Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አርማጭሆ መልስ፤ ወደ ወገራ ጉዞ –ከሙሉቀን ተስፋው

$
0
0
gonder
ክፍል ፬  
ከአርማጭሆ ጎንደር ስገባ ድርገት ነበር፡፡ በጣም መሽቷል፡፡ ቀበሌ 12 ቢራ ለመጠጣትና ወሬ ለመቃረም ገባሁ፡፡ የገባሁባት ቤት አንድ ጊዜ ከአንድ ወዳጄ ጋር አውቃታለሁ፡፡ የቀበሌ ቤት ናት፡፡ ቤቷ ከዐሥር ሰዎች በላይ በአንድ ጊዜ ማስተናገድ አትችልም፡፡ ስለዚህ ደንበኞች በአንድ ሰዓት ከገቡ ሌላ የውጭ ሰው መግባት አይችልም፡፡ ከዚህች ቤት የማይዳሰስ ፖለቲካ አሊያም አገራዊ ጉዳይ የለም ማለት ይችላል፡፡ ቤቷን በወሬ ማድመቅ የሚችል ሰው መቼም ቢሆን ቢራ ከፍሎ ላይጠጣ ይችላል፡፡ ሞቅ ያለው የሰሊጥ ነጋዴ ‹‹አባቴ ይሙት!›› እያለ የሁሉንም ሰው የሳምንት ሒሳብ ሊዘጋ ይችላል፡፡ የቻልከውን ያክል እየጠጣህ መጫወት ነው፡፡ ከዚህች ቤት ብዙ ነገር ለመረዳት ችያለሁ፡፡ የተሸከምነው አምባገነን ሥርዓት በዜጎች መካከል አለመተማመን ፈጥሯል፡፡ የዚች ቤት ደንበኞች ሕወሓት በዐማራው ሕዝብ ላይ የሚያደርሰው ግፍ ከመጠን የዘለለ መሆኑን ያምናሉ፡፡ ከመጠጥ ደንበኞች መካከል የሰሜን ጎንደር ፖሊስ መምሪያ በኃላፊነት ቦታ ላይ እንዳሉ የተረደዋቸው ሰዎች ሁሉ ነበሩበት፡፡ የጎንደር ዐማሮች ሕወሓትንና የትግራይ ሕዝብን አንድ አድርገው ይመለከታሉ፤ እርግጥ ነው ይህ በብዙ የአገራችን አካባቢዎች እንዳለ አውቃለሁ፡፡ ጎንደር ግን በግልጽ ያለ ምንም ፍርሐት እከሌ አለ የለም ሳይባል በግልጽ የሚወራ አሊያም የሚነገር ነው፡፡ ከዚችው መሸታ ቤት የሰማሁት እውነታ (ቀልድ ሊሆን ይችላል) አስተሳሰቡ ምን ያክል የሰረጸ እንደሆነ ሊሳይ ይችላል፡፡ አንድ ከሽሬ የመጣ ሰው ቸቸላ ሆስፒታሉ ጋር ለመሔድ መስቀል አደባባይ ላይ ባጃጅ ኮንትራት ይጠይቃል፡፡ ‹‹ዋይ! አንተ ቸቸላ ሆስፒታል ስንት ትወስደኛለህ ኮንትራት?›› ይላል ከትግራይ የመጣው ሰው፡፡ የባጃጅ ሾፌሩ ‹‹መቶ ብር!›› በማለት ይመልሳል፡፡ ከመስቀል አደባባይ እስከ ቸቸላ ሆስፒታል የኹለት ብር ታክሲ ትራንስፖርት ነው፡፡ ኮንትራት የሚይዝ ሰው ከዐሥር ብር የበለጠ አይከፍልም፡፡ ሆኖም እንግዳው ሰው ባልጠበቀው የዋጋ መናር ተገርሞ ‹‹ዋይ አቡነ አረጋይ! አንተ ለዚህ ቸቸላ ሙቶ ብር ያልከኝ አገሬን ሽረ አድርሰኝ ብልህ ስንት ልትወስደኝ ነው?›› በማለት የባጃጅ ሾፌሩን ጠየቀው፡፡ ‹‹ተመልሰህ ካልመጣህ በነጻ እወስድሃለሁ!›› በማለት መለሰለት፡፡
ይህ እዚች መሸታ ቤት ሲነገር የሰማሁት ነው፡፡ መሸተኞች የራሳቸው ጓደኛ እንደተናገረው አድርገው ነው ያወሩት፡፡ ቁም ነገሩ እውነት ወይም ቀልድ መሆኑ ላይ አይደለም፡፡ የትኛውም ቢሆን አገዛዙ የትግራይ ተወላጆች እንደ ባዕድ እንዲቆጠሩ አድርጓቸዋል፤ ትግሬዎች በየትኛውም የአማራ አካባቢ በጥርጣሬ ይታያሉ፡፡ ይህ ከኹለት ነገር ሊፈጠር ችሏል፡፡ አንደኛ አገዛዙ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚልካቸው ደኅንነቶች የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው ትግሬ የተባለ ፍጥረት ሁሉ የአገዛዙ አጋዥ እንደሆኑ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ሌላኛው ምክንያት ደግሞ አገዛዙ የትግሬዎችን መጠላት የሚፈልገው ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ትግሬዎች በሌሎች ኢትዮጵያውያን እንደጠላት ሲቆጠሩ አንድነታቸውን አጠናክረው ሕወሓትን ሊደግፉ ይችላሉ ከሚል ያረጀ ያፈጀ የፖለቲካ ፍልስፍና የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ በጣም ረጅም የበረሀ መንገዶችን ሳቆራርጥ ሰንብቼ በምሽትም መሸታ ለመሸታ ቤት መንከራተቴ ያለኝን ጊዜ ለመቆጠብ መሆኑን አንባቢ ይረደዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ካደርኩበት የ‹ኤል ሸፕ› ሆቴል ሰማዩ ገና የአህያ ሆድ ሳይመስል ነቃው፡፡ በድካም የሰነበተ ሰውነቴን በቀዝቃዛ ውኃ ነክሬ በጠዋት ወደ ደባርቅ አቅጣጫ ወጣሁ፡፡ ትናንት ወደ አርማጭሆ የሔድኩበትን አቅጣጫ ትቼ ወደ ኮሶዬ አመራሁ፡፡ የዛሬው መንገዴ ትናንት የሔድኩበትን በርሀ ወደ ታች እየተመለከትኩ ደጋ ደጋውን ነው፡፡ ከጎንደር ከተማ ርቄ አሁን ወገራ ወረዳ እገኛለሁ፡፡ በደጋማው የወጋራ አፋፍ ላይ ሆኘ የአርማጭሆና የኹመራ ጫካ ታዬኝ፡፡ ‹‹ኧረ ጥራኝ ጫካው›› አልኩኝ በውስጤ፡፡ የወገራ እረኛ በቅርርቶ፤ ‹‹ኧረ ጥራኝ ጫካው ኧረ ጥራኝ ዱሩ ላንተም ይሻልሃል ብቻን ከማደሩ፡፡ ተንኮለኛው ገደል በሬ ያሳልፋል፤ ዝንጀሮን ይጠልፋል ጂል ያመጣው ነገር ለሁሉም ይተርፋል›› ኮሶዬ አፋፉ ላይ ሆኖ ዋሽንቱን ከድምጹ ጋር እያቀናጀ ይሸልላል፡፡ ምን ታደርገዋልህ! እኔ ከጫካ ጋር የማደር ልምድ የለኝም፡፡ ከራማዬ ከአርማጭሆና ከቋራ ጫካዎች ጋር ስላልሆነ ቻው ብያቸው መጥቻለሁ፡፡ እተራራው ላይ ሆኜ እንደገና ሳያቸው ለምን እንደ እናቴ ልጅ እንደናፈቁኝ አላውቅም፡፡ የምር ግን በጭጋግ የተሸፈነውን ከአድማስ ማዶ ዓይኔ እስኪታክተኝ የማየው የሆነ የሚናፍቅ፣ የሚስብ ነገር አለው፡፡ ‹‹አልበር እንዳሞራ›› ነው ነገሩ፡፡ ወይ እንደ አእዋፋት አሊያም እንደ መላእክት ሆኜ ክንፍ ቢኖረኝ ኖሮ ምንኛ በታደልኩ፡፡ በ‹‹ኖሮ›› አይኖርም፤ ወደ ከምናቤ ልወጣ ግድ ነው፡፡ የኮሶዬ ነፋሻማ ሜዳ ከጎንደር በግምት 15 ኪሎ ሜትሮች አካባቢ ይርቃል፡፡ ኮሶዬ ለዓይን የሚስብ ገደል ጫፍ ያለ ሜዳማ ቦታ ነው፡፡ ነፋሻማና ብርዳማ ነው፡፡ በጠዋት ስለደርስኩ የብርዱ ነገር አይጣል ነው፡፡ የኮሶዬ ሜዳ ገደሉ ጫፍ ላይ ሎጅ አለ፡፡ የሎጂው አልቤርጎዎች በእሳር ክዳን (ትኩል) የተሠሩና በነገሥታቱ የተሠየሙ ናቸው፡፡ ሎጂውን እየዞርኩ ስመለከት በአጼ ኃይለ ሥላሴና በንግሥት ኤልሳቤጥ የተሰየሙ የጎጆ አልቤርጎዎች (ትኩል) ሳይ ጊዜ ለምን እንደሆነ ሰዎችን ጠየቅኩ፡፡
ንግሥት ኤልሳቤጥ ኢትዮጵያን በ1956/7 ዓ.ም. ከንጉሠ ነገሥት አጼ ኃይለ ሥላሴ ጋር ስትጎበኝ ካየቻቸው ቦታዎች መካከል የጢስ አባይ ፏፏቴና የሰሜን ተራሮች ይገኙበታል፡፡ የሰሜን ተራሮችን ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ጎብኝታ ስተመለስ መስንግዶ የሚደረግበትን ቦታ መምረጥ ያስፈልግ ነበር፡፡ ከዚህ አካባቢ ከኮሶየ የተሻለ መስህብነት ያለው ቦታ ጠፋ፡፡ ከእከሌ ሆቴል አሊያም ሎጅ የሚሉት ነገር አልነበረም፡፡ ኮሶዬ መስኩ ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች የሰባውን ሰንጋ አርደው በብላክ ሌቨል ፋንታ የወገራን ጠላ ዘልለው፤ በእንግሊዝ ኬክ ፋንታ የጎንደርን እንጀራ አዋጥተው የታላቋን ኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትና የታላቋን ብሪታኒያ ንግሥተ ነገሥት ለመቀበል ዳስ ሠሩ፡፡ በዚህ ቦታ የሁለት ታላላቅ ርዕሳነ ብሔራት ተስተናግደዋል፡፡ ያኔ አሁን ከተራራው አናት ላይ ያለው ሎጂ አልነበረም፡፡ ያኔ ሎጅ ሳይሆን የቆርቆሮ ክዳን የነበረው ቤት አልነበረም፡፡ የሰው ልጅ ከሠራው ይልቅ ተፈጥሮ ያበጀችው እይታ ይማርክ ነበርና ነገሥታቱ ይህን ቦታ በድንኳንና በዳስ አረፉበት፡፡ እንኳን እኔ ሐበሻው ንግሥት ኤልሳቤጥም በዚህ ቦታ ውበት ለመማረኳ አልጠራጠርም፡፡ አሁን ካለው ዘመናዊ ሎጅ የሚያስተናግድ ልጅ ‹‹የታላቋን ብሪታኒያ ንግሥትና የታላቋን ኢትዮጵያ ንጉሥ በጊዜው ያስተናገዱ አዛውንት እዚያ ጋ አሉ፤ ማገኘት ትችላለህ›› አለኝ፡፡ በደስታ እየሮጥኩ ወደ አመላከተኝ ቤት ሔድኩ፡፡ የባህር ዛፍ መከላከያ ለበቅ ባልይዝ ኖሮ ቤት የነበረው ውሻ ይበላኝ ነበር፡፡ ሆኖም ውሻው ሲታገለኝ እደጅ የነበሩ የቤተሰቡ አባለት ደረሱልኝና በውሻ ከመነከስ ተረፍኩ፡፡ የታላላቅ አገሮቹን ንጉሥና ንግሥት ያስተናገዷቸው ሰው ማግኘት እንደምፈልግ ነገርኳቸው፡፡ መደብ ላይ የተቀመጡ አዛውንት አመላከቱኝ፡፡ ጠየቅኳቸው፡፡ እድልለኛ አልነበርኩም፡፡ እኔ ያገኘዋቸው የእድሜ ባለጸጋ ንጉሡና ንግሥቲቱ ሲስተናገዱ የተመለከቱ እንጅ እራሳቸው አስተናጋጅ አልነበሩም፡፡ የሆነው ሆኖ የእድሜ ባለጸጋው ከቤታቸው ወጣ ብለው ወደ ሜዳው በብትራቸው እያመለከቱ ‹‹ድንኳን የተጣለው እዚያ ላይ ነበር፤ አይ ምን የመሠለ ሠንጋ አርደን ነበር መሠለህ! ግን ያዘጋጀነውን ሁሉ በደንብ ሳይበሉ ትተውን ሔዱ›› አሉኝ፡፡ በጊዜው ርዕሳነ ብሔሮቹን ለማስተናገድ የተመረጠ ሰው አልነበረም ወይ? የሚል ጥያቄ አቀረብኩ፡፡ አሁንም በድጋሚ ከቤታቸው በላይ ወደ ተራራማው ጫፍ እያመላከቱ ‹‹ወደ አቀበቱ መውጣት የምትችል ከሆነ መንገድ የሚመራህ ሰው ልስጥህ›› አሉኝ፡፡ የምችል አይደለሁም፡፡ ሩጫዬ ከጊዜም ከገንዘብም ጋር ነው፡፡ አንድ ቀን የጉዞዬን ጊዜ ባራዘምኩ ቁጥር የጋዜጣው መውጣት አለመውጣት ያሳስበኛል፡፡ ደግሞም በመንገድ ላይ የያዝኩት ስንቅ ቢያልቅ መመለሻ እንኳ አይኖረኝም፡፡ ስለዚህ በያዝኩት የጊዜ ገደብ መሠረት መጓዝ አለብኝ፡፡ የኮሶዬ ተራራ አናት ላይ ሆኜ ወደ በርሀው ስመለከት የተራራ ሰንሰለቶችን በጭጋግ ተሸፍነው አየሁ፡፡ ትናንት የነበርኩበት የአርማጭሆና የጠገዴ በርሃ በርቀት ይታየኛል፡፡ በእጄ የምነካት የምትመሥለው የጩጌ ማርያም ገዳምም ከሥሬ ናት፡፡ የጩጌ ማርያም ገዳም በድንጋያማ የተራራ ሰንሰለት ላይ ያለችና በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተገደመች ናት፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት ሒጄ አይቻታለሁ፡፡ አካባቢውን ለማያውቁ አንባቢያን የጩጌ ማርያም ገዳምን በትንሹም ቢሆን መናገር ያለብኝ ይመስለኛል፡፡ ገዳሙን ለማየት ስሔድ የያዝኩትን ማስታዎሻ ሳገላብጥ የሚከተለውን አገኘሁ፡፡ የአገሬዉ ሰዉ ለሰዉ ብርታት የሚሰጥበትን ዘዴ ሳስብ ይገርመኛል፡፡ የወገራ ሰዉ ‹በአገጩ በዚህ በኩል በጣም ቅርብ ነዉ!› ካለህ ቢያንስ ለሰዓታት ትጓዛለህ፡፡ በትሩን በረጅሙ እያጠቆመ ‹በዚያ በኩል ቅርብ ነዉ!› ካለህ ቢያንስ ለግማሽ ቀን ትሔዳለህ፡፡ ኮሶዬ ያገኘሁት ሰው ወደ ጩጊ በየት በኩል እንደምሔድ እንዲያሳየኝ አቅጣጫውን ስጠይቀው ሊነካት ያሰባት ይመስል እያንጋጠጠ ‹‹እዚች ተራራ ገደሉ ላይ የሆነ ቤት የሚመስል ነገር ይታይሃል?›› ሲል ጠየቀኝ፡፡
ከአለንበት አፋፍ ገደል ሥር እየተመለከትኩ ጫካና አምባ ተራራ እንጅ ቤት አለመኖሩን ነገርኩት፡፡ ‹‹ያችን አምባ እያት እንጅ! ከአምባዋ ጎን ካለዉ ገደሉ ላይ ተመልከት ቤት ታያለህ!›› አለኝ፡፡ እንደምንም ከርቀት ከጭጋግ ጋር ለመለየት የሚያስቸግር ቤት አየሁ፡፡ ‹‹አየሁት አየሁት!›› ስል አጻፋ መለስኩ፡፡ ‹‹ያች ብዙ ተዐምራት የተሰራባት ጩጊ ማርያም ገዳም ናት›› አለኝ፡፡ ‹‹በየት በኩል ነዉ መንገዱ?›› ተጨማሪ ጥያቄ አስከተልኩ፡፡ ‹‹በዚህ ነዋ›› በግንጭሉ እየጠቆመ ገደሉን አሳዬኝ፡፡ ‹‹እንዴ! ይህ እኮ እንኳን ለሰዉ ለዝንጀሮም አይመችም!›› አልኩት፡፡ ሳቀብኝና ‹‹ቅርብ ነች፡፡ በአንድ ሰዓት ውስጥ ደርሰህ መመለስ ትችላለህ!›› አለኝ፡፡ በወኔ መንገዱን ጀመርኩት፡፡ ይህን ገደል በሽርታቴ ተያያዝኩት፡፡ ገደሉ ያን ያክል እንዳየሁት የሚያስፈራ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡ በቀላሉ በስበት ኃይል እየተምዘገዘግኩ ወረድኩት፡፡ በጫካ ውስጥ ፈንዛ ጅራት ካላቸዉን ጉሬዛዎች እና ዝንጀሮዎች ጋር እየተላጋሁ ከራሴ ጋር እያወራሁ ሸመጠጥኩ፡፡ ዝንጀሮዎች እየጮሁ ገደል ለገደል ሲሮጡ መርግ ቢልኩብኝ እያልኩ በፍርሃት አስጨንቀውኝ ነበር፡፡ ደግነቱ በዛፎቹ ጥላ ሥር ስለምጓዝ ትንሽ ያስፈራል እንጅ ሙቀቱ አይታወቅም፡፡ በርቀት ገዳሙን እያየሁ የደረስኩ እየመሰለኝ እኔም በአገጬ ለመንካት እየሞከርኩ ለአንድ ሰዓት ያክል ለመጓዝ ተገደድኩ፡፡ ገዳሙ መግቢያ አካባቢ አፈሩ አንሸራቶ ጉድ ሰርቶኝ ነበር፡፡ ከዚያ ቦታ ላይ ብወድቅ ማንም ሳያየኝ መዳረሻዬ ተጨማሪ ኹለት ሰዓት የሚያስኬድ ገደልን እጨርስ ነበር፡፡ ሸርተት ካሉ መዳረሻው የማይታወቅ አገርና ዓለም ነው፡፡ ገዳሙ ያለበት እጅግ ገደል የበዛበት ሰንሰለታማ የድንጋይ አምባ ነዉ፡፡ መነኮሳቱና አርድዕቱ በገደሉ ላይ እንደዚያ ሲሮጡ በዝንጅሮቹ የገደል ላይ ጉዞ መደነቄ አናደደኝ፡፡ በዚያ ገደል ‹ሰዉ ዓለምን ንቆ በባዕት ለእድሜ ልካቸዉ የሚኖሩ መነኮሳት› እንዳሉ ማየት እጅግ ይገርማል፡፡ እኔ ላንድ ቀን እንቅልፍ ወስዶኝ የምተኛ አይመስለኝም፡፡ ይህ ገዳም የተገደመው በአባ ምዕመነ ድንግል በአስራ ሰባተኛዉ ክ/ዘመን ነዉ፡፡ በአጼ ሱስንዮስ ዘመነ መንግሥት (ከ1600- 1624 ዓ.ም.) አባ ምዕመነ ድንግል ብዙ መከራንና እንግልትን እንደተቀበሉ ገድላቸው ይመሰክራል፡፡ ገዳሙ ካለበት የቋጥኝ ተራራ ወገብ ላይ ዋሻ አለ፡፡ ዋሻዉ ውስጥ ደግሞ በክረምትም በበጋም የማይሞላ የማይጎድል ‹ማዬ ዮርዳኖስ› ወይም ‹የዮርዳኖስ ዉኃ› የሚሉት አለ፡፡ ጸበሉ በርካታ ምዕመናን ይጠመቁበታል፡፡ ግን አይጎድልም፡፡ የሚጠመቅ ሰዉ ከሌለም ሞልቶ አይፈስም፡፡ አፈር በሆነበት ቦታ ምንጮች እየደረቁ ባለበት ጊዜ ግጥም ካለ ቋጥኝ ተራራ ላይ ይህ መሆኑ ለእንደኔ ዓይነቱ ተጠራጣሪ አጃኢብ ያስብላል፡፡ ጸበሉን ጠጣሁት- አይሰለችም፡፡ እንዲያዉም እዉነት ለመናገር ከመጣሁ በኋላ ናፍቆኛል፡፡ መልኩ ሀጫ በረዶ ይመስላል፡፡ በመቆሙ ብዛት አረንጓዴ (አልጌ) አልጣለበትም፡፡ ይህን ጸበል ጠጣሁትም፤ ሲያጠምቁ ያገኘዋቸው አባም አጠመቁኝ፡፡ ብቻ ግሩም ነዉ እላችኋለሁ፡፡ ጸበሉን የሚጠጡ ፍጥረታት ገላቸው (አካላቸዉ) አይፈርስም፡፡ ጸበሉን የጠጡ 16 ፍየሎች ከነ ሙሉ አካላቸዉ ለ400 ዓመታት ለገባሬ ታእምር እስካሁን አሉ፡፡ ወልደዉ ለመሳም ያልታደሉ ሰዎች ከዚህ ቦታ መጥተዉ ተጠምቀዉ ጸበሉን ቢጠጡ የልጅ ጉጉታቸዉን እዉን ለማድረግ ዘጠኝ ወራት ብቻ እንደሚያስፈልጋቸው ከገዳሙ ያገኘዋቸው አርድእት ነግረውኛል፡፡
ቦታዉ የዋልድባዉ ሰቋር ኪዳነ ምህረት ዓይነት ነዳላ አምባ አለዉ፡፡ ወደ ነዳላዉ አምባ ለመሄድ ጸበሉን የጠመቁኝ አባት በዚህ በኩል ሒድ አሉኝ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ እያመለከቱ፡፡ በተቀደሰዉ ቦታ ጫማህን አዉልቅ በሚለዉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ መሠረት ጫማ መልበስ ክልክል ነዉ፡፡ ጫማ የለመደ እግር በሚያቃጥል አለትና በሚቆረቁር አሸዋ ላይ መሔድ ይጠበቃል፡፡ በዚያ ድንጋያማ ተራራ እንደ ገበሎ አስተኔ በልብ አሊያም በአራት እግር መጓዝ ይጠይቃል፡፡ ከዋሻዉ ማዶ ‹ሰማያዊ ኬንዳ› የመሰለ ነገር ማዶ ካለዉ ገደል ላይ ተንጣሎ ይታያል፡፡ ያ ኬንዳ ምንድን ነዉ? ስል ጠየቅኩ፡፡ በተቀደደዉ የቋጥኝ ተራራ አልፎ የሚታየዉ ሰማይ ነዉ አሉን አባ፡፡ ከጸበሉ የነበረች አንዲት እናት ጋር አብረን እንድንሔድ አባ ነገሩን፡፡ ጉዞ ወደ ነዳላዉ አምባ፡፡ አብራኝ የምትጓዘዉ እናት እጅግ የበረታች ናት፡፡ እርሷ በዚያ ገደል ላይ ከዝንጀሮ እኩል ትፈጥናለች፡፡ ተከተልኳት፡፡ ድንጋይ በድንጋይ ላይ እየወጣን ወደ ነዳላዉ አምባ ተቃረብን፡፡ ወደ ገደሉ ስንወጣ በእጃችን እየቧጠጥን ነው፤ በእጃችን አጥብቀን ከመያዛችን በፊት ያገኘነውን ጎቶ ጥንካሬ መለካት ያሻል፤ አሊያ ዲካው ወደ ማይታወቀው ገደል መጓዝ ይመጣል፡፡ ከቦታዉ ስንደርስ አንድ ሽማግሌ አባት ከንቃቃት ድንጋይ ሥር እንደቤት አደርገዉ ሲጸልዩ ደረስን፡፡ አባ ከባዕታቸዉ ፈጽመዉ አይወጡም፡፡ የምጽዋት ገንዘብም ፈጽመዉ አይቀበሉም፡፡ ፎቶ ግራፍና ምስል እንድወስድ ብጠይቃቸዉ ‹‹ልጄ አወግዝሃለሁ›› አሉኝ ተቆጥተዉ፡፡ ይቅርታ ጠይቄ አቡነ ዘበሰማያት ደግመዉልኝ በበረከት ተለየዋቸዉ፡፡ በመጨረሻ እኔን ጠየቅኩት? ‹አባቶች ለነፍሳቸዉ እና ለአገር ደኅንነት ከዱር አራዊት፣ በልባቸዉ ከሚሳቡ ነፍሳት ጋር ሁሉ እንዲህ ይታገላሉ፡፡ እኔ ግን ከዚህ ድረስ መጥቼ በረከት እንኳ መውሰድ እንዴት ተሳነኝ?› እማሆይ ማዕድ አቀረቡልን፡፡ በላን፡፡ በልቤ የአባቶቼን ጽናት እያሰብኩ ወደ መጣሁበት ዓለም ለመመለስ ተነሳሁ፡፡ ከፊቴ አምዘግዝጎ ያረወደኝን ገደልና ጫካ ለመዉጣት፡፡ ዝንጀሮዎቹን ቢያዝሉኝ ስል ተመኘሁ፡፡ ዛፍ ለዛፍ የሚሯሯጡት ዝጉርጉር ጉሬዛዎች አስቀኑኝ፡፡ በ180 ዲግሪ ቀጥ ያለው የወገራ አቀበት ፊቴ ላይ ተደቀነ፡፡ ………. ወደ አያሌው ብሩ አገር ዳባት መንገድ ጀምርኩ፡፡ አምባ ጊዎርጊስ፣ ገደብዬ፣ ዳባት፣ ወቅን፣ ደባርቅ…፡፡ ዳባት ላይ የአያሌው ብሩ ቤተ መንግሥት አለ፡፡ አያሌው ብሩ የወገራ ገዥ የነበሩ ሲሆን በአጼ ኃይለ ሥላሴ ሀትሪክ ተሠርተዋል አሉ፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሴ ወደ አዲስ አበባ እንዲሔዱ ጥሪ ሲልኩባቸው የወገራ ሰው እንዳይሔዱ መክሯቸው ነበር፡፡ ነገር ግን የወገራን ሰው ምክር ባለመሥማታቸው የአጼው ተንኮል ሰለባ ሆነዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ድፍን በጌምደሬ ሲዘፍን ‹‹አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ ሰው አማኙ፤ ኧረ አያሌው ተው በለው ተው በለው›› የሚለው የእርሳቸውን ሞኝነት ለማመለከት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ቀሪውን ማጣራት የባህል ተመራማሪዎች ፋንታ ይሆናል፡፡ አምባ ጊወርጊስ ላይ ሆኖ ወደ ደባርቅ ሲመለከቱ አንዲት ኮረብታ በርቀት ትታያለች፡፡ ዳባት ላይ ሆኖም ይህችው ተራራ ከትክተት አትሰወርም፡፡ ዳባትን አልፈን ደባርቅ ሆነንም እናያታለን፡፡ የሰሜን ተራሮች አናት ላይ ብንወጣም ይህችን ተራራ ማንም አይጋርደንም፡፡ ይህች ተራራ ‹‹ወቅን›› ከተባለች አነስተኛ ከተማ ራስጌ ላይ የምትገኝ ስትራቴጂክ አምባ ናት፡፡ ስያሜዋም ‹‹ዞሮ ዞሮ ወቅን›› ትሰኛለች፡፡ ዞሮ ዞሮ ወቅን ከወገራ እስከ ኹመራ፣ ከአርማጭሆ እስከ ጃናሞራ፣ ከአዲአረቃይ እስከ ሽሬ ድረስ ቁልጭ ብላ በጉልህ ትታያለች፤ ዞሮ ዞሮ ወቅን፡፡

