Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

“[የአርባምንጩ] ጥቃት ወደፊት ከምንወስዳቸው ጥቃቶች ጋር ሲነጻጸር ትንሹ ነው”ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከVOA ጋር

0
0

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ማምሻውን ከአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በአርባ ምንጭ ድርጅታቸው ስለወሰደው እርምጃ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በአጭሩ ተነጋግረዋል:: ፕሮፌሰሩ ለአሜሪካ ድምጽ ጋዜጠኛው እንደገለጹት “ትግላችንን የምናካሂደው እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሆነን ነው:: በአርባምንጭ የወሰድነው እርምጃ በቀጣይ በተለያዩ የኢትዮጵያ ቦታዎች ከምንወስደው እርምጃ ጋር ሲነጻጸር ትንሹ ነው” ብለዋል::

ቃለምልልሱን ያዳምጡት


የመቶ በመቶ የምርጫ ውጤት –አንደኛ ዓመት (ይገረም አለሙ)

0
0

ያለምንም ተወዳዳሪ ብቻውን ለምርጫ የቀረበ ይመስል ወያኔ መቶ በመቶ አሸነፈ ተብሎ በጉዳይ አስፈጻሚው ምርጫ ቦርድ የተነገረበትና በአንድ ወንበር ስሙ ይጠራ የነበረውን የተቃውሞ ጎራ ጠራርጎ ከፓርላማ ያስወጣበት ግዜ አንሆ አንድ ዓመት ሞላው፡፡ ይህ ውጤት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ብሎ ነገር አለመኖሩን ብቻ ሳይሆን ከዚህ በኋላም በወያኔ የሥልጣን ዘመን አይታሰቤ መሆኑን ያረጋገጠ ቢሆንም  አንደ ነገሩ ክብደትና ክፋት የተሰጠው ትኩረት አምብዛም ነው፡፡ ሰለ ዴሞክራሲ የሚያወሩት፣ ስለ መድብለ ፓርቲ ፖለቲካ የሚሰብኩት  መንግሥታት  የወያኔ መቶ በመቶ አሸናፊነት ሲያስቃቸው እንጂ ሲያስጨንቃቸው አላያንም፤ የምርጫውን በሰላም መጠናቀቅ ሲመሰክሩ እንጂ የውጤቱን ኢ-ዴሞክራሲያዊነትና አደጋ ጋባዥነት ሲናገሩ አልሰማንም፡፡ወዳጅነታቸውን ማጥባቸውን እንጂ ከዴሞክራሲ ተለያይታችሁ ከእኛ አትወዳጁም ሲሉ አልታዘብንም፡፡ የወያኔን ምርጫ በማጀብ ምርጫው ሰላማዊ ነው እንዲባል ያበቁት ፓርቲ ነን ባዮችም ቢሆኑ ከአንድ ሰሞን የተለመደ ጩኸትና ጫጫታ በስተቀር ያሉትም የሰሩትም ነገር የለም፡፡

election

ወያኔ ግን እየሰራ ነው፡፡ ሲመቸው በፍጥነት፣አልመች ሲለው እያዘገመ፣ ግን ወደ ፊት ደደቢት ሆኖ ወደ አለመው ግቡ እየተጓዘ ነው፡፡ከእንግዲህ በምንም መልኩ ሥልጣኑን እንዳያጣ እየገደለም እየደለለም፤ እያስፈራራም ይቅርታ እየጠየቀም፤ እየሾመ እየሻረ አንዳንዶቹን የጭዳ ዶሮ እያደረገም ቀጥሏል፡፡ ከመቼውም ግዜ ይልቅ ውሾቹም ይጮኻሉ ግመሉም ይሄዳል ማለት አሁን የተቃውሞው ጎራ ግን ያው ነው፤ እንደ ቡና ውኃ እያደር የሚያንስ እንጂ ባለበት አድሮ እንኳን  የማይገኝ፡፡ ይህን ስል ወያኔን በሚገባው ቋንቋ ማነጋር ብለው የተሰለፉትን፣ መነጣጠሉ አልጠቀመንም ብለው አንድ ወደ መሆን የመጡትን በመረሳት አይደለም፡፡አጠቃላይ የተቃውሞው ጎራ እንቅስቃሴ ሲጤን ሕዝብ እየከፈለ ካለው መስዋዕትነትና ወያኔ ወደ ግቡ ከሚያደርገው ፈጣን ጉዞ እንዲሁም ሀገርና ትውልድ ከሚገኙበት ፈጣን የቁልቁለት መንገድ  አኳያ በቂም ተመጣጣኝም አለመሆኑ እንጂ፡፡

 

በደርግ የሽንፈት ምክንያትነት ወያኔ ኢትዮጵያዉያንን መቶ በመቶ ያሸነፈው በ1983 ዓም ቢሆንም በተለያዩ የማስመሰያ ቃላቶችና ድርጊቶች  እየሸፋፈነ እስከ 1987 ዓም ቆይቶ ነበር፡፡ ዋንኛ ሽፋን ሆኖ ሲያገለግለው  የነበረው ምርጫ  የሽፋን አገልግሎቱ በ2007 የተጠናቀቀ ቢሆንም  ወያኔ ግን  ለጉልበት አገዛዙ  ቡራኬ ማግኛ ሌላ ምርጫም አማራጭም የለውምና  ጊዜውን እየጠበቀ ምርጫ ማድረጉ አልቀረም፡፡  ፖለቲከኞቻችንም  ማሸነፉ ቀርቶ የፓርላማን ደጅ ላይረግጡ፣ በአጃቢነት እየተሰለፉ ማድመቅ መቀጠላቸው አልቀረም፡፡  ዕድሜ ከሰጠን  ከሶስት ዓመት በኋላም ይህንኑ እናያለን፡፡

 

የታውሞው ጎራ በምርጫ 92 ከአስር በላይ የፓርላማ ወንበር፣ በምርጫ 97 ደግሞ ከመቶ በላይ ወንበር ማግኘቱ   ለወያኔ ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሯ ትሄዳለች ነው የሆነበት፡፡ እሱ ለማስመሰል በሚያካሂደው ምርጫ ተቃዋሚዎች እየተጠናከሩ ሕዝቡም ምርጫ ኮሮጆ ውስጥ በሚከታት አንድ ድምጹ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል እየተለማመደ መሄዱ ከቀጠለ አንድ ቀን ሥልጣን ወይንም ሞት ብሎ ከያዘው ወንበር በምርጫ ካርድ ተገፍትሮ አንደሚወርድ ግልጽ ሆኖ እንደታየውና  ስጋት አንደፈጠረበት  በምርጫ 97 ሽንፈቱን ከቀለበሰበት ድርጊቱ ባሻገር ከዛ በኋላ በተካሄዱ ሁለት ምርጫዎች የፈጸማቸው ተግባራት  በቂ ምስክሮች ናቸው፡፡

 

በምርጫ 2002 አዲስ አበባ ከመሳለሚያ አካባቢ አቶ ግርማ ሰይፉ አሸንፈው ሾልከው ፓርላማ መግባታቸው የወያኔ ምርጫ የማስመሰያ ድራማ የመሆኑን ሀቅ ሙሉ ለሙሉ ከመጋለጥ አድኖት ነበር፡፡ ምንም ተወዳዳሪ ያልነበረበት ምርጫ ያስመሰለው የ2007 የመቶ በመቶ አሸናፊነት ውጤት ግን ያመስመሰያ ካባውን ሙሉ ለሙሉ ገፎ  ጣለው፡፡ ነገር ግን ከድርጊቱ ኢ-ዴሞክራሲያዊነት እና ወደ ፊት ሊያስከትል ከሚችለው ችግር አንጻር ሲታይ ከውስጥም ሆነ ከውጪ የገጠመው ተቃውሞ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ከሁሉ በላይ ለወያኔም የልብ ልብ የሚሰጠው ለአለም አቀፉ ማህበረሰብም ትኩረት ማጣት ምክንያት የሚሆነው  ምርጫ ተወዳደርን ብለው መቶ በመቶ መሸነፋቸው የተነገራቸው ፖለቲከኞች በዛ ቁጭት አድሮባቸው፣ አልህም ገብቶአቸው፣ መስቃ መሮአቸው፣ ከሆነው ተምረው የተሻለ ለመስራት አለመነሳሳታቸው ነው፡፡

 

ለአንድ ሳምንት የተለመደ ምርጫው ተጭበርብሯል ጩኸታቸውን ጮኹ በቃ! ከአንድ አመት ጉዞአቸው አንደታዘብነው ከዛ በኋላ  እንደልማዳቸው እስከሚቀጥለው ምርጫ 20012 ላይሰሙ ላይለሙ ተከናበው የተኙ ነው የሚመስሉት ፡፡ በርግጥ ለአንዳንዶቹ ለእነርሱም አንደ ወያኔ ምርጫ  እድሜ ማረዘሚያ መድሀኒታቸው ይመስላል፡፡ ሌላ ቢቀር የአራት አመት ቀለብ ያገኙበታል፡፡እልሞትኩም አለሁ ፉከራ ያሰሙበታል፤ በየኤምባሲው ይጋበዙበታል፣ወዘተ ስለሆነም አልቻልኩም ብለው አይለቁም፤በቃኝ ብለው ጡረታ አይወጡም፣ ወይንም በግል ተጠናከረው አለያም ተባብረው ከምቾት ባሻገር ለመታገል  ወስነው ከራስ በላይ ሀገር  ብለው ጠንካራ ተፎካካሪ መሆንን አያልሙም፡፡  ብቻ እንዳሉ ሆነው በያዙት የፓርቲ ሥልጣን እየተጠሩ መኖር፡፡

 

ምርጫ የአንድ ሰሞን ተግባር አይደለም፡፡ የአንድ አመት ክንውን ውጤትም አይደለም፡፡ አምስት አመትም በቂው አይደለም፡፡ ራዕይ ያለው ለሀገር የሚጠቅም ፕሮግራም የነደፈ ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ትግሉን  ሰላማዊ፣  ግቡን ስልጣን መያዝ ያደረገ  ሀይል ትግሉን ከጀመረበት እለት አንስቶ የሚያከናውነው እያንዳንዱ የእለት ተእለት እንቅስቃሴው በዚሁ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ በሰላማዊ ትግል ሥልጣን መያዝ የሚቻለው በምርጫ ብቻ እንደመሆኑ ራስን ለብቁ የምርጫ ተወዳዳሪነት  ከማዘጋጀት በተጨማሪ ከምርጫ ጋር ተዛምዶ ያላቸው ጥያቄዎች መነሳት ያለባቸውም ሆነ ተቃውሞዎች መሰማት ያለባቸው በምርጫው ዋዜማ ሳይሆን አራት ዓመቱን ሙሉ ውጤት እስከሚገኝ ድረስ ነው፡፡

 

በምርጫ ሥልጣን ለመያዝ ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ መኖር አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ ገለልተኛ ምርጫ አስፈጻሚ ተቋም፣ነጻ የፍትህ ስርዓት፣አሳታፊ የፖለቲካ ምህዳር ወዘተ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም በምርጫ ለሥልጣን ለመብቃት የሚያስቡ ኃይሎች ቀዳሚውና ወሳኙ ተግባራቸው እነዚህ ሶስቱ ተግባራዊ እንዲሆኑ መታገል ነው፡፡ ይህ ደግሞ በምርጫ ዋዜማ የሚሆን አይደለም፡፡

 

ወያኔ መቶ በመቶ ያሸነፈው  ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ባለመሆኑ፣ የፖለቲካ ምህዳሩ በመጥበቡ እንደሆነና ውጤቱን ባለመቀበልም ወደ ፍርድ ቤት ያልሄዱት ነጻ የፍትህ አካል ባለመኖሩ አንደሆነ የሚናገሩት ፖለቲከኞች እነዚህ እስካልተለወጡ ድረስ መቼም ሆነ መቼ በምርጫ ማሸነፍ ብሎ ነገር እንደማይኖር እያወቁ ይህን ለመለወጥ ባለፈው አንድ አመት አንድም ነገር ሲያደርጉ አልታዩም፡፡  ወይንም በየምርጫዎቹ ወቅቶች ሞከርን ወያኔ ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ዝግጁ ባለመሆኑ አልቻልንም ብለው ሕዝቡ የራሱን ምርጫና አማራጭ አንዲፈልግ  ከመድረኩ ገለል አላሉም፡፡

 

መቶ በመቶ መሸነፋቸው እንደተነገራቸው ከማግስቱ ጀምረው ቢችሉ ተነጋግረውና ተባብረው ባይችሉ በየራሳቸው በቂ ጥናት አድርገው ስራ መጀመር  የነበረባቸው ፖለቲከኞች ባለፈው አንድ ኣመት እንዳየናቸውና  እንደሰማናቸው ከሆነ  ለመጪው ምርጫ ሊሰሩ ቀርቶ ያለፈ ሽንፈታቸውንም የረሱት ነው የሚመስሉት፡፡ ምን ይሄ ብቻ በምርጫው ምክንያት የተገደሉ፤የታሰሩ ቤታቸው የፈረሰ ቤተሰባቸው የተበተነ አባሎቻቸውንም ረስተዋቸዋል፡፡ ህም ይሆኖ ግን በስራቸው አያፍሩም ሕዝብንም አይፈሩምና አራት አመት  ተኝተው ከርመው የወያኔ የምርጫ ደወል ሲደወል የእነርሱም ጩኸት ይጀምራል፡፡ በምርጫ ለማሸነፍ አይደለም የተወሰነ የፓርላማ ወንበር ለማግኘት የሚያበቃቸው ሁኔታ እንደሌለ እያወቁም የአንድ ሰሞን ከበሮ እየደለቁ ምርጫ ይገባሉ፡፡ አባልና ደጋፊውን አስገድለው አሳስረው ምርጫው ተጭበርብሯል የሚለውን የተለመደ ጩኸታቸውን ለአንድ ሳምንት ያሰሙና  ወደ ተለምዶ ህይወታቸው ይመለሳሉ፡፡

 

እስከ 2012 ተአምር ተፈጥሮ በኢትዮጵያ ለውጥ ካልመጣ የማስመሰያ ምርጫው ይደረግና ወያኔ በአውራ ፓርቲነቱ ፓርቲ ተብየዎቹ በስመ ተቀዋሚነታቸው ሕዘቡም (እኛ) በግዞቱ ይቀጥላሉ፡፡

‎የምስራቅ‬ ዕዝ ጦር አባላት የሆኑ 12 ከፍተኛ መስመራዊ መኮንኖች ተይዘው ታሰሩ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

0
0

ግንቦት 5 ቀን 2008 ዓ.ም.
ርዕሰ ዜና
የምስራቅ ዕዝ ጦር አባላት የሆኑ አስራ ሁለት ከፍተኛ መስመራዊ መኮንኖች ተይዘው ታሰሩ
 የዛምቢያ ፍርድ ቤት በ41 ኢትዮጵያውያን ላይ የእስር ቅጣት በየነ
 በኢትዮጵያ የጎርፍ አደጋ ከባድ ጉዳት ማስከተሉን የ.ተ.መ.ድ ገለጸ
 የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ማዕደን ሰራተኞች አሰሪዎቻቸውን እንዲከሱ ተፈቀደላቸው
 የስደተኞችን ጉዞ ለመቆጣጠር የተቋቋመው የአውሮፓው ህብረት የባህር ኃይል ቡድን ውጤት አልባ ነው ተባለ
 አሜሪካ በሰው አልባ መንኮራኩር አምስት የአልሸባብ አባላትን ገደለች
 የቱኒዚያ መንግስት ሰላሳ ሰባት የአሸባሪ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር አደርኩ አለ

ዝርዝር ዜናዎች
 የወያኔ መሪዎች ያደራጇቸውና በዘርና በቋንቋቸው ፕሬዚዳንት የሚል ማዕረግ የጫኑባቸው ሹመኞች ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ ማሰርና ማሳሰር የዘወትር ተግባራችው መሆኑ ይታወቃል። የወያኔው የሀረር ክልል ፕሬዚዳንት ተብየው ሙራድ አብዱላሂ ባቀርበው ውንጀላ ምክንያት የምስራቅ ዕዝ ጦር አባላት የሆኑ አስራ ሁለት ከፍተኛ መስመራዊ መኮንኖች ተይዘው መታሰራቸውን የመከላከያ ምንጮች አጋልጠዋል። የሀረር ከተማ አንድ የሀረሬ ፕሬዚዳንትና አንድ የኦሮሞ ም/ፕሬዚዳንት ያላት ስትሆን ብዙ ጊዜ በሚደረጉ የሃሳብና የስራ ግጭቶች የተነሳ ወያኔ ጣልቃ መግባቱን ያስታወሱት ወገኖች የአሁኑ እስር ከዚህ ውዝግብ ጋር የተያያዘ መሆኑን ያሰምሩበታል።

File Photo

File Photo


 ዛምቢያ ውስጥ የሉንግዋ ከተማ ፍርድ ቤት ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በ41 ኢትዮጵያውያውያን ስደተኞች ላይ ያለጉዞ ሰነድና ፈቃድ ወደ ዛምቢያ ግዛት ገብታችኋል በማለት በስደተኞቹ ላይ የእስር ቅጣት መወሰኑ የዛምቢያ ጋዜጣ ዘግቧል። እንደጋዜጠው ከሆነ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሚያደርጉት ጉዞ በዛምቢያ በኩል አቋረጠው ወደ ዚምባብዌ ሲያልፉ በመያዛቸው መሆኑን ገልጾ የዛምቢያው ፍርድ ቤት አርባ አንዱንም ስደተኞች 1500 የኬኒያ ሽልግ እንዲከፍሉ ወይንም በሶስት ወር እስራት እንዲቀጡ ፈርዶባቸዋል።

 የድርቅና የረሃብ አደጋ ደመና ከኢትዮጵያ ባልገፈፈበትና ይልቁንም በጠቆረበት ሰዓት የጎርፍ አደጋና መፈናቀል ለኢትዮጵያውያን ሌላ አስቸጋሪ ፈተና እየሆነ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት አስታውቋል። እንደ ተመድ ሪፖርት ከሆነ በድርቅና በረሃብ ተጠቅተው ባሉ አካባቢዎች በጣለው ኃይለኛ ዝናብና ተከትሎት በመጣው ጎርፍ የተነሳ በርካታ ህይወት ማለፉን ብዙ ንብረት መውደሙንና 120 ሺ ሰዎች ደግሞ መፈናቀላችውን አስታውቋል። በመጭው የክረምት ወራት
የዝናሙ መጠን በዚሁ ከቀጠለ አስራ አምስት ሚሊዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን በጎርፉ አደጋ ጥላ ስር ይሆናሉ በማለትም አስጠንቅቋል።

 በሳምባ በሽታ የሚሰቃዩ የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ የማዕደን ሰራተኞችን አሰሪዎቻቸው የነበሩትን የማእድን ኩባንያዎች በመክሰስ ካሳ ማግኘት የሚችሉ መቻላቸውን አንድ የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፈቀደ መሆኑ ተነገረ። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የማዕድንሰራተኞች አሰራዎቻቸውን ለመክሰስ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራላቸዋል ይባላል። ለረጅም ጊዜ በተለይ የሲሊኮን ማዕድን የማውጣት ላይ የነበሩ የማዕድን ሰራተኞች ሲሊኮሲስ በተባለ ፈውስ በሌለው የሳምባ በሽታ የሚሰቃዩ ሲሆን ፋብሪካዎችን በመክሰስ 30 ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር የገንዘብ ካሳ ማግኘት ይችላሉ ተብሏል። የክስ ሂደት ከአስር ዓመት በላይ ሊወስድ የሚችል ቢሆንም ካሳው 400 የሚሆኑ በበሽታው የሚሰቃዩ ሰራተኞችን የኑሮ ሁኔታ ሊያሻሽል እንደሚችል ይገመታል።

