Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት |ከዳንኤል ክብረት (ዲ/ን)

0
0

‹የክርስቶስ አንዲት በግ መከራን ስትቀበል ከማይ እኔ የበጉ እረኛ መከራ መቀበልን እመርጣለሁ›
daniel
ይህንን የተናገረው ዮሐንስ አፈወርቅ ነበር፡፡ የቁስጥንጥንያዋ ንግሥት አውዶቅስያ የአንዲት ክርስቲያን ምእመንን መሬት ወስዳ ባሰቃየቻት ጊዜ ለተግሣጽ የተናገረው ነው፡፡ እንዳለው አልቀረም አውዶቅስያ ባደረሰችበት መከራ ተግዞ በዚያው ሞትን ተቀብሏል፡፡ እውነተኛ አባት ስለ በጎቹ ራሱን አሳልፎ ይሰጣል እንጂ በጎቹን ለራሱ ክብርና ጥቅም ሲል አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ፓትርያርክ ማለት በግሪክ ‹ታላቅ አባት› ማለት ነው፡፡ የታላቅ አባት ተግባር የልጆቹን ሥራ ማፍረስ አይደለም፤ ለዚህማ አባት አያስፈልግም ሰይጣን እንጂ፤ የታላቅ አባት ሥራ ልጆቹን መክሰስ አይደለም፤ ለዚህማ ሰይጣን እንጂ አባት አያስፈልግም፡፤ የታላቅ አባት ሥራ ልጆቹን ጠርቶ መውቀስ እንጂ በር መዝጋት አይደለም፤ ለዚህማ አባት አያስፈልግም ሰይጣን እንጂ፡፡ የታላቅ አባት ሥራ ልጆቹን ማቀፍ እንጂ ማባረር አይደለም፤ ለዚህማ ሰይጣን አለ፡፡
abune Matias
ፓትርያርኩ እንጨት የሚሸጡ እናቶች ካወጡት የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገንዘብ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደዋዛ በአንድ ሙሰኛ ሲነጠቅ ተኝተዋል፤ በመሐል ከተማ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተሠሩ ሕንጻዎች በጎጆ ቤት ዋጋ በሙስና ለዐሠርት ዓመታት ሲከራዩ ተኝተዋል፤ ከመንበረ ፕትርክናቸው ሥር ባለች አጥቢያ የቤተ ክርስቲንን ገንዘብ አናስበላም ያሉ ካህናትና ምእመናን ሲባረሩ ተኝተዋል፡፡ በሕዝብ ጥያቄ ሽፋን ጽንፈኛ አቋምን በሚያራምዱ ሰዎች አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ ይተኛሉ፤ የስልጤ ዞን ምእመናን በሃይማኖታችን ምክንያት መከራ እየተቀበልን ነው ሲሉ ይተኛሉ፤ ቤተ ክህነቱ የኑፋቄ ማኅደር ሲሆን ይተኛሉ፤ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ሲዘጉ፣ ገዳማትና አድባራት ሲፈርሱ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች ሲበተኑ ይተኛሉ፤ በመሥዋዕትነት የተመሠረቱት የደቡብ አፍሪካ አብያት ክርስቲያናት በሙሰኛ አመራሮች አደጋ ላይ ሲወድቁ ይተኛሉ፣ ይሄ ሁሉ ዘለፋና ኑፋቄ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሲዘንብ ይተኛሉ፡፡

መናፍቃንን የሚተች ጽሑፍ በኦርቶዶሳውያን ተጻፈ ሲሏቸው፤ ምእመናንን የሚያጸና ጉባኤ ሊዘጋጅ ነው ሲሏቸው፤ ሕዝቡ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየመጣ ነው ሲሏቸው፤ ወጣቱ ትውልድ ቤተ ክርስቲያኑን ለማገልገል እየተጋ ነው ሲሏቸው፤ ዲያስጶራው ሕዝብ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ሆነ ሲሏቸው፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚገልጥ ዐውደ ርእይ ሊዘጋጅ ነው ሲሏቸው፤ መንፈሳዊ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ሊቀርብ ነው ሲሏቸው ያን ጊዜ ብዕራቸውን ይዘው ለማገድና ለመክሰስ ይነቃሉ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ‹ድንግል ሆይ የአንቺን ምስጋና ለመጻፍ ምንጊዜም ብእሬ ቀለም እንደያዘ ነው› ነበር ያለው፡፡ የፓትርያርኩ ብእር ግን ምእመናንን የሚያጽናና ጦማር ለመጻፍ ወይም ድንግልን የሚያመሰግን ድርሳን ለመድረስ የሚጨበጥ አይደለም፡፡ እንደ ጠንቋይ ብዕር ለማፍዘዝና ለማደንገዝ እንጂ፡፡

የፓትርያርክ ዋናው ሥራው የሀገር ደኅንነት እንዲጠበቅ ‹ዕቀብ ሕዝባ ወሠራዊታ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ› እያለ መጸለይ፤ የምእመናን ድኅነት እንዲረጋገጥም ሃይማኖት ማስተማር፣ በጎችን መሠማራትና ቀኖናን መጠበቅ ነበረ፡፡ ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹በጎቼን ጠብቅ፣ አሠማራ› ነበር የተባለው፡፡ መጠበቅ- ከክህደት፣ ከኑፋቄ፣ ከኃጢአት ከበደል፤ ማሠማራት – በትምህርት፣ በምግባር፣ በትሩፋት፣ በአገልግሎት፣ በጽድቅ መስክ ላይ፡፡

‹ባለሞያ ሴት የሠፋችውን ወራንታ፣ ጅል ትተረትረዋለች› እንደተባለው በደኅና ጊዜ ትጉኃን አበው የሰበሰቧቸውን ወጣቶች ካልበተንኩ ብሎ እንዴት አንድ ፓትርያርክ ይነሣል፡፡ ወጣቶቹ ሊሳሳቱ፣ ሊያጠፉም ይችላሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን ለዚህም መንገድ ያላት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ሳይቀሩ የገዛ ልጆችዎን ያወያዩ ሲሏቸው በራቸውን ጠርቅመው የሚዘጉ ፓትርያርክ በታሪክ የሚጀመሪያው መሆን አለባቸው፡፡ በሱራፊ ነበልባል የተዘጋች ገነት ስትከፈት በፓትርያርክ የተዘጋች የቤተ ክህነት በር ልትከፈት አልቻለችም፡፡ ሰይጣንን ከእግዚአብሔር ጋር ለማነጋገር የደከሙ እነ ክርስቶስ ሠምራን የመሰሉ ቅዱሳን ባሉባት ቤተ ክርስቲያን እረኛው ከመንጋው ጋር መነጋገር አቃተው፡፡ ኢየሱሳውያንን በዐደባባይ ሳናነጋግራቸው መሄድ የለባቸውም ብለው የተሟገቱ እነ እጨጌ በትረ ጊዮርጊስ በነበሩባት ቤተ ክርስቲያን የገዛ ልጆቹን ለማነጋገር በር የሚዘጋ እጨጌ ተፈጠረ፡፡ የመካ ቁራይሾችን አሳልፈን ለጠላቶቻቸው አንሰጥም የሚሉ አበው በነበሩባት ቤተ ክርስቲያን የገዛ ልጆቹን አሳልፎ የሚሰጥ አባት መጣ፡፡
የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት በ1972 እኤአ ካይሮ ላይ ባደረጉት ጉባኤ ከተስማሙባቸው ነገሮች አንዱ የኦርቶዶክሳውያን ጳጳሳት ተልዕኮ ነበረ፡፡ እንዲህ ይላል ‹ኦርቶዶክሳውያን ጳጳሳት አምስት ተልዕኮ አላቸው፡፡ እነዚህም

1. ወንጌልን መስበክ(Preach the Gospel)
2. ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን መፈጸም(Administer the Sacraments of the Gospel.)
3. የቤተ ክርስቲያንን እምነት፣ አንድነትና ቀኖና መጠበቅ(Guard the faith, unity, and discipline of the church.)
4. ለካህናትና ለምእመናን የቅድስና ምሳሌ መሆን(Be a moral example of holiness and wholesomeness.)
5. በእረኛውና በበጎች መካከል ያለውን ክፍተት ማጠበብ(Diminish the distance between bishops and their flock.)
ለመሆኑ የእኛ አባት የቱን ነው እየፈጸሙ ያሉት? ወይስ ከኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት ማኅበር ውጭ ሆነናል?

ዐውደ ርእዩ የማይደረግበት በቂ ምክንያት ከነበረ ቢያንስ ከሳምንት በፊት መግለጥ ይቻል ነበር፡፡ ዓላማው ግን ማበሳጨት፣ ዐመጽ ማስነሣት፣ ተሥፋ ማስቆረጥና ምእመናንን ወደማይፈልጉት መሥመር መውሰድ ነው፡፡ ለዚህ ነው ፈያታዊ ዘየማን ገነት በገባባት ሰዓት ዐውደ ርእዩ እንዲዘጋ የተደረገው፡፡ የዚህች ሀገር ሰላም አይፈለገም? ምእመናን ሀገር እንደሌላቸውና መብት እንደሌላቸው ራሳቸውን እንዲቆጥሩ ይፈለጋል? ‹ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል› እንዲል ሀገሪቱ ያለባት ችግር አይበቃትም? ተጨማሪ ችግር ማምረት ይፈለጋል?

ችግሩ ሁሉ እየተፈጠረ ያለው በመንግሥት ስም ነው፡፡ ‹መንግሥት አዞናል፤ እገሌ የተባለ ባለ ሥልጣን ብሎናል፤ ፖሊስ እንጠራለን፤ ደኅንነት እናዛለን› ነው በቤተ ክህነቱ ዘንድ የሚባለው፡፡ እውነት መንግሥት በስሙ የሚሠራውን ያውቀዋል፤ ካወቀውስ ዝም ይላል? ቤተ ክህነቱ በሚያመጣው ዳፋ መከራ ለመቀበልስ ዝግጁ ነው? ይህ አካሄድስ ለሀገሪቱ ደኅንነት የሚበጅ ነው? ዐውደ ርእዩ እንዲዘጋ ያዘዘውስ የትኛው መንግሥት ነው? አንዱ የሚፈቅድ ሌላው የሚዘጋ ስንት መንግሥት ነው ያለው? ወይስ ‹ደብዳቤ መጻፉ አላዋጣምና ዝጋልኝ› ተብሎ እጅ የተሰነዘረለት አካል ያደረገው ነው? መጽሐፉ እንደሚል ‹የማይገለጥ የተሠወረ› አይኖርምና ዐውቀነዋልም፣ እናውቀዋለንም፡፡
የገዛ ፓትርያርካችን ለእኛ ለምእመናን ድኅነትን እንዳናገኝ ሥጋት ሆነውብናል፡፡ የታገሡትን ሁሉ ለክፋት በማነሣሣት ደግሞ ለሀገሪቱ ደኅንነት ሥጋት እየሆኑ ነው፡፡

የምእመናኑን ሥጋት ሲኖዶሱ፤ የሀገሪቱንም ሥጋት መንግሥቱ ሊያስቡበት ይገባል፡፡ ከቤተ መቅደስ የተነሣ ችግር መጀመሪያው እንጂ መጨረሻው አይታወቅምና፡፡ እንዲህ ያሉ ነገሮች የምእመኑን የአስተሳሰብ ቅርጽ ይቀይራሉ፡፡ የሐበሻን ሥነ ልቡና ለሚረዳ ደግሞ ሲረገጥ እንደሚጠክር ጭቃ ያጠነክራሉ፡፡ ሲሞረድ እንደሚሳል ቢላዋ፣ ሲቀረጽ እንደሚሾል እርሳስ ያደርጋሉ፡፡ በዐውደ ርእዩ የሚማሩት የሚያዩት ብቻ ነበሩ፡፡ አሁን ግን ያላዩትም እንዲማሩ አድርገዋል፡፡ ሐሳብና ርእዮት ሊያስተባብረው የማይችለውን ተጠቂነት ያስተባብረዋል፡፡ ተጠቂነት ክርክርና ውይይት፣ ማስረጃና መረጃ አይጠይቅም፡፡ መጠቃቱን ያወቀ ሁሉ ራሱ ገብቶት ይተባበራልና፡፡ ምናልባትም ምእመናንን ከገድል ተራኪነት ወደ ገድል ሠሪነት ያሻግራቸው ይሆናል፡፡ ‹እዚያም ቤት እሳት አለ› አሉ አለቃ፡፡

እንደ ሶምሶን ከአንበሳ ሬሳ ማር ለማውጣት ግን በሳል አመራር ይጠይቃል፡፡ የማኅበሩ አመራርም ቢሆን ጊዜውን አይቶ የሚሣለጥ አመራር እንጂ የተቸከለ አመራር መሆን የለበትም፡፡ የፓትርያርክ ማትያስ ዘመን እንደ ፓትርያርክ ጳውሎስ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምም ዘመን እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አይደለም፡፡ አሁን የሆነው ነገር ሊሆን እንደሚችል ቀድሞ እየታወቀ ከግንቡ ጋር እስኪጋጩ ድረስ ቆሞ መጠበቅ ብልህነት አይደለም፡፡ አሁንም ‹እገሌ የተባለ ባለሥልጣንን አናግረናል፤ እገሌ የተባሉ አባት አይዟችሁ ብለውናል› እያሉ መጓዝ የሚያዋጣ አይደለም፡፡ ለጉባኤ ተሰብስቦ ‹ ለፓትርያርኩ የተጻፈው ደብዳቤ አንጀት አርስ ነው› ብሎ አጨብጭቦ የሚበተን አመራር ጊዜው ሊያልፍበት ይገባል፡፡ ከዲሚትሪ ሆቴል እስከ ፌዴራል ጉዳዮች የተደረጉትን ውይይቶች ገምግሞ አዲስ አቅጣጫ መያዝ ይገባ ነበር፡፡ የሚሰበሰብ ብቻ ሳይሆን የሚተነብይ አመራርም ያስፈልጋል፤ ካልሆነ ግን
‹ከክምር ድንጋይ ላይ ይበቅላል ደደኾ
የፈራሁት ነገር መጣ ድኾ ድኾ› የተባለው ይደርሳል፡፡

The post ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት | ከዳንኤል ክብረት (ዲ/ን) appeared first on Zehabesha Amharic.


የሽብርተኛ ትርጉም –መስፍን ወልደ ማርያም

0
0

መጋቢት 2008

mesfin

መስፍን ወልደ ማርያም

የሚማር የለም እንጂ የሚማር ቢኖር የሽብርተኛነትን ትርጉም ሰሞኑን በቤልጂክ እያየንና እየሰማን ነው፤ በኢትዮጵያ ያሉ የእውቀት ምልክቶችን በዶላር እየገዙ ስማቸው ላይ የለጠፉ ጉልበተኞች ተናገርክ(ሽ) ብለው ብቻ ሳይሆን አሰብህ(ሽ) ብለው ሰፋፊ እስር ቤቶች እያሰሩ ወጣቶችን ሲያጉሩበት ምክንያታቸው ሽብርተኛነት ነው፤ ሽብር ማለት ሰሞኑን በቤልጂክ አውሮጵላን ጣቢያና በባቡር ጣቢያ ላይ እንደታየው ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ አልታየም፤ ከታየም በአገዛዙ ኃይሎች የተፈጸመ ነው፤ ለብዙ ዓመታት ሲፈጸም የቆየ ነው፤ የኢትዮጵያ ጉልበተኞች ከቻሉ ሊያስተውሉት የሚገባ አንድ ነገር አለ፡- ሽብርም ነጻነትን ይፈልጋል፤ በቤልጂክ ሽብሩን የፈጸሙት ሁሉ ነጻነትን ፈልገው ከአገራቸው የተሰደዱና በአገራቸው ያላገኙትን ነጻነት በሰው አገር እየተሞላቀቁበት እንደሆነ የሚያመለክት ነው፤ ትርጉሙ፡- ነጻነት በሌለበት ሽብር አይኖርም፤ እንዴት ብሎ? የት ተደብቆ? የት ሸምቆ?

ሽብርን የጸነሰውን እንዳያስብ አፍኖ፣ እንዳይናገር አንደበቱን መርጎ፣ እንዳይንቃሳቀስ በዳኛ ትእዛዝ ወህኒ ቤት ውስጥ ቆልፎ ሽብርን ማቆም አይቻልም፤ የሚቻለው፣ እየሆነ ያለውም ዝንባሌው ያላቸው ኢትዮጵያውያን ለሽብር ትምህርት ወደአውሮፓና ወደአሜሪካ እንዲሄዱ የሚገፋፋቸው ነው፤ የዚህን ግፊት ውጤት የኢትዮጵያ ጉልበተኞች የሚወዱት አይመስለኝም፤ መጠቃት እንደማጥቃት አያስደስትም!

የእኝ ጉልበተኞች ሽብር ምን እንደሆነ አያውቁም፡፡

የእኛ ጉልበተኞች በንግግርና በተግባር መሀከል ያለውን ልዩነት አያውቁም፤ በቤልጂክ ሽብር የተባለው ሠላሳ አንድ ያህል ሰዎች የሞቱበት፣ ወደሦስት መቶ ሠላሳ ያህል ሰዎች የተጎዱበት ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ያለ ነገር ደርሶ ያውቃል? እንዴታ! በዙ ጊዜ፤ ግን ሽብርተኞች በተባሉትና በታሰሩት አይደለም፤ በተመቻቸውና ሕግ በማይደርስባቸው ሌሎች ጉልበተኞች የተፈጸመ ነው፡፡

የእኛ ጉልበተኞች በፍርሃት የደነዘዘው አንጎላቸው ዓይናቸው እውነቱን እንዲያይ፣ ጆሮአቸው እውነትን እንዲሰማና ልባቸው ወደመወያየትና ወደእርቅ እንዲያቀና አያደርጋቸውም፤ ወላጆቻቸውን ንቀው ብቻቸውን የቆሙ ስለሆኑ መካሪ የላቸውም፤ መንፈስ ስለሌላቸው መንፈሳዊ አባት የላቸውም፤ ያሳዝናሉ፡–

ሀሳቤን አንዱ ግጥሜ ይገልጽልኛል መሰለኝ፡– የሞተ ኅሊና

የማይጣላ ኅሊና ያለው

እንዴት የታደለ ነው!

እግዜር ብቻ ነው ኅሊና የሌለው፤

የማይሳሳት የማየወቆጨው፡፡

ሰው ሰውነቱ፣ ጭንቀቱና ልፋቱ፣

ኅሊናው ከስሜቱና ከፈላጎቱ መጣላቱ፣

የሚረሳ የሚሳሰት፣ የማይታየው የፊቱ፣

የሚወድ፣ የሚጠላ፣ የሚፈራ፣

ከሳሽ፣ ተከሳሽ፣ ዳኛ መሆን

እንዴት ይችላል መበየን?

ሲያፍነው ግን ኅሊናውን

አይለይም ጨለማውን ከብርሃን!

ኅሊናውን ገደለ ሰው

ማን ሊቀረው? ምን ሊያቅተው?

የጉልበቱ መሣሪያ ነው፤

ጊዜ ጉልበቱን እስቲሰብረው! … …

እውነተኞቹ ሽብርተኞች በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ከሥልጣን ውጭ አይደሉም፤ ከሥልጣን ውጭ ሆነው ቅራኔ የሚያሰሙ ጉልበታቸው እዚያው ላይ ያበቃል፤ በምድረ ኢትዮጵያ ሽብርን መቃወም ሽብርተኛ ያደርጋል፤ ወህኒ ያስገባል፤ ተመስገን ደሳለኝ፣ እስክንድር ነጋ፣ አብርሃ ደስታ፣ … በወህኒ ቤት የሚማቅቁት ቅንጣት የሚያህል የሽብር ተግባር ፈጽመው አይደለም፤ ሽብር እንዳይፈጸም ስለታገሉ ነው፤ ሽብር ከነገሠ ሰላም ወንጀል ይሆናል፤ በኢትዮጵያ ሰላም ዋጋ እያጣ መሄድ ላይ መሆኑን የሚጠራጠር የለም፤ ከባሕር ማዶ የተጀመረው ቀረርቶ ወደተግባር ሲለወጥ መፍራት ፋይዳ የለውም፤ ለጉልበተኞቹ የሚያዋጣው የፍርሃት ጊዜው አሁን ነው! እንደሳዳም ሁሴንና እንደጋዳፊ እንደአይጥ ከተሸጎጡበት ስርቻ እየተጎተቱ ሲወጡ አይደለም፡፡

The post የሽብርተኛ ትርጉም – መስፍን ወልደ ማርያም appeared first on Zehabesha Amharic.

የዶክተር» ገላውዲዮስ አርኣያ አይን ያወጣ ውሸት! አቻምየልህ ታምሩ

0
0

ኒዮርክ ውስጥ «ታሪክ» የሚያስተምሩት የትግራይ ብሔርተኛው «የታሪክ ዶክተር» ገላውዲዮስ አርኣያ፤ ትናንትና በአሜሪካ ድምጽ ትግርኛ ክልፍ ቀርበው «በታሪክ ወልቃይት የትግራይ እንደነበር» ሲያስረዱ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በElizabel Filleul በፖርቹጋል ቋንቋ የተጻፈውን «Tractatus tres historico-geographici (1634): A seventeenth century historical and geographical account of Tigray, Ethiopia (Aethiopistische Forschungen)» መጽሀፍ ጠቅሰው ነበር። ይህ መጽሀፍ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሟል።
እስቲ ዶክተር ገላውዲዮስ አርኣያ የጠቀሱት የElizabel Filleulን መጽሀፍ ስለ 17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የትግራይ ግዛት ምን ይነግረናል? ዶክተር ገላውዲዮስ አርኣያ በጠቀሱት መጽሀፍ የመጀመሪያ ምዕራፍ የመጀመሪያ ገጽ ላይ ስለትግራይ ግዛት [ ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ] እንዲህ ተጽፎ እናገኛለን፤
>
ይህ በመጽሀፉ የመጀመሪያ ገጽ ላይ የሰፈረ ጥሬ ሀቅ ነው። መጽሀፉ ውስጥ ይህ ሀቅ ተቀምጦ ሳለ ዘረኛው ዶክተር ገላውዲዮስ አርኣያ ግን ትግርኛ ማንም አይሰማም ብለውና መጽሀፉን ፈልጎ የሚያጋልጠኝ ሰው አይኖርም በሚል መጽሀፉ ላይ ያልተጠቀሰ ታሪክ በቃለ መጠይቃቸው ወቅት በማቅረብ ክህደት ፈጽመው አጭበርብረዋል። በነገራችን ላይ ይህ የዶክተር ገላውዲዮስ አርኣያ ማጭበርበር በacademic crime የሚያስቀጣ ትልቅ ወንጀል ነው። ቀስፎ የያዛቸው የአማራ ጥላቻ እድሜ ልካቸውን ከኖሩበት ሞያቸው ጋር አፋትቶ academic crime አሰርቷቸዋል።
ዶክተር ገላውዲዮስ አርኣያ የተዋረዱት በምሁርነት ካባ የወያኔ ፕሮጀክት ለሆነው አማራን የማጥፋት ፕሮግራም በግብረ አበርነት ለማገዝ ባደረጉት የክህደት ምስክርነታቸው ነው። እኒህ ሆዳም ምሁር የታሪክ እውቀታቸውንና ሽማግሌነታቸውን በቅሌት መንዝረው ከታሪክ «ምሁርነት» ወደ ትንሽ ካድሬነት የወረዱ ተራ ዋሾ ናቸው።
አንድ የታሪክ «ዶክተር ነኝ» የሚል ግለሰብ ማንም ተራ አንባቢ ሊያረጋግጠው የሚችለውን የታሪክ እውነት ባደባባይ በማዛባት የታሪክ ሀቅን ለዘረኝነት ጥማቱ ማርኪያ እየጠመዘመ በማበላሸት የሚያቀርበው ከሆነ፤ ሌላው «በሞያው» የሚጽፈው «የታሪክ ጭብጥ» እንዴት ሊታመንለት ይችላል?
እንግዲህ ዶክተር ገላውዲዮስ አርኣያ በአደባባይ የሚዋሹ ተራ ግለሰብና በዘረኝነት የታጠቡ ውሸታም አስተማሪ እንጂ የታሪክ ምሁር እንዳልሆኑ ማንም ሊያውቅ ይገባል። የምሁርነትን ዋነኛ ባህሪ ማለትም integrityን የማያሟሉትን እኒህን ተራ ዋሾ ግለሰብ ኒዮርክ ውስጥ ለሚያስተምሩበት የታሪክ ትምህርት ክፍል በስልክና በኢሜል ይህንን ጉዳቸውን ሪፖርት በማድረግ ማጋለጥ አለብን። እንደዚህ አይነቱ ዘረኛና ለራሱ ክብር የሌለው ተራ ሸበቶ ግለሰብ «የኢትዮጵያን ታሪክ አጥኚ» ተብሎ በስማችን ሊጠራ አይገባም።
ዶክተር ገላውዲዮስ አርኣያ በቪኦኤ ላይ ቅርጥፍ አድርገው የዋሹበት ቃለ መጠይቃቸው እነሆ፤
http://m.tigrigna.voanews.com/a/welkite-tseged…/3253236.html
ዶክተር ገላውዲዮስ አርኣያ የተዋረዱበት የElizabel Filleul መጽሀፍ፡ «Tractatus tres historico-geographici (1634): A seventeenth century historical and geographical account of Tigray, Ethiopia (Aethiopistische Forschungen)» ውስጥ ስለ ትግራይ ግዛት የተጠቀሰውንና ከፍ ብዬ ያቀረብሁትን የታሪክ እውነት ከመጽሀፉ ገጽ ሁለት ፎቶ አንስቼ ከታች በድጋሜ ለጥፌዋለሁ።
12794622_10153313800772245_5049952786310433958_n

