Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የምሥራች –ትግርኛና ዐማርኛም በላቲን ፊደል ሊጻፉ ነው!

$
0
0

Memher Leulekal Akalu
ይሄይስ አእምሮ

መምህር ልዑለቃል አካሉ የተባሉ ኢትዮጵያዊ በቅርቡ በኦሮምኛ ቋንቋ የላቲን ፊደል አጠቃቀም ዙሪያ የጻፉትን መጣጥፍ ቆየት ብዬም ቢሆን ዛሬ አነበብኩት፤ ግሩም ነው፡፡ እሳቸው የሚሉት “ለኦሮምኛው ከላቲን ይልቅ የግዕዙ ፊደል አይቀርብም ወይ?” ነው፡፡ ይሄን ያህል ለምን ሩቅ ተሄደ ነው ጥያቄያቸው፡፡ ላቲኑን ለመጠቀም ለምን ያን ያህል ሩቅ መንገድ መጓዝ አንዳስፈለገም መልሱ በመጣጥፉ ውስጥ አለ – ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች በወያኔ በመታገዝ ሀገሪቱን ለመበታተን ከሸረቡት ሤራ አንዱ መሆኑ በስፋት ተጠቅሷል፡፡ በሚከተለው የመጣጥፉ ስም ከድረገፆች መፈለግና ማንበብ ይቻላል፡፡

“ ከኢትዮጵያውያን ቋንቋዎች አንዱ የሆነው ኦሮምኛ ቋንቋ መጻፍ ያለበት በግእዝ ፊደል ወይስ በላቲን ፊደል? (ከኢትዮጵያዊ ማንነት አንጻር ለውይይት መነሻ እንዲሆን የቀረበ ጽሁፍ)”

እኔ የምለው ደግሞ ትግርኛም ዐማርኛም የላቲኑ ፊደል ያስፈልጋቸዋል ነው፡፡ የግዕዝ ፊደል ባየን ቁጥር በአንጻራዊ አነጋገር በጣም ውብና ቆንጆ የነበረችዋን የቀድሞዋን ኢትዮጵያ እያስታወስን በትዝታ ሰቀቀን ከምንንገላታ እንደኔ እንደኔ ሁለቱንም እትማማች ቋንቋዎች በላቲኑ እንጻፋቸውና ከዚህ ወያኔን ሽብር ከሚለቅበት ግዕዛዊ የአጻጻፍ ሥልት እንገላገል፡፡ ግን ግን ወያኔዎች ላማሮች ካላቸው ሥር የሰደደ ጥላቻ አንጻር የትግርኛውን ቋንቋችንን በላቲን እንዲጽፍ የትግራይን ሕዝብ ያኔ ጥንት ሲነሱ ጀምሮ ያላስገደዱት ምን ወይም ማንን ፈርተው ይሆን? አስበውት አስበውት ሊሆንላቸው እንደማይችል ሲረዱት እነሱ የኛ ነው የሚሉትን ሕዝብ የአጻጻፍ ዘይቤ ወደ ላቲን ሊለውጡ እንዳልቻሉ መገመት አያቅትም – ይብላኝ እንጂ ለሌላው ገራገር ወገኔ፡፡ የዐማራው ሕዝብም ከዚህ ወያኔያዊ መቅሰፍት ለጥቂት የዳነው በ“ኢሕዲን/ብአዴን ተጋድሎ” ሊሆን ስለሚችል የዐማራው ሕዝብ ለዚህ ብርቅዬና ቅን አሳቢ ቅንቅን ድርጅቱ ባለውለታ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እግዜር ይስጥልን ውድ የዐማራው ሕወሓት ብአዴንዬ፡፡ እናንተ ባትኖሩ ኖሮ ይሄኔ baattam eenichagaar nebbber, “በጣም እንቸገር ነበር” ለማለት ፈልጌ ነው በላቲን ፊደል ስራቀቅባችሁ፡፡

እኔ ዛሬ ልጀምረውና ከሁለቱም ቋንቋዎች አንድ አንድ አንቀጽ በመጻፍ በላቲን ፊደል መጠቀም እጅግ ቀላል መሆኑን ለትግርኛና ዐማርኛ ተናጋሪ ወገኖቼ በተግባር ላስረግጥ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ታዲያ በላቲን ፊደል የማይጽፍ ትግሬና ዐማራ ቢገኝ ውርድ ከራስ – ሁልሽም ይህን አጻጻፍ ልመጂና አንድ ዐረፍተ ነገር ለመጻፍ ዕንቅብ ሙሉ ወረቀት ፍጂ፡፡ ይህን ትዕዛዝ አለመፈጸም ከሦስት ዓመት እስ 15 ዓመት ጽኑ እሥራት ያስቀጣል – ልክ የቀድሞውን ሰንደቅ ዓላማ ሲያውለበልብ እንደሚያዝ “ፌዴራላዊ” ዜጋ! ወይ እኚህ ነጫጭባዎች! የዐድዋንና የአምባላጄን ሽንፈታቸውን ሳይዘነጉ ዘመን ጠብቀው ወኔያችን ላልቶ ክንዳችን መዛሉን፣ ዝናችን መጠየሙንና ታሪካችን መደብዘዙን አይተው በገዛ ሽንቶቻችን ተበቀሉን አይደል? ግዴለም፡፡ እነሱንም እንዲህ የሚያዝረጠርጥ መከራና ስቃይ ይመጣባቸዋል፡፡ እነሲአይኤና ሞሳድ የስም አጠራራቸው እንኳን በታሪክ የማይወሳበት ወርቃማ ዘመን እየመጣ ነው – ሊነጋጋ ሲል መጨላለሙ እውነት በመሆኑ ይህ ዘመን የድቅድቅ ጨለማ ዘመን መሆኑ የግድ ነው፡፡ ለአብነት ወደምጽፍላችሁ ወያኔያዊ የፊደል ሠራዊት ልውሰዳችሁና ዛሬስ በጊዜ እንፋታ፡፡ እንዲያው የላየ ላይ በል በል እያለኝ እንጂ የሚጻፍበት አጀንዳ ተሟጦ አዲስ ነገር እያጣሁ ተቸግሬያለሁ፤ የምጽፈው የማይገባው ኦነግንና ሕወሓትን ይጠይቅ፡፡

Yaamariignaw aanniqaatsii yiihhinnin yiimmaassillal
Huulaachihoom aammaarouch beyyaalaachihuubett enniddamiiin saanabbettachchihuu. Inniee fattarrii yeemaasgheen dahhinnaa naagn. Baallaafaouw ssemmoon aaandi mattattiiiff be’intterrneeit likkee sle’eettioopiaa ayyyer maanghed enndaasneebebbkuachihhuu aatzannagguum. … ኤጭ የምን መጃጃል ነው – በቃኝ እባክህ፡፡ አጃጅሎ ከሚያጃጅል የብልጥ ሰው ዐረመኔያዊ የተንኮል ሤራ ይጠብቃችሁ፡፡

naayttigirrignaa aanniqaatsii kaammzzisseeb yiimasssiil
ziittefaattewukeen ziittefeeqqerkeen aaddii seebb Tiigraayy keemeelaahuummeyii, anne biiffiirqqi’aan naattkhan zikhonkooo wooddii eettioppia Yiihheyyiss aaaemroo ziibbhaal see’eb khaab zelookhuowo aaddii koyyinney zeeseddidelkka ddebbddabbe khemzziibetsihakha ye’aamminn. Bezhhaaleffe soomunzii bizza’eba eeettioopia nefariit maanghaddi ghhelle tsiihhuuf saaddide nee’yyirre khhemzenbbebbkha yeeammin… ዋይ የአኽለኒባ፣ ከመይ ዓይነት አሌታዊ ሸግር እዩ ዝገጠመና!

አዎ፣ ውድ ኢትዮጵያውያን ማሽላ ሲያር ይስቃል፡፡ ውኃም ሲወስድ እንደዚሁ እያሳሳቀ ነው፡፡ ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት እነዚህ ፈረንጆች የገዛ ሰዎቻችንን ተጠቅመው ታሪካዊ ቂማቸውን እየተወጡ ነው፡፡ በሰው ቁስል እንጨት መስደድ ቀላል ነው፡፡ ወያኔዎች ማድረግ ስለቻሉ ብቻ ብዙ ኢትዮጵያውንን ከኢትዮጵያዊነት የጋራ ኑባሬና ማዕድ እያስወጡ ነው፡፡ ሸሩን ያላወቁና አዲስ ነገር ብርቅ የመሰላቸው የዋሃን ደግሞ የተጠመደባቸውን ፈንጂ ሳይረዱ ወጥተው አናቱ ላይ ቁብ ብለው የመፈንጃውን ጊዜ በጉጉት እየተጠባበቁ ያሉ ይመስላል፡፡ ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ነበር ጠልፈው የጣሏት፡፡ “እንዴ፣ አንቺስ ምን ይጎድልሻል? በሬ እኮ ነሽ! በይ ነይ በዚህ ገመድ ውስጥ አንገትሽን አስገቢና ወጉ ይድረስሽ፡፡” የወደደ በገመዱ ይግባበት፡፡ ሲነጋ ግን ሁሏም የሀፍረት ሸማዋን ተከናንባ መግቢያ ቀዳዳ ታጣለች፡፡ ክፋትን መሥራት የመጨረሻው ቀላል ነገር ነው፤ እነዚህ ምሥጦች አንቺን በላቲን ሲያጽፉ፣ አንተን በነገር ጎነታትለው ስሜትህን በማጎፍነን አማራን ሲያስገድሉ፣ እናንተን ደግሞ በታሣሪ ዐማሮች ላይ እንድትተፉና እንድታሰቃዩዋቸው ሲያስገድዱ፣ እነዚያን እዚያ ታች ያሉ ወንድሞቼን የዐማራ ሴቶችን እንዲደፍሩና እንዲያስወልዷቸው መሬታቸውንም እንዲነጥቋቸው ሲያደርጉ ሁልሽም ፀጥ-ረጭ ብለሽ ታዘሻቸዋል – ከዕዳሪ ለማያልፍ እህል ውኃ ተገዝተሸ ለዚያውም፡፡ ዋጋሽን ታገኛለሽ፤ በሠፈርሽው ቁናም ተንደርብቦ ይሠፈርልሻል፡፡ የእግዜር ፍርድ ሲዘገይ የቀረ የሚመስላቸው ገልቱዎች እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ሞት ሲዘገይ በዚያው የሚቀር የሚመስላቸውም እንዲሁ፡፡

በመሠረቱ አንተ የምትጸየፈውን ምግብ ለሰው አተስጥም፤ አንተ የምትጠላውን ልብስም ሆነ ማናቸውም ነገር ለሰው ብትመጸውት ነውር ነው፡፡ አንተ የማትጠጣውን መጠጥ ለሰው ብትጋብዝ ወንጀልም ነውርም ኃጢኣትም ነው፡፡ ወያኔዎች የላቲንን ፊደል ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ዜጎች በግዳጅ የጣሉባቸው ኢትዮጵያን ያፈራረሱ መስሏቸው ነው – በርግጥም ለተወሰነ ጊዜ ይህን የዘመናት ተጋምዶና ተመሳሳይ ሥነ ልቦና ሊያደበዝዙት ይችሉ ይሆናል፤ እየቻሉም ነው፡፡ ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ ልናየው እንደምንችለው እነዚህ የእፉኝት ልጆች ተገቢውን ብድራታቸውን ያገኛሉ፡፡ ቁናውን ባሰፉት ቁጥር ይበልጥ የሚጎዱት እነሱ እንጂ ተቀባዩ ብቻ አይደለም፡፡ ለነሱ መልካም የብቀላ ዘመን ይሁንላቸው፡፡ እኛ ግን ወያኔያዊ ብል የቀዳደደውን የታሪካችንን ቡልኮ በአፋጣኝ ለመጠገንና ወደቀድሟችን ለመመለስ እንዘጋጅ፤ ኢትዮጵያ ለየት ትላለች፤ ነገ ሌላ ቀን መሆኑን የምናይ እናያለን፡፡ ይህ ደግሞ እንደኒኩሌር ሣይንስ የመንኮራኩር ማምጠቂያ ፊዚክሳዊ ቀመር የሚከብድ ሣይሆን አምናና ታች-አምናን በማየት ብቻ በቀላሉ የምትደርስበት ታሪካዊና ለሚያምኑ ደግሞ መለኮታዊ ብይን ነው፡፡…


በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምሬት እና ሮሮ በረከተ…ዋ.ዋ.ዋ! በሰንበቴ ቶማ የሁለት ግራ እግር አመራር አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ ጉዞ!!

$
0
0

welayta Sodo Univesity

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመልካም አስተዳደር እና ኪራይ ሰብሳቢነት ችግር ከተንሰራፋባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል የመጀመሪያውን ሥፍራ ተቆጣጥሯል፡፡ በተቋሙ ሥራዎች የሚከናወኑት እና ውሳኔዎች የሚሰጡት ህግንና አሰራርን መሰረት በማድረግ ሳይሆን በግለሰቦችና በቡድኖች ፍላጎትና በጎ ፈቃድ በመሆኑ የሰራተኞች ቅሬታና አቤቱታ በርክቷል፡፡ በተለይ ሰንበቴ የሚባል ፕሬዚዳንት ከመጣ በኋላ የመንግስት ሥራ ህግንና አሰራርን ተከትሎ የመስራት አዝማሚያ በመጥፋቱ ጥቂት በጥላቻ የተሞሉ ገለሰቦች ይህን ክፍተት በመጠቀም በኪራይ ሰብሳቢነት ከመሰማራታቸውም በላይ ተቋሙ ውስጥ ኔትወርክ እና ጎጠኝነት እንዲስፋፋ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ሰንበቴ እና መሰሎቹ የሰራተኛውን ቅሬታና አቤቱታ ተቀብለው ብልሹ አሰራራቸውን ከማስተካከል ይልቅ ሰራተኛውን በማስፈራራት እና በማሸማቀቅ ተግባር መሰማራትን መርጠዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ተቋሙ አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ ጉዞ ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ የሰራተኛው የሥራ ሞራል እና ፍላጎት በመውደቁ ምክንያት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሥራ የሚለቀው ሰራተኛ ቁጥር ጨምሯል፡፡

በሰንበቴ በመሰለኝ እና በደሳለኝ አመራር ተቋሙ ከማይወጣበት አዘቅጥ ውስጥ ገብቷል፡፡ ሰውየው በራሱ የአመራር ክህሎት፣ እውቀትና ልምድ ማነስ የተከሰቱ ችግሮቸን ወደ ቀድሞ አመራር በማላከክ የራሱን ውድቀት ለመሸፋፈን እሞከረ ይገኛል፡፡ ከሱ ከማይሻሉ ተከታዮች ጋር በመሆን በተቋሙ ውስጥ የጥላቻና የጠባብ ብሄርተኝነት ዘር በመዝራት ላይ ይገኛል፡፡ በራስ የመተማመን አቅም የሌለው ከመሆኑም በላይ በየበታችነት ስሜት ውዝግብ ውስጥ መግባቱን በዙሪያው የሰበሰባቸው ግለሰቦች ጭምር ወደ አደባባይ ለማውጣት ተገደዋል፡፡

በሌላ በኩል በተቋሙ ውስጥ በርካታ አቅም ያላቸው ዶክተሮች ቢኖሩም ትኩረት ሰቶ አቅማቸውን ለተቋሙ ቀጣይ እድገት ከመጠቀም ይልቅ እንደራሱ ሁለት ግራ እግር የሆኑትንና አቅመቢሶቹን በመሰብሰብ ተቋሙ ላይ መቀመጥን መርጧል፡፡ የሰውየውን ሥራ የተመለከቱ ብዙዎች ህንድ ከመማር ከልምድ መማር ይሻላል ብለው ወደ ህንድ ለትምህርት ከመሄድ ተቆጥበዋል፡፡

ሰንበቴ ከሰራቸው ስህተቶች አንዱ የኪራይ ሰብሳቢነትን ማስፋፋቱ ሲሆን ሌላው በቀድሞ አመራር በአቅም ማነስ፣ በድሲፕሊን ችግር እና በኪራይ ሰብሳቢነት ከኃላፊነት የተነሱ ገለሰቦችን ወደ ኃላፊነት ማምጣቱ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት እየታገለ ቢሆንም ከፌደራል መንግስት ተቋማት ተጨማሪ ድጋፍና ከትትል ይሻል፡፡

በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ የሚያሳስበው ቀጣዩ ፕሬዚዳንት እንዴትና ኬት ይመደባል የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ይህን በተመለከተ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ እናሳስባለን፡፡ በተለይ ባለፈው ከጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በነበረው የውይይት መድረክ ላይ የተነሱ ጉዳዮች መዘንጋት የለባቸውም፡፡

ሰላም ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ!

በጋራ ትግል ብልሹ አሰራሮችንና ኪራይ ሰብሳቢነትን እናስወግዳለን!!

ፌደሬሽኑ ለብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በወር 80 ሺህ ብር ለመክፈል ተስማማ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የብሔራዊ ቡድኑን አሰልጣኝ ባለፈው ሳምንት ያባረረውና በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌን የቀጠረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ለሚዲያዎች “በፌዴሬሽኑና በአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ መካከል የሥራ ውል ስምምነት ተፈረመ” ሲል በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለአሰልጣኙ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ሳይጨምር በወር 80 ሺህ ብር ለመክፈል ተስማምቷል::

ጋዜጣዊ መግለጫው እንደወረደ እነሆ
Geberemedhin

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን ከሥራ ማሰናበቱን ተከትሎ ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2008 ዓ.ም በፌዴሬሽኑና በአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ መካከል የሥራ ውል ስምምነት ተፈርሟል፡፡
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በገብረመድን ኃይሌ መካከል የተፈረመው የሥራ ውል ከግንቦት 1 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2009 ዓ.ም ለአምስት ወራት የሚቆይ ነው፡፡

በተጠቀሱት ወራት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ በየወሩ ያልተጣራ ብር 80,000.00/ሰማኒያ ሺህ ብር/ ይከፍላል፡፡ የቴሌፎን ፣ የኃላፊነትና የነዳጅ ጥቅማ ጥቅሞችንም ይጠብቃል፡፡

አሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ሁለት ቀሪ የማጣሪያ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

በአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌና በፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች መካከል ውይይት በተደረገበት ወቅት አሰልጣኝ ገብረመድን እንደገለፀው ለብሔራዊ ቡድን በመጫወት ያገኘው ትልቅ ክብር ለእዚህ ከባድ ሃገራዊ ኃላፊነት ስምምነቱንና ፈቃደኝነቱን በመግለፅ ብሔራዊ ግዴታውን ለመወጣት ያስገደደው ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከሲሼልስ የማጣሪያ ጨዋታ ጀምሮ ያስመዘገበውን ዝቅተኛ ውጤት ተከትሎ ፌዴሬሽኑ ፈጣን ርምጃ አለመውሰዱ ክፍተት እንደፈጠረ በመቁጠር የተቀበለው ሲሆን በቀጣይነት ውስጣዊ የአሠራር ሥርዓት ማስተካከያ ለማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

በሂሳባዊ ስሌት የቡድናችን ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ተስፋው ሙሉ በሙሉ ያልተሟጠጠ በመሆኑም ፌዴሬሽኑ በእግር ኳስ ቤተሰቦች ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ የሚሰጠውን ገብረመድን ኃይሌን በጊዜያዊ አሠልጣኝነት እንዲሾም አድርጓል፡፡ አሠልጣኝ ገብረመድን የተረከበውን ከባድ ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣና ቡድናችን የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ የእግር ኳስ ቤተሰቦች የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉም ፌዴሬሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አንቶኒ ማርሻል ለዛሬ (ማክሰኞ) የማን.ዩናይትድ እና ዌስትሃም ፍልሚያ የመሰለፍ ዕድሉ ምን ያህል ነው?