 በሊቢያ በኩል ከአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ አውሮፓ የሚገርፉትን ስደተኞች ለመቆጣጠር ተቋቁሞ የነበረው የአውሮፓ ህብረት የባህር ኃይል የቁጥጥር ተልእኮ የተሰጠውን ስራ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረገ ያልቻለ መሆኑን አንድ የእንግሊዝ ፓርላማ ንኡስ ኮሚቴ ዘገባ በቅርቡ ይፋ አድርጓል። ኦፕሬሽን ሶፊያ በሚል ስም ከተለያዩ አገሮች የባህር ኃይል ተቋሞች ተውጣጥቶ ተመስርቶ የነበረው አካል የአስተላላፊዎችን ግንኙነት በመበጠስ፤ ስደተኞችን አሰርገው
በማስገባት ስራ ላይ ተሰማርተውን የነበሩትን የተሰማሩትን የንግድ ተቋሞች በመቆጣጠርና በማፍረስ በኩል ኃላፊነት ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ኃላፊነቱን በተግባር ለማዋል ያልቻለ መሆኑ የኮሚቴው ዘገባ ገልጿል። ኦፕሬሽን ሶፊያ አስተላላፊዎችን ለመቆጣጠር የወሰዳቸው እርምጃዎች ስራውን ጨርሶ ከማጥፋት ይልቅ አስተላላፊዎቹ ታክቲካቸውን ቀይረው በአዲስ ተግባር እንዲሰለፉ ስላደረጋቸው ስደተኞችን ወደ አውሮፓ አስርጎ የማስገባት ተግባር የቀጠለ መሆኑ ተነግሯል። የባህር
ኃይሉ ተልእኮ ያልሰራ በመሆኑ ሌላ መንገድ መፈለግ አለበት በማለት አንዳንድ የፓርላማ አባላት እየተናገሩ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል።

 በደቡብ ሶማሊያ ድሮን የተባለው የአሜሪካ ሰው አልባ መንኮራኩር አምስት የአልሸባብ አባላትን የገደለ መሆኑን የአሜሪካ ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል፡፤ በደቡብ ሱማሊያ ከዋናው ከተማ ከሞጋዲሾ በስተምዕራብ በሚገኝ ቦታ ላይ አንድ የገጠር መንገድ ዘግተው ቀርጥ እያስከፈሉ የነበሩትን የአልሸባብ አባላት ከቦታው ለማስወገድ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ተኩስ በመክፈት ያደረጉት ሙከራ ከአልሸባብ በኩል በተደረገ የተኩስ መልስ ከፍተኛ ችግር ስለገጠመው የአሜሪካ እርዳታ ደርሶላቸው በድሮን በተደረገ የአየር ጥቃት አምስት የአልሸባብ አባላት መገደላቸው ተነግሯል። በአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከአባሪ ኃይል አባላት ላይ የደረሰ ጉዳት
ስለመኖሩ የተሰጠ መግለጫ የለም።

 የቱኒዚያ መንግስት ረቡዕ ግንቦት 3 ቀን በጀመረው አሰሳ ባጠቃላይ ሰላሳ ሰባት የአሸባሪ ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን በሰጠው መግለጫ ገልጿል። በአሰሳው ወቅት ሁለት የአሸባሪ ቡድን አባላት የተገደሉ መሆናችውም ተነግሯል። የተያዙት ግለሰቦች ላለፉት አራት ወራት በጸጥታ ኃይሎች ክትትል ሲካሄድባቸው የነበሩ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ሁሉም የአሸባሪው ቡድን አባላት መሆናቸው ተረጋግጧል። በቁጥጥር ስር የዋሉት በሙሉ መሳሪያ
የመግጠምና የመተኮስ እንዲሁም ቦምብ የማፈንዳት ትምህርት የወሰዱ መሆናቸው ሲታወቅ የተያዙት ግለሰቦች ከፍተኛ የሽብር ተግባር ለመፈጸም በመሰናዳት ላይ የነብሩ መሆናችው ታውቋል።
አንዳንዶቹም ቀደም ብሎ በባርዶ ሙዚየምና ሱስ በሚባለው የመዝናኛ ወደብ ላይ በደረሰው የሽብር ጥቃት ውስጥ ተሳታፊ የነበሩ ሳይሆኑ አይቀሩም ተብሏል።
በተያያዘ ዜና አሸባሪዎችን በቀለጠፈ መንገድ ለመዋጋት እንዲያስችል በማለት አሜሪካ ከፍተኛ ግምት ያለው የመሳሪያ እርዳታ ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን 2008 ዓም ለቱኒዚያ መስጠቷ ተገልጿል። ከወታደራዊ እርዳታው መካከል አነስተኛ የስለላ አውሮፕላኖች፤ የጂፕ መኪኖችና እንዲሁም የተለያዩ ዘመናዊ የመገናኚያ መሳሪያዎች እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።

 የሱዳኑ ፕሬዚዳንት በሽር በዩጋንዳው ፕሬዚዳንት የቃለ መሃላ ስነስርዓት ላይ መገኘትን አስመልክቶ ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን የአሜሪካ መንግስት ድርጊቱን በይፋ አውግዟል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳዮ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ሐሙስ ዕለት በሰጡት መግለጫ በሽር የሰው ልጆችን በጦርነት በማጥፋት ወንጀል በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የተከሰሱ በመሆናቸው የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመጣስ በየአገሮቹ እንደልብ መዘዋወር መቻላቸው አሜሪካን የሚያሳስብ መሆኑን ጠቁመው ሐሙስ ዕለት የበሽርን መገኘት በመቃወም የአሜሪካ የአውሮፓው ህብረት እና የካናዳ ተወካዮች የዩጋንዳውን ፕሬዚዳንት ቃለ መሃላ ስነስርዓት ለቀው የወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል። የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በ1986 ዓም.ሮም ላይ ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን አሜሪካ ይሁንታዋን ሰጥታ አባልነቷን ያላጸደቀች መሆኑ ይታወቃል።

ከነዚህ ጋር አፍሪካዊ መባል አያሳፍርም?

0
0

ነፃነት ዘለቀ

ይሄ አፍሪካዊነት አሁን አሁንስ አይክዱት ነገር ሆኖ እንጂ በእጅጉ እያሳፈረኝ ነው፡፡ ከደቂቃዎች በፊት በኢሳት አንድ ዜና ተከታተልኩ፡፡ በዚያ እየጨስኩና እየተከንኩ ወደ ሥራ ገባሁ፡፡ ከዚህ አስጠሊታ አምባገነንነት መቼ እንደምንላቀቅ እግዜር ይወቀው፡፡
uganda

ዜናው የዩጋንዳን “ምርጫ” ተከትሎ በተከናወነው የአፄ ሙሴቪኒ “የሥልጣን ሽግግር” ላይ ስለተከሰተ አንድ አጋጣሚ ነበር፡፡ እሱም የአሜሪካና አውሮፓ ዲፕሎማቶች ሥነ ሥርዓቱን ረግጠው መውጣታቸውን የሚያትተው ዜና ነው፡፡ ምክንያታቸው እርግጥ ነው ዴሞክራሲ ተጨቆነች ወይ ተረገጠች ብለው ሳይሆን ሙሴቪኒ አይሲስን ማነው አይሲሲን ተናገረብን ብለው በማኩረፋቸው ነው፡፡ እንጂ ለዴሞክራሲማ እነሱ አይጨነቁም – እነሱ የሚጨነቁት ለፖለቲካዊ ጥቅማቸውና ፍላጎታቸው ብቻ ነው፤ የአፍሪካም ሆነ የላቲን አሜሪካና የእስያ ሕዝቦች ቢጠበሱም ሆነ ቢገነተሩ አይሸቷቸውም – እንደሕዝብ ካልሆነ በስተቀር እንደመንግሥት ከሆነ ምዕራባውያን በጥቅሉ አደገኞችና የዚህች ዓለም ዳግም ምፅዓት ዋና ሰበቦች ናቸው፡፡ እነአሜሪካ እኮ ጥንት ያኔ በደጉ ዘመን በግሪኮች አብባ ያፈራች ዴሞክራሲን ዛሬ እጅግ ሠለጠነ በተባለው በትክክል ከታዘብነው ግን ክፉኛ በሰየጠነው በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ውስጥ ገድለው የቀበሩ አስመሳዮች ናቸው፡፡ በዴምራሲ ስም አንዱን ሲገድሉ ሌላውን ያድናሉ፤ አንዱን በመርዝ ሌላውን በጨረር እስከወዲያኛው ያሰናብታሉ፡፡ ሲፈልጉ በልዩ የኮማንዶ ኃይል ያገር መሪን ከቤተ መንግሥቱ ጠልፈው ይወስዳሉ፡፡ በምድር ጎስቋሎች ላይ የምድር ንጉሦች፡፡ የዴሞክራሲ ካርድ የዕቃቃ መጫወቻቸው ናት – ግብዞች!

ከብዙዎች ምሣሌዎች አንዱን ብቻ ወስደን ሳውዲ ዐረቢያን በጨረፍታ እንመልከት፡፡ በቅድመ ልደተ ነቢዩ ሙሀመድ ዘመን በነበረ የቅጣት ሥልት ሐሙስ ሐሙስ አንገት በሰላ ጎራዴ ሲቀነጠስ አጠገብ ሆነው እያዩ (ምናልባትም በድጋፍ እያጨበጨቡ)፣ ሴት አትመርጥም አትመረጥም ብቻ ሳይሆን መኪና እንኳን ማሽከርከር አትችልም ተብሎ በተግባር መገለጹን እያዩ፣ ሴት በፍርድ ቤት ከወንድ እኩል ለምሥክርነት አትበቃም መባልን እያወቁ፣ ሴት ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ካልተሸፋፈነች ከቤት ውጪ መሄድ እትችልም መባልን እየተረዱ፣ አንድ ፉኣድና ቤተሰቡ ሚሊዮኖችን ዝንታለሙን አንቀጥቅጦ እንደሚገዛ ባይናቸው በብረቱ እየተመለከቱ….ይህን ሁሉ ጉድ እያዩ አሜሪካኖች የዚህች ሀገር ጥብቅ ጓደኛና የጭንቅ ቀን ደራሽ ሆነው ስናይ በአሜሪካ እስፊንክሳዊ ተፈጥሮ ሳንገረም ሳንጨነቅም አንቀርም፤ ብቻ ትኑርልን፡፡ ትልቅ ጦር ባይወጉበት ያስፈራሩበት – በጭንቅ ቀናችን የብዙ ወገኖቻችን መጠጊያ ሆናለችና ብድራታችንን በዚሁ በምድር ባንከፍላትም ለማንኛውም የከዳችው እግዜር ከሁሉም የሚጠቅሟት ነገሮች ጨማምሮ ይስጣት፡፡ ክፉ ብቻ የሆኑ አገሮችስ አሉ አይደል? ይህንንስ ማን አይቶበት! በነፃነት ዘመን የሚጠቅሙንን ስንቱን ምሁር ነው አቅፋ የያዘችልን፡፡ የክፉ ቀን ማኩረፊያ አያሳጣ፡፡ ቅጣት አድራሻውን ሲለውጥ ኢትዮጵያ አምራና ተውባ ካሁኑ ትታየኛለች፡፡
ሙሴቪኒ ባለባት አህጉር አባል መሆን አስጠላኝ፡፡ ሀፍረትና አምባገነኖች አይተዋወቁም – ይሉኝታና ወያኔ እንደማይተዋወቁት ሁሉ፡፡ ይህ ሰው ዩጋንዳን ለ5ኛ ዙር ሊቀጠቅጥ በማጭበርበር የወሰደውን መዶሻ ትናንት ተቀበለ – ከማን ተቀበለ ብሎ መጠየቅ ብልህነት ነው – ከራሱ፡፡ ራሱ ከ25 ዓመታት በላይ ጨብጧት የነበረችዋን መዶሻ ከግራ ወደቀኝ አዟዟራትና ራሱን በራሱ መርጦ ራሱ ያዛት፤ ምን ዓይነት ሞኝነት ነው? የምረቃው አጃቢስ ምን ዓይነት ነፈዝ ነው? በመሠረቱ ሰው ሳይቀየር ለምን የምረቃ ሥነ ሥርዓት እንዲደረግ መድረክ ይዘጋጃል? ለምን አላግባብ ወጪ ይወጣል? ኤርትራ ማሪኝ ያስብላል፡፡ ኢሴ እውነቱን ነው፡፡ “ምርጫ እንደኢትዮጵያ ከሆነ በየስድስት ወሩም ማድረግ እንችላለን” ያለው ታሪካዊና በጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ መመዝገብ ያለበት ነው፡፡ በኛ ሀገር እንኳን ለዚህ ማፈሪያ ምርጫ የሚወጣውን ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ እስኪ አስቡት፡፡ በገንዘብ ዕጥረት ምክንያት ስንት ፕሮጀክት አፉን ከፍቶ ተቀምጦ ወዘና ለሌለው የቸከና የመነቸከ ሀገራዊ የፌዝ ቲያትር በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በሰበቡም ለተጓዳኝ ምዝበራ ሲከሰከስ የሚያናድደው አንድም ባለሥልጣን ሲጠፋ በርግጥም ሀገር ለይቶላት እንደጠፋች መረዳት ይቻላል – ሁሉም ተያይዞ ነሆለል ሲሆን ይገርማል፡፡ ምን ዓይነት ወረርሽኝ ገባብን በል? በርሀብና በበሽታ የሚያልቀው ሕዝብ ደንታ የማይሰጣቸው፣ በስደትና በአስተዳደራዊ በደል ወደውጪ የሚጎርፈውና ውስጠቃው በዘራፊዎች የሚቦጠቦጠው፣ የምድርና የባህር ዐውሬ ሲሳይ ሆኖ የሚቀረው ሕዝብ የማይታያቸው፣ ሆዳቸው ከሞላ ሌላ ነገር ትውስ የማይላቸው ዓሣማና ጅብ ባለሥልጣን ይስጠን? ሆ! ወይ ዘመን፡፡

ያኛው ሙጋቤ የሚሉት አኞ ደግሞ ከሁሉም የባሰበት ነው፤ “ሞቼም ቢሆን ከሥልጣን እንዳታወርዱኝ” ብሎ እንደኛው ጉድ እንደመለስ በዐፅሙ ሳይገዛ አይቀርም፡፡ አፍሪካ ትገርማለች – እኔስ ሳስበው በአዋላጆች የህክምና ስህተት እውነተኛ ልጆቿ እየተቀበሩ እንግዴ ልጆቿ የሚያድጉባት ክፍለ ዓለም ሣትሆን አትቀርም – አሁን እስኪ አስቡት – እንዲያው በፈጣሪ ይሁንባችሁና እነመለስና ሙሴቪኒ ሰው ናቸው ትላላችሁ? በተለይ በአፍሪካ ሁሉን ነገር ስታዩት የሚሠራው ሁላ ከጤናማ ሰው የሚጠበቅ አይመስልም – ከጥቂት ነገሮች በስተቀር፡፡ ኦማር አልበሽር የሚሉት ደንቆሮ ደግሞ እኔ ጥንት ከዩንቨርስቲ ተምረቄ በወጣሁ ማግሥት ሥልጣን ላይ ሙጭጭ ያለ ይሄው እኔ በቀደም ለት የልጅ ልጄን ድል ባለ ድግስ ባለም እስከምድረበት ጊዜ ድረስም ያው ሥልጣን ላይ ፊጥ እንዳለ አለ፤ ይሄ ሥልጣን የሚሉት ነገር ምን ዓይነት ሀሽሽ ነው – እርግጠኛ ነኝ የሥልጣንና የሀብት ሱስ ከማንኛውም የአደንዛዥ ዕፅ ሱስ ይበልጣል፤ በህልምም በውንም እየመጣ የሚያርዥ ኃይለኛ ንጥረ ነገር ሳይኖርበት አይቀርም፤ ሰው ሁሉ ሲባላ የማየው በሀብትና በሥልጣን ነው – በተለይ በአፍሪካማ ያለው የተለዬ ነው፡፡ የኞቹን በዋናነት ሳንረሳ በሥልጣን ፍቅር ያበዱ ብዙ ናቸው፡፡ ወይ ሰው መሆን! ወይ አንቺ አፍሪካ! ምን ይዋጥሽ ከቶ! ሥልጣን የሚሉት ደዌ ኅሊናን የሚያስትና በውሸት ካባ የሚያዘንጥ ሆኖ ይቅር?

አንድ ሰው ከአንድ ትውልድ በላይ ሥልጣን ላይ ለመቆየት ድፍረቱን ከየት ያመጣዋል? አጨብጫቢውና አቸፍቻፊውስ እንዴት ያስችለዋል? አንድ ልጅ ከተወለደ ጀምሮ ዐርባና ሃምሳ ዓመት እስኪሆነውና ከዚያም በላይ ካለአንድ መሪ ሌላ እኮ ላያይ ነው፡፡ ያኔ ሀገርም ዜጋም ባለበት መሄድ እንጂ ማደግ ብሎ ነገር አይታሰብም፡፡ መሪው ባለጌና እንደልቡ ይሆናል፡፡ ማንም ከሥልጣን እንደማያወርደው ስለሚያውቅ ለይስሙላና በአሜሪካ የሚወከለውን የፈረደበት የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተብዬውን ለማጭበርበር በሚደረግ የምርጫ ድራማ ራሱን እየደጋገመ ይሾማል፡፡ ዙፋኑ ላይ እንዳለ ያረጃል፤ እዚያው እየሸና እዚያው…እየተጸዳዳ፡፡ ያኔ ሕዝቡም ሀገሪቱም እየለየላቸው ይሄዱና ሁሉም ሳያምርባቸው ያረጃሉ፤ያፈጃሉ፡፡ ልጓም የሌለው ሥልጣን ሕጻን ያደርጋልና መሪው ሕዝቡን እንደብረት ቀጥቅጦ እንደሰም አቅልጦ ይገዛዋል፡፡ ያኔም we all willy-nilly vegetate and in the mean time we all die; here I should say ‘thanks’ to Mr. Death who knows no border when commanding people to stop breathing, be it a king or General, a president or PM, all are his slaves in time of his calling; nobody has the right to defy his order; thanks again Your Excellency Mr. Death who make us all equal at the end of the day. ውይ ሞት ባይኖር ምን ይውጠን ነበር?በ ኧረ የሞትን ዘር ያለምልምልን!
….ይህ ነው የሁላችን አፍሪካውያን ዕጣ! Ciao.

