Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ለሱማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውድድር ራሷን ያዘጋጀችው ብቸኛ ሴት ፋጡማ ዳይብ

$
0
0

fatuma

ፋጡማ ዳይብ ለፕሬዘዳንታዊው ውድድር ራሷን በማቅረብ የመጀመሪያዋ ሴት ሱማሊያዊት ሆናለች፡፡

በያዝነው ዓመት በነሐሴ ወር እንደሚካሄድ በሚጠበቀው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ለመሳተፍ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ እንደምትገኝ የምትናገረው ፋጡማ በምርጫው አሸናፊ በመሆን አገሪቱን የመምራት ዕድል ካገኘች ከአልሻባብ ጋር ለመነጋገር በጠረጴዛ ዙሪያ እንደምትቀመጥ አስታውቃለች፡፡‹‹ከአልሻባብ መሪዎች ጋር በመነጋገር ችግሮችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት እሞክራለሁ››ብላለች፡፡

ለራዲዩ ዳልሳን ቃለ ምልልስ የሰጠችው ፋጡማ ይህንን ትበል እንጂ አልሻባብ አጥባቂ የእስልምና ህግ ተከታይ በመሆኑና በአገሪቱ ያለው የባህል ገደብ ምኞቷን ማሳካት መቻሏን ጥርጣሬ ውስጥ ይጥሉታል፡፡

‹‹እነርሱ የእኛ ወንድሞችና ልጆች ናቸው፡፡እኛን እየጎዳን በሚገኘው ችግር ዙሪያ መነጋገር ይኖርብናል፡፡ይህንን የማድረግ ስህተት ደግሞ አይታየኝም››ማለቷ ተሰምቷል፡፡

በምርጫው አሸናፊ ከሆነችም ቀዳሚ ተግባርዋ የሴቶችንና የልጆችን አቅም ማጎልበት እንደሚሆን የምትናገረው ፋጢማ ‹‹የሚበዙት የዚህች አገር ልጆች የትምህርትና የጤና ሽፋን ያላገኙ ናቸው፡፡ተገቢውን እንክብካቤ ያላገኙ በመሆናቸውም ይህንን የማድረግ ኃላፊነት አለብን››ብላለች፡፡

አሁን ላሉት የአገሪቱ የፓርላማ አባላት ባስተላለፈችው መልእክትም ከምንም ነገር በላይ ለአገራቸው ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት የምርጫው ጊዜ ሲደርስ ድምጻቸውን እንዲሰጡ ተማጽናለች፡፡

የአራት ልጆች እናት የሆነችው ፋጢማ በወንዶች ቁጥጥር ስር በወደቀችው አገሯ ፕሬዘዳንታዊ ውድድር ላይ ለመሳተፍ መፈለጓን በገለጸችበት ቅጽበት የግድያ ዛቻ የደረሳት ቢሆንም ህልሟን ከማሳካት ምንም ነገር እንደማያቆማት አስታውቃለች፡፡

ምንጭ ቢቢሲ

The post ለሱማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውድድር ራሷን ያዘጋጀችው ብቸኛ ሴት ፋጡማ ዳይብ appeared first on Zehabesha Amharic.


Health: የወንዶች ሳይኮሎጂ |ወንዶች የማያውቋቸው በሳይንስ የተደረሰባቸው 7 ጉዳዮች

$
0
0

 

ታይም መጽሔት ይዞት የወጣው ጉዳይ በጣም እያነጋገረ ነው፡፡ መጽሔቱ ‹‹የወንዶች ሳይኮሎጂ›› በሚለው ርዕሰ ጉዳዩ ስር ወንዶችና ሴቶች፣ ፍቅርን እንዲሁም ወሲብን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ በስፋት ይተነትናል፡፡ ለትንታኔውም ዋቢ ያደረገው የተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶችን ነው፡፡ እኛም በአጭሩ በሚገባ መልኩ እንዲህ አቀናብረነዋል፡፡

make love

1. ቆንጆ ወንዶች ሃብታም በሆኑ ቁጥር ሴቶች ለጋብቻ አይመርጧቸውም እየተባለ ነው (ይፈሯቸዋል)

ሴቶች ውበት፤ ሀብትና ዝና ካላቸው ወንዶች ጋር ለፍቅር ካልሆነ በስተቀር ትዳር ውስጥ ዘሎ ለመግባት ይቸገራሉ ይላል አንዱ ጥናት፡፡ በተለይ ወንዱ ውበትና ሃብትን በአንድ ላይ አጣምሮ ከያዘ እንዲሁም ዝናና ሀብትን ካጣመረ ወይም ውበትና ዝና ካለው በትዳር ውስጥ ታማኝ አይሆንም የሚል እምነት አላቸው፤ ሴቶች፡፡ እንዲህ አይነት ወንዶች ሌሎች ሴቶችን በቀላሉ የማማለል አቅም ስላላቸው በትዳር ውስጥ አዋጭ አይደሉም ብለው ያምናሉ፡፡ በመሆኑም ይላል ጥናቱ የሴቶችን እምነት ጠንካራ ለማድረግ እንዲህ መሰል ወንዶች ታማኝነታቸውን በተደጋጋ ሊያሳዩ ይገባል ይላል፡፡

በዚህ ረገድ የተሰራው ጥናትም በአካላዊ ውበታቸው ሳቢ የሆኑ ወንዶች ተመረጡ፡፡ ከዚያም እነዚህን ወንዶች ከፍተኛ፤ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እንደሆኑ አድርገው መደቡና ሴቶች ከታማኝነትና ከላቀ የባልነት ዋጋ አንፃር የራሳቸውን የግል ምርጫ እንዲያደርጉ ቀርቦላቸው የተገኘው ውጤት ከላይ ያለውን አስገራሚ ውጤት ያስገኝ ነበር ይላል መፅሔቱ፡፡

2. ወንዶች ቀልድ አዋቂነታቸው በጨመረ ቁጥር የሚወዷቸው ሴቶች ቁጥር ይንራል ተብሏል (አደጋ አለው)

አንድ ወንድ በቀልዱ ብዛት ከምን ያህል ሴቶች ጋር ሊተኛ እንደቻለ ማወቅ ይፈልጋሉ? ሲል ይጠይቃል፡፡ አስቂኝ ቀልድ የሚችሉ ወንዶች ከሌሎች ወንዶች ይልቅ ለፍቅር በተሻለ ደረጃ በሴቶች ይመረጣሉ ይላል፡፡ ይህም የሚሆነው አስቂኝ ባህሪ በራሱ የልዩ አዕምሯዊ ብቃትና የፈጠራ ችሎታን እንዲሁም የመልካም አባታዊ ባህሪን ለሴቶች የመጠቆም ኃይል ያለው በመሆኑ ነው ይላል መፅሔቱ፡፡ ልዩ የአዕምሮ ብቃት በራሱ አስቂኝ ነገሮችን የመፍጠር ችሎታ አለው፤ የማሳቅ ችሎታ ደግሞ በራሱ የፍቅር ጥምርታ ስኬትን ይጠቁማል፡፡

በዚህ ረገድ 400 የሚሆኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች (200 ወንዶችና 200 ሴቶች) ላይ ጥናት ተደርጎ ነበር፡፡ የመጀመሪያው ጥናትም አስቂኝ ነገሮችን ለመፍጠር የሚያስፈልጉ ሁለት መሰረታዊ ብቃቶች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ የመጀመሪያው ንግግራዊ ብቃት (Verbal intelligence) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አጠቃላይ የአዕምሮ ብቃት (General intellignece) ላይ ነበር፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም አስቂኝ ነገሮችን የመስራት ችሎታን የሚመረምር ፈተናም ነበር፡፡ በጥናቱ ውጤትም ከፍተኛ ብቃት (ኢንተለጀንስና) አስቂኝነት ከፍተኛ ትስስር ያላቸው ሲሆን እነዚህ ወንዶች ደግሞ በሴቶች ዘንድ ከሌሎች ይልቅ በከፍተኛ ደረጃ ለፍቅር መመረጣቸውን አመልክቷል፡፡ በጥናቱ ላይ እንደታየው ወንዶች ከሴቶች ይልቅ የበለጠ ቀልድ ይችላሉም ብሏል፡፡ በወንዶችም ዘንድ የበለጠ ለፍቅር የተመረጡት ቀልድ የሚችሉት ሴቶች ሆነው ተገኝተዋል፡፡

አስቂኝነት ፍቅርና ወሲብ ቀስቃሽነት ያለውም ከኢንተለጀንስ (ልዩ ብቃት) ጋር የሚያያዝ ስለሆነ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ደግሞ ብቃት ያለውን ሰው ማፍቀር ይፈልጋል፡፡ ልዩ ብቃት የጥሩ ዝርያ መገለጫ መጠቆሚያ ስለሆነም ሲሆን ከእንዲህ መሰሉ ምርጥ ዘር ባለቤትም ዘር መቀላቀልንም ተቃራኒ ፆታዎች ይፈልጉታል ይላል ጥናቱ፡፡

3. ሴት የወለዱ የመስሪያ ቤት አለቆች ለሴት ሠራተኞቻቸው ከፍተኛ ደመወዝ በመክፈል ያዳላሉ ተብሏል (የበለጠ ሴት ይውለዱ ያሰኛል)

ሴት ልጅ ያላቸው የድርጅት አመራሮች ለሴቶች ሠራተኞቻቸው የተሻለ ደመወዝ ይከፍላሉ ይላል ሌላኛው ጥናት፡፡ (Women’s salaries are higher when the boss has a daughter)፡፡ በዚህ ረገድም የተደረገው ጥናት ይህንኑ አመልክቷል ይላል ታይም መፅሔት፡፡ የወንዶች ፆታ ተኮር ገፀ ባህሪና ጾታዊ አመለካከት በሴት ልጆቻቸው አማካኝነት ተፅዕኖ ትንሽ የባንክ አካውንት እንዳላቸው አድርገው ያሰቡት የፍቅር ምርጫቸው ሳያውቁት ተቀይሮ ወፍራም ዳሌና ጡት ያላቸውን ሲመርጡ ቀሪዎቹ ደግሞ ቀጫጭኖቹን መርጠዋል ይላል ጥናቱ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም ሆዳቸው የጠገበና የተራቡ ተማሪዎች ላይ የተገኘው ውጤት ሆዳቸው የሞላ ወንዶች ቀጫጭን ሴቶችን ሲመርጡ ሆዳቸው የተራቡ ደግሞ ተጨማሪ ቅባት የተሸከሙ ሴቶችን መርጠዋል ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም የተራቡት ከጠገቡ በኋላ፤ የጠገቡትም እንደገና ከተራቡ በኋላ በተደረገው ቅኝትም ምርጫቸው ከበፊቱ ተቃራኒ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ይህም ምንን ሊያመለክት እንደሚችል ባለሙያዎቹ ሲያብራሩም ወንዶች ገንዘብ ሲያጡ ህይወት የምትታያቸው ከምግብ እጥረት ጋር ነው፡፡ ሲራቡም ይህንኑ ያስባሉ፣ ይላሉ አጥኚዎቹ፡፡ በመሆኑም ሰውነታቸው በውስጡ ለተጨማሪ ካሎሪ እንዲጓጓ ይሆናል፡፡ ይህም ተጨማሪ ካሎሪ ደግሞ ከስብ (ቅባት) ጋር የተያያዘ በመሆኑ ወንዶች ኪሳቸው ሲዳከምና ሆዳቸው ሲጎድል ወፈርፈር ባሉ ሴቶች የበለጠ ተፈጥሯዊ ስሪታቸው ይማልላል በማለት ጉዳዩን ይፈቱታል፡፡ ይህ የሚያሳየው እንግዲህ በፆም ወቅት ወፍራም ሴቶች አማላይ ሲሆኑ በሀብታሞች ሰፈር ደግሞ ቀጫጭኖቹ ልብ ሰቃይ ናቸው እንደማለትም ነው፡፡

4. ወንዶች ሚስቶቻቸውን በተጠራጠሩ ቁጥር ልጆቻቸው የእነሱ ያለመሆን ዕድላቸው ይጨምራል

አንድ ወንድ ልጅ የወለዳቸው ልጆቹ ከእሱ ዘር ያልተወለዱ የመሆናቸው ዕድል ምንያህል ሊሆን እንደሚችል ያውቃሉ? በአማካይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ10 ልጆች ውስጥ አንዱ (ዷ) ከአሳዳጊ አባቱ ያልተወለደ(ች) ነው ይላሉ ጥናቶች፡፡ ነገር ግን ይህ ቁጥር በጣም ትንሽ ወይም በጣም ትልቅ የሚሆንበት ዕድልም አለ ተብሏል፡፡

እንደሚታወቀው ምን ጊዜም ልጅን አምጣ የምትወልደው እናት ስትሆን ወንዱ ለፅንስ የሚሆን ዘር ከማበርከት የዘለለ ሚና የሌለው በመሆኑ እናትነት ምንጊዜም እርግጠኝነት ሲሆን አባትነት ግን እምነት ነው ይላሉ አበው ሲተርቱ፡፡ ተመራማሪዎችም ጉዳዩን ‹‹አዎ ትክክል ነው!›› እያሉ ነው፡፡ አንድ ወንድ ሚስቱን በጣም የሚያምናት ከሆነ የወለዳቸው ልጆች የእሱ የመሆን ዕድላቸው በጣም ከፍተኛ ነው ማለትም የእሱ ያለመሆን ዕድላቸው ከ10 በመቶ ያነሰ ሲሆን (ዜሮ ግን ሊሆን አይችልም)፤ ነገር ግን ወንዱ ሚስቱን የሚያምናት ከሆነ የወለዳቸው ልጆ የእሱ የመሆን ዕድላቸው እስከ 33 በመቶ ከፍ ይላል ተብሏል፡፡ (ከ3 ልጆች ውስጥ አንዱ) የእሱ ላይሆን ይችላል ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ይላሉ ባለሙያዎቹ ሚስቶቻቸውን ባለማመን (አባትነታቸውን በመጠራጠር) ልጆቻቸውን ዲኤንኤ የሚያስመረምሩ ወንዶች አባት ያለመሆን ዕድላቸው ከአማኞች ይልቅ ጨምሮ ተገኝቷል፡፡

5. ወንዶች በቆንጆ ሴቶች የሚቀርቡ የቴሌቪዥን ዜናዎችን ማስታወስ አይችሉም ተብሏል (የት እየሄዱ ይሆን?)

በቆንጆ ሴቶች የቀረቡ የቴሌቪዥን ዜናዎች ወንዶች መልሰው የማስታወስ አቅማቸው ደካማ ሆኖ መገኘቱ ሌላው የወንዶች አስቂኝ ባህሪ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ እንደ ጥናቱ እይታም ወሲብ ቀስቃሽ መልክ፣ አለባበስና ቁመና ባላቸው የሚቀርቡ ዜናዎች በወንዶች ሴቶች ልብ ውስጥ ዘልቀው የመግባትና የመታወስ ዕድላቸው ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ወንዶች እንዲህ አይነት መስህብነት ያላት ሴት ፖለቲካ፣ ስፖርታዊና ጦርነት ነክ ጉዳዮች መያያዝ አለባት (ሪፖርት ማድረግ አለበት) ብለው ለመቀበል ውስጣቸው ስለሚቸገር ነው ይላል ሪፖርቱ፡፡ ይህችው ሴት መስህነት በሌለው አለባበስ ቀርባ ዜናውን ስትሰራ ግን መረጃውን በውስጣቸው የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ይሁን እንጂ ተመሳሳዩ የትውስታ ጥንካሬና ድክመት በሴት ቴሌቪዥን ተመልካቾች ላይ አልታየም፡፡ ለሴቶች ዜናው መስህብነት ባላቸውም ሆነ በሌላቸው ሴቶች ላይ መቅረቡ በትውስታቸው ላይ ለውጥ አላመጣባቸውም፡፡ እንደውም ወሲብ ቀስቃሽ በሚያንፀባርቅ መልኩ በቀረቡ ሴቶች በበለጠ መልኩ ሴት ተመልካቾች የበለጠ የማስታወስ ብቃታቸው ጨምሮ ተገኝቷል፡፡ (ከወንዶቹ ፈፅሞ ተቃራኒ መሆኑ ነው) ምናልባት ይህ የሚሆነውም ወንዶቹ ሳያውቁት በመስህባዊ ሴቷ አለባበስ ልባቸው ስለሚሰረቅም ነው ተብሏል፡፡

6. ወንዶች ሴቶችን ለማማለል በማያግዝ መስሪያ ቤት ውስጥ ለመቆየት ይቸገራሉ ተብሏል

ወንዶች የተሰማሩበት የሙያ መስክ ወይም የሚሰማሩበት መስሪያ ቤት ሴቶችን በቀላሉ ለመሳብ የማያስችላቸው ከሆነ የሥራ ፍላጎታቸው ይቀንሳል ይላል አዲሱ ጥናት፡፡ ባለሙያዎች እንደሚሉት ወንዶች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ ሳያውቁት የሙያ ምርጫቸው ላይ ተፅዕኖ የሚያደርግባቸው አንዱ ምክንያት ሙያው ወደ ፊት የሚፈልጉትን አይነት ሴት ለመሳብና ለማግባት የሚያግዝ ሚና የመኖሩ ወይም ያለመኖሩ ጉዳይ ነው፡፡

በዚህ ረገድ ዕድሜያቸው ከ16-36 ዓመት በሆናቸው ወንዶች የመረጡት የሙያ ዘርፍ ወደፊት የሚፈልጉትን አይነት ሴት ለማግባት የማያስችላቸው ከሆነ በኮሌጅ ደረጃ የማጥናት እና የመማር ፍላጎታቸው እንደሚቀንስ በሥራም ቦታ የሥራ ትጋታቸው እንደሚወርድ ነው፡፡ የጥናቱ ባለሙያዎች እንደሚሉትም ወንዶች የሚመርጡትን ሙያና የሚሰሩትን ሥራ ለመምረጥና የበለጠ ለመትጋት ወደፊት ከሚያመጣላቸው ክፍያ ባሻገር ለሴት አፍቃሪ ምርጫቸውም የጎላ ሚና ለሚጫወተው መሆኑ ሌላው አጃኢብ ያሰኘ የወንዶች ጉድ ሆኗል፡፡

7. ወንዶችም በወሲብ እርካታ እንደ ሴቶች ያጭበረብራሉ ተብሏል (ሴቶች ነቃ በሉ)

ወንዶች እንደ ሴቶች በወሲብ የመርካት ምልክቶችን እንደሚያጭበረብሩም በጥናት ከታዩት አስገራሚ ትዕይንቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ከአሁን ቀደም የሚታመነው ሴቶች ብቻ ወንዶቻቸውን ላለማጣት ሲሉ በወሲብ ሳይረኩም እንደ ረኩ የማስመሰል ዝንባሌ እንዳላቸው የታወቀና አብዛኛዎቹ ሴቶችም ‹‹Sake Orgasm›› ማለትም የማስመሰል እርካታን እንደሚያሳዩ ይታወቅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ሴቶቹ ባይበዛም 50 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች በተመሳሳይ መልኩ የወሲብ እርካታን እንደረኩ አድርጎ የማስመሰል ዝንባሌን ይከተላሉ ይላል መጽሔቱ ተብሏል፡፡ ወንዶች ለምን እንዲህ እንደሚያደርጉም ባለሙያዎቹ የደረሱበት ጉዳይ ሴቷ ባታረካቸውም ለሴቷ ስነልቦና ሲሉ ወይም ሁኔታው ስላላስደሰታቸው ቶሎወ ሲባዊ ክንዋኔውን ለማቆም ሲፈልጉ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ሆኖም ባለሙያዎች የሚመክሩት እርካታን በተመለከተ ወንዱ ሴቷ ሳትጨርስ (ስትረካ) ቀድሞ መጨረስ (የእርካታ ጣሪያ ላይ መድረስ) እንደሌለበት ነው፡፡

The post Health: የወንዶች ሳይኮሎጂ | ወንዶች የማያውቋቸው በሳይንስ የተደረሰባቸው 7 ጉዳዮች appeared first on Zehabesha Amharic.

