Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የትግራይ “ልማታዊ” የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና የወልቃይት ጠገዴ ህዝብን የማጥፋት ጥማታቸው!!!

0
0

መጋቢት 27 /2008 አ/ም

Wolqite Newsይህን ፅሑፍ እንድጽፍ ያስገደደኝ አሳዛኝና አጸያፊ ድርጊት በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ መሀል ሲፈጸም በማየቴ ነው። በወያኔና ማስተዋል በተሳናቸው የትግራይ ደጋፊዎቹ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ዘሩን የማጥፋት ውሳኔዎቻቸውና ዘመቻቸው ስላዘንኩና ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማሳሰብ ጭምርም ነው። በእርግጥ በዚህ የአማራ ህዝብ ላይ ከ1972 አ/ም ጀምሮ በተለይ ደግሞ ከ1983 አ/ም ጀምሮ ማንም ኢትዮጵያዊ ወገኑ እንዳይሰማ በማድረግ ሰፊ የሆነና የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ስራ ሲሰሩ መቆየታቸውንና በዚህ የእግዚአብሔር ህዝብ ያልፈጸሙት የግፍ አይነት እንደሌለ በቅርቡ በተለያዩ ፀሓፍትና ሚዲያዎች እየተረጋገጠ ያለ ሀቅ ነው።

ወያኔና የትግራይ ሰዎች በ25 አመታት ውስጥ ሙሉ ገድለውት፣ አስረውት፣ አሰድደውት፣ ደብደበውት፣ ንብረቱን አጉዘውበት፣ ሴት ልጆቹ ደፍረውበት፣ መሬቱን ቀምተውት እንዲሁም ልዩ ልዩ አይነት ስቃይ ፈጽመውበት ደሙን ጠጥተውና አፍሰው የማይረኩበት እንዲያውም የበለጠ የሚጠሙበትና የሚሰክሩበት የኢትዮጵያ ህዝብ ማን ነው ቢባል መልሱ በእርግጠኝነት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ነው። የሰው ልጆች ሊያምኑት ቀርቶ ሊያስቡት ከሚችሉት በላይ እጅግ እጅግ በጣም የከፉ የተባሉ ዘግናኝ ግፎችና በደል የደረሰበት ህዝብ ነው። እንዲህ ስል ታድያ በሌላው የኢትዮጵያ ወገኖቼ ላይ በየቦታው የደረሰው ስቃይና ግፍ እረስቼእንዳልሆነ ታሳቢ መሆን አለበት።

ከአንድ አመት ከ6 ወራት በላይ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ኮሚቴ አቋቁሞ በግድ የተነጠኩትን የአማራ ማንነቴ ይከበርልኝ ብሎ ለትግራይ ክልል ከዛም ለፌደረሽን ምክር ቤት የአማራ ማንነት ጥያቄ ለማቅረብ ችሏል። አሁን ግን በጣም ያሳዘነኝ ጉዳይ በቅርቡ ይሔን ተከትሎ የትግራይ መንግስት ጥያቄውን ለማዳፈን ጥያቄውን በአስተዳደራዊ በደል ስም በማድበስበስ ህዝቡ በወከለው ኮሚቴ የተለያዩ የሽብር ስሞችን በመለጠፍ ከወከላቸው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ በሕጋዊ ኮሚቴ አባላቶቹና መላው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ አፈና፣አዛውንትን በአስተዳደርና ባልታወቁ ታርጋ በሌላቸው መኪኖችም ጭምር ገጭቶ በመግደል፣በጣት በሚቆጠሩ ተወላጅ ካድሬዎች ስም የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ‘ትግሬ ነን’ ብሎ በሚዲያ በማስነገርና ልዩ ቀረጻ በማዘጋጀት ባለው ሚዲያን የመቆጣጠር የበላይነት የተሳሳት የውሸት መረጃ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለትግራይ ህዝብ አዘጋጅቶ ማስተላለፍ፣ እስር፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ ስደት፣ ማሸማቀቅ፣ የንብረት መወረስና ልዩ ልዩ መካራዎችን  የሚያደርስ ሴራዊ ፕሮግራም ነድፎ ህጋዊ ጥያቄው አቅጣጫው እንዲቀይር ይህ ቀረሽ የማይባል ከባድ ጫና ሲያደርስ ቆይቷል።

ይሔን ሲያደርግ የትግራይ ልዩ ኅይል፣ የትግራይ ሚሊሺያ፣ የትግራይ አጋዚ ጦር፣ የሱዳን ደህንነቶች፣ የትግራይ የድሮ ታጋዮች፣ አዲስና ነባር የመከላከያ ስልጡን ሰራዊትና ጀሌዎችን እየተጠቀመ ነው። ተያዥ ማስረጃ ከመስጠት አንጻር ከትግራይ ባዶ እጃቸውን ጥብቆ ለብሰው በህዝቡ ውስጥ ‘ልዋጭ! ቆራሊዮ!’ እያሉ እየቃተቱ ሲዞሩ የነበሩት በወልቃይት ጠገዴ በዳንሻ ከተማ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን እየተደፋላቸው  በወራት ውስጥ ሊታመን የማይችል ሀብት አካብተው ህዝቡን እያስጨረሱ ያሉት ከጀሌዎቹ ሲቪል ደህንነቶች ዉስጥ ለምሳሌ ንጉሰ ገብረሂወት  የተባለ በአሁኑ ስአት ባለወርቅ ቤት የሽሬ ተወላጅ፣ ከንጉስ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ የሚሰራው ሃዱሽ ትካቦ የተባለ በአሁኑ ስአት ባለቡቲክ፣ የማነ አበራ፣ተድላ ካሳሁን፣ተክላይ ሃበሽና ገብረእግዚአብሔር ነጋሽ በጥቂቱ ለምሳሌ ያህል የሚጠቀሱ ናቸው።

እስካሁኗ ስአት ሃይ ባይ በሌለው ወንበዴ የክልሉ ፈርዖን እየተጨፈጨፉ ባሉበት ሁኔታና በየደረጃው የሚገጥማቸውን መጉላላቱንም ተቋቁመው ህገ-መንግስቱን ባከበረ መልኩ በጣም በከፍተኛ ትዕግስት ጥያቄያቸውን ህጋዊ ሆነው እያቀረቡ የወያኔን ውስብስብ የውንጀላ ሴራዎችን በመበጣጠስ ለሚታገሉና ለሚያታግሉ በመጀመሪያ በፈተና አጽንቶ በሞት ባህር ለሚያሻግር ለልዑል እግዚአብሔር በመቀጠል ደግሞ ለጠንካራው ኮሚቴና ለጀግናውና ትዕግስተኛው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከፍ ያለውን ምስጋና እንዳደርስ ይፈቀድልኝ።

ይሔን ካልኩኝ ብሗላ ወደ ዛሬው የፅሑፌ ትኩረት ልመልሳችሁ ወደድሁ። የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ አንድ የትግራይ የፖሊቲካ ሰው ነኝ ያሉ በስብሰባ ላይ እንደተናገሩት ከሆነ “90 በመቶው የትግራይ ህዝብ ‘ከወያኔ ውጭ መኖር አንችልም!’ ብሎ ያምናል፤ ታድያ ለምን በትግራይ ህዝብ ላይ የመልካም አስተዳደር ክፍተት እንዲኖር እናደርጋለን?” ብለው ነበር። እኛ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብም ወያኔ የትግራይን ህዝብ ልቦና በምን መንገድና አካሄድ እንደሰለበው የምናውቀው ነገር ባይኖርም እንኳ የምናውቀው እውነት ግን የትግራይ ህዝብ ‘ካለ ወያኔ መኖር አንችልም’ ብለው እንደሚያምኑ ነው።

በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ መሃል በሰፋሪነትም በወራሪነትም ብቻ በተለያየ መንገድ መጥተው የሚኖሩት ጥጋበኛና ተስፋፊ ‘የትግራይ ሰዎች’ ግን “ወያኔ ምርኩዛችን ነው፤ ወያኔ ክብርና ኩራታችን ነው፣ ወያኔ ኑሯችን ነው፣ ወያኔ ዋስትናችን ነው” ሲሉን ነው የኖርነው እየኖርንም ያለነው። እኛ የወልቃይት ጠገዴ አማሮች በዚህ አቋማቸው ምንም አይነት ችግር የለብንም የፈለጉትን የፖሊቲካ ፓርቲ መደገፍና የፈለጉትን ሓሳብ ማራመድ ይችላሉ። ነገር ግን እነርሱ ይህን ሲያደርጉ እኛን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ እየገደሉንና የወግኖቻችን ሬሳ እንኳን በወግ በስርአቱ እንድንቀብር እየፈቀዱልን አይደለም። በቃ የኛን ዘር በተለያየ መልኩ እያጸዱ ሃብት ንብረታችንን እየወረሱ መኖር መውደዳቸውን ነው የማንቀበለው!!! የተለያየ አይነት ግፍና መከራ የደረሰብንም አሁንም እየደረሰብን ያለውም በእነዚህና በአስተዳደሩ ነው።

አሁን አሁን ደግሞ ጥቃቱ እየደረሰብን ያለው ከማንጠብቀውና ካላሰብነው አቅጣጫ ነው፤ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመሸጉ ከ‘ልማታዊ የትግራይ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች’ በኩል ነው። ወያኔ የትግራይ የቤተ- ክህነት ሰዎችን ሳይቀር ልቦናቸውን አጥተው ድንዙዛን ካድሬዎች ማድረግ የቻለ የሴጣን ድርጅት ነው። የተለያዩ አይነት ሆድ-አደር ካድሬዎች በቅድስት ቤተ-ክርስቲያኒቱ ሰርጎና አሰርጎ በማስገባት ተደማጭነት ያላቸውን የተለያዩ ብዙሓን ግእዝ ቀመስ  ምድራዊውን ውዳቂ ወያኔን የሚባርኩና የሚቀድሱ የእግዚአብሔርን ቤት ግን የሚያረክሱ ‘ልማታዊ የትግራይ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች’ ማፍራቱ በእኛ በወልቃይት ጠገዴ በሚገኙ አቢያተ-ክርስቲያኖቻችን የሚታይ እሙን እውነታ ነው። ሲከፋን ሄደን አምላካችንን አመስግነን እንዳንጸናና እንኳን በዚያ መሃል የሴጣንን ስራ የሚሰሩ ሴጣንን የሚባርኩ ሴጣናውያን ልማታዊ አገልጋዮቹ ህሊናችንን ለማቆሸሽ የሚሞክሩና ህልውናችንን በእጅጉ የሚፈታተኑ ዘረኛ፣ ግዜያዊ ምድራዊውን ፍርፋሪ የሚቃርሙ፣ የተለያየ አስተዳደራዊ ችግር የሚፈጥሩና ጥጋበኛ ፈሪሳውያንና ጸሓፍት አስቀመጦልናል።

በእርግጥ እንኳን በዚህ ግዜ ሰማያዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን አገልግሎት ጥለው የእግዚአብሔርን ኅይል በመናቅ በራሳቸው የኅይል ትምክህት ድል ለማድረግ ክህነታቸውን አፍርሰው ደርግን ለመውጋት በደርግ ዘመን ጠብመንጃ አንስተው ታጋይ የሆኑ መአት ቀሳውስትና ዲያቆናት እንዳሉ ይታወቃል። ነገ ጥሏቸው ለሚያልፍ ወያኔ በአመጻ እዚህ አድርሰውታል፤ እንግዲህ እግዚአብሔር ደግሞ በአመጻቸው ምክንያት  በነዚህ ‘የጥፋት ልማታዊ ሰዎች’  ላይ ምን ሊፈርድላቸው እንዳሰበ እርሱ ብቻውን ያውቃል። እኛ ግን በፈጠሩብን መከራ ውስጥ ሆነንም ስለነርሱ ያለ እረፍት እየጸለይን ነው። ባልፉት 25 አምታት ወያኔ የትግራይን ህዝብ አይምሮ እራሱና አማካሪው ሴጣን ብቻ የሚያውቁት ‘አጃክስና ኦሞ’ ተጠቅሞ የትግራይን ህዝብ ልብና አይምሮ እንዲህ በቀላሉ ሙልጭ አድርጎ አጥቦ የራሱን የጥፋት ዕቅድ መጫን የሚቻልበት የእባብነትም የእርግብነትም ባህሪይ ያለው መራዥ አሳ ማይህበረሰብ መፍጠር ችሏል።

እንግዲህ ከላይ በድፍረት እንዲህ እንድል ያስገደዱኝ እማኝና ግልጽ ማስረጃዎችን እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ። የመጀመሪያው ማስረጃ ከወያኔ እጅ አፈትልኮ በወጣው “ህወሓት በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ ያቀደው ድቡቁ የህወሓት ሴራ ሲጋለጥ” በሚል ርዕስ በወልቃይት ጠገዴ ውስጥ በሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናትና በህዝበ-ክርስቲያኑ ላይ በስውር በውስጣዊ አሰራር በትግራይ የሐይማኖት አባቶች ሊተገበሩ የሚገባቸው ግዴታዎች ተብለው ከተቀመጡት መርሃ-ግብሮች መካከል ሲያስቀምጥ “በአካባቢው (በወልቃይት ጠገዴ አካባቢ ማለቱ ነው) አብዛኛው የኦርቶዶክስ ሐይማኖት እምነት ተከታይና የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆኑ በአብያተ-ክርስቲያናት ላይ የሚደረጉት ስብከቶችና አገልግሎቶች ከአማርኛ ሙሉ በሙሉ ነፃ እንዲሆኑ በማድረግ በትግርኛ እንዲገለገሉ ማድረግ። በአከባቢው ወደሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናት የሚመደቡ ገበዝ፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ከአካባቢ ሰዎች እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ ትግርኛ ብቻ የሚናገሩ አገልጋዮች ከሁሉም የደጋው የትግራይ አካበቢ  የሚመደቡበት ሁኔታ በማመቻቸት የመስበኪያ ቋንቋ ትግርኛ እንዲቆጣጠረው ማድረግ። ይህም ማለት ያ አሁን ያለው የአካባቢው የአብያተ-ክርስቲያናት አገልግሎት የአማርኛ ቋንቋ የበላይነት የሚያራምዱ የጎንደሬዎችና የጎጃሞች ቋንቋ ለትግርኛ  ቋንቋ የሚቆጣጠረው ስለሆነ ነው” የሚል ይገኝበታል” (ምንጭ፦ http://welkait.com/?p=4463 ) በማለት ነበር።

ሁለተኛው ማስረጃ ደግሞ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አይደለም ሰላማዊ ሰልፍ የአማራ ማንነቱን ስለ ጠየቀ ብቻ ከላይ በትንሹ የጠቀስኩትን ግፍና የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲደርስበት በአንጻሩ ደግሞ በወልቃይት ጠገዴ የሚገኙ ሰፋሪዎችን ጨምሮ ከትግራይ በመቶዎች በሚቆጠሩ መኪኖች እየተጫኑ በተለያዩ የሙዚቃ ባንዶች ታጅበው በህዝቡ መሀል ብጥብጣዊና አሽማቃቂ የዛቻና ስድብ ጦርነታዊ ስልፍ እያደረጉ ይገኛሉ። በእርግጥ እነርሱን ማንም ‘እናንተ ትግሬ አይደላችሁም አማራ ናችሁ’ ያላቸው አካል የለም። የወልቃይት ጠገዴ አካባቢ ተወላጅ መስለው ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደናግሩ ይልቁንስ እውነትነት የሌላቸው አሳሳች እባቦች ናቸው እንጂ። ድርጊታቸው ሁሉ ህሊና ቢስና መላው የኢትዮጵያ ህዝብና የአለም ህዝብ የሚያወግዘው ነው። የግፋቸው ብዛት ከንቱነታቸውን ሲገልጡት ደግሞ ሰልፋቸውን ተቀላቅለን እራሳችንን እንድናወግዝና እንድናጠፋ ካልሆነ ግን ‘ለሞት እንደሚነዱን’ ሲነግሩንም ለሞት መነዳቱን መርጠን “ሰልፉን አንቀላቀልም” ብለናቸዋል፤ ‘ትግሬ ነን’ ሲሉን “እውነት ነው ትክክል ብላችሗል እናንተማ ትግሬ ናችሁ፤እኛ ግን አማሮች ነን” ብለናቸዋል።

በዚህ መሀል ግን በጣም ያስገረመንና ያሳዘነን ነገር አሁንም ልማታዊ የሆኑትን ወያኔ ‘የቤተ-ክስርቲያን አገልጋዮች’ ጉዳይ ነው። በሁመራ፣ ዳንሻ፣ ማይካድራና አዲ-ረመጥ እሊህ ልማታዊ ‘የትግራይ የቤተ- ክስርቲያን አገልጋዮች’ ያን ጦርነታዊ ሰልፋቸውን ልብሰ-ተክህኖ ለብሰው፣ ታቦት ተሸክመው፣  የመለስን ፎቶ ይዘውበተለያዩ መፎክሮችና ባንድ ታጅበው በማይክሮፎን ውግዘታቸውን መለስ አልሞተም የመልስ ራእይ እውን ሆኖ ይኖራል፤ የወያኔ ጠላት ሴጣን ብቻ ነው፤ጠላትን የምናጠፋ ብዙ ሚሊዮን መለሶች አለን ፤  እናንተ ታውቁናላችሁ አርፋችሁ ተቀመጡ! ትግሬነትን ካልፈለጋችሁ ከዛሬ ጀምሮ አገራችን ትግራይን ለቃችሁ ውጡ፤ ለሴጣን አንበረከክም” እያሉ ሲያሰሙ ለእኛ በጣም አሳዛኝና አሳፋሪ ተአምር ነው የሆነብን። በነገራችን ላይ የኢህዴግ ኮሙኒኬሽን ሚኒስተር አቶ ጌታቸው ረዳ ለኦሮሞ ህዝብ “የተለቀቁ ጋኔሎች” ማለታቸውን ነው ትዝ ያለኝ። ሲጀመር የሚመሩትን ህዝብ ሴጣን ጋኔል እያሉ መምራት እንደማይቻልና ወያኔ የፈለገውን ነገር ቢያደርግም ምስጥ እንደበላው እንጨት በስብሶ መውደቁን የሚያስረዳ ለኢትዮጵያ ህዝብ የምስራችን የሚነግር ሁኔታ ነው።

ህሊናዬም በመቀጠል ወደ ሁላችንም የምናውቀውው የጣልያን ፋሽስት ኢትዮጵያን የመውረሩ ታሪክ ወሰደኝ። የሮማ ካቶሊክ ቤት ክርስቲያን ፋሽስት ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን እንዲያጠፋ ሰራዊቱንና መሳሪያውን ባርካ ቀድሳ በመላክ በአዲስ አበባ በአንድ ቀን ከ30,000 በላይ ህዝብ ማለቁ ትዝ አለኝ። ለዚህ ድርጊቷ የሮማ ካቶሊካዊት ቤት ክርስቲያን እስካሁን ለኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ አለመጠየቋ አጠያያቂ በሆነበት ግዜ ከዚሁ ትውሳታዬ ጋር ተገጣጥሞ በትውስታዬ ላይ ክው ብዬ እንዳዝን ያደረገኝ ነገር ደግሞ “ልማታዊው ፋሽስት ፓትሪያርኩ አባታችንiii” አባ ማቲያስ ለሮማ ፖፑ ‘የድሮ ፍቅራችንን እንመልሰዋለንi’ ማለታቸውን ቅድስና በራቀው በመለሳዊ መፎክራቸው መናገራቸውን ሳስብ ነበር። ‘የድሮ ቅሬታችንን በይቅርታ እናስተካክለዋለን!”’ ሊሉ አስበው ይሆን ብዬ ማሰብ ልጅምር ስል ግን ራሴን ማሞኘቴን ቁልጭ ብሎ ታየኝ!!! በፍጹም እሊህ ‘ልማታዊ አባት’ ሆን ብለው ያሉት ‘ፍቅርiii’ ያሉት ነገር ነው እንጂ። በዛ ላይ ይህ ሁሉ የሚሆነው ከሲኖዶስ ፈቃድና ይሁንታ  ውጭ ተጋብዘው እዛው ጣሊያን ውስጥ የፍቅሩን አጀንዳ በማጠናከር ጉዳይ ባካልም በሀሳብም እንደተጠመዱም ታሰበኝ። በዚያ ላይ የጣሊያኑ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ወያኔን የመጎብኘት ጉዳይም ውር አለብኝ። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ አስገደ ገስላሴ የተባሉ የአረና ፓርቲ አመራር “ጣሊያን ጉድ ሰራችን” በማለት ዛሬ መጋቢት 27 በፌስቡክ ገጻቸው ላይ “የጣልያን የተቀበሩ የድሮ ንብረቶች ፍለጋ በትግራይ ተራሮች ቁፋሮ እንዲካሔድ ትዕዛዝ ተላልፏል” ካሉ ብሗላ “ይህም  በቁፋሮ  ከሚገነው ንብረት 60 በመቶው ለቆፋሪው  ሲሆን 40 በመቶው ደግሞ መንግስት እንደሚወስድ” በመተንተን “አሳፋሪ ድርጊት ነው” በማለት በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ ማቅረባቸውን አነበብኩ። ይህ ሁሉ መገጣጠም ብቻ ነው ትላላችሁ ወገኖቼ።  ኅሳባቸው የሚደገፍ ቢሆንም ካሁኑ ጽሑፌ በተያያዘ መልኩ በየድረገጹ ከሚጽፉት ጽሑፍ በመነሳት እሊህ ግለሰብ ስልጣን ቢይዙ ግን ሌላኛው የወያኔ ክንፍ መሆናቸውንና በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከወያኔ በላይ ግፍ ሊፈጽሙ ያቀዱ ‘ዲክታተር’ መሆናቸውን አስቤ የኣዞ እንባቸውን ኣይቼ ታዘቤያቸውዋለሁ።