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ማን.ዩናይትድ ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ የሚወስደውን መንገድ የሚወስነው ዛሬ ማክሰኞ ከዌስትሃም ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ ጋር ነው:: ከትናንት በስቲያ እሁድ አርሰናል ከማን.ሲቲ ጋር ነጥብ መጋራቱ ሲቲ በቻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ያለውን እድል ማን.ዩናይትድ እንዲሸነፍ ከመጸለይ ጋር አያይዞበታል::
Manchester United v Sunderland - Premier League

በዘንድሮው ሲዝን ለማን.ዩናይትድ ወሳኝ ተጫዋች የነበረው አንቶኒ ማርሻል ነበር:: ይህ ወጣት ተጫዋች በእንግሊዙ ክለብ የመጀመሪያ ዓመት ተሳትፎው በስሙ 15 ጎሎችን አስመዝግቧል:: ይህ ተጫዋች ባለፈው ቅዳሜ ከኖርዊች ሲቲ ጋር በተደረገው የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ለጨዋታው ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት በልምምድ ላይ ጉዳት ደርሶበት ሳይጫወት ቀርቷል:: ይህም ለማን.ዩናይትድ አጥቂ ክፍል ራስ ምታት ሆኗል::

የ እንግሊዙ ዝነኛ ታብሎይድ ዘሰን እንደዘገበው የውድድር ዓመቱ ምርጥ አጥቂ አንቶኒ ማርሻል ክለቡ ከዌስትሃም ጋር በሚያደርገው የሻምፒዮንስ ሊጉን ተሳትፎ በሚወስንበት ወሳኝ ጨዋታ ላይ አይደርስም:: በዚህም የተነሳ በአማካኝ ክፍል ሲጫወት የነበረው ሩኒ ወደ ፊት መጥቶ የማን.ዩናይትድን የፊት መስመር ይመራል ተብሎ ይጠበቃል::

አንቶኒ ማርሻልን በቀጣዩ እሁድ ከቦርንማውዝ ለሚደረገው የመጨረሻ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታና ከዛ በመቀጠል ከክሪስታል ፓላስ ጋር ለሚደረገው የኤፍ ኤ ካፕ ፍጻሜ ፍልሚያ ለማድረስ የማንችስተር ዩናይትድ ሀኪሞች እየተረባረቡ እንደሚገኙ ዘሰን ዘግቧል:: ከዚህ በኋላ ሌሎች ተጫዋቾቻቸውን በጉዳት ማጣት የማይፈልጉት ቫንግሃል በተጫዋቾቼ ላይ በልምምድ ወቅት ጫና አላበዛባቸውም ብለዋል::

በካናዳ ስለተከሰተው የሰደድ እሳት እዚያው ከሚኖረው ጋዜጠኛ ሰይፉ መኮንን ጋር የተደረገ ቃለምልልስ |ያድምጡት

$
0
0

በካናዳ አልበርታ ግዛት የተከሰተውን የሰደድ እሳት አደጋና በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶ የከተማው ነዋሪ ከሆነው ጋዜጠኛ ሰይፉ መኮንን ጋር ያደረግነው ቆይታ (ሙሉውን አድምጡት):: ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ አነጋግሮታል::

ባሌ በጎርፍ ተመታች |በጎርፍ አደጋው 9 ሰዎች አለቁ

$
0
0

ፎቶ ምንጭ: መንግስታዊ ሚዲያዎች

ፎቶ ምንጭ: መንግስታዊ ሚዲያዎች


(ዘ-ሐበሻ) ድሬደዋ ከደረሰውና ንብረትና የሰው ሕይወት ካወደመው ጎርፍ ሳናገግም በባሌ ዞን በጣለ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የ9 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተዘገበ::

መንግስት የሚቆጣጠራቸው ሚድያዎች እንደዘገቡት በባሌ ዞን በደረሰው አደጋ በንብረት ላይ ያደረሰው ውድመትም ከፍተኛ ነው::

የባሌ ዞን የአደጋ መከላከል እና ዝግጁ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብረሃም ኃይሌ እንዳስታወቁት ሰሞኑን በዚሁ በባሌ ዞን በአምስት ወረዳዎች ውስጥ በተለያዩ ቀናት ለሰዓታት በጣለው ከባድ ዝናብ ሰበብ በተከሰተ ጎርፍ የተነሳ የሰዎች ሕይወት ሊጠፋ ችሏል::
እንደ ሃላፊው ዘገባም እንዲሁም 1 ሺህ 136 የቤት እንስሳት ሲሞቱ 559 ሄክታር መሬት ላይ የነበረን የእህል ቡቃያ ከጥቅም ውጭ አድርጓል::

በኢትዮጵያ መንገዶችን በመስራት ልማትን እያፋጠንኩ ነው የሚለው ኢህ አዴግ መራሹ መንግስት መንገዶችን በጥራት አለመስራቱና በየጊዜውም የፍሳሽ ውሃ ማስወገጃ ቱቦዎችን አለመጥረጉ ለአደጋው መባባስ እንደምክንያትነት የሚቆጥሩ አስተያየት ሰጪዎች አሉ::

ከሞጆ ደረቅ ወደብና ከጂቡቲ ወደብ በወቅቱ ዕቃቸውን የማያነሱ ነጋዴዎች ንግድ ፈቃዳቸው ሊቀማ ነው |የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0


Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News
የግንቦት 01 ቀን 2008 ዓ.ም. (May 09, 2016 NEWS)


#ከሞጆ ደረቅ ወደብና ከጂቡቲ ወደብ በወቅቱ ዕቃቸውን የማያነሱ ነጋዴዎች ንግድ ፈቃዳቸው ሊቀማ ነው
#ሩዋንዳ ውስጥ በከባድ ዝናም ምክንያት 500 ቤቶች ፈርሰው ከ40 በላይ ሰዎች ሞቱ
#በሶማሊያ ዋና ከተማ አልሸባብ በሰነዘረው ጥቃት ሁለት የፖሊስ መኮንኖችና ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ
#በግብጽ ከአይሲስ ጋር ግንኙነት ያለው አንድ ቡድን ስምንት ፖሊሶችን ገደለ
#አንድ የጂሃዲስቶች ቡድን ምክትል ኃላፊ በማሊ የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ዋለ

modjo dry port
በሞጆ ደረቅ ወደብ ላይ የተከማቹት ኮንቴኔሮች ባስቸኳይ ካልተነሱ ውርስ እንደሚሆኑ በመግለጽ የወያኔ መሪዎች መመሪያ ማስተላልፋቸውን ከጥቂት ቀና በፊት ባስተላልፈነው ዜና መግለጣችን ይታወሳል። የወያኔ ባለስልጣኖች በጉዳዩ ላይ በሰጡት ተጨማሪ መመሪያ ከጂቡቲና ከሞጆ ሸቀጦቻቸውን በወቅቱ የማያነሱ ነጋዴዎች ከአስመጭነት ስራቸው ሊታገዱ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። ነጋዴዎቹ በደረቅ ወደብ ያላቸውን ዕቃ ለማውጣት ከአገዛዙ አካላት ጋር በመነጋገር መፍትኄ ለመፈለግ ያቀረቡትን ጥያቄ የወያኔ መሪዎች ውድቅ ያደረጉት ሲሆን የተወረሱትን ሸቀጦች አስመልክቶ የተበላሸው እንደሚጣልና ያልተበላሸው በጨረታ እንደሚሸጥ ገልጸዋል። በንግዱ ስራ ላይ የተሰማሩት ነጋዴዎች የወያኔ ባለስልጣናት የሰጡት መመሪያና ትዕዛዝ ዱብ ዕዳ እንደሆነባቸውና የነጋዴውን ችግር ያላገናዘበ የአገሪቱንም ሁኔታ ያላጤነ ነበር በማለት ገልጸው የተሰጠው መመሪያና ትዕዛዝ ሆን ተብሎ ከአንድ ዘር ውጭ ያሉ ነጋዴዎችንና አስመጭዎችን ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ የታቀደና የታለመ መሆኑን ይናገራሉ።

 በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በሩዋንዳ ከተማ በማከታተል በጣለው ከባድ ዝናም ምክንያት የመሬት መደርመስ ተፈጥሮ 40 ሰዎች የሞቱ መሆናቸው የዜና ምንጮች ዘግበዋል። የጣለው ከባድ ዝናም ከፍተኛ የሆነ የመሬት መደርመስን ያደረሰ ሲሆን 500 መኖሪያ ቤቶችን እንዳልነበሩ አፍርሷል። በሩዋንዳ የዘንድሮ የክረምት ወራት ከወትሮው ለየት ያለ ከበድ ያለ ዝናም መዝነቡ እየተነገረ ሲሆን በኬኒያም ባለፈው ሳምንት የጣለው ከባድ ዝናም ለ42 ሰዎችም መሞትና ለበርካታዎች መቁሰል ምክንያት የሆነውን ባለስድስት ፎቅ ሕንጻ የደረመሰ መሆኑ ይታወቃል።

 ዛሬ ሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2008 ዓ.ም. በሶማሊያ አልሸባብ የተባለው ቡድን አባላት የሆኑ ሁለት ግለሰቦች በፈንጅ የጠመደ መኪና እያሸረከሩ በሞቃዲሾ ዋና ከተማ በሚገኘው የትራፊክ ፖሊስ ጽ/ቤት ላይ ባካሄዱት ጥቃት ቢያንስ ሁለት የፖሊስ መኮንኖች ሌሎች ሌሎች ሁለት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውና ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል። በመኪናው ላይ የነበረ የቡድኑ አባል የመስርያ ቤቱን ቅጥር ግቢ በሚጠብቁት ላይ ተኩስ ከፍቶ ጥቃት ሲሰነዝር በጥይት ተመቶ የሞተ ሲሆን የመኪናው አሽከርካሪ በፈንጅው ራሱን አጥፍቷል። በሱማሊያ ተዳክሟል እየተባለ ሲነገርለት የቆየው አልሸባብ ጥቃቱ እያጠናከረ መምጣቱ ባለስልጣኖችን እያሳሳሰበ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

 እሁድ ሚያዚያ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. በግብጽ ዋና ከተማ በካይሮ ሄልዋን በሚባለው አካባቢ በካሚዮን ላይ የተጨኑ አራት ታጣቂዎች በአንድ የፖሊስ ቫን መኪና ላይ ባካሄዱት የሩምታ ተኩስ በመኪናዋ ውስጥ የነበሩ ስምንት ፖሊሶች መገደላቸው ታውቋል። በሲና ባህረሰላጤ የሚንቀሳቀሰው እና ከአይሲስ ጋር ግንኘነት እንዳለው የሚነገርለት አሸባሪ ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል። “የሲና ክፍለሀገር” በሚል ራሱን የሚጠራው ይኸው ቡድን የቀደሞ ፕሬዚዳንት ሞርሲ ከስልጣናቸው ከተነሱ ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ በሲና ባህረ ሰላጤ በመቶ የሚቆጠሩ የግብጽ የጸጥታ ኃይል አባላትን የገደለ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ በካይሮ በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት እየሰነዘረ ይገኛል።

 ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በብሩንዲ ዋና ከተማ በተለያዩ ቦታዎች በተጣሉ የእጅ ቦምቦች ሶስት ሰዎች ተገድለው ከ20 በላይ ሰዎች የቆሰሉ መሆናችው ታውቋል። አርብ ሚያዚያ 28 ቀን 2008 ዓም በተወረወረ የእጅ ቦምብ 8 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን ቅዳሜ ሚያዚያ 29 ቀን በአንድ አነስተኛ ገበያ ላይ የተወረወረ ቦምብ ሁለት ሴቶች መግደሉ ተዘግቧል፡፤ እሁድ ሚያዚያ 30 ቀን ብዊዝ በሚባለው አካባቢ በአንድ የመጠጥ ቤት ውስጥ ቦምብ ተወርውሮ አንድ ሰው መሞቱና 5 ሰዎች መቁሰለቻው የዜና ምንጮች ተናግረዋል። የብሩንዲው ዋና ከተማ የቡጁምቡራ ከንቲባ ሰኞ ግንቦት 1 ቀን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አሸባሪዎች የሚሏቸው የሽብር ተግባር እያስፋፉ የመጡ መሆናቸውን ጠቅሰው ሽብረተኞችን ጨርሶ ለማጥፋት አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል። ካለፈው ዓመት ጀምሮ በብሩንዲ በተከሰተው የፖሊቲካ ውጥረት በርካታ ሰዎች መገደላቸውና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ መሰደዳቸው ይታወቃል።

የማሊ የጸጥታ ልዩ ኃይሎች አንድ የጂሃዲስት መሪ ነው ተብለው የሚጠረጠር ግለሰብ በቁጥጥራችው ስር ያደረጉ መሆናቸው እሁድ ሚያዚያ 30 ቀን 2008 ባለስልጣኖች ለዜና ምንጮች ከሰጡት መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ያኩባ ቱሬ እየተባለ የሚጠራውና አንሳር ዲን የተባለ ድርጅት ሁለተኛ ሰው እንደሆነ የሚነገርለት ግለስብ የተያዘው ሐሙስ ሚያዚያ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. መሆኑን ባለስልጣኖቹ ጨምረው የገለጹ ሲሆን ከአንድ ወር በፊት የቡድኑ ዋና መሪ በደቡብ ማሊ ግዛት ውስጥ ተያዞ በቁጥጥር ስር መደረጉ ይታወቃል። ቡድኑ በደቡብ ማሊ እና በቡርኪና ፋሶ ለሚንቀሳቀሱ ሌሎች የጂሃዲስት ቡድኖች መሳሪያ በማቀበል ስራ ላይ እንደተሰማራ ይጠረጠራል።

Health: ሙሉ ጨረቃና እብደት፣ ራስን ማጥፋትና የእንቅልፍ እጦት ምን አገናኛቸው?

$
0
0

የእኛ ምላሽ!
በጠፍ ጨረቃ ደጃፌ ላይ ቁጭ ብያለሁ፡፡ ቤት መግባት ያሰኘኝ አይመስለኝም፡፡ ብቻ የጨረቃዋ ድምቀት ፍጥጥ አድርጎኝ ቁጭ ብያለሁ፡፡ እንቅልፍ ያስፈለገኝ አይመስለኝም፡፡ ነገሩ ደግሞ ጥሎብኝ ነው መሰል፣ ከዋክብትንና ጨረቃን ለስለስ ባለ ነፋሻ አየር መታደም እጅግ ሐሴትን ይሰጠኛል፡፡ ዛሬ ግን በጠራው ድቅድቅ ጨለማ ወለል ብላ የምትታየኝ የኛዋ ብቸኛዋ ጨረቃ ናት፡፡ በእርግጥ ከቅርብ ርቀት እነ ኔቡላን የመሰሉ የሰማዩ ግርማዎች ሲንቦገቦጉ ይታዩኛል፡፡ በዚህ ትዕይንት መሀል ግን ትኩረቴን ስቦት እያነበብኩት ያለ ነገር አለ፡፡ ጆርናል ኦፍ ሳይካትሪ ሰርቪስስ፣ በመድረ አሜሪካ የሳይንሳዊ ጥናት ጆርናል፡፡ ከዚህ ጆርናል ላይ አንድ ትኩረቴን የሳበ ጥናት ይገኛል፡፡ በጨረቃና በሰው ልጅ መካከል ያለ ጥብቅ ቁርኝት፡፡ ወደድንም ጠላንም ጨረቃ በእኛ ላይ የማይካድ ተፅዕኖ አላት ብለን እንድናስብ የሚያደርጉ ነገሮችን አስፍሯል፡፡
ask your doctor zehabesha

እርግጠኛ ነኝ፣ ብዙዎቻችን በተለይም የሆሊውድ ፊልም ያየን ሰዎች በአስፈሪና አስደንጋጭ ዘውግ ፊልሞቻቸው፣ ጨረቃና የሰው ልጅ ምትሃታዊ ለውጦችን በብዛት አይነት ይሆናል፡፡ ነገሩ ከፊልምነት የዘለለ ነገር የለውም ብለንን እናልፍ ሆናል፡፡ ሆኖም ግን ትንሽ ቢሆን አሊያም እንደ ፊልሙ የተጋነነ ባይሆንም ጨረቃና እኛን የሚያቆራኙን፣ ብዙ ጉዳዮች መኖራቸው እውነትነት አለው የሚሉ ወገኖች መኖቸው እሙን ነው፡፡

ጨረቃና አደጋዎቿ

ብታምኑም ባታምኑም ሙሉ ጨረቃ በምትውልበት ወቅት፣ ሰዎች እንቅልፍ በአግባቡ ለመተኛት ያቅታቸዋል ይለናል ጆርናል ኦፍ አፌክቲቭ ዲስ ኦርደርስ በ1999 ላይ ደረስኩበት ባለው ጥናት፡፡ አስገራሚው ቁም ነገር ደግሞ ለዚህ ምክንያት ነው ብሎ ያስቀመጠው ትንታኔ፣ የፊዚክስ እውነታዎች ላይ ተመርኩዞ መሆኑ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ምድር ላይ ያሉ የውሃማ አካላትን ወጀብ (ማዕበል) የሚፈጥሩት ፀሐይና ጨረቃ ናቸው፡፡ ይህ የወጀብ እንቅስቃሴም ወደ ጨረቃ አቅጣጫ ያለ ውሃማ አካልን በስበት ኃይል ወደ ጨረቃ ስለሚጎትት፣ ወጀቡ ይፈጠራል ወደ ፀሐይ አቅጣጫ ያለውም ውሃማ አካል እንዲሁ ወደ ፀሐይ ይሳባል፤ ይህም (ታይዳል ዌቭ) በአማርኛችን ስንመልሰው ወጀብ ይፈጠራል፡፡ ሆኖም የሰው ልጅ አካል 75 በመቶው ውሃ በመሆኑ፣ ሙሉ ጨረቃ በሚሆንበት ወቅት ይኸው የስበት ኃይል ተፅዕኖ ሳይፈጠርብን እንደማይቀር ይገመታሉ፡፡

በምድረ አሜሪካ 11940 የደረሱ አደጋዎች ላይ ያተኮረ ጥናት፣ በኮሎራዶ ቬቴሪናሪ ሜዲካል ሴንተር ተመራማሪዎች ሲያካሂዱ፣ ደረስንበት ያሉት መረጃ እንደሚያሳየው ዘወትር ከሚደርሰው ውድመቶች ላይ 23 በመቶ የመጎዳዳት አደጋ በዚህ የሙሉ ጨረቃ ወቅት ደርሷል፡፡

የአሜሪካ አብስቴትሪክስና ጋይናኮሎጂ ጆርናል ጥናት ደግሞ፣ በሴቶች የወር አበባ ላይ አተኩሮ በሙሉ ጨረቃ ወቅት ያለውን ሁኔታ ከተለመዶው ምሽት ጋር አነፃፅሮ አጥንቷል፡፡ በእርግጥ የሴቶች የወር አበባ አመጣጥ በራሱ የሚለያይና ቋሚ ሂደት የሌለው የተፈጥሮ ክስተት ነው፡፡ ክስተቱም በየ28 ቀናት ውስጥ የሚከሰትና ከእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ በአንዱ ሊመጣ የሚችል ቢሆንም፣ በሙሉ ጨረቃ ዕለት ግን በ29 እና 30 ቀናት ውስጥ መከሰቱ፣ ይህም የተከሰተባቸው 60 በመቶ የሚሆኑት ጥናት የተካሄደባቸው ሴቶች መሆናቸው ነው፡፡

ሙሉ ጨረቃ ስትሆን ራስ ህመም ይበረታል፣ እንቅልፍ ቶሎ አይመጣም አንዳንዶችንም ታሳብዳለች?

ሙሉ ጨረቃ በምትታይበት ወቅት፣ አንዳንድ ግለሰቦች ሊያብዱ ይችላሉ የሚለውን የቆየ እምነት ለመፈተን፣ ቆርጠው ከተነሱ ተመራማሪዎች መካከል የፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲው፣ ጀምስ ሮትንና የሳስካችዌን ዩኒቨርሲቲው ኢቫን ኬሊ ናቸው፡፡ በ37 ተመሳሳይ ጥናቶች ላይ ተመርኩዘው ለረጅም ጊዜ ጉዳዩን መረመሩት፡፡ የአእምሮ ህመምተኞች ሆስፒታሎችንም ሁኔታ አጠኑ፡፡ ነገር ግን ሰዎች እንደሚያስቡት፣ ጨረቃ ያን ያህል ለእብደግ አታደርስም አልያም ተጋንኖ የሚታየን በጨረቃ ወቅት ነው እንጂ፣ በሌላ ጊዜያትም ሰዎች በተመሳሳይ ቁጥር እንደሚያብዱ ጥናታቸው ይጠቁማል፡፡ ራስ ህመምንም ቢሆን የተለየ ራስ ህመም ምልክቶችን በዚህ ወቅት እንዳላዩ ጥናታቸው ይናገራል፡፡ ሰዎች ቀደም ሲሉ ሙሉ ጨረቃ ስትውል ችግሩ እንደሚባባስ ስለሚያስቡ፣ በሙሉ ጨረቃ ዕለት ችግሩ እንደተከሰተባቸው አድርገው ስለሚያስቡ እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ያምናሉ፡፡

እንቅልፍ እጦትን በተመለከተ ግን ሙሉ ጨረቃ በምትውልበት ወቅት ሰዎች ቶሎ እንደማይተኙ ጥናታቸው ያትታል፡፡ እንደነ ጀምስ ሮተን እምነት ይህ ሊሆን የሚችለው፣ የጨረቃዋ ረጅም ሰዓት ደምቃ መታየት ሰዎች ቶሎ እንዳይተኙ የሚመች ሁኔታዎችን ስለምትፈጥር ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ፡፡ እናም ሰዎች በነፋሻ አየርና በደማቅ የጨረቃ ብርሃን ታግዘው፣ እንቅልፋቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደሚያርቁት ይታሰባልም፡፡

ሁለት ጥናቶች እርስ በእርሳቸው እንዳይስማሙ ያደረገ ክስተት ደግሞ በእንስሳቶች ላይ የሚታየው ሁኔታ ነው፡፡ በእንግሊዝ የተደረገ አንድ ጥናት በ2001 ላይ በብሪቲሽ ሜዲካል ጆርናል ላይ ለህትመት ሲበቃ፣ ውሾች በሙሉ በጨረቃ ወቅት ሰዎች ላይ ከባድ አደጋ ያደርሳሉ፡፡ ውሾች ቀዳሚዎች ሆነው በጥናቱ ላይ ተመዝግበዋልም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በአውስትራሊያ የተደረገ ጥናት በዚሁ ጆርናል ላይ ታት እንደሚነበበው፣ ውሾች በማንኛውም ምሽ ሰዎች ላይ ጉዳት የማድረስ እድላቸው ሰፊ እንደሆነ በመረጃ የተደገፈ ነገር አሳይቷል፡፡ ይህ ጥናት እንደሚያምነው፣ ውሾች ምሽት ከሆነ በማንኛውም ወቅት አደጋ የማድረስ እድላቸው ከቀን ይበልጣል፡፡ በመሆኑም የውሾች አደጋ ከጨረቃ ጋር ምንም እንደማያያይዘው ጥናቱ ይደመድማል፡፡

በተደጋጋሚ ከሚነሱ ቆየት ያሉና ጥናታዊ ግምቶች መካከል፣ ጨረቃና እብደትን የሚያይዙ አመለካከቶች ናቸው፡፡ ከ2004 ጀምሮ በምድረ ካናዳ ጥናት ያካሄዱ ሳይንቲስቶች፣ በጆርናል ኦፍ ኢፔሌፕሲና ቢሄቪየር ላይ እንዳሰፈሩት ሰዎች እንደሚያምኑት፣ ሙሉ ጨረቃ በምትውልበት ወቅት ምንም አይነት የተለየ የአዕምሮ ችግር እንደሌለ እና ጥናታቸውም የሚፈራውን ነገር ማግኘት እንዳልቻለ ያትታል፡፡

አሜሪካዊው የሳይንስ ጋዜጠኛና የባድ ሳይንስ አምደኛ፣ ‹‹ፖሊሶችም ሆኑ ነዋሪው በሙሉ ጨረቃ ወቅት ከባድ አደጋ ይደርሳል አልያም ያጋጥመናል ብለው ካመኑ ብዙ ችግሮችና አደጋዎች ከወትሮው በተለየ ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ ይህ ማለት ሙሉ ጨረቃ ስለዋለች ሳይሆን፣ ሰዎች አመለካከታችን ውሏችንን ስለሚፈጥረው ነው፡፡ የምናስበው ነገር የምንፈልገውን ክስተት ተፅዕኖ ውስጥ ያሳድረዋል…›› ይላል፡፡

እውነቱ ወዴት ይሆን?

