Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የደም አበባ Blood Flower

$
0
0

 

“ የፍቅርና  የደስታ መግለጫ የሆነው አበባ በኢትዮጵያ ውስጥ የስቃይና የበሽታ ምክንያት  ሆኗል።” ዜምብላ የደች ቴሌቪዥን ፕሮግራም 18-05-2016

በአፍሪካ ውስጥ ከሚካሄደው ዓይን ያወጣ ዓለም አቀፍ ብዝበዛ ኢትዮጵያም አላመለጠችም።በላይቤሪያ፣በአይቮሪኮስት፣በኮንጎ፣በናይጀሪያና እንዲሁም በቀሩት የአፍሪካ አገሮች የአውሮፓውያን ኩባንያዎችና ባለጸጎች የሚካሄደው የማዕድን ብዝበዛው ጣራ ነክቶ፣ በባለጸጎቹ ቀስቃሽነት በአገር በቀሎቹ ተባባሪዎች መካከል በተነሳው የጥቅም ግጭት ምክንያት የብዙ ሕዝብ ህይወት ጠፍቷል።ለአገራቸው ጥቅምና ለሕዝባቸው መብት የተከራከሩት በዓለም አቀፍ የብዝበዛ ተቋማት ጥያቄና ትእዛዝ በአደባባይ ተረሽነዋል። እንደ ናይጀሪያ ባሉት አገሮችም በደችና በእንግሊዞች ንብረት በሆነው የሼል መልቲናሽናል የነዳጅ ኩባንያ ትእዛዝና ጥያቄ በስቅላት ተቀጥተዋል።በተለያዩት የአፍሪካ አገሮች እየተዘረፈ በሚወጣው ማዕድን ምክንያት በአገሮች የደረሰውን ቀውስና የጠፋውን የሰው ህይወት በሚመለከት በታዛቢዎች አጠራር ና ስያሜ የደም አልማዝ፣የደም ወርቅ፣የደም ዘይት(Blood Daimond,Blood Gold,Blood oil…)የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል።በኢትዮጵያም ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ከሚካሄዱት የዘረፋ ክንውኖች መካከል አንዱና ትልቁ የደቾች የአበባ እርሻ ነው።ይህም እንደሌሎቹ የ ደም አበባ ተብሎ ቢሰየም ትክክልና አግባብ አለው ብዬ አምናለሁ። ለዚህም ነው እርእሱን የመረጥኩት።

red flower with blood

ከአስራ ሁለት ዓመት በፊት ማለትም በ2004 እ.አ.አ.የዛሬ አስራ ሁለት ዓመት ሸር/Share/በሚል ስም የተቋቋመው የአበባ እርሻ ኩባንያ ባለቤቱ ባርነሆልም/Baarnholm/ የተባለ ባለጸጋና ልጁ ናቸው፤ እናት ኩባንያው/Mother company/ አፍሪ ፍሎራ /Afri Flora/የተባለ ሲሆን አልስሚር/Aalsmeer/በተባለው የአበባ አምራችና አሰራጭ ማእከል (ሴንተር) አካባቢ የሚንቀሳቀስ ነው።

ይህ ኩባንያ በመጀመሪያ በ1997 እ.አ.አ.በኬንያ ውስጥ ተመሳሳይ የአበባ እርሻ ጀምሮ ከባቢውን ከበከለና ፣የውሃ ሃብቱን ካመከነ በዃላ የሥራው እንቅስቃሴ በመዳከሙ ንብረቱን በ50 ሚሊየን ኤሮ ሸጦ ፊቱን ወደ ኢትዮጵያ አዞረ።በመንግሥት ባለስልጣኖች ተባባሪነትና ሽርክና ብሎም የሙስና ሰንሰለት በዝዋይ ሃይቅ አካባቢ በ1000(አንድ ሽህ)የእግር ኳስ ሜዳ በሚሆን ሰፊ የእርሻ መስክ ላይ ስራውን ጀመረ።የከባቢውን የውሃ ሃብት እንደልቡ ካለምንም ቁጥጥር ለመጠቀም የከባቢውና የሃይቁ ባለቤት ለመሆን በቃ።

በመንግሥትና በኩባንያው ባለቤቶች የሚሰጠው መግለጫ ለከባቢው ልማትና ለነዋሪው የሥራ እድል የሚፈጥር እንደሆነ ተደርጎ ቢሆንም በተግባር ግን ሲታይ የዚያ ተጻራሪ ሆነ።በእርሻው መስክና በአበባው እንክብካቤ አስር ሽህ የሚሆኑ ሰራተኞች በተለይም ወጣቶች የተሰማሩ ሲሆን የሚከፈላቸው ደመወዝ ከዝቅተኛ መደብ ያነሰ ከመሆኑም በተጨማሪ ለእርሻው የተባይ መከላከያ ለሚረጨው መርዝ የተጋለጡና ለልዩ ልዩ በሽታ ሰለባ ሆነዋል።ይህን በሚመለከት ከአስር ዓመት በፊት “ትዝብት” በሚለው እርእስ  በተከታታይ አወጣው በነበረው ጽሁፍ የሚካሄደውን በደልና ሊያደርስ የሚችለውን የከባቢ አደጋ በማመልከት ላገርና ለወገን የሚቆረቆሩ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቤ ነበር።በኔዘርላንድ የሶሻሊስት ፓርቲም ባለኝ ግንኙነት ሁኔታውን አስረድቼ ጉዳዩ በይፋ እንዲወጣና የሰራተኛው ደመወዝ፣የጤና እንክብካቤና መከላከያ እንዲሟላ እንዲከታተሉ ጥያቄ አቅርቤ ነበር። በወቅቱ ይፋ ማድረጉ በስራው የተሰማራውን ደሃ  በዛን ጊዜ የሚያገኘውን በቀን ስምንት የኢትዮጵያ ብር እንዲያጣና  ለችግር ሊያጋልጥ ስለሚችል ኩባንያው ገና ሳይጠናከርና ለመውጣት በሚቀልበት ሁኔታ ጉዳዩን ከማንሳት ይልቅ ብዙ ወጭ ካደረገና ከተንሰራራ በዃላ መጠየቁ ይጠቅማል የሚል ውሳኔ ላይ ተደረሰ። በደች ኤምባሲ ዙሪያ በኢትዮጵያኑ ላይ የሚደርሰው መንገላታትና እንደውሻ በአገራቸው መጠለያ በሌለው በራፍ ላይ ለጠራራ  መጋለጣቸውን አስመልክቶ ላቀረብኩት አቤቱታ ከብዙ ውጣ ውረድ በዃላ ባለጉዳዩ በኤምባሲው ግቢ ውስጥ መጠለያ ክፍል ተሰርቶለት እንዲስተናገድ ለማድረግ ተችሏል።

በአበባው እርሻ ዙሪያ ግን ምንም ስር ነቀል መሻሻል ሳይታይ አንዳንድ የጥገና ለውጦች ተደረጉ ፤ከነዚያም ውስጥ የሰራተኛው ልጆች የሚማሩበት ትምህርት ቤትና የነጻ ህክምና አገልግሎት መቋቋማቸው ነው።ትምህርት ቤቱ ለከባቢው ኑዋሪ ልጆች የተከፈተ ሳይሆን ለሰራተኞቹ ልጆች ብቻ ነው፤ወላጆቻቸው ከኩባንያው ቢለቁ ወይም ቢባረሩ ልጆቹም ከትምህርት ቤቱ ይባረራሉ።የጤና አገልግሎቱም የተሟላ አይደለም።በሚረጨው መርዝ ሰውነታቸው የተጎዳው ሠራተኞች የህክምና እርዳታ ሲጠይቁ እርካሽና ቀላል መድሃኒት ተሰጥቷቸው ግፋ ቢል ከሶስት ቀናት እረፍት በዃላ ተመልሰው በዛው መርዘኛ ስራ ላይ እንዲሰማሩ ይገደዳሉ።ካሳና ድጎማ የሚባል ነገር አይታወቅም፤ለሕዝቡም፣ ለሠራተኛውም ታምርና ባዳ ነገር ነው።

ከጧቱ አንድ ሰዓት እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት በቀን ከአስራ አራት ሰዓት በላይ በሳምንት ስድስት ቀን ለሚደክሙበት ሥራ የሚከፈላቸው ደመወዝ በጣም የሚዘገንን ነው።በወር 700 የኢትዮጵያ ብር በኢሮ ሲሰላ € 29.00 ብቻ ነው። በደች ገበያ የአንድ ዘለላ ጽጌሬዳ ዋጋ አንድ ኤሮ ተኩል ማለትም ከ35 የኢትዮጵያ ብር በላይ እንደሆነ ከግንዛቤ ውስጥ አስገብተን ከሰራተኛው የቀን ደመወዝ ጋር ሲነጻጸር የአንድ ዘለላ ጽጌሬዳ ሽያጭ ከፍተኛ እንሆነ እንረዳለን። ለአሁኑ የኑሮ ወጭ የሚበቃ አይደለም።አነሰ ሲሉ ተቀነሰ ነውና ከዚህም ላይ ግብር ተከፍሎበት በሰራተኛው እጅ ላይ በወር የሚገባው 650 የኢትዮጵያ ብር ይሆናል፡፤ለቤት ኪራይ ከአራት መቶ ብር በላይ ሲወጣ በቀሪው ገንዘብ በልቶና ጠጥቶ ለብሶ ለመኖር አለመቻሉን በቪዲዮው ላይ የተቀረጸውን ብሶት ማዳማጡ በቂ ነው።በጣም የሚገርመው ደግሞ ለአስር ሽህ  ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች የሚከፈለው ደመወዝ 290.000 ሆኖ ሳለ ለ42 የደች ዜጎች የሚከፈለው ከሁለት ሚሊየን ኤሮ በላይ መሆኑ ነው።

የዚህን አይነት ሕገወጥ ተግባር በየአገሩ የሚፈጽሙ ድርጅቶች የሚያጭበረብሩበት መንገድ ፌር ትሬድ(fair trade) የሚል ሰሌዳ በመለጠፍ ነው። ይህ የአበባ እርሻ ተቋም በዓለም አቀፍ የንግድ ሕግ መሰረት የተደነገገውን የዚህን የመልካም የንግድ አሰራር መመዘኛ የተከተለ አለመሆኑን ስለ ሰራተኛ መብት የሚከራከሩ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሰራተኛውን ደመወዝ፣የስራውን ሁኔታ(salary and working conditions)በመከታተል የተሰጠው ስያሜ ትክክለኛና ተገቢ አለመሆኑን አረጋግጠዋል። እርሻው በከባቢ፣ በሕዝቡ ጤናና ኑሮ ላይ ያመጣውን አደጋ በሚመለከት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፤አንድ ዘለላ ጽጌሬዳ ለማምረት ከአምስት እስከ አስር ሊትር ውሃ ፣ለአንድ ሄክታር የአበባ እርሻ ስድስት የኦሎምፒክ የዋና ገንዳ ውሃ፣ በየቀኑ እየተመረተ ወደ ሆላንድ ለገበያ ለሚቀረበው ሶስት ሚሊዮን ተኩል(3.5 ሚሊየን)፣በዓመት ደግሞ 1.5 ቢሊዬን ጽጌሬዳ ምርት በሄክታር 2000 የኦሎምፒክ የዋና ገንዳ ውሃ በዓመት እንደሚያስፈልግና ይህም ከዝዋይ ሃይቅ እየተሳበ/እየተመጠጠ እንደሚውል ባለሙያዎቹ  ባደረጉት ክትትልና ጥናት አረጋግጠዋል።የሃይቁ መጠን እየቀነሰ ከመምጣቱም በላይ በከባቢው የሚኖረው ሕዝብ ከሃይቁ የሚያገኘው ጥቅም በተለይም በአሳ ምርቱ ላይ ያደረሰውን ተጽእኖና ብከላ ብሎም ተመጋቢው የደረሰበት በሽታ ለአበባው መከላከያ ከሚረጨው መርዝ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ጉዳዩን ይፋ ያደረጉት  የዜምብላ ፕሮግራም አዘጋጅ የሆኑት የደች ጋዤጠኞችና በከባቢው ያሉ የሕክምና ባለሙያዎች አጋልጠዋል።የጽንስ ማስወረድና ከዚህ በፊት የማይታወቁ በሽታዎች መከሰታቸውን ሃኪሙ አልደበቁም።የሃይቁ የውሃ መጠን እየቀነሰ በመምጣቱም የመሬት ውስጥ ውሃ ለመሳብ ጉድጓድ በመቆፈር ላይ እንዳሉ የሚያሳየው ስእላዊ ማስረጃ በመታገዱና በመከልከሉ የተሟላም ባይሆን በጥቂቱ  በሪፖርቱ ውስጥ ቀርቧል።የሃይቁና የመሬት ውስጥ ውሃው ሲነጥፍ  በኬንያ እንዳደረጉትና እንደለመዱት ለሕዝቡ የዘላለም በሽታና ለከባቢው ውድመት ዳርገው ጓዛቸውን ጠቅለው መውጣታቸው አይቀሬ ነው። ቀደም ሲል በሃረር ከተማ ዓለም ማያ ሃይቅ ላይ በጫት እርሻ ምክንያት የደረሰው ጥፋት ውድመት ሊታወሰን ይገባል።

ዜምብላ የተሰኘው ፕሮግራም በየአገሩ የሚካሄዱትን ተንኮሎችና ዘረፋዎች የሚያጋልጥ ሲሆን ከዚህም ቀደም ሲል H₰M የተባለው የስዊድን የልብስና ሞድ ኩባንያ በርካሽ የሰራተኛ ደመወዝና ወጭ ምክንያት ከባንግላዴሽ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን እንዳጋለጠ በጊዜው ለኢትዮጵያውያን ማሳወቄ የሚታወስ ነው። የቻይናዎችም የጫማ ፋብሪካ ባልታደለው የኢትዮጵያ ወጣት ላይ የሚያካሂደውን ኢሰብአዊ ተግባርና ዘረፋ በወቅቱ ያስተላለፈውን ማጋለጥና መረጃ ኢትዮጵያኑ እንዲያውቁት አድርጌአለሁ፤አሁንም የዚህ መልእክት ዓላማ እንደኔና በኔዘርላንድ ውስጥ ተቀምጠው በቴሌቪዥን የቀረበውን ዝርዝር ለመመልከት ያልቻሉትን በሌላ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያን እንዲረዱት  ሲሆን ሰምተው እንዲቀመጡ ሳይሆን ተገቢውን የመከላከል እርምጃ ተባብረው እንዲወስዱም ለማሳሰብ ነው።እንዳለፉት ጊዜያቶች ሰምቶ መቀመጡ ለወንጀለኞቹ ድጋፍና ማበረታቻ ከመሆን ሌላ በወገናችንና በአገራችን  ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ወዶ መቀበል ይሆናል።በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት የውጭ አገርና የአገር ውስጥ የንግድ ተቋማት ለሰራተኛው ብቻ ሳይሆን ለአገሪቱ መክፈል የሚገባቸውን ግብርና ታክስ አይከፍሉም።ለማንኛውም ዝርዝሩን ከዚህ በታች ካለው የቪዲዮ ቅጅ ለመረዳት ይቻላል። በጣም የሚያሳዝነው በሆላንድ ውስጥ ይኖር የነበረውና ከጎሹ ወልዴ ጋር “መድህን”የተባለውን የፖለቲካ ፓርቲ የመሰረተው ዶር.ፍስሃ ጽዮን መንግስቱ ለተጠየቀው ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ በመስጠት ፈንታ የሃብታምና የደሃው ልዩነት ማደጉን ብቻ መግለጹ የሚያስተዛዝብ ሆኖ አገኝቸዋለሁ።ከሙስና ጋር የተቆራኘው የስርዓቱና የመንግሥቱ መመሪያ መሆኑ ሲታወቅ ያንን ለማለት አለመፍቀዱና አለመድፈሩን ሕዝብ የሚያውቀውን መልስ አድርጎ ማቅረቡን በፕሮግራሙ ውስጥ ልትገነዘቡት ትችላላችሁ።ይህ የግብርና ታክስ ምሁር የተለያዩ ኩባንያዎች  በተለይም ይህ የአበባ አምራች ኩባንያ ለአገሪቱ መክፈል የሚገባውን ግብር አለማሟላቱን በድፍረት መግለጽ ሲገባው መሸፋፈኑ የምሁር ስነምግባሩን ከጥያቄ ውስጥ ጨምሮታል።

አብዛኛዎቹ  በተቃዋሚው ጎራ የሚገኙት የከባቢና የጎሳ ድርጅት መሪዎች የውጭ አገር ዘራፊዎችን የሚቃወሙት የጥቅም ተካፋይ ባለመሆናቸው እንጂ  ስልጣን ይዘው ለዚህ ዕድል ቢበቁ ከወያኔ የልተለዬ መመሪያ ይከተላሉ ብዬ አላምንም። አሁንም በአውሮፓ፣በአሜሪካና በካናዳ እየተዘዋወሩ የውጭ ባለሃብቶች ገብተው እንዲዘርፉ ቅስቀሳና ጥሪ የሚያደረጉት የአማራ ክልል ባለስልጣኖች የዚሁ ተባብረህ ዘርፈህ ጥፋ ዓላማ አካል ነው።

ሙሉውን የዜምብላ ቅጅ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ መከታተል ይቻላል፣

http://www.npo.nl/zembla/18-05-2016/VARA_101377865

ሰምቶ እየተበሳጩ ከመቀመጥ ተባብሮ ችግሩን ማሶገድ ይሻላል

አገሬ አዲስ

 


Health: ኤስትሮጂን ንጥረ ቅመም (ሆርሞን) – ከወሲብ ፍላጎት ማጣት እስከ መካንነት (ከዶክተሩ ጋር የተደረገ ልዩ ቃለምልልስ)

$
0
0

 

 

የኤስትሮጅን ንጥረ ቅመም (ሆርሞን) ሴትነትን ከመወሰን በተጨማሪ በተለያየ መልክ የሚገለፅ ተፅዕኖ አለው፡፡ ይህ ሆርሞን በሰውነት ውስጥ ከሚፈለገው መጠን በላይ ሲመረት ወይም ዝቅተኛ ሲሆን፣ አልያም ጭራሹን ሳይመረት ሲቀር የተለያዩ የጤና ችግሮችን ያስከትላል፡፡ በኤስትሮጂን ሆርሞን (ንጥረ ቅመም) ምንነት፣ በጥቅሙ፣ እሱን ተከትለው በሚከሰቱ የጤና ችግሮችና በመፍትሄያቸው ዙሪያ አንድ የማህፀንና ጽንስ ስፔሻሊስትን አነጋግረንልዎታል፡፡

Making-Love

ጥያቄ፡ኤስትሮጂን ሆርሞን (ንጥረ ቅመም) ምንድነው? የሚመረተውስ እንዴት ነው?