‹‹ሲደበድቡኝም አንተ አማራ፣ አንተ ትምክተኛ… እያሉ ነው፤ በአማራነቴ ሲደበድቡኝና ሲሰድቡኝ እኔ ለእነርሱ አዝን ነበር›› አቶ ዘመነ ምሕረት

0
0

ጥያቄ፡ መቼና እንዴት ወደፖለቲካ እንደገቡ፤ በፖለቲካ ውስጥ ለስንት ጊዜ እንደቆዩ ቢገልጹልን?
ዘመነ ምሕረት፡ ቀጥታ ወደ ፖለቲካ የገባሁት በ1997 ዓ.ም. በቅንጅት ጊዜ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ግን በቀጥታ ባይሆንም የፖለቲካ ተሳትፎ ነበረኝ፡፡ ከ91 ዓ.ም. ከአገዛዙ ጋር በኢትዮጵያዊነት ላይና ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጋር ተያይዞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርር ቤት ተማሪ በነበርኩ ጊዜ ያሳድዱኝ ነበር፡፡ ፈጽሞ ተግባብተን አናውቅም፡፡ በ1993 ዓ.ም በነበረው የአዲስ አበባና በሌሎች ዩንቨርሲቲዎች በነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ እኔ ጎንደር ነበር፤ ሆኖም በቀጥታ እሳተፍ ነበር፡፡ ሆኖም የፖለቲካ ፓርቲ አባል የሆንኩት በ1997 ዓ.ም. የመለው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን በመቀላቀል ነበር፤ ወዲያው ቅንጅት ሲመሠረት ወደ ቅንጅት አብረን ገባን፡፡

13241299_1209752182382726_681976981679470613_n

የፖለቲካ ፓርቲ አባል እንድሆን የአሳደጉኝ ቤተሰቦች አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ አያቶቼ አርበኞች ነበሩ፡፡ ሕጻን እያለሁ ቤት ውስጥ የሚወራው ሁሉ ስለአርበኞች ነበር፡፡ የምንወረው ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያዊነትና የነገሥታቱን የእነ አጼ ቴዎድሮስን፣ ምኒልክን ብሎም የአርበኞችን ወሬ ነበር፡፡ የታሪክ መምህርም የሆንኩት በዚሁ ምክንያት ነው ማለት ይቻላል፡፡ የአኔ ቤተሰቦች በደርግ ብዙ በደል ደርሶባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ እነርሱ በጊዜው ይሉት የነበረው ‹ከእንግዲህ የሚመጣው መንግሥት (በገጠር ተሓት ነበር የሚሉት) ኢትዮጵያን የሚቆራርስ፣ አገር የሚያፈርስ የትግሬ መንግሥት ነው› እያሉ ይነግሩን ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ከሕጻንነቴ ዘመን አንስቶ ምንም ዓይነት ኢሕአዴጋዊ ባሕሪ የለኝም ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የፖለቲካ ትግልን ተቀላቅያለሁ፡፡

ጥያቄ፡ በፖለቲካ ተሳትፎዎ የገጠመዎ ችግር ምንድነው?
ዘመነ ምሕረት፡
በፖለቲካ ትግል ብዙ ችግሮች ደርሰውብኛል፡፡ ለአብነት ያክል እንኳን ሌሊት ቤቴ የማላውቃቸው ሰዎች መጥተው በ1997 ዓ.ም. በጥይት ተስቻለሁ፤ በሰሜን ጎንደር አለፋ ጣቁሳ ወረዳ ነው በጥይት የተሳትኩት፡፡ ደኅንቶች በተለያየ ጊዜ ያሳድዱኝ ነበር፤ ተደጋጋሚም ተክስሻለሁ፡፡ ከሥራ ሁሉ ታግጄ ነበር፤ ስብሰባ ላይ እንዳልሳተፍ ተክልክያለሁ፡፡ በሙያየ የማደግ መብት ተከልክያለሁ፡፡ ከመምህርነት በግዴታ አስወጥተው የቢሮ ሥራ ላይ መድበውኝም ነበር፡፡ እኔ የተማርኩት ታሪክ ነው፤ ነገር ግን እነርሱ የጂአይ ኤስ ባለሙያ አድርገው መደቡኝ፡፡ እንኳን እኔ በእኔ የተነሳ ብዙ ጓደኞቼና ዘመዶቼ ከሥራ ታግደዋል፡፡ በመምህራን ማኅበር ጊዜ ራሱ ብዙ ሰዎች ነው ከሥራ የተባረሩት ከእኔ ጋር ይገናኛሉ ተብለው፡፡

የሚገርምህ ሰዎቹ የኢሕአዴግ አባል ናቸው፤ ነገር ግን ከዘመነ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ቁረጡ ተብለው ነው የተባረሩት፡፡ ለምሳሌ ሙሌ ፍስሃ የማክሰኝት ርእሰ መምህር፣ አቶ አማው እባቡ የጎንደር ዙሪያ መምህራን ማኅበር ሰብሳቢ፣ ይታየው ገበያው የጎንደር ዙሪያ ሱፐርቫይዘር፣ በለጠ ታከለ የሚባል የማክሰኝት ምክትል ርእሰ መምህርና ሌሎች ብዙ ሰዎችም ከእኔ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ከሥራ ወይ ይባረራሉ ወይም ደግሞ ደረጃቸው ዝቅ ብሎ እንዲሠሩ ይደረጋል፡፡ ብዙ ሰዎች የኢሕአዴግ ባለሥልጣን ቢሆኑ በራሱ ከመባረር አይድኑም ነበር፡፡ ይህን ሁሉ የሚያደርገው አንድ የብአዴን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ደሳለኝ አስራደ የሚባል ሰው ነው፡፡ አሁንም ድረስ ብዙዎች እየተሳደዱ ነው፡፡
ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው በፍርሃት ነው፡፡ እርሱ ሌሎችን ሰዎች ስለሚያደራጅ እንዲሁም በዙሪያው ሰው እንዳይቀርበው ካደረግን በፍርሃት ወደ እኛ ይመጣል ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡

ጥያቄ፡ በቅርቡ ታስረው ከፍተኛ የሆነ ቶርቸር እንደተፈጸመብዎ ተገልጿል፡፡ ስለተፈጸመብዎ ነገር በዝርዝር ያጫውቱን?

ዘመነ ምሕረት፡
ጥር 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ማክሰኝት የጽዮን ማርያም ታቦትን ወደ ጥምቀተ ባሕር ስናወርድ በኋላየ የማላውቃቸው ሰዎች መጥተው ያዙኝ፡፡ ሲይዙኝ ምንድን ነው ብየ ገጠምኳቸው፡፡ ከያዙኝ ሰዎች ጋር ስንተናነቅ ፌደራል ፖሊስ ወረረኝ፡፡ የፌደራል ፖሊሶች ከስድስት መኪና በላይ ይሆናሉ፡፡ መጥተው ከዚያው ላይ በአፈ ሙዝ ደበደቡኝ፡፡ ዕውነት ለመናገር መጀመሪያ ሲይዙኝ የሆነ ከቤተሰብ ጋር እኔ ሳላውቀው በተፈጠረ ችግር ሊይዙኝ የመጡ ወንበዴዎች ናቸው የመሠሉኝ እንጅ በመንግሥት የተላኩ እንደሆኑ አላወቅኩም ነበር፡፡ የፖሊስ ዩኒፎርም አልለበሱም፤ ሲቪሎች ናቸው፡፡ ወታደሮቹ ከሕዝብ ፊት ደበደቡኝ፡፡ ልጄና ሚስቴ አብረውኝ ነበሩ፡፡ ልጄ ሕጻን ነው እኔን ሲደበድቡኝ እያለቀሰ መጣ፡፡ የሚገርምህ ልጄን በአፈሙዝ ደበደቡት፡፡ የቀበርከውን አምጣ፣ መሣሪያህን አምጣ አሉኝ፡፡ ቤቴን ሲፈትሹ ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ የሰበሰብኩትን የአዲስ ራዕይ መጽሔት አገኙ፡፡ ምክንያቱም በየወሩ የሚሉትን ለማየት ስበስበው ነበር፡፡ በኋላ የደበቅኩት ቦንብ እርሱ ነው አልኳቸው፡፡ የተለያዩ የፖለቲካና የታሪክ መጽሐፍት እንዳገኙ አሁንም ከልጄም ከሚስቴም ፊት ደበደቡኝ፡፡ ሚስቴ ከፊት አትምቱት ብላ እየጮኸች ወጣች፡፡ ጫማዬን አስወልቀው ካሰሩኝ ወደ መኪና ሲወረውሩኝ ሦስት ዓመት የሚሆነው ልጄ መጥቶ ሲይዘኝ መጥቶ ሲይዘኝ በአፈሙዝ መቱት፡፡ ከዚያ ወደ ጉማራ ወንዝ ስንደርስ ዓይኔን ሸፈኑኝ፤ ከዚያ በኋላ የት እንዳስገቡኝ አላውቅም፡፡ አዘዞ ተክለ ሃይማኖት አካባቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡ መጀመሪያ የያዘኝ ሰው አሸናፊ ተስፋው የሚባል ነው፤ ከዚያ በኋላ ግን አላውቃቸውም፤ ትግሬዎች ናቸው፡፡ ትግርኛ ቋንቋ ተናገር፤ አንተ ትምክተኛ፣ ነፍጠኛ፣ የአማራን የበላይነት ለማምጣት የምትጥር፣… ብዙ ብዙ ነገር ነው የሚሰድቡኝ፡፡ የዱላው ነገር ቅጥ የለውም፡፡ ከአውሬም አይጠበቅ እንኳን ከሰው፡፡ እኔን በጣም ደብድበውኛል፤ የኔ ሳይሆን ልጄ ላይ የሠሩት ነው የሚያሳዝነኝ፡፡ እኔማ መቼም አንድ ጊዜ የፖለቲካ ተሳትፎ አድርጌያለሁ፡፡ ወንጀል ባይሆንም ተቃውሚያለሁ፤ አምኜበትም ነው የገባሁ፡፡ ልጄ ግን ምንም ሳይሠራ መደብደቡ ያሳዝነኛል፡፡
ወያኔዎቹ ከአማራው ላይ ያላቸው ጥላቻ በጣም ከፍተኛ ነው ብልህ አልገልጸውም፤ በጣም በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ሕወሓቶች በተቃዋሚ ላይ ሳይሆን በአማራ ላይ ጥላቻ እንዳላቸው ነው የተገነዘብኩት፡፡ ሲደበድቡኝም አንተ አማራ፣ አንተ ትምክተኛ… እያሉ ነው፡፡ ስታያቸው ጥላቻቸው ከፍተኛ በሽታ የሆነባቸው ይመስለኛል፡፡ በአማራነቴ ሲደበድቡኝና ሲሰድቡኝ እኔ ለእነርሱ አዝን ነበር፡፡ የሚናገሩት ቋንቋ ከሰው የማይጠበቅ የአውሬ ልትለው ትችላለህ፡፡ አማራ ሆኖ መወለድ ወንጀል ነው ለእነርሱ፤ አማራ ምን እንዳደረጋቸው አንተ ንገረኝ፣ ሌላም ሰው ካለ ቢያስረዳኝ ደስ ይለኛል፤ የታሪክ መረጃም ባገኝ ደስ ባለኝ፤ ያሳዝናል፡፡ ከሚደበድቡኝ ይልቅ አነጋገራቸው ነው የሚያመኝ ለእኔ፡፡ ዱላቸውማ ማንንም በተለይ አማራ ሁሉ እንደሚደበድቡት ነው የደበደቡኝ፡፡ አነጋገራቸው ከጤነኛ ሰው ሳይሆን አእምሮው ከታወከ ሰው እንኳ የማይጠበቅ ነው፡፡
ጉድጓድ ውስጥ ራቁቴን ከተው ይሸኑብኛል፤ ይተፉብኛል፤ ትግርኛ ቋንቋ ተናገር ይሉኝ ነበር፡፡ ሱሪየን ፓንቴን ሁሉ ጨምሮ አስወልቀውኛል፡፡ ከላየ ላይ ከሸሚዜ ውጭ አልነበረም፡፡ ዓይኔ ተሸፍኖ ስለነበር የሚደበድቡኝን ሰዎች አላውቃቸውም፡፡ የምሰማው ስድባቸውን ብቻ ነው፡፡ ከፈለጉ ደግሞ አንስተው ሰቅለው እያገላበጡ ይደበድቡኛል፡፡ ያሳዝናል፤ ሁሉንም ለመናገር ቃላት የለኝም፤ አልችልምም፡፡ በጠቅላላው ደስ የማይል ነገር ነው፡፡
ወደ አዲስ አበባ ሲያመጡኝ ወዴት እየወሰዱኝ እንደሆነ አላወቅኩም ነበር፡፡ ማርቆስ ስደርስ ዓይኔን ገለጡልኝ፡፡ የመኢአድ አባል የሆነው መለሰ መንገሻን ማሰራቸውን አላወቅኩም ነበር፡፡ በድብደባ ብዛት ሁለታችንም ራሳችን ስተን ነበር፡፡ ዓይናችን ማርቆስ ላይ የተሸፈነውን አንስተውልን ማርቆስ ካለፍን በኋላ ሽንት እንድንሸና ከመኪና ወረድን ወረድን፡፡ ከዚያ መለሰ መንገሻ መሆኑን በዓይኑ ለየሁት እንጅ የሁለታችንም ሰውነት በድብደባ ብዛት ተለዋውጠን ስለነበር ማን ማን መሆናችን ራሱ አይለይም ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ስንገባ ጨለማ ቤት ውስጥ ቢሆንም ከሰው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተጨመርን፡፡

የተያዝንበት ምክንያት ከፓርቲው እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እነርሱ ሲጠይቁኝ የነበረው ለምን ከአቶ አበባው መሐሪ ጋር አብረህ አትሠራም? የመኢአድ አመራር ሆኖ ከአንተ ጋር አብረው የሚሠራውን ሰው ንገረን፡፡ ያደረጀውን ሰው ንገረን፡፡ ለምን አርፈህ አትቀመጥም? የአማራ የበላይነትን ልታመጣነው የምትታገለው የሚሉ ነገሮችን ነው የጠየቁኝ፡፡ ከግንቦት ሰባት ጋር ትገናኛለህ ምናም የሚሉትን ለስሙ ነው የሚጠይቁኝ፡፡ ወዲያውኑ ከአማራ ጋር አያይዘው ነው የሚወርዱብኝ፡፡ ማጠንጠኛቸው ዞረው ዞረው ከአማራ ጋር ነው የሚያይዙት፡፡

በማዕካላዊም በቃሊቲም ከ14 ሕፃናት እስከ 70 ዓመት የሚሆናቸው አዛውንት አማሮች ታስረዋል፡፡ ከእኔ ላይ የደረሰው ድብደባና ማሰቃየት ከሕፃናትም ከሽማግሌዎችም ላይ ደርሷል፡፡ ልዩነት የለውም፡፡ በደረጃ ባስቀምጥልህ በዓይኔ እንዳየሁት እንደ አበበ ካሴ የተጎዳ የለም፡፡ አበበ ካሴ አሁን ሰባት ዓመት ተፈርዶበት ዝዋይ ነው፡፡ እሱን ጓያ የሰበረው አስመስለው ሽባ ሆኖ ነው እየሔደ ያለው፤ አካሉ ስንኩል ሆኗል፡፡ እንደነገረኝ ከሆነ መውለድም ከዚህ በኋላ አይችልም፡፡ አበበ አካሉ የተባለው የመኢአድ አባልም በድደባ እጁ ሽባ ሆኗል፡፡ ሦስተኛ እንደ ጌትነት ደርሶ፣ መቶ አለቃ ጌታቸውና ቢሆን አለነ ዓይነት ድብደባና ቶርቸር የደረሰሰበት ሰው የለም፡፡ የአግበው ሰጠኝ፣ የመለሰና የእኔ ተመሳሳይ ነው፡፡ የእኔን ድብደባና ቶርቸር ከእነርሱ ጋር አላወዳድረውም፡፡ የእነርሱ ፈታኝ ነው፤ ይከብዳል፡፡
በተለይ ሲመረምሩህ ብሔርህ ማን ነው? ሲሉህ አማራ ነው ካሉህ ጥላቻቸው ይበረታል፤ በጣም ይገናል፡፡ ከዱላቸው ፊታቸው ያስፈራል፡፡ በጣም የተለየ ያደርጉታል፡፡ ገምናናው ጨቅሌ የሚባል የ14 ዓመት ልጅ ከቤተሰቦቹ ጋር ተጣልቶ ከአጎቱ ልጅ ጋር የቀን ሥራ ለመሥራት ሲሔድ ዳንሻ ላይ ያዙት፡፡ ታጥቀህ ኹመራን ልታስመልስ ነው ብለው ነው የደበደቡት፡፡ እዚያ አካባቢ አማራዎች ከተያዙ የሚያገናኙት ከወልቃይትና ጠገዴ ድንበር ጋር ነው፤ ከሥልጣናቸው ጋር ነው የሚያገናኙት፡፡
አስበው ሕፃን ነው፤ ከፍተኛ ድብደባ ደብድበውት አእምሮው ተጎድቷል፡፡ ሲተኛ ይቃዥ ነበር፡፡ እኔና በላይነህ ከመካከላችን እየተኛ ‹‹መጡብኝ!›› እያለ ሲባባ እንደግም ነበር፡፡ አስበው ይህ ልጅ ጭልጋ አካባቢ የገበሬ ልጅ ነው፡፡ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ በአእምሮው ገና ልጅ ነው፡፡ የራሳቸውን መሬት ቀምተው እነርሱ ኢንቨስተር ሆነው፤ ከእነርሱ በቀን ሥራ ለመሥራት ሲሔዱ አንተ ኤርትራ ልትሔድ ነው ተብለው ነው የሚደበደቡት፡፡ እትብታቸው በተቀበረበት መሬት ላይ ነው አማሮች ግፍ የሚቀምሱት፡፡

ጥያቄ፡ እንዴት ተፈተ? አሁንስ ሕይወትዎ አስተማማኝ ነው ወይ?

ዘመነ ምሕረት፡
አሁን ካለሁበት በእርግጥ እስሩ ይሻለኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም ክትትሉ ቤተሰቦቼም እኔም ላይ በጣም ከባድ ነው፡፡ ሕይወቴ አሁን የበለጠ አደጋ ላይ እንዳለ አምናለሁ፡፡ የተፈታሁት አቃቢ ሕግ አስተማማኝ ማስረጃ ማቅረብ ስላልቻለ ነው፡፡ ስለዚህ ፍርድ ቤቱ ከሽብር አውጥቶ ወደ ወንጀል ክስ ቀየረው፡፡ ስለዚህ በወንጀል ሕጉ መሠረት ነው በዋስትና የወጣሁት፡፡ ገና ዋስትና ተሰጠኝ እንጅ ነጻ ነህ አልተባልኩም፡፡
ከሥራ ታግጃለሁ (ደብዳቤውን እያሳየ)፡፡ ባለቤቴ መምህር ናት በእርሷ ደመወዝ ነው ቤተሰብ የምናስተዳድር፡፡ ከሥራየ ያታገድኩት ደግሞ በሽብር ወንጀል የተከሰስክ በመሆኑ ነው የሚለው፡፡ እና ከሥራ አንቀበልህም ብለው አባረሩኝ፡፡ በካፌ ብቀመጥ፣ ገጠር ብሔድ ከጎኔ የማይከተሉኝ ጊዜ የለም፡፡

ጥያቄ፡ በትግሉ ይቀጥላሉ?
ዘመነ ምሕረት፡
አዎ በእርግጠኛነት በትግሉ እቀጥላለሁ፡፡ ምንም ጥርጣሬ አይግባህ፡፡ የትግላችን ሁኔታ በጣም ጠንካራ ጓዶቻችን አሉ እና እነርሱ ጋር ሆነን ውሳኔ ላይ እንደርሳለን፡፡ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክረን እንቀጥላለን፤ በኮረኮሙን ቁጥር ካላማችን የምንሸሽ ሰዎች አይደለንም፡፡ ከእነ አቶ ማሙሸት አማረና አቶ አብርሐም ጌጡ ጋር ተማክረን ወደፊት እንቀጥላለን፡፡ የመንፈስና የጽናት አባታችን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ካስቀመጡልን የትግል መስመር ፈቀቅ አንልም፡፡

የሕወሓት ደህንነት ከዚህ ቀደም በግንቦት 7 ስም የታሰሩ ሰዎችን እንደ አዲስ እንደተያዙ በማስመሰል ፕሮፓጋንዳ ሊሰራ መሆኑ ተጋለጠ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) አርበኞች ግንቦት 7 በአርባምንጭ ከተማ በወሰድኩት እርምጃ 20 የሚሆኑ የመንግት ወታደሮችን ገደልኩ ሲል መንግስት ደግሞ በኡጋንዳ በኩል አድርገው በኬንያ አቋርጠው በደቡብ ክልል ውስጥ ጥቃት ሊያደርሱ የተዘጋጁ አሸባሪዎችን ይዣለሁ ሲል መግለጫ ማውጣቱ አይዘነጋም:: ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከአሸባሪዎች ያዝኩት ብሎ በድረገጹ ያሳየው ፎቶ ግራፍ የአሜሪካ ወታደሮች ከዚህ ቀደም ሶሪያ ላይ የማረኩትን ፎቶ ግራፍ ነበር::

File Photo

File Photo

እንደ ምንጮች ገለጻ ሕወሃት መራሹ መንግስት አሸባሪዎችን ይዣለሁ ይበል እንጂ.. ወታደሮቹን ከገደሉት የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ውስጥ 4ቱ ሕይወታቸው ከማለፉ ውጭ ሌሎቹ ተሰውረውበታል:: በዚህም የተነሳ ማስረጃ በማጣቱ እንደውም ከዚህ ቀደም በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎችን እንደ አዲስ እስረኛ በማስመሰል ለማቅረብና በዚህ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ሊሰራ መሆኑ ተጋልጧል:: ቦታዎችን በማስጠናትና ከኤርትራ እንደተላኩ በማስመሰል የተለያዩ ፕሮፓጋንዳዎች ሊቀርቡ በዝግጅት ላይ ናቸው::

ምንጮቹ እንደሚሉት ከኤርትራ የተላክን ነን ብላችሁ እመኑ እየተባሉ ብዙዎቹ እየተገረፉ ሲሆን ይህን አምነው በቴሌቭዥን ከቀረቡ ሊፈቱ እንደሚችሉ አለበለዚያ ግን አሰቃይተው እንደሚገድሏቸው እንደተነገራቸው ምንጮች ገልጸዋል::

 

የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ድርጅታቸው በአርባምንጭ በወሰደው ጥቃት አባሎቻቸው የሕይወት ዋጋ እንደከፈሉ መግለጻቸውና ቁጥሩን ግን አለመናገራቸው ይታወሳል::

Sport: የምርጥ ስብዕና ባለቤት የሆነው –ሁዋን ማታ

0
0

 

በማንችስተር ከተማ ፉትቦል ሆቴል ሁዋን ማታ ኦልድ ትራፎርድ እና የሰር ማት በስፒን ጎዳና እየቃኘ ተመስጧል፡፡ በቅርቡ 28ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ያከበረው ስፔናዊው አማካይ እግርኳስን በደስታ ስሜት ውስጥ ሆኖ እየተጫወተ ይገኛል፡፡

