Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ወያኔ ለሕዝብ የሚያከፋፍላቸው አደንዛዥ ዕፆች –ፍርዱ ዘገዬ

$
0
0

እያንዳንዱ መንግሥት በተለይ ደግሞ ዴሞክራሲን የሚጠየፍ አምባገነን መንግሥት የሚገዛውን ሕዝብ የሚያደነዝዝበት የተለያዩ ሥልቶችን ይነድፋል፤ እነዚህንም ሥልቶች እያፈራረቀና እንዳስፈላጊነቱም በጅምላ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ በብልግናና በኢሞራላዊ ምግባራት የተሞሉ የሙዚቃና የፊልም ኢንዱስተሪዎችን ማስፋፋትና በአደንዛዥ ዕፅ በተለይ ወጣቱን ትውልድ መበከል ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ እግር ኳስንና የውሸቱን የነፃ ትግል ትርዒት (wrestling) የመሳሰሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችንም በዚሁ የሕዝብን የትኩረት አቅጣጫ ማስለወጫ መንግሥታዊ “ጥበቦች” ውስጥ ማካተት ይቻላል፡፡ የዛሬውን አያድርገውና በቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረት የነቮድካን ዋጋ እጅግ በማርከስና ማንኛውንም የውጭ ሚዲያ ዝግ በማድረግ ሕዝቡን አደንዝዘው ይገዙ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ ወያኔ ግን የመጠጦችንም ዋጋ ከሰማይ አዝልቆ እየሰቀለ መደበሪያና መቆዘሚያም እያሳጣን ነው – የ330ሚ.ሊ ቢራ በዚያን ክፉ ዘመን ሊያውም ተወደደ ተብሎ በ40ሣ. እንዳልተጎነጨናት ዛሬ በዝቅተኛ ሆቴሎች ባማካይ ከ16 ብር በታች አልገኝ ብላለች፤ እሷም ባቅሟ ተንጠባረረችብን፡፡ ያገር ተወላጇ ካታማይሲን(ቁንድፍት) ራሷ ከንፈርን ለማታረጥብ ቀልበ-ቢስ መለኪያ 3 ብር እንከፍላለን – በቅርቡ ከዚያ ከዓመታት ሁሉ ተለይቶ ባይፈጠር የሚሻለው 97ዓ.ም የምርጫ ወቅት በፊት በስሙኒ ነበር የምንቸልሳት፡፡ ባይገርማችሁ የቼልሲ ደጋፊ ነኝ – የማታ ቸልሲ እንጂ ለቅሪላ ደንታም የለኝ ታዲያ፡፡

kana

በቀጥታ ወደ ሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ እንግባና የሀሽሽ ዓይነቶችን እንመልከት፡፡ ወያኔዎች በተንኮል ሥራ እጅግ የተጠበቡና የተራቀቁ አማካሪዎች እንዳሏቸው (ከሚሠሩት ወንጀልና ጥፋት አንጻር) ከዕድሜያቸው መንዘላዘል ብቻ ሣይሆን ዘወትር ከሚያከናውኗቸው ነገር ግን ከነርሱ በፍጹም ሊጠበቁ ከማይችሉ ዕኩይ ተግባሮቻቸው በሚገባ መረዳት ይቻላል፡፡ ጎሣን ከጎሣና ሃይማኖትን ከሃይማኖት ማጋጨቱን የተበላ ዕቁብ ይዘን ቤተሰብን እስከማፋጀት የሚደርሰውን የሸር ሥራቸውን ስናጤን በማይምነትና ምናልባትም በየዋህነት የምናውቃቸው እነዚህ ወንድሞቻችን ይህ ሁሉ ከተዓምር ያላነሰ ድርጊታቸው ካላንዳች ረዳት እንደማይሆን እንገነዘባለን፡፡ ለኛ ከማይተኛ ትልቅ ኃይል ጋር እንደሚሠሩ ለማወቅ ነቢይነትን አይጠይቅም፡፡ የዋህ ታዛቢ ግን ወያኔዎች ብቻቸውን የሚገዙን እየመሰለው በኛ በብዙዎች “ፍርሀትና ትግስት” መደነቁ አይቀርም፡፡

እናም ሕዝብን በዚህና በዚያ ከማናከሱና የተወሰነ ፖለቲካዊ ትርፍ ከማጋበሱ በተጓዳኝ ዜጎች እንዲደነዝዙ የሚያድርጉበት ከፍ ሲል የተጠቀሱትን የመሳሰሉ ልዩ ልዩ ዘዴዎች አሏቸው – ወያኔዎችም ሆኑ ጌቶቻቸው፡፡ ዓለማችን አእምሮን በሚቆጣጠሩ መሠሪዎች ተወጥራለች፤ የጓድ መንግሥቱን አነጋገር ልዋስና – ብታምኑም ባታምኑም “የምትናገረውን ቀርቶ የምታስበውን ደርሰንበታል” በሚሉ የስምንተኛው ሺህ ሐሣይ መሲሆች ተወረናል፤ ደፍረውናል፤ ንቀውናል፡፡
በበክት ስሙ ማለቴ በክት ስሙ ሕወሓት የምንለው የኛው ወፍዘራሽ ፍጡር ሕዝቡን የሚያደነዝዝባቸው መንገዶች በርካታ ናቸው፡፡ የዐዋጁን በጆሮ እንዳይሆንብኝ እንጂ ቀዳሚው የወያኔ ሀገርን ማውደሚያ የቆረጣ ሥልት ወጣቶችንና ታዳጊዎችን ከትምህርት ገበታ መለየት ወይም እዚህ ግባ በማይባል የትምህርት ሥርዓት ማደደብና ዲግሪ እንኳን ይዘው ስማቸውን አስተካክለው መጻፍ የማይችሉ የምሁር ማይማን ማድረግ ነው፤ ይህ በተግባር ተፈትኖ ፍሬያማ የሆነላቸው ትልቁ ሥልታቸው ነው፡፡ በዚህ ረገድ የጠፋውን ትውልድ ለመመለስ ወደፊት ብዙ መማሰን ይኖርብናል፡፡

የውሸት ቱሪናፋና የሀሰት ዘገባ እያቀረቡ ሕዝቡን በባዶ ጩኸት ጆሮውን ሲጠልዙ የሚውሉ ቲቪዎችንና ራዲዮኖችን ማስፋፋት ደግሞ ሌላኛው ሀሽሽ ነው፡፡ ስሙን እንደሸሚዝ ከሚለዋውጠው ኢቲቪ ጀምረህ ኢቢኤስን፣ ናሁን፣ ዋልታን፣ ቃናን፣ ቲጂን …ኤፍኤሞችን፣ አይጋፎረምን የመሰሉ ድረገፆችን፣ ጋዜጦችን … ብትመለከት ሁሉም የወያኔ ሕዝብን የማደንቆሪያ ሀሽሾች ናቸው፡፡ በብዙ ጫና ውስጥ ከሚያልፉ በጣም ጥቂት የኤፌም ፕሮግራሞች በስተቀር አብዛኛዎቹ በሬ ወለደ ዓይነትና ከሕዝብ ችግር ጋር ጭራሽ የማይገናኝ ዝግጅት ነው የሚያቀርቡት፡፡ አንድም የረባ ነገር ሲሠሩ አታይም፡፡ የሚያወሩት ሁሉ ከወሲብና ከስፖርት ያውም በአብዛኛው ከእግር ኳስ አይወጣም – እግር ኳስ ስልህ ደግሞ ተጫዋቹ ስንት ግራም ቁርስ እንደበላና ከሚስቱ ጋር ስንቴ እንደተሳሳመ ወይም… ሳይቀር መዘክዘክን ይጨምራል – “ራሷን በልቷት እግሯን ያኩላታል” አሉ? እንደ ወላይታ ሶዶ ዳጣና እንደሸዋ ሚጥሚጣ ስለሚፋጀው የኑሮ ውድነትና የሙስና መረብ ግን አንድም ትንፍሽ አይሉም፤ ጉዶች! የሕዝብን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ችግር ነቅሶ የሚያወጣና መፍትሔ እንዲገኝ የሚያደርግ ጋዜጠኛም ሆነ የሚዲያ ተቋም በሀገራችን የለም – ሁሉም ተለባብሶ መጓዝን፣ ከወያኔ ጋር ተሞዳምዶ የግል ብልግና ማለትም ብልጽግና መሻትን መርጦ እውነትን አርቆ እየቀበራት ይገኛል፡፡
zana ana chandra
አሁን አሁን ብዙ የሣተላይት ቴሌቪዥን ሥርጭቶች አየር ላይ እየዋሉ ነው፡፡ ከሞላ ጎደል የሁሉም ዓላማ አንድና አንድ ነው – ባጭር ታጥቆ ወያኔን ማገልገል፡፡ እውነትን መደበቅ፣ ሀሰተኛ ሀገራዊ ምስል በመፍጠር ወያኔ ልማታዊ መንግሥት እንደሆነ መስበክና በተለይ በውጪ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊና ስለኢትዮጵያ ቀናውን የሚያስብ የዓለም ዜጋን ማታለል፣ ወጣቱን በሙዚቃና ዳንኪራ ቱማታ ጠምዶ ሌት ከቀን ማስጨፈር፣ ርሀብንና ጥምን፣ በሽታንና ዕርዛትን ግን መደበቅ … ዋና ተልዕኳቸው ነው፡፡ እንግዲህ እኔ አዲስ አበባ እንደመኖሬ እነዚህ ቱልቱላዎች የሚያሳዩትንና በገሃድ እየሆነ ያለውን ሰቅጣጭ ሀገራዊ ምስል በሚገባ አውቃለሁና በነሱ አስነዋሪ ድርጊትና በኛ አስከፊ የሕይወት ገጽታ መካከል ያለውን ልዩነት በማንበብ በሰው ልጅ በተለይም በዘመናችን በምንገኝ ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ዋሾነትና መስሎ አዳሪነት ከልክ በላይ ማዘኔ አልቀረም – ውሸት እንደባህል ተወስዶ ትውልድ ሁሉ በውሸት እንዲቀረጽ መንግሥታዊ በጀት የተመደበበት ብቸኛ የዓለም ሀገር ቢኖር ሀገራችን ኢትዮጵያ ትመስለኛለች፡፡ እውነትን ከመናገር አንጻር ሰው ኅሊናውን በሆዱ ከለወጠ የመጨረሻው ቆርጦ ቀጥል ይሆናል – እንደዚያ መስፍን በዙ እንደሚሉት አጋሰስ ሰውዬ ማለት ነው፡፡ (እንዴት ያለው ሆዳም መሰላችሁ እናንተዬ፤ ሰው ማማት ስለማልወድ ግን ስለዚህ የወያኔ ቅጥር ሚዲያ-ገዳይ፣ ስለዚህ እምብርት የለሽ ሆድ-አደር የወያኔ አጨብጫቢ አሁን ምንም መናገር አልፈልግም፡፡ ስለግለሰብ ማውራት ከሞራል አኳያም ቢታይ ትክክል አልሆንምና ስለዚህ ባለጌና ስድ አደግ ሰውዬ ትንፍሽ አልልም፡፡ ስለሆነም ሌሎቻችሁም ብትሆኑ ስለነዚህ ዓይነቶቹ የሀገር አራሙቻዎችና የታሪክ አተላዎች ማውራት የለባችሁም – የደርግ አማርኛ እንዴት ትዝ አለኝ እባካችሁ?)

ዛሬ ኢትዮጵያንሪቪውን ስዳስስ አንድ ጽሑፍ ቀልቤን ሳበውና ገለጥኩት – አነበብኩትም፡፡ ያን መሰል ጽሑፍ ልጽፍ ካሰብኩ ደግሞ ቆይቻለሁ – በይዘት የሚመሳሰል፡፡ ይህ ሰው – ኢድሪስ ሙክታር የተባለ ዜጋ – ቀደመኝና አወጣው፡፡ ዕጥር ምጥን ባለ አቀራረብ ግማሽ ገጽ እንኳን በማትሞላ ወረቀት ስለቃና ቲቪ አደገኛነት አፍረጥርጦ ነገረን – ቢገባን፡፡

እኔ ደግሞ ኅያው ምሥክር ነኝ፤ ልጽፍ የነበረውም በዚሁ ጦሰኛ ጣቢያ ምክንያት የደረሰብኝን የራሴን ተሞክሮ ነበር፡፡ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው ጓዶች!!

ነገሩ ወዲህ ነው፡፡ ባለፈው ሰሞን – ቀልድ አይደለም እውነቴን ነው – ባለፈው ሰሞን ሥራ ውዬ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት አካባቢ ቤቴ እገባለሁ – ድክም ብዬ፡፡ ሣሎን ውስጥ ባለቤቴና ልጆቼ ያው እንደዱሮው ይሄን የፈረደበት ቃና ቲቪን ይመለከታሉ፡፡ እኔ በጣም እርቦኛል፡፡ ራት ትሰጠኛለች ብዬ ወደባለቤቴ አቅጣጫ እያማተርኩ ብቁለጨለጭ እሷ ያለችው እነኦማርና ጁሊያን ጋር ናት – ቃና ውስጥ – “ውስጤ ነው” በሚሉት አዲስ ፈሊጥ ተወስዳለች፡፡ አፍ አውጥቼ ራት ብዬ ተናገርኩ – ማንን ወንድ ብላ! መልሱ ዝም ጭጭ ሆነ፡፡ ትንሹ ልጄ ሰማኝና “እየተሠራ ስለሆነ ትንሽ ጠብቅ አለኝ፡፡ ያኔ ብልጭ አለብኝ፡፡ እንደዱሮው ቢሆን በዚያ ቅጽበት ውስጥ የባለቤቴ ጉንጮች ከደረሰባቸው መብረቃዊ የአይበሉባም በሉት የቃሪያና የበርበሬ ጥፊ የማጥቃት እርምጃ የተነሣ ማበጥ ጀምረው ነበር፡፡ ዛሬ ግን ወንድም ሴትም አልለይ ብሎን ሁለት አባውራ ባንድ ቤት ውስጥ መኖር ተጀመረና አዛዥና ታዛዥ ጠፋ፡፡ ወደኪችን አፍንጫየንና ፊቴን ባዞር ገና የተመታ ሽሮ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል – ዱሮ በደህናው ቀን እኮ አንድ ዓይነት ይቅርና ሲመቻትና ከልደታ እስከባታ አካባቢ ሁለትም ሦስትም ዓይነት ወጥ ሠርታ ገና የበሩን ደፍ ሳላልፍ ታቀርብ ነበር፡፡ አሁን ዕድሜ ለቃና – ቅንቅን ይውረሰውና – የሚጠበቀው ዐረፋው እስኪከትና ጥሬ ሽሮው እስኪጠፋ ኖሮ በ15 ቁጥር ምሥማር ጥርቅም አድርገው ዘጉኝ – ቤተሰቦቼ፡፡ የቡና ዘነዘና አንስቼ ቲቪውን የዶጋመድ ላደርገው ቃጣኝ፡፡ ግን አንድ ሞኝ ወገናችን አንድ ወቅት በራሱ ላይ የወሰደው የቂል እርምጃ ወዲያው ትዝ አለኝና ተውኩት – (ያ ሞኝ ሰው ምን አደረገ መሰለህ – ባለቤቱ እጅግ ቀናተኛ ነበረችና በወጣ በገባ ቁጥር “ከእገሊት ጋር እንዲህ እንዲህ ስታደርግ ቆይተህ ነው አይደል ያመሸኸው? አልተነቃብኝም ብለህ ነው አይደል? በላ ምን ይዘጋሃል?” እያለች ትነዘንዘው ገብታለች፡፡ ሰውዬው ስልችት አለው፡፡ ከቀን እቀን እየባሰ የሄደው የፍቅር አይሉት የጠብ ንዝነዛዋ በዛበት፡፡ አይፍረድባችሁ ወገኖቼ፡፡ አንድ ቀን ግን ስሜቱን መቆጣጠር አቃተውና የሚስቱን የተሣለ የሽንኩርት ቢላዎ አንስቶ ያን የቅናት መንስዔ የሆነ የአካል ክፍሉን ከመባቀያው ጀምሮ ይሸረክትና “በይ የኔ እህት ከእንግዲህ አትነዝንዢኝ፤ ንብረትሽ ይሄውልሽ፤ ብትፈልጊ አዝለሽው ዙሪ… ከፈለግሽም ቀቅለሽ ብይው…”ይልና አለቬርባል ያስረክባታል፡፡ በዜና ነው የሰማሁት – ኢትዮጵያ ውስጥ መሰለኝ የሆነው፡፡) እኔ ግን በጣም ከመናደዴ የተነሣ ወጥቼ ሄድኩ፡፡ ዕውር ቢሸፍት ጓሮ ለጓሮ እንዲሉ ሆኖ ግን ምሽቱ ስለጠነነብኝ ሩቅ መሄድ አልቻልኩምና ሠፈር ውስጥ ጥቂት ተንጎራድጄ ተመለስኩ፤ ያቺኑ ሽሮየንም በልቼ ነገር በሆዴ ይዤ እያብሰለሰልኩ ተኛሁ – እልኹ ስላለ ሌሊቱ አልበረደኝም፡፡ ለዚያ ያበቃኝ እንግዲህ ይሄ ቃና የሚሉት ከይሲ ቴሌቪዥን ነው – ትናጋውን የሚዘጋ ነገር ፈጣሪ ከላይ ይላክበት እንጂ ትዳርን ሳይቀር እየበተነ ነው፡፡ እሱው ላይ ተጎልታ ውላ ዋናውን የትዳሯን ምሰሶ አናጋችው – ከያ ቀን ወዲህ አሁንም ድረስ ኩርፍ ነን፡፡ እኔ ችየው እንጂ “የነገር አባትሽንና ነፍስ አባታችንን ጥሪና ያለያዩን፤ አሁንስ አበዛሽው!” ብል እችል ነበር፤ ግን በዚህ ዘመን እንኳንስ ተፋትተው ተጋብተውም አልሆነ፡፡ የቃና ጣጣ ብዙ ነው፡፡

ለመሆኑ ቃናን ማን ፈትቶ ለቀቀብን? ጣቢያው ምን እያደረገ ነው?

በመሠረቱ ይህ ጣቢያ ብዙ የተለፋበትና የተደከመበት መሆኑ ያስታውቃል፤ ብዙ ወጪም ሳይጠይቅ አልቀረም፡፡ ጅምሩ ደግሞ በጣም ጥሩ ነው፤ እኔ በበኩሌ አቀራረቡንና ዝግጅቱን ወድጄዋለሁ፤ በዘርፉ ትልቅ እመርታ እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ነገር ግን ለኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አይሆንም፡፡ ይህ ዓይነቱ ጣቢያ እንደኛ ባለው በዕውቀትም በንቃተ ኅሊና ደረጃም በማኅበራዊ ሥነ ልቦናና በመሳሰሉ ነባራዊ ሁኔታዎች ዳዴ ለሚል ማኅበረሰብ ሣይሆን ለሠለጠነ ሕዝብና ሀገር ነው ግሩም የሚሆነው፡፡ እኛ እኮ ፍላጎታችንን ራሱን በመፈለግ የምንባዝንና ማናችንም የምንፈልገውን ነገር ሳናገኝ ወይም ያገኘን ሳይመስለኘን ከዚህች ዓለም የምንሰናበት ነን፤ አንዳንዶቻችን እኮ ያቺ የዱሮው ሁለተኛ ነው ሦስተኛ ክፍል የአማርኛ መጽሐፍ ውስጥ እንዳለችው አላዋቂ ኮራጅ ጦጣ ነን – ኩረጃን እንኳን የማናውቅ ፋራዎች – ግን ግን የሰለጠንንና ያወቅን የሚመስለን ግብዞች፡፡ አማራጮችን በአግባቡ መርምሮ የሚሆነውን ማለትም የሚጠቅመውን ከማይጠቅመው ለይቶ ጥሩውን ለመያዝ በቅድሚያ የግንዛቤ ማዳበሪያ ትምህርት ሊሰጥ ይገባል፡፡ ሕጻን ልጅ ማርና መርዝ ቢቀርቡለት ማሩን ትቶ መርዙን ሊመርጥ ይችላል፡፡ ማኅበረሰብም አንዳንዴ እንደሕጻን ቢቆጠር ለርሱ ከመጨነቅ አኳያ ነውና እኔን መሰሉ አስተያየተኛ ሊነወር አይገባም፡፡ ወያኔና ደርግ ቁልቁል እንጂ ሽቅብ እንድንሄድ አላደረጉንም፤ ማጣትን እንጂ ማግኘትን አላስለመዱንም፡፡ ድንቁርናን እንጂ ዕውቀትን አላወረሱንም፡፡ ትዕቢትን እንጂ ትህትናን አላሳዩንም፡፡ ስለዚህ ማንም ቅራቅንቦውን እያመጣ ቢደፋብን በጣም እንጎዳለን፤ በሂደት ከሀገርና ከሕዝብ ደረጃም ልንወጣ እንችላለን፡፡ ዴንማርክ ሄደህ ይህን መሰል ቲቪ ብትከፍት ምንም ማት አይደለም – The society is well informed and knows what is bad and good – እንዴ፣ እኔስ እንግሊዝኛ አያምረኝም እንዴ? ምርጫውን የሚያውቅና ስለምርጫም ግንዛቤ ያለው ሕዝብ ነውና ተጎጂ ጭራሹንም አይኖርም ባይባልም መጎዳቱን የሚረዳና ከአጓጉል ነገር ራሱንና ቤተሰቡን የሚጠብቅ ብዙ የነቃና የተደራጀ (የታጠቀም ልበል ይሆን?) ሕዝብ ስላለ ሀገር በቀላሉ አትፈረካከስም፤ ትውልድም በመጤ ባህል እንደኛ በዋዛ አይፍረከረክም፡፡ እዚህ ግን … እስኪ ተወኝ ወንድሜ፡፡

ቃና አንዱ የወያኔ መርዝ ወይም ሀሽሽ እንደሆነ ያመንኩት እንግዲህ እኔን ጦም ለማሳደር የገባውን ቁርጠኝነት ስታዘብ ነው – በኔ ውስጥ ደግሞ ሚሊዮኖችን፣ በሚሊዮኖች ውስጥ ደግሞ “እንኳንስ ዘምቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ”ን ውድ ሀገሬን ኢትዮጵያን አየሁ፡፡ በርግጥም ስናስበው ቃና በአንድ ምሥኪን ሰው ቤት ገብቶ ይህን ዓይነት ተዓምር ከሠራ በሀገር ደረጃማ እንዴት ዓይነት ጉድ አይሠራ፡፡ ኢድሪስ እንዳለው በቅርቡ ሥራም ትምህርትም ቀጥ ሳይል አይቀርም፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ሰው ሁሉ እየተጃጃለ ነው፡፡ ሆዱን ሳይሞላ ራሱን በፊልም እያታለለ ይኖራል፡፡ በዚህ መሀል ስለ ሀገር ማሰብ፣ ስለኑሮ መጨነቅ፣ ግፈኛውን የወያኔ አገዛዝ ስለማስወገድ ማሰብ፣ ስለነፃነት ማሰብ፣ ስለሕይወት መሻሻል ማሰብ፣ ስለትምህርት ማሰብ፣…. ዕርም ሊሆን ነው፡፡ ይህ ችግር ቦሃ ላይ ቆረቆር እንደማለት ነው – ዕንቅርትም ላይ ጆሮ ደግፍ፡፡ እንኳንስ ቃናን የመሰለ የጼጼ ዝምብ (tsetse fly) ታክሎብን ዱሮውንም ብዙዎቻችን እንቅልፋሞች ነን፡፡ ወያኔ ደግሞ ኢቲቪው ሲፈልግ ሰሚና ተመልካች አጥቶ ድርግም ይበል እንጂ እንደቃና ያሉ ቲቪዎችን እየደጎመም ቢሆን ለምልመው እንዲኖሩ ያደርጋል – ጥሩ ቫሊየሞች ናቸዋ! ጥሩ babysitters ናቸዋ! ግሩም lullabies ናቸው እኮ! – ምድረ አበሻን ከገረድ እስከ ፕሮፌሰር ጥልቅ እንቅልፍ አስወስደው ሀገረ ቱርክንና ሩቅ ምሥራቅን በምናብ የሚያስጎበኙ ትክክለኛ አስማተ ዲያብሎስ ናቸው፡፡ አቤት ሀገራችን የገባችበትን ማጥ ሲያስቡት!