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ ወደ የት? -ትብብር ወይንስ ውድድር?- አክሎግ ቢራራ (ዶር)

0
0

rp_aklog_birara1.jpg
የብዙ ሽህዎች አመታት ተከታታይ ታሪክ፤ መንግሥታትና ዝና ያላት ኢትዮጵያ የምትታወቀው ከሁሉም ብሄር፤ ብሄረሰብና ሕዝቦች ተወጣጥተው ግዛታዊ አንድነቷን፤ ነጻነቷን፤ ክብሯን፤ ዘላቂ ጥቅሟንና ሉዐላዊነቷን ባስጠበቁት ጀግኖቿ መስዋእት ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም። አፍሪካ፤ የመካከለኛው ምስራቅ፤ የላቲን አሜሪካና ካሪቢያን እና የኤዥያ አገሮች በቅኝ ገዢዎች እጅ ወድቀው ሲማቅቁ፤ ድሃና ኋላቀርም ብትሆን፤ ኢትዮጵያ ነጻነቷንና ሉዐላዊነቷን በራሷ አቅም አስከብራ ለተከታታይ ትውልድ አስተላልፋለች። በጀግኖቿ ትግል ከፋሽስት ወረራ ነጻ ከሆነች በኋላ በዓለም ደረጃ እውቅና ያገኘችው ከሰማይ የወረደ አይደለም። አገር ወዳድ የሆኑ ልጆቿ ጠንክረውና ተባብረው ስለሰሩ ነው። ለምሳሌ፤ ኢትዮጵያ ሌሎች ታዳጊ አገሮች ገና ከቅኝ ገዢዎች መዳፍ ነጻ ሳይወጡ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ የተባለውን አቅም የሌለው ዓለም አቀፍ ድርጅት ተክቶ በአዲስ መልክ በ1945 ዓ.ም. የተቋቋመውን የተባበሩት መንግሥታትን ከመሰረቱት አገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት። ወጣቱ ትውልድ እንዲያስታውሰው የምፈልገው አንድ ነጥብ አፄ ኃይለ ሥላሴ በሊጉ ቀርበው ለአገራቸው ነጻነት ሲሟገቱ ታሪክ የሚያስታውሰውን ንግግራቸውን ከራሳቸው መሰረተ ሃሳብ ጨምቀው ንግግሩን ካዘጋጁት ኢትዮጵያዊያን መካከል ከፍተኛውን ቦታ የያዙት ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር አክሊሉ ኃብተወልድ ናቸው። የአጼ ኃይለ ሥላሴ አቤቱታ፤ የቀረበው ንግግርና የሰጡት ታሪካዊ ማስጠንቀቂያ ድጋፍ ባያገኝም፤ የተገኘው ትምህርት ከፍተኛ ነበር። ክቡር አቶ አክሊሉ ሊጉ ደካማ ስለሆነ ኢትዮጵያን ለፋሺስቶች ጥቃት እንዳጋለጠ ያውቁ ነበር። የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ከተካሄደ በኋላ፤ የዓለም ጦርነት ተደጋጋሚ እንዳይይሆን ከተፈለገ ወደፊት የሚቋቋመው ድርጅት የተለየ መሆን አለበት የሚል እምነት እንደነበራቸው ይጠቀሳል። በአዲስ መልክ የተቋቋመው የተባበሩት መንግሥታት ከሊጉ የተለየና ለጋራ ደህንነት (Collective Security) አስተማማኝ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት ካደረጉት መንግሥታት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነበረች። በተለይ የተባበሩት መንግሥታት አካል የሆነው የደህንነቱ አካልይ (UN Security Council) እንዲመሰረት በተደረገው ጠረት ልይ። ይኼን ታሪክ የመዘገበውን የኢትዮጵያ አስተዋፆ ስኬታማ ያደረጉት ደርግ በጭካኔ የገደላቸው ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አክሊሉ ኃብተወልድ እንደነበሩ መረጃዎች ያሳያሉ። እኒህ ከራሳቸው ጥቅምና ዝና ባሻገር ለአገራቸው ነጻነት፤ ክብር፤ ግዛታዊ አንድነት፤ ሉዐላዊነትና ዘመናዊነት ቀን ከሌት ይሰሩ የነበሩ ትሁት፤ ብሩህና አስተዋይ ኢትዮጵያዊ ለአገራቸው ያበረከቱት አስተዋፆ በዚህ የተወሰነ አልነበረም። የአገራቸውን ታሪክ ሂደት መሰረት በማድረግ የወደፊቱ ደህንነቷና ዘመናዊነቷ አስተማማኝ የሚሆነው ጣሊያኖች በመሳሪያ ኃይል ቅኝ ያደረጓት የኢትዮጵያ አካል የነበረችው ኤርትራ ወደ እናት አገሯ ስትቀላቀል ብቻ መሆኑን የተገነዘቡ መሪ ነበሩ። ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የዲፕሎማሲ እውቀትና ጥበብ አስፈላጊ መሆኑን የተገነዘቡት እኒህ የታወቀው የፈረንሳይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሶቦርን ምሩቅ፤ ታሪካቸው እና ለአገራቸው ያበረከቱት ግዙፍ አስተዋፆ በሚገባ ያልተመዘገበና እኛ ኢትዮጵያዊያን እንደ ጥሩ ምሳሌ ልንጠቅሳቸው የሚገባ አገር ወዳድ ናቸው። በእኔ ግምት፤ ሌሎች አገሮች እንዳደረጉትና እሁንም እንደሚያደርጉት የኢትዮጵያ ተከታታይ ትውልድ የእኒህን አገር ወዳድ ታሪክና ልዩ አስተዋፆ ለማስታወስ ኃውልት ቢሰራላቸው አግባብ ይኖረዋል። ኢትዮጵያ እንድትጠፋ ሆነ ተብሎ የተደረገው፤ አሁንም የሚደረገው አገር ወዳዶችን በማጥፋት ነው። ስለሆነም፤ ይህ ወንጀል በተካሄደባት ኢትዮጵያ እንደሳቸው ያሉትን ማስታወስ አግባብ አለው። ከጀርባ ሆነው፤ ሌሎችን፤ በተለይ የታባበሩት መንግሥታት አባላት አገሮችን በማሳመን ያደረጉት የተቀደሰ ተግባር ውጤት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ተመልሳ እንድትቀላቀል ማድረጋቸው ነው። ይኼን ታሪክ የመዘገበው የብዙ መቶ ሺህ ኢትዮጵያዊያን ህይወታና ንብረት የወደመበት የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት እንዲፈርስና ኢትዮጵያ ለጥቃት እንድትጋለጥ ያደረጉት ህወሓትና ሻቢያ ናቸው። ይህ ክህደት አገሪቱን ለጥቃት አጋልጧታል። የባህር በሯ ከተዘጋ በኋላ የሌሎች ጥገኛ ሆናለች። በተጨማሪ፤ ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር ያላት ግንኙነት ጠንካራ እንዲሆን ካደረጉት ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዱ ናቸው። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አዲስ አበባ ላይ እንዲቋቋም አገሪቱ ካላት የተወሰነ ኃብት ቀንሳ እንድታበረክት ማድረጓን ታሪክ ያስታውሳል። ምጣኔ ኃብቷን ተጠቅማ ለአፍሪካዊያን ነጻነት አስተዋፆ አድርጋለች።

ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ነጻነት፤ ግዛታዊ አንድነት፤ ዘላቂ ጥቅምና ሉዐላዊነት አስተማማኝ የሚሆነው ኢትዮጵያ ዘመናዊ ኢኮኖሚ ሲኖራት፤ ሕዝቧ ከድህነት፤ ከረሃብና ከጥግኝነት ራሱን ነጻ ሲያወጣ ብቻ መሆኑን የተገነዘቡ በራሳቸውና በሃገራቸው ሕዝብ እምነት የነበራቸውና የኋላውን ትምህርት አድርገው የወደፊቱን ለመቀየስ ያልተቆጠበ ጥረት ያደረጉ አስተዋይ ግለሰብ ነበሩ። የተባበሩት መንግሥታትን ለመመስረት ለተደረገው ጥረት ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ የሚጓጓዙበት የራሳቸው አየር መንገድ የላቸውም ነበር። የሚጓጓዙት በአሜሪካኖች ችሮታና አውሮፕላኖች ነበር። ይኼን ግልጽ የሆነ የእድገት ክፍተትና ተግዳሮት መቋቋም ብሄራዊ ግዴታችን ነው ብለው ያመኑት አክሊሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲቋቋም ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉበት ምክንያት ይኼው ነው። አየር መንገድ ዘላቂ ብሄራዊ ተቋም ነው፤ እንዲሁ በምኞት አይመሰረትም። የአቅም ግንባታ ያስፈልገዋል። ሜካኒኮች፤ አውሮፕላን አብራሪዎች፤ አስተናጋጆች፤ ጠጋኞች ወዘተ ያስፈልጋሉ። ለዚህ አመቻች የሆነው ከአሜሪካው ትራንስ ወርልድ አየር መንገድ ጋር የተደረገው ስምምነት ነበር። በተፈጥሯቸው አገር ወዳድና በፍጥነት ለመማር የሚችሉት ኢትዮጵያዊያን በአጭር ጊዜ አየር መንገዱ ራሱን እንዲችል አድርገዋል። ዛሬ ህወሓት በበላይነት የሚቆጣጠረውና የሚነግድበት አየር መንገድ የተቋቋመው የተባበሩት መንግሥታት ሲቋቋም ነው። ዛሬ ኢትዮጵያዊያንን ከአየር መንገዱ አገልግሎት እንዲባረሩ እያደረገ፤ የውጭ ዜጋዎችን ቀጥሮ ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፈልበት አየር መንገድ በሰው ኃይል ራሱን ከመቻል ታግቦ ጥገኛና የፖለቲካ መሳሪያ ሆኗል። አገር ተከል ተቋምና እድገት አስፈላጊ ነው የሚለውን መርህ ካስተማሩን ኢትዮጵያዊያን መካከል አክሊሉ ኃብተወልድ ከፍተኛ ቦታ ቢኖራችውም ዛሬ የሚካሄደው ጎሳዊ ፖለቲካና የተቋማት መዳከም ጥገኝነትን እያጠናከረ ነው። ጥገኝነት ኢትዮጵያዊያን የማይቀበሉት የሉዐላዊነት ጸር ነው።
እኒህን አስተዋይ፤ አገር ወዳድና ለኢትዮጵያ እውቅና ያበረከቱ ኢትዮጵያዊ በክፉ ጊዜ ያፈራቸው ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። የፖለቲካ ፓርቲ ወይንም አንድ ጎሳ አይደለም። አጋጣሚ ሆኖ ለጥቂት ደቂቃዎችም ቢሆን በ1972 በአካል አነጋግረውኝ ነበር። በአጭሩ የተማሪው እንቅስቃሴ በጦፈበት እና ተገንጣይ ኃይሎች ስር ሰደው ኢትዮጵያዊያንን እንዲከፋፈሉ ባደረጉብት ቀውጢ ቀን ከአሜሪካ ተመልሸ አገሬን ለመጎብኘትና ወላጆቸን ለመጠየቅ፤ ትዳር ለመያዝና ለዶክተሬቴ ምርምር ለማድረግ ስሄድ ቦሌ እንደደረስኩ ፖሊስ ወደ እስር ቤት ወሰደኝ። ነገሩ ሲጣራ የታሰርኩበት ምክንያት Challenge በተባለው የተማሪዎች መጽሄት በስሜ፤ ማለትም በውሸት “የኤርትራን መገንጠል” እደግፋለሁ የሚል ግዙፍ ድርሰት በራሴ ስም ተጽፎ ለመረጃ ስለደረሰ ነበር። ይኼን ድርሰት ያዘጋጁት እነማን እንደሆኑ አውቃለሁ። ተጠቃሚዎቹሻቢያናሌሎችተገንጣይኃይሎችነበሩ።“የውሸቱተግዳሮት(TheforgedChallenge)” በሚል አርእስት ማስተባበያ ጽፌ፤ ሰነዱን በእጀ ይዠ ነበር። የፖሊስ ጣቢው መሪዎች እኔን ስላላመኑኝ ጉዳዩ ለበላይ ባለሥልጣናት እንዲቀርብ ያደረጉልኝ ምንም የማላውቃቸው፤ አሁን “የነፍስ አባቴ” የሆኑት ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው መንፈሳዊ መሪዎችና አባቶች መካከል ከፍተኛ ቦታ የያዙት “አባታችን” አቡነ መልከፀዲቅ ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትሩና የደህንነት ሃላፊው ኮሎኔል ሶሎሞን ከዲር በየተራ በግል አነጋገሩኝ። ጽሁፉን እኔ እንዳልጻፍኩት፤ እንዲያውም በብሄረሰቦች የመገንጠል ጥያቄ ላይ የማያወላውል አቋም እንዳለኝ፤ ዲሞክራሳዊ ስርዓት እንዲመሰረት እንጅ መገንጠልን እንደማልደግፍ፤ የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ገዢ ጥያቄ ሳይሆን የመደብ፤ የአስተዳደር፤ የሰብአዊ መብቶች አለመከበር፤ የዲሞክራሲ አለመኖር ወዘተ ጥያቄ መሆኑን አስረዳሁ። “ካሰራችሁኝ የመሳፍንቱን አገዛዝ ተቃውመሃል ብላችሁ እሰሩኝ… በኤርትራ መገንጠል ጥያቄ ግን ልታስሩኝ አትችሉም” ብየ ተከራከርኩ። ይህ ለፖለቲካ ጥቅም የሚደረግ የውሸት ፖለቲካ ባህል አሁንም ቀጥሏል።
ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ እውቅና አግኝታ አሁንም ፌውዳል፤ ኋላ ቀርና ከሌሎች ነጻ ከሆኑ የአፍሪካ አገሮች–ጋና፤ ኬንያ፤ ናይጀሪያ ወዘተ ጋር ተመጣጣኝ እድገት የማታሳይ መሆኑን ለማሳየት ሞክሬ ነበር። የንጉሰ ነገሥቱ ስርዓት ዘመናዊ ካልሆነ አደጋው እየተባባሰ እንደሚሄድ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች፤ በተለይ ግብጾች አገሪቱ እንዳትቀጥል ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። እኔም በበኩሌ የውጭ ጠላቶች የሚገቡባቸው ቀዳዳዎች ኢትዮጵያዊያንን በመለያየትና ረቂቅ በሆነ መንገድ በመጠቀም፤ በማሳደድ ኢንዲገደሉ በማድረግ መሆኑን ተጋርተናል።
ከሁሉም በላይ ትዝ የሚለኝ ጠቅላይ ሚንስትሩ የማዳመጥ ችሎታ ያላቸው፤ በፈገግታ፤ በትህትና፤ በአስተዋይነትና የወደፊቱን በማሰብ ምክር የሚሰጡ መሆናቸው ነው። ስለራሳቸው አንድም ጉዳይ አልነገሩኝም። ጭንቀታቸው ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ ሁኔታ ነበር። “አንተና ሌሎቻችሁ፤ እኛ እንዳደረግነው ወደ አገራችሁ ተመልሳችሁ ኢትዮጵያን ማገልገል፤ ዘመናዊ ማድረግ” ወዘተ ግዴታችሁ ነው የሚል ምክር ለግሰውኝ ተሰናበትኩ። ይኼን ምክራቸውን ስራ ላይ አውየዋለሁ። ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ፊት ቀርቤ “ይቅርታ” ጠይቄ እንደምለቀቅ ቃል ገቡልኝ። “ይቅርታ” ለምን እጠይቃለሁ አላልኩም፤ ሌላ መዘዝ ላለማምጣት። የተባልኩትን አድርጌ ከእስር ቤት ተፈታሁ። ቁም ነገሩ የእኔ መታሰር አይደለም። ስንት ኢትዮጵያዊያን ታስረዋል፤ ተገድለዋል፤ ተሰደዋል። ቁም ነገሩ ስለ እኔ አይደለም፤ እኒህ አስተዋይ መሪ

የሚመጣው አደጋ የታያቸው መሆኑን ለማስታወስ ነው። See DireTube TV: The Untold Story of Aklilu Habte-Wold – NEW! Documentary. http://www.diretube.com/diretube-tv-the-untold-story-of-aklilu- habte-wold-new-documentary_d3714ad21.html
የዚህ ሃተታ መሰረት እኛ ኢትዮጵያዊያን የምንከተለው ጎሳዊ የሆነ የፖለቲካ ባህል ለኢትዮጵያ አፍራሽ መሆኑን ለማቅረብና አስቸኳይ የሆነ ብሄራዊ ውይይት እንዲካሄድ ደጋግሜ ለማሳሰብ ነው። ባለፉት አርባ ሁለት ዓመታት ከላይ በአጭሩ ያቀረብኩትን የነጻነትና የሉዐላዊነት ታሪክ እንደ ተራ ነገር እያየን አባክነነዋል። ብንቀበልም ብንክድም የእኛ መነታረክ፤ መጨቃጨቅ፤ መጠላለፍ፤ መናናቅ፤ እርስ በርስ አለመተማመን፤ ልዩነቶችን በጨዋነት ለመፍታት አለመፈለግ፤ ራስንና ቡድንን፤ ራስንና ጎሳን፤ ራስንና ኃይማኖትን፤ ራስንና ንብረትን ወዘተ ከአገር በላይ ማስቀመጥ ወዘተ አገራችን እንድታመልጠን ግብአቶች እያደረጉ ነው። ይህ የፖለቲካ ባህል በፍጥነት ካልተለወጠ አገራችን ለማደን አንችልም። ደርግና ህወሓት ካደረጓቸው ጥፋቶች መካከል የኢትዮጵያን የሰው ኃይል፤ በተለይ አገር ወዳዱንና ዲሞክራቱን እየገደሉና እያሳደዱ ማባከናቸው ነው። እንዴት? ብለን ብንጠይቅ፤ ለሃገራችን ነጻነት፤ ደህንነት፤ ሉዐላዊነትና ዘላቂነት እና ለመላው ሕዝቧ ህብረት የቆሙትን ኢትዮጵያዊያን ግለሰቦችና ተቋሞች አውድመዋል፤ እንዲከፋፈል አድርገዋል። ለምሳሌ፤ ህወሓትና ሻቢያ የሚያኮራ ታሪክና ከፍተኛ አስተዋፆ ያበረከተውን፤ የኢትዮጵያን ስብጥር ሕዝብ የወከለውን የኢትዮጵያን መከላከያ ኃይል አፍርሰዋል። በምትኩ የህወሓትን መከላከያ እዝ ተቋማዊ አድርገዋል። ይኼን የምልበት ምክንያት፤ የደርግንና የአሁኑን አገዛዞች የፖለቲካ የበላይነት እና ለይቶ የማጥቃት ታሪክ ሁኔታ ቀረብ ብሎ መመርመር ለውይይቱና ችግሩን እንዳንደግመው ስለሚረዳ ነው።
ከዚህ ላይ ለማሳሰብ የምገደደው ማንም መንግሥት ለአገር ተቆርቋሪ የሆነውን ትውልድ አጥፍቶ በጎሰኛ ትውልድ ሲተካው የአገር አስተማማኝነትን ለማጠናከርና ዘላቂነትና ተደጋጋፊነት ያለውን ዘመናዊ ሕብረተሰብ ለመመስረት አይችልም። የኢትዮጵያን የወደፊት እድል የሚወስነው ሕዝብ መሆኑ አያከራክርም። ሆኖም፤ ሕዝብ በጎሳና በኃይማኖት ከተከፋፈለ አገርን የመደገፍና አምርቶ ራሱን የመቻል አቅሙ ደካማ ይሆናል። ከደርግ አገዛዝና ራሱ ባባባሰው ድክመትና ውድቀት በኋላ እንዳየነው ከሕዝብ ዐመጽ የሚመጣ እድል የፖለቲካ ፓርቲዎችና የስልጣን ፈላጊዎች ውሳኔ ብቻ ሊሆን አይችልም። ጥንካሬና ዘላቂነት የሚኖረው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዜግነቱን መብት ተጠቅሞ ውሳኔ ለማድረግ ሲችል ነው።
ካልረባ የስልጣን ውድድር ወደ ብሄራዊ ትብብር መሸጋገር ወሳኝ ነው
ኢትዮጵያ የምትባል አገር “አለች ወይንስ የለችም?” የሚለው ጥያቄ አነጋጋሪ መሆኑ እንዴት የፖለቲካ ልሂቃንና ምሁራን ሕዝቡን በጎሳ አደራጅተው፤ ባያደራጁም የገዢውን ፓርቲ የጎሳ ፖለቲካ አጀንዳ እየተከተሉ ኢትዮጵያን ለአደጋ እንዳጋለጧት ያሳያል። ከደርግና ከአሁኑ መንግሥታት በፊት በማይታሰብ ደረጃ የኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች ጥይት ሳይተኩሱ ያገኙት እድልና ድል እንደተከሰተ መጠራጠር አይቻልም። ያለፉትን አገር ወዳዶች ከመቃብራቸው የሚቀሰቅስ ክስተት ነው። ለምን እዚህ ደረጃ ደረስን የሚለውን ጥያቄ ሳንሰላስል ባለፉት 25 ዓመታት በስርዓት ደረጃ የተካሄደውን የፖለቲካ፤ በተለይ የሕገመንግሥቱን ሂደት ማንሳት ተገቢ ሆኖ አገኘዋለሁ። ETHIOPIA’S CONSTITUTION: CAN IT STAND THE TEST OF TIME? MARCH 11, 2016 ADDISSTANDARD
በተባለው ጋዜጣ ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፤ የመጀመሪያው የኢህአዴግ ፕሬዝደንት አገር ወዳድ የሆኑ ግለሰቦችንና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን አግልሎ የተመሰረተውን ሕገመንግሥት እንዲህ ሲሉ አቅርበውታል። “ወደኋላ ዞር ብየ ስመለከተው ከፍተኛ ስህተት ያደረግነው ከዚህ ላይ ነው…ቢያንስ ቢያንስ ረቂቁን መልሰን ለሕዝቡ ማቅረብና ድምፅ እንዲሰጥበት ማድረግ ነበረብን። የሕዝቡን ተስፋና ምኞት የሚያንጸባርቅ ወይንም የማያንጸባርቅ መሆኑን መፈተሽ ነበረብን። Looking back at it today, I would say this was where the biggest mistake was committed…. we should have presented it back to the people of Ethiopia in a form of referendum where the people could have had the chance to decide on whether what we formulated was according to their wish or not. That we did not do and I believe it was a mistake.” አንድ የቀድሞም ሆነ የአሁን የአገር መሪና ታዋቂነት ያለው ግለሰብ እንደዚህ በግልጽና በድፍረት ስህተቱን ሲቀበል ዶር ነጋሶ የመጀመሪያው ሳይሆኑ አይቀሩም። በዚህ አጋጣሚ ለዶር ነጋሶ የግሌን አድናቆትና ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለኝን ተስፋ አስመርበታለሁ። ከላይ ጠቅላይ ሚንስትር አክሊሉ ኃብተወልድን የጠቀስኩበት ዋና ምክንያት በዘመነ ህወሓት/ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ መሪዎች የሌሉ መሆናቸውን ስላየሁ ነው።
ህገመንግሥቱ ጉድለት ያሳየበት ምክንያት ብዙ ቢሆንም ጥቂቶቹን ማቅረብ ተገቢ ነው። አገር ወዳድ ምሁራን፤ አባቶች፤ ባለሞያዎች፤ የቀድሞ ባለሥልጣናት፤ ሕብረ ብሄር ፓርቲዎች እንዳይሳተፉ ተደርጓል። ኢህአፓ፤ መኤሶን፤ ኢዲዩ፤