አቶ መለስን የሸለመው ”ያራ”የተሰኘው የኖርዌይ ማዳበርያ አምራች ኩባንያ በሌላ ዓለም አቀፍ ቅሌት ተጋለጠ!

$
0
0
 ይህንን ፅሁፍ ከመፃፌ አስር  ደቂቃዎች  በፊት ”አፍተን ፖስተን” የተሰኘው የኖርዌይ አንጋፋ ጋዜጣ በድረ-ገፁ አንድ መረጃ ለቀቀ።ይህ ዜና ምናልባት ነገ የሚታተመው የጋዜጣው ገፅ ላይ  የሚወጣ ነው።ጉዳዩ ”ያራ” የተሰኘው የኖርዌይ መንግስታዊ የማዳበርያ አምራች ኩባንያ ስለገባበት ሌላ ቅሌት ያትታል። ”ያራ” የተሰኘው የኖርዌይ የማዳበርያ ፋብሪካ ደግሞ ከኢትዮጵያ እርሻ ጋር ባለፉት ሃያ አራት አመታት ውስጥ አንድ አነታራኪ ጉዳይ አለው።ይሄውም የኢትዮጵያ ገበሬ በብድር በብዛት ምርቱን እንዲወስድ በአቶ መለስ  የስልጣን ዘመን መገደዱ እና አቶ መለስ ከድርጅቱ ሽልማት ማግኘታቸው ዙርያ ያጠነጥናል።
አቶ መለስን የሸለመው ''ያራ'' የተሰኘው የኖርዌይ ማዳበርያ አምራች ኩባንያ በሌላ ዓለም አቀፍ ቅሌት ተጋለጠ!

አቶ መለስን የሸለመው ”ያራ” የተሰኘው የኖርዌይ ማዳበርያ አምራች ኩባንያ በሌላ ዓለም አቀፍ ቅሌት ተጋለጠ!

የኢትዮጵያ የእርሻ መሬት በአቶ መለስ ዘመን ከተፈፀመበት ወንጀል ውስጥ አንዱ የኬሚካል ማዳበርያ ገበሬው በግድ እንዲወስድ መደረጉ ነው። በእርግጥ ማዳበርያ ለአንድ አገር እርሻ ምርታማነት አስፈላጊ ነው።ለእዚህም  የተፈጥሮ ማዳበርያ ተመራጭ እንደሆነ ይታወቃል።የተፈጥሮ ማዳበርያ ተመራጭ የሚሆንባቸው ምክንያቶች ውስጥ  የተፈጥሮ ማዳበርያ ምንም አይነት ለጤና የሚያመጣው ጉዳት የሌለ ከመሆኑም በላይ በእየዓመቱ መሬቱ ለምዶ ካለማዳበርያ ምርት አልሰጥም አለማለቱ ነው። የኬሚካል ማዳበርያ ግን ምርቱ ለጤና እስከ ካንሰር እና ተያያዥ በሽታዎች ሁሉ የሚያጋልጥ ከመሆኑም በላይ ማዳበርያውን የለመደ መሬት በእራሱ ቶሎ የመምከን ዕድል ስለሚኖረው በእየዓመቱ ሱስ እንደያዘው ሰው ካለ ማዳበርያ ምርት የመስጠት አቅሙ በብዙ ደረጃ ስለሚቀንስ ነው።
በ1983 ዓም አቶ መለስ እና ሰራዊታቸው መንበረ ስልጣኑን ሲቆናጠጡ በመጀመርያ ያደረጉት ገበሬው የኬሚካል ማዳበርያ በብድር እንዲወስድ ማድረግ ነው።በወቅቱ የእርሻ ምርምር ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት የተፈጥሮ ማዳበርያ እንደ ፍግ፣እና ብስባሽ እንጂ ኬሚካል ማዳበርያ መጠቀም የለብንም በማለት መንግስትን ለማስረዳት ሞከሩ። አቶ መለስ እና ስርዓታቸው ግን ፈፅሞ አልተቀበለውም። ለእዚህም ዋነኛ ምክንያቱ እንደ ”ያራ” ከመሰሉ ኩባንያዎች ጋር ያላቸው የውስጥ የጥቅም ግንኙነት ነው በማለት ብዙዎች አስተያየታቸውን ሲሰጡ ነበር።ይብሱን ”ያራ” መስከረም፣2005 ዓም እ ኤ አቆጣጠር አቶ መለስን እንደሚሸልም መግለጡ እና ለሽልማቱ የተሰጠው ምክንያት ግልፅነት ማጣት ከፍተኛ ጥርጣሬ በብዙዎች ዘንድ አደረ።በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ጉዳዩን ይፋ አውጥተው በግልፅ ያራን እና አቶ መለስ ግንኙነት ጤናማ አለመሆኑን በተቃውሞ ሰልፍ ጭምር ገለጡ።
የሽልማቱ ጉዳይ የዓለም አቀፍ ዜና ድርጅቶችንም ጭምር ግራ አጋብቶ ነበር።የአቶ መለስ እና የያራ ግንኙነት ምንድነው? አቶ መለስ ምን ስላደረጉ ነው የተሸለሙት? የሚለውን ጥያቄ ለመፍታት ብዙዎች ጉዳዩን ደጋግመው አብላሉት።ከእዚህ ሁሉ ሂደት በኃላ ግን ነጥሮ የወጣው ጉዳይ አቶ መለስ ቢሮአቸው ላይ የመጣውን የግዥ ስምምነት እየፈረሙ መፍቀዳቸው እና ኢትዮጵያ  ከተፈጥሮ ማዳበርያ ይልቅ የኬሚካል ማዳበርያ ገበሬው እንዲጠቀም እስከታች ድረስ ትእዛዝ መውረዱ ነበር። ከእዚህ በተጨማሪ ማዳበርያ  አልፈልግም ያለ ገበሬ እንደ ፀረ-ምርታማ አስተሳሰብ አራማጅ እየተወሰደ በካድሬዎች እና በግብርና ኤክስተሽን ሰራተኞች የግድ የማዳበርያ ብድር ውስጥ እንዲዘፈቅ እና ማዳበርያው እንዲገዛ መገደዱ ሌላው አቶ መለስ እና አመራራቸው በኢትዮጵያ ገበሬ ላይ የጣሉት ቀንበር ነበር። በእዚህም ሥራ የ”ያራ” ኩባንያ ሽያጭ እንዲንር ተደረገ።
ከእዚህ በስተጀርባ ሌላ የሕወሃቱ የንግድ ድርጅት ኤፈርት እጅ ደግሞ ጎልቶ ወጥቷል።በዘመነ ደርግ የኢትዮጵያ ራድዮ እና ቴሌቭዥን በነበራቸው የግብርና ፕሮግራም ላይ ሁሉ ለገበሬው የሚያስተላልፉት መልእክት የተፈጥሮ ማዳበርያ የመጠቀምን ሁለት ጥቅም ነበር። አንዱ ለመሬቱ ጤናማነት ሲሆን ሁለተኛው ደርግ ትልቅ እራስ ምታት የነበረበት የውጭ ምንዛሪ የማዳን ጥቅም በመግለፅ ነበር። አቶ መለስ እና አቶ ተፈራ ዋልዋ ግን ገበሬውን የመከሩት ዘመናዊ ማዳበርያ ተበድሮ ገዝቶ መሬቱን እንዲያመክን ነበር።እግረ መንገዳቸውንም ቀድሞ በርካታ ምርቶችን በማስመጣት የሚታወቀውን ”አማልጋሜትድ” ኩባንያ አዋክበው ማፈረስ እና ማዳበርያ የማስመጣት ንግዱን የኤፈርት ኩባንያ እንዲወስድ አደረጉ። የእዚህ አይነቱ ድርጊት በኢትዮጵያ እርሻ ላይ እና አገራዊ ሀብት ላይ ያመጣው ውድመት በአግባቡ ቢጠና በርካታ መዘዞችን ይዞ ብቅ ማለቱ አይቀርም።
ይሄው አቶ መለስን ከአስር ዓመት በፊት ሸለምኩ ያለው ኩባንያ ዛሬ በሌላ የጉቦ መስጠት ቅሌት ተጋልጧል።በኖርዌይ ሲታተም ከ150 አመታት በላይ ያስቆጠረው  እና አንጋፋው  ”አፍተን ፖስተን” ጋዜጣ ”የኖርዌይ መንግስት ንብረት የሆነው ያራ ኩባንያ ካሪብያን ለሚገኙ የሼል ኩባንያዎች የ2.6 ሚልዮን ዶላር ጉቦ ሰጠ” ”State-owned Yara paid $ 2.6 million in bribes to shell companies in the Caribbean” በሚል ርዕስ ስር  ሰፊ ዘገባ አዘጋጅቷል።ጋዜጣው በኖርዌይኛ ስለተፃፈ  ቋንቋውን ለማትረዱ  ወደ ጉግል ወስዳችሁ ወደ እንግሊዝኛ ወይንም አማርኛ መተርጎም ይፈልጋል።
የአፍተን ፖስተን ጋዜጣ ያወጣው ዘገባ ሊንክ  ለማንበብይህንን  ይጫኑ።በተጨማሪም ጋዜጣው   ስለ ያራ የወጣው ዘገባ  ለኖርዌይ ህዝብም አዲስ መሆኑን  ያብራራል።ሰሞኑን ያራ የብዙሃን መገናኛዎች መነጋገርያ ርዕስ ቢሆን ብዙም እንዳትገረሙ።

ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
መጋቢት 29/2008 ዓም (አፕሪል 7/2016)

ዘማሪ እንግዳወርቅ በቀለ “ታቦቱ በህጋዊ መንገድ የተቀረጸ ነው””አለ |ስለእስሩ ሁኔታ ይናገራል

$
0
0

ዘ-ሐበሻ ዘማሪ እንግዳወርቅ በቀለ ከታቦት ሽያጭ ጋር በተያያዘ በተከሰሰበት ክስ መታሰሩን እና በዋስ መፈታቱን መዘገቧ አይዘነጋም:: የሳተናው እና የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ዘማሪ እንግዳወርቅን ከአዲስ አበባ አነጋግሮት የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሯል::

engdawork

“ታቦቱ በህጋዊ መንገድ የተቀረጸ ነው”

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዘማሪነት የሚታወቁት ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ ለ13 ቀናት ከሌሎች አራት ሰዎች ጋር ታስረው በዋስ  መፈታታቸውን ከቅርብ ሰዎቻቸው በደረሰን መረጃ መሰረት ለማወቅ ከቻልንበት ደቂቃ ጀምሮ ቀሲስን በማግኘት ከራሳቸው አንደበት የእስራቸው ምክንያት ምን እንደነበር ለማወቅ ይገኙበታል የተባለን የስልክ ቁጥር ስንቀጠቅጥ አምሽተን በስተመጨረሻ ተሳክቶልን አግኝተናቸዋል::

ትናንት ገና ወደመኖሪያ ቤታቸው መግባታቸውን የገለጹልን ቀሲስ የእስራታቸው መንስኤ በህጋዊ መንገድ ተቀርጾ ኮሎራዶ ውስጥ ለምትገኝ ቤተክርስቲያን ሊላክ የነበረ ታቦት መሆኑን አጫውተውናል፡፡

ወደ አሜሪካ ለአገልግሎት ለማቅናት ተዘጋጅተው የነበሩት አባ ገ/ወልድ ቀሲስን በማግኘት ወደ አሜሪካ ለመሄድ መዘጋጀታቸውን በዚያ የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮችም ማግኘት ከቻሉ ሁለት ታቦቶችን ይዘው እንዲመጡላቸው እንደጠየቋቸው በመንገር ታቦት ስለሚዘጋጅበት መንገድ ቀሲስ የሚያውቁት ነገር ስለመኖሩ እንደጠየቋቸው ያስታወሱት ዘማሪው ‹‹ጸጋዘዓብ የተባለ ሰውን እንዲያገኙና ታቦቱን ካዘጋጀላቸው በኋላ ለአባቶች በመንገር እንዲያስባርኩ በመምከር ሁለቱን ሰዎች አገናኘኋቸው››ይላሉ፡፡

ታቦት እንዴት በግለሰብ ይሰራል ይህንን የሚያክል ነገርስ ከቤተክህነቱ ውጪ እንዴት ይዘጋጃል በማለት ለቀሲስ ባቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹ታቦቱን ግለሰቡ የሚያዘጋጀው በቤተክህነቱ ፈቃድ ነው፡፡የተባለው ታቦት እንዲዘጋጅም በመጀመሪያ የአቡነ ሳሙኤል ፈቃድ ተገኝቷል፡፡አቡነ ሳሙኤል ታቦቱ እንዲቀረጽ የፈቀዱበት ወረቀትም እጃችን ላይ ይገኛል››ብለዋል፡፡

ሁለቱን ሰዎች ካገናኙ በኋላ ምን ደረጃ እንደደረሱ ጠይቀዋቸው ጭምር እንደማያውቁ የሚናገሩት ቀሲስ ‹‹ታቦቱን ለማሰራት ተነጋግረው የርክክቡ ሰዓት ሲደርስ አራዳ ጊዮርጊስ በተቃጠሩበት ወቅት ግርግር ተነስቶ ይከታተሏቸው በነበሩ ሰዎች አማካኝነት ፖሊስ ተጠርቶ ሲያዙ አባ ገ/ወልድ ደውለው አስጠርተውኝ ስለሁኔታው ለማስረዳት በሄድኩበት ፖሊስ አንተንም ለጥያቄ እንፈልግሃለን በማለት ለ13 ቀናት አስሮ ፈትቶኛል››ብለዋል፡፡

ታቦት ማስቀረጹ ህጋዊ ከሆነ ለምን ወዲያውኑ ንጹህነታችሁ ተረጋግጦ አልወጣችሁም በማለት ላቀረብንላቸው ጥያቄ ቀሲስ ‹‹ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦ የማጣራው ነገር አለ በማለቱ የምርመራ ጊዜ ጠይቆብን እንድንቆይ ተደርገናል፡፡በመጨረሻ ግን ምንም ነገር ስላልተገኘብን ሁላችንም እንድንወጣ ተደርገናል››፡፡

መዝገቡ ተዘግቶ በነጻ ተሰናበታችሁ ወይስ ዋስ እንድትጠሩ ተደረጋችሁ ብለናቸው ነበር በምላሻቸውም ‹‹ታቦቱን የቀረጸው 20.000 ፣ሊወስዱ የነበሩት እና እኔ 15.000 ሌሎቹ ደግሞ 10.000 ብር አስይዘን ወጥተናል››ብለዋል፡፡

ታቦቱ በህጋዊ መንገድ የተሰራ ነው የሚሉት ቀሲስ ተሐድሶዎች ስሜን ለማስጠፋት ሲሉ ያልተደረገ ነገር እንደተደረገ በማድረግ ቢያስወሩም ተቀበለ ስለተባልኩት ገንዘብ የማውቀው ምንም ነገር የለም››ማተቤን በገንዘብ እንደማልሸጥም ማንም ሰው ይመሰክርልኛል፡፡የእምነት ሰው በመሆኔ ይህ ለእኔ ፈተና ነው፡፡ነገር ግን እውነት ነጻ አውጥታኛለች››በማለት ማብራሪያቸውን አጠናቅቀዋል፡፡

የኦሕዴድ በዓል በመንዲ ከተማ ተቃውሞ ገጠመው – VOA Amharic

$
0
0

148F359A-E35E-41FF-8B81-448751E92987_cx20_cy0_cw60_w1000_r1_s_r1የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት(ኦሕዴድ)ባንዲራ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) 26ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ ነዋሪዎችና ተማሪዎች ተቃውሞ ገጠመው፡፡

የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) 26ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ ነዋሪዎችና ተማሪዎች ተቃውሞ ገጠመው፡፡ ተቃውሞውን ያሰሙ ተማሪዎችና ነዋሪዎች እንደተደበደቡ ሲናገሩ ፖሊስ ተቃውሞውን ያሰሙት ከ20 የማይበለጡ ሕፃናት እንደኾኑ ገልጾ፤እነሱንም ወዲያው እንደተበተኑ ተናግሯል። የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረባ ቱጁቤ ኩሳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች።ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

 

“የዐማራው ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለቱ ብቻ እንዳሁን ግፍ የተፈፀመበትና ማንነቱ የተደፈረበት ወቅት አልነበረም”–ዳግማዊ መዐሕድ

$
0
0

AAPO !!
ከዳግማዊ መዐሕድ የተሰጠ መግለጫ:-

ወያኔ በዐማራው ላይ መዝመት የጀመረው በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ወገኖቻችን ላይ ነው። ላለፉት 36 ዓመታት ፋሽስቱ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር፣ በዚህ ሕዝብ ላይ የፈፀመው አረመኔዓዊ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በቀላሉ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። በ 1972 ዓ ም አድህርዲ በምትባል ትንሽ ከተማ 12 ንጹሃን ቤተሰቦችን ገድሎ 18 አቁስሏል። በ 1973 ዓ ም በሃምሌ ወር አዲ ጎሹ አካባቢ፣ ሌሊት የገበሬ ቤቶችን ወሮ 20 የወልቃይት ዐማራ ልጆች ደብዛቸው ጠፍቷል። እስከ 1983 ዓ ም፣ በ10 ዓመት ውስጥ ብቻ “ባዶ ስድስት” በተባለ የምድር ውስጥ እስር ቤት ከ20000 በላይ የሚሆኑ ንጹህ ወገኖቻችን በግፍ አልቀዋል….. Read Full story in PDF

ዘውግና ብሄራዊ አንድነት እንዴት ይታረቃሉ? |በፕ/ር መሳይ ከበደ የመፍትሄ ኣሳብ ላይ ሊነሱ የሚችሉ የሰሉ ጥያቄዎች

$
0
0

mesay kebede
ገለታው ዘለቀ

ይህን ርእስ የወሰድኩት በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ “የኢትዮጵያ ዘውጋዊ ክፍፍሎችና የመፍትሄ ኣሳብ” በሚል ርእስ ስር ካቀረቡት መሳጭ ጥናታዊ ጽሁፋቸው ስር ካነሷቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መሃል ኣንዱን መዝዤ ነው። ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ በዚህ ፕሮግራም ላይ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፋቸው በርግጥ ደረጃውን የጠበቀና በሚገባ የተደራጀ ነው። ፕሮፌሰሩ ፈላስፋም ስለሆኑ ኣሳባቸውን በሚገባ ገልጸዋል። ኣስበውበት ተፈላስፈውበት በመሆኑ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል። በእንዲህ ዓይነት ስብሰባዎች ላይም እንዲህ ዓይነት ትንተና መኖሩ መልካም ነው። በአሁኑ ሰዓትም አገራችን ኢትዮጵያ ከተወደዱ ምሁራኖቿ የምትሻውና የተራበችው ነገር ምሁራን ተጨንቀው ኣስበው ኣማራጭ መፍትሄዎችን እንዲያመጡላት ነው። በእንዲህ ዓይነት ከፍ ያሉ ጉባዔዎች ላይ የሚቀርብ ጥናታዊ ጽሁፍ ከተራ ንግግር ኣይነት ወጣ ብሎ አማራጭ መፍትሄ የሚጠቁም መሆን ኣለበት። ፕሮፌሰሩ ኣስበውበት ደክመውበት እንደመጡ ስለተሰማኝና ለውይይት የሚጋብዝ በመሆኑ እንደ ዜጋ ኣመስግናቸው ኣመስግናቸው ብሎኛል። ታዲያ ይህንን ስል ኣሳባቸውን የተቀበልኩት እንዳይመስላቸው ደሞ። ባልቀበልስ ምንቸገራቸው እንጂ::

ፕሮፌሰር መሳይ ኣቀራረባቸውንና ያመጡትን ኣሳብ ለመሞገት ያላቸውን የሃሳብ ኣደረጃጀትና ትንተና ብማርበትም በዚህ በዛሬው ጥናታዊ ጽሁፋቸው ውስጥ ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግሮች “መፍትሄ” ብለው ባቀረቡት ኣሳብ ዘንድ ብዙ ጥያቄዎችን ኣስነስቶብኛል። ጥያቄ ኣስነስቶብኛል ብቻም ሳይሆን የመፍትሄ ኣሳብ ያሏቸው ኣቅጣጫዎች የኢትዮጵያን ማህበረ ፖለቲካ ችግር ፈጽሞ የሚፈታው ኣይነት መስሎ ኣልታየኝም። እናም ዛሬ ፕሮፈሰር መሳይ ባቀረቡት ኣሳብ ላይ ጥያቄ ላነሳባቸው እነሆ እርሳሴን ኣነሳሁ።

