Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

“የፈጠራ ዉንጀላ ማካሄድና ሠላማዊ ዜጎችን ማፈንና መግደል ይቁም”–ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ የተሰጠ መግለጫ

0
0

OFC
ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንም ሆነ የኦሮሚያ ከተሞች አዲሱ አወቃቀር በገጠመዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ምክንያት ሳይተገበር እንዲቆይ በኦህዴድ/ኢህአዴግ የተወሰነ ቢሆንም፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተቀጣጠለዉ ሕዝባዊ ንቅናቄ የመጠንና የዓይነት ለዉጥ እያስከተለ ቀጥሏል፡፡ ገዥዉ ፓርቲም የችግሩ መንስኤ የኦሮሚያ ክልል አካሉ ኦህዴድ መሆኑን በሕዝብ ዜና ማሰራጫዎች ቢገልጽም፤ ነገር ግን ለጥፋቱ ይቅርታ እንደመጠየቅ ፋንታ ባለፉት አራት ወራት ዉስጥ ዉስጥ ብቻ ከ270 በላይ የኦሮሞ ዜጎች ተገድለዋል፤ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎችን ጨምሮ ንፁሐን ዜጎች ታስረዋል፤ ከመኖሪያ ቀዬያቸዉ እንዲሰደዱ ተደርገዋል፡፡ ይባስ ብሎም፣ ጅራፍ እራሱ ገርፎ ለራሱ ይጮሃል እንዲሉ መንግስት ሠላማዊ የመብት ጥያቄ በአቀረቡ ዜጎች ላይ ያላንዳች ርህራሄ የጭካኔ እርምጃ መዉሰዱን እንዲያቆም ደጋግመን በመጠየቃችንና የሕዝብን ሠላማዊ የመብት ጥያቄ ደግፈን በመቆማችን የአህአዴግ መንግስት ባለሥልጣናት ድርጅታችንና አባሎቻችንን መክሰስ ገፍተዉበታል፡፡

ኦፌኮ በሠላማዊ አግባብ ታግሎ ዲሞክራሲያዊ የሕዝብ መንግስትን ለመመስረት የሚታገል ፓርቲ እንጂ በሽብር ፈጠራ ሥልጣን ለመያዝ ዓላማና ዕቅድ የለዉም፡፡ ከዚህ መሠረታዊ ዓላማችን የተነሳም በአጠቃላይ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ፣ በተለይ ደግሞ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት በማግኘታችን ሁሉንም ዜጎች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ የመንግስት ሥርአትን ዕዉን ለማድረግ የሄድንበት ርቀት የድሉ ጊዜ ሩቅ እንዳልሆነ አመላካች ነዉ፡፡ ዲሞክራሲያዊ የመንግስት አስተዳደር ዕዉን ከሆነ ደግሞ ሙሰኛነት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ የመልካም አስተዳደር ዕጦት እና ከሕገ መንግስታዊ አግባብ ዉጭ ሥልጣን መያዝ ብቻ ሳይሆን ከሕገ መንግስታዊ አግባብ ዉጭ ሥልጣን ላይ መቆየትም የማይታለም ይሆናል፡፡ በፖለቲካ ልዩነት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን መወንጀልም በበኢህአዴግ አገዛዝ ላይ ያበቃል፡፡

የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብታቸዉን ለማስከበር የሚያደርጉትን መነሳሳት ከሕገ መንግስታዊ አግባብ ዉጭ ሥልጣን የያዙም ሆነ ሥልጣን ላይ የቆዩት ኃይሎች ግን፤ ኦፌኮን የመሳሰሉ ሐቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሕዝብን ዓላማ ደግፈዉ ሲሰለፉ የገዥዉ መንግስት አባላት የአሸባሪነት ታፔላ ይለጥፉባቸዋል፡፡ ከፖለቲካ ጨዋታ ዉጭም ለማድረግ የማይሰጡት መግለጫ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ዉስጥም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚነሳሱ የሕዝብ ጥያቄዎች ሠላማዊ በመሆናቸዉ መንግስት ሕጋዊና ተገቢ መልስ መስጠት ኃላፊነቱና ግዴታዉ እንደሆነ ኦፌኮ ዛሬም ያምናል፡፡ ሠላማዊ ሰልፍ በወጡና የመብት ጥያቄ በሚያቀርቡ ዜጎች ላይ የሚተኩስ መንግስት ለሕዝብ መብት መከበር ደንታ እንደሌለዉ ከዚህ የበለጠ ተጨማሪ ማስረጃ የማያስፈልግና ፓርቲያችንና አባላቱ የሕዝብን ጥያቄ ደግፈዉ የተሰለፉ እንጂ የአሸባሪነት ታፔላ ሊለጠፍባቸዉ እንደማይገባ ሚሊዮኖች የሚመሰክሩት ጉዳይ ነዉ፡፡ የሕዝብን ሠላማዊ ጥያቄ ደግፌንና ዜጎች መገደላቸዉ፣ መታሰራቸዉ፣ መሰደዳቸዉ፣ መቁሰላቸዉ፣ መደፈራቸዉ፣ መንገላታታቸዉ፣ ወዘተ እንደማይገባ መቃወማችን በምንም ዓይነት መስፈርት አሸባሪ የሚያስብል አይደለም፡፡

አሸባሪነት በፓርቲያችንም ላይ ሆነ በአባሎቻችንን ላይ መለጠፍን አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ በሠላማዊ አግባብ ዲሞክራሲያዊ መንግስት እንዲቋቋም የመፈለጋችን ያህል የዜጎች ሕይወት በመንግስት ሠራዊት መቀጠፉን እናወግዛለን፡፡ በተለይ እስካሁን ከሁለት መቶ ሰባ በላይ ለተገደሉ ዜጎች የኢህአዴግ መንግስት ሙሉ ኃላፊነት መዉሰድ አለበት ብለን እናምናለን፡፡

ስለሆነም፤ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ አባላትና ደጋፊዎች ሕዝባዊ ዓላማን አንግቤን የሕዝባችንን ሠላማዊ ጥያቄ እየደገፍን፤ አንደኛ ሠላማዊ የመብት ጥያቄ ባቀረቡ ሕዝቦች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ሕፃናትና አዛዉንቶች ላይ በጦር መሳሪያ የታገዘ እርምጃ መዉሰድን እናወግዛለን፡፡ ሁለተኛ በኢህአዴግ ባለሥልጣናት ክስ ሳንሸማቀቅ ትግላችንን እንደምንቀጥል ቃል እንገባለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለምናራምደዉ የተቀደሰ ዓላማ መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦችና ዓለም አቀፍ ሕብረተሰብ ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
ለኦሮሞ ሕዝብ የመብት ትግል መልሱ የጠመንጃ አፌሙዝ መሆን የለበትም!
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
መጋቢት 2 ቀን 2008
ፊንፊኔ

The post “የፈጠራ ዉንጀላ ማካሄድና ሠላማዊ ዜጎችን ማፈንና መግደል ይቁም” – ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ የተሰጠ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.


አድዋ መታወቂያችን፤ ምኒልክ ታዳጊያችን |የአድዋ ጦርነት በኢትዮጵያውያን እይታ –ከኃይሌ ላሬቦ

0
0

Adwa

በዚህ ወር መግቢያ ላይ ኢትዮጵያዉያን የአድዋን መቶ ኻያኛውን ያመት በዓል በያሉበት በአድናቆት አክብረውታል። በየሬድዮ ጣቢያዎቹ፣ በየፓልቶኮቹ፣ በየማኅበራዊ ድርጅቶችና ኢትዮጵያውያን በየተሰበሰቡበት ሁሉ ስለአድዋ ያልተናገረ፣ ያላሰበ፣ ወኔው ያልተቀሰቀሰ የለም ማለት ይቻላል።

እንደታላቅነቱና ታሪክነቱ ከሆነ፣ የአድዋ ድል ያንድ ቀን ብቻ በዓል መሆን የለበትም። የትም አገር ሂደን ታሪክ ብንመረምር፣ መዛግብታቸውን ብንገለባብጥ፣ የአድዋን ዐይነት ታሪክ የሠራ ሕዝብም አገርም የለምና። የአድዋ ድል አሜሪቃ ነፃነቷን ካገኘችበት ድል፣ ከፈረንሳይና ከሩሲያ አብዮት፣ የደቡብ አፍሪቃ ጥቊሮች በጨቋኞቻቸው ነጮች ላይ ካገኙት የእሪና ድል እጅግ ይበልጣል። ጦርነቱ ከውጩ ሲታይ በሁለት ራሳቸውን በቻሉ ነፃና ልዑላን በሆኑ አገሮች መካክል ቢሆንም፣ ጥያቄው ቀጥለን እንደምናየው ስለሰው ዘር መብትና እኩልነት ነው።

ሙሉውን በወርድ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

The post አድዋ መታወቂያችን፤ ምኒልክ ታዳጊያችን | የአድዋ ጦርነት በኢትዮጵያውያን እይታ – ከኃይሌ ላሬቦ appeared first on Zehabesha Amharic.

የጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ሪፖርት መድረሻው |“የመልካም አስተዳደር ችግር እንፈታለን፤ ሰልጣን ግን አንለቅም” መሆኑ ነው?

0
0

ከግርማ ሰይፉ ማሩ

 

የጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ሪፖርትን በወፍ በረር ስንቃኛው የሚከተለው ይዘት እንዳለው መረዳት እንችላለን፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓመቱ ከመጠናቀቁ ቀደም ብለው የዕድገት ቅናሽ እንደሚኖር በሰበብ ደግፈው አምነዋል፡፡ ይህም ደግሞ ገዢው ፓርቲ ከአስራ አንድ በመቶ የእድገት ልክፍት በግድም ቢሆን መላቀቁን የሚያሳይ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የፈለገውን ያህል ተግዳሮት ቢፈጠር ያልተተገበሩ ግዙፍ ዕቅዶች ዝርዝር ቢቀርብም “ቢሆንም 11 ከመቶ አድገናል” እንደ ነበር አንዘነጋውም፡፡ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ የእድገት ቅናሽ መኖሩን  ቢያምኑም “ትንሽ ቅናሽ ያሳያል” በሚል ማለፋቸው ዝናብ ከዘነበ መልሶ ለማቅራራት ዝግጅት እንዳለ አመላካች ነው፡፡

Girma seifu

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት ማጠቃለያ ሪፖርት ሲያቀርቡ የሰበታ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ጥቅምት/2008 ላይ እንደሚጠናቀቅ ተናግረው የነበረ መሆኑን ሳንዘነጋ ዛሬም 97 ከመቶ ተጠናቆዋል ብለውናል፤ ይህ አፈፃፀም ስራ ለመጀመር የሚያስችል እንደሚሆን ቢታመንም ባቡሩ አሁንም ስራ አልጀመረም፡፡ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በኤሌትሪክ ችግር ፈተና እየገጠመው ጄኔሬተር ሊገዛ ነው እየተባለ ባለበት ሁኔታ አሁን ባለው የኤሌትሪክ አቅርቦት ችግር ከ700 ኪሜ በላይ መስመር እንዴት ሊያደርጉት እንደሆነ የጠየቃቸውም የለ፤ ጠቅላይ ሚኒሰትሩም መረጃ ሊሰጡን አልቻሉም፡፡ ከባቡር መሰረተ ልማት ጋር ተያይዞ የቀረበው አስቂኝ ነገር “በዓለም ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ” በሚል ሰበብ ሌሎች በዕቅድ የተያዙ መስመሮች ስራ ሊጀመር እንደማይችል ፍንጭ ስጥተውናል፡፡

በተመሳሳይ የስኳር ነገር ለኢህአዴጎች ገዳቸው አይደለም፡፡ ከታቀደው ተቀንሶ በተወሰኑት ትኩረት ይሰጥ የሚል ሃሳብ መያዙን ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ይፋ አድርገዋል፡፡ ደስ የሚለው የጠቅላይ ሚኒሰትሩ አባባል ደግሞ “ጓጉተን የምናወጣው ዕቅድ የማሰፈጸም አቅማችንን ጋር አልተመጣጠነም” የሚለው ነው፡፡ እኛም እያልን የነበረው አሁንም የምንለው አቅም የላችሁም ነው፡፡ የገንዘብ ብቻ አይደለም – ገንዘብ የማሰባሰብ አቅም ማለት ነው፡፡ የዕውቀት ብቻ አይደለም – እውቀት የማሰተባበር አቅም ነው፡፡ ተገባብቶ አሰተባብሮ የመስራት አቅም የላችሁም ነው ያለነው፡፡ ጉጉት ብቻ ናቸሁ!!!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ውስጥ ቁጠባን ከማሳደግ አንፃር ዋነኛ ያልዋቸውን የመኖሪያ ቤት እና የጡረታ መዋጮ በሪፖርታቸው ውስጥ አንስተዋል፡፡ በእርግጥም ቆጥቦ ህዝቡ የሚጠቀምባቸው ሳይሆን መንግሰት ከአቅሙ በላይ እየለጠጠ ለሚይዛቸው ፕሮጀክቶች ፋይናንስ ማድረጊያ እንደሆኑ ከጅምሩም ግልፅ ነበር፡፡ ለምሳሌ 40/60 በሚል ቆጥቡ ቤት ታገኛላችሁ ተበሎ በጉጉት የቆጠቡ ሰዎች ፕሮግራሙን 100/0 በማድረግ የዜጎችን ሀበት ይዞ በኋላ ብር አትሞ ለመመለስ የተዘጋጀ ይመስላል፡፡ ሌላው ጡረታን በሚመለከት አብዛኛው በአነሰተኛ ስራ ላይ የተሰማራ ዜጋ ትክክለኛ የግብረ ከፋይ መለያ በሌለበት ሁኔታ ከድሆች ላይ በጡረታ ስም ገንዘብ መንግሰት እየዘረፈ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ አንድ በሰተናጋጅነት የሚሰራ ሰራተና ሰድሰት ወር ጡረታ ከፍሎ የሚሰራበትን ድርጅት ቢለቅ ጡረታ ስለመክፈሉ የሚሰጠው ምንም መረጃ የለም፡፡ ቀጣይ የሚገባበት ድርጅት እንደ አዲስ ጡረታ እየቆረጠ ለመንግሰት ገቢ ያደረግል፡፡ ይህ ዜጋ በምንም ሁኔታ የዚህ የጡረታ መርሃ ግብር ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ ደግሞ አሁን በግልፅ የሚታይ ዘረፋ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ዜጎች በግል ዘርፍ ውስጥ በጡረታ መዋጮ ስም እየተዘረፉ መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው በቅጡ መረጃ ሳይስጡ ያለፉት የውጭ ኢንቨስትመንት የሚመለከተውን ክፍል ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ አካባቢ የተነሳውን ንቅናቄ አሰመልክት በኢንቨስትመንት ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ተፅዕኖ ያብራራው ስለሆነ እዚህ መድገሙ አስፈላጊ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡ ለማነኛውም አሁንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ኢንቨሰትመንት የተሻለ ነው በሚል አልፈውታል፡፡ በምንም መለኪያ ግን አሁን የተፈጠረው ሁኔታ የውጭ ኢንቨስትመንት ሊስብ አይችልም፡፡ በተለይ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ እንዳመኑት “ይህ ችግር ከትግራይ እስከ ደቡብ ጫፍ” መሆኑን በኦሮሚያ ቀድሞ መታየቱ ሌሎቹ ችግር የለባቸው ማለት እንዳልሆነ ማረጋገጣቸው በኢንቨስትመንት ላይ ጉልዕ ጫና አለው፡፡ ኢንቨሰተሮች ደግሞ ይህን ለማወቅ አይቸገሩም፡፡ ይህ ደግሞ የሚታየው በቀጣይ ዓመታት ሲሆን እስከ አሁን ድረስም በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ የጀመሩትም በሆን ቢያንስ ረዘም ያለ የዝግጅት ጊዜ መውሰዳቸው የግድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በተለያየ መልኩ በተግባራ ተመልክተነውል፡፡ ሰለዚህ የውጭ ኢንቨስትመንት በቅርቡ ያድጋል ብሎ መገመት አይቻለም፡፡ ሰለዚህ በሪፖርቱ በደፈናው የውጭ ኢንቨስትመንት ካለፈው የተሻለ በሚል የቀረበው ተዓማኒነት የለውም፡፡

በሀገራችን ዙራ መለስ የሚታየው ያለመረጋጋት በኢንቨስትመንት ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር መቀጠላችንን ስጋት ላይ ሊጥል ይችላል የሚል ግምት ያላቸው ሰዎች ቀላል አይደሉም፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን ገዢው ፓርቲ ነገሩን ከስሩ አጥንቶ ሁሉንም ያገባኛል ባይ የሚያሳትፍ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ አሁን በተለመደ አሮጌ መንገድ መሄድ የመረጠ ይመስላል፡፡ ከወትሮ በተለይ “በሌላው አካል ላይ ጣት መቀስር ይቁም” የሚል ሃሳብ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ያነሱ ቢሆንም አሁንም ቢሆን ግን ለመፍትሔው እሩቅ እንደሆኑ የሚያሳያው “በተሃድሶ” ጊዜ ችግር የፈቱበትን መንገድ አሁንም ሊደግሙት ያሰቡ ይመስላል፡፡ ኢህአዴግ የዚህችን ሀገር ለመፍታት ከእኔ ሌላ ማንም የለም የሚል ይመስላል፡፡ አሁን ያለውን በመልካም አስተዳደር ተሸፍኖ የሚቀርብልንን መንግሰታዊ ሌብነት እና ውስልትና በቸልታ እንድናልፈው የሚጠይቁን በሚመስል ሁኔታ መቶ በመቶ ተመርጠናል ባሉበት ዓመት መቶ በመቶ ሲከሸፉ ሌላ አማራጭ ማሰብ አልተቻላቸውም፡፡ መልዕክቱ ግልፅ ነው፡፡ “የመልካም አስተዳደር ችግር እንፈታለን፣ ስልጣን መልቀቅ ግን አይታሰብም” የሚል ነው፡፡

የመልካም አስተዳደር ችግሩን ደግሞ የሚፈቱት ለወጣቱ የስራ እድል የሚፈጥሩ ከዚህ ቀደም ሲዘረዝሩልን የነበሩትን “በጉጉት” ላይ የተመሰረቱ ዕቅዶችን በማቅረብ ነው፡፡ ወጣቱ ስራ ካገኘ ሌላ ጥያቄ ያለው አልመስላቸውም፡፡ የወጣቱ ጥያቄ የስራ መፍታት ብቻ አይመስለኝም፡፡ በሀገሩ እኩል እንደ ዜጋ መቆጠር እና በነፃነት የመኖር ጭምር ነው፡፡ በስራ ፈጠራ ቢሆን አሁን የሚታየውን ስራ አጥነት እንፈታለን እየተባለ በጎን ደግሞ በስራ ላይ ያሉትን የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን በመንግሰት ጣልቃ ገብነት ከስራ ለማስወጣት እቅድ እንዳለም ከሪፖርቱ ለመረዳት ከባድ አይደለም፡፡ በቅርቡ ወደ ስራ እንዲገቡ የሚታሰቡት “የቢሾፍቱ” አውቶብሶች ዋና ዓላማቸው ባለፈው የስራ ማቆም አድማ በማድረግ አንገታቸውን ቀና ያደረጉትን ዜጎች አንገት ለማስደፋት ነው፡፡ ለማነኛውም ቀኑ ደርሱ ውጤቱን አብረን የምናየው ይሆናል፡፡ ይህ አካሄድ የቁርጡ ቀን መቃረቡን የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትራችን በሰጡት ማብራሪያ አንድ አዲስ ነገርም አስረግጠው ነግረውናል፡፡ በሀገራችን “የማንነት ጥያቄ የተመለሰ ጉዳይ ነው” ብለውናል፡፡ ማንነት “ኢቮልቭ” የሚያደርግ የሚፈጠርና የሚጠፋ መሆኑ አብቅቶለታል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአሁን በኋላ አዲስ ማንነት አይፈጠርም፡፡ ይህን ደግሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና ክልሎች ተነጋግረው ቋጠሮ ማበጀት አለባቸው የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ይህን ንግግር የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገውት ቢሆን እንደ ህግ ልንወስደው እንችል ነበር፡፡ አሁን ግን እንደ የግል አስተያየት አድርገን ከመውሰድ ውጭ ህግ ነው ለማለት ውጤቱን መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ እነ ዳንኤል ሺበሽ “ቁጫ ቁጫ ነው ጋሞ አይደለም” በሚል በኢህአዴግ መስመር ጥያቄ በማቅረባቸው ዛሬ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢህአዴግ የማንነት ድንበር ምን ጋ ሲደርስ እንደሚቆም ዝርዝር መመሪያ ሊሰጥ ይገባል፡፡ በእግረ መንገድ የጉራጌ ብሔር/ብሔረሰብ የባህል ልብስ ደንብ ወጣ ሲባል ሰምቻለሁ …. አውነት ይሆን?

ባጠቃላይ የጠቅላይ ሚኒትሩ ሪፖርት በእኔ ግምት ሪፖርት ሳይሆን አሁንም ሌላ እቅድ ነው አበክረን፣ጠንክረነት እንሰራለን የሚል፡፡አሁንም ልምድ የሚቀመርበት … የሚማሩበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ዋነኛው ችግር ደግሞ ሰማርት ስልክ መሆኑ ተደርሶበት ሰማርት ስልክ በተመጣጣኝ ዋጋ እንድናገኝ ጥረት ይደረጋል የሚል እቅድ ቀርቦልናል፡፡ በስብሰባው ላይ ህውሃት ከሞላ ጎደል የተሟላ ሲሆን የሌሎች ድርጅት ከፍተኛ ሃላፊዎች ያለመገኘት ምን ማለት ይሆን?

ቸር ይግጠመን

ግርማ ሠይፉ ማሩ

The post የጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ሪፖርት መድረሻው | “የመልካም አስተዳደር ችግር እንፈታለን፤ ሰልጣን ግን አንለቅም” መሆኑ ነው? appeared first on Zehabesha Amharic.

ሕወሓት አሉኝ የሚላቸዉ ጄኔራሎቹን አጣጣለ |“አሁን ባሉን ጀነራሎች መዋጋት አንችልም”

0
0

militeryከልዑል ዓለሜ
በ 03/11/2016 በመከላከያ ሚኒስቴር ቅጥር ዉስጥ በተደረገ ድንገተኛ ስብሰባ ላይ የተገኙ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጄኔራሎች እራሳቸዉን ከኤርትራ ጄኔራሎች ብቃት ጋር በማወዳደር መናቆራቸዉን ምንጮች እየገለጹ ይገኛሉ።
በሚኒስቴር ጀኔራል ሲራጅ ፈጀታ የዉስጥ ደንብና ምክክር የተጠራዉ ይህ ድንገተኛ ስብሰባ አሉ የሚባሉ የወያኔ ጄኔራሎችን ያካተተ ሲሆን የምክክር መድረኩ ባስገራሚ መልኩ ይዘቱን ቀይሯል። ይህዉም የኤርትራ ጄኔራሎችን ብቃት በተመለከተ ጠቅለል ያለ መረጃ ያቀረቡት ጠ/ሚኒስቴር ጄኔራል ሲራጅ ፈጀታ ለሻቢያ ስራዊት የመጀመሪያዉን ጥይት ከተኮሱ ከነ ሃሚድ ኢድሪስ አዉት ጀምሮ እስከ አሁኑ የጸጥታ ሐላፊ የበላይ ጠባቂ ከሜጄር ጄኔራል ፊሊፖስ ወልደዮሓንስ እንዲሁም እስከ እታች ለመዉረድ የሞከረ ሲሆን በንግግሩ መደምደሚያ ላይ ኤርትራን ለመዉጋት ብንነሳ እነዚህ የሻቢያ መኮንኖች ምን ያህል ይከላከላሉ የሚል እሳቤ ነበርዉ።
ከዚህ ወዲህ የቀረቡት አስተያየቶች እጅግ አስደንጋጭ የንበሩ ሲሆን… በሰሜኑ እዝ የጠ/ላይ መምሪያ አዛዥ እንዳስቀመጡት

” እስካሁን የተጠቀሱት የሻቢያ ጄኔራሎች በዉጊያዉ ላይ ጉልህ አስተዋጾ አያደርጉም ባይባልም ጠላት ግን አይናቅም ! ! በመሆኑም ዋነኞቹ እና ቀንደኞቹ ግን አልተጠቀሱም ለምሳሌ በባድሜ ጦርነት ወቅት የአሰብን እራስ ገዝ ሲጠብቅና ሲያጠቃ የነበረዉ በቡሬ ግንባር መሬት ወርዶ ሲያርመሰምሰን የኖረዉ ግንባር 71 የሚባለዉን የኢትዮ ኤርትራን ድንበር ቆርሶ አስገራሚዉን ምሽግ የገነባዉ በ70ዎቹ የእድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኘዉ ሜጀር ጄኔራል ዳንኤል አብረሃ በምን መልኩ ነዉ የታየዉ!!! የኛ ጄኔራሎች በተንጣለለ መኖሪያ ቤት ዉስጥ በከተማ ይኖራሉ የኤርትራ ሰራዊት ጄነራሎች አስቸጋሪዉን የሬንጀር ኮርስ የበረሃ ጉዞ 50 ኪ/ሜ ከወታደሮቻቸዉ ጋር ያሳልፋሉ መመሪያ ይሰጣሉ በኮምፒተር ከመታገዝ አልፈዉ መሬት እየሰነጠቁ የጦር ምህንድስናዉን ይጠልፋሉ! የትኛዉ የኛ ሰራዊት አዛዥ ነዉ ኤርትራን ለመዉጋት የሚዘልቀዉን ጦራችንን ከጎኑ ሆኖ አይዞህ የሚለዉ ሳሞራ የኑስ ነዉ! ወይስ እርሶ ክቡር ሚኒስቴር አቶ ሲራጅ ! ” በማለት ያንጓጠጠ ሲሆን ከእርሱ በመቀጠል ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ ቤተ መንግስት የሆነ የቤተ መንግስቱ የክፍለ ጦር መምሪያና የብርጌድ ሃላፊ በበኩሉ

 

” እኔም በዚህ ሐሳብ እስማማለዉ በተለይም ወታደራዊ ፖለቲካ ሳይንስ አወራረዳችን ዜሮ በመቶ ነዉ ቢባል አያሳፍርም ለምሳሌ የኤርትራዉን ወታደራዊ ፖለቲካ ብንመለከት ጄኔራል ስብሓት ኤፍሬምን መዉሰድ በቂ ነዉ እርሱ የረገጠበት ቦታ ላይ እኛ ምን ያህል ዘልቀን ገብተናል በእርሱ አንጻር የሚገኙ የእኛ ጀኔራል የፖለቲካዉ አመራሮች እነማን ናቸዉ ! ዉጊያ እንጀመር ይባል ከጀመርን ደግሞ እንድንገባ የተነደፈዉ በአሰብ በኩል ያለዉ አንዱ መንገድ ነዉ!! ከዚያ ዉጪ በአማሐጅር ጀርባ አድርገን በባረንቱ ቆርጠን እስከ ተሰኔ ሊሆን ይችላል ነዉ የሚባለዉ!! ሁለቱም መንገድ ያዋጣናል የሚል እምነት የለኝም ” በማለት አስተያየታቸዉን ከሰጡ ወዲህ ሌላኛዉ ተናጋሪ በተመሳሳይ መልኩ

