Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0

ፍካሬ ዜና
ሚያዚያ 9 ቀን2008 ዓ.ም.

 የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በተለይም ካታር በአሰብ የባህር የጦር ሰፈር እየሰእራች ለመሆኗ በቂ ማስረጃ ተገኝቷል ያሉ ክፍሎች በወደቡ የሚገኙት የኤሚራቷ መርከቦች ብቻ ሳይሆኑ የሌላም ሀገር መርከቦች ታይተዋል ብለው አያይዘውም ሳውዲ አረቢያ ልትሆን መቻሏን ጠቁመዋል ፡፡ ሳውዲና ቃታር በኤርትራ ጦር ሰፈሮች መሰጠታቸውን፤ ቃታር አሰብን መግዛቷን የተነገረ ሲሆን ሳውዲን ለመርዳት ወደ የመን ወታደር የላከው ሻዕቢያ ግን ሲያስተባብል መቆየቱ ይታወቃል ።ሻዕቢያ ኤርትራን ለሳውዲና ካታር መሸጡ ለኢትዮጵያ እያመጣ ያለውን አደጋ ሕዝብ በግምት ማስገባትና መጠንቀቅም አለበት ተብሏል ።

asab port የሀገርን ህልውና በአደጋ ከሚጥሉት አንዱ ሁኔታ ግብጽን የሚመለከት መሆኑ ተደጋግሞ የተጠቀሰ ሲሆን በቅርቡ እየጠነከረ የመጣው የግብጽና የሳውዲ አረቢያ ወዳጅነት ደግሞ አካባቢያችንን ለከፍተኛ አደጋ መጣሉ እየተነገረ ነው ። ግብጽ ሁለት ደሴቶቿን ለሳውዲ መለገሷን በመቃወም የግብስ ተራማጅና ዴሞክራቶች ተቅውሞ እያሰሙ መሆናቸው ም ታይቷል ።ሳውዲ ቀደም ስትል ጸረ ሲሲ የሆኑትን የሙስሊም ወንድማማቾች ስትረዳ የቆየች ቢሆንም በአሁኑ ጊዜከግብጹ አምባገነን አል ሲ ጋር መዛመድን መምረጧ ይታያል ። የሳውዲ ጥቃት በየመን ላይ፤ ሳውዲ በጦር ደረጃ ወደ ኢርትራ መግባት፤ ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ያላት ጣውንትነት–ይህ ሁሉ መጪውን አደጋ ይጠቁማልም ተብሏል ።በቅርቡ በአዲስ አበባ የግብጽ አምባሳደር ልዑክ ይዞ የበርበራ ወደብ የሚገኝባትን ሶማሊላንድን መጎብኘቱና ከመሪዎቹ ጋር መገናኘቱ ም አንደምታው አስጊ ነው መባሉም ተጠቅሷል ።

አርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. የደቡብ ሱዳን መንግስት ወታደሮችና የሙርሌ ጎሳ አባላት ታጣቂዎች በአንድ ላይ ወደኢትዮጵያ ግዛት ገብተው 10 የሚሆኑ መንደሮችን ማጥቃታቸውና 170 የኑዊር ጎሳ አባላትን መግደላቸውን ሱዳን ትሪቡን የተባለው ጋዜጣ በአርብ ዕለት እትሙ ዘግቧል። ከተገደሉት ውስጥ አብዛኞቹ ሴቶች እና ሕጻናት መሆናቸው ተነግሯል። የተገደሉት የኑዌር ጎሳ አባላት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ በወረራው ወቅት የሚደርስላቸው ኃይል ባለመኖሩና መሳርያ አልባ በመሆናቸው ሊጠቁ ችለዋል ተብሏል። ዘግይቶ በደረሰው ዜና የተገደሉት የተገደሉት ዜጎች ከ200 በላይ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ያለ ሲሆን ህጻናት ታፍነው የተወሰዱ መሆናቸውም ተነግሯል:: በግጭቱ ቢያንስ 51 የሚሆኑ የሙርሌ ጎሳ አባላትም የተገደሉ መሆናቸው ታውቋል።

 እውቁ የማሲንቆ ተጫዋችና ድምጻዊው ጌታ መሳይ አበበ በተወለደ በ 72 ዓመቱ በዚህ ሳምንት ማረፉ ተነግሯል። አርቲስት ጌታ መሳይ ከልጅነቱ ጀምሮ በሙዚቃና የኪነት ላይ የነበረ ሲሆን በአዲስ አበባ በቀድሞ የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ የባህል ማዕከል በኋላም በሀገር ፍቅር ትያትር በሙዚቀኛነት በድምጻዊነት አገልግሏል። የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ አምባሰደር በመሆንም በተለያዩ የዓለም አገሮች በመዘዋወር በማሲንቆ ተጫዋችነትና በድምጻዊነት ተመልካቹን ሲያስደስት ቆይቷል ። አርቲስት ጌታ መሳይ አበበ በሕይወት ዘመኑ ከ 200 በላይ ዜማዎችን የተጫወተ ሲሆን ከአስር በላይ ትያትሮችንም በመድረክ ላይ ከውኗል። በኪነት ዓለም ውስጥም በማሲንቆ ተጫዋችነት በድምጻዊነት በመህርነትና በኃላፊነት አስተዋጽኦ ያደረገውና የኢትዮጵያን ባህል በዓለም ያስተዋወቀው አርቲስት ጌታ መሳይ አበበ ከ 966 ዓ ም ድምጽ ባደረበት የጭንቅላት ህመም የተነሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የኮሚፒዩተር ግንኙነቶችን ለመቆጣጠር አዋጅ ሊወጣ መሆኑ ታወቀ

 ወያኔ በእጅ ስልክና በኮምፒዩተር የሚደረጉ የጽሁፍና የድምጽ ግንኙነቶች ላይ እስከ ዛሬ እያካሄደ ያለውን ህገ-ወጥ ስለላ ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት ረቂቅ አዋጅ ለወያኔ ፓርላማ መቅረቡ ታውቋል፡፡ በዚህ ፀረ-ሕዝብ አዋጅ በኮምፒዩተር ሕዝብን ለፀረ-ወያኔ ትግል የሚያነሳሳ ጽሁፍና ተንቀሳቃሽ ምስል ያሰራጨ፣ የወያኔን የሚስጥር ቁልፎችን ሰብሮ በመግባት የጠለፈ፣ የፖሊስ፣ የደህንነት፣ የመከላከያ ኃይሉን ሰነዶች ጠልፎ ያጋለጠ በሃያ አምስት አመታት እስራት የሚያስቀጣ አዋጅ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ወያኔ የመደራጀት፣ የመሰብሰብ፣ ሀሳብን በነፃነት በጽሁፍም ይሁን በንግግር የመግለጽ መብቶች ሙሉ በሙሉ ማፈኑ ይታወቃል፡፡ ይህ የኮምፒዩተር ግንኙነቶችን ለመግታት ሆን ተብሎ የታለመና አገሪቱን እስካሁን ካለችበት የጨለማ ሁኔታ ወደ ፍጹም ደይን የሚወስድ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ያስረዳሉ፡፡

ኢትዮጵያ በመረጃ ልማት ሰንጠረዥ የመጨረሻ ሶስተኛ ቦታ ላይ እንደምትገኝ አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ግልጽ አድርጓል። የኢንፎርሜሽን ዲቨሎፕመንት ኢንዴክስ ባለፈው ዓመት በ1967 የዓለም አገሮች ያደረገውን ጥናት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። ጥናቱ በየአየገሮቹ ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት ስፋትና ጥራት የተንቀሳቃሽ ስልኮች ስርጭትና ኔትወርክ የማግኘት አቅም የኢንተርኔት ተጠቃሚ ብዛትን ለኢንተርኔት የደረሱ ዜጎች ቁጥርን ግምት ውስጥ ያስገባ እንደነረ ሲታወቅ በውጤቱ በሰንስጠረዥ መጨርሻ 167 ኛ ያወጣቸው ቻድ ስትሆን 166ኛ የሻዕቢያዋ ኤርትራ 165 ኛ ደግሞ ወያኔ በዘረኛንት የሚገዛት ኢትዮጵያ ሆናለች በጥናቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጆ ለዜጎቻቸው በአስተማማኝ መንገድ ብቻ ሳይሆን በጥራት በማቅረብ ኮሪያ ቀዳም ስትሆን ዴንማርክና አይስላንድ አንደ ቅደም ተከተላችው ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነዋል። በጥፋቱ ሰንጠረዥ ትናንት ነጻነት አገኘሁ ያለችው ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ በልጣና ተሽላ መገኘቷዘረኛዎቹ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ላይ የሚሸርቡን ደባ ሸርና በግልጽ አሳይቷል።

በተያያዘ ዜና የወያኔ ቡድን ባለስልጣኖች በከፊል ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ በደቡብ አካባቢ ለሚገኘው ተጠቃሚ የትዊተር የዋትስ አብፕ ና የሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ከአንድ ወር በላይ ለሆነ ጊዜ ዘግቶ የነበረ መሆኑ ብሉመርግ የተባለ የዜና ወኪል አጋልጧል። የወያኔ አገልጋይ የሆነው የኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒከሽን መስሪያ ቤት የአገሪቷን የኢንተርኔት አገልግሎት በሞኖፖል የያዘ ሲሆን ተቀጣጥሎ ከተያያዘው ሕዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የኢንተርኔት አገግልጎትን በተለይም የሞባይል አገልግሎት ለመግዛት ማቀደቀዱ ቀደም ብሎ የተዘገበ መሆኑ ይታወቃል። የወያኔ ባለስልጣኖች የኢንተርኔት አገልግሎት ደካማ መሆን ነው እንጅ ሆን ተብሎ የተወሰደ የመንግስት እርምጃ አይደለም ብለው በማለት መግለጫ ለመስጠት ቢሞክሩም አፈናው እንቅስቃሴውን ለማዳከም የተጠቀሙበት እርምጃ መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑና ብሶት የገፋፋው የሕዝብ አመጽ በማናቸውም ዓይነት አፈና ሊዳከም እንደማይችል ብዙዎች ይናገራሉ፡፡

ወያኔ የተንቀሳቃሽ ስልኮችን ምዝገባ ሊያካሂድ መሆኑ ተሰማ

 ወያኔ ዓለም አቀፍ የሆነውን “ቫይበር” የተሰኘውን የነጻ የስልክ መደወያና መቀበያ አገንግሎትንና እንደ “ኋትስ አፕ” የተሰኙት የነፃ የአጭር መልዕክት መላኪያዎችን ማስከፈል የሚያስችለውን መሳሪያ እንደገጠመና በቀርቡ በተግባር እንደሚያውል ይፋ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተንቀሳቃሽ ስልኮችን ምዝገባ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለማካሄድ እንዳቀደ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዚህ ድርጊት ቀረጥ ሳይከፈልባቸው የገቡ ስልኮች ላይ ቀረጥ በመጣል ለማስከፈል እንደሆነና ከዚህ በተጨማሪም በተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ላይ የሚደረገውን ክትትል ጠበቅ ለማድረግ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ይህንን ምዝገባ የማያኬሄድ ማንኛውም የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ ሲም ካርዱ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን ይደረግበታል፡፡ ይህንን ሁኔታ በአንክሮ ያጤኑ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ይህ የወያኔ ዘመቻ በመጀመሪያ ደረጃ እየበረታበት በመሄድ ላያ ያለውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማዳከም ሲሆን በተጓዳኝም ከደረሰበት የገንዘብ ኪሳራ ለማንሰራራት እንዲረዳው ታስቦ የተደረገ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ወያኔ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ድረ- ገጾች ማለትም የኢሕአፓን፣ ደብተራውን፣ አሲምባን፣ እንዲሁም የሌሎች ድርጅቶችንና ፀረ-ወያኔ የሆኑ ድረ-ገጾችን በቻይናዎቹ አጋሮቹ መዝጋቱ የሚታወስ ሲሆን እንዲሁም በተላይት የሚሰራጩ የቴሌቪዥንና የሬድዮ እንደ ፍኖተ ዲሚክራሲ የመሳሰሉትን ማዘጋቱ ይታወቃል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በተንቀሳቃሽ ስልኮች ንግድ ላይና ጥገና ላይ የተሰማሩ እንደሚያስረዱት እንደ አይ ፎንና የመሳሰሉ ስልኮች ለመጥለፍ አስቸጋሪ በመሆኑና የቻይናው ሁዋዌ ተንቀሳቃሽ ስልክ በቀላ ሊጠለፍ ስለሚችልና ለኩባንያው ገበያ ለመክፈትና የጥቅሙ ተጋሪ ለመሆን የታለመ መሆኑን አበክረው ያስረዳሉ፡፡

ድርቁ እየከፋ በመሄድ ላይ መሆኑ ተጋለጠ

 ይህ በወያኔ የዘር ፖለቲካና የኤኮኖሚ ስርዐት ሳቢያ የተከሰተው ድርቅና ርሀብ እንደ ቆላ ሰደድ እሳት መላ ሀገሪቱን እያዳረሰ ይገኛል፡፡ ከወሎና ከትግራይ ርሀብ ከጎጇቸውና ከቀያቸው ያሳደዳቸው በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ርሀብተኞች በደብረብረብርሀን ከተማ በየቤቱ እየዞሩ ቁራሽ እየለመኑ ህይወታቸውን እየታደጉ እንደነበር ታዛቢዎች ያስረዳሉ፡፡ ይሀ ሁኔታ መልከ ጥፉው ወያኔ ሁኔታው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሊያስነሳበት እንደሚችል በመስጋት ርሀብተኞቹን እያፈሰ የሚላስ የሚቀመስ ወደ ሌለበት ቀያቸው መልሷቸዋል፡፡ ርሀቡ በጂግጂጋ፣ በቀብሪደሀር፣ በቀላፎ፣ በሽንሌ፣ ከዘጠና አምስት ከመቶ በላይ ከብቶችን ፍጅቷል፡፡ ሴቶችና ህፃናት በጠኔ እየተሰቃዩ መሆናቸውን እርዳታ ከሚሰጡ ድርጅቶች ማወቅ ተችሏል፡፡
በዚህ ሳምንት ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ጥረት ያደረጉ ከወሎ የተሰደዱ ረሃብተኞች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ ተከልክለው በፖሊስ ተወስደዋል። በዘንድሮ ድርቅና ረሃብ የተጎዱና ዕርዳታ ማግኘት ባለማቻላቸው ወደ አዲስ አበባ በስደት ያቀኑ ተረጅዎች አዲስ አበባ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከላቸው ታውቋል። ለመከልከላቸው ዋና ምክንያት የሆነው የወያኔን ገጸታ ታበላሻላችሁ የሚል ነው።

በዚህ ሳምንት ተመድ ይፋ ባደረገው መግለጫ በኢትዮጵያ አሁን የዕርዳታ ፈላጊው ቁጥር ወደ 20 ሚሊዮን መጠጋቱና ይህ አሀዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት አንድ አምስተኛውን የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጿል። በረሃብና በድርቅ የተጎዱት አካባቢዎች ከ186 ወደ 219 ክፍ ያሉ ሲሆን ተረጅዎችም በከፋ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን በአንዳንድ አካባቢ ስደት መጀመሩና በዚህ ከቀጠለ የረሃብ አደጋ ዕልቂትን ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በመሆን በድርቅና በረሃብ ለተጎዱ ኢትጵያውያንና በጦርነት ለተጎዱ ሶርያውያን 2.2 ሚሊዮን ዕርዳታ እየተማጸኑ ሲሆን 480 ሚሊዮን ዶላር በድርቁና በረሃንብ ሳቢያ ጤንነታቸው ለተዛባ ኢትዮጵያውያንና በጦርነት ለተጎዳ ሶርያውያን ይውላል ተብሏል። የወያኔ ባለስልጣኖች በወደብ የተከማቸ የእርዳታ እህል ለማንሳት ከመረባረብ ይልቅ በረሃብተኞች ህይወት ቁማር እየተጫወቱ መሆናቸው እየተጋለጠ ነው ተብሏል

ከሀገር ውስጥ በስውር የወጣ ገንዘብ በቻይና አውሮፕላን ጣቢያ ተገኘ፡፡
 በወያኔ ቁንጮዎች እየተዘረፈ ያለው የሀገር ገንዘብና ንብረት ወደ አሜሪካን ዶላር እየተቀየረ ከአገር ውስጥ እየወጣና በዓለም ዙሪያ እንዲህ ያለ ገንዘብ በአደራ የሚያስቀምጡ ድርጅቶች ውስጥ እየተቀመጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ባለፈው ሰሞን በደቡባዊ ቻይና ጉዋንግዡ ክፍለ ሀገር ቦዩን በተባለ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ 370 ሺ የአሜሪካ ዶላር በላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የወረቀት ከረጢት ውስጥ በሁለት ቻይናውያን መገኘቱን ቻይና ዴይሊ የተባለ ተቋም ካሰራጨው መረዳት ተችሏል፡፡ የገንዘቡ ባለቤቶች ሆነው የተገኙት የኢትዮጵያ ቱርሲቶች ተብለው ተገልጸዋል ። ይህን ያህል ዶአል ይዞ የሚጓዝ የኢትዮጵያ ሀገር ጎብኚ ማነው ? ባለገንዘቦቹ ወያኔዎች መሆናቸው ከቶም አያጠራጥርም ያሉ ታዛቢዎች የኢትዮጵያ ገንዘብ በወያኔ በየአቅጣቻው እየተጓዘና በየባንኩ እየተቀመጠ መሆኑ ምስጢር አይደለም ብለዋል ።
የመምህራንን ብሶት ለማቀዝቀዝ የቤት ኪራይ አበል ክፍያ ላይ ጭማሪ ሊደረግ እንደሆነ ተሰማ፡፡

የወያኔ ስርዐት በከፋ መልኩ እያጠቃቸው ከሚገኙ የህብተሰብ ክፍሎች ከመጀመሪያ ተርታ የሚሰለፉት መምህራን ናቸው፡፡ የመምህራን ደሞዝ እንኳ አጠቃላይ የኑሮ ወጮዎችን ሊሸፍን ቀርቶ በቀን አንዴ ለሚሆን የምግብ ወጪ ከመሸፈን እንደማልፍ እራሳቸው መምህራኑ በቁጫት ያስረዳሉ፡፡ ይህ ማለት የመምህራን ደሞዝ ከእጅ ወደ አፍ ከሆነ ኑሮም እጅግ የወረደ መሆኑ ነው፡፡ መምህራን በተለያዩ አጋጣሚዎች የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው ለወያኔ ሹማምንት በተናጠል ጥያቄ ቢያቀርቡም ወያኔ ጆሮ ዳባ ልበስ ምላሽ ከመስጠት ባለፈ እስከ ዛሬ በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ ጭማሬዎች ሁሉ ከይስሙላነት የሚያልፉ አልሆኑም፡፡ የደሞዝ ጭማሪ ጭምጭምታ በተሰማ ቁጥር የቤት ኪራይ ከሃያ ከመቶ በላይ ይጨምራል፡፡ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች እንደ ተማሪዎች በስፋትና በተደጋጋሚ ባይከሰትም በጠኔ የሚወድቁ መምህራን ታይተዋል፡፡ ወያኔ ትምህርትን ሲገድል አብሮ መምህራንን እየገደለ መሆኑን የሚያስረዱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህንን የተረዱ የወያኔ አጋሮች የአሜሪካው ተራድኦ ድርጅትና የመሳሰሉት ትምህርትን መደጎሚያ ካዋሉት ገንዘብ ውስጥ ለመምህራን ከሦስት መቶ እስከ ሦስት መቶ ሃምሳ ብር የቤት ኪራይ ድጎማ ይከፈል የነበረውን በእጥፍ ለመጨመር መታቀዱ ታውቋል፡፡ ይህ ሁኔታ አዲስ አበባ ውስጥ ለሚያስተምሩ
መምህራን እንደሆነ የደረሰን ዜና ያስረዳል፡፡ ወያኔ ለመምህራን ከመደበኛ ደሞዛቸው ውጪ የቤት ኪራይ ድጎማ የሚለውን አንድ ሺ ብር ቢያደርሰውም ስም እንጂ የመምህራንን ኑሮ ኢምንት እንደማይደጉም ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡
የውጭ አገር ዜናዎች

 ቅዳሜ ሚያዚያ 9 ቀን 2008 ዓ.ም በደቡብ አሜሪካ ግዛት በኢኩዌደር ውስጥ የኃይሉ መጠን 7.2 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በመከሰቱ 77 ሰዎች ሲሞቱ ከ500 በላይ የሆኑ ደግሞ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል። ላለፉት ሰላሳ ሰባት ዓመታት በኢኩዌደር ይህን ያህል መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ሲደርስ ይኸኛው የመጀመሪያው ሲሆን በመሬት መንቀጥቀጡ ዋና ከተማዋን ኩዌቶን ጨምሮ ምእራባዊ የባህር ዳርቻ ያሉ ኣካባቢዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዋና ከተማዋ በርካታ የመኖሪያ ህንጻዎችን የተደረመሱ ሲሆን መንገዶችና ድልድዮች ፈራርሰዋል፤ የኤሌክትሪክ መስመሮች ተበጣጥሰዋል። በጣሊያን አገር የሚያደርጉትን ጉብኝት አቋርጠው ወደ አገራቸው እየተመለሱ ያሉት የኢኩዌደር ፕሬዚዳንት በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል። ፍርሃትና ስጋት በከፍተኛ ደረጃ በመስፈኑ ምክንያት አለመረጋጋት በመኖሩና በአንዳንድ ቦታዎችም ዝርፊያዎች በመካሄዳቸው ምክንያት መንግስት የተቻለውን እንደሚያደርግና መረጋጋት እንዲፈጠር ተማጽነዋል። ከ 10 ሺ በላይ የሚሆኑ ወታደሮችና ከ3000 በላይ ፖሊሶች በእርዳታ ተግባር እንዲሰማሩ ወደ ቦታው ተልከዋል።

 ከፓሲፊክ ውቅያኖስ ማዶ በምትገኘው ጃፓን ደግሞ በዚ ሳምንት ሁለት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ደርሷል። በመሀሙስ ሚያዚያ 6 ቀን በከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የተመታውና ገና በማገገም ላይ የነበረው የደቡብ ጃፓን ግዛት ነዋሪ ቅዳሜ ሚያዚያ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. መጠኑ 7.3 በሆኑ ሌላ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመቷል። በሁለቱም ቀናት በደረሱት የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች 41 ሰዎች መሞታቸውና በመቶ የሚቆጠሩ መቁሰላቸው ተዘግቧል። በርካታ ህንጻዎች በመድርመሳቸው ከህንጻዎች ስር ብዙ ሰዎች ከእነህይወታቸው ተቀብረው ይገኛሉ የሚል ስጋት አለ። በአካባቢው የሚገኙትን ፖሊሶችና የእርዳታ ሰጭ ሠራተኞችን ለመርዳት 20 ሺ ወታደሮች ወደ አካባቢው ተልከዋል። መንገዶች የፈራረሱ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የመሬት መድርመስ የደረሰ መሆኑም ታይቷል። መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ዝናም ይዘንማል የሚል ግምት ስላለም የመሬት መደርመሱ በስፋት ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት አለ። ከ200 ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጭ መሆናቸውም ተነግሯል። የቅዳሜው የመሬት መንቀጥቀጥ መጠን ሚያዚያ 6 ቀን ከደረሰው ጠንካራ ሲሆን ያጠቃቸው ክልሎችም ሰፊ እንደሆኑ ታውቋል። በአሁኑ ወቅት ከ2000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የሆስፒታል አገልግሎት እየተሰጣቸው ሲሆን ከ92 ሺ ሰዎች በላይ ቤታቸው ለቀው በመጠለያ ካምፖች መቆየት ተገደዋል። ሰንዴ በሚባለው ቦታ ላይ የሚገኘው የኑክሊየር ቦታ የመፍረስ አደጋ ያላጋጠመው መሆኑ ተገልጿል። የቅዳሜው የመሬት መንቀጥቀጥ መጠን ከአምስት ዓመት በፊት ከደረሰውና ሱናሚ አስነስቶ በተለይ በፉኪሽማ በሚገኘው የኑክሊየር ቦታ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካመጣው የመሬት መንቀጥቀጥ የሚበልጥ መሆኑን አዋቂዎች ይናገራሉ።

 የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ጀንቲሎኒ ለሊቢያ የአንድነት መንግስት የፖሊቲካና የዲፕሎማሲያዊ እርዳታ ለማድረግ ማክሰኞ ሚያዚያ 4 ቀን 2008 ዓም ትሪፖሊ ገብተዋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግፊትና አስተባባሪነት የተቋቋመው የአንድነት መንግስት በባህር በኩል ትሪፖሊ ከተማ ከገባ ጀምሮ አንድ የአውሮፓ ባለስልጣን በሊቢያ ጉብኝት ሲያደርግ ጀንቲሎኒ የመጀመሪያ መሆናቸው ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአንድነት መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሚስተር ፋየዝ ሴራጅ ጋር ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ በሰጡት መግለጫ የአውሮፓ አገሮች አዲሱን መንግስት ለመርዳት እና ለማጠናከር ሙሉ በሙሉ የቆረጡ መሆናቸውን ገልጸው ከእሳችው በኋላ በርካታ ባለስልጣኖች ወደሊቢያ በመምጣት የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ዋናው ቁልፉ አይሲስ እንዳይጠናከርና እንዲወገድ ማድረግ ነው ካሉ በኋላ በርካታ የአውሮፓ አገሮች ኢምባሲዎቻቸውን በትሪፖሊ ሊከፍቱ የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። እሳቸውንም ተከተሎ ሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2008 ዓም. የፈረንሳይ አምባሰደር እንዲሁም የእንግሊዝ እና የስፔን ከፍተኛ የልኡካን ከየሚገኙበት የአውሮፓ ህብረት ልኡካን ቡድን ሊቢያ ገብቶ ከአንድነት መንግስት አባሎች ጋር ተነጋግሯል።

 በሰሜን ናይጄሪያ ቺቦክ ከተባለችው ከተማ 276 የሚሆኑ በትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ ልጃገረዶች ቦኮ ሃራም በተባለው አሸባሪ ቡድን ተጠልፈው ከተወሰዱ ሁለት ዓመት ያለፋቸውሲሆን ባለፈው ታኅሳስ ወር በተደራዳሪዎች አማካይነት ከቦኮ ሃራም ተገኘ ከሚባለውና ባሰለፍነው ሳምንት የሲ ኤን ኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ካሳየው የቪዲዮ ቅጅ በርከት ያሉት ልጃገረዶች በህይወት መኖራቸው ታውቋል። ረቡዕ ሚያዚያ 5 ቀን 2008 ዓም ሲ ኤን ኤን ያሳየው ቪዲዮ ተቀረጸ የተባለው ታኅሳስ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. በፈረጆቹ የገና በዓል ዕለት ሲሆን ከተጠለፉት ልጃገረዶች መካከል 15 ቱ በቪዲዮ ላይ ታይተዋል። ቪዲዮን የተመለከቱት አንዳንድ እናቶችና በዚያን ወቅት ያመለጡና ጓደኞቻችው የተመሰቃቀለ ስሜት ያደረባቸው መሆኑንና በአንድ በኩል ልጆቹ በህይወት መኖራቸው ሲያስደስታቸው በሌላ በኩል ያሉበት ሁኔታ በጣም እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል። ቦኮ ሃራም የተባለው አሸባሪ ድርጅት ለዓመታት ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ የቆየ ቢሆንም ልጃገረዶችን በጅምላ ጠልፎ ሲወስድ በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ውግዘት የደረሰበት መሆኑ ይታወሳል፡፤ በወቅቱ የነበረው የናይጄሪው የሚስተር ጉድላክ ጆናታን መንግስት በመጀመሪያ ልጃገረዶቹ መጠለፋቸውን ቢክድም በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ግፊት ለመቀበል ተገዷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ልጆቹን ለማስፈታት በድርድርም ሆነ በሌላ መልክ ጥረት ቢደረግም እስካሁን የተገኘ መፍትሄ እንደሌለ ታውቋል። ባለፈው ሳምንት የናይጄሪያ ወታደራዊ ተቋም ቦኮ ሃራም ከሚቆጣጠራቸው ቦታዎች 11698 ሰላማዊ ሰዎችን ነጻ ማውጣቱን ቢገልጽም ነጻ ወጡ የተባሉት ሰዎች ከቺቦክ የተያዙ ልጃገረዶችን አያካትቱም። ላለፉት ሁለት ዓመታት በቺቦክና በአካባቢው ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ምክንያት ከ20 ሺ በላይ ህጻናት የትምህርት ዕድል ተነፍገው ይገኛሉ።

በዚህ ሳምንት በዚምባዌ በደቡብ አፍሪካ እና በግብጽ ህዝባዊ የተቃውሞ ስልፎች ተደረገዋል። ሐሙስ ሚያዚያ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ዚምባብዌ ውስጥ በተቃዋሚ ፓርቲ የተደራጀና የተቀነባበረ ከፍተኛ ተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ መሆኑ ታውቋል። ሰልፈኞቹ ፕሬዝዳንቱ ሚስተር ሙጋቢ ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ ልዩ ልዩ መፈክሮችን ይዘው የነበረ ሲሆን በርካታ ሴቶችና ወጣቶች እንደነብሩበት ለማወቅ ተችሏል። ስልፉን ቀደም ብሎ የጸጥታ ኃይሎች ከልክለው የነበረ ቢሆንም ረቡዕ ሚያዚያ 5 ቀን 2008 ዓም የዚምባብዌ ፍርድ ቤት የፖሊስ እገዳ እንዲነሳ ትእዛዝ በመስጠቱ ምክንያት ሰልፉ ሊካሄድ ችሏል። ሙጋቤ የሚመሩት የዚምባብዌ ገዥ ፓርቲ አርብ ዕለት በሰጠው መግለጫ ፕሬዚዳንቱ ስልጣን እንዲለቁ ተቃዋሚዎችን የሚጠይቁትን ጥያቄ አውግዞ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ለማውረድ ትክክለኛው መንገድ ምርጫ ነው ብሏል። ከሶስት አመት በፊት በተካሄደው ምርጫ ሚስተር ሙጋቤ በድጋሚ የተመረጡ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን በወቅቱ በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የምዕራብ አገሮች ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ አይደለም በማለት ድምጽ ማሰማታቸው ይታወሳል።

አርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. የደቡብ አፍሪካ ዜጎች በጆሃንዝበርግ ከተማ ፕሬዚዳንት ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ በመጠየቅ ትእይንተ ህዝብ ያደረጉ መሆናቸው ተነግሯል። ሰላማዊ ሰልፉና ያዘጋጁት የተቃዋሚ ድርጅቶች ሲሆኑ ሰልፈኞቹ ” ሙስና ይቁም” ” ለለውጥ ድምጻችንን እንሰጥ” የሚሉ መፈክሮችን ይዘው እንደነበር ማወቅ ተችሏል። ከጥቂት ቀናት በፊት የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቱ ለገጠር ቤታቸው ማስፋፊያ በርካታ የመንግስት ገንዘብ መውሰዳቸው አግባብ አለመሆኑን ገልጾ ገንዘቡን እንዲመልሱ መወሰኑ ይታወሳል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ታዋቂ ግለሰቦችና የሃይማኖት ድርጅቶች
መሪዎች ሚስተር ዙማ ከስልጣን እንዲወርዱ ቢጠይቁም ከገዥው ፓርቲ አባላት በኩል ያላቸው ድጋፍ ከፍተኛ በመሆኑ በምክር ቤት ውስጥ እሳቸውን ከስልጣን ለማስወገድ የቀረበው ሕዝበ ውሳኔ ውድቅ መሆኑ ይታወቃል።

እንዲሁም አርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ ውስጥ የፕሬዚዳንት ሲሲን አስተዳደር በመቃወም ቁጥራቸው ከ 1000 በላይ የሚሆኑ ግብጻውያን የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸውን የዜና ምንጮች ገልጸዋል። ሰልፉ የተጠራው ቀደም ብሎ ሁለት የግብጽ ደሴቶች ለሳኡዲ አረቢያ መሰጣቸውን ለመቃወም ቢሆንም ሰልፈኞች ያሰሙ በነበረው መፈክር ውስጥ የሲሲ መንግስት የሚያወግዙና ሲሲ ባስቸኳይ ከስልጣን እንዲወገዱ የሚጠይቁ እንደሚገኙበት ታውቋል። ስልፉ እስከምሽት ድረስ የቆየ ሲሆን አብዛኛው ሰልፈኛ ከሄደ በኋላ የቀሩትን ጥቂት ሰዎች ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ የተጠቀመ መሆኑ ተገልጿል። ቀደም ብሎ በሌላው የከተማው ክፍል የተደረገውን ስልፍ ለመበተን ፖሊስ እርምጃ የወሰደ ሲሆን 12 ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውም ተዘግቧል።

 የምእራብ ሳህራ ግዛትን አስመልክቶ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተለይም የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በሞሮኮ መንግስት ላይ ተገቢውን ተጽእኖ ማድረግ ካልቻሉ ሞሮኮ በምእራብ ሳህራ ሕዝብ ላይ የምትፈጸመው አፈናና በደል ሊፋፋም እንደሚችል የፖሊሳሪዮ ግምባር መሪ ሚስተር ሞሃመድ አብዱላዚ በዚህ ሳምንት አስታውቀዋል። በሕዝብ ላይ የሚካሄድ አፈናና በደል የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ ይህን ለመቋቋም ከትጥቅ ትግልን ጀምሮ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ እንገደዳለን በማለት ጦርነት እንደገና ሊጀመር የሚችልበትን ሁኔታ ጠቁመዋል። ማስጠንቂቂያው የተሰጠው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በምእራብ ሳህራ ስለሚገኘው የተመድ ተል እኮ የወደፊት እጣ እየመከረ ባለበት ወቅት ነው። ባለፈው ወር ሞሮኮ በተመድ ዋና ጸሐፊ መግለጫ በመቆጣት ከአገሩዋ ዲፕሎማቶችን ማስወጣቷ ይታወቃል። የተባበሩት መንግስታት ከ1983 ዓም የምእራብ ሳህራን ጉዳይ ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ የቆየ ቢሆንም ጥረቱ እስካሁን ጥረቱ ያልተሳካ መሆኑ ይታወቃል። የአገሪቱን የወደፊት እጣ ለመወሰን ውሳኔ ሕዝብ ይደረግ ቢባልም በፖሊሳርዩ ግምባርና በሞሮኮ መካከል በጉዳዩ ላይ ልዩነት በመፈጠሩ እስካሁን ሳይካሄድ ቆይቷል። ግዛቱ የሞሮኮ ነው የሚለውን ሀሳብ ፈረንሳይና ሴኒጋል የሚደግፉት ሲሆን ሌሎች የጸጥታው ምክር ቤት አባላት የሚቃወሙት መሆኑ ይታወቃል።

 ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ሱዳን ሁለት የእርዳታ ሰጭ ድርጅት ሠራተኞች በታጣቂ ኃይሎች የተገደሉ መሆናቸው ተገድለዋል። ዳኒሽ ዲማይኒንግ ግሩፕ (Dannish Demining Group) ለሚባለው የቦምብ አምካኝ የሰብአዊ መብት ድርጅት ይሰሩ የነበሩት ሁለቱ ግለሰቦች የደቡብ ሱዳን ዜጎች ሲሆኑ ወደስራ ከሚሄዱበት መኪና በታጣቂዎች እንዲወርዱ ተገድደው በጥይት ተመተው የተገደሉ መሆናቸውን የዓይን እማኞች ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ በደቡብ ሱዳን በታጣቂዎች የተገደሉ የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች አባላት 51 የደረሰ ሲሆን ግጭቱ እስከቀጠለ ድረስ ቁጥሩ ሊቀጥል እንደሚችል ተገምቷል፡፡

 በተያያዘ ዜና የደቡብ ሱዳን አማጽያን ኃይል ምክትል መሪ ሚስተር አልፍሬድ ላዱ ጎሬ በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ የገቡ መሆናቸው ተነግሯል። በተደረገው ስምምነት መሰረት የጸጥታውን ሁኔታ የሚያስከብር 1300 የሚሆኑ የአማጽያኑ ኃይል ወታደሮችና የጸጥታ ኃይሎች ቀደም ብለው ጁባ መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን ዋና መሪ ሚስተር ሪክ ማቻርም በሚቀጥለው ሰኞ ጁባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የምክትል መሪው ጁባ መግባት በእርግጥም በአገሪቱ ላይ ሰላም እየሰፈነ ነው የሚለውን ግምት ከፍ አድርጎታል ተብሏል። ሚስተር ጎሬ ጁባ ሲገቡ በተናገሩት ቃል ከእንግዲህ ሰላም አይቀለበስም የሚል መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን 16 የአማጽያኑ ኃይል አባላት በመንግስት ኃይሎች መታሰራቸውንና ተደብድበው መለቀቃቸውን አውግዘዋል። ከዚህ ሌላ አንድ የአፍሪካ ህብረት የመልክተኛ ቡድን በደቡብ ሱዳን የአንድነቱን የሽግግር መንግስት ለማጠናከር ጁባ የገባ መሆኑ ተገልጿል።

↧

↧

በጋምቤላው እልቂት ዙሪያ መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ ባለ3 ነጥብ መግለጫ አወጡ

$
0
0

ሚያዚያ 6 ቀን 2008 ዓ ም በጋምቤላ ክልል ነዋሪ በሆኑ ሰላማዊ የኑዌር ብሔረሰብ አባላት ላይ በጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን ነዋሪ በሆኑ ታጠቂዎች የተፈጸመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በመስማታችን መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ እጅግ ልብ የሚሰብር ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል፡፡

130153
ከመንግሥት ባገኘነው መረጃ መሠረት ብቻ 208 ዜጎቻችን በዚሁ ጭፍጨፋ በአንድ ሌሊት ሕይወታቸውን ማጣታቸውና 102 ሕፃናት ታፍነው መወሰዳቸው በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከፍተኛና ዘግናኝ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ዜጎቻችን ለዚህ ያህል ትልቅ ጥቃት የተዳረጉት ደግሞ ቀደም ሲልም ጥቃት ሲፈጸሚባቸው እንደነበረ እየታወቀ የኢህአዴግ መንግሥት እራሳቸውን የሚከላከሉበትን ትጥቅ በማስፈታቱ የመከላከያ መሣሪያ እንዳይኖራቸው በመደረጉና ባዶ እጃቸውን በቀሩበት ሁኔታ ለደህንነታቸው ተገቢው ጥበቃ ስላልተደረገላቸው መሆኑን መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ ይገነዘባሉ፡፡

ከዚህም ሌላ ቀደም ባሉት መንግሥታት በየጠረፉ አከባቢዎች ይመደብ የነበረው ጠረፍ ጠባቂ ኃይል እንዳይኖር በመደረጉ የውጭ ሀገር ታጣቂዎች እንደፈለጉ ድንበር ጥሰው የሚገቡበትና ወገኖቻችን ላይ ጥቃት የሚያደርሱበት ሁኔታ የተፈጠረ መሆኑንም ለመረዳት ችለናል፡፡

ስለዚህም፡-
1ኛ፡- በጥቃቱ ምክንያት የቤተሰብ አባሎቻቸውን ላጡ የኑዌር ብሄረሰብ አባላት ለሆኑ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንደዚሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን፡፡
2ኛ፡- በአጥቂዎቹ ታፍነው የተወሰዱት ሕፃናት በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ መንግሥትና የዓለም ማሕበረሰብ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ተገቢውን ጥረት ሁሉ እንዲያደርጉ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
3ኛ፡- ለወደፊቱ በጋምቤላም ሆነ በሌሎች ክልሎች በጠረፍ አከባቢዎች በሚገኙ ዜጎቻችን ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ሕዝቡ ራሱን መከላከል የሚያስችልበትና ተገቢውን የደህንነት ጥበቃ የሚያገኝበት ሁኔታ በአስቸኳይ በመንግሥት በኩል እንዲመቻች አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
ሰላም ለሕዝባችን!!
ድል ለሕዝባዊ ትግላችን!!
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ
ሚያዚያ 9 ቀን 2008 ዓ ም
አዲስ አበባ

↧

ዮናታን ወልዴና ባህሩ ደጉ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተፈተው ከሰዓታት በኋላ ማዕከላዊ እስር ቤት ታሰሩ

$
0
0

Bahiru-Degu

yonatan-tesfaye (1)
(ዘ-ሐበሻ) ላለፉት 647 ቀናት በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ቤት የነበሩትና ባለፈው አርብ በከፍተኛው ፍርድ ቤት በነፃ እንዲለቀቁ የተፈረደላቸው ባህሩ ደጉ እና ዮናታን ወልዴ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተፈተው ከተለቀቁ በኋላ ከሰዓታት በኋላ እንደገና ተይዘው ማዕከላዊ መታሰራቸው ተሰማ::

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሁለቱም ወጣቶች በማዕከላዊ እስር ቤት ይገኛሉ:: እነዚሁ እስረኞች ለምን እንደገና እንደታሰሩ የታወቀ ነገር የለም::

↧

የዩኤስኤአይዲ/USAID የምግብ እጥረት ጨዋታዎች በኢትዮጵያ

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ 
የረሀብ ወይም የድርቅ ጨዋታዎች በኢትዮጵያ?

ዩኤስኤአይዲ/USAID በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የምግብ እጥረት እንጅ ረሀብ አይደለም ይላል፡፡ (ኤል ኒኖ የተባለው የአየር ለውጥ ባስከተለው ችግር ምክንያት ያለው ነገር አስከፊ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ የምግብ ዋስትና እጦት፣ የምግብ እጥረት፣ በቂ ምግብ ያለመኖር፣ የምግብ እጦት፣ አስከፊ የምግብ እጦት፣ አስከፊ የምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ ጥልቅ የምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ ወዘተ ብቻ ነው) ይላል ዩኤስኤአይዲ፡፡

Konyndykእኔ ደግሞ ረሀብ አለ እላለሁ! ረ-ሀ-ብ  አለ !!!

ባለፉት ስምንት ዓመታት ሳቀርባቸው በነበሩት በርካታ ትችቶቼ ረሀብ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ሲከሰት፣ ተደጋግሞ ሲከሰት እና በድንገተኛ መልኩ ሲንሰራፋ የቆየ መሆኑን ትኩረት በመስጠት ሳሳስብ ቆይቻለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2016 በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ አለ ወይስ የለም?

በኢትዮጵያ ውስጥ ይህንን ጥያቄ መመለስ የሚችሉት የምጽዓት ቀን የሆነውን ባለጥቁር ፈረሱን ረሀብ ፊት ለፊት በተጨባጭ ተጋፍጠው የሚገኙት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ብቻ ናቸው፡፡

እነዚህ ሕዝቦች ተናግረዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ ከመቸውም ጊዜ በላይ አስከፊ በሆነ ረሀብ ውስጥ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ለዩኤስኤአይዲ/USAID ተናግረዋል፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የትግራይ ሕዝብ ለዩኤስ አሜሪካ የውጭ አደጋ ረዳት የዩኤስኤአይዲ/USAID ጽ/ቤት ዳይሬክተር ለሆኑት ለጀርሚ ኮኒንዲክ በረሀቡ ምክንያት ጠቅላላ ለመጥፋት በቋፍ ላይ እንደሚገኙ  ተናግረዋል፡፡

ኮኒንዲክ የትግራይ ሕዝብ የነገረውን እንዲህ በማለት አጠቃልሎ አቅርቦታል፡

“ይህ ድርቅ መጠነ ሰፊ ነው፡፡ በሀገሪቱ በአብዛኛው አካባቢ ካለፉት 50 ዓመታት ወዲህ ታይቶ የማያውቅ አስከፊ የሆነ ድርቅ ነው…በትላንትናው ዕለት ከትግራይ እየወጣን በነበርንበት ጊዜ ከዚህ ቀደም በህይወታቸው ውስጥ እንደዚህ ያለ አስከፊ ረሀብ አይተው እንደማያውቁ – በበርካታ መንገዶች እ.ኤአ. በ1983፣ 1984 ከተከሰተው ድርቅ እጅግ የከፋ መሆኑን ከበርካታ ማህበሰቦች ጋር ባደረግነው ውይይት ነግረውኛል፡፡ እንደዚህም ሆኖ ይህ በአሁኑ ጊዜ የተከሰተው ድርቅ ውጤቱ እ.ኤ.አ በ1984 ከተከሰተው ድርቅ ውጤት ጋር ተመሳሳይ እንደማይሆን እናውቃለን…” (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

እ.ኤ.አ በ1984 የተከሰተው ድርቅ ውጤቶች ምን ነበሩ?

ከ32 ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ በ1984 በትግራይ ክልል እና በሌሎች የኢትዮጵያ ሰሜናዊ የሀገሪቱ አካባቢዎች ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን አውዳሚ ለሆነ የረሀብ ሰለባነት ተዳርገው ነበር፡፡

በአሁኑ ጊዜ የትግራይ ሕዝብ ከኮኒንዲክ እና ለዩኤስኤአይዲ/USAID በህይወታቸው እንደዚህ ያለ ድርቅ አይተው እንደማያውቁ የተናገሩ ቢሆንም ኮኒንዲክ እራሱም ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ እንደዚህ ያለ አስከፊ ድርቅ ተከስቶ እንደማያውቅ አምኗል፡፡ ኮኒንዲክ እና ዩኤስኤአይዲ/USAID እንደዚህ ያለ አሰቃቂ ሁኔታ መፈጠሩን ለመግለጽ  “ረ”ሀብ  የምትለዋን ቃል በፍጹም ደፍረው አይጠሯትም፡፡ ይፈራታል !
ኮኒንዲክ በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ያለውን አስከፊ ችግር ባለማወቅ በድንቁርና ነው ወይስ ደግሞ ለአስከፊው ቀውስ ምንም ዓይነት ትኩረት ባለመስጠት ጀሮ ዳባ ልበስ ለማለት ነው?

ኮኒንዲክ በዚህ አስከፊ ድርቅ/ረሀብ ክፉኛ የተጠቁትን በርካታዎችን የኦሮሚያ፣ አፋር፣ አማራ እና የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችን ክልሎች ቢጎበኝ ኖሮ ከዚህ ጋር የተያያዘ ታሪክ ይሰማ እንደነበር የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም፡፡

እውነት ለመናገር ኮኒንዲክ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ለምን እንዳልሄደ የማውቀው ነገር የለም፡፡

ምናልባትም ኮኒንዲክ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እንዳይሄድ ዘ-ህወሀት (ዘራፊ ህወሀት)  ባለመፍቀዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባት ኮኒንዲክ ወደ ትግራይ ክልል ሄዶ ስለአስከፊ አልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት ጉዳይ የዘ-ህወሀትን ፕሮፓጋንዳ መስመር አይቶ እና ሰምቶ ፎቶግራፎችን በማንሳት በመመለስ በአዲስ አበባ በባለ “5 ኮከብ ሆቴል” ውስጥ በመገኘት መግለጫ እንዲሰጥ ታስቦ ሊሆን ይችላል፡፡

ሆኖም ግን የትግራይ ሕዝብ የሚላስ የሚቀመስ ምንም ዓይነት ነገር ጠፍቶ በከፍተኛ የረሀብ ስቃይ ውስጥየሚገኝ እንጅ በአስከፊ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት ተዳርገው እንደሚገኙ የማስመሰያ ውሸትአይናገሩም፡፡ ለኮኒንዲክ እውነታውን ፍርጥ አድርገው ነግረውታል፡፡ አውዳሚ በሆነ ረሀብ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ነግረውታል!

የዩኤስ አሜሪካ የውጭ አደጋ ረዳት ዋና ሹም የተሟላ ስዕል ሊሰጥ የሚችል መረጃ ለማግኘት እንዲችል በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ቢያንስ ጥቂት አካባቢዎችን ማየት ምንም ዓይነት ትርጉም አልሰጠውም ማለት ነውን?

ምናልባትም ኮኒንዲክ ድርቅ/ረሀብ ያለበትን አንዱን አካባቢ ካየህ ሁሉም ያው ነው ተብሎ ስለሚነገረው ሌሎች የሀገሪቱን አካባቢዎች ለመጎብኘት ደንታ ሳይሰጠው ቀርቶ ሊሆን ይችላል!

ኮኒንዲክ እና ዩኤስኤአይዲ/USAID ስለድርቅ፣ ድርቅ፣ ድርቅ ደግመው ደጋግሞ ያወራል …?

ሆኖም ግን እንዲህ የሚለውን ተገቢ የሆነ ጥያቄ እና ምላሽ ለሕዝብ ይፋ አያደርጉም፡ የድርቅመንስኤዎች እና ውጤቶች ምንድን ናቸው?

ኮኒንዲክ ሲደረግለት የነበረውን ቃለ መጠይቅ ጥያቄ ግልጽ አድርጓል፡፡ እንዲህ ብሏል፣ “የዚህ የ[2016]  የድርቅ ውጤት እ.ኤ.አ በ1984 ከነበረው የድርቅ ውጤት ጋር አንድ ዓይነት አይሆንም፡፡“

እ.ኤ.አ በ1984 የደረሰሱ የድርቅ ውጤጦች በእርግጠኝነት ምንድን ናቸው?

ኮኒንዲክ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ አጋጥሟት የማያውቅ መጠነሰፊ ለሆነ የድርቅ አደጋ ተዳርጋ ትገኛለች ይላል!

እ.ኤ.አ በ1984-85 ተከስቶ የነበረው መጠነሰፊ ድርቅ መጠነሰፊ የሆነ ረሀብን አስከትሎ ነበር፡፡ ሆኖምግን ኮኒንዲክ እ.ኤ.አ በ2016 የተከሰተው መጠነሰፊ ድርቅ የሚያስከትለው መጠነሰፊ ድርቅ እንደሆነብቻ አድርጎ በማረብ እንድናምን ይፈልጋልን?

“ወይ ጉድ ! ገና ከመጀመሪያው ማታለል ስንጀምር ምን ዓይነት ድር ነው እያደራን ያለነው፡፡”

ዩኤስኤአይዲ/USAID በኢትዮጵያ ውስጥ ተከስቶ ስለነበረው ድርቅ/ረሀብ እውነተኛው ነው ብሎ የተናገረበት ጊዜ ነበር፡፡

ያ ጊዜ ከሶስት አስርት ዓመታት በፊት ነበር፡፡ ጊዜ እና ታላቅ ውሸት ከጊዜ ጋር እንዴት ይበራል እባካችሁ!

ዩኤስኤአይዲ/USAID “የመጨረሻ የአደጋ ዘገባ፡ እ.ኢ.አ የ1985-86 የኢትዮጵያ ድርቅ/ረሀብ“ በሚል ርዕስ (ገጽ iii) ባቀረበው የአደጋ ዘገባው እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፡

“እ.ኤ.አ በ1984 በጠንካራው የቴሌቪዥን አዲስ ማሰራጫ አማካይነት በኢትዮጵያ ውስጥ ለአሰቃቂ ረሀብ ተዳርገው የነበሩትን ኢትዮጵያውያን ለማወቅ በቅቶ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1984 መጨረሻ በረሀቡ ምክንያት 8 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ለሞት አደጋ ተግልጠው እንደነበር እና 1.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምግብ እና ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች በሚሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር የአስቸኳይ ጊዜ የእርዳታ አቅርቦት እንደሚያስፈልግ ግልጽ ተደርጎ ነበር፡፡ የተሰጡት ምላሾች እጅግ የገዘፉ ነበሩ፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2016 ኮኒንዲክ እንዲህ ይላል፡

“ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ተከስቶ የማያውቅ አስከፊ ድርቅ ነው…ቁጥሩ ማለትም የእርዳታ ፈላጊው ብዛት ከ10 ሚሊዮን ይበልጣል እናም በአሁኑ ጊዜ ያለው ትንበያ የሚያሳየውይህንን ነው፡፡ ቀጣዩ የክረምት ወቅት ከዚህ የከፋ እንደሚሆን እንገምታለን…“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

ኢትዮጵያ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ አጋጥሟት ለማያውቅ ድርቅ ተዳርጋ የምትገኝ ቢሆንም ኮኒንዲክ “ረ“ሀብ የምትለዋን ቃል ለመጥራት አፉን ተለጉሞ ይገኛል፡፡

በአንድ ወቅት ቮልቴር እንቆቅልሹን እጅግ ጥልቅ በሆነ መልኩ በማሰብ “አስመሳይነትን ለመግለጽ ምን ያህል አስቸጋሪ ነገር ነው! ማጭበርበር እና ጭካኔ የተመላበት አስመሳይ መሆን ምን አይነት አስፈሪ ነገር ነው?” ብለው ነበር፡፡

የዓለም ህዝብ ሆዳቸው የተነፋውን እና ሰውነታቸው እየሟሸሸ ያለቀውን የኢትዮጵያ ህጻናት በኃይለኛውአዲሱ የቴሌቪዥን ማሰራጫ እንዴት ማየት ይሳነዋል?

መልሱ እንዲህ የሚል ቀላል ነገር ነው፡ “ዘ-ህወሀት በድርቅ ክፉኛ ከተመቱ አካባቢዎች ሁሉንም ዓይነት መረጃዎች ደብቆ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ በመገኘቱ ምክንያት ነው፡፡“

የድርቅ አደጋው ካለባቸው ማናቸውም አካባቢ ቢሆን ማንም ጋዜጠኛ በመሄድ ዘገባ የሚያቀርብ ከሆነ በዘ-ህወሀት በጸረ አሸባሪነት ሕግ የሸፍጥ ክስ ይመሰረትበታል፡፡

ሆኖም ግን በዘ-ህወሀት የሚመረመሩት እና የሚከለከሉት ጋዤጠኞች ብቻ አይደሉም፡፡

ከዚህም በላይ ዘ-ህወሀት “ረ“ሀብ ወይም ደግሞ “ቸነፈር“ የሚሉ ቃላትን እና ሀረጎችን ለምሳሌ ያህልም “ህጻናት በየዕለቱ ይሞታሉ“፣ “ለተፈጠረው ችግር የመንግስት ፖሊሲዎች በከፊል አስተዋጽኦ አላቸው“  የሚሉ መግለጫዎችን የሚያወጡትን መንግስታዊ ያልሆኑ የውጭ ድርጅቶችን ከፍተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል፣ የማስፈራራት ድርጊትም ይፈጸምባቸዋል፡፡ ከዚያም ጭራቸውን ወትፈው ወደመጡበት እንዲሄዱ ይገደዳሉ ወይም ደግሞ ምንም ነገር ትንፍሽ ሳይሉ እንዲቀመጡ ይደረጋሉ!

በኃይለኞቹ እና በአዲሶቹ የቴሌቪዥን ማሰራጫዎች በድብቅ ተቀርጾ ምስላቸው የወጣ ሆዳቸው የተነፋ እና ሰውነታቸው የሟሸሸ ጥቂት የኢትዮጵያ ህጻናት ፎቶግራፎችን ማየት የምንጀምረው መቼ ይሆን?

ይኸ ቀላል ነገር ነው፡፡ ዘ-ህወሀት ዓለም አቀፍ የዜና ማሰራጫዎች በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን በነጻ መመልከት እንዲችሉ ሲፈቅድላቸው ወዲያውኑ ነው፡፡

ኮኒንዲክ ከእርሱ ጋር ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች የትግራይ ክልልን እና ሌሎችንም በድርቁ/ረሀብ የተመቱ የሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እንዲጎበኙ እና በነጻ ዘገባቸውን እንዲያቀርቡ የሚያደርግ ከሆነ ለአሜሪካ ግብር ከፋይ ሕዝብ ትልቅ አገልግሎት እንደፈጸመ ይቆጠራል፡፡

እንደገና ተወልጃለሁ/ተሀድሶ አድርጊያለሁ በምትል ሀገር ላይ ዩኤስኤአይዲ/USAID ግልጽነትበጎደለው መልኩ እየሰራ ነወይ ብሎ መጠየቅ የሚበዛ ሊሆን ይችልን? 

ኮኒንዲክ በአዲስ አበባ ከተማ በባለ5 ኮከብ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ ጊዜውን እያሳለፈ ከዓለም አቀፍ ብዙሀን መገናኛዎች ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች እንዲህ እያለ ምላሽ ይሰጣል፡ “

(እንዴት ያለ የሚያስገርም ሁኔታ ነው! በባለ5 ኮከብ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ ስለተራቡ ሕዝቦች መናገርአስደናቂ ነገር አይደለምን? ምን ዓይነት አስደማሚ ነገር ነው እባካችሁ!!!“)

ፓውል ሸም (ከአሶሺየት ፕሬስ/ዋሺንግተን ፖስት) እንዲህ ብሎ ነበር፡ “በርካታ የእርዳታ ድርጅቶች ከአንድ ወይም ከሁለት ወራት በፊት የምግብ እርዳታ አቅርቦቱ ምንጭ ሊቋረጥ ይችላል…“ በማለት ተናግረው ነበር፡፡

ኮኒንዲክ በበኩሉ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ስለምግብ አቅርቦት ምንጭ ጉዳይ…  ይህንን ነገር ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ካለው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተነጋግረናል…በምግብ አቅርቦት ምንጩ ላይ የመቋረጥ ሁኔታ እንዳይፈጠር አዘጋጅተውት ካለው ዕቅድ ጋር በተያያዘ መልኩ ከእነርሱ ጋር እስማማለሁ…?“

አትለኝም !?

እስክንድር (ከአሜሪካ ድምጽ የአፍሪካ ቀንድ ሬዲዮ አገልግሎት) እንዲህ የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር፣ “የሰብአዊ ፍላጎቶች ሰነድ በኢትዮጵያ መንግስት እና በአጋሮቹ በመከለስ ላይ እንደሆነ አያለሁ፡፡ ይኸ ማለት አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልጉ 10.2 ሚሊዮን እንደሆኑ ተገንዝበናል ማለት ነውን?“

ኮኒንዲክ፡ “ይህንን ቁጥሩን በመጨረሻ የሚወስነው የኢትዮጵያ መንግስት ነው፣ እና በዚያ ሂደትመሰረት መንግስትን እንረዳለን”  አትለኝም !?

ዩኤስኤአይዲ/USAID በሸፍጥ የተሞላውን የ10 በመቶ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕደገት መጣኔ የአገዛዙን የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ እንደሚደግፍ አይነት መሆኑ ነውን?

አንዷለም ሲሳይ (ከብሔራዊ ሜዲያ ቡድን) እንደህ የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር፣ “የእኔ ጥያቄ ለእንደዚህ ዓይነቱ አሰቃቂ ሰብአዊ ቀውስ ዘለቄታዊ መፍትሄው ምንድን ነው የሚል ነው፡፡ በየሶስት እና በየአራት ወይም ደግሞ በየአምስት ዓመቱ በእንደዚህ ያለ ሁኔታ ውስጥ እየተገባ ነው፡፡ ስለሆነም ለእንደዚህ ዓይነት ቀውሶች ዘላቂ መፍትሄው ምንድን ነው ብለው ያስባሉ?“

ኮኒንዲክ፡ “ይኸ ታላቅ እና በእርግጠኝነት ጠቃሚ ጥያቄ ነው…ይህ በየአራት ወይም ደግሞ በየአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚከሰት ድርቅ አይደለም፡፡ ይኸ በየ50 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚከሰት ድርቅ ነው…ይኸ ልዩ እና በጣም ኃይለኛ የሆነ ዓለም አቀፋዊ ኤል ኒኖ ነው…ኢትዮጵያ በዚህ የአየር ለውጥመነሻነት እስከ አሁን ድረስ ባስከተለው ቀውስ ተጠቅታለች፣ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ ደቡባዊ የአፍሪከ ሀገሮች በከፍተኛ ሁኔታ በመጎዳት ላይ ይገኛሉ፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

አትለኝም !? ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በኢል ኒኖ የተመረጠች ሀገር ናት?