Juan matta

እግርኳስ ተጫዋቾች በዚህ ወቅት የሚያገኙት ደመወዝ ከፍተኛ ነው ሲባል እርሱ ግን ይሄንን አመለካከት የሚቀይር አስተያየትን ይሰጣል፡፡ ማታ በኦልድ ትራፎርድ ሳምንታዊው 150 ሺ ፓውንድ ማግኘቱ ከከፍተኛ ተከፋይ ተጨዋቾች መሀከል አንድ ቢያደርገውም እርሱ ግን ያን ያህል የተደነቀ አይመስልም፡፡

‹‹ከቀሪው ማህበረሰብ አንፃር የሚከፈለን ክፍያ በጣም ትንሽ ነው›› የሚል አስተያየትን የሚሰጠው ማታ፣ ‹‹ነገሩ ተጋንኖ መቅረቡ ተገቢ አይደለም›› በማለት ይናገራል፡፡

በመንገድ ላይ እግርኳስ የሚከፈለን ክፍያ በጣም ትንሽ ነው›› የሚል አስተያየትን የሚሰጠው ማታ፤ ‹‹ነገሩ ተጋንኖ መቅረቡ ተገቢ አይደለም›› በማለት ይናገራል፡፡

በመንገድ ላይ እግርኳስ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ግሎባል አምባሳደር መሆኑ ደግሞ ምን ያህል ለእግርኳስ የቀረበ ስሜት እንዳለው ማረጋገጫ ነው፡፡ ማታ ነገሮችን የሚመለከተው በጣም በጥልቀት ነው፡፡

የምርጥ ስብዕና ባለቤት የሆነው የቀድሞው የቫሌንሲያ ኮከብ በሜዳ ውስጥ ደግሞ እግርኳስን ውብ አድርጎ መጫወት ይችልበታል፡፡ አማካዩን የእግርኳሱ ዓለም በከፍተኛ ክፍያ ያበደ ነው? የሚል ጥያቄ ስታነሱበት በጣም በተረጋጋ ስሜት ውስጥ ሆኖ ‹‹የምሰጠው አስተያየትን የመሰለኝን እንጂ ምላሽ ለማግኘት ፈልጌ አይደለም፤ ስለ እግርኳስ እና ህይወት ስጠየቅ የመሰለኝን ምላሽ እሰጣለሁኝ፡፡ እግርኳስን በጥልቀት እረዳለሁኝ፡፡ ይሄንን ስፖርት በሚገባ እረዳለሁኝ፤ ህይወቴን እወደዋለሁኝ፡፡ እግር ኳስን መጫወትም ያስደስተኛል፤ እግርኳስ ተጨዋቾች የሰው ልጆች ናቸው፤ ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ሰብዕና አለው፤ ሁላችንም የራሳችን የሆነ እይታ አለን፡፡ በመካከለኛ ደረጃ ላይ የምገኝ ተጨዋች እንደሆንኩኝ አላውቅም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ራሴን መሆን እፈልጋለሁኝ፡፡ የምሰጠው አስተያየት ምላሽ ካለው ምክንያቱ አስተያየቱ የተለየ በመሆኑ ሊሆን ይችላል›› የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡

ማታ ባለፈው ሐሙስ በካሪንግተን የልምምድ ማዕከል የልደት በዓሉን ኬክ በመቁረስ ሲያከብር ከቆየ በኋላ ምሽት ላይ ከቡድን ጓደኞቹ ጋር ራት ለመመገብ ወደ ማንቸስተር ከተማ ወጣ ብሏል፡፡ በማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ወደ ማንቸስተር ከተማ ወጣ ብሏል፡፡ በማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሉዊ ቫን ሃል ወደ ዋናው ቡድን ያሳደጓቸው ተጨዋቾች ስጋት ቢሆንም ግን ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር የአውሮፓ እና ዓለም ዋንጫ ያነሳው ማታ በቀጣይ አቅሙን አውጥቶ በመጠቀም በቋሚነት መጫወት እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡

‹‹በቀጣይ የእግርኳስ ብቃቴ ጫፍ ላይ እንደምገኝ ተስፋ አደርጋለሁኝ›› ይላል በጃንዋሪ 2014 ከቼልሲ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ሲዘዋወር 37.1 ሚሊዮን ፓውንድ የወጣበት አማካይ፣ ‹‹ከ27-30 ዓመት የአንድ ተጨዋች የብቃቱ ጫፍ መገኛ ዕድሜ ነው፡፡ ከምንም በላይ በዚህ ዕድሜህ ከፍ ያለ ልምድ ታገኛለህ፤ ተደጋጋሚ ጨዋታዎችን ታከናውናለህ፤ በእግርኳስ ህይወቴ ጠንከር ያለ ጉዳት አለማስተናገድ በጣም ያስደስታል፡፡ በቀጣይ የተሻለ ብቃት ማግኘት እንደምችል ተስፋ አደርጋለሁኝ፡፡

mata juan

‹‹እስካሁን በተጫወትኩባቸው ክለቦች ቫሌሲያ እና ቼልሲ እንዲሁም ብሔራዊ ቡድን በዕድሜ ትንሹ እኔ ነበርኩኝ፤ በአሁኑ ሰዓት በ1995 እና 1996 የተወለዱ ተጨዋቾችን በቡድናችን ውስጥ እየተመለከትኩኝ ነው፡፡ እኔ የተወለድኩት ደግሞ በ1988 ነው፡፡ ይሄ የህይወቱ ጉዳይ ነው፡፡ እያወራን ያለነው ስለ እግርኳስ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ዕድሜዬ እየገፋ እንደሆነ አውቃለሁኝ፡፡

‹‹አሁን በምገኝበት ሁኔታ የእግርኳስ ህይወቴ መጠናቀቂያ ላይ እገኛለሁኝ ብዬ አላስብም፡፡ ምክንያቱም ሁልጊዜም ልምምድ እሰራለሁኝ፡፡ እጫወታለሁኝ፤ አስደሳች ህይወትን እየመራሁኝ እገኛለሁኝ፡፡ በልምምድ ሜዳ ላይ ጠንክሬ መስራቴ ተጠቃሚ አደርጎኛል፡፡

በማንቸስተር ዩናይትድ ህይወት ለማታ ቀላል ነው ማለት አይቻልም፡፡ ስፔናዊው በቫን ሃል ሁለተኛ ዓመት ውጤታማ ለመሆን የተቸገረው ቡድን አባል በመሆኑ እያንዳንዱ ውጣ ውረድ ፍፁም አደጋች ነው፡፡ ለከርሞ በቻምፒዮንስ ሊጉ የሚያሳትፈውን ውጤት ለማግኘት እየታገለ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ በኤፍኤካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ሜይ 21 ከክሪስታል ፓላስ ጋር ይጫወታል፡፡

ማታ በሌይስተር ሲቲ ብቃት በጣም ተገርሟል፡፡ ዘንድሮ የአሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኒዮሪ ቡድኑ በማይዋዥቅ አቋም ስኬታማ ሆኗል፡፡ ስፔናዊው አማካይ ‹‹ሌይስተር ሲቲዎች ዘንድሮ በጣም ጥሩ ናቸው፡፡ የእነርሱ ሻምፒዮን መሆን ያን ያህል አስገራሚ አይደለም፡፡ በጣም መኩራት አለባቸው›› የሚል መረጃን ሰጥቶ፤ ‹‹እርግጥ ነው ይሄ የውድድር ዓመት ለእኛ ቀላል አይደለም፡፡ በተለይ ዲሴምበር እና ጃንዋሪ ላይ ተደጋጋሚ ሽንፈት አስተናግደናል፡፡ ነገር ግን እንደ ማንቸስተር ዩናይትድ አይነት ትልቅ ክለብ ውስጥ ስትጫወት ሁሉም ነገር ፈታኝ ነው፡፡ ሆኖም ጫናውን በሚገባ መቋቋም ግድ ይልሃል፡፡ ተደራራቢ ጨዋታዎችን ስታሸንፍ ሁሉም ነገር አስቸጋሪ ነው፡፡ ቀሪዎቹን ጨዋታዎች በሙሉ በድል ይዘን እንፈፅማለን፡፡ ይሄንን አሳክተን ለጥቂት ዓመታት ያጣነውን የኤፍኤ ካፕ ዋንጫ ብናነሳ የስኬት ዓመት ተደርጎ ሊታይ ይችላል፡፡ ይሄንን ዋንጫ ካነሳን 12 ዓመታት ተቆጥሯል›› ይላል፡፡

የጆዜ ሞውሪንሆ ስም ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር መያያዙን ተከትሎ ከስታምፎርድ ብሪጅ ለመሰናበት ምክንያት ስለሆኑት አሰልጣኝ ጥያቄ ስታስከትሉ፤ ‹‹በቀጣይ ሊሆን ስለሚችል ነገር ማውራት ፍትሃዊ አይደለም፤ ከፊታችን ወሳኝ ጨዋታዎች ይጠብቁናል፤ ይሄ ለአሰልጣኙ ክብር መንፈግ ነው፡፡ ይሄንን ጉዳይ ለማውራት ጊዜው አሁን አይደለም የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡

 

 

Sport: ባርሴሎና የስፔን ሻምፒዮን ሆነ

0
0

Barcelona

(ዘ-ሐበሻ) የካታሎናዊው ክለብ ባርሴሎና የስፔን ላሊጋን አንሳ:: ባርሴሎና በመጨረሻዎቹ ጥቂት ጨዋታዎች ነጥቦችን በመጣሉ ተከታዮቹ ሲጠጋጉት የቆዩ ሲሆን በዚህም ሻምፒዮን ይሆናል ወይ? የሚለው አጠያያቂ ሆኖ ነበር::

ሆኖም ግን ባርሳ ዛሬ በተደረገው የላሊጋው የመጨረሻ ጨዋታው ግራናዳን 3 -0 አሸንፎ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን አረጋግጧል:: ጎሎቹን ያስቆጠረው ደግሞ የፒቺቺ አሸናፊ ሆኖ ያጠናቀቀው ስዋሬዝ ነው። ስዋሬዝ ከመስመር ተጨዋቾቹ አልባ እና አልቬዝ የተሻገለት ኳስ አጨራረሱን በማሳመር አስቆጥሯል:: ለ3ኛው ጎል አመቻችቶ ኳሱን ያቀበለው ደግሞ ብራዚላዊው ኔማር ነበር::

ባርሴሎና የስፔንን ላሊጋ 24 ጊዜ ሲያሸንፍ ሪያል ማድሪድ 32 ጊዜ አሸንፏል:: ባርሴሎና ባለፈው ዓመትም የላሊጋው ሻምፒዮን ነበር::


አትሌቶቻችን ዛሬ በተደረገው ዳይመንድ ሊግ ውድድር አመርቂ ውጤት አስመዘገቡ –ሙክታር ያሸነፈበትን ቪዲዮ ይዘናል

0
0

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ ቅዳሜ ሜይ 14, 2016 በተደረገው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ዘርፎው ድል እንደቀናቸው ታወቀ::

የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ድረገጽ እንዳስታወቀው በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያዊው ሙክታር ኢድሪስ 12:59.96. 2 በመግባት አንደኛ ወጥቷል:: እንዲሁም አባዲ እምባዬ; ዮሴፍ ቀጀላና ሃጎስ ገብረህይወት በዚሁ በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ውድድር ከ4 እስከ 6ኛ ደርጃ ወጥተዋል::
በ1500 ሜትር ውድድር ዳዊት ስዩም; በሱ ሳዶ; ጉዳፍ ጸጋዬ ከ3 እስከ 5ኛ ወጥተዋል::

በ3000 ሜትር ውድድር ሶፊያ አሰፋ 9:21.07. 4 በመግባት 3ኛ ወጥታለች::
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዛሬ በተደረገው ዳይመንድ ሊግ ውድድር አመርቂ ውጤት አስመዘገቡ

ከእስር የተፈታው ታጋይ ዳንኤል ሺበሺ ልብ የሚነካ ቃለምልልስ ”የደረሰብኝን በደልና ስቃይ በቃላት ለመግለፅ ይከብደኛል”|መነበብ ያለበት

0
0

daniel shibeshi
ከአዘጋጁ: በነአብርሃ ደስታ የክስ መዝገብ ተከሶ ከ22 ወራት እስር በኋላ የተፈታው የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር ታጋይ ዳንኤል ሺበሺ ከ እስር ከተፈታ በኋላ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ቃል ልብ የሚሰብር ቃለምልልስ አድርጓል:: ይህን ታጋይ በገንዘብና በሞራል የመደገፍ ሃላፊነት እንዳለብን ከቃለምልልሱ በፊት እያስታወስን የአዲስ አድማስ ጋዜጣን ዘገባ እንደወረደ ለግንዛቤዎ አቅርበናል::

የመጣሁት ከትግል እንጂ ከሽርሽር አይደለም ይላሉ
ዳንኤል ሺበሺ የቀድሞው አንድት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል
ኃላፊና የደቡብ ቀጠና ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበረ ሲሆን ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም
በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ ላለፉት 22 ወራት በእስር ላይ
ቆይተው ባለፈው ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ከእሥር ተፈትተዋል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ
ናፍቆት ዮሴፍ አየር ጤና አካባ በተለምዶ ቻይና ካምፕ በተሰኘው የአቶ ዳንኤል መኖሪያ ቤት
ተገኝታ በእስር ቆይታቸው ስላሳለፏቸው ነገሮች፣ ስለወደፊት ሀሳባቸውና ተያያዥ በሆኑ
ጉዳዮች ዙሪያ ተከታዩን ቃለ ምልልስ አድርጋለች

እንዴትና በምን ሁኔታ ነበር የተያዙት?
የተያዝኩት ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በተለምዶ ጀርመን አደባባይ በሚባለው ቦታ ነው፡፡ ከያዙኝ በኋላ ከፍተኛ ድብደባ አደረሱብኝ፡፡ ከድብደባው በኋላ ራሳቸው እየመሩ ወደ መኖሪያ ቤቴ ይዘውኝ መጡና ቤቴ እስከ ምሽቱ 2፡30 ሰዓት ድረስ ሲበረበርና ሲፈተሽ አምሽቶ መጨረሻ ላይ ወደ ማዕከላዊ ምርመራው ተወሰድኩ፡፡ እንግዲህ እዚያ ለ120 (አራት ወራት) ቆይቻለሁ ማለት ነው፡፡

በማዕከላዊ ስለነበርዎ የእስር ቤት ቆይታና ሁኔታ ሊነግሩኝ ይችላሉ?
ማዕከላዊ ከባድ ጊዜ ነው ያሳለፍኩት፡፡ ሳይቤሪያ ተብሎ በሚጠራውና እጅግ ቀዝቃዛ ክፍል ነው ታስሬ የነበረው፡፡ ክፍሉ ቀዝቃዛ ብቻ ሳይሆን በረዷማ ነው ቢባል ይቀላል፡፡ በዚህ ቆይታዬ ግራ እጄ ከትከሻዬ እስከ ጣቶቼ ድረስ ደንዝዞ ሽባ ሆኖ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ እየተሻሻለ መጣ እንጂ አይሰራም ነበር፡፡ አሁንም ቅዝቃዜ ሲሆን ያመኛል፤ ሙቀት ሳገኝ ትንሽ ይሻለኛል፡፡ እና ማዕከላዊ ሁኔታዎች ከባድ ነበሩ፡፡

ከማዕከላዊ በኋላስ የት ነበር የታሰሩት?
ወደ ቅሊንጦ ነው የተወሰድኩት፡፡ በጣም የሚገርመው ለምን እንደሆነ ባላውቅም፡፡ እኔ ላይ ሁኔታዎች ጠንክረው ነበር፤ እርግጥ የጉዳት መጠኑ እኔም ሀብታሙ አያሌውም የሺዋስም ሆነ አብርሃ ደስታ ላይ እኩል ነው፤ ግን ዝም ብዬ ሳየው እኔ ከወዲያ ወዲህ ብዙ ተንገላትቻለሁ፡፡ በመጀመሪያ ቂሊንጦ ዞን አንድ አስገቡኝ፡፡ ከዞን አንድ ወደ ዞን ሶስት ወሰዱኝ። ከቂሊንጦ ዞን ሶስት እንደገና ወደ ቃሊቲ ዞን ሶስት አመጡኝ። ከቃሊቲ ዞን ሶስት ወደ ዞን ስድስት ወሰዱኝ፤ ከዞን ስድስት አወጡና ደግሞ ወደ ዞን ሁለት አመጡኝ፡፡ ከዞን ሁለት አንደኛ ቤት አውጥተው ደግሞ መስኮትም ምንም የሌለው ጨለማ ቤት 60 ቀናት አሰሩኝ፡፡ ብቻ ምን አለፋሽ.. ብዙ አንከራትተውኛል፡፡ ከዚያ ከጭለማ ቤት አውጥተው ዞን ሁለት ሁለተኛ ቤት አስገቡኝ። እንደገና ደግሞ ዞን አንድ ጭለማ ቤት ውስጥ 120 ቀናት (አራት ወር) አሰሩኝ፡፡ ያላዳረስኩት እስር ቤት የለም፡፡

ከዞን ዞን፣ ከክፍል ክፍል ሲዘዋወሩ ምክንያቱን ያውቁታል?
እኔ እስከዛሬ የማውቀው አንዱን ምክንያት ነው፤ ሌላውን አላውቀውም፡፡
እስኪ እሱን ይንገሩኝ…
አንዱ ምክንያት አንድ ጊዜ ቤተ – መፃህፍት ቁጭ ብዬ አንድ መፅሀፍ ሳነብ ታሪኩ መሰጠኝና ወደ ሶስት ገፅ የሚሆን ማስታወሻ ፃፍኩኝ፡፡ ከዚያ በፍተሻ ወቅት ወረቀቱ ተያዘ፡፡ “ቤተ መፅሐፍት ውስጥ ያለውን ማንኛውንም መፅሀፍ ማንበብ ይቻላል፤ መፃፍና ወረቀት ይዞ መውጣት አይቻልም” በሚል ምክንያት ነው ጭለማ ቤት እንድታሰር የተደረግሁት፡፡ ከዞን ዞን፣ ከቂሊንጦ ቃሊቲ ለምን ያዘዋውሩኝና ያንከራትቱኝ እንደነበር ግን አላውቅም፡፡ መጨረሻ ላይ ከዞን አንድ ጨለማ ቤት ወደ ዞን ስድስት ወደነ አብረሀ ደስታ ክፍል ተወስጄ የመጨረሻዎቹን አስር ቀናት አሳለፍኩኝ፡፡ እስር ቤት ከገባሁ አልጋ ላይ የተኛሁትም እነዚህን አስር ቀናት ብቻ ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች ሳይ በእኔ ላይ ፈተናዎች ጠንክረውብኝ ነበር እላለሁ፡፡ ምክንያቱም አልጋ ከልክለውኝ ሲሚንቶ ላይ ስተኛ ነው የከረምኩት፤ ህክምናም ተከልክያለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ ጠይቄ ህክምና ከተወሰድኩ በኋላ ጤና ጣቢያ ህክምና እንዳላገኝ ተደርጌያለሁ፤ ህክምና እንዳላገኝ ያደረጉትን ሰዎች ስምም አውቃለሁ፤ ቤተሰቤ እንዳይጠይቀኝ ተከልክያለሁ፡፡ ለምሳሌ እናት፣ አባት፣ ሚስት፣ እህት፣ ወንድም እንዲጠይቅ ይፈቀዳል ተብሎ፣ ከእኔ ጋር የአባቱ ስም ተመሳሳይ ያልሆነ ወንድም እህት መጠየቅ አይችልም፡፡ እንዴ! የእናትሽ ልጅ የሆነ ወንድምና እህት ይኖርሻል፤ ያ ሰው የግድ እከሌ ሺበሺ ካልተባለ እኔን መጠየቅ አይችልም ነበር። እናትና አባቴ ክፍለ ሀገር ናቸው፤ በየጊዜው እየተመላለሱ መጠየቅ አይችሉም። ባለቤቴ ነበረች ስትንከራተት የነበረችው፡፡ ቤተሰብ እያስተዳደረች፣ የውጭውንና የቤቱን ስራ ሰርታ በየጊዜው እኔን ለመጠየቅ መመላለስ ምን ያህል ፈተና እንደሆነ ማሰብ ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ የደረሰብኝን በደልና ስቃይ በቃላት ለመግለፅ ይከብደኛል፡፡ በምኖርባት አገር የገዛ ወገኔ እንዲህ አይነት በደል በእኔ ላይ ማድረሱ ጭካኔው ከምን እንደሚመነጭ አይገባኝም። በጤናም በህይወትም የወጣሁት በፈጣሪ እርዳታ ነው፡፡