ቃና ቲቪ በተዛዋሪ ኢሳትንም ከአየር እያወረደው ነው፡፡ ወያኔ መለኛ ነው፡፡ በነዚያ ጮንጯና የቻይና ቴክኒሻኖችና በሼህ እንትናዬ ገንዘብ ኢሳትን ከአየር ማውረድና መስቀል ሲሰለቸው ጊዜ ሌላ ዘዴ አመጡ – መላ ካልተፈለገለት እጅግ በጣም አደገኛ ዘዴ ተከሰተላቸው፡፡ እኔ ለምሣሌ ኢሳትን ከማየት ተከልክያለሁ – በወያኔ ሳይሆን በእንቅልፋሙ ቤተሰቤ ነው የተከለከልኩት – “እንቅልፋሙ” ስል ፍካሬያዊውን እንቅልፍ እንጂ እማሬያዊውን አትዩ፡፡ ወደምኝታቸው ሄደው ሲተኙልኝ ብቻ ነው የማየው፡፡ አለበለዚያ ይሄ ቃና ከመጣ ወዲህ አብሶ ምንም አላይም፡፡ እርግጥ ነው በድረገፅ ሁሉን ነገር እከታተላለሁ፡፡ በቲቪ ኢሳትን ልይ ብል “እንዴ! የጀመርኩት ፊልም አለ፤ ጥቁር ፍቅርን ጀምሬያለሁ፤ የውበት እስረኞችን ጀምሬያለሁ” እያሉ ቤተሰዎቼ ከግራ ከቀኝ ይንጫጫሉ፡፡ ያኔ እበሳጭና እተኛለሁ፡፡ እነሱ እሚፈልጉትም ያን ነው – እኔንም እንቅልፋም ማድረግ፡፡ ወያኔ በቤቴ ተሳክቶለታል፡፡ ለነገሩ በቅርቡ የራሴን ቲቪ መግዛቴና መገላገሌ አይቀርም – ጥሩ አማራጭ፤ ዲሹን በጋራ ሪሲቨርንና ቲቪን በግል፡፡ ደሞስ የራሴን ሣተላይት ቲቪ ብከፍትስ? ይሄውና ያ አንዱ ብርቅዬ ልጃችንስ በቅርቡ ጄቲቪ ብሎ ጀምሮ የለ? ምን ይጎለኛል፡፡ ጆሲን ግን አደራችሁን ተከታተሉለት፤ እደግ ተመንደግ በሉት፡፡ ግሩም ልጅ ነው፡፡ የልጅ ዐዋቂ፡፡ እነቴዲንና እነጆሲን ይባርክልን፡፡ እነሁሉን ላገር አሳቢና ተቆርቋሪዎች ይጠብቅልን፡፡

ግን ግን ምን እንሁን? ምን ይብቃን? ወዴትስ እንሂድ? ከወያኔ ሀሽሽ እንዴት እንዳን?
ቀደም ብዬ የጠቀስኩላችሁን አጭር ጽሑፍ እዚሁ እንድታገኙት ከዚህ በታች አኑሬላችኋለሁ፡፡
ቃና የሚባል የቴሌቪዥን ፕሮግራም መላ ካልተበጀለት በቅርብ ቀናቶች ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ እውነታዎች
1) ከፍተኛ የሆነ የትዳር መቃወስ ይፈጠራል
2) ትምህት ቤቶች ይዘጋሉ(የቤት ስራ የሚባል ነገር ይቀራል
3) መስሪያ ቤቶች የስራ ሳይሆን የእንቅልፍ ቦታ ይሆናሉ
4) የሚወለዱ ህፃናት በሙሉ ዘሀራ ወይም ቻንድራ የሚል ስም ይወጣላቸዋል
5)EBC “ ebc ውስጤ ነው#” በሚል logo ይቀይራል
6) አውቶብሶች በሙሉ ዲሽ ያስፈልገናል በሚል አድማ ይመታሉ
7) መንገዶች በሙሉ ቃና ቃና በሚል እግረኞች ይጨናነቃሉ
8) ፍቅረኛሞች እወድሻለው የሚል ቃል ቀርቶ ውስጤ ነህ በሚል ቃል ይተካል ይመ አስተናጋጆች ሜኑ ሲጠየቁ ቃናም አለ ይላሉ
10) የካፌ፡የሆቴል የምግብ ዋጋ በ3እጥፍ ይጨምራል
11) ሳያዙ ሳይሆን ” እነ እንትናን ሊያዪ መቀመጥ ክልክል ነው “በሚል ማስጠንቀቂያ ሬስቶራቶች ይጨናነቃሉ …
12) የሰዓት መለኪያችን ቃና ላይ በሚታዩት ፊልሞች ይሆናል ማለትም “ፍሬንዴ ሰዓት ሲባል ባክ ገና ነው ጥቁር ፍቅር አልጀመረም” መባባላችን የማይቀር ነው
13) የፌስ ቡክ ፕሮፋይል ፒክቸሮች በነቻንድራ,በነ ኦማር,በነ ጁሊያ.. … ምስል ይቀየራል
14) በአንፃሩም የፌስ ቡክ የፕሮፍይል ስሞች በቃና ፊልሞች ስሞች ይቀየራሉ በአብዛኛው የሴቶች ስም ለምሳሌ;አበሩ ኦማር ጋል፣ኪዱ ጁሊያን ወጥመድ…..ሌላው ደግሞ ከበፊቶቹ የተበረዙስሞች ጋር ..ቻንድራ ብሪዚ ብራውን…. በሚል መቀየራቸው የማይቀር ነው
“ባጠቃላይ ሀገሪቷ እንቅልፋም፡የደነዘዘ፡…… ዜጋን ማምረት ትጀምራለች”
በእንድሪስ ሙክታር


በብራዚሉ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ታወቁ – (ዝርዝራቸውን ይዘናል)

$
0
0

meseret mosinet-geremew

ስሜነህ ታደሰ | ለዘ-ሐበሻ ስፖርት

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ31ኛው የብራዚሉ ሪዮ ኦሎምፒክ በአትሌቲክስ ስፖርት ዘርፍ የመለመላቸውን አትሌቶች በሆቴል አስቀምጦ አቋማቸውን እየተከታተለ ሲሆን ሃገሪቱን በላቲን አሜሪካ ምድር በሚደረገው የኦሎፒክ ውድድር የሚወክሉ አትሌቶችን አሳውቋል::

እንደ ፌዴሬሽኑ ገለጻ ከተመረጡት ከነዚህ አትሌቶች ውስጥ በሚደረጉ ልምምዶች አቋማቸው ከወረደ ሊቀነሱም ይችላሉ::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት በሪዮ ኦሎምፒክ ሃገራችንን የሚወክሉትን አትሌቶች ዝርዝር ከነዘርፉ አድርሰውናል:: የማራቶን ወኪሎች ከ10 ቀን በኋላ ይታወቃልም ተብሏል::

በወንዶች 10 ሺህ ሜትር:
1.ቀነኒሳ በቀለ
2 ታሪኩ በቀለ
3. ሙክታር እንድሪስ
4. ኢማና መርጊያ
5. ሞሰነት ገረመው
6. አዱኛ ታከለ
7. ፀበሉ ዘውዴ
8. ታምራት ቶላ
9. ሙሴ ዋሲሁን
10. ይገረም ደመላሽ
11. ኢብራሒም ጀይላ
12. ብርሃኑ ለገሰ

በሴቶች 10 ሺህ ሜትር
1. ጥሩነሽ ዲባባ
2. ገለቴ ቡርቃ
3. በላይነሽ ኦልጅራ
4. ዓለሚቱ ሃሮዬ
5 ነፃነት ጉደታ
6. ጐይተቶም ገ/ስላሴ

በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች

1. ያሲን ሃጂ
2. ዮሚፍ ቀልጀልቻ
3. ሐጎስ ገብረሕይወት
4. ጌታነህ ሞላ
5. ደጀን ገብረመስቀል
6. የኔው አላምረው
7. ልዑል ገብረ ሥላሴ

በሴቶች 5ሺህና 10 ሺህ ሜትር
1. አልማዝ አያና
2. ሰንበሬ ተፈሪ
3. ገንዘቤ ዲባባ
4. መሠረት ደፋር
5. ዓለሚቱ ሐዊ
6. ሐብታምነሽ ተስፋዬ

በ1500 ሜትር ወንዶች
1. አማን ወጤ
2. ዳዊት ወልዴ
3. አማን ቃዲ
4. በቀለ ጉተማ
5. መኮንን ገብረመድህን

በ1500 ሜትር ሴቶች
1. ዳዊት ስዩም
2. ጉደፋይ ፀጋዬ
3. ባሶ ጎዶ
4. አክሱማዊት አምባዬ

በ800 ሜትር ወንዶች
1. መሐመድ አማን
2. ጃና ኡመር
3. ማሞሻ ሌንጮ
4. ዮብሷን ግርማ

በ800 ሜትር ሴቶች
1. ት ዕግስት አሰፋ
2. ሃብታም ዓለም
3. ጫልቱ ሹሜ
4, ሊዲያ መለስ

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሩጫ ወንዶች
1. አምሳሉ በላይ
2. ኃይለ ማርያም አማረ
3. ታደሰ ሰቦቃ
4 ጫላ ባዩ
5. ጅግሳ ቶሎሳ
6. ጌትነት ዋለ

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሩጫ ወንዶች
1. አብዱራህማን አብዶ
2. ጌቹ ዓለሙ

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሩጫ ሴቶች
1. ትዕግሥት ታማኙ
2. ማህሌት ፍቅሬ

የርምጃ ውድድር ተካፋይ ሴቶች
1. ዓናለም እሸቱ
2. አስካለ ቲክስ
3. የኃልዩ በለጠው
4. አያልነሽ በለጠው

የረዥም ርቀት ውድድሮች አሰልጣኞች

1ዋ/ሱ/ኢ/ሁሴን ሽቦ5000/10000 ዋና  አሠልጣኝ
2መላኩ ደረሰ5000/10000 ም/ዋና አሠልጣኝ
3አድማሱ ሳጂ5000/10000   አሠልጣኝ
4ም/ኮ ቶሌራ ዲንቃ5000/10000  አሠልጣኝ
5ብርሃኑ መኮንን5000/10000  አሠልጣኝ

የአጭር ርቀት ውድድሮች አሰልጣኞች

1ንጉሴ ጌቻሞወንድዋና አሠልጣኝ
2ዳዊት ጥሩነህወንድም/ዋና አሠልጣኝ

የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል አሰልጣኞች

1ብዙአየሁ ታረቀኝዋና አሠልጣኝ
2ተሾመ ከበደም/ዋና አሠልጣኝ

የርምጃ ውድድር አሰልጣኞች

5.ባዬ አሰፋዋና አሠልጣኝ
6.አምሳለ ያዕቆብአሠልጣኝ

አትሌት ኩለኒ ገልቻ በፍቅረኛዋ በስለት ተወግታ ተገደለች

$
0
0

Zehabesha-News.jpg
(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ በመካከለኛ ርቀት 800 ሜትር ተወዳዳሪ የነበረችውና በብሔራዊ ቡድን ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ተመራጭ በመሆን የምትታወቀው የ19 አመትዋ አትሌት ኩለኒ ገለልቻ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በጓደኛዋ እጅ ህይወቷ አልፏል::

አትሌቷ ተስፋ ያላትና በጥሩ የአትሌቲክስ ውጤት ላይ የምትገኝ እንደነበረች የአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኞች ማህበር ድረ ገፅ መረጃ ያሳያል ያለው የፌዴሬሽኑ ዘገባ በ800 ሜትር ሴቶች 2 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ከ68 ማይክሮ ሰከንድ የግል ምርጥ ሰዓት ነበራት ብሏል::

አትሌቷን የገደለው ወጣት ወዲያውኑ ለፖሊስ እጁን መስጠቱን ምንጮች ሲጠቅሱ አስከሬኗ በምኒሊክ ሆስፒታል ምርመራ ሲደረግለት ቆይቶ ግንቦት 5/2008 ዓ. ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ በትውልድ አካባቢዋ ኦሮሚያ ክልል አምቦ ከተማ የቀብር ስነስርአት እንደተካሄደ ተገልጿል::

የስደት ፖለቲካ ትዝብቴ እፍታ |ከሶልያና ሽመልስ (ውይይት መጽሔት)

$
0
0

ከአዘጋጁ: ይህ ጽሁፍ በኢትዮጵያ ታትሞ በወጣው ‘ውይይት’ መጽሔት ላይ ታትሞ ወጥቷል:: በሃገር ቤት ያላችሁ አንባቢዎች መጽሔቷን ገዝተው እንዲያነቧት ትበረታታላችሁ::

ፎቶ ከአልጀዚራ ቲቪ ስክሪን

ፎቶ ከአልጀዚራ ቲቪ ስክሪን

ከሶልያና ሽመልስ

ከተሰደድኩ ሁለት ዓመት ሊሆነኝ ነው። አቆጣጠሬ በሽብርተኝነት ከተከሰስኩበት ቀን ጀምሮ ሆነ እንጂ ከአገር ከወጣሁ ከተቆጠረ ደግሞ ሁለት ዓመት ከአንድ ወር አካባቢ ሆነኝ። የስደቴን ቀን የክሱ ቀን አድርጌ የምቆጥረው በሁለት ምክንያቶች ነው። አንደኛው፣ ከወዳጆቼ እስር ጀምሮ ያልቆረጠልኝ ‹ላልመለስ እችላለሁ› የሚለው ሐሳብ የተረጋገጠው በክሱ በመሆኑ ሲሆን፤ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ፣ እንደፖለቲካ ስደተኛ ወደ ዋሽንግተን ያቀናሁበትና ፖለቲካውን ማጤን የጀመርኩት በይፋ ከተከሰስኩ በኋላ በመሆኑ ነው። ስደት የጀመርኩት እንደማንኛውም አገር ቤት ውስጥ ፖለቲካ በቅርበት እንደሚከታተል ሰው የዳያስፖራን ፖለቲካ በቅርቡ እንደማውቀው እየተሰማኝ ነበር።

በቅድመ ስደት ኑሮዬ ከአገር ውጪ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ላይ ትችቶች ቢኖሩኝም በአብዛኛው የተስፋ ምንጭ አድርገው ከሚወስዱት ሰዎች የምመደብ ነበርኩ። ‹የቦታ ልዩነት ለፖለቲካ ተሳትፎ ብዙም ለውጥ የማያመጣ፣ ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ከውጪም ያለው ኃይል ወሳኝ ሚና ያለውና ሚናውን አውቆ ለዚያ የተዘጋጀ ነው› የሚሉት እምነቶቼ ለተስፈኝነት ካበቁኝ ምክንያቶች ጥቂቶቹ ነበሩ።

የስደት ፖለቲካ 101

ከቀናት በኋላ ስደት ‹አውቶማቲክ› በሆነ መልኩ በጣም ፖለቲካዊ እንደሆነ ተረዳሁ። በአንድ በኩል አገር ቤት የሚቸግረኝን ፖለቲካ የሚያዋራ የቀድሞ ወዳጅ ወይም የትምህርት ቤት ጓደኛ ማግኘት አለመቻል እዚህ ተቃራኒ ሆኖ አገኘሁት። አገር ቤት ሴት ጓደኞቼን ሳገኝ ሁለተኛ ደረጃ አብሬ የተማርኳቸውን ጓደኞቼን ሳዋራ ፖለቲካዊ ወሬ ጭራሽ አይታሰብም ነበር። ሌላ፣ ሌላ “ኖርማል ነገር” አውርተን

እንለያያለን። የፖለቲካ ወሬ፣ ከፖለቲካ ወዳጆች ጋር ብቻ የተወሰነ ነበር። በተቃራኒው ስደት ላይ ሁሉም ሰው ፖለቲካ ያወራል፣ ለዛውም በሙሉ መብት እና እርግጠኝት። የመጀመሪያ ሰሞን ቢገርመኝም በአንድ በኩል ደግሞ ደስ አለኝ። ብዙው ሰው የአገር ጉዳይ የሚሳስበውና የሚወያይ መሆኑ አሪፍ ነገር አይደል?! ሌላው የስደት ‹ሀሁ› ከጥቃቅን ነገሮች ይጀምራል። የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. መንግሥትን ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ብሎ የሚጠራ ሰው ማግኘት አይታሰብም። እንደው የሕ.ወ.ሓ.ት. ደጋፊ የሆነ ሰው የማግኘት ዕድል አልገጠመኝም እንጂ ቢያጋጥመኝ እነሱም ቢሆን ሕ.ወ.ሓ.ት.ንም ሆነ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን በአደባባይ ሥሙ የሚጠሩት አይመስለኝም። (ማንኛውም መንግሥትና ከመንግሥት ጋር የተያያዘ ነገር ሥሙ “ወያኔ” ነው)። ባንዲራው ልዩ ነው፤ ንግግሩ ልዩ ነው። ስደት ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. የሌለበት የአገር ቤት ‹ኮፒ› መስሎኝ እንዳልነበር፣ እኖርበት ስጀምር ግን ግር አለኝ። ምኑም አገር ቤት አይመስልም። መንገዱም፣ ሰዉም፣ ወሬውም፣ ፖለቲካውም፣ ሥራውም። እንደውም፣ ‹ስለስደት ፖለቲካ ሳስብ በስርዓት አላሰብኩም ነበር ማለት ነው?› ብዬ ተገረምኩ። ብዙ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ከዛም በተጨማሪ የፖለቲካ ውይይት ፍላጎቱ ከፍተኛ መሆኑን በማየት ብቻ አገር ቤት ከማውቀው የተቃውሞ የፖለቲካ ውይይት እና ምኅዳር ጋር ይመሳሰላል ብዬ ማሰቤ ስህተት ነበር። በእርግጥ በውጪ የሚኖሩ እና የፖለቲካ አመለካከታቸው (ቢያንስ በውይይት ባሕላቸው) ከእኔ ጋር የሚመሳሰሉ የአሜሪካን ነዋሪዎችንም ማወቄ ለስደት ፖለቲካ የቀድሞ አረዳዴ የዋሕነት አስተዋ ዖ እንዳደረገም ገባኝ።

ብዙው የፖለቲካ ስደተኛ አገር ቤት ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ጊዜውን፣ ገንዘቡን እና ጉልበቱን መስዋዕት ለማድረግ ወደኋላ የማይል ነው። ገንዘብ ያዋጣል። ሰልፍ ይሰለፋል። የተጠየቀውን ይሰጣል። ፍጹም ለአገራቸው ቀንአዊ የሆኑ ብዙ ሰዎች አሉ። ድምጻቸው የተሰማ ሳይመስላቸው  ሲቀር ተስፋ ሳይቆርጡ፣ ዐሥርት ዓመታትን አሳልፈዋል። የሚያውቁኝ ወይም በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ስለ ዞን9 የጦማሪዎች ስብስብ የሰሙ ሰዎች የሰጡኝ ማ ናኛና ማበረታቻ ብዙዎቹ በበጎ አስተዋ ዖ የሚያደርግ ማንኛውንም እንቅስቃሴ እንደሚያበረታቱ በግል እንድረዳም አስችሎኛል። ይህ ሁሉ ቅንነት ባለበት ቦታ ግን ብዙ ‹የስትራቴጂ› መሠረታዊ መግባባት ማጣትና የፖለቲካ ውጥንቅጥም አብሮ ይታያል። በስደት ያለው ፖለቲካ አገር ቤት ካለው ፖለቲካ በተሻለ የመሆን ዕድሎች ቢኖሩትም እኔ ካየኋቸው መሠረታዊ ትምህርቶች በመነሳት ከስር ያሉት ሦስት ዋና ዋና ተግዳሮቶች የብዙ ከላይ የጠቀስኳቸውን ዜጎች አቅም በአግባቡ የፖለቲካ ሂደቱን ወደፊት እንዳይገፋ አድርገውታል እላለሁ። በእኔ ግምገማ መሠረት ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን እና ጭቆናውን ከስሌቱ አውጥተን ብናሰላው በንጽጽር አገር ቤት ያለው የተቃውሞ ፖለቲካ በሁሉም መልክ በስደት ካለው የተሻለ ውስጣዊ መርሕ (internal principle) ላይ የቆመም ይመስለኛል።