እናማ ወደ የወልቃይት ጠገዴ ጉዳዩ ስመልሳችሁ  ተአምርነቱ ምኑ ላይ ነው ቢሉ አንደኛ የቤተ-ክርስቲያን አባቶች “አስታርቁ፤ በእግዚአሔር ፊት የተወደደችውን መልካም የሆነችውን እውነትን አድርጉ፤ ሰላምን ስበኩ፤ በጎችን ጠብቁ” ተባሉ እንጂ ‘ጥልንና ጦርነትን ስበኩ፤ በጎችን በትኑ” አልተባሉምና። እኛ ግን እሊህ ‘የትግራይ ኣዛውንትና የቤተ-ክርስቲያን ልማታዊ ኣገልጋዮችiii’ የጌታችንና የመድሐኒታችን ትምህርት በተቃርኖው ሲተገብሩ ነው ያስተዋልነው። እሊህ ልማታዊ አገልጋዮች ማስተዋል የተሳናቸው ልባቸው ከንቱ ነገርን የተሞላ የሴጣን ደንገጡርነታቸውን ነው ያስመሰከሩት። እና እነዚህ “ልማታዊ የትግራይ ቤተ-ክርስቲያን አገልጋዮችም” የጌታቸን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋና ደም በፈተተ እጃቸው እራሳቸውን አርክሰው ለክፉው ስራቸው ፅዋ መሙላት ድምዳሜ ይሆናቸው ግድ ሆኖ ካቶሊካዊት የሮም ቤት ክርስትያን ለሞሶሎኑ የሰጠችውን አይነት እርኩስ ቡራኬ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ  ይጠፋ ዘንድ  ለወያኔና ካድሬዎቹ በዚህ መልኩ እርኩስ ቡራኬያቸውን በይፋ ሰጡ።

እዚህ ላይ ወያኔ ለሐይማኖት አባቶችን የሚያማክሩ እንደ የድሮ የትግርኛ ጋዜጠኛ የአሁኑ የቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ዘራፊ የማነ ዘመንፈስቅዱስ የመሰሉ አማሳኝ ወያኔዎች ብቻ ሳይሆን የሚመደበው ከአሸባሪ ቃላት በዘለለ ሐይማኖታዊ ቃላት እንዲጠቀሙ ለወያኔ የሚያማክሩ ልማታዊ የሙስሊምም የክርስቲያንም አገልጋዮች መኖራቸውን እነርሱ እንዲህ በድፍረት የህዝባችን ንብረት በሆነው ቴሌቭዥን ነገር ግን የኛ ባልሆኑ ኅሳዊያን ‘ልማታዊ ጋዜጠኞችና ባለስልጣናት’ በኩል አወቅን። “መንግስት በሐይማኖት ጣልቃ አይገባም፤ ሐይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም” የሚለውን ታላቅ የኢትዮጵያዉያን የህገ- መንግስታችን መርህም በወያኔና ልማታዊ ካህናትና ልማታዊ ሼኮች በይፋ በዚህ መልኩ በወልቃይት ጠገዴ በይፋ ተጣሰ።

ሶስተኛው ማስረጃም በባለፈው ሳምንት በመቀሌ ከተማ ወልቃይትን የተመለከተ በጣም ብዙ ህዝብ የተገኘበት ስብሰባ አድርገው ነበረ። ከወጣት እስከደቂቅ፣ ከሙሁር እስከጨዋው፣ ከተማሪው እስከገበሬው፣ ከነጋዴው እስከወታደሩ፣ ከወያኔ እስከ አረና ያሉ የትግራይ ሰዎች በተገኙበት በዚህ ስብሰባ ላይ በጣም ብዙ አይነት ሚስጥራዊ ምክክር ከተደረገ ብሗላ እሊህ የትግራይ ልማታዊ የቤተ-ክህነት አገልጋይ ነን ባዮች ተነሱና “ወልቃይት ጠገዴ የአማራ የሚሆኑት ትግራይ የወላድ መሃን ስትሆን ብቻ ነው” ብለው ህዝቡን ካስጨበጨቡ ብሗላ “ትግራይ ግን እናንተን የመሰሉ ጀግኖች ይዛ የመለስ ውርሳችንን ለትምክህተኞቹ አሳልፈን ልንሰጥ አንችልም፤ ትግራይ የወላድ መሀን ስላልሆነች በአካባቢው የሚኖሩትን ትግራይ ያልሆኑት መንጥረን አካባቢው የኛ ይሆናል” ብለው ተናገሩ።

ሊሰሩት የሚገባቸው ስንት ክርስቲያናዊ መርሀ-ግብር እያላቸው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ዘሩን የማጥፋት አዋጅ በማስረገጥ የዘር ማጥፋት ጥማቸውን ቆረጡ። እሊህ ለሆዳቸው ያደሩ ጠፊ ልማታዊ የቤተ ክህነት ይሁዳውያን የመለስን የጥፋት ራእይ መንገድ ጠራጊዎች ስግብግብ አርዮሳውያን  በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ‘በደም ከተማዋ’ በመቀሌ በድጋሚ ሞትን ፈረዱበት።

እንግዲህ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በልማታዊ  የቤተ ክህነት አገልጋዮች የተፈጸመውን ግፍ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል። እዚህ ላይ ለማሳሰብ እምፈልገው ጥብቅ ጉዳይ  ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ‘በልማታዊ አገልጋዮች’ አገዛዝ ስር መውደቋ ከምንም በላይ በጣም ያሳዝናል!!! በእርግጥ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ሰማያዊት እየሩሳሌም የክርስቶስ ሙሽራ ስለሆነች የገሃነም ደጆችም ቢሆኑ እንኳ አይችሏትም፤ ለዘላለም ጸንታም ትኖራለች። እውነታው እንዲያ ሆኖ ሳለ ወያኔና ልማታዊው የትግራይ ቤተ ክህነት አገልጋዮችና ልጆቻቸው ግን በፈቃዳቸው ባመነጩት ፍላጎት ለሴጣን የማገልገልና የመገዛት ፈቃዳቸው ተገልጦ ጥፋታቸው ፍጹም ይሆን ዘንዳ ይህ ድርጊት መፈጸሙ እነሆ ልብ፣ አይንና ጀሮ ላለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያስተውል፣ ያይና ይሰማ ዘንዳ የትንቢት ፍጻሜ የሆነውን ‘የፍቅር መጥፋት’ መገለጫ ድርጊቶች ኢትዮጵያውያን በሆንን በእኛ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በይፋ መተግበሩ ለህዝባችን ተናገርን። ይህ ህዝብ የዋልድባን ገዳም የሚያነግስ ከሙስሊም ወገኖቹ ‘በፍጹም ኢትዮጵያዊ ፍቅር’ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ህዝብ ነው፤ ይህ ሁሉ ግፍ የሚገባው ሆኖ አልነበረም። ሆኖም ግን ይህ ሁሉ በእርሱ ፈቃድ እርሱ ለሚያውቀው ምክንያት ሆኗልና የእርሱ የጌታችንና የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስሙና ፈቃዱ ይሁን ብለን በፍጹም የምስጋና አርምሞ ስሜት በተመስጦ ውስጥ ሆነን በፍጹም በእምነትና ተስፋ እንገኛለን።

ለአስጨናቂዎቻችንና ገዳዮቻችን ፈርዖናውያን ‘ልማታዊና ተስፋፊ የትግራይ ሰዎች’ ሰጥቶ እንደማይተወንና ወደ ወገኖቻችን እንደሚጨምረን በሙሉ ልብ በመተማመን ፈቃዱንና ጥበቡን እንዲሁም አዳኝነቱን፣  ፍቅሩን፣ ድል አድራጊነቱን፣ ሁሉ ቻይነቱን፣ ነጻነት  መስበኩን፣ ጠላት መምታቱንና ዘላለማዊ ቤት ለልጆቹ ማዘጋጀቱን እያሰብንን በመከራና ሞት ሸሎቆ ውስጥ ብንገኝም በእውነት በከፍተኛ የሐሴት ስሜት ውስጥ ሆነን በልበ-ሙሉነት እየኖርን ስለሆነ ቅዱስ ስሙ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማሪያም ጋር ለዘላለሙ ይመስጌን።

ምንም ቢታጠቁም እግዚአብሔር ያመነ ህዝብ ምን ተአምር መስራት እንደሚችል ልበ-ደንዳና አንበጦቹ በደምብ ያውቃሉ፤ እነሆ ከቅዱሱ የእግዚአብሔር ተራራና የዋልድባ ገዳም ታላቅ ድምጽ ተሰምቷል!!! ጥፋት ለጥፋቱ በዚህ ጉዳይ ማን ሙሉ ለሙሉ ጥፋት ሊገጥመው እንደሚችል እነዚህ ሰዎች በግልጽ ያውቃሉ ብለን ግምት እንይዛለን። ሰፊው የኣማራው ህዝብ እንደሆነ እነርሱ ሰላምን ካልወደዱ ባላወቁት መልኩ ከሚያስቡት በላይ በሆነ በከፍተኛ ህቡእ ዝግጅትና ኣደረጃጀት ቆርጦ መነሳቱን እነሆ ከዛሬ ጀምሮ እነርሱም ይዘጋጁ ዘንድ በግልጽ በዚህች ኣንድ ተለላ መስመር ኣቋማችንን በልበሙሉነት ነገርናቸው።

ያለምንም ወንጀል በዱላ፣ ርሃብና ልዩ ልዩ ስቃይ በከፍተኛ ሙቀት በሁመራ ማረሚያ ቤት ታፍነው የሚገኝቱን የወልቃይት ጠገዴ ልጆች በፍጥነት ልቀቋቸው። ስለ ኢትዮጵያ ሲባል በእግዛብሔር ቅዱስ መንፈስ አዛዥነት በትዕግስት እየጠበቅን ነው፤ ለሰላም የምትተጉ ከሆነ ለሁላችን የሚበጀን በጣም አጭር የተባለ ግዜ ብቻ ነው ያለን። ይህን ስናሳውቅ ስለ ቅድስት ሃገሪቱና ህዝቦቿ ህልውና በከፍተኛ ሁኔታ ከማሰብ አንጻር ነው። እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን እንላለን፤ ውሳኔውና ምርጫው በእጃችሁ ነው ያለውና!!!

ምንም እንኳን ኅጢአተኛ ያልሆነ ሰው በሁላችን መሀል ባይገኝም የነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር ቤት ወደው በድፍረት በቅዱስ ቤተ-መቅደሱ እየፈጸሙ ያሉትን የጥፋት ርኩሰት ግን ከመጠን በላይ ያለፈ ስለሆነና ስተው የኔን ቢጤ ጨዋውን የትግራይ ህዝብ እያሳቱ ስለሆነ ፈጥነው ንስሃ ይገቡበት ዘንዳና አገሪቱ ወደ እርስ በርስ ጦርነት የሚነዱ እያንዳንዳቸው ‘የኦራል ጎማዎች’ ሆነው እያገለገሉ እንደሆነ ‘የጥፋት መዐት ደዎል’ እያሰሙ ስለሆነ ክፉው ምግባራቸውን በመርመር የእራሳቸውን ሴጣናዊ ክፉው ድርጊታቸው በራሳቸው አውግዘው ለህዝባቸው (ወያኔን ጨምሮ) እንዲመክሩም ‘እራሳቸው ጠፍተው ሌላውን በከፊል እንዳያጠፉ’  ጨው ለራሽ ስትል ጣፍጥ የተባለውን የኣስተዋይ ኣባቶች ምክርን ላስታውሳቸው ወደድኩ። ኢትዮጵያ  በክብርና በሰላም ከነልጆቿ ለዘላለም ትኑር፤ እግዚኣብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፤ኣሜን!!!

 

ተግታችሁ ጸልዩ፤ ልዑል እግዚአብሔር ታላቅ ስራን ለመስራት ተዘጋጅቷልና!!!

ተጻፈ በወልቃይት ጠገዴ                           

ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር ፤ጎንደር  ኢትዮጵያ

መጋቢት 27 /2008 አ/ም

 

 


የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በጎንደር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፈተ

0
0
(ጎንደር ፋሲል ግምብ - ፎቶ ፋይል)

(ጎንደር ፋሲል ግምብ – ፎቶ ፋይል)

ይድረስ ለጎንደር ህዝብ ቁጥር # 8

ወያኔ ገና ካፈጣጠሩ ጀምሮ አማራን ለማጥፋት ዓላማው አድርጎ የተነሳ መሆኑ ቢታወቅም፤ በተለይ በጎንደር/አማራ ህዝብ ላይ ለሃያ አምስት ዓመታት ያህል የወልቃይት ጠገዴ፤ ካፍቲያ፤ ሁመራና ጠለምት ህዝብ በገሃድ ባካሄደዉ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማመን የሚከብድ አሰቃቂ ድርጊት ፈጽሟል። ጀግናዉ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ፤ የወያኔ አረመኒያዊ ጭፍጨፋ ሳይበግረው፤ ትግስትና ጥበብ በተላበሰ መልኩ ለብዙ ዓመታት “ጎንደሬ፤ አማራ ነን፤ ለወያኔ አንገዛም” በማለት በቆራጥነት ለማንነቱ በመታገል መስዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል።

Read Full Story in PDF – ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከተቃዋሚዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ

0
0

back1663በአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ የሶሻሊስት ዴሞክራት ጥምረት አባላት የልዑካን ቡድን ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በዴሞክራሲያዊ ጉዳዮችና በመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ላይ ሲወያዩ፣ በፖለቲካ ምኅዳር ዙሪያ ተቃዋሚ ፓርቲዎችንም አነጋግረዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ መሪ ጂያኒ ፒቴላ ይህን ያስታወቁት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ካካሄዱ በኋላ በአውሮፓ ኅብረት ዋና ጽሕፈት ቤት መጋቢት 23  ቀን 2008 ዓ.ም. ውይይቱን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር የተደረገው ውይይት አንድ ሰዓት ያህል መፍጀቱንም ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የልዑካን ቡድኑ ከአራት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ጠቁመው፣ ከፓርቲዎቹ ተወካዮች የተቃውሞ ሰነድ እንደቀረበላቸውም አስታውቀዋል፡፡
‹‹ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ባደረግነው ውይይት መንግሥትን በፅኑ የሚተቹ አስተያየቶችን አድምጠናል፡፡ በተለይም ደግሞ የምርጫ 2007 ውጤት ሕገወጥ መሆኑን ገልጸውልናል፤›› በማለት ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጋር ስላደረጉት ውይይት ይዘት ጠቁመዋል፡፡
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በተደረገው ውይይት በቅርቡ በአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ጨምሮ የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ የሕገወጥ ሰዎች ዝውውርና የዴሞክራሲ ባህል መዳበር የውይይት አጀንዳዎች እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡
‹‹ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ዴሞክራሲን፣ የዜጎችን ነፃነትንና የሐሳብ ብዙኃነትን በተመለከተ መንግሥታቸው የተጠናከሩ ሥራዎችን መሥራት እንዳለበት አስረድቻለሁ፤›› ሲሉ የልዑካን ቡድኑ መሪ ገልጸዋል፡፡ በዚህ ረገድ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽም በጎ እንደሆነ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ መንግሥታቸው እየሠራ እንደሆነ እንዳስረዷቸውም ተናግረዋል፡፡
የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ በቅርቡ ባወጣው ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ላይ በኦሮሚያ የተከሰተውን አለመረጋጋት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ራፖርተር ምርመራ እንዲያካሂድ መጠየቁ የሚታወስ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የዚህ ገለልተኛ አጣሪ ቡድንን የማሰማራት ዕቅድ ከምን ደርሷል? ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በዚህ ጉዳይ ተወያይታችኋል ወይ? ተብሎ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ፣ ጉዳዩ በውይይቱ ወቅት አልተነሳም ብለዋል፡፡
የኅብረቱ ፓርላማ ከ97ቱ ምርጫ ጀምሮ ጠንካራ ትችቶችን ያዘሉ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳቦች ያቀርባል፡፡ ነገር ግን የውሳኔ ሐሳቦቹ ውጤት ምንድነው ለሚለው ጥያቄ ደግሞ፣ ‹‹በተደጋጋሚ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳቦችን እናወጣለን፡፡ በቅርቡ ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ካወጣን በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጉዳዩን በአንክሮ እንደተከታተሉት እናውቃለን፡፡ ይህ አንድ ውጤት ነው፡፡ ነገሩ ሁልጊዜ የሚነሳ ነው፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የመንግሥት ባለሥልጣናት የአውሮፓ ኅብረት ካሉት ተቋማት መካከል ከፓርላማው የተወሰኑ አባላት ሞጋች ሆነው መቅረባቸው የተለመደ መሆኑን የሚያምኑ ሲሆን፣ ሌሎች ተቋማት በተለይ የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት እንዳለው ይገልጻሉ፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር

 

ግብጽ ለኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎች የተለየ ድጋፍ አላደረግኩም አለች

0
0

ባሳለፍነው ወር 1000 የሚደርሱ በካይሮ የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን የኦሮሞ ተወላጆች የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ የተመሰረተበትን ሁለተኛ ዓመት በድምቀት ማክበራቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ግብጽ ተቃዋሚዎችን ማደራጀት ጀምራለች የሚል ስሞታ በማቅረባቸው ግብጽ ማስተባበያ አውጥታለች፡፡
Zehabesha News
በህዳር ወር የኦሮሞ ወጣቶች በኢትዮጵያ ከጀመሩት ህዝባዊ ተቃውሞ በኋላ በካይሮ ደመቅ ያለ ዝግጅት በስደተኞች ሲደረግ የካይሮው የመጀመሪያ በመሆን ተመዝግቧል፡፡ህዝባዊ ተቃውሞው በተቀጣጠለበት ወቅትም የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር መስሪያ ቤት አውጥቶት በነበረው መግለጫ ‹‹ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ ግብጽ ጣልቃ አትገባም››ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ግብጽን በአገር ውስጥ ጉዳያቸው ጣልቃ እንደምትገባ በመግለጽ ውንጀላ ሲያቀርቡ የመጀመሪያቸው አለመሆኑን ያስታወሰው መረጃውን ይፋ ያደረገው ጋዜጣ በ2002 በቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በሆስኒ ሙባረክ አስተዳደር ላይ በተደጋጋሚ ስሞታ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ተናግሯል፡፡

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክን የምስረታ በዓል በካይሮ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጅ ስደተኞች በድምቀት ማክበራቸውን ተከትሎ ግብጽ ለተሰነዘረባት ወቀሳ ስማቸውን በቃለ አቀባይዋ በኩል በሰጠችው ማስተባበያ ‹‹ከዝግጅቱ ጋር የግብጽን ባለስልጣናት የሚያገናኛቸው ምንም ነገር የለም ››ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡

ባለስልጣኑ ‹‹ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን አክቲቪስቶች ለዝግጅቱ የደህንነት ዋስትና እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡ይህም በካይሮ ለሚገኙ የሌሎች አገራት ስደተኞች የምናደርገው በመሆኑ የተለመደ ነው፡፡ግብጽ በአለም አቀፍ ደረጃ የገባቻቸውን ውሎች በማክበር የምትፈጽም በመሆኗም ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ ወደ አገር የገቡ ቢሆኑም ብሄራዊ አደጋ እስካልሆኑ ድረስ ከለላ ታደርግላቸዋለች››ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

ባለስልጣኑ አገራቸው ለስደተኞቹ ዝግጅት ፈቃድ ከመስጠት ውጪ የተለየ ድጋፍ አለማድረጓንና ወደፊትም እንደማታደርግ መግለጻቸውንም አል ሞኒተር የተባለው ጋዜጣ ለንባብ አብቅቷል፡፡

የእንግሊዝ ፓርላማ የአንዳርጋቸውን ጉዳይ በዝርዝርና በጥልቀት ላየው ነው አለ

0
0

andargachew Tsege
የእንግሊዝ ፓርላማ የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ በውጪ አገራት በእስር ላይ የሚገኙ እንግሊዛዊ ዜግነት ያላቸውን (በኢትዮጵያ የሚገኙትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ) እስረኞች ጉዳይ በማጥናት መንግስት በውጪ አገራት በሚገኙ እንግሊዛዊያን ላይ የሚፈጸምን የሰብዓዊ መብት ረገጣን ለማስቀረት የሚያሳየውን ቁርጠኝነት እመዝናለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡

ትናንት ይፋ የተደረገው ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነም ብዛት ያላቸው እንግሊዛዊያን በውጪ አገራት ታስረው የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች ሲፈጸምባቸው መንግስት የሚጠበቅበትን ጫና በማሳረፍ ዜጎቹን ከሚደርስባቸው ጥቃት መከላከል አልቻለም፡፡ባለፈው ዓመት የነሐሴ ወር የወጣን ሪፖርት ኮሚቴው መመልከቱ የተገለጸ ሲሆን በሪፖርቱ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚፈጽሙ አገራት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ለሰብዓዊ መብት መከበር ግድ የማይሰጠው መሆኑን ታዝበዋል ተብሏል፡፡

በፓርላማው የተዋቀረው የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ በመንግስት የሰብዓዊ መብት አከባበር ስራ ዙሪያ ጥልቅ ምርመራ እንደሚያደርግ በመግለጽ በውጪ አገራት የሚገኙ እንግሊዛዊያን እየደረሰባቸው የሚገኝን የመብት ጥሰት በዝርዝርና በጥልቀት በመመልከት የሰብዓዊ መብትን ለማስከበር መንግስት የተጓዘውን ርቀት እንደሚቃኝ አውስቷል፡፡

በለንደን የአንዳርጋቸውን ቤተሰቦች በመርዳት ላይ የሚገኘው ሪፕራይቭ የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀው ከሆነም የፓርላማ ቡድኑ በዋናነት የአቶ አንዳጋቸውን ጉዳይ መመርመር ይጀምራል፡፡

አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ከህግ አግባብ ውጪ መያዛቸውን በመቃወም የተባበሩት መንግስታትና የአውሮፓ ፓርላማ አንዳርጋቸውን ኢትዮጵያ በነጻ እንድትለቅ ሲጠይቁ የእንግሊዝ መንግስት ተመሳሳይ ጥያቄ ሳያቀርብ በመቆየቱ ትችት ሲሰነዘርበት ቆይቷል፡፡ሪፕራይቭ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርትም የዴቪድ ካሜሮን መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት መስሪያ ቤት ዋነኛው ደጋፍ አድራጊ መሆኑን ማጋለጡ አይዘነጋም፡፡

ምንጭ ሪፕራይቭ

ከአማራ ክልል የመጡ ስደተኞች በአ.አ. ጎዳናዎች ላይ ካለመጠለያ ተበትነዋል –ልመና ጀምረዋል (ይናገራል ፎቶው)

0
0

የአይን እማኞች ዘገባ ከአዲስ አበባ

ለዘ-ሐበሻ ዛሬ ከአዲስ አበባ የመጡ በርካታ ፎቶ ግራፎች እንደሚያሳዩት ከተማዋ ከአማራ ክልል በመጡ ስደተኛ የኔብጤዎች ተጥለቅልቃለች:: እንደፖለቲካ ተንታኞች አስተያየት በኢሕአዴግ የሥልጣን ዘመን ሁሉም ኢትዮጵያውያን እየደረሰባቸው ያለው ሰቆቃ ከፍተኛ ቢሆንም በአማራው ላይ ግን በጣም ለየት ያሉ ሰቆቃዎች እየተፈጸሙበት ነው:: የትግራይ ነፃ አውጪ መሪዎች ሳይቀሩ በአደባባይ “አማራው ጠላታችን ነው; እንዳያንሰራራ አድርገን ቅስሙን ሰብረነዋል” በሚናገሩባት በዚህች ሃገር አማራው ከተለያዩ ክልሎች ሰርቶ ያፈራውን ለቆ እንዲወጣ ሲደረግ; ሲገደል ንብረቱ ሲቃጠል ቆይቷል:: ከበደኖ እና ከአርባ ጉጉ ጭፍጨፋ ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜው ጉራፈርዳ አማራው ሕይወቱን እየገበረ በሃገሩ ላይ እንደሁለተኛ ዜጋ ሲቆጠር ከቆየ ውሎ አድሯል::

ከአዲስ አበባ የመጡ ፎቶግራፎች እንደሚያሳዩት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ከጎጃም; ከጎንደር እና ከወሎ የመጡ የአማራ ተወላጆች ቀያቸውን በስር ዓቱ በሚደርስባቸው ከፍተኛ በደል በመልቀቅ ወደ አዲስ አበባ እየተሰደዱ ነው:: በፎቶዎቹ ላይ እንደምትመለከቱት እናቶች አደባባይ ላይ ካለምንም መኖሪያና መጠለያ ተኝተዋል:: ልጆች ተበትነዋል:: አባቶች የሰው እጅ እያዩ ነው:: ይህ ሰቆቃ የሚያበቃው መቼ ይሆን? እነስብሃት ነጋ እንዳሉት “አማራውን እና ኦርቶዶክሱን እናጠፋዋለን” ፉከራ እየሰራ ይሆን? አስተያየት በመስጠትና መረጃውን በማስተላለፍ የአማራውን በደል እና ሰቆቃ በማሰማት ይተባበሩ::
amahara gebere

amhara gebere 3

amhara gebere 5

amhara gebere 6

amhara gebere1

ammhara gebere 4

ከአማራ ክልል የመጡ ስደተኞች በአ.አ. ጎዳናዎች ላይ ካለመጠለያ ተበትነዋል –ልመና ጀምረዋል (ይናገራል ፎቶው)

0
0

የአይን እማኞች ዘገባ ከአዲስ አበባ

ለዘ-ሐበሻ ዛሬ ከአዲስ አበባ የመጡ በርካታ ፎቶ ግራፎች እንደሚያሳዩት ከተማዋ ከአማራ ክልል በመጡ ስደተኛ የኔብጤዎች ተጥለቅልቃለች:: እንደፖለቲካ ተንታኞች አስተያየት በኢሕአዴግ የሥልጣን ዘመን ሁሉም ኢትዮጵያውያን እየደረሰባቸው ያለው ሰቆቃ ከፍተኛ ቢሆንም በአማራው ላይ ግን በጣም ለየት ያሉ ሰቆቃዎች እየተፈጸሙበት ነው:: የትግራይ ነፃ አውጪ መሪዎች ሳይቀሩ በአደባባይ “አማራው ጠላታችን ነው; እንዳያንሰራራ አድርገን ቅስሙን ሰብረነዋል” በሚናገሩባት በዚህች ሃገር አማራው ከተለያዩ ክልሎች ሰርቶ ያፈራውን ለቆ እንዲወጣ ሲደረግ; ሲገደል ንብረቱ ሲቃጠል ቆይቷል:: ከበደኖ እና ከአርባ ጉጉ ጭፍጨፋ ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜው ጉራፈርዳ አማራው ሕይወቱን እየገበረ በሃገሩ ላይ እንደሁለተኛ ዜጋ ሲቆጠር ከቆየ ውሎ አድሯል::

ከአዲስ አበባ የመጡ ፎቶግራፎች እንደሚያሳዩት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ከጎጃም; ከጎንደር እና ከወሎ የመጡ የአማራ ተወላጆች ቀያቸውን በስር ዓቱ በሚደርስባቸው ከፍተኛ በደል በመልቀቅ ወደ አዲስ አበባ እየተሰደዱ ነው:: በፎቶዎቹ ላይ እንደምትመለከቱት እናቶች አደባባይ ላይ ካለምንም መኖሪያና መጠለያ ተኝተዋል:: ልጆች ተበትነዋል:: አባቶች የሰው እጅ እያዩ ነው:: ይህ ሰቆቃ የሚያበቃው መቼ ይሆን? እነስብሃት ነጋ እንዳሉት “አማራውን እና ኦርቶዶክሱን እናጠፋዋለን” ፉከራ እየሰራ ይሆን? አስተያየት በመስጠትና መረጃውን በማስተላለፍ የአማራውን በደል እና ሰቆቃ በማሰማት ይተባበሩ::
amahara gebere

amhara gebere 3

amhara gebere 5

amhara gebere 6

amhara gebere1

ammhara gebere 4

የግድያው ተዋናይ መለስ ዜናዊ ናቸው ያሉት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕ/ት ጥፋተኛ ተባሉ

0
0

ኦኬሎ አኳይ

(ዘ-ሐበሻ) ልክ የመን አንዳርጋቸው ጽጌን ሕወሓት ለሚመራው መንግስት አሳልፋ እንደሰጠችው ሁሉ የደቡብ ሱዳን መግስትም አቶ ኦኬሎ አኳይን ለዚሁ መንግስት አሳልፎ መስጠቱን በተደጋጋሚ በዘ-ሐበሻ ላይ ስንዘግብ ቆይተናል::

ዛሬ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው የኖርዌይ ዜግነት እንዳላቸው የሚነገረው የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል::

በአኙዋክና ኑዌር ጎሳዎች መካከል ከተፈጠረው ግጭት ጋር ተያይዞ ከሀገር የተሰደዱት አቶ ኦኬሎ፣ የብዙዎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭት የተቀናበረውና በግድያውም የተሳተፉት የመንግስት ወታደሮች እንደነበሩ ለተለያዩ የዜና አውታሮች መግለፃቸው ይታወሳል።

ከአቶ ኦኬሎ ጋር በአባሪነት የከሰሱ ሌሎች 5 ግለሰቦችም ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን የካንጋሮው ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ከ20 ቀናት በኋላ ቀጥሯቸዋል ተብሏል::

አቶ ኦኬሎ የጋቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር በነበሩበት ወቅት ከ 400 በላይ ሰዎች በመንግስት ወታደሮች በግፍ ተገለው 60 ሰዎች ብቻ ናቸው እንድል ታዝዤ ፍቃደኛ ሳልሆን ቀርቻለው ማለታቸውን;  ከ 10 አመት በፊት የተፍፀመውን ግድያ ዋነኛ ተዋናዮች አቶ መለስ ዜናዊ አቶ አዲሱ ለገሰና አቶ በረከት ስምዖን እንደሆኑና በዛን ግዜ የፌደራል ፖሊስ ጉዳዮች ሚንስትር ዴኤታ የነበሩት ዶክተር ገብረአብ ባላባራስ ወንጀሉን በቀዳሚነት አስፍፃሚ እንደነበሩ በፍርድ ቤት የክስ ክርክር ወቅት መናገራቸውን ዘ-ሐበሻ መዘግቧ አይዘነጋም::


በስሉልታ ፌደራል ፖሊስ ከወጣቶች ጋር ተፋጧል –የአላሙዲ መኪኖች ተሰባበሩ * ፖሊስ እየተኮሰ ነው

0
0

Zehabesha News

(ዘ-ሐበሻ) ከአዲስ አበባው ቤተመንግስት 28.4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሱሉልታ ከተማ የአካባቢው ወጣቶች ከፌደራል ፖሊሶች ጋር በፋጠጣቸው ተሰማ:: ከአካባቢው የሚመጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የሱሉልታ ወጣቶች የኢትዮጵያን ሕዝብ እየገደለ ያለውን የሕወሓት መንግስት በገንዘብ ይደግፋሉ ያላቸውን የሼህ መሀመድ አላሙዲ 3 መኪኖችን በድንጋይ ሰባብሯል::

በሱሉልታ ከተማ የሚገኘ አንድ የኤሌክትሪክ ትራንፎርሜሽን መፈንዳቱን ተከትሎ አካባቢው በፌደራል ፖሊሶች በመከበቡ የተነሳ ሕዝቡ ፖሊሶቹን አትወክሉንም; ከአካባቢያችን ዞር በሉ በሚል ተቃውሞውን ማሰማቱን ተከትሎ ፖሊሶች በወጣቶች ላይ ዱላ ሰንዝረዋል:: አንዳንድ ወታቶችም አጸፋውን በፖሊሶች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ፖሊሶች በተኩስ የወጣቱን ተቃውሞ ለመበተን ሞክረዋል ብለዋል::

ይህ ተቃውሞ እየተደረገ ባለበት ወቅት በአካባቢው ይንቀሳቀሱ የነበሩ የሼህ መሀመድ አላሙዲ ንብረት የሆኑ መኪኖች በድንጋይ ሲደበደቡ የሦስቱም መኪኖች መስታወቶች መርገፋቸው ተሰምቷል::

በሌላ በኩልም በሰበታ የሁለተኛና የፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ወታደሮች እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አስታውቀዋል::

በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በደረሰ ቃጠሎ የተማሪዎች ንብረት ወደመ –የክልል ተማሪዎች ወደ መጡበት እየሄዱ ነው

0
0

Haromaya u Haromaya

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት ማምሻውን በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የመኝታ ህንፃ ላይ በተነሳ ቃጠሎ በርካታ የተማሪ መኝታ ክፍሎች መውደማቸው ተሰማ::

የአካባቢው ነዋሪም ሆነ መንግስት በቶሎ ሊቆጣጠረው ያልቻለው ይኸው እሳት በዚህ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሄዱ ተማሪዎች ንብረቶች መውደማቸው ታውቋል::

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሰጡት አስተያየት ከሆነ ይህ የ እሳት ቃጠሎ ለረዥም ሰዓታት የቆየ ሲሆን መንግስት በአፋጣኝ ሊያጠፋው ያልቻለው አንድ ተንኮል ቢኖረው ነው ብሏል:: በተለይ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያና በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እየተነሱ ያሉ የሕዝብ አመጾችን ከሽብርተኝነት ጋር ለማያያዝና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን ማሳየት የሚፈልገው ሕወሃት መራሹ መንግስት ሆን ብሎ እንዲህ ያለውን ጥፋት አይፈጽምም ማለት አይቻልም የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ::

በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ መኝታቸው እና ንብረቶቻቸውን ያጡ ተማሪዎች በችግር ላይ እንደሆኑ የሚናገሩት የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ከክፍለሃገር የመጡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመጣል ወደ ቤተሰቦቻቸው ጋር መሄድ መጀመራቸውንም ዘግበዋል::

ሟች ይዞ ይሞታል

0
0

oromo2

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ከሰሃራ በታች ሀገር አለኝ ማለት፤

ዋ! ብሎ መቅረት ነው ትግሬ የገዛ’ለት፡፡

የሚል ባህላዊ የዘፈን ግጥም ትዝ አይላችሁም? ትዝ እንደሚላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ትዝ ባይላችሁ ደግሞ የዱሮን ነገር የመርሳት ሁኔታ ላይ ናችሁ ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም ሀገራችሁ በመጥፋት ሁኔታ ላይ መገኘቷን ለአፍታም እንዳትዘነጉ ያህል አሁን በቀድሞዋ ኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ከእንቅልፌ ነቅቼ – እኚህ ነቀዞች እንቅልፍም እኮ እኮ ከለከሉን እናንተዬ – አዎ፣ እምቢ ካለኝ እንቅልፍ ተስፈንጥሬ በመነሣት ብቻየን ተጎልቼ አንዳንድ ነገር ልነግራችሁ የምችልበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ይሄኔ አብዛኛው ምድረ አበሻ ተጋድሞ እንቅልፉን ይለሽልሻል፡፡ ወይ ወያኔ! ደርጎች የጃቸውን አይጡ፤ ለነዚህ እርጉሞች አሣልፈውን ሄዱ፡፡

ወያኔ በዕቅዱ መሠረት ሀገር የማጥፋቱን ሥራ በስኬት እያጠናቀቀ መሆኑን በጥቂት ወቅታዊ መረጃዎች እንመልከት፡-

  • ብዙ ዩኒቨርስዎች ትምህርት አቁመዋል፡፡ ለምሳሌ ከደብረ ብርሃን አካባቢ የሰማሁት የቅርብ ሰዓት ሰበር ዜና ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ መምህራን የማስተማር ሥራቸውን እንዳልጀመሩ ታውቋል፡፡ ተማሪዎች ቢገኙም አስተማሪዎች ወደ ክፍል አይገቡም ወይም የመምህር ዕጥረት ሊኖር እንደሚችል ተገምቷል – ብዙ ቦታ ይህ (የብቁ) መምህራን ዕጥረት አለ ይባላል፡፡ ዋናው ነገር ግን ሁለተኛው ሴሚስተር ከተጀመረ አምስት ሣምንታት ቢያልፉም ከወለም ዘለም ውጪ የሚታይ ዕርባና ያለው ነገር የለም እየተባለ ነው፡፡ አንድ መምህር ባለ ሦስት ክሬዲት አወር ትምህርት እንዲያስተምር ሲመደብ ወደ ክፍል የሚገባው በሣምንት አንዴ ይሆንና ከዚያም ውስጥ ትምህርት በተጀመረ በሦስተኛው ሣምንት አካባቢ ለ10 ደቂቃ ያህል የኮርሱን ቢጋር (ኮርስ አውት ላይን) “አብራርቶ” ከክፍል ይወጣል፡፡ በቀጣዩ ሣምንት የጫት ምርቃና ተከታይ በሆነው ሃንጎቨር ምክንያት ይቀራል፡፡ በሌላው ቀጣይ ሣምንት ለሃያ ደቂቃ ያህል “ያስተምር”ና ሲጃራ ለመጠጣት እያዛጋ ከክፍል ወጥቶ ይሄዳል፡፡ እያለ እያለ ይልና … በሴምስተሩ ማገባደጃ ላይ የኮርሱ ምዕራፎች በቅጡ ሳይሸፈኑ ተማሪዎች ለፈተና እንዲዘጋጁ ይነገራቸዋል፡፡! ከዚያም ይፈተኑና “ይታረም”ና ውጤት ይለጠፍና ኤና ቢው በሎተሪ መልክ ለቀረበ ተማሪ፣ ሲና ዲው በጠበል መልክ ለተሣታፊው ይረጫል፡፡ … ከዚያም ምረቃ ደርሳል፡፡ ባልተማሩ መምህራን ያልተማሩ ምሩቃን ጋውን ይለብሱናም መነሳነሳቸውን ከአናት ወደግርጌ ያነሳሉ፡፡ ተመረቁ ይባላል፤ ሥራ ፈልገው የሚያገኙት በቀድሞዎቹ የስድስተኛና ስምንተኛ ክፍል ምሩቃን እንደገና እየሠለጠኑ ሥራውን ይለማመዳሉ – በሁሉም የሙያ ዘርፍ ነው ታዲያ፡፡ ይህ ዓይነቱ አሠራር በትግራይ ውስጥ ተግባራዊ ይሁን አይሁን አላውቅም፡፡ በሌሎች ግዛቶች ግን በአብዛኛው እንዲህ ያለ ወይም ወደዚህ በእጅጉ የቀረበ ሼክስፒራዊ ድራማ በብላሽ አለክፍያ እየታዬ ነው – ለነገሩ በነፃ አይደለም፤ ኢትዮጵያ በውድመቷ ስፖንሰር አድርጋ ከባድ ዋጋ እየከፈለችልን ነውች፡፡ በአንጻራዊ ሁኔታ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቢያንስ በ“አቴንዳንስ” ደረጃ ሳይሻሉ አይቀሩም፡፡ የጥራቱ ነገር ግን የሚነሣ አይደለም፡፡ ሀገርና ወገን የሚባል አስተሳሰብ ከሀገር በመሟጠጡ በእውነተኛ ብሔራዊ ስሜት ትውልድን የመቅረጽ ኃላፊነት የሚሰማው የትምህርት ሥርዓትና ተጓዳኝ አንቀሳቃሽ ኃይል የለም፡፡ አብዛኛው ሆድ አደር በመሆኑ፣ በዚያም ላይና በዋናነት የሙያ ሥነ ምግባርም ሆነ የሙያ ዕውቀትና ችሎታ ከሀገር ስለሸፈቱ ትውልድ በፓንጋ(በሜንጫ) እየተረፈረፈ ነው፡፡ የሚያስጨንቀው አቢይ ነገር በሰው አምሳል የሚንቀሳቀስ አጥፊ ሮቦት ሀገር ምድሩን ከወረረውና የጥፋት ተልእኮውን ከጽንፍ እስካጽናፍ ካዳረሰው በኋላ እንዴት አድርገን ኢትዮጵያን ከእንደገና መሥራት እንደምንችል ሲታሰብ ነው፡፡ ለሰው የማይቻለው ለፈጣሪ ይቻላልና እርሱው ይሁነን እንጂ አያያዛችን ሽል በእግር ዓይነት ነው፡፡ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ማሕፀን አለደንቡ በእግራቸው የመጡ ገደቢስ ገፊዎች ናቸው፡፡ በእግሩ የመጣ ጽንስ አብዛኛውን ጊዜና ጥሩና ዘመናዊ አዋላጅ ከሌለ እናቱን ይገድላል፡፡ … ሰፊው በውጭ ሀገር ያለህ ምዕመን እንግዲህ የሀገርህን መሞት ተረዳ – ማለቴ አትርሳ!