የተፐወዙት የነዳባ ደበሌ ጉዳይ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ እስኪወስን እየተጠበቀ መሆኑ ተሰማ

$
0
0

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ በአዳማ ለአምስት ቀናት ባደረገው ኮንፈረንስ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ሁለት የድርጅቱን ከፍተኛ ባለስልጣናት ማንሳቱን ባሳለፍነው ወር ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡ሁለቱ ባለስልጣናት ከቦታቸው እንዲነሱ የተደረጉትም ከአመራር ጉድለት ጋር በተያያያ መሆኑን ድርጅቱ ያወጣው መግለጫ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

ዳባ ደበሌ

ዳባ ደበሌ

የኦህዴድና የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣የኦህዴድ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊና የክልሉ ምክትል ፕሬዘዳንት የነበሩት ዳባ ደበሌ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ቢወሰንም የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እንደሆኑ ይቀጥሉ ተብሎ ነበር፡፡

እንደ ዳባ ደበሌ ሁሉ የአህዴድና የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩትና በኦሮሚያ ክልል የተፈጥሮ ሐብት ቢሮን ሲመሩ የቆዩት ዘላለም ጀማነህ ከሁለቱም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸውና ከስራቸው እንዲነሱና ድርጅቱ በቀጣይ የሚያሳልፈውን ውሳኔ እንዲጠባበቁ ተነግሯቸዋል፡፡

ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በተባረሩበት ወቅትም የክልሉ የደህንነትና የአስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ሰለሞን ቁጩም መባረራቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ተባራሪዎቹ የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት እስካሁን ላልበረደው የህዝብ ተቃውሞ መባባስ ምክንያት ተደርገው ተወስደዋል፡፡የህዝቡን ጥያቄ በፍጥነት ለመመለስና መፍትሄ ለመፈለግ በመዘግየታችሁ እዚህ ደርሰናል ተብለው መወቀሳቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኦህዴድ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት ዳባ ደበሌ የተቃውሞ እንቅስቃሴውን በተመለከተ በየጊዜው ለጋዜጠኞች መረጃዎችን በመስጠትና ህዝቡ ያነሳው ጥያቄም ተገቢና ኦህዴድም የሚያምንበት መሆኑን ሲናገሩ መቆየታቸው አይዘነጋም፡፡

ዳባ ደበሌና ዘላለም ጀማነህን በተመለከተ ኦህዴድ የወሰደውን ውሳኔ በመደገፍም የፌዴራል መንግስቱ የኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት አስተያየቱን መስጠቱ ተስተውሏል፡፡የኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤቱ በሰነዘረው አስተያየት ‹‹ሰዎቹ የተባረሩት በአቅም ማነስ፣የስራ ኃለፊነትን በአግባቡ ባለመወጣትና በኪራይ ሰብሳቢነት ተገምግመው የታገዱ ናቸው››ብሏል፡፡

የኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት በይፋዊው የማህበረሰብ ገጹ ባሰፈረው መልእክት ዘላለም ጀማነህ በህግ የሚጠየቅበት አግባብ ሊኖር እንደሚችልም አመልክቷል፡፡

ለሳተናው እንደደረሰው መረጃም ከሆነም በቅርቡ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የተሰናበቱትን ሰዎች በተመለከተ ሊወሰድ ስለሚገባው ህጋዊ እርምጃ በመነጋገር ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃሉ፡፡ጉዳዩ አፋጣኝና እልባት ማግኘት የሚገባው ሆኖ በመገኘቱም በይደር መተው የለበትም በማለት የተከራከሩ አባላት ቢኖሩም በቀጣይ በሚደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ውሳኔ እንደሚሰጥ መነገሩንም ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡

አቶ ዘላለም ጀማነህ የቁም እስር በሚመስል መልኩ የመንቀሳቀስ መብታቸው ተገፉ እንደሚገኙ የሚናገሩ የሳተናው ምንጮች ዳባም ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ ብዙም እንደማይታዩ ይናገራሉ፡፡በጣም በቅርቡ ኦህዴድ በሚያደርገው ስብሰባም በዋናነት ዳባና ዘላለም የእጅ ካቴና ሊጠልቅላቸው እንደሚችልም ምንጮቻችን ግምታቸውን ያሰቀምጣሉ፡፡

The post የተፐወዙት የነዳባ ደበሌ ጉዳይ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ እስኪወስን እየተጠበቀ መሆኑ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሕወሓት ልዩ ኃይል በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ካምፓስ የተማሪዎች መኝታ ክፍል ተኩስ ተከፈተ

$
0
0
File Photo

File Photo

(ዘ-ሐበሻ) በጅማ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ካምፓስ ተማሪዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ በሕወሓት ወታደሮች በቅጥር ጊቢውና በተማሪዎች መኝታ ክፍል ተክስ መክፈታቸው ተሰማ::

ከአካባቢው ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች እንዳመለከቱት ኦሮሚያን በ8 ዞኖች ከፋፈለው ከሚመሩት የሕወሓት የመከላከያ ሰዎች መካከል የሆኑት ወታደሮች በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመቀጥቀጥ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው የደረሰን መረጃ አመልክቷል::

እንደ ዓይን እማኞች ገለጻ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ካምፓስ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ይገኛል:: በርካታ ተማሪዎች በጥይት እና በደረሰባቸው ቅጥቀጣ ተጎድተዋል::

The post የሕወሓት ልዩ ኃይል በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ካምፓስ የተማሪዎች መኝታ ክፍል ተኩስ ተከፈተ appeared first on Zehabesha Amharic.

ወልቃይት ፀገዴና ፀለምት፥ በዐይኔ ካየሁትና ከታዘብኩት |በያሬድ ጥበቡ

$
0
0

Yared Tibebu

መግቢያ

የዛሬ 39 አመት ግድም ለሶስት አመታት ያህል ከሰኔ 1969 እስከ ሰኔ 1972 አም ድረስ በፀለምት፥ ዋልድባ፥ ቆላወገራና ወልቃይት ውስጥ የኢህአፓ ሰራዊት አባል በመሆን በእግሬ ተጉዣለሁ ። በአማካይ በቀን 5 ሰአት እንጉዋዝ ስለነበር ፥ በአመት 9000 ኪሎሜትር፥ በሶስቱ አመት ቆይታዬ 27000 ኪሎሜትር ያህል መንገድ ተጉዣለሁ ማለት ነው። ዛሬ እነዚህ አካባቢዎች በነዋሪው ህዝብና በአገዛዙ መሃል የማንነት ጥያቄ የውጥረት ማእከል ሆነዋል ። ከ39 አመታት በፊት ወልቃይትንና ፀለምትን ሳውቃቸው ምን ይመስሉ እንደነበር የማስታውሰውን ያህል ባካፍልስ ብዬ ብእሬን አነሳሁ ።

የምሰጠው ምስክርነትና የማነሳው ክርክር በማውቀው የመልክእምድር አቀማመጥና የህዝቡ ባህል ላይ የተመሰረተ ነው ። የክርክሬ ማጠንጠኛ፥ እንደ ተከዜ አይነት ታላላቅ የተፈጥሮ ወሰኖች በትናንሽ አይዲዮሎጂዎች ቢገሰሱ ከፍተኛ ውዝግብና አለመረጋጋትን
ስለሚያስከትሉ ጥንቃቄን ይሻሉ የሚል ነው ። በተጨማሪም የተከዜን አይነት የተፈጥሮ ወሰኖች ተሻግረው ከአጎራባች ህዝብ እቅፍ ውስጥ የተስተናገዱ ማህበረሰቦች፥ ያስጠጋቸውን ህዝብ ማንነት የመፈታተን መብት ሊኖራቸው አይገባም ብዬም ለመከራከርም ነው ።

ተከዜ ፥ ታላቁ የተፈጥሮ ወሰን
ወሎና ጎንደርን አያዋሰነ ተከዜን ከሚቀላቀለው የፅላሬ ( ጥራሪ) ወንዝ ጀምሮ፣ ትግራይንና ወሎን፣ ትግራይንና ጎንደርን፣ ከዚያም ጎንደርንና ኤርትራን የሚያዋስነውን ታላቁን የተከዜ ወንዝ፣ ከምንጩ ከኩል መስክ ተነስቶ ሱዳን ከሰላ አካባቢ እስኪገባና አትባራ ተብሎ
እስኪሰየም፣ በነዚህ በተጠቀሱት የክፍላተሃገራት ወሰኖች ሁሉ በእግሬ ያቆራረጥኩና በሁለቱ አይኖቼ ያየሁ ሰው በመሆኔ፣ ስለ ድንበር አካለዩ ተከዜ መናገር ከሚችሉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን መሃል ነኝ ።

በመጀመሪያ ተከዜን ያየሁት በሰኔ 1969 ሀይል 17 የምትባል የኢህአፓ ሰራዊት አባል ሆኜ፣ ከአሲምባ ትግራይ ተነስተን ወደ ፀለምት ጎንደር ባደረግነው ጉዞ ወቅት ነው ። የግባን ወንዝ ስንሻገር የኮንጎ ላስቲክ ጫማዬን የሰኔ ውሃ ሙላት ይዞት ሄዶ ስለነበር፣ በጨርቅ በተጠቀለለ እግር እየተጓዝኩ ነው ተከዜን የተሻገርኩት ። ወደፀለምት መሻገሪያው በጣም ረበዳ ሸለቆ ስለነበር፣ የተከዜን ገመገም ጠዋት መውረድ የጀመርን፣ ወንዙን ተሻግረን አቀበቱን እስክንወጣ ቢያንስ የስድስት ሰአት መንገድ እንደወሰደብን ትዝ ይለኛል ። እጅግ አድካሚ ጉዞ ነበር ። ከሰአት በኋላ ፀለምት ውስጥ ከሚገኝ መንደር ደረስን ። ከፀሀይመግቢያ አቅጣጫ ታላቁ የአቤር ተራራ ቁልቁል በንቀት ይመለከተንም፣ ያስፈራምእንደነበር ትዝ ይለኛል ። ቁልቁል ወደመጣንበት የተከዜ ሸለቆ የሚገፈትረን ነበር የሚመስለው ። ልክ እንደኛ ሁሉ አስቸጋሪውን የተከዜ ሸለቆ አቋርጠው የመጡ የትግራይሰዎች ከነባሩ የስሜን ሰው ጋር የፀለምትን ማህበረሰብ መስርተው፣ ትግርኛም አማርኛም እየተናገሩ ይኖራሉ ። ከአዴት፣ ከአቢይ አዲ፣ ከአክሱም አካባቢ ከጉማ አምልጠው ወይም የሰው ህይወት አጥፍተው፣ ወይም ችግር አብሮአቸው ፀለምት ላይ ከወባና ወበቅ ጋር እየታገሉ፣ የተከዜን ገመገም ይዘው የሰፈሩ የትግራይ ሰዎች ብዙ ናቸው ። ጎንደር መሬት ላይ የሰፈሩ ትግራዋዮች።

አሲምባ የነበረው የኢህአፓ ሰራዊት በየካቲት 1970 አም “ትግራይ ለትግሬዎች” በሚል በህወሐት ድንገት ያልታሰበ ጥቃት ተሰንዝሮበት በብዙ መቶ ለሚቆጠሩ ጓዶች ሞትና መቁሰል ምክንያት ሆነ። ትግራይ ውስጥ መቆየት ስላልተቻለም ወደ ኤርትራ ማፈግፈግ የግድ ሆነ። ሰራዊቱ በጀብሀ አስጠላይነት ስር ስድስት ወራት ተኮምቢያ አካባቢ፣ ጋሽ ወንዝ ዳር ከከረመ በኋላ መሰከረም 1971 ላይ ወደ ፀለምት ሲመጣ፣ የተከዜን ወንዝ ለመሻገር ስንት መከራና ችግር ማለፍ ነበረበት ። ተከዜ እስኪጎድል ኤርትራ ውስጥ በነበረው ቆይታ ወቅት በረሃብ የተነሳ የሰንሰል ቅጠል እንደ ጎመን እየቀቀለ ተመግቧል፣ ጋሽ ወንዝ እያላጋ ያመጣውን የግመል ሬሳ ስጋ በልቶ በተቅማጥ ተሰቃይቷል ። ፀሊም ቤቶች የሚኖሩበትን የወልቃይት ቆላ መዘጋ አቆራርጦ ዛሬማ ወንዝን ተሻግሮ፣ በዋልድባ ገዳም አልፎ ፀለምት መምጣት ነበረበት። ከዋልድባ ወደፀለምት ለመሻገር ግን ወደ ተከዜ የሚገብረው የእንስያ ወንዝ የማይበገር ስለነበር፣ ሰውና አጋሰስ የሚያሻግር ከብረትና ሲሚንቶ የተሰራ አነስተኛ ድልድይ ፀለምት ያለው የሪጅን አመራር አዘጋጅቶ መጠበቅ ነበረበት ። ይህ ሁሉ አበሳ ታይቶ ነበር ሰራዊቱ ከመንፈቅ እንግልት በኋላ ፀለምት የደረሰው ። ፀለምት እንደደረሰም ደርጉ ወረራ አዘጋጅቶ ጠበቀው ። ያንን መመከት የግድ ነበር ። ከደርጉ ጋር የሚደረጉት የመከላከል ውጊያዎች እንደተጠናቀቁም፣ የአሲምባውና የጎንደሩ ጦር
እንዲዋሃድ ተደረገ በዚያን ዘመን ቋንቋ ተቅሊጥ ይባል ነበር፣ አረብኛ ሳይሆን አይቀርም፣ ከኤርትራ ግንባሮች ከወረስናቸው የሽምቅ ቃላቶች መሀል መሆኑ ነው ።

ወልቃይትን እንዳየሁት

የሰራዊቱ ውህደት እንደተፈፀመ፣ እኔ አዲስ በሚከፈተው ሪጅን አራት ውስጥ ተመደብኩና፣ በመጀመሪያ ቆላወገራን ከፀለምት የሚያገናኘውን መስመር ለማለሳለስ እስከ ጃኖራና አጅሬ ድረስ ተጓዝን ። ከዚያም መልስ ወልቃይትን ከኢዴህና ደርጉ ቁጥጥር ነፃ ለማድረግ፣ ከተማይቱን አዲ ረመፅን ለመቆጣጠር ኦፐሬሽን ተዘጋጀ ። ተልእኮውም በቀላሉ ተፈፀመ ። ወልቃይትን ማስተዳደርም ጀመርን ። በሥነምግባራችን ከኢዴህ ቀማኛ ሰራዊትም ሆነ ከደርጉ ማዳፋት ተግባር እጅግ የተሻልን ብቻም ሳይሆን፣ የወልቃይት ህዝብ በመቶ አመታት ታሪኩ ሰምቶትና ገምቶት የማያውቅ ህዝብን አገልጋይ ሰራዊት ሰለነበረን፣ ሊወደንና ሊያፈቅረን ጊዜ አልወሰደበትም ። ቤቱን፣ ማእዱን፣ ጎተራውን ከፍቶ በፍቅር ተቀበለን ። ፍርሃቱ ጥለነው እንዳንሄድ ብቻ ነበር ። የህዝብ አስተዳደር ኮሚቴዎች እያቋቋምን፣ ወንጀለኛ እየቀጣን፣ ቀማኛ እያደንን በሄድን ቁጥር፣ “ፈጣሪ ይህን መልካም አሳይቶ መልሶ አይነሳንም” የሚል የመተማመን ሃሳቡን ህዝቡ ያካፍለን ጀመር ።

የኢህአፓ ተዋጊ ክንፍ የአንዲት አሃዱ ወይም ጋንታ የፖለቲካ ኮሚሳር በመሆን ከፅልእሎ እስከ ቀፍቲያ ፣ ከአዲ ረመፅ እስከ አዲ ጎሹ የህዝብ አደራጅ በመሆን ከወልቃይት ህዝብ ጋር ኖሬአለሁ። ከመሶባቸው ተመግቤአለሁ፣ መደባቸው ላይ ተኝቻለሁ፣ በልጆቻቸው
ሠርግ ታድሜአለሁ፣ በለቅሶና አጎበራቸው ላይ ተቀምጫለሁ። አስተምሬአለሁ፣ ቀስቅሻለሁ ። ከኢዴህ ጋር ሆነው፣ ወያኔን ሲታገሉ ስለከፈሉት መስዋእትነት ሲተርኩ አድምጫለሁ። “ገዳይ ደደቢት ፣ መጠጊያ ድንጋይ በሌለበት”ብለው ሲፈክሩ ተመልክቻለሁ ። ብቻዬንም አልነበርኩም፥ በመቶ የሚቆጠሩ አብረውኝ የነበሩ ታጋዮች ዛሬም በአሜሪካ ይገኛሉ ። የትግራይ ልጆች የነበሩም ብዙ ናቸው ። እንዲያውም ህዝብ በማደራጀቱ ስራ የበለጠ እነርሱ ተመድበው ስለሰሩ፥ የተሻለ መመስከር ይችላሉ ። ወደ አሲምባ ካቀናሁበት ከጥር 1969 ጀምሮ፣ በትግራይም ሆነ ጎንደር ካየሁዋቸው በሺህ ከሚቆጠሩ መንደሮች፣ የወልቃይት መንደሮች በሶስት ነገሮች ጉልህ ልዩነት ነበራቸው ።

አንደኛው፣ ከፍተኛ የሆነ የቆርቆሮ ቤቶች ከምችት ያሉባቸው መንደሮች ብዙ ነበሩ ። በተለይ ከአዲ ረመፅ ወደ ቀፍቲያ መሻገሪያ አቅጣጫ ያሉት መንደሮች፣ እነ ብላምባ ሉቃስና ብላምባ ቅርሺ የመሰሉት ማህበረሰቦች የሳንቃ ወለል የሌላቸው ከመሆናቸው በቀር፣
በስርአት የተገጠሙ የተላጉ በሮችና መስኮቶች ያሉዋቸው፣ የመኝታ ክፍሎቻቸው የተለዩ፣ የቦንዳ አልጋዎች ያሉዋቸውና በዘመናዊ የቤት እቃዎች የሚገለገሉ ነበሩ ። ወተቱ፣ ቅቤው፣ እርጎው፣ ጠላው እንደ ልብ ነበር ። ሴት ወይዘሮው ንፁህ የሚለብስ፣ ወንዱ አውቶማቲክ
ጠብመንጃ የታጠቀ የጠገበና የኮራ ህዝብ ነበር ።

ለሁለተኛ ጊዜ ተከዜን የተሻገርኩት ከአዲ ጎሹ አካባቢ ወደ ኤርትራ መሻገር በተገደድኩበት ወቅት ነው ። ቀኝ እግሬ ላይ መጅ ወይም callus አብቅዬ መራመድ ተቸግሬ ስለነበር፣ የሰራዊታችን ሀኪሞች የነበሩት ስእለና መልአኩ ቀዶጥገና አድርገውልኝ ማገገም ላይ
በነበርኩበት ወቅት ነበር ወያኔ ወልቃይትን የወረረው ። በየቦታው ተበታትነን የነበርን ጥቂት ታጋዮች፥ ከአዲ ረመፅ ወጣ ባለች መንደር ስለወረራው ሁኔታና ሰራዊታችንም የት እንደሚገኝ ከአርሶአደሮቹ ለማጣራት በምንሞክርበት ጊዜ እዚያ መንደር ውስጥ እንደምንገኝ ወያኔ ስላወቀች አመሻሽ ላይ ታጋዮቿን ልካ በተኩስ አጣደፈችን ። ተኩስ በሌለበት አቅጣጫ እያፈገፈግን ተበታተንን ። ብላምባ ሉቃስ አድሬ የበለጠ መረጃ ሳሰባስብ፣ አዲ ጎሹ አካባቢ የነበሩት ተዋጊ አሃዱዎች ወደ ኤርትራ መሻገራቸውን አስተማማኝ ወሬ ሰማሁ ።
ከሌሊቱ በአስር ሰአት ላይ ተነስቼ ገበሬዎቹ ወደቆላ እርሻቸው በሚወርዱበት አሳቻ ቁልቁለት ከደጋው መሬት ወደ አዲ ጎሹ አቅጣጫ ወደሚወስደው በረሃ ወረድኩ ። ድንገት የወያኔ አባላት ቢይዙኝ ወደኤርትራ ጠብመንጃ ለመግዛት እንደሚሄድ የጠገዴ ነዋሪ በመንገድ ላይ ትብብር እንዲደረግልኝ የሚያሳስብ ባለማህተም ደብዳቤ ይዤ የኢህአፓ ሰራዊት አባልነቴን የሚጠቁሙ ቁሶችን በሙሉ አሳዳሪዎቼ ጋ ትቼ ነበር ። ከደጋው ወርዶ ሰው የማይኖርበትን በረሃማ ስፍራ ብቻ ይዞ መጓዙ ከፀሀዩ ቃጠሎና ከውሃ እጦቱ ጋር ተዳብሎ መቋቋም
የሚቻል አልነበረም ። ሆኖም ከአስር ሰአት ያህል የእግር ጉዞ በኋላ ከተከዜ ወንዝ ደረስኩ ። ለመጀመሪያ ጊዜም ለላንቃዬ ማርጠቢያ የሚሆን ውሃ አግኝቼ ጠጣሁ ። ከወንዙ ማዶ እረኞች ከብቶቻቸውን ሲጠብቁ ተመለከትኩ ። ተሻግሬም ተገናኘኋቸው ። ኤርትራውያን
እረኞች ነበሩ ። በጋይት የሚባሉ ላምና በሬዎቻቸውም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምናውቃቸው ለየት ያሉና እጅግ የደለቡ ነበሩ ።

