሎ አምሮ የሚታየውም ሆነ በእግር ጣቶች ላይ የምትበቅለዋ ስስ የሆነች ፀጉር፣ ሁሉም እስከሚረግፉ እኩል ይበቅላሉ፡፡ በወር ከአንድ እስከ 1.5 አፅቅ (ሳ.ሜ) የበቀለ ፀጉር አድጎ ሲያበቃ ይረግፋል፡፡ የፀጉር ዕድገት ጊዜም እንደ ፀጉሩ አይነት ይለያያል፣ ርዝመቱም በዚያው ይወሰናል፡፡ ለምሳሌ የእግር ፀጉር ዕድገቱን በሁለት ወራት ያቋርጣል፣ የብብት ፀጉር ለስድስት ወራት፣ የራስ ፀጉር ግን ያለማቋረጥ ዕድገቱ ከስድስት ዓመት በላይ ይዘልቃል፡፡

እጅግም የማይታወቀው የፀጉራችን አስተዳደግ ስልተ ምስጢሩ ሲሆን ወደፊት ግን የሚደረስበት ይሆናል፡፡ ለመሆኑ መቼ ነው የሰው ልጆች የራስ ፀጉር በማያቋርጥ ሁኔታ ማደግ የጀመረው? ተብሎ ሲጠየቅ የዛሬ 240,000 ዓመታት፣ የሰው ልጅ እሳት ማቀጣጠል ከጀመረበት ጊዜ በኋላ ነው ይባላል፡፡ እናም ከብርድ መከላከያ ብልሃት እስካገኘበት ጊዜ ድረስ በፀጉሩ ላይ የአይነትም ሆነ የመጠን/የብዛት ለውጥ ማስከተሉና፣ በለውጡም የማይፈለግ ቦታ የበቀለ ፀጉር ከጊዜ ወደ ጊዜ መርገፉ/መሳሳቱ የዝግመት ለውጥ ሀቅ እንደሆነ ይታሰባል፡፡

የፀጉር መሳሳት በበኩሉ አያሌ ጠቀሜታዎች እንዳሉትም አለመዘንጋት ነው፡፡ ይኸውም ፀጉር ውስጥ ተደብቀውና ተራብተው በሽታ አምጪ የሆኑ ተባዮችን መቀነሱ፣ ከአስቸጋሪው የጫካ ኑሮ ወደ ሜዳማ፣ ሙቀታማና ወደ ባህር አካባቢዎች ሲጠጋ ከፀሐይ ከሚከላከልበት የራስ ፀጉር በስተቀር፣ ራሱን ለማቀዝቀዝ የፀጉሩ ከቀድሞው መቀነስ ላብ በብዛት ለማመንጨት ረድቶታል፡፡ በዚያ ላይ ሰው ልጅ ፀጉሩ እያነሰ በሄደና፣ ለስላሳ ቆዳ በኖረው ቁጥር ይበልጥ ለፍቅር እየተፈላለገ፣ ባለ አናሳ ፀጉሮቹ እየተራቡ፣ ፀጉራሞቹ በብዛት እየቀነሱ እንደሄዱ ይገመታል፡፡ በተባይ አምጪነቱም ይሁን በሌላ ምክንያት የማይፈለግ የነበረው ፀጉር፣ አሁን ደግሞ በአንፃሩ ምን እየተደረገ ነው?

በአሁኑ ጊዜ፣ ፀጉራችንን እጅግ ሲበዛ እንንከባከበዋለን፡፡ ፀጉር የማንነት መገለጫ ሆኗል፡፡ በወጉ የተሰራ ፀጉር አደባባይ ሲወጣ ያስከብራል፣ አድናቂዎችም ያስገኛል፡፡ ሰው ፀጉሩን አበጣጥሮ የሚወጣው ወድዶ አይደለም፡፡ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሰውም፣ ለሰው ብቻ ሳይሆን ለራሱም ሲል ነው፡፡ ያለበለዚያ ፀጉሩን አንጨባሮ/አንጨፍሮ የወጣ ሰው ምንም ብሩህ አዕምሮ ቢኖው፣ የውስጡን የሚያውቅለት ስለሌለ በቦዘኔነት ወይም ግዴየለሽነት ይፈረጃል፡፡

ፀጉርን አሳምሮ ሽክ ማለት እኮ ብዙ ይናገራል፣ ያናግራልም፡፡ ‹‹ፀጉሯ ወርዶ፣ ወርዶ!›› እየተባለ ይዘፈን የለም? ይሄ እኮ ዛሬ ተጀመረ ሳይሆን ጥንት ጥንታውያንም ያደርጉት ነበር፡፡ የጥንት ሰዎች (አሁንም እንደ ጥንቱ መለመላቸውን በሚኖሩ ማህበረሰቦች ውስጥ እንደሚታየው) የተዋበ የፀጉር አሰራር ዘዴ አላቸው፡፡ የፀጉራቸው አሰራር ዝርያቸውን ወይም ማህበራዊ ማንነታቸውን ገላጭ ነው፡፡ በአገራችንም እንደየአካባቢው ጎገሬ፣ ቁንጮ፣ ጋሜ፣ ጉድሮ፣ ሽሩባ ወዘተ… ወይም ‹‹ፍሪዝ›› የሚሰጠው ትርጉም እንዳለ ሁሉ፣ በሌላው ዓለምም ‹‹እንቁላል ራሶችን››፣ ‹‹ራስ ተፈሪያንስን›› እና የመሳሰሉትን መጠቃቀስ ይቻላል፡፡

የሰው ልጅ ከ2300 ዓመታት በፊት የፀጉር ቅባት፣ ከ8000 ዓመታት በፊት ደግሞ ማበጠሪያ ይጠቀም እንደነበር በጥናት ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ ሰዎች የፀጉር ማስዋብን ዘዴ ይጠቀሙ የነበረው ጊዜ ርቀት በ10 ሺዎች ዓመታት እንደሚቆጠሩ ከተገኙ ቅርሶች ታውቋል፡፡ አሁን ላይ ቆመን ጥንተ ጥንታውያን የዋሻ ሰዎች፣ እንዴት እንደኖሩ በዓይነ ህሊናችን መዳሰስ እንችል ይሆናል፡፡

ፀጉራቸውን ለመንከባከብና ለማስዋብ በቂ ጊዜ እንደነበራቸው እንገምታለን፡፡ እነሱ ቀልጣፎች ነበሩ፤ በቀላሉ የማደንና ምግብ የመሰብሰብ ብቃት ነበራቸው፡፡ ስለሆነም ለማህበራዊ ክንውኖች በቂ ትርፍ ጊዜ ነበራቸው፡፡ ለመዋቢያ፣ ማስዋቢያ ቁሳቁሶችን ለመስራት ጭምር ኋላ ቀር ከተባለ ማህበረሰብ ጀምሮ እስከ ዘመኑ የቁንጅና ሳሎኖች ድረስ፣ የፀጉር እንክብካቤ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ በሂደት አንዳንዶቹ ከሌሎቹ የላቁ እንደሚሆኑና የበለጠ ተረፈላጊነት እንደሚኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ የፀጉር ማስዋብ ስራ እጅግ ጥንታዊ ከሆኑት የሙያ መስኮች አንዱ እንደሆነ አይጠረጠርም፡፡

ስለ ፀጉራችን ለምን እንጨነቃለን?

በርካታ ሰዎች የፀጉራቸውን ሁኔታ በመስተዋት እያዩ በየቀኑ ብዙ ሰዓት ያሳልፋሉ፡፡ ስለ ፀጉር ማሰብ ወንድ ሴት የማይል ከመሆንም በላይ ትልቅ ጭንቀት የሚፈጥርበት ጊዜም አለ፡፡

ስለ ፀጉርህ ሁኔታዎች እወቅ

በራስ ቅል ላይ በአማካይ 100,00 የሚደርሱ ፀጉሮች እንዳሉ ይገመታል፡፡ አንድ ነጠላ ፀጉር የሚያድገው  ዕድሜ ልክ ሳይሆን ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ይረግፍና ከጥቂት የሽግግር ጊዜ በኋላ ከዚያው ቀዳዳ አዲስ ፀጉር መብቀል ይጀምራል፡፡ አንድ ነጠላ ፀጉር የራሱ የሆነ የአስተዳደግ ኡደት አለው፡፡ በዚህ ኡደት ምክንያት ምንም አይነት የፀጉር ችግር ከሌለበት ሰው እንኳን በእያንዳንዱ ቀን ከ70 እስከ 100 የሚደርሱ ፀጉሮች ይረግፋሉ፡፡

የፀጉር ቀለም የሚለያየው በምን ምክንያት ነው? ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፒዲያ እንዲህ በማለት ያብራራል፡፡ ‹‹የፀጉር ቀለም በአብዛኛው የሚወሰነው ሜላኒን የተባለው ጥቁር ቡናማ ቀለም ባለው ስርጭትና መጠን ነው›› ሜላኒን በፀጉር፣ በቆዳና በዓይን ውስጥ የሚገኝ የተፈጥሮ ቀለም ነው፡፡ የቀለሙ መጠን በጨመረ መጠን ፀጉርም ጠቆር እያለ ይሄዳል፡፡ የሜላኒን መጠን እያነሰ ሲሄድ ደግሞ የፀጉር ቀለም ከጥቁር ወደ ቡናማነት ወይም ወደ ቢጫነት ያደላ ይሆናል፡፡ ፀጉር ምንም ሜላኒን ከሌለው ግን ሙሉ በሙሉ ነጭ ይሆናል፡፡

ከፎረፎር ሌላ ብዙዎችን የማያሳስባቸው የፀጉር መርገፍ አለዚያም የፀጉር መሸበት ነው፡፡

የፀጉር አስተዳደግ

የፀጉራችን አስተዳደግ የራሱ ዑደት አለው፡፡ ፀጉር የማደጊያ፣ የመሸጋገሪያና የማረፊያ ጊዜ አለው፡፡ ዘ ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፒዲያ እንዲህ በማለት ያብራራል፡፡ ‹‹ፀጉር በማረፊያ ጊዜ ማደጉን ያቆማል፡፡ በዚህ ጊዜ አሮጌው ፀጉር የማደጊያው ጊዜ እስኪ ደርስ ድረስ በስሩ ላይ እንዳለ ይቆያል፡፡ በማደጊያ ጊዜ አሮጌው ፀጉር ይረግፍና አዲስ ፀጉር ከስር ይወጣል፡፡ ‹‹በማንኛውም ወቅት ከ85 እከ 90 በመቶ የሚደርስ ፀጉር በዕድገት ላይ ሲሆን ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆነው በማረፊያ፣ በመቶ የሚሆነው በመሸጋገሪያ ጊዜ ላይ ይሆናል፡፡

ፀጉርህ ሸብቷል?