ኢሰፓ፤ የመምህራን ማህበር፤ የሰራተኞች ድርጅቶች…,The All Ethiopian Socialist Movement (AESM), the Ethiopian Workers Party (EWP), and the Ethiopian People’s Revolutionary Party (EPRP) should have participated but unfortunately they didn’t.” በወቅቱ ከፕሮፌሰር አስራት የአቤቱታ ድምጽ ውጭ ለኢትዮጵያ ሉዐላዊነትና ለመላው ሕዝቧ አንድነት የቆመ ኃይል የለም ነበር። የትግል ሜዳው የተሰጠው ለነጻነት ለቆሙት የጎሳ ቡድኖች ብቻ ሆነ። የዚህን አደጋ ቀደም ሲል ለማወቅ ይቻል ነበር። እነዚህና ሌሎች የህብረብሄር ድርጅቶች ቢሳተፉ ኖሮ ህገመንግሥቱ እንደ ጋናና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች “የኢትዮጵያ ሕዝብ” የሚል መግቢያ ይኖረው ነበር፤ አንቀጽ 39 አይታሰብም ነበር።
“የመገንጠል መብትና የመሬት ይዞታ አከራካሪ ነበሩ…በእነዚህ አበይት ጉዳዮች ላይ የተደረጉት ውሳኔዎች በሕዝብ ውይይት አይደለም፤ በሽግግሩ መንግሥትና በሚቆጣጠረው ፓርላማ ነው…The two questions that I remember vividly: the right to self-determination, which is now Article 39, and the question of land. These were very controversial even for the Commission. So what we did was put two alternative versions for each of these articles and brought the draft constitution to the Transitional Parliament. The Transitional Parliament discussed on that draft and brought it to the Constitutional Assembly for adoption.” እነዚህን አዲስ ተቋሞች ማን በጀርባ ሆኖ ይቆጣጠራቸው ነበር? ሻቢያ፤ ህወሓትና ኦነግ ናቸው። አገር ወዳዶች አገርን የሚያፈራርስ አንቀጽ ህጋዊ አድርገው “ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሄር፤ ብሄረሰብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን እስከመገንጠል ያለው መብቱ በማናቸውም መልኩ የተጠበቀ ነው” ብለው አገራቸውን ለማፈራረስ ቃል ኪዳን አይገቡም። ይኼን የሚያደርግ ቡድን ኢትዮጵያን የሚጠላ እንጅ ታሪኩን የሚቀበል አይደለም። አንቀጽ 39 (1). የመጀመሪያው ውጤት ኤርትራ ከእናት አገሯ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል አደረገ፤ እነ መለስ የፈለጉት ሆነ። በዚህ አላቆመም፤ መገንጠል መብት ነው የሚለው ወሳኝ መርህ ህጋዊ ሆነ። ያመቻቸው የኢትዮጵያን ፈራሽነት እንጅ አንድነት እና ሉዐላዊነት አይደለም።
ፈረንጆች እንደሚሉት “You reap what you sow.” አንድ ግለሰብ ወይንም ቡድን፤ ወይንም መንግሥት የዘራው ፍሬ ምን ውጤት እንደሚያስከትል አስቀድሞ ማወቅ ግዴታው ነው። የመከፋፈልን ፖለቲካና ባህል የዘራ መከፋፈልን ስኬታማ ያደርጋል። ጥላቻን የዘራ ጥላቻው ወደራሱ እንደሚመጣ አስቀድሞ ማወቅ ግዴታው ነው። የመገንጠል መብት አለ ከተባለ መገንጠል የሚፈልጉ ኃይሎችን በማባበል ሊገታቸው አይችልም። በተጻራሪው በሕዝብ መካከል የማይታረቅ ልዩነት የለም፤ መደጋገፍ የአንድ ህብረተሰብ ጥንካሬ ምልክት ነው ወዘተ የሚል መልእክትና ትምኅርት ማስተላለፍ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ያጠናክራል። ህወሓት የዘራው ፍሬ ጥላቻን፤ አለመተማመንን፤ መከፋፈልን፤ ስስታምነትን፤ ስግብግብነትን፤ ራስ ወዳድነትን፤ ቂም በቀለኛነትን፤ ዘረኛነትን ወዘተ ነው። የዘራውን ፍሬ እያመረተ ነው። ይኼን ተቋማዊ ያደረገው የአንድን ትውልድ ስነልቦናና አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ በመማረክና በመለወጥ ነው። አማራው ትግራዩን፤ ኦሮሞው አማራውንና ትግራዩን፤ አማርው ኦሮሞውንና ትግራዩን፤ ደቡቡ ኦሮሞውንና አማራውን፤ አኟኩ አማራውንና ትግራዩን ወዘተ ይጠራጠረዋል። በአገር ደረጃ ለመተባበር አስቸጋሪ የሆነው የጎሳው ባህል ጥልቀት ስለያዘ ነው። የኦሮሞው ወጣት በገፍ ሲገደል፤ ሲታሰርና እንዲሰወር ሲደረግ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ነጻነትና ሰብአዊ መብት እድል ከፍቷል። ቀደም ሲልና አሁንም፤ አማራው በየቦታው እልቂትና ውርደት ሲካሄድበት ሌላው ዝም ብሎ አይቷል። የአሁኑ መሰረታዊ ጥያቄ አንድ ነው። ይኼን ከሕዝብ እምቢተኛነት እድል ወደ አገር አቀፍ ሕዝብዊ ዐመጽ ለመለወጥ ምን ጎደለን? የሚለው ነው።
የሕገመንግሥቱ ችግር የመገንጠሉ መብት አንቀጽ ብቻ አይደለም። በተመሳስይም ባይሆን በአፍራሽነቱ ማህበራዊ ግንኙነቶችን፤ ተቻችሎ መኖርን፤ ተደጋጋፊነትን፤ ሰጥቶ መቀበልን ወደጎን ትቶ “ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሄር፤ ብሄረሰብ ራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለው” የሚለው አንቀጽ 39 (3)ን ያጠናከረው የተገንጣይነትንና ያለመቻቻል ፖለቲካን ነው። ራስን በራስ ማስተዳደር ዲሞክራሳዊ መሆኑን እቀበላለሁ። ሆኖም ሚዛናዊ ያልሆነ ራስን በራስ ማስተዳደር ማለት ከመሳፍንት ዘመን በምንም አይለይም። ይህ አንቀጽ በጎሳ መሪዎች ሲተረጎም ማንኛውም የተፈጥሮ ኃብት “የእኛ እንጅ” (ክልል) የሌለው ኢትዮጵያዊ ሊሆን አይችልም የሚል አስጊ የሆነ ውድድርን አስከትሏል። የብሄረሰብ ማጽዳት ቀላል የሆነበት መሰረት ህገመንግሥቱ ነው። ባይሆን ኖሮ አንቀጽ 32 “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሕጋዊ መንገድ በመረጠው የሃገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቤት የመስራት ነጻነት” አለው የሚለው ሕግ ያለምንም ገደብ ስራ ላይ ይውል ነበር፤ አልዋለም። ከማንነት ጋር እንዲያያዝ የተደረገው የመሬትና ሌላ የተፈጥሮ ኃብት ይገባኛልነት በሕገመንግሥቱም መግቢያ ላይ ተሰምሮበታል። “እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦች፤ ሕዝቦች” ብሎ ጀምሮ “የራሳችንን እድል በራሳችን የመወሰን መብታችንን ተጠቅመን፤ በነጻ ፍላጎታችን፤ በሕግ የበላይነት እና በራሳችን ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ መስርተናል” ይላል። “ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ መስርተናል”

ሲባል የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ዘጋ፤ በዜግነቱ ብቻ ተቀብለናል ማለት ነው ወይንስ ሌላ? የሕግ የበላይነትን ስራ ላይ የሚውለው ማነውና ለማን?
“ አንድ ማህበረሰብ” ሲባል ማንን ያካትታል፤ ማንን ለማግለል ያስችላል፤ ይኼንን ማን ይወስናል? ብለን ብንጠይቅ የሚወስኑት ሕገመንግሥቱን የመሰረቱት የጎሳ ልሂቃንና ተተኪዎቻቸው ይሆናሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ አይደለም። ለምሳሌ፤ አኟክ ያልሆነው ኢትዮጵያዊ በጋምቤላ ለመኖር የሚችለው ህወሓቶችና የህወሓት ደጋፊ የጎሳ ልሂቃን ሲፈቅዱ ብቻ ነው። ቁጥራቸው በቅጡ ባይታወቅም ብዙ ሚሊየን ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን በኦሮምያ ይኖራሉ። እነዚህ ሰብአዊ መብት አላቸው። እንደ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸው መብታቸው ምንድን ነው እና ምን ዋስትና አላቸው? በደቡብ ክልሎች የሚኖሩ የትግራይ፤ የጉራጌ የአፋር፤ የኦጋዴን ሶማሌ፤ የአማራ ወዘተ ብሄር አባላት ምን ህገመንግሥታዊ መብት አላቸው? በእነዚህ ክልሎች የሚኖሩ “የውጭ” ተወላጆች (ከጎሳው ውጭ) የመምረጥና የመመረጥ መብት አላቸው ወይንስ የላቸውም? ራስን በራስ ማስተዳደር ማለት ሌላውን ማግለል፤ ሌላውን ከቀዩ ማባረር፤ የሌላውን መብት ማፈን፤ ሌላውን መግደል ሊሆን አይችልም። ይህ ጸረ ሕዝብና ጸረ ዲሞክራሲ ነው። የጎሳ ልሂቃን ይኼን ለመቀበል ችግር ሆኖባቸዋል። “ወደቀድሞው ስርዓት አትውሰዱን” የሚሉም አሉ። በእኔ ግምት ወደ አፄውም ሆነ ወደ ደርግ ስርዓት እንመለስ የሚል ግለሰብ ወይንም ቡድን የለም። ይኼን በማስረጃ የልተደገፈ የፈጠራ ወሬ ሆነ ብለው የሚያስተጋቡት ህወሓቶችና አጋሮቻቸው ናቸው። ያነጋገርና የአቀራረብ ግድፈት ካልሆነ በስተቀር፤ እኔ እስከማውቀው ድረስ በህበረብሄር ፖለቲካ ውድድር የሚያምኑ ግለሰቦችና ስብስቦች ወደ ኋላዎቹ አገዛዞች እንመለስ የሚሉ ፈልጌ አላገኘሁ።
በአጭሩ ግን “የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦች፤ ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉዐላዊ ስልጣን (Sovereign Power) ባለቤቶች ናቸው” የሚለው አንቀጽ 8 ያጠናከረው መገንጠልንና በጎሳ መለያየትን ነው። መገንጠልንም ባይሆን ልክ የደቡብ አፍሪካን የሚመስል አፓርታይድ ወይንም መለያየትን ነው። የጎሳ ክልሎች “የኢትዮጵያ ሉዐላዊ ስልጣን ባለቤቶች” ስለሆኑ የተለያዩ አገሮች ተፈጥረዋል ወይንም እንዲፈጠሩ ተደርጓል:: ልክ እንደ ደቡብ ሱዳንና ኬንያ ጎረቤት አገሮች እየተመሰረቱ ነው። ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መብቶች መከበር አንጻር ብናየው እነዚህ “ሉዐላዊነታቻው” በህገመንግሥቱ የጸደቀላቸው ክልሎች ሌላውን ለማገልል፤ ለማባረር ቢችሉ አያስገርምም። ራስን በራስ በማስተዳደር ብሂል የሞተው፤ ከኃብቱ የተፈናቀለውና የተሰደደው ሕዝብ ብዛት ግዙፍ ነው። የመሳሪያ አቅም ያላቸው የሌላውን መሬት ቢነጥቁ አያስደንቅም። ህወሓት የሚከተለው የከፋፍለህ ግዛው፤ በተለይ የማንነት ፖለቲካው ድንበርና ገደብ የሌለው ሆኗል። ሌላው ቀርቶ አማራውን ከአማራው ለመከፋፈልና ለማዳከም ልዩ ዞኖች ተፈጥረዋል። ኦሮሞውን ከኦሮሞው ለመለየያት ተመሳሳይ ሁኔታ ቢፈጠር ምን ያስደንቃል።
የዚህ ውጤት ምን ይሆናል?
ዶር ነጋሶ ያሉት አግባብ አለው። “እኔ የምፈራው ህገመንግሥቱ አሁን ( የእኔ ነጥብ) ካልተሻሻለ አገሪቱን በአንድነት የሚያቆያት ነገር፤ ተቋም ( የእኔ ነጥብ) የለም…ሁኔታዎች ከእጃችን ውጭ ይወጣሉ፤ አገሪቱ ለአደጋ ትጋለጣለች፤ አንድ ነገር መደረግ አለበት… I fear if something is not done this constitution will not hold the country together; people will eventually ask why we should have this constitution. If things are not improved, I fear the controversies will get out of hand and eventually put the country’s unity in danger. Something has to be done.” ከላይ እንዳልኩት፤ ከጅምሩ ኢትዮጵያ አስተማማኝ መከላከያ ኃይል እንዳይኖራት ሻቢና ህወሓት በትነውታል። የአንድ አናሳ ብሄር የበላይ እዝ አስተማማኝ የሆነ ውጤት ሊያስገኝ አይችልም።
ማንኛውም አገር ዘላቂነት የሚኖረው ተቆርቋሪ ትውልድ ለማፍራት ሲችል ነው። በደርግ አገዛዝ የተወለደው፤ ወጣት የነበረውና ህወሓት/ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ በኋላ የተወለድውና የተማረው ወጣት ትውልድ ኢትዮጵያን እንዳያውቅ ተደርጓል። የአሁኑ ገዢ ፓርቲ ያስተማረው የአገሪቱን ረጂም ታሪክ፤ የሕዝቧን ተቻችሎ መኖር አይደለም። የጎሳ ፖለቲካን፤ ማንነትንና ክልላዊነትን ነው። ማንነት ብዙ ትርጉም እንዳለው ከዚህ በፊት ባቀርብኳቸው ሃተታዎች አሳይቻለሁ። የአንድን ግለስብ ወይንም ጎሳ ማንነት መቀበል የሁላችንም ግዴታ ነው። የተለያዩ ዜጎች በሚኖሩበት አገር ማንነት ትርጉምና ዘላቂነት የሚኖረው አንዱ የሌላውን ሰብእነት ሲቀበልና ሲያከብር ነው። ይኼ ተቀባይነት እንዳይኖረው የምናደርገው ራሳችን ነን። የራሳችን አመለካከት ካልተለወጠ ችግሩ ይባባሳል።
የአሁኑን የጎሳ ህገመንግሥት አደጋ ብዙ ምሁራንና ባለሞያዎች ተችተውታል። ከእነዚህ መካከል ጆን አቢንክ ያቀረበውን ጥናት እጋራለሁ። እንዲህ ይላል “In contemporary Ethiopia thé discourse of ethnicity has become strongly politicized, more so than ever before, and has created “realities” which did not

previously exist. Few of the parties concerned (libération movements which emerged largely in the 1970s and largely “mono-ethnic” political parties dating from the early 1990s) fully realize the artificial aspect of the matter or the implications of their aspirations, especially when they are cast in the inevitable and ubiquitous idiom of “national self-détermination”. Neither do they recognize the fact that Ethiopian government discourse on ethnicity, and its political government —be established. በአሁኗ ኢትዮጵያ ስለ ብሄረሰብ የሚነገረው ሁሉ ፖለቲካዊ ሆኗል፤ ከመቸውም በበለጠ ደረጃ አዲስ ሃቆችን ፈጥሯል። በ70ዎቹ የተመሰረቱት የብሄር ነጻ አውጭ ግንባሮችና በ1990ዎቹ የተቋቋሙት የብሄር ፖለቲካ ፓርቲዎች የፈጠሩት ሰው ሰራሽ የፖለቲካ ባህልና የራስን እድል በራስ የመወሰን ሕጋዊ መብት የሚያስከትለውን አደጋ በሚገባ አላወቁትም። የኢትዮጵያ መንግሥትም የተከተለውና ስራ ላይ ያዋለው መርህና ተቋም የአገሪቱን የወደፊት እድል ወደየት እንደሚያመራ አላጤነውም” ይልና በዚህ ይደመድማል።
“The issue of recognizing ethnic diversity in a polyethnic polity like Ethiopia deserves much attention. The present government has made a serious effort, although its societal and institutional basis for constitution-making, and for decision-making in general has been slim. There is no going back to a unitary state structure in Ethiopia which denies ethnoregional différences and rights, or which Iets one group dominate the state. The formula of ethnicization (although in a different, more effective, fédéral form) should perhaps be encouraged if, first, it is generally interpreted and implemented as libération and democratization; secondly, it is sustained also in the domain of respecting individual human rights within the ethno-regions; thirdly, it works in the economie domain: and finally, it is a tendency and a frame of mind accepted by the “rural masses”, the majority. If, however, all this does not happen and if the ethnic emphasis combined with economie problems would instead lead to ethnocentrism, regional economie disparities and a reproduction of inequalities on the intermediate level of the new ethno-regional states, then one wonders what is new, and whether the Ethiopian people have won anything yet by the constitutional récognition of their being ethnically separate.” JON ABBINK, Journal of African Law, 41: 159-174 ETHNICITY AND CONSTITUTIONALISM IN CONTEMPORARY ETHIOPIA.
በአጭሩ “ኢትዮጵያ ወደኋላ መመለስ አትችልም….የብሄረሰብ ፖለቲካ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ እስከሆነ ድረስ አግባብ አለው። ይኼም መደገፍ ያለበት በሁሉም ክልሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ግለሰቦች ሰብአዊ መብት በሕግ ሲከበር ነው፤ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የኢኮኖሚ መብትና ተሳትፎ ሲከበር ነው፤ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ተስማምቶ ሲቀበለው ነው… ይኼ ካልሆነና የጎሳ ፖለቲካው ትኩረት ከኢኮኖሚው ችግሮች ጋር (ለምሳሌ ድህነት፤ ረሃብ፤ ስራ አጥነት)፤ በሕዝቦችና በክልሎች መካከል ከሚታየው የተዛባ እድገትና በዜጎች መካከል ከተከሰተው (የሚዘገንን) የገቢና የኑሮ ልዩነት ጋር ተደማምሮ ከቀጠለ እኔ የምደመድመው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ አገዛዝ ያገኘው አዲስ ጥቅም የለም” የሚል ነው። የህገመንግሥቱ ተጠቃሚዎች የህወሓት የበላዮች፤ ቤተሰቦችና አጋሮች መሆናችው በብዙ ማስረጃ ቀርቧል። ደራሲው እንደሚለው የጎሳው ፖለቲካ ፍትሃዊና ዲሞክራሳዊ አይደለም፤ ለሁሉም ዜጎች፤ ብሄሮች ጥቅም አላገለገለም።
ለማጠቃለል ዛሬ ያለው አደገኛ የፖለቲካ ቀውስ ከልዩ ልዩ አቅጣጫዎች በፉክክርና ውድድር ይንጸባረቃል፤
 የፖለቲካ ስልጣን ሽሚያና ውድድር
 የመገንጠል መብት ውድድር
 የተፈጥሮ ኃብት ባለቤትነትና ማንነት ውድድር
 የውጭ ኃይሎች የበላይነት ውድድር
 የኃይማኖት የበላይነት ውድድር (ሳውዲዎች፤ ካታሪዎች፤ ኢራኖች፤ ፓኪስታኖች፤ ግብጾች ወዘተ)
 የምሁራንና ልሂቃን ግለሰባዊነትና ቡድናዊነት ውድድር
 የሕብረብሄር ድርጅቶች ድክመት፤ መከፋፈል፤ መጠላለፍና አለመተማመን ወዘተ

ይህ በአገር ብሄራዊ ልእልናና በሕዝብ እኩልነትና የፖለቲካ የበላይነት ላይ ትኩረት ያልሰጠ ውድድር ለገዢው ፓርቲ ድጋፍ እየሰጠ ህልውናውን አራዝሞታል። ህወሓት፤ ኢህአዴግን ከማውገዝና ከመቃወም ባሻገር ለኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ አማራጭ አልተፈጠረም። ያም ሆነ ይህ ከፊታችን ላይ የተደቀነው ተግዳሮት አገሪቱን ተባብሮ ከመፈራረስ ማዳንና ሽግግሩን ማመመቻቸት ነው። አገርን ማዳን ስል በኢህአዴግ ውስጥ የተሰበሰቡትንም ኢትዮጵያዊያን ያካትታል።
ለማጠቃለል፤ የመንግሥትና ተቃዋሚ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ስብስቦችና ግለሰቦች በመግባባትና በአንድነት አገሪቱን ከጥፋት ማዳን የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው። በመግቢያው እንዳሳሰብኩት፤ የጣሊያን ወረራ ሆነ ሌላ ብሄራዊ ተግዳሮት ያስተማረን አገር ከሌለ የእርስ በርስ ግጭት፤ ባርነት፤ ጥገኝነት፤ ኋላ ቀርነት፤ ረሃብና ድህነት የሚቀጥል መሆኑን ነው። ኢትዮጵያ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሚሆን መሬት አላት። የጠፋው አብሮና ተከባብሮ የመኖር የፖለቲካ ባህሪና ለአገር ተቆርቋሪ የሆነ ዲሚክራሳዊ መንግሥትና አመራር ነው። ኢትዮጵያ አለች ወይ? የሚለው ጥያቄ የሚያመራን ተቆርቋሪ መንግሥት፤ መሪዎችና ተቃዋሚ ክፍሎች የሉም ወደሚለው ድምዳሜ ነው። ስለሆነም፤ ለሕዝብ የስልጣን የበላይነት፤ ለፍትህ፤ ለእውነተኛ የሕዝብ እኩልነት፤ ለዲሞክራሲ ምስረታ አብሮና ተባብሮ መቆም ወሳኝ ነው።
ዞር ብለን ማየት ያለብን አንድ ክስተት አለ። ይኼውም ሁሉም እንተባበር፤ አብረን እንስራ ወዘተ ሲል አርባ ዓመታት አልፈዋል። ለመተባበር በሚል እምነት ተወያይተን መለያየት የፖለቲካ ልማዳችን ሆኗል። የጎደለው ክፍተት ዲስኩሩን ተግባራዊ ከማድረጉ ላይ ነው።
በመጨረሻ፤ ኢትዮጵያ ከሌለች የምናወራው ፌዝ ይመስላል። ከማፌዝ በላይ ለመሄድ ከተፈለገ መጀመሪያ አገሪቱን ተባብሮ ከጥፋት አድኖ እነዚህ መርሆዎችና እሴትቾ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆኑ የተለያዩ አመለካከቶችንና አማራጮችን ማስተናገድ ግዴታ ነው። እንደገና ከተለመደው የፍክክር ባህል መጥቀን ወጥተን የጋራ አገራችን ከመፈራረስ አድንነን ወደሚቀጥለው የማይቀርና ወሳኝ ወደሆነው አገር አቀፍና የተቀነባበረ ሕዝባዊ፤ ዲሞክራሳዊ ትግል እንሸጋገር እላለሁ።

ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ድንገተኛ ተቃዉሞ አደረጉ – BBN Radio

0
0

ፍርሃትን እምቢኝ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች በአዲስ አበባ ዉስጥ በሚገኘዉ የሜክሲኮ ተዉፊቅ መስጊድ ድንገተኛ ተቃዉሞ አድርገዋል። ተሳታፊዎቹ ተቃዉሞዉን ምንም የፖሊስ ትንኮሳ የነበረበት እንደነበረ ቢያስረዱም የተሳካ እንደነበር ይገልጻሉ።በፖሊስና በሰልፈኞቹ መካከል ግጭት ተነስቶ ድንጋይ ዉርወራ እንደነበር የሚያስረዱት ወጣቶች የአሚሮቻችን (የመሪዎቻችንን)ትእዛዝ ለመተግበር ብቻ ቢሆን እንጂ የጨቋኞችን እርግጫ ፈርተን አይደለም ሰላማዊ ትግልን የመረጥነዉ ይላሉ።

 

BBN

 