በነገራችን ላይ ዩኤስኤአይዲ/USAID የመነጋገሪያ ነጥቦችን እንዴት አድርጎ እንደሚያዘጋጅ ያውቃል፡፡ የዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ የሆነችው ጋይሌ ስሚዝ በአንድ በቅርብ ጊዜ አድርጋው በነበረ ቃለ መጠይቅ እንዲህ የሚል ተመሳሳይ ምላሽ ሰጥታ ነበር፣ “ይኸ ኤል ኒኖ እየተባለ የሚጠራው የአየር ንብረት ለውጥ በርካታ የዓለም ክፍሎችን በከፍተኛ ሁኔታ አጥቅቷል፣ ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ካደረሰው ጉዳት የከፋ በየትም አገርየለም፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

ሁሉም ከአንድ ምንጭ የተቀዳ ንግግርን ነው የሚያነበንቡት!

በርካታዎቹ የዓለም አቀፍ መገናኛዎች በድርቅ/ረሀብ በተጠቁ አካባቢዎች እየተገኙ ለምን እራሳቸው መዘገብ አይችሉም?

ምቾት ባላቸው በባለ5 ኮከብ ሆቴሎች ውስጥ እየተቀመጡ መረጃዎችን በማንኪያ እንዲጎርሱየሚደረገው ለምንድን ነው?

ኮኒንዲክ በባለ5 ኮከብ ሆቴል በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተቀምጦ ለእራሱ ድርጅት፣ ለዘ-ህወሀት፣ ለተባበሩት መንግስታት እና ለሌሎች አጋሮች በጥሩ ሁኔታ በተዘጋጀ ስራ ለራስ ጥቅም ብቻ የሚሰጡ ሀሳቦችን እና ተግባሮችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ኮኒንዲክ ለዘ-ህወሀት እንዲህ ይላል፣ “ጠቃሚ የሆነ የጉብኝት መስተንግዶ ስለተደረገልን እና ለበርካታ ዓመታታ ሁለታችንም ባለን መሰረተሰፊ አጋርነት እንደዚሁም ከዚህ ድርቅ ጋር በተያያዘ መልኩ ከምንሰጠው ምላሽ ካለን ጠንካራ አጋርነት አኳያ ለኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሆነ ምስጋናችንን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡“

“በርካታ በርካታ ዓመታት እና  ጠንካራ አጋርነት!“ ከዘ-ህወሀት ጋር!

ነገሩ ይገባኛል፡፡

ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ በ2015 ኢትዮጵን ጎበኘ፣ እናም ገዥው ፓርቲ ዘ-ህወሀት (የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና በአሁኑ ጊዜ ስሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ስም ዝርዝር ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘው እንዲሁም እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 ተደረገ በተባለው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ 100 በ100 አሸነፍኩ ብሎ ያወጀው) “ዴሞክራሲያዊ” ነው በማለት አወጀ፡፡

እንግዲህ ጠንካራ አጋርነት የሚሉት እንዲህ ዓይነቱን ጉዳይ አንዳቸው ለአንዳቸው እየሰሩ በእከክልኝ ልከክለህ መርህ እንደሆነ እገምታሁ፡፡ አንዳቸው ለአንዳቸው እስከ ጥርሳቸው ድረስ ይዋሻሉ፡፡

ባራክ ኦባማ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊት በመቆም ዘ–ህወሀትን ዴሞክራት ነው ብሎ ቢጠራው እናኮኒንዲክ  በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊት በመቆም በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ ተንሰራፍቶ  እያለ ረሀብየለም ብሎ ቢክድ ማንም የሚደነቅ ሰው አይኖርም ፡፡

አንድ የቆየ እና እንዲህ የሚል የኢትዮጵያውያን አባባል አለ “ዓሳ የሚገማው ከጭንቅላቱ ነው፡፡“

ኮኒንዲክ እንዲህ የሚል እውቅና ይሰጣል፣ “ለተባበሩት መንግስታት እና መንግስታዊ ላልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አጋሮቻችን በእርግጠኝነት ለዚህ ድርቅ ምላሽ በመስጠት ታላቅ እና የጀግንነት ስራን የሰሩ ስለሆነ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡“

እነዚህ የንግግር ቃላት በዓለም አቀፉ መገናኛ ብዙሀን ቢነገሩ ኖሮ የተሻለ አይሆንም ነበርን?

ዩኤስኤአይዲ/USAID በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚከሰተው ረሀብ (“በጣም አስከፊ የሆነ የምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣” ወዘተ እያለ የሚጠራው) መነሻው ኤል ኒኖ (የውቅያኖሶች የከርሰ ውኃ ገጽታ መሞቅ እና የአየር ግፊት ዝውውር በመፍጠር የዝናብ መጠኑ የመቀነስ ሁኔታ) ነው ይላል፡፡

የዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ የሆነችውን ጋይሌ ስሚዝን የሚያምን ከተገኘ የድርቁ መንስኤ ኤል ኒኖ ብቻ ነው ማለት ሳይበቃት እንዲያውም ኤል ኒኖ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለቅጣት የተላከ ልዩ ታምራዊ ኃይል ይመስላል፡፡

ጋይሌ ስሚዝ ሰጥታው በነበረው ትርጉም የለሽ መግለጫ እጅግ በጣም ተበሳጭቸ ስለነበር ኢትዮጵያ ከዓለም ሀገሮቸ ሁሉ ከፕላኔቷ ተነጥላ ለምን በከፍተኛ ሁኔታ በኤል ኒኖ ተመታች ብላ እንደተናገረች የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፌ ጠይቂያት ነበር፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ዘ-ህወሀት በመልካም አስተዳደር እጦት፣ አቅዶ እና አስተባብሮ መስራት ባለመቻሉ ምክንያት ድርቅ ሊከተል እንደቻለ ከፊል ምክንያት እንደሚሆን ወይም ደግሞ ለክስተቱ መነሻ፣ መስፋፋት እና/ወይም በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ድርቅ ዘለቄታዊ ሊሆን እንደሚችል ጋይሌ ስሚዝን ጠይቂያት ነበር፡፡

ስሚዝ የላኩላትን ደብዳቤ ከቁብ ባለመቁጠር ለረዳት አስተዳዳሪዋ አሳልፋ ሰጥታዋለች፡፡ ረዳት አስተዳዳሪው በጻፈው ምላሽ እንዲህ በማለት በቢሮክራሲያዊ ፍሬከርስኪ አባባል ለማታለል ሞክሯል፣ “በመጀመሪያ ደረጃ ከድርቁ ጋር በተያያዘ መልኩ የምግብ እጥረት እና የእንስሳት እልቂት ለመኖሩ እውቅና እንሰጣለን፣ እናም እነዚህ ነገሮች ሰዎች ለመኖር በሚያደርጉት ጥረት ላይ ከፍተኛ የሆነ ቀጥተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል“ ብሏል፡፡

ለመኖር ምንም ዓይነት ጥረት ለማድረግ የሚያስችል አቅም ለሌላቸው ሰዎች ይኸ ምን ሊሆን ይችላል፣ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ምንም ዓይነት የሚልሱት የሚቀምሱት ምግብ የላቸውምና?

እኔ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ የድርቅ መኖር ዋና መንስዔ የ”ኤል ዘ-ህወሀት” ነው እላለሁ፡፡

ኤል ዘ-ህወሀት ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጦ ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 ተደረገ በተባለው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ኤል ዘ-ህወሀት መቶ በመቶ አሸነፍኩ በማለት  የፓርላማውን መቀመጫ ወንበሮቸ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አወጀ፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 ኤል ዘ-ህወሀት ተደረገ በተባለው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ 99.6 በመቶውን አሸነፍኩ በማለት የፓርላማ ወንበሮችን ተቆጣጠረ፡፡

ኤል ዘ-ህወሀት የሸፍጥ ምርጫውን በማካሄድ ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስከፊ የሆነውን የምግብ ንጥረ ነገር እጥረትን ለመከላከል ምን ያደረገው ጥረት አለ?

ምንም !

ዘ-ህወሀት ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስከፊ የሆነው የምግብ ንጥረ ነገር እጥረት ያስከተለውን ጉዳት ለመቀነስ ምን ያደረገው ጥረት አለ?

ምንም !

ዘ-ህወሀት የሰራው ነገር አለ ከተባለ ሰብአዊ እርዳታውን በድበቅ ከሀገሪቱ ወደ ውጭ በማውጣት በእራሱ የባንክ ሂሳብ አካውንት ውስጥ እያጨቀ ይገኛል፡፡

ዘ-ህወሀት የሰራው ነገር አለ ከተባለ ከዓመት ወደ ዓመት ለዓለም አቀፍ ምጽዋት እና ልመና  የመለመኛ ሳህኑን መዘርጋት ነው፡፡

ከአፍሪካ ነባር ለማኝ መንግስት ከዚህ የበለጠ ነገር አይጠበቅም፡፡

ዩኤስኤአይዲ/USAID እና ዘ–ህወሀት በኢትዮጵያ በክህደት ጎዳና፣

ዩኤስኤአይዲ/USAID በኢትዮጵያ ውስጥ ተከስቶ ያለውን ረሀብ ጸጥ በማለት በክህደት ሸፍጥ ውስጥ ገብተዋል፡፡

እርስ በእርሳቸው እንኳን ደስ አለህ እየተባባሉ እና እራሳቸው ለእራሳቸው በኢትዮጵያ የክህደት ቃለ መጠይቅ በማድረግ የዓለም አቀፉ ማህበሰብ የእነርሱን ውሸት፣ ተራ ቅጥፈት እና አሀዝ አምኖ እንዲቀበል ይጠብቃሉ፡፡

ዘ-ህወሀት (T-TPLF በሚለው ቃል ውስጥ የመጨረሻዎቹ LF የሚሉት ፊደሎች Lie Factory/የውሸት ፋብሪካ የሚለውን ይወክላሉ) ቢያንስ ባለፉት ስምንት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ መከሰቱን ሲክድ ቆይቷል፡፡

የዘ-ህወሀት መሪዎች በጫካ በነበሩበት ጊዜ ረሀብ በሁለግብ መልኩ በጣም ጠቃሚው ጉዳይ እና የመነጋገሪያ አጀንዳቸው ነበር፡፡ ረሀብን ማጥፋት እና መከላከል የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ማጠናቀቂያ እንደሆነ አድርገው ይቆጥሩት ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ1985 በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በረሀብ ምክንያት እያለቁ በነበረበት ጊዜ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እንዲህ ብሎ ነበር፡

“ሕዝቦች በረሀቡ ካለቁ መዋጋቱ ምንም ዓይነት ዋጋ የለውም፡፡ ይህ በህይወቴ በጣም አሳዛኙ ክስተት ነው፡፡ በርካታ ተስፋየለሽ የሆኑ ጊዚያትን አይቻለሁ፣ ሆኖም ግን ሁሉም ቢሆኑ እንደ አሁኑ ያህል ተስፋየለሽ አልነበሩም፡፡ ምክንያቱም እየተዋጋሁላቸው ያሉት ሕዝቦች በምግብ እጥረት ምክንያት በረሀብ እያለቁነው፡፡ ጠንካራ ሰራተኞች ናቸው፣ ሆኖም ግን  በድጋፍ እጥረት ምክንያት፣ ሳይንሳዊ የግብርና የአስተራረስ ተሞክሮ እጥረት ምክንያት እነዚህ ህዝቦች እየሞቱ ነው፡፡ በእራሳቸው ላይ ምንም ዓይነት የጥፋት ምክንት ሳይኖርባቸው እያለቁ ነው፡፡ አንድ ታጋይ በህይወቱ ሊጋፈጠው የሚችለው ጠንካራው ነገር ይኸ ነው፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

አዎ እውነት ነው የእኛ ቅቤ አንጓጭ የሕዝብ አዛኝ ይህንን ቢል አይደንቅም!

እ.ኤ.አ በ1984-86 መለስ እና ግብረ አበሮቹ ለትግራይ ክልል የተመደበውን በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች የሰብአዊ እርዳታ እየመነተፉ ወደ ውጭ ሀገር በመውሰድ የጦር መሳሪያ መግዣ እና የግል መበልጸጊያ አድርገው ተጠቅመውበታል፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት “ዘ-ህወሀት ለመስረቅ ፈቃድ ያለው ድርጅት“ በሚል ርዕስ ቀደም ሲል ያቀረብኩትን ትችት ልብ ይሏል፡፡ እንግዲህ ለጠንካራ ታጋይ ምንም ዓይነት ጥረት ሳይደረግ የተገኘ ገንዘብ እያልኩ የምጠራው ይህንን ነው፡፡

አምባገነኑ መለስ መለስዊ በስልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጠ ከ17 ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ ነሐሴ 2008 ለታይምስ መጽሔት በሰጠው ቃለ መጠይቅ እንዲህ የሚል ፍልስፍና ያዘለ የሚመስል ዲስኩር በማሰማት እራሱን ከፍ ከፍ አድርጎ ተናግሯል፣ “ረሀብ በኢትዮጵያ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል፣ እንደዚህ ያለ ሁኔታ በሚከሰትበት ጊዜ ጉዳት አያስከትልም ብሎ ማሰብ ደደብነት ነው፡፡ ሆኖም ግን በእኛ እይታ በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት ረሀብ የለም፣ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ ነው፣ ግን ምንም ዓይነት ረሀብ በፍጹም የለም፡፡“

የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የግብርና እና የገጠር ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የነበረው ምትኩ ካሳ አለቃው ያለውን በመከተል እንዲህ በማለት እንደ ገደል ማሚቶ አስተጋብቶ ነበር፣ “በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ረሀብ የለም፣ ቸነፈር የለም…ረሀብ አለ የሚለው መሰረተቢስ አባባል ነው፣ እናም በመሬት ላይ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ በተጻራሪ የቆመ አባባል ነው፡፡ በመረጃ ላይ የተደገፈ አይደለም፡፡ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡“

እ.ኤ.አ በ2011 መለስ ዜናዊ እራሱን ከፍ ከፍ እያደረገ እንዲህ በማለት ድንፋታ አሰምቶ ነበር፣ “በአጭር ጊዜውስጥ ትርፍ አምራች ለመሆን የሚያስችለንን ዘዴ ቀምረናል፣ እናም እ.ኤ.አ በ2015 ምንም ዓይነትየውጭ እርዳታ ሳያስፈልገን እራሳችንን መመገብ እንችላለን፡፡ በሌላ አገላለጽ ረሀብ፣ ቸነፈር፣ ከፍተኛ የሆነ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ ወዘተ ከኢትዮጵያ ለዘላለም ይወገዳሉ“ ነበር ያለው፡፡ ድንቄም መወገድ መጽደቁ ቀረና ባግባብ በኮነነኝ ይላሉ አባቶች ሲተርቱ! እውነት ነው ሞት ቀደመው እንጅ በምግብ እራሳችንን ያስችለን ነበር፡፡ እናም በምግብ እህል እራሳችንን ችለን ምንም ዓይነት የውጭ እርዳታ አያስፈልገንም በማለት በተደሰኮረለት የዲስኩር የዕቅድ ዓመት እ.ኤ.አ በ2015 ሁኔታው ተለውጦ የሚላስ የሚቀመስ የሚታጣበት እና ሰብአዊ እርዳታ እቅራቢ የውጭ ድርጅቶችን እርዱን፣ ምጽዋት አቅርቡልን በማለት የልመና ኮሮጇቸውን ይዘው በመለመን ላይ የሚገኙበት ለመሆን በቅቷል፡፡

እ.ኤ.አ ጥር 2012 ሲኤንኤን ለአምባገነኑ መለስ ዜናዊ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቅርቦለት ነበር፣ “ኢትዮጵያ ከፍተኛ ለሆነ ረሀብ ተዳርጋለች፡፡ የእራስዎ ሕዝብ እየተራበ ባለበት ሁኔታ በሌላ ሀገር ጉዳይ ላይ ወታደራዊ ወጭ ለማውጣት የሚችሉት እንዴት ነው?“ ዜናዊ እንዲህ በማለት ምላሽ ሰጠ፣ “የሰብአዊ እርዳታ ለጋሽ ድርጅቶች እንደሚነግሩህ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ረሀብ የለም፡፡ አስከፊ የሆነ ድርቅ ነውያለው፣ ሆኖም ግን ህዝባችንን በመመገብ ላይ እንገኛለን…“

እ.ኤ.አ ሰኔ 2012 ዩኤስኤአይዲ እንዲህ የሚል ዘገባ አቀረበ፡

“በአንዳንድ ክልል አካባቢዎች ድርቁ ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማያውቅ እና በአፍሪካ ቀንድ 13.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችን ለአስከፊ ጉዳት ይዳረግ እንደነበር ይታሰባል፡፡ ይፋ መግለጫ ከመስጠቱ ከአንድ ወር በፊት የዩኤስኤአይዲ/USAID የረሀብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ኔትወርክ (ረቅማስኔ) /Famine Early Warning Systems Network (FEWS NET) እንዲህ በማለት አስጠንቅቆ ነበር፡ ‘በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ በጣም አስከፊ የሆነ አስቸኳይ የምግብ ዋስትና እጦት ነው፡፡‘“

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 የዘ-ህወሀት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሆነው ደመቀ መኮንን አንዲህ አለ፣ “የውጭ መገናኛ ብዙሀን ልዩ ፍላጎት እና ድብቅ ዓላማ ካላቸው አካሎች ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝ ግልጽ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ረሀብ የሚባል ነገር የለም፡፡“

እ.ኤ.አ ሚያዝ 11/2016 ዩኤስኤአይዲ/USAID እንዲህ የሚል ዘገባ አቀረበ፣ “እ.ኤ.አ በ2016 ለኢትዮጵያ ለምግብ እርዳታ የሚያስፈልገው የተረጅ ህዝብ ቁጥር 10.2 ሚሊዮን እንደሚሆን ተተንብዮአል፡፡“

ያ 10.2 ሚሊዮን ተረጅ ህዝብ የሚበላው ምንም ዓይነት ነገር የለውም ማለት ነውን፣ እናም ይህ ከሆነ የእርዳታ አቅርቦቱ በወቅቱ ካልተገኘ ሁሉም በረሀብ ያልቃሉ ማለት ነውን?!

ይህ ነው እንግዲህ የዘ-ህወሀት-ዩኤስኤአይዲ/USAID አጋርነት በኢትዮጵያ ላይ እያካሄዱት ያለው ክህደት፡፡ ምንም ዓይነት ረሀብ የለም! ምንም ዓይነት ቸነፈር የለም! ምንም የሌለ ነገር የለም፡፡ ኤል ኒኖ ብቻ የድርቁ መንስኤ ነው፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በ1991 በፍጹማዊ የስልጣን ኮርቻው ላይ ተደላድሎ መቀመጡን ካረጋገጠ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጠውን የፕሬስ መግለጫ ምንጊዜም ቢሆን አልረሳውም፡፡ አምባገነኑ መለስ እንዲህ ነበር ያለው፣ “ኢትዮጵያውያን በቀን ሶስት ጊዜ መመገብ የሚችሉ ከሆነ የእኔ መንግስት ስኬት የሚለካው በዚያ ነው፡፡“

በአሁኑ ጊዜ ከ10 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በረሀብ በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ  ጊዜ የዘ-ህወሀት አለቆች እና ጋሻጃግሬዎች የተቀማጠለ የድሎት ኑሮ በመኖር ላይ ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የዘ-ህወሀት መሪዎች በመስራቹ እና በባለራዕይው መሪ ታስቦ የነበረው   ስኬታማ ሆነናል ብለው ያስባሉን?

በአሁኑ ጊዜ የዘ-ህወሀት መሪዎች አሁን በህይወት ስለሌለው ባለራዕይው መሪ በቀን ሶስት ጊዜ ኢትዮጵያውያንን ስለመመገብ ወይም ደግሞ በሚሊዮኖች ስለሚቆጠሩት እና በረሀብ ስለሚሞቱት ኢትዮጵያውን ምንም የሚያስቡት ነገር የለም!

ይኸ ተጨባጭ እውነታ ነው!

ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ ረሀብ በኢትዮጵያ ውስጥ አስከፊ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ ከዓለም ላይ የተደበቁ ሆኖም ግን ቁጥራቸው ያልተነገሩ እና በሞት እየተነጠቁ ያሉ ዜጎች አሉ፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 12/2016 ብሉምበርግ ኒውስ የተባበሩት መንግስታትን ምንጭ ዋቢ አድርጎ በመጥቀስ እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፣ “በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተለዩ እና በድርቅ የተጎዱ የአስቸኳይ ጊዜ የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወረዳዎች በድርቁ አስከፊ እየሆነ መምጣት ምክንያት በ18 በመቶ በመጨመር ከታህሳስእስከ መጋቢት ባለው ጊዜ ውስጥ ቁጥራቸው 216 ደርሷል፡፡

በተከታታይ በመከኑት የዝናብ ወቅቶች ምክንያት ባለፈው ዓመት በውቅያኖሶች መሞቅ በተከሰተው ኤል ኒኖ ውጤት መሰረት ከመቶ ሚሊዮን ከሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ አንድ አምስተኛው የምግብ እህል እርዳታ ይፈልጋል፡፡ በጠቅላላው 443 ወረዳዎች ቢያንስ የተወሰነ ችግር ያለባቸው ተብለው የተመደቡ ሲሆን ይህም ቁጥር በታህሳስ ወር ከነበረው ከ429 ተነስቶ ከዚህ ለመድረስ መቻሉን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታ ጽ/ቤት ማክሰኞ ባሰራጨው የኢሜል መጽሔቱ ግልጽ አድርጓል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 219 ወረዳዎች ውስጥ “በጣም አስከፊ የምግብ ዋስትና እጦት” የተከሰተባቸው እናከፍተኛ የሆነ የሞት መጠንን የሚያካትቱ፣ ከፍተኛ የሆነ እና እየጨመረ የመጣ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ ሊመለስ የማይችል እና የወደመ የኑሮ ዋስትና ቋሚ ሀብቶች ተብለው ተመድበዋል፡፡ በኢትዮጵያ መንግስት ምደባ መሰረት ኢትዮጵያ በጠቅላላው 800 አካባቢዎችን ወይም ወረዳዎችን ትይዛለች፡፡“ አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

በጣም አስከፊ የምግብ ዋስትና እጦት የሚለው እንደምታውቁት ሌላ ምንም ሳይሆን በአጭሩ ለእኔ ረሀብማለት ነው፡፡

ከአስከፊ የምግብ ዋስትና እጦት በላይ ሌላ ምን የከፋ ነገር ሊኖር ይችላል?

በጣም፣ በጣም፣ በጣም፣ በጣም… አስከፈፊ የምግብ ዋስትና እጦት?

አስከፊ የሆነ የሆነ የምግብ ዋስትና እጦት መኖር ከፍተኛ ሞትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ረሀብን ለመጥራት ቆንጆው ስያሜ እንግዲህ ይህ ነው (ወይስ ደግሞ ድርቅ ነው?) በርካታ ኢትዮጵያውያንን የሚጨርሰው?

ጆርጅ ኦርዌል በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “የፖለቲካ ቋንቋ የተፈጠረው ውሸትን በመፈብረክ እውነት ለማስመሰል እና የተከበረውን ነገር ለመግደል እና ንጹህ ጋስ የሆነውን ነፋስ የጠጣርነት ቅርጽ ያለው  አስመስሎ ለማቅረብ ነው፡፡“

ዩኤስኤአይዲ/USAID፣ ዘ-ህወሀት እና የተባበሩት መንግስታት እ.ኤ.አ በ2016 በተከሰተው ረሀብ 10 ሚሊዮን ኢትዮጵያውን ከሰዓት በኋላ ሊቀርብ የሚችለውን መክሰሳቸውን ብቻ እንዳጡ አድርገው የቃላት ትርጉም ስንጠቃ የጅምናስቲክ ጨዋታቸው ላይ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡

ለምንድን ነው ዩኤስኤአይዲ/USAID፣ የተባበሩት መንግስታት እና ሌሎችም በኢትዮጵያ ላይ ስለሚከሰተው ረሀብ እስከጥርሳቸው ድረስ የሚዋሹት?

እኮ ለምን?

እ.ኤ.አ ግንቦት 2012 “የአፍሪካ የረሀብ ጨዋታዎች በካምፕ ዴቪድ የሽርሽር ቦታ“ በሚል ርዕስ አንድ ትችት ጽፌ ነበር፡፡ በዚያ ትችቴ ላይ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እና የእርሱ ዓለም አቀፍ ደጋፊዎች እና ዓለም አቀፍ የደህነት ወትዋች አቃጣሪዎች በኢትዮጵያ ሕዝብ ረሀብ እና ቸነፈር ላይ የሕዝብ ግንኙነት ስራ  እና የቃላት ትርጉም ስንጠቃ እየተጫወቱ በመሆናቸው የተሰማኝን ቅሬታ ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡

አሁን እውነታውን ወገግ ብሎ አገኘሁት!

ከ10 – 11 በመቶ አማካይ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግቢያለሁ እያለ ላለፉት አስር ዓመታት በሸፍጥ አባዜ ተወጥሮ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያራግብ የቆየ አገዛዝ በሀገሪቱ ውስጥ አስከፊ ረሀብ መኖሩን ማመኑ እጅግ በጣም አሳፋሪ ነገር ው፡፡

ዩኤስኤአይዲ/USAID እና ዓለም አቀፍ አጋሮቻቸው “F“ amine ረ-ሃ-ብ የምትለዋን ቃል መጠቀም ሲጀምሩ የዩኤስ አሜሪካ ኮንግረስ ስለመነሻው እና ውጤቱ መስማት አለበት፡፡ ይህም ማለት ዩኤስኤአይዲ/USAID ለተጠያቂነት ብቁ ሆነ ማለት ነው፡፡

የዓለም አቀፍ ፕሬስ ተደራሽነት እና ተጠያቂነት እንዲኖር መጠየቅ አለበት፣ እናም ሁሉም የገሀነም አሰራር ይወገዳል፡፡

ማርቲን ፕላውት አሁን በቅርብ ጊዜ በኒውስ ሰቴትስማን በወጣው ጽሑፍ እንዲህ በማለት ተሟግተዋል፣ “እ.ኤ.አ. በ1973 – 74 እና በ1984 – 85 ተከስተው በነበሩት የኢትዮጵያ አውዳሚ ረሀቦች በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት የተቀጠፈ ሲሆን ምናልባትም እንደየአግባቡ 200 መቶ ሺ እና 400 መቶ ሺ ሰዎች አልቀዋል፡፡ የመጀመሪያው ረሀብ አጼ ኃይለ ስላሤን ከስልጣናቸው እንዲወገዱ ሲያደርግ ሁለተኛው ረሀብ ደግሞ ለመንግስቱ ኃይለማርም ማርክሲስታዊ አገዛዝ ውድቀት የእራሱን ድርሻ አበርክቷል፡፡“

ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ ያለውን ረሀብ ስፋት እና ጥልቀት የኢትዮጵያ ሕዝብ መርምሮ በሚደርስበት ጊዜ ወያኔም እንዳለፉት የኢትዮጵያ መንግስታት እንደደረሰው ዕጣ ፋንታ እንደሚደርሰው ዘ-ህወሀት ሊያውቀው ይገባል፡፡

ለዚህም ነው “F“ amine ረ-ሃ-ብ የሚለው ቃል በሚሰማበት ጊዜ ለመከላከል ሲሉ ዩኤስኤአይዲ/USAID እና ዘ-ህወሀት በደመ ነብስ ምላሽ እየሰጡ ያሉት፡፡ የዓለም አቀፍ ፕሬስ በሀገሪቱ ውስጥ ስላለው የምግብ ሁኔታ እውነተኛ መረጃ ለማግኘት ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ የዘ-ህወሀት ሎሌዎች እጅግ በጣም በመቆጣት የዓለም አቀፉን ፕሬስ መግለጫ መሰረተቢስ እና የሀገሪቱን ገጽታ ጥላሸት ለመቀባት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ናቸው በማለት ዓለም አቀፉን ፕሬስ በማውገዝ ላይ ይገኛሉ፡፡

የዩኤስኤአይዲ/USAID ቸነፈር/ረሀብ/ድርቅ የትርጉም ጨዋታዎች፣

 ዘ-ህወሀትን ከማንኛውም የሕግ፣ የሞራል እና የፖለቲካ ኃላፊነት ተጠያቂነት ለመከላከል እና ለመጠበቅ ሲል በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ስለመለጣው ድርቅ/ረሀብ ዘገምተኛ የመሆን እና ምንም ዓይነት አፋጣኝ ምላሽ ያለመስጠት ሁኔታ የዩኤስኤአይድ/USAID መልዕክት እና የመነጋገሪያ ነጥቦች በጥንቃቄ የተሰሉ ናቸው፡፡

ዩኤስኤአይድ/USAID እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ስለረሀብ ጉዳይ በግልጽ የመወያየት ጉዳይ ስለሚያስከትለው ውጤት በሚገባ ያውቃሉ፡፡

ሆኖም ግን ዩኤስኤአይድ/USAID ሁለት ቀላል የሆኑ እውነታዎችን ማወቅ ይገባዋል፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) እነርሱ እንደሚያስቡት ሁሉ ኢትዮጵያውያን ደደቦች አይደሉም፡፡ ቀጥ ብላችሁ በመቆም በዘ-ህወሀት አምባገነናዊ አገዛዝ ሕወይታችሁ ዴሞክራሲያዊ ነው በማለት ልትነግሯቸው ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም ግን እንደ ድንጋይ ዝም በማለታቸው እንደ ድድብና የሚቆጠር ነው ብላችሁ ስህተት አትስሩ፡፡ የማሰብ ደረጃቸውን አትሳደቡ፡፡ ረሀብተኛ እና ደኃ መሆን ከድድብና እና ከድንቁርና ጋር እኩል ነው ብላችሁ አትቁጠሩ፡፡ 

2ኛ) ጽጌረዳ በሌላ በማንኛውም ስም ብትጠራ ያው ጣፋጭ የሆነ ሽታዋን አይለውጥም፡፡ ሆኖም ግን ረሀብበሌላ በማናቸውም ስያሜ ቢሰየም (“በጣም አስከፊ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት“፣ “ኤል ኒኖአመጣሽ ድርቅ“፣ ወዘተ የጭቆና አገዛዝ መራራ ፍሬ ውጤት ነው፡፡

የዩኤስኤአይድ/USAID የእርሱን ዘ-ህወሀት አጋሮች ለመከላከል፣ ለመሸፈን እና ለእነርሱ ሲሉ ውሸት ለመዋሸት እና ሌላም የፈለጉትን ነገር ሁሉ ለማድረግ ነጻ ነው፡፡ ኤሚሌ ዞላ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “እውነትን በቀበርካት ቁጥር እና በጣም አርቀህ ወደ መሬት ውስጥ በቀበርካት ቁጥር ትበቅላለች፡፡“

ህይወትን የሚያቆዩ ዘሮች በኢትዮጵያ ውስጥ አይበቅሉም ሆኖም ግን ስለዘ-ህወሀት እና የዩኤስኤአይድ/USAID እንደ አረሞች የሚበቅሉ የጫካ እውነታዎች አሉ፡፡

የዩኤስኤአይድ/USAID ስለመልም አስተዳደር ውድቀት፣ ድረሀብ/ድርቅን በበቂ ሁኔታ አቅዶለማስወገድ ስላልቻለበት ሁኔታ አንድም ነገር (አንድ) መጥቀስ ያለመቻሉ ምን ዓይነት አሳፋሪ ነገርነው? 