 

  • ርሀቡ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ የገጠሩ ርሀብ የታወቀ ነው፡፡ ፀሐዩ ንዳድ ሆንዋል፡፡ ቅጠልና ሣር ደርቋል፡፡ የሚላስ የሚቀመስ የጠፋባቸው አካባቢዎች ብዙ ናቸው፡፡ ወያኔ በተለይ ዐማራውን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የተያያዘው ዘመቻ በዚህ የርሀብ አጋጣሚ ሊሣካለት የተቃረበ ይመስላል፡፡ ኢሰብኣውያኑ – ጭራቆቹ ወያኔዎች ይህን ዓይነቱን ዕድል እልል በቅምጤ የሚሉት ሰይጣናዊ ስጦታ ነው፡፡ ልትፈጀው ዘዴና ብልሃት ቀይሰህ በጥርስህም በጥፍርህም እያሳደድከው ባለኸው ሕዝብ ላይ እንዲህ የመሰለ አጋጣሚ ሲፈጠር ለዐረመኔዎቹ ወያኔዎች ፈልገው የማያገኙት ወርቃማ ዕድል ነው፡፡ ጥይት ይቆጥብላቸዋል፤ ሰይጣናዊ ዕውቀትንም ይቆጥብላቸዋል፤ ጉልበት ይቆጥብላቸዋል፤ ዓለም አቀፍ ትዝብትን ይቀንስላቸዋል፤ … ለዞረ ድምሩ ዋይታ ዝግጁ ይሁኑ እንጂ ዐማራን በመጨረስ ረገድ ወያኔዎች አሁን ብዙ የቀናቸው ይመስላል፡፡ ዐማራነቷን በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ያሟሟችውና ከኢትዮጵያዊነት የወረደ ዘውጋዊ ማንነት ያላዳበረችው ምድረ ዐማራም የሚዘንብባትን ወያኔያዊ ውርጅብኝ ሁሉ በ“አንተ ታውቃለህ” ዕድሜ ጠገብ ጸሎት ምርኩዝ በነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ጣዕረ ሞት ትሰቃይ ይዛለች፡፡

በከተሞች አካባቢ ከፍተኛ ርሀብ አለ፡፡ አስፋልትና መኪና፣ ሕንፃና ፋብሪካ የጥቂት ባለፀጋዎችን መንፈላሰስ ከማሳየት በዘለለ የብዙኃንን በርሀብ አለንጋ መገረፍ አያመለክትም፡፡ እናም በከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ ትልቅ ርሀብ እየተከሰተ ነው፡፡ ጤፍ (ነጩ) 2500 ብር አካባቢ ነው – ጥቁሩ 2000 ገደማ – የሌሎች የምግብ ሸቀጦች ዋጋ አይነሣ፤ ብሩ ዜሮ ሊሆን ምንም አልቀረውም፤ ገቢና ወጪ ሰማይና ምድር ሆኑ፡፡ ብዙኃኑ በጥቂ-ትኋኑ ደማቸው በቀሰም እየተመጠጠ፣ መቅኒያቸው በስሪንጋ እየተነቀረ የቁም ሬሣ ሆነዋል፡፡ የባለስድስት መቶ ብር ደሞዝ ከሁለትና ሦስት ሕጻናት  ልጆቹና ከአንዲት የቤት እመቤቱ ጋር እንዴት እንደሚኖር አስቡት፡፡ ምን ዓይነት ድንጋይ ራስ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ፈጣሪ ለቅጣት እንደሰጠን ደግሞ አብራችሁ በዐይነ ኅሊናችሁ ቃኙት፡፡ እነሱ እንዴት እንደሚኖሩ እናውቃለን፤ የደመሞዛቸውን መጠን እናውቃለን፤ በንግድና በሙስና የሚዘርፉትን በሚሊዮንና ከዛም ባለፈ ያላቸውን ሀብትና ገንዘብ እናውቃለን፤ ደሞዛቸው ለይስሙላ እንጂ በርሱ እንደማይኖሩ እነሱ ብቻ ሣይሆኑ እኛም እናውቃለን፤ … የድንጋይነታቸው ብዛት እዚህ ላይ ነው፡፡ በዚህ የጦፈ የኑሮ ውድነት – በዚህ እናትና ልጅን በሚያባላ የሕይወት ምስቅልቅሎሽ – በዚህ ለትራንስፖርት ብቻ እንኳን የሚወጣው ከአንድ አነስተኛ ደሞዝ የሚበልጥ በሆነበት እሳት ዘመን የሠራተኛውን ኑሮ ለምን ማየት እንዳልቻሉ ይገርማል – በበኩሌ “ሚኒስትሮቻችን” ሰዎች ስለመሆናቸው እጠራጠራለሁ፤ “መሪዎቻችን” እንደኛው ከሰው ደምና ጅማት ስለመሠራታቸው እጠራጠራለሁ፤ “መንግሥታችን” የአጋንንት ስብስብ መሆኑን ለማይረዳ ወገን በርግጥም የነዚህ “ሰዎች” ተፈጥሮ በእጅጉ ሳያስደነግጠው አይቀርም፡፡ የሆኖ ሆኖ  …  አብዛኛው የመንግሥት ሠራተኛ በርሀብ እያለቀ ነው – ከሙሰኞች በስተቀር ሌላው በርሀብ አንጀቱ እየታጠፈ ለልመናና ለአልባሌ ድርጊቶች እየተጋለጠ ነው፡፡ ወንዱ ለስርቆትና ለዝርፊያ፣ ሴቱ ለሽርሙጥናና መሰል የማኅበረሰብ ነቀርሣዎች እየተዳረጉ ነው – እንዴ፣ ኧረ ወንዶችም … ገብተውበታል እየተባለ ነው! ኢትዮጵያን ለማርከስ ቆርጦ የተነሣው የወደቀው መልአክ የሚሣነው ምን ነገር አለ? ወዲህም አለ ወዲያ የርሀቡ ጦርነት አዲስ አበባን እያመሳት ነው፡፡ ሥራና የገቢ ምንጭ ያለውም እየተራበ ነው እያልኩ ነው፡፡

 

አንድ መምህር እንዲህ ሆነ፡፡ በሚያስተምርበት ክፍል ልጆች “ፌይንት” እያደረጉ ይወድቃሉ፡፡ መምህሩ ይጨነቃል፡፡ አሰበ፡፡ “ርቧቸው ይሆን?” ብሎም ገመተ፡፡ ባለችው ውሱን ገቢ ዳቦና ሙዝ እየገዛ ሲያቀምሳቸው ደህና ይሆናሉ፡፡ እንዲህ እያደረገ ጥቂት ቀናትን ገፋ – (ባይገርማችሁ እርሱ ራሱም እኮ ርሀብተኛ ነው፤ በመምህር ደሞዝ የትኛው የተመጣጠነ ምግብ ይሟላል? በሊትር የ20 ብሩን ወተት በህልሙ ካልጠጣ፣ በኪሎ በትንሹ የ250 ብሩን ሥጋ በቅዠት ካላኘከ፣ ኪሎው 50 ብር የደረሰውን ብርቱካን በቅብዥር ካልበላ … በስተቀር እመኑኝ ይህ ሰው እንደኔ ርሀብተኛ ነው!)፡፡ አንድ ቀን ታዲያላችሁ ልጆቹ ሲዝለፈለፉበት በኪሱ ዱዲም ስላልነበረው አምርሮ አለቀሰና ዕድሉን ተራገመ – ክፍል ውስጥ፡፡ ያቺን ክፍለ ጊዜ ሳይጨርሳት የማስተማር ሥራውን ወዲያዉኑ በመተው ግቢውን ለቅቆ ወጣ፡፡ “አእምሮየ እንዲህ እየተሰቃዬ የምበላው እንጀራ በአፍንጫየ ይውጣ!” ብሎ የትሚናውን ሄደ፡፡ … በብዙ ትምህርት ቤት ያለው እውነታ ይሄው ነው – በብዙ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በወላጆችና መምህራን ተዘርግቶ ድሆች ልጆች ምሣ ይመገባሉ፡፡ እንደአጠቃላይ እውነታ ግን አብዛኛው ተማሪና ምግብ ተለያይተዋል፡፡ ወላጅነትና ልጅን በወግ በማዕረግ አሳድጎ መዳርና መኳል  ዐይንና ናጫ ሆነዋል፡፡ ዛሬ ያለው በዕድል ማደግ ነው፡፡ ወያኔዎች የትምህርትን ዋጋ ከዜሮ በታች ስላዋሉት ለመማር የሚተጋው ዜጋ ቁጥር እጅግ ጥቂት ነው – መስረቅና መዝረፍ፣ መቅጠፍና ማጭበርበር፣ በዘር ተቧደኖና በሃይማኖት ተደራጅቶ ሕዝብን መንጨት፣ በፎርጅድ ዲግሪ መምበሽበሽና በዚያም ያለተቆጣጣሪ በተለይ ባለቤት የሌለውን የመንግሥትን ሥራ መያዝ … እንደጽድቅ … እንደግምቢ ባህል እንዲታይ በመደረጉ ትውልድ ካላንዳች ቦምብና ጥይት … ካላንዳች መትረየስና ባዙቃ … ካለምንም የኒኩሌር መሣሪያ በወያኔያዊ ትውልድን የማምከን ትልቅ “ጥበብ” የሀገር ወረደ መቃብር እየተፈጸመ ነው – ልብ አድርጉ! የምነግራችሁ በስማ በለው ያገኘሁትን ሸፋፋ መረጃ ሳይሆን ራሴም በውስጡ ያለሁበትን እውነተኛ ሀገራዊ ዘግናኝ ክስተት ነው፤ ይህ ሥዕል አጠቃላዩ እውነተኛ የሀገር ምስል  ሲሆን እዚህና እዚያ ሊታዩ የሚችሉና የምገልጥላችሁን እውነት ሊያስተሃቅሩ የሚሞክሩ ተቃራኒ እውነቶች ቢኖሩ ከንፍሮ ጥሬ የማግኘት ያህል እንጂ ዋናውን ሀገራዊ ምስል አይለውጡም፡፡ እንጂ በቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ወይም በናዝሬት የሴቶች ትምህርት ቤት ከሚማሩ ልጆች መካከል ተስፋ የሚጣልባቸው ዜጎች አናገኝም ማለት አይደለም – እንዲያም ሆኖ ግን ከሞላ ጎደል የሁሉም ዜጋ ምኞትና ፍላጎት በተቻለው አቅም ሀገሪቱን በባሌ ወይም በቦሌ ለቅቆ መውጣት ስለሆነ እዚህ ላይ የምለው ነገር ሀገሪቷን ስለመጥቀሙ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ሁሉም ሰው በመንፈስ ሸፍቷል፤ ሰውነቱ ሀገር ውስጥ ቢገኝም ልቡ አውሮፓና አሜሪካ ነው፡፡ ደርግና ወያኔ ምሥጋን ይንሳቸውና ኢትዮጵያ የወላድ መካን ሆናለች፡፡ ነቃ ነቃ ያለው ዜጋ አንጋጦ ተስፋ የሚያደርገው የተስፋይቱን ምድር አሜሪካንን ነው፤ ኢትዮጵያን ከነመፈጠሯም ረስቷል፡፡ በወያኔና ወያኔን ከነሙሉ ትጥቁና የጥፋት ጓዙ ጃዝ ብለው ባሠማሩት ወገኖች ዘንድ የሚፈለገው ደግሞ ይሄው ነው፡፡ ኢትዮጵያን የማጥፋት ህልም አንግበው የተነሡ ታሪካዊ ጠላቶቿ በአሁኑ ወቅት ጽዋቸውን እያጋጩ እንደሆነ በምናቤ ይታዩኛል፡፡ ለማንኛውም ርሀብ ጊዜ አይሰጥምና ርሀቡን ብቻ ሣይሆን የርሀቡን መንስኤ ወያኔን በማጥፋት የጋራና የእኩል ሀገር እንድትኖረን እንጣር፡፡ የጸሎት ኃይል ከሁሉም ጦር ይበልጣልና ወደፈጣሪ ተመልሰን የተገፈፍነውን ፀጋ እንድንላበስ እንለምነው፡፡ በሰው ብቻ አንመካ፡፡ ሰው ደካማ ነው፡፡ ሰው ሟች ነው፡፡ ሰው ወዳቂና ሲለውም ውዳቂ ሆኖ የሚገኝ ዕቡይ ነው፡፡ ሰው ባስቀመጡት የማይገኝ ተንሸራታች ፍጡር ነው፡፡ ሰው ተለዋጭና ተለዋዋጭ  ነው፡፡ በጥቅም ይለወጣል፤ በአስተሳሰብና አመለካከት ይለወጣል፤ በዘርና በሃይማኖት ይሳባል፤ እናም ይለወጣል፤ ሰው ጤናማ አእምሮውን በተለያዩ አደጋዎችና አስገዳጅ ሁኔታዎች ሊነጠቅ ይችላል፡፡ ስለዚህ የምናምን ሰዎች ፈጣሪን የሙጥኝ ብለን እንጠይቀው፡፡ ለነሱ የሰጠውን ዲያብሎሣዊ አፍራሽ ኃይል ቀምቶ ለኛ መለኮታዊውን ግምቢ ኃይል ሊያጎናጽፈን ይችላል፡፡ ለቅጣት የታዘዙብን ዓመታት ሊያጥሩልን የሚችሉት በዐመፃ ተግባራችን በመቀጠል ሣይሆን ከነውር ተግባራችን በመመለስና በመፀፀት ለፈጣሪ ትዕዛዛት – ለጤናማ ኅሊና መርኆዎችም ጭምር – በመገዛት ነው፡፡  ሃይማኖት ባይኖረን እንኳን ክፉንና ደግን መለየትና ከሕጻናት የበለጠ ማሰብ የሚያስችለን ጭንቅላት ተፈጥሮ አድላናለችና ያን በመጠቀም ቀና ቀናውን እናስብ፤ እንመኝም፡፡

 

  • ኦሮምያ የሚባል ሀገር የለም – “ይሄኔ ነው መሸሽ!” የምትሉ አንባዎች እንደምትኖሩ ከቅርብ ጊዜው ውሽልሽል ታሪካችን በመነሣት መገመት አይከብደኝም – ግን እውነቱን መናገር ስላለብኝ ነው፡፡ ውሸት ከአሁን በኋላ በተለይ አይጠቅመንም፡፡ እያለባበሱ ማረስም አረሙ ሲወጣ መንቀሉ ዕዳ ነው፤ ሰውን በቃላት ማስደሰት ወይም ማሳዘን እንደሚቻል ግልጽ ነው፡፡ እውነትን በመሸፈን የሚገኝ ደስታ ግን ጊዜያዊና የጉሽ ጠላ ስካር የሚሉት ዓይነት ነው፤ በዚህ ውስጥ ብዙ ዳከርንበት – የተገኘ እውናዊ ለውጥ ግን የለም – ድፍን ግማሽ ምዕተ ዓመት ሆነን ሌባና ፖሊስ ስንጫወት፡፡ ለኔ ቁልጭ ብሎ እንደሚታየኝ ከአሁን ወዲያ ያለው የኢትዮጵያ ታሪክ የሚገነባው በመለማመጥና በይሉኝታ እንደማይሆን ስድስተኛው ሕዋሴ ይነግረኛል፡፡ ለማንኛውም የፈለግኸውን ስም ልትሰጠኝ ትችላለህ፡፡ አማሪያም ሆነ ትግሪያ የሚባል ሀገርም የለም፡፡ ይህን እውነት ማንም ወገን ሊረዳ ይገባዋል፡፡ ጠላት በቀደደልን ቦይ እየፈሰስን የሀገራችንን ቁስል አናነፍርቅ፡፡ እርግጥ ነው ሁሉም በጊዜው መስተካከሉ የማይቀር እንደሆነ መጠቆሙ የዐዋጅን በጆሮ እንደመንገር ነው፡፡ ዛሬ በዘረኝነት አበሾ አዳሜ ሰክሮ ቢወላገድ ነገ ጧት እውነት ቦታዋን ስትይዝ በስካራችን ጡዘት ባደረግነው ጠያፍ ተግባር እንጸጸታለን፡፡ ስለዚህ ከትዕቢትም በሉት ከዕብሪት መቆጠብና ወደኅሊና መመለስ ተገቢ ነው – ብዙም ሳይረፍድ፡፡ “ፍቅር ያዘኝ ብለሽ አትበይ ደምበር ገተር፤ እኛም አንድ ሰሞን እንዲህ አር’ጎን ነበር” የሚሏትን ባህላዊ ግጥም ማስታወስ ይገባል፡፡ አንዳንድ ሰው ይገርመኛል – ቀፎ ነው፡፡ የራሱ የሚለው የሌለው የገደል ማሚቶ ነው፡፡ ቀድሞውንም ቢሆን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ያሤሩና ለጊዜው የተሣካላቸው የሚመስሉት ታሪካዊ ጠላቶቻችን በቤተ ሙከራቸው እየፈበረኩ በሚያከፋፍሉን ሀገር አፍራሽ ዘይቤ መጠለፍ አልነበረብንም፤ በየትም ሀገር እንደሚታየው ሁሉ በመካከላችን በደልና ጥፋትም እንኳን ቢኖር እርስ በርስ መተራረም እንጂ የጋራ ጎጆን ነቅንቆ እስከማፍረስ ወደሚደርስ የጠላት ተንኮል ልባችንንና መላ ትኩረታችንን መስጠት አይገባንም ነበር – “ይሁን ግዴለም”ን በዘለለ ሰቅጣጭ ሁኔታ አንዴ ተሳስተናል፤ ከአሁን በኋላ ግን መሳሳት አይኖርብንም፡፡ ነገር ግን አያርመን ብሎ – ለመብል መጠጥም ይሁን ለልዩ ዓላማ ስኬት ብለን በስህተታችን ብንቀጥል የእስከዛሬው ሞኛሞኝ ታሪክ አይደለም የሚበቀለን – እኛ ታላላቆች በፈጠርነው እሳት ክፉኛ የተለበለበውና መቆሚያ መቀመጫ ያሳጠነው ቀጣይ ትውልድ ድራሻችንን ከማጥፋት አይመለስም፡፡ ባሏን የጎዳች መስሏት የገዛ ሰውነቷን በጋሬጣ እንደቧጨረችው ገልቱ ሴት ሆነን በተለይ ላለፉት 25 ዓመታት ራሳችንን በጦርና በጎራዴ ስንመትር ቆየን፡፡ አሁን አይበቃንም ታዲያ? ምን እስክንሆን ነው የምንጠብቀው? በዚህች አንቀጽ አነሳሴ ኦሮሚያ የሚባል ሀገር የለም የሚል ነበር፡፡ ይህ ስያሜ መቼና በማን እንደተፈጠረ ፣ ለምን ዓላማ እንደተፈጠረ … ብዙ ስለሚያናግር አንገባበትም፡፡ ለምን ወደዚህ ርዕሰ ጉዳይ እንደገባሁ የሚጠቁም አንድ ትዝብት ግን ላስቀምጥ፡-

በቅርብ ጊዜ ነቀምት ላይ አንድ ሠርግ ላይ ተገኘሁ – በተዛዋሪ፡፡ አስገራሚ ሠርግ ነው፡፡ በዚያ ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች በታደሙበት ሠርግ ላይ አንድም የዐማርኛም ሆነ የትግርኛ ወይም የሌላ ብሔር/ብሔረሰብ ሙዚቃ እንዲዘፈን አልተደረገም ማለትም አልተፈቀደም፡፡ አለመዘፈኑ የምርጫ ጉዳይ ስለሆነ ምንም አይደለም ሊባል ይችላል፡፡ መጥፎነቱ ግን መልእክቱ ነው፡፡ አንጀት በጣሽ መልእክት ነው የተላለፈው በዚያ ሠርግ – የማዕቀቡም ዋና ዓላማ ይሄው ነው፡፡ ሕዝብን ከሕዝብ ማቆራረጥ ነው ዓላማው፡፡ ያን ያደረገው አንድ ወይ ሁለት ሰዎች ቢሆኑ ነው፡፡ እነዚያ ሰዎች ጥረታቸው የኦሮሚያን ኑባሬ ማግነንና ሌሎችን ማስረሳት ወይም ማስጠላት ነው፡፡ በዚያ ሠርግ ላይ “ሙሽራየ” ወይም “አምሯል ሸገኑ” ቢዘፈን “ኦሮሚያ” አትዋረድም ወይም አይዋረድም – በምን ፆታ እንደሚጠቀሙ አላውቅም – የጀርመን ተፅዕኖ ካለባቸው ወንድ መሆን አለበት(በነገራችን ላይ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ኦሮሞ ያልሆነ ሰው ይኖር ይሆን? ዐይናችሁን ጨፍኑና እስኪ ለጥቂት ጊዜ አስቡ፡፡ እናሳ የቱ ነው ኦሮሚያ የቱስ ነው “ኢምፓየሩ”? “ሲነጋ ለማፈር!” አሉ እመት ብርጣሉ!)፡፡ የሆኖ ሆኖ ያ የጉሽ ጠላ ጰራቅሊጦሳዊ የዘፈን ዕቀባ ስሜታዊ እንጂ ምክንያታዊ እንዳልነበር አንዳንዶች አጉርምርመዋል፤ በዚህ መልክ የትም አይደረስም፤ ሰውን በፍቅር ልታቀርበው እንጂ በጥላቻ ልታርቀው አይገባም፡፡ የዘመናት የታሪክ ሽመና የተሣሠረን ሕዝብ በዘመን አመጣሽ ወያኔያዊ ሽብልቅ መሰነጣጠቅ እንደማይቻል እፍኝ የማይሞሉ ነውጠኞችን ሣይሆን  የብዙኃኑን መስተጋብራዊ ሕይወት በመመልከት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ በተረፈ ዝርዝሩን በነገይቷ ከወያኔና መሰል ጎጠኞች ነፃ የሆነች ኢትዮጵያ በግልጽ የምናየው ይሆናል፡፡ (በነገራን ላይ አዲሲቱ “የጎረቤት ሀገር” ኤርትራ ላይ –  አሥመራ ውስጥ ከአሥር ዘፈኖች ሁለትና ሦስቱ ዐማርኛ መሆኑን በኢሳት አንድ ዝግጅት ተረድተናል፡፡ ስለዐማርኛ የተቆረቆርኩ እንዳይመስላችሁ – ስለኢትዮጵያ እንጂ፡፡ ዐማርኛ ደግሞ የዐማሮች ቋንቋ ሣይሆን የኢትዮጵያውያን ነው፡፡ ዐማርኛን መናቅ ኢትዮጵያን መናቅ ነው – ዐማሮችማ ከታወጀባቸው ዘርን የማጽዳት ወያኔያዊ ዐዋጅ ገና መቼ ተላቀቁና ስለቋንቋ ጉዳይ ይነጋገራሉ? “ጽድቁ ቀርቶብኝ…” እንዲሉ ነው፡፡)