ስለ ተመስገን ለምን እንደምፅፍ |ከታሪኩ ደሳለኝ

0
0

Temesgen Desalegn behindbar

ተመስገን እስካሁን የታሰረባቸውን 1 ዓመት ከ5 ወር ከ14 ቀንናት በንግልት ውስጥ አሳላፏል። እያሳለፈም ነው። በነዚህ ግዚያት ውስጥ መንግስት ሲያሻው ቤተሰብም ሆነ ወዳጅ እንዳይጠይቀው ሲል ሲፈልግ ከቤተሰብ ውጪ ማንም እንዳያየው ሲል ሲያሰኝው ደግሞ ተመስገን አአስሮ ብቻ ማስቀመጤ ስላላረካኝ በማለት እንዴ ጭለማ ቤት አንድ ግዜ ቅጣት ቤት አንድ ግዜ አደገኛ የእስር ክፍል የሚለው ውስጥ ሲያንገላታው ከርሟል። እየከረመም ነው። እንዲሁም የጀርባ፣ የወገብና የጆሮ ህመሙ ምንም ያህል ቢያሰቀይህ እንድትታከም አላደርግህም በማለት ትእቢቱን አሳይቷል እያሳየም ነው። ደግሞም ምንም አይነት መፅሀፍ አታነብም፣ ከማንም እስረኛ ጋርም አትነጋገርም በማለት የእሰር ቤት አለቃነቱን አሳይቷል እያሳየም ነው። ለተመስገን አልተኛም ያለው መንግስት ከየካቲት 9/2008ዓም ጀምሮ ለ 40 እስረኛ ይበቃኛል ብሎ በሰራው የእስር ክፍል ውስጥ 167ተኛ አድርጎ ተመስገን አጎሮታል። በዚህ ክፍል አልጋ የለም፣ የአምሮ ህመምተኞች ይገኛሉ፣በተደጋጋሚ በመንግስት የሚመሩ ፀበኛ እስረኞች ይኖራሉ። በዚህ የሰር ክፍል ውስጥ በአሁን ሰዓት ተመስገን በቀን 1 ግዜ እንኳን የመፀዳጃ ቤትና የውሃ አገልግሎት አያገኝም። ተመስገን ከታሰረበት ቀን አንስቷ እስካሁን ድረስ ይህ ሁሉ ሲሆን ለአንድ ሰከንድም እንኳን እንዲህ ሆኛለሁ እንዲህ ተደርጌለሁ ይህ እየተፈፀመብኝ ነው ብሎ ነገሮኛ አያውቅም። ይህ የሱ ባሀሪ አይደለምና። እኔ ግን ህመሙን አይቻለሁ፣ እንግልቱን ሰምቻለሁ ፣ በደሎቹን ታዝቤለሁ አረጋግጫለሁም። ተሜ እንዲዚህ እየሆንክ ነው እለዋለሁ ሳቅ ብሎ ዝም ይለኛል ድጋሜ እጠይቀዋለሁ ያኔ አገጩን እየዳበሰ ፈግግታው ከፊቱ ሳይጠፋ አሻግሮ ይመለከታል። ምን አንደሚያስብ አስባለሁ ምንድን ነው የምታስበው ግን ብዬው አላውቅም። ግን እርግጠኛ ነኝ “ለምን ይህ ሁሉ ሆነብኝ ብሎ እንደማያስብ” ህልሙ ሁሉ ሀገሩ ለሆነው ተሜ ለምን በሎ በሆነው ሁሉ ይቆጫል? ስለ ምንስ ይከፋል? የሆነውም የሚሆነውም ለተሜ ከሀገሩ በታች እና በታች ነው።
እንግዲህ የተመስገን ነገር ይህ ነው።
temesgen desalegn

አንዳንዶች በመልዕክተና በአካል ተመስገን የፈታ ፣ ተመስገን ተንገላታ ፣ተመስገን ታመመ፣ ተመስገንን መጠየቅ ተከለከልን፣ ተመስገን ጨለማ ቤት ገባ ተመስገን እንዲህ እንዲህ ሆነ አትበል መክኒያቱም ተመስገን ለሀገሩ ሲል ነው የታሰረው ተመስገን አሁን ላላቸው ኢትዮጲያ በቻ ሳይሆን የወደ ፊቷን ኢትዮጵያ ለሁላችንም እንድትሆን ያሳየ ያሳሰበ የመለከተ ነው፣ ተመስገን ያሰበውን የኖረ ነው፣ ኢትዮጲያዊነትን ዳግም የቀሰቀሰ ነው። ድግሞስ ለሀገሬ ስለ ጉዞዬ ቀራኒዮ ድረስ ነው ማለቱስ ቀደሞ ለሀገሩ ለመሰዋት ያተዘጋጀ መሆኑን ያሳያል ስዚህ ነው ስለ ተመስገን እንደዚህ አትበል የምንልህ ይሉኛል።

ልክ ናችሁ። ትክክል መሆናቹህንም እመሰክራለሁ። በንግግሮቻቹ ሁሉ እስማማለው። በተመስገንም እኮራሁ እለቸዋለሁ።
yetemesgen enat
ግን ተመስገን ለደካማዋ እናታቸን ልጇ የዓይኗ መርፊያዋ ጧሪዋ ነው ለኔ አባትም ወንድሜን ነው። ታዲያ ወንድሜ ታሞል ግን ህክምና ተከልክሏል፣ ወንድሜ ጭለማ ቤት ነው፣ ወንድሜን አንድትጠይቅ ተበልኩኝ እንዲህ ሆነ እንዲህ ተደረገ የምለው ለኔ የወንድሜ ጉዳይ ሆኖብኝ ለናቴ ደግሞ የልጃ ነገር ሆኖባት ነው እንጂ የተመስገን ጀግንነት በኛ እሮሮ ለመሸፈን አይደለም። የሆነው ሁሉ ቢሆንም ግን ዛሬ “ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የታሰረችውን ሀገሩን ለማስፈታት ታስሯል”

የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እገዳ በፓትርያርኩ ትእዛዝ ተነሳ

0
0

ዛሬ በኢትዮጵያ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ለልጃቸው ሕክምና ችየገንዘብ ርዳታ የወሰኑላቸውን የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳም 10 የአስተዳደር ኮሚቴ አባላትን  ከሥራና ከደሞዝ ያገዱ ቢሆንም ፓትርያርኩ እግዱን ሽረውታል፡፡ ሥራ አስኪያጁ፣ “ለታማሚ ልጃቸው ማሳከሚያ” በሚል ገንዘብ በማሠባሰብ ላይ እንደነበሩ መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን፤ ከእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ገዳም ብቻ ግማሽ ሚሊዮን ብር በገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ እንዲሰጣቸው ቢወስንም፤ የገዳሙ ሒሳብ ሹም ክፍያውን አልፈጽምም በማለታቸው ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር ይታወቃል፡፡

abune-matyas

ከትላንት በስቲያ በሥራ አስኪያጁ እግድ ተላልፎባቸው ከነበሩት የአስተዳደር ኮሚቴ አባላት አንዱ፣ ሥራ አስኪያጁ በፅ/ቤታቸው ጠርተዋቸው ሁሉንም የአስተዳደር አካላት “ስሜን ለማስጠፋት ሆን ብላችሁ ሳላዛችሁ የሰራችሁት ነው፤” በሚል ቃለ ጉባኤውን በቃለ ጉባኤ ካልሻራችሁ፤” በሚል ሁሉንም ማገዳቸውን እንዳሳወቋቸው ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ “ሥራ አስኪያጁ እገዳውን ካስተላለፉብን በኋላ የታገድንበትን ደብዳቤና የገንዘብ ርዳታውን የወሰንበትን ቃለ ጉባኤ ይዘን ቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር በመግባት አስረዳናቸው፤” ያሉት የአስተዳደር ኮሚቴው አባላት፤ በሌሎች አድባራትና ገዳማት እንደተደረገው ሁሉ እርዳታውን የሰጡት ለዚሁ ዓላማ ተዋቅሮ በተላከ ኮሚቴ በተጠየቁት መሠረት መሆኑን ለፓትርያርኩ ማሳወቃቸውን  ገልጸዋል፡፡

 

አቤቱታውን ያዳመጡት ፓትርያርኩ፤ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅና የገንዘብ ርዳታ የወሰኑትን አቤቱታ አቅራቢዎች ገሥጸው፣ የሥራ አስኪያጁን እገዳ በማንሳት የገዳሙ የአስተዳደር ኮሚቴ  አባላት ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በላኩት ደብዳቤ ማዘዛቸው
ታውቋል፡፡

ሕወሓቶች ገዱ አንዳርጋቸውን አንገቱን ለማስደፋት ዘምተዋል |“ግንቦት 7 ነው…የአንዳርጋቸውን ራዕይ እያስፈጸመ ነው”እያሉ እየወነጀሉት ነው

0
0
የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ወልቃይትን ጨምሮ በአማራ ክልል እየተነሱ ያሉትን የመብት ጥያቄዎች ተከትሎ ሕወሓቶች “ገዱ አማራውን በትግራይ ሕዝብ ላይ እያስነሳው ነው” የሚሉ ዘመቻዎችን መክፈታቸው ታወቀ:: ይህም ዘመቻዎች የአማራ ክልል ር ዕሰ መስተዳደርን አንገት ለማስደፋት የታቀደ ሲሆን ዘመቻው በድርጅቱ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሶሻል ሚድያዎችም ጭምር ተጀምሯል:: ከሕወሓቱ አባይ ወልዱ ጽህፈት ቤት በወጣ ትዕዛዝ የወልቃይትን እና ሌሎች የአማራ ሕዝብን ጥያቄ ተከትሎ በገዱ አንዳርጋቸው ላይ እየተሠራጩ ካሉት ጽሁፎች መካከል አንዱ የሚከተለው ነው:: ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ያንብቡት::

የገዱ ነገር፤
—————————-
-ገዱን ሳስበው በገዱ አንዳርጋው ፅጌ መታሰር ውስጡ ብግን እርር ድብን ያለ ዓይነት ሰው ይመስለኛል፡፡
የገዱን የባለፉት ሁለት ዓመታት ድርጊቶች መለስ ብሎ ላስታወሰ፤
-አንደኛ፤ የምዕራብ ትግራይ አካበቢዎችን የሃሰት አማራ ማንነት ኮሚቴ በስውር አደራጅቶና ረድቶ ለፌደሬሽን ም/ቤት አብቅቶዋል፡፡
-ሁለተኛ፤የቅማንትን ህዝብ መብት ለማፈን ባደረገው ጥረት ህዝብን በወታደሮቹ እስከማስጨፍጨፍ ደርሶዋል፡፡
-ሶስተኛ፤ በአሁኑ ግዜ ደግሞ በትግራይ ተመርተው በትግራይ ልጆች በአመራ ክልል የሚከፋፈሉ ምርቶች ላይ የተለያዪ ችግሮች በመፍጠር ላይ ነው፡፡
-አራተኛ በክልሉ የሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች መጠርያዎችን በክልሉ ም/ቤት እያስፀደቀ በማስቀየር ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ መተማ ዪሃንስን ወደ መተማ…በአማራ ክልል ያለውን የፀገዴ ክፍልን ወደ ጠገዴ፣ፀለምቲን ወደ ጨለምት አንዳንዴ ደግሞ ወደ ጠለምት ወዘተ፡፡

በተለይ ከላይ ከተገለጡት ውስጥ እጅግ በጣም አሳሳቢዊ ጉዳይ ደግሞ ገዱ በሚመራው ክልል በተለይ በአርማጭሆና ሌሎች አካባቢዎች የግንቦት ሰባት ሃይሎች እንደፈለጉ የሚፈነጩበት በተለይ በአካባቢው የትግራይ ነዋሪዎች ላይ የተለያዪ ጥቃቶችን የሚፈፅሙበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
ይህ ነገር በትልቁ አንድ ነገር እንድናስታውስ ያስገድደናል፤ ይሀውም የአሸባሪው ግንቦት 7 መሪ ብርሃኑ ነጋ ትግላችን ወደ አገር ውስጥ ገብቶዋል ያሉበትን አጋጣሚ፡፡
እንግዲህ የብርሃኑ ነጋን አነጋገር ልብ ላለው ሰው የገዱ ክልሉን ያለመጠበቅ ጉዳይን ለምን ብሎ መጠየቅ አለበት፡፡

በበኩሌ አንዳርጋቸው ፅጌ የታሰረው በአካል እንጂ በዓላማና በመንፈስ ግን እነ ገዱ በእልህ ራዕዪን እያስቀጠሉ ያሉበት ሁኔታ በተግባር እያየን ነው፡፡

እስኪ ራሳችሁን ጠይቁ፤ አንዳርጋቸው ፅጌ ባይታሰር ኑሮ አሁን በአማራ ክልል ከምናየው ሁኔታ የተለየ ምን ይፈጥር ነበር! መልሱ ምንም ነው፡፡ ግንቦት በአማራ ክልል ምዕራባዊና ሰሜናዊ አከባቢዎች ሽፍቶችን አሰማርቶ የሰላማዊ የሰዎችን ሰላምና ልማት ማወክ የጀመረው በምን ምክንያት ነው፡፡
እንግዲህ ኢህአዴግ ውስጡን ማየት ያለበት እንዚህ ከላይ የተገለጡት ሌሎችንም ክስተቶች በማገናዘብ መሆን አለበት፡፡
በበኩሌ የግንቦት 7 ትግል የገባው አማራ ክልል ብቻ አይደለም ቤተ-መንግስት ጭምር እንጂ!
ኢህአዴግ ውስጡን ከትምክህተኞችና የምኒሊክ ዙፋን አስመላሾች ያፅዳ!
(አንዳርጋቸው ጽጌስ ከዚህ በላይ ምን ያደርግ ነበር…..ምንም!)


የሄነከን ቢራ ዘረፋ ምስጢር በኢትዮጵያ ሲጋለጥ –ክንፉ አሰፋ

0
0

Kinfu Asefaየሆላንድ ዜምብላ[1] ጋዜጠኞች የኦሮሞ ጸሃፊው የሆነውን ያሶ ካባባን ይዘው ወደ ጊንጪ ያመራሉ። እግረመንገድ ላይ  የሚያገኟቸው ገበሬዎችም ሲጠይቋቸው በምስሉ ይታያል።  እነዚያ በቀያቸው ማረፍያ እንኳን የሌላቸው ገበሬዎች የጋዜጠኞቹን መኪና ከብበው እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ።  “መሬታችንን ቀምተው ለነጮች ሰጡብን። እኛንም በታተኑን…”

በገዛ ቀያቸው ስደተኛ የሆኑ እነዚህ ወገኖቻቸን ሰቆቃቸው የከፋ ነበር። በመጨረሻ ተሰባሰቡና መከሩ።  ሰባት ሺህ የሚሆኑ የጊንጪ ተወላጆች ሆ! ብለው ወጥተው ይህንን የሁለት ሚሊዮን ዩሮ (ሃምሳ ሚልዮን ብር) ንብረት በሰኮንዶች ውስጥ አወደሙት። ምስላቸውን ለካሜራ ሳይደብቁ፣ ስሜታቸውን እና የወደፊት እቅዳቸውን ይናገራሉ። “ከአንባገነን መንግስት ጋር አብሮ ከመስራት ይልቅ የአካባቢው ነዋሪዎች ሊጠቀሙ በሚችሉበት መንገድ መስራት እንደሚችሉም።” ለፈረንጆቹ ይመክራሉ። “ይህ ካልሆነ ግን ማውደሙን እንቀጥልበታለን!” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።  ይህ ማስጠንቀቅያ  ግዙፉ አለም አቀፍ ኩባንያ የሆነው ሄነከን ቢራንም ይመለከታል።

ባለፈው ሳምንት በሆላንድ ብሄራዊ ቴለቭዥን የተላለፈው ዜምብላ ፕሮግራም የሚሊዮኖችን ቀልብ ስቧል። ለዚህም ምክንያቶች አሉት። አንደኛው ምክንያት፤ የዜምብላ ፕሮግራም በምርመራ ጋዜጠኞች የሚሰራ በመሆኑ እጅግ የሚፈራ እና በሃገሪቱ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳደሩ ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ በኢትዮጵያ እየወደመ ያለው ይህ ንብረት የተቋቋመው በሆላንድ መንግስት ድጎማ ሲሆን፣  ይህ ደግሞ የእያንዳንዱ ሆላንዳዊ ግብር ከፋይ ገንዘብ በመሆኑ ነው።

b3bf67fb-a059-4244-9e16-d0395498d386የሆላንድ የልማትና ትብብር ሚንስተር ለድሃ ሀገሮች እርዳታ ከመለገስ ይልቅ ወደ ንግድ ድጎማ ፊቱን ባዞረ ግዜ፣ 130 አትራፊ የንግድ ድርጅቶች ድጎማ እየተቀበሉ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።  ከነዚህ ውስጥ ትልቁን የድጎማ ድርሻ የወሰደው ሄነከን ቢራ ነው። ሄነከን ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ  የሆላንድ መንግስት አንድ ቢሊየን ዩሮ ድጎማ አድርጓል። እንደ ሆላንድ መንግስት እሳቤ፣  ይህንን የልማት ትብብር ገንዘብ በእርዳታ መልክ ከመስጠት ይልቅ ይህንን አትራፊ ተቋም አበራትቶ ስራ በመፍጠር እና በንግድና በስራ ታክስ ሃገሪቱ ተጠቃሚ እንድትሆን ማድረግ ነበር።  የሆነው ግን በተቃራኒ ነው።

የዜምብላ ቴሌቭዥን ዘገባ ያጋለጠው ጉዳይ በእጅጉ ያስደምማል። እንዲህ ነው የሆነው። እ.ኤ.አ. በ 2011 ሄነከን ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ የቢራ ስራ አዋጭ መሆኑን ስለተገነዘበ ስመ ጥሮቹን በደሌ እና ሃረር ቢራን ገዛቸው።  ስራውንም በእጅጉ አስፋፋ። በአኢትዮጵያ የቢራ ተጠቃሚዎች ቁጥር በእጥፍ እንዳደገም ዘገባው አስምሮበታል። ትርፉም እንደዚያው አደገ።

በደሌ ቢራ ከመሸጡ በፊት አንድ ነጥብ አምስት ሚሊየን ዩሮ ግብር ይከፍል ነበር።  ሄነከን ከገዛው በኋላ ግን የከፈለው ዘጠኝ መቶ ሺህ ዩሮ ብቻ ነው። አንድ ሚሊየን ዩሮ ግብር ይከፍል የነበረው ሃረር ቢራም አሁን ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ዩሮ ብቻ ነው ያስገባው። ትርፉ ከእጥፍ በላይ እያደገ፣ ግብሩ ከእጥፍ በላይ የመቀነሱ ምስጢር ምን ይሆን?

የግብር ማጭበርበር ጥቆማ የደረሳቸው እነዚህ ጋዜጠኞች ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ንግድ ሚንስትር ሄዱ። ምኒስትሩ በዚህ የማጣራት ጉዳይ ላይ ሊተባባራቸው ፈቃደኛ አልነበረም። ከዚያም ወደ ጉምሩክ እና ቀረጥ ቢሮ አመሩ። እዚያም ምንም መረጃ እንሰጥም ይሏቸዋል። ምስጢሩን ለማውጣት የጓጉት እነዚህ ጋዜጠኖች ተስፋ አልቆረጡም። በመጨረሻ ወደ ንግድ ምክር ቤት አመሩ።  የዚያ ባለስልጣን የሰጧቸው ምላሽ የሚያስቅ ነው። “የንግድና ትርፍ ዘገባ አይደርሰንም።” አሉ። ታዲያ ንግድ ምክር ቤት ይህንን ካልመዘገበ ምን ይሆን የሚሰራው?

የንግድና የስራ ግብር መቀነሱ ብቻ አይደለም። ቀድሞ በሃረር እና በበደሌ ቢራ ቋሚ ሰራተኛ የነበሩ 699 (44%) ሰራተኞችም ከሄነከን ቢራ ተቀንሰዋል።  የሆላንድ መንግስት ስራ ፍጠሩ ብሎ ድጎማ ሲያደርግ፣ ይልቁንም ነባሩን ሰራተኛ ከስራው አፈናቀሉት።

በኢትዮጵያ የሄነከን ተወካይ ሆላንዳዊ ነው። የዜምብላ ጋዜጠኖች የዚህን እንቆቅልሽ ለመፍታት እሱን ማፋጠጥ ይችላሉ። ስለዚህም ወደሱ አመሩ።  የገቢና ወጪ ዘገባውን እንዲሰጣቸው ጠየቁት።  እንቢ እንዳይል ቸገረው። ምክንያቱም በዚያ ዘገባ የሆላንድ መንግስት የድጎማ ገንዘብ ሰላለበት። እሺ ብሎ ይፋ እንዳያደርገው ደግሞ ምስጢሩ ለህዝብ ሊወጣ ነው። እሱም አለ። “የፋይናንስ ሪፖርቱን እሰጣችኋለሁ። እናንተ ግን ለህዝብ ይፋ እንደማታደርጉት ቃል ግቡልኝ።”

ዘገባውን በእጃቸው ያስገቡት እነዚህ ጋዜጠኖች፣ ዶክመንቱን አለም አቀፉ የገንዘብ ተቁዋም አማካሪዎች ጋ ይዘውት ሄዱ። የ አይ. ኤም. ኤፍ. ባለሙያው ወረቀቱን እንዳየ ምስጢሩን ለማወቅ ሰከንዶች አልፈጁበትም። የኢትዮጵያ ህዝብ በታክስ ተዘርፏል። ሰራተኛውም ወገን ከስራው እንዲፈናቀል ተደርጓል።

የመንግስት ባለስልጣን ሃገር ሲዘረፍ እና ወገን ከስራ ሲፈናቀል፣ ጉዳዩን ማፈን መርጠዋል። ምክንያት ቢኖራቸው እንጂ ይህን መረጃ መስጠት ሀገርን የሚጠቅም ነበር።  በእርግጥ ይህ የግብር ማጭበርበር ተግባር እነሱ ሳያውቁት ሊሆን አይችልም። “የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ!”  ነው ነገሩ። እንዲህ እየተዘረፈ ኢኮኖሚው እንዴት ነው በ 11 በመቶ የሚያድገው?

እንግዲህ ይህ በኢትዮጵያ ከዘመቱት 130 የሆላድ የንግድ ድርጅቶች አንዱ ታሪክ ነው። ገቢውና ወጭው በግልጽ የሚታይ፣  ግዙፍ እና አለም አቀፍ ድርጅት። ሄነከን ከገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ይህንን ያህል ከዘረፈ የሌሎቹ – የማይታወቁት ምን ያህ ይሆን?