አዳር ከኤርትራ እረኞች ጋር

እረኞቹ በረሃብና ጥም መጎዳቴን ሲያዩ በእንጨት ጮጮ ከያዙት ወተት አጠጡኝ ። አብሬያቸው አድሬ በበነጋታው መንገዴን ብቀጥል እንደሚሻልና፣ የኤርትራ መንደሮች እስክደርስ የብዙ ሰአት እግር መንገድ ስለሚቀረኝ ልቸገር እንደምችል ነገሩኝ ። በሃሳባቸውም ተስማማሁ ። ፀሀይ ከማዘቅዘቋ በፊት ከብቶቻቸውን ወደነፋሻማው ዳገት መንዳት ጀመሩ ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ላሞችና በሬዎች በአንድ ላይ ሲታገዱና ሲጠበቁ ሳይ የመጀመሪያዬ ነበር ። ወደ በረታቸው የሚያመሩበት ዳገት ለከባድ መኪና የተሰራ ጥርጊያ ይመስል ነበር ። ዳገቱን ለአንድ ሰአት ያህል ከወጣን በኋላ ከከብቶቹ በረት ደረስን ። እረኞቹ ከብቶቹን በረት ውስጥ ካስገቡ በኋላ፣ ትልቅ የካምፕ እሳት ማዘጋጀት ጀመሩ ። ከተከዜ ወንዝ ዳርቻዎች የሰበሰቧቸውን ጠጠሮች በማሽላ ሊጥ እየጠቀለሉ የሚነደው እሳት
ውስጥ ይዶሉ ጀመር ። ብርኩታ ተብሎ የሚጠራው እራታቸው እንደሆነ ነገሩኝ ። ሆዴ እስኪቆዘር ብዙ ብርኩታ በላሁ ።

የምግብ ማብሰያ ብረትድስት ስላልነበራቸው እሳት ውስጥ የጋሙና ፍም የመሰሉ የወንዝ ዳር ጠጠሮችን በመቆንጠጫ ባላ እንጨት እያወጡ አዲስ የታለበው የጮጮ ወተት ውስጥ እያስገቡ ቸስ ብሎ ሲቀዝቅዝ ፣ ያንን ጠጠር ወደእሳቱ መልሰው እየወረወሩ ሌላ የጋለ ጠጠር ጮጮው ውስጥ በመጨመር ወተቱ እንፋሎት ማውጣት እስኪጀምር ድረስ እየተቀባበሉ አፈሉት ። ከዚያ የፈላው ወተት ላይ የማሽላና በቆሎ ዱቄት በመጨመር ገንፎ አገነፉ ። እንዴት እንደሚጣፍጥ ማመን አትችሉም ። ገንፎ በልተን እንደጨረስን፣ ከሰው ወደሰው ጮጮው እየተላለፈ፣ አዲስ የታለበ ትኩስ ወተት ፉት ስንልና ስናወራ አምሽተን፥ እዚያው እሳቱ ዳር ተኛን ። በጣም ከሩቅ ሃገር፣ ለሳምንታት ተጉዘው መምጣታቸውንና፣ እስከ ክረምቱ ወራት ድረስም ተከዜ አካባቢ እንደሚቆዩ አጫወቱኝ ። በማግስቱ ተሰነባብተን የተከዜን አቀበት መውጣቴን ስቀጥል፣ እነርሱም ትተውት ወደመጡት ተከዜ ለምለም ሳር ፍለጋ ከብቶቻቸውን ይዘው ወረዱ ።

ከኤርትራ ወደ ፀለምት መልስ

ከሁለት ቀናት በኋላ የጀብሃ ሚሊሺያዎች ለአካባቢው የፀጥታ ሹም ለነበረው ለጆርጅ ወስደው አስረከቡኝ ። ገና ስንተያይ ከጆርጅ ጋር ኮከባችን ገጠመ ። ለአመታት ተለያይቶ እንደተገናኘ ጓደኛ ማውራትና መከራከር ጀመርን ። ስለጀብሀ የማላውቃቸውን ብዙ ነገሮች
አጫወተኝ ። ለካስ ጀብሃ፣ ተራ የእስልምና አክራሪዎች ድርጅት ሳይሆን ፣ በውስጡ የአንጃዎችን መኖር የሚቀበል፣ ከባዚስቶች እስከ ሊበራሎች በአንጃ በአንጃ ተደራጅተው ለጋራ አላማ የሚሰሩበት ግንባር ነበር ። ስብዞዎቻችን ኢህአፓ ውስጥ ሳለን ይህን ዴሞክራሲያዊ ገፅታቸውን ፈፅሞ አናውቅም ነበር ። ጆርጅ ኤርትራ ከገባችው የኢህአፓ አሃዱ ጋር አገናኘኝና፣ ወደፀለምት ለመመለስ ተወሰነ ።
ወልቃይት በወያኔ ስለተያዘ፣ በዚያ ማለፍ የሚታሰብ አልነበረም ። እስከ ዛሬማ ወንዝ መገናኛ ድረስ ዋልድባ ገዳም እስክንቃረብ የተከዜን ወንዝ ተከትለን ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ልንሄድ ወሰንን ።

ቀኑን ሙሉ ተከዜን ግራና ቀኝ እያቆራረጥን ውለን አመሻሽ ላይ ደከመን ። ረሃቡም የሚቻል አልሆነም ። መጋቢዎች ከተከዜ ወጥተው ምግብ ፍለጋ ወደመንደሮቹ እንዲሄዱ ታቀደ ። ይህን አደገኛ ተልእኮ የሚፈፅም ፈቀደኛ የሰራዊት አባል ማግኘት አልተቻለም ። በመጨረሻ እኔና አንድ ስሙ የተዘነጋኝ የአምባ ማድሬ አርሶአደር ታጋይ ሄደን ምግብ ለመሰብሰብ ፈቃደኛ ሆንን ። አመሻሽ ላይ መንደሩ ውስጥ የወያኔ ጦር አለመኖሩን አጣርተን ገባን ። ከነዋሪውም ምግብ እንዲሰበሰብልን አደረግን። ብዙም ሳንቆይ የህወሐት ታጋዮች መጥተው በተኩስ ያጣድፉን ጀመር ። ሁለታችንም ምግቡን ትተን ላለመሸሽና የተኩስ አፀፋ ላለመስጠትም ወሰንን። የተሰበሰበውን እንጀራና ወጥ በነጠላዎቻችን ላይ እያሰርን ተኩስ የሌለበትን አቅጣጫ መቃኘት ያዝን። እንጀራና ወጡን በነጠላችን አስረን ከተሸከምን በኋላ የተኩስ ክፍተት በነበረበት ቀዳዳ ድምፃችንን አጥፍተን ተሰለብን ። ወደተከዜ የሚያወርደውን ገመገም ተከትለንም ከጓዶቻችን ተቀላቀልን፣ እራታቸውንም አበላን ።

ስለ ወልቃይት ምስክርነት

ቀደም ብዬ ወልቃይቴ ሃብታም ነው ብዬ ነበር ። በሌላው የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ያላየኸው የተሻለ ህይወት ወልቃይት ከየት አመጣው ትሉ ይሆናል ። ስለ ወልቃይት ስናወራ፣ ወልቃይቴው ማለት ደጋው ላይ የሚኖረው በፅልእሎ፣ ሽሬላ፣ ደጀና፣ አዲ ረመፅ፣ የብላምባ መንደሮች፣ ብርኩታና ቀፍቲያ እንዲሁም ቆላው ላይ አዲ ጎሹ የሚኖረው ወልቀታይ ነው ። ይህ ህዝብ በቆርቆሮ ቤቶች በተሻለ ህይወት መኖር ብቻ ሳይሆን፣ አልፎ አልፎም የእርሻ መኪናዎችም ያሏቸው ጥቂት ባለሃብቶችም ነበሩ ። ቆላ መዘጋው ላይ ከወባና ጊንጥ እንዲሁም ከቆላው ወበቅ ጋር እየታገለ የሚኖረው የፀሊም ቤትና የትግራይ ስደተኛ፣ የደገኛው ወልቃይቴው አገልጋይና ተጠማኝ (share cropper) በመሆኑ፣ የወልቀታዩ መሬት ላይ ከሚያርሰው አዝመራ አካፍሎ የሚኖር ህዝብ በመሆኑ፣ የደገኛው ሃብት አንዱ ምንጩ ከዚህ ተጠማኝ አራሽ የሚሰበስበው ሰብል ነበር ። የ1966ቱ አብዮት መጥቶ የሁመራ እርሻ ስራቸው እስኪተጓጎል
ድረስም፣ የወልቃይት ሰው ሁመራ ላይ የሰሊጥ እርሻ ባለቤት ስለነበር፣ በቅድመ አብዮት አመታት ያካበተው ሃብት ብዙ ነበር ። ከሃብታቸው ብዛት እንደ ቀኛዝማች ገብሩ ያሉ ሃብታሞች ሰራዊታችን በሰፈራቸው ሲያርፍ፣ አመራር አባላቱን ጠርተው እንደ እናትና ልጅ አይነት ፋብሪካ ውስጥ የተመረቱ መጠጦችን እስከመጋበዝ የሚችሉ ሰዎች ነበሩባቸው ።

ሁለተኛው ወልቃይትን ልዩ የሚያደርገው ነገር፣ በየመንደሩ ከፍተኛ የሆኑ የእድሜ ባለፀጋዎችና፣ ጎንደርና አዲስ አበባን፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ገዳሪፍ ወይም ካርቱምን ደጋግመው የጎበኙ ሰዎች በብዛት ይገኙባቸው ነበር ። ብላምባ ሉቃስ ውስጥ የሚኖሩ አቶ ጥላሁን
የሚባሉ የቭላድሚር ሌኒን መንታ የሚመስሉ ሰው አንዱ የማስታውሳቸው ነበሩ ። ደጀና ውስጥ የአየር ሃይል አዛዥ የነበሩት የጄኔራል አሰፋ አያና አጎት የሆኑ ግራዝማች መስፍን የሚባሉ ሌላ ምሁርና የታሪክ ሰውም አስታውሳለሁ ። ሁሌም ብዛታቸውና፣ በአንድ ቦታም
ተከማችተው መገኘታቸው ይገርመኝ ነበር ። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ጓደኛዬ የነበረው አንዳርጋቸው አያልነህ ስለወልቃይት ሃብትና ወንዳወንድነት (ብረት ወዳድነት) ያወራን የነበረውን ለማመን እንቸገር እንደነበር አስታውስና፣ ኋላ የአንዳርጋቸውን የትውልድ
መንደር ቃቃን (በትክክል ካስታወስኩ ከአዲ ረመፅ በእግር የአንድ ሰአት ተኩል መንገድ ቢሆን ይመስለኛል) ስጎበኝ ከታዘብኩት ጋር ሳመዛዝን፣ ሁሌም ይደንቀኛል ።

ሌላው ወልቃይትን ከብዙ ሌሎች ህዝቦች የሚለየው፣ የለት ከለትና የስራ ቋንቋው ከማንነቱ ጋር የተለየ መሆኑ ነው ። በየእለቱ ወልቀታዩ እርስ በርሱም ሆነ ከተጠማኝ ገባሮቹ ትግሬዎች ጋር የሚገለገልበት ቋንቋ ትግርኛ ነው ። ከፈለገም አማርኛን ይጠቀማል ። ባለ
ሁለት ቋንቋ ህዝብ ነበር ። ሆኖም በትግሪኛ ልጁን መዳርም ሆነ፣ ወዳጁ ሲሞትበት በትግሪኛ ማልቀስ ግን አይሆንለትም ። የሰርግ ዘፈኑና ለቅሶው፣ ፉከራው፣ ሽለላው፣ የመጫቷ አንቀልባ እሹሩሩ ዜማም ሆነ፣ የፈጪታዋ እንጉርጉሮ አማርኛ ነው ። የሚያስገርም
የሚያስደምም ኩነት ነው ። ወልቃይቴው ትግሪኛ ይናገር እንጂ ፈፅሞ የትግራዋይ ስነልቡና የሌለው፣ እራሱን እንደ ኩሩ ጎንደሬ የሚያይ ጅንን ነው ። እንዴት ሊሆን ቻለ? ምናልባት ወልቃይቴው ለህይወቱ የሚያስፈልገውን የምርት ሂደት የሚያከናውኑለት የቆላ መዘጋ ፀሊም ቤቶችም ሆኑ ተጠማኝ የሆኑት የትግራይ ስደተኞችን ለማናገርና፣ ምርቱ ሳይተጓጎል በሰላም ለመጨረስ አስፈላጊ የሆነው የትግርኛ ቋንቋ፣ የእለት ተለት ህይወቱን ተፅኖ አድርጎበት ሊሆን ይችላል፣ ወይስ በሌላ ምክንያት? ምርምርን የሚሻ ጉዳይ ይመስለኛል ።

ወልቃይትና ነፃ የትግራይ ሪፐብሊክ ጥያቄ ትስስር

ወያኔ የነፃ ትግራይ ሪፐብሊክ ማቋቋም አላማ በነበረው ሰአት፣ አንደኛ ከውጪው አለም የሚያገናኝ መስመር ፍለጋ፣ ከፖርት ሱዳን ወደብ ጋር የሚያገናኝ ወሰን በመፈለግ፣ ሁለተኛ፣ ትግራይ የሶስት ሺህ አመታት ስልጣኔና መሬቱ ያለእረፍት ሲታረስ በመኖሩ ምርቱ እየደከመ የመጣ በመሆኑና በአንፃሩ ወልቃይት/ሁመራ ሰፊ ያልታረሰ ድንግል መሬትና እንደ ሰሊጥ አይነት ካሽ ክሮፕ ሰብል የሚያመርት በመሆኑ፣ ነፃ ለምትወጣው ትግራይ ትልቅ ለም መሬት ስለሚያስገኝ፣ ወልቃይትንና ሁመራን ለመጠቅለል ታቀደ ። የህወሐት መሪዎች ፀገዴ የቢትወደድ አዳነ አገር መሆኑን ያውቁ ስለነበር፥ በትጥቅ ትግሉ ማጠናቀቂያ አመታት ክሳድ
ግመል ውስጥ ቤዝ አምባ የመሰረቱ ቢሆንም፥ የትግራይ ነው ሲሉ ሰምቼም አላውቅም ። በግርግር የጨመሩት መሬት ነው ። የትግራይን ነፃ ሪፐብሊክ የማቋቋም አላማ ትተናል በሚባልበት ወቅት፣ ወልቃይትንና ፀገዴን ትግሬ የማድረግ ህልሙ ግን አልቆመም ። ለምን?

በ1972 አጋማሽ ላይ ወያኔ ወልቃይትን ለመውረር ሲመጣ በመጀመሪያ የኢህአፓን ጦር መደምሰስ ነበረበት ። የኢህአፓ ሰራዊት ከየሪጅኑ የተውጣጣ ሃይል ሰብስቦ ደባርቅና ዳባት አካባቢ ለመንቀሳቀስ አብዛኛውን ሀይሉን ከወልቃይት ባራቀበት ወቅት ህወሐት ድንገት ከፍተኛ የሰራዊት ሀይሉን ይዞ ወልቃይትን ወረረ ። ከያዘ በኋላ ለማስለቀቅ ቀላል አልሆነም ። ብዙ የኢህአፓም ሆነ የወያኔ የሰራዊት አባላት የተሰውበት የሽሬላና የቆላ መዘጋ ጦርነቶችት የተካሄዱ ቢሆንም፣ ወያኔን ከወልቃይት መንቀል ግን አልተቻለም ። እንደገና ወደፀለምት ማፈግፈግ ተገደድን ።
ወያኔ ከ1972 አጋማሽ ጀምሮ የወልቃት ይዞታውን ለማጠናከር በከፍተኛ ደረጃ የመሬት ችግር ያለበቸውን ትግሬዎች እያመጣም አሰፈረ ። ባለፉት 30 አመታት እስከ 80 ሺህ ህዝብ ከትግራይ አምጥቶ እንዳሰፈረ ይነገራል ። አዲስ አበባም እንደገባ ከምእራባውያን ጋር
የሰራዊት ቅነሳ ለማድረግ ሲስማማም፣ ለቅነሳው ማካሄጃ የተሰጠውን ድጎማ በመጠቀም፣ ተቀናሾቹን የወያኔ ሰራዊት አባላት በቀፍቲያና ዳንሻ አካባቢ 30 ሺህ የቀድሞ ወያኔ አባላትን ከነትጥቃቸው አስፍሯል ። ህወሐት ነባሩን የወልቃይት ህዝብ በአዲስ ስደተኛ ካጥለቀለቀና ፣ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ በአመፅ ከቀየረ በኋላ “ብትፈልጉ ህዝበ ውሳኔ ወይም ሪፍረንደም ይካሄድ” ፥ ወይም
ሲነሽጠው “ወደ ትግራይ ከመጠቅለሌ በፊት ህዝበ ውሳኔ አካሂጃለሁ” ብሎ ያላግጣል ። ይህ ግን ተራ ቧልት ነው ። ከማንኛውም ህዝበ ውሳኔ በፊት ወልቃይት ወደነበረበት መመለስና አሁን በቦታው ላይ ያለው የወያኔ የግፍ አገዛዝ መልቀቅ ይኖርበታል ። ይህ ቅድመ
ሁኔታ ሳይሟላ ስለ ህዝበ ውሳኔ ማውራት አይቻልም ።

የተፈጥሮ ወሰን ይከበር

እኔ የአራዳ ልጅ ነኝ ። ዛሬ ጊኒር ባሌ ወይም ወለጋ ቄለም የሚኖር የኦሮሞ ወጣት በወያኔ አይዲዮሎጂ ተኮትኩቶ “ፊንፊኔ የኔ ናት” በሚልበት ወቅት ይበልጥ የሚያንገበግበኝ ጉዳይ ስላለ፥ የወልቃይት ጉዳይ ላይመለከተኝ ይችላል ። ሆኖም፥ ሁለቱም ጥያቄዎች የተሳሰሩ
ናቸው ። የቁዋንቁዋ ክልል አይዲዮሎጂ የወለዳቸው ። በተጨማሪም የህይወት አጋጣሚ ሆኖ በፀለምት ወልቃይትና ተከዜ ሸለቆዎች ትዳር መስርቼ ስለነበር፥ የእማኝ ቃሌን የመስጠት የህሊና ግዴታ አለብኝ ። ተከዜንም ብቻ ሳይሆን፣ ገባሮቹ የሆኑትን ጥራሬን፣ፍራፍራን፣ እንስያን፣ ዛሬማን ወንዞች ለቀናት ተጉዤባቸዋለሁ፣ አድሬባቸዋለሁ ። የጥራሬን ወንዝ የጓዳዬን ያህል አውቀዋለሁ ብል ማጋነን አይመስለኝም ። ከወያኔ ጋር ድርጅታዊ ግንኙነት ለማድረግ ከሰቆጣ አካባቢ ተነስቼ አንዲት ቦንብ ወይም አንድ ሽጉጥ ታጥቄ ሙሉ ቀን ወይም ሙሉ ሌሊት ብቻዬን ስጓዝ የጥራሬን ወንዝ ብዙ ጊዜ ተሻግሬአለሁ ።

በጥቅምት 1971 ከፀለምት ተነስተን ወደ ቆላወገራ ስንሄድና ወደ ወልቃይት ስንመለስ በዛሬማ ወንዝ ዳርቻዎች ለቀናት ኖረናል ። የሚበላ እህል ስላልነበር፣ ወንዙ ዳር የነበሩትን የሸምበቆ ተክሎች እየቆረጥን ከሸምበቆ አገዳ በተሰሩ ቢላዋዎች የሰንጋ ቁርጥ እየጎመድን በዛሬማ ወንዝ ውሃ እያወራረድን በብስናት አልቀናል ። በስኔ 1972 የፀለምት የኢህአፓ የአርሶአደር ሚሊሺያዎች ሊከዱ ነው ብለው ጠርጥረውን 13 የሰራዊቱን አባላት ካስሩን በኋላ “ሲነጋ እንዳናገኛችሁ” ብለው ሲለቁን፣ ሰኔ 4 ሌሊቱን ሙሉ የፍራፍራ ወንዝን ግራና ቀኝ ስናቆራርጥ አድረን ከፀሐይ ጋር ቀጠሮ ያለን ይመስል ልክ ስትወጣ ከተከዜ ወንዝ ደረስን፣ ተከዜንም ለሶስተኛ ጊዜ አየሁት ፣ ዳግምም ወደ ትግራይ ኣቋረጥኩት ። እንኩዋንስ ተከዜ ገባሮቹ እንኩዋ ፥ ሃያል ነበሩ ። የተፈጥሮ ወሰኖች ።