ተቋም መፍጠር ያለመቻል (Lack of institution)

የስደት ፖለቲካው ተቋማት የሉትም ማለት ይቻላል። እንዳለመታደል ሆኖ አገር ውስጥ ያጣነው ነጻ ተቋማትን ማቋቋም አለመቻል ስደት ላይም ተከትሎን ይታያል። አገር ውስጥ ቢሆን የሃብት ማጣት (lack of resource)፣ የነጻነት ማጣት (freedom of association) እና የዕውቀት ማጣት (lack of capacity and knowledge/skill) ዋና ዋናዎቹ ተቋም መመሥረት ያሉበት ችግሮች ናቸው። በውጪ አገር ግን የሀብት ችግር ሳይታይ (የኢትዮጵያውን እንዲሁም የሌሎች አጋዥ ሰዎችን ሀብት መጠቀም እየተቻለ)፣ የነጻነት ችግር ሳይኖር (የተመዘገበ ድርጅት እና የማኅበረሰብ ሚዲያ ማቋቋም ያለምንም ከባድ መሥፈርት ማድረግ እየተቻለ)፣ የዕውቀት ችግር ሳይኖር (ብዙ የተማሩ እና የመማር ፍላጎት ላላቸውም አቅም ማጎልበቻ ዕድሎች እያሉ)፣ ይህ ነው የሚባል ፖለቲካዊ ተቋም ማየት አይታሰብም። ይህ ነው የሚባል የኢትዮጵያውያንን መብት (በስደት) የሚያስጠብቅ ተቋም የለም። ይህ ነው የሚባል ጠንካራ ማኅበረሰብ (ኮሚኒቲ) ቢፈለግ አይገኝም። ምናልባት ከነተግዳሮቶቻቸው የሰሜን አሜሪካው የስፖርት ፊስቲቫልና፣ የቅርቦቹ ሚዲያ ተቋማት አንደሙከራ ይጠቀሱ ይሆናል። የእነሱንም ቢሆን የተቋማዊነት መሥፈርቶችን በዝርዝር ብናስቀምጥና ብናይ ማሟላታቸው ላይ ብዙ አተካሮ እንደሚኖር ይሰማኛል።

ይህ ራስን አሰባስቦ ተቋማትን መፍጠር አለመቻል (ተቋማት ስል፣ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የፖለቲካ አቀንቃኝ ቡድን፣ የፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ቡድን፣ የማኅበረሰብ እና የሞያ ድርጅቶች የመሳሰሉትን እያልኩ እንደሆነ ይታሰብልኝ) ከላይ ከላይ ብናየው እንኳን ብዙ ችግሮች አሉ። የመጀመሪያው ተቋም ከሌለ በግል የታሰበበት ራዕይ፣ ዓላማ እና ግብ አይኖርም። ምን ማድረግ ነው የምንፈልገው? ማን ላይ ተ ዕኖ ለማድረግ ነው የምንፈልገው? መቼ እና እንዴት አድርገውን ነው ያንን የሚፈለገውን ተ ዕኖ/ አስተዋ ዖ የምናደርገው? የሚሉት ጥያቄዎች በቂ መልስ አይኖራቸውም። ይሄ ደሞ ይደረጋል የሚባለውን የፖለቲካ/የመብት/ማኅበራዊ ትግል አስተዋ ዖ እጅግ በጣም ይጎዳዋል። ከዛም በላይ ትግሉ በግለሰቦች ዙሪያ እንዲንጠለጠል (አሁን እንዳለው) በር ከፍቶለታል። ግለሰቦች ምንም ያህል ቁርጠኛ ታጋይ ቢሆኑ የተቋማትን ቦታ መተካት አይችሉም። በዚህም የተነሳ ስደተኛው፣ በትንሹ ባለፉት 25 ዓመታት የአሜሪካን እና ዓለም አቀፍ ተቋማትን ፖሊሲ ለውጥ እንዲያደርጉ ሲጎተገትም ሆነ አገር ቤት ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ብርቱ እንቅስቃሴ ሲያደርግ አይታይም። ይህ ችግር በቁጥር ከፍተኛ የሆነውን እና በቀጥታም ሆነ በተዘዋወሪ ትልቅ ፖለቲካዊ ኃይል ሊሆን የሚችለውን ዳያስፖራ ሰልፍ ሜዳ ላይ ብቻ አስቀርቶታል።

ተቋማት አለመኖራቸው እና በግለሰቦች የሚመራ እንቅስቃሴ ሌላው ችግሩ ለፈጠራ፣ ለአዲስ ሐሳብ እና ከጊዜ ጋር ለሚፈጠር ለውጥ ክፍት አለመሆኑ ነው። ይህ ሁለተኛው ትልቁ ተግዳሮት ነው የምለውን የስደት የተቃውሞ ጎራ ውስጣዊ ልዩነትን እንደ አደጋ የመመልከት አባዜን ያስከትላል።

ውስጣዊ ልዩነትን እንደ አደጋ መመልከት

ይህንን በተቃውሞ ጎራ ያሉ የሐሳብ ልዩነቶችን እንደጠላትነት የመመልከት አባዜን ብዙዎች (አልፎ አልፎ እኔን ጨምሮ) ከገዥው መንግሥት ዕኩል በተቃዋሚው ጎራ ዘንድ ሐሳብን በነጻነት መግለ ትልቅ አደጋ አለበት ተብሎ ሲነገር ይታያል። ለዛሬ እዛ ድረስ ጎትቼ ሐሳብን በነጻነት የመግለ መብት በተቃውሞ (ለዚህ ሑፍ ሲባል ‹የስደት ተቃውሞ›) ጎራ ያለበት ሁኔታ መንግሥት ከሚጋርጥብን አደጋ ዕኩል ነው ብዬ መደምደም አልፈለኩም (ምክንያቱም ለመ ናናትም ይሁን ጠንካራ ክርክር ለማድረግ በቂ ማስረጃ የለም)። ነገር ግን ውስጣዊ የሐሳብም ሆነ የርዕዮተ-ዓለማዊ አመለካከት ልዩነት የሚስተናግድበት መንገድ በጣም ደካማ እና ሰዎች የማሰብ መብታቸው ጭምር ጥያቄ ውስጥ የሚገባበት መሆኑ የሚያከራክር አይደለም። ይህ በአደባባይ ከማኅበረሰብ ሚዲያ ጀምሮ በግል የተለየ ሐሳብ ያቀረቡ ሰዎች ሁሉ የሚደርስባቸው መገለል፣ ወከባ እና ስድብ ዋና ማሳያ ነው። እየተደረገ ያለውን ነገር የጠየቀ/የሞገተ ሁሉ የመንግሥት ደጋፊ፣ ትግሉን አጣጣይ ከዛም አለፍ ሲል የግል ችግር ያለበት ተደርጎ ይቀርባል። ይሰደባል። ይህ ሒደት ሰው ርዕዮተ-ዓለምን ፣ የትግል ‹ስትራቴጂ›ን እና ስልትን ውጤታማነት፣ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን ሳይጠይቅ በጅምላ እንዲደግፍ ያስገድደዋል። ከዚህ ወጣ ያለ ሐሳብ ያላቸውም ካሉ ወይ በስድብ እና ማሸማቀቅ ከፍ ካለም ደሞ በማግለል እና ሥም በማጥፋት ከመድረኩ ይገለላሉ።

ከሁለት ዓመት በፊት በጻፍኩት (“በተቃዋሚ ሥም ተቃቅፎ መሳሳም፤ ለትልቁ ስዕል ሲባል” የሚል) ሑፍ ‹አገር ቤት ከነበረው የተቃውሞ ጎራ ያሉ ሰዎች ጋር ያለመርሕ መስማማት፣ ለተቃውሞ ሲባል ብቻ ኅብረት መፍጠር እና አጋርነት ማሳየት ላይ ግፊት ማድረግ ጉዳት አለው› የሚል ነገር አስፍሬ ነበር። በወቅቱ አገር ውስጥ ያለው የተቃውሞ ጎራ ውስጣዊ ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ በመሠረታዊ ደረጃ በሚያስማማው ጉዳይ ላይ ብቻ እንዲሠራ እና ለውስጣዊ ልዩነት ቦታ እንዲሰጥ መጠቆሜ ነበር። በወቅቱ ጫን ብዬ የወቀስኳቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሚዲያዎችም ነበሩ። ያኔ የስደት ፖለቲካውን ሳላይ በመሆኑ አሁን ሳስበው የምጠብቀው ‹ስታንዳርድ›ን ከፍ አድርጌ ነው እንጂ “ይቅር በሉኝ” ለማለት ሁሉ አምሮኛል። ቢያንስ ከዚያ በኋላ ባለው ልምድ ከነችግሮቹ አገር ቤት ያለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከሚከፍለው መስዋዕትነት አንጻር ውስጣዊ ልዩነትን በመቀበል ረገድ በስደቱ ፖለቲካ በጣም በብዙ ይሻላል። በክፉ ቀንም ልዩነትን አቻችሎ በመደጋገፍ ረገድ የአገር ውስጡ ፖለቲካ የተሻለ ነው።

እነዚህን የስደት ፖለቲካ ተግዳሮቶች እያሰብኩ ሳለ አንደኛው ምክንያቱ ምናልባትም ለረጅም ዓመት የቆዩ የዕድሜ ባለጸጋዎች እና ፖለቲካው ላይ ረጅም ዓመት የቆዩ ግለሰቦች ስብስብ መሆኑ ይሆናል የሚል ሐሳብ መጣብኝ፤ ይህ ወደ ሦስተኛው ተግዳሮት ይወስደኛል።

ለመታደስ ያልተዘጋጀ

ፖለቲካም ሆነ ርዕዮተ-ዓለም ይታደሳል፤ ይቀየራል፤ አዲስ ሰዎችን እና ሐሳቦችን እያካተተ መሄድ አለበት። ይህ በስደት ፖለቲካው ላይ የሚሠራ አይመስልም። ብዙ የፖለቲካው ፊቶችም ሆኑ ተሳታፊዎች ለዐሥርት ዓመታት ፖለቲካው ላይ የቆዩ ናቸው። ይህ አገር ቤትም እውነት ቢሆንም ልዩነቱ አገር ቤት ወጣት መሪዎች እና አባላት እየተቀላለቀሉት ከነባራዊው እውነታው ሳይርቁ (with context) የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ‹ኮንቴክስቱ› ለለውጥ ይገፋቸዋል። ስደት መረጃ እንጂ ‹ኮንቴክሰት› የለውም። ይህ ከ‹ኮንቴክስት› መራቅ የስደት ፖለቲካውን አስፈላጊ ለውጥ/መሻሽል የማድረግ ችሎታ ያሳንሰዋል። (ወይም መታደስ እንዳለበት አይገባውም)። የአባይን መሠራት እየደገፈ መንግሥትን የሚቃወም ወጣት እንዳለ መስማት ስደት ፖለቲካው ላይ ላሉ ጥቂት ለማይባሉ ሰዎች “ወያኔነት” ነው። ይህ ለመታደስ አለመዘጋጀቱን ለማሳየት በየፖለቲካ ስብሰባው የሚሄደውን ሰው የዕድሜ እርከን ማየቱ ብቻ ይበቃል። ከቁጥሩ ማነስና የተለመዱ ፊቶች መብዛት በተጨማሪ የወጣቶች ተሳትፎ በጣም ውስን ነው። ወጣቶች ፖለቲካዊ ውይይቱን ስለማይወዱት ወይም ስለማይፈልጉት አይመለስኝም ስብሰባዎቹ ላይ የማይገኙት። ከዚያ ይልቅ የፖለቲካ እንቅስቃሴው ከነሱ አስተሳስብ ጋር የሚሄድ ስለማይመስላቸው ነው ብዬ ነው የምገምተው። እንደ አለመታደል ሆኖ የዳያስፖራ ፖለቲካ በነዚህ ጥቂት ፊቶች ነው የሚመሰለው። ይበልጥ የሚያሳስበው ደግሞ ችግሮችን የመገምገም እና የሥራ አቅጣጫን የመገምገም ባሕል እና ለክፍተቶች መፍትሔ የመስጠት ተቋማዊ አሠራር ስለሌለ ይህ ነው የሚባል መፍትሔ ወይም ውይይት ሲደረግበት አይታይም። ከዚህም በተጨማሪ በማኅበራዊ፣ በመዝናኛ እና በመሳሰሉት መልኩ የኢትዮጵያውያንን ተሳትፎ የሚያጎለብቱ ዕድሎች ካለመኖራቸውም በተጨማሪ (ካሉም በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በፓርቲ ፖለቲካ የተያዙ ወይም መጠጋጋት የሚጠበቅባቸው በመሆናቸው) ኢ-ፖለቲካዊ (apolitical) በሆነ ሥራ ብዙ ኢትዮጵያውያንን የመሳብ ዕድላቸው ደካማ ነው።

ይሄ እንግዲህ በጥቅሉ ለእኔ የታየኝ የውጪው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ተግዳሮት ነው። የማውቀው አብዛኛው የሰሜን አሜሪካውን ስደተኛ እና ፖለቲካውን ቢሆንም የወል ከሆነው ማኅበረሰባዊ አመጣጣችን አንጻር ግን አውሮፓም ከዚህ የተለየ እንደማይሆን እገምታለሁ። ይህ ሑፍ ሁሉንም ተግዳሮቶች በጥልቅ እና መፍትሔ አይዳስስም። ከትልቁ የተግዳሮት ተራራ በእፍኝ እንዳካፈልኳችሁ ቁጠሩልኝ። ችግሩን መናገር መጀመር ለመፍትሔ ፍለጋው አንድ አካል ነውና።

ወ/ሪት ሶልያና ሽመልስ የዞን ፱ ኢ-መደበኛ የጦማሪዎች ስብስብ መሥራች አባል እና የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ፕሮጀክት ሥራ አስፈፃሚ ኃላፊ በመሆን እያገለገለች ነው፡፡ በኢሜይል አድራሻዋ soliyesami@gmail.com ሊያገኟት ይችላሉ፡፡

ትህዴን 15 የኢህአዴግ ወታደሮች እንደተቀላቀሉት አስታወቀ (ስም ዝርዝራቸውን አሳውቋል)

$
0
0

ኤርሚያስ አመልጋ በመጨረሻም “ለጊዜው”ተፈታ

$
0
0

Ermias Amelga

(ዘ-ሐበሻ) በአንዱ ክስ በዋስ ሲፈታ እንደገና በሌላው ሲታሰር የቆየው ነጋዴ ኤርሚያስ አመልጋ 3ኛው ክስ ከተመሰረተበት በሗላ ትናንት መፈታቱ ተሰማ::

ኤርሚያስ አመልጋ ለጊዜውም ቢሆን ትናንት ተፈቶ ቤተሰቡን የተቀላቀለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛው ችሎት የቀረበበትን 3ኛ ክስ ውድቅ ካደረገው ከ11 ቀናት በኋላ ነው:: ፖሊስ አቶ ኤርሚያስን ፍርድ ቤት ከለቀቃቸው በኋላ ለምርመራ አቆይቷቸው እንደነበር መዘገቡ አይዘነጋም””

በአጠቃላይ በቀረቡበት ክሶች 1.1 ሚሊዮን ብር በዋስትና ያስያዘው ኤርሚያስ አመልጋ አሁንም እንደማይታሰር ምንም ማረጋገጫ የለም:: እንደ አስተያየት ሰጪዎች ገለጻ ከአንድም 3 ጊዜ ሲፈታ ፖሊስ አዳዲስ ክሶችን እየፈለገ ሲያስረው ቆይቷል::

ከቤት መስራት ጋር በተያያዘ ገንዘብ ወስዶ ቤቶችን አላስረከበም በሚል የሚሰሰው ይኸው ነጋዴ ገንዘቡን በኮንስትራሽን ሰበብ የተቀብሉት የሕወሓት ሰዎች እንደሆኑ ይነገራል::

የ59 ዓመቱ ኤርሚያስ በአሜሪካ የተሳካለት የንግድ ሰው የነበረ ቢሆንም በሃገሬ ላይ ሰርቼ እኖራለሁ ብሎ ገብቶ በሕወሓት ነጋዴዎች የሚሰቃይ ሰው ሆኗል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በርካታ ናቸው::

አዲስ አጭር መረጃ ስለታላቁ የነጻነት ታጋይ አንዳርጋቸዉ ጽጌ!!

$
0
0

ከልዑል ዓለሜ

በመላዉ ኢትዮጵያዊያን ልቦና ዉስጥ ሰርጾ መግባት የቻለና የማይበርድ የትግል ምእራፍን በመንደፍ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ነጻነትን የቀለመ አባት ነዉ ! እ.ኤ.አ በግንቦት ወር /2014 የየመን ዋና ከተማ ሰናአ ላይ ተሰወረ! የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ለወንበሬ ያሰጋኛል ብሎ በጠላትነት የተነሳበት የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ ክቡር አንዳርጋቸዉ ጽጌ በግፍ ለወንጀለኛዉ የወያኔ ቡድን ተላልፈዉ ተሰጡ!

andargachew new picture
ነጻነት ላያንቀላፋና ነጻነት ላይታሰር አንድነትና ኢትዮጵያዊነትን በጫንቃዉ ተሸክሞ በማረፊያዉ ወቅትና ሰአት የጎረመሰዉ አባት አንዳርጋቸዉ ጽጌ ብዙሃንን አፍርቷል!! ዛሬ የፍሬዉ ትሩፋቶች አደራቸዉን ተቀብለዉ ሐገራቸዉንና ትዉልዳቸዉን ለመታደግ ዳር በደረሱበት ወቅት ወያኔያዉያን ግን ታላቁን አባት ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ላይ ይገኛሉ! ከሰሞኑ በደረሰን መረጃ መሰረት የተከበሩት የነጻነት አባት ክቡር አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ የፌደራል ፖሊስ ህንጻ ስር ምድር ቤት ዉስጥ ( underground ) ክፍል ዉስጥ መወሰዳቸዉን የሚያረጋግጡ ሲሆን የብሔራዊ መረጃ ምንጮቻችን በበኩላቸዉ ሌሎች ተጨማሪ ግለሰቦች በዚያዉ በፌደራል ፖሊስ የምድር ቤት ብቸኛ ክፍል ዉስጥ ከታላቁ የነጻነት አባት ጋር እንደሚገኙ ፍንጭ ሰጥተዋል።


ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

ሜይ 18 ለኛ አዲስ አመታችን ፥ ለካድሬዎቹ ደሞ ከዘመነ መለስ ወደ ዘመነ መንፈስ የተሻገሩበት ሌላ የባርነት አመት ( ሄኖክ የሺጥላ )

$
0
0

screen_2016-05-17 10.17.36ቀዳማይ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጎላ ባንድ ወቅት ህዝብ ለማያውቃቸው የቤት ጋዜጠኖች በሰጠችው ቃለ መጠይቅ ፥ ልጆቿን ከዚህም ከዚያም እያብቃቃች ሳንፎርድ እና ሊሴ እንዳስተማረቻቸው የምትተርክበትን መሳጭ ቃለ መጠይቅ ድጋሜ ዛሬ ከአራት አመት በኋላ አደመጥኩት ። ለልጆቿ የትምህርት የምትከፍለው ስታጣ እንደ ሷ ኣባባል « ሊሴ ይማር የነበረውን ሳንፎርድ ፥ ሳንፎርድ ይማር የነበረውን ሊሴ እያሸጋሸገች » ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ስለማድረጓ ስትናገር ስሰማ « እኔን አንዴ ቄስ ትምህርት ቤት ፥ ሌላ ጊዜ ደሞ ሰንበት ትምህርት ቤት እያሸጋሸጉ ያስተማሩኝ ቤተሰቦቼ ባይኔ ውል አሉብኝ » ።

የሷ ወሬ ገንዘብ ማጣት ነው ወይስ አይን ማውጣት ወይስ ለዛ ማጣት ? አጣሪ ኮሚሽን እነ ገብረዋህድን በነካ እጅህ ባክህ ብለናል !!!

«መንግስት አንድ ሁለት ብሎ ቆጥሮ ከሚሰጠን ደሞዝ ውጭ ቤሳ ቤስቲን የለንም» ያለችው ወይዘሮ አዜብ ፥ ከሱም ላይ 11 የጎዳና ልጆች ቦሌ አካባቢ እንደምታሳድግ ነገረችን ። ያው በተዘዋዋሪ ቦሌ ነው የምኖረው ማለቷ ነው ። በተዘዋዋሪ መንግስት አንድ ሁለት ብሎ ቆጥሮ የሰጣቸው ገንዘብ ቦሌ ቤት ገዝቶ ለመኖር በቅቶናል ለማለት ነው ።

እኔን ያልገባኝ ታዲያ የኛን ቤቴሰቦች መንግስት እንዴት ቆጥሮ ቢሰጣቸው ነው ገንዘቡ አልበረክት ያለላቸው ። ለነሱ ሲሆን ከአንድ ሳይሆን ከሺ ነው የሚጀምረው ማለት ነው ? ይህንንም አጣሩልን ! መቼም ያልተጣራ ውሃ መጠጣት ቢያቅተን የተጣራ ወሬ መስማት አያቅተንም ። ለነገሩ ወሬው ይጣራ ብንል ደሞ የተጣራበትን የ ቫት ክፈሉ ቢሉንስ ። እንደለመደብን ቆሻሻውን ጋቱን !