የቀድሞው የሆላንድ ልማትና ትብብር ሚንስቴር የነበሩት ጃን ፕሮንክ፣ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከልማት እና እደገት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ለሌላቸው የንግድ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግን ክፉኛ ይወቅሳሉ። በተለይ መንግስታቸው በልማትና ትብብር ስም፣ በብሄራው ጥቅም ስም የስብአዊ መብት ረገጣን ችላ ማለቱን ያወግዛሉ።

በልማት ስም በሚሊዮኖች እየፈሰሰ ያለው የሆላንድ ግብር ከፋዮች ገንዘብ በኢትዮጵያ ስራ አልፈጠረም። እንደውም ሰራተኞችን አፈናቀለ። ሀገሪቱን በበለጠ የስራና የንግድ ግብር ተጠቃሚ ያደርጋል ይባል እንጂ ግብሩ በ 70 እጅ ያነሰ ሆኗል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የገበሬው መሬት እየተነጠቀ ለነዚህ ዘራፊዎች መሰጠቱ የህዝብ ቁጣን አስነስቷል።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት  እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ አመጽ የገዥው ፓርቲ ችግር ብቻ ሳይሆን የሆላንድም ችግር መሆኑን በመግለጽ ዜምብላ ዘገባውን ይደመድማል።

[1] http://zembla.vara.nl/seizoenen/2016/afleveringen/23-03-2016

የሕወሓት የመስፋፋት እቅድ የወለደው የእርስ በእርስ ጦርነት በተክል ድንጋይ ፈንድቷል

0
0

Begemiderከትላንትና ጠዋት ጀምሮ የሚደርሱ መረጃዎችን ተከትሎ ለማረጋገጥ እንደተቻለው የሕወሓት የመስፋፋት ፖሊሲ እና ታላቋን ትግራይ የመመስረት አላማውን ለማሳካት ሲል የሚሰራቸው እኩይ ተግባራት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈራው የእርስ በእርስ ጦርነት በጎንደር ክፍለሃገር ተክል ድንጋይ መፈንዳቱን ከአከባቢው የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል::ሕወሓት የቅማንት ሕዝብን ለእኩይ ተግባሩ ሊጠቀምበት በማሰብ ከፍተና የሆነ የጦር መሳሪያ እያስገባ ነው የሚሉ የተክል ድንጋይ ነዋሪዎች ይናገራሉ::በአምቡላስ ላይ የደረሰን የፈንጂ አደጋ ተከትሎ ከትላንትና ጀምሮ በሕወሓት የጦር ሰራዊት እና በጎንደር ክፍለሃገር ሕዝብ መካከል ግጭቶች ወደ ተኩስ በመለወጣቸው አከባቢውን የጦር አውድማ አድርገውታል::

በትላንትናው እለት በትክል ድንጋይ በአምቡላንስ ላይ የፈንጂ ጥቃት ደርሶ በአምቡላንሱ ውስጥ የነበሩ ሁለት ሲገደሉ በአንዱ ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሶ የነበረ ሲሆን የአከባቢው ሕዝብ ለአደጋው የሕወሓትን ሰራዊት ተጠያቂ አድርጓል::እንዲሁም ሁለት ታዳጊ ወጣቶች በሕወሓት ጦር መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ::ወደ ተክል ድንጋይ የሚያስገቡ መንገዶች የተዘጉ ሲሆን የሕወሓት ጦር በአከባቢው ውጥረት በመፈጠሩ መሳሪያ ያልታጠቁ ነዋሪዎች ራሳቸውን ከሕወሓት ጦር ለማዳን ወደ ጎረበት ወረዳዎች እየሸሹ ይገኛሉ::መሳሪያ የታጠቁ የተክል ድንጋይ ነዋሪዎች ከወያኔ ጦር ጋር እየተታኮሱ ይገኛሉ::

‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ መንገድ

0
0

pol1660ከትጥቅ ትግል ጊዜ ጀምሮ በኢሕአዴግ ቁልፍ መሪነት ለሦስት አሥርት ዓመታት፣ በመንግሥት ኃላፊነት ላይ ደግሞ ለሁለት አሥርት ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆዩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ፣ ብዙ ነገሮች እየተለወጡ ይመስላል፡፡

በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ወንበር ላይ የተቀመጡት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የኢንጂነሪንግ ምሩቅ ሲሆኑ፣ ለአሥር ዓመታት ያህል በማስተማርና በአስተዳደር በአርባ ምንጭ የውኃ ቴክኖሎጂ ተቋም (በኋላ ዩኒቨርሲቲ) ያገለገሉ ምሁር ናቸው፡፡ በአንባቢነታቸው፣ በታጋይነታቸው፣ ተናግሮ በማሳመንና ሰዎችን ወደ ፓርቲው ሐሳብ ለማምጣት ወደር የላቸውም ተብለው በብዙዎች የሚደነቁትን አቶ መለስን መተካት ከባድ እንደሚሆን ተተንብዮ ነበር፡፡ አሁን ግን አቶ ኃይለ ማርያም በአቶ መለስ ወይስ በራሳቸው መንገድ እየሄዱ ነው የሚለው ጥያቄ በስፋት ይደመጣል፡፡

አቶ መለስ በፖለቲካ ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው ከድርጅታቸው አልፎ በአገር ደረጃ እንዲሁም ከአካባቢው አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተነገረላቸው ነበሩ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚያሰሙዋቸው ንግግሮችና በሚያካሂዷቸው ለአፍሪካ ያደሉ ሙግቶች፣ ‹‹የአፍሪካ ቃል አቀባይ›› የሚል ቅፅል ስም እስከ ማግኘት ደርሰው ነበር፡፡ ታዋቂ የዓለም አቀፍ ሚዲያ ጋዜጠኞች፣ ተመራማሪዎችና አዋቂዎች ከአቶ መለስ ጋር መነጋገር ከመፈለጋቸውም በተጨማሪ አድናቆታቸውንም ይገልጹላቸው ነበር፡፡

ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ላይ ቀላል የማይባል ነበር፡፡ ብዙ መሪዎችና ጋዜጠኞች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋቸዋል፡፡ ሐዘናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ‹‹የእሳቸው ወንበር ላይ ማን ይቀመጣል?›› በማለት በአፍሪካ በሕዝቧ ብዛት ሁለተኛ የሆነችው አገራቸውም ተጨንቃ ነበር፡፡

አቶ መለስ በሽግግር ላይ የነበረች አገር፣ በብሔር ብዝኃነትና በማንነት ጥያቄዎች የምትታመስ አገር፣ በታሪክ ቅራኔዎች የተሞላች አገር በዚሁ በውስብስብ ግጭቶችና ድህነት የሚታመስ ቀጣና ዕምብርት የሆነች አገር፣ የምዕራቡ ዓለምና የምሥራቁ ዓለም የፖለቲካ ፉክክር የሚያካሂዱበት አገር በብቃት መምራት መቻላቸው በስፋት ይነገርላቸዋል፡፡ በከፍተኛ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሽግግር ላይ ያለችውን ኢትዮጵያ፣ በእሳቸው ቦታ ላይ ቆሞ መምራት የሚችል ሰው ናፍቆት የነበራት ይመስላል፡፡ እንዲህም ሆኖ ግን አቶ መለስ በርካታ ተቺዎች ነበሩዋቸው፡፡

የቀድሞውን መንግሥት ለመታገል በነበረው የትጥቅ ትግል ተሳትፎ ያልነበራቸውንና የአዲሱ ትውልድ አባል የሆኑት፣ ብዙ የተባለለት የድርጅቱ የመተካካት አካል ተደርገው የሚታሰቡት አቶ ኃይለ ማርያም፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ምክትልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ኃላፊነት ይዘው ለጥቂት ጊዜ ቆይተዋል፡፡ በቅድመ ታሪካቸው በትምህርታቸው ምክንያት ‘ቴክኖክራት’ የሚባሉ መሪ ናቸው፡፡ በመጀመሪያ ሳምንታት የቀድሞውን አለቃቸውን ቦታ መሙላት ተስኗቸዋል ተብለው ሲተቹ ነበሩ፡፡ በአኳኋናቸውም ሆነ በፖለቲካ ትንታኔያቸው አቶ መለስን ለመምሰል ጥረት ያደርጋሉ በመባልም ሲተቹ ነበር፡፡

ከመነሻው፣ ‹‹የእኔ ኃላፊነት የአቶ መለስ ራዕይ ማስፈጸም ነው፤›› ማለታቸውም አዲስ ፊት እንጂ አዲስ የፖለቲካ እሳቤና ርዕዮት እንዳይጠበቅ አድርጎ ነበር፡፡ ቢያንስ በአቀራረብ ደረጃ፣ በአነጋገር ዘይቤና በአተያይ አቅጣጫ ለመለየት ባለመሞከራቸው፣ ራሳቸውን መስለው በራሳቸው መንገድ ነገሮችን የሚያዩበት መድረክ እንዲፈጥሩ ሲጐተጉቱ የነበሩ በርካቶች ናቸው፡፡

በእርግጥ በብዙዎች አዲስ የፖለቲካ አቅጣጫ ተደርጎ አልተወሰደም እንጂ፣ ከዚህ በፊት ኢሕአዴግ ያልሞከረው አገሪቱን በሦስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንድትመራ ማድረግ፣ ድርጅቱ ውስጥ የሚታየውን የአባል ፓርቲዎች የሥልጣን ‹‹ሽሚያ›› ለማርካትም ይሁን የጋራ አመራርን ለመፍጠር ያደረጉት ሙከራ ነበር፡፡

በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ተቀጥሮ የሚሠራ ግለሰብ በቅርቡ የመንፈቅ ዓመት ሪፖርታቸውን ሲያቀርቡ ካደመጠ በኋላ፣ ‹‹የሰውየው አልታይ ያለን የፖለቲካ ሰብዕና መውጣት ጀምሯል፡፡ አሁን ገና ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው እየተሰማኝ ነው፤›› በማለት ነበር የገለጻቸው፡፡

የኃይለ ማርያም መንገድ

ቀደም ሲል ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ጀምሮ የነበራቸውን ባህሪ በመለወጥ አዲስ የፖለቲካ አካሄድ የጀመሩት አቶ ኃይለ ማርያም ለዘብተኛና የማይቆጡ፣ ጥያቄ የሚወዱ፣ እንዲሁም የመርህ ሰው የሚያስመስሉዋቸው አካሄዶችም ታይተውባቸዋል፡፡

በአገሪቱ የሚታየው የአስተዳደር ችግር የቆየ ቢሆንም እየተባባሰ መምጣቱን ዛሬ ተገንዝበዋል፡፡ በእርግጥ ኢሕአዴግ ውስጥ የሚደረገውን የመገማገምና የመጎሻሸም ባህል፣ እንዲሁም በፅኑ የተገመገመ ሰው ከአንድ ቦታ ተነስቶ ሌላ ኃላፊነት ላይ ማስቀመጥ ዛሬም ድረስ የቀጠለ ቢመስልም፣ በአሠራር ለመለወጥ የሚያስችል መንገድ እየተከተሉ ይመስላል፡፡

በአሥረኛው የድርጅቱ ጉባዔ ላይ በተለይ በዋናው መሥራች ድርጅቱ በሕወሓት ውስጥ የሰላ መገማገምና መተቻቸት በገሐድ ሲታይ በአጠቃላይ በአገሪቱ ሙስና፣ ሕገወጥነት፣ ኔትወርክ፣ እንዲሁም ሥርዓት አልበኝነት መስፈኑ በስፋት ተወስቷል፡፡ ድርጅቱም በዚህ ደረጃ ሲያምን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ማለት ይቻላል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ሊቀመንበርነት በአገሪቱ የተንሰራፋው የአስተዳደር ብልሹነት በውል እንዲጠናናሰ እንዲፈተሽ የተደረገው በእሳቸው ጊዜ ነው፡፡ በኢሕአዴግ የአገዛዝ ዘመን በሕዝቡ ሲቀርቡ የሰነበቱ ነገር ግን ሰሚ ያጡ ሥር የሰደዱ ቅሬታዎች፣ በአዲሱ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ተቋም ተጠንቶ የተረጋገጠው በእሳቸው ጊዜ ነው፡፡

በትግራይ ክልል ሳይቀር ለዘመናት የታፈነው የሕዝብ ቅሬታ በሳይንሳዊ መንገድ ጥናት መካሄዱን ተከትሎ በባለሥልጣናት መካከል በተደረገው ውይይት፣ ጠቅላይ ማኒስትሩ ራሳቸው ችግሩን አምነው በመቀበልና ሌሎችም እንዲቀበሉ ተፅዕኖ ሲፈጥሩ ተስተውሏል፡፡

ጥናቱ ከአሥራ አንድ በላይ ግኝቶች ሲኖሩት፣ በተለይ በመሬት አስተዳደር፣ በንግድና በኢንቨስትመንት፣ በፍትሕና በመሳሰሉ አገልግሎቶች መንግሥት ያልተሳካለት መሆኑን አመላክተዋል፡፡ ሕዝብን በማሳተፍ የሚመካው ኢሕአዴግ ሕዝብን ለውይይት የሚጠራው አንድን ነገር ከጨረሰ በኋላ እንዲያፀድቅለት መሆኑ፣ ድርጅቱ በሙሰኛ ባለሥልጣናቱ ላይ ዕርምጃ እንደማይወሰድ፣ ፍትሕ በገንዘብ እየተገዛ እንደሆነ፣ እንዲሁም የሹማምንቶቹ ተጠያቂነት የወረደ መሆኑን በተጠናው ጥናት መረጋገጡን ገዥው ፓርቲ አምኖ ሲቀበል በአቶ ኃይለ ማርያም ዘመን ለመጀመርያ ጊዜ ነው፡፡

በኦሮሚያ የተጋለጠው የአስተዳደር ቀውስ

የኢሕአዴግ አመራሮች በዚሁ በአራቱ ክልሎች ላይ የተካሄደውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ጥናት በተወያዩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ፣ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ችግሩ ውስጣዊ ለመሆኑ ማረጋገጫ መሆኑን አቶ ኃይለ ማርያም ተናግረዋል፡፡

‹‹ሌላ አካል ላይ ጣት ከመቀሰር ይልቅ ችግሩ የራሳችን እንደሆነ አስምረን መሄድ አለብን፤›› በማለት ነበር ሁኔታውን የገለጹት፡፡ ቀደም ሲል በውጭ ኃይሎች የተቀሰቀሰ ተደርጎ ሲገለጽ የነበረውን ወደ ውስጥ አምጥተውታል፡፡ ‹‹በእኛ ውስጥ ባለ መበላሸት ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ የሕዝቡን ጥያቄዎች ፈጥኖ ምላሽ ባለመስጠት ከሕዝቡ ጋር ቅራኔ ውስጥ እየገባን መጥተናል፤›› ብለዋል፡፡ ቅራኔው ከሰሜን እስከ ደቡብ የአገሪቱ ክፍል መሆኑን ሳያመነቱ የተቀበሉ ሲሆን፣ ‹‹በትከሻው ላይ ተጣበቅንበት›› ያሉት አርሶ አደሩ፣ ‹‹ዞር በሉ ሲል አንዳንዴ በአንደበቱ አንዳንዴ በእጁ ይላል፡፡ አንዳንድ ቦታ ላይ አሁን በእጁ ነው ዞር በሉ ያለው፤›› ሲሉም በድፍረት ተጠያቂነቱን ወስደዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገሪቱ በዚሁ ደረጃ የገለጹት የአስተዳደር ብልሹነት እየተነገረ ያለው ድርጅታቸው መቶ በመቶ ባሸነፈበት ምርጫ ማግሥት ነው፡፡ ተቃዋሚዎችም፣ ‹‹አሁንም ችግሩን ኢሕአዴግ አልተገነዘበውም፡፡ ሕዝቡ ሐሳብ የሚገልጽባቸው መንገዶች በመታፈናቸው የመጣ ችግር ነው፤›› ይላሉ፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግር የፖለቲካ መታፈን ውጤት ይሁን ወይም በራሱ ተነጥሎ የሚታይ አከራካሪ ቢሆንም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ግን በተለይ በኦሮሚያ በተቀሰቀሰው ግጭት ለጠፋው የሰው ሕይወትና ለችግሩ መፈጠር መንግሥታቸውን ተጠያቂ ማድረጋቸው በድርጅቱ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ይመስላል የሚሉ አሉ፡፡

ይህ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ‹‹ይቅር ባይነት›› እና ወደ ውስጥ የመመልከት ጉዳይ ሪፖርተር ላነጋገራቸው የተለያዩ አካላት የተለያየ ትርጉም የሰጠ ይመስላል፡፡ የኢዴፓ መሥራችና የቀድሞ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ሙሼ ሰሙ፣ ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊት ይህንን ይቅርታ የመጠየቅ ባህል እንደነበረው ማንበባቸውን ገልጸው፣ ‹‹ሥልጣን ከያዘ በኋላ ግን ይቅርታን እርግፍ አድርጐ ትቶ ነበር፤›› ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የጠየቁት ይቅርታ፣ ተቋማዊ ይሁን ግለሰባዊ ግን ጥያቄ እንደጫረባቸው ይናገራሉ፡፡ ‹‹ይቅርታው ከረጅም ጊዜ በኋላ የመጣ ባህሪ ነው፡፡ በግልጽና በማያሻማ ቋንቋ ነው የቀረበው፡፡ የቀረበበት መንገድም ኃላፊነትን ሙሉ በመውሰድና ራስን ተጠያቂ በማድረግ ነበር፤›› በማለት አክለዋል፡፡ በደርግ ዘመን ሰው መግደል ለአብዮቱ ሲባል ልክ እንደሆነ ይገለጽ ነበር፡፡ በኢሕአዴግም ዘመን ሰው ለመግደል ‹‹ሁኔታው አስገደደኝ›› የሚባል እንደነበር ገልጸው፣ ‹‹የአሁኑ ይቅርታ ግን ሙሉ ያልተሸራረፈና በፖለቲካ ያልታጀበ መሆኑን በኢሕአዴግ የሥልጣን ዘመን ታይቶ የማይታወቅ ነው፤›› ብለዋል፡፡

አንድ የጐደለ ነገር እንዳለ ግን አመልክተዋል፡፡ ‹‹ይቅርታ የቅሬታ ማብረጃ ነው፡፡ ቂምና ቁርሾ ያበርዳል፡፡ ከመጠን በላይ ኃይል የተጠቀሙ ሰዎች ግን ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው አልተጠቀሰም፡፡ እንዲሁም ለሟች ቤተሰብ በቂ ካሳ መክፈል ያስፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡ ይቅርታው የተጠየቀበት ጊዜ የዘገየና ትንሽ ነው የሚሉ አስተያየቶችን አቶ ሙሼ አይቀበሉም፡፡

የመድረክ አመራር አባልና ነባሩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ግን የአቶ ኃይለ ማርያም አነጋገር የፈጠረላቸው አዲስ ነገር የለም፡፡ ለፕሮፌሰሩ ይቅርታው እንዲደርስ የተፈለገው መንግሥት ለዕርዳታ እጁን ለሚዘረጋለት ዓለም አቀፍ ማኅብረሰብ እንጂ ሰለባ ለሆነው ሕዝብ አይደለም፡፡

‹‹ለተራ ሰው ይቅርታ የተጠየቀ ሊመስለው ይችላል፡፡ የአቀራረቡ ጉዳይ ካልሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስም ሲያደርጉት የነበረ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ይህቺ በኢሕአዴግ የተመረጠች ታክቲክ ነች፡፡ ይቅርታ አልጠየቁም፡፡ የደረሰውን ጉዳት ዘርዝረው አላቀረቡም፡፡ ሕዝቡ እንዲቆጣ በማድረጋችን ይቅርታ ነው የተባለው፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

‹‹20 ዓመት ሙሉ አጥፍተናል እየተባለ የት አለ በተግባር ለውጥ የመጣው?›› ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅላጼ ቀይረው ነው የቀረቡት፤›› ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ በኦሮሚያ ክልል በተከሰተው ግጭት የጠበቁትን ያህል ኢሕአዴግ ምላሽ አልሰጠም፡፡ ‹‹እስቲ ማነው ተጠያቂ የተደረገው? ለጉዳዩ ተጠያቂ የሆነ የኦሮሚያ መንግሥት ማንን ከሥልጣን አወረደ?›› በማለት አሁንም ይጠይቃሉ፡፡ ከኃላፊነታቸው ተነሱ የተባሉ ሰዎች በሌላ ቦታ መሾማቸውንም ለዚህ እንደ ማስረጃ ያቀርባሉ፡፡

ለአቶ ሙሼ ይቅርታው ከልብ የመነጨና በኢሕአዴግ ያልተለመደ አካሄድ ሲሆን፣ ለፕሮፌሰር ግን ሥልት ነው፡፡ አቶ ሙሼ ኢሕአዴግ በአዲሱ አመራር እየተለወጠ መምጣቱንና በምርጫ አገኘሁት ያለውን የሕዝብ ውክልና በቂ እንዳልሆነ የተረዳ መሪ ማግኘቱን አመልክተዋል፡፡ ለፕሮፌሰር በየነ ግን የአቀራረብ ለውጥ እንጂ፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከቆየው የኢሕአዴግ ባህሪና ከአቶ መለስ አካሄድ መውጣቱን የሚያሳይ አይደለም፡፡

አቶ አበበ አይነቴ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የስትራቴጂክ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ ናቸው፡፡ ‹‹መንግሥት በይፋ ይቅርታ ሲጠይቅ የተለመደ አይደለም፡፡ አዲስም ጅምር ነው፤›› ይላሉ፡፡ ችግርን በፓርቲው ውስጥ መገምገም የተለመደ መሆኑን የሚናገሩ አቶ አበበ፣ በሕዝብ ፊት በግልጽ አጥፍቻለሁ ሲል ኢሕአዴግ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

‹‹በእኔ እምነት አንድ መሪና መንግሥት የሕዝበ አገልጋይ መሆኑን ለማሳየት ትልቅ አብነት ነው፤›› ብለዋል፡፡ ቀደም ሲል ተጠና በተባለው መሠረት ከተካሄደ ድርጅቱ ቀደም ሲል ተግባራዊ ያደርግ የነበረውን ፖለቲካ ታማኝነት ቅድሚያ መስጠት አስቀርቶ፣ ብቃትን መሠረት ያደረገ እንዲሆን በር የሚከፍት እንደሚሆንም አቶ አበበ እምነታቸው ነው፡፡ ‹‹የሕዝብ አገልጋይነተ ስሜት ይፈጥራል፤›› ብለዋል፡፡

የመለስ ውርስ

አቶ መለስ የድርጅታቸው የውስጥ ፖለቲካ፣ የአገሪቱ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም፣ እንዲሁም የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ቀያሽና ተንታኝ ነበሩ፡፡ ይህ ተግባራቸው ለኢሕአዴግም ለአገሪቱም ያስገኙት ለውጥና ጥንካሬ የማይካድ ቢሆንም፣ በዚህ ጠቅላይነታቸው ድርጅታቸው ውስጥ ሌሎች መሪዎች ዕውቀት እንዳያፈልቁና የፖለቲካ ሰብዕና እንዳያገኙ አድርገዋል ተብለው ይተቻሉ፡፡ ይኼም ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ከፍተኛ የሕዝብ ተቀባይነት ያገኙ መሪዎችም፣ ያልተገባ ትችትና ወቀሳ በመሰንዘር በአጠገባቸው እንዳይታዩ አድርገዋል ተብለውም ይታማሉ፡፡ እሳቸው በሕይወት ሳሉ እንደተናገሩት ‹‹የድርጅታቸው ፍሬ›› እንደሆኑ ቢገልጽም፣ በተግባር የድርጅቱ ፈጣሪ ሆነው ሲታዩ ነበር የሚሉዋቸው አሉ፡፡ ያለእሳቸው ድርጅቱ ህልውና የሌለው መምሰሉን በድፍረት የሚናገሩ አሉ፡፡ በእርግጥ የሕወሓት አባት ተደርገው የሚታዩ አቶ (አቦይ) ስብሓት ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ ‹‹የመለስ ሞት ከድርጅቱ የአንድ ሰው መቀነስ ያህል ነው፤›› ብለው፣ ድርጅቱ በእሳቤዎችና በርዕዮተ ላይ የተመሠረተ እንጂ ከግለሰብ ህልውና ጋር ትስስር የለውም በሚል መሞገታቸው ይታወሳል፡፡ ባለፈው ዓመት በመቐለ ከተማ በተካሄደው የድርጅቱ አሥረኛ ጉባዔም ላይ፣ ‹‹መለስ በአንድ ሺሕ ዓመት የሚፈጠር ዓይነት ሰው ነበር፤›› በማለት አቶ በረከት ስምኦን የሰጡትን አስተያየት በመቃወም፣ ‹‹ሁኔታው ከጠየቀ በየዓመቱ ሺሕ መለሶች መፍጠር እንችላለን፡፡ መሪን የሚፈጥረው ሁኔታ ነው፤›› በማለት መሞገታቸው ይታወሳል፡፡

‹‹የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ሐሳብ አመንጪ ሲሆኑ፣ በተለይ ከ1997 ዓ.ም. የፖለቲካ ቀውስ በኋላ በፀደቁ አዋጆች ወይም በተቃዋሚዎች መዳከም፣ አቶ መለስ ራሳቸው እንደቀየሱት የሚታመንበት የምርጫና የፖለቲካ መሣሪያ ተደርጎ የሚወሰደው ‹‹የልማት ሠራዊት›› አደረጃጀት ሒደት፣ ድርጅቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓርላማውን መቶ በመቶ መቆጣጠር ተችሏል ተብሎ ይታመንበታል፡፡ በአሁኑ ወቅት የታየው የመልካም አስተዳደር ቀውስ የልማታዊ መንግሥት መርህ ውጤት አድርገው የተመለከቱት ተቃዋሚዎችም፣ ‹‹የአንድ ፓርቲ›› ሥርዓት መመሥረቱና የመድበለ ፓርቲ ፖለቲካ ሥርዓት መጨንገፉን ተናግረው ነበር፡፡ አቶ መለስ ግን ድርጅታቸው አውራ ፓርቲ ሆኖ እንደቀጠለ ነበር ከዚህ ዓለም የተለዩት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የቀድሞ አለቃቸውን መንገድ አልለቀቁም ተብለው የተተቹት፣ በተቃዋሚዎች ላይ በሚሰነዘሩት የሰላ ትችትና በጠላትነት የመመልከት አባዜ አንዱ ሲሆን፣ በእሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትርነት ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው አምስተኛው ዙር ምርጫም የባሰ የሚባል ውጤት ማስገኘቱ ይወሳል፡፡ በማናቸውም የዴሞክራሲ አቀንቃኝ የሆኑ አገሮች ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ፓርላማውን መቶ በመቶ ኢሕአዴግ መቆጣጠሩ አሳዛኝ መሆኑ ይነገራል፡፡

በኤርትራ ላይ ባላቸው አቋምና በተቃዋሚዎች ላይ በሚከተሉት ፖሊሲ፣ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ባላቸው ግንኙነት፣ እንዲሁም በአገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲና ቀደም ብለው በወጡ አፋኝ ተብለው በሚተቹ ሕጎች ላይ ድርጅቱ በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አማካይነት ምንም ለውጥ ሳይደረግባቸው ላለፉት አራት ዓመታት መጓዙም ብዙ ይባልበታል፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር

 