ሳይንስ እርስ በእርሱ መስማማት ያልቻለበት ጉዳይ ይመስላል፡፡ በተለይም እንቅልፍ ላይ ሙሉ ጨረቃ በምትውልበት ምሽት፣ ተፅዕኖ እንዳለው የሚያምኑ ሳይንቲስቶች መኖራቸውና በተቃራኒው ደግሞ፣ ይህን የሚቃወሙና ከጨረቃ ጋር ምንም የሚያያይዘው ጉዳይ እንደሌለ የሚጠቁሙ ሳይንቲስቶች በሌላኛው ወገን ሆነው እሰጥ አገባቸውን የቀጠሉ ይመስላል፡፡

አብዛኞቹ ሳይንሳዊ ጥናቶች፣ የመረጃ አሰባሰባቸው ተቀራራቢ በመሆኑ ደግሞ ጉዳዩን እንቆቅልሽ ያደርገዋል፡፡ ሆኖም ግን አብዛኞቹ ተመማሪዎች ጠንከር ያለው አመለካከቶች ላይ አንድ አቋም ያላቸው ይመስላል፡፡ ለምሳሌ ያህል ከሌላው ጊዜ በተለየ ለአዕምሮ ህመም የሚጋለጡ ሰዎች፣ ሙሉ ጨረቃ ወቅት ያብዳሉ አልያም አቅላቸውን ስተው፣ ጨርቃቸውን ጥለው ጎዳና ይወጣሉ የሚባለው የቆየ አመለካት እውነት እንዳልሆና፣ እስካሁን ድረስ ሳይንስ ይህን ነገር ባያረጋግጥም እውነት የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ወደፊትም ጥናቶች የዚህ አመለካከትን እውነትነት አልያም ውሸትነት ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ነገር ግን ትልቁ ጉዳይና ብዙዎቹን ሳይንቲቶች አላግባብ ያለው አመለካከት ሙሉ ጨረቃና የሰዎች እንቅልፍ ዑደት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይም ሳይንቲስቶች ለሁለት ተከፍለዋል፡፡ እንቆቅልሽ የሆነው ጉዳይ ደግሞ፣ ሁለቱም ጎራዎች የተለያዩ ጥናቶችን አድርገው ደረስንበት ያሉት ውጤት ተቃራኒ የማያስማማ መሆኑ ነው፡፡

ሆኖም የሰሞነኛ ጨረቃችን፣ የበልግ ዝናባችን እንደቀረ ምልክት መሆኑን ደግሞ የተለያዩ የስፔስ ሳይንስ፣ የአየር ንብረት ጥናቶችን ተመርኩዘን መገመት እንችላለን፡፡ በእርግጥም ዘንድሮ የበልግ ዝናብ፣ በብዙዎቹ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም ሙሉ ጨረቃ በታየችባቸው አካባቢዎች አለመኖሩ እሙን ነው፡፡
መቼም ይቺ ሙሉ ጨረቃ የማታመጣብን የለምና፣ ከዝናብ እጥረት አልፎም ጤናችን ላይ ታሳድራለች የተባለው ተፅዕኖም እውነት ይሆን? በእርግጥ ጨረቃ የሰውን ልጅ የማሳበድ አቅም ይኖት ይሆን? ሰዎችንስ እንቅልፍ የምትነሳበት ወቅት አላት ይሆን? ጊዜና ሳይንስ ይፍቱት እላለሁ፡፡


የእግዚአብሔር ቁጣ በኢትዮጵያ –በወላይታ 41 ሰዎች ሞቱ

$
0
0

kuta

ethiopia 2

ethiopia

(ዘ-ሐበሻ) በሚያዝያ እና በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ እየተሰሙ ያሉት ነገሮች የ እግዚአብሔር ቁጣ ናቸው ያስብላሉ ያሉን አንድ አስተያየት ሰጪ ናቸው:: ከሚያዝያ ወር ጀምሮ እየተሰማ ያለው ነገር እጅጉን የሚዘገንና ሃገሪቱ በተፈጥሮ ቁጣ እየተገረፈች ዜጎቿም እያለቁ ነው:: በባሌ ዞን 9 ሰዎች በጎርፍ አደጋ መሞታቸው በዘ-ሐበሻ የተዘገበ ሲሆን ከሃገር ቤት ሚዲያዎች መረዳት እንደተቻለውም በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳይ ወረዳ በአምስት ቀበሌዎች ላይ ግንቦት 1 ቀን 2008 ዓ.ም በደረሰ የመሬት ናዳ 41 ሰዎች ሞተዋል:: በመሬት ናዳው የተነሳ የሞቱ የሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ እንደሚሆን የሚገመት ሲሆን የአስከሬን መፈለጉና የነብስ አድኑ ሥራ እንደቀጠለ ከመረጃዎች መረዳት ይቻላል::

በባሌ ዞን በደረሰ የጎርፍ አደጋ 9 ሰዎች እንዲሁም በወላይታ ዞን 41 ሰዎች ከማለቃቸው 3 ቀናት በፊት በአዲስ አበባ አዳማ ፈጣን መንገድ ላይ ዛሬ በደረሰ አሰቃቂ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በዘ-ሐበሻ ላይ አንብበን ነበር:: ምንም እንኳን ሰው ሰራሽ አደጋ ቢሆንም ከ4 ቀናት በፊትም እንዲሁ በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 2፣ ልዩ ቦታው ጭላሎ ሆቴል ገባ ብሎ እድሜው 55 ዓመት ገደማ ይሆናል የተባለ ጎልማሳ ራሱን አቃጥሎ ገድሏል:: ይህ ሰው ራሱን ለማቃጠልና ለመግደል የወሰነበት ምክንያት አይገለጽ እንጂ ሰላማዊ ሰው እንደነበር ታውቋል::

በተጨማሪም በ ዕለተ ትንሣኤ ዋዜማ በምዕራብ አርሲ ዞን ዱምቡሬ ቃቻ ወረዳ መሬት ተሰንጥቆ ሸለቆ በመፍጠሩ ወደ ወላይታና አርባምንጭ የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ማለፍ እንዳልቻሉና በሰው ሕይወትላይ ከፍተኛ አደጋ ማድረሱ ተዘግቧል:: የተሰነጠቀው መሬት በግምት 50 ሜትር ጥልቀትና 50 ሜትር ርዝመት እንዳለው ታውቋል::

በሌላ በኩል በሻሸመኔ አካባቢ የተከሰተ የመሬት መንሸራተትም እንዲሁ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል:: ከሻሸመኔ አጄ እስከ አላባ ና ወላይታ እስከ አርባምንጭ የሚያስኬደው መንገድ አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት ሳቢያ ለመንቀሳቀስ ህዝብ ተቸግሯል::

ይህ ብቻ አይደለም ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ለብሔራዊ ስታዲየም ፕሮጀከት ግንባታ በቁፋሮ ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎች የተከመረ አፈር ተደርምሶባቸው ሕይወታቸው አልፏል::

ከሁለት ሳምንት በፊት ማለዳ 12 ሰአት ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሰሚት አካባቢ ባለ 5 ፎቅ ህንፃ ተደርምሶ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል:: ቁጣው ይህ ብቻ አይደለም ሸዋሮቢት ከተማ ሚያዚያ 10 ቀን 2008ዓ.ም. ከጠዋቱ 1:30 – 4:30 ሰዓት በጣለው ከባድ ዝናብ በታሪኳ አይታው በማታውቀው ከባድ የጎርፍ አደጋ ተመታለች። ከ400 በላይ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ሲፈናቀሉ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ንብረት አውድሟል፡፡

ድሬደዋ ከተማም በ10 ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተጠቅታ በርካቶች ተጎድተዋል:: በአካባቢው ከዚህ ቀደም ሕይወት በቀጠፈው የጎርፍ አደጋ ከተከሰተ በኋላ የተሰራው ድልድይም ጉዳት ደርሶበታል::

የሚሰማው ነገር ሁሉ የሚያሳዝን በመሆኑ በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለው የ እግዚአብሄር ቁጣን ለመመለስ ሁሉም በየሃይማኖቶ ሊጸልይበት ይገባል::

የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሃገሩን ጥሎ ተሰደደ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በቅርብ ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ተወዳጅነትን እያገኘች የመጣችው የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ሃገሩን ጥሎ መሰደዱ ተሰማ::
የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሃገሩን ጥሎ ተሰደደ
እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ ጋዜጠኛው በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ የሚገኝ ሲሆን እዚያው ጥገኝነት ጠይቋል::

በተለይ በኦሮሚያ በተከሰተው የሕዝብ ቁጣ እና በጎንደር በተለይም በወልቃይት ሕዝብ ማንነት ዙሪያ ቦታው ድረስ በመሄድ ልዩ ልዩ ዘገባዎችን ሲያቀርብ የነበረው ጋዜጠኛው ሃገሩን ጥሎ የተሰደደው ከመንግስት ኃይሎች በሚደርስበት ጫናና ማስፈራሪያ እንደሆነ የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል::

ጋዜጠኛው ከሃገሩ ከመሰደዱ አስቀድሞ ለህብር ራድዮ የሰጠውን ቃለምልልስ ያድምጡት::

ግራ ተጋብተው ግራ አያጋቡ (ከይገርማል)

$
0
0

girma seifu
የተከበሩ አቶ ግርማ ሠይፉ ማሩ “ቅንጅት ፓርላማ አልገባም አላለም” በሚል ርእስ አንድ ጽሁፍ በኢትዮሜዲያ ላይ አስነብበውናል:: የተከበሩ አቶ ግርማ ቅንጅት የሚሉት ጠ/ጉባኤውን ከሆነ እውነት አላቸው:: ይህን ለማለት ያበቃኝ አምባገነኖች ራሳቸውን እንደ ድርጅት: ሌላውን ተከታይና አድናቂ አድርገው የሚያምኑ እንደሆነ ስለሚታወቅ ነው:: እነርሱ ያነሱት ይነሳል የጣሉት ይወድቃል: በቃ እንዲህ ነው:: አቶ ግርማ እንዳሉት ጠ/ጉባኤው ፓርላማ መግባት የለብንም ብሎ አልወሰነም:: የቅንጅት ላእላይ ም/ቤትም ቢሆን ፓርላማ አንገባም ብሎ ወስኗል ማለት አይቻልም::

ምንም እንኳ የመኢአድ ሰወች ፓርላማ መገባት የለበትም በሚል የሞገቱ ቢሆንም አብዛኛው አባል ግን በተቻለ መጠን መኢአዶችን ለማለሳለስ ብዙ መድከማቸው አይዘነጋም:: ራሳቸውን ከጠ/ጉባኤውም ሆነ ከላእላይ ም/ቤቱ በላይ አድርገው የሚመለከቱት የመኢአድ ሰወች የስብሰባውን መንፈስ እንዴት ያውኩት እንደነበር በስፍራው ለነበረ ሁሉ የሚዘነጋ አይደለም:: ፓርላማ እንግባ ወይስ አንግባ የሚል ክርክር ይደረግ በነበረበት ወቅት በህክምና ላይ የነበሩት ኢንጅነር ሀይሉ ሻውል ከአሜሪካ (በስልክ) ቅንጅት ፓርላማ የሚገባ ከሆነ መኢአድ ከቅንጅት እንደሚወጣ ነበር የገለጹት::

ፓርላማ መገባት አለበት ሲሉ ይከራከሩ ከነበሩት የመኢአድ ሰወች መካከል አንዱ ሻለቃ አድማሴ ነበሩ:: ሌሎች የመኢአድ አመራሮች አቶ አባይነህና ሻለቃ ጌታቸውን ጨምሮ የሀይሉ ሻውልን አቋም በማስተጋባት ቅንጅት ፓርላማ እንዳይገባ ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ ነበር:: ከድርጅታቸው የተለየ አቋም ሲያራምዱ የነበሩት ሻለቃ አድማሴ በብዙሀኑ የመኢአድ አመራር ዘንድ እንደ ከሀዲ ስላስቆጠራቸውና ስለተገለሉ ፊት ለፊት መጋፈጡን ሊያቆሙ ተገደዱ::
ኢንጅነር ሀይሉ አቋማቸውን እንዲያለሳልሱ ከቀስተዳመናና ከኢዴሊ ለቀረበላቸው ተደጋጋሚ ጥያቄ መኢአድ እንኳ ፓርላማ ቢገባ እርሳቸው በግል ፓርላማ እንደማይገቡ አስረግጠው በመናገራቸው የተነሳ ሌላ ዘዴ መዘየድ አስፈላጊ ነው ተብሎ ታመነ::

እንደሚታወቀው ሀይሉ ሻወል ማለት መኢአድ መኢአድ ማለት ደግሞ ሀይሉ ሻወል ማለት ነበሩ:: በመኢአድ አሰራር ኢንጅነሩ የፈቀዱት ይሆናል ያልፈቀዱት አይሆንም:: እርሳቸው በግላቸውም ቢሆን ፓርላማ አልገባም ካሉ መኢአድም የርሳቸውን አቋም ተከትሎ እንደማይገባ ግልጽ ነበር:: ይህ አካሄድ ደግሞ ፓርላማ ባለመግባት ውጤት ሊገኝ ይችላል ብሎ ባመነው ህዝብ ዘንድ መገለልን ሊያስከትል ይችላል ብሎ የሰጋው የላእላይ ኮሚቴ መኢአድን በቅንጅት ውስጥ ለማስቀጠል የመደራደሪያ ሀሳቦችን እናቅርብ በሚል 8ቱን ነጥቦች ወደማውጣት አዘነበለ:: ይሁንና መኢአድ ከቅንጅት እንዳይወጣ በሚል የአመራሮችን አቋም ለማለሳለስ ይረዳሉ ተብለው የቀረቡት የመደራደሪያ ነጥቦች ለወያኔ አዲስ የእድል በር ከፈቱለት::

ፓርላማ ከመከፈቱ ከሦስት ቀናት በፊት የአዲስ አበባ ምክር ቤት ተመራጮች በቅንጅት ጽ/ቤት ግራውንድፍሎር ውስጥ ስብሰባ አድርገው ነበር:: በወቅቱ ዋናው የመወያያ ነጥብ ሆኖ የቀረበው የአዲስ አበባን ም/ቤት መረከብን የሚመለከተው አጀንዳ ነበር:: አዲስ አበባን መረከብ ያስፈልጋል የሚለው አመለካከት በአመራሩ የታመነበት ስለነበር ውይይቱ ካለምንም ተቃውሞ በስምምነት ነው የተጠናቀቀው:: ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድ ድምጽ ”አዲሳበባን መረከብ አለብን” የሚል ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ ስልጣኑንና የምክርቤቱን ቁልፍ የሚረከቡ ሰዎችን መርጦ አርከበ እቁባይ ይመራው ወደነበረው የቀድሞው የአዲስ አበባ ም/ቤት ላከ:: ይኸኔ ነበር በአርከበ እቁባይ ይመራ የነበረው ም/ቤት ”ፓርላማ የማትገቡ ከሆነ አዲሳበባን አናስረክባችሁም” ያለው::

በሌላ በኩል የአዲሳበባ ምክር ቤት ተመራጮች አዲስ አበባን ሊረከቡ እንደሆነ የሰሙ ለፓርላማ ተወዳድረው ያሸነፉ የቅንጅት ሰወች ተቃውሟቸውን ለማሰማት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲደረግ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳንና አቶ ልደቱ አያሌውን አነጋግረው ስብሰባው ተደረገ:: በስብሰባው ወቅት የተነሳው ዋናው ጉዳይ
“በአንድ የምርጫ ወቅት አንድን ድርጅት ወክለን ነው ለውድድር የቀረብነው:: የምናሳልፈው ውስኔ አንድ ወጥ መሆን አለበት:: የአዲስአበባ ም/ቤት ተመራጮች ም/ቤቱን የሚረከቡ ከሆነ እኛም ያሸነፍነውን ወንበር ለመረከብ የሚያግደን ነገር አይኖርም”

የሚለው ነበር:: ስብሰባውን የመሩት ሁለቱ ም/ሊቀመናብርት የተሰብሳቢውን መንፈስ ከአመራሩ እምነት ጋር አጣጥመው ማስኬድ ባለመቻላቸው ስብሰባው ካለስምምነት ተጠናቆ ወዲያውኑ ፓራላማ እንገባለን የሚል ፔቲሽን መፈራረም ተጀመረ::

ያ ብልሀት የጎደለው: ሁሉንም አስተያይቶ ማስኬድ ያልቻለው አመራር: የፓርላማ አባላቱን ሳይቀር ለሁለት እንዲከፈሉ መንገዱን በማመቻቸቱ ፔቲሽን የተፈራረሙት ከሀያ በላይ ሰወች ተመዝግበው ሰኞ እለት ፓርላማው ሲከፈት በአካል ፓርላማ እንዲገኙ ምክንያት ሆነ::

የአመራሩን ትእዛዝ ተላልፈው በፓርላማ መክፈቻ ስነስርአቱ ላይ የተገኙትን የቅንጅት ሰዎች ማንነት እንዲለዩ የተላኩት ሰላዮች በሰጡት መረጃ በመመርኮዝ ለማስደንበር የተደረገው ሙከራ ትርጉም አልባ ነበር:: በዚህም ምክንያት በተደፈርን ስሜት አንጀታቸው ያረረው ከስህተት ሊማሩ ያልፈቀዱት አመራሮች ፓርላማ በገቡት የቅንጅት አባላት ላይ ”የመረጣቸው ህዝብ ውክልናውን እንዲያነሳ እናስደርጋለን” በሚል ያስወሩት ወሬና ያደረጉት ፍሬ አልባ እንቅስቃሴ በአባላቱ መሀከል የተፈጠረውን ልዩነት የባሰ አሰፋው እንጅ ያስገኘው ጥቅም አልነበረም::

በሌላ በኩል እንደቅንጅት አመራር ሁሉ ኢህአዴግም ፓርላማ የገቡትን የቅንጅት ሰወች ፓርቲያቸውን የከዱ ናቸው በሚል በየተመረጡበት አካባቢ ባሉት የደህንነት ሰወቹ አማካኝነት እንዲወራባቸው ስላደረገ በሁሉም ዘንድ እንዲጠሉና አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገቡ ጣምራ ስራ ተሰራ::

ኢህአዴግ ፓርላማ በገቡት ሰወች ላይ ይህን ሁሉ ያደረገው ፓርላማ መግባታቸውን በመጥላት አልነበረም:: የእኒህ ሰወች ፓርላማ መግባት ልዩነትን በመፍጠር የቅንጅትን አቅም ለመሸርሸር: የፓርቲውን የተሳሳተ አካሄድ ለማሳየትና የራሱን በጎ ጎን ለመገንባት እንደሚጠቅመው አጥቶት ሳይሆን በሁሉም ዘንድ የተገፉት የቅንጅት ሰወች መግቢያ ሲያጡ እጉም ብለው ወደኔ ይሰባሰባሉ ብሎ በማመን ነበር:: በዚህ መሀል ከሁሉም ያጣ ባተሌ ላለመሆን ሲሉ እንደተባለውም በአባልነት ተመዝግበው ወደኢህአዴግ የተጠቃለሉ ነበሩ::

አንድ መታወቅ ያለበት እውነት አለ: ከአያያዝ ጉድለት የመጨረሻው ወዳጅ የመጨረሻው ጠላት ሊሆን እንደሚችል:: ሰወች የሰሩትንና የደከሙበትን ትግል እውቅና መንፈግና አቅልሎ ማየት የሚያደርስባቸው የመንፈስ ጉዳት ቀላል አይደለም:: በአመራር ላይ የሚቀመጡ ሰወች አፋቸው እንዳመጣ የማይናገሩ: የሰወችን ስሜት የሚጠብቁና ፍላጎታቸውንም የሚረዱም መሆን ይኖርባቸዋል:: የሕዝብ ድጋፍ ተችሮት ነገር ግን ብልሀት የጎደለው ቅንጅት በየአካባቢው ያለተመልካች አኩሪ መስዋእትነት ከፍለው ለድል ያበቁትን አባላቱን አሰባስቦ መቀጠል አልችል ብሎ ቀስ በቀስ መፍረስ ያዘ::