ፕሮፈሰር መሳይ ከበደ ከፍ ሲል እንዳልኩት ፈላስፋ በመሆናቸው ጽንሰ ሃሳቦች ይማርኳቸዋል። እሳቸውም ይህንኑ ብለዋል። ይሄ ደስ ይላል። በመሆኑም ከመግቢያ ላይ ስለ ዘውግ ፖለቲካ ምንነት የተለያዩ ኣስተምህሮቶችን (school of thoughts) በማንሳት ኣሰርድተውናል። በውነት ትምህርት ይሰጣል። priordialism, instrumentalism and constructivism የተባሉ ጽንሰ ሃሳቦችን ተንትነዋል። በዚህ ዙሪያ የፕሮፌሰር መሳይን ትንተና ለማዳመጥ እነሆ ማስፈንጠሪያው::

ወደ ውይይታችን ማእከላዊ ጉዳይ እንግባና በአሁኑ ሰዓት ስልጣን ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት የሚገልጸው የፍልስፍና መሰረት ማለትም (priordialism) በሚገባ ሊታይ ይገባዋል። priordialism የቋንቋና ባህል ልዩነትን በጣም የሚያጎላና ቡድኖች ዘውገኝነታቸውን አጥብቀው እንዲይዙ የሚጨቀጭቅ ኣስተምህሮ ነው። ምሁራን ከፖለቲካ አንጻር ይህን ትምህርት ሲያነሱ ለሩዋንዳው እልቂት መናጆ አድርገው ይወስዱታል። የብሄር ፖለቲካም ቡድናዊ ልዩነትን የሚያየው priordialism መነጽርን በማድረግ ነው። የብሄር ወይም የዘውግ ፖለቲካ በዘር፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ በደም ተፈጥሮ በሚገኝ ትስስር ላይ የሚቆም የፖለቲካ ስርዓት መሆኑን እንረዳለን። ፖለቲካው በነዚህ ተፈጥሯዊ ትስስሮች ላይ የሚቆመው ዘውጋዊ ስሜት በፈጠረው የስሜት ኤነርጂ ላይ ስለሚቋምጥ፣ ስለሚመካበት ነው። ይህ ስሜት ገንኖ የሚታየው ደግሞ በራሱ በቡድኑ ውስጥ ሳይሆን ቡድኑ ከሌሎች ቡድኖች ጋር በሆነ ኣጋጣሚ ሲገናኝና ለሆነ ዓላማ ሲወዳደር ወይም ውድድር ውስጥ ነኝ ብሎ ሲያምን ነው እጅግ ሃይለኛ ሆኖ የሚገለጸው። ይህንን ሃይለኛ ስሜት የዘውግ ፖለቲከኞች ቤታቸውን ሊሰሩበት ሲያስቡ በሃይለኛ ስሜቱ በጣም ይታመናሉ። ለሚፈልጉት ዓላማም ይህ ሃይለኛ ስሜት አድራሽ ከፍተኛ ኤነርጂ እንደሚሆን ስለሚያውቁ የማንነት ፖለቲከኞች ፖለቲካቸውን በዚህ በተፈጥሮ ተሳስሮ ባለ ስብስብ ላይ ያንጻሉ። የዘውግ ፖለቲከኞች priordialist ነን ይበሉ እንጂ በተግባር ግን ዘውግ የፈጠረውን ትስስር ለፖለቲካ ስልጣን መጠቀሚያ ማድረጋቸውን የሚያሳየው እነዚህ ፖለቲከኞች ይህንን ስብስብ ለስልጣን ሩጫ ሲጠቀሙበት ኣንዱ ችግር ዘመናዊ የሆነን የፖለቲካ ኣስተሳሰብንም በኣንድ እጃቸው ለመጎተት እየሞከሩ መሆኑ ነው። የቋንቋና የባህል ትስስር የፈጠረውን ስብስብ ለፖለቲካ ዓላማ የሚጠቀሙበት ወገኖች የፖለቲካቸው ኣጀንዳ ቆመንለታል የሚሉትን ዘውግ ባህላዊ ማንነት መሰረት ያደረገ ኣይደለም። ከዚያ ስብስብ የሚፈልጉት በዋናነት ኤነርጂውን ሲሆን ፕሮግራሞቻቸው በዘመኑ ካሉ ዓለማቀፋዊና ዘውግ ዘለል ከሆኑ የፖለቲካ ኣስተሳሰቦች ጋር የሚሄድ ነው። ለምሳሌ ያህል ኣንድ የኦሮሞ ህዝብ ድርጅት ነኝ የሚል ቡድንን ብንወስድ ይህ ቡድን የኦሮሞን ባህላዊ ቡድን መሰረት ያደረገ የማንነት ጥያቄ ያነሳና ነገር ግን የገዳን ስርዓት መሉበሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ባህሉ ሳይበረዝ ለመቀጠል ኣይደለም የሚጥረው። ወይም ሊመሰርት የፈለገው ስርዓት የገዳ ስርዓት አይደለም። ስልጣን ቢይዝ ኦሮምያን በገዳ ስርዓት ኣይደለም የሚያስተዳድረው። ገዳ ለዴሞክራሲ ማስተማሪያ ኣድርጎ ነገር ግን ከዘመኑ ኣስተሳሰብ ጋር ቀላቅሎ ነው ሊቀጥል የሚፈልገው። ከመነሻው priordialism ኣስተሳሰብ ቢያሳይም ነገር ግን የቡድኑን ባህላዊ ማንነቶች በተሃድሶ ስም ራሱ ሲቀይር ይታያል። ከገዳ የምወስደው ኣለ ይላል ግን ደግሞ ሌላ ኣዲስ ስርዓትም ያሳያል። ዴሞክራሲ የሚባለውን ኣዲስ የኣስተዳደር ጥበብ ይጠቅሳል። ይህ ጥበብ ደግሞ የሁሉም ቡድኖች ባህል ነው በርግጥ። ይህንን ዘውግ ዘለል የኣስተዳደር ጥበብ ይዞ ነው ዘውጌ ፖለቲካ የሚመሰርተው። ይህ ጉዳይ በርግጥ የሚያሳየው ፖለቲካው ምንም እንኳን በባህላዊ ቡድኑ ትስስር ላይ የቆመ ቢሆንም የሚፈጥረው ማንነት ግን ቅልቅል በመሆኑ ሳያስተውል ኣዲስ ማንነትን መፍጠሩ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ዘውጋዊ ፖለቲካዊ ማንነት ኣይባልም ማለት ነው። በዘውጉ ማንነት ላይ የቆመ ሳይሆን በኣብዛኛው ዘውግ ዘለል የሆነውን የዴሞክራሲ ባህል በማቀንቀን ላይ የተመሰረት በመሆኑ ዘውጋዊ ፖለቲካዊ ማንነት ሊባል ኣይችልም። ነገር ግን ለሂቃኑ የሚሹትና የሚጓጉለት በርግጥ ያንን ወደ ፈለጉት ኣቅጣጫ ሊወስድ የሚችልን ኤነርጂ በመሆኑ ስለባህሉ መቀየጥ ኣይጨንቃቸውም።

ፕሮፌሰር መሳይ የዚህን ኣስተምህሮ ነቀፌታ ሲጠቅሱ በስሜት ላይ ተመርኩዞ በመሄድ ደም እስከማፋሰስ የሚደርስ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ቡድኖች ለምን ይከተሉታል? የሚል ነገር አንስተዋል። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የዘውግ ፖለቲካን መሰረት መፈተሽ ኣለብን። የብሄር ኢንተርፕሩነርስ ወይም ለሂቃን እንበላቸው ያንን ዘውግ የፈጠረውን የትስስር ስሜት ወደ ፖለቲካል ኤነርጂ ቀይረው ሲሄዱ ዋናው መሰረታቸው ስሜት ነው በሚለው ላይ ስምምነት ኣለ። ዋናው መሰረት ራሽናል ኣሳብ፣ ወይም መርህ ኣይደለም። የዘውገኝነትን ስሜት መጠቀም በመሆኑ ነው በቀላሉ ቡድኑን ማንቀሳቀስ የሚችሉት። በስሜት ላይ ወይም በሰው ልጆች ድክመት ላይ የሚቆም ፖለቲካ በመሆኑ ነው ግድፈቶች ሲፈጸሙ ሰው ኣስተውሎ ሁኔታውን በቶሎ ለመመርመር የማያስችለው። ይሄ ተፈጥሯዊ ነው። በአለፈው ጊዜ ዶክተር ዲባባ በኢሳት ቴሌቪዥን የትምህርት ብልጭታ ፕሮግራም ላይ ጥሩ ኣድርጎ ገልጾታል። የሰው ልጅ ውሱንነት ኣለው። ፍጹም ባለመሆኑ ማለት ነው። ከነዚህ ውሱን መገለጫዎች ኣንዱ ደግሞ ኣንዳንዴ በስሜት ላይ ተመርኩዞ የሚያደርጋቸው ግድፈቶቹ ናቸው። በስነ-ልቡና ሳይንስ ውስጥም ታላቁ የስነ-ልቡና ጠበብት ሲግማን ፍሮይድ እንደሚለው የሰው ልጅ ስብእና የተገነባው ከሶስት ጉዳዮች ነው። እነዚህም ኢድ፣ ኢጎ እና ሱፐር ኢጎ ይባላሉ።

የዘውግ ፖለቲካ የሰው ልጆችን የታችኛውን የስብእና ኣካል የሆነውን ኢድ (id) ነው ሊጠቀምበት የሚሻው። ቅጽበታዊ አካባቢያዊ ርካታዎችን በማጉላት የሚቀሰቅስ ሲሆን ይህ ነገር የቡድን አባላት ስሜት ቢያስነሳ ኣይገርምም። ኣንድ ዘውጌኛ ካድሬ ሱፐርኢጎን ማለትም የሰዎችን ከፍ ያሉ የሞራልና የመርህ ፍላጎትች ተጭኖ የቡድኑን ኣባላት በመቀስቀስ ጥፋት ሊያመጣ ይችላል። ሰው ለምን ይሀን ይከተላል? ፍጹም ስላልሆንና አንዳንዴ በስሜት የምናደርጋቸው ጉዳዮች ስላሉ። ለዚህ ነው ፖለቲካ ሃላፊነት የተሞላበት የቅስቀሳ ስራ እንዲሰራና፣ የሰው ልጆችን ከፍተኛ የመርህ ስብእና በማዳበር ላይ ያተኮረ ፕሮግራም እንዲኖረው የሚያስፈልገው። በ1997 ዓ .ም በሰላም ኣገር የወያኔ መንግስት በቅንጅት መሪዎች በመድረክ በዝረራ ሲሸነፍ ቶሎ ወደ ጓዳው ሮጦ የመዘዘው ሰይፍ “ኢንተርሃሞይ” የሚል ነበር። በመርህ ላይ መወዳደር ሲያቅተው ቶሎ ብሎ ወደ ስሜት ቅስቀሳ የገባው የቆመበት የፍልስፍና መሰረት ይሄው በመሆኑና በክፉ ጊዜ አንድን ቡድን በስሜት በማነሳሳት ስልጣኑን ማቆየት ዋናው መሳሪያ በመሆኑ ነው። ይህ የፖለቲካው ተፈጥሮ ነው። በአለማችን የተደረጉ የዘር ማጥፋት ድርጊቶች በስሜት ላይ በሚነዱ መሪዎች የተደረጉ ቅስቀሳዎች ነበሩ። የኣንድን ተፈጥሮኣዊ ቡድን ማንነት በማራገብና የቡድኑን ኣባላት በከፍተኛ ስሜት ውስጥ በመክተት ይህ ቡድን ለህልውናህ ጸር ነው በሚል ወንጀል ያስፈጸሙ መሪዎች ብዙ ኣሉ። አካባቢያዊ ጥያቄዎችን በማጉላትና ሱፐርኢጎ የተባለውን የሰው ልጆች ስብእና መሰረት በመጫን በብሄራዊ ደረጃ ወይም በማህራዊ ደረጃ ትክክል ነው ኣይደለም የሚለውን ፍርድ የቡድን ኣባላት እንዳያደርጉ በማዋከብና ኢድ እንዲያሸንፍ በማድረግ ወንጀል ያስፈጸሙ ህዝብን ያሳሳቱ ብዙ ፖለቲከኞች ኣሉ። ለምሳሌ ሩዋንዳ ውስጥ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ይፈጽሙ የነበሩትን ግለሰቦች ስናይ ፖለቲከኞች በስሜት እንዲሰክሩ ስላደረጓቸው ነበር። የብሄር ማንነታቸውን በማራገብና የቱትሲ አባላት ለሁቱዎች ፍላጎት ጠላት እንደሆኑ ኣድርጎ በማሳየትና ኣባላት ሱፐር የሆነውን መርህና ሰብዓዊነትን የሚመዝነውን የሰውነት ክፍላቸውን በመጫን የሃይማኖትና የባህል ቆባቸውን ሳይቀር በማስጣልና በማሳበድ ዓለም የማይረሳውን ወንጀል እንዲፈጽሙ ኣድርገዋል። በኢንተርሃሞይ ቅስቀሳ ያበዱት ሰዎች በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ነበሩ። በ 1994 E.C ሩዋንዳ ውስጥ ለመቶ ቀናት በየሰዓቱ ወደ ሶስት መቶ ሰላሳ ኣራት ሰዎች ይታረዱ ነበር። አገር በኢንተር ሃሞይ ኦፐሬሽን ኣብዶ ነበር። ወንጀሉ የተፈጸመው በስሜት ነው:: ኣይገርምም? በስሜት ስምንት መቶ ሺህ የሚሆኑ ዜጎች በመቶ ቀናት ብቻ አልቀዋል። ወንጀሉ ካበቃ በሁዋላ ሰው ሁሉ ወደ ነፍሱ ሲመለስ እየተላቀሰ ይቅርታ…. በስሜት ነው ያደረኩት…ራሴን አላውቅም ነበር…. በማለት ሲጠይቁ ይታያል። ከዓመታት በፊት አንድ ጊዜ በአንድ አለማቀፍ ኮንፈረንስ ላይ አንድ ሩዋንዳዊ ወጣት አግኝቼ ነበር። ትንሽ አወጋኝ። ይህ ወጣት ከአጠቃላይ ቤተሰቡ ለምልክት የተረፈ ነበር። የቱትሲ ጎሳ ኣባል ነው። ወደዚህ ኮንፈረንስም የመጣው ለጉባኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ነበር። በጣም ያሳዝናል። ከቤታቸው ድረስ መጥረቢያ ይዘው እየገቡ ጨፍጭፈዋቸዋል። ጨፍጫፊዎቹ በትክክል በፖለቲከኞቹ ፕሮፓጋንዳ ሰክረው ኣብደው ነበር።

ለዚህ ነው በደም፣ ወይ በሃይማኖት ወይም በባህል ትስስር ላይ የቆመ ኣስተዳደራዊ ኣይዲዮሎጂ ኣደገኛ ነገር ኣለው የሚያስብለው። ከኣንድ በላይ ባሉ የቡድን ኣባላት በኣንድ መንግስት ስር ራሳቸውን ካገኙ በሁዋላ የጋራ ኣስተዳደር መስርተው ለመኖር ካማራቸው የመጀመሪያው ርምጃ ፖለቲካቸውን ከዘውግ ነጥቀው ማውጣት ነው። ኣገር ይህን ይጠይቃላ። የጋራ ኣገር መመስረት ካስፈለገ ያ የጋራ ኣገር ወደ ህልውና የሚመጣው ቢቻል ከሁለቱ ቡድኖች ውጭ ባለ የጋራ ማንነት ላይ ሲቆም ነው። ይህ ሲሆን ግን ቡድኖች ኣንድ የሚያደርጉት ነገር ኣለ። ቋንቋና ባህላቸውን ሜዳ ላይ መጣል ሳይሆን ይህንን ባህላቸውን በሌላ የባህል ኣሰተዳደር ለማስተዳደር ቢስማሙ ጥሩ ነው። ኣንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ ፈጥረው በሌላ በኩል ደግሞ ባህላዊ ጉዳዮቻቸውንና ቋንቋቸውን በተለየ ኣስተዳደር መምራት ይችላሉ። ፕሮፌሰር መሳይ የግለሰቦች መብት መከበር ብቻውን ዘውግ የሚያነሳውን ጥያቄ አይመልስም ብለዋል። ይህንን እቀበላለሁ። የግለሰብ መብት ተከበረ ማለት የቡድንም መብት ተከበረ ማለት ነው የሚለው ኣሳብ የቡድኖችን መብቶች ለንፋስ ያጋልጣቸዋል። ነገር ግን የቡድን መብት ምንድን ነው? የሚለው ላይ ነው ብዙ ማስብ የሚጠይቀው። ቡድን እንደ ቡድን የሚይዟቸው እንደ ቋንቋና ባህል ወግ ልማዶች ዋናዎቹ ናቸው። እነዚህን መጠበቅ በጣም ኣስፈላጊ ነው። ይህ ማለት ግን ዘውጌኛ ፖለቲካ መቀፍቀፍ ማለት ኣይደለም። የቡድኖችን መብት መጠበቅና የዘውግ ፖለቲከኛ መሆን ለየቅል ናቸውና።

ኣገር ሲመሰርቱ ሁሉን ወዶ ኣይሆንም። ከዚህ በፊት በጻፍኳት ጦማር ላይ እንደገለጽኩት ኣገር መስዋእትነትን ይጠይቃል። ኣገር ግዙፍ ጉዳይ ነው:: ቡድኖች አገር ሊመሰርቱ ወጥተው ደግሞ ሰስተው አይሆንም። የዓለም ኣገራት ሁሉ የቆሙትና ወደ “እኛ ህዝቦች” የተሻገሩት እያዋጡ እያደባለቁ ነው። ኣገር እንዲሁ በሰንካላ ምልክቶችና በሆታ ኣይቆምም። የጠራ ኪዳን ይጠይቃል። ወደ ፕሮፌሰር መሳይ የመፍትሄ ኣሳብ እንመለስና እሳቸው የሚሉት ኢትዮጵያ ውስጥ የዘውግ ፖለቲካ ይጠፋል ማለት ዘበት እንደሆነ ነው። ዘበት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ጎጂ ኣሳብም ነው ይላሉ። ይልቅስ የዘውግ ፖለቲካንና ብሄራዊ ኣንድነትን ኣብሮ የሚያስኬድ ሞደሬት ኣሳብ ያስፈልጋል ይላሉ። ዋናው ጥያቄም እዚህ ጋር ነው እንግዲህ። እንደሚመስለኝ እሳቸው ራሳቸው በጥቂቱ priordialist ናቸው። ይህ ደግሞ ከዘመናዊው ኣስተዳደር ጥበብ ከዴሞክራሲ ጋር አይጋጭም ወይ። ቡድኖች ከስሜት ወጥተው በመርህ ላይ ካልቆሙ በፌደራል ስርዓትም ሆነ በአሃዳዊ ስርዓት ስር መኖር ኣይችሉም። በዘውግ ፖለቲካና በብሄራዊ ፖለቲካ መካከል ሞደሬሽን የለም። ሁለቱም ቁጭ ብለው የሚወያዩ በአይዲዮሎጂ የተጋጩ የፖሊሲ ጉዳይ የሚያፋጫቸው ኣይደሉም። በዴሞክራሲያዊ መንገድ ስልጣን እየተለዋወጡ በህዝብ ድምጽ ኣሸናፊና ተሸናፊ አየሆኑ የሚኖሩ ኣይደሉም። ጽንፍ የወጣ ልዩነቶች ያላቸው ስለሆነ ሃገሪቱን ቀጣይ በሆነ ህይወት ውስጥ እየተፈራረቁ አይመሯትም። ወይም ደግሞ ኣገሪቱ የፖለቲካ መሰረቷን በዘውግ ላይ ኣድርጋ ለጋራ ጉዳይ ፌደራል ላይ እንገናኝ ከሆነ ይህ ኣይነት የፖለቲካ ኣሰላለፍ በኮንፌደሬሽን ኣይነት ስርዓት ካልሆነ በፌደሬሽን ስርዓት የሚቻል ኣይሆንም። በእንዲህ ዓይነት ስርዓት ላይ ኣንድ ዘውግ ሾልኮ ሃይለኛ እንዲሆንና ብሄራዊ ተቋማትን ሃይጃክ ኣድርጎ እንዲኖር በር ይከፍታል። በብሄር ፖለቲካ ጊዜ ኣንድ በብሄር ላይ የቆመ ሃይለኛ ቡድን ሲኖር ደግሞ ያ ቡድን ኣምባገነን ሆኖ ጥቂት መኖር ይቻላል። ይሁን እንጂ ሁሉም የዘውግ ፖለቲከኞች ጥቂት የሃይል መመጣጠን ካላቸው የፖለቲካው መሰረት ራሱ ለመርህ የማይጨነቅ በመሆኑ ኣገሪቱን ወደ ኣለመረጋጋት ከማምራቱም በላይ ወደ እልቂት ሊወስድ የሚችል ነገር ነው። በተለይ በኢኮኖሚ ያልዳበርን መሆናችንን ተከትሎ በብሄራዊ ሃብት ክፍፍል ዙሪያ ችሮች ሲከሰቱ ቶሎ ዘውጋዊ ጥያቄ ሆነው ስለሚመጡ ኣገሪቱን ወደ ኣለመረጋጋት ነው የሚወስድብን። የዘውግ ፖለቲካ ሌላው ትልቅ ችግር ደግሞ የተፈጥሮ ሃብት ክፍፍል ላይ የሚፈጥረው ግዙፍ ችግር ነው። በመሬት አጠቃቀም፣ በማእድናት አጠቃቀምና በመከፋፈል በኩል ችግሮችን ያመጣል። በብሄራዊ ሃብትና በዘውግ ሃብት መካከል ግጭቶችን የሚያስነሳ ሃይል ይኖረዋል። ይበልጥ ፕሮፌሰር መሳይን ለመጠየቅ እንድንችል ኣሳባቸውን በቀጥታ እንመልከት።

ፕሮፈሰር መሳይ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ያለባት እንድትሆን ኣሁን ያለውን ክልል ማጥፋት ተገቢ ኣይሆንም ይላሉ። የሚሻለው እነዚህን ክልሎች ተቀብለን በዘውጎች መካከል ኣብሮ መስራትን ማበረታታት ነው ይላሉ። በርግጥ የሚነግሩን ኣሁን ስላሉት ሰለነዚህ ዘጠኝ ክልሎች መሆኑ ነው? እነዚህ ዘጠኝ ክልሎች ምንድናቸውና ነው በኣዲሲቱ ኢትዮጵያ የማይነኩት? ማን ፈጠራቸው? ተፈጥሯቸውስ ምን ይመስላል? የሚለውን ማንሳት ተገቢነው። ኢትዮጵያ ስትፈጠር ዘጠኝ ክልል ኣልነበረችም። ኢትዮጵያ ከሰማኒያ በላይ ብሄር ያላት ኣገር ናት። በዘጠኝ የተሸነሸነችው በአቶ መለስ ነው። ኣቶ መለስ ለምን በዘጠኝ እንደከፈሏት የሚያውቅ እስካሁን ኣልተገኘም። ክልሎቹ በዘውግ ላይ የተመሰረቱም እንኳን ኣይደሉም። ኣብዛኛዎቹ ክልሎች ህብረ ብሄራዊ ይዘት ኣላቸው። በተለይ ደቡብን ካየን በዘውግ የማይገናኙ ቡድኖች የሚኖሩበት ከመሆኑም የተነሳ ከሌሎች በተለየ በአሁኑ ሰዓት በዘውግ ላይ የቆመ ፖለቲካ አፍርሷል። ፕሮፌሰር መሳይ የደቡብ ህዝብ የተገላገለውን እንደገና ወደ ዘውግ ፖለቲካ ይመለስ ሊሉ ነው? የደኢህዴን አባላት ማለት(የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) በዚህ ክልል ስር ያሉ ወደ ኣምሳ ስደስት የሚደርሱ ዘውጎች ፖለቲካዊ ዘውጋዊ ማንነታቸውን በመልክዓምድር ላይ ለቆመ ኣዲስ ማንነት መስዋእት ኣድርገውና ተዋህደው ይታያል። በ 1995 ዓ.ም የየብሄሩን የዘውግ ፓርቲዎች ኣፍርሰው ኣንድ ወጥ ክልላዊ ፓርቲ ኣቋቁመናል ነው የሚሉት።