” በአሰብ በኩል ሻቢያን ለመዉጋት የታሰበዉ እቅድ ዋና ፍሬ ነገሩ ተቃዋሚዎቻችን ናቸዉ ዛሬ እነርሱ እኛ ከመጣንበት አይነት ስፍራ በረሃዉን ተሸክመዉ ይገኛሉ ከዚህ ቀደም ባደረግነዉ ዉጊያ በአሰብ በኩል ግንባር 71 ላይ የሰፈርዉን የሻቢያ ሰራዊት ምሽግ ለመታት የአየር ሐይላችን ሙከራ ትዝብት ዉስጥ ጥሎናል እንኳን ያንን ምሽግ መምታቱ ይቅርና ሶጃ የተባለ የመንገድ ስራ ድርጅት የሰራዉን በኢትዮ ኤርትራ መንገድ ላይ የተገነቡ ድልድዮችን ማፍረስ እንክዋን ተስኖን ነበር:: ዛሬ አሰብ በነ ሳኡዲ አረቢያ መዳፍ ዉስጥ ነች ወደ አሰብ የምናደርገዉ ግስጋሴ ከጅምሩ አደጋ ይገጥመዋል ከሳዉዲ አሰብ የሚወረወሩት አሜሪካን ሰራሽ የጦር መርከቦች ከበዛ 60 ደቂቃ ካነሰ 42 ደቂቃ ዉስጥ አሰብ ይደርሳሉ የጦር ጀቶቹ ከ15_20 ደቂቃ አሰብን ይጎበኛሉ ወደድንም ጠላንም በአሰብ በኩል ያሉትን እነ አርበኖች ግንቦት 7ን ለማጥቃት ስንነሳ በአሰብ ወደብ ላይ የሚገኙት ጸረ ሽብር ጥምር ሐይሎች ከሸባሪዎቹ እንደ አንዱ ነዉ የሚቆጥሩን!!! በተለይም አሁን ባሉን ጄነራሎችም የመዋጋት ብቃት የለንም ! ! ‘ በማለት እጅግ አንገት የሚያስደፋ ትችቶችን በማቅረግ ስብሰባዉ በከንቱ በኤርትራ ጄኔራሎች ብቃት የበላይነት የተከካሄደ እና ለ3 ሰአታት የዘለቀ ሲሆን በመጨረሻም ዉጊያዉ የማይቀር ነገር ግን አለም አቀፍ ትኩረትን ወደኛ እንዲያዘነብል በማድረግ በኩል ስራ እንዲሰራ ተወስኖ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ተወስኗል::

The post ሕወሓት አሉኝ የሚላቸዉ ጄኔራሎቹን አጣጣለ | “አሁን ባሉን ጀነራሎች መዋጋት አንችልም” appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: ኢትዮጵያ የአሰብ እና የምጽዋ ወደብን ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ማጓጓዣ እንድትጠቀም ጥሪ ቀረበላት፣ በኦጋዴን ውስጥ በኢሕአዲግ፣ በቻይና እና በጅቡቲ መካከል የተፈረመው ግዙፍ የነዳጅ ፕሮጀክት ከአካባቢው ተቆርቋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመውና ሌሎችም

0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ መጋቢት 4 ቀን 2008 ፕሮግራም

ዶ/ር መረራ ጉዲና የኦፌኮ ሊቀመንበር በአቶ ሀይለማሪያም በኦሮሚያ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ለፓርላማ ላቀረቡት አስተያየት ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

>

አክቲቪስትና የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል ሙሉነህ ዮሐንስ በሲያትል ባለፈው አርብ በአገር ቤት በኦሮሞ ወገኖቻችን እና በሌሎቹም ላይ የሚደረገውን ግድያ በመቃወም የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ያደረገውን ንግግር መሰረት አድርገን ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

አቶኦባንግ ሜቶ የትብብር ለአዲሲቱ ኢትዮጵአ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ከአሜሪካ የህወሃት ኤምባሲ ጽፎ ወደ አገር ቤት ስለወሰዳቸው ስደተኞችና በሙርሲዎች ላይ የስኳር ልማት በሚል ስለሚደርሰው የሰብኣዊ መብት ጥሰት ተጠይቆ ከሰተው ምላሽ(ሙሉውን ያድምጡ)

ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስትን በአለማ ቀፍ የፍትህ አደባባይ የረታቸው እና ትምህርት የሰጠችው የወሲብ ተጠቂዋ ወይንሸት ዘበነ ሰሞነኛ ውሎ ሲዳሰስ ( ልዩ ጥንቅር) ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ኢትዮጵያ የአሰብ እና የ ምጽዋ ወደብን ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ማጓጓዣ እንድትጠቀም ጥሪ ቀረበላት

ዶ/ር መረራ ጉዲና ኢህአዴግ የቃላት ጨዋታውን ትቶ በኦሮሚያ የሕዝቡን ሰላማዊ ጥያቄ ተከትሎ የገደሉትን ለፍርድ እንዲያቀርብ የታሰሩትን እንዲፈታጠየቁ

ተቃዋሚዎች ተባብረው መቆም አለባቸው ወሳኝ ወቅት መሆኑን ገለጹ

በኦሮሚያ ተቃውሞው ቀጥሏል በመላው ኣለም በሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች የአገዛዙ አፈና ላይ ጠንካራ ተቃውሞ ቀረበ

በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ የሚማቅቀው “የሙስሊሞች ጉዳይ” መጽሄት አዘጋጅ የእስራት ቅጣት ተበየነበት

በመርካቶ በርካታ ሱቆች ሕገ ወጥ ሞባይልና ዕቃ አስገብታችሁዋል በሚል በዘመቻ ታሸጉ

ሶማሊያ ውስጥ ስልጠና ወስደዋል የተባሉ በርካታ ሰዎች ሰሞኑን በጸረ-ሽብሩ ህግ ሽፋን አ/አ ውስጥ የከባድ ቅጣት ሰለባዎች ሆኑ

በኦጋዴን ውስጥ በኢሕአዲግ፣ በቻይና እና በጅቡቲ መካከል የተፈረመው ግዙፍ የነዳጅ ፕሮጀክት ከአካባቢው ተቆርቋሪዎች ዘንድ ከፈተኛ ተቃውሞ ገጠመው

“የቻይና እና ጅቡቲ መንግስታት እጆቻቸውን ከኦጋዴን ሕዝብ ሃብት ላይ ባሰቸኳይ ያንሱ”ተቆርቋሪ ድርጅቶች

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: ኢትዮጵያ የአሰብ እና የምጽዋ ወደብን ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ማጓጓዣ እንድትጠቀም ጥሪ ቀረበላት፣ በኦጋዴን ውስጥ በኢሕአዲግ፣ በቻይና እና በጅቡቲ መካከል የተፈረመው ግዙፍ የነዳጅ ፕሮጀክት ከአካባቢው ተቆርቋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመውና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

“አሁን የተነሳው የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ በመንግሥት ውስጥ ባሉ የኦሕዴድ አባላት መቶ በመቶ ልል በምችልበት መልኩ ድጋፍ ያለው ነው።” –ጃዋር መሐመድ

0
0

Interview with Dr Tsegaye Ararsa and Jawar Mohamed – Pt 2 | SBS Amharic Radio

ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳና አቶ ጃዋር መሐመድ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) 2ኛ ዓመት ክብረ በዓልንና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ተከስቶ ያለውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ይናገራሉ።

“አሁን የተነሳው የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ በመንግሥት ውስጥ ባሉ የኦሕዴድ አባላት መቶ በመቶ ልል በምችልበት መልኩ ድጋፍ ያለው ነው።” – ጃዋር መሐመድ

“በማንኛውም የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የሚደረግ የፖለቲካ ጥያቄ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ ነው ብዬ ነው የማየው።” – ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ

“አሁን የተነሳው የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ በመንግሥት ውስጥ ባሉ የኦሕዴድ አባላት መቶ በመቶ ልል በምችልበት መልኩ ድጋፍ ያለው ነው።” – ጃዋር መሐመድ

The post “አሁን የተነሳው የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ በመንግሥት ውስጥ ባሉ የኦሕዴድ አባላት መቶ በመቶ ልል በምችልበት መልኩ ድጋፍ ያለው ነው።” – ጃዋር መሐመድ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዛሬው ማንነታችን ፥ ሁላችንም ባንድነት የወደቅንበት የጋራ ዋጋችን ነው (ሄኖክ የሺጥላ )

0
0

minilikኣጤ ምኒልክን ሲወቅስ 100 ኣመት የፈጀው ትውልድ ፥ እሱ የኖረበትን መቶ ኣመት ምን ሰራበት ? ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴን ሲተች የኖረው « ያ ትውልድ » ንጉሱ ከወደቁ ወዲያ እሱ የኖረበትን 42 ኣመታት ምን ጠቃሚ ነገር ኣደረገበት ? ደርግን 17 ኣመት በርሃ ሲታገል የኖረው ህውሃት ስልጣን በእጁ ላይ ኣስገብቶ የኖረበትን 25 ኣመታት የእርዳታ ስንዴ ከመለመን ውጪ ፥ የቀደሙ ስርዓቶችን በደልን እየዘከዘከ ፥ ባለፈ ስርኣት በደል ኣይን ንፁህ ነኝ ቢለንም በስራው ስንለካው ፥ ጨካኝ ከሚባለው የደርግ ዘመነ መንግስት የባሰ ጠርናፊ እና ገዳይ መሆኑን ነው ያየነው ።

እኛስ 25 ኣመት በኣንድ ጨቋኝ ስርኣት ክርን ስንደቆስ ፥ እንደ ባቢሎኖች መግባባት ኣቅቶን ከመናከስ ውጪለሃገራችን የሚበጀውን ነገር ለማድረግ ምን ሰራን ? የሃገራችን ቁስል የውሻ ቁስል እንዲሆን ኣንድነትን ከመምረጥ ይልቅ ፥ በክክል በጎጥ በብሄር ተቧድኖነን ፥ በቁስላችን ላይ እንጨት እየሰደድን ፥ ማንነታችንን መርዘኛ የጎሳ ተውሳክ እንደ ማር ኣልሰን ፥ በቀበሌ ልክ ሃገር መስለን መታየት ኣሻን እንጂ ፥ እንደው ምን ሰራን ?

ትናንት ቤተ እምነቱን በመናቅ ፥ የሶሻሊስት እምነት ኣራማጆች የነበሩት ፥ በሃሉን ለማያከብሩለት ህብረተሰብ ስለ ህብረተሰባዊነት እየደሰኮሩ፥ እምነቱን የግሪክ ኣማልክት ዘመነኛ ተረት እንደሆነ በኣደባባይ እያወሩ፥ ስለ ኣንድነት ቢሰብኩም ፥ ስለ ሃገር ፍቅር እጃቸውን « ኢትዮጵያ ወይም ሞት » ብለው ወደ ሰማይ እንደ ሮኬት ቢለቁም ፥ ኢትዮጵያ ሳትሞት እነሱ ግን ካፈሯ ስር ተቀብረዋል ። ዛሬም የለውጥ ፥ የእድገት ፥ የመሻል እና የመሻሻል ማሳያዎቻችን በሰው ላይ ሳይሆን በድርብርብ ብሎኬቶች የተሰሩ ፎቆች ማንነት ላይ የቆሙ በማስመሰል ፥ ህዝቡ እየተራበ « ልማት » ብለው ሲደሰኩሩ ፥ ንፁሃን ዜጎቿን እንደ ከብት በ ቃጫ እያሰሩ የብሄር ብሄሬሰቦች መብት እያሉ በሃገር ዱካ ላይ ሲያሴሩ እያየን ነው ። እጅግ የሚያሳዝነው ደሞ ቢያንስ ሰው መሆናቸውን ኣለማወቃቸው ፥ ደካሞች ፥ ተሰባሪዎች ፥ ሟቾች መሆናቸውን ኣለመገንዘባቸው ።

እኛ ዛሬ ላይ ኣድራጊ ፈጣሪዎቹ ፥ ዛሬ ላይ ባለ ጉልበቶቹ ፥ ዛሬ ላይ ባለ ሰራዊቶቹ ፥ ያለፈውን ስንጠላ ፥ ስናጣጥል እና ስናብጠለጥል እኛ ግን በነበርንበት ዘመናችን ፥ በኖርንበት የጉብዝና ወራታችን ምን ሰራን ? የዛሬው ማንነታችን ፥ ሁላችንም ባንድነት የወደቅንበት የጋራ ዋጋችን ነው።

ለሁሉም ነገሮች መልስ ኣለኝ ለሚል ግን ኣንዱንም መልሶ ለማያውቅ ስርኣት እኛ የምን ኣይነት ቅሌታም መንፈስ ባለቤቶች ብንሆን ነው ይህን ሁሉ ዘመን ድንቁርናውን ተስፋ ኣድርገን የኖርነው ? በየትኛው የጀግንነት ስሌት ነው ሚኒሊክን የሚረግሙ ኣንደበቶች ለወያኔ ተንበርክከው የሚገዙት ? በየትኛው የሰውኛ ሂሳብ ነው መንግስቱ ሃይለማሪያምን ኣሰይጥነው የሚያቀርቡ ሚዲያዎች ስለ መለስ ራዕይ ሊነግሩን የቻሉት ? ምን ያህል ነው የተናቅነው ? ምን ያህልስ ነው ግድ የማይሰጠን ? ኣረ እንደውም « ወያኔ በደለን » ብለን እለት እለት ከምናላዝነው ምን ያህሉ ነው የወያኔ ? በወያኔ መበደልን እንደ « ጎመን በጤና ኑሮ » የምናይ ሰዎች እንደው በምን ኣይነት ግንዛቤ ነው ስለ ሌላ ስርኣት በደል ልናወራ የምንችለው ? ወያኔን ተሸክሞ የኖረ ትከሻ እንዴት ምኒሊክን ለማዋረድ ተውረገረገ ? ወያኔን ኣምልኮ የሚኖር ህዝብ እንዴት የኣሉላ ዘር ነኝ ብሎ ሊፎክር ይችላል ? 10 ሚሊዮን ህዝብ ተርቦ ኣድገናል የሚል መሪ ከመሃከላችን እስኪገኝ የት ነበርን ? ኣክሱም ለወላይታው ምኑ ነው የሚል ባለጌ ባለ ራዕይ ተብሎ ሲሞካሽ ፥ በሃገር ላይ ሬሳ ሲሳለቅ እኛ የት ነበርን ? ኣዎ የዛሬው ማንነታችን ፥ ሁላችንም ባንድነት የወደቅንበት የጋራ ዋጋችን ነው!

 

The post የዛሬው ማንነታችን ፥ ሁላችንም ባንድነት የወደቅንበት የጋራ ዋጋችን ነው (ሄኖክ የሺጥላ ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢሳት የሳምንቱ እንግዳ _ አቶ ሌንጮ ለታ —–(ግዜነው ደም መላሽ)

0
0

wikileaks-on-lencho-leta-top-secret-must-listenወደ ዋናው አርስት ከመግባቴ በፊት ለመንደርደሪያ የሚሆኑ ሁለት ነጥቦችን ላንሳ። በቅርቡ “አቤል ዋበላ” የተባለ ወንድም አራዳ ፍርድ ቤት የጏደኛውን የፍርድ ሂደት ለመከታተል በታደመመበት እርሱ ቃሊቲ በታሰረበት ወቅት  እጁን በካቴና ወደኋላ  አስሮ  ፣ ወለል ላይ እያንከባለለ ጀርባው እስኪቀደድ የገረፈውን  ፣  ሰብአዊ ክብሩን ገፎ   አካላዊና ስነ ልቦናዊ በደል የፈፀመበትን ግለሰብ አይቶት የተፈጠረበትን ስሜት “ገራፊዬን አየኹት” በሚል እርህስ ውብ አድርጎ ከትቦ አስነብቦን ነበር።ስሜቱን ለመረዳት እራስን አቤል ቦታ ላይ ማስቀመጥና ማሰብ ብቻ ነው የሚበቃው።ይህንን መሰል ከባድ ጉዳት ይቅርና በግዜአዊ  ግጭት ሀይለ ቃል የተለዋወጡትን ሰው በአጋጣሚ ፊት ለፊት መገጣጠም ስሜት የሚረብሽ ጉዳይ ነው ። አንድ እዚህ ግባ የማይባል ፍልጥ ደንቆሮ አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚሰማ ፀያፍ ቃላትን በአንተና በዘሮችላ ላይ እያዘነበ የቀጠቀጠህን ግለሰብ በአካል ማየት ይቅርና ስለሱ ሲወራ ብትሰማም ቁስልህ እንደ አዲስ ይጠዘጥዝኸልና ስሜቱን እረዳለሁኝ።

ዛሬ ደግሞ እኔ እንደ ኢትዮጵያዊ ሀገራችንን በቋንቋና በዘር ከፋፍሎ የሚበታትነውን ስርሀት ከዘረጉት ሦስት ቡድኖች የአንዱ መሪና የሀሳቡ ዋና አመንጪ የሆነውን፣ እንደ አማራነቴ ደግሞ አማራ በመሆናቸው እፃናትን፣ ፅንስ በሆዳቻው የያዙ እናቶችን፣ አረጋዊያንን በአጠቃላይ  በርካታ አማራ ወገኖችን  እንዲታረዱ፣ ከነ ሕይወታቸው ወደገደል እንዲወረወሩ ትዛዝ መስጠቱና ማስፈፀሙ  በበርካታ ወገኖች የሚታመነው ሌንጮ ለታን ኢሳት ላይ ዳግም አየሁት።በአረመኔው የኦነግ ቡድን  አረጋዊ አባትና እናታቸውን በግፍ ፣ በጠራራ ፀሀይ የተነጠቁ ልጆች፣ የሚወዷቸው ባሎቻቸው ፊትታቸው በስለት የታረዱባቸው ሚስቶች፣ የአብራክ ክፋይ፣ የአይን ማረፊያ፣ የነገ ተስፋቸውን ልጆቻቸውን እንደ እንስሳ አንገታቸውን ተቆልምመው የታረዱባቸው የአማራ ወላጆች  ይህንን እርኩስ ተግባር ፈፅሟል የተባለውን የኦነግ አበጋዝ ሌንጮ ለታን እንዲያዩና በሀዘን የቋሰለ ልባቸው (ልባችን) ዳግም እንዲመረቅዝ ተደረጎልና ስሜቱን ለሚጋሩ ወገኖች ዳግም መፅናናትና ብርታት እመኛለሁ።

እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ሁሌ የሚረብሹኝን የህሌና ጥያቄዎች ልሰንዝርና ወደተነሳሁበትጉዳይ እመለሳለሁ።ፖለቲካ ነክ ችግሮችን በዲሞክራሲያዊ መንገድ መፍታት እስከሌለ ድረስ ለነፃነት የሚደረግ የትጥቅ ትግል ይኖራል ። ይህንን በመሰለ ትግል ውስጥ ያልታጠቀው ሰላማዊ ዜጋ ላይ የሚፈፀም ወንጀል በመረጃ መደገፍ እስከቻለ ድረስ በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት የሚዳኝና የሚያስቀጣ ጉዳይ ነው። ይህንንም የተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት ተጠቅመውበታል።የኛ የኢትዮጵያዊያን ነገር ግን የተገላቢጦሽ ሆኖ ነው የማየው።አንድ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከባድ ወንጀል ፈፅሞል የሚባል የነፃነት ታጋይ መሪ ፣ ወይ ደግሞ የጨቋኝ ስርሀት አካል የነበረና ስርሀቱ ውስጥ በነበረው ስልጣን ተጠቅሞ ሕዝብ ሲበድልና ሀገር ሲዘርፍ ኖሮ በሆነ አጋጣሚ ስርሀቱን ከድቶ በአንዱ ምራባዊ ሀገር ጥገኝነት ከጠየቀ የሰራው ወንጀል ይደመሰስለትና የጀግና አቀባበል ተደርጎለት እናያለን። በዲያስፖራው ዘንድ በሚደረጉ ስብሰባዎች ፣ ሚዲያዎች ላይ ዋና ተጋባዥ ከመሆን አንስቶ እስከ መሪነት ቦታ ተሰጥቶቸው ታዝበናል። ለምሳሌ በመሰረቷቸውና በመሮቸው ቡድኖች ኢትዮጵያን ጎድተዋል፣ብዙ ኢትዮጵያዊን አስረዋል፣ገርፈዋል፣ገለዋል ዛሬ ላለንበት አጣብቂን ሁናቴ ዳርገውና በማለት ከሚነሱት ግለሰቦች መካካል መለሰ ዜናዊ ፣ ሌንጮ ለታና ኢሳያስ አፈወርቂ ግምባር ቀደሞቹ ይመስሉኛል።ከተወሰኑ ወራቶች በፊት ኢሳያስ አፍቂን የኢትይጵያ የነፃነት ታጋይ እስኪመስለን ድረስ በኢሳት ጋዜጠኞች ሞገስ ተሰጦት እንደነበር እናስታውሳለን። ይችን ሶስት ወር ደግሞ ሌንጮ ለታ ከፍተኛ ሽፋን ተሰጥቶት ነው የሰነበተው። ከዚህ ተነስተን ስንገመም ምናልባት መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድመው ኖሮ የክብር እንግዳ ሆኖ የማናይበት አንዳች ምክንያት አይኖርም ነበር ማለት ይቻላል።ስለዚህ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ወንጀልና ወንጀለኛ ምን ማለት ይሆን? አንድ ሰው ይህንን አይነት ወንጀል ብፈፅም በመላው አለም በሚገኙት ኢትዮጵያዊያን ዘንድ መገለል ይገጥመኛል፣ በግልም ሆን በቡድን ጥቃት ሊያደርሱብኝ ይችላሉ ፣ ተጋግዘውና መረጃ አሰባስበው ፍርድቤት ይገትሩኛል ብሎ ሊያሸማቅቀው የሚችለው እነዚህ አገር ያፈረሱና በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ከተደራደሩት ሰዎች ከፈፀሙብን ወንጀል የተለየ ምን አይነት ወንጀል ቢፈፅምብን ነዉ? ቀላል በማይባል ማሕበረሰብ ዘንድ በዚህ መልኩ የሚታወቁ ሰዎችን በመንከባከብስ ለባለተራ ባለስልጣናት የምናስተላልፈው መልክትስ ምንድን ነው? ይህንን በመሰለ አካሄድስ ወጀልን የሚፀየፍና ወንለኛን የሚዋጋ ትውልድ እንዴት ማፍራት ይቻላል? የሚሉትን መጠይቆች ለኢሳት ሰዎችም ሆና ለአምባቢ የህሌና ፍርድ እንዲሰጡ ጋብዤ ወደ ተነሳሁበት ዋና አጀንዳ እመለሳለሁ።

አቶ ሌንጮ ለታ ሰሞኑን ኢሳት እስቲዲዮ ተጋብዞ ከሲሳይ አጌና ጋር ያደረገው የፊት ለፊት ቆይታ በርካታ ሀሳቦች የተነሱ ቢሆንም እኔ የታዘብኮቸውን አንድ አራት የሚሆኑ ነጥቦች እቃኛለሁ። ትኩርቴን ከሳቡት ሀሳቦች የመጀመሪያው የኦነግን የጫካ ቆይታ አስመልክቶ በተነሳ ጥያቄና በተሰጠው ማብራሪያ ላይ ነው። ጥያቄው የነበረው  “ኦነግ በሕዝብ ብዛት አንፃር  ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኦሮሞን ሕዝብ እወክላለሁ የሚል ቡድን ነው ። ነገር ግን በቁጥር ሲታይ አናሳ ከሆነ ማሕበረሰብ የተውጣጣው ህውሃት ድል ሲቀናው ኦነግ ግን በትጥቅ ትግሉ ያስመዘገበው ይህ ነው የሚባል ፋይዳ የለም” የሚል ነበር። ከተሰጡት ማብራሪያ በከፊል  “ኦነግ በምስራቅ ያደርገው የነበረው የትጥቅ ትግል ሻብያና ወያኔ ሲያደርጉት ከነበረው ትግል የተለየ እንደነበር፤ የኦነግ ትጥቅ ትግሉ ከደርግ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሱማሌዎችም ጋር ግጭት እንደነበርው ፣ ይህም የሆነው ሱማሌዎቹ ሐረርጌን፣ባሌን፣ሲዳሞን በሙሉ ጠቅልለው የሱማሌ አካል ለማድርግ እቅድ ስለነበራቸው እንደሆነ” ያስረዳል። በመቀጠልም ከሱማሌዎች ጋር የነበረውን ግጭት ለመፍታት በወቅቱ ፀረ ደርግ (ፀረ ኢትዮጵያ) ትግል ያደርጉ የነበሩ ለሱማሌው መንግስት እንደማያዋጣው መክረው እንዳቃታቸው ፤ሽምግልናው ላይም አንጋፋ የሻብያው አርክቴክቶች የነበሩት እነ እርመዳን ማሕመድ ኑርና ዑስማን ሳልህ ሲያድ ባሬን እንዳነጋገሩና ማሳመን እንዳልተቻለ ይገልፅልንና ሲያጠቃልል ፦

“ሱማሊያን እንድትወድም ያደረገ ያ ስህተት ነው ። መተባበር ከነበረባቸው ሀይሎች ጋር ሲጋጩ የነሱም ያቀዱት ሀሳብ  <<<ከሸፈባቸው>>> ። የኛንም ወደ ኋላ <<<እንዲጏተት (እንዲዘገይ)>>>”  አደረጉብን” ይለናል።

እዚህ ሀሳብ ላይ ሁለት ነገሮችን ማስተዋል እንችላለን። የመጀመሪያው እነዚህ ሶስት ሀይሎች (ሶማሌ፣ ሻብያ እና ኦነግ) በወቅቱ ኢትዮጵያን አስመልክቶ የነበራቸው አቋም ተመሳሳይ ነበር። ይኸውም ኢትዮጵያን በታትኖ የየራሳቸውን ድርሻ መውሰድ። በሱማሌዎችና በኦነጎች መካከል የነበረው ግጭት ኢትዮጵያን ካፈረሱ በኋላ ፍራሹ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ሊፈጠር ይችላል በማለት ነበር። እዚህ ላይ ቆመን የሌንጮን “ሱማሊያን እንድትወድም ያደረገ ያ ስህተት ነው” የሚለውን የፀፀት ስሜት ስናይ ባይሳሳቱ ኖሮስ?  ብለን እንድናስብና የግለሰቡን ፊት ለፊት ከሚናገረው በስተጀርባ ያለውን ስሜቱን እንድንረዳ ያደርገናል።ሁለተኛው በስተመጨረሻ እንደዋዛ ጣል የተደረገችው “አጏተቱብን (አዘገዩብን) የምትለዋ ቃል ናት።ይህንን ሀሳብ ከቃላት ስንጠቃ አንፃር የሚወስዱ ወገኖች  እንዳሉ ብረዳም ለኔ እንደ ሌንጮ ያለ ፖለቲከኛ ቃላትን በዘፈቀደ ይገድፋሉ ብየአልወስድም።  ስለዚህ ሌንጮ “አዘገዩብን” የሚለን ምንድን ነው??  ብለን ብንፈትሽ “በእንጥልጥል” ያለው ወይም “የተጏተተው” ኦሮሞን እንገንጥል የሚለው ሀሳብ ሆኖ ነው የምናገኘው። እንደሚታዎቀው ትላንትም ሆነ ዛሬ የኦነግ አቋም ኦሮሞን መገንጠል ነው ።ዛሬ እሳቸው የሚመሩት ቡድን ደግሞ ቢያስ ከላይ “የኦሮሞ ሕዝብ የዲሞክራሲ ጥያቄ በኢትዮጵያ ማህቀፍ ውስጥ ሆኖ <<ሕገ መንግስቱን እንዲተገበር በማድረግ>>> መፈታት ይቻላል” የሚል ይመስለኛል። ይህ ሆኖ ባለበት ዛሬ ላይ ቆሞ “ሱማሌዎቹ ትግላችንን “አጏተቱብን” ብሎ መብሰልሰል ምን አመጣው? ብሎ መጠየቅ ይገባል ለማለት ነው።