የዩኤስኤአይድ/USAID በ50 ዓመታት ድርቅ አንድም ሰው መሞቱን (አንድምም ሰው) መግለጽያለመቻሉ እንዴት ያለ አሳፋሪ ነገር ነው!!!

ዩኤስኤአይድ/USAID ባዶ ፕሮፓጋንዳ እየነዛ የህልም እንጀራ በመመገብ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዳታለለ አድርጎ ያስባል፡፡

“ለተባበሩት መንግስታት እና መንግስታዊ ላልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አጋሮቻችን በእርግጠኝነት ለዚህ ድርቅ ምላሽ በመስጠት ታላቅ እና የጀግንነት ስራን የሰሩ ስለሆነ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡“

ይኸ ድርቅ ያለምንም ጥያቄ አደገኛ ነው፡፡ የግድ ግን አውዳሚ አይደለም፡፡

በአጠቃላይ መልኩ በድርቁ ምክንያት አስከፊ እና አውዳሚ የሆነ ውጤት መከሰቱን ሊያረጋግጥ የሚችል ነገር አላየንም፡፡

ይህንን ድርቅ ለመቋቋም በኢትዮጵያ መንግስት በጣም ግልጽ የሆነ አመራር አይተናል፡፡ አጠቃላይ በሆነ መልኩ ጠንካራ የፖለቲካ ፈቃደኝነት፣ ጠንካራ ቁርጠኝነት ስላለ ይህ ድርቅ አውዳሚ ሊሆን እንደማይችል ማረጋገጫ አይቻለሁ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ከ30 ዓመታት በፊት የሌለን አቅም እና ባለሙያነት ስላለን እ.ኤ.አ በ2016 ድርቁን ማሸነፍ እንችላለን፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከዚህ ቀደም የሌሉን ቴክኒኮች እና ቴክኖሎጂዎች አሉን፡፡ ልዩ የሆኑ የምግብ ውጤቶች አሉን፡፡

ከመንግስት ጎን በመሰለፍ እንሰራለን፡፡ መንግስት በከፍተኛ እርምጃ ወደፊት ተራምዷል፡፡ ስለሆነም በርካታ የተሰሩ ነገሮቸ አሉ፣ በርካታ ስኬታማ የሆነ ነገሮች አሉ፡፡ ሌሎች በስርዓቱ ውስጥ ያሉ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡

የዩኤስኤአይዲ/USAID የውጭ አደጋ ረዳት ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ድርቅ ወደ ሙሉ ሰብአዊቀውስ ከመቀየሩ በፊት እርዳታውን በማቀላጠፍ የሚያግዝ ቡድን አሰማርቷል፡፡ (ሙሉ ሰብአዊ ቀውስ “ረሀብ” ነውን?!

ዩኤስኤአይዲ/USAID ረሀብ የምትለዋን ቃል የማይተቀምባት ለምንድን ነው? እ.ኤ.አ. በ2016 በኢትዮጵያ ድርቁ ወደ ሙሉ ሰብአዊ ቀውስ ሊቀየር ይችላል፡፡

ዩኤስኤአይዲ/USAIDን ከስሸዋለሁ!

በኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅን ለመከላክል እና ለመቋቋም ዩኤስኤአይዲ/USAID እያራመደው ያለው አቀራረብ ምጽዋት እና የበለጠ ምጽዋት መስጠትን ነው፡፡

የህንድ የኢኮኖሚክስ የኖቬል ተሸላሚ የሆኑት አማርትያ ሴን ረሀብን ለማጥፋት ዋናው መንገድ ዴሞክራሲን ተቋማዊ ማድረግ እና የሰብአዊ መብቶችን ጥበቃ ማጠናከር ነው፡ በዓለም ታሪክ ውስጥ በመስራት ላይ ባለ የዴሞክራሲ ስርዓት ውስጥ ምንም ዓይነት ረሀብ ተከስቶ አያውቅም፣ ምክንያቱም ዴሞክራሲያዊ መንግስታት ምርጫን አሸንፈው ስለሚይዙ እና የህዝብን ትችትም ስለሚቀበሉ እንዲሁም ረሀብን እና ሌሎች መቅሰፍቶን ለማጥፋት የሚያበረታቱ ጠንካራ እርምጃዎችን ስለሚወስዱ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ባልሆኑ ሀገሮች ግን በሚከሰተው ረሀብ ላይ የማስጠንቀቂያ ደወል የሚያሰሙትን የተቃዋሚ መሪዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና የሲቪክ ማህበረሰብ ወትዋቾችን በማሰር ረሀብ ድብቅ ሆኖ እንዲቀር ይደረጋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥያለው ሁኔታ በእርግጠኝነት ይኸ ነው!

ባለፈው ሀምሌ ባራክ ኦባማ በአዲስ አበባ ቆሞ ዘ-ህወሀት ዴሞክራሲያዊ መንግስት ነው ብሎ አወጀ፡፡ ሆኖም ግን በመከላከሉ ደረጃ “የሚሰራ” ዴሞክራሲ ነው አላለም፡፡

የማይሰራ ዴሞክራሲ ወሮበላ የዘራፊነት አገዛዝ ነው፡፡ (እንግዲህ ዴሞክራሲን ወደወሮበላነት ዴሞክራሲ ስትቀይረው ወይም ደግሞ ወሮበሎች ዴሞክራሲን ሲጠልፉ የምታገኘው የማይሰራ የወሮበላ አገዛዝ ዴሞክራንሲን ነው፡፡)

ዘ-ህወሀት ወሮበላ የዘራፊ አገዛዝ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ስላለው ረሀብ እውነታ አንዳንድ ጊዜ ታማኝ በሆኑ ዓለም አቀፍ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች ይነገራል፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 የዓለም ባንክ ዋና ኢኮኖኖሚስት የሆኑት ወልፍጋንግ ፌንግለር እንደ የዓለም ባንክ ባለሙያነት ታማኝነትን ባገናዘበ አጋጣሚ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ያለው ረሀብ ከተፈጥሮ እና ከአካባቢያዊ ምክንያቶች የበለጠ በሰው ሰራሽነት እያሻቀበ በመጣው የምግብ ዋጋ ንረት እና በሲቪል ግጭቶች አማካይነት የሚከሰት ነው፡፡ ይህ ቀውስ ሰው ሰራሽ ነው፡፡ ድርቆች ደግመው እና ደጋግመው ይከሰታሉ፣ሆኖም ግን ወደ ረሀብነት እንዲቀየሩ ዋናው መንስኤ መጥፎ ፖሊሲን አውጥቶ ተግባራዊ የማድረጉሁኔታ ነው፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

በሌላ አባባል በኢትዮጵያ ውስጥ የረሀብ ዋናው መንስኤ መጥፎ እና ደካማ አስተዳደር እንጅ ድርቅ፣ ኤል ኒኖ ወይም ኤል ኒና አይደለም፡፡

የኦክስፋም ዓለም አቀፍ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ፔኒ ላውሬንስ ኢትዮጵያን ከጎበኙ በኋላ የሚከተለውን ምልከታ አስቀምጠዋል፡

“ድርቅ ማለት ረሀብ ወይም ፍጹም የሆነ እጦት ማለት አይደለም፡፡ ማህበረሰቦች ለሰብሎች የመስኖ ውኃ የሚኖራቸው ከሆነ፣ የእህል ማጠራቀሚያ ጎተራ እና የዝናብ ውኃን ለመሰብሰብ የሚያስችል ጉድጓድ የሚኖራቸው ከሆነ በእነርሱ ላይ ምንም ዓይነት አደጋ ወደ እነርሱ ቢወረወርም ያለምንም ችግር መኖር ይችላሉ፡፡“

የቢቢሲ ዓለም አቀፍ ዜና አገልግሎት የአፍሪካ አርታኢ/editor የሆኑት ማርቲን ፕላውት በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ቀውስ ከፊል መንስኤው ገበሬዎችን የመንግስት በሆነው መሬት ላይ አስሮ በማስቀመጥ እና የግላቸው መሬት ኖሯቸው ለመሸጥ ለመለወጥ እንዳይችሉ ቀፍድዶ በያዛቸው ፖሊሲ ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ስለሆነም ግልጽ የሆኑት ጥያቄዎች እንዲህ የሚሉ ይሆናሉ፡

1ኛ) ህብረተሰባዊነትን አሽቀንጥሮ የጣለ እና ምናልባትም ለነጻ ገበያ የኢኮኖሚ ስርዓት እራሱን ተገዥ ያደረገ አገዛዝ መሬትን ሙሉ በሙሉ በእራሱ ቁጥጥር ስር የሚያደርገው ለምንድን ነው?

2ኛ) በሀገሪቱ ውስጥ በቂ የሆኑ የምግብ ሰብሎችን ማምረት የሚያስችሉ የመስኖ፣ የእህል ማጠራቀሚያ ጎተራ እና የዝናብ ውኃ መሰብሰቢያ የጉድጓ ስርዓቶች የማይኖሩት ለምንድን ነው?

3ኛ) ስለኢትዮጵያ ዘ-ህወሀት ያለው የምግብ ዋስትና ፖሊሲ ምንድን ነው?

4ኛ) አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በ2015 ኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ አትፈልግም ብሎ ነበር፡፡ ይኸ ነገር የዘ-ህወሀት ፖሊሲ ነውን?

እ.ኤ.አ በ1992 ባቀረቡት ጽሁፍ ፕሮፌሰር ኤድሞንድ ጀ.ክለር እንዲህ በማለት ሞግተው ነበር፡

“ እ.ኤ.አ የ1983 – 86 ተከስቶ የነበረው ታላቅ ረሀብ በደርግ ደካማ ፖሊሲዎች የተባባበሰ ነበር፡፡ የአየር ንብረት ለውጦች በከመሰታቸው ምክንያት፣ በዚያን ጊዜ የነበረው ድርቅ ትልቅ ነበር፡፡ ሆኖም ግን በማንኛውም ረገድ ቢሆን የድርቁ ውጤቶች ውጤታማ በሆኑ የፖሊሲ መሳሪያዎች እና በውጭ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታን በመጠቀም መወገድ ይችሉ ነበር፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያው የደርግ አገዛዝ ለጉዳዩ የበለጠ የፖለቲካ አጀንዳን ለማራመድ ፍላጎት አሳየ፣ ተገቢ ስልቶችን በመንደፍ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ይልቅ አሀዛዊ መረጃዎች እንዳይወጡ መቆጣጠር ጀመረ፡፡“

በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት የበለጠ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ያለው ለፖለቲካ አጀንዳው የመሬት ባለቤትነትን በማረጋገጥ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ስልትን ከመጠቀም ይልቅ  መሬትን በሙሉ በእራሱ ቁጥጥር ስር አድርጎ የመሬት ቅርምትን በመፈጸም እና አሃዛዊ መረጃዎችን በመቆጣጠር ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡

ዩኤስኤአይዲ/USAID በኤል ኒኖ እያሳበበ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ድርቅ ኤል ዘ–ህወሀትንተጠያቂ ከመሆን በፍጹም ሊያድነው አይችልም፡፡ 

ዩኤስኤአይዲ/USAIDን ከስሸዋለሁ! 

ዩኤስኤአይዲ/USAID! የኢትዮጵያ ሕዝቦች በረሀብ ሲሰቃዩ በመመልከት የማሰብ ደረጃቸውን አትዘልፍ፡፡

ዩኤስኤአይዲ/USAID ሁሉንም መምሰል አለበት!

አንድ ነፍሳት ዳኪዬ  ከመሰለ አንዴ ዳክየ  ከጮሕ  እንደ ዳክየ  ከተራመደ  ዳክየ መሆን አለበት!

ድርቅ ረሃብን ከመሰለ፣ አንደ ረሃብ ካንገበገ  አንደ  ረሃብ ከገደለ ረሀብ መሆን አለበት!

የዩኤስኤአይዲ/USAID  ይህን እንደ ሃስብ ምግብ ይውሰደው ፡፡

ለዩኤስኤአይዲ/USAID ሊቃወመው የማይችል አንድ የስመምነት ሃሳብ አቀርብለታለሁ ፡

የዩኤስኤአይዲ/USAID በኢትዮጵያ ውስጥ ረሀብ የለም የሚለውን ውሸት መናገሩን የሚያቆም ከሆነ እኔም የዩኤስኤአይዲ/USAIDን ኤል ኒኖ እና አስከፊ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት የሚለውን ቅጥፈቱን በማጋለጥ መናገሬን አቆማለሁ፡፡

እሺ እንስማማለን ዩኤስኤአይዲ/?!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ሚያዝያ 11 ቀን 2008 ዓ.ም

↧

እኛ የወልቃይት ጠገዴ የጎንደር አማራ ህዝብ የወያኔ ሴራዋን አውቀን ብንታገስም ወደ ግጭት እንድንገባ በማድረግ ህዝባችንን ለመጨረስ ዝግጅት እያደረገች ነው

$
0
0

Wolqite News

ቀን፡ ሚያዝያ 10/2008 ዓ/ም

እኛ የወልቃይት ጠገዴ የጎንደር አማራ ህዝብ የወያኔ ሴራዋን አውቀን ብንታገስም እንኳ በምታደርስብን ስቃይ ወደ ግጭት እንድንገባ በማድረግ ህዝባችንን ለመጨረስ ዝግጅት እያደረገች ነው!!!

በዚህ ሳምንት በወልቃይት ጠገዴ በዳንሻ ከተማ የሚገኙ ሁለት የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች “የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጎንደሬ አማራ ነው” ብላችሗል ተብለው ከትምህርት ገበታቸው ተባረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በትምህርት ቤቱ የሚያስተምር አንድ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ መምህር ገ/ፃድቃን ከተባለ

ትግሬ የኬምስትሪ መምህር ጋር “ወልቃይት ጠገዴ አማራ ነው” ብሎ ስለ ተከራከረው ብቻ ከትግራይ አስተዳደሩ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰበት ይገኛል።

ሌላው አስገራሚ የሆነው ክስተት ደግሞ በትላንት እለት በቃብቲያ በጠቅላላው ደግሞ በዚህ ሳምንት በአዲረመጥ የወልቃይት ህዝብን የክልል ሃላፊዎች ስብሰባ በማካሄድ “መሬት እንስጣችሁ ፤ ተሰብሰቡ”

ሲሏቸው “ይህ የቆማችሁበት ወልቃይት የተባለ መሬትና ህዝብ እናንተ እንደምትሉት የእናንተ የትግራይ ሳይሆን የጎንደር ስለሆነ መሬቱ የኛ የራሳችን የጎንደሬዎቹ ሆኖ ሳለ ከየት ያገኛቹሁት

መሬት ነው የምትሠጡን?” ብለው በጥያቄ ካፋጠጧቸው ብሗላ “ይልቁንስ ልትረዱት የሚገባችሁ እውነት የእናንተ መሬት ከተከዜ ማዶ ያለውን ትግራይ የተባለው መሬት ስለሆነ ተከዜ ማዶ ሂዳችሁ አስተዳድሩ” በማለት ጀግናው ህዝብ በጀግንነት አቋሙን አሳውቋቸዋል።

ይሔን ሃፍረት የተከናነበው የትግራይ መንግስት በብስጭት በዛሬው ቀን በዳንሻ ከተማ ልዩ የሆነ የጅንጀና ስብሰባ ሲያካሂድ ዉሏል። ኒዮሊባራሊዝም የሚባል ፖሊቲካ ለህዝቡ ሲለፈለፍ ውሏል። ህዝቡን “እኛ ትግሬ ነን፤ ኮሚቴው እኛን አይወክልም” ብላችሁ ሰላማዊ ሰልፍ ውጡ። ይህን ካደረጋችሁ የልዩ ልዩ መሰረተ ልማት ተጠቃሚ ትሆናላችሁ በሰላምም ትኖራላችሁ እያሉ በጥብቅ ሲያሳስቡ ውለዋል።

ወያኔ ለድሮ ሰፋሪ ታጋዮቹም ሆነ ለአዲሶቹ ሰፋሪዎቹ ትግሬዎች ቅስቀሳ እያካሄደ መሳሪያ እያደላቸው ነው። የማይታወቁ አዳዲስ ትግሬዎች በየቀኑ በህዝባችን መሃል እየተገኙ ፍርሃትና ዛቻ እያደረሱብን ነው። ሌላው ከዚህ ጋር የተያያዘ በዚህ ሳምንት ያየነው አዲስ ክስተት ደግሞ ከአሁን በፊት አይተናቸው የማናቅ ብዙ አዳዲስ ፖሊሶችም ህዝባችንን እያንገራገሩ ኑሯችንን ምስቅልቅል በማድረግ አገራችንን ጥለን እንድንሰደድ በአይነቱ ልዩ ልዩ የሆነ ጫና እያደረሱብን ነው። ሳንወድ በግድ ህልውናችንን ለማስቀጠል ስንል ወደማይቀረው ጦርነት እንድንገባ በጣም እየገፋፉን ስለሆነ የፍትህ ያለህ እንላለን!!!

እኛ እንደ ህዝብ ወደ ጦርነት መግባት አንፈልግም ጉዳይችን ሁሉ በሰላማዊ መንገድ ህገ- መንግስታችን እንዲፈታልን ነው የምንጠይቀው። የትግራይ መንግስት ግን በህዝባችን ግጭት የተፈጠረ በማስመሰል ወይንም በሚደርስብን ልዩ ልዩ ስቃይ ተነስተን ወደ ግጭት እንድናመራ በማድረግ ሆን ብሎ በህዝባችን ላይ ጦርነት በመክፈት ሊጨርሰን እየተዘጋጀ ነው ያለው። የትግራይ መንግስት እያንዳንዱ በወልቃይት ጠገዴ የሚገኙትን ትግሬዎች የሞት ድግስ በመደገስ “ተጋዳላይ ትግራይን” የሚለውን ዘፈን ከፍቶ በማስጨፈርና በማስታጠቅ ሊያጫርሰን ተዘጋጅቷል። እኛ እንደሆን ወደሗላ አንልም!!! ማንነታችንን ማስከበር ህገ-መንግስታዊ መብታችን ስለሆነ ማንኛውም አይነት መስዋዕት ለመክፈል ዝግጁ ነን። ይህን ስንል ግን የሚዳኘን መንግስትና ህዝብ አለን ብለን ስለምናምን ወደ ጦርነት መግባት አንፍልግም እንላለን እንጂ ፍርሃት እንዳልሆነ ሊረዱት ይገባል። ይገርማችሗል የሚነፍሰው ነፋስ ሁሉ ባሩድ ባሩድ ይሸታል፤ አዝማሚያው ሁሉ ደም ወደ መፋሰስ እየመራው ነው!!! ወንዶቻችንም ይሁን ሴቶቻችን በሰላም ውለው መመለስ እየቻሉ አይደለም፤ ይህ ነገር በቃላት ከምገልጥላችሁ በላይ ሆኖ አሳራችንን እየበላን ነው። እያንዳንዷ ሴኮንድ የአንድ ቀን ያህል እየረዘመብን ስለአማራ ማንነታችን ስንል በልዩ ልዩ የስቃይ ወላፍን እየተገረፍን ነው ያለነው።

ከስብሰባ ውጭ እያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ “እናንተ ፈሪዎች ጀግንነታችሁ ታድያ የት አለ? ወልቃይት ጠገዴ ደፋር ነው ምናምንቴ የምትሉት አጉል ጉራ ነው! እንዲያውም አማራ በጉራ ነው የሚኖረው” በማለት እነርሱ የኛን አማራነት ቢያረጋግጡም ስድባቸውና ጫናቸው ግን ትዕግስታችንን በጣም እየተፈታተነን ነው። እንዲህ በማድረግ ሰላማዊ ጥያቄያችንን በማደፍረስ ወደ ግጭት እንዲያመራ መፈለጋቸውን አውቀን በትዕግስት የሚያደርሱብንን ግፍ ለመቋቃም ብንሞክርም በነውረኛ ውንብድናቸው በሰላም ወጥተን እንዳንገባ በማድረግ ለሰላም ስንል በቁም እስር እንገኛለንና የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ሆይ የአማራ ማንነታችንንና ሰላማችን እንዲከበርልን እርዳታችሁ አይለየን። የትግራይ መንስግስትና ሰፋሪ ካድረዎቿ እያደረሱብን ያለውን ግፍና ሰቀቀን እንዲያቆሙ በፍጥነት አሳስቡልን!!!

በእርግጥ እነዚህ ሰዎች ወገናችን የሆነውን የትግራይን ህዝብ ይወክላሉ በለን አናምንም፤ እምነታችን ይህ ሆኖ ሳለ ግን የትግራይ መንግስት ከአሁን በፊት የደረሰብንን ግፍ ይቅርታ እንደመጠየቅ በእኛ ህዝብና በትግራይ ህዝብ መካከል የትውልድ ደምነት ለመትከል ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። ለትግራይ ህዝብ ማሳሰብ የምንፈልገው ጉዳይ ቢኖረን በክፉም በደጉም ለብዙ ሺ ዘመናት በፍቅር እንዳልኖርን ልጆቻችሁ እየፈፀሙብን ያለውን ግፍ እንዲያቆሙ ምከሩዋቸው አለያም በሰላማዊ ሰልፍ አስረዱዋቸው እንላለን።

ጦርነትን ለማወጅማ እኛው ነበር ማወጅ የነበረብን ነገር ግን እኛ እንደነርሱ እብዶች አይደለንም አርቆ አሳቢዎች ነን። ለውጭ ጠላት ቢሆንማ ኖሮ እንዴት ፈጣን ጀግኖች እንደሆን እነርሱም በደምብ

ያውቃሉ። እኛ ግን እጅግ በጣም ሰላም ወዳዶች ነን። ልጆቻችሁ ምንም ክፉ ቢሆኑም ኢትዮጵያውያን እንደመሆናቸው መጠን ጦርነት በማወጅ ድል የእኛ ብትሆንም እንኳ እንደ ድል የማይቆጥር አስተዋይ ህሊና ስላለን ልጆቻችሁ ሴት አዛውንቱ ሳይቀር ጠብመንጃ ይዘው አፎሙዙ በእኛ ግምባር ላይ እያነጣጠሩ ጦርነታዊ ሰልፍ ቢያደርጉብንም እብደታቸውን በፍጥነት እስኪያቆሙ ይሔው በትዕግስት እንጠብቃለን። በእርግጥ ‘የግዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውምና’ የግዜ ባለቤት የሆነው ግፍን አጥብቆ የሚጠላ አምላክ ከእኛ ጋር እንደሆነ በሙሉ ልባችን እናምናለን። ወያኔና ካድሬዎቿ ማንነታቸውን ተነጥቀው አላዩትም እንጂ የማንነት መነጠቅ ማለት በዚህች ምድር ላይ የሞት ሞት መሆኑ ማን ባስረዳቸው? ሞትኮ ለተገፋና ለተከፋ ህዝብ ድልን እንደሚያቀዳጀው ገና አልተረዱትም። ነገር ግን የተገፋ ህዝብ ሲሞት ጠላቱን ድል እያደረገ ነው። በሞቱ የተገፋ ህዝብ ህያው ሲሆን ጠላት ግን ነገሩ ተገልብጦበት የሞት ሞት ሞት ነው የሚሞተው ከሁሉም በላይ ደግሞ አሟሟቱ የሞት ሞት ሞት የሆነ ሞት ነው።

እንደ ኢትዮጵያውያን ነገሩን ሰፋ አድርገን ስናየው በእኛ እምነት ወገንን ለመግደል በሚደረግ የእርስ በርስ ጦርነት በሁለቱም በኩል ኪሳራ ብቻ የሚያጭድ አካል እንጂ ድል አድራጊ አካል ሊኖር አይችልም የሚል ጽኑ ኢትዮጵያዊ አቋም አለን። ልንታገስ የመረጥነውም ከዚህ አስተሳሰብ አንጻር ነው እንጂ እኛ የወልቃይት አማራ ህዝብ በጦርነት ውስጥ ክር እንደምንበጥስ እያጣጣሉን ያሉት ወያኔና ካድሬዎቿ እንኳ በደምብ ያውቁናሉ። ወያኔዎች ጉዳዩ ወደ ሌላ የማይመለስ ግልፅ እርስ በርስ ጦርነት እየነዱት ነውና አሳፋሪ ሊሆን የሚችለው ድርጊት ከመከሰቱ በፊት አስቸኳይ መፍትሔ ትፈልጉለት ዘንድ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ሆይ እነሆ ፍፁም ኢትዮጵያዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ጉዳያችንን በሰላምዊ መንገድ መፍታት የሚችል የህገ-መንግስት ሰነድ እያለን ለማንነት ሲባል በሰለጠነው አለም ለ21ኛው መ.ከ.ዘ የማይመጥን ዋጋ አገራችን በወንበዴዎቹ ክፉ አሰራርና መንፈስ ምክንያት ከመክፈል ትታደጓት ዘንድ አሁንም ጥሪያችንን ደግመን እናቀርባለን። ግዜ የሚሰጥበት ሁኔታ አይደልም ያለው!!!

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በልዩ ሁኔታ ደግሞ የአማራ ህዝብ አሁንም ቢሆን ከጎናችን እንድትቆሙና የወያኔ ግፍ “ይብቃ!” ትሉልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን። በመላው አለም ያላችሁ ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዉን ሰቆቃችን ለአለም ህዝብ ታሰሙልን ዘንድ በፈጣሪ ስም እንማጸናለን!!!

