Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ESAT Special Program Vision Ethiopia & ESAT Conference – Part 5

$
0
0
ESAT Special Program Vision Ethiopia & ESAT Conference – Part 5

These runners from Ethiopia take inspiration from Boston Marathon’s defending champion

$
0
0
PRI They’re both 18, both high-school seniors in Massachusetts, both headed into their final season on the track team competing in the mile and two-mile. If you see one running, you’ll probably see the other. Daniel Aschale and Esu Alemseged met in middle school when they were both recent immigrants from Ethiopia, learning English and […]

Drought threatens Canadian-backed development gains in Ethiopia

$
0
0
MICHELLE ZILIO OTTAWA — The Globe and Mail Aid groups say millions of dollars’ worth of Canadian development advances in Ethiopia are at risk as the East African country deals with its worst drought in 30 years, leaving more than 10 million people in need of food assistance. Ethiopia is a country of focus for […]

Israelis To Build Condominiums And Industrial Parks In Ethiopia

$
0
0
Ethiopia approaches Israeli Real Estate entrepreneurs: “Come to build our condominiums and Industrial Parks”. By Jewish Business News Ethiopia calls Israeli investors to take part in the Ethiopian governmental scheme for the next 5 years, where 2.4 million new apartments will be built, out of which 900,000 units in the capital, Addis Ababa. In addition, […]

Hijab for Aanolee, Please! – Melaku Girma

$
0
0
The ‘Trojan Horse’ is from a Greek mythology where the Greeks in their last resort to break into the well-guarded city of Troy, came up with an idea of a horse like statue. As the deceitful statue, hid with soldiers, was entering the city, there were Troy residents who suspected trickery insisting that the gift […]

Ethiopia on the brink as drought bites

$
0
0
Ethiopia is currently dealing with the worst drought in the region in decades. Lives and livelihoods are at stake, as Sophie Cousins reports from Belaya district. Fighting back tears in her mud house in rural Ethiopia, a young woman’s son grabs her breast in hope of finding some milk to drink. But there is none. […]

Health: 9 Liver Detox Super Stars

$
0
0
(Zehabesha Health Info.) Written by: Steve Fillmore When you hear of liver detoxing, you may think that you are going to have to go on some sort of expensive juice fast or use some unknown herbal magic formula from ancient China. But that is not necessarily the case. Truthfully, those methods can be expensive and time consuming. […]

Ethiopia: Armed Group Kills More Than 140 Near South Sudan | AP

$
0
0
By ELIAS MESERET, ASSOCIATED PRESS An Ethiopian official says that armed groups have killed more than 140 civilians near Ethiopia’s border with South Sudan. The attackers came from South Sudan and killed civilians, including women and children, Getachew Reda, Ethiopia’s communications minister, told the Associated Press on Saturday. “The Ethiopian defense force is currently chasing after the […]

ጸ በቃን!

$
0
0

ስሞኑን ለአንድ ጉዳይ ዳውን ታዎን ደርሼ ስመለስ የባህል ምግብ መአዛው ናፍቆኝ ከአንድ የኢትዮጵያኖች ቅመማ ቅመም መሸጪያ ቤት ጎራ አልኩኝ፡፡የምሸምተውን ሸምቼ ከሱቁ ስውጣ አንድ ጎለማሳ ሰው አቆመኝና ጃማካዊ ነህ ብሎ ጠየቀኝ፡፡አይደለሁም አልኩት፡፡ ቀጠለና ኤርትራዊ፣ሩዋንዳዊ…ኢትዮጵያዊ የሚለው ጋር ሲደርስ፣ መሆኔን አረጋገጥኩለት፡፡ለካስ ሰውዬው የሀገር ልጅ ኖሮ፣ ቋንቋ ቀይረን ስለሀገር ቤት ሁኔታ ማውራት ቀጠልን፡፡

Tse Bekan

የሚያጨሰውን ሲጋራ እንደጨረሰ፡፡ ሲጋራ ሊያጨስ እንደወጣ እንጂ ከአውራ ጎዳናው ማዶ ያለው የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ውስጥ ቢራ አስከፍቶ እንደመጣ ነግሮኝ ፣ከብዙ ማግባባት በኋላ አንድ ቢራ ሊጋብዘኝ ተስማምቼ ወደ ሬስቶራንቱ አመራን፡፡ መግቢው ላይ አሱ የሚጠጣውን ቢራ እንዲያዝልኝ ነግሬው ወደ መታጠቢያ ቤት ሄድኩ፡፡

ይዞ ይጠብቀኝ የነበረው ቦታ ላይ ተደላድዬ እነደተቀመጥኩ፣ ከቢራው አንድ ሁለት ተጎነጨሁና  ትንፋሽ ወስጄ  ዙሪያ ገባውን ማስተዋል ጀመርኩ፡፡ቡና ቤቱ ውስጥ ያሉ ወንበሮች ሁሉ፣ የባልኮኒዎቹ እንኳን ሳይቀሩ በግማሽ ቅርጽ ተደርድረው ቤቱ አምፊ ቲያትር መስሏል፡፡

ታዳሚዎቹ በእጃቸው የሚጠጣ ነገር ቢይዙም ስብሰባ ላይ እንደሆኑ ያስታውቃል፡፡ አጠገቤ ወደ ነበረው ስው ጠጋ ብዬ ስብሰባው ስለምንድን ነው ብዬ ጠየቅኩት፡፡ “ ፀ በቃን !” ነው ብሎ በኃይለ ቃል መለሰልኝ፡፡ ንግግሩን በቃ ዝም በል እንደ ማለት ነው ብዬ በመውሰድ  ታዳሚዎቹን ማጤን ጀመርኩ፡፡

ከሁለቱ ሰብሳቢዎች  ጎልማሳው የውይቱን ሃሳብ ባህረ መዝገብ ላይ ያሰፍራል፡፡ ሌላኛው ፀጉረ መላጣው ሸበታም ሰውዬ አወያይ ሳይሆን አይቀርም ስብሰባውን ለመምራት ይሞክራል፡፡ ነገር ግን ታዳሚዎቹ ሲናገሩ ተራ አይጠብቁም፤ ድብልቅልቅ ያለ ንግግር ነበር የሚሰማኝ፡፡

“ በቃ ፀ በቃን! ነው የምንለው፡፡” ሽማግለየው ሰውዬ በመኃል ገባና “ፀ ብሎ ፀሓይ ይጻፋል፡፡ እንዴት ነው ፀ በቃን የምንለው? ”

“እኛ ይሄኛውን ፀ አላልንም፡፡ ባለ ሁለት እግሩን ነው የምንለው፡፡” ቤቱ ድምጹን ተቀብሎ አስተጋባ“ ስንት አመት ሙሉ ጺውጺውታ ዘፍን ከፍቶ የእናት ኢትዮጵያን ሆድ መመጥመጥ፣ ከዚያም በክንፎቿ ጥላ ስር እያደሩ አንቺ ዶሮ ነሽ ፤የእኔ እናት እንቁላል ናት ማለት! አረ በቃን! አረ በቃን! ጎተና አውጥቶ እንደ ጫጩት መጮኽ፡፡ ጸ በቃን ይህ ፊደል ከ ፊደል ገበታ ላይ ይሰረዝ!” ንግግሩን ተከትሎ አብዛኞቹ ታዳሚዎች ቤቱን በፉጨትና በጭብጭባ አደበላለቁት፡፡

ሽማግሌው “አረ የለም፣ አረ ሗላ አይሆንም፡፡ሁሉም ፊደሎች የሚወክሉትን ድምጽ ብዛት ይዘው መቀመጥ አለባቸው ፡፡ ጸ ብሎ ጸሎት፣ ጸ ብሎ ጽድቅ አለ እኮ፣ ታዲ እነዚህ ሃሳቦች በምን ፊደል ይገለጹ?” ጉባኤተኛውን ጠየቁ፡፡ድንገት አንዱ ከመሃል ተነስቶ “በቃ እነዚህ ሁለት ፊደላት በ ፊደል ጠ ይተኩ” ብሎ ተቀመጠ፡፡ሌላኛው ደግሞ ተነስቶ“ በቃ እነዚህ ፊደላት ይጥፉ፣ የሚጽፍባቸውም አይገኘ፡፡ ከፊደላቱ ጋር የተነካካ  ሁሉ የተረገመ ይሁን! ” እርግማኑን አወረደው፡፡

ይህን ጊዜ ከጎኑ ከተቀመጠው በኋላ በሹክሽታ ወንድሙ ነው ሲሉ ከሰማሁት ሰው ጋር የሁለቱ ሰዎች ንግግር ከጉባኤተኛው ጩኸት በልጦ እስኪሰማ ድረስ ተጨቃጨቁ፡፡

“ስማ ዱሮ አምስተኛ ክፍል እያለህ በእንግሊዝኛ  “the” ተብሎ የተጻፈውን “ተለሮ” ብለህ በአማርኛ ካነበብክ ጀምረህ ለዚህ ሁሉ ያበቃኝ የኢትዬጵያ ፊደል ነው በማለት ጥላቻ እንዳደረብህ አውቃለው፡፡ ስትናገር ምክነያታዊ ሁን እንጂ በስሜት የምትነዳ አትሁን” አለው ፊደላቱን ረግሞ ለተቀመጠው ሰው፡፡

ጉባኤተኛውም “ተለሮ፣ ተለሮ፣ተለሮ…” እያለ ወንበር ይደበድብ ጀመር፡፡ እኔም ምን አይነቱ ጉባኤ አብዳን ላይ ነው እግር የጣለኝ ብዬ እራሴን ጠየቅኩ፡፡ ሽበታሙ ሰውዬ በመሃል ገባ፡፡ ሰውዬው ሰብሳቢ ሳይሆን ሃሳብ በማቀረጥ አቃቢ ሰዓት እንደሆነ እየተገለጠልኝ መጣ፡፡

“አክሱማውያኑ ከአንድ ሺህ አመታት በፊት ከላይ ከሰሜን ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ፈልሰው በድንጋይ ሐውልታት የጥቁር ህዝብ ታሪክን ሲጽፉ ብዙ አልጮሁም፣ ስራቸው ነው እስካሁን ድረስ ምስክር ሆኖ እየተናገረ ያለው፡፡ አንድ ጊዜ ጨጨብሳ የሚባል ጠፋጭ ምግብ አጋጠማቸውና ከነባሩ ህዝብ ጋር ለመግባባት ጠ ከሚለው ፊደል ጨ ን ፈጠሩ፡፡

ልክ እንደነሱ ከቦታ ቦታ እየዞረ የሚሰፍር ደፋር፤ጀግናና ኩሩ ህዝብ ስላጋጠማቸው በአለም ታሪክ እንደሆነው ሁሉ በነበረው መስተጋብር ቃላት መዋዋስ ሲጀምሩ ጀብደኛ የሚለውን ቃል ለመጻፍ ከፊደል ደ ፊደል ጀ ን ፈጠሩ፡፡ ታሪክን በነባራዊው ሁኔታ በጊዜውና በቦታው ላይ ሆነን በአለማቀፋዊ መስፈርት መመዘን ብቻ ነው መጪውን ጊዜ ብሩህ የሚያደርግልን፡፡ ”የሽማግሌውን ዲስኩር ተከትሎ በቤቱ ውስጥ ለጥቂት ጊዜ ፀጥታ ከሰፈነ በኋላ ሌላ ትርምስ ተነሳ፡፡

“አይገርማችሁም፣ ንጉሱ ሠ የሚባል ፊደል አለ፡፡ የአብሲኒያ ነገስታት ብቻ ናቸው የሚጠቀሙበት፡፡ደግሞ ኃይለመለኮት፣ ኃይለስላሴ ለሚባል መጠሪያቸው ነገስታቱ ንጉሱ ኃ የተባለ ፊደል አስፈጥረው ነበር፡፡ አሁን ሦስት ሀ ፊደላት ምን ይሰራሉ፣ አንድ አይበቃም? ወቼ ጉድ ደርግ መጥቶ ነጻ ባያወጣን ኖሮ እኮ አማርኛ እራሱ የጭሰኛ፣የቀጥቀጭና የፈላጭ ቆራጭ ፊውዳል ሆኖ ሶስት ቦታ ይከፈል ነበር፡፡ ” አለ በደር ጊዜ ከድሬ የነበረው ሻምበል ባሻ፡፡ ከግራ ጥግ በኩል የተነሱት ሁለት ሰዎች ደግሞ ከኛ በፊት የተናገሩት ምሁር እንደገለጹት በማለት የሻምበል ባሻ ሀሳብ ላይ በመመርኮዝ አስተያት አቀረቡ፡፡

የስብሰባው አቅጣጫና ኢሳይንሳዊ አካሄድ መጨረሻ ያሰጋቸው ሽማግሌው ሰው “እሺ እንግዲህ ሰው ሲፈጠር ቃልና ቃልን የሚወክል ፊደል ይዞ አልተፈጠረም፣ የሚናገርበትን አካል ብቻ እንጂ፡፡ የሰው ልጅ ተፈጥሮን አሸንፎ ህይወትን ቀጣይ ለማድረግ ባህልን ፈጠረ፡፡የዚህ ሁሉ ማሳረጊያው ሰውን መግቦ ደህንነቱን በመጠበቅ ድህነትን አሸንፎ ማኖር ነው፡፡ ታዲያ ፤ ድህነትን ፀጥ ጭጭ እናደርጋለን ብለን ለመፎከር ብንፈልግ እንዴት እንጻፈው?” አቃቢ ሰዓቱ ወይም ሰብሳቢው ከሻምበል ባሻ ጀምረው ጉባኤተኛውን በአይናቸው ቃኙ፡፡

ሁለት ሶስተኛው የሚሆነው ተሰብሳቢ ”“ድህነትን ጠጥ ጥጥ እናደርጋለን!” ብሎ ፎከረ፡፡

“ይህማ ድህነትን ጭራሽኑ አስክረን እላያችን ላይ ጣልነው ማለት ነው፡፡” የሽማግሌው የመጨረሻ ቃላቸው ነበር፡፡ ይህን ተናግረው ወደ ሰማይ ይውጡ ወይም ወደ መሬት ይስረጉ ሳይታወቅ ከመድረኩ ላይ ተሰወሩ፡፡ እኔም በቃለ ጉባኤ ጸሐፊ ብቻ የሚመራ ስብሰባ የትም እንደማይደርስ ሰለተረዳሁ ከቡናቤቱ ለመውጣት ወደ ኃለኛው በር አመራሁ፡፡

በሩ ጋር እንደደረስኩ አስተናጋጇ ተከትላኝ መጥታ እጄን ያዝ አድርጋ አቆመችኝ፡፡

እጄን ወደ ኪሴ እየከተትኩ“ሂሳብ ስንት አለብኝ?” አልኳት፡፡

“ቢራውን እኮ የጋበዘህ እሱ ነው፡፡” ጋበዘህ ያለቺኝን ሰውዬ ዞር ብዬ ተመለከትኩት፡፡ ትንሽ ትንሽ መልኩ ትዝ አለኝ ፤የት እንደማውቅው ግን አልከሰትልህ አለኝ፡፡ በጥያቄ አስተያየት መልሼ ተመለከትኩት፡፡ ፈራ ተባ እያለች፣