ሀሳቦቹ በተነሱበትን ቅደም ተከተል ለመተቸት ቀጣዩ ሀሳብ  በወቅቱ ኤርትራው ለመገንጠል ይታገል የነበረው አማፂ ሌሎችን የመገንጠል ሀሳባቸውን  እንዲቀይሩ ተፅእኖ ያደርግ ነበር የሚለው  ነጥብ ነው። ይህ ሀሳብ በአቶ ሌንጮ “በሻብያዎቹ አካባቢ የነበረው ስሜት ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚል ነበር። ወያኔንም የመገንጠል አቋሙን ያስለወጠው ሻቢያ ነው”  በሚል ነው የተገለፀው።ይህ ሀሳብ እንግዲህ የዛሬውን በኤርትራ የሚደረገውን ትግል አዋጭነት ለማሳየት ታቅዶ የተወረወረ ሀሳብ ነው። ኢሳት እንደ ሚዲያ በኤርትራ በኩል ያለውን የትግል መስመር ደጋፊ እንደመሆኑና የግንቦት ሰባት አርበኞች ግንባር ልሳን እንደመሆኑ ነጥቡ እደሚነሳ የሚጠበቅ ነበር። ምናልባትም አቶ ሌንጮ “በአጋጣሚ አሜሪካ ለስራ ጉዳይ በሄዱበት” የኢሳት እንግዳ እንዲሆኑ የተፈለገበትም አንደኛ ምክንያት ይኸው ይመስላል።ከአቶ መለስ ጋር  እስከ ሕይዎት ፍፃሜያቸው ድረስ ግኑኝነት የነበራቸውና ይማከሩ እንደነበር የነገረን አቶ ሌንጮ መሳሪያና ቀለብ ይሰፍሩላቸው ከነበሩት ኢሳያስ አፍወርቂ ጋርም ተመሳሳይ አገልግሎት አይሰጡም ለማለት አይቻልምና። ወደ ሀሳቡ ስንመለስ  ሻብያዎች በወቅቱ የሌሎችን ተገንጣዮችን አቋም ይቃወምም እንዲቀይሩ ያስገድዱም ነበር የሚለው ሀሳብ በሁለት ምክንያቶች እውነትነት ይኖረዋል። የመጀመሪያው ኤርትራ ዛሬ በምናውቃት መልኩ እንድትገነጠል በተቀሪዋ ኢትዮጵያ በኩል ሆኖ እውቅና የሚሰጥና የሚፈራረም አካል መኖርን ይጠይቃል። ሁሉም ከፈረሰ ከማን ጋር ተደራደርኩ ይባላል። ሁለተኛ ምክንያት የሚሆነው የግብፁን ጎራ ብንተወው ሻብያን ያስታጥቁ የነበሩ ምራባዊያን ደርግን መጣልና ኤርትራን ነፃ ማውጣትን እንጂ  የኢትዮጵያን መበታተን ይደግፋሉ ተብሎ አይጠበቅም።ስለዚህ ሁሉም እንገንጠል ካሉ የአለም ማሕበረሰብ ኤርትራን ጨምሮ ሁሉንም እውቅና ሊነሳቸው ይችላል። ይህንን ተራ ነገር ሻብያዎች ያጡታል ማለት አይቻልምና የሌሎችን መገንጠል ይቃወሙ ነበር የሚለው እውነታ አለው።ይህ ማለት ግን ዛሬም ተመሳሳይ አቋም አላቸው ወደሚል ድምዳሜ አያደርስም።ዛሬን ዛሬ ላይ ቆመን ነው የምንገመግመው።የኢትዮጵያ አንድነትና ጥንካሬ ለኤርትራ ምን ማለት ነው?  ፣ኤርትራ እንደነ ተስፋየ ገ/አብ አይነት ሰላዮችን አሰማራ እየሰራች ያለችው ስራ የኢትዮጵያን አንድነት ከሚፈልግ ወዳጅ ሀገር የሚጠበቅ ነው ወይ?  ለበርካታ አመታት ኤርትራ ውስጥ የመሸጉት አማፅያን ምን ምን ድሎችን አስመዘገቡ?  እና በርካታ መሰል መጠይቆችን እያነሳን የምናሰላስለው ጉዳይ ነው የሚሆነው።

ሶስተኛ የማነሳው ሀሳብ በሽግግር መንግስት ወቅት በህውሃትና በኦነግ መካከል በነበረው ድርድር የአቶ ሌንጮ ቡድን ይዞት ነበር የተባለውን አቋም ነው።እንደ ግለሰቡ አቀራረብ “በሽግግሩ ወቅት የስልጣን ድልድል በሚደረግበት ሰሀት እኛን ያስጨንቀንና ትኩረት ሰጥተን እንሰራው የነበረው የክልል አከላለል ጉዳይ እንጂ የስልጣን ሽሚያውን አልነበረም” ነው የተባለው።

በግሌ መለሰ ዜናዊ በስልጣን በቆየባቸው ግዜዎች ሁሉ አንድም ቦታ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ለኢትዮጵያ ዘብ ቆሟል የሚል እምነት የለኝም። ስለዚህ ያደረጋቸውን ፀረ ኢትዮጵያ ድርጊቶች በኤርትራዊ ደሙ ነው ብየ ነው የማምነው።ነገር ግን በሽግግሩ ወቅት መለስ እንደ አንድ የትግራይ ሰው ኢትዮጵያዊ ሆኖ ነው ይደራደር የነበረው ከተባለ በኦነጉ ሌንጮ ለታ በፖለቲካ ተበልጦ እንደነበር ነው የምረዳው።ለዚህ አስተየት በሽግግሩ ወቅት “ኢትዮጵያን አፄ ምኒሊክ የመሰረቶት የመቶ አመት ታሪክ ብቻ ያላት ሀገር ናት” ተብሎ ይካሄድ የነበረው ፕሮፖጋንዳ ጠቀሜታነት የነበረው ለማን ነበር ብለን ማየት ብቻ በቂ ይሆናል። ከሶስት ሺህ በላይ ታሪክ ያላትን አገር ታሪኮን  ወደ መቶ ዝቅ እንዲል የተደረገው የትግል መሰረቱን ከጣልያን ቅኝ መገዛት ጋር ለሚያያይዘው ሻብያና  ዘፍጥረትን ከሚኒሊክ ንግስና ጋር ለሚጀምረው ኦነግ  ተብሎ እንጂ  ለትግራይ  አንዳች የሚጠቅመው ነገር ያለ አይመስለኝም። የትግሬ ታሪክ ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር አብሮ ወደ ኋላ የሚለጠጥ ስለሆነ ይህንን መሰል የታሪክ አቀራረብ ህውሃቶች እንወክለዋለን ለሚሉት ማሕበረሰብ የሚዋጥ አይሆንምና ። ውጤቱንም  ስናይ ኤርትራ ሁለት ወደቦችን ይዛ እንድትገነጠል ሲሆን ፣ ኦነግም “ምኒሊክ በሀይል አስገብረውት ነው እንጅ ከመቶ አመት በፊት ኦሮሞ የሰፈረበት መሬት ነበር” በማለት ዛሬ “ኦሮሚያ”  ብለው የከለሉት የኢትዮጵያ ግዛት የኦሮሞ ሀገር ብቻ ለማድረግ የመሰረት ድንጋይ ጥለዋል።

እዚጋ ህውሃት እንዴት በፖለቲካ ተበለጠ ይባላል? ስልጣኑን በሙሉ ጠቅልሎ በመውሰድ ላለፉት ሃያ አምስት አመታት በስልጣኑ ሙሉ ተጠቃሚ ሆኖል አይደል? የሚል ሀሳብ ሊነሳ ችላል።እውነት ነው።ለግዜው ስናየው እንደዛ ሊመስለን ይችላል ። ዛሬ ያለው ካትግራይ የበቀለው ቡድን አይኑን ጨፍኖ፣ ሕሌናውን ዘግቶ አይን ያወጣ ዘረፉ እያካሄደና በመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ግፍ እየፈፀመ ነው። ካባቶቹ ያልወረሰውን የጎንደርና የወሎ መሬት በማናለብኝነት እየቆረሰ ፣ ባለርስቶችን እያፈናቀለ፣ ዘር ማጥፋት ላይ ተሰማርቶል። እወክለዋለሁ ከሚለው ብሔር ውጭ ያሉት ብሔሮች ነገ ተጠናክረው እንዳይገዳደሩኝ በሚል ስሌ በሕዝቦች መካከል ጠላትነት እንዲነግስ፣እንዳይተባበሩ ፣እንዳይተማመኑ ሌት ተቀን እንደ ትል ሳያንቀላፋ እየታተረ ነው።መጠጊያና መደበቂያ እንዲያጡም የገዛ መሬታቸውን ለባእዳን አገራት እየሰጠና እየሸጠ ወዳጅ ለማፍራት እየተሮሮጠ ነው።ይህ ሁሉ ደረቅ ወንጀል ግን ግዜአዊ ነው።መጭውን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ድባብ ስንታዘብ ጉዳዩ በዚህ የሚቀጥል አይመስልም። ዛሬ ላይ የተደረሰበትን ተጨባጭ ሁኔታ እንኮን ብናይ “ኦሮሚያ” የተባለውን ክልል ከህዉሃት ግልፅና ቀጥተኛ ከሆነ ዘረፋ የሚያስጥል ትልቅና ወሳኝ እርምጃ ተወስዶበታል። እንደምገምተው ከዚህ በኋላ እዛ መንደር የገዢዎች ወገን ነኝና ያሻኝን እዘርፋለሁ፣የተመኘሁትን መሬት ነባር ሕዝብና አፈናቅየ እሸጣለሁ ወይም ለዘሮቸ አከፋፍላለሁ፣ ያይኑ ቀለም ያላመረኝን አስራለሁና እገድላለሁ የሚል ድፍረት አይኖርም።”ኦሮሚያ” ከአሁን በኋላ በስርሀቱ ተማምነው ይቦርቁ ለነበሩ ግለሰቦች አስፈሪ ድባብ ያላትና የሰቀቀን ሕይዎት የሚገባት ክልል ወደ መሆን ተሸጋግራለች። ከኦሮሞ ውጭ ላሉ ሕዝቦች ቀድሞውንም ያው ነበርች ። ለዚህም የራሳቸው የህውሃቶቹ ሙሉ ድጋፍ ነበረበት ። “ማነህ ባለተራ ማነህ ባለሳምን” ነው ዛሬ።።ነገ ከነገወዲያ ደግሞ በሌሎችም ክልሎች ተመሳሳይ ክስተት እንደሚፈጠር ምንም ጥርጥር አይኖርም።

እንደኔ ዛሬ የህውሃትን ዘራፊ ቡድን በማህከላዊው ኢትዮጵያ የሚፈፅመውን ዝርፊያ በመሀል አዲስ አበባ ብቻ እንዲዎሰን ያስገደደውና “ልክ እንዲገባ” ያደረገው ድርጊት ቀደሞ ያልታሰበበትና በዘፈቀደ የተፈጠረ ነው የሚል ካለ እነ ሌንጮ ከሃያ አመት በፊት የቀረፁትን ሕገ መንግስት ምንነት ያልተረዳ ብቻ መሆን አለበት። የሆነውን በአጭሩ ለመቃኘት ሌንጮና ጎዶቹ በድል አጥቢያ የጥይት ድምፅ ሳያሰሙ የሽግግሩ ዋና ተዋናኝ እንዲሆኑ ተጋበዙ። ኤርትራ የኢትዮጵያን ጥቅም በሚጎዳ ሁኔታ እንድትገነጠል ተባብረሩ። ለዚህ ውለታቸውም  በህልማቸው ሲያልሙት የኖሩትን የኢትዮጵያ መሬት ለራሳቻው ሕዝብ ብቻ በሚሆንበት መንገድ እንዲከልሉ ከሻብያ(መለስንም ይጨምራል)  ይሁንታን አገኙና ከለሉ። ህልማቸውን ተፈፃሚ ሊያደርግ የሚችል “ሕገ መንግስት” ቀርፀው እንዳገባባቸው አንዲትም የጥይት ድምፅ ሳያሰሙ ሹልክ ብለው ወጡ። በመጀመሪያቹ የስልጣን አመታት ህውሃት ሻብያን በኢትዮጵያ ሕዝብና ሀብት ላይ እንደልቡ እንዲቦርቅ ፈቅዶለት  እንደነበር ሁሉ ኦነግም ህውሃትን ያሻውን እንዲያደርግ ነበር ለቆለት የወጣው።ህውሃት በአንፃራዊነት አናሳ ቁጥር ካላው የተውጣጣ ወንጀለኛ ቡድን እንደመሆኑ አዲስ አበባን በቅርብ እርቀት ከቦ የሚገኘው የኦሮሞ ማሕበረሰብ አንድ ቀን በቃኸን ብሎ እንደሚነሳበት መገመቱ ቀላል ነበር።

እንደሚታወቀው የህውሃት የመጨረሻው ግቡ ከትግራይ ውጭ ያሉትን የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሀብትና ንብረት ዘርፎ “ታላቋን ትግራይ” መመስረት ነው። ይህ ደግሞ ዘር ማጥፋትን ጨምሮ በርካታ ደረቅ ወንጀሎችን መስራት የግድ እንደሚል እንኮን ፖለቲከኛው ሌንጮ ማንም የሚረዳው ጉዳይ ነው። በተጨማሪም ላለፉት ሁለት አስት አመታት እንደታዘብው ህውሃት የነገዋ “ታላቋ ትግራይ ዘላቂ ሰላም” በተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝች መካከል በሚፈጠር ዘላቂ ጠላትነት ላይ ነው ብሎ የሚያስብ ቡድን ነው። ለዚህም በተቀሩት የኢትዮያ ሕዝቦች መካከል ልዩነቶችን እያጎላና ሕዝብን ከሕዝብ እያናከሰ ወደ አንቀፅ 39 የሚወደውን መንገድ ጠረጋ አንዱና ዋናው የሂደቱ አካል ነውና የትግራይን መገንጠል የኦሮሞ ሀገርን ለመመስረት ለተነሱት ኦነጎች  በረከት ይዞ ዳግም እንደሚጋብዛቸው  ቀደም ብለው ቢተነብዩ የሚጠበቅ ነገር ነው።ስለዚህ በሽግግር መንግስቱ ወቅት ያገኙትን ስልጣን ይዘው የግፉ አካል ከመሆን  ትላንት የሻብያዎቹ ገረድና ጉዳይ አስፈፃሚ በመሆን የኢትዮጵያን ወደብ አሳልፎ የሰጠው ፣ ዛሬ ከባእድ ጎረቤት ሀገር ጋር አብሮ ድንበራችንን ቆርሶ ለመስጠት ጫፍ የደረሰው ፣ በአገርና በሕዝብ ላይ ለሚፈፅመው ክህደት አቻ የማይገኝለት፣ቅንታት ታህል ጥበብና ይሉኝታ ያልፈጠረበት፣ ሙትቻውን ህውሃት መንገዱን እንዲጠርግ ማድረግ። በመጨረሻም በሻብያ ተሸርቦ ኢትዮጵያን በዘርና በቋንቋ እንዲበታትን ተደርጎ የተተከለዉንና ሌንጮ “እኔ ነኝ ዋናው የሀሳቡ አመንጪው” ያለንን “ሕገ መንግስት” ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ይዋልን የምትል ውብ  “የዲሞክራሲ ጥያቄ” ይዞ መቅረብና ህልምን እውን ማድረግ ነው አላማው ። እየተሳካም ይመስላል።

በመጨረሻ የማነሳው በሌንጮ ቡድንም ሆነ በተቀሩት የኦሮሞ ፖለቲከኞች አዲስ አበባን አስመልክቶ እየተነሳ ስላለው ጉዳይ ይሆናል። እንደሚታወቀው “ማስተር ፕላኑን” ተከትሎ በኦሮሞ ማሕበረሰብ ዘድ የተደረገው ተቋውሞ ገዢው መንግስት ፕላኑን ሰርዠዋለሁ ካለ በኋላ ጥቄው እየተለጠጠ መጥቶል። በተቋውሞው ምክንያት የታሰሩ፣ አካላቸው የጎደለ፣ ንብረታቸው የወደመ እንዲሁም ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች በመኖራቸው ተጨማሪ ጥያቄች እንደሚነሱ የሚጠበቅ ነገር ነው።እንግዲህ ከላይ ከተዘረዘሩትንና ተመሳሳይ አግባብነት ከላቸው የዲሞክራሲ ጥያቄዎቻ ጎን ለጎን አንድ የሚገርምና መሰረተ ቢስ የሆነ ጥያቄ ከፊት መስመር ቀድሞና ደምቆ እየወጣ እንዳለ እያየን ነው። “አዲስ አበባ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ትደረግ” የሚለው ጥያቄ። ይህ ጥያቄ አቶ ሌንጮ ዛሬ የሚመሩት ድርጅትን ጨምሮ በበርካታ ኦሮሞ ፖለቲከኞች እንደ ዋና አጀንዳ ሆኖ ብቅ ብሎል።“ብረትን መቀጥቀት እንደጋለ” እንዲሉ አበው የኦሮሞ ሕዝብ ጭቆናና መገፉት ይብቃን ብሎ የወሰደው እርምጃ ህውሃትን አብረክርኮታልና ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም እንደ ሌንጮ ያሉ ብልጣ ብልጥ ፓለቲከኞች ሌላ ተጨማሪ የፓለቲካ ትርፍ ሊያገኙበት ድርድር ላይ ናቸው።የቅሚያና የዝርፊያ ዘመን ላይ ሆነንና ስለ ሀገር ታሪክ መተንተን፣የአባትን አጥቢያ መሻት ሰሚ ጆሮ ያጣበት ወቅት ሆነና ላለፉት 25 ዓመታት ሲደረግ የነበረው ዛሬም የማይሆንበት ነገር የለም።ሲጀመርም ዛሬ ያለውን ሕገ መንግስት የቀረፁትም ሆነ ለሕዝቦች የክልል አጥር ያበጁት በጂኦግራፊ የማይገናኙ (በመካከላቸው የድንበር ይገባኛል ችግር የሌለባቸው)፣ ዋና ጠላታችን የአማራ ሕዝብን ነው ብለው የተነሱና ጠላታቸንም ለማጥት እስከ አሁኖ ሰሀት ድረስ ጠንክረው እየሰሩ ያሉ ፣ መገንጠልን የትግላቸው ዋና ምሰሶ አድርገው የታገሉ ቡድኖች ናቸው።ለማንኛም ሀሳቡን ለማንሳት ያህል ኢትዮጵያን በዘር መቀራመት ከመጣ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የመአከላዊ የኢትዮጵያ ታሪክ በሰፊው የሚታወቅ በመሆኑ ያንን እዚህ ማንሳት ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል። ከላይ የጠቀስኩት የኢትዮጵያን ታሪክ ከአፄ ምኒሊክ የግዛት ማስመለስ ጋር የማስተሳሰሩ ዋናው ግብም ይኸዉ ነበር።ለማንኛውም አዲስ አበባ በቋንቋ ፣በባህል፣ነዋሪዎቾ ባላቸው ስነ ልቦና ፣በታሪክ ሲታይ የኦሮሞ ዞን የሚያደርጋት አንዳች ነገር የለም።ሌላው የሚገርመው ነገር ደግሞ  ከ95 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ያላት የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋና ከተማ ፣የአፍሪካ ህብረት ዋና መዲና፣ የተለያዩ አለምአቀፍ ተቋማት መቀመጫ ፣ኢትዮዽያ ውስጥ ዛሬ ካሉት ክልሎች ወደ 40 ፐርሰንት ከሚጠጉት ክልሎች በላይ የሕዝብ ቁጥርና ስብጥር ያላትን አዲስ አበባ የኦሮሞ አንድ ዞን ትሁን ብሎ ሀሳብ ማንሳት በራሱ አስቂኝና አሳፋሪም ነው።ቢሆንም ግን ይህ እንዳሆን ለመከላል የሚያስችል ጉልበት መፍጠር አልተቻለምና በቅንጅትን ወቅት ተነስቶ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ አዲስ አበባን “የኦሮሚያ” ዋና መቀመጫ እንድትሆን እንደተደረገ ሁሉ ዛሬም “የኦሮሚያ” አንድ ዞን ትሁን አትሁን የሚለው ጉዳይ በነዛው ቡድኖች እጅ ላይ ነው።

ኢትዮጵያ ዛሬ ላለችበት አጣብቂኝ ሁናቴ እኔ እንደመፍትሄ የሚታየኝን ሀሳብ ላንሳና ሀሳቤን ልሰብስብ።ሁሉም ወገን እንደሚስማማበት ኢትዮጵያ ዛሬ አደጋ ላይ ናት። ዘርን መሰረት አድርጎ ለ25ዓመታት በተሰራው ፀያፍ ፕሮፖጋንዳ “እኛ”ና “እነሱ” የሚል አስተሳሰብ ተፈጥሮል ። ተጠንቶና ታስቦበት በሕዝቦች መካከል እንዲፈጠር በተደረገ ጥላቻ መተማመንና መተባበር እንዳይኖር ተደርጎል። የአብሮነቱን ታሪክን በማንቋሸስና በመበረዝ መቀራረብን ፣መተሳሰርን፣መፋቀርን ያመጣሉ የሚባሉ ሕዝባዊ ባህሎችና ልምዶችን ፣ የአብሮነት የትግል ውሎዎች፣ የወል የድል ባህላትን ትኩረት እንዳይሰጣቸው በማድረግ ለመጪው ትውልድ እንዳይተላለፋ ፣ እንዲከስም እየተደረገ ብሔራዊ ስሜት እንዲጠፋ ተደርጎልም እየተደረገም ነው።ይህንንም ተከትሎ ሀገራዊ አጀንዳ ይዘው የሚነሱ የፓለቲካ ቡድኖች በዋናነት በገዢው ፖርቲ አልፍ አልፎም ሰርገው በሚገቡ ብሔርተኞች በቀላሉ እንዲከስሙ ሲደረግ ዘርና ቋንቋን መሰረት ያደረጉ የፖለቲካ ፖርቲዎች በአንፃራዊነት እየጎለበቱና ተፅእኖ ፈጣሪ እየሆን መምጣታቸውን እያየን ነው።ይህ መሬት ላይ ያለ ሀቅ ነው። እኔ በግል እስከማውቀው ድረስ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ ብሔርን መሰረት አድርጎ ተቋቁሞ በገዢው ፓርቲ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት እንዲጠፋና አባላቱም ለሞትና ለእስራት የተዳረጉበት ፖርቲ ካለ የፕ/ር አስራቱ መአድ ብቻ ነው።

በኔ አመለካከት በመንግስ ሙሉ ድጋፍ የሚደረግለት ዘርና ቋንቋን መሰረት ያደረገ ብሔርተኝነት ባለበት ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ጎጣዊ አደረጃጀቱን መንግስ ቀጥተኛ ድጋፍ የማይሰጠው ሆኖ በዘር ላይ በተመሰረተ ፖርቲና በብሔራዊ ፖርቲ መካከል አቻ ትግል ቢደረግ አሸናፊነቱ የሚያመዝነው ወደ ዘርን መሰረት ወዳደረገው ፖርቲ ነው።ብሔራዊ ፖርቲዎች ሁሉን አሳታፊ በመሆናቸው ለሰርጎ ገቦች አመች ናቸውና ሚስጥራቸውን ለመጠበቅ ይቸገራሉ።በታሪካችንም የምናየው ይህንኑ ነው።ደርግ ብሔራዊ መንግስት ነበር።ታግለው የገፈተሩትና ዛሬ ሁለት መንግስት ያቋቋሙት ደግሞ ዘርና ቋንቋን መሰረት አድርገው የተደራጁ ቡድኖች ናቸው።ደርግ ለመውደቁ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም አንዱና ዋናው በመረጃ መበለጡ ነበር። በሁለቱም ወገን ትግሬዎችና ኦሮሞዎች በመኖራቸው የመረጃው ፍሰት ወደ ጎጣዊ ቡድን ያመዝናል።ተፈጥሮአዊም ነው። እንደሚታወቀው የደርጉ ቡድን የመጀመሪያውን ደም ያፈሰሰውና በኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ በአለም አቀፉ ማሕበረሰብ ዘንድ አይንህን ላፈር የተባለው ጠቅላይ ሚ/ር አክሊሉ ሀብተ ወልድንና ጎዶቻቸውን በረሸነበት ወቅት ነው። ፕ/ር መስፍን ከአሻራ መጽሄት ጋር ባደረጉት ቃለመጠየቅ ይህንን ጉዳይ አስመልክተው እንደገለፁት “የባለስልጣናቱን ጉዳይ እንዲዳኝ በተቋቋመው መርማሪ ኮሚሲዮኑ ዉስጥ ደርግ ባለስልጣናቱን እንዲረሽን ይገፋፉ ከነበሩት ግለሰቦች “መሰሪ” ብለው የጠቀሶቸው የኦነግ መስራቹ ባሮ ቱምሳና ሻብያ በረከተ አብ ወልደስላሴ” ነበሩበት። ጎጠኞቹ ይህንን መሰለ አሻጥር በመስራት ብሔራዊ ቡድን የነበረውን ደርግ እጁን በደም እንዲጨማለቅና ከሕዝብ እንዲነጠል አድርገው ወደ ጎጣቸው ኮበለሉ።ሌሎችንም ተመሳሳይ ክስተቶች ብንፈትሽ የተለዩ አሆኑም።

ስለዚህም “እኛ”ና “እነሱ” የሚለው አመለካከት ገዢ በሆነበትና የብሔራዊው (የአንደነቱ) ቡድን እየተዳከመ በመጣበት ሁኔታ የኢትዮጵያን ችግር መፍታት የሚቻለው እንዴት ነው ? የሚለውን ጉዳይ ስንመረምር “እሳትን በሳት” ወደሚል ጥግ እንደርሳለን።ሁሉም እንደሚስማማበት ዛሬ በኢትዮጵያ አንድ ብሔር ያለ እስከሚመስል ድርስ ተጠናክሮ የሚገኘውና መንግስትን እየተገዳደረ ያለው የኦሮሞ ብሔርተኝነት ነው።በሀገርም ሆነ በውጭ የሚገኙ ሚድያዎችን ተቆጣጥረው ያሉት የኦሮሞ ፖለቲከኞች ናቸው።በኢትዮጵያ ከሚገኙት ሕዝቦች ዉስጥ መበደሉ፣መገፋቱ ጎልቶ እተሰማ ያለውና የአለም አቀፍ እውቅና የተሰጠውም ይሄኛው ወገን ብቻ ነው ብል ማጋነን አይሆንም።እንደተቀሩት የኢትዮጵያ ሕዝቦች መገፋቱ ፣ መበደሉ እውነት ነውና ለመብቱ መታገሉ የሚደገፍና የሚመሰገን ሆኖ እያለ ብቻውን ጎልቶ መውጣቱ ግን ከኢትዮጵያ መፃሂ እድልና ከሌሎች ሕዝቦች እጣ ፋንታ ጋር ስንመረምረው አሉታዊነት ሊኖረውም ይችላል።