መይሳው ካሳ ነኝ ከወልቃይት ጠገዴ፤ በጌምድር፤ጎንደር ሚያዝያ 10/2008 ዓ/ም

↧
↧

የጋምቤላው ዕልቂት |ኢትዮጵያዊነት ነው የሞተው! |ከዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ

$
0
0

ከዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ

ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ

ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ

ሰሞኑን በጋምቤላ ክልል በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች አሳዛኝ ጭፍጨፋ ደርሶባቸዋል፡፡ የኮምኒኬሽን ሚንስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ትላንት (እሁድ) ለሮይተርስ የዜና አገልግሎት በሰጡት መግለጫ የሟቾቹ ቁጥር 208 እንደደረሰና 79 ሰዎች እንደቆሰሉ፣ በርካታ ህጻናት ታፍነው እንደተወሰዱ፣ 2000 ገደማ የቀንድና የጋማ ከብቶች እንደተነዱ ተናግረዋል፡፡ አሶሽየትድ ፕረስ እንደገለጸው፣ ከዚህ መግለጫቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ፣ ሚንስትሩ ጥቃቱን የፈጸሙት የደቡብ ሱዳን ሙርሌ አባላት መሆናቸውንና ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው አስታውቀዋል፡፡ ለአልጃዚራም ቅዳሜ እለት፣ “They haven’t crossed the border [yet], but they will if that’s what it takes” ( የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እስካሁን ድንበሩን አልተሻገሩም፤ አስፈላጊ ከሆነ ግን ያደርጉታል)፡፡ ምን ሲሆን ነው ድንበር ማቋረጥ የሚያስፈልገው? በመሰረቱ ሚንስትሩ የሰጡት አስተያየት የኢህአዴግ መንግስት ስለዜጎቹ ያለውን አቋም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ እንጂ አዲስ አይደለም፡፡ ቀደም ብሎ አሸባሪው አይ.ኤስ ዜጎቻችንን እንደከብት ሲያርድ፣ በእሳቸው ቦታ የነበሩት ባለስልጣን፣ አለም ኢትዮጵያዊነታቸውን እየመሰከረ እሳቸው፣‹‹ገና ኢትዮጵያዊ መሆናቸው አልተረጋገጠም›› ብለው ነበር፡፡

Gambela

እኔ ለአቶ ጌታቸው ጥያቄ አለኝ፡፡ ታጣቂዎቹ ከደ.ሱዳን መንግስት ጋር ግኝኙነት የላቸውም የሚለው እኛን የሚያሳስብ ጉዳይ ነው? ይህንን መግለጫ መስጠት የነበረበት የኢትዮጵያ መንግስት ወይስ የደ.ሱዳን? የአካባቢው የአይን ዕማኞች ከታጣቂዎቹ መካከል የደ.ሱዳንን ወታደሮች የደንብ ልብስ የለበሱ እንዳሉበትና እስከ አርፒጂ ከባድ መትረየስ የታጠቁም እንደሆኑ ለተለያዩ የውጭ የዜና አገልግሎቶች ተናግረዋል፡፡ የደ.ሱዳንም እስካሁን ድረስ ስለጉዳዩ መግለጫ እንዳልሰጠ ነው የማውቀው፡፡ ኢህአዴግ ጉዳዩን በመንግስት ደረጃ ላለማየት ለምን እንደፈለገ አይገባኝም፤ ሁለቱ ሀገሮች ጦርነት ቢገጥሙ እንኳን ይህን ያህል ሰው በአንድ ቀን የሚሞት አይመስለኝም፡፡ ኢህአዴግ ደ.ሱዳንንም በለመደ የብሄር-ብሄረሰብ መነጽሩ ካልተመለከታት በስተቀር፣ ይህ ወንጀል የደ.ሱዳንን መንግስትንም ያስጠይቃል፡፡
.
በምን ሚዛን ነው አንድ መንግስት የሚያስተዳድረው ህዝብ እንዲህ አይነት ውንብድና ሲፈጽም፣ ከወንጀሉ ነጻ የሚሆነው? የኢትዮጵያ መንግስት በርግጥ ድንበር አቋርጦ 60 ሰው መግደሉን ይፋ አድርጓል፤ ይህ ግን መፍትሄ አይደለም፡፡ ይህ ጥቃት በአካባቢው በተደጋጋሚ እንደሚፈጸም፣ ይህንን ከቀደሙት የሚለየው ብዙ ወገኖቻችን የተጨፈጨፉበት መሆኑ እንደሆነ የውጭ የዜና አውታሮች እየገለጹ ነው፡፡ እና መንግስታችን ለምን እስካሁን እንደልሰማና እንዳላየ ዝም አለ?
.
ሌላው ጥያቄዬ ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን ነው፤ ባህር ዳር ጣና ፎረም ስብሰባ ላይ እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ አብሮት የተሰበሰበው የሙኒክ ሴኩሪቲ ኮንፍረንስ ሰብሳቢ አንባሳደር ዎልፍ ጋንግ ኢስቺንገር፣ ለረዥም ጊዜ ጀርመንን ያገለገሉና በጡረታ ላይ የሚገኙ ሰው በመሞታቸው ስብሰባውን አቋርጠው ሲሄዱ ተመልክተዋል፤ ለቀብር፡፡ የሁለት መቶ ሰው መሞት ለእርስዎ ስብሰባ ለማቋረጥ በቂ አይደለም? በኦሮምያ አመጽ (በሚዲያ አጣራር ሽብር) ልማቱ ሲደናቀፍ፣ ንብረት ሲወድም ካንዴም ሁለቴ ጋዜጠኛ ሰብስበው መግለጫ ሰጥተዋል፤ የስንት ዜጎቻችን ህይወት ነው ከልማቱ እኩል ዋጋ የሚኖረው? በዚሁ ስብሰባ ላይ ለቀድሞው ጠ.ሚንስትር ክቡር መለስ ዜናዊ የህሊና ጸሎት ተደርጓል፤ እነዚህ ወገኖቻችንስ የህሊና ጸሎት አያሽፈልጋቻም ነበር?

↧

በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ከመላው አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል |ነገ ጠዋት የዪኤስ ኮንግረስ የኢትዮጵያን ጉዳይ ያዳምጣል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ሕወሓት በሚመራው መንግስት የተወሰዱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ነገ ማክሰኞ ጠዋት በዋሽንግተን ዲሲ የአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ ገለጻ እንደሚደረግ ታወቀ:: ይህን ተከትሎ በአሜሪካ እና በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቶም ላንቶስ ሂውማን ራይት ኮሚሽን ባዘጋጀው በዚህ አጭር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደዋሽንግተን ዲሲ እንዳመሩ ታውቋል::

በዚህ አጭር ጉባኤ ላይ በፓናሊስትነት ተገኝተው ገለጻ የሚያደርጉት የኦክላንድ ኢኒስቲትዩት መስራችና ዳይሬክተር አኑራዳ ሚታል; የአልጀዚራ አሜሪካ ጋዜጠኛ ማህመድ አደሞና የአሜሪካው አመነስቲ ኢንተርናሽናል ማኔጂንግ ዳይሬክተር አዶሲ አክዊ ናቸው::

የነገው የኮንግረሱ አጭር ጉባኤ በፊት ዛሬ ማምሻውን እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ ስብሰባ (ፎቶ ከጃዋር መሐመድ)

የነገው የቶም ላንቶስ ሂውማን ራይት ኮሚሽን አጭር ጉባኤ በፊት ዛሬ ማምሻውን እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ ስብሰባ (ፎቶ ከጃዋር መሐመድ)

የነገው የኮንግረሱ አጭር ጉባኤ በፊት ዛሬ ማምሻውን እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ ስብሰባ (ፎቶ ከጃዋር መሐመድ)

የነገው የቶም ላንቶስ ሂውማን ራይት ኮሚሽን አጭር ጉባኤ በፊት ዛሬ ማምሻውን እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ ስብሰባ (ፎቶ ከጃዋር መሐመድ)

ከዘ-ሐበሻ መቀመጫ ሚኒያፖሊስ በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሲያመሩ በኤርፖርት ተገኝተን የተመለከትን ሲሆን ከሌሎች ከ30 የማያንሱ ስቴቶችም እንዲሁ በዚሁ ዝግጅት ላይ ለመታደም እና አጋርነታቸውን ለማሳየት እንዳመሩ ዛሬ ማምሻውን በዋሽንግተን ዲሲ እየተደረገ ባለው ስብሰባ ላይ ተገልጿል::

በዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮ ፖይንት ሆቴል ስለነገው የኮንግረሱ በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለውን የሰ አዊ መብት ጥሰት የሚያዳመጥበት አጭር ጉባኤና ያንን ተከትሎም ስለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ከየ ስቴቱ ለመጡ ኢትዮጵያውያን ገለጻ እየተደረገ ነው:: በተለይም በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ አባላት የተውጣጡ ወገኖች በዚሁ ስብሰባ ላይ በመገኘት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲነጋገሩ አምሽተዋል::

የአሜሪካ ኮንግረስ በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ነገ ማክሰኞ ኤፕሪል 19, 2016 የሚያደምጥበት አጭር ጉባኤ የሚጀመርበት ሰዓት ከጠዋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ መሆኑ ታውቋል:: ከዚያ ቀደም ብሎም በ9 ሰዓት ለጋዜጠኞች ገለጻ ይሰጣል ተብሎ ቀጠሮ ተይዟል:: ይህ አጭር ጉባኤ እንደተጠናቀቀም ከዋሽንግተን ዲሲ ካፒቶል እስከ ኋይት ሃውስ የሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ይኖራል ተብሏል:: ሰላማዊ ሰልፉም ከቀኑ በ1:00 ሰዓት እንደሚደረግ የተያዘው መርሃ ግብር ያስረዳል::

ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን ተከታትላ ለማቅረብ ትሞክራለች::

↧

Health: ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ ምን ማረጋገጫ አለህ? | 10 መላዎችን ና ተማር

$
0
0

ይህ ጽሁፍ በዘሐበሻ ጋዜጣ ላይም ታትሞ ወጥቱዋል

የቅርብ ጊዜ የስነ ልቦና ጥናታዊ ሪፖርቶች… ሴት ልጅ ለአንተ ልዩ ፍቅርና መውደድ እንዳላትና እንደሌላት አዕምሮዋን በአካላዊ እንቅስቃሴዎቿ በኩል በቀላሉ እንድታነብ ያስችሉሃል!!

አካላዊ እንቅስቃሴዎች ዋነኛዎቹ የመግባቢያ መንገዶች ናቸው፡፡ እነዚህ እንቅስቃሴዎች ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴና ዝግ አካላዊ እንቅስቃሴ ይባላሉ፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴዎች በራሳቸው ቋንቋ በመሆን ከንግግርም በላይ በሆነ መልኩ መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ እንዲህ አይነት ተግባቦት በአብዛኛው በተቃራ ፆታ ግንኙነት ውስጥ በተለይም በሴቶች ላይ ይስተዋላሉ፡፡
how do u know
ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴ

አንድ ጊዜ ከሴት ጋር አይን ለአይን ከተገጣጠምክ ፊቷን ካዞረች በኋላ ያላትንም እንቅስቃሴዎች አስተውል፡፡ አይናች በመጋጨቱ አፍረት ወይም መጨናነቅ ነገር ከታየበት ተመችተሃታል ወይም ወዳሃለች ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ፀጉሯን እንደማፍተልተል፣ ልብሷን ወይም ጌጣጌጧን ማስተካከል ወይም ደግሞ እጇ ላይ ባለው ነገር መጫወት ከጀመረች እነዚህ ግልፅ የሆኑ ማረጋገጫዎችህ ናቸው፡፡

– ውስጥ እጇን አንብብላት፡- በአጋጣሚዎች እና አንድ ላይ በምትሆኑባቸው ሁኔታዎች ውስጥ እጇን ብትመለከት እሷም አሳልፋ ውስጥ እጇንና የእጇን አንጓ እንድትነካ ከፈቀደችልህ ሌላው ያንተ እሷን የመመቸት የአዕምሮ ፍቃድ ማሳያ አንዱ መንገድ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ ‹‹ከፈለከኝ ያንተው ነኝ›› እንደማለት ነው፡፡
– ማጎንበስ፡- በምታጎነብስበት ጊዜ ትከሻዋን ወደ አንተ በመስበቅ ካጎነበሰች ዕድል በእጅህ ገብታለች ማለት ነው፡፡

– እግሮቿን ከፍታ በምትቀመጥባቸው አጋጣሚዎች ካሉ አንተ ጋር በመሆኗ ምቾት ተሰምቷታል ማለት ነው፡፡
– አንድ ሴት አንድን ሰው በምታይበት ጊዜ የአይን ብሌኗ ከሰፋ ያንን ሰው እንደምትወደው በተቃራኒው ደግሞ የአይን ብሌኗን ካጠበበች ለዛ ሰው ጥሩ ስሜት እንደሌላት አንድ መገለጫ ነው፡፡ አይን ለአይን በምትጋጩበት ጊዜ ፈገግታን ከቸረችህ ወደ እሷ ሂድና አነጋግራት፡፡ ሌላው እንደ መልካም ነገር መገለጫ የሚወሰደው አንተ በምታወራበት ጊዜ ለረባ ባልረባው ፈገግ የምትል ወይም ሳቅ የምታበዛ ከሆነ በእርግጠኝነት በደንብ ተመችተሃታል ይሄ ደግሞ የበለጠ የተሻለ ነው፡፡
– በምታወሩበት ጊዜ ሁሉ በተለይ ደግሞ እሷ ስታወራ አንተን በተለያዩ አጋጣሚዎች የምትነካህ ከሆነ መልካም ነገር አለ ማለት ነው፡፡ አይኖቻችሁ በሚጋጠሙበት ጊዜም ምቾት የማይሰጥ ቢሆን እንኳን እንደተፋጠጣችሁ ልትቆዩ ትችላላችሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ላይ መርሳት የሌለብህ ነገር ቢኖር ፊትህን ከማዞርህ በፊት ፈገግ ማለትን ነው፡፡

ይህ ሁኔታ ታዲያ የአንተ እሷን መውደድና መልካም ሰውነት ያሳያል፡፡ ከዚህ በመቀጠልም በአንዳንድ አጋጣሚዎች እየሰረቀቸፍ ስታይህ ልታጋጥምህ ትችላለች፡፡ ከሁለተኛውና ከሶስተኛው መገጣጠም በኋላ እንድታናግራት መፈለጓን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡
እንደ መልካም ተጫዋችነትህ የጨዋታውን ህግ በማክበር የፈለገችውን ነገር ማሟላት ግድ ይልሃል፡፡
መሽከርከር፡- አንድ ሴት ፀጉሯን አየር ላይ ወርውራ ወዲያው ዞራ ካየችህ አንተ እንድታያት ለማድረግ እየጣረች መሆኑን ማመን ትችላለህ፡፡
ዝግ አካላዊ እንቅስቃሴዎች

በማንኛውም ሁኔታ ስትመለከታት አይኗን ውስጡን የምታሽከረክረው ከሆነ በአንተ አቀራረብ ማፈሯንና እንዲሁም በአንተ ደስተኛ አለመሆኗን ለሰዎች ለማሳየት እየጣረች መሆኑን ማወቅ አለብህ፡፡ ይህ ነገር ከተፈጠረ እሷን የማግኘት እድልህ ትንሽ በመሆኑ ማድረግ ያለብህ ፊትህን አዙሮ መሄድ ነው፡፡

– በምታወሩበት ጊዜ እጇን ካጣመረች መጨናነቋን ወይም በሁኔታው ምቾት እንዳልተሰማትአመላካች በመሆኑ እስትራቴጂህን ወይም ስልትህን በፍጥነት መቀየር ይኖርብሃል፡፡ ሌላው ከዚሁ ከማጣመር ጎን የሚያያዘው የእግር ማጣመር ነው፡፡ እግር ማጣመር ልክ እጅን የማታመር ያህል መጥፎ ሲሆን ይህን አጋጣሚ የበለጠ መጥፎ የሚያደርገው ደግሞ አንድ ጊዜ እግሯን ካጣመረች እጇንም የማጣመር ሁኔታ ከፍተኛ መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና እግሯን አጣምራም ቢሆን ጉልበቶቿ ወደ አንተ ከዞሩ ትንሽ ከመጨነቋ ውጪ ከአንተ ላይ ፍላጎት እንዳላት ያመላክታል፡፡ ተቃራኒው ሆኖ ጉልበቷ በሌላ አቅጣጫ ከዞረ ግን ችግር ውስጥ ነህ ማለት ነው፡፡

ወደኋላ መሸሽ ወይም መለጠጥ፡- ወንበር ላይ ከአንተ ራቅ ብላ ወይም ተለጥጣ የምትቀመጥ ከመሆን በደንብ የሚስተዋል አንተን ያለመሻቷ መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ የእኔ ምክር የሚሆነው የዚህ አይነት አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በምታይበት አጋጣሚ ጨዋታውን ጥሎ መውጣት ብቻ ነው መፍትሄ የሚሆነው በእንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሴቷን የራሳቸው ማድረግ የሚችሉት ልምዱ ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡

የአካላዊ እንቅስቃሴ ማታለያዎች

አንድ ሴት አንተን እየተከታተለችህ መሆኑንና ያለመሆኑን ለማወቅ አንድ የሚያስቅና የሚሰራ ማታለያ ልንገርህ፡፡ እሷ አንተን በምታይበት ሁኔታ ላይ ሆነህ ሰዓትህን እያየህ በዝግታ ከ1-3 ቁጠርና ቀና ብለህ እያት፡፡ እሷም ሰዓቷን እያየች ከሆነ አንተን ስታይህ እንደነበር እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ የሆነ አንተን የሚወድ ሰው ባህሪ ነው፡፡ ልክ አንተ ሰዓትህን ማየት ስትጀምር እሷም ምን እየጠበክ እንደሆነ በማሰብ ሰዓቷን ታያለች፡፡
ተጨማሪ የአካላዊ እንቅስቃሴ መረጃዎች

1. ፀጉር ማፍተልተል

አብዛኛውን ጊዜ ፀጉሯን የምታስተካክል ወይም የምታፍተለትል ሴት የወንዶችን አይን ለመማረክ የምትሞክረው ናት፡፡ ፀጉር ማፍተልተሏንም ሆነ መነካካቷን በደቂቃ ውስጥ ሶስት ጊዜ የምታደርገው ከሆነ መያዝም ሆነ መታየትን የምትፈልግ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ሌላው ደግሞ ፀጉሯንየምትነካበት መንገድም የራሱ የሆነ መልዕክት እንዳለው መዘንጋት የለብህም፡፡ ይህም ፀጉሯን በቀስታ የምትነካካ ከሆነ የፍቅር ጥበብ እንዳላት ማወቅ የምትችል ሲሆን ከፈጠነች ደግሞ ማፈሯንና ትዕግስት አልባ መሆኗን ማየት ትችላለህ፡፡

2. የብርጭቆ ጠርዝ ላይ እጅን ማሽከርከር

በሲግመንድ ፎርይድ ቲዎሪ መሰረት ይህ ምልክት ለወሲብ የመጋበዝ ያህል ነው፡፡ ይህ አባባል ታዲያ በብዙ ሴቶች ተደግፏል፡፡ ይህን ጊዜ ታዲያ የጣቶቿን እንቅስቃሴ ልብ ማለት አለብህ፡፡ በዝግታ ጣቶቿን የምታሽከረክር ወይም የምታንቀሳቅስ ከሆነ ጥልቅ የሆነ እርጋታን፣ እራስ መቆጣጠርንና ጥበቃን አመላካች ስለሆነ ከጎኗ ልትቀመጥ ትችላለህ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ በጥፍሯ ብርጭቆውን መምታት ከጀመረች ለነገሮች ትዕግስት ማጣቷንና መቸኮልን ወይም በሌላ መልኩ በወንድ ጓደኛዋ መናደዷን አመላካች ነው፡፡

3. በክንዷ ስትደገፍ

አሪስቶትል እንዳለው ከሆነ የሴት እጅ ብዙ ነገር ያወራል፡፡ በአካል እንቅስቃሴ ላይ ጥናት አድራጊዎች ደግሞ ሴቶች በእንቅስቃሴያቸው የበለጠ ነገሮችን እንደሚገልፁ ያብራራሉ፡፡ በክንዷ ደገፍ ብላ እጇን አገጯ ስር በማስቀመጥ አይኗ በሀሳብ ከዋለለ ተመስጣብኛለች ብለህ በማሰብ እንዳትሳሳት እንደውም በዛ ሰዓት ላይ እራሷን በመጠየቅ ላይ ስለምትገኝ ትንሽ ታገሳት፡፡ እሷም በዛ ሰዓት እያሰበች ከምትሆናቸው ጥያቄዎች አንዱ ‹‹ለዚህ ሰው እገባዋለሁ?›› ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሴቶች ብዙ ጊዜ ለጥያቄዎቻቸው መልስ የሚፈልጉት በዚህ መልኩ ስለሆነ ነው፡፡ መልሱ ምን እንደሆነ አንተ ታውቀዋለህ፡፡ ስለዚህ በተሳካ ሁኔታ እረጋ በማለትና በቀልድ በማዋዛት ውሳኔዋን ልታስቀይራት ትችላለህ፡፡

4. እጇን በማጣመር ተደግፋ ስትቀመጥ

ይህ አጋጣሚ በጭፈራ ቤትም ሆነ በየትኛውም ቦታ ሴት በማደን ላይ ከሆንክና ካጋጠመህ ዕድለኛ አይደለህም ማለት ነው፡፡ በዚህ አይነት አጋጣሚ ያለች ሴት ሁኔታህ አልተመቻትም ወይም አልተማመነችብህም ማለት ነው፡፡ ይህ ሲሆን ታዲያ የተዘጋጀህበትም ቀልድም ሆነ ፈርጣማ ሰውነትህ ትርጉም ስለሌላቸው ባትለፋ ይሻላል፡፡ አይ ካልክ ደግሞ ቀለል ያለ የወሬ መጀመሪያ መንገድ ብትፈልግ ያዋጣሃል፡፡

5. ከንፈሯን ስታረጥብ

አንድ ሴት ከአንተ ጋር እያወራች በተደጋጋሚ ከንፈሯን የምታረጥብ ከሆነ ለፍቅር ያላትን ተነሳሽነት ይገልፃል፡፡ የስነ ባህል ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ሴቶች እንደዚህ አይነት ምልክት የሚሰጡት ከንፈራቸው ላይ ሌላ ነገር እንዲቀመጥ ሲፈልጉ ነው፡፡ ምን ሊፈልጉ እንደሚችሉ መቼም ላንተ መንገር የለብኝም፡፡

6. ሽፋሽፍቶቿን የምትነካካ

ሽፋሽፍቶቿን የምትነካካ ከሆነ ነፃነት ያላት ሴት መሆኗን መናገር ይቻላል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ውስጥ መቀለድም ሆነ በትልቁ መሳቅ ላይጠበቅብህ ይችላል፡፡ ተነሳሽነቱን እሷ መውሰዷ ካልደበረህ በሁኔታዎቹ አብራችሁ ልትዝናኑ ትችላላችሁ፡፡
7. እግር ማወዛወዝ

እግር ማወዛወዝም ሆነ በፍጥነት ማጣጠፍ ሴቷ ለወሲብ ያላትን ተነሳሽነት ያሳያል፡፡ ይህን አጋጣሚ ደግሞ የበለጠ የሚያበረታታው እግሯን በማንቀሳቀስ ላይ እያለች ሳታስበው የምትከፍት ከሆነ ነው፡፡ በሲግመንድ ፎርይድ ክላሲካል ቲዮሪ መሰረት ይህ አጋጣሚ ለወሲብም ክፍት መሆኗን ጠቋሚ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሳይነሳ የማይታለፈው የምታደርገው የጫማ አይነት ነው፡፡ የጫማው አይነት ለማውለቅ የበለጠ ቀለል ያለ ከሆነ ለነገሮች ያላትም ተነሳሽነት ቀላል መሆኑን የበለጠ አመላካች ነው፡፡ ለዚህ እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው በቤዚክ ኢንስትኒክት /Basic Instinct/ ፊልም ላይ የሻሮን ስቶን እግር አከፋፈት ነው፡፡

8. የጣቶች አይነት

አንድ ሴት ለእጇ ያላት አመለካከት የበለጠ ነገሮችንገላጭ ሲሆን በደንብ የተሰሩ ረጃጅም ጣቶች በጥንቃቄ የተቀለሙ ጥፍሮች መልካም የሆኑ አነቃቂ ነገሮች ናቸው፡፡ ይሁንና ሴቷ እጆቿን የምታንቀሳቅስበት መንገድ የበለጠ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባው ነው፡፡ ለረጅም ሰዓት እጆቿ ላይ በመፍጠጥ ከቆየች መናደዷን መረዳት ትችላለህ /ምናልባት ባንተ?/ ጠረጴዛውንም በጥፍሮቿ የምትመታ ከሆነ ተመሳሳይ መልዕክት ስለያዘ ብታስብበት ይሻላል፡፡

9. ከንፈሯን ከበላች

በመሳሳም ወቅት ከንፈርህን ከነከሰችህ ፍፁም አታቋርጣት፡፡ ምንም መጥፎ የሆነ ነገረ የለም፡፡ ግን እሷ በራሷ የራሷን የምትነክስ ከሆነ ለመጨናነቋ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ለምን? ለሚለው መልስ ምናልባት በጥያቄ አይን አፍጥጠህባት ይሆን?

10. ነፍሷን አዳምጠው

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ መደበኛ ወንድና ሴት ግንኙነት ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች ሲሆኑ በወሲብ ላይ ጤናማ የሆነ መልዕክት ያላቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህን መልዕክቶች አንብቦ መተርጎምና በእንቅስቃሴው ውስጥ የራስህን ድርሻ መውሰድ ያንተ ፋንታ ነው፡፡ ሌላው ግን በደንብ እሷን መከታተልና ነፍስያዋ ማዳመጥ ዋናው ነገር ነው፡፡ አንድን ሴት አይተህ ከአንተ ምን እንደምትፈልግ ወሲብ፣ ፍቅር ወይስ ጥልቅ ቅርርብ የሚለውን ነገር ለማወቅ እነዚህን ከታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ማስተዋልና ነፍሷን ማወቅ ትችላለህ፡፡

ጮክ ብላ የምትስቅ ከሆነ፣ ከንፈሯን ካረጠበች፣ በጡቷ ወይም በዳሌዋ ከገፋችህ፣ በጥልቅ ካዳመጠችህ፣ በኩራት ከተራመደች፣ ዳሌዋን ካማታች፣ የአይን አሰባበሯ፣ እግሯን አጣምራ ወደኋላ ከገፋችው፣ ፊቷን ከሸፈነች፣ በጣቶቿ ፀጉሯን ካበጠረች፣ የማይነኩ የሰውነት ክፍሎችህ ውስጥ እጆቿን ከሰደደች፣ እስቶኪንጓን ካስተካከለች ወይም በሹራቧ ቁልፍ ስትጫወት፣ በጣም ከዘነጠች ከተኳኳለችና ሽቶ ከተጋነነ፣ በጆሮህ በተደጋጋሚ በመምጣት የምታንሾካሹክ ከሆነ ወይም ደግሞ ፍቅራዊ የሆነ ሌላ መንገድ ከተጠቀመች፣ በጥልቀት ካፈጠጠችብህ፣ እንዲሁም በአይኗ መዝናህ ካንተጋር የበለጠ ሰዓት ለማሳለፍ ከፈለገች በነገሮች ላይ እርግጠና ልትሆንና የራስህን ውሳኔና እንቅስቃሴ ልታሳልፍ ትችላለህ፡፡

↧

በትናንትናዉ እለት የደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ከፍተኛ አመራሮች ተወያይተዋል!!

$
0
0

New-Picture-1 ዉይይቱ እጅግ የሱዳናዊያን ብቻ ነበር የሚመስለዉ ያሉት ዉስጥ አዋቂ መረጃችን…. ተቆርቋሪነታቸዉ ለሱዳናዊያን የሙርሲ ብሔር ወንጀለኞች የሆኑ ሁለት ወታደራዊ አመራሮች በተለየ መልኩ በድንበር ማስጠበቁ እና የድንበር ማካለሉ ስራን አስረግጠዉ አስቀምጠዋል

” እንደዚህ ያሉ የብሔር ግጭቶች በሰሜኑ የሱዳን ድንበርና ኢትዮጵያ መካከልም ይፈጠራል ያሉት የኛዎቹ የመከላከያ ጀኔራል ጉዶች ድንበር እስኪካለል ድረስ የሰሜን ሱዳናና የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አብረዉ በጥምረት እየሰሩ እንደሆነና የደቡብ ሱዳኑም ያንኑ እንዲያደርግ ሐሳብ አቅርበዋል”

የጋምቤላ ወገኖቻችንን ከ10 ቀበሌዎች በላይ ዘልቀዉ በመግባት የገደሉ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ወይም ወንጀለኞቹ በሕግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ እንዲሁም ታፍነዉ በተወሰዱት 103 ሕጻናት ዙሪያ እና የደቡብ ሱዳኑ መንግስት ካሳ እንዲከፍል በመጠየቅ በኩል ያልተሳተፈዉ የወያኔ መንግስት ነገሩን ሆን ብሎ እንዲፈጸም ያደረገ መሆኑን ከስብሰባዉ መንፈስ ለመረዳት ተችሏል።

በመጀመሪያ ደረጃ ጋንቤላን በፌደራል መንግስት እጠቀልላለዉ ያለዉ ህወሃት የክልሉን መከላከያ ሰራዊት በመበረዝ ከቦርደር ላይ እንዲነሱ በማድረግና በምትካቸዉ ምንም አይነት ሰራዊት ሳያመጣ መሰንበቱ! እንዲሁም በሁለቱ ብሔሮች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት አዲስ እንዳልሆነና በማንኛዉም ወቅት እንዲህ ያለ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል መረጃ እያለዉ ጉዳዩን በቸልተኝነት ያለፈዉ የድንበር ማካለሉን ጉዳይ ከጋምበላ ወደ ጎንደር ለመዉሰድ የታለመ ሳይሆን እንዳልቀረ ተንታኞች እየገለጹ ነዉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሙርሌ ብሔረሰብ ታጣቂ የተባሉት ወታደራዊ አቋም ያላቸዉና ልዩ ስልጠና የወሰዱ የደቡብ ሱዳን ወታደርዊ ዩኒፎርም እንዲሁም አንዳንዶቹ የኢትዮጵያን መከላከያ የደንብ ልብስ የለበሱ ሲሆኑ ግድያዉን ከፈጸሙ በኃላ የኢትዮጵያ መከላከያ ፈጽሞ ያለመኖሩን የተገነዘቡት የጋንቤላ ህዝቦች በመተባበር የሙርሲ ብሔር የተባሉትን ነፍሰ ገዳዮች በማሳደድ የመልሶ ማጥቃት እንደፈጸሙ ምንጫችን አረጋግጠዋል።    ፎቶ Ethnic Murle gunmen

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

↧
↧

የጋምቤላው ዕልቂት|የደቡብ ሱዳን እና የኢትዮጵያ ወታደራዊ አመራሮች መወያየታቸው ተሰማ

$
0
0
 Ethnic Murle gunmen

Ethnic Murle gunmen

ከልዑል ዓለሜ

በትናንትናዉ እለት የደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ከፍተኛ አመራሮች መወያየታቸው ተሰማ:: ዉይይቱ እጅግ የሱዳናዊያን ብቻ ነበር የሚመስለዉ ያሉት ዉስጥ አዋቂ መረጃችን…. ተቆርቋሪነታቸዉ ለሱዳናዊያን የሙርሲ ብሔር ወንጀለኞች የሆኑ ሁለት ወታደራዊ አመራሮች በተለየ መልኩ በድንበር ማስጠበቁ እና የድንበር ማካለሉ ስራን አስረግጠዉ አስቀምጠዋል::

” እንደዚህ ያሉ የብሔር ግጭቶች በሰሜኑ የሱዳን ድንበርና ኢትዮጵያ መካከልም ይፈጠራል ያሉት የኛዎቹ የመከላከያ ጀኔራል ጉዶች ድንበር እስኪካለል ድረስ የሰሜን ሱዳናና የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አብረዉ በጥምረት እየሰሩ እንደሆነና የደቡብ ሱዳኑም ያንኑ እንዲያደርግ ሐሳብ አቅርበዋል”