ዶ/ር፡- ኤስትሮጂን ሆርሞን በሴቶች ሰውነት ውስጥ ከሚመነጩ ሆርሞኖች መካከል አንዱ ነው፡፡ ከዚህ ሆርሞን ጋር የመተጋገዝ ስራ የሚያከናውን ፕሮጀስትሮን የሚባል ንጥረ ቅመም አለ፡፡ እነዚህ ንጥረ ቅመሞች በስነ ተዋልዶ ጤና ውስጥ ከፍተኛ ሚና ያላቸው ናቸው፡፡ የምናተኩረው በኤስትሮጂን ንጥረ ቅመም ላይ በመሆኑ፣ ይህ ንጥረ ቅመም በተፈጥሮ የሚመነጭ ነው፡፡ ሆርሞኑ E, E2 እና E3 ተብለው በሶት ይከፈላሉ፡፡ የሚመነጨውም በአብዛኛው በሴቶች የዕንቁላል ማፍሪያ ክፍል ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በእርግዝና ወቅት በእንግዴ ልጅ አማካኝነት፣ ንጥረ ቅመሙ የሚመረትበት ሁኔታ አለ፡፡ ሆርሞኑ የሚመረተው ሴቶች ለአቅመ ሔዋን ሲደርሱ ነው፡፡

በደም ውስጥ ከሚገኙ ቅባቶች አንዱ የሆነው ኮሌስትሮል፣ በተለያዩ አብላይ ኢንዛይሞች አማካኝነት በቅድሚያ አንድርስቶንና ቴስቴስትሮን ወደተባለ የወንድነት ሆርሞኖች ይለውጣል፡፡ ቀጥሎም የተለያዩ የኤስትሮጂን ንጥረ ቅመም አይነቶች ይመረታል፡፡ የመመረት መጠናቸውም የአንዲትን ሴት የወር አበባ ዑደትን ተከትሎ ይለያያል፡፡ በተለይም በወር አበባ መምጫ 12ኛውና 13ኛው ቀን አካባቢና የሁለተኛው ወር አበባ ሊመጣ ሲል የኤስትሮጂን ምርቱ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ የወር አበባን ለአራት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

  1. ደም የሚታይበት ጊዜ
  2. እንቁላል ከመውጣቱ በፊት ያለው ጊዜ
  3. እንቁላል የምትወጣበት ጊዜ እና
  4. እንቁላል ከወጣ በኋላ ያሉት ጊዜያት ተብለው በአራት ይከፈላሉ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ የአስትሮጂን መጠን ከፍ የሚልበትና ዝቅ የሚልበት ሁኔታ አለ፡፡ መጠናቸውን በተመለከተ እንቁላል ሊወጣ ሲል 380 ማይክሮ ግራም ሲሆን፣ በሚቀጥለው የወር አበባ ጊዜ ደግሞ 250 ማይክሮ ግራም ዝቅ ይላል፡፡ መጠኑ ሲቀንስ እስከ 36 ማይክሮ ግራም ዝቅ የሚልበት ሁኔታ ይኖራል፡፡

አንዲት ሴት በፅንስ ላይ እያለች 7 ሚሊየን የሚሆኑ ዕንቁላሎች በተፈጥሮ ይኖሯታል፡፡ በውልደት ጊዜ የዕንቁላል መጠኑ ከ1 እስከ 2 ሚሊየን ዝቅ ይላል፡፡ ይህ ቁጥር ከውልደት በኋላ በየጊዜው እየቀነሰ በመሄድ፣ በ14ኛ ዕድሜዋ አካባቢ ከ300 እስከ 400 ሺ ይደርሳል፡፡ ወደ ጉርምስና ዕድሜዋ ስትገባ የኤስትሮጂን ሆርሞን በሚፈለገው መጠን መመረት ይጀምራል፡፡ ይህ ሁሉ ትዕዛዝ የሚመጣው ከአእምሮ ነው፡፡

አዕምሮ ውስጥ ሃይፓታለመስ እና ፒቱታሪ ግላንድ የሚባሉ ክፍሎች አሉ፡፡ ቀጥሎም የእንቁላል መስሪያው ክፍል አለ፡፡ እነዚህ ሶስት የአካል ክፍሎች በቅንጅት በመስራት፣ አዕምሮ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በጉርምስና ዕድሜ ላይ እንቁላል ጊዜውን ጠብቆ መምረት ይጀምራል፡፡ የተሟላ ጤንነት ላይ ያለች ሴት በየወሩ በግራ እና በቀኝ ሁለት እንቁላሎችን ታኮርታለች፡፡

የተመረተው እንቁላል እንደወጣ ከወንድ ዘር ፍሬ ጋር ከተገናኘ ፅንስ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ፅንስ ከሌለ የተዘጋጀው የማህፀን ግድግዳ፣ በሚቀጥለው 28 ቀን የንጥረ ቅመሞች ድጋፍ ስለማይኖረው ይፈርስና ደም ሆኖ ይወጣል፡፡ አንዲት ሴት በየወሩ መጠኑ ከ3 እስከ 80 ሚሊ ሊትር ሊሆን የሚችል የወር አበባ ታያለች፡፡ የወር አበባ ዑደቱ የሚከናወነው፣ በኤስትሮጅንና በፕሮስቴስትሮን ሆርሞኖች መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ይሆናል፡፡

 

ጥያቄ፡ኤስትሮጂን ከላይ ከተገለፁት ተግባራት ባሻገር ሌሎች ጠቀሜታዎች ካሉት ብናይ?

ዶ/ር፡- ኤስትሮጂን የሚባለው ንጥረ ቅመም፣ የወር አበባ ዑደትን የተሳካ ለማድረግ ከሚሰጠው ጠቀሜታ ባሻገር ሌሎች ጥቅሞችም አሉት፡፡ ዋና ዋና የሚባሉትን ቀጥለን እናያለን፡፡

– በጡቶቿ ላይ በጉርምስና ዕድሜዋ ላይ ለውጦች እንዲመጡ ያደርጋል፤

– በጡት ውስጥ የወተት ማምረቻ ቧንቧዎች እንዲወፍሩና እንዲበዙ ያደርጋል፤

– የጡት ጫፍ ጥቁር እንዲልና የተለየ ቀለም እንዲኖረው የሚያደርግ ነው፤

– በብብትና በብልት አካባቢ ፀጉር እንዲወጣ የሚያደርግ ነው፤

– የወር አበባ ዑደት እንዲጀመር የሚያደርግ ነው፤

– አንዲት ሴት የሴትነት አካላዊ ቅርፅ እንዲኖት ያደርጋል፤

– በሴቶች ጡትና መቀመጫቸው አካባቢ የቅባት መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

– ሴቶች ድምፃቸው ቀጭን እንዲሆን ያደርጋል፤

– በሰውነታቸው ላይ ሴቶች ፀጉር እንዳይኖራቸውና የጭንቅላታቸው ፀጉር ግን እየበዛና እየተለቀ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡

– ማህፀን መጠኑን ጠብቆና ዳብሮ እንዲቀጥል ያደርጋል፡፡ በአጠቃላይ ኤስትሮጂን ሆርሞን ለሴቶች ከላይ የዘረዘርናቸውን ጥቅሞች ያስገኝላቸዋል፡፡

 

ጥያቄ፡የኤስትሮጂን ሆርሞንን መጣባት እንዲከሰት የሚያደርጉ ምክንያቶች ምንድናቸው?

ዶ/ር፡- የተለያዩ ምክንያቶች አሉ፡፡ ዋና ዋና የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡

– ዕድሜ በመግፋቱ ምክንያት በቂ የኤስትሮጂን መጠን አለመመረቱ፤

– ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በደም አማካኝነት የሚመጡ ኢንፌክሽኖች የዕንቁላል ማኳራቸውን ማጥቃታቸው፤

– በቀዶ ህክምና ኦቫሪ ሲወጣ፤

– በተፈጥሮ ኦቫሪው ኤስትሮጂን ማምረት አለመቻሉ፤

 

ጥያቄ፡የኤስትሮጂን ሆርሞን መዛባት መኖሩን የሚጠቁሙ ምልክቶች የትኞቹ ናቸው?

ዶ/ር፡- ተለዋዋጭ የሰውነት ሙቀት፣ ላብ ጥምቅ ጥምቅ ማድረግ፣ የወር አበባ መዛባት፣ የብልት መድረቅ፣ የአጥንት መሳሳት፣ በወሲብ ወቅት ህመም መከሰትና የሆድ መነፋት በቀዳሚነት የሚታዩ ምልክቶች ናቸው፡፡

 

ጥያቄ፡ከሴቶች ጡት ማነስ እና ፀጉር ዕድገት ጋር የኤስትሮጂን ንጥረ ቅመም ያለው ግንኙነት ምን ይሆን?

ዶ/ር፡- የጡት ማነስም ሆነ መተለቅ ቀጥታ ከኤስትሮጂን ሆርሞን ጋር ብቻ የሚያያዝ አይደለም፡፡ ኤስትሮጂን አንዱ መንስኤ ይሁን እንጂ ሌሎች ሆርሞኖች በተጣጣመ መልኩ የማይሰሩ ወይም ደግሞ መጠናቸውን የማይጠብቁ ከሆነ የአስትሮጂንን ጤናማ ተግባር ያበላሹታል፡፡ ስለዚህ የአንዲት ሴት ሆርሞን መጠኑ ከፍ ካለ ፂም ሊኖራት ይችላል፤ ስለዚህ የጡት ማነስ (መተለቅ) የፀጉር ዕድገት መቀጨጭና የሴትነት መለያ ባህሪያት መዛባት የሚከሰተው፣ በኤስትሮጂን ማነስና በሌሎች ሆርሞኖች መብዛት ምክንያት ነው፡፡

 

ጥያቄ፡የኤስትሮጂን ንጥረ ቅመም ከወሲብ ፍላጎት መቀነስ /መብዛት/ ጋር የሚያያዝበት ሁኔታ አለ?

ዶ/ር፡- በእርግጥም ይገናኛል፡፡ የኤስትሮጂንና የቴስቴስትሮን ንጥረ ቅመሞች አለመመጣጠን፣ በሴቶችም በወንዶችም የወሲብ ፍላጎት መቀነስና መጨመር ሁኔታዎችን ያሳያል፡፡ ሆርሞኑ ብቻውን ሳይሆን በአካባቢ ሁኔታዎችና ከበሽታዎች ጋር በተገናኘ መልኩ፣ በሴቶች የወሲብ ፍላጎት ማጣት ላይ አልያም መብዛት ምክንያት ይሆናል፡፡

 

ጥያቄ፡የንጥረ ቅመሙ አለጊዜው መመረት፣ ማነስና መብዛትን ተከትለው የሚከሰቱ የጤና ችግሮች የትኞቹ ናቸው?

ዶ/ር፡- ዕድሜያቸው ከ10 በላይ ሲሆን የጉልምስና ምልክት መታየት ሲገባው አስቀድሞ በ5 እና በ6 ዕድሜያቸው ጡት ማውጣት፣ ዳሌአቸው ሰፋ ማለትና የወር አበባ መታየት ቢያጋጥማቸው ይሄ የኤስትሮጂን መጠን በተፈጥሮ በብዛት መመረቱን ያሳያል፡፡ አልያም ደግሞ ሳይታወቅ በመድሃኒት መልክ ኤስትሮጂን ሆርሞን ከውጭ መወሰዱን ያመላክታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የኤስትሮጂን ማነስ ካለ ደግሞ የጉርምስና ዕድሜያቸው ይዘገያል፡፡ ይህም ማለት 18 ዓመታቸው ድረስ ጡታቸው ላያድግና የወር አበባ ላያዩ ይችላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኤስትሮጂን ሆርሞን መብዛት በሚከሰትበት ወቅት፣ የወር አበባ መብዛትና መርዘም እንዲሁም የማህፀን ዕጢዎችና የተለያዩ ቦታዎች ላይ ፀጉር የመውጣት ሁኔታ ይከሰታል፡፡ እንደዚሁም የማህፀን ግድግዳ እና የኦቫሪ ካንሰር ይከሰታል፡፡ በሰውነት ውስጥ የቴስቴስትሮን ሆርሞን በብዛት ስለሚመረት፣ የቅርፅ መበላሸትን በተለይም የወንድነት ባህሪን መላበስ፣ ያልተፈለገ ቦታ ላይ ፀጉር መውጣት እና ድምፅ እንደ ወንድ የመወፈር ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

ሆርሞኑ በማይመረትበት ጊዜ ደግሞ ሌሎች ችግሮችን ያስከትላል፡፡ ለምሳሌ አንዲት ሴት በ51 ዓመቷ የወር አበባ ማቆም ሲገባት በ28 እና በ30 ዕድሜዋ የወር አበባ ሊጠፋባት ይችላል፡፡ ከዕድሜ የቀደመ የዕንቁላል ማፍሪያ አካል ስራውን የማቆም ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ በዚህ ወቅት መውለድ አይችሉም፡፡ ያለማቋረጥ ትኩሳትና በብዛት ላብ የመፈጠር ሁኔታ ይከሰታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በረጅም ጊዜ የአጥንት መሳሳትና የልብ ነክ ጤና ችግሮች ይፈጠራሉ፡፡ እንደዚሁም የአጥንት ጥንካሬ ማጣት፣ ከዕድሜ ቀድመው የእርጅና ምልክቶች እና ከዕድሜ የቀደመ ማረጥ ይከሰታል፡፡

 

ጥያቄ፡በንጥረ ቅመሙ አለመመረት ወይም የመጠን ማዛባት የበለጠ ተጋላጭ የሚሆኑ ሴቶች ይኖሩ ይሆን?

ዶ/ር፡- ይኖራሉ፡፡ የሥራ ውጥረት ያለባቸው፣ ለረጅም ጊዜ የሚሮጡ፣ በትላልቅ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያሉ ሴቶች ለችግሩ ይበልጥ ተጋላጭ የሚሆኑበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ የስኳር፣ የቲቢ፣ ኤች.አይ.ቪ የጭንቅላት ዕጢዎች፣ የእንቅርትና መሰል ለረጅም ጊዜ የሰውነት ጤናን የሚያውኩ በሽታዎች ሴቶችን የኤስትሮጅን ሆርሞን መዛባት ያስከትላሉ፡፡ በዚህም ሳቢያ የወር አበባ ዑደት መዛባትም ሊፈጠርባቸው ይችላል፡፡ ሌላው የዕንቁላል ማፍሪያው አካባቢ ያለው ክፍል በጨረር፣ በኢንፌክሽን በዘር የሚተላለፍ የጤና ችግር ያጋጠማቸው ሴቶችም፣ የሆርሞን አለመመረት ወይም የመጠን መዛባት ሊገጥማቸው ይችላል፡፡

 

ጥያቄ፡የሆርሞን መዛባቱን ለማረጋገጥ የሚዳረጉ ምርመራዎች ምንድናቸው?

ዶ/ር፡-በደም አማካይነት የሆርሞን ምርመራ በማድረግ ማነሱንም ሆነ ከሚጠበቀው መጠን በላይ መመረቱን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኤስትሮጅን ሆርሞን መዛባትን ተከትሎ፣ ሌሎች የጤና ችግሮች መከሰታቸውንና ያስከተሉት ጉዳት መኖሩን ለማወቅ የአልትራ ሳውንድ ምርመራ እናደርጋለን፡፡

 

ጥያቄ፡ከኤስትሮጂን ሆርሞን ሚዛን መሳት ጋር በተያያዙ ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄው ምንድነው?

ዶ/ር፡- ከሁሉም የሚቀድመው የሆርሞን ባለመመረት አልያም ደግሞ ከመጠን መዛባት ጋር በተያያዘ፣ የሚከሰቱ የጤና ባለሙያን ማማከር ተገቢ ነው የሚሆነው፡፡ ሐኪሙ በሚያደርገው ሁሉ አቀፍ ምርመራ ችግሩ ከተለየ በኋላ የመውለድ ችግር ከሆነ፣ የወር አበባ መቋረጥና ሌሎች መሰል ችግሮች ከሆኑ እንደየባህሪያቸው በህክምናው የሚሰጡ መፍትሄዎች አሉ፡፡ በሌላም በኩል የወር አበባ መዛባት ካለ የሆርሞን ችግር ብቻውን ሳይሆን፣ ከሌሎች የጤና ችግሮች ጋር የሚቆራኝበት ሁኔታ ስላለ የሌሎች ጤና ችግሮች ምርመራ ተደርጎ መፍትሄ ይሰጠዋል፡፡

የኤስትሮጅን ሆርሞን ማነስ ሲኖር በመድሃኒት መልክ የኤስትሮጅን ሆርሞን በመስጠት እናክማለን፡፡ በአጠቃላይ ከሆርሞን መዛባት ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮች በህክምና መፍትሄ የመስጠት ሥራ በመስራት መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡

 

 

 

ሻምበል በላይነህ ስለ’ወልቃይት’ነጠላ ዜማ ለቀቀ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በተለያዩ ሃገርኛ እና ስሜት ቀስቃሽ ዘፈኖች የሚታወቀው አንጋፋው ድምፃዊ ሻምበል በላይነህ በቅርቡ “አማራ ነን… በግድ የተጫነብን የትግራይ ማንነት ይገፈፍልን” ሲሉ ለተነሱት የወልቃይት ሕዝቦች አንድ ነጠላ ዜማ ለቀቀ:: ያድምጡት:: ነጠላ ዜማው “ወልቃይት ጎንደር ነው” ይላል መጠሪያው::


shambel belayeneh

ቃና ቴሌቪዥን ንብረትነቱ የማን ነው? ዓላማውስ ምንድን ነው? |ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

$
0
0

ቃና ቴሌቪዥን (ምርዓየኩነት) እንደ ፋና ራዲዮ (ነጋሪተ ወግ) ሁሉ መቀመጫውን በዓረብ ሀገር ያደረገ ሞቢ ግሩፕ በሚባል የውጭ ድርጅት ስም የተመዘገበ የአገዛዙ ባለሥልጣናት እንደሆነ ይነገራል፡፡ አቶ ዘረሰናይ ብርሃነ፣ አቶ መሐሪ፣ አቶ ኤልያስ ሽሉዝ፣ የ251 ኮሙዩኒኬሽን ባለቤቶች አቶ ናዝራዊ ገብረ ሥላሴና አቶ አዲስ ዓለማየሁ የተባሉ ግለሰቦች ደግሞ በመሠረቱት የጋራ የሽርክና ድርጅታቸው የቴሌቪዥን ጣቢያው የሚልክላቸውን ፊልሞች (ምትርኢቶች) በተለምዶ የጃፓን አምባሳደሮች መኖሪያ ከሚባለው አካባቢ በሚገኝ ሕንፃ ላይ በተከራዩት ሦስት ፎቆች ስድስት ስቱዲዮዎችን (መከወኛ ክፍሎችን) ገንብተው ፊልሞችን (ምትርኢቶችን) እየተረጎሙ ለጣቢያው ያቀርባሉ፡፡
zana ana chandra
kkanaየቴሌቪዥን ጣቢያው ዋና መቀመጫው ከሀገር ውጭ እንዲሆን የተደረገውም ሆን ተብሎ ለዓላማና በምክንያት ነው፡፡ ይሄንን ጣቢያ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን የአሁኑን ኢቢሲን አስጎምጅ የማስታወቂያ ገቢ ለመውሰድ ያሰቡ የወያኔ ባለሥልጣናት ናቸው ያቋቋሙት፡፡ ይሁን እንጅ ዋና ዓላማው ግን ይሄ አይደለም፡፡

አስቀድሞ ግን የውጭ ሀገራትን ፊልሞች ወደ አማርኛ በመተርጎም ለተመልካች ለማቅረብ የአየር ሰዓት በኪራይ እንዲሰጣቸው ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ማለት ለኢቢሲ ፕሮፖሳል (ንድፈ ሥራ) ያቀረቡ ሌሎች ነበሩ፡፡ ወያኔ እንደልማዱ ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከግለሰቦች ፕሮፖዛል (ንድፈ ሥራ) ሲቀርብ ለእሱ ጠቃሚ መስሎ ከታየው ፕሮፖሳሉን ያቀረበውን ወይም ያቀረቡትን ግለሰቦች ፈንግሎ ነጥቆ ይወስድና ለራሱ ሰዎች እንዲጠቀሙበት እንደሚያደርግ ሁሉ ይሄንንም ሊጠቀሙበት ስለፈለጉ ካቀረቡት ሰዎች እጅ በመንጠቅ ለራሳቸው አገረጉት፡፡ ፕሮፖሳሉን ለኢቲቪ ያቀረቡት ግለሰቦች ግን የሚያውቁት ኢቲቪ ለጥያቄያቸው በወቅቱ ተገቢውን ምላሽ በወቅቱ ሳይሰጣቸው ጉዳያቸውን በማዘግየቱ በመጥፎ ባጋጣሚ በውጭ ድርጅት መቀደማቸውን ነው፡፡