“ከመታጠቢያ ቤት ተመልሰህ ስትመጣ፣ ተሳስተህ እሱ የቀዳውን ቢራ ነበር የጠጣህው፡፡ዶዲ ደግሞ ሁል ግዜ ምናምን ቢራው ውስጥ ጨምሮ ነው የሚጠጣው” ደህንነቴን በማጠየቅ አመለካከት ዓይኖቿን በመላ አከላቴ ላይ አሯሯጠቻቸው፡፡

“ዶዲ የምትይው ዳዲ ለማለት ፈልገሽ ነው ወይስ… ” አላስጨረሰችኝም፣

“ዶክተር ዲፕሬሽን ወይንም ድብርት ብለን ነው የምንጠራው፡፡ ሩስያ ሃገር ቋንቋ ተምሮ ነበር ሲሉ ሰምቼአለሁ፡፡የድብርት በሽታ ሰላለበት እራሱን ዘና ለማድረግ ቢራው ውስጥ ዕጠ ምናምኑ ይከታል፡፡ ሰውዬው የሚታወቀው ከማንም ወገን የተጠራ  ስብሰባ ላይ በመገኘት ነው፡፡ ለአንድ ሰዓት ያህል ነትርኮሃል እኮ ”

ዶክተር ዶዲን ዞር ብዬ ተመለከትኩት፡፡ መልኩ ቀስ ብሎ መጣልኝ፡፡ ስብሰባው ላይ ቃለ ጉባኤ ያዢው እሱ ነበር፡፡ ልከፍለው የነበርውን ብር ለአስተናጋጁ ሰጥቼ ዕጠ ፋሪስ በቢራ ያስጠጣኝን ዕድሌን ረገምኩ፡፡ ቡናቤቱን ለቅቄ ከመውጣቴ በፊት ዶዲን ለመጨረሻ ጊዜ ተመለከትኩት፡፡ ቦታ ቀይሮ ሶስት ሰዎች መሃል ተቀምጦ ያወራል፤ ምናልባትም ከቀናው ከዚህም ከዚያም የሰበሰበውን  በዕጠፋሪስ ቢራ ያንሾካሽክባቸው ይሆናል፡፡ ዶዲስ ቢሆን ለህመሙ መድሃኒት ያጣ የተሳከረ ዘመን ውጤት አይደል? ቅብብሎሹ ግን ይገርማል፡፡ እኔም ከዕጠፋሪስ ፈረስ ተቀብሎ ቤቴ የሚያደርሰኝን ባቡር ለመያዝ ወደ ሰብዌይ አመራሁ፡፡

ከአስቻለው ከበደ አበበ

ሚያዝያ 8፣ 2008ዓ.ም( April 16,2016)

ካናዳ

የጋምቤላዉ ዘግናኝ ጥቃትና የህወሃት ቸልታ |ከሳዲቅ አህመድ

$
0
0

sadik
ያኔ ወጣቶቹ “ያገር አንበሳ የዉጭ እሬሳ!” በማለት ድምጻቸዉን ሲያሰሙ ዱላና እስር እጣ ፈንታቸዉ ሆኖ ነበር። ለወራት በኦሮሚያ ዉስጥ ንጹሃንን ወገኖቻችንን ሲገድል፣ሲጨፈጭፍ፣ሲያሰቃይና ሲያስር የነበረዉ ጀግና ነኝ ባዩ የህወሃት የአጋዚ ጦር ምነዉ ለጋምቤላ ወገኖቻችን ለመድረስ እጅ ወረደዉ? በዚህ ሒደት ዉስጥ አሸባሪው ህወሃት ለዜጎቹ ደንታ ቢስ መሆንኑንን እንረዳለን። በአንጻሩ አሸባሪው ህወሃት አገርን አተራምሶ ሽብር ከመፍጠር በስተቀር ዜጎችን የመጠበቅ ብቃት የሌልዉ መሆኑን አሳይቷል። አሸባሪዉ ህወሃት የደረሰበትን የፖለቲካ ኪሳራ ለመታደግ ወዲያዉኑ ጋምቤላ ገብቶ “አለሁ አለሁ” ባለ ነበር። ግን እራሱን ከሚገባዉ በላይ እዚህም እዚያም በመወጠሩ ይህንን ማድረግ ተስኖታል። ዜጎችን ከዉጭ አጥቂ መከላከል ባለመቻሉ ስስ ብልቱ ታይቶበታል። ህወሃት ቅልብ ጦሩን ጋምቤላ የሚያሰፍረዉ መሬትን ለመቀራመትና የጋምቤላ ህዝብን ለማሽመድመድ እንጂ የጋምቤላ ህዝብ ሲጠቃ ጥቃቱን ለመመከት አለመሆኑን በሚያሳፍር መልኩ አሳይቷል።ጥያቄዉ በኦሮሚያ የተነሳዉ አይነት ንቅናቄ ዳግም ቢጀመር፣ የሰሜኑ (የጎንደር-የወልቃይት) ንቅናቄ ዳግም ቢጠናከር፣ የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ህዝባዊ እምቢተኝነት ቢገነፍል፣ ኮንሶዉ ዳግም እምቢኝ ማለቱ ቢያገረሻ፣አፋሩም ሶማሌውም ቢጨመር ህወሃት ይህንን መቋቋም ይችላልን? አላህ ለተጠቁት የጋምቤላ ወገኖቻችን ይድረስላቸዉ።

ማኅበረ ቅዱሳንና አራቱ ፈታኞች |ክፍል 2

$
0
0

በተክሉ አባተ (ዶ/ር)

መግቢያ

mahibere-kidusan-logo
በክፍል 1 ጽሑፌ ስለማኅበረ ቅዱሳን (ማቅ) መጻፍ ለምን እንዳስፈለገ፣ ማኅበሩን እንዴት እንዳወቅኩትና ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የማኅበሩን አመሰራረትና ዓላማ በጥቂቱ አቅርቤያለሁ። በዚህ ክፍል ደግሞ ማቅን አብዝተው የሚፈትኑ አካላት እነማን እንደሆኑ በደረጃ ከነምክንያቶቻቸው አቀርባለሁ። ይህ ጽሑፍ በክፍል 1 እንደተጠቀሰው ማቅንም ሆነ ሌላ አካልን ለመቃወምም ሆነ ለመደገፍ የተዘጋጀ አይደለም። ያሉ እውነታዎችን ከግል እይታዬ በመነሳት በትንተና መልክ ለአንባቢ ማስገንዘብ እንጅ። በዚህ ጽሑፍ ምክንያት ሊነሱ የሚችሉ ውይይቶችና ሙግቶች በመጨረሻ የተሻለ ግንዛቤ እንዲመጣ ያደርጋሉ ብዬ አምናለሁ። ለጽሑፎቼ እንደ ግብዓት ያገለገሉኝ የግል ተሞክሮዬ፣ የማቅ ገጸ ድርና እትሞች እንዲሁም ስለማቅ በተለያዩ ሚዲያዎች የተነሱ ዘገባዎች ናቸው።

አራቱ ፈታኞች

ማቅ ከምስረታው ጀምሮ ከተለያዩ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ አካላት የተለያየ ግምት ወይም ተቀብሎ አለው። ማቅ በተለያዩ  አካላት ምን አይነት ግምት እንደሚሰጠው ለመጠቆምና ፈታኞችን ለምን አራት እንዳደረስኳቸው ለማሳየት ያህል እነዚህን አካላት ደጋፊዎች፣ ተቃዋሚዎች፣ ገለልተኞች፣ ተቃደጋፊዎችና ፈታኞች ወይም አሳዳጆች ብዬ ከፋፍያቸዋለሁ። እነዚህ አካላት ለማቅ ያላቸውን ግንዛቤና ግምት በተመለከተ እንደሚከተለው ባጭር ባጭሩ ለመግለጽ ሞክሬያለሁ።

ደጋፊዎች

ደጋፊዎች ማቅ በቤተ ክርስቲያን ስር ታቅፎ ወጣቶችና ምሁራን ሃይማኖታቸውን ከነትውፊቱ ጠንቅቀው አውቀው ለትውልድ እንዲያስተላልፉ የሚጥር ማኅበር እንደሆነ በማመን ሙሉ ድጋፋቸውን ይሰጣሉ። ከቤተ ክህነት ቀጥሎ ለቤተ ክርስቲያን አለሁ ባይ አካል እንደሆነ ያምናሉ። ባጠቃላይ ደጋፊዎች ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ከፍዘትና ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል በሚደረግ ጥረት ማቅ ልዩ ቦታ እንዳለው ስለሚያምኑ በሞራል፣ በዕውቀት፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስና በተቻለው ሁሉ ይራዳሉ። የማቅን ደካማ ጎን ሲያገኙ በመምከርና በመገሰጽ ለማስተካከል ይጥራሉ።

በዚህ ስር ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አብዛኞቹ ሰንበት ትምህርት ቤቶች (በተለይ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ካየለበት ጊዜ ጀምሮ)፣ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ ዘመናዊ ትምህርት የተማረውና የሰው ሕይወት እንጅ የሃይማኖት ትምህርት መታደስ የለበትም ብሎ የሚያምነው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ እንዲሁም ሰፊው ህዝብ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ይጠቀሳሉ። ማቅ በውጭው ዓለምም ቀላል የማይባል ደጋፊ አለው።

ተቃዋሚዎች

በአንጻሩ ደግሞ ተቃዋሚዎች (የፖለቲካ ተቃዋሚዎች አላልኩም!) የማቅን ዓላማ በይፋ ባይቃወሙም በማቅ የአሠራር ሂደት ላይ በመመርኮዝ አብዝተው ይቃወማሉ። ማቅ የሚሠራውን ማናቸውንም ሥራ ማብጠልጠልና ውድቅ ማድረግ ይቀናቸዋል። በመሆኑም የማቅ አባላትን ለማየትም ከነሱም ጋር መሆንን አብዝተው አይወድዱም። ማቅን ለምን አምርረው እንደሚጠሉና እንደሚቃወሙ ሲጠየቁ በአብዛኛው የሚያቀርቧቸው ምክንያቶች ማቲያሲያዊ ይመስላሉ። ማለትም ብፁዕ ፓትርያርክ አባ ማቲያስ ሁሌ የሚያቀርቧቸው «ማቅ ከቤተ ክርስቲያን በላይ ገዘፈ፣ በሁሉ ረገድ ቤተ ክርስቲያን አነሰች ማቅ አየለ፣ ማቅ  ሀብታም ሆነ፣ ማቅ ገንዘቡን ለቤተ ክርስቲያን አያስገባም» ወዘተ የሚሉ ናቸው።

ባጠቃላይ ተቃዎሚዎች ማቅን ከነፍሳቸው ቢጠሉትም ማኅበሩን ለማጥፋት ግን በእቅድና በስልት አይንቀሳቀሱም። ንዴታቸውና ቅናታቸው በተቃውሟቸው ይበርድላቸዋል። በዚህ ስር ኢትዮጵያም ሆነ ውጭ አገር የሚኖሩ ግለሰቦች፣ አንዳንድ የቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፣ አንዳንድ የደብር አስተዳዳሪዎችና የመንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደሮች ሊጠቀሱ ይችላሉ። ተቃዋሚዎች ብዛታቸው ከደጋፊዎች ቢያንስም  ልዩ ልዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ሌሎች ሰዎችን ለጊዜውም ቢሆን በማደራጀት አቧራ ማስነሳት ይችላሉ! ችለውም ነበር።

 

ገለልተኞች

በደጋፊዎችና በተቃዋሚዎች መካከል ገለልተኞች ይገኛሉ። ገለልተኞች በማቅና በቤተ ክርስቲያን መካከል ያለውን ተስተጋብሮት በደንብ አይረዱም። ቢረዱትም እንኳን ሁኔታዎችን ገምግመው ሀሳብ ወይም ፍርድ ለመስጠት ይቸገራሉ። ስለማቅ ውይይት ሲነሳ እንደማይም ለመሆን ይጥራሉ። ገለልተኛ ሆኖ መታየት ብልህነት ስለሚመስላቸውና ሰላም እንደሚሰጣቸው ራሳቸውን ስላሳመኑ በጉዳዮች ላይ «ጀሮ  ዳባ ልበስ!» ብለው ይኖራሉ። አስተያየት እንዲሰጡ በግልጽ ሲጋበዙ «ይቅርታ እኔ ስለጉዳዩ ብዙ አላውቅም! በቡድንም በማኅበርም በሚደረጉ ውይይቶች አላምንም! ለኔ ቤተ ክርስቲያኔ ብቻ ትበቃኛለች!» አይነት መልስ ይሰጣሉ። ገለልተኞች «ማቅን በሩቁ!» ቢሉም ማኅበሩን ለማጥፋት ወይም ለማዳከም ግን ፍላጎት የላቸውም። በዚህ ስር ቀላል የማይባሉ የሃይማኖት ማኅበራትና የሲቪክ ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች ይጠቃለላሉ።

ተቃደጋፊዎች

ሁሉም ባይባልም በውጭው ዓለም በተለይም በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያዊያንንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በአባልነት ያቀፉ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ግብረ ኃይሎችና የድጋፍ ኮሚቴዎች ለማቅ ያላቸው ግምት ለየት ይላል። እነዚህን አካላት ተቃደጋፊዎች ብያቸዋለሁ! ተቃዋሚም ደጋፊም ናቸውና። ማቅ የኢትዮጵያን ታሪክ ያለምንም ፍርሃትና ስጋት ለወጣቱ በማስተማሩ፣ ማቅ በብሄረሰብ ሳይሆን በብሄራዊ ደረጃ በመዋቀሩ፣ ማቅ በልዩ ልዩ አገልግሎቶቹ ኢትዮጵያዊነትን እንጅ ዘውግን ባለማንጸባረቁ፣ ማቅ በቤተ ክርስቲያንና በአገር ዙሪያ ያለውን ሙስናና አስተዳደራዊ ዝርክርክነትን በመቃወሙ፣ በነዚህና  በሌሎችም ጉዳዮች ማቅ ለመንግስት የራስ ምታት በመሆኑ ወዘተ እነዚህ አካላት በይፋ ለመደገፍ የሞራል ብቃት ቢያጥራቸውም በልባቸው ያመሰግናሉ። የማቅንም ፈጽሞ መጥፋት ወይም መዳከም አይመኙምም።

ይሁን እንጅ ማቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የመንግስት አገልጋይ እንደሆነ የሚነገረውን ቅዱስ ሲኖዶስ ደግፎ ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር አብሮ እንደሆነ የሚነገረውን ውጭ አገር ያለውን ቅዱስ ሲኖዶስ ባለመቀበሉ፣ መንግስት በሚያደርጋቸው መጠነ ሰፊ ግፎች ማቅ በይፋ ባለመቃወሙ፣ ማቅ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ባለመሥራቱ፣ በውጭ አገር የሚገኙ ገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት ወደኢትዮጵያው ሲኖዶስ እንዲገቡ ማቅ ትልቅ ሚና እንደተጫወተ በመነገሩ ወዘተ ማቅን አጥብቀው ይቃወማሉ። በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ያለውን የማቅን እንቅስቃሴም በጥንቃቄ ይከታተላሉ። እንዲያውም ማቅ የመንግስት ደጋፊና ዲያስፖራውን ለመከፋፈል የሚጠቀምበት መሣሪያ ነው ብለው የሚያምኑም አሉ። ይህን የፖለቲካ ትኩሳት በመጠቀም የራሳቸውን የግል ጥላቻ በማኅበሩ ላይ የሚወጣጡም ይገኛሉ። ይህ ሁሉ ቢሆንም ማቅን በተቀናጀ ስልትና እቅድ ለማዳከም ብሎም ለማጥፋት ከሚደረገው ጥረት ጋር ተቃደጋፊዎች አይተባበሩም።

