Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አንድነት፤ አንድነት ስንል ከአራባ ዓመታት በላይ አሳልፈናል —–ፈቃደኛነት ካለ ለመተባበር ይቻላል (አክሎግ ቢራራ (ዶር)

0
0
ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

እኛ ለኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ ቆመናል የምንለው ሁሉ አንድነት፤ አንድነት፤ ህብረት፤ ህብረት ስንል ከአርባ ዓመታት በላይ አሳልፈናል። አንድም ውጤት አላስገኘነም። የፖለቲካ ባህላችን ድርጅትን ፈጥሮ መከፋፈል፤ ማጥፋት፤ መተካትና መጠላለፍ እየሆነ አንዱ ሌላውን በመተቸት ሁለት ትውልዶች አልፈው ሶስተኛውን ጀምረናል። ይህ በአንድ በኩል ተስፋ ሰጭ፤ በሌላ በኩል አድካሚ የፖለቲካ፤ የማህበረሰብና የመነፈስ ባህርይ የጀመረው በንጉሱ ዘመነ መንግሥት በተማሪዎች እንቅስቃሴ ነው። በዚያ ወቅት የነበረው ትውልድ ከራሱ በላይ ለአገሩና ለወገኖቹ የሚያስብ ነበር ለማለት እደፍራለሁ። የአሁኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይተቸው። የብሄረሰብ ፖለቲካም መሰረት የያዘው በዚያ በእኔ ትውልድ አካባቢ ነው። በተከታታይነቱ ሲታይ፤ የኢትዮጵያ ምሁራንና ልሂቃን ባህል ሁለት ወሳኝ የሆኑ ገጽታዎች አሉት። –— [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ}


የዘንድሮዋ ግንቦት 20 –እስክንድር ነጋ ፤ የሕሊና እስረኛ (ከቃሊቲ)

0
0

Eskinder-Nega

ይኸው የወርሃ ሚያዝያ 2008ን የመጀምሪያ ሳምንት አገባደድን:: ግንቦት ተንደርድሮ እየመጣ ነው:: ኢሕአዴግ ሥልጣን የያዘበትን 25ኛ ዓመት ለማክበር ደፋ ቀና ማለት ጀምሯል:: ሩብ ምዕተ ዓመታትን በታላቁ ቤተመንግስት ማሳለፍ ቀላል አይደለም:: የአንድ ትውልድ ዕድሜ ነው:: እንኳን በተማሪዎች አብራክ ውስጥ ለተወለደ ድርጅት ይቅርና፣ በነባሮቹ የኢትዮጵያ ነገሥታት ሚዛንም ረዥም የሥልጣን ዕድሜ ነው:: ሥልጣን ላይ ለረዥም ጊዜ መቆይታቸውን እንደጀብድ ለሚቆጥሩት የኢሕአዴግ ነባር መሪዎች፣ የዘንድሮዋ ግንቦት 20 በተለየ ሁኔታ ጮቤ የሚረገጥባት ናት::

ኢሕአዴግ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ትሩፋት ነው:: ንቅናቄው ከውልደት እስከ ህልፈቱ ከ1953 – 1966 – 13 ዓመታትን አስቆጥሯል:: ከ1966ቱ አብዮት በኋላ፣ የአባላቱ ብርቱ ሕልም ፍሬ አፍርቶ ወደ ተደራጀ የፖለቲካ ትግል ቢያድግም፣ በአንድ ጥላ ሥር ሊያስገባቸው የሚችል መሪ ድርጅት Vanguard Party የሚሉትን መፍጠር ባለመቻሉ ተማሪዎቹ ወደ ተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደጨው ተበትነዋል:: በትህምርት ቤት የነበራቸው መፈቃቀር፣ መተሳሰብ፣ በቅንነትና ተስፋ የውሃ ሽታ ሆኖ፣ ወደ መወነጃጀሉ ፣ ወደ መከፋፈሉ፣ ወደ መካካዱ፣ ወደ መቀኛነቱ፣ ወደ ክፋቱና ወደ መጠፋፋቱ ዓለም ጭው ብለው ገብተዋል::

1

2 001

2

4

5

6 (1) ይህ ሂደት ብልጭ ድርግም እያሉ የኖሩ በርካታ የፖለቲካ ቃላትን አፍርቷል::: አብዮት፣ ኢምፔሪሊያዝም፣ ፊውዳሊዝም፣ ተራማጅ፣ አድሃሪ፣ በዝባዥ፣ ጨቋኝ ፣ ፋሺስት፣ አናርኪስት፣ ጠባብ፣ ትምክህት፣ አምባገነን፣ ዴሞክራሲ፣ ገንጣይ፣ አስገንጣይ፣ አክራሪ፣ ለዘብተኛ፣ ጽኑ፣ ወላዋይ፣ ሐቀኛ፣ አስመሳይ፣ ጀግና፣ ባንዳ፣ ታማኝ፣ ከሃዲ፣ ሃገር ወዳድ፣ ቅጥረኛ፣ ታጋይ፣ ነፍጠኛ፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ ሊብራል ዲሞክራሲ፣ ቦናፖርቲስት፣ ተንበርካኪ፣ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ሕዝቦች፣ ወዘተ::

እነዚህ ቃላት የሚጋሩን የአፍሪቃ ሃገራት ማግኘት በእጅጉ ይከብዳል:: ኢትዮጵያ እንደሃይማኖቶቿ፣ እንደ ምግቦቿ፣ እንደ አላብስቶቿ፣ እንደዜማዎቿ፣ እንደነሥነጽሁፏ፣ እንደ ስዕሎቿ፣ እንደ ታሪኳ፣ እንደ መሬት አቀማመጧ ሁሉ በፖለቲካውም ልዩ ናት::

እንዲህ ዓይነቱን የተለየ ማንነት አሜሪካውያን ኤክሴፕሽናሊዝም (exceptional-ism) ይሉታል:: በብዙ መመዘኛዎች አሜሪካ ኤክሴፕሽናል ናት ብለው ያምናሉ:: በዚህ እሳቤ እስከ ሁለተኛው ዓለም ጦርነት ድረስ ራሳቸውን ከዓለም ፖለቲካ አግልለው ኖረዋል:: በአውሮፓ እንግሊዞች፣ በኤሺያ ጃፓኖች፣ በመካከለኛው ምስራቅ ኢራኖች፣ ይህን ስሜት ይጋሩታል:: በላቲን አሜሪካ “ኤክሴፕሽናል ነኝ” የሚል ሃገር ስለመኖሩ አላውቅም:: ዓለም ላይ ካሉት 200 ሃገራት መካከል በዚህ ምድብ ሊካተቱ የሚሉት ከአስር ቢያንሱ እንጂ አይበልጡም:: ለጥሩም ሆነ ለመጥፎ፣ ስብሰቡ የጥቂቶች ነው::

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄም ከሃገሪቱ ታሪክ ባልተለየ መልኩ ልዩ የሚያደርጉት ገጽታዎች አሉት:: “ሙሉ ለሙሉ የተለየ ነበር” ማለት ግን አይቻልም:: ይህን መንታ ባህሪ “በ66ቱ አብዮት ላይ ጥሩ መጽሐፍ ነው” የሚባለው የጆን ማርካኪስ (John Markakis) – አናቶሚ ኦፍ ኤ ትራዴሽናል ፖሊቲ ( Anatomy of a Traditional Polity) ውስጥ ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል::

ንቅናቄዎን ልዩ ከማያደርጉት ባህሪያቱ መካከል፣ በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በብዙ ሃገራትም የተማሪዎች እንቅስቃሴ የነበረ መሆኑ አንዱ ነው:: በሌላ አነጋገር፣ የተማሪዎች ንቅናቄ የዘመኑ ፋሽን ነበር:: ጆን ማርካኪስ እንዲህ ያስቀምጡታል::
“Radical student agitation was a hallmark of the 1960s in all non-communist Countries Ethiopia Students, eager to imitate western models, naturally became engaged”
“በ1960ዎቹ ( እ.ኤ.አ) ኮሚኒስት ባልነበሩት ሃገራት የተጋጋለ የተማሪዎች ንቅናቄ የዘመኑ መለያ ነበር:: ይህ የምዕራባዊያንን ፈለግ ለመከከተል ጉጉት የነበራቸው የኢትዮጵያ ተማሪዎች የራሳቸውን ንቅናቄ አቀጣጥለዋል” (በcontext የተተረጎመ ነው::)

ልዩ ከሚያደርጉት መካከል ደግሞ ሦስት ባህሪያቱን ማንሳት ይቻላል:: በቀዳሚነት ተማሪዎቹ ለሥልጣንና ለሹመት የነበራቸው ከፍተኛ ጉጉት ይገኛል:: ይህ ጥማት በምዕራዊያኑ ተማሪዎች ዘንድ አልነበረም:: ማርካኪስ እንዲህ ያስቀመጡታል:-

“The First Ethiopians who came back with degrees from abroad had become ministers and ambassadors. Students felt entitled to advance as rapidly. Law and Humanities courses were overflowing. Engineering and since were less appealing. Many students disdained and avoided teaching or other forms of social service in the province.”
“ከውጭ ሃገራት ድግሪ ይዘው ወደ ሃገራቸው የተመለሱት የመጀመሪዎቹ ኢትዮጵያውያን ሚኒስተሮችና አምባሳደሮች ሆነዋል:: (እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ የነበሩት) ተማሪዎችም “በዚያው ፍጥነት የማደግ መብት አለን” የሚል ስሜት ነበራቸው:: (በተማሪዎቹ ዘንድ) ምህንድስናና ሳይንስ ብዙም ተፈላጊ አልነበሩም:: ወደ ክፍለሃገር ሄዶ ማስተማርም ሆነ ማህበራዊ አገልግሎት መስጠትን ይጠሉና ይሸሹ ነበር::”

በዚያ ዘመን የነበረው ቢሮክራሲ ግን፣ እንኳን ሚኒስትርና አምባሳደር ሊያደርጋቸው ቀርቶ ፣ የተመረቁትን ሁሉ ተቀብሎ ሥራ ለመስጠት እየተንገዳገደ ነበር:: የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ፣ “ከምረቃ በኋላ ሥራ እናጣለን” ብለው የሰጉ ተማሪዎች ንቁ ተሳትፎ ያደረጉበት ነበር:: ተማሪው ለሃገርና ለሕዝብ ብቻ ብሎ አልተነሳም::: ከኢትዮጵያ ሌላ ለየትኛውም ሃገር ንቅናቄ ይህን ማለት አይቻልም::

ማርካኪስ፣ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የነበረውን ነፃነት ለንቅናቄው መወለድና ማበብ እንደ አበይት ምክንያት ያስቀምጡታል:: ይህም የኢትዮጵያን ተማሪዎች ንቅናቄ ልዩ ከሚያደርጉት – በሦስተኛ ዓለም ከነበሩት – ገጽታዎቹ አንዱ ነበር::

ማርካኪስ እንዲህ ብለዋል:-

“With the university, the students succeeded in joining almost complete freedom of expression, and their publications launched quite uninhibited attacks on the regime although they refrain from attacking the person of the emperor”

“ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ሃሳብን በነጽሳነት የመግለጽን መብት ከሞላ ጎደል ሙሉ ለሙሉ ለማስከበር ችለዋል:: ሕትመቶቻቸውን የአጼውን ስብዕና ከማጥቃት ቢቆጠቡም መንግስትን ግን ያለምንም ፍርሃት ይተቹ ነበር” ((በcontext የተተረጎመ)

የተማሪዎቹን ቀልብ በዋናነት የሳበው ግን፣ ወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አልሆነም:: ወሳኝ የሆኑትን የሃገራቸውን ታሪክ፣ ፖለቲካና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አልሆነም:: ወሳኝ የሆኑትን የሃገራቸውን ታሪክ፣ ፖለቲካና ኢኮኖሚ በሁለተኛ ደረጃ አስቀምተው ማርክሲም ላይ አተኩረዋል:: ይህ ሲሆን መንግስት ጣልጋ አልገባባቸውም:: በዚህ ሳቢያ ማርክሲዝም በአደባባይ ከተሰበከባቸው ጥቂት የአፍሪካ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ለመሆን በቅታለች:: ይህ እውነታ የተማሪውን ንቅናቄ የአጼው መንግስት የአካዳሚ ነፃነት ውጤት ያደርገዋል:

በሦስተኝነት፣ የኢትዮጵያን ተማሪዎች ንቅናቄ ልዩ ከሚያደርጉት ባህሪያቱ መካከል የአባላቱ ድህነት ጉልህ ስፍራ ይሰጠዋል:: ይህ ክፍተት ንቅናቄው የግድ የውጭ ኃይሎች፣ ጥገኛ አድርጎታል:: የንቅናቄው አድማስ ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ውጥቶ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲዛመት፣ ከተማሪዎች በሚሰብሰብ መዋጮ የተደራረበውን ወጪ የሚሸፈንበት ሁኔታ አልነበረም:: በዚህ ክፍተት፣ በዘመኑ ከነበሩት ሁለት ልዕለ ኃያላን መካከል አንዷ የነበረችው ማርክሲሥቷ ሶቭየት ኅብረት ተማሪዎቹን ስኳር ታልሳቸው እንደነበር ማርካኪስ ጽፈዋል::

“After Haile Selassie expelled several soviet and East European embassy officers in 1968 and 1969 for subversive contacts with students, Moscow refined its techniques. It was less risky to work with Ethiopian students abroad. Hence forth, money, propaganda and advice for student’s agitation in Ethiopia came in large part through Marxist- dominated Ethiopia student organizations in Europe and America. Under the guise of supporting literacy campaigns and welfare projects, these organizations sent far larger sums of money than they would conceivably have collected on their won to their counter parts in Addis Ababa’

“እ.ኤ.አ በ1968 እና በ1964 የሶቭየትና የምሥራቅ አውሮፓ ዲፕሎማቶች ‘ከተማሪዎች ጋር ሕገ-ወጥ ግንኙነት አድርጋችኋል’ ተብለው ከተባረሩ በኋላ፣ ሞስኮ ስልቷን ቀየረች:: ውጭ ካሉት ተማሪዎች ጋር መሥራቱ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ተገኘ:: ከዚህ በኋላ ሃገር ውስጥ ለነበረው የተማሪዎች ንቅናቄኤ የሚሰጠው የገንዘብ፣ የፕሮፓጋንዳና የምክር ድጋፍ፣ ማርክሲስቶች በሚመሯቸውና በአውሮፓና በአሜሪካ በነበሩ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበራት በኩል እንዲላክ ተደረገ:: እነዚህ ማህበራት ለመሰረተ ትምህርትና ለማህበራዊ ዋስትና ድጋፍ እንሰጣለን’ በሚል ሽፋን ከአባላቶቻቸው ሊያሰባስቡት ከሚችሉት በላይ ገንዘብ ወደ አዲስ አበባ ልከዋል::”

ይህ ሁሉ በጥቂት ተማሪዎች ፈቃድ የተፈጸመ ሲሆን በእኔ ግምት በክሮኮዳይሎች crocodiles ብዙሃኑ ተማሪዎች እስከአሁን ድረስ ምን እንደተደረገ አያውቁም:: ይህ መረጃ ጨለማ፣ በብዙሃኑ ተማሪ በጭፍን ይከተላቸው የነበሩትን የንቅናቄው መሪዎች፣ ማርክሲዝምን የተቀበሉት ለገንዘብ ብለው ነበር ወይ? የሚል ጥያቄ እንዳስነሳ ያስገድደኛል:: የተማሪው ንቅናቄ ከከሰመ በኋላ እንደታየው፣ በመሪዎቹም ሆነ በብዙሃኑ ተማሪ ዘንድ፣ ማርክሲዝም ቅብ ነበር እንጂ ውስጣቸው ሰርጾ የገባ እምነት አልነበረም::

ፈረንጆች “…with the benefit of hindsight…” የሚሉት ነገር አላቸው:: “ግዜው ካለፈ በኋላ በአንክሮ ሲታይ” እንደማለት ነው:: የተማሪው ንቅናቄ በዚህ ዓይነቱ መነጽር ሲቃኝ የውጭ ኃይሎች መሣሪያ መሆኑ ብዙም አያስደንቅም:: የገንዘብ ብቻ ሳይሆን የታሪክም ደሃ ነበርና:: ጥራዝ ነጠቅ ማርክሲዝምን በተላበሰው ንቅናቄ ዘንድ፣ ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ኃይማኖት የመሳሰሉ ነገሮች በመደብ የተከፋፈለ ማህበረሰብ ኋላቀር ቅሪቶች ናቸው ተብለው በመፈረጃቸው በንቀት የሚታዩ ነበሩ:: ለኢትዮጵያ የተለየ ታሪክና ማንነት ቦታ አልነበረውም::

በዚህ ሳቢያ፣ ስለ1984ቱ “ፓሪስ ኮሚውን” (የፓሪስ አመጽ) መወያየትና መከራከር ይወዱ የነበሩት የተማሪው ንቅናቄ አባላት – ልክ የዛሬ ዘመን ወጣቶች ስለ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በአንክሮ እንደሚከራከሩት – እንኳን የጥንቱን የኢትዮጵያ ታሪክ ይቅርና፣ በፓሪስ ኮሚውን የቅርብ ርቀት (እ.ኤ.አ በ1860ዎቹ) የእንግሊዝ ጦር በኢትዮጵያ ላይ ስለፈጸመው ወረራና ስላስከተለው እንደምታ ምንም እውቀት ሳይቀራምቱና ሳይመጋገቡ ቀርተዋል::

ተማሪዎች በዚህ መልክ እስከ 1966 ድረስ ከቀጠሉ በኋላ፣ በአብዮቱ ፍንዳታ ማግስት ያቋቋሟቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ወስደዋቸዋል:: ህብረብሄራዊ ድርጅቶች ያቋቋሙትም ማክርሲዝም ላይ ተቸክለው በመቅረታቸው መንግስታዊ ጭቆናን እስከመጨረሻው ድረስ መቋቋም የሚችሉ አባላትን ማፍራት ሳይችሉ ቀርተዋል:: እነ ኢሕ አፓና መኢሶን በደርግ ጭፍጨፋና አፈና ብቻ አልጠፉም:: በማርክሲዝም ብቻ የታነጹት አባሎቻቸው፣ በድንጋያማ መሬት ላይ እንደወደቀ ዛፍ፣ ጸሃይ ሲበረታባቸው – በመከራ ጊዜ – በቀላሉ ደርቀዋል:: በአንጻሩ፣ የብሄር ድርጅቶች ያቋቋሙት ተማሪዎች – የኤርትራ፣ የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የሲዳማ፣ ወዘተ – ሃገራዊውን ታሪክ ከማርክሲዝም ያልተናነሰ ቦታ በመስጠታቸው፣ ብርቱ መከራን መቋቋም የሚችሉ አባላትን አፍርተው – በተለይ የኤርትራና የትግራዮቹ – ደርግን ለመጣል በቅተዋል:: የሕብረብሄራዊ ድርጅቶች ማርክሲስቶች እንደተመኙት፣ ታሪክን ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ነቅሎ ማውጣት አልተቻለም::

ተማሪዎቹ እንቅስቃሴያቸውን ከጀመሩ 55 ዓመታት በኋላም ከ1953 – 2003 የዮሐንስና የምኒልክ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ፖለቲካ የፈጠረው ሽኩቻ፣ የኢሕአዴግ ቅኝት ጸረ-ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ምክንያት ከሆኑት ግብአቶች መካከል አንዱ ሆኖ ይገኛል:: የታሪክ ጣጣ የኦሮሞና የተማሪ ብሄረተኞችን ነፍስ እረፍት እንደነሳ ነው:: የታሪክን ህጸጾች የማይቀበሉ ቀላል የማይባል የፖለቲካ ኃይልም አለ:: ይህ ሁሉ ተደማምሮ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተጋረጠ አደጋ ነው:: መፍትሄው ከአዲሱ ዘመን ዴሞክራቶች ይጠበቃል::