ህውሃት አናሳ ቁጥር ካለው ሕዝብ የተውጣጣ፣ ለኢትዮጵያ ፀር የሆነ ብሔርተኛ ቡድን ነው።ከኦሮሞ ፖለቲከኞችም አገራዊ አጀንዳ አንግበው ሳይሆን አዲስ አገር መመስረትን መሰረት አድርገው የሚንቀሳቀሱ ቀላል የማይባሉ ሀይሎች አሉ።በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሁለቱ ቡድኖች ብቻ እየጠነከሩ መምጣት ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለው ጭቆናና ግፍ በማንኛውም አካል የሚቀሰቀሱ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ህውሃትን ባስደነበሩት ቁጥር እንቅስቃሴውን ለማፈን ድርድሩ በነዚህ ቡድኖች መካከልና ሁለቱ ቡድኖችን ብቻ በሚጠቅም ላይ ነው የሚሆነው። ይህን መሰል ክስተቶችን ደግሞ ደጋግመን ታዝበናል ። ለምሳሌ ከላይ እንደጠቀስኩት 97 ምርጫን ተከትሎ የተፈጠረው ሕዝባዊ አመፅ ሕብረ ብሔራዊ መሰረት የነበረው ቢሆንም እንዲኮላሽ የተደረገው በዋናነት በህውሃት የሀይል እርምጃ ሲሆን በወቅቱ ቅንጅትን “በነፍጠኝነት” ፈርጆ ትልግሉን ላለመደገፍ በኦሮሞ ብሔርተኛ ፖለቲከኞች የተወሰደው አቋም ቀላል የማይባል ሚና ተጫዉቷል።ውጤቱም የሞተው ሞቶ የታሰረው ታስሮ አዲስ አበባን “የኦሮሞ” ዋና መቀመጫ አድርጎ ነው የተደመደመው።የሰሞኑንም እንቅስቃሴ ብንወስድም ኢሳትን ጨምሮ  በውጪ የሚገኘው ማህበረሰብ እንቅስቃሴዉን ከሰባዊ መብት አንፃር በማየት “ማስተር ፕላኑን”  ለማስቀረትና የኦሮሞ ወገኖችን ድምፅ ለማሰማት  ከፍተኛ አስተዋፅሆ አርጎ ነበር።”ማስተር ፕላኑ” በተሰረዘ ማግስት ግን ኦሮሞ ፖለቲከኞት አጀንዳውን ወደ “አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዞን መሆን አለባት”፣ “ኦሮሚያ የኦሮሞ ብቻ”  እንደሆነችና፣ ኦሮሚያ ዉስጥ የሚኖረው ሌላውን ኢትዮጵያዊ እንደ ኬንያዊና ቻይናዊ ናቸው የሚሉ አግላይ ድምፆችና መግለጫዎች መሰማት ጀመሩ።ስለዚህ ይህንን መሰል ክስተት ሊገዳደርና ሊያሰቀር የሚችል ፣ሰፊ ዕራይ ያለው ነገር ግን ብሔርን መሰረት አድርጎ የተደራጀ ጠንካራ አካል መምጣት አለበት ብየ ነው የማምነው።ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት ላይ ያለው  አሰላለፍ ይኸው በመሆኑ ጉዳዩን በብሔሮች መካከል እንደሚደረግ ገመድ ጉተታ አርጎ መውሰድ ይቻላል።ይህ ማለት ሳይዘገይ አዲሱና ጠንካራ ብሔርተኛ ቡድን ተቋቁሞ ፣ የመደራደር አቅም አጎልብቶ ገመዱን በተቃራኒው በኩል መጎተትና ወደ መሀል ማምጣት   (counter balance)  ማድረግ ይኖርበታል።ይህንን ማድረግ እስካልተቻለ ድረስ ተመሳሳይ ሁኔታወች በተከሰቱ ቁጥር ዛሬ ተበታትነው ድምፃቸው የታፈኑ ሕዝቦች  ወደ ጠነከረው ሀይል መጎተታቸው ብቻ ሳይሆን ይህ ዛሬ ያለው ከፍተኛ የሀይል አለመመጣጠን የሚፈጥረው የስባት ፍጥነት(inertia) ሌሎችን ክፋኛየመጨፍለቅ አቅም ይኖረዋል።ይህንን እውነታ ሊታደግና እራሱንም ሆነ ሌሎችን ማዳን የሚችለው ብሔር ደግሞ አማራ ነው።የአማራ በብሔርተኝነት መሰባሰብና መደራጀት ግዜ ሊሰጠው የማገባ ጉዳይ ነው።

ቸር እንሰንብት!!!

E-mail

gizdemelash@gmail.com

 

 

The post የኢሳት የሳምንቱ እንግዳ _ አቶ ሌንጮ ለታ —–(ግዜነው ደም መላሽ) appeared first on Zehabesha Amharic.


አስታዉሳለሁ መቼ እረሳለሁ! የመጋቢት 1960 እልቂት በደቡብ አፍሪካ ሻርፕቪል ከተማ

0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም   

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

Sharpeville-Massacre-20
በየዓመቱ በአፍሪካ ውስጥ የተፈጸሙ ሁለት የሕዝብ እልቂቶችን አስታውሳለሁ፡፡

በወርሃ መጋቢት በደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች የበላይነት ዘረኛ አገዛዝ/apartheid በሻርፕቪሌ ከተማ እ.ኤ.አ መጋቢት 21/1960 የፈጸመውን ዘግናኝ እልቂት አስታውሳለሁ፡፡

እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በህይወት በሌለው በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ልዩ ትዕዛዝ እ.ኤ.አ ሰኔ 8/2005 እና ከህዳር 1-10/2005 እንዲሁም ከ14-16 በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) የጥቂት ጥቁሮች የበላይነት የጎሳ አገዛዝ/apartheid የተፈጸመውን አሰቃቂ እልቂት አስታውሳለሁ፡፡

በዘር እና በጎሳ የጥቂት አፓርታይድ አናሳ ቡድኖች የበላይ አገዛዝ መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም፡፡

በዘር መድልኦ እና በጎሳ መድልኦ መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም፡፡

በጥቂት ነጮች የበላይ የዘር አገዛዝ “ባንቱስታንስ“ (መኖሪያ መንደሮች) እና በዘ-ህወሀት (የማጎሪያ በረት) “ክልሎች“ መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም፡፡

“የተለያየ ህዝብ ራሱን በግሉ ማልማት” እየተባለ ይጠራ በነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ሄንድሪክ ቬርወርድ የጥቂት ነጮች የደቡብ አፍሪካ ዘረኛ የበላይ አገዛዝ ፖሊሲ እና በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የጥቂት ጥቁሮች “የጎሳ ፌዴራሊዝም” የበላይ አገዛዝ ፖሊሲ መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም፡፡

አፓርታይድ የቆዳ ቀለም ዘር የለውም፣ ጎሳ የለውም፣ ኃይማኖት የለውም፣ ቋንቋ የለውም፣ እናም ምንም ዓይነት የብሄራዊነት ባህሪያት የሉትም፡፡ ሆኖም ግን በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ አሰቃቂ ስቃይ ነው፡፡

ከዛሬ 56 ዓመታት በፊት በመጋቢት ወር በሻርፕቪሌ (ከጁሀንስበርግ በስተደቡብ አቅጣጭ በትራንስቫል ግዛት በሚገኘው እና በአሁኑ ጊዜ ጓቴንግ እየተባለ በሚጠራው ከደቡብ አፍሪካ 9 ክልሎች መካከል አንዱ በሆነው ግዛት ውስጥ የምትገኘው) ተካሂዶ በነበረው በዚያ ጥላቻ በተመላበት ዕለት የጥቁር አፍሪካውያንን የአካል እንቅስቃሴ ለመገደብ ወጥቶ እና በጥቂት የነጮች የበላይ አገዛዝ ጸድቆ የነበረውን ሕግ (የአገር ዉስጥ ፓስፖርት ጥቁር አፍሪካውያኖችን አንቀሰቃሴ ለመገደብ) ለመቃወም ከፖሊስ ጣቢያው ፊት ለፊት 5 ሺ   (የአፓርታይድ ፖሊስ የወሰደው የኃይል እርምጃ ትክክለኛ መሆኑን ለማሳየት አጋንኖ በማቅረብ  ቁጥሩን እስከ 20 ሺ ያደርሰዋል) ተቃዋሚዎች ተሰባሰቡ፡፡

ምንም ዓይነት መሳሪያ ያልታጠቁት ሰላማዊ ሰልፈኞች የፖሊስ ቅጥር ግቢውን ሰብረው ለመግባት ሙከራ አደረጉ፡፡ ፖሊስ በመጀመሪያ በአስለቃሽ ጭስ እና በፖሊስ ቆመጥ በመጠቀም አመጹን ለማክሸፍ ምላሽ ሰጠ፡፡ ጥቂት ተቃዋሚዎች የፖሊስ ቅጥር ግቢ በሩን ሰብረው ለመግባት ሞከሩ፡፡ በዚህ ጊዜ ፖሊስ በተቃዋሚ ስብስቡ ላይ በአውቶማቲክ እና ሌሎች መሳሪያዎች አማካይነት የእሩምታ ተኩስ ከፈተ፡፡

ይፋ በሆኑ መረጃዎች መሰረት ፖሊስ 705 ጥይቶችን በመተኮስ 69 ተቃዋሚዎችን 8 ሴቶችን እና 10 ልጆችን ጨምሮ ገድሏል፡፡ የቆሰሉት  ሰዎች ቁጥር እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች 31 ሴቶችን እና 19 ልጆችን ጨምሮ 180ይዘላል፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 1960 በተቃውሞ ሰልፉ የተሳተፉ እና ደጋፊዎች ናቸው ተብለው የተወነጀሉ 18,011 የሻርፕቪሌ ተቃዋሚዎች እየተያዙ ወደ እስር ቤት ታጎሩ፡፡ አብዛኞቹ የጥቃት ሰለባ የሆኑት ተቃዋሚዎች ከድርጊቱ ለማምለጥ ወደ ኋላ በመሸሽ ላይ እንዳሉ ከጀርባቸው በተተኮሱ ጥይቶች እየተመቱ የተገደሉ ነበሩ፡፡

በሻርፕቪል በተጨማሪነት የፖሊስ ኃይሉን ለማጠናከር የመጣው ፖሊስ ዋና አዛዥ የነበሩት ሌተና ኮሎኔል ፒናር ለጋርዲያን ቃለ መጠይቅ በሚያደርጉበት ጊዜ ደረታቸውን ነፍተው ምንም ነገር እንዳልተደረገ በሚመስል መልኩ እንዲህ ነበር ያሉት፣ “ይህ ሁሉ ድርጊት የተፈጸመው የተሰበሰበው የአካባቢው ህዝብ የፖሊስ ጣቢያውን መክበብ በጀመረበት ጊዜ ነበር፡፡ መኪናዬ በድንጋይ ተመትታ ነበር፡፡ እንደዚህ ያለ ድርጊት ከፈጸሙ ከባድ ነገር ሊገጥማቸው እንደሚችል መማር አለባቸው፡፡” የፖሊስ አዛዡ ሌላም ነገር በመጨመር እንዲህ ብለው ነበር፣ “የአካባቢው ተወላጅ ሰዎች አስተሳሰብ በሰላማዊ መንገድ ተሰብስበው ሀሳባቸውን ለመግለጽ ችሎታውም ሆነ ፍላጎቱ የላቸውም፡፡ ለእነርሱ መሰብሰብ ማለት ኃይል የተቀላቀለበት እርምጃ መውሰድ ማለት ነው፡፡“

እ.ኤ.አ ሰኔ 8/2005 በአዲስ አበባ ከተማ እና እ.ኤ.አ ከሕዳር 1-10 እና ከሕዳር 14-16/2005 ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ እና በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የዘህወሀት አፓርታይድ ኃይሎች መሳሪያ ባልታጠቁ ተቃዋሚ ስብስቦች ላይ የእሩምታ ተኩስ በመክፈት 193 ሰላማዊ ዜጎችን በመግደል 763 የሚሆኑትን ደግሞ ቁስለኛ አድርገዋል፡፡ ይህ መረጃ አሁን በህይወት በሌለው እና የዘ-ህወሀት ፈላጭ ቆራጭ መሪ በነበረው በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ በተሾመው የምርመራ አጣሪ ኮሚሽን ይፋ የተደረገ ነው፡፡ የምርመራ አጣሪ ኮሚሽኑ እ.ኤ.አ በግንቦት 16 እና በታህሳስ 2005 መካከል የተፈጸሙትንበመቶዎች የሚቆጠሩ የሞት ሰለባ እና ቁስለኛ የሆኑትን የሌሎች ዜጎችን ዘገባ እንዲያቀርብ አልተፈቀደለትም፡፡ (የትዕዛዝአዋጁን ለማንበብ እዚህ ጋ ይጫኑ ፡፡)

የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የእልቂት ምላሽ በሚያስገርም ሁኔታ ከኮሎኔል ፒናር ምላሽ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ አምባገነኑ መለስ እንዲህ የሚል ገላጻ አድርጎ ነበር፣ “ሰላማዊ የሆነ ሰልፍ አልነበረም እላለሁ፡፡ እየተካሄደ የነበረው አመጽ ነበር፣ እናም ህዝባዊ አመጹን አስተንፍሰነዋል፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ የሰው ህይወት ጠፍቷል፡፡ ሆኖም ግን በምንም ዓይነት መልኩ በፍጹም ሰላማዊ ሰልፍ አልነበረም፡፡“

እ.ኤ.አ በ2005 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ተከትሎ ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ ጋር በተያዘ መልኩ 30 ሰላማዊ ዜጎች በዘህወሀት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ወደ ዘብጥያ በመወርወር ለእስር ተዳርገዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ጥቂት የነጮች ዘረኛ አገዛዝ በአፓርታይድ በሰው ልጆች ላይ የፈጸማቸው ኢሰብአዊ ድርጊቶች በፊልም ተቀድተው ተቀምጠዋል፡፡ (አንዱን አሳዛኝ የቪዲዮ ምስል ለመመልከት እዚህ ጋ ይጫኑ ፡)

.. 2005 በዘህወሀት አናሳ የጎሳ አፓርታይድ አገዛዝ በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመውን እልቂት የሚያሳይ የቪዲዮምስል በይፋ የለም፡፡ ሆኖም ግን የአምባገነኑ መለስ የጥቃት ሰለባ የሆነ የእያንዳንዱ ሰው ስም ዝርዝር ይታወቃል፡፡ ጥቂትፎቶግራፎች (በጣም አሰቃቂ ፎቶግራፎች ስለሆኑ ተመልካቾችን አናስተነቀቃለን :: የጥቃት ሰለባዎቹን ፎቶግራፍየጥቃት ሰለባዎች ስም ዝርዝር ቀጥሎ ይገኛል አዚህ ይጫኑ ለማየት)፡፡

የሻርፕቪሌን እልቂት ማስታወስ ያለብን ለምንድን ነው?

እ.ኤ.አ በ1960 በሻርፕቪሌ የተፈጸመውን እልቂት በምናስታውስበት ጊዜ እንደዚሁም ሁሉ ከዚህም በላይ በመቶዎች የሚቆጠሩትን በአፍሪካ በአሁኑ ጊዜ እየተፈጸሙ ያሉትን፣ ትላንት የተፈጸሙትን፣ ባለፈው ዓመት የተፈጸሙትን፣ ከ10 ዓመታት በፊት የተፈጸሙትን እና ከ100 ዓመታት በፊት የተፈጸሙትን እልቂቶች እናስታውሳለን፡፡

ባለፈው ዓመት ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እና ሌሎች የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአብዛኞቹ የሰብ አፍሪካ ሀገሮች ውስጥ ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈጸሙትን መጠነ ሰፊ ግድያዎች መዝግበው ይዘዋል፡፡

ባለፈው ወር ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፣የኢትዮጵያ የደህንነት ኃይሎች .. በሕዳር 2015 በኦሮሚያ ክልል የተጀመረውን መጠነ ሰፊ ሰላማዊ ህዝባዊተቃውሞ ኃይልን በመጠቀም በመጨፍለቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ አዲሱ ዓመት እ.ኤ.አ 2016 ከባተ ጊዜ ጀምሮ ሂዩማን ራይትስ ዎች በየዕለቱ በሚባል መልኩ የዘፈቀደ ግድያዎችን እና እስራቶችን እየመዘገበ ይገኛል፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን ወሮበላ ዘራፊዎች በምዕራቡ ዓለም እና በቻይና መልካም ፈቃድ እና ግዙፍ የገንዘብ ድጋፍ እየታገዙ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እልቂቶችን ከመፈጸማቸው በስተቀር “ሻርፕቪሌዎች” በአፍሪካ በየዕለቱ ይፈጸማሉ፡፡

በሱዳን፣ በላይቤሪያ፣ በሴራሊዮን፣ በማዕከላዊ አፍሪካ ሬፐብሊክ፣ በማሊ፣ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፐብሊክ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች በአፍሪካ ውስጥ በደህንነት ኃይሎች፣ በወታደር እና በፖሊስ ኃይሎች እየተፈጸሙ ያሉት የዘፈቀደ ግድያዎች ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ተንሰራፍተው ይገኛሉ፡፡ ጥቂቶች አዲስ እልቂቶች ደግሞ እጅግ በጣም የሚዘገንኑ እና አስደንጋጭ እየሆኑ መጥተዋል፡፡

ቀላሉ እውነታ ሲታይ ግን ታላላቆቹ የምዕራብ ሃያላን ሀገሮች በአፍሪካ ውስጥ ስለሚፈጸም የሰው ልጆች ዕልቂት መስማት አይፈልጉም፡፡ ይልቁንም የመንግስት ስልጣንን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሳይሆን የህዝቦችን ፍላጎት በኃይል በመጨፍለቅ በመንግስት ስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው የሚገኙትን ወሮበላ ዘራፊ ገዳይ መንግስታት ለመጠበቅ ሲሉ ጥርሳቸውን ነክሰው በመዋሸት ላይ ይገኛሉ፡፡

ባለፈው ዓመት የኬንያ ፕሬዚዳንት የሆነው ኡሁሩ ኬንያታ በሰው ልጆች ላይ በተፈጸመ ሰብአዊ ወንጀል አምስት የውንጀላ ክሶች ቀርበውበት ሄግ ውስጥ በሚገኘው በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ቀርቦ ጉዳዩ መታት እንዲችል ዝግጅት ተደርጎ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2007/08 ተደርጎ የነበረውን የኬንያ ድህረ ምርጫ ውዝግብ ተከትሎ ከ1,200 በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን 600 ሺ ዜጎች ደግሞ ከመኖሪያ ቦታቸው ተፈናቅለው ነበር፡፡

ኬንያታ ሙንጉኪ እየተባለ የሚጠራ የማፊያ ዓይነት ወንጀለኛ ድርጅት በማሰማራት ከናይሮቢ በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በሚገኘው እና ከአፍሪካ ታላላቅ የቆሻሻ ስፍራዎች መካከል አንዱ በሆነው እና ኪቤራ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ጎሳን መሰረት ባደረገ መልኩ በስሜት በመነሳሳት ግድያ እና የአካል ጉዳት ማድረሱን የሚያመላክቱ በርካታ ማስረጃዎች ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን የምዕራቡ ዓለም ኃያላን መንግስታት በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/International Criminal Court (ICC) ዋና አቃቤ ሕግ ላይ ተጽዕኖ በማድረግ በኬንያታ ላይ የተያዘው የወንጀል ክስ እንዲቋረጥ አድርገዋል፡፡ (ከአመት በፊት አስቀድሜ ኬንያታ ሙሉ በሙሉ ከICC በነጻ ተሰናብቶ ደረቱን ገልብጦ እንደሚሄድ ስተነብይ ቆይቻለሁ፡፡)

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2014 በICC ተይዞ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው ኬንያታ ተለቅቆ እንደ ወፍ በመብረር ከወጣ በኋላ ቅጥፈቱን በመንዛት ደረቱን ገልብጦ በመንገዳወል ላይ ይገኛል፡፡

ለአፍሪካ ወሮበላ ዘራፊዎች ደግ እና ትህትና የተመላበት መስተንግዶ ማድረግ በዚህ ላይ ብቻ የሚያቆም አይደለም፡፡

የነጻው ዓለም ታላቅ መሪ የተባለው ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “እንደዚህ ያሉ ጉዳዮች በሚመጡበት ጊዜ ምላሴን አላጥፍም፡፡ መንግስትን በኃይል ለማስወገድ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያን መንግስትም ጨምሮ ዓላማ ያደረገን ማነኛውንም ቡድን እንቃወማለን፡፡“

ኦባማ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን እያለ የሚጠራው ሌላ ማንንም ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ በአሸባሪነት የተፈረጀውን እና በዓለም አቀፍ የአሸባሪዎች መረጃ ቋት ስም ዝርዝር ውስጥ ስሙ ሰፍሮ የሚገኘውን የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን (ዘ-ህወሀትን) ነው፡፡

ኦባማ በተግባር የማያውለውን ሆኖም ግን እራሱን ከፍ ከፍ እያደረገ ለአራት ዓመታት ያህል እንዲህ በማለት ሲቀጥፍ ቆይቷል፣ “አፍሪካ ጠንካራ ሰዎችን አትፈልግም፡፡ አፍሪካ የምትፈልገው ጠንካራ ተቋማትን ነው፡፡ የአፍሪካ ጠንካራ ሰዎች በተሳሳተው የታሪክ መንገድ ላይ የሚጓዙ ናቸው፡፡“

አዬ! ለምንድን ነው ኦባማ በመንታ ምላስ የሚናገረው!

የኦባማ መንታ ምላስ እንዲህ የሚሉትን  የሸክስፒር ማክቤዝ ጥቂት ዓረፍተ ነገሮች አስታወሱኝ፡ “የአንተ እጆች፣ የአንተ ምላስ:: ልብ ብለህ ተመልከት  ውብ አበቦች ይመስላሉ፡፡ ሆኖም ግን በመርዝ የተሞላ እባብ ማለት ናቸው፡፡“

ኢትዮጵያውያን እንደዚህ ባለ መንታ ምላስ ለተካነ ሰው እንዲህ የሚል የአባባል ተረት አላቸው፣ “አፉ ቅቤ ሆዱ (ልቡ) ጩቤ ከሆነ ሰው ተጠንቀቁ፡፡“

በኦባማ ምላስ ላይ ካለው ተለዋዋጭ መርዛማ እባብ ተጠንቀቁ!

የአፍሪካ ህይወቶች ለኦባማ ጉዳዮቹ ናቸውን? (ይኸ አወዛጋቢ ጥያቄ ነው አትመለስ ገና፡፡)

ኦባማ እና የምዕራቡ ዓለም በአፍሪካ በስልጣን ላይ ተፈናጥጠው ላሉት ወሮበላ ዘራፊዎች መንታ ምላስን በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፡፡

የምዕራቡ ዓለም ኃያላን መንግስታት ወሮበላ ዘራፊዎቹ ከእስር ቤት በነጻ እንዲወጡ ማድረግ ብቻ አይደለም እየፈጸሙ ያሉት፣ ሆኖም ግን በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠረውን የእራሳቸውን ግብር ከፋይ ህዝቦች ዶላሮችን እና ዩሮዎችን በመሰብሰብ በባንክ ሂሳባቸው ውስጥ ያጭቁላቸዋል፡፡

እንግዲህ ኦባማ ለዘ-ህወሀት በትክክል ያደረገው ይህንን ነው፡፡ ዴሞክራት በማለት የይለፍ ወረቀት ይሰጣቸዋል፡፡ አባማ በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉት ጨካኝ እና ሙሰኛ ወሮበላ ዘራፊዎች በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ግብር ከፋይ ህዝብ ዶላሮችን ያስታቅፋቸዋል፡፡

.. ነሀሴ 2012 የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፖሊስ ኃላፊዎች በሰሜናዊ ምዕራብ ደቡብ አፍሪካ በምትገኘው በማራኪና የማዕድን ቁፋሮ አመጽ ያካሄዱ ሰራተኞች ላይ የእሩምታ ተኩስ በመክፈት 44 ዜጎችን ሲገድሉ 78ቱ ደግሞ ቁስለኞች እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ (መሳሪያ ባልታጠቁ አማጺዎች ላይ የተፈጸመውን እና ለማመን የሚያስቸግረውን እና ልብ የሚያደማውን የጥይት ድብደባ ትክክለኛውን የቪዲዮ ምስሉን እዚህ ጋ በመጫን  ይመልከቱ [ዝርዝር ምስሉን]፡፡

በዚያን ጊዜ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “በዚህ ትርጉም የለሽ ጥቃት ደንግጠናል፣ አዝነናልም፡፡“ “ትርጉም የለሽ ጥቃት” የሚለው ማንም ሰው በለማዳ እንስሳት ላይ የሚፈጸም ትቃትን ለመግለጽ የሚጠቀምባቸው ቃላት ናቸው፡፡

ዙማ እ.ኤ.አ በ1960 የተፈጸመውን የሻርፕቪሌ እልቂት ለመግለጽ እንደዚህ ያሉትን የተለሳለሱ እና ፍጹም በሆነ መልኩ ኢሰብአዊ የሆኑትን የቢሮክራሲ ቋንቋዎች ለመጠቀም ባይመርጥ ኖሮ የሚገርመኝ ይሆን ነበር፡፡

ኦባማ ስለማራኪና እልቂት ምንም ትንፍሽ ያለው ነገር የለም፡፡ ኦባማ እ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ በሀገር ውስጥ እና በውጭ አሸባሪዎች ሲፈጸሙ በቆዩት የህዝብ እልቂቶች ላይ የተሰማውን ሀዘን ሲገልጽ ቆይቶ ነበር፡፡ ሆኖም ግን የአፍሪካ ወሮበላ ዘራፊ አገዛዞች በአፍሪካ ህዝቦች ላይ ሲፈጽሙት በቆዩት እልቂት ላይ አንዲትም ቃል ትንፍሽ ሳይል ቆይቷል!

አሁን እንዲህ የሚለውን ጥያቄ መመለስ ትችላላችሁ፣ “የአፍሪካ ህዝቦች ህይወት ለኦባማ ጉዳዩ ነውን?“

የማራኪና እልቂት ተፈጽሟል ምክንያቱም የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ኮንግራስ አመራር ለፈጸማቸው የወንጀል ድርጊቶች እና ጉድለቶች በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ቀርቦ ተጠያቂ ሊሆን እንደማይችል አስቀድሞ ያውቅ ነበርና ነው፡፡

በቁስል ላይ እንጨት ስደድ እንዲሉ የማራኪናን እልቂት የማጣራት ስራ ከተጀመረ ከሶስት ዓመታት በኋላ ህዝባዊ ነጻ የሆነ የፖሊስ ምርመራ ሲያካሂዱ የቆዩት መርማሪዎች ለእንዲዚያ ዓይነቱ የህዝብ ፍጅት አንድንም የፖሊስ አባል እስከ አሁንምድረስ ተጠያቂ ማድረግ ሳይችል ቆይቷል፡፡ በማራኪና በግፍ 44 ንጹሀን ዜጎችን በጥይት እየደበደቡ የገደሉ እና 78 የሚሆኑትን ዜጎች ያቆሰሉት አንዳቸውም የፖሊስ ኃላፊዎች እስከ አሁን ድረስ ወደ ፍትህ አካል ፍጹም አልቀረቡም!!!