አዲስ አበባን ለመረከብ ፓርላማ መግባት አለባችሁ የተባሉት ቅንጅቶች ውሳኔያቸውን ለመከለስ አለመፈለጋቸው አንዱ ትልቁ ችግራቸው ነበር:: አቶ ግርማ “ቅንጅት ፓርላማ አልገባም አዲስ አበባንም አልረከበም የሚል አቋም አልወሰደም” የሚለው አባባላቸው ትክክል አይደለም::

ኢህአዴግ የተገኘውን ሁሉ ምክንያት ተጠቅሞ ማደናቀፍ ይፈልግ እንደነበር ግልጽ ነው:: ያንን መሰናክል በብልሀት ተሻግሮ ለተሻለ ውጤት መብቃት የተፎካካሪው ድርጅት ድርሻ መሆን ነበረበት:: ኢህአዴግ “ፓርላማ ካልገባችሁ አዲስአበባን አናስረክባችሁም” ሲል ቅድመ ሁኔታ ማመቻቸቱ ሳይሆን ምክንያት ማብዛቱ: ሰበብ መፍጠሩ ነበር::

አንዳንድ የቅንጅት አመራሮችን ግትርነት ጠንቅቆ የሚያውቀው ወያኔ “እኔ ያልሁት ካልሆነ ሞቸ እገኛለሁ” በሚል መንፈስ የሆነ ነገር ያበላሽሉ በሚል መልካም አጋጣሚ እየጠበቀ ነበር::

ሊከሰት የሚችለውን ነገር አስቀድሞ ማስተዋል የተሳናቸው የቅንጅት አመራሮች ናቸው ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጡት:: “ተነጥቀናል የምትሉትን ወንበር ለማስመለስም ይሁን ለወደፊቱ ምርጫ ፍትሀዊነት መሟላት ይገባቸውዋል የምትሏቸው ነጥቦች ላይ ስምምነት ለመድረስ በቅድሚያ ወንበራችሁን ይዛችሁ ነው ልታነሷቸውና ልትከራከሩባቸው የምትችሉት” ሲባሉ ቆም ብለው ማሰብ ነበረባቸው::

ፓርላማ እንግባ ቢሉ መኢአድ እንደሚያኮርፍ የሚያውቁት የቅንጅት አመራሮች ፓርላማ እንድንገባ እኒህ ነጥቦች ሊሟሉ ይገባል በማለት የተሻለ አካሄድ ነው ብለው ቅድመሁኔታ ያስቀመጡት ራሳቸው ቅንጅቶች ናቸው:: አቶ ግርማ እርስዎ የፓርላማ ወንበር ባሸነፉ ጊዜም ቢሆን ፓርላማ እንዳይገቡ ግፊት ተደርጎብወት እንደነበር የሚዘነጉት አይሆንም::

ሌላው የሚገርመው የቅንጅትን ፓርላማ ስለመግባትና ስላለመግባት ጉዳይ ሕዝብን ማወያየት አስፈላጊ ነበር ብለው ማመንወ ነው:: እንዴት ያለ ነገር ነው! ሕዝቡ እኮ አንድ ጊዜ መርጧል:: የመረጠው ደግሞ ተመራጮቹ ፓርላማ ገብተው እንዲከራከሩ ነው:: አይደለም እንዴ?
በእርግጥ የህዝብ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች በማንኛውም ጊዜ አይከሰቱም ማለት አይቻልም:: ነገር ግን ከምርጫ በኋላ ፓርላማ እንግባ ወይስ አንግባ: በግራ እንሂድ በቀኝ: ስብሰባ እንጥራ አንጥራ: – – – እያሉ በያንዳንዱ ጉዳይ ሕዝብን እንጠይቅ ማለት ሀላፊነትን አለመረዳት የሚሰሩትንም አለማወቅ ነው::
ፓርቲ የራሱ አላማና ግብ አለው:: አላማውን ለማሳካትና ግቡን ለመምታት የሚነድፋቸው መርሀግብሮችና የሚከተላቸው ስልቶች ደግሞ ይኖሩታል:: ይህን ሲያደርግ ለህዝብ ይጠቅማል ብሎ የያዘውን ጉዳይ ከዳር ለማድረስ ነው:: ሕዝብ ደግሞ የፓርቲውን ፕርግራም አይቶ ይመርጠዋል ወይም ይጥለዋል::
አያያዙን አይተው ጭብጦውን ቀሙት እንዲሉ ቅንጅት ሲንከረፈፍ የጨበጠውን ለቀቀ:: ወዲያና ወዲህ ሲዳክሩ የነበሩት የቅንጅት አመራሮችም በአንድነት መቆም ተስኗቸው አባሉንም: ትግሉንም: ተስፍችንንም በተኑት::

የጠላትን እንቅስቃሴ ገምቶና አስልቶ: ጠንካራና ደካማ ጎኑን ለይቶ ስስ ብልት ፈልጎ በዚያ ለመጠቀም በብልሀት መንቀሳቀስ የማይችል ድርጅት መሞቱ ስለማይቀር የቅንጅትም እጣ ፈንታ ያው ሆነ:: ትግል እንደሚታገሉት አካል ሁኔታ ሊቃኝና የጠላትን አካሄድ እየገመገሙ ለድል የሚያበቃ ስልት ሊነደፍለት ይገባል:: ትግል ውስጥ ገብቶ ከተወደቀ ችግሩ የራስ እንጅ የሌላ ሊሆን አይችልም:: ስለዚህ ይህን ማድረግ ተስኖት የወደቀው ቅንጅት ችግሩ የራሱ (የአመራሩ) እንደነበር መገንዘብ ያስፈልጋል::

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ከኢትዮጵያውያን ጋር ሊወያዩ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ከድርጅታቸው ጋር ስብሰባ ሊያደርጉ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መግለጫ አስታወቀ:: ከኖርዌይና ስዊዘርላንድ የአርበኞች ግንቦት 7 ደጋፊዎች በደረሰን ፍላየር መሰረት ፕሮፌሰሩ ከጁን አራት ጀምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ተዘዋውረው በትግሉ ሁኔታ ገለጻ ያደርጋሉ::

 

ከኖርዌይ እና ከስዊዘርላንድ የደረሱንን የጥሪ ፍላየሮች ይመልከቱና ከታች በኖርዌይ ከአዘጋጆቹ የተሰጠውን መግለጫ እንደወረደ ያንብቡ::

gebi masebaseb norway

swiz

ጁን 4፥ 2016 የሚያካሂደዉን የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሰሜን አዉሮፓ አቀፍ ህዝባዊ ውይይትና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተመለከተ የተሰጠ አጭር ጋዜጣዊ መግለጫ

ሃገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ካለችበት ውስብስብ ችግር ለመታደግ ለሃገሪቱና ህዝቧ ቅን የሚመኝ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ህወሓትን ለማስወገድ በሚደረገዉ ተግባራዊ ትግል ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን።
ኢትዮጵያ በአጣብቂኝና በመንታ መንገድ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑንና፣ ፋሽስቱን የህወሓት አገዛዝ ከመደገፍ ተለይቶ እንደማይታይ ብዙዎቻችን እንስማማበታለን።
አርበኞች ግንቦት ሰባት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ መሰማራት ይችል ዘንድ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ጥሪዉን ካስተላለፈ ሰንበት ብሏል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ አርበኛ ታጋዮችና ከፍተኛ የአመራር ብቃት ያላቸዉን ምሁራን ጨምሮ በረሃ ወርደው የወያኔን አገዛዝ መፋለም ጀምረዋል። በግምባር መሰለፍ ያልቻሉት ደግሞ በገንዘባቸዉና በእዉቀታቸዉ የሚፈለግባቸዉን በማበርከት ላይ ይገኛሉ፣
ትግሉ የሚካሄደዉ ሃገሪቱን ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠረ፣ ብሎም የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት፣እንዲሁም በልመናና በብድር የሚገኘዉን መዋእለ ንዋይ በማሟጠጥ ተቃዋሚዎቹን ለማጥፋት በሚንቀሳቀስ የወንበዴ ቡድንና ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ዉጭ ሌላ ምንም አጋር በሌለዉ የነጻነት ታጋይ መካከል ነዉ፣፣
ለነጻነት የሚደረግ ትግል እልህ አስጨራሽና አድካሚ ነዉ፣ ዉድ ዋጋና በገንዘብ የማይተመነዉን ህይወትም ያስከፍላል፣ዉጤቱ ግን ከሁሉም ነገር የበለጠና ዉድ ነዉ፣፣ በመሆኑም ይህ ወሳኝ ሐገርን የማዳን ጥረት ዉጤታማ እስኪሆን ድረስ ነጻነት ናፋቂ የሆን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ያላሳለሰና ሁለገብ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል፣፣
ይህንን መሰረት በማድረግ June 4, 2016 የሰሜን አዉሮፓ ሃገራትን ያማከለ ታላቅ ህዝባዊ ዉይይትና የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራም በኖርዌ ሃገር ኦስሎ ከተማ ተዘጋጅቷል፣፣
በዚህ ፕሮግራም ላይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ መሪ ታጋይ አርበኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከበረሃ በመንቀሳቀስ በመካከላችን በአካል በመገኘት ስለትግሉ ማብራሪያ ይሰጣሉ።
ፕሮግራሙ የተዘጋጀዉ ከተለያዩ የሰሜን አዉሮፓ ሃገሮች ተዉጣጥቶ በተቋቋመ ግብረ ሃይል ሲሆን በኖርዌ ሃገር በሚገኘዉ የዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት የበላይ አሰተባባሪነት ነዉ፣፣ በዚህ ታላቅ አህጉራዊ ስብሰባ ላይ በኖርዌይና በተለያዩ የሰሜን አዉሮፓ ሃገራት የሚኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በብዛት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፣
ፕሮግራሙ ከየትኛዉም የአለማችን ክፍል ለሚመጣ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጅ ክፍት ነዉ፣፣ በተለይም በስካንዲኒቪያንና፣ በአጎራባች የአውሮፓ ሃገራት የምንኖር ነጻነት ናፋቂ ዜጎች የፕሮግራሙ ታዳሚዎች በመሆን የበኩላችንን እንድንወጣ ግብረሃይሉ በትህትና ያሳስባል፣፣
በተለያዩ አህጉራት ያላችሁና በአካል መገኘት የማትችሉ ኢትዮጵያዊያን ለዚህ ሃገር የማዳን ጥሪ የትግል አጋርነታችሁን በሚያመቻችሁ መንገድ ታሳዩ ዘንድ አስተባባሪ ግብረ ሃይሉ በአክብሮት ይጋብዛል።
የፕሮጋራሙ ቀን፣ June 4, 2016
ሰአት፣ ከ14፣00 ሰአት ጀምሮ
የፕሮግራሙ ቦታ፣ በቀጣይ የሚገለጽ ይሆናል
ተጋባዥ እንግዳ፣ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ መሪ ከኤርትራ

ኢትዮጵያችን በክብር ለዘላለም ትኖራለች!!
የዲሞራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ
ሜይ 13፣ 2016 ኖርዌይ፣ ኦስሎ,

በአላህ ስም ለሚፈጸም ወንጀልና ጭፍጨፋ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ምን ይላሉ? –አገሬ አዲስ

$
0
0

Daesh Executes over a Dozen Ethiopian Christians in Libyaበኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል መጠንና ድካ የለውም።ያለፉትን ስርዓቶች ትተን ለአለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሥልጣኑን በጉልበት የያዘው ጎሰኛ ቡድን በሕዝቡ ላይ የፈጸመውና እየፈጸመው ያለው ግፍና በደል ሳያንሰው ፣ ወጣቱ ሰላም አገኛለሁ፣ኑሮየን አሻሽዬ ዘመዶቼን እረዳለሁ ብሎ ወደ ውጭ አገር ቢሰደድም ከመከራው አላመለጠም። በቆዳው ቀለምና በዜግነቱ በስደት አገር ከሚገጥመው መጠነ ሰፊ ችግር የበለጠ በእምነቱና በሃይማኖቱ ላይ የታወጀ ጦርነት ሰለባ ለመሆን በቅቷል።

አልካይዳና አይሲስ የተባሉት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች የሆኑት አክራሪና  አሸባሪ ቡድኖች ከመነሳታቸው በፊትም ሆነ በዃላ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ላይ የሚመዘዘው ሃይማኖትን የተላበሰ የጥፋት ሰይፍ እያደገ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም።

የአገሪቱን አንድነትና የሕዝቡን ሰላምና እድገት የማይወዱ የቅርብና የእሩቅ ጠላቶች በየሁኔታውና በየወቅቱ መልካቸውን እየቀያየሩ ሰርገው ለመግባትና ዓላማቸውን ከግቡ ለማድረስ ያልሞከሩበት ጊዜና መንገድ የለም።ያንን ሙከራቸውን ግን ኢትዮጵያዊው ሁሉ ሃይማኖትና ጎሳ፣ቋንቋና ክልል ሳያግደው ተባብሮ ለመመለስ ችሏል፣አገራችን እስከ አሁን ለመኖሯም ምክንያት የሆነው ይኸው የሕዝቡ አንድነት በመኖሩና  ሁሉም እስላሙም ሆነ ክርስቲያኑ ለሃገሩ ነጻነት በከፈለው መስዋእትነት ነው።

ከአሁንስ በዃላ ኢትዮጵያውያን የአገራቸውን ነጻነትና አንድነት አስጠብቀው ለመኖር ይችሉ ይሆን?ይህንን ለመመለስ ያለንበትን ሁኔታ ማጤኑ ተገቢ ነው።ለአንድ አገር ዘላቂ ሰላምና ነጻነት ብሎም  አገራዊ አንድነት የሕዝቡ መተባበርና በአንድነት መቆም ወሳኝ ነው። በቋንቋ፣በክልል፣በጎሳ፣ በሃይማኖትና በፖለቲካ አስተሳሰብ ተለያይቶ እርስ በራሱ የሚናቆር ከሆነ አደጋ ለመመለስ ሳይሆን አደጋን ለመጋበዝ ምቹና ተባባሪ ይሆናል። ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባበታል እንዲሉ።

እርግጥ ነው የተለያየ የፖለቲካ አስተሳሰብና እምነት፣ባህልና ቋንቋ በአንድ አገር ውስጥ ለምን ይኖራል አይባልም። የሕዝቡን ሰላማዊ ኑሮ እስካላናጋ፣ተከባብሮና ለአገራዊ አንድነት አደጋ እስካልፈጠረ ድረስ እያንዳንዱ የሚፈቅደውንና የሚያምንበትን  የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ተቋም መከተሉ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቱ  ነው።እስከ ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያዊ  በእምነትና በባህሉ ብሎም በቋንቋው ሳይፈረጅ ለመኖር ችሏል።ያማ ባይሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች የሚናገሩና የተለያዩ እምነቶች የሚከተሉ ዜጎች ባልኖሩ ነበር። እርግጥ ነው እድገታቸው እኩልና ተመጣጣን አልነበረም።ያ ደግሞ በሰፈኑት ስርዓቶች በተለይም በመሪዎቹ አመለካከትና ንቃት የተወሰነ እንጂ በተራው ሕዝብ ወይም ዜጋ ውሳኔ የተደነገገ አልነበረም፤ አሁንም አይደለም።ሕዝብ መርጦና ተቀብሎ ባላሰፈነው ስርዓትና መሪ በሚፈጸመው ስህተት ሊጠየቅ አይገባውም።

አገራችንንም ሆነ እኛን ኢትዮጵያውያንን ብዙ አደጋዎች ከፊታችን ተደቅነውብናል።ኢትዮጵያ አገራችን ከሌለች ኢትዮጵያውያንነታችን ያከስምና ነበር ወይም ነበሩ ሆነን የምንቀርበት የጥፋት አደጋው ብዙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በእምነታችን ዙሪያ የሚፈጸመው ወንጀልና ጭፍጨፋ አንዱ ነው።

ዓለምን በሽብር እየናጣት የሚገኘው በልዩ ልዩ ስም የሚንቀሳቀሰው አክራሪ የሙስሊም ቡድን የሚፈጽመው ወንጀልና ግድያ በአረብና በሙስሊም አገሮችና ሕዝቦች ላይ ብቻ ተወስኖ የቀረ የሥልጣን ፉክክር የሚነዳው እና ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዳለው  በሙስሊሞችና ሙስሊም ባልሆኑት ሕዝቦች ላይ ጭምር የሚፈጽመውን ግፍና ጭፍጨፋ የማያውቅ የዚች ምድር ነዋሪ የሆነ ሰው የለም።ጭፍጨፋው አገርና ዜጋ አይመርጥም። እነዚህ ስልጣንና ብር ያሳበዳቸው፣ በህይወታቸው ተስፋ የቆረጡ የተሰባሰቡበት ቡድን ሴት፣ ህጻን፣አሮጊት፣ሽማግሌ ወጣት ብለው አያዝኑም።እንኳንስ ለሌላው ቀርቶ ለቤተሰባቸው አይሳሱም።የነሱ ተከታይና አገልጋይ ያልሆነውን ሁሉ፣ አላህ አኩበር እያሉ አላህ አኩበር የሚለውንና የሚሰግደውን እስላሙንም ሳይቀር ያጭዱታል፣ በሚዘገንን መንገድ ይገሉታል፤እስላም ስለሆነ አይራሩለትም። ኢትዮጵያውያንም  በተከታታይ የዚህ የግድያና ጭካኔ ሰለባ ሆነዋል።

የዛሬ ዓመት በሊቢያ ውስጥ ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በክርስቲያንነታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው  በኢሲስ ታርደው ደማቸው ከቀይ ባህር አሸዋ ላይ መፍሰሱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።አሁን ደግሞ በተመሳሳይ መንገድ  በሊቢያ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ዳይስ ታክፊሪ የተባለው የኢስስ ክንፍ የሆነ አሸባሪ ቡድን ከአስራ ስድስት በላይ የሆኑትን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በተመሳሳይ መንገድ በጥይትና በስለት አንገታቸውን በመቅላት ገሏቸዋል።

ሙሉ ታሪኩን በሚከተለው የድረገጽ መልእክት መረዳት ይቻላል።

http://www.zehabesha.com/daesh-executes-over-a-dozen-ethiopian-christians-in-libya/

ኢትዮጵያኑን ለዚህ አይነቱ አደጋ የዳረጋቸው በአገራቸው ላይ የሰፈነው ዘረኛ ስርዓትና ድህነት እንደሆነ ሁሉም ያውቀዋል። ጎሳ ተኮሩ መንግሥትና ችግሩ ቢወገድ፣ ሕዝቡ የእኔ ነው የሚለው መንግሥትና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ቢሰፍን ማንም አገሩን ጥሎ ለመውጣት አይገደድም ነበር።የስደት ሰለባ የሆኑት ኢትዮጵያውያን የአንድ ሃይማኖትና፣የአንድ ጎሳ አባሎች አይደሉም።በሳውዲ አረቢያና በሌሎቹ መካከለኛው ምስራቅ የአረብና ሙስሊም አገሮች ለአደጋ ከተጋለጡት ኢትዮጵያውያን መካከል አብዛኛዎቹ ከወሎ ክፍለ ሃገር የተሰደዱ ሙስሊም ህጻናት ልጃገረዶች ናቸው።ሙስሊም በመሆናቸው የአመጸኞች እጅ አልራራላቸውም።ኢስስም ሆነ ሌላው የሽብር ቡድን ከአመለካከቱ ውጭ የሆነውን ሙስሊም እንደማይምረው በተደጋጋሚ ታይቷል።ይህ የሽብር ሰንሰለት በአፍሪካ ውስጥ እየሰረገ በመግባት ተመሳሳይ ቀውስና ሽብር በመፍጠር ላይ ነው።ከሽብርተኞቹ ወጥመድ ውስጥ የሚገቡት አብዛኛዎቹ  የግንዛቤ እጥረትና፣በኑሮ ተስፋ መቁረጥ ያደረባቸው ወጣቶች ናቸው።የዚህ አይነት ችግር ያለባቸው ኢትዮጵያንም ስለማይጠፉ በቅድሚያ አደገኛ መንገድ ውስጥ እንዳይገቡ መከላከል የሁሉም ድርሻ ነው።በተለይም ሙስሊም ወጣቶች በዚህ መርዘኛ እባብ ሊነደፉ የሚችሉበት መንገድ ሰፊ ስለሆነ ስለእስልምና እምነት ሃቀኛ ትምህርት የሚሰብኩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን አደጋውን በግንባር ቀደምትነት ሊከላከሉት ይገባል፤ወጣቱ በዚህ በተሳሳተ የጥፋት ማእበል ውስጥ እንዳይገባ ሊመክሩትና ሊያድኑት ይገባል።

ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች በመብታቸው ዙሪያ ለሚፈጸመው በደል ድምጻቸውን ማሰማት ከጀመሩ ከአራት ዓመት በላይ ሆኗል፣መሪዎቻቸውም  በእስር ቤት እየማቀቁ ነው።ይህን ግፍና በደል የሚፈጽመውን መንግሥት ሲታገሉ ክርስቲያኑና ሙስሊም ያልሆነው ወገናቸው ከጎናቸው ቆሟል፤ትግላቸውን ትግሉ አድርጎ ተሰልፏል፣በውጭ አገርም በየመድረኩ ድምጻቸውን አስተጋብቷል፤አሁንም እያስተጋባ ነው።የእኛ እንጂ የነሱ ብሎ ከዳር አልቆመም።

በክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውና የሚፈጸመው ግፍ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ሊቆረቁራቸውና ሊሰማቸው ይገባል።በእምነታቸው ዙሪያ የሚደርስባቸውን የመንግሥት ተጽእኖ እንደሚያወግዙትና እንደሚታገሉት ሁሉ በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ላይ በአላህና በእምነታቸው ስም የሚፈጸመውን ግፍና ኢሰብአዊ ድርጊት ሊያወግዙትና ከክርስቲያን ወገናቸው ጎን መሆናቸውን በይፋ ማሳየት ይገባቸዋል።በሌላው አገር የሚገኘው ሙስሊም “በእስልምና ስም እምነቴን አትጠቀሙበት”( Not In My Name) እንዳለው ሁሉ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም “ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ወገኔን በሃይማኖቴ ስም አትጉዱት” ብለው ሊጮሁና አድራጎቱን ሊያወግዙ ይገባቸዋል። የነብዩ ሞሃመድን ትምህርትና ትእዛዝ በተግባር ሊተረጉሙት ይገባል።ለሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ ከክርስቲያኑ ኢትዮጵያዊ፣ለክርስቲያኑ ኢትዮጵያዊ  ከሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ የተሻለ አጋርና ወገን አይመጣለትም።የአንድ አገር ልጆች፣በአንድ አገር መሬት ተወልደው ያደጉ፣ሲሞቱም የአንድ አገር አፈር የሚለብሱ፣ የአንድ አገር ወንዝ ውሃ እየጠጡ ፣ተጋብተውና ተዋልደው የኖሩና የሚኖሩ፣ በአንድ አይነት ስርዓት እየተረገጡ ያደሩና የሚያድሩ ናቸው። አንዱ ከሌላው ተለይቶ የተጠቀመበት ስርዓት የለም።ክርስቲያን መሪዎች ለክርስቲያኑ ገበሬ አልራሩለትም።ፍዳውን ሲያሳዩት ኖረው አልፈዋል።አሁንም እያሳዩት ነው።ስልጣንና ጥቅም ሃይማኖትና ጎሳ አይለይም። ስልጣን ለመያዝ የሚሽቀዳደሙና የሚጥሩ ግን ሃይማኖትና ጎሳን እንደመሰላል ለጊዜው ሊጠቀሙበት ይችላሉ ።ያንንም በአገራችንና በሌሎች አገሮች እያየነው ነው።

የአንዱ ጉዳት ለሌላው ጉዳቱ ነው።ለጋራ ጥቅም በጋራ መቆምና መሰለፍ ይጠበቅባቸዋል።ለሁሉም አደጋ ያጋለጣቸውን ስርዓት ለመደምሰስና  ሁሉም ተከባብሮ የሚኖርበትን ሕዝባዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመስረት እጅ ለእጅ ተያይዘው ከመታገል የተሻለ ቁም ነገር የለም።

በዚህ አጋጣሚ በቅርቡ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የራዲዮ ስርጭት የተላለፈውን ውይይት ለግንዛቤ አያይዤዋለሁና ጊዜ ወስዶ ማዳመጡ አይከፋም።ብዙ ትምህርት ይገኝበታል እላለሁ።ብሶታቸውን አዳምጦ ተገቢ መልስ መስጠት ከሁሉም ቀና አሳቢ ወገን ይጠበቃል። ስህተትም ከሆነ ማስተማርና ማረም ተገቢ ነው።አገራችን ላይ ከተደቀኑት ችግሮች አንዱና አሳሳቢው ስለሆነ ሊታሰብበት ይገባል።እነኢሲስም ሊገቡበት የሚችሉበት ቀዳዳ ሊሆን ስለሚችል ክፍተቱን መድፈንና በሩን መዝጋት ተገቢ ነው።መዘንጋት የሌለበት ግን በሰጥቶ መቀበል ጽንሰሃሳብ ማመን አስፈላጊና ተገቢ መሆኑን ነው።መግባባትም የሚቻለው በዚሁ ጽንሰሃሳብ ከተመሩና ካመኑ ነው።

‘Ethiopian Muslims Perspective, Ethiopia’s Foreign Policy And The Myth Of Historical Enemies. (P 1)’

https://youtu.be/5f0u3Ub_vOw

 

ለስደትና ለአደጋ ሳንጋለጥ ተከብረንና ተከባብረን ለምንኖርበት አገርና ስርዓት በጋራ እንታገል!

ዘረኞችንና አክራሪዎችን በጋራ እንቋቋም!!

አገሬ አዲስ

 

 

ጦርነትን የሸሹ የመኖች ወደ ጅቡቲ ሲኮበልሉ ፣10 ሺህ ኢትዮጵያኖች ወደ የመን ይጎርፋሉ

$
0
0

“ታጣቂዎች አራት ኢትዮጵያዊያኖችን ገንዘብ አምጡ ብለው አይኔ እያየ ገድለዋቸዋል” የሰደተኛው ትውስታ

ከታምሩ ገዳ

በሰውዲ አረቢያ መራሹ ጦር የአየር ላይ ድብደባ እና በአርሰ በርስ ጦረነት እየፈራረሰች ያለቸው ጎረቤት የመን ዜጎቿ ነፍሳቸውን ለመታደግ ሲሉ ወደ ጅቡቱ ሲሰደዱ በተቃራኒው ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያዊያኖች በአገራቸው እየደረሰባቸው ያለው የሰብ አዊ መብት ረገጣን በመሸሸሸ እና ለተሻለ ኑሮ ሲሉ እጅግ አሰከፊውን እና አሰቸጋሪዉን የበረሃ እና የባህር ላይ ጉዞ በማድረግ ወደ ሰላም አልባዋ የመን እየጎረፉ አንደሚገኙ ታውቋል።

yemen

በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ የሚያተኩረው የመንግስታቱ የመረጃ መረብ(IRIN) ማክሰኞ ግንቦት 10 /2016አኤ አ ባወጣው ዘገባ ባለፈው አመት(2015 ) ወደ የመን ከጎረፉት 90ሺህ ሰደተኞች ውስጥ 90% ያህሉ(ከመቶው ዘጠናው እጆች) ከኢትዮጵያ የተሰደዱ ሲሆን የተቀሩት ብቻ ከ ጎረቤት ሶማሊያ የመጡ ናቸው ብሏል። የኢትዮጵያዊያኑ ሰደት ዛሬም ያለማቋረጡን የገለጸው ዘገባው ባለፈው መጋቢት ወር ብቻ በ 10ሺህ የሚቆጠሩ ከኦሮሚያ ክልል የወጡ ወጣት ኢትዮጵያዊያኖች በአገራቸው ውስጥ ከደረሰባቸው በደል እና መገለል አኳያ ወደ ሰውዲ አሪቢያ እና የባሕረ ሰላጤው አገሮች ስራ ፍለጋ ለመጓዝ ሲሉ ወደ ሰላም አልባዋ የመን መሰደድን መርጠዋል ፣ ከእነዚህ መካከል ከ 65 በላይ የባሕር ላይ አውሬዎች ሲሳይ ሆነዋል።
በሶማሊ ላንድ እና በጅቡቲ በኩል ወደ የመን ከተሰደዱት ኢትዮጵያዊያኖች መካከል ከ አሊቲና/ትግራይ የተሰደደው የ 31 አመቱ ከማል ፈረጃ አንዱ ሲሆን ሰኣታት የፈጀብትን የባህር ጉዞውን አጠቃሎ ከየመን ዳርቻ ሲደረሱ የተቀበሏቸው ደላላዎች/ህገወጥ አሸጋጋሪዎች ሳይሆኑ የየመን ታጣቂዎች እንደነበሩ አወስቶ በወቅቱም ሰለደረሰባቸው ግፍ እና በደል ሲዘረዝር “ ከአንዲት ጠባብ ቤት ውስጥ ለሳምንታት አሰረውን ከአገር ቤት/ከ ኢትዮጵያ ገንዘብ እንዲላክልን ለዘመዶቻችን ስልክ እንድንደውል አሰግደዱን። ገንዘብ መክፈል ያልቻሉ አራት ወገኖቻቸንን አይናችን እያየ ገደሏቸው “ሲል ሕይወቱን ብቻ ማትረፍ የቻለው ከማል አሰቀያሚው የሰደት ጠባሳውን ለኢሪን ዘጋቢ ተናግሯል።ባለቤቱን እና ልጁን ኢትዮጵያ ውስጥ ጥሎ ለተሻለ ኑሮ ወደ የመን የተሰደደው ከማል በአሁኑ ወቅት የየመኑ ጦርነት ጋብ እስኪል ድረስ የመን ወስጥ የጫት እርሻ ውስጥ በቀን ስራ በማገልገል ሰለ ስውዲ አረቢያ ጉዞው ኣና ህልሙ እየወጠነ ይገኛል።
በብዙ ሰደተኞች ዘንድ የተሻለች አገር ሆና የምትታየው ስውዲ አረቢያ በየመን ውስጥ በሚካሂደው ጦርነት ውስጥ እጆቿን በማሰገባቷ እና የየመን ሸማቂዎቹ/ሁቲዎች በበኩላቸው በጋራ ደንበሮች ላይ የፈተሻ ኪላዎችን በመቆርቆራቸው ሳቢያ የአትዮጵያዊያኖቹ ሰደተኞችም ከየመን ወደ ስውዲ አረቢያ የመሻገር እጣ ፈንታቸው የተመናመነ ሆኗል ተብሏል። ሰደተኞችን ይረዳ የነበረው የአለማቀፉ ከሰደት ተመላሶች ድርጅት (IOM) ባለፈው አመት ጥቃት ደርሶበት አምስት ኢትዮጵያዊያኖች መሞታቸውን ተከተሎ አገልግሎቱን ያቋረጠ ቢሆንም ካለፈው አመት ጀምሮ ከ 3ሺህ በላይ ሰደተኞችን ከየመን እስር ቤቶች ሰብሰቦ ወደ አገራቸው ወደ ኢትዮጵያ በፈቃደኝነት ያጓጓዘው ይሀው ድርጅት/IOM/መካከል የስውዲ አረቢያ ጉዞውን እውን ለማድረግ ከ ኦሮሚያ አካባቢ ከብቶቹን በመሽጥ ወደ የመን የተሰደደው የ 25 አመቱ አሊ አህመድ ኢብራሂም አንዱ ሲሆን አሊ ሰለ ወደፊቱ ተሰፋው ምን እንደሚያስብ ለኢሪን ዘጋቢ ሲናገር” በእውነቱ በአሁኑ ወቅት ምንም የማሰበው ነገር የለም ፣በኢትዮጵያ ውስጥ ተሰፋውም ጨልሞብኛል፣ ምናልባት የመን አንጻራዊ ሰላሟ ስታገኝ ዳግም ወደ የመን እሰደድ ይሆናል”ብሏል።

የዛሬ ስደስት ወራት ከአማራ ክልል ተነስቶ የቀይ ባህርን በማቋረጥ ወደ የመን የተሰደደው የ 40 አመቱ ኢብራሂም አሊ የሱፍ በበኩሉ የየመኑ ሰደቱ እንዳልተመቸው ፣ ስውዲ አረቢያም ብሯን እንደዘጋችበት ፣በሰነኣ/የመን የሚገኘውም የአኢትዮጵያ ኢምባሲም ጀርባውን እንዳዞረበት አምረሮ ይናገራል። በስተመጭረሻም”መሄጃው ጠፈቶን ወጥመድ ውስጥ እንገኛለን “ሲል ምሬቱን እና ሰጋቱን የገልጻል።
እኛም ብንሆን እነዚህ አገራቸውን ፣ ቤት ንብረታቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ጥለው እና ውድ እና መተኪያ የሌለው ነፍፍሳቸውን ሸጠው ለምይሳካው የሰድት ኑሮ የተዳረጉ እነዚህ በሺዎች የሚቆጠሩ ምስኪን ወገኖቻቸንን በትቻለን መጠን ልንድርሰላቸው እንደሚገባ ሊዘነጋ አይገባም ።

ሰቆቃዎ ብሔረ ዐማራ

$
0
0

ከብሥራት ደረሰ

ይህን ጽሑፍ ከዐማራ ውጪ ማንም ባያነበው ይመረጣል፡፡ ምክንያቱም ዐማራን በተለዬ ሁኔታ የሚወቅስ ጽሑፍ በመሆኑ ለሌሎች ብዙም የሚጠቅም ነገር የለውም፡፡ መወቃቀስ ለዕድገት መሠረት ነው፤ ጉድፍን ለማጥራትና ጠንካራ ጎንን አጠናክሮ ለመቀጠል ሂስና ግለሂስ ጠቃሚ ናቸው፡፡ ተድበስብሶ መጓዝ ግን በግልም ሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ጠንቅ ነው፡፡

Displaced-Amharas-from-West-Shewa-Aremya-province-Dec-2015-1.jpg

ውድ ዐማሮች እንደምን ከረማችሁልኝ? ያለፉትን 40 ዓመታት እንዴት አያችኋቸው? የደርግ መንግሥት አስብቶ ለወያኔው የባንዳዎች ቡድን ለዕርድ አመቻችቷሁ መሄዱን ቀስ እያላችሁ በጊዜ ሂደት ስትነገዘቡ ምን ተሰማችሁ? አሁንስ እንዴት እየሆናችሁ ናችሁ? ስደቱ፣ሞቱ፣ ወያኔ ያወጀባችሁ የዘር ፍጅቱና ዐማራን ከየቦታው ማጽዳቱ፣ እስር-እንግልቱ፣ ከመንግሥት ሥራና ከንግድ – ከቤትና ከመሬት –  ከሕይወትና ከሃይማኖት፣ ከርስትና ከሚስት መፈናቀሉ፣ በጥይት መቆላቱ፣ እንዳትዋለዱና ዘር እንዳትተኩ በትግሬ ዶክተሮች መምከኑ – (አዎና በትግሬ የህክምና ዶክተር! እነፕሮፌሰር አሥራትን የገደለ መርፌ ባላገርን ማምከን ደግሞ ያቅተው እንዴ? ብዙ የሚወራረድ ዕዳ አለባቸው ትግሬ ወያኔዎች!!)፣ በማይድን በሽታ መለከፉ፣ በኑሮ ውድነት መጠበሱ፣ በማይምነት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ መንጠራወዙ፣… እንዴት ይዟችኋል ወንድሞቼና እህቶቼ? የማይለመድ የለምና መቼም ይህን ሁሉ ዘመን አመጣሽ ግፍና በደል ሳትለምዱት እንደማትቀሩ አምናለሁ – ኑሮ ካሉት ፍሪጅስ ማለቴ መቃብርስ ይሞቅ የለም? ደርጎች “የማይለመድ የለም፤ ውስኪውንም ለመድነው “ ብለው ነበር ያኔ ካረቂ መለኪያና ከጠላ ሽክና ወደዊስኪ ብርጭቆ ሲንጠለጠሉ፡፡ እንደምታዘበው በዚህች ምሥኪን ሀገራችን ምድረ ደንቆሮ ከቀበሮ ጉድጓድ ወጥቶም ይሁን ከበረሃ ገስግሶ ሥልጣን የሚይዘውና ለመያዝም የሚቋምጠው መቼም ለዚያ ለፈረደበት ሆድ እንጂ ለመንፈሣዊ እርካታና ለሀገር ባለው ብሔራዊ ስሜት አልሆነም፡፡

 

ውድ ዐማሮች የረባ ነገር ልነግራችሁ አይደለም ብዕሬን ያነሳሁት፡፡ ይልቁንም ላናድዳችሁ ነው፡፡ መናደድ ደግሞ ሰውኛ ነውና ብትናደዱ ቅር አይበላችሁ፡፡ ያው ተናዳችሁ ተናዳችሁ ትቀዘቅዛላችሁ፡፡ ምን ምርጫ አለ?

 

ለመነሻ ይቺን በጣም የተለመደች ግን ተጣምማ የተነገረች ታሪክ ላስታውሳችሁ፡፡ በቀ.ኃ.ሥ. ዘመን ነው፡፡ ዐፄው ለአንዲት ወይዘሮ ብር 500 ለሽቶ ይፈቅዱላትና በወቅቱ የገንዘብ ሚኒስትር ለነበሩት ለአቶ ይልማ ደሬሣ ማዘዣውን ሴትወዋ ታቀርባለች አሉ፡፡ ያኔ ሚኒስትሩ “ኢንዴት ቢቲገማቸው ነው ኢሄን ሁሉ ገንዘብ የፈቀዱት?” በማለት በንጉሡም በሥርዓቱም በኛ በሕዝቡም ላይ ቀለዱ ይባላል (ያን በመሰለ የመኳንንትን ሚስት ሣይቀር ለሹመትና ለሽልማት ሲባል በግብር መልክ በሚቀበል ንጉሣዊ ፈላጭ ቆራጭነት በሚተዳደር ሕዝብ ላይ ቢቀለድም ነውር ያለበት አይመስለኝም)፡፡ ነገሩ ማለቴ ንጉሣዊ ችሮታው እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ ሚኒስትሩ የቀለዱባቸው በኦሮሞው ንጉሥ በአፄ ኃ. ሥላሤ መሆኑን በእግረ መንገድ ልብ ይሏል ግን፡፡ በሚኒስትሩ ለማላገጥ የፈለገው ሰው ግን አንድም ሣቅ መፍጠር የፈለገ ዐማራ ወይም ኦሮሞም ሆኖ መቀለድ የሚወድና የሚያምረውም ወገኔ ሊሆን ይችላል፤ አንድም የሌላ ኢትዮጵያዊ ቋንቋ ተናጋሪ ወገናችን ሊሆን ይችላል፤ አንድም ሌላ የማላውቀው ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ መሠረታዊው እውነት ግን እንዲህ ነው፡- አንደኛ ሚኒስትሩ ከዐማሮችም በላይ ዐማርኛ መናገር የሚችሉና በዐማርኛ የሚራቀቁ ስለነበሩ “ቢቲገማቸው”ን የመሰለ ዐማርኛን እየተለማመደ ከሚገኝ የኦሮምኛ- ዐማርኛ አንደበት የሚወጣ ቃል ቀርቶ አንዳችም እንከን የሚወጣላቸው አልነበሩም፡፡ ሁለተኛ ያኔ ዐማርኛን እንደከተሜ በደምብ አለመናገር ያስተርብ ነበርና ከተረብ የሚያመልጥ ኦሮሞና ጉራጌ ይቅርና አንድም ዐማራ አልነበረም፡፡ የኔ እህት ስሟን ከ“አንጓች ጓንጉል” ወደ “ሊሊ ጓንጉል” የለወጠችው ወድዳ እንዳልነበር አሁን ድረስ የምናስታውሰው የቅርብ ዘመን ቤተሰባዊ ታሪክ ነው – የአባቷን ግን አልቻለችምና ተወችው – ምን ታድርግ – አዲስ ሰው ልትሆን ሆነ እኮ – የአያቷን የአባባ አሊጋዝን ስትቀይር ደግሞ ኢትዮጵያዊ ማንነቷ ከናካቴው ድራሹ ሊጠፋ ነው፡፡ ዐማሮችም በዚህ የዐማርኛ ጣጣ ይሰቃዩ እንደነበር የማይረዳ ሰው ደምበኛ ድንጋይ ወይም እርሱ ከያዘው እውነት የተለዬ እውነትን ማየት የማይችል ልበ-ድፍን መሆን አለበት፡፡ የዛሬ 30 ዓመታት ገደማ እንኳን – እኔ ራሴ  የወለድኳትን ዲቃላ ልጄን ከአገር ቤት ወደ አዲስ አበባ ሳስመጣት ያዬነውን አበሳ እኔና ልጄ ብቻ ነን የምናስታውሰው፡፡ አንደበቷን ከገጠር ዐማርኛ ወደ ከተማ ዐማርኛ ለመመለስ(ለመግራት)፣ ስሟ ያስከተለባትን ሥነ ልቦናዊ ጫና ለመግፈፍ እኔና የእንጀራ እናቷ ያየነው አበሳ ቀላል አልነበረም – ደስ ይበላችሁና ግን በተሎ ተስተካከለችና እሷም እኛም “ከሀፍረት ዳንን”፡፡ ስለዚህ አንዳንድ የወቅቱ “ባለጌ” ተረበኞችና “ትምክህተኞች” ይፈጥሩት የነበረው ተፅዕኖ በሌሎች ዘውጎች ብቻ ሣይሆን በዐማርኛ ተናጋሪዎችም ላይ እንደነበር፣ እነዚሁ ተዋንያንም ከዐማራው ብቻ ሣይሆን ኦሮሞን በዋናነት ጨምሮ ከሁሉም ነገዶችና ጎሣዎች የተገኙ እንደነበሩና ነገር ግን የዞረ ድምሩ በዐማሮች ላይ ብቻ እንዲወድቅ መደረጉን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡

 

ውድ ዐማሮች ሆይ! አንዷ ሴት “ዕድሌ ሆኖ ፈሴ ይሸታል” አለች አሉ – የማን ጥራጥ ማትም ፈስ እንደማይሸት እርሷው ትወቀውና፡፡ የዐማራ ዕድል ሆኖ በኢትዮጵያ ውስጥ የተደረጉና አሁንም ድረስ የሚደረጉ መጥፎ ነገሮች ሁሉ የሚላከኩት በዚህ ቀን በጣለው ዐማራ ላይ ሆነ፡፡ ዕድል ነው፡፡ እርግጥ ነው የዕድል መጣመም ሊያሳዝን ይችላል፡፡ እንደዐማራ ዕድል ደግሞ የተጣመመና የሚያሳዝን የለም፡፡ “እስከማዕዜኑ አነብ..” አለ ዳዊት?

