Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የክርስቲያኖ ሮናልዶ 28 ልዩ ቀናት

0
0

ከ ይርጋ አበበ
የክርስቲያኖ ሮናልዶ 28 ወርቃማ ቀናት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የካቲት 5/ 1985 ዓ.ም በፖርቹጋሏ ገጠራማ ከተማ ሳንቶ አንቶኒዮ የተወለደው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዶሳንቶስ አቬሮ የዛሬ የእዚህ ገጽ እንግዳችን ነው።
የእግር ኳስ ሕይወቱን ገና በ8 ዓመቱ ነው የጀመረው። አንዶሪና ለሚባለው የአካባቢው አማተር ክለብ በእዚህ ዕድሜው መጫወት ጀምሮ በሲ.ዲ ናሽናል ጎለበተ። በሲ. ዲ ናሽናል ክለብ ለሁለት ዓመታት ቆይታ ካደረገ በኋላ የፖርቹጋሉን ኃያል ስፖርቲንግ ሊዝበን የግሉ አደረገው። 28 ቁጥር ማሊያ ለብሶ በፖርቹጋል ሊግ መታየት የጀመረው የዛሬው የ28 ዓመት ኮከብ በስፖርቲንግ ሊዝበን የአንድ ዓመት ቆይታው አርሰን ቬንገርንና አሌክስ ፈርጉሰንን ጨምሮ የታላላቅ ክለብ አሠልጣኞች ዓይን ያርፍበት ጀመር። በውድድሩ በለስ የቀናው ግን የላንክቫየሩ ክለብ ማንዩናይትድ ነበር በ12 ነጥብ 24 ሚሊዮን ፓውንድ የግሉ አደረገው።
ምንም እንኳ በእንግሊዙ ታላቅ ክለብ በርካታ ሥራዎችን የሠራ ቢሆንም በእዚህ ጽሑፍ ለአንባቢያን ለማቅረብ የሞከርነው ግን በሪያል ማድሪድ ክለብ ውስጥ ያከናወናቸውን አብይ ክንዋኔዎች ለይተን 28ቱን ብቻ ነው። በእዚህ ጽሑፍ ውስጥ የምንጠቀመው የአውሮፓውያን አቆጣጠር መሆኑንም እንገልጻለን።

ክፍል 1
ሐምሌ 1/ 2009
በወላጅ እናቱ ጎትጓችነት የሚወደውን የሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ቡድን ለቅቆ ወደሚወዱት ሪያል ማድሪድ ክለብ የተዘዋወረበት ቀን ነው። 80 ሚሊዮን ፓውንድ ወይም 131 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር ማሬንጌዎቹን ያስወጣው ፖርቹጋላዊ በእዚህች ቀን የ6 ዓመት ኮንትራቱን ሲፈራረም ከ80 ሺ በላይ ደጋፊዎች በደማቅ ሥነ ሥርዓት ነበር የተቀበሉት። ይህ የደጋፊዎች ቁጥር ደግሞ ዲያጎ ማራዶና ከባርሴሎና ወደ ናፖሊ ሲዘዋወር ከተቀበሉት 75,000 ደጋፊዎች የላቀ ሆኖ ተመዝግቧል።
ነሐሴ 29 ቀን 2009 የስፔኗ ዋና ከተማ ክለብ በሜዳው ዲፖርቲቮ ላኮሮኛን 3ለ2 ሲያሸንፍ ግብ የማግባት ሥራውን አንድ ብሎ የጀመረበት እለት ነው። በሪያል ማድሪድ እግር ኳስ ክለብ ታሪክ ከፍተኛ ክብር የሚሰጠውን የአልፍሬድ ዲስቲፋኖን 9 ቁጥር ማሊያ ለብሶ መጫወት የጀመረው CRገ አሁን ለክለቡ ካስቆጠራቸው 193 ግቦች ሁሉ ቀዳሚዋን ግብ ያስቆጠረው በእዚህ እለት ነበር።
ግንቦት 5/ 2010
በእዚህ ዕለት ደግሞ የቀድሞው የሳሙኤል ኤቶ ክለብ የነበረው ሪያል ማዮርካ የክርስቲያኖ ሮናልዶን ሦስት ግቦች (ሀትሪክ) የተስተናገደበት ክለብ ነው። በማሬንጌዎቹ ቆይታው በድምሩ 15 ሀትሪኮችን ቢሠራም የመጀመሪያውን ሀትሪክ ለማስቆጠር ሪያል ማዮርካዎችን መጠበቅ ግድ ሆኖበት ነበር።
ሐምሌ 3/ 2010
ለነጭ ለባሾቹ የፈረመበትን የመጀመሪያ ዓመት እያከበረ ነው። ይህች እለት ግን ሌላ ዜና ይዛለት መጥታለች። ዜናው ከመስከረም 2005 በ52 ዓመታቸው ሕይወታቸው ያለፈውን ወላጅ አባቱን ማስረሻ የሚሆን ነው። እ.አ.አ ሐምሌ 3/ 2010 ክርስትያኖ ሮናልዶ የልጅ አባት ሆነ። የልጁ እናት ማንነት አወዛጋቢ ቢሆንም ክርስቲያኖ ሮናልዶ ግን ሮናልዶ ጁኒየር የሚል ስም የተሰጠውን ልጅ ያገኘው ከላይ በተጠቀሱት እለት ነበር።
መጋቢት/3/ 2011
ለሀገሩ ሲጫወት ከደረሰበት ጉዳት አገግሞ ወደ ሜዳ የገባበት እና በማላጋ መረብ ላይ ሦስት ግቦችን ያሳረፈበት እለት። ለ10 ቀናት ቁምጣና ታኬታ መልበስ ያልቻለው ፈጣኑ ልጅ በእዚህ ዕለት ኳስ ናፍቆት እንደነበር ያሳየበትን ጨዋታ ነበር ያደረገው።
ሚያዝያ 20/2011
ከመጋቢት ሦስት እስከ ሚያዝያ 20 ድረስ ባሉት 6ሳምንታት ውስጥ 6 ግቦችን በማስቆጠር እ.አ.አ በ2007/08 ማንቸስተር ዩናይትድ በነበረበት ጊዜ በዓመቱ ያስቆጠረውን 42 ግብ የማግባት ክብረ ወሰን የተጋራበትን ጀብዱ ፈጽሞ ነበር ለሚያዝያ 20 የኤል ክላስኮ ጨዋታ የደረሰው። 103 ደቂቃዎችን በፈጀው በእዚሁ የኤል ክላሲክ ፍልሚያ ማሬንጌዎቹ ብዎሉ ግራናዎቹን አሸንፈው የኮፓ ዴልሬይ ዋንጫን ሲያነሱ መልከ መለካሙ ሮናልዶ ከኢማኑኤል አዲባየር የተሻገረችለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ከቪክቶር ቫልዴዝ መረብ ውስጥ ጨመራት።
ግንቦት 7/ 2011
የኢንዶኔዢያ ክለብ ሲቪያ በሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት አንገት የሚያስደፋ ውጤት ሲያስመዘግቡ ግብ አነፍንፊው ፖርቹጋላዊ 4 ግቦችን ለግሉ ሲያስመዝግብ ለቀሪዎቹ ሁለት ግቦች የነበረው ሚናም ከፍተኛ ነበር። እነዚህ ግቦች በዓመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች ድምር ወደ 46 ያሳደጉለት ነበሩ።
ሜይ 15/2011
ከአራት ቀን በፊት በጌታፌዎች መረብ ላይ የዶላቸው ሦስት ግቦች 49ኛ የውድድር ግቦች ሲደርስ ግንቦት 15/2011 ምሽት ደግሞ ሌላ ታሪክ ሠራ። ቀደም በሁጎ ሳንቼዝ እና በቴልሞ ዛኑ ተይዞ የነበረውን 38 የሊግ ግብ የተጋራበትን ግብ ቪላሪያል መረብ ላይ አሳረፈ።
ግንቦት 21/2011
የዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታ አልሜሪያ ከሪያል ማድሪድ በሳንቲያጎ ባበርናባው ክለቡ ሪያል ማድረድ በ37 ጨዋታዎች 97 ነጥቦችን ሰብስቦ ከባርሴሎና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት 8 አድርሷል። በአንፃሩ የቀድሞው የማን/ ዩናይትድ ወጣት 38 ግቦችን አስቆጥሮ የፒቺቺ ኮከብ ግብ ማስቆጠሩን አረጋግጧል። የአልሜሪያ ጨዋታው ግን ለልጁም ሆነ ለክለቡ ታሪክ የሚሠራበት ቀን ነበር። ሪያል ማድሪድ ካሸነፈ 100 ነጥቦችን በአንድ የውድድር ዓመት የሰበሰበ ብቸኛው የላሊ ክለብ ይሆናል። በአንፃሩ ሮናልዶ ግብ ማስቆጠር ከቻለ ደግሞ ከፍተኛ ኮከብ ግብ አስቆጣሪነቱን በሪከርድ መዝገብ ላይ ማስቀመጥ ይችላል። ጨዋታው ከተጀመረ ደቂቃዎች ሄዱ። ሪያል ማድሪድ አልሜሪያን ሲያሸንፍ ኮከባቸው ሮናልዶም ሁለት ግቦችን አስቆጥሮ በ40 ግቦች የውድድር ዘመኑ ከፍተኛ ግብ አግቢ ሆኖ አጠናቀቀ።
ነሐሴ 17 /2011
የስፓኒሽ ሱፐር ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ የመጀመሪያ ዙር በካምፕኑ ምሽት የምንጊዜም ተቀናቀኞቹ ባርሴሎና ከሪያል ማድሪድ ከዕረፍት በፊት ዴቪድ ቪያ ባስቆጠረው ግብ ባርሴሎና መምሪት ጀመረ። ከደቂቃዎች በኋላ ግን ከራኡል ጎንዛሌዝ ክለቡን መልቀቅ በኋላ «7 ቁጥር» ማሊያ የለበሰው የፖርቺጋል ብሔራዊ ቡድን አምበል ማሪጌዎቹን አቻ አደረገ። ይህች ግብ በሪያል ማድሪድ ማሊያ ያስቆጠራቸውን ጠቅላላ ግቦች ድምር 100 ማድረስ የቻለች ነበረች። መቶኛ ግቡን በካምፕኑ። (ይቀጥላል)


ሆሣዕና በአርያም …!!! –በፍቅር ለይኩን

0
0

በፍቅር ለይኩን፡፡
 

‹‹ሆሣዕና›› ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን ትርጓሜውም ‹‹አሁን አድን›› ማለት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ከፋሲካ በፊት ያለው እሁድ የሆሣዕና እሁድ በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ዕለትም በቤተ ክርስቲያን የሚዘመረው መዝሙር፣ ማኅሌቱ፣ ቅዳሴውና ማንኛውም መንፈሳዊ አገልግሎት ዕለቱ በታላቅና እጅግ ደማቅ በሆነ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት የሚዘከርበት ነው፡፡ ይህ በዓል እጅግ በደማቅና ልብን በሚመስጥ መንፈሳዊ ሥርዓትና ድምቀት ከሚከበርባቸው ቅዱሳን ገዳማትና መካናት መካከል የአክሱሟ ርዕሰ አድባራት ጽዮን ማርያም እና በዚህ በአዲስ አበባችን ደግሞ የእንጦጦ ማርያም በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

hosaena
 

ሆሣዕና የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ ኢሩሳሌም በታላቅ ድል የገባበት ዕለት ነው፡፡ አስቀድሞ በመጽሐፍ ቅዱስ በነቢዩ ዘካርያስ፡- ‹‹ለጽዮን ልጅ፡- እነሆ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያቱ ግልገል በውርንጭላይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት፡፡›› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ፡፡ ጌታ፣ አምላክና መድኃኒት የሆነው ኢየሱስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡

 

እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ሊቃውንት በብሉይ ኪዳን ዘመን የእግዚአብሔር ነቢያት መልካም የሆነ ትንቢትን ከፈጣሪ ዘንድ ይዘው ሲመጡና መጪው ጊዜ ሰላምና ብልጽግና የሞላበት መሆኑን ለመግለጽ በአህያ ላይ ሆነው ነበር እየዞሩ ትንቢት የሚናገሩት፡፡ ዘመኑ የጦርነት፣ የራብ የግዞት ዘመን ከሆነ ደግሞ በፈረስ ላይ ሆነው ይናገሩ እንደነበረ ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በመጥቀስ፣ እግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ የሰላም አለቃ ለኢየሩሳሌምና ለዓለም ሁሉ ሰላምንና ፍቅርን ያውጅ ዘንድ በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገብቷል ሲሉ ያመሰጥራሉ፡፡

 

የዋህና ትሑት ሆኖ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ በታላቅ ድልና ክብር ወደ ኢየሩሳሌም የገባው የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ለታላቅ ክብሩና ማዳኑ ሰዎች ሁሉ ኢየሱስ በሚያልፍበት መንገድ ልብሳቸውንና የዛፍ ቅርንጫፎችን በማንጠፍና በመጎዝጎዝ ለክብር ጌታ ክብርን፣ ምስጋናንና ውዳሴን አቀረቡለት፡፡

 

በመቅደስም ሳለ ሕፃናቱ፡- ‹‹ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሣዕና በአርያም!›› እያሉ በታላቅ ድምጽ እየጮኹ አመሰገኑት፡፡ አስቀድሞም ነቢይ ወካህን በሆነው በንጉሥ ዳዊት አፍ እንደተነገረው፡- ‹‹ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋን ለራስህ አዘጋጀህ፡፡›› የሚለው ትንቢትም ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ፡፡ የቤተክርስቲያን አባትና ሊቅ የሆነው አባ ጎርጎሪዮስም በቅዳሴው፡-

 

የካህናት አለቃ ወደ መጋረጃ ውስጥ በገባ ጊዜ በጸሎት ቤት የተደረገውን ድንቅ ነገር ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ ሁሉም መለኮትን የምትሸሽግ ኅሊናትንም የምትሰውር ናት ይሏታል፡፡ የአጋዕዝትና የመናፍስት ጌታ በተዋረደ አህያ ውርንጫ ተቀምጦ ወደርስዋ ገባ፡፡ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው፡፡ አንተም የአማልክት አምላክ የእስራኤልም ንጉሥ እግዚአብሔር ብሩክ ነህ እያሉ ለሚያመሰግኑ ሕፃናት ሁሉ ጌትነቱን አሳየ፡፡ … ከመድኃኒትነቱ የተነሳ ከቤቱ መሠረት ሳይናወጥ ከልዑል መንበሩ ወርዶ ጸጋንና ኃይልን አሳየ፡፡ ሆሣዕና በአርያም፣ ሆሣዕና በአርያም፣ ሆሣዕና በአርያም…፡፡ ብሎ እንዳመሰገነ፡፡

 

የክብርን ጌታ፣ የሕይወትን ራስ ‹‹ሆሣዕና… ሆሣዕና… ሆሣዕና በአርያም፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው!›› እያሉ በእናታቸው ጀርባና እቅፍ ያሉ ሕፃናትና የቢታንያ ድንጋዮች ሁሉ ሳይቀሩ በታላቅ ደስታና ሐሴት ሆነው መድኃኒት፣ አደኝና ቤዛ ለሆነው ለኢየሱስ ክርስቶስ በአንድ ድምፅ በንጹሕ አንደበት ዘምሩለት፡፡ ምድርምና ሞላዋ፣ ውቅያኖሶች፣ ባሕሮችና ተራሮች፣ ሰማይ፣ ሰማየ ሰማያት፣ ከሰማይም በላይ ያለ ሰማይ፣ የእግዚአብሔር ፍጥረታት ሁሉ በዚህ ልዩ የሕፃናት የምስጋና ጥዑም ዜማ ተሞሉ፣ በደስታም እንደ እንቦሳ ዘለሉ፡፡

 

በዚህ ልዩ ሰማያዊ ቅኔ የሰማይ ሠራዊት፡- መላእክት፣ ሊቃናት፣ አጋእዝትና መናብርት ሁሉ በአንድነት ታደሙ፣ በዚህ ታላቅ የምስጋና ዜማ ምድርን በሐሴትና በደስታ ተናወጠች፣ መሠረቶቿም ተነቃነቁ፣ የፍቅር አምላክ፣ የሰማይና የምድር ሁሉ ፈጣሪ ራሱን ባዶ አድርጎ፣ የዋህና ትሑት ሆኖ በአህያ ውርንጫ ላይ ሆኖ በግልጽ መጥቷልና፡፡

 

ወንጌላዊው ማቴዎስ በወንጌሉ እንደጻፈልን ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በቀረበ ጊዜ መላው ከተማ ይህ ማነው ብሎ ተናወጠ ይለናል፡፡ ዛሬም ይህ ማነው ለሚሉ፡- በእውነት እርሱ፡- በጽኑ ፍቅሩ ጨለማውን ኃይላትን፣ የሞትን መውጊያ፣ የሲኦልን ሥልጣን፣ የኃጢአትን ኃይልና ብርታት ሁሉ የሻረ፣ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ፣ ወልደ አብ ወልደ ማርያም፣ ድንቅ፣ መካር፣ ኃያል አምላክ፤ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!!!

 

በዕለት ሆሣዕና ሐዋርያት፣ ሕፃናት፣ ሕዝቡና የተከተሉት ሁሉ ቃላት በማይገልጸው ደስታና ሐሴት ውስጥ ሆነው ሲዘምሩና ሲያመሰግኑ ክርስቶስ ኢየሱስ ግን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌም በበደሏና በኃጢአቷ ምክንያት ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀጠረላትን የመዓት፣ የጥፋትና የመፍረስ ቀን አሻግሮ አይቶ ሩኅሩኁ ጌታችን እምባውን አፈሰሰላት፤ በሐዘን መንፈስ እያያትም አለቀሰላት እንዲህ ሲል ይለናል ሐኪሙና ታሪክ ጸሐፊው፣ ወንጌላዊው ሉቃስ፡- ‹‹ለሰላምሽ የሚሆነውን በዚህ ቀን አንቺስ ብታውቂ አሁን ግን ከዓይንሽ ተሰውሮአል…፡፡››

 

የሰላሟን አምላክ፣ የሕይወትን ራስ የገፋችው፣ አሳልፋ በመስጠትም የሰቀለችው ኢየሩሳሌም ጌታችን እንደተናገረ ቅጥሮቿ ፈርሰው፣ ሕዝቧ እርስ በርሱ ተራርዶ፣ ልጆቿም ያለ እናት ተበትነው፣ እንዲያ የሚኮሩበትና የሚኮፈሱበት መቅደሳቸውም በአሕዛብ ተርግጦና ተዋርዶ ድንጋይ በድንጋይ ሳይቀር በፈራረሰበት፣ ሕዝቦቿም በታላቅ ሀፍረትና ውርደት ተሸማቀው፣ በዓለም ሁሉ ዙሪያ እንደ ጨው ዘር ተበትነው፣ ለ1800 ዓመት በላይ እስራኤል የምትባል ሀገር ከምድረ ገጽና ከካርታ ላይ ከጠፋች በኋላ ነበር እንደ ገና እንደ አዲስ ሙሽራ ጎጆ በመውጣት እ.ኤ.አ በ1948 ዓ.ም ዳግም ዓለም ሁሉ እንደ ሀገር የተቀበላት፡፡

 

ይሁን እንጂ ያቺ ምድር ዛሬም ቢሆን መሽቶ በነጋ ቁጥር የጥይት ባሩድና የሮኬት አረር ጭስን የምትታጠን፣ ፍጹም ሰላምና መረጋጋት የራቃት የዓለም ሁሉ ዜና መክፈቻና መነጋገሪያ እንደሆነች አለች፡፡ የእርሷ ሰላም ማጣት የዓለም ሀገራት ሁሉ የሚታወኩበትና የሚጨነቁበት የሌት ተቀን ጉዳያቸው እንደሆነ በየቀኑ እየታዘብን ነው፡፡

 

የእስራኤልና የዐረቡ ዓለም ፍጥጫ፣ የፍልስጤማውያን የልዑላዊነትና የነጻነት ጥያቄ፣ የመካከለኛው ምስራቅ የነዳጅ ዘይት፣ የአካባቢው ሀገራት የሚገኙ የሀማስና የሂዝቦላ ጽንፈኞች ታጣቂ ኃይላት፣ የኢራን የኑክሌየር፣ የጅምላ ጨራሽ ኬሚካልና ባይሎጂካል መሳሪያዎች የማምረት ሽር ጉድ በአሜሪካና በምዕራባውያኑ ሀገራት መካከል ያነገሰው ውጥረትና ጥርጣሬ፣ ለእስራኤል ታላቅ ስጋት ነው በሚል አሜሪካና የምዕራቡ ዓለም ከኢራን ጋር የገቡበት ውዝግብና ክስ፣ ከአፍሪካ እስከ አሜሪካ፣ ከኤዥያ እስከ አውስትራሊያ፣ ከአውሮፓ እስከ ሩሲያ፣ ከቻይና እስከ ፓሲፊክ ሀገራት ድረስ የተዘረጋ ትልቅ የዓላማችን የመነጋገሪያ አጀንዳ ነው፡፡

 

ግና በእውነትም የኢየሩሳሌም ሰላም ያለው በገፋችው በሰላሟ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እጅ ነውና ወደ እርሱ ፊቷን እስካላዞረች ድረስ እንደታወከች፣ እንደተናወጸች ለዓለም ሁሉ ጭንቅትና ውጥረት እንደሆነች ትዘልቃለች፡፡

 

በዘመናችንም ሰላም የሁሉም ሰው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡ ሰላም በቤተሰብ፣ ሰላም በሀገራት፣ ሰላም በመንግሥታት፣ ሰላም በባልና ሚስት፣ ሰላም በአብያተ ክርስቲያናት እና በሃይማኖት ተቋማት፣ ብቻ ሰላም በሁሉም ስፍራ በሁሉ ዘንድ በመብራት የምትፈለግ እንቁ ሆናለች፡፡ ስለሆነም ሀገራት ሁሉ ከፍተኛ ወጪ የሚመድቡት ለውስጥ ሰላማቸው፣ ጸጥታና የደህንነት ጉዳያቸው ነው፡፡ ስለ ሰላም ዓለማችን የዘንባባ ዝንጣፊን በማወዛወዝ ዘምራለች፣ ስለ ሰላምም ሲባል ነጫጭ ርግቦችን በሰማይ ላይ ለቃለች፡፡

 

ይሁን እንጂ ዓለማችን የተመኘችው ሰላም ዛሬም የሰማይ ያህል እንደራቃትና እንደሸሻት ነው፡፡ በውስጣቸው ሰይፍ፣ ሰልፍና ጠብ ያለባቸው ሀገራትና ሰዎች በአፋቸው ሰላም ሰላም በማለት ቢሰብኩም የሰላሙ አለቃ ኢየሱስ ከልባቸው ዙፋን ተሰዷልና ሰላምን ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች ሊያረጋግጡ አልቻሉም፡፡

 

የጥበብና የሕይወት ምንጭ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ለምድራችን፣ ለዓለም፣ ለሀገራትና ለሰዎች ሁሉ ሰላም መፍትሔው የሰላም አለቃ የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ኢየሱስም በወንጌል፡- ‹‹ሰላምን እተውላችኋለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም፡፡›› በማለት ለደቀመዛሙርቱ የሰላምን የዘላለም ዋስትና ሕያው የሆነ ተስፋን ሰጥቷቸዋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ለኤፌሶን ክርስቲያን በፃፈላቸው መልእክቱ፡- ‹‹እርሱ ሰላማችን ነውና!›› እንዳለ፡፡

 

በዓለ ሆሣዕና ክርስቶስ የጽድቅ የትሕትና እና የድኅነት ንጉሥ እንደሆነ በአደባባይ የተገለጠበት ነው፡፡ ሕዝብና አሕዛብን አንድ ለማድረግ እንደመጣ በምሥጢር የገለጠበት ዕለት ነው፡፡ በዚህች ቅድስት የሆሣዕና በዓል ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ዘንድ ለተቀበልነው ሰላማችን ማብሰሪያ ምልክት ይሆነን ዘንድ በግንባራችንና በጣቶቻችን ከምናስረው ዘንባባ ባሻገር ለልባችን፣ ለቤታችን፣ ለትዳራችን፣ ለቤተሰባችን፣ ለኑሮአችንና ለሀገራችንና ለዓለም ሁሉ ሰላም የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ሰላምና ፍቅር በተግባር የምናሳይበትና የምናውጅበት በዓል ይሁንልን!

 

ለሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ መልካም የሆሣዕና በዓል!

ሰላም! ሻሎም!

‹‹313 ሚሊዮኑ ለልማት!›› በሚል መሪ ቃል የተደረገው የሚያዚያ 18 አገር አቀፍ ተቃውሞ ቪዲዮዎች

0
0

‹‹313 ሚሊዮኑ ለልማት!›› በሚል መሪ ቃል የተደረገው የሚያዚያ 18 አገር አቀፍ ተቃውሞ በታላቁ አንዋር መስጊድ 1&2


‹‹313 ሚሊዮኑ ለልማት!›› በሚል መሪ ቃል የተደረገው የሚያዚያ 18 አገር አቀፍ ተቃውሞ በአንዋር ሴቶች መስጊድ

‹‹313 ሚሊዮኑ ለልማት!›› በሚል መሪ ቃል የተደረገው የሚያዚያ 18 አገር አቀፍ ተቃውሞ በአጋሮ ከተማ

‹‹313 ሚሊዮኑ ለልማት!›› በሚል መሪ ቃል የተደረገው የሚያዚያ 18 አገር አቀፍ ተቃውሞ በባህር ዳር የዱአ ስነስርአት

ዛሬም የኢትዮጵያ ሙስሊም ድምጹ ከፍ ብሎ ተሰማ፤ ‹‹313 ሚሊዮን ብሩን ለልማት!›› ሲል ዋለ

0
0

ከ ድምፃችን ይሰማ
‹‹313 ሚሊዮኑ ለልማት!›› በሚል መሪ ቃል የተደረገው የሚያዚያ 18 አገር አቀፍ ተቃውሞ ቪዲዮዎች
በእርግጥ ጥያቄው ትላንትም ዛሬም አንድ ነው፡፡

የሃይማኖት ነጻነትና እኩልነት መሰረታዊ ከሚባሉ የሰው ልጅ መብቶች ይመደባል፡፡ ‹‹መንግስት እምነታችን ላይ በጀመረው ኢፍትሀዊ ዘመቻ ነጻነታችንን ነፈገን! ሃይማኖታቸንን በግድ ሊያስለውጠን እየሞከረ ነው! ድምጻችን ይሰማ!›› በሚል ለመብቱ ሲታገል የነበረው የኢትዮጵያ ሙስሊም አደባባይ መዋል ከጀመረ ብዙ ጊዜ ሆነው፡፡ በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ በርካታ መስዋእትነቶች እና ዘርፈ ብዙ የመብት ጥሰቶች ከትግሉ ሊያስቆሙት አልቻሉም፡፡ አሁንም ጠንክሮ እግሮቹን አደላድሎ ‹‹ለመብቴ በሰላማዊነት እታገላለሁ›› የሚል ቁርጠኝነቱ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም፡፡ ከትግሉ መጀመር አንስቶ እለተ አርብ ለሙስሊሞች ብዙ አደጋን ያዘለች፣ በርካቶች የሚደበደቡባት፣ በርካቶች የሚታሰሩባት፣ በርካቶች በግፍ የሚጉላሉባት ብትሆንም ህዝበ ሙስሊሙ ግን በጉጉት ይጠብቃታል፡፡ ለምን? ለመብቱ የሚታገልባት፣ ድምጹን የሚያሰማባት፣ ህመሙን የሚተነፍስባት እለት ስለሆነች ነው! በማንነቱ ተከብሮ የመኖር መብቱን የሚጠይቅባት ቀን ስለሆነች ነው፡፡ ለዚያም አይደል በየጁሙአዎቹ የህዝቡ ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ሲሄድ የምናየው?

እንደወትሮው ሁሉ የዛሬዋም ጁምአ በሙስሊሞች ተቃውሞ ደምቃ፣ በፍትህ ጥሪ ተንቆጥቁጣ ነው የዋለችው፡፡ በአገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ደማቅ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል፡፡ እጆች ለዱአ ተዘርግተዋል፡፡ ወንድማማችነት እና አንድነት፣ የአላማ ጽናት እና ቁርጠኝነት ገኖ የወጣባት ከብዙ ያማሩ ጁምአዎች መካከል ደምቃ የወጣች ጁምአ ነበረች፡፡ በዚህች ቀን መንግስት በማን አለብኝነት የአህባሽን ስልጠና እንደአዲስ ለማስቀጠል 313 ሚሊየን ብር በጀት መድቦ ከመጅሊስ ጋር ስምምነት ማድረጉ ያስቆጣቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአገሪቱ የተለያዩ አቅጣጫዎች ‹‹313 ሚሊዮን ብሩን ለልማት›› እያሉ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ውለዋል፡፡ የተወሰኑት አብረን እንያቸው፡፡

የህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞ መነሻ እና መዳበሪያ ሆና የቆየችው፣ የትግሉ ጽንስ የተወለደባትን አወሊያን በያዘችው አዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጊድ ሰው በጠዋቱ መትመም ጀምሮ ነበር፡፡ አንዋር በአራቱም አቅጣጫ በሰው ተሞላ፡፡ በርካታ ፖሊሶች በጠዋቱ ቢስ መብራት በሚገኘው ጅንአድ ግቢ ውስጥ ተጠቅጥቀው የነበረ መሆኑን ያየ የህዝበ ሙስሊሙን ጨዋነት መንግስት የማያውቀው ይመስላል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ግን ሁሉም ሰላምን ትጥቁ አድርጎ ነበር የተገኘው፡፡

ሰላቱ ከተሰገደ በኋላ አፍታም ሳይቆይ ደማቁ ተቃውሞ ተጀመረ፡፡ እጆች የያዙትን ወረቀት አውለበለቡ፡፡ በነዚያ ወረቀቶች ላይ የተጻፉ መልእክቶች የህዝቡን የልብ ትርታ መናገር የሚችሉ ናቸው – ከድምጹ ጋር ተደባልቀው ሩቅ ይሰማሉ፡፡ ‹‹313 ሚሊየን ብሩ ለልማት!›› ብዙዎቹ የያዙት ወረቀት ነበር፡፡ በኮምፒውተር ህትመት፣ አንዳንዶቹ በማርከር፣ አንዳንዶቹ በስክሪብቶ የተጻፉ ናቸው፡፡ ትኩር ብሎ ላየው ይህ ራሱ መልእክት ነው፡፡ ‹‹በእጄ ባለው ነገርና በአቅሜ ለመብቴ እታገላለሁ! ለትግሉ የምችለውን አበረክታለሁ!›› ነው መልእክቱ፤ የያዙት ደግሞ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ጎልማሶች፣ አዛውንቶችና ህጻናቶች ናቸው፡፡ ሁሉም ቁርጠኝነታቸወን ታጥቀው፣ መስዋእትነት ሊከፍሉ ተዘጋጅተው ነው የመጡት፡፡ ሁሉም በአንድ ድምጽ፣ በአንድ ጽሁፍ፣ የአገር ሀብት የህዝብ ነውና ህዝብን በሚጠቅም ነገር ላይ እንዲውል፣ ያ ቢቀር እንኳ ህዝብን በሚጎዳ ነገር ላይ እንዳይውል ይጠይቃሉ፡፡ ‹‹ሰሚው አካል የታለ?›› ይላሉ ከሳምንት ሳምንት!

በአንዋር መስጊድ በሴቶች መስጊድ በኩል የታየው የእህቶቻችን ጠንካራ ተቃውሞ አስደማሚ ነበር፡፡ ሴቶቻችንም ለመብታቸው የሚተኙ አይደሉም፡፡ ለሃይማኖታቸው መከበር ዱላን ተጋፍጠው፣ እስርን ገላምጠው መብታቸውን ጠይቀዋል፡፡ ‹‹እኛም ለመብታችን እንታገላለን!›› ብለዋል፡፡ ‹‹ኢስላም ሰላም! ብራችን ለልማት!›› እያሉ በአንድ ድምጽ አድማሱን ሲሞሉት ያየ በእህቶቻችን ምንኛ ይደሰት?
ይህን በመሰለ ውብ ገጽታ የአንዋሩ ተቃውሞ ያለአንዳች ችግር ተፈጽሟል፡፡ በመሀል ለየት ያሉ መፈክሮችን ለማስረጽ የተደረገው ሙከራም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ በሰላም ተቃውሞውን አሰምቶ ወደየፊናው ተበታትኗል፡፡ ሁሉም ወደቤት ሲመለስ በተስፋ መቁረጥ ሳይሆን በቁርጠኝነትና በታደሰ መንፈስ፣ መብቱ እስኪከበርለት ድረስ በሚያታግለው መጠን ኃይል የተሞላ ነበር – አልሐምዱሊላህ!!!

በተቃውሞ ደምቃ የዋለችው ሌላኛዋ ከተማ ወልቂጤ ናት፡፡ የወልቂጤ ሰላማዊ ሙስሊም ማህበረሰብ በጊዜ ነበር ወደ ጃሚአል ከቢር መስጊድ መትመም የጀመረው፡፡ ትልቁ መስጊድ ሞልቶ በዙሪያው የሚገኘው ገላጣ ቦታ ዲናቸው ላይ የሚደርሰው ጥቃት ባሳሰባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተከቧል፡፡ ሁሉም ቁጡ፣ ግን ፍጹም ሰላማዊ ናቸው፡፡ ኢማሙ ሰላት ሰግደው አሰላምተው ሲጨርሱ መስጊዱ በተቃውሞ ተክቢራ ተሞላ፡፡ የእለቱን ተቃውሞ መሪ መፈክር የያዙ እጆች ወደላይ ከፍ አሉ፡፡ በርካታ መፈክሮች በዚያ አስገምጋሚ ድምጽ ተስተጋቡ… ‹‹ፍትሕ!››፣ ‹‹ድምፃችን ይሰማ!››፣ ‹‹አህባሽ አይጫንብንም!››፣ ‹‹አሽእብ ዩሪድ ኢስቃጠል መጅሊስ!››፣ ‹‹ፍትሕ ናፈቀን!››፣ ‹‹ለኢስላም እንሞታለን!››፣ ‹‹የታሰሩት ይፈቱ!››፣ ‹‹ባገራችን ሰላም አጣን!››፣ ‹‹እኛም አቡበክር ነን!›› እና ሌሎችም መፈክሮች በህዝቡ ተሰምተዋል፡፡ ደማቁ ተቃውሞ ያለምንም እንከን በሰላም ተጠናቆ ህዝቡ ወደየመጣበት ተመልሷል፡፡

በተመሳሳይ ጊዜ በስልጢ ዞን ወራቤ በአቡበክር መስጊድ በርካታ ህዝብ በተገኘበት ደማቅ ተቃውሞ ተደርጎ ውሏል፡፡ ትልቁ መስጊድ በተባበሩ ድምጾች ተንጧል፡፡ የትግሉን መንፈስ የሚያንጸባርቁ በርካታ መፈክሮችም በድምጽ ተስተጋብተዋል፡፡ ተቃውሞው የተበተነው በሰላም ያለ አንዳች እንከን ነበር፤ ዱሮውንስ ከጨዋ ህዝብ ከሰላም ውጭ መች ሌላ ይጠበቃል!