በእኔ አስተያየት፣ መገናኛና መጓጓዣ አስቸጋሪ በነበረባቸው ዘመናት አንድ ማህበረሰብ ከዘመዶቹ ርቆ፣ በመሃሉ ከሶስት ወራት በላይ የሚያቆራርጠው ተከዜን ያህል ወንዝ ተሻግሮ ኑሮ የሚመሰርተው አስገዳጅ የህይወት ገጠመኞች ሲኖሩት ይመስለኛል ። ራሱን ከጥቃት
ለመከላከል ሲልም ሆነ ራሱን ጠብቆ ለማቆየት፣ የሱን ቋንቋ ከሚናገሩ ህዝቦች ጋር መቆየትን ይመርጣል ። ለዚህም ነው በኢትዮጵያችንም ሆነ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ታላላቅ ወንዞች የህዝቦች ተፈጥሯዊ ወሰን ሆነው የኖሩት። በኢትዮጵያም ብቻ ሳይሆን በመላው አለም፥ የተራራ ሰንሰለቶች፣ ወንዞችና፣ በረሃዎች ተፈጥሯዊ ወሰን ሆነው የተለያዩ ማህበረሰቦችን አካልለው በሰላም አኑረዋል ። አሁን ህወሐት ያንን አለማዊ አሰፋፈር ነው በቋንቋ ክልል አይዲዮሎጂ መለወጥ የሚፈልገው ። መልክአ ምድር ወይም ጂኦግራፊ በማህበረሰቦች አሰፋፈርና ተፈጥሮአዊ ድንበር ሆኖ ስለሰጠው ግልጋሎትና ስላደረገው ተፅእኖ፥ ለመስኩ ባለሙያዎች እተወዋለሁ ። እኔ ግን በአስር አመት የበረሃ እንግልቴ የታዘብኩት ተፈጥሮ በህዝብ አሰፋፈር ላይ ያደረገውን ተፅእኖ ነው ።

ይህንን ተፈጥሮአዊ የህዝብ አሰፋፈር ሎጂክ በቋንቋ ክልል ፌዴሬሽን ሎጂክ በመተካት፣ ህወሐት በፀለምት በኩልም የብራ ዋሰያንና የዋልድባን ለም መሬቶች ከጎንደር በመዝረፍ ከዛሬማ ወንዝ ምላሽ ያለውን ሃገር በሙሉ፣ ትግርኛ እስከተናገረ ድረስ ትግሬ መሆን አለበት በሚል በጉልበት ወስዷል ። ትናንት ነፃይቱን የትግራይ ሪፐብሊክ በሚመኙበት ሰአት በወጣትነት ትኩስ አእምሮ የነደፉትን ጨቅላ አስተሳሰብ፣ ዛሬ ኢትዮጵያን የሚያህል አገር እየገዙ ባለበት ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ እንደደፈሩ ሳስበው ከወቅቱ ጋር መራመድ ለምን እንደማይችሉና፣ ለምን ከሃቅ ጋር እንደሚላተሙ ሁሌም ይገርመኛል ።

አንድ መታወቅ ያለበት ነገር፣ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከስልጣናቸው ከተወገዱ ጥቂት ወራት በኋላ ፣ ኢዴህ (የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ህብረት) ሲመሰረት፥ የወልቃይትና ፀገዴ መሳፍንትና የሁመራ ባለሃብቶች፣ ሁመራ ላይ ያገለግሏቸው የነበሩትን ከትግራይ የመጡ
የዘመናዊ እርሻ ሰራተኞችን (ወዛደሮችን) አስታጥቀው በደርግ ጦር ላይ ዘመቻ ከከፈቱበት ሰአት ጀምሮ ላለፉት 40 አመታት ከፍተኛ የጦር አውድማ ሆኖ የቆየ አካባቢ ነው ። የታክስ መረጃዎች ተበትነዋል፥ መዝገብ ቤቶች ተቃጥለዋል፥ ታሪኩን የሚያውቁ አዛውንት
አልቀዋል ። ወልቃይት ፀገዴ እምብዛም እረፍትና ሰላማዊ አስተዳደር አግኝቶ አያውቅም ። እኔ ወልቃይት በነበርኩባቸው የ1971 እስከ 72 አመታት ብቻ እንኳ በእኛና ኢዴህ መካከል ሥፍራ ሃፀይ አካባቢ፣ በእኛና ወያኔ መካከል በሽሬላና ቆላ መዘጋ አካባቢዎች ውጊያዎች ተደርገዋል ። ወያኔ አካባቢውን ከተቆጣጠረም በኋላ፣ “ተገደን ትግሬ አንደረግም” የሚለው የትጥቅ ተቃውሞ ቀጥሎ ባለፉት 35 አመታት ከፋኝ፣ አርበኞች ግንባር ወዘተ የሚሰኙ ሃይሎች ከወያኔ ጦር ጋር መቆራቆሳቸውን አላቆሙም ። በእነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች እካባቢው ተተራምሷል ። የህወሐት “ትግርኛ የተናገር ሁሉ ትግሬ ነው” አይዲዮሎጂ የበለጠ ትርምስና የንብረትና ህይወት ውድመትን የሚያስከትል ነው ።

በእኔ እምነት መፈቀድ የሌለበት፣ ተከዜን አይነት የተፈጥሮ ወሰን ተሻግሮ በሌላ ማህበረሰብ እቅፍ ውስጥ ተጠግቶ የኖረ የወሰን ተጎራባች ህዝብ፣ ካስጠጋው ህዝብ መሬት ላይ ቆርሶ በመውሰድም ሆነ፣ ቁጥሩ ከአስጠጊው መብለጡን እርግጠኛ ሲሆን፣ በህዝበ ውሳኔ
(ሪፍረንደም) ሽፋን ያስጠጊውን ህዝብ መሬትና አስተዳደር መንጠቅ ሊፈቀድለት አይገባም።

ሆኖም ህወሐት በሶሻል ኢንጂነሪንግ ስለሚያምን፣ ይህን ሃሳብ አይቀበልም ። በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ ስለቀየርኩ ማንም አይነካኝም ብሎ እግሩን አንፈራጦ ተቀምጧል ። ሆኖም የወልቃይት ፀገዴ ችግር ውሎ አድሮ ኢህአዴግን ከውስጡ የሚሰረስር ጉዳይ ነው ። እንደ
ኦህዴድ ሁሉ ብአዴንንም ማስሸፈቱ አይቀርም ። የህዝቡን ጥሪና አቤቱታ ተቀብሎ፣ አማራ ነን በማለታቸው ከሚደርስባቸው መበሳበስና እንግልት ሊታደጋቸው ይነሳ ይመስለኛል ። የብአዴን መፈተኛው ደረሰ መሰለኝ ። ከኦህዴድ መማር ይችላል ። የወያኔ ተባባሪና መንገድ መሪ ያለመሆን አማራጭ ከፊቱ ተደቅኗል ። በጣም ትንሽ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ጉዳይ ይመስለኛል ። የህወሐት ዐይንና ጆሮ ላለመሆን እንደ ኦህዴድ መወሰን ። አዎን ይቻላል!

The post ወልቃይት ፀገዴና ፀለምት፥ በዐይኔ ካየሁትና ከታዘብኩት | በያሬድ ጥበቡ appeared first on Zehabesha Amharic.

ግብጽ የአባይን ግድብ ለመከታተል አሮጌውን አንስታ አዲስ ሳተላይት ተከለች

$
0
0

grand-renaissance-dam-1
አል አህራም የተባለው የግብጽ የመረጃ መረብ እንደዘገበው ግብጽ በኢትዮጵያ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ግድብ ለመከታተል ያስችላት ዘንድ ቀደም ብላ ሳታላይት ተከላለች:: ግብጽ በተተከለው ሳታላይት አቅም ደስተኛ ባለመሆኗ ግድቡን በተመለከተ የተሻለ መረጃ ያቀብለኛል ያለችውን አዲስ ሳታላይት መትከሏን የአገሪቱ የሳታላይት ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡

በኢጂሳት የተተከሉት ሳታላይቶች የግድቡን ሁኔታ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ሲያቀርቡ መቆየታቸው የሚታወቅ ቢሆንም የግብጽ የህዋ ሳይንስ ብሄራዊ ባለስልጣን ምክትል ፕሬዘዳንት አላ አል ዲን አዲሱ ሳታላይት በጣም ዘመናዊ የሆኑ ካሜራዎች የተገጠሙለት በመሆኑ ግድቡንና በወንዙ አካባቢዎች የሚካሄዱ ሌሎች እንቅስቃሴዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን ያቀርባል” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመነጭ የምትናገርለት ግድብ ግማሽ ያህሉ መጠናቀቁን መንግስት እየገለጸ ባለበት በዚህ ወቅት ግብጽ በበኩሏ ግድቡ ወደ አስዋን ግድብ ይገባ የነበረውን አመታዊ የውሃ መጠን ይቀንሳል የሚል ስጋት ገብቷታል፡፡

ኤል ዲን ሳታላይቱ የሁለት ወራት ሙከራ ካደረገ በኋላ ሙሉ ለሙሉ በመጪው ሰኔ ወር ስራውን ይጀምራል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡የግድቡን መጠን፣ውሃ የመያዝ አቅም፣ውሃ የሚለቅበትን ሁኔታና ኮንጎ በናይል ወንዝ ላይ ለመስራት ያቀደችውን ግድብም የተመለከቱ መረጃዎችን ያቀርባል ተብሎለታል፡፡

ሳተላይቱ ለግብጽ ግድቡን በተመለከተ አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ በመሆን እንደሚያገለግል የሚናገሩት ባለስልጣናቱ ምናልባት በተስማማንባቸው ጉዳዩች ዙሪያ ግድቡ የማይሄድ ከሆነም ወደአለምአቀፍ ፍርድ ቤቶች ከሄድን ከሳታላይቱ የምናገኘው መረጃ ማስረጃ ሊሆነን ይችላል ማለታቸውን አል ሃራም ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ ግብጽ ተከለቻቸው ስለሚባሉ ሳታላይቶች እስካሁን የሰጠችው ምንም አይነት አስተያየት የለም፡፡

The post ግብጽ የአባይን ግድብ ለመከታተል አሮጌውን አንስታ አዲስ ሳተላይት ተከለች appeared first on Zehabesha Amharic.

እልባት ያላገኘው የኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር ክለላ |ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

Ethiosudan

የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር ክለላ ጉዳይ ለአመታት ከድንበር ነዋሪ እስከ መሐል ከተማ ነዋሪው ፣ ከፖለቲካኛ እስከ ልሂቃን ሁሉንም በየፈርጁ ግራ ሲያጋባን የቆየ ጉዳይ ሆኖ ቆጥሏል ! ከዘመነ ጃንሆይ ደርግ ውል ያልተበጀለት ጎንደርን የሚያዋስነው የሱዳንና የኢትዮጵያ ድንበር በዘመነ ኢህአዴግ የከፋ ስጋት መሆኑ በብሔራዊ ክብር ማስጠበቅ ዙሪያ ያለው አለመተማመን በመጉላቱ ቢሆን ደስ ባለን ነበር ። ያን ሰሞን በድንበር ማካለሉ ሰሞነኛ አጀንዳ መባቻ ያየነው የአማራ ክልል ካርታን ጨምሮ የቀድሞው የኢህአዴግ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር የነገሩን ትግራይን ከሱዳን ጋር የሚያያይዝ ብለው ተንትነው እያሳዩን ” ሚስጥር ነበር ” ያሉት ካርታ ጉዳይ ያላመመው ሐገር ወዳድ አለ አልልም !
የኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር በእንጥልጥል ግማሽ ክፍለ ዘመን ሲነጉፍ ፣ ከምንም በላይ የተጎዳውና የከበደ መስዋዕትነት ያስከፈለና ያለው የሀገሬ ገበሬ መከራ ግን ትናንትም ዛሬ ሆኖ ቀጥሏል … የድንበሩ ማካለል ዙሪያ ዝግጅት ውሳኔው በጠረጴዛ ስር በተደረገ ድርድር ተከውኗል ተብሎ ሲጮህ ፣ ኢህአዴግ ሆየ ምንም የተደረሰ ስምምነት እንደሌለ ይነግረናል ! ይህ በእንዲህ እንዳለ ስንባጅ ድንበሩን ለማካለል ኮሜቴ መቋቋሙ እንደተሰማ የጀርመን ራዲዮ በዛሬው ዜና መጽሔት መረጃ እንደሚያቀርብ ሰምተናል ! መረጃው እንዲህ ይላል … ”

በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር ክለላ እንዲደረግ ራሱን የቻለ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩን እንዲከታተል መደረጉ ተሰምቷል። ሆኖም መቼ ወይም እንዴት የድንበር ማካለሉ እንደሚደረግ ከኢትዮጵያም ሆነ ከሱዳን መንግስት ብዙም የተነገረ የለም። በአካባቢዉ ከሚኖሩ ወገኖች ግን እንቅስቃሴ ተጀምሮ እንደነበር የሚናገሩ አሉ። … ”
ዝርዝሩን ከምሽቱ የጀርመን ራዲዮ የዛሬ ስርጭታችን ይከታተሉ ዘንድ በቀጭኑ የዋትሳፕ መስመር የተሰራጨው የጀርመን ራዲዮ መረጃ ይጠቁማል…

ቸር ያሰማን !

መጋቢት 7 ቀን 2008 ዓም

The post እልባት ያላገኘው የኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር ክለላ | ነቢዩ ሲራክ appeared first on Zehabesha Amharic.

በኦሮሚያ ክልል የደረሰውን የሰብዓዊ ጉዳት አስመልክቶ በ33 ወረዳዎች ብቻ 103 ዜጎች መገደላቸውን የሚገልፅ ገለልተኛ የምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆነ

$
0
0

ከህዳር አጋማሽ 2008 ዓ.ም. በምዕራብ ሸዋ ተጀምሮ በነበረው እና መላው ኦሮሚያ ክልልን ያዳረሰው ህዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ የደረሰው ሰብዓዊ ጉዳት ልዩ የምርመራ ሪፖርት መግለጫ ይፋ ሆነ፡፡ ልዩ መግለጫው ይፋ የሆነው መጋቢት 5 ቀን 2008 ዓ.ም. አዲስ አበባ በሚገኘው የሰመጉ ዋና ጽህፈት ቤት ሲሆን፤ መግለጫውም የ103 ዜጎች ህይወት መጥፋቱን አስታውቋል፡፡

Oromo

ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ይባል የነበረውና በኋላም የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ(ሰመጉ) እየተባለ የሚጠራው ብቸኛው ሀገር በቀል መነግሥታዊ ያልሆነ ገለልተኛ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሲሆን፤ ባለፉት አራት ወራት በተጀመረውና እስካሁንም በቀጠለው የኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞ የሰብዓዊ ጉዳት ቀዳሚውን ልዩ መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡ ሰመጉ በ140ኛው የተቋሙ ሪፖርት “የኦሮሚያ ክልል በ18 ዞኖች እና በ342 ወረዳዎች የተከፋፈለ ሲሆን ሰመጉ ከ9 ዞኖች ውስጥ በ33 ወረዳዎች ብቻ ባደረገው የመስክ ምርመራ ባገኘው ውጤት መሰረት 103 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን 57 ሰዎች በጥይት የመቁሰል እና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡” ብሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከተገደሉትና ከቆሰሉት በተጨማሪ በ22 ሰዎች ላይ ማሰቃየት እና ድብደባ መፈፀሙን፣ 84 ሰዎች መታሰራቸውን እንዲሁም 12 ሰዎች የደረሱበት ወይም ያሉበት አለመታወቁንም ጠቁሟል፡፡

ሰመጉ 34 ገፅ ባለው ልዩ መግለጫው እንዳስታወቀው ከሆነ፤ የደረሰው የሰብዓዊ ጉዳት ምርመራ የሚያካትተው ከህዳር 2 ቀን እስከ የካቲት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. የደረሱ የሰብዓዊ ጉዳቶች ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በተለይ በምርመራ ወቅት ድርጅቱ የጋጠሙትን ችግሮችም የጠቀሰ ሲሆን በተለይም የገንዘብ ፣ የሰው ኃይልና የምርመራ መሳሪያ እጥረት፣ በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ውጥረት የተሞላበት በመሆኑ በኦሮሚያ ክልል በተከሰተው ቀውስ እንደልብ ተዘዋውሮ ለመስራት አለመቻል፣የመንግሥት የደህንነት እና የፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ጫና እና ክትትል ማድረጋቸው፣ ሕዝቡ ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ በመግባት ማንንም ሰው አለማመን እና መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን ዋነኞቹ መሆናቸው ጠቅሷል፡፡

በክልሉ አሁንም በተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞች መቀጠላቸውንም በመጥቀስ፣ ማንኛውም የሰብዓዊ መብት የሚመለከተው አካል የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎችን ሰብዓዊ መብት እንዲያከብር፣ እንዲያስከብርና እንዲያስጠበቅ ጫና እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡

The post በኦሮሚያ ክልል የደረሰውን የሰብዓዊ ጉዳት አስመልክቶ በ33 ወረዳዎች ብቻ 103 ዜጎች መገደላቸውን የሚገልፅ ገለልተኛ የምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆነ appeared first on Zehabesha Amharic.


ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ኢንጂኒየር ይልቃል ጌትነትን ከአውሮፓ ሕብረት ተወካዮች ጋር ስለተነጋገሩበት ጉዳይ አውርቷቸዋል |ያድምጡ

$
0
0

Sadik and Yilkal

የሰማያዊ ሊቀመንበር ኢንጂኒየር ይልቃል ጌትነት መቀመጫውን አዲስ አበባ ላደረገው የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ተወካዮች በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ወቅታዊ ጉዳይ ገለፃ አደረጉ

በጉዳዩ ላይ የቢቢኤኑ ሳዲቅ አህመድ ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸዋል።

The post ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ኢንጂኒየር ይልቃል ጌትነትን ከአውሮፓ ሕብረት ተወካዮች ጋር ስለተነጋገሩበት ጉዳይ አውርቷቸዋል | ያድምጡ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ መንግስትን በዓለም የፍትህ አደባባይ የረታቸው የወሲብ ተጠቂዋ ወይንሸት ዘበነ እና የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሲዳሰስ |ልዩ ጥንቅር

$
0
0

የኢትዮጵያ መንግስትን በዓለም አቀፍ የፍትህ አደባባይ የረታቸው እና ትምህርት የሰጠችው የወሲብ ተጠቂዋ ወይንሸት ዘበነ እና የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሲዳሰስ ( ልዩ ጥንቅር)

The post የኢትዮጵያ መንግስትን በዓለም የፍትህ አደባባይ የረታቸው የወሲብ ተጠቂዋ ወይንሸት ዘበነ እና የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሲዳሰስ | ልዩ ጥንቅር appeared first on Zehabesha Amharic.

በኩዌት ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ለቪዛና የመኖሪያ ፈቃድ እድሳት አዳዲስ መረጃዎች

$
0
0

kuwait

[በኒዛር ዳጊ]

በአብዛኛው ኩዌት ውስጥ ነዋሪ በሆኑ የቤት ስራተኞች ዙሪያ እየተወራ ያለው እና የብዙዎች ጭንቀት የሆነው ዋነኛ ጉዳይ የቪዛ እድሳት ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ሆኗል ።
ኡትዬጵያኖች የመኖሪያ ፈቃዳቸው ካለቀ በዋላ እይታደስላቸውም ተብሏል የሚለው ወሬ መናፈስ ከጀመረ ትንሽ የቆየ ቢሆንም በየጊዜው ኩዌት ውስጥ በሚከስቱ ክስተቶች እየተቀያየረ ይወራል ።

ከመጀመሪያው ጀምሮ ያለውን ተጨባጭ እውነታ ስናይ ግን የመኖሪያ ፈቃድ እድሳትን እና ኢትዬጵያኖች ከኩዌት ይውጡ የሚል ሃሳብ አቀረቡ የተባሉት የተወስኑ የፓርላማ አባላት ሲሆኑ ይሄ ጥያቄ እስካሁን ድረስ ተቀባይነትም አላገኝም የኩዌት መንግስትም አላጸደቀውም ምንም አይነት ይፋ የሆነ መግለጫ አልስጠም አሁንም ድረስ ያለው አስራር እንደቀጠለ ነው ።
በእንደዚ አይነት ተጨባጭነት በጎደላቸው ወሬዎች ስዎች መጨነቃቸው የማይቀር ቢሆንም ማንኛውም ትክክለኛ የሆነ ህግ ሲወጣ ግን የሚመለከተው አካል ለዜጎች ሳያሳውቅ አያልፍም ይህም ግዴታ ነው ከዛ ውጭ ባለው ነገር ብዙም መረበሽ አያስፈልግም ።

ግርግር ለሌባ ይመቻል እንደሚባለው ኢትዬጵያኖች ውጡ ተባለ ፣ የመኖሪያ ፈቃድ እይታደስም ሌላም ሌላም አሉባልታ በስተጀርባ የህገወጥ ስዎች እጅ አለበት ። ምንም ባልተፈጠረ እና ባልጸቀደ ህግ አርፈው የሚስሩ ልጆችን ከቤት በማስጠፋት ወዳልሆነ ችግር የሚከቱ ስዎች እንዳሉ በመረዳት በምንም አይነት ምክንያት ጠፍታችው ውጡ መኖሪያ ፈቃዳችው ቢያልቅም እኛ እንድትስሩ እናደርጋለን ከሚሉ ማባቢያዎች መቆጠብ ያስፈልጋል ዋነኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያለባችው በቤት ውስጥ ምትስሩ እህቶች ናችው ።

በሁለተኛ ደረጃ ያለው የስሞኑን የኩዌት ጥብቅ ፍተሻ እና ህገወጥ ዜጎችን የማባረር ተግባር እንደቀጠለ ሲሆን በዚህም ህገወጥ አፈሳ እስካሁን እየተያዙ ያትሉ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ፣ ህገወጥ ስራ ላይ የተስማሩ በአጠቃላይ የኩዌት ህግ በማይፈቅደው ተግባር ላይ የተገኙ የሁሉም ሀገር ዜጎች ላይ ጥብቅ እርምጃ እየተወስደ ነው ።

በዚህም አፈሳ ላይ ኢትዬጵያኖች መያዛቸው እንዳለ ሆኖ አሁንም በተመሳሳይ ሌላ ችግር ውስጥ ላለመግባት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እናድርግ ። ህጋዊነት ያለው የራሳችንን መኖሪያ ፈቃድ ወይም ፓስፓርት መያዝ ፣ በቤት ውስጥ የምትስሩ ለእረፍትም ሆነ ለተለያየ ጉዳይ ከቤት ስትወጡ መኖሪያ ፈቃድ እና የአስሪዎቻችውን ስልክ ሙሉ አድራሻ ይዞ መገኝት ካላስፈላጊ እንግልት ያድናል እራሳችውንም ተጠያቂ ሊያደርግ ከሚችል ተግባር ተቆጠቡ ።

The post በኩዌት ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ለቪዛና የመኖሪያ ፈቃድ እድሳት አዳዲስ መረጃዎች appeared first on Zehabesha Amharic.