ለነገሩ ምን ብዙ አስለፈለፈኝ? እንዲያው ተናደድ ቢለኝ እንጂ ሁን ያለው ከመሆን አይዘልም፡፡ ሁሉም ግን ሆኖ ያልፋል እንጂ እንደሆነ አይቀርም፡፡ መሆንና አለመሆን የሞትና የሕይወት ያህል ቁርኝት ያላቸው ጓደኛሞች ናቸው፡፡ ይህ ጉድፋምና ዕድፋም ዘመን ወደታሪክ ጥቁር መዝገብ ሊገባ የቀረው ጊዜ በጣም ኢምንት መሆኑ ያስታውቃል – እጅግ ምናልባት ከአምስት ዓመት በታች! የጨለማው ዘመን ሲያልፍ ወርቃማው ዘመን ይብታል፡፡ ካልሞትን ያኔም እንገናኛለን፡፡

 

ልብ አድርጉ! “የናቁሽ ሁሉ እግርሽ ሥር ተደፍተው ይሰግዱልሻል” የተባለው በሥውር ለኢትዮጵያም ነው፡፡ አሁን መናገር አልፈልግም፡፡ ግን ኢትዮጵያን የሚሠሩ ጀግኖች ታዘዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ይበሠራል፡፡ ልዑል እግዚአብሔር እንደተደበቀ የቀረበት የመከራ ዘመን በየትም ሀገር አልታየም፤ ችግሩ የርሱ የጊዜ ቀመርና የኛ የምድራውያን ሰዎች የጊዜ ቀመር በእጅጉ መለያየቱ ነው፡፡ በሌላም በኩል ችግሩ የኛ ወደርሱ ከልብ አለመቅረብ ነው፡፡ ሰውነታችን ቤተክርስቲያን ደጅ ተነጥፎ ያረፍዳል – አብዛኞቻችን ግን እንዴት እንደ፣ጸለይ እንኳን አናውቅም፡፡ በደለን የምንለውንና የምንጠላውን ሰው “ልቡን አራራልኝ” እንደማለት “በወር ውስጥ ደፍተህ ተዝካሩን አብላኝ!” እንላለን፡፡ ጌታ ስንቱን ደፍቶ ይጨርሰው? ለቁልቢ ገብርኤል በስለት ቅማልና ዐይጥ ይዘን እየሄድን ከፈጣ ጋር እንዴት ዕርቅ ልንፈጥር እንችላለን? እረኞቻችንስ በዚህ በመከራ ዘመን የት አሉ? ዋናው እረኛ የዲያብሎስ አሽከር የሆነበት ምክንያት ከዘላለማዊው የእግዚአብሔር መንፈስ ይልቅ አላፊና ጠፊው የሥጋ ፈቃዱ የዘረኝነት ሰይጣናዊ ልማዱ በልጦበት አይደለምን? ያሣፍራል፡፡ ለዚህም ነው ቫቲካንን ጨምሮ ብዙዎቹን የሃይማኖት ተቋማት የጥልቁ ባሕር ገዢ በእጅ አዙር እንደተቆጣጠራቸው የሚነገረው፡፡ በዚህ ሁኔታ ፈጣሪ ፊቱን ባይመልስልን እንዴት ልንፈርድበት እንችላለን ታዲያ? በቆሻሻ ቱቦ ውስጥ ንጹሕ ውኃ ሊያልፍ አይገባም፤ በቆሸሸ ልብ ውስጥ ፈጣሪ ማደሪያ ቤት አያዘጋጅም፡፡ ስለዚህ ጥፋቱ በዋናነት ከኛው ነው፡፡ “ቤታቸውን ክፍት ትተው ሰው ሌባ ይላሉ” ይላሉ ወጣቶች በአዲስ ተረታቸው፡፡ እውነት ነው፡፡

ለማንኛውም ያልታመመ ጤነኛ፣ ያልሞተ በሽተኛ፣ ያልደኸዬ ከበርቴ፣ ያላረጀ ጎረምሣ፣ ያልመለጠ ጎፈሬ፣ ያልሸበተ ኮበሌ፣ ያልጎበጠ ሸበላ፣ ያልከሰመ ወዘና… በየአካባቢያችሁ ፈልጉና ካገኛችሁ በርግጥም ኢትዮጵያም እንዲህ እንደሆነች ትቀራለች ብዬ ልመናችሁ፡፡ የነገ ሰው ለመሆን ከወረት ንፋስ፣ ከዘመን አንከሊስ ራሳችንን እንጠብቅ፡፡ የስሜት ፈረስ የትም እንደማያደርስ እንገንዘብ፡፡ ከሁሉም ከሁሉም “አገባሻለሁ ያለሽ ላያገባሽ፤ ከባልሽ ሆድ አትባባሽ” የምትለዋን ነባር ምሣሌያዊ ብሂል አንርሣ፡፡ ከሁሉም በበለጠ “ሟች ይዞ ይሞታል” እንዲሉ ወያኔ ወደግባተ መሬቱ ሲጠጋ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ መዘንጋት አይገባንም፡፡  የነጋበት ጅብም ያገኘውን እየጠረገ ይሞታል እንጂ እንዲሁ እጅ አይሰጥም፡፡ ወያኔም መሞቱ ለማይቀረው ብዙ ጥፋት እንደሚያስከትል የታወቀ ነው፤ እልኽና ቁጪት ውስጥ ሲገቡ መናገር የሚከብድና የማያስፈልግም ወንጀል እንደሚሠሩ መገንዘብ አለብን፤ ላለመሞት የሚንፈራገጥ አንድ ነገር ያልታሰበ ጥፋት እንዳያስከትል መጠንቀቅ ብልህነት ነው፤ “ዐይቡን ሳያዩት አጓቱን ጨለጡት” ይባላልና በተለይ ያን ደግና ሩህሩህ የትግራይ ሰፊ ሕዝብ ከወያኔዎች አፍራሽ ተልእኮ በመነጠል እነዚህ ጉዶች ብቻ ለተገቢው የታሪክ ፍርድ እንዲጋለጡ ከጀግኖች ኢትዮጵያውያን ብዙ የአስተዋይነት ሥራ ይጠበቃል፡፡ ደም ደምን እንደምትጠራ የታወቀ ነው፡፡ ፍቅር ግን ሁሉንም ታሸንፋለች፡፡ እናም በሁሉም ረገድ ጥንቃቄና ብልሃት የተሞላበት ትግል ማካሄድ ተገቢ ነው፡፡ … ሌሊት ነው የጻፍኩት – አሁን ገና ከማለዳው  12፡05 ሆነ፡፡ አይዞነ – ይህን ነገር የጻፍኩት በምንም ተፅዕኖ ሥር ሆኜ አይደለም፤ እግዚአብሔር ግን ከጎኔ እንደነበር በፍጹም ልቤ አምናለሁ – ከእምነት ውጪ የሚጨበጥ ማስረጃ ላቀርብላችሁ ባለመቻሌ ደግሞ አዝናለሁ፡፡ ደከመኝ…

 

አባይ ወዲያ ማዶ ዘመድ አለኝ ማለት፤

ዋ! ብሎ መቅረት ነው አባይ የሞላ’ለት፡፡

በኤርትራ በስልጠና ላይ የነበሩ ወታደሮች ሊያመልጡ ሲሉ ተተኮሰባቸው

0
0
ፋይል ፎቶ - የኤርትራ ወታደሮች በአስመራ ከተማ እ.አ.አ. 2007

ፋይል ፎቶ – የኤርትራ ወታደሮች በአስመራ ከተማ እ.አ.አ. 2007

(ዘ-ሐበሻ) የአስመራ ከተማ ባለፈው እሁድ ኤፕሪል 3, 2016 ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ዘገበ:: ራድዮው ምንጮቹን ጥቅሶ ባሰራጨው መረጃ በወታደራዊ ስልጠና ላይ የነበሩ ወጣቶች በወታደራዊ መኪኖች ተጭነው ያልፉ በነበረበት ወቅት አንዳንዶቹ ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ ተከፍቶባቸው ነበር::

በተኩሱና ተያይዘው በደረሱ ጉዳቶች የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ በተለያዩ የተቃዋሚዎች ሚድያ እየተገለጸ ነው ያለው ራድዮው ስለሞቱትም ሆነ ስለቆሰሉት ሰዎች በነጻ ምንጭ ማረጋገጥ አልቻልኩም ብሏል::

የኤርትራ ባለስልጣናትም እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አልሰጡም::

“አማራው፣ ኦሮሞውና ትግሬው አንጋፋ ብሔር በመሆናቸው 86ቱን ብሔረሰቦች መጠበቅ አለባቸው”| Video

0
0

የመዠንገር ኮምዩኒቲ መሪ አቶ ቢያንያም በንቲን ንግግር ቢያደምጡት አይቆጩበትም:: “አማራው; ኦሮሞውና ትግሬው አንጋፋ ብሔር በመሆናቸው 86ቱን ብሔረሰቦች መጠበቅ አለባቸው” ይለናል:: እንዴት ወደ ሰላም እና አንድነት መምጣት እንዳለብን ከመዠንገር ሕዝብ ተሞክሮ አኳያ ያዋየናል… ያድምጡት::

“እኛ ለኛ ሕዝባዊ መድረክ!” በሚል ባለፈው ቅዳሜ በሚኒሶታ በተደረገው የኢትዮጵያ የዕርቅና ርትዓዊ ፍትሕ ምክርቤት የመነጋገር፤ መተማመን፤ መተራረቅ ስብሰባ ላይ ነው አቶ ቢኒያም ይህንን ንግግር ያደረገው::

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም ከቢቢኤን ጋር

0
0

BBN

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም ከቢቢኤን ጋር

በድርቁ ምክንያት ከሰቆጣ ወደ ደብረብርሃን የሰፈሩ ወገኖች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተነገራቸው

0
0

Zehabesha News
በድርቁ ምክንያት ከሰቆጣ ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ውስጥ የሰፈሩ ከ250 አስከ 300 የሚሆኑ ዜጎች በዛሬው እለት በደብረ ብርሃኑ መስተዳድር ወደመጡበት እንደሚመለሱ ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ታወቀ::

ስደተኞቹ ወደ መጡበት ከተመለሱ ለእነሱም ሆነ ለልጆቻቸው የሚጠብቃቸው ሞት እንደሆነ በመግለፅ ለወገን የድረሱልን ጥሪ አስተላልፈዋል።

የደብረ ብርሃን ህዝብ ስደተኞቹን በአቅሙ ለመርዳት የበኩሉን ጥረት እያደረገ ሲሆን ሕወሓት የሚመራው መንግስት ቀጭን ትዕዛዝ በስደተኞቹ ላይ በተላለፈው ኢ-ሰብአዊ ውሳኔ ክፉኛ ልቡ መሰበሩን ከአካባቢው ከስፍራው እየመጡ ያሉ መረጃዎች ጠቁመዋል።

የመላው አማራ ህዝብ ለእነዚህ ሞት ለተፈረደባቸው ወገኖቹ ድምፅ በመሆን በነፍስ እንዲደርስላቸው የአማራ ሕዝብ አክቲቭስቶች እንቅስቃሴ ጀምረዋል::


ዐማራው ከወልቃይት፣ጠገዴ እና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄ ጎን ሊቆም ይገባዋል! –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት     

0
0

 ረቡዕ መጋቢት 29 ቀን 2ሺህ8 ዓ.ም                         ቅጽ 4 ቁጥር  12

moreshየማንኛውም አመፅ መነሻ መሠረቱ፣ ገዥዎች በሕዝብ ላይ የሚያደርሱት፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛ፣ የመብት ረገጣ፣ የማንነት ነጠቃ እና የሥነ-ልቦና ሰለባ ልኩን አልፎ ገደብ ሲጥስ የሚፈጥረው ምሬት እንደሆነ ይታወቃል። የትግሬ ወያኔ ዘረኛ እና ከፋፋይ የፋሽስት ሞሶሎኒ ዓላማ አራማጅ ቡድን፣ በወልቃት ፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት እና በአርማጭሆ ሕዝብ ላይ በተናጠል፣ እንዲሁም  በዐማራው ነገድ ላይ በወል፣ ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ከ1972ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 36 ዓመታት በተከታታይ ፈጽሟል፤ እየፈጸመም ነው። በዚህ ረገድ የወረዳ ግዛቶቹም ሆኑ ነዋሪው ሕዝብ በየትኛውም ጊዜ፣ የትግራይ የግዛት አካል ሆነው አያውቁም። የትግሬ ግዛት ደንበርም ተከዜን ተሻግሮ አያውቅም። ሕዝቡም ጥንትም ሆነ ዛሬ፣ በጉርብትና ከሚናገረው ትግርኛ፣ ዐረብኛ እና መሰል ቋንቋዎች በቀር፣ የትግሬነት ባህል፣ ታሪክ፣ ወግ፤ ሥነልቦና እና መሰል የማንነት ማረጋገጫ ዕሴቶች ኖሮት አያውቅም፤ እንዲኖረውም አይሻም።

የትግራይ ሕዝብ በተከታታይ በድርቅ እና በርሃብ ሲጠቃ እየፈለሰ የተጠጋው በእነዚህ የሰሜን ጎንደር ወረዳዎች ነው። ስለዚህ በድርቅ እና በርሃብ ምክንያት ከትግራይ የሚሰደዱት ሰዎች ኑሯቸውን ሲደጉሙ የኖሩት በቀን ሠራተኝነት እየተቀጠሩ የወልቃይቶችን የሠሊጥ እና የማሽላ አዝመራ በማረስ፣ በማረም እና በመሰብሰብ እንደነበረ የቅርብ ዘመን ትውስታችን ነው። ሆኖም፣ «እንግዳ ሲሰነብት፣ ባለቤት የሆነ ይመስለዋል» የሚሉት አባባል ዕውነት ሆኖ፣ የዐማራው ነገድ ባለው የእንግዳ ተቀባይነት የዳበረ ባህሉ ተቀብሎ ባስተናገዳቸው ሰዎች የውስጥ አርበኝነት፣ ወያኔ ዐማራን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት ላደረገው ዝግጅት፣ የጥቃቱ የቅድሚያ ሰላባ የሆነው በነዚህ ወረዳዎች ይኖሩ በነበሩ ዐማሮች ላይ እንደነበር በተደጋጋሚ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።  በዚህም መሠረት በወልቃይት ፣ በጠገዴ ፣ በጠለምት ፣ በሠቲት እና በአርማጭ ሕዝብ ላይ የትግሬ ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ከፈጸማቸው እጅግ የበዙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች መካከል የሚከተሉት ለናሙና ያህል የቀረቡ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።

ሀ)         በ1972 ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ የትግራይ እና የጎንደር ክፍለ ሀገሮች የተፈጥሮ ወሰን የሆነውን የተከዜን ወንዝ ተሻግረው የሚከተሉትን ያገርዘቦች በግፍ ገደሉ። እነዚህም፦

  1. አቶ ማሞ ዘውዴ፣
  2. አቶ እንደሻው ታፈረ፣
  3. አቶ አያሌው ሰሙ፣
  4. አቶ በርሄ ጎይቶም፣
  5. አቶ ሐጎስ ኃይሉ፣
  6. አቶ  ልጃለም ታዬ፣
  7. ግራዝማች ወልዴ የኔሁን፣
  8. ቄስ በለጠው ተስፋይ፣
  9. ቄስ ትዕዛዙ ቀለመወርቅ፣
  10. ቄስ አለነ ቀለመወርቅ፣
  11. ወጣት ግዛቸው ዳኜው፣
  12. ወጣት አዲስይ ልጃለም፣
  13. ወጣት ደረጀ አንጋው፣
  14. ወጣት ዋኘው መንበሩ፣
  15. ወጣት ሕይዎት አብርሃ፣
  16. ወጣት ታደለ አዛናው፣
  17. ወጣት ማሞ አጀበ ናቸው።

ለ)         በ1986 ዓ.ም. «ርዋሳ» የተባለውን ከ500 በላይ ቤቶች የነበሩበትን የገበሬ መንደር አቃጥለው ትግሬ አሰፈሩበት። በዚህ ቀበሌ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎለከፍተኛ ችግር ከተጋለጡት መካከል አቶ ጫቅሉ አብርሃ፣ አቶ አብርሃ ሣህሉ፣ ወይዘሮ ስንዱ ተስፋይ፣ አቶ ዋኜው ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ሐ)        ከ1988 እስከ 1989 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ከ3,000 (ሦስት ሺህ) በላይ ጥማድ በሬዎች ባለቤቶች የነበሩ ገበሬዎችን ገድለውና አሰድደው ትግሬአስፍረውበታል። ሠፈራ የተካሄደባቸው ቦታዎችም ማይደሌ፣ አንድ አይቀዳሽ፣ እምባ ጋላይ እና ትርካን ናቸው።

መ)        ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ ማይ ኽርገጽ፣ ቤት ሞሎ፣ ማይ ጋባ፣ ቃሌማ፣ እጣኖ፣ መጉዕ ወዘተ ይኖሩ የነበሩ ነባር የዐማራ ነገድ ተወላጆችን አባረው ትግሬንአስፍረዋል። በአጠቃላይ በጎንደር ለም መሬቶች ከ500,000 (አምስት መቶ ሺ) በላይ ትግሬ እንዲሰፍር ተደርጓል።

ሠ)        የትግሬ-ወያኔዎች ዐማራዎችን የጎንደር ክፍለሀገር ተወላጆችን አደህይተው እና አዋርደው፣ ከሰው በታች አድርገው ይገዛሉ። በአካባቢው የትግሬን የበላይነትአስፍነው ቀጥቅጠው እና አዋርደው ለመግዛት እንዲያመቻቸው የአካባቢውን ታዋቂ እና ባለሀብት ሰዎች አስረዋል፣ ገድለዋል፣ ሀብት ንብረታቸውን ዘርፈዋል። በዚህረገድ ለአብነት ከሚጠቀሱት መካከል የሚከተሉት አዛውንቶችን የቁም ከብቶቻቸውን መዘረፋቸውን የወልቃይት ጠደገዴ ተወላጆች ያስረዳሉ።

  1. ከአቶ ዘነበ ሐጎስ ከ450 ባላይ የቀንድ ከብቶች ዘርፈዋል፤
  2. ከአቶ ባየው ቢያድግልኝ ከ600 በላይ ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈው በመጨረሻም ባለሀብቱን ገድለዋቸዋል፤
  3. ከአቶ ገብረሕዎት ኃይሌ ከ80 በላይ የቀንድ ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈዋል፤
  4. በ1981 ዓ.ም. ከአቶ አለባው ሕደጎ ከ500 በላይ የቀንድ ከብቶች እና በርካታ ኩንታል እህል ተዘርፏል።
  5. የቀኛዝማች ገብሩ ገብረመስቀል 24 በሬዎቹ ታርደው ከ900 መቶ ባላይ ማድጋ እህል ተወርሷል።

ረ)         የካቲት 21 ቀን 1972 ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔ የቃብትያ አዲህርድ ከተማን ለመቆጣጠር በነዋሪው ላይ በከፈተው ጦርነት 9(ዘጠኝ) ሰዎችን ገድሎ 18(አሥራስምንት) ማቁሰሉን የዓይን እማኝ የሆኑት ተሰደው በብሪዝበን ከተማ፣ አውስትራሊያ፣ ነዋሪ የሆኑት አቶ ፈረደ ያስረዳሉ። በዚያ በትግሬ-ወያኔ እና በነዋሪው መካከልበተደረገው ጦርነት ከሞቱት እና ከቆሰሉት መካከል ስማቸውን ማስታወስ የተቻለው የሚከተሉት ይገኙበታል።