ሽበት ብዙውን ጊዜ የእርጅና እና የአረጋዊነት ምልክት ተደርጎ ይታያል፡፡ እርግጥ ነው፣ ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ ፀጉር ይሸብታል፡፡ ይሁን እንጂ ሽበት የሚመጣው በእርጅና ምክንያት ብቻ አይደለም፡፡ ሽበት ጠቆር ያለ ፀጉር ባላቸው ላይ ጎልቶ የሚታይ ይሁን እንጂ ፆታም ሆነ የፀጉር ቀለም አይመርጥም፡፡

አንዳንዶች በመሸበታቸው ምክንያት ከዕድሜያቸው በላይ ያረጁ መስለው ሊታዩና ይህም አሳሳቢ ሊሆንባቸው ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ባለመሸበታቸው ምክንያት ትክክለኛው ዕድሜያቸውና መልካቸው አለመመሳሰሉ የሚያሳስባቸው ሰዎችም አይጠፉም፡፡

ፀጉር ከሸበተ ሞተ ማለት አይደለም፡፡ እርግጥ ነው በዓይን የሚታየው ውጪያዊ የፀጉር ክፍል በድን ነው፡፡ የእያንዳንዱ ፀጉር ስር ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ህይወት ያለው የፀጉር ክፍል ይህ ብቻ ነው፡፡ የፀጉር ስር እንደ ፀጉር ፋብሪካ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በስሩ ውስጥ ያሉት ሌሎች በብዛት ተራብተው ፀጉር ሲፈጠር የቀለም ሴሎች የሚሰሩትን ሜላኒን ይቀባል፡፡ በዚህም የተነሳ የቀለም ሴሎች ሜላኒን መስራት ካቆሙ ፀጉር ነጭ ይሆናል፡፡

የቀለም ሴሎች በድንገት ሜላኒን መስራታቸውን የሚያቆሙት ለምን እንደሆነ ማንም የማያውቅ የለም፡፡ በዚህም ምክንያት ለሽበት የሚሆን አስተማማኝ መድሃኒት ሊገኝ አልተቻለም፡፡ በተጨማሪም ስራቸውን አቁመው የነበሩ የቀለም ሴሎች እንደገና መስራት ሊጀምሩ እንደሚችሉ ተደርሶበታል፡፡

አንዳንዶች ሜላኒን እንደመወጋት ያሉትን አዳዲስ ህክምናዎች ይሞክራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ፀጉራቸውን ቀለም ይቀባሉ፡፡ ይህም ቢሆን ዛሬ የመጣ ልማድ አይደለም፡፡ የጥንቶቹ ግሪካውያንና ሮማውያን ፀጉራቸውን ቀለም ይቀበሉ ነበር፡፡ የጥንት ግብፃውያን በበሬ ደም ፀጉራቸውን ያቀልሙ ነበር፡፡

ይሁን እንጀ በየጊዜው ቀለም መቀባት ጊዜና ጥረት የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ የአንዳንዶችን ቆዳ ሊያስቆጣ ወይም ሊያቆስል ይችላል፡፡ ሽበትን በቀለም ማጥቆር ብንወስንም መቀባትን ለማቆም የምንፈልግበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ከስር የሚያድገውን ሽበት መሸሸግ አስቸጋሪ ይሆንብናል፡፡ ሽት በአዎንታዊ ጎኑ የሚያምርና ከዚህ በፊት ያልነበረህን ግርማ ሞስ የሚያስገኝልህ ሊሆን ይችላል፡፡

የፀጉር መሳሳትና ራስ በራነት

ሌላው የተለመደ የፀጉር ችግር የፀጉር መሳሳትና ራሰ በራነት ነው፡፡ እነዚህም ችግሮች ቢሆኑ ዛሬ የተፈጠሩ አይደሉም፡፡ በጥንቷ ግብፅ ለራስ በራነት ከአንበሳ፣ ከጉማሬ፣ ከአዞ፣ ከድመትት ከእባብና ከዝይ ስብ የተቀመመ መድሃኒት ይሰጥ ነበር፡፡ በዛሬው ጊዜ ራስ በራነትንና የፀጉር መሳሳት ይከላከላሉ የሚባሉ በርካታ ሸቀጦች ሲኖሩ ለእነዚህ ሸቀጦች በየዓመቱ የሚፈሰው ገንዘብ በጣም ብዙ ነው፡፡

በራነት የሚጀምረው ትክክለኛው የፀጉር አበቃቀል ሲዛባ ነው፡፡ ትክክለኛው የፀጉር አበቃቀል በምግብ አለ መመጣጠን፣ ረዥም ጊዜ በሚቆይ ትኩሳት ወይም በቆዳ በሽታ ባሉ ምክንያት የተነሳ ሊዛባ ይችላል፡፡ በተጨማሪም የፀጉር አበቃቀል እንደ እርግዝናና ልጅ መውለድ ባሉ ምክንያቶች ስለሚዛባ አዲስ ፀጉር መበቀል ከመጀመሩ በፊት ብዙ ፀጉር ሊረግፍ ይችላል፡፡ የፀጉሩን አስተዳደግ ያዛባው ምክንያት ሲወገድ ግን እንዲህ ያለው የፀጉር መርገፍ ይቆምና ወደ መደበኛው ሁኔታ ይመለሳል፡፡

ሌላው አይነት የፀጉር መርገፍ ደግሞ ላሽ ይባላል፡፡ ይህ ችግር በሚኖርበት ጊዜ በአንዱ አካባቢ ያለ በርካታ ፀጉር አንድ ጊዜ ይረግፋል፡፡ ላሽ የሚመጣው በሰውነት የበሽታ ተከላካይ ሕዋሳት ላይ በሚደርስ ቀውስ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር በቅርቡ የተደረጉ የህክምና ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

በጣም የተለመደው የፀጉር መርገፍ በወንዶች ላይ የሚደርሰው የራስ በራነት አይነት ነው፡፡ ከፊት ያለው ፀጉር ገባ ገባ በማለት ወይም መሀል አናት ላይ ሳሳ በማለት ይጀምርና ቀስ በቀስ እየተባባሰ ይሄዳል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች ያለው የፀጉር እድገት የተዛባ ሆኖ ከቆየ በኋላ ቀስ በቀስ ጨርሶ ወደ ማቆም ይደርሳል፡፡ ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንዲህ በማለት ያብራራል- ‹‹በራነት በጀመረው አካባቢ በነበረው ረዥም፣ ጠንካራና ባለቀለም ፀጉር መብቀል ይጀምራል›› የፀጉር ዕድገት እየቀጠለ ሲሄድ እየሳሳና ዕድሜው እያጠረ ሄዶ ምንም ፀጉር ከማይበቅልበት ደረጃ ላይ ይደርሳል፡፡ ይህ የሚሆነው በዘር ውርሻና በወንዶች ሆርሞኖች ምክንያት ነው፡፡

የወንዶች ራስ በራን  ከአፍላ የጉርምስና  ዕድሜ አንስቶ ሊጀምር ቢችልም አብዛኛውን ጊዜ የሚጀምረው በ30ዎቹ ዓመት መገባደጃና በ40ዎቹ ዓመታት ዕድሜ ነው፡፡ እንዲህ ያለው የፀጉር መርገፍ በብዙ ወንዶች ላይ የሚደርስ ቢሆንም መጠኑ ከዘር ወደ ዘርና ከግለሰብ ወደ ግለሰብ ይለያል፡፡ ያም ሆነ ይህ ለዚህ ችግር የተረጋገጠ መድሃኒት ማግኘት አልተቻለም፡፡ አንዳንዶች በራቸውን ለመሸፈን ሰው ሰራሽ ፀጉር ለማድረግ ወይም በቀዶ ህክምና ፀጉር ለማስተካከል ይመርጡ ይሆናል፡፡ ለተቀረው ፀጉር ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ ፀጉር እንዳይረግፍ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡

የአንድ ሰው ፀጉር አንዴ መሳሳት ከጀመረ ጨርሶ ይመለጣል ማለት አይደለም፡፡ ነጠላ ፀጉሮች በመቅጠናቸው ምክንያት ሳስቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ለመሆኑ የፀጉር ውፍረት ምን ያል ነው? አንድ ጥናት እዳመለከተው ከ50 እስከ 100 ማይክሮ ሊደርስ ይችላል አንድ ሰው እያረጀ ሲሄድ ፀጉሩ ይቀጥናል፡፡ የጥቂት ማይክሮኖች መቀነስ ብዙም ለውጥ የሚያመጣ ላይመስል ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ 100,000 የሚያክሉ ፀጉሮች መኖራቸውን አትዘንጉ፡፡ ስለዚህ ነጠላ ፀጉሮች በትንሹ እንኳን ቢቀጥኑ በጠቅላላው የፀጉር ብዛት ላይ የሚያስከትለው ለውጥ ከፍተኛ ይሆናል፡፡

ለፀጉር እንክብካቤ ማድረግ

ፀጉር በየወሩ 10 ሚሊ ሜትር ያህል ያድጋል፡፡ ፈጣን ዕድገት ካላቸው የሰውነት ክፍሎች አንዱ ነው፡፡ የሰውነት ፀጉሮች ዕድገት በሙሉ አንድ ላይ ቢጀመር በየቀኑ 20 ሜትር ያህል ያድጋል ማለት ነው፡፡

ለሽትና ለራስ በራነት ፍቱን የሆነ መድሃኒት ገና ያልተገኘ ቢሆንም ያለንን ፀጉር ለመንከባከብ ብዙ ልናደርግ የምንችለው ነገር አለ፡፡ በቂና የተመጣጠነ ምግብ መመገብና የራስ ቅል በቂ የደም ዝውውር እንዲያገኝ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ከመጠን በላይ ምግብ መቀነስ ወይም የተመጣጠነ ምግብ አለመመገብ ሽበትና የፀጉር መሳት ሊያፋጥን ይችላል፡፡ አዘውትረን ፀጉራችንን መታጠብና የራስ ቅል ቆዳን በጥፍር ሳይቧጥጡ ጥሩ አድርጎ ማሸት ጥሩ እንደሆነ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ ይህን ለማድረግ የራስ ቅል ጥሩ የደም ዝውውር እንዲያገኝ ያስችላል፡፡ ፀጉራችሁ በሳሙና ወይም በሻምፖ ከታጠባችሁ በኋላ ጥሩ አድርጋችሁ አለቅልቁት፡፡

ፀጉራችሁን በኃይል አታበጥሩ፡፡ ፀጉራችሁ ረዥም ከሆነ መጀመሪያ ላይ ከስራ ጀምሮ እስከጫፍ አለማበጠር ጥሩ ይሆናል፡፡ ከዚህ ይልቅ በመጀመሪያ ፀጉራችሁን መሀል ላይ ይዛችሁ ጫፍ ጫፉን በማበጠር አፍታቱት፡፡ ቀጥላችሁ ከመሀል አንስታችሁ እስከ ጫፍ አበጥሩ፡፡ በመጨረሻም ፀጉራችሁን ወደታች ልቀቁትና ከስር እስከ ጫፍ አበጥሩት፡፡

ፀጉራችሁ ሸብቶ ስታዩት ወይም ሲረግፍ ሊያሳስባችሁ ይችላል፡፡ ቢሆንም የፀጉራችሁ ሁኔታ አብዛኛውን ጊዜ እናንተን የማያሳስባችሁን ያህል ሌሎችን እንደማያሳስብ አስታውሱ፡፡ ፀጉራችሁን ቀለም መቀባት፣ ሰው ሰራሽ ፀጉር ማድረግ ወይም ህክምና ማድረግ ተፈልጎ ይሆናል፡፡ እንዲህ ማድረጉ ለእናንተ የተተወ ነው፡፡ የፀጉራችሁ ቀለም ምንም አይነት ይሁን ወይም ምንም ያህል ፀጉር ይኑራችሁ ዋና አስፈላጊው ነገር በንፅህናና በስርዓት መያዛችሁ ነው፡፡

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትሉ ድንገት ከስልጣናቸው ተነሱ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ ድንገተኛ አስቸኳይ ስብሰባ የተቀመጠው የጨፌ ኦሮሚያ ፓርላማ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዋና ፕሬዚዳንት እና ምክትሉን አባረረ::

Zehabesha-News.jpg

ሁለቱ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዋና አመራሮች አቶ ደመዎዝ ማሜ እና ቦጃ ታደሰ  የተባረሩት ባለፉት 6 ወራት በኦሮሚያ ክልል ተቀጣጥሎ በቀጠለው ሕዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ምንጮች ሲናገሩ የክልሉ ፓርላማ ወዲያውኑ በጠራው ስብሰባ ሁለቱን አመራሮች አሰናብቶ የደቡብ ምስራቅ ሸዋውን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አዲሱ ቀንቤሳን እና የአሪሲ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ ሁሴን አደምን ሾሟል::

