Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ይድረስ ለመላው የአማራ ህዝብ: የአቋም መግለጫ…. የመጨረሻ የክተት ጥሪ!!!  – (ከባህርዳር ፤ ጎጃም ፤ ኢትዮጵያ)

0
0

ግንቦት 14 /2008 አ/ም

መላው የአማራ ህዝብ የወልቃይት ህዝብ ያነሳው ፍፁም ሰላማዊ የአማራ ማንነት ይከበርልኝ ጥያቄ መላው የአማራ ህዝብ ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ እጃችን ሳንከት በጥሞና ስንከታተል መቆየታችን ሁላችን የምናውቀው ጉዳይ ነው።ጉዳዩ የወልቃይት ህዝብ በራሱ ያለምንም ተፅእኖ ህገ-መንግስቱ ወቅቱን በጠበቀ ሁኔታ ፈጣን ምላሽ ይሰጠዋል ብለን ተስፋ ስናደርግ ቆይተናል። በህዝቡ ብዙ የሚባል ልዩ ልዩ ግፍ ሲደርስ አይተን እንዳላየን ሰምተን እንዳልሰማን በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብ በወልቃይት ህዝብ ላይ መሳሪያቸውን ይዘው የፊጥኝ ማሰቃየታቸውን የፌደራል መንግስት ለመራሹ የትግራይ ክልል መንግስትና ህዝብ ተጠያቂ ሆነው ከህግ ስር እንዲውል ለክልሉ አምባገነን አመራር ላይም እርምጃ ይወስዳል ብለን ተስፋ ስናደርግ ቆይተናል። እንዲሁም በጉዳዩ ላይም የብአዴን አመራሮች ህገ-መንግስቱን በፈቀደው አግባብ አንድ ነገር ይላሉ ብለን አሁንም በተስፋ ቆይተናል።

Tigray-after-1991

እየሆነ ያለው ነገር ግን የዚህ የተስፋችን ተቀራኒው በሆነ ሁኔታ የአማራ ህዝብ ህልውናን የሚክድና የሚያጠፋ ሆኖ አግኝተነዋል። የትግራይ መራሹ ሃይል ጫና፣ የፌደራል መንግስት ምክር ቤቱ ስልጣኑ በወያኔ መነጠቅና የህዝባችን መሰቃየት ለወልቃይት ህዝብ ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ይልቁንስ የመላው አማራ ህዝብ ጥያቄና የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳይ መሆኑን አምነንበታል። ህዝባችንን ይበልጥ ያሳዘነው ደግሞ ብአዴን ጉዳዩን የራሴ ብሎ ይይዘዋል ብለን ተስፋ ስናደርግ ከዚህ በተቃራኒው ብአዴንም በአንዳንድ ታማኝ ካድሬዎቹ በኩል ጉዳዩን ጭራሽ የጠላት ጥያቄ ብሎ ወገኖቹን ጠላት እያለን ነው። ስለዚህ መላው የአማራ ህዝብ እራሳችን በራስችን ነፃነት የምናውጅበት ግዜ ላይ ደርሰናል። በመሆኑም ሰላማዊ የወገናችን ጥያቄ የኛም ጥያቄ ሆኖ ሳለ የወገናችን በገዛ ርስታቸው መሰቃየታቸው ልባችን ሳይፈቅደው እያየን እንዳላየን እየሰማን እንዳልሰማን ሆነን እንደትግራይ ህዝብ የእርጎ ዝምብ ሳንሆን ከአባቶቻችን በተማርነው ትእግስት ዝምታን መርጠን ቆይተናል። ይህም ትእግስታችን ለምንወስደው እርምጃ ፀፀት እንዳይኖርበት ይሆነን ዘንድ ህጋዊ አካሄዱም ለመጠበቅ ነው። ቢሆንም ግን በአሁኑ ግዜ የወልቃይት ህዝብ ወገናችን ጭራሽ ወደ ሞት አፋፍ እየተገፋ፣ የአማራ ማንነት የጠየቁ ልጆቹ በማረሚያ ቤቶች በማጋዝ፣ በትግራይ ወንበዴ ህዝብ እየተደበደበ፣ ቤቱ በአፍራሽ ግብረ ኅይልና በሰፋሪዎች በላዩ ላይ እየፈረሰበት በዚህ በክረምት ወራት ወደ አራጆቹ ወደ ሱዳን እየተሰደደ ይገኛል። ስለዚህ የኛ ህዝባችን የምንታደግበት መንገድ ሰላማዊ ሳይሆን በራሳችን እርምጃ ይሆናል። ይህ ከመሆኑ በፊት ግን ለፌደረሽን ምክር ቤቱ ጥያቄውን የሚመልስበት የሁለት ሳምንት እድል እንሰጠዋለን። እስካሁን ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ሲባል በትእግስት ጠብቀናል። በዚህ የአቋማችን መግለጫ ላይ የወልቃይት ህዝብም ይሁን የወልቃይት ማንነት ጠያቂ ኮሚቴው እጅ ባይኖርበትም፣ ይህ የመላ አማራ ህዝብ በራሱ በፈጠረው አደረጃጀት የተወሰደ አቋም  ቢሆንም ግዜውን የጠበቀ ደራሽነታችን ግን እንደሚያስፈልጋቸው አጠራጣሪ አይደለም።

በተለያየ ግፊት በዚህ ሁለት ሳምንት መሳሪያን በተመለከተ የሚመጣልህን ጥያቄ አይሆንም አሻፈረኝ ማለት እንዳለብህ እናሳስባለን።
ሌላው እንዳለ እንደተጠበቀ ነው:………………………………….
<> <> በኩል <> ቀን <:> … ሰአት <> ሞ<ከ>  <> ጋር
<
> <> በኩል <> ቀን <:> …<> ሰአት ሞ<በ> ከ <> ጋር
<
> <> በኩል <> ቀን <:> …<> ሰአት ሞ<ደ> ከ <> ጋር
<
> <> በኩል <> ቀን <:> …<> ሰአት ሞ<ቨ> ከ <> ጋር
<
> <> በኩል <> ቀን <:> …<> ሰአት ሞ<ፀ> ከ <> ጋር
<
> <> በኩል <> ቀን <:> …<> ሰአት ሞ<ቨ> ከ <> ጋር
<
> <> በኩል <> ቀን <:> …<> ሰአት ሞ<ዘ> ከ <> ጋር
<
> <> በኩል <> ቀን <:> …<> ሰአት ሞ<ረ> <> ጋር
<
> <> በኩል <> ቀን <:> …<> ሰአት ሞ<ዠ>   <> ጋር
በቅደም ተከተል ዛኬሌቂበቀከፈኆ
ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቅደም ተከተል ረደተፖ-ኘዸቴኀቶዎ ልዩ ግንዛቤ በመላው የአማራና የኢትዮጵያ በከተማም በገጠርም ሁሉ ይጠናቀቃል….

ሁሉም <> ጋር በ<> ለ<> በደስታ በ<<<ሜጌኄ>>>ና <<<>>ኄጴፌ>የመጨረሻ <> ይደረጋል።
እኛ ከደሙ ንፁህ ነን። ይህ ሳንወድ በግዳችን በግፈኛው አሸባሪው ወያኔ ተገፍተን የገባነው የመላ አማራ ህዝብ ውሳኔ ነው። ስለ አገሪቱ ሰላም ሲባል በጣም በከፍተኛ ትእግስት ጠበቅን አሁን ግን የአገሪቱ ሰላም የኛ መጥፊያችን ሊሆን ስለማይገባ ይልቁንስ የኛ ሰላም የአገሪቱን ሰላም እንደሚያረጋግጥ ውሳኔ ላይ ደርሰናል። ሰላም ትነግስ ዘንድ ይህ የመላ አማራ የአቋም መግለጫ በተግባር ተፈፃሚ ከመሆኑ በፊት ስለአገሪቱ ሲባል ያሉትን አማራጮች አሟጦ ለመጠቀም ያህል ስንል ብቻ ስልጣኑ በህወሃት የተነጠቀው የፌደረሽን ምክር ቤቱ ዲጋሚ ወኔ ይዞት እንደገና የወገናችን የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይመለስላቸው ይችል እንደሆነ እንዲሁም ያለምንም በደል በማረሚያ ቤት ታጉረው የሚገኙ የወልቃይት ልጆቻችን ያስፈታ እንደሆን ከነገ ጀምሮ የ10 ቀናት ብቻ  አንድ  እድል  ብቻ መስጠታችን እያሳወቅን በከፍተኛ የዝግጅትና ትግበራ መንፈስ ጠብቁ። በአለም ዙሪያ ያላችሁ የአማራ ልጆችና ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህን የህዝባችን ንቅናቄ በአጭር ግዜ ውስጥ ይጠናቀቃል የሚል ግምት ቢኖረንም በተለያየ መንገድ ከወግናችሁ ጎን ትቆሙ ዘንድ ጥሪያችን ነው።

ድል ለጭቁኑ የአማራ ህዝብ፤ ሰላም ለኢትዮጵያ!!!

የአደረጃጀቱ አስተባባሪዎች

ከባህርዳር ፤ ጎጃም ፤ ኢትዮጵያ

ግንቦት 14 /2008 አ/ም


ተጠራጣሪነት ለኛ ለኢትዮጵያዊያኖች አዲስ ነገር ነው እንዴ?

0
0

nega

(ሄኖክ የሺጥላ)

አርበኛ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ሰሞኑን በሲያትል ተገኝተው ያሰሙትን ቅንጭብ ( ወይም ጭላጭ) መልዕክት አደመጥኩ። የንግግራቸው አንኳር ሃሳብ ይሁን አይሁን ወደፊት የምገነዘበው ጉዳይ ቢሆንም ፥ ስለ ተጠራጣሪነት በጣም በግርድፉ እና በጨረፍታ « ከአንድ ኢኮኖሚስት የሚጠበቅ ነው » አንስተው ያልፋሉ ። በዚህ ንግግራቸው ፥ የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠራጣሪነት የገረማቸው ይመስላል ። በእውነት ተገርመው ከሆነ ፥ እኔ ደሞ መገረማቸው የምር ሊገርመኝ ይችላል ። ምክንያቴን እንደሚከተለው አቀርባለሁ ።

ተጠራጣሪነት ለኛ ለኢትዮጵያዊያን አዲስ ግኝት አይደለም ። ቀደም ባሉት ዘመናት ለምሳሌ የዘመነ መሳፍንት ግብዓተ መሬት ከተፈጠመ ብኋላ ፥ በአፄ ቴዎድሮስ አማካኝነት ፥ ሃጋሪቱን ወደ ተማከለ እና ጠንካራ አስተዳደር ለማምጣት ሲባል ዘመናዊ ስልጣኔን ከ ኣውሮጳ ለማስገባት ንጉሱ ያደረጉትን ጥረት ፥ በንጉሱ አካባቢ ያሉ የቅርብ ረዳቶቻቸው እና ባለ ሟሎቻቸው ይኽን ጉዳይ ሃገርን ለባዕዳን የመክፈት ጉዳይ እንደሆነ አድርገው ወስደውት ነበር ። የንጉስን አስተሳሰብ « ታሪክን እና በህልን የሚመርዝ ፥ ሃይማኖትን የሚቀይጥ ፥ እና የሚለውጥ ፥ ሃገሪቱን ለውጭ ሃይሎች ( ባዕዳን ) ክፍት የሚያደርግ አካሄድ ስለሆነ ፥ ይህን ከውጭ ሃገራት ጋ ሊደረግ የታሰበውን የዕውቀት ልውውጥ እንዳይፈጠም ለማድረግ የሞከሩ ጥቂቶች አልነበሩም ። ምንም የማያውቁትን እና ለአንድ ቀን እንኳን ያልሰሙትን አካል አጥፊ ብሎ መፈረጅ ከልክ ያለፈ የተጠራጣሪነት መንፈስ ውጭ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል ?

በአጤ ሚኒሊክ ዘመንም ጊዜ ይሄው የጥርጣሬ ማዕበል ነገስታቱን እና መነኩሳቱን ያሰመጠ እና የዋጠ ታሪክ ስለመሆኑ ተጥፎ እናያለን ። በይበልጥ አጤ ምኒሊክ ከአድዋ ድል ማግስት ፥ ከውጭ መንግስታት ጋ በመገናኘት ሃገራቸውን በእድገት ጎዳና ለመምራት ማቀዳቸውን ለካህናቱ እና «መሳፍንቱ» ሲያስረዱ ፥ ካህናቱ « እንደነሱ የጠራ መሳሪያ ባይኖረንም ፥ ጠላቶቻችንን የኢትዮጵያ አምላክ ድል ስለሚያደርግልን ፥ ከነሱ ጋ ይየምናደርገው ትውውቅ እና ትስስር ቢቆም ይሻላል » እያሉ ይመክሯቸው ነበር ። ይህ የተጠራጣሪነታችን አንዱ ማሳያ ነው ።

«በመሳፍንቱ እና መኳንንቱ» ፥ ብሎም በካህናቱ ቁጥጥር ስር የነበረው ማህበረሰብ የሚያሳየው ወግን የማጥበቅ ስርዓት እና ነገሮቹን ሁሉ በጥርጣሬ አይን የማየት እውነታ ፥ ስልጣኔን ለመቀበል ፥ ወደፊት ለመራመድ እና ካደጉት ከተፈሩት እና ከተከበሩት ሃገሮች ተርታ ለመቆም የሚደረገውን ጉዞ እጅግ አዳጋች ብቻ ሳይሆን የማይቻል አድርጎት ነበር ። ዛሬም ከዚያ የተለየ ነገር ያለ አይመስለኝም። የስልክ መምጣት ፥ የባቡር መንገድ መዘርጋት እና መሰል ነገሮች በህዝቡ ዘንድ የፈጠረው ከፍተኛ ጥርጣሬ ወደር የሌለው እንደነበረ አሁንም የታሪክ መዘክሮች ይዘግባሉ ። ወመዘክሩ በኪሉ ባይሸጥ ኖሮ መጥሃፍ በጠቆምኳችሁ ።

ንጉስን የሾመው እግዚያብሄር ነው ብሎ የሚያምን ማህበረሰብ ፥ እንደ አፈ ወርቅ ገብረየሱስ አይነት ተራማጅ አስተሳሰብ ፥ እንደ ነጋድራስ ገብርህይወት ባይከዳኝ አይነት ባለ ሰላ ብዕር ፥ እንደ አለቃ ታዬ ያሉትን ባለ ተራራ መስተሃልይ ግለሰቦች ያቀርቡት የነበረው የህብረተሰቡን ስር የሰደደ የተጠራጣሪነት መንፈስ ፥ የካህናቱን በአንድ አይነት አስተሳሰብ ላይ ተተክሎ መቆም እና አደጋውን መተቸት ራሱ በህብረተሰቡ ዘንድ መማሪያ ከመሆን ይልቅ እነዚህ ምሁራኖችንም ፈርጆ በተመሳሳይ የጥርጣሬ ኮሮጆ ውስጥ ከቶ የነጮች ( የባዕዳን ቅጥረኞች ) ፥ ሃገራቸውን ለማጥፋት የሚያሴሩ የውጭ ሃገራት ተላላኪዎች ተደርገው ይታዩ ነበር ። ምክንያቱ ደም ምንም አይደለም፥ ያው ጥርጣሬ እንጂ !

ጥርጣሬ እና ተጠራጣሪነት ለኛ ለኢትዮጵያዊያኖች በእርግጥ አዲስ ነገር አይደለም ። ድክመታችንን በተራ አሉባልታ ፥ ውድቀታችንን በማጥላላት ፥ ሽንፈታችንን በጥርጣሬ ፥ አለመቻላችንን በእምነታችን እያሳበብን የኖርን ህዝቦች ስለመሆናችን ከበቂ በላይ ማስረጃም መረጃም አለን ። በታሪካችን መስራት መቻል የሚያስቀቅስ ፥ አፈድፋጅነት የሚያስሞግስ እንደነበር የታወቀን ነው ። ብረት ሰሪውን ጠይብ ፥ጠሃፊውን ጠንቋይ ፥ ሸማ ሰርቶ እራቁት ከመሄድ ቢታደግ ሸማኔ እና ቡዳ ፥ ቤተክርስቲያን ቢያገለግል ደብተራ ፥ ብረት ቢያቀልጥ ባለ እጅ ፥ ሸክላ ቢጠፈጥፍ ሟርተኛ ፥ ሬሳ ገልባጭ እና ወዘተ እያልን እያንዳንዱን መልካም ነገር ስንጠራጠር የኖርን ስለመሆናችን ከማንም የተደበቀ አይደለም ።

ማህተመ ስላሴ ወልደ መስቀል ( ብላቴን ጌታ ) ፥ ዝክረ ነገር በተባለው ሁለተኛ መጥሃፋቸው ፥ አጤ ሚኒሊክ ራሳቸው በዚህ ህብረተሰብ ከልክ ያለፈ የመጠራጠር አባዜ ተቆጥተው በ ጥር 17 ቀን 1900 ዓ.ም የሚከተለውን አዋጅ አውጀው እንደነበር ከትበውልናል

” ሰራተኛውን በስራው የምትሰድብብኝ ተወኝ ። ከዚህ ቀደም ብረት ቢሰራ ጠይብ ፥ ሸማ ቢሰራ ሸማኔ ፥ ቢፅፍ ጠንቋይ ፥ ቤተስኪያን ቢያገለግል ደብተራ ፥ እያላችሁ አርሶ ነጩን ከጥቁር አምርቶ የሚያገባውን አራሽ ፥ ከዘውድ ይበልጣል የሚባለውን ገበሬ እያላችሁ ፥ ነጋዴ ነግዶ ወርቁን ግምጃውን ይዞ ሲገባ አንተ ነጋዴ ገጣባ ( ያህያ ፥ የበቅሎ የፈረስ አጣቢ )፥ እያላችሁ በየስራው ሁሉ ትሳደባላችሁ ። እጁ ምናምን ስራ የማያውቀው ሰነፉ ብልኹን እየሰደበ አስቸገረ ። ” እያሉ ይገልጡና ይህንን ሁሉ ለማስቆም ” ዳግመኛ ሲሳደብ የተገኘ መቀጫው አንድ አመት ይሆናል !” ። ይላሉ ።

ጥርጣሬ የማንነታችን አካል ነው ። እስከ አሁን ማሸነፍ ያቃተን ከነፃነት በላይ ለትግላችን ማነቆ ፥ ለመንገዳችን እሾህ የሆነ ።

ሌላ ምሳሌ ልጥቀስ
ተፈሪ መኮንን ( ግርማዊ ንጉስ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ በወቅቱ ራስ ተፈሪ ) የሲኒማ ቤትን ሲያስተዋውቁ ፥ ህብረተሰቡ በጥርጣሬ ነበር የተቀበለው ። ለዚህም የሰይጣን ቤት የሚል ስም ሰጥቶታል ። የድሃ ልጆችን ሰብስበው ሲያስተምሩ ፥ ትምህርቱን በጥርጣሪ ያዩት መሳፍንቱ እና መኳንንቱ ንጉሱ ለድሃ ልጆች ደብተር እና እስክርቢቶ ገዝቶ ማስተማር በመወሰናቸው ተቃውመው ለንግስት ዘውዲቱ አቤቱታ አቅርበው ነበር ። ምክንያታቸው ደሞ የባዕዳን ትምህርትን ልጆቻችን ሊማሩብን ነው የሚል መሰረት የሌለው ጥርጣሬ ነበር ። የ ዘውዴ ረታን ( የቀዳማዊ ሃይለስላሴ መንግስት) መጥሃፍ ማንበብ የተሻለ ነገሩን ለመረዳት ይጠቅማችኋል።

ሌላ ምሳሌ ልጥቀስ ( እየሰማሁ ሳይሆን እያየሁ ካደግሁት )

እናቶቻችን ጠላ ከቀዱ በኋላ ካናቱ የሚቀምሱት ነገር ምንጩ ባህል ሳይሆን የተጠራጣሪ ካቲካለኛ መንፈስ ለማረጋጋት የሚደረግ ጥረት እንደሆነ በጥናትም ፥ በንባብም ፥ በመኖርም ያገኘኋቸው መረጃዎች ያስረዳሉ ። በቀደመው ዘመን ደብተራዎች ፥ አፈ ሹሞች ፥ ከፍ ሲልም የንጉሱ ባለ ሟሎች እና ካህናቶቹ የሚጠፋፉበት አንዱ መንገድ የተመረዘ መጠጥ እንደሆነ መዛግብት ይናገራሉ ። ይኽም ታሪክ የጥርጣሬ መንፈስን በተዋረድ የመንደር ካቲካላ መሸጫ ድረስ ይዞት ተመመ ። ዛሬም ድረስ ታዲያ ፥ አንድ ሰባራ ስልጣንም ይሁን ድንቡሉ ሳንቲም የሌለው ሰካራም ጠላ ቤት ገብቶ የሚያዘውን አንድ ጣሳ ጠላ አስቀምሶ ( ወይም እመነኝ መርዝ የለውም ) ተብሎ እንደሚጠጣ እናውቃለን ።

አክሱምን እና ፋሲልን የመገንባት ባህላችን ሳይሆን ጠላ አስቀምሶ የመጠጣት ባህላችን ዘመን የተሻገረበትም ዋናው ምክንያት ከእድገት እና ለውጥ ይልቅ ለተጠራጣሪነት የቀረብን ህዝቦች ስለሆነንን ይመስለኛል ። አዎ ተጠራጣሪነት ለኛ ለኢትዮጵያዊያኖች አዲስ ነገር አይደለም !

Hiber Radio: የአንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ሐዘን ላይ መሆናቸውን ገለጹ * ቀነኒሳ በቀለ ቅሬታውን አሰማ –ወልቃይት ተወጥራለች

0
0

Habitamu

Hiber Radio: የወልቃይት ሕዝብ ዳግም በሕዝባዊ ስብሰባ አማራነታችን ይከበር በትግራይ ክልል አስተዳደር አንመራም ሲል ቁጣውን ገለጸ፣የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ዛሬም ሐዘን ላይ መሆናቸውን ገለጹ፣አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለማራቶን በተደረገው ምርጫ ላይ ቅሬታውን ከድል በሁዋላ ይፋ አደረገ የሚሉና ሌሎችም ዜናዎችና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች በፕሮግራሙ ተካተዋል

የህብር ሬዲዮ  ግንቦት 14 ቀን  2008 ፕሮግራም

<…ኢሳት እንደ ማንኛውም ሚዲያ እንቅስቃሴ ባለበት የበለጠ ትኩረት ይሰጣል። ከዛ ውጭ የማንንም ሀሳብ አናፍንም ነገር ግን በፖለቲካ ፓርቲ ስም የተቋቋመ ሁሉ መግለጫ ባወጣ ቁጥር ያንን ተከታትለን እንዘግባለን ማለት አይደለም።ቅሬታ ያላቸው ወገኖች የቅሬታቸው መነሻ ምክንያቱ የተለያየ ነው…ኢሳትን በዘረኝነት ለመክሰስ የሚሞክሩት የገዢው ፓርቲ ሰዎች የመከላከያ ሰራዊቱ ዋና ዋና ባለስልጣናት ከአንድ አካባቢ ከአንድ ብሄር መጡ ተብሎ ዕውነታው መዘገቡ ያበሳጫቸዋል።ዘረኛው ያንን ያደረገው ስርዓት ነው ወይስ ዕውነታውን የዘገበው? …> ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ለኢሳት ስድስተኛ ዓመት በቬጋስ ያደረገውን ቆየታ መሰረት አድርገን  ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውንአድምጡት)

<…ኤምባሲ የሚባለው መጀመሪያ የአሜሪካ ኢሚግሬሽን መታወቂያችንን ሲጠይቀው ሀሰተኛ ነው አለ ቆይተው ያንኑ ሀሰተኛ ያሉትን መታወቂያ ሕጋዊ አድርገው ወደ ኢትዮጵያ ዲፖርት እንድንደረግ እየላኩ ነው ። ወገኖቻችን ድረሱልን እርዱን እኛን እየደገፉ ካሉት ጋር ቆማችሁ ካለንበት እስር ቤት እንድንወጣ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይልኩን ድምጻችንን አሰሙልን ዛሬም መፍትሄ አላገኘንም…> በፍሎሪዳ በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ ሀያ አንድ ኢትዮጵያውያን ስደተኛ እስረኞች መካከል ጥቂቶቹ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በእዚህ በፍሎሪዳ በሁለት የተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙት ኢትዮጵአውአን ስደተኞች በአምስት ሺህ ጠበቃ ቆሞላቸዋል ግን ያ በቂ አይደለም በተለይ ሰባቱ ከፍተና ችግር ላይ ናቸው ዲፖርት ለመደረግ የሚጠባበቁም አሉ ለእነዚህ ወገኖች ተረባርበን ልንደርስላቸው ይገባል አንዳንዶቺ ከመሀከላቸው በጭንቀት ለአእምሮ ህመም የተጋለቱ አሉ…> አቶ ከፍያለው ፈቃደ ከሚያሚ እና አቶ ሌሊሳ ሂካ በታምፓ ፍሎሪዳ የኦሮሞ ኮሚኒቲ ም/ሊቀመንበር ኢትዮጵያውያኑ ስላሉበት ሁኔታ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን አዳምጡት)

ቃለ መጠይቅ በእስር ቤት የሚገኘውን ወታቱን ፖለቲከና አብርሃ ደስታን ለመደገፍ በጎ ፈንድ ጥረት ከጀመረው ወጣት ጋር (አድምጡት)

በሲያትል የአርበኞች ግንቦት ሰባት የገቢ ማሰባሰቢያ ሊቀመንበሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በተገኙበት ተካሄደ ለጨረታ የቀረበው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምስል በ72 ሺህ ዶላር ተሸጠ (ቃለ መጠይቅ በዝግጅቱ ላይ ከቬጋስ ተጉዞ ከተሳተፈው ወጣት ጋር ሙሉውን አዳምጡት

 ከፓሪስ ፈረንሳይ ወደ  ግብጽ ሲበር የነበረው  የመንገደኞች መጓጓዣ አውሮፕላን  ባለፈው ሃሙስ በሜዲትራኒያን ባህር ላይምስጢራዊ  አወዳደቅ እና ከጀርባው የነበሩ መላምቶች  ሲዳሰሱ።”ይህን አውሮፕላን እንከሰክሰዋለን “ማለት ለምን አሰፈለገ? (ልዩ ዘገባ)

በቬጋስ ሊፍት በጠራው ስብሳባ የዋጋ ማስተካከያን ጨምሮ የተሌአዩ የማሻሻያ እርምጃዎች እወስዳለሁ ብላል(የስብሰባውን ውሳኔ መሰረት ያደረገ ማብራሪያ)

 ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የወልቃይት ሕዝብ ዳግም በሕዝባዊ ስብሰባ አማራነታችን ይከበር በትግራይ ክልል አስተዳደር አንመራም ሲል ቁጣውን ገለጸ

የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች ዛሬም ሐዘን ላይ መሆናቸውን ገለጹ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለማራቶን በተደረገው ምርጫ ላይ ቅሬታውን ገድል በሁዋላ ገለጸ

በቦሌ ወረዳ ዜሮ ስምንት ውስጥ ሕገ ወጥ በሚል የልደታ ቤተክርስቲያን በግብረ ሀይል ፈረሰ

በኦሮሚያ ክልል አሁንም የአገዛዙ ጥቃት አላቆመም 60 ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከአለማያ ዩኒቨርስቲ በአጋዚ ወታደሮች ታፍነው ተወሰዱ

የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ከጋምቤላ ከታፈኑት ህጻናት ግማሹን መልሰናል አሉ

በከበባ ስም የዋሸው የኢትዮጵያው አገዛዝ ሁሉም እንዲመቱ ቀነ ገደብ ሰጥቻለሁ አለ

ንብረትነቱ የግርማዊ ጃንሆይ የሆነ የወርቅ ሰዓት ጄነቫ ውስጥ ታላቅ ውዝግብ አሰነሳ

ኤሪትራ  ወደ ግዛቴ ዘልቀው ገብተዋል በማለት ለወራት ያስረቻቸውን የውጪ ዜጎችን በነጻ መልቀቋ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በብድርና በልገሳ ያገኘችው ገንዘብ በስርዓቱ ባይዘረፍ ኖሮ በወሬ ሳይሆን በተግባር የተረጋገጠ ልማት ይታይ ነበር ተባለ እና  ሌሎችም  ዜናዎች አሉን

ዛሬ በመርካቶ አሜሪካን ጊቢ አካባቢ የበርካታ ድሆች ቤት እየፈረሰ ነው

0
0

america gibi 1

america
(ዘ-ሐበሻ) ካለምንም በቂ ካሳና ካለምንም የሕዝብ ይሁንታ በመርካቶ አካባቢ በተለምዶው አሜሪካን ጊቢ አካባቢ በርካታ የድሆች መኖሪያ ቤቶች  እና የንግድ ቤቶች በልማት ሰበብ ዛሬ እንደፈረሱ ከስፍራው የደረሱን መረጃዎች አመለከቱ::

እነዚህ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ለረዥም ዓመታት የኖሩት ወገኖች የሚኖሩበት ቤት ለሃብታሞች በሚሊዮኖች ብር ስር ዓቱ እየቸበቸበው ሲሆን ለነዋሪዎቹ በቂ የሆነ ካሳ አለመከፈሉ ብዙዎችን እያስቆጣ ነው::

ዛሬ ከፈረሱት መኖሪያ ቤቶች በተቸማሪ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶችም እንደፈረሱ ያስታወቁት ምንጮች ሕዝቡ መሬቱ ለሃብታሞች ሲሰጥበት በቁጭት እየተምከነከነ መሆኑን አስረድተዋል::

በኢትዮጵያ ዘረፋው እየተባባሰ መጥቷል –ግብፅ የኤሌክትሪክ ኃይል የማምረት አቅሟን በእጅጉ እያሳደገች መሆኑ ታወቀ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራዲዮ አጫጭር ዜናዎች)

0
0

ፍካሬ ዜና

ግንቦት 14 ቀን 2008 ዓ.ም.

አጫጭር ዜናዎች
የወያኔ ዘረፋ ከዓመት ዓመት እየተባባሰ መሄዱ ይፋ ሆነ
የወያኔ ምርጫ ቦርድ የአስራ አራት ፓርቲዎችን ፍቃድ መሰረዙ ታወቀ
ወያኔ በቀሰቀሰው ቀውስ አገሪቱ ላይ ስጋት እንዲያንዣብብ ማድረጉ ተገለጸ
ግብፅ የኤሌክትሪክ ኃይል የማምረት አቅሟን በእጅጉ እያሳዳገች መሆኑ ታወቀ
በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በበረካታ ህዝብ ላይ ደንገተኛ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ተገለጸ
የውጭ አገር ዜናዎች

አጫጭር ዜናዎች
 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ይባል የነበረውና ዛሬ የስም ለውጥ አድርጎ የአፍሪካ ሕብረት የሚባለው ተቋም መስራቾቹ የወጠኑትን ግብ አሁንም መምታት እንዳልቻለ ዳግም ተዘገብ ። በመጭው ሳምንት የአፍሪካ ቀን በሚል የምስረታ በዓሉን የሚያከብረው ይህ ተቋም ለባዕዳን የተሸጡ መሪዎችና አምባገነኖች መሰብሰቢያና መሳሪያ ከመሆን አልፎ ለአህጉሪቷ የሚጠቅም ይህ ነው የሚባል ስራ አልሰራም የሚሉ ታዛቢዎች አሁንም ቢሆን ለአፍሪካ አንድነት ጠንቅ
ሆነው ያለው አሜሪካ የጦር ተቋሙ ፔንታጎንና የስለላ ግዙፍ መስሪያ ቤቱ ሲአዬ የአፍሪካ አንድነት እንዳይጠናከር ዋና ዕንቅፋቶች ሆነው ቀጥለዋል ተብለዋል ። በአህጉሪቷ ባሉት የጦርነት ፍንዳታዎች በስተጀርባ የምዕራባውያን እጅ እንዳለ ግልጽ ከሆነ ውሎ አድሯል የሚሉት እነዚህ ተቺዎች የአፍሪካን ሀብት በመዝረፉ ስምሪት ቻይናም ዋና ሆና ብቅ ማለቷንም ጫና ሰጠው አቅርበውታል ። ሁሉም ግን ከአምባገነኖች በስተጀርባ ሆነው አፍሪካን እየጎዱ መቀጠላቸውን ክብደት ሰጥቶ ማየት ይገባል ተብሏል ።
Africa_Union_hq
 የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች መተባበር ተስኗቸው ለሚገኙበት አሳዛኝና ጎጂ ሁኔታ በቅድሚያ ተጠያቂ ራሳቸው ናቸው ቢባልም ህብረት እንዳይመሰረት ዕንቅፋት የሆኑት ሻዕቢያና አሜርካ ናቸው ተባለ ። ይህን ያሉ የፖለቲካ ታዛቢዎች ግምገማቸውን ሲያብራሩ ሻዕቢያ የሀቀኛ ሀገር ወዳዶች ህብረት መመስረቱ ላለው ዕቅድ ጎጂ ነው ብሎ አምኖ በመቀጠሉ በኤኤፍዲ ምስረታ ጊዜ እንደታየው የህብረት ጥረቶችን በአቋራጭ ጠልፎ እየጣለና በህብረት ደጋፊነት ሽፋን ክፍፍልን እያስፋፋ ሲሄድ ቆይቷል ብለዋል ። የወያኔ ደጋፊ አጋር የሆነችውም አሜሪካ እንዲሁ የህገርን ሉ ዓላዊነት የሚያስከብር ሀገር ወዳድ ሀይል በኢትዮጵያ በስልጣን እንዲመጣ ስለማትፈልግ የሀገር ወዳዶችን ህብረት ከማደናቅፍና ለወያኔ ከመታደግ ወደኋላ ብላ አታውቅም በሚልም ትችት ቀርቧል ። አሜሪካ በተለይ በውጭ ሀገር ሆነ በውስጥ ሰላዮቿና ቅጥረኞቿን አሰማርታ ሀገር ወዳድ ሀይሎችን እየከፋፈለችና እያጠቃች መሆኑን በአሁኑ ጊዜ አሌ የሚል ብዙ ሰው የለም ሲሉ ተቺዎቹ አረጋግጠዋል ። ወያኔና አሜሪካን በመከተል የህብረት ጥረቶችን በዚህም በዚያም የሚያደናቅፉትን አስመሳይ ሀገር ወዳዶችና ተቃዋሚዎችም ሕዝብ እያደር ነቅቶባቸዋልም በሚልም መረጃ ተሰንዝሯል ።

 በቀይ ባሕር አካባቢ እየተካሄደ ባለው የጦር መሳሪያ ንግድ ኢራን፤ግብጽ፤ ሳውዲ አረቢያ፤ ሻእቢያና ወያኔም አሉበት ተባለ። ባለፉት ወራቶች በርካታ ጀልባዎች መሳሪያ ጭነው ወደ ፑንትላንድና የመን ሲጓዙ መያዛቸውን ያጋለጡ ክፍሎች በሶማሊያ ውስጥ አል ሸባብ የተባለውን ጽንፈኛ ቡድን እንዋጋለን ከሚሉት የአፍሪካ ህብረት ሀይሎች ውስጥም ኬንያና ዩጋንዳ መሳሪያ ሲሸጡ መገኘታቸው ተጠቅሰዋል ። የኢራን መሳሪያ የሚላከው ለየመን ሁቲ አማጽያን ብቻ ሳይሆን በሶማሊያ ላሉም ጂሃዲስት ለሚባሉ ሀይሎች ነው ያሉ ክፍሎች ደግሞ ወደ ፑንትላንድ በብዛት እየመጣው ያለ የጦር መሳሪያ አንዱ ዋናው ምንጭ ወያኔ ነው ተብሎም ተጠርጥሯል ።  በቅርቡ የባዕድ የንግድ ምክር ቤቶች በኢትዮጵያ መሬት ቢሮዎችን ከፍተው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል ህጎችን ወያኔ ሊያጸድቅ ነው ተብሏል ። የወያኔ ኤኮኖሚ ደቆ ባለበትና የውጭ ምንዛሪ እጥረት በሰፈነበት ይህ እርምጃ ለኢትዮጵያ ይጠቅማል ወይስ ይጎዳል የሚለውን ወያኔ እንዳልመረመረውና ደንታም እንዳልሰጠው ውስጠ አዋቂዎች ይናገራሉ።

 ከወያኔው አየር መንገድ ጋር ንትርክ የገባው የአሜሪካ ፕሪንስ ሰርቪስስ ኢንተርናሽናል ኩባንያ ለፕሬዚዳንት ኦባማ የተቃውሞ ደብዳቤ መላኩ ተነገረ። ፕሪንስ ሰርቪስስ ተቃውሞ ያሰማው የአሜሪካ መንግስት ምንም ድጋፍ ሳይሰጠው መቆየቱን በተመለከተ ሲሆን የወያኔ ወዳጅ የሆነችው ሂላሪ ክሊንተን የአየር መንገዱ ጠበቃ የሆነው ከሚካኤል አታዲካ የቅርብ ትውውቅ ያላት መሆኗንም አጋልጧል ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚባለው ተቋም በወያኔ ሙሉ ቁጥጥር ስር መግባቱና ከሰራተኞቹ ዘጠና በመቶ የሚሆኑት የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውና የወያኔ አየር መንገድ ይባል የሚሉ ክፍሎች አጋልጠዋል ።

 ወያኔ የሀገር ወደቦችን አሳልፎ ከሰጠ በኋላ በጅቡቲ ሲጠቀም መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን ከሶማሊያ የተገነጠለችው የሶማሌላንድ ወደብን በርበራንም መጠቅም መጀመሩ ሲነገር ቆዩታል ። ጅቡቲ ወደቧን ለዱባይ አኮናትራ ብትቆይም በጅቡቲና ዱባይ መሃል በተነሳው ንትርክ ግንኙነታቸው ሻክሮ አሁን ደግሞ ዱባይ የበርበራን ወደብ ለመጠቀም የ30 ዓመት ፍቃድ፤ሊዝን ወስዳለች ተብሏል ። ወያኔ ይህን ሁኔታ–እንደ አልጄርሱ ስምምነት–ድል ና ጠቃሚ ብሎ ሊያቀርብ ደፋ ቀና እያለ መሆኑን የነቀፉ ክፍሎች የሳውዲና የካታር ወደ ኢርትራ በጦር ደረጃ ሳይቀር መግባት፤ ግብጽ አሁንም ኢላማዋን ያልቀየረች ሆና ባለበት በርበራ ላይ የዱባይ/የአረብ ቁጥጥር መስፈኑ ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት ሳይሆን ከበባውን የሚያጠናክርና የሚጎዳት ይሆናል ሲሉ ታዛቢዎች ገምግመዋል ። ይህ በዚህ እንዳለ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኔታናሁ በሐምሌ ወር ኢትዮጵያን ይጎበኛል ተብሏል ።

 በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቦሌ ቡልቡላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ግንቦት 10 ቀን በህገ ወጥ መንገድ
ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ የወያኔ ፌዴራል ፖሊስና የቤት አፍራሽ ኃይል ቤት ከሚፈርስባቸው ዜጎችና
ከአካባቢው ሕዝብ ጋር ባደረጉት ግጭት በትንሹ ሰባት ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች ሰዎች መቁሰላቸው ታውቋል።
ሕዝቡ ክረምት እየመጣ እያለ ያለማስጠንቀቂያ ቤታችን አይፈርስም ብሎ በማመጹ የወያኔ ፌዴራል ፖሊስ
በጥይት ዜጎችን የገደለ መሆኑ ታውቋል። በተከታታይ ቀናትም አመጽ በማነሳሳትና በመቀስቀስ በሚል ምክንያት
በርካታ ሰዎች ተወስደው መታሰራቸውም ተዘግቧል። ባለስልጣኖቹ የዜጎችን ቤት አፍርሰው ቦታውን ኢንቬስተር
ለተባሉ ሀብታሞች ለመስጠት እንዳቀዱ ተደርሶበታል።

 በዚህ ሳምንት የወያኔ አግአዚ ጦርና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በዓላማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጽመው
ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። ተማሪዎቹ የተደበደቡት በሰላማዊ መንገድ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ የመብት ጥያቄ
በማንሳታቸው ሲሆን ብዙዎቹ ከቀላል መፈንከት እስከ ስብራት ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል።

የወያኔ ዘረፋ ከዓመት ዓመት እየተባባሰ መሄዱ ይፋ ሆነ
 ዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት ለወያኔ ፓርላማ ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ባቀረበው ሪፖርት ላይ ከዓመት ዓመት የገንዘብ መባከንና የንብረት ዘረፋ እየተካሄደ መሆኑን አመልክቷል፡፡ ለገንዘብ ብክነቱ እንዲያመች የገንዘብ ክፍያዎች በአብዛኛው የሚፈጸሙት የሂሳብ አሰራርን በጣሰ መልኩ እንደሆነ ተገጿል፡፡ በዚህ መሠረት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደ መሆኑ ታውቋል፡፡ በሂሳብ አሰራር ያልተወራረደ የሚባል ሂሳብ የተዘረፈ ማለት እንደሆነ ከፍተኛ የሂሳብ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ በሪፖርቱ ላይ ከተገለጹት ጉዳዮች መሀል የወያኔ ሹመኞችን አረመኔነት ቁልጭ አድርጎ ያሳየው የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎችን ለአርሶ አደሮች እየሸጠ መሆኑ ነው፡፡ በተመሳሳይም የአምስት መቶ ሰባ ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው መድሀኒቶች በመድሀኒት ፈንድ አቅርቦት መጋዘን ውስጥ መገኘታቸው ተጨማሪ ዘግናኝ ጉዳይ ሆኗል፡ ፡ መድሀኒቶቹ የተቀመጡት አዲስ ከሚገቡ መድሀኒቶች ጋር እየተመሳጠሩ ሊታደሉ እንደሆነ የመስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ያስረዳሉ፡፡ በርካታ ንብረትም እንደተዘረፈ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ በኢትዮጵያ ብዝሀ-ህይወት ኢንስቲቲዩት ስም ከተመዘገቡ መኪናዎች አስሩ መዘረፋቸው በሪፖርቱ ተጠቁሟል፡፡ ይህ ድርጊት መሬት ውስጥ እንደሚባሉት የጠፉት ሰማያ ስምንት የኮንዶሚኒየም ህንፃዎች ዓይነት መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ዘረፋ ላይ ግንባር ቀደም የሆኑት ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ የትምህርት ሚንስቴር፣ ምርጫ ቦርድ፣ መከላከያ ሚንስቴር፣ ደብረ ማርቆስ
ዩኒቭርሲቲ፣ ወላታ ሶዶ ዩኒቭርሲቲ፣ ሐዋሳ ዩኒቭርሲቲ፣ ባህር ዳር የኒቭርሲቲ፣ መቀሌ ዩኒቭርሲቲ ሲሆኑ በአጠቃላይ ዩኒቭርሲቲዎቹ የዘረፋ ተቋማት እንደሆኑ ሪፖርቱ ያሳያል፡፡ በተመሳሳም አብዛኛዎቹ ሆስፒታሎችም በዘረፋ የተጨማለቁ እንደሆነ ከሪፖርቱ መረዳት ተችሏል፡፡