የወያኔ ባለሥልጣናት ቃና ቴሌቪዥንን (ምርዓየኩነትን) ያቋቋሙበት ዓላማ አንደኛው ከላይ እንደጠቆምኩት ለጥቅም ማለትም ከማስታወቂያ የሚገኘውን ከፍተኛ ገቢ በግል ለማግኘት ሲሆን፡፡ ዋናው ጥቅምና ዓላማ ግን የሕዝብን ትኩረት በመያዝና ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይሔድ በማቀብ ተቆጣጥሮ በመያዝ አገዛዙ ከሚፈጥረው ከወቅታዊና ነባራዊ ችግሮች የሚነሣን የሚቀሰቀስን ሕዝባዊ ዐመፅን አለመረጋጋትንና እንቢጠኝነትን ከሩቁ ለመከላከል ነው፡፡ ዓላማው ይሄ ይሁን እንጅ “በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ” እንዲሉ ቃና ለወያኔ የሚሰጠው ጥቅም ከሁለት ወፍም በላይ በርካታ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የሚፈልገውን የጥፋት ውጤት ለማምጣት ብዙ ሲደክምበት የቆየውን ነግር ሁሉ በአቋራጭ በአጭር ጊዜ እያመጣለት ነው፡፡ ወደ ኋላ እንመለስበታለን፡፡

ቃና ቲቪን ለመክፈት ባለሙያ ለማሠልጠን ብቻ ከሁለት ዓመታት በላይ ጊዜ ወስዷል፡፡ በቅድሚያ ኢ.ቢ.ኤስ. የተባለው ጣቢያ እንዲከፈት የተደረገው ለማላመጃ ነው፡፡ ስለ ኢ.ቢ.ኤስ. አገልግሎትና ዓላማ ከዓመታት በፊት “ቶክ ሾው (ትዕይንተ-ወግ) ከያኔያንና ጥበብ በሀገራችን” በተሰኘው ጽሑፍ ላይ መግለጤ ይታወሳል፡፡

ታስታውሱ እንደሆነ የሀገሪቱ ብቸኛው ቴሌቪዥን (ምርዓኩነት) ኢቲቪ የአሁኑ ኢቢሲ ለረጅም ዓመታት ድራማን (ትውንተ ኩነትን) ጨምሮ ለመዝናኛ ዝግጅቶች ትኩረት ነፍጎ ቆይቶ ነበር፡፡ የጣቢያው ሙሉ ትኩረትና ሥራ ፕሮፖጋንዳ (ልፈፋ) ብቻ ሆኖ እጅግ አሰልቺ በሆነ መንገድ የወያኔን አደንቋሪ ልፈፋዎችንና ሐሰተኛ ወሬዎችን ማስተላለፍ ብቻ ሆኖ ቆይቶ ነበር ሥራው፡፡ በዚህ ረጅም ወቅት ጣቢያው የነበረውን ክብር ተአማኒነትና መወደድ ለማጣት ተገዷል፡፡

ከምርጫ 97ዓ.ም. በኋላ ወያኔ የደረሰበትን ኪሳራ ለመቀልበስ ከነደፋቸው አቅዶች አንዱ አስቀድሞ ሕዝቡን መዝናኛ ዝግጅቶችን ነፍጎ ያላ አማራጭ የራሱን አደንቋሪ አሰልቺ አስቀያሚና አስጠሊታ ልፈፋ ብቻ እንዲሰማ ማስገደዱ ሕዝቡን ምሬቱና መታፈኑ እንዲሰማው እንዲታወቀውና አሻፈረኝ እንዲል እንዳደረገው በመረዳቱ ጨርሶ ትኩረት ነፍጎት የነበረውን የመዝናኛ ዝግጅት ከፍተኛ ትኩረት ሰጠውና በተለይ ድራማዎችን (ትውንተ ኩነቶችን) በገፍ እንዲቀርቡ በማድረጉ ከሀገር ውስጥ እስከ በባዕዳን ሀገራት በስደት እስካለው ወገን ድረስ ሕዝቡ የወሬው የወጉ የጫወታው ርእስ እየቀረቡ ያሉት ድራማዎች (ትውንተ ኩነቶች) ሆነው ሲያይና በዚህም ምን ያህል ትኩረት ማስቀየስና መያዝ እንደቻለ እንደተጠቀመም ሲረዳ በዚህ ጉዳይ ላይ የበለጠ ቢሠራበት ሕዝብን ማዘናጋትና ትኩረቱን ወደሌላ ሳያደርግ መያዝ እንደሚችል በማመኑ የበለጠ ሊሠራበት የሚችልበትን መንገድ በሚያሰላስልበት ወቅት ነው የእነዚያ ሰዎች ንድፈ ሥራ (ፕሮፖዛል) በእጁ የገባው፡፡

ፕሮፖሳሉ (ንድፈ ሥራው) በእኛው ባለሙያዎች እየተዘጋጁ የሚቀርቡት ድራማዎች (ትውንተ ኩነቶች) ከሚጠይቁት ወጭና ተጓዳኝ ሁኔታዎች አንጻር የውጪ ፊልሞችን (ምትርኢቶችን) ተርጉሞ ማቅረብ በጣም በቀላል ወጭ የሚከወንና እጅግ በጣም ወጭ ቆጣቢ አትራፊም መሆኑን በመረዳት ከዚህ ዝግጅት የሚገኘውን ፖለቲካዊ ጥቅም ከፍተኛ ለማድረግ በኢቲቪ አጭር ሰዓታትን ሰጥቶ ከማስተናገድ ይልቅ 24 ሰዓታት የሚተላለፍበትን የራሱን መስመር በመክፈት ዝግጅቱ እንዲተላለፍ ቢደረግ ጥቅማቸው ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ስለተረዱ ባለቤቶቹ እነሱ እንደሆኑ እንዳይታወቅ በከፍተኛ ምሥጢር ተይዞ መቀመጫውንም ከሀገር ውጭ በማድረግ ሥራውን እንዲሠራ ተደረገ፡፡

ይሄው እያየለው እንዳለውም ሕዝብ ትኩረቱን ወደሌላ እንዳያዞርና ባሉበት በተጋፈጣቸውም በችግሮቹ ላይ አተኩሮ መፍትሔ እንዳይሻ እንዳያፈላልግ፣ ችግር እንዳይፈጥር ተቆጣጥሮ ከመያዝ አኳያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከጠበቁት በላይ እጅግ አመርቂ ውጤት ሊያስመዘግብላቸው ችሏል፡፡ ያስገኘው ውጤት የሕዝቡን ትኩረት ቀፍድዶ ይዞ በችግሮቹ ላይ እንዳያተኩርና መፍትሔም እንዳይሻ እንዳያፈላልግ ሌላ ነገር እንዳያስብ ከማድረግም ተሻግሮ ትምህርትንና ሥራንም ጨርሶ ማስረሳቱ ማዘንጋቱ ነው አስገራሚውና ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም አንጻር ሌላው ተጨማሪ እጅግ አደገኛና አሳሳቢ ጉዳቱ፡፡
በቃና የሚተላለፉ የሚከታተሏቸውን ፊልሞችን (ምትርኢቶችን) እንዲያልፏቸው እንዲያመልጧቸው ካለመፈለግ የተነሣ ተማሪዎች እንኳንና ጥናት ሊያጠኑ ቀርቶ ከትምህርት ቤት የተሰጣቸውን የቤት ሥራዎች እንኳን ሳይሠሩ ወደ ትምህርት ቤት ለመሔድ ተገደዋል፣ ክፍል ውስጥ ወሬያቸው ሁሉ በቃና የሚቀርቡ ምትርኢቶች ሆነዋል፣ ከትምህርት ገበታቸው እየቀሩ ወይም አቋርጠው እየወጡም የቃና ፊልሞችን (ምትርኢቶችን) በመመልክት በሕይዎታቸው ላይ የሚቀልዱ ሆነዋል፡፡

ይህ ምን ማለት እንደሆነና ውጤቱ ትውልዱን እንኩቶ ገለባ አድርጎ ሀገርን ሊገለጽ ከሚችለው በላይ ከባድ ኪሳራ ላይ ሊዘፍቃት የሚችል አደጋ እንደሆነ፣ ሕዝባችን አሁን ካለበት የድህነት ወለል በታች ቦታው ጭራሽኑ ወደ መቀመቁ የድህነት ደረጃ ቁልቁል የሚወረውረው መሆኑን መረዳት የማይችል ዜጋ ካለ የተሸከመው የሰው ጭንቅላት ሳይሆን ድንጋይ እንደሆነ የትም ቦታ ሔዶ ማረጋገጥ ሳያስፈልገው እርግጠኛ ሊሆን ይችላል፡፡

በሥራ ቦታዎች ያለው ሁኔታም ተመሳሳይ ነው፡፡ ይሄ እንግዲህ በዚህ ቴሌቪዥን (ምርዓየኩነት) የሚቀርቡ የባዕዳን ምትርኢቶች በሚያደርሱት አሉታዊ ተጽእኖ ሕዝቡን ለባሕል ወረራ ጥቃት አጋልጦት ማንነቱን ሊበርዙበት ከማንነቱ ሊያራርቁት ሊያቆራርጡት ብሎም ማንነቱን ሊያጠፉት የሚችል መሆኑን ትተን ከዚህ በመለስ ያስከተለውንና እያስከተለ ያለውን ጉዳት ብቻ ስንመለከት ነው፡፡
ጣቢያው በዚህ ዘርፍ በተሠማሩ ዜጎች እንጀራ ላይ እንደመምጣቱም ምንም እንኳ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ወያኔ ገበያውን በሕገወጥ ቅጅ የሚያጥለቀልቁ ግለሰቦችን አደራጅቶ በማሰማራት ሥነኪንን (በዘልማድ ሥነ ጥበብን) ከማሽመድመዱና ሥነኪን ሀገርንና ሕዝብን ለማገልገል ከተጣለባት ተፈጥሯዊ ኃላፊነት አኳያ ወያኔ እንድትንቀሳቀስ ፈጽሞ ስለማይፈቅድ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ሥነ ኪን የሚጠበቅባትን ተግባርና ኃላፊነት እንድትወጣ ባያደርጉም ቃና ቲቪ በእነዚሁ ሁኔታውና አቅማቸው የፈቀደላቸውን ያህል እየተንቀሳቀሱ ባሉት ባለሙያዎች ባለድርሻ አካላትና በስራቸው በሚያስተዳድሯቸው ቤተሰቦች ላይ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳትም እንዲሁ አሳሳቢ ነው፡፡ የአገሪቱ የባሕል ፖሊሲ (መመሪያ) ግን ለአገርኛ የጥበብ ሥራዎች መደረግ ስላለበት ድጋፍ ያትታል፡፡ “ጽድቁ ቀርቶ” አሉ! ድጋፉ ቀርቶ ማደናቀፉን ማሰናከሉን ክልከላውን አፈናውን ቢተው ድጋፉ ሳያስፈልግ ሥነኪናችን የት በደረሰ ነበር፡፡

የፊልም (የምትርኢት) እና የቲያትር (የተውኔት) ተመልካቹ አይደለም ከምትርኢትና ተውኔት ቤቶች ከትምህርት በመቅረትና ሥራን በማስተጓጎል ቃና ላይ ተጥዶ እየዋለና እያመሸ ነውና ለቃና ብሎ ትምህርቱንና ሥራውን የበደለ ገንዘብ አውጥቶ ከሚመለከትበት ከፊልም (ከምትርኢት) እና ከቲያትር (ከተውኔት) ቤቶችማ የሚቀር የሚርቅ መሆኑ ምንም የሚያጠራጥር አይሆንም፡፡
“እንዲህ ዓይነት የቴሌቪዥን ጣቢያ ስርጭቶች በተማሪዎችና በሠራተኞች ላይ የተገለጸውን ዓይነት ችግር የሚያስከትል ከሆነ እንዴት ታዲያ ባደጉ ሀገራት ባሉ ማኅበረሰቦች ላይ ተመሳሳይ ችግር ፈጥሮ ሀገሮቻቸውን ሳይጎዳ ቀረ?” የሚል ጥያቄ ይነሣ ይሆናል፡፡ በምእራቡ ሀገራት ተሰዶ የሚኖር ዘመድ ካላቹህ እሱ በሚኖርበት ሀገር እንኳን እንዲህ እኛ እንደምናደርገው ትምህርቱንና የሥራ ሰዓቱን በእጅጉ እየጎዳ በራሱ ላይ በሕይዎቱ ሊቀልድ ይቅርና ኑሮን ለመግፋት እንኳ ያለውን 24 ሰዓት ከስንት በጣጥሶ ስንት ሥራ እየሠራና እየተማረ በቀን ውስጥ ለሁለትና ቢበዛም ለአራት ሰዓታት ብቻ እየተኛ ሕይዎቱን እንዴት አድርጎ እንደሚገፋ ኑሮን እንዴት እንደሚኖር እየጠቃቀሰ ቢነግራቹህ አጥጋቢ ምላሽ ባገኛቹህ ነበር፡፡

እዚያ እንኳንና መሀከለኛና ዝቅተኛ ኗሪው የኅብረተሰብ ክፍል ቀርቶ ሀብታሞቹም እንኳ እረፍት አያውቁም፡፡ እረፍት ካላቸው የአጭር ጊዜ ቆይታ ሆና በእቅድ የምትስተናገድ ናት፡፡ ከትልቅ እስከ ትንሽ ከተማሪ እስከ ሠራተኛ ጊዜ እንደ ቁምጣ ያጠረውና ሕይዎቱ የሩጫ ነው፡፡ ሁሉም ዜጋ የጊዜ አጠቃቀምን (Time management) ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ምእራባዊያኑ ሕዝባቸው በእንደዚህ ዓይነት አዘናጊ ነገሮች ሕዝባቸው እንዳይዘነጋ ማድረግ የሚችል የሕይዎት ሥርዓት (System) አላቸው፡፡ በዚህ ሥርዓት የማይመራና የማይሯሯጥ ሰው ቢኖር ሥርዓቱ ራሱ ይተፋዋል፡፡ የፈጠሩት ሥርዓት አንድ ዜጋ በራሱ ስንፍናና መጃጃል ምክንያት ተተፍቶ ሲወድቅ የሱ መውደቅ ጉዳቱ የራሱ እንጅ የሀገርም እንዳይሆን ወይም ለሀገር የሚደርሳት ጉዳት በጣም አነስተኛ እንዲሆን ማድረግ እስከሚችል ድረስ ነው ሥርዓቱን የገነቡት፡፡ በዚህም ምክንያት እንደዚህ ዓይነት የ24 ሰዓታት ዝግጅቶች በእኛ ላይ ማኅበራዊ ቀውስና ምጣኔ ሀብታዊ (ኢኮኖሚያዊ) አደጋ ማድረስ የሚችሉበትን ያህል ከባድ ጉልበትና አቅም በእነሱ ላይ ጨርሶ የላቸውም፡፡ የደረሱበት ሥልጣኔ ለዚህ በእጅጉ ረድቷቸዋል፡፡

ወደ እኛ ስንመጣ ግን ያለው ነገር ሁሉ ከእነሱ በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ ሕይዎትን እንመራታለን እንጅ እንደነሱ ሕይዎት አትመራንም፡፡ ስለሆነም እነሱ ላይ አደጋ አልፈጠረምና እኛ ላይም አይፈጥርም ማለት አንችልም፡፡ ሥርዓቱ አልተገነባማ! የለማ! አልሠለጠንማ! ጊዜን በአግባቡ አንጠቀምማ! በዚህም ምክንያት ነው በርካታ በራሳችን በሕይዎታችን የመቀለጃ ጊዜያት ያሉን፡፡ ሥራችንን ሠርተን ትምህርታችንን ተምረን ትርፍና የእረፍት ጊዜ በምንለው ረጅም ጊዜያችን እንኳን ባላገጥን ምንም ባልነበር፡፡ እኛ እኮ በትምህርትና በሥራ ጊዜ በመቀለድ ዋናውንም ውድ የሕይዎት ጊዜ ነው እየበላን እየቀለድን እየተጫወትንበት ያለነው፡፡

የወያኔ ባለሥልጣናት እንዲህ ዓይነት አደጋና መቅሰፍት በሀገር ላይ እያወረደና ሊያወርድ ያለው ይህ ጣቢያ “የእኛ አይደለም!” ብለው ሸምጥጠው በመካድ ለትርፍ የሚሠራ የባዕዳን የግል ድርጅት ነው የሚሉ ከሆነና ይህ ሁሉ መዓት በዚህች ሀገርና በሕዝቧ ላይ እንዳይደርስ የሚፈልጉ ከሆነ ይሄንን ጣቢያ በቀላሉ መዝጋት የሚችሉበት መንገድ አለ፡፡ ጣቢያው መቀመጫው ከሀገር ውጭ ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ ውስጥ ፈቃድ ተሰጥቶት አጋርና ወኪል ድርጅቶች መሥሪያ ቤት ከፍተው ፊልሞቹን (ምትርኢቶችን) ተርጎሞ ከማዘጋጀት አንሥቶ የንግድ ማስታወቂያዎችን እየተቀበሉ በማስተናገድ ላይ ያሉ ድርጅት እንደመሆናቸው ቃና ቴሌቪዥንን ማዘጋት ቢፈለግ ለሕዝብና ሀገር ህልውናና ደህንነት አደጋ የጋረጠ በመሆኑ በሕገ ወጥነት ፈርጆ እዚህ ያለውን ወኪልና አጋር ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ ሰርዞ ቢዘጋው እንበልና ድርጅቱ ሌላ ዓላማ ሳይኖረው ለትርፍ የሚሠራ የግል ድርጅት ከሆነ ትርፍ የሚያገኝባቸውን የንግድ ማስታወቂያዎች ማግኘት አይችልምና ወዲያውኑ ራሱን ለመዝጋት እንዲገደድና እንዲዘጋ ማድረግ ይቻላል፡፡

ለትርፍ የተቋቋመ የግል ድርጅት ነው እየተባለ በሀገር ውስጥ እንዲዘጋ ተደርጎ ማስታዎቂያዎችን ሳያገኝ ያለትርፍ በኪሳራ ከሆነ አካል እየተደጎመ ስርጭቱን የሚቀጥል ሆኖ ከተገኘ ያኔ ዓላማው በግልጽ የሚታወቅ ይሆናል፡፡ ውጊያውም ግልጥ በግልጥ ይሆንልናል፡፡ ስርጭቱንም ለማስቆም የሚወሰደው እርምጃ ሌላ ይሆናል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ግን ይሄ ሁሉ በሚያሳዝን ሁኔታ ከንቱና የማይሆን ምኞት ነው፡፡ ያሉ ነገሮች ግልጽና የታወቁ እንደመሆናቸው የተጀመረው የጥፋት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል እንጅ የተለየ እርምጃ ሊወሰድ የሚችልበት ዕድል እንደማይኖር ሳረዳቹህ በታላቅ ሐዘን ነው፡፡
የሚመለከታቸው የአገዛዙ ሹማምንት ጉዳዩን “ሕዝብ ይወስንበት! አይጠቅመኝም ካለ እራሱ ወይም ገበያው ይጣለው!” በማለት በሕዝብ ላይ ሲቀልዱ ተደምጠዋል፡፡ ነው እንዴ! ጨዋታው እንዲያ ከሆነ ታዲያ ምነዋ ኢሳትን እንዲያ እየወደድነው እየናፈቅነው ቤታችን ድርሽ እንዳይል አድርጋቹህ ካለበት የምታስቀሩብን ለምንድን ነው? “ለማያውቅሽ ታጠኝ” አለ ያገሬ ሰው፡፡
ይሄንን እያሉ ያሉ የወያኔ ሹማምንት በእርግጠኝነት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ፈጽሞ የማያውቁ ናቸው፡፡ ይህ ጉዳይ “ሕዝብ ወይም ገበያው ይጣለው!” በመባል የሚታይ ከሆነ ለእነኝህ ደናቁርት ባለሥልጣናት ልጠይቀው የምፈልገው ጥያቄ ቢኖር፡- አደንዛዥ ዕፆች ምንም እንኳን ጎጂ መሆናቸው ቢታወቅም ተጠቃሚዎቹ ግን ይጠቅመናል እስካሉ ጊዜ ድረስ ለምንድነው ታዲያ እንዲጠቀሙና እንዲያዘዋውሩም ሕግ የማይፈቅድላቸው? እንዲህ እንዲህ እያልን በሕግ የተከለከሉ በርካታ ነገሮችን በመጥቀስ ጎጅነት እንዳለው እየታወቀ ይጠቅመናል ይሆነናል የሚሉ ወገኖች እስካሉ ጊዜ ድረስ ብቻ ፈቃድ እንደማያገኙ እንደሚከለከሉ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

አንዳች ተንኮል ከሌለው በስተቀር “ሕዝቡ ይወስን! ገበያው ይጣለው!” ልንባል አይገባም፡፡ ማኅበረሰባችን የመዝናኛ ዝግጅቶች ባላቸው ከፍተኛ የመማረክ ጉልበትና ኃይል ስለተሸነፈ እንጅ በብዙ መልኩ እንደሚጎዳው እንደሚያዘናጋው ሳያውቅ ሳይረዳ ቀርቶ አይደለም በዚህ መልኩ እራሱን እያጃጃለና እየጎዳ ያለው፡፡ ይህ የወያኔ ባለሥልጣናት አባባል ሕዝባችን ከመጃጃሉ የተነሳ “ይቅርብኝ! ይዘጋ!” ብሎ እንደማይወስን በማወቃቸው የሚሰነዝሩት ንቀት የተሞላበት አነጋገር ነው፡፡

ወያኔ አንዴ በማያገባን በማናውቃቸው ኪሳራ እንጅ በሕይዎታችን አንዳችም የሚጨምርልን ትርፍ በሌለው የአውሮፓ ሀገራት እግር ኳስ፣ ሌላ ጊዜ በጫትና በሺሻ ሱስ፣ ሌላ ጊዜ በድራማ (ትውንተ ኩነት) እና በፊልም (ምትርኢት) ወዘተረፈ. አንተን በጊዜህ በሕይዎትህ ቀልደህ አረንቋ ውስጥ እንድትሰምጥ ለማድረግ የፈለገውን ያህል ሴራ ቢሸርብ እኛ ነቅተን አንሰማም! አንመለከትም! አንዘናጋም! አንጃጃልም! ብንል ሴራው ምን ይፈይድለት እሱስ የት ይደርስ ነበር? የትም!