ኃይለማርያም ደሳለኝ እስር ቤት ያደራጁ ነጋዴዎች አሉ ሲሉ ነገሩን |ግርማ ሠይፉ ማሩ

$
0
0

girma seifu

ባለፈው ማክሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምሁራን ጋር ውይይት ደርጋሉ የሚለውን መረጃ ሰምቼ፣ ቅርባቸው ነው ላልኩት ሹም በስብሰባው እንድገኝ ጥያቄ አቅርቤ ነበር፡፡ ዋናው ምክንያቴ ባለፈው ምክር ቤት ተገኝተው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ አንድም የምክር ቤት አባል የሪፖርታቸውን ይዘት መሰረት አድርጎ በዚህ ገፅ በዚህ መስመር እንዲህ የሚለው ልክ አይደለም ማለቱ ቢቀር ይብራራ የሚል ሰው ባለማግኘታቸው በዚሁ አጋጣሚ እድል ቢያገኙ በሚል ነበር፡፡ ለማነኛውም የተገኙት ተሳተፊዎችም ቢሆኑ የዋዛ የማይባል ጥያቄ ማንሳታቸውን እኛ አድማጮ ደግሞ በተሰጠው ማብራሪያ ሳይሆን በጥያቄዎቹ መስመር ላይ መሆናችንን ማሳታወስ ግድ ነው፡፡ ምን ማለት ነው፡፡ ይህች ሀገር ነፃነት ያለው ህዝብ መኖሪያ አይደለችም፡፡ ጋዜጣኛም፣ ነጋዴም፣ ፖለቲከኛም፣ ተማሪም፣ ወዘተ በነፃነት የሚኖርበት ሀገር አይደለም፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ደረታችሁን ነፍታችሁ የምትሄዱት በሚል ከናይሮቢ ጋር ያደረጉት ንፅፅር በምንም መመዘኛ ትክክል አይደለም፡፡ ኬኒያዊ የኬኒያ መንግሰት ስጋቱ አይደለም፡፡ እኛ ግን መንግሰታችን ስጋታችን ነው፡፡ በእኛ ሀገር ሀፈና የሚፈፀመው ሊጠብቅህ በሚገባ መንግሰት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ እስከ ዛሬ ከሸብርተኛ ቡድን ነፃ የሆነችውን ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ስምም ፆታም አልገልፅም ብለው ነገር ግን እስከ አያት ስሟ የነገሩን ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ጉቤቦ በማሰራቸው አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ በዚህ ደረጃ ለሸብር የደረሰ ሰነ ልቦና ስለሌለው ነው፡፡ ርዕዮትን የፈቷት በግፊት መሆንን ማመናቸው አንድ ነገር ሆኖ በህገወጥ ሁኔታ በእስር እንደነበረች ግን የምንረሳው አይደለም፡፡ (የፍርድ ቤቶች ውሳኔ ልክ ነው ቢባል እንኳን የእስር ጊዜ ጨርሳ አንፈታም ብለው አስረው ነበር ያስቀመጧት)፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትራችነ ነጋዴዎች እስር ቤት እንዳላቸው የነገሩን ነገር ብዙ የሚገርም አይደለም፡፡ በእኛ ሀገር ኤምባሲዎች እስር ቤት እንደነበራቸው ይውራ ነበር (ኤርትራ ኤምባሲ)፡፡ ይህ ግን የሚሆነው በመንግሰት የደህንነት ሰዎች ድጋፍና ትብብር ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንም የትኛው ነጋዴ የት ቦታ እስር ቤት አደራጅቶ ከማን ጋር ይስራ እንደነበር በግልፅ በስም ሊገልፁልን በዚሁ ሁኔታም ክስ ተመስርቶ ማየት እንፈልጋል፡፡ (Name and Shame)፡፡ የነጋዴ ነገር ከተነሳ ነጋዴ በሙሉ ሌባ ነው ያሉትን ግን ትክክለኛ የንግድ ምክር ቤት ተወካይ ቢኖር ይቅርታ እንዲጠይቁ ማድረግ ነበረበት፡፡ ይህ ሁሉ ነጋዴ ግብር እየከፈለ ያቆማትን ሀገር ሁላችሁም ሌቦች ናችሁ ማሰር ብንፈልግ ማለት በፍፁም ልክ አይደለም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን አንድም ቀን በንግድ ተሳትፈው ስለማያውቅ ነጋዴዎች ትርፍ ለማሳደግ ሚወሰዷቸው እርምጃዎች በሙሉ የሌብነት ስራ ነው፡፡ ህጋዊ የሆነ የታክስ መቀነስ እንቅስቃሴ በትምህርት/በህውቀት (Legal Tax Evation) የተደገፈ መሆኑን የሚነግራቸው አማካሪ የላቸውም፡፡
አሁንም ዜጎችን ከሰላማዊ ትግል ወደ ትጥቅ ትግል እየገፋ ያለው መንግሰት መሆኑን፣ ሌባ ያሉትን ነጋዴ ይቅርታ መጠየቅ እንደሚገባ፣ እስር ቤት ያደራጁ ነጋዴዎች ካሉ በይፋ ለህዝብ ይፋ መደረግ ይኖርበታል፡፡

The post ኃይለማርያም ደሳለኝ እስር ቤት ያደራጁ ነጋዴዎች አሉ ሲሉ ነገሩን | ግርማ ሠይፉ ማሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

“ይቅርታ” ወይም “ሰላም” |ከተስፋዬ ገ/አብ

$
0
0

ሃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት ያደረጉት ቃለመጠይቅ አነጋጋሪ ነበር። ከኦሮሞ ህዝብ አመፅ ጋር በተያያዘ የሰነበተውን ችግር ሌላ አካል ላይ ማላከክ እንደማይገባ መናገራቸው ከኢህአዴግ ጠባይ አንፃር ያልተለመደ ነበር። በውስጥ ባለ ችግር ምክንያት የህዝብ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ባለማግኘታቸው ህዝብና መንግስት ተቃቅረው ጉዳዩ ወደ ግጭት ደረጃ መድረሱን ማመናቸው አንድ እርምጃ ወደፊት ነው። ችግሩ የመልካም አስተዳደር እጦት መሆኑን መግለፅ መቻላቸው ይደነቃል። ሃይለማርያም በዚህ ደረጃ ችግሩን አምነውና ተቀብለው ሲያበቁ፤ በመጨረሻ ለተፈጠረው ችግር በጥቅሉ ህዝብን ይቅርታ ጠይቀዋል። ይቅርታ ጥየቃው ካንገት በላይ ነው ወይስ ካንገት በታች ለጊዜው ባናውቅም፤ ይቅርታ መጠየቅ በራሱ ስልጣኔ ነው። 

(ተስፋዬ ገብረአብ)

(ተስፋዬ ገብረአብ)

እንግዲህ በመቀጠል ወደ ዝርዝር ጉዳይ እንግባ።

ሃይለማርያምይቅርታ ሲጠይቁ በመሰረቱ ምን ማለታቸው ነው? ከዚህ በሁዋላ ኢትዮጵያ ላይ በህጉ መሰረት ሰላማዊ ተቃውሞ ማካሄድ ተፈቅዶአል ማለት ነው? ከዚህ በሁዋላ የፌደራል ፖሊስ ሰላማዊ ሰዎችን በየጎዳናው አይገድልም? ባለፉት አራት ወራት እና ከዚያም በፊት በየጎዳናው ለተገደሉት ንፁሃን ዜጎች ወላጆችና ቤተሰብ ካሳ ይሰጣል? ንፁሃን ዜጎችን የገደሉና ያስገደሉ ለፍርድ ይቀርባሉ? የታሰሩት በአስር ሺዎች የሚገመቱ የፖለቲካ እስረኞች ይፈታሉ? መሬታቸው ተነጥቆ ለተፈናቀሉ ገበሬዎች ተገቢው ካሳ ተከፍሎ እንዲቋቋሙ ይደረጋል?ይቅርታውን ተከትሎ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ አንዳችም ያሉት ነገር የለም። በደፈናው ሸውዶ ለማለፍ የተደረገ የለበጣ ይቅርታከሆነቅዳሴና ዳንኪራንእንደመደባለቅ ይቆጠራል።

ከአንድ ሰው ጋር ስለዚሁ ጉዳይ ስንወያይ፣ “ሃይለማርያም ይቅርታ ጠየቀ ለማለት አይቻልም።ይቅርታውን መልሶአፍርሶታል።” አለኝ። ሌላው ደግሞ፣ “ሃይለማርያም ከዚህ ቀደም ‘አስመራ ሄጄ ከኢሳይያስ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ’ ሲሉ እንደተናገረው አሁንም የግሉን ይቅርታ ደባልቆይሆናል።” አለ። ከዚህ በተጨማሪ “የይቅርታው ቃል በአሜሪካኖች አስገዳጅነት በህወሃት እውቅና የመጣ ነው።” የሚል የውስጥ አዋቂ መረጃም ሰምቻለሁ። ከአስተያየቶች ሁሉ “ይቅርታ” የምትለው ቃል በአሜሪካኖች ተፅእኖ የተነገረች ልትሆን መቻሏ ወደ እውነት የሚጠጋ ይመስለኛል። ሲፃፍ እንደሰነበተው ወያኔ ችግር ውስጥ መገኘቱ አከራካሪ አይደለም። አስረጅ ሊሆን ከሚችለው መካከል፣ “ከኦሮሞ ህዝብ አመፅ ጀርባ የኤርትራ እና የግብፅ ተላላኪዎች አሉ” የሚለውን ክስ ለመተው መገደዳቸው አንዱ ነው። የኦሮሞ ህዝብ አመፅ መነሻ የመልካም አስተዳደር እጦት መሆኑን ማመን እስከዛሬ ጌታቸው ረዳ ሲነግረን የነበረውን ይቃረናል።

ርግጥ ነው፤ ከሃይለማርያም ይቅርታ መጠየቅ ጋር በተያያዘ ከሚሰሙጭምጭምታዎች ዋናው የአሜሪካኖች ተፅእኖ ሚዛን የሚደፋ መስሎ መታየቱ ነው። የፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ“ሰላም” የተባለው የማሸማገል ሂደትም የቀጠለ በመሆኑ ምን መልክ ይዞ ይፋ እንደሚሆን በቀጣዩ ጊዜያት የምንሰማው ይሆናል። በአንድ ወቅት CUD የተባለውን ቅንጅት ይመሩ የነበሩ ሰዎች በፕሮፌሰር ኤፍሬም አሸማጋይነት ከእስርቤት ከወጡ በሁዋላ የወያኔ ፍላጎት እንደምንም ተያይዘው ከአገር እንዲወጡለት መንገድ መክፈት ነበር። በርግጥም አብዛኞቹ ባገኙት እድል ሁሉ ተጠቅመው የታገሉላትን አገር ትተው እንደማይመለሱ ሆነው ርቀው ሄደዋል። ይህ ለህወሃት አገዛዝጥሩ እድል ነበር።አብዛኞቹየCUD ሰዎች ከኮበለሉ በሁዋላ ወያኔ እንደ ብርቱካን ሚደቅሳ ያሉትን ነጥሎ ለመምታት አልተቸገረም።

ህወሃት ቅንጅትን አዳክሞ ባጠፋው መንገድ የኦሮሞ አማፅያንን በዚያው ዘዴ ለማኮላሸት ማሰቡ ገና ያልተፈፀመ በሂደት ላይ ያለ ተግባር ነው። እንደሚሰማው የኢትዮጵያ መንግስት ህዝቡን ይቅርታ ጠይቆ እስረኞችን ለመፍታት ለአሜሪካኖቹ ቃል ገብቶ ከሰነበተ እንግዲህ ይቅርታዋ እንደምንምተነግራለች።  እስረኞችን መፍታትግን ገና አልተፈፀመም። እንደ ውስጥ አዋቂዎች ጥቆማ ከሆነ በእስርቤት ካጎሯቸው በአስር ሺህዎች የሚገመቱ ኦሮሞ እስረኞች መካከል የአመፁ አስተባባሪ ሊሆኑ ይችላሉ ብለው የገመቷቸውን በመለየት ስራ ተጠምደዋል። አመፁን ያስተባብራሉ ብለው የሚገምቷቸውን ለይተው ካበቁ በሁዋላ ወደ ስደት የሚሄዱበትን መንገድ ያመቻቻሉ ተብሎ ይታሰባል። ይህን ማድረግ የኦሮሞን ህዝብ ትግል ያዳክማል፤ ስርአቱ ትንፋሽ እንዲያገኝም ፋታ ይሰጠዋል ብለው ቢያስቡ ከልምዳቸው አንፃር ስህተት አይሆንም። የነቃው እና የተደራጀው ግለሰብ ከሜዳው ገለል ካለ አመፁ ጠቅልሎ ባይቆም እንኳ ፋታ ሊገኝ ይችላል።በርግጥ እንደ እስክንድር ነጋ፤ እንደ በቀለ ገርባ ለመኮብለል ፈቃደኛ የማይሆኑ ሲገጥሙ ቀመሩ ተገላቢጦሽ ይሆናል።

የኦሮሚያ ወጣቶች ሴራውን ባለመረዳት ለአዲስ ዙር ስደት ከተነሱ ‘በአገሩ የሌለ – የትም የለም።’ እንደሚባለው ለህወሃት ድል ይሆናል።ኮብላዮች ድጋፍ ሰጪ ከመሆን ያለፈ አቅም አይኖራቸውም።የኦሮሞ ህዝብ አሁን ከደረሰበት የተሰሚነት አቅም ላይ እንዲደርስ ያደረጉት በግንባር ቀደምትነት ተጋፍጠው መስዋእትነት የከፈሉት ጥቂት ወጣቶችናቸው። ድጋፍ ሰጪ ስደተኛ የማድረግ ችሎታው በጣም ውሱን ነው። ሃርቫርድ ከሚገኝ አንድ ተራ ፕሮፌሰር፤ ሃሮማያ የሚገኝ አንድ ተራ የገበሬ ልጅ የተሻለ የማድረግ ችሎታ አለው።ህወሃት ከዳያስፖራ ይልቅ አጠገቡ ያሉትን ተራ ዜጎች ይሰጋል። ስለዚህ የማስቸገር ብቃት ያላቸው ይኮበልሉ ዘንድ ተግቶ ይሰራል። ማሰርና መግደል የህወሃት የመጀመሪያ ምርጫ ሆነው አያውቁም። የኮበለለ ሁሉ የወያኔን የመጀመሪያ ምርጫ እንደተቀበለና እንደተሸወደ ማወቅ አለበት።

ባለፈው ሳምንት “የቅዳሜ ማስታወሻ” ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅን በጨረፍታም ቢሆን ነካ አድርጌያቸው ነበር።በላኩልኝ ኢሜይል ስለርሳቸው ያለኝ ግንዛቤ ስህተት መሆኑን ጠቁመውኛል። እርሳቸው እንደገመቱት ሳይሆን ስለ ፕሮፌሰሩ ብዙም ባይሆን ጥቂት አውቃለሁ። የት ከማን እንደተወለዱ፣ የት ምን እንደተማሩ፣ የት ምን እንደሚያስተምሩ አውቃለሁ። ደረጀ ደሬሳ በአጤ ሃይለስላሴ ዘመን በወቅቱ የ31 አመት ጎረምሳ ለነበሩትለአቶ ኤፍሬም ይስሃቅ የፃፈውን መወድስም ኢትዮጵያ ሳለሁአንብቤያለሁ። በተማሪዎች እንቅስቃሴ ዘመን ለአገራቸው ብዙ ቁምነገር የሰሩ ሰው መሆናቸውን ቀደም ብዬም አውቅ ነበር። ሽማግሌው ፕሮፌሰር በጎልማሳነታቸው ዘመን ለደቡብ አፍሪቃ ጥቁሮች መብት መከበር መታገላቸውን በርግጥ አላውቅም ነበር።ዞረም ቀረ የተሰራው መልካም ነገር ሁሉ በቦታው አለ። ታሪክ አይረሳውም፤ ታሪክ ያመሰግናቸዋል።ፕሮፌሰሩ የአባት አገራቸው ታማኝ ልጅ ቢሆኑም፤ መወለድ ቋንቋ ነውና ልክ እንደኔው እሳቸውም የትውልድ አገራቸውን እንደሚወዱ እረዳለሁ።

ፕሮፌሰር ኤፍሬም በደርግ ውድቀት ማግስት የመሸጋገሪያው መንግስት ምስረታ ላይ፣ ታምራት ላይኔን ለማሞገስ፣ “ተአምራት ለአይኔ፣ ተአምር በአይኔ አየሁ” ብለው ቅኔ ሲቀኙ በደማቁ ካጨበጨቡላቸው አንዱ እንደነበርኩ አልክድም። በወቅቱ ሁላችንም ተአምራት በአይናችን ያየን መስሎን ነበር። ታምራትና መለስ የተሸፈነ ጠባያቸው ሳይገለጥ ጥቂት አመታት እንኳ መጓዝ እንደማይችሉ አልገመትንም ነበር። ጃኬትና መኪና ወደ ማማረጥ ይገባሉ ብሎ የጠረጠረ አልነበረም። የሆነው ሆኖ የስካሩ አቧራ ገለል ሲል ፕሮፌሰር ኤፍሬም በአይናቸው ተአምራት ሳይሆን መቅሰፍት ነበር ያዩት። ያም ሆኖ ወዳጅነታቸውን ከወያኔ ጋር ቀጥለዋል።እዚህ ላይ እንግዲህ መነፅራችንን ዝቅ አድርገን፣ “ጤናይስጥልኝ ፕሮፌሰር!” ለማለት እንገደዳለን።

ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ የኦሮሞን ህዝብ ከገዢው ግንባር ጋር ለማስታረቅ በሚያደርጉት ሙከራ፣ “ሰላም” የሚለውን ቃል ሲጠቀሙ “የማን ሰላም?” የሚለውንም ጥያቄ ይመልሱት ዘንድ ይጠበቃል።ሰላምን ለማስገኘት ሽምግልና ከመጀመራቸው በፊት “ፀረ ሰላም ማነው? ለሰላም ጠንቅ የሆነው ማነው?” ለሚለው ጥያቄ ምላሽማግኘት ይገባል። የቀድሞ በጎ ስራ ለዛሬው ስህተት ላጲስ ሆኖ አያገለግልም። “ሰላም ወዳድ” የሚለው ማእረግ “አሻጥረኛ”  ወደሚል ከተለወጠ ለመመለስ ያስቸግራል። የኦሮሞ ህዝብ በአገሩ ላይ የተረጋገጠ ሰላም ለማግኘት መስዋእትነት መክፈል እንዳለበት የተረዳበት ጊዜ ላይ ነው። በርግጥም የአዲሱ ትውልድ መሪ መፈክር አንድ ብቻ ሆኖአል። ይህም፣ “ዛሬ አንድ ነገር ማድረግ አለብን። ወይም ደግሞ መሞት አለብን!” የሚል ነው። እና ማገዙ ካልተቻለ ቢያንስ “እንኳን ለዚህ አበቃችሁ!” ማለት ይገባል።