እስክንድር ነጋ፣
የሕሊና እስረኛ፣
ቃሊቲ::

(የጋዜጠኛ እስክንድርን የእጅ ጽሁፍ በኮምፒተር የለቀመው ጋዜጠኛ ሔኖክ ዓለማየሁ ነው)

አረጋኸኝ ወራሽ በዊልቸርና በሰው ድጋፍ እየተንቀሳቀሰ ነው

0
0

አረጋኸኝ ወራሽ በዊልቸርና በሰው ድጋፍ እየተንቀሳቀሰ ነው

(ዘ-ሐበሻ) ከኢትዮጵያ አንጋፋ ድምፃውያን መካከል አንዱ የሆነው ድምፃዊ አረጋኸኝ ወራሽ ታሞ ኮሪያ ሆስፒታል መተኛቱ ተሰምቷል:: እንደ ዜና ምንጮች ገለጻ አረጋኸኝ በሽታው የጀመረው ከአንድ ሳምንት በፊት ነው::

ድምፃዊው ከታዲያስ አዲስ ራድዮ ጣቢያ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንደገለጸው ድንገት ከሻወር ሲወጣ የግራ እግሩን እንደ ኤሌክትሪክ እንደነዘረውና እጁም መንቀጥቀጥ እንደጀመረ ገልጿል:: ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ መንቀጥቀጡ የተወው ሲሆን እግሩም መታዘዝ ማቆሙን አስረድቷል::

አርቲስቱ በአሁኑ ወቅት በዊልቸርና በሰው ኃይል ድጋፍ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል:: ህክምናውንም በኮሪያ ሆስፒታል እየተከታተለ ነው::

 

በድሬደዋ ደቻቱ የደረሰው የጎርፍ አደጋ ቪዲዮ ይመልከቱ

0
0

ትናንት በድሬደዋ ደቻቱ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተከስቶ ንብረት ማውደሙ መዘገቡ አይዘነጋም:: የጎርፉን ሁኔታ የሚያሳየውን ቪዲዮውን ይመልከቱ::

Zehabesha News

ማስተዋል ይኑረን እንጂ

0
0

130153
ግርማ ቢረጋ

ግፉ በፍፁም የሚገታ አልሆነም አባት እናቶች ወንድሞች እህቶች እንዲሁም ህፃናት ልጆቻችን መሬት ንብረታቸውን ከመቀራመት ባለፈ ህይወታቸው እንደሰው ማሰብን ባልፈጠረባቸው በወያኔ ሰራዊት መገደልና እንዲሁም በቅጥረኛ ጎረቤት ሃገራት ጭምር እንግልቱ ስቃዩ ሳያንስ ህይወታቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ እስከማጣት ከደረስን ሰንበትበት ሳይሆን በጣም ከረምረም ብለናል።

ታዲያ ምን ይሻላል ትሉ ይሆናል ይህ የሁላችን ጭንቀት ነው ።አሁንማ አንዳንዶች የሚደርሱብንን ሃዘኖች እየለመድናቸው ሲመስለንም ይታያል ግን በጋምቤላም ሆነ በሌሎች አካባዎች የፈሰሰው ደም ይጮሃል ነገሩ ግራ ከመጋባት ባለፈ እያንዳንዱ አትዮጵያዊ እራሱን ሊሆን ይገባወዋል ማለቴ ምነው አገራችንን ለዚህ ሁሉ ግፍ የዳረጋት ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው የሳጥናኤል ቁራጭ ወደ ገሃነም በወረደ ግዜ የመንግስት ሰራተኞች ተገደው ስራቸውን ላለማጣት አንዳንዶች ደግም ቤተመንግስት ምን እንደሆነ ለማየት ጥቂት ሆድ አደር የሆኑ ልማታዊ አርቲስቶች ደግሞ በለቅሶዋቸው ልክ ሊከፈላቸው የተላኩና ለዚህ ያበቃቸውን የኢትዮጵያን ህዝብ ውለታ ረስተው ህሊናቸውን በጥቅም ደፍነው ያን ሁሉ እንባ ለዚያ የሳጥናኤል ቁራጭ ሲያፈሱ አይተናል::

ከዚያም ባለፍ የወያኔን ግዳይ ለማየት በሚል ከህዝብ ወገንተኝነት ርቀው ሲያሽቃብጡና ጭራቸውን ሲቆሉ አይተናል:: ታዲያ ..ታዲያ ያ ሁሉ ለሳጥናኤል ያፈሰሱት እንባ ወገኖቻቸው በባህር ሲያልቁ በበረሃ ሆዳቸው እየተቀደደ ኩላሊታቸው እየተሰረቀ ሌሎች ደግሞ በአረብ ሃገራት በአሰቃቂ ሁኔታ የፈላ ውሃ ሲደፋባቸው ከፎቅ ሲጣሉና በመንገድ ላይ ሲጎተቱ በሃገር ውስጥም በወያኔና ቡችሎቹ በዘረኝነት በሽታ ተለይተው ሞት እየተደገሰላቸው ከሰብአዊነት ባለፈ ሁኔታ ለአካለ ጎደሎነትና ህይወታቸው ሲቀጠፍ ከዚያም ባለፈ በእጅ አዙር በጎረቤት ሃገር አስፈፃሚነት ወገኖቻችን እንዲያ በደም ተጨማልቀው ተጨፍጭፈው ከማየት በላይ ምን የሚያንገበግብ እና እንባን መገደብ እስከማቃት የሚያሳዝን ምን በደል አለ።

እንዲያው መንግስት ወይም ልማታዊ አርቲስት ጠፍቶ ነው የሃዘን ቀን ያልታወጀው ወይም ወገንተኝነትን ለመግለፅ ያህል ዝግጅት ያልታየው እሺ ሁሉም ይቅርና ለዚያ ለኢትዮጵያ ህዝብ ስቃይና መከራ እንዲሁም ለሃገራችን ሉዓላዊነት የጥፋት መስረት ለነበረው ባንዳ የባንዳ ልጅ ያፈሰሳችሁት እንባ የት አለ እሱንም በልማታዊ አርቲስትነት ወያኔ ገደበባቹ ??? ሁኔታዎች ሁሉ አቅጣጫቸው ሁሉ የተመቻቸ ሊመስላችሁ ይችላል ግን በናንተ ላይ የሚመጣው የምፅዓት ቅን በርግጠኝነት ልዩ ነው። አላግባብ የፈሰሱ የንፁሃን ደም አሁንም ይጮሃል ሃብታም የወያኔ ቡችሎችን ቁጭ ብሎ ከማጫወት ባለፈ የትም ልትደርሱ እንደማትችሉ ማስተዋል ይኑራቹ አሊያ ህዝብ ሃይል መሆኑን ማስተዋል ካልቻላቹ መጭው ግዜ እያንዳንዳችንን በሰፈርንበት ቁና መስፈሩ አይቀርምና እዚያው ያገናኘን ።
ሞት ለባንዳዎቹ የወያኔ ቡችሎች!!

ድል የወገናቸው ህመም ለሚሰማቸው የነፃነት ታጋዮች!!!
ስቶክሆልም
Ethiofri@gmail.com
April2016

ዲና አንተነህ ከታማኝ ሾ ጋር ያደረገችው ቃለምልልስ: “ዘፈን ልሠራ ሄጄ አድጌ አባቴን አወቅኩት”

0
0


ዲና አንተነህ ከታማኝ ሾ ጋር ያደረገችው ቃለምልልስ: “ዘፈን ልሠራ ሄጄ አባቴን አገኘሁት”
ዲና አንተነህ ከታማኝ ሾ ጋር ያደረገችው ቃለምልልስ: “ዘፈን ልሠራ ሄጄ አድጌ አባቴን አገኘሁት”

ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሜዲትራኒያን ባህር ስለበላቸው ወገኖች አሳዛኝ መጨረሻ |ልዩ ጥንቅር

0
0

በሜድትራኒያን ባሕር ላይ ሰሞኑን በተከሰተው የስደተኞች እልቂት በርካታ ኢትዮጵያዊያኖች ስለመኖራቸው፣ አሳዛኙ ድርጊት ሲፈጸም በስፍራው የነበረው ባለቤቱን እና ህጻን ልጁን ያጣው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ መሪር ትዝታው የተዳሰሰበት ዘገባ (ልዩ ጥንቅር)


ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ  የሜዲትራኒያን ባህር ስለበላቸው ወገኖች አሳዛኝ መጨረሻ | ልዩ ጥንቅር

ግልፅ ደብዳቤ ለአቶ ባራክ ኦባማ –አንዱዓለም አራጌ (ከቃሊቲ) ትርጉም –መስፍን ማሞ ተሰማ (ሲድኒ)

0
0

የተከበሩ ፕሬዚዳንት ኦባማ
እኔ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የግብርና ህይወት ቤተሰቡን ሲያስተዳድር የኖረና አሁንም የሚኖር የድሃ ገበሬ ልጅ ነኝ። እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ቤተሰብ ለመበልፀግ የህብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች በአግባቡ ሲስተናገዱ ነው ብሎ – በሩቅም ቢሆን – በማመን የአባቱንም ሆነ የራሱን የህይወት ዘይቤ ያልቀየረው የዚያ ገበሬ ልጅ ነኝ፤ እኔ። ክቡር ፕሬዚዳንት፤ በኢትዮጵያ አገዛዝ በሽብርተኝነት ተፈርጄ ራሴን ከማግኘቴ በፊት – በዩኒቨርሲቲ ካምፓስ በነበርኩበት ወቅት እንደ ተማሪው መሪነቴም ሆነ ሁዋላም እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኛ መሪነቴ በነበረኝ ህልም የህዝብን የኑሮ ሁኔታ በተሻለ ለመለወጥ የጣርኩ የዚያ ገበሬ ልጅ ነኝ። ከኢትዮጵያ የሰቆቃ እስር ቤቶች መካከል ቀንደኛ በሆነው ቃሊቲ ወህኒ ቤት ዕድሜ ልክ ተበይኖብኝ በመማቀቅ ላይ እገኛለሁ።

Andualem-Aragie-5ክቡር ፕሬዚዳንት፤ የሰው ልጅ መገኛ ዕምብርት (ራስዎም ሉሲን በጎበኙበት ውቅት እንዳረጋገጡት)፤ የጥንታዊ ሥልጣኔና የገዳ ዴሞክራሲ ባለቤት፤ ከቶም በቅኝ አገዛዝ ሥር ካልወደቁት ሁለት የአፍሪካ ሀገራት አንዷ፤ ከድፍን አፍሪካ የራስዋ መለያ ፊደል ያላት ብቸኛ ሀገር በመሆንዋ – ኩራት የሚሰማው <em>‘ሽብርተኛ’ </em>ነኝ። ደግሞም የዛሬ 120 ዓመት በአድዋ ጦርነት ጀግኖች ሴትና ወንድ አያቶቻችን በፈፀሙት ገድልም የምኮራ <em>‘ሽብርተኛ’ </em> ነኝ። እርስዎም እንደሚያውቁት የአድዋው ድል በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ሲማቅቁ ለኖሩት በአፍሪካና በመላው ዓለም ለሚኖሩ ትውልደ አፍሪካ ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ፋና ወጊ ድል ነው። የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት ላደረጉት ጦርነት “አዋላጅ” የሆነችው ሀገሩ ባበረከተችው ሚና የምኮራም ነኝ።

በሀገሬ በተንሰራፋው ፀረ ዴሞክራሲ አስተዳደራዊ ሥርዐት፤ ዓመታትን ባስቆጠረውና ለአያሌ ወጣቶች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት በሆነው የርስ በርስ ጦርነት፤ በአስከፊው ድህነት፤ ተደጋጋሚ ድርቅና ረሀብ ሁሉ የምንገፈገፍና የምቆጭ ‘<em>ሽብርተኛ’</em>ም ነኝ። የችግራችን ምንጭ የሆነውን አምባገነናዊነት ከሥሩ መንግሎ ለመጣል ሠላማዊ ትግልን እንደ ሃይማኖት የተቀበልኩና የተገበርኩ <em>‘ሽብርተኛ’</em>ም ነኝ።

ክቡር ፕሬዚዳንት፤ ‘ኢትዮጵያውያን ሀይለኛ ተዋጊዎች ናቸው’ ብለዋል። አዎ፤ ሉዐላዊነታችን በወራሪዎች ሲደፈር ለመከላከል ሀይለኛ ተዋጊዎች ነን። ይሁንና በሚያሳዝን ጎኑ ደግሞ ሉዐላዊነታችን ከራሳችን በወጡ አምባገነኖች ሲደፈር ሀይለኛ ተዋጊነታችን ሲደገም አይታይም። ለአስራሰባት ዓመት የዘለቀው ከደርግ ወታደራዊ ጁንታ ጋር የተካሄደው እልህ አስጨራሽ ጦርነት በደርግ መገርሰስ ሲጠናቀቅ ለብዙዎቻችን በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጎህ የቀደደ መስሎን ነበር። አለመታደል ሆኖ ግን እስካሁን ያለን ከወደቀው የተሻለ አይደለም። ከላፉት 25 ዓመታት ጀምሮ በጭቆና ማጥ ውስጥ እንደተሰቃየን አለን። ቢሆንም ታዲያ እጆቻችንን አጣጥፈን ግን አልተቀመጥንም።

የአድዋ ጦርነት በቅኝ ግዛትና በጭቆና አገዛዝ ውስጥ የሚማስኑትን ለመብታቸው እንዲዋጉ እንዳነሳሳቸው ሁሉ፤ የህንድ ህዝብና በአሜሪካ የሲቪል መብት ንቅናቄ ተሟጋቾች ያካሄዱት ሠላማዊ ትግል ደግሞ ለአንዳንዶቻችን አርአያ ሆኖን በሀገራችን ዴሞክራሲን ለማስፈን በምናደርገው ትግል ተጠቅመንበታል።

በ2005 (እአአ) በተደረገው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ የትግላችን ጥረት የሰመረ መስሎ ነበር። ተስፋችን ግን ምርጫውን ባጭበረበረው አምባገነን መንግሥት ጨለመ። ይባስ ብሎ መረን የለቀቀውን የአገዛዙን በትር በአብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፤ ለምሳሌ ምርጫውን ባሸነፈው ቅንጅት (እኔም ከአመራሮቹ አንዱ የሆንኩበት) መሪዎች፤ ደጋፊዎችና አባላት ላይ በማሳረፍ ወደ ወህኒ ቤት አግዟቸዋል። ዴሞክራሲን የማፈን ተግባሩ ዓይን ያወጣ ከመሆኑ የተነሳ ዓለም ዐቀፉ ማህበረሰብ በአጠቃላይ በተለይ ደግሞ የአውሮፓ ምርጫ ታዛቢ ልዑክ ሞራለ ቢስ የሆነውን የአገዛዙን ተግባር አውግዘዋል። ይሁን እንጂ የሁዋሊት ጉዞውን በቀላሉ መቀልበስ አልተቻለም።

እነሆ በዚህን ወቅት – በመጀመሪያው የወህኒ ቤት ቆይታ ጊዜዬ – ነበር በአንድ መፅሄት አማካኝነት ከእርስዎ አዲስ አስተሳሰብ ጋር የተዋወቅሁት። ከሃያ ወራት እስር በሁዋላ – ሃያ አራት የምንሆነው የዕድሜ ልክ እስራት ተበይኖብን ነበር – በምህረት ተለቀቅን። ከወህኒ እንደወጣሁ፤ የህይወቴ የፍቅር ቀንዲል ከሆነችው ከዶ/ር ሠላም አስቻለ ጋር ተጋባን። ከእስር ነፃ በቆየሁባቸው ቀጣይ አራት ዓመታት እኔና ባለቤቴ የሁለት ወንዶች ልጆች ወላጆች በመሆን ተባረክን። ይሁን እንጂ በውስጤ እንደ ወላጅ የማሳደግ ዕድል የሌለኝን ልጆች ወደዚህች ምድር እንዳመጣሁ ይሰማኝ ነበር። ለዚህም ዕለት ተዕለት ይካሄድ የነበረው ክትትል መጪውን ፅልመት ጠቋሚ ነበርና።

<em>ይህም ሆኖ ታዲያ በልቡናዬ ያኔም ሆነ አሁን በጥልቅ እንደማምነው ለአረመኔ አምባገነን ሰግዶና አደግድጎ ከመኖር ይልቅ በወህኒ ቤት መሞት ክብር ነው።</em>

በእኒያ ከወህኒ ውጪ በቆየሁባቸው ዓመታት እርስዎ ለተባበረው የአሜሪካ መንግሥት ቢሮ ፕሬዚዳንትነት ያደረጉትን የመጀመሪያ ዘመቻ ለማየት ታድያለሁ። ያካሄዷቸውንም የመድረክ ክርክሮች በሙሉ በቀጥታ ስርጭት ተከታትያለሁ። ተሳትፎዬ ሁሉ ከግምት ውስጥ ይገባል ብዬ ባይሆንም – በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ደጋፊዎችዎን ተቀላቅዬ በየጊዜው ወቅታዊ የሆነ የኢሜል መልዕክት ከሚደርሳቸው አንዱ ነበርኩ። ሴናተር ጆን ማኬን እና እርስዎ ያደረጓቸውን የቅበላ ንግግሮችንም በቀጥታ ሥርጭት አዳምጫለሁ። ዕውነቱን ለመናገር፤ ክቡር ፕሬዚዳንት፤ በሀገርዎ ምርጥ የዴሞክራሲ ባህል በእጅጉ ነበር የተመሰጥኩት – በሀገሬ ውስጥ እንደዚያ ያለ ባህል ይኖር ዘንድ ካለኝ ፍላጎት።

በኢትዮጵያ ሀገሬ እንደዚያ ያለ ዴሞክራሲ መመኘት ይቅርታ የማያስገኝ ሀጢያት ነው። ወ/ሮ ሮዛ ፓርክስ መቀመጫዋን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆንዋ ታስራ 14 ዶላር እንደተቀጣችው፤ እኔም ፓርቲዬን – አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ – በምክትል ፕሬዚዳንትነትና በህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊነት በኢትዮጵያ ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ሳገለግል ነበር የታሰርኩት። ለሁለተኛ ጊዜ <em>‘ሽብርተኛ’ </em> በሚል ክስ የዕድሜ ልክ እስራት ተበየነብኝ። እነሆም ላለፈው አራት ዓመት ተኩል ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያ ካሉት ጋር እንኳ ሲነፃፀር በአስከፊነቱ ወደር ከማይገኝለት ወህኒ ቤት ውስጥ በመማቀቅ ላይ እገኛለሁ።

ከእጅ መዳፍ የማትበልጠውን ሠማይ አሻቅቤ እያየሁ አእምሮዬ በየአቅጣጫው ሲባዝን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን አውጠነጥናለሁ። በቃሊቲ ወህኒ ቤት ውስጥ ከራሴ ጋር ስሟገት፤ በቆምኩለት ዓላማ ንፁህነትና ቀናነት ውስጥ መሸሸጊያ እያገኘሁ፤ የእስር ቤቱን ሰቆቃ አስችሎኝ የሠላም እንቅልፍ እተኛለሁ።