የኦሮሚያ ለኦሮሞዎች አስተሳሰብን እንዴት ያዩታል; –ሰርጸ ደስታ

0
0

በመጀመሪያ ከይቅርታ ጋር ኦሮምኛ ተናጋሪው እያልኩ እንድጽፍ የሚያስድደኝ የማውቀውን እውነት ላለመካድ ነው፡፡ አማራ ለሚባለውም፣ ትግሬም ለሚባለው ሌላም ይሄንኑ ነው የምጠቀመው፡፡

ethiopian-oromosበትላንትናው ዕለት ያለወትሮዬ ሰይፈ ነበልባል ሬድዮንን ሳደምጥ ነበር፡፡ በእርግጥም የዶ/ር መረራን ቃለመጠይቅ ሊንክ ተከትዬ ነው እዛ የገባሁት፡፡ በአጋጣሚው ግን ከዶ/መረራ ቃለምልልስ በተጨማሪ የሌላ ዶ/ር ጌታቸው እጅጊ(ይቅርታ የአባታቸውን ስም ከተሳሳትሁ)ን ቃለምልልስ ተከታተልሁት፡፡ የሰይፈ ነበልባሉ ጋዜጠኛ ኢዮብ ለሁለቱም አንድ መሠረታዊ ጥያቄ አንስቶ ነበር፡፡ ዶ/ር መረራ ጥያቄውን በግልጽ ይለፈኝ ብለውት አልፈውታል፡፡ ዶ/ር መረራ የራሳቸው ምክነያት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ እንደ እኔ ግን ባያልፉት ጥሩ ነበር ባይ ነኝ፡፡ ዶ/ር ጌታቸው ግን በግርድፍድፍ ሊመልሱት ሞክረዋል፡፡ ጥያቄው ኦሮምያ ለኦሮሞዎች የሚለውን አመለካከት በተመለከተ ነው፡፡ርዕስም ያደረኩት ልክ ኢዮብ እንደጠየቀው ነው፡፡  እርግጥ ጥያቄው ለዶ/ር መረራ በቀጥታ እንደቀረበው አይደለም ለዶ/ር ጌታቸው የቀረበው፡፡ ዶ/ር ጌታቸው ብዙዎችን ጥያቄዎች ሲመልሱ ስሜተኛ ሆነው ስለነበር ነባራዊውን ሁኔታ በትክክል በሚገልፅ አልመሰለኝም፡፡ በስሜተኝነታቸው ግን ልወቅሳቸው አልፈልግም ሁኔታዎች በእርግጥም የሚያሳዝኑና የሚያበሳጩ ናቸውና፡፡ ሆኖም ስሜታቸውን መቆጣጠር ቢችሉ ጥሩ የተሻለ ነበር፡፡ በዚህ ቃለምልልሳቸው ሌላው ሕዝብ የኦሮሞን ትግል ያለመቀላቀሉ የኦሮሞ ሕዝብ ችግር አይደለም ብለዋል፡፡ መሠረታዊ ችግሩ ግን በእርግጥም በዋነኛነት የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ እያነሳቸው ያሉት ጥያቄዎች ሌላውን ለማሳተፍ ዝግ በመሆናቸው አልፎም ለሌላው ስጋት በመሆናቸው ነው፡፡

የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ጥያቄ እንዴት ለሌላው ስጋት ይሆናለ ከተባለ በጥቂቱ እንደምሳሌ እያነሳሁ ልጠቁም፡፡

ምሳሌ 1፡ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ችግር፡- ዛሬ ኦሮምያ የሚባውን ክልል ያጥለቀለቀው የሕዝብ ተቃውሞ መነሻው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንደሆነ ሆላችንም እናስታውሳለን፡፡ የዚህን ማስተር ፕላን የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ በተናጥል መቃወሙ ከዚያም በላይ ተቃውሞው መሠረት ያደረገው ከፍትህና መብት ውጭ በሆነ በዘር በተከለለ ጉዳይ መሆኑ አንድምታውም ሌሎችን አይመለከትም እንደውም ሌሎች አዲስ አበባና አካባቢው ላይ መወሰን አይችሉም ስለነበር ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ስጋት እንደሆነ አንካካድ፡፡ ልብ በሉ የአካባቢው ገበሬዎች መፈናቀልና ቀጥሎ የሚመጣውም የኑሮ መመሳቀል የሁሉም ዜጋ ሊቃወመው የሚገባ ጉዳይ ነበር እንጂ ለኦሮሞ ሕዝብ የተለየ ጉዳይ ባልሆነም፡፡ ያም ሆኖ ተቃውሞውን እውን ሌሎችን ለጥሪ የጋበዘ ቢሆን ኖሮ ሌሎች ይቀላቀሉት ነበር ወይ የሚለው እኔም አይመስለኝም ከሚሉት ነኝ፡፡ ቢያንስ ግን ሌሎችን በማያገል መልኩ ስልታዊ መሆን ነበረበት ባይ ነኝ፡፡ ማግለሉ ባይኖር ሌሎች ዘግይተውም ቢሆን ተቃውሞውን ይቀላቀሉ ነበር ባይ ነኝ፡፡ የሆነው ግን ተቃራኒው ነው፡፡  ብዙ ጊዜ የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ እንቅስቃሴዎች ሌላውን በማግለል ናቸው፡፡  እኔ ትዝ ከሚለኝ አንዱ በአንደ ወቅት በቦረናና ባሌ አካባቢ የሰደድ እሳት ተነስቶ ብዙ ደናችንን ሲያወድም ብዙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እሳቱን ለማጥፋት በአንድነት ጥያቄ እያቀረቡ ሳለ  ጉዳዩን አጥበውት የሀገር መሆኑ ቀርቶ የኦሮሞ ተማሪዎች ብቻን የሚመለከት እንደሆነ በይፋ ሌላው ተነገረው በዚህም ብዙ ተማሪዎች አንዳዘኑ አስታውሳለሁ፡፡ የሚገርመው ግን የተቃጠሉትን ደን ቦታዎች በአካል የሚያቋቸው ተማሪዎች እያሉ በኦሮሞነት ብቻ የማይገባውና የማይመለከተውም ተግበስብሶ እንደሄደም አስታውሳለሁ፡፡ ደኖቹን በአካል የሚያውቁዋቸውና ያደጉባቸው ለእነሱ ምን ማለት እንደሆኑ እናስተውል፡፡ ወለጋ ያደገ ቦረና ወይም ባሌ ከአደገው እኩል ስለ ሐረና ደን ከጫካነት ያለፈ ትርጉም አይሰጠውም፡፡  ያኔስ አልፎ አልፎም ቢሆን በዩኒቨረሲቲዎች አካባቢ የተማሪዎች አንድነት ጭልጭል ይል ነበር፡፡ ዛሬ ያ ከጠፋ ብዙ ዓመታት ቆጠርን፡፡

ምሳሌ 2. ኦሮምያ የኦሮሞዎች የሚለው አስተሳሰብ፡- ይሄ አስተሳሰብ ራስን በራስ ከማጥፋት ያልተሻለ እንደሆነ መረዳት እንኳን የቻልን አልመሰለኝም፡፡ እንዲህ በሚባልበት ተቃውሞ እንዴት ሌሎች የተቃውሞው ተሳታፊ ይሆናሉ; ከጥንትም ጀምሮ ኦሮምኛ መነገርም ከመጀመሩ በፊት ዛሬ ኦሮሚያ የተባለው ክልል ውስጥ እኮ የሚኖሩ ሕዝቦች አሉ፡፡ ሲጀምር አገሩ እኮ ከመሠረቱ  የኦሮምኛ ተናጋሪው አይደለም፡፡ ኦሮምኛ ተናጋረው እንደ አንድ የሕዝብ አካል በአገሩ የመኖር እንጂ ሌላውን የማስወጣት መብትም ማን ሰጠው; ይህን ጉዳይ የሰይፈ ነበልባሉ ኢዮብ ለታዳሚዎቹ ማነሳቱን አደንቃለሁ፡፡ ጥያቄው ግን አልተመለሰም፡፡ ይህ አንኳር ጉዳይ ነው፡፡ የዚህ አስተሳሰብ አቀንቃኞች እነማን ናቸው; ዛሬ ኦሮምያ ውስጥ የሚኖረው ሕዝብ በጣም የተወሳሰበ ማሕበራዊና ባሕላዊ እንዲሁም ሀይማኖታዊ ብዝሀነት ያለው እንደሆነ ለማያውቁት ቆመው ሊቃዡት ይችላሉ፡፡ በዚህ ምክነያት ግን ሕዝብ በራሱ ላይ የመጡበትን ጠላቶቹን በጋራ እንዳይዋጋቸው ጎልበቱን በመሸንሸን ያደክሙታል፡፡ ኦሮምያም ሌላውም የኢትዮጵያ አካል በእንደዚህ ያሉ አስተሳሰቦች ሽባ እንደሆነ ልገልጽ እወዳለሁ፡፡ በቅረቡ ባሌ ሮቤ ላይ ሕዝብ የሞቱ ወገኖችን ፍትህ ለመጠየቅ ለወጣብት ሰላማዊ ሰልፍ የተወሰኑ እዛ ደግሞ ሀይማኖትም የታከለበት ማግለል የተነሳ የተባለው ሰልፍ እንደቀረ ሰምቻለሁ፡፡ አጋጣሚውን እንኳን ተፈጥሮላቸው ራሳቸውም ለሚፈጥሩት የሕዝብ ጠላቶች ግን ድል ነው፡፡

ምሳሌ3. ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ ያነጣጠረ ጥላቻ፡፡ እንደ እኔ እምነት የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ሙሉ የኢትዮጰያዊነት ወኔ እስከሌለው ድረስ ራሱም ነጻ አይወጣም እሱ ካልወጣ ደግሞ ሌሎች ነጻ  መሆን አይችሉም ባይ ነኝ፡፡ ያለ ኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ነጻነት የሌላው ሕዝብ ነፃነት ሁሉ አደጋ ላይ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ በመሪነት ሌላውን መጋበዝ ሲገባው ብዙ የሚባለው የዚህ ሕዝብ አካል ኦሮሞ ብቻ ከዚያም በላይ ኢትዮጵያ የሚባል ቃል እያስደነበረው እንዴት ፍትህ የሰፈነባት ኢትዮጵያ የምትባል አገር ማየት ይቻላል፡፡ ዛሬ እኮ ወይኔ በሉት ሌላው እንደልቡ የሆነው ይሄ አስተሳሰብ ጽኑ መከላከያ ግንብ ሆኖት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ አንስቼዋለሁ አሁንም አነሳዋለሁ ግልጽ የሆነው የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ የበላይ የሆነበት የታላቁ ሚንሊክን ታሪክ ይህ ትውልድ እስከሚረዳው ድረስ የሌሎች ተገዥነቱ ይቀጥላል፡፡ ዶ/ር ጌታቸው በንግግራቸው ልጅ ኢያሱን ከእነ ታደሰ ብሩና፣ ሌሎቻ ጋር  እንደ አንድ የኦሮሞ ልጅ ሰለባ አንስተዋል፡፡ እዚህ ጋር እኔና ዶ/ር ጌታቸው እንስማማለን፡፡ ስለምኒሊክ ግን ምን እንደሚያስቡ ስለማላውቅ ምንም ማለት አልችልም፡፡ አንድ ነገር ግን እኔ የማውቀውን እናገራለሁ፡፡ ሁሉም ኢያሱ የምኒሊክ የልጅልጅ እንሆኑና ምኒሊክ ስልጣናቸውን ሰጥተዋቸው እንዳለፉ ያውቃል፡፡ ምን አልባት ብዙው የማያውቀው ምኒሊክ እንዴት ስልጣንን ለልጅ ልጃቸው ሰጡ የሚለውን ነው፡፡ ለዛሬው ኦነግና ወያኔ የፈጠሩት የቁቤ ትውልድም የማይገባው ይሄ ነው ቢገባውም እንዲገባው አይፈልግም፡፡ እውነታው ምኒሊክ ሥልጣን የመንግስታቸው ምሰሶ ለነበረው ለኦሮምኛ ተናጋሪወ ሕዝብ መስጠታቸው ነበር፡፡ አልያማ ኢያሱ እኮ በእድሜም ልጅ፣ በትውልድም የልጅ ልጅ እንጂ ቀጥታ ልጅም አልነበሩም፡፡ ከዚህ በኋላ ስለተደረገውና እስከዛሬም ያ ታሪክ ይፋ እንዳይሆን ሌት ከቀን  ስለሚያሴሩት ለሕዝብ እተዋለሁ፡፡ ይህን ታሪክ በደንብ የተረዳ ሕዝብ ማንም እንደፈለገው እንደማይዘውረውና ለማንም እንደማይበገር ከኃ/ስላሴ ጀምሮ ያሉ ባለስልጣኖች በድንብ ያውቁታል፡፡ የአሁኖቹ ደግሞ እጅግ ያስፈራቸዋል፡፡ ይህን ታሪክ ግን በኢትዮጵያዊነቱ የሚመካ ሁሉ ይፈልገዋል፡፡ ክብርና ኩራቱም ነውና፡፡

ምሳሌ4፡-ጎሰኝነት ብዝሀነትን ያለመውደድ፡- ራሱ የኦሮምኛ ታናጋሪው ሕዝብ በዘርም፣ በባሕልም፣ በእምነትም ብዝሀነት ያለው ሲሆን አሮሞ በምትባል ቃል ብቻ ራሱን አስሮ ሌላውን ያገላል፡፡ ለሌሎችም ከእነሱ ለመለየት ስም ይሰጣል፡፡ብዙ የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ሐበሽነቱን ክዶ ለሌሎች ሰጥቷል፡፡ ሐበሻ የሚባለው ሕዝብ ግን ሱዳንን፣ ሶማሌን፣ የመንን ጨምሮ የሚኖረው ሕዝብ ባለ የተለያየ ቀለም (ቀይ፣ ጠየም፣ ጥቁር …) በሚል የሚታወቅ ሕዝብ መጠረያ መሆኑን ብዞዎች አንረዳም፡፡ የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ከዚህ የሚለይብት አንድም እውነት የለም፡፡ ስሜት እንጂ፡፡ ከዛም ባላይ ኦሮምኛ ተናጋሪው ጥንታውያን አባቶቹ ዛሬ ሐበሻ እያለ ባዕድ የሚያደርጋቸው እንጂ ወላቡ አይደለም፡፡ ይህንን እውነት እንድንነጋገር እድል የሚሰጥ መድረክ ቢኖር በስሜትና በቲፎዞ ሳይሆን በግልጽ በሚቀርብ መረጃ ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ አሁን ከአለንበት ሳይንስ እንጻር ከባድ አይደለም፡፡  የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ይህን ያህል ግዙፍ ሆኖ ራሱን ባጣም እያጠበበ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ዘፈኖች ሳይቀሩ አሮሞ በሚል እጂ እንደ ድሮው ብዝሀነቱን በሚገልጽ የሰፈረባቸውን አካባቢዎች በሚወክል መዘፈን አቁመዋል፡፡ ኢጆሌ ሻምቡ፣ ኢጆሌ ሀሮ፣ ኢጆሌ ባሌ፣ በረዱ ሀረር፣ በረዱ ጂማ ወዘተ በሚል የምናውቃቸው ዘፈኖች ሁሉ አሮሞ በሚል ታጥፈዋል፡፡ አንዳንዶችም ከሌሎች የሆኑ ያሳመሩ መስሏቸው ትርጉሙን ሳይረዱ እንድሁ በሬዱ ኦሮሞ በሚል ዘፈናቸው ሲያደነቁሩን እናያለን፡፡ ሕዝብ ማንነቱና አካባቢው ተመሳሳይ ስያሜ ካለው በዛው ቢዘፈንለት ችግር የለውም፡፡ ለምሳሌ ጉራጌ፡፡ ግዙፍና ሰፊ ቦታን ያካለለ፣ የተለያየ በሕልና እምነት ያለው ሕዝብ ግን እራስን እንደማሳነስ ነው የማየው፡፡ አስቡት እስኪ የአማራ ቆንጆ ተብሎ ቢዘፈን፡፡ ዘረኝነት ከመናገር ውጭ ምን ጣዕም ይሰጣል፡፡ አማርኛ ተናጋሪ ሁሉ አንድ ሕዝብ ነው ብሎ ከማለት በስተቀር፡፡

አንግዲህ እንዲህና አነዚህን በመሳሰሉ ምክነያቶች የኦሮምኛ ተናጋሪው ራሱን ከሌሎች እያራቅ  ሌሎች ከእሱ ጋር ባይተባበሩ ለምን ይደንቃል፡፡ ይልቁንም ሌሎችን እንቅስቃሴዎቹ ስጋት እየሆኑ፡፡ የኦሮሞን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ሁሉ እውን የሕዝቡን ነጻነት የሚፈልጉ ከሆነ እነዚህን አስተሳሰቦች በይፋ እያወገዙ ኢትዮጵያዊነትን ለሕዝቡ ጉልበት ይስጡት፡፡ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ በሆኑ አማራጮች ነገሮች እጅግ የከበዱ እንደሆኑ ይረዱ፡፡ ዶ/ር ጌታቸውም ሌሎችን ሊወቅሱ ሞክረዋል፡፡ መወቃቀሱን አልጠላውም፡፡ ግን የምንወቃቀሰው አንድ መሆን ስንችል ነው፡፡ መውቀስ የሚቻለው የራስን ሰው እንጂ ወዳጅ፣ ወጋን ያልሆነን አይደለም፡፡ ወቀሳ እንዴት እኔ እየተጎዳሁ አንተ ዝም ትላለህ የሚል የወንድማዊነት ስሜት እንጂ እኔ እንጂ አነተ ባለመብት አይደለህም በሚባባሉ ወገኖች መካከል የሚሆን አይደለም፡፡ እላለሁ አሁንም የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት እንዲህ እንደአሁኑ ባይሸረሸር ዛሬ 4 ወር ያስቆጠረው ተቃውሞ ባነሰ ጊዜ የምንፈልገው ለውጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ማምጣት በተቻለ ነበር፡፡ እንዲህ ከሕዝብ ጋር አይንና በርበሬ የሆኑ ባለስልጣኖች አገሪቷን እንደልብ የሚጋልቡት በዋነኝነት በኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ የአመለካከት ችግር እንደሆነ ልናገር እወዳለሁ፡፡ ሊያውም መሀል ኢትዮጵያ ውስጥ፡፡ የኦሮምኛ ተናጋሪውን ሕዝብ ጉዳይ እንደተለየ ጉዳይ አድርጎ በማቅረብ ከማንነቱ እንዲመክንና እንዲባዚን ጎልበትም እንዳይኖረው የተደረገውን ያህል ኢትዮጵየውነቱ ላይ ሩቡ ተሰርቶ ቢሆን ሊሆን የሚችለውን እናስብ፡፡ አሁንም ቢሆን የዚህን ሕዝብ ጉዳይ ይዘናል የምትሉ ሁሉ ከኢትዮጵያዊነት ውጭና ሌላው በማግለል የምታደርጉትን እንቅስቃሴ አስቡበት፡፡ ይሄው 70 ዓመት ሆኖናል እያላችሁን ነው፡፡ ሕዝቡ ግን ጭራሽ ስቃዩ እየበዛ ነው፡፡  ዛሬም አልመሸም በይፋ በኢትዮጵያዊነት ላይ የተመሠረተ እንቅስቃሴ ጀምሩት ያኔ ምን ያህል ሕዝብ ደጋፊያችሁ እንደሚሆነ ታዩታላችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት ሌላ አንድ ሊያደረገውት ጉልበት የሚሰጠው የለም፡፡ ሁሉም ያስተውል ወደ ኢሳያስን የሸወዳቸው ሟቹን ጠቅላይ ሚኒስታር ማመን ያዳገታው ለኢትዮ-ኤርትራ ጦር ጥሪ ሲደረግለት እንዴት እንደወጣ፡፡ መለስ ግን ከጦርነቱም በኋላ የዚህ ሕዝብ ኢትዮጵያ ለሚለው ቃል ያለው ሕብረት ያስደሰታቸው አልነበረም ነግ በእኔ በሚል አሳሰባቸው እጂ፡፡ እውንም እንደፈሩት በ1997ዓ.ም ምርጫ መጣባቸው፡፡ የአደዋ ድል እኮ የኢትዮጵያዊነት ወኔ ነው፡፡ ዛሬ ያሉት ባለስልጣኖች ከዚህ በላይ የሚፈሩት ነገር እንደሌለ እናውቃለን፡፡ ለምን በዘር ልክፍት እንድንበከል እንዳደረጉን እንንቃ፡፡ የጠላቶቻችን ምኞትና ዕቅድ ፈጻሚ አንሁን! መጀመሪያ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን ያግኝ፡፡ በዚህ ጉዳይ ምሁራንም አበክረው ቢያስቡበትና ቢነጋገሩበት ሕዝቡንም ወደዚሁ መንፈስ አንድ አደርገውት ጉልበት ቢሰጡት መልካም ነው፡፡ እኔም እንዳቅሜ ሌላውም እንደዛው መፍትሄ የሚሆን ነገር አለን፡፡

 

አመሰግናለሁ

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

የዕለቱ ምርጥ ካርቱን |ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 7ለ1 ሽንፈት

0
0

Cartoon of the day
የዕለቱ ምርጥ ካርቱን | ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 7ለ1 ሽንፈት

የሰማያዊ ፓርቲ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ሊቀመንበሩን ኢንጂነር ይልቃልን እና አቶ ወረታውን አባረርኩ አለ

0
0

(ምንሊክ ሳልሳዊ) – ጠንካራ ፓርቲዎችን ሰርጎ ገብ አስገብቶ በመበታተን ጠንካራ አመራሮችን በመወንጀል ፓርቲዎችን አዳክሞ ብመቃብራቸው ላይ ተለጣፊ ታማኝ ተቃዋሚዎችን የሚተክለው ኢሕኣዴግ በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ገብቶ እየበጠበጠ እንደሚገኝ ከተለያዩ ምንጮች የሚወጡ ዘገባዎችን ተመልክተናል::
Yilikal Getenet
ፓርቲውን ለመቆጣጠር ፍላጎት ያለው ኢሕኣዴግ በሚደጉባቸው ሪፖርተር እና አዲስ አድማስ ጋዜጦች በኩል የፓርቲ አመራሮችን ስም ካለማስረጃ እና የፍትህ ውሳኔ ሲያጠፉ ከርመዋል::

በዛሬው እለት የተሰማው ዜና ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን የነገረ ኢትዮጵያ አዘጋጅ በትዊተር ገጹ በዚህ መሰረት የድርጅቱ ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነት እና ወረታው ዋሴ ከፓርቲው ሲባረሩ ወይንሸት ሞላ እና ስለሺ ፈይሳ ለ2 አምት ከማነኛውም የአመራርነት ቦታ ታግደዋል።ሰማያዊፓርቲ ሊቀመንበሩንና የቀድሞው የፋይናንስ ኃላፊን ከፓርቲው አባረረ። ሆኖም የሊቀመንበሩ መባረር ተግባራዊ የሚሆነው ከጠቅላላ ጉባኤ በኁዋላ መሆኑን እርምጃውን የወሰድው የዲስፕሊን ኮሚቴ ገልጹዋል ሲል ጽፏል::

በጎንደር ስታዲየም “ወልቃይት ይመለስ…አማራ ነን”እየተባለ ሲዘመር ዋለ

0
0


(ዘ-ሐበሻ) መሰብሰብ እና መደራጀት በተከለከለባት ኢትዮጵያ ህዝብ ባገኘው አጋጣሚ ብሶቱን ማሰማቱን ቀጥሏል:: ዛሬ በጎንደር ስታዲየም የተፈጠረውም ይኸው ነው:: እግር ኳስ ጨዋታ ለማየት የተሰበሰበው ሕዝብ እግረመንገዱን ተቃውሞውን ሲያሰማበት ውሏል::

ዛሬ በብሔራዊ ሊግ ጨዋታ በጎንደር ከተማ ስታዲየም የጎንደር ከነማ እና የትግራይ አዲግራቱን ውልዋሎ ክለብን ይገጥም ነበር:: ጨዋታው አንድ ለአንድ ቢፈጸምም የጎንደር ሕዝብ የታመቀ ጩኸቱን ሲያሰማበት ውሏል::

ወልቃይት ይመለስ…. አማራ ነን… ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ… ተሰድበን ተዋርደን አንቀርም… የወያኔ አፈና የትግራይ የበላይነት በቃን የሚሉ መፈክሮችን በዝማሬ ሕዝቡ በስታዲየም እያሰማ ሕዝቡ ለስር ዓቱ ያለውን ጥላቻ ሲገልጽ ውሏል::
Screen Shot 2016-03-27 at 8.36.06 PM