ፈታኞች

ፈታኞች ወይም አሳዳጆች ግን እጅግ የተለዩ አካላት ናቸው። የመጨረሻ ዓላማቸው ማቅን ማጥፋት ያም ካልተቻለ ወገቡን እንደተመታ እባብ ማኅበሩ ሲሽመደመድ ማየት ነው። ይህን ዓላማ ለማሳካት ማንኛውንም አዋጭ መንገድና ስልት ይጠቀማሉ። እንዲሁም በመሠረታዊ ዓላማ ከማይመስሏቸው ሌሎች ተቋማት ጋርም ትብብርና ትስስር ይፈጽማሉ። በተለያዩ ዘዴዎች ማቅን እንደ ጭራቅ ወይም ሰይጣን ስለው ለማሳየት ይሞክራሉ። ጉልበት፣ ውግዘትና ክስ ዋነኞች የተቃውሟቸው መገለጫዎች ናቸው።

እነዚህን አካላት ፈታኝ ብያቸዋለሁ። እንደሚታወቀው ፈተና በመንፈሳዊውም በዓለማዊውም ሕይወት ብዙ አይወደድም። ፈታኙ በተፈታኙ ላይ የበላይነት አለው። ፈተናውን ማቅለል ማክበድም ይችላል። እንደዚህም ሁሉ ማቅን በተለያዩ መንገዶች የሚያስጨንቁ የተለያዩ አካላት ናቸው።

እነዚህ አካላት እነማን ናቸው? ማቅን የሚያስጨንቁባቸው መሠረታዊው ምክንያቶችስ ምንድን ናቸው? ምክንያቶችስ በትክክል የማቅን ችግር ያሳያሉ? በዚህ ማቅን በመፈተኑ ሂደት የሚጎዳው ማቅ ብቻ ይሆን? ለመሆኑ ማቅ ለኢትዮጵያና ለቤተ ክርስቲያን ምን ያህል ጠቃሚ ነው? ፈተናዎችን ለማለፍስ ከማቅ እንዲሁም ከተለያዩ አካላት ምን ይጠበቃል? ይህ ጽሑፍና ቀጣይ ክፍሎች ለእነዚህ ከባድ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ይሞክራሉ።

ፈታኞች እነማን ናቸው?

ማቅን በቋሚነትና በስልት የሚፈትኑ አካላት አያሌ ናቸው። ዋናዎቹ ግን የተሐድሶ አቀንቃኞችና ደጋፊዎቻቸው፣ የፕሮቴስታንት እምነት ድርጅቶችና ደጋፊዎቻቸው፣ የእስልምና ሃይማኖት ድርጅቶች፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንና ጣሊያን፣ የኢትዮጵያ መንግስት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክና ጽ/ቤታቸው፣ ሙዘረኞች፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በውጭ አገር ባለው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር ያሉ ካህናትና አገልጋዮች ናቸው።

ማቅ ሲቋቋም ጀምሮ ትልቁ ሥራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት፣ ቀኖናና ትውፊት ለትውልዱ በማስተማር መጠበቅና ማስጠበቅ ስለሆነ «የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እድሳት ያስፈልገዋል!» ከሚሉ የተሐድሶ አቀንቃኞችና ደጋፊዎቻቸው ጋር ጭድና እሳት መሆኑ አይገርምም። ተሐድሶዎች ከምእራቡ ዓለም በሚያገኙት ገንዘብ በመታገዝ ለመስፋፋት ጥረት ያደርጋሉ። ማቅ ደግሞ ትውልዱን በማንቃትና መረጃና ማስረጃ ሰብስቦ ለሚመለከተው ክፍል በማቅረብ ፍልሚያውን ቀጥሏል። ተሐድሶዎች ራሳቸው በሚዲያ እንደተናገሩት ከቤተ ክህነት ይልቅ ማቅ የራስ ምታት እንደሆነባቸውና እንቅስቃሴያቸውን በብዙ መንገድ እንደገደበባቸው ያምናሉ። የፕሮቴስታንት እምነት ድርጅቶችና ደጋፊዎቻቸው እንዲሁም የእስልምና ሃይማኖት ድርጅቶች ግልጽ በሆኑ ምክንያቶች ማቅን አምርረው ይጠላሉ።

ጣሊያንና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንም ማቅን ይጠላሉ። ማቅ በአድዋና በሌሎችም ጦርነቶች ጣሊያንና ቫቲካን ያደረጉትን ግፍ በጥናት አስደግፎ ለህዝብ አቅርቧል። እንዲያውም ጣሊያንና ቫቲካን ኢትዮጵያን ይቅርታ እንዲጠይቁ ካሳም እንዲከፍሉ የሚጠቁሙ መደምደሚያዎችን ሰጥቷል ማቅ። አንድም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በደቡብና በሌሎችም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ውስጥ በምታደርገው የመስፋፋት እንቅስቃሴ ማቅን እንደ ተቀናቃኝ ታያለች። ማቅ ከየሀገረ ስብከቶች ጋር በመተባበር በአካባቢው የሚኖሩ አያሌ ኢትዮጵያዊያንን ወደኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት እያመጣ ነውና።

ምንም እንኳን የተሐድሶ አቀንቃኞችና ደጋፊዎቻቸው፣ የፕሮቴስታንት እምነት ድርጅቶችና ደጋፊዎቻቸው፣ የእስልምና ሃይማኖት ድርጅቶች እና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንና ጣሊያን ለማቅ የዕለት ዕለት ፈተናዎች ቢሆኑም ኅልውናውን የሚያሰጉ ግን አይደሉም። ማቅ በዋናነት እነዚህ አካላት በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያደርሱትን እንግልት ለመከላከል ተቋቁሟልና። እነዚህን አካላት ለመቋቋም ድርጅታዊ ልምድ ዝግጅትና አቅም አለው ቢባል የከበደ ንግግር አይሆንም። ማቅ ይህን ያህል ዘመን ሊቆይ የቻለው እነዚህ አካላት የሚያደርሱበትን ልዩ ልዩ ጫናዎች ተቋቁሞ ነውና።

ዳሩ ግን የኢትዮጵያ መንግስት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክና ጽ/ቤታቸው፣ ሙዘረኞች እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በውጭ አገር ባለው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር ያሉ ካህናትና አገልጋዮች ለማቅ ልዩ ፈተናዎች ናቸው። ከሌሎቹ ይልቅ እነዚህ አራት አካላት ማቅን አስጨንቀው ይዘዋል። እነዚህን አካላት በይፋ ለመፋለም የተቋቋመበት ዓላማ ስላልሆነ አስቸጋሪ ነው። ዝም እንዳይልም በኅልውናው መጥተውበታል። ማቅ እስካሁን ድረስ ስልታዊነትን ያገናዘበ አካሄድን በመምረጥ ለመቋቋም ሞክሯል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ጥንካሬ ያላቸውን መግለጫዎች በማውጣት ራሱን ከመከላከል ወደ ማጥቃትም መውሰድ እንደሚችል አመላክቷል። ይህ መንገድ የት ያደርሳል? ለመሆኑ እነዚህ ፈታኝ አካላት እንዴትና ለምንድን ነው ማቅን ለማፈን የፈለጉት?

ይቀጥላል!

ገንቢ አስተያየት ካለዎት በteklu.abate@gmail.com ይላኩልኝ!

ወያኔ በመቀሌ ከተማ “ኢትዮጵያውያንን በዘር እና ሐይማኖት ከፋፍሎ ስለሚያካሂደው ዘመቻ” ስውር ስብሰባ አደረገ

$
0
0

ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር ፤ጎንደር ኢትዮጵያ

በከፍተኛ የህወሃት ማይከላዊ አመራሮች በሆኑት አቶ ተክለወይኒና አባይ ወልዱ እንዲሁም የትግራይ ክልል የደህንነት ቢሮ ሓላፊ የሆኑ አቶ ዘነበ ሐዱሽ የተመራው ጥቂት ታማኝ ካድሬዎች ብቻ የተገኙበት የትላንት ወዲያ (የሚያዚያ 08/2008 አ/ም) የመቀሌው ስብሰባ ከአንድ በመቀሌ ኗሪ የሆነ የአዲግራት አከባቢ ተወላጅ “ባስቸኳይ ለኢትዮጵያውያንና ለመላው የአለም ህዝብ ይጋለጥ” ብሎ የደረሰኝ መረጃ፣ ልጁ በላከልኝ መረጃ መሰረት እንደወረደ ያለ አንዳች ማሻሸያ እንዲህ ከታች ቀርቧል። ዘጋቢው የህወሀት አባል ሲሆን መረጃው ያገኘው በስብሰባው ከተሳተፈው የልብ ካድሬ ጓደኛው በቀጥታ ከነገረው እንደሆነ ጠቁሞናል።

abay weldu

አመሻሹ ላይ  ይህን ዘገባ የላከልኝ ውዱ ዘጋቢ “ህወሃት መሞቱ የሚታወቀው ገና የስብሰባው አዳራሽ ሳይከፈት መረጃው ቀድሞ ህዝቡ ጋር ይደርሳል፤ ከዚህ በላይ ያንድን መንግስት ተሰባብሮ መውደቁንና መበስበሱን አማላካች ሊሆን የሚችል ነገር የለም” ብሎኛል።ምስጋናዬን ለዚህ ውድ ኢትዮጵያዊ ላቅርብና ዘጋቢው “ምንም ይሁን ምንም አገሬ ኢትዮጵያን እወዳለሁ” ያለ ሲሆን “ህዝባችን የወያኔ ተንኮል አውቆ መጠንቀቅ እንዲችል ሆኖ ባጭር ግዜ ውስጥ ማስወገደ አለበት” ብሏል።

“የወያኔ ኢትዮጵያዉያንን በዘርና ሐይማኖት ከፋፍሎ የማጋጨትን ዘመቻ ግምገማ በትላንትናው ቀን 08 ሚያዚያ 2008  አ/ም በመቀሌ ከተማ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ህልውናን ሙሉ ለሙሉ እንዲያከትም ለማድረግ በጣም አስገራሚ የሆነ ስብሰባ ተደርጓል። ስብሰባው አንድን ወሳኝ የተባለን  ኦፕሬሽን  ግምገማ በማካሔድ ለቀጣይ አፈጻጸሙ እርማት በማድረግ እንዴት በተሳካ ሁኔታ ማስኬድ እንደሚገባ አቅጣጫን ለማስያዝ ነበር። የስብሰባው ትእዛዝ የወረደውም ከአዲስ አበባ ከአቦይ ስብሓት ነጋና አባይ ጸሓየ ሲሆን ወደ ስብሰባው መጨረሻ አካባቢም አቶ አባይ ጸሐየ በስልክ ደዉለው በማያክሮፎን ላውድ ተደርጎ ቀጭን ትእዛዝ ለተሰባሳቢው ተላልፏል። ትእዛዙ ከታች ባጭሩ የጽሑፌ  መጨረሻ አከባቢ እገልጸዋለሁ።

የስብሰባው ዋና አላማም የህወሀት ካድሬዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የዘርና የሐይማኖት መከፋፈል ወደ ግጭት እንዴት ስውር በሆነ መንገድ በባለፉት 7 ወራት ሲያካሒዱ እንደቆዩ የሚገመግም ሲሆን በጣም ብዙ የተባሉ ክፍተቶች እንደድክመት ተነስተዋል። ይህም ከግምገማው ብሗላ በተደረገው  የችግሩ ምክንያቱ የተባሉት ደግሞ አንደኛው የአንዳንድ ካድሬዎች አለመታመን ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የህዝቡ በነገሮች ላይ መጠነኛ  መባነን ሊሆን ይችላል ተብሎ ደምዳሜ ተሰጥቶታል።

ኦፕሬሽኑ  ከተግባራዊነቱ  አንጻር ከሞላ ጎደል የተሳካ አፈጻጸም ያለበት ነው ቢባልለትም  ደካማ ጎኖች  ከተባሉ ዋነኛ ነጥቦች መካከል ደግሞ ከያንዳንድዋ ኦፕሬሽን ብሗላ ህዝቡ በቀላሉ ጣቱ እኛ ጋር እየቀሰረ ነው ያለው ይላል።  ለምሳሌ የአንዋር መስጊዱ ጥቃት ህዝበ ሙስሊሙ በሚነቃበት ሁኔታ ነው  የተከናወነው ከዚህም የተነሳ የታሰበ ግቡ አልመታም፤ በኦሮሚያ አመጽ የተከናወነው የቤተ-ክርስቲያናት ቃጠሎ የአንዱዋ የፕሮቴስታንት ቸርች ብቻ  በአካባቢው ባሉ አክራሪ ሙስሊሞች የተፈጸመ ቢሆንም የእኛው ካድሬዎች የሰሩት ተልእኮ ግን በክፊል የተነቃበት ሁኔታ ነው ያለው። ሌላው የአማራውና የቅማንቱ ዘር ግጭት በብዙ ኢትዮጵያውኖች መንግስት እንዳቀነባበረው የተደረሰብት የሚመስል እምነት በህዝቡ ዘንድ እንዳለ ታማኝ ካድሬዎቻችን አድርሰውናል። ይህ ሊሆን የቻለውም  ከትግራይ ተወላጆች ውጭ ያሉት ካድሬዎቻችን በብዛት ታማኝ ሆነው ሳይሆኑ ለሆዳቸው ብቻ ብለው ግዳጅ እየፈጸሙ እንደሆነ ነው የሚያሳየው። ከጎንደሩ የአማራና ቅማንት  የዘር ግጭት ውጭ በኦሮሚያ በሚገኙ አንዳንድ አከባቢዎች በከፊል አማሮች ከደረሰው ነገር  በቀር እንዲያውም ባልጠበቅነው ሁኔታ የኦሮሞ አባቶች ከለላ የሰጡበት ሁኔታ ሁሉ ስለነበር በተግባር እንደ እቅዳችን ተሳክቷል ለማለት አያስደፍርም። እንዲህም ሆኖ ግን ኦፕሬሽኑ ፍርሀትንና ጭንቀትን፤ ውጥረት፣ አለመተባበርንና አለመተማመንን ከመፍጠር አኳያ ግን እጅግ አጥጋቢ የተባለን ውጤት አስገኝቷል። ይህም በተለያዩ የአገሪቱ አከባቢዎች የተነሱ አመጾችን ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ከማምጣትና መንግስትን ከመዳፈር ውጭ የተበጣጠሱና ለውጥ የማያመጡ አድርጓቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ኦፕሬሽኑ ከፍተኛ በሆነ የመባነን ሰለባ ሆኗል የምንለው ደግሞ በዩኒቨርሲትዎች የደረሱት የቦንብ ፍንዳታዎችና ቃጠሎዎች በብዛት ማለት ይቻላል መንግስት እንዳደረሰው ነው ህዝቡ ካድሬዎቻችንን ሳይፈራ  በየሻይ ቤቱና መጠጥ ቤቱ በንቀት የሚያወራው፤ ይህ ለእኛ ውርደት ከመሆን በዘለለ መልኩ ህልውናችንን የሚፈታተን ነገር ነው። እይህ ድፍረትም ካድሬዎቻችን የበለጠ እንዲፈሩና የሚፈጸሙት ተልእኮ ይባስ የተባነነበት እንዲሆን ያደርገዋልና ታማኝና ቆራጥ ካድሬዎችን ለተልእኮው ማሰልፍ የግድ ይላል። ካልሆነ ግን በፍርሃታቸው እንዲህ አይነት የተንዘላዘለ የጅል አሰራር የሚሰሩ ካድሬዎች ባስቸኳይ  ሊወገዱ ይገባል።