በተመሳሳይ ሁኔታ 193 መሳሪያ ያልታጠቁ ሰላማዊ ተቃዋሚ ዜጎችን በጥይት በመደብደብ የገደሉት የአምባገነኑ መለስ የፖሊስ እና የደህንነት ኃይሎች እስከ አሁን ድረስ ለፍትህ አካል ሳይቀርቡ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን በፖሊስ እና በደህንነት መምሪያዎች ሰላማዊ ዜጋ መስለው የሚኖሩ ሆኖም ግን እጃቸው በንጹሀን ደም ተጨማልቆ የሚገኘው የ237 የፖሊስ እናየደህንነት ወሮበላ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ስም ዝርዝር ተይዞ ይገኛል፡፡

የማራኪና እልቂት እ.ኤ.አ በ2012 በደቡብ አፍሪካ መፈጸም የሚችል ከሆነ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት በሻርፕቪል  መሬት ላይ የተፈጸመው እልቂት እና በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያ ወይም በአፍሪካ በተለያዩ ቦታዎች ውስጥ እ.ኤ.አ በ2016 ተመሳሳይ እልቂቶች ቢፈጸሙ የሚያስደንቀን ነገር ሊሆን ይችላልን?

ወሰን የማይገድበው ሰይጣናዊነት፣

በአፍሪካ ውስጥ ሁሉም እልቂቶች በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጠው በሚገኙት ወሮበላ ዘራፊዎች እና አንዳንድ ጊዜም ለወደፊት ስልጣን ለማግኘት ሲሉ ስልጣን በሌላቸው ዘራፊዎች በውል ታስቦባቸው የተቀነባበሩ ስሌቶች ናቸው፡፡

በአፍሪካ ውስጥ የሚፈጸሙ እልቂቶች ህዝባዊ ፍጅትን ለማድረግ የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ናቸው፡፡

በሻርፕቪል በጥቂት ነጮች የበላይ ዘረኛ የአፓራታይድ አገዛዝ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ወንጀል እና እ.ኤ.አ በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ በተፈጸመው እልቂት ወይም ደግም በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ላይ በተደረገው የዘር ማጥፋት ወንጀል መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም፡፡ ምንም!

አናሳው የደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች የበላይነት አገዛዝ የነበረው እና አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ በስልጣን እርካብ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ዘ-ህወሀት በስልጣኖቻቸው ላይ የሚመጡባቸውን ማናቸውንም ነገሮች ቢሆን መግደል እና ማጥፋት እንደሚችሉ ለህዝቡ በማሳያነት በማቅረብ እልቂቶችን እና የኃይል ጥቃቶችን ይጠቀማሉ፡፡

የሻርፕቪል  እልቂት የጥቂት ነጮች ዘረኛ የበላይ አገዛዝ ቃፊር [በደቡብ አፍሪካ ነጮች የተናቁ ጎሳዎች] እያሉ ለሚጠሯቸው የደቡብ አፍሪካ ጎሳዎች ሊረሱት በማይችሉት መልኩ ዘላለማዊ ትምህርት ለመስጠት ታስቦ የተፈጸመ እልቂት ነበር፡፡

መልዕክታቸውም ቀላል እና እንዲህ የሚል ነበር፣ “የአናሳዎቹን የነጮች የበላይ አገዛዝ መገዳደር እርባናየለሽ ሙከራ ነው፡፡“

የአምባገነኑ የመለስ እልቂት እና በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት ቀጥለው የሚገኙት እልቂቶች ለብዙሀኑ ህዝብ እንዲህ የሚለውን አንድ ዓይነት መልዕክት ለማስተላለፍ ዓላማ በማድረግ እየተሰራበት ይገኛል፣ “የአናሳውን የዘ-ህወሀትን የበላይ አገዛዝ መገዳደር እርባናየለሽ ሙከራ ነው፡፡“

ልዩ በሆነ መልኩ የሚፈጸም የኃይል ጥቃት እና እልቂት የሰይጣናዊነት ትሩፋት ውርስ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ጥልቀት ባለው ሁኔታ ተከፋፍላለች፣ እናም ብዙሀኑ ህዝብ በመበሳጨት ላይ የሚገኝ ሲሆን ደቡብ አፍሪካ በሰዓት የተሞላንየጊዜ ቦምብ በመጠባበቅ ላይ እንደሆነች በቂ መረጃ ያላቸው ተመልካቾች ያምናሉ፡፡

በዘህወሀት አገዛዝ ስር ባለችው ኢትዮጵያም  ተመሳሳይ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ባለፉት ጥቂት  ሳምንታት ውስጥ ባቀረብኳቸው ሶስት ተከታታይ ትችቶቼ እንደ ደቡብ አፍሪካ ሁሉ በኢትዮጵያ ውስጥም በባሩድ በተሞላ ሳጥን ውስጥ የተቀመጠ ቦምብ እንዳለ እና የማቀጣጠያ ፊዩዟ ከተሳበች ሊፈነዳ እንደሚችል ለማሳየት ሞክሪያለሁ፡፡ ጥያቄ ሆኖ የሚቀርበው ግን መቼ ነው ይኸ በሰዓት የተሞላ ቦምብ የሚፈነዳው የሚለው ነው እንጅ በባሩድ ሳጥኑ ላይ ያለው የማቀጣጠያ ፊዩዝ ቦምቡን ሊያፈነዳው ይችላል ወይ የሚለው ጥያቄ አይደለም፡፡

ሰይጣናዊነት ድልን ሊቀዳጅ የሚችልበት ዋናው አስፈላጊ ነገር ጥሩ ወንዶች እና ሴቶች ምንም ነገር ማድረግ ሳይችሉሲቀሩ ብቻ ነው…“ 

ሰይጣናዊነት ድልን ሊቀዳጅ የሚችለው እያንዳንዱ ሰው ምንም ዓይነት ሰይጣናዊነት አልሰማሁም፣ ምንም ዓይነት ሰይጣናዊነት አላየሁም እና ምንም ዓይነት ሰይጣናዊነት አልተባለም የሚሉ በውል የተጠኑ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ በሚችልበት ጊዜ ነው፡፡ ለእውነት በመቆም የትኛው ጥሩ እና ትክክለኛ ነው የሚለው የሁሉም ሰዎች ጠንካራ ምርጫ ነው ምክንያቱም ይኸ ጉዳይ የሞራል ግልጽነትን እና ለህሊና የማደር ድፍረትን ይጠይቃል፡፡

ከሰይጣናዊነት እጅግ በጣም የከፋው ሰይጣናዊነት ደግሞ እንዲህ የሚሉ ቀላል ምርጫዎችን የሚሰጡን ናቸው፡ ጸጥ ማለት፣ የምንግዴለሽነት ባህሪ ማሳየት፣ ተበድሎም ቢሆን ይቅርታ ጠያቂዎች ሆኖ መቅረብ እና የሰይጣናዊነትን ድርጊቶች መፈጸም ናቸው፡፡

እኛ ብቻ እንደ ግለሰብ በሞራል ልዕልና ድፍረት እና በሰይጣናዊነት ድርጊቶች መካከል ያሉትን ምርጫዎች በመለየት መተግበር መቻል ይኖርብናል፡፡

ሮበርት ኬኔዲ የሰይጣናዊነት ድርጊት እንቆቅልሽ ባጋጠመን ጊዜ ማድረግ የሚገባንን የሞራል ልዕልና እንዲህ በማለት አቅርበውልናል፡

“በእያንዳንዷ ጊዜ ወንድ [ሴት] ላመነበት ሀሳብ ሲቆም፣ ወይም ደግሞ የሌሎችን የበርካታዎችን ህይወት ለማሻሻል ሲሰራ፣ ወይም በኢፍትሀዊነት ላይ ሲያምጽ፣ የተስፋ ፍንጣቂዎችን ያሰራጫል፣ እናም እነዚህ የተስፋ ፍንጣቂዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የተለያዩ የኃይል እና የድፍረት ማዕከሎችን ሲያቋርጡ የጭቆና እና የተግዳሮት ዋና ኃይል የሆነውን ኃይለኛውን ግንብ ሊደረምስ የሚችል የፍንጣቂ ኃይል ይገነባል፡፡“

በአፍሪካ ውስጥ የሚፈጸሙትን እልቂቶች ማስታወስ ያለብን ለምንድን ነው?

በአምባገነኖች የሚፈጸሙ እልቂቶች አብዛኛውን ጊዜ የአምባገነኖቹ ደካማነት፣ ለአደጋ ተጋላጭነት እና የህዝባዊ አመጽን የመፍራት መገለጫዎች ናቸው፡፡

ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የጥቂት ነጮች የበላይ የዘር አገዛዝ ያወጣውን ዘረኛ ሕግ በመጣስ ለተፈጸሚነቱ አንገዛም በማለት የሻርፕቪልን የፖሊስ ጣቢያ ጥሰው ባለፉ ጊዜ እነዚህ ህዝቦች ምንም ዓይነት ፍርሀት እንደሌለባቸው እና ማንኛውንም ዓይነት መስዋዕትነት የሚያስከፍል ሁኔታ ቢመጣም እንኳ አንገታቸውን እንደማያጥፉ ለጥቂት ነጮች የበላይ ዘረኛ አፓርታይድ አገዛዝ ግልጽ የሆነ መልዕክት ያስተላለፉ መሆናቸውን ያመላክታል፡፡

የጥቂት ነጮች የበላይ ዘረኛ የአፓርታይድ አገዛዝ የሻርፕቪሌ አመጾች በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ይስፋፋሉ ብሎ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ በመወሸቅ አመጸኞቹ ከጉልበታቸው ስር ያንበረክኩኛል በሚል ስጋት ውስጥ ወድቆ ነበር፡፡

የጥቂት ነጮች የበላይ ዘረኛ የአፓርታይድ አገዛዝ ጥቁር አፍሪካውያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወታደራዊ የበላይነትን ሊቀዳጁ ይችላሉ ብሎ አልነበረም ይፈራ የነበረው፡፡ የእነርሱ ታላቁ ፍርሀት የነበረው ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ከኃይል ነጻ የሆኑ ሰላማዊ ትግሎችን፣ የሰራተኞች የስራ ማቆም አድማዎችን፣ ሙሉ የስራ አቅምን አለመጠቀምን እና ምርት መቀነስን፣ ኃይል ያልተቀላቀለባቸው መገዳደሮችን መፈጸምን፣ የመንገድ ላይ አመጾች እና ጉዞዎችን ማድረግን፣ ከህንጻዎች ውጭ የተቃውሞ አመጾችን ማካሄድን፣ ተጠቃሚዎች የሚመረቱ ምርቶችን አለመጠቀም እና የመሳሉትን ነገሮች ነበር፡፡

ዘ-ህወሀትም የጥቂት ነጮች የበላይ ዘረኛ የአፓርታይድ አገዛዝ እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ እና በ1980ዎቹ ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ እርሱም በተመሳሳይ ድርጊት ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡

ሆኖም ግን የዘ-ህወሀት መሪዎች የጥቂት ነጮች የበላይ ዘረኛ የአፓርታይድ አገዛዝ መሪዎች ለብዙሀኑ በመገዛት ስምምነት በማድረግ ቀልጣፎች በመሆን የተደላደለውን ኑሯቸውን በሰላማዊ መንገድ ሲገፉ እንደነበሩት ሊሆኑ ስለማይችሉ በዘ-ህወሀት መጨረሻ ላይ ስጋት አለኝ፡፡

እንዲህ ዓይነቱ እርምጃ ለዘ-ህወሀት ከባድ እና እሾሀማ ይሆናል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ውስጥ ለሚፈጸሙ እልቂቶች ተጠያቂ ያለመሆን ጉዳይ መቆም አለበት!

የሻርፕቪልን እና የአምባገነኑን መለስ እልቂቶች እና ሌሎችን በርካታዎችን የሀገር ክዳት ወንጀሎች ማስታወስ ዋናው እና የመጀመሪያው ጉዳይ በአፍሪካ በሰው ልጆች ላይ ወንጀሎችን በሚፈጽሙ ወሮበላ ዘራፊዎች ላይ ከእንግዲህ ወዲያ የወንጀል ተጠያቂነት መኖር እንዳለበት ለማረጋገጥ እንዲቻል ነው፡፡ ይህም ሲባል እስከ አሁን ድረስ በሰው ልጆች ላይ በተፈጸሙት ወንጀሎች ላይ ተጠያቂነት አይኖርም ለማለትም አይደለም፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡

እ.ኤ.አ በ1994 የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል በተፈጸመ ጊዜ አብዛኛው የዓለም ህዝብ ጸጥ ብሎ ይመለከት ነበር፡፡ ያ አስከፊ የሆነ የዘር ፍጅት ከተፈጸመ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ፕሬዚዳንት ክሊንተን እንዲህ ብለው ነበር፣ “በወቅቱ አስቸኳይ የሆነ እርምጃ ብንወስድ ኖሮ ቢያንስ ያለቀውን ህዝብ አንድ ሶስተኛ ያህል ህወይወት ማትረፍ እንችል ነበር… እንዲህ ዓይነቱ ነገር ተፈጻሚነት ቢኖረው ኖሮ ለእኔ ጽናት ያለው ፋይዳ ሊያመጣ እንደሚችል ይሰማኛለል፡፡“

የሩዋንዳን የዘር ማጥፋት ፍጅት ለመከላከል ምንም ዓይነት እርምጃ ባለመወሰዱ ምክንያት እ.ኤ.አ በ2003 በሱዳን በዳርፉር ተመሳሳይ ዓይነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጸመ፡፡ የኦማር አልባሽር አገዛዝ አረባዊ ደም በሌላቸው እና በዳርፉር በሚኖሩ የሱዳን ዜጎች ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈጸም ቢያንስ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ንጹሀን ዜጎች እንዲገደሉ አድርጓል፡፡

የዓለም ህዝብ ለአልባሽር እልቂት ነጻ የይለፍ ካርድ በመስጠቱ ምክንያት አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እና ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ በ2005 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ተከትሎ ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ በመቶዎች በሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች ላይ እልቂት ፈጽመዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት ያንን ገዳይ የሆነ ባህሉን በበለጠ ደረጃ ቀጥሎበት ይገኛል፡፡

የዓለም ህዝብ ለአምባገነኑ መለስ ዜናዊ እልቂት የይለፍ ካርድ በመስጠቱ ምክንያት እ.ኤ.አ በ2007 ኡሁሩ ኬንያታ እና ግብረ አበሮቹ ወንጀለኛ የማፊያ ድርጅትን በመጠቀም ከ2007 ምርጫ በኋላ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት/ICC ዋና አቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተበት ኬንያታ በንጹሀን ህዝቦች ላይ እልቂትን ፈጽሟል፡፡ በኬንያታ ላይ ICC የመሰረተበት የወንወጀል ክስ እንዲቋረጥ ተደርጎ እጁ በደም የተጨማለቀው ወንጀለኛ ደረቱን ነፍቶ በመንገዳወል ላይ ይገኛል፡፡

የሻርፕቪልን እና የአምባገነኑን መለስ እልቂቶች እና ሌሎችን በርካታዎችን የሀገር ክዳት ወንጀሎች ማስታወስ ሁለተኛው ዋና ጉዳይ “የአፍሪካ እልቂት መርሳት” እና “የኢትዮጵያ እልቂት መርሳት” እያልኩ የምጠራውን የቡድን እልቂት መርሳትን ለመዋጋት ነው፡፡ ለእኔ  በአጠቃላይ አፍሪካውያን በእራሳቸው ላይ የተፈጸሙትን ሰብአዊ ወንጀሎችን የማስታወስ ዝንባሌ እያስወገዱ ያሉበት ሁኔታ መስሎ ይታየኛል፡፡ በእርግጥ ማስታወሱ እጅግ በጣም የሚያም ጉዳይ ነው፡፡

በአንድ ወቅት ስለአምባገነኑ መለስ እልቂት ሁልጊዜ ለምን እንደምናገር የእራሴ መልካም ጓደኛ ጠይቆኝ ነበር፡፡ ስለሞተው መለስ ለምን ትናገራለህ? ጓደኛዬ ይኸ ጉዳይ “ልቆጣጠረው የማልችለው እና በአእምሮየ ውስጥ ያለ ሀሳብ” እንደሆ አድርጎ ቆጠረኝ፡፡ ይኸ አንዴ የተደረገ ያለፈ ጉዳይ ነው፡፡ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ስለዚያ ነገር መርሳት እንዳለብኝ፣ ቢያንስ ሁልጊዜ ማስታወስ እንደሌለብኝ እና ወደ ሌላ ነገር መሄድ እንዳለብኝ ይነግረኝ ነበር፡፡ ይህንን ዓይነት አመለካከት ሊጋሩ የሚችሉ ሌሎችም ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡

እንዲህ የሚለውን የሸክስፒርን ብልህ ምክር ለጓደኛየ ላካፍለው እችላለሁን? “ሰይጣናዊትን የሰሩ ሰዎች ከሞቱ በኋላም ቢሆን ሰይጣዊው ድርጊታቸው ይኖራል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ መልካሙ ነገር ከአጥንታቸው ውስጥ አብሯቸው ይቀበራል፡፡“

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በህይወት ባይኖርም ቅሉ ሰይጣናዊ ድርጊቱ ግን አሁንም አብሮን በመኖር ላይ ይገኛል፡፡ ያ ሰይጣናዊነት ድርጊት ህይወት ዘርቶ መልካም ነገር ባይሆንም እንደ ኮሶ ትል የዘ-ህወሀትን ስብዕና ተጣብቶ አብሮ በመኖር ላይ ይገኛል፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በእርሱ አሻንጉሊት ፍጡር በሆነው በኃይለማርያም ደሳለኝ እምነት መሰረት አልሞተም በህይወት ነው ያለው፡፡

ኃይለማርያም ደግሞ እና ደጋግሞ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳይደረግበት የአምባገነኑን የመለስ ዜናዊን ትሩፋት ለማስቀጠል እያለ እንደ በቀቀን ሁልጊዜ እንደ መዝሙረ ዳዊት ይደግመዋል፡፡ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳይደረግ ያ ትክክለኛ እንደሆነ አድርጎ ይለፈልፋል፡፡

በኃይለማርያም ደሳለኝ ቁሳዊ አካል እና መንፈስ ውስጥ የዘ-ህወሀት ትንሹ አምላክ አምባገነኑ መለስ ህያው ሆኖ ይኖራል፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ለዘ-ህወሀት እና ለእርሱ ያልተቀደሱ ፍጡሮች ሁሉ እንደ ክርስቶስ ለሁለተኛ ጊዚ ተመልሶ ይመጣል፡፡

ዘ-ህወሀት በህይወት እስከኖረ ድረስ አምባገነኑ መለስ ዜናዊም በህይወት መኖሩን ይቀጥላል፡፡

በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች ማጎሪያ የሆነው እስር ቤት እስካለ ድረስ አምባገነኑ መለስ ዜናዊም በህይወት መኖሩን ይቀጥላል፡፡

ዘ-ህወሀት ኢትዮጵያን የግሉ መዝናኛ ሆቴል (ወሲባዊ ቱሪዝም አላልኩም) እና የመጫወቻ ማድረጉን እስካላቆመ ድረስ አምባገነኑ መለስ ዜናዊም በህይወት መኖሩን ይቀጥላል፡፡

የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የጥቃት ሰለባዎች የሆኑት የእኔ ጓደኞች እናት፣ አባት፣ እህት፣ ወንድም፣ ዘመዶች እና ጓደኞች መሆናቸውን ጓደኛዬ ቢሆኑ ኖሮዝም በል ይለኝ ነበር ፡፡ አንዲህስ ለማለት ይችላል- “ስማኝ የእኔ ቤተሰቦች በአምባገነኑ መለስ እና በእርሱ ዘ-ህወሀት ተጨፍጭፈዋል ምን ይደረግ ያለፍ ነገር ነው ተዋቸው እርሳው ሁሉንም ነገር፡፡

የእኔ መልስ እንዲህ የሚል ቀላል ጥያቄ ነው፡ በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ እና በዘህወሀት እልቂቶች የጥቃት ሰለባ ለሆኑወገኖቼ እኔ ካልተናገርኩ ከቶ ማን ሊናገርላቸው ነው? እኮ ? ንገረኛ ምስኪኑ ጓደኛዬ!

ለነገሩ ግን ማናቸዉም ሰው የእራሱን ውክልና እራሱ በመያዝ በግፍ ስለተገደሉት ወገኖች መናገር ቢጀምር እኔ ራሴ ዝም እላለሁ፡፡ እስከዚያው ድረስ ግን ሁልጊዜ ሰኞ ሰኞ የአምባገነኑ መለስ የጥቃት ሰለባዎች ድምጽ ሆኘ መዝለቁን አጠናክሬ እቀጥልበታለሁ፡፡

ሆኖም ግን እኔ እየተከራከርኩለት ያለው መሰረታዊ መርህ ምንም ዓይነት ማስታወስ ሳይኖር ወንጀሎችን በፈጸሙት ወንጀለኞች ላይ ምንም ዓይነት ተጠያቂነት አይኖርም የሚል ነው፡፡ ተጠያቂነት ሳይኖር አንድ ዓይነት ሰብአዊ ወንጀሎች በየጊዜው ደግመው እና ደጋግመው ይፈጸማሉ፡፡

እንግዲህ በአፍሪካ ውስጥ የሚፈጸሙ እልቂቶች እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ታሪክ ይህንን ይመስላል፡፡ ምንም ዓይነት ተጠያቂነት የማይኖር ከሆነ በየዕለቱ እልቂቶች ይፈጸማሉ፡፡

ሁሉም አፍሪካውያን የወሮበላ ዘራፊ አምባገነን አገዛዞች ሰለባ በሚሆኑበት ጊዜ ለወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው በግዴለሽነት ዝም ብለው መመልከት ሳይሆን ስለእነርሱ ሆነው የመናገር እና የማስታወስ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በአፍሪካ እልቂቶች ዘወትር ይፈጸማሉ፣ እናም ስለእነዚህ እልቂቶች ደጋግሞ ማንሳቱ ቂልነት ነው ብለው እራሳቸውን የሚያታልሉ ሰዎች አሉ፡፡ ደንታቢሶች!

እልቂቶች የአጋጣሚ ድርጊቶች እና ክስተቶች ናቸው በማለት አቅልሎ መናገር ይቻላል፡፡

ለተከታታይ ስቃዮች የሚዳረጉ ሰዎች፣ በተከታታይ ሰብአዊ መብቶቻቸው የሚደፈጠጡባቸው ሰዎች ያለፈውን ከማስታወስ ይልቅ እንደሚረሱ እገነዘባለሁ፡፡ ማስታወስ እጅግ በጣም የሚያም ነገር ነው፡፡ የእልቂት ክስተቶችን መርሳት ወይም ደግሞ ለመፈጸማቸው መጠራጠር የበለጠ ቀላል ነገር ነው፡፡

የብዙሀን አፍሪካውንን እልቂቶች የመርሳት እና የኢትዮጵያውንን እልቂቶች የመርሳት ባህል እንዲኖር መፍቀድ በወጣቱ ትውልድ እና ወደፊትም በሚመጣው አዲሱ ትውልድ ላይ ወንጀልን መስራት ማለት ነው፡፡

የአፍሪካ ወጣት ሰዎች ክብረ ቢስ የሆነውን “ታላቅ ኃይል እውነታን ያመጣል“ የሚለውን የብሂል ባህል ማውገዝ አለባቸው፡፡ እውነት ብቻ፣ የፍትህ የበላይነት እና ፍትሀዊ ሕጎች ብቻ እውነትን ያስገኛሉ፡፡

የሕግ ባህልን ለማጎልበት የአፍሪካ ወጣቶች የአፍሪካ ወሮበላ የዘራፊ አገዛዝ ወንጀሎች አሁኑኑ እንዲቆሙ ማድረግ እና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ማስታወስ እና እንዲታወሱ ማድረግ አለባቸው!

ባለፉት ጊዚያት በአፍሪካ ውስጥ በወሮበላ ዘራፊ አገዛዞች የተፈጸሙ እልቂቶች ጠንካራ በሆነ ታሪካዊ ትንታኔ እየታገዙ መመርመር እና ለመጭው ትውልድ ትምህርት እንዲሆን እና ለሁለተኛ ጊዜም እንዳይደገሙ ማረጋገጫ መሰጠት አለበት፡፡

ለዚህም ነው ወጣት አፍሪካውያን በአፍሪካ አህጉር ውስጥ እየተፈጸሙ ስለነበሩት  ስለሻርፕቪል እልቂት፣ ስለኪቤራ እና ስለአምባገነኑ መለስ እና ስለሌሎችም እልቂቶች ማስታወስ እና መማር ያለባቸው፡፡

እነዚህን የተንሰራፉ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች ዋና መንስዔዎች መገንዘብ እና የጥቃት ሰለባዎችን ትውስታ ማስቀጠል የወደፊቱ ትውልድ እልቂቶችን መከላከል እንዲችል ለማገዝ  ጠንካራ መሳሪያ ነው፡፡

አልበርት ኤንስታይን በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ዓለም ለመኖሪያነት እጅግ በጣም አደገኛ ቦታ ናት፣ ይህም የሆነው ሰይጣናዊነት ስራን በሚሰሩ ሰዎች ምክንያት ብቻ አይደለም፣ ሆኖም ግን ስለእነዚህ ሰይጣናዊ ድርጊቶች ምንም ሳያደርጉ እጆቻቸውን አጣጥፈው በመቀመጥ በሚመለከቱ ሰዎች ጭምር እንጅ፡፡“

ከዚህ ጋር አንድ ዓይነት በሆነ መልኩ አፍሪካ በተንሰራፉ ሰብአዊ ወንጀሎች፣ በዘር ማጥፋት ወንጀሎች እና በጦር ወንጀሎች ለመኖሪያነት እጅግ በጣም አደገኛ  የሆነች አህጉር ናት፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ሰይጣናዊ በሆኑ ወሮበላ ዘራፊ አምባገነኖች ምክንያት ብቻ አይደለም፣ ሆኖም ግን በዋናነት በቂ የሆኑ በጎ ነገር አሳቢ የአፍሪካ ሰዎች በተለይም ወጣቶች (እና የአፍሪካ ጓደኞች) በአንድ ላይ በጽናት በመቆም መናገር በማይችሉ እና በአህጉሩ ውስጥ ስለጅምላ የሰብአዊ መብት ረገጣው ምንም ዓይነት ድርጊት በማይፈጽሙ ሰዎች ጭምር እንጅ፡፡

በደቡብ አፍሪካ ውስጥ .. መጋቢት 21/1960 በሻርፕቪሌ የተፈጸመውን እልቂት አስታውሳለሁ፡፡

በደቡብ አፍሪካ ውስጥ .. ነሀሴ 16/2012 በማራኪና የተፈጸመውን እልቂት አስታውሳለሁ፡፡

በኬንያ ውስጥ .. ታህሳስ 2007 እና ጥር 2008 በኪቤራ የተፈጸሙትን እልቂቶች አስታውሳለሁ፡፡

በሩዋንዳ እና በሱዳን ዳርፉር ውስጥ የተፈጸሙትን የዘር ማጥፋት እልቂቶች አስታውሳለሁ፡፡

በአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች በአፍሪካ ውስጥ በአፍሪካውያን ላይ የተፈጸሙትን እልቂቶች አስታውሳለሁ፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ .. ሰኔ 8/2005 እና ከሕዳር 1-10 እና 14-16 በአምባገነኑ መለስ  የተፈጸሙትን እልቂቶች አስታውሳለሁ፡፡

እነዚህን እልቂቶች በማስታወሱ ረገድ ከእኔ ጋር ልትቀላቀሉ አትችሉምን?

የአፍሪካውያን ህይወቶች ጉዳዮቼ ናቸው! የአፍሪካውያን ህይወቶች ጉዳዮቼ ናቸው! የአፍሪካውያን ህይወቶች ጉዳዮቼናቸው!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

መጋቢት 6 ቀን 2008 .