ወያኔ ለምንና እንዴት ትውልድን መቀመቅ ውስጥ ለማስጠም ሆን ብሎ ይሄንን እንደሚያደርግ ከዓመታት በፊት “ሱስ ትውልድና ሀገር” በሚል ርእስ የጻፍኩትን ጽሑፍ ጎግል አድርገህ በመመልከት ማረጋገጥ ትችላለህ፡፡

እርግጥ ነው ሆንብሎ ለማጥፋት ትውልድን መቀመቅ ለማስመጥ ተግቶ የሚሠራ በመንግሥት ቦታ ያለ የጥፋ ኃይል ባለበት ሁኔታ ምን ብታደርግ ከወጥመዱ አመልጣለሁ ማለት ዘበት ሊሆን ይችላል፡፡ እንግዲህ ታዲያ ምን ይዋጥህ ወገን? ወያኔ እንደ አህያነቱ በ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” አስተሳሰቡ ለግል ጥቅሙ ሲል ሀገርንና ሕዝብን የሚጎዱ ተግባራትን በመሸረብ መጠመዱ ግራ የሚያጋባው፣ የሚደንቀው፣ የሚገርመው ዜጋ ይኖር ይሆን? ወያኔ ነኝ ብሎ ማንነቱን በራሱ አንደበት በግልጽ እየተናገረ የጠላትነት ስሜት ተሞልቶ፣ ጥፋት ተጭኖ ከመጣ ጠባብና ደንቆሮ የወሮበላ ቡድን ታዲያ ከዚህ የተለየ ምን ይጠበቅና ነው ግራ የሚገባው? የሚገርመው? የሚደንቀው? እያንዳንድሽ አርፈሽ ጸጥ ብለሽ መቀመቅሽን ውረጅ! በፊትስ እሽ ሳታውቂው ቀርተሽ ይባል በኋላ ላይ ግን የወያኔን ማንነት ከተግባሮቹ ካወቅሽ በኋላ እያንዳንድሽ ላለመበላት፣ ላለመታረድ፣ ላለመነቀል፣ መቀመቅ ላመውረድ ምን ያደረግሽው ነገር አለ? ምንም! ስለዚህ አርፈሽ ዝም ብለሽ ተጋድመሽ ታረጅ!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

ግርግዳ የሌለው  ቤት በሩ ይቆለፋል ወይ? |ከመኳንንት ታዬ (መ..ታ )

$
0
0

ethiopia

የምንኖርባት አለም ሰዎች የሚተዳደሩባት የሚያስተዳድሩባትም ፤ ብበሎም  ገዢና ተገዢ ሃብታም እና ደሃ ፤እያለ ይቀጥላል ።እንዲህ ባለው ስርአት ውስጥ  የተፈቀደልንን መስመር እየረገጥን እንኖራል።በዚህ ሄደት  አንዳንዶች ቆዳቸው ሲሰፋቸውና ጫማቸው ሲያድግባቸው  እሰው መስመር ልኬት ገብተው በመርገጥ ፉርሽ ነው ይሉናል ። የረገጥነው የተፈቀደልንን መሆኑን ስናቅ ፤የለም በልኬ ነው ያለሁት ባልን ግዜ  ያልተገቡ ረጋጮች  ይጣሉን ይጀምራሉ።በዚህን ግዜ በንኪኪ የሚመጣ ጥል ይፈጠርና በቅርብ በሚያስቡና በሚያዩ ዘንድ  ጥፋተኛነታችን ሲነገረን ይኖራል።አርግጥ በዚህ ምሃል ግጭት የመነሳቱ ሁነት  አውነት ነው ። አሸናፊው  እንደ አያያዙ  ይሆናል። አብዛኛውን ግዜ እራስ ወዳዶች  ጫማቸውም  የራስ ቅላቸውም ሰፊ ስለሆነ  የሰው መስመር መርገጥ ይቀናቸዋል ።እንዲህ ካለ ስርአት እያደገ ሄዶ ሐገር ጥግ ሲደርስ  የራሳቸውንም የሰውንም መስመር መርገጥ የሚቀናቸው አስተዳዳደሪዎች ይፈጠራሉ። የዛኔ ሃገርም ፤መኖሪያ ሰፈርም ፤መኖሪያ ቤትም ፤በልኩ የሚረግጡ ሰዎች ባለቤቷ አይሆኑም ።ምክንያት ከላይ ሲውርድ እንደመጣው አይነት የእድገት ደረጃ  ባለቤቱ  ሆኖ የተፈጠረው ግለሰብ ነውና ።

ለመንደርደሪያ ታህል ይህን ካልን ግርግዳ የሌለው  ቤት በሩ ይቆለፋል ውይ ? ወደሚለው ርእስ  እንዲህ እንዝግም። በዚህ ርእስ ሰንሰለት  አጥርና በር ብሎም ግርግዳ የሌላት ሃገራችንን እናስታውስና እንዲህ እንበል። መሪዎቻችን ሊያኖሩን አልያም እየቆጠሩ ህዝብ አለ ሊሰኙበት ሃገሪቷን ከተረከቡ  ብዙ ዘመን አለፈ።ቁጥሩን መጥቀስ አስፈላጊነቱ አላመንኩበትም። ለማውራት የፈለኩት ከታች ጀምሮ ከሆነ እለቀ መሳፍርት  ወረቀት አይበቃም። ስለዚህ በቅርብ ከተፈጠረው  ከጋንቤላ እንነሳ ።መገደል ብርቃችን አደለም ።ምን እሱ ብቻ ገዳዮቻችንንም  መቃወም ያስገድላል።ይህ አይነት አስተዳደር ለማንኛውም  አለም ላይ ለሚገኝ ፍጡር  ያማል ።በር የሌላት ሃገር፤ህዝቦቿ በሄዱበት እየተዋረዱ  የሚሸማቀቁባት ሃገር ፤ ሃገር ፤ሀገር ……፤እያለ በየማዝናቱ አሳፋሪና አስፈሪ ነገሮች ባለቤት የሆኑ ህዝቦች ፤ስሟ  ኢትዮጲያ በተባለ ሃገር እንኖራለን። በዚህ ምክንያት  ሃገር ስም  የያዙትስ ትልቅናቸውና  ትንሽ ልብ ባለው  መንግስት  ከቶ ይፈሩ ይሆናል ።እንዴት  የአንድ ብሔረስብ ወሮ በላ ጎሳውች የአንድን ሐገር  ህዝብ ገድለውና ልጆ ቻቸውን ከብቶቻቸውን  ወስደው ሲያበቁ  በድርድር ለማስመለስ በሚል ደካማ ሃሳብ ይኖራል ። አረ እንደውም  የጋምቤላው አስተዳዳሪ እንዳሉት ልጆቹ ይመለሱ እንጂ ከነኚ ጋር ማን ይነጋገራል አይነት ነው። በቃ ኢትዮጲያዊ እንዲህ ነው ።አለቀ ።ይህ በርግጥ ከሙት ባህር አጠገብ  የተቀመጠ ሙት አስተዳደር ነው እንጂ፤ በእውነቱ ስም ያላት ሀገርን የሚያስተዳደር መንግስት  ከቶ ሊዋጥለት አያስፈልግም።አስከመቼስ  የታጠቀውን መሳሪያ  የገዛ ህዝቡን የሚያስፈራራበት ይሆናል ።ለሚቃወሙተስ ስንት አስር ቤት? ስንት አሳሪ ፖሊስ?  ስንት ፈራጅ ዳኛ? ስን ስንት ስንት ያስፈልጋል። በአገዛዝ ደረጃ  ለተቀመጡት  ባለዱላዎቸስ በስልጣን   የተቀመጡ መሪዎች ጉልበታችሁን እንዴት አሳንሰው እንደሚመለከቱት  አለመገንዘባችሁ ምን ቢጠፋችሁ ወይስ ምን ብታጡ ነው።ትልቅነት ነገን  ማየት እንጂ  ዛሬ ላይ በድንግዝግዝ እየኖሩ በዳበሳ መሄድ አደለም።

ማንነታችን እኛነታችንን የምናፅበት መስመር የተሰራልን ያለሙግት  የምንኖርባት ሐገር ባለቤቶች ነን።ትልቅነታችን ሲያስመሰግነንና ሲያስከብረን ኖረን የእኛ ባማይሏት ገዢዎች መስመሯን ስታ  የነገ ባለ እራቁት ሐገር ለማድረግ ደርሻዬ ከሚሉት ባለፈ ሐገርን በገፈፋ እና በብትር ለማስተዳደር መሞከር ክብሩ ምን ያህል ነው?።ሕዝቦች መሪዬ የሚሉት ሲጠፋ እንደመንደር ሰው እየተከተሉ የሚሰድቡት ባለስልጣን ማየት የ25 አመቱ የመልካም አስተዳር  ውጤት  አማራጭ የሌለው አድገት  መሆኑን የተቀረው አለም እንዴት የሚያው ይመስላቸውኋል?።ህዝቦች ብዙዎች ናቸው ያስፈራሉ።የመንግስት ባለስልጣናት ጥቂቶች ናቸው ይፈራሉ።ምክንያቱም የኔ የሚሉት  ሀገር በስማቸው አለችና ነው።ከሀገሩ ክብር  የሸሸ ባለስልጣን ከሚመራው ህዝብ ለሱ ብሎ የተቀመጠ ባለሞኖሩ ዛሬ የምናነየውን  አሰዛዥ  እጣ ፋንታ  ሁሉም በየተሰለፈበት መስመር ሲፈፅም ማየት ነው ።ከወንበሩ በስተቀር በስፋት  የተለየ ነገር  ባለመኖሩ ወደታች በመውረድ በትልቅ ደረጃ አሰራር ያለት ሐገር ግለሰቦች  ከሀገር እንዳይወጡ ፓስፖርታቸው  ዘይት ነካው በሚል ጎስቋላ ምክንያት  ብሎም  በየአይሮፕላን ጣቢያ ተቀምጦ ግለሰቦችን ከስራቸው በማጎሳቆል  ማሰቃየት  ይህ የወንበርን ስፋት ከማየት የመጣ የአንቶ ፈንቶ አስተዳደር  ስርአት  ነው። የሚያሳዝነው  ወደፊት ለመሄድ ከኋላ ስንት ሜትር እንዳለፉ አለማስታወሳችሁ ነው። ዛሬን  በዚህ ስርአትና ውርደት ለመኖር ከሆነ ትላንት የታገላችሁት ሃሰባችሁ ረፍዶበታል ።አልተኛችሁም ለማለት ከሚመጣው  የጋራ ክፉ ነገር  ወንበራችሁ  ላይ  እንዳይነጋ የማታዋን ፀሃይ ተጠቅሞ  ከግርግር መንግስት  የሽግግር መንግስት ብታቋቁሙ ለቤቱ ግርግዳ  ለመዝጊያውም በር  ከህዝቡ ጋር ሆናችሁ ትሰራላችሁ ማለት ነው ።

ቸር እንሰንብተ

ድርቅ፣ ስደት፣ መፈናቀል፣ ጎርፍ እና ሞት እያመሰው ያለው ወቅታዊው የኢትዮጵያ እና የሕዝቧ ችግሮች ሲዳሰሱ (ልዩ ዘገባ)

$
0
0

ድርቅ፣ ስደት፣መፈናቀል፣ ጎርፍ እና ሞት እያመሰው ያለው ወቅታዊው የኢትዮጵያ እና የሕዝቧ ችግሮች ሲዳሰሱ (ልዩ ዘገባ)


ድርቅ፣ ስደት፣መፈናቀል፣ ጎርፍ እና ሞት እያመሰው ያለው ወቅታዊው የኢትዮጵያ እና የሕዝቧ ችግሮች ሲዳሰሱ (ልዩ ዘገባ)

“እንደኔ ምኞት ምነው ሰው እንደ ጋሞ በሆነ፤ መላው የእትዮጵያ ሕዝብ ቢቻል እንደ ጨንቻ በሆነ።” –አሰፋ ጫቦ

$
0
0

ደራሲ አሰፋ ጫቦ፤ ስለ አዲሱ መጽሐፋቸው “የትዝታ ፈለግ” ይናገራሉ።
“እንደኔ ምኞት ምነው ሰው እንደ ጋሞ በሆነ፤ መላው የእትዮጵያ ሕዝብ ቢቻል እንደ ጨንቻ በሆነ።” – አሰፋ ጫቦ


አቶ አሰፋ ጫቦ

አቶ አሰፋ ጫቦ

ሙላቱ አስታጥቄ፤ ስለ ኢትዮ ጃዝ አፈጣጠርና በወርኃ ጁን አውስትራሊያ ውስጥ ስለሚያቀርበው የሙዚቃ ዝግጅቱ ያወጋል

$
0
0

የኢትዮ-ጃዝ አባት – ሙላቱ አስታጥቄ፤ ስለ ኢትዮ ጃዝ አፈጣጠርና በወርኃ ጁን አውስትራሊያ ውስጥ ከBlack Jesus Experience ባንድ ጋር ስለሚያቀርበው የሙዚቃ ዝግጅቱ ያወጋል።

ሙላቱ አስታጥቄ፤ ስለ ኢትዮ ጃዝ አፈጣጠርና በወርኃ ጁን አውስትራሊያ ውስጥ ስለሚያቀርበው የሙዚቃ ዝግጅቱ ያወጋል


Sport: ኢትዮጵያና ጋና እሁድ ይጋጠማሉ

$
0
0

addis ababa stadium

ድል የተጠማው የብሔራዊ ቡድናችን ደጋፊ (ፎቶ ከፋይል)

 ስሜነህ ታደሰ | ለዘ-ሐበሻ ስፖርት

(ዘ-ሐበሻ) ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የጋና አቻው የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚጋጠሙ ታወቀ:: የጋና ብሄራዊ ቡድን ኢትዮጵያን ለመግጠም አዲስ አበባ መግባቱም ተሰምቷል::

የጋና ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ ጨዋታ ቀደም ብል ከናሚቢያ ብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ በፍጹም የበላይነት 4ለ0 ማሸነፉ ይታወሳል::

የኢትዮጵያ ወጣቶች ቡድን ብዙ ዝግጅት ሲያደርግ እንደቆየ ከፌዴሬሽኑ የተሰጠው መግለጫ ሲያስረዳ ከኢትዮጵያና ጋና ብሄርዊ ቡድኖች አሸናፊ የሚሆነው ከቱኒዚያ እና ሴኔጋል አሸናፊ ጋር እንደሚጫወት የወጣው መርሃ ግብር ያስረዳል::

 

የኢትዮጵያ ወጣቶች ቡድን የሶማሊያ አቻውን አሸንፎ ከጋና ጋር የደረሰው ሲሆን ሶማሊያን በማሸነፉም በፌደሬሽኑ ለቡድኑ አባላይ ለያንዳንዳቸው አስር ሺ ብር መሸለሙ ይታወሳል::

በሪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በማራቶን የሚወክሏት አትሌቶች ታወቁ

$
0
0

Mare dibaba ethiopia

 ስሜነህ ታደሰ | ለዘ-ሐበሻ ስፖርት

(ዘ-ሐበሻ) ሊጀመር 77 ቀናት የቀሩት አጓጊው የብራዚሉ ኦሎምፒክ ሃገራት የሚወክሏቸውን አትሌቶች በማሳወቅ ላይ ይገኛሉ:: ኢትዮያም ባለፈው ሳምንት በአጭር ርቀት ሩጫዎች የሚወክሏትን አትሌቶች አሳውቃ የነበረ ሲሆን የማራቶን ወኪሎቿን እስካሁን ስታሳውቅ ቀርታ ነበር::

ዘ-ሐበሻ ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ድረገጽ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ በሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ኢትዮጵያን ከሚወክሉት ታላላቅ አትሌቶች መካከል የዓለም ሻምፒዮኗ ማሬ ዲባባ እንደምትገኝበት ታውቋል::

ማሬ ዲባባ ኦገስት 30, 2015 በቤጂንግ ቻይና በተደረገው 15ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ2:27:35 በመግባት አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል::

ኦክቶበር 20, 1989 የተወለደችው ማሬ የማራቶን ቡድናችን መሪ ትሆናለች::
በወንዶች ተስፋዬ አበራ; ለሚ ብርሃኑ እና ፈይሳ ላሊሳ ሲመረጡ በተጠባባቂነት ቀነኒሳ በቀለ; አድሃነ የማነና ለሊሳ ዲሳሳ በማራቶን እንዲወክሉ ተመርጠዋል::

በሴቶች ማራቶን ማሬ ዲባባ; አበሩ ከበደና አሰለፈች መርጊያ ሲመረጡ በተጠባባቂነት ት ዕግስት ቱፋ እና ትርፌ ጸጋዬ ተመርጠዋል::

በሬዮው ኦሎምፒክ  206 ሃገራት ሲሳተፉ 42 ዓይነት ስፖርቶች ይካሄዳሉ::

ብራዚል ይህንታላቁን ኦሎምፒክ ለማዘጋጀት 37 የስፖርት ማከናወኛዎችን ገምብታለች::

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን::

በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከትናንት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ እየተቀጠቀጡ ነው –አንዱን ፖሊስ ከህንጻ ገፍትረው ጣሉት (ፎቶዎች ይዘናል)

$
0
0

13087681_10102296231705053_4077424415859432752_n 13221028_10102296231635193_759698516884747726_n
13254093_10102296231320823_8172214177964234618_n

(ዘ-ሐበሻ) ተማሪዎች በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የመብት ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ የፌደራል ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸማቸውንና ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም በተማሪዎቹ ላይ የሚደርሰው ጉዳት ማየሉ ተዘገበ::

ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ያነሱትን ተማሪዎች ፖሊስ ዛሬ ጠዋት ድረስ መኝታ ክፍላቸው ውስጥ በመግባት እንደቀጠቀጠና ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰ የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች በተለይም አብዛኞቹ ተማሪዎች መፈነካከታቸውና ከ15 የማያንሱ ተማሪዎች በከፍተኛ ጉዳት ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል::