የወሎዋ ደሴ ከተማ በበኩሏ ተቃውሞዋን አሰምታ ውላለች፡፡ ጠዋት በዋለው የደሴ ችሎት ለ 260 ቀናት ያለምንም ክስ የታሰሩት እውቅ የዲን አስተማሪ አባቶች በዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔውን ያሳለፈ ሲሆን የጀግኖቹን መፈታት በጉጉት የሚጠብቀው ህዝበ ሙስሊም በጦልሀ መስጊድ ተሰባስቦ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡ ሰላቱ ከወትሮው ቀደም ብሎ 6፡42 ላይ መሰገዱ ብዙዎች ሰላቱ እንዲያመልጣቸውና እንዲዘገዩ ያደረገ ቢሆንም ከሰላቱ በኋላ ግን ህዝቡ ተቃውሞውን አሰምቶ በሰላም ተበትኗል፡፡ የትግሉን መንፈስ የሚያንጸባርቁ በርካታ መፈክሮችም ተደርገዋል፡፡

በተደጋጋሚና ተቃውሞዋ የምናውቃት ሻሸመኔ የኦሮሚያ ክልልን ለመብት በሚደረግ ትግል ካደመቁ በርካታ ከተሞች አንዷ ነች፡፡ እንደተለመደው ጀግናው የሻሸመኔ ሙስሊም በአራዳ መስጊድ በጊዜ በመሰብሰብ ሰላቱን በስርአቱ የሰገደ ሲሆን ከሰላቱ መጠናቀቅ በኋላ ከፍተኛና ደማቅ ተቃውሞ አሰምቷል፡፡ ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› እና ‹‹የታሰሩት ይፈቱ!›› የሚሉት መፈክሮች የተስተጋቡ ሲሆን ያለአንዳች የጸጥታ ችግር ህዝቡ ብሶቱን አሰምቶ ወደየመጣበት ተመልሷል፡፡ በተመሳሳይ ሰአት በዚያው በኦሮሚያ ዞን ነጌሌ ቦረና ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ መሰማቱም ተዘግቧል፡፡ የነጌሌውን ለየት የሚያደርገው ረዘም ላለ ጊዜ ሰላማዊው የነጌሌ ህዝብ መፈክር እያሰማ፣ ብሶቱን እየተነፈሰ የቆየ መሆኑ ሲሆን ተቃውሞው የተጠናቀቀውም ያለአንዳች የጸጥታ እንከን ነበር፡፡

ኦሮሚያ ክልል በዚህ ብቻ አልበቃትም፡፡ በኮፈሌ ከተማ ሰላም መስጊድ ውስጥ የተሰባሰቡ ምእመኖቿ ‹‹እኛም ለመብታችን ቆመናል!›› የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈውባታል፡፡ ሰጋጆች በሙሉ በከፍተኛ ድምቀት በርካታ መፈክሮችን ሲያሰሙ የነበረ ሲሆን ‹‹አላሁ አክበር!››፣ ‹‹ድምፃችን ይሰማ!››፣ ‹‹ኮሚቴው ይፈታ!››፣ ‹‹ፍትህ ናፈቀን!››፣ ‹‹ህገወጡ መጅሊስ አይወክለንም!›› እና የእለቱ ዋና መፈክር የነበረውን ‹‹313 ሚለዮን ብሩ ለልማት!›› በደማቅ ሁኔታ ሲያስተጋቡ ቆይተዋል፡፡ የኮፈሌ ከተማ አጎራባች በሆኑት ቃጬቀታ እና ቃበቴ ከተሞች ላይም በመስጊዶቻቸው እንዲሁ ከፍተኛ ተቃውሞ ተደርጓል፡፡ ተቃውሞዎቹ ያለ አንዳች የጸጥታ ችግር ነበር የተጠናቀቁት፡፡
ካሁን ቀደም ፖሊሶች ሰላማዊውን ሙስሊም መስጊድ ደፍረው በደበደቡባት አጋሮ ከተማም እንዲሁ ከፍተኛ ተቃውሞ ተደርጎ ውሏል፡፡ በርካታዎች በተገኙበት የተስተጋባው ይህ ተቃውሞ የአጋሮ ሙስሊሞች ወኔ በፖሊስ ዱላ ሊሰበር እንደማይችል ዳግም አረጋግጦ የዋለ ነበር፡፡ የድምጽ ተቃውሞው ከተደረገ በኋላ የፖሊስ ሰራዊት መስጊዱን እና መተላለፊያውን ዘግቶ ከበባ በማድረግ ጥቃት ለማድረስ አስቦ ነበረ ቢሆንም በአላህ ጸጋ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ መስጊዱን የከበበውን ሰራዊት ገብቶ ህዝቡ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ሲማጸኑ የነበሩት የመስጊዱ ኢማም ድርጊት ብዙዎን አሳዝኖ የነበረ ሲሆን ጥቃት ግን ሳይሰነዘር ቀርቷል፡፡ ሶስት ያህል ሰዎች ከሙስሊሞች መካከል ታስረው ተወስደዋል፡፡ በቦታው የተገኙ የመንግስት አካላትም ተቃዋሚዎችን ለማስፈራራት ፎቶዎችን እያነሱ የነበረ ቢሆንም ጀግናው የአጋሮ ሰላማዊ ህዝብ ግን ያለአንዳች መሸማቀቅ ከበባው ሲበተን ወደየመጣበት ተመልሷል፡፡

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የዱአ ተቃውሞ እንዲካሄድባት ታስባ በነበረችው ኮምቦልቻ ከተማ ላይ በኻሊድ መስጊድ በርካታ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት ሰደቃና ዱአ መደረጉም ተዘግቧል፡፡ ገና በጊዜ ወደመስጊድ ሲመጣ ለችግረኞችና ለየቲሞች ሰደቃ በመስጠት የጀመረው የኮምቦልቻ ኻሊድ መስጊድ ሰጋጅ ከሰላቱ መጠናቀቅ በኋላ ቋጥሮ የመጣውን ብስኩት እየተካፈለ በመብላት ድንቅ ወንድማማችነት አሳይቷል፡፡ ከሰደቃው መጠናቀቅ በኋላም በእስር እየተንገላቱ ላሉ ሙስሊሞች አላህ ፈረጃውን እንዲያመጣ ዱአ በማድረግ ሰዉ ወደየመጣበት ተመልሷል፡፡ በዚያው ሰሜን ኢትዮጵያ ባህር ዳር እና ጎንደር ላይ የዱአ ተቃውሞ መደረጉም ተዘግቧል፡፡ በባህር ዳር በሰላም በር መሰጊድ ከወትሮው በተለየ ከፍተኛ ቁጥር የተሰባሰቡ ሙስሊሞች ደማቅ የዱአ ስነስርአት ያካሄዱ ሲሆን ስነስርአቱ ያለአንዳች የጸጥታ ችግር ተጠናቋል፡፡ የባህርዳሮች የዛሬ እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪና ገና ብዙ እንደሚያሰዩን በተግባር ያስመሰከሩበት ቀን ነው፡፡

በሶስተኛው እርከን በአንድ መስጊድ ተሰባስቦ የመስገድና አጋርነትን የማሳየት ተቃውሞው በታሰበላቸው ከተሞች ላይ በድምቀት ተደርጎ መዋሉም ተዘግቧል፡፡ መቀሌና አላማጣን የመሳሰሉ የትግራይ ከተሞችና በሎጊያ፣ ዱብቲ፣ ደወይና አይሳይታ የሚገኙ ሙስሊሞች በየከተሞቻቸው ማእከላዊ መስጊድ በበርካታ ቁጥር በመገኘት አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡ የአማራ ክልሎቹ መካነሰላም፣ ባቲ እና ጃማ ከተሞችም አጋርነታቸውን ካስመሰከሩ ከተሞች መካከል ነበሩ፡፡ በኦሮሚያ በሚገኙት አወዳይ፣ ጭሮ፣ ሀሮማ፣ ያያቤሎ ቦረና፣ ጎሬ እና ሮቤ ከተሞች ላይም ከፍተኛ አጋርነትን የማሳየት እንቅስቃሴ ተደርጎ ነበር፡፡ በደቡቧ አዋሳ እና በሱማሌዋ ጅጅጋ፣ እንዲሁም በአሶሳና በጋምቤላ ከተሞች የሚገኙ ሙስሊሞችም ድምጻቸው ከቀሪው የኢትዮጵያ ሙስሊም ጋር አንድ መሆኑን በአጋርነታቸው አስመስክረዋል፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ ዛሬም እንደ ትላንቱ በሰከነ ልቦና በማሰብ ፍፁም ሠላማዊ በሆነ ስርዓት ሁለንተናዊ የተቃውሞ ዘዴዎችን በመጠቀም ከጫፍ እስከ ጫፍ ድምፁን ሲያስተጋባ ውሏል፡፡ ይህ እውነታ የታሪክ አካል ሊሆን ግድ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ለዕምነታቸው ባላቸው ጥልቅ ቀናዒነት ብቻ የሌሎችን መብት ፍፁም ሳይነኩ፣ የአገር ደህንነት ቀዳሚ ትኩረታቸው ሆኖ፣ ተደራራቢ በደል እየተፈፀመባቸው፣ ውስጣዊም ውጫዊም ሴራዎች እየተጎነጎኑባቸውም ጭምር እሾሀማውን ዳገት ሽቅብ መጓዙን ተያይዘውታል፡፡ ይህ ጉዳይ የሐይማኖት ጉዳይ ነው፡፡ በእርግጥም የሐይማኖት ጉዳይ በመሆኑ ልጅ አዋቂ፣ ወንድ ሴት፣ ሀብታም ድሀ ሳይል ሁሉም ጉዳዩ አድርጎ ይዞታል፡፡ ከደም ከስጋው ተዋህዷል፡፡ ጉዞው አድካሚ፣ ስጋት የተሞላበትና አሰልቺ የመሆኑ እውነታ የተረታበት ሚስጥርም ይኸው ነው፡፡
ትግላችን በአላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ፈቃድ ሁለንተናዊ የሠላማዊ ትግል ገፅታን ተላብሶ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ዳግም ያረጋገጡት እውነታ ሆኗል፡፡ እንቅስቃሴው ‹‹ሀ›› ብሎ ሲነሳ ያነገበው ዓላማ ሳይበረዝ፣ ሳይከለስና ሳይሸረሸር በቀጥተኛና የጠራ አቅጣጫ ላይ ይገኛል፡፡ ምንም የሚያሻማ፣ የሚያከራክር፣ ብሎም የተደበቀ ነገር የለውም፡፡ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ህገመንግስታዊ መብታችን ተጥሷል፡፡ የእምነት ተቋማችን የእኛ የእምነት ባለቤቶቹ ንብረት ነው፡፡ የምንመርጠውም፣ የምናስመርጠውም፣ የምንሾመውም፣ የምንሽረውም እኛው ነን፡፡ ይህንን መብት በአደባባ ፀሀይ ተክደናል፡፡ተቋማችንን የተቆጣጠሩት አካላት ሕዝበ ሙስሊሙ እንዳልመረጣቸው ዛሬም አደባባይ ወጥቶ ድምፁን ያሰማው ወገን ማረጋገጫ ካልሆነ ምን ማረጋገጫ ይመጣለት ይሆን? የመጅሊሱ አመራር ነን ብለው የተቀመጡት አካላት የሙስሊሙን ህዝብ አይወክሉትም፡፡ በሕዝበ ሙስሊሙ ስም የሚያደርጉት ማንኛውም እንቅስቃሴ ዛሬም ነገም ከህዝበ ሙስሊሙ እውቅና ውጭ ነው፡፡ ይህንን እስከ መጨረሻው ድረስ በሰላማዊ መንገድ እንቃወማለን፡፡

የአሕባሽ አስተምህሮት የተቋማችን እና የመንግሰት ድጋፍ ተችሮት በሰፊው ሙስሊም ጫንቃ ላይ ለመጫን እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዛሬም ውርደትን ተከናንቦ ይቀለበሳል፡፡ በዚህ ስም እየባከነ ስላለው የሀገርና የህዝብ ሀብት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚኖሩ መላ ሀገር ወዳድ ወገኖች እንዲሁም እርዳታ ሰጪም ሆኑ አበዳሪ ወዳጅ ሀገራት እውነታው ይደርስ ዘንዳ የበኩላችንን ተወጥተናል፡፡ ይህንኑ መልእክታችንን ለማስተላለፍም ተደጋጋሚ ጥረቶችን ማድረጋችንን እንቀጥላለን፡፡

በዜጎች ላይ በሐይማኖት ሰበብ የሚደርሰውን በደል በመቃወም በምድራችን ላይ ሆነን እያደረግነው ያለው በርካታ ወራትን ያስቆጠረው ይህ የትግላችን ሂደት መቋጫው ሩቅ አይደለም፡፡ በዚህ ሁሉ ሂደታችን ድፍን ዓለም የመሰከረለትን ሠላማዊነታችንንና ጨዋነታችንን፣ እንዲሁም ያነሳናቸውን ጥያቄዎች ዳግም በማጤን በሰከነ ልቦና ምላሽ ለመስጠት ያኮረፈውን ዜጋ ለመጠገን፣ ከቤቱ የወጣውን ወገን ለመመለስ፣ ብሎም ፊቱን ወደ ልማት እንዲዞር ለማድረግ ከበቂ በላይ ነው እንላለን፡፡ መብታችን እስኪከበርልን ድረስም በቁርጠኝነትና በሰላማዊነት ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡
ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም!

አላሁ አክበር!

የጥፍርዎ ቀለም ስለጤናዎ ምን ይናገራል? (ሊያነቡት የሚገባ)

0
0

በግርማ ብርሀኑ ጤና
nail 2

nail 3

nail 4

nailየቀለም አልባ (የገረጣ) ጥፍር
ጥፍርዎ እጅግ የገረጣ ከሆነ ከባድ የሆነ የጤና ችግር መከሰቱን አመላካች ሊሆን ሲችል ከእነዚህ የህመም አይነቶች ውስጥም ደም ማነስ፣ የልብ ህመም፣ የጉበት ችግርና የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ያመላክታል።
ነጭ ጥፍር /
white nails/

ጥፍርዎ ነጭ ሆኖ ዳርዳሩ ጠቆር ያለ መልክ ከያዘ ሄፒታይተስን ለመሰሉ የጉበት በሽታ ችግሮች የተጋለጡ መሆኑን አመላካች ሲሆን ምንም እንኳ ሄፒታይተስ ባይገኝም ለሌሎች የጉበት ችግሮች ተጋልጠው ሊሆን ይችላሉና ትኩረትን ይስጡት።
ቢጫ ጥፍር
/Yellow Nails/

የጥፍር ቢጫ መሆን ከምንም በላይ በፈንገስ ኢንፌክሽን የመጠቃት ምልክት ሲሆን ኢንፌክሽኑ እየባሰ ከመጣም በጥፍሮችዎ ስር የሚገኘው ቆዳ የመሰነጣጠቅና የመፈረካከስ ምልክት ያሳያል። ጥፍሮችዎም በጣም ከመጠንከር በተጨማሪ የመሰባበርና የመሰነጣጠቅ ባህሪ ያሳያል። አልፎ አልፎም ቢሆን ቢጫ ጥፍር በጣም አደገኛ በሆነ የታይሮድ ችግር፣ የሳንባ በሽታና ስኳርን የመሰሉ ህመሞች መከሰታቸውን አመላካች ነው።
ሰማያዊ ጥፍር
/Bluise Nails/

ጥፍርዎ ወደሰማያዊነት ያመዘነ ቀለምን ከተላበሰ በቂ የሚባል ኦክሲጅን እያገኙ እንዳልሆነ አመላካች ሲሆን ይህም በሳንባ ኢንፌክሽን ወይም ኒሞኒያን በመሠሉ ከባድ የሳንባ ህመሞች መጠቃትዎን ሊያመላክት ይችላል። በእርግጥ አንዳንድ ጊዜም ሰማያዊ የጥፍር ቀለም ከልብ ችግሮች ጋር ይያያዛል።
የተሰነጠቀ ጥፍር
/cracked or split Nails/

ደረቅና በቀላሉ የሚሸራረፍ ጥፍር በተለይ ከታይሮይድ ጋር የተያያዙ በሽታዎች መገለጫ ነው። ጥፍር ከመድረቅና ከመሸራረፉም በላይ ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ቦታዎች የሚሰነጠቅ ሲሆን በፈንገስ ኢንፌክሽን ወቅት እንደሚከሰተው ቢጫ አይነት መልክ ሊያሳይም ይችላል።
ባለጥቁር መስመር ጥፍር
/Dark Lines beneate the Nails /

ጥቁር መስመር በጥፍሮቻችን ላይ ሲከሰት አስቸኳይ የጤና ምርመራ ማድረግ የሚያስፈልግ ሲሆን ይህ አይነቱ ምልክት በገዳይነታቸው ግንባር ቀደም ከሆኑት የቆዳ ካንሠሮች አንዱ የሆነው የ‹melanoma› ካንሠር ምልክት ነው።
የተበሉ ጥፍሮች
/gnawed Nails/

ብዙ ሰዎች ጥፍር መብላትን እንደ አጉል ልማድ እንጂ እንደጤና እክል አይቆጥሩትም። ይሁን እንጂ አብዝተው ጥፍራቸውን የሚበሉ ሰዎች በጭንቀትና በውጥረት የተጠቁ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ‘obsessive compulsive disorder’ ለሚባል ስነልቦናዊ ችግር የተጋለጡ ናቸው።

ከላይ በጥቂቱ እንደተመለከትነው የጥፍራችን ቀለምና ይዘት መቀየር የተለያዩ የጤና ችግሮች መከሠታቸውን አመላካች እንደሆነ ቢታመንም የጥፍራችን ቀለም መቀየር በእርግጠኝነት የጤና ቀውስ ለመፈጠሩ ምልክት መሆኑን ለማረጋገጥ ሀኪም መጐብኘት እንዳለብን ማስታወስ ይገባል። የጥፍር ቀለምን በማየት ብቻም በዚህ ህመም ተጠቅቻለሁ ብሎ መደምደም አስቸጋሪ ሲሆን ህክምናዎን ሳያማክሩም ምንም አይነት መድሃኒትም መውሰድም አይመከርም።

ክፉን ሰውና ክፋተኝነትን እንዴት እናውቃለን? በይሄይስ አእምሮ

0
0

ይሄይስ አእምሮ

comment pic  ርዕሴ በጣም እንዳይጮኽብኝ ፈርቼ እንጂ ላደርገው አስቤና ፈልጌም የነበረው “ሰይጣንና ሰይጣናዊነት እንዴት ይታወቃሉ?” የሚል ነበር፡፡ ይህ ጽሑፌ በዚሁ ተመሳሳይ ጉዳይ ዙሪያ ባለፈው ሰሞን በአንዳንድ ድረ ገፆች የወጣውን በሴቴኒስቶች የሰላምታ መለዋወጫ ምልክቶች ምስል የተደገፈ አነስተኛ መጣጥፍ የተከተለ  ነው፡፡ ከሁሉ በፊት ግን ቀጣዩን ሥነ ቃላዊ ትውፊት ለነገሬ መነሻነት ባስቀድም ደስ ይለኛል፡፡

የቸገረው ሰው ከገባበት የችግር ማጥ ለመውጣት የማያደርገው ነገር የለም፡፡ አንዲት ሴት፣ ልጅ መውለድ እምቢ ይላትና ለዐርባ አራቱም ታቦት ትሳላለች፤ በዚያም አልሆነላትም፡፡ በየጠንቋዩና በየደብተራው ቤትም ደጅ ትጠናለች፤ በዚያም አልሆነም፡፡ በየጠበሉና በየሀኪም ቤቱም ትንከራተታለች፤ አሁንም በዚያም አይሆን ይላታል፡፡ ቢጨንቃት ለሰይጣን ትሳላለች፡፡ ስለቷም “አንተ እንደኔው የእግዜር ፍጡር የሆንክ ሰይጣን ሆይ! ልጅ እወልድ ብዬ ብዙ ተሳልሁ፤ ወጣሁ ወረድሁ ግን አልሆነልኝም፡፡ አሁን ደግሞ ባንተ በኩል ልሞክር ወስኛለሁ፡፡ ስለዚህ እስከዛሬ ዓመት ድረስ ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ ከሰጠኸኝ ራሴው ፈትዬ አንድ ቡልኮ በስለት አስገባልሃለሁ” የሚል ነው፡፡

የአጋጣሚ ነገር ሆነና ልክ ባመቱ የሰማ ሰምቷት አንድ ወንድ ልጅ ከነቅጭልጭሉ ትወልዳለች፡፡ ደስታዋም ከጣሪያ በላይ ይሆናል፡፡ ከአራስ ቤት ጀምራ ትፈትልና በክርስትናው ማግሥት ለሰይጣን የተሳለችውን ቡልኮ በዕውቅ ሸማኔ አሠርታ ዝግጁ ታደርጋለች፡፡ ነገር ግን ያላሰበችው ችግር ይገጥማታል፡፡ ሰይጣንን የት አግኝታ ትስጠው? ችግር እኮ ነው፤ አንዱ ሲሟላ አንዱ አይሟላም፡፡

በየመንደሩና በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እየዞረች “የሰይጣንን ቤተ ‹ክርስቲያን› ያያችሁ ነይ ወዲህ በሉኝ” ብትል ማን ዐውቆት ያሳያት? ብዙ ትለፋለች፤ ትደክማለችም፤ ነገር ግን በክንዷ አንጠልጥላ የምትዞረውን ቡልኮ ወይም ጋቢ የሚረከባት አንድም ሰይጣን ይጠፋል፡፡

ችግሯን ያስረዳቻቸውና የገባቸው አንድ ብልህ ሽማግሌ ግን እንዲህ ሲሉ ይመክሯታል፡፡ “አንቺ ሴትዮ፣ ልጅ ለመውለድ ያደረግሽው ጥረት በውነቱ የሚገርምና ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማያውቅ ነው፡፡ አሁን ሰይጣንን ካላገኘሽውና ቤቱንም ካጣሽው በአማራጭነት እንዲህ አድርጊ፡- እሁድ ቀን ወደ አንዱ ቤተ ክርስቲያን ሂጂ፡፡ ከዚያም ማርገጃው አካባቢ ሽማግሌዎች ተሰብስበው የተጣሉ ወይም የተቀያየሙ ሰዎችን በሚያስታርቁ ጊዜ የሽማግሌ ቃል አልሰማም ብሎ ንቋቸው ከጉባኤው እመር ብሎ የሚወጣ ሰው ስታገኚ ‹በስምህ የተሳልሁትን ልሰጥህ ስፈልግህ ኖሬ ዛሬ ገና አገኘሁህ፤ ይሄውልህ ቡልኮህ› በይና ትከሻው ላይ ጣይለት፤ ሰይጣን ማለት ዕርቅና ሰላምን የማይወድና የማይፈልግ ነውና እዚያ ማርገጃው ላይ በሰው ተመስሎ ታገኝዋለሽ፡፡” ይላታል፡፡

‹ሞኝ የነገሩትን፤ ብልህ የመከሩትን› ነውና ያቺ ሴት እንደተባለችው ቤተ ክርስቲያን እየሄደች ያን መሳይ ሰው ታጠምድ ያዘች፡፡ አንድ ቀንም እንደድንገት ሃሳቧ የሚሣካበት ምቹ አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ አንድ ደመ ሞቃት ሰው የሽማግሌዎችን ምክርና ተግሣጽ እንዲሁም የማስታረቂያ ሃሳብ ንቆ “ደግሞ እናንተን ብሎ አስታራቂ! ቀልማዳ ሁላ፤ እኔ ነኝ ደግሞ ‹በድየሃለሁና ይቅር በለኝ ብዬ እሱ እግር ላይ የምወድቅ?› የወሬ ቋቶች! …” በማለት ተስፈንጥሮ ከጉባኤው ሲወጣ ታየዋለች፡፡ ይሄኔ በደስታ እየተፍነከነከች አፈንጋጭ ጎልማሣውን ጠጋ ትልና “እሰይ! እንኳን አገኘሁህ! አሁን ገና ገበያየ ሞላ! ለስንት ጊዜ ስፈልግህ ኖሬ ዛሬ ገና ተሳካልኝ፡፡ በል ስለትህን ተረከበኝ” ትልና ቡልኮውን እሰውዬው ትከሻ ላይ ትጥልለታለች፡፡

ሰውዬውም ይደነግጥና ‹እንዴ? ምንድነው እሱ – ምን አድርጌልሻለሁ?…› በማለት ምክንያቱን ይጠይቃታል፤ እሷም በተመከረችው መሠረት ነገሩን ከሥሩ ታስረዳዋለች፡፡ ይሄኔ ያ ሰው ‹ሰይጣንነቱ› ይከሰትለታል፤ እሱ ሰው እንጂ ሰይጣን እንዳልሆነ በማስረዳት ጋቢውን ይመልስላትና ወደጉባኤው ተመልሶ ሽማግሌዎቹንም ይቅርታ ጠይቆ ቀድሞ በተነገረው የማስማሚያ ቃላዊ ሠነድ መሠረት ከባላንጣው ጋር ይታረቃል፡፡

ብልሁ መካሪ ሽማግሌ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መምታታቸውን ልብ ይሏል፡፡ መግቢያየ ይህን ይመስላል – አሁን ወደዋናው መስመር ልመልሳችሁ፡፡

ሰይጣን እንዴት ይታወቃል? ተከታይ ጋሻ ጃግሬዎቹስ እንዴት ይለያሉ? በጣም ቀላል ነው፡፡ በቅድሚያ ግን እንደመነሻ ከአሥራ አንዱ ሰይጣናዊ መመሪያዎች ሦስቱንና(4ኛውን፣ 7ኛውንና 11ኛውን) ዘጠኙን ሰይጣናዊ ኃጢኣቶች ቀጥለን እንመልከት፡፡

4.  በቤትህ የመጣ እንግዳ ካበሳጨህ ያለአንዳች ርህራሄ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ አጸፋውን መልስለት፡፡ (ዐይንን ላጠፋ ዐይንን ማጥፋት ከሚለው የሀሙራቢ ሕግ ጋር የሚመሳሰል)

7. ፍላጎቶችህን ለማሳካት ጥንቆላና መተት ተጠቅመህ ከሆነ ለዚህ (ሰይጣናዊ) አበርክቶ ዕውቅና ስጥ፤ ምሥጋናም አቅርብ፡፡ ይሁንና በጥንቆላና በምትሃት ስኬት ጫፍ ላይ ከደረስክ በኋላ የበላህበትን ወጪት ሰባሪ ሆነህ ሰይጣንን ብትክድ ያገኘኸውን ሁሉ ታጣለህ፤ የሰይጣን በረከትም ይለይሃል፡፡

11. በየትኛውም ግዛት ስትጓዝ ስለምንም ነገር ሃሳብ አይግባህ፤ በጉዞህ ላይ የሚያስቸግርህ ሰው ቢገጥምህ በቅድሚያ እንዲተውህ አስጠንቅቀው፤ ካልተወህ ግን ድራሹን አጥፋው፤ ድባቅ ምታው፡፡

 

ዘጠኙ ኃጢኣቶች (ሴቴኒስቶች ሊተላለፏቸው የማይገቡ የሃይማኖቱ መሥራች አንቶን ሌቪ የቀመራቸው)

  1. ደደብ መሆንና በሌሎች ተበልጦ መገኘት (ኃጢኣት ነው!)
  2. እውነትን እንዳመጣጧ በኃይልም በዘዴም በተገኘው ሥልት ሁሉ ከመጋፈጥ ይልቅ እንደቀሪው ማኅበረሰብ በአስመሳይነትና በነባር ባህል ለመመሳሰል መሞከር
  3. የኃይል ግብረ መልስ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች በታጋሽነት ማለፍ
  4. የሆነን እንዳልሆነ ወይም ያልሆነን እንደሆነ አድርጎ ራስን ማታለል
  5. የራስን ስሜት ከመከተል ይልቅ በይሉኝታና በሀፍረት ታስሮ የሌሎችን ፍላጎት ተቀብሎ በየዋህነት ከጎጋው ሕዝብ ጋር መንከርፈፍ
  6. ወደተፈለገው ግብ የሚያደርስ (ማንኛውም ዓይነት) ራዕይና ዓላማ አለመያዝ
  7. ያለፈን የሃይማኖትና የማኅበረሰብ ትውፊት መርሣት ሲገባ ያን ማስታወስ
  8. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በራስ ስኬት መኩራት ያለመፈለግና ያለመቻል
  9. በሁሉም ዘርፍ ሁሉንም ቀድሞ ለመገኘት በማንኛውም መንገድ የተቻለውን ሁሉ ጥረት አለማድረግ

 

ሰይጣናዊነትና ተከታዮቻቸው (Satanism and Satanists) በይፋ ቤተ አምልኮ (Church of Satan) አቁመው ሰይጣንን ማምለክ የጀመሩበት ዘመን የቅርብ ጊዜ ክስተት ቢሆንም ይህ ሃይማኖት በድብቅም ይሁን ሲቻል በግልጽ፣ በሰይጣን ስምም ይሁን በሌሎች መጠሪያዎች በዚህች ዓለም ውስጥ ኅልውናውን ያገኘው ከሰው ልጆች መፈጠር ጋር እንደሚያያዝ መገመት አይከብድም፡፡ “ሊበሉት የፈለጉትን አሞራ ስሙን ይሉታል ጅግራ” እንዲሉ ሆኖ በስያሜ ለሰይጣን የቀረበም ይሁን የራቀ በተግባር ግን ሰይጣናዊ የሆነ የእምነት አካሄድ በዓለማችን ከረጂም ዘመን ጀምሮ በገሃድ ይታይ እንደነበር ለማንም መዝገብ አገላባጭ እንግዳ ነገር አይሆንም፡፡ ባገራችን የቆሌ ባዲገዝና የቦረንትቻ ባህል፣ ‹እነዚህ ባለውቃቢዎች ለካንስ ክርስቲያኖች ናቸው› በሚል የዋህነት ሰው እንዲከተላቸው ‹ገብርኤልንና አቡየ ፃዲቁን ዘክሪ፣ የሚካኤልን ጠበል ለሦስት ሰባት ጠጪ…› የሚሉትን አጭበርባሪ ባለአውሊያዎች፣ ሌሊት ቅኔ ማኅሌት ላይ ቃለ እግዚአብሔርን በዕዝልና በአራራይ እያንበለበሉ ቀንና ባሳቻ ሥፍራ ግን መጥሐፍ የሚገልጡ ደባትርና ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት… በሙሉ የአጋንንት ጭፍራዎች መሆናቸውንና ይህም ዕኩይ ተግባር ከጥንት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ማኅበረሰብኣዊና ሃይማኖታዊ ክዋኔ እንደሆነ መገንዘብ አይቸግርም – የሁለት ጌቶች አሽከር መሆን የሚፈልግ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ሣይሆን የሰይጣን አሽከር ነው፡፡ በዚህ መስመር መጓዙ ብዙ ያደክመናልና ባጭሩ እንመለስ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ “ጣፋጭ ፍሬ ከዛፍ ላይ እንዳለ ያስታውቃል” ይላል፡፡ የክርስትና እምነት ቁንጮ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስም እዚህ የምናነሳቸውን ሰዎች “በሥራቸው ታውቋቸዋላችሁ” ይለናል፡፡ አዎ፣ የማን ማንነት በሥራው ይታወቃል፡፡ አዋዋላችንም የሚናገረው ብዙ ነው፡፡ ከነተረቱ “ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን ልንገርህ” ይባላል፡፡ ስለዚህ ከየትኛው ወገን እንደሆንን ለመለየት ቀላሉና ብቸኛው መንገድ በሥራችን ማለትም በዘወትር ተግባራችን የምንገልጠው የዕኩይነት ወይም የደግነት መገለጫ ምግባራችን እንጂ የአነጋገራችን ለዛና መስህብ ወይም የአለባበሳችን ማማር ወይም የፂማችን መንዠርገግ አይደሉም፡፡ የምንከተለው ሃይማኖትም ምናልባት ጠቋሚ እንጂ ትክክለኛው የመጽደቃችን ዋስትና አመላካች ሊሆን አይችልም፡፡ በአላህ ስም አንገት እየቀሉ፣ በእግዚአብሔር ስም ግድያን ጨምሮ ሕዝብ ላይ ሰይጣናዊ ቁማር እየተጫወቱ፣ ኩነኔ ካልሆነ ጽድቅ ይገኛል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ ሰይጣን ደግሞ ብልጥ ነው፤ የምታደርገው ነገር እንጂ የምትከተለው ሃይማኖት ጉዳዩ አይደለም፤ በሥራህ ካከበርከው ፓትርያርክም ሁን ኢማምም ሁን ራባይም ሁን ኮርተህ የመንግሥቱ ወራሽ ነህ፤ እርሱም የአንተን ነፍስ ካለተቀናቃኝ ተረካቢ ነው፡፡ ምሥጢሩ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ያለው ነገር ሁሉ ለ‹ምሁራዊ› ፍልስፍናና ለጉንጭ አልፋ ክርክር ፍጆታ የሚውል እንቶፈንቶ ነው፡፡