የወያኔ ምርጫ ቦርድ የአስራ አራት ፓርቲዎችን ፍቃድ መሰረዙ ታወቀ

 ወያኔ ምርጫ ቦርድ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት አስራ አራት የወያኔ ተቃዋሚ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችን ፍቃድ መሰረዙን አስታውቋል፡፡ ወያኔ አሁን ፍቃዳቸው መሰረዙን ይፋ ያደረጋቸው ድርጅቶች በተለያየ መንገድ እያዳካማቸውና እያሽመደመዳቸው እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ከእነዚህ ከተሰረዙት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ይህ ድርጅት የተመሰረተው በ1997 ዓ.ም. የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች በህብረት ለመታገል በተስማሙበት መሰረት መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ኢሕአፓ የዚህ ህብረት አባል በመሆን የበኩሉን ጠንካራ ተሳትፎ አድርጎ እንደነበር ብዙዎች ያስታውሳሉ፡፡

ወያኔ በቀሰቀሰው ቀውስ አገሪቱ ላይ ስጋት እንዲያንዣብብ ማድረጉ ተገለጸ

 ወያኔ ሕዝብን በዘር፣ በሀይማኖት፣ በጎሳ በጎጥ ከፋፍሎና ሕዝብን እያፈነና እያሰረ ሕዝብን ማሸበር እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም 25 የግፍ አገዛዝ አመታት አሳልፏል፡፡ ወያኔ እራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካና የግፍ አገዛዝ ዘመኑን ለማርዘም ካለ በቂ ጥናት በርካታ ሕዝብን የሚጎዱና የሀገርን አንድነት የሚንዱ እኩይ ተግባራትን እየፈጸመ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ከወያኔ ውስጥ አወቆች የሚወጣው መረጃ የሚያስረዳው ወያኔ በስጋ መወጠሩን ነው፡፡ በትግራይ ወርቅ አውጪዎች ታፍነዋል፡፤ በጋምቤላ ታፍነው ከተወሰዱት ህፃናት እስካንሁን ከሰማንያ ከመቶ በላይ የሚሆኑት አልተመለሱም፡፡ በቅርቡ ቤንሻንጉል ድንበር አካባቢ እርሻ ላይ የነበሩ ገበሬዎች ከሱዳን ድንበር ዘለው በገቡ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል፡፡ እስካሁንም በወያኔ በኩል ምንም የተባለ ነገር አለመኖሩ ሕዝቡን መስቆጨቱ ታውቋል፡፡ ወያኔን እያተራመሰ ያለው ግብፅ ሙሉ ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቀ እግረኛ ጦሯን ሰሜን ሶማሌ ሀርጌሳ ላይ ማስፈሯ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች ለሚከሰቱ የፍንዳታ አደጋዎችና የታጠቁ ኃይሎች እንቅስቃሴን ከኤርትራ ጋር በማያያዝ ያቀርብ የነበረው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ግብፅን ሊጨምር እንደሚችል እነዚሁ ወያኔ ውስጥ ያሉ ይህን መረጃ ያደረሱን ያስረዳሉ፡፡

ግብፅ የኤሌክትሪክ ኃይል የማምረት አቅሟን በእጅጉ እያሳዳገች መሆኑ ታወቀ

 የግብፁ አህራም ጋዜጣ እንደዘገበው በአሁኑ ሰዓት ግብፅ የነበራትን 32 ሺ 15 ሜጋ ዋት ሰሞኑን ግንባታቸው ተጠናቆ ሥራ የጀመሩት ሲጨመሩ 35 ሺ 615 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ ኃይል እንዳላት ተገልጿል፡፡ አትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የምታመርተው ከ2 ሺ 400 ሜጋ ዋት በላይ እንደማይበልጥ የታወቀ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከንፋስ ኃይልና በቅርቡ ግንባታው እንደተጀመረ የተነገረለት የግልገል ግቤ 3 እና ቅዠት የሆነው የዓባይ ግድብ ከተጠናቀቁ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ኤሌክትሪክ የማመንጨት ኃይል ከአስር ሺ ሜጋ ዋት በላይ እንደማዘል የታወቀ ነው፡፡ የሚገርመው ወያኔ ከግብፅ ጋር በዓባይ ግድብ ላይ ለገጠመው ግብግብ እያቀረበ ያለው ከግድቡ የሚወጣውን ኃይል ሃምሳ ከመቶ የሚሆነውን ሱዳንና ግብፅ እንዲጠቀሙበት ለመደራደሪያነት ማቅረቡ ነው፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የግብጽ ኢጂሳት የሚባለው የስለላ ሳተላይት በአባይ ላይ ይሰራል የተባለውን ግድብ በቅርብ እየተከታተለ መሆኑ ሲነገር በግድቡ ላይ ዋና ስራ መቆሙን ወይም መጓተቱን ለመሰለል መቻሉም ተዘግቧል ።

በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በበረካታ ህዝብ ላይ ደንገተኛ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ተገለጸ

 ከሚያዚያ ወር አጋማሽ አንስቶ የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰው፣ በእንስሳትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እደረሰመሆኑ በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወቃል፡፡ በጅጅጋና በድሬዳዋ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በመላው አገሪቱ እየተዳረሰ መሆኑን ከየአካባው ከሚደርሱን መረጃዎች መረዳት ችለናል፡፡ እስካሁን ወደ 200 ሰዎች በጎርፍ አደጋ ብቻ ህይወታቸውን እንዳጡ ከሚደርሱ መረጃዎች ተገንዝበናል፡፡ በወላይታ የደረሰው የመሬት መንሸራተት ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል ስጋት አለ፡፡ በዋና ዋና ከተሞች አደጋ ቢደርስ ይህን ለመከላከል የተዘጋጀ አቅም ያለው ተቋም አለመኖሩም በዚያው ልክ ተጋልጧል ።

የውጭ አገር ዜናዎች
 የደቡብ አፍሪካ እውቁ ታጋይና የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ሚስተር ኔልሰን ማንዴላ የዛሬ 54 ዓመት
በዘረኛው የደቡብ አፍሪካ የነጮች መንግስት ሊያዙ የቻሉት በአሜሪካ የስለላ ተቋም በሲ አይ አባል ጥቆማ አንድ
የእንግሊዝ ጋዜጣ አጋልጧል። በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ ዲፕሎማት የነበሩት የሲ አይ ኤ አባል ዶናልድ ሪካርድ
ከመሞታቸው በፊት “ የማንዴላ ጠመንጃ” ( “Mandela’s Gun”) በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ፊልም ዳይሬክተር
ላደረጉላቸው ቃለ ምልልስ በሰጡት መልስ ኔልሰን ማንዴላን ማጋለጣቸውን ያመኑ መሆኑን ሰንደይ ታይምስ
የተባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ እሁድ ግንቦት 7 ቀን ባወጣው እትሙ ገልጿል። ከዚህ በፊት የሲ አይ ኤው ድርጅት
ሚስተር ማንዴላን ከመያዛቸው በፊት ሲከተታል የነበረ መሆኑና በመጨረሻም እንዲያዙ የጠቆመው የዚሁ ድርጅት
አባል ነው የሚለው ወሬ በሰፊው ሲሰራጭ የኖረ ቢሆንም የሲ አይ ኤ ባለስልጣኖች በተለያዩ ጊዜያት ሲክዱ
ቆይተዋል። ማንዴላ ለረጅም ጊዜ በልዩ ልዩ መንገድ ከደቡብ አፍሪካ የጸጥታ ኃይሎች ሲያመልጡ ከቆዩ በኋላ
ተይዘውና ተፈርዶባቸው ለ27 ዓመታት ያህል በእስር ቤት አሳልፈዋል። ማንዴላ ሲመሩት የቆየቱ የአፍሪካ ብሔራዊ
ኮንግሬስ በሬገን ዘመነ መንግስት በአሜሪካ ሽብረተኛ ድርጅት ሊስት ውስጥ ተመዝግቦ የቆየ ሲሆን ሽብረተኛ
የሚለው ስም የተነሳለት በ2000 ዓም መሆኑ ይታወቃል።

 በኮንጎ ዴሞክራቲክ ረፐብሊክ ሊደረግ በታቀደው ብሔራዊ ምርጫ በግምባር ቀደምትነት ተወዳዳሪ ሆነው ይቀርባሉ
የተባሉት ሚስተር ካቱምቢ ለህክምና ወደ ደቡብ አፍሪካ የሄዱ መሆናቸው ተገለጸ። ግለሰቡ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሄዱት በመንግስት ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ የውጭ አገር ወታደሮችን በገንዘብ ቀጥረሃል የሚል ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ በቁጥጥር ስር ውለው ክሳቸው እንዲታይ ፍርድ ቤቱ ማዘዣ በሰጠበት ቀን ነው። የሚስተር ካቱምቢ ጠበቃ የተሰነዘረባቸው ክስ መሰረተ ቢስ መሆኑና በሚገባ ለመከላከል የሚቻል መሆኑን ገልጾ ሚስተር ካቱምቢ ቀደም ብሎ በተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በፓሊሶች በተተኮሰ አስለቃሽ ጋዝ ሚስተር ካቱምቢ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱ በኋላ ሰውነታችው እየተዳከመ በመምጣቱ ለህክምና ወደ ደቡብ አፍሪካ ሂደው መታከም ግድ ሆኖባቸዋል ብሏል። የአገሪቱ አቃቤ ህግ ሚስተር ካቱምቢ ተመልሰው ፍርድ ቤት ለመቅረብ ፈቃደኛ እስከሆኑ ድረስ እንዲወጡ ፈቅዷል። ሚስተር ካቱምቢ የደቡብ ካታንጋ ግዛት አስተዳዳሪ የነበሩና የአፍሪካ ሻምፒዮን ዋንጫን በተደጋጋሚ የወሰደው ቲፒ ማዜምቤ የተባለው የእግር ኳስ ክለብ ፕረዚዳንት በመሆን ያገለገሉ ሃብታም የንግድ ሰው ሲሆኑ በሕዝቡ ተወዳጅነት ያላቸው መሆኑ ይነገራል። ቀደም ብሎ የገዥው ፓርቲ አባል የነበሩ ቢሆንም ሚስተር ካቢላ የአገሪቱ ህገ መንግስትን በመጻረር ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር ተዘጋጅተዋል በማለት ሌላ ፓርቲ የመሰረቱና ለመወዳደር የተመዘገቡ ናቸው። በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ስላላቸው ምርጫውንም ያሸንፋሉ የሚለው ግምት ከፍተኛ ነው። ህገ መንግስት ከሚፈቅደው ውጭ ሚስተር ካቢላ ለሶስተኛ ጊዜ ለምርጫ ሊቀርቡ ይችላሉ የሚለው ዜና የምዕራብ አገሮች እየተከታተሉት መሆኑ ተገልጿል። ሰሞኑን የሚስተር ካቢላ ተቃዋሚዎች ወደ አሜሪካ በመሄድ በሚስተር ካቢላ አገዛዝ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጠይቀዋል። በፖለቲካ ውጥረት ምክንያት የአገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ሊባባስ ይችላል የሚለውም ስጋት ከፍተኛ ነው።

 የ25 አገሮች ተወካዮች በቪየና ባደረጉት ስብሰባ በቅርቡ ለተቋቋመው ለሊቢያ የአንድነት መንግስት የወታደራዊ ስልጠናና የመሳሪያ እርዳታ ለማድረግ ተስማምተዋል። ስምምነቱ ቀደም ብሎ በሊቢያ ላይ የተደረገው የመሳሪያ ዕቀባ በአንድነት መንግስቱ ወታደራዊ ኃይል ላይ እንዳይደረግና ለዚሁ ኃይ የመሳሪያና እርዳታና ወታደራዊ ስልጠና እንዲደረግ ነው። በሌሎች ሚሊሺያ ቡድኖች ላይ የሚደረገው ማዕቀብ የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል። ይህ በተደረገ በጥቂት ቀናት ውስጥ ለአንድነት መንግስት ታዛዥ የሆነ የሊቢያ ጦር ቀደም ብሎ በአይሲስ ኃይሎች ተይዞ የነበረውንና አቡ ግሬን የተባለውንና ሁለት ታላላቅ መንገዶች የሚገናኙበትን ቁልፍ ቦታ ከአይሲስ ኃይሎች አስለቅቆ የያዘ መሆኑን ገልጿል። ይኸው ጦር በተጨማሪም አይሲስ ወደ ተቆጣጠራትና በርካታ ኃይሎች በማስፈር ወታደራዊ ይዞታውን አጠናክሮ ወደ ሚገኝባት ሰርት ወደተባለችው ከተማ ሄዶ ከተማዋን ለማስለቀቅ ጥረት አድርጓል። ሁለትንም ቦታዎች ለማስለቀቅ በተደረጉ ውጊያዎች የአንድነት መንግስቱ 32 ወታደሮች የተገደሉበት መሆኑና ሌሎች 50 የሚሆኑ የቆሰሉ መሆኑን ገልጿል። የሊቢያ አንድነት መንግስት የአይሲስ ኃይሎችን ለመደምሰስ ተዋጊ አይውሮፕላኖች እንዲሰጡት የምእራብ መንግስታትን ጠይቋል።

 በዚህ ሳምንት ከፓሪስ ወደ ካይሮ ሲበር የነበረ አንድ የግብጽ የመጓጓዣ አውሮፕላን በአየር ላይ እንዳለ በደረሰበት አደጋ ሚዲትራኒያን ባህር ላይ ወድቆ መሰባበሩ ተነግሯል። 56 መንገደኞች እና 10 የአውሮፕላኑ ሰራተኞች አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው አውሮፕላን የጠፋው ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ በግብጽ ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 8 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ላይ ለግብጽ የአየር ክልል 10 ማይልስ ያህል ሲቀረው እንደነበር ተነግሯል። መሬት ባለ መሳሪያ የተመዘገቡ መረጃዎች አውሮፕላኑ ግንኙነት ከማቋረጡ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ በአውሮፕላኑ የመጸዳጃ ክፍል ውስጥ እና በኢሌክቶርኒክስ መሳሪያ አካባቢ ጭስ የነበረ መሆኑ የተዘገበ ቢሆን በእርግጠኛነት የአደጋው መነሻ ምን እንደሆነ እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም። የግብጽ ባለስልጣኖች አውሮፕላን በሽብር ተግባር ተመቶ ወድቋል የሚል መላ ምት
ሲሰጡ የፈረንሳይ ባለስልጣኖች ደግሞ የአደጋው መነሻ ይህ ነው ብሎ ለመደምደም መረጃ የለም ብለዋል። የአውሮፕላኑን አካልና በተለይም ድምጽና መረጃ የሚቀዳውን መሳሪ ያ ለማግኘት ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ ኃይሎች ፍለጋቸውቸውን በሰፊው የቀጠሉ መሆናቸው ታውቋል። ባለፈው መጋቢት ወር አንድ የግብጽ አውሮፕላን ተጠልፎ ወደ ሳይፕረስ እንዲበር ከተደረገ በኋላ ጠላፊው እጁን መስጠቱ ይታወቃል። በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ውስጥ ደግሞ አንድ የሩሲያ አውሮፕላን ከሻርም አል ሼክ የመዝናኚያ ቦታ ተነስቶ ወደ ሩሲያ ሲበር በሲና በረሃ በፈንጅ በመመታቱ አውሮፕላን ተሰባብሮ በውስጡ የነበሩ 224 ሰዎች በሙሉ መሞታቸው ይታወሳል።

 ብሩንዲ ውስጥ የሚታየወን የእርስ በርስ ግጭት ለማብረድ አንድ የዓለም አቀፍ የፖሊስ ኃይል ወደ ብሩንዲ እንዲሄድ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች እየተቀነቀነ ያለውን ሀሳብ የአፍሪካ ኅበረት የሚደግፍ መሆኑን የሰብአዊ መብት ዘገባ ገልጿል። ባለፈው ዓመት የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የጸጥታ ካውንስል አለም አቀፍ ወታደራዊ ኃይል ወደ ብሩንዲ እንዲላክ የወሰነውን ውሳኔ የብሩንዲ መንግስት በጽኑ በመቃወሙ ምክንያት የአፍረካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ የሰረዘው መሆኑ ይታወሳል። የአፍሪካ ኅብረት የሰባአዊ መብት ዘገባ ዓለም አቀፍ የፖሊስ ኃይል እንዲላክ የሚለውን ሀሳብ ያቀረበው ሙያተኞች በቅርቡ በብሩንዲ ተገኝተው መረጃዎችን ካሰባሰቡ በኋላ መሆኑ ታውቋል።

 ሕጻናት የአይምሮ በሸተኞች ሆነው እንዲወለዱ ያደርጋል የሚባለው ዚካ ቫይረስ በደቡባዊ አሜሪካ በተለይም በብራዚል ውስጥ በሰፊው መከሰቱ የዓለም አቀፍ ህብረተሰብን አሳስቦ የቆየ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ኬፕ ቬርድ ተብላ በምትጠራው በአፍሪካ ሰሜን ምስራቅ በምትገኘው ደሴት ውስጥ የገባ መሆኑ በዚህ ሳምንት ተነገረ። እስካሁን ድረሰ በኬፕ ቬርዴ ደሰት 7000 በበሽታው የሚጠረጠሩ ሰዎች እንዳሉና ከእነዚህም ውስጥ 180 የሚሆኑ እርጉዝ ሰዎች እንደሆኑ በተጨማሪም ሶስት ሕጻናት የአይምሮ ጉዳተኛ ሆነው መወለዳቸውን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል። ሌሎች የአፍሪካ አገሮች በሽታው ወደ አገራቸው እንዳይገባ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ድርጅቱ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

ሆዜ ሞሪንሆ ወደ ማን.ዩናይትድ ሊያመጧቸው የሚችሉት 8 ተጫዋቾች

0
0

Jose-Mourinho-United-mainስሜነህ ታደሰ | ለዘ-ሐበሻ ስፖርት

(ዘ-ሐበሻ) ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ልዊስ ቫንግሃልን ያሰናበተው ማን.ዩናይትድ ፖርቱጋላዊውን ሆዜ ሞርንሆ የክለቡ አዲስ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን በዚህ ሳምንት ይፋ ያደርጋል እየተባለ እየተጠበቀ ነው::

በተጠናቀቀው የፕሪምየር ሊግ ሲዝን 5ኛ ሆኖ በመጨረሱ ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ በቀጣዩ ዓመት የማናየውን ማን.ዩናይትድን ጠንካራ ቡድን አድርጎ በቀጣይ ሲዝን ማቅረብ የሆዜ ሞሪንሆ ሃላፊነት ይሆናል:: ሞሪንሆ ማን. ዩናይትድን ከተቀላቀሉ በኋላ ወደ ክለቡ ሊያስመጧቸው የሚችሏቸው ተጫዋቾች እነማን ይሆኑ?

ዘ-ሐበሻ ከ እንግሊዝ ጋዜጦች ያሰባሰበቻቸው መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው::

1ኛ. ኔማንጃ ማቲክ
በ2014 ከቤንፊካ ወደ ቸልሲ በሞሪንሆ አማካኝነት የተሸጋገረው ኔማጃ ማቲክ 25 ሚሊዮን ፓውንድ የሚወጣ ተከላካይ አማካኝ ነው:: ተጨዋቹ በቸልሲ የተደበላለቀ ሲዝን አሳልፏል:: ከሞሪንሆ ጋር ወደ ኦልትራፎርድ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል::

2ኛ. ሃኦ ማሪዎ
የስፖርቲንግ ሊዝበኑ የማህል ሚድፊ;ደር የማን.ዩናይትድን የመሃል ክፍል ያጠናክራል ተብሎ በሞሪንሆ ተስፋ ተጥሎበታል:: የ23 ዓመቱ ፖርቱጋላዊ ሚድፊልደር በአሁኑ ወቅት በማን.ሲቲና ቸልሲ እንዲሁም ሊቨርፑልና የተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች እየተፈለገ ሲሆን 35 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣል ተብሏል::

3ኛ. ዝላታን አብራሞቭች
የፓሪስ ሰንት ጀርመኑ የፊት አጥቂ ዝላታን አምራሞቭች ሲዝኑ እንዳለቀ ክለቡን እንደሚለቅ መናገሩ ይታወሳል:: ይህ በልምድ የታጨቀው አጥቂ ባህሪው ትንሽ ሊታሰብበት የሚገባ ቢሆንም ልምዱ ግን ለወጣቶቹ የዩናይትድ አጥቂዎች ማርቆስ ራሽፎርድ እና አንቶኒ ማርሻል ይጠቅማል ተብሎ ይታሰባል:: ዝላታን የሞሪንሆን ቡድን ከተቀላቀለ ዋጋው በነፃ ነው የሚሆነው::

4ኛ. አንቶኒ ግሪዝማን

የአትሌቲኮ ማድሪዱ ግሪዝማን 63 ሚልዮን ፓውንድ ያወጣል:: ይህን የፈረንሳዩን ኢንተርናሽናል ሞሪንሆ እጃቸው ለማስገባት ከባርሴሎና ጋር ግብ ግብ ውስጥ መግባታቸው የማይቀር ነው:: ግሪዝማን ወደ ዩናይትድ ለመምጣት ምናልባት በሚቀጥለው ዓመት ቻምፒዮንስ ሊግ አለመሳተፉ ይሆናል እንጂ ሞሪንሆ ይሟሟቱበታል ተብሎ ይጠበቃል::

5ኛ. ጎንዛሉ ሂጉዋይን

ለጣሊያኑ ናፖሊ 36 ጎሎችን ባለቀው ሲዝን ያገባው አርጀንቲናዊው ጎንዛሎን ሞሪንሆ በጥብቅ ይፈልጉታል:: ጎንዛሉን በርካታ የፕሪምየር ሊጎች እየፈለጉት ሲሆን ናፖሊስ በ72 ሚሊዮን ፓውንድ ሊለቀው ይችላል እየተባለ ነው::

6ኛ. ጆን ስቶን
የኤቨርተኑ ተከላካይ ጆን ስቶን በሞሪንሆ የሚፈለግ ተከላካይ ነው:: 45 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያወጣው እንግሊዛዊ ጆን ማንቸስተር ሲቲ አይን ውስጥ መግባቱ ትንሽ ፈተና ሊሆንባቸው ይችላል::

በሌላ በኩል ሞርንሆ የሪያል ማድሪዱን ራፋኤል ቫራኒን በ35 ሚሊዮን ፓውንድ ማዘዋወር ይፈልጋሉ:: ራፋኤል በሪያል ማድሪድ እያሳለፈ ያለው ጊዜ ደስተኛ እንዳላደረገው በተደጋጋሚ እየተዘገበ ነው:: እንዲሁም በአርሰናል በጥብቅ እየተፈለገ ያለው አልቫሮ ሞራታም የሞሪንሆ ዓይን ውስጥ ነው::

የፓርቲ ፖለቲካ የትግል እርሻ – (ከዘላለም ክብረት እና በፍቃዱ ኃይሉ)

0
0

weyeyet

ከጠዋቱ ጤዛ እስከ ምሽቱ ቁር

አንጋው ተገኝ በሠላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ያለ ወጣት ነው። ፀጉሩን ያጎፍራል። ሲናገር በብዙ ነገሮች እየተደነቀ ነው። አንጋው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አብረሃ ጅራ ወረዳ ኃላፊ በመሆን እጅግ ፈታኝ ጊዜያትን አሳልፏል። የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የሀገሪቱ ክፍሎች መንቀሳቀስ የሚያስከፍለው ዋጋ ከባድ መሆኑን ደጋግሞ ይናገራል። የፓርቲው አመራር ሁኖ በሠራበት ወቅት ፓርቲ ስብሰባ እንኳን ማድረግ እጅግ ከባድ መሆኑን ያስታውሳል። ፖሊስና የደኅንነት ኃይሎች አመራሮቹን እየተከታተሉ ሲያስጨንቋቸው ‹የፓርቲው ሥራ ከሚቆም በሚል አንገረብ ወንዝ ወርደን እየዋኘን እንሰበሰብ ነበር› ይላል። እየዋኘን ሰው ወደኛ በመጣ ቁጥር እየተበታተንን፤ ሰው ራቅ ሲልልን ደግሞ እዛው ውኃው ውስጥ ሰብሰብ ብለን እየተንሳፈፍን ነበር ስብሰባ የምናደርገው የሚለው አንጋው በፓርቲ እንቅስቃሴ ምክንያት ስድስት ጊዜ ከሥራ ተባሮ ስድስት ጊዜ መመለሱን ሲገልጽ አንዳንዴ በሕይወት መቆየቴም ለኔ ግርም ይለኛል እያለ ነው። ይባስ ብሎ በሠላማዊ ትግል ቆርቦ በዚህ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ የነበረው አንጋው ተገኝ የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ ሳይቀርብበት አሁን ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለህ በሚል ምክንያት በመጨረሻ ለእስር የተዳረገ ሲሆን፤ እስር ቤት ሁኖም የታገለለትና የደከመለት አንድነት ፓርቲ ሲፈርስና በእሱ አባባል ‹መፈንቅለ አመራር› ሲካሄድበት ተመልክቶ ያዝናል። ለዚህ ሁሉ መሆን አንጋው ተጠያቂ የሚያደርገው ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ነው። ‹ሕግ የማይገዛው መንግሥት› እያለ ሁሌም ይገረማል። ይህ የኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ ችግር የገዥው ፓርቲ ቅጥ ማጣት ነው ከሚሉት ወገን የሚቀርበው ሐሳብ ትክክለኛ ተምሳሌት ነው።

ከዚህ አሳዛኝ ኹነት መለስ ብለን አርብ ሚያዚያ 28፣ 2008 ከጠዋቱ 4፡30 እስከ 5፡30 ድረስ በአንድ ሰዓት ውስጥ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጆች ለጽሑፉ ግብዓት የሚሆን መረጃ ለማግኘት በማሰብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ መሠረት እንዲሁ አለፍ አለፍ እያልን በአሁኑ ወቅት በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ከሚገኙ ሰባ አምስት ፓርቲዎች መካከል የሃያ አምስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የስልክ አድራሻ ላይ ስልክ የደወልን ሲሆን፤ ከሃያ አምስቱ ሙከራዎች መካከል ሁለቱን ስልኮች ያነሱልን ሕፃናት ሲሆኑ፣ የሰባቱ ስልክ ቢጠራም አይነሳም፤ የዐሥራ አምስቱ ስልክ ደግሞ ከነአካቴው የማይሠራ ሲሆን፤ የአንዱ ብቻ ማለትም ‘የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት’ ስልክ ላይ የፓርቲውን አመራር ልናገኝ ችለናል። በተመሳሳይ ጊዜ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያደረግነው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪም ስልኩ ሊነሳ ባለመቻሉ ማብራሪያ ማግኝት አልቻልንም። እንግዲህ ‹የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ ሰሞን ግርግር ከመፍጠር ያለፈ ምንም አይፈይዱም የሚለው ሐሳብ እንዲሁ ያለውን ሁኔታ ቀረብ ብሎ ካለማየት የሚመጣ ነው› የሚሉ ተችዎችም ሁሌም የሚፈተኑበት ጉዳይም ይሄው ተቃዋሚ ፓርቲ ተብለው የተመዘገቡት ፓርቲዎች በሚገባቸው ቦታ አለመዋላቸው ነው። ፓርቲዎቹ የስልክ እንኳን አድራሻ የሌላቸው/ቢኖራቸው እንኳን የማይሠሩ ስልኮችን ይዘው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የለውጥ መሠረት ይሆናሉ ብሎ ማሰቡንም ያከብደዋል። ይህ ደግሞ ተቃዋሚዎች የራሳቸው ሥራ ሳይሠሩ ገዥውን ፓርቲ ማውገዛቸው ተገቢ አይደለም የሚለው ሐሳብ ተምሳሌት ነው።

 

የጠዋቱ ጤዛ

‹የፓርቲ ፖለቲካ ማለት በሕግ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን አደራጅተው ለምርጫ የሚያደርጉት ትግል ነው› የሚለው ጠቅለል ያለ ትርጉም በኢትዮጵያ ፖለቲካ አኳያ ይሠራል ማለት ከባድ ነው። ከተመዘገቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች በማይተናነስ መልኩ የራሳቸው ፍላጎት እና ዓላማ ያላቸው ብዙ ቡድኖች ራሳቸውን የፖለቲካ ፓርቲ ብለው ሰይመው የሚንቀሳቀሱ ከመሆናቸው አንፃር የፓርቲ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ ዐውድ አንፃር ለምርጫ የሚደረግ ሠላማዊ ትግል ነው ከሚለው ትርጉም ፈቅ ያለ መሆኑንም ነው እነዚህ ፓርቲዎች የሚያስረዱን።

 

በቡድን ተደራጅቶ የፖለቲካ ፓርቲ የሚባል ድርጅት ፈጥሮ መንቀሳቀስ የተጀመረው ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲ ሞዴል (Party Political Model) የፖለቲካ ሒደት ከመጀመሯ ብዙ ቀደም ብሎ እንደሆነ የተለያዩ ጸሐፊዎች ያመላክታሉ። ከጣሊያን የአምስት ዓመታት ቆይታ በኋላ በተለይም ውጭ አገር ቆይተው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን በአውሮፓና በአሜሪካ ካዩት አሠራር በመነሳት የፓርቲ አደረጃጀት ኑሮ ፖለቲካው በዛው መሥመር እንዲቃኝ መፈለጋቸው አልቀረም። ዘውዴ ረታ ‹የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት› ባሉት መጽሐፋቸው በመጋቢት 1939 ንጉሠ ነገሥቱ ራሳቸው ስለ አገራችን ጠቅላላ ሁኔታና ስለ እኛ አመራር ሐሳባችሁን አቅርቡልኝ ባሉት መሠረት በወቅቱ የጽሕፈትና የሀገር ግዛት ሚኒስትርነትን ደርበው ይዘው የነበሩት ጸሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ ከሦስቱ የማሻሻያ ሐሳብ አቅራቢዎች መካከል አንዱ ነበሩ። በወቅቱ ወልደጊዮርጊስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት እየተንቀሳቀሱ ነው የሚል ሐሜት ይሰማባቸው ስለነበር ይሄን ሐሜት “እኔና አቶ መኰንን [ሀብተወልድ] እየተግባባንና እየተረዳዳን በመሥራታችን የፖለቲካ ፓርቲዎች በመሆናቸው ነው እየተባለ የሚነገርብን ደህና አድርገን እናውቀዋለን። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚያውቁት፤ የፖለቲካ ፓርቲ በአገራችን የለም።” በማለት ካስተባበሉ በኋላ ስለፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀት ሲያስረዱ “እኔ በዚያ በመከራው የስደት ዘመን እንዳየሁት፤ ዛሬ በአለንበት ሰዓት ለኢትዮጵያ አስተዳደር እንደ እንግሊዝ አገር፤ ንጉሥ የታሪክና የባሕል የበላይ ጠበቂ ሆኖ ይነግሳል፤ መንግሥት ደግሞ በፓርላማ ሕዝብ ቀጥታ ከመረጠባቸው እንደራሴዎች መካከል በፖለቲካ ፓርቲ አሸናፊ የሆነው ይመረጣል፤ የሚለውን ሐሳብ ወስዶ መጠቀም ይቻላል ብዬ አላምንም። እንደ እንግሊዝ አገር መሆን እንችላለን ብሎ ማሰብ፤ አቅምን ካለማወቅ የተነሳ በሸንበቆ ላይ እንደሚገነባ ምኞት የሚቆጠር ይሆናል” በማለት ነበር። ይህ ሐሳብ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ለቀጣዮቹ ሃያ ሰባት ዓመታት ንጉሠ ነገሥቱ የፖለቲካ ፓርቲ የሚባለውን አደረጃጀት በጥርጣሬ እንደተመለከቱት ከመንበራቸው ሳይወዱ በግድ ተወገዱ። በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የፖለቲካ ፓርቲ የማቋቋምም ሆነ የፓርቲ ፖለቲካን ለማካሄድ የሚያስችል ምንም ዓይነት የሕግ ማዕቀፍም ሆነ ቀናነት ያልነበረ ቢሆንም የፓርቲ ቅርፅ ያላቸው አደረጃጀቶች በተለይም በመጨረሻዎቹ የንጉሡ አምስት የሥልጣን ዘመናት አቆጥቆጠዋል። አንትሮፖሎጅስቱ ዶ/ር ወንድወሰን ተሸመ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የፖለቲካ ፓርቲ የዛሬ ሃምሳ ዓመት በ1958 የተመሰረተው ‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ካውንስል› ነው የሚሉ ሲሆን፤ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እዚህም እዚያም ማቆጥቆጥ የጀመሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ሲወጡና ሲወርዱ ቆይተዋል።

 

ከንጉሠ ነገሥቱ ስርዓት ማብቃት ጋር ተያይዘው ብቅ ብቅ ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች በግራ የፖለቲካ አስተሳሰብ የተቃኙና በፍጥነት ወደመጠፋፋት በመዝለቃቸው ተስፋ የተደረገበትን የፓርቲ ፖለቲካ አካሔድ እዛው ካለበት ላይንቀሳቀስ ተተክሎ ቆይቶ ከኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ወደ ሥልጣን መምጣት ጋር ተያይዞ አዲስ ተስፋ በብዙዎች ዘንድ ማደሩ አልቀረም። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ከሚወደስባቸው ጉዳዮች አንዱ የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን (multi-party system) በሕግ ተቀብሎ በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጋዊ ዕውቅና የሚሰጥ ስርዓት መዘርጋቱ ነው።

የሃምሳ ዓመታት የሙከራ ታሪክ፤ የሃያ አምስት ዓመታት ሕጋዊ ዕውቅና ያለው የፓርቲ ፖለቲካ ከዕድሜው አንጻር ምን ትርፍ አመጣ? ለምንስ ፈተናና እክል በየቀኑ እያጋጠመው ይወድቃል የሚሉት ጥያቄዎች መሠረታዊና የወደፊቱን ለመረዳት የሚረዱ ናቸው። በኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ እንዳያብብ እና እንዲቀጭጭ ምን እክል አጋጠመው? ለሚለው ጥያቄ አንድ ዓይነት ምላሽ መስጠት አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም እንደ መላሾቹ የተለያ መልሶችን እናገኛለን።

 

ዴሞክራሲ የማያበቅል መሬት?

የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሒደት በቅርበት የሚከታተሉ ምሁራን ለፓርቲ ፖለቲካ ስኬት ማጣትና ብሎም ዴሞክራሲ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይደረጅ መሠረታዊውን አስተዋፅኦ ያደረገው የመጠላለፍና አምባገነኖችን የሚያበቅል የፖለቲካ ባሕል መኖሩ ነው ይላሉ። በኢትዮጵያ ላይ ብዙ ጥናት ያደረጉት ጆን ያንግ በዐሥር ዓመታት ልዩነት በኢትዮጵያ የፓርቲ የፖለቲካ ሒደት ላይ በጻፏቸው ሁለት ጽሑፎቻቸው ላይ ለኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካና ዴሞክራሲ ዋነኛ እክል አድርገው የሚያቀርቡት በኢትዮጵያ ያለውን ከመንግሥታዊ መዋቅሩ ውጭ ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ ተቋም እንዲፈጠር ያለመፍቀድ አባዜንና በእርሳቸው ቋንቋ በሃገሪቱ ውስጥ ከ11ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን የቀጠለው ፈላጭ ቆራጭ የፖለቲካ ባሕልን (Authoritarian Political Tradition) ነው። እንደ ጆን ያንግ ሁሉ ዶ/ር በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳዩች ላይ አብዝተው የተመራመሩት ጆን አቢኒክና ማሪና ኦታዌ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የትናንት የባሕል ሸክም እንዳጎበጠው እየገለጹ መፍትሔውን ይሄን ባሕል መቀየር ላይ ያደርጋሉ። እንዲሁም ሳራ ቮጋን እና ኬቲል ትሮንቮል የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አወቃቀር፣ ከልጅነት እስከ ዕውቀት ድረስ በተዋረድ (hierarchy) የተሞላ መሆኑ ለዚህ የፖለቲካ ባሕል አለመዳበር እንደመንስኤ ይወስዱታል። “አብዛኞቹ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ዜጎች ተከራክረው፣ ሕይወታቸውን በተሻለ መንገድ ለመዘወር የሚያስችላቸውን አማራጭ ስለመለየት አያስቡም። ሌሎችም ይህንን ያደርጋሉ ብለው አይጠብቁም፤ የበላይ ወይም የበታች ከሚሏቸው ጋር ይህንን ማድረግ ደግሞ ጨርሶ የማይታሰብ ነው” ይላሉ።

ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግን ጨምሮ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በሙሉ በጋራ የሚስማሙበት የሚመስለው ጉዳይ ‹የኢትዮጵ የፖለቲካ ባሕል አለማደግን› ነው። የፖለቲካ ባሕል ሊገለጽ የሚችልባቸው ብዙ መንገዶች ቢኖሩም፣ ‹ጠርዘኝነት› ግን ዋነኛውና ብዙዎቹ የፖለቲካ አመራሮች እንደፈታኝ የሚወስዱት ችግር ነው። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት “የፖለቲካ ባሕላችን ቀኖናዊ ነው” ወይም በሌላ አነጋገር “perfectionist (ፍፁማዊ)… ወይ አርዮስ ወይ ቅዱስ ብሎ የመፈረጅ አባዜ አለበት” የሚሉ ሲሆን፤ አያይዘውም “በእኛ ባሕል የፖለቲካ ሐሳብ ልዩነት ሲኖርህ መጠፋፋት ነው” ይላሉ። ይህ የኢንጅነር ይልቃል ምልከታ ከላይ የጠቀስናቸው ሳራ ቮጋን እና ኬቲል ትሮንቮል ‹The Culture of Power in Contemporary Ethiopian Political Life› በሚል ጥናታቸውን ከደረሱበት ድምዳሜ ጋር የሚስማማ ነው። ምሁራኑ በጥናታቸው ‹መንግሥት እና ተቃዋሚዎች በነገሮች እና ርዕዮተ-ዓለም ጉዳዮች ላይ አይወያዩም። የራሳቸውን ብቻ የፖለቲካ አመለካከት ይዘው እርስ በርስ በመነጋገር ፈንታ፣ አንዱ ሌላውን ይወቅሳል።› አጥኚዎቹ አክለውም፣ ሌላው ቀርቶ በፌዴራል መንግሥቱ ቋንቋ አማርኛ ውስጥ እንደሁለት የተነጣጠሉ አካላት የሚታዩት ‘state’ እና ‘government’ ተነጣጥለው የማይታዩ እና ‹መንግሥት› በሚለው ቃል ብቻ የሚተረጎሙ መሆኑ አንዱ የፖለቲካ ባሕሉ አለማደግ ምልክት አድርገው ይወስዱታል።

የኢ.ዴ.ፓ. የቀድሞው ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው ከፖለቲካ ባሕል አለማደግ ጋር አያይዘው ‹የእኛ የፖለቲካ ባሕል በጦርነትና በመገዳደል ሥልጣን መያዝ ነው፤ የእኛ ፖለቲካ ሲታይ አንዱ ባለኃይል ሌላኛውን ባለኃይል ሥልጣን የሚቀማበት ነው› የሚሉ ሲሆን አያይዘውም “ሕዝብ እንደሚሳሳት ማወቅና እና ሲሳትም ተሳስተሃል ሊባል እንደሚገባው መስማማት ይኖርብናል።” በማለት ባሕሉን እየተቸን ካላሳደግነው የፖለቲካ ሒደቱ የትም አይደርስም የሚል መደምደሚያ ይሰጣሉ።

ነገር ግን ይህ የፖለቲካ ባሕል አለማደግ ነው፣ የፖለቲካችን መሠረታዊ ችግር በሚለው ሐሳብ ሁሉም ምሁራን አይስማሙም። በዚህ ከማይስማሙት ምሁራን አንዱ ቶቢያስ ሐግማን ናቸው። “የኢትዮጵያን ፖለቲካ ከባሕል አንፃር ብቻ መተርጎም ስህተት ነው” ይላሉ ሐግማን ጆን አቢኒክ ከምርጫ 97 በኋላ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ለጻፉት ጽሑፍ ምላሽ በሰጡበት ጽሑፋቸው። “ከዚህ እይታ ባለፈ ገዥው ፓርቲ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ከውስጡ ምን ያህል የተማከለ እና ፈላጭ ቆራጭ እንደሆነ መረዳቱ ነው ወሳኙ የፖለቲካው ውድቀት መነሻ” የሚሉት ሐግማን “ከዚህ ባለፈ ግን ችግሩን ወደ ባሕል መውሰዱ ገዥውን ቡድን ነጻ ማውጣት ነው የሚሆነው” ብለው የችግሩ መነሻና መድረሻ ገዥው ቡድን እንደሆነ አጽንኦት ይሰጣሉ። ነገር ግን ምሁራኑም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ ባሕልን እንደ አንድ የችግሩ ምንጭ እንጅ የችግሩ ብቸኛው መነሻ አድርገው ላለመውሰዳቸው ጽሑፎቻቸውና አስተያየቶቻቸው ይገልጻሉ።

 