ርግጥ ነው፤ “የሰላም መጥፎ፣  የጦርነት ጥሩ የለውም” የሚለው ነባር አባባል በጥቅሉ ተቀባይነት አለው። ልጇ የሞተባት እናት፤ አባቱ የሞተበት ልጅ ሃዘን ላይ ናቸው። ሃዘናቸውን ለመረዳት እግራችንን እነርሱ ጫማ ውስጥ መጨመር ይገባል። ቢሆንም ግን ለሰላም ሲባል ሰላምን ለማደፍረስ፤ ጦርነትን ለማስወገድ ጦርነት መለኮስ ግዴታ ሆኖ ሊመጣ ይችላል። ሲደፈርስ በርግጥ ብዙ ህይወት ይቀጠፋል። ባይሆን ጥሩ ነበር። ህይወት ሳይከፈል የብዙሃን ሰላም የማይገኝ ከሆነ ግን መደፍረሱ ግድ ይሆናል። ህይወት በሚቀጠፍበት መንገድ ብቻ ማለፍ ግድ መሆኑ ያሳዝናል። በጦርነት ድል ቢገኝም እንኳ ከድሉ ባሻገር አሸናፊውም ልክ እንደ ተሸናፊው እኩል ኪሳራ ይቀበላል። ሰላም አንፃራዊ ነው። በሚዛናዊ መነፅር ስንመለከተው ዚምቧቡዌ ከቀድሞ ሰላሟ ይልቅ የአሁኑ መተራመሷ ይሻላት ይሆናል። በዚህ የዚምቧቤ መተራመስ ውስጥ 300 ሺህ የአገሬው ሰዎች ከዘበኛነትና ከግርድና ስራ ተላቀው ባለመሬት መሆናቸውን መዘንጋት አይገባም። የኦሮሞ ወጣቶች በዚህ ዘመን የተተወላቸው ስራ በተነጠቀ መሬታቸው ላይ ዘበኝነት መቀጠር ሆኖአል። ከመሬታቸው የተፈናቀሉ የገበሬ ልጆች በዘበኛነት የስራ ዘርፍ አዲሳባን እንደወረሩ፣ በበረንዳ አዳሪነት ከተማዋን እንዳጥለቀለቁ  በቂ መረጃ አለ። እነዚህ ወጣቶች ከጥቂት አመታት በፊት ባለመሬት ነበሩ። ሃብታም መሬት ያርሱ ነበር። ሳሞራ ማሼል ስልጣኑን በያዘባት ሌሊት ያንን ዝነኛ አዋጅ ያወጀው የነፃነትን የተሟላ ትርጉም ለወገኖቹ ለማቅመስ ነበር። ነፃነት ሲባል የከበርቴ ሰዎች ዘበኛ ሆነህ መለፍለፍ መቻል ማለት አይደለም። ነፃነት ከመሬት ባለቤትነት ይጀምራል። እና ሞዛምቢካውያን ከነሙሉ ችግራቸው ዛሬም ቢሆን ሳሞራን በበጎ ያስታውሱታል።

የኦሮሞ ህዝብ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ስርአቱ የጫነበትን የሰቆቃ ህይወት እየተቃወመ ረጅም ተጉዟል። ሸክሙ ሲበዛበት ግን ቀንበሩን ወረወረና አታላዩን ሰላምና ፀጥታ ክፉኛ አደፈረሰው። የህልውና ጉዳይ ሆነበት። አይኑ እያየ የማያውቃቸው ሰዎች መጥተው የአያቱን መሬት ሲሸጡ ሲመለከት የሰላም ትርጉሙ ጠፋበት። መሞትን መረጠ። እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰን ሰው “ለሰላም ሲባል”፤ “ለአንድነት ሲባል” ብለህ ልታግባባው አትችልም። አይሰማህም። በአንድ ወቅት የOPDO ምክትል ሊቀመንበር እንደነበረው እንደ ኢብራሂም መልካ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ለኦሮሞ ያልሆነች ኢትዮጵያ አስር ቦታ ትበጣጠስ!!” ሊልህ ይችላል። በመሆኑም ፕሮፌሰር ኤፍሬም ለማን ጥቅም እየሰሩ እንዳሉ ማወቅ አለባቸው። ለኢትዮጵያ አንድነት? ለተጨቆኑ ህዝቦች ሰላም? ወይስ ለአንድ ቡድን ስልጣን? ምላሹ ለህሊናቸው ይሁን።

የጃዋር መሃመድን መረጃ ከያዝን ሌላው ይቆይልንና ባለፉት አራት ወራት በኦሮሚያ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 500 አሻቅቦአል። ይህ ብቻውን እንኳ ለወያኔ ትልቅ እዳ ነው። ክፍያው ሊቸግር ይችላል። የህይወት እዳ ወለዱ ውድ ነው። ሃይለማርያም በቅርቡ ሴት ልጃቸውን በሞቀ ሰርግ ድረዋል። ሟቾቹ ወጣቶች በተመሳሳይ ለወግ ለማእረግ እንዲበቁ ወላጆቻቸው ይመኙ ነበር። ልጆቻቸውን ያጡ፣ አባታቸውን የተነጠቁ ወገኖች ሃዘኑን አይችሉትም። ሃይለማርያም ይቅርታ የጠየቁት በራሳቸው ተነሳሽነት ከሆነ ከዚያም በላይ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ርግጥ ነው፤ “የኦሮሚያ አመፅ” የሚለው የጨዋታ ካርድ ላለፉት አራት ወራት ከፖለቲካ ሜዳው ላይ ሊወርድ አልቻለም። ከቀዳሚ ዜናነቱ ሊገፈተር አልቻለም።ሰበር ዜና ከመሆን ሊታቀብ አልቻለም።ሃይለማርያም የበታች አለቆቻቸውን ስነልቦና መረዳት ይጠበቅባቸዋል። አባይ ፀሃዬ እና ስብሃት ነጋ “ጥቂት ታገስ! ከዚያም ጊዜ ጠብቀህ የጨዋታውን ካርድ ቀይረው” የሚለውን የሰርቫንቴስ አባባል ደጋግመውም ይጠቀሙበታል። የ“ይቅርታ” እና የ“ሰላም” ወጎች የትእግስት ምእራፍሲሆኑ፤ ከረምረም ብለው የጨዋታውን ካርድ ለመቀየር መሸጋገሪያ ይሆናሉ። ያንጊዜ ጊሎቲን አንገት ቆረጣውን እንዳዲስ ይጀምራል።

በመጨረሻ አንድ ነጥብ ላይ ላስምር። የኦሮሞ ህዝብ እየከፈለ ያለው የህይወት መስዋእትነት ኪሳራ አይደለም። ግብና አላማ አለው። ለመጪው ትውልድ እየተከፈለ ያለ የክብር ዋጋ ነው። እና የኦሮሞ ህዝብ ጨክኖ እንደጀመረ ከመግፋት በቀር አማራጭ የለውም። ወደሁዋላ ማየት እንደገና መቶ አመታት ሊያስተኛ ይችላል። መስዋእትነቱን አያስቀረውም። ከመሬት መፈናቀሉን፣ ስደቱን አያስቀረውም። የኦሮሞ ህዝብ ትልቅ ህዝብ እንደመሆኑ ሌሎችንም ኢትዮጵያውያን አስተባብሮ፣ አቅፎ ወደ ተሻለው ዘመን የመጓዝ ብቃቱና ችሎታው አለው። ያለ ኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያ ምትባል አገር የለችም። እና የኦሮሞ ህዝብ ራሱን ነፃ ከማውጣት ባሻገር ከባድ ሃላፊነት አለበት። የተረጋገጠውን ሰላም ለማግኘትና በረጅሙ ለማረፍ ጨለማማውን ጫካ በድፍረት ማለፍ ይገባዋል። ይቻለዋልም። አሳምሮ ይቻለዋል። ታግለው ነፃ የወጡ የአለም ህዝቦች ታሪክ የሚነግረን ይህንኑ ነው።

The post “ይቅርታ” ወይም “ሰላም” | ከተስፋዬ ገ/አብ appeared first on Zehabesha Amharic.

የወልቃይቱ ታዋቂ ባለሀብት አቶ ሹምዬ ገብሩ በመርዝ ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ

$
0
0

Breaking News zehabesha

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)  የወልቃይቱ ታዋቂ ባለሀብት የሆኑት አቶ ሹምዬ ገብሩ በትናንትናው ዕለት ተመርዘው ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ፡፡

አቶ ሹምዬ ገብሩ በእርሻው እና በንግዱ ዘርፍ በጎንደር ከተማ እና አካባቢው፣ ወልቃይት፣ እንዲሁም አርማጭሆን ጨምሮ ደህና የሚንቀሳቀሱ ነብስ ያላቸው ሀብታም ነጋዴ ነበሩ፡፡

ትናንት የካቲት 7/07/2008 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ለስራ ወዲያ ወዲህ በሚሯሯጡበት ጊዜ በበሉት ምግብና መጠጥ አካላቸው ተመርዞ ወደ ህክምና ቢወሰዱም በተደረገላቸው እርዳታ በህይወት ሊተርፉ ባለመቻላቸው ሳይታሰብ በድንገት ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

አቶ ሹምዬ ገብሩ በአሁኑ ወቅት እየከረረ መጥቶ ከጫፍ የደረሰው የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ዋነኛ አቀንቃኝ ከመሆናቸው ባለፈ ለኮሚቴው ያልተቋረጠ የገንዘብ፣ የሀሳብና የሞራል ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩ ናቸው ተብሏል፡፡

ስለሆነም በአቶ ሹምዬ ገብሩ በምግብ ተመርዞ በድንገት ለህልፈት መብቃት የህወሓት አገዛዝ ስውር አጅ እንዳለበት ፍንጭ የሚሰጡ መረጃዎች እንዳሉ ዜናውን ያደረሱን ምንጮች ገልፀዋል፡፡

The post የወልቃይቱ ታዋቂ ባለሀብት አቶ ሹምዬ ገብሩ በመርዝ ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሞረሽ የዐማራ ድምፅ የሬድዮ ጣቢያ ማቋቋም ለምን አስፈለገ? –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

Moreshባለፉት ፳፭(ሃያ አምሥት) ዓመታት በዐማራው ላይ የሚፈጸመው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ከችግሩ ሥፋት እና ጥልቀት አንፃር ተመጣጣኝ የሆነ የሚዲያ ሽፋን አልተሰጠውም። በ«ኢትዮጵያዊነት» ስም በተቋቋሙት ድርጅቶችም ሆነ በተለያዩ አገሮች መንግሥታት ሥር የሬድዮ እና የቴሌቪዥን መርኃ-ግብሮችን በአማርኛ ቋንቋ የሚያሠራጩ ሚዲያዎች በዐማራው ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እና በደል የዓለም ማኅበረሰብ እንዲያውቀው የማድረግ ፈቃደኝነታቸው እጅግ ውስን መሆኑን በተደጋጋሚ ታይቷል። ይህም «ችግሩ ችግራችን ነው» ብሎ የሚይዝ ሚዲያ አለመኖሩን ያረጋግጣል። ስለሆነም እኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አባሎች እና ደጋፊዎች ለመላው የዐማራ ሕዝብ ድምጽ የሚሆን የሬድዮ ጣቢያ ለማቋቋም ቆርጠን ተነስተናል። ዐማራው በተገንጣይ እና ጠባብ የጎጠኞች ቡድኖች የተክፈተበትን የሥነ-ልቦና ጦርነት ተመጣጣኝ በሆነ ኃይል በመመከት እውነተኛውን ገፅታ ለማሣየት፣ የሚያስችል የአጸፋ ፕሮፓጋንዳ እና ቅስቀሣ ለመሥራት፣ «ሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ» በአየር ላይ መዋል ለነገዳችን ህልውና በጣም አስፈልጓል።

ለሩብ ምዕተ-ዓመት በዘለቀው የትግሬ ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ፣ ክ፭(አምሥት) ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን በልዩ ልዩ መንገዶች ከምድረ ገፅ እንዲጠፉ ተደርጓል። ይህን ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን ለፍትኅ ለማቅረብ የተቀነባበረ የመረጃ ልውውጥ አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይደለም። የዐማራውን ነገድ ለመታደግ የሚቻለው ዐማራው ተደራጅቶ በኅብረት ጥቃቱን ሲመክት ነው። ሰለሆነም ዐማራው የሚፈጸምበትን የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ለመቋቋም የሚችለው፣ በጠንካራ መሠረት ላይ ተደራጅቶ የሚደርስበትን ጥቃት ለመቋቋም ሲዘጋጅ መሆኑን መቀመበል ያስፈልጋል። ለዚህም ተጣጣኝ የሥነ-ልቦና ትጥቅ ለመታጠቅ የሬድዮ ድምጽ አስፈላጊ ነው። በዚህ ረገድ የዐማራው ልጆች «የወገናችን ችግር ችግራችን ነው፤ ብሦቱም ብሦታችን ነው፤ ከሁሉም በላይ ዘራችን መጥፋት የለበትም» ብለን ከተነሣን፣ እንኳንስ እንዲት የአጭር ሞገድ የሬድዮ ጣቢያ ማቋቋም ቀርቶ፣ ሁሉን-አቀፍ የሆነ የዐማራ ሚዲያ ማዕከል ለመመሥረት መቻላችን ጥርጥር የለውም።

በመሠረቱ የዐማራው ሕዝብ ጠላቶች በቅድሚያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቶች ናቸው። ዐማራው እንዲጠፋ የተወሰነበት አብይ ምክንያት በታሪኩ የሚተማመን፤ አትንኩኝ ባይ፤ ለነፃነቱ ቀናዒ፤ ለህልውናው እና ለአገር ዳር ደንበር ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ሟች ፍፁም ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ነው። በዐማራው ነገድ ላይ ጥቃት የተጀመረው ዛሬ ሣይሆን ከ፭፻(አምሥት መቶ) ዓመታት በፊት በቱርኮች እና በአረቦች ድጋፍ ግራኝ አሕመድ ካካሄደብን የጅምላ ጭፍጨፋ ጀምሮ እንደሆነ ይታወቃል። ከግራኝ ጭፍጨፋ ተከትሎ የኦሮሞዎች ወረራ ተከተለ፤ ከዚያም በዘመነ-መሣፍንት ከፍተኛ የሆነ ዕልቂት የደረሰው በዐማራው ላይ ነበር። ፋሽስት ኢጣሊያም ከአንዴም ሁለቴ ከፍተኛ ጥፋት ያደረሰችው በዐማራው ላይ ነበር። ደርግ ገና ሥልጣን ከመያዙ አስቀድሞ የዘመተው በዐማራው ላይ መሆኑ የቅርብ ዘመን ትውስታችን ነው። የትግሬ-ወያኔ ዘረኞች ገና ከጠዋቱ በርሃ ሲገቡ ጀምረው በፕሮግራማቸው ያሰፈሩት ዋና ጠላታቸው ዐማራ እንደሆነ እና ከተቻለም ከኢትዮጵያ ምድረ ገጽ እንዲጠፋ፣ ካልሆነ ደግሞ አቅመቢስ ባርያቸው አድርገው  ለመግዛት መሆኑ ግልፅ ነው። ይህንን ጽኑ ፍላጎታቸውን እውን ለማድረግ ከበረሃ ጀምረው በዐማራ ሕዝብ ላይ በፍርሃት ተጨምድደው በመሠረቱት ጥላቻ፣ በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስሙን ጥላሸት ቀብተውታል፤ መሬቱን ቀምተውታል፤ በአገሩ ላይ ሁለተኛ ዜጋ በማድረግ ከኖረበት ቀዬው እንዲፈናቀል አድርገውት እናያለን። ለዚህም ማረጋገጫው ላለፉት ፶(ሃምሣ) ዓመታት በሻቢያ፣ በትግሬ-ወያኔ እና  በኦነግ አማካይነት በዐማራው ሕዝብ የተፈጸመው የሥነ-ልቦና ጥቃት ሕዝባችንን ከነበረበት በራስ የመተማመን ደረጃ አወርዶት ይገኛል። ዐማራው ይህን በረቀቀ እና በግልፅ በተቀነባበረ ሥልት የሚፈፀምበትን አደገኛ የሥነ-ልቦና ምት፣ ሁለገብ የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሊቋቋም የሚችለው በአንድ ዐላማ ሥር አንድ ሆኖ ሲቆም ብቻ ነው። ሰለሆነም «ሞረሽ የዐማራ ሬድዮ ድምፅ» የተጎዳውን የወገኖቻችን ሥነ-ልቦና ለማደስም ሆነ የወንድማማችነት  መንፈስ ለማጎልበት ያገለግለናል።

ለአንድ ዓላማ ግብ መምታት በሥርዐት ላይ የተመሠረተ ዝግጅት እና መሠናዶ እጅግ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው። ይህ አካሄድ በግል ሕይዎታችንም ስኬት ለማግኘት ያስችላል። ለመዘጋጀት እና ለመስናዳት ደግሞ ቅንብር እና ድርጅት ያስፈልጋሉ። መደራጀት ጠላትን ለይቶ ለመመከት እና አሸንፎ ለመውጣት ያግዛል።                                                                          መደራጀት ተመጣጣኝ ኃይል ፈጥሮ በማናቸውም ጊዜ እና ቦታ  ለድርድር ያበቃል። ስለሆነም የሬድዮው ድምጽ በትግሬ-ወያኔ የተመዘዘበትን የጥፋት ሰይፍ ወደ አፎቱ ለማስገባት ዐማራው ለአንድ ዓላማ፣ በአንድ ልብ፣ በፍጹም የወንድማማችነት መንፈስ መነሣት እንዲችል፣ በእውነት እና በእውቀት ላይ የቆመ የፕሮፓጋንዳ እና የቅስቀሣ ስራዎችን ለማክናወን የሚያስችል ፍቱን መሳሪያ ነው። ሞረሽ የዐማራ ድምጽ ሬድዮ «ዐማራው ከገባበት አጣብቂኝ ወጥመድ ሰብሮ ለማምለጥ ምን ማድረ አለበት? እንዴትስ በይፋ በአገር አቀፍ ከታወጀበት የዘር ማጽዳት ሤራ እርምጃ ሊተርፍ ይችላል?» የሚሉትን እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በመዳሰስ በኢትዮጵያ ምድር እንደስፌድ ቆሎ ተብትኖ ለሚገኙት ዐማራ ወገኖቻችን ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን እንዲደርስ ያደርጋል።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የካቲት 1 ቀን 2008 ዓ.ም. በቁጥር ሞወዐድ 000100-08 «ሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ጥሪ» በዓለም ለሚገኙ ዐማራ ወገኖች እና ወዳጆች ማቅረቡን በዚህ አጋጣሚ ለማስታወስ እንወዳለን። «ለወገን ችግር ፈጥኖ ደራሹ ወገን ነውና» በሜልበርን (አውስትራሊያ) እና በካልገሪ (ካናዳ) የሚገኙ የሞረሽ-ወገኔ  መሠረታዊ ማኅበራት አባሎች እና ደጋፊዎች የጉዳዩን አጣዳፊነት እና አስፈላጊነት ጠንቅቀው በመገንዘባቸው፣ እሑድ የካቲት 27 ቀን 2008 ዓ.ም. የመጀመሪያ ዙር የገንዘብ እርዳታ ማሰብሰብ ዝግጅት አከናውነዋል። ይህ ጥረት በሚገባ ተጠናክሮ በሁሉም የዓለማችን ክፍሎች ሊቀጥል ይገባዋል። ዐማራው ከገባበት የሚያባራ ጥቃት እና ሰለባ ሊያመልጥ የሚችለው፣ በንጹህ የመላው ዐማራ የወንድማማችነት/እህትማማችነት መንፈስ በአንድነት ቆሞ በምድር ውስጥ የቁም ስቃይ እና መከራ ለሚበላው ወገናችን ድምፅ ሲሆን ብቻ ነው። በመሆኑም «ሞረሽ የዐማራ ድምጽ ሬድዮን» ተረባርበን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአየር እንድናበቃው በዐማራነታችን የሚጠበቅብንን ግዴታ እንድንወጣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ለመላው የዐማራ ሕዝብ ያስተጋባል።

የዐማራው ኅልውና ጉዳይ ለዐማራው ብቻ ሊተው አይገባም። የእንቁጣጣሽ በግ ሲታረድ የመስቀሉ በግ ይስቃል እንዳይሆን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከአገራችን ምድረ ገጽ እንዲጠፋ ከተበየነበት የዐማራ ሕዝብ ጎን በመቆም የዜግነት እና የንፁህ ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነት/እህትማማችነት ድርሻ ሊወጣ ይገባዋልና ሞረሽ የዐማራ ሬድዮ ድምጽ እንድትረዱ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናቀርባለን።

 

በግፈኛ ዘረኞች ድምፁ ለታፈነው ዐማራ ድምፅ እንሁነው!