 

ለዕድሉ መጣመም አስተዋፅዖ ካደረጉ ነገሮች አንዱ እንግዲህ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን የመሰሉ ቀደም ባሉ ሥርዓቶች የተፈጠሩ – ፈጣሪያቸው ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሆነ – አንዳንድ መራራ ቀልዶች መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡ መዘንጋት የሌለበት ዋና ጉዳይ ግን የጥንቱን የአለቃ ገ/ሃናን ወይም የቅርቡን የጓድ ቆምጫምባውን ቀልዶች ስንታዘብ በነሱ ሠርጎ በመግባት ተደማጭነትን ለማግኘት የፈለገ ዚቀኛ ሁሉ በነሱ ስም ያሻውን ቀልድ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንደለቀቀብን ሁሉ ሌሎች ዘውጎችም የሚፈጥሯቸውን ጋብቻ ከልክል ዘረኛ ስድቦችና አጓጉል ቀልዶች ሁሉ በዐማራ ላይ እየለጠፉ ዐማራን በሌላው ሊያስጠሉ መሞከራቸው ነው፡፡ ይህ ትልቅ ታሪካዊ ጥፋት ነውና መታረም ይኖርበታል፡፡ ዐማራ ብቻውን ለነዚያ ቀፋፊ ቀልዶች ተጠያቂ አይደለም፤ ሊሆንም አይገባውም፡፡ የአንደበትን መኮለታተፍ በተመለከተ እንደኔ ችግር የለውም፡፡ እኔም ኦሮምኛ ስናገር የማሳየውን የቅላጼም ሆነ የሆሄ ግድፈት እየነቀሱ በቀልድም ሆነ በምር ቢናገሩ ቅር አይለኝም – እንኳንስ በምማረው ቋንቋ በኔ በራሴው ቋንቋስ ይቀልዱብኝ የለም? ምን ችግር አለው? አሉ እንጂ እዚህ የማይነሱ – ለሞኝ ሰው በተለይ – አጥንት ሰርሳሪ ቀልዶችና ተረቦች፤ ለምሣሌ ጎጃሜና ተልባ፣ ወሎና ገለባ… ዓይነት ደም የሚያንተከትኩ ትረባዎች፡፡ ገራገር ተረቦች ግን በየማኅበረሰቡ ያሉ ይመስለኛልና በቀላሉ የምንከፋ ሰዎች ኩፍ አንበል፡፡ መጥፎ የሚባሉትን ተረቦች እንኳን ተስቶት የሚናገር ሰው ቢኖር እናስተምረው እንጂ ቱግ ብለን ወደከፋ እርምጃ አንግባ፡፡ የአፍ ልማድ ሆኖበት አንዳንድ ሰው ሊዘባርቅ ይችላል፡፡ ከመቀያየም ማስተማር ይቅደም፡፡ ማስተማር ዐውሬን ሰው የመግራት ባሕርይ አለው – እንዲገባው አድርገን በቅጡ ካስተምርነው፡፡

 

የኔ ነገር የተነሣሁበትን ትቼ ሌላ ማውራት ሆነ፡፡ እናም ውድ ዐማሮች ባለፉት 40 ያህል ዓመታት ብዙ ነገር ተምራችሁ ከአንደኛና ሁለተኛ ዲግሪ በሚበልጥ ማዕረግ የተመረቃችሁ ይመስለኛል፡፡ በከባድ መስዋዕትነት መማር አይረሴ ትምህርትን ያስገኛልና የሆነው ሁሉ ለበጎ ነው፡፡

 

… ዐማራ የምትባይ ፍጡር እያንዳንድሽ “ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ” ስትይ፣ “አንድነት፣ አንድነት” ስትይ የኢትዮጵያዊነትሽንና የአንድነት ፈላጊነትሽን ምስ በወያኔና ግብረ አበሮቹ ክንድ ቀመስሻት፡፡ ሳታስቢው በደረሰብሽ ዘግናኝና ለዘመናት ያልተቋረጠ ሁለገብ ድብደባ መንፈሣዊና አካላዊ ክንድሽ ዝሎ ተዝለፈለፍሽ፡፡ በዚያም ምክንያት አንዳንድሽ በእግር አውጪኝ ወደሚያሳድዱሽ ቤት ሮጠሸ ገባሽና ዩኒቨርስቲያቸውንና ኩሽናቸውን አደመቅሽ፡፡ አንድሽ በግርድና፣ አንድሽ በዘበኝነት አንድሽ በሣይንቲስትነት … ጓዳ ጎድጓዳቸውን ሞልተሸ አገለገለሻቸው፡፡ ያንቺ ጓዳ ግን በዐይጦችና በምሥጦች ተይዞ ይቦጠቦጥልሻል፡፡ … አዲስ ታሪክ በሀገርሽ እየተሠራ አንቺ የፈረንጅ አሽከር ሆነሽ በምናባዊት ኢትዮጵያ ውስጥ በአካልም በምናብም እንዳመቺነቱ እየተመላለስሸ ትኖሪያለሽ፡፡ እስከመቼ? Is our question, of course. በ“ቋንቋሽ” ተጠይቀሻል መልሽልኝ፡፡ ያኔ አንቺ ኢትዮጵያን ገዛሽ በሚባልበት ክፉና የአድልዖ ዘመን ጎጃምን፣ ጎንደርን፣ ወሎንና ሸዋን ትምህርት ቤት በትምህርት ቤት፣ ፋብሪካ በፋብሪካ፣ አስፋልት በአስፋልት፣ ኢንዱስትሪ በኢንዱስትሪ፣ ዩንቨርስቲ በዩንቨርስቲ… ባታደርጊ ኖሮ ይሄኔ ልጆችሽ ማይም ሆነውልሽ ታርፊያትና ለፀፀት ተዳርገሽ ነበር፡፡ እንኳን ያኔ ለዐማራው ለዘርሽ ያዳላሽና እንኳንስ እነዚህ የተጠቀሱና ያልተጠቀሱ የዐማራ ሥርፋዎች ሁሉ በዘመናዊነት ተንቆጠቆጡ!!!!! እንኳን ባዶ ሆነው አልቀሩ፡፡ … አርቆ ማሰብ ቅርብ እንደሚያሳድር ማወቅ አይከፋም፡፡ ቅርብ አስቦ ቅርብ በማደር ምክንያት በሩቅ ከመወገዝ ይልቅ በርቀት ለርቀት ማሰብ የተሻለ ነውና የዐማሮችን ከአድማስ ወዲያ ማዶ ተሻግሮ የሄደ ሀገራዊ አስተሳብና ከዘረኝነት ልምሻ የፀዳ ተግባራችንን እኛም ማወደስ አለብን – ራሴን በራሴ አፌን በምላሴ ካላንቆለጳጰስኩት ማን ያንቆለጳጵስልኛል ተብሎ የለ፡፡

አሁን ዳር ዳርታው ይቅርብኝና ወደዋናው ልግባ፡፡ ለመሆኑ ዐማራ ይህን ያህል የተቀጣውና የሚቀጣው ለምን ይሆን? ከአንዳንድ ልበ-ሥውራን ዐማሮች ታሪካዊ ጥፋት በስተቀር – ከማንኛውም ነገድና ጎሣ እንዳለው ሁሉ –  ገሣ ለብሦ በዱር በገደል የሚኖረውን የደብረ ብርሃንና አካባቢዋን ዐማራ ጨምሮ ቀሪው ኢትዮጵያዊ ዐማራ ምን በደል ፈጽሞ ይሆን እንዲህ ቤተስኪያን እንደገባች ውሻ የወያኔና መሰል የአጋንንት ጭፍሮች መጫወቻ የሆነው? ዐማራን አንዳች ነገር ካልያዘው በስተቀር ከ5 እስከ 6 ሚሊዮን ከሚገመት የትግራይ ሕዝብ በወጡ በጣት በሚቆጠሩ የጣሊያን ባንዳዎች ልጆች እግር ከወርች ሊታሠርና ለዕልቂት ሊዳረግበት የቻለበት ምክኛት ምንድነው? በውነቱ ይህን ነገር ሲያስቡት ራሱ የሚያስጨንቅ ሁኔታ ነው ገጥሞን ያለ፡፡ ትልቅ ታሪካዊ አፍዝ አደንግዝ ነው ይህ ነገር – abracadabra.

ውጫዊ ምክንያቶችን አሁን አላነሳም፡፡ በውስጣዊ ምክንያቶች ትንሽ ልንፈራገጥና ጽሑፌን ልቋጭ፡፡ በነገራችን ላይ ይህችን ጽሑፍ ልጽፍ የተነሣሁት የአንድ ሰው ጽሑፍ በድረገፅ ዛሬ ሳነብ በጽሑፉ መጨረሻ አካባቢ ያገኘሁትና እኔም በሌሎች ጽሑፎቼ በተደጋጋሚ ያነሳሁት ጉዳይ ትኩረቴን ስለሳበው ነው፡፡ ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን የተባለ “አክራሪ ዐማራ” የጻፈውን ጽሑፍ ከዘሃበሻ ቀደምት ልጥፎች አግኝቼ ሳነበው እየሳበኝ መጣና ሁሉንም ወረድኩት፤ ብዙው ነገር ጥሩ ነው – ግን ትንሽ ጠነን ይላል – ከርደድ፡፡ ለማንቻውም ለኔ ዓላማ የመረጥኩትን በዚህ ገጽ መጨረሻ አስቀምጨዋለሁ፡፡

ውድ ዐማራዎች ሆይ!

ለምትገኙበት የመከራ ሕይወት ተጠያቂዎቹ በአብዛኛው እናንተ ራሳችሁ ናችሁ፡፡ ወደ ውስጣችሁ ተመልከቱና ራሳችሁን መርምሩ፡፡ በቶሎም ለመስተካከል ሞክሩ፡፡ ብዙ አልመሸም፡፡

ለመሆኑ እርስ በርስ ትዋደዳላችሁ? ዐማራ ለዐማራን ተውት – ህልምና ቅዠት ነው፡፡ ኧረ እንዲያው ሌላውስ ይቅርና ቤተሰባችሁንስ ከልብ ትወዳላችሁ? ቅናትና ምቀኝነት የት በቀለ? ከዐማራ ለማለት የሞራል ብቃት የለኝም፤ ግን በዐማራ እንደሚብስ በትክክል መረዳት አያቅትም፡፡ እስኪ በየጠበሉ እንሂድ፤ እስኪ በየገዳማቱ እንሂድ፡፡ በሰዎች የሚያድር እርኩስ መንፈስ ወይም ሰይጣን ሲለፈልፍ እስኪ እንስማ፡፡ ከየጠበልተኛው ሰው ሆድ ዕቃና ልዩ ልዩ የሰውነት ክፍሎች የሚወጣውን ፈሣሽና ጠጣር ጉድ እስኪ እንመልከት፡፡ በዕጀሰብና በሟርት ተለክፎ – ወይ አይሞት ወይ አይድን –  በየጠበሉና በየደብተራው፣ በየጠንቋዩና በየሰይጣን ጎታቹ ደጅ የሚንከራተተውን የሕዝብ ቁጥር እስኪ እንታዘብ – ሥራና ቤት ንብረቱን የትም ጥሎ(ኦፋ ለገሠ የሚባለውን የሰሜን ሸዋ ጠንቋይ የሚያውቅ አለ? አይሆኑ ሆኖ በቅርብ ሞተ አሉ)፡፡ ለመሆኑ ሰው በቤቱ የቀረ ይመስላል እንዴ? ጠንቋይ አስጠንቋዩን፣ ደብተራውን፣ አበጋሩን፣ ድቤ መቺውን፣ ቅጠል በጣሹን፣ ኮከብ ቆጣሪውን፣ ስኒ ተመልካቹን፣ መታች አስመታቹን፣ … እስኪ ለአፍታ በምናባችን እንቃኝ – አዲስ አበባ ሳይቀር ምድረ ሀብታምና አትሌት እቤቱ የሚያድር መሰላችሁ? ወይ ይቺ አንዲት እንጀራ የምታሳየን ተዓምር! ይህ እርስ በርስ የተቆላለፈና አንዱ ለአንዱ የማይተኛ ሕዝብ እንዴት ያልፍለታል? ጧት ቤተ ክርስቲያን፣ ማታ ቃልቻ ቤት እየተሄደ፣ ከትዕዛዙ ውጪ ለሁለት ጌቶች እየተገዛ፣ እህት በወንድሟ፣ ልጅ በአባቱ እየተተበተበበት፣ ባል በሚስቱ ሚስት በባልዋ እየዋለችበት፣ ጎረቤት በጎረቤቱ፣ አበልጅ በአበልጁ፣ ቄሱ በዲያቆኑ፣ ጳጳሱ በኤጲስ ቆጶሱ ደንቃራና ሟርት እየተጣጣሉ እንዴት አንድ ሕዝብ በሥልጣኔ ወደፊት ፈቀቅ ሊል ይችላል? ይህን ሁሉ የውስጥ ጉዳጉድ የተሸከመ ማኅበረሰብ ከእግዚአብሔር ጋር እንዴትና መቼ ሊታረቅ ይቻለዋል? ይህን ሁሉ ገመና ተሸክመን እንደሀገርና ሕዝብ እስካሁን መኖራችንም እኮ በራሱ አስደናቂ ነው፡፡ እንዴ፣ ወያኔ እኮ እኮ ከሚገባን በታች ነው – ያንሰናል እንጂ ወገኖቼ፡፡

ይህ የተጠቀሰው ሁሉ እውነት ነው ውሸት? ይህን ዓይነቱን ከታች እስከላይ የተስፋፋ የወንጀልና የኃጢኣት ድርጊት በጥልቀት ለተመለከተ ዐማራው በተለይ ኢትዮጵያ ደግሞ በአጠቃላይ በወያኔ የሰይጣን ጭፍራ መመታቷ ሲያንሳቸው እንጂ እንደማይበዛባቸው በግልጽ ይረዳል፡፡ …

ምን እናድርግ ታዲያ? ለሕዝብ የሚቆረቆር እውነተኛ መንግሥት ቢኖረን ብዙ ነገሮችን ማድረግ እንደምንችል ግልጽ ነው፡፡ ጥሩ መንግሥት ስለሌለን ግን አሁን ማድረግ የሚቻለን ምንም ወይም ከምንም ብዙም የማይሻል በጣም ኢምንት ነው፡፡ ምክንያቱም ሕዝብን ለመለወጥ ሚዲያና የተማረ ሰው ወሳኝ ነውና እነዚህ ቁልፍ ነገሮች በሌሉበት ወይም አሉ ብንል እንኳን ዕድል ባላገኙበት ሁኔታ ዝም ብሎ በንዴት ከመንጨርጨር ባለፈ የረባ ነገር መሥራት አንችልም፡፡ ጊዜው ገና ሆነና ተቸገርን ጓዶች፡፡

ተስፋ ቆርጠን መቀመጥ ግን የለብንም፡፡ ይህችን ማስታወሻ ያነብብን ወገኖች ቢያንስ በውስጧ የተጠቀሱትን ፍሬ ነገሮች ልብ በማለት ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ አንዳች መልካም ተግባር ለማከናወን እንሞክር፡፡ የዐማራው የአንድነት ስሜት እንዳይሸረሸር ከመጣር በተጓደኝ ዐማራው ራሱ ለራሱ ዘውግ ያለውን አመለካከት እንዲያሻሽል በተቻለን እናግዘው – ከዚህ ነጥብ አኳያ ከሃይማኖት አባቶች ብዙ ይጠበቃል – ዘመቻውን ግን ከራሳቸው ይጀምሩ፡፡ እርስ በርሱ እንዲፋቀርና ከተገለጹት የክፋትና የምቀኝነት አባዜዎች እንዲላቀቅ ፍቅርንና መተሳሰብን መስበክ ይገባናል፡፡ የራሱን ወገን በተቻለው ዘዴና ብልኃት ሁሉ ለማጥፋት ቀን ከሌት ቆርጦ ከሚማስን ወገን አመርቂ የሆነ ሀገራዊ መልካም ነገር አይጠበቅምና መጀመሪያ ከነዚህ ነውረኛ ባህላዊና ባዕድ አምልኮታዊ ነገሮች እንዲርቅ እናስተምር፡፡ በግልብ የሚሰበከውን ሃይማኖት ጥልቀትና ትርጉም ባለው መንገድ እናድርግለት፡፡ የጠፋነው ከላይ እስከታች በመሆኑ ሁለመናችንን እናድስና አዲስ ሰው ለመሆን እንሞክር፡፡ ኤሊት የሚባለውም ወገን ከእንቅልፉ ይንቃ፡፡ ዐማራ የሚባል እንደዐይጥ እየተጨፈጨፈ የሚገኝ ወገን እንዳለው ይረዳና ከዚህ ጥፋት ወገኑነን ለመታደግ በተቻለው መጠን ይታገል፤ ፕሮፌሰር አሥራት ከተናገሩት – እጠቅሳለሁ “ከሆዳምነት የጅብ ባሕርይ” – በአፋጣኝ እንውጣና ራሳችን በቅድሚያ ሰው ሆነን ሰው እንፍጠር፡፡

እንደታሪክ አጋጣሚ ሆኖ በሀገራችን አዲስ ታሪክ ተፈጠረና ጥቂቶች ብዙዎችን በጄኖሳይድ ይፈጁ ገባ እንጂ እኛ የምናውቀው ማወቅ አትበሉትና ብዙዎች ጥቂቶችን ሲጨርሱ ነበር፡፡ የኛ ግን የተገላቢጦሽ ነው፡፡ በሩዋንዳም ሆነ በዩጎዝላቪያ የታዬው ሰይጣናዊ ፍጅት ብዙዎች ጥቂቶችን ሲጨፈጭፉ ነው፡፡ የኞች ወያኔዎች ግን የተማመኑትን ነገር ከግምት ባለፈ ጠልቄ  አላውቅም ድፍረታቸው ግና እጅግ አስገራሚ ነው – ሊጨርሱት የማይችሉትን ሕዝብ ነው የጀመሩት – ምናልባት የመካሪ ስህተት ወይም መካሪ አሳስቷቸው እንዳይሆን እሰጋለሁ – እንጂ ጥላቻ ብቻውን ለዚህን ከተራራ ለገዘፈ የዕብደት ደረጃ ያደርሳል ብዬ ማመን ይከብደኛል፡፡ ለነገሩ በጌታዋ የተማመነች በግ ላቷን ውጭ እንደምታሳድር እነዚህ ባለጌ ወያኔዎችን አይዟችሁ ብሎ ጃዝ ያላቸው ዓለም አቀፍ ኃይል ሳይኖር ይህን ትልቅ ጀብድና የተንሻፈፈ ዘረመላዊ ተፈጥሮ የሚጠይቅ ድርጊት እንደማይፈጽሙ መገመት ይቻላል፡፡ ማጣፊያውን አንድዬ ይወቅላቸው እንጂ እስካሁን እንደጆኒ ዎከር በርትተው በመጓዝ ላይ ናቸው – ምንም የሆኑት ነገር የለም “still going strong”፡፡ ይህን ከፍ ሲል የተናርኩትን የጥቂቶችና የብዙኃን የመገዳደል መጥፎ ተሞክሮ የማነሣው እውነታውን ለመጠቆም እንጂ ማንም ማንንም ተነስቶ ይጨፍጭፍ እያልኩ አይደለም፡፡ መግደል የሰይጣን ነው፤ የሰይጣን ትልቁ ግብሩ የሰው ደም ነውና፡፡ ከዚህ ደግሞ ይሠውረን፡፡ ይሠውረን ስል ደግሞ ፈጣሪያችን ኩክየለሽ ይሁንልንና ይሄንን እንኳንስ ሊኖሩት በታሪክ መዝገብ ተቀርጾ ሲቀመጥ ወደፊት ሊያስታውሱት እንኳን የሚዘገንን ክፉ ዘመን አንስቶ ወደታሪክ መዝገብ ቤት ይጨምርልን፣ በጉጉት የምንጠብቀውንና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚሆነውን ወርቃማ ዘመን ያምጣልን ማለቴ ነው፡፡ እንጂ መጨፋጨፍ የአጋንንት መዝናኛ በእግዚአብሔር ቤት ግን ማዘኛና ማልቀሻ ድርጊት መሆኑን አውቃለሁ፤ (የሚያባላን) መንፈስ ሲለቀን የዚህን አባባል እውነተኛ ትርጉም እንረዳለን፡፡