13230103_10102296234803843_6114860639105908605_n

ተማሪዎቹ ከመኝታ ክፍላቸው እንዳይወጡ ህንጻዎች በሙሉ በፌደራል ፖሊሶች እንደተከበበ የሚገልጹት ምንጮች ከሚደርስባቸው ድብደባ ለማምለጥ ሲሞክሩም አንዱን ፌደራል ፖሊስ ከህንፃ ላይ ገፍትረው እንደጣሉትና ፖሊሱም ጉዳት እንደደረሰበት ገልጸዋል::

ፌደራል ፖሊሶቹ በተማሪዎቹ ላይ የሚፈጽሟቸው ግፎች ከድብደባ በላይ አንዳንዱን ተማሪ በጠራራ ጸሀይ ላይ እያንበረከኩ ጸሐይ በማስደብድበ በግሩፕ እንደሚገርፉቸው ያስታወቁት ምንጮቻችን በሴት ተማሪዎች ላይ ሳይቀር ከትናንት ጀምሮ እየተፈጸመ ያለው ድብደባ የሚዘገንን ነው ብለዋል::

በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ውጥረቱ እንዳየለ ሲሆን ዘ-ሐበሻ እየተከታተለች ጉዳዩን ለመዘገብ ትሞክራለች::

 

ፎቶዎቹን ያሰባሰብናቸው ከሶሻል ሚዲያዎች ነው::

በፌስቡክ ምክንያት በርካታ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ

$
0
0

BC40B698-9797-4026-80F2-3BC5CE7651AA_cx0_cy5_cw0_w987_r1_s_r1 (1)ከረጅም ዓመታት በፊት በፖለቲካ ምክንያት በሶማሊያ መኖር እንዳልቻሉ በመግለጽ በኖርዌይ ያቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይንት አግኝቶ ፤ የመኖሪያ ፈቃድ እና ዜግነንት ተሰጥቷቸው የነበሩ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ። ለዚህ ሁሉ የዳረጋቸው ደግሞ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ስለራሳቸው የሚያወጡት መረጃ ጥገኝነት ካቀረቡበት ታሪካቸው ጋር ስለማይመሳሰል ነው።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ከ1992 ዓ.ም እስከ 2000 ድረስ ባለው ጊዜ በተለያየ መንገድ ኖርዌይ ገብተው የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው የነበሩ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ሶማሌያውያን ናቸው፤ በኖርዌይ ያገኙትን ዜግነት የተነጠቁትና የመኖሪያ ፈቃድ አግኝተው የነበሩትም እንዳይታደስላቸው እግድ የተጣለባቸው።

የኖርዌይ መንግሥት የአብዛኞቹን የፌስቡክ ገጾች ሲመረምር ግለሰቦቹ የጥገኝነት ጥያቄያቸውን አቅርበው በነበረበት ወቅት የሰጡት መረጃ እና ስለ እራሳቸው አሁን የሚለጥፉት መረጃ የተለያያ ኾኖ እንዳገኘውና ይህንንም መሠረት አድርጎ ተጨማሪ ማጣራት ሲያደርግ ዋሽተዋል ብሎ በማመኑ ዜግነታቸውን እንደነጠቃቸው አስታውቋል።
አቶ በሻሕ ሙሴ
በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ምክር ቤት ተመራጭ የኾኑት አቶ በሻህ ሙሴ መሐመድ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፤ ግለሰቦቹ ለኖርዌይ መንግሥት ያቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄ፤ ሶማሌያ ውስጥ በተፈጠረው አለመረጋጋት መኖር ባለመቻላቸው መሰደዳቸውን በማስረዳት ነው። ይህ ጥያቄያቸውም ተቀባይነት አግኝቶ አንዳንዶቹ ዜግነታቸውን ካገኙ 16 ዓመታት አስቆጥረዋል። አንዳንዶቹ ደግሞ የመኖሪያ ፈቃድ አግኝተው ኑሮአቸውን ቀጥለዋል።

የኖርዌይ የፍልሰተኛ ጉዳዮች መሥሪያ ቤት፤ እነዚህ ዜጎች የዜግነቱንም ኾነ የመኖሪያ ፈቃዱን ያገኙት በሐሰት ላይ በተመሰረተ መረጃ እና ማስረጃ ነው የሚል ጥቆማ ስለደረሰው ለሁለት ዓመት ምርመራ አድርጌያለሁ ማለቱን አቶ በሻሕ ሙሴ ይናገራሉ።

“የኖርዌይ መንግሥት መረጃዎቹን አሰባሰብኩ ካለበት መንገዶች አንዱ የሰዎቹን የፌስቡክ ገፆች ነው። መንግሥቱ የአብዛኞቹን የፌስቡክ ገጾች ሲመረምር ግለሰቦቹ የጥገኝነት ጥያቄያቸውን አቅርበው በነበረበት ወቅት የሰጡት መረጃ እና ስለ እራሳቸው አሁን የሚለጥፉት መረጃ የተለያያ ኾኖ እንዳገኘውና ይህንንም መሠረት አድርጎ ተጨማሪ ማጣራት ሲያደርግ ዋሽተዋል ብሎ በማመኑ ዜግነታቸውን እንደነጠቃቸው አስታውቋል”

አቶ በሻሕ አያይዘው፤ የኖርዌይ የፍልሰተኛ ጉዳዮች መሥሪያ ቤት አገኘሁት ባለው የምርመራ ውጤት፤ አንዳንዶቹ ሶማሌያውያን ነን ከሞቃዲሾ ነው የመጣነው ብለው ጥገኝነት ጠይቀው ፌስቡካቸው ላይ የጅቡቲ እና የሌሎች ጎረቤት ሀገር ዜጎች መኾናቸውን የሚያሳይ ፎቶ ግራፍና ቪዲዮ ለጥፈዋል።
ከጓደኞቻቸውና ቤተሰቦቻቸ ጋር የተነሷቸ ፎቶዎች፣ የሚለዋወጧቸው መልዕክቶች ፈጽሞ ካቀረቡት ታሪክ ጋር እንደማይሄድ ተነግሯል። አንዳንዶቹ ደግሞ መኖር አልቻልንም ወዳሉት ሀገር ተመልሰው መሄዳቸውን መኖሪታ ቤትና ንግድቤት

መስራታቸውን የሚያሳዩ ምስሎች እና አስተያየቶች ማስፈራቸው የኖርዌይ የፍልሰተኞች ጉዳዮች መሥሪያ ቤቱ ደርሼበታለሁ ይላል።

መሥሪያ ቤቱ ይህንኑ በፌስ ቡክ ላይ የሰፈረ መረጃ ተከትሎም ምርመራ ሲያደርግ አንዳንዶቹ በጭራሽ ሶማሌኛ ቋንቋ የማይችሉና ሶማሌያ ከምትባለው አገር ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው የጎረቤት ሀገር ዜጎች ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ ከሌላ ሶማሌኛ ቋንቋ ተናጋሪ ከኾኑ ጎረቤት አገራት የመጡ ናቸው። ለዚህ ደግሞ ያደረጓቸው የመልዕክት ልውውጦች እና ወደ ቤተሰቦቻቸው የላኩት ገንዘብ በማስረጃ ተያይዞባቸዋል ተብሏል።

አሁን አሁን አገራት እንደ ፌስቡክ ባሉ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚውጡ ታሪኮችን እንደ የጀረባ ታሪክ ማጣሪያ መንገድ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። የዩናይትድ ስቴትስ የሠራተኛ አስተዳደር ጉዳዮች ቢሮ የተቀጣሪ ሠራተኞቹን የደህንነት ዳራ ፍተሻ ለማጥራት አዲስ ለሕዝብ ክፍት የኾኑ ማኅበራዊ ድረ ገፆች ላይ የጀመረውን ዘዴ በድረ ገጹ ላይ አስፍሯል።

አቶ በሻህ ሙሴም የኖርዌይ የፍልሰተኞች ጉዳዮች መሥሪያ ቤት ሌላ እያጣራቸው የሚገኙ ሰዎች እንዳሉ ተናግሯል። በዚህ ምክንያት ብቻ የኖርዌይ ዜግነታቸው መነጠቃቸው፣ የመኖሪያ ፈቃዳቸው እንዳይታደስ መከልከሉ እና ወደየ አገራቸው ይመለሳሉ መባሉን በመቃወም ፊርማ አሰባስበው አቤቱታቸውን ሊያቀርቡ ነው ብለዋል።

የቬኦኤ ሶማለኛ ቋንቋ ዘገባን ጽዮን ግርማ አጠናቅራዋለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

በፌስቡክ ምክንያት በርካታ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ (5:05)

ጎሰኝነት የሰው ልጅ ጠላት –ጌታቸው ኃይሌ

$
0
0

getachewአደጋው እንዳይደርስ የሚጥሩትም እንዲደርስ የሚገፋፉም ወገኖች ድምፃቸው እኩል ይሰማል። ሁለቱም ወገኖች “ሕዝቡ ይጠየቅ” እያሉ በሕዝብ ስም ይምላሉ። መሐላው ቢያንስ ሦስት ጕልሕ ችግሮች አሉት፤ አንደኛ፥ ሕዝብ የሚጠየቀው ብዙ ሀገሮችን አንድ ሀገር ለማድረግ እንጂ አንድን ሀገር ብዙ ሀገሮች ለማድረግ አይደለም። ይኸንን እክል ውድቅ ለማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች የሶቪየት አንድነትንና የዩጎዝላቪያን መፈራረስ፥ የቸኮዝሎቫኪያን ሁለት አገሮች መሆን ለምሳሌነት ይጠቅሳሉ። ሆኖም እነዚህ ሀገሮች የተከፋፈሉት የፈጠሩት የነፃ ሀገሮች አንድነት አልሠምር ስላለ ነው። አልሠምር ስላለ፡ ቀረ። ኢትዮጵያ ግን ቆዳዋ ሲጠብ ሲሰፋ የኖረች አንድ አገር እንጂ የነፃ ሀገሮች ስብስብ አይደለችም። የሀገር ገዳዮች ግፊት ወደቀድሞው እንመለስ ሳይሆን፥ አንድ ፍሬ ስትቀበር ብዙ ፍሬ እንደሚወለድባት ኢትዮጵያን እንቅበርና ብዙ አገሮች እናስወልዳት ነው። እነዚህ ሰዎች የረሱት አገሮቹ ሲወለዱ የተጠላውን የባህል ጭቆና ይዘው መሆኑን ነው፤ ማለትም፥ የአሁኒቱ ኢትዮጵያ እንድትከፋፈል የተፈለገው ከባህል ጭቆና ለመዳን ከሆነ፥ የባህል ጭቆና የሌለበት አገር አይወለድም። ልዩነቱ ለያንዳንዱ አዲስ አገር አዲስ ጨቋኝ ማንገሥ ነው።

ሙሉውን ጋዜጣ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ

መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ያላት የሰው ድሀ ሀገር ኢትዮጵያ –ይገረም ዓለሙ

$
0
0

Ethiopian-Flag.jpgበ1982 ዓም  ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆነ አይደለም የት ላይ አንዳለች አንኳን መናገር የማይቻልበት ወቅት .ከአንድ ባልንጀራየ ጋር እየሄድን እኔ ከማላውቀው የእርሱ ጓደኛ ጋር መንገድ አገናኘን፡፡ እናም ሰላምታ ተለዋውጠው  ታዲያስ አንዲት ነህ እንዴት ናችሁ ሲለው  ምን እባክህ ሰውም አለን ሰውም የለንም  ሲል መለሰለት፡፡

ሁለቱ ተለያይተው እኛ መንገድ እንደጀመርን ምንድን ነው ያለው ስል ባልንጀራየን ጠየኩት፡፡ እባክህ እሱ አመሉ ነው፡ ከርሱ ጋር ስናወራ ጓደኞቹ ሁሉ አንደተቸገርን ነው፤ በቀጥታ መናገር አይሆንለትም አለኝ፡፡ ምንድን ነው ስራው ስል ጥያቄ አከልኩ ስራው ወታደራዊ ካድሬ ፣ትውልዱ ጎንደሬ፣ፖለቲካውን በጎንደር አማርኛ እየመሰጠረ ነው የሚያስቸግረን  በማለት ባላንጀራየም እንደመራቀቅ እያደረገው መለሰልኝ፡፡ ሰው አለን ሰው የለንም  የሚለውን አባባል ምንነት ለመረዳት ከባልንጀራየ ጋር ብዙ አውርተንበታል፤ብቻየንም ብዙ ግዜ አውጥቼ አውርጄዋለሁ፡፡

ይህ በሆነ  አስር ዓመት ግድም ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም በጦቢያ መጽሄት ላይ ኢትዮጵያ የሰው ድሀ ካልሆነች ታዲያ የምን ድሀ ልትሆን ነው የሚል ጽሁፍ  አስነበቡን፡፡ ይህም ከሆነ አስር ዓመት ግድም (አጋጣሚው ሊገርም ይችላል)   ፕ/ር መስፍንን አግኝቻቸው  ከላይ የጠቀስኩትን ጽሁፋቸውን አስታውሼ ከ90 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ያላት፣ በተለያዩ የዓለም ሀገራት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተሰማርተው የሚሰሩ አንቱ የተባሉ ልጆች ያሏት በማለት ብዙ ነገር ዘረዘርኩና እንዴት የሰው ድሀ ትባላለች ስል ጠየኳቸው ፡፡ በጥሞና አዳምጠው በርጋታ የሰጡኝ ማብራሪያ ረዥምና አጥጋቢ ነበር፡፡ ከግዜው ርዝመት አንጻር ማስታወስ ቢገደኝም አንኳር ነጥቡ እነዚህ የምትላቸው ሰዎች ለራሳቸው ኖረው ሊሆን ይችላል፤ ላስተማራቸው ሀገርና ሕዝብ ምን ሰርተዋል? ከአገዛዝ አላቀውታል? ከድህነት አውጥተውታል? ሰው በሚፈለግበት ግዜና ቦታ ካልተገኘ መኖሩ ብቻ ለሀገር ምን ይጠቅማል የሚል ነበር፡፡

የርሳቸውን ማብራሪያ እያዳመጥኩ አስር ዓመት ያህል ወደ ኋላ ተመልሼ ሰው አለን ሰው የለንም ያለውን የወዳጄን ወዳጅ አስታወስኩት፡፡ የአባባሉ ምንነትና እንደዛ ለማለት ያበቃውም ምክንያት በፕ/ር ንግግር ውስጥ ግልጽ ብሎ ታየኝ፡፡ በቁጥር ብዙ ሰው አለ፤ በቁም ነገር መድረክ በተግባሩ መስክ ግን  ..ማለቱ ነበር የሰው ድሀ ማለት ይህ አይደል ታዲያ፡፡

ብቸኛው ፓርቲ ኢሰፓ ከሲቭልም ሆነ ወታደራዊ ማዕረጋቸው የሚቀድመውን ጓድ መጠሪያቸው ያደረጉ ብዙ እጅግ ብዙ አባላት ነበሩት፡፡ነገር ግን አባሉ በቁጥር በዝቶ  ቁም ነገር ያለው ግን አንሶ  አይደለም ሀገሪቱን ሲያንቆለጳጵሱዋቸው የነበሩትን መሪ ከስደት፤ ፓርቲውን ከሞት፤ ራሳቸውን ከውርደት መታደግ ሳይችሉ ቀሩ፡፡

ኢሰፓ ያልነበሩ እንደውም ኢሰፓን ተቃውመው መንግስቱን አውግዘው ሲታገሉ የነበሩ ባይታገሉም ሥርዓቱን ይቃወሙ ዴሞክራሲን ይመኙ የነበሩ በቁጥር ብዙ  ነበሩ፡፡ ግና ቁም ነገራቸው ሚዛን የሚደፋ የተግባር ሰውነታቸው እስከመስዋዕትነት የደረሰ ጥቂቶች ሆኑና ኢትዮፕያ ሰው እያላት የሰው ድሀ ሆነችና  ከወታደራዊ አገዛዝ ወደ ተጋዳላዮች አገዛዝ ለመሸጋገር በቃች፡፡

ዘመነ ወያኔንም ስናይ ከመነሻው ጀምሮ ወያኔን የሚቃወመው፣ ስለ ለውጥ  የሚደሰኩረው፣  ስለ ዴሞክራሲ  የሚሰብከው፣ ወዘተ ቁጥሩ የትየለሌ ነው፡፡ ግና ከቁም ነገሩ መድረክ ከተግባሩ ስፍራ የሚገኙት ጥቂት በጣም ጥቂት ሆኑና ወያኔ ማን አለኝ ከልካይ እያለ የሻውን እየፈጸመ ሀያ አራት ዓመታት ለመግዛት ቻለ፡፡ ሌላው ቀርቶ በቅርቡ ኢሳትና ቪዥን ኢትዮጵያ በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡትን  በተለያየ የሙያና የእውቀት ዘርፍ ከጫፍ የደረሱ ምሁራንን የተመለከተ  የእነርሱ መሰሎች ሀገር ኢትዮጵያ እንዲህ በአገዛዝ ስትማቅቅ፤፣ከዴሞክራሲ ጋር ሆድና ጀርባ ሆና ስትኖር፣ ሕዝቡ በየግዜው በረሀብ አለንጋ ሲገረፍ ሰው እያላት ሰው ያጣች ሀገር አያሰኝም ትላላችሁ!