የታጠረው ምኅዳር

የፖለቲካ እሳቤዎች መዝገበ ቃላት እንደሚያስነብቡት የመድብለ ፓርቲ ስርዓት (multi-party system) ማለት በቁጥር የበዙ እና አሸንፈው መንግሥት በተናጥል ወይም በጥምረት የመመሥረት ዕድል ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ለብሔራዊ ምርጫ የሚሳተፉበት ስርዓት ነው። ሌላው ቀርቶ በእነዚህ ብያኔዎች መሠረት የዴሞክራሲያውያኑ ምዕራብ አገሮች፣ ለምሳሌ የአሜሪካ የፖለቲካ ስርዓት የሁለት-ፓርቲ ስርዓት ነው። በአሜሪካ ከስልሳ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢኖሩም ከሪፐብሊካን እና ዴሞክራቶች በቀር አሸንፈው መንግሥት ለመመሥረት የሚችሉበት ዕድል ስለሌላቸው (ወይም ዕድላቸው እጅግ ጠባብ ስለሆነ) የአሜሪካ ስርዓት የሁለት-ፓርቲ ስርዓት እንጂ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ሊባል አይችልም።

ከገዢው ፓርቲ ውጪ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል እና አንድ በግል የተመረጡ አባላት ብቻ ከተወከሉበት ምርጫ 2002 ወዲህ ገዢው ፓርቲ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ራሱን ‹አውራ ፓርቲ› በማለት መጥራት ጀምሯል። ይህንኑም ልማታዊ ዴሞክራሲ እያለ ከሚጠራው ከኢኮኖሚ ዕቅዱ ጋር አዋድዶ ለመቀጠል ትልሙ እንዳለው በተለያዩ መድረኮቹ አስታውቋል። ይሁን እንጂ  ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ‘የአውራ ፓርቲ’ (dominant party) ስርዓት እያራመደ ሳይሆን በኢፍትሐዊ መንገድ ያገኘውን የሕዝብ ተወካዮች ወንበር በሕዝባዊ ይሁንታ ያገኘው ለማስመሰል ከመጣሩም ባሻገር ምጣኔሀብታዊ ጠቀሜታ ያለው በማስመሰል ሕዝባዊ ቅቡልነት ለመግዣ እየተጠቀመበት ነው ከሚል ትችት አልዳነም። የአውራ ፓርቲ አካዳሚያዊ ብያኔ ‹አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ተከታታይ ምርጫዎችን በበላይነት ሲያሸንፍ፣ ወደፊትም የመሸነፍ ዕድሉ አነስተኛ ሆኖ ለመገመት የሚያስቸግርበት ስርዓት› እንደሆነ ይደነግጋል። ይህ ዓይነቱ ስርዓት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የታየው በተለይ በጃፓኑ ዴሞክራቲክ ሊበራል ፓርቲ እና ሌሎች ጥቂት አገራት ብቻ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ የአውራ ፓርቲ ስርዓት የተከሰተባቸው አገራት ታሪክ የሚያሳየው አውራ ፓርቲው ‹አውቶክራት› (ለዴሞክራሲ ያልበቃ፣ በሌላ በኩል የወጣለት አምባገነንም ያልሆነ) ስርዓት ነው።

ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ራሱን አውራ ፓርቲ በማለት መጥራት የጀመረው ፓርቲው ‹ልማታዊ ዴሞክራሲያዊነት በተግባር ተፈትሾ ነጥሮ ወጥቷል› እንዲሁም ምርጫው ‹በኪራይ ሰብሳቢዎች ካምፕ ድንጋጤና ውዥንብር ፈጥሯል› ብሎ በገመገመው ምርጫ 2002 ማግስት ነበር። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ይሄን ‹አውራ ፓርቲ› የሚል ማዕረግ ለራሱ ሲሰጥ የአውራ ፓርቲ ስርዓት የዘረጉ ዴሞክራሲያዊ አገሮችን ሲዊዲንና ደቡብ ኮሪያ እያለ እያጣቀሰ የአንድ ፓርቲ ስርዓት ሳይሆን ወደ አውራ ፓርቲ ስርዓት እያመራን ነው፤ ይሄም ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ታላቅ እመርታ ነው በማለት ግምገማውን በወቅቱ አስቀምጧል። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ራሱን አውራ ፓርቲ ብሎ ከመሰየሙ ሦስት ዓመታት ቀደም ብሎ በ1999 የፓርቲዎች የሥነ ምግባር ደንብ ሙሉ ለሙሉ ተገልብጦ መጥቶበታል የተባለው ‹International Institute for Democracy and Electoral Assistance (IDEA)› የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ባቀረበው ሪፖርት ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ከምርጫ 97 ማግስት ወዲህ አውራ ፓርቲ እንደሆነ የሚያትት ነው። ‹IDEA› የአውራ ፓርቲ ስርዓት የሚባለው ስርዓት በአራት መልኩ የዴሞክራሲ ፀር እንደሆነ በሰነዱ ላይ የገለጸ ሲሆን እነዚህም አንደኛ፣ የፉክክር ፖለቲካን ያቀጭጫል፤ ሁለተኛ፣ የሕግ አውጭውን ሥልጣን ጠቅልለው በመያዝ በአንድ አገር ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ፍላጎቶች ይቆጣጠራል፤ በሶስተኝነት፣ ጠያቂ ስለማይኖርበት ተጠያቂነት የሌለበት ስርዓት ይፈጥራል እንዲሁም በመጨረሻም፣ የሥልጣን ትዕቢት በመፍጠር ለዜጎች ጥያቄ ደንታ ቢስ መንግሥት እንዲፈጠር ያደርጋል የሚሉ ናቸው። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የምርጫ ሥነ ምግባር ሕጉንና የአውራ ፓርቲ ፅንሰ ሐሳብን ከ‹IDEA› ወስዶ ይሄን የድርጅቱን የአውራ ፓርቲ የሰላ ትችት እንዳላየ ሁኖ በማለፍ በተለያዩ የፓርቲው ሰነዶች አሁንም አውራ ፓርቲ መሆኑን እየገለጸ ይገኛል።

የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ታላቁ ሊቅ ሳሙኤል ሀንቲንግተን ‹ዴሞክራሲ ሊጠናከር የሚችለው መንግሥት በምርጫ ሥልጣን ሊያጣ ሲችልና ሥልጣን ላይ የወጣው አዲስ ፓርቲም እንዲሁ ሥልጣኑን በምርጫ ሊያጣ ሲችል ብቻ ነው› በማለት የሥልጣን ሽግግር የዴሞክራሲ ምሰሶ መሆኑን ያስረዳሉ። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የወዳጆቹንም የጠላቶቹንም ምክር ወደ ጎን ብሎ የት እንደሚያደርሰው ባይታወቅም አሁንም የፖለቲካ ሥልጣኑን ሙሉ ለሙሉ ጠቅልሎ ይዞ ይገኛል።

አሁን አሁን ደግሞ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ራሱን የሚጠራበት ‹አውራ ፓርቲ› የሚለው ስያሜ የሚያንሰው እንደሆነ ተቺዎች መናገር ጀምረዋል። አንዳንዶች አሁን ፓርቲው ከመሠረቱ ሲያራምደው ከነበረው ሶሻሊስታዊ የብዝኃ አደረጃጀት (Mass Party) ቅርፅ ላይ የመንግሥታዊ ፓርቲነት (Cartel Party) ካባ ደርቦ ወፍሯል የሚለው ትችት ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው። መንግሥታዊ ፓርቲዎች የመንግሥትን ሀብት እንደፈለጉ የሚጠቀሙ ፓርቲዎች ሲሆኑ፤ አንዳንዴ የፓርቲና የመንግሥት መዋቅሮችን መለየት እስኪያስቸግር ድረስ አንድ ላይ የሚያዋህድ ቅርፅ ነው። ከዚህ መንግሥትና ፓርቲን ካልለየ አካሄድ ጋር ተያይዞ “ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ” የጣሊያናዊውን ማውሮ ሴሊዜን (Mauro Calise) ቋንቋ በመዋስ “ወደ ፓርቲክራሲ (Particracy) ቀይሮታል” ወደሚል መደምደሚያ ላይ እየደረሱ የሚገኙ ብዙዎች ናቸው።

በዚህ የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የመጠቅለል አካሄድ ላይ ስጋት የገባቸው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢ.ዴ.ፓ.) የቀድሞ ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው “ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. በይዘት ከቻይና አስተሳሰብ ብዙም አይለይም” ይላሉ። የቻይና አስተሳሰብ የሚሉት፣ ‹አሁን ባለንበት ሁኔታ ዴሞክራሲ አያስፈልገንም፣ የሚያስፈልገን የኢኮኖሚ ሪፎርም ነው› የሚለውን ነው። የቻይና መንግሥት ይህንን የሚያደርገው በይፋ የአንድ ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲን ደንግጎ ነው። በቻይና ሕጋዊ ዕውቅና ያለው አንድ ‹የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ› ብቻ ነው። የቻይና የፖለቲካ ስርዓት አሀዳዊ እንጂ አውራ ፓርቲ ስርዓት አይባልም። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ግን ይህንን ማድረግ ያልቻለው፣ ደርግን ጥሎ አዲስ አበባ እግሩ በረገጠበት ሰዓት የቀዝቃዛው ጦርነት እየከሰመ ዓለም በሁለት ‹ብሎክ› የሚጠራበት ስርዓት እያበቃ በአንድ ዓለምዐቀፍ አስተሳሰብ እየተጠራ ስለነበር “የቻይና አካሔድ የሚበጅ ሆኖ ባለማግኘቱ” እንደሆነ አቶ ልደቱ ይናገራሉ። ስለሆነም “በወረቀት የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን ደንግጎ፣ በተግባር ግን የቻይናን መንገድ ይከተላል”።

እንደ አቶ ልደቱ ገለጻ “ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ያስፈልገዋል ብሎ አያምንም። ለዚህ ሕዝብ አሁን ዴሞክራሲ አያስፈልገውም… የዳቦ ጥያቄው ከተመለሰ በኋላ ይደርስበታል ብሎ ነው የሚያምነው።”

የኦሮሞ ፌዴራል ኮንግረስ (ኦ.ፌ.ኮ.) ሊቀመንበር እና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዶ/ር መረራ ጉዲናም ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የመድብለ ፓርቲን የሚያስተናግድ አስተሳሰብ እንደሌለው ይናገራሉ። “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ይላሉ ዶ/ር መረራ “የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን ለማስተናገድ የተፈጠረ አይደለም”። በኢትዮጵያ መድብለ ስርዓትን የሚፈቅድ “የይስሙላ ጨዋታ” የተፈቀደው ዕርዳታ ለጋሽ አገራትን ለማስደሰት ብቻ ነው” በሚል ነው ዶ/ር መረራ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት አለ ሊባል የሚችለው ብለው የሚያስቡት።

የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን የመጀምሪያ የሥልጣን ዘመናት በገመገሙበት ጽሑፋቸው ይሄን አካሄድ የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የአግላይነት ፖለቲካ (politics of exclusion) ያሉት ሲሆን፤ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ያልተመቸውን ሰውም ሆነ ድርጅት ወደ ጎን እየገፋ ዙሪያውን በራሱ ሰዎች መክበብን እንደ ዋነኛ የሥልጣን ላይ መቆያ ዘዴ እንዳደረገው አያይዘውም ይገልጻሉ። ዶ/ር ካሳሁን ይህን ካሉ ከ15 ዓመታት በኋላ ይህ አካሄድ መባስ እንጅ መሻሻልን እያወቀ አይደለም።

 

የተበላሸ ዘርና ተጣሞ ‘ያደገ’ ተክል

የፓርቲ ፖለቲካ ላይ የሚቀርበው ሌላው መሠረታዊ ትችት የፖለቲካው ተዋንያንንና ከተዋንያኑ አደረጃጀት ጋር ተያይዞ የሚቀርብ ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያቋቁሟቸው ግለሰቦች በራሳቸው ብዙ የራሳቸው የግል ፍላጎት ያሏቸውና ተደራጅተው ከሌሎች ጋር መሥራት የሚቸግራቸው ናቸው ከሚለው ሐሳብ ነው ትችቱ የሚጀምረው። ዶ/ር ወንድወሰን ተሾመ በአሁኑ ወቅት ያሉ የኢትዮጵያ ፓርቲ ፖለቲካ ተዋንያንን በሰባት መደቦች ያስቀምጧቸዋል። በዐፄ ኃይለሥላሴ ስርዓት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ (ex-minsters of the ancien régime)፣ የግራ ፖለቲከኞች (leftists)፣ የቀድሞ የግራ ፖለቲከኞች (ex-leftists)፣ ፋኖ ያሉ ፓርቲዎች (rebels)፣ ታማኝ ተቃዋሚዎች (loyal oppositions)፣ አስመሳይ ተቃዋሚዎች (phony oppositions) እና በፊት ኢሕአዴግ ውስጥ የነበሩ (ex-EPRDF members) በማለት። እንግዲህ እነዚህ በተለያዩ የዕድሜ ክልሎች ላይ ያሉ ተዋናዮች (አንዳንድ ከሁለት በላይ ባሉ መደቦች ውስጥ እየገቡ) የራሳቸውን ፍላጎት ለማራመድ ሲሉ ሌሎችን እየጠለፉ ሁሉም የፖለቲካው ከፍታ ላይ መድረስ እንዳይችሉ ሁኗል።

 

የኢትዮጵያ የፖለቲካ የውስጥ ፓርቲ የዴሞክራሲያዊነት (intra-party democracy) ችግር እንዲሁም ተቋማዊ ቁመና (Institutionalization ) የመያዝ ችግር አለባቸው የሚለው ትችትም ሁሌም የሚሰማ ነው። ሮበርት ሚሸልስ የተባሉ ምሁር የውስጥ ፓርቲ ዴሞክራሲን ይዞ የተደራጀ መዋቅር ያለውና ተቋማዊ ቁመና ያለው ፓርቲ ማቋቋም አብረው ሊሄዱ የማይችሉ (inconsistent) ጉዳዩች ናቸው ይላሉ። ፓርቲን ተቋማዊ ቅርፅ አስይዞ በተመሰሳይ ወቅት ዴሞክራሲያዊ ላድርግ ማለት የኋላ ኋላ ሁለቱንም ያሳጣል የሚል ነው የሐሳቡ አንኳር። ኢንጅነር ይልቃል በዚህ ሐሳብ የሚስማሙ ይመስላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ‹የፓርቲ አባላትን ዲስፕሊንድ አድርጌ የውስጥ ፓርቲን ዴሞክራሲ አሰፍናለሁ ማለት በዚህ ዘመን ከባድ ነው› ይላሉ። አያይዘውም የውስጥ ዴሞክራሲን በፓርቲ ውስጥ አስፍኖ የፓርቲ ዲሲፕሊን የሚባለውን ጉዳይ ወደ ጎን  ብሎ የንቅናቄ ቅርፅ ያለው ፓርቲ ይዞ መቀጠልን እንደሚመርጡ ይገልጻሉ።

የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ አሉባቸው ከተባሉት የአባላት ችግር እና የውስጠ ፓርቲ ቁመና ችግር ባለፈ ያለምንም ዓላማ አዳዲስ ፓርቲዎች እየተቋቋሙ እርስ በርሳቸው ይጠላለፋሉ የሚል ትችት ይቀርብባቸዋል።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ድረ-ገጽ ላይ (ሚያዝያ 28/2008 እንዳየነው) የተዘረዘሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች 75 ናቸው። ከ2007 ምርጫ በፊት ‹ለቀጣዩ ምርጫ በንቃት የሚሳተፉ ፓርቲዎች ዝርዝር› በሚለው ስር የተዘረዘሩት ፓርቲዎች ቁጥር ግን ጠቅላላ ከተባለው የፓርቲዎች ዝርዝር ይበልጣል። እሱም በእንግሊዝኛው እና በአማርኛው ላይ የተለያየ ሁኖ እናገኘዋለን። በእንግሊዝኛው 79 ሲሆኑ፣ በአማርኛው 76 ናቸው። ከዚህ የቁጥር ዝብርቅርቅ በተቃራኒው፣ ብዙዎች የሚተቹት ብዛታቸው እና የርዕዮተ-ዓለም ልዩነታቸው የማይጣጣም መሆኑን ነው። ምንም እንኳን ብዙዎቹ ፓርቲዎች በዘውግ ከመደራጀታቸው በቀር ልዩነት ባይኖራቸውም መንግሥት ለመመሥረት በሚያስችላቸው ቁመና ለመቆም ጥምረት ወይም ግንባር ሲፈጥሩ አይታዩም። ኅብረ-ብሔራዊ መሠረት ይዘው የተደራጁትም፣ ግልጽ የሆነ የርዕዮተ-ዓለም ልዩነት ባይኖራቸውም ተደራጅተው ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ለመገዳደር በሚያስችላቸው መዋቅር ለመቅረብ አልሞከሩም፣ ቢሞክሩም አልተሳካለቸውም።

ዶ/ር መረራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር መብዛት ችግር ነው ብለው አያምኑም። “እስራኤል 5 ሚሊዮን ሕዝብ ብቻ ነው ያላት፤ ነገር ግን ከ30 በላይ በአገሪቱ ሕልውና የማይደራደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ስለዚህ ለ100 ሚሊዮን ሕዝብ ብዙ ፓርቲዎቹ ቢኖርም ያን ያክል ችግር አይደለም። ችግሩ፣ እነዚህ ፓርቲዎች ለሕዝብ ጥቅም የቆሙ ናቸው ወይስ አይደሉም፤ ለራሳቸውም ሥልጣን ለማግኘት ቢሆን ችግር የለውም፤ እንዲሁ የገዢው ፓርቲ ቀለብ የሚሰፍርላቸው ናቸው የሚለው ነው የሚያሳስበው” ይላሉ። የሌሎች አገራትን ተሞክሮ ስንመለከትም ዶ/ር መረራ ከሚሉት እውነታ ብዙም የራቀ ድምዳሜ ላይ አንደርስም። ኬኒያ በአንድ ወቅት እስከ 160 የሚደርሱ የተመዘገቡ ፓርቲዎች ነበሯት፤ ናይጄሪያም 60 የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ደቡብ አፍሪካንም የወሰድን እንደሆን ከ80 በላይ ፓርቲዎች ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱባት ሀገር ነች። ከዚህም አንፃር ኢትዮጵያ ውስጥ የፓርቲዎች መብዛት መሠረታዊ ችግር ነው የሚለው ሐሳብ ትክክል ነው ማለት አይቻልም። መሠረታዊው ችግር ያለው ‹እነዚህ ፓርቲዎች እንቅስቃሴያቸው ምን ይመስላል? የፓርላማ ውክልናቸውስ?› የሚለው ነው የሚሆነው። ኬኒያ ካሏት ፓርቲዎች መካከል 23 የሚሆኑት የፓርላማ ውክልና አላቸው፤ በናይጀሪያም 6 ፓርቲዎች በፓርላማ መቀመጫ ያለቸው ሲሆን፤ ደቡብ አፍሪካ ደግሞ 13 በፓርላማ ወንበር ያላቸው የፓርላማ ፓርቲዎች (Parliamentary Parties) አሏት። እንግዲህ የኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ አሳዛኝና አሳሳቢ የሚሆነውም ከዚህ አንጻር ስንመለከተው ነው። በአሁኑ ወቅት ገዥው ፓርቲ ብቻ በፓርላማ ተወክሎ የፈለገውን የሚወስንበት ጊዜ ሲሆን፤ ይሄም የፓርቲ ፖለቲካ የሚባለውን ሐሳብ ሙሉ ለሙሉ እንዳይቀብረው የብዙዎች ስጋት ነው።

ዶ/ር መረራ በኢትዮጵያ ‹የፈሉትን› የፖለቲካ ፓርቲዎች “አንዳንዶቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከራሳቸው [ከሊቀመንበሮቹ] የግል ዝና ያለፈ ቁመና ያላቸው አይመስለኝም…” ሲሉ አቶ ግርማ ሰይፉ ደግሞ “በአንድ ሰው የሚዘወሩ ሱቆች ወይም ከሱቅ በላይ ማዕረግ የሌላቸው ናቸው” ይሏቸዋል። አቶ ግርማ የሚያስገርማቸው “አንደኛ፣ እንደዚህ ዓይነት ፓርቲዎች እንዲቋቋሙ የሚፈቅድ መንግሥት መኖሩ እና ፓርቲዎቹ ውስጥ ለመሰባሰብ የሚፈቅዱ አባላት መኖራቸው” ነው። አቶ ግርማ፣ ሲቪክ ማኅበራት ሲዋቀሩ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያስቀምጥ መንግሥት፣ አገር እንመራለን ብለው የሚደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ‹በነጻ የመደራጀት መብትን ለማክበር› በሚል ሰበብ ብቻ እንዲሁ መተው ተገቢ እንዳልሆኑ ይናገራሉ። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕ/ር መርጋ በቃና በሕዳር ወር 2007 በሰጡት ይፋ ቃለ ምልልስ “75 [የፖለቲካ ፓርቲዎች] አሉ። ነገር ግን የሕግ ጉዳይ ያላሟሉና ሥልጣንን ሞኖፖላይዝ ያደረጉ እንዲሁም ራሳቸው ባወጡት ደንብ መሠረት ለ18 ዓመታት ጠቅላላ ጉባኤ ያልጠሩ አንዳንድ ፓርቲዎች ይገኙበታል። ለዴሞክራሲው ስንል በሆደ ሰፊነት ነው የምንይዛቸው” ብለው ነበር። አመራር የነበሩበት አንድነት ፓርቲ በእርሳቸው አገላለጽ ‹ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ› በምርጫ ቦርድ ጣልቃ ገብነት የተሰነጠቀባቸው እና ለሌሎች ተላልፎ የተሰጠባቸው አቶ ግርማ ሰይፉ ግን ይህ አባባል አይዋጥላቸውም። “ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. እንዲህ ዓይነቶቹን ‹ሱቅ› የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝም የሚላቸው ለሥልጣኑ ስለማያሰጉት እና ስለሚፈልጋቸው ነው።” በማለት ነው ሐሳባቸው የሚገልጹት።

አቶ ልደቱ አያሌው “ኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ የተመዘገበ፣ ሰርቲፊኬት ያለው ተቃዋሚ ፓርቲ እንጂ በተግባር ግን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የትግል እንቅስቃሴ የሚመጥን ተቃዋሚ ፓርቲ እስካሁን አልተፈጠረም። በምርጫ ቦርድ መስፈርቱን አዘጋጅተን ተመዝግበናል። ሕጋዊ ፈቃድ አለን፣ ቢሮ አለን፣ እንንቀሳቀሳለን። ምርጫ እንወዳደራለን። አሁን ካለው የኢትዮጵያ ሁኔታ አንፃር ግን፣ በተለይ የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ዓይነት ግዙፍ ድርጅት ተቋቁሞ ለሥልጣን መብቃት የሚችል የፖለቲካ ፓርቲ እስካሁንም አልተፈጠረም፤ አሁንም የለም።” በማለት አቶ ግርማ ‹ሱቅ› እያሉ የሚጠሯቸው ብቻ ሳይሆኑ ሌሎቹም ፓርቲዎች ሕዝቡን በሚመጥን ቁመና ላይ እንደሌሉ ይሟገታሉ። አቶ ልደቱ ለዚህ ችግር መንስኤ ናቸው የሚሏቸውን አምስት ነጥቦች ዘርዝረዋል። “አንደኛ፣ ፖለቲካችን የሐሳብ ፖለቲካ አልሆነም፤ ሁለተኛ፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና መጫወት የሚችለው የኅብረተሰብ ክፍል በተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ ተሳትፎ አያደርግም፤ ሦስተኛ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጣዊ ዴሞክራሲ የላቸውም፤ አራተኛ፣ አካባቢያዊ ስሜት በፓርቲዎች ውስጥ ነግሷል፤ አምስተኛ፣ ፓርቲዎቹ የውጪ ፖለቲከኞች ላይ ጥገኛ ናቸው” በማለት ያስቀምጧቸዋል።

የኢትዮጵያ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥራቸው ቢበዛም በአሁኑ ወቅት አንድም የፓርላማ ወንበር መያዝ አልቻሉም። ከላይ ካነሳናቸው የውጭና የውስጥ ችግሮች በተጨማሪ ከውሕደትና ጥምረት ጋር ተያይዘው የሚቀርቡባቸው ትችቶችም አሉ። ትችቱ ተዋሃዱ የሚል ብቻ ሳይሆን ለመዋሃድ ሲባል ፓርቲዎች መሠረታቸውን እየናዱ ይፈርሳሉ፤ መዋሃድን እንደ ግብ መውሰዳቸው ስህተት ነው የሚልም ነው። በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ከሁሉም ፈታኝ የሆነ ችግር እንደሆነ ብዙዎች የሚስማሙበት መተባበር አለመቻልን ነው። መተባበሩ ቀርቶ አንድ ፓርቲ ሳይሰነጠቅ እየጎለበተ መሄድ የሚችልበት ሁኔታም በተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሚናፈቅ ነገር ሆኗል የሚሉም አልታጡም። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ አቶ አስናቀ ከፋሌ ‹The (un)making of opposition coalitions and the challenge of democratization in Ethiopia, 1991–2011› በሚል ርዕስ ባሳተሙት ጥናታቸው ላይ ምርጫ 97 ላይ የመተባበር (coalition) ፖለቲካ እመርታ ታይቶ እንደነበር ይገልጻሉ። በዚህም ተቃዋሚዎች ‹ለምርጫ ሕጎች መሻሻል እና በአካባቢያዊ እና ብሔራዊ ደረጃ ጉልህ ውክልናን ለማሸነፍ በሚያስችል ሁኔታ መደራደር ቢችሉም፣ ያንን ማስቀጠል አልቻሉም። ያኔ እና ከዚያ በኋላ ትብብሮች ውጤታማ ሊሆኑ አልቻሉም› ብለዋል።

አቶ አስናቀ በዚሁ ጥናታቸው፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ትብብር አለመሳካት መንስኤ ሆነዋል የሚሏቸውን ሰባት ምክንያቶች በጽሑፋቸው ላይ ዘርዝረዋል። 1ኛ፣ ከልካዩ የፖለቲካ ምኅዳር እና የመንግሥት ተፅዕኖ፤ 2ኛ፣ በርዕዮተ-ዓለማዊ መግባባት ሳይሆን በሥመ-ተቃዋሚነት ብቻ ለመተባባር መስማማት፤ 3ኛ፣ የዳያስፖራ ፖለቲከኞች በተለያዩ ቡድኖች የመቧደን ተፅዕኖ፤ 4ኛ፣ የጋራ መግባቢያ የመፍጠር ልምድ ማነስ እና የዴሞክራሲ ባሕል እጦት፤ 5ኛ፣ የድርጅት ነጻነት (independence) ከግምት ውስጥ ያላስገባ ‹ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ› በሚለው ግፊት ብቻ የማይዘልቅ ጥምረት መመሥረት፤ 6ኛ፣ በተጣማሪዎቹ ድርጅቶች መካከል ያለ የኃይል/ሥልጣን ሽሚያ፤ እና 7ኛ፣ በተጣማሪ ቡድኖች መካከል መተማመን አለመኖር ለብዙዎቹ ጥምረቶች ስኬት ማጣት እና መልሶ መፍረስ ሰበቦች መሆናቸውን አመላክተዋል።

ከዚህ ከአቶ አስናቀ ትችት በተመሳሳይ አቶ ልደቱ አያሌው ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች ‹አንዱ መተባበርን እንደግዴታ የሚወስድ ባሕል መኖሩ እንደሆነ ይናገራሉ። የተለያየ የፖለቲካ ግብ ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ለመገዳደር ብቻ ሲባል እንዲተባበሩ ግፊት ይደረግባቸዋል። የሚተባበሩት በርዕዮተ-ዓለም አንድ ሆነው ስላይደለ ኅብረታቸው አይሰምርም› ይላሉ። ማኅበር (ወይም የፖለቲካ ድርጅት) መመሥረት በራሱ መተባበር እንደሚጠይቅ የሚናገሩት ኢ/ር ይልቃል ደግሞ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል “የመተባበር አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነገር አይደለም” ባይ ናቸው። ይልቁንም፣ ኢንጅነር ይልቃል እንደችግር የሚወስዱት ያላደገው የፖለቲካ ባሕላችን ችኩልነትን እና ፍፁማዊነትን መሻቱን ነው። ማኅበሮች በችኮላ እንዲመሠረቱ እና ፍፁማዊ ስኬት እንዲያስመዘግቡ ይጠበቃል። ይህ ደግሞ አይሳካም ይላሉ። “አለመተባበርም፣ ለውጤት የመጓጓትም ችግሮቹ አንድ ናቸው፤ ምንጩን ስናየው ውጤቱን በአንድ ሌሊት ለማየት መጓጓት ነው። ቅንጅትንም ያፈረሰው ይሄው ነው” ብለዋል።

በመጨረሻም ፓርቲዎች ውጤት ለማምጣት ላለመቻላቸው የሚጠቀሰው ምክንያት የአደረጃጀታቸው ጉዳይ ነው። ይሄም ሕብረ-ብሔራዊና የዘውግ (ethnicity) አደረጃጀት የሚለው ክፍፍል ኅብረ-ብሔራዊ የሚባሉት ፓርቲዎች ጎልተው እንዳይወጡ አድርጓቸዋል፤ የብሔር መሠረት ያላቸው ፓርቲዎች ደግሞ ከራሳቸው ማዕቀፍ ወጥተው ጠንካራ ተገዳዳሪ መሆን እንዳይችሉ አደረጃጀታቸው በራሱ ያግዳቸዋል የሚለው ነው።

በ1960ዎቹ በጋናዊው ኩዋሚ ኑኩሩማህ ጀማሪነት የተጀመረው የአፍሪካ ፓርቲዎችን በንዑስ መሠረት (particularistic) ላይ እንዳይመሠረቱ መከልከል እየተለመደ መጥቶ ከ1990ዎቹ ወዲህ እጅግ ሰፍቶ በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ውጭ ፓርቲዎች ዘውግንም ሆነ ሃይማኖትን መሠረት አድርገው የተደራጁበት የሰሃራ በታች የሚገኝ የአፍሪካ ሀገር አለ ማለት አይቻልም። አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ፓርቲዎች ዘውግን መሠረት አድርገው የሚደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሕግ የተከለከሉ ናቸው። ለዚህም የሚሰጠው ዋነኛ ምክንያት እንደዚህ ያሉ አደረጃጀቶች ከፋፋይና (divisive) የሲቪል የፖለቲካ ሂደት እክል ናቸው የሚል ነው። ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ከላይ ባየነው የአፍሪካ እውነታ በተቃራኒው በአሁኑ ወቅት ገዥውን ግንባር ጨምሮ አብዛኞቹ ሕጋዊ ዕውቅና ያላቸው ፓርቲዎች የአደረጃጀት መሠረታቸው ዘውግ ነው።

ከዚህ መሬት ላይ ያለ እውነታም በመነሳት ‹በአሁኑ ወቅት በተሻለ የጥንካሬ ቁመና ላይ የሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች በብሔር ወይም በዘውግ የተደራጁት ናቸው፤ ኅብረ-ብሔራውያኑ ተዳክመዋል። ኅብረ-ብሔራውያኑ ፓርቲዎች የመሰነጣጠቅ አደጋ የሚያንዣብብባቸው በውስጣቸው በዘውግ የመቧደን አባዜ ስለሚከሰት ነው› በማለት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሚከሰቱ ውስጣዊ መዳከሞች እና መከፋፈሎች ላይ መንስኤው በዘውግ መደራጀት መፈቀዱ ነው የሚሉ ፖለቲከኞች ጥቂት አይደሉም። በአፍሪካ ውስጥ (ኬንያ እና ጋናን ጨምሮ) በዴሞክራሲ እያበቡ ያሉ አገራት በዘውግ መደራጀትን በይፋ በማገዳቸው የመድብለ ፓርቲ ስርዓታቸው ፈተና ውስጥ እንዳልወደቀ የሚከራከሩ አሉ።

አቶ ልደቱ አያሌውም ፖለቲካችን በከፍተኛ ሁኔታ የብሔር ፖለቲካ ያጠላበት መሆኑን አምነው፤ እንደሌሎች የአፍሪካ አገራት በዘውግ መደራጀትን ማገድ ያስፈልግ ይሆን ወይ ለሚለው ጥያቄ “የብሔር ፖለቲካን በሕግ ማገድ ያስፈልጋል ባልልም፣ እንደማይጠቅም ግን አምናለሁ” ይላሉ።

በሌላ በኩል በዘውግ የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ‹ኅብረ-ብሔራዊ የሚባል ፓርቲ የለም። ኅብረ-ብሔራዊ ነን ብለው የሚደራጁት የአንድ ብሔር ሰዎች እና የከተማ ሰዎች ብቻ ናቸው› ብለው በተቃራኒው ይከራከራሉ። ባለፈው የፓርላማ ዘመን በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ እና የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አባል የነበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ ይህንን አስመልክቶ “አንድነት ፓርቲ የሁሉም ቤት ይሁን ብለን ስንሠራ ትልቁ ተግዳሮት የሆነብን ብሔር ተኮር የሆነው አመለካከት የሚጎትታቸው ብዙ ሰዎች መኖራቸው ነው። ለምሳሌ አንዳንድ አባላት የብሔር ፖለቲካ ታማኝነታችን መድረክ [አሁን የብሔር ድርጅቶች ብቻ ስብስብ] ውስጥ በመቆየት የሚገለጽ የሚመስላቸው አሉ። አንድነት ፓርቲ ውስጥ አባል ሆነው የሚቆዩት ፓርቲው የመድረክ አባል ሆኖ እስከ ቆየ ድረስ እንደሆነ ቅድመ ሁኔታ አድርገው የሚያስቀምጡ አሉ። ኅብረ-ብሔር ነኝ ብሎ ተደራጅቶ ውስጣዊ ፍልስፍናው ዘውጋዊ የሚሆንበትም ጊዜ አለ” ብለዋል።

አቶ ልደቱ የአንድ ብሔር ሰዎች አንድ ድርጅት ውስጥ በዝተው ስለታዩ ፓርቲው ኅብረ-ብሔራዊ አይደለም አያሰኘውም። ይልቁንም “ፓርቲው የተደራጀበት አስተሳሰብ ነው ድርጅቱ ኅብረ-ብሔራዊ ነው አይደለም የሚለውን የሚወስነው” ይላሉ። ለምሳሌ ‹ኢዴፓ 46 በመቶ የሚሆኑት አባላቱ የደቡብ አካባቢ ሰዎች ናቸው› በማለት፣ ከአስተሳሰባቸው በተጨማሪ ኅብረ-ብሔራውያን ነን የሚሉት የአንድ አካባቢ ሰዎች ናቸው የሚባለው ሁሉ እውነት እንዳልሆነ ይከራከራሉ። አቶ ልደቱ “በተጨማሪም፣ አንዳንድ ጊዜ የመረጃ እጥረት ያለ ይመስለኛል” ይላሉ። “ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ ጠንካራዎቹ እነማን ናቸው የሚለው ላይ እስካሁን ድረስ በተካሄዱት ምርጫዎች ላይ የተገኙትን ድምፆች መለስ ብለን ብናየው፣ ብዙ ድምፅ ያገኙት የብሔር ድርጅቶች ሳይሆኑ ኅብረ-ብሔር ድርጅቶች ናቸው” ይላሉ።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ከዚህ የተለየ አመለካከት ነው ያላቸው። ኢ/ር ይልቃል “ኅብረ-ብሔራዊ” በሚለው አላምንም ይላሉ። እንደእርሳቸው ሰማያዊ ፓርቲ ራሱን “ኅብረ-ብሔራዊ” ብሎ አይጠራም። “ምናልባት አንዳርጋቸው ጽጌ በሚጠቀምበት አማርኛ ‹ዘውግ-ዘለል› ብንለው ይሻል እንደሆን አላውቅም፤ ፓርቲዎች ወይ የዘውግ ፓርቲዎች ናቸው አለበለዚያ ደግሞ የርዕዮት-ዓለም ፓርቲዎች ናቸው ማለት ነው። በሐሳብ ደረጃ በዜግነት ላይ የተመሠረቱ ፓርቲዎች አሉ፤ አለበለዚያ ‹ኅብረ-ብሔር› የሚለው ቃል ራሱ የመጣው የአንድ ብሔር አደለንም ለማለት ነው እንጂ ዘውግን መሠረት አላደረጉም ማለት አይደለም” ይላሉ። ይሁን እንጂ ኢ/ር ይልቃል የዘውግ አደረጃጀት በቅርብ የሚያስተሳስሩ የወል ሥነ-ልቦና ስለሚኖሩት በፍጥነት የተወሰነ ጊዜ መዝለቅ የሚችል ድርጅት ለመፍጠር እንደሚጠቅምም አበክረው ይናገራሉ። ‹ዘውግ-ዘለል› የሆነ ተቋም ለመመሥረት ግን ጊዜ ስለሚወስድ በመሐል ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ም በቀላሉ መስበር የሚችልበት ዕድል ይኖረዋል፤ ሌሎችም ሁኔታዎች ይፈታተኑታል በማለት በርዕዮት-ዓለም የሚደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘውግ ከሚደራጁት ይልቅ ከፍተኛ ተግዳሮት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

አቶ ግርማ ሰይፉ በዘውግ መደራጀት “ግብ የለውም” ብለው ነው የሚያምኑት። “ሌላው ቀርቶ ብዙ ሕዝብ ያለው የኦሮሚያ ክልል ነው። ኦሮሚያ ክልልን መሠረት አድርገው የተደራጁት እንኳን አገር የማስተዳደር ግብ የላቸውም። ክልል ማስተዳደርን ግብ ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ይህ ግን ሰንካላ ግብ ነው። አገር የማስተዳደር ግብ ሊኖራቸው አይችልም። አገር ለመምራት ከፈለጉ ሌላ አንድ ድርጅት መፈለግ አለባቸው። አንድ ፓርቲ ሲቋቋም በራሱ መንግሥት ለመመሥረት እንዲችል ሆኖ መሆን አለበት።” በማለት መንግሥት ለመመሥረት ከሚያስችል ባነሰ አደረጃጀት የሚቋቋሙ ድርጅቶች ግብ የላቸውም በማለት አምርረው ይተቻሉ። “በደቡብ ክልል አንዳንዶች አንድ የፌዴራል ምክር ቤት መቀመጫ የሚያስገኝ የዘውግ አደረጃጀት ይዋቀራሉ፤” የሚሉት አቶ ግርማ “እነዚህኞቹ ድርጅቶች በክልል ምክር ቤትም ይሁን በፌዴራል ደረጃ ምንም ፋይዳ የላቸውም። ግብ የላቸውም” ብለዋል።

ዶ/ር መረራ ጉዲና በዚህ ዘውጋዊ አደረጃጀትን የማይቀበል አካሄድ አይስማሙም። “[በዘውግ መደራጀት በሌሎቹ አገራት] በሕግ ባይፈቀድም በተግባር ግን አለ፤ ኬንያን ለምሳሌ ብትወስድ ኪኩዩ ካልሆንክ ለፕሬዚዳንትነት ተወዳድረህ ማሸነፍ ያስቸግርሃል።… ለምሳሌ ኦዲንጋ እና ኡሁሩ ኬንያታ በምንም አይገናኙም። ኦዲንጋ በልምድም በዕውቀትም ይበልጠዋል። ኡሁሩ ያሸነፈው ኪኩዩ ስለሆነ ነው። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ዙማ ፕሬዚዳንት የሆነው ዙሉ ስለሆነ ነው እንጂ በመደበኛ ትምህርት እንኳን አልዘለቀም። እኔ የአፍሪካ ፖለቲካን እስካነበብኩ ድረስ ታንዛንያውያን ብቻ ነው ይሄ ነገር የሌለባቸው። እነሱም [የዘውግ] ቡድኖቻቸው ትንንሽ በመሆናቸው ነው። ይሄ ነገር የሚቀንሰው ካፒታሊስቶቹ ጋር ነው። እነሱ የሚደራጁት በጥቅም ፍልስፍና ነው። ነገር ግን በዘር መቧደን እዛም ይቀራል ማለት አይደለም። ለምሳሌ ጥቁር አሜሪካውያን 80 በመቶ ኦባማን ሲመርጡ እንደነበር ይታወቃል” ይላሉ። አያይዘውም አንድ ፓርቲ ኅብረ-ብሔራዊ ነኝ ስላለ ብቻ የብሔር መሠረት የለውም ማለት አይደለም በማለት መከልከሉ ምንም ዓይነት ውጤት ያመጣል ብለው እንደማያስቡ ይገልጻሉ።

ነገሩ መነሳቱ በአደረጃጀት ደረጃ ያለውን ግንዛቤ ያጠራዋል በሚል ሐሳብ እንጅ ገዥው ፓርቲ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ራሱ በዘውግ የተደራጀ ፓርቲ ሆኖና ሕግ የማውጣቱን ሒደትና መሣሪያ ሙሉ ለሙሉ ተቆጣትሮት ባለበት ሁኔታ የራሱን አደረጃጃች ሕገ ወጥ የሚያደርግ መመሪያ ያወጣል ብለን ማሰብ ቅዥት ነው የሚሆነው።

 

ቻው ቻው የፓርቲ ፖለቲካ?

አሁን አሁን በኢትዮጵያ የሠላማዊ የፖለቲካ መድረክ ላይ ለብዙ ዓመታት ተዋናይ የነበሩ ግለሰቦችን ጨምሮ በብዙዎች ዘንድ የፓርቲ ፖለቲካን በአሁኗ ኢትዮጵያ ማካሄድ አይቻልም የሚል ድምዳሜ ላይ ሲደርሱ ይታያል። ከእነዚህ የፓርቲ ፖለቲካ ተስፋ ከቆረጡ ግለሰቦች መካከል አቶ ግርማ ሰይፉ አንዱ ናቸው። አቶ ግርማ ‹ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን የሚያክል የሠላማዊ ትግል እክል ባለበት አገር ተቃዋሚዎችን ለመውቀስ የሞራል ብቃቱ የለኝም› ይላሉ። ለአቶ ግርማ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. በኢትዮጵያ ተወልዶ የነበረውን የፖለቲካ ፓርቲ ትግል ወደ መቃብር ሸኝቶታል የሚል እምነት አላቸው። ከዚህ በኋላ በፓርቲ ቁመና ተደራጅቶ ልታገል ማለት ተደራጅቶ ለኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. መመቸትና ለመጥፋት መንደርደርም ነው ብለው ያምናሉ። ከዚህም ተነስተው ከዚህ በኋላ አራማጅነትን (Activism) መሠረት ያደረጉ እንቅስቃሴዎች እንጅ የፓርቲ ፖለቲካ ለውጥ ያመጣል ብለው እንደማያምኑ ይናገራሉ። “አሁን ያለው የፓርቲ ፖለቲካና የእስካሁኑ ትግል እርሾ ሁኖ ይቀጥል በሚለው ሐሳብ አልስማም” የሚሉት አቶ ግርማ ነገሮችን በአዲስ አተያይና አዲስ አካሄድ ማስጀመር መልካም መሆኑን ይገልጻሉ።

 

“ተስፋ ብንቆርጥማ እዚህ ምን እንሠራለን?”