  1. አቶ የልፋዓለም ተኮላ፣ ዕድሜ 65፣
  2. አቶ ጎኦይ መብራቱ፣ ዕድሜ 30፣
  3. አቶ አለነ ክንድሽ፣ ዕድሜ 60፣
  4. አቶ አታላይ አበራ፣ ዕድሜ 64፣
  5. አቶ ባሕታይ ወንድምአገኘሁ፤
  6. አቶ በለጠ ወንድምአገኘሁ፤
  7. አቶ በየነ ያዕብዮ፣ ዕድሜ 70፣
  8. አባ ኃይሌ፣
  9. አቶ ገብሩ ጋሼ፣ ሲሆኑ

ከቆሰሉት መካከል ደግሞ፦

  1. አቶ አሰፋ ገብረመድኅን፣
  2. ሙላው ኃይሌ (አለቃቸው ኃይሌ)፣
  3. አቶ መብራቱ ዋሴ፣
  4. አባ ጎላ ዘለለው፣
  5. አቶ አነጋው ገብረእግዚአብሔር፣
  6. አቶ አበራ አጀቢ፣
  7. አቶ ጥሩነህ ከሰተ፣ እና
  8. አቶ ፈቃዱ ይገኙበታል።

ሰ)         ነሐሴ 10 ቀን 1972 ዓ.ም. ወያኔ ከወልቃይት እና ከጠገዴ ወረዳዎች አስሮ የወሰዳቸው እና እስካሁን የደረሱበት ያልታወቁ የአገር አዛውንቶች የሚከተሉትናቸው።

  1. አቶ ሞላ ዘውዴ፣
  2. አቶ ተበጄ በቀለ፣
  3. አቶ አያሌው ሰሙ፣
  4. አቶ እንደሻው ታፈረ፣
  5. አቶ እሸቴ አያልነህ፣
  6. አቶ ጎኢቶም ሐጎስ፣
  7. አቶ በርሄ ሐጎስ ታፈረ፣
  8. አቶ በየነ አየልኝ፣
  9. አቶ ኃይሉ ልዩነህ፣
  10. አቶ አብርሃ ነጋ፣
  11. አቶ አለባቸው መብራት፣
  12. አቶ ድራር ገሠሠው፣
  13. አቶ ገብረሥላሴ ረዳ፣
  14. አቶ ገብረሕይዎት ባሕታ፣
  15. አቶ ኃየሎም ይርጋ፣
  16. አቶ አለባቸው ደፈርሻ፣
  17. አቶ ሊላይ ሐድጎ፣
  18. አቶ ጎኢቶም ምህረት፣
  19. አቶ ታገለ ወርቄ፣
  20. አቶ መሓሪ አዱኛ፣
  21. አቶ ባየው ቢያድግልኝ፣
  22. አቶ ሢሣይ ዘነበ፣
  23. አቶ አታላይ ዘነበ፣
  24. አቶ ተፈራ ሊላይ፣
  25. አቶ ገብረመድኅን የኋላ፣
  26. አቶ ነጋሺ ተበጄ (አራት አንበሣ ገዳይ የነበረ ጀግና፣ ሆኖም በመኮንን ዘለለው የታፈነ)
  27. ወጣት ግፋባቸው ዳኛቸው፣
  28. አቶ ጌትየው ታምሬ፣
  29. አቶ ርስቀይ ኃይሌ፣
  30. አቶ ተድላ ርስቀይ፣
  31. ቄስ ትዛዙ ቀለመወርቅ፣
  32. ቄስ አለነ ቀለመወርቅ፣

በአጠቃላይ ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ የትግሬ-ወያኔ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት እና በሠቲት ወረዳዎች ዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ግድያ፣ አፈና እና ደብዛ ማጥፋት እጅግ ብዙ ትላልቅ ጥራዞች እንደሚሆን ይታመናል። ሆኖም ሞረሽ-ወገኔ ካሰባሰባቸው መረጃዎች መካከል ለአብነት የሚከተለው ሠንጠረዥ በዝርዝር ቀርቧል።

 ሠንጠረዥ፦ በወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች ላይ ወያኔ ግፍ የፈጸመባቸው ሰዎች በከፊል፣

ይህ ሁሉ ወንጀል እየተሠራ ያለው በሁለቱም መሪዎቻችን ግፊት ነው! –ምሕረቱ ዘገዬ

0
0

በተለይ ካለፉት 25 ዓመታት ወዲህ ዓለምን የሚያስደምም ወንጀል በሀገራችን ውስጥ እየተሠራ ይገኛል፡፡ በዓለማችን የእስካሁንም ይሁን የወደፊት ታሪክ በፍጹም ያልታዬና ሊታይም የማይችል ወንጀል ወያኔ ትግሬዎች እንደልባቸው እየሠሩ ናቸው፡፡ እነዚህ በጣት የሚቆጠሩና የዋናው ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ቡድን አባላት የሆኑ ጥቂት ትግሬዎች እየሠሩት ያለውን የከፋና የከረፋ ወንጀል ሁለቱም መሪዎቻችን በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ነገር ግን ሁለቱም መሪዎቻችን እልህ የተጋቡና አንዳቸው በአንዳቸው ጣልቃ ላለመግባት የወሰኑ ይመስላል በድርድርም ይሁን በመሸናነፍ ቅራኔያቸውን አስወግደው እኛን ሰላም ሊሰጡን አልቻሉም ወይም ምናባልት ጊዜው ገና ነው፡፡ የዝኆኖች መራገጥ ለሣር እንደማይበጅ ሁሉ እኛም በነሱ ሰበብ እየተደቆስን አለን፡፡

እነዚህ ሁለት መሪዎች የሰማይና የምድር ጌቶች ናቸው፡፡ የሰማዩ ጌታ በኔ ግንዛቤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሲሆን የምድራችን የወቅቱ ገዢ ደግሞ የ13 ቁጥር እመቤት ልዕልት አሜሪካ ናት፡፡ ሁለቱ ናቸው ዓለምን የፊጥኝ አስረው በፉክክር አሣራችንን እያበሉን የሚገኙት፡፡ በነዚህ በሁለቱ መሪዎቻችን ፊትና ግፊት ነው እንግዲህ ከዚህ በታች የምገልጸው ወንጀል በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተፈጸመ የሚገኘው፡፡

ሰሞኑን ወደ ማርካቶ የምሄድበት ጉዳይ ነበረኝ፡፡

ከማርካቶ በፊት ወደ ጎንደር ጎራ ልበል መሰለኝ፡፡ ጎንደር ክፍለ ሀገር ውስጥ ወልቃይትና አካባቢው ቀደም ካለ ጊዜ ጀምሮ ወያኔ ከትግራይ በርካታ ትግሬዎችን እያመጣ በመሰግሰግ የሕዝቡን አሰፋፈር እየለወጠው እንደነበረ የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ ጎንደሬውን ወልቃይቴ በማንኛውም ዘዴ ከአካባቢው እያፈናቀለና በግልጽም በሥውርም እንደዐይጥ ጨፍጭፎ እየገደለ  የጎንደርን ነባር ይዞታዎች በትግሬ መሙላቱና የጎንደርን መሬት ወደትግራይ ክልል በጉልበት ማካተቱ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ ያልሆነ ሰው ሠራሽ የሕዝብ አሰፋፈር አሁንና ዛሬ ብቻ ሣይሆን ነገና ከነገ ወዲያ ምን ዓይነት ሀገራዊና ክልላዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ዕድሜ የሰጠው ኋላ ላይ የሚያየው መሆኑ እንዳለ ሆኖ በወያኔ ሤራ እየተከናወነ ያለው አጠቃላይ ወንጀል ሲዳሰስ ግን ነውረኛ ድርጊቱ በአንድ አካባቢ ብቻ የተወሰነ ሣይሆን መላ ሀገሪቱንና የፌዴራል ተብዬውን የይስሙላ መዋቅር ሁሉ በስፋት የሚያዳርስ ትልቅ የክፍለ ዘመኑ ወንጀል ሆኗል፡፡

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የሥራ አቀጣጠር ስናይ ትግሬ ዜጋ አጥተው ካልሆነ በስተቀር ሌላውን በምንም መንገድ ሥልጣንና የጥቅም ቦታ ላይ እንደማያስቀምጡና ሀገሪቱ የትግሬዎች ጥገት መሆኗን ከመነሻው እናውቃለን፡፡ እነሱ ሀፍረትና ይሉኝታ ባለማወቃቸው እኛው ስለነሱ እየተሸማቀቅንና አንገታችንን እየደፋን መኖር ከጀመርን 25 ዓመታችን ሆነ፡፡

የትግሬዎች ቁጥር ከኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር አንጻር ሲሰላ ዱሮ 6 በመቶ ነበር፡፡ አሁን ምናልባት ሌላውን በተለይም ዐማራውን እያመከኑና በሚችሉት ሁሉ እየጨፈጨፉ ስላሳነሱት፣ በሌላም በኩል የነሱን ዘር በሌሎች ላይ ለማንገሥ ባላቸው ቁርጠኝነት የተነሣ የወሊድ መከላከያ የሚባል ሲያልፍ አይነካቸውም ስለሚባል ያ አኃዝ ዛሬ ላይ ተለውጦ 10 በመቶ ሆነዋል ብንል ከዚህ አጠቃላይ ሕዝብ የወጡ ጥቂት ወራሪዎች ናቸው ከነጀሌያቸው የመላዋን ኢትዮጵያ ሀብትና ሥልጣን በግል ተቆጣጥረው የሚገኙት፡፡ ይህ በጣም የታወቀና ፀሐይ የሞቀው እውነታ ስለሆነ ወደ ዝርዝሩ መግባት አስፈላጊ አይደለም፡፡

እንጂ በተለይ አመራርን በሚመለከት ጦሩን ሙሉ በሙሉ፣ ደኅንነቱንና ፖሊሱን ሙሉ በሙሉ፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ፣ ሕይወት (እስትንፋስ) ባይኖራቸውም ፍርድ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ፣ የክልል መንግሥታት ተብዬዎችን ሙሉ በሙሉ፣ የልማት ፕሮጀክቶችን ሙሉ በሙሉ፣ የማዕድንና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብት ምንጮችን ሙሉ በሙሉ፣ የመንግሥት ተቋማትን ሙሉ በሙሉ፣ የገቢና ወጪ ንግዶችን ሙሉ በሙሉ፣ እርሻና ኢንዱስትሪን ሙሉ በሙሉ፣ ሪል እስቴትና ቤት ግንባታን ሙሉ በሙሉ፣ የመሬት አስተዳደርን ሙሉ በሙሉ፣ ማዘጋጃና ከፍተኛን እንዲሁም የወረዳ አስተዳድርን (በጭምብል እንደራሴዎቻቸውና ኮንዶማዊ ምስለኔዎቻቸው ጭምር) ሙሉ በሙሉ፣ ኪነ ጥበብንና ሙዚቃን ሙሉ በሙሉ፣ የመጻሕፍት ኅትመትንና የትምህርት መሣሪያዎች ምርትን ሙሉ በሙሉ፣ የትምህርት ተቋማትንና መያዶችን ሙሉ በሙሉ፣ የሃይማኖት ተቋማትንና አመራሩን ሙሉ በሙሉ፣ የዜጎችን የማሰብ፣ የመናገር፣ በሕይወት የመኖር፣ የመንቀሳቀስና ያለመንቀሳቀስ መብት ሙሉ በሙሉ፣ … ከሰማይ በታች ሁሉንም ነገር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን መናገር በተቻለ ነበር፡፡ እነሱ የሌሉበትና ራዳራቸውን ያልተከሉበት፣ በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ የማይቆጣጠሩት ነገር የለም – ፀሐይዋና አየሩም ሣይቀሩ በነሱ ቁጥጥር ሥር ሳይገቡ አይቀርም፤ የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና አሁን አንድ ነገር ቀርቷቸዋል ብዬ እማስበው እኛ ባሎች ከሚስቶቻችን፣ ሚስቶቻችን ደግሞ ከኛ ከባሎቻቸው የምናገኘውን የወሲብ እርካታ በየጭኖቻችን መካከል በሚያስቀምጡት ቆጣሪ ወይ ባልቦላ በመለካት ወርኃዊ ግብር ማስከፈል እንዳይጀምሩ ነው – በሌላ የገቢ ርዕስ በኅቡዕ መድበው እስካሁን የማያስከፍሉን ከሆነ ነው እሱንም፡፡ የሚገርመው ይህን ሁሉ ወያኔያዊ ወንጀልና የአካይስት ተግባር ሁለቱም መሪዎቻችን ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ የምድሪቱ ንግሥት ዓላማዋና ተልእኮዋም ስለሚታወቅ በበኩሌ የርሷ አይገርመኝም፡፡ ከቁጥር ዕውቀቴ አንጻር የ13ንም ሆነ የ666ንና መሰል ቁጥሮችን መነሻና መድረሻ እረዳለሁና በነሱ ምክንያት እንዲህ እንዲህ ሆን ብዬ አላማርርም፡፡ እኔ የሚያሳስበኝ ይልቁንስ ባለብዙ ዐይኑ ፈጣሪያችን ለባለአንድ ዐይኑ የጨለማው ገዢ አስረክቦን በነሱ ልጆች ይህን ያህል እንድንሰቃይ ፈቃዱ ሆኖ የመገኘቱ ክፍለ ዘመናዊ ምሥጢር ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ – ከኛ በኩል ትልቅ የምናወራርደው ታሪካዊ ስህተት ፈጽመን መሆን አለበት! የወላጆቻችንን ታሪክ እንመርምርና ጌታ ምሕረቱን እንዲልክልን እንማጠነው፡፡ አለበለዚያ በዚህ አያያዝ ዘር ላይተርፍ ነው፡፡ የሰይጣን መንጋ ተለቆብናል፡፡ በሀገራችን ብቻ እንዳይመስላችሁ – በሌላውም፡፡

ብዙውን ጊዜ ማርካቶ እሄዳለሁ፡፡ ዱሮ በጉራጌ ተጥልቅልቆ አይ ነበር፡፡ እንደዚያም የሆነው ጉራጌዎች በንግድ ጎበዞች ስለነበሩ የዱሮዎቹ ብልህ የሀገር መሪዎች ባመቻቹት መንገድ ነበር  – ለሸርና በሸር ሣይሆን ለሀገር በሚጠቅም ተፈጥሯዊ መንገድ፡፡ ወያኔ ሀገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ ግን ያ ሁኔታ በእጅጉ ተለውጦ ሌላ መልክ ይዟል – በአሣፋሪነቱ ወደር የሌለው መልክ፡፡

ተክለ ሃይማኖት አካባቢ ዱሮም ትግሬ ይበዛበታል፡፡ ወደላይ ሂዱ – ወደ መስጊዱ – ወደ ጎጃም በረንዳ(አሁን ትግሬ በረንዳ ቢባልስ?) – ወደሰባተኛ – ወደ ጭድ ተራ – ምን አለፋችሁ ወደየትም ሂዱ ማርካቶ ስትገቡ መቀሌ የገባችሁ ያህል ይሰማችኋል፡፡ ይህ ዓይነቱ የአንድ ነገር ጣልቃ ገብት በግልጽ የሚንጸባረቅበት የዜጎች መፈናቀልና በአንድ ዘር ብቻ የመተካት ሂደት አሳሳቢ ነው፡፡ አሁን አሁን እኔ ማርካቶ ስሄድ በእጅጉ እደነግጣለሁ፡፡ ለነገሩ አዲስ አበባ ውስጥ የትም ስሄድ የማየው የትግሬዎችን መብዛት ነው፡፡ ይቅርታ አድርጉልኝና በየቦታው የማየውን ይህን የሀገሬን ሰዎች ብዛት ስታዘብ በተፈጥሯዊ መዋሰብ የተገኙ ስለመሆናቸው እጠራጠራለሁ፡፡ ሌላው ወዴት እየገባ እንደሆነ ማወቅ ባለመቻሌም እጨነቃለሁ፡፡ በከተማዋ ከዳር እዳር ብትሄድ ንግዱንና መላውን ማኅበራዊ እንቅስቃሴ የተቆጣጠሩት በአብዛኛው ትግሬዎች ናቸው – ሆቴሎችንና መዝናኛ ቤቶችንማ ተዋቸው – ሌላ ዜጋ በሀገሪቱ ያለም አይመስል፡፡ እኔ ማንም ቢቆጣጠር ችግር የለብኝም፡፡ ነገር ግን ሌላውን አፈር ድሜ እያስጋጡና መርዝ ጠጥቶ ወይም በገመድ ታንቆ እንዲሞት በኪራይና በግብር እያበሳጩ አንዱን ወገን ብቻ ያለውድድር ማንገሣቸው ወንጀል ብቻ ሣይሆን ኃጢኣትም ጭምር ነው፡፡ እግዚአብሔር ከ“እንቅልፉ ሲነቃ” ብዙ የሚያወራርዱት ሒሣብ ተዘፍዝፎ ይጠብቃቸዋል፡፡ ሰው የዘራውን ያጭዳልና፡፡

እንደምንም እየተውተረተረ የምታገኙትን የማርካቶ ጉራጌ ጠጋ ብላችሁ ብትጠይቁት የሚነግራችሁ ሁሉ ጉድ ነው፡፡ ወያኔ ትግሬዎች በሌሎች ዜጎች የሚሠሩት ወንጀል ተወርቶ አያልቅም፡፡ ለምሳሌ በዓመት 15ሺህ ብር ለማይገኝባት የሱቅ በደረቴ ዓይነት ሚጢጢዬ ሱቅ ወያኔዎች ከንግድ ጽ/ቤት ውሾቻቸውን ‹ጃዝ ቡቺ› ብለው ይልኩና 150ሺ ብር ዓመታዊ ግብር ያስመድቡበታል – ወገብ ቆራጩ የቤት ኪራይ ሳይነሳ ነው እንግዲህ፡፡ ያኔ ያ ጉራጌ ያለው አማራጭ ሁለት ቢበዛ ሦስት ብቻ ነው፡፡ አንደኛ ራሱን ማጥፋት፣ ሁለተኛ ብዙ ጉቦ ከፍሎ ያን የገንዘብ ክምር ማስቀነስ፣ ሦስተኛ በረንዳ አዳሪ መሆን፡፡ በዚህ ሁኔታ ራሳቸውን ያጠፉ፣ ወደበረንዳ ሕይወት የተዛወሩ ወይም ዐብደው ጨርቃቸውን የጣሉ ሞልተዋል፡፡ በነሱ ምትክ ታዲያ እዚህ ግባ በማይባል የቦታና የቤት ኪራይ በዚያ ላይ አላንዳች ግብር ወይም ለወጉ ያህል ብቻ ትንሽ እንዲከፍል ተደርጎ ትግሬው ገብቶ ይነግዳል – (ይህን ድርጊት ጤናማ ነን የምትሉ ትግሬዎቸ እባካችሁ በጥሞና አስቡትና “ይሄ ነገር በውነቱ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ለወደፊት ሊያቀባብረን ይችላል ወይ ብላችሁ?” አጢኑት፤ ራሳችሁን በሌላው ዜጋ ጫማ ውስጥ አስገቡና “በነሱ ቦታ እኔስ ብሆን ኖሮ ?” ብላችሁ እንደ አንድ አስተዋይ ሰው አስቡት፤ ይህን ስታደርጉ ግን ከሆድና ከዘረኝነት ተፅዕኖዎች ራሳችሁን ነፃ አድርጋችሁ መሆን አለበት)፡፡ አንድ ሰው የዐርባ ቀን ዕድሉ ቀንቶት ትግሬ ሆኖ ከተፈጠረና ኅሊናውን በዘረኝነት ካሳወረ በአሁኑ ወቅት ምንም ምድራዊ ችግር የለበትም – ከገንዘብ አኳያ ማለቴ ነው፡፡ ካለቫት ቢነግድ የሚደርስበት ነገር እንደሌለ ስለሚያውቀው ደረቱን ነፍቶ ነው ዕቃውነን ሰጥቶህ ገንዘቡን አለደረሰኝ ይዘህ ከሱቁ ውልቅ እንድትል በዐይኑ የሚሸኝህ፡፡ ከውጭ የምትመጡ ሰዎች በትግሬና በሌላው ዜጋ መካከል ያለው ልዩነት ቦሌ አየር ማረፊያ እንደደረሳችሁ አፍ አውጥቶ ሲናገር ትሰማላችሁ፡፡ አይ፣ ምነው ሸዋ! ሰው መሆን እንጀምር እንጂ እናንተ፡፡ እስከመቼ ደንቆሮና ዐይነ ሥውር ሆኖ መኖር ይቻላል? አንገት የተፈጠረውስ ዞሮ ለማየት አይደለምን? አብረን እንደነበርን አብረን እንኖር ይሆናልና እናስብበት ጎበዝ፡፡ ወረት አላፊ ነው፡፡ ጥጋብ አላፊ ነው፡፡ ሰው ሟች ነው፡፡ ሥርዓት በሥርዓ ይተካል፡፡ ቋሚ ነገር የለም፡፡ ዮዲት ጉዲትና ግራኝም ታይተው እንደበራሪ ከዋክብት በቅጽበት አልፈዋል፡፡ ታዲያ ተጋሩ ወንድሞቼ ከታሪክ ተምረን ለምን አንጨምትም እነዚህን ጉግማንጉጎች እንራቃቸው፤ እንኮንናቸው፤ እንታገላቸውና የጋራ የሆነ ሥርዓት እንትከል፡፡ በቃ፡፡ እሹሩሩ ይብቃን፡፡