 

The post አስታዉሳለሁ መቼ እረሳለሁ! የመጋቢት 1960 እልቂት በደቡብ አፍሪካ ሻርፕቪል ከተማ appeared first on Zehabesha Amharic.

ግፍ በገፍ የሞላበት አገር! |ከደቡብ ኦሞ እስከ መተማ፤ ከጅጅጋ እስከ ጋምቤላ፤ ከመቀሌ እስከ ባሌ፤ ከወልቃይት እስከ ኮንሶ |ያሬድ ኃይለማርያም 

0
0

 

ከቤልጂየም፤    መጋቢት 14፣ 2016 እ.ኤ.አ

ያሬድ ኃይለማርያም 

ያሬድ ኃይለማርያም

በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ቅድመ-አያቶች፣ አያቶች፣ ወላጆችና ልጆች፤ ሦስትና ከዛም በላይ የሆነ ትውልድ ተመሳሳይ በሆኑ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መሃል ተተብትቦ የሚማቅቅ ከሆነ የዛ ማህበረሰብ ጉዞ ጤናማነትና አቅጣጫ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል፡፡ በእንዲህ አይነት ማህበረሰብ ውስጥ መሰረታዊ የሆኑና የጎሉ ለውጦች ብዙም አይስተዋሉም፡፡ አንዳንዶቹም ለውጦች የቁልቁለት ጉዞ ውጤቶች ይሆኑና በራሱ ብቻ ሳይሆን በአያቶቹም ቁስል የሚማቅቅ፣ መቃብር ቆፋሪና ሸክሙ የከበደው ትውልድ ይፈጠራል፡፡ ይህ አይነቱ ትውልድ የተጫነውን ሸክሙን አራግፎ በነገ ህይወቱና ጥቅሞቹ ዙሪያ ላይ በማተኮር ለፈጠራና ለምርምር ሊያውለው የሚችለውን አቅሙንና ጊዜውን ያልኖረበትን ትላንትን እያመነዠከና የወረሰውን ቁስል እየጎደፈረ ይቆዝማል፣ ያቄማል፣ እርስ በእርሱ ይጎነታተላል፤ ሲከፋም ወደ እልቂት ያመራል፡፡ እንዲህ አይነቱ አዙሪትም ከመስመር በወጣ ጊዜ በሌላው አለም እንደተስተዋለው ለአገራት መበታተንና ውድቀት፤ በሚሊዮኖችም ለሚቆጠሩ ሰዎችም እልቂት መንስዔ ይሆናል፡፡

ግፍ በገፍ የሆነባት አገራችን፤ በዚህ አይነቱ የመከራ አዙሪት ውስጥ ከሚሽከረከሩ ጥቂት አገራት አንዷ ነች፡፡ በእርግጥ እርሃብ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ጭቆና እና አፈና፣ የጎሣ ግጭቶችና ሌሎች መሰል አደጋዎች ለኢትዮጵያ አዲስ ነገሮች አይደሉም፡፡ ባለፉት 50 እና 60 አመታት ውስጥ እንኳ እነዚህ አደጋዎች ተደጋገመው፤ አንዳንዶቹም ያለማቋረጥ ተከስተዋል፡፡ እነዚህ አደጋዎች ኢትዮጵያን አራቁተዋታል፣ አዋርደዋታል፣ ከሥልጣኔና እድገት ጎዳናም አሽሽተዋታል፡፡ በእነዚህ አደጋዎችም ዜጎቿ አንገቸውን ደፍተዋል፣ ለስደት፣ ለግዞት፣ ለእርሃብና እርዛትም ተዳርገዋል፤ የብዙዎችም ሕይወት ተቀጥፏል፡፡

ግፍ በገፍ የሆነባት አገራችን፤ እኩይ በሆኑ ልጆቿ እጅግ ሰቅጣጭና አስነዋሪ የሆኑ ድርጊቶችንም በተደጋጋሚ ጊዜያት አስተናግዳለች፡፡ ግፈኛን በግፈኛ የሚተካው የፖለቲካ አዙሪታችንም የግፉአን ልጆች ግፈኛ፤ የግፈኛም ልጆች ግፉአን እየሆኑ ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ ብዙም ሳንርቅ አንባገነንነትን፣ አፈናን እና ጭቆናን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋትና ነፃነት፣ እኩልነትና ፍትሕ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ቆርጦ የተነሳውን እና በብሶት ተጸንሶ፣ በብሶት ተወልዶ፣ በብሶት ያደገውን የ60ዎቹን ትውልድ ጉዞ በቅጡ ማጤንም ይቻላል፡፡ ከዛ ትውልድ ውስጥ አብዛኛው ከብሶቱ ጋር አብሮ ያረጀ ሲሆን ብዙዎቹም ካለሙበት ሳይደርሱና የአገራቸውንም ትንሳዔ ሳያዩ አልፈዋል፡፡ ጥቂቶቹም በለስ እየቀናቸው ሆድ አስባሽ እየሆኑ አዙሪቱን የአንድ ጎልማሳ ሰው እድሜን እንዲያስቆጥር አድርገውታል፡፡

oromo2

ግፍ በገፍ የሆነባት አገራችን፤ ዛሬም በከፋ የርሃብ አደጋ እየተለበለበችና በአስር ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎቿ በሞት አፋፍ ላይ ሆነው ችጋር እያሰቃያቸው ይገኛል፡፡ አሥር አመታትን እያሰለሰ ይከሰት የነበረው ችጋርም በየሁለት እና ሦስት አመታቱ እየተከሰተ በአለም አቀፉ ማህበረሰቡ ዘንድ የተሰጠንን የእርሃብተኝነት መለያ እያደሰልንና የምጽዋት ጠባቂውንው ቁጥር በብዙ እጥፍ እያሳደገ ከእኛነታችን ጋር ተጣብቶ ብዙ ዘመናትን አብሮን እየተሻገረ እዚህ ደርሰናል፡፡ የወያኔ ‘የልማት’ ፕሮፓጋንዳ ሊጋርደው ያልቻለው ይህ የችጋር አደጋ የስንት ወገኖቻችንን ሕይወት እንደቀጠፈ ቤት ይቁጠረው፡፡

ግፍ በገፍ የሆነባት አገራችን፤ በሁሉም አቅጣጫ የአገዛዝ ሥርዓቱ ጭቆና እና አፈና ባንገሸገሻቸው ብሶተኞች አመጽ እየተናወጠች ትገኛለች፡፡ ሦስት አመታትን ያስቆጠረው የሙስሊሙ ማህበረሰብ የመብት እንቅስቃሴ፣ ከአራት ወራት በላይ ያስቆጠረውና የበርካታ ንጹሃን ወገኖቻችንን ደም ያፈሰሰውና ሕይወት የቀጠፈው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ ቁጣና የነጻነት ጥያቄ፤ እንዲሁም የማንነት ጥያቄን መሰረት ያደረገው የወልቃይት ሕዝብ ንቅናቄና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የሚታዩት የፖለቲካ ኃይሎች መነቃቃት ሥርአቱን ብቻ ሳይሆን ሕዝቡንም ስጋት ውስጥ ከተውታል፡፡ ከዚያም ባለፈ አገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት አለመኖሩን እና ችግሩ በዚሁም ከቀጠለ አስፈሪ የሆነ አቅጣጫን ሊይዝ እንደሚቻል የሚያመላክቱ በርካታ ነገሮች ከወዲሁ እየተስተዋሉ ነው፡፡

ግፍ በገፍ የሆነባት አገራችን፤ የብሄር ብሔረሰቦች መብትና እኩልነት ተረጋግጧል እየተባለ ለ25 አመታት ሲደሰኮርና ሲጨፈርባት እንዳልኖረ ዛሬም ማንነታችን ይታወቅልን፣ እንደ ሕዝብም እንደሰውም እየተቆጠርን አይደለም የሚሉ ወገኖች ጥያቄ አንስተው መልስ የተነፈጉባት አገር ሆናለች፡፡ የወልቃይትና የኮንሶ ሕዝብ ጥያቄ ከብዙዎቹ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የመብት ጥያቄዎቹን ያነሱ የሕዝብ ተወካዮችም ለእስርና እንግልት ተዳርገዋል፡፡ ለብሔረሰቦች መብት ቆሜያለው የሚለው ወያኔ የድል በዓሉ ሲደርስ በአመት አንዴ የሚያስታውሳቸውና ከያሉበት በውሎ አበል እያባበለ በየአደባባዩ የሚያስጨፍራቸውና የበዓሉ ማድመቂ ያደረጋቸው ህዳጣኖች በምን ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ በቅርቡ በማህበራዊ ድረ-ገጾች የተሰራጨውና የብዙዎችን ቀልብ የሳበው የሱርማ ብሔረሰብ አባላት ላይ የደረሰው ዘግናኝ ሁኔታ የበደላቸውን መጠን በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡ ምስሉ ለሰው ልጅ ክብር ከሚገባው አያያዝ ውጭ እጅና አንገታቸውን አቆራኝተው በሲባጎ እያሰሩ ድብደባ የፈጸሙባቸው መሆኑንና የአድራጊዎቹንም ማንነት በግልጽ ያሳያል፡፡ በአገዛዙ የጎሣ ፖለቲካ ሳቢያም ኢትዮጵያውያን በዘር ተቧድነው ወደ ግጭት እያመሩ ያሉበትና እርስ በእርስም በጥርጣሬ የሚተያዩባት አገር ሆናለች፡፡

የወያኔ ሥርዓት በሂደት ይለወጣል፣ ለሕግና ለሥርዓትም ተገዢ ይሆናለ፣ ያጠበበውንም የፖለቲካ ምህዳር በሂደት የእያሰፋና የሕዝቡን የፖለቲካ ተሳትፎ እያበረታታ አገሪቱ ወደ ዲሞከራሲያዊ ጎዳና እንድታቀና ያደርጋል የሚለው የብዙዎች ተስፋ የተሟጠጠበት ደረጃ ላይ የደረስን ይመስለኛል፡፡ የመብት ጥያቄ ለሚያቀረቡ ሕፃናት ተማሪዎችም ሆነ ሥርዓቱን በአደባባይ በሃሳብ ለሚሞግቱ ጎምቱ ፖለቲከኞች የሥርዓቱ ምላሽ ጡንቻና ጠመንጃ ነው፡፡ ወያኔ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ ዘር፣ ጽኦታ፣ ኃይማኖት፣ እድሜ፣ የፖለቲካ ምልከታ ወይም ሌሎች ልዩነቶች ሳይገድቡት በጠላትነት የፈረጃቸውን ሁሉ ሲያስር፣ አስሮም ሲያሰቃይ፣ ሲገድልና ሲያስገድል፣ ሲያሳድድና ሲያፈናቅል፣ ሲዘርፍና ሲያዘርፍ፣ በሃሰት ሲከስና በሃሰት ሲያስፈርድ ቆይቷል፡፡ የሥርዓቱ ጡንቻ የሕግም ሆነ የሞራል ልጓም እንደሌለው ተደጋግሞ ተስተውሏል፡፡

ይህ አይነቱ ሁኔታ ግን ሊቀጥል እንደማይችል ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች እየታዩ ያሉት ሕዝባዊ ቁጣዎችና የለውጥ መነቃቃቶች ጠሩ ምልክቶች ናቸው፡፡ ቀደም ሲል በሙስሊሙ ማህበረሰብ የተጀመረው የሰከነ የተቃውሞ ንቅናቄ ተገቢውን ምላሽ ሳያገን እጅግ ከፍተኛ ቁጣ በተቀላቀለበት የኦሮሚያ ክልል ሕዝባዊ አመጽ ታጅቦ ሥርዓቱን ሊወጣ ወደማይችለው አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል፡፡ በወልቃይት፣ በኮንሶ እና በጋምቤላም የተቀሰቀሱት እሳቶችም ተደማምረው የአገዛዙን እድሜ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱንም ዘላቂ ሰላምና ደህንነት አደጋ ውስጥ ሊጥሉ እንደሚችሉ አደጋዎች አንጃበዋል፡፡

የአገዛዝ ሥርዓቱ ላለፉት 25 ዓመታት የገነባው አጥርና ያሰመረው ቀይ መስመር ዛሬ ግፍ ባሰከራቸው ግፉዋን እየተጣሰና እየተደረመሰ ነው፡፡ ባደባባይ በሰለጠነ መንገድ የተቃወሙትን፣ የሃሳብ ልዩነት ያላቸውን፣ የተቹትንም ይሁን ለሥርዓቱ አገልጋይ ሆነው የቆዩትንና በጥርጣሬ ያያቸውን ሁሉ በፈረጠመ ጡንቻው እየደቆሰ እዚህ የደረሰው ወያኔ ፈተና ላይ የወደቀ ይመስለኛል፡፡ ጡንቻ ልብን ቢያደነድንም፣ ማናለብኝነትን ቢያነግስም፣ አእምሮን አዶልዱሞና የማሰብ ችሎታን አቀጭጮ ለሌላው የሰው ዘር እንዳንራራ ቢያደፋፍርም መሰረቱ ግን ጥልቅ ፍርሃት ነው፡፡ በፍርሃት ውስጥ የሚኖር የፖለቲካ ሥርዓት ብቻ ነው ጡንቻውን በሕዝብ ሃብት እያሳበጠ መልሶ ቀለቡን የሚሰፍርለትን ሕዝብ እየጨፈለቀና እያስፈራራ መኖር የሚፈልገው፡፡

አገሪቷ ላይ ያንጃበቡት እነዚህ አደጋዎች የኢትዮጵያን ቀጣይ ጉዞ የሚወስኑ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ትርምስና አስፈሪ ሁኔታ በቀላሉ አገግመንና በድል አድራጊነት ልንወጣ የምንችለው እንደ እኔ እምነት ከዚህ በሚከተሉት ሃሳቦች ዙሪያ መግባባትና አብሮ መስራት ሲቻል ይመስለኛል፡፡

1ኛ. ከአፋኝና ታፋኝ የፖለቲካ አዙሪት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልንላቀቅና ጭቆናን ታሪክ አድርገን ወደ ዲሞክራሲያዊ ጎዳና ለንሸጋገር የምንችለው ግፉአን ብቻ ሳይሆኑ ግፍ ፈጻሚዎቹም አብረው ነጻ ሲወጡ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም አገርን የማዳን ትግሉ ለአገዛዝ ሥርዓቱ የመጨቆኛ መሳሪያ በመሆን እያገለገሉ ያሉ አጋር ድርጅቶችን እና ግለሰቦችን ከወያኔ ጉያ ማውጣትና የሕዝብ ወገንተኛ እንዲሆኑ ማድረግን ዋና ግቡ ማድረግ አለበት፡፡ ለዚህም በመሳሪያ አቅም፣ በፖለቲካ አደረጃጀት፣ በገንዘብም አቅም ይሁን ሰፊውን የአገሪቱን ክፍል በማስተዳደር ዕረገድ የማይናቅ ድርሻ ያላቸውን ኦህዴድ (የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት)፣ ብአዴን (የብሔራዊ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) እና ሌሎች አጋር ድርጅቶችን የትግሉ አካል እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ከወዲሁ ማመቻቸት ትግሉን ከማፋጠን ባለፈም ሊደርስ የሚችለውን የጥፋትና እልቂት አደጋም የመቀነስ ኃይል ይኖረዋል፡፡ የህዝብ እሮሮዎችና ትያቄዎች ሆኖ በማያውቅ ምልኩ በእነዚህ ሁለት ድርጅቶች ውስጥ በይፋ እየተንጸባረቀ እንደሆነ በየጊዜው ከድርጅቶቹ እያፈተለኩ የሚወጡት መረጃዎች በግልጽ ያሳያሉ፡፡ በምን መልኩ እነዚህን ድርጅቶች ከወያኔ ጉያ ማላቀቅና ነጻ ማውጣት እንደሚቻል ዝርዝሩን በጉዳዩ ላይ ለመስራት ፍላጎቱና አቅሙ ላላቸው አካላት እተወዋለሁ፡፡

2ኛ. ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከተሰነቀሩበት ቅርቃር ለማማቀቅና ዴሞክራሲ፣ ፍትህ፣ እኩልነትና ሰላም የተረጋገጠባት እና የሁሉም የሆነች ኢትዮጵያን ለማምጣት የተደራጁ የፖለቲካ ኃይሎች መቀናጀት ባለመቻላቸው የተነሳ ለለውጥ አመቺ የሆኑ በርካታ አጋጣሚዎች እየተፈጠሩ ሊጠቀምባቸው የሚችል ኃይል ባለመፈጠሩ እልም እየሆኑ አልፈዋል፡፡ ዛሬ ግን ከመቼውም ጊዜ የተሻለ ሁኔታ የተፈጠረ ይመስለኛል፡፡ በመላ አገሪቷ ሰፊ የሆነ ሕዝባዊ መነቃቃት እየተስተዋለ ነው፡፡ በመሆኑም የፖለቲካ አመራር ኃይሎች በተለይም በውጭ የሚገኙ ድርጅቶች በየመድረኩና በየመገናኛ ብዙሃኑ ከመነታረክ፣ አሰልቺ የሆኑና የተለመዱ የፖለቲካ ትንታኔያቸውን ከመስጠት፣ እርስ በእርስ ከመናቆርና አንዳንዴም በባዶ ሜዳ ‘ወሬ የፈታው’ አይነት ፉከራና ቀረርቶ ከማሰማት ተቆጥበው ለጋራና የተቀናጀ ትግል ቢሰሩ እና ያለመሪ በተበታተነ መልኩ በየቦታው የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ ንቅናቄና የለውጥ ጥያቄም አቅጣጫ ቢያሲዙት ለውጡም ይፋጠናል፤ ያንጃበቡትም አደጋዎች ብዙ የህይወት ዋጋ ሳያስከፍሉ የኢትዮጵያ ትንሳዔ እውን ይሆናል፡፡

ለመብታቸውና ለነጻነታቸው ሲታገሉ የተሰዉትን ሰማዕታት ነፍሳቸውን ይማር!

በቸር እንሰንበት!

ያሬድ ኃይለማርያም ፡ yhailema@gmail.com

The post ግፍ በገፍ የሞላበት አገር! | ከደቡብ ኦሞ እስከ መተማ፤ ከጅጅጋ እስከ ጋምቤላ፤ ከመቀሌ እስከ ባሌ፤ ከወልቃይት እስከ ኮንሶ | ያሬድ ኃይለማርያም  appeared first on Zehabesha Amharic.

የወቅታዊ ተግባራዊ ትግል (ወተት) መልዕክት: በግልጽ ጦርነት ውስጥ ካልሆን በህቡዕ ጦርነት እንሳተፍ !(ክፍል 1)

0
0
Tadesse Biru

ታደሰ ብሩ

የህወሓት/ኢህአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝን አዳክሞ ለመጣል እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት ለመመሥረት የሚደረገው ሁለገብ ትግል ዘርፈ ብዙ ነው። በህወሓት/ኢህአዴድ ላይ የታወጁ የጦርነት ዓይነቶች “ግልጽ ጦርነት” እና “ህቡዕ ጦርነት” ብለን በሁለት ልንከፍላቸው እንችላለን።

የግልጽ ጦርነት ዓይነቶች ብዙ ቢሆኑም እንኳን አንድ የጋራ ባህሪያቸው በሁለቱም ወገን ተፋላሚዎች በኩል እየፎከረ፣ እየሸለለ፣ እያወገዘ ምሬቱን በገሀድ እየገለፀ ያለ ሠራዊት አለ። በትጥቅ ትግል የተሰማሩ ጓዶች የትኛውም ስልት ይጠቀሙ ከጠላት ጋር ግልጽ ጦርነት ውስጥ ገብተዋል። በደል በዝቶባቸው ባዶ እጃቸውን አደባባይ የወጡ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አርበኞችም እንደዚሁ ከጠላት ጋር ግልጽ ጦርነት ገብተዋል።

በአንፃሩ ደግሞ ጦርነት ውስጥ መሆናቸው እንኳን ሳይገልጹ በህቡዕ አምባነኑን ሥርዓት እየተፋለሙ ያሉ ወገኖች አሉ። የዚህ ጦርነት ውጤት እንጂ ተፋማላዎቹ አይታዩም፤ እነማን እንደሆኑ መለየትም ከባድ ነው። አምባገነን ሥርዓቱ ዘይት እንዳጣ መዘዉር እርስ በርሱ ሲፋተግና ሲያልቅ ይታያል፤ ማን ዘይቱን እንደነፈገው ግን በግልጽ የሚታወቅ ነገር አይኖርም።
ህቡዕ ጦርነት እንደ ግልጽ ጦርነት ሁሉ ጠላትን የማዳከም ከፍተኛ አቅም አለው። ግልጽ ጦርነት እና ህቡዕ ጦርነት ተደጋግፈው ከሄዱ ባነሰ ወጪና ድካም አምባገነን ሥርዓትን ማዳከም ቀጥሎ ጨርሶ ማንበርከክ ይቻላል። በግልጽ ጦርነት እየተሳተፍን ካልሆነ በህቡዕ ጦርነት መሳተፍ ሁሌም በእጃችን ያሉ አማራጭ ነው።

ስለዚሆነም የዛሬው የወተት መልዕክት “በግልጽ ጦርነት ውስጥ ካልሆንን በህቡዕ ጦርነት እንሳተፍ!” የሚል ነው። “እንዴት?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የሚቀርበርበው አጭር ማብራሪያ ተዘጋጅቷል።

እያንዳንዱ ነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ሊሳተፍባቸው የሚችሉ የህቡዕ ጦርነት ስልቶች በርካታ ቢሆኑም አሻጥር፣ የስነ-ልቦና ጦርነት፣ የኢኮኖሚ ጦርነት፣ እና ኢህአዴግን እርስበርሱ ማናከስ የተባሉት ለአብነት ቀርበዋል።

ሀ. አሻጭር (sabotage) – አንድን አምባገነን የአገዛዝ ሥርዓት ለማዳከም በሥራ ከሚውሉ የህቡዕ ጦርነት የትግል ስልቶች በቀዳሚነት የማነሳው አሻጥርን ነው። “አሻጥር” የሚለው ቃል ለቅን አሳቢዎች አሉታዊ መልዕክት ይኖረው ይሆናል፤ ይህን ለመከላከል “አሻጥር ለምን ዓላማ?” እና “አሻጥር በማን ላይ?” ተብሎ መጠየቅ ይኖርበታል። የበዳዮች፣ ግፈኞች፣ ገዳዮችና ዘራፊዎች ሥራ ስኬታማ እንዳይሆን አሻጥር መሥራት ከስነምግባር አንፃር የሚያስመሰግን ተግባር መሆኑ አጽንኦት ሊሰጠው ይገባል።

የአገራችን ወታደሮችና ፓሊሶች “ሥራዬ ነው” ወይም “የታዘዝኩትን መፈፀም ሙያዬ ያስገድደኛል” እያሉ እራሳቸውን በመሸንገል ወገኖቻቸውን ይደበድባሉ፣ ይገድላሉ። ህሊና ለአለቃ ትዕዛዝ ይቅርታ አታደርግምና እነዚህ ሰዎች ወደ ህሊናቸው በተመለሱ ጊዜ ከገዛ ራሳቸው ጋር መጣላታቸው አይቀርም። ህሊና ብቻ ሳይሆን ፍትህም ይቅርታ አታደርግላቸውም። እነዚህ ወገኖች ግን የታዘዙትን እየፈፀሙ ያሉ መስለው ተቃራኒውን በመፈፀም በህቡዕ ጦርነት ሥርዓቱን መፋለምና ከህሊናቸው ጋር ታርቀው መኖር ይችላሉ። የሚገርፉ መስለው ባለመግረፍ፤ የሚገድሉ መስለው ጥይት በመጨረስ፤ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እስረኞችን በማስመለጥ፤ የነፃነት ታጋዮችን ቢያዩም እንዳላዩ ሆነው በማለፍ፤ የመሥሪያ ቤታቸውን የምስጢር ሰነዶች ለነፃነት ታጋዮች አሳልፈው በመስጠት፤ በአቅርቦት እጥረት ወይም በተሳሳተ እቅድ ምክንያት ኦፕሬሽኖት እንዲሰናከሉ በማድረግ፣ … ወዘተ በህቡዕ ጦርነት በመሳተፍ በግልጽ ሥርዓቱን በመዋጋት ላይ ያሉ ወገኖችን ማገዝ ይችላሉ።

በመብራት ኃይልና በቴሌኮሚኬሽን መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሠሩ ወገኖች ሙያቸውና የሥራ ኃላፊነታቸው ተጠቅመው በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የሚያስከትሉ የመሣሪያዎች ወይም የሲስተም ብልሽቶችን ማድረስ፤ ፕሮጀክቶችን ማጓተት ወይም ማሰናከል ይችላሉ። በፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ወገኖች በእጃቸው ትልቅ መሣሪያ እንዳለ ይገንዘቡ – ያለ እነሱ አገልግሎት ኤፈርትም ሆነ ሌሎች የሥርዓቱ አገልጋይ ቢስነሶች አገራችንን ማራቆት አይችሉም። በገንዘብ ዝውውራቸው ላይ እንቅፋቶችን መፍጠር፤ ሂሳቦቻቸውን ማዛባት፤ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ማድረግ፤ ህገወጥ ድርጊቶቻቸውን በማስረጃ ማጋለጥ (በህግ ባይቻል ለአደባባይ ዜና ማብቃት) … ወዘተ እና ሌሎች በርካታ እዚህ ላይ ያልተፃፉ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን (IT) ባለሙያዎች ሙያቸውን ተጠቀመው የአምባገነን ሥርዓቱን የ IT ሲስተም ማበላሸት ይችላሉ። እንዲህ ለማድረግ የሚደፍሩ ወገኖች በህቡዕ ጦርነት ውስጥ በግንባር የተሰፉ፤ በግልጽ ጦርነት በግንባር ከተሰፉ ጓዶች እኩል ክብር የሚሰጣቸው ናቸው።

የህቡዕ ጦርነት ተሳታፊዎች በተራቀቁ የሙያ መስኮች ውስጥ ያሉ ሰዎች አድርገን መውሰድ የለብንም። ገበሬዎች የመንግሥት ግብር ሲበዛባቸው በግልጽ ከማመፃቸው በፊት ግብርን ማዘግየት፤ ግብር ሰብሳቢውን ማጉላላት፤ ምርታቸውን ቀንሰው መናገር ይችላሉ። ቅራኔዎቻቸውን በባህላዊ መንገድ በመፍታት ወደ ፓሊስና ፍርድ መሄድን ነውር ሊያደርጉት፤ ቀጥሎ፣ “አትድረሱብን አንደርስባችሁም” ሊሏቸው ይችላሉ። ነጋዴዎች ከውጭ የሚያስገቧቸው ሸቀጦችን ዋጋ ማዛነፍ፤ ሰው ሰራሽ እጥረት መፍጠር፤ “አትሽጡ” የተባሉትን በድብቅ መሸጥ፤ “ሽጡ” የተባሉትን አለመሸጥ ይችላሉ። የመንግሥት ሠራተኞች ሥራን ማጓተት በቀላሉ ተግባራዊ ሊያደርጉት የሚችሉት ስልት ነው። የጽዳት ሠራተኞች፣ የጥበቃ ባለሙያዎች፣ የመዝገብ ቤት ሠራተኞች … ወዘተ በሥራ ላይ በመለገም ብቻ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን ይችላሉ፤ እነዚህ ወገኖች ለብዙ ምስጢራዊ ሰነዶች ቅርብ በመሆናቸው በግልጽ ጦርነት ውስጥ ያሉ ወገኞችን በከፍተኛ መጠን መርዳት ይችላሉ። በአጭሩ የመንግሥት ሠራተኞች አምባገነኑን ሥርዓት የሚያስወቅሱ በርካታ ተግባራትን ማከናወን ይችላሉ። አሻጥር እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በቀላሉ ሊሳተፍበት የሚችለው የህቡዕ ጦርነት ስልት ነው።

ታደሰ ብሩ
………. ይቀጥላል …

The post የወቅታዊ ተግባራዊ ትግል (ወተት) መልዕክት: በግልጽ ጦርነት ውስጥ ካልሆን በህቡዕ ጦርነት እንሳተፍ !(ክፍል 1) appeared first on Zehabesha Amharic.