በታኅሣሥ 2001 የብዙ ግለሰቦችን ጥያቄ ይፈታል የተባለለት በኦሮሞ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ እና የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ ፓርቲዎች ሁለት መሆናቸውን ትተው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦ.ፌ.ኮ.) በሚል አዲስ ስያሜ ተዋህደው አንድ ወደ እንቅስቃሴ መግባታቸው ለብዙዎች ተስፋ የሰጠ እርምጃ ነበር። ኦ.ፌ.ኮ. ከዛን ጊዜ ወዲህ ከሌሎች አራት ፓርቲዎች ጋር በመሆን ‹መድረክ› የተባለ ግንባር በመፍጠር እየተንቀሳቀሰም ይገኛል።

ኦ.ፌ.ኮ. በሐገሪቱ ውስጥ ካሉት ዘጠኝ የፌደራል ክልሎች መካከል በሕዝብ ብዛትና በቆዳ ስፋት ደረጃ ትልቁ በሆነው የኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው ብቸኛው ፓርቲ ነው ለማለት በሚያስችል መልኩ የሚገኝ ሲሆን፤ ፓርቲው የብዙዎችን ትኩረት የሚስበውም ከዚህ አቅሙ አንፃር ነው። ነገር ግን ባለፉት አምስት ወራት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከተካሔዱት ሕዝባዊ ተቃውሞች ጋር በተያያዘ የድርጅቱ ዋነኛ አመራሮች የታሰሩበት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በክልሉ ውስጥ በቡሌ ሆራ ከተማ የቀረች አንድ የፓርቲ ቢሮ ብቻ እንዳለችው የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በጥርጣሬ ይገልጻሉ። የድርጅቱ ሠላማዊ ታጋዮች ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. በክልሉ እየወሰደው ባለው ርምጃ ተጠቂዎች እንደሆኑ የገለጹት ዶ/ር መረራ የፓርቲያቸው ድል አድርገው የሚቆጥሩት “ሕዝቡን በተለያዩ መንገዶች አንቅተነው አሁን እኛ ባንኖርም መብቱን የሚያውቅና ለማስከበርም ቆርጦ የተነሳ ሕዝብ መፈጠሩ ነው” ይላሉ። ከዚህም ተነስተው “በፓርቲ ፖለቲካማ ተስፋ እንዴት እንቆርጣለን? ተስፋ የምንቆርጥ ከሆነማ እዚህ ምን እንሠራለን?” በማለት ተስፋ አስቆራጭ ነው ስለሚባለው የፖለቲካ ምኅዳር ላቀረብንላቸው ጥያቄ ምላሻቸውን ይሰጣሉ። “ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ከመቼውም ጊዜ በላይ የተዳከመው አሁን ነው” የሚሉት ዶ/ር መረራ “ኢሕአዴግ በ101 ችግሮች ተብትቦ ቢይዘንም አሁንም የሚሻለው ያሉብንን የመተባበር ችግሮች ተሻግረን ወደፊት መሄድ ነው” ይላሉ። መሪ የሚሆን ፓርቲ በሌለበት ሁኔታ ለውጥ እንኳን ቢመጣ በለውጥ ማግስት የሚፈጠረው ክፍተት የመረራ ስጋት ነው።

 

ፍሬውን ለማየት

በኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ እና የፖለቲካ ባሕል ውስጥ ተዘርዝረው የማያልቁ ችግሮች አሉ። ለችግሮቹ ተጠያቂ የሆኑ ዐብይ አካላት ቢኖሩም፣ ችግሮቹን ሁሉ ለአንድ ወገን ብቻ ጠቅልሎ መስጠት የትም እንደማያደርስ ከአጥኚዎች እስከ ፖለቲከኞች ድረስ ይስማማሉ።

አቶ ልደቱ አያሌው “ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዋነኛው ችግር ቢሆንም ብቸኛው አይደለም፤” ይላሉ። “ኢሕአዴግን የችግሩ አካል ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ የመፍትሔ አካል አድርጎ ማየት ያስፈልጋል። እስከዛሬ ድረስ የሚጠቆሙት መፍትሔዎች በሙሉ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. መቃብር ላይ ለማድረግ የሚታሰቡ መሆናቸው ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. በተፃራሪው እንዲሠራ አድርጎታል” ይላሉ። ስለዚህ ወደ መድብለ ፓርቲ የሚደረገው ጉዞ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን የችግሩ ብቻ ሳይሆን የመፍትሔው አካል ማድረግ አለበት። በሁለተኝነት፣ አቶ ልደቱ በተመሳሳይ መንገድ “ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመፍትሔው አካል ነን፤ ነገር ግን የችግሮቹም አካል እንደሆንን ማመን አለብን። ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ውስጥ ያሉ ችግሮች በሙሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ውስጥም አሉ። ይህንን አምነን የተሻለ ሁነን ለመገኘት ራሳችንን የመገምገም እና ውስጣዊ ዴሞክራሲን ለመለማመድ መሥራት አለብን” ይላሉ።

ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው፣ “ችግር ስላለ ነው እዚህ ያለነው” በማለት ነው ነገሩን የሚያብራሩት። “ፓርቲ መመሥረት አንችልም፤ ማኅበረሰባችን ለድርጅት ግንባታ ገና ነው፤ አምባገነንም ድርጅቶች አማራጭ ሆነው እንዲያድጉ አይፈልግም፤ ይሄ ወደትግል የመጣንበት ምክንያት ነው። ስለዚህ… ወደትግል የመጣንበት ምክንያት ውጤት ሆኖ ከትግል ሊያስወጣን አያስፈልግም።… ሁሉ ነገር የተደላደለ ከሆነማ ቀድሞውን መምጣት አያስፈልገንም ነበር።” በማለት ችግሩ ስላለ ነው የገባንበት፣ ከውድቀቶቻችን እየተማርን እንቀጥላለን እንጂ ልንቀርፈው በገባነው ችግር ተገፍተን አንወጣም በማለት የፖለቲካ ትግሉ እስኪያፈራ ድረስ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ እንዲቀጥል ይመክራሉ።

አንጋው ተገኝ በሠላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ያለ ወጣት ነው። ፀጉሩን ያጎፍራል። ሲናገር በብዙ ነገሮች እየተደነቀ ነው። አንጋው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አብረሃ ጅራ ወረዳ ኃላፊ በመሆን እጅግ ፈታኝ ጊዜያትን አሳልፏል። የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የሀገሪቱ ክፍሎች መንቀሳቀስ የሚያስከፍለው ዋጋ ከባድ መሆኑን ደጋግሞ ይናገራል። የፓርቲው አመራር ሁኖ በሠራበት ወቅት ፓርቲ ስብሰባ እንኳን ማድረግ እጅግ ከባድ መሆኑን ያስታውሳል። ፖሊስና የደኅንነት ኃይሎች አመራሮቹን እየተከታተሉ ሲያስጨንቋቸው ‹የፓርቲው ሥራ ከሚቆም በሚል አንገረብ ወንዝ ወርደን እየዋኘን እንሰበሰብ ነበር› ይላል። እየዋኘን ሰው ወደኛ በመጣ ቁጥር እየተበታተንን፤ ሰው ራቅ ሲልልን ደግሞ እዛው ውኃው ውስጥ ሰብሰብ ብለን እየተንሳፈፍን ነበር ስብሰባ የምናደርገው የሚለው አንጋው በፓርቲ እንቅስቃሴ ምክንያት ስድስት ጊዜ ከሥራ ተባሮ ስድስት ጊዜ መመለሱን ሲገልጽ አንዳንዴ በሕይወት መቆየቴም ለኔ ግርም ይለኛል እያለ ነው። ይባስ ብሎ በሠላማዊ ትግል ቆርቦ በዚህ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ የነበረው አንጋው ተገኝ የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ ሳይቀርብበት አሁን ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለህ በሚል ምክንያት በመጨረሻ ለእስር የተዳረገ ሲሆን፤ እስር ቤት ሁኖም የታገለለትና የደከመለት አንድነት ፓርቲ ሲፈርስና በእሱ አባባል ‹መፈንቅለ አመራር› ሲካሄድበት ተመልክቶ ያዝናል። ለዚህ ሁሉ መሆን አንጋው ተጠያቂ የሚያደርገው ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ነው። ‹ሕግ የማይገዛው መንግሥት› እያለ ሁሌም ይገረማል። ይህ የኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ ችግር የገዥው ፓርቲ ቅጥ ማጣት ነው ከሚሉት ወገን የሚቀርበው ሐሳብ ትክክለኛ ተምሳሌት ነው።

ከዚህ አሳዛኝ ኹነት መለስ ብለን አርብ ሚያዚያ 28፣ 2008 ከጠዋቱ 4፡30 እስከ 5፡30 ድረስ በአንድ ሰዓት ውስጥ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጆች ለጽሑፉ ግብዓት የሚሆን መረጃ ለማግኘት በማሰብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ መሠረት እንዲሁ አለፍ አለፍ እያልን በአሁኑ ወቅት በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ከሚገኙ ሰባ አምስት ፓርቲዎች መካከል የሃያ አምስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የስልክ አድራሻ ላይ ስልክ የደወልን ሲሆን፤ ከሃያ አምስቱ ሙከራዎች መካከል ሁለቱን ስልኮች ያነሱልን ሕፃናት ሲሆኑ፣ የሰባቱ ስልክ ቢጠራም አይነሳም፤ የዐሥራ አምስቱ ስልክ ደግሞ ከነአካቴው የማይሠራ ሲሆን፤ የአንዱ ብቻ ማለትም ‘የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕብረት’ ስልክ ላይ የፓርቲውን አመራር ልናገኝ ችለናል። በተመሳሳይ ጊዜ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያደረግነው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪም ስልኩ ሊነሳ ባለመቻሉ ማብራሪያ ማግኝት አልቻልንም። እንግዲህ ‹የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫ ሰሞን ግርግር ከመፍጠር ያለፈ ምንም አይፈይዱም የሚለው ሐሳብ እንዲሁ ያለውን ሁኔታ ቀረብ ብሎ ካለማየት የሚመጣ ነው› የሚሉ ተችዎችም ሁሌም የሚፈተኑበት ጉዳይም ይሄው ተቃዋሚ ፓርቲ ተብለው የተመዘገቡት ፓርቲዎች በሚገባቸው ቦታ አለመዋላቸው ነው። ፓርቲዎቹ የስልክ እንኳን አድራሻ የሌላቸው/ቢኖራቸው እንኳን የማይሠሩ ስልኮችን ይዘው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የለውጥ መሠረት ይሆናሉ ብሎ ማሰቡንም ያከብደዋል። ይህ ደግሞ ተቃዋሚዎች የራሳቸው ሥራ ሳይሠሩ ገዥውን ፓርቲ ማውገዛቸው ተገቢ አይደለም የሚለው ሐሳብ ተምሳሌት ነው።

 

ይህ ጽሑፍ በሃገር ቤት ታትሞ በወጣው ውይይት መጽሄት ላይ የወጣ ነው:: በሃገር ቤት ያላችሁ መጽሄቱን ገዝታችሁ በማንበብ ጋዜጠኞቹን አበረታቷቸው::

የኦሮሚያ ተማሪዎችና ሕዝብ ተቃውሞ ከማስተር ፕላን ባሻገር – (ከአምባሳደር ተስፋዬ ሃቢሶ)

0
0

“የሰማይ አዕዋፋት እንኳ ማረፊያ አላቸው፣ የሰው ልጅ በቁሙም ሆነ በመቃብሩ ማረፊያ ያጣበት ዘመን ይመጣል ብለን አስበን አናውቅም ነበር፤ ግን እነሆ መጣ፣ ወዴት እንጥፋ?” (ቀሎ ቀዌሳ፣ ጅጌሳ፣ ሻሸመኔ)

“የኔ ደም ለጭቁኑ የኦሮሞ ሕዝብ መብት መከበር የሚፈስ ደም በመሆኑ ደመ ከልብ አይደለሁም። ባልሠራሁት ሥራ ወንጅለው በኔ ላይ የሞት ቅጣት የፈረዱት ንጉሡም ሆኑ ባለሥልጣኖቻቸው ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተገቢውን ዋጋቸውን በዚህችው ሥፍራ እንደሚያገኙ እርግጠኛ ነኝ፣ ይዋል ይደር እንጂ የኦሮሞ ሕዝብ መብትም ሙሉ በሙሉ በታጋይ ልጆቹ ደም የሚከበር መሆኑም የማይቀር ነው።” (የመቶ አለቃ ማሞ መዘምር፣ 1959፣ በስቅላት ከመቀጣቱ በፊት በአደባባይ የተናገረው፣ “ግዝትና ግዞት”፣ ኦላና ዞጋ፣ 1985)

የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት በ19ኛው ምዕተ ዓመት መገባደጃ በዐፄ ዳግማዊ ምኒልክ ከተመሠረተበት ዘመን አንስቶ የኦሮሞ ሕዝብ እንደተቀሩት የ“ዳር አገር” ሕዝቦች ሁሉ ከደረሰበት ኢሰብኣዊ ጭቆናና በደል የተነሳ ምንጊዜም የማይረሳቸው የታሪክ በደሎችና ብሶቶች አሉበት። ከላይ የተጠቀሰው የኦሮሞ ጀግና የመጨረሻ ቃላትም ለሕዝቡ ሙሉ መብት መከበር ሲታገል የከፈለው መስዋዕትነት በመሆኑ ምንም ሐዘን ሳይሰማው በወኔ የሞት ፅዋን ለመጎንጨት መዘጋጀቱን የሚያመላክት የተስፋ ኑዛዜ ነበር። ዛሬ ከ59 ዓመታት መራራ የትግል ጉዞ በኋላ የኦሮሞ ታጋዮች በከፈሉት መስዋዕትነት የኦሮሞ ሕዝብ በርካታ አንፀባራቂ ድሎችን መጎናፀፉ የማይካድ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ መብቱን ለማስከበር ገና ብዙ እንደሚቀረው ለማስተባበል አዳጋች ይሆናል። ይህም ረጅም ጊዜ እንደሚፈጅ አያጠያይቅም፣ የማናቸውንም ብሔረሰብ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ለማስከበር የሚቻልበት ሁኔታ በቀላሉ የሚሳካ አይደለምና። ይህ እስኪሳካ ድረስም እንዳሁኑ በጦር መሣሪያ ጭምር የታገዘ የአመፅ መንገድና ዘዴ በመጠቀም ሳይሆን በሠላማዊ መንገድ ያለማሰለስ መታገል የግድ ይሆናል፡፡ ማናቸውም የጦርነትና የአመፅ ጎዳና ሕገወጥ ከመሆኑም በላይ ላልተገመቱና ላልታሰቡ አደጋዎች የሚዳርግ ስለሆነ ከዚህ ዓይነቱ አፍራሽ አማራጭ መታቀብ የበሳል ፖለቲካ መሪዎችን የቅርብ አመራር ይጠይቃል።

oromia

መጀመሪያ “ቤትን ማጽዳት”

የአዲስ አበባና የአጎራባች ኦሮሚያ ከተሞች የኢኮኖሚ ትስስር ጥያቄም ሆነ ሌሎች የመብት ጥያቄዎች ተአማኒነት ያላቸው ክቡር ዓላማዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች ለማቅረብ የአመፅን መንገድ መከተል በሞራልም ሆነ በሕግ አግባብ ተቀባይነት የላቸውም። አመፅ ሌላ አመፅን ይወልዳል፡፡ የሰዎችን ሕይወትና ንብረት ያወድማል፣ ከሁሉም በላይ ሠላማዊ ዜጎች ለሞትና ለመፈናቀል ይዳረጋሉ፣ የመንግሥትና የባለሀብቶች ንብረት ይወድማል። የውጪ እና የውስጥ ኢንቨስትመንትን ያመክናል፣ በግለሰቦችና በማኅበረሰቦች ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል። ይህ በዚህ እንዳለ ቢሆንም፣ ባለፉት 25 ዓመታት የኦሮሞ ሕዝብ የተቀዳጃቸው ድሎች በርካታ መሆናቸው ባይካድም፣ በዚህ ረገድ ምን ያህል መብቱን አስከብሮ እንደሆነና ምን ምን እንደሚቀሩት ፍርዱን ለሕዝቡ ለራሱ መተውን እመርጣለሁ፣ ዛሬም የኦሮሞ ልጆች ለሕዝባቸው የተሟላ መብት ሲታገሉ የሚደርስባቸው ሞትና መስዋዕትነት አሁንም አልተገታምና።

ከሁሉም በላይ ማንንም ጤነኛ አእምሮ ያለውን ዜጋ እርር ድብን እንዲል የሚያስገድደው ጉዳይ፣ 400 ያህል የኦሮሞ ልጆች ተገድለውና በብዙ ሺሕዎች የሚገመቱ ወገኖች በየአካባቢው እስር ቤቶች ታጉረው እንደሚገኙ ታውቆ በዚህ የተነሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት በነዚህ ግድያ የተሰማውን ሐዘንና ቁጭት ገልፆ ሕዝቡን ይቅርታ በመጠየቅና ለነዚህም ተጠያቂ የሚሆኑትን በመለየት እንደሚያስቀጣና ለተጎጂዎች ቤተሰቦች ተገቢውን የደም ካሳ እንደሚያገኙ ካረጋገጠ በኋላ ከሥልጣኑ በገዛፈቃዱ መውረድ የሚገባው አቶ ሙክታር ከድር ለገዳዮቹ የግዳይ መጣያ ይመስል የምስጋናና የሙገሳ መግለጫ በኢቲቪ ማውጣቱ ነው፣ በወገኖቹ ቁስል ውስጥ ስንጥር መስደድ ነው፣ አሳፋሪና አስነዋሪ ታሪክ!

አንዳንዶቻችን እንደምናምንበት፣ ባለፉት አንድ መቶ ዓመታት በኦሮሞም ሆነ በሌሎች ጭቁን ብሔረሰቦች ላይ የደረሰባቸውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ በደሎችና ብሶቶች ለመገርሰስና የታሪክ ቁስለኞችን ለመፈወስ ይቻላል ተብሎ ነበር፡፡ ከአያሌ ዓመታት መራራ ሕዝባዊ ትግሎች በኋላ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገመንግሥታዊ ስርዓት ተዘርግቶ የብሔረሰቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትና ብሔር ተኮር ፌዴራላዊ ስርዓት ሕገመንግሥታዊ ዕውቅናና ዋስትና ያገኘው። በዚህ ሕገመንግሥት መሠረትም ሁሉም ብሔረሰቦች በኢፌዴሪ ሕገመንግሥት ድንጋጌና በፌዴራል መንግሥቱ በተቀረፀው ፖሊሲ መሠረት የየክልላቸውን የመንግሥት ተቋማት፣ መሬትና ሀብት ሁሉ ለማስተዳደር መሉ ሥልጣን አላቸው፤ ያለፌደራል መንግሥቱ ጣልቃገብነት። የብሔር ጥያቄ እና የመሬት ጥያቄ ለነዚህ ሕዝቦች የዘመናት የማንነትና የክብር ጥያቄዎች ነበሩ። እነዚህ መብቶችም ሆኑ ሌሎች ሕገመንግሥታዊ ዋስትናዎቻቸው ሁሉ በማንኛውም ምክንያት በፌዴራል መንግሥቱ ከተደፈሩ ያለፈው የታሪክ ቁስሎች እያገረሹ አዳዲስ ብሶቶችን መውለዳቸው አይቀሬ ይሆናል። ብሶት ወያኔ/ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን እንደወለደ ሁሉ ሌሎች ቡድኖችንም ይወልዳልና። ይህን አጭር መጣጥፍ እንድጽፍና ለአንባብያን እንዳቀርብ ያስገደደኝ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት የተከበሩ አቶ ሙክታር ከድር ሸሞኑን በአሮሚያ አንዳንድ ከተሞችና የገጠር አካባቢዎች ለተቀሰቀሱት የተማሪዎች ተቃውሞዎች፣ ሕዝባዊ ሠላማዊ ሰልፎችና ግጭቶች ተጠያቂና ዋነኛ ምክንያት “ጥቂት የጥፋት ኃይሎች የጎነጎኑት ሴራ” ነው በማለት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና በፌስቡክ ያሰፈሩት መግለጫ እንዲሁም ታኅሣሥ 03፣ 2008 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ የተከበሩ አባዱላ ገመዳ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጡት የዘገየ ሐተታና የኦሮሞን ሕዝብ የመማፀን አቤቱታ ነው።

በእኔ እምነት እነዚህ መግለጫዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችና ግጭቶች ሳይከሰቱ በፊት ቢሰጡ ኖሮ ተአማኒነት ይኖራቸው ነበር፡፡ የብዙ ወገኖች ሕይወትም በከንቱ ባልጠፋ ነበር። ይህ ሁሉ ጥፋት ከደረሰ በኋላ የተሰጡት መግለጫዎች ለማንም ገለልተኛ ታዛቢ እጅግ የዘገዩ፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነትን ለመሸሽ የተደረጉ ከንቱ ሙከራዎች ከመሆን አይዘሉም። አላስፈላጊና ሊመለስ የማይቻል ጉዳት በሕዝብ ወገኖች ላይ ደርሰዋል። እነዚህ መግለጫዎች ቀደም ተብሎ ቢሰጡ ኖሮ በእርግጥም የብዙ ወገኖች ሕይወት በፖሊስና በፀጥታ ኃይሎች ጥይት ባልረገፈ ነበር። ለተከሰቱት ተቃውሞዎች እና ሕዝባዊ ቁጣዎች መነሻና መንስኤ የሆኑትም በዋነኛነት ውስጣዊ እንጂ ውጫዊ ምክንያቶች አይደሉም። ውጫዊ ኃይሎች እና የእነዚህ ፕሮፓጋንዳ መሣሪያ የሆኑት የ‹Oromo Media Network› እና የ‹ESAT› የወሬ ጦርነቶች ያሳደሩት አፍራሽ ተፅዕኖ ቀላል ባይሆኑም እነዚህ ሁሉ በውስጣዊ ድክመቶች ላይ የተመረኮዙ መሆናቸውን ለመካድ አንችልም፣ “ቤታችንን ፅዱ ካደረግን” የውጪዎቹ አሉታዊና አፍራሽ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎች የሚያደርሱብን ጥቃቶች ውስንና ጊዜያዊ ከመሆን በጭራሽ አያልፉም። ይህ ቢሆንም፣ በግንጪ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሕዳር ወር የተቀሰቀሱት ተቃውሞዎችና ሕዝባዊ መነሳሳት በአንድ ክልል የተወሰኑ ከተሞችና ዩኒቨርሲቲዎች የተገደቡና በተማሪዎች የተቀሰቀሱ፣ግልጽ አጀንዳ የሌላቸውና መሪ—አልባ የሆኑ እንቅስቃሴዎች በመሆናቸው ያለውን የክልሉን አገዛዝ ለመገርሰስ አቅም ባይኖራቸውም የራሳቸውን መጥፎ ጠባሳ በክልሉ አስተዳደር እና በአገሪቱ የፖለቲካ ስርዓት ላይ ትተው ወይም አሳርፈው እንደሚያልፉ ጥርጥር የለውም። እነዚህም ተቃውሞዎች የተጫሩት በግንጪው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠገብ ያለው መሬትና ጫካ ያለሕዝቡ ተሳትፎና ውሳኔ ለአንድ ኢንቨስተር በመከራየቱ ነበር። ይህም አካሄድ በዛሬው ገዥዎቻችን ረዘም ላሉ ዓመታት የተቀኘ ስልት እንደሆነ ለመካድ አይቻልም። ይህችን አገር ከድህነት አረንቋ በአጭር ጊዜ መንጭቀው ለማውጣት በሚል ምክንያታዊ እንቅስቃሴ የገዢው ፓርቲና መንግሥት አመራሮች ካለፉት ብዙ ዓመታት ጀምሮ የተከተሉት የማንአለብኝነትና የእናውቅልሃለን አቋም በማንኛውም ታላላቅ የፕሮጀክቶች አቀራረፅና አፈፃፀም ረገድ ሳይቀር (ለምሳሌ፣ የአዲስ አበባና የተለያዩ ከተሞችን መሬት በልማት ሰበብ ለሀብታም ግለሰቦች ማከፋፈል የቀድሞ ነዋሪዎችን በማፈናቀል፣ የዋልድባ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ፣ የደቡብ ኦሞ የስኳር ልማት ፕሮጀክት ፣ የአፋር ክልል የስኳር ልማት ፕሮጀክት፣ የጋምቤላ መሬትን ለውጭ አገሮች ኢንቨስቴሮችና ኩባንያዎች ለረጅም ዓመታት ማከራየት፣ የሱዳንና የኢትዮጵያን ድንበር ለማካለል የታቀደው ውጥን ወዘተ) የሚመለከታቸውን ክልሎች ሕዝቦች ለማሳተፍና ሙሉ ስምምነት እንዲሁም የሚመለከታቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመንግሥት በኩል ፅኑ የፓለቲካ እምነትም ሆነ ተነሳሽነት አለመኖሩን በገሃድ አመላክቷል።

በዚህም የተነሳ የተለያዩ ሕዝቦች ከፍተኛ ቅሬታዎች ስላደረባቸውና የኑሮ ጉዳቶች ስለደረሱባቸው የመንግሥትን ውሳኔ ለመቋቋምና ለመቃወም አቅም ባይኖራቸውም በሁሉም ክልሎች  ውስጥ ውስጡን የሚብላሉና የሚንቦገቡጉ እሳቶች መኖራቸውን መካድ ለአደጋ ይዳርገናልና አስቀድሞ መጠንቀቁ ይበጃል እላለሁ። ሌሎች ሰበቦች እና ምክንያቶች ሁሉ በሁለተኛ ደረጃ ሊጠቀሱ የሚችሉ ጉዳዮች ናቸው። ሁላችንም በቀላሉ ለመገንዘብ እንደምንችለው፣ ማናቸውም ፕሮጀክት (የከተማ ማስተር ፕላንም ሆነ ሌላ) በሠላማዊ መንገድ ተግባራዊና ውጤታማ የሚሆነው በዋናነት ያ ፕሮጀክት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚነካውና የሚመለከተው ሕዝብ ባለው አቅም መጠን ሲሳተፍበትና የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ስለመሆኑ ሙሉ በሙሉ ሲያምንበት ብቻ ነው። ይህ ካልሆነ የፓርቲና የመንግሥት ባለሥልጣናት ስለፕሮጀክቱ ጠቃሚነት ስላመኑበት ብቻ ሕዝብ ይደግፋል እንዲሁም ፕሮጀክቱ ውጤታማ ይሆናል ማለት ሲያንስ የዋህነት፣ ሲብስ ደግሞ አጉል ጀብደኝነት ነው። ሕዝብን ከጥንስሱ ጀምሮ ማሳተፍ የሕዝቡ መሠረታዊ መብቱ ከመሆኑም በላይ ለ‹ዴሞክራታይዜሽን› ሒደትና ለኢኮኖሚያዊ ልማት ማሳለጥ ዓይነተኛ ሚና እንዳለው የማኅበራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎች በአፅንኦት ይከራከራሉ።

 

ዴሞክራሲያዊ መፍትሔ

የሕዝብ ተሳትፎ የአሳታፊ ዴሞክራሲ (participatory democracy) እና የአሳታፊ ልማት (participatory development) ዋነኛ ገጽታ ሲሆን ለማንኛውም ፕሮጀክት ስኬታማነት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። ለዚህም ነው ማናቸውም ፕሮጀክት ትልቅም ሆነ ትንሽ ሲታቀድና ሲጠና በቅድሚያ የሕዝብ ተቀባይነት ይኖረዋል ወይስ አይኖረውም ተብሎ የአሰሳ/የዳሰሳ ጥናት (economic sensitivity test) የሚካሄደው። ዋናው ቁምነገር፣ ሕዝብን ያላሳተፈና ሕዝብ ያላመነበት ማንኛውም ፕሮጀክት ሊሳካ እንደማይችል በርካታ ማስረጃዎች አሉ። በደርግ ዘመነ አገዛዝ የተገነቡት የመቂ ዝዋይ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት እና የሻሾጎ ቦዮ ተመሳሳይ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት (ሀዲያ ዞን) ዓይነተኛ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ የሁለቱም አካባቢዎች ሕዝቦች ሳይሳተፉባቸው ስለተሠሩ ብቻ ምንም እንኳ ጠቃሚነታቸው አጠያያቂ ባይሆንም ልክ የደርግ መንግሥት ሲወድቅ በርካታ ሚሊዮኖች የፈሰሱባቸውን ፕሮጀክቶች ሕዝቦቹ ሆ! ብለው በመውጣት በአንድ ቀን ያፈራረሱዋቸውና ዶጋአመድ ያደረጉዋቸው። ሌላም ምሳሌ ለመጥቀስ ይቻላል፣ አሁንም በደርግ ጊዜ ከውጭ ለጋሾች በተገኘ ብድር በጋምቤላ ወይንም በቤኒሻንጉል ክልል (የውኃ ልማት መሐንዲሶች በትክክል ሊገልጹት ይችላሉ) የውኃ ጉድጓዶች ተቆፍረውና የማሰራጫ ቧንቧዎች ተዘርግተው ንጹሕ ውኃ ለነዋሪዎቹ ሲቀርብላቸው አንጠጣም ብለው እርፍ፣ ምነው ቢባሉ፣ አባቶቻችን እና አያቶቻችን ከተቀበሩበት ሥፍራ ተቆፍሮ የወጣውን ውኃ እንዴት እንጠጣለን? የሚል ቁርጠኛ አቋማቸውንና ውሳኔአቸውን ገለጹ። ምነው ያ ሁሉ የገንዘብና የጉልበት ወጭ ሳይወጣ በፊት ሕዝቡን ማሳተፍና ማማከር ቢቀድም ኖሮ። ዛሬ በኦሮሚያ እና በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ብልጭ ድርግም የሚሉ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችና ግጭቶች እየተከሰቱ ያሉትም በዋነኝነት ይህ መሠረታዊ መርሕ ባለመከበሩና የሕዝብ ተሳትፎ ባለመኖሩ እንደሆነ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገዥዎቻችን ተገቢውን ግንዛቤ ማግኘት አለባቸው። “ጢስ በሚታይበት እሳት አይጠፋም” እንዲሉ፣ ይህ ሁሉ ሕዝባዊ ተቃውሞ እየተካሄደ እንደሆነ እየታዘብን ምንም እንከን በመንግሥት በኩል የለም፣ ምንም ጥፋትና በደል በሕዝብ ላይ አላደረስንም በሚል አቋም የሴራ ኅልዮት (Conspiracy Theory) እየጠቀሱ እና “የጥቂት የጥፋት ኃይሎች ሴራ” እያመካኙ ለመከላከል መሞከር ብቻውን ፍቱን መፍትሔም ሆነ አሳማኝ ምክንያት ሊሆን አይችልም። “ጦር ከፈታው፣ ወሬ የፈታው”፣ እንዲሉ ለችግሮቻችን ውጫዊ ምክንያቶች መደርደር (እንዳለፉት አገዛዞች ሁሉ) የራሳችንን ድክመቶች አለመቀበልና “ለጥፋት ኃይሎች ሴራ” የማይገባውን ሚናና ዕውቅና መስጠት ነው።

ይህ የማያዋጣ ታክቲክ እና ‹ስትራቴጂ› መከተል ይሆናል። አሁን በኦሮሚያ አካባቢዎች ለተከሰቱት ተቃውሞዎች ዋነኛ መንስኤ ለአዲስ አበባ ከተማና ለአጎራባች የኦሮሚያ ከተሞች የልማት ትስስር የታቀደውን ማስተር ፕላን በተመለከተ የክልሉ ተማሪዎችና በኦሮሞ ሕዝብ ሥም የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዚህ ፕሮጀክት ረገድ ከዕቅዱ አንስቶ ስላልተሳተፉበትና ስላላመኑበት እንዲሁም ስለጠቀሜታውም ከፍተኛ ጥርጣሬ ስላደረባቸው ይህንኑ ሥጋታቸውን ለመላው የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ በማዛመታቸው እንደሆነ በግልጽ የምናየው የአደባባይ ምሥጢር ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከዛሬ ስድስት ወር በፊት ግንቦት 17፣ 2007 በተካሄደው አገርዐቀፍ ምርጫ የኦሮሞን ሕዝብ መሬት አንቀጥቅጥ ድጋፍና ሙሉ ይሁንታ አግኝቼ (100%) ተመርጫለሁ ያለው ኦ.ሕ.ዴ.ድ. ዛሬ ከስድስት ወሮች በኋላ የሕዝባዊ ድጋፌን መሠረት “የጥፋት ኃይሎች” ተቆጣጥረውብኛል ብሎ በአደባባይ ማወጅ የሚያሳፍር ኑዛዜና የሚያስገምት ትዝብት ከመሆን አያልፍም።

በኔ የግል እምነት፣ በማስተር ፕላን ሰበብ የተነሳው ተቃውሞ ለረጅም ጊዜ ሲፈፀም የቆየው የገጠር መሬት ነጠቃና የገበሬዎች መፈናቀል ያስከተለው ብሶት ቢሆንም የአገራችንን የፖለቲካ ስርዓት ካንሰር እንጭፍጫፊ ምልክቶች (symptoms) የሚመለከት እንጂ ራሱን ካንሰሩን ዓላማ ያደረገ የጦርነት ትግል አይደለም። ለዘመናት የተሰራጨው ካንሰር፣ በአገራችን ደገኛ ገዥዎችና ፖለቲከኞች (highlanders) ዘንድ ለዘመናት ተንሰራፍቶ የቆየው “እኛ ካልመራን አገር ትበታተናለች የሚል አጉል ቅዠትና” አምባገነናዊ የፖለቲካ ስርዓት፣ የሰጥቶ መቀበልና የመቻቻል ባሕል አለመኖር (absence of culture of compromise and tolerance) እና የቂም በቀል፣ የተንኮልና የዱለታ/ሴራ ባሕል መንሰራፋት ሲሆኑ በሌላው ወገን ባለፉት ዘመናት የታሪክ በደሎች (historical injustices) ደርሰውብናል፣ “አበሾችን (ሰሜኖችን) ማመን ቀብሮ ነው” በማለት የተለየ ዋስትና የሚሹና የታሪክ እስረኞች የሆኑ ብሶተኞች የሚያሳዩት የመገንጠል እና የመለያየት አዝማሚያዎች ናቸው፤ በትምክህተኝነትና ትምክህተኝነት በወለደው የጠባብ ብሄርተኝነት መካከል የሚካሔድ ግብግብና ፍትግያ። ሌላው ብሔራዊ ሳንካ በአገሪቱ ብሔረሰቦች ልኂቃን መካከል ላለፉት 25 ዓመታት በተዘረጋው የፖለቲካ ስርዓት ላይ ብሔራዊ መግባባት (national consensus) አለመኖሩ ነው። በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የፖለቲካ ግብግብ በአገሪቱ ማኅበራዊ ኃይሎችና ልኂቃን መካከል እያገረሸ በመሄድ ላይ ይገኛል። ስለዚህም የፖለቲካ ችግሮቻችን ምንጮች በወሳኝነት ውስጣዊ እንጂ ውጫዊ አይደሉም። ስለዚህም ሁሉንም የፖለቲካ ልሂቃን ወደመቀራረብና ወደውይይት መድረኮች መሳብ የገዢው ፓርቲና መንግሥት ጥበብ ይሆናል እንጂ የሚያስገምት ውርደት አይሆንም፣ ካወቁበት።

በእኔ እምነት በዋናነት መጠቀስ የሚገባቸው ችግሮችና ተግዳሮቶች ብዙዎች ናቸው፣ በዚህ ረገድ። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገመንግሥታዊ ስርዓት እና ፌደራላዊ አደረጃጀት በተግባር በሚያስተማምን ሁኔታ አለመተርጎምና የሕግ የበላይነትም ሆነ የመልካም አስተዳደር አለመኖር፣ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በተሟላ ሁኔታ አለመከበር በዋነኛነት የሚጠቀሱ ችግሮች ናቸው። በዚህ ረገድ፣ በርካታ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች፣ ፖለቲከኞች እና የሙስሊም መሪዎች በየሰበብ አስባቡ በእስር ቤቶች ታጉረው ይገኛሉ። የዴሞክራሲ ተስፋ፣ የፕሬስ ነጻነትና የሲቪል ማኅበራት እየደበዘዙና እየተዳከሙ በመሔድ ላይ ይገኛሉ፣ በሐሳብ የመለየት ነጻነት (the freedom to differ) የለም ለማለት ይቻላል። የአገሪቱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሪሶርስስ በአገሪቱ ብሔረሰቦችና ማኅበረሰቦች መካከል በተመጣጣኝ ሁኔታ የተከፋፈሉ አይደሉም፤ ለአንድ ብሔረሰብ አባላት ብቻ ያጋደለ ነው የሚል ከፍተኛ ቅሬታ በተለያዩ ብሔረሰቦች የፖለቲካ ልኂቃን ዘንድ በሰፊው የሚስተጋባ ስሞታ አለ። በተጨማሪም የተለያዩ የፌደራል መንግሥት ተቋማት የአገር መከላከያና የደኅንነት መ/ቤቶች ጭምር የሕገመንግሥቱን ድንጋጌዎች በሚጥስ ሁኔታ የአገሪቱን በሀውርታዊነት የሚያንፀባርቁ እንዳልሆኑና አድልኦዎች እንደሚስተዋሉ ከረር ያሉ ስሞታዎች በሰፊው ይነገራሉ።

በሌላው ረገድ የፓርቲውና የመንግሥት ባለሥልጣናት ከፌደራል እስከ ክልሎች በሙስና፣ በኪራይ ሰብሳቢነት እና በብልሹ አሠራር ህፀፆች የተጨማለቁ እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ሆኗል፣ ባለፉት ዓመታት ብቻ እነዚህ ባለሥልጣናት የምዝበራ ሰንሰለታቸውን በመዘርጋት በየዓመቱ ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ካፒታል ወደውጭ አገሮች ባንኮች ሲያሸሹ እንደነበረ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እየገለጹና እያስጠነቀቁ ናቸው። በየእስር ቤቶች ከታጎሩትና ከሚሰቃዩት ብዙ ሺሕ እስረኞች መካከል 95% የሚያህሉት የኦሮሞ ልጆች እንደሆኑ ብዙ የቀድሞ እስረኞች በተለያዩ ጊዜያት መስክረዋል። እነዚህ ሁሉ ቅሬታዎች በሕዝቦች ዘንድ በሰፊው የተሰራጩና የናኙ መረጃዎች ናቸው። ይህ ብቻ አይደለም። የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የፍትህ ተደራሽነት የትየለሌ መሆን አንገብጋቢ ጉዳዮች ናቸው። የአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ቀስ በቀስ ለተቃዋሚዎች እየተዘጋ መምጣት ሌላው አሳሳቢ ችግር ነው፣ በዚህም የተነሳ የተቃዋሚው ጎራ ድምፅ መታፈንን አስከትሏል። የኑሮ ዋጋዎች እየናሩ መሔድና ሕዝቡ በየዕለቱ የሚያጋጥሙት የኑሮ ችግሮች ሌሎቹ ማነቆዎች ናቸው። የሕግ የበላይነትና የሰብኣዊ መብቶች አለመከበር ያስከተሉዋቸው ቅሬታዎችና ብሶቶች ናቸው። በዚህም የተነሳ እነዚህ ችግሮች ተደማምረው ከፍተኛ ውጥረቶችን ለመፍጠር በቅተዋል፣ የተወጠረና የከረረ ነገር ሁሉ ጊዜውን ጠብቆ መበጠሱ አይቀሬ ነውና ታፍኖ የነበረው የሕዝብ ወገኖች ብሶት አሁን እየፈነዳ ነው፣ ተቃውሞዎች እየተስፋፉ ናቸው። ማናቸውንም የመንግሥትን ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች ከመተግበራችን በፊት አስቀድሞ እነዚህ ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች/ፕሮጀክቶች በቀጥታ የሚመለከቱዋቸውን ወገኖች (ግለሰቦችም ሆኑ ማኅበረሰቦች) ማወያየትና ማሳመን የዴሞክራሲ ‹ሀሁ› ይመስለኛል።