በዚያ ላይ ዛቻው፣ ማስፈራሪያው፣ “እንተያያለን አስክሬንህ ነው የሚወጣው” ይሉኝ ነበር፡፡ ብቻ የማይሆንና የማይደረግ ነገር አልነበረም፡፡ “እነ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እንኳን አስክሬናቸው ነው የወጣው እንኳን አንተ” ይላሉ፤ ምን የማይዝቱት አለ… ብቻ አለፈ፡፡ ሌላው ቀርቶ ቀጠሮ ያላቸው እስረኞች ወደ ፍ/ቤት ሊሄዱ ሲሉ የሚያርፉበት የእስረኞች መቆያ አለ፡፡ እኔን ከሌሎቹ ጋር እዚያ እንድቀላቀል እንኳን አያደርጉም፤ ከአጃቢዬ ጋር ለብቻዬ እንድቆም ነበር የሚያደርጉኝ፡፡ ይህን ሁሉ ጫና ለምን አበዙብኝ ብዬ ስጠይቅ ለራሴ መልስ አላገኝም፡፡ እዚያ ግቢ ውስጥ ምንም ጥያቄ ብትጠይቂ መልስ አታገኚም፡፡

እስር ቤት ከገባችሁ በኋላ “አንድነት” የመሰንጠቅ አደጋ ገጥሞታል…?
“አንድነት” ተሰነጣጥቋል ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ፈርሷል፡፡ ያፈረሰው ደግሞ ራሱ መንግስት ነው፡፡ በጠራራ ፀሐይ ሰራዊት ልኮ ነው ያፈረሰው፡፡
ለዚህ ማረጋገጫው ምንድን ነው?
መንግስት “አንድነት”ን አፍርሶ በ“አንድነት” ስም ፓርቲውን ለራሱ ሰው ሰጥቷል፡፡ ለዚህ ማረጋገጫው አንዱ የእኛ የአመራሮቹ መታሰር ነው፡፡ በመጀመሪያ ሀብታሙንና እኔን አሰረ። ከዚያም አጋዥ የሆኑ ሰዎችን አስፈራራ፡፡ ወቅቱ የምርጫ ቅስቀሳ መጀመሪያ ነበር፡፡
በተቃውሞ ጎራው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያላቸውን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለማዳከም አመራሮችን ከየፓርቲው ማሰር ጀመረ፡፡ ከ“አንድነት” እኔና ሀብታሙን፣ ከ“ሰማያዊ” ፓርቲ የሺዋስን፣ ከ“አረና” አብረሀ ደስታን አሰረና ፓርቲያችንን ማተራመስ ጀመረ።

አሁን “አንድነት”ን እየመሩ ያሉት አቶ ትዕግስቱ አወሉ የትግል አጋራችሁ ነበሩ፡፡ በተለይ በእርሰወዎ የትውልድ አካባቢ ቁጫ ድረስ በመሄድ የቁጫን ህዝብ የማንነት ጥያቄ አቤቱታ ሲያዳምጡ ነበር፡፡ እንዴት የመንግስት ደጋፊ ሊሆኑ ቻሉ ብለው ያስባሉ?
በጣም ጥሩ! እኛ ከታሰርን በኋላ መንግስት ትዕግስቱንና ሰፊው የሚባለውን ልጅ ይዞ ፓርቲውን ካተራመሰ በኋላ አንድነቶች እርስ በእርስ ተተራመሱ ለማለት አድርጐት የማያውቀውን ያንን ሁሉ የሚዲያ ሽፋን (የቴሌቪዥን) ሰጠ፡፡ እኛ እስር ቤት ውስጥ ሆነን በቴሌቪዥን እንከታተል ነበር፡፡ እኔ በበኩሌ እንዲህ አይነት የቴሌቪዥን ሽፋን ያየሁት መለስ ዜናዊ ሲሞት ብቻ ነው፡፡ እንዲህ ነው ፓርቲውን ያተራመሰው፡፡ “እንዴት ትዕግስቱ አወሉ የመንግስት ደጋፊ ሆነ? አብራችሁ ብዙ መስዋዕትነት የከፈለ አይደለም ወይ?” ብለሻል፤ ትክክል ነሽ፤ ሀሰት አልተናገርሽም፡፡ በፊትማ አቶ ልደቱ አያሌውም ትክክለኛ መስዋዕትነት ከፍሏል፡፡ የቅንጅቱ አየለ ጫሚሶም መጀመሪያ ላይ ለትግል ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለ ሰው ነበር፡፡ ነገር ግን ሰዎች በተለያየ ምክንያት አቋማቸውን ይቀይራሉ፡፡ ለምሳሌ በኢኮኖሚ ችግር ሊሆን ይችላል አሊያም ከገዢው ፓርቲ በሚደርስባቸው ጫናና ማስፈራሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ በስልጣንና በጥቅም ተደልለው ሊሆን ይችላል፡፡ ብቻ በምንም ምክንያት ይሁን ሰዎች የቀድሞ አቋማቸውን ከቀየሩ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡

እስር ቤት እያሉ ስለሁኔታው ሲሰሙ ምን ተሰማዎት?
እኔ እታገል የነበረው ለፓርቲ አይደለም፤ ፓርቲ ሊጠፋ አሊያም ሰው ሊቀየር ይችላል። ሊሻሻልም ይችላል፡፡ እኔ እታገል የነበረው ለነፃነት፣ ለፍትህና ለዴሞክራሲ ነው፡፡ ይህም ደግሞ ትክክል መሆኑን እስር ቤት ውስጥ አረጋግጫለሁ፡፡ በደረሰብኝ መከራ ውስጥ ሆኜ የታገልነው ትግል ምን ያህል ትክክለኛ እንደሆነ ተገንዝቤያለሁ፡፡ “አንድነት” ከምስረታው፣ ከስያሜው ጥቆማና ማርቀቅ ጀምሮ ሀሳብ በማሰባሰብም ጭምር ነበርኩበት፤ መስራችም ነኝ፡፡ ለዚህ ፓርቲ ብዙ መስዋዕትነት፣ ብዙ ገንዘብ፣ ብዙ ጉልበት አፍስሼበታለሁ፡፡ ይህን ሁሉም ያውቃል፡፡ በአጠቃላይ “አንድነት” ፓርቲ ለእኔ ፕሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክት ደግሞ አንዳንዴ ውጤታማ ላይሆን ይችላል። አንድ ፕሮጀክት ሲከሽፍ በቀጣይ ምን ማድረግ አለብኝ የሚለውን ወደ ማሰብ ነው የምሄደው። “አንድነት” በመፍረሱ አላዘንኩም አልልም። ሀዘኔ ግን ፓርቲው በመፍረሱ ሳይሆን በአጠቃላይ በአገሪቱ ላይ እየተሰራ ስላለው ሴራና በአገሪቱ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ነው። ኢህአዴግ፤ ተቃዋሚ የሚባል ነገር እንዲኖር፣ ድርጅት የሚባል ነገር እንዲፈጠር በተለይም በድርጅት ውስጥ የመሪነት ተፅዕኖ ያላቸው ሰዎች እንዲኖሩ አይፈልግም፡፡ በዚህ ምክንያት “አንድነት” ከምስረታው ጀምሮ ነው የማፍረስ ሙከራ ሲቃጣበት የኖረው፡፡

እንዴት ማለት?
በ2000 ፓርቲው ሲቋቋም ምስረታውን ለማድረግ የሞከርነው ገርጂ አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ነበር፡፡ ህንፃውን መከላከያ ገዝቶት ነበር መሰለኝ ተከለከልንና ወደ ቢሮ መጣን። ከዚያም አንድ ዓመት 2001ን አረፍንና 2002 ላይ መሪያችን ብርቱካን ሚደቅሳ ታሰረች። 2003ን አልፈን 2004 ላይ ደግሞ ከፍተኛ አመራሮቻችን አንዱአለም አራጌና ናትናኤል መኮንን ታሰሩብን። አሁንም 2005ን አረፍንና 2006 ላይ እኔና ሀብታሙን አስረው የፓርቲውን ግብአተ መሬት ፈፀሙ፤ ፓርቲውን አጠፉ፡፡ አሁንም የቀድሞው ፓርቲ አባላት አሉ፤ እምነታቸውን አቋማቸውን የያዙ፤ ፓርቲው ግን ድራሹ ጠፍቷል፡፡

እስር ቤት ውስጥ ከባድ ጊዜ እንዳሳለፉ በአዎንታዊ መልኩስ? …
እኔ እስር ቤት አገኘሁ የምለው በጣም አሪፍ ነገር አለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ብዙ ስራ ትሰሪ ትሰሪና ትክክለኛ ነገር ነው አይደለም የሚለውን ለማረጋገጥ ጊዜ ወስደሽ ትመረምሪያለሽ፡፡ ያመጣሽውን ውጤት በጥያቄ ውስጥ ከትተሽ የምታረጋግጪበት አሰራር በሂሳብና በፊዚክስ ትምህርት ላይ አለ፡፡ ቼክ ስታደርጊ በሁለቱም በኩል ወይ ዜሮ ዜሮ አልያም አምስት አምስት ብቻ የሆነ ቁጥር እኩል ከመጣ፣ ስራው ትክክልና ውጤታማ ነው ማለት ነው፡፡ እስር ቤት ሳልታሰር በፊት ስታገል የነበረበት መንገድ እንዴት ነበር የሚለውን በጥሞና ለማየት አስችሎኛል፡፡ ከ97 ወዲህ ስታሰር የመጀመሪያዬ ነው፤ በ97 ዓ.ም ትንሽ ታስሬአለሁ፤ ብዙ ተደብድቤያለሁ ግን ደግሞ እኔ ከእስር ውጭ ሆኜ በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ግፍና በደል በማየት የሰብአዊ መብት ጥሰትን በመቃወም የታገልኩት ትግልና የታገልኩበት መንገድ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጬአለሁ፡፡

በሌላ በኩል የተሰሩ ስህተቶችንም ስገመግም ዝም ብሎ ኢህአዴግን ከማውገዝና ከመጮህ ባሻገር ምን ማድረግ ነበረብን የሚለውን ተገንዝቤያለሁ፡፡ የኢህአዴግን ባህሪ ያለመረዳት ችግርም እንደነበር በጥሞና ተረድቻለሁ፡፡ ኢህአዴግ ይህን ቢያደርግ እኛ በምን መከላከል አለብን የሚለውን የመተንበይና ቀድሞ የማሰብ ችግር በመጠኑ በእኛ በተቃዋሚዎች አካባቢም እንደነበር አሰላስዬበታለሁ፡፡ እንግዲህ ይሄን ነው አገኘሁ የምለው፡፡
በተቃውሞ ትግል ውስጥ 18 ዓመታትን አሳልፌያለሁ፡፡ በነዚህ ዓመታት ውስጥ ህይወቴን … ትዳሬን … ቤተሰቤን ጎድቻለሁ። ብዙ ነገሮችን አጥቻለሁ፡፡ አሁን ሳስብ ግን ሰዎችን ለማዳን ሌሎች ሰዎች መሞት የለባቸውም፡፡ ሰዎች ሳይሞቱ እንዴት ነው ሌሎችን ማዳን የሚቻለው የሚለውን ሀሳብ ለማሰላሰል ጊዜ አግኝቻለሁ ማለት ነው፡፡

በሌላ በኩል፤ እጅግ በጣም ብዙ ችግሮችና ቀውሶች ደርሰውብኛል፡፡ ለምሳሌ በግል ት/ቤት የማስተምራቸው ልጆቼ የመንግስት ት/ቤት ገብተዋል፡፡
ይሄ የሆነውም የሚከፍሉት በማጣት ነው። ይሄ በልጆቹ ላይ ምን ያህል የሞራል ችግር እንደሚፈጥርባቸው፣ ምን ያህል የትምህርት ጥራት ችግር እንደሚያጋጥማቸው ማሰብ ነው። ከስምንት በላይ የወንድም ልጅ፣ የእህት ልጅ፣ በባለቤቴም በኩል የምናሳድጋቸው ልጆች ችግር ውስጥ ወድቀው ነው የጠበቁኝ፡፡

እንዲህ አይነት ትግል ውስጥ በሚገባበት ጊዜ ይህን ቤተሰብ የሚታደግ ነገር ማበጀት ግድ ነው። ያለበለዚያ እዚያ ያለውን ለማዳን ስንታገል፣ እዚህ ያሉት ከሞቱ ሁሉም ትክክል አይመጣም፡፡ በእስር የጥሞና ጊዜ በጥልቀት ካሰብኩባቸው ነገሮች አንዱ ይሄው ጉዳይ ነው።

ከፓርቲ ስራ ውጭ የራስዎ ስራ እንደነበረዎት ይታወቃል፡፡ አሁን ወደ ቀድሞ ስራ ይመለሳሉ?
ይሄ ቀልድ ይመስለኛል፡፡ ስራ ከየት ይመጣል? በቃ ስራ አጥ ነኝ፡፡ ቤተሰቤም ስንቅ በማመላለስ ተንገላቶ የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ ተዘፍቋል፡፡
ወደፊት አገሬ ላይ ሰርቼ ለመኖር ምን ዋስትና አለኝ የሚል ጥያቄ በውስጤ አለ፡፡ በሌላ በኩል ስራ ፍለጋ ሲኬድ የፖለቲካ እስረኛ ነው ሲባል፣ እኔን ለማሰራት ብዙ ፍላጎት የሚኖር አይመስለኝም። ያም ሆኖ ስራ መፈለጌን እቀጥላለሁ፡፡ ብዙዎች ኢህአዴግ በአሸባሪነት ከስሶ ያሰረውን ሰው ለመቅጠር ይቸገራሉ። እኔ መሀንዲስ ነኝ ግን አሁን የጉልበት ስራ ለማግኘት እንኳን መቸገሬ አይቀርም፡፡

አንዳንድ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ታስረው ከተፈቱ በኋላ ወደ ውጭ ይወጣሉ፡፡ እርስዎ በፖለቲካ ትግሉ ይቀጥላሉ ወይስ?
ትግሉን ትቀጥላለህ ወይ የሚለው ትክክለኛ ጥያቄ አይደለም፤ አሁንም የመጣሁት ከሽርሽር አይደለም፤ ከትግል እንጂ፡፡ 22 ወራት ስታገልና ስሰቃይ ቆይቼ ነው የመጣሁት፡፡ ይሄ በዚህ ይታረም፡፡ ከአገር ትወጣለህ ወይ ላልሺው እኔ ባህታዊ ነኝ፤ ባህታዊ ማለት ዓለም በቃኝ ብሎ ለነፍሱ ያደረና ገዳም የገባ ሰው ነው፡፡ እኔ ገንዘብና ጥቅም ፍለጋ አይደለም ትግል ውስጥ የገባሁት፡፡ አገሬን ጥዬ የትም የምሄድበት ጉዳይ የለም፡፡ መሄድ ካስፈለገ በፊትም መሄድ እችል ነበር፡፡ የሄዱትንም አከብራለሁ፤ ምርጫቸው ስለሆነ፡፡

በግሌ ግን ሰዎች ስለሄዱ አልሄድም፤ አምኜበት የታገልኩበት ጉዳይ ነው ከአገሬ አልወጣም፡፡ ለዚህ ነው በትግል የቆረብኩ ባህታዊ ነኝ የምልሽ። ማዕከላዊም ቃሊቲም፣ ቂሊንጦም ፍርድ ቤትም ለእኔ የትግል ሜዳዎች ነበሩ፡፡ ምክንያቱም ምንም በማታውቂው፣ ሰርተሽ ለመለወጥ፣ ቤተሰብሽን ለመምራት ትታገይ አሸባሪ ተብሎ መታሰር ማለት እንግዲህ ይታይሽ …

የቀድሞው አንድነት ፈርሷል ብለዋል። ይህንን ፓርቲ ከአጋሮችዎ ጋር እንደገና ለመፍጠር ሀሳብ የላችሁም?
በነገራችን ላይ አሁን እረፍትና ማሰብ እንዲሁም ከመረጃ ርቄ በነበርኩበት የሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ስለተፈጠረው ነገር ማወቅና መገንዘብ ነው የምፈልገው፡፡ አይደለም ሁለት ዓመት፣ ሁለት ቀን ከመረጃ መራቅ በእውቀት ላይ የሚፈጥረው ጫና ቀላል አይደለም።
ስለዚህ ይሄን እመረምራለሁ፤ በበቂ ሁኔታ እረፍት እወስዳለሁ፡፡ ከመረጃ በራቅሁበት ሁኔታ ስለ አንድነት እንዲህ ነው እንዲያ ነው ለማለት እቸገራለሁ፡፡
እስካሁን ያወራሁትም በነበረኝ መረጃ ላይ ተመስርቼ ነው፡፡ አሁን ስለአንድነት ምንም ማለት አልችልም፡፡
በመጨረሻ የሚሉት አለ …

ጉዳያችንን ሲከታተሉ የነበሩትን የሚዲያ ሰዎች፣ ቤተሰቤን፣ በተለይ ባለቤቴን፣ የኢትዮጵያን ህዝብ፣ ጠበቆቻችንን አመሀ መኮንን እና ተማም አባቡልጉን በጣም አመሰግናለሁ፡፡ በክፉ ጊዜ የከዱን አሉ፤ ለእነሱም ፈጣሪ ልቦና ይስጣቸው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

በሲኤምሲ ያሉ ነዋሪዎች ቤታችን እየፈረሰ ነዉ አሉ

0
0

CMC

BBN news May 14, 2016
በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ ዘጠኝ በሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ቤታችን ፈርሶ ያለመጠለያ እየቀረን ነዉ ሲሉ ቅሬታ አሰሙ። በሰዉ አገር ተሰደን ያጠራቀምነዉ መና ቀረ የሚሉት የሲኤምሲ ነዋሪዎች አሉ። የህይወት መስዋእትነት ከፍለዉ የተሰደዱ የቤተ ሰብ አባላቶቻችን በላኩልን ገንዘብ የገነባነው ቤት ያለምንም ርህራሔ ፈረሰብን ወገን ይድረስልን በማለት የጥሪ ድምጻቸዉን ያሰሙም አሉ። ድሆች አዝነዋል። ያለ ረዳትና ደጋፊ ባዶ ቀረን የሚሉ አቅመ ደካሞች ቢቢኤን ድምጻችንን ለአለም ያሰማልን ሲሉ ተማጽነዋል።

መንግስት ለድሃ ዜጎቹ እርዳታና ጥበቃ ማድረግ ሲገባዉ ቤታቸዉን በላያቸዉ ላይ እያፈረሰ ለአደጋ እያጋለጻቸዉ መሆኑን በምሬት ይገልጻሉ።

የወረዳዉ ባለ ስልጣናት ገንዘብ መክፈል የሚችለዉን ነዋሪ ገንዘብ እየተቀበሉ ሲያልፉ ገንዘብ መክፍል የማይችለዉ ድሃው ነዋሪ እቃዉን እንኳ ማዉጣት ሳይችል በላዩ ላይ ቤት እየፈረሰበት መሆኑን በሲቃ ያስረዳሉ።ቦታዉ ለምንም የማይሆን በቆሻሳ የተከበበ መሆኑ የሚገልጹት የሲ.ኤም.ሲ ነዋሪዎች፤ ቤተሰብን ይዞ ጎዳና ላይ ከመሆን ይሻላል በማለት የቀየሱት ጎጆ ያለምንም ርህራሔ መፍረሱ እንዳሳዘናቸዉ ገልጸዋል።

በወረዳዉ እዉቅና ቤት እንደሰሩ የሚናገሩት ነዋሪዎች ቦታዉ ለምንም ነገር መዋል የማይችል ቢሆንም የአቅመ ደካማና የድሃዉ ቦታ ብቻ ተመርጦ የፈረሰ መሆኑ ግራ እንዳጋባቸዉ ይናገራሉ። ለወራት ቤትን በመገንባት ያሳለፉት ነዋሪዎች እንደ አቅማቸዉ በሺዎች የሚቆጠሩ ብሮችን ማፍሰሳቸዉን ያስረዳሉ።

የሚረዳን በሌለበት መልኩ እቃችንን መንገድ ላይ ከምረን ጎረቤት ዘንድ ለግዜዉ ተጠልለናል የሚሉት የሲ.ኤም.ሲ ነዋሪዎች ያለብንን አደጋ ከግምት ዉስጥ በማስገባት የወረዳዉ ባለስልጣናት አስተያየት ያድርጉልን ሲሉም ተማጽነዋል።

በመጪዉ ሮመዳን ያለ መጠለያ ሜዳ ላይ የተጣልን አቅመ ደካሞች በመሆናችን በአገርም ይሁን በዉጭ ያለዉ ወገን እኛንም ልጆቻችንንም ከአደጋ ይታደግ ሲሉ ለቢቢኤን ገልጸዋል።

የማንቸስተር ዩናይትድ ስታዲየም ውስጥ የሚያጠራጥር ቦርሳ በመገኘቱ ዛሬ የሚደረገው ጨዋታ ተሰረዘ

0
0

wesha

ስሜነህ ታደሰ | ለዘ-ሐበሻ ስፖርት

(ዘ-ሐበሻ) በፕሪምየር ሊጉ የመጨረሻው ጨዋታ ላይ ዛሬ ማንቸስተር ዩናይትድ ከበርንማውዝ ጋር ወሳኝ ጨዋታ የነበረው ቢሆንም በስታዲየሙ ውስጥ አሸባሪዎች ያስቀመጡት ሊሆን የሚችል አጠራጣሪ ቦርሳ በመገኘቱ ጨዋታው ለሕዝብ ደህንነት ሲባል መሰረዙ ተዘገበ::

ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት አነፍናፊ ውሾች በስታዲየሙ ውስጥ ይህ አጠራጣሪ ቦርሳን እንደጠቆሙ በሁለት ክንፍ በኩል ያሉ መቀመጫዎች በሙሉ ህዝብ እንዲወጣ ተደርጎ ነበር:: በምርመራውም ጨዋታው ዘግየት ብሎ ይጀምራል ተብሎ የታሰበ ቢሆንም ለሕዝብ ደህንነት ሲባል መሰረዙን የማን.ዩናይትድ ድረገጽ ዘግቧል::

 

ሃገርንን የማዳን ጥሪ በሲያትል –ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሚገኙበት

0
0

(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ሳምንት ከኤርትራ ወደ አሜሪካ ከሥራ ጉዳይ እንደመጡ የሚነገርላቸው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፊታችን እሁድ ሜይ 22, 2016 ለአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰቢያ ወደ ሲያትል አምርተው ከሕዝብ ጋር ይወያያሉ:: አዘጋጆቹ የሚከተለው የጥሪ ወረቀት በዘ-ሐበሻ ላይ እንዲታተም ልከዋል – አስተናግደናል::

ethiopia Seattle

Health: ስትሮክ ሊመታኝ ነው እያልኩ እየተረበሸኩ ነው፤ ምን ይሻለኛል?