ለማንኛውም ዐማራዎች ሆይ – ችግራችንን ዕንወቅ፡፡ ለተዘፈቅንበት ችግር ደግሞ ዋና ተጠያቂዎቹ እኛው ነን፡፡ እግዚአብሔርንም በከንቱ አናማርር፡፡ እናንተ ለምሣሌ ከሁለት ተፋላሚ ሰይጣኖች መካከል አንዱን ምረጡና አግዙት ብትባሉ የትኛውን ትመርጣላችሁ? የእግዜርንም “ዳተኝነት” ከዚህ ነጥብ አንጻር መመልከት ይቻላል፡፡ በእውነትም ይሁን በምናብ የሚዋጉ ሁለት ክፉዎች ቢኖሩ እንደፍጥርጠራቸው ብሎ መተው እንጂ እግዜር አንዱን ክፉ ትቶ ለሌላው ክፉ የሚያዳላ አይመስለኝም፡፡ ስለሆነም አጠገቤ ያለውን ወንድሜን ከሀብት ንብረቱና ከሞቀ ትዳሩ በድግምትና በደንቃራ እያለያየሁና እያሳበድኩ በሌላ አቅጣጫ ደግሞ “ጌታ ሆይ! ወያኔን ለመሰለ ጭራቅ ለምን ዳረግኸኝ?” ብል “ቂም ይዞ ጸሎት፣ ሣል ይዞ ስርቆት” እንዲሉ ነውና ትክክል አልሆንም – ቀድሞ የራስን ምግባርና ጠባይ መቃኘት ተገቢ ነው፡፡ ልባችንን ሳናጠራና ከኃጢኣት ሳንቆጠብ የምንጸልየው ጸሎት ሁሉ ከዳመና በታች እንደሚቀር የምናውቅ በጣም ጥቂቶች ነን፡፡ በቤት ወይም በቤተክርስቲያን ግቢ ተገኝቶ 24 ሰዓት መጸለይ በራሱና ብቻውን ምንም ዋጋ የለውም፡፡ “የማያዛልቅ ጸሎት ለብራቅ ይዳርጋል” የሚባለውም ለዚህ ይመስለኛል፡፡ ጸሎትና ፆም ከሥራና ከእምነት ጋር ሲዋሃድ ፍሬ የሚሰጥ ፍቅርን ያፈራል፤ ፍቅር ባለበት ደግሞ ጠብና ግጭት፣ ዘረኝነትና መድሎ የሉም፡፡ እርሱ እኛ እንድንቀጣ የፈቀደው ወያኔዎችን ወድዶ ወይም እኛን ጠልቶ አይደለም ወይም አይመስለኝም – ሁላችንም የየሥራችንን ነው እያገኘን ያለነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ከገባንበት የዲያብሎስ መንገድ ዛሬ አመሻሽ ላይ ከልብ ከወጣን ነገ ጧትንም ሳይጠብቅ ዛሬውኑ ጨለማው ዐይንን ሳይዝ ጌታ ይምረናል፤ ያኔ የኛ የጋራችን የምንላቸውና ስለኛ የሚጨነቁ ጥሩ ገዢዎችን ይልክልናል፡፡ ለዚያ ያብቃን፤ አሜን በሉ፡፡

መጸዳጃ ቤት ውስጥ ተቀምጦ ግን ሠገራ ሸተተኝ ቢባል አስቂኝ ተውኔት ከመሆን አይዘልም፡፡ ስለዚህ ከየተወሸቅንበት ሥርቻ እንመለስና ሰው እንሁን፤ ከግል ጥቅም ይልቅ ለወል ጥቅሞች እንበርታ፡፡ ለኔ ከሚል ፍልስፍና ወጥተን የኛ እንበል፡፡ ደግሞም አንናናቅ፡፡ የዐማራ ኤሊት አንዱ መሠረታዊ ችግር በባዶ መኮፈስና ወንድም ወንድሙን መናቅ ነው፡፡ ተማርክ አልተማርክ የት ትደርሳለህ? ሞትን አታሸንፍ፤ እንኳንስ ሀገርህንና ወገንህን አንተ ራስህንም ከድህነት አላወጣህ፤ ከወያኔ የጥላቻ ፖለቲካ አልዳንክ፤ ከስደት አልተረፍክ፤… ታዲያ አጉል መጀነኑ ምን ይጠቅምሃል? ባልተማሩ ወገኖችህስ ላይ ለምን ትኮራለህ? ብትማር ለራስህ ነው፤ ብትሰልጥን ለግልህ ነው፤ ብትኮነን ለነፍስህ፣ ብትከብር ለሥጋህ፡፡ አዎ፣ ብዙ በጣም ብዙ ነገር መናገር ይቻል ነበር – ግን አኩራፊን ለመቀነስ ሲባል በዚሁ ይብቃኝ፡፡ ለዚህ ጽሑፍ ያነሳሳኝ ጽሑፍ ቀጣዩ ነው፡፡ ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ፡፡[ሼራተን አዲስ በተደረገ ጉባኤ ላይ ያቀረብኩት ጽሑፍ አልመሰለም?]

     እንዲያው ግን ለነገሩ በተለይ አማራ “እግዚአብሔርን ምን ያህል ብንበድለው ነው በእነኝህ ጉዶች አስወርሮ ያዋረደንና ፍዳችንን እያበላን ያለው?” ብላቹህ ጠይቃቹህና ወደ ውስጣቹህ ተመልክታቹህ ታውቃላቹህ? እኔ “ሲያንሰን ነው” ነው የምለው፡፡ ይገርማቹሀል ዘመዶቸ ወያኔን ያህል የሀገርና የሕዝብ ጠላት እያለ በማይረባ በኢምንቱ ነገር እየተጣሉ ተጋድለው አለቁብኝ፡፡ የወንድማማች ልጆች ደም ለመመላለስ የሚጠቀሙትን የሚያባክኑትን የሚፈጁትን ቁርጠኝነት፣ ወንድነት፣ እልህ፣ ጽናት፣ ዘዴ፣ ብልጠት፣ ስልት፣ ንቃት፣ ትጋት፣ ጭካኔ ወዘተረፈ. ብትመለከቱ ጉድ ነው የምትሉት፡፡ ወንድም የገዛ የሥጋ ወንድሙን ለመግደል፡፡

ይሄ የኔ ዘመዶች ገጠመኝ የሁሉም የአማራ ሕዝብ ገጠመኝ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እግዚአብሔር የጨከነው የተናቀውን ወያኔን ከትቢያ አንሥቶ ያመጣውና የሚያስቀጠቅጥህ፣ ሰማይንም ለጉሞ በረሀብ የሚቆላህ ወዘተረፈ. በዚህ ኃጢአትህ ነው፡፡ በርካታ የንጹሐን ደም በከንቱ ፈሷል እየፈሰሰም ነው፡፡ አማራ እድሜውን የፈጀው እርስ በእርሱ ወንድም ወንድሙን ለመግደል በማድባትና በመግደል ነው፡፡ የበርካታ ንጹሐን አቤሎች ደም በእግዚአንሔር ፊት ጮኸ እግዚአብሔር ሰማ እንዲያና እንዲያ ያለ መከራም ታዘዘብህ፡፡

የዓረብ መተተኞች ወይም ቃልቾች ናቸው አሉ አማራን እንዲሁ ባረባው ነገር እርስ በእርሱ አጋድሎ አፋጅቶ የሚያጫርስ የአጋንንት መንፈስ በየዘመኑ እየላኩ እንዲህ እጅግ በሚገርም ሁኔታ እንኳን ለመጋደል አይደለም የጎሪጥ ለመተያየትም እንኳ በማያበቃ የማይረባ ምክንያት ወንድም ወንድሙን እየገደለ እንዲተላለቅ ያደረጉት፡፡ ሱዳን ተሰዶ ይኖር የነበረ አንድ አብሮ አደጌም ልጃቸውን ሊያገባ የነበሩትን አንድ ሀብታም ሱዳናዊ ሸክ ይሄንን እንደሚያደርጉ የነገሩትን ይዞ እሱም ነግሮኛል፡፡

ሕዝባችን ይሄንን የሚላክበትን የአጋንንት መንፈስ በመንፈሳዊነቱ እንዳይከላከልም ከግራኝ አሕመድ ወረራ ወዲህ ሕዝቡ አስቀድሞ የነበረው መንፈሳዊ ሕይዎት የ15 ዓመቱ የግራኝ የጭፍጨፋ ዘመን ባደረሰው ውድመት ቅዱሳት መጻሕፍት ተቃጥለው መምህራንና አባቶችም ተሰይፈው በማለቃቸው የሚያስተምረው የሚመክረው የሚገስጸው የሚሰብከው መንገድ የሚመራው አባትና መምህር በማጣቱ ከወረራው በኋላ እንደ ውሽማ መያዝ፣ ማመንዘር፣ ለባዕድ አምልኮ መገዛት፣ ለሟርት ለመተት ለጥንቆላ መገዛት በመሳሰሉት ያልተገባና ኢክርስቲያናዊ ወይም አረማዊ ግብሮች በመርከሱ በአብዛኛው ሕይዎቱ ዘልማዳዊ በመሆኑ ዙሪያችንን ከበውን ያሉት የዓረብ መጥቁሎች ወይም ቃልቾች የሚልኩበትን እርስ በእርስ የሚያፋጅ የአጋንንትን መንፈስ መከላከል ድል መንሳት ወይም በእነሱ አለመያዝ መይም ማደሪያ አለመሆንና ያሻቸውን እንዲፈጽም እንዳያደርጉት ማድረግ አልቻለም፡፡ ተሸነፈ ተረታ ይሄው እንደምናየው ለሰሚው ግራ በሆነ መንገድ በማይረባ ነገር ነፍስን ያህል ነገር እየተጠፋፋ ለመኖር ተገዷል፡፡

እንግዲህ ግራም ነፈሰ ቀኝ ውጊያው ከአጋንንት ጋር እንደመሆኑ ይሄንን የአጋንንት ውጊያ መመከትና ድል መንሳት የሚቻለው እግዚአብሔርን በመያዝ በመሆኑ የሚቻላቹህን ያህል ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ፣ ንስሐ እንዲገባ፣ አርስ መእርስ እያተጋደለ አንድያ ነፍሱን በከንቱ ከሚያጠፋት በሀገሩ በሃይማኖቱና በሕዝቡ ጠላቶች ላይ እንዲያነጣጥር ብትመክሩ ብታስተምሩ ብትመክሩና ብትጸልዩ መልካም ነውና እባካቹህ እባካቹህ ወገናችን እርስ በእርሱ ተባልቶም በጠላት ተፈጅቶም ከማለቁ በፊት ይሄንን በማድረግ ትጉ???

 


አርበኞች ግንቦት 7 በአርባ ምንጭ 20 የመንግስት ወታደሮችን ገደልኩ ባለ ማግስት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አሜሪካ ገቡ

$
0
0

Dr Birhanu Nega

(ዘ-ሐበሻ) በአርባ ምንጭ 20 የመንግስት ወታደሮችን ገድያለሁ ያለው አርበኞች ግንቦት 7 ሃገር ቤት ውስጥ እያደረገ ያለው እንዲህ ያለው ትግል እንደሚቀጥል በገለጸበት ማግስት የድርጅቱ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለሥራ ጉዳይ አሜሪካ መግባታቸው ተሰማ::

የአርበኞች ግንቦት 7 የዜና ምንጮች እንደገለጹት ፕሮፌሰሩ በአሜሪካ ቆይታ ካደረጉ በኋላ ወደ አውሮፓ ጁን ላይ ጉዞ ያደርጋሉ::

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደም ከአስመራ ወደ አሜሪካ በመጡበት ወቅት “ትግላችን ያለው ሃገር ቤት ነው” ያሉ ሲሆን ትላንት ለኢሳት ራድዮ በሰጡት መግለጫ “ቃላችንን እያከበርን ነው… በአርባምንጭ እንደወሰድነው እርምጃ በተለያዩ ቦታዎች እርምጃዎችን እንወስዳለን” ብለዋል::

አርበኞች ግንቦት 7 በመንግስት ወታደሮች ላይ እንዲህ ያለውን ጥቃት በአርባምንጭ ከወሰደ በኋላ የሥርዓቱ ደጋፊ የሆኑ ግለሰቦች ካሁን በኋላ “ፕሮፌሰሩ አሜሪካ አይመጡም; አሜሪካ እንዲህ ያለውን የግንቦት 7 ድርጊት አትደግፍም”እያሉ አስተያየት ሲሰጡ ቢቆዩም ፕሮፈሰሩ ግን ለሥራ ጉዳይ እዚህ ገብተዋል::

Sport: ቸልሲ ጆን ቴሪ ለአንድ ዓመት ያህል እንዲቆይለት ጠየቀ

$
0
0

johnterry

(ዘ-ሐበሻ) ከቸልሲ ጋር 703 ጨዋታዎችን ያደረገው አንጋፋው ተከላካይ ጆን ቴሪ በስታንፎርድ ብሪጅ የሚያቆየው ኮንትራት የሚጠናቀቀው በዚህ ሲዝን መጨረሻ ላይ ሲሆን ክለቡ ተጫዋቹ ለአንድ ዓመት ያህል እንዲቆይለት ጥሪ ማቅረቡን የ እንግሊዝ ጋዜጦች ዛሬ ዘግበዋል::

እንደዘገባዎች ከሆነ የ35 ዓመቱ ጎልማሳ ጆን ቴሪ በክፍተኛ ገንዘብ ክፍያ ለቻይና ክለብ ሄዶ በሚቀጥለው ሲዝን ይጫወታል ተብሎ እየተጠበቀ ሲሆን በቸልሲ ለቀረበለት የ አንድ አመት ኮንትራት ማራዘሚያ ለ እርሱና ለቤተሰቡ ትልቅ ውሳኔ ይሆናል ተብሏል::

ቸልሲን ከጆሴ ሞሪንሆ ተረክበው በጊዜያዊነት ያሰለጠኑት ጉስ ሂዲኒክ በሚቀጥለው ዓመት ክለቡን ከሚይዙት ጣሊያናዊው አንቶኒዮ ኮንቴ ጋር ከተወያዩ በኋላ በክለቡ ውስጥ ትላልቅ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች እንዲኖሯቸው ይፈልጋሉ:: በዚህም የተነሳ ጣሊያናዊው ኮንቴ ጆን ቴሪን በቀጣዩ ሲዝን ከክለባቸው ማጣት እንደማይፈጉ ጋዜጦቹ ዘግበዋል::

ጆን ቴሪ ቸልሲ በፕሪምየር ሊጉ በስታንፎርድ ብሪጅ ከሌስተር ሲቲ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ በቅጣት ምክንያት አይሰለፍም:: ቸልሲን ለመልቀቅ ከወሰነም ከደጋፊው ጋር ዳግም ላይገናኝ ይችላል::

“በሊቢያ ዳግም አንገታቸውን የተቀሉ ኢትዮጵያውያን አናውቅም ! ”ኢትዮጵያውያን ከሊቢያ

$
0
0

የማለዳ ወግ… “በሊቢያ ዳግም አንገታቸውን የተቀሉ ኢትዮጵያውያን አናውቅም ! ” ኢትዮጵያውያን ከሊቢያ
================================

* ከየትኛውም ISIS የመረጃ ምንጭ መረጃው አልተሰራጨም
* ” 16 ኢትዮጵያውያን ተቀሉ የሚለው መረጃ ጭብጥ የለውም! ” የአረብ ጋዜጠኞች

ከነቢዩ ሲራክ

File Photo

File Photo

በአለም ላይ ማንም የማይስተካከለው ጨካኙ ISIS በሊቢያ ዳግም ኢትዮጵያውያን ክርስትያኖች ለይቶ መቅላቱን በሚመለከት የተሰራጨው መረጃ መሰረት የሌለው መሆኑን ካደረግኩት ማጣራት ለመረዳት ችያለሁ ። ከትናንት ምሽት እስከ ዛሬ ማለዳ ትክክለኛ መረጃውን ለማግኘት ካደረግኳቸው ቀዳሚ ማጣራቶች መካከል ከወደ ሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ማነጋገርና እዚህ በአረቡ ሀገር ለመረጃው ከቀረቡት መረጃ ማፈላለግ ነበር ።

ኢትዮጵያውያን በሊቢያ …
================
በዋና ከተማዋ በትሪፖሊ ያገኘኋቸው ወገኖቸን መረጃውን ሰምተው እነሱም ግራ መጋባታቸውን ገልጸው ፣ ወደ ኋላ አጣርተው ስለደረሱበት መረጃ በሰጡኝ መላሽ እንዲህ ብለዋል ” እርግጥ ነው ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለን ኢትዮጵያውያን ለተሻለ ኑሮና በፖለቲካው ግፊት ከሀገር እየተሰደድን ነው ፣ በስደቱ መከራ እየተንገላታን ያለበት ሁኔታ የከፋ ነው … ከዚህ ውጭ 16 ኢትዮጵያውያውን አንገታቸው ተቀላ ተብሎ በ Press Tv የቀረበው መረጃ ምንም ማረጋገጫ የለውም ፣ ዳግም አንገቱን የተቀላ ኢትዮጵያዊ አናውቅም !” በማለት በዝርዝር ስለ ስደቱ ሰቆቃ ሲናገሩት አንገት ከመቀላት በላይ የሚያመውን የስደት ሰቆቃ በተጎዳ ስሜት አውግተውኛል ! እኒሁ ኢትዮጵያውያንን ትናንት ምሽት አግኝቸ አንገታቸው ተቀላ ስለተባሉት ኢትዮጵያውያን ጉዳይ እንዲያጣሩልኝ በጠየቅኳቸው መሰረት የደረሱበትን ሁኔታ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አድርሰውኛል። በተለይም በሁለተኛዋ የሊቢያ መዲና በጠረፍ ከተማዋ በቢንጋዚና በተለያዩ ከተማዎች ያሉ ኢትዮጵያውንን ስልክ በመደወልና በማጣራት ባደረሱኝ መረጃ መሰረት ” በእስከ አሁኗ ሰዓት ባለን መረጃ በሊቢያ በ ISIS አንገታቸው የተቀላ ኢትዮጵያውያን የሉም !” በማለት አስረግጠው ነግረውኛል !

የድረ ገጽ ባለሙያዎችና የአረብ መገናኛ ብዙሃን …
=================================
ሌላው መረጃውን ያጣራሁት በአሸባሪው ISIS ድረ ገጽ የተቀሉትን ኢትዮጵያውያን በሚመለከት መረጃ ተላልፎ እንደሁ ማጣራት ነበር። በዚህ ዙሪያ ጥልቅ ፍተሻ ያደረጉ የዘርፉ ባለሙያዎች በየትኛውም የአሸባሪው ISIS ቡድን ድረ ገጾችና የመረጃ ማቀበያ መንገዶች ” በሊቢያ 16 ኢትዮጵያውያን አንገት ቀልቻለሁ !” የሚል መረጃ አለማሰራጨቱን ከባለሙያዎች አረጋግጫለሁ ። ከዚህ ጋር በተያያዝ ዜናውን ለማጣራት እስከ እኩለ ሌሊት ጥረት ተደርጎ ማረጋገጥ አለመቻሉን አንድ ከፍተኛ የአረብ ኒውስ ጋዜጣ አዘጋጅ ወዳጀ ገልጸውልኛል ። የተሰጨውን መረጃ ማረጋገጥ ባለመቻሉም አረብ ኒውስ በዛሬው የማለዳ እትሙ መጨበጫ የሌለውን ዜና ይዞ ለመውጣት አለመፍቀዱን አስረግጠው ነግረውኛል !
ይህም ሰናይ መረጃ ነው !

የእኛ ስጋት ፣ ጭንቀትና የመንግስት የሀዘን መግለጫ …
====================================
ትናንት ከቀትር በኋላ የመረጃ ግብአት ” ISIS በሊቢያ 16 ኢትዮጵያውያን አረደ !” የሚለው ስጋትና ጭንቀት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነበር ፣ እናም ” ያልተረጋገጠ ዜና ነው!” የሚል አንድምታ ያለው መረጃ እኔም ሆንኩ በርካቶች ያገባናል ያልን ወገኖች ሰፋ ያሉ መረጃዎችን ከነማስረጃቸው አቅርበን ነበር ። በተለይም የኢራኑ Press TV እና የብሪታንያው Express የዜና አውታሮች ያሰራጩት መረጃ ብዙዎችን ማጋባቱን አውስተን ከዚህ በኢትዮጵያውያን ላይ ከዚህ በፊት በሊቢያ የተፈጸመውን ግድያ የሚያሳይ ፎቶ ይዘው ከወጡት የዜና አውታሮች ባለፈ መረጃውን እስካሁን ያረጋገጠ አለመኖሩን ጠቁመንም እንደነበር አይዘነጋም ። በግል እዚህ ሳውዲ ሳውዲ ከሚገኙ የአል አረቢያና የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ዘጋቢዎችና ከሳውዲ አረብ ኒውስና ሳውዲ ጋዜጥ ታዋቂ ጋዜጣ አዘጋጆች ለማጣራት ሙከራ አድርጌ መረጃው ያልተረጋገጠ ተባራሪ ሊሆን እንደሚችል መጠቆማቸው አይዘነጋም !

በኢራኑ የ Press Tv የተሰራጨውን መሰረት የሌለው ዜና በመመርኮዝ በሊቢያ ውስጥ ዳግም በኢትዮጵያውያን ላይ ተፈጸመ የተባለውን ግድያ በሚመለከት የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ የሀዘን መግለጫ ለኢትዮጵያውያንና ህዝብና ለሟች ቤተሰቦች ማስተላለፋቸው ይጠቀሳል ፣ ሳሩ ግን የሀዘን መግለጫው ከተጨበጠ መረጃ ጋር የተገናዘበ አይደለም በሚል ብዙዎችን ግራ ማጋባቱ ይጠቀሳል !

የእስካሁኑ የተጨበጠ መረጃ ይህ ነው …ለሁሉም በሊቢያው ስደት በጭንቅ ላይ ያሉት ወገኖች መከራና ጻዕር ከባድ ነው …” አንድ ፊቱን አንገቴ ተቀልቶ ሰማዕት በሆንኩ ይሻል ነበር … ” ያለኝን ወንድም መከራ የመስማት ህመምን ያማል ፣ ያማል ብሎ መግለጽ አይቻለኝም ! አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ አውጭ ሆኛለሁ … frown emoticonለሁሉም ከአገር አልባ ስሜት ያድነን ፣ ለሁሉም በጸሎት መትጋት ይመከራል …

አቤቱ ! የከፋውን መርዶ አታሰማን … አቤቱ ! በምህረትህ ጎብኘን … አቤቱ ! የተባረከ የተቀደሰ ቀን ያድርግልን … !