አብዛኛውን ጊዜ በፓርቲውና በመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከላይ ወደታች በሚተላለፉ ውሳኔዎች ብቻ የሚተገበሩ ፖሊሲዎችና ፕሮጄክቶች ናቸው ሲፈፀሙ የነበሩት። የዚህ ዓይነቱ ኢዴሞክራሲያዊ አሠራር በሰፈነበት ሁኔታ ሲፈፀሙ የቆዩት የሕዝብ ወገኖችን ያፈናቀሉ ፕሮጄክቶች ባስከተሉዋቸው ምሬቶችና ብሶቶች የተነሣ ዛሬ በየአካባቢው ብልጭ ድርግም የሚሉ የተቃውሞ ሠልፎችና ግጭቶች እየተባባሱ እንጂ እየቀነሱ ሊሄዱ አይችሉም። የኃይል እርምጃዎችን ለመውሰድ ከመቻኮል ይልቅ ቆም ብሎ መፈተሽ፣ ጥፋቶች እና ስህተቶች/ጉድለቶች ካሉ ማረምና ማስተካከል ይበጃል። አሁን በኦሮሚያ በአንዳንድ ከተሞችና አካባቢዎች የተቀጣጠሉትን ተቃውሞዎች ለማብረድና ልማታዊ ጉዟችንን በሠላም ለመቀጠል ከተፈለገ በጨፌ ኦሮሚያ፣ በኦ.ሕ.ዴ.ድ. ሥራ አስፈፃሚና በካድሬዎች ደረጃ እንዲሁም በኦሮሞ ሕዝብ ሥም በሠላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካ ፓርቲዎች አስቸኳይ ስብሰባዎችን በመጥራት መወያየትና መፍትሔ መፈለግ ጊዜ የሚሰጥ አጀንዳ አይመስለኝም። ከሁሉም በላይ የኦሮሞን ሕዝብ (ወጣቱንም ሆነ አዛውንት ሳይቀሩ) ማነጋገርና ማሳመን የግድ ይሆናል። ሕዝብ ሲባል ደግሞ የኦ.ሕ.ዴ.ድ. አባላትና ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የዞኑን/የወረዳውን የኦሮሞ ሕዝብ (የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን አባላትና ደጋፊዎች ጭምር) የሚያጠቃልል መሆን ይኖርበታል፡፡ እነዚህ እኮ ሌላ አገር፣ ሕዝብና መንግሥት የላቸውም፡፡ የሚገዙትና የሚተዳደሩት በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. አገዛዝ ስር ነው፡፡ ታክስ የሚከፍሉትም ለዚሁ አገዛዝ ነው። በተለይ ደግሞ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ከገዛ መሬታቸው የሚፈናቀሉት ወገኖች በቅድሚያ ሳይወያዩበት፣ ሳይስማሙበትና ተገቢው ክፍያ በወቅቱ ሳይከፈላቸው እንዲሁም በዘላቂነት የሚቋቋሙባቸውን ‹ፕሮጀክቶች› በቅድሚያ ሳያዘጋጁ የመንግሥት ባለሥልጣናት የሚተምኑትን ገንዘብ ብቻ እንደምፅዋት እየቸሩና እያከፋፈሉ ዜጎችን መሸኘት እስከዛሬ ድረስ እነዚህን ምስኪን ወገኖች ለከፉ ችግሮች ሲያጋልጡዋቸው እንደነበር በውል ማጤንና እነዚህን ህፀፆች በአስቸኳይ ማረም አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑ ሊጤን ይገባዋል፡፡ የሰማይ አእዋፋት እንኳ ማረፊያ አላቸው፡፡ የሕዝብ ወገኖችን ማረፊያ ማሳጣት በሕይወት እያሉ ብቻ ሳይሆን ሞተው ተቀብረውም ሳለ የግፍ ግፍ ነው። ይህ አሠራር ይዋል ይደር እንጂ ጊዜን ጠብቆ የሚፈነዳ ቦምብ ከመቅበር የተለየ ውጤት እንደማይኖረውም አርቆ ማስተዋል ብልህነት ነው፤ “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ”፣ ነውና። በልማት ሰበብ እስከመቼ የወገኖቻችንን ህይወት በጅምላ እየቀጠፍን ለመቀጠል እንችላለን? አንዳንድ ጊዜ ‹tactical retreat› ሽንፈት ሳይሆን ቆም ብሎ ለመንደርደር የሚያግዝ ስትራቴጂ ነውና በጥሞና ታስቦበት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ጭምር ለማዘግየት ወይንም ከነጭራሹ ለመሰረዝ መወሰኑ አማራጭ ላይኖረው ይችላል። በመጨረሻም እየገነባን የምንገኘው የፖለቲካ ኢኮኖሚ፣ ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደመሆኑ መጠን የዴሞክራሲ እና የኢኮኖሚ ልማት ጎን ለጎን የሚገነቡ ግቦች እንጂ ተነጣጥለው የሚካሄዱ ትግሎች አይደሉም። የዴሞክራሲም ሆነ የኢኮኖሚ ልማት ዓላማ ዞሮ ዞሮ የሰው ልጆች ልማትና ደኅንነት እንዲፋጠንና እንዲለመልም እንጂ በሰዎች የግፍ ጭፍጨፋና በሰብኣዊ መብቶች መቃብር ላይ የሚከናወን ትርኢት ሊሆን አይገባም። ስለዚህም ለሰብአዊ መብቶችና ለሰው ልጆች ደኅንነት፣ ለተረጋጋ ሠላምና የሕግ የበላይነት መከበር ሌት ተቀን በተጠንቀቅ እንቁም።

ይህ ጽሁፍ በሃገር ቤት ታትሞ በሚወጣው ውይይት መጽሔት ላይ ወጥቷል:: በሃገር ቤት ያላችሁ መጽሄቱን ገዝታችሁ በማንበብ ጋዜጠኞቹን አበረታቷቸው::


ትውልድ የሚሻገር መፍትሔ: እንዴት? –ሰቦቃ ዋቅቶላ

0
0

የዚህ ፅሁፍ ፀሐፊ የየትኛውም የ ፖለቲካ ድርጅት አባል አይደለም:: ሃሳቡም የግሉ ነው::

imagesየ ዛሬዋ ኢትዮጵያ የህዝቦችዋን የፖለቲካ ጥያቄን ፈትቻለሁ ብላ ብትፎክርም: ያው የተለመደ መፈክር ብቻ ከመሆን የዘለለ አይደለም:: ተደጋግሞ አንደሚባለው አሁን ያለው ህገ መንግስት አናሳ በሆነው ነገር ግን በታሪክ አጋጣሚ የመሳሪያ የበላይነት ያገኘው ወገን የፖለቲካ ፍላጎቴን ያስጠብቅልኛል በሚል ያረቀቀው: የመሳሪያ የበላይነቱን ተጠቅሞ ያስፀደቀው ነው:: ህገ መንግስቱ የፈታው የፖለቲካ ጥያቄ ቢኖር: የመሳሪያ የበላይነት ያገኘውን የትግራይ ብሔር ጥያቄ ብቻ ነው:: የ አንድ ብሄር  የፖለቲካ ቡድን: ከሌሎች የፖለቲካ ቡድኖች ጋር ትርጉም ያለው ወይይት አና ድርድር ሳያደርግ: እንዲያውም ተቃዋሚዎቹን አጥፍቶ ለመጨረስ በዘመቻ ላይ ሆኖ:  ያቀረበው ‘እኔ አውቅልህ’ መፍትሄ: የኢትዮጵያን የብሔር ጥያቄ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት የነበረውን ዕድል ገደል የከተተ: ለአንድ ወይም ለብዙ መቶ አመታት ሊቆይ የሚችል ህገ መንግስት የመቅረጽ ዕድል ያጨናገፈ ነው::

ትውልዶችን ሊሻገር የሚችል መፍትሄ ማቅረብ : የህዝቦችን የፖለቲካ ፍላጎቶች  ማወቅ ይጠይቃል:: የህዝቦች የፖለቲካ ፍላጎት ለማወቅ ደግሞ ዲሞክራሲ ቅድመ ሁኔታ ነው:: ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ዕድል አግኝተው  የፖለቲካ ፍላጎታቸውን በቀጥታም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲ በመምረጥ ወይም በሌላ መንገድ ሊወስኑ ይችላሉ: በዚህን ጊዜ የአንድ ህዝብ የፖለቲካ ፍላጎት ታውቆል ማለት ይቻላል:: ‘እኔ አውቅልህ’ የፖለቲካ አራማጆች ቅድመ ሁኔታ የሆነውን የህዝብን በ ነጻ የመደራጀት: የመሰብሰብ: ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ የመሳሰሉትን ዲሞክራሲያዊ መብቶች አፍነው የህዝቦችን የፖለቲካ ፍላጎቶች ራሳቸው ይወስናሉ::

ትውልዶችን ሊሻገር የሚችል መፍትሄ ማቅረብ : ለሕዝቦች የፖለቲካ ፍላጎቶች ምላሽ መስጠት ይጠይቃል:: ለሕዝብ የ ፖለቲካ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት መሰረቱ የህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ እንጂ የመሳሪያ የበላይነት የያዘው ቡድን ፈቃድ አይደለም:: በመሳሪያ የበላይነት ስልጣን የያዙ የፖለቲካ ቡድኖች በእኔ አውቅልህ የህዝቦችን የፖለቲካ ፍላጎቶች እንደሚወስኑ ሁሉ ለሕዝቦች የፖለቲካ ፍላጎቶች ምላሽ የሚሰጡት ራሳቸው  በፈቀዱት ልክ ብቻ ነው::

ህወሀት/ ኢህአዲግ ያቀረበው መፍትሄ የህወሐትን የበላይነት ለዘለቄታው የሚያስጠብቅ ነው:: የዚህ ፅሁፍ አላማ መፍትሄዎቹን በዝርዝር የመቃኘት አይደለም:: ብዙዎችም ብዙ አንደፃፉ አገምታለሁ: ነገር ግን በጥቂቱ ላንሳው::  የ ህወሐት ታጋዮች የ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አሾሾም ና ስልጣን እንዲሁም : የፕሬዚደንቱን አሾሾምና ስልጣን ሲወስኑ: የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ከ ህወሐት ቁጥጥር አንዳይወጣ አድርገው ነው:: ኢህአድግ ያለ ህወሀት ስውር ሆነ ግልፅ መሪነት ህልውና አይኖረውም:: የኢሕአድግ መሪ  ደግሞ ሁልጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሆናል:; ታጋዮቹ የክልልና የፌደራል ግኑኝነቶችንና የሀብት ክፍፍል ሲወስኑ የክልሎች ጠቃሚ ሀብቶች በሙሉ በ ፌዴራልና በሕህወሐት ስር አንዲሆኑ በማድረግ ነው:: ከዚህም በተጨማሪ ታዋቂውን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት በሕገ  መንግስቱ ሲያካትቱ “እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው” እንዲሉ ነው:: የፍንፍኔ/ አዲስ አበባ የፖለቲካ ስልጣን መነፈግ የህወሀት ታጋዮችን የፖለቲካ ፍላጎት የማሳካት አላማ ያለው እንጂ አንዳዶች እንደሚያስቡት የ ኦሮሞ ን ህዝብ ፍላጎት ለመጠበቅ አይመስለኝም::

ከዚህ ብዙ ልንማር ይገባናል:: ከአንድ ትውልድ የማይሻገር ህገ መንግስት ከእንግዲህ ሊኖረን አይገባም:: ከ እኔ አውቅልህ ፖለቲካ መላቀቅ ይኖርብናል:: የፖለቲካ ድርጅቶች ሊታገሉለት የሚገባ ነገር ቢኖር  የህዝቦች መሰረታዊ  መብቶች እንዲከበሩ ነው:: ህዝቦች የሚፈልጉትን እንደሚያውቁ ከልብ መቀበል ያስፈልጋል::

አንዳንድ ጊዜ በመንግስት ሚዲያ ላይ ተቃዋሚዎች ሲከራከሩ እሰማለሁ:: ዋናው ጉዳይ ሁልጊዜ ይድበሰበሳል:: እንደኔ አመለካከት ዋናው የ ፖለቲካ ጉዳይ አሁንም የብሔር ጥያቄ ነው:: የክልሎች አና የ ፌደራል ግኑኝነት ጥያቄ ነው:: ይህ ጥያቄ ሰፊ ነው:: የ ኦሮሞ ህዝብ አና የ ፖለቲካ ድርጅቶች ለረጅም ጊዜ ሲያነሱትና ሲታገሉለት የቆዩትን ጥያቄ የያዘ ነው:: ይህ ጥያቄ በኦሮምያ ክልል ውስጥ ያሉትን ከኦሮሞ ዉጭ ያሉ ህዝቦችን ይመለከታል:: ይህ ጥያቄ በፍንፍኔ/አዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩትን የተለያዩ ህዝቦችን ይመለከታል:: የ ኦሮሞ ህዝብ በፌደራል መንግስት ላይ የሚያነሳው የ ይገባኛል ጥያቄ የአማራና የሶማሌ የትግራይ እንዲሁም የሁሉንም ሌሎች ህዝቦችን ይመለከታል:: ይህ ጥያቄ ከ ኦሮሞ ዉጭ ያሉ ሌሎች ህዝቦች ከፌዴራል መንግስት ጋር ባላቸው ግንኙነት የሚያነሱትንና  የሚታገሉለትን  የስልጣን ክፍፍል ጥያቄዎች የያዘ ነው::

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ አይዶሎጅን መሰረት አድርገው የሚደራጁ መኖራቸው ይታወቃል:: ዋነኞቹ ሊበራል ዲሞክራሲን እንከተላለን ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ ሶሻል ዲሞክራሲን እንከተላለን ይላሉ:: ህወሀት/ ኢህአድግ ደግሞ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ነኝ ይላል/ አንዳንዴም ነጭ ካፒታሊስት/ ነኝ ይላል::  እነዚህ የፖለቲካ ቡድኖች በላይኛው ፓራግራፍ በተመለከተው ጥያቄ ግልፅ ልዩነት አላቸው:: ከ አድዮሎጂ ልዩነት ይልቅ ዋናው ልዩነታቸው አሱ ይመሰለኛል:: በክልልና በፌደራል ግኑኝነት ላይ ያላቸውን ፕሮግራም በቅጡ ሳይፈተሽ ወደ ፖለቲካ ሰልጣን ቢመጡ የራሳቸውን ዲዛይን በህዝቦች ፍላጎቶች ላይ አንደማይጭኑ ምንም ዋስትና የለም::

የፖለቲካ ድርጅቶች በክልልና የፌደራል ግኑኝነት ላይ ግልፅ የሆነ ፕሮግራም ሊኖራቸው ይገባል:: እንደ አኔ አመለካከት  የክልሎችና የፌደራል ግኑኝነት በዲሞክራሲያዊ መንገድ በሕዝብ ይወሰናል የሚሉትም ወገኖች ሆኑ: ግልፅ አቆም የያዙት ወገኖች የሕዝብን መደናገር በመቀነስ በኩል ምስጋና የሚገባቸው ናቸው:: በ ዲሞክራሲያዊ መንገድ ይወሰናል የሚሉት በዲሞክራሲያዊ ባህል አመኔታን  መገንባት አለባቸው::

የፌደራልና የክልል ግኑኝነት ጥያቄ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ቁልፍ ጥያቄ ነው:: የፌደራል አና የክልል ግኑኝነት ምንም ማሻሻያ አያስፈልገውም  በሚለው በ ህወሀት ኢህአድግ ዘንድ: ጥያቄውን ማንሳት የሕገ መንግስቱን የበላይነት አለመቀበል ነው:: የፌደራል አና የክልል ግኑኝነት ጥያቄ በሌሎች  ወገኖች ደግሞ የ ኢትዮጵያን አንድነት አንደማዳከም ይወሰዳል:: የፌደራልና የክልል ጥያቄ የብሔር ጥያቄን በሚያነሱ ህዝቦች የህልውናቸው መሰረት: ጭቆናን የሚከላከሉበት: እኩልነታቸውን የሚያረጋግጡበት: ከሌሎች ህዝቦች ጋር የማይጋሩትን የራሳቸው የሆነውን ታሪካቸውን የሚያስተምሩበት:ባሕላቸውን የሚያሳድጉበት ዋስትና ሆኖ ይቀርባል::

የህወሀት ኢህአድግ የብሔር ጥያቄን በዋነኛነት ሲያቀንቅን አንዳልነበረ ሁሉ በአሁኑ ጊዜ የብሔር ጥያቄን የሚያነሱ ወገኖችን ሁሉ በዘረኝነትና በሽብርተኛነት በመክሰስ ላይ ነው:: ይኽም የሕገ መንግስቱ አላማ የ ኤርትራ ከ ኢትዮጵያ መገንጠል ሽፋን ለመስጠትና የትግራይን ህዝብ የብሔር ጥያቄ የመመለስ ውስን አላማ ብቻ አንዳለው ያረግግጣል:: የብሔር ጥያቄ የኢትዮጵያን አንድነት ያዳክማል የሚሉ ወገኖች “ኢትዮጵያ” ሲሉ ሚዛናውነት ሲለቁ ይታያል:: የራሳቸው ብሔር ታሪክና ባህል: ከኢትዮጵያ ታሪክና ባህል ለይተው ማየት ይሳናቸዋል :: የነሱ ብሔር ታሪክና ባህል  ከሌሎች ብሔሮች  ባህልና ታሪክ እኩል ሲሆን ሊደሰቱ እንጂ ሊከፉ አይገባም ነበር:: የኢትዮጵያ ብሔሮች ጥሩም ሆነ መጥፎ: የጋራ ታሪክ አላቸው:: የጋራና የግል ታሪካቸው ላይ መግባባት ይኖርባቸዋል:: የጋራ ታሪኩም ብቻ የኢትዮጵያ ታርክ ተብሎ ሊገለፅ ይገባል::

ሁሉም የፖለቲካ ሀይሎች: የሀወሀት/ ኢህአዴግ የፖለቲካ ሀይል: የአማራ ብሔር: የኦሮሞና የሌሎች የብሔሮች የፖለቲካ ሀይሎች ለሰላማዊውም ሆነ ውጤታማ የሆነ የፖለቲካ ሰልጣን ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ እዱሉ አላቸው::

የህወሀት ኢህአድግ የፖለቲካ ሀይሎች ፀሐይ አየጠለቀች መሆኑን መቀበል አለባቸው:: የህወሀት ኢህአዲግ የፖለቲካ ስልጣን ለጅትማሲ የነበረው የብሔር በሄረሰቦች መብት መከበር ጥያቄ የኦሮሞ ተቃውሞን: የጋምቤላን: የወልቃይትን: በደቡብ ኢትዮጵያ የተነሱ ተገቢ ጥያቄዎችን: በሀይል ለመመለስ ሀወሀት/ ኢህአድግ በወሰደው እርምጃ እርቃኑን ቀርቶል:: የህወሀት ኢህአዲግ ለራሱ ልማታዊ መንግስት የሚል ለጅትማሲ ለመፍጠር ቢሞክርም: ይኽ ምክንያት የውጭ መንግስታትን ከሚያማልል በስተቀር በሀገር ውስጥ ከጅምሩም ተቀባይነት ያገኘ አይደለም::

የህወሀት ኢህአዴግ የፖለቲካ ሀይሎች በሰላማዊ መንገድ የሰልጣን ሽግግር አንዲያደርጉ የታሪክ ሀላፊነት አለባቸው:: ይኽንን በሁለት አይነት መንገድ ማድረግ ይችላሉ:: የመጀመሪያው መንገድ በሀገሪቱ በጠቅላላ ነፃ አና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲደረግ ማድረግ ነው::  ይኽም በአንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ በሀገር ውስጥ አንዳይንቀሳቀሱ የወጡ አዋጆችን መሰረዝና: ለነዚህ የፖለቲካ ሀይሎች በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ዋስትና መስጠትን ይጠይቃል:: የምርጫውን ውድድር የሚመራው አካል በተወዳዳሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነትን ያገኘና ዋስትና ያለው መሆን ይኖርበታል:: ምርጫው በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች የሚመራ ሆኖ ቢቻል የተባበሩት መንግሥታት በዋነኛት የታዛቢዎችን ቡድን አንዲመራ መደረግ አለበት:: ሀወሐት ኢህአድግ በፓርላማ አብላጫ ድምፅ ላገኘው የ ፖለቲካ ድርጅት ስልጣኑን በማሸጋገር ታሪክ መሰራት ይችላል:: በምርጫው ሂደት በአሁኑ ወቅት ያለው የፖሊስ ሰራዊትና የመከላከያ ሰራዊት ሚና የህገር ውስጥ ሰላምና የውጭ ጥቃትን በመከላከል መወሰን አለበት::

የህወሀት ኢህአድግ የፖለቲካ ኃይሎች ሌላ ሊያደርጉት የሚችሉት አሁንም  በአንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ በሀገር ውስጥ የመንቀሳቀስ ገደብ የሚጥሉትን አዋጆችና ዉሳኔዎች በመሻር: ከሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በመወያየትና በመደራደር ትውልድ የሚሻገር መፍተሄ መፈለግ ነው::

የህወሀት ኢህአድግ የፖለቲካ ቡድን የአንድን ብሔር ጥያቄ ከመመለስ ውጭ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ትርጉም ያለው የፖለቲካ መፍትሄ ያለመጣ ቢሆንም: ከሌሎች ብሔሮች ቀላል የማይባል የፖለቲካ ሀይል አሰልፎል:: ይኽ አሰላለፍ ግን ዘላቂነት የሌለውና  በሌላ አማራጭ ማጣት የተፈጠረ አሰላለፍ በመሆኑ  በማናቸውም ጊዜ ሊፈርስ አንደሚችል ሁለት ታላላቅ የፖለቲካ ክስተቶች አመላክተዋል:: የመጀመሪያው የ ፩፱፱፯ ምርጫ ሲሆን ሌላው ደግሞ በአሁኑ ወቅት በመካሄድ ላይ ያለው የኦሮሞ  ተቃውሞ ነው::

ሀወሀት ኢህአድግ በእድሉ ሳይጠቀም ከቀረ ሌሎቹ የፖለቲካ ሀይሎች ትውልድን የሚሻገር መፍትሄ  ለማምጣት መተባበር አለባቸው:: ህወሀት ኢህአድግ ማዕቀብ የጣለባቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች ማዕቀብ ያንሳ ስንል በተመሳሳይ ለሌሎቹም የፖለቲካ ድርጅቶች መስራት አለበት:: የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ከትብብር ውጭ መሆን የለበትም:: በመካከላቸው አስፈላጊ ያልሆነ  ግጭት ሊያመጡ ከሚችሉ ድርጊቶች መቆጠብ አለባቸው:: የትኛውንም የ ፖለቲካ ፕሮግራም ቢያራምዱ: በትብብሩ ሂደት ገና የህዝብ አዎንታ የሚፈልግ ፕሮግራም አንደያዙ አንጂ: በሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ዉሳኔ አዎንታ ያገኘ የፖለቲካ ፕሮግራም አንደያዙ መቁጠር የለባቸውም::  በአሁኑ ውቅት ባገኙት ድጋፍ አና አቅም ተኩራርተው ከትብብር ዉጭ መሆንም  የለባቸውም::

የአማራ የፖለቲካ ሀይሎች መሰረቱ የቀድሞ የፖለቲካ ስልጣን ነው:: ይኽ የፖለቲካ ሀይል በአብዛኛው ቀደም ስል በነበሩ ስርዓቶች ከ አማራው ተራማጅ አስተሳሰቦችን ሲያራምድ የነበረው ክፍል የፖለቲካ አስተሳሰብን የወረሰ ነው:: የዚህ የፖለቲካ ሀይል ደጋፊዎች ከብሄር ጭቆና ዉጭ ስለነበሩ ከሌሎች የፖለቲካ ሀይሎች በተሻለ ያለፉ ስርዓቶች የፈጠሩት የኢኮኖሚና የባህል የታሪክ የበላይነት የነሱ ነበሩ: ህወሀት ኢህአድግ የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ ሆነ የኢኮኖሚ የባህልና የታሪክ የበላይነት ለመያዝ በሚሰነዝረው ጥቃት ሁሉ የመጀመሪያ ኢላማው ናቸው:: ይኽ የፖለቲካ ሀይል በአሁኑ ወቅት  የፖለቲካ ስልጣን የሚያስገኘውን ጥቅም ቢያጣም  የቀዱሙት ስርዓቶች በፈጠሩለት መልካም አጋጣሚ በሌሎች ዘርፎች  የያዘውን የበላይነት አሁንም ሙሉ በሙሉ  አላጣም::  የፖለቲካ ስልጣንም ትግል በማድረግ ላይ ነው:: ፍትህ ዲሞክራሲና አንድነት ማምጣት የፖለቲካ ትግሉ ግብ አድርጎ ይገልፃል:: በህወሓት ኢህአድግ  የፖለቲካ ሀይሎች የፖለቲካ ህይሉ የሚታገለው አማራን ወደ ፖለቲካ ስልጣን ለመመለስ አና የአማራ የፖለቲካ የኢኮኖሚ የባህል የታሪክ የበላይነትን ለማስመለስ የሚታገል የፖለቲካ ሀይል ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን  ነገር ግን አንድ ስንዝር አንዳይራመድ ጥበቃ የሚደረግበት ነው:: ይኽ የፖለቲካ ሀይል በብሄር ጥያቄ ላይ ከሚያራምደው አቆም አንፃር በኦሮሞ ና በሌሎች የብሔር ጥያቄ በሚያነሱ የፖለቲካ ሀይሎች በጥርጣሬ የሚታይ ነው:: የአማራ የፖለቲካ ኃይሎች በሚመሩት አሰላለፍ ከሁሉም ብሔሮች የተሳተፉ ግለሰቦች ባይጠፉም በዋነኛነት በተለይ ከ አናሳ ብሄሮች በርከት ያሉ ደጋፊዎችን ማሰለፍ ችለዋል::  ይኽ አሰላለፍ አናሳ ብሄሮችም የብሔር ጥያቄ ያላቸው በመሆኑ: ዘለቄታው አስተማማኝ  አይመስለኝም::

የኦሮሞ የፖለቲካ ሀይሎች የብሔር ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል:: ይኽ የፖለቲካ ሀይል ከዚህ ቀደም በነበሩ ስርዓቶች በሀይል የተነጠቃቸውን: ያልተመለሱ የፖለቲካ ጥያቀዎችን ለማስመለስ አንደሚታገል ይገልፃል: ይኽ  የፖለቲካ ሀይል የኦሮሞ ህዝብ ከዚህ ቀደም በነበሩ የፖለቲካ ስርዓቶች በሀይል የተነጠቀው: ተመልሶለታል/ይበቃዋል በሚለው ሀወሀት ኢህአድግ የመረረ ጠላት ተደርጎ ተወስዶል:; ይኽ የፖለቲካ ሀይል በራሱ የፖለቲካ ሀይሎች ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን ተመሳሳይ የብሔር ጥያቄ ያላቸው አጋሮች አሉት:: ይኽ የፖለቲካ ሀይል  በአማራ የፖለቲካ ኃይሎችና በሰልፉ ውስጥ በተካተቱት ሁሉ ወዳጅነትን ሲነፈግ ይታያል::

ትውልድ የሚሻገር መፍትሄ ለማምጣት በነዚህ የፖለቲካ ሀይሎች መካከል ወይይት: መተባበር; ድርድር ያሰፈልጋል:: ከትንሽ ወደ ትልቅ የሚያድግ ትብብር ቢሆን ይመረጣል:: ትብብር ማድረግ አስቸጋሪና ፈታኝ መሆኑን በቅድሚያ መቀበል ያስፈልጋል::  በ መሳሪያ ሀይል አንዱ የፖለቲካ ሀይል ሌላውን ለማንበርከክ የሚያደርጉት ጥረት ዉሀ ቢወቅጡት አንቦጭ እንዲሉ ከሚሆን ዉጭ ትውልድ የሚሻገር መፍትሄ ሊያመጣ አይችልም:: ለብዙ መቶ አመታት የቆዩ የሌሎች ሀገሮችን ሕገ መንግስቶች እያየን አድናቂ ብቻ ሆነን: ሌሎች ግን አንደተደነቁብን አንቀራለን::

ቸር እንሰንበት::

 

ስንት ሚሊዮን ኪዩቢክ ሊትር ጠበል ቢረጭ ይበቃ ይሆን? –ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

0
0

WoyaneEFFORTCompaniesአይድረስባችሁና አንዳንዴ እንዲህ ይገጥማል፡፡ የሆነ መጥፎ አጋጣሚ  ይከሰትና አንዲት ሴት እንኳንስ ሊያዩት ስለርሱ ሊሰሙት የሚዘገንን አስቀያሚ ፍጡር ትወልዳለች፤ እናትና አባት ደህና ሆነው ሳለ መልክና ጠባይ እስከሰባት ትውልድ ይሳሳባል ይባላልና በዝርያ ወይም በበሽታ ወይንም ደግሞ በእርግማን ምክንያት ሰዎች “ወላድ አትይህ” የሚባል አስጠሊታ ፍጡር ሊወልዱ የሚችሉበት አጋጣሚ ከስንት አንዴ ይከሰታል፡፡ ምንም አልደብቃችሁም – በቡዳዎች መንደር እንዲያውም ጅብ ከሰው ማኅፀን ሊወለድ ይችላል፡፡ ዓለማችን የብዙ ዕፁብ ድንቅ ክንዋኔዎችና አስደማሚ ክስተቶች መድረክ እንደመሆኗ በዳዴ ደረጃ ከሚገኘው የሣይንስና ቴክሎጂ ክበብ ወጥተን በሜታፊዚክሳዊ የፓራኖርማል (paranormal ) መነጽር ከታዘብን በመለሳዊ ፍልስፍና አገላለጽ መሠረት በአንድ ስኒ ውኃ ውስጥ በሚነሣ ማዕበል ብዙ መርከቦች ሲሰምጡ ልናይ ሁሉ እንችላለን፡፡ እናም ዳግማይ ወያኔን የፈጠረች እናት ትግራይ አለደንቡ በእግሩ ተገልብጦ የተወለደባት ሕወሓት ምሥጋን ይንሳውና በጥቁር ደመናና በደማቅ ቀይ ቀለም ተጀቡና ስመለከታት ለማንም አዝኜ በማላውቀው የሀዘን ድባብ ተውጬ ከአሁኑ ተጨነቅሁላት፡፡

ትግራይ በወለደቻቸው የ“ወላድ አትያችሁ” ልጆቿ ምክንያት ማቅ ትለብሳለች፡፡ መጽሐፍ መክብብ ዘዳግማዊ ጉዱ ካሣ ሊቀጥል ነው – የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም፡፡ እንደመነሻ ግን …

11ሰዎች ሆን ብለው ወንጀል የሚሠሩት ለምንድነው ? የዚህ ምክንያት ሌላ ሣይሆን ወንጀል በሚሠሩ ሰዎች ላይ ፈጣን የቅጣት ፍርድ ባለመሰጠቱ ነው፡፡ 12ይኼውም ኃጢኣተኞች መቶ ጊዜ ወንጀል እየሠሩ ለረዥም ዘመን ይኖራሉ፤ በእርግጥ ሰዎች የሚሉትንም ዐውቃለሁ፤ እነርሱም “ለእግዚአብሔር ታዛዥ ከሆንክ ሁሉ ነገር ይሠምርልሃል፤  13ክፉ ሰዎች ግን ሁሉ ነገር ስለማይሠምርላቸው ሕይወታቸው እንደጥላ  ያልፋል፤ ለእግዚአብሔርም ባለመታዘዛቸው ምክንያት ገና በወጣትነት ጊዜያቸው ሕይወታቸው ይቀጫል” የሚሉት ፈሊጥ አላቸው፤  14አባባላቸው ግን ከንቱ ነው፤ እስቲ በዓለም የሚሆነውን ነገር ሁሉ ተመልከት፤ አንዳንድ ጊዜ ደጋግ ሰዎች ለክፉ ሰዎች  የሚገባውን ቅጣት ይቀበላሉ፤ ክፉ ሰዎች ደግሞ ለደጋግ ሰዎች የሚገባውን ሽልማት ያገኛሉ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ነው አልሁ፡፡   መጽሐፈ መክብብ 7፡ 11 – 14

ከፍ ሲል የተቀመጠው መጽሐፍ ቅዱሣዊ ጥቅስ እንደሚጠቁመን በመጠንም ሆነ በዓይነት የወያኔ-ትግሬን ያህል ባይሆንም በተወሰነ የክፋት ደረጃ ወንጀልና ኃጢኣት ይሠሩ የነበሩ ክፉ ሰዎች  በጥንት ዘመንም እንደነበሩ ነው፡፡ የአሁኖቹ የትግራይ ምድር ያፈራቻቸው ወያኔዎች ግን ዓለም አቀፍን የክፋት ሪከርድ ሁሉ በ40 ዓመታት የዐመፃና የጽንፈኝነት ልክፍታቸው  ሰባብረው ከሰይጣንም የበለጡ ሰይጣኖች  በመሆን ይሄውና የዚህችን የቀድሞ ታሪካዊት ኢትዮጵያዊት ምድር እያረከሷትና በሌሎች ዘንድ “ዘር አይውጣብሽ!” የሚል የመርገምት አበሳ እያተረፉላት ይገኛሉ፤ የዚህ ሁሉ እርግማንና የደምና የአጥንት ደለል፣ የዚህ ሁሉ ሕዝብ ዕንባና ዋይታ፣ የዚህ ሁሉ መከራና ሰቆቃ የዞረ ድምር በዚህች ክፍለ ሀገር ምን ሊያስከትል እንደሚችል በተለይ አሁን አሁን ለማንም ሰብኣዊ ፍጡር ሊደበቅ የሚችል አልሆነም፡፡ የመከራ ዝልል እየተንተከተከ ነው፡፡

አንዳንድ ገር ጠላት በጊዜ ሂደትና እውነታዎች እየተገለጡለት ሲሄዱ ወዳጅ የሚሆንበት አጋጣሚ አለ፡፡ የሩቁን ትተን ከሰሞነኛ ክስተቶች አንድ ምሣሌ ብናይ እንኳን የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ዝኆኖች በሥልጣንና በጥቅም ምናልባትም በፍትህ ዕጦት ሳቢያ ለበርካታ ጊዜያት ከተራገጡና ብዙ “ሣር” ከረመረሙ በኋላ ትናንት ይሁን ዛሬ ታርቀው የጋራ መንግሥት መሥርተዋል – ልዑል ማቻርና ዐፄ ሳልቫኬር፡፡ ከመልክ አንጻር አትውሰዱብኝና እኚያ ፈረንጆች እኛን አፍሪካውያንን በዝንጀሮ የሚመስሉን አንዳንዴ ሲያስቡት ልክ ናቸው ያስብላል፤ ዝንጀሮ ለትዳሩ ቀናተኛ የሆነውን ያህል የኛ መሪዎች ደግሞ ለሥልጣንና ለጥቅማቸው እጅግ ቀናኢ መሆናቸው ራሱና ብቻውን ከዝንጀሮ ተርታ ቢያስመድበን በበኩሌ ቅዋሜ የለኝም፡፡ መሪዎቻችን እኛን ሁላችንን አርደውና አሳርደው ሥልጣናቸውንና ሀብታቸውን ቢያተርፉ ይመርጣሉ፤ ይህን እውነት  በተጨባጭ ኹነት ለማስረገጥ ያን መንግሥቱ የተባለ ደመሞቃት ወታደር ማስታወሱ በቂ ነው – ሥልጣኑን ለድርድር ሳያቀርብ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ማዳን እየቻለ ለቀን ጅብ ዳርጎን ኮበለለ – እግዜር ይይለት፡፡ ወያኔ ትግሬዎች ደግሞ ከሁሉም የባሰባቸው ናቸው፤ ከመሪነት መደዳም አይገቡም፡፡ ቂመኞችና ያባቶቻቸውን የገማ ታሪክ የሚደግሙ የመጨረሻ ደደቦች መሆናቸውን ለመረዳት እንደተመለደው ጥቂት አንቀጾችን  አብረን መጓዝ ሊኖርብን ነው – እንዲያው ለማስታወስ ያህል ብቻ፡፡

በቀደምለት ጓደኛሞች ጋር እንጨዋወት ነበር፡፡ መጽሐፈ መክብብ ዘዳግማዊ ጉዱ ካሣ አሁንም ቀጠለ፡፡

የዛሬ መቶ ምናምን ዓመት ገደማ ዐፄ ዮሐንስ አራተኛ ሠራዊታቸውን ወደጎጃም ልከው ንጉሥ ተክለ ሃይማኖትን በጦርነት አሸነፉና አካባቢውን በትግሬ ጦር ያዙ፡፡ የትግሬው ጦር ለተወሰኑ ወራት እዚያው ቆይቶ በመጨረሻ አካባቢውን ለቅቆ ሲወጣ በየገበሬው ቤት እየገባ ያልሰረቀውና በኃይል ያልዘረፈው ነገር አልነበረም፡፡ ከንፈር የማያስገጥመው ዘረፋ ግን ትግሬዎቹ ጦረኞች የሚቀሙት የተሻለ ነገር ከማጣት ይሁን ወይም ከመቸገራቸው የተነሣ ወንፊትና ምራን፣ ወገልና አቅማዳ የመሳሰሉ የቤት ውስጥና የበሬ ዕቃዎችን ሣይቀር ዘርፈው መውሰዳቸው ነው፡፡ ከዚያ በባሰ እጅግ የሚሰቀጥጠው ነገር ደግሞ የዐማራው ሕዝብ ሚስቱንና ልጆቹን የትግሬው ወታደር ሲደፍርበት ለንጉሠ ነገሥቱ ለዐፄ ዮሐንስ አቤት ቢል “እኛ ለወታደራችን እንትን ከትግራይ ስላላመጣንለት ተካፍላችሁ ኑሩ እንጂ ምንም ማድረግ አንችልም” የሚል መልስ መስጠታቸው ነው፡፡ የሚገርም ፍርድ – ከመለስ አባት ዱሮውንስ ምን ሊጠበቅ? ዘረመላዊ ድድብና! ይህን ዓይነት ኢሃይማኖታዊና ኢሞራላዊ ፍርድ የሚሰጥ ንጉሠ ነገሥት በሃይማኖት ሰበብ አንገትን ሲቀላ ደግሞ በሌላ አቅጣጫ ይታያችሁ፤ ዕንቆቅልሽ፡፡

ያ ዕንቆቅልሽ በዚያ ብቻ ቢያበቃ አሁን ባላስታወስነው፡፡ ነገር ግን ያኔ በታሪክ ሂደት pause ተደርጎ የቆየውን የቀድሞውን ዐፄ ክርፋትና ግማት የተሞላበት  የጭካኔና የዐረመኔነት ተግባር በዚህ ሠለጠነ በሚባለው የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ውስጥ በለስ የቀናቸው እሳት የላሱ ልጆቻቸው  ዕጥፍ ድርብ በሚያስከነዳ መልኩ በድጋሚ እውን ማድረጋቸው ነው፡፡ የታሪክ ምፀት ማለት እንዲህ ነው፡፡ ይህ ግጥምጥሞሽ የሚጠቁመን ይህችን መሬት ከዳር እዳር ጠበል መርጨት እንደሚገባ ነው፡፡ ከሃዲና ሀገር ሻጭ የሚያበቅል መሬት፣ ሰው ጨፍጫፊና ሕዝብን ከፋፋይ የሚጸንስ ምድር… በጠበል ብቻም ከተፈወሰ እሰዬው ነው እንጂ ክፋት ያለው አይመስለኝም፡፡ እናም ክፍሏን አስቆጥሩና ለሰባ ሰባቶች ያህል አስጠምቋት፡፡ እርግጥ ነው እነ አሉላ አባነጋን የመሳሰሉ የቁርጥ ልጆችንም መውለዷን አንዘነጋም – የአሁኑ አጀንዳችን እርሱ አይደለም እንጂ፡፡ ቢሆንም የደጋጎቹ ዘመን ወደኋላ እየቀረ በአሁኑ ወቅት የአረሞቹ ግነት ግዘፍ ነስቶ መገኘቱን ልብ ይሏል – ከላይ እስከታች፡፡

ያኔ ቢያጡ ቢያጡ ወንፊት ነበር የዘረፉት፡፡ ዛሬ ግን ዕድሜ ለታሪካዊ ጠላቶቻችን ከሰው ነፍስ ጀምሮ የማይዘርፉት ነገር የለም፡፡ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ በቀንና በሌሊት ቢዘርፉ፣ ቢዘርፉ፣ ቢዘርፉ፣ ቢዘርፉ፣ ቢዘርፉና ቢዘርፉ…. አልጠግብ ብለው ይሄውና አሁንም ድረስ በማያቋርጥ የዝርፊያ ተግባር እየማሰኑ ናቸው – ጠግበው መጥገባቸውን አያምኑም፤ ከብረው መክበራቸውን ሣይሆን ድህነታቸውን ነው የሚያስቡት – ወፍረው ሳለ ክሳታቸው እየታያቸው በሥነ ልቦና ቀውስ ተዘፍቀው ይሰቃያሉ – ስቃያቸውንም ለመርሣት ንጹሓን ዜጎችን ያሰቃያሉ፡፡ ስንቱን ኢትዮጵያዊ ሙልጭ አወጡት መሰላችሁ(የአቶ ገ/የስ ቤኛንና የሲሳይን ውይይት ቅድም በኢሳት አይቼ ንዴቴን መቻል አቃተኝ)፡፡ ይሄ የኢትዮጵያ ሀብት ተዘርፎ የማያልቅ ጉደኛ ክምችት ነው፡፡ ከማይም እስከ ምሁር ከትግራይ እየተጠራራ ነቃ ነቃ ያለው ትግሬ ሁሉ የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያንን ሀብትና ንብረት ባጭር ታጥቆ ይዘርፋል – እነሱም ባገኙት አይረኩ – ሀብቱም አያልቅ፡፡ ምን ዓይነት ትንቢት ነው እውን እየሆነ ያለው?

የሚዘርፉት የትኞቹ ናቸው? የማይዘርፉትስ?

እባካችሁ ፍቀዱልኝና ወደ ጎልዳፋ እንግሊዝኛየ ልሂድ፡፡

To give them the benefit of the doubt, I shall give my humble estimate and say that one percent of Tigrians are reserved from looting. And about 60 – 65% of the 90% of the population seem to be engaged in plundering the nation by controlling everything and anything thereof. I guess the rest of the population, i.e 34 – 39%, lives in Tigray and receives the booty. This public secret is well known by the Big Brothers. And the Big Brothers are happy with them, for these crooked Tigrians are messengers of the entire campaign to destroy Ethiopia along with her ancient history, a(an?) history which deprives them of unilateral supremacy over or an exclusive monopolization in the annals of military conquests and triumphant victories in human history. There is rivalry between the known and the unknown forces in Ethiopia. The unknown force had been waiting for so long until it finally got an appropriate internal instrument to carry out its mission of annihilating this seemingly- small –but- great country. In the past 40 years, as had been the case in the past scores of hundred years, the Big Brothers somehow succeeded in molding the Ethiopian version of the Trojan horse. By the way what is the average age of a horse? Maybe not more than 40!(I suppose.)