ማርካቶ ውስጥ ስሙን ከድር ወይም ዘበርጋ ወይም ፈይሣ ሲሉት ትሰማለህ፡፡ ዘወር ብሎ ከጓደኞቹ ጋር ሲነጋገር ግን በትግርኛ ነው፤ ሲያስመስል እንጂ ትግሬ ነው፡፡ እስስቶች መልካቸውን እንደሚለዋውጡ ወያኔዎችም ስማቸውንና እንዳስፈላጊነቱም ሥራቸውን እንደየአካባቢው በመለዋወጥ ኢትዮጵያን መቦጥቦጡን፣ ሌሎች ዜጎችን ማፈናቀሉንና መከራ ውስጥ መክተቱን በስፋትና በጥልቀት ቀጥለዋል፡፡ ሁለቱ መሪዎቻችንም ተፋጠዋል፤ ምናልባት በቅርብ ይለይላቸውና አንዳቸው አሸናፊ ሌላኛቸው ተሸናፊ ይሆኑ ይሆናል፡፡ እኔ በበኩሌ ይህን አስገራሚ ትርዒት በጉጉት ከሚጠባበቁ የዓለም ዜጎች አንደኛው ነኝ፡፡ ለማንኛውም የሥጋ ፍላጎትን መቆጣጠር ተስኖት በወንድሞቹ ሞትና አጠቃላይ ኪሣራ የሚደሰት ወገን የማይኖርባትን ኢትዮጵያ ሳላይ እንዳልሞት እጸልያለሁ፡፡ ጌታ የሚሳነው ነገር የለምና ምኞቴን እንደሚያሳካልኝም አምናለሁ፡፡

comment pic

ትግሉ ሰፊ የምሁራን ተሳትፎ ይሻል! – አርበኞች ግንቦት 7

0
0

pg7-logo-1ኢትዮጵያ በበብዛትም ይሁን በጥራት በውጭው አለምም ይሁን በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ምሁራን ያፈራች ሀገር ነች። በጅጉ የሚያሳዝነው ግን በሀገሪቱና በሕዝቧ ችግር ላይ ሀሳብ ሲሰጡ ፣ ባደባባይ ሲከራከሩና ሲታገሉ የሚታዩት በጅጉ ጥቂቶች ናቸው። ርግጥ ነው ተከታታይ መንግስታት በምሁራን ላይ ያደረሱት ጥቃትና ማግለል ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት ብዙዎች መከራን ከህዝብ ጋር ከመጋፈጥ ይልቅ አጎንብሶ ማሳለፈን የመረጡበት ሁኔታ አለ። ቁጥራቸው ጥቂት ያልሆኑም ለግል ጥቅማቸው ቅድሚያ በመስጠት ከጨቋኝ ገዥዎች ጋር በመተባበር የሚሰሩ መኖራቸውም አይካደም። አብዛኛው ምሁራን በተለይም በብዙ የሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ጠለቅ ያለ እውቀት ያላቸው ጭምር ሀገሪቱን ከገባችበት ማጥ ለማውጣት በሚደረገው ትግል ውስጥ እየተሳተፉ አይደለም። ይህ ዛሬ ባለው ችግርም ይሁን በታሪክ ፊት አሳዛኝ ነው።

ሀገራችን ዛሬ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች። የተማሩ ልጆቿ መላ እንዲመቱ በመጠየቅ ላይ ትገኛለች። ይልቁንም በሀገራችን ያለው ችግርና ሀገሪቱ እየሄደች ያለችበት መንገድና አቅጣጫ በተለይ ምሁራንን እንቅልፍ ሊነሰ ይገባል። ዕውነታው ከዚህም አልፎ የሀገሪቱን አሳዛኝና አደገኛ ሁኔታ ለመቀየር በሚደረገው ትግል ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ግድ ይላል። የመንግስት ግፍና ሰቆቃ በበዛበትና የሀገራችን ሕልውና አደጋ ላይ በወደቀበት በአሁኑ ሰዓት ምሁራን ላለመሳተፍ ምክንያት ማቅረብ የማይችሉበት ወቅት ላይ ደርሰናል። እንደማንኛውም ሀገር ምሁራን የኢትዮጵያ ምሁራን በሀገራችን ውስጥ ሰላምና ዲሞክራሲ እንዲሰፍንና ፍትሕ የሰፈነበት ስርዓት እንዲመሰረት ሊሸሹት የማይገባ ትልቅ ሚና አላቸው።

ዛሬ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች መንግስት በልማትና በልማት እያመካኘ የሚያካሂደውን ሰፊ ዝርፊያ እንዲሁም ወያኔ ሩብ ምዕተ አመት ሙሉ በብሄረሰብ እኩልነት ስም እየማለ የሚያደርሰውን ያንድ ብሄረሰብ ጉጅሌ የበላይነት ማስፋፋት እምርረው በመታገል ላይ ናቸው። መስዋዕትነቱን እየከፈሉ የሚታገሉትና የሚወድቁ የሚነሱት ወጣቶችና ምስኪን ገበሬዎች ናቸው። እነዚህ ወገኖቻችን ሕይወታቸውን ሳይቀር ሲገብሩ በየቀኑ እየሰማንና እያየን ነው። ይህንን የህዝብ ጥያቄና ትግል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ምሁር ተመልካች ሆኖ ሊቀመጥ አይገባም። ትግሉን ከመምራት ጀምሮ እስከ ተራ ታጋይነት ባሉት ረድፎች ሁሉ ምሁራን ቀጥተኛ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል። ሰለትግሉ እቅጣጫም ሆነ ስለሀገሪቱ መጻዔ ዕድል ሃሳብ ማመንጨትና ማሰራጨት ይኖርበታል። ሀገራችን የደለቡ ችግሮቿን ተቋቁማ ፍትሕ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ሀገር የሚያደርጋትን የምህንድስና ስራ አስቀድሞ ማሰብና ማመቻቸት ይኖርበታል። ርግጥ ነው ይህን መሰል ተሳትፎ የሚያደርጉ ምሁራን አሁንም አሉ። ቁጥራቸው ግን ሊሆን ከሚገባው ጋር ሲወዳደር በጅጉ አነስተኛ ነው።

ምሁርነት ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ መቀዳጀት ብቻ እንዳልሆነ የታወቀ ነገር ነው። ምሁርነት ምሉዕ የሚሆነው መላውን የተፈጥሮ ከባቢ ከህዝብ ማህበራዊ ሕይወት ጋር አጣምሮ የሚያስብ አዕምሮን በዕውነት ላይ ለተመሰረተ ሀሳብና ዕውቀት ክብር መስጠትን ለተግባራዊነቱ መሟገትን የጨመረ ሲሆን ነው ። በመሆኑም ሁሌ እንደሚባለው ምሁርነት የጋን መብራትነት አይደለም። ምሁርነት በጨለማ ውስጥ ችቦ ሆኖ ብርሃን መፈንጠቅን ይመለከታል። ምስዋዕትነትንም ይጠይቃል።
ያለንበት ወቅት ለኢትዮጵያ ምሁራን ከፍተኛ ፈተናም ዕድልም ይዞ ቀርቧል። ይህ ልሽሽህ ቢሉት የማይሸሽ ፈተና ከመሆኑ ባልተናነሰ በታሪካችን እንድ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የጎላ አሻራን ለማኖርም ትልቅ የታሪክ ዕድል ነው። ይህ ፈተና ከፍተኛ ያርበኝነት ስሜትንና ሀላፊነት መውሰድን ይጠይቃል። አገር በተወሳሰበ ችግር ምክንያት ወደ አረንቋ እየገባች ምንም ሳይሰሩ መቀመጥ ወይም ዝም ብሎ ከመመልከት የበለጠ ለምሁር ሂሊና የሚከብድ ነገር ሊኖር አይችልም:: በጣም ላስተዋለ ሰው እንዲህ አይነት ዝምታ ሐጢያትም ነው። በእንዲህ አይነት ፈታኝ ወቅት የኢትዮጵያ ምሁራን ሀገሪቱን ወደተሻለ አቅጣጫ እንድትሔድ ላለመታጋል ምንም ምክንያት ማቅረብ አይችሉም። ሀሳብ የሚሰራጭባቸው የሀሳብ ክርክር የሚካሔድባቸው መድረኮች ፣ አደባባዮች ፣ የመገናኛ መሳሪያ አይነቶች የፖለቲካና የሲቪክ ማህበሮች ባገር ውስጥም በውጭም ያሉት መሳተፊያ ናቸው።

ድርጅታችን አርበኞች ግንቦት 7 ምሁራን በሰፊውና እንደየፍላጎቶቻቸውና ችሎታቸው ሊሳተፉ የሚችሉባቸው በርካታ የትግል መስኮች አሉት። የሀገሪቱን ውስብስብ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ የጥናት ውጤቶች ፣ ሀሳቦች ፣ ምክሮችም ሆነ ቀጥተኛ የምሁራን ተሳትፎ ለማስተናገድ አመቺ ሁኔታ ያለበት ድርጅት ነን። ወደፊትም የምሁራን ተሳትፎ እንዲጎለብት ሁኔታዎችን ይበልጥ ለማመቻቸት እንሰራለን። ዽርጅታችን የሀገራችን ችግር የሚወገደውና ዲሞክራሲና የዜጎች እኩልነት የሚረጋገጠው በበሰለና ከተራ ዜጋ እስከ ብስል ምሁራን በሚያከሂዱት ክርክርና የበሰለ ሃሳብ ላይ ተመስርቶ መሆኑን ያምናል። አሁን ያለው የሀገራችን ምሁራን ተሳትፎ ደረጃ ሁላችንም ከምንጠብቀው በታች በጅጉ ያነሰ መሆኑ ሁላችንንም ከማሳዘን አልፎ የሚያስቆጭና የሚያንገበግብ ሆኖአል:: አገርና ህዝብ ድረሱልኝ እያለ በሚጣራበት በዚህ የታሪክ አጋጣሚ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ የተለያዩ ምክንያቶችን እየደረደሩ ማለፍ ይቻል ይሆናል። ይዋል ይደር እንጂ ለነጻነቱ ቀናዕ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የደረሰበትን አፈናና ጭቆና እምቢኝ ብሎ ነጻነቱን ሲቀዳጅ ግን ከታሪክ ፍርድና ከህዝብ ትዝብት ማምለጥ አይቻለም።

አርበኞች ግንቦት 7 በአገር ውስጥም ሆነ በተለያየ ምክንያት በአለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ምሁር ለወገን ደራሽነቱንና አለኝታነቱን አሁኑኑ ይወጣ ዘንድ ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

ዘማሪ እንግዳወርቅ በቀለ በዋስ ተፈታ –‘ታቦት ሲሸጥ እጅ ከፍንጅ ተይዟል’የሚል ክስ ቀርቦበታል

0
0

engedawork bekle
(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዘማሪነት የሚታወቀው ዘማሪ እንግዳወርቅ በቀለ ትናንት ከ እስር መፈታቱን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከአዲስ አበባ ዘገቡ::

እንደ ዘጋቢዎቻቸን ገለጻ ከሆነ ላለፉት 2 ሳምንታት እስር ቤት የቆየው ዘማሪው ከታቦት ሽያጭ ጋር የተያያዘ ክስ ቀርቦበታል::

ፖሊስ በዘማሪው ላይ ያስቀመጠው ክስ እንደሚያሳየው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ የሄዱ አባ ገብረወልድ የተባሉ መነኩሴ በሰሜን አሜሪካ ቤተክርስቲያን ለማቋቋም በማቀድ ከእንግዳወርቅ ታቦቱን በ90 ሺህ ብር ሲሸጥ እጅ ከፍንጅ ተይዟል የሚል ነው::

እንግዳወርቅ በተጠረጠረበት ወንጀል አዲስ አበባ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ከሚገኘው መዝሙር ቤቱ ቅዳሜ ማርች 26, 2016 ሲያዝ ታቦቱን ከሚነዳት ቭትስ መኪና እንዳወጣው ፖሊስ ባቀረበበት ክስ ላይ ተቀምጧል ተብሏል:: ከዘማሪው ጋር አብሮ የተጠረጠረ አንድ ሰው መታሰሩን የሚገልጹት ምንጮች ታቦቱን ይቀርጻል የተባለው ሰው መሰወሩና ፖሊስም በክትትል ላይ እንደሆነ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

ትናንት ራስ ደስታ አካባቢ ከሚገኘው ፖሊስ በዋስ ከ እስር የተፈታውን ዘማሪ እንግዳወርቅ በቀለን ዘ-ሐበሻ ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም::

በመጀመሪያ ነጻነታችንን –ዓቢይ. መ.

0
0
በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ነፃነት ላይ፣ ሁለት ዓይነት በሽታዎች መኖራቸውን መቀበልና፤ ለመፍትሄው:- በቃ!!!ለደዌ-ሥጋ ሲሆን፤ ንቁ !!!ደግሞ በርኩስ-መንፈስ ላይ ነው።
 
    የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ። 
ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫፥ ቁጥር ፯ 
 
“ቡዳና ከሃዲ ካልተተፋባቸው:-
ድፍን አገር ያውቃል አይረክስም ጅኒያቸው::”
                Freedomይህን የደዌ በሽታ ግኝትን ርዕስ ለምን መረጥኩት?ለምንስ ኢትዮጵያችንን ከደዌ በሽታ ምርምር ጋር አያያዝኳት?ምክንያቱም የበሽታዋ ግኝቶች በመርምር እና ጥናት ላይ ስለተመሰረቱ።ሥራዎቹ ከጥፋት ይልቅ ለልማት፤ከክፋት በተሻለ ደግሞ ለበጎ ተግባር እንደሚውሉ በደምብ አድርጌ ስለማውቅ ነው።በመንፈሳዊ ጉዳዮችም ያሉትን ስናይ:-በየቤተክርስቲያን እና በየመስጊዶቹም ሆኑ በዕምነት ተቋማት የምናያቸው ፈተናዎች ድብቅ አይደሉም።
ኢትዮጵያ አገራችን ለዘመናት በመታመሟ እና ሐኪሞቿ(በጎ አሳቢ ምሁራን ዜጎቿ) ለማከም ቢጥሩም (በክፉ አሳቢ ምሁራን ደግሞ) እንዳትታከም በመደረጓ እነዚያ (በሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ የተፈጠሩት የሰባ አመታት ችግሮቿ  እየተባባሱ)የያዟት በሽታዎቿ ዛሬ ነቀርሳ እና ደዌ ስለሆኑባት ነው።አንዳንድ የሥጋ ትል የሆኑባት ኢትዮጵያውያንም ቢሆኑ “ማነው ኢትዮጵያ ታማለች የሚለው?”በማለት ሽንጣቸውን ገትረው አይናቸውን በጨው አጥበው እንደትል በቃላት ክርክር ይቦረቡሯታል። ከዚሁ ጋር ሁለት ዓይነት ዜጎች ያሏት ኢትዮጵያ አገራችን ከጣሊያን ሽንፈት በኋላ እሷን ለመጥቀም ወይም ለመጉዳትየተሰለፉ መኖራቸውን ማጤን ይገባናል።እነሱም “በግልፅ በሽታዋ ይነገር፤ ይታወቅ፤” የሚሉ እና “በፍፁም አይነገርም፤ አልታመመችም፤” የሚሉ ናቸው።እርስዎ በየትኛው በኩል ነው የቆሙት?።የሚያሳዝነው እንደጀርሞቹ ሁሉ፣ በዲባቶዎች (ዶክተሮች)ውስጥ፣በተቃርኖ ስላሉ፣ ገዳይ ዲባቶዎች መኖራቸውና ለጥቅማቸው ሲሉ ያዩትን እንዳላዩ ሆነው፤”ኢትዮጵያ በሽታ አልያዛትም” ማለታቸው ነው።  ብታምኑም ባታምኑም በኢትዮጵያ ነፃነት የደዌ በሽታዋ የትግራይ ጉጅሌ መሆኑ ፀሀይ የሞቀው አገር ያወቀው፤መረጃ የሚቆጠርለት፣ምስክር የሚቀርብለት፣ታሪክ የተጻፈለት ብዙ የተባለለት የፋሺሽስት
ሴራ ነው። ለመሆኑ ክርስቶስን የሰቀሉት ሮማውያን ስለክርስትና ዕምነት ተቆርቋሪዎች ያደርጋቸው ማነው?በእኛ ትውልድ ዳግም የ’ከደሙ ንፁህነኝ፣እጃቸውን ለመታጠብ በተለይም ኢትዮጵያን ለመያዝ ዘመናት እየቆጠሩ የሚመላለሱት ለምን ይሆን???
             
              በሽታዎች ሁሉ የሚመጡት ከጀርሞች፣የሚወገዱትም ደግሞ በጀርሞች ሲሆን፤ግዴታችንም ሆኖ፣እኛም የሰው ልጆች የምንኖረው  ደግሞ ከጀርሞች ጋር ነው።ጀርሞች ሁለት አይነቶች በመሆናቸው የጠቃሚነታቸውን ያህል የጎጂዎቹ ጀርሞች ልዩነት በሕላዌ ባሕርያቸው ተረጋግጧል።በሌላ በኩል ያኔ ነቢዩ ዕንባቆም የታየው የኢትዮጵያ ሸክም ትንቢት ሆኖ ይነገር እንጂ በዘመናችንም በግልጽ እየተፈጸመ ይገኛል።
           እናም የዘመናችን ፈላስፎች ምሥጋና ይግባቸውና ዲባቶ (ዶክተር) ሉዊስ ፓስተር እና ዲባቶ(ዶክተር) ሮበርት ኮች የተባሉ የምርምር ሰዎች እስከ ፲፰ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የሳይንስ ሊቃውንት ሳያዩዋቸው በምልክታቸው ብቻ ያጨቃጬቋቸው የነበሩትን የበሽታዎች ግኝት፤ በአጉሊ መነፅር መገኘት ምክንያት በአይናቸው ሐቁን እንዲያዩ እና ምርምሮቹን ከመላ-ምት አውጥተው በገሃድ በሽታዎቹ ራሳቸው እንዲመሰክሩ አድርገዋቸዋል።በዚህ ሐቅ መሠረት እኛን የሰው ልጆችን ሁሉ በውጤቱ ረድተውናል፤ምንም እንኳን የምርምራቸው ግኝት የርኩስ-መናፍስትን በሽታዎች ለማየት የማያስችሉ ቢሆኑም።
ይሁንና ኢትዮጵያውያን ግን ከእግዚአብሔር ከራሱ የተሰጣቸው ፀጋ እና በረከት አለና(ለዚሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መረጃዎቿ ሰፍረዋል።ትንቢተ አሞጽ ምዕ ፱ ቁ ፯ የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር፡፡ እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?)እሷን የሚሿት ሁሉ ያገኟታል። ምክንያቱም በአይን የሚታየውም ሆነ የማይታየው ረቂቅ በሽታ በምርምር በአጉሊ መነፅር እንደሚገኝ ተረጋግጧልና ነው።ይሁንና የርኩስ መንፈስ በሽታ ግን የተለየ በመሆኑና ከኢትዮጵያውያን መካከልም በእርኩሰ-መናፍስት ጭምር የተያዙ በመኖራቸው ለዚህ መፍትሔ ደግሞ የአጉሊ መነፅር ሳይሆን ከጥንትም ጀምሮ በታደላት መለኮታዊ ኃይል እና በረከቶቿ እየተፈወሱ ይገኛሉ።ይህን ሥጦታ ተመራማሪዎችም ያልደረሱበት በመሆኑ ለዚህ ችግር ደግሞ በመፍትሄነት ኢትዮጵያውያን(ኤፌሶን ምዕ ፮ ቁ ፲፪  መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ) ከመጽሐፍ ቅዱስ በስተቀር ሌላ አማራጭ አይሹም።
 