ይህ የሚያሳየው በአሁኑ ሰዓት በህወሃት (ኢህዓዴግ) ስልጣን ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ዘውጎች ኣብዛኛው ዘውግ ፖለቲካዊ ዘውጋዊ ማንነቱን የሰዋበት ሁኔታ ነው ያለው ማለት ነው። ይሄ ከግንዛቤ መግባት ኣለበት። የደቡብ ህዝብ መፈክርም ኣንድነት ሃይል ነው፣ እኛ የደቡብ ህዝቦች ኣንድ ነን የሚል ነው። ምን ኣልባት ወደ ፊት ያንን ለመልክዓ ምድራዊ ትስስር የሰውትን ዘውጋዊ ፖለቲካቸውን ለሰፊዋ ኢትዮጵያ ይሰውታል። ለጊዜው ግን ደቡብ በዘውግ ላይ የቆመ ፖለቲካው ረግቧል። ሌሎች ክልሎችን ለምሳሌ ሃረሪን፣ በንሻንጉልን፣ ጋምቤላን ብንወስድ ህብረ ብሄራዊ ናቸው። ከአንድ በላይ ብሄርን የያዙ ዘውጎች ኣቶ መለስ በሰጧቸው ክልል መሰረት ይኖራሉ። ኣንድ የክልል ህገ መንግስት ይዘው እስካሁን ኣሉ። እነዚህን ክልሎች እንደማይነኩ ኣድርጎ ማቅረቡን ፕሮፈሰር መሳይ እንዴት እንዳዩት ኣላውቅም። ኣንዱ ጉዳይ ይሄ ነው። ወጥ የሆነ ኣሰራር የሌለውና ምን ኣይነት መርህ እንዳለው የማይታወቅ የአቶ መለስን ክልል መንካቱ ትክክል ኣይሆንም ማለት መነሻው ኣልገባኝም። በርግጥ ኣዲሲቱ ኢትዮጵያ ልታስብበትና ልታስተካክለው የሚገባው ዋና ጉዳይ ይህ የክልል ጉዳይ ነው። ስለ ዘውግ ፖለቲካ ሌላው በኢትዮጵያ ሁኔታ መታሰብ ያለበት ነገር ደግሞ ከሁለትና ከሶስት ከዚያም በላይ ዘውጎች ተቀይጦ የተወለደውን ትውልድ ነው። ይህ ትውልድ በቁጥሩ ካሉት ሰማኒያ ሁለት ገደማ ብሄሮች ሰማኒያ የሚሆኑትን ይበልጥ ይመስላል። በግዙፎቹ ብሄሮች ማለትም በኦሮሞና በኣማራ ነው የሚቀደመው። ከትግራይ፣ ከሲዳማ፣ ከአኙዋክ፣ ከደራሼ ወዘተ ብሄሮች ሁሉ በቁጥሩ ይበልጥ ይበልጥ ይመስላል። ነገር ግን ይህ በቁጥሩ በሶስተኛ ደረጃ ኣካባቢ የሚገኝ ሰፊ ኢትዮጵያዊ መሬት የለውም። ክልል የለውም። ይህ ቡድን ኢትዮጵያዊነትን እንደ ብሄር ወስዶ መኖርን እንደሚመርጥ ብዙ ጊዜ ይታያል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በምስለት ባህር ላይ የዋኙና የተመቻቸው የማንም ብሄር መባል የማይፈልጉና ኢትዮጵያዊ ብቻ መባል የሚሹ ብዙ ሰዎች ኣሉ። የነዚህን የፖለቲካ ተሳትፎም ማገናዘብ ጠቃሚ ነው። ደግሞ ይህ ቁጥር ገና ያድጋል። የወደፊቱን ማየት አለብን:: ምን ኣልባትም ከዓመታት በሁዋላ በቁጥሩ ሁሉንም ብሄሮች በልጦ ኣንደኛ ይሆናል። ስለዚህ እነዚህን ተለዋዋጮችም ከግምት ስናስገባ የዘውግ ፖለቲካ በኢትዮጵያ ሜዳ ላይ ሊጥላቸው የሚችላቸው ብዙ ዜጎች እንዳሉና ዘውጋዊ ፖለቲካ ረጅም እድሜ የሌለው እንደሆነ ይታያል።

ሌላው መታሰብ ያለበት ጉዳይ ደግሞ የዘውግ ፖለቲካና የወያኔ የብሄር ፌደራሊዝም የሚያመጣውን የዴሞክራሲ ችግር (Democratic deficit) ነው። የወያኔ አባላትም ይህንን ነገር ይቀበላሉ። ከክልላቸው ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የፖለቲካ ተሳትፎ የሚገድብ ዴሞክራሲን ለማንሸራሸር የሚያስቸግር መሆኑን ማየት ይቻላል። በአሁኑ ሰዓት በኦሮምያ ብቻ 11 ሚሊዮን ኣማራዎች ይኖራሉ። የሃረሪ ክልል፣ የቤንሻንጉል ክልል፣ የኣፋር ክልል፣ የጋምቤላ ክልል፣ የትግራይ ክልል እና የሶማሌ ክልል ህዝብ ብዛት ተደምሮ በኦሮምያ ውስጥ የሚኖረው አማራ በቁጥር ይበልጣል። ከኦሮምያ ክልል ውጭ በአማራና በተለያዩ ክልሎች የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከብዙ የደቡብ ብሄሮች በቁጥር ይበልጣሉ። በተለያዩ ክልሎች ኢትዮጵያውያን ተበትነው አገሬ ብለው ይኖራሉና የዘውግ ፖለቲካ ኣንዱ ችግር ይህን ግዙፍ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ተሳትፎ ይገድባል ሰፊ Democratic deficit አለው።

ለአብነት የሃረሪን ክልል ስናይ የኢትዮጵያን የፌደረል ስርዓት ውጥንቅጥ በሚገባ ያሳያል። ፕሮፌሰር መሳይ እንደሚያውቁት ሃረሪ የቆዳ ስፋቷ 334 ኪሎ ሜትር ስኩየር ያህል ሲሆን 183,415 የሚሆኑ ወንድና ሴት ኢትዮጵያውያንን ይዛለች። ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በህዝብ ብዛት ታንሳለች። ይህ ክልል ሲዋቀር ለብቻው አንድ ክልል ይሆን ዘንድ የሚቀሰቅስ ምን ነገር እንዳለ አይታወቅም። የሆነ ሆኖ ግን ከሌሎች ክልሎች በጣም በተለየ መንገድ የሚታይ ጉዳይ አለው። ሃረሪ ካሏት ህዝብ መካከል 56.4% ኦሮሞዎች፣ 22.7% አማራዎች፣ 4.3% ጉራጌዎች፣ 1.53 % ትግሬዎች፣ 8.65% ሃረሪዎች፣ 1.26% አርጎባዎች ናቸው:: ይህ ክልል ሲዋቀር ከሃረሪ ከተማ በተጨማሪ አስራ ዘጠኝ ወረዳዎች ከኦሮምያ ተጨምረውበት እንደሆነ በዚህ ዙሪያ ጥናት ያካሄዱ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። የኦሮሞው ቁጥር በአንደኛነት የበዛውና ከአጠቃላዩ የህዝብ ብዛት ከግማሽ በላይ የሆነው እነዚህ ቀበሌዎች ስለተጨመሩ ነው ማለት ነው። የሃረሪ ክልል የተቋቋመው ሀረሪ ባህሏን እንድትጠብቅ ነው እንዳይባል እጅግ ብዙ ኦሮሞዎችን ከኦሮምያ ክልል ኣምጥተው አቀላቅለዋቸዋል። ይህ ሁኔታ ደግሞ ብዙሃን ቡድን ኣነስተኛ በሆነው ህዝብ ላይ ሲጨመር የባህልና ቋንቋ መዋጥን ያመጣል እንጂ ለባህል ቀጥታ እድገት ኣይረዳም። በዚህ ክልል አወቃቀር ጊዜ ምንም ተጠይቅ የማይታይ ብቻም ሳይሆን የሚገርምም ነው። የክልሉ ባለቤት የሆነው 8.65% የሚሆነው ህዝብ ሲሆን 91% በላይ የሆነው ህዝብ የዚህ ክልል ዋና ባለቤት አይደለም:: ፕሮፌሰር መሳይ ይህንን ምን ይሉታል? የሃረሪ ክልል የኢትዮጵያ ፌደራል ስርዓት ውጥንቅጥ ማሳያ ናት። እንዲህ ዓይነት ለዴሞክራሲ መንሸራሸር ኣስቸጋሪ የሆነ ሳይንስ የጎደለው ክልል ያልተነካ ከቶ ምን ሊነካ። የወልቃይት ጠገዴ ጠለምትን ጉዳይ ስናይ የወያኔ ክልል ሲበዛ ችግር ያለበት መሆኑን እናያለንና እንዲህ ዓይነት ክልሎች በሚገባ መስተካከል ኣለባቸው።

ፕሮፈሰር መሳይ በዋናው የመፍትሄ ኣሳብ ባሉት ክፍል ላይ ሲያቀርቡ ኣገሪቱ ዘውጋዊ ፖለቲካንና ብሄራዊ ኣንድነትን ኣቻችላ እንድትኖር ይመክሩና በዘውግና በብሄራዊ ኣንድነት መካከል መጣጣምን የሚያመጣ ነው ካሏቸው ኣሳቦች ውስጥ ኣዲሲቱ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ተቋማትን፣ ብሄራዊ መግለጫዎችንና ምልክቶችን ማጎልበት እንደሚረዳት ይገልጻሉ። ይሄ ኣሳብ በጣም ኣሳባዊ ኣይደለም ወይ? ነው ጥያቄው። የዘውግ ፖለቲካ እውቅና ኣግኝቶ ከተንሰራፋ በሁዋላ የዘውጎች መቀራረብ እንዲኖር መካከለኛነት እንዲመሰረት ይመክራሉ። ለመሆኑ ይህ መካከለኛነት ከየት ይመጣል? ዜጎች ይህን የመካከለኛነት ስሜት ሊያዳብሩ የሚችሉበትን፣ ይህን የመካከለኛነት ባህል ሊያደብሩ የሚችሉበትን ግሩም እርሻ መቼ ኣዘጋጀን? መካከለኛነት እኮ የባህርይ ለውጥ ነው። ይህን ለውጥ የሚያመጣው ደግሞ የፖለቲከኞችን ተክለ ሰውነት መካከለኛ ኣድርጎ የሚቀርጽ የፖለቲካ እምነት ነው። መጀመሪያ ኦሮሞ ነኝ፣ መጀመሪያ ትግሬ ነኝ፣ መጀመሪያ ኣደሬ ነኝ ወዘተ ከሚል የፖለቲካ ስሜትና ኢትዮጵያዊነትን በስሱ ከሚያሳይ የፖለቲካ እምነት እንዴት የመካከለኛ ኣገልግሎት ሰጩ ካህናትን ለማግኘት እንሞክራለን? በዘውግ ፖለቲካ ስር ያደጉና የዘውግ ፖለቲካ የቀፈቀፋቸው ፖለቲከኞች ኣዲስ ኣበባ ሲገናኙ ደርሶ ድንገት መካከለኛ ሊያደርጋቸው የሚችል ምን መሰረት ይኖራል። በስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ መካከለኛ እንሁን እያሉ በማወጅ ይህ የመካከለኛነት ኣገልግሎት ስሜት ኣይዳብርም። በዘውግ ላይ የተመሰረቱ ፖለቲከኞች፣ ዘውጋቻውን ኣጥብቀው ይዘው በሚታገሉበት የፖለቲካ ድባብ ስር የዘውግ ፖለቲካ ልእልና በረበበበት ኣገር ውስጥ በርግጥ ብሄራዊ ተቋማትን ማጎልበት ይቻላል ወይ? የሚል በጣም ሃቀኛ ጥያቄ መነሳት ኣለበት። የፖለቲካው መሰረት ዘውግ ሆኖና ኣካባቢያዊ ማንነቶች ጡንቻቸው በፈረጠመበት ኣገር እነዚህ ብሄራዊ ተቋማት የሚባሉት ለሃይለኛው የዘውግ ፖለቲካ ድርጅት መጠቀሚያ ከመሆን ኣልፈው በራሳቸው በሁለት እግራቸው የሚቆሙበት መሬት ኣያገኙም። እርሻው ኣይመችምና ኣይበቅሉም።

መቼም ክርስቶስ ግሩም ኣስተማሪ ነው። ኣንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ሲያስተምር ስለ ዘር ያስተምራቸው ነበርና እንዲህ ኣለ። “እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ። ሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው በሉት። ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀና ጥልቅ መሬት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤ ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ። ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው፥ ፍሬም አልሰጠም። ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀና ወጥቶ አድጎ ፍሬ ሰጠ፥ አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ አፈራ።” ይላል። በርግጥም ዘውግን ባስቀደሙና ፖለቲካዊ ማንነታቸውን መስዋእት ለማድረግ በሰሰቱ ቡድኖች እርሻ ላይ ብሄራዊ ተቋማት ይጎለብታሉ ማለት ከንቱ ምኞት ነው። በቡድኑ ጥቅም የሰከረ ፓርቲ ሃይለኛ ሆኖ ስልጣን ሲይዝ እነዚህን ምልክቶች እያጠፋ ብሄራዊ ተቋማቱን ለራሱ መጠቀሚያ እያደረገ ይኖራል። ሁል ጊዜም በእንዲህ ኣይነት ኣስፈሪ ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ተቋማት ይሆናሉና ይሄ እንዴት መፍትሄ ኣሳብ ሊሆነን ይችላል? ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ያመጣልናል ወይ? የሚለው ጉዳይ በጣም ትልቅ ጥያቄ ነው።ፖለቲካውን ዘውጌ ኣድርገን ስለብሄራዊ ምልክቶች ትምሀር ቤት ብናስተምር ምንም ጠብ ኣይልም። ብሄራዊ ተቋማትም ይሁኑ ምልክቶች የሚባሉት ሁሉ ጉልበት ኣይኖራቸውም። ይህን የሚያደርገው ወያኔ ብቻ ኣይደለም። ማንም በዘውግ ላይ የቆመ ሃይለኛ ፓርቲ ሲመጣ እነዚህን ምልክቶች መጠቀሚያ ነው የሚያደርጋቸው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሃገርን የሚያህል ነገር እንዲህ በጣም በቀጠነ ምልክት ለማቆም መሞከሩ ራሱ ለመረጋጋት መፍትሄ ኣይሆንም ብቻ ሳይሆን ኣለመረጋጋትን የሚያመጣ ነው።

ኣንዱ የፕሮፌሰር መሳይ የመፍትሄ ኣሳብ ችግር ይሄ ነው። አገርን የሚያህል ግዙፍ ማንነት በጣም በቀጠነ ምልክት ሊያቆሙ ይፈልጋሉ። ብሄራዊ ተቋማትንና ምልክቶችን መገለጫዎችን በዘውግ ፖለቲካ መሃል ኣብቦ ማየት ይፈልጋሉ። ዘውግ መኖሩ በራሱ ኣይደለም ችግሩ። ዘውጎችማ ይኑሩ። ጥንካሬና ውበት ይሆናሉ። ዘውግን ማጥፋት ሳይሆን ነገር ግን ዘውጎች ተሰባስበው መኖር ሲሹ ኣንድ የጋራ ኣዲስ ማንነት መፍጠር ኣለባቸው:: ይህ ማንነት ማንንም ሳይጨፈልቅ መሆን ኣለበት። ቡድኖች የጠሉት ነገር ብሄራዊ ማንነት ሲፈጠር ቡድኖችን እየጨፈለቀና በኣንዱ ቡድን ኣምሳል ሌላው እየተቀረጸ መሆኑን ነው። ይህንን ማስተካከል በርግጥ ያስፈልጋል። ሁለት የተለያዩ ባህል ያላቸው ቡድኖች ኣንድ የጋራ ቤት መስራት ካማራቸው ኣንድ ሌላ ሶስተኛ ባህል ኣምጥተው ያ ሶስተኛ ባህል ሁለቱንም ቡድኖች ሊያያይዛቸው ይችላል። ይህ ሶስተኛ ባህል ደግሞ ዴሞክራሲ ሊሆን ይችላል። ይህ ባህል የሁሉ የጋራ ከሆነ ፖለቲካዊ ማንነታቸውን በኣንድ ድንኳን ስር ለማድረግ እንዴት ይሳናቸዋል።

ሁለተኛው የፕሮፌሰሩ ኣሳብ ደግሞ የዘውግ ፖለቲካና ብሄራዊ ኣንድነት ሳይቃረኑ ይኖሩ ዘንድ ፕሬዚደንታዊ ኣስተዳደር የመከከለኛነት ኣገልግሎት በመሰጠት ሊያገለግል ይችላል ይላሉ። ፕሬዚዳንታዊ ሲሆን በቡድኖች ምርጫ የሚመጣው ፕሬዚደንት የብሄራዊ ኣንድነት መገለጫ ምልክት ሆኖ ይኖራል ማለት ነው። ይሄም ጥያቄ ኣለበት። በዘውግ ፖለቲካ ጨዋታ ውስጥ ያደገ ፕሬዚዳንት ልንመርጥ ነው ማለት ነው። ይህን ፖለቲካዊ ስብእና የያዘን ሰው የቱንም ያህል ህግ ቢኖር በህግ የበላይነት ላይ ጥያቄ ያስነሳል። ዋናው ተፈላጊው ነገር ህጉ ብቻ ሳይሆን የባህሪ ለውጥ ነው። የሚፈለገው የዳበረ ጸባይ (character)ና ፖለቲካዊ ስብእና ነው። በፕሬዚደንቱ ህይወት ውስጥ ከውስጥ የሚመነጭ የሃገር ፍቅር ስሜት ነው እንጂ መለኪያው ጥሩ ህግ ኣውጥቶ ኣንድ ዘረኛ ቢመጣ ያው ህጉን መጫወቻ ነው የሚያደርገው። የህወሃት ሰዎች ይሄውና ጥሩ ህግ እያሳዩ ኣይደል የሚጫወቱብን። ኣድልዎ የሚፈጽሙት የፖለቲካ ስብእናቸው ኣካባቢ ችግር ስላለ ነው። ከውስጥ የሆነ የባህሪ ለውጥ ነው የሚያስፈልገን። ይህ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ዋናው ችግር ኣገሪቱ በከፍተኛ የዘውግ ፖለቲካ ስር ባለችበት ሰዓት የምርጫ ጉዳይ በሚገባ መጠናት ኣለበት። በዘውግ ጊዜ ብሄራዊ ምርጫ ሁል ጊዜ ለማንነት ድምጽ (identity vote) በከፍተኛ ሁኔታ ይጋለጣል። ከራሱ ከፕሬዚዳንቱ የፖለቲካ መሰረትና ስብዕና በተጨማሪ ዜጎችንም በማንነት ድምጽ ውስጥ ወስዶ የሚዘፍቅ የፖለቲካ ከባቢ በሚኖርበት ኣገር ውስጥ ገለልተኛና የሁሉ ኣባት የሚሆን ፕሬዚዳንት መፈለግ ላም ካልዋለበት ሜዳ ኩበት ለቀማ መውጣት ኣይሆንብንም ወይ ነው ጥያቄው። ሰፊው ፖለቲካዊ ስልጣን በዘውገኞች ተይዞ ኣንድ ፕሬዚዳንት ብንመርጥስ ይሄን ያህል ምን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። ፓርላማውም ይሰራ ዘንድ ከማንነት ፖለቲካ መጽዳት ኣለበት። ምን ኣልባት ኣገሪቱ በኮንፌደሬሽን ኣይነት ኣስተዳደር ስር ከተዳደረች ትክክል ነው። ፕሮፈሰር ያነሷቸው ምልክቶች ሊሰሩ ይችላሉ። ነገር ግን በፌደራል ስርዓትና በኣሃዳዊ ስርዓት ውስጥ እነዚህ ያነሷቸው ምልክቶች በተግባር ኣሜኬላ ያለባቸው በመሆኑ ሊሰሩ የማይችሉ ናቸውና ለዚያች ኣገር መፍትሄ ይሆናል ወይ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። ሌላው የዘውግ ፖለቲካ እንዳይነካ የሚፈልጉትን ፕሮፌሰር መሳይን መጠየቅ ያለብን ነገር የቀመር ጉዳይን ነው። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በቁጥራቸው እጅግ የሚራራቁ ብሄሮች የሚኖሩባት ኣገር ናት። እነዚህ ዘውጎች ከፍተኛ የሆነውን ስልጣን በምን ቀመር ሊከፋፈሉት ነው? በህዝብ ብዛት ከሆነ በቁጥራቸው የሚያንሱትን ቡድኖች ተስፋ የሚያስቆርጥ ከመሆኑ የተነሳ ወደ መገንጠል ሊወስዳቸው ይችላል። በከፍተኛ ቁጥር ኣካባቢ ያሉትም ፉክክር መግባታቸው አይቀርም። አንዱ የሚገጥመን ትልቅ ችግር ይሄ ነው። የጠራ ቀመር እናጣለን። ይህ ደግሞ ውሎ ሲያድር አለመረጋጋትን ያመጣል።

ከሁሉ በላይ ግን ፕሮፌሰር መሳይ ከበደን ወደዚህ ኣሳብ ምን ኣመጣቸው? የሚለውን ነገር ማንሳት ተገቢ ይመስለኛል። እንደሚመስለኝ ፖለቲካዊ ዘውገኝነትን በኢትዮጵያ ከሚገባው በላይ ኣጉልተው ያዩት ይመስላሉ። በጣም ስር የሰደደና ወደፊትም ጨርሶ የማንላቀቀው ኣድረገው ከማሰብ የመጣ ይመስላል። አለም ሁሉ ከዘውግ ፖለቲካ እየተላቀቀ ወደ ዴሞክራሲ ኣድጎ ሳለ ኢትዮጵያ ከዘውግ ፖለቲካ እስከ ሃቹ መውጣት እንደማትችል ኣድርገው ለምን ያስባሉ? ኢትዮጵያን ለምን ከዓለም ያወጧታል? ከዘውግ ወደ ዴሞክራሲ ወደ መርህ ፖለቲካ ማደግ እኮ የሰው ልጆች የእድገት ውጤት ነው። የመማር ውጤት ነው። ስለዚህ ይህን የፕሮፈሰሩን ኣሳብ እቃወማለሁ። መሬቱ ላይ ያለው እውነት ከፕሮፈሰር መሳይ የተለየ ነው የሚመስለኝ። ከፍ ሲል እንዳልኩት ብዙው የኢትዮጵያ ቡድን የደቡብ ህዝብ የዘውግ ፖለቲካ የለውም። በኣሁኑ ዘውግ በጣም ገነነ በተባለበት ዘመን እንኳን ማለቴ ነው። ሌላው ጉዳይ ደግሞ ዘውጌኛ ፖለቲካ በኢትዮጵያ መሰረተ ቢስ መሆኑን ለፕሮፌሰር መሳይ መግለጽ እወዳለሁ። በሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የተጠላ ነው።ሰፊ ህዝባዊ መሰረት የለውም ማለቴ ነው። ኣንዱ ይሄ ነው። ሌላው ጉዳይ ግን ፕሮፌሰር ኣልማርያም ያሉት ጉዳይ ነው። ፕሮፌሰር ኣልማርያም በዚሁ ስብሰባ ወቅት ኣሜሪካውያን ከመላው ኣለም ተሰባስበው “እኛ ህዝቦች….” ማለት ከቻሉ እኛ ኢትዮጵያውያን ተስኖናል ብሎ ማሰቡ ትክክል ኣይደለም። የዘውግ ፖለቲካ በኢትዮጵያ በጥቂት ኤሊቶች የተጫነብን እንጂ የመረጥነው ኣድርጎ መቅረብ የለበትም። ሌላው መሰረታዊ ጉዳይ ደግሞ የዘውግ ፖለቲካ ስንል በኢትዮጵያ ምን ማለት ነው? ተብሎ መተንተን ኣለበት። በኢትዮጵያ ውስጥ ወገን ለይ ብሎ ብቅ ያለው ፖለቲካ ሃይማኖት ኣይደለም። የቋንቋና የባህል ቡድነኝነት ነው።ይህ ልዩነት ደግሞ ከዘር ልዩነት በታች ነው። ባህላዊ ቡድኖች የፖለቲካ ስልጣን ኣምሯቸዋል። ምንም እንኳን ብዙሃኑን ባይወክሉም። እነዚህ ቡድኖች ስልጣን በሃይል ያማራቸው ደግሞ እዚያው ክልላቸውን በማስተዳደር ላይ ኣይደለም እውነቱን ለመናገር። ዋናው ልባቸው የቋመጠው የፌደራል መንግስቱን መቆጣጠር ነው። ለምን ከተባለ በዴሞክራሲና በፍትህ ላይ ተረማምዶም ቢሆን የቡድናቸውን ህልውና ለማስጠበቅና እድገትን ለማምጣት ጥሩ ስትረተጂክ ቦታ መስሎ ስለሚታያቸው ነው። በተለይ ኢኮኖሚክ ኣድቫንቴጆችን ለመውሰድ ስትራተጂክ ቦታ ነው ብለው ያስባሉ። ህወሃት የዘውግን ፌደራሊዝም ለኢኮኖሚክ ኣድቫንቴጅ ነው እየተጠቀመብት ያለው። ስለዚህ ነው ብሄራዊ ተቋማት ሁል ጊዜ በኣደጋ ከባቢ ውስጥ እንዲኖሩ እንዲኮስሱ የሚያደርጋቸው። ወደ ኢትዮጵያ የዘውግ ፖለቲካ ጉዳይ እንመለስና እንግዲህ ዘውግ ስንል በኣማርኛ ወገን ማለት ነው። የምን ወገንተኛ ስንል ደግሞ የባህልና ቋንቋ ኣርበኞች እንደማለት ነው። መቼም የኢትዮጵያ ቡድኖች በሰው ልጆች ከፍተኛ የሆነ የዘር ልዩነት ውስጥ ኣይገቡም። ሁሉም ጥቁር፣ ምስራቅ ኣፍሪቃውያን ናቸውና። ሊያነሱ የሚችሉት ልዩነት በቋንቋ ማህበረሰብ ወገንተኝነት ላይ የተመረኮዘ ነው ማለት ነው። ታዲያ እንዲህ ኣይነቱ ልዩነት በራሱ የማይለወጥ የማይነቃነቅ ማንነት ነው ወይ ወደሚል ጥያቄ እንመጣለን። ዛሬ ደቡብ ኣፍሪካ ውስጥ ነጭ፣ ጥቁር፣ ከለር ሁሉም በአንድ የፖለቲካ ድንኳን ውስጥ ገብተው ስለ ዴሞክራሲ ሲያወሩ እኛ ኢትዮጵያውያን ይህቺን የባህልና የቋንቋ ልዩነታችንን ኣጉልተን ዘውጌኛ ፖለቲከኞች ስንሆን ዓለም ምን ይላል?