Thanks to Machiavelli and his consultant Mr. Satan, selecting from the existing ones or creating and assigning an enemy to one’s real or imagined enemy seems to be easy. Adam and his wife Eve were presumably leading a happiest life in Eden Paradise. But the fallen angel envied, so he sent the serpent to Eve and tempted her to eat from the forbidden tree. The cause was jealousy; the godly grace the couple had was the reason for the temptation and the resultant humiliation. Cain was the brother of Abel; and it was not difficult for Satan to create cleavage between these brethren and instigate one against the other as a result of which the first death occurred on Abel by his brother Cain. The cause  here was jealousy, too. … That ancient arch-enemy of Son of Man is currently more active now than any historical conjuncture hitherto. And he will never sleep until he shuts all mouths that praise God and kills people that cause the unity of Ethiopia wherein He is worshiped day in and day out in big cathedrals and small churches all over the country; this situation makes Satan feel uncomfortable. He is the cause of our suffering and death and eventually the reason for the second coming of our redemption to where we are. …

Truth be told, the Amharas and Tigrians are two facets of the same coin (I have no any intention of appeasing these Satanic creatures and beg them for mercy not because I don’t need mercy but because they don’t have such humane words in their vocabulary). In whichever way you analyze their semblance, at the end of your search, you will end up your comparative study by saying, “Wow, what a wonderful similarity!” But as a matter of fact, the oral literature endorses it as well, the animosity between similar entities must be bitterer than the animosity between dissimilar ones. What I mean is the negative outcome is more severe when you quarrel with an intimate friend than when you do so with an acquaintance, perhaps you know his weak and strong sides very well, or maybe  you have developed some sort of complex, be it inferiority or otherwise based on the axiom “familiarity makes contempt.” In any case, take the language, take the social psychology that is opposed to egalitarianism and subservient to hierarchical lordship, take the religion, take the economic life (not necessarily in the present day Ethiopia, ha..ha..ha), … almost everything is the same in these twin ethnic groups; of course, I would be happy if I could be able to assign the Amharas and Tigrians into the same ethnic group had I been someone in something. If this is the reality, besides the aforesaid major cause of our discord, what could be the reason behind all this genocidal massacre and eviction imposed upon the Amhara by TPLF? And what do the Big Brothers profit out of the misery of these poverini? Why should Talmudic punishment be forcibly imposed on these defenseless human beings, the Amharas? What if, for example, certain celestial colonizers come and annex the US or UK and mercilessly annihilate the populace? Should we Ethiopians, as a people or as a government, endorse the killing and give all the support the aliens need to go ahead with their plan of eradicating innocent citizens? What is the rationale behind the CIA’s and other intelligence organs’ incessant support to TPLF’s survival in power? What is the cause of this entire puzzle? We are equal creatures in this universe; the shift in the  balance of power is just a matter of time. Who knows, Fiji might lead the world militarily or economically after 100 years or so. We don’t have to forget the fact that Ethiopia was one of the four powerful global powers before even the US was born and gradually became  the naughtiest daughter of this planet. Please show this grievance of mine to at least an American VIP. And tell them also that any evil has its own reprisal consequence, in our case not through ICBM or WMD such as nuclear bomb, but the power of prayer; our tears are our missiles. We have been crying for the last good number of centuries. Nature has every means to compensate those who depend upon her, if at all you tend to deny God’s existence. And no power has been able to escape the merciless wrath of Ms. Nature after having committed serious foul upon her subjects.

With respect to the TPLF’s determination to eradicate the Amharas, we can say that poverty might have served as an impetus. But can poverty alone change the majority of a community into an absolute madness and force them to launch an all out war against its own brothers and sisters? I don’t think so. We  have to do some research to know why these people of Tigray have changed their mode of thought especially in the past 25 years. They should know TPLF is nothing when compared to Ethiopia and her existence. And they should realize that killing the Amharas has nothing to do with destroying Ethiopia, for Ethiopia is the habitat of more than 90 million people out of whom about 20 million are Amharas. They should understand that they are dismantling the home of some 84 million people excluding Tigray which is fortified by TPLF’s mechanized brigades along with an abundance of looted wealth. This pillaged wealth of TPLF is well known by the Big Brothers. Where are you, you poor justice? Who are stifling you?…

What should we do now?

Socialization is the best panacea. I think millions of Tigrians should get freed from the shackle of ethnocentric mode of thinking; they have to get out of that narrow world of animalism. They way they perceive this world is belittling them to the extent of being less human than the stupidest person on this planet. It is being less important than any creature if you kill your brother for the sake of filling your belly which is the case in our country. They are not doing what they are doing for the sake of bringing about justice; they are doing all what they have been doing since the beginning just for the sake of their material satisfaction. In terms of ethnicity, mathematically speaking, the Amharas and Tigrians are inversely related. The ethnicity in Tigrians is so high while it is almost non-existent in the Amharas. This is the enigma that has contributed the lion’s share in the successful accomplishment of the spell conjured upon the Amharas by their historical opponents. Suppose your little brother is badmouthing you in front of your friends; perhaps your sister is slapping you in your face, what would you do? It depends; you may become dumfounded and remain in disbelief throughout or take the necessary preventive measure and safeguard yourself from being a victim of the foolish siblings. But it is unfortunate for the Amharas that they seem to have chosen the former option, at least up until the time the infliction is felt to the marrow, if at all that stage is not yet nigh. …

የሰው ወርቅ አያደምቅ ነው ወዳጄ፡፡ ወዳገሬ መልሽኝ ብሏል አሉ ሰውዬው – እኔም ተመለስኩ፡፡ ተጋሩ ወንድሞቻችን ከተደጋጋሚ ስህተት ይወጡ ዘንድ ታሪክን በመመርመር የአስተሳሰብና የአመለካከት ለውጥ ሊያመጡ ይገባል፡፡ ሌላውም ሕዝብ በዚህ ረገድ ብዙ ይጠበቅበታል፡፡ ስለሌላው ሌላ ጊዜ ብንነጋርበት ይሻላል – ስለትግራይ ወገናችን ግን የሚታየንን በዚህች አጋጣሚ እንጠቁም፡፡ ተደጋጋሚ ስህተት መቆራረጥን ሊያስከትል እንዳይችል በግልጽ እንነጋገር፡፡

ከዘረኝነት ለመውጣት ብርቱ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ዘረኝነት መጥፎ በሽታ ነው፡፡ መድሓኒትም የለውም፡፡ አሽመድምዶ የሚያስቀር መሆኑን በተለይ ባለፉት 25 ዓመታት አይተነዋል፡፡ ዘረኝነት ሆዳም ያደርጋል – ሊያውም እምብርትየለሽ አጋሰስ፡፡ ዘረኝነት ዐይንንም ጆሮንም ያሣውራል፡፡ ዘረኝነት ይሉኝታንና ሀፍረትን ከመዝገበ ቃላት ሳይቀር ፍቆ ያስወጣል – በአሁኒቷ ትግራይ በግልጽ እንደሚታየው፡፡ ስለጥቂቶች የምናወራበት ጊዜ የለንምና ጥቂቶች ታገሱኝ ታዲያ፡፡ ዘረኝነት በአስተሳሰብ ያለማደግንና የአእምሮን መቀጨጭ የሚያመለክት ትልቅ ደዌ ነው፡፡ ውሻና ዝንጀሮ፣ ዐይጥና ድመት፣ ነብርና ፍየል፣ አህያና ጅብ…  እየተላመዱ ወዳጅነት በሚመሠርቱበት በዚህ የአስተሳሰብ ዕድገት ዘመን የአንድ ቋንቋና ባህል ተጋሪዎች የሆኑ ዐማራና ትግሬ በእህል ውኃ ምክንያት ቢተላለቁ ሞኝነት ብቻ ሣይሆን የለዬለት ዕብደት ነው፡፡ አንዳንዴ በቃኝን ማወቅም ተገቢ ነው፡፡ አንዳንዴ ጭካኔን ማለዘብም አግባብ ነው፡፡ አንዳንዴ ነገን ማሰብም ብልህነት ነው፡፡ አንዳንዴ  እንደሰው ለማሰብ መሞከርም አስተዋይነት ነው፡፡ አንዳንዴ ከችኮነት ተላቅቆ እውነትን ለመጋፈጥ መቁረጥም ደግ ነው፡፡ አንዳንዴ ሲመቸን እንደባህታዊ ዘግተን ከተቀመጥንበት ጥንታዊ አስተሳሰብና የመረረ ጥላቻ መውጣትም ጥሩ እመርታ ነው፡፡ እርግጥ ነው ባህልና አስተዳደግ ትልቅ ጫና ሊፈጥሩብን ይችላሉ፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ በዐማራ ጥላቻ ተኮትኩቶ ያደገን ሰው፣ በወራሪነት ዘመኑ “አዲስ አበባን ስንቆጣጠር መኪናና ቤት በነፃ ታገኛለህ፤ ናይ ሃድጊታ ሀፍትን ንብረትን ወሲድና ንኣሃ ክንኽበካ ኢና፤ ሀፍቲ ደርጊን ኢሠፓን ክንወርስኢናሞ ውፈር ተበገስ” ተብሎ ቃል የተገባለትና በሀሽሽና በኃይል ሰጪ ዕፆች አደፋፋሪነት እየተዋጋ ቤተ መንግሥት የገባን ማይም ተዋጊ  እንደሰው እንዲያስብ ማድረግ ሊከብድ ይችላል፤ በታላቁ ጠላትነየመረጃ፣ የስለላና የበጀት ድጋፍ ሆ ብሎ የዘመተን የውስጥ ምንደኛ ለመቋቋም ጊዜና ጥበብ ማስፈለጉ ደግሞ አይቀርም፡፡ አብዛኛው ወያኔ ከዚህ ከፍ ሲል እንደተገለጸው  ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ ማኅበራዊነት የጎደለውን ሰው እንደሰው እንዲያስብ ለማድረግ ከመጣር ይልቅ አንዲትን ጦጣ ንግግር እንድትለምድ ማሠልጠን ሳይቀል አይቀርም፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ተንሻፍፎ ካደገ በኋላ በጣም አደገኛ ፍጡር ነውና፡፡ ወያኔዎችን ከ25 ዓመታትም በኋላ ከዐውሬነትና ቀጥሎም ከጅብነትና ከዓሣማነት ነፃ ማውጣት ያልተቻለው እንግዲህ ለዚህ ነው – ለዚያውም ስንትና ስንት ኢሰብኣዊ ግፍና በደልን በገፍ በሚያስተናግድ የትግል ሥልት፡፡ ስኳና ጨው ከቀመሱ በኋላማ በተለይ የለየላቸው ፊጋ በሬ ሆኑና መንገዳቸው ላይ የሚያገኙትንና መብቱን የሚጠይቅን ዜጋ ሁሉ በሹል ቀንዳቸው እየደለቁ ፍዳውን ያሣዩታል፡፡ ለዚህ ነው እነዚህን ጉዶች ከጦር በስተቀር ሌላ የሚያሸንፋቸው የለም የምንለው፡፡ የተራበ ጅብ አህያን ነክሶ ከያዘ በድርድር አይለቃትም፤ በዱላ ብቻ ነው የሚፈታው፡፡ ወያኔ እንደማፊያዊ ተቋምነቱ እንደጪስ በንኖ የሚጠፋ መሆኑ ከዘመናት በፊት የተነገረለት የመጨረሻ ዕጣው ቢሆንም እስከዚያው ግን ሊያደርሰው የሚችለው ጥፋት ግንዛቤ ማግኘትና ጥንቃቄ መደረግ ይገባዋል፡፡ የዘረኝነት አባዜ አሣሩ ብዙ ነው፡፡

እውነትን ብቻ እንነጋገርና አንድ ትግሬ ጓደኛ አለህ እንበል፡፡ ያ ትግሬ ጓደኛህ ለ300 ዓመታት ያንተ የልብ ጓደኛ ነበር ብለን ደግሞ እናስብ – 300 ዓመ(ታ)ት ነው ያልኩት፡፡ ለዚህን ያሀል ዘመን አብራችሁ ከቆያችሁ በኋላ ዛሬ ተሲያት ላይ ይህ ጓደኛህ አንድ ትግሬ አገኘ እንበል፡፡ ከሴከንዶች በኋላ ይሄ የዋህና ግሩም ጠባይ የነበረው ጓደኛህ አንተን እስከመፈጠርህ ረስቶ ከዚያ ዛሬ ካገኘው ትግሬ ጋር አሼሼ ገዳሜ ሲል ልታይ ትችላለሀ፤ በዚህ በመሀል አገር  ብዙም ባልተለመደ ጠባይ ልታዝን ትችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን አይግርመህ፡፡ አስተዳደጉና ባህላዊ ተፅዕኖ አሉታዊ ጥላቸውን ስለሚያጠሉበት የአካባቢውን ሰው በማስቀደም አንተን ማራቁ በክፋትና ለክፋት ሣይሆን ልማድ ነው፡፡ ይህን ጠባይ የሚያሣዩት ደግሞ በትንሽም ቢሆን ትግሬ የሆኑትም ጭምር ናቸው፡፡ ትግርኛ የማይችሉ ትግሬዎች ሣይቀሩ በዚህ ልምሻ የመሽመድመድ ጠባይ ያሣያሉ፡፡ ለዚህም ነው ንፋስ ሳይገባባቸው ከነሱ ቁጥር አኳያ ሲታይ ኆልቁ መሣፍርት የሌለውን ሕዝብ እንደከብት ሲነዱት የሚታዩት፡፡ ዘረኝነት ንፋስ የማስገባት ዕድሉ በጣም ጠባብ ነው፡፡ ከእስራኤሎችም ብዙ ይማሯል፡፡ ከነዚህን መሰሉ ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ኅቡኣን ድርጅቶች ጋር መታገል እልህን ያስጨርሳል – የኛ እልህ ግን የኛ ሣይሆን የአንድዬ ነውና በርሱ ታመኑ – በቅርብ አንድ ጉድ እናያለን!

ይህን ከፍ ሲል ስለ አብዛኛው ትግሬ የጎሠኝነት ልክፍት እውነትነት ተቃውሞ እምቧ ዘራፍ የሚል ሰሜነኛ ቢኖር አንድም ከአንድ በመቶዎቹ ጥሩዎች ትግሬዎች የሚመደብ ነው ብለን በየዋህነት እንቀበለዋለን፡፡ አንድም ስለትግሬነቱ  የሚንጨረጨር የዘር በሽታ ሰለባ ነው፡፡ አንድም ወያኔ ይሆንና በለምን ተደፈርኩ ቡራ ከረዩ የሚል ዕብሪተኛ ነው፡፡ እንጂ የምለው ነገር ከእውነትም በላይ የእውነቶች ቁንጮ ነው፡፡ የምናገረው ነገር በተግባር የገጠማችሁ ካላችሁ ንገሩን፡፡ ዐማራ ነኝ የሚል ጓደኛህ ግን ምናልባት ሆዱን ተከትሎ ይነጉድ እንደሆነ እንጂ ሌላ ዐማራ በማግኘቱ ይከዳሃል ብዬ አላስብም፡፡ በሰው ልጅነት መረዳዳት ሲቻል ዘርና ጎሣ እየተቋጠሩ መሳሳብ በጣም አደገኛ ነው፡፡ የወያኔ ኢትዮጵያ በዚህ በሽታ ተመትታ በመንግሥት መሥሪያ ቤትና በኤምባሲዎች እንዲሁም በኤንጂኦዎች በተለይ ትግሬ ካልሆንክ ያለመቀጠር ዕድልህ የተምቦረቀቀ ነው – ሰርቲፊኬት የያዘ ትግሬ ያንተን ማስትሬት ዲግሪ ይረጋግጥልህና  በተመሳሳይ ቦታና ደረጃ አንተ ብትቀጠር ከሚከፈልህ ደሞዝ በዕጥፍ ድርብ መኻያ ይቀጠራል – ለዚያውም ሥውር የሙስናና መሰል ጥቅሞቹን ሳይጨምር፡፡ እናት ኢትዮጵያ በአሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፡፡ እርግጥ ነው ማለፉ አይቀርም፡፡ ግን ግን ብዙ የሚነፈርቅ ቁስልና የታሪክ ጠባሳ እየጣለና የአብሮነታችንን ክር እየበጣጠሰ እንደሚገኝ መረዳት ይገባል፡፡ ለትግሬዎች ጥቂት የቀረቻቸው የማሰቢያ ጊዜ ያለች ትመስለኛለችና እንድትጠቀሙባት ከአደራ ጭምር ለመጠቆም እወዳለሁ፡፡ ለመልካምነት የጊዜ ገደብ የለውምና፡፡

መሰነባበቻ፡፡ ለሰላም ማስከበር ወደ ውጪ የሚላኩ ወታደሮች ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ትግሬዎች ናቸው – ምናልባት አንድ ሁለት ሦስት ለማስመሰያ ሊጨምሩ ይችላ ሉ – ይህም የሚሆነው እንደዕድል ሆኖ  ማስመሰልንና ይሉኝታን የሚያውቅ ትግሬ ባለሥልጣን ካጋጠመ ነው፡፡ የተዋጊው ኮታ ቢሞላ እንኳን መቶ አለቃውና ሻምበሉ ትግሬ በወጥቤትነትና በጽዳት ስም እንዲሄድ ይደረጋል፡፡ ምክንያቱም ባገር ቤት ለሚዘርፈው ሀብት ሸፋን ለመስጠት ሲባል “ከውጪ ሀገር በተባበሩት መንግሥታት ለሰላም አስከባሪነት ተልእኮ ሄዶ ባገኘው ገንዘብ የሠራው ህንፃ ነው” እየተባለ የሽፋን ምክንያት መስጠት እንዲያስችላቸው መሆኑ ይነገራል፡፡ በሌላም በኩል ወገናቸውን ለመጥቀምና ሌላውን ለማደኸየት ሲባልም ነው፡፡ ወያኔ የሚጠላውን ወገን ከሁሉም ዓይነት ጥቅሞች ይከለክላል፡፡ የዐማራው ሕዝብ እንደሚደረግበት አፈናና የበሽታ ሥርጭት እስካሁን አለማለቁ ሲታይ ደግሞ የእግዜር ጥበቃ እንጂ ሌላ አጥጋቢ ምክንያት እንደማይኖረው ግልጽ ነው፡፡ ከማዳበሪያ አቅም እንኳን ይከለከላል፡፡ ባሕርዳርን ከመሰሉ ጥቂት ከተሞች በስተቀር አብዛኛዎቹ የዐማራ ከተሞች የተወረሩ ይመስላሉ – በርካታዎቹን የማየት ዕድል ገጥሞኛል፡፡ ከዚህ በላይ ግፍና በደል የለም – ሌላውንና በኢሳትና በሌሎች ሚዲያዎች ዘወትር የሚነገረውን ትተን ማለቴ ነው፡፡ ግፍ በዝቷልና የፈጣሪ ፍርድ በቅርብ ይመጣል – ፍርዱ እንዳይጠንና ከአቅማችን በላይ እንዳይሆን ታዲያን በጸሎትና በምህላ እንጠብቅ፡፡

የሰላም አስከባሪነትን በሚመለከት አንድ ወቅት እንዲህ ሆነ – ከተባራሪ የቃረምኩት እውነተኛ መረጃ ነው፡፡ ባልናገረው ደስ ባለኝ፡፡ ኦ!ኦ!ኦ! ግን ግን ይቅርብኝ፡፡ ብዙ ነገር መናገር በቻልኩ – ይሁንና  ግለሰቦችን አስጠቃለሁ፡፡

ለነገሩ ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ ስለወያኔ ያልተነገረ ነገር የለም፡፡ እነሱ እንደሆኑ ከብት ላይ ተጣብቆ ሊፈነዳ እንደደረሰ አልቅትና መዥገር ኢትዮጵያ ላይ ተጣብቀው ሀኪም ይንቀለን ብለዋል፡፡ እብጠታቸው ግን ከነርሱም ቁጥጥር ወጥቶ ማንም ባይነካቸው እንኳን በራሳቸው ጊዜ ሊፈነዱ መቃረባቸውን እኛ ብቻ ሣንሆን እነሱም አውቀውታል፡፡ “አወዳደቃቸው እንዲያምር” ኃጢኣታቸውን እያበዙ እንጂ ፀሐያቸው እየጠለቀች እንደሆነ ከከባቢያዊ ሁኔታዎች መገንዘብ አያዳግትም፡፡

እኛ ግን ከነሱ ቀትረ ቀላልነትና ተፈጥሯዊ ጥመት በመማር ራሳችንን ማረቅ አለብን፡፡ ከሁሉም በበለጠ ለብቀላ የሚነሣሣ ስሜታችንን መቆጣጠር ይኖርብናል፡፡ እነሱ ይህን ወይ ያን አደረጉ ብለን ለብቀላ ጦር ብንሰብቅ አዙሪቱ አይለቀንም፡፡ ቀን ቆጥሮ ወደዚያው አረንቋ ይዘፍቀናል፡፡ ስለሆነም ነፃ ለመውጣት ከምናደርገው ሕጋዊ የብረትም እንበለው ሁለገብ ትግል ውጪ በጥላቻና በበቀል ስሜት ተገፋፍተን ተመሣሣይ የነፍስ ማጥፋትና የንብረት ማውደም ድርጊት ውስጥ መግባት የለብንም፡፡ የዘረፉትን ወደሕጋዊ ቦታው ማስመለስ፣ የገደሉትን በሕጉ መሠረት መጠየቅና ችሎት ማቆም ይገባናል፡፡ እንደነሱ በሞቅታ ፈረስ እየጋለብን የእንስሳነት ባሕርይ እንዳያጠቃን በጣም መጠንቀቅ አለብን፡፡ የገደለን መግደል ተካካይ ቅጣት ነው፡፡ የገደለን መማር፣ እንዲጸጸትም ጊዜና ዕድል መስጠት ግን ትልቅ ቅጣት ነው፡፡ እነሱ አቅል አጥተውና በበቀልና በጥላቻ ሰክረው ሰማይና መድር ሊሸከሙት የሚከብዳቸውን ይህን ሁሉ ግፍ ቢፈጽሙም የሚጸጸቱበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርም፤ ያኔ እርግጥ ነው ደብቁኝ ደብቁኝ ማለታቸው አይቀርም፤ መደበቂያ ዋሻ የሚያገኙ ግን አይመስለኝም፤ ኢትዮጵያን ያወደሙ መስሏቸው ነዳጅ እያከፈከፉ በአብሪ ጥይትና ክብሪት እየጫሩ ያቃጠሉትና እየመነጠሩ ያወደሙት ደንም ቂሙን ሳይወጣባቸው አይቀርም፡፡ የሆኖ ሆኖ ግን ነፃ መውጣችን ምድራዊኛ ብቻ ሣይሆን ሰማያዊም ጭምር በመሆኑ የሚቀር አይደለም፡፡ እስከዚያው ለሁላችንም መልካም የስቃይ ዘመን ያድርግልን፤ ቻው፡፡

ጎኔ ይውጋህ እንዳልልህ- አስራት አብርሃም

0
0
Asrat Abrha

አስራት አብርሃም

ጎኔ ይውጋህ እንዳልልህ!

እኔ ሞኙ፤ እኔ ተታላዩ “ከጎንህ ነኝ” ስትለኝ፤

                                                  ሞቴን፣ መከራዬን፣ ትግሌን፣ እስራቴን የምትካፈል መሰለኝ፤

ኖሯል ለካ በከንቱ፣  በብላሽ ስ’ሸነግለኝ፤

በአለማዊ ቃል፣ ለአፍህ ስ’ደልልኝ!

በቃሊቲ፣ በቅሊንጦ፣ በማዕከላዊ ስሰቃይ

ዝዋይ፣ ሽዋ ሮቢት ግዞት ስወሰድ፣ መከራ ሳይ

ከፎቶዬ ጀርባ ተለጥፈህ “ከጎንህ ነኝ” ስትለኝ

ወንድሜ ይሙት!

የማውቀው የጎን ትርጉም የተቀየረ መሰለኝ።

እኔ ሞኙ፤ እኔ ተታላዩ መድፍና ዲሞፍተር ይዤ ስዋጋ

“ከጎንህ ነኝ” እያልክ እጆችህን በጭብጨባ ‘ምታላጋ

እግር ኳስ አይደለ፤ ሚስማር ተራ፣ ካታንጋ!

ደም የሚፈስበት ነው፤ የሚከፍልበት ውድ ዋጋ!!

የኢየሱስን መስቀል መሸከም እንዳቃተው፤

በእጀታው  ልክ የራሱን መስቀል እንደሚያሰራ ካህን

መስቀሉን በሚጢጢ ምስል አሳምሮ

አንገቱ ላይ ለጌጥ እንደሚያንጠለጥለው ምእመን

መከራ ከማይገኝበት፤ ወላፈኑ ከማይደርስበት

ጥግ ይዘህ “ከጎንህ ነኝ” ስትለኝ

ወንድዬ ይሙት!

አሁንስ እያሾፎክ፣ እየቀለድክ መሰለኝ።

ልጆቼ በለጋ እድሚያቸው

የአባት ናፍቆት፣ የኑሮ ክብደት ተጭናቸው

ውዴ ያገር ዕዳ ለብቻ ወድቆባት፣ ኑሮ  ከብዷት፤

እናቴ በስተርጅናዋ፣ በመቁረቢያዋ ሀዘን አጥልቶባት፤

ሰርክ ወህኒ ተመላላሽ፣ ልጅ ጠያቂ እንድትሆን ተፈርዶበት፤

እያየህ እንዳላየህ፤ እየሰማህ እንዳልሰማህ ሆነህ የኖረከው

በአደባባይ፣ በምኩራብ “ከጎንህ ነኝ!” ለማለት እንዴት ቻልከው?!

ወንድዬ ይሙት!

እኔ አማሁህ፤

“ሞቴን፣ እስራቴን፣ እንግልቴን፣ መከራዬን

በሚያዋጠው መቶ ዲናር እየለካ

“ከጎንህ ነኝ!” የሚለው፣ ይህን እያሰላ ኖሯል ለካ!”

ብዬ አማሁህ።

ወንድሜ ይሙት፤ አዘንኩብህ፤

“እሱ ‘ሚያስበው እኔ ስሰዋ

ስለሚያገኘው ድል፤ ስለሚቀኘው ቅኔ ነው”

ብዬ አማሁህ።

አንተና እኔ “መስቀላችን ረጅም፤ ሸክማችን ከባድ ነው”

ብለን ነበር የተነሳነው፤

“ስቅለታችን፣ ሞታችን፣ ትንሳኤችን አንድ ላይ ነው”

የሚል ነበር የተማማልነው።

ዳሩ ግን በማተብህ አልኖርክም፤ በቃልህ አልተገኘህም፤

ሐሙስ እንጂ ዓርብ፣ በሰዓቱ፣ በስቅለቱ አልነበርክም።

ጎለጎታ የወጣነው፤ መስቀሉን የተሸከምነው፤

 መራራውን ፅዋ የጠጣነው እኔና ሌላውን ነው።

ልብ አላልከውም እንጂ!

ትግላችን እኮ ትንሳኤ ያላገኘነው፤

የድል ብስራቱን ያልሰማነው፤

ጥቂት የሚታገሉ፤

ሌላው፣ አብዛኛው፣ ድል ጠባቂ ሆኖ ነው።

አስራት አብርሃም (03/09/2008 ዓ.ም. ከምሽቱ 3:45)

*ይህ ግጥም መታሰቢያቱ ለሃገርና ለህዝብ በሚደረግ ትግል ውስጥ ቤታቸው ለፈረሰ፤ ህይወታቸው ለተበላሸ፤ ለተሰዉ፤ ጤናቸው ላጡ፤ ልጆቻቸው ያለአባት፤ የትዳር ተጋሪዎቻቸው ያለአጋር፣  ወላጆቻቸው ያለጧሪ ለቀሩ ታጋዮች ሁሉ ይሁን!

ሃራም ቦኮ ሃራም -ሃራም አልሸባብ –ገለታው ዘለቀ

0
0

0,,18049387_303,00
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአፍሪካውያንን ህልውና እየተፈታተኑ ካሉ ጉልህ ችግሮች መካከል ኣሸባሪነት ዋና ጉዳይ ሆኗል። ISIl በሊቢያ፣ ኣልሸባብ በምስራቅ ኣፍሪካ፣ ቦኮ ሃራም በምእራብ ኣፍሪካ   በከባድ ፍጥነት እያደጉ ነው። አፍሪካውያን ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ በሽብር ስራዎች ላይ የተባበረ ክንዳቸውን ሊያነሱ የሚገባበት፣ ህዝቦች ግንዛቤያቸውን በማስፋትና የዚህን ኣሸባሪ መንፈስ ሊዋጉ የሚገባበት ሰዓት ላይ ነንና እኛ ኢትዮጵያውያን በዚህ ጉዳይ ላይ በጽኑ መወያየት ያሻናል።  በተለይ ወጣቱ በኣህጉራችን ስላለው የሽብር እንቅስቃሴ በሚገባ ሊረዳ ይገባዋል:: መምህራን አፍሪካ ውስጥ ስላጠላው የሽብር ጥላ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ኖሯቸው ተማሪዎቻቸውን ሊያስተምሩ ይገባል።

 

ወደ ዋናው ውይይታችን እናምራ። ስለ ሽብርተኞች ሲነሳ  የሚነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎች ይኖራሉ። ለመሆኑ እነዚህ ኣሸባሪ ቡድኖች ምንድነው ወደ ጫካና ጭካኔ የሚመራቸው? ሽብርተኛነት እንዴት በፍጥነት በአህጉራችን ሊያድግ ቻለ? ኣሸባሪነት በተለይ በኣፍሪካ ክፍለ ዓለም ውስጥ ያለው ኣደጋና የስጋት ደረጃው ምን ያህል ነው? እውን ሳናውቀው ወይም በስህተት ለኣሸባሪነት መፈልፈል የፈጠርነው ምቹ ሁኔታ ኣለ ወይ? እንዴትስ ነው ይህንን ኣሁን በፍጥነት እያደገ ያለ ኣሸባሪነት የምንገታውና ኣፍሪካን ከኣሸባሪነት ነጻ የምናደርገው? የሚሉት ጥያቄዎች የኛ የዜጎች ሁሉ የመወያያ ኣጀንዳዎች መሆን ኣለባቸው። ዜጎች በኣሸባሪዎች ዙሪያ የጠራ ግንዛቤ ይዘው መንግስታቸው በኣሸባሪዎች ላይ ንቁ ካልሆነና መመከትና ማቆም ከተሳነው ውረድ ሊሉት ይገባል። የኣሸባሪዎች ጉዳይ ከሁሉ በላይ የሃገርና የህዝብ ጉዳይ ነውና። ይህ የኣሸባሪነት ጉዳይ ከፖለቲካ ልዮነቶች ሁሉ በላይ በመሆኑ ከፖለቲካ ኣመለካከቶቻችንና ከውስጥ ችግሮቻችን ከፍ ብለንና ከላይ ከኣህጉር ማማ ላይ ቆመን በጋራ ልንዋጋው የሚገባ ጉዳይ ነው።

 

ከፍ ሲል ለመወያያ ማጠንጠኛ ይሆናሉ ያልኳቸውን ነጥቦች ወደ ሁዋላ ወደ ፊት እየተንሸራሸርን እንወያይባቸው። በኣጠቃላይ በዓለማችን ያሉ ቀንደኛ ኣሸባሪዎች ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ሲሆን አፍሪካ ውስጥ የተፈለፈሉትን እንደ ኣልሸባብና ቦኮ ሃራም ያሉትን የሽብር ቡድኖች ተፈጥሮና ፍላጎት እንዲሁም ስነ ልቦና ነጥለን እናንሳ። ለምሳሌ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2002 ዓ.ም ናይጀሪያ ውስጥ የተፈጠረውን ቦኮ ሃራምን ስናይ ይዞት የተነሳውና ጫካ የሰደደውን ነገር በሚገባ መመረመር ጥሩ ነው። ይህ ቡዳን ከፋኝ ብሎ የሚለውና በእስልምና ሃይማኖት ሃራም (ውጉዝ) ያለው የምእራቡን ዓለም ትምህርት ነው። ቦኮ ሃራም ማለትም የምእራብን ትምህርት ውጉዝ ከመ አርዮስ እንደማለት ነው። ይህ ቡድን የተቋቋመው አንድ መሃመድ የሱፍ በተባለ የሽብር ስሜት በተጠናወተው ሰው ነው። በርግጥ ድርጅቱን ከመሰረተ ከጥቂት አመታት በሁዋላ በናይጀሪያ የጸጥታ ሃይሎች ተገድሏል። ይሁን እንጂ መሃመድ የሱፍ የጠነሰሰው የምእራብን ትምህርት ውግዘት ጥቂት የማይባሉ  ሰዎች ኣላማውን ተቀብለው በፍጥነት ኣድጎ ይታያል። በአሁኑ ሰዓት ቦኮ ሃራም ከኣሸባሪ ድርጅቶች ሁሉ በጀሃድ ርምጃው ብዙ ሰዎችን በመግደል የሚደርስበት ኣልተገኘም። ቦኮ ሃራም ናይጀሪያ ውስጥ ይጠንሰስ እንጂ በቅርብ ጊዜ። “ራእዩን” ሰፋ ኣድርጎ ምእራብ ኣፍሪካን የሚያካልል ISWA (Islamic State West Africa) የተባለ ስያሜን ለራሱ ሸልሟል። የእንቅስቃሴ ዞኑን ኣስፍቶ በቻድ፣ በካሜሩን፣ በኒጀርና በሌሎችም የምእራብ ኣፍሪካ ሃገራት እየተንቀሳቀሰ ነው። እ.አ.አ. በ2014 ሚያዝያ ወር ላይ 276 ሴት ተማሪዎችን ሰርቆ የጠፋ ባለም ያልታየ የሴቶች ሌባ ነው። ይህ ቡድን የሚያመጣው ትምህርትና እንቅስቃሴ ሁሉ በተለይ በተለይ ለአፍሪካ ሴቶች ትልቅ ስጋት ነው። የሚከተለው ዶክትሪን ከተለያዩ ጎጂ ልማዶችና ከጭቆና ለመላቀቅ ደፋ ቀና የሚሉትን የአፍሪካን ግማሽ ህዝብ ሴቶችን ወደ ባሰ ጭቆና ሊመልስ የተነሳ ኣደገኛ ቡድን ነው።

 

ስለዚህ ኣሸባሪ ቡድን ስናስብ ጠልቀን መመራመር መፈለጋችን አይቀርም። መቼም ኣንድን ሰው ጫካ የሚከተው ከባድ በደል መኖር ኣለበት። የመረረው፣ ከፍተኛ ብሶት ያለበት ሰው ጫካ ይገባል። ይሸፍታል። ቦኮ ሃራምን ጫካ የከተተውና ያስከፋው የምእራብ ትምህርት ጉዳይ ነው ይላል። በርግጥ ይህ ጥያቄ  ዋና ጥያቄው ነው ወይ? ብለንም መደመም ኣለብን:: መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የቦኮ ሃራም መስራች የነበረው መሃመድ የሱፍ የምእራቡን ኣለም የቴክኖሎጂ ውጤቶች ኣጣጥሞ ይጠቀም የነበረ ሰው ነበር። ዘመናዊ መኪና ይነዳ የነበረ፣ ዘመናዊ ላብታፕ የነበረው፣ የአለምን የምግብ ኣይነቶች እያማረጠ የሚበላ ጥሩ ጥሩ ጫማዎችን የሚያደርግ ሰው ነበር። ቴክኖሎጂውን ይደሰት የነበረ ሰው ነበር። የምእራቡን ኣለም  የበረከት እጅ  በዚህ በኩል ወዶታል ወይም በረከት ነው ብሎታል ማለት ነው። በርግጥ ቲሸርትና ጂንስ መልበስ  ከልክሏል። ይህ እንግዲህ በራሱ ጫካ የሚከተ ነው ወይ ? የሚለውን  ጥያቄ ያስነሳል። ቦኮ ሃራም የምእራብ ትምህርት ከሚላቸው ውስጥ ኣምርሮ የጠላው ከምእራብ የተነሳውን የዴሞክራሲ ባህል ነው። ምርጫን፣ የህዝቦች ልእልና ጉዳይን ሃራም ብሎታል። እነዚህ እሴቶች በርግጥ ከምእራብና ከአሜሪካ ኣካባቢ የተነሱና የዳበሩ ቢሆኑም ዛሬ ዘመን ግን በመላው ዓለም ተቀባይነት ያገኙ የዓለም እሴቶች ሆነዋል። የሰው ልጆች የስልጣኔ ደረጃዎች በመሆናቸው አንዳንዶች ቀደም ብለው ሌሎች ዘግየት እያሉም ቢሆን ዓለሞች ወደነዚህ እሴቶች እየተዘረጉ ነው። ሃይማኖት ሳይለይ የዓለም ህዝብ ተካፍሏቸዋልና ቦኮ ሃራም ይህንን ባህል ሃራም ሲል ሃራም ያለው ምእራቡን ብቻ ሳይሆን የዓለምን ህዝቦች እሴቶች ነው። ለዚህም ነው ሽብረተኝነት ኣለማቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው ያደረገው። ከሁሉ በላይ ቦኮ ሃራምም ይሁን ኣልሸባብ ወይም ኣልቃይዳ ወይም ኣይሲስ ከዴሞክራሲ ባህል ጋር መጋጨታቸውና ይህንን ባህል ለመቀልበስ መሞከራቸው ከማንም በላይ ከምእራብም በላይ ጠላትነቱ ለራሳቸው ለአፍሪካ ሃገራት ነው። ለምሳሌ ቦኮ ሃራምን ብንወስድ ቦኮ ሃራም የምእራብን ትምህርት ሃራም ካለ በሁዋላ ሊያመጣ የፈለገው ዓለም የተለየ ነው። የትምህርት ካሪኩለሙ ምን ሊሆን እንደሚችል ባናውቅም ነገር ግን በሸሪያ ህግ የምትመራ እስላማዊት ሃገር ፈልጓል። ይህቺ ኣገር ደግሞ ከኣንድ መቶ ሃምሳ በላይ ቋንቋዎች የሚነገሩባት፣ በህዝብ ብዛቷ ከኣፍሪካ ኣንደኛ የሆነች፣ከሃይማኖት ኣኳያ ሃምሳ በመቶ የሚሆነው ክርስቲያን በሆነበትና ኣርባ ሶስት በመቶ ገደማ ሙስሊም በሆነባት ኣገር ናይጀሪያ ነው። ቦኮ ሃራም ለኣፍሪካ ከማንም በላይ ኣደገኛ ነው የሚያሰኘን ይህንን የሸሪያ ህግ ተግባራዊ ሊያደርግ ያሰበው እንደ ናጀሪያ ባለ ክርስቲያን በሚበዛበት ኣገር፣ እንደ ካሜሩን ባለ ሰባ በመቶ የሚሆነው ህዝብ ክርስቲያን በሚሆንበት ኣገር ውስጥ መሆኑ ነው። ቦኮ ሃራም ይህንን ኣላማውን ተግባራዊ ለማድረግና እስላማዊ መንግስት ካሜሩንን ለመመስረት ሰባ በመቶ የሚሆነውን ሙስሊም ያልሆነውን ህዝብ ማረድ ሊኖርበት ነው ማለት ነው። ናይጀሪያ ውስጥ ግማሽ በላይ የሚሆነውን ህዝብ በጅሃድ ሊጨርስ ነው ማለት ነው። ምእራብ ኣፍሪካን እስላማዊ ግዛት ለማድረግ ሚሊዮኖችን ሊያጠፋ ነው ማለት ነው። ይሄ ነው ኣንዱ የቦኮ ሃራም ትልቅ ኣሸባሪነት። ኣሸባሪነት ለዚያ ቀጠና ከሁሉ በላይ ኣስጊ የሚያደርገው የህዝቡ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ብዝሃነት ነው። በርግጥ እስላማዊ መንግስት እንመሰርታለን የሚሉ ኣሸባሪ ቡድኖች እንደ ሊቢያ ባሉ ህዝባቸው መቶ በመቶ ሙስሊም በሆነበትም መረጋጋትን አላመጡም። ይህ የሚያሳየው ኣይሲስ በዓለም ላይ የሙስሊሙ ጥያቄ ኣለመሆኑንና መርሆዎቹ የሙስሊሙን ሃይማኖት የጣሰ መሆኑን ነው። ይሁን  እንጂ ግን በፍጥነት ያድጋል። አልሸባብ በሁለት ሺህ ኣራት ኣካባቢ ሲመሰረት ከነበረው ኣቅም ዛሬ ጠንክሯል። በዚህ ቀጣና አሸባሪነት የቦኮ ሃራምን መንፈስ ተከትሎ በቅርቡ  Jahba East Africa (የምስራቅ ኣፍሪካ ግንባር) የተሰኘ እስላማዊ ሚሊሺያ የተቋቋመ ሲሆን አሸባሪነት ኣፍሪካን በምእራብና በምስራቅ ለማመስ ተዘጋጅቷል። እንደሚታወቀው ጽንፈኝነት በአፍረካ ቀንድ አካባቢ ረዥም ታሪክ አለው። አክራሪነት ለዚህ ቀጣና አዲስ አይደለም። በ15ኛው ክፍለ ዘመን አንድ አህመድ ግራኝ የተባለ ጽንፈኛ ተነስቶ ኣይ ኤስን (IS) በአፍሪካ ቀንድ ለመመስረት ሞክሯል። ጅቡቲን፣ሶማሊያን፣ኢትዮጵያንና ኤርትራንና ጠቅልሎ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ብዙ ጥሯል። በዚህ ጊዜም በኢትዮጵያ ውስጥ ከትግራይ ጀምሮ ጎጃም፣ ጎንደር ወሎ ሸዋ ድረስ እጅግ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን ኣቃጥሏል፣ እጅግ ብዙ ክርስቲያኖችን የመስቀሉ ተከታዮች እያለ ገድሏል። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥም የግራኝ ኣህመድ አልጋዚ አይ ኤስ እንቅስቃሴ መቼም የማይረሳ ግዙፍ ታሪክ ነው። ግራኝ አህመድ ኣስቦት የነበረው የእስልምና መንግስት በአፍሪካ ቀንድ ሳይሳካ ቢቀርም ይህ መንፈስ ግን ኣልተመታም ነበርና ዛሬ ከመቶዎች አመታት በኋላ በተለያየ ስም ተከስቷል። ወጣቱ አህመድ ግራኝ የሚመስጣቸው አንዳንድ ወጣቶች የዚህን ሰው ህልም እውን ለማድረግ የወጣቶች ንቅናቄ ወይም አልሸባብ የሚል ድርጅት መስርተው ጅሃድ አውጀዋል።

 