የጋምቤላ ወገኖቻችንን ከ10 ቀበሌዎች በላይ ዘልቀዉ በመግባት የገደሉ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ወይም ወንጀለኞቹ በሕግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ እንዲሁም ታፍነዉ በተወሰዱት 103 ሕጻናት ዙሪያ እና የደቡብ ሱዳኑ መንግስት ካሳ እንዲከፍል በመጠየቅ በኩል ያልተሳተፈዉ የወያኔ መንግስት ነገሩን ሆን ብሎ እንዲፈጸም ያደረገ መሆኑን ከስብሰባዉ መንፈስ ለመረዳት ተችሏል።

በመጀመሪያ ደረጃ ጋንቤላን በፌደራል መንግስት እጠቀልላለዉ ያለዉ ህወሃት የክልሉን መከላከያ ሰራዊት በመበረዝ ከቦርደር ላይ እንዲነሱ በማድረግና በምትካቸዉ ምንም አይነት ሰራዊት ሳያመጣ መሰንበቱ! እንዲሁም በሁለቱ ብሔሮች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት አዲስ እንዳልሆነና በማንኛዉም ወቅት እንዲህ ያለ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል መረጃ እያለዉ ጉዳዩን በቸልተኝነት ያለፈዉ የድንበር ማካለሉን ጉዳይ ከጋምበላ ወደ ጎንደር ለመዉሰድ የታለመ ሳይሆን እንዳልቀረ ተንታኞች እየገለጹ ነዉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሙርሌ ብሔረሰብ ታጣቂ የተባሉት ወታደራዊ አቋም ያላቸዉና ልዩ ስልጠና የወሰዱ የደቡብ ሱዳን ወታደርዊ ዩኒፎርም እንዲሁም አንዳንዶቹ የኢትዮጵያን መከላከያ የደንብ ልብስ የለበሱ ሲሆኑ ግድያዉን ከፈጸሙ በኃላ የኢትዮጵያ መከላከያ ፈጽሞ ያለመኖሩን የተገነዘቡት የጋንቤላ ህዝቦች በመተባበር የሙርሲ ብሔር የተባሉትን ነፍሰ ገዳዮች በማሳደድ የመልሶ ማጥቃት እንደፈጸሙ ምንጫችን አረጋግጠዋል።

↧

ኢትዮጵያውያን በስዊድን ቴዎድሮስ አድሃኖምን ተጋፈጡ –ቭዲዮ ይዘናል

$
0
0

በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ተጋፈጧቸው:: ለስብሰባ ወደዚያው ያመሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ በኢትዮጵያውያኑ ተቃውሞ ሲደርስባቸው የሚያሳይ ቭዲዮ ተለቋል – ይመልከቱት::

Tewodros Adhanom

↧

የጽጌ ሽሮ ነገር.. በፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

$
0
0

ኣንድ ግደይ ገብረኪዳን የተባለ የሴራ ታሪክ ተንታኝ ወጣት፤ ብዙ ጽፎ ጽፎ ደከመውና “የሰይጣን ማሕበርተኞቹ ‹‹እኛ ሰይጣንን እናመልካለን፣ በደስታም ወደ እሳቱ እየዘለልን እንገባለን›› ሲሉ እኛ “ሃይማኖተኞቹ” ግን እየወረብን፣ እያሸበሸብን እየዘመርን ወደ ገሃነም መሄዳችን ነው ልዩነቱ ሲል የገለጸበት መንገድ አስታውሳለሁ…!
mesfin
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነገሮች በሙሉ ግልጽ እየሆኑ የመጡ መሆናቸውን እየተረዳን ነው፡፡ ይሕም ሲባል ሥለ ፍትህ፣ ሕጋዊነት እና የአራዊቶች መስመርን ለመከታተል እናም ለመግታት የሰውአዊ መተዳደሪያ ደንቦች/ሕገ-ኀልዮት/ ይስፈን እያልን ለዘመናት ተሟገትን…፡፡

ትላንት ስለ ፖለቲካ እና ስለ ማሕበረሰባዊ ኢፍትሃዊነት ጆሮ ዳባ ይሉ የነበሩ ዜጎች ፤ አሁን ላይ አፎቶቻቸው ከማንም በላይ የሠለ/ሉ “ፖለቲካዊ ኂሰኞች” ሲሆኑ እያየን ነው፤ ፖለቲካ እና ስለ አገር መቆርቆር ማለት ዘረኛ መሆን እስኪመስላቸው ድረስ፤ አሁን ስለ አገሬ እቆረቆራሉ በሚል ስሜት የዘረኛነትን የዘመን መንፈስ እንደ ድግምት ተቀብለውታል፡፡

/ድግምት በፈቃድ የሆነበት ዘመን/
ጽጌ ሽሮ የሚባል ዝነኛ ቤት ከተከፈተ ዓመታት ተቆጥረዋል፡ ትግራይ በሽራሮ ብቻም ሳይሆን በሽሮ ጥበብ እንደምትታወቅ ፤ በኢትዮጵያ በታሪክ መስመር ውስጥ መሠረት የጣለች መሆኗን እያስገነዘበች፤ ያስመሰከረች ሴት/ቤት ናት፤ እንደውም ከአንድም 6 ቅርንጫፎችን ከፍታ ከመካከለኛ ደረጃ በላይ ገቢ ያላቸውን ዜጎች እያበላች ነው፡፡ ልብ በሉ ዜጎች ነው ያለኩት!
ታድያ በገላጣው ኢፍትሃዊነትን የሚመለከት ሰው አሁን አሁን በቀላሉ ስስ የአስተሳሰቡ ብልት እየተነካ ዘረኛ የሆነውን የፖለቲካ ኂሱን ሲሰጥ የሚውል ሰው አጋጥሞን ይሆናል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
ጽጌ ሽሮም ሆነ አዝመራ ሽሮ የሚታወቁበት ሁለት ነገር አለ፡-
አንደኛው የወፈረ ድፍድፍ ሽሮ ማብላታቸው ሲሆን
ሌላኛው ደግሞ ለተከፈለበት ሽሮ ደረሰኝ አለማቅረባቸው ነው፡፡ የጠላ ድፍድፍ አሁን አሁን እየቀረ ባለበት ሰዓት፤ የሽሮ ድፍድፍ ማዬት ያስመሰግናል፤ ጣዕሙም አብሮ እጅ ያስቆረጥማል፤ የኪስንም ቁርጥማት ሲቀሰቅስ በዛው ልክ ነው፡፡
ደረሰኝ ያለመስጠቱ ጉዳይ ግን የዘመኑ ፖለቲካ ውጤት እና የዘመኑ የፖለቲካ ኂስ ሰጭዎች የተንጠላጠሉበት ገመድ ነው፡፡
ልጁ በምን መልኩ ስለ ፖለቲካ ኣያገባኝም ሲል የነበረ ልሳን ታቅፎ፤ አሁን ደረሰኝ ለምን አይሰጡኝም ያላቸውን ምግብ ቤቶች በመቁረጥ ዘረኛ እነዲሆን ምክንያት ሆኖታል!

ይሕ ትክክል እደለም፤ ስንቃወምም ሆነ ሐሰባችን ስናነሳ አጠቃላይ አውነት እና ሕጋዊ መስመርን ተንነርሰን መሆን ነበረበት፤ አሁን አሁን ከዛሬ 25 ዓመት በፊት እንዳይሆን ስንታገል የነበረውን የዘረኝነት ፖለቲካ አስተሳሰብ አሁን በዚህ መልኩ ቀለብ ሲያደርገን፤ ከላይኛው የዘረኝነት መንፈስ ጋር አብረን ስንሳከር ማዬት ያሳዝናል፡፡ ምን ለማለት ነው…፡፡ ትላንት መለስ ዜናዊን ሲያመልኩና ሲያወድሱ የነበሩ ዜጎች ዛሬ እርሱ በፈጠረው የዘረኝነት የፖለቲካ ባሕር ውስጥ እየዋኙ በዘረኝነት ሰክረው አገርን ያሳብዳሉ! “እርሱ ቢኖር እኮ እንዲህ አይሆንም ነበር” እያሉ ያሟርታሉ!!

የዘረኝነት አስተሳሰብ ለዬት ያለበት ዋናው ምክንያት መንፈስን ከማበላሸቱ እና ከማቀላቀሉ በላይ ኪሳራው መመለሻ የሌለው ንጉደት ነው! ሽሮ ተወደደ፣ ደረሰኝ አይሰጡንም እና ትግሬን ሁሉ እጠላለሁ ብሎ ወደ ዘረኝነት ባሕር መድፈቅ መታመም ነው! አሁን በከተማችን ብሎም አገራችንን እያጠቃ ያለው አስተሳሰብ ይሕ ነው! እየሸበሸቡ እየዘመሩ ወደ ገሃነም መውረድ ይሉታል ይሄ ነው!! አሁን የፖለቲካ ኂሶች እንደ ከተማችን የመኪና ሽያጭ ቤቶች፣ ሽሮ ቤቶች፣ የጀበና ቡና ቤቶች እና የግል እስር ቤቶች ተበራክተዋል!!

ከዚህ ሁሉ የሚቀድመው አስተሳሰብን ወደ ሕግ፣ ፍትህ እና ነጻነት እንዲሁም እኩልነት መግራት ነው! የአሁን የዘረኝነት ጥላቻ ነገ ባዶ በተሞላነው የብሄር አጽቅ ውስጥ ለመታሰር እና ሌሎችን ለማሰር ነው…!

↧

ታግዶ የነበረው የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ ተፈቀደ

$
0
0

mahebere kidusan
ሐራ ተዋሕዶ የተሰኘው ድረገጽ እንደዘገበው የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ ከግንቦት 17 – 22 ቀን በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ዕውቅና አገኘ:: ማኅበረ ቅዱሳን፣ ከመጋቢት 15 እስከ 21 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን: አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ” በሚል መሪ ቃል በኤግዚቢሽን ማዕከል ለማካሔድ ዐቅዶ ቅድመ ዝግጅቱን ያጠናቀቀበት ዐውደ ርእይ ለጉብኝት ክፍት የሚኾንበት የመጨረሻ ሰዓት በመንግስት መታገዱ ይታወቃል::

እንደ ድረገጹ ዘገባ “የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ማሳወቅ” በሚል ዓላማ ባገኘው ዕውቅና ከግንቦት 17 – 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሸት 4፡00 ድረስ ለሚካሔደውና ከ100 ሺሕ በላይ ተመልካች እንደሚጎበኘው ለሚጠበቀው የ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ መንግሥት የፖሊስ ጥበቃ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

↧
↧

ኢትዮጵያ ዉስጥ ርሃብተኛው አምስት ኪሎ ደርሷል; ወያኔና አሽቋላጮቹ ዳላስ ላይ ልማት እያልን እንጫወት ይሉናል

$
0
0

demeke Mekonnenከዳላስ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ጥሪ

የወያኔ ኢምባሲና የዳላስ አልማ ቻርተር ብሎ ራሱን የሚጠራ ቡድን ስብሰባ መጥራታቸውን አሜሪካ በሚገኘው ቆንሲላ ስም የተጻፈ ለተወሰኑ ሰዎች የተላከ ጥሪና የመግቢያ ትኬት ደረሰን።

ቦታው፤
Hyatt Place Dallas
5101 George Bush HWY
Garland, TX 75040
በ4/24/16 ዕሁድ ቀን ሁለት ስዓት ላይ
እንግዳው አቶ ደመቀ መኮንን የተባለ የወያኔ ምክትል ጠቅላይ ሚንስቴር ነው። ይህ ሰው ለዚህ ሹመት የበቃው 1600 ኪሜ የሚረዝመዉን ያገራችን መሬት ለሱዳን አሳልፎ የሰጠውን የወያኔ-ትግሬዎች ስምምነት በመፈረም ነው። ወያኔዎች ዝለል ሲሉት ምን ያህል ከፍታ? ብሎ የሚጠይቅ ሆድ አደር ነው። ደመቀ።

ደጋሾቹ፦

አንደኛ ተኮላ መኮንን የተባለ የቀድሞው ስመ ጥር አየርውለድ አባል የነበረ -ድርጊቱ በጀግንነታቸው የሚታወቁትን ያን ብርቅየ ትውልድ ስም የሚያጠለሽ። ዳላስ ዉስጥ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ለምን በወየናኔው ሲኖዶስ ስም ካልሆነ ብሎ ክስ መስርቶ በፍርድ ቤት የተረታ። ከሱ አልፎ ትክለሃይማኖትን በመሰለ ቅዱስ ስም የሚጠራን ታቦት ተለጣፊ ያደረገ መሰሪ ፍጥረት ነው።

ሁለተኛው ጽሃይ ጽድቅ የሚባል የምዕመናኑን ገንዘብ መዋጮ ሰብስቦ ለወያኔ እጅ መንሻ ያስረከበና ሸራተን ላይ በውጭ የሚንቀሳቀሱትን አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ስም በቲቭ ይዘልፍ የነበረ።

ሶስተኛው አባቡ የሚባል ባህርዳር ላይ ህንጻ አለኝ ብሎ ነጻነቱን አሳልፎ የስጠ ሆድ አደር ናቸው።

በደረሰን መረጃ መሰረት ስብሰባው በዳላስ አካባቢ ለሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጆች በክልሉ ስለሚደረጉ ንግድና ኢንቨስትመንት፣በቤቶች ልማት ፕሮግራሞችና በክልሉ ስለሚደረጉ ልማቶች ለመወያየት ነው።

ይህ ያጼ ቴዎድሮስን የትውልድ ቦታ ቋራን አስልፎ ለሱዳን ያስረከበ ባንዳ፣ የወልቅይት ህዝብ “አገር አልባ” ሆኖ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ከወያኔ ጋር በሚተናነቅበት ወቅት አማራውን አሰባስበን ልማት ልናስፋፋ ነው ይለናል።

ነገሩ ግን ወዲህ ነው። የወልቃይት ህዝብ ላለፉት ሃያ አምስት አመታት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበት፣ ከትውልድ ትውልድ ከኖረበት መሬት አየተፈናቀለ፣ አማራነቱን ትቶ ትግራዋይነትን ካልተቀበልክ ተብሎ በሚጋዝበት፣ በሚታሰርበት፣ ሴቶቹ ተገደው በሚደፈሩበትና በግፍ በሚገደልበት ወቅት ኑ! ተሰብሰቡና ስለልማት እናውራችሁ ይሉናል። እነ ደመቀ።

በተወሰኑ ባገሪቱ ክፍሎች በተከሰተው ድርቅ 20 ሚሊዮን የሚሆኑ ወገኖቻችን በርሃብ አያለቁ ባሉበት ወቅት እነ ተኮላ የተባሉ ጉዶች ኑ! ተሰብሰቡና ባማራው ክልል ስለሚደረገው የልማት እንቅስቃሴ እናውራችሁ ይሉናል።

ከመሬታችን ተፈናቅለን ለማኝ መሆን በቃን ያሉ የኦሮሞ ወገኖቻችን አንደቅጠል እየረገፉ ባሉበት ወቅት ኑ! አገሪቷ እየለማች ነው እድሉ እንዳያመልጣችሁ ይሉናል፣ እነ ጽሃይ ጽድቅ።

በኦሞ ውንዝ አካባቢ የሚኖሩ የሙርሲ ወገኖቻችን እንደ እንስሳ አንገታቸው ታስሮ ባስቃቂ ሁኔታ በሚጋዙበት ባሁኑ ወቅት እነኝህ ሆዳሞች ተሰብስበን ገዳዩን የወንበዴ መንግስት በልማት ስም ይበልጥ እያወድልንና አያደነደን ህዝባችን አናስጨርስ ይሉናል።
መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ በሚጠይቁ ዜጎች ላይ ሃይሉን ለማሳየት ደክሞ የማያውቅ መንግስት፣ ሰራዊታችን ካለም አራተኛ ነው አያለ የሚያቅራራ መንግስት፣ ከሶስት ቀን በፊት ጋምቤላ ዉስጥ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች 208 ሰዎች ሲገሉ ምንም አይነት መልስ ያልሰጠ የወንበዴ መንግስት ዳላስ ድረስ ዘልቆ ኑና ኣለም ባንክንና ኣይ.ኤም.ኤፍን ባሞኘሁበት ምህታታዊ የዕድገት አሃዝ ላሞኛችሁ ይለናል።

የዳላስ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ያለወያኔ አመራርና የሆድ አደሮች ግፊት ለወገን ደራሽ መሆናቸውን አስመስክረዋል። የህዝብ መብት ሳይከበር፣ ያንድ ብሄረሰብ ሁሉንም ያገሪቱን ልማታዊ መዋቅሮችና ወታደራዊ ሃይሉን በተቆጣጠረበት ሁኔታ፤ አገር አንደማይለማ አነሱም ያውቁታል አኛም አይጠፋንም። አነኝህን የታሪክ አተላዎች በጠሩበት ቦታና ጊዜ ተገኝተን አድቡ ልንላቸው ይገባል።
የአማራው፣ የኦሮሞ፣ የሙርሲው፣ የጋምቤላው በጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝባችን ደም ዳላስ ድረስ ይጮሃል!

↧

ከመቀሌ የመጣ ከባድ መኪና እና ወደ አላማጣ የሚጓዝ ሚኒባስ ተጋጭተው የ25 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ

$
0
0

bus

(ዘ-ሐበሻ) በየቀኑ መልካም ዜና የማይሰማባት ሃገር እየሆነች በመጣችው ዛሬም ከባድ አደጋ ተከስቷል:: በቅርቡ በጋምቤላ ክልል ያለቁት ወገኖቻችን ሃዘን ሳይቆርጥልን ዛሬ ደግሞ ሌላ አሳዛኝ ዜና ተከስቷል:;

የአይን እማኞች እንደሚገልጹት ዛሬ በሰሜን ወሎ በቆቦ ከተማ እጅግ አሳዛኝ የመኪና አደጋ ደርሷል:: አደጋው የተከሰተው በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 10 ሰዓት ሲሆን የአደጋው መነሻም የሁለት መኪኖች ግጭት ነው::

የአይን እማኞች እንደሚናገሩት ከመቀሌ ከተማ ሸቀጣ ሸቀጥ የጫነ ከባድ መኪና ከነተሳቢው ወደ ወልዲያ ሲጓዝ የነበረና ከቆቦ ወደ አላማጣ 16 ተሳፋሪዎችን ጭኖ የሚሄድ በተለምዶ አባዱላ የሚባለው የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ቆቦ ከተማ ላይ ተጋጭተው እስካሁን የ25 ሰዎች ሕይወት አልፏል::

በዚህ መኪና አደጋ እግረኞች እና በሳይክል የሚጓዙ ሰዎችም ሕይወት መጥፋቱ ተዘግቧል:: ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን::

↧

የሊቢያ ሰማዕታት መታሰቢያ |መጽሐፍ ቅዱስና ቅዱስ ቁርአን በአይሲስ ስለተገደሉት ወገኖቻችን ምን ይላል? |ልዩ የድምጽ መሰናዶ

$
0
0

የታምሩ ገዳ ጥንቅር
በሊቢያ በረሃዎች እና የባሕር ዳርቻዎች ላይ የዛሬ ዓመት በአረመኔዎቹ አይሲስ ታጣቂዎች በግፍ ስለተገደሉት 30 የሚጠጉ ወገኖቻችን ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ቁርዓኑስ? ስለ ከፈሉት ሐይማኖታዊና ኢትዮጵያዊ ተጋድሎ የሚዘክር መሰናዶ (ልዩ ጥንቅር)

↧

ትዝብት

$
0
0

ቀኑ ቅዳሜ የካቲት 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ነዉ። በጠዋት ተነሳሁ።

5 ሰዓት ከጠዋቱ ቡና ሳልጠጣ እራሴን ካዘጋጀሁ በሁዋላ 6 ሰዓት ሲሆን መንገድ ጀመርኩ። የምሄደዉ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ የሚካሄደዉን Vision Ethiopia (ራዕይ ለኢትዮጵያ) “የሚባለዉ የምሁራን ስብስብ እጠራዉ “ሽግግር/ዲሞክራሲ/ የብሔሮች አንድነትና ግንኙነት” በተባለዉ ርእስ የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት አካሎች፣ ምሁራንና የተለያዩ ግለሰቦች በአንድነት ተሰባስበዉ ቅራኔን አስታርቀን የኢትዮጵያችንን አንድነት ጠብቀን ለመጉዋዝ ትርጉም ያለዉ የጋራ ትግል ለመቀጠል ነፃ ዉይይት ለመካፈልና የረዥም ግዜ የትግል አጋሬ የነበረዉን የድሉ (አቶ ዘላለም ብርሃን) የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ነበር።
neamin zeleke

ልቤ በተመሰቃቀለ የቅርብና የሩቅ ትዝታ እየተጨነቀ ባማረዉ “freeway” ጎዳና ገሰገስኩ:: የ3 ሰዓቱን መንገድ ለመጨረስና ቀብሩን አጠናቅቄ ወደ ስብሰባዉ በሰዓቱ ለመገኘት ፈልጌ ከሐሳቤ ገር እየተጫወትኩ መንገዴን ቀጠልኩ።

ይህች ሀገር በስብሰባ ነፃ ብትወጣ ኖሮ እንኩዋን የእኛን ሀገር አፍሪካንም የነፃንት መናኸሪያ ባደረግናት ነበር አልኩ በልቤ። ”ከመቀመጥ መገላበጥ” ይባላልና ሄጄ ልየዉ፣ የጋራ ትግል ዉጤታማ ነዉ ብለን ካመንን ይህን መደገፍና ለዚህ የሚደረጉ ጥረቶችን ማበረታታት ወቅቱ የሚጠይቀዉ ሀቅ ይሆናልና በአካል መገኘት አለብኝ አልኩ። ከልቤ ጋር በዚሁ ተስማምተን መኪናዬን በፍጥነት እያሽከረከርኩ የፀሐይዋን ወጋጋን ከፊት ለፊቴ እያደነቅሁና ተፈጥሮን እያገናዘብኩ ስጉዋዝኩ። ልቤም ተመልሶ ወደ ቀብሩ ሄደ። በሕይወቴ በሞት የተነጠኩት እጅግ ብዙ ወንድሞችና እህቶች ቢኖሩም፤ ደረት መትቼ፣ ሙሾ አውርጄ የቀበርኩት በጣም ጥቂቶቸን ስለሆነ ከነዚህ አንዱ ሲነጠቅ ህልማችን ህልም፣ ተስፋችንም እዉን ሳይሆን እንደወጡ ቀሩ መባላችን ሆድ ያስብሰኛል። በተለይም በቅርብና በአጭር ግዜ ዉስጥ 3 ስመጥሩ ሰዎች ስቀብር ባዘንና በመጨናነቅ እስከመቼ እላለሁ። አሁን አሁንማ የሚያወሩትም ሊጠፋ ነዉ።ይህንና ያንን የመሳሰሉ ያለፈዉንና የወደፊቱን የሀገርና የህዝብ የእራሴም ጉዳይ ጋር ትግል እንደገጠምኩ ዋሽንግተንን አልፌ ሜሪላንድ ገባሁ። ከቀጠሮየ ሰዓት ቀደም ብዬ በመድረሴ ደሰ ደሰ እያለኝ የተቃጠርኩበትን ቤት ደወል ስደዉል እቤታቸዉ በሄድኩ ቁጥር ከልብ የፈለቀ ፍቅራቸዉንና ፈጋግታችዉን የሚለግሱኝ እጅግ የማከብራቸዉ ባልና ሚስቶች በተለመደዉ እንከን በማይወጣለት ቀልድና ጨዋታ በስስት ሲቀበለኙ ያ በትርምስምስ አሳብ የተጐሳቆለዉ ልቤ ፈካ አለ። ለመጀመሪያ ግዜም ፊቴ ፈገግ ብሎ ሁሉን ነገር ተወት አድርጎ ከእነሱ ጋር የድሮዉን ያሁኑን እየተጫወትን እተየሳሳቅን ቆንጆ ቁርስ በልተን ወደ ቀብሩ ሄድን።

አንዳንድ ግዜ በህይወት ተርፈዉ ባጠገባችን በመገኘት የሥጋና የመንፈስ ተሐድሶ የሚሰጡንን ያምላክ ፀጋዎች እህቶችና ወንድሞች እንረሳቸዉና በሞቱና ባላፉ ሰዎች ትዝታ እንገላታለን። ይህች ታጋሽና ታላቅ መምህሬ በህይወት ተርፋ አሁንም ያላለቀዉን ጉዞ በስተርጅና አብረን በመጉዋዛችን አክብሮቴና ፍቅሬ በየግዜው ይጨምራል። እንዳሰብኩት የእኛ የቀብር ሥነ ስርዓት የመገናኛ ግብዣ ይመስላል። ብዙ ሰዉ ተገናኝተን ሐዘንና ደስታ የተቀላቀለበት የቀብር ሥነ ስርዓት አሳልፈን ወደ ስብሰባዉ ሄድን ለምሳም ግዜ አልነበረንም።

የጠዋቱ ስብሰባ አልቆ ስለነበር እከሰዓቱ ስብሰባ ላይ መሉ ለሙሉ ተሳተፍን፡፡ አቶ አክሊሉ ወንድአፈራው የሸንጎ አመራር ኮሚቴ የመጀመሪያ ተናጋሪ በመሆን የሸንጎን ዓላማና የወደፊት ፕላን ባጭሩ ካስረዱ በሁዋላ የተቀዋሚወች በአንድነት ተባብሮ መሰለፍ የማያወላዉልና አማራጭ የሌለዉ የወቅቱ አንገብገቢ ጥያቄ በመሆኑ የተቃዋሚ ቡድን መሪዎች ሊያስቡበት ይገባል በማለት ደመደሙ።

ጥያቄና መልስ ተጀምሮ “ሽንጎ ማንነቱን በተግባር እስከአሁን ያሳያቸዉ ዉጤቶች ምንድን ናቸዉ?” በሚለዉ ላይ ተነጋገርን። እነዚህ ጥያቄዎች ተደጋግመዉ የተነሱ ቢሆኑም የተቃዋሚ ቡድን መሪዎች ግን ተባብሮ ለመስራት ያሳዩት ጥረት ጎልቶ አልታየም። ’’ ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ” የህዝብ ጥያቄ ከሆነ ዉሎ አደረ፤ ሰሚ ጠፋ እንጂ።

ሁለተኛዉ ተናጋሪ አቶ ሌንጮ ባቲ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር የሥራ አስኪያጂ ኮሚቴ አባል ነበሩ። እረጋ ባለ አንደበት “የኦሮሞ ሕዝብ በማንኛዉም የኢትዮጵያ ክልል ተጋብቶና ተዋልዶ የሚኖር ተገንጥሎ ብቻዉን እንኑር የማይል ነዉ። እናንተ ቤታችሁን ዘግታችሁ ለብቻችሁ ሰለምታወሩ ችግሩን ለማየት አልቻላቸሁም። አሁን እንኩዋን የኦሮሞ ወጣቶች ሲጨፈጨፉ ማንኛችሁም እንዴት እንዲህ ያለ ኢስብአዊ ድርጊት ይፈፀማል? የሰዉ ሕይወትና ደም መፍሰስ ይብቃ፤ ብላችሁ ከጐናችን አልተሰለፋችሁም።” በማለት ልናደርግና ሊያቀራርበን ይችላል የሚሉትን ሀሳቦች በእርጋታ ከገለፁ በሁዋላ በዚህ አቅጣጫ የሁለቱን ወገን ትግል ለማቀራረብ ብዙ የጣሩትን ፕሮፌሰር ጌታቸዉ በጋሻዉንም ላደረጉት ጥረት አመስግነዋል።

በበኩሌ እራሴን ስጠይቅ እንዲህ ያለ ወንድማማችነትን፣ መተሳሰብን፣ መደማመጥን የተጎናፀፈ አዲስ የተሰፋ ጭላንጭል የሚታይበት ስብሰባ ስካፈል የመጀመሪያዬ በመሆኑ እዉነትም ቤታችንን ዘግተን ነበር አልኩ። በዚህ አጋጣሚም አቶ ሌንጮን ላመሰግናቸዉና በዚሁ ይግፉ ተሰፋችን አንድነታችን ነዉና ይበርቱ እላለሁ።
ለአቶ ሌንጮ በርካታ ጥያቄና መልሶች ተደርገዉ ወደ አቶ ነአምን ዘለቀ የዉጭ ጉዳይ መኮንንና የአርበኞች ግንባር ያመራር ኮሚቴ አባል የሆኑትን ማዳመጥ ቀጠልን። አቶ ነአምንም ለዘብ ባለ አንደበት ሀገራችን ላይ የሚካሄደዉን ግፍና ግድያ፣ በኦሮሞ ወጣቶችና በወልቃይትና ፀገዴ ሕዝብ ላይ የደረሰዉን ጭፍጨፋ አዉግዘዉ፣ ድርጅታቸዉ ከማንኛዉም ተቃዋሚ ቡድን ጋር አብሮ ለመስራትና ለመታገል ዝግጁ እንደሆነ ገለፁ። በኤርትራ ሕዝብ ለይ የሚካሄደዉ ጭቆና ሊታያቸዉ ባይችልም የአምባገነኖች ግፍ በሁለቱም ሀገር ሕዝቦች ላይ ከባድ ጫናዉን ጭኖ ህዝብን እየጨፈጨፈ መሆኑን የሁለቱም ሀገር ሕዝቦች በሚያደርጉት ትግልና እልቂት እያስመሰከሩ ነዉ። ይሕ ሀቅ አይካድም።