እንደዛም ሆኖ ግን አመጹ አሁንም ቢሆን ለመንግስት ስጋት ስለሆነ ይህ ኦፕሬሽን ክፍተቶቹን በመዝጋትና  ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በተጠናከረ መንገድ መቀጠል አለበት። ቁልፍ መርሗችን እስከሆነ ድረስ በታማኝነትና ቆራጥነት ልንወጣው ግድ ይለናል። ለምሳሌ የወልቃይት ጉዳይ ለእኛ በጣም  አሳሳቢ ደረጃ  ላይ ደርሷል። ጥያቄያቸውም ህገ-መንግስታዊ ሽፋን ያለው በመሆኑና የተለያዩ ሚዲያዎች ሽፋን ስለሰጡት በቀላሉ ለማጥቃት ቢያስቸግረንም የስልክ ኔትዎርክና የመረጃ መረቡን በመዝጋት የሚቻለንን ያህል እይደረግንን ነው። ህዝቡም በጣም እልኸኛና ቆራጥ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ህጋዊ የፌደረሽን ምክር ቤቱ ውሳኔ በትዕግስት መስማት ስለፈ ለገ ነው እንጂ ውሳኔው አይሆንም ከተባለ በቀላሉ ወደ ጦርነት ገብቶ ከፍተኛ ኪሳራ ሊያደርስብን የሚችል ህዝብ ስለሆነ የፌደርሽኑ ውሳኔ በማዘግየት ወደ ሗላ በሳል ስራዎችን ከመስራት በቀር ምንም ልናደርገው አንችልም።  ነገር ግን ይህ ኦፕሬሽን በወልቃይት ተፈጻሚ ሲሆን በዛ አካባቢ ያሉ ሙስሊምና ክርስቲያኖች በመተማመን ስለሚኖር በህዝቡ መከፋፈል ለመፍጠር  መሞከር ኪሳራ እንጂ ውጤት አያመጣም፤ ግን ደግሞ የአካባቢው ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ኦፕሬሽን ለየት ባለ መልኩ ነው ባስቸኳይ መፈጸም ያለበት።

ህዝቡ በቀላሉ የመባነን ባህሪ ስላለው በህዝቡ እማኝነት እንዲኖረው ለማድረግ አካባቢው ክርስቲያን የበዛበት እንደመሆኑ መጠን የታጠቁ  አክራሪ እስላሞች ከሰሜን ሱዳን እንዲዘልቁ በማድረግ የድንበር ችግር ያለባቸው በማስመሰል እዛ በአከባቢው ያሉ የትግራይ ተወላጆችና ባለ የመከላከያ እዝ ተመጣጣኝ ስትራተጂያዊ  ዋጋ በመክፈልና የሚዲያ ሽፋን በማሰጠት ሌላ ቋሚ መፍትሔ እስኪገኝለት ድረስ ጉዳዩ እንዲበርድ ማድረግ ይቻላል።  የህወሃት መቃብር የተቆፈረው  በመቀሌ ሳይሆን በወልቃይት እንደመሆኑ መጠን ከሁኔታው አንገብጋቢነት አንጻር  ይህ የምናወራው  ኦፕሬሽን  ባስቸኳይ መፈጸም ያለበት  በዚህ መልኩ ከሆነ ፍጹም አመርቂ የሆነ ግን ደግሞ ያለተባነነበት ሁኔታውን ያገናዘበ ኦፕሬሽን ተካሔደ ማለት ነው።

አሁንም ቢሆን  ግጭቱ በዋነኝነት በሙስሊምና  ክርስቲያኖች፣ በክርስቲያኖችና ፕሮቴስታንቶች፣ በሙስሊልምና ፕሮቴስታንቶች  እንዲሁም  በተለያዩ ብሔረስቦች መካከል ባስቸኳይ እውን መሆን አለበት። ከብሔር አንጻር  ሲታይም ግጭቱ በኦሮሞዎችና በአማሮች፤ በኦሮሞዎችና በሶማሊዎች፣ በሶማሊዎችና አፋሮች፣ በአፋሮችና የጁቡቲ ድንበር አፋሮች፣በጋምቤላና በደቡብ ሱዳን ድንበርተኞች፣ በኦሮሞዎችና ደቡቦች እንዲሁም በእነዚህ የተጠቀሱ አካባቢ ህዝቦች በውስጣቸው በተለያየ መንገድ መከፋፈልና ግጭት በሰፊው እንዲከሰት በማድረግ ጣታቸውን ከመንግስት ቅሰራ እንዲቆረጡ በማድረግ መንግስትን  ለአስታራቂነት እንዲለምኑ መደረግ አለበት። ስብሰባው ሊያልቅ ወደ 40 ደቂቃ ገደማ ሲቀረው አቶ አባይ ጸሐየ በስልክ ደዉለው በማይክሮፎፎን ላውድ ተደርጎ እጅግ በጣም በተበሳጨ ስሜት ሆኖ በቀጥታ በስልክ በተላለፈው ቀጭን ትእዛዛቸው ‘ስትነጋገሩበት የቆያችሁ አገራዊ አጀንዳ በውስጥ መስመር ሲደርሰኝ ነበር’ ካሉ ብሗላ ‘አንዳንድ ማጉረምረም በሚሰማባቸው የትግራይ አካባቢዎች ቢሆንም እንኳ ኦፕሬሽኑ ካስፈለገ ተግባራዊ ይደረግ’ ከእንግዲህ ወደሗላ ማለት የለም” ካሉ ብሗላ ሁለት ካድሬዎች በፍጥነት ሲያጨበጭቡ ሌላውም በፍርሃት እየተያየ ደማቅ ጭብጨባ አሰምቷል” ተብሏል።

በአሁኑ ስአት ስለብሔርና ስለሐይማኖት ልዩነት የሚያወሩ ሰዎች የወያኔ ካድሬ አለያም ደግሞ ወያኔ ባይሆኑም በስራቸው ተባባሪዎችመሆናቸውን አውቃችሁ እንደትጠነቀቁ በማሳሰብ አስፈላጊውን ኢትዮጵያዊ መልስ እንድተሰጧቸው አሳስባለው። በተባበረው ክንዳችን ወያኔን በፍጥነት እናስወግድ!!! ይህ ሲባል ታድያ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ስለብሔሩ ችግር አያውራ ወይንም ደግሞ አይደራጅ ማለት አይደለም። ነገር ግን ብሔርነታችን ለኢትዮጵያዊነታችን ዋስትና ሊሆነው ይገባል፤ ኢትዮጵያዊነታችንም ለብሔራችን ዋስትና ሊሆነው እስከቻለ ድረስ። ከዚህ ውጭ ግን ኢትዮጵያውያን ሆነን በሃይማኖትና በብሔር ያተኮረ ስድብና የፈጠራ ታሪክ  ነገር ሁሉ መጥፊያችን ነው። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

ሞትና ውድቀት ለወያኔ ትንሳኤ ደግሞ በውርደት ላለች አገራችን ይሁን፤እግዚአብሔር ኢትዮጵያንይጠብቅ!!!

[የጋምቤላው ጉዳይ] ለዛሬ ደማችንን እንልሳለን |ከታምራት ነገራ

$
0
0
ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ

ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ

ከማንኛውም አደጋ ሊጠብቁን ሲገባቸው ከውስጣችን ሆነው የሚያጠቁንን ፤ ለጠላት አልሞ ተኳሽ አስተኳሽ የሆኑብንን ምን እንደምናደርግ ግራ ገባን እንጂ በውጭ ኃሎች መጠቃቱንም፤ የመጣውንም ኃይል መክቶ መመለሱንማ በሚገባ እናውቅበታለን፡፡ የውጭ ሚዲያ “በሊቢያ ኢትዮጵውያን እንደ ዶሮ ታረዱ” ብሎ ሲነግረን የኛው የእራሳችን የተባለው መንግስት ደግሞ “ሟቾቹ ኢትዮጵያውዊ መሆናቸው አልተጣራም” አለን፡፡ የሟቾች ፎቶ ሲመጣ አብረን ብይ ተጫውተን ፤ ጮርናቄ ተቃምተን ፤ቪዲዮ ቤት ተጋፍተን ያየነው አብሮ አደግ ጓደኞቻችን ሆነው አረፍነው፡፡ ዛሬ ደግሞ የሱዳን ሚዲያዎች እራሳቸው “ጋምቤላ ውስጥ የተገደሉት ኢትዮጵውያን ቁጥር ከ 200 በላይ ነው” ብሎ ሲዘግብ የእኛው መንግስት “የሞቱት ቁጥር 140 አልበለጠም” ይለናል፡፡ በእኛ ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ትክክለኛ መረጃ እንኳ ለማግኘት መንግስታችንን ማመን አቃተን፡፡

ፎቶ ምንጭ: ሐና

ፎቶ ምንጭ: ሐና

በባዕድ ከተጠቃነው በእኛው ወገን፤ በእኛው መንግስት የተጠቃነው በዛ፡፡ ጥቃቱም፤ የደረሰብንም ቁስል ፤የቁስሉ ሕመምም እኛው በእኛው ሆኖብን ከባዕድ እጅ ይልቅ አመመን፡፡ በዚህች አላቂ ትንሽ እድሜ ለአንድ ቀን እንኳን አንገታችንን ቀና በሚያስደርግ በምናምነው መንግስት መወከል የመይጨበጥ ሕልም ሆነብን፡፡ በዚህ ሁሉ ውርጅብኝ ውስጥም ሆነን፤ ከእኩለሌሊት በበረታ ጭለማ ውስጥም ታስረን አንድ ተስፋ ይታያል፡፡ ምን ብንቆስል መቆጨት አላቆመንም፡፡ ምን ያህል ደጋግመው ቢያቆስሉን ለአገራችን እህህ እማማ ብሎ ማብሰልሰሉን መታመሙን አልተውንም፡፡ ግድ መስጠት ያቆምን መታመም ያቆምን ቀን ያን ቀን ሞትን፡፡
ደማችንን እየላስንም፤ ቁስላችንን እያስታመምንም ቀን እንጠብቃለን፡፡ ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ሲሰብር አይተናል፡፡ ቀን የወጣለት አንበሳ ደግሞ ምን እነደሚያደርግ እናያለን፡፡ ይህን ቀን እኛ ባናይ እንኳን ቁስላችንን ፤ቁጭታችንን ለልጆቻችንም ቢሆን እናስተላልፋለን፡፡
ለዛሬ እናለቅሳለን፤ ለዛሬ ደማችንን እንልሳለን…

ኢትዮጵያውያኑ በሎንደን የሕወሓትን ስብሰባ አወኩት |ቪዲዮ ይዘናል

$
0
0

የሕወሓት መንግስት በዲያስፖራ ሕዝባዊ ስብሰባ ማድረግ ሕልም ከሆነበት ሰነባብቷል:: እነሆ ዛሬም በለንደን የጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ በኢትዮጵያውያኑ ተቃዋሚዎች ታውኳል:: ይመልከቱት

London

ጋምቤላ በኛ ዕድሜ |ከአፈንዲ ሙተኪ

$
0
0

“ጋምቤላ” የሚለውን ስም ካወቅነው ድፍን ሃያ ስምንት ዓመታት ሆኖታል፡፡ ከስሙ ጋር የተዋወቅንበት አጋጣሚ ደግሞ የሚረሳ አይደለም፡፡ እንዲህ ነው!!
የአራተኛ ክፍል የህብረተሰብ ትምህርትን ታስተውሱታላችሁ… አዎን! ህብረተሰብ በፍቅር ከምንማራቸው ጥቂት የትምህርት ዓይነቶች አንዱ ነው፡፡ ትምህርቱ “ህብረተሰብ” ቢባልም ጂኦግራፊን፣ ታሪክንና ሶስዮሎጂን የሚያካትት ዓይነት ነበር፡፡ የመማሪያ መጽሐፋችን በጣም ግሩም ነበር፡፡ ከርሱ በተጨማሪ በሬድዮ የሚሰጠው የአንድ ፔሬድ (ክፍለ ጊዜ) የማጠናከሪያ ትምህርት በመጽሐፉ የሌሉ በርካታ ቁም ነገሮችን የሚያስጨብጥ ነበር፡፡
Gambella4

ታዲያ በገጠር የምትኖር አያቴ ሞታ ለሀዘኗ ስል ለአንድ ሳምንት ከክፍል ጠፋሁ፡፡ ሀዘኑ ተጠናቆ ወደ ከተማ በተመለከስኩበት በሁለተኛው ቀን የህብረተሰብ ትምህርት አስተማሪያችን የሙከራ ፈተና (“ቴስት” የሚባለው) ሰጠን፡፡ ከአስር ጥያቄዎች ዘጠኙን መለስኩ፡፡ አንደኛው ግን አቃተኝና ባዶውን ተውኩት፡፡ የሚገርመው ነገር አብዛኛው ተማሪ የመለሰው ጥያቄ ነበር የከበደኝ፡፡ እንዲህ ይላል፡፡

“በኢትዮጵያ በዱር አራዊት ሃብቱ አንደኛ የሆነው አውራጃ የትኛው ነው”
አስተማሪያችን (ጸጋ መለሰ ይባላል) ጠራኝና “ሁሉንም መልሰህ ይሄ ጥያቄ ብቻ እንዴት ከበደህ አለኝ” በማለት ጠየቀኝ፡፡ በህብረተሰብ መማሪያ መጽሐፋችን ላይ እንዲህ የሚል መረጃ እንደሌለ ነገርኩት፡፡ “ባለፈው ሳምንት” ትምህርት በሬድዮ አልተከታተልክም” በማለት ጠየቀኝ፡፡ ፈቃድ ወስጄ ገጠር እንደሄድኩ ነገርኩት፡፡ መምህራችን የተሸወድኩበትን ምክንያት አወቀ፡፡ እናም የጥያቄውን መልስ እንዲህ በማለት መለሰልኝ፡፡

“በኢሉባቦር ክፍለ ሀገር ጋምቤላ አውራጃ”