ሲኖ ትራክ (Sino Truck) ሲኖ ጭራቅ፣ ቀይ ሽብር –ከ ሚኪያስ ግዛው 

0
0
imagesእነዚያ ቀያዮቹን የቻይኖች መኪኖች ገና ከሩቅ ሲያዩ ጭራቅ የመጣባቸው ያህል ልጆች ይርበደበዳሉ። ገና የሲኖ ትራኩን ድምጽ ሲሰሙ የከለላና መከታ አያያዝ ስልትን ያልተማሩት እነዚያ ጨቅሎች የሚደበቁበትን ቦታ ለመምረጥ ሲባዝኑ ይታያሉ። ሲኖ ትራክን ገና ከሩቁ ስታዩ…” እያሉ ወላጆቻቸው ጠዋት ጠዋት የሚነግሯቸው የጥንቃቄ አወሳሰድ ምክር ትምህርቱን አስረስቷቸዋል። ይህንኑ አደገኛ ቀይ መኪና ወላጆች በዘመናቸው ካዩት ዘግናኝ ድርጊት ጋር በማመሳሰል ቀይ ሽብር” ብለውታል።

ሃገራችን ኢትዮጵያን አንገቷን ካስደፋት ትላልቆቹ ክፋቶች መካከል የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ስግብግብነትና የኅሊና መሸርሸሩ እጅግ አሳዛኞቹ ናቸው። ሃገር የቱንም ያህል ለማች፣ በሰማይ ጥቀስ ሕንጻዎች አሸበረቀችም ሆነ ዘመናዊ መንገዶች ተነጠፉላት ሥነምግባርና ግብረገብነት ከተሸረሸሩ ውሃ ቢወቅጡት እምቦጭ” ነው።

በንጉሡም ይሁን በደርግ ዘመን ሙስናና ጉቦ ቢኖርም እንዲህ እንዳሁን ሕዝቡን አላንገሸገሸም ነበር። አብዛኛው ሰው ፈሪሃ እግዚአብሄርነት በውስጡ ስላደረ በኅሊናው ይተዳደር ነበር። በደርግ ዘመን መንጃ ፍቃድ በጉቦ አውጣ፣ መንጃ ፈቃድ ቤቱ ድረስ መጣለት፣ ሲባል ሰው ወሬውን እንደ ጉድ ተገረሞ ያዳምጥ ነበር። ሰውንም ራስንም አደጋ ውስጥ የሚከት መርዝን በጉቦ መሸጥ የቴክንሽያኑን ኅሊና ቢስነት ደረጃ መገመቻ ነበር። መንጃ ፈቃድ በጉቦ መስጠት የሞት ፍርድ ያህል ነበር። ዛሬ እፍረት መሆኑ ቀርቶ ሁሉም ነገር ሙስናና ጉቦ ሆኗል። ሙስና ሞትንም ትሸጣለች። መሬት በጉቦ ይቸረቸራል። ባለገንዘብ መሬት ገዝቶ ጭሰኞች ይቀጥራል። የሠማይ ስባሪን ያህል ሹመት ተሸካሚ ግለሠብ ሕንጻ አከራይ ሁኗል። የሕዝብ አደራ የተሸከመው አገልጋይ አስመጭና ላኪ ነጋዴ ሆኗል። አለማየሁ እሼቴ ምናልባት በስድሳዎቹ መግቢያ ላይ ነው መሰለኝ፣ ባማረ ድምጹ – “ማን ይሁን ትልቅ ሰው” – በሚለው ዘፈኑ ላይ – “እባክህ አምላኬ ደጉን ዘመን አምጣ” – ሲል ለእግዚአብሄር ምልጃውን አቅርቦ ነበር። የየኔውን ዘመን ገምቶ አምላኩን የተማጸነው ከያኒ ዛሬስ ምን ታዝቧልምናልባት አለማየሁ እሼቴ እንደገና ቢያንጎራጉር እባክህ አምላኬ ያን ዘመን መልሰው” ይል ይሆንበእርግጥ የዘንድሮው ከተሻለ ያምናው ታሪክ ነበር። አለመታደል ሆኖ እንጂ ከዘመን ዘመን አሸጋግረን” ማለት ከኋለኛው ዘመን ወደ አዲሱ ዘመን በላቀ መንፈሳዊ ጽናት፣ በተሻለ ሠላምና ብልጽግና አሸጋግረን ማለት ነው። ልማታዊው መንግሥት” ሥነምግባሩንና ግብረገብነቱን ሸርሽሮ ሁሉንም ደረመሰው።

ሲኖ ትራክ ምንም አላጠፋም። ሲኖ ትራክ በቻይና የተፈረበከ ፈጣን ጉልበታማ መኪና ነው። ጥፋቱ የሹፌሩ ነው። ጥፋቱ የአሽከርካሪው ነው። በእርግጥ ጥፋቱ የአሽከርካሪው አይደለም። ጥፋቱ የሥርዓቱ ነው። ጥፋቱ በእድሜው ለጋ ለሆነው ወጣት ወይም ሱሰኛ ካለችሎታው አራተኛና አምስተኛ ደረጃ መንጃ ፈቃድ የሚሰጠው የየክልሉ መሥሪያ ቤት ነው። ቀድሞ መንጃ ፈቃድ በትምህርት ዲግሬ ከማግኘት ያላነሰ ፈተናና ውጣ ውረድ ነበረው። ቀድሞ መንጃ ፈቃድ ለማግኘት ከሁለተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ፣ ከሶስተኛ ወደ አራተኛ፣ ከአራተኛ ወደ አምስተኛ፣ ለመዝለል እጅግ ከፍተኛ ልምድንና ብስለትን ይጠይቅ ነበር። ዛሬ መንጃ ፈቃድ በጉቦ መያዝ ከጉልት በቆሎ የመሸመትን ያህል እንኳን አይከብዱም። ዛሬ ሹፌሮችንና ረዳቶችን ለይቶ ማየት አይቻልም። ሹፌሩ አራራ ይዞት ጫት ለመቃም አንዱ ሥርቻ ጎራ ሲል ረዳቱ መኪናውን ያሽከረክራል። የታክሲው አሽከርካሪ ዕቃ ለመግዛት ሱቅ ሲገባ ወያላው ሁለት ቢያጆ ሰርቶ ይጠብቀዋል። የታክሲው ባለቤት ይህን ሁሉ ጉድ አያውቁም። ቢያውቁም፣ ታክሲው የዕለቱን ገቢ ይዞላቸው እስከመጣ ድረስ ለተሽከርካሪው ደህንነትም ሆነ ለተሳፋሪዎቹ ነፍስ፣ ቅጠል ተሸክማ አስፋልቱን ለምትሻገረዋ ባልቴትም ሆነ ወደ ቄስ ትምህርት ቤት ለሚጓዙት ጨቅሎች አይጨነቁም። እሳቸውስ ቢሆን ምን ያድርጉ – ለሾፌራቸውና ረዳቱ መንጃ ፈቃዱን የሠጠው መሥሪያ ቤትን የሕዝብ ጉዳይ ካልቆረቆረው።

ሥርዓቱ መንጃ ፈቃድ አስጣጡም ላይ ሆነ የበሰለ ልምድ ያላቸው የከባድ መኪና አሽከርካሪዎችን በአግባቡ እንዲሰማሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ነበረበት። ይህ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ የሚታየው የበርካታ ሰዎች ውድ ሕይወጥ መጥፋትም ሆነ የንብረት መውደም ባልተከሰተ ነበር። ሥርዓቱ ዘመናዊ መንገድን ማንጠፍ ብቻ ሳይሆን አነዳድን፣ በርጋታ መቅደምንም ሆነ በመስመሮቹ ማህል ረግቶ የመንዳትን ሥነጥበብ ቀርጾ ትምህርቱን ማሰራጨት ነበረበት። ፈጣን መንገድን ሥልጣኔ ለጎደለው አሽከርካሪፈንጭበት” ብሎ መልቀቅ ራሱ ቀይ ሽብርን” ማፋፋም ነው። ሲኖ ትራኮች ቀይ ሽብር” የተባሉት ለዚህ ነው። ከአዲስ አበባ አዳማ የተዘረጋው አውራ ጎዳና (motor way) ላይ መንዳት ከተክለ ኃይማኖት መርካቶ እየተሽለኮለኩ የመንዳትን ችሎታ ማሳያ መንገድ አይደለም። በፈጣን መንገድ ላይ ፍሬቻ ሳያበሩ መታጠፍ ወደ ሽንኩርት ተራው ተጋፍቶ እንደመግባት ቀላል አይደለም። በዘመናዊው መንገድ መንዳት ሥልጣኔን” እንጂ አራዳነትን” አይጠይቅም። የመንገዶቹን መስመሮች ማህል (driving field)ጠብቆ መንዳት፣ ወደ ሌላ መሥመር ለመግባት ፍሬቻ ማሳየት (turn signal)፣ እስር የተወተፈ መኪና ወይም ሞተር ሳይክል መኖር አለመኖሩን (blind spot) ማረጋገጥ፣ በጥንቃቄ የመቅደም ስልትን (take over) እንዲሁም ፍጥነትን መቆጣጠርና (speed control) ከፊት ካለው ተሽከርካሪ እርቀትን መጠበቅ (safe gap) ወዘተ፣ የመንዳት ችሎታ ብቻ ሳይሆን ሥልጣኔና (civilization) ለነፍሳት ሁሉ የመጠንቀቅ ሠብዓዊነት (humanity) ነው። በከተማ ውስጥ ለእግረኞች ቅድሚያ መስጠት ከሁሉም በላይ አስተዋይነት ነው። ምናልባት መኪና ማሽከርከር ፈቃድ ያላቸውን ዲያስፖራዎችን አሰባስቦ በአውራጎዳና ላይ አነዳድን በኤግዚቢት መንገድ የማሳየት ወርክ ሾፕ ቢዘጋጅ ጠቃሚ ይመስለኛል። ይህን ስል ካገራችን በቂ ችሎታ ያላቸው አስተዋይ አሽከርካሪዎች ጠፍተዋል ማለቴ ሳይሆን የውስጡንም የውጭውንም ልምድ መለዋወጡ ትምህርትን ከመቅሰምያ ዘዴዎች አንደኛው ነው ማሌቴ ነው። አምላክ ሀገራችንን፣ ወገናችንን ይጠብቀን፣ አሜን።

The post ሲኖ ትራክ (Sino Truck) ሲኖ ጭራቅ፣ ቀይ ሽብር – ከ ሚኪያስ ግዛው  appeared first on Zehabesha Amharic.

በኮንሶ ገበሬዎች በስርዓቱ ወታደሮች የተገደሉትን 3 ሰዎች አስከሬን ይዘው አደባባይ ለተቃውሞ ወጡ |ቪዲዮ ይመልከቱ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኮንሶ የተነሳው ሕዝባዊ ቁጣ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በካራት ከተማ የኮንሶ ገበሬዎች ከትናንት በስቲያ ማርች 13, 2016 በስርዓቱ ወታደሮች የተገደሉትን 3 ወገኖች አስከሬን በመያዝ ዛሬ በአደባባይ ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል::

በዳዋና ከተማ የስርዓቱ ወታደሮች ከገደሏቸው መካከል የ3ቱን አስከሬን ለመቅበር የወጡት እነዚሁ ሰልፈኞች ቁጣቸውን ገልጸዋል::
ቪዲዮ ይመልከቱ::

Screen Shot 2016-03-15 at 7.51.38 AM

The post በኮንሶ ገበሬዎች በስርዓቱ ወታደሮች የተገደሉትን 3 ሰዎች አስከሬን ይዘው አደባባይ ለተቃውሞ ወጡ | ቪዲዮ ይመልከቱ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያ ወዴት? –ግርማ ሞገስ

0
0

ማክሰኞ መጋቢት 6/2008 (Tuesday March 15/2016)

 

Girma Mogesየዛሬው ያረጀ አምባገነናዊ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት እንደ ትናንቱ ታላቅ ወንድሙ የደርግ መንግስት የኢትዮጵያችንን የነገ ተረካቢዎች ህጻናት እና ወጣቶች እያሰረ እና በጥይት እየገደለ የስልጣን ዘመኑን ማራዘም ብልህነት አድርጎ ተያይዞታል። 100% መርጦኛል የምትለውን  ህዝብ እየገደልክ በስልጣን ላይ መቆየት አትችልም። ያረጀው ወጣቱን እየበላ የሚኖርበት ዘመን በኢትዮጵያችን ማክተም አለበት። ወጣቱ አገሩን ካረጀው ህወሃት/ኢህአዴግ መንጋጋ ፈልቅቆ በመውሰድ ማስተዳደር መጀመር አለበት። ሰላማዊው ትግል ገና መጀመሩ ነው። እገሌ ከገሌ ሳንል በአገር ውስጥ እና በውጭ የምንኖር የአገር ሽማግሌዎችም ሆነን ተቃዋሚ ፓርቲዎች የወጣቱ ምኞት ይሳካ ዘንድ ተገቢ የአጋዥነት ሚናችንን ልንጫውት ይገባል። ለማንኛውም ይህቺ አጭር ጽሑፍ ባለፉት አራት ወሮች በኢትዮጵያችን ሰላማዊ አቤቱታ በማሰማታቸው እና ሰላማዊ ተቃውሞ በማድረጋቸው ብቻ በኦሮሚያ ክልል በጥይት ሕይወታቸውን ለተነጠቁ ህጻናት እና ወጣቶች ማስታወሻ/መታሰቢያ ትሆን ዘንድ ምኞቴ ነው።!

 

ኢትዮጵያ ወዴት? በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ውይይት እንድከፍት ያነሳሳኝ ኢትዮጵያችን ባለፉት አራት ወሮች ያደረገችው የለውጥ እንቅስቃሴ፣ እንቅስቃሴውን በመምራት ላይ ያሉት ወጣቶች የምር ስራ ላይ መሆናቸው እና የህዝባችን ብስለት ተደማምረው ነው። በሰፊው እንደሚታወቀው ባለፉት አራት ወሮች የኦሮሚያ ወጣት ሳይገድል እየሞተ የለውጥ አስፈላጊነትን በሰላማዊ ተቃውሞ መፈክሮቹ ሲያሰማን ቆይቷል። ዛሬ በህይወት የሊሉትም የለውጥ ጥሪ ድምጻቸው ይሰማናል። እንግዲህ በአንድ አገር ባለፉት አራት ወሮች ያስተዋልነው አይነት በአይን የሚታይ፣ በጆሮ የሚሰማ፣ በእጅ የሚዳሰስ አልፎም በህልም ሳይቀር የሚመጣ የለውጥ እንቅስቃሴ ሲፈጠር ማንኛውም አገሩን እና ህዝቡን የሚወድ ዜጋ በጭንቅላቱ እና በህሊናው “ወዴት እየሄድን ነው?” የሚለው ጥያቄ መመላለሱ የማይቀር ነው። የዚህ ጽሑፍ ግብም በዚህ ጥያቄ ዙሪያ የኢትዮጵያን የቀድሞዎቹን የለውጥ እንቅስቃሴዎች በአጭሩ በማስታወስ እና የዛሬውን የለውጥ እንቅስቃሴ በመመርመር “ወዴት እየሄድን ነው?” ለሚለው ጥያቄ አንባቢን ሊያወያይ የሚችል መልስ መስጠት ነው። በተጨማሪ ይህ ጽሑፍ በመኪያሄድ ላይ የሚገኘውን የሰላማዊ ትግል አቅም ውቂያኖስነት ያመላክታል። የሰላማዊ ትግሉን ደህንነት እና ቀጣይነት ዘላቂ ሊያደርጉ የሚችሉ ጥቂት ምክሮችንም ይሰነዝራል።

 

ኢትዮጵያ ባለፈው በ20ኛው እና አሁን በያዝነው በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለለውጥ በርካታ እንቅስቃሴዎች አድርጋለች። በኢትዮጵያችን በግልጽ የሚታይ እና የሚጨበት የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት እንቅስቃሴ የተጀመረው በ1950ዎቹ በመንግስቱ ንዋይ በተመራው መፈንቅለ መንግስት እና መፈንቅለ መንግስቱን ደግፎ እና ዘውዳዊውን አገዛዝ ተቃውሞ በአዲስ አበባ መንገዶች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረገው  የኢትዮጵያ ተማሪዎች ነበር ማለት ይቻላል። የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ መሬት ለአራሹ፣ የብሔር እኩልነት፣ ህዝባዊ መንግስት፣ የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብ ወ.ዘ.ተ. መብቶች የሚሉትን የመብት መከበር ጥያቄዎች መፈክር ቀርጾ ቀደም ብለው የነበሩትን ጭቆናዎች ተከታታይ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች በማድረግ ለህዝብ አስተዋወቀ። ይህን በማድረጉ የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ በርካታ አባላቱን ለዘውዳዊው አገዛዝ የጸጥታ ኃይሎች ጥይት ከፍሏል። የዚሁ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ውጤት የሆኑት በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ አንጋፋዎቹ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢሕአፓ እና መኢሶንም የዴሞክራሲ ሽግግርን ጥያቄ አንስተው አንድ ትውልድ ከፍለዋል። ሻቢያ፣ ኦሌፍ እና ህወሃትም ይኸው የተማሪዎች እንቅስቃሴ የወለዳቸው ተቃዋሚ ድርጅቶች ናቸው። ያም ሆነ ይኽ ዘውዳዊውን አገዛዝ የገረሰሰው ህዝባዊ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ድል ፍሬ በአውሬው ወታደራዊ ደርግ ተሰረቀ። በዚህ አይነት እስከዚህ ድረስ የተደረጉት እንቅስቃሴዎች የተፈለገውን የፖለቲካ ለውጥ አላመጡም። ከዚያ ከደርግ ወደ ህወሃት/ኢህአዴግ የተደረገው የመንግስት ስልጣን ሽግግር ወደ ነፃነት እና ዴሞክራሲ ሽግግር ያመራል የሚል ተስፋ በብዙ ወጣቶች ዘንድ ፈጥሮ ነበር። እሱም ሳይሆን ቀርቷል። በቅርቡ ደግሞ በምርጫ 97 ሰላማዊ የፖለቲካ ስርዓት ለውጥ ሽግግር ቢሞከረም በአንድ በኩል በህወሃት/ኢህአዴግ ስልጣን ጥመኛነት እና በሌላ በኩል ደግሞ በተቃዋሚው መካከል ህብረት አለመኖር፣ የድል ሰብሳቢነት ልምድ አልባነት እና የሰላማዊ ትግል ቀጣይነት ባህል ማጣት ተደማምረው የተገኘው መለስተኛ ድል ሳይቀር ባክኖ በምትኩ በቆሻሻው መለስ ዜናዊ የሚመራ ፍጹም አምባገነንነት ሌባ መንግስት በኢትዮጵያ ነግሷል። እነዚህ ሁሉ በወጣቶች የተመሩ እንቅስቃሴዎች የፖለቲካ ምኞታቸውን (ግባቸውን) ተፈጻሚ ማድረግ ባይችሉም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ብሩህ ወጣቶችን በመስዋትነት ከፍለው ሄደዋል።

 

በየዘመኑ በስልጣን ላይ የነበሩት አምባገነኖች የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ሲሉ የለውጥ ጥያቄ ያነሳውን ወጣት ቢፈጁም በሚያፈቅሩት ስልጣን ላይ ብዙም ሳይቆዩ  እነሱም ጠፍተዋል። ካለፈው ስህተታቸው መማር አለመቻል የአምባገነኖች ሁሉ የጋራ ባህሪያቸው መሆኑን ታሪክ ደግማ ደጋግማ ታስተምራለች። እነሱም ደግመው ደጋግመው አይማሩም።  ስለዚህ ዛሬም በስልጣን ላይ የሚገኘው አምባገነናዊ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት እንደ ቀድሞው በመንግስቱ ኃይለማሪያም ሲመራ እንደነበረው አምባገነኑ ደርግ ስልጣን ከያዘ ወዲህ ባለፉት 22 አመቶች ግድም ውስጥ ቀደም ሲል በፍጹም አምባገነኑ ሟቹ መለስ ዜናዊ መሪነት አሁን ደግሞ በቀጣዩ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መሪነት ሰላማዊ አቤቱታ እና ሰላማዊ ተቃውሞ በማሰማታቸው ብቻ በየአደባባዩ በጥይት አንደበታቸውን የተነጠቁ (የተገደሉ) ወጣቶች ቁጥር ጥቂት አይደለም። ጥቂት ልጥቀስ። እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1994 ዓ.ም. የኤርትራ ሬፌረንደም በሰላማዊ መንገድ በመቃወማቸው ወጣቶች በህወሃት/ኢህአዴግ ጥይት ተደብደበዋል። በ2001 ዓ.ም. ድህረ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ የተደረገውን ስምምነት በመቃወማቸው ወጣቶች በህወሃት/ኢህአዴግ ተደብድበዋል። የ2005 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 1997) ምርጫን ተከትሎ በሰላማዊ መንገድ የህዝብ ድምጽ ይከበር በማለታቸው ብቻ ሰላማዊ አቤቱታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮባቸው በህወሃት/ኢህአዴግ ጥይት ወጣቶች በግንባራቸው ሳይቀር በጥይት ተደብድበዋል። በየአደባባዩ የተረሸኑት ወጣቶች አይረሱንም። በ2014 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በህዳር ወር 2008) ዓ.ም. ጀመሮ የኦሮሚያ ወጣቶች ማስተር ፕላኑን በመቃወማቸው፣ የኦሮምኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋ ይሁን በሚል በጀመሩት ሰላማዊ አቤቱታ እና ተቃውሞ የአምባገነኖችን ጥይት በግንባር፣ በአንገት፣ በደረት እና በቀረ አካላቸው እየተቀበሉ እንዲወድቁ መደረጋቸው ትኩስ ሐዘናችን ነው። የኢትዮጵያን ወጣት የነፃነት እና የዴሞክራሲ ጥም በግድያ ማቆም እንደማይቻል የማይማሩት አምባገነኖች ብቻ ናቸው።

 

በነፃነት እና በዴሞክራሲ መኖር የአሜሪካኖች ወይንም የእንግሊዞች ወይንም የአውሮፓውያን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የሰው ዘር ሁሉ ምኞት እና ፍላጎት ነው። አለም አቀፋዊ መስፈርትን የሚያሟሉት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት፣ የመቃወም፣ መሪዎችን የመምረጥ ነፃነቶች በኢትዮጵያ የሉም።! ልብ በሉ! እነዚህ ነፃነቶች “ለሶስት ሺ አመት ‘ነፃነቷ’ ተከበሮ የኖረች ኢትዮጵያ” የምንለው አይነት “ነፃነት” አይደሉም። እነዚህ ነፃነቶች ጎረቤት ኤርትራን የሚያስተዳድረው ሻቢያ የሚለፍፈው አይነት “ነፃነትም” እንዳልሆኑ ልብ በሉ። እነዚህ ነፃነቶች የመናገር፣ የመቃወም፣ የመደራጀት፣ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተሰብስቦ ተቃውሞ ማሰማትን፣ ወ.ዘ.ተ. የመሳሰሉትን ያካትታል። ለነዚህ ነፃነቶች መኖር ደግሞ ዴሞክራሲ የግድ መኖር አለበት። ዴሞክራሲ ከሌለ ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት፣ የመቃወም፣ መሪዎችን የመምረጥ ነፃነቶች አይኖሩም። እነዚህ ነፃነቶች እና ዴሞክራሲ አይነጣጠሉም። ስለዚህ በነፃነት እና በዴሞክራሲ ስርዓት መተዳደር የኢትዮጵያውያንም ምኞት እና ፍላጎት በመሆኑ ላለፉት አርባ እና ሃምሳ አመታት በተከታታይ የመጣ የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ እነዚህን ጥያቄዎች አንስቷል።

 

በኦሮሚያ ክልልም ወጣቶች ያነሷቸው ጥያቄዎችም የተለዩ አይደሉም። የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት ይከበር፣ የዜጎቿን ሰብዓዊ  መብቶች ይከበሩ፣ የዜጎች የመናገር፣ የመቃወም፣ የመምረጥ፣ የዴሞክራሲ መብቶች ይከበሩ የሚሉ ናቸው። ኢትዮጵያ የህግ-በላይነት የሚከበርባት  እና የዜጎቿን መብት የምታከብር አገር እንድትሆን የሚጠይቁ ናቸው። እነዚህ ጥያቄዎች ኢትዮጵያችንን ወደ ኋላ የሚጎትቱ ሳይሆኑ ወደፊት፣ ወደ ስልጣኔ የሚገፉ ናቸው። ባለፉት አራት ወሮች እንዳስተዋልነው ከሆነ ለእዚነህ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ሽግግር ጥያቄዎች በተለይ በኦሮሚያ ክልል የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ወጣት ያልተመጣጠነ መስዋዕት ከፍሏል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን ዳር ቆሞ በመመልከት የምናግዘው የአምባገነኖች የገዢነት ዘመን መሆኑን የምር ልብ ልንለው የሚገባ ጉዳይ ነው። አምባገነኖች ችግሩን ይበልጥ አወሳስበው ኢትዮጵያችንን ይበልጥ ወደ ተወሳሰበ እና ልንፈታው ወደ ማንችለው ችግር ውስጥ ሊከቷት እንደሚችሉ አገር ወዳዶች በሙሉ ከወዲሁ ልናስብበት የማይገባ አብይ ጉዳይ ነው። ዛሬ አምባገነኖች ኦሮሚያን በወታደራዊ እዝ እናስተዳድራልን ማለት ጀምረዋል። ይኽ እርምጃቸው ችግሩን ይበልጥ ማወሳሰብ ነው። አምባገነኖች በተቀነባበረ ህዝባዊ እምቢተኛነት ተገደው ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመጡ እስካልተደረጉ ድረስ ወይንም እንዲሄዱ እስካልተደረጉ ድረስ ቀዳሚ ግባቸው ለሆነው ስልጣን ሲሉ ችግሩን ይበልጥ ማወሳሰባቸው የማይቀር ነው። በኦሮሚያ የተነሳው መጠነ ሰፊ ህዝባዊ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነገ በአማራው ወይንም በደቡብ ክልል ቢነሳ የአምባገነኖች መፍትሄ እነዚህንም ክልልሎች በወታደራዊ እዝ ማስተዳደር እንደሚሆን ከወዲሁ መገመት ይቻላል። ሁልሽም ተራሽን ጠብቂ መሆኑ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የምንል አገር ወዳዶች በሙሉ በቻልነው መንገድ እና ባለን አቅም ሁሉ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ልንተባበር ይገባል። ስለዚህ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ህዳር ሁለት 2 ቀን በኦሮሚያ ጊንጪ ከተማ ተጀምሮ ባለፊት አራት ወሮች ውስጥ ወደ ቀረው ኦሮሚያ በመዝመት በወለጋ፣ በአንቦ፣ በጅማ፣ በአርሲ፣ በምስራቅ ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በምስራቅ ሐረርጌ፣ በምዕራብ ሐረርጌ፣ በቦረና፣ በባሌ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ውስጥ የተቀጣጠለው ሰላማዊ ተቃውሞ ቀጣይነት ሊኖረው እና ወደ ቀረው ኢትዮጵያ እንድ ሰደድ እሳት መቀጣጠል አለበት። ማለትም ሰላማዊው ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ይበልጥ ሊሰፋ፣ ይበልጥ ሊቀናበር እና አመትም ይፍጅ ከዚያ በላይ ቀጣይነቱን እንዳያጣ ማድረግ አለብን።