ይህች ድንቅ ቀዳማዊ እስስት ( ይቅርታ እንስት ለማለት ፈልጌ ነው ) ፥ በየሶስት ወሩ ደሞዟን እያጠራቀመች ፥ ልጆቿን እንደምትደጉምና ፥ ትልቋ ልጇ ( ሰመሃል ማለት ይመስለኛል ) የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ሳለች ፥ የስድስተኛ «SAT» ውጤቷ ግሩም ስለነበር ፥ እንግሊዝ ሃገር የነፃ የ ቦርዲንግ እድል አግኝታ ፥ ልጄን በስድስት አመቷ አልክም ፥ ይልቅስ የነፃ ትምህርት እድሉን እዚህ እንድትማር ደጉሙልኝ ብያቸው እሺ በማለታቸው ፥ እሱ እንድትማር አገዘኝ ትለናለች ። ይህንን አባባል በአጭሩ ስናስቀምጠው ምን ማለት ነው « አሜሪካን ሃገር የገዛሁትን ቤት ፥ አዲስ አበባ ጭኜ አምጥቼ እየኖርኩበት ነው » ማለት ነው ። ለአዜብ እና ለባሏ ምን ይሳናቸው ነበር እናንተዬ !!!? አለመሞት ብቻ !

አራት መስመር ወደታች ወርዳ ደሞ « የመለስ ጭንቅላት ተሽጦ ለኔ ቤት ይገዛል ፥ እኔ ቤት ብፈልግ መለስን ከዚህ ስራው ላይ አስነሳው ነበር » ትለናለች ። « እስኪ ወንድ !? » እንዳንልሽ ፥ የመሌ ጭንቅላት ዛሬ እንኳን ቤት ሊገዛልሽ ፥ አይዞህ ( አጆሃ) የሚለው አጥቶ ፥ መለመሉን ቀርቶ፥ የነቀዝ እና የ ጉንዳን መጫወቻ ሆኗል። የመሌ ጭንቅላት እንኳን ቤት ሊገዛ ፥ አናቱ ላይ የተከመረውን የድንጋይ ክምር መግፋት አቅቶት ፥ ያ ያለ አጃቢ መንገድ ሳያዘጋ የማያልፈው መሪ ፥ ጎዳና ላይ ወድቆልሻል ። እንደውም ከምታሳድጊያቸው 11 የጎዳና ልጆች ጋ ጨምረሽ የማታሳድጊውሳ!
ወይ መሌ እሳቱ ፥ ልጆችሽን እንኳ ፈታ ብለሽ ሳታስተምሪ በማሳለጫው መንገድ አርፋ ይዘሽ ወደ ስላሴ ጓሮ ተቀየሽ ። ገገማ ነሽ ፍቅር አታውቂም !! የጭንቅላትሽን ዋጋ ኣታውቂም ። ይሄን የሚያክል ጭንቄ በወር 250 ዶላር ብቻ አስቀጥረሽው ልጆችሽን ሳንፎርድ እና ሊሴ ያስተማርሽ ባለ ራዕይ እንበለው ባለ መተት እኮ ነሽ። ለማንኛውም ሙተሻል ። ለሞትሽ ምክንያት የሆነሽን የድንጋጤ ሪምክስም ከሰማሽው አራት አመት ሊሆን የሰዓታት ጊዜ ብቻ ይቀራል ። ሜይ 18 የኔ አዲስ አመት ነው ። ቅዱስ አበበ ፥ መለስ ጣጣጣሽ !
ለካድሬ እና ሆድ አደሮች ደሞ እንኳን ከዘመነ መለስ ወደ ዘመነ መንፈስ አሸጋገራችሁ!


የግንቦት 20 ፍሬዎች ከብዙ በጥቂቱ!

$
0
0

ኔልሰን ማንዴላን በነጮቹ መንግስት ያሲያዛቸው የአሜሪካው የስለላ ድርጅት CIA ነው ተባለ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

$
0
0
#ለድርቅና ለረሃብ የተሰበሰበው ገንዘብ ከሚያስፈልገው 54 ከመቶ ብቻ ነው ተባለ
#ኔልሰን ማንዴላን በነጮቹ መንግስት ያሲያዛቸው የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲ አይ ኤ ነው ተባለ
#የአምስቱ አገሮች ጥምር ኃይል አምስት የቦኮ ሃራም መሪዎችን ያዝኩ፣ በርከት ያሉ ዜጎችንም አስለቀቅኩ አለ
#የኮንጎ ወታደሮች እና ፖሊሶች በሰሜን ኮሪያ ወታደሮች እየሰለጠኑ መሆናቸውና የሰሜን ኮሪያ ሽጉጦችን መታጠቃቸው ተገለጸ
#የግብጽ ፍርድ ቤቶች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉ ዜጎች ላይ የእስራት ቅጣት በየኑ

 በተፈጥሮ የአየር መዛባት፣ በዝናም እጥረትና ወያኔ በሚከተለው ዘረኛና የተበላሸ ፖሊሲ ምክንያት በኢትዮጵያ በ50 ዓመት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ድርቅና ረሃብ ከተከሰተ ወዲህ ዓለም አቀፍ ድድየዕርዳታ ድርጅቶች በድርቁ ለተጎዳው ወገን የእርዳታ እጃቸውን ዘርግተው የተማጽኖ ድምፅ ቢያሰሙም ከተጠየቀው 1.4 ቢሊሆን ዶላር ውስጥ እስከ አሁን የተገኘው 54 ከመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ አሜሪካ 705 ሚሊዮን ዶላር መርዳቷ ሲታወቅ በሶሪያ ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉትና ወደ አውሮፓ ለሚፈልሱት ስደተኞች የሚደረገው እርዳታ ለኢትዮጵያ ድርቅና ረሃብ ጉዳተኞች ሊሰጥ በሚችለው አጠቃላይ የዕርዳታ መጠን ላይ ተጽእኖ መፍጠሩ ተጠቅሷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጎርፉ አደጋ በኢትዮጵያ የዕለት ተዕለት ክስተት እየሆነ መምጣቱና ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ በጎርፉ አደጋና በመሬት መደርመስ ከ 100 በላይ ሰዎች መገዳልቸውና በሽህ የሚቆጠሩ የቤት እንስሳት ማለቃቸው እንዲሁም በሚሊዮን የሚቆጠር ብረት መውደሙ አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ሲሆን የዝናቡ መጠን በዚህ ከቀጠለ መጭው ክረምት ከመጠናቀቁ በፊት 500 ሺ ሲዎች ከቀያቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተሰግቷል።
mandela3.jpg

 የደቡብ አፍሪካ እውቁ ታጋይና የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ሚስተር ኔልሰን ማንዴላ የዛሬ 54 ዓመት በዘረኛው የደቡብ አፍሪካ የነጮች መንግስት ሊያዙ የቻሉት በአሜሪካ የስለላ ተቋም በሲ አይ አባል ጥቆማ እንደሆነ ተጋለጠ። ሚስጥሩ ሊጋለጥ የቻለው ጥቆማውን ያካሄዱት በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ ዲፕሎማት የነበሩት የሲ አይ ኤ አባል ዶናልድ ሪካርድ ከመሞታቸው በፊት “ የማንዴላ ጠመንጃ” ( “Mandela’s Gun”) በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ፊልም ዳይሬክተር
ላደረጉላቸው ቃለ ምልልስ በሰጡት መልስ መሆኑን ሰንደይ ታይምስ የተባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ እሁድ ግንቦት 7 ቀን ባወጣው እትሙ ገልጿል። ከዚህ በፊት የሲ አይ ኤው ድርጅት ሚስተር ማንዴላን ከመያዛቸው በፊት ሲከተታል የነበረ መሆኑና በመጨረሻም እንዲያዙ የጠቆመው የዚሁ ድርጅት አባል ነው የሚለው ወሬ በሰፊው ሲሰራጭ የኖረ ቢሆንም የሲ አይ ኤ ባለስልጣኖች በተለያዩ ጊዜያት ሲክዱ የቆዩ መሆናቸው ይታወሳል። ማንዴላ ለረጅም ጊዜ በልዩ ልዩ መንገድ
ከደቡብ አፍሪካ የጸጥታ ኃይሎች ሲያመልጡ ከቆዩ በኋላ ተይዘውና ተፈርዶባቸው ለ27 ዓመታት ያህል በእስር ቤት አሳልፈዋል። ማንዴላ ሲመሩት የቆየቱ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግሬስ በሬገን ዘመነ መንግስት በአሜሪካ ሽብረተኛ ድርጅት ሊስት ውስጥ ተመዝግቦ የቆየ ሲሆን ሽብረተኛ የሚለው ስም የተነሳለት በ2000 ዓም መሆኑ ይታወቃል።

 ቦኮ ሃራምን ለማዳከም የተቋቋመው የአምስት አገሮች ጥምር ኃይል ባካሄዳቸው ተከታታይ አሰሳዎች አምስት የቡድኑን ከፍተኛ መሪዎች የያዘ መሆኑና በቡድኑ ታግተው የነበሩ በርካታ ሴቶችንና ህጻናትን ያስፈታ መሆኑን የካሜሩን መንግስት ቃል አቀባይ ገልጿል። አሰሳዎቹ የተካሄዱት ማዳዋ በሚባለው ጫካ ውስጥ መሆኑ ሲገለጽ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ናይጄሪያ ውስጥ ያላቸው የጦር ስፈር ሲደመስስ የተጠቀሰውን ጫካ የጦር ሰፈር ማድረጋቸው ተደርሶበታል። ይህ ዜና የተሰጠው
የምዕራብ አፍሪካ አገሮች መሪዎች የፍረንሳዩ ፕሬዚዳንት ሆላንድ በተገኙበት የቦኮ ሃራምን እንቅስቃሴ ለመግታት አቡጃ ላይ ከፍተኛ ስብሰባ ባደረጉበት ወቅት ነው።

 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤክስፐርት ቡድን የሴሜን ኮሪያ ወታደራዊ ተቋም አባላት ለኮንጎ ወታደሮችና ፖሊሶች ስልጠና እየሰጡ መሆናቸውንና የኮንጎ ፖሊሶች ሰሜን ኮሪያ የተሰሩ ሽጉጦች መታጠቃቸውን ያረጋገጠ መሆኑን ገልጿል። ቡድኑ ተመሳሳይ ሽጉጦች በአገሪቱ ዋና ከተማ ኪንሻሳ ውስጥም በጥቁር ገበያ እንደሚሸጡ መረጃ የደረሰው መሆኑን ጠቁሟል። ሰሜን ኮሪያ ማንኛቸውንም ዓይነት መሳራሪያ በዓለም ገበያ እንዳትሸጥና ወታደራዊ ስልጠና እንዳትሰጥ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የታገደች በመሆኑ ኮንጎ ውስጥ በማስልጠን ስራና በመሳሪያ ሽያጭ ንግድ መሰማራቷ በሁለቱም አገሮች በኩል ህግን መተላለፍ ነው በሚል የኤክስፐርቱ ቡድን ገልጿል።

 ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የግብጽ ፍርድ ቤቶች ያልተፈቀደ ሰላማዊ ስልፍ አድርገዋል የተባሉ 152 ሰዎችን ከ2 እስከ አምስት አመት በሚደርስ እስራት የበየኑባቸው ታውቋል። የተፈረደባቸው የግብጽ ዜጎች ብዙዎቹ በቅርቡ የሲሲ መንግስት በቀይ ባህር ላይ የሚገኙ ሁለት የግብጽ ዴሴቶችን ለሳኡዲ አረበያ መስጠቱን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ ናቸው። የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ ድርጅቶች ሲሲ ስልጣን ከያዙ በኋላ ተቃውሞን ለማስተናገድ የማይፈልጉ ፍጹም አምባገነን መሆናቸውን አውግዘው ሁኔታው በጣም ያሳሰባችው መሆኑን ተናግረዋል።

ሶስና በኢትዮጵያ – (ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት)

$
0
0

daniel

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ አስደናቂ የፍርድ ታሪኮች አንዱ የሶስና ፍርድ ነው፡፡ እሥራኤል ወደ ባቢሎን ተማርከው በነበሩ ጊዜ ኢዮአቄም እና ሶስና የተባሉ ባልና ሚስቶችም ተማርከው ነበር፡፡ የባቢሎን ሥርዓተ መንግሥት ከየሀገሩ የተማረኩ ፈላስያን የራሳቸውን ጉዳይ በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ፈቅዶ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ የራሳቸውን ፍርድ ቤቶች አቋቁመው የራሳቸውን ጉዳዮች ይዳኙ ነበር፡፡ በዚህ የእሥራኤል ዳኝነት አንድ ጉዳይ ቀረበ፡ሶስና የምትባል በመልኳ ይህ ቀረሽ የማትባለው የኢዮአቄም ባለቤት በሞት በሚያስቀጣው የአመንዝራነት ወንጀል ተከሰሰች፡፡ በዚያ ዘመን በሀብት ሻል ያሉ የባቢሎን ሰዎች ቤታቸውን በኤፍራጥስ ወንዝ አቅራቢያ ሠርተው በወንዙ ዳር በሚገኙት የአትክልት ሥፍራዎች ውስጥ የገላ መታጠቢያዎችንና የመዋኛ ገንዳዎችን ያዘጋጁ ነበር፡፡ እነዚህ የመናፈሻ ሥፍራዎች በአጥር የታጠሩ ሆነው የራሳቸው በር ነበራቸው፡፡

ኢዮአቄምና ሶስና ከፈላስያኑ ወገን በሀብትም በክብርም ላቅ ያሉ ስለነበሩ ይህ ሀብት ነበራቸው፡፡ ሀብት ክብር ብቻ ሳይሆን መዘዝም ያመጣል፡፡ በኢዮአቄም ቤት ለችሮታም፣ ለመጠለልም፣ ከባቢሎን ባለ ሥልጣናት ለመገናኘትም እያሉ የሚሰበሰቡ ብዙ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ መካከል ሁለቱ የተከበሩ የሕዝብ መምህራን ናቸው፡፡ ሕዝቡ በዐዋቂነታቸውና በወንበራቸው ያውቃቸዋል፣ ያከብራቸዋል፡፡ ‹በካባ ውስጥ ያለን ኃጢአት፣ በኮት ውስጥ ያለን ጽድቅ እግዜር ብቻ ነው የሚያውቀው› እንዲሉ እነዚህ ሁለት የተከበሩ ባለ ካባዎች ጠባያቸው እንደ ካባቸው አልነበረም፡፡ የኢዮአቄምን ሚስት ሶስናን ለመኝታ ይፈልጓት ነበር፡፡ ነገር ግን አመቺ ጊዜ አላገኙም፡፡ አንድ ቀን ገላዋን ልትታጠብ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ስትወርድ እነርሱም በድብቅ ወደ መታጠቢያው የአትክልት ሥፍራ ገቡና ተደበቁ፡፡

አገልጋዮቿ የመታጠቢያ ነገሮችን ሊያመጡ በኋላው በር ሲወጡ ከተደበቁበት ወጡና ያዟት፡፡ ከዚያም ‹ከአንቺ ጋር መተኛት እንፈልጋለን› አሉ፡፡ እርሷ ግን ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል ፈቃዳቸውን ለመፈጸም እንደማትፈልግ በቁርጥ ነገረቻቸው፡፡ እንደዚያ ካልሆነ ‹ከጎረምሳ ጋር አይተናታል ብለን እኛ ምስክር ሆነን እንከስሻለን› አሏት፡፡ ነገሩ ምን ቢያስጨንቃት የእነዚህን ምግባረ ቢሶች ፈቃድ ከመፈጸም ሞትን መረጠቺና ጮኸች፡፡ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል እንዲሉ እነዚያም ሰዎች አብረዋት ጮኹ፡፡ አንደኛውም ሮጦ የአጥሩን በር ከፈተው፡፡ የአካባው ሰዎች ጩኸቷን ሰምተው ሲመጡ እነዚያ ሰዎች ‹ሶስናን ከጎረምሳ ጋር ተኝታ በዚህ ቦታ አየናት፡፡ እርሱንም ልንይዘው ስንል ኃይለኛ ነበርና በሩን ከፍቶ አመለጠን› ብለው ተናገሩ፡፡ የተናገሩት ሰዎች የከበሩ መምህራን ስለነበሩ ሊጠራጠራቸው የቻለ ሰው አልነበረም፡፡

የሕዝቡ ሸንጎ በማግሥቱ ተሰብስቦ ጉዳዩን አየው፡፡ እነዚያ ሁለት መምህራን አይተናል ያሉትን ተናገሩ፡፡ ሰዎቹ የሚከበሩ በመሆናቸው ቃላቸውም ተከበረና በሶስና ላይ የሞት ፍርድ ተፈረደባት፡፡ ወደ ፍርድ መፈጸሚያው ሥፍራ ልትሄድ ስትል ግን ፍርዱን እንደገና ለማየት የሚያስገድድ ነገር ተፈጠረ፡፡ ነቢዩ ዳንኤል ‹እኔ በዚህ ፍርድ አልስማማም› አለ፡፡ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ያደረገውን ያውቁ ስለነበር ሕዝቡ ሁሉ ሊሰሙት ፈለጉ፡፡ ዳንኤል አንዱ ያንዱን ቃል ሊሰማ በማይችልበት ቦታ ሁለቱን ሰዎች ለየብቻ አቁሞ የትኛው ዛፍ ሥር ተኝታ እንዳዩዋት ጠየቃቸው፡፡ አንዱ በኮክ ዛፍ ሥር ሲል ሌላው በሮማን ዛፍ ሥር ነው አለ፡፡ ይህንን ሲመለከቱ የሕዝቡ ሸንጎ የሞት ፍርዱን እንዲከልስ ተገደደ፡፡ ሶስናን በነጻ አሰናብቶ በምስክሮቹ ላይ የቅጣት ውሳኔን አስተላለፈ፡፡

ሶስና ኢትዮጵያዊት ሆና፣ ድርጊቱ የተፈጸመው ዛሬ ቢሆን ኖሮ ግን የመትረፍ ዕድል አልነበራትም፡፡ ምንም ንጹሕ ብትሆን፣ ምንም ምስክሮቹ የሐሰት ምስክሮች መሆናቸው በኋላ ቢረጋገጥ፣ ምንም እንኳን ከፍርዱ ውሳኔ በኋላ የፍርዱን ውሳኔ የሚያስገለብጥ ማስረጃ ቢገኝ ሶስና ከመሞት ውጭ አማራጭ አልነበራትም፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ በወንጀል ጉዳይ የተሰጠ ውሳኔ እንደገና የሚከለስበትን ዕድል ስለማይሰጥ፡፡ በታች ፍርድ ቤት የታየ ጉዳይ በይግባኝ በላይኛው ፍርድ ቤት ይታይ ይሆናል እንጂ አንድ የወንጀል ፍርድ ከተሰጠ በኋላ የቀረበው ማስረጃ ስሕተት ነበረ፣ የተፈረደበት ሰው በስመ ሞክሼ ነው፤ ተፈጸመ የተባለው ድርጊት አለመፈጸሙ ተረጋገጠ፣ የወንጀሉን ፍርድ ሊያስገለብጥ የሚችል ሌላ ማስረጃ ተገኘ ቢባል እንኳን የሀገራችን የወንጀል ፍርድ ‹ከፈሰሰ የማይታፈስ› ነው፡፡ በፍትሐ ብሔር መሥመሩ እንደገና ሊታይ የሚችልበት ዕድል በመጠኑም ቢሆን ገርበብ ብሎ ተከፍቷል፡፡ በወንጀል ሕጉ ግን የተከረቸመ በር ነው፡፡
ከወጣ ከግማሽ ምእተ ዓመት በላይ የሆነው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጋችን በዚህ ሁሉ ዘመን በሩን እንደዘጋው ይገኛል፡፡

ሰሞኑን ወደ ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሄጄ በነበረ ጊዜ ሁለት ‹የሶስና ፍርዶችን› ሰምቼ መጣሁ፡፡ አንደኛው ሰውዬ ሰው ገደልክ ተብሎ ይከሰሳል፡፡ ምስክርና ማስረጃ ይቀርብበታል፡፡ ሰውዬው አልገደልኩም ብሎ ቢከራከርም በመጨረሻ በሰባት ዓመት ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡ እርሱም ወኅኒ ወርዶ ፍርዱን ማድረስ ይቀጥላል፡፡ ለሁለት ዓመታት ያህል ከታሠረ በኋላ ግን ሞተ የተባለው ሰው ወደ መንደሩ ይመጣል፡፡ በእርሱ ምክንያት ሰው መታሠሩንም ይሰማል፡፡ ሰውዬውም ወደ ፍርድ ቤቱ ይመጣና ‹ተገደልኩ የተባልኩት ሰው አለሁ፤ ገደለኝ የተባለውን ሰው ፍቱልኝ› ይላል፡፡ ልክ በሞገደኛው ነውጤ ላይ አበራ ለማ እንደጻፈው፡፡ ዳኞቹ ሁኔታውን ሲያጣሩ በርግጥም ሞተ የተባለው ሰው ይህ ከፊታቸው የቆመው ነው፡፡ አሁን ችግሩ ‹ቀጥሎ ምን ይደረግ?› የሚለውን የሀገራችን የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ አለመመለሱ ነው፡፡

በወንጀል የተሰጠን ፍርድ እንደገና ለመከለስ የሚያስችል ዕድል የለም፡፡ በዚህ የተነሣ አለመግደሉ የተረጋገጠው ሰው የእሥር ጊዜውን ከመጨረስ ያለፈ ውሳኔ ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ይህን የተዘጋ በር እስከዛሬም ብዙዎችን ንጽሕናቸው እንዳያድናቸው፣ ዘመን በወለደውና ጊዜ በወደደው ሰው እጅ እንዲወድቁ፣ በአንድ ወቅት በተፈጠረ ስሕተት በተሰጠ ፍርድ እንዲማቅቁ አድርጓቸዋል፡፡ የዚህን በር መከፈት በመቃወም የሚከራከሩ ወገኖች የሚያነሡት ሁለት ጉዳይ ነው፡፡ አንደኛው የወንጀል ፍርድ እንዴትና በማን ነው ሊከለስ የሚችለው? ሁሉም የወንጀል ችሎቶች ይህ ሥልጣን ከተሰጣቸው ላልተገባ ተግባር የመዋል ዕድል አይኖረውም ወይ? የሚል ነው፡፡ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ጉዳዩ መጀመሪያ ለቀረበበት ችሎት ነው የሚቀርበው፡፡