በሌላ በኩልም የቀድሞው የኦህዴድ ሥራ አስፈጻሚ ኮሜቴ አባል የነበረው አቶ ዘላለም ጀማነህም ይመራው ከነበረው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ም/ፕሬዚዳንትና የግብርና ቢሮ ኃላፊነት ስልጣኑ ሙሉ በሙሉ መባረሩን ምክር ቤቱ አጽድቋል:: አቶ ዘላለም ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ ከኦሮሞ ተማሪዎች አምጽ ጋር ተያይዞ ከማንኛውም የድርጅት ጉዳይ መታገዳቸውን ዘ-ሐበሻ በወቅቱ መዘገቧ ይታወሳል::

ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት (ጨፌ አሮሚያ) በሐምሌ ወር 2012 በተመሳሳይ ሁኔታ በአዳማ ከተማ ባደረገው ዓመታዊ ጉባዔ፣ ባልተጠበቀ ሁኔታ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ታደለ ነጊሾና ምክትላቸው አቶ ሰዒድ ጁንዲን ማንሳቱና ዛሬ የተባረሩትን አቶ ደመዎዝ ማሜ እና ቦጃ ታደሰን መሾሙ አይዘነጋም::


ከፍትህና ከዲሞክራሲ እየተጣሉ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ መቆም አይቻልም! |ምላሽ ለአቶ ነአምንና ግንቦት 7

$
0
0
ያሬድ ኃይለማርያም ለ7 ዓመታት ያህል ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ካውንስል ጋር አብሮ የሠራና የኖቬምበር 1 እማ 2ቱን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከሃገር ብዙ ምስጢሮችን ይዞ በመውጣት ለአውሮፓ ሕብረት ያቀረበ ነው።

ያሬድ ኃይለማርያም ለ7 ዓመታት ያህል ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ካውንስል ጋር አብሮ የሠራና የኖቬምበር 1 እና 2ቱን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከሃገር ብዙ ምስጢሮችን ይዞ በመውጣት ለአውሮፓ ሕብረት ያቀረበ ነው።

ያሬድ ኃይለማርያም | ሰኔ 2008 ዓ.ም

ለትግላችን ብቸኛውን ሚና የሚጫወተውን የኤርትራ ሕዝብና መንግስትን ለማዳከም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያደርገውን ሴራ ለመቃወም ይህንን ፒትሽን ፈርሙ” – ነአምን ዘለቀ (አ. ግንቦት 7)

“particular individuals, including officials at the highest levels of State, the ruling party – the People’s Front for Democracy and Justice – and commanding officers bear responsibility for crimes against humanity and other gross human rights violations.” UN UN Commission of Inquiry on Human Rights in Eritrea

ሰሞኑን በማህበረ-ድረገጾች ላይ ግንቦት 7 በአመራሩ አቶ ነአምን ዘለቀ በኩል ያቀረበውን የኤርትራን መንግስት ደግፉልን የሚል ጥሪ የያዘ አንድ የቪዲዮ ምስል ተመልክቼ ነበር፡፡ ላላያችሁት ቪዲዮው ይህንን ቢጫኑ ያገኙታል፡-  https://www.facebook.com/search/top/?q=petition%20for%20eritrea&em=1 ወይም

ዘ-ሃበሻ በተሰኘው የዜና ምንጭ የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ያገኙታል፡- https://www.facebook.com/Zehabesha/videos/1100393513366187/

የድርጅታቸው ጥሪ ባጭሩ ጥላና ከለላ የሆነንን የኤርትራን መንግሥት የአለም አቀፉ ማህበረሰቡ በክፉ አይን እያየብን ነውና  የኢሳያስን መንግስት በክፉ አይን ያየውን የተባበሩት መንግስታት በማውገዝ ለኢሳያስ ያለንን የወዳጅነት ድጋፍ ለማሳየት ከዚህ የሚከተለውን ፊርማ በመፈረም አጋርነታችሁን ግለጹ የሚል ነው፡፡ የፊርማ ማሰባሰቢያው መልዕክትም ይህን ይመስላል፡- https://hagger.wufoo.eu/forms/i-reject-the-coie-and-sr-report/

I Reject the COIE and SR Report

  • I the undersigned, categorically and unequivocally reject the politically motivated report of the Report of the Commission of Inquiry on Human Rights in Eritrea (COIE) and the Special Rapporteur (SR) on the Human Rights Situation in Eritrea.The resolution and the appointment of the SR and establishment of the COIE are in fact a continuation of an orchestrated 16-year long political campaign that seeks to demonize and delegitimize Eritrea in the international arena, and erode the final and binding Eritrea Ethiopia Boundary Commissions delimitation and demarcation decisions.

ወደ ግል አስተያዬቴ ከመግባቴ በፊት ይህ የኤርትራን መንግስት ሰላም የነሳውና ስጋት ውስጥ የጣለው፤ እንዲሁም የግንቦት 7 አመራሮች አይናቸውን በጨው አጥበው ያለ አንዳች ሃፍረት በአደባባይ የተቃውሞ ጥሪ ያቀረቡበትን ሪፖርት ይዘት ላላያችው ሰዎች ነገሩን ለማመዛዘን ያመቻችሁ ዘንድ ይህን ቪዲና የተባበሩት መንግስታትን መግለጫ ከዚህ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች በመጨቆን ልትመለከቱዋቸው ትችላላችዉ፡፡

Defenders Speaking Out: “The regime in Eritrea is a crime in itself.” from Defend Defenders on Vimeo.

http://www.ohchr.org/EN/NewsEvents/Pages/DisplayNews.aspx?NewsID=20067&LangID=E

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ ትላንት ባወጣው በዚህ ሪፖርት አንባገነኑ የኤርትራ መሪ አቶ ኢሳያስ በዜጎቻቸው ላይ የሰውን ስብእናን የሚጻረር ከፍተኛ ወንጀል መፈጸማቸውን ያረጋገጠ መሆኑን እና ለዚህም ወንጀላቸው ተጠያቂ መሆናቸውን ገልጽዋል፡፡ እንዲህም ሲል በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የከፋ ሁኔታ ገልፆጻል፡-

“There is no genuine prospect of the Eritrean judicial system holding perpetrators to account in a fair and transparent manner. The perpetrators of these crimes must face justice and the victims’ voices must be heard. The international community should now take steps, including using the International Criminal Court, national courts and other available mechanisms to ensure there is accountability for the atrocities being committed in Eritrea,” – See more at: http://www.ohchr.org/EN/NewsEvents/Pages/DisplayNews.aspx?NewsID=20067&LangID=E#sthash.xO8q0CsB.dpuf 

አንባገነኑ ኢሳያሳ አፎረቄ አመራር በዙ ሺ ዎች ተገድለዋል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኤርትራዊያንን ከአገር ተሰድደዋላ፤ በሪፖርቱ ላይ እንደተገለጸው በ2015 ብቻ ከ42 ሺ በላይ ኤርትራዊያን ከአገር ተሰደዋል፣ እጅግ በርካቶች ታፍነው የደረሰቡበት አይታወቅም፤ ይህም ጋዜጠኞችን እና ምሁራንን ያካትታል፡፡

ከዚህ አይነቱ አውሬ አንባገነናዊ ሥርዓት ጋር ግንባር ፈጥሮ ሥልታዊ የሆነ የመታገያ መንገድ ማመቻቸት አልበቃ ብሎ ይህ ወንጀለኛ ሥርዓት እንዳይወገድ በፊርማችሁ ድጋፍ አድርጉለት ብሎ አይን ባወጣ መልኩ በአደባባይ ጥሪ ማድረግ የግንቦት 7 አመራሮችን ከግራ መጋባት ያለፈ ክሽፈት ከማሳየት ባለፈ እንታገልለታለን ከሚሉት የፍትህና የዴሞክራሲያዊ መርህ በምን ያህል ጥልቀት በተቃርኖ መቆማቸውንም ነው የሚያመላክተው፡፡

Neamin Zelekeበአዲስ አበባ የከተመውን እና ለ25 አመታት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያስለቅስ፣ ሲገድል፣ ሲያፍን፣ ሲያስርና ለስደት ሲዳርግ የኖረውን የወያኔን ክፉና አፋኝ ሥርዓት ሊዋጋ አደባባይ የወጣና ጫካ የገባ ኃይል፣ ወያኔ ማቅ ያለበሰውን እና መቀመቅ የከተተውን የፍትህ፣ የዴሞክራሲና የሕግ ልዕልና ጭላንጭል በትግላችን ከወደቀበት ቅርቃር አውጥተን ኢትዮጵያን የሰላም፣ የልማትና የዜጎች ነጻነት ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠባት አገር እናደርጋለን ብለው ሌት ተቀን የሚምሉና የሚገዘቱ የግንቦት 7 አመራሮች ምን ግራ ቢገባቸው ነው በአደባባይ አለም በሰው ዘር ላይ የከፋ ወንጀል በመፈጸም ተጠታቂ ያደረገውን የኤርትራን መንግስት ለመታደግ ባደባባይ ድጋፍ የሚያሰባስቡት፡፡

ለሻቢያ እድሜ እየለመኑ የወያኔን እድሜ ያሳጥርንልን ማለት ለእኔ ግራ ከመጋባት ያለፈ ትርጉም የለውም፡፡ ሁለትም ከአንድ ምንጭ የተቀዱ፣ በአንድ መስክ ያደጉ፣ በአንድ አይነት መርዝ የናወዙ፣ በተመሳሳይ የጥፋት ተልኮ ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያንና የዛሬዋን ኤርትራን ተባብረው መቀመቅ የከተቱና ሕዝቦቹንም ያዋረዱ እኩይ ስርዓቶች ናቸው፡፡ እንደ ግንቦት 7 ላለ ድርጅት መመሸጊያ በማጣት ኤርትራ በርሃዎች ውስጥ መከተሙና ወያኔን ለማስወገድ ከኢሳያስ ጋር ማደሙ አማራጭ ላይኖረው ይችላል፡፡ ከዚያ ባለፈ ኢሳያስን ታላቅና ተወዳጅ መሪ በማስመሰልና ሌላው አለም፤ የተባበሩት መንግስታትና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በኢሳያስ ላይ የሚያሰሙትን እሮሮና ውንጀላ ለመከላከል እሱን በማውገዝ ለኢሳያስ ጥብቅና መቆም በታሪክ ተጠያቂ ያደርጋል፤ በነገው የሁለቱ አገሮችና ሕዝቦች ግንኙነትም ላይ መጥፎ ጠባሳን ይተዋል፡፡ ከዚያም ባለፈ ይህ አይነቱ ድርጊት ኢሳያስን ከመደገፍ ባለፈ በኤርትራ በየማጎሪያ ቤቱ ታስረው ስቃይ በሚፈጸምባቸው ግፉአን ላይ ማላገጥ ነው የሚሆነው፡፡ ለብዙ ሚሊዮን ኤርትራዊያን ሲዖል የሆነችው አገራቸው ለእኛ መሸሸጊያ ሆናናለች በሚል እርካሽ ስሌት የኢሳያስን እድሜ ያርዝምልን፣ ሻቢያንም በመንበሩ ያቆይልን የሚለው ጸሎት በምድርም በሰማዩም ሰሚ ባይኖረውም ያስተዛዝባል፡፡ ከግፉአን ጎን አብረን መቆም ቢያቅተን እንኳ በበደላቸው ላይ ሌላ በደል እንዲፈጸም በሃሊዮም ይሁን በግብር ከግፍ ፈጻሚዎቹ ጎን እንዳንቆም የሚያደርገን ትንሽም የሞራን እንጥፍጣፊ ካለች ትበቃናለች፡፡ የግንቦት 7ቱ አቶ ነአምን ዘለቀ ጥሪ ግን በ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ የፓርቲዎች ክርክር ወቅት “ማፈር ድሮ ቀረ” የምትለዋን የፕ/ር መስፍን ወልደማርያምን ንግግር አስታወሰኝ፡፡

አገርን የማዳኑ ትግል እየተስተዋለ ቢሆን ይበጃል!