ከዚህ በተያያዘ ግን በቅድሚያ የጋራ መግባባት እንዲኖረን የሚያስልግ ጉዳይ አለ፡፡ እሱም ዕኩይ ስንል ምን ማለታችን ነው? ደግ ስንልስ? ለሁለቱም መለኪያችን ምንድነው? በማንስ ዕይታ? ለአንተ ዕኩይ የሆነ ነገር ለእኔ ደግ ከሆነ ዳኛችን ማን ሊሆን ነው? በአንድ ሀገር ወንጀል የሆነ ነገር በሌላ ሀገር ፍቁድ ከሆነ የጋራ መግባቢያው የወል ስምምነት እንዴት ሊፈጠር ይችላል? ነገሩ ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ክርክር ያለው ነገር ነው፡፡

ምሳሌ ወስደን ማየት እንችላለን፡፡ በአንዳንድ የክርስትና ሃይማኖት ዘርፎች የተመሳሳይ ፆታዎች ወሲባዊ ግንኙነት ከቀሲስ እስከ ሊቃነ ጳጳሣት ድረስ እንደሰደድ እሳት የተዛመተ በመሆኑ “የኔ ሶዶማዊ መሆን እግዚአብሔርን በ‹ቅንነት› ከማገልገል ጋር ምን ያገናኘዋል?” በማለት በምድራዊ መንግሥቶቻቸው ሕጎች ብቻ ሳይሆን በቀኖና ቤተ ክርስቲያንም ውስጥ በቃለ ዐዋዲነት እንዲጽድቅላቸው የሚታገሉ ‹የእግዚአብሔር ቤተሰቦች› በብዛት መታየት ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ በሌላ በኩል ከሰይጣን አምላኪዎች አካባቢ ለዘብተኛ የሚባሉት ይህን እኛ ብዙዎቻችን በሰይጣናዊነት የምንፈርጀውን የግብረ ሶዶም ተግባር የሚቃወሙና እንዲያውም ‹ሰው ካልተነኮሰህ አንተ ቀድመህ አትተንኩሳቸው› ብለው የሚያምኑ “ደጋግ” ሰይጣናውያን አሉ፡፡ በክርስትና ሃይማኖት መስጠት (በብቸኝነት ባይሆንም) እንደሚያጸድቅ ይሰበካል፤ በሌላም በኩል በዚሁ ሃይማኖት አንዳንድ የተማሩ ተከታዮች ዘንድ መስጠት ሰውን ስለሚያሰንፍ ከአጽዳቂነቱ ይልቅ አስኮናኝነቱ ይበዛል የሚሉ ወገኖችም አሉ፡፡ የክርክሬ አካሄድ ለሁሉም ግልጽ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡

ስለዚህ ዕኩይነትና ደግነት እንደቁንጅና ሁሉ የተመልካቹን ፍርድ የሚጠባበቅ ዋጋው በታሳቢነት የሚሰላ ሊሆን ነው ማለት ነው፡፡ ነገሩን ብዙ አናራቅቀውና ሰይጣናዊነትንና ሰይጣን አምላኪነትን እስካሁን ብዙዎቻችን የሚገባንን ያህል አድርገን እንውሰደው፡፡ በነገራችን ላይ በግርድፍ ግምት አራት ዋና ዋና ቅርንጫፎች እንዳለው ከሚገመተው የሰይጣናዊነት እምነት ውስጥ ‹አማፂ ሰይጣናዊነት/Rebel Satanism›ን ያህል የከፋ የክፋትና የአመፃ ድርጊት የሚፈጽም እንደሌለ በዘርፉ ዕውቀት ያላቸው ሰዎች ይናገራሉ፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት ዓለምን ከጽንፍ እስከ አጽናፍ እያመሳት ያለው አፍራሽ ኃይል (Negative Energy) እንግዲህ ይሄኛው ነው ማለት ነው፡፡ ተከታይ የጥፋት ኃይሎቹም በሀገራቱ መንግሥታትና በኅቡዕም ይሁን በግልጽ በሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ቡድኖች ውስጥ የተሰገሰጉ በደም የሚነግዱ ጨካኝ ዜጎች ናቸው፡፡ የነሱ ጭካኔ በጨለማው ንጉሥ በዲያብሎስ ዘንድ የሚያሸልምና የሚያሾም ድንቅ ሥራ ነው፡፡ በገደሉ ቁጥር ደስታቸው ይበዛል፤ ባሰቃዩ ቁጥር የመንፈስ መነቃቃትን ያገኛሉ፡፡ የደግነት ምግባር የሚያስከፋቸው፣ የክፋት ሥራ ጮቤ እሚያስረግጣቸው የተንኮልና ሸር አምባሳደሮች ናቸው፡፡ በግዛታቸውና በዘመነ ሥልጣናቸው የተገኘን ምሥኪኖች ግን እናሳዝናለን – ከልባዊ በስማምና አቡነ ዘበሰማያት ሌላ ምንም ጦር የሌለን ድሃ ወገኖች ይህ ዘመነ ሰልቢያኖስ ክፍላችን አይደለም፡፡

ጉንጭ አልፋ ክርክራችንን ትተናል፡፡ ክፉ ማለት ሆን ብሎና አለ አንዳች ምክንያት – ለሥጋዊ ጥቅምና ፍላጎቱ ሲል የሚገድል፣ የሚያሥር፣ የሚያሰቃይ፣ የሚጠላ፣ የሚያዳላ፣ ሆን ብሎ የሚጎዳ፣ የማይስማማ፣ የሚያስርብ፣ የሚያስጠማ፣ የሚያሰድድ፣ የሚያሳድድ፣ የሚከፋፍል፣  … ነው ብለን ለጊዜው እንስማማ – እንደወያኔዎች፡፡ እነዚህንና ሌሎች ብዙዎቻችን በክፉ ሥራነት የምንስማማባቸውን የክፋተኝነት ድርጊቶች የሚፈጽም ዐወቀውም አላወቀውም – ወደ ቤተ ሣጥናኤል ሄዶ ጸለየ አልጸለየ – የቤተ ሰይጣን ተከታይ (ሴቴኒስት) ነው፡፡ እርግጥ ነው ከሴቴኒስቶችም ‹ዘመናዊ ሴቴኒስቶች(Modern Satanists)› የሚባሉት በስም ብቻ ሣይሆን በተግባርም ‹ክርስቲያን ነን› ከሚሉ አንዳንድ አስመሳይ ወገኖች ጋር የተቀራረበ እንዲያውም የተሻለ ባሕርይና አመለካከት እንዳላቸው በዘወርዋራም ቢሆን ከፍ ሲል ዐይተናል፡፡ ትልቁ ቁም ነገር ስማዊው የየሃይማኖቶቻችን መጠሪያ ሳይሆን ዋና የማንነት መገለጫችን ተግባራችን ነው፡፡ እናም እንደኔ እንደኔ ክፉኛ ግራ ከመጋባቱ የተነሣ በሰይጣን ግዛት ሥር አድሮ ነገር ግና መልካም ሥራ የሚሠራ ሰው በእግዚአብሔር ግዛት ሥር ሆኖ በማወቅ ክፉ ሥራ ከሚሠራ ሰው ያነሰ ዋጋ ያገኛል ብዬ አልገምትም፡፡ ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዋጋችንን የሚተምነውና የየመክሊታችንን የሚሰጠን በሰው – ሠራሽ የልዩነቶች ጎራ ተመሥርቶ ሳይሆን በግብር በምናሳየው መልካም ሥራችን ላይ ተመሥርቶ መሆኑን አምናለሁ፡፡ የሆነው ቢሆን ግን “ዕብድ ቢጨምት እስከ ዕኩለ ቀን ነው” እንዲሉ ነውና በተለይ ሰይጣናዊነትን በምንም መንገድ የማላበረታታ መሆኔን በዚህ አጋጣሚ ላሰምርበት እወዳለሁ፡፡

ዓለማችንን የሠይጣን መፈንጫ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ እጅግ በጣም የቆዬ እንደሆነ ይነገራል፡፡ እንደዚህ ዘመን ግን ሰይጣናዊነት በምልዓት የተገለጠበት ዘመን ታይቶ አይታወቅም ነው የሚባለው፡፡ በተለይ የፊልምና የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ግዘፍ ነስቶ እንዲህ ጫፍ በደረስ ሁኔታ የዓለም ወጣት ዜጎችን መጫወቻ ማድረግ ከተጀመረ ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ወዲህ የእግዚአብሔር ስም እንዳይጠራ እንኳን እዬተደረገ ያለው ሰፊ ዘመቻ በታላቅነቱ ወደር የሚገኝለት አልሆነም – እውነቱን ለመናገር የእግዚአብሔርን ስም መጥራት በርሱም ማመን ፋራና ኋላ ቀር እያስባለ፣ ብዙዎችንም እስከማሣፈር በደረሰ ሁኔታ ከእውነተኛው መንገድ እያሰናከለ የምንገኝበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ በተቃራኒው ግን ዱሮ ያሣፍር የነበረ ጠንቋይና ደብተራ ቤት እየሄዱ መጎናበስና የሰዎችን ጫማ መላስ ዛሬ ዛሬ የሚያኮራ የዘመኑ ፋሽን ሆኗል፡፡ ጎረቤትህን፣ ጓደኛህን፣ ሀብታምን፣ ታማሚን፣ ምቀኛ ድሃን… ተመልከትና ይህ የምልህ ነገር እውነት ሀሰትነቱን አጢን፡፡ የጠፋንበት ዘመን ላይ እንደምንገኝ አትጠራጠር፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ባለፀጋና የተደላደለ ኑሮ የሚኖር አብዛኛው ሰው አንድም የሰይጣን አምላኪ ነው፤ አንድም በተለያዩ ወንጀሎች የሚታማ ነው – ሁሉም ግን የሰይጣናዊነት መገለጫ በመሆኑ ሰውዬው ያው ሴቴኒስት ነው – እንደአካሄድ ቅዱስ ሰይጣንና እርኩስ መልአክ የሉም – ምርጫው አንድና አንድ ብቻ ነው፤ እግዚአብሔር ወይ ሰይጣን – ብርሃን ወይ ጨለማ፡፡ የምልህ ነገር የምቀኛ ወሬ እንዳይመስልህ፡፡ አንተም ብልጥ ከሆንክ ሰይጣን የመሆንና እንደነሱ የመክበር ቦርቃቃ ዕድል አለህ፤ አለበለዚያ ለፍተህና ጥረህ ግረህ በወዝህ መኖር፡፡ በበኩሌ ሰይጣን የመሆን ዕድሉ ነበረኝ፤አለኝም፡፡ ግን አልተጠቀምኩበትም፤ወደፊትም የምጠቀምበት አይመስለኝም፡፡ ስለወደፊት እርግጠኛ መሆን ስለማይቻል ነው የተጠራጠርኩ የመሰልኩት፡፡ እንጂ የሰይጣን ሀብት ምኑ ሊያስቀና! በአፍንጫየ ይውጣ!

ከፍ ሲል እንደተገለጸው ወጣቱን ማግኘት የሚቻለው በአብዛኛው በሙዚቃና በፊልም እነዚህንም ዋነኛ መደላድል በሚያደርገው በወሲብ አማካኝነት ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች ለማሣካት ደግሞ የገንዘብ አስፈላጊነት አማራጭ የለውም፡፡ ለዚህም ነው መጽሐፉ “ገንዘብ የኃጢኣት ምንጭ ናት” የሚለው፡፡ በእያንዳንዱ ሀብት በስተጀርባ ወንጀል ስለመኖሩ በተደጋጋሚ የሚወሳውም የገንዘብን የነፍስ አማሣኝነት አጉልቶ ለማሳየት ነው፡፡ አሁን በዘመናችን ከፈጣሪ ይልቅ ቤተ አምልኮ አልቆመለትም ጽላትም አልተበጀለትም እንጂ ገንዘብ እስከመመለክ የደረሰው ሰው ራሱ በሠራው የምድር ንዋይ ፈጣሪን መለወጡን የሚያሳይ የዝቅጠት ምልክት ነው፡፡ በዚህ ዘመን እጅግ ብዙ ሰዎች ሁሉንም የሃይማኖትና የሞራል ድንበሮች ጥሰው አቅላቸውን በመሳት ገንዘብን የሚያሳድዱት የዓለም ብልጭልጭ ነገሮች ካለገንዘብ እንዲሁ በምኞት ብቻ ሊገኙ ስለማይችሉ ነው፡፡ እዚህ ላይ ምርጫው ሁለት ነው – ከጤናማ ኅሊና ጋር በእውነተኛው ገቢ በድህነት እየኖሩ መቸገር ወይም በሰይጣናዊ ቀድዶ ሕክምና ኅሊናን ከጭንቅላት አውጥቶ በ‹ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ› ዘይቤ በተገኘው መንገድ ሁሉ ለቁሣዊ ሕይወት ብልፅግና መጣር፡፡ በዚህኛው አቅጣጫ ለሚመራ ሰው ገንዘብ እስካስገኘ ድረስ ማንኛውም እንቅስቃሴ በሕግ ቢከለከልም በተግባር የተፈቀደና ያልተከለከለ ያህል የሚቆጠር ነው፡፡

መንግሥታዊ ሥርዓቶችም የዚሁ የንቅዘት ሥርዓት አባላት በመሆናቸው እነሱም የበኩላቸውን ይሞስናሉ፤ ከቢጤዎቻቸውም ጋር ይተባበራሉ፤ ያስተባብራሉ፡፡ የማይሞስን የነሱ ፀር መስሎ ስለሚታያቸው ባገኙት ዘዴ ሁሉ ያጠፉታል – በ‹የምዬን እከክ ወዳብዬ› ሥልት ሙሰኛ ነው ብለውም ዘብጥያ ሊያወርዱትና በፈጠራ ክስ ሊያሰፈርዱበትም ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ሞሳኝና አስሞሳኝ፣ በራሱ አንጡራ ገቢ የማይኖር፣ ያልተፈቀደለትን ማንኛውንም ነገር ከሰው የሚቀማ፣ ሥልጣኑን ለመጨቆኛ እንጂ ባግባቡ የማይጠቀም፣ ሕዝብን በሥልጣኑ የሚበድልና የሚያጉላላ ሁሉ የሰይጣን ወገን ነው፡፡ በዚህም የሰይጣን ወገን ይታወቃል፡፡

ወደሰይጣናዊ ተቋማትና አመራሮቻቸው እንመለስ፡፡ ብዙዎቹ ምናልባትም ሁሉም የነዚህ ዓለም አቀፍ ታላላቅ ተቋማት ባለቤቶች በኢኒሼሽን ፒራሚዳዊ የደረጃ ሠንጠረዥ ከፍተኛውን ዲግሪ በያዙ የዚህኛው ወይም የዚያኛው ምሥጢራዊ ሰይጣናዊ ድርጅት አባላት ናቸው፡፡ (ለጠቅላላ ዕውቀት፣ የቤተ ሣጥናኤል አመራር መዋቅር ዲግሪ ከ1-5 ሲሆን ‘the Skull and Bones’ን የመሳሰሉ ከዓለማችን ሀብትና ሥልጣን ጀርባ የሚገኙና ወደጥልቁ የጥፋት ባህርም እያዳፉን የሚገኙት የምሥጢራዊ ድርጅቶች ዲግሪ ደግሞ ከ1-33 እንደሚደርስ ይነገራል፡፡ ይህ ዲግሪ ለነሱ እንደማዕረግ የሚቆጠር ነው – በልፋት(በጥፋት?) የሚገኝ!)

የሚደነግጥ እንዳይኖርብኝ እሰጋለሁ እንጂ በአሁኑ ወቅት ሴተኒስቶች ሁሉንም የዓለም ነገር ተቆጣጥረዋል፡፡ የቀራቸው ያለ አይመስልም፡፡ አንተንም አንቺንም እኔንም ተቆጣጥረውናል፡፡ በምትበላው፣ በምትጠጣው፣ በምትለብሰው፣ በምትጓጓዝበት… ይመጡብሃል – በዕቃዎች ላይ በግልጥም ይሁን በሥውር በሚለጥፉብህ የ666 ምልክታቸው ብቻ እንዳይመስልህ – እስትንፋስህን ሳይቀር ተቆጣጥረውታል እያልኩህ ነው ወንድሜ (ፈገግ በል አስኪ፡- ሽንት ቤት ገብተህ ወደዋናው ጉዳይ ከመግባትህ በፊት በእንትንህ ሙዚቃ ስንቴ እንደተዝናናህ ሳይቀር እነሱ ከፈለጉ ያውቁታል፡፡ አዲዮስ ‹privacy›፣ ገባህ? አትታዘበኝ – አዲስ ነገር የለም፡፡ )

በተለይ ኢትዮጵያን በመሰሉ ድሃ ሀገሮች ውስጥ የሚገኘውን የድሃ ገበሬ ማሣ በማዳበሪያ አፈር ድሜ አብልተውታል፤ በኬሚካላቸው የገበሬውን መተዳደሪያ የተፈጥሮ ማዕድን ሲያቃጥሉት በውድ ከሚገዛው የነሱ ማዳበሪያ ውጪ አፈሩ ዘር ማብቀሉን ተወ – ኬሚካሉን ልግዛ ሲል እነጉናና አምባሰልን በመሰሉ የሀገር ውስጥ ወያኔያዊ ሼሪኮቻቸው አማካኝነት ዋጋውን ሰማይ ሰቀሉት፤ እኛንም ገበሬውንም ለችግር ዳረጉንና ሁላችንም ኤሎሄ እንል ጀመር፡፡ በግብርናውም ሆነ በኢንዱስትሪውና በፖለቲካው መስክ ከነሱ ቁጥጥር እንዳትወጣ የማያደርጉት ነገር የለም፡፡ ድመት የገደለቻትን ዐይጥ እስክትበላት ድረስ እንደምትጫወትባት ሁሉ እነዚህ ጥቂት የአጋንንት ውላጆች እንዳሳሁርታ በቅጽበቶች እየተራባ የሰባት ቢሊዮንን ጉበን በቅርቡ ያለፈውን የዓለም ሕዝብ ጢባጢቤ እየተጫወቱበት ናቸው፡፡ በቁራጭ አሞሌ ጨው በሬ ወደመታረጃው እንደሚሄድ እነዚህ ገብጋቦች የዓለምን ሀብትና ፖለቲካ በቀጥታና በእጅ አዙር ተቆጣጥረው ወደ አጠቃላይ ውድመት እየመሩን ናቸው፡፡ በዚህም ሰይጣኖችን ታውቃለህ!

የትም ሂድ የትም ግባ ቤተ ክርስቲያንን ሳይቀር በአለቃቸው የሰይጣን መንፈስ ተቆጣጥረዋል – ኢትዮጵያ ውስጥ ለምሳሌ እስከቅርብ ሩቅ ድረስ ዋልድባ ገዳምን ሰይጣን እምብዝም አይደፍርም ነበር (ይባላል)፤ አሁን ግን ገዳሟ መንፈላሰሻቸው ሆናለች – የነደብረ ሊባኖስና የሌሎች ደብረዎች ነገር ተከድኖ ይብሰል፡፡ እነዚህ ገዳማትና አድባራት ዋና መሥፈሪያ ቆጣቸው ናቸው፤ ጸሎቱ የማያርገው፣ ስብከቱ የደነደነ ልብን አሟምቶ ከኃጢኣት መንገድ የማይመልሰው፣ ሕዝበ ክርስቲያን የዳነ እየመሰለው ሃይማኖቱን እንደሸሚዝ የሚቀያይረው ከዚህ የተነሣ ነው – ሀሰት ከተናገርኩ … ዳሩ አይማልም ለኬ፡፡ የምለው ግን እውነቴን ነው!

ዘመኑ የጭንቀትና የጥበት ነው፡፡ መዳን በዚህ ወይ በዚያ አለ የሚባልበት ድኅነት ግን የሌለችበት እጅግ አስጨናቂ ዘመን ላይ ልንገኝ የቻልነው አእምሮኣችንን የስንግ በያዙን ሴቴኒስት መሪዎቻችን አማካይነት ራሱ ዲያቢሎስ የፊጥኝ ስላሰረን ነው፤ አሳዳጃችን ሰይጣን በምንሄድበት ቦታ ሁሉ ቀድሞ ይጠብቀናል፡፡ እሥረኞቹ ደግሞ በጎቹ ብቻ ሣንሆን እረኞቻችንም ናቸው፡፡ አዲስ አበባን ተመልከት፡፡ በዲኤክስና በቪታራ… የሚዝመነመነውን የደብር አለቃና የሀገረ ስብከት ባለሥልጣን ካህን ስታይ፣ የየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ታዋቂ ቀሣውስትና መዘምራን ወሰባኪያን በምቾት አብጠው እንደ እምቧይ ሊፈርጡ ተቃርበው ስታይ ያቺ ካላት ሳይሆን ያላትን ከመቀነቷ ፈትታ ወደ ሙዳየ ምጽዋት የምትጨምር ሴት በዐይነ ልቦናህ ትታይሃለች፡፡ እኛ እየኮሰመንን እነሱ እየተነፉ፣ እኛ እየደኸየን እነሱ እየከበሩ፣ እኛ እየፆምን እነሱ እየፈሰኩ፣ … መኖር ተብሎ አለሃይማኖትና አለመሪ የአጋንንት ወጀብ እያላጋን ተገትረን አለን፡፡ ዘመኑ ቀርቧል የምንለው እንግዲህ ከነዚህ ነገሮች አንጻርም ነው፡፡ ሁሉም የውሸት ነው – የታይታ፡፡ ይህን ግን አስብ፡- ‹የእግዚአብሔርና የሰይጣን ሰዎች በሥራቸው ይታወቃሉ፤ የታይታ ፆምና ስግደት ወይም የፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ዓይነቱ የአለባበስና የአነጋገር ላህይ ሳይሆን – እምነት፣ ሥራና ፍቅር የሰውን ምግባር ይገልጣሉ፡፡› በቃ፡፡

የሌሎችን የእምነት ቤቶችም ተቆጣጥረዋል፡፡ ሚዲያውም በነሱው ቁጥጥር ሥር ነው፡፡ እነሱ የሚፈልጉት ዜናም ሆነ ሀተታ ይነገራል፤ ሌላውና ከነሱ ፍላጎት ውጪ የሆነው ግን ይታፈናል፡፡ የየሀገራቱ መሪዎች ሴቴኒስት ካልሆኑ ከሥልጣን የሚወርዱበት መንገድ ይጠናና ተግባራዊ ይደረጋል፤ ምክንያቱም እንደኃያላኑ መንግሥታት መሪዎች ሌሎቹም ሴቴኒስቶች ካልሆኑ እንደልብ አይታዘዟቸውም – ሰይጣንና መልአክ – እርኩስና ቅዱስ ውሃና ዘይት ናቸውና፡፡ የሆሊውድንና የሌሎች -ውዶችን ፊልሞችና ሙዚቃዎች ቃኙ፤ ከሞላ ጎደል ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ አገልግሎታቸው በሰይጣናዊው አዲሱ የዓለም ሥርዓት [The New World Order] መሠረት የተቃኘ ነው፡፡ ለነሱ የማይስማማ ይወገዛል – ተጠርጎ ይጣላልም፤ ለነሱ የሚስማማ ጨካኝና አውሬም ቢሆን እንደጫጩት ጉያ ውስጥ ይታቀፋል(ሳዑዲንና ባሕሬይንን ያስቧል)፤ (የቬንዞላ ሕዝብ አሜሪካ የምትፈልገውን ካፒሪሌን ትቶ ማዱሮን መምረጡ ስህተት ነው፤ እና አሜሪካ የምርጫውን ውጤት አትቀበልም፡፡ የኢትዮጵያው የ97 ምርጫ ግን – ዌል – እንደዴሞክራሲያዊ ተሞክሮ ስለሚቆጠር – ተቃዋሚ በዝረራ ቢያሸንፍም – እርግጥ ነው – ወያኔ አሸንፏል ማለት ይቻላል፡፡ ተቃዋሚዎች የተሰጣቸውን ወንበር መቀበልና በመናጆነት በወያኔ ፓርላማ በረት ገብተው ማንቀላፋት ነበረባቸው፡፡ … የጉዶች ምድር፣ የምፀት ዓለም… “ሥራ ለሠሪው እሾህ ላጣሪው…”ይብላኝ ለንጹሑ ሰላማዊ ሕዝብ! ዐይጥ በበላ ዳዋ ተመታ …

በነገራችን ላይ ሁለት ወጣቶች ብቻ አሜሪካውያንን በ‹ጦር ሜዳ ውሎ›ና በፕሮፓጋንዳ እንዲህ ‹ሽንት በሽንት› ያደረጉ፣ የዓለምን ሚዲያ በመሪና በሰበር ዜናነት ከዳር እዳር ያጥለቀለቁ፣ ፕሬዝደንት ኦባማን ሣይቀር እንቅልፍ አሳጥተው ያስጨነቁና ዕንባ በዕንባ ያስደረጉ አሥርና አሥራ አምስት ቢሆኑ ምን ያሳዩ ይሆን? በዛሬዋ ቀን እያዘንኩም ቢሆን ሁለት ዜናዎች ፈገግ አድርገውኛል፡፡ አንደኛው እነኢራንንና ሰሜን ኮሪያን ፌሽታ በፌሽታ የሚያደርገው ምናልባትም በሣቅ የሚያፈነዳው የቦስተኑ ክስተት ሲሆን ሁለተኛው ያ ሙሻራፍ የሚባል ገልቱ ሰውዬ በሀገር ክህደትና በሌሎች ወንጀሎች ዘብጥያ ሊወርድ ከሞቀ የስደት ኑሮው መመለሱና ዛሬ በፖሊስ መያዙ ናቸው – የሥልጣን ፍቅር አነሁልሎት እውነቱ ተሸፈነበትና ጉድ ተሠራ፡፡ በጊዜያችን ብዙ ነገሮች ከመግረም እያለፉ እንደጅል በሞኝነት ማሣቅ ይዘዋል፡፡ ፈገግ ብትሰኙልኝ አንድ አስቂኝ ታሪክ እዚች ላይ ባጭሩ ላስታውሳችሁ፡፡(የአሜሪካው ትዕይንት ግን ሆሊውድ በቦስተን የቀረጻ ልምምድ እያደረገ አልመሰላችሁም?)

በዱሮ ጊዜ ነው አሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት አንድ የጦር ቡድን ወደ አንድ ጫካ ይልካል፡፡ ያስቸገረ አስቸግሮ ነበርና፡፡ ከጦርነቱ መልስ አንድ ሰውዬ የጦር አዛዡን ጠጋ ይልና እንደሚከተለው ይጠይቀዋል፡፡

ጠያቂ፡- ውጊያው እንዴት ነበር? በቀላሉ ቀናችሁ ወይንስ ጉዳት ደረሰባችሁ?

አዛዥ፡- ኧረ ምኑ ይወራል! በጣም ኃይለኛ ጦርነት ነበር፤ ያልጠበቅነው ብዙ ጉዳት ደረሰብን…

ጠያቂ፡- እንዴ? ብዙ የጠላት ኃይል ነበር እንዴ የገጠማችሁ? ማለቴ ከእናንተ የሚበልጥ…

አዛዥ፡- አሄሄ… እንደሱማ ቢሆን በማን ዕድላችን፤ የገጠመን አንድ ሰው ብቻ ሆኖ ውር ውር እያለና            እየተሽሎከለከ ፈጀን እንጂ፡፡ በስንት መስዋዕትነት መሰለህ መጨረሻ ላይ የገደልነው …

 

ኢትዮጵያችን በሰይጣን ግዛት ከገባች ቆይታለች፡፡ በፊትም ግማሽ እግር በሰይጣን ግዛት ግማሽ እግር በእግዜር ግዛት ውስጥ በጨለማና በብርሃን በሚመላለስ የአገዛዝ ሥርዓት ውስጥ ነበረች፡፡ እየቆዬ ደግሞ በለዬለት ሁኔታ እዚያው እጨለማው ግዛት ገባችና አሁንም ድረስ በዚያው አለች፡፡ እግዚአብሔር ይርዳት፡፡

በእስልምና ስም እየታዬ ያለውም የሚዘገንን ነው፡፡ ሰሞኑን ከድረ ገፆች ስለአንዲት ኢትዮጵያዊት ልጃችን ያነበብኩት ሰቅጣጭ ታሪክ ወደውስጤ አስለቅሶኛል – ወደ ውጪ የማፈስሰው ዕንባ የለኝም፤ ለጊዜው ጨርሻለሁ፡፡ ይህች ልጅ እንደብዙዎቹ ከርታታ ወገኖቻችን ሁሉ ያልፍልኛል ብላ ወደዐረብ ሀገር ትሄዳለች፡፡ ሦርያ ውስጥ ገብታ ሥራ ትይዛለች፡፡ ነገር ግን ‹አንበሣን ፈርቼ ዛፍ ላይ ብወጣ ነብር ጠበቀኝ› እንዲሉ ሀገሯ ያስወጣት ችግር መልኩን ቀይሮ ሦርያ ላይ ጠበቃት – ጦርነት፡፡ ከርሀብ ስትሸሽ ጦርነት አፉን ከፍቶ ጠበቃት፡፡ በዚህ የርስ በርስ ውጊያ ሰበብ ቀጣሪዎቿ ቤቱን ጥለውላት ወደዉጭ ይሰደዳሉ፡፡ ዝርዝሩን ከነዚያው ድረ ገፆች አንብቡ፡፡

ሳላነሳው ማለፍ የማልፈልገው ግን ለዚህ መጣጥፍ መነሻ የሆነኝ የዚህች ልጅ ስቃይ ነው፡፡ ይህች ልጅ ደማስቆስ የመሬት ለመሬት የውስጠኛ ክፍል ውስጥ በመሸጉ አሸባሪዎች እጅ ትወድቃለች፡፡ በነዚህ የእስላም አክራሪ ሰይጣኖች ቁጥጥር ከገባች በኋላ የምታየው አበሳ በቃላት የሚገለጽ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የሰይጣኑን የመለስ ዜናዊን ነፍስ ተገቢ ዋጋዋን ይስጣትና በሱ የተንሸዋረረና በዘረኝነት የበከተ አገዛዝ ምክንያት ወደዉጭ የሚሰደዱ ወገኖቻችን ምን ዓይነት መከራና ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ይህች ልጅ አብነት ናት፡፡ በብዙ ሺዎች የሚገመቱ ወገኖቻችንም በዚህ ዓይነት አሰቃቂ ሁኔታ እንደሚኖሩ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ ለቤት ቀጋ ለውጭ አልጋ የሆነ ሥርዓት በቶሎ ካልተወገደ በሀገራችን ምን ያህል ውድመት እየደረሰ እንዳለና ወደፊትም የሚመጣብን መከራ በዚህች ልጅ አማካይነት ቁልጭ ብሎ ይታያልና ወደየኅሊናችን ተመልሰን ለጋራ ጉዳያችን በጋራ እንድናስብ ይህ ዓይነቱ አስከፊው ተሞክሮኣችን ያስተምረን፡፡ በፈጠረን ይሁንብን!