ከማንነቶች መካከል የለውጥ ህግ የሚሰራበት ኣንዱ ማንነት ባህል ነው። ባህልና ቋንቋ የሚያድግ የሚሞት የሚለውጥ ነገር ነው። የብዓዴን፣ የኦህዴድ፣ የደኢህድን፣ የህወሃት ኣባላት ተሰብሰበው ሲነጋገሩ ሶስቱም ሱፍ ለብሰው ነው የሚታዩት። በኣለማቀፉና በእርስ በርሱ የባህል ልውውጥና ውህደት ባህር ላይ ይዋኛሉ። ባህል በሁለት ኣቅጣጫ ያደጋል። ኣንደኛው በራሱ የለውጥ ኣቅጣጫ ያድጋል። ትውልድ ኣልፎ ትውልድ ሲተካ ባህሉን እያሻሻለው ይሄዳል። ይለወጣል። ሁለተኛው ደግሞ ኣብሮ ከሚኖራቸው ቡድኖች ጋር እየተዋሃደ ሳያውቀው ኣዳዲስ ባህሎችን እያሳደገ ይሄዳል። በመሆኑም ባህል የማይናወጥ የፖለቲካ የማእዘን ራስ ማድረጉ ሩቅ ኣለማየት ያስመስላል የሚሉ ወገኖች ኣሉ።

ዋናው ጉዳይ ለፕሮፌሰር መሳይ የሚቀርበው ጥያቄ ግን ወገንተኛ ፖለቲካ በብዙህ ኣገር ውስጥ ሳይንሳዊ ካለመሆኑ የተነሳ ኣገሮች ሁሉ ከዘውጋዊነት ወደ መርህ እያደጉ ወደ ዴሞክራሲ እያደጉ በሚመጡበት ሰዓት ኢትዮጵያ ዋና የፖለቲካ መሰረቷን ዘውግ ኣድርጋ ብሄራዊ ኣንድነቷን በምልክት እንድትኖር ለምን ትመከራለች ነው። ለምን የተገላቢጦሽ ኣይሆንም። ዘውጋዊ ማንነቷን ከፖለቲካ ኣላቃ ባህላዊ ማንነቷን ደግሞ በተደራጃ ምልክት ለምን ኣታደርገውም ነው። ባህላዊ ማንነቶችን ለምን በቀጥታ ባህል ኣይረከብምና ኣሁን የመጣውን ኣዲሱን የኣስተዳደር ዘየ ደግሞ ቶሎ ብለን ለሁላችን ኣድረገን ኣብረን ኣንኖርም። ሃረሪ ውስጥ ላእላይ ምክር ቤቱ የሃረሪን ባህል ጠባቂ ነው ይባላል። የፖለቲካ ውክልና ያለው፣ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ኣርበኛ ባህልን ለመጠበቅ ይሞክራል። ይሄ የሚያሳየው ፖለቲካው ራሱ ባህላዊ ፖለቲካ መሆኑን ነው። ይሄ ተለውጦ የባህል ኣርበኞች ቤት ለብቻው ቢበጅና ባህልና ፖለቲካ ቢሊያይ ጥሩ ነው። ልክ ሃይማኖትና ፖለቲካ የተለያዩ ናቸው እንደምንለው ባህልን ለብቻው ማስተዳደር ብንችል ቡድኖችን ከባህል ኣንጻር እንዳይዋጡ ማድረግና ሁሉም በባህሉ እንዲኮራ ማድረግ እንችላለን። በሌላ በኩል ደግሞ የምንፈጥረው የጋራ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ህይወት አድልዎ እንዳይኖረው የፍትህ ኣካሉን በጥሩ መሰረት ላይ ማቆም ይቻላል። ብሄራዊ ተቋማት በለሰለሰ እርሻ ላይ ስለሚዘሩ ዴሞክራሲያዊ ባህርያትን እያፈሩ ያድጋሉ። ከውጭው ኣለም ጋርም ሳንቸገር መኖር እንችላለን።

የፕሮፌሰር መሳይ ዓላማ ዘውግንና ብሄራዊ አንድነትን ማስታረቅ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ዘውግ (በኢትዮጵያ ሁኔታ) ና ብሄራዊ ኣንድነት መቼ ይጣላሉ። ኣይጣሉም እኮ። ባለፈው በጻፍኳት ጦማር ላይ የጠቀስኩትን እንደገና ኣሁንም መግለጽ እፈልጋለሁ። ቡድኖች በተፈጥሯቸው ላይ ኣይነቃቀፉም። ያንተ የልብስ ባህል ኣያምርም የእኔ ያምራል፣ ያንተ ቋንቋ ኣይጥምም የኔ መልካም ነው፣ ያንተ ምግብ ወዲያ የኔ ይጣፍጣል ወዘተ በሚል ኣይጋጩም። ይህ ልዩነታቸው ኣያጣላቸውም። ቡድኖችን ወደ ግጭት የሚወስደው ይህንን ጥበባቸውን ይዞ የፖለቲካ መጫወቻ የሚያደርግ ኣካል ሲፈጠር ያ ኣካል የሚቀሰቅሰው ኣስተዳደራዊ ችሎታን ወይም ጥበብን ከተፈጥሮ ጋር ስለሚያያይዘው ብርታትም ሆነ ድክመት የቡድኑን ስሜት ቶሎ የሚኮረኩርና የሚያነቃ ይሆናል። ከዚህ ክብ ውስጥ የወጣ ኣንድ ሰው በሚያደርገው መልካም ስራ ቡድኑ ይረካል። ያጋንናል። ድክመቶች ሲታዩ ደግሞ ይደብቃል። ያፍራል። በኣንጻራዊ ያሉት ቡድኖች የዚያን ሰው ድክመት ኣጠቃለው የቡድኑ ኣድርገው ያዩታል የሚል እምነት ያድርበታል። የተፈጥሮ ድክመት ኣድርገው ሌሎች ያስባሉ ብሎ ያስባል። እናም በዚህ ዙሪያ በሚደረጉ ክርክሮች ዙሪያ ሃፍረቱን ኣውልቆ ጥሎ ኣምክህኖትን ወዲያ ጥሎ ሞራልንና መርህን እየረመረመ ያ ጥፋተኛ ትክክል ነው ብሎ ይከራከራል። ከፍ ሲል እንዳልነው መሰረቱ ስሜት በመሆኑና ለሱፐር ኢጎ ቦታ ስለማይሰጥ መርህ በአደባባይ ይጣሳል። ይህ ነው ወደ ግጭት የሚያመራው። በመሆኑም በኢትዮጵያ ውስጥ ዘውግን ከብሄራዊ ኣንድነት ጋር ኣሳልጦ ለማስኬድ ፖለቲካን አውጥቶ በዴሞክራሲ ባህል ኣንጾ ያንን ሶስተኛ ባህል ኣድርጎና የጋራ ኣድርጎ በኣንድ የፖለቲካ ጥላ ስር መኖር ነው ትልቁ መፍትሄ።

ሌላ ቁም ነገር ላንሳ። የኢትዮጵያን የቡድኖች ጥያቄ በሚገባ መግለጽ የተቻለ ኣይመስለኝም። በሃገራችን የቡድን ጥያቄ የለም ማለት ጥሩ ኣይደለም። በሚገባ ኣለ። በኢኮኖሚ ህይወቱ ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ተመሳሳይ ኑሮ ነው የሚኖረው። የሰሜን ገበሬ ከደቡቡ ከምእራቡ ከምስራቁ ጋር ያው ነው። ከተሞች ኣካባቢ ሚዛናዊ ያልሆነ የሃብት ክምችት ይኖራል። ስለ ሰማኒያ በመቶው የኢትዮጵያ ህዝብ ስናወራ ግን ኣንድ ኣይነት የኢኮኖሚ ህይወትን ይኖራል። የደቡቡ ገበሬ በሰሜኑ ህይወት ኣልቀናም። የኦሮሞው ገበሬ በሲዳማው ኣልቀናም። ኢትዮጵያ ውስጥ ቡድን ከቡድን አልተጎዳዳም። በኢትዮጵያ ሁኔታ በቡድን ሊገለጽ የሚችል ችግር ካለ ከባህልና ቋንቋ ኣያያዛችን ጋር የተገናኘ ነው። በርግጥ ይህንን ችግር ለመፍታት ኣንዳንዴ የፖለቲካ ስልጣንን መሳሪያ ለማድረግ ይሞከራል። ይሁን እንጂ ችግሩ በግልጽ ባህላዊ ነው። ባለፈው ጊዜ አቶ ሌንጮ ባቲ ጥሩ ነገር ተናግረዋል። እኛ ኦሮሞዎች የሚሰማን ነገር ኣለ። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ስትሉ እኛን ያካተታችሁን ኣይመስለንም ኣይነት ተናግረዋል ። ይሄን መረዳት ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ኣስፈላጊ ነው። በመሆኑም የሚታየው ችግር የባህል መዋጥ ችግር ነው። ኣንድ ባህል ሌሎቹን በከፍተኛ ሁኔታ ውጦ ይታያል። ይህንን ጥያቄ አቅልሎ የምግብ የልብስ የምናምን ጥያቄ ነው ማለት ጥሩ ኣይደለም። የቡድኖች ጥበብ ማንነትን የሚገልጽ በመሆኑ ጥንቃቄ ይሻል። ጥያቄያቸውን ዜጎች በተለያየ መንገድ ሊገልጹት ይሞክሩ ይሆናል እንጂ ኣንዱ ችግር የባህላዊ ማንነት መዋጥ ነው። ኣንድ ጊዜ ደቡብ ሄጄ የሆነውን ላውጋችሁ።

ቦታው ቡርጂ ነው። ቡርጂ የምትገኘው ወደ ኬንያ ጠረፍ ኣካባቢ ሲሆን በኣማሮ፣ በጉጂ፣ በኮንሶ ብሄሮች ተከባለች። ብሄረሰቡ በቁጥር ብዙ የሚባል ኣይደለም። በኣሁኑ ኣደረጃጀት በልዩ ወረዳ የተከለለ ኣካባቢ ነው። ዋና ከተማዋ ሶያማ ትባላለች። እዛች ትንሽየ ከተማ ውስጥ ጥቂት የምግብ ቤቶች ኣሉ። ታዲያ ከእለታት ኣንድ ቀን ወደ ኣንዲቱ ምግብ ቤት ኣመራሁና ለምሳ ተሰየምኩ። ታዛዣ መጣች….
“ምን ላምጣ?”
“ኩርኩፋ” ትንሽ ላስፈግጋት ብየ እንጂ ምንም ምርምር ኣስቤ ኣልነበረም::
“ኩርኩፋ?”
“ኣዎ ትኩሱን ቶሎ በይ”
ሳቀች። አየደገመች ሳቀች። እኔም ኣላማየ ደክሟት ከሆነ ነቃ እንድትልና ዘና ባላ ከባቢ ተስተናግጄ እንድሄድ ዘና ብየ በለቼ እንድሄድ ነበርና ዓላማየ ግቡን መታ ማለት ነው። ስለዚህ ወደ እውነተኛው ፍላጎቴ ተመለስኩና ኮስተር ብየ ያንኑ ጥብሴን ኣዘዝኩ። ኣመጣችልኝና ምግቡን ቁጭ እያደረገች።
“የምርህን ነው ግን?” ኣለችኝ።
“ምኑን?”
“ኩርኩፋ ኣላልከኝም። ከፈለክ ኣለ እሰጥሃለሁ::” ኣለችኝ።
ያዘዝኩት ምግብ ስላለና በውነት ማስቸገርም ስለመሰለኝ ግዴለም ሌላ ጊዜ…… ብየ ኣመስግኘ ንግግራችን ተቋጨና ለቀልድ ብየ ያመጣሁት ነገር የእለቱ ኣስተማሪ መሪ ኣሳብ ሆነና ሲያናውዘኝ ዋለ። በዚያች ከተማ ውስጥ ኣንድም የኩርኩፋ ምግብ ቤት የለም። የእንጀራና ወጥ ምግብ ቤት ብቻ ነው ያለው። ይህ የሆነው ደግሞ የሰሜን ሰዎች ስለሚበዙ ኣይደለም። ብዙ የሉም። ለራሳቸው ለቡርጂዎች የተዘጋጀ ምግብ ቤት ነው። በዚያ ማህበረሰብ ኣይምሮ ውስጥ ምግብ ቤት ሲባል እንጀራ በወጥ ብቻ ነው። የሰሜን ባህል ውጧቸዋል። ጨርሶ ባይምሯቸው የራሳቸው ምግብ ለገበያ የሚውል ኣድርገው እንዳያስቡ ኣድርጓቸዋል ማለት ነው የሚል ከአቅሜ በላይ የሆነ ጥያቄ መጣና ትንሽ ኣንገላጀጀኝ። የቡርጂዎች ባህል እንኳን ወደ ብሄራዊ ከተማዎች ቀርቶ በቡርጂዎች ከተማ ሶያማ ውስጥ ገበያ ላይ ኣልወጣም ። ኩርኩፋ በነገራችን ላይ በጣም የወደድኩት ምግብ ነበር። ይህ ለእኔ ያስተማረኝ የኢትዮጵያ የባህል ፍስሰት ፈጽሞ ሊስተካከል ይገባዋል። መስተካከሉ ደግሞ ለሁላችን ጠቃሚ ነው። ኣገራችን የባህል ቫራይቲ እንዲኖራት ከመርዳቱም በላይ ለምግብ ዋስትናና ከድህነት ለመውጣት ለምናደርገው ጥረት ትልቅ ጥቅም ኣለው። ገበያ ያደራል:: ከሁሉ በላይ ግን ቡድኖችን ኣንዳንዴ የሚያነጫንጫቸውን ሚስጥር መረዳት ኣለብን። ጥያቄው በፖለቲካ በኩል መልስ የሚያገኝ እየመሰላቸው ወደዚያ ይሮጣሉ እንጂ ከሚገባው በላይ የተጫናቸው ባህል ኣለ። በብሄር ዘለል ግንኙነት ጊዜ ሊያነጫንጫቸው ቢችል እውነት ኣለው። ኦሮሞ ነኝ ማለት የኦሮሞ ጥበቦችና ቋንቋ ሁሉ ባለቤት ነኝ ማለት ነው። እነዚህ ጥበቦች ገበያ ላይ ውለው ቢያይ ኮራ ብሎ ይናገራል። አዲስ ኣበባ ከተማ ውስጥ የኦሮምኛ ቋንቋ ኣካዳሚዎች ቢያይ ደስ ይለዋል። ከገበያ ተከልተው በሌላ ባህል ተውጦ ሲያይ እኔ ጥበብ የለኝም ወይ የሚል የችሎታ ጥያቄ በነፍሱ ሊያነሳ ይችላል። ሙሉ ቀን ራሴን ኦሮሞ ኣድርጌ እዚህ የምኖርበት ኣገር ሆኘ ኣስቤ ኣውቃለሁ። በትክክል የባህላዊ ማንነት ጥያቄ ሊያነሳ ይገባዋል። ታዲያ ይህንን የባህል መዋጥ ጥያቄ የሚፈጥረውን ስሜት ከተረዳን ማስተካከያውም ኣይከብድም። ወደ ፖለቲካ መሮጥና ፖለቲካን ለኢኮኖሚና ለባህል ማጉያ መሳሪያ ኣድርጎ ማሰብ ሙስና ኣለበት። ፖለቲካን የሁሉ መፍትሄ ሰጪ ኣድርጎ ማሰቡ ትክክል ኣይደለም። ማህበራዊ ችግሮቻችንን ማህበራዊ በሆነ መንገድ መፍታት ይሻላል። የባህል ጥያቄ የሚመለሰው ባህላዊ ኣስተዳደርን በተጠናከረና በተደራጀ ሁኔታ ስናዋቅረው ነው። ይሄ ነው የሃገሪቱን የማንነት ጥያቄ የሚፈታው። የእኩነትን ጥያቄ የሚፈታው።

ይህን ለማደረግ ደግሞ ባህላዊ ኣስተዳደሩ በስርዓት መደራጀት ኣለበት። ኦሮሞ የገዳ ተወካዮቹን ይዞ፣ ኮንሶ ንጉሱን ይዞ ሌላው መሪውን የገደለውም እንዲሁ የማስመለስ ስራ ሰርቶ ወይም የቋንቋና የባህሉን ማህበረሰብ ተወካይ ሾሞ የባህል ኣርበኞች ቤት ማቋቋም ጥሩ ነው። ይህ የባህል ኣርበኞች ቤት ደግሞ በሆነ ኪዳን ሊያዝ ይገባዋል። ቡድኖች ባህላቸውን ለኢትዮጵያዊነት ሰውተው መልሰው የሚንከባከቡበትን ኪዳን ከገቡ የኢትዮጵያን ቡድኖች ባህል ሁሉ ሁልም ኢትዮጵያዊ ይደሰታል ደግሞም ይጠብቃል። እነዚህ ቡድኖች በኣንድ ሃገር ጥላ ስር ይኖራሉና ኣንድ ከፍ ያለ ኪዳን መጀመሪያ መግባት ኣለባቸው። ኪዳን ህገ መንግስት ሳይሆን ከዚያ በላይ የሚውል ከፍ ያለ ኪዳን ማለቴ ነው። የባህል ኣስተዳደሩ የራሱ ኣሰራር ኖሮት ባህልን እየጠበቀ፣ የእርቅና የሰላም ስራዎችን እየሰራ መኖር ይችላል። ባህል ኣስተዳዳሪ ሲኖረው የተዋጠው ባህል ከገባበት ኣዘቅት እንዲወጣ በማድረግ የእኩልነት ስሜትን በኣደባባይ ያሳያል። ሌላው ኣስተዳደር ደግሞ ፖለቲካዊ ሲሆን ቡድኖች ሁሉ በያሉበት ተወያይተው ለመስዋእት ተዘጋጅተው የሚፈጥሩት ማንነት ነው። ኢኮኖሚያቸውንና ፖለቲካዊ ህይወታቸውን ኣተኩሮ የሚሰራ ስርዓት ፈጥረው ይህ ስርዓት ህይወታቸውን ወደ ተሻለ ኣቅጣጫ ይመራል። ብሄርን፣ ዘውግን ተገን ኣድርጎ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማእከላዊ ሃይል ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት ሁሉ ሙስና ኣድርገው ኣውግዘው በህጋቸው ከልክለው ቢኖሩ ችግሮች ሁሉ በሂደት እየተፈቱ ይመጣሉ። ኣንድነት በጣም ኣይቀጥንም። ፕሮፈሰር መሳይ ባሉዋቸው ምልክቶች ላይ የሚቆም ሳይሆን በተደላደለ መሰረት ላይ የቆመ ብቻውን መቆም የሚችል ኣካል ያለው ማንነት መፍጠር ይችላሉ። ከፍ ሲል እንዳልኩት የኣንዳንድ ቡድን ኣባላት የቡድንን ስሜት በመጠቀም የኢኮኖሚና የማእከላዊ ስልጣን ፍላጎት ካለ ይህ ስሜት በራሱ ፍትሃዊ ኣለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ ያልሆነ ሙስና ነው። በአንጻሩ ባህላዊ ማንነትን መንከባከብና ማንነቴ ተጎዳብኝ ራሴ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ ኣይሸተኝም ማለት ግን ፍትሃዊ ጥያቄ ነው።

አንድ ሌላ ነገር ከግንዛቤ መግባት ያለበት ይመስላል። እንደ ኢትዮጵያ ባለ ብዙ ዘውግ ባለበት ኣገር ፖለቲካው ዘውጌኛ ሲሆን የዘውግ ኣባላት በተለይም በፖለቲካ የበላይነት ያለው የቡድኑ ኣባላት ሲበዛ ትጉ ይሆኑ ይሆናል። ሲበዛ ምስጢር ጠባቂዎች፣ ሲበዛ ጠርጣሮች፣ ሲበዛ ስጉዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ይህን ስነልቦና ከየት ኣመጡት? ብንል ቡድናዊ ህይወታቸው ኣንጻራዊ ፍክክር ውስጥ ገብቷል ብለው ስላመኑ ነው። አሁን የሚታየው ኣንጻራዊ የስሜት ጉልበታቸው ምን ኣልባትም ኣንድ ከቡድናቸው መሃል የበቀለ የሆነ ቡድን ማእከላዊ ስልጣኑን ይቆጣጠርና ከዚያ በሁዋላ የነብር ጅራት ጨብጫለሁና አግዙኝ ይላል። ከለቀቅኩት ሌላው ቡድን ይመጣና ስልጣን ላይ ሆኖ ወገኖቹን ሲጠቅም ነበር ብሎ ሁላችንን ስለሚፈጅ ኣያይዙኝ ብሎ በሚስጥር በቋንቋቸው ሹክ ይላል። ከፍ ሲል እንዳልነው የዘውግ ፖለቲካ ስሜታዊ በመሆኑ ቀላል የማይባል ደጋፊ ሊያገኝና ጅራት የመወጠሩን ስራ ሊያግዙ የሚነሱ ሰዎችን ሊያገኝ ይችላል። ጅራቱን የያዘው ዋና ቡድን ኤነርጂ ለመጨመር ሲል “የኔ” ያላቸውን ቡድን ኣባላት ከሌሎቹ እንዲጋጩ ያደርጋል። ፕሮፓጋንዳዎች እየነዛ በሚገባ ይጠቀምባቸዋል። አልፎ ኣልፎም ትንሽ ጣል የሚያደርግላቸውም ጥቅማጥቅም የውሎ አበል ይኖራል። ይህንን የዘውግ ፖለቲካ ስነልቡና ማጤንም ተገቢ ነው። የመስኩ ተመራማሪዎች እንደሚናገሩት በዘውግ ኣገዛዝ ጊዜ ወደ ስልጣን የመጣው ቡድን በቁጥሩ በጣም ኣነስተኛ ከሆነና ከጠቅላላው የሃገሪቱ ህዝብ ከሃያ በመቶ በታች ከሆነ ኣገዛዙ በጣም በጭካኔ ላይ ይመሰረታል ይላሉ። ኣሳማኝ ነው። ስጋት ስለሚኖርባቸው ኣንዴ የነብር ጅራት ጨብጠናልና ኣይነት ኑሮ ስለሚሆን ነው የሚጨክኑት። የሶርያን ጉዳይ ስናይ ኣሳድ ወደ 10 በመቶ ከሚሆነው አለዊትስ ብሄር ኣባላት የወጣ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የራሱን ክብ በመስራት ስልጣን ላይ ያለ ሰው ነው። ጭካኔውን አለም ያወቀው ነው። እዚህ ላይ ማብራራት ኣያስፈልግም።