ነቢዩ ሲራክ
ግንቦት 5 ቀን 2008 ዓም

ዘ-ፀዓት!….ውጣ!

$
0
0

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1500  ዓመተ ዓለም አንድ የነጻነት መሪ ነበር። በዘመናዊ የማኔጅመንት ትምህርት ውስጥ የስራ ክፍፍልን የፈጠረና መሰረት የጣለ ትልቅ ሰው ነው።  ይህ ሰው የተወለደው በጭንቅ ሰዓት ነበር። እስራዔላውያን በግብጽ ምድር በባርነት ቀንበር ስር ባሉበት ሰዓት። ንጉስ ፈርዖን የእስራዔላውያንን የጥበብ ስራዎች፣ የሚሰሯቸውን ጡቦች ቢወድም ነገር ግን በቁጥር እየበዙ ከመጡ መንግስቴን ይነጥቁኛል ብሎ ስለፈራ ህጻናትን ሁሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ የተላለፈበት የጨለማ ዘመን ነበር። በዚህ ወቅት የተወለደው ይህ ሰው ወላጅ እናቱ በዓባይ ወንዝ ላይ በእንዲት ቅርጫት ኣሳፈረችው። መደበቋ ነው። በርግጥም ከወታደሮች ሰይፍ መትረፍ ችሏል። ለሶስት ወራት በዚህ ሁኔታ ወላጅ እናቱ ደበቀችው። ታዲያ ከእለታት ኣንድ ቀን ልእልት እየችው:: ልእልት ይህን ህጻን ስታየው ያማረ ነበርና ቤተመንግስት ያድግ ዘንድ ተደረገ። እድለኛ ነው ቢባልም ከፍ ሲል እብራዊነቱን ኣጥብቆ ያዘ።ሙሴ በንጉስ ቤት ከሚኖረው ኑሮ ይልቅ የወገኖቹ የባርነት ኑሮ ያንገበግበው ነበርና የፈርዓን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢኝ ኣለ።

Ze tseat

ሙሴ በአካልም በመንፈስም ከጠነከረ በሁዋላ የእብራውያን ከግብጽ መውጣት ጉዳይ በጣም በራለት። መውጣት አለብን አለ……..ዘ-ፀዓት ልቡን ሞላው። የዓያቶቹን የተስፋይቱን ምድር ከነዓንን ናፈቀ። ወተትና ማር የምታፈልቀው የአባቶቻቸው ምድር ከነዓን ወለል ብላ ታየችው። ቅስቀሳዎችን ጀመረ….. እብራውያን የዓያቶቻቸውን ምድር ማሰብ…. ማሰላሰል ጀመሩ። ከነዓንን ያቺን የተስፋይቱን ምድር………

 

እብራውያን የግብጽ ባርነት ኣሰቃይቷቸው ነበርና የተስፋ ምድራቸውን ናፈቁ—ናፈቁ ያለ ልክ። ሙሴ ወገኖቹን በመወከል ብዙ ጊዜ በንጉስ ፍርዖን ፊት ቆመላቸው…..ሽንጡን ገትሮ ተሟገተላቸው። ይሁን እንጂ ፈርዖን የነዚህ ጥበበኞች ጥበብና ጉልበት ጥሞት ነበርና እምቢኝ  ኣለ። እግዚአብሄር የግብጻውያንን የበኩር ልጆች ሁሉ መግደል ሲጀምር ፈርዖን እጅ ሰጠ። ከዚህ በሁዋላ ሙሴ ኣንድ ቀን ህዝቡን ይነሱና ግብጽን ለቀው ይወጡ ዘንድ ጥሪ ሲያደርግ በእብራውያን ዘንድ ፈንጠዝያ ሆነ። እስራዔላውያን የተስፋ ምድራቸውን ለማየት እጅግ ቋምጠው ነበር። ከዚህም የተነሳ የውጡ (exodus) ደወል ሲመታ ሊጋግሩት ያቦኩትን የዳቦ ሊጥ እንኳን በዚያ የባርነት ኣገር ውስጥ ሊያበስሉት ኣልፈለጉም። ጨርቃቸውን እያንጠለጠሉ ከነሊጣቸው ወጡ። ለነጻነት ቸኩለው ነበርና። ለከነዓን ለተስፋ ምድራቸው ቸኩለው ነበርና ነው። ሙሴ የወገኖቹ ብሶት የገባው ቆራጥ መሪ ስለነበር ንቅናቄውን መርቶ ጉዞ ጀመሩ። እነዚህ ባለ ተስፋ ህዝቦች ተስፋን ሰንቀው ወደ ከነዓን ጉዞ በጀመሩ ለታ በነጻነት ኣየር ውስጥ ናቸው። ይሁን እንጂ ግን ወደ አገራቸው ገብተው ተረጋግተው ለመኖር ገና በጉዞ ላይ ናቸው። ታዲያ ግን ጉዞው የሚፈጀው ሁለት ሳምንት ገደማ ቢሆንም በሚገርም መልኩ አርባ አመት ፈጀባቸው። በርግጥ ሙሴ እጅግ ግልጽ የሆነ መድረሻ ቢኖረውም፣ ከባርነት ሰፈር በመውጣቱ ጉዳይ ላይ የማይናወጥ ኣቋም ቢኖረውም ፣ ግልጽ መነሻ ቢኖረውም ወደዚያ ወደ ተስፋቸው ምድር በሚወስደው ካርታ (Roadmap) ላይ ግን የተጨነቀ ኣይመስልም። ምን ኣልባትም ከመነሻውም መነሻና መድረሻውን ቢያውቅም በመሃል ወደዚያ በሚወስደው መንገድ ላይ ግልጽ መረጃ ያለው ኣይመስልም። መድረሻውና መነሻው መስጠውታል:: የግብጽ ኑሮ ወገኖቹን ያለ ልክ ጎድቷልና  የመውጣቱ ጉዳይ ብዙውን ሃይሉን ሳይወስድበት ኣይቀርም ይሆናል። እናም የኣስራ ኣንድ ቀን ጉዞ ኣርባ ኣመት ፈጀና ብዙ ትውልድ ከነዓንን ሳያይ ቀረ። ይሁን እንጂ ግን ነጻነታቸውን በጉዞ ላይ ሳሉም ቢሆን ተቀዳጅተው ነበር። እብራውያን በጉዞው ተሰላችተው ወደ ግብጽ መልሰን ብለው ሙሴን የጠየቁት በርግጥ የግብጽን ኑሮ ናፍቀው ኣይደለም። ሙሴን እልህ ውስጥ በማስገባት ቶሎ ካርታውን ኣስተካክሎ ኮምፓሱን ኣስተካክሎ ወደ ኣባቶቻቸው ምድር እንዲያስገባቸው ነው እንጂ እብራውያን ከግብጽ ኑሮ ሞትን መርጠዋል።ወደ ግብጽ ከመመለስ በዚያው በምድረ በዳ የእምላካቸውን መና እየበሉ ቢኖሩ እጅግ ይሻላቸዋል።  ይሁን እንጂ ሙሴ እንዴት ወደከነዓን መግባት እንደሚቻል አምላኩንም ሲጠይቅ ስለ ካርታው ሲጨነቅ ኣይታይም። ያንን በምድረ በዳም ቢሆን ያገኙትን ነጻነት እያየ ረክቶ ተዘናጋ ይሆን፣ ከሰማይ የሚወርደውን መና እያየ ቶሎ ወደ ተስፋይቱ ምድር በመግባቱ ጉዳይ ላይ ብዙ ሳይጨነቅ ቀረ ይሁን ኣይታወቅም። ብቻ ግን አዘገያቸው።

 

የሙሴ ታሪክ ለኛ ለኢትዮጵያውያን ኣስተማሪ ሆኖ ኣየሁትና ነው ይህን ኣሳብ ያስቀደምኩት እንጂ ስብከት ኣምሮኝ እውቀቱ ኖሮኝም ኣይደለም። መጽሃፉን በሚገባ የሚያውቁ ሰዎች እንዴት እንደሚገልጹት ኣላወቅም። የሆነ ሆኖ ግን ለዛሬው የኢትዮጵያ የነጻነት መሪዎችና ለኛም ይህ ታሪክ ተምሳሊታዊ ኣስተማሪነት ኣየሁበት። ውጣ (exodus) የሚለው ቃልም በርግጥ መሰጠኝ። ወቅታዊ ጥሪ መስሎ ተሰማኝ።

የኢትዮጵያ ዘ-ፀዓት

አገራች ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ደረጃ ጊዜ ሳትወስድ ልትወጣባቸው የሚገባት ጉዳዮች ኣሉ። ትውልዱ የውጣ ስሜትን ሊያመጣ የሚገባበት ዘመን ላይ ነን። ውጣ ሲባል ከምን ከምን ልንል እንችላለን። ኣንደኛው ከጎሰኝነት እስራት፣ ሌላው ከጥላቻ ፖለቲካ፣ ሌላው ከድህነት፣ ሌላው ከአምባገነኖች ጭቆና፣ ከኣደገኛ ባህሎች ሁሉ ነው የውጣ ክተት ኣዋጅ መትተን ልንወጣ የሚገባው። ነገር ግን መውጣት ብቻ ኣይደለም። ከጎሰኝነት ወጥተን በምን ኣይነት የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ እንደምንገባ ግልጽ የሆነ መድረሻ ሊኖረን ይገባል። ሙሴ መድረሻው ግልጽ ነበር። የኛ ፖለቲካ ችግር ሁላችን መውጣት እንዳለብን ብናይም በመድረሻችን ላይ ብዙ ግልጽ ያልሆኑ ነገሮች ኣሉ። መድረሻችንን በሚገባ ሳናውቅ ከቀረንና “የሚጋጩ ህልሞች” ካሉን በርግጥ ለመውጣት እንቸገራለን። ሌላው የፖለቲካችን ችግር ደግሞ ወደ ለውጥ የሚወስደንን መንገድም እንዲሁ ግልጽ ሆኖ ያለማየት ችግር ነው። ለመውጣት (exodus) ሶስት ነገሮች ያሻናል። ኣንደኛው የመውጣት ኣዋጅ፣ ግንዛቤ፣ ህዝባዊ ንቅናቄ ነው። ይህን ንቅናቄ ደግሞ ወደ ተሻለች የኣዲስ ኪዳን ኢትዮጵያ ቤት ውስጥ የሚወስድ መሆን ኣለበት። ኣዲሲቱን ኢትዮጵያን በኣይምሯችን ስለን ሲስተሙን በተግባር ኣይተነው ልንቋምጥለት ይገባል። ያ ነው የመውጣታችን ሃይል የሚሆነው። እስራዔላውያን ስለተስፋ ምድራቸው ሲሰሙ፣ ኣገር የሌላቸው ሳይሆኑ ነገር ግን ከሁሉ የበለጠ ምድር እንዳላቸው ሲገነዘቡ ለመውጣት ትልቅ ሃይልን እንዲሰንቁ ኣድርጓቸዋል። ኣገር እንደሌለው እንዴት እንደዚህ እንሆናለን፣ ጥበብ እያለን እንዴት እንዲህ ባሪያ እንሆናለን የሚለው ስሜት እብራውያንን ጨርቅ ያስጣለ፣ ከነሊጣቸው እንዲወጡ ያደረገ ትልቅ የለውጥ ሃይል ነበር። በመሆኑም ኢትዮጵያ ሃገራችንም ኣዲሲቱ ኢትዮጵያ የቡድኖችን ማንነት ሳትጨፈልቅ፣ ቋንቋዎችንና ባህልን ኣክብራ የምትኖርበትን ስርዓተ-መንግስት ሰርታ ስታሳይ ወጣቱ ለለውጥ ይነሳል። ያ ትውልድ የሚባለው ወጣት ቀልቡን የሳበው ኣንድ ጉዳይ ኣንድ ያየው መድረሻ ስለነበር ነው። የሶሻሊዝም ትምህርት የሚፈጥረው ስእል(image) በወጣቱ ኣይምሮ ውስጥ ተስሎ ነበር። ገነት የሆነች ኢትዮጵያን ሳያዩ ኣይቀሩም። ለነገሩ ሶሻሊዝም የዓለምን ወጣቶች በየኣገሩ ኣሳብዶ ነበር። የሚያሳየው ዓለም ያማልላል። መንግስተ ሰማያትን እዚህ መሬት ላይ ኣምጥቶ ያሳያል። እኩልነት የሰፈነባት ዓለም፣ የኔ የኔ የሌለባት ዓለም፣ ድሃና ሃብታም የማይባልባት ዓለም፣ ሰላም የሰፈነባት የበለጸገች ኣለምን በጥሩ የስነ ጽሁፍ ቋንቋ ያሳያል። ነገር ግን ያ ዓለም ምናባዊ በመሆኑና ወደዚያ የሚያደርሰው መንገድ የተሳሳተ በመሆኑ ሩቅ ሳይሄድ ሰዎች እየተገነዘቡት ቀዝቀዝ ኣሉ። ስለሆነም ወደ ኣዲሲቱ ኢትዮጵያ የመውጣት ንቅናቄ ለማድረግ መጀመሪያ ተጨባጭ የሆነች የተሻለች ኢትዮጵያን በተለይ መሪዎች ሊያዩልን ይገባል።

 

ሃገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት ዙሪያ መለስ ችግሮች ለመውጣትና የተሻለ ዓለም ለማየት ፖለቲካዊ ለውጥ ብቻውን ኣይበቃትም። ፖለቲካዊ ለውጥ ብቻውን ይጠባል። የግድ ሁለንተናዊ ለውጥ ውስጥ መግባት ኣለብን። ማህበራዊ ለውጥ ውስጥ መግባት ኣለብን። ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል ምርት መጨመር ብቻ ሳይሆን የሪሶርስ ኣጠቃቀሟንም ልታሻሽል ይገባል። ያሉብን ችግሮች ማህበራዊ ሲደመር ፖለቲካዊ በመሆኑ የግድ ማህበረ ፖለቲካችን ኣካባቢ ልንወጣ የሚገባን ጉዳዮች ኣሉ። ልክ እስራዔላውያን አንድ ተራራ እየዞሩ የሁለት ሳምንቱ መንገድ ኣርባ ኣመት እንደፈጀባቸው  የብሄር ብሄረሰብ ጥያቄ ኣርባ ኣመት በላይ ፈጅቷል። የመሬት ላራሹ ጥያቄ ከሌላው ዓለም በተለየ ሁኔታ ከኣርባ ኣመት በላይ ፈጅቷል። ኢትዮጵያ ከፊውዳሉ ስርዓት ከተላቀቀች በሁውላ በፍጥነት ልታሻሽለው የሚገባውን ይህን መሰራታዊ ጉዳይ ኣርባ ኣመት ሙሉ ይህን ተራራ ስንዞር ይታያል። ህወሃት ኢህዓዴግ ወደስልጣን ከመጣ በሁዋላ የገባንበት  ስስታም ፖለቲካ ደግሞ ኣንዱ ኢትዮጵያውያን የውጣ ክተት ልናውጅበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ ሃገራችን ከእኔ እኔ እኔ ከሚል ራስወዳድና ጠባብ ኣስተሳሰብ ወጥታ ወደ እኛ ኣስተሳሰብ መግባት ያስፈልጋታል። ከዚህ በፊት ደጋግመን እንዳልነው ኣገር በእኔ… እኔ… እኔ…  ኣይቆምም። የግድ ከዚህ የወጡና ለመስዋእትነት የተዘጋጁ ቡድኖችን ይጠይቃል። ያለንን የቡድን ሃብት ኣጥብቀን ይዘን ደግሞ ኣገር የሚባል ነገር ናፍቆን ኣይሆንም። መውጣት ኣለብን። በሌላ በኩል ትምክህተኝነት ኣስተሳሰብም ከዚሁ ከጠባብነት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ስሜት በመሆኑ ወጣቶች የመውጣት(exodus) ኣዋጅ ሊያውጁበት ይገባል። በነገራችን ላይ   exodus ማለት የግሪክ ቃል ሲሆን በእንግሊዘኛ mass departure ወይም የህዝቡ መነሳትና መውጣት ማለት ነው። ታላቅ ህዝባዊ ውሳኔ የሚጠይቅ ንቅናቄ ነው። የሃገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ ለሃገር የሚቆረቆሩ ሁሉ ወደዚህ ቆፍጣና ስሜት ውስጥ ገብተው ካልተሻገርን አገራችን የተቀመጠችበት ወለል ጥሩ ኣይደለም። የራሷ ኣኩሪ ታሪክ ያላት ኣገር እንዴት በኛ ዘመን እንዲህ ትሆናለች? ብሎ መቆጨት ያስፈልጋል። አንድ ጊዜ ፌስ ቡክ ላይ ኣንድ ነገር ኣየሁ። የላሊበላን ውቅር ቤተክርስቲያን ያየሰው እንዲህ ይላል። ይህ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያዊ ሊሰራ ኣይችልም ምናልባት  የሚሆነው ኣንድ የውጭ ኣገር ዜጋ መጥቶ ሰርቶላቸው ሄዶ ነው ይላል። ይህ ሰው እንዲህ እንዲል ያደረገው ነገር ኣሁን ያለንበትን ድህነትና ዓለም ከደረሰችበት ኣንጻር እኛ ወደ ሁውላ መቅረታችን ነው። ዛሬ ላይ ስንታይ ያንን የመሰለ ጥበብ የነበረን ሰዎች  ኣንመስልም ማለት ነው። ለነገሩ ግን ይህ ሰው መገንዘብ ያለበት ያ የውጭ ኣገር ዜጋ ይህን መስራት ከቻለ ለምን ራሱ ኣገሩ ላይ ኣልሰራውም ነበር? ይህን የሚመስል ወይም የተሻለ የመስራት ጥበብ ከነበረው በሃገሩ ከዚህም የተሻለ ተሰርቶ ባየን። ነገር ግን ይህ ጥበብ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የተገኘው፣ ለዚህም ነው የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበው። በትክክልም የኛው ኣባቶች ስራ ነበር። በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ስንዞር ኣሰደናቂ ጥበቦች ይታያሉ። የኣባቶች ስራ ነው። የራስ ፈደል መኖር ትልቅ የስልጣኔ መሰረት ነው። ኢትዮጵያ ተወዳዳሪ የነበረች የሰለጠነች እንደነበረች እነዚህ ጥበቦች ህያው ምስክር ናቸው። ይሁን እንጂ ኣሁን ያለው ትውልድ በብሄር ብሄረሰብ ጥያቄ ዙሪያ ኣንድ ተራራ ኣርባ ኣመት ሙሉ ይዞራል። ዞሮ ዞሮ ተመልሶ ትናንት ያደረበት ቦታ ሲያድር ኧረ ይሄ ቦታ ትናንት መጥተንበት ነበር ተሳስተናል ኣይልም። ዝም ብሎ ይዞራል። ከዚህ ነው መውጣት ያለብን። ወጣቶች በልበ ህሊናቸው የመውጣትን ስሜት ካልጻፉ፣ ከባርነት መቼም ኣንወጣም።

 

አብያተ ክርስቲያናትና የባህል መሪዎችም ኣዋጅ ሊያሰሙ ይገባል። ዘ-ጸኣት ሊያውጂ ይገባል። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በኣንዳንድ ቡድኖች ኣካባቢ ከፍተኛ የሆነ የኔጌቲቭ ሶሻል ካፒታል ክምችት ኣለ። ያልጠረግነው ብዙ ጎታች ባህል ኣለ። በህጻናት፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ብዙ ባህል ነክ ወንጀል ኣለ። ሰዓትን የማክበር ፈጣን የመሆን ባህል ማዳበር ያስፈልጋል። ፓርቲዎች ህብረትን ሊያጓትቱ ኣይገባም። ኣሳማኝ ምክንያት ለሌለው ነገር ጊዜ መግደል ኣንድ ትልቅ ችግር ነው። በነጻነት ትግል ውስጥ ትልቁ ቁም ነገር ጊዜ ነው። ብዙ እስራዔላውያን ከነዓን ያልገቡት ረጅም ጊዜ እንድ ተራራ በመዞር ስለፈጁ ነው። ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበረሰብ ኣካላት በየፊናቸው የዘጸዓት ኣዋጅ ነጋሪት ሊመቱ ይገባል። በጎጂ ባህል ማስወገድ ኣካባቢ የሚሰሩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ዘጸዓት ሊሉ ይገባል፣ ድህነትን የሚዋጉ ድርጅቶች ዘጸዓት ሊሉ ይገባል፣ የተጨቆኑ ህዝቦችን ከጭቆና ቀንበር ለማላቀቅ የሚጥሩ ፓርቲዎች ዘጸዓት ሊያውጁ ይገባል። ዘጸዓት የፖለቲካ ርእዮት ኣይደለም። ኢትዮጵያውያን ከከበባቸው ዙሪያ መለስ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሁሉ ለመውጣት የሚሰንቁት የሞራል ስንቅ ነው። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ።

 

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አርበኞች ግንቦት 7 በአርባ ምንጭ ስለሰነዘረው ጥቃት ይናገራሉ

$
0
0

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አርበኞች ግንቦት 7 በአርባ ምንጭ ስለሰነዘረው ጥቃት ይናገራሉ

birhanu nega

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live