ስለባለቤቴ አስባለሁ፤ በተለይም ያለአባት ተምሳሌ ስለሚያድጉት ሁለቱ ልጆቼ። የበኸር ልጄ ሩህ፤ የሶስት ዓመት ልጅ ሆኖና ት/ቤት በመግቢያው የመጀመሪያ ቀን፤ ኖላዊ ደግሞ የአስር ወር ህፃን እንደነበር ነው እኔ ወደ ወህኒ ቤት የተጋዝኩት።

እርስዎ በመፅሀፍዎ “<em>the Audacity of Hope” </em>ገፅ 72 ላይ ሲያወጉ ስለሴቶች ልጆችዎ አንስተው ሌሎቹም ታዳጊ ቤተሰቦች ያሏቸው ሴኔተሮች ከቤተሰቦቻቸው ርቀው ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ስለሚያደርጉት ጥረት ገልፀዋል። ክቡር ፕሬዚዳንት፤ በቤተሰቦቼ በተለይም በልጆቼ ላይ እየደረሰ ያለውን የስቃይ ስሜት ይጋሩኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

የእኔ ልጆችና በእስር ላይ የሚገኙት <em>የአያሌ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ልጆች</em> ማባሪያ የሌለውንና መልስ የማይገኝለትን የተለያዩ ጥያቄዎች ይጠይቃሉ፤ ለምሳሌ አባቶቻቸው ወደ ቤታቸው ሳይመጡ የቆዩበትን ምክንያት። ክቡር ፕሬዚዳንት፤ ይህንን የመሳሰሉ ነፍስና ሥጋን የሚያስጨንቁ ጥያቄዎችን ላለፉት አራት ዓመታት ሲጠይቁ ስለቆዩት ልጆቼ አንስቼ ጊዜዎን ላባክን አልሻም።

ክቡር ፕሬዚዳንት፤ እንኳንና እንደ ኢትዮጵያ ባለው ላለፈው ሩብ ምዕተ ዓመት የተንሰራፋውን አምባገነንነቱን መሸፈኛ ምርጫን በጭንብልነት ለሚጠቀም አገዛዝ ቀርቶ በዴሞክራሲ ሀገራትም የህዝብ ውክልና እስከምን ድረስ እንደሆን ጠይቆ ቀላል መልስ ማግኘት ይከብዳል።

በ2005 (እአአ) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ወቅት የተጀቦነበት ጭምብል ቢገፈፍም ቅሉ አገዛዙ ግን ምርጫውን በ99.6% ‘ሲያሸንፍ’ በ2015 (እአአ) ደግሞ 100% ‘በማሸነፍ’ ዴሞክራሲ በምድረ ኢትዮጵያ እንደ ፀሀይ ብርሃን በማንፀባረቅ ላይ መሆኑን እየሰበከ ይገኛል። ዓለምም ይህንን ቅጥፈት ለመቀበል ዝግጁ ሆኗል። እርስዎም እንኳን ሳይቀሩ፤ ክቡር ፕሬዚዳን፤ በጉብኝትዎ ወቅት – የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የህዝብ ድጋፍ ያለው መሆኑን ሲናገሩ ተደምጠዋል። ዕውን ይህንን የተናገሩት ከልብዎ ነበርን?

<strong>“ሁሉም ሰው እኩል ነው”</strong>

<strong>    </strong>የሀገርዎ መስራች አባቶች አሳምረው እንዳስቀመጡት – ክቡር ፕሬዚዳንት – ሁላችንም የተፈጠርነው እኩል ሆነን ነው። በመንገድ ደርዝ የሚገኝ “የድሃ ድሃም” ይሁን ወይም በቤተመንግሥት ያለ “የንጉሦች ንጉሥ” ሁላችንም በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠርን እኩዮች ነን። በመሆኑም ሁላችንም በተስተካከለ መንገድ ልንስተናገድ ተገቢ ይሆናል። ማንም በማንም የበላይነት ስር በማንኛውም አይነት ሁኔታ ሊገዛ አይገባውም።

የዴሞክራሲንና የፍትህን ጉዳይ አስመልክተው በመጀመሪያው የፕሬዚዳንትነት ውድድር ዘመቻ ወቅት ያደረጉትን መሳጭና ውብ ንግግር ማንም የሚክደው አይደለም። ይህንንም “<em>the Audacity of Hope” </em>በሚለው መፅሀፍዎ ውስጥ አስቀምጠውታል። የርስዎ ክርክርና ስኬታማ መሆን አንዳንዶቻችንን ራሳችንን ለማንኛውም ጉዳይ ካዘጋጀን የማይቻል ነገር አለመኖሩን እንድናምን አድርጎን ነበር። ይሁንና <em>በአፍሪካ ለምንገኘው እንደንግግርዎ ሁሉ ተግባርዎም ልባችንን የነካው አይመስለኝም።</em>

እንደ ኢትዮጵያ በርቀት በሚገኙ ሀገሮችም ይሁን ወይም እንደ ጎረቤት ሀገር ኩባ፤ ግንኙነቱም ኢኮኖሚያዊ ትሩፋት ይኑረው ወይም አይኑረው፤ በሀገራት መካከል ዕውነተኛው ወዳጅነት ሊገነባ የሚገባው የህዝብን የሉዐላዊነት መብት መሰረት በማድረግ ሊሆን ይገባዋል። እርስዎ ራስዎ በሚገባ ጠንቅቀው እንደሚረዱት በኢትዮጵያና በዩኤስ አሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ይህንን መሰረት ያደረገ አይመስለኝም። የኢትዮጵያ ህዝብ ቃልዎን ተንተርሶ ሊራመድ ሲሻ ቡጢ ጨብጦ የተነሳው ክንድዎ የታለ፤ ክቡር ፕሬዚዳንት? በኢትዮጵያ ጉብኝትዎ ወቅት መሪዎቻችንን እንዳብጠለጠሉ ሰምቻለሁ። የኢትዮጵያ ህዝብ ለፍትህና ለዴሞክራሲ በሚያደርገው ትግል የተባበረው የአሜሪካ መንግሥት ፕሬዚዳንት ማድረግ የሚችለው ርዳታ – በቃ ይኸው ነው?

ክቡር ፕሬዚዳንት፤ እርስዎ በሀገርዎ ታሪክ ከአሜሪካ ታላላቅ ፕሬዚዳንቶች አንዱ ሆነው እንደሚሰፍሩ አምናለሁ። ደግሞም፤ እንደ ዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንትነት በቆዩባቸው ሁለት የአገልግሎት ዘመናት አፍሪካውያን ለዴሞክራሲና ለፍትህ በሚያደርጉት ትግል ውስጥ አንዳችም ፋይዳ ያላበረከተ አፍሪካዊ ትውልድ ያለው የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ተብለው በታሪክ እንደሚፈረጁም አምናለሁ።

ገና በጠዋቱ፤ ብዙዎች እርስዎ ያደርጓቸው የነበሩትን ፖለቲካዊ ህብስተ ዲስኩሮች፤ ከዋሽንግተን የፖለቲካ መዘውር አንፃር፤ ወደ ተግባር የማይተረጎሙ ናቸው በማለት ጥርጣሬያቸውን ይናገሩ ነበር። መለስ ብዬ ሳየው፤ ለካስ ዕውነታቸውን ኖሯል።

ዛሬ ድረስ የሚገርመኝ ቢኖር፤ እንደርስዎ ብቃት ያለው ፕሬዚዳንት ህዝቦች እግዚአብሄር የሰጣቸውን ሰብዓዊ መብት ሲገፈፉ በዝምታ መመልከት መቻሉ ነው። ይህ የሆነው፤ ከተግባር ፖለቲካ ምልከታ አንፃር {ፕራግማቲዝም}? በገንቢ ውይይት በማመን? ወይስ ‘ውስጥን በመፈተሽና ማስተካከያም በማድረግ’ ወደ ቀድሞው ዘመን የግንኙነት መስመር መመለስ አስፈላጊ በመሆኑ?

ዕውነቱን ለማናገር በእስር እየማቀቅሁ እንኳን የእርስዎን ወደ ተወዳጅዋ ሀገሬ ለጉብኝት መምጣት በልቡናዬ አበክሬ ነበር የደገፍኩት። የእርስዎ ጉብኝት ለፍትህና ለዴሞክራሲ መስፈን የሚደረገውን ትግል ይረዳል የሚል ዕምነትና ተስፋ በውስጤ ውስጥ ነበረኝና።

እርስዎ ግን ጭርሱኑ “አገዛዙ ህዝባዊ ነው” በማለት አደባባይ ተናገሩ። ዕውን ይህ ምን ማለት ነው፤ ክቡር ፕሬዚዳንት? እንደማምንበት ከሆነ ህዝባዊነትን አሳምሮ መግለጫው ነፃና ወገንተኛ ያልሆነ ምርጫ ሲኖር ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ ነፃና ወገንተኛ ያልሆነ ምርጫ በታሪካችን እስካሁን ተካሂዶ አያውቅም። እና እንደምን  ቢሆን ነው አገዛዙ ህዝባዊነቱ የተረጋገጠለት? ሳዳም ሁሴን በ100% ምርጫ ‘ሲያሸንፍ’ ህዝባዊ ነበርን?

አገዛዙ ምርጫውን በ100% ካሸነፈ ዓመት ገደማ ሲሆነው፤ ታዲያ እንዴት ቢሆን ነው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች፤ ለምሳሌ በኦሮምያ በትግራይ በጋምቤላ ለመብታቸው በመታገል ላይ የሚገኙት? ህዝቡ በገፍ እየተገደለና እየታሰረም ነው። ማንም ቢሆን ይህንን ከህዝብ መንግሥት የሚጠብቀው አይደለም።

የህዝብ ድጋፍ አላቸው ተብለው የሚታመኑትን ፓርቲዎች ሰርጎ የሚገባ፤ መሪዎችንም የሚያስር፤ የፕሬስ ነፃነትን የሚቀበትት፤ ጋዜጠኞችን ወህኒ የሚያጉርና ህዝብን በጠመንጃ አፈሙዝ ገድቦ የያዘ አገዛዝ እንደምን ህዝባዊ ሊሆን ይችላል?

ለአስራሁለት ተከታታይ ዓመታት ኢኮኖሚው በጥንድ አሃዝ ያለማቋረጥ በማደግና የህዝቡም የገቢ መጠን መራራቅ እየጠበበ በመሄድ ላይ ነው ብሎ በሚናገር አገዛዝ ውስጥ፤ ከአስር ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ከለጋሽ ማህበረሰባት ምፅዋት እየጠበቁ ይገኛሉ። በማደግ ላይ ነው የሚባልለት ኢኮኖሚ ለአንድ ዓመት እንኳን የተራቡ ኢትዮጵያውያንን ሊታደግ አልቻለም። ይህ በራሱ ህዝባዊ ድግፍ ያለው መንግሥት ሥራ ውጤት አይመስለኝም።

የኢትዮጵያ ወጣት ባገኘበት አቅጣጫ ከሀገሩ እየኮበለለ ይገኛል። ከህዝባዊ መንግሥታቸው የሚኮበልሉት ስለምን ይመስልዎታል፤ ክቡር ፕሬዚዳንት? እርስዎም አሳምረው እንደሚያውቁት እኒህ አንዳቸውም የዲሞክራሲያዊ መንግሥት ምልክቶች አይደሉም። ዴሞክራሲያዊ አስተዳደሮች ፓለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መረጋጋቶቻቸው ናቸው መለያቸው።

ጀምስ ሜርዴዝን መቸም ጠንቅቀው ያውቁታል ብዬ አምናለሁ። በጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ – አስተዳደሩ ምንም ያህል ቢቃወምም – ሚሲሲፒ ዩኑቨርሲቱ ለመግባት ችሏል። በሳውዝ አፍሪካ የዘር መድልዖ ዘመን እንኳን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እስር ቤቶቹ በፍትህ ሥርዐቱ ላይ ዕምነት ነበራቸው።

በኢትዮጵያ በሽብርተኝነት ሲከሰሱ አይደለም የሚታሰሩበት ዘመን ብዛት የሚታወቀው። እንደ <em>እስክንድር ነጋ፤ ውብሸት ታዬ፤ ተመስገን ደሳለኝ እና አያሌ ጋዜጠኞች </em>የአገዛዙን ተግባራት ተቃውመው ስለፃፉ ወይም <em>እንደ በቀለ ገርባ እና ሀብታሙ አያሌው የመሳሰሉ ልበ ሙሉ ፖለቲከኞች</em> ተቃዋሚዎችን በመቀላቀላቸው ምክንያት በወህኒ ቤቶች ሲማቅቁ ሲታይ እንጂ። ደግሞም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብቻም ሳይሆን ትዕዛዙ ከቤተመንግሥትም ጭምር ሲወጣ ሲታይ ጭምር እንጂ። መዋቅራት የአንድን ፓርቲ ህልውና ለማስረገጥ የቆሙ ናቸው፤ ክቡር ፕሬዚዳንት።

ሀገሩን የሚወድ የትኛውም ግለሰብ የሀገሩን ገፅታ ማጥለም አይፈልግም። እኔ ሀገሬን እያሳጣዃት አይደለም፤ እወዳታለሁና። ልጆቼና ባለቤቴ ሳይቀሩ እየተጋቱት ያለውን – በሀገሬ የሰፈነውን ኢፍትሃዊ መራራ ዕውነት ለማሳየት እንጂ፤ ክቡር ፕሬዚዳንት።

አራት ሰዎች በእኔ ላይ የሀሰት ምሥክርነት እንዲሰጡ ተገርፈዋል። ሁለቱ አልቻሉም። እና አድርጉ የተባሉትን ፈፅመው ተለቀዋል። የተቀሩት ሁለቱ፤ <em>ናትናኤል መኮንን</em> እና <em>ክንፈሚካኤል ደበበ</em> ግርፋቱን ችለው በዚሁ ሳቢያ ይኸው እስካሁን እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ሁለቱም ናትናኤልና ክንፈሚካኤል የ18 እና የ16 ዓመት ፍርደኞች ናቸው፤ በቅደም ተከተል። መቸም አገዛዙን በህዝባዊነት በማወደስ ከእርስዎ ጋር ባለመወገኔ አዝናለሁ።

<strong>የዘመናችን አድዋ</strong>

በሀገርዎ በ1868፤ ጆን ዊልክስ ቡዝ፤ አብረሃም ሊንከንን ለመግደል ተሳክቶለታል። ነገር ግን በዘር መድልዖ ላይ መንጋቱን ግና ሊያቆመው አልቻለም። ሰው ሁሉ እኩል ተፈጥሯልና፤ የእርሱ ዓለማ ግን ዕኩይ ነበርና። የህንዱ ጋንዲ ከእንግሊዝ ዘውዳዊ አገዛዝ የህንድን ህዝብ ነፃነቱን እንዲቀዳጅ አድርጓል። ሰው ሁሉ እኩል ተፈጥሯልና፤ የጋንዲም ዓላማ የእኩልነት ነበርና። ክቡር ፕሬዚዳንት እንደሚያውቁት፤ አዶልፍ ሂትለር የአርያን ጎሳ የበላይነት ለማስረገጥ ያደረገው ጥረት መክኗል። ሰው ሁሉ እኩል ተፈጥሯልና፤ የርሱ ዓላማ ግን ዕኩይ ነበርና። ልክ የዛሬ 120 ዓመት ሴቶችና ወንዶች አያቶቻችን በአንድነት ቆመው የጣሊያንን ወራሪ ሃይል አሸንፈዋል፤ ምክንያቱም ዓላማችን ፍትሃዊ ነበርና – ሁሉም ሰው እኩል ተፈጥሯልና። ማንም የማንንም ሀገር ወይም መብት የመውረር መብት የለውና።

ነገር ግን ሴትና ወንድ አያቶቻችን በሀገራቸው ‘ሰው ሁሉ እኩል ተፈጥሯል’ በሚለው ማዕቀፍ ውስጥ የማደር እድል አልገጠማቸውም። በኮርያና በኮንጎ በተሳተፉት የሠላም አስከባሪ አያቶቻችንና ዛሬ ደግሞ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ሠላምን ለማስከበር በተሰለፉት ሁሉ ተግባር እኮራለሁ። ታዲያ የዚህ ሽሙጥ የሆነው ደግሞ፤ ለሌሎች ሀገራት በገፍ የሚሞቱት ኢትዮጵያውያን ለራሳቸው የራሳችን ነው የሚሉት መንግሥት የሌላቸው መሆኑ ነው። ኢትዮጵያውያን በቤታቸው ገና ያላጠናቀቁት ሥራ አለባቸው።

በተባበረው የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ በ60ዎቹ እንደነበሩት የሲቪል መብቶች ተሟጋቾች እኛም በዕውነት በሠላማዊ ትግል ዕምነታችን ፅኑ ነው። ታዲያን አክራሪ ሃይማኖተኞች በመሆናችን አይደለም። ነገር ግን ከአምባገነን ጋር በሚደረግ ትግል ዘላቂ ሠላምንና ብልፅግናን ለማምጣት የማይመክን መሳሪያ በመሆኑ እንጂ። የመጣው ቢመጣ፤ በትግላችን ድልን እንደምንቀዳጅ አንዳችም ጥርጣሬ የለኝም። ምክንያቱም ዓላማችን ፍትሃዊ ስለሆነ፤ ሁሉም ሰው እኩል ተፈጥሯልና።

እኛ ሽብርተኞች አይደለንም፤ ክቡር ፕሬዚዳንት። እኛ የዕውነተኛ ዴሞክራሲና ፍትህ ርዕያን እንጂ። እኛ የነፃነት ታጋዮች ነን። በዘመኑ ከቶም ይሆናል ያልተባለው ነገር ግን የእኛ ሴትና ወንድ አያቶቻችን በአድዋ ጦርነት ድልን እንደተቀዳጁ፤ እኛም የግፍ አገዛዝን መንግለን የዴሞክራሲ ገነት የሆነች ኢትዮጵያን በመመሥረት ዘመናዊውን የአድዋ ድል እንፅፋለን። የችግራችን ሁሉ አስኳል የዴሞክራሲ ዕጦት ነው ብዬ አምናለሁና። ትግላችን ያፈራ ዘንዳም አያሌ ኢትዮጵያውያን ተነግሮ የማያባራ መስዋዕትነትን እየከፈሉ ይገኛሉ፤ ክቡር ፕሬዚዳንት።

እኛ አሳሪዎቻችን እንደሚሰይሙን አይደለንም። የእኛን ግብና የዓላማችንንም ንፁህነት ጠንቅቀው ያውቃሉ። ጉዳዩ፤ የእኛ ግብ የእነሱ አይደለም፤ የእነሱም የእኛ አይደለምና። መሠረቱ ይኸው ነው።

ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በአንድ ወቅት እንደተናገረው፤ <em>ክፉ ዓላማ ያላቸው ሰዎች የሚፈልጉትን ለማግኘት በሚፈጥሩት ዘዴና በጊዜ አጠቃቀማቸው በጣም ብልጦች ናቸው</em> – ብሎ ነበር። በኢትዮጵያ ገዢዎቻችን የሚያደርጉትም ይህንኑ ነው። ይሁን እንጂ የማታ ማታ ድሉ የእኛ ይሆናል።

<strong>    መታሰቢያዎን እያኖሩ ነው</strong>

ክቡር ፕሬዚዳንት፤ የእርስዎ ተቀዳሚ ተግባርና ሃላፊነት የአሜሪካንን ህዝብ ፍላጎት ማስጠበቅ መሆኑን በሚገባ እገነዘባለሁ። ይሁንና ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳመለከተው – <em>የሰው ልጆች ሁሉ ዕጣ ፈንታ የተቋጠረው በአንድ እራፊ ጨርቅ ነው።</em> የዴሞክራሲና የፍትህ ግብ የሰው ልጆች ሁሉ ግብ ሊሆን ይገባዋል። ይህም ከማንም የማይጎዳኝ መብት ጋር የሚፃረር አይደለም። እንደውም ከማንኛውም ሀገር ዘላቂ ሠላምና ብልፅግና ጋር የሚጎዳኝ እንጂ።

የግፍ አገዛዝ ምንጭ አንድ ሀገር አይደለም፤ አይሆንምም። ለተለያዩ አምባገነኖች የተለያዩ የአሜሪካ መንግሥት መሪዎች የሚያደርጉት ድጋፍ አፍራሽ ውጤት ያለው መሆኑ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው። በሌላ ወገን ደግሞ ለዴሞክራሲና ለፍትህ የሚደረግን ትግል መደገፍ ከሀገርዎ መስራች አባቶች መርህና የዴሞክራሲ መብቶችን ፍሬዎች ከሚያጣጥሙት የሀገርዎ ሰዎች መስመር ጋር የሚስማማ ነው።

ክቡር ፕሬዚዳንት፤ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ  ጁኒየር፤ <em>ኢፍትሃዊነት በየትኛውም ሀገር ለሚገኝ ፍትህ አደገኛ ነው</em> – ብሎ መናገሩ ስህተት ይሆን? በ21ኛው ክፍለ ዘመን በሚገኝ ‘ግሎባላይዜሽን’ ይህ አባባል ስሜት አይሰጥምን? በእርስዎ አስተሳሰብ፤ እኛ ብቻችንን መራመድ አለብን ይሆን፤ ክቡር ፕሬዚዳንት?