እነዚህ ገዢውን ክፍል ለማኖር በትጋትና በከፍተኛ ምስጢር የሚያገለግሉ ዘውጎች ቢገነጠሉና ራሳቸውን ሜዳ ላይ ለብቻው ቢያገኙት ደግሞ ይህ ትጋት፣ ስጋትና፣ ምስጢረኛነት ይጠፋል። በስቴት ጉዳይ መከፋፈል ይመጣል:: ምን ኣልባትም ኣሁን ማይክሮ ልዮነት የሆኑ ልዩነቶች ተነስተው መከፋፈል ሊመጣ ይችላል።

በብሄር ፖለቲካ ጊዜ ስልጣን ላይ ያለው ዘውግ እንዲህ ሲተጋ ሌሎች ቡድኖች ተገቢውን ቦታና ጥቅም ኣላገኘንም ያሉ ደግሞ በወቅቱ ስልጣን ላይ ያለውን የራሳቸውን ቡድን ተወካይ ኣያምኑትም። ያፍሩበታል። ኣይተጉም። ችላ ይላሉ ማለት ነው። በዘውግ ላይ የሚቆም ፖለቲካ ትልቁ ችግር እንዲህ ቡድኖችን ሁሉ ግራ ማጋባቱና የመርህን ቆብ ማስጣሉ ነው። ከዘውግ ፖለቲካ መሃል ሞደሬሽን መጠበቅ ተላላነት ነው። ኣገርን የሚያህል ግዙፍ ጉዳይ በእንዲህ ዓይነት ጨዋታ ውስጥ መክተት ኣደጋ ይኖረዋል። ለዚህ ነው በባህላዊ ወገንተኛነት ላይ መሰረቱን የጣለ ፖለቲካ እርስ በርስ ከማናቆር ይልቅ ወደ ልማትና ዘመናዊ ኣስተሳሰብ ኣይመራንም የሚያሰኘን ለዚህም ነው። ባህላዊ ፖለቲካ እንኳን በብዙህ ሃገር ይቅርና ለሆሞጂኒየስ ኣገሮችም ኣይጠቅምም። ሆሞጂኒየስ የሆኑ ኣገሮችም ቢሆኑ ፖለቲካቸውን ማራገብ ያለባቸው በሃይማኖታቸው ወይ በባህላቸው ሳይሆን በመርህ በዴሞክራሲ ዙሪያ ቢሆን ነው የተሻለ ስብእና ያለው ዜጋ ማፍራት የሚችሉት። ባህልንና ቋንቋን ከሚገባው በላይ ማረገብና የፖለቲካ ዋና መሰረት ማድረግ ሆሞጂኒየስ የሆኑ ኣገሮችን ምን ኣልባትም ከውጭ ሃገር ዜጎች ጋር የመኖር ክህሎታቸውን ሊጎዳ ብሎም ዚኖፎቢያም ሊያመጣ ይችላል። ቶለራንስ የምንለውን ሊጎዳባቸው ይችላል። መልቲ ካልቸራሊዝምን ይጎዳል። ስለዚህ የማንነት ፖለቲካ ለሆሞጂኒየስ ሃገራትም እንኳን ኣይመከርም።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት ኢትዮጵያን ዘላለማዊ ለማድረግ የዘውግ ፖለቲካ ፈጽሞ አይጠቅመንም። በዘውግ ፖለቲካና በብሄራዊ ፖለቲካ መካከል ደግሞ መሃል መንገድ የለም። ምን አልባት ፖለቲካችንን ከዘውግ ነጥቀን ካወጣን በሁዋላ ፌደራሊዝሙ በቋንቋ ኮሙዩኒቲ ይዘርጋ የሚል ኣሳብ ይመጣ ይሆናል። ይሄኛው ቢያንስ ትንሽ ይሻላል። ይሁን እንጂ አገሪቱ ከዚህም የተሻለ የፌደራል ስርዓት መዘርጋት ትችላለች። ከፍ ሲል እንዳልኩት ኢትዮጵያ ዘውጎችን የሚንከባከብ አንድ ባህላዊ ኣስተዳደር የሚያሻት ሲሆን ይህ ኣስተዳደር የራሱ የሆኑ ፌደሬሽኖችን ሊመሰርት ይችላል። ይህ ፌደሬሽን በመሬት ላይ የማይነበብ ፌደሬሽን ቢሆንና በሌላ በኩል ለኢኮኖሚ እድገትና ለአሰራር ኣመቺነት ያለው ሳይንሳዊ የፌደራል ስርዓት ቢፈጠር ኣገሪቱ ንጹህ ዴሞክራሲን እየተደሰተች በሌላ ብኩል ባህሏን እየተደሰተች መኖር ትችላለች። ፕሮፌሰር መሳይ እንዳሉት ምርጫዋን ደግሞ ፕሬዚደንታዊ ብታደርገው እጅግ ጥሩ ይሆናል። ከዚህ በፊት ከዘውግ ፖለቲካ ጋር በተያያዘ የመጣውን ክፍተት በመዝጋትና ኣንድነትን በማሳደግ በኩል ጉልህ ሚና ይኖረዋል። ይህ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ግን በዘውግ ፖለቲካ ስር ሳይሆን ፖለቲካው ከዘውግ ወጥቶ በንጹህ ኣይዲዮሎጂ ላይ ተመስርቶ ቢሆን ነው የሚሻለን።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት ኢትዮጵያን ዘላለማዊ ለማድረግ የዘውግ ፖለቲካ ፈጽሞ አይጠቅመንም። በዘውግ ፖለቲካና በብሄራዊ ፖለቲካ መካከል ደግሞ መሃል መንገድ የለም። ምን አልባት ፖለቲካችንን ከዘውግ ነጥቀን ካወጣን በሁዋላ ፌደራሊዝሙ በቋንቋ ኮሙዩኒቲ ይዘርጋ የሚል ኣሳብ ይመጣ ይሆናል። ይሄኛው ቢያንስ ይሻላል። ይሁን እንጂ አገሪቱ ከዚህም የተሻለ የፌደራል ስርዓት መዘርጋት ትችላለች። ከፍ ሲል እንዳልኩት ኢትዮጵያ ዘውጎችን የሚንከባከብ አንድ ባህላዊ ኣስተዳደር የሚያሻት ሲሆን ይህ ኣስተዳደር የራሱ የሆኑ ፌደሬሽኖችን ሊመሰርት ይችላል። ፕሮፌሰር መሳይ እንዳሉት ምርጫዋን ደግሞ ፕሬዚደንታዊ ብታደርገው እጅግ ጥሩ ይሆናል። ከዚህ በፊት ከዘውግ ፖለቲካ ጋር በተያያዘ የመጣውን ክፍተት በመዝጋትና ኣንድነትን በማሳደግ በኩል ጉልህ ሚና ይኖረዋል። ይህ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ግን በዘውግ ፖለቲካ ስር ሳይሆን ፖለቲካው ከዘውግ ወጥቶ በንጹህ ኣይዲዮሎጂ ላይ ተመስርቶ ቢሆን ነው የሚሻለን። እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ።

አስተያየት ካለ ኣድራሻየ እነሆ
geletawzeleke@gmail.com

ማኅበረ ቅዱሳንና አራቱ ፈታኞች –በተክሉ አባተ (ዶ/ር)

$
0
0

mahebere kidusan
ማኅበረ ቅዱሳንን በሚገባ ያወቅሁት የዛሬ 20 ዓመት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ግቢ የመጀመሪያ ድግሪ ተማሪ እያለሁ ነው። ማኅበሩ ገና በእግሩ ለመቆም ጥረት በሚያደርግበት ወቅት። ማኅበረ ቅዱሳን (ከዚህ በኋላ ለማሳጠር ያህል ማቅ ወይም ማኅበሩ እያልኩ እጽፋለሁ) ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ በዩኒቨርስቲው ዋና ግቢ ያሉትን ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ በሚገኘው ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ባቋቋሙት ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ጋበዘ። ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ በሰንበት ትምህርት ቤት ተሳታፊ ስለነበርኩና የዕውቀትም ጥማት ስለነበረብኝ የማኅበሩን ግብዣ በታላቅ ደስታ ተቀበልኩት።

Read Full Story in PDF

የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0

ርዕሰ ዜና

·         የእስራኤል መንግስት ተጨማሪ ቤተእስራኤሎች ወደ እስራኤል እንዲገቡ ፈቀደ

·         በጂቡቲ ምርጫ እየተካሄደ ነው

·         በሊቢያ የአሲስ አባላት ቁጥር እየጨመረ መጣ ተባለ

·         የሴየራ ሊዮን ፕሬዚዳንት የውጭ ባለሀብቶችን ተማጸኑ

·         ሞሮኮ የውጭ ዜጎች ከሀገሯ አባረረች

መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም.

Ø ተጨማሪ የቤት እስራዔሎች ቤተሰቦች በዚህ አመት ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ሊመጡ ስለሚችሉበት ሁኔታ የእስራዔል ገዥ ፓርቲ ከአጋሮቹ ጋር ስምምነት የደረሰ መሆኑን ሐሙስ መጋቢት 29 ቀን ማምሻውን በሰጠው መግለጫ ገልጿል። በዚህ 1300 የሚሆኑት እንዲመጡ የተፈቀደ ሲሆን ወደፊት ቁጥሩ  ከዚህ በላይ ሊጨምር የሚችል መሆኑን ተገልጿል። ባለፈው ወር በእስራዔል አገር የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘመዶቻቸው ወደ እስራኤል እንዲመጡ በመጠየቅ ከፍተኛ ትዕየንተ ሕዝብ ማካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን የእስራዔል መንግስት ነገሩን ችላ በማለት ኢትዮጵያውያኑን  የፈቃዱን ውሳኔ ሲያስተላልፍ መቆየቱ ይታወሳል። ባለፉት ጥቂት ቀናት አንዳንድ የፓርላማ አባላት ባደረጉ ጥረትና እንዲሁም ተቃውሞውና አድማው የጋራ መንግስቱን ህልውና አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል መሆኑ ስለገባው  ገዥው ፓርቲ ሀሳቡን ቀይሮ ቤተእስራኤሎቹ ወደ እእስራኤል እንዲመጡ ፈቅዷል።

File Photo

File Photo

 

Ø በጂቡቲ ዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2008 ዓም  ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን የጂቡቲው ፕሬዚዳንት አሸናፊ ሆነው እንድሚቀርቡ አስቀድሞ ታውቋል። ስድስት ተወዳዳሪዎች ለምርጫው ቢቀርቡም ላለፉት 17 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዚዳንት አሸናፊ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም በማለት ታዛቢዎች ይተቻሉ። ከተቃዋሚዎች ውስጥ የተወሰኑት በምርጫው ላለመሳተፍ የወሰኑ ሲሆን ተወዳዳሪ ሆነው የቀረቡት ደግሞ የፖሊሶች አፈና መጠናከሩንና የመገናኚያ ብዙሃን አድላዊነትን በመግለጽ ክስ እያሰሙ ይገኛሉ። ድምጹን የሚሰጠው  የጂቡቲ ሕዝብ ቁጥር አነስተኛ ነው የተባለ ሲሆን ፕሬዚዳንት ጉሌህ ከየመን የመጡ ስደተኞችን አስመዝገበው ድምጽ እንዲሰጡ እያደረጉ ነው ተብሏል። የተቃዋሚዎች መከፋፈል ጉሌህን ሊጠቅም ችሏል የሚሉ አልጠፉም። ከሶስት አመት በፊት የጉሌህ ተቃዋሚ የሆኑ ፓርቲዎች ትብብር ቢፈጥሩም ጉሌህ ተወዳድሮ ሊያሸንፍ የሚችል አንድ የጋራ ተወዳዳሪ ማውጣት ላይ ሊስማሙ አልቻሉም።  የምዕራብ አገሮች ጂቡቲ ውስጥ ባላቸው ጥቅም ምክንያት ስለምርጫው አስተያየት ሲሰጡ አይሰማም።

 

 

Ø በሊቢያ የአይሲስ አባላት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋም አዛዥ ተናገሩ። አዛዡ ላለፉት 12 እስከ 18 ወራት ባሉት ጊዚያት ወደሊቢያ የገቡት የአይሲስ አባላት ቁጥር ከ4 ሺ ወደ 6 ሺ ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸው አሸባሪዎቹ በብዛት ሊገቡ የቻሉት በአገሪቷ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ እና የጸጥታ አለመረጋጋት ተጠቅመው ነው ብለዋል። አብዛኞቹ ከውጭ የመጡ በመሆናቸውና አገር በቀል የሆኑ አባሎች አነሰተኛ በመሆናቸው እንደ ኢራክና እንደ ሶሪያ የተወሰነ ክልል ይዘው ለመቆጣጠር አይችሉም የሚል አስተያያት አዛዡ ጨምረው ገልጸዋል። በሊቢያ የሚገኙት ልዩ ልዩ የሚሊሺያ ቡድኖች በየቦታው ከአይሲስ ኃይሎች ጋር እየተጋጩ ስለሆነ በራሳቸው የሚጠናከሩበት ሁኔታ አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ።

 

Ø የሴየራ ሊዮን ፕሬዚዳንት በአገራቸው የኢቦላ በሽታ የታደከመ መሆኑን ገልጸው የአገሪቷ ኢኮኖሚ ከወደቀበት ቦታ እንዲያንሰራራ ለማደረግ የውጭ አገር መዋእለ ንዋይ እንደሚያስፈልግ ተናገሩ። ከምዕራብ አፍሪካ አገሮች 11 ሺ ዜጎችን የገደለው የኢቦላ በሽታ የሲየራ ሊዮንን ኢኮኖሚ በተለይም የእርሻውን መስክ ክፉኛ ያጠቃው በመሆኑ የውጭ አገር ሀብታሞች ገንዘባቸውን በልዩ ልዩ የስራ መስክ ላይ በማዋል ኢኮኖሚው እንዲያንሰራራ እንዲያደርጉ ተማጽነዋል። ፕሬዚዳንቱ በቅርቡ ቱርክ ውስጥ  በሚደረገው የእስላማውያን አገሮች አመታዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ተመሳሳይ ልመና የሚያቀርቡ መሆናችውን ገልጸዋል። 

 

Ø የሞሮኮ መንግስት 8 የውጭ አገር ዜጎችን ከአገሩ ያባረረ መሆኑን ገለጸ። ተባረሩ የተባሉት ግለሰቦች ሁለት የፈረንሳይ አንድ የቤልጂክ እና አምስት የስፔይን ዜጎች ሲሆኑ ለመባረራቸው ምክንያት የሆነው በእስር ላይ ለሚገኙት የምዕራብ ሳህራ ዜጎች እርዳታና ትብብር አድርገዋል የሚል ነው። ከስድስት ዓመት በፊት ግድም ኢዚክ (Gdem Izik) በሚባለው በምዕራብ ሳህራ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የተቀጣጠለው ዓመጽ  ከሞሮኮ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት 11 ፖሊሶችና ሁለት ሰላማዊ ሰዎች መገደላችው አይዘነጋም። ፖሊስ  አመጹን ለማስቆም  ካምፑ እንዲፈርስ ያደረገ ሲሆን በርካታ ሰዎችን ወስዶ ማስሩ ይታወቃል። ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው ድርጅት ባለፈው ህዳር ወር ተይዘው የሚገኙት የምዕራብ ሳህራ ዜጎች እንዲፈቱ መጠየቁ ይታወሳል።

 

 

Ø በዳርፉር አካባቢ የሽብር ተግባር ፈጽመዋል በሚል ክስ አንድ የሱዳን ፍርድ ቤት በ22 የደቡብ ሱዳን ዜጎች ላይ የሞት እና የእድሜ ልክ እስራት ቅጣት የበየነ መሆኑ ተገልጿል። ክስ የቀረበባቸው 22 ሰዎች ጀስቲስ ኤንድ ኢኩዋሊቲ ሙቭመንት የሚባለው የዳርፉ አማጽያን ቡድን አባላት ሲሆኑ ድርጅቱ ከሶስት አመት በፊት ከሱዳን መንግስት ጋር የእርቅ ስምምነት ፈርሞ የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ማቆሙ ይታወቃል። ባለፈው ጥር ወር 22 የደቡብ ሱዳን ዜጎች የአማጽያኑ ድርጅት አባል ሆነው መንቀሳቀሳቸው በመጋለጡ የውጭ አገር ዜጎች በመሆናችው ብቻ በቁጥጥር ስር ውለው ለፍርድ እንዲቀርቡ ተደርጓል። ባሁኑ ጊዜ በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን መካከል ያለው ግንኙነት ከምንጊዜውም በላይ ዝቅተኛ ሆኖ የሚታይበት ሲሆን በሰዎቹ ላይ የተበየነው የፍርድ ውሳኔ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ይበልጥ ሊያሻክረው እንደሚችል ተገምቷል። የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት በፕሬዚዳንት በሽር ላይ የወንጀለኛነት ክስ ለመመስረት ምክንያት በሆነው በዳርፉር ጦርነት 300 ሺ ሰው ያህል ህይወቱ ሲጠፋ ከ2.5 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎ ስደተኛ መሆኑ ይታወቃል።

 

 

 

መጋቢት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.

Ø በሱሉልታ ከተማ በወያኔ ወታደሮችና በከተማዋ ወጣቶች መካከል ፍጥጫና ውጥረት መፈጠሩ ታወቀ። ፍትጫው የተነሳው በሱልልታ ከተማ የሚገኝ አንድ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር መፈንዳቱን ተከትሎ የወያኔ ፖሊሶችና ጦር የከተማዋን ጥበቃ በማጠናከራቸው ሲሆን ወጣቶቹ ተቃውሞ በማሰማታቸው የወያኔ ፖሊስና ጦር ስትተኩስ ለመበተን የሞከሩ ሲሆን ከፍተኛ የዱላ ድብደባም መፈጸማቸው ታውቋል። የወጣቶቹ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በሚደግበት ወቅት የወያኔ የንግድ ሸሪክ የሆነው የመሀመድ አላሙዲን ንብረት የሆኑ 3 መኪኖች ሲያልፉ በድንጋይ ተደብድበዋል።

 

Ø በሐረር ዓለማያ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች መኝታ ቤት ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ስለደረሰበት ተማሪዎች ትምሀርት አቋርጠው ወደ ቤተ ሰቦቻቸው ለመሄድ የተገደዱ መሆናቸው ከዓለማያ የመጣው መረጃ ያመለክታል። የእሳቱ አደጋ እንዴት እንደተቀሰቀሰና ለምን ሳይጠፋ ረጅም ሰዓት እንደቆየ የታወቀ ነገር ባይኖርም የዓለማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ግን የወያኔ ደህንነት ኃይሎች የተማሪዎቹን መኝታ ክፍሎች ሆን ብለው በማቃጠል ያነጣጠሩባቸው ተማሪዎችንን መምህራንን በሽብረተኛነት ለመክሰስ በማሰብ ነው በማለት ይናገራሉ።

 

 

Ø ከ10 አመት በፊት በጋምቤላ ከ400 በላይ አኙዋኮች ግድያን ተከትሎ ከወያኔ ጋር ሆድና ጀርባ በመሆን ከሀገር ወጥቶ በኖርዌይ በጥገኝነት ይኖር የነበረው ኦኬሎ አኳይ በወያኔው ፖለቲካ ፍርድ ቤት በሽብረተኛነት ጥፋተኛ ተብሎ የተፈረደበት ሲሆን ከሶስት ሳምንት በኋላ የቅጣቱ ብይን እንደሚሰጠው ተገልጿል። ኦኬሎ አኳይ በአኝዋኮች ፍጅት ወቅት የጋምቤላ ፕሬዚዳንት የነበረ ሲሆን በጋምቤላ የአኙዋኮችንና የኑዌር ግጭትን ወያኔዎች እንደቀሰቀሱት እና የአኙዋኮቹ ፍጅት በወቅቱ የወያኔ መሪ በነበረው በመለሰ ዜናዊ ትዕዛዝ እንደተፈጸመ ቀደም ሲል አስታውቆ የነበረ ሲሆን አሁንም በወያኔው የፖሊቲካ ፍርድ ቤት ደግሞታል። የወያኔ ወታደሮች 400 አኙዋኮችን ገድለው 60 ብቻ ነው የሞቱት የሚል ማስተባበያ ኦኬሎ እንዲሰጥ አስገድደውት እንደነበርና አዲሱ ለገሰ በረከት ስምኦንና ገብረአብ ባርናባስ የወያኔው ትዕዛዝ በማስፈጸም እጃቸው እንዳለበት ገልጿል። አኮሌ አኳይ ከዓመታት በፊት ወደ ደቡብ ሱዳን በሄደበት ወቅት የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣኖች ከወያኔ ደህንነት ጋር በመሳጠር ከጁባ ጠልፈውት ወደ አዲስ አበባ እንደመለሱትና በሽብረተኛነት ክስ እንደመሰረቱበት ይታወሳል።

 

Ø በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነትና ስልጣን ተቀምጠው እጅግ አስነዋሪ ተግባር ሲፈጽሙ የተገኙ የወያኔ ካባ ለባሽ ካድሬዎች ከስልጣናቸው መባረር መጀመራቸውና ዋና ጠባቂው አቡነ ማትያስም ምንም ማድረግ ባለመቻላቸው ለማባረር መገደዳቸው ታውቋል። የአቡነ ማትያስ ቀኝ እጅ የነበረውና የአዲስ አበባ ሀገር ስብከት ስራ አሲያጅ የነበረው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከየቤተክርስቲያኑና ገዳማቱ ያለውን ንብረት መዝረፉ ብቻ ሳይሆን ለልጁ መታከሚያ በሚል ሰበብ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከቤተ ክርስቲያኗ ካዝና በመሰብሰቡ ከስልጣኑ የተባረረ ሲሆን በእርሱ ምትክ ሌላው ካባ ለባሽ ካድሬ ጎይቶም ያይኔ ተተክቷል። ከየማነ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ኃላፊዎችም ተባረዋል። የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ያሉ ማንኛውም ከፍተኛ ኃላፊነትና ስልጣን በትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዲያዝ ባወጣው መመሪያ መሠርት በመንፈሳዊና ሐዋርያዊ ስራ በምትሰራው ቤት ክርስቲያን ውስጥ የዘር መድልዎን በማምጣት ቤተ ክርስትያኗን እያመሳት መሆኑ ምዕመናኑን ካህናቱ በጀመሩት ግፊት ካባ ለባሽ ካድሬዎች ቢነሱም ሌላ ዘረኛ ካባ ለባሽ መተካት ውጤት ስለሌለው ቤተ ክርስቲያኗን ከዘረኛ ካድሬ ቄስና መነኩሴ ማጽዳት የዛሬ ሰራ ነው የሚሉ ምዕመናን ብዙ ናቸው።  

 

 

Ø በአስመራ ከተማ በግድ ታፍሰው በካሚዮን ተጭነው ወደ ጦር ማሰልጠኛ ሲወሰዱ የነበሩ ወጣቶች ከተሳፈሩባቸው መኪናዎች ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ በሻዕቢያ ወታደሮች በጥይት የተገደሉ መሆናቸው ታውቋል። የተገደሉትና እና ምን ያህል እንደሆኑ ለጊዜው ባይታወቅም ቁጥራቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል። በተጨማሪም  ካሚዮኖቹ የሚሄዱበትን መንገዶ በአውቶቡስ አማካይነት  ለመዝጋት ሙከራ ያደረጉ የወጣቶቹ ዘመዶችና ጓደኞች በሙሉ በጥይት የተገደሉ መሆናቸው ተነግሯል። የሻዕቢያ መንግስት እስካሁን በጉዳዩ የሰጠው መግለጫ የለም። በሻዕቢያ ውስጥ የወታደራዊ አገልግሎት የጊዜ ወሰን የሌለው መሆኑ ሲታወቅ አብዛኛዎቹ እድሜ ልካቸውን ሲያገለግሉ የሚቆዩ መሆናቸውና  የኑሮው ሁኔታቸውም በጣም አሰቃቂ እንደሆነ ይነገራል። ይህ አሰቃቂ የኑሮ ሁኔታና የሻዕቢያን አፈና ለማምለጥ በርካታ ወጣቶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገሮች እና ወደ አውሮፓ መሰደዳቸው በየጊዜው የተገለጸ መሆኑ ሲታወቅ የሻዕቢያ አገዛዝ ከፍተኛ አፈናና ጭፍጨፋ ከሚያካሄዱ የአለም አገሮች ውስጥ ዋነኛው ነው በማለት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ድምጻቸው በተደጋጋሚ ሲያሰሙ ቆይተዋል።

 