አዎን! “ጋምቤላ” የሚለውን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት በዚያች አጋጣሚ ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስለርሱ ክፉና ደጉን እየሰማን እስከ አሁን ድረስ አለን፡፡ በተለይም ስለጋምቤላ ከሚታወሱኝ መካከል በ1981 የጋምቤላ ተወላጅ የሆነው ታዋቂው ጊታሪስ ኩት ኡጁሉ የሚገኝበት የኪነት ቡድን ወደ ከተማችን መምጣቱ (ነዋይ ደበበ፣ ሂሩት በቀለና ሐመልማል አባተም በቡድኑ ውስጥ ነበሩ)፣ በተመሳሳይ ዓመት ጋምቤላ ከኢሉባቦር ስር ወጥቶ ራሱን የቻለ የአስተዳደር አካባቢ መሆኑ እንዲሁም አሜሪካዊው ኮንግረስማን ሚኪ ሌላንድ “ፑኝዶ” በተባለችው የጋምቤላ መንደር የሰፈሩትን የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ለመጎብኘት ሲጓዙ ደብዛቸው መጥፋቱና ከሁለት ወር ፍለጋ በኋላ አውሮፕላናቸው መገኘቷ ወዘተ…. ከማይረሱኝ ጋምቤላ ተኮር የደርግ ዘመን ትዝታዎቼ መካከል ናቸው፡፡
——–
በዘመነ ኢህአዴግ ደግሞ ጋምቤላ ወደ ክልል አደገ፡፡ በዚህ ዘመን በደምብ ከሚታወሱን ትዕይንቶች መካከል ቀዳሚ ሆኖ የሚወሳው በተከታታይ የተሾሙ ሶስት የክልሉ ፕሬዚዳንቶች “ኦኬሎ” የሚል ስም የነበራቸው መሆኑ ነው፡፡ ይህ የስም መመሳሰል ብዙዎችን ሲያነጋግር እንደነበረ አስታውሳለሁ፡፡ ከዚያ በፊት ደግሞ በጋምቤላ በመምህርነት የተመደበው “ቶማስ መንግሥቱ” የተባለ የገለምሶ ተወላጅ የተማሪዎቹን የስም መመሳሰል እንደ ትንግርት ሲያወራ እንደነበረ ከአንድ አጎቴ አንደበት ሰምቻለሁ፡፡

ከዚህ የስም መመሳሰል ጀርባ ያለው ሚስጢር የተገለጸልን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በ1992 በአሶሳ ከተማ አንድ ልዩ ዝግጅት ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡ በዝግጅቱ ላይ የተገኙ ሽማግሌዎች የልዩ ልዩ ብሄረሰቦችን የስም አወጣጥ ሲናገሩ የጋምቤላው የአኙዋክ ብሄረሰብ እንደምሳሌ ተጠቃሽ ሆኖ ቀረበ፡፡ ሽማግሌዎቹ እንደተናገሩት በአኙዋክ ብሄረሰብ ደምብ መሠረት የመጀመሪያ ልጅ ምንጊዜም ቢሆን “ኦኬሎ” ተብሎ ነው የሚጠራው፡፡ ሁለተኛ ልጅ ደግሞ “ኡጁሉ” የሚል ስም ይሰጠዋል፡፡ የመጀመሪያ ልጅ ሴት ከሆነች ደግሞ “አሪየት” ተብላ ትጠራለች (ሁለተኛዋ ልጅ የምትጠራበትን ስም ረስቼዋለሁ፤ የምታስታውሱ ንግሩን)፡፡ በዚያው ዓመት አንድ የናሽናል ጂኦግራፊ ጋዜጠኛ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ዘመን ፎቶዋን አንስቶ በዓለም ላይ ያስተዋወቃት የጋምቤላዋ ኮረዳ ትልቅ ሴት ሆና ለጋዜጣ ኢንተርቪው ቀርባ አንብበናታል፡፡
በዚህ ክልል በጥሩነታቸው ከሚታወሱት ዜናዎች አንዱ ነዳጅ ተገኘ መባሉ ነው፡፡ ነገር ግን ነዳጁ እስከዛሬ ድረስ አልወጣ ብሏል፡፡ ወሬው ብቻ በየጊዜው ይመላለሳል፡፡ ግምባታ ተካሂዷል፣ ዩኒቨርሲቲ ተከፍቷልም ይባላል፡፡ ይሁንና ከክልሉ የሚመነጩት ዜናዎች በአብዛኛው ጥሩ አልነበሩም፡፡ የትናንቱን ዓይነት ልብ ሰባሪ ወሬ ነው በአብዛኛው የምንሰማው፡፡ ጋምቤላዎች ሁሌም ሐዘንተኞች ናቸው፡፡ ያሳዝናል!!
የሞቱትን ነፍስ ይማር!!


የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የአማራ ማንነት ጠያቂ ኮሚቴ በኮሎምቦስ ኦሃዮ የጠራው ስብሰባ በስኬት ተጠናቀቀ

$
0
0

Wolqite News

ሚያዝያ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. (April 9, 2016) በ 179 Fairway Boulevard በሚገኘው አዳራሽ ቁጥሩ ከፍ ያለ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት እንዲሁም የአርማጭሆና ጎንደር ክ/ሀገር ተወላጆች ኢትዮጵያዊያን ስብሰባውን ተካፍለዋል።

በአገር ቤት ሰለተቋቋመው የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባብሪ ኮሚቴ እንቅስቃሴና ለፌደረሽን ምክር ቤት ያቀረቡት ፅሁፍ ተነቧል።

በውጭ አገር ያለው የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የአማራ ብሔረትኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ በተናጠል ለብዙ አመታት የተደረገው ጩኸት ውጤት ባለማምጣቱ በዛሬው ቀን የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የጎንደር ሕዝብ ብሎም አማራውና ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚህ ስብሰባ ተገኝቶ በሰፊው እንዲወያይበት መድረኩን ክፍት አድርገዋል።

አባቶችም የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ማንነት፣ አመጣጡና የዘር ሃረጉ፣ ከጎንደር ጋር ያለው ቁርኝት እንዲሁም ይህ ኩሩ ሕዝብ በልማትና የእናት ሃገሩን ዳር ድንበር ለማስከበር በተለያዩ ጊዜያት የከፈለው መስዋእትነት ለተሰብሳቢው በስሜት ገልጸዋል።

የተፈጥሮ ድንበሩን የተከዜ ወንዝን ተሻግረው ከሕዝቡ ፍላጎት ውጭ የተደረገው ማካለል ህገ-ወጥ እርምጃ በመሆኑ ሕዝቡም ይሁንታ ስላልሰጠው ይኸውና ከ37 አመት በኋላ የተዳፈነ ነገር ግን ያልጠፋ እሳት ዛሬ ተቀጣጥሎ ጥያቄው ለም መሬታችን ተቀማን፣ አስተዳደራዊ አድልዎና በደል ደረሰብን የሚል ብቻ ሳይሆን በሆዱ አምቆ ያቆየው የማንነት ጥያቄ በግልጽና ድምፁን ከፍ አድርጎ እኛ ጎንደሬዎችና አማራ ነን ብሏል። አራት ነጥብ!!

በዚህ ደማቅ ስብሰባ ከተሰብሳቢው ብዙ ጥያቄዎች ተነስተው መልስ ተሰጥቶባቸዋል። ብዙ ሃሳብ ቀርቦ ቤቱ በጥሞና ከተወያየ በኋላ አገር ቤት ከተቋቋመው ኮሚቴ ጐን በመቆም አስፈላጊ የሞራልና የቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚያደርግ በሙሉ ድምጽ ቃል ገብቷል።

ጉባኤው ህዝባዊውን ጥያቄ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ካለው የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አስተባባሪ ኮሚቴ በተጨማሪ ሶስት (3) ሰዎች በመምረጥ በጠቅላላው አስር (10) አባላት ያሉት ኮሚቴ ሆኖ እንዲሰራ እና ለወደፊቱ ሰፋ ባለ መንገድ የጎንደር ክ/ሃገር እና አጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ስብሰባ ተጠርቶ በጉዳዩ ጠለቅ ያለ ውይይት እንዲደረግበት ለኮሚቴው ሃላፊነት ሰጥቷል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት ተገን አድርገው በዲሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ መንገድ የማንነት መብታቸውን በጠየቁ የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ህዝቦች በትግራይ ክልል መንግስት እየደረሰ ያለው የአፈና፣ ማስፈራራት፣ ዛቻ፣ የሞራልና ይስነ-ልቦና ተፅእኖ ባስቸኳይ እንዲያቆም ጠ ይቋል።

በዚሁ የወልቃይት ጠገዴና እና ጠለምት ህዝብ የአማራ ብሄረተኘነት የማንነት ጥያቄ በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ጥያቄውን ስላነሱና ሃሳቡን ስለደገፉ በትግራይ ክልል መንግስት በግፍ ታፍነው በእስር ቤት እየተሰቃዩ የሚገኙትን የሕብረተሰብ አባላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲፈቱ ጉባኤው ጠይቋል።

በመጨረሻም በአገር ቤት በሰላማዊ መንገድ የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት እንዲሁም ሌሎች ማንነታቸውና መብታቸው ለማስከበር ጥያቄ እያቀረቡ ያሉትን ወገኖችን ለመደገፍ በቅርቡ ሌላ አጠቃላይ ህዝባዊ ስብሰባ እንዲጠራ በመወሰን ጉባኤው በሰላም ተጠናቋል።

የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ህዝብ የማንነት ጠያቂ አስተባባሪ ኮሚቴ ኮሎምቦስ፤ ኦሃዮ

የብሔረሰብ እኩልነት ጥያቄ  የኢትዮጵያ አብይ ችግር ነው; –ሰርጸ ደሰታ

$
0
0

ethiopian-montage23423በ60ዎቹ አብዮት ከትነሱት አብይ ጥያቄዎች አንዱ የብሔረሰብ እኩልነት ጥያቄ ይመስለኛል፡፡ ይህ ጥያቄ ግን ዛሬም መልስ አግኝቶ ጠያቂዎቹን ያረካ አይመስለኝም፡፡ ሰሞኑን ለዘውጋዊው ፖለቲካ መፍትሄ በሚሉ ነጥቦች ላይ አንዳንድ ምሁራን ሀሳብ ሰጥተውም አንብበናል፡፡ እኔ ግን የብሔረሰብ እኩልነት የሚለው ጥያቄ ራሱ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የሕዝብ አብይ ጥያቄ ነው ወይ የሚል ጥያቄን ማንሳት እወዳለሁ፡፡ በእኔ እምነት የብሔር ማንነት ችግር ጎልቶ የመጣው ከሕዝብ ሳይሆን አወቅን በሚሉ (ኤሊትሰ) ሰዎች ነው ባይ ነኝ፡፡ ችግሩ የለም እያልኩ ግን አይደለም፡፡ የሕዝብ መሠረታዊ ችግር አይደለም ባይ ነኝ እንጂ፡፡ በምሁራንን አወቅን በሚሉ እጅግ እየገዘፈና ከጊዜ ወደ ጊዜም እየጦዘ መጣ እንጂ ሕዝቦች በሚኖሩበት አካባቢ ማንነታቸውን የሚጋፋ ሥርዓት ያን ያወካቸው አይመስለኝም፡፡ ቋንቋቸውንም፣ ሌሎች ባህሎቻቸውንም ለመጠቀም ብዙ የተቸገሩበት ጊዜም የለም፡፡ ከዚህ ይልቅ ሕዝብ የአስተዳደር በደል፣ የልማት እጦት፣ በአጠቃላይ ለኑሮው መመቻቸት የሚፈልጋቸውን ነገሮች በማጣቱ ብዙ ይቸገራል፡፡ መሠረታዊ ጥያቄዎቹም ከእነዚህ ጋር የተያያዙ እንጂ ከማንነቱ ጋር የተያያዙ ናቸው የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሆኖም እነዚህ ችግሮች ሳይሆን የብሔረሰብና የማንነት ጥያቄዎች ፖለቲካውን በሚዘውሩት እናውቃለን ባዮች (ኢሊትሰ) እና ተደማጭነት ባላቸው ሰዎች ትልቅ ቦታ ስሌዙ የሕዝቡን መሠረታዊ ችግር ቦታ የሚሰጠው የጠፋ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ በከፋ ግን የሄው የዘውግን ጥያቄ መከታ አድርጎ ይሄው አወቅሁ የሚለው አካል ሕዝቡን ለራሱ መጠቀሚያ እያደረገውና ይልቁንም የኖረ ማንነቱንም በሚያመክን ሁኔታ እርስ በእርስ እንዲለያይ በማድረግ በእንቅርት ላይ ጆር ደግፍ እንደሚባለው ሌላ ተጨማሪ ችግር ፈጥሮበታል፡፡

ዘውጋዊ ሥርዓትን በይፋ አውጀን መተግበር ከጀመርን እንኳን ዛሬ 25 ዓመት አለፈን፡፡ ለተባለው የብሔር ጥያቄ መልስ ይሠጣል የተባለው ዘውጋዊነቱ ይሄው አሁን ጭራሻ የማንነት መሠረቱ የጠፋውን የባዘነ ትውልድ ፈጥሮ እናየዋለን፡፡ የሕዝብ መሠረታዊ ችግሮችን በዘውጋዊነት ቅብ ጀቡነናቸው ዓለም ቀኑን ሙሉ እያመነዠከ ባለበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚበላው አጥቶ በረሐብ ይሰቃያል፡፡ አለም በብዙ ዘመኑ በሠጠው ቴክኖሎጂ በሚታገዝበት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሁሉም ተርፎ እንጥፍጣፊው ነው የሚደረሰው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዛሬም ድረስ ኑሮው የሚወዳደርለት ከሌሎች አገሮች አንጻር ሳይሆን ከዘመናት በፊት ካለፉ ሥርዓቶች ጋር ነው፡፡ በደርግ ጊዜ ይሄ አልነበረም ዛሬ ይሄ አለ ነው ውድድሩ፡፡ በደርግ ሞባይል የለም ዛሬ አለ፣ ኢነተርኔት በደርግ የለም ዛሬ አለ፡፡ እንደህ ባለና በመሳሰሉ አስተሳሰቦች አገርንና ሕዝብን ከዚህ በላይ አያሰፈልጋችሁም እያልን የአገርና የሕዝብ ጠላት መሆናችን ትንሽም አልከበደንም፡፡ ረሐቡ፣ ችግሩ፣ በአስተዳደር ምክነያት እየደረሰበት ያው በደል ምናችንም አልሆነም፡፡ ዛሬም ትልቁ ጉዳያችን የብሔር ጥያቄ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ረሐብም በሉት፣ ሰውኛው አስተዳደረዊ በደል ሳይቀር ግን የሁሉም ሕዝብ የጋራ ችግር እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ እኛ የሕዝብን ችግር መፍታቱ አቅሙ ስለሌለን ሌላ የሕዝብ ያልሆነ ጥያቄ አንስተን መደበቂያ እንዳደረግንውም ይሰማኛል፡፡