0
0

የደም ግፊት በሽተኛ ነኝ፡፡ በተለያየ ጊዜ ብታከምም ልድን አልቻልኩም፡፡ አሁን አሁን ደግሞ በሽታው ለተለያዩ ህመሞች ያጋልጣል የሚል ወሬ ሰምቻለሁ፡፡ ታዲያ ከዚህ መሰል ችግር ራስን ነፃ ለማድረግ በየጊዜው ምርመራ ማድረግ እንዳለብኝ በዚሁ ህመም የ10 ዓመት ተሞክሮ ያለው አንድ ታካሚ ባልደረባዬ አጫውቶኛል፡፡ ለመሆኑ እንዴት አይነትና በየስንት ጊዜው መመርመር ይኖርብኝ ይሆን? የትስ ቦታ ብመረመር ይሻላል ትላላችሁ? ይኸው አንድ ቀን ያልሆነ ቦታ ሊጥለኝ ይችላል እያልኩ እየሰጋሁ ነው፡፡ በተለይ ትንሽ ድክም ሲለኝ፣ ራሴን ጭው ሲያደርገኝ፣ ድንገት እግሬ ከዳ ሲያደርገኝ ከአሁን አሁን ስትሮክ ሊመታኝ ነው እያልኩ እረበሻለሁ፡፡ ስለዚህ መልሳችሁን በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡
መሐመድ ነኝ

ask your doctor zehabesha

ውድ ጠያቂያችን መሐመድ በእውነቱ ከህመሙ በላይ የጎዳህ ጭንቀትህ ይመስለኛል፡፡ ስትሮክ ሳይከሰትብህ በየቀኑ በራስህ ጭንቀት ራስህ ላይ እየጠራኸው ነው፡፡ የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል እንደሚባለው ጥንቃቄ በሚገባ መተግበር እንጂ ትንሽ እንከን በተሰማህ ቁጥር መበርገጉ ራሱን የቻለ ህመም ነው፡፡ ከደም ግፊት የልቅ የጭንቀት ግፊቱ የበዛብህ ነው የሚመስለው፡፡

ውድ ወንድማችን መሐመድ ከድር መቼም አንድን ህገወጥና ተቀባይነት የሌለውን ድርጊት የፈፀመ ወንጀለኛ መንጥሮ ለማውጣት ፖሊሲው ምርመራ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም፡፡ ድርጊቱን የፈፀመውም እጁን ካልሰጠ በቀር ታዲያ ፈልጎ ለማግኘት ብዙ ጥረትን ይጠይቃል፡፡ ከቀላል የምስክር ቃል የሚጀምረው ይህ ውስብስብ ምርመራ እስከ ዲኤንኤ ምርመራ ድረስ ይቀጥላል፡፡ ይህ እንግዲህ የፖሊሶችን ጥልቅ ምርመራ ይመለከታል፡፡ ለከፍተኛ ደም ግፊትስ?

ከፍተኛ ደም ግፊትን ያክል በቀላል የማይታይ በደል በአንድ ሰውም ላይ ሲፈፀም ከከባድ ወንጀል ተነጥሎ የማይታይ ነውና ምርመራው እስከ ወዲያኛው ድረስ ሳይቋረጥ ሊቀጥል ይችላል፡፡ የምርመራው አብይ አላማዎችም ሁለት ናቸው፡፡ አንዱ ህመሙን ያስከተለው ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ/ወንጀል ፈፃሚው መሆኑ ነው/ ሲሆን ሌላው ደግሞ ህመሙ በራሱ ከተከሰተ በኋላ በሌላው የአካል ክፍል ላይ ያደረሰው አደጋ ካለ ለመለየት ነው፡፡ የህመሙ መንስኤ ከተገኘ መንስኤውን በማስወገድ ህመሙን ማስወገድ ወይም ማስተካከል እንዲቻል ያግዛል፡፡ ምርመራው በሌላ የሰውነት ክፍሎች የማስተካከያ እርምጃ/ተግሳፅ/ ለመውሰድ ወሳኝ ይሆናል ማለት ነው፡፡

የምርመራውን ጥቅምና አስፈላጊነት በአጭሩ እንዲህ ከተረዳን ታዲያ እንደ አንተ ያለ ግለሰብ በሐኪም የሚያደርግለት ወይም ሊደረጉለት የሚገቡ ምርመራዎች የትኞቹ ናቸው? ላልከው ጥያቄ እንዲህ አቅርቤያቸዋለሁ፡፡

1. የደም ሴሎች ምርመራ (CBC Count)፡- ይህ ምርመራ የቀይ የደም ሴሎች፣ የነጭ የደም ሴሎችና የፕላትሌቶች ቁጥርን ማወቂያ ሲሆን ጤናማ ቁጥር እንዲኖራቸው ይጠበቃል፡፡

2. የሰውነት ማዕድን ምርመራ (Serum Electrolytes)፡- ሰውነታችን ውስጥ በፔሬዲክ ቴብል ውስጥ ካሉት ከ110 በላይ ማዕድኖች (Elements) ውስጥ የማይገኙት ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ በዋናነት ግን የደም ውስጥ ሶዲየም፣ ክሎራይድ፣ ፖታሲየም፣ ካልሲየም፣ ፎስፎረስ ጤናማ መጠን እንዲኖራቸው ይጠበቃል፡፡

3. የኩላሊትን ጤናማነት መለያ ምርመራ (Renal Function Tests or RFT)፡- ከፍተኛ ደም ግፊትን በማስከተል ረገድ አንዱ ምክንያት ኩላሊት ሊሆን ሲችል ከፍተኛ ደም ግፊትም በራሱ በኩላሊት ላይ ጫና በማድረስ በመጨረሻ ለኩላሊት ድክመት ያጋልጣል፡፡ በመሆኑም የኩላሊትን ጤናማነት ከምንለይባቸው የደም ምርመራ አይነቶች ውስጥ ‹‹ክሬያቲኒን›› እና ‹‹ዩሪያ›› ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እንዲሁም የኩላሊትን አካላዊ ጤናማነት ለመመልከት ልዩ የኩላሊት ራጅ ምርመራ (IVP RENAL ANGIOGRAPHY) ሊያስፈልጉ ይችላሉ፡፡

4. የደም ስኳር መጠን (Blood glucose test):- ከፍተኛ ደም ግፊትና ስኳር ህመም 50 በመቶ በሆነ ዕድል በጣምራነት የሚከሰቱ ህመሞች ናቸው፡፡ በመሆኑም ለየትኛውም የደም ግፊት ህሙማን የደም ስኳር ጤናማነቱ መታየት ይኖርበታል ማለት ነው፡፡

5. (Urinalysis)፡- ይህ ምርመራ በሽንት ውስጥ የሚኖሩ ኬሚካላዊ ለውጦችን የሚቃኝ ሲሆን በዋናነትም ‹‹albumen›› እና ‹‹glucose›› ለማየት ያግዛል፡፡ በሽንት ምርመራ በተለይ ‹‹albumen›› ከታየ የኩላሊት ህመም መከሰቱን ይጠቁማል፡፡

6. (Lipid Profile):- በምግባችን ይዘት ከፊል ካርቦሃይድሬት፣ ከፊል ፕሮቲንና ከፊል ቅባት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ካርቦሃይድሬትና ፕሪቲን ባመዛኙ ወደ ግሉኮስነት /ስኳርነት/ በመቀየር ለሰውነት የኃይል ምንጭ ሲሆኑ የቅባት ምግቦች ደግሞ ወደ ትራይግሊስራይድስ /ቅባትነት/ በመለወጥ ነው ለኃይል ምንጭነት የሚጠቅሙት፡፡ ከፍተኛ የደም ቅባት ክምችት መኖር ለከፍተኛ ደም ግፊትና ስኳር ከማጋለጡም አልፎ ተርፎ የህመሞቹን አደጋም ይጨምራል፡፡ በመሆኑም የእነዚህን የቅባት ክምችቶች ከምናውቅባቸው የምርመራ አይነቶች ‹‹total cholesterol, low density lipoprotein (LDL), High density lipoprotien (HDL) and Triglycerides›› ተጠቃሽ ናቸው፡፡

7. የታይሮይድ ዕጢ ምርመራ፡- ታይሮይድ ዕጢ የሰውነትን አጠቃላይ አሰራር /ሜታቦሊዝም/ በበላይነት የሚቆጣጠር ሲሆን ከዚህ አብጥ ስራውም ከወትሮ ከፍ ወይም ዝቅ ካለ ለደም ግፊት ህመም ያጋልጣል፡፡ ስለሆነም የዚህን ዕጢ አሰራር የሚጠቁሙ ምርመራዎች እንዳስፈላጊነቱ ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ እነሱም (T3/T4 and TSH) በመባል ይታወቃሉ፡፡

8. የልብ ምርመራ፡- ከፍተኛ ደም ግፊት ተፅዕኖ ከሚያሳድርባቸው የሰውነት ክፍሎች ውስጥ ልብ ግንባር ቀደም ተጠቃሹ ነው፡፡ በመሆኑም የልብን ጤናማነት ከሚያሳውቁ ምርመራዎች ውስጥ ‹‹ኢሲጂና ኢኮካርዲዮግራፊ›› ይጠቀሳሉ፡፡ በተለይ በኢኮካርዲዮግራፊ ምርመራ የግራው የልብ ክፍል ላይ ችግር ከታየ ለደም ግፊት ህመሙ ወዲያው መድሃኒት እንዲጀምር ያስገድዳል፡፡

9. የዓይን ምርመራ፡- ይህ ምርመራ ደም ግፊት በዓይን ካሜራ ክፍል ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመለየት የሚያግዝ ሲሆን አስፈላጊ ቅድመ ጥንቃቄያዊ እርምጃ ለመውሰድም ይጠቅማል፡፡

ውድ ወንድማችን መሐመድ ከድር መቼም እንደህመም ተቆጥሮ የማይታከም ነገር ቢኖር ፍቅር ብቻ ነው ይባል እንጂ ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም ግን ራሱንየቻለ ህክምና ያለው ነው፡፡ ያውም ከአንድ አይሉ ብዙ አይነት ህክምናዎች አሉት፡፡ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር አይደል የሚባለው፡፡ ምንም እንኳን መቶ በመቶ ባይፈውሱም፡፡ እናም ታዲያ አማራጩ ብዙ ነው፡፡

እንግዲህ የደም ግፊት ህመም አንድና አንድ የሆነ መድሃኒት የለውም፡፡ የሚዋጡም ሆነ የማይዋጡ መፍትሄዎች ያሉት ነው፡፡ ካለ መድሃኒት አስፈላጊነት የሚታከም የደም ግፊት ህመም አለ፡፡ በአንድ አይነት መድሃኒት ብቻም ይሁን ከአንድ በላይ ጣምራ መድሃኒቶች የማያስፈልጉትም የደም ግፊት ህመም አለ፡፡ ሁሉም እንደየአይነታቸው ህክምናቸው ይለያያል፡፡ የሀገሩን በሬ በአገሩ ሰርዶ እንዲሉ፡፡

መድሃኒት ሁሉ እንደስሙ አይደለም፡፡ የራሱ የሆነ ጉዳትም አለው፡፡ ጉዳቱ ከጥቅሙ ስለሚያንስ ግን እንወስደዋለን፡፡ ከመድሃኒት ሌላ መዳኛ ወይም በሽታውን ማስተካከያ መንገድ ካለ ግን መድሃኒቱን ለመውሰድ በጨረታው አንገደድም፡፡ የግድ መወሰድ ካለበት ወይም አማራጮች ከሌሉ ግን የጎንዮሽ ጉቱን ተቀብለን እንወስደዋለን፡፡ ነገሮች እንዲህ ከመሰሉ ታዲያ የደም ግፊት መጠንህን በአመጋገብ፣ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስተካከል አንዱ መላ ሲሆን ነገር ግን በመድሃኒት የግድ መታከም አለባቸው የሚባሉ ህመምተኞች የሚከተሉት ናቸው፡፡

የታችኛው የግፊት መጠን ከ90mmhg ቢሆንም የግድ ህክምናው ያስፈልገዋል፡፡

አንድ የደም ግፊት ህመም ታካሚ የግፊት መጠኑ እስከ 140 በ90 mmhg ዝቅ እንዲያደርግ ይመከራል፡፡ ለሁሉም አይነት ህሙማን ግን አይደለም፡፡ አንድ ደባል የስኳር ህመም ያለበት ሰው የደም ግፊት መጠኑ እስከ 130 በ85 mmhg ያህል እንዲወርድ ይመከራል፡፡ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንዳመለከቱትም የትኛው /ዲያስቶሊክ/ የግፊት መጠን ከ90 mmhg እንዳይበልጥ ተደርጎ ቁጥጥር ስር ከዋለ በህመሙ የመሞት ዕድሉ እጅግ አናሳ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በተለይ ደግሞ የላይኛውን የግፊት መጠን 120 mmhg ላይ ካደረስከው እጅግ የተዋታለት ቁጥጥር በመባል ይጠራል፡፡

ስለሆነም ወንድማችን ከላይ የተጠቀሱት ምርመራዎች በተለይ ከልብና ከዓይን ምርመራዎች ውጭ በየትኛውም ቦታ የሚታዩ ናቸው፡፡ የምርመራ ጊዜው እንደ ህክምና ታሪክህና ዕድሜህ የሚወሰን በመሆኑ ከሐኪምህ ጋር ቀርበህ ተነጋገርበት፡፡ እነዚህ ምርመራዎች እንዳስፈላጊነቱ ሊደረጉ የሚችሉ እንጂ ለሁሉም የግድ ሊደረጉ የሚገባቸው ናቸው ለማለትም ስላልሆነ የትኞቹ መቼ ሊደረጉ እንደሚገባ ሐኪምህ የበለጠ ግልፅ ሊያደርግልህ ይችላል እላለሁ፡፡ በተረፈ አላህ ከስትሮክ የፀዳ አስተሳሰብ ይስጥህ እያልኩ ልሰናበትህ፡፡

1.3 ሚሊየን ብር የነፈግናቸው ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ

0
0

kostere

ስሜነህ ታደሰ | ለዘ-ሐበሻ ስፖርት

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥር 2005 ዓ.ም አካባቢ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታላቁ ባለውለታ ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ ለሕክምና 1.3 ሚሊዮን ብር አስፈለጋቸው:: ወልደመስቀል በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ የጣሉት አሻራ የማይሻር ነው:: በርካታ አትሌቶችን ከጃንሜዳ ሃገር አቋራጭ እስከ ኦሎምፒክ ድረስ አፍርተዋል:: ውለታቸውን ግን የቆጠርልናቸው አይመስለኝም:: እንዴት? እዘረዝረዋለሁ:-

በ1990 ዓ.ም ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ እግራቸው ላይ የደረሰባቸው ጉዳት ከ እድሜ መግፋት ጋርም ተያይዞ በ2005 አካባቢ አላስቆም አላስቀምጥ የሚል ህመም አስከተለባቸው:: ይህ የ እግር ህመም በሃገር ውስጥ ብቻ ታክሞ ለመዳን የማይቻል ባይሆንም ለመታከም የሚያስፈልገው ወጪ 1.3 ሆነ:: ዶክተሩ ለሃገራችን በአትሌቲክሱ ዘርፍ የሰሩትን ታላቅ ገድል በማውሳት አንዳንድ ግለሰቦች ለህክምና የሚሆነውን ገንዘብ ለማሰባሰብ ተንቀሳቀሱ:: ሰሚ ግን አልነበረም:: ጥቂቶች ጥቂት ገንዘብ ቢያሰባስቡም 1.3 ሚሊዮን ብር ሊደርስ አልቻለም:: ዶክተሩ በከዘራ እስኪሄዱ በመኪና አደጋው በደረሰባቸው አደጋ ለ15 ዓመታት ቢሰቃዩም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባቅሙ ከ200 ሺህ ብር የዘለለ እርዳታ ማድረግ አልቻለም ነበር:: ፌዴሬሽኑ ይህን ልገሳ ያደረገውም እኚህ ታላቅ ባለውለታ ብዙ ልመና ካደረጉ በኋላ እንጂ እንደው አዝኖም አልነበረም::

የሚገርመው ለዓለም አቀፍ ዝና ያበቋቸው ታላላቅ አትሌቶች እንኳ በታመሙ ጊዜ አልደረሱላቸውም:: 1.3 ሚሊዮን ብር ያላዋጣንላቸውና ያላሳከምናቸው ዶክተር ወልደመስቀል የመኪና አደጋው ከደረሰባቸው ከ13 ዓመታት በኋላ ዛሬ ሕይወታቸው በሌላ ህመም አልፏል::

ነብሳቸውን በገነት ያኑርልን! ለሃገራችን ውለታ የዋሉ ሰዎችን በቁም የምንረዳና የምናስባቸው ያድርገን::


ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በሒላሪ ክሊንተን 100 ኢሜይሎች |ዘላለም ክብረት (ውይይት መጽሄት)

0
0

Hiari

ከአዘጋጁ: ይህ ጽሁፍ በኢትዮጵያ ታትሞ በወጣው ‘ውይይት’ መጽሔት ላይ ታትሞ ወጥቷል:: በሃገር ቤት ያላችሁ አንባቢዎች መጽሔቷን ገዝተው እንዲያነቧት ትበረታታላችሁ::

ለዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ቅድመ-ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከዴሞክራት ፓርቲ ተቀናቃኞቻቸው በርኒ ሳንደርስ ጋር እየተፎካከሩ ያሉት ወ/ሮ ሒላሪ ክሊንተን በሥራ ጉዳይ እ.አ.አ. ከ2009 እስከ 2013 ሲለዋወጧቸው የነበሩ በዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢሜይሎቻቸው ከአጠቃቀም ግድፈት ጋር በተያያዘ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይፋ ሆነዋል፡፡ ከነዚህ ኢሜይሎ መካከል ዘላለም ክብረት ኢትዮጵያን የሚመለከቱትን 100 ኢሜይሎች ተመልክቶ ስለአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት ያላቸውን አንድምታ እንደሚከተለው አቅርቦልናል፡፡