አሸባሪዎቹ ይህችን ልጅ በሚስቶቻቸው ፊት ሳይቀር ይደፍሯታል፤ ሌሎችን በኮረንቲ እንድትጠብስ ያደርጓታል፤ ሽንታቸውን እንድትጠጣ – የርሷንም ሽንት ሌሎችን እንድታጠጣ ያደርጓታል፤ ሬሣ መሀል እንድታድርና አእምሮዋን ስታ ወደአውሬነትም ተለውጣ ለአጥፍቶ መጥፋት ተልእኮ ፈቃደኛ እንድትሆን ያስገድዷታል፡፡ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል የዚህችን ልጅ ስቃይ ያላነበበ ከአንዱ ድረ ገጽ ቢያነብ ደስ ይለኛል (በዚህ በኩል ልምዱ ያላችሁ የዘሀበሻ ድረገፅ ሰዎች እባካችሁን እዚህች ቦታ ላይ የዚያን ጽሑፍ አድራሻ አጣቅሱት – እኔ ያነበብኩት በኢትዮሚዲያ ላይ ነው፤ ርዕሱ ‹ኢትዮጵያዊቷ በሦርያ ያሳለፈችውን ስቃይ…› የሚል ነው – ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ነው የወሰዱት)፡፡ የእርሷ ስቃይ የኛ ስቃይ ነው፡፡ ይህች ልጅ የኔንም ምስል የምታሳይ ሴት ክርስቶስ ናት፡፡ የገማና የሻገተው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሥርዓታችን ነፀብራቅ ናት፤ የመለስ ራዕይ ውጤት ያስገኘልን ድል መገለጫ የኅሊና ጸጸታችንና የጋራ ቁጭታችንም መንስኤ ናት፡፡ ያንዳችን ቁስል ላንዳችን ካልተሰማን ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳንሆን ሰዎችም አይደለንም ማለት ነው፤ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ አንዳችን ለአንዳችን እንተዛዘን፡፡ በነገራችን ላይ ይህች ልጅ ፈጣሪ በሰዎች አማካይነት ረድቷት ከዚያ የቁም መቃብር ተርፋ አሁን በሕይወት አለች፡፡

እንግዲህ ሰይጣን ማለት ከፍ ሲል እንደተመለከትነው ነው – ዕልቂትና ትርምስ የሚወድ፡፡ በሦርያ፣ በኢራቅ፣ በአፍጋኒስታን፣ በፓኪስታን፣ በሕንድ፣ በሶማሊያ፣ በግብጽ፣ በፍልስጥኤም፣ በበርማ፣ በኢንዶኔዥያ፣ በአሜሪካዎች፣ በማሊ፣ በሴንትራል አፍሪካ ‹ሪፓፕሊክ›፣ በጊኒ፣ … ሠይፉን መዝዞ ሕዝበ አዳምን እያንቆራጠጠ የሚገኘው ሰይጣን በሰዎች ተመስሎ ነው – (በነገራችን ላይ ሰይጣንም ሆነ እግዚአብሔር – በጨለማና በብርሃን በሚመሰል የመንፈስ ኃይል እንጂ የራሳቸው ቁሣዊ መገለጫ እንደሌላቸው የታወቀ ነው፡፡) ቦስተን ላይ የፈነዱት ሁለት ቦምቦች የሰይጣን ናቸው፤ ኢራቅ ውስጥ በየቀኑ የሚፈነዱ ቦምቦችና የአጥፍቶ ጠፊ ተልእኮዎች ከሰይጣን የሚላኩ ናቸው፡፡ ሶማሊያ ውስጥ የሚፈነዱ ቦምቦች የሰይጣን ናቸው፡፡ እስላም እማሬያዊ ትርጉሙ ‹ሰላም› ሆኖ ሳለ ሰይጣን አእምሮኣቸውን የሠረራቸው ሰዎች በዚህ ሰላምን በሚሰብክ ሃይማኖት ሽፋን ስም ገብተው ዓለምን ወዴት እያቀጣጯት እንደሆነ ልብ እንበል፡፡ የዕብድ ገላጋይ ድንጋይ እንደሚያቀብል ሁሉ በሌላው ጫፍ ያሉ የሰይጣን ሎሌዎችና ደንገጡሮችም የጠቡን አድማስ ከማጥበብ ይልቅ እዬለጠጡና ነገር እየተነኮሱ አለይዞታቸውም በሰው ግዛት ጥልቅ እያሉ በሚያቀጣጥሉት የ‹አሸባሪነትና ተሸባሪነት› አሸናፊ የሌለው ጦርነት ውስጥ የስንቶች ንጹሓን ዜጎች ሕይወት በየቀኑ እንደሚረግፍ እናስተውል፡፡ አስቂኝ ቀልድ – አሸባሪነትን በአሸባሪነት ለማሸነፍ የመሞከር ልዩ የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ትራጂኮሜዲ ድራማ፡፡ በሰዎች ዕልቂት ሰዎች የሚጨፍሩበት አሣዛኝ ተውኔት፡፡ ዓሣሞችና አጋሰሶች – ማነው – ዝኆኖች ሲጣሉ ሣሮች የሚረጋገጡበት ክፉ ዘመን፡፡ ምን ይሻለናል? ጊዜው አያስፈራም? የኔ ስሜት ድብልቅ ነው – ያስፈራል ፤ አያስፈራምም፡፡

የእንቅስቃሴውን ስም አልቃኢዳም እንበለው አልሻባብ፣ አል ኑስራም እንበለው አል ዛዋሪ – ሃይማኖቱ እስልምናም ይሁን ክርስትና ቡድሂዝምም ይባል አይሁድ ተግባሩ ሰዎችን መጨረስ ከሆነ ያው ሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣናዊነት ሰብኣዊነት የሌለው በግድያ እንድትዝናና የሚያደርግ የጭካኔ አምልኮት ነው፡፡ በሰው ስቃይ የሚደሰት ሁሉ ሰይጣን ነው፡፡ የተቀደሰ ግድያ የለም፡፡ ግድያ በማንም ይሁን በማን፣ ማንም ላይና ለምንም ዓይነት ዓላማ  ይፈጸም አስከፊ ነገር ነው፤ አስተማሪነትም የለውም፡፡ የሞተም አልተማረም፤ የተመለከተም ኅሊናውን በሚያሰቃይ ቁስል አነፈረቀ እንጂ ትምህርት አልቀሰመም፡፡ በተጨማሪም ግድያን ምንም ዓይነት ሕጋዊም ይሁን ሞራላዊ ልባስ ቢሰጡት ያው ግድያ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ ሞትን አፈጠንከው አዘገየኸው መቼም ቢሆን ለማንም አይቀርም፡፡ እናም የፈጠረ ይግደል፤ ያልፈጠረ ያልፈጠራትን ነፍስ ከሥጋዋ አለጊዜዋ ለምን ይለያል? “አትግደል” የሚለውን የፈጣሪ ሕግና ትዕዛዝ የሚተላለፍ ሁሉ ኃጢኣትን አደረገ፡፡ ስለዚህም ሰውን በመግደልም ይሁን በማሰቃየት የሚደሰቱ ሁሉ ምድባቸው ከሰይጣን መሆኑን በመረዳት ምርጫችንን እናስተካክል፡፡ ከሁለቱ አማራጮች ውጪ ሌላ አማራጭ የለም፤ አንድም የፍቅርና የሰላም የእግዚአብሄር መንፈስ ያለን መሆን ወይም በተቃራኒው የጠብና የአምባጓሮ፣ የግድያና በሰው ስቃይ የመደሰት ሰይጣናዊ መንፈስ ያለን መሆን፡፡ ምርጫው በእጃችን ነው፡፡ መሆን ወይም አለመሆን – በግዛታችን ያለ ነጻ ምርጫ፡፡

 

በቬጋስ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ የታክሲ አሽከርካሪ ወገኖቻቸውን ለመርዳት በአንድ ላይ እንደሚቆሙ ገለጹ

0
0

vegas 1 vegas 2

የጋራ ኮሚኒቲ ለማቋቋም ሀሳብ ቀርቧል

በቬጋስ የሚገኙና በሁለት የከተማዎ ታላላቅ የታክሲ ኩባንያዎች ፈራይስና የሎ ቼከር ስታር የሚሰሩና ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ የስራ ማቆም አድማ ተሳታፊዎችና በተቃራኒው የስራ ማቆም አድማውን ሳይቀላቀሉ የቀሩ ወገኖች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በማርገብ የተጀመረው ትግል ውጤት እንዲያመጣ የተጠራው በኢትዮጵያውያንና ኤርትራዊያን ድጋፍ ስብሰባ ባለፈው ረቡዕ አፕሪል 24/2013 በከተማዋ ተካሔደ። የማህበረሰቡ አባላት ትግሉ ውጤት እንዲያመጣ ከአሽከርካሪዎች  ጎን እንደሚቆሙ ገልፀዋል። የስብሰባው አዘጋጆች የሥራ ማቆም አድማ ተሳታፊዎችን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠት ከኩባንያው ጎን በመቆም

የኢትዮጵያውያንና የኤርትራውያን የድጋፍ ኮሚቴ በሚል በራሳቸው ፍላጎት የተሰባሰቡ ከማህበረሰቡ የተውጣጡና ከታክሲ ማሽከርከር ስራ ውጭ ያሉ ወገኖች በጠሩት በዚህ ስብሰባ በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ ባሉና በተቃውሞ አድራጊዎቹ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በውይይት የመፍታት፣የተጀመረው የመብት ጥያቄ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝ ድጋፍ እና ምክር መስጠት መሆኑን ኮሚቴውን በመወከል አቶ ሙሉነህ ጠና ተናግረዋል። በስራ ላይ ያሉ በተለይ በርካታ የፍራይስ አሽከርካሪዎች የወገናቸውን የመብት ትግል እያስተጓጎሉ  በመሆኑ ከድርጊታቸው ተቆጥበው የስራ ማቆም አድማውን እንዲቀላቀሉ የስብሰባው አዘጋጆች የመሸምገል ሃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

በከተማው በሚገኘው ፓላስ ስቴሽን ካዚኖ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ቁጥራቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራዊያን የማህበረሰቡ አባላት የተገኙ ሲሆን በሥራ ማቆም አድማ ላይ የሚገኙትን ለመደገፍ መጠነኛ የገቢ ማሰባሰቢያ የሚሆን ትኬት ተዘጋጅቶ ለሽያጭ ቀርቧል።

በስብሰባው ላይ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የኔቫዳ የዩታሃና  የአሪዞና ሊቀ ጰጳስና የቅዱስ ሲኖዶሱ ም/ዋና ጸሀፊ እና ከእስልምና ዕምነት ተከታዮችም ኡስታዝ ኑር ሐሰን  በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል።  በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በርካታ ወገኖች የሥራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውንና በሥራ ላይ ካሉ ወገኖች ጋር መካከል በአንዳንዶች የተጀመረው የእርስ በእርስ መሰዳደብ እያደገ ወደ ግጭት እንዳያመራ ስጋታቸውን ገልፀዋል። በውይይት ችግሩ ተፈቶ የሥራ ማቆም  አድማው መነሻ የሆነው የመብት ጥያቄ  በጋራ ትግል መፍትሔ እንዲያገኝ ጠይቀዋል። ጠበቃ ማቆምም ቢያስፈልግ በአንድ ላይ መምከር በአንድ መቆም ይገባል ብለዋል።

“የመብት ጥያቄ የዴሞክራሲ ጥያቄ ነው ማንም ሊደግፈው ይገባል>> ያሉት አቶ ረዳ መሀሪ የአፍሪካ ኮሚዩኒቲ ሴንተር ማኔጅንግ ዳይሬክተር ሲሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያንም ሆኑ ኤርትራዊያን ተደራጅተን የድምፆቻችንን ዋጋ ማሳየትና ተደማጭነት ማግኘት አለብን ሲሉ ከወቅቱ የስራ ማቆም አድማ በላይ ማሰብ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

አቶ ሽመልስ ደረሱ የየሎ ቼከር ስታር የታክሲ አሽከርካሪዎች የሥራ ማቆም አድማ አስተባባሪ ከማርች 3 ጀምሮ በሥራ ማቆም አድማው ላይ መቆየታቸውን ገልፆ የፍራይስ አሽከርካሪዎችም ከማርች 29 ጀምሮ በተመሳሳይ ሥራ ማቆም አድማ ላይ ቢኖሩም የተጀመረው ትግል እንዳይሳካ የገዛ ወገኖቻችን እንደ ጠላት እየተደዋወሉ አትጫኑ ካልናቸው  ቦታዎች  እንኳ ይጭናሉ ሲሉ ወቅሰዋል።

<<ከሐበሻ ባህል ውጭ የሆነ የገዛ ወገናችን እኛ የስራ ማቆም አድማ ላይ እያለን ከኩባንያው ጎን ቆሞ መስራቱ ሳያንስ እኛን ሊሰድብ የማይታየውን አካሉን አሳየን።ካሜራ አለ አጋለጠው>>  ሲሉ በምሬት የገለፁት አቶ ሽመልስ ይህንን ድርጊት የፈፀመው በአሁኑ ወቅት ከስራ ተባሮ በየትኛውም ኩባንያ እንዳይቀጠር መደረጉን አመልክቷል።

ከስራ ማቆም አድማ ተሳታፊዎች ውስጥ የአራት ልጆች አባት ባለቤቱ የማትሰራ ጭምር እያሉ ሚስቶቻቸው በተለያየ ቦታ የሚሰሩ ጭምር ከኩባንያው ጎን ቆመው የጀመርነውን የስራ ማቆም አድማ እንዳይሳካ ተሰደብን በሚል ምክንያት የገዛ ወገኖቻችን እያጠቁን ነው ብሏል።

“የኢትዮጵያና የኤርትራ ኮሚኒቲ የሚባል መነጣጠል ቆሞ አንድ ኮሚኒቱ ሊኖረን ይገባል ” ሲሉ ሃሳብ ያቀረቡት አቶ ሽመልስ ከሁለቱ ኩባንያ በስራ ላይ ያሉ ወገኖቻችን እንዲቀላቀሉን የሚሳደቡም ሰዎች ስድብ ቢያንስ ሙሉ ለሙሉ ለአንድ ሳምንት እንዲቆምና ሳምንቱ የፍቅር ሳምንት ሆኖ የተጀመረው የመብት ትግል ውጤት እንዲያመጣ እየሰሩ ያሉት ይቀላቀሉን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ማህበረሰቡ ኢትዮጵያዊያን ኤርትራውያን እየተባባሉ ሳይከፋፈል በአንድ ላይ ለመብታችን እንቁም እስቲ እጅ ለእጅ እንያያዝ ሲሉ ባቀረበው ጥሪ መሰረት የሀይማኖት አባቶችን ጨምሮ ሁሉም ተሳታፊዎች እጅ ለእጅ በመያያዝ አንድነትን ለማሳየት ሞክረዋል። ለሰብሰባው አዘጋጆች የሚሰሩት ሰዎች ላይ ጫና እንዲፈጥሩ ጠይቀዋል። <<ነፃነት ባለበት አገር በቬጋስ በባርነት የምንኖር የታክሲ ሾፌሮች ነን ።ባርነት በቃን ብለን ወጥተናል አሁንም አልረፈደም  የቀሩት ወገኖቻችን ይቀላቀሉን >> ሲሉ አጽንዎት ሰጥተዋል።

ዮናስ ተሰማ በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉት የፍራይስ አሽከርካሪዎች ተወካይ በበኩሉ <<ትላንት መብታችን ተነካ፣ ለምን የስራ መቆም አድማ አንወጣም ሲሉ ከነበሩ ብዙዎቹ በሥራ ላይ ናቸው። በሰሩት ተግባር ሊያፍሩ ይገባል ያለ ሲሆን ሌላው በስራ ማቆም አድማ ላይ ያለ ልጁን በፀሐይ ብርሃን የሚያሳድግ ይመስል የተለያዩ ምክንያት እየሰጡ ከኩባንያው በላይ እየጎዱን ያሉት በስራ ላይ ያሉና ተቃውሞውን ያልተቀላቀሉ ወገኖቻችን ናቸው ብሏል።

በስብሰባው ላይ የተሳተፉ የኢትዮጵያና የኤርትራ ኮሚኒቲ ተወካዮች በየበኩላቸው ንግግር ያደረጉ ሲሆን የተጀመረው የመብት ትግል ውጤታማ እንዲሆን መተባበሩ ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል።

ከሥራ ማቆም አድማ ተሳታፊዎች አንዱ የሆኑት የኤርትራ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ዓለም በውስጥ ሆነው የሚሰሩና ተቃውሞውን ያልተቃላቀሉ ኢትዮጵያውያን ና ኤርትራዊያንን በአንድነት ወቅሰው ስድብ የሚባለውን በግላቸው እንደማይደግፉ ነገር ግን የእያንዳንዱ ወጣት አፍ ስለማንቆልፍ የተጀመረው የመብት ትግል እንዳይሳካ ከሚሰሩትም የሚሳደቡ ስላሉ ተሰደብኩ የሚለው ምክንያት ተቀባይነት እንደሌለው ገልፀዋል።

የአቤ ጉበኛን አልወለድም ለንግግራቸው ማጣቀሻነት ያነሱት የኤርትራው ኮሚኒቲ ሊቀመንበር በዚያ መፅሐፍ ውስጥ “ወገን ሲባል ያገር ሰው ሲባል ከወገኑ ጋር የሚቆም አንጂ ነፃነትህና መብትህን የሚገፍ ወገንህ ግን ጠላትህ ነው ይባላል” የሚል ጥቅስ  አንስተው ከኩባንያው ጋር በመቆም ባርነት በቃን ላልነው ወገኖች በተቃራኒው የቆሙት ግን <<እኔ የማርክ ጄምስ ባሪያ ነኝ>> የሚል ቲሸርት አሰርተው ለብሰው ታክሲያቸውን ይንዱ ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

ከስብሰባው ተሳታፊዎች መካከል በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት የስብሰባው አዘጋጆች ውስጥ ሆነው የሚሰሩ ሰዎችን አስቀድመው ስብሰባ መጥራት እንደነበረባቸው በመግለፅ  በማህበረሰቡ ውስጥ ሰላም የሚኖረው በሥራ ላይ ያሉ ሲቀላቀሉዋቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ በአማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጽዳትና ማጥፋት ዘመቻ አስመልክቶ ጥሪ አቀረበ

0
0

eotc22(ዘ-ሐበሻ) ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ በአማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጽዳትና ማጥፋት ዘመቻ አስመልክቶ ጥሪ አቀረበ። ቅዱስ ሲኖዶሱ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ  ” ሀገራችን ኢትዮጵያ በአምላኳ ጥበቃና በሕዝቧ ፍቅር ነፃነቷንና አንድነቷን ጠብቃ ለብዙ ዘመን ኖራለች። አንድነቷን ከነፃነቷ አስተባብራ የኖረች በመሆኗም ነፃነትን ለሚናፍቁ ሕዝቦች ሁሉ ምልክት ነበረች። በዚህም ምክንያት ለነፃነት የተነሡ ሁሉ ሰንደቅ ዓላማዋን አርማቸው ኢትዮጵያዊነትን አርማቸው አድርገው በነፃነት መንገድ ላይ ተጉዘዋል። እግዚአብሔር አምላክም ለሕዝባችን በሰጠው አርቆ አስተዋይነትም፥ አገሩን የሚከፋፍል ነገር በመካከሉ እንዳይገባና አገራችን በቅኝ ገዢዎች እጅ እንዳትወድቅ ሕዝቡ በአንድነት ቆሞ ኖሮአል። እንግዶችን መቀበል፥ አብሮ መብላት፥ አገር ማልመድ የቆየ ኢትዮጵያዊ ባሕላችን ነው። በዚህ ኢትዮጵያ ባህል ሕዝብ ከሕዝብ ጋር ባህል ከባህል ጋር ተስማምቶ ኢትዮጵያዊ ውበት ያለው ሕብር ፈጥሮአል።” ካለ በኋላ ” የኢሕአዴግ መንግሥት አገራችንን ኢትዮጵያን በጠመንጃ ኃይል ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንሥቶ ግን ይህ የኢትዮጵያ አንድነት ከባድ አደጋ ውስጥ ይገኛል። አገሪቱን በዘርና በጎሣ በመሽንሸን፥ አንዳች ችግር ቢፈጠር በአንድነት አገራዊ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ እንዲበታተኑ የሚያደርግ የጎሣ ፖለቲካ በሕገ መንግሥቱ ላይ ቀርጾ አስቀምጧል። ይህን ያደረገው የራሱን እድሜ ለማርዘም ነው። በዚሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ የሰብአዊ መብት ጥሰት፤ የመልካም አስተዳደር እጦት እና የኑሮ ውድነት እየጨመረ መምጣቱ የሚታወቅ ነው። የዘር ማጥፋት ዘመቻውንም መልኩን በመቀያየር በቦረናና በአርባ ጉጉ፥ በጋምቤላና በኦጋዴን፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በአፋር፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በቤኒሻንጉል በሚኖሩት ወገኖቻችን ላይ በማከናወን ላይ ነው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህ እየተከናወነ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ጥቂቶች በብዙዎች ላይ ነግሠው እንዲኖሩ ለማድረግ የታቀደና የኢትዮጵያን አንድነት አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ በመላው ዓለም ያለን ሕዝቦች የወገኖቻችንን ግፍና ስቃይ ተረድተን ጩኸታችንን በማሰማት ድምጹ ለታፈነበትና በሰቆቃ ላለው ሕዝብ ድምጽ በመሆን በዓለም የተለያዩ መድረኮች ጩኸቱን እንድናደርስለት ጥሪ ታቀርባለች።” ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫውን ቀጥሎ ” በኤርምያስ ዘመን አምባገነን መሪዎች የነበሩ ሲሆን እምነት የሌላቸው እውነት የተለያቸው እግዚአብሔርን የማያከብሩ ሰውን የማይፈሩ ጨካኞች እውነትን የማይወዱ ሥልጣናቸውን ለማቆየት ሲሉ ብቻ እግዚአብሔርን የሚዋሹ ክፉዎች ነበሩ። ከዚህ የተነሳ ሕጻናትን በሥጋና በመንፈስ ይገሉ ነበር። ለዚህ ነበር እግዚአብሔር በኤርምያስ አድሮ ይህን የዋይታ መልዕክት ያስተላለፈው፤ ራሔል የምትወክለው ጠቅላላ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ነበር፣ ዋይታዋ ጩኸቷም በግፍ በጨካኞች ስላለቁት የእግዚአብሔር ሕዝብ ሕጻናት ነበር። ምክንያቱም ሕጻናቱ ከፉዎች ስለ ገደሏቸው አልቀዋል የሉም ሞተዋልና ነው። በክርሰቶስ ጊዜ የነበረው ሄሮድስም በደሉን እንደገና ስለደገመው ማቴዎስ ይህንኑ ቃል ተጠቅሟል፤ እኛም ዛሬ እየተጠቀምንበት ነው። ምክንያቱም በሄሮድስም በኤርምያስም ጊዜ የነበሩ መሪዎች ክፉ መንፈስም አሁን በኢትዮጵያ በአሉ መሪዎች ልብ ስለ አለ ነው፤ በአገሪቱ የመንግሥትን ሥልጣን የያዘው አካል በዚያን ወቅት ከነበሩት ሰዎች ጋር አንድ ዓይነት ስለሆነ ያንኑ ጩኸት እንጮኸለን። የኢትዮጵያ ወላጆች አሁን የራሔልን ጮኸት እየጮሁ ነው።

“ዛሬ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከፍ ብለን ከጠቀስነው ጊዜና ሁኔታ ይበልጥ የከፋ ሁኖ እናገኘዋልን። እናቶች እንባቸው ደርቆ የደም እንባ እያነቡ ይገኛሉ። ይሄው ከፋፋይ መንግስት ተከባብሮና ተፋቅሮ አብሮ የኖረውን ህዝባችንን በሃይማኖትና በዘር ማለትም እስላሙን ከክርስቲያኑ፤ ኦሮሞውን ከአማራው፤ ሱማሌዉን ከኦሮሞው፤ ስልጤውን ከጉራጌ፤ ከንባታ ከወላይታ፤ አፋርን ከኢሳ፤ ሲዳማውን ከጌዶ፤ አኚዋክን ከኑር ፤ ትግሬውን ከቀረው ኢትዮጵያዊ ጋር ለማለያየት ወይም ለመከፋፈል እየሞከረ ነው። ይህ አልበቃ ብሎ አንድ ኢትዮጵያዊ በትውልድ ሀገሩ የመኖርና የዜግነት መብቱ ተነፍጎ አንዱን ዜጋ ከፍ አድረጎ በአንጻሩ ሌላውን ግን እንደ አውሬ በመቁጠር ከሰባዊ ፍጡር አሳንሶ በመመልከት በዜጎች ላይ የሚደረገው የዘር ማጥፋትና ማጥራት ግፍ ሲታይ ከዚህ በላይ ከተጮኸው ጩኸት የበለጠ ያስጮኻል።” ሲል ይቀጥላል።

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


“የተዘነጉት እስረኞች” እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ (ልብ የሚነካ ታሪክ)

0
0

Nardos(የሚከተለው ጽሑፍ በኢትዮጵያ ውስጥ እየታተመ በሚወጣው ዕንቁ መጽሔት ላይ ታትሞ የወጣ ነው)

በፍቃዱ ዘ- ኃይሉ

ላለፉት አራትዓመታት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅዳሜ እና እሁድ የሄደ ሰው ወጣቷን ናርዶስን ሳያገኝ አይመለስም፡፡ ናርዶስ ገና የ20 ዓመት ወጣትእና በኪያሜድ የመጀመሪያ ዓመት የነርሲንግ ተማሪ ናት፡፡ ናርዶስ ዘሪሁን በየሳምንቱ  ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ‹በእነብርጋዴር ጄኔራልተፈራ ማሞ መዝገብ› ከተከሰሱት 36 ሰዎች መካከል ዕድሜ ልክ የተፈረደባትን እናቷን ልትጎበኝ ነው፡፡ እነዚህ እስረኞች ሚያዝያ16/2001 አመሻሹ 12 ሰዓት አካባቢ ነበር ሁሉም በያሉበት በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ እኛም 4ኛ ዓመታቸውን ለማሰብ ተሰባስበንወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት በተለይ እማዋይሽ ዓለሙን ለመጠየቅ ሄደን ነበር፡፡ እንደተለመደው ናርዶስንም አገኘናት እና ብዙ ነገሮችንአጫወተችን፡፡

 

ናርዶስ ትረካዋን  የጀመረችው እናቷን እና ሌሎችም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሰው የተፈረደባቸውንሰዎች አያያዝ ነበር፡፡ ‹‹ሳስበው የተረሱ ያህል እየተሰማኝ ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ሚዲያዎች ስለነሱ አይደለም እያነሱ ያሉት፡፡በእናቴ ክስ የታሰሩት ከ30 ሰዎች በላይ ናቸው፡፡ አንድ ሰሞን ከይቅርታ ጋር በተያያዘ ስማቸው እየተነሳ ነበር አሁን ግን ሁሉነገር የተረሳ ይመስለኛል›› በማለት የእስሩ ሕመም ለታሳሪዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው ግን የሚረሳ ዓይነት አለመሆኑን ነገረችን፡፡

 

‹‹ሚያዝያ16፣ አርብ ቀን ነበር ሁሉም የተያዙት›› በማለት ሲታሰሩ የነበረውን ጠቅላላ ሁኔታ በማስታወስ ትጀምራለች፡፡ ‹‹ለአንድ ሰው የመጡየማይመስሉ ብዙ ሲቪል የለበሱ እና የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ ፖሊሶች መሳሪያቸውን አቀባብለው ነበር ወደቤት የገቡት፡፡ ስልካችሁንአጥፉ ወደማንም እንዳትደውሉ አሉን፡፡ የብርበራ ማዘዣ ይዘው ነበር፤ ‹ቤት ልንፈትሽ ነው የመጣነው እማዋይሽ ዓለሙ በቁጥጥር ስርውለሻል› አሏት ቤት ፍተሻው እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ቀጥሏል፡፡ ቀኑ አርብ ነበር፤ እናቴ ደግሞ እስከ 12 ሰዓት ትጾምስለነበር ከሥራ ወደቤት እንደገባች ‹ምግብ ስጡኝ› እያለች እያለ ነበር ፖሊሶች የገቡት ስለዚህ ምግብ ሳትበላ ውላ ነው ወደ እስርቤት የወሰዷት፡፡ ከዚያ በኋላ አራት ወራት ያክል ዓይኗን አላየነውም ነበር፤ ትሙት ትኑር የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡  ደግነቱ በሌላ ጉዳይ ታስራ በተፈታች ሴት አማካይነት መልዕክት ደረሰኝ፡፡ ‹አንቺደህና ከሆንሽ ሽሮ እና ጎመን ሰርተሸ አስገቢልኝ፤ እኔ ደግሞ ደኅንነቴነን የባናና ማስቲካ ወረቀት እልክልሻለሁ፡፡ ደኅና ካልሆንኩኝግን ያ ነገር ይቀራል› ብላ ላከችብኝ፡፡ ከዚያ እኔም ሽሮ እና ጎመን ሠርቼ በመላክ፣ እሷም የባናና ወረቀት በመላክ ደኅንነታችንንየሚገልፅ መልዕክት እንለዋወጥ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሰዓት እኛ በሌለንበት ጉዳያቸው ፍርድቤት ይታይ ነበር፡፡›› በማለትጉዳያቸው በኢፍትሐዊ መንገድ በመንግሥት እንደተያዘ አጫውታናለች፡፡

 

‹‹እናቴ ስዕልመሳል ትወዳለች፡፡ እናም በየጊዜው የጀመረቻቸው ስዕሎች የተበላሹ ሲመስሏት ቅርጫት ውስጥ ትጥላቸዋለች፡፡ ይመስለኛል፤  የቤት ሠራተኛችን እጅ አለበት፡፡ ስትታሰር የቀረበባት መረጃ እነዚህ የተጣሉወረቀቶች ተሰብስበው ‹የድርጅቱን አርማ ስታዘጋጅ ነው› የሚል ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፈቃድ የነበረው፣ ያውም የማይሠራ ሽጉጥም እንዲሁበማስረጃነት የቀረበባት መሆኑ ነው፡፡›› በማለት ለእርሷ ፍርዱ ፍትሐዊ አለመሆኑን እና እናቷም ነጻ መሆኗን እንደምታምን ነግራናለች፡፡

 

‹‹የሚያሳዝነውነገር ደግሞ ሲታሰሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈው ዜና ነው፤ እንኳን አገር ወዳዷ እናቴ ማንም ባገሩ ላይ የሚያደርገውን ነገርነው አደረጉ ያለው፤›› የዜናውን ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ወቅሳለች፡፡ እናቷ ሕዝብና አገር የማሸበር ፍላጎት ሊኖራት ለአገር ፍቅርሕይወቷን የሰጠች መሆኗን ስታጫውተን ‹‹እናቴ ሁልጊዜ የምትነግረኝ ነገር አለ፤ ሕይወቴ ማለፍ ካለበት አገሬን በሚጠቅም ነገር መሆንአለበት ትለኝ ነበር፤›› ብላናለች፡፡ ነገር ግን መንግሥት በአንድ በኩል ‹‹ሕገ መንግሥቱን ለመናድ በመሞከር ነው ያሰርኳችሁ እያለበሌላ በኩል ደግሞ የፖለቲካ እስረኞች የሉኝም ይላል፤›› ካለች በኋላ ‹‹ተቃዋሚ መባላቸው ካልቀረ የኢሕአዴግ መንግሥት የፖለቲካእስረኞች እንደሆኑ ቢያምን  እንኳ ጥሩ ነው፤›› ብላናለች፡፡ ‹‹እናቴለአገሯ ከማንም  በላይ ሠርታለች ብዬ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን አገራችንለእናቴ ውለታዋን እየከፈለቻት ነው ብዬ አላምንም፡፡ ያለሃጢያታቸው ሃጢያት ተሰጥቷቸው ነው ያሉት›› በማለት ፍርዱ አገር ወዳድእናቷን የሚያዋርድ እንደሆነ በሐዘን  ተርካልናለች፡፡

 

የእናቷ በአሸባሪነትመፈረጅ ለናርዶስ ማኅበራዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እያደረሰባት መሆኑንም አጫውታናለች፡፡ ‹‹ለትምህርቴ መስጠት የሚገባኝ ጊዜ ያህልመስጠት አልቻልኩም፤ እናቴ የታሰረችው እኔ ስምንተኛ ክፍል እያለሁ ነበር፡፡ ዩንቨርስቲ መግባት ሲኖርብኝ አሁን ግን ‹ነርሲንግ›እየተማርኩ ያለሁት በዚሁ ተፅዕኖ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የእነርሱን የእስር ዜና ኢቲቪ ከአቀረበበት መንገድ አኳያ ትምህርት ቤት ውስጥራሱ እኔን መቅረብ የሚፈሩ ሰዎች አሉ፤› በማለት የእናቷ እስር በእርሷ ማኅበራዊ ሕይወቷ ላይ ያጠላበትን ጥላ አጫውታናለች፡፡

 

‹‹እስጢፋኖስአካባቢ የሚገኘው እና በእናቴ ስም  ተይዞ የነበረው የቀበሌ ቤታችንበልማት ስም ሲፈርስ እንኳን ለጎረቤቶቻችን በምትኩ ሲሰጣቸው ለእኛ ግን አልተሰጠንም፡፡ ሌላው ቀርቶ መታወቂያ እንኳን ለኛ ለመስጠትፈቃደኞች አይደሉም›› ቤታቸውን ካፈረሱባቸው በኋላ አክስቷ ጋር እየኖረች እንደሆነ ስትነግረን በየመሐሉ እየገታችው ታወራልን የነበረውእምባዋ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሲወርድ ማድረግ የቻልነው ነገር ቢኖር በዝምታ ማጀብ ነበር፡፡

 

‹‹ያለአባትያሳደገችኝን የእናቴን ፍቅሯን አልጠገብኩትም›› የምትለን ናርዶስ ‹‹በዚህ ዕድሜዬ ለኔ የሚገባኝ ቦታ ቃሊቲ አልነበረም፡፡›› በማለትብዙ ነገር መሥራት በነበረባት ጊዜ ቃሊቲ በመመላለስ እንዲባክን መንግሥት እንደፈረደባት እንደሚሰማት ነግራናለች፡፡ ‹‹አራት ዓመቱን  በአሰቃቂ ሁኔታ ነው ያሳለፍኩት፤ ከ16 ዓመታት በኋላ ከእስር የተፈታው አባቴየራሱን ሁሉ ነገር ትቶ ሕይወቱን ለኔ መስዋዕት ባያደርግ ኖሮ አልወጣውም ነበር›› በማለት እንደዕድል እናቷ ከመታሰሯ ሁለት ወርያክል ቀድሞ በተፈታው አባቷ ድጋፍ ከብዙ ቀውስ እንደተረፈች እየነገረችን ከናቷ ጋር የነበራትን ፍቅር ‹‹እናቴ ሁለ ነገሬ ነች!››ብላለች፡፡

 

‹‹እናቴንሊጎዳ የሚያስብ ሰው እኔን  አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል በሚል ተሳቅቄነው የምኖረው›› በማለት በዙሪያዋ ያለውን ወዳጅ እና ጠላት እንኳን ማመን እየቸገራት እሷ ራሷም ቢሆን ከማኅበረሰብ የመነጠል እናየመስጋት ስነልቦናዊ ችግር ውስጥ እንደሆነች አስረድታናለች፡፡

 

‹‹የርዕዮትዓለሙእህት እስከዳር ዓለሙ ‹የቤታችን ሰላም እና ፍቅር ከርዕዮት ዓለሙ ጋር ታስሯል› ያለችው በጣም ትክክል  ነው›› በማለት በታሰሩት ሰዎች ቁጥር እኩል የሚሆኑ ቤተሰቦች በከፍተኛ ፈተናውስጥ እያለፉ መሆኑን አበክራ ነግራናለች፡፡

 

የናርዶስ  ታሪክ የብቻዋ ታሪክ አይደለም፡፡ የሌሎች የብዙ ቤተሰቦቻቸው የታሰሩባቸውቤተሰቦች ታሪክ ነው፡፡ ናርዶስም ‹‹እንደኔ ሁሉ ችግር ላይ ያሉ፣ አባቶቻቸው የታሰሩባቸው ብዙ ልጆች አሉ›› ብላናለች፡፡ በዚሁመዝገብ ተከሰው የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው አቶ መላኩ ተፈራ ቤተሰቦችም ከሰኞ እስከ እሁድ ቃሊቲ ደጃፍ ላይ ከማይጠፉት ሰዎች ውስጥይመደባሉ፡፡ በሥራ ጉዳይ ከአገር ውጪ ያለችው ልጃቸው ፅዮንም አባቷን ለመጎብኘት ሲባል ቶሎ፣ ቶሎ እንድትመላለስ ተገድዳለች፡፡እነጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ እነአሳምነው  ፅጌ እና ሌሎችም ደግሞ በእስረኞችመሐል ‹‹ተነስቷል በሚል ፀብ›› ሰበብ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደዝዋይ እንዲዛወሩ ተደርገዋል፡፡ ይህ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙሌላ ተጨማሪ ጫና አሳድሮባቸዋል ብላናለች፡፡ እዚህ የቀሩት ታሳሪዎችም አጋሮቻቸውን በማጣት ለብቸኝነት ስሜት ተዳርገዋል፡፡

 

ከነርሱ መዝገብውጪ ያሉ ሌሎችም እስረኞች እና ቤተሰቦቻቸው በተመሳሳይ ፈተና ውስጥ መሆናቸውን እስረኞችን ለመጎብኘት በሄድንባቸው ጊዜያት ተረድተናል፡፡መንግሥት ለፖለቲካ ግብአቱ የይቅርታ ደብዳቤ ካስፈረማቸው በኋላ እንኳን ለመፍታት ፍላጎት አያሳይም፡፡ ይልቁንም፤ ከቦታ ቦታ እያዘዋወረስቃያቸውን ያበዛል፡፡ ለዚህ እንደምሳሌ ባለፈው አርብ (ሚያዝያ 11/2005) ወደዝዋይ እንዲዘዋወር የተደረገው ጋዜጠኛ ውብሸትታዬ ተጠቃሽ ነው፡፡ በእርሱ የጋዜጠኝነት ደሞዝ ላይ ጥገኛ የነበሩት ባለቤቱ እና ልጁ (ፍትሕ ውብሸት) በእናትዬው መፍጨርጨር ሕይወታቸውንእንዲመሩ ከመገደዳቸውም በላይ አሁን የቤቱን አባውራ ለመጠየቅ ዝዋይ ድረስ እንዲመላለሱ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ለዚህም ነው መንግሥት የፖለቲካ አይደሉም የሚላቸውን የፖለቲካ እስረኞችን ከነቤተሰቦቻቸው ከሚቀጣበት መንገድ ይታረም ዘንድ ሊጠየቅ ይገባዋል በማለት የምንመክረው፡፡

—-

ይህ ጽሑፍ ዕንቁ መጽሔት ላይ ታትሟል!