የወንጀል ጉዳዮች ሀገርንና ማኅበረሰብን የሚመለከቱ ስለሆኑ ይህንን ነገር ሊያዩ የሚችሉ ችሎቶችን መመደብ ወይም ከፍ ያለ ሥልጣን ለተሰጠው የፍርድ አካል መስጠት ይቻላል፡፡ በሌላም በኩል አንድ ንጹሕ በስሕተት ከሚታሠር ዐሥር ወንጀለኞች ቢለቀቁ ይሻላል የሚለውን የሕግ ምክር ተግባራዊ አድርጎ መጠቀም ነው፡፡ ሌላው የሚነሣው ጉዳይ ደግሞ የካሣ ጉዳይ ነው፡፡ ‹በስሕተት ነው የታሠርከው› የተባለ ሰው ለተፈጸመበት ነገር ምን ሊደረግለት ይችላል? መንግሥትስ ለእነዚህ ሰዎች ካሣ ለመክፈል ኢኮኖሚያዊ ዐቅም አለው ወይ? የሚለውን የሚያነሡ አሉ፡፡ በስሕተት የተፈረደበት ሰው ኢኮኖሚያዊ፣ ሞራላዊና ማኅበራዊ ኪሣራ ያገኘዋል፡፡ ከሥራው ይወጣል፣ ንግዱ ይበላሻል፣ በሞያው ያፈራቸውን ደንበኞች ያጣል፡፡ ወንጀለኛ ተብሎ ስለተፈረደበት በማኅበረሰቡ ዘንድ ይገለላል፣ ስሙ ይጠፋል፣ ክብሩ ይቀንሳል፡፡ በእነዚህ ሁለት ምክንያቶችም ሞራሉ ይነካል፡፡ የፍርዱ ዘመን ረዥም ከሆነም የማይተካው እድሜው ይወሰድበታል፡፡

መንግሥት ለእነዚህ ነገሮች ሦስት ካሣዎችን ማዘጋጀት ይችላል፡፡ የሞራል፣ የማረሚያና የገንዘብ፡፡ የሞራል ካሣው ሰውዬው በስሕተት እንደታሠረ የሚገልጥ ማስረጃ(የምስክር ወረቀት) በመስጠት፣ አመቺ በሆነው ሚዲያ ወይም በአካባቢው ሊለጠፍ በሚችል ማስታወቂያ በስሕተት የታሠረ ንጹሕ ሰው መሆኑን በመግለጥ መካስ ይቻላል፡፡ የማረሚያ ካሣ ደግሞ ወደ ሥራው እንዲመለስ፣ በመታሠሩ ምክንያት ያጣቸው ጥቅሞች እንዲከበሩለት፣ የተወሰደበት እንዲመለስለት፣ ያለፉት ነገሮች ካሉ እንዲሟሉለት ማድረግ ይችላል፡፡ የሀገሪቱ ዐቅም በሚፈቅደው መጠንም የገንዘብ ካሣ መስጠት ነው፡፡ መንግሥት በፍርድ ሂደት የሚያገኛቸው ገቢዎች አሉ፡፡ ከገንዘብ መቀጮዎች፣ ከውርሶች፣ ወዘተ፡፡ ከእነዚህ ሸረፍ አድርገው ሙሰኞቹ ከሚወስዱ ንጹሐኑ ቢካፈሉ ምን አለ?

አንዳንድ ልሂቃን ‹የተወሰኑ የሕግ አካላት በሠሩት ስሕተት እንዴት መንግሥት ይቀጣል?› የሚል መከራከሪያ ያቀርባሉ፡፡ መንግሥት ድሮውንም በሰዎች የሚመራ መዋቅር ነው፡፡ መንግሥት የሾማቸው ሰዎች ለሚሠሩት ስሕተት አንዱ ተጠያቂም ራሱ መንግሥት ነው፡፡ ለዚህም ነው በሌሎች ሀገሮች የበታች አካላት ለሠሩት ስሕተት ከፍተኛ ኃላፊዎች ሥልጣን እስከ መልቀቅ የሚደርሱት፡፡ ይህ በር እንደተዘጋ ከቀጠለ ግን ከባድ ማኅበራዊ ኪሣራ ያመጣል፡፡ ሰዎች ንጽሕናን እንዲጠየፉ ያደርጋል፡፡ ዘመኑ በተራቀቀበት በዚህ ወቅት ማስረጃዎችን መፈብረክ ቀላል ነውና አያሌ ንጹሐን ለዚህ በተዘጋጁ ማስረጃ ፈብራኪዎች እጅ እንዲወድቁ ያደርጋቸዋል፡፡ ያለ ሥራቸው ወንጀል ሠርታችኋል የተባሉትንም ለበቀል ያነሣሣል፡፡

ሁለተኛውን ታሪክ እዚህ ላይ ላውጋችሁ፡፡ ሰውዬው በነፍስ ግድያ ተከሰሰ፡፡ በርግጥ ተኩሶ ሰው መትቷል፡፡ ሲተኩስም ሰዎች አይተውታል፡፡ በተኮሰበት ቦታም ደም ፈስሷል፡፡ ይህንን ሰውዬውም አልካደም፡፡ ምስክሮችም መስክረዋል፡፡ የሟች አስከሬን ግን ሊገኝ አልቻለም፡፡ ከተኩሱ ቦታ በታች ዝንጀሮ ብቻ የሚወርደው ገደል አለ፡፡ እዚያ ውስጥ ስለገባ ሊገኝ አልቻለም ተባለ፡፡ ተኳሹ ግን ‹በርግጥ ተኩሻለሁ ግን አልገደልኩትም› ብሎ ተከራከረ፡፡ ፍርድ ቤቱ የምስክሮችንና የማስረጃውን ነገር መዝኖ አምስት ዓመት ፈረደበት፡፡ ከዓመታት በኋላ ሞቷል የተባለው ሰው ሌላ መንደር እንደሚኖር ተሰማ፡፡ የታሣሪው ዘመዶችም ሄደው አረጋገጡ፡፡ ሰውዬው በጥይት ተመትቶ ነበር፡፡ ሲመታ ቢያውቀው ገደል ተንከባልሎ ገባ፡፡ በጋቢው ቁስሉን አሥሮ ገደል ለገደል ተንኳቶ ሌላ ሀገር ተደበቀ፡፡ እዚያ ጥይቱን አስወጥቶ ታክሞ ዳነ፡፡ ወደ መንደሩ ለመመለስ ስለፈራ ሌላ ቦታ ጎጆ ቀልሶ ተቀመጠ፡፡ ታሪኩ ይሄ ነው፡፡

ታሣሪው ሰው ይህንን ሲሰማ አልተናደደም፡፡ እንዲያውም ደስ አለው፡፡ ‹ለማንም አትናገሩ› ብሎ ዘመዶቹን አስጠነቀቀ፡፡ አምስት ዓመቱን ጨረሰና ከወኅኒ ቤት ወጣ፡፡ ጠመንጃውን ወለወለ፣ ጥይቱን አቀባበለ፡፡ ‹ሟች› ይኖርበታል ወደተባለው ሥፍራ ሄደና ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ተኩሶ ገደለው፡፡ ሲገድለው ሰው አይቷል፡፡ እርሱም አልተደበቀም፣ ቤቱ ነው የተቀመጠው፡፡ ፖሊስ ግን እንዴት ይክሰሰው፡፡ አንድ ሰው ሁለት ጊዜ ሊሞት አይችልምና፡፡ በፍርድ ቤት ውሳኔ አሁን የተገደለው ሰው ከሞተ አምስት ዓመት አልፎታል፡፡ ይፈረድበት ቢባልም በአንድ ወንጀል ሁለት ጊዜ ፍርድ የለም፡፡ የተዘጋ የፍትሕ በር ዕዳው ይኼ ነው፡፡

የአሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኒዮሪ አስደናቂ የስኬት መንገድ

$
0
0

 ስሜነህ ታደሰ | ለዘ-ሐበሻ ስፖርት

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኒዮሪ በአሰልጣኝነት ህይወታቸው እጅግ የተገፉ ነበሩ፡፡  አሰልጣኙ በሌይስተር ሲቲ ስኬታማ ጊዜያትን ከማሳለፋቸው በፊት በርካታ ክለቦችን አሰልጥነዋል፡፡ የመጀመሪያ ክለባቸው ካግሊያሪ ነበር፤ አሰልጣኙ የጣልያኑን ክለብ በ1988 ተረክበው ከሴሪ ቸ ወደ ሴሪ አው እንዲያድግ አስችለዋል፡፡

claudio Ranieri

ቀጥሎ የተረከቡት ናፖሊን በ1991 ነበር፡፡ ያም ቢሆን በወቅቱ ዲያጎ ማራዶና ከአበረታች ዕፅ ጋር በተያያዘ ለ15 ወራት በመታገዱ ራኒዮሪ ከአርጀንቲናዊው ጋር አብረው ለመስራት አልታደሉም፡፡ በሳን ፓውሎ ሁለት ዓመት ቢቆዩም ምንም አይነት ስኬት አላስመዘገቡም፡፡ እዚያ በነበራቸው ቆይታ በበጎ ጎኑ ሊነገርላቸው የሚችለው ነጥብ ጂያንፍራንኮ ዛላን ወደ ዋናው ቡድን ማምጣታቸው ነው፡፡

ናፖሊን ከለቀቁ በኋላ ቀጣይ ማረፊያቸው ፊዮረንቲና ነበር፡፡ የፍሎረንሱን ክለብ ከሴሪ ቢ ወደ ሴሪ አው በማምጣት ከጋብሪዬል ባቲስቱታ ጋር አስደሳች ጊዜያትን አሳልፈዋል፡፡ ከፊዮረንቲና ጋር የ1996 የኮፓ ኤታሊያ እና ሱፐር ካፕ ዋንጫዎችን አንስተዋል፡፡

ከፊዮረንቲና ጋር ስኬታማ ዓመት ካሳለፉ በኋላ ቀጣይ ማረፊያቸው ቫሌንሲያ ነበር፡፡ ከሜዲትራኒያኑ ክለብ ጋር የኮፓ ዴልሬይ ዋንጫ በ1999 ካነሱ በኋላ በዚያኑ ክረምት አትሌቲኮ ማድሪድን ተረክበዋል፡፡ አሁን በሚገኝበት ደረጃ ላይ ያልነበረው አትሌቲኮ ማድሪድ ከሶስት ዓመት ቀደም ብሎ የላ ሊጋ እና ኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫ አንስቶ የጥምር ድል ባለቤት ቢሆንም ራኒዮሪ ወደ ቪቼንቴ ካልዴሮን ባመሩበት ወቅት በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ችግር ውስጥ ወድቆ ነበር፡ በሊጉ መጠናቀቂያ አካባቢ ከወራጅ ቀጣና አንድ ደረጃ ብቻ ከፍ ብሎ ሲቀመጥ ራኒዮሪ በገባ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡

ያም ቢሆን ራኒዮሪ ከቀዩ እና ነጩ ቤት ከተሰናበቱ በኋላ ሴፕቴምበር 18/2000 ወደ እንግሊዝ በማምራት የቼልሲ ሁለተኛው ጣልያናዊው አሰልጣኝ ሆኑ፡፡ በስታምፎርድ ብሪጅ በነበራቸው የአራት ዓመት ቆይታ ግን ስኬታማ መሆን አልቻሉም፡፡ ከእርሳቸው በፊት ቼልሲ ሁለት የኤፍኤ ካፕ እና ሊግ ካፕ ዋንጫዎችን ማንሳት ቢችልም እርሳቸው ይሄንን ማሳካት አልቻሉም፡፡

በቼልሲ ሳሉ እንግሊዘኛ ለመናገር ተቸግረው የነበሩት ራኒዮሪ አስተርጓሚ አለመፈለጋቸው አስገራሚ አጋጣሚ ነበር፡፡ በንፅፅር ጥቂት ስኬት ያስመዘገቡት ክላውዲዮ በየጨዋታው ቋሚ 11 መለዋወጣቸው ‹‹ፈላስፋው አሰልጣኝ›› አስብሏቸዋል፡፡

በመጀመሪያ ዓመታቸው ዊሊያም ጋላስ እና ፍራንክ ላምፓርድን አስፈርመው ለቡድኑ መሰረት የጣሉት ራኒዮሪ ከቼልሲ በተሰናበቱበት የመጨረሻው ዓመት ክለቡን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ እንዲሆን አስችለው ሩብ ፍፃሜ እንዲደርስ አድርገዋል፡፡

በወቅቱ እንግሊዝን በመወከል በቻምፒዮንስ ሊጉ የሚሳተፉ ክለቦች ቁጥር ሶስት ነበር፡፡ ማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል የመጀመሪያዎቹ ሁለት ደረጃዎች ያለማቋረጥ መቆናጠጣቸው እንዲሁም ሊቨርፑል እና ሌድስ ዩናይትድ እየተፈራረቁ ሶስት ደረጃ መያዛቸው ለራኒዮሪ ፈታኝ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ሆኖም ራኒዮሪ በቼልሲ ሁለተኛ ዓመታቸውን ከያዙ በኋላ እንግሊዝን በመወከል በአውሮፓ የሚሳተፉ ክለቦች ቁጥር ወደ አራት ከፍ አለ፡፡ ሆኖም ሊድስ ዩናይትድ በገንዘብ ችግር ምክንያት እየወረደ ሲመጣ ኒውካስል ዩናይትድ በቼልሲ ላይ የበላይነቱን ወሰደ፡፡

ቼልሲ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በቻምፒዮንስ ሊጉ መሳተፍ የቻለው በራኒዮሪ ሶስተኛ ዓመት የመጨረሻ ጨዋታ ሊቨርፑል በማሸነፍ ነበር፡፡ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ በታላቁ የአውሮፓ መድረክ በተሳተፈበት ዓመት የራሺያው ከበርቴ ሮማን አብራሞቪች ክለቡን ተረከቡ፡፡ ከፍተኛ ክፍያ ፈፅመውም ዳሚዬን ዳፍ፣ ሄርናን ክሬስፓ እና በሪያል ማድሪድ የተገፋውን ክሎድ ማኬሌሌን አስፈረሙ፡፡

Claudio+Ranieri+

ሆኖም አርሰናል ያለሽንፈት የሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ ቼልሲ የሊጉ ሻምፒዮን ማንቸስተር ዩናይትድ በልጦ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ መፈፀሙ የመሻሻሉ በጎ ምልክት ነበር፡፡ በ1965 የሊጉን ዋንጫ ካነሳ በኋላ ትልቁ ውጤት መሆኑ በበጎ ጎኑ ታይቷል፡፡

ራኒዬሪ በቼልሲ አራት ዓመት ከቆዩ በኋላ በአሰልጣኝ ጆዜ ሞውሪንሆ ተተክተው ከስታምፎርድ ብሪጅ ጋር ተለያዩ፡፡ ሆኖም በዚያ የውድድር ዘመን ሩብ ፍፃሜ ላይ አርሰናልን አሸንፈው ግማሽ ፍፃሜ መድረሳቸው አስደሳች ነበር፡፡ ጋላስ እና ላምፓርድን ማምጣታቸው በቀጣይ ለተመዘገበው ስኬት እጃቸው ነበረበት አስብሏል፡፡

ጣልያናዊው የእንግሊዝ ቆይታቸው አስደሳች ሊባል ይችላል፤ ጥሩ ሰብዕና አላቸው፡፡ ከሚዲያው ጋር ያላቸው ግንኙነት በወዳጅነት ስሜት የተሞላ ነው፡፡ የሞውሪንሆን ያህል የስኬት ታሪክ ባይኖራቸውም ቼልሲን ከተሰናበቱ በኋላ የላ ሊጋ እና ዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ባነሱት ራፋ ቤኒቴዝን ተክተው ቫሌንሲያን በድጋሚ ተረከቡ፡፡

በአዲሱ ክለባቸው የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫን ማንሳት ቢችሉም አራት ጣልያናውያን ተጨዋቾችን ማስፈረማቸው በደጋፊዎቹ ዘንድ አልተወደደላቸውም ነበር፡፡ ቫሌንሲያ ከምድቡ ማለፍ ተስኖት በቻምፒዮንስ ሊጉ በጊዜ ሲሰናበት፤ በዩሮፓ ሊግ በስቱዋ ቡካሪስት ሽንፈትን አስተናግዶ ከውድድሩ ውጭ ሆነ፣ ራኒዮሪም ለስንበት ተዳረጉ፡፡

ከሁለት ዓመት በኋላ አሰልጣኙ ፓርማን ተረከቡ፣ ታሪካውያን ክለብ በሴሪአው እንዲቆይ ማድረጋቸው በበጎ ጎን ሊታይ ቢችልም እዚያ ብዙም ሳይቆዩ ዲዲዬ ዴቮ ከሴሪ ቢ ወደ ሴሪ አው ያሳደገውን ጁቬንቱስ ተረከቡ፡፡

ከአንፃሩ በጁቬንቱስ የጨዋታ ማጭበርበር ቅሌት ምክንያት ሴሪ አውን በበላይነት የተቆጣጠረው ኢንተር ሚላን የራኒዮሪን ተቀናቃኝ ጆዜ ሞውሪንሆን ሾመ፡፡ በጁቬንቱስ ሁለት ዓመት ቆይተው ስኬት ማምጣት ያልቻሉት ክላውዲዮም ከኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡

የራኒዮሪ ጉዞ አሁንም ቀጥሏል፡፡

በቀጣይ ሮማ አና ኢንተር ሚላንን ቢረከቡም የተለየ ውጤት ማምጣት ተሳናቸው፡፡ በ2012 ሞናኮን ተረከቡ፤ የፈረንሳዩን ክለብ ከፈረንሳይ ሊግ ደ ወደ ፈረንሳይ ሊግ ኧ ማሳደግ ቻሉ፡፡ በ2014 በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ እንዲፈፅም ማድረግ ቢችሉም ክለቡ የውድድር ዓመቱ ሲጠናቀቅ ኮንትራታቸውን ሊያራዝም ፍላጎት አልነበረውም፡፡

ከፈረንሳይ መለስ ቀጣይ ጉዞዋቸው ወደ ግሪክ ሆነ፡፡ እዚያ ሁለት ዓመት ቆይተው የነበረ ቢሆንም ስንብታቸው አስደሳች አልነበረም፡፡ ከምንም በላይ በሜዳቸው በፋሮ ደሴቶች የደረሰባቸው ሽንፈት የስንብታቸው ዋነኛ ምክንያት ነበር፡፡

ከዘመናት ትዕግስት በኋላ ግን በሌይስተር ሲቲ ህልማቸውን ማሳካት ችለዋል፡፡ ሌይስተር ሲቲ ከሌሎች እርሳቸው ካሰለጠኗቸው ክለቦች በሙሉ ያነሰ ቢሆንም ከስኬት ጎዳና ተጉዘዋል፡፡ የ64 ዓመቱ አሰልጣኝ በ16 አጋጣሚዎች በአሰልጣኝንነት ካመሩ በኋላ በአውሮፓ እግርኳስ ታሪክ ምርጡን ውጤት ለማስመዝገብ ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል፡፡

ለራሳቸው ‹‹ክርስቶፎር ኮሎምበስ›› የሚል ስም የሰጡት አሰልጣኝ ማንም ግምት ያልሰጣቸውን ጂሚ ቫርዲ፣ ንጎሎ ካንቴ እና ሪያድ ማህሬዝን ለታላቅ ስኬት አብቅተዋል፡፡ የውድድር ዓመቱ ሲጀመር የ40 ነጥብ ግብ አስቀምጠው ዓላማቸው በሊጉ መቆየት እንደሆነ ያረጋገጡት ራኒዬሪ በመጨረሻም የሊጉ ሻምፒዮን በመሆን ክብር መቀዳጀታቸው በጣም ይገርማል፡፡

ሌይስተር ሲቲ ባለፈው ዓመት ከሊጉ ላለመውረድ በጣም ብዙ ታግሏል፡፡ አሰልጣኝ ናይጅል ፒርሰን እና ተጨዋቾቻቸው እጅግ በጣም ለፍተዋል፡፡ ያም ቢሆን ፒርሰን ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ ኃላፊነቱን ራኒዬሪ ተረክበዋል፡፡

‹‹በኦስትርያ የቅድመ ውድድር ዝግጅታችንን እየሰራን ይበልጥ ትኩረት አድርጎ ሲነግረን የነበረው ባለፈው ዓመት የተቸገርንበትን ምስጢር ማወቅ ነበር›› ይላል- ተከላካይ ክሪስቲያን ፋችስ፡፡ ‹‹በዚህ አካሄድ ሁሉም የቡድናችን ተጨዋቾች ፍፁም ደስተኛ ነበሩ፤ ይሄንን ቡድን በምን አይነት መልኩ መሻሻል እንደሚችል ነግሮን የራሱን የጨዋታ ፍልስፍና አስረዳን፤ የነገረን ነገር ቡድናችንን አሻሽለው፤ ይበልጥ እንዲረጋጋ አደረገው፤ ጣልያናዊ በመሆኑ መከላከል ይወድዳል››

ሌይስተር ሲቲ በሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ሰንደርላንድን 4-5 ካሸነፈ በኋላ ወደ ኋላ አልተመለሰም፡፡ በስምንተኛው ጨዋታ ቡድኑ 5-2 እስኪሸነፍ ድረስ ያለሽንፈት የተጓዘው የራኒዬሪ ቡድን ቀጥሎ በነበሩት 10 ጨዋታዎች ላይ በድጋሚ ሽንፈት ሳያስተናግድ ጉዞውን ቀጠለ፤ ይሄ ደግሞ የአሸናፊ ቡድኖች ምልክት ነው፡፡