እንደርስዎ ሀገር ካሉ ዴሞክራሲያዊ ሀገራት ድጋፍ ያለመኖሩና ገደብ የለሹ የገዢዎቻችን ረገጣ በኢትዮጵያ የነፃነት ጎህ መጥቢያውን ጊዜ ሊያዘገየው ይችል ይሆናል። በበኩሌ ተረግጦ ለማይቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነት ትግል ያለኝን ቁርጠኛ ዕምነት እነሆ ዳግም አረጋግጣለሁ።

እርስዎ የእኛን ጉዳይ ጣጥለውታል ማለት እችላለሁን? አልችልም፤ ስለምን? ምክንያቱም፤ በእርስዎ በኩል ቀናነቱና ውስጣዊ ግፊቱ ካለ በፖለቲካው ጎራ ካልዎት ተደማጭነት ጋር ተዳምሮ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በአፍሪካ ለዴሞክራሲና ለፍትህ የሚደረገውን ትግል ለመርዳት አሁንም ጊዜው አልዘገየብዎትም ብዬ አምናለሁና።

የእርስዎ ዘላቂ መታሰቢያ በአፀደ ሥጋዎ {በአፍሪካዊ ደምዎ} ብቻ ሳይሆን በመንፈስም ጭምር ክብራቸውን በገዢዎቻቸው እጅ ከተገፈፉት ህዝቦች ጋር የተቆራኘ ሊሆን ይገባዋል። በአጠቃላይ በአፍሪካ እንዲሁም በኢትዮጵያ ለፍትህና ለዴሞክራሲ ህዝቡ የሚያደርገውን ትግል ጊዜ ሰጥተው በማስታወስ አስፈላጊውን ድጋፍና ርምጃ ይወስዱ ዘንድ በትህትና አሳስባለሁ።

&nbsp;

ከአክብሮት ጋር

አንዱዓለም አራጌ ወሌ

(የህሊኛ እስረኛ)

ማርች 2 2016

*************/////////////*****************

<em>    </em>

ምንጭ፤ <a href=”http://www.freeandualemaragie.org/archives/641″>http://www.freeandualemaragie.org/archives/641</a>

(ትርጉም፤ ሚያዚያ 2008 ዓ/ም {ኤፕሪል 2016} ሲድኒ፤ አውስትራሊያ)

<a href=”mailto:mmtessema@gmail.com”>mmtessema@gmail.com</a>

****************************************************************************************************

&nbsp;


የቀድሞ የጋምቤላ ፕ/ት 9 ዓመት ተፈረደባቸው (በእጅ ጽሁፋቸው የጻፉትና ምስጢር የያዘው የክስ መቃወሚያቸው እጃችን ገብቷል)

0
0

okello
(ዘ-ሐበሻ) የኖርዌይ ዜግነት እንዳላቸው የሚነገርላቸውና ደቡብ ሱዳን ላይ ታፍነው ተወስደው የታሰሩት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦኬሎ አኳይ “አገርን ለመገንጠል” በሚል በቀረበባቸው ክስ የ9 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው:: ኦኬሎ ከፍርድ በፊት ለሚዲያ ይድረስልኝ በሚል የላኩትና ለፍርድ ቤቱም በእጅ ጽፉፋቸው አስገብተውት የነበረው የክስ መቃወሚያ ዘሐበሻ እጅ ደርሷል:: ይዘነዋል::

ከኦኬሎ ጋር በተባባሪነት የተቀሰሱት ዴቭድ ኡጁሉ 9 ዓመት; ኡቻን ኦፔይ 7 ዓመት; ኡማን ኝክየው 7ዓመት; .ኡጁሉ ቻም 7ዓመት; ኦታካ ኡዋር 7ዓመት እና ኡባንግ ኡመድ 7 ዓመት ተፈርዶባቸዋል::

“ኦኬሎ አኳይ የአገሪቱን የፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካት ለቀረበው ክስ መቃወሚያ” በሚል ከፍርድ በፊት ክሱን ለመቃወም ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡትና ሕዝብም በሚድያ በኩል እንዲያውቀው የበተኑትን ደብዳቤን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ:-

ይድረስ ለስምንቱ ጌቶቻችን

0
0

 

TPLF

ነፃነት ዘለቀ (አዲስ አበባ)

 

የዚህን ደብዳቤ ርዕስ ለማውጣት እንደተቸገርሁት ያለ ችግር ለልጆቼ ስም ለማውጣት እንኳን አልተቸገርኩም፡፡ ቀላል ተቸገርኩ መሰላችሁ? ብዙ ጊዜ ፈጅቶብኝ ነው በዚህኛው የጠናሁት፡፡ በቅድሚያ ግን “እንኳን ለበዓለ ትንሣዔው [በሰላም] አደረሳችሁ” ማለት እፈልጋለሁ፡፡

“ይድረስ ለኢሕአዲግ” ማለት ፈለግሁ – ግን ኢሕአዴግ የሚባል የሕወሓት መሀል-አገራዊ ካባ እንጂ እውነተኛ ድርጅት አይደለምና የሰውን ሣይሆን የገዛ ኅሊናየን ትዝብታዊ አሽሙር ፈርቼ ተውኩት፡፡ “ይድረስ ለኢትዮጵያ ፓርላማ (እምጵ…ሣቄ አመለጠኝና መቆጣጠር አቃተኝ)” ልል ፈለግሁና አሁንም ኅሊናየ “አንተ ነፃነት! እንዲህ ያለ ቀልድ ይቅርብህ፤ ኢትዮጵያ ከመቼ ወዲህ ነው ፓርላማ ኖሯት የሚያውቀው? በየሥርዓቱ አንድ ከእግዜር የተላክሁ ነኝ ብሎ በሕዝብ የሚያፌዝ ኩርኩባ ወይም አብዮት ጠራችኝ ብሎ ትወልድንና ዘርን የሚያመክን ደመ-ሞቃት ያልተማረና ያልሠለጠነ ወታደር እየተነሣ የሚያላግጥበትን የእንቅልፋሞችና የደናቁርት ስብስብ ‹ፓርላማ› ብለህ አንተም እንዲሣቅብህ ትፈልጋለህ? በል እኮ አትቅለል!” ሲለኝ አፈር አልኩና ተውኩት፡፡ “ይድረስ ለኢትዮጵያ መንግሥት” ብዬ ልጀምር ስል ደግሞ “አይ፣ አሁንስ አበዛኸው! እንኳንስ ባንተ ከጥንት ጀምረህ በምትብሰከሰከው ኢሳትን ጨምሮ በሌሎች የተቃዋሚ ሚዲያዎችም ይህ ዓይነቱ አጠራር አላማረባቸውም፡፡ ምን ማለትህ ነው? ጥቂት ወሮበሎች ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆነው እንደፈለጉ የሚያሽከረክሩትን የዓሣሞች ማኅበር ነው እንደመንግሥት ቆጥረህ ‹ይድረስ ለኢትዮጵያ መንግሥት› ብለህ ለመጻፍ ያቆበቆብከው? ወሬኛ! በል እሱን ተወው – ሲያምርህ ይቅር፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥ  ‹መንግሥት አለ› ሲባል ምን ማለት እንደሆነ አንብብና ተረዳ፡፡ ሕዝብን ባልተወለደ አንጀት በርሀብና በአፓርታይድ አገዛዝ የሚያንገበግብ፣ ዜጋውንና የሚገዛውን አገር  ‹የኔ አገርና የኔ ዜጋ› ብሎ የማይቀበል ዐውሬና በሙስና የተጨመላለቀ ተቋም በምን ሒሣብ በመንግሥትነት ታውቆ ሊጠራበት ይችላል? ይህን ጉደኛ የምሥጦችና የአልቅቶች ቡድን በዚህ ስም መጥራት በ‹መንግሥት› መሠረታዊ ትርጉም ላይ እንደማሾፍ ይቆጠራል፡፡…” በማለት ኅሊናየ ተቆጣኝ፡፡ “ይድረስ ለሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ” ማለትም ወደድኩ፡፡ ኅሊናየ ግን “ሆ! መለስ ገድሏት የሄደውን ውድብ አለች ብለህ በርሷ አድራሻ ብትጽፍ ሌላውን ተወው ውስጠ ምሥጢሩን የሚያውቁ ወያኔዎችና ትግሬዎች ራሳቸው ይታዘቡሃል፡፡ ከ93ዓ.ም ዘመነ ህንፍሽፍሽ ወዲህ ለመሆኑ ሕወሓት አለች እንዴ? ‹ለመሆኑ አሁን ደርግ አለ?› እንደተባለው እንዳይመስልህ – ያ ሰው ያን ሲል ደርግ ልብስና ማዕረግ ለውጦ እዚያው ቦታ ነበርና፡፡ መለስ ግን በደንብ ገድሏታል ሕወሓትን፡፡ መጀመሪያ ከ93 በኋላ ሕወሓት ማለት መለስ ነበር፡፡ እሱ ሲሞት ግን የግለሰቦች ቡድን እንጂ ውድቢቱም ሆነች ውቃቢዋ ተያይዘው ጠፍተዋል፡፡ ማድመጥ እንጂ መደማመጥ የሌለበት፣ መታዘዝ እንጂ መተዛዘዝ የሌለበት የጌታና ሎሌ ሥርዓት ነው የተተከለባት – በፎቶ ብቻ በቀረችው ሕወሓት…፡፡” አለኝ፡፡ የቀን ጎደሎ አይግጠማችሁ፡፡ ለርዕስም እንዲህ መቸገር?

ታዲያ እንዴት አድርጌ address ላድርጋቸው? አልኩት ኅሊናየን – ምን ማለት እንዳለብኝ ግራ ቢገባኝ፡፡ “ ‹address› ላድርጋቸው? አንተም ተበላሸህ? በንግግርህስ ግዴለም – እንደብዙዎች የዘመኑ ቅንጡ ዜጎች አማረብኝ ብለህም ይሁን ራስህን በማጣት ሂደት ‹busy‹ ሆነህ ላያምርብህና አንተም የነሱ እነሱም ያንተ ላይሆኑ – በጉራማይሌህ ልትዥጎረጎር ትችላለህ፡፡ በጽሑፍ ግን …” ሲለኝ እኔም የራሴን ኅሊና ሲሳሳት ያዝኩትና “አሃ፣ አንተስ ይሄውና ‹ቢዚ› ብለህ ተናገርህ አይደል?” ስለው አፈር ብሎ “ምክሬን እንጂ አድራጎቴን አትከተል አላልኩህም?” አለኝና እንዳሻኝ እንደሆን ትቶኝ ነጎደ – ኅሊናየ፡፡

እኔም “ይድረስ ለስምንቱ ጌቶቻችን” በሚል ርዕስ ቀጣዩን አጭር መልእክት ለመጻፍ ተነሣሁ፡፡

Samora (2)

ይድረስ ለውድ ወንድሞቼ የሀገሬ ልጆች

አባይ ፀሐይ፣ አባይ ወልዱ፣ ዶክተር ደብረ ጽዮን፣ ዶክተር አርከበ፣ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ “ፕሮፌሰር ኢንጂኔር ጄኔራል” ሣሞራ የኑስ (የዩጋንዳው ኢዲያን ዳዳ ትዝ አላላችሁም?) አቦይ ስብሃትና ሥዩም መስፍን (ስምንት ሞሉ አይደል?)

 

ሕዝባችሁ በብዙ ነገር ከሕይወት መንገድ ወጥቶ በስቃይ ላይ መሆኑን የማታውቁ ከሆነ ይህን ግልጽ ደብዳቤ ከምጽፍላችሁ አንድ ምሥኪን ዜጋ“ችሁ” ተረዱ፡፡ የዚህን ደብዳቤ በድረገፆች መውጣት የተመለከተና ምናልባትም ያነበበ ዘመድና ወዳጅ ቢነግራችሁ በመሽቀዳደም አንብቡት – ልቦና ካላችሁ ያኔ እናንተም እኛም መጠነኛ የዕፎይታ ጊዜ ይኖረን ይሆናል፡፡

 

በሚሊዮን የሚቆጠር የመንግሥት ሠራተኛ አለ፡፡ ከነቤተሰቡ ቢሰላ ብዙ ሚሊዮን ይሆናል፡፡ ይህ ሕዝብ እንደእዮብ በኑሮ ቁስል ነፍሮ ሌት ከቀን እያለቀሰባችሁ ነው፡፡ አነስተኛና መካከለኛው ነጋዴም በተመሣሣይ ሁኔታ እያለቀሰባችሁ ነው፡፡ እርግጥ ነው በኢትዮጵያ ውስጥ የማያለቅስባችሁ የለም፡፡ እንደናንተ አመራርም በሉት ወይም እንደኛው አጠራር አገዛዝም እንበለው ሕይወታቸውን ያመሰቃቀላችሁባቸው የቤትና የዱር እንስሳት ሣይቀሩ ሁሉም ፍጡር አዝኖባችኋል፤ ሁሉም በየፊነው እያዘነባችሁና ለፈጣሪ ቅጣትም እያመቻቻችሁ ነው – ይህን በሚገባ አውቃለሁ፤ እናንተም የማታውቁት አይመስለኝም፡፡

 

አሁን እንዲህ አድርጉ፡- የሥራ ግብርና የንግድ ቀረጥ ቀንሱ፤ ከሌላው ዓለም ግብርና ቀረጥ ጋርም የናንተን አነጻጽሩ – መማር ያሳድጋል እንጂ አይገድልም፡፡ ትዕቢትና ዕብሪት ግን ውሎ አድሮ ለከፋ አደጋ ይዳርጋል፡፡  ምክሬን ብትሰሙ ትንሽ ዕድሜ ታገኛላችሁ፡፡ እርግጥ ነው – እናንተን በኃይልም ሆነ በምኞትና እንደኔ በዶልዷማ ብዕር እየታገሉ ያሉ ወገኖች ይህን ምክሬን እንደማይወዱትና እኔንም በወያኔነት ሊፈርጁኝ እንደሚችሉ እገምታለሁ፡፡ ምክንያቱም በናንተ ላይ ምሣር ማብዛት ሲገባ በሕዝብ ሊያስወድዳችሁ የሚችልን ነገር በተለይ አሁን በመጨረሻው ሰዓት እናንተን ለመምከር መቃጣት ለውግዘትና ለእርግማን እንደሚዳርግ አጥቼው አይደለም፡፡ ግን ግዴለም ልረገም፤ ልወገዝም፡፡ እናም ትንፋሽ ስጡን፡፡ እያቃሰትን ነፃ ከምንወጣ እስትንፋስ እያገኘን እናንተም ያማረ ስንብት እንድታደርጉ እየጸለይንላችሁ ሁላችን ብንኖር ይሻላል – ተያይዘን ከምንጠፋ፡፡ ስለዚህ በተለይ የአዲስ አበባንና ባጠቃላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመበቀል የገባችሁትን ውልና ሰይጣናዊ ቃል ኪዳን አሁኑኑ አፍርሱና ተመራርቀን እንለያይ፡፡ እናንተም ለክፉ ቀን ወዳስቀመጣችሁት ቢሊዮኖቻችሁ – እኛም እግዜሩ ወዳዘጋጀልን ቀጣይ ሕይወት፡፡ እንዲህ የምለው ይህ ስንብታችን የማይቀር የታሪክና የተፈጥሮ ዕዳ ስለሆነ እንጂ  አራት ኪሎን የሚቆጣጠር የኢትዮጵያ ትንሣኤ ሠራዊት በግልጽ እየታየኝ አይደለም፡፡ ቢታየኝ ምን አስደበቀኝ?

የሠራተኛን የገቢ ግብር እንመልከት፡፡ የምናገረው በጥራዝ ነጠቅ ዕውቀቴ ነው – የኢኮኖሚ ባለሙያ አይደለሁም፡፡ ኧረ የምንም ሙያ ባለቤት አይደለሁኝም – ከወሬ በስተቀር፡፡

 

ሠራተኛው የገቢ ግብር ከደሞዙ ይቆረጣል – እንደብዙ ነጋዴ የሚያምታታበትና ግብር የሚያጭበረብርበት ወይም ከግብር ከፋይነት የሚያመልጥት አንዳችም መንገድ የለውም (tax evasion/tax avoidance)፤ ምክንያቱም በአባይም ይሁን በተከዜ እዚያው ሒሣብ ክፍል ውስጥ ተጎማምዶ ብጫቂው ስለሚደርሰው በገቢው ላይ ምንም ሥልጣን የለውምና፡፡ ይህ ግብር የተመደበው በቀዳማዊ ኃ. ሥላሤ ዘመን ነው – መጠነኛ መሻሻል ተደርጎ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁንና ከልምድ እንደምንረዳው ምናልባት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ኃላፊዎች በደሞዛቸው እንደሚኖሩ ስለማይገመት እነዚህ ሰዎች የተራውን ሠራተኛ ብሶትና የአኗኗር ሁኔታ ማወቅ እንደተሳናቸውና እንደማያስቡለትም በጣም የታወቀ ግን መፍትሔ የራቀው መሪር እውነታ ሆኗል፡፡ ፓርላማ ተብዬውም አሻንጉሊት በመሆኑ ወከለው የሚባለውን ሕዝብ ችግር አጢኖ ለለውጥ አይታገልም – ትምህርት የሌለውና ከቡሃቃ ሊጥና ከእርሻ ቀምበር በጅ ጥቅሻ ተነስቶ ፓርላማ የሚገባ ደንቆሮ ዜጋ የቆመበትን ዓላማ ያውቃል ብሎ ማሰብም አይቻልምና ከነሱ ምንም አልጠበቅንም፤ አንጠብቅምም፡፡ ከነሱ ይልቅ ወደላይ ማንጋጠጥ በጣም የተሻለ ነው፡፡ ቢዘገይም መልስ አይጠፋም፡፡ “አላህ ዳተኛ ነህ ታስጨርሰናለህ” ተብሎ በተራው የጀማ አባል የተነገረውን ዚቅም አንርሳ ታዲያ፡፡ ማንጋጠጥ ብቻውን ዋጋ የለቀውም፡፡ ያለ ሥራ ተጎልተው ቢያንጋጥጡ አንገትን ማድከም ነው ትርፉ፡፡ እኛው ለእኛው ያልሆንን ከሩቅ ብዙ አንጠብቅ፡፡ ጊዜ ይፈጃልና፡፡

 

እናንተ ግን የተወሰነ እፎይታ እንድናደርግ ማድረግ የምትችሉት ብዙ ነገር አለ፡፡ በማታዋ ዝግ ስብሰባችሁ ይቺን ደብዳቤ ተመልከቷትና አንዳች ነገር አድርጉ፡፡ አጉራችሁ ጠናን!