                 በሌላ በኩል ግን የትግራይ ጉጅሌን ደዌነት በአይናችን ፍጹም እንዳናይ በነገር ሲሙለጨለጩና በደረቅ ቃላት ሲለፋደዱ ይታያል። እንደጀርሞቹ ባሕርይ ተከፋፍሎ:- ማለትም ቫይረስ እና ባክቴሪያ በሽታ ከሚባሉት የሚመደቡ አሉ፤በአንፃሩም ደግሞ ፈንጊ፣ፕሮቲስቲ እና ፕሪኦንስ ተብለው በጀርም ውስጥ በተጨማሪነት የሚጠቃለሉ አሉ፤እንደዚያ መልኩን እየለዋወጠ፣ ባህርዩን እያመሳሰለ፣እየተጠቀለለ፣ እየተዘረጋ እየተዳቀለ፣ እየተጥመለመለ፣እየተገለባበጠ አስማት እስኪመስል ሕዝቡን ግራ የሚያጋባ ፍጡር ነው።ከመነሻዬ እንደገለፅኩት ስለጀርም ዝርያዎቹ ለማውሳት ሳይሆን፣ (እኔ ከምገልፀው ይልቅ በበለጠ ዲባቶዎቹ እና ምሁራን በደምብ አድርገው ያብራሩታል።)የተነሳሁበት ዋናውና አቢይ ጭብጥ ግን የኢትዮጵያ ነፃነት በደዌ በሽታ መታመሙን ሲነገረን በዜግነታችን ምን እያደረግን እንደሆነ ለማመላከት ነው።በመሆኑም ታሪክ  የኢትዮጵያ ነፃነት በሽታ እንደነበረና ዛሬ ግን ደዌ ወይም ነቅርሳ የሆነባትን ሐቅ ደግሞ ከታሪክ እንመልከት።
 
        በመሠረቱ ነቀርሳ ወይም ደዌ በአካላችን ላይ ወይም በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠርና ቢያንስ የመቶ ዓይነት ጀርሞች በደማችን ውስጥ መገኘት ነው እናም በቀጥታ የሚገድሉን ቆርጠን ለማውጣት በማንችልበት አካል ውስጥ ከተፈጠሩ ብቻ ነው።ስለዚህ አሁን ካለንበት ትውልድ ጀምሮ ስንመለከት የኢትዮጵያ ነፃነት-ደዌ በሽታ መሆኑን መጀመሪያ በይፋ ያረጋገጡት ዲባቶ ብርሃኑ ነጋ እና የትግል ጓዱ አርበኛው አንዳርጋቸው ፅጌ ናቸው።
 
               በትዕግስት ጠብቀው የጉጅሌዎችን ባሕርይ በሕሊና ማጉያ መነፅራቸው በጣም ተጠግተው በመርመር ያለምንም ሐፍረት{“ንጉሱ ራቁታቸውን ናቸው”እንደአለች  ሕፃን} በአደባባይ በድፍረት”የኢትዮጵያ የነፃነት በሽታ፣በጉጅሌው ሴራ የደዌ በሽታ ሆኖባታል” በማለት ከረዳቱ አርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር በድፍረት በይፋ ያጋለጠው ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ነው።ብዙ ዶክተሮች የኢትዮጵያ ነፃነት በበሽታ እንደታመመ ይመኑ እንጂ፣ደዌ(ካንሰር)መሆኑን አፍ አውጥተው የመሰከሩ የሉም። የሚያስድስተው ደግሞ በደዌ መታመሟን ብቻ ሳይሆን በአመፅ ቆርጦ ከማውጣት  በስተቀር መፍትሄ የለውም ብለው በሙሉ-ልብነት ከነቁርጥ-እርምጃው አስቀምጠውልናል።ሲገልፁም የበሽታዋ ምክንያት ደዌም በመሆኑ ለጤናዋ በመስጋት ሁሉም እንደተቻለው መድኃኒት እንዲያፈላልግና የፈለገም ጠበል ያስረጫት አሊያም ቅጠላ-ቅጠል ወይም ሥራ-ስር እንዲፈልጉላት ብለዋል።በዕውነቱ የያዛት ደዌ ስለሆነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ደግሞ ኦፕሬሽን አደርግላታለሁና ደዌዋን ቆርጬ አወጣዋለሁ ብሎ የአርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌን በአጋርነት ይዞ ፊት ለፊት በመጋፈጥ ትግሉን አቀጣጥሎታል።
           አርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌማ፣ዕድሜውን ሙሉ ከአያቶቹ የነፃነት አርበኝነቱን በንቃተ-ህሊና የተረከበ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ሲሆን፣አለቃ ሳይፈልግ ምቾት ሳያታለው፣ጉጅሌዎችን ከውስጣቸው ያውቅ ስለነበረ እንደጦር ነበር ይፈሩት የነበረው፤ዛሬ ግን እሱ በአረቦቹ ተሽጦ ጉጅሌዎቹ እጅ መብረቅ ሆኖ ወደቀላቸው።”እስኪ ትበላት!!!አያ ጅቦ”እንደተባለው ሆኖባቸውና ፈረንጁ የጉጂሌዎች ጌቶቻቸውን ትዕዛዝ ይጠብቃሉ።
እኚያ ሰባዊነት የማይለያቸው ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስም ቢሆኑ አፈሩን ገለባ ያድርግላቸውና:-በእጃቸው እሳት ሆነው ስለወድቁላቸው ነው በየዋህነት ነብሳቸውን ይማርልንና ያወቁትን በማሳወቃቸው “አውቆብናል” ብለው የገደሏቸው።እሳቸው ያኔውኑ ኢትዮጵያ ወደቀዶ ጥገናው በአስቸኳይ እንድትገባ ምርመራ ይደረግላት ዘንድ ተማጽነዋል።በደዌ መያዟን አረጋግጠው አልገለፁም(ዶክተር ብርሃኑ ነጋና አርበኛ አንዳርጋቸው ፅጌ በአሲምባ የትግል በረሃ ውስጥ ጉጅሌን ያውቃሉና)እንጂ የኢትዮጵያ ነፃነት በሽታዋ ደዌ ሊሆን እንደሚችል አፅንዖት ሰጥተዋል።በዚህም የሐቅ ንግግራቸው(ምክንያት ሰይጣንን ድንገት እንዳየ ሰው)በእጅ አዙር ግድያ እስር ቤት ውስጥ በበሽታቸው ታፍነው እንዲገደሉ በመደረግ ወንጀል ነው የተፈፀመባቸው።
 ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምም ቢሆኑ የታሪክ መዝገባቸውን ከወገኖቻቸው ጋር አጭቀው ከወጣት ምሁራን ጋር በመሆን አቅማቸው የፈቀደውን ያህል ባደባባይ እየተንከራተቱ ከውስጥ ሆድ-አምላኩ ምሁራንን እና ምድረ-ፈረንጅን ከጥቅም እጋሮቻቸው ጋር የጥቅም-መግቢያ በማሳጣት በኢትዮጵያዊነት ሥም ታግለዋቸዋል፤ተሟግተዋቸዋል።ሌሎች ምሁራንና ፕሮፌሰሮችም ነበሩ በሽምግልና ሥም እየተልመጠመጡ፤ይህን ዓይነት የነፃነት በሽታ አቅልለው በሽታዋ የደዌ ሳይሆን  የጉንፋን ዓይነት ነው በማለት በፕሮፓጋንዳና በባዶ-ተስፋ ይከስማል ይሉን የነበሩ የፋሺሽቱ ጉጅሌ ሹማምንታት የነበሩ።
          ድንክዬውም የገና አባትን የመሰለው እና እንደየገና አባት ማጭበርበርን የተካነው *ቱኒው* (ትርጉሙን”በጦርነት ላይ ጓደኛውን አጋልጦ ትን ብሎ የሚሸሽ፣ፈሪ፣ቶስቶአሳ….”ከሳቴ ብርሃን**:- ይመልከቱ።)ወቸገል-ዜናዊ የትግል አጋሮቹን ገድሎ እና አስገድሎ ሥልጣን የጨበጠው በሌለው ዕውቀት :በተንኮሉ ብቻ ሲሆን፤ከሕዝብ ባዘረፈው የትጥቅ ብረት እየተኩራራ በትዕቢቱ አብጦ የፖለቲካ ዶክተር ነኝ ብሎ ነበር።
እነ ታጋይ ገብረ መድህን አረዓያ የኢትዮጵያ ሐቀኛ አባቶች ሲያጋልጡት ግን፤*ቱኒው* ዜናዊ ያኔ እንደገባ ኢትዮጵያን በባንዳዎች መቀስ እየቀደደ፤በቻይና፣ በኮሪያና በሩሲያ አምባገነንነትን አብዮታዊ መርፌ እየወጋ፤በስደተኝነት ሕይወቱ በእንግሊዝ አገር ያየውን የዘርኝነት ልሳን”እንኳን ከወርቅ ዘር ተፈጠርኩ፤” እያለ አፉን በትዕቢቱ ከፍቶ ራሱን አዋርዷል።ልዋጭ-ልዋጭ ሲልበት የነበረውንም የሸበጥ ጫማውን ገና ሳያወልቅ  ቁንጮ እንዳማረው ላይመለስ ከእነኮዳ-ቀዳዳ የፈሪ-ሥሙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ እንደኮነነው እና ትውልድ እንደረገመው ሊወሳ ባደባባይ ተቀጭቷል። በግድያው የተሰማሩት የባንዳ ልጆች ግን እነሆ ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያን እያደሟት ያጣችውን ነፃነት ወደደዌ በሽታ እያባባሱባት ወደ መላ አካሏ ለማሰራጨት ደፋ ቀና ይላሉ።ለዚሁም በመለስ ጣዕረ-መንፈሱ ተለክፈው የኢትዮጵያን ነፃነት በደዌ በሽታ መ-ያ-ዝ የሚክዱ፤ከደሞዛቸው በተጨማሪ ለለዘብተኝነታቸው ምንዳ እየተከፈላቸው በምቾት የሚኖሩ ምሁራን ሞልተዋል።
 ካህናት እንኳ ሳይቀሩ፣ኢትዮጵያ አልታመመችም፤ ጠበልም ሆነ ፆም ፀሎት አያስፈልጋትም፤ መድኃኒትም አያሻትም እያሉ በየገዳማቱ ያሉትን ባሕታውያንን ሳይቀር ደፍረው የኃጢያት ደሞዛቸውን ተቀብለዋል።ይህንን ሐቅ የካዱት ካህናት ከአባ ጳውሎስ ጀምሮ መለስን አስከትለው ከመቀጨት ጋራ እግዚአብሔር በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ መናገሩን ንቀው የሃጢያት ደሞዛቸውን ስለጠየቁ ተከፍሏቸዋል።ለዚህ የመለኮት ውድመታቸው የተከፈላቸውን ደሞዝ በማጉያ መነፅር ማግኘት ወይም ማየት አይቻልም፤በዕምነት ብቻ የሚፈጸም ነው።ሐቁንም ለማየት በአባታችን መምህር ግርማ ወንድሙ “በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ሥም”በአደባባይ አጋንንትን እና እርኩሰ-መናፍስትን ሲያወጡ ማየት ብቻ ይጠቅማል።
                በሌላ በኩል ደግሞ እነዚሁ ምሁራን ነን የሚሉን ሆድ-አደሮች የንዋይ ተገዥዎች በመሆናቸው ምግብ ተትረፍርፏል ሕዝቧም ጠግቦ ነው  የሚያድረው ሲሉን፣ወጣቱ ከየሆቴል ቤቶቹ ጓሮ ትርፍራፊ ለመቃረም በወረፋ ሲጠብቅ፣በየቆሻሻ መጣያዎቹ መኪናዎች ጎማ ሥር ያለፍላጎቱ ሲወድቅ፣ በየአውራ መንገዶቹ ከየውሻዎቻቸው ጋር እንደሬሳ በየጥጋጥጉ ተጋድመው፤ያለመጠለያ በቁርና በጠራራ ጸሀይ ሲሰጣ፤አገሪቷም ሰላም ነች በሚሉበት አፋቸው፣የማጎሪያ ቤቶች እስር ቤት ተብለው በየቀኑ በድብቅ ሰዎች ተገድለው ደመ-ከልብ ሆነው ሲቀሩ እያዩ፤ ኢኮኖሚውም ተመንድጓል ብለው አፍ ሞልተው ይመሰክራሉ።እሺ! አደባባይ ይውጣና ለሕዝብ ይታይ ሲባሉ ግን እኛ በመንግሥትነታችን ሳንፈቅድ አይደረግም እያሉ ቢያንስ በዚህች ዕድሜ እንኳ ሃያ አራት አመታትን አስቆጠርን። 
     አንባቢዎቼ ሆይ:- ስለአገሩ የማይቆረቆር ዜጋ የለም።ኢትዮጵያ አገራችን የነፃነት በሽታ እንደያዛት የታወቀው የፋሺሽቱ አብራሪ (ፓይለት) ቲቶ ሚኒቲ በትዕዛዝ 26 ዲሴምበር 1935 (እ ኤ አ) ባዘነበው የጋዝ መርዝ በርሜልም አይደለም። አሊያም  ቀ.ኃ.ሥ. በጦርነቱ ምክንያት የተባበሩት መንግሥታት በወሰነው መሠረት የጠፋ ንብረት ማካካሻ ከጣሊያን ስለተከፈለን የ$250,000,000 የጣሊያን ክፍያ ካሳ የት እንዳስገቡት አለመታወቅ እና በ 525,000 ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ቤቶች መውደም ሥም ምክንያት ባልተከፈላቸው ኢትዮጵያውያኖች ገንዘብ ጉድለትም አይደለም።አልፎ ተርፎም በመጀመሪያው የጣሊያን ጦር ወረራ ማለትም ከ1895 እስከ 1896 (እኤአ) በዳግማዊ ምኒልክ አሸናፊነት በተጠናቀቀው የጦርነት ድል ጊዜ ሰበብም አይደለም።እንደውም የመጀመሪያው የጣሊያኖች ወረራ ሽንፈትማ ልዩ ስያሜ ተሰጥቶት፣ የአድዋው ድል በሚል ጣሊያኖች በገቡበት ቀዳዳ በኩል የተቀበሩበት ስያሜ  አግኝቶ የጥቁር-ሕዝቦች ድል እንደሆነ በታሪክ ተመዝግቦ አልፏል።የኢትዮጵያ የነፃነት በሽታ የጀመራት ግን በሁለተኛው እና በመጨረሻው የጣሊያን የበቀል ወረራ ዋዜማ ጀምሮ ነው። 
 
        ሁለተኛው እና የመጨረሻው  ኢትዮጵያ ከፋሺሽት ጣሊያን ጋር ያደረገችው ጦርነት ከ1935 እስከ1936 ለአንድ ዓመት ይቆይ እንጂ ከ”ኖቬምበር” 1934 ጀምሮ እስከ 1943 ድረስ የነፃነት ውጊያው ውስጥ ውስጡን በባንዳዎች ላይ ተፋፍሞ ባደባባይ ወጥቶ እንደተፋፋመ ለቅኝ ግዛት ማስፋፋት የጣሊያን ጦር ሲጣደፍ ተበትኖ ነበር።ኋላም እስከ 10 ፌብሯሪ 1947 የተረፉት የሞት ሽረት ደፈጣ ውጊያ እያደረጉ ኢትዮጵያ በረሓ ውስጥ ይቆዩ እንጂ አረንጓዴ፣ቢጫ እና ቀይ ሰንደቅ-ዓላማዋን  ያላስወረደ ወረራ ነበር።እናም በአርበኞች የደፈጣ ውጊያ አፃፋ ምክንያት የጣሊያን ሰራዊት ጥሩምባውን አስነፍቶ ሕዝብ እንዳያስተዳድር እና የሐገር መሪ እንዳይሆን ከ 45,000  በላይ የሚበልጡ አርበኞች ውድ ሕይወታቸውን በስቅላት ገብረው ሰላም በማሳጣታቸው ጣሊያን በመንግሥትነት መቀመጥ ሳይችል ቀርቷል።በዚህም ምክንያት አገሪቷን ኢትዮጵያን ያዛት እንጂ ቅኝ አላደረጋትም ተብሎ በደም ተጻፈ።ስለሆነም በምንሊክ የተጠበቀው ነፃነቷ እንደፀና ባንዳዎችም ሆኑ የናዚ እና የፋሺሽት ርዝራዦች ወደዱም ጠሉም፤በተባበሩት መንግሥታት በደም ብዕር የታሪክ መዝገብ ላይ መኖሩን አረጋግጠዋል። 
 
               በዚህም ጠንካራ የታሪክ ትግል የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አስተዋፅዖ በግንባር ቀደምትነት ሲወሳ ይኖራል፤ይሁን እንጂ በነዚያ የስደታቸው ዓመታት የተዋጉት አርበኞች አስታዋሽ አጥተዋል።በጦርነቱ ወቅት ተጠቃሚዎቹ የባንዳ ልጆች ነበሩና ትምህርት የቀሰሙት የባንዳ ልጆች ብቻ በመሆናቸው አርበኞች ከነቤተሰቦቻቸው በባንዳዎች የቢሮክራሲው ወጥመድ ተወታተቡ።እነ በላይ ዘለቀን የመሳሰሉ በሺህ በሚቆጠሩ የድል አጥቢያ አርበኞች እየተተኩ :-ጀግናዎቹን ደግሞ እያሸሹ እንኳን ካሳ ሊከፈላቸው ይባስ ሰበብ እየተፈለገላቸው ባደባባይ ተሰቅለዋል።የተረፉትም የለማኝ ሕይወት ኖረው፣ታሪካቸው እንደ ጀግናው አብዲሳ አጋ እንኳ ሳይነገርላቸው በሜዳ ተበትነው ቀርተዋል።ያኔም”…የገደለሽ በላ።”እንደተባለ ዛሬም ድረስ የገድሏት ይበሏታል፤አሁንም የሚገድሏት ቀጥለውበት ሊበሏት ልጆቻቸውን በየፈረንጅ አገሮች የተሻለ ትምህርት እያስተማሯቸው ያሳድጓቸዋል።በየምርጫ ሰበብ የምናየው መራር-ትግል ይህንኑ የዘመናዊ ባንዳዎችን አፈጣጠርና የቀስበቀስ መደላደል ለማፈራረስ ነው፤የኢትዮጵያ ነፃነት የደዌ በሽታ መሆኑን አጥብቀን ስለምናውቅ።
ይህም የትውልድ ጥያቄ በመሆኑ አሮጌዎቹ የኢትዮጵያ ነፃነት ደዌ በሽታዎች ተቆርጠው እየተንጠባጠቡ ሲሞቱ፣የሚበላው እንዳጣ የደዌ በሽታ ራሳቸውን ሲያበሰብሱት የምናየው በዚሁ ምክንያት ነው።የኢትዮጵያ ነፃነት ደዌ በሽታ የሆነው የትግሬው ጉጅሌ ቡድን ግን አይታወቅበትም መስሎታል።የእነዶክተር ብርሃኑ ነጋን ዕድሜና ጤና ሰጥቶ ሲይቆይልን እነፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ደግሞ ነፍሳቸውን በመንግሥተ ሰማያት የኢትዮጵያ አምላክ ያሳርፍላቸውና የነፃነት ደዌ በሽታዋን ቆርጦ ለመጣል በሁለ-ገብ የኢትዮጵያ አርበኞቹ፦በእነተከበሩት አቶ ገብረ-መድህን አረዓያ፣ዖባንግ ሜቶ፣አል ማርያም ጦማሪው፣ታማኝ በየነ፣ሻምበል በላይነህ አዝማሪው፣ዘላለም የለንደኑ፣በሌሎቹም ሁሉ ትግሉን ቢቀጥሉም በማጉሊያ መነፅሮቹ በሃቀኞቹ ጋዜጠኞቻችን፦ በእነ አበበ ገላው፣በእነ ርዕዮት ዓለሙ፣በነአበበ በለው፣በነደሳለኝ  አማካኝነት በሚገባ አይተንዋል።ከእንግዲህ ሕሊና ያለው ዕውነቱን ለመፈለግ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እንዳለው እያንዳነዱ ኢትዮጵያዊ ለሁለ-ገብ ትግሉ ህሊናውን ያዘጋጅ።
 
             እናም መጀመሪያ ነፃነታችንን በግድ እንዲያስረክብ የጉጅሌውን ቡድን በቃ ብለን ለመናገር ስንችል:-በማስገደድ አምርሮ መታገል ሲሆን፣እምቢታው በእሺታ ካልተለወጠ ነው፣ለማሽቀንጠር በብልሃት እና በልበ-ሙሉነት አምርረን የምንነሳው።መጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም ሥጋ መሆኑንም ማመን ሊኖርብን ነውና ከሁሉም በፊት ነፃነታችንን መንጭቀን ካልወሰድን ዋጋ የለንም። ከዚያም በኋላ እኛ እንደ እነርሱ የደዌ በሽታቸውን እንዳናዛምትና ሕዝብ እንዲዳኘን በግልፅነት መድኅኒት በጥበብ ችሎታ እንመራ።የኢትዮጵያ የደዌ በሽታዋ የግልፅነት አለመኖር ብቻ ነውና፤ያለበለዚያ ግን ግልፅነትን የሚፈራ ተሸፋፍኖ መኖርን ይፈልጋልና ሊትዮጵያ ነፃነት የደዌ በሽታ አዲስ ጀርም፣አዲስ ቫይረስ ወይም አዲስ ዓይነት ባክቴሪያ ተሸካሚዎች ሆነን እንቀርባታለን። ስለዚህ በግልጽነት ዲምክራሲን አምጥተን በሕግ የበላይነት እየተዳደርን አዲስቱን ኢትዮጵያን እንገንባ። 
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live