Sport: “ከሉዊ ቫንሃል ይልቅ መውቀስ ያለብን ራሳችንን ነው”ዋይኒ ሩኒ

0
0

የማንችስተር ዩናይትድ አምበል ዋይኒ ሩኒ ቡድናቸው በዘንድሮው ሲዝን በማስመዝገብ ላይ ካለው ደካማ ውጤት መወቀስ ያለባቸው ራሳቸው መሆናቸውን ያመነበትን መግለጫን ሰጥቷል፡፡

የውድድር ዘመኑ ወደ 2016 አዲስ ዓመት ከተሸጋገረ ወዲህ በዘጠኝ ግጥሚያዎች ላይ ለማንችስተር ዩናይትድ ሰባት ጎሎችን በማስቆጠር ወደ ጥሩ አቋሙ ለማንሰራራት የቻለው የ30 ዓመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ በቡድናቸው ላይ በተፈጠረው የውጤት ቀውስ ከአሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ይልቅ ራሳቸው በሜዳ ላይ ያሉት የቡድናቸው ተጨዋቾች መሆናቸውን በማመን በሰነዘረው አስተያየቱ የቡድናቸውን የእስካሁኑ የአቋም አለመረጋጋት ችግርን ለመቅረፍ በአሁኑና በሲዝኑ መጨረሻ በሚደረጉት ግጥሚያዎች እያንዳንዱ የቡድናቸው ተሰላፊዎች እስካሁን የተሻለ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት እንዲነሳሱ ጥሪውን አስተላልፎላቸዋል፡፡

Luis
‹‹በስኳዳችን በርካታ ተደናቂ ብቃት ያላቸው ተጨዋቾችን ይዘናል፡፡ ሆኖም ግን በአንዳንድ ግጥሚያዎች ላይ የቡድናችን ተሰላፊዎች ከያዙት አቋም የወረደ የጨዋታ እንቅስቃሴን ሲያሳዩ ማየት በከፍተኛ ደረጃ የሚያስጨንቅ ጉዳይ ሆኖብኛል›› በማለት ለዴይሊ ሚረር ጋዜጣ መግለጫውን መስጠት የጀመረው የማንችስተር ዩናይትድ አምበል በመቀጠልም ‹‹በአንዳንድ ግጥሚያዎች ላይ ቡድናችን መጥፎ ውጤቶች ሲፈጠሩበት በግንባር ቀደምትነት ሲወቀሱ የሚታዩ አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በጥፋተኝነት መፈረጅ ያለብን ወደ ሜዳ በመግባት ግጥሚያዎችን የምናደርገው ራሳችን የቡድናችን ተጨዋቾች ነን፡፡ ምክንያቱም ሉዊ ቫንሃል ይጠቅሙኛል ብለው ያመኑበት የጨዋታ ፕላንን ይዘው ወደ ሜዳ በመግባት የራሳቸውን ትልቅ ኃላፊነትን በመፈፀም ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር በእያንዳንዱ ግጥሚያዎችን በድል ለማጠናቀቅ የምንችልባቸው ጎሎችን ከመረብ ማገናኘት በሜዳ ላይ ያለነው ተጨዋቾች እንጂ የሉዊ ቫንሃል ኃላፊነት ሊሆን አይገባውም›› የሚል አስተያየቱን አክሏል፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ የዘንድሮው ሲዝንን ያጋመሰው የቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳትፎውን ወደ መጨረሻዎቹ 16 ቡድኖች ደረጃ ለማሸጋገር በተሳነው ሁኔታ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንን መጥፎ ውጤቶችን ለማካካስ የሚችሉት በአሁኑና በሲዝኑ መጨረሻ መካከል ለሚያደርጓቸው የሶስት ውድድሮች ማለትም የፕሪሚየር ሊግ፣ የኤፍ.ኤ.ካፕና የዩሮፓ ሊግ ግጥሚያዎች ተራ በተራ ሙሉ ትኩረትን በመስጠት እንደሚሆን በማመን የ30 ዓመቱ የማንቸስተር ዩናይትድና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል በመቀጠል መግለጫውን የሰጠው ‹‹…በእስካሁኑ ሲዝን በተፈጠረብን የአቋም አለመረጋጋት የክለባችን ደጋፊዎችን ላስከፋንበት ጉዳይ ትክክለኛውን ማካካሻን የምናስገኝላቸው በቀሪው ሲዝን የፕሪሚየር ሊግ ዘመቻችንን እስከ 4ኛ ስፍራ ድረስ በመግባት ለማጠናቀቅ በዩሮፓ ሊግ ወይም በኤፍ.ኤ ካፕ ውድድሮች የዋንጫ ሽልማቶችን ለማግኘት ከፍተኛ የሆነ ጥረትን የምናደርግ ሲሆን ይሆናል፡፡

በእርግጥ የዘንድሮ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት የነበረን ዋነኛ አላማ የዩሮፓ ሊግ የዋንጫ ድልን መቀዳጀት አለመሆኑን አምናለሁ፡፡ ሆኖም ግን በክለባችን ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተፈጠረው አስቸጋሪ ሁኔታዎች አንፃር በፍጥነት የዋንጫ ሽልማቶችን ለማግኘት በምናደርገው ጥረትን በቸልታ የምንመለከተው ሊሆን አይገባም›› በማለት ነው፡፡
‹‹ከቼልሲና ከሰንደርላንድ ጋር ባደረግናቸው ያለፉት ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎቻችንን በድምሩ አምስት ነጥቦችን ለማባከን በመገደዳችን የውድድር ዘመኑን እስከ 4ኛ ስፍራ በመግባት በምናደርገው ከፍተኛ የሆነ ጥረት ደካማ አቋም ማዘኑን ባለመደበቅ ሩኒ በሰነዘረው አስተያየት ‹‹በምንመኘው መልኩ በበቂ ሁኔታ ጎሎችን የማስቆጠር እድሎችን ለመፍጠር ሲሳነን የታየው ግጥሚያ ነው በመከላከሉ ተግባርም ከዚህ ግጥሚያ ይልቅ ከዚህ ግጥሚያ ልዩ ትኩረትን ሰጥተን ስንሰራበት የዘለቅነው ከቆሙ ኳሶች የሚደረጉ ጥቃቶችን የመቋቋም ተግባርን በአግባቡ ለመፈፀም ሲሳነን ታይቷል፡፡ ከዚህ አንፃር ከግጥሚያው አንድ ነጥብ እንኳን ሳናገኝ በመቅረታችን የምንወቀሰው ራሳችንን ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም የምንመኘው አይነት ጥሩ አቋምን ለመያዝ ያልቻልንበት ግጥሚያ ነው ከመከላከሉ ተግባርም ከዚህ ግጥሚያ ልዩ ትኩረትን ሰጥተን ስንሰራበት የዘለቅነው ከቆሙ ኳሶች የሚደረጉ ጥቃቶችን የመቋቋም ተግባርን በአግባቡ ለመፈፀም ሲሳነን ታይቷል፡፡

ከዚህ አንፃር ከግጥሚያው አንድ ነጥብ እንኳን ሳናገኝ በመቅረታችን የምንወቅሰው ራሳችንን ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም የምንመኘው አይነት ጥሩ አቋምን ለመያዝ ያልቻልንበት ግጥሚያ ነው፡፡ ከቼልሲ ከሰንደርላንድ ጋር ባደረግናቸው ሁለት ተከታታይ ግጥሚያዎች በአጠቃላይ ለሶስት ነጥቦችን በመጣላችን ምናልባትም በቀጣዩ ሲዝን ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳትፎ ለመመለስ የምንችለው የዩሮፓ ሊግ ውድድር የዋንጫ ሽልማትን ለማግኘት ስንችል ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን ስ ግን በአሁኑና በሲዝኑ መጨረሻ መካከል 12 የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች በመኖራቸው የሚፈጠረውን ነገርን እርግጠኛ ሆነን ለመናገር የማንችል መሆኑን በማመን ነው›› ብሏል፡፡

ደግሞም የዋንጫ ሽልማትን ካገኘን የሶስት ዓመታት ጊዜ በመቆጠሩ ከእንግዲህ የምናማርጠው ውድድር ሊኖረን አይገባም፡፡ የዘንድሮ የዩሮፓ ሊግ ተሳትፎአችንን በዋንጫ ለማጠናቀቅ ከኤፍ.ሲ ሚትላንድ ጋር የሚጠበቅብን የደርሶ መልስ አንስቶ ለእያንዳንዱ በውድድሩ ጨዋታዎች ሙሉ ትኩረትን በመስጠት እስከ ሲዝኑ መጨረሻ ድረስ ለመዝለቅ የዋንጫውን ድል ለመቀዳጀት የተቻለንን ሁሉ ጥረት እንድናደርግ ለቡድናችን ተሰላፊዎች ከዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፍላቸዋለሁ›› በማለት ነው፡፡

ማንቸስተር ዩናይትድ የዩሮፓ ሊግ ውድድር ሲሳተፍ የዘንድሮው ከአራት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜው ነው፡፡ ከዚህ በፊት በጨመረሻ ጊዜ በ2011-12 ሲዝን በዚህ ውድድር ተሳትፎው ከመጨረሻዎቹ 16 ቡድኖች ደረጃ ለመሸጋገር አለመቻሉ ይታወሳል፡፡ በዚህ ውድድር ከዚህ በፊት ዘጠኝ ጊዜ የመሳተፍ እድልን አግኝቶም ከሩብ ፍፃሜው የተሻለ ውጤትን ያስመዘገበው አንድ ጊዜ ብቻ ማለትም ከ1964-65 ሲዝን ነበር፡፡

ያኔ በሃንጋሪው ፌሬንቾቫሮቭ በግማሽ ፍፃሜው ደረጃ ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኖ ነበር፡፡ የዘንድሮው ሲዝን ቢሆን ማንቸስተር ዩናይትድ የዩሮፓ ሊግ /የቀድሞው የማህበረሰቡ ዋንጫ/ ውድድርን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋንጫ ባለቤትነት ለማጠናቀቅ የሚጠበቀው ፈተና ቀላል አይሆንለትም፡፡ ምክንያቱም በውድድሩ የመጨረሻው 16 ቡድኖች ደረጃ ቦሪሽያ ዶርትሙንድ፣ ናፖሊ፣ ሴቪያ፣ ሊቨርፑል፣ ቶተንሃም፣ ፊዮረንቲና፣ ባየር ሌቨርኩዘንና ኤፍ.ሲ ፖርቶን የመሳሰሉት ጠንካራ ክለቦች አብረውት ይገኛሉ፡፡
ከዚህ ባሻገር የእንግሊዝ ክለቦች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዚህ ውድድር ተሳትፏቸው ሊጠቀስ የሚችል ትልቅ ስኬት የሌላቸው መሆኑ ከግንዛቤ ሲገባም ማንቸስተር ዩናይትድ የዘንድሮን ሲዝንን በዩሮፓ ሊግ የሻምፒዮንነት ክብር ለማጠናቀቅ የሚኖረው ተስፋ ዝቅተኛ ሊባል የሚገባው ነው፡፡

የማንቸስተር ዩናይትድ ቀጣይ ግጥሚያውን የሚያደርገው በያዝነው ሳምንት መጨረሻ በዝቅተኛ ዲቪዚዮኑ ሽዌስበሪ ሜዳ ነው፡፡ ከሽዌስበሪ ጋር በሚረገው የኤፍ.ኤ.ካፕ 5ኛው ዙር ግጥሚያን በማንቸስተር ዩናይትድ መደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት ይጀምራሉ የሚል ግምት ከተሰጣቸው ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ የሆነው ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽናል ማሮዋን ፊላኒ የክለባችን ሲዝንን እስከ አራተኛ የማጠናቀቅ ተስፋን በማስመልከት ምን አይነት አስተያየት አለህ በሚል ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን የሰጠው ‹‹በአሁኑ ወቅት እያንዳንዱ ግጥሚያዎችን በጠንካራ የመሸናነፍ ፉክክር በመዳረግ ላይ በመሆናቸው ይህንን አላማችንን ለማሳካት ከፊታችን ባሉት 12 የሊጉ ጨዋታዎች የሚጠብቀን ፈተና ቀላል አይሆንም፡፡
ከዚህ አንፃር እስከ 4ኛ ስፍራ በመግባት አላማችንን ለማሳካት በእያንዳንዱ ግጥሚያዎች በበቂ ሁኔታ ጎሎችን የማስቆጠር እድሎችን በመፍጠር ብዛት ያላቸው ጎሎችን የማስቆጠር ትልቅ ኃላፊነት እንደሚጠብቀን አምናለሁ፡፡

ይህንን ስል ግን በአሁኑ ወቅት 4ኛ ስፍራን ከያዘው ክለብ ጋር ያለን የነጥብ ልዩነት ያንን ያህል ሰፊ የሚባል ባለመሆኑ እስካሁንም ድረስ የውድድር ዘመኑን ቢያንስ እስከ አራተኛ ስፍራ በግባት የማጠናቀቅ ተስፋ እንዳለን አምናለሁ፡፡ ይህንን አላማችንን በአግባቡ ለመፈፀም እንምንችል ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ የምንሆነው ከፊታችን ያሉት እያንዳንዱ ግጥሚያዎችን በድል ለማጠናቀቅ ስንችል ብቻ ይሆናል፡፡ በአሁኑና በሲዝኑ መጨረሻ መካከል በሚደረጉት ግጥሚያዎች ከእኛ በላይ ካሉት ክለቦች ውስጥ አርሰናል፣ ቶተንሃምና ሌስተር ሲቲን የምናገኝባቸው በመሆኑም በመሀላችን ያለውን የነጥቦች ልዩነት ለመቅረፍ የበኩሉን አስተዋፅኦ የሚያበረክትልን እንደሚሆን አምናለሁ፡፡ በሰንደርላንድ 2ለ1 የተሸነፍንበት ጨዋታ ያለመውረድ ትግልን በማድረግ ላይ ያሉትን ክለቦችን መግጠም ምን እንደሚመስል ትምህርትን ሰጥቶናል፡፡ በእኔ አመለካት በሲዝኑ ወሳኝ ወቅት አንድ ትልቁ ፈተና የመውረድ ስጋት ያለባቸው ቡድኖችን መፋለም ነው፡፡ ይህንን ለመቋቋም ግን ከሁሉም በላይ ከፍተኛ ወሳኝነት ያለው ጉይ ጎል የማስቆጠር ቅድሚያን መያዝ መሆኑን አምናለሁ›› በማለት ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በግልህ ስለ ያዝከው አቋም ምን አስተያየት አለህ በሚል ለቀረለበት ጥያቄ ደግሞ ‹‹በተከታታይ ግጥሚያዎች የመጀመሪያው ምርጫዬ በሆነው በመሃለ ማካይ ሚና በመሰለፍ ላይ በመሆኔ በራሴ የመተማመን መንፈሴን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ያማረ አድርጎልኛል ለማለት እችላለሁ፡፡ ተስፋ የማደርገውም በራስ የመተማመን መንፈሴ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በተሻለ ሁኔታ ያማረ ለመሆን በመቻሉ ከፊታችን የመሰለፍ ዕድልን በማገኝባቸው ግጥሚያዎች በእስካሁኑም በተሻለ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት እችላለሁ ብዬ የቅርብ ጊዜ አቋሜ ጥሩ እንዲሆን ከረዳኝ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

የሌላው ከአብዛኛዎቹ የቡድናችን ተጨዋቾች ጋር ለሁለት ዓመት ተኩል ያህል አብረን ለመሰለፍ መቻላችን ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ በመሀላችን ያለውን የጨዋታ እንቅስቃሴን መናበብን ይበልጥ አሳድጎታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በማይክል ካሪክ ባሻገር ሞርጋን ሽኔደርሊንና ባስቲያን ሽዌንሲቲገር ተደናቂ ብቃቶችና ሰፊ ልምድን የተላበሱ ተጨዋቾች መሆናቸው ማንኛውም ጋር ጥምረትን ፈጥሮ መጫወት ያንን ያህል አስቸጋሪ አልሆነብኝም፡፡

እርግጠኛ ሆኜ የምናገረውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለማንቸስተር ዩናይትድ በተሰለፍኩባቸው በእያንዳንዱ ግጥሚያዎች በሜዳ ላይ በለኝ የጨዋታ እንቅስቃሴዬ ሙሉ ደስተኛ የመሆን ባህል እስኪደርሱ መምጣት ችያለሁ፡፡ በተለይም ለማንቸስተር ዩናይትድ የምሰለፍበት ቀጣዩ የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዬ ወደ እንግሊዝ ከመጣሁ ወዲህ 200ኛው የውድድሩ ጨዋታዬ ስለሚሆን ከወዲሁ በጉጉት እየተጠባበቅኩት መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ›› የሚል ምላሽን ሰጥቷል፡፡
 
 

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ የራሳቸውን ሰብዕና ማስረገጥ አለባቸው፤ ከመለስ ጥላ ስር መውጣት አለባቸው።” –ፕ/ር ገብሩ ታረቀ

0
0

ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ፤ ስለ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአገዛዝ ዘመናትና ሂደት ይናራሉ። ፕሮፌሰር ገብሩ “The Ethiopian Revolution: War in the Horn of Africa” እና “Ethiopia: Power and Protest: Peasant Revolts in the Twentieth Century” መጻሕፍት ደራሲ ናቸው።

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ የራሳቸውን ሰብዕና ማስረገጥ አለባቸው፤ ከመለስ ጥላ ስር መውጣት አለባቸው።” – ፕ/ር ገብሩ ታረቀ

የህወሀት ኢህአዴግ ፖሊሲ ወጣቱን ወዴት እየወሰደው ነው?

0
0

UNiversity students

tplf

| ኤድመን ተስፋዬ

ከአፍሪካ አጠቃላይ ህዝብ ከ60 ፐርሰንት በላይ የሚሆነው ከ ሰላሳ አምስት አመት በታች በሆነ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ እንደ መሆኑ አንባገነናዊ ስርአትን ከአፍሪካ  ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ወጣቶች ላይ ትኩረት ማድረግ የውዴታ ግዴታ ነው፡፡ ይህን የተናገሩት የዘር ሀረጋቸው ከጎረቤት ኬኒያ የሚመዘዘው የመጀመሪያው ጥቁር የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት ባራክ ኦባማ ናቸው፡፡ ፕሬዝዳንት ኦባማ  ከላይ የጠቀስኩትን ቁጭት አዘል የሆነ ንግግራቸውን ከንግግር ባለፈ ተግባራዊ ለማድረግ መንግስታቸው በነደፈው ፖሊሲ መነሻነት  እ.ኤ.አ በ2012 ከመላው አፍሪካ ለተውጣጡ ስልሳ ለሚሆኑ ወጣቶች ከአመራር ጋር የተገኛኘ ስልጠና  በአሜሪካ እንዲከታተሉ አድርገዋል፣እያደረጉም ነው፡፡ እንደ አሜሪካ የስለላ ተቋም ሲአይኤ የመረጃ ቋት ከሀገራችን አጠቃላይ የህዝብ ብዛት ውስጥ 64.3 ፐርሰንት የሚሆነው ከዜሮ አመት እስከ ሀያ አራት አመት በሆነ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ የእድሜ ክልሉን ከ 0 እስከ ሰላሳ አምስት ክልል ውስጥ ከፍ ስናደርገው ደግሞ አሃዙ ወደ 74 ፐርሰንት ይደርሳል፡፡ ይህም የሚያሳየን  ሀገራችን በወጣትነት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህዝቦች በብዛት የሚኖሩባት ሀገር እንደሆነች ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ከአጠቃላይ የሀገራችን ህዝብ አብዛኛው በወጣትነት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ እንደመሆኑ ሀገራችንን በየአምስት አመቱ በሚታደስ የምርጫ ውል እያስተዳደረ ያለውን ኢህአዴግን ፖሊሲዎቹን መነሻ በማድረግ   የወጣቱን ተጠቃሚነት እንዲሁም ወጣቱ ትውልድ የሀገሪቷ ሀብት ክፍፍል ላይ ተገቢውን ድርሻ ስለማግኘቱ ወጣቱ ትውልድ በኢኮኖሚ ስርአቱ ላይ ያለውን ተሳታፊነት መነሻ በማድረግ ማየት ተገቢ ይመስለኛል፡፡

ገዢው ፖርቲ ኢህአዴግ ወጣቶችን ማእከል ባደረገ መልኩ ያደረገውን እንቅስቃሴ በተመለከተ በዋኛነት የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋፋቱ እና የስራ እድል መፈጠሩ ላይ ትኩረት ባደረገ ምልኩ የሚገልፅ ሲሆን፣ በዋነኛነትም አስፋፋዉት የሚለው የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር እንዳለ ሆኖ የዩኒቨርስቲዎችን ማስፋፋቱን፣የሞያ እና ቴክኒክ ት/ም ቤቶችን ማስፋፋቱን እና በጥቃቅን እና አነስተኛ ወጣቶችን በማደረጀት ወጣቱን  የንብረት ባለቤት ማድረጉን ለማሳያነት ያቀርባል፡፡ እንደ እኔ እምነት ትልቁ ጥያቄ ገዢው ፖርቲ የሚለፍፈለትን  ወጣቱን ተጠቃሚ የሚያደርግ እና ያደረገውን ፖሊሲው  ነባራዊ የሆነ የሚታይ ለውጥ በብዙሀኑ ወጣት ላይ አምጥቷል ወይ የሚለው ሲሆን፣ ይህንንም  ለመፈተሸ ኢህአዴግ አስፋፋውት የሚለውን ዩኒቨርስቲዎችን፣ የጥቃቅን እና አነስተኛ ፖሊሲውን ወጤት እና ምንን መሰረት አድርጎ እንደተዋቀረ ግልፅ ያልሆነውን የፌደራሊዝም ስርአትን  ማእከል በማድረግ ማየት ተገቢ ይመስለኛል፡፡

ወጣቱን ተምሮ ስራ ፈት ያደረገው ኢህአዴግአዊ ፖሊሲ ለስራ ፈጣሪነትስ ምቹ ነው?    