የኢትዮጵያ የሰው ድሀነት በወያኔም ውስጥ በገሀድ ይታያል፡፡ በተለያየ መንገድ የድርጅቱ አባልም ደጋፊም የሆኑ አባልና ደጋፊም ባይሆኑ ደግሞ የማይቃወሙ በተለያየ የእውቀትና የሙያ መስክ ላይ የሚገኙ በውጪም በውስጥ ብዙ ዜጎች አሉ፡፡ነገር ግን እነርሱም ቁጥራቸው እንጂ ቁም ነገራቸው የሚታይ ባለመሆኑ ድርጅታቸው በሀገርና  በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ጥፋት ማሰቆም ቀርቶ አንድ መለስ ያለእኔ ማን አለ ብለው ፓርቲም መንግሥትም ግለሰብም ሆነው ናውዘው ለሞት ሲበቁ ሊታደጉዋቸው አልቻሉም፡፡

ይህም ብቻ አይደለም ከአስር ዓመት በፊት ከአምስት ሚሊዮን በላይ አባላት አሉኝ ያለ ድርጅት በቁጥር እንጂ በቁም ነገር (ከሱ ፍላጎት አንጻር) ሚዛን የሚደፋ ሰው አጥቶ ከቦታ ቦታ የሚያገላብጣቸው የተወሰኑ ሰዎችን ነው፡፡ ሴቶችማ ለቁጥርም የሉ፡፡የአሁኑ አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ አንዴ ጀነራል አንዴ አቶ እየተባሉ ስንት ቦታ አንደተገለባበጡ ማስታወሱ ብቻ ለዚህ በቂ ይመስለኛል፡፡

የትውልድ ድርሻውንና የዜግነት ግዴታውን ቅንጣት ሳይከውን በሥልጣኔ ስም ሰይጥኖ ወደ ላይ አንጋጦ ትናትን የማውገዝ ድፍረት በተላበሰው ትውልድ የሚነቀፉ የሚዘለፉት አባቶቻችን በቁጥር ጥቂት ሆነው ከነዛው መካከል ግን የቁም ነገር ሰዎች ብዙም ብርቱም የነበሩ በመሆናቸው ነበር በዙሪያችን ያሉ ሀገሮች በቅኝ ግዛት ሲማቅቁ ኢትዮጵያ በነጻነት የዘለቀችው፤ ዳር ድንበሯን አስከብራ የባህር በሯን አስጠብቃ ለመኖር የቻለችው፡፡ለዓለም ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተምሳሌት ሆና የኖረችው፡፡

ዛሬ ግን አንደ ቁጥራችን ብዛት ከቁም ነገር ያፋቱን፣ ከተግባር ያራቁን ችግሮቻችን በዝተው እኛ የሚናቁት የሚወገዙና የሚኮነኑት አባት እናቶቻችን የቆዩንን ሀገር፣  ዳር ድንበር፣ የባህር በር፣ወዘተ ማስከበርና መጠበቅ ሳንችል ቀረን፡፡  ከወያኔ አገዛዝ ተላቀን የምናወራለትን ዴሞክራሲ እውን ለማድረግ  መስኩ ላይ መገኘት አቃተን፡፡ በእውቀት የበለጸጉ በሙያ የተካኑ በልምድ የዳበሩ አያሌ ልጆቿ  በመላው ዓለም በተለይም በምእራቡ የዓለም ክፍል ተሰማርተው እውቀት ጉልበታቸውን ለሌላ ሀገር እየሸጡ የተደላደለ ኑሮ መኖር ቢቻላቸውም  እውቀታቸውም ሆነ ሙያቸው፣ ልምዳቸውም ሆነ ጉልበታቸው፣ ለሀገራቸው የሚፈይድ አልሆነም፡፡ አንዲህም ሆነና እናት ሀገር ኢትዮጵያ መቶ ሚሊዮን የሚሆን ሰው እያላት  የሰው ድሀ ሆና  አገዛዝ እንደተፈራረቀባት፣ ዴሞክራሲ አንደናፈቃት፣ ረሀብ ልጇን እንዳሰቃየባት ትኖራለች፡፡ ዛሬ እየሆነ ካለው በላይ  የነገው ተስፋ የለሽነት  ይብስ ይከፋል፡፡

መቼ ይሆን! ኢትዮጵያ ልጆቿ  ቁጥራችን ብቻ ሳይሆን ቁም ነገራችንም በዝቶ ሰው እያላት የሌላት የሰው ድሀ ከመሆን የምትወጣው? መቼ ይሆን! በዘር፣ በሀይማኖት፣ በአመለካከት ልዩነት ተለያይተው የመቶ ሚሊዮኖች እናት ግን የሰው ድሀ ያደረጉዋት ልጇቿ ከምንም ነገር በፊት እናታችን ብለው እውቀታቸውን አቀናጅተው ሀይላቸውን አስተባብረው  ነጻነት የሚያቀዳጇት? መቼ ይሆን! ልጆቿ ከራስ በላይ ነፋስ አስተሳሰብ ተላቀው፣ ከመጠላለፍ አዙሪት ወጥተው፣ ከቁልቁለት ጉዞ የሚያቃኑዋትና  የነበረ ዝናና ክብሯን መልሰው የሚያቀዳጁዋት? አረ መቼ ይሆን! ልጆቿ  ዴሞክራሲ እየተረገዘ የሚጨነገፍበትን ሲወለድም   በአጭር የሚቀርበትን በሽታ ተርደተው መድሀኒትም አግኝተውለት ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊት ሀገር ለማድረግ የሚበቁት ? አረ መቼ ይሆን! ልጆቿ የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ሀገር የሰው ድሀ የሆነችው እነርሱ ተለያይተው በመቆማቸው፤ በስልጣን ጥም በመታወራቸው፤ ከእኔ በላይ በሚል አስተሳሰብ በመታጠራቸው፣ለራስ እንጂ ለመጪው ትውልድ የማይጨነቁ በመሆናቸው ወዘተ መሆኑን ተረድተው ከየራሳቸው ታርቀው፣ ርስ በርሳቸው ፍቅር መስርተው፣ አንደ ብዛታቸው ቁም ነገራቸውም ለሀገርና ለወገን ሲበጅ የሚታየው መ? መቼ አረ መቼ !

ተዋቂው የብእር ሰው ሎሬት ጸጋየ ገብረ መድህን  ይድረስ ከእኛ ለእኛ በሚለው ተከታታይ ግጥም ውስጥ እንዲህ ብሎ ነበር፡፡

ይድረስ ወገን ከእኛ ለኛ “እሳት አንሆን ወይ አበባ”

የነገን ራዕይ አንዳናይ ፣በሐቅ እንቅ ስንባባ

መክሊታችንም ባከነች፣ዕድሜአችንን ስናነባ፡፡

ፍቅር ፈርተን፣ሰላም ፈርተን

አንድታችንን ጠልተን ፣ተስፋችንን አጨልመን

የነፍስን አንደበት ዘጋን፣

የልጆቻንን ተስፋ ፣እምቡጥ ሕልማቸውን በላን፡፡

ሳይነጋ እየጨለመ ነው፣ተው ወንድሜ እንተማመን፣

ዓለም ባበደበት ዘመን፣የብረት ምሽግ ነው ወገን፡፡

ኢትዮጵያ ዘለዓለሚቷ፣አንድነት ነው መድኃኒቷ

ሕብረት ነው መፍትሔው ስልቷ፡፡

 

 

 

ፈላስፋው መምህር (መላከ መንክራት) ግርማ ወንድሙ ቀጣይ ጉዞ

$
0
0

girma wendimuበባሌ ክፍለ ሀገር ጎባ እንደተወለዱና የልጅነት ጊዜያቸውንም በዛው እንዳሳለፉ የሚናገሩት መምህር (መላከ መንክራት) ግርማ ወንድሙ ለበርካታ አመታት ክፉ መናፍስትን ከሰዎች ልጆች በማስወጣት የሚታወቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት የሐይማኖት አባት ነቸው፡፡ መምህሩ በዚህ አገልግሎታቸው በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ከክፉ መናፍስት እስራት እዳላቀቁ ይነገርላቸዋል፡፡ የዚሁ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑትም በርካታ ሰዎች ስለዚሁ ይመሰክራሉ፡፡ የክፉ መናፍስትን ከማስወጣቱ በተጨማሪ መምህሩ በኢትዮጵያ ለዘመናት የተዘነጉና ሕዝብን ለመናፍስት ወረራ የዳረጉ የሚሏቸውን የተለያዩ መረጃዎችን  ፈውስ በሚሰጡባቸው በጉባዔያትና አሜሪካን አገር በሚገኝ ራዲዮ አቢሲኒያ በሚባል ሬድዮ ለሕዝብ ያስተምራሉ፡፡ በዚህም አገልግሎታቸው ብዙዎች ልዩ ዕውቀት እንዳገኙና ራሳቸውንም እንደቀየሩ ይናገራሉ፡፡

እኔ እንደ አስተዋልኩት እኚህ ሰው ከብዙ የዘመኑ የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮች የሚለይዋቸው ፍልስፍናዎች አሉ፣ ተግባሮች አሉ፡፡ ምንዓልባትም በመናፍስት ላይ ያላቸው ኃይል ከዚህ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል አስባለሁ፡፡ በመድረክም ከላይ በጠቀስኩትም ሬዲዮ መምህሩ ሲያስተምሩ ከተለመደው የሀይማኖት ስብከት ከሚባለው ለየት ያለ ነው፡፡ ትምህርታቸው የመጽሐፍ ጥቅስ በማብዛት ሳይሆን ከመጽሐፉ ክፍል አንድ ወይም ጥቂት ዓረፍተ ነገር በመውሰድ እሱን ከነባራዊው የሰዎች አኗኗር ጋር በመተንትን ነው፡፡ በእርግጥም ብዙ ጊዜ አንብበንው ያለፍነው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እሳቸው ሲተነትኑት ራሳችንን እስከምንታዘብ ድረስ እንዳልገባን ይሰማናል፡፡ መምህሩ ሲያስተምሩ በመጻሐፍ ያለውን ዛሬም እየሆነ እደሆነ በመስረገጥ ነው በማለት እንጂ እንደሌሎች ይላል በሚል አይደለም፡፡ የሚናገሩትም እንደ ፈላስፋ እንጂ እንደ ሰባኪም አይደለም፡፡ በበርካታ ትምህርቶቻቸውም አብዝተው ስለ ሕዝብና አገር በቁጭት ይናገራሉ፡፡

መምህሩ ባሳለፏቸው የአገልግሎት ዘመናት አግልግሎት የሚሰጡት በነጻ ነው፡፡ በነጻ ያገኛችሁትን በነጻ ስጡ የሚለው ቃል በተግባር የገባቸው ይመስላል፡፡ ለበርካታ ዓመታትም አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ሲሉ በኑሮ ብዙ ተፈትነዋል፡፡ ብዙ ሕዝብ እያገለገሉም ይሄው የኑሮ ችግራቸው የከፋ ነበር፡፡ በተገኙበት ጉበኤ ሁሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ለሚያገለገሉበት ደብር እየስገቡ እሳቸው  በማጠት የተቸገሩባቸውን ብዙ አመታት መምህሩ ይዘክራሉ፡፡  ከብዙ ዘመን በኋላ ነበር ታዲያ  ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር ኑሯቸውን ያስተዋሉ አንዳንድ ግለሰቦች በኑሮ እንዳይፈተኑ ያገዟቸው፡፡ ቤት የገዙላቸው ባልና ሚስት በመምህሩ እንደ ልዩ የእግዚአብሔር መልክተኞች ይታያሉ፡፡ ለዘመናት በቤት ጉዳይ ተፈትነዋልና፡፡ የሚሰጡትንም የአጋንንት ማስወጣቱን ተግባር ከሌላ አንጻር እየተመለከቱባቸው ቤት አከራዮቻቸውም ብዙ ፈትነዋቸዋል፡፡ ወደ መጨረሻ እንደውም ቤት የሚያከራያቸው ራሱ እንዳጡ መምህሩ ይናገራሉ፡፡ እንግዲህ እሳቸው ጋር ያለ ኃይል እንዲህ ባለ ፈተና ካልሆነ አፀና ይሆን; በዚህ ሁሉ ግን መምህሩ እጅ ሳይሰጡ፣ ገነዘብም፣ ዝናም፣ ሰውም ሳይጥላቸው አሁን ያሉበት ደረሱ፡፡  አሁን ፈተናው ቢኖርም እንደ ድሮው አይደለም፡፡ ብዙ ሕዝብም የፈተናቸውም ተጋሪ ሆኗል፡፡

ብዙ ሕዝብ በትክክል እየተረዳቸው ሲመጣ ፈተናው በዛው ልክ መዋቅራዊ ሆኖ ዛሬ ቤት፣ ልብስ፣ ምግብ ሳይሆን የሚያገለገልሏት ቤተክርስቲያን ኃላፊዎች ዋና ፈተና ሆነውባቸዋል፡፡ ብዙ ያሴሩባቸዋል፡፡ ሆኖም አሁን እየገጠማቸው ያለው ፈተና በሕዝብ ዘንድ ብዙ የታወቁበት ዘመን በመሆኑ ፈታኞቹ መምህሩን በሚከሱበት ሁሉ ትዝብት ውስጥ እየገቡ ይመስላል፡፡ ብዙዎችም እውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለዘመናት ዋና ሆነው ያሉት እነማን ናቸው የሚል ጥያቄን እያነሱ ነው፡፡ በቅርቡ መምህሩ በተለያየ የሐሰት ክሶች ለእስር ተዳርገው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ክሶቹ መጀመሪያ የግለሰብ እንዲመስሉ ቢደረግም እየቆየ ከቤተክርስቲያኒቱ ዋና ከተበሉት እንደሆነ ተረዳን፡፡ የፖለቲካ አንድምታም እንዳለውም በማሰብ፡፡ ዛሬ በቤተክርስቲያኒቱ የተለያየ ቦታ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ ዋናው ችግር ከገንዘብ ጋር የተያየዘ ነው፡፡ ከሳቸው ጋር ያለው ችግር ግን ትንሽ ረቀቅ ያለ ይመስላል፡፡ በሥጋ በማይገለጥ የመንፈሳዊ ጦርነት ይመስላል፡፡ ለብዙዎች የመምህሩ አጋንንትን ከሰው ልጆች ማውጣት ሠላም እየሰጣቸው ያለ አይመስልም፡፡ የቤተክርስቲያኗን መንፈሳዊ አገልግሎት ዕውቀት ያላቸውና በመንፈሳዊ ሕወታቸውም ጠንካራ የሚባሉት የሲኖዶስ አባላት ጳጳሳት ሳይቀር መምህሩ ትክክለኛ እንደሆኑ በብዙ መድረኮች ሲናገሩ እንሰማለን፡፡ ሌሎች ግን ሥራቸውን ከጥንቆላ ጋር አገናኝተው ሊያወግዙ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ግን በሕዝብ ዘንድ ሌላ ጥያቄን ፈጥሮ ይገኛል፡፡ በቤተክርስቲያኗ ተንሰራፍቶ ያለው የጥንቆላ ሥራ የበለጠ ስለሚታመንበት በእግዚአብሔር ኃይል ለሚደረግ አገልግሎት ዋጋ መስጠትን እንደተረሳ ብዙዎች ተረድተዋል፡፡ መምህሩን ዛሬ ፈታኝ የሆኑባቸውም ራሳቸው በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ዋና ሆነው በጥንቆላ ሥራ የሚታወቁ ናቸው የሚል ትዝብትን አምጥቷል፡፡ በእርግጥም ይህ አስተሳሰብ በሕዝብ ዘንድ ቢኖር አይገርምም፡፡

መምህሩ ተግባራቸው በግልጽ በኃያሉ በእግዚአብሔርና በቅዱሳኑ ሥም አጋንንትን ሲያሶጡ የሚያሳይ ነው፡፡ ለገንዘብ ቦታ የላቸውም፡፡ ዘር ጎሳ ሐይማኖት ጭምር ሳይለዩ በተሰጣቸው ጸጋ ሁሉንም ያገለግላሉ፡፡  በዚህም በትምህርታቸውም ሆነ በፈውስ አገልግሎታቸው ተጠቃሚ እየሆነ ያለው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ብቻም ሳይሆን ሁሉም ነው፡፡  ለአገርና ሕዝብ ያላቸው ቁጭት እጅግ ታላቅ ነው፡፡  በዘር የተከፋፈለች በመሆኗ ያዝነሉ፡፡ በአደባባይም ይሄንኑ በቁጭት ይናገራሉ፡፡  በአንድ ወቅት በጊምቢ ምዕራብ ወለጋ በአንድ ደብር የተናገሩት በብዞዎች ይታወሳል ከጎጃም የመጣ በሬና ከወለጋ የመጣ በሬ አብረው አንድ ላይ ሳር ይግጣሉ እኛ ግን ዘር እየቆጠርን እንናከሳለን ብለው ነበር፡፡ በብዙ መድረክም እንዲህ ያለውን ነገር ይናገራሉ፡፡ የኤርትራውያን ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ ድሮ በአውቶብስ እንደልብ የሚገናኙ ሕዝቦች ዛሬ ያለፍላጎታቸው ታግደው በሌላ አገራት ሲገናኙ በማየታቸው እጅግ ያዝናሉ፡፡ ብዙም ጊዜ ይናገሩታል፡፡ እንዲህ ያለው በዘር መከፋፈል አስከፊነቱን ለአገልግሎት በተንቀሳቀሱባቸው የውጭ አገራት ትልቅ ትኩረት ሰጥተው ተናግረውታል፡፡ ይሄ ግን አሁን በሥልጣን ላይ ላለው መንግስትና በዘርና በተለያየ ጥቅም ለተበከሉ የቤተክርስቲያኒቱ ባለስልጣኖች እንደ ክፉ ሳይታይባቸው አልቀረም፡፡ በቅርብ የታሰሩበት መሠረታዊ ምክነያቱም የሕዝብ እንድነትን መስበካቸው ይመስላል፡፡ ከእስር ከተፈቱም በኋላ በሲኖዶስ አባል በሆኑ ጳጳስ በምድብ አገልግሎት እንዲሰጡ ደብዳቤ ቢጻፍላቸውም ከዋናው ፓትሪያርክ በወጣ ሌላ ደብዳቤ ታግደዋል፡፡  ከዚህም በፊት ብዙ ደብዳቤ ተጽፎላቸዋል ተጽፎባቸዋልም፡፡

በአሁኑ ወቅት  መምህሩ በየትኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንዳያገለግሉ ታግደው ቀድሞ ይስጡት የነበሩትን አገልግሎት አቋርጠዋል፡፡ ሆኖም ትምህርታቸው አቢሲኒያ በሚባለው ሬደዮ ቀጥሏል፡፡ እሳቸውም ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ወገኖችን ይዘው የበለጠ ወደሚሆን ልዩ አገልግሎት እየገቡ ያለ ይመስላል፡፡ ከዚህ በፊት ለየደብሩ ብዙ ገንዘብ በማስገባት የሚተወቁት እኝህ መምህር አሁን የተጎዱ ወገኖቼን በሚል ወደበጎ አድራጎት ድርጅቶች ፊታቸውን አዙረዋል፡፡ በቅርብ የአንድ የድኩማንና አንድ ሌላ ወላጅ የሌላቸው ሕጻናት የሚማሩበትን ተቋማት መረዳታቸውን እናስታውሳለን፡፡ ሰሞኑን ደግሞ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ዕርዳታ የሚሆን ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ በ15 ቀን ውስጥ አሰባሰበው ለኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር አበርክተዋል፡፡  የመምህሩ በእንደዚህ ያለ አጭር ጊዜ ይሄን የሚያህል ገንዘብ ማሰበሰብ መቻል ለብዙዎች ሊገርም ይችላል ሆኖም መምህሩ ለየደብራቱ በተገኙበት አጭር ሰዓታት የሚያስገቡትን ላየ ብዙም አይገርምም፡፡  በአንድ ደብር ከግባሽ ሚሊየን ብር በላይ የአስገቡበትን አንድ ከ2-3ሰዓት የሆነ ጉባዔያቸውን ብዙዎች በአይናቸው አይተዋል፡፡ መምህሩ እንደተናገሩትም አገር ውስጥ ያለው ጉባዔያቸው ቀጥሎ ቢሆን አሁን ለቀይመስቀል ያበረከቱት ከአምስት ሚሊየን በላይ ይሆን ነበር፡፡

ቀጣዩ የመምህሩ ጉዞ ከዚህ በላይ ቢሆን ተመኘሁ፡፡ ከላይ እንደጠቆምኳችሁ፡፡ መምህሩ ለአገርና ሕዝብ ትልቅ ቁጭት አላቸው፡፡ የሕዝብ ኑሮ ከአገር መሰደድ ብዙ ይሰመቸዋል፡፡ በእሳቸው ዘንድ ኢትዮጵያዊነት (ለእሳቸው የኤርትራን ሕዝብ ጨምሮ ነው) ትልቅ ሥፍራ አለው፡፡ በዛው ልክ ትምህርታቸውን በሚከታተሉትም ዘንድ እንደዛው ነው ኤርትራውያኑን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘር (አሮሞ፣ አማራ ትግሬ… ምናምን)፣ ሐይማኖት (ኦርቶዶክስ፣ እስላም፣ ፕሮቴስታንት) ሳይል ሁሉም ይወዳቸዋል፡፡ ቀጥሎ የመምህሩ ጉዞ በዘር የተከፋፈለውን ሕዝብ አንድ የሚያደርግና ዜጎች በሰላም፣ በሠላም፣ በብልፅግና ፍትሕ የሰፈነባት አገር ለመገንባት ወደሚያስችል ተግባር ቢሆን ተመኘሁ፡፡ መምህሩ ከጠለቀ የሀይማኖትና የሰውልጅ ደህንነት ፍልስፍናቸው አንጻር ተቃራኒ ቡድኖችን በማቀራረብ፣ ሕዝብንም ለሠላምና አገርን በአንድነት ለመገንባት የማነሳሳት አቅሙ እንዳላቸው አሰብኩ፡፡ መምህሩ የሚከተሉት እንደተረት የምንሰማቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ያነበብናቸውን ፈላስፋዎች እንደነ ቅዱስ ጳውሎስ ያለውን ፍልስፍና ነው፡፡ በዚያ ዘመን ያለች ጥበብ አሁንም እንዳለች በቃልም በተግባርም እያሳዩን ነው፡፡  ወገኔ ሕዝቤ የሚሉትን ዛሬ ተከታዮቻቸውን በማስተባበር ለዕለት ችግሩ የሚሆን ዕርዳታ እያበረከቱ ያሉትን ተግባር በዘላቂነት ኑሮው የተሻለ እንዲሆን አሁን የሚከታተሏቸውን ሌሎችንም ወገኖች በመያዝ ወደ አንድነትና አገር ልማት ለማመጣት ተጽኖ መፍጠር ከሚችሉ ሰው አንዱ ሆነው ይታዮኛል፡፡ እሳቸውም በዚህ ሂደት ተሳታፊ ቢሆኑ ደስተኛ እንደሚሆኑ ይሰማኛል፡፡ ከሁሉ በላይ ዘለቀታዊ የሆነ ሠላም፣ ፍትሕ፣ እንድነትና ልማት ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል፡፡ ዜጎች በብዙ መልኩ አእምሮ በሚያም ሁኔታ እተጎዱ ነው!