ያሬድ ኃይለማርያም

ከብራስልስ፣ ቤልጂየም

ትግራይ ውስጥ ሕዝቡ በእርዳታ የመጣ እህል እንዳይወሰድ ተከለከለ|የፍኖተ ዴሞ.ራድዮ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0

ሰኔ1 ቀን2009 ዓም
ርዕሰ ዜና
 የዓለም ባንክ ለወያኔ ተጨማሪ ብድር ሰጠ
 ትግራይ ውስጥ ሕዝቡ በእርዳታ የመጣ እህል እንዳይወሰድ ተከላከለ
 ግብጽ ውስጥ ሙስናን ያጋለጡ የሂሳብ መርማሪ ተከሰሱ
 በተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ስር የተመደቡ የኮንጎ ዴሞክ. ሪ. ወታደሮች ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸውን የተመድ ዘገባ አጋለጠ
 በኬኒያ የጸጥታ ኃይሎች ሁለት ሰልፈኞችን ገደሉ
 የናይጄሪያ መንግሥት ከደቡብ አማጽያን ጋር ያለውን ችግር
በውይይት ለመፍታት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ
 ሙሰቨኒ ባለቤታቸውን የትምህርትና የስፖርት ሚኒስቴር አድርገው ሾሙ

ዝርዝር ዜናዎች
 የዓለም ባንክ ለወያኔ አገዛዝ ተጨማሪ የ300 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለመስጠት መስማማቱን አስታውቋል። ባንኩ ለወያኔ አገዛዝና ለዘረኛ መሪዎቹ በልማት ስም ጠርቀም ያለ ገንዘብ በማበደር መጭውን ትውልድ በዕዳ ሰንሰለት ይዞ እያሰራ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ባሁኑ ወቅት ለመስጠት የተስማማው ብድር የትራንስፖርት ውጤታማነትን ለማጎልበትና የመንገድ ድህነነትን ለመጨመር ነው ተብሏል። ይሁን እንጅ የብድሩ ገንዘብ በአብዛኛው በወያኔ መሪዎች የውጭ ባንክ ሂሳብ ውስጥ እንደሚጨመር አጠያያቂ አልሆነም። የዓለም ባንክ ፀረ ኢትዮጵያ ለሆነው ለአምባገነኑና ዘረኛው የወያኔ ቡድን ለአንድ ዓመት የሚሰጠው የብድር መጠን ለቀድሞ መንግሥታት በ40 ዓመት ያላደረገው እንደነበር የሚገልጹ ወገኖች የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ልማትና ዕደገት ሳይሆን የወያኔን ዕድሜ ዘላለማዊ ለማድረግ ከገባበት የውጭ ምንዛሪ ዕጥረትም ለማውጣት የቆመ ድርጅት መሆኑን በመግለፅ፤ የዓለም ባንክ ለወያኔ መሪዎች በኢትዮጵያ ስም ብድር የሚሰጠውን መጠየቅ ይገባል ይላሉ።

File Photo

File Photo


 ሰሞኑን ትግራይ ውስጥ የወያኔ መሪዎች በድርቅና በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች እንዲከፋፈል የተቀመጠውን የእርዳታ እህል የማዳበሪያ ዕዳ ካልከፈላችሁ አናከፋፍልም በማለት የዕርዳታ አህሉን በመኪና በመጫን ወደ መቀሌ ለመውሰድ ሲሞክሩ በሕዝብ ትብብርና ቁጣ የተዘረፈውእህል ሊያዝ መቻሉ ውቋል። የወያኔ መሪዎች በድርቅና በረሃብ በመነገድ ገንዘብ መሰብሰቡ በረሃ እያሉ የተካኑበት ሰይጣናዊ ተግባራቸው መሆኑ ይታወቃል።

 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ከሳምንታት በኋላ ለሚጀመረው የብራዚል አትሌክቲክስ ውድድር በልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮች የሚሳተፉትን አትሌቶች ይፋ ማድረጉንና ይህን ተከትሎም የአመራረጡ ሂደት ላይ ውዝግብ መነሳቱ ይታወቃል። ይህን በሚመለከት ማክሰኞ ዕለት የአትሌቶች ማህበር አስቸኳይ የምክክር ስብሰባ ካደረገ ወዲህ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለብራዚሉ ኦሎምፒክ ባካሄደው የአትሌቶች ምርጫ ላይ ግልጽ ተቃውሞንና ቅሬታውን አቅርቧል። የአትሌቶቹ ማህበር አሁን ባለው አመራር ላይ ቅሬታ ማቅረቡ ተዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪ የአትሌክስ ፌዴሬሽን በባለሙያ የማይመራና ሃገርን ከመጥቀም ይልቅ ግለሰቦችን እየጠቀመ መሆኑንም አትሌቶቹ አውስተው፤ የአትሌቲክስ ማህበር በአትሌቲክስ ፌዴረሽን ውስጥ ተወካይ ቢያስቀምጥም ለይስሙላ ብቻ በመሆኑ አትሌቶች ፌዴሬሽኑን በአጋርነት እንዲመሩ ጠይቋል። አትሌቶቹ ጥያቄያቸውንና ቅሬታቸውን የሚከታተል አንጋፋ አትሌቶቹ ያሉበት አንድ ኮሚቴም ማቋቋሙ ታውቋል።

 በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከግብጽ የአስተዳደር ተቋሞች 67.6 ቢሊዮን ዶላር ተሰርቋል በማለት አጋልጠው የነበሩት የቀድሞ ከፍተኛ የሂሳብ መርማሪ ሚስተር ሂሻም ገኒና ሀሰት ዜና አሰራጭተዋል በሚል ክስ የፕሬዚዳንት ሲሲ አገዛዝ ፍርድ ቤት ያቀረባችው መሆኑ ታውቋል። ባለፈው መጋቢት ወር በዚሁ ምክንያት ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገው የነበሩት የሂሳብ መርማሪ (ኦዲተር) ሂሳቡን መርመረው መደምደሚያ ላይ የደረሱት በተጨባጭ ማስረጃዎች ተመስርተው መሆኑ ጠቅሰው የተሰነዘረባቸውን ክስ የፖለቲካ ምክንያት ያለው መሆኑን መግለጻቸው ይታወቃል። የፕሬዚዳንት አል ሲሲ መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ አምባገነን እየሆነ መምጣቱ በአገሪቱ ውስጥ ሆን ብሎ ሙስናን እያስፋፋ መሆኑን በመጥቀስ በርካታ ዜጎች እየወነጀሉት ይገኛሉ።

 ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2008 ዓም ይፋ ባደረገው ዘገባ ከታህሣስ 2006 እስከ ሰኔ 2007 ዓም ባለው የአንድ ዓመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ በአፍሪካ ኅብረት እና በተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ስር በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ተሰማርተው የነበሩ የኮንጎ ዴ. ሪፐብሊክ ወታደሮች 18 ሰላማዊ ሰዎችን ገድለው የነበሩ መሆናቸውን አጋልጧል። ባለፈው የካቲት ወር በነዚህ ወታደሮች የተገደለኡ የ12 ሰዎች አስከሬን በጅምላ ከተቀበረበት ጉድጓድ የወጣ ሲሆን በሌላ ወቅትና ቦታ የተገደሉ አራት የክርስቲያን ሚሊሺያ መሪዎች እና አባላት እንዲሁም ሌሎች ሁለት የሰላማዊ ሰዎች አስከሬኖች መገኘታቸው ታውቋል። በተገኘው የጅምላ መቃብር ውስጥ አንዲት እርጉዝ ሴትን ጨምሮ በጠቅላላው የአምስት ሴቶችና የሁለት ህጻናት አስከሬኖች እንደሚገኝበት ታውቋል። ሁኔታው ተጣርቶ በወንጀለኞቹ ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ድርጅቱ ለኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መሪ ደብዳቤ የጻፈ መሆኑም ተነግሯል።

 ሰኞ ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓም በኬኒያ ምዕራባዊ ከተማ በኪስማዩ ሁለት ሰልፈኞች መገደላቸውን ተከትሎ በተቃዋሚዎች የተደራጁ ማንኛውም ዓይነት ሰልፎች የተከለከሉ መሆናቸው የኬኒያ መንግስት በይፋ አውጇል። የኬኒያ የምርጫ ቦርድ አባላት ሙስና ውስጥ የተዘፈቁ በመሆናቸውና ቦርዱም አድሏዊ በመሆኑ መፍረስ አለበት በሚል መፈክር በተቃዋሚ ኃይሎች የተደራጁ ስልፎች ላለፉት ጥቂት ወራት በየሳምንቱ ሰኞ ሲካሄዱ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን አንዳንዶቹ ሰልፈኞች ከፖሊሶች ጋር ግጭት መፍጠራቸው ይታወቃል። ኳሊሽን ፎር ሪፎርምስ ኤንድ ዴሞክራሲ (Coalition for reforms and Democracy) የተባለው የተቃዋሚዎች ትብብር መሪ ሰላማዊ የተቃውሞ ስልፍ ማካሄድ በመንግስት የተቸረ ስጦታ ሳይሆን ሕገ መንግስቱ ለዜጎቹ ያጎናጸፈው መብት ነው በማለት በሚቀጥለው ሳምንት ሰኞና ሐሙስ ሰልፉ የሚቀጥል መሆኑን ተናገረዋል። ህገ መንግስቱን የሚጥስ አፋኝ አካል በተገቢው መንገድ መልስ ይሰጠዋል ብለዋል።

 የናይጄሪያ መንግስት በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ከሚንቀሳቀሱት አማጽያን ጋር እርቅ ለመፍጠር ፍላጎት ያለው መሆኑን ገለጸ። በሎንደን ህክምና እያደረጉ ያሉትን የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትን በመተካት አገሪቱን እያስተዳድሩ ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ የነዳጅ ሚኒስትሩ እና የወታደራዊ ተቋም ኃላፊዎች ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2008 ዓም. የነዳጅ አምራች ከሆኑ ጠቅላይ ግዛቶች አስተዳዳሪዎች ጋር ተገናኝተው እርቅ ስለሚደረግበት ጉዳይ መወያየታቸው ታውቋል። በውይይቱ በጠቅላላው እርቅ ስለሚደረግበት ሁኔታና እስከዚያው ድረስ በአካባቢው የሚደረገው ወታደራዊ ዘመቻ ስለሚቀንስበት ሁኔታ ስምምነት የተደረሰ መሆኑ ተገልጿል። ከአማጽያኑ ጋር ቀጥተኛ ንግግር ለማድረግ በናይጀሪያ መንግስት የጸጥታ አማካሪ ቡድን የሚመራ አንድ ኮሚቴ የተቋቋመ መሆኑም ተነግሯል።፡ ከጥቂት ጊዜ ወዲህ በአካባቢው የአማጽያን እንቅስቃሴ በመስፋፋቱ በቀን 2.2 ሚሊዮን በርሚል ነዳጅ ሲመረት የነበረው በቀን ወደ 1.6 ሚሊዮን በርሚል ዝቅ ማለቱ አገሪቱን በኢኮኖሚ ክፉኛ እየጎዳት ነው ተብሏል። የናይጀር ዴልታ ተበቃዮች የሚባለው ቡድን ረቡዕ ሰኔ 1 ቀን 2008ዓም በቲውተር ባሰራጨው መግለጫ በቀጥታ ከመንግስት ጋር በስተቀር ከሌላ አካል ወይም ከተቋቋመ ኮሚቴ ጋር ድርድር ለማድረግ ዝግጁ ያልሆነ መሆኑን ገልጿል። በዚህ ቡድን ስር የሚንቀሳቀሱት ግለሰቦች አብዛኞቹ ከሰባት ዓመት በፊት በአካባቢው ሲንቀሳቀስ የነበረ የአማጽያን ቡድን መሪ የነበረውና አሁን በሙስና እየተፈለገ ያለው ግለሰብ አድናቂዎችና ተከታዮች መሆናቸው ይነገራል።