 

የኛ ሀገር የገቢ ገብር (income tax) ከሌሎች ሀገሮች ጋር ሲወዳደር እርግጥ ነው ብዙ ነው ተብሎ የሚደነቅለት አይደለም፡፡ ትንሽም ነው አይባልም፡፡ ይሁንና የአሁኑ ግብር የተመደበው ገንዘባችን ትርጉም በነበረው ሰዓት መሆኑን ማንም ያጤነው አይመስልም፡፡ የዱሮው የቀ.ኃ.ሥ አንድ ብር አሁን በአማካይ 500 ብር ገደማ ነው፡፡ አሰብ ላይ በአራት ብር፣ አዲስ አበባ ላይ በስድስት ብር ይገዛ የነበረው አንድ ሬድ ሌብል ዊስኪ ዛሬ ሊያውም አንደኛ ደረጃ ፎርጅድ ተብሎ በግልጽ እየተነገረህ 800 ብር ገደማ ነው(ከቡና ቤቶች ውጪ!)፤ በቀ.ኃ.ሥ ዘመን በኩንታል ብር 12 የነበረው የአድኣ ማኛ ጤፍ ዛሬ በአማካይ ብር 2300 ነው፤ በቀ.ኃ.ሥ ከ3 – 5 ብር የነበረው አንድ ወቄት የ18 ካራት ወርቅ አሁን ተክሉ ደስታ ሂድና ጠይቅ – ከ1000 ብር በላይ ነው፤ ልቀጥል? ለምን በትዝታ ባህር አስዋኝሃለሁ! ይበቃል፡፡ እንግዲህ ልብ አድርግ፡- የቀድሞው አንድ ብር አሁን በአማካይ 500 ከሆነ የኔ ደሞዝ ደግሞ በያኔው መነሻ እንኳን ታስቦልኝ – ካልኩሌተር ስጠኝማ – 600×500=300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) ሊሆን ይገባው ነበር – ይህም በጣም ባነሰ ግምት ነው – (ያኔ ዱሮ የ30 ብር ደሞዝተኛ ቤቱ ሳይጓደል ዕቁብ ገብቶ አዲስ አበባ እምብርት ላይ ቆንጆ ቪላ ይገነባ ነበር፤ አሁን የ30 ሺህ ብር ደሞዝተኛ ወር እስከወር ድራፍትና ቢራ ይጠጣ እንደሆነ እንጂ ቁም ነገር አይሠራበትም)፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ ሌላ ስሌት አለ፡፡ ያም ዱሮ ለምሣሌ 10 በመቶ ግብር የሚጀምረው የአንድ መቶ ብር ደሞዝ ላይ ቢሆን (ከዚያ በታች ያለው ዜሮ ሆኖ) አሁን እስከ 100ሺህ ብር ድረስ ነፃ ሊሆን እንደሚገባ ያስቧል፡፡ ምኞት አይከለከልም – የተናጠል ዕድገትም ነውር ነው – ይህ ዘመን ወለድ ችግር ለማይገባችሁ ሞልቃቆች ነው እንዲህ የምለው፡፡

abay weldu 2

እነአባይ ሆይ! ሠራተኛችሁ በቁሙ እየሞተ ነው፡፡ ደመወዙን አሻሽሉለት – ቢያንስ ዳቦ በልቶ እንኳን ይሙት – ቢጥሌ ዳቦ በ3 ብር ቢገዛ አንጀቱ ላይ ጠብ አትልም፡፡ እናንተ ቤት ድመት የሰለቻት ሥጋ፣ ውሻ ያንገሸገሸው አጥንት በድሃው ሠራተኛ ቤት በህልም የሚታይ ቅዠት እንጂ በእውን የሚገኝ ሲሳይ አልሆነም – በሌብነት ወይም በሀብታም ዘመድ አዝማድ ካልተደጎመ በስተቀር ማንም የመንግሥት ሠራተኛ ሥጋ የመብላት አይደለም የማየትም መብት የለውም፡፡ ትልቅ ደሞዝ ተብሎ 2000 ብር የምትከፍሉት ሠራተኛችሁ በረንዳ አዳሪ ነው – በረንዳ ስለሞላ እሱም እንደሎተሪ ሆኖበት በየድልድዩ ሥር እየተኛላችሁ ነው፤ ይህ ደግሞ ግፍ ነው፡፡ በእናንተ ባይደርስ በልጅ ልጆቻችሁ ተመልሶ በተለያዬ መንገድ ታገኙታላችሁ፡፡ በነገራችን ላይ የግፍ ብድራት በግድ በገንዘብ ማጣት ብቻ አይመለስም፤ ፍቅርን ማጣት ችግር ነው፤ የኅሊና ሰላም ማጣት ችግር ነው፤ የአእምሮን ጤንነት መነጠቅ ችግር ነው፤ የሚስት/የባል ክህደት ራስን ሊያሰቅል የሚችል ሥነ ልቦናዊና ማኅበራዊ ችግር ነው፡፡ ስለዚህ ወንደሞቼ “ሁሉ በጄ ሁሉ በደጄ” ብላችሁ በሕዝብ ስቃይ መዝናናታችሁን ብትቀጥሉ የፈጣሪ ቁጣ መምጫው አይታወቅምና በአንዱ ወይ በሌላው አኮርባጅ አሣራችሁን ታያላችሁ፤ ስለሆነም እኛን አሁን ተመልከቱን፤ ሕዝቡን “ሕዝባችን” በሉና ዛሬውኑ ይህን ችግር ቅረፉ፡፡ ታረቁት፤ ይታረቃችኋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የዋህ ነው፤ ይምራችኋል፡፡ ያኔ ዘር ይወጣላችኋል፡፡ አለዚያ ምን አለ በሉኝ እንደተቅበዘበዛችሁ ትቀራላችሁ፡፡

 

አንድ ወዳጄ 3ሜ. በ4ሜ. ቤት ዛሬ ጧት ገርጂ አካባቢ በ3000 ብር መከራየቱን ቅድም ነገረኝ – ሌላ ምርጫ የለውም፤ አዘንኩለት፡፡ “እንዲያውም የኔ ርካሽ ነው!” አለኝና ያ ቤት መሀል ከተማ ቢሆን ከ4000 ብር በታች እንደማይገኝ አስረዳኝ – 3ሜ. በ 4ሜ. ጠባብ ክፍል፡፡ ከደመወዙ ተቆራርጦ የሚደርሰው ብር 5000 አካባቢ ነው – የሱ ትልቅ ደሞዝ ሆኖ ሊያውም፡፡ ተሯሩጦ ሌላም ስለሚሠራ ቀሪውን ለመሸፈን ይሞክራል እንጂ በ2000 ብር ከ3 ቤተሰቡ ጋር አንድ ወር ቀርቶ አንድ ሣምንት ሊኖር አይችልም – ይሄ ተሯሩጦ መሥራት ደግሞ ሰውን ሁሉ ፉዞና ግዴለሽ እያደረገው ነው – ለምንም ነገር በቂ ትኩረት አይሰጥም፤ ለእንጀራ እንጂ ለኅሊናና ለሀገር እየኖረ ባለመሆኑ በሥጋው ምሪት ይነጉዳል – እናም ሥራውን ይበድላል፤ ይዋሻል- ይቀጥፋል… በአንድ ጊዜ ብዙ ቦታ የመገኘት አባዜ ችግሩ ይህ ነው – እዚህ ነው ሲሉት እዚያ ነው፤ እዚያ ነው ሲሉት እዚህ ነው…. ይህ ነገር በቅጡ ይታሰብበት፤ በአንድ ቦታ ጥሩ ይከፈለው – ቀሪ ጊዜውን ለራሱ ችግርና ለማኅበራዊ ሕይወቱ እንዲያውለው ይደረግ፡፡ ማንም የሚኖረው አንዴ አይደለም እንዴ?

 

ስለዚህ እነአባይ ሆይ ጥቂት ፋታ ስጡን፡፡ ትንሽ እፎይ እንበል፤ ደግሞም ካሻችሁና ጊዜ ካላችሁ ቆይታችሁ የእሳት ግርፊያችሁን ትቀጥላላችሁ፡፡ አሁን ግን ትንሽዬ ዕረፍት – ሲዖል ውስጥ እሁድ እሁድ አለ እንደሚባለው ያለ ዕረፍት – ስጡንና ተንፈስ እንበል፡፡

 

የዓለም ሀገራት የገቢ ግብር(income tax) ከዜሮ እስ 60 በመቶ እንደሚደርስ ቅድም ድረገፃዊ መዝገብ  ሳገላብጥ አየሁ፡፡ አሥር አካባቢ የዐረብ ሀገራት ግብር ሀራም ነው ብለው ምንም አያስከፍሉም፡፡ ቻድ፣ አይቮሪኮስትና አሩባ የሚሏቸው ጉደኛ ሀገሮች ደግሞ 60 በመቶ የሚደርስ ግብር ያስከፍላሉ፡፡ ከስንት ደሞዝ እስከስንት ደሞዝ የሚለውን ግን ማየት ያስፈልጋል፡፡ ራሽያ ለሠራተኞቻቸው ቅን ከሚያስቡ ደጋግ ሀገሮች ውስጥ  ትመደባለች – 13 በመቶ ነው ትልቁ የገቢ ግብር፡፡ ጓቴማላና ሞንቴኔግሮ ደግሞ በጣም ሩህሩህ ናቸው – 7 እና 9 በመቶ ብቻ! በተረፈ ሊቢያን ጨምሮ በርከት ያሉ ሀገሮች ከሠራተኞቻቸው የሚቆርጡት ትልቁ የገቢ ግብር ከ10 እስከ 20 በመቶ ነው፡፡

 

የኛ ግን ያለ ዕውቀትና ያለርህራሄ ብዙ ብር የሚመዘበርበትን ቫትን ጨምሮ ከ50 በመቶ ይበልጣል፡፡ የኛ ሰዎች ቫት የሚቆረጥበትንና የማይቆረጥበትን እንኳን ለይተው አያውቁም – በሁሉም መቁረጥ ነው፤ የወያኔ ትክኖክራች ካለገንዘብ ዐይናቸው አይከፈትም – በየምትሄድበት ቢሮ አምጡ ነው፤ በዚያ ላይ ጉቦው አይጣል ነው፡፡ (እንደኔው ከት ብላችሁ እንዳትስቁ እንጂ አንድ ምሥጢር በቅንፍ ልንገራችሁ፡፡ አንድ የሕዝብ መዝናኛ ቀበሌ ትርፍራፊ ምግብ ለውሻቸው ለተከራዩ ሰዎች ‹ቱሬውን› ቫት እያስከፈለ ይሸጥላቸው ነበር፡፡ በኋላ አፈሩ መሰለኝ ቫቱን ሳይተውት አይቀርም፡፡ ተርፎ በተጣለ ምግብ ቫት ሲከፈል ይታያችሁ – ይህ የሚሆነው ደግሞ ድንቁርና እየተስፋፋ፣ ዕውቀት እየጫጫና እየተሰደደ በሚገኝባት ኢትዮጵያ ሀገራችን ውስጥ ብቻ ነው፡፡ የቫት አከፋል ጉዳይ ቢመረመር ብዙ ጉድ አለው፡፡ ተናደዱ እንጂ ታዲያ የምን ዝምታ ነው!)

 

በውጭ ንግድ ዘርፍ ወደ ሀገር የሚገቡ ዕቃዎች ላይ የሚጣልን ቀረጥ ካየን ጤናማ ነን የምንል ወገኖች ልናብድ እንችላለን፡፡ ልብ አድርግ፡- ዱባይ ላይ በ50 እና በ60 ሽህ የኢት› ብር የሚገዛ ያገለገለ መኪና በምን ሥሌት አዲስ አበባ  ላይ 300 እና 500 ሽህ ብር እንደሚሸጥ ስትጠይቅ የሚሰጥህ መልስ በዋናነት ቀረጡ እጅግ ውድ መሆኑ ነው – ሌላ ሀገር በሠራው መኪናና የፋብሪካ ውጤት የደከሙት በህልም እንኳን የማያስቡትን የገንዘብ መጠን የወያኔው መንግሥት ካላንዳች ልፋት በቀረጥ ብቻ እንዲህ ሲዝቅበት አውሮፓውያን ቢሰሙ ምን እንደሚሉ አላውቅም – ግፍ እየተሠራባቸው እንደሆነ ካላወቁ ተሞኝተዋል፡፡ ለማንኛውም መንግሥትና ትላልቅ ነጋዴዎች እየተመሳጠሩ ሕዝቡን ፈጁት፤ አንገቱን በንዋይ ቢላዎ አረዱት፡፡ ከቻይና በሣንቲሞች ግፋ ቢል በጥቂት ብሮች የሚመጣ ከደረጃ በታች የሆነ ጨምዳዳ ሸሚዝ ሸገር ላይ ከብር 500 በላይ መሸጡን ስታይና ስትሰማ በሀገርህ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ግራ ይገባሃል፡፡ እኛና ቁጥር አዲዮስ – ተለያየን አለች ያቺ የኩታበር ምሥኪን ሴት ልጇን ደራሽ ጎርፍ ሲወስድባት፡፡

 

እነአባይ ጥቂት አሰብ አድርጉና በዚህ በምላችሁ ጉዳይ ላይ አንዳች ነገር አድርጉ፡፡ ሀገሪቱ የምትተዳደረው በግብርና በቀረጥ አስመሰላችኋት፡፡ እንደምገምተው የሀገራችን ብሄራዊ በጀት 80 በመቶ የሚሆነው ምንጩ ቅጣት፣ ብድርና ዕርዳታ፣ የገቢ ግብርና ቀረጥ ሣይሆን አይቀርም፡፡ ለዚህም እኮ ነው አንድ የትራፊክ ፖሊስ በተወሰነ ጊዜ በቅጣት ገቢ ካላስገኘ በኪራይ ሰብሳቢነት ተገምግሞ ከሥራ የሚቀነሰው ወይም ወደሌላ ክፍል የሚዛወረው፡፡ እባካችሁ ሀገሪቱ በደናቁርት እየተመራች መሆኗን ሌሎች ሀገራት እንዳይጠረጥሩ ሰልጠን ያላችሁ ወያኔዎች ከዚህ ዛሬ ከቀበጣጠርኩት ነገር አንዳች ነገር ቅሰሙና የሆነ ነገር አድርጉ፡፡ ደግሞም ትችላላችሁ፡፡

አቶ አባይ ጸሐዬ

አቶ አባይ ጸሐዬ

በሌላ በኩል የሚታየኝን ልንገራችሁ፤ ሰው መግደላችሁን አሁኑኑ አቁሙ – ባትገሉትም በቁሙ ሞቷልና  የሞተንና ተስፋ ያጣን ትውልድ መግደል ጀግና አያስብላችሁም፤ የጀግንነት መሠረት ሕይወትን ከሞትና ከጥፋት መታደግና  የጠወለ ተስፋን ማንሠራራት እንጂ አለኝታና ዋስ ጠበቃ የሌለውን ምሥኪን ዜጋ ማንገላታት፣ መግደልና በገባበት እያሳደዱ የተፈጠሩበትን ቀን ማስረገም አይደለም፡፡ ማንኛውንም  ኅቡዕና ግልጽ የማሰቃያ ማዕከላችሁን በአስቸኳይ ዝጉ፡፡ የሂትለር ጁስታፖ ምን እንደደረሰበት ዕወቁ፡፡ የሁሉም ክፉ ነገሮች መጨረሻ እንደማያምር ከደርግና ከቀደሙ መጥፎ ሥርዓቶች ብቻ ሣይሆን ከአለቃችሁ ከመለስ ዜናዊም ተማሩ – መለስ መንስኤው ምንም ይሁን ምን ግን እንዲያ ተበለሻሽቶ የሞተው በሠራው ወንጀልና ባፈሰሰው ደም ምክንያት ሕዝብ አልቅሶበትና ፈጣሪ ቀኑን አሳጥሮ ቆርጦበት ነው፡፡ ስለዚህ ማሰሩ፣ ማሰቃየቱ፣ መግደሉና በሰው ልጅ መከራ መደሰቱ የትም አያደርሳችሁምና ባፋጣኝ ወደኅሊናችሁ ተመለሱ – ይህን የምላችሁ እናንተ ገና ያልተበላሸ ወርቃማ ዕድል ስላላችሁ ነው፤ ካበላሻችሁት በኋላ ግን መፀፀቱ ፋይዳ የለውም፤ እኔን ግን አይቆጨኝም፡፡

 

ሁሉን አያችሁት፤ አሁን አጉል እልህ ይዟችሁ እንጂ ሁሉም ነገር እንደሰለቻችሁ አምናለሁ፡፡ ግዴላችሁም ዛሬስ ተሸነፉ፡፡ አሸናፊ ሲጠፋ አንዳንዴ ራስን በማሸነፍ ድል መቀዳጀት ይቻላልና አዲስ ኢትዮጵያዊ ታሪክ ሥሩ – በአንዴ ላይሆንላችሁ ይችላል – ግን ሞክሩት፤ ታተርፉበታላችሁ እንጂ አትከስሩበትም፡፡ እንዲህ ብታደርጉ ኢትዮጵያም፣ ታሪክም፣ ትውልድም ብፍላይ ድማ ጎይታና እግዚአብሔር እውን ይäረታ ክገብረልኹም ይክዕል – ንዕዑ ዝሰኣኖ ነገር ስለዘይብሉ፡፡ ኤዲያ እናንተዬ ስናደድ ትግርኛ ነው የሚቀናኝ – ዱሮ ጣሊያንኛ ነበር እንዲህ ስበሳጭ ጣልቃ እየገባ የሚያስቸግረኝ፡፡  ለነገሩ በትግርኛና በጣሊያንኛ መናደድ ስሜትን በቀላሉ ሳይገልጥ የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም “እንኳዕ ካብትን ክልትዔን ቋንቋታት ተፈጢርና!” አሪቬዴርቺ፡፡

በጋምቤላ ውጥረቱ እየተባባሰ መሆኑ ተገለጸ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

0
0

ሚያዚያ 18 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (April 26, 2016 NEWS)
# በጋምቤላ ውጥረቱ እየተባባሰ መሆኑ ተገለጸ
# ለጥጥ ልማት በማለት ብድር ወስደውና ደን መንጥረው የነበሩ ግለሰቦች ጠፉ ተባለ
# የትንሣዔ በዓልን አስታኮ ወያኔ የሸማቾች ማህበራት ሱቆች እያቋቋመ ነው
# የጄኔራሉን ገዳዮች ባስቸኳይ እንዲይዙ የብሩንዲው ፕሬዚዳንት ለጦር ኃይሉ መመሪያ ሰጡ
# አልሸባብ በባይደዋ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦር ሰፈርን ወርሮ ጉዳት አደረሰ
# የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በሱማሊያ የገባውን ድርቅና ረሃብ ለመቋቋም የምግብ እርዳታ ያስፈልጋል አሉ
#ሬክ ማቻር ጁባ ገቡ