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ! አሜን!

 

ሰርጸ ደስታ


ኢትዮጵያዊው ነጋዴ ደ/አፍሪካ ውስጥ ሊዘረፈው የመጣ ሌባን ገደለ ተብሎ ለእስራት ተዳረገ

$
0
0

በታምሩ ገዳ

south-africa-zono-002በደቡብ አፍርሪካ ከሜዲናይቱ ጆሃንሰበርግ ሰሜናዊ አቅጣጫ ከምትገኘው ዲፕስሎት ከተባለችው ከተማ ውስ ጥ በንግድ ስራ የተሰማራው የ 35 አመቱ ኢትዮጵያዊ ንብርቱን ለመዝረፍ ከመጡ ወሮበላዎች መካክል አንዱን ደብድበህ ገደለሃል የሚል ወንጀል ቀርቦበት ከሕግ ጥላ ስር እንደሚገኝ ተዘገበ።

ኒወስ 24 የተባለ ድህረ ግጽ የፖሊስ ምንጩን ዋቢ በማድረግ እሮብ እለት እንደዘገበው ከሆነ ለጊዜው ስሙ ያለተጠቀሰው ኢትዮጵያዊው ነጋዴ ማክሰኞ እለት ለመታሰሩ እና በበነጋታው ሃሙስ እለት ከ ፍርድ ቤት ለመቅረቡ ምክንያት የሆነው ሟቹ እና ዘራፊው ከግብረ አብሩ ጋር ከኢትዮጵያዊው ነጋዴ ሱቅ በያዘነው አመት ውስጥ ጨለማን ተገን አድርገው እኩለ ለሊት ላይ ዘልቀው በመግባት የጦር መሳሪያቸውን/ሽጉጥ በማውጣት እና በማሰፍራራት ከመደብሩ ውስጥ መጠኑ በውል ያልተገለጸ ገንዘብ እና የተለያዩ ሸቀጦችን ዘርፈው ለመወጣት ሲሉ በወቅቱ ከመደብራቸው ውስጥ ተኝተው የነበሩት ተከሳሹ ኢትዮጵያዊው ነጋዴ እና ጓደኛው ከዘራፊዎቹ አንደኛውን በጣሪያ ላይ ለማምለጥ ሲጣጣር በመያዝ እንደ ደበደቡት እና ጩሀቱንም የሰሙ ጎረቤቶች (ኢትዮጵያዊያኖች?) ከመቀሰፈት ደረሰው ሌባውን ደጋግመው በመውገራቸው ሌባውም ከድብደባው የተነሳ ምንም ኣንኳን የህክምና ባለሙያዎች ወደ ስፍራው ቢመጡም የሌባውን ህይወት ሊታደጓት አልቻሉም። ሌባውም ብዙም ሳይቆይ ሞቷል የሚል የአይን ምስክሮች ከፖሊስ ዘንድ ቀርቧል።

ከተፈጠረው ዝርፊያ እና ደብደባ የተነሳ አካባቢው ሊጊዜው ውጥረት ውስጥ ቢገባም ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ/ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞችን ለህግ እንደሚያቀረብ ቃል በመግባቱ ለጊዜው ሰላም ወርዷል ይላል ዘገባው።

የኢትዮጵያዊው ነጋዴ እጣፈንታ ምን አንደሚሆን ለጊዜው በውል ያልታውቀ ሲሆን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን ያልተደላደለ ፖለቲካዊ ምህዳር እና ያልተመጣጠነ የኢኮኖሚያዊ መዋቅር ተስፋ ያሰቆረጣቸው በሺዎች የሚቆጥሩ ኢትዮጵያዊያኖች በኬኒያ፣ በታንዛኒያ፣ በዛምቢያ ፣በማላዊ እና በመሳሰሉት አገሮች እጅግ ዘግናኝ የሆነ ግፍ እና በደል እየደረሰባቸው የተስፋይቱ ምድር ከሚሏት ደ/አፍሪካም ሲደርሱ ያቺ የ ነጻነት ታጋዩ፣ የመጀመሪያው የ የአገሪቱ ጥቁር ፕ/ት የኒልሰን ማንዴላ አገር ከአፓርታይድ የአገዛዝ ቀንበር ነጻ ትወጣ ዘንድ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ጉልህ ሚና ለተጫወተችው ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ልጆች ምድራዊ ገነት መሆኗ ቀርቶ ምድራዊ ሴኦል በመሆን ያ ሁሉ ውለታ ተረስቶ ”አትጵያዊያኖችን ጨምሮ ሰደተኞች ከአገራችን የውጡልን!! ፣አይናቸውንም ልናየው በጭራሽ አንሻም!! ወዘተ” በሚሉ የአገሪቱ ወጣት ጥቁር ዜጎች ከደበደባ አንስቶ ንብረታቸውን መነጠቅ ፣ማቃጠል፣ በህይወታቸውም እሰከ መቃጠል እና ስደስት የሚድረሱ ወገኖቻቸንን መግደላቸው እና በተመለከተ የተለያዩ አለማቀፍ የዜና አውታሮች ዋንኛ የመወያያ አጀንዳቸው አንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ። ሰሞነኛውም መጠፎ አጋጣሚ ቢሆን ምን ይዞ ኣንደሚመጣ ለጊዜው መገመት ያዳግታል። ለማንኛውም እንደ አሸዋ የተበተኑት ወገኖቻቸን ወደ እናት አገራቸው በሰላም እስኪመለሱ ድረሰ ባሉበት ሰላም እንዲበዛላቸው መጸለዩ እና ደግ ደግ መመኘቱ አይከፋም።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

መቀለ በቅዳሜና እሁድ በግዳጅ ሠልፍ ተንጣ ዋለች !! –አስገደ ገብረስላሴ

$
0
0

mekele የመቀሌ ህዝብ ፣የባጃጅ ፣ የታክሥ ሽፈሮችና በለንብረቶች የተቃውሞ አድማ በግልፅ ታዬ !!
የተግራይ ህዝብ ለካቲት 11 ህወሃት ትጥቅ ትግል የጀመረበትና የጉንበት 20 ደርግ ተሸሮ የተወገደበት የድል በአላት ለማክበር ገና ጊዜው ሣይደርሥ በሽኮላና በጉጉት በመጠባበቅ በራሡ ተነሣሽነት ማንም ሣያንቀሣቅሠው ግብዣና ሞፎከር ያዛጋጅ ነበር ። በተለይ ደግሞ ለካቲት 11 የህወሓት የመሥረታ በአል በትጥቅ ትግል ጊዜ ከማንም አማልክት በላይ በማምለክ በቤቱና ህዝብ በተሠበሠበበት እጅግ ቡዙ ወጭ በማድረግ ግብዣ አድርጎ የአድባራት ታቦት በሠልፍ ወጥተው ከማክበር አልፈው ሁሉ ወላጅ ከ15 አመት እድሜ በላይ ከዛ በታችም ህፃናት ፣ለብሥ አልብሦ ወደትግል ሜዳ ለመሥዋእት ልብሥ አልብሦ ፣አሥፈለጊ ሥንቅ ሠጥቶ በጭፈራ፣በእልልታይሸኝ ነበር ።
ለጉንበት 20የድል በአልም በመጀመሪያዎቹ አመታት በደሥታ ያከብር ነበር ።
ያሁሉ የሚያደርጉት የነበረ ገዥዎች ያደርሡበት የነበረ ግፍና ጭቆና አሥወግዶ ረሀብ ሥደት ጠፍቶ ፣ሠላም ፍትህ ነፃነት ፣ የህግ የበላይነት ፣ የዲሞክራሢና የዜጎች ሠብአዊ መብቶች መከበር ተረጋግጦ ፣ዲሞክራሢያዊ ህዝባዊ መንግሥት በመመሥረት ልማት ተሥፋፍቶ ፣ የበለፀገች ኢትዮጱያ ለማየት ነበር ።
ያሁሉ የተመኜው ነገር ግን ሣይሆን ቀርቶ የህወሃት ኢህአደግ ሥርአት ከነዛ በሥብሠውና ፣ላሽቀው የወደቁ ሥርአቶች የባሠ የሠለጠነ አንባገነን ፣ወደ ፋሸዝም ጎደና ያመራና ፣በተግባርም ከደርግ በባሠ የሠለጠነ ፈሽሽት ሆኖ በመገኜቱ ፣የኢትዮጱያ ህዝቦች የተመኙትን ሁሉ ውሃ ዘግነው ቀሩ!!! ።
በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብ በቅርብ የህወሃት አጋር ሆኖ ለ17 አመት ሙሉ ሁሉም አይነት ሀብቱ ፣ልጆቹ አማጡጦ የጨረሠ ህዝብ በመሆኑ ፣ የተገባለት ቃል 100%ሥለካዱት ፣ በአሁኑ ጊዜ ለህወሃት መሪዎችና አጋራቻቸው ፓርቲዎች ከነመዋቅራቸው ከአእምረው አውጥቶ ተፍቶዋቸው ይታል ።
ለዚሁ አንድ መሥረጃ የትላንተና የታክሥ ፣የባጃጅና የታክሥ የግዳጅ ጉንበት 20 አሥመልክቶ ሠልፍ ፣የታየው ተቀውሞ ድሮ ከአንድ በላይ ባነዴራ ያደርጉ የነበረ የዛሬው ሠልፍ አለፎ አልፎ ባንዴራ ያደረጉ ቢኖሩም በየመንገዱ ጥለውታል ፣ ቡዙ ታክሢዎች ደግሞ ባዶ ትላልቅ ሃይላንድ ቁልቁል አፉ በእንጨት ሠክተው አንደበንዴራ እያውለበለቡ ታይተዋል ። እነዚህ ባለታክሢዎች ተገደው በተሠበሠቡበት በጉሩፕ በጉሩፕ ሇነው ከነዚህ ሠወች መቸ ነው እምንላቀቀው እያሉም ይናገራሉ ።
እነዚህ ባለታክሢዎችና በለባጃጆች ከ6 ሠአት እሥከ 12 ሠአት ማታ በግዳጅ ሠልፍ ሥለታሠሩ የመቀሌ ታክሥ ተገልጋይ ህብረተሠብ ፣ተመሪዎች ፣ ሠራተኞች ምሬታቸውነ ይገልፁ ነበሩ ። በኢኮኖ ሚ አይን ሢታይም ባለታክሢዎች የከሠሩት እያሠሉ ሢናገሩ ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ እንደከሠሩ ተናረለዋል ።
በሌላ በኩሉ ለዛሬ ቅዳሜ ጥዋት የመቀሌና የአጓራባች ቀበሌዎች ጉንበት 20 አሥመልክቶ በግድ ሠልፍ እንዲወጣ ታዞ የመነግሥት ሠራተኛ በከፊል ፣ የኤፈርት ሠራተኞችም በከፊሌ ፣ የቀበሌ ተላላኪ ሤቶችና ተጠቃሚዎች ፣የሀገር መከላከያ ሠራዊት ፣ ፖሊሥ ፣ እንዲሁም ተማሪዎች ያልመጣ የአመት መጣቃለያ ፈተና አትፈተኑም በሚል በማሥፈራራት የተሠለፉ በሥተቀር የመቀሌ ህዝብ ሠልፍ አልወጣም ። ይህ የሚያሣዬው ህወሃት ኢህአደግ ምን ያ
ህል ከህዝብ ልብና አእምሮ ወጥቶና ርቆ እንዳለ ያሣያል ።
ግን እነዚህ ሠዎች ለምን ካለፉት ሠርአቶችና ፣ የአካባቢያቸው አንባገነኖች መንግሥታት አዋዳደቅ አይማሩም ?እነዚህ ሠዎች መንግሥታት ወታደር መድፍ ምሣይል ፣ሚግ ተዋጊ ፣ መንጋ ሥለላ ቢሠበሥቡ ፣ በያረዱ ፣ቢ ሠቅሉ ፣ቢያሥሩ ፣ ህዝብ እንደማይሸነፍ ያውቃሉ ። ለምን አይማሩም ???????

የሚዲያና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በኢሕአዴግ ላይ የሰላ ትችት አቀረቡ

$
0
0

‹‹ሙስና የሥርዓቱ ባህል እየሆነ መጥቷል›› በማለት ኢሕአዴግ ላይ የሰላ ትችት ያቀረቡት የሚዲያና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ባለፉት 25 ዓመታት ሙሉ የሚወራው ስለሙስና መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Bribeባለፈው ዓርብ ግንቦት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. 25ኛውን ዓመት የግንቦት 20 የብር ኢዮቤልዮ በዓል አስመልክቶ ከጋዜጠኞችና ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር በብሔራዊ ቴአትር በተደረገው ውይይት፣ ተሳታፊዎቹ ኢሕአዴግንና እሱን የሚመራው መንግሥትን ገምግመዋል፡፡ ድርጅቱ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ስለሙስና፣ ስለኪራይ ሰብሳቢነትና በሥልጣን ስለመባለግ ቢወራም ተመጣጣኝ ዕርምጃ ሲወሰድ አልታየም በማለት ክፉኛ ተችተዋል፡፡

ለውይይቱ መነሻ የሚሆን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬሕይወት አያሌው የግምገማ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት ይደበቃል፡፡ ሕዝቡ ግልጽ ሆኖለት ከተታገለው ግን እታች ተወርዶ ማቃጠል ይቻላል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ይህች አገር ፈርሳ ነው እየተሠራች ያለችው፡፡ እስካሁን ያስመዘገብናቸው ድሎችም ሊፈርሱ ይችላሉ፤›› በማለት ነበር የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋን አስመልክተው በሰጡት ሐሳብ ጽሑፋቸውን የደመደሙት፡፡ ‹‹ኢሕአዴግ ፈተናው ትልቅ ነው ይላል፡፡ አይደለም ድልን ልናስመዘግብ ያረጋገጥነውም ሊበላብን ይችላል፣ ወደኋላ ሊወረውረንም ይችላል፤›› በማለት፡፡

ውይይቱን የመሩት የብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ኃላፊ አቶ ዘርአይ አስገዶም መድረኩን ለተሳታፊዎች ክፍት ሲያደርጉ አንዳንድ አድናቆቶች የቀረቡ ቢሆንም፣ በአብዛኛው የትችት ሐሳቦች ተንፀባርቀዋል፡፡

አቶ እንድርያስ ተረፈ አስተያየት ከሰጡት መካከል የመጀመርያው ናቸው፡፡ ‹‹ኢሕአዴግ ወደ አዲስ አበባ ሲገባ ‘ሌባ አይወድም’ ይባል ነበር፡፡ ዛሬ ግን ራሱ ኢሕአዴግ ሌብነት መገለጫው እየሆነ መጥቷል፡፡ 25 ዓመት ሙሉ የምናወራው ስለሙስና ነው፡፡ ሌብነት የሥርዓቱ ባህል እስከመሆን ደርሷል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹መኖር ከአቅም በላይ በሆነበት ዘመን ዛሬም የምናወራው ስለሙስና ነው፡፡ ከ25 ዓመት በኋላ ዛሬ ምን ተለወጠ? ምን አገኘንና በምን እንለካው?›› በማለት አክለዋል፡፡

‹‹ቤት አገኛለሁ ብዬ ኮንዶሚኒየም የተመዘገብኩት 97 ላይ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ቤቶቹ ጠፉ እየተባሉ ነው፡፡ አንድ ሕንፃ ሲጠፋ ማን ተጠየቀ? ሕንፃዎቹ እስኪጠፉ መንግሥት የት ነበር?›› ብለዋል፡፡

የኪነጥበብ ባለሙያው አቶ ኃይላይ ታደሰ በበኩላቸው የቀረበው ሪፖርት ወደ ጥንካሬው ያመዘነ መሆኑን ገልጸው ነበር ትችታቸውን ያቀረቡት፡፡ ‹‹እንደ ባለሙያዎች እምብዛም ተጠቃሚ አይደለንም፡፡ አንቀጽ 29 ላይ የተቀመጡ መብቶችን እንዳንጠቀም የሚያግዱ አፋኝ ደንቦች እየተረቀቁ ይገኛሉ፡፡ ይኼ ከሴንሰርሺፕ (ሳንሱር) ተለይቶ የሚታይ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

አቶ ኃይላይ ትችታቸውን በመቀጠል፣ ‹‹ኢሕአዴግ ከአፄ ኃይለ ሥላሴና ከደርግ ጋር ራሱን እያወዳደረ ዕድገት አስመዘገብኩ ሲለኝ ያንስብኛል፣ ይወርድብኛል፤›› በማለት ድርጅቱ እንደ መንግሥት በራሱ ከያዘው ዕቅድ አንፃር፣ ከሰፊው ሕዝብ ተጠቃሚነት አንፃር መመዘን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

‹‹ስብሰባና በዓል ታበዛላችሁ፡፡ ይኼ ሁሉ የተከፈለው መስዋዕትነት በተግባር ቢለካ አንድ ሰው ሌባ ከሆነ ሌብነቱን በሕዝብ ፊት አጋልጡት፡፡ አለበለዚያ ቁርጠኝነቱ ያላችሁ አይመስለንም፡፡ ከአንድ ቦታ አንስታችሁ ሌላ ቦታ ትሾሙታላችሁ፡፡ ለእኔ ቀልድ ነው የሚመስለኝ፡፡ ተግባብቶ ለውጥ የሚያመጣ ተግባር እያካሄዳችሁ አይመስለኝም፤›› በማለት ቀጥለዋል፡፡

‹‹አንድ ለልማት ተነሽ የሆነ አካባቢ ስታፈርሱትና ስታነሱት በጣም ነው የምትጣደፉት፡፡ አጥራችሁ ስታስቀምጡ ግን ረዥም ጊዜ ነው፡፡ አራት ከንቲባዎች ሲቀያየሩ ታጥሮ የተቀመጠ ቦታ የለም ወይ?›› በማለት የፍትሕ ማጣትና ሌሎች ማሳያዎችንም አቅርበዋል፡፡

ሕዝቡ የዕድገቱ ተጠቃሚ አለመሆኑንና ከአቅሙ በላይ በኑሮ እየተሰቃየ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ ‹‹ዕድገቱ ጤነኛ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ጥቂት ከጉምሩክና ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር የሚመሳጠሩ ዜጎች ያገኙትና የተሠሩ ነገሮች እንደ ዕድገት ከተለኩ እኔ ትክክል አይመስለኝም፡፡ የሕዝቡ ቁጥር መጨመርና ዘመኑ የደረሰበት ቴክኖሎጂ መለኪያው ያ ከሆነ አይገባኝም፤›› በማለት መንግሥት ባልተሠሩ ነገሮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲንቀሳቀስ አሳስበዋል፡፡ ‹‹ችግሮቹ ያመዝናሉ፤›› በማለት፡፡

‹‹ሥርዓቱ ውስጥ በተደራጀ በቡድን አንዱ ሌላውን የሚጠልፍበት ሁኔታ የለም? ከሕዝብ የተደበቀ ነው? አይመስለኝም፡፡ ራሳችሁን ፈትሹ፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነትን የፈጠራችሁት እናንተ ናችሁ፡፡ ከሕዝብ የተደበቀ ነገር የለም፡፡ የክፍለ ከተማ ሹማምንቶች ቪ-8 አይደለም የሚያሽከረክሩት? ቪ-8 የሚነዳባት አገር ናት እንዴ ይህች አገር? ታክስ አልከፈልክም ተብሎ ግን ዘብጥያ ይወርዳል፤›› በማለት አስተያየታቸውን የቀጠሉት አቶ ኃይላይ፣ ‹‹ትግሉን ረስታችሁታል፡፡ ከተከፈለው መስዋዕትነት አንፃር ያማል፡፡ ስለዚህ የዚች 25 ዓመታት ስኬት እንደ ትምክህት እንድትወስዷት አልፈቅድም፡፡ መውደቂያችሁ እሱ ነው የሚመስለኝ፡፡ በ1993 ዓ.ም. ታደስን ትላላችሁ፡፡ እሱ ህዳሴ አልነበረም፡፡ መታደስ ያለባችሁ ዛሬ ነው፤›› በማለት ሐሳባቸውን ቀጠሉ፡፡