የአማራን ዘ ር የማጥፋት እኩይ የወያኔ ሤራ

0
0
Amhara Women Cry

Amhara Women Cry on Eviction from her home by TPLF policy:See the picture

አማራ ሆኖ መኖር በወያኔ መራሹ መንግሥት ዘንድ ወንጀል ነዉ ዋጋ ያስከፍላል በዚህም መሰረት አማራ ለ21ዓመታት በሀገሩ ላይ  ስደት ሞት ውርደት እንግልት ግርፋት መብት የለሽ ሆኖ በመኖር ዋጋ በመክፈል ላይ ይገኛል ወንጀል የሆነበት ዋናው ምክንያት  በዋናነት ኢትዮጵያን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ከጠላት  ጠብቆ መኖሩ ነዉ ምክንያቱም አሁን በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ አመራር አባላት ሀገር ከድተው በተለይም የጣሊያን የባንዳ ልጆች መሆናቸው ነው በቀልን ጥላቻን ይዘው ሀገርን ሰላም በመንሳት ተግተዉ እየሰሩ ያሉት በዚህም መሰረት እንደየደረጃው በተለያዩ ጎሳዎች ግፍ እየተፈጸመ  ይገኛል በቀዳሚነት አማራና ኦሮሞን መጥቀስ በቂ ብቻ ሳይሆን ከበቂ በላይ ነው በተለይ አማራ ማለት ትምክህተኛ ነፍጠኛ በሚለው የስድብ ቃል ሃያ አራት ሰዓት በወያኔ  የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ጣቢያዎች ኢቲቪ ሬድዮ ፋና  ኤፍኤም በየቀኑ መስማት የተለመደ ነው

ወያኔ ከደደቢት አዲስአበባ ቤተ መንግሥት የሚደክመውና ተግቶ እየሰራ ያለው አማራን ከኢትዮጵያ  ዘሩን ጨርሶ በአማራ መቃብር ላይ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ማጥፋት በኦሮሞ ህዝብ  በጉራጌ ህዝብ በሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ላይም ተመሳሳይ ግፍ እየተፈጸመ ያለው ኢትጵያዊነት ለማጥፋት ካለው አጀንዳ ነው

አቦይ ስብሃት እኔ ግን አቦይ የሚለውን የክብር ስም ሊጠራበት አይገባውም ይልቁንም ዕቡይ ስብሃት ተብሎ ቢጠራየተሻለ ነው እላለሁ ይህ ክፉ መንፈስ ያደረበት ሰው በተደጋጋሚ ሲፎክር እንደሰማነው  አማራና ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን አጥፍተናቸዋል  ቦታ የላቸውም የሚል ነበር ነገሩን እንደቀላል ነገር ልናየው እንችላለን ይህ ዘመን የሰጠው  እንደልቡ ተናጋሪ የሆነ ሰው  የተናገረው የሰሩትን እውነታና እየሰሩ ያሉትን ነገር ነው

አዲስአበባ እንደገቡ ያለምንም ጥፋት ብቻ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ምሁራን በሀገራቸው ላይ ስራ እንዳይሰሩ ታግደዋል ከአዲስአበባ ዩኒቨርቲና ከተለያዩ ተቋማት ተባረዋል ይህ ሆን ብሎ የአማራን ተወላጅ ለማጥፋት ካለው መሰረታዊ አጀንዳ የመነጨ ነው በምትካቸው ከሌሎች ሀገሮች ማለትም ከሕንድ፣ከጋና መምህራኖች ቀጥሮ ያመጣው  በዚሁ ምክንያት ነው

በጎንደር በተለይም በወልቃይት ፣በጠገዴ ፣በጠለምት፣በደብረታቦር በጎጃም በሰሜን ሸዋ በደብረብርሃን ይህ ነው የማይባል የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል,በጥናት ላይ የተመሰረተ ከባድ የሆነ የዘርማጥፋት ወንጀል ዛሬም በመፈጸም ላይ ይገኛል

የበደኖ የአርባ ጉጉ ወዘተ ወንጀሎች ሁሉ ወዘተ ተመሳሳይ ወንጀሎች ተፈጽመዋል ሁሉም ጊዜውን ጠብቆ ይወጣል ሰው ሊያውቀዉ በማይችለው ሁኔታ በሕክምና ተቋማት በኩል በክትባት ስም በአማራ ሕፃናት ላይየHIV vires ጨምሮ የተለያዩ ኢሰብአዊ  ድርጊቶች ተፈጽመዋል፣ነገር ግን ለሁሉም ጊዜ አለው እንደተባለው ለጊዜ መተው ይሻላል

አማራነት ካመጣቸው ችግሮች  ትንሾቹን እንይ

ወያኔ ኢህአዴግ አዲስ አበባ እንደገባ በአማራ ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች

1ኛ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው ወይም ከሥልጣናቸው እንዲወርዱና እንዲገላቱ በመጨረሻም በሃገራቸው መኖር ባለመቻላቸው እንደሌሎች የአማራ ተወላጆች አማራ በመሆናቸው ብቻ ለስደት ፣ለዕንግልት፣ ተዳርገዋል,

ዛሬ ወያኔ  የራሱን ምልምል ፓትርያርክ በማስቀመጥ ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የአንድ የወያኔ  ተቋም ሁና በመስራት ላይ መሆኗን እያየን ነው በዚህም መሰረት በዕቡይ ስብሐት  ንግግር መሰረት የኢትዮጵን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አጥፍተናታል እንዳለው ዛሬ ቤተ ክርስቲያኗ ከመንፈሳዊና ከማኅበራዊ አገልግሎት ውጭ ሁና የሚታየው መሞቷን የሚያረጋግጥልን ጉዳይ ነው

2ኛ ፕሮፌሰር አስራት ወ/ ኢየሱስን ያሳሰረ ያንገላታ ያሰቃየ ለሞትም ያደረሰ ሌላ ወንጀል አይደለም አማራነት ብቻ ነው

3ኛ አቶ ተስፋየ ማሩን በጠራራ ፀሀይ በጥይት ያስገደለ ወንጀል አማራነት ብቻ ነው

አማራ እንደማንኛውም የሃገሪቱ ዜጎች አፈር ገፍቶ አዳረ ሠራተኛ ታታሪ ሀገሩን የሚወድ ሕዝብ ነው፣ ይህ ህዝብ  ከሌሎች ኢትዮጵያውን ጋር ማለትም ከትግራይ ወገኖቹ ጋርም በሰላምም በችግርም ወቅት አብሮ የኖረ መሆኑ ቀርቶ እንደ ክፉጠላትተቆጥሮ መከራ እየተቀበለ ያለ ህዝብ ነው

አማራ ለችግሩ ደራሽ ወገን አጥቶ 21 ዓመታት የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችል የመከራ ጽዋን እየተጋተ የሚገኝ አሳዛኝ ሕዝብ መሆኑ ግልፅ ነው

አንድ እዉነተኛ ታሪከ ልንገራችሁ የውጭ ሀገር የትምህረት ዕድል  ይገኝና ወደ ዉጭ ሄዶ መማር የሚፈልግ ተማሪ ሁሉ መመዝገብ ይችላል የሚል ማስታወቂያ ይወጣና ሁሉም ተማረ እንደፍላጎቱ  ለመመዝገብ ወደ መመዝገቢያ ቦታው ሲሄዱ አንድ ካድሪ ተኮፍሶ ቁጭ ብሎአል ከዚያም ተመዝጋቢዎችም ቀርበው ስም ሲጠየቁ በመጀመሪያ የትግራይ ልጆች ቀርበው ይመዘገባሉ ሁሉም መመዘኛዉን አለፉ መመዘኛዉም ዕዉቀት መሆኑ ቀርቶ ብሔር በመሆኑ ሌሎችም እየቀረቡ ይመዘገባሉ በመጨረሻ አንድ የዋህ ተማሪ ተራዉ ደርሶ ይቀርባል፣ መዝጋቢዉ ካድሪ ቀና ብሎ ያየዉና ከፊቱ የቆመዉን ተማሪ ብሄር ህ ምንድ ነው  ይለዋል ተማሪዉም በፍርሃት አማራ ይላል ያኔ ካድሪዉ ቆም ብሎ በቁጣ ከአማራ የሆናችሁ ዉጡ ከአማራ ብሄር አንወስድም የምንመዘገበው ከሌሎች ብሔሮች ብቻ ነው ይላል ይህን የሰማ ወላጆቹ አማራ የሆኑ ተማሪ ሌሎች የአማራ ተወላጆች የሆኑ ተማሪዎች ሲወጡ በድፍረት ይቀርና ሰልፉን እንደያዘ ይቆያል ተራው ደርሶት ወደ ካድሪው ቀርቦ ብሄር ይጠየቃል እሱም ኮራ ብሎ ደቡብ ሕዝቦች ይላል ወዲያዉኑ ከአፉ ተቀብሎ ካድሪዉ በብሔርህ አልፈሃል ግን ለሌሎች ብሔሮች ቅድሚያ ስለሚሰጥ ምናልባት ቦታ ካለ ስምህ በማስታወቂያ መለጥፊያ ቦታ በ15 ቀናት ዉስጥ ይወጣል ተከታተል ተብሎ ሲከታተል እንዳጋጣሚ ዕድሉን አግኝቶ ወደ ዉጭ ሃገር መጥቶ ትምህርቱን በመከታተል ይገኛል ከወደ ኋላ መለስ ብሎ በማሰብ ደፋርና ጭስ መዉጫ አያጣም ሆኖ ነዉ እንጂ ያኔ መንዜ መሆኔን ቢያዉቁ በሽርብተኝነት ወንጀል  ዘብጥያ ያወርዱኝ ነበር በማለት በሃዘን ትዝታ ያጫወተኝ

በአማራ ላይ ያልተፈጸመ ኢሰብአዊ ድርጊት የለም ሌላዉ ቀርቶ ብአዴን የሚሉት ድርጅት  አማራዉን እወክላለሁ ብሎ በሕወሐት የሚመራው ፓርቲ ዉስጥ አማራዉን የሚወክል ሰዉ እንደጠፋ ሁሉ ሆን ተብሎ አማራዉን ለማጥፋት ከሚሰራዉ ሕወሐትና ከሌሎች ብሄሮች የተዉጣጡ የጸረ አማራ ስብስብ መሆኑ ግልጽ ነዉ ድርጅቱ መለያ አርማውም ሆነ አመራሮቹ የሕወሐት ሰዎች መሆናቸዉን ለአብነት እንይ ,

እኔ እስከማዉቀዉ ድረስ ዋና ዋናዎቹ የአመራር አባላት

1ኛ ተሰማ  ገ/ሕይወት 2ኛ አቶ ካሣ ተ/ብርሃን 3ኛ አቶ አዲሱ ለገሰ 4ኛ ህላዌ ዮሴፍ ወዘተ የአማራ ተወላጆች ናቸዉ የምትሉ ካላችሁ የዋሆች ናችሁ አማራ ማለት በሕወሐት ዕምነት ጠላት ነዉ ዘፈኑን  እስቲ እናስታዉስ ገረብ ገረብ ትግራይ መቃብር አምሃራይ የትግራይ ሸለቆዎች ተራራዎች የአማራ መቃብር ናቸዉ  ወይም ይሆናሉ እያለ በቅዠትም በህልምም በዉኑ ም ጸረ አማራ ሆኖ የተፈጠረዉ ወያኔ ነዉ ብአዴን ማለት

አማራ መሆን እንዲያሳፍር አንገት እንዲያስቀልስ  እንዲያሸማቅቅ ለ21 ዓመታት ሲሰራ የኖረዉ አማራ ፈሪ ነዉ በሚለዉ በኢያሱ በርሄ ዜማ አማራን እየተከታተለ ዘሩን በማጥፋትና በኢትዮጵያዊነቱ ተከብሮ ሌላዉንም አክብሮ ከሚኖርበት አካባቢ እተፈናቀለ የሚገኘዉ ከደደቢት ጀምሮ አማራን ለማጥፋት በተያዘዉ  ዕቅድ መሰረት እተፈጸመ ያለ ሂደት ነዉ ,

አማራን ከቤንሻንጉል ጉምዝ ማስወጣት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሕሊና ያለዉ ሁሉ ሰዉ በራሱ ዳኝነት ይየዉ

አማራን መዉጫ መግቢያ በማሳጣት ከዚያች ሃገር ማጥፋት ነዉ,ከ2 4 ሚሊዮን የአማራ ሕዝብ በወያኔ አረመኒያዊ ተግባር ወንጀል ተፈጽሞበት ጠፍቷል እንዴት ጠፋ ወደፊት ኢትዮጵያዊ መንግስት ሲኖር የሚታይ ይሆናል የአማራ ወንጀል ኢትዮጵያዊነቱ እንደሆነ ግልፅ ነዉ  ይችን ሃገር ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን ደሙን አፍሶ ከጠላት ጠብቆ መኖሩ ነዉ  ወንጀሉ ሌላ ምንም ወንጀል የለበትም

አሁን ከጉራ ፈርዳ ከቤንሻንጉል ክልሎች የሚፈናቀሉት አማራ ሆኖ መኖር ወንጀል በመሆኑ ብቻ ነዉ ይህም እየሆነ ያለዉ በህወሐት ጨካኝና ጎጠኛ ድርጅት ስለሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድ ሆኖ ሊጋፈጠዉ ይገባል ይህ ጊዜ ያልፋል በሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ታሪክ ሰርተን ማለፍ  አለብን በሰላማዊ ትግል መታገል አይቻልም በተለይ አማራ ሆኖ የማይታሰብ ጉዳይ ነው ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ በሰላም መታገሉ ወንጀል ሆኖበት ቃሊቲ እንዲወረወር ያደረገዉ አማራ መሆኑ ብቻ ነው

በቤንሻጉል የዘር ማፅዳት ወንጀል ነዉ እየተፈጸመ ያለዉ ዘርን መሰረት አድርጎ ሌሎችን በማነሳሳት የሚፈጸም ወንጀል ነው በዚህ ወንጀል ሌሎች ኢትዮጵያዉያን እጃችሁን ባታስገቡ መልካም ነ ዉ ይህ ነገር ዝም ብሎ

የሚቀር   አይሆነም ዋጋ ያስከፍላል ዐይንና ጆሮ የሌለዉ ህወሃት ዛሬ አማራን ማጥፋቱን እ ንጂ ነገ ሊያመጣ የሚለውዉን  ችግር የሚያይበት ዐይን የለዉም , ምክንያቱም ዕብሪተኛ  ስለሆነ ብቻ ,ሰው በሃገሩ ላይ ከተፈናቀለ ምን ሃገር አለዉ ሊባል  ይችላል ሊባል የሚችለዉ በሀገሩ ላይ ስደተኛ የሆነ ማለት ነዉ ይህ ይህ ደግሞ ለማንም አይበጅም ተጎጂ የሚሆነዉ አማራ ብቻ አይሆንም የሁሉንም  ቤት ያንኳኩል,የትግራይ ተወላጆችስ አማራ ውስጥ የሉም ወይ እንዲያዉም ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ደሴ የትግራይ ከተሞች እስኪመስሉ ድረስ የትግራይ ልጆች መኖሪያ መስሪያ ከተሞች ናቸዉ ሌላዉ ቀርቶ የአማራ ቲሺ አንባቢዎች   በነክብሮም ወ/ስላሴ በነ ህሊና መብራቱ የተያዘዉ አማርኛ ዜና አንባቢ ክአማራ ተወላጆች ሰው  ስለጠፋ ሊሆን እንደማይችል ተስፋ አደርጋለሁ ይህን የምለዉ በወያኔ ስሌት እንጂ በእኔ ዕምነት ትግሬዎችም በአማራም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ሰርቶ መኖር ኢትዮጵያዊ መብታቸዉ ነው ስለዚህ የትግራይ ልጆች በአማራዉ ወንድማቸዉ እየደረሰ ያለዉን ችግር ከአማራዉ ከኦሮ

ሞዉ ከጉራጌዉ ከአፋሩ ጎን በመቆም ወገናዊነታቸዉን ማሳየት ከምንጊዜዉም በበለጠ ይጠበቅባቸዋል,ወያኔ  ሁሉንም አጋጭቶ ማለፍ ስለሆነ አላማዉ ጥላቻን አስወግደን ወያኔን ልንፋለመዉ ይገባል በአማራ ተወላጅ ላይ በወያኔ የግፍ አገዛዝ ያልሆነ ምንም ነገር የለም በቤት ዉስጥ እንዳሉ በዕሳት ተቃጥለዋል ,በተኙበት ተደብድበዉ ተገለዋል እንደእንስሳ ታርደዋል ተገለዋል ይህ ሁሉ የሆነ አንድ  ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ አይደለም ወያኔ ከጫካ ህይወቱ ጀምሮ እስካሁን በአማራ ሕዝብ ላይ እያደረሰዉ ያለዉ ግፍና መከራ  ነዉ

አንድ በዕድሜዉ ሸምገል ያለ ሰዉ ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ ብቻዉን እያወራ ይሄዳል ምን እንደሚል ጠጋ ብዬ ለመስማት ወደ ሰዉዬዉ  ሄድኩ ድምጹን ከፍ አድርጎ ቢገሉህ የማታልቅ ህዝብ ነበር የሚለዉ እዉነትም ቢገሉት የማያልቅ ህዝብ ልክ እንደ አማራ ህዝብ የኦሮሞ ህዝብ በሃገሩ ላይ ተዋርዷል፣ ታስሯል ፣ተገርፏል ፣ተገሏል በሙሉ ኢትዮጵያዉያን  የዜግነት መብታቸዉን ተገፈዋል , በሀገራቸዉ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረዋል,ዛሬ በኢትዮጵያ ዉስጥ በየትኛዉም ቦታ ከትግራይ ተወላጆች ውጭ በወያኔ ሥርዓት ተጠቃሚ የሆነ ከአንዳንድ ካድሪዎች ዉጭ አንድም የሌላ የኢትዮጵያ ብሔር ተወላጅ የለም ,ሌላዉ ቀርቶ በዉጭ ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችን በየሃገሩ መመልከት ይቻላል በሚያሳፍር ሁኔታ ለትግራይ ልጆች ብቻ አገልግሎት እንዲሰጥ ሁኖ የተዋቀረ መሆኑን ላለፉት 21 ዓመታት ያየነዉ ይህ ደግሞ ለአንድነታችን አደጋኛ ሁኔታ መሆኑን አዉቀዉ እንዲህ ዐይነቱን ሥራ መቃወም የግድ ይላል , በየሀገሩ ኢትዮጵያዉን በኢትዮጵያ ኤምባሲ በር ላይ እንደ እባብ ራስ ራሳቸዉን ተቀጥቅጠዉ ሲሞቱ ማን ደረሰላቸዉ ማንም የደረሰላቸዉ የለም ምክንያቱም የሕወሃት አባል ወይም የትግራይ ተወላጅ እስካልሆኑ ድረስ ኤምባሲዉ እንደማይመለከተዉ ያየነዉ ጉዳይ ነዉ ,አንድ ጊዜ ሀገር ቤት የሆነዉን ማስታወስ የግድ ሆነብኝ በኦሮምያ ክልል ዉስጥ አንድ የትግራይ ተወላጅ በሆነ በተፈጠረ ግጭት ህይወቱ አለፈች , በዚህም ምክንያት አካባቢዉ ቀዉጢ ሆነ በሙሉ ትንሽ ትልቁ ተጋፎ ወደ እስር ቤት ገባ ከዚያ በኋላ በእስር ቤት ዉስጥ የሆነዉን እግዚአብሔር ይወቀዉ ,የሟቹ አስከሬንም በክብር ወደ ትግራይ ሄዶ መስሪያ ቤት ተዘግቶ የሀዘን ቀን ሆኖ ሥርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል,ታዲያ ለሌላዉ ኢትዮጵያዊ ማን ይድረስለት አሁን ያለዉ የወያኔ መንግስት ዘረኛ ስለሆነ ተፈጥሮዉ ኢትዮጵያዊ ስላልሆነ አሁንም ኢትዮጵያን ከማፍረስ ዉጭ ሌላ ነገር መጠበቅ ከዕባብ ዕንቁላል የርግብ ጫጩት እንደመጠበቅ ይቆጠራል,የአማራ፣የኦሮሞ

፣የጋምቤላ፣ የአፋር የጉራጌ ወዘተ ልጆች ግን በየቀኑ ወያኔ ባዘጋጀዉ ወጥመድ ዉስጥ ገብተዉ ምንም የማያዉቁ ሕጻናት በየቀኑ ሕይወታቸዉ በማለፍ ላይ ይገኛል,

በቤንሻጉል በጉራፈርዳ በጋምቤላ አሁንም ግፍ እየተፈጸመ ነዉ ያለዉ አማራዎቹ ወደ መጡበትይመለሱ እንጂ በዚያ ምን ዐይነት ወንጀል እየተፈጸመባቸዉ እንደሆነ የምናዉቀዉ ምንም ነገር የለም ,የምንሰማዉ ነገር ግን ከሚዲያ እንዲርቁ            አድርጎ የዘር ማጥፋቱ ወንጀል በከፋ ሁኔታ እየተፈጸመባቸዉ ነዉ ,አሁን የሞተዉን ህዝብ ታሪክ ማዉራቱ ምንም ፋይዳ የለም ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ሞት፣ ስደት፣  ዉርደት በአማራ ህዝብ ላይ የማይቋረጥ ሂደት ነዉ ,

በአማራ ሰላማዉያን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለዉን አደጋ ወያኔ እንዲያቆም ከተፈለገ ስራ መስራት ያስፈልጋል,አሁን ይህንን ወንጀል የፈጸመዉ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዉንን በማጥፋት ያለዉ ወያኔ ብቻ ሳይሆን ይህ ድርጊት ሲፈጸም ዝም ብለዉ

ያዩ የሃይማኖት መሪዎች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ምሁራን ፣ታዋቂ ግለሰቦች ሁሉ በተባባሪነት ወንጀል ይጠየቃሉ,ሁላችንም ተጠያቂዎች ከመሆን ለመዳን ከጎሳ ፖለቲካ በመዉጣት እጅ ለእጅ ተያይዘን ወያኔን መታገል የግድ ነዉ ,ካሁን በኋላ ከወሬ ያለፈ ሥራ መስራት ካልቻልን የወያኔ የዘር ማጥፋት ወንጀል አያቆምም ምናልባት የሚሆነው ከአማራዉ ወደ ኦሮሞዉ ከኦሮሞዉ ወደ ወላይታዉ በፈረቃ እንደ አዲስአበባ መብራት እየተዘዋወረ ይቀጥላል እንጂ አይቆምም እየሞቱ ከመኖር እየኖሩ መሞት አማራጭ የሌለዉ መፍትሔ ይሆናል,ወያኔ በየጊዜዉ ወንጀል በፈጸመ ቁጥር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያዉቀዉ ከማድረጉ ባሻገር ለዘላቂ መፍትሔ የትግል መስመር መቀየስ ያስፈልጋል ,የሰላማዊ ትግል ሁኔታ ሃያ አንድ ዓመታት የታዬ ስለሆነ በሱ ላይ ጊዜ ማጥፋት አያስፈልግም ,የሰላማዊ ትግል ሂደትበሽብርተኛ ስም ጉዞዉ እስከቃሊቲ ድረስ ብቻ ይሆናል,ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልዩነቱን አስወግዶ በኣንድነት በመታገል ነጻ ሊወጣ ወይም በጎሳ ተከፋፍሎ

በሀገሩ ላይ ስደተኛ ባሪያ ሁኖ በወያኔ የባርነት ወጥመድ ዉስጥ ለዘለዓም መኖር ይሆናል ,

ወያኔን በጸረ ኢትዮጵያዊነት የሚቀድመዉ እንጅ የሚበልጠዉ የለም እንደዚህ ዐይነት የዉርደት ፣የስቃይ፣ የጥፋት ዘመን በታሪክ ተፈጥሮ አያዉቅም ESAT TVን  በመደገፍ የምናሳየዉ ትብብር ከቀጠለና ለሌላዉም የትግል መስመር እንደዚህ ከተባበርን ወያኔን የማናጠፋበት ምንም ምክንያት አይኖርም

ወያኔን በቃ ብለን እንነሳ በየቀኑ እንደቅጠል ለሚረግፉ ወገኖቻችን እንድረስላቸዉ ወያኔን በሚገባው ቋንቋ እናነጋግረዉ

ሰላም ድል ለኢትዮጵያዉን

 

 

 

ዲያቆን /መምህር/ ፍስሓ ዘዳሞት

በኖርዌይ የሚኖሩ ጀግና ኢትዮጵያውያን በድጋሚ የወያኔዋን አምባሳደር በድጋሚ አዋረዱ (Video)

0
0

በኦስሎ ኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአባይ ግድብ ስም የወያኔ ተላላኪዎች ያዘጋጁትን ስብሰባ በከፍተኛ ተቃውሞ እንዲበተን አደረጉ። ዝርዝሩን እስከምናቀርብ ድረስ ቪድዮውን ይመልከቱ።/

የዘረፋ ውሎ በእንዳማሪያም – (በገብረመድህን አርዓያ)