ዘመናዊዎቹ የኣይ ኤስ  ተከታዮች አፍሪካን ምን ሊያደርጓት ነው ካልን ኣንዱ ትልቁ ጉዳይ ኣፍሪካን ከምርጫ ስርአት ማውጣት ወይም ወደዚያ የምታደርገውን ግስጋሴ ማቆም ይፈልጋሉ። ኣፍሪካን ወደ እስላማዊ ግዛትነት የመቀየር ፍላጎት ኣላቸው። ይህ ሙከራ ኣደገኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የዚህ የኣይ ኤስ መንፈስ ራሱ ከስልጣኔ ከሰው ልጆች ገስጋሽ ተፈጥሮ ጋር የተጋጨ ነው። አፍሪካ ከድህነት ለመውጣት ከሚያስችሉዋት መሳሪያዎች ኣንዱና ትልቁ ጉዳይ ትምህርት ሲሆን በተለይ ከምእራቡ ኣለም የምታገኘው ተጨባጭ የሆኑ የማቴሪያል ባህሎችና ተጨባጭ ያልሆኑ የኣስተዳደር  ባህሎች ወሳኝ ናቸው። በርግጥ ኣፍሪካ ራሷ ያሏት ግሩም ባህሎችም ካለችበት ዝቅተኛ የድህነት ወለል እንድትነሳ ኣቅም ይሰጡዋታል። ገስጋሽ እንድትሆን የተውጣጡ ጥበቦችን በተግባር እያዋለች ነው የምታድገው። ወደ ኣነሳነው ጉዳይ እንመለስና ቦኮ ሃራምና ኣልሸባብ የዴሞክራሲ ባህልን ሲዋጉ መጥፎ እና ሃራም ባህል ሲሉ የሚገርመው ግን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለመጥፎ ስራ በመጠቀም ለጅሃድ ተግባር ማዋል ጀምረዋል። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን በቅርቡ ኬንያ ውስጥ የተሞከረው የኣንትራክስ ስነ ህይወታዊ የሽብር ስራ ነው። ኬንያ ውስጥ የተያዘው ይህ የአንትራክስ ቫይረስን በመጠቀም ሊሰራ የነበረ ወንጀል ያጋለጠው ነገር ቢኖር ይህ ቡድን መልካም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እየረገመ ነገር ግን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ደግሞ ለግድያ ስራ ይጠቀማል ማለት ነው። ሃራም መባል የነበረበት እንዲህ ኣይነት ባህልን ማዳበር ነበር። የዘመኑን የቴክኖሎጂ ውጤቶች የማህበራዊ ድረገጾችንም እንደዚሁ ወንጀል የሚሰሩባቸው በመሆኑ ይህ ቡድን በእስልምናም ሆነ በሰው ልጆች የሞራል መለኪያ በየትኛውም እምነት ሃራም ነው። ጅንስ መልበስን ሃራም እያለ በአንትራክስ ቫይረስ ጅሃድ መፈጸምን ቅዱስ ካደረገው ይህ ቡድን በርግጥ ሰይጣናዊ ነው።

 

 

ዝንባሌ ወደ ሚስብ ጥያቄ እንመለስ። ተመልከቱ ይህ ቡድን ከሙስሊሙ፣ ከስልጣኔ፣ ከክርስቲያኑ፣ ከዓለም ሁሉ የተጣላ ነው። ግን ደግሞ ኣፍሪካ ውስጥ ያድጋል። ኣንድ ጊዜ ብቅ ብሎ እልም እንደሚል ሽፍታ ኣይደለም። ለምን እንደዚህ ሆነ? ምን ምቹ ሀኔታ ኣግኝቶ ነው ሽብርተኝነት የሚያድገው የሚለው ጥያቄ በጣም መሳጭ ነው። አፍሪካ በተለይ ለሽብርተኞች ምቹ የሆኑ አካባቢዎችን የፈጠረችበት ሁኔታ ኣለ። ከነዚህ ምቹ ሁኔታ መገለጫዎች መካከል አንዱ የማህበራዊ ፍትህ መጓደል፣ ሌላው ደግሞ ከፍተኛ ስራ ኣጥነትና ድህነት፣ ሌላው ደግሞ የአፍሪካ ሰኪዩሪቲ አቅም ውሱንነት፣ የትምህርት አለመዳበር፣ ምቹ መልክአ ምድራዊ ሁኔታዎች (ያልዳበረ ኢንፍራስትራክቸር) ተደማምረው ነው። ኣሸባሪን የሚረዱ ቡድኖች በተለያየ ገንዘብ ድሃውን ወጣት መያዝ የሚችሉባት ኣህጉር በመሆኑዋ ለኣሸባሪነት ማደግ ኣስተዋጾ ያደርጋል። መሄጃ ያጡና የመረራቸውን ወጣቶች በትንሽ ጥቅም ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ የኣፍሪካ ሃገራት ከፍተኛ የሆነ የመብት ረገጣ ያለ በመሆኑ ግፍ የበዛበት ወጣት ኣለምን ጠልቶ የኣሸባሪነት መንፈስ ቢጠናወተው ብዙ ኣይገርምም። ሌላው ጉዳይ የትምህርት ማነስና የዋህነትም ይኖራል። ኣንዳንድ ለሃይማኖታቸው በጣም ቅንዓት ያላቸውን የዋህ ሙስሊሞች እየመለመሉ ኣሸባሪ ሊያደርጓቸው የሚችሉባቸው ሁኔታዎች ኣፍሪካ ውስጥ ይሰፋል። የመንግስታት ኣምባገነናዊ ባህርያት በራሳቸው በኣንድም በሌላም መንገድ ጽንፈኛ ዜጎችን ሊያፈራ ይችላል። በሌላ በኩል በኣፍሪካ ውስጥ በግልጽም ይሁን በህቡእ በማንነት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ  ኣመለካከት ካለ ኣክራሪነት እንዲያድግ ያደርጋል። የቡድን ጭቆናዎች ኣክራሪዎች እንዲበዙ ስለሚያደርግ ይህ ሁኔታ ኣሸባሪነትን እንዲያድግ ያደርገዋል።

 

ስለ ኣሸባሪዎች ስናስብ ትልቁ ስጋት ያላቸው ዓላማ ብቻ አይደለም። ወደዚያ ህልም ኣይደርሱም። ነገር ግን ወደ ህልማቸው የሚወስደው ስትራተጂ ነው ለኣፍሪካ በጣም ኣደገኛው ነገር። ለማይደርሱበት ህልም የሚሄዱበት ጎዳና ብዙ ችግሮችን ያመጣል። ወደ ኣላማቸው የሚወስደው የትግል ስትራተጂ ደግሞ ጅሃድ በተለይም ኣጥፍቶ መጥፋት ነው። በብሄር ላይ ወይም በፖለቲካ ርእዮት ላይ የሚደረግ ልዩነት የቱንም ያህል ቢከር ኣጥፍቶ ጠፊነት ኣይኖረውም። ሃይማኖታዊ ጽንፈኝነት ግን ይህን ስትራተጂ ተግባራዊ ለማድረግ የተወሰኑ የዋህ ሰዎችን ያስገኛቸዋል። ከሞት ወዲያ ለሚኖር ኣዲስ ህይወት እንዲቋምጡ በማድረግ፣ በጅሃድ ስራቸው ከአምላክ ሽልማት እንደሚጠብቃቸው በማሳመን የዋሆች በኣጥፍቶ ጥፋት ስራ ላይ እንዲሰማሩ ያደርጋል። ታዲያ ከሙስሊሙ አካባቢ እንዲህ አይነት አንዳንድ አሸባሪዎች ቢነሱም አብዛኛው የሙስሊሙ ማህበረሰብ በየትም አለም ዴሞክራሲን ፈልጓል። እነሆ ዛሬ የአረብ ሃገራትም በዴሞክራሲ ትግል ላይ ይገኛሉ።

 

በቅርብ አምታት የተነሳውን የአረብ ስፕሪንግ በሚመለከት አስተያየቶች ይሰጣሉ። አንዳንዶች የአረብ ስፕሪንግ ውጤታማ ኣልሆነም ይላሉ። ነገር ግን ኣይደለም። ትግል እኮ ነው የተያዘው። ወደ ዴሞክራሲ ለመግባት በኣንድ ሰሞን ተቃውሞ መንግስትን በመጣል የዴሞክራሲ ባህልን መገንባት ይከብዳል። የኣረብ ኣገራት ከነበሩበት ኣስተዳደር ዘየ ወጥተው ወደ ዴሞክራሲ ለመግባት የሚጠይቋቸው ዋጋዎች ይኖራሉ። መውደቅ መነሳት ይኖራል። የሚያስደስተው ነገር ግን የአረብ ህዝቦች ልባቸው በዴሞክራሲ ኣሳቦች ተማርኳል። አረብ ላይ የተነሳው የለውጥ ባቡር ይዘገይ ይሆናል እንጂ ወደ ሁዋላ አይመለስም። በርግጥ ወደ ዴሞክራሲ ስርዓት ለመግባት የህዝቦች ትግል እንዳለ ሆኖ የዴሞክራሲውን ስርዓት የሚመሩ የበሰሉ ፓርቲዎችና ለዴሞክራሲ ምቹ የሆነ ሲስተም ይሻሉ። ለምሳሌ ግብጽ ውስጥ የነበረውን የህዝቡን የዴሞክራሲ ትግል ስናይ ኣስደናቂ ነበር። ህዝቡ ለውጥና ዴሞክራሲ ፈልጓል። በመሆኑም ታገለና ሙባረክን ከጣለ በሁዋላ ስልጣን ላይ የወጣው መንግስት ግን በሃይማኖት ማንነት ላይ የቆመ የሙስሊም ወንድማማቾች ድርጅት ነበር። ይህ ድርጅት ጽንፈኛ ባይባልም ነገር ግን ጥርት ያለ ዴሞክራቲክ ድርጅት ኣይደለም።  ከማህበራዊ የኢኮኖሚ ተቋምነት ወደ ፖለቲካ የመጣ በመሆኑ ከፓለቲካ ስራው በመረዳጃ ሥራው የተሻለ መስራት የሚችል ነበር። ይህ ድርጅት ዴሞክራት የሆነ በመርህ ላይ የቆመ ባለመሆኑ  ሃገሪቱን ቶሎ ብሎ ወደ ዴሞክራሲ ለማሻገር ኣልቻለም። ግብጽ በዚህ በአረብ ስፕሪንግ ንቅናቄ ሰአት ያጣችው ዴሞክራሲን ሊቀበል የሚችል ሲስተም ነበር። ግብጽ አዲስ ዴሞክራሲ የሚባል ስርዓት መቀበል ስትሻ አዲስ አቁማዳ ያስፈልጋት ነበር።  አዲሱን የወይን ጠጅ በአሮጌ  አቁማዳ አያስቀምጡምና። ስለዚህ ለዴሞክራሲ ታገለች ግን ፓለቲካዋና ስልጣን ላይ የነበረው ፓርቲ ገና ከማንነት ፓለቲካ አልተላቀቀም ነበር። የግብጽን ዴሞክራሲ ሊያራምድ የሚችል ሲስተም መጀመሪያ ያስፈልጋል። አለዚያ  ከፈረሱ ጋሪው ይቀድምና ቁጭ ይላል።  ኣሁንም ግብጽ ገና ዳዴ እያለች ነው። ሌሎች የኣረብ ስፕሪንግ ያናወጣቸው ኣገሮችም ብዙ ስኬታማ ባይሆኑም ግን ርምጃ ጀምረዋል። ትግላቸው ቀጥሎም ብዙ ኣመት ሳይወስዱ ወደ ዴሞክራሲ ባህል ይገባሉ።እንደነ አልሸባብ ያሉና ቦኮሃራም ያሉ ኣሸባሪዎች የሚታገሉት ኣንድ ጉዳይ ይህን የኣረብ ስፕሪንግ ነውና ኣደገኝነታቸው ለተባበረችው ኣሜሪካ ወይም ለምእራብ ኣገሮች ብቻ ሳይሆን በዋናነት የሙስሊሙ ማህበረሰብና የኣፍሪካ ስጋቶች ናቸው። የራሳችንን ቀጣና ጉዳይ ስናይ እ.አ.አ. በ 2004  ዓ.ም ኣልሸባብ ከተመሰረት በሁዋላ ከበባድ ወንጀሎችን ፈጽሟል ኣሁንም ለቀጣናው ስጋትነቱ ቀጥሏል። የኣልሸባብ ኣንዱ ትልቅ ህልም ወጣቱን ወይም ኣዲሱን ትውልድ መያዝ ነው። በተለይ ሶማሊያ መንግስት ኣልባ ሆና በመቆየቷ ተስፋ የቆረጠውንና ስደት ያልተሳካለትን ወጣት እየመለመለ የተጠናከር  ድርጅት ነው። ከኣልቃይዳ፣ ኣይሲስና ቦኮ ሃራም ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገረው ይህ የቀጠናችን ኣሸባሪ በወጣቶች ላይ የሚሰራውን የምልመላ ስራ ለማስቆም የዚህ ቀጣና ወጣቶች የተደራጀ ስራ ሊሰሩ ይገባል። የምስራቅና ምእራብ አፍሪካ ወጣቶች አልሸባብ ሃራም ፣ ቦኮሃራም ሃራም፣ አልቃይዳ ሃራም፣አይሲስ ሃራም የሚል ድርጅት መስርተው አሳቡን በአሳብ ሊዋጉት ይገባል። ይህ ነው አንዱ የጸረ ሽብር ትግል ታክቲክ። አክራሪነት የአንድ ወቅት የሚሊተሪ ትግል ብቻ አይደለም። ሁል ጊዜም አሳብና .መንፈሱን መዋጋት ያስፈልጋል። የስልጣኔ የዴሞክራሲ የሴቶች መብትና ነጻነትን የሚታገል አሳብ ለመዋጋት ረዘም ያለ ጊዜን ይወስዳል። አሸባሪነት እንደሌላው ሽፍትነት ቦግ ብሎ ቶሎ የማይጠፋበት ምክንያት ሃይማኖታዊ ካባ ስለለበሰ ነው። ስለዚህ   የሃይማኖት ተቋማትም ትልቅ የጸረ አክራሪነት ትምህርት መስጠት አለባቸው።ስለዚህ አጠቃላይ ትግሉ ሁለት አቅጣጫ ያለው ሲሆን አንዱ የታጠቀን አሸባሪ ቡድን የተባበረ የሚሊተሪ አክሽን ሌላው ደግሞ የህዝባዊ ኢንተለጀንስ ስራና የጸረ ጽንፈኛነት ትምህርቶች ናቸው።

 

አልሽባብ በምስራቅ አፍሪካ የሚያልመው የእስልምና መንግስት ህልም መቼም ባይሳካም ነገር ግን ብዙ ወንጀል እየፈጸመ ኣገር ሊበጠብጥ መቻሉ ጥያቄ የለውም። ሶማሊያም ሆነች ሌሎች የቀጣናው ኣገራት ለኣልሸባብ የሚመቹ ሁኔታዎችን መቀነስ ኣለባቸው። በዌስት ጌት ሾፒንግ ሞል ውስጥ በመስከረም 2013   እ. አ. አ. ኣልሸባብ ባደረሰው ጥቃት ወደ ስልሳ ዘጠኝ ሰዎች ተገድለዋል እጅግ ብዙ ቆስለዋል። በሚያዝያ 2015 እ. አ. አ.   በጋሪሳ ዮኒቨርሲቲ ኮሌጅ ውስጥ በፈጸመው ጥቃት ወደ ኣንድ መቶ ኣርባ ስምንት ሰዎች ሲሞቱ ብዙዎች ቆስለዋል። ከሁለት አመታት በፊት ጂቡቲ ውስጥ በኣንድ ምግብ ቤት ውስጥ ይህ ኣሸባሪ ቡድን ጥቃት ፈጽሟል። ኣልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለማድረስ ሁል ጊዜም ማሰቡ ኣይቀሬ ነው። በአጠቃላይ የቀንዱ ሃገራት ለዚህ ኣሸባሪ ቡድን ሁልጊዜም ተጋላጭ ናቸው።አልሸባብ እየተጠናከረ የዔደን ባህረ ሰላጤና የቀይ ባህር ሰላም ሊያገኙ ኣይችሉም። የዓለም ህዝቦች ያለ ኣሳብ በዚህ ቀጣና ሊዘዋወሩ የሚችሉት የዚህ ቀጣና ስጋቶች ሲጠፉ ነውና እንደ ኣልሸባብ ኣይነቱን ኣሸባሪ ለመምታት ትልቅ ኣለማቀፋዊ ድጋፍ ኣለ።

 

ስለ ኣሸባሪዎች ማውራቱ ብቻ ሳይሆን መፍትሄዎች ኣምጡ ተብሎ መጠየቅም ይኖራል። የኣፍሪካ ሃገራት መንግስታት ይህን የኣሸባሪነት መንፈስና ስሜት ምን ያህል መምታትና ማንበርከክ ችለዋል የሚለውን መጠየቅ ተገቢ ነው። ከፍ ሲል እንዳልነው ጥረቱ ቢታይም ነገር ግን ስትራተጂዎቹ በሚገባ መጠናት ኣለባቸው። ኣንደኛ ኣፍሪካ መረዳት ያለባት ነገር ኣሸባሪነትን ብቻዋን ተዋግታ የምትጨርሰው ባለ መሆኑ ከተባበሩት መንግስታት ጋርና ከተባበረችው ኣሜሪካ ጋር ጠንካራ ህብረት መፍጠር ኣስፈላጊ ነው። እነዚህ ሁለት ኣካላት በተለይ በኣሸባሪነት ላይ ያላቸው አቋም ጠንካራ በመሆኑና አቅሙም ስላላቸው በጋራ መስራት ኣፍሪካውያን ለሚያደርጉት የጸረ ሽብር ዘመቻ ይረዳቸዋል። ይህ ትብብር በሚሊተሪ አክሽን ላይ ያተኮረ ብቻ ሳይሆን ህዝባዊ ግንዛቤንም እንደ አንድ ጸረ ሽብር ኦፐሬሽን የያዘ ቢሆን መልካም ነው። የትብብሩ አንድ መሰረት ኣሸባሪነት በባህርይው ኣለማቀፋዊ ይዘት ያለው በመሆኑ ነው። እንደነ ቻድና ኒጀር ሶማሊያ ያሉ በኢኮኖሚ የደከሙ ኣገራት እነ ቦኮ ሃራምንና አልሸባብን በራሳቸው ተዋግተው  ኣይጨርሱትም። ያላቸው የሰኪዩሪቲ ኣቅም ውሱንነት ጸጥታን ለማስከበር ያስቸግራቸዋል ወይም እጅግ ብዙ ዋጋ ያስከፍላቸዋልና ይህንን ሃይል ለመዋጋት ጥምረት ወሳኝ ነው።ኣፍሪካውያን ጥምረት ሲመሰርቱ ይህን የኣሸባሪነትን ችግር ከላይ ከኣህጉር ችግር ኣንጻር ኣይተው ክብደት ሊሰጡት ይገባል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገራት ኣሸባሪነት የሚለውን ስያሜ መጫወቻ ሊያደርጉት ኣይገባም። በኣለም ኣቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ ኣሸባሪዎችን እንዋጋ በጋራ እንታገል ሲባል የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችንና ተቃዋሚዎቹን ከነዚህ ቡድኖች ጋር እንዲመዘገቡለትና ኣብረው እንዲመቱለት ማስላቱ በጣም ርካሽነት ነው። ስሌቱ ራሱ የሽብርተኝነትን ብያኔ ያወርዳል። በመሆኑም ክብደት ያለው የጸረ ሽብር ኣካል ተቋቁሞ በጋራ ክንድ አሸባሪነትን መዋጋት ያስፈልጋል። እነ ግንቦት ሰባትና ኦነግ ጋዜጠኞች ከነኣልሸባብ ጋር ካልተመዘገቡልኝ ኣልሸባብን ኣልዋጋም ካለ በርግጥ የኢትዮጵያ መንግስት የዚህ ኣሸባሪ መንፈስ ኣልገባውም ማለት ነው ወይም ከልቡ የኣሸባሪዎች ተዋጊ ኣይደለም ማለት ነው። ሌላው ጉልህ ጉዳይ ደግሞ ኣሸባሪነት በቀጥታ በጦርነት ብቻ ሊጠፋ የማይችል  ጉዳይ መሆኑን መገንዘብ ነው። ኣሸባሪነት መሪዎች ሲመቱ ቢጠፋ ኦሳማ ቢላደን ሲሞት ኣልቃይዳ ደብዛው በጠፋ ነበር። ስለዚህ ኣፍሪካውያን ያለብን ውጊያ የሚሊተሪ ኦፐሬሽን ብቻ ኣይደለም። በርግጥ የሚሊተሪ ኣክሽኖች በስፋት ካልተካሄዱ ይህ ኣሸባሪ ቡድን ኣይመታም። ይሁን እንጂ ኣሸባሪነትን እስከ ሃቹ ለመምታት ኣፍሪካ ልታደርግ የሚገባት ትልቁ ውጊያ ኣሳብን መዋጋት መሆኑን ተረድታ ይህንን ተግባራዊ ስታደርግ ነው። ኣሸባሪነት ኣሳብ ነው። ኣሳብ የሚመታው ደግሞ በኣሳብ ነውና የኣሸባሪዎችን ትምህርት በማጋለጥና ኣሳቡን በተለይም ለሙስሊሙ ማህበረሰብ በማስረዳት የዋህ ደጋፊዎችን ማዳን ኣሸባሪነት መቆሚያ መሰረት እንዳይኖረው ያደርጋል። የሪጅን ትብብር ያስፈልጋል። ኬንያና ሶማሊያ ኢትዮጵያና ጂቡቲ ከዓለም ኣቀፉ ማህበረሰብ ጋር መስራት ኣለባቸው። ሌላው ጉዳይ ደግሞ ኣሸባሪ ቡድኖች እንዲመቻቸው የሚያደገውን ከባቢ መስበር ነው። ከዚህ ውስጥ ኣንዱ የማንነት ፖለቲካ ድባብን መስበር ነው። ኢትዮጵያ በብሄር ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዋ በኣንድም በሌላም መንገድ ሰው በቡድናዊ ማንነቱ ላይ የፖለቲካ ቤት እንዲሰራ የሚያበረታታ በመሆኑና ለጽንፈኝነት ቦታ ያለው በመሆኑ ቶሎ መውጣት ኣለባት። ኬንያ ምንም እንኳን በብሄር ላይ የቆመ ፖለቲካ ቢከለከልምና በብሄር ላይ መደራጀት በህግ የሚያሰቀጣ ወንጀል ቢሆንም ነገር ግን የቡድነኝነት ስሜት በህቡእ ያለ በመሆኑ ቡድኖች ከዚህ ስሜት መውጣት ይጠበቅባቸዋል። የሶማሊያ ሁኔታም በጣም ተሻሽሎ ሰኪዩላር መንግስት መመስረትና በመርህና ዴሞክራሲ ላይ መመስረት በዚህ ቀጣና ኣሸባሪነት እንዳይቀጥል ያደርጋል። ማህበራዊ ፍትህን ማሻሻል ተስፋ ቆርጦ ወደ ኣልሸባብ የሚጎርፈውን ወጣት ያነጥፋል። በኢኮኖሚ እድገቱ ላይ መስራት ወጣቱን ለስደትና http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61292ለኣሸባሪነት እንዳይጋለጥ ያደርገዋል። የማህበራዊ ፍትህ መጓደል፣ የመብት መታፈን፣ የደሞክራሲ እጦትና ድህነት በቀጥታ ለኣሸባሪነት ጥሩ ከባቢዎች በመሆናቸው ኣሸባሪነት ከዚህ ቀጣና እስከ ሃቹ ይመታ ዘንድ የኣፍሪካ ሃገራት ኣልሸባብንና ቦኮሃራምን ወይም ኣልቃይዳን በሚሊተሪ ኣክሽን ለመምታት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን የሃሳብ ውጊያ ያስፈልጋል። የጽንፈኝነትን ስሜት ለጊዜው በጠመንጃ እየመከትን ብንቆይም እስከ ሃቹ ጽንፈኝነትን የሚያጠፋልን ግን የዴሞክራሲን ባህል ስናዳብር ነው። ይህ ባህል በራሱ ጽንፈኝነትን ኣስወግዶ ከኣሸባሪነት ነጻ ያደርገናል።   የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ወንዶችና ሴቶች ወጣቶች መወያየት ግንዛቤ መያዝ ኣንዱ የትግል ስልት ነው። ጠንካራ ኣህጉራዊ ጸረ ኣሸባሪነት ትብብር ማድረግ ኣፍሪካውያን ይጠበቅብናል። ወጣቱ ትውልድ የኣሸባሪዎች ትምህርት ሃራም መሆኑን በሚገባ ሊረዱት ይገባል። ኣልሸባብ፣ ኣልቃይዳ፣ ኣይሲስና ሌሎችም ተመሳሳይ ድርጅቶች የያዙት ኣስተምህሮ በሙስሊሙ፣ በክርስቲያኑ፣ በቡድሂስቱ፣ በሰው ልጆች የሞራል መለኪያ፣ በኣለም ኣቀፍ የሰባዊ መብት መስፈርቶች ሁሉ ሃራም ነውና።

 

 

እግዚአብሔር ኢትዮጽያን ይባርክ

 

geletawzeleke@gmail.com

 

 

 

 

የቅኝ ገዢዎች ቀን –ቢንያም ሙሉጌታ ከኖርዌ

0
0

 

woyane
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አገዛዝ ቀኔ የሚለውን ግንቦት 20 ሊያከብር ከካድሬዎች ጋር ቀና ደፋ እያለ ነው። ለአንድ ብሄር የቆመ እንደሆነ ከጅምሩ ይፋ ያደረገው ወያኔ ለ25 ዓመታት አንድ አይነት አቁዋም በመውሰድ በቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ያለው መሆኑን በይፋ እያሳየ ይገኛል። ይህንን እኩይ ተግባር ስልጣን ከያዘ በኃላ እስከ ዛሬዋ ቀን በስራ ላይ በማዋል ላይ ነው። ታዲያ ይህንንም የወያኔ ታላቅ ሴራ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን የተደበቀ አይደለም።

የተወሰኑ የሕወሀት(ወያኔ) ቡድን አመራሮች ስልጣን ሙሉ በሙሉ ይዘው የሚያሽከረክሩት ከአንድ ጎሳ የመጡ ግለሰቦች የዘረኝነትንት መርዝ ነዝተው ሀገሪቱን በማበጣበጥ የስልጣን ጥማቸውን እየተወጡ ይገኛል። ይህንንና እርኩስ ራዕያቸውን ስራ ላይ ማዋል የጀመሩበትን ግንቦት 20 ሊያከብር በመሯሯጥ ላይ ናቸው።

በዘር መርህና በመከፋፈል የሚመራው ወያኔ ዛሬ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያን የመበታተንና የመከፋፈል ጉዞ የጀመረበትን ቀን ሊያከብር በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር የህዝብ ገንዘብ መድቦ አሸሼ ገዳሜ ሊል ዝግጁን አጠናቁዋል። በሀገራችን ውስጥ የብሄረሰቦች እኩልነት ሳይኖር ሰላም ሳይሰፍን በሀገሪቷ በተለያዩ ከልሎች ውስጥ የተለያዩ አስጨናቂ ሁኔታዎችና ነውጦች ነግሰው ባለበት ሰአት እነርሱ ሆዳቸውን ሊሞሉ ሻምፓኛቸውን ሊራጩ ከጫፍ ደርሰዋል።

ወያኔ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ አባላትን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጠንከር ያለ ሂስና ትችት የሚሰነዝሩበትን ዜጎች በማሰርና ደብዛቸውን በማጥፋት እንዲሁ በማሸማቀቅና የፀረ ሽብር ህግ እያለ ዜጎችን እየከሰሰ ሲሻው የሀገርን ሰላም በማደፍረስ እያለ ሲያሻው ህገመንግስት ስርአቱን ለመናድ እያለ ሲያሰፈልገው ዘር በማጥፋት ወዘተ የሚሉ ወንጀልና ክሶችን በማቅረብ አላማቸው ግልፅ የሆነና ዜጎችን ማጥቂያ አድርጎ የሚጠቀምበትን ጠላቶቼ ናቸው ብሎ በሚያስባቸው ኢትዮጵያውያን ላይ መከራን የሚያዘንብበትን ስልት ተጠቅሞ እየገዛ ይገኛል።

በአንድ ጎሳ የበላይነት የተገነባው ሰራዊት የግፍ ቋት የሞላባቸው የሀገራችን ህዝቦች በጠንካራና በአንድነት መንፈስ ተደራጅተው ለሚያቀርቡት ጥያቄ ምላሹ ጥይት ነው። የወያኔንም ስርዓት በተቻለው መንገድ ሁሉ እየታገለ ብዙ የደም ግብር ከፍሏል ኢትዮጵያዊ ዜጋ።

አሁን ላይ ግንቦት 20 ሊከበር ባለበት ወቅት ነፃነት፣ ዲሞክራሲ፣ ፍትህ፣ እኩልነት በሀገር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ደብዛቸው ጠፍቱዋል። የኑሮ ውድነት ጣራ ነክቶ ስራ አጥነት ተባብሶ ዜጎች ተስፋ ቆርጠው በተሽከርካሪ በእግርም የሀገሪቱን ድንበሮች አቁዋርጠው የሚሰደዱ በየመንገዱ የሚሞቱ ዛሬም ቁጥራቸው በአሳሳቢ ደረጃ ጨምሩዋል። ግንቦት 20 እኮ ለማን?

ወያኔ በኦሮሚያና በአከባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮችን አፈናቅሎ መሬት ዘረፋ ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ማድረጉ ግልፅ ነው። ህዝብን ጠርቶ ሳያወያይ የተቀናጀ የጋሪ ማስተር ፕላን በሚል ለአርሶ አደር ምንም ጥቅም በማያስገኝበት ሁኔታ በግዳጅ ወደ ተግባር በመግባት አርሶ አደርን ከነቤተሰብ ለችግር ዳርጎታል ታዲያ ይህንንም የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም በሁሉ የኦሮሚያ ክልል የሚገኝ ወጣቶችና ተማሪዎች ባደረጉት ተቃውሞ ውድ ሒወታቸውን በወያኔ ታጣቂዎች ተቀጥፈዋል።

በሌላ በኩል ባለፉት አመታት የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላማዊ መንገድን በመጠቀም ድምፃቸውን ለማሰማት ባደረጉት ሙከራ እስክ አሁንም ድረስ እያሰማ ያለውን ድምፅ ወያኔ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል። ታድያ የሙስሊም ማህበረሰብ የሰላማዊ ስልቶችን ተጠቅሞ ድምፁን ለማሰማትና የሚፈፀሙትን ህገወጥ ድርጊቶች እንዲቆም ለማስደረግ ሲጥር ቆይቷዋል።

በቀላሉ ከአንዱ ወደ ሌላው የሚዛመትና ለወያኔም ጠንካራ መልክቶችን የሚያስተላለፍ የትግል ስልቶችን ተጠቅመዋል ሆኖም ወያኔ መስሚያዬ ድፍን ነው በማለት የብዙሃኑንን ጥያቄ ንቆ ይልቁንም የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ ሌላ ስም በመስጠት ማንም በማያየውና በማይሰማው የቴሌቭዥን ጣቢያው ቅጥፈታዊ ሃረካቱን አስተላለፉዋል። ለኢትዮጵያውያን የሙስሊም ማህበረሰብስ የሚከበረው የወያኔ የግፍ በዓል ግንቦት 20 ምኑ ነው?

ወያኔ ወልቃይት ጠገዴ በትግራይ ክልል ስር በግድ እንዲተዳደሩ ማድረጉ በነዋሪዎችም እምቢተኛነት መቀጠሉ የሚታወቅ ነው። የገዢው ቡድን ይህንን አቋሙን አፅንቶ ቀጥሏል በነዋሪዎችም ሲነሳ የቆየው ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ እንዳለ አለ። በአከባቢው ዛሬም ድረስ ውጥረት ነግሷል። የወያኔ የፀጥታ ሀይሎች በስፋት ሰፍረው ይገኛሉ በዚህ የማንነት ጥያቄ ብዙዎች ለእስር ተዳርገዋል ብዙዎች ተፈናቅለዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ውስጥ ወያኔ እረጅም እጁን በማስገባት ባለፉት ጊዜያት በታሪካዊ ገዳማት ላይ በልማት ስም በገዳማውያን አባቶች ላይ እየፈፀመ ያለው እንግልትና መፈናቀል በቅድሳን መናኸሪያነታቸው በመናንያን መሸሸጊያነታቸው የሚታወቅና ከ1600 ዓመታት በላይ እድሜ እንዳላቸው የሚነገርላቸው ክብራቸውና ሞገሳቸው ተጠብቆ የቆዩ እንደ ዋልድባ ገዳም በልማት ስም ወያኔ ክብራቸውን ደፍሩዋል።ታሪክነታቸውን አስረስቶ ለስኳር ፋብሪካነት በሚል ቦታውን እያረሰ ገዳማዊያኑ እንዲሰደዱ አድርጉዋል። ወያኔ የገዳማዊያን መብት ማክበርና ማስከበር ቅርስና ታሪክን በክብር መጠበቅ ሲገባው ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ነው የወያኔ ነገር።

የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ግድ የማይለው ስርአቱ ከፍተኛ የተፈጥሮ ሀብት ክምችት ያላቸውን ድንበር አካባቢ የሚገኙ መሬቶችን ቆርሶ ለጎረቤት ሀገር ሱዳን አሳልፎ ሰጧል። ወያኔ የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም የሚፃረር የለም መሬት ነጠቃንና ወረራን ላለፉት 25 ዓመታት በማን አለብኝነት ሲዘርፍ ሲያዘርፍ ቆይቱዋል።

ወያኔ ስለጣን ከያዘ ጀምሮ ህዝባችንና ሀገራችን ቃላት የማይገልፀውን መከራ አስተናግደዋል። ግንቦት 20 የሚያስታውሰን የመከራ ዘመናችን ምን ያህል እንደተጏዘ ነው። ፀረ ኢትዮጵያውያን ስርዓት ከስሩ ነቅለን ጥለን ሉዓላዊነቷና የግዛቷ አንድነት የተከበረባት እኩልነት፣ የህግ የበላይነትና ዲሞክራሲ የሰፈነባት የበለፀገች ሀገር መስርተን ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ በአንድነት እንነሳ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

 

ኳስን እንደ ተቀጣጣይ ቦምብ! –ሃብታሙ ይግዛው: ኖርወይ

0
0

82e80af3-f106-4179-a09f-0e167efbcea7ገና ከጅምሩ ጥሩ ድጋፍ ያልተለየው የእግር ኳስ ጨዋታችን አንድ ጊዜ ሲያዝናናን አብዛኛውን ጊዜም እርር፣ ድብን እያደረገን ብዙ የሚባል ዕድሜን አስቆጥሯል። የሰሙኑ ደግሞ ብስጭት ብቻ ሳይሆን ቁጭትም ነው።
ለኳስ ያለንን ከፍተኛ ፍቅር በጊዜ ጠንቅቆ ያወቀው መሰሪው መንግስታችን ይህን አባዜአችን አሁን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ለጥፋት ሊጠቀምበት ደፋ ቀና ሲል በግልጽ እየታየ ነው።

እኔ ምልከታየን እንዲህ ላስቀምጥ። እናንተ ደግሞ በእግር ኳስ ሱስ ለሰከሩት ውድ ወንድሞቼ ይህን መልዕክት አድርሱልኝ።

ለየት ባለ ሁኔታ ላለፉት 25 ዓመታት በብሄራዊ ደርጃ የታየው የውጤት ማሽቆልቆልም ሳይበግረው ኳስ ቀንደኛ የወጣቶች ማሰሪያ ሱስ ሆኖ ቀጥሏል።
ጥያቄው፦ለምን ይህ ሊሆን ቻለ?

መልሱን አብረን እንይ፣ በመጀመሪያ ከዚህ ጋር ተያይዘው መነሳት የሚገባቸውን ሌሎች ጥያቄዎችን አናንሳለን።
በአንድ ወቅት ሀገራችን ውስጥ አንድ ደህና የሚባል ስታዲዮም መቼ ይገነባል? ተብሎ ለቀረበለት ጥይቄ መንግስታችን የመለሰውን መልስ ብዙዎቻችን እናስታውሳለን።
ታዲያ አሁን ላይ ምን አዲስ ነገር መጣ?
ምንስ ተለወጠ?
የህዝቡን ፍላጎት ባላገናዘበ መልኩ ታላላቅ ስታዲዮሞችን እንገነባለን ያሉን ምን ተገኝቶ ነው?
ርሃብ ከህዝባችን ስለተወገደ?
ችግር፣ ስድት ስለቀነሰ? የኑሮ ውድነቱ ጋብ ስላለ?
ወይስ አሳቢው መንግስታችን ለህዝቡ ስሜት ተቆርቁሮለት ይሆን?

ጭራሽ በአንድ ክልል ውስጥ ሁለትና ሶስት ታላላቅ ስታዲዮሞችን መገንባት ለድሃው ህዝብ የሚሰጠው ፋይዳስ ምንድን ነው?
ምቀኛ፣ ጸረ ልማት፣ በየቀበሌውስ ቢገነባ ምን አለበት? ምን ችግር አለው? የመሳሰሉ የቂሎች ማታለያ ሃሳቦችን ይዛችሁ እንደማትሞግቱኝ ተስፋ አደርጋለሁ፣ ምክኒያቱም እኔ ለልማታዊ ግንባታ ተቃውሞ የለኝም። ነገር ግን ሴራ ተጠንስሶለት፣ ነገር ተቆርጦበት ለጥፍት የሚገነባን ማናቸውንም ግንብ አጥብቄ እቃወማለሁ! የጥላቻ ሃውልቶችንም ጨምሮ።
አንድ ጊዜ ቆም ብለን ስናስተውል፣ ዕርስ ብዕርሳቸው እየተገፋፉ ከሚመጡብን ግርምታዎች አንዱ ይህ ይሆናል።
የስታዲዮም ግንባታን የፈቀድው “ልማታዊው መንግስታችን” ስታዲዮም ውስጥ ሆኖ ሃሳብን በጋራ መግለጽን ግን አጥብቆ ይቃወማል፣ የተገኙትንም አይቀጡ ቅጣት ይቀጣል። እየተገነቡ ያሉት አልያም ተገንብተው ያለቁት ስታዲዮሞች ታዲያ ጥቅማቸው ምንድን ነው?
መልሱ አጭርና ግልጽ ነው!
#አንድነት እና #ህብረትን ከበራሪ ጥይት አብልጦ የሚፈራው የውሸቱ መንግስታችን ኳስን እንደ ዕድሜ ማራዘሚያ እየተጠቀመበት ይገኛል።
ህዝብን ከህዝብ ማጋጨት ዋናው አላማው ነው። በተለይ በተለይም አልንበረከክ ያለውን የአማራውን ህዝብ እርስ በርሱ በማናከስ የለውጥ ሀይል የሆነውን ወጣት አብሮ በአንድ ላይ እንዳይታገል የታለመ መርዘኛ ሴራ ነው።
በተመሳሳይም አንድን ህዝብ ከሌላ ህዝብ ጋር ማቧጨቅ ትልቁ የመንግስታችን ህልም ነው። የመሃል ሀገሩን ህዝብ በዙሪያው ከከበበው ህዝብ ጋር ማተናኮስ አልፎ ተርፎም በክልሎች፣ በህዝቦች መካከል ያለውን አለመተማመን ጎልቶ እንዲወጣ ማድረግ የዕቅዶች ሁሉ አውራ ነው። ሰሞኑን ከወደ ጎንደር የሰማነው ዜና የዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው።

#ልብ ያለው ልብ #ይበል!
የባህር ዳር ወጣቶች የተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎችን ከከተማ ወጥተው አቃባበል ባደረጉላቸው በሳልስቱ
የጎንደር ወጣቶች የቡና ብድን ደጋፊዎችን ደበደቡ ተብሎ ሲራገብ ልንነቃ ይገባናል። እንደባላንጣው የሚቆጥረውን የመቀሌ ቡድን በሰላም ተቀብሎ የሸኘው ጀግናው የጎንደር ወጣት ገራገር እና አራዳ የሸገር ወጣቶችን ተተናኮሰ ሲባል አእምሮየ ለመቀበል ከበደኝ።

መንግስት ኳስ የሚሉትን አደገኛ ሱስ ወጣቱ ጫንቃ ላይ ጭኖ በሰላም መጨፈሩን ገፈቶበታል። ይህን ያልተረዳው ወጣት መብቴ ነው በማለት ትንሿን ኳስ ኑሮው አደረጋት።  በእለት ከእለት የማህበረዊ ኑሮው የሚያጋጥመውን ችግሮች ከመወያያት፤ የወደፊት ዕጣ ፍንታውን ላይ ከመነጋገር፣ እንዲሁም ስለሀገሩ ፓለቲካዊ ሂደቶች ከመማማር ይልቅ አብዛኛው የሀገሬ ወጣት ኳስን እንደስራው ቆጥሮ ቀን ከሌሊት ስለ ኳስ ሲወተውት ውሎ ያድራል። ይህ ነበር የሴረኛው መንግስታችን ዋና ዕላማ።
ታስቦበት እና ሆን ተብሎ የተደከመት የመንግስታችን ሴራ አሁን እሁን እየተሳካ ይመስላል! ወጣቱን ከሀገሩ የማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ ብሎም ከፓለቲካዊ ክስተቶች ጨርሰው የተገለሉ ወጣቶችን (disenfranchised youth) በመፍጠር ወጣቱን ብሎም ማህበረሰቡ አየር ላይ እንዲንሳፈፍ አድርጎታል።
በቁጥር ብቻውን አንድ ትልቅ ሀገር የሚወጣውን የኢትዮጵያ ወጣት እያለ እንደሌለ ሆኗል። አሁን አሁን ደግሞ ወጣቱ የሙት መንፈስ በላዩ ላይ ተነፍቶበት ራሱ መንፈስ ሆኖ ምንም ነገር ሲያደርግ አይታይም።

ምን ይሻላል?
መፍሄው አጠር ባለ አንድ ሀረግ ሲገለጽ ወጣቱ “ራሱን መውደድ” አለበት የሚል ይሆናል። ራስን መውደድ ማለት ወጣቱ ከሱስ ራሱን አላቆ አካባቢውን የራሱ ማድረግ ይኖርበታል። ለህይወቱ አላፊነትን መውሰድ ይጠበቅበታል። ራሱን ከሱስ ነጻ ያላወጣ ወጣት ማንንም ነጻ ለማውጣት ከቶውንም አይችልም። በሱስ የተነደፈ ወጣት በተሽከርካሪ መኪና ሊመሰል ይችላል፣ ሲጭኑት መጫን ፣ሲነዱት መነዳት ብቻ። ከሱስ ያልጸዳ ማህብረሰብ መጨረሻው ውድቀት ነው። አውሮፓ ሳንሻገር በሱዳን፣በሶማሊያ፣ብሎም በየመን የወጣቶችን ተሞክሮ ልንማርበት ግድ ይለናል። የመጀመሪያዎቹ ተጠቂዎች፣ ተጠያቂዎችም እኛው ራሳችን ነን።
ጎንደር፣ አዋሳ፣ አዳማ፣ ባህርዳርም ሆነ አዲስ አበባ ያላችሁ የኳስ ሱሰኞች በስማችሁ የሚፈጸመውን ተራ እንካስላንቲያ በአስቸኳይ አጣርታችሁ አስወግዱ። የሴረኛው መንግስታችን መጠቀሚያ ሆናችሁ ለሚደረገው የሞት ሽረት ትግል እንቅፋት መሆን የለባችሁም።

ኑ!  ስለ ሀገራችን በግልጽ እንወያይ።

ሰላም ይብዛላችሁ!