 ባለፈው የካቲት ወር ብሔራዊ ምርጫ በድጋሚ አሸንፈዋል ተብለው ለአምስተኛ ጊዜ በስልጣኑ የቀጠሉት የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ሙሰቨኒ የ67 ዓመት ሚስታቸውን የትምህርትና የስፖርት ሚኒስቴር በማድረግ የሾሟቸው መሆኑ ተገልጿል። የሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ጠርቀም ያለ በጀት የሚመደብለትና የሙስና ምንጭ ሲሆን በርካታ ሰዎች ቦታውን ለመያዝ ሲመኙና ከፍተኛ ጥረት ሲያድርጉ እንደነበር ይታወቃል። ሙሰቨኒ ለሚስታቸው ይህንን ሹመት የሰጡት በወታደራዊ ተቋም ውስጥ፡ላለው ልጃቸው ከብርጋዴር ጄኔራልነት ወደ ሜጀር ጄኔራልነት የማዕረግ እድገት በሰጡ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ነው። ሙሰቨኒ ዘመዶቻቸውን ሁሉ በመሾም የኦጋንዳን ፖለቲካ በቁጥጥር ስር ያደረጉ ሲሆን የማዕረግ እድገት በመስጠት ልጃቸው እሳቸውን እንዲተካ ሁኔታውን እያመቻቹ ነው የሚል ውንጀላ እየተካሄድባቸው መሆኑ ይታወቃል። ሙሰቨኒ ተቃዋሚዎቻቸውን በኃይል ሲያፍኑ የቆዩ መሆናቸው ሲታወቅ ባለፈው ምርጫ ተወዳድረው አሸንፈዋል የተባሉት ሚስተር ቢሲግየ በቁጥጥር ስር ውለው በሀገር ክህደት ወንጀል የተከሰሱ መሆናቸው ይታወሳል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ሾተላይ –ይገረም አለሙ

$
0
0

እናታችን ኢትዮጵያ ባሕላዊ ሾተላይ ናት መሰለኝ። ዲሞክራሲን በስድሳ ስድስት ወልዳ በላች። አስቀድሞም በሃምሳ ሶስት አስጨንግፏታል። ብትወልድም ብትገላገለውም ለዘለቄታ አያደርግላትም። የማሕፀን መርገምት አለባት። የዲሞክራሲ ሾተላይ ናት ኢትዮጵያ። በስድሳ ስድስትማ ወዲያው ማግስቱን መፈክር ተፎከረላት። ‘አብዮት ልጆቿን ትበላለች’ ተባለላት ተሸለለላት። የዲሞክራሲ ሾተላይ እናት፣ በላኤ ሰውነቷን መላው የአለም ሕዝብ አስጠንቅሮ አውቀላት።

…………………..//……………………………..        ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን

Tensaye የዚህ ጽሁፍ መነሻ ምክንያት ሰሞኑን እዚህ በሀገር ቤት አዲስ ፓርቲ ተመሰረተ የሚለው ዜና ነው፡፡ፓርቲ መሰረቱ የሚባሉት ሰዎች ደግሞ አዲሶች ሳይሆኑ ቀድሞ በተለያዩ ፓርቲ ውስጥ እናውቃቸው የነበሩ ለውጥ ማምጣት ቀርቶ የፓርቲያቸውንም ህልውና ማስጠበቅ ያልቻሉ ናቸውና ነው ይህችን አስተያየት ለመሰንዘር የተነሳሁት፡፡

ልጅ ተወልዶ የማይድግበት ወይንም ጽንሱ የሚጨነግፍበት ከወላጆች የሚመነጭ ችግር ሳይንሳዊ አጠራሩንና እንዴትነቱን ለባለሙያዎች ትተን በሀገራችን ልማዳዊ አጠራር ሾተላይ ይባላል፡፡ ሎሬት ጸጋየ በአንድ ወቅት አንደተናገረው ሀገራችን የዴሞክራሲ ሾተላይ ያለባት ይመስላል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ለዴሞክራሲ መሰረት የሚጥለውን ፖለቲካ እናራምዳለን የሚሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች  በሾተላይ መጠቃታቸውና በሽታቸውን ለማወቅና መድሀኒት ለመወስድ አለመቻላቸው ነው፡፡ የመጀመሪያ ልጃቸውን በሾተላይ  ምክንያት ያጡ ወላጆች ዳግም ልጅ ለመውለድ ከማሰባቸው በፊት ወደ ሐኪም ጎራ ብለው ምክርም ሆነ መድሀኒት ተቀብለው ተዘጋጅተው ካልሆነ ሁለተኛውንም በተመሳሳይ መልኩ ያጣሉ፡፡ ለመውለድ እንጂ ለማሳደግ ያልታደሉ ይሆናሉ፡፡

የሀገራችንም  ፖለቲከኞች ተግባር የዚህ ተመሳሳይ ነው፡፡ ፓርቲ ሲመሰርቱ እንጂ አሳድገው ለወግ ለማእረግ ሲያበቁ አይታዩም፤ ስለ ህብረት ውህደት ሲያወሩ እንጂ ተግባራዊ ሲያደርጉ አይታዩም፡፡ ተባበርን ግንባር ፈጠርን ብለው አየሩን በወሬ ሲያደምቁ እንጂ ፈጠርን ያሉትን ህብረትም ሆነ ግንባር ቅንጅትም ይሁን ውህደት ለውጤት ሊያበቁት ቀርቶ እድሜውን ሲያስረዝሙት አይታይም፡፡

የቀደሙት ፓርቲዎች ወፌ ቆመች ሳይባሉ የጠፉበት ወይም የተዳከሙበት ምክንያት ሳይመረመር፣ በሽታው ታውቆ መድሀኒት ሳይፈለግ የእርስ በርስ ውይይትና ምክክር ሳይደረግና የባለሙያ ምክር ሳይጠየቅ የችግሩ መፍትሄ የሾተላዩ መድሀኒት አዲስ ፓርቲ መመስረት ይሆንና  ያለፈውን ድክመት ያወገዙ፣ አካሄድ አሰራሩን የኮነኑ  ይሰባሰቡና ፓርቲ ይመሰርታሉ፡፡ ነገር ግን ከምርጫ ቦርድ ሕጋዊ የምስክር ወረቀት በተቀበሉ ማግስት ስንጥቅ ማሳየት፣ ዋል አደር ሲሉ ደግሞ ርስ በርስ መናቆር ውስጥ ይገቡና አዲሱ ፓርቲያቸው ወግ ማእረግ ሳያይና ሳያሳይ  ወይ ይከስማል ወይ ተሸመድምዶ ይቀመጣል ወይም ለወያኔ ሎሌ ሆኖ ይሰግዳል፡፡

ብዙዎቹ ፓርቲዎች በዚህ መንግድ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ መኢአድ፣  ኢዴፓ፣ መኢዴፓ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ ወደ ኋላ ሀረጋቸው ቢመዘዝ መዐህድ ላይ  ነው የሚያርፈው፡፣ ሀገር ውስጥም ውጪም ያሉትን ፓርቲዎች ብንፈትሽ ብዙዎቹ በመለያየት የተፈጠሩ ናቸው፡አንድነትን በምርጫ ቦርድ ውሳኔ በፖሊስ አስገዳጅነት ለመረከብ የበቃው አቶ ትዕግስቱ አዎሉ አባል የነረበት የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ህብረት (ብዴህ)  በ1997 ምርጫ ዋዜማ ከመኢአድ ተቀላቀለ ተባለ፡፡ በምርጫው ማግስት ደግሞ እነዚሁ ሰዎች ጥቂት ሌሎች ሰዎችን ጨምረው ብርሀን ለኢትዮጵያ የተሰኘ ፓርቲ መሰረትን አሉ፡፡ በምርጫ 2002 ሰሞን ደግሞ ከአንድነት ተዋሀድን አሉ፡፡ አቶ ትዕግስቱ  በዚህ ሁሉ ጉዞው በእጅጉ የሚፈልገውን ሥልጣን ማግኘት አልቻለም ነበር፡፡ በርግጥም የፓርቲ መሪ መሆን የሚገባው ሰው አይደለም፡፡ አንድነት ፓርቲ በሽታውን አውቆ መድሀኒት የሚፈልግለት ሰው አጥቶ የትእግስቱን የሥልጣን ጥም ማሳኪያ ሆነ፡፡ የአንድነት በሽታ በቅጡና በወቅቱ ቢመረመርና መድሀኒት ቢገኝለት ኖሮ  አስቀድሞም ትእግስቱ የአንድነት አባል መሆን የሚገባው ሰው አልነበረም፡፡ የዛ በሽታ ሳይታወቅ ደግሞ አዲስ ፓርቲ!

መተባበርን በተመለከተም ኢዳቅ፤ ኢተፖድህ ፣ደቡብ ህብረት፣ጋፖመ፣  አማራጭ ኃይሎች ፤ኢዴኃህ፤ ቅንጅት ወዘተ እየተባለ አሁን በመኖርና ባለመኖር መካከል እስካለው መድረክ ድረስ ብዙ መተባበሮችን አይተናል ሰምተናል፡፡ ሁሉም ሲመሰረቱ ከእነርሱ ቀድሞ የነበሩ መተባበሮች ለምን ውጤታማ እንዳልሆኑ፤ ሽባ ያደረጋቸው በሽታ ምን እንደሆነ ወዘተ ሳይፈተሽና ያለፈው የመናቆርና የመለያየት በሽታ በመጪው ላይ እንዳይደገም መፍትሄ ሳይፈለግ በመሆኑ አንዳቸውም ውጤት ማስመዝገብ ቀርቶ ህልውናቸውን ማቆየት አልቻሉም፡፡ ቅንጅት የተሻለ ውጤት ማሳየቱ አሌ የሚባል ባይሆንም እሱም እንደሌሎቹ መተባበርን የሚያስጨነግፈው በሽታ በውል ሳይታወቅና መድሀኒት ሳይገኝለት የተመሰረተ በመሆኑ በበሽታው ተጠቅቶ መሪዎቹ የሰሩትን መልካም ታሪካዊ ሥራ ኋላ በፈጸሙት የመለያየት ተግባር ኦቆሸሹት፡፡

ወያኔ መቶ በመቶ አሸነፍኩዋችሁ እያለ በሚመጻደቅበት በአሁኑ ወቅት እንኳን የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚያስጨነግፋቸውንና በአጭር የሚያስቀራቸውን  ሾተላይ ለማወቅ የሚደረግ ጥረት ቀርቶ ሀሳብ መኖሩ አይሰማም፡፡ ብቻ ከልብ ያልሆነ የወቅታዊ አጀንዳ ማስቀያሻ የመተባበር ወሬ እንሰማለን፡፡ የመድረክ አባል ፓርቲዎች በጉባኤያቸው ማግስት እስከሚቀጥለው ጉባኤያቸው ስለ ውህደት እንደሚነጋገሩ ገልጸው የነበረ ቢሆንም  ባለፈው አንድ ዓመት ምንም  አልተሰማም፡፡ ኢዴፓ ራዕይና አንድ ሌላ ፓርቲ ተባብሮ ለመስራት እየተነጋገርን ነው በማለት ለአንድ ሳምንት አወሩ ጠፉ፡፡  ሰማያዊ ፓርቲ አንዴ ከኦብኮ ጋር አንዴ ከመድረክ ጋር እየሰራሁ ነው ቢልም ከአንድ ሰሞን ፕሮፓጋንዳ የዘለለ ነገር አይታይም፡፡ በዚህ ሁኔታ እያለን ነው እንግዲህ  የአዲስ ፓርቲ መመስረት ዜና የሚነገረን፡፡