ሜሪካዊው ፒተር ሺዌዘር ደርዘን የሚሆኑ መጽሐፍትን ጽፈዋል። የመጽሐፍቶቻቸው ዋነኛ የትኩረት ነጥብም በፖለቲከኞች የሚፈፀሙ የኢኮኖሚ ደባዎችን ማጋለጥ ነው። ከጻፏቸው መጽሐፍት መካከል ግን በዓለማቀፍ ደረጃ በግንቦት 2015 እንደጻፉት ‘Clinton Cash: The Untold Story of How and Why Foreign Governments and Businesses Helped Make Bill and Hillary Rich’ ባለረጅም ርዕስ መጽሐፋቸው ትኩረት የሳበ መጽሐፍ ነበራቸው ማለት አይቻልም። በዚህ ባለ 256 ገጽ መጽሐፋቸው አሁን የአሜሪካ ፕሬዘደንት ለመሆን ጫፍ ላይ ደርሰዋል ተብሎ እየተነገረላቸው ያሉት የቀድሞዋ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሒላሪ ክሊንተንና የባለቤታቸው የቢል ክሊንተን የዕርዳታ ተቋም የሆነው ‘Clinton Foundation’ ከተለያዩ አምባገነን መንግሥታትና ባለሀብቶች ገንዘብ በመቀበል ሒላሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር (ከ2008 – 2012) በነበሩባቸው አራት ዓመታት ውስጥ በአምባገነኖች የሚደረጉ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶችን አይተው እንዳላዩ አልፈዋል የሚል ነው። መጽሐፉ አንድ ሙሉ ምዕራፍ ሰጥቶ ትኩረት ካደረገባቸው የትኩረት ነጥቦች አንዱ “የኢትዮጵያ መንግሥት ለሚፈጽማቸው የሰብኣዊ መብት ጥሰቶችና የሙስና ተግባራት የአሜሪካ መንግሥት ምንም ዓይነት ተጠያቂነትን ሳያስቀምጥ ዕርዳታ ይሰጣል” የሚል ይገኝበታል። ጸሐፊው ለዚህም ጥሩ ማሳያ አድርገው ያቀረቡት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼኽ ሙሐመድ አል አሙዲን ለክሊንተን ፋውንዴሽን ሰጡት የተባለውን የ20 ሚሊዮን ዶላር ስጦታ ነበር። በወቅቱ ስጦታውን ሰጡ የተባሉት ግለሰብ “ስጦታ አልሰጠሁም” ቢሉም በኋላ ግን የተሰጠው ስጦታ 6 ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደሆነ ገልጸው፤ ስጦታው ኤድስን ለመከላከል ከመሆን በቀር ምንም የፖለቲካ ዓላማ የሌለው መሆኑን አስታውቀዋል።

ክሊንተን በምርጫ ሒደታቸው በተለይም ከሪፐብሊካን ተቀናቃኞቻቸው ይህ መረጃ እዚህም እዛም ሲነሳባቸው የነበረ ሲሆን፤ ከዚህ መረጃ ይልቅ ግን ክሊንተንን እስከ ምርመራ ያደረሳቸው ጉዳይ “ደኅንነቱ ባልተጠበቀ በግል ሰርቨራቸው በመጠቀም ጥብቅ ሚስጥር የያዙ መንግሥታዊ ጉዳዮችን ከሌሎች ባለሥልጣናት ጋር ኢሜይል ተላልከዋል” የሚለው ክስ ነው። በዚህም ምክንያት በአማካሪዎቻቸውና በባለሙያዎች የተጻፉትንና በአብዛኛው በሦስቱ ረዳቶቻቸው ማለትም ቼሪል ሚልስ፣ ጄክ ሱሊቫንና ሁማ አባዲን የተላኩላቸውን በፍርድ ቤት ከሃምሳ ሺሕ ገጽ የሚልቁትን ወደ ሠላሳ ሺሕ ኢሜይሎች በፍርድ ቤት ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ ከነዚህ ኢሜይሎች መካከል 100 የሚሆኑት ኢትዮጵያ ጋር በቀጥታና በተዘዋዋሪ የተገናኙ ናቸው።

ኢትዮጵያና ረኀብ

በ2003 እና በ2004 በምስራቅ አፍሪካ ከባድ የድርቅ አደጋ ተከስቶ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ሶማሊያዊያንና ኬኒያዊያን ለረኀብ ተጋልጠው ነበር። ከሒላሪ ክሊንተን ኢሜይሎች እንደምንረዳው ረኀቡ የአሜሪካን መንግሥት እጅግ አሳስቦት እንደነበረ ነው። ከመልዕክቶቹ በአንዱ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ስለረኀቡ ገለጻ ያደረጉት ቼርሊ ሚልስ “ረኀቡ እጅግ ሰቅጣጭ ነው። ነገር ግን በዚህ አሳዛኝ ሁኔታ መካከል መልካም ዜናም ይሰማል። ይሄውም ባለፈው ኢትዮጵያ በዚን ያህል ከባድ ድርቅ በተመታች ወቅት 14 ሚሊዮን ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን 4.5 ሚሊዮን ሰዎች ብቻ ናቸው ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ የተጋለጡት። ይሄም አሜሪካና ሌሎች አገራት የሠሩት የሴፍቲ ኔት ዕርዳታ ውጤት ነው” ይላሉ። ይሄን ተመልክትን ዛሬ ቁጥሩ በዐሥርና በሃያ ሚሊዮን መካከል ከፍ ዝቅ እያለ ለሚገኝው ለረኀብ የተጋለጡ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ስንመለከት ለጋሽ አገራት ያላቸው እምነት የተሳሳተ መሆኑን በቀላሉ መረዳት እንችላለን። ከዚህ ባለፈ ግን አስገራሚው ጉዳይ የኢትዮጵያ ረኀብ ጉዳይ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚቀባበሉት ብቻ ሳይሆን፤ ሚስጥራዊ የመልዕክት ልውውጦችም የሚገልጡት ያገጠጠ እውነታ መሆኑ ነው።

የአሁኑ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ና አሜሪካ

ከሰባት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያና በአሜሪካ ረጅም ግንኙነት ላይ ድንቅ መጽሐፍ የጻፉት ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ን ኢትዮጵያ ‘የአሜሪካ Gatekeeper’ ሲሉ ይጠሯታል።

አሜሪካ ከአፍሪካ ቀንድ መንጭተው ጥቅሟን ሊጎዱ የሚችሉ ጉዳዮችን ለማረጋጋት በማሰብ ኢትዮጵያን የአካባቢው አለቃ አድርጋ መሾሟ ያለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት ታሪክ እንደሆነ የሚገልጹት ዶ/ር ጌታቸው፤ ነገር ግን አሜሪካ ግንኙነቷን ከኢትዮጵያ ተቋማት ጋር ከማድረግ ይልቅ ከግለሰብ አመራሮች ጋር ማድረግን መርጣለች ይላሉ።

Hillary-clinton-in-addis-ababa-ethiopia

በነሐሴ 2004 ሒላሪ ክሊንተን የተለዋወጧቸው ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ኢሜይሎችም የሚያረጋግጡት ይሄንኑ ነው። ኢሜይሎቹ በወቅቱ የኢትዮጵያ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን መሞት ተከትሎ መለስ የአሜሪካ ሁነኛ ወዳጅ በመሆናቸው አሜሪካ ታላቅ ባለሥልጣናትን ለቀብር እንድትልክ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ሲጎተጉቱ የሚያሳዩ ናቸው። “አሜሪካ ትልቅ የዲፕሎማሲ ቡድን እንደምትልክ ስገልጽላቸው [በወቅቱ የኢትዮጵያ ምክትል የውጭ ጉዳይ የነበሩትና] መለስ ሲሞቱ አብረዋቸው ቤልጅየም፣ ብራሰልስ የነበሩት ብርሃነ [ገብረክርስቶስ] በደስታ ከሰው ፊት አቅፈው ሳሙኝ” ይላሉ በወቅቱ የሒላሪ ሁነኛ ወዳጅ የነበሩትና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የሥራ ኃላፊ የነበሩት ቼሪል ሚልስ ለሒላሪ በተላከ አንድ ኢሜይላቸው ላይ ከአዲስ አበባ የደረሳቸውን መረጃ መሠረት በማድረግ፣ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ያለውን እምነት አቶ መለስ ላይ ብቻ ጥሎት እንደነበርና የዶ/ር ጌታቸውን የአሜሪካና የኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ.ዋ ኢትዮጵያ ግንኙነት እንደ መለስ ባሉ ግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ ነው የሚል ሐሳብ የሚያረጋግጥልን ደግሞ በወቅቱ በምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ማዕረግ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ የፖለቲካል ጉዳዮች ኃላፊ የነበሩት ዊንዲ ሸርማን የመለስን ሞት አስመልክተው ለሒላሪ ክሊንተን የጻፉት ኢሜይል ነው። ዊንዲ በኢሜይላቸው “የመለስ ሞት ለኢትዮጵያም፣ ለአፍሪካም ለሁላችንም ጉዳት ነው። ካርሰን እንደሚያምነውም የመለስ ተተኪ የሚሆን ማንኛውም ቀጣዩ መሪ የበለጠ አምባገነንና ፈላጭ ቆራጭ፤ ለእኛም መጥፎና የሚጎረብጥ ይሆናል” በማለት የመለስ ሞት ለአሜሪካ ጥቅም ትልቅ ጉዳት መሆኑን ገልጸው፤ የመለስ ተተኪ ግን ለአሜሪካ ጥቅም የማይመች መሆኑን ገምተዋል። ይሄም የአሜሪካና የኢትዮጵያ ግንኙነት በመለስ ላይ እንጅ በተቋማት ላይ ያልተመሠረተ መሆኑን አመላካች ነው። ነገር ግን እንደ ተገመተው የመለስ ተተኪ ለአሜሪካ አልተመቻትም ማለት ደግሞ ከባድ ነው።

ሁሌ ‘deeply concerned’ የምትሆነው አሜሪካ

“አሜሪካ የዓለም አለቃ ናት” የሚለው አባባል ብዙ እውነትነት አለው። በመላው ዓለም ወደ ሦስት መቶ የሚጠጉ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች፣ የሁሉንም የዓለም ሐገራት ዓመታዊ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የደኅንነትና የሰብኣዊ ይዞታ አጥንቶ የሚተነትን ስርኣት ከአሜሪካ ውጭ ማንም የለውም። አዎ አሜሪካ ትልቅ አገር ናት። ለዚህም ነው በተለያዩ አገራት የመብት ጥሰትም ሆነ ብጥብጥ በተነሳ ቁጥር ከሁሉም ቀድማ አሜሪካ የተለመደውን ‘We are deeply concerned’ የሚል መግለጫ የምታወጣው። አሜሪካ ዝም ስትልም ‘እንዴት አሜሪካ ዝም ትላለች?’ የሚል ወቀሳ ቀድሞ የሚያርፍባት። ምናልባትም ይህ ‘አሜሪካ በተለያዩ የመንግሥታት ለውጦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጋለች’ የሚለው ሐሜት ተቀጥላ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ አሁን አሁን “አሜሪካ ‘We are deeply concerned’ (በፅኑ አሳስቦናል) የሚል የተለመደ መግለጫ ከማውጣት ባለፈ ለሰብኣዊ መብት ጥሰቶችም ሆነ ለአምባገነናዊ አገዛዞች ትኩረት አትሰጥም” የሚለው ሐሳብ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የብዙ የሰብኣዊ መብት ታጋዮች ድምዳሜ ነው። የአሜሪካ መንግሥት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማግስት ጀምሮ ‘We are deeply concerned’ የሚል ሁሉንም የማያስከፋ የሚመስል የዲፕሎማቲክ ቋንቋ (diplospeak) መጠቀም እንደጀመረ ጉዳዩን የተከታተሉ ሊቃውን ይገልጻሉ:: የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሠራተኛ የነበሩት ኮሪ ስኬክ (kori Schake) እንደሚሉት አሜሪካ ‘We are deeply concerned’ ስትል በዲፕሎማቲክ ቋንቋ [ሁለቱንም ወገኖች ላለማስከፋት] መሐሉን መያዟ እንደሆነ ከGoldilocks መርሁ “just rights’” ጋር በማመሳሰል ይገልጹታል። ኮሪ አያይዘውም “ጉዳዩ ያሳስበናል ማለት ቢሆንም በጣም አሳስቦናል ማለት ግን አይደለም” ይላሉ።

አሜሪካ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ‘We are deeply concerned’ ስትል ምን ማለቷ ነው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚመስሉ ጉዳዩች በሒላሪ ክሊንተን ኢሜይሎች ውስጥ ማየት እንችላለን።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሚያዚያ ወር መጨረሻ 2008 ባወጣው መግለጫው አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦ.ፌ.ኮ) አመራሮች በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ መሠረት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አባላት ናችሁ ተብለው መከሰሳቸው በጥብቅ እንዳሳሰበው (deeply concerned) ገልጾ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን በመጠቀም የሠላማዊ ዜጎችን ድምፅ ከማፈን እንዲታቀብ ጠይቆ ነበር። ነገር ግን ይህን መግለጫ በሰኔ 2003 ከቼሪል ሚልስ ለሒላሪ ክሊንተን ከተላከላቸው አንድ ኢሜይል አንፃር ስንገመግመው እውነትነቱን እንጠራጠራለን። በሰኔ 2003 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አባላት ናቸው የተባሉ ዐሥራ አራት ኢትዮጵያዊያን ላይ ከዘጠኝ ዓመት እስር እስከ ዕድሜ ልክ እስር መፍረዱን ተከትሎ ለሒላሪ በተላከላቸው አንድ ኢሜይል ላይ “የኢትዮጵያው ዴስካችን እንዳሳወቀን ከሆነ ይህ የፍርድቤቱ ውሳኔ መንግሥት በሽብርተኝነት ላይ እየወሰደ ካለው ጠንካራ እርምጃ ጋር አብሮ የሚሄድ ነው” በማለት ኦነግ የሽብርተኛ ድርጅት እንደሆነ በተዘዋዋሪ በመግለጽ፤ የመንግሥትን እርምጃ ያወድሳል።

ሌላው ለዚህ ጉዳይ ማሳያ ሊሆነን የሚችለው ጉዳይ በ2003 በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ረኀብ በአፍሪካ ቀንድ ማንዣበቡን ተከትሎ የወቅቱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሒላሪ ክሊንተን ድርቁ በኢትዮጵያ የሚገኙ ሰፋፊ የግል እርሻችን (commercial farms) አጥቅቶ እንደሆነ ላቀረቡት ጥያቄ በወቅቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዶናልድ ቡዝ ድርቁ በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል የተከሰተ

እንደሆነ ገልጸው፤ “ሰፋፊ የግል እርሻዎች ደግሞ የሚገኙት በምዕራቡ የአገሪቱ ክፍል ነው” ካሉ በኋላ፤ “ይሄ ብዙ መሬት ከገበሬዎች ተነጥቆ ለባለሀብቶች ተሰጥቷል የሚባለው ነገር ሚዲያዎች ያጋንኑታል” ብለው ይመልሳሉ። እንግዲህ የአሜሪካን መንግሥት (በአምባሳደሩ ደረጃ) በተለምዶ የመሬት ነጠቃ (land grab) እየተባለ የሚታወቀውን እና ብዙ የሰብኣዊ ተቋማት እያወገዙት የሚገኘውን ከገበሬዎች መሬት ነጥቆ ለባለሀብቶች የመስጠት ሒደት ነው “የተጋነነ ወሬ ነው” ሲል በአምባሳደሩ አማካኝነት የሚያጣጥለው።

የሒላሪ ክሊንተን ኢሜይሎች መካከል አሁንም የአሜሪካን አቋም ሊያሳየን የሚችለው ሌላው ጉዳይ አሜሪካ በምርጫ 2002 ላይ ያሳየችው አቋም ነው። ምርጫውን ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. ሙሉ ለሙሉ ከማሸነፉ ጋር ተያይዞ በወቅቱ የአሜሪካ ብሔራዊ የፀጥታ ካውንስል ቃለ አቀባይ የነበሩት ማይክ ሐመር ውጤቱን አስመልክተው “We are concerned that international observers found that the elections fell short of international commitments” በማለት የተለመደውን ‘We are [deeply] concerned’ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በወቅቱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃለ አቀባይ የነበሩት ፒ.ጀ. ክሮውሊም “ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን የጠበቀ ግንኙነት ከግምት ውስጥ አስገብታ የእኛን መግለጫ በጥሞና እንድታጤነው እንጠይቃለን” ብለው ነበር።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኢሜይል ላይ ግን ከዚህ ተቃራኒ የሆነ አቋምን እናገኛለን። ግንቦት 16፣ 2002 የሒላሪ ‘ስታፍ’ አባል የነበሩት ወጣቱ ጄክ ሱሊቫን ከአዲስ አበባ የደረሳቸውን መልዕክት ለሒላሪ ባስተላለፉት (Forward) ኢሜይል ”ምርጫው ብዙ ሰዎች መሳተፋቸው መልካም ነው። የመለስ ፓርቲ ምርጫውን እንደሚያሸንፍ ግልጽ ነው። እንደ 1997 ምርጫ ብጥብጥና ሁከት የሚፈጠርም አይመስልም” በማለት በምርጫው ውጤት ዙሪያ ምንም ዓይነት ቅሬታ የሌለበት ሐሳብ ይሰነዝራሉ። በአደባባይ የምርጫው ውጤት እንደሚያሳዝናት የገለጸችው አሜሪካ በውስጥ ብዙም ስትጨነቅ አይታይም።

ኢሜይሎቹ ምን ይነግሩናል?

በሒላሪ ክሊንተን ኢሜይሎች (ኢትዮጵያን በሚመለከት የተለዋወጧቸውን) ውስጥ ከዶ/ር ገቢሳ ኢጀታ እስከ የአሜሪካ ‘የድሮን’ ጣቢያ በአርባ ምንጭ፤ ከኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ቆይታ እስከ ለኢትዮጵያ የሚደረግ የአምባሳደር ሹመትና መረጣ ድረስ የሚገኙ ሲሆን፤ ከላይ መርጠን ያወጣናቸው ኢሜይሎች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚመጣን ለውጥ ከአሜሪካ ለሚጠብቅ ግለሰብ ጥሩ መረጃ የያዙ አይደሉም። አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግሥት ቀንደኛ አጋርነቷ አሁን ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ገዝፎም እንደሚታይም ማሳያ ናቸው። በብዙዎች ግምት አርባ አምስተኛዋ የአሜሪካ ፕሬዘደንት ይሆናሉ ተብለው ግምት እየተሰጣቸው ያሉት ሒላሪ ክሊንተን ወደ ፕሬዘደንትነቱ መንበር መምጣታቸው የኢትዮጵያን መንግሥት እና የአሜሪካን ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክረው እንጅ ኢትዮጵያ ውስጥ ለዴሞክራሲ የሚደረገውን ትግል ያግዘዋል ብሎ ማሰቡንም ሞኝነት ያስመስለዋል።

Health: ከባድ ላብ የጤና ነው? | Hyperhidrosis

0
0

Lab

ዶክተር ዓብይ ዓይናለም | ለዘ-ሐበሻ ጤና ዓምድ

<<ከፍተኛ የሆነ የላብ ችግር አለብኝ፡፡ ብብቴ ውስጥ፣ በግንባሬ ላይ በተለይም በመዳፌ ላይ እንደ ውሃ ይቀዳል፡፡ እግሬም እንደዚሁ በጣም ያልበኛል፡፡ ከሰው መቀላቀል ትቻለሁ፡፡ እባካችሁን ከዚህ እግር ከወርች ከያዘኝ የከባድ ላብ ችግር መፍትሄ ካለ ጠቁሙኝ፡፡>> ሲል አንድ የዘ-ሃበሻ አንባቢ በስልክ ያቀረበልንን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ጉዳዩን የዛሬ የጤና አምዳችን ጉዳይ አድርገነዋል፡፡

ላብ ሰውነታችን ራሱን የሚያቀዘቅበት ተፈጥሯዊ መንገድ ነው፡ ፡ አብዛኛው ይህ ሁኔታ ተፈጥሯዊ እና የጤንነት ምልክት ነው፡፡ አ ንዳንድ ሰዎች ግን ተደጋጋሚ እና የማያቋርጥ ላብ ይታይባቸዋል እ ና ይህ ሁኔታ በህክምና ቋንቋ ሃይፐርሃይድሮሲስ/Hyperhidrosis/ ይባላል፡፡

ሃይፐርሃይድሮሲስ/ከባድ ላብ/ በላብ ዕጢዎች የሚመረተው ላ ብ ሰውነት ራሱን ለማቀዝቀዝ ከሚፈልገው በላይ ነው፡፡ ይህ በሽታ በ አብዛኛው መዳፍንና የእግር ስርን እና ብብትን ያጠቃል፡፡ የዕለት ተዕ ለት ስራን ከማወኩም በተጨማሪ ከባድ ላብ ማህበራዊ ጭንቀት እና የመሸማቀቅ ስሜት ብሎም ራስን ማግለል ሊያስከትል ይችላል፡፡