0
0

ገብረመድህን አረአያ

ከፐርዝ፣ አውስትራሊያ

gebremedih areayaስብሃት ነጋ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ በሚታተመው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት:: ስብሃት ነጋ “ኢህዴግን የመሰለ ፓርቲ በአፍሪካ የለም” እና ሌላም ብዙ ፣ ብዙ ይላል:: ይዘብታል ፣ ይፎክራል፣ ይሸመጥጣል፣ ያቀረሻል፣ በህዝብ ሞራል ላይም ያላግጣል:: ብዙም አልደነቀኝም:: ስብሃትም ሆኑ የዚህ ፋሺስታዊ ስርዓት አንቀሳቃሾች በብዙሃን ደም ላለፉት አርባ አመታት ታጥበዋል ፣ ታሪክ አውድመዋል ፣ እጅግ ከፍተኛ ዘረፋ ፈጽመዋል ፣ አገር ቆርሰው ሸጠዋል:: በጣም ከፍተኛ ወንጀል የሰሩ ሰዎች እንደመሆናቸው በአገሪቷ የፖለቲካ ለውጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ መቀጣጠሉ እንቅልፍ እንደነሳቸው እያየን ነው:: አዎን ስብሃት ገና ፣ ገና ከዚህም በላይ ብዙ ይናገራል ፤ ቁጣው እያየለ በሄደ ቁጥር ብዙ ወንጀሎችም ይሰራል::
ዛሬ ወያኔ ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በበዛ ፍጥነት እና ማን አለብኝነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ መሰረቶችን የመናዱን ስራ አጠናክሮ እየሰራ ለመሆኑ በየእለቱ የምንሰማቸው ዜናዎች እና ዘገባዎች ያሳያሉ:: እንደ እኔ ፣ እንደ እኔ የወያኔ የጥፋት ስራ ሳይሆን የጨመረው ይልቁንስ ረጅም እድሜ ለኢሳት ይስጠውና የዜና ዘገባ ብዛት እና አይነቱ መጨመሩ ይመስለኛል:: ወያኔ ሲፈጠር ጀምሮ ኢትዮጵያዊ መሰረት ያላቸውን እሴቶችን የማጥቃት ስራን እንደ መጨረሻ ግብ(strategic goal) አስቀምጦ የሚንቀሳቀስ ድርጅት መሆኑን ቀድመን ላወቅን እና ለተረዳን ሰዎች ግን እምብዛም አዲስ ነገር አይደለም:: ዛሬ ላይ ከኢትዮጵያ ከሚወጡ ዜናዎች በብዛት የምንሰማው ብዙዎች ሲያለቅሱ እና ጥቂት ዘረኞች ደግሞ ያለ ይሉኝታ ሲዘርፉ ፣ ሰዎችን አስረው ሲያሰቃዩ፣ እና ኢትዮጵያውያንን ዘር ቆጥረው ከቀያቸው ሲያፈናቅሉ ሆኗል::
የኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ዋይታ በቤኒሻንጉል እና ጉራፈርዳ፣ የባህታውያን ለቅሶ በዋልድባ ፣ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን የፍትህ ጥያቄ በመላ ሃገሪቱ ፣ ሌላም ፣ ሌላም:: ወያኔ ኢህአዴግ በአገር እና በወገን ላይ የሚያደርሰው ጥቃት በግብ ደረጃ የተያዘ በመሆኑ ይብሱን ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል:: ዛሬ ላይ ከዳር ቆመው የሚመለከቱ ሰዎችም ሆነ በስርዓቱ ውስጥ ያሉ ካድሬዎች እና አገልጋዮች ይህንን ሃቅ በደንብ ልብ ብለው ሊመለከቱት ይገባል:: የጥቃት ዱላው በአንድ ወይም በሌላ በኩል አይደርስ የሚመስልበት ቦታ ሁላ ይደርሳል::
ኢትዮጵያውያን ከምንም ነገር በላይ ለሃይማኖት እና የእምነት ተቋሟት ታላቅ ክብር ይሰጣሉ:: በዛሬ ጽሁፌ ለማንሳት የፈለግኩት ጉዳይ በአንድ ወቅት በወያኔ ኢህአዴግ ውስጥ ታጋይ በነበርኩበት ወቅት በዘመቻ ከስብሃት ነጋ እና ከሃለቃ ጸጋይ በርሄ ጋር ሌሎች ሁለት ታጋዮችም ተጨምረውበት አንድ ገዳም እንዴት እንደፈርን እና እንደዘረፍን በማሳየት ስብሃትም ሆነ ድርጅቱ እንዴት ለአገራዊ እና ሃይማኖታዊ ተቋማት ያላቸውን ንቀት ለማሳየት ነው:: ጊዜው ሕዳር ወር 1971ዓ.ም. እና የተ.ሓ.ህ.ት. 1ኛ ጉባኤ እየተቃረበ የመጣበት ወቅት ነበር። ድርጅቱ ለጉባኤው ማካሄጃ በሚል ሰበብ የትግራይ ደሃ ገበሬዎችን ንብረት እና ገንዘብ በስፋት መቀማቱን በዘመቻ ተያይዞታል:: ሃብትና ንብረታቸው የተዘረፈ ንጹሃን የትግራይ ገበሬዎችንም ሃለዋ ወያኔ በማስገባት መፍጀቱ ተጧጡፏል፤ በወቅቱ የተ.ሓ.ህ.ት. ቤዝ በለሳ፤ እገላ ወረዳ ውስጥ ይገኛል። ብዙ ክፍሎች፤ ማለትም 02 ወታደራዊ ማሰልጠኛ፤ 03 ህክምና፤ 04 ፖለቲካ ጽ/ቤት፤ 05 ክፍሊ ኢኮኖሚ፤ 09 መሳሪያ ግምጃ ቤትና 06 ሃለዋ ወያነ ተበለው ተከፋፍለው እዚሁ ቦታ ላይ በተለያየ አቀማመጥ ሆነው ይሰራሉ። አቦይ ስብሃት በ04 ፖለቲካ ጽ/ቤት በሚታዘዙ እና በአዲ ጨጓር እና በለሳ ምይ ሃማቶ ላይ በሚገኙ ሁለት ሃለዋ ወያኔዎች(እስር ቤቶች) ንጹሃንን አሳስሮ ያስገርፋል፣ ያስገድላል:: እኔ በወቅቱ የህክምናው ክፍል ሃላፊ ነበርኩኝ:: እና ታዲያ በዚሁ አንድ የህዳር ቀን በስብሃት የተጻፈ ቀጭን ደብዳቤ በምሰራበት የህክምና ክፍል ደረሰኝ:: ደብዳቤው እንዲህ ይላል : ነገ ጠዋት ልክ በ2 ሰዓት መሬቶ እንድትጠብቀኝ፤ ወደ ሽራሮ ለሥራ ጉዳይ አብረን እንሄዳለን:: ለምን ፣ እንዴት ፣ በምን ተብሎ አይጠየቅም፤
በነጋታው እንደታዘዝኩት በተባለው ሰዓት መሬቶ ቁሽት ቀድሜ ደረሼ ቆየሁት። እሱም በሰዓቱ መጣ። ተያይዘን ጉዞአችንን ወደ ጭላ ወረዳ ቀጠልን። ቀኑን ሙሉ ስንጓዝ ውለን በመሃልም ግርማይ ጀብር የሚመራት አንድ ሃይል ተቀብላን አንድ ቦታ አደርን። ከአስመራ ወደ አድዋ የሚወስደውን መንገድ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ አሻገሩን። ይህ መንገድ ሁልጊዜ የኢትዮጵያ ጦር አይለየውምና ለመሻገር ጥንቃቄ ይሻል::
ጭላ ከጥዋቱ 2 ሰዓት ገባን። እዛ የቆዩን ሃለቃ ፀጋይ በርሄ–የላይ አድያቦ ሕዝብ ግንኙነት፤ አጽብሃ ሀ/ማርያም–የአንከረ ሕዝብ ግንኙነት፤ ቀሺ ታደሰ–የክርቢት ነውጠኛ መሪ ነበሩ። እኔና ስብሃት ተደምረን አምስታችን ጭላ ውለን ስብሃት ቀድሞ ለወጠነውና አስቅድሞ መረጃው ለሌለኝ የዘረፋ ስራ ወደ እንዳማርያም ገዳም ጉዞ ጀመርን:: ሃለቃ ፀጋይ በርሄ በስብሃት በታዘዘው መሰረት አስቀድሞ ጥናቱን ጨርሶ ስለነበር፤ የቤት ክርስትያኑን አቃቤ ግምጃ ቤት ባህታዊ ማን መሆናቸውን እና የት አካባቢ እንደሚኖሩ አውቋል። ሌሎቻችን ታጣፊ ክላሽንኮቭ ስብሃት ነጋ ደፍሞ ሽጉጥ ታጥቋል። ለምን እና ወዴት እንደምንሄድ ቀሺ ታደሰ፤ አጽብሃ ሃይለማርያምም ሆነ እኔ አናውቅም። ኋላም ተጉዘን እንዳማርያም ቤተ ክርስቲያን ገባን። ቤተ ክርስቲያኑ በጥንት ዘመን በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነመንግሥት የተሰራ፤ በጣም ሰፊና ብዙ የአትክልት እና ፍራፍሬ እርሻ የሚለማበት ገዳም ነው:: በመነኮሳት ጉልበት በመስኖ የለማ ሎሚ፤ ሙዝ፤ ብርቱካን፤ ትርንጎ፤ መንደሪን ገዳሙን ከቦታል። መቼም አካባቢው ውብ እና ለመንፈሳዊ ህይወት የተመቸ ነው:: በእድሜ የበለጸጉ ባህታውያን፤ ቀሳውስት፤ መናንያን እና ዲያቆናት በገዳሙ ዙሪያ መንፈሳዊ ህይወታቸውን ይመራሉ። ውስጥ ለውስጥ ብዙ ከሄድን በኋላ ከፊታችን አንድ ዲያቆን አገኘን። ሃለቃ ፀጋይ ዲያቆኑን ለብቻ ነጥሎ አናገረው፤ ምን እንደተነጋገሩ እኔ ካለሁበት ብዙም አይሰማም ብቻ ሁለቱ ተያይዘው ከፊት እየመሩ ወደ አንድ ቤት ውስጥ አስገቡን። ቀጥሎም ስብሃት ነጋ እንዲህ አለ፤ ሌሎቻችሁ እዚሁ ቆዩ:: እኔ ፣ ገ/መድህን እና ሃለቃ ፀጋይ ብቻ የገዳሙን አስተዳዳሪ ለማናገር እንሄዳለን:: ከዚያም ሶስታችንም ተያይዘን ከነትጥቃችን ወደ ገዳሙ አስተዳዳሪ ቤት አቀናን:: የገዳሙንም አስተዳዳሪ ከቤታቸው አገኘናቸው:: ለአፍ ያህል ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ስብሃት ጊዜ ሳያጠፋ “የመጣነው ገንዘብ እንዲሰጡን ስለሆነ ያለዎትን ሁሉ ይስጡን!” አላቸው። ለመነኩሴው ግር የሚል ትዕዛዝ ነበር:: ብዙም ሳያቅማሙ “እኔ አልሰጥም፤ የእመቤቴ ብርሃን ንብረትና ሃብት ላይ የማዘዝ መብት የለኝም:: አልሰጥም::” በማለት እቅጩን በግልጽ አማርኛ ተናገሩ:: ስብሃትም አይኑን እያጉረጠረጠ ድምጹን ከፍ አድርጎ አምጡ ማለቱን ቀጠለ:: ስብሃት በቀላሉ እንደማይመለስ በድምጽም ፊቱን በመቀያየርም እንዲረዱ አደረገ ፣ ምስኪኑ አባትም አማራጭ እንደሌላቸው ተረዱ::ትንሽ አስብ አደረጉና ወደውስጥ ገብተው የተቋጠረ ከረጢት ተሸክመው መጡ።
ባዘነ አንደበት እንዲህም ሲሉ ተናገሩ ፤ “የቤተ ክርስቲያን ሃብት ወድጄ ፈቅጄ ሳይሆን የሰጠኋችሁ አስገድዳችሁ እና አንቃችሁ እንደወሰዳችሁ እወቁት::” ከዚያም ከረጢቱን አልሰጥም በማለት ብር 50,000 የታሰረ ገንዘብ ከፊቱ ዘረገፉለት። ስብሃትም በፍጥነት ይዘነው በመጣነው ‘ሃቨር ሳክ’ በሚባል ወታደራዊ ሻንጣ ሞልተን ተሸክመን እንድንወጣ አዘዘ:: እኛም የተባልነውን አደረግን:: ባህታዊውም በመውጫችን ላይ እንዲህ አሉ፤ “ነገ ጠዋት ለሕዝበ ክርስቲያኑ የሆነውን ሁሉ እናገራለሁ::” የተዘረፈውን ገንዘብ እኔና ስብሃት ተሸክመን ተመልሰን በለሳ ማይሃምቶ ገባን።
የተፈጸመውን የዘረፋ እና የገዳም ደፈራ የአካባቢው ሕዝብ ሁሉ ሰማው፤ በተሰራው ስራም ክፉኛ አዘነ፤ አወገዘውም። ስብሃት ድርጊቱ የየግል ምስጢራችን ሆኖ መጠበቅ እንዳለበት አስጠነቀቀን። ለዘረፋው ስራም ባለን ድርጅታዊ ታማኝነት እንደተመረጥን ገለጸልን። እንግዲህ ይህ አንድ ገጠመኝ ብቻ ነው:: ዘረፋ፣ ማውደም ፣ ታሪክ እና ቅርስ ማጥፋት ፣ የእስላምም ይሁን የክርስቲያን ቤተ እምነቶችን መድፈር እና ማበላሸት ለህወሃት የሰርክ ስራዎች ናቸው::
በአለቃ ገበረ ሃና ስም የሚነገር አንድ ታሪክ አለ:: ልጅቷ አለቃ ጋር ሄዳ “ጎረምሶቹ ሁሉ ድንቼ ፣ ድንቼ እያሉ ይጠሩኛል:: ለምን ይመስልዎታል::” ብትላቸው አለቃም እንዲህ አሉ:: ” ሊልጡሽ ፈልገው ነዋ!”:: ትናንትና በዘር እና በሃይማኖት እየመረጠ የአንድን አገር ወንድማማቾችን አንዱን ለአንዱ ታሪካዊ ጠላትህ ነው ፤ ላንተ ህልውና ከኔ በላይ ላሳር እያለ ሲመጻድቅባቸው የነበሩ የሃይማኖትም ሆነ የብሄር ቡድኖችን ከነጠለ በኋላ ያለ ሃይ ባይ ሲያጠቃ እያየን ነው:: ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች አስር ሺህ በሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ታጭቀዋል:: በቃሊቲ ፣ በጨለንቆ ፣ በዝዋይ ፣ በሸዋ ሮቢት ፣ እና በሌሎችም በይፋ ባልተመዘገቡ የወያኔ ማጎሪያዎች ውስጥ ዜጎች ያለሃጥያታቸው ታስረው ይሰቃያሉ::
ስርዓቱ ዛሬ ላይ በሰፊው በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የመጨረሻውን ዱላ ከማንሳቱ በፊት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የማጥቃቱን ስራ ሙሉ አቅሙን አሳርፎ ሰርቷል:: ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በቀር በጉዳዩ ብዙም ግድ ያለው አልነበረም:: ነገ ደግሞ ተረኛ የካቶሊካዊት ወይም የሌላ ወንጌላውያን ቤተክርስቲያናት ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት አይከብድም:: ይህን ዘረኛ እና ከፋፋይ ስርዓት በመታገስ እና በማስታመም የትኛውም የህብረተሰብ ክፍል ነገ ጥቃት ተቀባይ ሊሆን አይገባም::
ስለወያኔ ማንነት ይኸው ለአመታት የተናገርኩት አንድ በአንድ ጊዜውን እየጠበቀ ሲፈጸም አየን:: አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምጽ በቃ የሚሉበት ጊዜ ላይ ደርሰናል:: የለውጥ ጊዜ እየቀረበ ነው:: ኢትዮጵያውያን አይን ለአይን ተያይተው ፤ ልብ ለልብ ተግባብተው ይህንን ዘረኛ እና ፋሺስታዊ ስርዓት ከዚያች ቅዱስ አገር የሚያጠፉበት ጊዜ በእውነትም እየቀረበ ነው:: ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሲሰሩ ምን ማድረግ እንደሚችሉ እስከ አፍንጫው በታጠቀው የወራሪው የፋሺስት ኢጣልያ ጦር ላይ የተቀዳጁትን የአድዋውን ድል ማስታወሱ ብቻ በቂ ነው::በአዲስ ተስፋ ለህልውናቸው እና ለቀጣይ ትውልድም የምትበቃ አገር እና መንግስት ለማቆም ሊሰሩ የሚገባበት ወቅት እየመጣ ነው:: በመጨረሻም ከሰሜን እስከ ደቡብ ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ:: እስላም እና ክርስቲያን ሳይሉ ፤ ኦሮሞ ፣ አማራ ፣ ትግሬ ፣ ጉራጌ ፣ ወላይታ ፣ አገው ፣ አፋር ፣ ቤኒሻንጉል ፣ ስልጤ ፣ አደሬ ነኝ ብለው ወያኔ በሰፋላቸው የዘረኝነት ወጥመድ ውስጥ ሳይወድቁ እጅ ለእጅ ተያይዘው ለወሳኝ የፖለቲካ ለውጥ እንዲሰሩ ጥሪዬን አስተላልፋለሁኝ::
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ገብረመድህን አርዓያ
ፕርዝ፣ አውስትራሊያ

Breaking News: በአማራ ክልል አዊ ዞን ፌደራል ፖሊስ እና ሕብረተሰቡ ወጊያ ገጠሙ፤ ሰዎች ሞተዋል

ድምፃዊት አስቴር ከበደ –ከ25 ዓመት በኋላም ዝናዋ ናኝቷል

0
0

ከዕጸገነት አክሊሉ
aster kebede
በአገሪቱ ሙዚቃ ውስጥ ተወዳጅና ስመጥር ከሆኑት ባለሙያዎች ተርታ ትመደባለች። በሙዚቃው ዓለም ለአጭር ጊዜ ብቅ ብለው አንቱታን ካተረፉና ዘመን ተሻጋሪ ሥራን ካኖሩ ሙዚቀኞች መካከል የምትጠቀስ ናት። ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በነበረችበት ወቅት ነው ወደ ሙዚቃው ዓለም ጎራ ያለችው።በአጭር ጊዜ ውስጥ ዘመን ተሻጋሪ ሥራን በመሥራት በትውልዱ ዘንድ አይረሴነትንም አትርፋለች።
ጥበብ ለእርሷ ሁሉም ነገር ቢሆንም የሕይወት አጋጣሚ ሆኖ ሳታስበው ከጥበቡ ዓለም ለ 25 ዓመታት ራሷን አግልላም ቆይታለች። የኋላ ኋላ የሙያው ፍቅር አስገድዶ ወደ መድረክ መልሷታል የዛሬዋን አምዳችንን – ድምፃዊት አስቴር ከበደን።
ድምፃዊት አስቴር ከበደ ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበባ ከተማ ቢሆንም በአባቷ የሥራ ፀባይ ምክንያት በተለያዩ አካባቢዎች የመዘዋወር አጋጣሚ ነበራት። ጅማ፣ ወልቂጤና ወሊሶ ጥሩ የልጅነት ጊዜያት ማሳለፏን አልዘነጋችውም።
እናትና አባቷ ካፈሯቸው ዘጠኝ ልጆች መካከል አስቴር ሦስተኛዋ ናት። በዚህ በቤተሰብ ውስጥ ይኸ ለወንድ ይህ ደግሞ ለሴት ተብሎ የተከፋፈለ አስተዳደር የለም። ሁሉም እኩል ነው፤ ሁሉም በነፃነት የመማር፣ የሚፈልገውን የማድረግ ዕድሜው ሲደርስም ያዋጣኛል ብሎ በመረጠው የሕይወት ጎዳና የመጓዝ ዕድል ተሰጥቶታል።
አስቴርም ከትምህርቷ ጎን ለጎን የሕይወት ጥሪዋን የምታስተናግድበትን ዕድል የነፈጋት አልነበረም። ለዚህም ነው በትምህርት ቤት በወላጆች ቀን ሙዚቃ የማቅረብ ዕድል ያገኘችውና ለሙዚቃ ሕይወቷም መሰረት የጣለችው።
« በትምህርት ቤታችን በየዓመቱ የሚከበረው የወላጆች ቀን ለእኔ ልዩ ስሜትን የሚፈጥርብኝ ነበር፤ ምክንያቱም ተሰጦዬን ላወጣበት የምችልበት ብቸኛው አጋጣሚ ነው። በዚያን ዕለት በጓደኞቼ ፊት ቆሜ የምዘፍንበት ጊዜ በመሆኑም እጅግ ደስ ይለኛል» ትላለች።
እንዲህ በትምህርት ቤት የተጀመረው የሙዚቃ ፍቅርና ተሰጥዖን የማውጣት ልምድ ደግሞ ከዕድሜ ጋር አብሮ እያደገ መጣ። በውስጧ የተፀነሰው የሙዚቃ ፍቅር እያደገ ሲሄድ ካልወጣሁ እያለ ይተናነቃት ጀመር ። ይህንን ያወቀችው አስቴርም ፍላጎቷን ለመገደብ አልሞከረችም ይልቁንም ፍላጎቴን ያወጣልኛል እንዲሁም ያሰብኩበት ደረጃ ያደርሰኛል ያለችውን መንገድ መፈለግ ጀመረች እንጂ። በወቅቱ ያገኘችው ብቸኛው አማራጯ የእድሜ እኩዮቿ ተሰጥዖአቸውን የሚያወጡበትን የቀበሌ ኪነት ነበር። ጊዜ ሳታጠፋም ወደ ቀበሌ ኪነት ተቀላቀለች። ከዚያም ደረጃዋን እያሻሻለች ወደ ከፍተኛ የኪነት ቡድን ገባች። ይህ አካሄዷ ደግሞ ቶሎ ወደ ቴአትር ቤቶች እንድትቀላቀል የራሱን መንገድ ጠረገላት።
በወቅቱ የነበረው አስተሳሰብ ቤተሰብ ልጆቹን በራሱ መንገድ ቀርጾ ማሳደግን የሚደግፍ ነበር ። ልጆቹ ወደ ጥበቡ ዓለም ለመግባት ሲያስቡ በሰላም ሁኔታዎችን የሚያመቻች ቤተሰብ ቁጥር እጅግ አናሳ ነበር። የአስቴር ከበደ ቤተሰቦች ግን ከዚህ ፍጹም የተለዩ ነበሩ። የልጃቸውን የጥበብ ጥሪ ለማስተናገድ አልተቸገሩም። ጥረቷን በማድነቅም እንድትገፋበት አበረታቷት።
«በቤተሰቤ በኩል ይህንን አትሆኚም። እንድትሆኚ የምንፈልገው ያንን ነው። የሚል ሙግት አልገጠመኝም። ሆኖም ከከፍተኛ ኪነት ወጥቼ ሲኒማ ራስ እንደተቀጠርኩ ብዙም ሳልቆይ ለመድረክ ሥራ ወደ ቀድሞው አሰብ ክፍለ ሀገር እንድሄድ ታዘዝኩ ፤ በዚያን ጊዜ ደግሞ ከቤት ወጥቼ አድሬ አላውቅም ነበር። ምን ብዬ ነው የምነግራቸው የሚለው ፍርሀት በጣም አስቸግሮኝ ነበር። ሆኖም ከቤታችን ውስጥ አንደኛው ወንድሜ በጣም ሙዚቃ ይወዳልና ለእርሱ ስነግረው ‘ ምንም ችግር የለውም ንገሪያቸው ‘ አለኝ። ነገርኳቸው ያንን ያህልም ጫና ሳያሳድሩብኝ ተቀበሉኝ።»
አሰብ የመጀመሪያ ሥራዋን ያቀረበችባት ቦታ ናት። በወቅቱ ከዘፈኑ ባሻገር የብሔር ብሔረሰቦችን ውዝዋዜም ደርባ ትሰራ ነበር። እናም አሰብ በቆየችባቸው ጊዜያት በይበልጥ የሰራችው የብሔር ብሔረሰቦችን ውዝዋዜ እንደነበርም ታስታውሳለች። የመጀመሪያዋ እንደመሆኑም የሕዝቡ አድናቆትና አቀባበል ይበልጥ ወደ ጥበቡ እንድታዘነብል አድርጓታል።
አንድ ሙዚቃ እንጋብዛችሁና ዘገባው ይቀጥላል

ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ለእርሷ ሞዴል እንደሆነቻት የምትናገረው አስቴር የራሷን ሥራ ከመሥራቷ በፊትም አዘውትራ ትጫወት የነበረው እንዲሁም ሲኒማ ቤት ለመቀጠር ተፈትና ያለፈችበት ሙዚቃም የሂሩት በቀለ መሆኑን ታስታውሳለች።
ከዛሬ 25 ዓመት በፊት የሠራችው የራሷ የሙዚቃ አልበም ደግሞ ብዙ አድናቂዎችን እንድታፈራ ከማድረጉም ባሻገር ዘመን ተሻጋሪ በመሆን እስከ አሁን ድረስ እየተደመጠ ይገኛል።
«ዘመን ተሻጋሪ ከሆኑ ጥቂት ሥራዎች መካከል አንዱ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ሥራዎቹ እጅግ የተለፋባቸው በመሆናቸው እንዲሁም ዜማና ግጥም የሰጡኝም ሰዎች በሙያው በሳል ስለነበሩ ነው»ትላለች ስለ መጀመሪያ ሥራዋ ስትገልጽ።
አስቴር ከበደ ዘመን አይሽሬ ስለሆነው ብቸኛው የሙዚቃ አልበሟ ስትገልጽም የስምንቱን ዘፈኖች ግጥምና ዜማ የሠራው አርቲስት ንዋይ ደበበ እንደሆነ ትናገራለች። «ፍቅር እንዳሰቡት» የሚለውን ዜማ ደግሞ አርቲስት ደበሽ ተመስገን እንዲሁም ሙሉ ገበየሁ እንደሰጧት ታስታውሳለች። እዚያው አልበም ላይ «ለጤና ያድርግልኝ» የሚለውን ዜማ ደግሞ እርሷና ሙሉ ገበየሁ በጋራ ነበር የሠሩት።
ድምፃዊት አስቴር ምንም እንኳን ከእነዚህ ታላላቅ ባለሙያዎች ጋር የመሥራት ዕድል አግኝታ የሙዚቃ አልበሟ እጅግ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ ቢሆንም ብዙ ሳትጠቀምበት፥ በአድናቂዎቿም ሳትጠገብ ነበር በትዳር ምክንያት ኑሮዋን ከኢትዮጵያ ውጭ ያደረገችውና ከሙዚቃው ዓለም ራሷን ያገለለችው።
«ሙዚቃዬ እንደወጣ ወዲያው ትዳር መስርቼ ወደ ሳውዲ አረቢያ ነበር የሄድኩት። በእዚያም ከ25 ያላነሱ ዓመታትን ቆይቻለሁ። ወደ አገሬ የመምጣት ዕድሉ ቢኖረኝም ሙዚቃን የመሥራት አጋጣሚ ግን አልተፈጠረልኝም ። ከሙዚቃ ተለይቶ መቆየቱ እጅግ ፈታኝ ቢሆንብኝም ልጆች የማሳደግ ድርብ ኃላፊነት ስለነበረብኝም ወደዚያ አዘምብዬ ለብዙ ዓመታት ከሙዚቃው ራቅሁ» በማለት ነው ለ25 ዓመታት ከሙዚቃ የራቀችበትን ምክንያት የምትገልጸው።
የሁለት ወንዶችና የአንዲት ሴት ልጅ እናት የሆነችው አስቴር «ልጆቼ አድገው እኔም ወደ ምወደው የሙዚቃ ሕይወት ተመልሼ» የሚለውን ምኞቷን ለማሳካት 25 ዓመታትን በትዕግስት ጠብቃለች። አሁን ደግሞ ያ የተመኘችው ቀን ደርሶ ልጆቿ አድገውላታል፤ ወደምትወደው የሙዚቃ ሥራም ተመልሳለች።
ከ25 ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ሙዚቃው ሕይወት ተመልሳ ለአድናቂዎቿ ያን ተስረቅራቂ ድምጿን ማስደመጥ ችላለች። ዳግም ወደ ሙዚቃ ስትመለስ እዚያው ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ከአርቲስት ታምራት ደስታ ጋር ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያዜመችው። ይህ ጅማሬ ደግሞ አገሯ ገብታ ተጨማሪ የሙዚቃ ሥራዎችን እንድትሠራ አድናቂዎቿንም እንድታዝናና መነሳሳትን እንደፈጠረባት ትናገራለች።
«ሳውዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ከታምራት ደስታ ጋር ሥራዬን ሳቀርብ ከተመልካቹ ጥሩ አቀባበልን አየሁ። ለካ አድናቂዎቼ አልረሱኝም የሚል ስሜትን ፈጠረብኝ። ይህ ደግሞ ቶሎ አገሬ ገብቼ የሙዚቃ ሥራን እንድሠራ አደረገኝ ።»
ከ25 ዓመታት የውጭ አገር ኑሮ በኋላ ጉዞ ወደ አገር ቤት ሆነ። አስቴር አገር ቤት የገባችው እንዲሁ ልጆቿን እያሳደገች ለመኖር ብቻ አልነበረም። ይልቁንም ሙዚቃዋን ሳይጠግቡ በድንገት የተለየቻቸውን አድናቂዎቿን በሙዚቃ ሥራዋ ለማዝናናትም እንጂ። እንደተመኘችውም ዳግም ከሙዚቃ ጋር ተገናኝታ ችሎታዋን ማስመስከር ጀመረች። በየመድረኩ በዚህ ትውልድም ተወዳጅ የሙዚቃ ሰው መሆኗን እያስመሰከረች ትገኛለች።
አስቴር ምንም እንኳን የተዋጣላት ሙዚቀኛ ብትሆንም ከብዙ ዓመታት ቆይታ በኋላ ነውና ወደ ሙያው የተመለሰችው እንግድነት ብጤ ሳይሰማት ይቀራል ብሎ መገመት ያስቸግራል። እርሷ በሙዚቃው ዓለም ነግሳ በነበረበት ወቅት እንዳለው ሳይሆን የሙዚቃ ሥራውም በእጅጉ ተለይቷል። በርካታ የሙዚቃ ባለሙያዎችም ተፈጥረዋልና እንዲያው የሙዚቃውን ኢንዱስትሪ እንዴት አገኘሽው? ስል ጥያቄዬን ሰነዘርኩ።
« በአሁኑ ወቅት ያለው የሙዚቃ ሁኔታ ጥሩ ነው። የባለሙያዎቹ የፈጠራ ችሎታ፣ የወጣቶቹ ጥረትና ስኬት ያስገርማል፤ የህብረተሰቡ ሙዚቃ አድማጭነት በአጠቃላይ የሚታየው ነገር ለመሥራት ያነሳሳል። በተጨማሪም የሙዚቃ ቀረፃውና ቅንብሩ ከድሮው ሙሉ በሙሉ ተለውጧል ማለት ይቻላል፤ በእኔ በኩል ደግሞ ብዙም ምክር የሚለግሱኝ ሰዎች ባለማግኘቴ ትንሽ ከብዶኝ ነበር» ትላለች ዘመንን እያነጻጸረች።
ቀደም ባሉት ጊዜያት ካሴት ሲሰራ በሙሉ የሙዚቃ መሣሪያ በመታገዝ ነበር።ዘፋኙ አንዴ ወደ ቀረጻ ከገባ ግጥም ቢሳሳተው እንኳን ለመመለስ ከባድ ነበር። ብዙ ጥንቃቄና ችሎታን የሚጠይቅ ነበር። ሥራው አድካሚ ቢሆንም ዘፈኖቹ በጥራትና በብቃት የተሰሩ በመሆናቸው ተወዳጅነታቸውና ተደማጭነታቸው ያንንኑ ያህል ነበር። አሁን ሥራው እጅግ ቀሏል፤ ብዙ ነገሮች በኮምፒውተር አጋዥነት ይሠራሉ። ሙዚቀኛው በቀረፃ ላይ ስህተት ቢፈጽም ያ ተሰርዞ እንደገና መቀዳት ይችላል፤ የልምምድ ጊዜውም ብዙ ነው። በአጠቃላይ እነዚህ የዘመን ልዩነቶች በመፈጠራቸው የሙዚቃ አሠራሩ ተለውጧል ትላለች።
ተጨማሪ ሙዚቃ ግብዣ….ከዘ-ሐበሻ – ዘገባው ከዘፈኑ በታች ይቀጥላል

አስቴር ሙዚቃ ለመሥራት ስትነሳ ከከበዳት ነገር መካከል በእርሷና ሙዚቃውን ሊሰሩላት በሚስማሙት ወገኖች መካከል የሚደረጉ ውሎች፥ የአከፋፈል ሁኔታና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች የማታውቃቸው መሆናቸው ነው። እርሷ ሥራው ላይ በማተኮሯ ስለምታገኘው ገንዘብ ተገቢውን ትኩረት ሰጥታ አልተከታተለችም። በጥንቃቄ መፈረም ስላለባቸው ጉዳዮች ባለማወቋ እንደተቸገረችም አጫውታኛለች።
ድምፃዊት አስቴር ወደ ሀገሯ ከመጣች ጥቂት ጊዜያት ተቆጥረዋል። ይሁን እንጂ አዳዲስ ሥራዎችን ለአድናቂዎቿ ለማቅረብ አልቻለችምና ምክንያቱ ምን ይሆን? ስል ጥያቄ አቀረብኩላት።
«ከዛሬ 25 ዓመት በፊት የዘፈንኩት ዘፈን አሁንም አዲሱ ትውልድ እየሰማውና በምሽት ክለቦች አካባቢም እየተዝናናባቸው ይገኛል። ይህ ደግሞ ለእኔ በጣም አስደሳች ነው። ስለዚህ እሱ ትንሽ ይሰማ ብዬ እንጂ አርፌ አልተቀመጥኩም። አዲስ ሥራ ለመስራት ከተለያዩ ሰዎች የግጥምና ዜማ ሥራዎችን እያሰባሰብኩ ነው።»
በአሁኑ ወቅት ሙዚቃ ከፍተኛ ገቢ የሚገኝበት ዘርፍ ሆኗል። ቀድሞ በእነርሱ ዘመን ትልቅ ገንዘብ አወጣ የተባለ ካሴት የሚሸጠው ከ2ሺ ብር ባልበለጠ ዋጋ እንደነበር የምትገልጸው አስቴር ፤ አሁን የቀድሞውን ዜማዎቿን በድጋሚ ሰርታ (ሪሚክስ ) በ3 መቶ ሺ ብር መሸጧንም ትናገራለች።
አስቴር ሁለተኛውን የሙዚቃ ሥራዋን ለመሥራት ስታስብ እጅግ ከባድና ፈታኝ የሆነባት ነገር የግጥምና ዜማ ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅት የሚዘጋጁ ግጥምና ዜማዎች የቶሎ ቶሎ ሥራ መሆናቸውን ታዝባለች። « መምረጥ ካልተቻለ እጅግ አስቸጋሪ ነው። ሁሉም በዘመኑ መልካም ቢሆንም የድሮ የግጥምና ዜማ ሥራዎችን የሚስተካከል ግን አላየሁም። ስለዚህም የተሻለ ሥራ ለመሥራት በጥንቃቄ መምረጥና ደጋግሞ ማሰብም ያስፈልጋል» ባይ ናት።
በርካታ ወጣቶች ወደ ሙዚቃው ዓለም ለመቀላቀል ይፈልጋሉ። ከዚያም ባሻገር በተለያዩ ሁኔታዎች እንደ ኢትዮጵያን አይዶል፣ባላገሩ አይዶል እንዲሁም ሌሎች መሰል ውድድሮች ላይ በመካፈል ተስጥዖአቸውን ይፈልጋሉ። «ይህ ሁሉ መልካም ነው» የምትለው አስቴር ሆኖም ታዋቂ ለመሆን አልያም ሙዚቀኛ ለመሆን መቻኮል ሳይሆን በትዕግሥት በሰል አድርጎ መሥራት ያስፈልጋል በማለት ትመክራለች። ዋናው ነገር ግን ውጤታማ ለመሆን በውስጣቸው የሥራውን ስሜት በማሳደግ ሳይታክቱ፣ ሳይሰላቹ መሥራት ነው ባይ ናት። «ዛሬ የሠራሁት ሙዚቃ ወይም ፊልም አድማጭ ተመልካች አላገኘም ብሎ መንገድን መሳት ተገቢ አይደለም። በትዕግሥት ያሰቡበት መድረስ ይቻላል» ስትልም መልዕክቷን አስተላልፋለች።
የቅጂ መብትን ከማስከበር አንፃር መንግሥትና የሚመለከታቸው አካላት ለጥበቡ የሰጡት ትኩረት እጅግ በጣም የሚያስመሰግን በመሆኑ ህብረተሰቡም የእዚህ ትግል ተባባሪ በመሆን ኦርጂናል ሥራዎችን በመግዛት የሚወዳቸውን አርቲስቶች ማበረታታትና መደገፍ እንደሚጠበቅም ትናገራለች።
አስቴር በአጭር ጊዜ ውስጥ እውቅናን ያተረፈች፤ ለ25 ዓመታት ከሙዚቃው ዓለም እርቃ ቆይታ በድጋሚ እውቅናዋንና ዝናዋን ያስመለሰች የሙዚቃ ሰው ናት። መዚቃ ለጥበብነቱ መሠራት አለበት የሚለው አቋም ያላት ሙዚቀኛ ናት። ለምትሠራቸው ሙዚቃዎችም ከፍተኛ ጥንቃቄ በማደረግ እውቅናዋንና ተወዳጅነቷን እንዳስጠበቀች ለመቀጠል እየሠራች ትገኛለች። ለሌሎች ወጣት ድምፃውያን አርአያ መሆን የምትችል መሆኗንም ዘመን ባልሻራቸው በሥራዎቿ አስመስክራለች።