ጥያቄው አዲስ ፓርቲ ለምን ተመሰረተ አይደለም፡፡ ፓርቲዎች በአጭር የሚያስቀራቸው ሾተላይ፣አለያም አንደፖሊዮ ሽባ የሚያደርጋቸው በሽታ ተጠንቶ  ታውቆ መድሀኒት ሳይገኝ ፓርቲ መመስረት ቁጥር ከመጨመር ያለፈ የሚፈይደው ነገር አለመኖሩን ያለፉት ልምዶቻችን ስለሚያሳዩን እንጂ፡፡ ፓርቲ ከመታገያ መድረክነቱ ይልቅ ለግለሰቦች የሚያስገኘው ጥቅም በመኖሩ አንዱን እያዳከሙ ወይንም እያፈረሱ አዲስ መመስረት ወይንም የግል ንብረት አድር ሙጢኝ ማለት የተለመደ ሆኗል፡፡ ነገር ግን ችግሩን አስወግዶ ለበሽታው ፍቱን መድሀኒት አግኝቶ የግለሰቦች መጠቀሚያ ሳይሆን ሕዝብ አታጋይ ፓርቲ እንዲኖር ለማድረግ ከልብ ከታሰበበት በሽታው ግልጽ፣  መድሀኒቱም ቀላልና በቅርብ የሚገኝ ነው፡፡ ችግሩ ለምርመራ ፈቃደኛ ሆኖ የሚቀርብ  መድሀኒቱንም ለመውሰድ  የሚዘጋጅ አለመገኘቱ ነው እንጂ፡፡

ምርመራው ውይይት ነው፡፡ መድሀኒቱ የራስን ችግርና ድክመት በወያኔ እያሳበቡ በዛ ውስጥ ተደብቆ ለማለፍ ከመጣር ራስን ለማየትና ለመጠየቅ  መድፈር ነው፡፡ የህክምናው ውጤት ለጋራ ድልና ለሀገራዊ ነጻነት የሚያበቃ ስልት ነድፎ ለግል ስልጣን መያዝ ሳይሆን ሕዝብን ከአገዛዝ ለማላቀቅ ተጨንቆ የቤተመንግሥቱ ወንበር ለአንድ ሰው ብቻ መሆኑን አምኖ ተባብሮና ተማምኖ መታገል ነው፡፡ ካልሆነም አንዱ ለአንዱ እንቅፋት አለመሆን ርስ በርስም አለመጠላለፍ ነው፡፡ የፖለቲካ ታሪካችን  የሚያሳየን ሥልጣን ላይ ያለን ኃይል ተቃውመው በማናቸውም መንገድ ትግል የጀመሩ ኃይሎች ጠላታችን የሚሉት ካደረሰባቸው ጥቃት ባልተናነሰ ርስ በርሳቸው መጠቃቃት መጠፋፋታቸውን ነው፡፡ የአንድት አመራሮች የግዛቸው የበላይ ተባብለው ለአደባባይ የበቃ ጦርነት ባይገጥሙ ምርጫ ቦርድ በምን ቀዳዳ ገብቶ ትእግስቱን ያነግስባቸው ነበር? ከራስ በላይ ነፋስ እየተባለ፣ቃልና ተግባር ሀራምባና ቆቦ ሆኖ፣ የእኔነት አብሪት ነግሶ፤ በሥልጣን ጥም ታውሮ ወዘተ  ሀገራዊ ትግል እንዴት ይሆናል፡፡

በትናንት መኩራት ዛሬ ሆኖ በመገኘት ካልተገለጸ  አይፈይድም፡፡  የትናንት አስተሳሰብም ሆነ የትግል ስልት በዛሬ  ካልተቃኘና ከዘመኑ ጋር ካልዘመነ  ውጤታማ አያደርግም፡፡ በየዘመናቱ የተደረገው ትግል ያስከፈለውን መስዋዕትነት ያህል ውጤት ላለማስገኘቱ ደረጃው ይለያይ ካልሆነ በስተቀር በወቅቱ የነበሩ ሁሉ ነጻ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ስለሆነም ለትውልድ መልካም ሀገር ለማቆየት ሲባል የድርሻ ድርሻ ተጠያቂነትን (አቶ አሰፋ ጫቦ ደጋግመው ይሉት እንደነበር) በመውሰድ  ከትላንቱ መንገድ ወጣ ብሎ ያልተሞከረውን ሳያስቡ ያልተሄደበትን መንገድ ሳይቃኙ ሮጦ  አዲስ ፓርቲ መመስረት ለትግል ነው ብሎ መቀበል ይከብዳል፡፡

በንቀትም በእብሪትም፤በጉልበትም በማስቀየስም የወያኔ አገዛዝ መቀጠሉ የእኛ ድክመት ውጤት መሆኑ አስቆጭቶን ሂሳብ ለማወራረድ ሳይሆን የፖለቲካችንን ሾተላይ ለማወቅና መድሀኒት ለማግኘት በሀቅ በግልጽና በመተማመን መነጋገሩ ነው የሚበጀው፡፡  ፓርቲ ማብዛት ሳይሆን ያሉትን ማጠናከርና ማሰባሰብን ፣ ፓርቲን የግል ንብረታቸው ያደረጉ ግለሰቦችን ደግሞ በሀቅና በድፍረት በማጋላጥ በሀገርና በሕዝብ አትቀልዱ ማለቱ ነው የሚሻለው፡፡  ለወያኔ የምርጫ አጃቢነት እንደሆነ ያሉት ፓርቲዎች ከበቂ በላይ ናቸው፡፡ እንደውም በዝተውበት ሰሞኑን የተወሰኑትን ከመዝገቡ ላይ ሰርዟቸዋል፡፡(መጀመሪያም በምርጫ ቦርድ መዝገብ ላይ እንጂ በመሬት ላይ አልነበሩም፡፡)

ከፖለቲከኞቹ በተጓዳኝ ደጋፊዎችም የጭፍን ድጋፍና ተቃውሞ ሾተላይ ተጠቂ በመሆናችን ለበሽታው መድሀኒት ማግኘት ሳይሆን ለመባባሱ ከአንዱ ወደ አንዱ እየተላለፈ ለመስፋፋቱ አስተዋጽኦ አድርገናል እያደረግንም ነው፡፡ የምንደግፈው አይነካብን እንላለን፤ የማንደግፈው ምን ጥሩ ቢሰራ አይታየንም፤ከዚህ በሽታ መላቀቅ ካቻልን ፖለቲካችን ፈውስ አያገኝም የፖለቲካ ፓርቲዎችም ከሾተላይ አይገላገሉም፡፡

 

 

ሲያልቅ አያምርም፤ በሠፈሩትም መሠፈር አይቀርም –ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

$
0
0

“አንበሣን ፈርቼ ዛፍ ላይ ብወጣ ነብር ጠበቀኝ” የምንለው አሉን የምንላቸው ሁለትና (ከዚያም በላይ) አማራጮች እንከን ገጥሟቸው ስንጨነቅና ስንጠበብ ነው፡፡ የአሁን የኛ ሁኔታስ? በተለይ እኛ ኢትዮጵያውያን አማራጮቻችንን ሁሉ አንድ ባንድ እያጣን አይደለምን? ምን ቀረን? ኢትዮጵያን ወደንና ፈቅደን ለወያኔ አስረክበናል፡፡ መሸሻዎቻችን አሜሪካና አውሮፓም በኢኮኖሚ ድቀትና በአክራሪ ሙስሊሞች እየተንኮታኮቱ ናቸው – ሊለይላቸው አንድ እሁድ ቢቀራቸው ነው፡፡ ጥጋብን መቻል የሚያቅተው የዐረቡ ዓለምም  በውስጥ ግጭቶች  ከመበጣበጡም በተጨማሪ ብቸኛ የተፈጥሮ ሀብቱን – ነዳጁን – ሊጨርስ የቀረው ዘመን ጥቂት አሠርት ዓመታት ብቻ ናቸው፡፡ አፍሪካ፣ ላቲን አሜሪካና ካሪቢያን እንዲሁም ኤዥያም በየራሳቸው ችግሮች ተወጥረዋል፡፡ ሁሉም ጋ እሳት ነው – አንዱ ጋ የተዳፈነ ቢመስል በሌላው እየነደደ ነው፡፡ የምፅዓት ጊዜ በየደጃፋችን እያንኳኳ ያለ ይመስላል፡፡ የህልምና የእውን ሩጫችንን ቆም በማድረግ ይህንን ገሃድ እውነት እናስብ፡፡ እናስብናም ዞሮ መግቢያ የወል ሀገር እንድትኖረን መጎሻመጡን ትተን በጋራ እንንቀሳቀስ፡፡

“ኑሮ በአሜሪካ”ንን በተመለከተ አንጀት የሚበላ መጣጥፍ ከደቂቃዎች በፊት አነበብኩ፡፡ በዚያም እዚያ ስላሉ ወገኖቼ አዘንኩ፡፡ “ዱሮ”ን ተሸክሞ መኖር እንደማይቻልም ተገነዘብኩ፡፡ ዱሮ ዱሮ ነው፡፡ አሁንና ዱሮ ኅብረት የላቸውም፡፡ “የነበር ሲያወሩት ይመስላል ያልነበር፤ ያባብዬ ፎቶ እንዲህ ያምር ነበር” ብላለች አሉ አንዲት ልጅ በአባቷ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ፣ የሙሾ ግጥሙን አስተካክዬ ባላስታውስ ይቅርታ፡፡ ለማንኛውም ብዙም ሳትደናገጡ ቀጣዮቹን አንቀጾች በጥሞና ተመልከቱ፤ ከዚያም ዓለም ወዴት እየነጎደች እንደሆነ ተረዱ፡፡ የአሜሪካና አውሮፓ ገነትነት በምን ፍጥነት ወደሲዖልነት እየተለወጠ እንደሆነም ተገንዘቡ፡፡ ማወቅ ቢጎዳም ካለማወቅ ግን ይሻላል፡፡

ስቲፍን ሌንድማን የተባለ አሜሪካዊ የፖለቲካ ተንታኝ የወቅቱን ፕሬዝደንታዊ የምረጡኝ ዘመቻ በሚመለከት ሰሞኑን ባስነበበን አስደንጋጭ ጽሑፉ የሚከተለውን ይላል፤

… ኦባማን ተክቶ ወደ ዋይትሃውስ የሚገባ ቀጣዩ የአሜሪካን ፕሬዝደንት የሚወርሰው  ከ1929ዓ.ምቱ የመጀመሪያው የኢኮኖሚ ቀውስ ቀጥሎ በዚህ ዘመን የተከሰተውን ሁለተኛውን ታላቅ የኢኮኖሚ ቀውስ (second Great Depression) ነው፡፡ ይህ ቀውስ በአሥር ሚሊዮኖች የሚገመቱ ሥራ አጦች ወይም ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋዮች የሚበዙበትና በኢኮኖሚና በሥልጣኔ ዳብሯል ከሚባለው የአንደኛው ዓለም ዜግነት ወጥተው ወደሦስተኛው ዓለም ደረጃ እንዲወርዱ በልዩ ሥልት እየተገፉ ያሉ አሜሪካውያንን የያዘ ነው፡፡ ፕሬዝደንቱ የሚረከበው ችግር ቃላት ሊገልጹት ከሚቻላቸው በላይ እጅግ ውጥንቅጥና ውስብስብ ነው፡፡

 ወደ ግማሽ አካባቢ የሚጠጋው የአሜሪካ ሕዝብ ድሃ ነው ወይም ወደ ድህነት ጫፍ እየተነዳ ነው፡፡ ብዙ ቤተሰቦች የዕለት እስትንፋሳቸውን ለማቆየት ከሁለት ቦታዎች በላይ መሥራት አለባቸው፡፡ ጥሩ ገቢ ያስገኛሉ የሚባሉ ብዙ ሥራዎች ከአሜሪካውያን ጉሮሮ እየተነጠቁ በርካሽ ደሞዝ ለሚቀጠሩ የውጭ ሀገራት ዜጎች እየተሰጡ ናቸው፡፡ ያሉት ሌሎች ሥራዎችም ቢሆኑ ደህና ደሞዝ የማያስገኙ፣ ጥቅማ ጥቅምም የሌላቸውና ጥቂት ሰዎች በጊዜያዊነት ወይም በትርፍ ሥራነት የሚቀጠሩባቸው ናቸው፡፡ የዜጎች ሕይወት አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል፡፡