ራኒዬሪ የተጨዋቾቻቸውን ኳሊቲ ከግምት ውስጥ አስገብተው የነደፉት ታክቲክ የስኬታቸው አንዱ ምክንያት ነው፡፡ በታክቲኩ ረገድ ከጣልያናዊውያን አሰልጣኞች ጋር ሲነፃፀሩ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡ ተደርገው ይታያሉ፡፡ ከጂዮቫኒ ትራፓቶኒ፣ አሪጎ ሳኪ እና ፋዚዮ ካፔሎ ጋር በጭራሽ አይነፃፀሩም፡፡ ከፊዮረንቲና የኮፓ ኢታልያ እንዲሁም በቫሌንሲያ የኮፓ ዴል ሬይ አንስተው ጥቂት መደነቅን ከመፍጠር ውጭ የስኬት ታሪክ አልነበራቸውም፡፡

በቼልሲ የመጨረሻ ዓመት ቆይታቸው ያስፈረሙት ክሎድ ማኬሌሌ የሰጣቸውን ግልጋሎት በሚገባ የተረዱት አሰልጣኝ ዘንድሮ ይሄንን ግልጋሎት በንጎሎ ካንቴ አግኝተዋል፡፡ ፈረንሳዊውን ‹‹አዲሱ ባትሪዬ›› ብለው ገልፀውታል፡፡ በአማካይ ተከላካይ ቦታ ለዚህ ተጨዋች ትልቁን ኃላፊነት የሰጡት ስዊዘርላንዳዊውን ጎክሃን ኢንለርን ችላ ብለው መሆኑ ደግሞ በጣም ይገርማል፡፡

በአጥቂ ቦታ ላይ ለቫርዲ የሰጡት ኃላፊነት በመጨረሻም ተጠቃሚ አድርጓቸዋል፡፡ እንግሊዛዊው ሳይጠበቅ ያለማቋረጥ በ11 ተከታታይ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ጎል በማስቆጠር በሩድ ቫን ኒስቴልሮይ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ አሻሽሏል፡፡

የተከላካይ መስመሩ ደግሞ በጣም ይገርማል፡፡ ቬዝ ሞርጋን፣ ሮበርት፣ ሁዝ፣ ካስፐር ሺማይክል እና ፋችስን የያዘ ነው፡፡ እነኚህ ተከላካዮች እጅግ ታታሪክ ናቸው፡፡ ቀድ የሚመጣውን አደጋ ማሽተት ይችላሉ፡፡

ሌይስተር ሲቲ ስዋንሲ ሲቲን 4-0 ካሸነፈ በኋላ የሰጡት አስተያየት ቡድናቸው ስኬታማ የውድድር ዓመት እያሳለፈ የሚገኝበትን ምስጢር ማወቅ ይችላል፤ ‹‹ተጨዋቾቹን ሁልጊዜ ቢሆን የዚህ አይነት ብቃት እንዲያሳዩ እጠይቃቸዋለሁኝ፤ ዕድል ያላቸው የረሃብ ስሜት እንዲጨምር፣ ጠንካራ እና በከፍተኛ ደረጃ ተጭነው እንዲጫወቱ ነግሬያቸው ነበር፤ ይኼንንም በሚገባ አሳክተዋል›› ብለው ተጨዋቾቻቸውን አወድሰዋል፡፡

የራኒዬሪ እቅድ እና ፍላጎት ግልፅ ነው፡፡ ተጨዋቾቹም የአሰልጣኙን ምክር ይሰማሉ፤ ይሄ ከሆነ ደግሞ የፈተናው 50 በመቶ ተቀርፏል ወደሚል ድምዳሜ ያደርሰናል፡፡

በ2004 ቼልሲ በቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ በሞናኮ ደርሶ መልስ ውጤት ተሸንፎ ፍፃሜ ለመግባት የነበረው ህልም ባልተሳካበት አጋጣሚ ትልቅ ትምህርት የቀሰሙት ራኒዬሪ አሁን ከስህተታቸው በጣም ብዙ ነገሮችን ተምረዋል፡፡ በቋሚ አሰላለፍ 27 ጊዜ ለውጥ ያደረጉት አሰልጣኝ አሁን ከተጨዋቾቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት በጣም ያስቀናል፡፡

በፒርሰን ዘመን የነበረውን በሶስት ተከላካዮች የመከላከል ታክቲክ በአራት ተከላካዮች ተክተዋል፡፡ ይሄ ውሳኔ የተከላካይ መስመሩን አሻሽሎታል፡፡ በመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ጎሉን አለማስደፈር ያልቻለው የተከላካይ መስመሩ ካለፉት 17 ጨዋታዎች በ12 ያህሉ ጎል ተቆጥሮበታል፡፡

‹‹በምን አይነት መልኩ በሊጉ መቆየት እንዳለብን ነግሮናል፡፡ በታክቲክ ጉዳዮች ላይ የነበረው ብቃት በጣም ይገርማል›› ይላል ሞርጋን፡፡

ጎሎችን ከተለያየ አቅጣጫ የሚያስቆጥረው የራኒዬሪ ቡድን የቫርዲ ጥገኛ ነው ቢባልም እንግሊዛዊው ባልተሰለፈባቸው ስድስት ጨዋታዎች በአምስቱ አሸንፏል፡፡ በአንዱ አቻ ተለያይቷል፤ ከቫርዲ ውጭ ማህራዝን አለማንሳት በጣም ከባድ ነው፡፡ 17 ጎሎችን አስቆጥሮ 11 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ያቀበለው አልጀርያዊው ኮከብ የፒኤፍኤ አሸናፊ ሆኗል፡፡ በአጠቃላይ በሌይስተር ሲቲ የዘንድሮ የስኬት ጉዞ የራኒዬሪ የጨዋታ እቅድ ተጨዋቾችን የመቆጣጠር ብቃት እና የቡድን ህብረት የፈጠሩበት መንገድ ትኩረትን እንዲስብ አድርጓል፡፡ አሁን ትኩረቱ በሙሉ ሌይስተር ሲቲ እና ራኒዬሪ ላይ አርፏል፡፡

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት መምህር ግርማ በድርቅ ለተጎዱት ወገኖች ከሚሊዮን ብር በላይ ረዱ

$
0
0


memihir grma

(ዘ-ሐበሻ) በቅርቡ ከተከሰሱባቸው ክሶች በዋስትና የተፈቱት መልዐከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በድርቅ ለተጎዱት ወገኖች መርጃ የሚሆን ገንዘብ በ እርዳታ መልክ ሰጡ::

መምህሩ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በኩል ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሁለት ሚሊዮን አርባ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ሁለት ብር ከሃምሳ ዘጠኝ ሳንቲም (2,048,892.59) ዛሬ ገቢ አድርገዋል::

 

የኢየሩሳሌም ተስፋው ደብዳቤ ከቃሊቲ እስር ቤት –ግንቦት 7

$
0
0

ግንቦት 7

ከእየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት)

(እየሩሳሌም ተስፋው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ስትሆን፣ በነብርሃኑ ተክለያሬድ መዝገብ ‹ግንቦት 7›ን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው አሁን የመከላከያ ምስክር ለማስደመጥ በቀጠሮ ላይ ናቸው፡፡ እየሩሳሌም ተስፋው ይህንን ደብዳቤ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት በግንቦት 7፣ 2008 እንዲታተም ያወጣችው ቢሆንም፤ በተለያዩ እንቅፋቶች በዕለቱ ለሕዝብ ሳይደርስላት ቀርቷል፡፡) 

eyerusalem

(የ እጅ ጽሁፏን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ) ይህቺ ቀን ከዛሬ 11 ዓመት በፊት በ1997 ዓ.ም. በዕለተ እሁድ ኢትዮጵያ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን ለመረጠው ፓርቲ ሊሰጥ የተሰለፈበት ዕለት ነበረች፡፡ ሕወሓት/ኢሕአዴግ እስቲ እንያቸው ምን ያመጣሉ በማለት ከዛ በፊትም ከዛ በኋላም ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ የምርጫ ምኅዳሩን ገርበብ አድርጎ ከፍቶ በሩን አልፈው እንዲገቡ ፈቀደላቸው፡፡ በዛች በር ገብተው ብዙ ነገር ሠሩ፡፡ በውጭ ሚዲያ ላይ እምናውቀውን hard talk በአገራችን ላይ በአገራችን ሚዲያ ለማየት በቃን ተስፋችንም ለመላው ይህ ትውልድ ታሪካዊ (ዕድለኛ) ትውልድ ነው አልን፡፡ ለአገራችን ታሪከ ለመጀመሪያ ጊዜ በመረጥነው መንግሥት ልንተዳደር ነው፡፡ በሠላማዊ መንገድ (በምርጫ) የመንግሥት ለውጥ ልናይ ነው እያልን ስንደሰት ወዲያው በዛች ቀን ምሽት ምርጫው ተጠናቆ ወደቆጠራው ሲገባ ሕወሓት/ኢሕአዴግ አልበዛም?! በሚል መልኩ እስርና ግድያውን ጀመረ፡፡ ብዙ ሺሕ ዜጎቻችንን እንደቀልድ አጣናቸው፡፡ በአልሞ ተኳሽ ግንባር ግንባራቸውን እየተባሉ በየደጃፋችን ተደፍተው ቀሩ፡፡ ኮሎኔል መንግሥ?ቱ ኃ/ማርያም ከዛሬ ጀምሮ ብሎ – መስቀል አደባባይ ላይ ቀይ ሽብርን እንዳወጀ – ታሪክ ራሱን ደገመና ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ዕዝ ስር በማለት የሞቱን ዐዋጅ ዐወጀ፡፡

ትዝ ይለኛል የዛሬ 3 ዓመት አካባቢ 2006 ላይ ሰኔ 3፣ 1997 ዓ.ም. በግፍ የተገደሉትን ንፁኃን ዜጎች ለማሰብ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ተሰባስበን ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እንባቸው በጉንጮቻቸው እየወረደ ‹የማይታመን አምነን ወገኖቻችን አለቁ፡፡ ሰው እንዴት መለስን ያምናል? እንዴት ሕወሓት/ኢሕአዴግ ይታመናል?› እያሉ በቁጭት የተናገሩት ትዝ አለኝ፡፡ አዎ፣ የማይታመነውን አምባገነን በዚች ዕለት ወገኖቻችን የጥይት ራት ሆኑ!! እነሆ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሠላማዊ ትግል በር ተዘጋ ብለው ያመኑ ድምፃቸው የታፈኑ መብታቸው የተረገጠ ንፁኃን ዜጎች እንዲሁም ከዚህ ቀን በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ሠላማዊ ትግል ተዘጋ ሲሉ ግንቦት 7 አሉት፡፡ ይህ ሕዝባዊ ኃይል የተመሠረተበት ዋናው ዓላማ የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ በሃገር ወዳድና ለሕዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች ምሁራንና ዜጎች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይልን መሠረቱ፡፡ ይህ ሕዝባዊ ኃይል ሰንቆ የተነሳው ራዕይ “የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠበት የዜጎች መብቶች፣ አገራዊ አንድነት፣ ደኅንነትና ጥቅም የተከበሩባት ጠንካራና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ሆና ማየት” ሲሆን ተልዕኮው ደግሞ “መንግሥትን በኃይል የማስወገድ ሠላማዊና የሥልጣን ሽግግር በአገሪቱ እንዲኖር የማስቻል እና ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነጻ እና ጠንካራ ብቃት ያላቸው ሕገ-መንግሥታዊ የመከላከያ የፖሊስና የደኅንነት ተቋማት እንዲኖሩ ማድረግ” ነው፡፡

Eyerusalemነገር ግን ሕወሓት/ኢሕአዴግ ለሕዝብ ድምፅ ሥልጣን ላይ የወጣ ፓርቲ አይደለምና በየዕለቱ የሚፈጠረው ኮሽታ ስለሚያስበረግገው እንዲሁም ንፁኃንን ለማሰር እና ለመግደል ምክንያት ይፈልግ ነበርና ይህ ሕዝባዊ ኃይል እንደተመሠረተ “ሽብርተኛ” ስለፈረጀው መስራቾቹን እንዲሁም ወደሃገር እንዲገቡ የማይፈልጋቸውን ተቃዋሚዎች በዚህ አጋጣሚ “አሸባሪዎች” ሲል ፈረጃቸው፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላም ለሥልጣኔ ያሰጉኛል ያላቸውን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሲቪክ ማኅበራት አመራሮች፣ ጦማሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች በአጠቃላይ ለም ብለው ጥያቄ እሚያነሱ ዜጎችን ግንቦት 7 በማለት በየወኅኒው እያሰራቸው ይገኛል፡፡

እንግዲህ ይህ ሕዝባዊ ኃይል ከላይ እንደገለጽኩላችሁ አሸባሪ ሊያሰኘው የሚችል ዓላማ፣ ራዕይም ሆነ ተልዕኮ የለውም፡፡ ለሠላማዊ መንገድ የተነጠቀውን መብቱን በሁለገብ ትግል ለማስከበር ዓልሞ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ ሠላማዊ ትግል ብቻውን ሕወሓት/ኢሕአዴግ ከወንበሩ እንደማያነቃንቀው እስካሁን የታዩት ሙከራዎች በቂ ናቸው ለዚህም ነው በዚህ ሰዐት ብዙ ወጣቶች ይህን ሕዝባዊ ኃይል በቆራጥነት እየተቀላቀሉት የሚገኙት፡፡

ሕወሓት/ኢሕአዴግ ባወጣው የፀረ-ሽብር ዐዋጅ (በነገራችን ላይ ይህን የፀረ-ሽብር ዐዋጅ ልብ ብላችሁ ካያችሁት ሕወሓት/ኢሕአዴግ ለራሱ ያወጣው ይመስላል፡፡ ለምሳሌ ሽብር በሌለበት ሽብር መንዛት አሸባሪነት ነው ይላል፡፡ ታዲያ በአገር ሠላም፣ በጠራራ ፀሐይ ቦንብ አፈነዱ እያለ documentary የሚሠራ ሕወሓት እንጂ ግንቦት 7 ነው እንዴ? በተረፈ ሁሉንም አንቀፆች ተመለከቷቸው ከግንቦት 7 ይልቅ ለሕወሓት ይቀርባሉና ገና ጫካ እያሉ የሕዝብን ተቀባይነት ለማግኘት ሲሉ በገዛ ሕዝባቸው (በሓውዜን) ላይ የጀመሩት እልቂት በደርግ ማሳበብ፣ አሁንም ከ25 ዓመት በኋላ ሳይቀነስ ሳይጨመር እንዳለ ነው፡፡ አሸባሪ ማነው?

እንግዲህ ይህ ሁሉ የተፈፀመው በዚህች ዕለት ነው፡፡ “ግንቦት 7” ይህቺ ቀን የትናንት አሰቃቂ ትዝታችን የዛሬ ክሳችን የነገ ተስፋችን ናት፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያልተማረ ዜጋ አይገኝም፡፡ ሁሉም ነጻነትን ይናፍቃል፡፡ ነጻ ለመውጣት ግን ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ይፈራል፡፡ የሆነ አካል መጥቶ ነጻ እንዲያወጣው ይፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን አይችልም፡፡ ነጻ ለመውጣት መጀመሪያ ራስን ከታሰሩበት የፍርሓት እስር ነጻ በማውጣት ትግሉን መቀላቀል ነው፡፡ ድርጅታችን ግንቦት 7 ለነጻነት፣ ለፍትሕና ለዴሞክራሲ የተቋቋመ ነጻ አውጪ ድርጅት እንጂ አሸባሪ አይደለም፡፡ ስለዚህ በድፍረት እናገራለሁ፡፡ እኔ ግንቦት 7 ነኝ፤ እናንተስ? ሁሌም እንደምለው የታሰረው አካሌ እንጂ ልቤ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው፡፡ ይህቺ ቀን ለብዙዎች ሞት፣ አካል መጉደል፣ እስራት አብቅታለች፡፡ መራራውን ሳያልፉ ጣፋጭ፤ ሳይሞቱ ትንሳኤ የለምና ባለፈው ከመፀፀት ባለፈ እልህ አስይዞን ይህንን ዘረኛና አምባገነን የሽፍታ ቡድን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መንግለን ለመጣል እንዘጋጅ፡፡ ከላይ እንዳልኩት የትላንት ጥቁር ጠባሳ፣ የዛሬ ግርፋትና እስራት፣ የነገ ተስፋ ናትና እንኳን ለዚች ቀን አደረሳችሁ፡፡ ይህች ቀን፣ የነጻነት እንዲሁም የድል ቀናችን እንደምትሆን አልጠራጠርም፡፡ ግንቦት 20 በግንቦት 7 እንደመስሰዋለን!!

የነጻነት ታጋዩ ጀግናው አንዳርጋቸው ፅጌ አንድ ጊቢ ብንኖርም መገናኘት አልቻልንም፡፡ እንኳን አካልህን ወሬህንም በስንት ስቃይ ነው፡፡ እምሰማው ያንተ መታፈን ወያኔ እንደጠበቀው ትግሉን አላሽመደመደውም፡፡ እንደውም፣ ይበልጥ አጦዘው ለኛ ከቤት መውጣት ምክንያት አንተ ነህ፡፡ እኛ የአንተ ፍሬዎች ነን፡፡ ዛሬ ታፍነህ ቀንና ሌሊቱን መለየት የማትችልበት ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም የነጻነት ቀን ቀርባለችና እስከዛው ዕድሜህን ያርዝምልን፡፡

“የትግላችን መሰረት ህዝባችን ነው እና ህዝባችንን ተደራሽ ለማድረግ የምናደገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል!”–ድምጻችን ይሰማ

$
0
0

ረቡእ ግንቦት 10/2008
ትግል ክስተት ሳይሆን ሂደት ነው፡፡ ይህን ሂደት የሚፈጥሩትም ሆነ ከዳር የሚያደርሱት ደግሞ የትግሉ ባለቤት የሆኑት ህዝቦች ናቸው፡፡ እንደአገራችን ባሉ ዲሞክራሲ ባልዳበረባቸው አገራትና አሁን ባለው አለም አቀፍ ተለዋዋጭ ፓለቲካ የትግል ሂደት እንደ ሜዳ ለጥ ያለና የተደላደለ አይደለም፡፡ እንቅፋትና አሜኬላ የበዛበት፣ በዳገትና ቁልቁለት የተሞላ ነው፡፡ የትግሉ ባለቤቶች በእነዚህ የትግል ተፈጥሯዊ ሂደቶች ውስጥ ሲያልፉ የሚኖራቸው ምላሽ እንደግለሰባዊ ጥንካሬያቸው፣ ለትግሉ እንዳላቸው እምነት፣ እንደ ልምድና እንደተሞክሯቸው ይለያያል፡፡ ጥቂት ነገሮች ውዥንብር የሚፈጥርባቸው እንዳሉ ሁሉ በፕሮፓጋንዳ እና በአሉባልታ ቀርቶ በኃይልም የማይፈቱ ቆራጥ ታጋዮች በርካቶች ናቸው፡፡

zehabesha-muslim.jpg
የአንድ የትግል ሂደት ከሚገጥሙት ተግዳሮቶች መካከል የብዙሀኑን ህዝብ ስሜት ከነባራዊው ሁኔታ ጋር በማጣጣም ትግሉን ስኬታማ የሚያደርግ የትግል አቅጣጫ መንደፍ ነው፡፡ ይህን የትግል አቅጣጫም የትግሉ ባልተቤት የሆነው ህዝብ በሚገባ ሊረዳው ይገባል። የትግሉን አቅጣጫ ህዝብ በትክክል ካልተረዳው ትግሉን ከዳር ማድረስ አስቸጋሪ ይሆናል። የትግሉ አቅጣጫ በትክክል ለህዝብ ባልደረሰበት ሁኔታ በትግሉ እና በደል በሚፈጥረው ህዝባዊ ቁጭት፣ ይህም በተራው በሚወልደው የህዝብ ስሜት መካከል ክፍተት ይፈጠራል፡፡ አንድ ህዝባዊ ትግል በቀዳሚነት ከሚይዛቸው ተግባራት መካከል የትግልን ሂደት እና አቅጣጫ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ታጋዩ ህዝብ ዘንድ ማድረስ እና ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማከናወን እና ህዝባዊ መነቃቃትንም መፍጠር አንዱ እና ወሳኙ ጉዳይ ነው። በተለይም ትግሉ የረጅም ጊዜ ትግል በሆነበት ተጨባጭ ከህዝብ ልብ ውስጥ አስጠብቆ ማቆየት እና የህዝብን ወኔ በበዳዮች ብትር ብዛት እንዳይሰበር ተከታታይ እና ቋሚ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራን መስራት የትግሉን ህልውና ማስጠበቂያ አንዱ መሳሪያ ተደርጎ ሊታይ ይችላል።
ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በመንግስት የተጫነብንን ብሄራዊ ጭቆና በዘላቂነት ለማስወገድ የሚያስችል የትግል አቅጣጫ አስምረን እንገኛለን። ይህ ትግላችን ጨቋኙ ስርዓት ትግስታችን እንዲሟጠጥ፣ ወኔያችን እንዲሰበር በማቀድ በሚከፍታቸው በሮች ውስጥ የሚያስገባ፣ ከተመከረበትና ከታሰበበት የትግል መስመር ወጥተን ግብታዊነትን ወይም ስሜታዊነትን እንድንከተል የሚያደርግ፣ ሁሉን አቀፍ በሆነ መብት የማስከበር ትግል ፋንታ ጥቃቅን ቀዳዳዎችን ብቻ በሚደፍኑ ጊዜያዊ የትግል ስልቶች ተሸብበን እንድንቀር የሚያደርግ ሂደትን የሚከተል አይደለም። ትግላችን የህዝብን ፍላጎት የተረዳ፣ ተለዋዋጭ ስሜትን ከነባራዊ ሁኔታው ጋር በማዛመድ እና ሚዛኑን በመጠበቅ ከጊዜያዊ ክስተቶች ይልቅ መርሆች ላይ የተመረኮዘ ነው። ትግላችን ወቅታዊ እና ተጫባጩን የሚያውቅ፣ የግንዛቤ አድማሱ ሰፊ የሆነ፣ የሚጠበቅበትን የተገነዘበ፣ የትግሉን ሂደትና ፍሰት በሚገባ የተረዳ፣ የአገሩን እና የማህበረሰቡን አብይ ችግሮች በመለየት ለችግሮቹ ተጨባጭ መፍትሄ የማስቀመጥ አቅም ያለው፣ እምነቱን በትክክል ተረድቶ ተግባራዊ የሆነ እና የሰለጠነ ማህበረሰብ በመፍጠር ሙሉ መብታችንን የምንጎናፀፍበት እና ይህንም በዘላቂነት የምናስጠብቅበት ትግል ነውና አቋራጭ መንገድ የለውም!