ግጭቱን ማን ለኮሰው? – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

0
0
አቶ አባይ ጸሐዬ

አቶ አባይ ጸሐዬ

ቀኑ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 22 1998 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ… አንድ የከተማ አንበሳ አውቶብስ ተሳፋሪ ሳይጭን ከመርካቶ ተነስቶ ወደ ጎማ ቁጠባ አቅጣጫ በባዶ እየከነፈ ቁልቁል ወርዶ ..ተ/ሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን አደባባይን ከዞረ በኋላ ጥግ ይዞ ቆመ። ሹፌሩ አውቶብሱን ገትሮ ወዲያው ከአካባቢው ጠፋ። ለሁለት ሰዓት ገደማ አውቶብሱ እንደተገሸረ ቆየ።…በዚህ ቅፅበት አንዲት ነጭ ቶዮታ ፒካፕ (ታርጋ የሌላት ወይም ያለጠፈች) ከሱማሌ ተራ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየከነፈች ከመጣች በኋላ < በላይ ተክሉ ኬክ> ቤትን አለፍ ብላ ቆመች። ከሹፌሩ ጎን ሲቪል የለበሰና ኮፍያ ያጠለቀ ሰው የተቀመጠ ሲሆን ከመኪናው ጋር ከተገጠመው ሬዲዮ መገናኛ በተጨማሪ ሁለት ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ይዟል።… 25 ወጠምሻዎች፣ ሁሉም ረዘም- ወፈር ያሉ ዱላዎችን፣ ገሚሶቹ ደግሞ ገጀራ እንደጨበጡ እንዲሁም ከመካከላቸው ሁለቱ አነስተኛ ጀሪካን እንደያዙ…ከመኪናዋ ዘለው ወረዱ። ሁሉም የተቀዳደ ተመሳሳይ ድሪቶ አጥልቀዋል፤ « አደገኛ ቦዘኔ» መሆናቸው ነው። ነገር ግን « ሆን ተብሎ » የተዘጋጀ ድሪቶ እንደሆነ የሚያሳብቀው ….በግልፅ የሚታየው የሁሉም ፈርጣማ ጡንቻ ከጥሩ እንክብካቤ ጋር በስፖርት የዳበረና ወታደራዊ አቋም እንዲይዝ ተደርጎ የተገነባ መሆኑ ነበር።
ከመኪናዋ ዘለው ከወረዱ በኋላ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ « አትነሳም ወይ…አትነሳም ወይ …ወያኔ…ወያኔ..» እያሉ በመጮህ አንበሳ አውቶብሱን ተጠጉ። በያዙት የብረት ዱላና ስለታማ ገጀራ አውቶብሱን እንክትክቱን ካወጡ በኋላ በያዙት ነዳጅ አርከፍክፈው አቃጠሉት፤…ተመሳሳይ ጩኸትና ቅስቀሳ እያሰሙ ሽቅብ ወደ ሲኒማ ራስ አመሩ። ነጯ መኪና ከኋላ ደርሳ ሁሉንም ጫነች…ከዛም ወደፊት በፍጥነት እየካለበች አዲስ ከተማ ት/ቤት አካባቢ ደረሰች። ወጠምሻዎቹ ..የ <አትነሳም ወይ…> ቅስቀሳቸውን ሲቀጥሉ..እግረመንገዳቸውን በቅርብ ርቀት የሚገኘው የቴሌ መ/ቤት ላይ ድንጋይ በመወርወርና ከደጃፍ ቆመው የነበሩ ሁለት መኪኖችን መሰባበር ይዘዋል። ከዚሁ ጐን ለጎን በመ/ቤቱ ግቢ የታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች ከድራማው መጀመር ቀደም ብሎ እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ያ ድርጊት ወይም ድራማ ሲፈፀም አይተው እንዳላዩ በማለፍ ቀጣዩን ይጠብቁ እንደነበረ በሰአታት ልዩነት አፈሙዝ በንፁሃን ላይ ሰድረው ይወስዱት የነበረው የጭካኔ እርምጃ በቂ ማመላከቻ ነበር፤ ዘግይቶ የሆነውም ይኸው ነው።..
በሰኔ ወር ግድያ ሲፈፀም በመጀመሪያ ኢላማ የነበረው ይህ ት/ቤት ነበር፤ በዛ ድርጊት ገና ያልሻረ ቁስል አለ። በሌሎች አካባቢዎችና ከተሞች የነበረው የተዳፈነ የተቃውሞ ቁስል ከዚህ የተለየ አልነበረም። በሕወሐት/ኢህአዴግ አስተዳደር የተንገሸገሸው ሕዝብ..እንኳን ቀዳዳ አግኝቶ ቀርቶ እንዲሁም፥ ትንሽ ነገር ቁጣውን እንደሚያገነፍለው ግልፅ ነበር። የተሰረቀ ድምፁን ለማስከበረም በፅኑ ይፈልጋል። ..በዚሁ መሰረት በአዲስ ከተማ ተማሪው ከአካባቢው ህዝብ ጋር በአንድነት ሆኖ ..<በተለኮሰው> ተቃውሞ ውስጥ ሰተት ብሎ ገባበት።..የተዳፈነው የሕዝብ እሳት በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተዛመተ ሔደ።…..
ያቺ ነጭ መኪና <ሴራዋን> ከውና በጎጃም በረንዳ በኩል ወደ ግራ ታጥፋ እየከነፈች…አባኮራን ሰፈርን እያሳበረች በዮሃንስ ቤ/ክ አድርጋ ወደ ሰሜን ሆቴል አመራች።.. <ቅልቦቹ> ተመሳሳይ የተቃውሞ ድራማ አቀጣጠሉ። ከዚህ በተጨማሪ መንግስት በቦዘኔነት <ሽፋን> ያሰማራቸው ቅልብ ሃይሎች በኮልፌ ቀራንዮ አካባቢ አሰማርቶ ተመሳሳይ <ድራማ> እያቀጣጠለ ነበር። ..የተቃውሞ እሳት የጫረችው ነጯ ቶዮታ ..የማሳረጊያ ግዳጇን በሰሜን ሆ/ል አካባቢ ከተወጣች በኋላ ወጠምሻዎቹን ጭና ቁልቁል በመውረድ ወደ ማእከላዊ ወንጀል ፖሊስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ነበር ሰተት ብላ የገባችው። በዚች መኪና ከፊት ተቀምጦ ትእዛዝ በመስጠትና ከበላይ አለቆቹ ጋር መረጃ ልውውጥ በማድረግ ሴራውን ሲመራና ሲያከናውን የነበረው ግርማይ (በቅፅል ስሙ ማንጁስ) የተባለ የሕወሐት አባልና በፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ የደህንነት ሃላፊ እንደሆነ በወቅቱ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ከዚህ ባሻገር በአንዱ ስልክ ከጠ/ሚ/ሩ ጋር በቀጥታ ይገናኝ እንደነበረ ተረጋግጦዋል። (በነገርራችን ላይ ስለዚህ ጉዳይ መረጃው ለህዝብ ሳይደርስ ጋዜጦች ወዲያው ተዘጉ)
ዘ-ሐበሻ ድረ ገጽን ሁሌም ያንብቡ
ባጠቃላይ በዚህ መልክ በገዢዎቹ ሆነ ተብሎ በተለኮሰው የጥፋት <ሴራ> በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን በአደባባይ በጥይት እንዲቀጠፉ ሲደረግ፣ በ10ሺህ የሚቆጠሩ ደግሞ እስር ቤት ተጋዙ። የነመለስ/በረከት ቀጣዩ <ኢላማ> የቅንጅት አመራሮችንና ደጋፊዎችን፣ጋዜጠኞችን እንዲሁም ሌሎች ወገኖችን ማሰርና ማሰቃየት ስለነበር፥ ያሰቡትን ተግባራዊ አድርገዋል። ከትግራይ ሃውዜን የጀመሩት ህዝብን በጅምላ የማስፈጀት አረመኒያዊ የሴራ ተግባራቸው፥ በአርባባ ጉጉ፣ በበደኖ፣ ትግራይ ሆቴል(ፒያሳ)፣ ጋምቤላ …እያለ በመቀጠል የ97/98 ምርጫን ተራምዶ እነሆ በህዝበ ሙስሊሙና በአማራ ተወላጆች ላይ ቀጥሎ ይገኛል። ከቤኒሻንጉል እንዲፈናቀሉ የተደረጉት የአማራ ተወላጆች በተራ የወረዳ ካድሬዎችና ሹሞች ትእዛዝ እንደማይፈፀም በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል። ለዚህ ማስረጃው በጋምቤላ አሰቃቂ ፍጅት እንዲደርስ የተደረገው በወቅቱ የፌደራል ጉዳዮች ሹማምንት በነበሩት አባይ ፀሃዬና በምክትላቸው ዶ/ር ገብረአብ ባርናባስ ቀጥተኛ ትእዛዝ ሰጪነት እንደሆነ የተረጋገጠና በወቅቱም የሁለቱ የሕወሐት ሹሞች ስም ጭምር ተጠቅሶ በኢትኦጵ ጋዜጣ ይፋ መደረጉ ነበር። እንዲያውም አባይ ፀሃዬ በግምገማ ላይ ዶ/ር ገ/አብን ጥፋተኛ ከማድረጋቸው በተጨማሪ < አብሬው መስራት አልችልም፤ ስለዚህ በአስቸኳይ ይነሳልኝ> በማለት የጋምቤላውን ፍጅት በዶክተሩ ላይ ከመደፍደፋቸው ባሻፈር ለ/ጠ/ሚሩ ጥያቄ አቅርበው ይኸው ተፈፀሚ ሆኗል። …ይህ በሆነበት ሁኔታ በቤኒሻንጉል በወገኖቻችን ላይ የደረሰውና ሆን ተብሎ እንዲደርስ የተደረገው መሰሪ ተግባር ከሕወሐት/ኢህአዴግ ቱባ ሹማምንት እውቅና ውጭ ብቻ ሳይሆን የነርሱ ቀጥተኛ ትእዝዛ ያለበት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል።
በመጨረሻም ፥ በህዝበ ሙስሊሙ እየተካሄደ ባለው ሰላማዊ የመብት ጥያቄና ተቃውሞ ውስጥ የተስተዋለው ጉዳይ፥ ህዝብ ምን ያክል ገዢዎቹን በአስተሳሰብ በልጦ እንደሄደ የሚያመላክት ጭምር ነው። ይኸውም በአንዋር መስጊድና ሰላማዊ ተቃውሞ በሚሰማባቸው አካባቢዎች አንበሳ አውቶብሶችን ሆን ተብሎ በማቆም ሙስሊሙ እንዲሰብራቸው በገዢዎቹ ሲሞከር ታይቶዋል፤ ገዚዎቹ እንዳቀዱት አውቶብሶቹ ሲሰባበሩ… የ97/98 ድራማ ለመድገምና በለመዱት ጭካኔ በጥይት የጅምላ ግድያቸውን ለመተገበር ነው። የሃይማኖቱ ተከታዮች ግን « አንሰብርም….አንሰብርም…» እየሉ በአንድ ድምፅ የነበረከትን የሴራ ድራማ በማክሸፍ ለመብታቸው መቆምንና ሰላምዊ ጥያቄ ማቅረብን ነው የቀጠሉት። ህዝብ ምን ያክል ቀድሟቸው እንደሄደ ጥሩ ማሳያ ነው።


አንድነት ፓርቲ በመድረክ ስር ያሉ ፓርቲዎች በአስቸኳይ እንዲዋሃዱ ጠየቀ

0
0

mederk_atlanta

ላለፉት 5 ወራቶች የመድረክን የስራ አፈፃፀም ሁኔታ በቅርብ ሲገመግም የነበረው የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት የመድረክ አባል ድርጅቶች በአስቸኳይ እንዲዋሀዱ ጠየቀ፡፡

ብሔራዊ ም/ቤቱ ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ቀን 2005 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የአራት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ላለፉት አራት ዓመታት አሳሳቢ በሆኑና በበርካታ ችግሮች ተተብትቦ የቆየ ቢሆንም ሀገራችንን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማሸጋገር በተደረገው ትግል ውስጥ የተጫወተው ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ብሔራዊ ም/ቤቱ በሰየመው ገምጋሚ ኮሚቴ አማካኝነት የመድረክ አጠቃላይ ሁኔታ በስድስት ዋና ዋና ክፍሎች ተገምግሞ ሚያዝያ 19/2005 ዓ.ም ለብሔራዊ ም/ቤቱ በግምገማው ሪፖርት ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ ከጠዋቱ 3፡00 – 1፡00 ሰዓት ስብሰባውን ያካሄደው የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት በዚሁ የግምገማ ሪፖርት ላይ ብቻ በመወያየት የመድረክ ጉዞ በውህደት እንዲጠናቀቅ ወስኗል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የወደቀችበት ሁኔታ በመኖሩ መድረክ ጉዳዩን በጥልቀት ገምግሞ ራሱን የኢትዮጵያ ህዝብ በሚፈልገው የለውጥ ደረጃ በማጠናከርን አማራጭ የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተገቢውን እንቅስቃሴ በማድረግ ሕዝቡን በዙሪያው የማሰባሰብ ተግባር እንዲያከናውን የላቀ ጥረት እንዲያደርግ ብሔራዊ ም/ቤቱ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
አንድነት ፓርቲ መድረክ ሊወስዳቸው የሚገባቸውን የመፍትሔ ሃሳቦች በጥልቀት የተወያዩት የብሔራዊ ም/ቤቱ አባላት የግንባሩ አባል ፓርቲዎች የፕሮግራምና የስትራቴጂ አንድነት በ 3 ወር ጊዜ ውስጥ በመፍጠር በቀጣዩ ሂደት በአስቸኳይ ወደ ውህደት መምጣት እንዳለባቸው ወስኗል፡፡ መድረክ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገውን የፖለቲካ ለውጥ ማሳካት በሚያስችለው ቁመና  እራሱን እንዲያዘጋጅ ለአንድነት ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ብ/ም/ቤቱ መመሪያም ሰጥቷል፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ የቀረበው የግምገማ ሪፖርትና በውይይቱ ላይ የተነሱት ተጨማሪ ሃሳቦች የም/ቤቱ ሠነድ ሆኖ እንዲመዘገብ በመወሰን ይኸው ሰነድ ለግንባሩ አባል ድርጅቶችና ለህዝብ ይፋ እንዲሆን  በመወሰን ብሔራዊ ም/ቤቱ የዕለቱን ስብሰባ አጠናቋል፡፡ (ፍኖተ ነፃነት)

በአዲሱ ሃይማኖቷ “የኦርቶዶክስ እምነትን ስህተት ነው”ያለችው አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን ታሰረች

0
0

Jemanesh Solomon
“የኢትዮጵያን ትንሣኤ ሊያረጋግጥ ሃያል ባለስልጣን ነብዩ ኤልያስ ከብሔረ ህያዋን ጳጉሜ 1/2003 ዓ.ም ወደ ምድር መጥቶ በመካከላችን ይገኛል፣ ኦርቶዶክስ የሚባለው የሃይማኖት ስም ስህተት ነው ተዋህዶ ነው መባል ያለበት፣ ሰንበት ቅዳሜ ብቻ ነው፣ መለበስ ያለበት እግዚአብሔር ለኖህ ቃል ኪዳን የገባበትን ቀስተ ደመና ቀለማት ያካተተ ጥለት ያላቸው ነጭ አልባሳት ናቸው” የሚል አዲስ እምነት እያራመደች ያለችውና ነብዩ ኤልያስ ወደ ምድር እንደመጣ የምታምነው አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን አዲስ ባቋቋመችው እምነት የተነሳ መታሰሯን ከአዲስ አበባ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገበ።
በተለያዩ የመድረክ ቴያትሮች፣ በቴሌቪዥንና በሬዲዮ ድራማዎች በተለይም “ገመና” በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ የእናትነት ገፀ – ባህሪን ተላብሳ በመተወን የምትታወቀው አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን ታሰረች፡፡ አርቲስቷ ማክሰኞ ማታ ተይዛ አራት ኪሎ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረች በኋላ ረቡዕ አመሻሽ ላይ ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ መዛወሯንና ከእርሷ ጋር ሌላ አንዲት ሴትና ሁለት ወንዶች መታሰራቸውን በስፍራው ተገኝተን አረጋግጠናል ያለው የአዲስ አድማስ ዘገባ አርቲስት ጀማነሽና አብረዋት የታሰሩት ግለሰቦች ሃሙስ እለት አፍንጮ በር መንገድ አዲስ አበባ ሬስቶራንት አካባቢ በሚገኝ የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው የታየ ሲሆን በድጋሚ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም ዘግቧል።

ጋዜጣው ዘገባውን በመቀጠል “አርቲስቷንና አብረዋት የታሰሩትን ሰዎች ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ከመጡ ግለሰቦች ለመረዳት እንደቻልነው፤ አርቲስቷና አብረዋት ያሉት ሰዎች የታሰሩት “ማህበረ ስላሴ ዘ ደቂቀ ኤልያስ” ከተባለው ማህበራቸውና ከሀይማኖት ጉዳይ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ጠቁመው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ከአርቲስቷ ጋር የታሰሩት አንድ የሃይማኖት አባት፤ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ በመሆኑ ከፍርድ ሂደቱ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ፣ አሁን ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ነግረውናል፡፡ አርቲስት ጀማነሽን ሊጠይቋት የመጡ ሰዎችን ለማነጋገር ስትወጣ በተመለከትናት ጊዜ በፈገግታ የታጀበች ሲሆን ጠያቂዎቿ “እንዴት ነሽ ተመቸሽ?” ብለው ሲጠይቋት “እግዚአብሔር ያለበት ቦታ ሁሉ ምቹ ነው” ስትል ምላሽ ሰጥታለች፡፡ አርቲስቷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “ተዋህዶ” በሚል ሃይማኖት ውስጥ ተሣታፊ በመሆን አነጋጋሪ ሆና መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡” ብሏል።

“ወረዳ ዘጠኝ ፖሊስ ጣቢያ በተገኘን ጊዜ የሃይማኖቱ ተከታዮች የሚለብሱት የቀስተደመና ቀለማት ያሉት ነጠላ አጣፍታ፣ ፀጉሯንም የቀስተ ደመና ቀለም ዙሪያውን ባቀለመው ሻሽ አስራለች፡፡ ማህበረ ስላሴ ዘ ደቂቀ ኤልያስ “የኢትዮጵያን ትንሣኤ ሊያረጋግጥ ሃያል ባለስልጣን ነብዩ ኤልያስ ከብሔረ ህያዋን ጳጉሜ 1/2003 ዓ.ም ወደ ምድር መጥቶ በመካከላችን ይገኛል፣ ኦርቶዶክስ የሚባለው የሃይማኖት ስም ስህተት ነው ተዋህዶ ነው መባል ያለበት፣ ሰንበት ቅዳሜ ብቻ ነው፣ መለበስ ያለበት እግዚአብሔር ለኖህ ቃል ኪዳን የገባበትን ቀስተ ደመና ቀለማት ያካተተ ጥለት ያላቸው ነጭ አልባሳት ናቸው” የሚሉትን የተለያዩ ጉባኤዎችን እያዘጋጀ የሚያስተምር ማህበር መሆኑን ያነጋገርናቸው የማህበሩ አባላት ገልፀውልናል፡፡ በተለያዩ ገዳማትም የሀይማኖቱ አራማጆች እንደሚገኙና እንደሚያስተምሩ ያገኘናቸው የሃይማኖቱ ተከታዮች ነግረውናል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ከፖሊስ መረጃ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም፣ ከመምሪያው የተፃፈ ፈቃድ ያስፈልጋል በሚል የወረዳው ፖሊስ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡” በማለት ዘገባውን አጠናቋል።

የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) የደቀነብን አደጋዎች! –ክፍል 1

0
0

ግርማ ሞገስ (girma.moges@yahoo.com)

ይኽ ጽሑፍ አራት ክፍሎች ይኖሩታል። የመጀመሪያው ክፍል ከአሚሪካ ቀድሞ ፕሬዘዳንቶች መታሰቢያ ተቋሞች ልምዶች ለመውሰድ ጥናት ያደርጋል። ሁለተኛው ክፍል የአቶ መለስ ቅርስ (Legacy) ኮሚቴ፣ ህውሃት እና እንድሪያስ እሸቴ (ፕሮፌሰር) ስለ አቶ መለስ አገር ወዳድነት፣ ፓን-አፍሪካዊነት፣ ሰላም ወዳድነት እና ሰላም አምጭነት፣ የፍትህ፣ የጥሩ አስተዳደር እና የዲሞክራሲ አባትነት፣ የልማት ጀግናነት የሚያሰራጩትን ፕሮፖጋንዳ ነጥብ በነጥብ በማንሳት መልስ ይሰጣል። ሶስተኛው ክፍል ስለ አቶ መለስ መታሰቢያ ተቋም አስፈላጊነት የታወጀው መንግስታዊ አዋጅ ዲሞክራሲያ አለመሆን፣ ስለ ስመ-ጥሩዎቹ የአነስታይን፣ የኖቤል እና ጆን ኦፍ ኬኔዲ መታሰቢያ ተቋሞች አጫጨር ማስታወሻዎች እና የሚለግሱን ትምህርቶች፣ በወይዘሮ አዜብ ፕሬዘዳንትነት ስለሚመራው የአቶ መለስ መታሰቢያ ተቋም አስፈሪ ግቦች፣ ስለ አቶ መለስ መታሰቢያ ተቋም አስተዳዳሪ ቦርድ አባላት አይነት እና አስደንጋጭነት፣ ጥቂት ምክሮች ለወይዘሮ አዜብ፣ የአቶ መለስ መታሰቢያ ተቋም ገንዘብ ምንጭ ህገ-ወጥነት እና ታክስ ከፋዮች ወደፊት ወይዘሮ አዜብን ህግ ፊት ሊያቀርቡ እንደሚችሉ የተነትናል። አራተኛው ክፍል “ምን ይበጃል?” የሚለው ሲሆን ቀደም ብለው የተነበቡትን ሶስት ክፍሎች መሰረት በማድረግ ጸሐፊው ይበጃሉ የሚላቸውን ተግባሮች ለውይይት ያቀርባል። [መልካም ንባብ!]

042513g12Bush Library.jpg

ክፍል አንድ (ከአራት ክፍሎች)፥ የአሜሪካ ቀድሞ ፕሬዘዳንቶች መታሰቢያ ተቋሞች

የአሜሪካው የቀድሞ ፕሬዘዳንት የአቶ ቡሽ (ትንሹ) ቤተ-መጽሐፍት እና ቤተ-መዘክር ያካተተ የመታሰቢያ ተቋሙ ምረቃ ስነስርዓት በዳላስ ከተማ (ቴክሳስ) ተፈጸመ። ዕለቱ ሐሙስ ሚያዚያ 17 ቀን 2005 (25 April, 2013) ዓመተ ምህረት። ሲ.ኤን.ኤን. (CNN) የምረቃውን ፕሮግራም ማሳየት ሲጀምር እንደአጋጣሚ ቴሌቪዥን አጠገብ ነበርኩ። በፕሮግራሙ ላይ አራቱ የቀድሞ ፕሬዘዳንቶች፣ ካርተር፣ ቡሽ (ትልቁ)፣ ክሊንተን፣ ቡሽ (ትንሹ) እና ፕሬዘዳንት ኦባማ በመታሰቢያ ተቋሙ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ነበሩ። በእንደዚኽ አይነት ፕሮግራም አምስት ፕሬዘዳንቶችን በአንድ ጊዜ ማግኘት ሁልጊዜ የሚሆን ባለመሆኑ እና ስለ አቶ መለስ መታሰቢያ ተቋም በመጻፍ ላይ ስለነበርኩ ፕሮግራሙን አፍ ተልብ ሆኜ ተከታተልኩ። እንደሚታወቀው ከእነዚህ አምስት ፕሬዘዳንቶች ውስጥ ቡሽ (ትልቁ እና ትንሹ) ረፓብሊካን ሲሆኑ የቀሩት ሶስቱ ዲሞክራቶች ናቸው። ስለዚህ በመካከላቸው የፖሊሲ ልዩነቶች እንደሚኖሩ ግልጽ ነው። ይሁን እንጂ በምረቃው ስነስርዓት ላይ ባደረጉዋቸው ንግግሮች ውስጥ በግልጽ ጎልቶ ይታይ የነበረው ልዩነታቸው ሳይሆን ተመሳሳይነታቸው ነበር። ሁሉም አሜሪካዊ መሆናቸው። በፖለቲካም። በተጨማሪ ከንግግሮቻቸው ውስጥ የሚከተሉትን ታዘብኩ፥ (1) አምስቱም ፕሬዘዳንቶች ስለዲሞክራሲ ሲያወሩ ዲሞክራሲ በሚለው ቃል ላይ ‘አብዮታዊ’ የሚል አጭበርባሪ ቅራቅንቦ አይለጥፉም ነበር። ለእነሱ ዲሞክራሲ አንድ እና አንድ አይነት ብቻ ነው። (2) መጠኑ ቢለያይም እያንዳንዳቸው የፖለቲካ እምነታቸውን በአገራቸው እና በህዝባቸው ላይ ተፈጻሚ በማድረግ የአገራቸውን ታሪክ አቅጣጫ ቀይረዋል። ይኽን ያደረጉት ግን ህዝቡ በነፃ ምርጫ ይሁንታውን ከሰጣቸው በኋላ ነው። የመንግስት ስልጣን የህዝብ መሆኑን በሚያረጋግጥ ነፃ ምርጫ ማለት ነው። አምባገነኖቹ መንግስቱ ኃይለማሪያም በመፈንቅለ መንግስት እና መለስ ዜናዊ ደግሞ በእርስ በርስ ጦርነት በኢትዮጵያ ስልጣን እንደያዙ እና የኢትዮጵያን ታሪክ አቅጣጫ አደበላልቀውት እንደሄዱ አስታወሱኝ። (3) የአሜሪካን መንግስትን ወክሎ በፕሮግራሙ ላይ የተገኘው ኦባማ ስለ ቡሽ (ትንሹ) መታሰቢያ ተቋም በፕሮግራሙ ላይ ከሚሰማው በስተቀር ቀደም ብሎ የሚያውቀው አንድም ነገር እንደሌለ ታዘብኩኝ። የቡሽ (ትንሹ) መታሰቢያ ተቋም ምስረታ በእሱ፣ በሚስቱ፣ ቤተሰቦቹ እና በደጋፊዎች እንደተጀመረ፣ ህንጻው የተገነባበትን መሬት እንዴት እንዳገኘ? ህንጻውን ለመገንባት 350 ሺ ያህል ደጋፊ ግብር ከፋይ አሜሪካውያን በፈቃዳቸው ከኪሳቸው እንደረዱት፣ መታሰቢያ ተቋሙን የሚመሩት እሱ እና ባለቤቱ ከመንግስት ነፃ ከሆነ ሙያተኛ ድርጅት ጋር ተቀናብረው እንደሆነ፣ ተቋሙ ትርፍ ከመስራት ነፃ እንደሆነ እና ሌሎች ጉዳዮችን በሙሉ ሲያብራራ ለእኔ አዲስ ዜና የነበረውን ያህል ለቀሩት የቀድሞ ፕረዘዳንቶች እና መንግስትን ወክሎ በፕሮግራሙ ላይ ለተገኘው ለወቅቱ ፕሬዘዳንት ኦባማም አዲስ ዜና ነበር። ስለዚህ የአሜሪካ መንግስት ከፕሬዘዳንቶች መታሰቢያ ተቋም ምስረታ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው በግልጽ አየሁኝ።
Azeb  Mesfin, wife of Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi
ፕረዘዳንቱ በአገሩ እና በለም አቀፍ ደረጃ ለህዝብ ታላላቅ ስራዎች ያከናወነ እና ከአገሩ አልፎ በአለም አቀፍ ያሉ ታሪክ ጸሐፊዎች ሰፋፊ ምዕራፎች ቢጽፉለትም መታሰቢያ ተቋም የራሱ የፕሬዘዳንቱ፣ የቤተሰቡ፣ የራሱ ፓርቲ፣ የደጋፊዎች የግል ጉዳይ ሲሆን መታሰቢያ ተቋሙን መገንቢያ ገንዘብ ምንጭም መንግስት ሳይሆን ደጋፊዎቹ ከግል ኪሳቸው በለገሱት ገንዘብ ነበር። ይኽን ነጥብ በአሜሪካ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ዛሬም ታዋቂ እና ተወዳጅ የሆነውን የፕሬዘዳንት ሩዝቬልትን አጭር ማስታወሻ እንድንመለከት ያስገድደናል።
ፕሬዘዳንት ፍራንክሊን ዲ. ሩዝቬልት (1933-1945) የአሜሪካ ፕረዜዳንት ሲሆን አሜሪካ ትልቅ ችግር ውስጥ ገብታ ስራ ጠፋ። ህዝብ የሚበላው ጠፍቶ የሩዝቬልት መንግስት ህዝቡን ማብላት ጀመረ። ረሃብ እና ጤና ማጣት እጅግ በበረታባቸው በርካታ የአሜሪካ ከተሞች መንግስት የምግብ ማብሰያ ካምፖች መስርቶ ህዝቡን በየቀኑ መመገብ ጀመረ። ሩዝቬልት በአንድ እጁ ህዝቡን ከሞት የማትረፍ ትግል እያደረገ በዚያኑ ጊዜ ብዙ ፕሮጀክቶች ወጥኖ ፕሮክቶቹ ሲጀመሩ የህዝብ መመገቡ ስራ እዚያው ፕሮጀክቶቹ ባሉበት አካባቢ እንዲቀጥል አደረገ። ከወጠናቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ አንደኛው ብዙ ያልተገሩ ጅረቶችን የሚገሩ የኤሊክትሪክ ማመንጫ ግድቦች መገንባት፣ የኤሊክትሪክ ኃይል ማመንጨት፣ ይኽን የኤሊክትሪክ ኃይል በመጠቀም ለህይወት የማይመቹ ግዛቶች መብራት እንዲያገኙ፣ የአየር ጸባያቸው እንዲቀየር፣ የእርሻ ስራ እንዲጀመርባቸው እና ህዝብ እንዲሰፍርባቸው ማድረግ ነበር። ይኽ ፕሮጀክት ብዙ ስራ ፈጠረ። በዚኽ ረገድ አብዛኛዎቹ ፕሮጀክቶች ተሳኩ። የዛሬዋ ዋሽንግተን ክፍለ አገር (ሲያትል) የታላቁ ኩሌ ግድብ (Grand Coulee Dam) ውጤት ነች። በረሃማው የካሊፎርኒያ ግዛት ልማት የሁቨር ግድብ (Hoover Dam) ውጤት ነው። የቴናሲ (Tennessee) ክፍለ አገር ልማት የኖሪስ ግድብ (Norris Dam) ውጤት ነው። እነዚህ ሶስቱ ታላላቅ ያልተገሩ ጅረቶችን ገርተው ለሰው ልጅ ትልቅ ጥቅም የሰጡ ግድቦች ሲሆኑ በሌሎች ግዛቶችም የተለያዩ የልማት ስራዎች ተሰርተዋል። ሁለተኛው ፕሮጀክት ደግሞ ክፍለ አገሮችን የሚያገናኙ ትላልቅ ጎዳናዎች መገንባት ሲሆን ይኽ ፕሮጀክትም ለህዝቡ ብዙ ስራ ከፈተ። ሶስተኛው ሩዝቬልት የፈጸመው ታሪካዊ ተግባር ደግሞ በአገሩ ልማት እና ግንባታን በመምራት ላይ ሳለ በአለም አቀፍ መድረክ አሜርካን በሁለተኛው አለም ጦርነት መምራት ነበር። ጦርነት ውስጥ የገባው ወዶ ሳይሆን ተገዶ ነበር። አሚሪካን በማልማት ላይ ሳለ ሁለተኛው አለም ጦርነት ተቀሰቀሰ። ጀርመን አውሮፓን መውረር ስትጀምር ጃፓን በአካባቢዋ ያሉትን አገሮች ከወረረች በኋል አሜሪካን በአየር ደበደበች። የጃፓንን ቦንብ ድብደባ ተከትሎ ሩዝቬልት “ምንም ነገር አንፈራም። የምንፈርው ነገር ቢኖር እራሱን ፍርሃትን ብቻ ነው” የሚል ምላሽ በአደባባይ ሰጠ። እስከዛሬ ድረስ ዝነኛ ጥቅስ ነች። የሆነው ሆኖ ሩዝቬልት ፓርላማውን አስፈቅዶ አሜሪካን ይዞ ሁለተኛውን አለም ጦርነት ተቀላቀለ። ትረካዬን ላሳጥር። ሩዝቬልት በአገሩ ውስጥ የመራውን ልማት እና አገር ግንባታ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ የመራውን ሁለተኛ አለም ጦርነት በድል ፈጸመ። በሙያዬ የኤሊክትሪክ ኃይል እንጂነር በመሆኔ የማወቅ ጉጉት ገፋፍቶኝ ዝነኞዎቹን የሩዝቬልት የኤሊክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቦች እና ከግድቦቹ የሚገኘው የኤሊክትሪክ ኃይል የሚሰጠውን ጥቅም ለማየት በአሜሪካ ተጓጉዣለሁ። የኖሪስ ግድብ በቴናሲ (Tennessee) እና የሁቨር ግድብን በካሊፎርኒያ በረኃ ላይ የፈጠሩትን ልማቶች ተዟዙሬ በአይኔ አይቻለሁ። የታላቁ ኩሌ ግድብ ለዋሽንግተን ክፍለ አገር የሰጠውን ልማት ለማየት እድሉን አላገኘሁም። ግድቡን እና የኤሊክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያውን ግን በቪዲዮ አይቻለሁ። ወደፊት በአካል የማየት እቅድ አለኝ።
ይኽ ፕሬዘዳንት በአሜሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ እና ለመጨረሻ ጊዜ (እስከዚኽ ድረስ) የአሜሪካ ህዝብ እራሱ ህገ-መንግስቱን ጥሶ ለሶስተኛ ዘመን (ለ12 አመቶች) አሜሪካን በፕሬዘዳንትነት እንዲመራ ያደረገው ተወዳጅ ፕሬዘዳንት ነው። ፕሬዘዳንት ፍራንክሊን ዲ. ሩዝቬልት (1933-1945) ቢሮው ውስጥ ስራ ላይ ሳለ ሞተ። ለምግብ ሊጠሩት ቢሮው ሲገቡ በወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ያገኙት እሬሳውን ነበር። ለዚህ የአገሩን ህዝብ ፍቅር እና አክብሮት ላገኘው የቀድሞ ፕሬዘዳንትም ቢሆን መታሰቢያ ተቋም በመንግስት አዋጅ አልተገነባለትም። አቶ መለስ ከሩዝቬልት ተርታ የሚቀመጥ ሰው አይደለም።
‘በአብዮታዊ ዲሞክራሲ’ አገሮች ካልሆነ በስተቀር በዲሞክራሲ አገሮች መንግስት የመሪዎች መታሰቢያ ህንጻ እወጃ እና ግንባታ ውስጥ አይገባም ማለት ነው። መንግስት የአጠቃላይ አሜሪካ ግብር ከፋይ ህዝብ አስተዳዳሪ እንጂ መታሰቢያ ተቋም የሚሰራለት ፕሬዘዳንት ደጋፊዎች ብቻ አስተዳዳሪ ስላልሆነ ከመታሰቢያ ተቋም መንግስት እራሱን ነፃ ማድረግ አለበት ማለት ነው። ስለዚኽ መንግስት ማለት የፖለቲካ ፓርቲ ማለት እንዳልሆነ የፖለቲካ ፓርቲ ማለትም መንግስት ማለት እንዳልሆነ እንዲሁም በመንግስት እና በፖለቲካ ፓርቲ መካከል ግልጽ የሆነ ልዩነት መኖሩን ማወቅ በአምስቱም ፕረዘዳንቶች ዘንድ የሰረጸ ልማድ መሆኑን በግልጽ ታዘብኩኝ። የነበረኝ እምነት ተጠናከረ። የአቶ መለስን መታሰቢያ ተቋም አስመልክቶ በጀመርኩት ጽሑፍ ውስጥ ስከተላቸው የነበሩት መርሆዎች ትክክል መሆናቸውን ቢያንስ እነዚህ አምስት ፕሬዘዳንቶች አረጋገጡልኝ ማለት ነው።
የሆነው ሆኖ የመጨረሻ ተናጋሪ የነበረው ቡሽ (ትንሹ) በንግግሩ መገባደጃ ግድም ሰለ አሜሪካ እና ኢራቅ ጦርነት በንግግሩ ጠቀሰ እና የጦርነት ፕሬዘዳንት መሆን ግን ምኞቱ እንዳልነበር ተናገረ። ለጥቆ “ህዝባችንን እና አገራችንን የተለያዩ እንቅፋቶች ቢገጥሙዋቸውም የአገራችን ብሩህ ቀኖች ገና ከፊታችን ስለመሆናቸው ያለኝ እምነት የማይናጋ ነው” በማለት ላይ ሳለ ድምጹ ተቀየረ። የአገር ወዳድነት ስሜቱ መጥቶበት ይሁን ወይንም በስልጣን ላይ ሳለ የጦር ጊዜ ፕሬዘዳንት በመሆን በአሚሪካ እና በኢራቅ ታሪክ ላይ ያስከተለው የታሪክ አቅጣጫ ለውጥ አስዝኖት ግልጽ አይደለም። ድምጹን እና አይኖቹን መፈታተን የጀመረው ስሜቱ ሳያሸንፈው ንግግሩን ቋጭቶ አይኖቹን በእጆቹ ጠረገ። የንግግር ወለሉን ለቆ ወደመቀመጫው አመራ። ባለቤቱ ሎራ ጎን ሊቀመጥ። በአጠገቡ የነበሩት አራት ፕሬዘዳንቶች ከነቤተሰባቸው እና በመታሰቢያ ተቋሙ ምርቃት ላይ እንዲገኝ የተጋበዘው ህዝብ በሙሉ ጸጥ አለ። ቡሽ (ትንሹ) ፊቱ ላይ ፈገግታ ለማስቀመጥ እየታገለ በአንድ እጁ አይኖቹን መጥረጉን ቀጠለ።
ክሊንተን ቀደም ብሎ በተራው ንግግር እያደረገ ሳለ ለፈገግታ ከማገልገልም ባሻገር አንድ ለጥናታችን ጠቃሚ የሆነ ቁምነገር እንደ ቀልድ አድርጎ ተናግሮ ነበር። እሱም፥ “ከስልጣን በኋላ የቀድሞ ፕረዘዳንቶች ፈተና መታሰቢያ ተቋሞች በመገንባት ታሪካቸውን እንደገና ለመጻፍ መታገል ነው እያልኩ ለኦባማ ሁልጊዜ እነግረዋለሁ” የሚል ነበር። ከፊል ያህሉ ተሰብሳቢ ስቆለታል። እርግጥ ነው አንዳንድ የቀድሞ ፕሬዘዳንቶች ወይንም ጠቅላይ ሚንስትሮች ከሞቱ በኋላ መጪ ትውልድ ጥሩ ሰው አድርጎ እንዲያስባቸው መመኘታቸው አይቀርም። ያን ማለቱ ነው። ያ እንዳይሆን ከዚህ በኋላ የቡሽ (ትንሹ) መታሰቢያ ተቋም የአሜሪካ ህዝብ ንብረት በመሆኑ ማንኛውም ጉብኚ ዜጋ የፈለገውን የመመርመር ህጋዊ መብት ይኖረዋል። በመሆኑም ቀጥሎ መሆን ያለበት በመታሰቢያ ተቋሙ ቤተ-መጽሐፍት እና ቤተ-መዘክር ውስጥ ለህዝብ ይፋ የተደረጉ እና ያልተደረጉ ሰነዶችን ታሪክ ጸሐፊዎች እና ተመራማሪዎች በጥልቀት እና በስፋት መመርመር ነው። ከምርምራቸው እና ከጥናታቸው በኋላ እነዚህ ሰዎች በዜና አውታሮች አማካኝነት ወይንም መጽሐፍት በመጻፍ ከህዝባቸው ጋር ውይይት ሊከፍቱ ይችላሉ። ይከፍታሉም። ታሪክም ዳኝነቷን ትሰጣለች።
እርግጥ የአቶ መለስ መታሰቢያ ተቋም ውጥን ኢላማ ያደረገው የአቶ መለስን ታሪክ አሻሽሎ ለመጻፍ ይሁን ወይንም በስኮላርሽፕ ስም ድጋፍ በመስጠት ብዛት ያላቸው ‘አብዮታዊ ዲሞክራሲ” ካድሬዎች አምርቶ አቶ መለስ በህይወት ሳለ በመገንጠል፣ በባህር በር፣ በነጻ ምርጫ፣ በዲሞክራሲ፣ በሰባዊ መብቶች እና በመሳሰሉ ጉዳዮች ዙሪያ ሲያራምዳቸው የነበሩትን አምባገነናዊ ፖሊሲዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ይሁን ግልጽ አይደለም። አዜብን ጨምሮ የመለስ ደቀመዝሙሮች የመታሰቢያ ተቋሙ ዋንኛ ግብ የአቶ መለስን ራዕይ ከትውልድ ትውልድ ማስተላለፍ እና ማስረጽ ነው ማለታቸው በሰፊው ተዘግቧል።
ያም ሆነ ይኽ በብእዴኑ በአቶ አዲሱ ለገሰ እና በህውሃቱ በአቶ ካሳ ተ/ብርሃን የሚመራው የአቶ መለስ ቅርስ (Legacy) ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና የአቶ መለስ አማካሪ የነበረው እንድሪያስ እሸቴ (ፕሮፈሰር) በአገር ውስጥ በጉባኤዎች እና በዜና ማሰራጫዎች (ኢቲቪ እና ሬዲዮኖች) የአቶ መለስ በሳል አመራር ለኢትዮጵያ እና ለአለም ህዝብ ያበረከታቸውን ውለታዎች በማተት ህዝብ ማጭበርበር ከጀመሩ ውለው አድረዋል። ክፍል አንድ ይኼን ፕሮፖጋንዳቸውን ነጥብ በነጥብ መርምሮ አጭበርባሪነቱን ለአንባቢ ያቀርባል።
[ክፍል ሁለት ይቀጥላል]