ለአቅመ ሥራ ከደረሰው የአሜሪካ ሕዝብ መካከል ሩብ ያህሉ ሥራ ማግኘት አይችልም – ይህም የሆነው ሥራ ስለሌለ ወይም የሥራ ዕድል ስላልተመቻቸለት ነው፡፡ የአዳዲስ ሥራዎችን መፈጠር የሚዘግበው የሌበር ዲፓርትመንት የሚያወጣው ወርኃዊ ዘገባም የውሸት ነው፡፡ ሥራዎች ተከፈቱ ብሎ የሚያወራው መዝገብ ላይ እንጂ መሬት ላይ የሉም [ወይ የቦለቲካ መመሳሰል! የአሜሪካ መንግሥትም ወያኔ ሆነ ማለት ነው?] ሕዝብን የተሳሳተ መረጃ መቀለብ ሆን ብለው ተያይዘውታል፡፡[የአሜሪካን ሕዝብ በ2016 ኤፕሪል ላይ በተካሄደ የሕዝብ ቆጠራ 323, 730, 000 መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ምንጭ – https://en.wikipedia.org/wiki/Demography_of_the_United_States]

የኦባማ መንግሥት ሥራን በመፍጠር ሣይሆን በተቃራኒው ሥራን በማጥፋት ይታወቃል፡፡ ስለሥራ መስክ ፈጠራና ስለማኅበራዊ ችግሮች ማስወገድ ዙሪያ አሁን ለዋይትሃውስ በመወዳደር ላይ የሚገኘው ትራምፕ ምንም ያለው ነገር አለመኖሩ ደግሞ ይገርማል፡፡…(በቅንፍ የተሰጡ አስተያየቶች/መረጃዎች የራሴ ናቸው)

 

አዎ፣ አሜሪካ ጣጣ ውስጥ ገብታለች፡፡ ዕዳዋ ራሱ 19.2 ትሪሊዮን ዶላር መሆኑ ራሱ ትልቅ ራስ ምታትና ከመሆኑም በተጨማሪ መቼ ተከፍሎ እንደሚያልቅ መገመትም አይቻልም – ይቺ ከመወለዷ እያረጀች የምትገኝ የዓለም ኃይል አገር ዐይን ገባት መሰል “ወፍራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል” ዓይነት ሆናለች፡፡ ይህ የቀልድ የሚመስል የዕዳ ቁጥር እየጨመረ እንጂ ባለበት እንኳን ሊረጋ አለመቻሉ ደግሞ ብዙዎችን እያስደነቀ የሚገኝ አሳዛኝ ክስተት ነው፡፡

አሜሪካ የሁሉም ዜጋ ንብረት እንደመሆኗ ሁላችንም “አንቺ ቸኳላ አሜሪካን ሆይ ወዴት እየሄድሽ ነው? አንቺ ቀልቃላ የምንዱባን መጠጊያ አሜሪካ ሆይ ሩጫሽ ለምን ፈጠነ?” ብለን በጋራ እንጠይቃት፡፡ “ስንት በረንዳ አዳሪዎችን፣ ስንት ባለዕዳ ዜጎችን፣ ስንት አደንዛዥ ዕፅ አዘዋራችንና ተጠቃሚዎችን፣ ስንት ከባህልና ከሃይማኖት ያፈነገጡ ጉግማንጉጎችንና ፍናፍንቶችን፣ ስንት የአፍሪካውያን ሀብትና ንብረቶችን፣ ስንት ኢትጵያውያን የፖለቲካና ኢኮኖሚ ወንጀለኞችን፣ ስንት ነፍሰ ገዳዮችን… በጉያሽ ውስጥ ወሽቀሽ ይዘሻል? እስከመቼስ የወመኔዎች ዋሻ እንደሆንሽ ትቆያለሽ?” ብለንም እንጠይቃት፡፡ እንዲህ ብለን ደግሞ እናስጠንቅቃት፡- “አሁን ግን ጉድሽ!! አንዳንድ ቅን መሥራች አባቶችሽ ካቀዱት መንገድ ውጪ የሚጓዙ ፒራሚዳውያኑ አሰለጥ ልጆችሽ ሞትሽን እያፋጠኑና አምነው የተጠጉ ሌሎች የዓለም ዜጎችንም መድረሻ እያሳጡ ይገኛሉ፤ ስላንቺ የተነገረውም ትንቢት ሙሉ በሙሉ ሊፈጸም የቀረው ጊዜ በጣም አጭር ይመስላል፡፡ ስለዚህ ባፋጣኝ ንስሃ ካልገባሽና ወደ ቀናው መንገድ ካልተመለስሽ አንቺን አያድርግ፡፡ አሣርሽ ይበዛልና፡፡”

 

አውሮፓስ?

 

የአውሮፓም ዕጣ ፋንታ ከአሜሪካው የተለዬ አይደለም፤ እዚያም ቤት ነገር አለ፡፡ በዚያ በኩልም የሚያስደስት ነገር የለም – መልካም ዜና ዱሮ ቀረ፡፡ አይሲስ የሚባለው አሜሪካን ሠራሹ አሸባሪ ቡድን ከመካከለኛው ምሥራቅ በገፍ የሚያባርራቸው በጭካኔና በኋላ ቀርነት ከርሱ ብዙም የማይተናነሱ ዜጎች አውሮፓን እያጥለቀለቁ ናቸው፡፡ የአውሮፓ ድንበሮች ወትሮም ልል በመሆናቸው ማንም እየገባ በአሁኑ ወቅት አውሮፓውያኑ ራሳቸው በስቃይና በመከራ እንዲኖሩ ተገደዋል፡፡ የሚገቡባቸው ስደተኞች በሃይማኖትና በሥልጣኔ ደረጃ ከአውሮፓውያኑ በእጅጉ ስለሚለዩና ኋላ ቀርም ስለሆኑ ፈረንጆቹ ተራ ዜጎች የሚያደርጉትን አጥተው ግራ ተጋብተዋል፡፡ ከእሥር የተፈቱ ያህል የሚቆጠሩት ስደተኞች ዕድሜ ልካቸውን ባገራቸው ታፍነው ስለከረሙ በተለይ አውሮፓውኑን ሴቶችና ሕጻናነት አስገድደው በመድፈርና የተለያዬ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ አደጋ በማድረስ የተረጋጋና ሰውኛ ሕይወት ይኖር የነበረውን አውሮፓዊ እንደጭራቅ እያሸበሩት ይገኛሉ፤ ነፃነትን የማያውቅ ሰው ነፃነትን ሲያገኝ አጠቃቀሙን አያውቅበትምና እነዚህ መጤዎች በሰው ሀገር ውስጥ ባለቤቶቹን መቆሚያ መቀመጫ እያሳጡ አስመርረዋቸዋል፡፡ መንግሥታቱም በዚህ በፈረደበት ሰብኣዊ መብት ጥበቃ ተብዬና እንግዳን ማክበር በሚለው ፈሊጥ እየተዘናጉ የገዛ ዜጎቻቸውን ለጭራቆች አጋልጠው ይልቁንም ይባስ ብለው ለወንጀለኛ ስደተኞች ከለላና ጥበቃ እያደረጉ ናቸው – ዕንቆቅልሽ ነው፡፡ ስለዚህም ነዋሪው ዜጋ የሚደርስበትን ነገር በማመንና ባለማመን መካከል ፈዝዞና ደንግዞ “የፈጣ ያለህ” እያለ ይገኛል – ሊያውም ከፈጣ ጋር ያልተቆራረጠው ጥቂቱ ዜጋ፤ ሌላውማ ነገር ዓለሙን እርግፍ አድርጎ ትቶ የራሱን ሥልጣኔ አምላኪ ሆኗል፡፡ ከጥቃት የማይከላከልልህ መንግሥት አይግጠምህ – ኢትዮጵያውያንም የገጠመን ችግር አንደኛው ይህን መሰሉ ነው፡፡ ለምሣሌ ጋምቤላ ውስጥ ያ ሁሉ ሕዝብ ሲያልቅና ሰውን ያህል ትልቅ ሀገራዊ ሀብት ተዘርፎ እንዲለቀቅ በገንዘብ ለድርድር ሲቀርብ መንግሥት ቢኖረን ኖሮ ስንትና ስንት የመልሶ ማጥቃትና የበቀል እርምጃ በተወሰደ ነበር፡፡ አልታደልንም፡፡

አውሮፓን እያሰጋት ያለው በዋናነት እስላማዊ አክራሪነት ነው፡፡ እንደሚታወቀው የአውሮፓ ሕዝብ ቁጥሩ ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰ መጥቶ አሁን አሁን እንዲያውም – የተለዬ እርምጃ ተወስዶ ችግሩ እየተሻሻለ ካልመጣ በስተቀር – በሚቀጥሉት  ሃምሣና ስልሣ ዓመታት ውስጥ የሕዝብ ቁጥራቸው ወደ ዜሮ የሚወርድባቸው ሀገራት ሊኖሩ እንደሚችሉ እየተነገረ ነው፡፡ በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው በዚህ መሠረታዊ ችግራቸው ላይ ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው በሃይማኖትም በባህልም በሥነ ልቦናም በአስተሳሰብና አመለካከትም በሌላውም ሁሉ በፍጹም የማይገናኙ በአብዛኛው ባላገር የሆኑ ስደተኞች ሲያጥለቀልቋቸው እነዚህ የአውሮፓ ሰዎች እንኳንስ ሰው ሊፈጥሩ የራሳቸውን መፈጠር ራሱ ሊጠሉና ሊረግሙ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም አውሮፓ ቀስ በቀስ የአይሲስ ግዛት ልትሆን የምትችልበት አሣዛኝ አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል፡፡ አይሲሶች ራሳቸው እንደሚሉት ሮም ከተማን  የካሊፌቱ ዋና መቀመጫና መናገሻቸው አድርገው አውሮፓንና መላውን ዓለም በሸሪዓ ለማስተዳደር ትልቅ ዕቅድ አላቸው፡፡ አይሆንም ደግሞ አይባልም፡፡ ሰባራ ክላሽን የያዙ ሰባት ንፍጣቸውን ያልጠረጉ ሕጻናት ወያኔዎች ለ17 ዓመታት ታግለውና ከተባበራቸው ኃይል ጋር ተባብረው ኢትዮጵያን የመሰለች ትልቅ ታሪካዊት ሀገር እንዲህ ማዋረድና ማበለሻሸት ከቻሉ አይሲስን የመሰለ ዐረመኔና ጨካኝ ሰይጣናዊ ፍጡር ዓለምን አይቆጣጠርም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ የሚፈልጉትን ግብ ለመምታት ፍቅርና ውዴታ አላዋጣ ካለ እንደ ጭካኔ የሚያዋጣ ትልቅ ግብኣት የለም፡፡ የጭካኔ ተግባር መጨረሻው አያምርም እንጂ የፈለግኸውን ግብ መምታት ያስችልሃል፡፡ “ደፋርና ጭስ” የምንለውም እኮ ለዚህ ነው፡፡ እንጂ ከስድስት ሚሊዮን ሕዝብ አብራክ የወጡ ቆራጥ ጮሌዎች በምን ሒሣብ ነው 90 ሚሊዮን ሕዝብ ሊያሸኑ የሚቻላቸው? አስቡት፤ የፈለገ የውጪ ኃይል በምክርም ይሁን በመረጃና በሎጂስቲክስ ቢያግዛቸው እኛ ወንዶች ብንሆን (ሴቶችም ጭምር ብንሆን of course) ዝምባችንን እሽ ማለት ይቻላቸው ነበርን? እንዴት ተደርጎ!  እነዚህ እርጉም ወያኔዎች  ወንዝ ቀርቶ የደረቀ ቦይ የማያሻግር ያን የመሰለ ቆሻሻ ዓላማ ይዘው እዚህ የደረሱት በተንኮላቸውና በዐረመኔያዊ ተግባራቸው መሆኑን እንግዲህ ልብ ይሏል፡፡ ደህና ዓላማ ቢኖርህም አንዳንዴ ጨከን ካላልክ ጉድ ትሆናለህ ወንድሜ፤

comment symbol icon

comment symbol icon

ትመር እንደሆነ ምረር እንደኮሶ

አልመር ብሎ ነው የተበላው ዱባ (ኤዲያ!ግጥሙ ጠፋኝ እባክህ) የሚባለውስ ለዚህም አይደል?