ጥሩው ነገር ግን ይህንን ችግር ለማከም የተለያዩ ዘዴዎች መኖራ ቸው ነው፡፡ ከባድ ላብ እጅግ ከባድ ሲሆን እስከ ቀዶ ጥገና የሚያደር ስ ህክምና አለው፡፡ ምንም እንኳን መቼ የት እና ምን ያክል ያልበናል የሚለው በስፋት ቢለያይም አብዛኛው ሰው ከበድ ያለ የጉል በት ስራ ሲሰራ፣ ሞቃታማ ቦታ ሲሆን፣ ድንጋጤ ወይም ጭ ንቀት እና አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሲሆን ያልበዋል፡፡ ከባድ ላብ ሃይፐርሃይድሮሲስ ያለበት ሰው የላብ ሁኔታ ግን ከላይ ከ ተጠቀሰው በእጅጉ ከፍ ያለ ነው፡፡

የከባድ ላብ ዋና ዋና ምልክቶች ቶሎ ቶሎ መምጣቱ የሚ ታይ ከሚገባው በላይ የሆነ እና ብብትን የሚያበሰብስ ሲሆን ነው፡፡ ከሚገባው በላይ የሆነ የሚያስጨንቅ የላብ መኖር በ ተለይም በእግር ስር፣ በብብት፣ በራስ እና በፊት ላይ የሚታ ይ ሲሆን፣ የቆዳ ማጣበቅ ወይም ከእጅ መዳፍና ከእግር መር ገጫ ጠብ ጠብ የሚል ላብ ሲታይ ነው፡፡

ሃይፐርሃይድሮሲስ የሚለው ስያሜ የሚሰጠውን የተቸ ጋሪውን የዕለት ተዕለት ስራን የሚያደናቅፍ ከፍተኛ የላብ መ ጠን/ከባድ ላብ ሲኖር ነው፡፡ ይህ ክስተት ያለ ምንም በቂ ም ክንያት ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ይታያል፡፡ ለእነዚህ ሰዎ ች ከባድ ላብ የማህበራዊ ህይወትን ያውክባቸዋል፡፡

እጃቸው ያለማቋረጥ ስለሚረጥብ ስራ መስራትም ሆነ መዝናኛ ቦታ ራሳቸውን ማዝናናት ይሳናቸዋል፡፡ በዚህም ም ክንያት ከሰው ጋር ሲጨባበጡ በእጃቸው ላብ ምክንያት እ ና ሸሚዛቸው የላብ ቅርፅ ስለሚያሳይ አንዳንዴ ላቡ ጠረን ስለሚኖረው በዚህ በሚፈጠርባቸው መሸበር ራሳቸውን ከ ሰው ያገላሉ፡፡

እንደዚህ ያለ ችግር ያለበት ሰው ከተለመደው በላይ ድ ንት ከፍ ያለ ላብ ሲያይ፣ ላብ የዕለት ተዕለት ስራውን ሲያደ ናቅፍበት፣ እና የሌሊት ላብ ያለ በቂ ምክንያት ሲኖረው ሐኪ ም ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የብርድ ላብ የታየበት ማንኛ ውም ሰው ሐኪም ዘንድ መቅረብ አለበት፡፡ በተለይም ደግ ሞ ሁኔታው ከጭንቅላት ቅል መቅለል እና የደረት ወይም የ ሆድ ህመም ስሜት ጋር አብሮ ከመጣ የልብ በሽታ፣ የጭንቀ ት ወይም የሌላ ከፍተኛ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ጊ ዜ ሊሰጠው አይገባም፡፡

የከባድ ላብ ምንጩ ሰውነታችን ሙቀቱን ከሚቆጣጠርበት የቁጥጥር ስርዓት ይመነጫል በተለይ ደግሞ የላብ ዕጢዎች ቆዳችን ሁለት አይነት የላብ ዕጢዎች አሉት፡፡ አንደኛው ኢክራይን ዕጢ ሲባል ሌላኛው ደግሞ አፓክራይን ዕጢ ሲባል ሌላኛ ው ደግሞ አፓክራይን ዕጢዎች ይባላሉ፡፡ ኢክራይን ዕጢዎች በአብ ዛኛው ሰውነታችን ውስጥ ሲገኙ በቀጥታ አፋቸው ወደ ቆዳ ላይኛው ክፍል ይከፈታል፡፡ አፓክራይን ዕጢዎች ግን የሚገኙት በብዛት ፀጉር በሚሸፍናቸው የቆዳ ክፍሎች ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ የራስ ቅል፣ ብብት እና ጭገር አካባቢ ነው፡፡

የሰውነታችን ሙቀት ሲጨምር አውቶኖሚክ ነርቨስ ሲስተም የ ተባለው የአዕምሮ ክፍል እነዚህን ዕጢዎች ላብ ወደ ቆዳ የላይኛው ክፍል እንዲለቁ ያደርጋል፡፡ ላቡም ሰውነታችንን ከቀዘቀዘ በኋላ ይ ተንና ቆዳችን ይደርቃል፡፡ ይህ ላብ በውስጡ በአብዛኛው ውሃ እ ና ጨው ይይዛል አልፎ አልፎ ደግሞ ሌሎች ኬሚካሎችም በተጨ ማሪ ይይዛል፡፡

ከባድ ላብ በአንድ ቦታ የተወሰነ ወይም ጠቅላላ ወይም በርካታ ሰውነታችንን የሚያካትት /generalized hyperhidrosis/ በመባል ይከፋፈላል፡፡ የመዳፍና የእግር ከባድ ላብ በአብዛኛው ቀን ቀን የሚ ከሰት ነው፡፡ አንዳንዴም በብብት አካባቢም ይታያል፡፡ ይህ ላብ ሌሊ ት በአመዛኝ አይታይም፡፡ በሁለቱም የሰውነታችን ክፍል በእኩል መ ልኩ ይታያል፡፡ ይህ አይነት ከባድ ላብ ወደ ሃያው የዕድሜ ክልል አ ካባቢ በአብዛኛው ይጀምራል፡፡ ከሌላ በሽታ ጋር ግንኙነት የሌለውና ራሱን የቻለ ችግር ነው፡፡ ትክክለኛው ምክንያት ወይም መነሻ ገና አይታወቅም፡፡ ነገር ግን በዘር የመምጣት አዝማሚያም ይኖረዋል፡፡ በርካታ የሰውነት ክፍልን የሚያጠቃው የከባድ ላብ ችግር አይነ ት በድንገት የሚጀምር ነው፡፡ በርካታ የሰውነት ክፍልን ያጠቃል፡፡ በ አብዛኛው ሌላ ምክንያት አለው፡፡ ለምሳሌ የመድሃኒት የጎንዮሽ ጉዳ ት፣ የበሽ ምልክት፣ የማረጥ ምልክት፣ የስኳር መጠን በደም ውስጥ ዝ ቅ ማለት፣ የታይሮይድ በሽታ፣ የደም ካንሰር በሽታ፣ የልብ ድካም በሽ ታ ወይም የአንድ ወይም የሌላ ኢንፌክሽን በሽታ ምልክት ሊሆን ይ ችላል፡፡ በዚህ ጊዜ አስፈላጊውን መድሃኒት በመውሰድ ወይም መንስ ኤውን በሽታ በማከም ላቡን ያጠፋዋል፡፡

በከባድ ላብ መንስኤነት የሚመጡ በርካታ የአካልና የስነ ልቦና ች ግሮች መካከል የፈንገስ ኢንፌክሽን፣ በባክቴሪያ ምክንያት የቆዳ እና የቆዳ ፀጉር አካባቢ ኢንፌክሽን በእግር ጣቶች አካባቢ የሚመጡ ኢ ንፌክሽኖች፣ የጎዳ ኪንታሮት /warth/ በሽታ ወይም ኪንታሮት ሲታ ከም ቶሎ ያለመዳን ችግር፣ በቆዳ ላይ በሙቀት የሚመጡ ሽፍታዎች መብዛት፣ እና ማህበራዊ መገለል ከላይ እንደተጠቀሰው ግለሰቡ ራሱ

ጥ መግባት አንባቢያን ማደናገር ነው፡፡ ይህም ዘዴ እንደየሁኔታው ባ ደጉ ሀገራት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

ለአንዳንድ ከባድ ላብ ላላባቸው ሰዎች መፍትሄው ቀላል ነው፡፡ ከፋርማሲ በሚገዛ ላብ መከላከያ ሊቆም ይችላል፡፡ እነዚህ የላብ ማቆ ሚያ መድሃኒቶች የላብ መተላለፊያ መንገዶችን በመዝጋት ይህንንም በአልሙኒየም ጨው አማካኝነት ወደ ቆዳ የሚደርሰውን የላብ መጠ ን ይቀይሳል፡፡ ማስታወስ ያለብን ላብ መከላከያ ላብ ሲከላከል ዲኦራ ንት ደግሞ የላብን መጥፎጠረን ብቻ ነው የሚከላከለው፡፡

ከላብ መከላከያ በተጨማሪ የሚከተሉትን ማድረግ ላብን ለመቀ ነስና ከላብ ጋር ለተያያዙ የሰውነት መጥፎ ጠረን ጠቃሚ ነው፡፡

1. ቢቻል በየቀኑ መታጠብ ይህ በቆዳችን ላይ ያሉ ባክቴሪያዎ ችን ይቀንሳል

2. ከመታጠብ በኋላ እግርን በፎጣ በደንብ ማድረቅ፡፡ ይህም ን ማግለል የመጀመር ሁኔታ ይታያል፡፡

በከባድ ላብ ምክንያት ወደ ሐኪም ዘንድ ሲቀርቡ ሐኪሙ የተ ለያዩ የበሽታ ታሪኮችን ይጠይቃሉ፡፡ የአካል ምርመራም ያደርጋሉ፡ ፡ የደምና የሽንት ምርመራ በማዘዝ በሽታው በምን ምክንያት እንደ መጣ ለማወቅ ይሞክራሉ፡፡ ከተገኘም ሐኪምዎ ቴርሞ ሬጉሌተር ቴ ስት ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡

የተለያዩ ምርመራዎች ካደረጉ በኋላ ሐኪሙ የተለያዩ የህክምና ዘዴዎችን ሊጠቀም ይችላል፡፡ ሐኪምዎ እንደ አልሙኒየም ክሎራይ ድ የመሰሉ የመድሃኒት ይዘት ያላቸውን ሊይዙ ይችላሉ፡፡ ይህ መድ ሃኒት ከቀላል እስከ መካከለኛ ደረጃ ሃይፐርናይድሮሲስን ለማከም ወ ይም ለመቀነስ ይችላል፡፡ ይህ መድሃኒት ከተገኘ ጥሩ ውጤት ለማግ ኘት ላብ በሚበዛበት አካል ላይ ሌሊት ሌሊት ማድረግ ነው፡፡ መድሃ ኒቱ ቆዳን የማሳበጥ፣ የማቅላት እና የማሳከክ ፀባይ ያለው ጠንካራ ኬ ሚካል ነው፡፡ ይህንን ለመከላከል ጠዋት በደምብ ማጠብ ያስፈልጋ ል፡፡ በርካታ የሰውነትን ክፍሎች የሚያጠቃልል የላብ ችግር ከሆነ ሐ ኪምዎ አንቲ ኮለነርጂክ መድሃኒቶችን ሊይዙ ይችላሉ፡፡ ይህም መድ ሃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች አሉት፡፡ የቆዳ ሐኪሞች ደግሞ አዩንቶፎረሲ ስ በሚባል ዘዴ ያክሙታል፡፡ ከዚህም ሌላ በቶሊየም ቶክሲን የተባለ መድሃኒት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ ይህ ኬሚካል የተወሰኑ ጡ ንቻዎችን ፓራላይዝ በማድረግ የቆዳን የእርጅና ገፅታ ለማጥፋት ባደ ጉት ሀገሮች ጥቅም ላይ የሚውልበት ጊዜ አለ፡፡ይህም የሚደረገው ላ ብን በሚመለከት አዕምሮ ወደ ላብ ዕጢዎች የሚመጣውን የነርቭ ሂ ደት በማቋረጥ ነው፡፡ ወደዚህ ቀዶ ጥገና አሰራር ዝርዝር ሂደት ውስ ባክቴሪያዎች እና ሌላ ጀርሞች ለመራባት የሚያመቻቸውን እርጥበ ት ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም እርጥበት የሚመጥ ፓውደር መጠቀም ይቻላል፡፡

3. ከተፈጥሮ ማቴሪያል የተሰሩ ጫማ እና ካልሲ መጠቀም ከ ቆዳ የተሰራ ጫማ እግራችን አየር እንዲያገኝ በማድረግ የእግር ላብ ን ይቀንሳል፡፡

4. ጫማ ውስጡ ቶሎ ስለማይደርቅ እያቀያየሩ /በየቀኑ/ ማድረ ግ ላብ በብዛት ያለበት እግርን ችግር ይቀንሳል፡፡

5. የጥጥና የሱፍ ካልሲ በመጠቀም እግርን እርጥበት ስለሚመጥ በተለይ ደግሞ ሯጭ ሰው እርጥበት መጣጭ ስፔሺያል ካልሲ እንዲ ጠቀም ይመከራል፡፡

6. ካልሲን በየቀኑ መቀየር ቢቻል በቀን ሁለቴ በመቀየር ካልሲ በ ተደረገ ቁጥር ታጥቦ እና በደንብ እግርን እንዲደርቅ በማድረግ ተጨ ማሪ መፍትሄ ይሆናል፡፡

7. እግርን ማናፈስ ከተቻለ በባዶ እግር መሄድ ካልሆነም ቶሎ ቶ ሎ እግርን እያወጡ ማናፈስ (ቢቻል በቀን ለ30 ደቂቃ እግርን ከጫ ማ አውጥቶ ማናፈስ ቢቻል)

8. በአጠቃላይ የተፈጥሮ ክር ልብሶች መልበስ /የጥጥ የሱፍ እና የሀገር ልብሶች ሰውነት በቂ አየር እንዲያገኝ ያደርጋሉ/

9. አንድ ዮጋ፣ ሜዲቴሽን ወዘተ… የመሳሰሉ ዘዴዎችን በመጠቀ ም ጭንቀትን በማስወገድ የላብ መከሰትን መቀነስ ይቻላል፡፡

ስለዚህ ጠያቂያችን ከላይ የተጠቀሱትን በማድረግና መፍትሄ ካ ልሆኑ ወደ ሐኪም ዘንድ በመሄድ መፍትሄ መሻት ይመከራል፡፡

“በአሁኑ ወቅት፤ እውነቱን ለመናገር ድርጅታችን በጣም፤ በጣም እጅጉን የተዳከመ ድርጅት ነው። ይህንን መካድ አይቻልም።” –ዶ/ር ነገደ ጎበዜ

0
0

ዶ/ር ነገደ ጎበዜ፤ መሥራችና የቀድሞው የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) ከፍተኛ አመራር አባል፤ ስለ ድርጅቱ አመሰራረት፣ የትግል እንቅስቃሴ ታሪክና ሚናዎች ይናገራሉ።

“በአሁኑ ወቅት፤ እውነቱን ለመናገር ድርጅታችን በጣም፤ በጣም እጅጉን የተዳከመ ድርጅት ነው። ይህንን መካድ አይቻልም።” – ዶ/ር ነገደ ጎበዜ

የዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ ቀብር ሥነስርዓት ነገ ይፈጸማል

0
0

የዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ የቀብር ስነ ስርዓት ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ይፈፀማል፡፡
አንጋፋው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አባት ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬን ቀብር ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ የቀብር ስነስርአቱ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ነገ ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀኑ 7 ሰዓት እንደሚፈፀም አስታወቀ፡፡ በ80 አመታቸው እሁድ ግንቦት 7 ቀን 2008 ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ካሳንችስ ቶታል አጠገብ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ዶ/ር ወልደመስቀል አስከሬን በአሁኑ ወቅት ቤተዛታ ሆስፒታል ይገኛል፡፡

ዶ/ር ወልደመስቀል ከአንድ ልጃቸው ጋር

ዶ/ር ወልደመስቀል ከአንድ ልጃቸው ጋር

ዶክተሩ ባጋጠማቸው ስትሮክ የተነሳ ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ሶስቴ ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው ሲሆን ለህልፈት የዳረጋቸውም ስትሮክ እንደሆነ ከምንጮች ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ህመሙ ከገጠማቸው በኋላ መናገርና መንቀሳቀስ ሁሉ አቅቷቸው እንደነበር የገለፁ ምንጮች ሁለት ነርሶች 24 ሰዓት ሙሉ ይንከባከቧቸው እንደነበርም ነግረውናል፡፡

Hiber Radio: አገዛዙ በአርባምንጭ የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይን ልጃችሁ ሞቷል ብሎ ካረዳ በኋላ መረጃው ሐሰት በመሆኑ ቤተሰብ ከለቅሶ ተነሳ –ወጣቶች እየታፈሱ ነው

0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ግንቦት 7 ቀን 2008 ፕሮግራም

<... . ...> አቶ ጴጥሮስ አሸናፊ ከስዊዘርላንድ ስለ ረዳት አብራሪ ሐይለመድን አበራ አንዳንዶች የተለየ ትርጉም የሰጡትን ትክክለኛውን የፍርድ ቤት ውሳኔና ወቅታዊ የረዳት አብራሪውን ሁኔታ አብራርቶልናል (ሙሉውን ያዳምጡት)

ሁበር የዋጋ አሽከርካሪዎች የዋጋ ማስተካኬአ እንዲያደርግ ጥአቄ አቅርበውለት በቅርቡ ዋጋ አስተካክላለሁ ማለቱና በሌሎች የሁበር ተወካዮች እና የአሽከርካሪዎች ስብሰባ በተመለከተ ቃለ መጠይቅ ከአቶ ፍቅረስላሴ ወልደየስ የሙሉ ጊዜ ሁበር አሽከርካሪ ጋር የተደረገ ቆይታ(ሙሉውን አድምጡት)

ድርቅ፣ሰደት፣መፈናቀል ፣ጎርፍ እና ሞት እያመሰው ያለው ወቅታዊው የኢትዮጵያ እና የሕዝቧ ችግሮች ሲዳሰሱ (ልዩ ዘገባ))

የኢሳት ስድስተኛ ዓመት ዝግጅትን በተመለከተ በቬጋስ ከአዘጋጅ ኮሚቴው ጋር ያደረግነው ቃለ ምልልስ

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሕይወት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑ ተገለጸ

ሊገድሉትም ሆነ ሊመርዙት ይችላሉ የሚል ስጋት አለ

በአርባ ምንጭ አካባቢ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ጥቃትን ተከትሎ በከተማዋ በርካታ ወጣቶች እየታሰሩ ነው

አገዛዙ ልጃችሁ ሞቷል ብሎ ያረዳቸው የአንድ አርበኛ ቤተሰብ መረጃው ሀሰተና መሆኑን አውቀው የጀመሩትን ለቅሶ አቁመዋል

አቶ ሐይለማሪአም ደሳለኝ ሱዳን ከኤርትራ ጋር እንድታስታርቃቸው እንደሚሹ ተናገሩ

ኢትዮጵያዊው ወጣት አክቲቪስት እና ጦማሪ በእስር ቤት ውስጥ ከደረሰበት ድብደባ ሳያገግም በአገዛዙ ፍርድ ቤት የአምስት ዓመት እስራት ተፈረደበት

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አባት አሰልጣኝ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ አረፉ

አዲሱ የለንደን ሙስሊም ከንቲባ አሜሪካዊ እጩ ፕ/ታዊ ተወዳዳሪ ዶናል ትራምፕን ስለ እስልምና ታላቅነት ሊያስተምሯቸው እንደሚፈልጉ ተናገሩ

የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ እስር ቤት ሳለ አስከሬንህ እንደ ፕ/ር አስራት ወልደየስ ከእስር ቤት ይወጣል መባሉንና ተደጋጋሚ በደል በእስር ቤት እንደተፈጸመበት ገለጸ

ለሕዝቡ ሚታገሉ ሲታሰሩ ቤተሰቦቻቸው እንዳይጎዱ መታሰብ እንዳለበት ጠቀሰ

ኢትዮጵያ አንድ የኬኒያ ኩባንያ ሀብት የሆነ ከሁለት ሚሊዮን በላይ በመያዣነት አገተች

ድርጊቱ የዲፕሎማሲ ቻና በአዲስ አበባ ገዢዎች ላይ ሊአሳድር ይችላል ተብላል

የሕወሓት-ኢህአዴግ መንግስት ሰሞኑን ከግንቦት ሰባት ማረኳቸው ብሎ ለሕዝቡ አሰራጨው የጦር መሳሪአዎች ምስል የተሳሳተ መሆኑ ተጋለጠ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live