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

ኢትዮጵያ በጀግኖች እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

 

 

 

 

The post ሞረሽ የዐማራ ድምፅ የሬድዮ ጣቢያ ማቋቋም ለምን አስፈለገ? – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት appeared first on Zehabesha Amharic.


ሸንጎ መግለጫ አወጣ |“ሀላፊነት እወስዳለሁ ማለትና ይቅርታ በተግባር መተርጎም አለበት”

$
0
0

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)
Ethiopian People’s Congress for United Struggle (Shengo) www.ethioshengo.org shengo.derbiaber@gmail.com


 

መጋቢት 7፣ 2008፣ ማርች 14፣ 2016

ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርአም ደሳለኝ ከጥቂት ቀናት በፊት ለፓርላማው ባቀረቡት ዘገባ ውስጥ ጨምረው በሀገራችን ባሁኑ ሰአት በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ጎልቶ የሚታየውን የህዝን መነሳሳት ከመልካም አስተዳደር መጥፋትና ከስርአቱ ብልሽት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ለተፈጸመው በደል ተጠያቂ እንደሆኑም አምነው “ይቅርታ “ ጠይቀዋል።

shengo
እጅግ የዘገየ ቢሆንም ሀላፊነት እወስዳለሁ ፣ ለተሰራው ወንጀልም ተጠያቂ ነን ማለትና ይቅርታ መጠየቅ አበረታች ነው። ሆኖም ይሀ ተራ ቃል ብቻ እንዳይሆን በግልጽ በተግባር ሊታገዝ ይገባዋል።
ሁሉም እንደሚያውቀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተቀሰቀሰው የህዝብ መነሳሳት ጋር በተያያዘ ሰበብ ወደ እስር የተወረወሩ የፖለቲካ መሪወች ለምሳሌ አቶ በቀለ ገርባ እና በሽወች የሚቆጠሩ ዜጎች ይገኛሉ። በወልቃይትና ጠገዴም እንዲሁ ተመሳሳይ ሁኔታወች ተከስተዋል። ስህተተኛ ነን ካሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ እነዚህን ያላግባብ ታሰረው የሚማቅቁ ወገኖቻችንን ሁሉ ባስቸኳይ ከእስር መፍታት ይጠበቅባቸዋል። የተፈጠረው ስህተትና ቀውስ ከራሱ ከስርአቱ ፖሊሲና አሰራር የመነጨ መሆኑን ካመነ ፣ መሰረታዊ መብታቸውን በመግለጽ ላይ እያሉ የታሰሩ ሁሉ አሁኑኑ ከእስር መለቀቅ አለባቸው።ቀጣይ የመብት ረገጣውንም አሁኑኑ ማስቆም ያሰፈልጋል።
ደጋግመን እንዳልነው ሁሉ ከዚህም በተጨማሪ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ህይወታቸው ለጠፋው ፣ ንብረታቸው ለወደመው ሁሉ አስፈላጊውን ካሳ መክፈል የግድ ይላል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ፍትህን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነውና የዚህን ወንጀል ሁኔታ በነጻ የሚመረምር ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ አጣሪ አካል መስርቶ ያለአንዳች ጣልቃ ገብነት ተግባሩን እንዲያከናውን ውጤቱንም ባጭር ጊዜ በይፋ ለህዝብ እንዲያሳውቅ ማድረግ ትእዛዙን የሰጡም ሆኑ በስላማዊው ህዝብ ላይ ጥቃት የፈጸሙ ሁሉ በይፋ ለፍርድ ባስቸኻይ እንዲቀርቡ ማድረግ ያሰፋልጋል።
ይህ ሳይሆን “ይቅርታ ጠይቀናል፣ ሀላፊነት እንወስዳለን “ ወዘተ የሚሉ ቃላቶች ተራ ቃላት ብቻ ሆነው ይቀራሉ። ያለፉት 24 አመታት ከስርአቱ መሪወች ተመሳሳይ በተግባር ያልተደገፈ ንግግርን በተደጋጋሚ እንደሰማን የሚዘነጋ አይደለም። ይህ ደግሞ የህዝባችንም ቁጣ ይበልጥ ያብሰዋል እንጂ ሊያበርደው ከቶውንም አይችልም።

በመጨረሻም በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ስርአቱ ለ24 አመታት እንዳደረገው በማፈን፣ በመግደል፣ በመከፋፈልና የህዝብን ጥያቄ በማስፈራሪያነት በመጠቀም ለመቀጠል የማይችልበት ሁኔታ ላይ እንደደረሰና ሀገራችንም አስፈሪ ወደሆነ ቀውስ እንደተገፋች ተገንዝቦ ራስን ከማታለል ተላቆ የሀገሪቱን ችግሮች ሁሉን አቀፍ በሆነ በብሄራዊ መግባባትና በብሄራዊ እርቅ ለመፍታት ሳይዘገይ ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ አለበት አንላላን። የሀገራችን ውስብስብ ችግሮች ባንድ ድርጅት ብቻ ሊፈታ እንደማይችል መገንዘብ የግድ ነው።
ለስርአቱ ቅርበት ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ያለውን እውነታ በጊዜ ተገንዝባችሁ አደጋውን ለመቀነስና የኢትዮጵያን ህዝብ የነጻነት ፍላጎት ተግባራዊ ለማድረግ ከህዝብ ጎን እንድትሰለፉ በድጋሜ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
በተደጋጋሚ እንዳሳየነው ብሄራዊ መግባባትና እርቅ እንዲሁም ሀላፊነት እወስዳለሁ ማለት ካንገት በላይ ሳይሆን ከልብ መሆን አለበት።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
Tel: 44 7937600756 , +1 9168486790 E-mail : shengo.derbiaber@gmail.com

The post ሸንጎ መግለጫ አወጣ | “ሀላፊነት እወስዳለሁ ማለትና ይቅርታ በተግባር መተርጎም አለበት” appeared first on Zehabesha Amharic.

ዶ/ር መረራ ጉዲና ለኃይለማርያም ደሳለኝ ምላሽ ሰጡ |ልዩ ቃለምልልስ |“ተቃዋሚዎች ላለፉት 40 ዓመታት መተባበር የሚለውን ፈተና አላለፉም”

$
0
0

Gudina
* ኢህአዴግ የቃላት ጨዋታውን ማቆም አለበት”
* ተቃዋሚዎች ባለፉት አርባ ዓመታት ማለፍ ያልቻሉት ፈተና መተባበር እና ባንድ ላይ መቆም አለመቻል ነው
* ምርጫ ቦርድ ዘጠና ምናምን ተቃዋሚ አለ ይላል በጣት ከሚቆጠሩት በስተቀር ብዙዎቹ የመንግስት ቅልብ ናቸው
* የሰከነ ትግል በአቅም ላይ የተመሰረተ ትግል ከሁሉም በላይ የተባበረ ትግል ላይ ካልገባን ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ነው የሚሆነው
* ብሔራዊ እርቅ እና መግባባት ኢህአዴግ እንደሚጠላ ባውቅም ወደዚያ ካልተሄደ ሁኔታዎች ወደ አደገኛ መንገድ ሊያመሩ ይችላሉ
* የአቶ ሀይለማሪያም ንግግር የቃላት ሽንገላ ካልሆነ በስተቀር መሬት ላይ አዲስ ነገር የለም… የገደለ ባለስልጣን ለፍርድ አልቀረበም..የታሰሩት አልተፈቱም

The post ዶ/ር መረራ ጉዲና ለኃይለማርያም ደሳለኝ ምላሽ ሰጡ | ልዩ ቃለምልልስ | “ተቃዋሚዎች ላለፉት 40 ዓመታት መተባበር የሚለውን ፈተና አላለፉም” appeared first on Zehabesha Amharic.

የአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ስብሰባ |ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

$
0
0

Pro Mesfin
መጋቢት 2008

(ይህ ጽሑፍ ሪፖርተር ጋዜጣ በጻፈው ግምገማ ላይ የተመሠረተ ነው፤ የምጠቅሰው ሁሉ ከዚያው ነው፤ ብዙ ቪድዮዎችን ለማየት ሞክሬ አፈናው ከባድ ስለሆነ አልቻልሁም፡፡)

አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከሥልጣን ውጭ ያሉ ሰዎችን ሰብስቦ ለማነጋገር የመወሰኑን ሀሳብ መንፈስ ቅዱስ ሹክ ያለው ይመስላል፤ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስና በኃይለ ማርያም ደሳለኝ መሀከል ጣልቃ የገባና መልእክቱን የለወጠው ኃይል አለ፤ ‹‹በብሔራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት — ስለኢትዮጵያ ሕዳሴ›› መነጋገር የሚለው ሀሳብ በመሠረቱ ጠቃሚና ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ፤ ሆኖም ይህ ጉዳይ የሚመለከታቸውና የሚያገባቸው ‹‹ምሁራን›› ብቻ ናቸው የሚል ቅዠት የለኝም፤ በተለይ ምሁራን ማለት ‹‹እኛው … ነን›› እንዳለው ከሆነ!
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር ሁሉ እያለቀሱ የሚኖሩት ምሁራን አይደሉም፤ ችግሩን በትክክል ሳይረዱ ስለመፍትሔ ማሰብ የጉልበተኞች መንገድ መሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን፤ መፍትሔ የሚፈልግ ሰው ሰብስቦ ማነጋገር የሚያስፈልገው ችግሩ በየዕለቱ የሚገርፋቸውን የሚወክሉ ሰዎችን ነው፤ የተወሰኑ ምሁራን ለመፍትሔው ስለሚያስፈልጉ በታዛቢነት ቢኖሩ ጥሩ ነው፤ እንደዚያም ሆኖ ችግሩን የሚናገሩ ሰዎች ከፍርሃት ነጻ የሚሆኑበት መድረክ መኖሩን ማረጋገጥ ያሻል፡፡
አሁን አቶ ኃይለ ማርያም ያደረገው ስብሰባ ከጥቂት ዓመታት በፊት መለስ ዜናዊ ካደረገው እምብዛም የተለየ አይደለም፤ የመለስም ሆነ የኃይለ ማርያም ዓላማ ከሥልጣን ውጭ ከሆኑ ዜጎች ጋር በአገር ጉዳይ ላይ ለመመካከር፣ ለመከራከር፣ ለመወያየትና ወደስምምነት ላይ ለመድረስ አይደለም፤ በእንደዚህ ዓይነቱ ሥርዓት ውስጥ ይህ ሊሆን አይችልም፤ ጉልበተኞቹ እንደተለመደው የሚፈልጉት ሀሳባቸውን በጉልበት ለማጽደቅ ነው፤ ከተጋበዙት መሀከል አንድ ሰው ተነሥቶ ጋዜጠኞችን ሁሉ አስራችሁ፣ ጋዜጦቹን ሁሉ አግዳችሁ፣ የተለያዩ ድርጅቶች ሕዝቡን እየሰበሰቡ እንዳያወያዩ እየከለከላችሁ፣ የሃይማኖት መሪዎች እንኳን በነጻነት እንዳይሠሩ እያደረጋችሁ እኛን የመረጣችሁን እንድትነግሩን ነው? ወይስ እንድንነግራችሁና ነገ ቃሊቲ እንድንገባ ነው? ብሎ ቢጠይቅ መጋረጃው ይቀደድ ነበር፤ ይህ ጥያቄ ወይም አስተያየት ከተሰብሳቢው ቢሰነዘር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ‹‹ፖሊቲከኛው ጥግ ጥጉን ይዞ ከመታኮስ ባለፈ … ዴሞክራሲያዊ ባህል ማዳበር እንዳቃተው …›› ብሎ መናገር አይደፍርም ነበር፤ ‹‹ፖሊቲከኛ›› የተባለውን መተኮስ ያስተማረው ማነው? ተብሎ ቢጠየቅ ምን ይመልሳል፤ መለስ ዜናዊን ጠይቄው ነበር፤ ‹‹መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸው›› ነው ያለው!
እዚያ ለተሰበሰቡት ‹‹ምሁራን›› ፖሊቲከኛው ‹ዴሞክራሲያዊ ባህልን ማዳበር› አቅቶታል ሲል መልስ ተሰጥቶት እንደሆነ አላውቅም፤ ካልተሰጠው ግን የያዘው ሰይፍ ግለቱ ‹ምሁራኑን› እንዳቀለጣቸው ሌላ ማስረጃ አያስፈልግም፤ ሀሳብን የመግለጽን ነጻነት፣ የመደራጀትን፣ የመሰብሰብን፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን በማይቻልበት፣ በፖሊቲካው ቀርቶ በሃይማኖትም በኩል ሰዎች በነጻነት መወያየትና መሪዎቻቸውን የመምረጥ መብት ተነጥቀው ባለበት አገር ጩኸቴን ቀሙኝ እንደሚባለው ምንም ሥልጣን የሌላቸውን የተቀናቃኝ ክፍል ፖሊቲከኞች የዴሞክራሲ ባህል አላዳበሩም ብሎ ለመውቀስ የሚችልበት መድረክ በእርግጥ ‹የምሁራን› ሊሆን አይችልም፤ አቶ ኃይለ ማርያም የበዳይ ወቃሽ በመሆኑ ላይ ይገፋበታል፤ ‹‹ዓመጽ የማይቀሰቅስ የሀሳብ ብዝኃነት እንዴት ነው እዚህ አገር መፍጠር የሚቻለው?›› ብሎ ይጠይቃል፤ በአዳራሹ ውስጥ የተሰበሰቡት ሁሉ በአንድ ላይ ‹‹በነጻነት!›› ብለው ቢጮሁ ያስተምሩት ነበር፡፡
አቶ ኃይለ ማርያም አያይዞም ‹‹የሀሳብ ልዩነት ብዙ አያስፈራንም፤ የሚገለጹበት መንገድ ነው የሚያስፈራው››፣ ‹‹ከኋላ ጦር አሰልፎ ከፊት በሀሳብ ልፋለም .. የሚለው ነው ያስቸገረን፤›› ተቀናቃኞቹ ጦር እንዳላቸው አግአዚ ይመስክር!
አቶ ኃይለ ማርያም ‹‹በአንድ ትውልድ የተጣመመ የፖሊቲካ ባህል ተሸክመን ቁርሾን ለዚህ ትውልድ እያስተላለፍን ነው፤›› ያለው እውነት አለበት፤ እሱ በዚያ ‹‹የተጣመመ የፖሊቲካ ባህል›› ባመጣው ትውልድ ውስጥ ነበረ? ነበረም አልነበረም ዛሬ እሱ የሚያገለግለው ያንን ትውልድ እንደሆነ የተገነዘበ አይመስለኝም፡፡
በአቶ ኃይለ ማርያም ንግግር ውስጥ የሚያስገርመውና ግራ የሚያጋባው ጣል አድርጎ ያለፋት አንዲት ዓረፍተ ነገር ነች፡– ‹‹አንድ ትልቅ ነጋዴ የራሱ እስር ቤት አለው ቢባል ታምናላችሁ?›› ማመን የሚያስቸግረኝ አንድ የትልቅ አገር ጠቅላይ ሚኒስትር ይህንን መናገሩ እንጂ በጉልበተኞች አገር አንድ ጉልበተኛ የራሱ እስር ቤት ቢኖረው ምን ያስደንቃል!
የሪፖርተር አንባቢዎች በሰጡት አስተያየት፡—

6 ከመቶ የሚሆኑት ተደስተዋል፤
4 ከመቶ አልተደሰቱም፤
71 ከመቶ የተሻለ የሚፈልግ፤
በሪፖርተር መረጃ መሠረት የአቶ ኃይለ ማርያም ስብሰባ የራሱን ተከታዮች እንኳን በከፊልም ያላስደሰተ ይመስላል፤ ምናልባት የመንፈስ ቅዱስን ሹክታ አክብሮ እንደገና እንዲያስብበት ይርዳው፡፡

The post የአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ስብሰባ | ከፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም appeared first on Zehabesha Amharic.

የተሰደዱና በየእስር ቤቱ የታጎሩትን ጋዜጠኞች እና ጸሃፍትን ብዛት ላሰበ ሰው አማርኛ አሁንም የሚጻፍበት ቋንቋ ሆኖ መዝለቁ እሰየው ነው

$
0
0

amharic

አሊ ጓንጉል

ደርጉ ሲረገምበት ከሚኖርባቸው ሌሎች ብዙ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ፣ በማንኛውም ስነ-ጽሁፍ ላይ ያደርገው የነበረው ”ሳንሱር” እና፣ ሊሾም ሊሸለም ይገባው የነበረውን በዓሉ ግርማን ያህል ታላቅ ደራሲ መግደሉ ነው። ይኼም ሆኖ ግን፣ በደርጉ ጊዜ ይታተሙ በነበሩ መጽሃፎች ዙሪያ በእነ “መጽሃፈ ሲራቅ”፣ “አቸናፊ ዘደቡብ አዲስ አበባ”፣ ጠንክር ዘካዛንችስ፣ “ዳግላስ ጴጥሮስ” … ወዘተ በመሳሰሉት የብዕር ስሞች ይቀርቡ የነበሩት ስነ-ጽሁፋዊ ትችቶች ብስለት እና የስነ-ጽሁፉን እድገት የምታውቀው ያንዱን ትችት አንብበህ እና “ፖ!” ብለህ አድንቀህ ሳታበቃ አንዱ አዲስ አርታዒ የፊተኛውን ተችቶ ስታነብብ፣ ያን “ፖ!” ያስባለህን ጽሁፍ ታወርደዋለህ፣ እንደገና ይኼኛውን ደግሞ ሌላው ጸሃፊ ሲተች ስታነብ፣ የፊተኛው ተቺ ያላያቸውን አዳዲስ ጉዳዩች ሲያነሳልህ ታደንቃለህ። የደርጉ የሳንሱር ማነቆ እንዳለ ሆኖ፣ ይህ የስነ-ጽሁፍ እድገት መገለጫው ነው።

ዛሬ ዛሬ በሩብ ክ/ዘመን ወደ ኋላ ቀረንና፣ አለማዊ በሚሰኘው ጽሁፍ ዙሪያ ሁሉ ባብዛኛው ሲጽፉ የምናየው ዲያቆናት እና ደብተራዎች ብቻ የሆኑ ይመስላል። በቅርቡ በውቀቱ ስዩም በጻፈው “ከአሜን ባሻገር” መጽሃፍ ላይ ከወጡት አንድ አራት ትችቶች ውስጥ፣ ስሙን መጥቀስ ካልፈለገው አንድ በሳል ጸሃፊ እና ከኔው በስተቀር፣ ሁለቱ በጽሁፋቸው እንደምንረዳው እና በማእረጋቸውም ባደባባይ እንደነገሩን ዲያቆን እና የቤተ-ክህነት ሰዎች ናቸው። ዲያቆን እና ደብተራ አለማዊ ጽሁፍን አይተችም አይባልም። መተቸት የማንኛውም ሰው መብት ነው። የአርታኢነት ስነ-ምግባር እንዲኖር ግን ያስፈልጋል፤ ከተራ ስድብ እና ዘለፋ ያለፈ፣ አስተማሪ እና ሚዛናዊ ሊሆን ይገባዋል። ከቤተ-ክህነት ጋር ግንኙነት ካላቸው ታዋቂ ጸሃፊያን አንዱ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ነው። ሰለሱ ታች ላይ እመለስበታለሁ።

ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ “የመቀሌ አማርኛ በአዲስ አበባ” በሚል ርዕስ የወጣውን ጽሁፍ አይቶ ያልገረመው ሰው፤ በተለይም መገናኛ ብዙሃን እና ቋንቋ አካባቢ የሰራ ወይም እየሰራ ያለ ሰው ቢኖር ይገርመኛል። ጽሁፉ የሚያሳየው ነገር ቢኖር፣ ያገሪቱ የትምህርት ስርዐት እየሞተ መሆኑንም ነው። በርካታ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል።

ቃላት ካንዱ ቋንቋ ወደ ሌላው የመዋዋስ እና የማልመድ ነገር አዲስ አይደለም። አማርኛ ሆኖ ለምዶ የቀረ በርካታ እንግሊዝኛ ወይም ፈረንሳይኛ ቃላትን (እንደ “ሸሚዝ” የመሳሰሉ) በምሣሌ መጥቀስ ይቻላል። ስረ-መሰረታቸው አንድ ግዕዝ የሆነው አማርኛ እና ትግርኛም ሲወራረሱ እና አንዱ ከሌላው ጋር የመመሳሰላቸው ጉዳይ አያስገርምም። የየቋንቋዎቹን የሰዋሰው ስርዓት ማዛባት ግን ስህተት ነው። አቅሙ ካለ እንኳንስ የፌደራል የስራ ቋንቋ የሆነው አማርኛ፣ ቋንቋዎች ሁሉ በጥናት እና ክትትል እንዲጎለብቱ ማድረግ ተገቢ ነበር። በ“የመቀሌ አማርኛ በአዲስ አበባ” ላይ በግልጽ እንደተዘረዘሩት አይነት ስህተቶች ደግሞ የቋንቋ/ው እውቀት በሌላቸው ሰዎች የሆነም ይመስለኛል።