 

አባ ወልደትንሳኤ አያልነህ፣ የኤጲስ ቆጶስነት ማእረግን ተሾሙ

$
0
0

aba woldetensae

“ኤጲስ ቆጶስ ሆይ ለማስተማር ትጋ፣የበደለውንም … ወደ ቤ/ክን መልሰው እንጂ…”ፍትሃ ነገስት

ከታምሩ ገዳ
ለሰበከተ ወንጌል መሰፋፋት እና ለሃዋሪያዊ ተልእኮ ሲባል ወደ ሰሜን አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አወሮፓ፣ ምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ፣ አወስትራሊያ ፣ኒውዚላንድ እና የመሳሰሉት አህጉራት እና አገሮች በመጓዝ በመንፈሳዊ ርሃብ እና ጉስቁልና የሚሰቃዩ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮችን በማጸናናት እና በማበረታት የሚታወቁት አባ ወልደትንሳአኤ አያልነህ ለከፈሉት መሰዋትነት እና በመከፈል ላይ ላሉት መንፈሳዊ እና ሃዋሪያዊ አገልገሎት በወጪ አገር የምትገኘው የኢ/አ/ተ/ቤ/ክ ሰሞኑን አዲስ የመንፈሳዊ አባትነት ሹመት እና ሓላፊነት አንደሰጠቻቸው ታወቀ።

ባለፈው እሁድ እ ኤ አ ሰኔ 5/ 20 16 በሎሳንጀለስ ከተማ በምትገኘው እና ኣባ ወልደተንሳኤ አብዛኛውን ጊዜያት በክህነት እና በሰብከተ ወንጌል የሚያገለግሉባት የድንግል ማሪያም የ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተካሄደው የቅዳሴ መረሃ ግብርን ለጥቆ የሰልጣነ ክህነቱ እና የምስራች ዜናው ለምእመናኖች በአውደ ምህረቱ ላይ የተበሰረ ሲሆን በእለቱ በ ስፍራው የነበሩ በርካታ መእመናኖችም እዲሱን የ እባ ወልድትንሳኤን ሹመት የደልዎ ወይም”አባታችን ይገባዎታል” በማለት ደሰታቸውን በእልልታ እና በጭብጨባ ገልጸዋል። ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት እንደተቻለው በ ስላጣነ ክህነት ዋስጥ ከፈተኛ ማረግ የሆነው አባ ወልደተንሳኤ የተሰጣቸውን የ ኤጲስ ቆጶስ ማእረግን እና ሃላፊነትን በመጪው ቅዳሜ ሰኔ 18 /2016 እኤ አ በካሊፎርኒያው ፣ኦክላንድ፣ በሚደረገው ልዩ መንፈሳዊ ፕሮግራም ላይ ታላላቅ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች እና ምእመናኖች ፊት በመቅረብ የሚሾሙ እና ተጥጨማሪ ሃላፊነቶችን የሚቀበሉ ሲሆን ከዚሁም ጋር በተያያዘ ኣባ ወልደትንሳኤ ከአለማቀፍዊ እና ሃዋሪያዊ ተልእኳቸው መልስ አብዛኛውን ጊዜያት የሚያገለግሉበት የሎሳንጀለስ ድንግል ማሪያም ቤተክርስቲያን መእመናኖች እና በርካታ የመንፈስ ልጆቻቸውም በከብረ በአሉ እና ሹመቱ ላይ ለመገኘት በኮንትራት እወቶቡሶች እና በግል መኪኖቻቸው በመጓዝ የክብረ በአሉ ታዳሚዎች እና የበረከቱም ተሳታፊዎች ለመሆን በዝግጅት ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከዚያም በሁዋላ የደንግል ማሪያም ቤተክርስቲያን እና ምእመናኖቿ ለብጹነታቸው ልዩ “የእንኳን ደስ ያሎት እና እንኳን ደስ ያለን የምስጋና መረሃ ግብር ” ከ ባአለ ስሜቱ በሁዋላ በቀጣዩ ሳምንት ማዘጋጀቷ ተገልጿል።

ኣባ ወልደተንሳኤ ቤተክርስቲያኒቱ እና ልጆቿ በሚፈልጓቸው ጊዜያት እና ቦታዎች “ደከመኝ ፣ሰለቸኝ” ሳይሉ ፣ ግላዊ ክብር እና ሙገሳን ሳይሹ በተጠሩበት እና የመምህራን እጥረት እና ክፍተት አለ ብለው በሚያምኑባቸው የአለም ዳርቻዎች በመጓዝ ሃዋሪያዊ ተልእኳቸውን ከሚወጡ ታዋቂ የወንጌል ገበሬዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ ቅዱስ መጽሃፍ እንደሚለው ሰጋ ለባሽ ሁሉ ሃጢያተኛ እንደ መሆኑ ሁሉ አንዳንዴ እርሳቸውን ጨምሮ ከካህናቶች በኩል ሰህተቶች ሲፈጸሙ በግንባር ቀደምነት ወጥተው የሚቃወሙ ፣የሚያወግዙ እና ይቅርታን የሚያስቀድሙ ፣በገሃዱ አለምም ቢሆን የህግ ጥሰቶች ሲኖሩ ፣ ደሃዎች እና ደካሞች ሲገፉ ዘር ቀለም ሳይለዩ ሁሉንም ወገኖችን የሚገስጹ መንፈሳዊ አባት ሰለመሆናቸው እንዲሁም ህገ ኦሪትን ከ ሕገ ወንጌል ጋር በማጣቀስ በቀልድ እና በምሳሌ መልክ የምእመናኖችን መንሰፈን እና ልቦችን በእግዜ አብሔር ቃላት የሚያረሰረሱ ታላቅ የወንጌል መምህር /ገበሬ እንደሆኑ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል።

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሃይማኖት እና ስርአት መሰረት የኤጵስ ቆጶስነት ሹመት የሚሰጠው አንድ አገልጋይ ሰለ ሃይማኖቱ፣ስለ እወቀቱ፣ስለ አኗኗሩ፣ስለ መልካም ምግባሩ በ መእመናኖች እና በጳጳስ ሲረጋገጥለት ብቻ እንደሆነ የቤተክርስቲያኒቱ ዋንኛ መተዳደሪያ የሆነው ፍተሃ ነገስት ይደነግጋል።የ አንድ ኤጵስ ቆጶስ ሃላፊነቱም ከ ብዙ በጥቂቱ “ኤጲስ ቆጶስ ሆይ ለማስተማር ትጋ።መጽሃፍትን ሁሉ ለመተርጎም ብትችል ህዝብህን ትምህርት አጥግባቸው።በብዙ ትምህርት ባለጠጎች ይሆኑ ዘንድ ከህጎችህ ብርሃን አብራላቸው።የበደለውን አውግዘህ ብትለየው በውጭ አትተወው ወደ ቤተክርስቲያን መልሰው እንጂ።የጠፋውንም ፈልግ።ስለ ሃጢያቱ ብዛት እድናለሁ ብሎ ተሰፋ የማያደረገውን በሁሉ ጠፍቶ ይቀር ዘንድ አትተወው።እንዲህም ኤጲስ ቆጶስ የሃጡን ሃጢያት ሊሸከም ይገባዋል።” ይላል።
በውጪ አገር የምትገኘው የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ሰሞኑን ለተለያዩ ታላላቅ መንፈሳዊ አገልጋዮቿ ሹመት እና ማእረግ እንደሰጠች የታወቀ ሲሆን ለአብነት ያህል አባ ሳሙኤል ከዲንቨር ፣አባ ጽጌ ከ ሎሳንጀለስ ቅድስት ማሪያም (ስላውስን አጥቢያ)፣አባ ሳሙኢል ከካንዳ፣ አባ ወልደተንሳኤ ከሎሳንጀልስ ድንግል ማሪያም(ሜን ስትሪት አጥቢያ)፣ አባ ገብረ ስላሴ ከ አትላንታ እና አባ ተሰፋሚካኤል ከብዙ በጥቂቱ ተጠቃሾች ናቸው ።ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በምእራብ አውሮፓ ሎንዶን ከተማ ወስጥ የሚኖሩ አቶ ያእቆብ አድማሱ ለዚህ ጸሃፊ እንደገለጹት “ በርካታ ታላላቅ አባቶች በእድሜ መግፋት እና በጤንነት መታወክ ምክንያት ከመደበኛ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው መስተጓጎላቸው የግድ በመሆኑ እና የቤተክርስቲያኒቱ ሃዋሪይዊት ተልእኮም እየተበራከተ እና እየተስፋፋ በመምጣቱ ሳቢያ ተጨማሪ እና አዳዲስ አገልጋዩችን መሾም እና ክፍተቱን መሙላት ተገቢ እና ለ ነገ የማይባል ጉዳይ ነው።” በማለት አሰታያየታቸውን ሰጥተዋል።

በሎሳንጀለሰ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በድንግል ማሪያም ቤ/ክ ለበረካታ አመታተ የተገለገሉባት እና በመገልገል ላይ የሚገኙት፣ በክርስትና ሰማቸው ቤተማሪያም የተባሉ አንድ ምእመን በበኩላቸው የእባ ወልደትንሳኤ መሾምን በተመለከተ ለዚህ ጸሃፊ በሰጡት አስተያየት ” አኛ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው አባታችን የደል ዎ /ይሁን ብለናል” በማለት ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን ሰለ አጠቃልይ የእምነቱ ተከታዮች በሰጡት የግሌ አሰተያየት ነው ባሉት ”ይህቺ በተከታዮቿ ብዛት ከሩሲያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተከታዮች በመቀጠል በአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምተገኘው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ከተመሰረተች ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ለትምህርት፣ ለፍትህ ፣ ለአንድነት እና ለመሳሰሉት አገራዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ፋና ወጊ በመሆን አስከ ዛሬው ትወልድ ድረስ ያደረሰች ታላቅ ባለውለታ የእምነት ተቋም መሆኗን በማንኛውም ወገን በኩል ለአፈታ እንኳን ሊዘነጋ አይገባም። ክብር ለሚገባው ክብር የመስጠት ባህል ሊለመድ ይገባል። የሃይማኖት አባቶችም ቢሆኑ ዘመን አመጣሹ ልዩነቶቻቸውን እና የመወጋገዝ ዘያቸውን ወደጎን በማድረግ ቤተከርስቲያኒቱ ስርእቷን እና ወጓን ጠበቃ ቀደምት አባቶች ሰለእምነታቸው ሲሉ የከፈሉትን መሰዋእትነትን ወደኋላ መልስ ብለው በመመልከት እና የቆሙበትንም ምድር በማጤን በ21ኛው ክፍለዘመን ውስጥ በሚደረጉ ማንኛውም እንቀሰቃሴዎች ላይ ግንባር ቀደም ሚና ተጫዋች እንድትሆን የማድረግ ታላቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው መገንዘብ ይኖርባቸዋል።” በማለት የታናሽነት ምክራቸውን ሰጠተዋል።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live