ከፋውንዴሽኑ ጀርባ… (ክፍል ፩) –ከተመስገን ደሳለኝ

0
0

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ያለ ወቅቱ በደረሰ ዝናብ እየራሰች ያለችው አዲስ አበባ ዛሬም ከመለስ መንፈስ ተፅእኖ ነፃ አልወጣችም፤ ጣራና ግድግዳዎቿ እንዲህ በምስሉ እና በድርጅቱ አርማ መዥጎርጎሯን ያስተዋለ አንድ ቀልደኛ የባህር ማዶ ወዳጄ ‹‹እኔ ከሀገሬ ከወጣሁ በኋላ የኢህአዴግ ዋና ከተማ ሆነች እንዴ?›› ብሎ ፈገግ አሰኝቶኛል፡፡ በእርግጥ ይህችን ቀልድ ስንፍቃት የምናገኘው ቁም ነገር፡- ከተማዋ በመለስ ውርስ ድንዛዜ ላይ መሆኗ፣ አስተዳደሯም ያለ ቅድመ-ዝግጅት ‹‹አፍርሼ ካልሰራሁሽ›› በሚሉ ካድሬዎች ጫጫታና ሩጫ ልቧን እያጠፋት እንደሆነ፣ አንድ ፓርቲ ተመራጭ፣ አስመራጭ፣ ታዛቢ መሆኑን እና የመሳሰሉትን ነው፡፡ የአቶ መለስ ሞትም ወቅቱን የጠበቀ ባለመሆኑ ስርዓቱን እያንገጫገጨው ነው፡፡ በግሌ በመለስ ህልፈት ያለማዘን በሥነ-ምግባር የመዝቀጥ ጉዳይ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ምክንያቴ ሰውየው ክፉ አምባገነን ከመሆኑም በላይ በዙፋኑ ሙጭጭ እንዳለ ህይወቱ በማለፉ ነው፤ ታዲያ ይህንን ሰው እንዴት አድርገን ነበር ከስልጣን ማውረድ የምንችለው? መቼም አቅመቢሶች ከመሆንም አልፈን በተራራና ሸንተረር ሳይቀር የተከፋፈልን ለመሆናችን ከራሳችን በላይ መስካሪ የሚያሻን አይመስለኝም፡፡ እዚህች ጋ ከሩሲያዊው ሌኒን ህልፈት ጋር የተያያዘ አንድ ነገር ትዝ ስላለኝ ልንገራችሁ፡-
እንደሚታወቀው ሌኒን የሩሲያ አብዮትን የመራ ሁነኛ ኮሚዩኒስት ቢሆንም፣ ምሁራዊ ሰውነቱ ከሌሎች አብዮተኞች በእጅጉ ይገዝፍ እንደነበረ ጠላቶቹም ሳይቀር የመሰከሩለት ጉዳይ ነው፡፡ እናም ህልፈቱ ሲሰማ፣ ሩሲያን በአይነ ቁራኛ ይከታተሉ የነበሩ ምዕራባውያን ድንጋጤ አደረባቸው፡፡ ከእነዚህ ሀገራት የአንዱ መሪም ድንጋጤውን እንዲህ ሲል ገልጾ ነበር አሉ፡-. ‹‹ሌኒን ሆይ፣ ባትወለድ መልካም ነበር፤ ከተወለድክ ደግሞ ትንሽ ብትቆይ ይሻል ነበር፤ ምክንያቱም ለማን ትተኽን እንደሄድክ እኔ አውቃለሁና!›› በእርግጥም ሌኒንን የተካው ባለ ብረት መዳፉ ጆሴፍ ስታሊን መሆኑን ስናስተውል የሰውየው ቁጭት ይገባናል፤ ግና ከአስር ወር በኋላም
ሊገባን ያልቻለው የእኛው መለስ ለማን ትቶን እንደሄደ ነው፡፡ ከስታሊንም ለባሱት? ወይስ… የሆነ ሆኖ መለስን ተክተው ከጀርባ የሚዘውሩትን አንጋፋ ታጋዮች ለጊዜው ባሉበት አቆይተን፣ ገብስ ገብሱን እንነጋገር ካልን የኃይለማርያም ደሳለኝ ሹመት ወቅቱን የጠበቀ አይደለም የሚለው አያከራክረንም፡፡ የሶስቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመትም እንዲሁ፡፡ የእነዚህ ድምር ውጤት ነው አገዛዙን ወቅቱን ባልጠበቀ አጀንዳ እንዲወጠር ያደረገው፡፡
samora ያለወቅታቸው ‹‹ተከሰቱ›› ተብለው ሊጠቀሱ ከሚችሉ አጀንዳዎች መካከል ‹‹የመለስ ፋውንዴሽን ምስረታ›› አንዱ ነው፡፡ በእርግጥ መለስ ባይሞት ኖሮ፤ ከሞተም በኋላ ስርዓተ ቀብሩ ትኩረት ባይስብ ኖሮ፤ ከተቀበረ በኋላም ‹‹ሌጋሲው ይቀጥላል›› ባይባል ኖሮ፤ ከሌጋሲው ውስጥም ‹‹ራዕዩ ፈለቀ›› ባይባል ኖሮ… ‹‹ፋውንዴሽን›› ጂኒ ቋልቋል… ባልተከታተለብን ነበር እያልን መቆጨታችን አይቀሬ ነው፡፡ ኢህአዴግ ከመለስ ህልፈት በኋላ ‹‹የመለስ ራዕይ›› እያለ መጮኹ አናዳጅ ብቻ ሳይሆን ‹‹እመራዋለሁ›› ለሚለው ህዝብም ያለውን ንቀት የሚያሳይ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ፕሮፓጋንዳም ነው ‹‹መለስ ኖሮ፣ ራዕዩ በሞተ›› የሚያስብለው (አሁን የፋውንዴሽኑ ምስረታ ዕለት የተከሰቱ ፖለቲካዊ አንድምታ ያላቸውን ጉዳዮች በአዲስ መስመር ጨርፎ ወደማየቱ እንለፍ) ፋውንዴሽኑ ደረጃውን የጠበቀ መናፈሻ፣ ቤተ መፅሀፍት (የመለስ ስራዎች በአማርኛ ተተርጉመው ይቀመጡበታልም) እና የተለያዩ መዝናኛዎችን ጨምሮ አስክሬኑ የሚያርፍበት ልዩ ስፍራ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ በግልባጩ ግንባታው የሚካሄድበት ቦታ አዲስ አበባ ነው ከማለት ባለፈ በትክክል የት አካባቢ እንደሆነ ተለይቶ አልተገለፀም፡፡ ሆኖም ለግንባታው ተብሎ በግዴታ በርከት ያሉ መኖሪያ ቤቶች ከይዞታቸው እንደሚነሱ ተነግሯል፡፡ በግሌ ይህ አግባብ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ምንም እንኳ በ‹‹ስመ-ልማት›› እየተደረገ ያለውን ማፈናቀል ጠቀሜታው የሀገር ነው ብለን ልንወስደው ብንችልም፤ ይህ ግን… (አጀንዳዬ የፋውንዴሽኑን ጥቅም ወይም ጉጂ ጎን መተንተን ሳይሆን፣ በምስረታው እለት የታዩ ጥቂት ተመንዛሪ ክስተቶችን መተንተን ነው ብያለሁና ወደዚያው አልፋለሁ)
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝከዚህ ቀደም የህወሓት አመራር አባላት የመለስ ህልፈትን ተከትሎ በሁለት ጎራ ተቧድነው ‹‹ቀዝቃዛ ጦርነት›› ውስጥ መግባታቸውን ያመላክታሉ ያልኳቸውን ፍንጮች ጠቅሼ መነጋገራችን አይዘነጋም፡፡ (‹‹ቀዝቃዛው ጦርነት፡- ከአመታት በፊት ዓለም በአሜሪካን እና
ሶቭየት ህብረት ፊት አውራሪነት በርዕዮተ-ዓለም ተከፍሎ ሲፋለም ነበር፤ ያለታንክና መድፍ፤ ያለ ተዋጊ ወታደርና ያለ አዛዥ ጄነራል፤ ፍልሚያው ሟችም ሆነ ቁስለኛ፣ አሊያም ምርኮኛ አልነበረውም፤ የርዕዮተ-ዓለምን ልዩነት በበላይነት ለመወጣት ነበርና፡፡ አንደኛው ከሌላኛው ጎራ ከቻለ ሀገርን፣ ካልቻለም ስልጣን ላይ ያለ ግለሰብን ለማስኮብለል ይቀምራል፣ ያሴራል፣ ይሰልላል…፤ ይህንን ሁኔታ ነው የፖለቲካ ተንታኞች ‹‹ቀዝቃዛው ጦርነት›› (Cold War) ያሉት) ዛሬ ደግሞ የህወሓት የአመራር አባላት በእንዲህ አይነት ጦርነት መጠመዳቸውን ጆሮአችን እስኪግል እየሰማን ነው፤ ልዩነቱ የህወሓት ችግር ርዕዮተ-ዓለምን መሰረት ያደረገ አለመሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ ህወሓት እንኳን ዛሬ፣ በትልቁ የተሰነጠቀ ጊዜም (በ1993 ዓ.ም.) ርዕዮተ-ዓለም አላጨቃጨቀውም፡፡ የስዬ አብርሃ ወደ አንድነት መግባትም ሆነ፣ የእነ ገብሩ አስራት በ‹‹ሶሻል ዴሞክራሲ›› አስተሳሰብ የሚመራውን አረናን መመስረት የልዩነቱ ምክንያት አልነበረም፡፡ እነገብሩ አረናን ለመመስረት ሲንቀሳቀሱ፣ በክፍፍሉ ወቅት ‹‹የቡድን አባታቸው›› እንደነበር የሚነገርለት ተወልደ ወ/ማርያም የአዲሱ ፓርቲ መስራች እንዲሆን ሲጠየቅ ‹‹ርዕዮተ-ዓለማችሁ ‘አብዮታዊ ዴሞክራሲ’ ከሆነ ብቻ ነው የምቀላቀለው›› አለ መባሉ መከራከሪያችንን ያጠነክረዋል፡፡
እናም የህወሓት ሰዎች (ከእነ አረጋዊና ግደይ ዘርአፅዮን ዘመን ጀምሮ) ስልጣን እንጂ፣ የፖለቲካ አመለካከት የፀብ መንስኤ ሆኗቸው አያውቅም፡፡ የዘንድሮውም ‹‹ቀዝቃዛ ጦርነት›› ቡድተኝነትና የስልጣን ፍላጎት የፈጠረው ቅራኔ ነው፤ አሊያም ከጆርጅ ኦርዌል ‹‹እንሰሳት ሁሉ እኩል ናቸው፤ አንዳንድ እንሰሳት ግን ከሌሎች ይበልጥ እኩል ናቸው›› መንፈስ የተናጠቀ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲሁም የፋውንዴሽኑ ምስረታ የእነአዜብን ቡድን የሚያጠናክር ፖለቲካዊ አንድምታ አለው፡፡ በእነአባይ ፀሀዬ ቡድን ውስጥ ከተሰባሰቡት አብዛኛው ለመለስ ያደሩት ፈርተው እንጂ አምነውበት ወይም ወደውት አይደለም፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከእነርሱ ቡድን አንድም
የአመራር አባል የፋውንዴሽኑ ቦርድ አባል ሆኖ ያልተመረጠው፡፡
የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ በ‹‹አባይ-ደብረፅዮ››ን እና በ‹‹አዜብ-አባይ ወልዱ›› አስተባባሪነት መሆኑን ሰምተናል (በነገራችን ላይ ከ1983-1993 ዓ.ም ኢህአዴግ ‹‹ሁሉም የግንባሩ አባል ፓርቲዎች እኩል ናቸው፤ ህወሓት ግን ከሁሉም ይበልጣል›› የሚል ያልተፃፈ ህግ ነበረው፡፡ በ93ቱ ክፍፍል አብዛኛው የህወሓት አመራር ከተባረረ በኋላ ደግሞ ያ ህግ ‹‹ሁሉም የኢህአዴግ የአመራር አባላት እኩል ናቸው፤ መለስ ግን ከሁሉም ይበልጣል›› ወደሚል ተቀይሮ ነበር፡፡ አሁን መለስ አልፏል፤ እናም አፍጦ የመጣው ጥያቄ ‹‹ከሁሉም የሚበልጠው ማን ነው?›› የሚለው ነው ብል ማጋነን አይሆንም)
የሆነ ሆኖ በ‹‹የመለስ ፋውንዴሽን ምስረታ›› ወቅት የታዩ ሁነቶች ሁለት ነገር ይፋ አድርገዋል፡፡ የመጀመሪያው በእነአዜብ ጎራ እነማን እንደተሰለፉ የሚያሳይ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የጦር አዛዦችም ፍልሚያውን መቀላቀላቸውን ማመላከቱ ነው፡፡ የእነአዲሱ ለገሰ-ብአዴን ገና ከመነሻው ከእነአዜብ ጎን መሰለፉ ይታወቃል፡፡ በፋውንዴሽኑ ምስረታ ወቅትም ይኸው ነው የታየው፡፡ ‹‹የጠቅላይ ሚንስትር መለስ የሌጋሲ ኮሚቴ›› ሰብሳቢ የነበረው አዲሱ ለገሰ፣ የስብሰባውን አካሄድ እየተከታተለ የተጣመመውን ሲያቃና፣ ማጣመም የፈለገውን ደግሞ ሲገፋ ተስተውሏል፡፡ ለምሳሌ የብአዴኑ ካሳ ተ/ብርሃን የፋውንዴሽኑ የቦርድ አባል ሆኖ መመረጡን ተቃውሞ በእርሱ ምትክ ሌላ ሰው እንዲመረጥ ሲጠይቅ፣ አዲሱ ስራው ጊዜን የማይሻማና ቦርዱን የሚመለከት ነገር ሲኖር ብቻ ውሳኔ መስጠት እንደሆነ ጠቅሶ ካሳ መቀጠል እንዳለበት ሲናገር፣ የመድረክ መሪው በፍጥነት ሃሳቡን ቤቱ እጅ በማውጣት እንዲደግፍ ቀስቅሶ የሰውየውን ተቃውሞ ውድቅ አድርጓል፡፡ በግልባጩ የኦህዴዱ ሙክታር ከድር ሲመረጥ፣ የብአዴኑ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) የሴቶች ተሳትፎ አናሳ መሆኑን መግለፁን ተከትሎ፣ ሙክታር ‹‹ድርጅቶቹ ራሳቸው ለምን አይጠቁሙም?›› ገና ከማለቱ፣ እነአዲሱ ተሽቀዳድመው ‹‹ከአንተ ነው መጀመር ያለበት›› የሚል ግፊት በማድረግ የተመረጠውን ሙክታር ከድርን በ‹‹ድርጅታዊ አሰራር›› ከጨዋታ ውጪ አድርገው፣ አስቴር ማሞን አስገብተዋል፡፡ ሶፍያን አህመድ፣ ቴዎድሮስ አድሀኖም፣ ቴዎድሮስ ሀጎስም የቦርዱ አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡ በመጨረሻም አዜብ የፋውንዴሽኑ ፕሬዚዳንት ሆና ስትመረጥ፣ ምክትሏ ደግሞ የብአዴኑ ካሳ ተ/ብርሃን እንዲሆን ተደርጓል (ሁሉም በእነአዜብ ቡድን ስር ናቸው) የሁለቱም ቡድን አባላት ‹‹ቃየል››ን እንጂ ‹‹አቤል››ን መሆን አይፈልጉም፡፡ እናም የከፋ ነገር ከመጣ ‹‹ቃየላዊ›› እርምጃዎችን እስከመውሰድ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ በእርግጥ ይህ ሁኔታም ሊሳካ የሚችለው የታጠቀውን ኃይል ፍላጎት ታሳቢ አድርጎ ለተንቀሳቀሰ ኃይል ነው፡፡ እናም ከእርስ በእርስ ግጭቱ በበላይነት ለመውጣት እንቅልፍ አጥተው እየሰሩ (እያሴሩ) ነው (እስከአሁን ባለው ሁኔታ ብአዴን ሙሉ ድጋፍ እያደረገለት ያለው የእነአባይ ወልዱ ቡድን ‹‹የተሻለ›› ሊባል የሚችል የበላይነት አሳይቷል)፡፡ በዚህን ጊዜም ከድንገቴ አደጋ ራስን መከላከል አስፈላጊ በመሆኑ የግል ጥበቃቸውን አጠናክረዋል፡፡ ለምሳሌ በረከት ስምዖን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጠባቂዎቹን ከሁለት ወደ ስድስት አሳድጓል፤ ሁለት ተጨማሪ መኪናዎችም ከፊትና ኋላ ሆነው እንዲያጅቡት አሰማርቷል፡፡ ባለፈው ወር በተካሄደው የግንባሩ ዘጠነኛ ጉባኤ አዜብ መስፍን ‹‹መለስ በስልጣን ላይ እያለ ደሞዙ ስለማይበቃን ብዙውን ጊዜ ከወር እስከ ወር ቀለብ ሳያልቅብን ለመድረስ እንቸገር ነበር›› የሚል አንድምታ ያለው ንግግር አድርጋ ካለቃቀሰች በኋላ ‹‹በደሞዝ (በፔሮል) የሚኖረው ባለስልጣን መለስ ብቻ ነው›› ስትል ማድመጣችን ይታወሳል፡፡ በእርግጥ አዜብ ልታስተላልፍ የፈለገችውን መልዕክት አንጓ ከ‹‹ሰሙ›› ለይተን ስናወጣው ‹‹ቅልጥ ባለ ዘረፋ ላይ የተሰማራችሁ ባለስልጣናት በልዩነታችን ላይ ካልተግባባን ላጋልጣችሁእንደምችል እንድታውቁት›› የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የበረከት ‹‹ቴሌቪዥን ጣቢያ››ም ይህንን ሃሳብ በተለየ ሁኔታ ያስተላለፈው ትርጉሙ ሳይገባው ቀርቶ አይመስለኝም፡፡ እነዚህን ኩነቶችም ስንጨምቃቸው ‹‹ህወሓት የውስጥ ችግሩ ከቀን ወደ ቀን እየባሰ ሄዶበታል›› የሚል ድምዳሜ ላይ ያደርሱናል (የአዜብን መልዕክት ባደመጥን ማግስት አራት ኪሎ አካባቢ ከአንድ የአረና አመራር አባል ጋር ድንገት ተገናኝተን ይህንን ሁኔታ አንስተን ስናወራ እንዲህ አለኝ፡- ‹‹እነርሱ ቀልደኞች ናቸው፤ በ1993 ዓ.ም የክፍፍሉ ወቅት መለስ ለቤተመንግስቱ የተመደበው ሁለት ሚሊዮን ባጀት የት እንደሚገባ ሲጠየቅ ‹ይሄ ግቢ እኮ ከምንሊክ ዘመን ጀምሮ ጮማ የለመደ ነው› ብሎ አድበስብሶ አልፎት እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በተቀረ አዜብ ‹በመለስ ደመወዝ ብቻ ስለምተዳደር ሽሮና በርበሬ እያለቀብኝ እቸገራለሁ› ማለቷ ከእርሷ ጋር የአቋም ልዩነት ላላቸው የህወሓት አመራር በጎንዮሽ የማስፈራሪያ መልዕክት ከማስተላለፍ የዘለለ ቁም-ነገር ያለው አይመስለኝም፡፡››)
seyoum_bereket_addisu
ሌላኛው በዕለቱ የታየው ዓብይ ጉዳይ መከላከያን የሚመለከተው ነው፡፡ የተመረጡት ሰዎች ውክልናቸው ተቋምን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረትም መከላከያን ወክለው የቀረቡት ጄነራል ሳሞራ የኑስና ጄነራል ሰዓረ መኮንን ናቸው፤ ሳሞራ ሙሉ ጀኔራል ነው፣ ሰዓረ ደግሞ ሌፍቴናንት፡፡ ስለዚህም መከላከያን ወክሎ የቦርድ አባል መሆን ያለበት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባለ አራት ኮከብ ጄነራል የሆነው ሳሞራ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የሆነውም ይኸው ነው፤ በዚህም ማንም አልተቃወመም-ከጄነራል ሰዓረ በቀር፡፡ ለምን? ሁለቱ ጄነራሎች በግል ስለማይግባቡ? በጥቅም ተጋጭተው? ሰዓረ ‹‹ሳሞራ አይመጥንም›› ብሎ አስቦ? እውነት ጉዳዩ የሁለቱ ብቻ ነው? ወይስ የሰዓረ ተቃውሞ መነሻ ምንድር ነው? …ይህንን ተቃውሞ የግለሰብ አድርገን እንዳንወስደው የሚያስገድዱ ገፊ ምክንያቶች የምላቸውን መጥቀስ እችላለሁ፡- ሁለቱም ተመሳሳይ ተቋም ወክለው መቅረባቸው አንዱ ነው፤ ሁለቱም ወታደሮች መሆናቸው ሌላኛው ነው (የወታደር ዲሲፕሊን በተለይም የኢህአዴግ ወታደራዊ አደረጃጀት ከታች ወደላይ ተቃውሞን እንደማያበረታታ ማንም አይጠፋውም) ሆኖም ‹‹የሳሞራን የቦርድ አባል መሆን በምን አያችሁት?›› ሲል የተቃውሞ ድምፁን አሰምቷል፡፡ በተጨማሪም ሰዓረ ያ ሁሉ ህዝብ በተሰበሰበበት አዳራሽ የሳሞራን ስም ሲያነሳ በሰራዊቱ ደንብ መሰረት በማዕረግ ስሙ አልነበረም፡፡ ለዚህም ነው በዕለቱ የተከሰተው ነገር ሁለቱ ጄነራሎች እያራመዱት ያለውን ልዩነት የሚያሳይ ነው የሚለውን መከራከሪያ የሚያጠናክረው፡፡ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለሚከታተል የሠራዊቱን ወሳኝ ጄነራሎች ከጎኑ ማሰለፍ የቻለ ማንኛውም ቡድን ዳዊት የማይኖርበት ጎልያድ ሊሆን እንደሚችል አይጠፋውም፡፡ እናም ይህ ኩነት አንደኛ ዓመቱን ሊደፍን እየተቃረበ ላለው የሁለቱ ቡድኖች ፍጥጫ የመቋጫው ቀናት እየቀረበ እንደሆነ የሚያመላክት ይመስለኛል (በነገራችን ላይ በመከላከያ ውስጥ ከሳሞራ ቀጥሎ ባለ የስልጣን ወንበር ላይ የምናገኘው በተመሳሳይ ማዕረግ የሚገኙ ሶስት አቻ ጄነራሎችን ነው፡፡ ሁለቱ ጄነራል አበባው ታደሰ እና ጄነራል ሰዓረ መኮንን ናቸው፡፡ እነዚህ ጄነራሎች አንም ቀን ተስማምተው ሰርተው አያውቁም፡፡ ስልጣናቸውና ኃላፊነታቸው ተመሳሳይ ቢሆንም አበባው የሚመራው ቢሮ በተሰሚነት ጎላ ያለ ነው፡፡ …ሳሞራ በግልፅ ‹‹በዚህ ቀን›› ብሎ ባይናገርም ከኤታማዦር ሹምነቱ የመልቀቅ እቅድ አለው፡፡ በአሁኑ አሰላለፍም ከእነአዜብ ጎን ይመደባል፡፡ አበባውና ሰዓረ ደግሞ የእርሱን ቦታ ይፈልጉታል፡፡ አበባው የሳሞራ የቅርብ ሰው ነው፡፡ ከሰዓረ ጋር ያለው ግጭትም ከሳሞራ ጋር ካለው ግንኙነት ጋር ይያያዛል)
የሆነ ሆኖ ‹‹ቀዝቃዛው ጦርነት››ን በሚመለከት ተጨማሪ ነጥብ ልጥቀስ፡፡ ከቀኑ ስብሰባ በኋላ በሸራተን ሆቴል ለፋውንዴሽኑ ገቢ ማሰባሰቢያ አንድ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ የጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ የክልል አስተዳደሮች ‹‹አቅማችን ይመጥናል›› ያሉትን ያህል የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ከሁሉም ቀድሞ አንድ ሚሊዮን ብር ያዋጣው እነአዲሱ ለገሰ እንደግል ንብረታቸው የሚቆጥሩት ‹‹ጥረት ኢንዶውመንት›› ሲሆን፣ የአላሙዲ ‹‹ሚድሮክ ኢትዮጵያ››ም ሃያ አምስት ሚሊዮን ብር ለመለገስ ቃል ገብቷል፡፡ ትኩረቴን የሳበው ግን ይህ አይደለም፤ ገቢና ወጪው ከህዝብ ብቻ ሳይሆን ከውጪ ኦዲተርም አይን የተሰወረ ነው
የሚባለው እጅግ ባለፀጋው የህወሓቱ ‹‹ኤፈርት›› በዕለቱ ሰባራ ሳንቲም ለማዋጣት ቃል አለመግባቱ እንጂ፡፡ ለምን? ኤፈርት በእነአዜብ ስር ከመሆኑ አኳያ ለትችት ያጋልጠናል በሚል? ወይስ ገና ያልተደረሰበት እንቆቅልሽ ይኖር ይሆን? ጥያቄው ይህ ነው፡፡ የዚህን መልስ ጨምሮ ከላይ ያነሳኋቸው ነጥቦች ሲፍታቱ ልዩነቱን እና አሰላላፉን ያጎሉታል ብዬ አስባለሁ፡፡
እንደመውጫ
በሀገራችን ላይ ‹‹ለውጥ አመጣለሁ›› የሚለው የተቀውሞ እንቅስቃሴ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ‹‹ይህን ዓመት አያልፍም!›› በሚል ሟርት ሲጠመድ፣ ድርጅቱ ግን ሃያ ሁለተኛ ዓመቱን ሻማ ለኩሶ ሊያከብር ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡ ዘንድሮም የመለስን ሞት ወይም የግንባሩን መከፋፈል ብቻ ስናመነዥክ የቋመጥንለት ለውጥ የውሃ ሽታ ሆኖ ነገሩ ሁሉ ‹‹የሞትንም እኛ፤ ያለንም…›› እንዳይሆን እሰጋለሁ፡፡ እናም በላያችን ላይ እያመፀ ያለውን ፍርሃት ማረቅ ያስፈልጋል፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነት ያስፈልገናል፤ ከኢህአዴግ በኃላም ሊኖር ስለሚገባው ለውጥ መነጋገር ያስፈልጋል፤ ስርዓቱ ሀገር የሚጠቅም አለመሆኑን በበቂ ሁኔታ ገብቶናልና፣ የርዕዮተ-ዓለም ወይም የፖሊሲ ድክመቱን በምክንያትና አመክንዮ (ሎጂክ) እየተነተንን ብቻ ተጨማሪ ጊዜ ማባከኑ ፋይዳ የለውም፡፡ ፋይዳ ያለው በሰላማዊ መንገድ አደባባይ ወጥቶ የስርዓት ለውጥ ማድረግ ነው፤ ትንተናዎችም ይህ አይነቱን እንቅስቃሴ ወደ መሬት ማውረድ የሚቻልበት እና ከኢህአዴግ በኋላስ? የሚለው ላይ ሲያተኩሩ ነው፡፡

Hiber Radio: ከኢትዮጵያ መሬት በርካሽ የተሰጠው ካራቱሪ ኩባንያ ኬኔያ ውስጥ በታክስ ማጭበርበር ተከሰሰ

0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ሚያዚያ 20 ቀን 2005 ፕሮግራም
>
ኦባንግ ሜቶ በካልጋሪ ለተጠራው የኢትዮጵያን ጉባዔ ያደረገውን ንግግር አስመልክቶ ከህብር ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ(ሙሉውን ያዳምጡ)
> የአብይ አፈወርቅ በጥናት ላይ የተመሰረተ ትንታኔ
ዜናዎቻችን
- ከኢትዮጵያ መሬት በርካሽ የተሰጠው ካራቱሪ ኩባንያ ኬኔያ ውስጥ በታክስ ማጭበርበር ተከሰሰ
- ኢትዮጵያዊያን የመብት ተቆርቋሪዎች ውሳኔውን አድንቀዋል
– ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የ15 አመታት ጽኑ እስራት እና የከባድ ጉልበት ስራ ተበየነባቸው
- የኮ\ሌ መንግስቱ ሃይለማሪያም “ሞቱ” የመባል ዜና ሰሞኑን በርካታ ኢትዮጵያዊኖችን ለቃላት ጦርነት ዳረገ
- ከኤርትራ የተሰረቀ አውሮፕላን ለማስመለስ የተላኩ ፓይለት እንደወጡ ቀሩ
- የአሰገደ ገ/ስላሴ ልጅ በትግራይ ታሰረ
- የሙስሊሙ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል
- በአማራው ላይ የሚደረገውን መፈናቀል በካልጋሪ የሚኖሩ አወገዙ
- በቬጋስ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የጋራ ኮሚኒቲ እንዲያቋቁሙ ጥሪ ቀረበ
ሌሎችም ዜናዎች አሉን:-
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live