ሚያዚያ 18 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø ጋምቤላ 18 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ባለው የደቡብ ሱዳን የጀዊ ስደተኞች ሰፈር የፈነዳው ግጭትና ግድያ ትላንትም ቀጥሎ እንደነበር በቦታው ያሉ ምስክሮች ገልጸዋል ። በቦታው የሰፈሩት ስደተኞች መቶ በመቶ የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ የሪያክ ማሻር ተከታዮችና የኑዌር ተወላጆች ሲሆኑ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ሾፌር የነበረው ኢትዮጵያው ሁለት ስደተኛ ህጻናትን በመኪና ገጭቶና ገድሎ በመሰወሩ ኑዌሮቹ በሰፈሩ ያሉትን ኢትዮጵያውያን ለመግደል ተነስተው ብዙዎችን እንደገደሉ ይታወቃል ። ከተገደሉት ውስጥ የስደተኛው ኮሚሽን ኢትዮጵያዊ ሰራተኞችም እንዳሉበት ታውቋል። ጀዊ የአንዋኮች አካባቢ ስትሆን ወያኔ ኑዌሮችን በዚያ ያሰፈረው ለተንኮል ነው ተብሎም ተጋልጧል። ወያኔ ከግድያው በኋላ ዜጎችን ለመከላከል ምንም እርምጃ ባለመውሰዱ ኢትዮጵያውያኑ ተደራጅተው የስደተኛውን ሰፈር ማጥቃታቸው ታውቋል። የሟቹ ቁጥርም ቀላል አልሆነም ። የተባበሩት መንግስታት የስድተኛ ኮሚሽን ሰራተኞቹን ከጀዊ አካባቢ አሽሽቷል። ግጭቱ ገና አልበረደም ሲል ዛሬም የደረስ ዜና ያረጋግጣል ።
Gambela

Ø ወያኔ ለዘረፋና ለስርቆት እንዲያመቸው ከ 100 ሺ ሄክታር በላይ የጋምቤላ መሬትን ለጥጥ እርሻ በማለት ለንግድ ሸሪኮቹ በመስጠትና ለልማትም በማለት 3 ቢሊዮን ብድር በመፍቀድ የጥጥ ምርትን እናሳድጋለን በማለት ፕሮፓጋንዳውን ካሰራጨ ወዲህ የጥጥ ምርቱም ሳይኖር ልማቱም ሳይካሄድ ደን ተጨፍጭፎ ከቆየ በኋላ በብድር የተሰጠው ገንዘብ ለምን ተግባር እንደዋለ እንኳ ለማወቅ አለምቻሉ ተገልጿል። ለጥጥ ልማት በማለት መሬት ወስደው ደን መንጥረው ገንዘብ ተበድረው ጠፉ የተባሉ ሰዎችና ኢንቬስተሮች እነማን እንደሆኑ ባይገለጽም ወያኔ ምርመራና ማጣራት ጀምሬያለሁ ብሏል። ጉዳዩን የተከታተሉ ወገኖች ግን ዘረፋውና የተፈጥሮ ወድመቱ በወያኔ አባላትና በንግድ ሸሪኮቻቸው መፈጸሙን ይናገራሉ።

Ø በአባይ ወንዝ ግድብና አጠቃቀም ዙሪያ ወያኔና ግብጽ የገቡበትን የፖሊቲካና የዲፕሎማሲ ውዝግብ ለማብረድ በወያኔ ፓርላማ አፈጉባዔ የሚመራ አንድ የልኡካን ቡድን ግብጽንና ሱዳንን መጎብኘቱ ይታወሳል። የጉብኝቱ ዓላማ የታሰበለትን ግብ ይምታ አይምታ ባይታወቅም በወቅቱ የነበረውን የዲፕሎማሲ ውጥረት ግን ሳያለዝበው እንዳልቀረ ተገምቷል፡፤ ወያኔ ከሱዳን ጋር መልካም ወዳጀነት ፈጥሮ በድንበር አካባቢ ለም መሬቶችን አሳልፎ ከሰጠና ሱዳንም በአገሩ የሚገኙ የወያኔ ተቃዋሚዎችን እያፈነ ለወያኔ ለመስጠት ጥረት በሚያደርግበትና በሁለቱ አገሮች መካከል የድንበር ጥበቃ ውል ተፈርሞ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የሱዳን ሕዝብ ዲፕሎማሲ የተባለ ቡድን የወያኔን ባለስልጣኖችን እንደሚያነጋግር ተገልጿል። ጉብኝቱ ግንቦት 1 ቀን 2008 ዓም የሚጀመር ሲሆን የዲፕሎማሲው ቡድን ከወያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ጀምሮ ከሌሎች የወያኔ ባለስልጣኖችን ያናገጋራል ተብሏል፡፤

Ø መጭውን የትንሳዔ በዓል አስታኮ የወያኔ አገዛዝ ሱቆችን በማደራጀት አባ ወራዎችን በቡድን እየመደበ እንደሚያሰማራ ታውቋል። ከአስራ አምስት እስከ ሃያ የሚደርሱ አባወራዎች በአንድና በሁለት ሱቆች ሸቀጦች እንዲሸጡ በማደራጀትና በማስገደድ ነዋሪዎንና የነጋዴው ህብረተሰብን ለማጋጨት እየተሞከረ መሆኑ ተገልጿል። ሱቆቹ በዋናነት ስኳርና ዘይት የሚያቀርቡ ሲሆን ሌሎች ሸቀጦችንም ሊጨምሩ እንደሚችሉ ተነግሯል። የወያኔ አገዛዝ በመላ ኢትዮጵያ ላንሳራፋው የኑሮ ውድነት ተጠያቂ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም የችግሩ መነሻና ምንጭ የነጋዴው ህብረተሰብ እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ ነጋዴዎችን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት የሸማቾች ማህበራትን ማቋቋሙ ይታወቃል። የፋሲካ በዓልን ተንተርሶ እንደ ቅቤ እንቁላል ዶሮ በግና በሬዎች የመሳሰሉ የምግብ አቅርቦቶች ዋጋ ጭማሪ እያሳየ መሆኑ ታውቋል።

Ø ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለወያኔ ማስረከብ የለመደበት የኬንያ መንግስት የታይዋን ተወላጅ ሆነው በህገወጥነት የወነጀላቸውን የታይዋን ተወላጆች አስሮ ለሀገራቸው ሳይሆን ለቻይና ማስረከቡ ተጋለጠ። ቻይና ታይዋን ግዛቴ ናት ብትልም ቻይናና ታይዋን ሁለት የተለያዩ ሀገሮች ሆነው እንድሉ ይታወቃል። ወያኔ በበኩል ኬንያ እንደ የመን የሚመጡ ተቃዋሚዎችን አግታ እንድታስረክብ ዝርዝር ስሞችን ሰጧል ተብሎም መረጃ አለ ።

Ø ከጥቂት ቀናት በፊት በብሩንዲ አንድ የጄኔራል ማእርግ ያላቸው ከፍተኛ ባለስልጣን ከነባለቤታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ገዳዮችን አፈላልገው እንድይዙ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ለወታደሮቻቸው የአንድ ሳምንት የጊዜ ገደብ ያለበት ጥብቅ መመሪያ የሰጡ መሆናቸው ታውቋል። ፕሬዚዳንቱ ለሟቾቹ ቤተሰቦች ሀዘናቸውን የገለጹ ሲሆን የአገሪቱ የጦር ኃይልም አንድነቱን አጠናክሮ ሁኔታውን በቁጥጥር ስር እንዲያደርግ ተማጽነዋል። የፕሬዚዳንቱ ትእዛዝ በብሩንዲ እየተካሄደ ያለውን ግድያ ያፋፍማል የሚል ስጋት ፈጥሯል። የብሩንዲ የእርስ በርስ ግጭት ከጀመረ ወዲህ የመንግስት ባለስልጣኖች ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች ሲገደሉ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ደግሞ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጅምላ ግድያ እያካሄዱ ከመሆናቸውም በላይ በርካታ ሰዎችን አስረው ሰቆቃዊ ድርጊት እየፈጸሙባቸው መሆኑ ይነገራል።

Ø በሱማሊያ ከዋናዋ ከተማ ከሞጋዲሾ ሰሜን ምዕራብ 250 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ከባይደዋ ከተማ አጠገብ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት እና የሱማሊያ መንግስት የጦር ካምፕ ላይ አልሸባብ ጥቃት ሰንስዝሮ ቢያንስ 20 ወታደሮችን የገደለ መሆኑ ከስፍራው የተገኘው ዜና ይገልጻል። ከተወሰነ የተኩስ ልውውጥ በኋላም የአፍሪካ ህብረት የሰላም አሰከባሪ ሃይሎች እና የሱማሊያ ወታደሮች የጦር ሰፍሩን መልሰው መቆጣጠራቸው ተነግሯል። የአልሸባብ አጥቂዎችም ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ቢገልጽም ከአልሸባብ በኩል የተሰማ ዜና የለም።

Ø መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የሰብአዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ በሱማሊያ የገባውን ከፍተኛ ድርቅና ረሃብ ለመቋቋም አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ድርጅቶቹ በጋራ መግለጫቸው ላለፉት አራት አመታት በሱማሊያ ዝናም በመጥፋቱ ምክንያት ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ መሰደዱን ገልጸው ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ከፍተኛ እልቂት ሊኖር እንደሚችል ተናግረዋል። ከስድስት ዓመት በፊት በሱማሊያ በገባው ድርቅ ምክንያት ከ250 ሺ ሰው በላይ የሞተ መሆኑን አስታውሰው ተመሳሳይ የሕዝብ እልቂት እንዳይደርስ ከፍተኛ እርዳታ መሰብሰብ አለበት ብለዋል።

Ø ከጥቂት ቀናት በፊት ከአንድ የቱርክ የንግድ መርከብ ላይ በባህር ላይ አፋኞች ተጠልፈው ተወስደው የነበሩ ስድስት የመርከቡ ሰራተኞች የተለቀቁ መሆናቸውን የንግድ መርከቡ ባለስልጣኖች ገልጸዋል። ሚያዚያ 3 ቀን 2008 ዓም. ማንነታቸው ያለታወቀ የባህር ላይ አፋኞች መርከቧ ላይ በመውጣቱ ካፕቴኑ የሚገኝበትን ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን ማክሰኞ ሚያዚያ 18 ቀን 2008 ለቀዋቸዋል ተብሏል። የተለቀቁት የመርከቧ ሰራተኞች በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ መሆናቸው ቢነገርም ለመለቀቃቸው ካሳ መከፈሉ እና አለመከፈሉ የተገለጸ ነገር የለም። በዚህ ዓመት ብቻ በናይጄሪያ ወደብ አካባቢ ከ32 በላይ የመርከብ ጠለፋዎች የተካሄዱ መሆናቸው ከተባበሩት መንግስታ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አካባቢ የተገኙ ዜናዎች ይጠቁማሉ።

Ø የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ ሪክ ማቻር ለአንድ ሳምንት ያህል ጉዟቸው ካዘገዩ በኋላ በዛሬው ቀን ጁባ ገብተዋል። የአማጽያኑ ድርጅት ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ ሚስተር ማቻር ዛሬ ሚያዚያ 18 ቀን ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ ጁባ የሚገቡ መሆናቸውን ገልጾ የነበረ ሲሆን በታቀደው መሰረት ለምክትል ፕሬዚዳንቱ ቦታ ለመያዝ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል ተብሏል። ሚስተር ማቻር ጁባ ይገባሉ ተብሎ ታቅዶ የነበረው ሚያዚያ 10 ቀን የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላ በተደጋጋሚ በታቀዱት ቀናት ወደ ጃባ ባለመለሳቸው በዓለም አቅፉ ህብረተሰብ በሌሎች ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮ እንድነበር አይዘነጋም።

በአዲስ አበባ ባለ5 ፎቅ ህንጻ ተደረመሰ

0
0

addis ababa
በአዲስ አበባ በተለምዶው ሠሚት የሚባለው የአዲስ አበባ ሰፈር የደረሰው ይኸው የህንፃ መደርመስ ዛሬ ንጋት ላይ ያጋጠመ ሲሆን በወቅቱ በፎቁ ላይ ሰው ስላልነበረ የሰው ህይወት ተርፏል ሲል አድማስ ራድዮ ዘገበ::

አድማስ ራድዮ እንደዘገበው ፎቁ የተጀመረ ፎቅ ነው። ከታች ግን ሁለት ባንኮች ባላለቀው ፎቅ ስር ሆነው አገልግሎት ይሰጡ ነበር። በአገር ቤት በያንዳንዱ ያላለቀ ፎቅ ሥር ባንኮች እንዳሉ ይታወቃል።

እንደራዲዮው ዘገባ የባንኮቹ የጥበቃ ሰራተኞች ህንፃው ከመድርመሱ በፊት ከባድ ድምፅ በመስማታቸው ከአደጋው ሊያመልጡ ችለዋል። በአዲስ አበባ የሚሰሩ ህንጻዎች ጥራት ጉዳይና ባላለቁ ህንጻዎች ውስጥ ሥራ መጀመር ሁልጊዜም ትችት ሲቀርብበት እንደነበር የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ተባረሩ

0
0

8b0067e1ba18cd789b122c804be56585_XL

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አቶ ዮሐንስ ሳህሌ ከአሰልጣነታቸው መባረራቸው ተሰማ:: በአንድ ወር የ75 ሺህ ብር ተከፋይ የነበሩት እኚሁ አሰልጣኝ ብሄራዊ ቡድኑን ከሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሲያሰለጥኑት ቆይተዋል::

የቀደሞው የደደቢት እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ አቶ ዮሐንስ ሳህሌ ከአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የተረከቡትን ብሄራዊ ቡድን ውጤታማ ሊያደርጉ ይችላሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው ቢሆንም በ እርሳቸው ዘመን ብሄራዊ ቡድኑ የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድንን ከማሸነፉ ውጭ ምንም አመርቂ ውጤት አላመጡም እየተባሉ በስፖርት ተንታኞች ዘንድ ሲተቹ ቆይተዋል::

75 000 ብር ወርሃዊ ደመወው; ተሽከርካሪ ከሾፌር ጋር እንዲሁም ባለመስመር የሞባይል ስልክና የጤና ኢንሹራንስ ከተለያዩ ጥቅማትቅሞች ጋር እየተከፈላቸው ብሐራዊ ቡድኑን ሲያሰለጥኑ የነበሩት አቶ ዮሐንስ በተጨማሪ ምክትል አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እና የበረኞች አሰልጣኝ አሊ ረዲም አብረው መሰናበታቸው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለከታል::

‹‹ የሰማያዊ ፓርቲ የውስጥ ፍትጊያ ለበጎ ወይስ ለጥፋት ? –ግርማ በቀለ

0
0

ሰማያዊ– ልንወጣው የተሳነን ‹‹ የክሽፈት አዙሪት ›› ባህር ውስጥ ወይስ…. ??
ባለፈው ሳምንት (ሚያዝያ 11/2008)
መልካሙን ማሰብ ከመልካም ያደርሳልና— ጠንካራውን ሰማያዊ እንጠብቅ//››

blue partyበሚል ርዕስ በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ የተከሰተውን የውስጥ ፍትጊያ ለቁልፍ ችግሩ መፍትሄ ሊያመጡ ይችላሉ ብዬ ያመንኩባቸው የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ -አቶ ይድነቃቸው ከበደ እና የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ተቀራርበው ስለችግሩ በግልጽ ተወያይተው መፍትሄ እንዲያበጁ የጀመርኩትን የሽምግልና ጥረት ተስፋ ባለመቁረጥ ለመቀጠልና ውጤቱን ይዤ ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ እንደምመለስ ለዚህም የሁለቱንም ይሁንታ ማግኘቴን መጻፌ ይታወቃል፡፡ ይህን የተመለከቱ ለጉዳዩ ትኩረት የሰጡ ወገኖች አስተያታቸውን በግንባርና በውስጥ መስመር ሰጥተውኛል፤ ብዙዎቹ የተለያያ ምክንያት በማቅረብ መፍትሄ ስለመበጀቱ ያላቸውን ከፍተኛ ጥርጣሬ ገልጸው መልካሙን ተመኝተዋል፡፡ ይህን ለመግቢያ ያህል ካልኩ በኋላ ወደ ጥረቱ ሂደትና ውጤት ልግባ ፡፡

ከዚህ ቀድሞ ካደረግናቸው ተደጋጋሚ የጋራ ውይይቶች በተጨማሪ፣ ከሚያዝያ 11/ 08 ወዲህ ባለው ጊዜ ከሁለቱም ጋር ሁለት ጊዜ በጋራ ተገናኝተን አምስት ሰዓት ለሚሆን ጊዜ በሰፊው ተወያይተናል፡፡ ስንጀምር ከዚህ በፊት የምናደርገው ጥረት ዓላማ ላይ ሙሉ ስምምነት በመድረሳችን ፣ ችግሩ ካልተፈታ በሚያስከትለው ችግር ላይ ልዩነት ስላልነበረን፣ ውይይቶቻችን ሁሉ በግልጽና በዝርዝር በጨዋ ደንብና በመከባበርና የጋራ ዓላማ ባለቤት- የትግል ጓድነት መንፈስ …የተደረጉና በአጠቃላይ የችግሩን መሰረትና አንድምታ በየጊዜው በምናደርገው ውይይት በስፋት የተመለከትነው በመሆኑ በዚህ ጊዜ የተመለከትነው ከመጀመሪያው ውይይታችን በኋላ ባለው ጊዜ የተከሰቱትን ለመፍትሄኣችን በተጨማሪ ግብኣትነት በመመልከት ነው፡፡ እንደባለፉት ጊዜያት ሁሉ ውይይቶቹ ‹‹የተሳኩ›› ነበሩ፡፡

በመጀመሪያ የተገናኘነው ቅዳሜ ሚያዝያ 15/2008 ዓ.ም ነበር፡፡ በዚህ ሰዓታት በወሰደው ሰፊ ውይይት ከሁለቱም ወገን ከመፍትሄ ለመድረስ የሚያስችሉ ሃሳቦች ቀርበው በዝርዝር ተነጋገርንባቸው፡፡ የእያንዳንዱን አስተያየት ለዘላቂ መፍትሄው ከምንም በላይ በፓርቲው የተለያዩ መዋቅሮችና አመራሮች መካከል ፓርቲው ከደረሰበት ዕድገት ደረጃ የሚመጥን ውጤታማ የጋራ /የቡድን አመራርና አሰራር ስለሚተገበርበትና ከመጓተት ወደ ተግባራዊ እንቅስቀቃሴ በአንድ ልብ ለመግባት የሚያስችል መፍትሄና ይህ በየት በኩል እና እንዴት መድረስ እንደሚቻል በሚለው ዙሪያ ያጠነጠነ ነበር፡፡ በዚሁ መሰረት በመጨረሻ ላይ መፍትሄው በሁለቱ አመራሮች ውሳኔ ላይ የመሰረተ ነው፤ የዚህ አስኳል ሁለቱ በጋራ የሚመርጡት ጽ/ቤት ኃላፊ ላይ የሚደረሰው መግባባት እንደሆነና ለዚህም ለፓርቲው ሁለቱም የሚስማሙበት አዲስ የጽ/ቤት ኃላፊ ለብሄራዊ ምክር ቤቱ እንደሚያቀርቡ ተስማማን ፡፡ የብሄራዊ ኮሚቴው ሊቀመንበር ይህንኑ ስምምነት የተቀበሉ መሆኑን፣ ግን ዛሬውኑ የመጨረሻ ውሳኔ ነው ለማለት እንደሚቸገሩ የማሰላሰያና የመመካከሪያ ቀናት እንደሚፈልጉ በመግለጻቸው ፣ ግን ሄዶ ሄዶ ውሳኔው የራሳቸው/በግላቸው የሚደርሱበት መሆኑን አረጋግጠው በዚሁ መሰረት ለቀጣይ ማክሰኞ (ሚያዝያ 18/2008) ቀጠሮ ይዘን ተለያየን፡፡