ኮሎኔል መንግስቱን ይዘዉ የወጡት ካፒቴን አዉሮፕላኑ ዉስጥ የሆነዉን ለመጀመሪያ ጊዜ ነገሩን Yederaw Chewata

0
0

ኮሎኔል መንግስቱን ይዘዉ የወጡት ካፒቴን አዉሮፕላኑ ዉስጥ የሆነዉን ለመጀመሪያ ጊዜ ነገሩን Yederaw Chewata

mengistu


አቶ ዮናታን ተስፋዬ የክስ መቃወሚያቸውን አቀረቡ

0
0

11915DCC-DC4C-4FA0-9E64-642C77ADD980_cx0_cy13_cw0_w987_r1_s_r1አቶ ዮናታን ተስፋዬ እስር ቤት እንደሚገኙ ይታወቃል። ጉዳዩን የሰማው ፍርድ ቤት አቃቤህግ መልስ እንዲሰጥ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በሽብር ድርጊት ወንጀል አቃቤ ህግ ክስ የመሰረተባቸው የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ትናንት የክስ መቃወሚያቸውን አቀረቡ። አቶ ዮናታን ተስፋዬ እስር ቤት እንደሚገኙ ይታወቃል። ጉዳዩን የሰማው ፍርድ ቤት አቃቤህግ መልስ እንዲሰጥ ቀጠሮ ሰጥቷል። የድምጽ ፋይሉን በመጫን መለስካቸው አምሃ ትናንት የላከውን ዘገባ ያድምጡ።
Source – VOA

ማኅበራዊ እሴት እንደ አገር እንድንኖር ካደረጉን ነገሮች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛ መሆኑን በኦስሎ የተደረገ ስብስባ ላይ ተገለጠ (ጉዳያችን ዜና)

0
0
የስብሰባው ማስታወቂያ 
unnamedበኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ሚያዝያ 29፣2008 ዓም ባባተሪ አዳራሽ በኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ አዘጋጅነት በማኅበራዊ እሴት ላይ ያተኮረ ትምህርታዊ  ውይይት ተደርጎ ነበር።በውይይቱ  ላይ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ በኖርዌይ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዙፋንን ጨምሮ ሌሎች ምሁራን እና በኦስሎ እና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል።
የውይይቱ መርሃ ግብር ከመጀመሩ በፊት የመርሃ ግብሩ መሪ የስብሰባው አላማዎች ማህበራዊ እሴት ምንነትን ማሳወቅ፣እንደ ሕብረተሰብ እና እንደ አገር ያለንበትን ደረጃ ማጤን እና ለመፍትሄው ያለንን ድርሻ መለየት መሆኑ ገልጦ ማሕበራዊ እሴት በሰዎች መካከል እና በማህበራዊ ተቋማት መካከል እና ግለሰቦችም ከእነኝህ ማህበራዊ ተቋማት ጋር ያላቸው ግንኙነት ሁሉ መሆኑን እና የእዚህ ሁሉ ትልቁ ዋጋ መተማመንመሆኑን አብራርቷል።
በመቀጠልም  በማኅበራዊ እሴት ዙርያ ፅሁፎችን ይዘው የቀረቡትን ሶስት እንግዶች ወደ መድረኩ ጋብዟል።
ፅሁፎች ይዘው የቀረቡት:
1ኛ/ ወ/ሮ ዙፋን አማረ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ሊቀመንበር፣
2ኛ/ አቶ እንግዳሸት ታደሰ የኖርወጅኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት መፅሐፍ አዘጋጅ እና
3ኛ/ አቶ አጥናፉ ወ/ማርያም በኖርዌይ አገር ከ24 አመታት በላይ በመምህርነት ያገለገሉ እና አሁንም እያገለገሉ ያሉ ናቸው።
በመጀመርያ ፅሁፋቸውን ያቀረቡት ወ/ሮ ዙፋን ሲሆኑ የእርሳቸው ፅሁፍ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር።ይሄውም:
– ሀብት በእራሱ ሁለት አይነት መሆኑን እርሱም ሙት ሀብት ወይንም ፍሬ የማያፈራ እና ትርፍ የሌለው እና ሕይወት ያለው እና ፍሬ የሚያፈራ መሆኑን፣
– ሕይወት ያለው ወይንም ፍሬ የሚያፈራ ከሚባለው ውስጥ ማሕበራዊ እሴት አንዱ መሆኑን፣
– ማኅበራዊ እሴት ከሌላው የሚለየው የጋራ መሆኑ እንደሆነ፣
– አስፈላጊነቱ ለጋራ መተማመን፣ስነ ምግባር እና ማሕበራዊ ትስስሮች መሆኑን፣
– ማኅበራዊ እሴት የማይዳሰስ ሀብት እና ከተንከባከብነው እየዳበረ የሚሄድ መሆኑን፣
– ማህበራዊ እሴት በጥርጣሬ በተሞላ መንፈስ ለማስኬድ ከተሞከረ ደግሞ እየቀጨጨ የሚሄድ እና በኃላ አገርንም አደጋ ላይ የሚጥል ደረጃ እንደሚያደርስ ገልጠዋል።
በመቀጠል አቶ እንግዳሸት ታደሰ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው አብራርተዋል። እነርሱም:
– ማኅበራዊ ካፒታል ማለት የማኅበረሰብ የባህል ካፒታል (ፋይናንሻል ያልሆነ) ለምሳሌ አመጋገብ፣ትምህርት፣አለባበስ ሁሉ ላይ እንደሚቀለጥ፣
– የቋንቋ አጠቃቀም አስፈላጊነትን በ1916 ዓም ወደ አውሮፓ የሚመጣ ተማሪ ይሰጠው የነበረው ዝርዝር መረጃ አብራርተዋል፣
– የእድር አስፈላጊነት እና በተለይ በውጭ አገር ለሚኖሩ  ኢትዮጵያውያንም ያለውን ፋይዳ ከኦስሎ አንፃር  በማገናዘብ አቅርበዋል፣
– ከሃይማኖት ተቋማት አንፃር እና አሁንም በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ አንፃር በምሳሌ አስረድተዋል።
በመጨረሻም አቶ አጥናፉ ወ/ማርያም በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ማብራርያ ሰጥተዋል።እነርሱም:
– ትምህርት ከማህበራዊ እሴት አንፃር ያለው አስተዋፅኦ፣
– በተለይ ትምህርት ምን ያህል አንድን ማህበረሰብ እንደሚቀይር ሲያስረዱ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ”መጪው የዓለም ዕድል የሚወሰነው  በተማሩ ሰዎች ነው” የሚለውን አባባል በመጥቀስ ሰፋ ያለ ማብራርያ ሰጥተዋል፣
– ከኖርዌይ የትምህርት ፖሊሲ አንፃር እንዴት አንድ ሕብረተሰብ እንደሚገነባ በዝርዝር ገልፀዋል፣
– ከኖርዌይ ጋር በማነፃፀር በኢትዮጵያ ያለው አምባገነናዊ ስርዓት ምን ያህል በትምህርት ላይ ውድቀት እንዳደረሰ እና  ተከትሎ የመጣው የትውልድ ክስረት ከቀድሞ የመምህራን ማኅበር ትግል ጋር እያነፃፀሩ አብራርተዋል፣
– በምሳሌነት የሂሳብ ትምህርትን አንስተው በኖርዌይ የሂሳብ ትምህርት ለበርካታ ጊዜ መሻሻሉን እና አሁን ሂሳብ ለማህበራዊ ትምህርት፣ሂሳብ ለተፈጥሮ ሳይንስ ወዘተ በሚል መሰጠት መጀመሩን አውስተው የኢትዮጵያ ትምህርት ለዘመናት መሻሻል የሌለው እና በጥናት ላይ የተመሰረተ ሥራ አለመሰራቱ በማህበራዊ እሴት  ላይ ያለውን አሉታዊ ተፅኖ አብራርተዋል።
በመቀጠለም የሻይ እረፍት ከተደረገ በኃላ የጥያቄ እና አስተያየት የመስጠት ጊዜ ተሰጥቶ በቀረቡት ፅሁፎች ላይ ጥያቄ እና አስተያየቶች ተሰጥተዋል።በተሰጡት አስተያየቶች ላይም :
– ማሕበራዊ እሴት ለኢትዮጵያ የመኖር እና አለመኖር ጉዳይ ወሳኝ የመሆኑን ፋይዳ፣
– በቀደመ ታሪካችንም እድር፣እቁብ፣የቤተዘመድ ማህበር፣ የመሳሰሉት ሁሉ ሕዝብ አብሮ እንዲኖር ያደረጉ  የማኅበራዊ ተቋማት መሆናቸው እና አሁን ያሉበት ሁኔታ እየመነመነ መሆኑ፣
– ለእዚህም አሁን በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት እነኝህ ማሕበራዊ ተቋማትን ሆን ብሎ የማዳከም ሥራ እንደሚሰራ እና በምሳሌነትም በእድሮች ላይ ያለው ማዋከብ እና የመቆጣጠር ተግባር ተጠቅሷል፣
– የሃይማኖት ተቋማት እውነቱን የመናገር እና ስለ አገር የመጮህ፣ድሃ ተበደለ ፍትህ ጠፋ ብለው የመናገር ድፍረት አስፈላጊነት ተወስቷል።
በመጨረሻም የመድረክ መሪው የማጠቃለያ ሃሳቦች ሰጥቶ በቀጣይ ጊዜ ውይይቱ በስፋት እና በጥልቀት በኢትዮጵያውያን የጋራ መወያያ መድረክ የሚቀርብ መሆኑ ተገልጦ በዕለቱ ለተገኙት እንግዶች እና ተሳታፊዎች ከፍ ያለ ምስጋና ቀርቧል።

ጉዳያችን GUDAYACHN 

ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ ምኑ ነው?

0
0

(በኤልሳቤጥ ግርማ ከኖርዌይ)

በዚህ በያዝነው ወር በየዓመቱ ስለግንቦት 20 በተለያየ መልኩ ይሰበካል፣ ይገለጻል። ለሀገራችን ኢትዮጵያ ታምራዊ ለውጥ እንዳስመሰገበ ሁሉ ወሩን ሙሉ ሲተረክ መስማት እንደ ሀገራዊ መዝሙር የተለመደ ሆኗል:: በተለይ የሥርዓቱ ባለቤቶችና ደጋፊዎች ምስኪኑን ሕብረትሰብ ሳይቀር በማስገደድ ቀኗን “ልዩ ቀን” “የድል ቀን” “የስኬት ቀን” በማለት ሰይመው በአስረሽ ምችው ሲከበር ማየት ድፍን 25 ዓመታትን አስቆጠረ።
eprdf-tplf
ጀግናው የኢህአዲግ ሰራዊት ደርግ ኢሰፓ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬዲዮ ጣቢያ ተቆጣጥሮታል ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሦስት ብለው እንዳበሰሩን በእርግጥ ለጥቂቶች ግንቦት 20 የድል ቀን ነው:: ምክንያቱም ሀገሪቱን በአንባገነናዊ አገዛዝ ለማስተዳደርና የስልጣን ጥማታቸውን ለማርካት መሰረት የጣሉባት እና የአስራ ሰባት ዓመት የልፋት ዋጋቸውን ያገኙባት ልዩ ቀን ናትና:: በዚች ቀን ህብረተሰቡን በምስጢራዊ የአገዛዝ ስልት ለማስተዳደርና ስልጣናቸውን ዘላለማዊ ለማድረግ የነበራቸው ሕልም እውን የሆነባት ቀን ናትና በልዩ አከባበር ቢያከብሯት ሲያንሳት እንጂ አይበዛባትም::

የተወሰኑ የስራዓቱ አቀንቃኞችም ስለቀኗ መልካምነትና ከዚያች ቀን በኃላ አገራችን ኢትዮጵያ በልማት ጎዳና የገስገሰች፣ የዜጎች አኩልነት የተረጋገጠባት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ ሰባዊ መብቶች የተከበሩባት፣ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የታየባት፣ ህብረተሰቡን በእኩል የሚያስተዳድር መንግስትና ሕግ መንግስት የተመሰረተባት አገር እንድትሆን ግንቦት 20 ታሪካዊ የድል አሻራ እንደጣለች በኩራት አፋቸውን መልተው ይናገራሉ:: ይባስ ብለው ከውጭ ወራሪ ወይም ቅኝ ግዛት ኢትዮጵያን ነፃ ያወጧት ይመስል ግንቦት 20ን የነፃነት/ሀገራዊ ቀን ለማድርግ የሚሞክሩ ብልጣብልጥ የስራዓቱ ደንገጡሮችም አሉ::

በእርግጥ የደርግ አንባገነን መንግስት የአጼ ኃይለ ስላሴ መንግስትን ገርስሦ በምትኩ ወታደራዊ ጁንታ በመመስረት ስሙን በመቀያየር አገዛዙ ለ17 ዓመታት ኢትዮጵያን በብዙ ዘርፈ ብዙ ችግሮች በተለይ ሀገሪቱን መለወጥ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡትን 60 ሚኒስተሮች በመረሸን፣ ነጭና ቀይ ሽብር በማለት ሀገር ተረካቢ ትውልድን በማስጨፍጨፉ የኢትዮጵያ ህዝብ የደርግን ስርዓት አንቅሮ ተፍቶት ነበር። የለውጥ ያለሽ ብሎ በመጮህ ከደርግ አረመኔያዊ የጭካኔ አገዛዝ ነጻ ሊያወጣው የሚችል መለኮታዊ ኃይል እስኪፈልግ ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ለውጥ ፈላጊ ሆነ።

ህወሓት የህዝቡን ብሶትና እሮሮ ተጠቅሞ 17 ዓመት ጫካ ውስጥ ያረገዘውን መርዝ ለመርጨት ግንቦት 20 ደርግን ገርስሦ በትረ ስልጣኑን ጨበጠ። እዚህ ላይ ወያኔ የደርግን ስርዓት ሳያይና በትንሹም ቢሆን ለውጥ እንዲመጣ ጥረት ሳያደርግ ለትግል ወደ ጫካ መግባቱ ሀገራዊ ለውጥ አሳስቦት ሳይሆን የብሄር ፖለቲካ ጥማት እንደሆነ በትክክል መገንዘብ ይቻላል፤እያየነውም ነው። የብሄር ፖለቲካ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ በርካታ ብሄር ብሄረሰቦችን ለምታስተናግድ ሀገር ቀርቶ ለየትኛውም የአለም ሀገራት የማይበጅ መሆኑ የታወቀ ነው። ኢትዮጵያም የከፋፍለህ ግዛውና የጎሳ ፖለቲካ እንደማይጠቅማት ከዘመነ መሣፍንት ትምህርት ቀስማ ነበር። ዳሩ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የደርግን ሥርዓት ጥላቻና ሽሽት ዘረኛው ወያኔን ግንቦት 20 በሩን ከፍቶ እጁን ዘርግቶ ተቀበለ።

ወያኔዎች የደርግን ሥርዓት ገርስሰው መንግስቱ ኃይለ ማርያምን ወደ ዝምባብዌ ካስኮበለሉ በኋላ ሥልጣናቸውን ለማጽናት የይስሙላ ህገ መንግሥት አርቅቀው አጸደቁ። ለተወሰኑ ዓመታትም የነጻነት በርን ለመከፈትና ስላምና መረጋጋትን ለማስፈን የመጡ እስኪመስል ድረስ ሰላምን ሰበኩ። ከደርግ ጋር ንክኪ አላቸው ተብሎ የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን በሙሉ እስር ቤት ወረወሯቸው። ከገጠር እስከ ከተማ ህብረተሰቡ ለራሱ መጠበቂያ ብሎ የገዛዉን ትጥቅ ሳይቀር በሙሉ አስፈቱ። የኢትዮጵያ ህዝብ ግንቦት 20 በየዓመቱ “የድል ቀን” እያለ እንዲዘምር ተደረገ።

በእውኑ ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ ምኑ ነው? ይህ ጥያቄ በተለያየ መልኩ በሁላችንም አይዕምሮ ውስጥ እንደሚመላለስ እርግጠኛ ነኝ። መልሳችን ግን በራሳችን ምዕናባዊ እይታ ስለምንመለከተው የተለያየ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም ግን ከሁለት አማራጮች ሊዘል አይችልም። ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔዎች እንደሚሉት “የድል ቀን” ወይም ብዙዎች እንደሚስማሙበት “የውድቀት ቀን” መሆን አለበት። ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው ግንቦት 20ን “የድል ቀን” ማለታቸው በእርግጥም ትክክል ናቸው። ምክንያቱም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የአንባገነን ስልጣናቸውን ያፀኑበት እና በሦስቱም ዘርፍ ማለትም ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩበት ቀን ነውና።

እውነታው ሲገለጥ ግን ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ የውድቀት እና የውርደት ቀን እንጂ በምንም መመዘኛ የድል ቀን ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ለአንድ ሀገር የድል ቀን ሲባል ዜጎቿ እኩል ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል በጎ አጋጣሚ ወይም የኩራት ምንጪ ሲፈጠር ብቻ ነው። ግንቦት 20 ግን ከዚህ በተቃራኒው መሆኑን ግልጽ ሊያደርግ የሚችል ብዙ ማሳያዎች ከመኖሩም ባሻገር በኢትዮጵያና በህዝቦቿ ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ችግር ዘርዝሮ መናገር ይቻላል።

“የድል ቀን ሆይ የት ነሽ?ምንጭሽስ ከቶ ከወደየት ይገኛል?”
የኢትዮጵያ ህዝብ ከግንቦት 20 የተቀበላቸውን ገጸ እርግማኖች ለማሳያ ያክል እንደሚከተለው እናያለን፤

የብሄር ፖለቲካ የተፀነሰበት

የህወሓት ማፍያ ቡድን ገና ከጅምሩ ሃገራዊ ፍቅር ሰንቆ እንዳልመጣ ከስሙ መረዳት ይቻላል። የትግራይ ነጻ አውጪ ቡድን ብሎ መሰየሙ ለኢትዮጵያና ለህዝቧ እንዳልቆመ ለመረዳት ነብይነት አያሻውም ነበር። የከፋፍለህ ግዛው መርህን በማንፌስቶው ይፋ አድርጎ ይንቀሳቀስ እንደነበር ሰነዶች ህያው ማስረጃ ናቸው። ለስልጣን ማራዘሚያ በዋናነት የተጠቀመበት ዋናና ትልቁ አጀንዳ የብሄር ፖለቲካን ነው። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ካልሆነ በስተቀር ከስልጣን ሊወርድ የሚችልበት ምንም አይነት አጋጣሚ እንደሌለ በሚገባ ያውቃልና። የብሄር ፖለቲካ እያራመደ እርስበርሳችን እንዳንተማመን በብሄር ለያይቶናል። ይሄ የናንተ መሬት ነው፣ ይህ ደግሞ የነሱ ነው ወዘተ እያለ በቡድን ከፋፍሎናል። በብሄሮች መካከል መግባባት እንዳይኖር እነእገሌ እንዲህ አደረጓቹህ፣ ታሪካችሁ እንዲህ ነው በማለት መጀመርያ መምጣት ያለበት ብሄር ነው ወዘተ እያለ የብሄር ጥላቻ እንዲሰፍን ሀውልት ሰርቶልናል። አንድ ዜጋ ኢትዮጵያዊ ነኝ ከማለት ይልቅ በውሸት የብሄር እኩልነት ስም ኦሮሞ፣አማራ፣ ጉራጌ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ እያለ በየቦታው እራሱን እያዋረደ እርስ በእርሳችን በጥላቻ እንድንናቆር ማድረጉ የወያኔ የብሄር ፖለቲካ ውጤት ነው። ስለዚህም ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ የድል ቀን ሳይሆን የብሄር ፖለቲካ የተፀነሰበት የውርደት ቀን ነው። “የድል ቀን ሆይ የት ነሽ?ምንጭሽስ ከቶ ከወደየት ይገኛል?”

ትውልድ ገዳይ ሥርዓተ ትምህርት የተቀረጸበት

ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሀገር ተተኪ ዜጋ ፈጣሪ ተቋም እንደመሆናቸው መጠን የሃገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ፣ ታሪክንና ባህልን ከማሳወቅ ባለፈም በማንነት ላይ የተመሰረተ ጥራት ያለው ዜጋ ለማፍራት የሚቀረጸው ሥራተ ትምህርት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። ነገር ግን ወያኔ የቀረጸው ሥርዓተ ትምህርት ግን ትውልድን ገዳይና የተማሪዎችን አይዕምሮ ለምርምርና ጥናት የማይጋብዝ ዘላቂና አስተማማኝ ያልሆነ ጥራት የጎደለው ሥርዓተ ትምህርት ነው። ትምህርት ቤቶችም ተማሪዎችን በጥሩ ሥነ ምግባርና ባህልን ከማሳዎቅ አንጻር አስተምሯቸው ዝቅተኛና ከዚህ ግባ የማይባል መሆኑ ለትውልዱ መጥፋት ሌላው የወያኔ የስርዓቱ ውጤት ነው። ትምህርት ቤቶችን ስንመለከት ከተቀረጸላቸው ሥርዓተ ት/ት ጀምሮ ትውልድን ለመቅረጽ ቀርቶ በዜግነት ደረጃም እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚናገር ትውልድ እንዲጠፋ በማድረግ ረገድ ግንቦት 20 የራሷን ጥቁር ጠባሳ ጥላለች። አንዳንድ የዘመነ ወያኔ ተማሪዎች የሀገረን ታሪክ በሚገባ ካለማዎቅ የተነሳ ቅኝ ግዛት በተገዛን ኑሮ ሲሉ መስማት የሥርዓተ ትምህርት ውድቀቱን ማሳያ አንዱ መንገድ ነው።

የሃገር ዳር ድንበር የተደፈረበት

አንድ ሀገር የድል ቀን የምታከብር ከሆነ ለሀገርና ለህዝብ የሚቆረቆር መንግሥት አላት ማለት ነው። መንግሥት ካለ ደግሞ የሃገር ሉዓላዊነት ተጠብቆ፣ ታሪኳ ሳይበረዝና ሳይፋለስ ለትውልድ መተላለፍ ይችላል ማለት ነው። ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ግን የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ዳር ድንበሯ የተደፈረባት፣ ወደቧን ያጣችበትና ታሪኳ የተበረዘበት ዘመን ነው። ድሮ አባቶቻችን ቅኝ አንገዛም በማለት ታሪካችንና ባህላችን ሊበረዝ ከቶ አይችልም ብለው አጥንታቸውን ከስክሰው፣ ደማቸውን አፍስሰው፣ ውድ ህይወታቸውን ሰውተው ዳር ድንበሯን ከነሙሉ ክብሯ ያቆዩልንን ሀገር ወያኔ ለአረብና ህንድ ባለሃብቶች ማቀራመቱ ሳያንሰው ሱዳን የድርሻሽን ውሰጅ ብለው በመማጸን ላይ እንደሆኑ ስንሰማ በእውነትም ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ የውርደትና የውድቀት ቀን ነው። ዜጎቿ በሄዱበት ሞትና እንግልቱ ሳያንሳቸው በእራሳቸው ሀገር በሌላ ዜጋ እንደ እንስሳ ደማቸው ሲፈስና ህጻናት በገፍ ተግዘው ሲሄዱ ከማየት በላይ ምን የተለየ ውርደትና ውድቀት ይኖራል። “የድል ቀን ሆይ የት ነሽ?ምንጭሽስ ከቶ ከወደየት ይገኛል?”

ህዝቦቿ ለሞት፣ለስርና በስደት ለውርደት የተዳረጉበት

በወያኔ አገዛዝ ከ1983 እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከግንቦት ወር ጀምረን በግፍ ውድ ህይወታቸውን በስውርና በአደባባይ የተቀሰፉ፣ ለስር፣ ለእንግልትና ለስደት የተዳረጉ ዜጎችን የሰማይ አምላክ ይቁጠራቸው እንጂ በአኃዝ ማስቀመጥ እጅጉን ይዘገንናል። ተፈጥሯዊና ሰባዊ መብቶች በይፋ ተገርስሰዋል። የስርዓቱ አባል፣ ደጋፊና አገልጋይ ካልሆነ በስተቀር በሀገሩ ምድር ቀና ብሎ የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመደራጀት እና የመስራት መብቶች ፈጽመው መገደባቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። ወያኔዎች ግንቦት 20ን የድል ቀን ብለው ማክበር ከጀመሩ ጀምሮ በሀገሪቱ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የግፍ ጽዋ ሞልቶ ፈሷል። ህዝቦቿ በሄዱበት ሁሉ የውርደት ካባ እየተከናነቡ ተቆርቋሪ ያጣ ዜጋ በመሆኑ ዋይታና ልቅሶው ከመቸውም በላይ ጨምሯል። “የድል ቀን ሆይ የት ነሽ?ምንጭሽስ ከቶ ከወደየት ይገኛል?”

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ አገራችን የተለያየ መልክና መገለጫ ያላቸው በርካታ መንግሥታትን ያስተናገደች አገር ብትሆንም ለዘመናት ታሪኳን፣ ባህሏን፣ እምነቷን፣ አንድነቷን፣ ድል አድራጊነትን እና ዳር ድንበሯን ጠብቃ አስጠብቃ የኖረች እና መተሳሰብን፣ መከባበርን፣ እንግዳ ተቀባይነትን፣ ዘርንና ጎሳን መሰረት ሳታደርግ ለዘመናት የቆየች የጀግኖች አገር ነበረች። ነገር ግን ግንቦት 20 የለገሰን የአሳርና የግፍ ፍሬዎች በቀላሉ የማይሽሩ እኩይ ተግባር ናቸውና ታሪካዊ አገራችንን አደጋ ላይ ጥሏታል። ስለሆም ጊዜ ሳንሰጥ “የድል ቀን” የሚለውን ተረት ተረት ወደ ጎን በመተው በአንድነትና በህብረት ዛሬውኑ የውርደትን ቀን ወደ የድልና የክብር ቀን ሊቀየር ይገባል። ግንቦት 20 ለኢትዮጵያ ህዝብ የድል ቀን ሳይሆን የሞት፣የውድቀትና የውርደት ቀን ተብሎ ይስተካከል!ምነው ሽዋ! ድንቄም የድል ቀን…………

ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር በጥቅም ቁርኝት ስሙ የሚነሳው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን የ1.86 ቢሊዮን ፓውንድ ፕሮጀክት ተፈቀደለት

0
0

1464162766_25may16-salini-ethiopia
(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ የሚደረጉ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር ባለው የጥቅም ቁርኝት እንዲያሸንፍ እየተደረገ ይሰጠዋል እየተባለ የሚከሰሰው የጣሊያኑ ሳሊኒ ኮንስትራሽክን ተጨማሪ ግድብ እንዲሰራ የ1.86 ቢሊዮን ፓውንድ ስምምነት ተፈራረመ::

አዲስ ሊሰራ በታሰበ የኮያሽ ሃይድሮ ግድብ ፕሮጀክትን እንዲያሸንፍ የተደረገው ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ይህን ፕሮጀክት እንዲያሸንፍ በግልጽ የተደረገና ሌሎች ታዋቂ ኩባንያዎችን ያካተተ ጨረታ አለመካሄዱን የሚከሱት የውስጥ ምንጮች አሁንም ይህ ድርጅት እንዲያሸንፍ የተደረገው ከስርዓቱ ሰዎች ጋር ባለው የጥቅም ቁርኝት ነው ይላሉ::

ፕሮጀክቱ 6,000 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ማጠራቀሚያ ድምጽ መፍጠር 170m-ከፍተኛ ሮለር የተጠቀጠቀ ግድብ የሚያካትተው የኮይሽ ሃይድሮ ግድብ ወደ 6.460 GWh የኤሌክትሪክ ሃይል ያመነጫል:: የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ከአዲሱ ሃይል ማመንጫ ወደ 2,200MW የኤሌክትሪክ ሃይል ለማከፋፈል ያግዘዋል ተብሏል::

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት በርካታ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሃይል በርካታ ችግሮችን እየፈጠረ ሲሆን ሃገሪቱ ግን የመብራት ሃይልን ልለኬንያ; ሱዳና ጅቡቲ እየሸጥኩ ነው እያለች ነው::

የጣሊያኑ ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሳሊኒ) ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ አካባቢ እያካሄደ በነበረው የግድብ ግንባታ በኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ዙሪያ በሚኖሩ ማህበረሰቦች ላይ የረሃብ አደጋ መፈጠሩን ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል የተሰኘ አለም አቀፍ ተቋም ማስታወቁና በስፍራው በመካሄድ ላይ የነበረው የግድብ ግንባታ የቱርካና ሃይቅ የውሃ መጠን እንዲቀንስ በማድረጉ በሺዎቹ የሚቆጠሩ የካሮ ጎሳ አባላት ለረሃብ መጋለጣቸውን ድርጅቱ ማሳሰቡ እንዲሁም በግልገል ጊቤ ሶስተኛ የሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ምክንያት በአካባቢው እያደረሰ ነው ያለውን ጉዳት ለአለም አቀፍ የኢኮኖሚና የትብብር ድርጅት ያቀረበው ሰርቫይባል ኢንተርናሽናል በቱርካና ሃይቅ ላይ ህይወታቸው የተመሰረተ ከ100ሺ በላይ የማህበረሰቡ አባላት ለችግር መጋለጣቸውንም መዘገቡ አይዘነጋም::

16 የግንቦት 20 ፍሬዎች!

0
0

TTPLF

  1. በዐፄ ሠርፀ ድንግል ዘመን ቱርኮች ሀገራችንን ቅኝ ለማድረግ በማሰብ ባሕረ ነጋሽ ይስሐቅን (አሁን ላይ ጥሊያኖች ኤርትራ ያሏት የባሕረ ምድርን ገዥ) በመደለል በገዛ ሀገሩና ሕዝቡ ላይ ክህደት በመፈጸም የሚገዛውን የሀገራችንን ክፍል ይዞ እንዲከዳ በማድረግ ተጀምሮ የነበረው ነገር ግን ወዲያውኑ 1571ዓ.ም. ዐፄ ሠርፀ ድንግል ወደቦታው ዘምተው የከሐዲውን የባሕረ ነጋሽ የይስሐቅንና የወራሪውን የቱርክን ጦር በመደምሰስ ከሽፎ የነበረው፤ በኋላ እንደገና ከአራት ምዕት ዓመታት በኋላ በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ለ50 ዓመታት ተነጥሎ የነበረውና ፋሽስት ለቆ መውጣቱን ተከትሎ በተደረገው ዲፕሎማሲያዊ (የአቅንኦተ ግንኙነት) ጥረት እንደገና ወደ እናት ሀገሯ እንድትቀላቀል በማድረግ እንደገና ከሽፎ የነበረው ለበርካታ ምዕት ዓመታት የተደረገው ሀገራችንን ገንጥሎ የመውሰድ የጠላት ሀገራት ጥረትና እንቅስቃሴ በዚያ ምድር ላይ የእነኝህን ጠላት ሀገራት ዓላማ ግብና አቅድ የሚደግፉ የሚያስፈጽሙ የባሪያ ሥነልቡናና ሰብእና ያላቸው የእፉኝት ልጆችን በማፍራቱ እነኝሁ ዜጎች የሚባሉት የገዛ ሀገራቸውን የማፈራረስ ዓላማ አንግበው በመነሣት አሁን ለጊዜው ተደጋጋሚ ሙከራ ሲደረግባት የነበረችውን ባሕረምድር (በባርነት ስሟ ኤርትራን) የገነጠሉና ያስገነጠሉ ገንጣይና አስገንጣይ የጥፋት ኃይሎችን ያገኘንበት፡፡
  2. ዜጎች በዘር በሃይማኖት እንዲከፋፈሉ በመደረጉ የነበረ ፍቅራቸው፣ ትስስራቸው፣ መተማመናቸው፣ ሰላማቸው፣ አንድነታቸው እንዲጠፋ ተደርጎ በጠላትነት እንዲፈላለጉ በጥርጣሬ እንዲተያዩ ሲደረግ ያየንበት፡፡
  3. ግንቦት 20 ያነገሣቸው የጥፋት ኃይሎች መጥተው ከማየታችን በፊት ሊኖሩ ይችላሉ ተብሎ በፍጹም በማይገመት መልኩ “ሰው እንዲህ ሆኖ ይፈጠራል?” በሚያስብል ደረጃ ጠባብ፣ ግፈኛ፣ አርቆና አስፍቶ ማየት ማሰብ የተሳናቸው፣ የማሳስተውሉ፣ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ባይ፣ ፈጽሞ ኃላፊነት የማይሰማቸውን የነውረኛ የጉድ ፍጥረቶች መንጋ ሀገረ እግዚአብሔር በምትባል ኢትዮጵያ መኖራቸውን ዓይተን ያረጋገጥንበት፡፡
  4. በ20/21ኛው መ/ክ/ዘ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዜጎች የአንድ ብሔር ተወላጆች በመሆናቸው ብቻ ለተለያየ ዓይነት ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ሲዳረጉ ያየንበት፡፡
  5. ለሽዎች ዓመታት የኖረች ሀገር ያካበተችው ያቆየችው የኖረችው ያለፈችበት ታሪክ፣ ቅርስ፣ እሴት፣ ማንነት ተቀብሮና እንዲጠፋ ተደርጎ በቦታው ለጥፋት ኃይሎቹ የጥፋት ሥራዎች የሚረዱ ሐሰተኛና የፈጠራ የጥፋት ታሪኮች ሀገር ስትሞላ ያየንበት፡፡
  6. “ከምን ጋር የዋለች ጊደር ምን ተምራ ትመጣለች” እንደተባለው በአብዛኛው ቅን፣ ቅዱስ፣ ጨዋ፣ ታማኝ፣ ደግ፣ አዛኝ፣ ተሳሳቢ ከነበረው ሕዝባችን ቀላል የማይባለው ቁጥር ሳይወድ በግዱ ከእነኝህ ጉዶች ክህደትን፣ እብለትን፣ ሐሰትን፣ ሆድ አምላኪነትን፣ ሸፍጥን፣ ማስመሰልን፣ ቀማኛነትን፣ ስግብግብነትን፣ ኅሊናቢስነትን፣ ነውረኛነትን ወዘተረፈ. ተምሮ ሲረክስ ሲባልግ ያየንበት፡፡
  7. ቀደም ሲል ከነበረው በተናጠል ይፈጸም የነበረው ከዝምድናና ከትውውቅ የሥራ ቅጥር፣ ከሙክትና በእጅ የመጨባበጥ ሰላምታ ከምትሰጥ ጥቂት ብር ጉቦና የሙስና አሠራር ወደ መቶ ሚሊዮኖችና ቢሊዮኖች (አእላፋትና ብልፎች) በግልና በቡድን ከሚዘረፍ የሀገር ገንዘብ ዘርን መሠረት ያደረገ የሥራ ቅጥርና የሙስና አሠራ ከመንኮራኩር በፈጠነ ፍጥነት ተወንጭፎ ሲያድግ ያየንበት፡፡
  8. ለመሠረተ ልማት ግንባታ ስም የሚመጣው ብድርና እርዳታ በጥቂቱ እጅ የወረደ የጥራት ደረጃ ያለው ብላሽ ሥራ ተሠርቶ አብዛኛው በብድርና እርዳታ የመጣ የሕዝብ ገንዘብ እየተዘረፈ እየተበላ ግለሰቦችና ቡድን ሲበለጽጉበት ሰማይ ሲተኮሱበት ሀገርና ሕዝብ ለድርብርብ ጉዳትና ኪሳራ ተዳርገው በትውልደ ትውልድ ተከፍሎ ከማያልቅ የዕዳ ማጥ ውስጥ ሲጠልቁ ሲሰምጡ ያየንበት፡፡
  9. የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀገሪቱ የጥቂቶች በመደረጓና እሱ መተፋቱን ዓይቶ በሀገሩ ተስፋ ከማጣቱና ከመቁረጡ የተነሣ ሀገሪቱን ጥሎ የትም ቢሆን ለመሰደድ የሌት ከቀን ሕልሙ የሆነበትና እየተሰደደም ለበረሀ አውሬ፣ ለባሕር ዓሣና ለአሕዛብ ካራ እንደተዳረገ ዕያየ ያላንዳች መደናገጥና ማቅማማት አሁንም ለመሰደድ ሲገደድ ያየንበት፡፡
  10. ዜጎች ኢትዮጵያዊያን በመሆናቸው ብቻ ስደት በየሔዱበት ሀገራት የሚዋረዱበት፣ የሚታሰሩበት፣ የሚገደሉበት፣ ኩራትና ክብር የነበረው ኢትዮጵያዊነት እርግማን ሆኖ በዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ፊት ብሔራዊ ውርደት ተከናንበን ተሸክመን ስንቀመጥ ያየንበት፡፡
  11. እንደ ሰባዎቹ (1961-1970ዓ.ም.) ዘመናት ወጣቶች ትውልዱ ጠያቂ ሞጋች ተቆርቋሪ አፋጣጭ፣ ሞትንም እንኳ ሳይፈራ የዜግነት ኃላፊነቱንና ግዴታውን ለመወጣት የሚተጋ ሆኖ ሥልጣናቸውና ደኅንነታቸው ችግር ላይ እንዳይወድቅ በማሰብ ትውልዱን ለማፍዘዝ ለማደነዝ በተሠራው ሥራ ትውልዱ በደረሰበት የቅስም (የሞራል) ልሽቀት ስብራት ድቀት ውድቀት የተነሣ ነፍዞና ደንዝዞ ድሮ ድሮ የድሩየነት የወሮበላነት የከንቱነት መለያ የነበረው ጫት ቃሚነትና ሱሰኝነት የዱርየነት መለያ ከመሆን ወጥቶ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችና መምህራን መለያ ሲሆን ያየንበት፤ አሁን አሁን ደግሞ በየቢሮው (በየመሥሪያ ቤቱ) በግላጭ ሲያመነዥኩትና ሲጠቀሙት ያየንበት፡፡
  12. የትምህርት ጥራት ድራሹ ጠፍቶ እንኳን ሌላ ስማቸውን እንኳ አስተካክለው የማይጽፉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎችን ያየንበት፡፡
  13. በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኃላፊነቱንና ግዴታውን የማያውቅ፣ የሀገር ፍቅር ስሜቱ የሞተ፣ ለማንነቱ ለክብሩ ለኩራቱ ክብርና ዋጋ የማይሰጥ፣ ከሆዱ በቀር ምንም የሚያሳስበው የሌለው፣ ለሆዱ ሲል ሀገሩን እናቱን ሌላው ቀርቶ “እኔ ከሌለሁ መቸ ልበላው ነው?” ብሎ እንኳ ሳያስብ ራሱንም የሚሸት ትውልድ ፈርቶ ያያንበት፡፡
  14. የኑሮ ውድነት ጣራ ነክቶ ሀብታም፣ መሀከለኛ፣ ድሀ የሚባል የነበረው የዜጎች የኑሮ ደረጃ ፈርሶ ማዕከላዊውን አጥፍቶ በጣም ጥቂት የናጠጡ ሀብታሞችን ጥቂት ድሆችንና እጅግ በጣም ብዙ የድሀ ድሀዎችን በመፍጠር የኑሮ ደረጃዎች ሲዛቡ ያየንበት፡፡
  15. የሀገሪቱ ቅርስና ባለውለታ የሆነችው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አስተምህሮዋ፣ ዶግማዋ፣ ቀኖናዋ፣ ክብሯ፣ መታፈሯ፣ መፈራቷ ተጥሶ ተድሶና ተገርስሶ የምናምንቴዎች መጫወቻና መቀለጃ ስትሆን ያየንበት፣ ምናምንቴዎቹም “እንዳታንሰራራ አድርገን አከርካሪዋን ሰብረናል!” ብለው ሲፎክሩ የሰማንበት፡፡
  16. ኧረ የግንቦት 20 ፍሬ ስንቱ ተወርቶ ይዘለቃል? እናንተን ሥራ ማስፈታት ይሆናል እንጅ ዓመት ቢወራ ያልቃል እንዴ! ባጠቃላይ ግንቦት 20 ኢትዮጵያ የጨለማ ዘመኗን ሀ ብላ የጀመረችበት፣ ሕዝብ ሀገሩን የተቀማበትና በገዛ ሀገሩ በቀየው በመንደሩ ግፍ ሰቆቃ የሚቆጥርበት የሚጋትበትን፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የወደቀችበት ሕዝቧ እንደ ሕዝብ የተዋረደበትን የአጋንንት መንጋና ዘመን ያገኘንበት ዕለት ነው ግንቦት 20፡፡

መድኃኔዓለም ክርስቶስ ፈጥኖ ከእንቅልፋችን ቀስቅሶ ማቃችንን አውልቀን እንድንጥል ያስችለና!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው amsalugkidan@gmail.com

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live