muslim a
የትግል አቅጣጫችን ራሳችንን በማጎልበት እና በመንግስት ላይ ጫና ሊፈጥሩ የሚችሉ ተለዋዋጭ ስልቶችን ቀርፆ ተግባራዊ ከማድረግ ባልተናነሰ የህዝቡን ግንዛቤ ከትግሉ አቅጣጫ ጋር ተመቻማች እንዲሆን ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት። ለትግላችን ስኬታማነት የተነደፈው የትግል አቅጣጫ ብቻውን በቂ አይደለም። ይህንን የትግል አቅጣጫ ተግባራዊ የሚያደርገው ህዝብ አቅጣጫውን በትክክል ተረድቶ፣ ይህንንም ጠብቆ እና አስጠብቆ በሚያደርገው የትግል እንቅስቃሴ ጭምር መሆኑንም በትክክል እንረዳለን።
በቀጣይ የትግል አቅጣጫችን እና ከህብረተሰባችን የሚጠበቀውን አስተዋጾ በተመለከተ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ እነዚህን ስራዎች ህዝብ ጋር ለማድረስ ያሉን አማራጮች ውስን በመሆናቸው ማህበራዊ ድህረ-ገፅን በጊዜያዊ አማራጭነት ለመጠቀም ተገደናል። በዚህም ምክንያት አስፈላጊ የሆኑ ርእሶች በፅሁፍ ሲዳሰሱ ቆይተዋል። ይህ ግን ብዙሃኑን ህዝብ ለመድረስ አላስቻለንም። ችግሩ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ቁጥር አናሳነት ብቻ እንዳለመሆኑ መጠን ማህበራዊ ሚዲያ ለመጠቀም እድሉ ያለው ህብረተሰባችንም መልእክቱን ሊያገኝ የሚችልባቸውን መንገዶችን ማመቻቸት እና አማራጮችንም ማቅረብ ያስፈልጋል። በዚህ ዙሪያ በቀጣይ ሰፊ ስራ ይጠብቀናል። በመሆኑም እስካሁን ከምናስተላልፋቸው የፅሁፍ መልዕክቶች ባሻገር በተለያዩ ርዕሶችና የትግል አቅጣጫችን ዙሪያ ሳምንታዊ የድምፅ መልዕክቶችን መጀመር ቀዳሚ አማራጭ እና ለቀጣይ ስራ አጋዥ ተደርጎ ተወስዷል። ከዚህ አንጻር እስካሁን በጽሁፍ የተለቀቁ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ጨምሮ ተከታታይ መልእክቶችን በቅርቡ በአላህ ፍቃድ በድምጽም የምናደርስ ይሆናል። ይህ ጅምር በሙያው ችሎታ እና ፍላጎት ያላቸው እህትና ወንድሞች ለትግሉ ቀጥተኛ አስተዋጾ ለማድረግ የሚያስችል አንድ በር ነው እና ይህን ሀላፊነታችንን ሁላችንም እንወጣ ዘንድ በአጽንኦት እንጠይቃለን።
ትግላችን በተጠናከረ መልኩ ሁሉን አሳታፊ ሆኖ ይቀጥላል!
ብሄራዊ ጭቆናን አንሽከምም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!


በቦሌ ቡልቡላ ቤታችን አይፈርስም ያሉ ወገኖች የፌደራል ፖሊሶች ጥይት ራት ሆኑ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶው ቦሌ ቡልቡላ በተሰኘው አካባቢ በሕገወጥ መንገድ ተሰርተዋል በሚል የፌደራል ፖሊሶች እና የአካባቢው አፍራሽ ግብረሃይል ዛሬ ጠዋት ቤቶችን ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ ከአካባቢው ሕዝብ ጋር በተነሳ ግጭት በርካቶች መቁሰላቸውና ህጻናት ሳይቀሩ መሞታቸው ተዘገበ::

ቦሌ ቡልቡላ (ፎቶ ከፋይል)

ቦሌ ቡልቡላ (ፎቶ ከፋይል)

ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች እንደሚያመለከቱት “ከቤታችን ወዴት እንሂድ?” ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊሶች እና በአፍራሽ ግብረሃይሉ ቤታቸው ሊፈርስባቸው ሲዘጋጁ ግጭቱ ጀምሯል:: ከዚያም የፌደራል ፖሊሶች ወደሕዝቡ የተኮሱ ሲሆን እስካሆን በግምት 9 ወይም 10 የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉና ሌሎችም በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል:: ቤቶችም መፍረሳቸውን ቀጥለዋል::

ምንጮች እንደሚሉት በኦሮሚያ ሕዝባዊው አመጽ ከተነሳ በኋላ ፌደራል ፖሊሶች ለህዝብ ተቃውሞ ምንም ዓይነት ሰላማዊ ምላሽ መስጠት አቁመዋል:: በቀጥታ ወደ ሕዝብ መተኮስ የጀመሩ ሲሆን ዛሬም ቤታችንን አታፍርስ; እኛን አፈናቅላችሁ መሬቱን አትሽጡ ባሉ ወገኖች ላይ ምላሹ ጥይት መሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ሕዝቡ በፌደራል ፖሊሶቹ ላይም ጥቃት ማድረሱን መረጃዎች የሚጠቁሙ ሲሆን ዘ-ሐበሻ ምን ዓይነት ጉዳት በፖሊሶቹና አፍራሽ ግብረሃይሉ ላይ እንደደረሰ ለማጣራት ያደረገችው ጥረት አልተሳካም::

በአካባቢው ያለው ውጥረት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ እንዳየለ ነው:: ጉዳዩን ተከታትለን ለመዘገብ እንሞክራለን::

“የታሰረው አካሌ እንጂ ልቤ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው”–እየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት)

$
0
0

ግንቦት 7

ከእየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት)

(እየሩሳሌም ተስፋው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ስትሆን፣ በነብርሃኑ ተክለያሬድ መዝገብ ‹ግንቦት 7›ን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው አሁን የመከላከያ ምስክር ለማስደመጥ በቀጠሮ ላይ ናቸው፡፡ እየሩሳሌም ተስፋው ይህንን ደብዳቤ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት በግንቦት 7፣ 2008 እንዲታተም ያወጣችው ቢሆንም፤ በተለያዩ እንቅፋቶች በዕለቱ ለሕዝብ ሳይደርስላት ቀርቷል፡፡) 

Eyerusalem-Tesfaw

(የ እጅ ጽሁፏን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ) ይህቺ ቀን ከዛሬ 11 ዓመት በፊት በ1997 ዓ.ም. በዕለተ እሁድ ኢትዮጵያ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን ለመረጠው ፓርቲ ሊሰጥ የተሰለፈበት ዕለት ነበረች፡፡ ሕወሓት/ኢሕአዴግ እስቲ እንያቸው ምን ያመጣሉ በማለት ከዛ በፊትም ከዛ በኋላም ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ የምርጫ ምኅዳሩን ገርበብ አድርጎ ከፍቶ በሩን አልፈው እንዲገቡ ፈቀደላቸው፡፡ በዛች በር ገብተው ብዙ ነገር ሠሩ፡፡ በውጭ ሚዲያ ላይ እምናውቀውን hard talk በአገራችን ላይ በአገራችን ሚዲያ ለማየት በቃን ተስፋችንም ለመላው ይህ ትውልድ ታሪካዊ (ዕድለኛ) ትውልድ ነው አልን፡፡ ለአገራችን ታሪከ ለመጀመሪያ ጊዜ በመረጥነው መንግሥት ልንተዳደር ነው፡፡ በሠላማዊ መንገድ (በምርጫ) የመንግሥት ለውጥ ልናይ ነው እያልን ስንደሰት ወዲያው በዛች ቀን ምሽት ምርጫው ተጠናቆ ወደቆጠራው ሲገባ ሕወሓት/ኢሕአዴግ አልበዛም?! በሚል መልኩ እስርና ግድያውን ጀመረ፡፡ ብዙ ሺሕ ዜጎቻችንን እንደቀልድ አጣናቸው፡፡ በአልሞ ተኳሽ ግንባር ግንባራቸውን እየተባሉ በየደጃፋችን ተደፍተው ቀሩ፡፡ ኮሎኔል መንግሥ?ቱ ኃ/ማርያም ከዛሬ ጀምሮ ብሎ – መስቀል አደባባይ ላይ ቀይ ሽብርን እንዳወጀ – ታሪክ ራሱን ደገመና ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ዕዝ ስር በማለት የሞቱን ዐዋጅ ዐወጀ፡፡

ትዝ ይለኛል የዛሬ 3 ዓመት አካባቢ 2006 ላይ ሰኔ 3፣ 1997 ዓ.ም. በግፍ የተገደሉትን ንፁኃን ዜጎች ለማሰብ በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ተሰባስበን ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እንባቸው በጉንጮቻቸው እየወረደ ‹የማይታመን አምነን ወገኖቻችን አለቁ፡፡ ሰው እንዴት መለስን ያምናል? እንዴት ሕወሓት/ኢሕአዴግ ይታመናል?› እያሉ በቁጭት የተናገሩት ትዝ አለኝ፡፡ አዎ፣ የማይታመነውን አምባገነን በዚች ዕለት ወገኖቻችን የጥይት ራት ሆኑ!! እነሆ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሠላማዊ ትግል በር ተዘጋ ብለው ያመኑ ድምፃቸው የታፈኑ መብታቸው የተረገጠ ንፁኃን ዜጎች እንዲሁም ከዚህ ቀን በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ሠላማዊ ትግል ተዘጋ ሲሉ ግንቦት 7 አሉት፡፡ ይህ ሕዝባዊ ኃይል የተመሠረተበት ዋናው ዓላማ የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ በሃገር ወዳድና ለሕዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች ምሁራንና ዜጎች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይልን መሠረቱ፡፡ ይህ ሕዝባዊ ኃይል ሰንቆ የተነሳው ራዕይ “የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠበት የዜጎች መብቶች፣ አገራዊ አንድነት፣ ደኅንነትና ጥቅም የተከበሩባት ጠንካራና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ሆና ማየት” ሲሆን ተልዕኮው ደግሞ “መንግሥትን በኃይል የማስወገድ ሠላማዊና የሥልጣን ሽግግር በአገሪቱ እንዲኖር የማስቻል እና ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ያልወገኑ ነጻ እና ጠንካራ ብቃት ያላቸው ሕገ-መንግሥታዊ የመከላከያ የፖሊስና የደኅንነት ተቋማት እንዲኖሩ ማድረግ” ነው፡፡

Eyerusalemነገር ግን ሕወሓት/ኢሕአዴግ ለሕዝብ ድምፅ ሥልጣን ላይ የወጣ ፓርቲ አይደለምና በየዕለቱ የሚፈጠረው ኮሽታ ስለሚያስበረግገው እንዲሁም ንፁኃንን ለማሰር እና ለመግደል ምክንያት ይፈልግ ነበርና ይህ ሕዝባዊ ኃይል እንደተመሠረተ “ሽብርተኛ” ስለፈረጀው መስራቾቹን እንዲሁም ወደሃገር እንዲገቡ የማይፈልጋቸውን ተቃዋሚዎች በዚህ አጋጣሚ “አሸባሪዎች” ሲል ፈረጃቸው፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላም ለሥልጣኔ ያሰጉኛል ያላቸውን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሲቪክ ማኅበራት አመራሮች፣ ጦማሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች በአጠቃላይ ለም ብለው ጥያቄ እሚያነሱ ዜጎችን ግንቦት 7 በማለት በየወኅኒው እያሰራቸው ይገኛል፡፡

እንግዲህ ይህ ሕዝባዊ ኃይል ከላይ እንደገለጽኩላችሁ አሸባሪ ሊያሰኘው የሚችል ዓላማ፣ ራዕይም ሆነ ተልዕኮ የለውም፡፡ ለሠላማዊ መንገድ የተነጠቀውን መብቱን በሁለገብ ትግል ለማስከበር ዓልሞ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ ሠላማዊ ትግል ብቻውን ሕወሓት/ኢሕአዴግ ከወንበሩ እንደማያነቃንቀው እስካሁን የታዩት ሙከራዎች በቂ ናቸው ለዚህም ነው በዚህ ሰዐት ብዙ ወጣቶች ይህን ሕዝባዊ ኃይል በቆራጥነት እየተቀላቀሉት የሚገኙት፡፡

ሕወሓት/ኢሕአዴግ ባወጣው የፀረ-ሽብር ዐዋጅ (በነገራችን ላይ ይህን የፀረ-ሽብር ዐዋጅ ልብ ብላችሁ ካያችሁት ሕወሓት/ኢሕአዴግ ለራሱ ያወጣው ይመስላል፡፡ ለምሳሌ ሽብር በሌለበት ሽብር መንዛት አሸባሪነት ነው ይላል፡፡ ታዲያ በአገር ሠላም፣ በጠራራ ፀሐይ ቦንብ አፈነዱ እያለ documentary የሚሠራ ሕወሓት እንጂ ግንቦት 7 ነው እንዴ? በተረፈ ሁሉንም አንቀፆች ተመለከቷቸው ከግንቦት 7 ይልቅ ለሕወሓት ይቀርባሉና ገና ጫካ እያሉ የሕዝብን ተቀባይነት ለማግኘት ሲሉ በገዛ ሕዝባቸው (በሓውዜን) ላይ የጀመሩት እልቂት በደርግ ማሳበብ፣ አሁንም ከ25 ዓመት በኋላ ሳይቀነስ ሳይጨመር እንዳለ ነው፡፡ አሸባሪ ማነው?

እንግዲህ ይህ ሁሉ የተፈፀመው በዚህች ዕለት ነው፡፡ “ግንቦት 7” ይህቺ ቀን የትናንት አሰቃቂ ትዝታችን የዛሬ ክሳችን የነገ ተስፋችን ናት፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያልተማረ ዜጋ አይገኝም፡፡ ሁሉም ነጻነትን ይናፍቃል፡፡ ነጻ ለመውጣት ግን ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ይፈራል፡፡ የሆነ አካል መጥቶ ነጻ እንዲያወጣው ይፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን አይችልም፡፡ ነጻ ለመውጣት መጀመሪያ ራስን ከታሰሩበት የፍርሓት እስር ነጻ በማውጣት ትግሉን መቀላቀል ነው፡፡ ድርጅታችን ግንቦት 7 ለነጻነት፣ ለፍትሕና ለዴሞክራሲ የተቋቋመ ነጻ አውጪ ድርጅት እንጂ አሸባሪ አይደለም፡፡ ስለዚህ በድፍረት እናገራለሁ፡፡ እኔ ግንቦት 7 ነኝ፤ እናንተስ? ሁሌም እንደምለው የታሰረው አካሌ እንጂ ልቤ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው፡፡ ይህቺ ቀን ለብዙዎች ሞት፣ አካል መጉደል፣ እስራት አብቅታለች፡፡ መራራውን ሳያልፉ ጣፋጭ፤ ሳይሞቱ ትንሳኤ የለምና ባለፈው ከመፀፀት ባለፈ እልህ አስይዞን ይህንን ዘረኛና አምባገነን የሽፍታ ቡድን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መንግለን ለመጣል እንዘጋጅ፡፡ ከላይ እንዳልኩት የትላንት ጥቁር ጠባሳ፣ የዛሬ ግርፋትና እስራት፣ የነገ ተስፋ ናትና እንኳን ለዚች ቀን አደረሳችሁ፡፡ ይህች ቀን፣ የነጻነት እንዲሁም የድል ቀናችን እንደምትሆን አልጠራጠርም፡፡ ግንቦት 20 በግንቦት 7 እንደመስሰዋለን!!

የነጻነት ታጋዩ ጀግናው አንዳርጋቸው ፅጌ አንድ ጊቢ ብንኖርም መገናኘት አልቻልንም፡፡ እንኳን አካልህን ወሬህንም በስንት ስቃይ ነው፡፡ እምሰማው ያንተ መታፈን ወያኔ እንደጠበቀው ትግሉን አላሽመደመደውም፡፡ እንደውም፣ ይበልጥ አጦዘው ለኛ ከቤት መውጣት ምክንያት አንተ ነህ፡፡ እኛ የአንተ ፍሬዎች ነን፡፡ ዛሬ ታፍነህ ቀንና ሌሊቱን መለየት የማትችልበት ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም የነጻነት ቀን ቀርባለችና እስከዛው ዕድሜህን ያርዝምልን፡፡

ኖርዌይ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከታዘብኩት –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

በ10.05.2016 ላይ ከመላው የኖርዌይ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የኖርዌይ መንግስ በህገ ወጥ መንገድ 800 ኢትዮጵውያንን በሃይል ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በራሳቸው ባለስልጣን እና በራሳቸው ሚዲያ ካስነገሩ በኋላ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያሳዘነ ብሎም ያስቆጣ ነበር። ያሳዘነበት ምክንያት ኖርዌይ የራሷን ዜጎች ከአንድም ሶስት ግዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ችግር ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ስታስጠነቅቅ በዚው ግዜ ውስጥ ከ800 በላይ 60 ህጻናትን ጨምሮ  ጸጥታዋ ወደተናጋው አገር እንመልሳለን በማለታቸው በአለም የሰባዊ መብት ከሚከበርባቸው ግንባር ቀደም እንደውም በአንደኝነት የምትጠቀሰው አገር በኢትዮጵያውያኖች ላይ የሰባዊ መብት ጥሰት መደረጉ አሳዝኖናል። ያስቆጣን ደግሞ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች መብታችን ተገፎ ያለ አግባብ ለረጅም አመታት በካንፕ ማስቀመጣቸው ሳያንሳቸው በግፍ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ አሳልፈው ለአንባ ገነን መንግስት  ሊሰጡን መሆኑን በሚዲያቸው መስማታችን ከዚህ ቀደም ተደርጎ የማይታወቅ ጠንከር ያለ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ቁጣችንን ለመግለጽ የችግሩ ተጠቂዎች ከያሉበት ተሰባስበው በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ በመገኘት ችግራችንን በቁጣ  ለኖርዌይ ማህበረሰብ ብሎም ለአለም ህብረተሰብ እንድናሰማ አዘጋጅቶን ነበር።

Norway Ethiopians

ከዋናው ከተማ ኦስሎ ራቅ ካለ ቦታ የመጣን ስለነበረ ሌሊቱን ተጉዘን ጠዋት ነበር የደረስነው። ኦስሎ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያኖችም ተቀብለውን ወደተዘጋጀው ማረፊያ ቦታ በመውሰድ የሰልፉ ሰዓት እስከሚደርስ ድረስ ከ18 ያላነስን ሰዎች ከሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ እና ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ኮሚቴዎች ጋር ስለ ሰላማዊ ሰልፉ እና ጠንከራ ተቃውሞ ሰልፍ ስለማድረጉ ጉዳይ ላይ የተለያዩ  ሃሳቦችን በማንሸራሸር ከተወያየን በኋላ በኖርዌይ ህግ መሰረት ጠንካራ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ከ25 ሰው በላይ መሆን አለበት ስለሚል ጠንካራ ሰልፉን ለመውሰድ ከ25 ሰው በላይ ሰው ካለ ተስማምተን ነበር። ከዚህ ስብሰባ የታዘብኩት ሁለት ነገርን ነው። የመጀመሪያው በመስማማት የተስማሙ እና  ሁለተኛው ደግሞ በመስማማት ያልተስማሙ ናቸው። እነዚህ ሁለት ሃሳቦች ተይዘው ወደ ሰልፉ መነሻ ቦታ ሄድን። ሰልፉ መነሻ ቦታ ላይ የጠበቁን ሰዎች በዛ ያሉ ነበሩ በግምት በመቶ የሚቆጠሩ ነበሩ። የዚን ግዜ በልቤ ውስጥ ከዚህ በፊት ተደርጎ የማይታወቀው ጠንካራው ሰላማዊ ሰልፍ ከበቂ በላይ ስለሆንን በኢትዮጵያ ያለውን ችግር እና የኛንም ችግር ለኖርዌይ ህዝብም ለአለምም ህብረተሰብ የምናሳውቅበት ግዜ በመሆኑ ልቤን ደስታ ሞልቶት ነበረ።