በቀጠሮኣችን መሰረት ስንገናኝ አቶ ይድነቃቸው ባለፈው በተደረሰበት ስምምነት ላይ ከራሳቸው እና ከጓዶቻቸው ጋር መክረው ስምምነት የተደረሰበት መፍትሄ በፓርቲው ውስጥ ያሉትን ችግሮች በሙሉ እንደማይፈታና ለዘላቂና ቀጣይ መፍትሄ እንደማይሆን በማመናቸው ኃሳባቸውን መቀየራቸውንና ሌላ የመፍትሄ ሃሳብ እንዳላቸው ገለጹ፡፡ ይህም ለፓርቲው ህልውናና ወደ ተግባር መግባት ፣እንዲሁም እርሳቸውንም ከገቡበት ውጥረትና ለጤናቸውም ራሳቸውን በግል ፍላጎት ከምክር ቤት ሰብሳቢነት ማንሳት መሆኑን ከውሳኔ መድረሳቸውን አሳወቁ፡፡ እኔና ሊቀመንበሩ ይህ የቀረበው መፍትሄ በግል ለራሳቸውም ላሉትም ሆነ ስለፓርቲው ባሉት መንገድ መፍትሄ እንደማይሆን አስረዳን፡፡ ከዚያም በመቀጠል በተጨማሪ ባለፈው የደረስንበት ስምምነት የሁለቱንም ዓላማ አሸናፊ ማድረግ እንዲችል በእርሳቸው የቀረቡትን ጥያቄዎች ማለትም- ከዚህ በፊት ሊቀመንበሩ የጠየቁትን የጉባኤ ጥሪ ጥያቄ ለማንሳት፣ በፓርቲው መዋቅሮች ላይ በሊቀመንበሩ የቀረቡ ትችቶችና ቅሬታዎችን በጋራ ለመስራት እንቅፋት እንደማይሆኑና በተደረሰው ስምምነት አብሮ ለመስራት ችግር እንደሌለባቸው በተለያዩ መድረኮችና መገናኛ ብዙሃን በአደባባይ እንዲገልጹ (ቢያስፈልግም ሶስታችንም በጋራ/በተናጠል ይህን ለመግለጽ) ለማድረግ ስምምነት ተደረሰ ፡፡ ሆኖም ከዚህ በኋላም አቶ ይድነቃቸው በኃሳባቸው /በውሳኔኣቸው ላይ ለውጥ እንደማያደርጉ በመግለጻቸው በዚሁ ተለያየን ፡፡ በመጨረሻ የተያዘው መንገድ ፣የደረስንበት ስምምነት መቀልበሱ ያሳደረብኝን የሃዘን ስሜትና ባለፈው ቀን ስለፓርቲው በቅርብ ጊዜ ወደ ተግባር መመለስ ሰንቄ የነበረው ተስፋ እንደተለየኝ፣ ሰማያዊ ከተለመደው የክሽፈት አዙሪት ለመውጣት ያለመቻሉ የፈጠረብኝን ስሜት ‹‹ አሁን የተያዘው ፍትጊያ የፈንጅ አምካኝ ስህተት /ትምህርት የማይወሰድበት ሆኖ እንደተሰማኝ) ገልጬ ፣ ሶስታችንም ሁሌ ስንገናኝና ስንለያይ ከነበረን በተለየ በጨፈገገ ስሜት ተለያየን፡፡
እንግዲህ በገባነው ቃል መሰረት የመጨረሻው ቀን ትናንት ቢሆንም በትናንትናው ዕለት ይህን አዘጋጅቼ ከጨረስኩ በኋላ አቶ ይድነቃቸው ደውለው ‹‹ ትንሽ ይቆይ/ያዘው›› ሲሉኝ ባቀረቡት የመፍትሄ ኃሳብ አዎንታዊ መሸጋሸግ ያመጣሉ በሚል ተስፋ አሳደርኩት፡፡ ዛሬ ደግሞ እስከ ዓርብ እንዳቆየው ብሉኝም እኔ የምለውን ለማለት ከዚህ በላይ መቆየት እንደሌለብኝ ፣ ግን ወደ ጋራ ስምምነት ለመምጣት የእኔ ይህን መግለጽ በሩን እንደማይዘጋ ገልጬ ተግባብተን ይሄው የደረስንበትን ይዤ ቀረብኩ፡፡

እስካሁን ስላደረግሁት ጥረትና ለዚህ ሪፖርት መረዳት ያግዝ ዘንድ ከዚህ በፊት ስለሰማያዊ ፓርቲ ያለኝን አተያይና ኃሳብ ያካፈልኩባቸውን ጽሁፎች፡- በተለይም –

1. ህዝብን ማዘናጋት ያብቃ– የውይይት መድረክ ይከፈት// 03/01/16
2. ዛሬም እንደትናንቱ–የቃላት ቸዋታ ? ያስተዛዝባል፣ ያጠያይቃል//
ክፍል ሁለት፤ ሥጋት፡- በሚጠበቀው ‹‹ የሰማያዊ ጠቅላላ ጉባኤ ››11/ 01/ 16
3. የሰማያዊ ችግር እንዳይሰፋ፣ 10/05/08
4. ጳጉሜ 2 /2007 በመኢአድ ግቢ ያቀረብኩትን ጽሁፍ፤
5. ሌሎች በፌስ ቡክ አካውንት ፕሮፋይል ላይ የሚገኙ ከሰላማዊ ፓርቲዎች እንቅስቃሴና ችግሮች ጋር የተገናኙ ጽሁፎች ፣ ማንበብ ይጠቅማል፡፡
ዛሬም የሰማያዊን ነገር በፌስ-ቡክ እንዳየሁት ‹‹ልጅ ያቦካው…..›› እንደተባለው እንዳይሆን፣ የትኛውም የመፍትሄ አማራጭ ከክፉዎች ሴራ አምልጦ የፓርቲው ህልውና እንዲቀጥልና ፓርቲው ወደሚታወቅበት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲመለስ በጎ ተመኝቼ እለያለሁ፡፡
አስከዚያው ደግ ደጉን፣ ለአገራችንና ህዝቧ የሚበጀውን ያሳስበን፣ ያስፈጽመን፣ ያሰማን ዘንድ ፈቃዱ ይሁን፡፡ አሜን //
ግርማ በቀለ፤ ሚያዝያ 19/ 2008 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ፡፡

ከ1983 እስከ 2007 ዓ.ም በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ ስለደረሰው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል የጥናት ውጤት ማጠቃለያ ዘገባ

0
0

(ክፍል 2)

ሀ)    መግቢያ

Moresh 90ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድነት ሃይሎችና በጎጠኞች መካከል የተካሄደው ፍልሚያ ፤ በጎጠኞች አሸናፊነት ከተደመደመ ወዲህ እራሱን የቻለ የፖለቲካ ውጥንቅጥ እስከትሎ እንደሚመጣ የተገመተ ቢሆንም ወደ ዘር ማጥፋትና ማጽዳት ያመራል ብሎ የተነበየ ከቶ አልነበረም። የጎጠኞች ያልተጠበቀ ድልና እሱንም ተከትሎ የመጣው ስካር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዐማሮችን ደም አፍሷል፤ እያፈሰሰም ነው። ክረምትና በጋ ፣ ቁር ፣ ሃሩር ሳይለይ ሌት ተቀን ሳይባል፤ ምስራቅ ይሁን ሰሜን ሳይል ፣ ክብረ በአልና የሰርክ ቀናት ሳይለይ ፣ ከ1983 እስከ ያዝነው 2008 ዓ.ም  የዐማሮች እጣ ፋንታቸው መፈናቀልና መገደል ሆኗል። እንደከብት የታረዱት ፣ እሳት የበላቸው ፣ በግፍ ያለቁት በሺዎችና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ዐማሮች ደም በኢትዮጵያ ምድር በአራቱም ማእዘናት በመጮህ ላይ ነው! –[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-

 


በጋምቤላው ጭፈጨፋ የደ/ሱዳን ሹመኞች እጅ መኖሩን አንድ የአገሪቱ የጦር ጄ/ል አጋለጡ |ኢትዮጵያ ዛሬም ለባእዳኖቹ ምቹ አልጋ ፣ለልጆቿ ግን ቀጋ የመሆኑዋ ጉዳይ እያነጋገረ ነው

0
0

“ ባለሰልጣኑ በጋምቤላው ጭፍጨፋ ዙሪያ አካፋን አካፋ ብለው መጥራት ይገባቸዋል” ሌ/ጄኔራል ዲቪድ ያ ኡ ያ ኡ
ኢትዮጵያ ዛሬም ለባእዳኖቹ ምቹ አልጋ ፣ለልጆቿ ግን ቀጋ የመሆኑዋ ጉዳይ እያነጋገረ ነው

ከታምሩ ገዳ

ከሳምንት በፊት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልላዊ መስተዳደር በሚገኙ የኑኢር ማህበረሰብ ላይ ከጎረቤት ደ/ሱዳን አንደመጡ የሚነገረላቸው እጅግ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እና የደ/ሱዳን የመከላከያ ሰራዊቱን የድምብ ልብስ ያጠለቁ መሆናቸው የተነገረላቸው የሞራሌ ጎሳ ተወላጆች በ 10 የኑዊር መንደሮች ላይ በከፈቱት የጅምላ የተኩስ እሩምታ ከ 200 በላይ ሰዎች ህይወትን በመቅጠፍ ከ100 በላይ ጨቅላ ህጻናትን ደግሞ አፍነው በመወሰድ ፣ከ 2ሺህ በላይ የቀንድ ከበቶቻቸውን በመዝረፋቸው ሳቢያ በበርካታ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊናኦች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ሃዘን እና ቁጭት መቀሰቀሱ አይዘነጋም።
tan
ታዲያ ከዚሁ ሰሞነኛው የጋምቤላው ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አሰተያየቶች እየተሰነዘሩ ሲሆን የተወሰኑ ወገኖች በጭፍጨፋው ላይ የደ/ሱዳን የመከላከያ ጦር እጁ እንደነበረበት የሚናገሩ ሲሆን በተቃራኒው ጎራ “ በጭፍጨፋው ላይ የተሳተፈው የደ/ሱዳን ስራዊት ሳይሆን ለስረቱ ቀረብ ያሉ የ አካባቢው ፖለቲከኞች ናቸው “የሚሉ ወገኖች ከደ/ሱዳን ባለሰልጣናት ዘንድ ብቅ ብቅ ማለታቸው ታውቋል። ይህንን (የሁለተኛውን )ሃሳብ ከሚያቀነቅኑት መካከል የደ/ሱዳን ዲሞክራቲክ ሙቭመንት (SSDM/SSDA) ዋና ሊቀመንበር የነበሩት ሌትናል ጄነራል ዲቪድ ያኡ ያኡ የሰሞኑን የጋምቤላውን ጭፍጨፋን በጸኑ ያወገዙ ሲሆን ጥቃቱን አድራሺዎቹ ሊኪዋንጋሎ ከተባለ አካባቢ ከሚገኙ ኒያርጀኒ፣ዎጎን፣ማንያታካ፣ቶልቶል እና ማንታይድ ከተባሉ መንደሮች በሚገባ የተደራጁ እንደሆኑ እና ይህ ክልል ደግሞ በአሁኑ ወቅት የቦማ ግዛት ሃገር ገዢ (ገቨርነር )የሆኑት ባባ ኒዳን የትውልድ ስፍራ ሲሆን አኚሁ ሃገረ ገዢው ከዚህ ቀደም ከነዋሪው ሕዝብ ጋር ስላላቸው ቁርኘት በተመለከት ሌ/ ጄ/ል ዲቪድ ሲገልጹ” ሃገረ ገዢው ቀደም ሲል ፒቦር የተባለች ከተማን ለመውረር ሕዝቡን የዘመናዊ የጦር መሳሪያ ባለቤት በማድረግ እና ጥይቶችን በገፍ በማቀበል ጥቃት ለመፈጸማቸው በግላጭ የሚታወቅ ሲሆን ይሄው የጦር መሳሪያ እ ወታራዊ ቁስ ሰሞኑን ጋምቤላ ወስጥ በኑኢር ልጆች ላይ ለተፈጸመው አሳቃቂ እና ተግባር ላይ ውሏል” ሲሉ የ ደ/ሱዳን ባለሰልጣኑ (የሞራሌ ተወላጆችን ያሰታጠቁ የአካባቢውን ሹምን) ቁጥር አንድ ተያቂ ናቸው ሲሉ ወንጅለዋቸዋል።
photo
የቦማ ግዛት ሃገረ ገዢው ከዚህ ቀደም በእልቂቱ ላይ የ ደ/ሱዳን ጦር እጆች ሰለመኖራቸው በተመለከት የሰጡትን ትችት በተመለከት ጄ/ል ዲቪድ ሲናገሩ “ እኛ አማጺያኖች ከወቅቱ ከጁባ መንግስት ጋር ስራዊታችን ኣንዲጣመር እና እርቀ ሰላም እንድናደረግ መንገድ በጠረገችልን አገር ( በ ኢትዮጵያ እና በሕዝቧ) ላይ የጦር መሳሪያ በጭራሽ አናነሳም ። ይልቁንም ለዚሁ የሰበ ጡራን ፍጅት እና ሰቆቃ ተጠያዊ የሆኑት የቦማ ግዛት ገዢው ባባ ኒዳን ለተፈጸመው ወንጀል ሃላፊነቱን እንዲወስዱ፣ አካፋንም አካፋ በሎ መጥራት (ወንጀለኞቹን የማጋለጥ እና ለፍርድ የማቅረቡ እርማጃን )መማር አለባቸው፣ ባለሰልጣኑ ተራ እና መሰረተ ቢስ ውንጀላቸውን ትተውም በግፍ ታፍነው የተወሰዱት 108 በላይ ኢትዮጵያዊያን ህጻናት እና የተዘረፉት የቀንድ ከብቶች ለህጋዊ ባለቤቶቻቸው (ለጋምቤላ ማህበረሰብ )ይመለሱ ዘንድ ከአካባቢው የጎበዝ አልቆች ጋር በግላጭ መነጋገር አለባቸው ።” በማለት ጄ/ል ዲቪድ ለሃገር ገዢው፣ ለ ባባ ፣የተማጸኖ መልእክት ለከዋል ። የቀደሞው ስራዊታቸንም “እጁ ከደሙ ንጹህ ነው” ሲል ትከላክለዋል።

ላለፉት ሁለት አመታት በአርሰ በርስ ጦርነት የታመሱት ት ፣ለበርካታ ሰላማዊ ዜጎች መሞት እና መሰደድ ምክንያት የሆኑት የደ/ሱዳን ዋንኛ ፖለቲከኞች ፕ/ቱ ሳልቫ ኪርር እና እስከ ትላንትናው እለት ድረስ ጋምቤላ እና አ/አ ውስጥ ሲዝናኑ ቆይተው በአለማቀፉ ማህበረሰብ ጫና እና ግፊት ወዳፈራረሷት የደ/ሱዳን መዲና የሆነቸው ጁባ ለመሄድ የተገደዱት ዶ/ር ሪክ መክችር የምክትል ቦታውን ዳግም እንዲይዙ የተደረገ ሲሆን ሁለቱ ፖለቲከኞች (ሳልቫ ኪርር እና መክቻር ) በአሁኑ ወቅት ሰለ ወንበራቸው እና ሰለ ራሳቸው መጻኢ ተስፋ ማሰብ እና ማሰላሰል አንጂ በእነርሱ ጦስ ሳቢያ ለተሰደዱ ከ200 ሺህ በላይ ዜጎቻቸውን ላሰጠለለች ከዚያም አልፎ ባለፈው ሳምንት በጋምቤላው የጃዊ የሰደተኞች ጣቢያ በተፈጠርው ድንገተኛ የመኪና ግጭት ሳቢያ የሁለት የደ/ሱዳን ሰደተኞች ህይወት መጥፋቱን ተከትሎ ከ 10 በላይ ሰላማዊ ኢትዮጵያዊያኖች በአካባቢው አጠራር (ደገኞች/የመሃል አገር ትወላጆች ) ላይ የደረሰው የብቀላ እና ሃይል የተቀላቀለበት እርምጃ ሳቢያ የህይውት መጥፋትን በተመለከተ (አንዲያውም በወቅት ዶ/ር ማክችር ድርጊቱ ሲፈጸም በከተማ ውስጥ ነበሩ ይባላል) ፣ ከዚያ በመለጠቅ የሞራሌ ጎሳዎች ባለፈው ሳምንት በእነርሱ ሹማምንቶች የተጥቅ ደጋፍ ታግዘው በ208 ላይ ሰላማዊ የጋምቤላ ነዋሪዎች ላይ ስለ ተፈጸመው ጭፍጨፋ እስከ አሁን ድረስ ጠጠር ያለ የማውገዝ እና ፈጣን እርምጃ የመወሰድ እንቀሰቃሴ ያለማድረጋቸው ጉዳይ “ኢትዮጵያ ድሮም ሆነ ዛሬ ለ ባእዳኖች የሞቀ አልጋ ፣ለልጆቿ ግን የቀጋ እሾህ ነች”የሚለው ብሄል በበዙዎች አይምሮ ውስጥ ሰሞኑን ዳግም እንዲመላለስ አድርጎታል።

ይህ ማለት ደግሞ ዛሬ በአንዳንድ አገሮች እንደምናየው እና ወግኖቻቸን እንደሚያበሻቅጧቸው “ሰደተኞች አገራችንን ለቀው ይወጡልን ዘመቻ አይነት እናካሄድ “ማለት ሳይሆን በኢትዮጵያ መሬት የሚገኙ የትኛውም አገር ሰደተኞች የአገሪቱን እና የህዝቧን ክብር እና ባህል በማይነካ መንገድ እንዲሰተናገዱ ፣ አደብ የሚያሰገዛ እና ለሰደተኞች ሲባል የዜጎቹንም ህይውት በግፍ እና በከንቱ የማይቀጭ ፣ ክብራችውን እና መብታቸውን የማይደፈጥጥ መንግስት፣የህግ አስከባሪ ሃይል ይኑር ። እንዲሁም ህዝባዊ ስር አትም ይዘርጋ ማለት ነው።

የይሳቅ ራቢን አስተሳሰብ እሩቡ ኢሕአዴጎችን ጋር ቢኖር ኖር |ግርማ ካሳ

0
0

eprdf

(አገር ቤት የሚታተመው የአዲስ ገጽ መጽሄት እትም ዘጠኝ ላይ የወጣ)