ገዢው ፖርቲ በሀገራችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለብዙሀኑ ወጣቶች ተደራሽ እንዲሆን አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎችን በመክፈትም ሆነ ነባሮቹን በማስፋፋት  አስፋፋውት የሚለውን የዩኒቨርስቲ ትምህርት በነባራዊነት በትውልድ ተጋሪዬ ወጣት ላይ ያመጣውን ለውጥ ለማየት የስራ እድልን፣  የወጣትነት ባህሪን እና የማሰብ ነፃነትን ማእከል በማድረግ ማየት ያስፈልጋል፡፡ ወጣትነት የእድሜ ክልል ራስን ከመቻል፣ቤተሰብን ከመርዳት ጋር ተገናኝ የሆኑ ፍላጎቶች የሚንሩበት እንደመሆኑ የከፍተኛ ተቋም ትምህርትን ለወጣቶች ተደራሽከማድረግ እኩል ታሳቢ መሆን ያለበት የስራ እድል የመሆኑን ሁነት እንደ ማርክ ዴን ያሉ የባህሪያዊ ኢኮኖሚደስቶች (Behavioural Economist) ይገልፃሉ፡፡ ሊዊንስተን በበኩሉ ከስራ እድል እና ራስን ከመቻል እና ቤተሰብን ከመርዳት ጋር የተገናኙ ፍላጎቶቹን ለማሳካት በገበያው ላይ ስራ ፈላጊ የሆነ ወጣት  ስራ ከማጣት ጋር በተያያዘ ለአይምሮ መታወክ እና ለድብርት ተጋላጭ የሚሆንበት እድል ከፍተኛ ስለመሆኑ ይተነትናል፡፡

እንደ ወጣት በዩኒቨርስቲ በሚኖረው ቀይታው በመጀመሪያ በነፃነት የሚማርበትን ስርአት መዘርጋት እና  ማመቻቸት የመንግስት ግዴታ ሲሆን ሲቀጥል ደግሞ በተማረው ሞያ ተቀጥሮ እንዲሰራ የስራ እድል ፈጣሪ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን በግብርናው፣በኢንደስትሪው እና በአገልግሎት ዘርፉ ከግል ባለሀብቱ ጋር በመተባበር መከወን ሌላው ግዴታው ነው፡፡ በእኔ እምነት ዋናው ቁምነገር ዩኒቨርስቲዎችን ከማስፋፋት ጎን ለጎን ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ለሚወጣው የስራ እድል መፍጠር እና ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ስርአት ማመቻቸት እንደመሆኑ ኢህአዴግ አስፋፋዋቸው እና አዲስ ከፈትኩአቸው ከሚለው ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው የሚወጡ የትውልድ ተጋሪዬ ወጣቶች በተማሩት ሞያ እንኳን የሀገራቸውን ችግር ሊፈቱ የራሳቸውን ችግር ሊፈቱ እንዳይችሉ ኢህአዴግአዊ ፖሊሲዎች ጋሬጣ ስለመሆናቸው መሞገት የሚቻል ይመስለኛል፡፡

 

ከየትኛውም የእድሜ ክልል በተለየ ወጣትነት ነፃነትን የሚፈልግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወጣት ትውልድ እምቅ ችሎታውን ተጠቅሞ የሀገሩንም ሆነ የራሱን የኑሮ ችግር ለመፍታት የሞያ ነፃነት ይፈልጋል፡፡ ኢህአዴግ አመጣውት የሚለውን የኢኮኖሚ እድገት ነባራዊነቱን፣ የዲሞራሲያዊ ስርአት በሀገራችን ለመተግበር ኢህአዴግ እስኬት ድረስ ይሄዳል፣ መንግስታዊ ሌብነት እና ሀገራዊ መመዙ ወዘተ  የሚሉ ጉዳዮችን ወጣቱ በዩኒቨርስቲ ቆይታው ሀገራዊ በሆነ ጥናት ከመፈተሸ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ፍላጎቱ ኢህአዴግ እንደ መንግስት  ድጋፍ  ያደርጋል ወይ የሚለውን መነሻ አድርገን ስናይ አንድ ለ አምስት  የሚለው የፖርቲው የጥርነፋ ስርአት በዩኒቨርስቲዎች ስርመስደዱ እና ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ስራ ለማግኘት ከዲግሪ ይልቅ የፖርቲ አባልነት መታወቂያ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑ በራሱ ከላይ የጠቀስኩትን ለመከወን መንግስታዊ እንቅፋት ስለመኖሩ አሳይ ከመሆኑም በላይ   የትውልድ ተጋሪዬ የሆነው ወጣቱ ትውልድ በዩኒቨርስቲ ቆይታው በነፃነት  የሀገሩን ችግር ከሞያው አኩአያ ለማየት ኢህአዴግአዊ የፖለቲካ ተግዳሮቶች እንቅፋት ስለመሆኑ አሳይ ይመስለኛል፡፡

በሀገራችን ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ የወጣ ወጣት ዲንጋይ ጠራቢ እና አስጠራቢ በሆነበት፣ ከዩኒቨርስቲ ተመርቃ የወጣች ወጣት ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል አልጋ አንጣፊ በሆነችበት ሁናቴ እንዲሁም በዩኒቨርስቲ ቆይታዋ  ብርን ማእከል በማድረግ ማህበረሰባዊ እና ሀገራዊ ዋጋ በማያውቅ ነፈዝ ብራም የወሲብ ማስተንፈሻነት ገላዋን እስከ መስጠት የሚደርስ ተስፋ አስቆራጭ ሁነት ውስጥ እንድትገባ መንስኤው ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ከመውጣት በሁአላ በሰራተኛ ገበያው ያለው ተስፋ አስቆራጭ ሁናቴ መሆኑን በመጥቀስ ኢህአዴግ አስፋፋውት የሚለው ዩኒቨርስቲ   ለወጣቱ ያተረፈው ድብርትን እና ለአይምሮ መታወክ ተጋላጭነትን ስለመሆኑ  አሳይ ይመስለኛል፡፡

ገዢው ፖርቲ ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ስራ አጥ የሆኑ ወጣቶችን በተመለከተ በሚመስል መልኩ ብዙን ጊዜ ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ የሚወጡ ወጣቶች ከመንግስት ስራ ከሚፈልጉ ስራ ፈጣሪ መሆን እንዳለባቸው ይናገራል፡፡ በእኔ እምነት ገዢው ፖርቲ ስለ ስራ ፈጠራ ሲያወራ የዘነጋው ነገር ወጣቱ ስራ ፈጣሪ እንዲሆን  ዋናው ቅድመ ሁኔታ ነፃነት  መሆኑን ነው፡፡ ከዩኒቨርስቲ ተምሮ ባገኘው እውቀት ሀገሩን ለመርዳት በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ለመስራት በውስጠ ታዋቂነት ከትምህርቱ ይልቅ የኢህአዴግ አባልነት መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠለት ወጣት ስራ ፈጣሪ ሆኖ በኢኮኖሚ ስርአቱ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን  እዛም ቤት እሳት አለ እንዲሉ ፖለቲካዊ ወገንተኝነትን ማእከል ያደረገው ኢህአዴግ የሚመራው የሀገራችን የኢኮኖሚ ስርአት ላይ ወጣቱን ትውልድ ውድ የሆነውን ነፃነቱን ካልገበረ በቀር በመንግስታዊ ድጋፍ (ብድር፣የስራ ቦታ ማመቻቸት ወዘተ) መነሻነት ተሳታፊ የመሆኑን ነገር አስቸጋሪ ማድረጉ በእኔ እምነት የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ አመላካች ከመሆኑም በላይ ወጣቱ እንደ ትውልድ በተጋረጠበት መንግስታዊ ዳራ የተነሳ ዳራውን የጋረጠበት መንግስት ላይ እንዲዞር መንስኤ የሚሆን ይመስለኛል፡፡

ከኤፍሬም ይሳቅና ከተስፋዬ ገ/አብ ኢትዮጵያዊ ማን ነው –ሰርጸ ደስታ

0
0

Tesfaye ephremሰሞኑን ተስፋዬ ገ/አብ የተባለ ግለሰብ ታዋቂውን አሸማጋይ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅን እያነሳ በኢትዮጵያ እየተቀጣጠለ ያለውን የሕዝብ አመጽ ለማርገብና ለኢሕአዴግ ፋታ ለመስጠት እየሰሩ እንደሆነ እየነገረን ነው፡፡ ራሱንም (ተስፋዬ) ከኤፍሬም ጋር እያወዳደረ ነግሮናል፡፡ መወለድ ቋንቋ  ነው ይለናል፡፡ የኤፍሬምና የእሱ መመሳሰል ደግሞ እሱ ኤርትራዊ ሆኖ የኢትዮጵያ አሳቢ መሆኑ ኤፍሬም ይሁዲ ሆነው የኢትዮጰያ ወዳጅ መሆናቸውን ነው፡፡ በአንድ ወቅትም ኢሕአዴግን በጋራ እንዳመሰጉኑ አንዳንድ ባለስልጣኖችንም በጋራ እንዳወደሱ ይጠቁመናል፡፡ ኋላ ግን እሱ ነገሩን እንደተረዳና ምስጋናውና መወድሱ ትክክል እንዳልሆነ እሱም ከኢሕአዴግ ሥርኣት ራሱን እንዳገለለ ይነግረናል፡፡ በተቃራኒወ ኤፍሬም ዛሬም ድረስ የኢሕአዴግ ወዳጅ እንደሆኑ እያስታወሰን ከኢኝህ ሰው እንድንጠነቀቅ ያሳስበናል፡፡

እንደእኔ ላሉት ኢትዮጵያዊ ግን ኤፍሬም መቼም ስጋት ሆነውበት አያውቅም፡፡ ይልቁንም ኤፍሬም ጸሐፊው ተስፋዬ ከራሱ ጋር ሊያወዳድራቸው እንደሞከረው ሳይሆን ከየትኛውም ኢትዮጵያዊ በላይ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ትልቅ ፍቅርና ግምት ያለቸው ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ ኤፍሬም ከኢሕአዴግ ያገኙት ልዩ ጥቅም ኖሮ አያውቅም፡፡ ተስፋዬ ግን የኢሕአዴግ ሥርዓት ዋነኛ ተጠቃሚ ከሚባሉት አንዱ ነበር፡፡ የኤፍሬም ምኞት ነፃነት የሰፈነባትን የበለፀገች ኢትዮጵያን እንጂ ገንዘብ፣ሥልጣን ወይም ሌላ ልዩ የግል ጥቅም አይደለም፡፡ ተስፋዬ ምን ሊለን እንደፈለገ አልገባኝ ይሆን; ኢሕአዴግ እሱ የጥቅም ተጋሪው በነበረበት ዘምንም ከአሁን ቢከፋ እንጂ የተሻለ አልነበረም፡፡ በትክክልም እንደ ተስፋዬ ያሉ ኤርትራዊ ደም ያላቸው ግለሰቦች ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በፊት ከኢትዮጵያውያን ይልቅ ልዩ ተጠቃሚዎች እንደነበሩ እናውቃለን፡፡ ለተሰፋዬ ኢሕአዴግ የከፋ ሥርዓት እንደሆነ የታየው እንግዲህ ተጠቃሚነቱን ካሳጣው ከዚህ ክስተት በኋላ ነው፡፡ ኤፍሬምን ግን የነገሮች መለዋወጥ አልቀየራቸውም፡፡ ሁሉንም ከልብ በሆነ እምነት እንጂ ከጥቅም የተነሳ የሚያደረጉት አይደለምና፡፡

ኤፍሬም የኢሕዴግ ባለስልጣናት ወዳጅ የሆኑት ለኢትዮጵያ ሊያበረክቱት በሚያስቡትና እያደረጉም ባሉት ጥረት እንጅ ለግል ጥቅም አይደለም፡፡ የዛንው ያህል ለተቃዋሚዎችም ጠላት አይደሉም፡፡ ሑሉንም በወዳጅነት ነው የሚቀረቡት እንጂ፡፡ችግሩ ግን የጠላቴ ወዳጅ ጠላቴ በሚል የተረገም የሀበሻ እምነት እንጂ፡፡ ኤፍሬም ሁለት እንደጠላት በሚተያዩ ወንድማማቸች መካከል ያሉ ንጹህ የሁለቱም ወገኖቻቸው ጉዳይ የሚያሳሰባቸው በዚህም ምክነያት አገርና ሕዝብ እየተጎዳ መሆኑን የሚያሳዝናቸው መሆናቸውን እናውቃለን፡፡ ተሰፋዬ ዛሬ እራሱን ከኤፍሬም የተሻለ የኢትዮጵያ አሳቢ ማድረጉ ለራሱ ትንሽ ቢያሳፍረው መልካም ነበር፡፡ ኢሕአዴግ እኮ የኢትዮጵያ ጠላት እንደሆነ ያወቅነው አገሪቱን ያለወደብ ያስቀረ ሕዝቡን በዘር እንዲከፋፈል ያደረገ እለት ነው፡፡ ያኔ ለተስፋዬ ኢሕአዴግ ትክክል ነበር፡፡ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በከፊልም ቢሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት ነበር፡፡ ለእነ ተስፋዬ ግን ከጥቅማቸው የሚያፈናቅላቸው ነበር፡፡ ኤርትራዊ ሀበሻ ወገኔ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ተስፋዬን ጨምሮ ኤርትራዊ ደም አለን ብለው የሚያምኑ ብዙዎች ግን ከማዝንባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ወገኖች ለኤርትራም ለኢትዮጵያም ሕዝብ ጠላቶች አንደሆኑ የማንረሳውን ጠባሳ ለብዙዎቻችን እንደተውልን አይረዱም፡፡ ግርግር ለሌባ ይመቻል እንዲሉ አሁንም ሌላ ጠባሳ ለማፍጠር ይሞክራሉ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ የራሱ ታሪክ ከሆነው የሚኒሊክ ታሪክ ጋር እንዲጣላ አስተዋጽዖ ካደረጉት በግለሰብ ደረጃ ተስፋዬ ገ/አብ አለበት፡፡ ኤፍሬም ግን ሶስት ሺ ዓመት ያንሳል 10000ዓመት የዘለቀ የሕዝብ ለሕዝብ እርስ በእረስ የተሳሰረ የባሕል፣ የደም፣ እና የቋንቋ መስተጋብር በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል አለ ብለው በጥናት ለማሳየት የሞከሩ ድንቅ የአገሪቷ ተወላጅ ናቸው፡፡ ይሄንን አንካካድም፡፡   ኤፍሬም ከኢሕዴግ ባለስልጣናት ጋር ያላቸውን ወዳጅነት ለኢትዮጵያ መልካም አስተዳደርና ፍትህ እንዲሆን ጥረት አደረጉበት እንጂ ለግል ጥቅማቸው አላዋሉትም፡፡ ይልቁንም ተስፋዬ በእነዚሁ ኤፍሬምን በሚያጣጥልበት ጽሑፎቹ እኳን ኢአዴግ ኦነግንና ግንቦት 7ን ማጣጣልን እየተወነው እያለ የዘናጋናል፡፡ ኢአዴግ ይህን ቢያደርግ ለምን ይገርመናል፡፡ ስልታዊ አካሄድ እንደሆነ አሳምረን እንረዳዋልን፡፡ ለሞቱትና ለተጎዱት ዜጎቻችን ኃላፊነቱ እወድዳለሁ፣ አጥፍቻለሁ እያለ እኮ ነው ውስጥ ውስጡን መግደሉንና ማሰሩን አጠናክሮ እየቀጠለ ያለው፡፡ ክልሎችን እኮ ጭራሽ በወታደራዊ አገዛዝ ሥር አድርጎ የበለጠ ሥቃይ እየፈጸመ እኮ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የምናውቀው ባሕሪው እኮ ነው፡፡ እንደ አዲስ እሱ የውስጥ አዋቂ ሆኖ ሊነግረን ይሞክራል፡፡ ሊየውም ዋናዊን ሴራ ሸሽጎ፡፡

ብዙዎቻችን  በአንዳንድ ሚዲያዎች ከምንሰማቸው ውጭ ኤፍሬም ማን እንደሆኑ በትክክል አንረዳም፡፡ ኤህአዴግም ቢሆን ኤፍሬምን የሚፈልጋቸው ለራሱ ጥቅም ነው፡፡ ኤፍሬም ግን ከኢሕአዴግ ጥቅም የሚፈልጉ አይደሉም፡፡ እኝህ ሰው ከዘመናት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ትምህርት እንዲስፋፋ፣ በሌለዎች በባእዳን አገራት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በልዩ ክብር እንዲታይ በተግባር ያሳዩ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ በአለባበስ እንኳን ኢትዮጵያዊነትን እኔነት ክብሬ ብለው የሚኖሩት ናቸው፡፡ ጦርነትን፣ መጠላላትን፣ ክፋትን ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሠላምን፣ ፍቅርን፣ በጎነትን የሚመኙ በመሆናቸው በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተፈጥሮ የለገሰቻቸውን በአላንጣዎች መካከል ሠላምን ማውረድን ተጠቅመው የሚመኟትን ኢትዮጵያ ማየት ነው የእሳቸው ፍላጎት፡፡

አሁንም ቢሆን ሁሉም ወገኖች እሺ ቢሏቸውና በአንድ መድረክ ማምጣት ቢችሉ እኚህ ሰው ከሁሉም በተሻለ የምንመኛትን ለዜጎቿ ሠላምና ምቹ መኖሪያ የምትሆን ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እድሉን ይፈጥራሉ የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ የእኚህን ሰው ፍልስፍና በትክክል የተረዱ ባዕዳን ሳይቀር ብዙ ጊዜ በትላልቅ የሠላም ጉዳዮች ተሳታፊ እንዳደረጓቸውም እናውቃለን፡፡ ከእነዚህም አፓርታይድን ለማስወገድና እንዲሁም በሰሜን አየርላንድ ሠላም እንዲሰፍን የተሳተፉባቸው ጉልሕ አስተዋፅዖአቸው ከሚታወቁት ናቸው፡፡ ለገዛ ሕዝባቸውና፣ ባሕሉንም፣ ቋንቋውንም ለሚጋሩት እማ የእኛ ጠማማነት እንጂ በቀላሉ በተሳካላቸው ነበር፡፡ ኤፍሬምን ዛሬ በኢትዮጵያውያን መካከል ያለው መከፋፈልና መጠላላት እጅግ ያሳስባቸዋል፡፡  ለእእሳቸውም ወደ አንድ መድረክ ሁሉንም አካል አምጥቶ ለማደራደር ዋናው ችግር ይሄ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ለዚህ ደግሞ እነተስፋዬና ወገኖቹ ትልቅ ሚና ነበራቸው፡፡ ዛሬም ተስፋዬ እየነገረን ያለው እውንም ኤፍሬም ተሳክቶላቸው በሠላማዊ መልክ የኢትዮጵያን ተቀናቃኝ ወገኖች ለአንድ አላማ ማሰለፍ ከቻሉ ለእሱና ወገኖቹ አደጋ እነደሀነ ነው፡፡

በዚህ አጋጣሚ ሁሉም አካላት ያላቸውን ይዘው በጥንቃቄ ኤፍሬም ወደሚሉት የሰላም መድረክ ቢመጡ ከሁሉም ቅድሚያ የሚሰጠውና ታላቅ ድል ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ሁሉም ተሰልፌበታለሁ ያለውን ጉዳይ ይዞ ጽኑ የሆነ አቋምን በድርድር ለሕዝብ ይፋ ሊያደረግ ይችላል፡፡ አሁንም እላለው እንዱን እነዱ ጠልፎ ለመጣል የሚያደርገው ሴራ የኤፍሬም ኃላፊነት አይደለም፡፡ ይህንን ኤፍሬም አያውቁትም አይቆጣጠሩትም፡፡ የልቁም የተንኮሉ አካል የሆኑት ተቀናቃኞቹ ያውቁታልና፡፡ የአገርና የሕዝብ ጉዳይ ግልጽና ግልፅ ነው፡፡ ችግሩ ያለው ሁሉም የየራሱ በውስጥ በአጋርና ሕዝብ ካባ ጀቡኖ የሚደራደረው የግልና የቡድን ጥቅም መኖሩ ነው፡፡ የአገርና የሕዝብ ጉዳይ አንደን ከአንዱ ጠላት ሊያደርገው አይችልም፡፡ እናም ጠመንጃም ያለው ጠመንጃውን በትከሻው እንደያዘ፣ ሠይፍም ያለው ሠይፉን ይዞ ብዕርም ያለው በጣቶቹ ብዕሩን ይዞ ሕዝብ የሚዳኘው ድርድር ያድርግ፡፡ ጥንቃቄው እባብ ሞኝን ሁለት ጌዜ ነደፈው የሚለው ተረት እንዳይመጣ ነው፡፡ በእርግጠኝነት ኤፍሬም አንተ መጀመሪያ ጠመንጃህን አውርድ፣ አንተም ሰይፍህን አንትመ ብዕርህን አይሉም፡፡ ሁላችሁም ከእነማንነታችሁ ኑ እንወቃቀስ ባይ ናቸው ኤፍሬም፡፡  ሌሎች በኢትዮጵያ ጉዳይ በተንኮል በገባችሁ መጠን ሴራችሁን ይፋ እያደረጋችሁ እነደሆነ ተረዱ እንጂ አይታወቅብንም ብላችሁ አታስቡ፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!

አሜን!!

ሰርጸ ደስታ

ሕብር ራድዮ ሙሉ ፕሮግራም: የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማሳፈን በሚሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ አውጥቷል የሚል ወቀሳ ቀረበበት.. እና ሌሎችም

0
0
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 18 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…መንግስት ራሱ ገዳይ ሆኖ በራሱ መዋቅር ውስጥ ያለ ከዚህ ቀደም ባለው ሪከርድ የመንግስትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመሸፋፈን ብቻ ሳይሆን ያንን የሚያጋልጡ ሪፖርቶችን የሚያወጡትን የሚያወግዝ የስርዓቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ የተደረገውን ግድያ አጣራለሁ ማለቱ ተአማኒነትም ተቀባይነትም የሚያመጣ አይመስለኝም …የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን መረጃ በተመለከተ ይሄ ተቋም መረጃዎችን ለማሸሽም ሆነ ለመደበቅ ከመሞከሩ በፊት ግን… >

አቶ ያሬድ ሀ/ማሪያም የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ለኢትዮጵያ ማህበር ዋና ዳይሬክተር ከቤልጂየም   በወቅታዊ አገዛዙ ራሱ ገሎ ራሱ አጣራለሁ ስላለው የኦሮሚያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት   ጉዳይ ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ   (የመጀመሪያውን ክፍል ያዳምጡት)

 <…የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ከተለያዩ ማህበረሰብ የመጡ የነገዋ ኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያሳስባቸው በሚያስማማቸውም በሚለያዩበትም ጉዳይ በቪዥን ኢትዮጵያው ጉዳዔ ላይ መክረዋል። ይሄ አስደሳች ነው   ኢትዮጵያውያን ለመተማመን መነጋገር አለብን ነው የእኛ መርህ እኔም በዚያ ተገኝቼ የሲቪል ማህበረሰቡ ሚናን በተመለከተ በተሰጠኝ ርዕስ ተናግሬያለሁ ይህ መሰሉ ውይይት በየቦታው መቀጠል አለበት የእኛም በሚኒሶታ በቅርቡ የምናደርገው ውይይት ጠቀሜታው ይሄው ነው።መነጋገር መቀራረብ መስማማት ያለብን ዛሬ ነው… >>

 አቶ ኦባንግ ሜቶ በዋሽንግተን ዲሲ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ጋር ያዘጋጁትን ጉባዔ አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

 <…የአሜሪካ ምርጫ በአሜሪካ የምንኖር ኢትዮጵያውያን የመምረጥ መብት ያለን መብታችንን ተጠቅመን መምረጥ አለብን…ከኢትዮጵያ የወደፊት ጉዳይ አንጻር ሳየው ከኦባማ አስተዳደር የክሊንተን የተለየ አይመስለኝም ። በበኩሌ ትራምፕ የሚያሸንፍ አይደለም ቢሆን ደስ የሚለኝ በርኒ ሳንደርስ ነው ግን የኔ ግምት… >

አቶ ከባዱ በላቸው ከዋሽንግተን ዲሲ የአሜሪካን የምርጫ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ አሜሪካውያን መራጮች ያለውን ጠቀሜታ አስመልክቶ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ከሰጡን ምላሽ( ሙሉውን ያዳምጡ)<… በምርጫው ውስጥ ያለንን ተሳትፎ ማሳደግ የመምረጥ መብታችንን መጠቀም እኛንም ሆነ ልጆቻችንን የሚመለከት ጉዳይ ነው ።የዲሞካራት ፓርቲን በተመለከተ አሁን ካለው የቅድሚያ የምርጫ ሒደት አኳያ ክሊንተን እየመራች ነው ።ፓርቲውን ወክላ ተወዳድራ ካሸነፈች የኦባማ አስተዳደር የሚከተላቸውን ጉዳዮች የምታስቀጥል ነው…የኔም ግምት…>

አቶ ዮሴፍ መንገሻ በቬጋስ የቀድሞው የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር ዋና ጸሐፊ ስለ አሜሪካ ወቅታዊ ምርጫ ከሰጡን ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉ ውይይቱን ያዳምጡት)

<…የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ያወጣው በቬጋስ የታክሲ ሊዝ ስለሚደረግበት ሁኔታ የሚመለከተው በአግባቡ መታየት አለበት ። ዲፖዚት ያስቀምጣል ይላል ይሄ ዲፖዚት ምን ያህል ነው ከዲፖዚቱ ላይ ኩባንያው የሚቀንሰው ለእንዴት ላሉ ጉዳዮች ነው? ግልጽ አይደለም…>  

አቶ ቢኒያም ሰመረአብ የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ያወጣውን የታክሲ ሊዝ ተግባራዊ ስለሚሆንበት ሁኔታ ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)የአውሮፓ ሕብረት እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን አገሮች (ናቶ) መዲና በሆነችው ቤልጂየም ብራስልስ ከተማ የሰሞኑ የሽብር ጥቃት ጠንሳሾች ማንነት እና ዓለማቀፋዊ ምላሾቹ ሲቃኙ ( ልዩ ጥንቅር) ሌሎችም

 ዜናዎቻችን

የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማሳፈን በሚሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ አውጥቷል የሚል ወቀሳ ቀረበበት

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቻይና ዕዳ ሳቢያ ጥንቃቄ ካልታከለበት ሊንኮታኮት እንደሚችል ታዋቂ የኢኮኖሚ ባለሙያ አስጠነቀቁ

በማዕከላዊ የታሰሩ የኦሮሞ ተወላጆች በረሃብ አድማ ሳቢያ ጉዳት ደርሶባቸው 31 ሆስፒታል ገቡ

በጎንደር ኳስ ጨዋታ ለማየት በስታዲየም የተገኘው ሕዝብ አገዛዙ በወልቃይት ላይ የሚወስደውን ግፍ አወገዘ

ይለያል ዘንድሮ የኢህአዴግ ኑሮ ሲል ተቃውሞ አስምቷል

በኢትዮጵያ የተከሰተው የረሃብ አደጋ አስከፊ እየሆነ መሄድ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ሆነ

በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዛሬም አላባራም

በትግራይ የባጃጅ ሾፌሮች የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ታገደ

በአዲስ አበባ ታክሲዎች ዳግም የስራ ማቆም አድማ ያደርጋሉ የሚል ግምት አለ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live