Ø በሊቢያ በፌስ ቡክ እና በሌሎች የማህበረሰባዊ መገናናዎች አማካይነት በድብቅ የሚካሄድ የመሳሪያ ገበያ በከፍተኛ ደረጃ እየደራ መምጣቱን ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 29 ቀን ይሰራጫል የተባለ አንድ ጥናታዊ ዘገባ አመለከተ። ለአርባ ዓመት ሊቢያን ሲገዛ የቆየው የኮሎኔል ጋዳፊ አገዛዝ በየጊዜው ያከማቸው መሳሪያ አገዛዙ ሲወድቅ በተለያዩ አማጽያን እጅ የገባው መሳሪያ ዛሬ በጥቁር ገበያ በሰፊው እየተሸጠ መሆኑን ጥናቱ ይዘረዝራል። በፌስ ቡክ፣ በኢንስታግራም፣ በዋትስ አፕ፣ እና በቴሌግራም አማካይነት በብዛት እየተሸጡ ያሉት መሳሪያዎች እንደሽጉጥና ካላሽንኮቭ የመሳሰሉት የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ሲሆኑ ለሽብርተኞች መገልገያ የሆኑ በትከሻ ላይ ሆነው የሚተኩሱ ጸረ አውሮፕላንና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎችም የሚሸጡ መሆናቸውም ተጠቁሟል። አንድ ካላሽንኮፍ መሳሪያ እስከ 1800 ዶላር ሲያወጣ በተለይ የመጓጓዣ አውሮፕላንን ሊመታ የሚችል ጸረ አውሮፕላን መሳሪያ ደግሞ እስከ 62 ሺ የአሜሪካን ዶላር እንደሚሸጥ ዘገባው ይገልጻል። የመሳሪያ ሽያጮቹ የሚከናውኑት በአብዛኛው እንደ ትሪፖሊ፣ ቤንጋዚ እና ሳብራታ በመሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች ሲሆን ንግዱ የሚካሄደው ወጣቶች በሆኑ የተለያዩ የሚሊሺያ አባላት መካከል መሆኑም ተድርሶበታል።  የፌስ ቡክ ቃል አቀባይ በሰጠው መግለጫ ይህን የመሰለ ንግድ በፌስ ቡክ አማካይነት መካሄዱ ወንጀል ገልጾ መረጃውን እየፌስ ቡክ አገግሎቱን እንዘጋዋለን ብሏል። የአውሮፓ ባለስልጣናትም ጉዳዩ ያሳሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፤

    በተያያዘ ዜና ትሪፖሊን መሰረት አድርጎ ሲንቀሳቀስ  የነበረው የመንግስት አካል በትናንተናው ዕለት ደም መፋሰስን ለማስወገድ ከስልጣን ወርጃለሁ የሚል መግለጫ በፍርድ ሚኒስቴሩ አማካይነት መስጠቱ የሚታወስ ሲሆን የዚሁ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ሚስተር ካሊፋ ገውሊ  ደግሞ በድረ ገጻቸው ላይ ባወጡት መግለጫ ቀደም ብሎ የወጣውን መግለጫ መቃወማችውን ገልጸዋል። መግለጫ  ማንም ሚኒስቴር ሆነ ሌላ ኃላፊነት የተሰጠው ግለስብ በተመድ ከተሰየመው የአንድነት መንግስት ጋር እንዳይተባበር የሚያሳስብ ሲሆን ተባባሪ ሆኖ ከተገኘ ከፍተኛ እርምጃ እንደሚወሰድበት ይገልጻል። ሚስተር ካሊፋ ገውሊ በተመድ የተቋቋመውን የአንድነት መንግስት በጽኑ ከሚቃወሙ ግለሰቦች መካከል አንዱ መሆናችው የሚታወቅ ሲሆን መግለጫቸው በሌሎች ዘንድ ምን ያህል ተቀባይነት እንዳለው ለጊዜው ለማወቅ አልተቻለም። በአሁኑ ወቅት ሚስተር ካሊፋ ይህንን እርምጃ እንዲወስዱ የገፋፋቸው ምክንያቶች ለጊዜው ግልጽ ባይሆኑም በቡድኑ ውስጥ ከፍተኛ ክፍፍል መኖሩን ያሳያል በማለት ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ይገልጻሉ።

Ø የሱዳኑ ፕሬዚዳንት አልበሽር ለቢቢሲ ጋዘጠኛ በሰጡት ቃለ ምልልስ የአሁኑ የስልጣን ዘመናቸው በ2013 ዓም ሲያልቅ ስልጣናቸውን የሚያስረክቡ መሆናቸውን ገልጸዋል። ግለሰቡ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ስልጣን የሚለቁ መሆናቸውን በመግለጽ የገቡትን ቃል በተደጋጋሚ ሲያጥፉ የነበሩ በመሆናቸው እለቃለሁ ብለው መናገራቸው የተለመደው ማጭበርበር ነው  የሚሉ በርካታ ናቸው። ፕሬዚዳንቱ በቃለ ምልልስ ወቅት በዳርፉር ከ10 ሺ በላይ ዜጎች ቤታቸው ጥለው ተሰደዋል፤ 2.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ በካምፕ ውስጥ ይኖራሉ  በሚል ተመድ ያሰራጨው መረጃ የተጋነነ ነው ከማለታቸውም በላይ የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች በዳርፉር የሚቆዩበት ምንም ምክንያት ስለሌለ ባስቸኳይ መውጣት አለባቸው ብለዋል። የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለፖሊቲካ ማራመጃ ተብሎ የተቋቋመ መሆኑን በመግለጽ በአገራቸው ሕዝብ ተወዳጅነት ስላላቸው የተመሰረተባችውን ክስ እንደማይቀበሉት በቃለ ምልልሱ ገልጸዋል።

 

  • በተያያዘ ዜና ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ከሳልቫ ኪር ጋር ከጥቂት ወራት በፊት እርቅ የተፈራረሙት ሪክ ማቻር በሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓም ጁባ የሚገቡ መሆናቸውንና በዚያም ከሳልቫ ኬር ጋር በመሆን የአንድነነቱን የሽግግር መንግስት እንደሚያቋቁሙ ገልጸዋል። ባሁኑ ጊዜ በአንዳንድ ቦታዎች የሚደረጉት ጦርነቶች ሙሉ በሙሉ ያልቆሙ በመሆናቸው ስምምነት የተደረገበት የአንድነት መንግስት ስራ አለመጀመሩ ብዙዎችን ሲያሳስብ ቆይቷል። በሌላ በኩል በደቡብ ሱዳን  መድኃኒት እና ሌሎች የህክምና አገልግሎት መሳሪያዎች ከፍተኛ እጥረት በመፈጠሩ ርዳታ ፈላጊዎችን ለመርዳት አዳጋች እየሆነ መምጣቱን ድንበር የለሽ ሃኪሞች የተባለው ድርጅት ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 29 ቀን 2008 ዓም በሰጠው መግለጫ ገልጿል። መግለጫው የእርዳታ ድርጅቶችና ሌሎች የአለም አቀፍ ተቋሞች ይህን ከፍተኛ የሆነ እጥረት ለማሟላት ባለመቻላቸው የብዙ ሰዎች ህይወት አደገኛ ሁኔታ ላይ ሊወድቅ ችሏል ብሏል።  የአለም የምግብ ፕሮግራም እና የዓለም አቀፉ የእርሻ እና የምግብ ድርጅት ማክሰኞ መጋቢት 27 በሰጡት መግለጫ በደቡብ ሱዳን የእርዳታ እህል እጥረት በመኖሩ ከፍተኛ ረሃብ እየተከሰተ መሆኑን የገለጹ መሆናቸው ይታወሳል።

ነጻነት

$
0
0

finote nestanet

 ጣሰው አሰፋ

ባለፈው “በሪሞት ኮንትሮል ትግል ማካሄድ …”  በሚል በጫጫርኩት መደምደሚያ ላይ ስለነጸነት ጉዳይ ያለችኝን ይዤ እመለሳለሁ ብየ ነበርና ተመልሻለሁ። ከዚያ ቀደም ብዬ ግን ከርዕሱ ጋር ያልተያያዘ አንድ ዳሰስ ላደርገው የፈለግሁት ድንገተኛ ስላጋጠመኝ ጣልቃ አስገብቼዋለሁ። ጉዳይ “ሐገራዊ እርቅ” የሚሉት  ነገር ነው። ይህ ጥያቄ በድርጅቶችም በግለሰቦችም እየተነሳ ይገኛል። በቅርቡም ዶ/ር አክሎግ ቢራራ “አገርን እንደ እናት ያለመቀበል አደጋ እና ብሔራዊ መግባባት አስፈላጊነት” በሚል ባቀረቡት 6 ገጽ ጽሁፍ ውስጥ በመደምደሚያው ላይ ይህንኑ የአገራዊ ዕርቅ ጥያቄ እንደሚከተለው አስቀምጠውታል፡

Dr Aklog Birara“ምን መፍትሄ አለ? ይሔን ጽሁፍ ለማጠቃለል፤ አፓርታይዷ ደቡብ አፍሪካ በዘር ጥላቻ የተመረዘች አገር ነበረች። የጥቁሩን ሕዝብ በጭካኔ ትጨፈጭፍ፤ ታስር፤ ታጉርና ታሳድድ ነበር። ለብዙ አስርት ዓመታት የደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚ፤ ለጥቂት ነጮች አይተውት የማያውቁት ገቢና የድሎት ኑሮ ከማመቻቸቱ ባሻገር ለማምረት፤ ለብዙሃኑ የጥቁር ሕዝብ የስራ እድል ለመፍጠር ያልቻለበት ዋና ምክንያት የስርዓቱ ትኩረት ሕዝብን አፍኖና ቀጥቅጦ በመግዛት ላይ ስለሆነ ነው። በጥቂት ነጮች የበላይነት ይተዳደር የነበረው ስርዓት ለስለላ፤ ለአፈናና ሌላ የሚያወጣው ኃብት ብዙ ፋብሪካዎች ሊያሰራና የስራ እድል ሊፈጥር  ይችል ነበር። ኔልሰን ማንዴላ አፈናውና ግድያው የማያዋጣ መሆኑን ካሳሰቡ በኋላ አማራጭ አቅርበው የስርዓት ለውጥ አምጥተው ነበር። ይኼም አማራጭ ሁሉን አቀፍ የሆነ ዲሞክራሳዊ መንግሥት እንዲቋቋም ማድረግ ነበር። አስተዋይ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ መሪዎችና አባቶች፤ በተለይ ማንዴላና ዴስሞንድ ቱቱ ለሃገራቸውና ለሕዝባቸው በመቆርቆር ስርዓቱ ከስሩ መለወጥና እንደገና መመስረት አለበት የሚል መርህ ተከተሉ። ብሄራዊ መግባባት፤ እርቅና ሰላም እንዲካሄድ አድርገው የሰላም መሰረት ጣሉ። ዛሬ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ገዢውን ፓርቲ፤ ሁሉንም የፖለቲካና የማህበረሰብ ስብስቦችና ተቋሞች፤ መንፈሳዊ መሪዎችና አባቶች፤ እውቅና ያላቸው ግለሰቦች የሚያካትት የብሄራዊ መግባባት፤ ውይይት፤ የፖለቲካ ድርድር፤ እርቅና ሰላም ጉባኤና ስብሰባ ማካሄድ  ነው።” (ስርዝ የኔ)

 

የደቡብ አፍሪካ  አፓርታይድ ስርዓት በሰው ልጆች ላይ ባደረሰው በደልና በሕዝብ መካከል ያሳደረውን ቂምና በቀል ቀርፎ  የሕዝብን አንድነት በማረጋገጥ፤ የደቡብ አፍሪካን ህዝብ ለሰላምና መረጋጋት፤ የተጠናከረ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመመስረት የወሰደው የሃገራዊ ዕርቅ መፍትሄ  የወያኔው የአፓርታይድ ስርዓትም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያደረሰውን በደልና በሕዝብ መካከል ባለፉት 25 ዓመታት  የዘራውን ቂም በቀል አሽሮ ወደተረጋጋችና የህዝብ አንድነት ብሎም ፍቅር የሰፈነባት ዴሞክራቲክ ኢትዮጵያን ለመመስረት፤ ለተመሳሳይ በሽታ ተመሳሳይ መድሃኒት – የደቡብ አፍሪካው አፓርታይድ በሽታ የተፈወሰበት ለወያኔው አፓረታይድ በሽታ መፈወሻ –  ይሆናል ብለው ዶ/ር አክሎግ ያመላከቱት አቅጣጫ የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የተቃኘ ስለሆነ፤  ጥበብ የተሞላበት አካሄድ ነው። ጎሽ የሚያሰኝ ነው።

 

ከዚያ በተረፈ ግን፤ ዶ/ር አክሎግ ያላነሱት ሃቅ የደቡብ አፍሪካ  የእርቅ ኮሚሺን መቼ እንደተቋቋመና ማንስ እንዳ ቋቋመው ግንዛቤ ውስጥ ሳያስገቡ በደፈናው ኢትዮጵያ ውስጥ ሃገራዊ እርቅ አሁን አስፈላጊ ነው ለሚለው ሃሳባቸው መደገፊያ አድርጎ ማቅረቡ ፋይዳ የሚኖረው አይመስለኝም።

 

Aklog Biraraዶ/ር አክሎግ “ዛሬ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ገዢውን ፓርቲ፤ ሁሉንም የፖለቲካና የማህበረሰብ ስብስቦችና ተቋሞች፤ መንፈሳዊ መሪዎችና አባቶች፤ እውቅና ያላቸው ግለሰቦች የሚያካትት የብሄራዊ መግባባት፤ ውይይት፤ የፖለቲካ ድርድር፤ እርቅና ሰላም ጉባኤና ስብሰባ ማካሄድ  ነው።” ሲሉን፤ በጎ አሳቢነታቸውን ባልጠራጠርም፤ የደረደሯቸው የተሳታፊ አካላት ስብጥርና የሚሳተፉባቸው የጉዳይ ዓይነቶች፤ ከደቡብ አፍሪካው የዕርቅ ኮሚሽን ተግባር ጋር በምንም፤ በምንም የሚያገኛኘው ነገር የለም። ነገሩ ፍየል ወደዚህ ቅዝምዝም ወደዚያ ይመስላል።

 

የደቡብ አፍሪካ የእርቅ ኮሚሽን የተቋቋመው በ1989 ዓ.ም የተጀመረው የአፓርታይድ ስርዓት መወገድ ሂደት በእንደ አኤንሲ የመሳሰሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ህጋዊነትን በማግኝት፤ በእነማንዴላ ከስር መፈታትና፤ በመንግስቱና በአኤንሲ መካከል ተደርሶ ወደዴሞክራሲ በተደረገ ሰላማዊ ሽግግር ብዙ ሪፎርሞች ተደርገው፤ በ1994 ዓ.ም. የመጀመሪያው ጥቁሮቹ የተካፈሉበት ምርጫ ተካሂዶ፤ ማንዴላ የሃገሩ ፕሬዚዴንት ሆነው ከተመረጡ፤ ደቡብ አፍሪካ የተረጋጋ ስርዓትና ዴሞክራሲያዊ ሁኔታዎች ከሰፈኑባት በሁዋላ፤ ምንም እንኳን የእርቅ ኮሚሽኑን ጥያቄ ቀደም ሲል በ1994 በሁለት ታዋቂ ሰዎች የተጀመረ ቢሆንም፤ ኮሚሽኑ የተቋቋመውና ሕልውናውን ያገኘው በ1996 ዓ.ም. በፕሬዝዳንቱ በራሳቸው ትዕዛዝ ነው ። ለማሰሪያ ያህል ወዶም ሆኖ ተገድዶ የአፓርታይዱ ስርዓት ከተንበረከከ በዃላ ነው።

 

ስለሆነም እንግዲህ ዛሬ ሃገራዊ እርቅ በኢትዮጵያ ያስፈልጋል በማለት በተለይም ዛሬውኑ የሚለውን ጥያቄ በማንሳት ለሚደረገው ጥሪ፤ ሐገራዊ እርቅ ስለማስፈለጉ ብቻ ሳይሆን፤ እንጥፍጣፊም ቢሆን እንኳን የወያኔ ስርዓት ሃገራዊ ዕርቅን ለማስጀመር የሚሰጠው አመቺ ሁኔታ አለ የሚባለውን በግልጽ በማመላከት ጭምር መሆን ይኖርበታል። ያ ካልሆነ ግን በወያኔ ላይ ከያቅጣጫው  የሚሰነዘሩትን የህዝብ ቁጣዎች አቅጣጫ በማሳት ለስርዓቱ ፋታ በማስገኘት ታውቆም ሆነ፤ ሳይታወቅ የሚደረግ ጥፋት መሆኑን መገንዘብ ያሻል።  ስለሃገራዊ እርቅ አስፈላጊነት ካሁን ቀደም በጁን ወር 2015 ገደማ አሸብር የተባሉ ሰው በጻፉት እንዲህ ሲሉ ይጀምራሉ፤- “… ዕርቅ በኢትዮጵያ ስል ሌላ ምንም ሳይሆን፤ ከዘረኛው የትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (TPLF) የባርነት አገዛዝ ነጻ ወጥታ በምትመሰረተው  ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ማለቴ መሆኑን ግንዛቤ እንዲያዝልኝ አሳስባለሁ።” ይሉና በመቀጠል፤ በሚከተሉት፤-  “1ኛ/ ስለ ሀገራዊ ዕርቅ አስፈላጊነት፤-  2ኛ/ የዘረኛው የትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባር (TPLF) አካሄድ፤ 3ኛ/ በቁጥር 2 የተጠቃቀሱትና የሌሎችም መሰል ሂደቶች ዕድል፤- 4ኛ/ የሃገራዊ እርቁ ቦታ ዩዳይ፤- 5ኛ/ የዚህ የአገራዊ ዕርቅ ጥያቄ ባሁኑ ጊዜ ስለመነሳቱ፤-” የጻፉትን እንድታነቡ ልጋብዛችሁ፤  ሊንኩም ያውላችሁ፤-

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41854

 

 

ወደዋናው ርዕስ – ወደነጻነቱ ጉዳይ ተሻግሬአለሁ፤- የነጻነቱን ጉዳይ እንዳነሳ ምክንያት የሆነኝ ባለፈው ጽሁፌ እንደጠቆምኩት በሃገር ቤት ሕጋዊ ሰውነት አግኝተው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች “ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ” ቢደረግ ወያኔን እናሸንፈው ነበር የሚሉት ትረካቸው ማርኮኝ  እንደነበር አስታውሳለሁ፤

 

ሆነናም ታዲያ፤ እንዴት ነው አንድ ምርጫ ነጻ ሊሆን የሚችለው? ምንስ መደረግ አለበት? የሚለው ጥያቄ ከፊቴ ስለተደቀነ፤ ተቃዋሚዎቹ የሚሰጡት መልስ እንደለ ስሻ፤ ያገነሁት መልስ የምርጫ ቦርድ፤ ሚዲያ፤ ፍርድ ቤት፤ ታዛቢ፤ ቆጣሪ  ወዘተ… ነጻ መሆን አለባቸው የሚል ነው። አሁንም እንደገና እነዚህ ተቋማትስ እንዴት ነው ነጻ የሚሆኑት የሚለው  ጥያቄ መልስ ጠየቀኝ፤ ለነሱ መልስ ሳሰላስል፤ ሳላስበው ለመሆኑ ምርጫ ምንድነው?  ወሚለው ጥያቄ ላይ  ተሻገርኩና ሁሉንም እርግፍ አድርጌ ትቼ አትኩሮቴን በሱ ላይ አደረግሁ። ምርጫ ድርጊት ነው። ድርጊት ደግሞ አድራጊ አለው። የምርጫ አድራጊ ማነው? ሰው ነው። አንድ ሰው ከብዙ ነገሮች መካከል አንዱን የምፈልገው ነው ብሎ ሲጠቁም ያ የተጠቆመ ነገር የሱ ምርጫ ነው ተብሎ ይቀመጥለታል። ከዚህ ጋር የሚነሳው ጥያቄ ይህ ምርጫ የተደረው በመራጬ ፍላጎት ነው ወይስ ተገዶ የመረጠው? የሚለው ነው። አንድ የተለመደ ምሳሌ፤- ዘራፊ ተዘራፊ ቤት ገብቶ ባለቤት አንገት ላይ ጩቤ ገትሮ ከህይወትህ ወይም ከገንዘብህ ቢለው ተዘራፊው በእርግጥ ምርጫ አለው። ከሁለቱ አንዱን ብቻ እንዲመርጥ የተደረገው ግን ተገድዶ ነው። ነጻ ቢሆን የሚመርጠው ህይወቱንም ገንዘቡንም ነበር፤ ከሁለት አንዱን ብቻ እንዲመርጥ ስለተገደደ አንዱን ይመርጣል፤ ነጻ ምርጫ ለማድረግ ከፈለገ የግድ ያንን ዘራፊ አስቀድሞ ከፊቱ ማስወገድና ነጻ መሆን አለበት ማለት ነው። የፓርላማ ምርጫ ጉዳይም የኸው ነው። አንዱ ሌላውን ሰው መምረጥ ፍላጎት አለው። ይህንን ፍላጎቱን ለማሟላት ይመዘገባል፤ በምርጫ ዕለት በቦታው ተገኝቶ ድምጹን ይሰጣል፤ ይህ የወሰደው እርምጃ በራሱ የተወሰ እንጂ በሌላ በማንም ጫና ያልተደረገ መሆኑ መረጋገጥ አለብ ማለት ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞም፤ ከምርጫው ጋር ወደተያያዙት  ከላይ የዘረዘርናቸው ተቋማት ውስጥ የሚንቀሳአሱና ያሚያንቀሳቅሱ ሰዎች በድርጊታቸው ላይ ከማንም ተጽዕኖ የጸዱና ለሚወስዱት ማንኛውም ውሳኔ ተገዠነታቸው ለህሊናቸው ብቻ የሆኑ መሆናቸው የተረጋገጠ መሆን አለበ ማለት ነው።

 

ይሁንምና፤ ዛሬ በሃገራች ላይ በሰፈነው የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ስር በምትገኘው ኢትዮጵያ የሚደረግ ምርጫ ነጻ ሊሆን እንደማይችል እስካሁን በተገኘው ተሞክሮ፤ ተረጋግጧል። ለዚህም ዋናው ምክንያት የግለሰቦች ነጻነት/መብት ያለተረጋገጠ መሆኑ ስለሆነ፤ ወደምርጫ ከመግባት በፊት መረጋገጥ ያለበት መራጭ የሚሰጠው ድምጽ በእርግጥ በነጻነት የሚሰጥ መሆኑን ማረጋገጥ ግድ ይላልና መራጮች ከሁሉ አስቀድሞ በነጻ የመምረጥ መብታቸው እንዲረጋገጥላቸው ትግል ማካሄድ አለባቸው ማለት ነው። ይህም ማለት ባጠቃላይ ሕብረተሰቡ ነጻ ምርጫ ለማካሄድ ለሚያስችል ነጻነት ትግል ማድረግ አለበት ማለት ነው።

 

ታዲያም ለነጻነት የተደረጉ ትግሎች ታሪክ እንደሚያመለክተው የሚከፈል ዋጋ አለው። ይህ ዋጋ ያነሰ ወይም የበዛ ነው ብሎ ከወዲሁ የሚወሰን አይደለም። በመጀመሪያ ደረጃ በአንድ አገር ላይ የሰፈነው ጨቋኝ ሥርዓት በታጋዮቹ ላይ በሚሰነዝረው ጨካኝ ክንድና ያንን የሚመጥን የተቃውሞ ሃይል በመኖር ወይም ባለመኖር የሚወሰን የሆነውን ያህል፤ በተጨባጩ በሃገራችን  የወያኔውን  ስርዓት ለመቋቋም የሚደረግ የነጻነት ትግል የሚያስከፍለው ከባድ ዋጋ የመኖሩ ጉዳይ ላይ ለማስመር ብዙ ማውጣት ማውረድን የሚጠይቅ አይደለም።

 

ለነጸነተ ትግል ዋናና ወሳኙ ጉዳይ፤  ሰዎች ለሰብአዊ መብት ረገጣ በመጋለጥ ለውርደትና ለጥቃት ተዳርገው፤ የበደል ተሸካሚ ሆኖ መኖራቸውን የረጋገጡና፤ ይህንንም  በደል አሜን ብሎ ተሸክሞ ለመጓዝ ትከሻቸው ያልደነደነና ለነጻነት የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈል  የሚያስችለውን ጽናትና ብርታትን ሰንቀው መነሳት ግድ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸው ነው።

 