ጥያቄና መልስ ተሰጥቶ የቀኑ ፕሮግራም ተጠናቀቀ። የግሩፕ ዉይይቶች ቀጠሉ። የተዋጣለት ጥሩ ቀን ነበር፡፡ ይህች ሀገር ተስፋ አላት ያሰኛል። ከዛም ለእራት ወደአንድ እህት ቤት ተያይዘን ሄድን። ዓይነቱ ዐይን የሚያደክም የፆም ምግብ ደርድራ ፈገግታዋንና ሳቅዋን ጨምራ በፍቅር ተቀበለችን። ሌሎች ባልና ሚስቶች ግብዣዉን ተቀላቀሉ። በርከት ብለን ጠረጴዛዉን ከበን እንደገና በቀኑ ዉይይት ላይ የብሄር ጥያቄና ኢትዮጵያ በሚለዉ በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ከነዚህ አብረዉ ከኖሩና እንደወንድምና እህት ከሚተያዩ፣ በሀገራቸዉ ፍቅር ለሕዝባቸዉ ደህንነት ከልባቸዉ ከሚቆረቆሩ፤ ወገኖች መሀል ተገኝቼ የዉይይታቸዉና የማእዳቸዉ ተካፈይ በመሆኔ ላመስግናቸዉ እወዳለሁ። በተለይም የቤቱ እመቤት ላደረገችዉ ፍቅርና ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ላዘለዉ መስተንግዶዋ በጣም ላመሰግናት እወዳለሁ።
Vision

እሁድ የሴቶች ጥያቄን የሚመለከት ዝግጅት በ9 ሰዓት ሰለሚጀምር በጠዋት ተነሰተን ጥሩ ቁርስ በልተን ከቤት ወጣን። በስዓቱ በመድረሳችን ያመለጠን ነገር አልነበረም። የመጀመሪያዋ ተናጋሪ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ላቀዉ የHoward ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪና የሞንቶጎሞሪ ካዉንቲ የሰባአዊ መብት አስጠባቂ አሰባሳቢ የሆነችዉ ይህች ወጣት ከሀገሩዋ ተርፋ አሜሪካ ለሚኖሩ ጥቁሮች መብትና ነፃነት የምታደርገዉ ተጋድሎ የሚያስደንቅ ነበር። የሀገራችን ሴቶችም ትግሉን በመቀላቀል ከቤት ወደ ሀገርቤት በመሸጋገር ለዘላቂዉና ለቋሚዉ የሕዝብ ነፃነት እንዲታገሉ ምን መደረግ አለበት? የሚለዉ ውይይት ቀጠለ። በእዉነቱ ሀገር አቋርጠዉ ዉቅያኖስ ሰንጥቀዉ የመጡትን ወ/ሮ ሰዋስዉንና ወ/ሮ አሳየሺ በመላዉ የኢትዮጵያ ሴቶች ስም ከልብ ልናመሰግናቸው ይገባል።

ሁለተኛዋ ተናጋሪ ወ/ሮ ሰዋሰው ጆ ማንገር (From The Ark of New Covenant Healing Ministry Norway) ነበሩ:: እሳቸዉም “ሰዎች እርህራሄን ለሰዉ ልጆች ስቃይና መጐሳቆል፣ መራብና መጠማት መቆርቆርን ከጌታችን ከክርስቶስ ሊማሩ ይገባል። ለሰዉ ልጆች ፍቅር እራሱን ሰጥቶአልና። በሀገራችንም የሚካሄደዉ ኢስብአዊ ድርጊት ለሰዉ ልጅ ፍቅር ያለዉን ማንኛዉንም ሰዉ ሊያስቆጣ ይጋባል” አሉ።

ጥያቄና መልስ ተካሄዶ ወደ ወ/ሮ አሳየሽ ታምሩ የስባአዊ መብት ታጋይ ወደሆኑትና ከፍራንክፈርት ጀርመን ከመጡት እህት ይንን ሰማን፤ “እኛ ሴቶች በሀገራቸዉ ጉዳይ ላይ መሳተፍ ይኖርብናል። በተለይም በአሁኑ ግዜ የሀገሪቱ ብዙሀን በሆንበት ሰዓት ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያና ሌሎችንም የዴሞክራሲ ጥያቄ በማንሳት ለሀገርና ለራሳችን ብሎም ለልጆቻችን ነፃነት መታገል ይኖርብናል። ከእናቶቻችን ከንግሥት ጣይቱ ጀግንነትን መማር አለብን፣ የነቁ ወንዶች የነቁ ሴቶችን ማፍራት አለባቸዉ” አሉ።

ጥያቄና መልስ ተካሂዶ ወደ ወ/ሮ ወሰኔ ደበላ የሰብአዊ መብት ታጋይና የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል አባል ተሻገርን። እሳቸዉም የኢትዮጵያ ሴቶች ትግል ከንግሥት ጣይቱ ጀምሮ ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጉን ጠቅሰዉ የእሳቸዉ ድርጅት ለረዥም ግዜ ባለማቋረጥ ሻማ በማብራትና በተቃዉሞ ሰልፍ በሀገራችን ሴቶች ላይ የሚደረገዉን መንግሥት ያወቀዉ፣ የፈቀደዉ የሴቶች የመብትና የሴትነት ክብራቸዉ ሳይጠበቅ፣ ሳይረጋገጥ ወደ አረብ ሀገር እየተላኩ መጫወቻ የሆኑትን እና እራሳቸዉን በፎቅ እየወረወሩ የሞቱትን በማንሳት ድርጅታቸዉ ያደረገዉን ትግል በማዉሳት “ሴቶች እራሳቸዉን አደራጅተዉ ጠንክረዉ ካልተገኙ ለእራሳቸዉም ሆነ ለቤተሰባቸዉ ለልጆቻቸዉ የነፃነት ጮራ ሊፈነጥቁ አይችሉም እና ድርጅቶችን በመቀላቀል እራሳቸዉን አስተምረዉ ሌሎችንም ማስተማር ይችላሉ።” ብለዋል።
ከዚያ በሁዋላ ለታዳሚው በተሰጠው የጥያቄና መልስ ዕድል በመጠቀም “እቴጌ ጣይቱ ለኢትዮጵያ አንድነትና ለግዛታቸዉ የታገሉ የዉጭ ጠላትንም ያስጎነበሱ ታላቅ ንግሥት ነበሩ። የኢትዮጵያን ጭቁን ሴቶችን ነፃ ለማዉጣት ታግለዉ የወደቁና የመጀመሪያዉን የሴቶች ቀን (March 8) በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲከበር በሴቶች አሰተባባሪ ኮሚቴ ስም ታግለዉ ያስፈቀዱ 14ቱ ሴቶች ስማቸዉ ሊጠራ ይገባል። እነሱም፦ መዝገብነሽ አባዩ፣ ሰላማዊት ኃይሌ፣ ንግሥት ተፈራ፣ ፍ.ገ.፣ ገ.ዘ.፣ ንግሥት አዳነ፣ ያአጥናፍ ዓለም የማነ፣ ጌራ ወርቅ እና ሌሎችም ለግዜው የተረሱ ያልተጠቀሱ ሲኖሩበት ከእነሱ በኋላ የሴቶች አሰተባባሪ ኮሚቴ በደርግ አፈና እና እመቃ ሲዘጋ ኢሴትድ (ኢትዮጵያ ሴቶች ትግላዊ ድርጅት) የተባለዉን በዕቡህ በመመስረት ትግሉን ቀጥለው በርካታ ወጣት ሴቶችን አታግለዋል። እንደ ወ/ሮ ዳሮ ነጋሽ ያሉ ቆራጥ ሴቶች ባደረጉት ቆፍጣና ትግል የ8 ወር እርጉዝ እንደሆነች ከሌሎች ጋር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በር ላይ በሳንጃ ተጨቅጨዉ ተገለዋል። ይህን የመሰለ ቆራጥነት ያሳዩ ሴቶች ሊነሱ ይገባል።” ብዬ ተናገርሁ፤ የግል ሀሳቤን ሰጠሁ።

ለእረፍት ስንወጣ ከፕሮግራሙ አዘጋጂ አንዱ የሆነዉና በአቶ ግዛዉ ለገሰ ወይም እራሱን ጌድዮን ብሎ የሚጠራ ግለሰብ መጥቶ “ታውቂኝአለሽ ? ጌድዮን ነኝ” አለ። እኔ በጭራሽ ላዉቀዉ አልቻልኩም። ጅንን ብሎ ስላናገረኝ ጨርሶ እነደማላዉቀዉ እርግጠኛ ነበርኩ። ከ37 ዓመት በፊት የሆነ ታሪክ አወሳልኝ።

“አንችና መዝገብ አሲምባ እያለን አላሳስራችሁኝም?” ሲል፤ በአሜሪካን ሀገር ፍላደልፊያ እባዶ ቤት ተገላ የተገኘችዉ እህቴ መዝገብነሽ እፊቴ ድቅን አለችብኝ። እጅጉን ስሜቴ ተቆጣ፣ ብልጭ አለብኝ “አስገድለሀት ይሆን?” አልኩት። ካጠገቤ ጠፋ። መዝገብ 8 ዓመት፣ እኔ ከ30 ዓመት በላይ አሜሪካ ሰንኖር ይህ ሰዉ መጥቶ “ለምን ይህን አደረግሽ?” በሎ አልጠየቀም። እኔ በስብሰባው መሃል እሰው ፊት ላቀረብኩት አስተያየት ተቃውሞ መቅረብ የነበረበት እዛው እስብሰባው በአደባባይ ቢሆን ምንኛ ባመሰገንኩት። ትክክለኛ የዴሞክራሲን አሰራርም የተከተለ በሆነ ነበር። የቅራኔዎች ትስስር፣ ውይይትና ትችት በሚባሉ የመግባቢያ ስልቶች ቀዝፈን በዴሞክራሲያዊ አካሄድ ተጉዘን ሰላምና አንድነትን መዋሃድና አብሮ መሥራትን ካላመጣን ነገሩ ሁሉ የከርሞ ጭቃ ይሆናል። ወገንተኝነትና ቡድናዊነት ይሰፍኑና ውድቀትን ያስከትላሉ ብዬ እሰጋለሁ። ከአሁኑ ቢታሰብበት አይከፋም። ከዚህ አጋጣሚ ምን እንማራለን? “ግዜ ያገኘ ቅል ድንጋይ ይሰብራል” ሆነና ህልመኛው ልቤ አልቆርጥ ብሎ ይህ ነገር ይሳካ ከሆነ እስኪ ሄጄ ላዳምጥ ብዬ ብመጣ አሳዛኝ ሁኔታ ገጠመኝ።

ለገዜዉ ተናድጄ የሱን ሊቀመንርነት እረግጬ ብወጣም፤ ያልተጨበጠ አሉባልታ በማዉራት በትግሉ ለይ ጠባሳ እየጣሉ ለጠላት ጉልበት የሚጨምሩ ወገኖች ይህን እንዲያቆሙ አደራ እላለሁ። ይህ ምክር ለእኛና እንደ እኛ ትውልድ በትርምስ ለአለፈ ሁሉ ብሎም “አብዮት ልጆቹዋን ትበላለች” ብሎ እርስ በርሱ ለተበላላ ቡድን ትምህርት ይሁን። ያለፈዉን ለታሪክና ለትዉልድ ትተን ያጠፋነዉን ጥፋት እንዳንደግም ከስህተታችን በመማር በተመክሮ ካልተጉዋዝን አሁንም አወዳደቃችን የከፋ እንዳይሆን ያሰጋል። በቂም በቀል የነበዘ ልብ ይዘን የምንጉዋዘዉ ጉዞ የእሳት ችቦ ይዞ እንደሚሮጥ ሰዉ ነዉ። ንፋስ ሲነካዉ በአካባቢዉ ያለዉን ሁሉ ያጋያል። ከጥፋት ትምህርት ካልተገኘ ሌላ ጥፋት ይወልዳል። ከአለፈዉ የተማርነዉ ይህንኑ ነዉ። ሰህተትን አለመድገም እኮ ታላቅ ብልህነትን ያሳያል።

እንዲሁም ለአንድ ወዳጀ ይህን ገጠመኝ አወራሁትና “አይገርምም ይህን የሚለኝ እኮ ከደርግ አባላቶች ጋር አብሮ እየሰራ ነዉ” አልኩት። ፈገግ ብሎ “አንችም እኮ ከሱ አልተሻልሽም” አለኝ። ቀጠል አድርጎ “ይህ የመከፋፈልና የመጠላለፍ ፖለቲካ ከልተወገደ ወያኔ ለሌላ 100 ዓመታት ይገዛል፤ ትግሉን አሰባስቦ አጠናክሮ መጓዝ አይቻልም” አለኝ። እኔም ፈገግ ብዬ ለእራሴ ይህን አባባል ላልደግም ቃል ገባሁ።

Eckhart Tolle A NEW EARTH በተሰኛዉ መፀሐፉ ላይ እንዲህ ይላል እኔን በጣም ስለጣመኝ ላካፍላችሁ። {You construct a conceptual identity for an individual or group and you Say. “This is what he is. This is who they are.” When you confuse the ego that you perceive in others with their identity, it is your own ego that uses misperception to Strengthen itself through being right and Therefore, SUPERIOR.}

ይህ ጽሁፍ ለቀድሞው ትውልድ የመወያያና የመነጋገሪያ በር ይከፍት ዘንድ ምኞቴ ነው። የሴቶችን ንቃተና የትግል ተሳትፎ የሚያበረታቱ ሁሉ ስማቸዉ ለዘላለም ይኑር።

↧
↧

“ለሕዝብ ያልቆመ መንግሥት በሕዝብ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት አይመክትም”|የሸንጎ መግለጫ በጋምቤላው ዕልቂት ላይ

$
0
0

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)

Ethiopian People’s Congress for United Struggle (Shengo) www.ethioshengo.org shengo.derbiaber@gmail.com

 

ሚያዝያ 11፣ 2008 (ኤፕሪል 19፣ 2016)

shengo

የአንድ አገር ድንበር የሚደፈረው ፣ሕዝቡ ለተለያዩ ጥቃቶች የሚጋለጠው የአገሩን ድንበርና የሕዝቡን ደህንነትና ሰላማዊ ኑሮ ዋስትና ሊሰጥ የሚችል በሕዝብ፣ለሕዝብ፣የሕዝብ የሆነ መንግሥት በሌለበትና ለጸረ ሕዝብ ሃይሎች አመቺ ሁኔታ ሲፈጠር ነው።

ለአለፉት ሃይአምስት ዓመታት ሥልጣኑን በሃይል የጨበጠው የጎሳ ስብስብ በተደጋጋሚ የአገራችንንና የሕዝባችንን ጥቅምና ደህንነት ለአደጋ እያጋለጠ እራሱም የአደጋው ፈጣሪ እየሆነ መቆየቱን የሥልጣን ዘመን ታሪኩ ይመሰክራል።

የስልጣን ዕድሜውን ለማርዘም በሁከትና በሽብር፣በብጥብጥና በእርስ በርስ ቀውስ አንድ ጊዜ ቀስቃሽ ሌላ ጊዜ ወቃሽ፣አንድ ጊዜ አዘጋጅ ሌላ ጊዜ አሶጋጅና አስታራቂ፣እየሆነ በመቅረብ ለማምታታት ቢሞክርም በየቀኑ እውነተኛ ገጹና ባህሪው እየተጋለጠ ሕዝብን ማታለል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።ውስጡም በቀውስ እየተናጠ ይገኛል።

ሰሞኑን የመንግሥት አልባነት እንዳለ የሚሰማቸው የወራሪና የሽብር ሃይሎች በከፍተኛ ዝግጅትና በዘመናዊ መሳሪያ ከፈጣሪው በቀር የት ደረስክ፣ምንስ ደረሰብህ የሚል መንግሥት በሌለው ኢትዮጵያዊ የጋምቤላ ሕዝብ ላይ የወሰዱት የጭካኔ እርምጃና ጭፍጨፋ ለአገሩና ለሕዝቡ የማይጨነቅና ደንታ የሌለው ፣ ለማንኛውም ጸረ ኢትዮጵያ አጋልጦ የሚሰጥ “መንግሥት” መኖሩን በማወቃቸው ነው።

የአገሪቱን ዳር ድንበርና የሕዝቡን መብትና ሰላማዊ ኑሮ የማያስከብርና የማያረጋግጥ ቡድን በመንግሥት የሥልጣን ቦታ ላይ ሊቀመጥ፣መንግሥትም ተብሎ ሊጠራ አይገባውም። ለአለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በአገሪቱና በሕዝቡ ላይ ለደረሰው መከራና ጥቃት በአንደኛ ደረጃ ተጠያቂው አሁን በሥልጣን ላይ ያለው ቡድን ነው።በሥልጣንም ላይ ኖረም አልኖረም ከፈጸማቸውና ካስፈጸማቸው ወንጀሎችና የአገር ክህደቶች ነጻ አይሆንም።በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ የፍትሕ መድረኮች ይጠየቅበታል፤ፍርዱንም ያገኛል።መሪዎች ገለውና ዘርፈው የሚደበቁበት ዋሻ እየተደፈነ መምጣቱን ሊያውቁት ይገባል።

130153

ኢትዮጵያውያን ማወቅና መረዳት ያለብን በሥልጣን ላይ ያለው ስብስብ የሥልጣን ዘመኑ እየተሟጠጠ፣ ከሕዝብ እየራቀና እየተነጠለ እየተጠላም ሲመጣ “ከደነገጠ የቆሰለ ነብር ይከፋል” እንደሚባለው የሞት የሽረትና አልሞት ባይ ተጋዳይ የግፍ እርምጃዎችን ሊፈጽም እንደሚችል ነው።የዚያ ሰለባ ላለመሆንና ለመመከት የግድ መደራጀትና መሰባሰብ አስፈላጊ ነው።የአሁኑም በጋምቤላና በቀረው ሕዝብ ላይ የሚፈጸመው የጥቃት እርምጃ የዚያው የተስፋ መቁረጥ ስሜት አካል ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ለተጎዱት የጋምቤላ ወገኖቻችን ሃዘኑንና የትግል አንድነቱን እየገለጸ ከሌሎቹ ተመሳሳይ የኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ጋር በመተባበር ጥቃቱን የፈጸሙት የመንግሥትም ሆነ የውጭ ታጣቂ ሰርጎ ገብ ሃይሎች ለፈጸሙት ጭፍጨፋ፣ሕጻናትን አፍኖና አግቶ የመውሰድ እርምጃ ለዓለም አቀፍ ፍርድ ቤትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አቤቱታውን በማቅረብ በሕግ የሚጠየቁበትን መንገድ ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚገኙ፣ለአገር አንድነት፣ ለዴሞክራሲ፣ለሕግ የበላይነት፣ለሰብአዊና ለዜጎች መብት፣ መከበር የቆሙ ድርጅቶች ይህን አሰቃቂ ድርጊትና አገር አጥፊ መንግሥት ከማውገዝ አልፈው በጋራ ግንባር ተሰልፈው ሊያሶግዱት ይገባል።ለዚህም አገር አድን የጋራ ዓላማ ልንታገልበት የምንችልበትን የጋራ አካል ለመፍጠር እንዳለፈው ጊዜ አሁንም ሸንጎ ጥሪ ያደርጋል። ጊዜውና ሁኔታው እያዘኑና እየተበሳጩ ብሎም እያወገዙ የሚቀመጡበት ሳይሆን በወሳኝ ትግል ላይ የሚሰማሩበት ወቅት ነው ብሎ ሸንጎ ያምናል።

አገራችንንና ሕዝባችንን ከተመሳሳይ ጥቃት በአንድነት ተደራጅተን እናድን! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!

Tel: 44 7937600756 , +1 9168486790 E-mail : shengo.derbiaber@gmail.com

↧

መንድሜ፣ እስክንድር (አይበገሬው) ነጋ፡ ብቻህን አይደለህም እናም እንወድሀለን!

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም    

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ወንድማችንን እስክንድር ነጋን እናስታውስ፣
Eskinderዘ-ህወሀት (የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ) ታላቁ እስክንድር ነጋ ከሕዝብ ትውስታ እና ህሊና ተፍቆ እና ጠፍቶ ከማየት በላይ የሚወደው ነገር የለም፡፡ ዘ-ህወሀት ዓለም እስክንድር ነጋን እንዲረሳው ይፈልጋል፡፡ የእርሱ ትዝታ እየደበዘዘ ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ ይፈልጋሉ፡፡ እርሱ መታወስ ያለበት ከሆነ ደግሞ የዓለም ሕዝብ እርሱን በአሸባሪነት ማስታወስ እንደሚኖርበት ይፈልጋሉ፡፡

የእስክንድር ጉዳይ እ.ኤ.አ በ1964 በደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች ዘረኛ የበላይ አገዛዝ አፓርታይድ ኔልሰን ማንዴላን አሸባሪ በማለት በሀሰት በመወንጀል የእድሜ ልክ እስራት በመበየን ወደ ሮቢን ደሴት የማጎሪያ እስር ቤት ወስደው ዘብጥያ ካወረዷቸው ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ ማንዴላ ከ27 ዓመታት የአፓርታይድ የእስራት ጊዜ በኋላ ከማጎሪያው እስር ቤት በመውጣት ደቡብ አፍሪካን ከመጥፎ አደጋ አድነዋታል፡፡

አናሳው የደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች የበላይነት አገዛዝ አፓርታይድ ማንዴላን ከሕዝብ ትውስታ ሰውሮ በማቆየት ጥረቱ ላይ ስኬታማ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ዘ-ህወሀትም በተመሳሳይ መልኩ እስክንድር ነጋን ከሕዝብ ትውስታ ለማጥፋት ከቶውንም አይችልም፡፡ እስክንድር ነጋ ከማጎሪያው እስር ቤት ይወጣል፣ ወዲያውኑም የእርሱን ቦታ አሳሪዎቹ ተክተው ይወስዳሉ፡፡

የእስክንድር ነጋ ምስል፣ ጽሑፎች እና ሌሎች የትችት ስራዎቹ እና በረከቶቹ ሁሉ በማህበራዊ ሜዲያዎች እና በበርካታ ድረ ገጾች ታላቅ ክብር ባላቸው ዓለም አቀፍ የፕሬስ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጭምር ይወጣል፡፡ ከሳምንት በፊት አንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት የእስክንድር እስራት በሕገወጥ መልኩ እና በዘ-ህወሀት አጭበርባሪነት መሆኑን ገልጾ  በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የእስክንድር ነጋ ምስል በማህበራዊ ድረ ገጼ አናት ላይ ይገኛል፡፡ በእኔ ማህበራዊ ድረ ገጽ (https://www.facebook.com/al.mariam) እኔን የማይመስል ምስል እንዳለ ሰው ሳይጠይቀኝ የዋለበት ጊዜ የለም፡፡ አትጨነቁ እያልኩ እንደህ በማለት እነግራቸዋለሁ፡፡ “ያ የወንድሜ የእስክንድር ነጋ ምስል ነው!”

አንባቢዎቼ ጥቂት ውለታዎችን እንድታደርጉልኝ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡

ይህንን ትችት ከማንበባችሁ በፊት የእስክንድርን የእጅ ጽሑፍ እና የዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር እየተባለ ከሚጠራው እስር ቤት ቤት የተጻፈውን ደብዳቤ እንድታነቡት እጠይቃለሁ፡፡ (ይህንን ደብዳቤ ለማንበብ በእንግሊዘኛ  እዚህ ጋ ይጫኑ፡፡)

(**የእስክንድርን የእጅ ጽሑፍ ደብዳቤ በማያቋርጥ መልኩ በዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር ቤት ዘበኞች እና ሰላዮች ክትትል ስር ሆኖ ይህንን የመሰለውን ጠንካራ ሀሳቡን ለመግለጽ ባደረገው ልዩ የሆነ ጥረት ምክንያት የኮምፒውተር የፊደላት መክተቢያ ቆልፎችን ሳንጠቀም ለክብሩ ስንል እንዳለ አቅርበነዋል፡፡)

ከዚህም በተጨማሪ በዋሺንግተን ፖስት ጋዜጠኛ በካርል በርነስተይን (እ.ኤ.አ ነሐሴ1974 የዋተርጌትን ቅሌት ያጋለጠው እና ፕሬዚዳንት ሪቻርድ ኒክሰንን ከስልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ያደረጋቸው እና በዓለም ላይ ታላቅ እውቅና ያለው ጋዜጠኛ) እና ሌቭ ሽሬበር (እ.ኤ.አ የ2016 የኦስካር ምርጥ ስዕሎች አሸናፊ የሆነው እና የተከበረ ዳይሬክተር፣ ያዘጋጁትን ተንቀሳቃሽ ፊልም አንባቢዎቼ እንዲመለከቱት እጠይቃለሁ፡፡

(የቪዲዮ ምስሉን ለመመልከት እዚህ ጋ ይጫኑ ፡፡ ካርል በርንስተይን እና ሌቭ ሽሬበር አሸባሪን ለመከላከል ብለው እንደዚህ ያለ በፍቅር የተሞላ መሳጭ ንግግር ያደርጋሉን?) 

ከሁሉም በላይ ደግሞ በእስክንድር ነጋ ላይ በባለቤቱ በሰርካለም ፋሲል (እርሷም የተከበረ የጋዜጠኝነት ሽልማት አሸናፊ ኢትዮጵያዊት ጋዜጠኛ እና ለመብቷ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ለፕሬስ ነጻነት መከላከል ከባለቤቷ ጋር ታስራ የነበረችው) አማካይነት (በእንግሊዝኛ ንኡስ ርዕሶች) የተዘጋጀውን እና ልብ የሚሰብረውን የ3 ደቂቃ የቪዲዮ ፊልም አንባቢዎቼ እንዲመለከቱት እጠይቃለሁ፡፡ (የቪዲዮኑን ፊልም  እዚህ ጋ በመጫን  መመልከት ይችላሉ፡፡)

ሰርካለም ልጇን ናፍቆትን በዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር ቤት እ.ኤ.አ በ2007 ተገላግላለች፡፡

Amnesty 4እስክንድርን ወንድሜ ብዬ ስጠራ እና ሰርካለምን እህቴ ብዬ ስጠራ ኩራት ይሰማኛል፡፡ በእነርሱ መስዋዕትነት፣ በእነርሱ ድፍረት፣ ጽናት እና አይበገሬ ታማኝነት እና በእነርሱ ግላዊ አርአያነት እራሴን ዝቅ አድርጌ እመለከታለሁ፡፡

እስክንድር ነጋ እና ሰርካለም ለኢትዮጵያ ምርጦች እና ባለብሩህ አእምሮ ጋዜጠኞች፣ ለሰላማዊ አማጺዎች፣ በዘ-ህወሀት ግልጽ እና ድብቅ የማጎሪያ እስር ቤቶች ውስጥ በመማቀቅ ላይ ለሚገኙት የፖለቲካ እና የሲቪክ ማህበረሰብ መሪዎች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አርአያ እና ቀንዲል ናቸው፡፡ እስክንድር ነጋን በማስብበት ጊዜ በቀለ ገርባን፣ አህመዲን ጀቤልን፣ ውብሸት ታዬን፣ ተመስገን ደሳለኝን፣ አንዷለም አራጌን፣ አንዳርጋቸው ጽጌን፣ እማዋይሽ ዓለሙን፣ ዴልዴሳ ዋቆ ጃርሶን፣ አኬሎ አቆይ ኡቹላን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማርያንን እና በሺዎች የሚቆጠሩትን የሌሎችን የፖለቲካ እስረኞችንም በተጨማሪ አስባለሁ፡፡

እስክንድር ነጋን በምናስብበት ጊዜ ሁሉንም በሙሉ እናስታውሳለን!

የእስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ሂደት እና ስቃይ፣

እስክንድር ነጋ ልዩ የሆነ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ እና በኢትዮጵያ ጽኑ የፕሬስ ነጻነት ተሟጋች  ነው፡፡ እ.ኤ.አ ከ1993 ጀምሮ የዘ-ህወሀት ፍርሀት የለሽ ተቺ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ እስክንድር እና ባለቤቱ ሰርካለም በዘ-ህወሀት የተዘጉ ጋዜጦችን ማለትም ኢትዮጲስ፣ አስኳል፣ ሳተናው እና ምኒልክን ጨምሮ የተለያዩ ጋዜጦችን እያቋቋሙ መስራት ጀምረው ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 በዘ-ህወሀት በቁጥጥር ስር ውሎ ወደማጎሪያው እስር ቤት እስከገባበት ጊዜ  ድረስ እስክንድር እረፍትየለሽ በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ዘንድ ሰፊ አንባቢ ያለው ጦማሪ ነበር፡፡ ዘ-ህወሀትን በተለይም አሁን በህይወት የሌለውን መሪውን አምባገነኑን መለስ ዜናዊን ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ መጠቀምን፣ ሙስና እና የመልካም አስተዳደር እጦት ጉዳዮች ላይ ግንባሩን ሳያጥፍ ፊት ለፊት ይታገል ነበር፡፡ ዘ-ህወሀት እስክንድር ነጋን ለመቁጠር በሚያዳግት ለበርካታ ጊዚያት በሸፍጥ ውንጀላ ክስ እየመሰረተ በማጎሪያው እስር ቤት ሲያስረው ቆይቷል፡፡

ዘ-ህወሀት እስክንድርን እ.ኤ.አ በ2011 አሸባሪነት የሚል የሸፍጥ ክስ በመመስረት ወደ ማጎሪያው እስር ቤት ዘብጥያ ወረወረው፡፡ የእርሱ ወንጀል ሆኖ የተቆጠረው፣

1ኛ) በፕሬስ ነጻነት ላይ ጭቆና እያራመደ ያለውን ዘ-ህወሀትን መተቸቱ፣

2ኛ) ዜጠኞች በጅምላ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እየተደረጉ ወደ ዘብጥያ መጣልን በመቃወሙ፣

3ኛ) የዓረብ የጸደይ አብዮት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረውን እንደምታ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማወያየቱ ነበር፡፡

ዘ-ህወሀት እስክንድር የአሸባሪ ቡድን አባል ነው፣ ለውጭ ኃይሎች ሰላይ ነው፣ እናም በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የአሸባሪዎች ጥቃት ለማሳለጥ የተዘጋጀ አሸባሪ ነው በማለት በእስክንድር ላይ ስም የማጥፋት እና የማጠልሸት ያልተሳካ የፕሮፓጋንዳ ሙከራ ዘመቻውን ለማሳየት ሞከረ፡፡

አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በግል በእስክንድር ላይ ከፍተኛ የሆነ ጥላቻ እንደነበረው ታማዕኒነት ያላቸው መረጃዎች አሉኝ፡፡ መለስ እስክንድር እንደሚያደርገው በተስፋ የተሞላ ንግግር ዓይነት ማድረጉን አይደግፍም፡፡

እስክንድር ለአምባገነኑ ለመለስ ቅንጣት የምታህል ፍርሀት አያሳይም፡፡ እስክንድር ስለመለስ የፈለገውን ያህል የሚመጣ ነገር ቢኖርም ባይኖርም በእራስ መተማመን ስሜት ይናገራል፡፡

አምባገነኑ መለስ እስክንድርን ይጠላዋል ምክንያቱም ይፈራዋል፡፡ አምባገነኑ መለስ የእስክንድርን ብዕር ይፈራዋል ምክንያቱም የእስክንድር ብዕር በመለስ ላይ ያለውን ያልተቀባባውን ደረቅ እውነታ መዞ ያወጣልና፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በርካታ ነገሮችን መከላከል ይችላል፡፡ ሆኖም ግን እውነትን መከላከል ፈጥሞ አይችልም፡፡

እ.ኤ.አ በመስከረም 2010 እስክንድር እና ሰርካለም የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለሆኑት ለሊ ቦሊንገር ደብዳቤ በመጻፍ ስለአምባገነኑ መለስ ያለውን እውነታ ተናግረዋል፡፡ በዚያ ደብዳቤ እስክንድር እና ሰርካለም አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በእነርሱ ላይ በግል እና በፕሬስ ነጻነት ላይ የሰራቸውን ወንጀሎች በሙሉ ዘርዝረው አቅርበዋል፡፡ ለአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ጥሪ እንዳይደረግለት እንዲህ የሚል ተመጽዕኖ አቅርበዋል፣ “በሀገሩ የመናገር ነጻነትን በትጋት የሚደፈጥጥ መሪ የእራሱን ሀሳብ በክብር ለመግለጽ በነሐሴ ወር በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሚደረገውን ጉባኤ በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡“

እ.ኤ.አ መጋቢት 2011 “ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ” በሚል ርዕስ እስክንድር ለአምባገነኑ መለስ እውነታውን እስከ ጥርሱ ድረስ ነግሮታል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አምባገነኑ መለስ ምናልባትም ስሙን መለስ ከሀዲው በሚል በመቀየር ባታላይነቱ እና በከሀዲነቱ ለበርካታዎቹ ለዘ-ህወሀት ለታገሉ እና ለሞቱ ጓደኞቹ እንዲህ የሚል የነብይነት ከሀዲ ዕጣ ፈንታውን በትክክል ይገልጻል፡

“ማናቸውም መሪዎች [ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ ወታደራዊው ጠንካራው መንግስቱ ኃይለማርያም እናም ሌሎችም የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች] ኢትዮጵያዊ ወይም ደግሞ አሜሪካዊም ቢሆኑ መለስ ዜናዊ እንዳደረገው ሁሉ በንዴት የሚጦፉ እና ስሜታዊነት የሚያጠቃቸው እና የጓደኝነት ምግባራቸውን ሊመለስ በማይችል መልኩ ሊያቋርጡ ይችላሉ፡፡ በመለስ ዜናዊ እና በስዬ አብረሃእንዲሁም በሌሎች መካከል የጠፋው ጓደኝነት በጣም አስቸጋሪ በሆነው ጊዜ ለሶስት አስርት ዓመታት ዘልቋል፡፡ አዲስ ጓደኞች በጠፉት በሌሎች የሚሸፈነውን ክፍተት ሊሞሉ አይችሉም፡፡ ሆኖም ግን አውሪያዊ ስሜታዊነት እና ከብቸኝነት ሊመጣ የሚችለው ባህሪ ግን ትንሹ የመለስ መገለጫ ነው፡፡“

በዚያ አንቀጽ ላይ የሰፈረው እውነታ የመለስን ውስጣዊ ባህሪ እንዴት እንደሚነጣጥለው ማሰብ እችላለሁ፡፡ አምባገነኑ መለስ በቅርብ ጓደኞቹ እና በወታደራዊ ጓደኞቹ ላይ ያደረገውን ነገር የሚያውቅ እና ጸጸትም የሚሰማው ነው ይባላል፡፡ (መለስ ለተፈጸመ ስቃይ እና መከራ ምንም ዓይነት ጸጸት እና ርህራሄ አለው ብዬ አላምንም፡፡) ሆኖም ግን ጸጸት እና ርህራሄ የሚኖረው ቢሆን እንኳን እንዲህ የሚለውን የሸክስፒርን ጥልቅ የግጥም ስሜት የሚያስብ ከሆነ በጣም የሚገርመኝ ይሆናል፡ “…እራሴን አከበርኩ እናም ለዕጣ ፈንታዬ ቃል ገባሁ፣/በተስፋ አንዱ ዋና ከበርቴ ለመሆን፣/ እንደ እርሱ ለመሆን፣ እርሱ እንዳሉት ጓደኞች ለመሆን…“ አምባገነኑ መለስ ጠላት እንጅ ጓደኞች አልነበሩትም፡፡

በዚያው ደብዳቤ ላይ እስክንድር ለአምባገነኑ መለስ ወደፊት ማለቱን ትቶ ስልጣኑን እንዲለቅ እንዲህ በማለት ነግሮታል፡

“አቶ መለስ ዜናዊ፡ አንተ ከስልጣንህ እንድትወርድ እና ቢሮህን እንድትለቅ ሕዝቡ ይፈልጋል፣ ሕዝቡ አንተን አይፈልግም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህንን ደብዳቤ እየጻፍኩ ባለበት ጊዜ ህዝቡ በሰሜን አፍሪካ እየተፈጸመ ያለውን ክስተት በቅርበት በመመልከት ላይ ነው፡፡ ሕዝቡ በአፍሪካ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሚኖሩት እንደምታዎች ላይ በመከራከር ላይ ይገኛል፡፡ እናም በተራዎቹ ሊቢያውን ጀግንነት ላይ በመደመም ላይ ይገኛሉ፡፡ ጊዜው ከመምሸቱ በፊት ሕዝቡን አዳምጥ፡፡“

እ.ኤ.አ ሐምሌ 2011 የጭቆና አገዛዝ ወደ ታሪክ ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ይጣላል፣ እናም ዴሞክራሲ በዘ-ህወሀት አመድ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያብባል በማለት እስክንድር ለመለስ እንዲህ ሲል በአጽንኦ ነግሮታል፡

“ዴሞክራሲ የሰው ልጆች ሁሉ የጋራ ዕጣፈንታ ነው፡፡ ኤስኪሞ ወይም ደግሞ ዙሉ፣ ክርሰቲያን ወይም ሙስሊም፣ ነጭ ወይም ጥቁር፣ የሰለጠነ ወይም በማደግ ላይ ያለ ብትሆንም እንኳ ልታስወግደው አትችልም፡፡ በእርግጠኝነት ይኸ ጉዳይ ዓለም አቀፋዊ ክስተት ነው፡፡ እናም ከረዥም ጉዞ በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ትግል እውን ለመሆን በማዕዘኑ አካባቢ በመዞር ላይ ይገኛል፡፡ ሁላችንም በዚያ አካባቢ ነን፡፡ ነጻ እንሆናለን!“

እ.ኤ.አ ነሐሴ 2011 ነገሮች ሁሉ አሁን ባሉበት ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነ መለስ የጋዳፊን ዓይነት አስፈሪ ዕጣ ፈንታ እንደሚገጥመው እንዲህ በማለት አስጠንቅቆት ነበር፡

“የአፍሪካን ግዙፍ አምባገነናዊ አገዛዝ የሚመራው የኢትዮጵያው መለስ ዜናዊ በርካታዎቹ እንደሚጠረጥሩት በመጀመሪያ ጋዳፊ እንዳደረገው ስሌት በመስራት ጽኑ ማስታወሻ ይይዛል…እናም የዓረቡ ዓለም ታላቋ አምባገነን ግብጽ በሙባረክ የአገዛዝ ዘመን እንደሆነችው የጸደይ አብዮት ወርቃማ ሽልማት እንደሆነችው ሁሉ የሰብ ሰሀራ ታላቋ አምባገነን ኢትዮጵያም በተመሳሳይ መልኩ የአፍሪካ የጸደይ አብዮት ሽልማት ትሆናለች፡፡ ካለግብጽ የዓረቡ ዓለም የጸደይ አብዮት ሊኖር አይችልም ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ከኢትዮጵያ ውጭ የአፍሪካ የጸደይ አብዮት ሊኖር አይችልም፡፡“

እስክንድር እ.ኤ.አ መስከረም 2/2011 አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ለሰላማዊ የለውጥ ሽግግር እንቅፋት እንዳይሆን እንዲህ በማለት መክሮት ነበር፡

“ለበርካታ ዘመናት ሰላማዊ ሽግግር ባለመኖሩ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ውድቀት፣ ምናልባትም አደገኛ የሆነ የኃይል እርምጃ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ማለት የተፈለገው የነበረው ሁኔታ በነበረበት መልኩ ሊቀጥል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በኢትዮጵያ ሰላማዊ እና ሕጋዊ የለውጥ እርምጃ ለማድረግ ጥሪ የሚደረግበት ጊዜ ደርሷል፡፡ ታሪክ ላልተወሰነ ጊዜ ሊተላለፍ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም፡፡“

እ.ኤ.አ መስከረም 14/2011 እስክንድር በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

እ.ኤ.አ ሐምሌ 13/2012 እስክንድር በዘ-ህወሀት የይስሙላ የዝንጀሮው ፍርድ ቤት የ18 ዓመታት እስራት ተበየነበት፡፡

ዘ-ህወሀት በእስክንድር ላይ የአሸባሪነት ወንጀል ማስረጃ ይሆነኛል ብሎ ያቀረበው በጥራት ያልተቀዳ በአንድ በከተማ አዳራሽ ለተሰበሰበሰ ሕዝብ የዓረቡ የጸደይ አብዮት በኢትዮጵያ ላይ ስለሚኖረው እንደምታ በሚል ርዕስ እስክንድር ያቀረበውን ንግግር ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ነሐሴ 20/2012 አምባገነኑ መለስ መሞቱ ይፋ ሆነ፡፡

የኢትዮጵያ ሳቴላይት ቴሌቪዥን እ.ኤ.አ ሐምሌ 20/2012 (እ.ኢ.አ ደግሞ ሐምሌ 13 ቀን 2004) አምባገነኑ መለስመሞቱን ይፋ አደረገ፡፡

ቅዱሳን ጽሑፎች አምላክ “ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ” ስራውን ይሰራል ይላሉ፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እስክንድርን የሚጠላው በሚያሳየው ድፍረት፣ ፍርሀትየለሽነት እና ባለው ጽናት ምክንያት ብቻ ኤደለም፡፡ ሆኖም ግን መለስ በእስክንድር ምሁራዊ ክህሎት ላይ ቅናት ያድርበት እንደነበር ጭምር ያሉኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ባለፉት አስር ዓመታት በተደጋጋሚ ስናገረው እንደቆየሁት መለስ የእራሱን ልዩ ክህሎት ተጠቅሞ እና የነገሮችን ውልመሰረት አጢኖ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶችን ማሳመን የሚችል ጎበዝ አፈ ምላጭ የውሸት ምሁር ነው፡፡ መለስ ፍሬከርስኪ ስለሆኑ እና ምንም ዓይነት እርባና ስለሌላቸው ነገሮች ብዙ የማውራት ተሰጥኦ የነበረው አጭበርበሪ ከመሆን የዘለለ ሰው አልነበረም፡፡ የቀድሞው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩትን ዶናልድ ያማማቶን እንዲህ በማለት በዊኪሊክስ በተለቀቀው መልዕክት የተታለሉ መሆናቸው ግልጽ ሆኗል፣ “በበርካታ አጋጣሚዎች መለስ ዝርዝር የሆኑ ምላሾችን በመስጠት ስለአንድ ጉዳይ አሳሳቢ ሁኔታ ያለባቸውን ቡድኖች በአንድ መስመር ላይ የማሰለፍ ችሎታ እንዳለው ተመልክተናል፡፡“ ቡድኖችን በአንድ መስመር ማሰለፍ እና በቀላሉ የሚሞኙ የምዕራብ ሀገሮች ዲፕሎማቶችን ማቅረብ የመለስ ዋናው ድብቅ ሚስጥር ነው፡፡ መለስን በሚገባ ለሚያውቁ የለየለት አታላይ መሆኑን በውል ይገነዘባሉ፡፡ እስክንድርም ይህንን ነገር አሳምሮ ያውቃል፡፡ መለስ እንደሚበሳጭ የውኃ ተርብ ዓይነት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ይቆጣል፣ ወዲያው ወዲያው በፍጥነት ይተነፍሳል እናም በላይ ያሉት የአካል ክፍሎቹ ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፡፡ ሆኖም ግን ከተቃዋሚዎቹ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ በመከራከር እና በመወያየት ተግባራት ላይ አይሰማራም፡፡

ለመሆኑ እስክንድር ነጋ ማን ነው?

እስክንድር ነጋን ለመግለጽ ቀላል እና እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ እስክንድር የኢትዮጵያ ታዋቂ ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ እስረኛ ነው፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2013 አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እስክንድር ነጋ “የህሊና እስረኛ” ነው የሚል መግለጫ አውጥቷል፡፡ የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ በተመሳሳይ መልኩ እስክንድር የህሊና እስረኛ ለመሆኑ እውቅና ሰጥቷል፡፡ ሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የፕሬስ ድርጅቶች ተመሳሳይ የሆኑ መግለጫዎችን አውጥተዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ እስክንድር በጽናት፣ በምክንያታዊነት እና የፕሬስ ነጻነትን በመከላክል ረገድ በርካታ የሆኑ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ሽልማቶችን አሸናፊ ነው፡፡

እስክንድር ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ሁሉ እና ሌላም ተጨማሪ ነገር ነው፡፡

እስክንድር ነጋ ለእኔ ልዩ ጀግናዬ የሆነው በርካታ ጽሑፎች መጻፍ በመጀመሩ፣ የፕሬስ ነጻነትን ለማስከበር ፍርሀት የለሽ በመሆኑ፣ ወይም ደግሞ ለእርሱ የሚገባውን ዓለም አቀፍ ክብር እና ዝናን በመጎናጸፉ ምክንያት አይደለም፡፡

እስክንድር ለእኔ ልዩ ጀግናዬ ነው ምክንይቱም የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘ የነጻነት ታጋይ ነው፡፡ ለመታገል ግን ጠብመንጃ፣ ቢላዋዎችን ወይም ሽብርን አይዝም፡፡

የእርሱ ምርጡ መሳሪያዎቹ ቁራጭ እርሳስ ወይም ደግሞ ብዕር ናቸው፡፡ የእርሱ ብዕር  እውነትን ዘክዝኮ በመትፋት ዘ-ህወሀትን ሽባ የሚያደርግ እና ግራ የሚያጋባ ክስተትን መፍጠር ነው፡፡ የእርሱ ሀሳቦች ተፈጥሯዊ ኃይል አላቸው፡፡

እስክንድር ውሸትን፣ ሙስናን፣ ከሕግ አግባብ ውጭ ስልጣንን መጠቀምን እና ሕገወጥነትን በእውነት ጎራዴ በመጠቀም የሚመትር ጀግና ነው፡፡

ብዕርን ብቻ በመታጠቅ እስክንድር ጨለምተኝነትን በተስፋ፣ ፍርሀትን በድፍረት፣ ቁጣን በምክንያታዊነት፣ እብሪትን በትህትና፣ ድንቁርናን በእውቀት፣ አለመቻቻልን በትዕግስት፣ ጭቆናን በጽናት፣ ጥርጣሬን በእምነት እና ጥላቻን በፍቅር ይዋጋል፡፡

ሆኖም ግን እስክንድር በብዕር ከመዋጋትም በላይ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ እስክንድር የደፋርነት ንጉስ ነው፡፡ እስክንድር በቀልተኛ የሆኑትን የዘ-ህወሀት አውሬ ዓይኖች ከተመለከተ በኋላ እንዲህ አለ፡

“ለስምንተኛ ጊዜ በቁጥጥር ስር ልታውሉኝ እና ልታስሩኝ ትችላላችሁ፡፡ ልትደበድቡኝ፣ ልታሰቃዩኝ እና ከሌላው እስረኛ ለብቻ ነጥላችሁ ልታስሩኝ ትችላላችሁ፡፡ መከራ ልታደርሱብኝ እና የሸፍጥ ክስ በመመስረት በተንዛዛ ቀጠሮ እያመላለሳችሁ ፍዳ ልታሳዩኝ ትችላላችሁ፡፡ በሚከረፋው የማጎሪያ እስር ቤታችሁ በረሀብ እንድቀጣ እና የሕክምና አገልግሎት እንዳጣ ልታደርጉ ትችላላችሁ፡፡ ስሜን ልታጠፉ እና ባሕሪዬን ጠላሸት ለመቀባት ትችላላችሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ባለቤቴን ልታዋርዷት እና የእናንተ ወሮበሎች በእኔ ላይ የሚያደርሱትን በደል እየተመለከተ ልጄ እንባ አውጥቶ ሲያለቅስ እናንተ ልትስቁ ትችላላችሁ፡፡ እኔን እና ቤተሰቤን ልታስፈራሩ፣ ልታሸማቅቁ እና ለእኛ ህይወት በመሬት ላይ ገሀነም እንድትሆን ልታደርጉ ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም ግን ለእናንተ የጭቆና አገዛዝ፣ ለእናንተ የበከተ ሙስና፣ ለእናንተ የጭካኔ ፌሽታ፣ ለእናንተ አረመኒያዊ ድርጊት እና እንስሳዊ ኋላቀርነት ባህሪ በፍጹም በፍጹም በፍጹም አላጎበድድም፡፡ እስክንድር ነጋ እንደመሆኔ መጠን የእራሴ ዕጣ ፈንታ አዛዥ እና የህይወቴ መርከብ ነጂ/ካፒቴን ሌላ ማንም ሳይሆን እኔው እራሴ ነኝ!“

ከእስክንድር ነጋ እና ከእርሱ ባለቤት ከሰርካለም ፋሲል የበለጠ የማከብራቸው፣ የማደንቃቸው እና የማወድሳቸው በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡ እነርሱን ለማክበር የምስጋና ደብዳቤ ጽፊያለሁ፡፡ እስክንድር፣ ሰርካለም እና ልጃቸው ናፍቆት (ቀኑ ሳይደርስ በእስር ቤት የተወለደ እና በአረመኔው በቀልተኛ በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የህይወት ማዳኛ ኢንኩቤተር የተከለከለው) ናቸው፡፡

እኔ ማድረግ የምችለው ቢሆን ኖሮ እነዚህን የተከበሩ እንቁዎች የሌላ የማንም ሀገር ወይም ደግሞ ተቋም የእኔ ናቸው ብሎ እንዳይጠይቅ ለማድረግ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ እሴቶች ናቸው በማለት አውጅ ነበር፡፡ በዚያ ጉዳይ ላይ ሌላ ምርጫ አይሰጣቸውም!

እስክንድርን የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ተሟጋች አድርጌ ለመናገር አልፈልግም፡፡ ከእኔ ይልቅ ስለዚህ ሁኔታ የበለጠ ግልጽ በሆነ መልኩ ሊናገሩ የሚችሉ በርካታዎቹ አሉ፡፡

እስክንድር በዓለም ሁሉ ካሉ የፕሬስ ነጻነት ጀግናዎች ሁሉ ጀግና ነው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ሰላማዊ አመጸኛ ጋዜጠኞች ሁሉ ስለእርሱ ተናግረዋል፣ በአስቸኳይ ከእስር ቤት እንዲለቀቅም ጠይቀዋል፡፡ ከበርካታዎቹ ጥቂቶቹ የሚከተሉትን ያካትታል፣ ኬኔት ቤስት ከላይቤሪያ፣ ሊዲያ ካቾ ከሜክሲኮ፣ ጁአን ፓብሎ ካርዲናስ ከችሌ፣ ሜይ ችዲያክ ከሊባኖስ፣ ሰር ሀሮልድ ኢቫንስ ከዩናይትድ ኪንግደም፣ አክባር ጋንጂ ከኢራን፣ አሚራ ሀስ ከእስራኤል፣ ዳውድ ክታብ ከዮርዳኖስ፣ ግዌን ሊስተር ከናሚቢያ፣ ሬይሞንድ ሎው ከደቡብ አፍሪካ፣ ቬራን ማቲክ ከሰርቢያ፣ አዳም ሚችንክ ከፖላንድ፣ ፍሬድ ሜምቤ ከዛምቢያ፣ ኒዛር ኔዩፍ ከሶርያ፣ ፓፕ ሳይኔ ከጋምቢያ፣ ፋራጅ ሳርኮሂ ከኢራን፣ ኔዲም ሴነር ከቱርክ፣ አሩን ሻውሬ ከሕንድ፣ ሪካርዶ ኡሴዳ ከፔሩ፣ ጆሴ ሩቤን ዛሞራ ከጓቲማላ ናቸው፡፡ ሌሎች የሰብአዊ መብቶች እና የፕሬስ ድርጅት መሪዎች ደግሞ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡ ማርክ ሀምሪክ የናሽናል ፕሬስ ክለብ ፕሬዚዳንት ከዋሺንግተን ዲ.ሲ፣ አርየህ ኔይር የኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽንስ ፕሬዚዳንት፣ ኬኔዝ ሮት የሂዩማን ራይተስ ዎች ዋና ዳይሬክተር፣ ጆኤል ሲሞን የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ ዋና ዳይሬክተር፣ ዊሊያም ኢስተርሊ በኒዮርክ ዩኒቨርሲሰቲ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡

እስክንድር ነጋ፡ አይዞህ ብቻህን አይደለህም!

እስክንድር ነጋ ያልተረሳ መሆኑን እንዲያውቅ እፈልጋለሁ፡፡ ሰርካለም እና ናፍቆት እስክንድር በፍጹም የማይረሳ መሆኑን እንዲያውቁት እፈልጋለሁ፡፡ ለክብራችን እና ለነጻነታችን ሲል ከዘ-ህወሀት ግንባር ለግንባር ገጥሞ እየተፋለመልን ያለውን እንቁ ጀግና እንደምን ልንረሳው እንችላለን?

በአሁኑ ጊዜ የዓለም ሕዝብ በኢትዮጵያ በማጎሪያው እስር ቤት ውስጥ እየማቀቁ ያሉትን እስክንድር ነጋን እና ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች እንዲያስታውስ እፈልጋለሁ፡፡

እስከንድር ነጋን እናስታውሳለን፣ ሁልጊዜ፡፡ እስክንድር ነጋን እናደንቃለን፣ እናከብራለን፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ አስደናቂ እና አፍቃሪ ባል እና አባት በመሆኑ እስክንድር ነጋን እንወደዋለን፡፡

ከሁሉም በላይ እስክንድር ነጋ የኩሩዋ ኢትዮጵያ ልጅ በመሆኑ እናከብረዋለን፣ እናስታውሰዋለን፡፡

የሚካኤል ጃክሰንን የግጥም ስንኞች ትንሽ ለወጥ በማድረግ እኛ የእስክንድር ነጋ ወንድሞች እና አህቶች ስለእርሱ ምን እንደሚሰማን ያለንን ስሜት እንዲህ በማለት ለመግለጽ እንወዳለን፡

…

ብቸኛ አይደለህም አለን ከጎንህ፣

ሌት ከቀን በማሰብ የምንሳሳልህ፣

ስለውሎ አዳርህ ጤናና ምግብህ፣

ስለጥልቅ ሀሳብህ የሕዝብ ፍቅርህ፡፡

 

አንተ ለኛ ብለህ፣

ባፋኞች ተወግረህ፣

ስቃይ ተሸክመህ፣

ከደስታ ርቀህ፣

ባጥር ተከልለህ፣

በሸፍጥ ተይዘህ፡፡

 

ብትኖር በስቃይ፣

ሁሉን ነገር ሳታይ፣

ቢደረመስ ሰማይ፣

ወይ ንቅንቅ ካላማህ ነጻነትን ሳታይ፡፡

 

በአካል ሩቅ ሆነን ካንተ ጋር ባንሆንም፣

የስቃይ ተጋሪህ ጓደኞች ባንሆንም፣

እኔ ልተካልህ የማንል ብንሆንም፣

በመንፈስ አንድ ነን ልዩነት የለንም፣

ብቸኛ ነኝ ብለህ ፍጹም እንዳትቆዝም፣

በጀግናው ጽናትህ ከቶ አንረሳህም፡፡

 

ፍቅርህ ቤቱን ሰርቶ በልባችን ውስጥ፣

ሌት ቀን እንድንተጋ ለወሳኙ ለውጥ፣

ለሕዝቦች አርነት ለእድገት መሳለጥ፡፡

 

አንደበተ ርትኡ የጠላት መጋኛ፣

የሕገወጥነት ታጋይ አመጸኛ፣

የዘር ናፋቂነት የአድልኦ ቀበኛ፣

ሙስናን ተዋጊ ተፋላሚ ዳኛ፣

የፍትህ መሀንዲስ የጠራ እውነተኛ

ፍትህ ሳያሰፍን ከቶ የማይተኛ፣

ብቸኛ አይደለህም ከጎንህ ነን እኛ::

 

አረመኔ ስርዓት በሸፍጥ ተነስቶ፣

በዘር በኃይማኖት ልዩነት መስርቶ፣

ጥላቻና በቀል በሀገር አስፋፍቶ፣

ነጻነትን ገፎ ፍቅርን አጥፍቶ፣

የሀገሪቱን ሕዝብ ረግጦ አደህይቶ፣

ጉልብትና ኃይሉን ሸፍጡን ተመክቶ፣

ለመጥፎው ድርጊቱ ህይወቱን ሰውቶ፣

በኢትዮጵያ ላይ አይቀር እንዲህ ተንሰራፍቶ፡፡

እኔ እስክንድር ነጋ ነኝ! 

አይበገሬው እስክንድር ነጋ! 

እስክንድር ነጋ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሁሉም የፖለቲካ አስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ!!!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ሚያዝያ 18 ቀን 2008 ዓ.ም 

↧

በኦሮሚያ ተከስቶ የነበረውን ሕዝባዊ ቁጣ ተከትሎ በነበቀለ ገርባ ላይ የተመሰረተውን ባለ 23 ገጽ የክስ ቻርጅ ይዘናል

$
0
0

bekele Gerba OFC
(ዘ-ሐበሻ) አቶ በቀለ ገርባን በ4ኛ ተከሳሽነት ያስቀመጠው አቃቤ ህግ እርሳቸውን ጨምሮ በ22 ሰዎች ላይ የሽብርተኝነት ክስ መስርቷል:: በአንደኛ ተከሳሽ ጉርሜሳ አያኖ ክስ መዝገብ የተከፈተው ይኸው የሽብርተኝነት ክስ በኦሮሚያ ከተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ጋር ተያይዟል:: “የኦሮሚያን ሕዝብ ነፃ ለማውጣት የኦሮሞ ሕዝብ አመጹን ከዳር እስከዳር እንዲያነሳ በማድረግ መንግስትን ከስልጣኑ ማውረድ አለብን በሚል ቅስቀሳና የማነሳሳት ተግባር በመፈጸምና በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ረብሻ እና አመጽ እንዲስፋፋ አድርገዋል” በሚል አንደኛ ተከሳሹ አቶ ጉርሜሳ አያኔ ክስ ተመስርቶባቸዋል::

በአብዛኞቹ ተከሳሾች ላይ ቀኑና ወሩ ያልታወቀ ቀን ወንጀል ሰርተዋል የሚሉ ክሶች መቅረባቸው እያነጋገረ ሲሆን እንዴት ቀኑና ወሩ ባልታወቀበት ቀን ተፈጸመ ለተባለ ድርጊት ተጠያቂ ይሆናሉ? የሚለው የሕግ ምላሽ ያስፈልገዋል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ::

2ኛ ተከሳሹ አቶ ደጀኔ ጣፋ “ቀኑ ባልታወቀ ከጥቅምት 2008 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ቡራዩ ከተማ ላይ የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ ማስተር ፕላን እና የኦሮሚያ ከተሞች የ ዕድገት ፕላን የኦሮሚያን ሕዝብ ቋንቋ; ባህል የሚያጠፋና የኦሮሚያን ሕዝብ ከመሬቱ የሚያፈናቅል በመሆኑ ማስተር ፕላኑ እና የኦሮሚያ ከተሞች እድገት ፕላን ከመጽደቁ በፊት በተለያዩ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን በማነሳሳት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ; በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ከተሞች እና ቀበሌሎች ውስጥ ተማሪዎች ትምህርት ቤት እንዳትማሩ; አስተማሪዎች እንዳያስተምሩ; የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖርና ለኦሮሞ ሚድያ ኔትወርክ መረጃ በመስጠት” የሚል ክስ ቀርቦበታል::

3ኛ ተከሳሽ አዲሱ ቡላላ “ቀኑ እና ወሩ በውል ተለይቶ ባልታወቀ 2007 ዓ.ም ከኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ኃላፊ ጃዋር መሃመድ ጋር በኤሌክትሮኒክስ ሚድያዎች በመገናኘት እና ገንዘብ እንዲላክለት በማድረግ በ2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ እና አዲስ አበባ ዙሪያ የተቀናጀ ማስተር ፕላንን እንደ ሽፋን በመጠቀም በክልሉ የተቀሰቀሰውን የሽብር አመጽ ያስተባበርና የመሩ የሽብር ቡድኑን አባሎች በህግ እንዳይጠየቁ ለማድረግ ሲንቀሳቀስ የነበርና ለኢሳት ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ እና ለጃዋር መሐመድ ሪፖርት አድርጓል” የሚል ክስ ቀርቦበታል::

በአቶ በቀለ ገርባና በሌሎቹ ላይ የቀረበውን የክሥ ዝርዝር እዚህ ጋር ተጭነው ያንብቡት:

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live




Latest Images