ሰልፉ ተጀመረ በተለያዩ  ወንድሞች እና እህቶች ማይክሮፎኑን በመያዝ የተቃውሞ መፈክሮችን እያሰማን በከተማው መሃል መንገድ ጀመርን ። የተቃውሞ ድምጻችንን እያሰማን ጥቂት የማይባል ጉዞ ከተጓዝን በኋላ የኖርዌጃን ሚዲያ TV2 የሚባለው መስራቤት ደረስን እዚህ ጋር ሁላችንንም እንድንቆም በማስደረግ ብዙ አመት ኖርዌይ የኖረ ኢትዮጵያዊ ወንድማችን ለግዜው ስሙን መግለጽ አይጠበቅብኝም የድምጽ ማጉያውን በመያዝ የሁሉንም ሰልፈኛ ስሜት በሚነካ መልኩ የኖርዌጃንን ሚዲያ መውቀስ ጀመረ ።《የኢትዮጵያን እውነተኛ ገጽታ ታውቃላችሁ በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰውን ግፍና በደል ታውቃላችሁ በኢትዮጵያን ላይ የሚደርሰውን እስራትና ሞታ ታውቃላችሁ ነገር ግን ይሄንን እያወቃችሁ እውነታውን ህዝባችሁ እንዲያውቀው አላደረጋችሁም TV2 በናንተ አፈርን》 በማለት በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰልፈኛ ልቦናውስጥ ያለውን ሃሳብ ስሜት በሚነካ መልኩ ኢትዮጵያውስ ያለውን ችግር ዘርዝሮ በመንገር የኖርዌጃን ጋዜጠኞች ግን እውነታውን እያወቁ ለህዝባቸው በመደበቃቸው ከፍተኛ ትችት እና ወቀሳ በማስተላለፍ ሰልፈኛው ድምጻችን እስከሚዘጋ ድረስ ያስጮሀ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ብየዋለው። ይሄንን ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ሳላደንቀው እና ሳላመሰግነው ማለፍ አልፈልግም በእውነት ላይ የቆምህ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ልጅ ምስጋናዬ ይድረስህ ብያለው።

ሰልፉ ወደፊት መጓዝ ጀመረ  ሁለት ፈረስ ላይ የተቀመጡ ፖሊሶች ከፊታችን ሰልፉን ይመሩታል ሁለት የፖሊስ መኪና ከፈረሶቹ ፊት አሉ የፖሊስ ልብስ ያለበሱ ፖሊሶች በርቀት ይከተሉናል። ጠንካራ ሰልፍ እንደሚደረግ መረጃው የደረሳቸው ይመስሉ ነበር ሁኔታቸውን ለተመለከተ…  እኛ ውስጣችን ተናዷል ኖርዌይ በኢትዮጵያ ስደተኛ ላይ ያላት አመለካከት ጤናማ አይደለምና። ሰልፉ ቀጥሏል የሰልፉ መጨረሻ ፍትህ ሚንስቴር በር ላይ ነበረ።

Norway

ከተማውን በተቃውሞ ድምጽ እያናወጠነው ወደ ፍትህ ሚንስቴር ህንጻ አመራን እዛም እንደደረስን ያ ጀግና ወንድማችን በድጋሚ ማይክራፎኑን ያዘው የኖርዌይ መንግስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለ አግባብ በመደገፋቸው ህዝባችን ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል የኖርዌይ መንግስ በሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍ እንደሆነ ይነግራቸው ጀመር። የቃላት አመራረጡ የድምጽ አወጣጡ ሰልፈኛውን ብቻ ሳይሆን የፍትህ ሚንስቴር በር የሚጠብቁትን ፖሊሶች እና አጅበውን የመጡትን ፖሊሶች ጭምር ቀልብ የገዛ ነበር። እውነት ለመናገር ሁሉም ኢትዮጵያ ቆርጦ ቢታገል  ትግሉ ትልቅ ደረጃ ላይ አድርሶ በአንድ ማስተሳሰር በተቻለ ነበር። በመጨረሻም ከፍትህ ሚንስተር መስሪያ ቤት በመውጣት ሰልፈኞችን አነጋግራለች። ስለ ሰልፋችን አላማ ከሚንስተር መስራቤት ለመጡት ገለጻ ከተደረገላት በኋላ ስለ ሰልፉ አላማ የሚነግር ደብዳቤ ከተሰጣት በኋላ እሷም ደብዳቤውን ከተቀበለች በኋላ ለሰልፈኞቹ ንግግር አድርጋለች።

ከሚንስተር መስራቤት የመጡት ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ ሰልፈኞቹ ወደ ተባለው ጠንካራ ሰልፍ ለመሄድ እየተነጋገርን እያለ ድንገት አንድ ሰው አዲስ ሃሳብ ይዞ ብቅ አለ የሰልፉን አዘጋጆችን በመለየት ጠንካራ ሰልፍ የተባለውን ማድረግ እንደሌለባቸው ይነግራቸው ጀመር። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ትልቅ የፖለቲካ ስራ ከኖርዌጃን ባለስልጣናት ጋር እየተሰራ እንደሆነ እና ጥሩ ደረጃ ላይ እንዳለ በማሳወቅ ዛሬ ጠንካራ ሰልፍ ቢደረግ እና ከፖሊሶች ጋር ብትጋጩ የተጀመረው ስራ እንደሚበላሽባቸው  በመግለጽ የታሰበው እና ከሁለት ወር በላይ የተዘጋጀንበት ሃሳብ በማስለወጥ ሊወሰድ የታሰበውን ጠንካራ ሰልፉን አስቀርቶታል። ሲጠቀልለው ከኖርዌይ ባለስልጣን ጋር የተጀመረው ውይይት ካልተሳካ ግን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በድጋሚ በመቀስቀስ ጠንካራ ሰልፉን እንደሚወሰድ አሳውቋል። ለዚህም አላፊነቱን እንደሚወስድ በመናገር የሰልፉን ድምዳሜ ነግሮ ሰልፉ ተጠናቋል።

እኛም ውሳኔውን በመጠባበቅ ላይ ነን ያለውን ሁኔታም እየተከታተልኩኝ ለሚዲያ ለማቅረብ እሞክራለው።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚሰራው ስራ ሃላፊነትን በመውሰድ ተጠያቂነት እንዲኖርበት ያስፈልጋል። መልካም የሰራ ክብር ልንሰጠው እንደሚገባ ሁሉ ስህተት የሰራም ስህተቱ በአደባባይ ሊነገረው ይገባል እላለው። ለጊዜው አበቃው።

 

ከተማ ዋቅጅራ

18.05.2016

Email- waqjirak@yahoo.com

የቤኒሻንጉል ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አህመድ ናስር አረፉ

$
0
0

ahmed

(ዘ-ሐበሻ) የቤኒሻንጉል ክልልን ከ2001 ጀምሮ በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩትእና የአማራን ሕዝብ ለይተው ከቤንሻንጉል በማፈናቀል ቤት እና ንብረታቸውን እንዲያጡ በማድረግ ወንጀል ከሚጠየቁ ባለስልጣናት መካከል አንዱ የነበሩት አቶ አህመድ ናስር ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ::

ከሃገር ቤት የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙትና የመንግስት ሚዲያዎችም እንደዘገቡት የርዕሰ መስተዳደሩ የቀብር ስነስርዓት አሶሳ ከተማ ውስጥ ይፈጸማል::

የኢህ አዴግ ተለጣፊ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆኖእው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) በምክትል ሊቀመንበር የነበሩት አቶ አህመድ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በእርሻ ምህንድስና፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በቻይና ሆሃ ዩኒቨርሲቲ በውሃ ምህንድስና የተከታተሉት አቶ አህመድ ናስር በአሁኑ ወቅት የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር በቀድሞው ግብርና ገጠር ልማት ሚኒስትር ዴኤታነት ማገልገላቸውን የመንግስት ሚድያዎች ዘግበዋል::

የበሽታው ዓይነት ባይገለጽም አቶ አህመድ ለረዥም ጊዜ በውጭ እና በሃገር ቤት ህክምና ሲከታተሉ መቆየታቸው ሲሰማ ሕይወታቸው ሲያልፍም የ51 ዓመት ጎልማሳ እንደነበሩ የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል::

በ1957 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ ጠዴቻ መልካ ቀበሌ የተወለዱት አቶ ናስር የአንድ ልጅ አባት ነበሩ ተብሏል::

አህመድ ናስር ከ2 ሺህ በላይ አማሮች ከቤንሻንጉል ክልል እንዲፈናቀሉ ካደረጉ በኋላ መጨረሻ ላይም “እነዚህን አማሮች ያፈናቀልነው በስህተት ነውና ወደ ክልላችን ይመለሱ:: አማሮቹ እንዲወጡ የተደረገው በበታች ባለስልጣናት ግብታዊነት ነው” በማለት ይቅርታ መጠየቃቸው በወቅቱ በዘ-ሐበሻ በኩል መዘገቡ አይዘነጋም::

 

 

የወያኔው የደህንነት መስርያ ቤት ሹም የነበረው የእስር ቅጣት ተበየነበት – (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ ራድዮ)

$
0
0
የግንቦት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ዜና (May 18, 2016 NEWS)
#  የወያኔው የድህንነት መስርያ ቤት ሹም የነበረው የእስር ቅጣት ተበየነበት
# የዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት ያልተወራረደ ሂሳብ ያለባቸው የመንግስት መ/ቤቶች መኖራቸውን ገለጸ
# ጌታቸው አምባዬ አዲሱን የጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዲመራ ተሾመ
# በናይጀሪያ የሰራተኞች ማህበር ሰራተኞች
# በሊቢያ በአንድነት መንግስቱ ስር ያለው ኃይል ቁልፍ የሆነ ቦታ ከአይሲስ አስለቀቀ
# በደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት ረብሻ ተነሳ
ዝርዝር ዜናዎች
weldesilase በወያኔው መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት የአገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ የነበረውና የወያኔው መሪ መለሰ ዜናዊ የቅርብ ወዳጅና ቀኝ እጅ እንደነበር የሚነገርለት ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል ከአንድ ወንድሙና ከእህቱ ጋር በተከሰሰበት የሙስና የክስ መዝገብ አስር ዓመት ጽኑ እስራትና 50 ሺ ብር እንዲከፍል የወያኔው የፖለቲካ ፍርድ ቤት ወስኖበታል። ከዚህ በተጨማሪ የወልደስላሴ ወልደሚካኤል ወንድም ዘርዓይ ወልደሚካኤል የአራት ዓመት ጽኑ እስራትና የ20 ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት ሲጣልበት እህቱ ትርሃስ ወልደሚካኤል ደግሞ ሶስት ዓመት ከሶስት ወር ጽኑ እስራትና 10 ሺ ብር እንድትከፍል ተወስኗል። በተከሳሾቹ ላይ የቀረበው የክስ መዝገብ እንኳን ቱባ የወያኔ ባለሥልጣን ቀርቶ ተራ የወያኔ አባል የሚፈጽመው ሙስናና ማጭበርበር መሆኑ እየታወቀ በወልደ ስላሴ ወልደሚካኤልና በወንድሙና በእህቱ ላይ የተሰጠው ቅጣት በወያኔ ውስጥ በነበረውና ባለው የፖሊቲካና የስልጣን ሽኩቻ እንዲሁም የጥቅም ጉትቻ የተነሳ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል። በወልደሥላሴ ወልደ ሚካኤል ይመራ የነበረው የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ለብዙ ንጹሃን ሰዎች ሞት ምክንያት የነበረና ጨካኝ ነፍሰ ገዳዮችን የሚያሰማራ መ/ቤት እንደሆነ ይታወቃል።  የወያኔው ዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት ሪፖርት እንደገለጸው በአገዛዝ ስር ያሉ መስሪያ ቤቶችና ዪኒቨርስቲዎች ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደ ሂሳብ እንዳለባቸው ለወያኔው ፓርላማ አሳውቀዋል። ዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት ከዚህ በተጨማሪ ለሕዝብ ጤንነት አደገኛ የተባሉና ጊዜ ያለፈባቸው መድሐኒትና ኬሚካሎቹ ለዜጎች እየተሸጡ መሆኑን ሊብሬ ያላቸው መኪናዎች በአካል የት እንደገባና ለማን እንደተዛወሩ እንደማይታወቅ የጉምሩክ ባለሥልጣን መሰብሰብ የሚገባውን እንደሰብሰብ ዩነቨርስቲዎች ያለ ህጋዊ አሰራር በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘብ እንደሚያባክኑ ሪፖርቱ ግልጽ አደርጓዋል። የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በየዓመቱ ተመሳሳይ ሪፖርት ለወያኔው ፓርላማ ያቅርብ እንጅ የአገዛዙ መስሪያ ቤቶች ምንም ዓይነት መሻሻል እንደሚያደርጉና ይልቁንም ከዓመት ወደ ዓመት የሚባክነውና የሚጠፋው የገንዘብ መጠን እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል። ሪፖርት ያነጣጠረባቸው መ/ቤቶችና ዩኒቨርስቲ ኃላፊዎች በሙሉ የወያኔ አባልና የዘር ትስስር ያላቸው በመሆኑ ተጠያቂነት እነርሱ ዘንድ ሲደርስ እንደቆመ ተነግሯል።
 የመጣለትን በጭበጨባ የቀረበለትን በጩኸት በፉጨት መቀበልና ማጽደቅ መለያ የሆነው የወያኔ ፓርላማ አዲስ ያዋቀረውና በፈረሰው የወያኔ ፍትሕ ሚኒስትር ምትክ የተቋቋመው የጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ቢሮን እንዲመራ የፈረሰው የወያኔ ፍትህ ሚኒስትር የነበረው ጊታቸው አምባዬ የወያኔ ጠቃላይ ዐቃቤ ሕግ ተብሎ በወያኔ መሾሙና በፓርላማው መጽደቁ ታውቋል። የወያኔ ቡድን ምክንያቱ ባልተገለጸ ሁኔታ የፍትህ ሚኒስትሩን በጠቅላይ አቃቤ ህግ ከተካ ወዲህ ሚኒስትሩን መልስ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግነት ማስቀመጡ የወያኔ መሪዎች ቀደሞውና ፍትህ የሚያውቀውን ሚኒስትር መስሪያ ቤታቸውን ለሕግና ለደንብ እንደገዛ ሳይሆን የበለጠ ፍትህ እንዲረገጥ ሚዛን እንዲዛባ ለማድረግ በማሰብ መሆኑን ስም እንጅ የተለወጠና የተቀየረ ነገር እንደሌለና እንደሚኖር የሕግ ባለሙያዎች በእርገጠኛነት ይናገራሉ።
parlama የወያኔ ቡድን አዲስ አበባን የተቆጣጠረበትን የአንድ ዘር ፓርቲ አገዛዝ የመሰረተበትን የግንቦት 20 ቀን በዓልን ለማክበር ደፋ ቀና ማለቱን ትዕዛዝና መመሪያ ማስተላለፉን በሰፊው እንደቀጠለ ከወያኔ መሪዎች አካባቢ የመጣው ዜና ያስረዳል። በዚህ መሠረት ለወያኔው ግንቦት 20 በአል ከሕዝብ ገንዘብ የሚሰበስብ የወያኔ ስዎች የተመደበ ሲሆን ለስንጋ ግዥ ለምግብ ዝግጅት እና መስተንግዶ የቤት ለቤት ጥሪ ወረቀት የሚያቀርቡ በኮሚቴ እየተቧደኑ በመመሪያ መሠረት እየተንቀሳቀሱ ሲሆን የወያኔ የሴቶች ሊግ መመሪያውን እንዲያስፈጽም ኃላፊነቱን ወስዷል። የወያኔው የወጣቶች ሊግ በበኩሉ በየአውራ ጎዳናውና በየአደባባዩ ድንኳኖችን በመትከል የግንቦት 20 ቀን እንዲዘክሩና እንዲቀሰቅሱ መመሪያ የተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል። ወያኔ ለግንቦት 20 ቀን ዝግጅቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የመደበም መሆኑ ተገልጿል።
 በናይጄሪያ የነዳጅ ዋጋ በ 67 ከመቶ እንዲጨምር መደረጉን በመቃወም ሁለት ታላላቅ የሰራተኛ ድርጅት ማህበሮች ጠቅላላ የስራ ማቆም አድማ ለዛሬ ለሮብ ግንቦት 10 ቀን 2008 ዓም ጠርተው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ያደረገው ማገጃ ሁለቱን ማህበሮች የከፋፈለ መሆኑ ታውቋል። መንግስት የነዳጅ ዋጋ በአሁኑ ወቅት ከሚሸጥበት .43 ዶላር በሊትር ወደ .72 ዶላር በሊትር ከፍ ለማድረግ የወጠነውን እቅድ በመቃወም የናይጄሪያ ሌበር ኮንግሬስ እና የትሬድ ዩኒየን ኮንግሬስ የሚባሉ ሁለት ታላላቅ የሰራተኛ ማህበሮች ከረቡዕ ግንቦት 10 ቀን ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ለማካሄድ አቅደው እንደነበር ይታወቃል። ከናይጄሪያ የፍርድ ሚኒስትር የቀረበውን የአቤቱታ ሰነድ ተቀብሎ አንድ የናይጄሪያ ፍርድ ቤት ጉዳዩ በድርድር እስኪያልቅ ድረስ የስራ ማቆም አድማው እንዲነሳ የወሰነውን ውሳኔ ትሬድ ዩኒየን ኮንግሬስ የተባለው የሰራተኛ ማህበር የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተቀብሎ ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው እንዲሄዱ መመሪያ ሲያስተላልፍ የናይጄሪያ ሌበር ፓርት የተባለው ግን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አልደረሰኝም በሚል አድማው እንዲቀጥል አዟል። መንግስት ለፍርድ ቤት ባቀረበው ሰነድ ላይ ማህበሮቹ ስራ ለማቆም የሚያስችላቸው ትክክለኛ መንገድ ያልተከተሉ መሆናቸውን እቅዳቸውን በቅድሚያ ለመንግስት ያላቀረቡ መሆናቸውን ይገልጻል። የስራ ማቆም አድማው በስራ ላይ የሚውል ከሆነም የናይጄሪያ መንግስት በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያጣ መሆኑን ከፍተኛ የጸጥታ ችግር ውስጥ እንደሚገባ ይገልጻል። በዛሬው ቀን የተደረገ የስራ ማቆም አድማ ስለመኖሩና አለመኖሩ ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ወቅት ድረስ የተገኘ መረጃ የለም። በሌላ ዜና ከሁለት አመት በፊት በቦኮሃራም ከተጠለፉት ወደ 200 ከሚሆኑት ልጃገረዶች መካከል አንደኛዋ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘቷ ረቡዕ ዕለት የዜና ምንጮች ገልጸዋል። ዝርዝሩን እንደንደደረሰን እናቀርባለን።
 ለአንድነት መንግስት ታዛዥ የሆነ የሊቢያ ጦር ቀደም ብሎ በአይሲስ ኃይሎች ተይዞ የነበረ አቡ ግሬን የተባለውንና ሁለት ታላላቅ መንገዶች የሚገናኙበትን ቁልፍ ቦታ ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓም. ከአይሲስ ኃይሎች አስለቅቆ የያዘ መሆኑን ገልጿል። ይኸው ጦር በተጨማሪም አይሲስ ወደ ተቆጣጠራትና በርካታ ኃይሎች በማስፈር ወታደራዊ ይዞታውን አጠናክሮ ወደ ሚገኝባት ሰርት ወደተባለችው ከተማ እየገሰገሰ መሆኑ ተነግሯል። የሊቢያ አንድነት መንግስት የአይሲስ ኃይሎችን ለመደምሰስ ተዋጊ አይውሮፕላኖች እንዲሰጡት የምእራብ መንግስታትን ጠይቋል። ከሁለት ቀን በፊት አሜሪካ ጣሊያንና ሌሎች መንግስታት ቪየና ላይ ባደረጉት ስብሰባ ቀደም ብሎ የተጣለው ማዕቀብ ተነስቶ ለሊቢያ አንድነት መንግስት ሰራዊት ወታደራዊ ስልጠናና የመሰሪያ እርዳታ ለማድረግ መስማማታቸው ይታወሳል።
 ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት ውስጥ ፕሬዚዳንት ዙማ ለፓርላማው አባላት ንግግር ለማድረግ ሲዘጋጁ የኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተርስ የሚባለው ፓርቲን በምክር ቤቱ ውስጥ የሚወክሉ የሆኑ ወደ 20 የሚሆኑ የምክር ቤት አባላት ፕሬዚዳንቱ እንዳናገሩ በጩኸት ለማገድ በመሞከራቸው ከፍተኛ ረብሽና ግርግር ተከስቶ እንደበር ለማወቅ ተችሏል። የጸጥታ ኃይሎች ሰዎችን ከምክር ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ለማስወጣት ባደረጉት ሙከራ የቦክስ ድብድብ እንደነብርም ታውቋል። ፕሬዚዳንት ዙማ የመንግስት ገንዘብ አለአግባብ በማውጣትና በሌሎች ክሶች በተደጋጋሚ ጉዳያቸውን የደበብ አፍሪካ ፍርድ ቤቶች በተደጋጋሚ የቀረበ ሲሆን በአንዳንዶቹ ላይ የተፈረደባችወ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ምክንያት በተቃዋሚዎቻቸውና እርሳቸው በሚመሩት የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግሬስ በአንዳንድ አባላት ጭምር ተቀባይነት ያጡ ቢሆንም አብዛኛቹ የፓርቲ አባላት ድጋፍ ስለሰጧቸው በስልጣን ሊቆዩ እንደቻሉ ይታወቃል። ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን ከፓርላማው መሰብሰቢያ አዳራሽ በፖሊስ ተገፍተው የወጡት የተቃዋሚው የ ኢኮኖሚ ፍሪደም ፋይተርስ ፓርቲ መሪ የአገሪቱ ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲወገዱ ለማድረግ ፓርቲያቸውን የጀመረውን ትግል የሚቀጥሉ መሆናቸውን ለጋዘጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።
 የቀድሞ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር ቤምባ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ የጠየቀ መሆኑን የዜና ምንጮች ገለጹ። ከአስራ አራት ዓመት በፊት መፈንቅለ መንግስት ለማክሸፍ በሚል ሰብበ ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ተልኮ የነበረው ሚስተር ቤምባ የሚመሩት የአማጺ ኃይል በሕዝብ ላይ በፈጸመው ግድያና ሴቶችን አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ባላፈው መጋቢት ወር በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ክስ የቀረረባችው መሆኑ ይታወሳል።
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live