ረሐብ በብዙ አገሮች ተከስቷል፡፡ ብዙ ሕዝብም ጨርሷል፡፡ አውሮፓ ተርቦ ለስደት የተዳረገበት ዘመን አለ፣ በጦርነትም ምክነያት በመጣበት ረሓብ ተገርፏል፡፡ ቻይና፣ ሕንድ የቀርብ ጊዜ የሚባል የረሐብ ታሪክ አስተናግደዋል፡፡ ለምሳሌ ቻይና የዛሬ 60 ዓመት ገደማ ይመስለኛል በገጠማት ረሀብ ከ30ሚሊየን በላይ ዜጎቿን እንዳጣች ይነገራል፡፡ ሕንድ ከእኛ በፊት በየመዝገበቃላቱ ሳይቀር የረሀብ ምሳሌ የሚሰጥባት አገር ነበረች፡፡ ሁለቱም አገሮች ዛሬ በምግብ ራሳቸውን መቻል ብቻም ሳይሆን ዓለምን በቴክኖሎጂ እየመሩት ይገኛሉ፡፡ እኛ በኃ/ሥላሴ ተከሰተ የተባለው የወሎ ረሀብ መዝገበ ቃላት ላይ እንዳስመዘገበን ዛሬም እዛው ነን፡፡ ምንም ሊሰማንም አልቻለም፡፡ እጅግ ያማል፡፡ ረሐብ በራሱ እጅግ አሳቃቂ ገጠመኝ ነው፡፡ የአገር ቤቱ ረሐብ አብሮን ሥም ሆኖን ከእኛው ጋር በየአገሩ መጓዙንም ምናችንም አልሆነም፡፡ በቅርቡ እኔን እንቆቅልሽ የሆነብኝን የአቶ ኃ/ማርም ደሳለኝን ንግግር ሰምቼ ጤነኝነታችንንም ተጠራጠርኩት፡፡ እርግጥ ነው ጤነኛ አይደለንም፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ኃ/ማርያም ራሳችንን በምግብ ችለናል ማለታቸው ሳያነሳቸው በአንዱ ሌላው ንግግራቸው ድርቅ በአውስተራሊያም፣ በካሊፎርኒያም በሌሎችም አገሮች አለ በሚል የኢትዮጵያም እንደዛው ነው አሉን፡፡ እውነታው ደግሞ ከአውስተራሊያና ካልፎረኒያ አንጻር ኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅ ተከስቶ አያውቅም ቢባል ማንም ባለሙያ የሚስማማበት ነው፡፡ እኛ አገር እኮ የወቅት መዛባት እንጂ እውነተኛ ድርቅ የለም፡፡ አንድ የሰብል ወቅት ከተዛባ በማግስቱ የሚራብን አገር 3 ዓመት ሙሉ ዝናብ ጠብ ሳይል (የካሊፎርኒያው ድርቅ እንዲህ ነው) ጠግቦ የሚያድርን ሕዝብ ማወዳደር ምን የሚሉት እንደሆነ እኔን አልገባኝም፡፡ የራሳችሁ ጉዳይ አይነት ንግግር ነበር፡፡

ሌላው ጋር ያለ የእድገት ሁኔታችን ሲታይ እንኳን ላለፉት 10 ዓመት ገደማ በሁለት ዲጂት ያደግን ኑሮው የተመሰቃቀለበትና በገዛ አገሩ የተማረረን ዜገ አቆይተናል፡፡ የዛሬ ዓመት ገደማ ነበር ዳቦ ፈልገው የወጡ ልጆቻችን  አንገታቸው ተቀልቶ በበረሀ የሰይጣኖቹ ግብር የሆኑት፡፡ በዛው ወቅት በደቡብ አፍሪካ አይናቸው እያየ በእሳት የጠቃጠሉ ወገኖቻችንን ተመለከትን፡፡ ሌላም ጊዜ በሌሎች አገሮች የእኛ መከራ ጽኑ፡፡ ሴቶቻችን በአረቡ አለም ብዙ መከራን ይቀበላሉ፡፡ እንዲህም እየሆነ ዛሬ አገር ቤት ያለው ከኢትዮጵያ ሲዖልም ይሻላል እየለ ተጨማሪ የሞት ግብር በሚሆንባቸው አደገኛ ቦታዎች ሳይቀር መሰደዱን አላቆመም፡፡ ይህ ሁሉ ለዜጎች መከራ የሆነ አስተዳደር ምክነያት ነው፡፡ የዜጎችን ሕይወት መለወጥ ሳይሆን ዜጎችን በኑሮ ተማረው ከአገር ብን ብለው እንዲጠፉ የሚያደርጋቸው ጨካኝ የሆነ ሥርዓት በመገንባታችን ነው፡፡ ትዝ ይለኛል የዛሬ ዓመት በሊቢያ አንገታቸው የታረደውን ጨምሮ ብዙ ሌሎች ከአገር የወጡበት አንዱና ዋነኛው ምክነያት የኮንደሚኒየም ቤት ለማግኘት ክፈሉ የተባሉትን መክፈል ባለመቻላቸው ነበር፡፡  አገሪቱ የጥቂት ጨካኞች መኖሪያ ስልሆነች ዜጎች አቅማቸውን የሚመጥን ሁኔታ አይደለም የሚስተናገዱት፡፡ ለእነዚህ የወጣውን እጣ አሳልፈው ለሌላ ገነዘብ ላለው ይሰጡታል፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ገንዘብ ያለው ደግሞ በዘራፊዎችና ለሕዝብ ምንም ርሕራሔ በሌላቸው እጅ ነው፡፡ የአገሪቷም የኑሮ መሻሻል መለኪየዎች እነሱ ናቸው፡፡ በዛው ወቅት ለሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ በጓደኞቹ ሞት እጅግ ያዘነው ወጣት ብሶቱን ሲያሰማ ፖለቲካ ብለው ወደ እስር አጋዙት፡፡ ሲሆን ሊካስ በተገባው ከሙሉ ይቅርታ ጋር፡፡ የጭካኔው ልክ ሙልቶ የተረፈ ስለሆነ የልጆቹንም ሐዘን ለመገለጽ ብሶቱን ማሰማት አልቻለም፡፡ በደርግ ጊዜ ልጁን ገድለው አባቱን ልጅህን የገደልንበት ጥይት ዋጋ ክፈል የባል ነበር አሉ፡፡ እንዲህ ያለ አረመኔ የ60ዎቹ ትዎልድ ነው ዛሬም አገሪቱን የሚመራት፡፡

ሰሞኑን ደግሞ በየአገሩ የተበተኑ ልጆቻቸውን እንኳን እንዳያገኙ እነ ቫይበርንና የመሳሰሉትን እዘጋለሁ የሚል አዋጅ አውጥቷል፡፡ ከሌላው አለም በመለየትም ሕዝቡን ከቀዬው ውጭ እንደይመኝም ነው፡፡ በዚህና በምሳሰሉት ሁሉ ሁኔታ ታዲያ ብዙዎች ፖለቲከኞቻችንና ምሁሮቻችን ዛሬም ያረጁባትን ፍልስፍና ለጊዜውም ቢሆን ትተው የሕዝቡን እውነተኛ ችግር ላይ መወያየትና መፍትሔ መስጠትን አልመጣላቸውም፡፡ ችግሩ ደግሞ የትምህርት ግዙፍነታችንን እየተጠቀምን የምንፈጥረው ማሳሳት ሌሎች መፍሕትሔ የሚሆን ሐሳብ ያላቸውንም ማቀጨጩ ነው፡፡ በፍልስፍናው ታዋቂነትን ተጠቅሞ የሚፈጸምን ማሳሳት ፋላሲ ኦፍ አድፖፕለም ይባላል፡፡ ምሁሮቻችን በአብዛኛው እያደረጉ ያሉት ይሄንን ነው፡፡

በአጠቃላይ የኢትዮጵያና ሕዝቦቿ አብይ ችግር ከኑሮና አስተዳደርና ጋር የተየያዘ እንጂ የብሔር ጉዳይ ዋና ችግሮች ውስጥ እንዳልሆነ ነው የሚሰማኝ፡፡ ቢሆንም ቅሉ ሰሞኑን አንድ ምሁር የነገሩን አይነት መፍትሔ ሳይሆን ሌሎች የሕዝቡን ነባራዊ ሁኔታ የሚያማክሉ መፍትሔዎች አሉ ባይ ነኝ፡፡ ወረቀት ላይ እንደምናሰፍረው ያለ ሕዝብ የለም፡፡ አሁን ግን አላለሁ የኢትዮጵያን ጉዳይ በማነሸዋረር ብዙ በማንነትና በሕወታችን ላይ የመጡብንን ችግሮቻችንን ትኩረት እንዳንሰጥ የሚነሱ ሐሳቦችን ቢያንስ እንድናዘገያቸው አለምናለሁ፡፡ የሕዝብና የአገር ጉዳይ ይሰማን፣ ይመመን፡፡ ቢያነስ ብዙ የገዛ ሥጋ የሆኑ ወንድሞችና እህቶች፣ ወላጆች እየተሰቃዩባቸው ያሉትን ችግሮች እኛው ምክነያት በመሆን በአረመኔነት አንሳተፍ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን በምሕረት ይመልከት!

አሜን!

 

ሰርጸ ደሰታ

የአሰፋ ጫቦ ወጎች (ግርማ አውግቸው ደመቀ)

$
0
0

አሰፋ ጫቦ። 2016 (እግአ)።[i] የትዝታ ፈለግ። ዳላስ፣ ቴክሳስ። ምዕራፍ ብዛት 28 (መግቢያና ቅሱም ‘index’ አለው)፣ ገፅ ብዛት 332፣ ዋጋ $24.95፣ ISBN: 978-0-98983131-4።

***************************

አቶ አሰፋ ጫቦ

አቶ አሰፋ ጫቦ

ይህ ስራ ከላይ የተጠቀሰው የአሰፋ ጫቦ መፅሀፍ ላይ የቀረበ አስተያየት ነው። መፅሀፉ በተለያዩ ወቅቶች በጋዜጦችና በመፅሄቶች ላይ የወጡ መጣጥፎች ስብስብ ነው። ስለስብስቡ አሰፋ እንዲህ ይላል፤

“መጀመሪያ ለጋዜጦች የጻፍኩት የወጣው በ1956፣ […]  ‘ፖሊስና እርምጃው’ ላይ ነበር። […] ከዚያ ወዲህ አልፎ አልፎ ቢሆንም ብዙ የጻፍኩ ይመስለኛል።

“የትዝታ ፈለግ በሚል እዚህ አሁን የተሰባሰቡት ከዚያ የተውጣጡ መሆናቸው ነው። እንደሚነገረኝ ከሆነ ይኸኛው ቅጽ አንድ ይሆንና በተከታታይ የሚወጣም ይኖራል። እንደሚነገረኝ ያሰኘኝ እኔ ምን ያህል እንደጻፍኩ፤ አሁን የትስ እንደሚገኙ አላውቅምና ነው” (ገፅ 1)።

መጣጥፎቹን ያሰባሰበው ደራሲው አይደለምና በምን መስፈርት እዚህ ቅፅ የቀረቡት እንደተመረጡ የነገረን ነገር የለም። ያሰባሰቡትም ሰዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ያሉት ነገር የለም። መጣጥፎቹ የተሰደሩበትም ቢሆን በምን መስፈርት እንደሆነ የተገለፀ ነገር የለም። በተፃፉበት/በታተሙበት ግዜ ቅደም-ተከተል እንደሆነ ለመናገር የሚያስችል በቂ መረጃም የለም። አንዳንዶቹን ከራሳቸው ከፅሁፎቹ ይዘት በመነሳት ቢያንስ የተፃፉበትን ዓመት መገመት ይቻል ይሆናል። ይህ ግን በቂ አይደለም።

በይዘታቸው የጉዞ ማስታወሻ፣ ትውስታ፣ ትዝብት/ማህበራዊ ሂስ፣ የማህበረሰብ ገፅታ እና አብዛኞቹ ፖለቲካ ነክ ናቸው። መፅሀፉ የመጣጥፎች ስብስብ ነውና ለምን የተለያዩ ይዘት ያላቸው አንድ ላይ ቀረቡ የሚል የወጥነት ጥያቄ ሊነሳበት የሚገባ አይመስለኝም። በይዘት የሚያራርቃቸውን ያህል የሚያቀራርባቸው ነገርም አለ። ይህም ቋንቋቸው ነው። አሰፋ ጫቦ ከፖለቲከኛነቱ ይልቅ በብዕሩ የሚታወቅ ይመስለኛል።

ሶስት ገጠመኞችን ልጥቀስ፤ አንደኛው፣ የዛሬ ሀያ ዓመት ገደማ አንድ ጓደኛችን አስቴር አወቀ የሌሎችን የዘፈነችውን ሰምቶ፣ ምናለ የሁሉንም ድምፃውያን ዘፈኖች ባዜመቻቸው ማለቱ ነው። እኔም የተስማማሁበት ነበር። ሁለተኛው፣ ብላቴ የጦር ማሰልጠኛ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች ገብተው በነበረበት ወቅት፣ ካልተሳሳትኩ በየሳምንቱ የኪነት ቡድን ይመጣ ነበር። ከኪነት ቡድኖቹ በፊት ይሁን በኋላ ወይም በየመሀከል አንዳንድ ሰዎች እየተነሱ (አንዳንዴ ግጥምም ቢቀርብም) በዋናነት ስለሀገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታና የተማሪው/ሰልጣኙ የወደፊት ድርሻ ምን መሆን እንደሚገባው ንግግር ያደርጉ ነበር። ውይይት ነበረ ለማለት ይከብዳል። ተናጋሪዎቹ በየሳምንቱ አብዛኞቹ ያው ናቸው።  ከነዚህ ውስጥ ግን ሁሌም በሚናገረው መሳጭ የነበረው ሰለሞን ኃይለማርያም የተባለ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሄደ ነበረ። የፈለገውን ያህል ሰዓት ወስዶ ረጅም ንግግር አድርጎ  ቢቀመጥም ሁለት ሶስት ሰዎች ከተናገሩ በኋላ ተማሪው/ሰልጣኙ ሰለሞን ይናገር እያለ በመጮህ፣ በድጋሜ እየወጣ ይናገር ነበር። እኔም የሰለሞን ንግግር ከሚመስጣቸው ውስጥ አንዱ ነበርኩ። ሶስተኛው ገጠመኝ፣ ይህ የአሰፋን ስራ ሳነብ የተሰማኝ ነው። አንብቤ ከጨረስኩ በኋላ አነበብኩ ብዬ አልረካሁም። ደጋግሜ እያነበብኩ እመሰጥበታለሁ። መላልሼ ካነበብኳቸው ውስጥ “ትዝታ ነው የሚርበኝ” በሚለው ርዕስ ስለ ትውልድ ሀገሩ ጨንቻ የገለፀበትንና “ዶሮ ራስ አንበል” በሚል ስለአንዲት ዶሮውና በግ የተረከበት መጣጥፍ ዋናዎቹ ናቸው። ይዘታቸው ጠጥሮ አይደለም። ማርኮኝም ነው ለማለት ይከብደኛል። አብዛኛው አዲስ ነገር አይደለምና። እንደዚያች አይነት ዶሮ እኔም አውቃለሁ። በጨንቻ የታየውም ለውጥ በብዙ የሀገራችን ክፍሎች ባሉት የታየ ነው። እኔን የሳበኝ ቋንቋቸው መሆን አለበት። አሰፋ እጁ ሳያቋርጥ ስለሁሉም ነገር በፃፈ ተሰኘሁ። ይህ መታደል ነው።