የአሥራ ሰባት አመት ወጣት ነዉ። ጥይት የጎረሰ ሽጉጥ በእጁ ይዟል። እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ፣ ንግግር አድርገዉ ወደ ጨረሱ አንድ የእድሜ ባለጸጋ ሰዉዬ ቀስ በቀስ ይጠጋል። ሳያስቡት የያዘዉን ሽጉጥ ወደ እርሳቸዉ ደቅኖ ይተኩሳል። ሰውየዉ ይወድቃሉ። አካባቢዉ ተረበሸ። ተናወጠ። አምቡላንስ ተጠርቶ በአፋጣኝ በስፍራዉ ደረሰ። የወደቁትን አባት በአምቡላንሱ የነበሩ የህክምና ባለሞያዎች አነሷቸዉ። የፍጥነት ጉዞ ወደ ሆስፒታል ጀመሩ። ሆስፒታል ሳይደርሱ በመንገድ ላይ የኝህ ሰዉ ሕይወት አለፈች።

ይህ ወጣት ይጋል አሚር ይባላል። ተኩሶ የገደላቸዉም ሰዉ፣ የቀድሞ የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር ይሳቅ ራቢን ነበሩ።

ይሳቅ ራቢን እድሜ ዘመናቸዉን በሙሉ የጥይትና የመድፍ ድምጽ በመስማት ያሳለፉ ጦረኛ ወታደር ነበሩ። በፈረንጆች አቆጣጠር በ1941 ከታዋቂዉ ሞሼ ዳያን ጋር የፓልማክ ግብረኃይል አባል ሆነዉ፣ ያኔ በፈረሳንዮች ቅኝ ግዛት ስር በነበረችዉ በሊባኖስ የናዚ ጀርመን ደጋፊ የነበረዉ የፈረንሳይ ቪቺ መንግስት ወታደሮች ጋር ተዋግተዋል። በዚያ ጦርነት ጊዜ ነበር ሞሼ ዳያን አንድ አይናቸዉን ያጡት።

ከዚያ በኋላ ከአረቦች ጋር በተደረጉት ተከታታይ ጦርነቶች ትልቅ ጀግንነትና የውትድርና ብቃት ያሳዩ፣ በእሥራኤል ታሪክ አሉ ይባሉ ከነበሩት ታላቅ የጦር መሪዎች አንዱ ነበሩ። የእሥራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የጦሩ የኢታ ማጆር ሹም ሆነውም አገልግለዋል።

ይሳቅ ራቢን «እኔ ሰላም ሳላይ እድሜዬን ጨርሻለሁ። ለልጆቻችን ሰላም ማምጣት አለብን» በሚል እምነት፣ ድፍረት የተሞላበት የሰላም እርምጃ ወሰዱ። የእሥራኤል ጠላቶች ከሚባሉ ጋር መነጋገር ጀመሩ።

ኢሳቅ ራቢን ከመገደላቸዉ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የተናገሩት፣ ለእኛ ለኢትዮጵያዉያንና ለመሪዎቻችን ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ አስደናቂ አባባል ነበር ። «የሰላም መንገድ ከጦርነት ይሻላል። ይሄን የምለዉ እንደ አንድ ወታደር ነዉ። መከላከያ ሚኒስቴር ሆኜ የእስራኤል ወታደሮች ቤተሰቦች ስቃይ ይሰማኛል። ለነርሱ፣ ለልጆቻችን፣ ለልጅ ልጆቻችን ስንል መንግስታችን ዘላቂ ሰላም እንዲገኝ ማንኛዉንም ቀዳዳ፣ ማንኛዉንም እድል መጠቀም አለበት። ሰላም አንድ ጸሎት ብቻ አይደለም። ሰላም የጸሎታችን መጀመሪያ ነዉ» ነበር ያሉት።

የጦርነትን ፣ የጥላቻና የእልህ ፖለቲካ አደገኛነቱን ያወቁታልና፣ አብረዋቸዉ የነበሩ ጓደኞቻቸዉ ሲረግፉ፣ አካለ ስንኩል ሲሆን፣ ንብረት ሲወድም ፣ ሰዉ በሰዉ ላይ ሲጨክንና አዉሬ ሲሆን አይተዋልና፣ እርሳቸዉ የኖሩበትን በጦርነት የተበከለን አየር ለልጅ ልጆቻቸዉ ማዉረስ አልፈለጉም። እርሳቸዉ ይመኙትና ይናፍቁት የነበረዉን ሰላም፣ እርሳቸዉ ባያገኙትም እንኳን፣ የልጅ ልጆቻቸዉ እንዲያገኙ መደረግ ያለበትን ሁሉ ማድረግ እንዳለባቸዉ ተገነዘቡ። «ለልጅ ልጆቻችን ስንል ሰላም እንዲመጣ የተገኘችዋን ቀዳዳ ሁሉ መጠቀም አለብን» በሚል ጽኑ አምነት፣ በጦርነት ያልሆነ፣ የወስጥና የልብ ጀግንነት ለማሳየት ተንቀሳቀሱ። የእሥራኤል ጠላት ከተባሉት ከነያሲር አራፋት ጋር መነጋገር ጀመሩ።

ብዙ ተቃዉሞ መጣባቸዉ። እነ ናታንያሁ ተነሱባቸዉ። ግትር ፖለቲካ የሚያራምዱ፣ በጭንቅላት ሳይሆን በጠመንጃ የሚያምኑ፣ እነርሱ ብቻ ከሌላዉ እንደተሻሉ አድርገዉ በመቆጠር በትእቢት የተወጠሩ፣ ከነርሱ ዘር ዉጫ ለሌላዉ ግድ የማይሰጣቸዉ ሰዎች በርሳቸዉ ላይ ማንጎራጎር ጀመሩ።

ኢሳቅ ራቢን ግን ወደ ኋላ አላሉም። «የሰላም ጠላቶች አሉ። ሊጎዱን፣ የሰላሙን መንገድ ሊያጨናግፉን የሚፈልጉ። በድፍረት እናገራለሁ። ከፍልስጤማዉያን መካከል የወጣዉ፣ በፊት ጠላታችን የነበረዉ የፍልስጤም ነጻ አውጭ ግንባር አሁን የሰላም አጋራችን ሆኗል» ሲሉ ከቀድሞ ጠላቶቻቸዉ መካከል ወዳጆችን እንዳፈሩ ተናገሩ። ከያሲር አራፋት ጋር በአንድ ላይ ለሰላም ቆሙ። ኢሳቅ ራቢን በጦርነት ሊያጠፉት ያልቻሉትን የያሲር አራፋትን ቡድን በሰላም አሸነፉት።

ታዲያ ለዘመናት በጦር ሜዳ ሲዋጉ በጥይት ያልተመቱት እኝህ ታላቅ ሰዉ፣ በሰላሙ ሜዳ በቴላቪቭ ከተማ ጥይት አገኘቻቸዉ። ለሰላም ለፍቅር ለወንድማማችነት ሲሉ ወደቁ። እጅግ ታሪካዊ፣ ተወዳጅ የሰላም ሰዉ !!!!

የይሳቅ ራቢንን ታሪክ ያለምክንያት አላመጣሁትም። አንዳንዶችን ተቃዋሚዎችን መጨፍለቅ ጀግንነት ይመስለናል። አንዳንዶች ኃይልን የምንመዝነዉ በያዝነዉ ብረትና በዘረጋነዉ የሥለላ አዉታር ነዉ። መነጋገር፣ መወያየት፣ ፍቅርና መግባባት ፣ በጦርነትም ሆነ በጉልበት ከሚገኝ ጊዚያዊ መፍትሄ የበለጠ ዘለቄታ ያለዉ ጥቅም ሊያመጣ እንዲሚችል አናስብም። የሩቁን፣ እኛ ካለፍን በኋላ በልጆቻችንና በልጅ ልጆቻችን ዘመን ሊፈጠር የሚችለዉን፣ ለሁላችንም የሚበጀዉን አንመለከትም። ጊዚያዊ ጥቅማችንንና ስልጣናችን ላይ ብቻ በማተኮር ግትር ፖለቲካ እናራምዳለን።

እንደ ኢሳቅ ራቢን አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት (ከአቶ ኃይለማሪያም ጀርባ ያሉት) ከወጣትነታቸዉ ጀምሮ ጦርነትን ያዩ፣ በጦርነት የኖሩ ሰዎች ናቸዉ። በታሪክ ስለሚኖራቸዉ ቦታ፣ ስለ ልጆቻቸዉና የልጅ ልጆቻቸዉ ማሰባ አለባቸዉ እላለሁኝ።
ጸረ-ሽብርተኝነትን ለመቋቋም ተብሎ የወጣዉ አዋጅ ፣ በዚህ አዋጅ መሰረትም፣ ለሰላማዊና ለሕጋዊ ትግል ጠንካራ አቋም ያላቸዉ እነ እስክንደር ነጋን አንዱዋለም አራጌ እንዲሁም ሌሎች በርካታ በሽብር ወንጀል ተከሰዉ ወደ ወህኒ መዉረዳቸዉ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ በተቃዋሚዎች ላይ በየወረዳዉና በየክልሉ የሚደርሰዉ ወከባ፣ የአንድነት ፓርቶ መታገድ … ኢሕአዴግን ከሕዝብ ጋር የሚያጣሉ፣ ጥላቻን እንዲሰፋ የሚያደርጉ፣ ዜጎች የበለጠ ወደ ከረረ አቋም እንዲሄዱ የሚገፋፉ እንጂ፣ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ አንድ ወቅት እንደ አጀንዳ እንደግፈዋለን ብለዉት የነበረዉን የመግባባትንና የእርቅን መንፈስ የሚያመጡ አይደለም።

ተናዶ የኃይል እርምጃ መወሰድ፣ በበቀል መነሳሳት፣ ሰውን ማዋረድ፣ ሰዉን መስደብ፣ ሰዉን መክሰስ በጣም ቀላል ነዉ። በአይናችን ላይ ትልቅ ምሰሶ እያለ የሌላዉን ጉዳፍ ማየት፣ የተገነባዉን ማፍረስ፣ አገርን ከድህነት ወደ ድህነት ማውረድ፣ ጠላቶችን ማፍራት፣ ሕዝብን ከሕዝብ መከፋፈል፣ ወንድምን ከወንድም ማጣላት አስቸጋሪ አይደለም።

ይሳቅ ራቢን እንዳደረጉት ጠላት የነበሩትን ወዳጅ ማድረግ፣ የፈረሰዉን መገንባት፣ አገርን ከድህነት ማውጣት፣ ችግሮችን በዉይይት መፍታት፣ የተጣሉትን ማስታረቅ፣ የተበተኑትን መሰብሰብ፣ ትችትና ወቀሳን በትህትና ተቀብሎ ስድብና አሉባልታን ደግሞ ንቆ ነገሮችን በትእግስት ማሳለፍ ግን እጅግ በጣም ከባድ ነገር ነዉ።

ስለሆነም ኢሕአዴጎች አሁንም የቀናዉን መንገድ እንዲይዙና ለእርቅና ለብሄራዊ መግባባት መዘጋጀታቸዉን ለማሳየት ተጨባጭ ሥራዎችን ለመሥራት እንዲነሱ ጥሪ እንደወትሮው በድጋሜ አቀርባለሁ። እርግጥ ነው በመልክም አስተዳደር ዙሪያ ችግር እንዳለባቸው በግልጽ አምነዋል። ከምሁራን ጋር፣ ከተቃዋሚ ደርጅቶች ጋር ለመነጋገር የሞከሩበት ሁኔታም አለ። ሆኖም ንግግር ብቻ በራሱ ምንም አይደለም። ኢሕአዴግ በርግጥም በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ቁርጠኝነት እንዳለው በተግባር ማሳየት አለበት። ተግባር ተግባር፣ ተግባር ያስፈልጋል። ለምሳሌ፣ አንሳ ሱኪ በበርማ እንዳደረገችው፣ የሕሊና እስረኞችን በሙሉ መፍታት፤ ከተቃዋሚዎች ጋር የዴሞክራሲ ተቋማት ነጻና ገለልተኛ የሚሆንበትን ሁኔታ ቅንነት ባለው ሁኔታ መነጋገር እና እንደ ጸረ-ሽብርተኝነት ያሉ አፋኝ ሕጎችን መሰረዝ ወይንም ማሻሻል ያሉት አገዛዙ በቀላሉ ሊተገብራቸው የሚችላቸው ተግባራት ናቸው።

በአገራችን እርቅና ሰላም እንዲመጣ ማድረጉ የኢሕአዴግ ብቻ ሃላፊነት አይደለም። ኢሕአዴግን እንቃወማለን በምንልም ወገኖች በኩል መደረግ ያለበት ቁልፍ ጉዳዮች አሉ ብዬ አምናለሁ። ሰላም በአንድ በኩል ብቻ አይደለም። እኛ «ኢሕአዴጎች ስልጣን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አይደሉም» ብለን እንደምንከሳቸው ሁሉ እነርሱም በበኩላቸዉ «ስልጣን ብንለቅ አይለቁንም፣ በሰላም መኖር አንችልም» የሚል ፍርሃት ሊኖርባቸው ይችላል ብዬ አምናለሁ። በዚህም ምክንያት እርቅ ለመመስረት ፍላጎቱ ቢኖራቸዉም፣ ከፍራቻ የተነሳ፣ በሰላም ስልጣን ከለቀቅን መገደላችን ካልቀረ፣ እስከተቻለን ድረስ ስልጣናችንን ማቆየት አለብን የሚል ድምዳሜ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ። ይህ እንግዲህ እርቅ እንዳይመጣ ሁላችንም ወደ ባሰ ደረጃ እንዳንደርስ የሚያደርገን ነዉ።

እንግዲህ በዚህ ረገድ የተቃዋሚ ጎራዉ፣ የሰለጠነ፣ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ (ኢሕአዴጎችን ጨምሮ) የሚያቀራርብ፣ በበቀልና በጥላቻ ላይ ሳይሆን በፍቅርና በይቅርታ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዎች ማራመድ ይጠበቅበታል። አሁን አሉ የሚባሉት ተቃዋሚ ደርጅቶች ትልቅ የብስለት ችግር አለባቸው። መብስል ይኖርባቸዋል። ብሶት ብቻ ነው የሚያሰሙት እንጂ አማራጫ በማሰማት ለሕዝቡ ተስፋ ሲሆኑ አይታዩም። ያ መለወጥ አለበት። አንዳንዶቹ ተቃዋሚዎችማ እንኳን ከኢሕአዴግ ጋር ተነጋግረው ሊስማሙ ቀርቶ፣ እርስ በርሳቸው መስማማት ያልቻሉ ደካሞች ናቸው። ስለዚህ ተቃዋሚዎችም የራሳቸው ቤት ሥራ መስራት ይጠበቅባቸዋል።

ሁላችንም በአስተሳሰብ ታድሰን የአገራችንን የተወሳሰቡ ችግሮች እንደ ወንድማማቾች፣ በዘር፣ በሃይማኖት ሳንከፋፈል፣ በመመካከር፣ በመቀባበለና በመያያዝ መፍታት ካልቻል፣ በመካከላችን ያሉትን ልዩነቶች እያሰፋን እና በነገሮች እያከረርን ከመጣን፣ የሰው ልጅ መሰረታዊ የስብእና እና የዜግነት መብቱ ያለ ገደብ የሚከበርባትና ሕግ የበላይ የሆነባትን ኢትዮጵያ ካልገነባን እንደ አገር እና እንደ ሕዝብ እንጠፋለን። በፍቅር አገራችንን እንገባ። የአመለካከት ለዉጦች እናደርግ። በዋናነት መልእክቱ አራት ኪሎ ላሉ ባለስልጣናት ቢሆንም፣ ሌሎቻችንን ይመለከታል:

ኤፍሬም ታምሩ የሰሜን አሜሪካ የሙዚቃ ኮንሰርት በሰሜን አሜሪካ የተለለያዩ ከተሞች ሊካሄድ ነው |ሚኒሶታ ሜይ 21 ይደረጋል

0
0

ephrem Tamiru 2015

(ዘ-ሐበሻ) የስመጥሩው አርቲስት ኤፍሬም ታምሩ የሙዚቃ ኮንሰርት በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች ሊካሄድ መሆኑ ተሰማ:: ከላስ ቬጋስ ከተማ ይጀመራል የተባለው የኤፍሬም የሙዚቃ ኮንሰርት ሜይ 21 በሚኒሶታ እንደሚካሄድም ታውቋል::

የላስቬጋስ ኮንሰርት ሜይ 10 እንደሚደረግ አዘጋጆቹ ይፋ ያደረጉ ሲሆን በሚኒያፖሊስ ሚኒሶታ የኤፍሬምን የሙዚቃ ኮንሰርት የሚያዘጋጁት ዘ-ሐበሻ; ሶል ዲዛይን እና ፕሮሞሽን እንዲሁም ራስ ላውንጅ ፕሮሞሽን እንዳስታወቁት ሜይ 21 በሴንት ፖል ዳንሰርስ ስቱዲዮ ይካሄዳል:: አብሮትም አቢሲኒያ ባንድ ወደ ሚኒሶታ ይመጣል::

ኤፍሬም በሲያትል; በዋሽንግተን ዲሲ; በአትላንታ እና በተለያዩ ከተሞችም በዚህ የበጋ ወራት ኮንሰርቶቹን ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል::

ኤፍሬም የቀድሞው ሥራዎቹን እንደአዲስ ከሮሃ ባንድ ጋር በመሆን እንደአዲስ ካወጣ በኋላ በተለያዩ ስቴቶች እየዞረ ኮንሰርቱን ሲያቀርብ የመጀመሪያው ይሆናል:: በተለይ ሚኒሶታ ኤፍሬም ለመጨረሻ ጊዜ የመጣው ከ9 ዓመት በፊት በመሆኑ አድናቂዎቹ በጉጉት ይጠብቁታል::

ጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳና ሳዲቅ አህመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ |በኦሮሚያ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ ቁጣ ብሔራዊ መልክ አለመያዙ ምክንያቱ ምንድነው? –ያዳምጡት

0
0

በኦሮሚያ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ብሔራዊ መልክ አለመያዙ ምክንያቱ ምንድነው? የተቃውሞው መሪዎች ማንነት አለመታወቅ ወይስ ሌላ? ሕዝባዊ ተቃውሞው ተገቢውን ውጤት እንዳያመጣ አድርጎታል? የትግሉ መሪዎችን ፣ የተቃዋሚዎች ሚናና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ እና በፍቃዱ ሞረዳ ከሕብር ሬዲዮ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ (ሊደመጥ የሚገባው)

በትምህርት ሥርዓቱና በመምህራን ላይ የተደቀነ አደጋ –ከቀድሞው መምህራን ማህበር የተሰጠ መግለጫ

0
0

Teachers Unionበታሪክ አጋጣሚ በሥልጣን ላይ የተቆናጠጡ ገዢ ሃይሎች ሁሉ ሕዝብ የሚያነሳቸውን የመብት ጥያቄዎች በአግባቡ ሲመልሱ አልታዩም። ከሕዝብ ፍላጎትና ጥያቄ ይልቅ የራሳቸውን የፖለቲካ ፍላጎትና ጥቅም በማስቀደም ሕዝቡን ለርሃብ፣ ለድንቁርና፣ ለስደትና ውርደት፣ አገሪቷን ለውድቀት ዳርገዋል። በተለይ ወያኔ/ኢህአዴግ በመማር ማስተማር ሙያ ላይ የተሰማራውን ሃይል የተለያዩ ስያሜዎችን በመስጠትና በወያኔያዊ ግምገማ በማስመረር ልምድ ያካበቱ መምህራንን ከሥራ ማባረሩና ሙያውን ለቀው እንዲሄዱ ተጽዕኖ ማድረጉ ለትምህርት ውድቀት አመላካች አርምጃ ነው። [ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live