ሳይቸግር በአማርኛ ውስጥ የትግርኛ ቃላት መሰንቀርም እየታየ ነው፣ ለዚያውም በቋንቋው ላይ በተከታታይ ጽሁፎችን እያቀረቡ ባሉ ሰዎች። ዳንኤል ክብረት የሚጽፋቸውን ጽሁፎች አነባለሁ (አንዳንዶቹን)። አንዳንድ ጊዜ የሚያነሳቸውን ጉዳዮች ያየባቸውን ማዕዘናት እወድለታለሁ።  ጥቂት ቀደም ብሎ  “አዳቦል” በሚል ርዕስ በለቀቀው ጽሁፍ ውስጥ “መመያየጥ/ምይይጥ” የሚለውን የትግርኛ ቃል በአማርኛ ጽሁፉ ውስጥ ሰንቅሮታል። ይኸው፦

“… ለሰው የሚገባው፣ ግልጽ የሆነና ፍሬ ያለው ነገር ለመና[ገ]ርና ለመጻፍ የቋንቋ ችሎታም ያስፈልጋል። … ሳይሰክን የተቀዳ ቡናና መግለጫ ያጣ ሐሳብ አቅራቢ አንድ ናቸው። …  የቋንቋ ችሎታ ማለት ጉዳዩን እስከ ጥግ ድረስ በመናገሪያው ቋንቋ አልቆ ለመናገር መቻል ነው።… ሐሳቡን በራስህ መንገድ ማቅረብ ስለማትችል በአሰልቺ ቃላት (ጃርገን) ትሞላዋለህ። አዳቦልነት … እየበዛ በሄደ ቁጥር የመልዕክት ልውውጡ የተሰበረ፣ አንጆ አንጆ የሚል፣ ችክታ የበዛበት፤ ተግባቦት የሚያጥረውና ሐሳቡ የነጠፈ ይሆናል። ይኼ ደግሞ የዕውቀት ሽግግርን፣ የሐሳብ ምይይጥን፣ የመልእክት ዝውውርን ይጎዳል…”

“ምይይጥ” ህወሃትን ተከትሎ መሃል አገር የገባ የትግርኛ ቃል ነው–ቃሉ እንደ ትግርኛ ቋንቋ ቃል ወትሮም የነበረ ቢሆንም። እኩያ አማርኛው “ውይይት”፣ እንግሊዝኛው ደግሞ “discussion” ይመስለኛል። ዳንኤል የተጠቀመበት አውድ ይህን የትግርኛ ቃል ለመጠቀም የሚያስችልም የሚያስፈልግም አልነበረም። ዳንኤል ቃሉን የተጠቀመበት፣ የሌሎች ሰዎችን ቋንቋ ለመተቸት በጻፈው ጽሁፍ ውስጥ መሆኑ ደግሞ “ምጸት” ያደርገዋል። በጽሁፉ ወስጥ የተበላሸው አማርኛው ብቻ ሳይሆን ትግርኛውም ነው። የቋንቋው የግስ እርባታ ህግም ነው የተበላሸው።

“… የቋንቋ ችሎታ ማለት ጉዳዩን እስከ ጥግ ድረስ በመናገሪያው ቋንቋ አልቆ ለመናገር መቻል…” እንደሆነ የሚነግረን ዳንኤል ክብረት፣ ቁልጭ ያለውን እና ምንም አይነት ማብራሪያም ሆነ ፍቺ የማያስፈልገውን የአማርኛውን “ውይይት” በትግርኛው “ምይይጥ” ተክቶ መጠቀም እና “አሰልቺ ቃላት” የሚለውን ሃረግ፣ በእንግሊዝኛው (ለዚያውም ጨርሶ በማይመስለው) “ጃርገን” መፍታት/ማብራራቱም ራሱ ስህተት ነው የሚመስለው። ምክንያቱም አንዱ ሌላውን ሊተካ አይችልም።

… ዳንኤል ‹‹የጠቅል አሽከር›› በሚል ርዕስ በለቀቀው በሌላ ጽሁፉም ውስጥ “አነዋወር” የሚለውን ቃል የ“ኑሮ” የግስ እርባታ አንዱ አድርጎ ነው የተጠቀመበት።

“… በርግጥ ያንን ሕዝብ አንድ ሕዝብ የሚያደርጉት የጋራ ባሕል፣ ቋንቋ፣ እምነት፣ የአነዋወር ዘይቤ ይኖረዋል። … በትውልድ የዚያ ማኅበረሰብ አባል ከመሆኑ በቀር በቋንቋ፣ በእምነት፣ በባሕል ወይም በአነዋወር ዘይቤ የማይመሳሰል ሰውም አለ።…”

“አነዋወር” የሚለው ቃል በዚህ ዓ.ነገር አውድ ውስጥ “አኗኗር” ለማለት ካልሆነ ሌላ ምን ለማለት ሊሆን እንደሚችል አይገባኝም።

“አነዋወር” የ“ነውር” እርባታ ይመስለኛል ሊሆን የሚችለው። [ሸፍጥ › ሸፍጠኛ › አሸፋፈጥ]  ሲል እንደሚረባው ሁሉ፤ [ነውር› ነውረኛ› አነዋወር] “ ቢባል ያስኬድ ይመስለኛል። ስለዚህ “አነዋወር” ካለቦታው የገባ ይመስላል–“አነዋወር” በግዕዝ ወይም በመጽሃፍ ቅዱስ ቋንቋ/ፍቺ “አኗኗር” ማለት ነው ካልተባለ በስተቀር። ብቻ… የመጽሃፍ ቅዱስ ስነ-ጽሁፍ እንደ አብዛኛው ያገሬ ሰው ሳይገለጥልኝ እንዳልሞት።

በተረፈ ዳንኤል ክብረት የ“የበጎ ሰው ሽልማት” ድርጅት መስራች መሆኑን በቅርቡ ባንዱ ጽሁፍ ውስጥ ያየሁ ይመስለኛል።  ስለ ራሳችን እርስ በርሳችን ስለ-አለመተማመናችን፣ …ወዘተ በርካታ ጸለምተኛ የሆኑ ነገሮቻችን ብቻ ጎልተው በሚወሩበት እና በሚነገሩበት በዚህ በኛ ማህበረሰብ ውስጥ እንዲህ በጎ ስራ የሰሩ ሰዎችን እየመረጡ ማቅረብ እና መሸለም፣ ተተኪው ትውልድም እንዲማርበት የሚያደርግ ነውና ዳንኤል ክብረትን በመልካም ስራው እጅግ አከብረዋለሁ– አገር እንዲያድግ እና እንዲለማ ምኞት እና ፍላጎት ያለው ሁሉ ይህ የዳንኤል ጅምር እንዲቀጥል የበኩሉን እንዲያደርግ አበረታታለሁ–አንዳንድ “በበጎ ሰውነት” በተመረጡት ሰዎች ላይ ቅሬታ ቢኖረኝም።

በጥቅሉ የቋንቋው እንዲህ እየሞተ መምጣት የትም/ስርዓቱ ሞት መገለጫም ነው። ፍትህ እና ነጻነት በሌለበት ማህበረስብ ውስጥ የትምህርት ስርዓቱ  ሁልጊዜም በነጻ ውድድር  በችሎታቸው እየተራቀቁ እና እየመጠቁ ሊወጡ የሚችሉ ሰዎችን ወደ ኋላ እያስቀረ እና አንገት እያስደፋ፣ አድርባይ እና ለጥቅም ያደሩ ስዎችን እያቀና እና እያግበሰበሰ ይጓዛል።

የአርባ ሁለት የአ.አ.ዩ. ፕሮፌሰሮች ባንድ ጊዜ በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ከስራ መባረር (ምሁራኑ ባሁኑ ጊዜ በየምዕራብ አገሩ ተበትነው፣ በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ውስጥ ከፍተኛ መምህራን ሆነው እየሰሩ ነው) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በቋንቋው ላይ ያሳደረው ጫና ቀላል አይደለም። በነጻነት እና ፍትህ ማጣት አገራቸውን ጥለው የተሰደዱ እና አገር ቤት ውስጥ በየእስር ቤቱ የታጎሩትን ጋዜጠኞች (እስክንድር ነጋ፣ እና ሌሎቹም) እና ጸሃፍትን ብዛት፣ ላሰበ ሰው አማርኛ አሁንም የሚጻፍበት ቋንቋ ሆኖ መዝለቁ እሰየው ነው።

አማርኛ እየወረደበት ያለው መቀመቅ አስፈሪ ነው። አሁን በዚያ የአረቦች አመጽ ሰሞን፣ በጀርመን ድምጽ ሬድዬ “አረብ ስፕሪንግ” የሚለውን እንግሊዝኛ “የአረብ ጸደይ” በሚል ተተርጉሞ ሲነበብ ሰምቻለሁ። በ“Arab spring” ውስጥ ያለው “spring” የሚለው ቃል፣ አመጹ ከቱኒዚያ ተነስቶ እና ባንዴ ተስፈንጥሮ ሌሎቹን የአረብ አገሮች እንዴት እንዳዳረሰ የአመጹን በፍጥነት ወደሌሎቹ አገሮች የ“መስፈንጠሩን” ሂደት የሚገልጽ ነው፤ እንጂ ከወቅት ገላጩ “spring” (ጸደይ) ጋር የሚያመሳስለውም ሆነ የሚያገናኘው ነገር የለም። የአሜሪካ ድምጽም ይኸኑ በቅርቡ ሲደግም ሰምቻለሁ ልበል?

የትርጉም ነገር ከተነሳ አይቀር በ1996 ዓ.ም “ሳባ” በሚል ርዕስ የታተመውን የ“እንግሊዝኛ-ትግርኛ-አማርኛ” መዝገበ ቃላት (ለምሳሌ “abyss”ን “ገደል” ብሎ ተርጉሞታል) ያነበበ ሰው፣ ድሮ ድሮ በ1950ዎቹ የታተመውን “ያለ-አስተማሪ” መዝገበ ቃላት፣ እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት ባንድ እግሩ ቆሞ ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ ያጨበጭብለት ይመስለኛል። በ“አረብ ስፕሪንግ=አረብ ጸደይ” ትርጉም አኳያ ሲታይ ደግሞ ለ“ሳባ” መዝገበ ቃላት ልናጨበጭብ ይገባል።

የጀርመን ድምጽ ሬድዮ፤ አንዳንዴ አማርኛ የሚቸግረው ጣቢያ ነው። እያንዳንዱ ቋንቋ የራሱ የሆነ የአነባበብ ስልት (ለምሳሌ ፍስሠት፣ “ፋታ” [pause?]፣ ድምጸት [tone?] ወዘተ …) አለው። የአንዳንድ ቀኑ አነባበብ የተለመደው የአማርኛ ቋንቋ ድምጸት የለውም። ፋታ በሚያስፈልገው ቦታ ላይ (ለምሳሌ የአንድ ዓ.ነገር ማሰሪያ/ማለቂያ) ላይ ፋታ-ቢስ ሆኖ ወደ ሌላው ዓ. ነገር ፈስሦ ይወርዳል፣ አንዳንዴ ደግሞ ፋታ በማያስፈልገው ቦታ ላይ (ለምሳሌ “አበበ በሶ…..[ረጅም ፋታ ይሆንና] … በላ”) አይነት አነባበብ የተለመደ ነው የሚመስለው። አንባቢው መቸስ ከአገር ከወጣ በጣም ቆይቶ ኖሮ፣ አማርኛ ቸግሮት ነው … አይባል ነገር፣ አማርኛው የጠራ ነው፣ ማለትም “አክሰንት” የለውም። የኖረበት የባህር ማዶ አገር ቋንቋ አነባበብ ተጽእኖ አሳድሮበት ሊሆን ይችል ይሆን? እላለሁ–አንዳንዴ … እንዲያው ሳስበው ግን ራስን ላለመሆን ከራስ ጋር በሚደረግ ግብ ግብ፣ ወይም ሌላውን ለመምሰል፣ የተከሰተ ይመስለኛል። እንዴ..? አንዳንዴ’ኮ ስረ መሰረቱ ያልታወቀ ዜማ የሚያዜም እንጂ ዜና የሚያነብ አይመስልም።

እያንዳንዱ አንባቢ የራሱ የሆነ “ስታይል” (ዘዬ?) ይዞ መውጣት ይችላል፣ የቋንቋውን አነባበብ ህግ እና ደንብ መስዋዕት እስከማድረግ መድረስ ግን የለበትም። ድምጽ ለማሳመር መሟሟት ያለበት ድምጻዊ (አቀንቃኝ/ዘፋኝ)፤ የሚጫወተውን ገፀ-ባህሪ ለመምሰል መሟሟት ያለበት ደግሞ የድምጽ ተራኪ ነው። የድምጽ ጋዜጠኛ እና አንባቢ ደግሞ እንደወረደ የቋንቋውን አነባበብ ህግ እና ደንብ ተከትሎ … በተፈጥሮ ያለን ድምጽ ዝም ብሎ ማፍሰስ ነው። ለምሳሌ በኢሳቱ “ሁሌ አዲስ” ዝግጅቱ መግቢያ ላይ አንባቢው የሚያወጣው ዜማዊ ድምጽ፣ የራሱ እና እንዳለ እየወረደ ያለ ድምጽ አይመስልም። ይህ አንባቢ ራሱ ሳይዘጋጅ “እንደወረደ” እንብቦ ራሱን ቀድቶ ቢያዳምጥ፣ የራሱን ድምጽ እና በኢሳቱ የ‘ሁሌ አዲስ’ ፕሮግራም መግቢያ ላይ የሚያቀርበውን በየተራ ቢያዳምጠው፣ ልዩነቱን ራሱ መታዘብ የሚችል ይመስለኛል።

አላግባብ አንድን ቃል “መጎተት” ለምሳሌ “ዘወትር” የሚለውን ቃል “ዘ—–ወትር” በሚል አነባበብ መጎተት ወይም ከ“ዘ” ፊደል በኋላ አላግባብ ረጅም pause “ፋታ”?) ማስገባት ባላስፈለገም ነበር። በዚህ አጋጣሚ፣ የኢሳቱ ብሩክ ይባስ፣ በድምጹ ጥራት እና በአነባበብ ፍሰት፣ አይኑን ከሚያነበው ወረቀት ላይ አንስቶ ወደ ተመልካቹ ወይም ካሜራው የሚመልስበት ጊዜ መገጥጠም፣ ኢሳት ካሉት በርካታ ግሩም አንባቢዎች ውስጥ አንዱ ነው። ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌናም ሌላው ግሩም አንባቢ እና አቀናባሪ ጋዜጠኛም ነው። የሚያወያያቸው ስዎች ከአጀንዳው ሲወጡ ወደ ጉዳዩ የሚመልስበት የጋዜጠኝነት ጥበቡ ግሩም ነው። ሰሞኑን ማንበብ የጀመረችው የኦሮምኛ ዜና አንባቢ ደግሞ፣ የተፈጥሮ ድምጿ ጥራት ጥሩ እና ዝነኛ አንባቢ እንደሚያደርጋት መገመት ይቻላል።

 

በሚቀጥለው ጽሁፌ፣ ከኢሳት እስከ ኢቲቪ፣ ከአዲስ አድማስ እስከ ሪፖርተር እና ሬዲዬ ፋና … ወዘተ፤ እንደ ተስቦ በሽታ በሚዛመት መልኩ እየተለመደ ያለውን የአማርኛ ሰዋሰው ግድፈት በተመለከተ ሌላ ጽሁፍ ይዤ ለመቅረብ እሞክራለሁ።

ቸር ይግጠመን።

አሊ ጓንጉል

The post የተሰደዱና በየእስር ቤቱ የታጎሩትን ጋዜጠኞች እና ጸሃፍትን ብዛት ላሰበ ሰው አማርኛ አሁንም የሚጻፍበት ቋንቋ ሆኖ መዝለቁ እሰየው ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

እየሰመጠ ካለ መርከብ ራስን የማዳኛ ጊዜ አሁን ነው! (ከአርበኞች ግንቦት 7 ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ)

$
0
0

pg7-logo-1| ዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2008 ዓ.ም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ አድርጎ በምክር ቤቱ የመጀመሪያ ጉባኤ የተላለፉትን ውሳኔዎች አፈፃፀም ገምግሞ፤ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ተግባራዊ ሊደረጉ የሚገባቸው ተግባራት ላይ ተነጋግሮ ውሳኔ አስተላልፏል።

በሥራ አስፈፃሚው ግምገማ መሠረት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የህወሓት አገዛዝ በሚያደርስበት በደል በቃኝ ካለ ቆይቷል፤ በዚህም ምክንያት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በሥርዓቱ ላይ እያመፀ ነው። በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ፣ በአፋር፣ በጠቅላላው በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሕዝባዊ እምቢተኝነት እየተቀጣጠለ ነው። የአዲስ አበባ የታክሲ ሾፌሮችና ባለንብረቶች እንዲሁም የረዥም ርቀት አውቶቡሶች አሽከርካሪዎች ያደረጉት የሥራ ማቆም አድማ ትግሉ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያረጋግጡ ናቸው።

አርበኞች ግንቦት 7፣ የህወሓት አምባገናዊ አገዛዝ በትጥቅ ትግልና በሕዝባዊ እምቢተኝነት መወገድ እና በምትኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ በነፃነት የመረጠው መንግሥት መተካት አለበት ብሎ ያምናል። በዚህም መሠረት በትጥቅ ትግሉ ዘርፍ የሚያደርገው ተጋድሎ ከዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ አደረጃጀት ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤ በየቦታው እየፈነዳዳ ያለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተቀናጅቶ አገራዊ እንቅስቃሴ ሆኖ እንዲወጣ የትግል አቅጣጫ ነድፎ ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በስብሰባዉ መጨረሻ የሚከተሉትን ጥሪዎች አድርጓል።

1. ለአርበኞች ግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች

ወሳኝ በሆነ የትግል ወቅት ላይ እንገኛለን፤ በዚህ ወቅት በትጥቅ ትግሉ በቀጥታ ተሰልፈው ያሉት አባሎቻችን፣ በአገር ውስጥ በሕዝባዊ እምቢተኝነት በመሳተፍ ላይ ያሉ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን እና በውጭ አገራት የሚገኙ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ሁሉ በአንድ ልብና መንፈስ ህወሓትን ከስልጣን የማስወገድ ሥራ ላይ እንዲረባረቡ ሥራ አስፈፃሚው ጥሪ ያደርጋል።

2. ለአገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለፓሊስና የደህንነት አባላት

ነገ ከሚወድቅ ሥርዓት ጎን ቆማችሁ ወገኖቻችሁን ማጥቃት ተው! የመሳሪያዎቻችሁ አፈሙዝ የሁላችንም ጠላት ወደሆነው አገዛዝ ይዙር! ከወያኔ በኋላ በሚመጣው ሥርዓት የመከላከያ ሠራዊትና ፓሊስ መበተን የለባቸውም ብለን እናምናለን፤ ይህ እንዲሆን ግን ዛሬ ከአምባገነን ሥርዓት ጎን ሳይሆን ከሕዝብ ጎን ቁሙ።

3. ለህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴግ እና የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች አባላት
እየሰመጠ ካለ መርከብ ራሳችሁን አውጡ! አባል የሆናችሁባቸው ድርጅቶች ለአገራችን ብቻ ሳይሆን ለእናንተም በግል የሚበጁ አይደሉም። ቢቻል በግልጽ፤ ካልተቻለም በስውር ድርጅቶቻችሁን በማዳከም የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግልን አግዙ።

4. በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲፈጠር ለሚታገሉ የፓለቲካና ሲቪክ ማኅበራት
በጋራ የምንቆምበት ወቅት አሁን ነው። ዛሬ የምናደርጋቸው ትብብሮች የረዥም ጊዜ ውጤት ያላቸው መሆኑን ተገንዝበን ኃይላችንን እንድናስተባብር ጥሪ እናደርጋለን።

5. ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ

ጥያቄዎቻችን አካባቢ ተኮር ሊሆኑ ይችላሉ፤ ግባችን ግን የጋራ ነው። ከህወሓት አምባገነን አገዛዝ ነፃ የወጣች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትኖረን ሁላችንም በአንድነት እንድንቆም የአርበኞች ግንቦት 7 ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጥሪ ያደርጋል።

አንድነት ኃይል ነው!

The post እየሰመጠ ካለ መርከብ ራስን የማዳኛ ጊዜ አሁን ነው! (ከአርበኞች ግንቦት 7 ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ) appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live