የአሰፋ ትውልድ ይገርመኛል። የአሰፋ ትውልድ የምለው ከ60 ዓመት በላይ ያለውን ሁሉ ነው። አሰፋ “ከ50 ዓመት በላይ ያለ ሁሉ ለኔ ወጣት ነው” ይላል (ገፅ 1)። ከሱ መስማማቴ ወይ መለየቴ አይደለም። በሀገራችን ታሪክ ላይ ከፍተኛ አሻራ የተወ ትውልድ ስለሆነ ነው። በተለይ ፊደል ቀመስ የሆነውን የሚመለከት ነው። ይህን ትውልድ ወደፊት ታሪክ አንድም በጥሩ፣ አብዛኛው በክፋት የሚዘክረው ይመስለኛል።

ምንም እንኳ የምዕራባዊያን አይነት አለማዊ ትምህርት በመንግስት ደረጃ በምኒልክ ግዜ ቢጀመርም፣ በጣም የተስፋፋውና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም የተከፈቱት በኃይለሥላሴ ወቅት ነበር። የዘመናዊ ትምህርቱ ከሀገራችን ነባር የትምህርት እድገት የተገኘ አለመሆኑና ከህብረተሰቡ ባህልና ልማዳዊ እውቀት ላይ አለመመስረቱ ወይም ለማዛማድ መንገድ ሳይፈልግ መካሄዱ የዚህ ዘመን አመጣሽ ትምህርት ቀማሽ የሆኑት እድሜያቸው ሰላሳን ያልዘለለ ከእኛ ወዲያ አዋቂ ማን አለ ባይ እንዲሆኑ መንገድ ከፈተ። አባቶቻቸው በዚያ ያለፉ አልነበሩምና እነሱን መስማት ኋላቀርነት ሆነ። የአባቶቻቸው አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን፣ አባቶች እራሳቸው ኋላቀር ተደርገው ተወሰዱ። ማን ከእድሜ ባለፀጋ አባቶች ምክር ይሰማል! የወቅቱ የአለማችን ፖለቲካ ተጨምሮ፣ ሀገሪቱ ከማትወጣበት አዘቅት ውስጥ ከተቷት። ነጭሽብር-ቀይሽብር፣ ከዚያም በላይ በጎጥ እና በመንደር ተቧድኖ እርስ በእርስ መጋደላቸው አንሶ በእድሜ ጠግበው ይማራሉ በሚባልበት ሰዓት፣ ወንድም ወንድሙን ገድሎ ኃውልት የሚሰሩ አሳፋሪዎች የወጡበት ትውልድ ለመሆን በቃ። ከታሪካዊ የጥቅም ጠላቶቻችን ጋር አብብሮ[ii] ወንድሙን የሚገድል፣ በዚህም የሚኮራ ትውልድ ሆነ። ጥራዝ ነጠቅ እውቀት ሁሌም አደገኛ ነው።

በምኒሊክ አድዋ ድል ማግስት አንድ የአሜሪካ ልዑካን ቡድን ወደኢትዮጵያ መጥቶ ነበር። የዚህ ቡድን መሪ የነበረው፣ ሮበርት ፒ. ስኪነር የተባለ ዲፕሎማት ነበር። ይህ ሰው ጉዞውን መዝግቦ በኋላ መፅሀፍ አድርጎ አሳትሞታል። ስኪነር በዚህ ላይ የታዘበውን እንዲህ ብሎ ነበር፤ “የተባበረች ኢትዮጵያ ነፃነቷን ለመድፈር የሚመጣባትን እስከመቼውም ልትቋቋም ትችላለች—ከዚህ በፊት እያንዳንዱን ወረራ በተሳካ ሁኔታ መክታ እንደመለሰችው። ኢትዮጵያ ልትሸነፍ የምትችለው፣ ህዝቦቿን አንዱ በአንዱ ላይ እንዲነሳ በማድረግ/ከተነሳ ብቻ ነው”።[iii] ጣልያን ከ30 ዓመት በኋላ ከሞላ ጎደል ይህንን ለመጠቀም ሞክራ ነበር። የጣልያን ባይሳካም ሀገር በቀል ወራሽ ግን አልጠፋም።

የአሰፋን ትውልድ በጅምላው እንዳንወቅስ የሚያደርገን በጣት ቢቆጠሩም የሚያስደንቁ ስብዕናዎችም መኖራቸው ነው። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ኃይሌ ገሪማ[iv] ነው። በብዕራቸው ብቻ የማይሞት ስም የተከሉና ለቀጣይ ትውልድ መኩሪያ ከሆኑት ውስጥ ደግሞ እነፀጋዬ ገብረመድህን እና በዓሉ ግርማን መጥቀስ ይቻላል። እነዚህ ሰዎች ብዕራቸውን ለሰብዓዊነትና እውነት ለመሰላቸው አውለውታል። አሰፋ ከእነዚህ (እና ሌሎች ስማቸውን ካልጠቀስኳቸው ጥቂት) ሰዎች ተርታ የሚገባ ይመስለኛል።[v]

አሰፋ፣ በዚህ መፅሀፉ በብዕሩ ያነሳቸው ጉዳዮች አንዳንዴ ይገርሙኛል። ለምሳሌ፣ “የኔይቱን ጀግና” ይመልከቱ። በቤት ሰራተኝነት የገባች ሴት እንዴት የቤት አስተዳዳሪና የቤቱ አርዓያ እንደሆነች የሚተርክበት ነው። ጀግና ፍለጋ ሩቅ አልሄደም። ስም ያለውንም አልፈለገም። እራሱ ስም አበጀ እንጂ። በዚያ ፅሁፍ ከሴትዮዋ ሰናይ ምግባርና አርአያነት በላይ እኔ ያየሁት ደራሲውን ነው—ለሰው ልጅ ያለውን ክብር።

በፖለቲካ አቋማቸው ቀናኢ ሆነው ለሚያምኑበት ሽንጣቸውን ገትረው በመሟገት የሚገርሙኝና የማደንቃቸው ሁለት ሰዎች ቢኖሩ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምና አሰፋ ጫቦ ናቸው። ሁለቱም ፍርሀት ማለት ምን እንደሆነ የሚያውቁ አይመስለኝም። ምሁር ተብዬ ስብዕና ቢስ ከበዛበት ትውልድ ቢወጡም፣ ለሆድ ብሎ ማደር እነሱ ጋ የለም። ይህ የአሰፋ ስብስብ ስራ የሚያመለክተን ይህንኑ ነው። ዛሬ፣ በሀገር ቤት ያለውን በጎሳ ከፋፈለ ብሎ የሚወቅስ በውጭ፣ በተለይ በምዕራባውያን ሀገሮች፣ የሚኖረው ዜጋ ፖለቲከኛው ቀርቶ  የሀይማኖት ሰው ነኝ ባዩ ሳይቀር እራሱ (በጎሳ-ፖለቲካ) ተከፋፍሎ (ከሀገር ቤት በባሰ ሁኔታ) ሲናቆር ይታያል። አሰፋ በዚህ አብሮት በሚኖረው ስደተኛ ላይም ቢሆን፣  ብዕሩን አልመለሰም። ምዕራፍ 24 ማርከሻው ጠበሉ! እንደጠፋ ቀረ…? እንደተሰወረ??! በሚለው ርዕስ ላይ የሚከተለውን ይላል፤ “በዚህ ላይ ትንሽ እዚህ አሜሪካ ቆየት ያልነው በሃብት (Material) ድህነትና በአእምሮ ድህነት መካከል ያለው ልዩነት የጠፋብን ይመስለኛል። ከኢትዮጵያ የሚመጣ ሰው የፈለገውን ያክል የተማረ የተመራመረ ቢሆን እንደ አላዋቂ የመውሰድ አዝማሚያ ሰፍኗል። ከዚህም የተነሳ ዛሬ ጧት ከኢትዮጵያ ለመውጣት [sic ለወጣ] ምሁር ‘የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ’ ‘ተንትኖ ለማስረዳት ለማስተማር’ እንሞክራለን። ነገሩ ያሳዝነኛል!!” (ገፅ 267)። እውነትም ያሳዝናል። የሚያሳዝነው የፖለቲካችን ነገር ብዙ ነው። እዚያ ውስጥ አልገባም—ለዚህ ከበቂ በላይ ፖለቲከኞችና ተንታኞች አሉና።[vi]

ግርማ አውግቸው ደመቀ

ትሪንተን፣ ኒውጀርሲ

ቀን: 4/10/2016 እግአ

[i]               እንደ ግሪጎሪያን አቆጣጠር

[ii]              በዚህ ቃል ላይ የ ‘ብ’ መደገም ጥብቀትን ለማመልከት ነው።

[iii]     ትርጉሙ ቃል በቃል አይደለምና የእንግሊዝኛውን ቃል ልስጥ፤ “A united Abyssinia would be able to resist indefinitely any ordinary attempt to break down an independence which has withstood assault successfully from every invasion […]. If independent Abyssinia falls, that contingency is most likely to result from dissensions among the Abyssinians themselves” (Skinner, Robert P. 1906. Abyssinia of To-Day: An Account of the First Mission Sent by the American Government to the Court of the King of Kings (1903-1904). London, New York: Longman, Green & Co., p. 178.)

[iv]     ኢትዮጵያም ሰፍታባቸው የመንደር ፖለቲካን ከጠነሰሱ ትውልድ መሀል ወጥቶ፣ ኃይሌ በተቃራኒው በሙያው የመላው ጥቁር ህዝብ ጉዳይ፣ ጉዳዩ አድርጎ በአለም ስሙን የተከለ የአፍሪካዊ መብት ተሟጋች ነው። ለዚህ “ሳንኮፋ” የተሰኘ ፊልሙን ብቻ መመልከት ይበቃል።

[v]      የእነዚህ ሰዎችን የታሪክ ቦታ ለመገንዘብ ከፀጋዬ “እሳት ወይ አበባ”ን (ወይም ከዚያ ውስጥ አንዲቷን ግጥም፣ “ሰቆቃወ ጴጥሮስ”ን)፣ ከበዓሉ “ከአድማስ ባሻገር”ን፣ እና ከአሰፋ ይህን መፅሀፉን ብቻ መመልከቱ በቂ ይመስለኛል።

[vi]     የፖለቲካው ችግር በቀጥታ የሚመለከታቸው ሀላፊዎች ግን፣ ለመፍትሄው (ቅንነቱ ካለ) ከመስፍንና ከአሰፋ ስራዎች በተጨማሪ ከሌሎች መሰል በሳልና ቅን አሳቢዎች ስራ ብዙ መማር የሚችሉ ይመስለኛል።

Hiber Radio: ለጋምቤላው እልቂት ሳሞራ የኑስ እና ጄ/ል አብርሃ ማንጁስ ተጠያቂዎች መሆናቸው ተገለጸ – (ልዩ ዘገባ በጋምቤላና በወቅታዊው የሃገራችን ጉዳይ)

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 10 ቀን  2008 ፕሮግራም

… በጋምቤላ የተከሰተው ግድያ ድንገተኛ አደጋ አይደለም በተደጋጋሚ እየተሰነዘረ የነበረ ጥቃት ነው።  ራሳቸው የሕወሓት ባለስልጣናትየሚያውቁት ነው። ጠረፍ ጠባቂ ማድረግ ሰራዊት እዛ መኖር ነበረበት ሀላፊነቱ የመንግስት ነው…መፍትሔው ይሄን ስርዓት መለወጥ ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ላይ ጫና መፍጠር ሕዝቡ በአንድ ላይ ለመብቱ እንዲቆም ማድረግ ካልተቻለ ግድያው ትላንትም ነበር ዛሬ አለ ነገም…>አቶ ኦባንግ ሜቶ የትብብር ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች  የተወሰደውን ግድያ አስመልክቶ  ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ     (ሙሉውን ያዳምጡት)

…ሰራዊቱ የሕወሃት ባለስልጣናትን ንብረት፣የነሱን ስልጣን ጠባቂ አድርገውታል። ኦሮሚያ ላይ ከፍተኛ ሰራዊት አላቸው፣በመሐል አገርበተለይም ከፍተኛ ቁጥር ያለው በሰሜን እዝ አለ ። ባለፈው በኤርትራ ወጣቶች ተወሰዱ ሲባል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አንቀሳቅሰዋልዛሬ ግን ሰው እንኳን ሞቶፈጣን እርምጃ አልወሰዱም በዚህ ጥፋት ተጠያቂዎቹ የሰራዊቱ አመራሮች ናቸው።ሰራዊቱ ግን በአሁኑ ወቅትእየጠየቀ ነው …> ኮሎኔል ደረሰ ተክሌ የቀድሞ የሰራዊቱ የጥናትና ፕላን ክፍል ሀላፊ በጋምቤላ የተከሰተውን ግድያ አስመልክቶ ለህብርከሰጡት ማብራሪያ(ሙሉውን ያዳምጡት)

…በጋምቤላ የተወሰደው ግድያ ከደቡብ ሱዳን ድንበር ጥሰው የገቡት የሙርሌ ታጣቂዎች ግድያ ሲፈጽሙ የዛሬው የመጀመሪያ አይደለም።ከሳምንት በፊት ፉኢዶ ላይ ሃያ አኙዋኮችን ገለው ከብት ዘርፈው አፍነው የወሰዱዋቸውን ሶስት ህጻናት ገለዋል። የወያኔ ባለስልጣናት ያሉትየለም። ሕዝቡን ትጥቅ አስፈትተው እርስ በእርሱ ከፋፍለው እየገደሉና እያስገደሉ ያሉት እነሱ ናቸው…ስርዓቱ ካልወደቀ ግድያውአይቆምም።…> አቶ ኡዶል ኡጁሉ የታህሳስ ሶስት መታሰቢያ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በጋምቤላ በንጹሃንላይ የፈጸሙትን ግድያ አስመልክቶ ከሰጡን ቃለ ምልልስ(ቀሪውን ያዳምጡ)

በሊቢያ በረሃዎች እና የባሕር ዳርቻዎች ላይ የዛሬ ዓመት በአረመኔዎቹ አይሲስ ታጣቂዎች በግፍ ስለተገደሉት 30 የሚጠጉ ወገኖቻችን ቅዱስመጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ቁርዓኑስ? ስለ ከፈሉት ሐይማኖታዊና ኢትዮጵያዊ ተጋድሎ የሚዘክር መሰናዶ(ልዩ ጥንቅር)

በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ሕዝባዊ ንቅናቄ በአገዛዙ የመብት ረገጣ እየተዳከመ ነው? የተቃውሞ አመራሮች ተገቢውን አመራር ሰጥተዋል እናሌሎችን ወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክቶ ከቢቢኤኑ ዋና ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሳዲቅ አሕመድና ከአንሃፋው ጋዜጠኛ በፍቃዱ ሞረዳ ጋርያደረግነው ሰፋ ያለ ውይይት የመጀመሪያ ክፍል(ያዳምጡት)