እነዚህ የነጻነት ታጋዮችን መኖርም ለመገንዘብ፤ እንደሚደበደቡ፤ እንደሚታሰሩ፤ እንደሚገረፉ፤ አልፎም የጥይት አራት እንደሚሆኑ እያወቁ፤ ከእቅፍ ያልወረዱ ህጻናት ልጆቻቸውን ታቅፈው፤ ስለነጻነታቸው ጩኸታቸውን ለማሰማት የተፈቀደና ያልተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ ብለው ሳያማርጡ፤ ለሰልፍ የሚወጡ፤ ለልጄ የሚወረስ አንዲት ዛኒጋባ ሳልቀልስ፤ ብለው ሳይሆን፤ ለልጄ እኔ ዛሬ የምኖረውን የባርነት ኑሮ ሳይሆን ነጻነትን አውርሼ አልፋለሁ ብለው የቆርጡ፤ እምቢ ባዮች፤ ብሶታቸው አይሎ  እሳት ሆኖ ያቃጠላቸው፤ ልጅ፤ ሚስት፤ ባል፤ ሳይሉ ዱር ቤቴ ብለው ነፍጥ አንግበው ጨቋኛቸውን ለመግጠም ወደበረሃ ያቀኑ፤ ከልጆቻቸው የወተት መግዣ ላይ ቀንሰው ለነዚህ በረኸኞች ስንቅና ትጥቅ የሚያቀብሉ ሁሉ የነጻነት ዋጋ ከፋዮች ናቸው።

 

“መልክ ስጠኝ እንጂ ሙያ ከጎረቤቴ እማራለሁ” አለች እንደተባለው፤ ለነጻነት ስለሚከፈል ከባድ ዋጋ ብዙ ርቀን ሳንሄድ  ዛሬ በዳዮቻችን ናቸው ከምንላቸው ወያኔዎቸ ወንድመቻችን  መማር እንችላለን፤ ነጻ ምርጫ ለማካሄድ መጀመሪያ መራጭ ነጻ መሆን አለበት ባልነው ቆይተን ስናየው፤ እነዚህ ከትግራይ ኢትዮጵያውያን እናቶችና ከትግራይ ኢትዮጵያውያን አባቶች አብራክ የተከፈሉና  የዘውጋቸው ነጻነት ተቆርቋሪ ይሆኑ ዘንድ አምላክ መርጦ የፈጠራቸው ወንደሞቻችን፤ የትግሬ ሕዝብ ነጻነት ግንባር በሚል ተቧድነው፤ ዛሬ የምናያትን ኢትዮጵያ ከካርታ አቀማመጧ ጀምሮ፤ ሕዝቧም አንዱ ዘውግ ሌላውን በጎረጥ እንዲያይ፤ በጋርዮሽ መተያት ቢታሰብም የነሱን በጎ ፈቃድ በቅድሚያ ያገኘ መሆኑ ሲተረጋገጥ – የዘውጎች ከየቦታው ተሰባስበው በየዓመቱ አብሮ መጨፈርን ልብ ይሏል – በነሱ አዛዥና አናዛዥነት፤ እነሱ በቀደዱለት መስመር ብቻ የሚሄድ፤ ከዚያ እዛነፋለሁ ቢል ግን ውርድ ከራሴ በማለት፤ በመደብደብ፤ በማሰር፤ ካስፈለገም እስከወዲያኛው እንዲሰናበት በማድረግ፤ አስፈራርተውና አንቀጥቅጠው የመግዛት፤ የሃገሪቱን ሃብት ከዚህ ተመለስ የሚላቸው ሳይኖር፤ የመዝረፍ ወዘተ… የመሳሰሉ ፍላጎቶች ስለነበራቸው፤ እነዚህ ፍላጎቶች ተሟልተው ለማየት የሚያስችላቸውን ነጻነት ለመጎናጸፍ  ከላይ ለነጻነት የሚከፈሉ ዋጋዎች ብዬ የዘረዘርኳቸውንና ሌሎችም መስዋዕትነቶች  ከፍለዋል። ታስረዋል፤ ተገርፈዋል፤ ተርበዋል ተጠምተዋል፤ ተሰደዋል፤ ሞተዋል ገለዋል፤ አስገድለዋል፤ ለምነዋል፤ ታርዘዋል፤ ተበርደዋል፤ ከስተዋል ጠቁረዋል፤ ትዳራቸውን በትነዋል፤ ትዳር ሳይመሰርቱም ዘር ሳይተኩም አልፈዋል፤ ወዘተ… እንበልና  መዘንጋት የሌለብን ጉዳይ ግን የተገኘው ውጤት ተካፋዮች ሁሉም እንደማይሆኑ፤ እንዳልሆኑ፤ ሊሆኑም እንደማይችሉ፤ የድሉ ተጠቃሚ ከሕይወት የተረፈውና ከዚያ የሚቀጥለው ትውልድ ብቻ እንደሚሆን ሳያስቡ እንደላደረጉት መሆኑን ነው። ይህ ትረካ ከትግራይ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ፍላጎትና ያ ፍላጎት በስራ ተፈጻሚ ሆኖ እንዲታይ ለማየት ስለተደረገ መስዋዕትነት ነው።

 

የኛስ ፍላጎት ምንድነው? ከሁሉ አስቀድሞ የህግ የበላይነት የሰፈናባት፤ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የግለሰብ መብቱ የተከበረባት፤ በዘሩ፤ በእምነቱ፤ በቋንቋው፤ በጾታው፤  አድልኦ የማይደረግበት፤ የመሰብሰብ፤ የመደራጀት፤ ከቦታ ኦታ የመንቀሳቀስ፤ የመናገር፤ የመጻፍ፤ መሪዎችን የመምረጥ ወዘተ … ነጻነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ማየት ነው። የዚች ዓይነቷ ኢትዮጵያ ማለት ታዲያ የሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሆነች አገር ነች ማለት ነው። ምናልባት አሁን ከትከሻችን አውርደን ለመጣል የምንፈልገው የባርነት አገዛዝ ባለቤት የትግሬ ሕዝብ ነጻነት ግንባር  ለሁሉም የምንላት ኢትዮጵያ ውስጥ ብን ብሎ የሚጠፋ የሚመስላቸው ሰዎች ካሉ፤ ተሳስተዋል። በዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ውስጥ የትግሬ ሕዝብ ነጻነት ግንባር፤ የሚባልን ነገር ዓይኔን አላይም የሚል ካለ፤ ዓይኑን መጨፈን ይችላል። ባለፈው ጽሁፌ “በሪሞት ኮንትሮል…. ” እንዳስቀመጥኩት፤ ዴሚክራቲክ ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ የሚነሱ ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ ማለቴን አስታውሳለሁ። የትግሬ ሕዝብን ነጻነት ግንባርን መባረር የምንፈልገው ከተጣበቀበት ሥልጣን አካባቢ ነው።  – መጣበቅ የሚለውን ቃል የቀለብኩት ከጠቅላይ ሚነሰትር  ሃይለማርያም ደሳለኝ አንደበት ሲወረወር አግኝቼ  ነው። ቃሉ አስበው የወረወሩት ይሆን ወይም  ባርቆባቸው ለጊዜው ይሄ ነው ለማለት እቸገራለሁ።

 

ያም ሆነ ይህ፤ ለነጻነቱ ትግል የሚከፈለው መስዋዕትነት ሕይወትን እስከማጣትም እንደሚደርስ ስናስብ፤ የሚፈስ ደም ዋጋ እንዲኖረው የማድረግ ሃላፊነትን አለመርሳት፤ ስለሚጠበቀው ውጤት አዎንታዊነት እርግጠኛ መሆን፤ ሁሉም ነገር ባፍጢም በሚደፋ ፍጥነት ይሳከል ብሎ ማሰብን ማረቅ! በ66 አብዮት ዘመን ከሚገባ በላይ ደም ፈስሶአል ይባላል፤     ያ ደም በይፈስ ኖሮ፤ ዛሬ የምናየውን ሸጋ ነገር አናይም ነበር የሚያሰኝ አኩሪ ቅርስ ጥሎ ሳይሆን፤ አሳዛኝ በሆነ ውጤት የመጠናቀቁ ግንዛቤ እንዳለን ባምንም፤ ያ ዘመን ግን፤ የእብደት ዘመን ስለነበረ የደም መፋሰሱ አስፈላጊነት ታስቦበት፤ ግራ ቀኙ ታይቶ የተካሄደ ስላልነበር፤ የማይሆነው አልነበረም የሆነው።  ዛሬ ግን አስቦና መክሮ የመስራት ዕድል መኖሩን አለመዘንጋት።

 

እስከዚህ ያልኩት እንደለ  ሆኖ ታዲያ፤ አሁንም እኮ እየተደረገ ያለው  ትግል የነጻነት ትግል ነው ስራ አልፈታንም የሚሉ  እነደሚኖሩም እርግጠኛ ነኝ። እርግጥ ነው ለነጻት የሚታገሉ አሉ!  የኔ ሃሳብ የሚያዘመው ወደነሱ አይደለም። እነሱን በርቱ ነው የምላቸው። ሃሳቤ የሚቃኘው የሰላማዊ ታጋዮች ነን የምንለውንና የነጻነት ታጋይ አስመስለን እራሳችንን ለማቅረብ የሚዳዳንን  ነው። ያሁኑ ሰላማዊ ታጋዮች ከምናደርገው ብዙ ጊዜ ከምናጠፋባቸው ጉደዮች ውስጥ አንድ ምሳሌ ላንሳ፤- ጊዜ የማይለውጠው 11 በመቶ የወያኔ ኢኮኖሚ እድገትን ይዘን አድጓል አላደገም፤ በሚል እንደትልቅ ጉዳይ አድርገን እየተወዘወዝን ነው መሽቶ የሚነጋው።  የነጻነት ታጋይ እንዲህ ያለ ጣጣ ውስጥ አይገባም። አንድ የነጻነት ታጋይ የዚህ ዓይነቱን ጉዳይ የሚያየው ባሪያ ከጌታው አምልጦ ሊጠፋ እየተዘጋጀ እያለ ዘንደሮ የጌታዬ ማሳ  በደንብ ታርሶላቸው ይሆን ብሎ እንደሚጠይቅ አድረጎ እንደሆነ ማንኛችንም የምንስተው አይመስለኝም። ኢኮኖሚው አድጎ ሰማይ ይጥቀስ፤ ሌላ ሌላውም የሚያድግ ነገር ሁሉ አድጎ አገር መሬቱን ያልብሰው። ያለነጻት ምን ፋይዳ አለው?

 

ማሳረጊያ፤ ከወያኔ ወንድሞቻችን መስዋዕትነት ትምህርት ቀስመን፤ እነሱ ለተጠቀሙበት ግብ ዓይነት ሳይሆን እኛ ለምንፈልገው ግብ የማዋል ጥበቡ ይኑረን፤  በከፈሉት መስዋዕትነት  ካገኙት ትርፍ ጋር በምንም መመዘኛ ሊወዳደር በማይችል ሁኔታ ከደረሰባቸው  ከፍተኛ “የኢትዮጵያን ሕዘብ ፍቅር የማጣት” ኪሳራ እግዜሩም አላሁም ይሰውሩን፤

 

በሰላማዊ እምቢተኝነትም ሆነ፤.

በአመጻዊ   ምት።!

በነጻነቱ  ትግል ወደፊት!

 

________________________________________________________________________________________________________________________________

ማስታወሻ ለአንባቢዎች

በጃንዋሪ 2016 መጀመሪያ ላይ የማስተባበር ጥሪ”

ለሚከተሉት ሁለት ሰፊ ስብስቦች አስተላልፌ ነበር።

  1. Peoples Alliance for Freedom & Democracy (PAFD)

 

2 .United Movement for Salvation of Ethiopia through Democracy (UMSED)

ሁለቱንም በድጋሚም ጠይቄ ያማራም የኦሮሞም ሳይሉ ቀርተዋል። እንድታውቁት

የሆነው ሆኖ ጥሪውን ያነበባችሁና ሃሳቡን ደግፋችሁ እንዲሳካ በጎ ምኖታችሁን፤ ሌሎችም ስብስቦች

እንዲታከሉበት ፍላጎታችሁንና ከዚያም አልፎ አስፈላጊ ለሆነ ትብብርም ዝግጁ መሆናችሁን

ለገለጻችሁልኝ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።

 

ተንኮል ከጀርባው ያለበት ነው፤ ደርሰንበታል በማለት ስጋታችሁን ለገለጸችሁም፤ አንተ ለመሆኑ ማን ሆነህ ነው

ሰብሳቢ የሆንከው? ለመሆኑ እንዴት ሃብት ቢተርፍህ ነው? ላላችሁትም አክብሮት አለኝ።

 

tassat@t-online.de

 

 

 

“ጠ/ሚ/ር ሃይለማሪያም ኤርትራን ለመውረር መዘጋጀታቸውን ነግረውኛል” –የአውሮፓ ህብረት ሹሙ ጅያኒ ፒቲላ

$
0
0

ከታምሩ ገዳ

የኢትዮጵያው ጠ/ሚ/ር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ መንግስታቸው በጎረቤት አገር በኤርትራ ላይ የወረራ ዘመቻ ሊያደርግ መዘጋጀቱን እና የአውሮፓ ህብረት ለኤርትራ ያለውን ቀና አመለካከት ካልለወጠ /ሁኔታዎች ግፍተው ከመጡ ኢትዮጵያ የአወሮፓ ጎዳናዎችን በሰደተኞች እንደምታጨናንቃቸው አቶ ሃይለማሪያም ለአንድ የአውሮፓ ህብረት ከፈተኛ የፓርላማ አባል ሰሞኑን ማስጠንቀቃቸው ተገለጸ።

Tamriu geda

hailemariam

ይህ “የማሰጠንቀቂያ” እና የማስፈራሪያ” ገለጻ የተደረገላቸው ሰሞኑን ከ አውሮፓ ህብረት መናገሻ ከተማ ቤልጂዩም/ ብራስለስ ወደ አዲስ አበባ ለሰራ ጉብኘት ያቀኑት በህብረቱ የሶሻሊስት እና የዲሞክራት ፓርቲ አባልት ጥምረት ፕሬዜዳንት የሆኑት ጅያኒ ፒቲላ ሲሆኑ የፓርላማው አባል እና የፓርቲው መሪ በአ/አ ቆይታቸው ከአቶ ሃይለማሪያም ደሳልኝ ጋር በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው የጠቀሰው ዘ ሁፊንግ ቶን ፖስት ድህረ ገጽ በእሮብ ሚያዚያ 6 / 2016 እኤአ እትሙ ሲያብራራው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካክል ባለፈው 1998 -2000 እኤአ ከተካሔደው ደም አፋስሽ የድንበር ይገባኛል ግጭት በሁዋላ የዘለቀው የውጥረት ደመና ዛሬም ማንጃበቡን የተናገሩት ሚስተር ጅያኒ “የተባበሩት መንግስትታት ያስተላለፈው ወሳኔን አሻፈረኝ ያለቸው አዲስ አበባ የመፍትሄ ሃሳቦች እንድታቀርብ ስትጠየቅ በአስመራ ያለው መንግስት አምባ ገነን በመሆኑ ለዚህም መፍትሄው የኤርትራ መንግስትን ማስወገድ እና ይህንንም ለማድረግ/ኤርትራን ለመውረር ተዘጋጅተናል። በለውናል ሲሉ የአውሮፓው ህብረት የሕዝብ እንደራሴው ፣የሶሻሊስት እና የዲሞክራሲ ፓርቲ ሹሙ ለዜናው ዘገባው በሰልክ ገልጸውለታል።

 

ሚስተር ጅያኒ ለጀርመን ራዲዮ የአማሪኛው ክፍለ ጊዜ የብራስልሱ ወኪል ይህንኑ ሁኔታ በተመለከተ ሲናገሩ ” የአወሮፓ ህብረት ለ ኤርትራ የሚያደረገው እርዳታን አቁሟል ።እርዳታው ከቀጠለ ግን ኢትዮጵያ በኤርትራ መንግስት ላይ ወረራ ለማድረግ መዘጋጀቷን እና በግዛቷ (በኢትዮጵያ ) ውስጥ የሚገኙ በ 10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣት ኤርትራዊያን ሰደተኞችን ወደ ጣሊያን እና ወደ አውሮፓ አባል አገራት እንዲጎርፉ እንደምታደርጋቸው ዝተዋል። “ሲሉ ሚስተር ጅያኒ ለዘጋቢው ተናግረዋል ። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ዛሬ ድርስ ያላቆመው “የገደብ የለሹ” ወታደራዊ ስልጠና የሚያደርገው “ኢትዮጵያ ልትወረን ሰለምትችል እራሳችንን በቅድሚያ ማዘጋጀት አለብን።” የሚል አቋም እንዳለው በሆፊንግተን ፖስት ላይ ተገልጿል። ከዚሁ ከወታደራዊ ስልጠና ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ወደ ስልጠና ማእከል ሊወስዱ ከነበሩ ወጣት ኤርትራዊያኖች መካከል ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያለታወቀ ምልምሎች ከ መኪና ላይ በመወረድ ለመጥፋት ሲሞክሩ አደጋ እንደደረሰባቸው የተለያዩ የኤርትራ ተቃዋሚ መገናኛ ብዙሃናትን ዋቢ ያደረገው የእንግሊዙ (ቢቢሲ )በሚያዚያ 6/2016 እኤአ ዘግቦታል። የኤርትራው የማስታወቂያ ሚ/ር አቶ የማነ ገ/መስቀል በበኩላቸው በወዳጆች መገናኛው ቲውተር አካውንታቸው”ለብሔራዊ አገልግሎት ወደ ስልጠና ማእከል በወታደራዊ ካሚዮን ሲጓዙ ከነበሩ መካከል ሁለት ምልምሎች አስመራ ከተማ ውስጥ ከመኪና ላይ ለመዝለል ሲሞክሩ ከደረሰባቸው ጉዳት ሳቢያ ሞተዋል።” በማለት የወጣቶቹ አሟሟት በራሳቸው ውስኔ እንደሆነ እና የሻቢያ መንግስት ታጣቂዎች ገደለዋች ዋል ተብሎ በአንዳንድ ሚዲያች የቀረበው ዘገባን አቶ የማነ ለማስተባበል ሞክረዋል።

 

የአቶ ሃይለማሪያም ሰሞነኛ “ኤርትራን ለመውረር ተዘጋጅተናል “ ዛቻ አንዳንድ ወገኖች በኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተከሰተውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት/ሕዝባዊ ቁጣን አቅጣጫን ለማስቀየር ፣አሊያም ከኤርትራ ጋር የዘለቀው “ጦርነት የለም፣ ሰላም የለም / No war , No peace “የሚለው አቀራረብን ለማጥበቅ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ይገምታሉ። “የኤርትራ ሰደተኞችን ወደ አውሮፓ እንጎርፋለን ” የሚለው የአቶ ሃይለማሪያም ሰሞነኛ ዛቻን በተመለከተ የቀደሞው የሊቢያው አምባገነን መሪ ኮ/ሌ መሃመድ ጋዳፊ በምእራባዊያን በተለይ ደግሞ አውሮፓዎች ባደረጉት ልግስና ሳቢያ ተቃዋሚዎችን በማስታጠቅ ሲዋጓቸው ጋዳፊ ”አርዳታችሁን ካላቆማችሁ በግዛቴ የሚገኙት በ10ሽዎች የሚቆጠሩ ህገ ዋጥ ሰደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲ ጎርፉ አደርጋለሁ።” በማለት መዛታቸው ይታወሳል። ጋዳፊም ተዋርደው ከስልጣን መውረዳቸው አይዘነጋም ፣የአውሮፓ ከተሞችም ዛሬ በመጠነ ሰፊ የስድተኞች ጎርፍ እየተጥለቀለቁ ይገኛሉ። የኤርትራ መንግስት ከ ኢትዮጵያ በኩል ሰለ ቀረበበት ሰሞነኛው “የጦርነት ነጋሪት” ዙሪያ በተመለከተ አስከ አሁን ድረስ የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።

 

ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖች እና ኤርትራዊያኖች በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የተገነባው “የጥላቻ ግንብን” ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመናድ እና በምትኩ ዘለቂታዊ ሰላም እና መረጋጋት ለመፍጠር ከተፈለገ ሁለቱ አምባገነኖች ( የ አ/አው ሕዋት/ኢሕ አዲግ እና የአስመራው አቻው ሻቢያን) ማስወገድ ብቸኛው መንገድ ነው ሲሉ ይደመጣሉ።

 

የአውሮፓ የፓርላማ አባላቱ በአዲስ አበባ ቆይታቸው የኢሕ አዲግ መንግስት በዜጎቹ በተለይ በኦሮሚያ ወስጥ እየፈጸመ ያለውን የሰበዊ መብት ጥሰቶች በተመለከተ ያሳደረደርባችው ስጋትን እና ሕብርቱም በቅርቡ በኢሕ አዲግ መንግስት ላይ ሰለ ወሰድው እርምጃ ሳይገልጹ አላለፉም።

ኢትዮጵያዊያኑ ወያኔ በፊላደልፊያ የጠራውን ምስጢራዊ ስብሰባ አሰናከሉ |ቪዲዮ ይዘናል

$
0
0

Phila

ኢትዮጵያዊያኑ ወያኔ በፊላደልፊያ የጠራውን ምስጢራዊ ስብሰባ አሰናከሉ | ቪዲዮ ይዘናል

Ethiopia: 28 people killed in floods in remote regions

$
0
0
(AP) ADDIS ABABA, Ethiopia – The state broadcaster in Ethiopia says 28 people have been killed in severe flooding in two remote regions. The Ethiopian Broadcasting Corporation reported Monday that 23 people were killed and 84 more people were injured when a river that crosses Jigjiga, the regional capital of the Somali region, burst its […]

Health- 43 Amazing Health Benefits of Lemon and Lemon Water

$
0
0
By Dr hitesh sharma Yes, Lemon. Discover amazing health benefits of Lemon that you have n’t heard before on this article. Everyone has a habit of taking either tea or coffee once they get up from the bed.Have you ever thought of an alternative? I would suggest you to ditch that coffee mug and start […]

Moresh: A Study Summary on the Crime of Ethnic Cleansing Perpetrated on the Amhara of Ethiopia, 1991-2016

$
0
0
To Members of European Parliament Wiertzstraat 60 B-1047 Brussels, Belgium From : Moresh Wegenie Amhara Organization (MWAO) 8221 Georgia Avenue Silver Spring, Maryland, MD 20901 USA A Study Summary on the Crime of Ethnic Cleansing Perpetrated on the Amhara of  Ethiopia, 1991-2016 Moresh Wogenie Amara Organization (MWAO), which sponsored the study on the Crime of […]

Libya’s Tripoli government to step down – BBC

$
0
0
One of two rival governments in Libya has announced that it is stepping down, a justice ministry statement has said. The announcement comes less than a week after the arrival in Tripoli of a UN-backed national unity government. The Tripoli-based administration said it was standing down to prevent further bloodshed. Since 2014 Libya has had […]

Visiting Jailed Journalist Woubshet Taye in Zeway Prison – By BefeQadu Z. Hailu

$
0
0
By BefeQadu Z. Hailu Ethiopian journalist Woubshet Taye was arrested in June 2011 and has been held behind bars since then. For doing his job as a journalist, he was sentenced 14 years on anti-state charges. Zone 9 Blogger BefeQadu Z. Hailu, who himself was jailed in 2014-2015, writes about his visit to Woubshet in […]

Events in Oromia have been described as the worst civil unrest in a decade

$
0
0
by Belén Fernández “This government is at least better than previous ones,” remarked a 74-year-old Eritrean man to me last month in the Ethiopian capital of Addis Ababa, his longtime residence. Clad in a tattered grey suit and speaking to me in Italian, the man was peddling a book of useful Amharic phrases he had […]

Ethiopia: Where do we go from here?

$
0
0
  By Teshome Abebe (PhD) The following text of the speech was presented at Vision Ethiopia Conference on March 27, 2016. Because of time limitations, some paragraphs may not have been presented. I attended the conference as an academic only representing myself, and not as a member of a political party or any other group. […]

A Call to Ethiopians from Marginalized Minorities: Can You Hear Us? | Video

$
0
0
by Zehabesha.com The Majangir people of Gambella are among the most marginalized of minority groups in Ethiopia. Binyam will address the problems facing minorities when mainstream groups do not speak up for them or include them, often making them even more vulnerable. He will challenge larger, mainstream groups to stand together for the well being […]

Mogachoch Part 66 – New Ethiopian Drama

$
0
0
Mogachoch Part 66 (ሞጋቾች ክፍል 66) New Ethiopian Drama
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live