የመድረክ መሪዎችም ተሳታፊዎችም በፅሞና እያዳመጡ ነው፡፡ አቶ ኃይላይ ግን ትችታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ‹‹ለምሳሌ ያ ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለበት አካባቢ ምን ይመስላል? ዛሬ ከማንም የተደበቀ አይደለም፤›› በማለት አንዳንድ የትግራይ ክልል አካባቢዎችን በመጥቀስ በትግል ጊዜ የተጠቀሙበት መንገድ ባለበትና አህያም ተጭና የማትሄድበት ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሌላው አስተያየት ሰጪ የዓባይ ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ሲሆን፣ ውይይቱ እንደተለመደው የፕሮግራም ማሟያ እንዳይሆን ሥጋቱን ገልጾ አስተያየቱን ጀመረ፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት የተሠሩ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ገልጾ፣ ‹‹የተሠሩ ትልልቅ ነገሮችን የሚሸፍኑ የማይረቡ ትንንሽ ስህተቶች ትሠራላችሁ፤›› ሲል በሕዝቡና በመንግሥት በኩል አሉ ያላቸውን ችግሮች ተናግረዋል፡፡ ‹‹በአሁኑ ጊዜ ወረዳዎችና ቀበሌዎች እኮ ትልልቅ መንግሥታት ናቸው፤›› በማለት የተዘረጋው ሥርዓት ለሌብነትና ለስርቆት የተመቸ መሆኑን ተናግሯል፡፡

በጋዜጠኛው ሌባ ለማስያዝ የሚደረግ ጥረት እንደማይሳካና ፍርድ ቤት ተሂዶም ፍትሕ እንደማይገኝ ገልጾ፣ ‹‹እንዲያው ሳስበው ዛሬ ፍትሕ ያለው በኢቢሲ የሚተላለፈው ‹‹ችሎት›› ፕሮግራም ላይ ብቻ ነው፤›› በማለት ተሰብሳቢዎችን ፈገግ አሰኝቷል፡፡ ‹‹ትልቅ ስህተት የምለው፣ የኢሕአዴግ ትልቅ ስህተት የምለው የቀበሌና የወረዳ አስተዳደሮች የፓርቲው አባል በመሆናቸው ነው፡፡ ከአንድ ቦታ በሌብነት የተባረረ ሌላ ቦታ ተቀይሮ ተሹሞ እናገኘዋለን፡፡ ደንበኛ የአሠራረቅ ልምድ ይዞ ሄዷል፡፡ እዚህ ቀበሌ ሌባ የነበረ ሰው እዚያ ሲሄድ ወንበዴ ይሆናል፡፡ ማንም የማይመልሰው ወንበዴ፡፡ ከዚህ በኋላ ያፈጠጡ ሌቦች እንዲሆኑ እያደረጋችኋቸው ነው፡፡ የፓርቲ አባል ስለሆኑ፡፡ በእኔ እምነት ይኼ ሁሉ የፓርቲ አባል አያስፈልጋችሁም፡፡ የፓርቲ ቁጥር አይደለም ሥራ የሚሠራው፡፡ አስተሳሰቡ ያልተለወጠ ሰው ለውጥ አያመጣም፤›› በማለት አንድ ምሳሌ አነሳ፡፡

‹‹በሌላ እንዳይያዝብኝ ስለፓርቲ አይደለም እያወራሁ ያለሁት፤›› በማለት ቀጥሎ ያቀረበው ምሳሌ በ1997 ዓ.ም. ምርጫ ቀንደኛ የቅንጅት ደጋፊ የነበረ ሰው፣ የኢሕአዴግ ደጋፊ ናቸው ብሎ ያሰባቸው ብዙ ሰዎችን ጉዳት እንዳደረሰባቸው ተናግሯል፡፡ ‹‹አሁን ብትሄዱ ወረዳውን አልነግራችሁም ራሳችሁ ድረሱበት፤›› ካለ በኋላ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውስጥ የአንድ ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ እንደሆነ በመግለጽ፣ ‹‹ያን ጊዜ ያላዳረሳቸውን አሁን ለማዳረስ እንዲመቸው ይሁን እኔ አልገባኝም፡፡ ይኼ ሰው በሌላ ማልያ እንዲጫወት ተፈቅዶለታል፡፡ በትክክል ሥራቸውን ሲሠሩ የነበሩ ሰዎች ደግሞ ችግር ደርሶባቸው ሌላ ችግር ላይ የወደቁ አሉ፤›› በማለት እንዲህ ዓይነት ችግሮች እንዲስተካከሉ አሳስቧል፡፡

እንደ ጋዜጠኛ በ2004 ዓ.ም. ተንዳሆ መሄዱን አስታውሶ ቦታው ላይ የነበረው ሥራ የሚያስደስት እንደነበር ይናገራል፡፡ ‹‹25 ሺሕ ቶን ስኳር ማምረት ይችል ነበር፡፡ በአፍሪካ ሁለተኛ መሆን ይችል ነበር፡፡ ያኔ መጠናቀቅ ነበረበት፡፡ ዛሬም ድረስ ግን አልተጠናቀቀም፡፡ ስኳር ፋብሪካው ሲወድቅ በሒደት ነው፡፡ በአንድ ጊዜ ግንድስ አላለም፡፡ በአንድ ጊዜ ግንድስ ቢል ይሰማ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ነው ዛሬ የተገነደሰው፡፡ የት ነበራችሁ? 88 ሕንፃዎች ጠፉ ሲባል የት ነበራችሁ? የተረከበውና ያስረከበውን የት ገቡ? ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው ፈርመው ያስረከቡት? ስለዚህ ችግሮቹ በአንድ ጊዜ የመጡ አይደሉም፡፡ ፀረ ሙስና ጠንካራ ነው ስትሉን ሳቄ ነው የሚመጣው፡፡ የሚከሰው የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ ነው፡፡ ፀረ ሙስና ይዞ የሚለቃቸው ሰዎች አሉ እሱም ተከፋይ ነው፤›› በማለት ጋዜጠኛው ምሳሌዎችን በመደርደር ወቀሳውን ደርድሯል፡፡

ወ/ሮ ፍሬሕይወት በሰጡት ምላሽ ያቀረቡት ሪፖርት ሚዛኑ የጠበቀ መሆኑን ተናግረው፣ የቀረቡትን ቅሬታዎች ማጣራት ያስፈልግ ይሆናል በማለት አልፈዋቸዋል፡፡

የኪራይ ሰብሳቢነት ምሽግ የተባሉ ዘርፎች ተለይተው በዚያ መሠረት ዕርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ፣ እያንዳንዱ ተቋም በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ የሚገመገምበት ቋሚ አሠራር መዘርጋቱን ተናግረዋል፡፡ ከቀበሌ ጀምሮ ላይ ያሉት ዥንጉርጉር አሠራሮች መስተካከል እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነትን በተመለከተ ግን፣ ‹‹መንግሥት ሊፈጥረው አይችልም፡፡ ሕዝብን አገለግላለሁ የሚል መንግሥት ሙስናን ሊፈጥር አይችልም፤›› በማለት ተመጣጣኝ ዕርምጃ አይወሰድም የሚለውን አልተቀበሉትም፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች ግን መንግሥትን ጨምሮ የማይረባ ሥራ እንደሚሠራ ተቀብለዋል፡፡

‹‹ዋናውን ጉዳይ ግን መንግሥት ሕዝባዊ ነው፣ ያነሳችኋቸው ችግሮች የሉም ማለት አይቻልም፣ ጨለማ ግን አይታየኝም፤›› ብለዋል፡፡

አቶ ዘርአይ በሰጡት የማጠቃለያ ሐሳብ፣ ‹‹ሥርዓቱ 100 ሺሕ፣ 200 መቶ ሺሕ መስዋዕትነት ተከፍሎበት የመጣ ነው፡፡ ሥርዓቱ በቃኝ ይኼን ሠርቼያለሁ ብሎ ከቆመ የሞተ ነው ማለት ነው፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡

‹‹ኢሕአዴግ የራሱን ሌቦችም እየቆረጠ የሚጥል ነው፡፡ ታጋይ የነበሩ በኃላፊነት ላይ ሆነው ሲባልጉ ቆርጦ የሚጥል ቆራጥ ነው፡፡ ኢሕአዴግ እንደ ኢሕአዴግ ሌባ አይደለም፡፡ አሁንም ቦታው ላይ ነው ያለው፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ በጋምቤላ በተፈጸመው ጥቃትና በኤርትራ በተፈጸሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ላይ ዕርምጃ ለምን አይወሰድም ተብሎ ጥያቄ ቀርቧል፡፡ አቶ ዘርዓይ፣ ‹‹የኤርትራ መንግሥት በ1993 ዓ.ም. አይደለም የገደልነው፡፡ አሁን ነው የገደልነው ጦርነት ባለመግጠም፤›› በማለት ሐሳባቸውን ደምድመዋል፡፡ ከዚህ ውጪ የመንግሥት ሚዲያን በተመለከተ በርከት ያሉ ትችቶች ቀርበዋል፡፡ ሚዲያው ራሱ ነፃና ሳይሆን የሕዝብ ሳይሆን፣ ሚዲያ ሳይያዝ ሙስናን እንዴት መታገል ይቻላል የሚሉ ጥያቄዎችም ቀርበዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ሕወሓት 40ኛ ዓመቱን ሲያከብር አርቲስቶችና ጋዜጠኞች ወደ ድርጅቱ ታሪካዊ ቦታዎች እንዲሄዱ ባደረገበት ወቅት፣ ለድርጅቱ ሹማምንት ተመሳሳይ ጥያቄዎች ቀርበው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር

በወልቃይት ቃብቲያ በህዝቡና በትግራይ ልዩ ሃይል ፍጥጫው ዛሬ ተጠናክሯል። ከ15 ሺህ በላይ ህዝብ ስብሰባ ወጥቷል

$
0
0

13244648_1119192481436583_3839692696073544650_nምንሊክ ሳልሳዊ

በወልቃይት ቃብቲያ በህዝቡና በትግራይ ልዩ ሃይል ፍጥጫው ዛሬ ተጠናክሯል። ከ15ሺህ በላይ ህዝብ ስብሰባ ወጥቷል። የትግራይ ልዩ ሃይል ስብሰባው ለመበተን ሞክሮ አልተሳካለትም። በህዝቡ ሃይል አፈግፍጓል። የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበረ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ‪

በ14/9/08 የቃብቲያ ህዝብ ያካሄደዉ ስብሰባ ከ15000 በላይ የወልቀቃይት አማራ ማንነት ደጋፊወች በድጋሚ የትግራይ ክልል የአማራ ማንነታ ያለአንዳች ቅደመ ሁኔታ ተቀብሎ አስተዳ ደሩ በወልቀቃይት አማራወችና በአማራ መንግስት ስር እነዲሆን ጥያቄዉን ከዛሪ ጀምሮ መቀበል ያለበት ህጋዊ የሆነ የፊደራል መንገስት ከትግራይ ተወላጆች ተጽእኖ ራሱን የቻለ የፊደራል ስብጥር ያለዉ የመንግስት አካል ካልሆነ የትግራይ አስተዳደር ከክልላችንና ከቦታችን ይልቀቅ፣ ህገ መንግስቱን መሰረት አድርገን የጠየቅነዉ ጥያቄ በአስቸኮይ መልስ ይሰጠን በማለት ድምፁን ሲያሰማ ውሏል። ምንም እንኮ በዛሪዉ ስብሰባ ከሁመራ ባህከር ማይካደረራ ከወልቃይት ጠገዴ ከ50000 ሺ በላይ ሰዉ ወደስብሰባዉ የተመመ ቢሆንም በሁለቱም አቅጣቻ ኬላወች የትግራይ ልዩ ሃይል ህዝቡን አግቶ ቢዉልም ከ15000 በላይ የሚሆን ጀግናዉ የቃብቲያ ህዝብ ስብሰባዉን ተካፍሎ አቆሙን በግልጽ አስቀምጦል።

⏯የትግራይ ክልል አማራን አይመራም ህገ- መንግስታዊ መብታችን ይከበር !!
⏯ወልቃይት የአማራ መነሻና ምድራዊ ገነት ናት !!
⏯የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎት ያሞላ የወልቃይት አማራወች መብት ይከበር
⏯ድል ለቃብቲያ ሰላማዊ ኮንፍረንስና ምስጋና ለጀግናዉ የቃብቲያ ህዝበ !!

መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ብሎ ሞተ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

$
0
0

መስፍን ወልደ ማርያም
Pro-Mesfin1.jpg
መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ፣ ይቅናችሁ ማለት ነው፤ ለልማት ለሚሰማሩ ሰዎች ምርቃት ይሆናል፤ ለጥፋት ለሚሰማሩ ሰዎች እርግማን ነው፤ እርግማን ብቻም አይደለም፤ የጥፋት ምኞትም ነው፤ ሰዎች ለጦርነት ሲዘጋጁ፣ ሰዎች ሌሎች ሰዎችን ለመግደል ሲሰናዱ፣ ሰዎች እርስበርሳቸው ለመገዳደል ጦራቸውን ሲስሉ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ማለት ከጀግና አንደበት የሚወጣ አይደለም፤ ብዙ ሰዎች ለእንጀራ ብለው ሕይወታቸውን ወደአጥርነት ለውጠው ሕይወቱን የሚጠብቁለት ሰው ጦር ቢወረወር አይደርስብኝም ብሎ ሌሎችን ለሞት ቢዳርግ አይደንቅም ይሆናል፤ አጥሩን ጥሶ ወደሱ የሚገሰግስ ሞት ሲያይ ቢፈረጥጥም አያስደንቅም፤ ሆኖም የሞት መንገድ ከጎን ብቻ ሳይሆን ከላይም ሊሆን እንደሚችል አለማወቁ ቀላል አለማወቅ አይባልም፡፡

ባህላችን ገዳይን የምናከብር፣ ለገዳይ የምንዘፍን ሕዝብ ቢያደርገንም፣ በድንቁርና ዘመን የነበረውን ይዘን ዛሬ ትንፋሽ የማትችለዋ ቢምቢ ሰውን መግደል እንደምትችል እያወቅን ለገዳይ ብንዘፍን ለሰውነታችን ውርደት ይሆናል፤ ይህንን ብለን ጉዳዩን እንዳንዘጋው በመግደል ልቡ የደነደነ፣ በድን ያልሆነለትን ሁሉ መግደል ልማዱ የሆነ፣ ከመግደል በቀር እምነቱን የሚገልጽበት መንገድ የሌለው፣ ከመግደል ሌላ እንጀራ የሚበላበት ሙያ የሌለው … እንዲህ ያሉ ሰዎች ሁሉ ተሰባስበው መገዳደልን የኑሮአቸው ዓላማና ዘዴ ሲያደርጉ በዝምታ መቀበል፣ ማለት አባቱ ሲገደል ልጁ ዝም ሲል፣ ባልዋ ሲገደል ሚስት ዝም ስትል፣ … ማንም ሰው አለፍርድ ሲጠቃ እያዩ ዝም ማለት ገዳዮችን ያራባል እንጂ ግድያን አያቆምም፤ እንዲህ ያለው በመንፈስ የሞቱ የበድኖች ዓለም ነው፤ በአውሬዎች ዓለም ጉልበት ያለው ደካማውን እየበላ ይኖራል፤ የተፈጥሮ ሕግ ነው፤ የሰው ልጅ በዚህ በአውሬዎች የተፈጥሮ ሕግ አይመራም፡፡

የሰው ልጅ በተፈጥሮ ሕግ የማይመራበት ምክንያት ምንድን ነው? አውሬዎች አያስቡም፤ የሰው ልጅ ግን ያስባል፤ የሰው ልጅ አእምሮ አለው፤ አእምሮ ስላለው ያስባል፤ ያስባል ማለት ከተግባር በፊት ትክክለኛውንና ስሕተት ያለበትን ለይቶ ያውቃል፤ ይህ የተፈጥሮ ሕግ አይደለም፤ የሰው ልጅ ሕግ ነው፤ ያሰበውንም ይናገራል፤ የሚወደውንና የሚጠላውን ስሜቱን ለይቶ ይናገራል፤ የሰው ልጅ ኅሊናም አለው፤ ‹‹ሌሎች ለአንተ እንዲያደርጉልህ የምትፈልገውን አንተም ለሌሎች አድርግ!›› ይላል፤ ይህ የተፈጥሮ ሕግ አይደለም፤ የሰው ሕግ ነው፤ ስለዚህም መግደል፣ በተለይም የመግደል ሱስ፣ የአራዊት እንጂ የሰው ልጅ የችግር መፍቻ ዘዴ አይደለም፤ አራዊት የሚገድሉት ሊበሉ ነው፤ ሰውም ወደአራዊትነት ሲለወጥ የሚገድለው ሊበላ ነው፤ እዚህ ላይ ሰውና አራዊት ይመሳሰላሉ፡፡

በመሠረቱ የመግደል ዓላማ ዝም ለማሰኘት ነው፤ ድንቁርና ነው እንጂ ካፍ ከወጣ አፋፍ ነውና የሚጠሉት ሀሳብ በሌላ ሰው አንደበት ይደገማል፤ መግደል የመጨረሻውን ዝምታ የሚያስከትል ቢሆን ክርስትናም እስልምናም 2007 ዓ.ም. አይደርሱም ነበር፤ ገዳዮች ሰዎችን ሁሉ ጨርሰው ብቻቸውን በመቅረት የሚያገኙት ጥቅም እንደሌለ ስለሚያውቁ የመግደል አማራጮች በሆኑ ሌሎች ዘዴዎች ይጠቀማሉ፤ አንዱ ማሰቃየት ነው፤ ሌላው ማሰር ነው፡፡

ሰዎችን በሀሳብና በእምነት ገባር ለማድረግ ጉልበተኞች የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች መግደል፣ መግደል አላዋጣ ሲል ማሰቃየት፣ ማሰቃየት አላዋጣ ሲል ማሰር፣ ማሰር አላዋጣ ሲል አስሮ ማሰቃየት ነው፡፡

አውሬነትን የተላበሱ ሰዎች የማይገባቸው አንድ ነገር አለ፤ የሚጠሉትና ሰዎችን እስከመግደል፣ እስከማሰርና ማሰቃየት የሚያደርሳቸው ነገር በውስጣቸው ተቀብሮ አለ፤ ነፍሳቸው ከዚያ ነገር ጋር ተቆራኝታለች፤ በመጨረሻም የሚሸነፉት በዚያው ነፍሳቸው ውስጥ በተቀበረው ነገር ነው፤ በውስጣቸው የተቀበረው ነገር አስገድሎ አስገድሎ በመጨረሻ ይገድላቸዋል፤ ጥላቻም አስገድሎ አስገድሎ ይገድላል! በጥላቻና በመጋደል ሰላም አይገኝም፤ ‹‹ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል እግዚአብሔር!›› (ኢሳይያስ 48/22)

መንገዱን ጨርቅ ያድርግልን! ለሰላም!
መንገዱን ጨርቅ ያድርግልን! ንስሐ ለመግባት!
መንገዱን ጨርቅ ያድርግልን! ይቅር ለእግዚአብሔር ለመባባል!

የዛሬ ዕብሪተኞች የሙሶሊኒን (ተዘቅዝቆ የተሰቀለውን)ና የጋዳፊን ቦይ ውስጥ ተወትፎ የተገኘውን አስበው ልባቸውን ለምሕረትና ለእርቅ እንዲከፍቱና ለልጆቻቸው የፍቅርና የመተማመን ዘመን እንዲያውጁ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ወኔ ይስጣቸው፡፡

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live