ኦቲዝም እና ልጆቻችን ወላጅና ባለሙያ ምን ይላሉ ቃለ መጠይቅ ተካቷል(ያዳምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በጋምቤላ በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ለተገደሉት ከ200 በላይ ንጹሃንና ለታፈኑት  ከመቶ በላይ ህጻናት የምዕራብ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል አብረሃማንጁስና ኤታማዦር ሹሙ ሳሞራ የኑሱ ተጠያቂዎች መሆናቸው ተገለጸ

ከግድያው የተረፉ እማኞች የክልሉን የዘገየ እርምጃ አውግዘዋል

አባዱላ ገመዳ ኢህአዴግ መቶ በመቶ በተቆጣጠረው ፓርላማ ተቀምጠው ጸሎት እንዲደረግላቸው መጋበዛቸው የስርዓቱ ደጋፊዎችን ጭምርአስቆጣ

የጋምቤላውን ጥቃት ተከትሎ ኢትዮጵያውያን የአገሪቱን ድንበር መጠበቅ የተሳነው አገዛዝ ላይ ቅሬታቸውን ማቅረብ ቀጥለዋል

የአረብ ኢሚሬት በአሰብ ወደብ ላይ ወታደራዊ ተቋም መገንባት ለኢትዮጵያ ስጋት መሆኑ ተነገረ

ኮስታሪካ በህገወጥ መንገድ ወደ ግዛቴ ገቡ ያለቻቸውን ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ዳግም ወደ ፓናማ ማባረሯ በሁለቱ አገሮች መካከልውጥረት ፈጠረ

በጣሊያኑ ላምባዱሳ ደሴት አቅራቢያ ለሰጠሙት ወገኖቻችን ተጠያቂ የሆነው ግለሰብ ጣሊያን ውስጥ ቅጣቱን አገኘ

ለስልጣኑ የሰጋው የኢትዮጵያው አገዛዝ የፈለገውን ኮምፒዩተር ለመሰለልም ሆነ የዜጎችን የዲጂታል እንቅስቃሴ ለመገደብ ሕግ አርቅቆ አቀረበ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ከጠቀመ ትንሽ ሀሳብ –ዳዊት ዳባ

$
0
0

130153መንግስት ዋና ሀላፊነቱ የዜጎቹን ደህንንት መጠበቅ ነበር። ጋንቤላ ውስጥ እየተፈፀመ ባለው ዘር ማጥፋት የተነሳ አልቻላችሁምና ስልጣን ልቀቁ ትክክለኛ ነው። መንግስት ቢሆኑ ሳይባሉም ስልጣን በለቀቁ ነበር። ያሉት አንድና አንድ ወያኔዎች ናቸው።  ያገር መከላከያና የፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም የደህንነት አባላት እራሳችሁን ነፃ ሳታወጡ ህዝባዊም አገራዊም መሆን አትችሉም። ትክክል።   ይህ ፅሁፍ በወገኖቼ እልቂት  የተሰማኝን መራራ ሀዘን የገለጥኩበት መንገድ ነው።

 

ስርአቱ እጅግ አስከፊ ከመሆኑ የተነሳ  እስካሁን በአንድ ቃል ለመግለፅ የቻለ የለም። አንባገነን፤ አገር ሻጭ። ጨፍጫፊ፤ ዘረኛ። አድሏዊ ባለጌዎች።  ደናቁርት፤ ጠይዎች። ትግሬዎች ዘራፊዎች። …..  ሁሉም ስሞች ግን ይገልፁታል። ለማንኛውም  “ሰዎች ናቸው”። ጀሌውንም ጨምርን ያን ያህል ጉልበት ሆኗቸዋል ሊባል በሚችል ደረጃ ቁጥራቸው ብዙ አይደለም። “ ጉድ” ሊሰኝ በሚችል ለረጅም ጊዜ መግዛት ግን ችለዋል።  ታዲያ የመግዛት ጉልበቱን ከምን አገኙት?። ለሚለው ከባድ ጥያቄ የምናገኘው መልስ  በጣም ቀላል ነው። ሁላችንም የምንስማማበት መልስም ነው ያለው። ብዙ አባሪ ሊሆኑ የሚችሉ መልሶች ቢኖሩም በዋናነት የመግዘት ጉልበቱ የሚመነጨው መከላካያ ፖሊስና በደህንነት ስራ ላይ ከተሰማሩ ዜጎች ነው።  ለመግበያ ያህል ነው እንጂ ዋናው አሳቤ ላይ እንዳያጠላ ትንታኔ ውስጥ አልግባ። ስልጣን ላይ በቆዩበት ጊዜ ሁሉ እነዚህን ሰዎች እየተቃወምን እየታገልናቸው አለን።  ለማሸነፍ  ቁልፍ የሆነው  ያላስፈላጊ ጉልበት የሆናቸው አካል ላይ የተሰራ ስራን በተመለከተ ጥረቶች አሉ ማለት ይቻል እንደው አላውቅም። በበቂ አልተሰራበትም ብሎ መናገር ግን ይቻላል። ለማንኛውም ይህ ጉዳይ ሌላም አስገራሚ ጎን ስላለው እሱን ብዬ ወደዋና አሳቤ ልግባ። አገዛዙ ውስጥ ያሉትን ሰዎች በሶስት መክፈል ይቻላል። ሙሉ ነፃነት ያላቸው እንዳሻቸው ተጠቃሚ ፈላጭ ቆራጮች ስብስብ። በገደብ ተጠቃሚ ግን ነፃነቱ እንደኛው የሌላቸው ይባስ ብሎ የተዋረዱ ስብስቦች።  ተከፋይ ግን እንደኛው ተጨቋኝ ብቻ ሳይሆኑ የተናቁ ግልጋሎት ሰጪዎች።  ከጥቂት አለቆች በቀር በሙሉ የመከላካያና የፖሊስ ሰራዊቱ አባላት ውስጥ ያሉ ዜጎቻችን ሶስተኛው ክፍል ውስጥ ነው የሚመደቡት። ይህ ክፍል ነው እንግዲ ላገዛዙ እስትንፋስ የሆነው።

 

 

ሀሳቡ ሚዛን ከደፋና ሊተገብረው ፍቃደኛ ከተገኘ እንድ ወር የመዘጋጃ ጊዜ ሰጥተን ለአንድ ወር የሚቆይ ሁሉ ድርሻ የሚያደርግበት ዘመቻ እናድርግ። በፈረንጅ አቆጣጠር ዛሬ ቀኑ መያዚያ 18 ነው። እስከ ሚቀጥለው ወር መጀመርያ ሀሳቡ ተቀባይ ሊሆን ይችላል እንበልና። ሙሉ ግንቦትን መዘጋጃ እናድርገው። ከዛም ሙሉ የሰኔ ወር ቀጥቅጠን የማሳወቅና የመማማር ዘመቻ የምናደርግበት ወር ይሆናል ማለት ነው። ይህ ታላቅ አገራዊ ቁም ነገር የሁለት ወር ካስራ አምስት ቀን ትኩረታችንን ያገኛል።

 

ይህን አይነት ዘመቻ በሌሎች አገራዊ ጉዳዬች ላይ መለስተኛ በሆነ ደረጃ ሲደረግ ነበር። መሳርያ በጁ ያለው ላይ የሚሰራውን ያህል ግን ሌሎች ጉዳዬች ላይ ጉልበት የለውም። አገዛዙን ገሸሽና ቀርቅበን  የምንሰራው ስለሆነም ነው። ጠቅለል አድርገን ስናየው የምናደርጋቸው ነገሮች በጣም ቀላል ናቸው። የምንናገር፤ የምንወያይ፤ የምንሰበሰብ፤ የምንፅፍ ላንድ ወር ፍፁም በሆነ ሁኔታ አንድና አንድ ይህንን አገራዊ ቁም ነገር የሰኔ ወር አርእስታችን እናደርገዋለን። ጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ካሉ ግኝታችውን በዚሁ ወር ያቀርባሉ። መናገርያ መሰብሰቢያ መወያያ መድረኮችን እናዘጋጃለን። በዚሁ ወር ውስጥ ቤተሰብ፤ ቤተዘመድ፤ ጓደኛ ሚሰት  በቁም ነገር ቁጭ አድርገውም ሆነ ደውለው መከላከያና የፖሊስ ሰራዊት ውስጥ ያሉ ልጆቻቸው ጋር አገራዊ ውይይት የሚከፍቱበት ወር ይሆናል። ዘመቻው በሙሉ አወንታዊ መንፈስ ያያዘ ስለምናደርገው ነጋዴዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ለፖሊስ ሰራዊቱና ለፖሊስ አባላት ወገኖቻችን ቅናሽ እንዲያደርጉ ትብብር ይጠየቃሉ። ሰልፎች፤ የሚበተኑ ወረቀቶች መልእክቶች ላገር መከላከያና የፖሊስ ሰራዊቱን የሚመለከቱ ይሆናል። ሜዲያዎቻችን የየለት ፕሮግራም ይኖራቸዋል። ከሞቀ ሰላምታና ፈገግታ ጀምሮ ህዘብ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በዚህ ግዚያት መልክም መቀራረብን ያደርጋል። ጠንካራ መልእክት ያላቸው አጫጫር ማስታወቂያዎች በብዛት ይተላለፋሉ። የኪነ ጥበብ ስራዎች ይጨመሩበታል። ብቻ የዚህ አይነት ቀላል ልናደርጋቸው የምንችላቸውን ነገሮች የምናስብበትና የምንፈጥርበት ወር ይሆናል። እውነት ለመናገር ጭንቅላታችንን ከሰጠነው በዙ መፈጥር እንችላለን። ለምሳሌ የእርስ በርስ ሰላምታችንን ላንድ ወር ወታደራዊ ማድረግ እንችላለን።  አሁን ማድረጉ ብዙ ተሳታፊን አገር ውስጥ ከማስገኘት አኳያ ጥቅሙ ያየለ ነው። አመት መጠበቁ የኦሮሞ ህዘብና የስልምና እምነት ተከታዬች እንዲሁም ሌሎችም በቀላሉ የትግላቸው አካል ሊያደርጉት የሚችሉበትን መልካም አጋጣሚ ሊያሳጣን ይችላል።  ጉጀሌው የመከላከያና የፖሊስ ሰራዊት ወር ብሎ በሰየመው በየአመቱ የካቲት ላይ የሚደረገው ጊዜም ተስማሚነት አለው የሚለው ስለታሰበኝም ነው። ይህን ሀሳቡ ተመችቷቸው ተፈፃሚ ለማድረግ ለደፈሩ የዘመቻወን ጊዜ በተመለከተ ውሳኔውን እንተወው። ከአረቡ አቢዬት ጀምሮ በሌላ መስመር ሀሳቡን ተፈፃሚ ለማድረግ ተሞክሮ ስላልተሳካ ወደ ህዝብ የመጣ መሆኑ ግን ይታወቅ።

 

ፋይዳው ምንድን ነው?። ምንም ካለማድረግ የሆነ ነገር መሞከር ይሻላል ከሚለው ጀምረን– ለዛሬው ብቻ ሳይሆን ለሁሌም የአገር መከላከያ፤ የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት አባላት ከመንግስት ጋር ያላቸው የተበላሸ የግንኙነትና ያሰራር ባህል በመጪው ማስተካካያ ሊበጅበት በሚቻልበት ቁም ነገር ላይ የምንመክርበት ይሆናል የሚል ድረስ የሚሄድ ነው። መሀል ላይ ያለው ተገልፆ የማያልቅ ጥቅም የተተወው ለማሳጠር ሲባል ነው። በጭራሽ ግን ከማሸነፍ አኳያ ብቻ  ፋይዳው የተሰላ አድርገን እንዳንወሰደው።

 

የዘመቻው ግብ ምንድን ነው?። የምንሰራውን ስራ ስኬታማነት የምንለካበት መስፈርት ማበጀት ሁሌም ያስፈልጋል።  የመጨረሻ ግቡ ወገንታዊነቱ ለዜጎችና ለአገር የሆነ የመከላከያ የፖሊስና የድህንነት አባላት እንዲኖሩን ማድረግ ነው። ያ ትልቁ ግብ ሆኖ በዚህ ዘመቻ ልንደርሳቸው እየጣርን እንደሆነ እንዲያውቁት ማድረግ ከቻልን ከበቂ በላይ ነው። ይህን ማድረግ ከቻልን ዘመቻውን በተሳካ ሁናቴ በበቂ ፈፅመንዋል ብለን እንወስደዋለን።

 

ልንሰራው የሚቻለን ነው ወይ?። በደንብ። ለለውጥ በሚታገለው ክፈል አቅም በቀላሉ ሊሰራ የሚችል ነው። ድርጅቶችን የሚያስተባብር  ከመሆኑም በላይ ዜጎች ሁሉ ድርሻ ሊያደርጉበት የሚችሉበትም ስራ ነው። ባሉን የመገናኛ አገልግሎቶች ለስራው በቂ ናቸው። ይህም ብቻ ሳይሆን መገናኛዎቻችን አንድ አገራዊ ቁም ነገር ላይ አነድ አይነት ስራ የመስራትን ልምድን እንዲዳብር የሚያደርግ ነው።

 

ሊኖሩ የሚችሉ ተግዳድራቶች ምንድን ናቸው?። የዚህ አይነት ስራ ውጤቱ ያኔውኑ የሚታይ ስላልሆነና ተሰልፎ እንደመቃወም የተለመደ ስላልሆነ መሳነፍ ሊኖር ይችላል። የነገሱብን ፈላጭ ቆራጮች ስለሆኑ ለምን ሰላም አላችሗቸው ማለታቸው ስለማይቀር አገር ውስጥ ያሉ ዜጎች በተሳትፏቸው በድርጊታቸውም ሆነ ቃላቶቻቸው ላይ ጥንቃቄን ማድርግ ሊኖርባቸው መቻላቸው ነው። ሲጀመር ሀሳቡን በመነሻነት ወስዶ አዳብሮ ሊተገብረው የሚችል መኖሩም ትልቁ ችግር ነው።

 

የተረገዘው አገራቀፋዊ እንቢተኝነት ከመወለድ በፊት በሗላ ችግር ከመዘርዘርና አጨናጋፊ እንዳይሆን ደግሞ መሰራት ያለበት ስራ አሁኑኑ ይሰራ። ኢሳትና ቪዥን ኢትዬጵያ ያዘጋጁት የውይይት መደርክ አገራዊ ፋይዳው የበለጠ የሚታወቀንና የምናደንቀው ዛሬ አይደለም። መቀጠል ያለበት ታላቅ  ስራ ብዬዋለው። በግሌ ሙዚቃም እንደዚህ መስጦኝ አላዳምጥም። እንደዚህ ዝግጅት የተማርኩበትም ተስፋም የሰጠኝ ነገር የለም። ምስጋና ለተሳታፊዎችም ላዘጋጆችም በሙሉ።

 

ብሄራዊ ጭቆና ይብቃ።

 

ዳዊት ዳባ dawitdaba@yahoo.com Monday, April 18,

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live