 

ቀደም ሲል መንግስት በኦሮሚያ የተፈጠረው ተቃውሞ መንስዔው የመልካም አስተዳደር እጦት ነው ሲለን ነበር። ለመሆኑ መልካም አስተዳደር ምንድን ነው? የፖለቲካ መልካም አስተዳደር አለመኖር ህጋዊ በሆነበት አገር ህዝብን በማጭበርበር ጊዜ እያባከኑ የስልጣን ዘመንን ለማራዘም እስካልሆነ ድረስ እንዴት ስለኢኮኖሚ እና ስለ ማህበራዊ ጉዳዮች መልካም አስተዳደር ማውራት ይቻላል።  ህወሃት/ኢህአዴግ በተደረጉ ምርጫዎች በሙሉ ስልጣን ላይ መቆየት የቻለው በፖለቲካ ሙስና ድምጽ በመስረቅ ነው። ይህ ደግሞ እራሱ ህወሃት/ኢህአዴግ ይሁን ብሎ ህጋዊ ያደረገው የፖለቲካ መልካም አስተዳደር አልባነት ነው። በዚህ የፖለቲካ ሙስናው ተባብረው በኦሮሚያ በ100% እንዲያሸንፍ ያገዙትን የኦፕዲኦ የፖለቲካ ሹሞች እና ካድሬዎች ዛሬ ዞሮ በመልካም አስተዳደር ማጉደል ቢከሳቸው ኩምክና ከመሆን ያለፈ ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ አይሆንም። በዚህ የፖለቲካ ሙስና ተግባሩ ነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ እንዳይደረግ በየክልሉ የሚተራመሱ ፀረ-ነፃነት እና ፀር-ዴሞክራሲ ካድሬዎቹን በየጊዜው በሚደረጉ ምርጫዎች ተቃዋሚዎችን በማዋከብ፣ በማሰር እና ድምጽ በመዝረፍ የፖለቲካ ሙስና ተግባር እንዲተባበሩት ደሞዝ እየከፈላቸው አይዟችሁ ሲላቸው ከርሞ ዛሬ የህዝብ ተቃውሞ ሲፈጠር ተጠያቂዎቹ እነሱ እንጂ እኔ አይደለሁም ማለቱ የንቀቱን መጠን ያሳየናል።

 

ዐርብ ቀን መጋቢት አንድ 2008 (March 10/2016) ደግሞ የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ ባለፉት አራት ወራት ውስጥ በኦሮሚያ እና በቀሩት የሃገሪቱ ክልሎች ውስጥ ለተፈጠረው የህዝብ ቅሬታ መንግስታቸው እና ፓርቲያቸው ሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስዱ አስታወቁን። ይህ ኃላፊነትን የመቀበል እርምጃ ቀደም ብሎ መደረግ የነበረበት ትክክለኛ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። ዘግይቶ በመምጣቱም አንቀበልም ባንልም ቃላቸውን በተግባር መደገፍ አለባቸው። ስለዚህ ፓለቲካዊ ኃላፊነትን በመውሰድ በአገሪቱ ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂ የሆኑ የፖለቲካ ሹሞችን ከስልጣን ማባረር አለባቸው። ህጋዊ ኃላፊነትም  መውሰድ አለባቸው። ስለዚህ ግድያ የፈጸሙ ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ፣ ሰላማዊ ተቃውሞ በማሰማታቸው ብቻ ለተገደሉ ወጣቶች ቤተሰቦች ካሳ መክፈል፣ እነ በቀለ ገርባን፣ እነ በቀለ ገና እና የመሳሰሉትን የኦፌኮ መሪዎች፣ አባላት፣ እና ደጋፊዎች እንዲሁም ጉዳዩን በመዘገባቸው የታሰሩ የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እና የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን በፍጥነት መልቀቅን ያካትታል። ችግሩ ግን “ይቅርታ መጠየቅ” እና “ስህተቴን ተቀብያለሁ” ማለት የህወሃት የቅርብ ጊዜ ማጭበርበሪያ ፈሊጥ እየሆነ መምጣቱን ካወቅን ውለን አድረናል። የህወሃት ይቅርታ ማለት አንተም ተቃውሞ አቁም እኔም ወደ ቀድሞ ገዢነት ስራዬ ልመለስ ማለት ነው። በአንድ በኩል ኦሮሚያን በወታደራዊ እዝ አስተዳደር ስር ለማድረግ ሽር ጉድ እያለ በሌላ በኩል “ይቅርታ” ማለት ቅንነትን አያሳይም።  ይኽ ሁሉ የህወሃት/ኢህአዴግ ግራ እና ቀኝ እስክስታ የሚያሳየን የተነሳውን ሰላማዊ አቤቱታ እና ተቃውሞ በራሱ አነሳሽነነት ፈቅዶ  (ሳይገደድ) በሰላማዊ መንገድ መፍታት ፍጹም ባህሪው እንዳልሆነ ነው። በጫካ ተወልዶ እና ተቃዋሚዎችን በመግደል አድጎ  ስልጣን ላይ ከወጣ ወታደራዊ ድርጅት ዴሞክራሲያዊ ጸባዮችን መጠበቅ የለብንም። ላብራራ።

 

እንደሚታወቀው ህወሃት ወታደራዊ ድርጅት ነው። በጦር ሜዳዎች የገጠሙትን ተመሳሳይ ወታደራዊ ድርጅቶችን TLF (የትግራይ ተወላጆች ድርጅት), EDU, EPRA/EPRP, DERG በጦር ሜዳ ደመሰሰ። የህወሃት መሪዎች እና የTLF (የትግራይ ተወላጆች ድርጅት) መሪዎች አብረው ለመስራት ህብረት ፈጥረናል ተባብለው እራት ከበሉ በኋላ በእምነት በህውሃት ካምፕ በተኙበት በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በጥይት ተደብድበው የተገደሉት። አረመኔው ህወሃት መንግስት ሊሆን አካባቢ ደግሞ የመንግስት መዋቅር (ዛሬ ፈደሬሽን የሚለንን) እንደሚከተለው አቋቋመ። በህዝብ ቁጥራቸው የሚፈራቸውን ኦሮሞዎችን፣ አማሮችን እና የደቡብ ህዝቦች በሞግዚትነት (በጠባቂነት) የሚገዙለትን (1) ኦፒዲዎ ፣ (2) ቀደም ሲል ከኢህአፓ ተገንጥሎ እራሱን EPDM ብሎ ሲጠራ የነበረው እና በስተኋላ ለTPLF የገበረውን ድርጅት (ብአዴን መሰለኝ የአሁኑ ስሙ?)፣ (3)  የደቡብ ህዝቦችን የሚገዛለት (ዛሬ በኃይለ ማሪያም ደሳለኝ የሚመራው) ድርጅት ፈጥሮ እና (4) ህወሃትን ጨምሮ፣ አራቱን ያካተተ ኢህአዴግ የተሰኘ ቡድን ፈጠረ። በተጨማሪ (5) በህዝባቸው ቁጥር የማይፈራቸውን እንደ እነ ቤንሻንጉል፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ እና የመሳሰሉትን ህዝቦችን ደግሞ አፍነው የሚገዙለት እንደ አስፈላጊነቱ የሚያነጋግራቸውን ድርጅቶች ደግሞ “አጋር ድርጅቶች” ብሎ ሰየማቸው። በዚህ አይነት ፌዴሬሽን ፈጠርኩላችሁ ብሎ ህወሃት ኢትዮጵያን ጠቅሎ በመግዛት ላይ ይገኛል።

 

የፈደሬሽን የሚለው አወቃቀር ትርጉም ከሞላ ጎደል አገርን በጋራ ማስተዳደርን አካባቢን ደግሞ ህዝቦች በግላቸው እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል ዴሞክራሲን ከላይ ወደ ታች የሚያደርስ የፖለቲካ አወቃቀር ነው። በሃቀኛ ፈዴሬሽን የፌዴራል መንግስት በየመንደሩ በካድሬዎች አማካኝነት ህዝብን የሚያሰቃይበት ምክንያት አይኖርም። የህወሃት ፌዴሬሽን ግን በዘር ከፋፍሎ የመግዣ መዋቅር ሲሆን በዚህ ላይ በ 1 ለ 5  የተሰኘው ጠርናፊ መዋቅር ጨምሮበት ህወሃት እስከ ቤተሰብ ድረስ ፖለቲካዊ ቁጥጥር ማድረግ ችሏል። ደርግ እስከ ቀበሌ ድረስ ብቻ ነበር ህዝብን የሚቆጣጠረው። ህወሃት ግን ከደርግ ዘመን የከፋ አምባገነናዊ የፖለቲካ ማዕከላዊ አገዛዝ ስርዓት በኢትዮጵያ አስፍኖ ኢትዮጵያን ህዝብ እስከ ቤተሰብ ደረጃ ወርዶ አፍኖ በመግዛት ላይ ይገኛል። ስለዚህ የህወሃት/ኢህአዴግ ፈዴሬሽን መለወጥ አለበት። 1 ለ 5 የሚለውም ጠርናፊ መዋቅር መፍረስ አለበት።

 

ከፍ ብለን እንዳነበብነው ህወሃት ስልጣን ላይ የወጣው በምርጫ ሳይሆን በጠበመንጃ ነው። ምርጫ የሚባለው ጣጣ ውስጥ የገባውም ወዶ ሳይሆን ተገዶ ነው። ከሶቪየት ህብረት ውድቀት በኋላ ምዕራቡ (አሜሪካ እና ምዕራብ አውሮፓ) ነፃ ፉክክር እና ምርጫ አዲሱ የአለም ስርዓት ነው በማለታቸው እርዳታቸው እና ድጎማቸው እንዳይለየው ሲል የማይተዋወቀውን እና የማያምንበትን የብዙሃን ፓርቲ እና የምርጫ ፖለቲካ ስርዓት ተቀብያለሁ አለ። ከዚያ በምርጫ ህዝቡ ከስልጣን እንዳያወርደው ህወሃት/ኢህአዴግ ስልጣን ላለመልቀቅ ሙሉ በሙሉ በፖለቲካ ሙስና ተሰማራ። ነፃ ምርጫ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑትን ሶስቱን የመንግስት ቅርንጫፎች ጠቅሎ ያዘ፣ ነፃ ፕሬስ እንዲዳከም ወይንም እንዳይኖር አደረገ፣ የምርጫ ቦርድ ፈጣሪም እሱ ሆነ። ስለዚህ ህወሃት/ኢህአዴግ በየአምስት አመት በግንቦት ወር በኢትዮጵያ የሚደረገውን ምርጫ እንደ ጦር ሜዳ ወሰደው።  በዚህ ላይ የቃዋሚ ህብረት የለም። በምርጫ ከተሳተፈ በኋላ ዛሬ በኦሮሚያ እንደምናየው ህዝባዊ እንቢተኛነት በመቀስቅስ “ድምጽ ማስከበር” የሚችል ህዝብ መፍጠር ባለመቻላችንም ታግዞ ህወሃት/ኢህአዴግ ተቃዋሚዎች ያገኙቱን ድምጽ በኃይል እየዘረፈ በምርጫ 2002 ዕ.ም. በ99.7% በቅርቡ በምርጫ 2007 ዓም ደግሞ በ100% አሸነፍኩ አለን።  በጠብ መንጃ አዲስ አበባን ሲይዝ አንተ ማነህ? ያለው እንደሌለ ሁሉ ድምጽ ማስከበር የሚችል ህዝብም ሆነ ተቃዋሚ ፓርት ባለመኖሩ ከምርጫዎች በኋላም አንተ ማነህ? ሳንለው ይኸው እስከ ዛሬ ስልጣን እንደጨበጠ ይገኛል። የተቃዋሚዎች ህብረት ቢኖር እና ዛሬ በኦሮሚያ የሚገኙት ወጣቶች ከሚያደርጉት ጋር ተመሳሳይ ህዝባዊ እምቢተኛነት በማድረግ “ድምጽ ይከበር” የሚል ህዝባዊ እንቅስቃሴ በመፍጠር ድምጹን ማስከበር የሚችል ህዝብ ቢኖር ኖሮ ሁኔታውን ለመቀየር ይሞከር ነበር። ዛሬ በኦሮሚያ መሚኪያሄድ ላይ የሚገኘው ህዝባዊ እምቢተኛነት እግረ መንገዱን ከምርጫም በኋላ ድምጹን የሚያስከብር ህዝብ ይፈጥራል የሚል እምነት አለኝ። የምርጫ 2007 ዓ.ም. ምርጫ 100% አሸናፊነት የኢትዮጵያን ወጣቶች አስመርሯል። በቃን አሰኝቷል። አውቀው ሲታለሉለት ከከረሙት ለጋሾቹ (ሸሪኮቹ) ምዕራባውያን ውስጥ እንኳን አንዳንዶቹ አሁንስ አበዛኸው ብለዋል። እውነት ነው። ህወሃት/ኢህአዴግ በስብሷል። መሄድ አለበት። በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎችን በሙሉ ያካተተ ሁሉን አቀፍ ህብረት መፈጠር ያስፈልጋል። ቢቻል ኢህአዴግን እና ህወሃት/ኢህአዴግ “አጋር” የሚላቸውን ድርጅቶችም ያካተተ። ካልሆነም ከህወሃት/ኢህአዴግም ሆነ ከአጋር ድርጅቶቹ ውስጥ ተራማጅ የሆኑቱን ግለሰቦች ያካተተ። ይኽን ማድረግ ሽግግሩን ሊያቀል ይችላል። የገዢው ፓርቲ  አባላት በሽግግሩ ወቅትም ሆነ እና ከሽግግሩ በኋላ በሰላም በአገራቸው መኖር እንደሚችሉ እንዲሰማቸው ማድረግ ያስፈልጋል። ስለዚህ ገዢው ፓርቲም ሆነ የወቅቱ ባለስልጣኖች ያላቸው የተሻለ አማራጭ ከተቃሚው የሽግግር ህብረት ጋር መተባበር ብቻ መሆኑን በውይይት እንዲገነዘቡ ማድረግ ያስፈልጋል።

 

እርግጥ ነው ለሁሉም አገር የሚሆን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ህብረት መፍጠሪያ አንድ አይነት ቀመር (ፎርሙላ) የለም። ከታሪካችንም እንደምንረዳው የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት እና ወደ ዴሞክራሲ ሽግግር መውሰድ እና ማስፈጸም የሚያስችል ህብረት መፍጠር እጅግ ፈታኝም አስሸጋሪም ጉዳይ ነው። የዴሞክራሲ ሽግግር የከሸፈባቸውም ሆነ የተሳካ ሽግግር ያደረጉ አገሮች ታሪክም የሚያስተምረን ህብረት መፍጠር ቀላል እንዳልሆነ ነው። ህብረት ለመፍጠር የዴሞክራሲ ሽግግር መሪዎች በትንሹ፥ አርቆ አስተዋይነትን፣ ብዙ ውጣ ውረድን፣  የእነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ መሆኑን መረዳትን፣ ረዘም ያለ እና ቀጣይነት ያለው ጥረት ማድረግን፣ የድርድር ክህሎት አቅም መገንባትን፣ ሰጥቶ በመቀበል መርህ መመራትን እና የመሳሰሉትን እልህ አስጨራሽ ስራዎች ይጠይቃል።  በዚህ አይነት የሚደረስ ስምምነት እና የሚፈጠር ህብረት (coalition) እያንዳንዱ ድርጅት ትንሽ ሰጥቶ እና ትንሽ አግኝቶ የሚፈጠር ህብረት ይሆናል።  በዘውዳዊው፣ በደርግ እና በህውሃት/ኢህአዴግ እንዲሁም በምርጫ 97 የተፈጠሩ ጥሩ የለውጥ እና የዴሞክራሲ ሽግግር አጋጣሚዎች ባክነዋል። አሁን የተፈጠረው የፖለቲካ ለውጥ እንቅስቃሴ እንደቀድሞዎቹ አጋጣሚዎች ሳይባክን ወደ ዴሞክራሲ ሽግግር እንዴት መግባት እንደሚቻል ከወዲሁ ሊታሰብበት ይገባል። ወጣቶቹን ማዘዝ ሳይሆን ልንተባበራቸው እና ልናግዛቸው ይገባል።

 

ህብረት (coalition) ሲባል የፓርቲዎች ውህደት ሳይሆን በተያዘው የለውጥ እንቅስቃሴ ብሎውም በዴሞክራሲ ሽግግር ዙሪያ በሚቀረጽ የጋራ አጀንዳ ዙሪያ ብቻ ተባብሮ አብሮ ለመስራት የሚፈጠር ቡድን ነው። ውህደት ለረጅም ጊዜ በትናንሽ ጉዳዮች ላይ ተጋግዞ በመስራት የሚፈጠር ትውውቅን እና መተማመንን ቅድሚያ ይላል። በጋራ መስራት የሚቻሉ ነገሮችን ለይቶ አውጥቶ በእነሱ ዙሪያ ተሰባስቦ ተጋግዞ አብሮ የመስራት ባህልን መገንባት ቅድሚያ ይላል።

 

በመጨረሻ የሰላማዊ ትግሉን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ ጥቂት ምክሮችን በመለገስ ጭቅጭቄን ላብቃ፡፡

(1) በስልጣን ላይ የሚገኘው አምባገነን ቡድን የተቃዋሚ መሪዎችን እና ብሩህ ለውጥ ተመኚ ወጣቶችን የሚገድለው እና የሚያስረው የሰላማዊውን ትግል ጭንቅላት በመቁረጥ ትግል ለመግደል እንደሆነ ልንዘነጋ አይገባም። ገዢው ቡድን ያሰበው እንዳይሳካለት ለማድረግ አንደኛው መድሃኒት የሰላማዊ ትግል እውቀት በማስፋፋት አዳዳሲ መሪዎች እና የሰላም ትግሉ ሰራዊት እንዲያድገ ማድረግ ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች የሰላማዊ ትግል እውቀት በቀጣይነት እንዲቀስሙ ማድረግ ከቻልን በስልጣን ላይ ላለው አምባገነን ቡድን ፈተናውን እናበዛበታለን ማለት ነው። ህወሃት/ኢህአዴግ ሰላማዊ ትግልን አለማወቁ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው በሚሊዮኖች የሚፈጠሩ ወጣቶችን ማሰር አይችልም። ስለዚህ ሰላማዊው ትግል ቀጣይነት ይኖረዋል። ሁለተኛው መድሃኒት ደግሞ የታሰሩት የሰላማዊ ትግል መሪዎች እና ታጋዮች በፍጥነት እንዲፈቱ ጥያቄያችን ማቋረጥ የለብንም። በዚህ ረገድ በተለይ በውጭ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ መንግስት ሸሪኮች እና ለጋሽ የምዕራቡ መንግስታት ከተሞች ሰልፎች በመውጣት የዲፕሎማሲ ጫና ማድረግ እንችላለን።

(2) ጥሩ የሰላማዊ ትግል እውቀት ያላቸው እና በየጊዜው በምድር ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች በፍጥነት መልስ እየሰጡ ሰላማዊ ትግሉ ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ የሚችሉ መሪዎች ሊኖሩ ይገባል።

(3) ዛሬ ቴክኖሎጂ የዴሞክራሲ ሽግግርን በከፍተኛ ደረጃ እየረዳ ነው። በእጅ ስልክ በሚሰራጩ አምባገነናዊ ጭፍጨዎች ብቻ የአለምን ህብረተሰብ ሃሳብ ማስቀየር እና በአገር ውስጥ እና በለጋሽ አገሮች መዲናዎች ትላልቅ ሰላማዊ ተቃውሞች መቀስቀስ ይቻላል። የሰላማዊ ትግል ሰራዊት የእጅ ስልኩን በመጠቀም ዜና ዘጋቢም ሊሆን ይችላል ማለት ነው። ስልጠና መስጠት ሊያስፈልግ ይችላል። እርግጥ ቴክኖሎጂ ብቻውን ህያው ሰዎችን አይተካም። ዜናዎቹን ለማብራራትም፣ ለድርድርም፣ ተቋሞችን ለመመስረት እና ለመገንባት እና ለበርካታ ጠቃሚ ተግባሮች በሰላም ትግል የሰለጠኑ ታታሪ መሪዎች ያስፈልጋሉ። አጀንዳዎች እና መፈክሮች መቅረጽ፣ ፓርቲ መገንባት፣ ህብረት (coalition) መፍጠር፣ ፕሮግራሞች እና ፖሊሲዎች ለመቅረጽ ብሎም  ለማሰራጨት፣ ህዝብ በዴሞክራሲ ሽግግር እንዲያምን እና ተሳታፊ ለማድረግ እና ለመሳሰሉት ወሳኝ ስራዎች በሙሉ  ብቃት ያላቸው የሰላማዊ ትግል መሪዎች ያስፈልጋሉ።

 

(4) ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ፍርሃትን ማስወገድ ወይንም ፍርሃትን መቆጣጠር መቻል የመጀመሪያ ጉዳይ ነው። በሰላማዊ ትግሉ መሳተፍ ሊያስከትል የሚችለውን ስቃይ እና መከራ በማሰብ ከትግሉ እራስን ማግለል ስርዓቱ የሚፈጽመው ስቃይ የተሻለ አድርጎ መቀበልን ሊያስከትል ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ የሰላም ትግሉ ሰራዊት ፍርሃትን ማስወገድ ወይንም መቆጣጠር አለበት ስንል የሰላማዊ ትግሉ ሰራዊት (በዘር፣ በቁንቋ፣ በይማኖት፣ በጾታ፣ በሃይማኖት፣ በአይዶሎጂ፣ ወ.ዘ.ተ.) እሱን ያለመሰሉትን ወይንም የመንግስት ባለስልጣናትን፣ የገዢውን ፓርቲ አባላት እና ተከታዮች በሆነ ባልሆነው ማስበርገግ የለበትም። የመንግስት ባለስልጣኖች፣ የገዢው ፓርቲ አባላት እና ተከታዮች በሽግግር ወቅት እና ከሽግግር በኋላ ስቃይ እና በቀል ይፈጸምብናል በሚል ስጋት እንዲናወጡ ካደረግን ሽግግሩን የተራዘመ እና የተወሳሰበ የማድረግ ችግር ውስጥ ልንገባ እንችላለን። ስለዚህ ፍርሃት ስለማስወገድ ስናስብ ግባችን እኛን ታጋዮችን ከፍርሃት ነፃ ማውጥት ብቻ ሳይሆን እኛን በማይመስሉ ወይንም በፖለቲካ ባላንጣዎቻችንም ዘንድ እንዳይፈሩን ማድረግንም ያካትታል።

 

(5) ሰላማዊ ትግሉን ከጥላቻ ነፃ እንዲሆን ማድረግ ይገባል። ጥላቻ ንጹህ በሆነ አዕምሮ እና ህሊና እንዳናስብ ያደርገናል። አዕምሮዋችን በጥላቻ ከተመረዘ የምንሰጠው ዳኝነትም ፍትሃዊ አይሆንም። በጥላቻ ከተመርዘን ወንጀል ወደ መፈጸም ልንሸራተት እንችላለን። ነገ እኝንም ሆነ እንወክለዋለን የምንለውን ወገን ሊያሳፍር የሚችል ተግባር ልንፈጽም እንችላለን። የምንቃወመው ገዢውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ስርዓት እንጂ እኛን የማይመስለውን ወይንም ተቃዋሚዎቻችን መሆን የለበትም። የሰላም ትግል ሰራዊት ከጥላቻ ነፃ የመሆን አቅም ሊኖረው ይገባል። ስለዚህ ከጥላቻ ነፃ የመሆን አቅም የመገንባት ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል። እርግጥ የፖለቲካ ባላንጣዎቻችንንም ማፍቀር አለብን ማለቴ አይደለም። ከጥላቻ ነፃ መሆን የሰላማዊ ትግሉን ማራኪነት፣ ተአማኒነት፣ አስማኝነት እና ስኪታማነት አቅሞች ከፍ ያደርጋል ማለቴ ነው።

 

(6) ሰላማዊ ትግል ከጉልበትም ነፃ መሆን አለበት። ጉልበት፣ ግድያ፣ ሽብር እና የመሳሰሉት ዘዴዎች የአምባገነኖች መንገዶች ናቸው። በዚህ አይነቱ መንገድ አምባገነኖች ይበልጡናል። እኛም ጉልበት እና  ግድያ መጠቀም ከጀመርን አምባገነኖች የረጅም ጊዜ ልምድ እና ቁጥር ስፍር በሌለው ለረጅም ጊዜ ባከማቹት ህይወት ማጥፊያ አቅማቸው እንዲገጥሙን እድል እንሰጣቸዋለን ማለት ነው። ባለፉት አራት ወሮች ብቻ እንኳን ምዕራቡ በኦሮሚያ ለሚካሄደው ሰላማዊ ትግል በፍጥነት ድጋፍ መግለጹን እናስታውሳለን። እኛ በሰላማዊ ትግሉ ላይ ግድያን እና ሽብርን ከቀላቀልን ግን ምዕራቡ ደንታ አይኖረውም። እንዲያውም የህወሃት/ኢህአዴግ ወታደራዊ አቅም ከፍ እስካለ ድረስ ምዕራቡ ከቀድሞ ወዳጁ ከህወሃት/ኢህአዴግ ጎን ነው የሚለጠፈው። የሚካሄደውን ሰላማዊ ትግሉም የአገር ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳይ በማስመሰል ህዝብን አደናግሮ ለማስተባበር እና ሰላማዊው ትግል ቶሎ እንዳይንሰራራ አድርጎ ለመምታት እንዲችል ቀዳዳ ይከፍትለታል። ስለዚህ ሰላማዊ ትግላችንን ከብክለት (Contamination) በንቃት መጠበቅ አለብን። ይኽን ማድረግ ለሰላማዊ ትግላችን ቀጣይነት እና ድል አድራጊነት የምንፈጽመው የደህንነት (የጸጥታ) ስራ አድርገን መውሰድ አለብን። ጀብዱኛ ግለሰቦች ወይንም ሌሎች ሰላማዊ ትግሉን ተቀላቅለው ጥይት የሚተኩሱም ከሆነ የሶሪያ አይነት ሁኔታ በኢትዮጵያችን ለፈጠር የማይችልበት ምክንያት አይኖርም። ሰላማዊ ትግሉ በፕላን የሚመራ እና በድስፕሊን እየታነጸ መሆን አለበት። ሰላማዊ ሰልፈኞችን ተቀላቅሎ በፖሊስ ላይ ድንጊያ መወርወርም ጉዳቱ ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል። ፖሊሶች በድንጋይ ከመገደላችን በፊት እራሳችንን ለመከላከል ነው ግድያ የፈጸምነው ሊሉ ይችላሉ።  ፖሊሶች እንዲፈሩን ማድረግ የለብንም። እንዲያውም የተወሰኑት እንዲቀላቀሉን ማድረግ አለብን። ብዙ የክልልም ሆነ የፌዴራል ፖሊሶችም ይህን መንግስት ከልብ በፍቅር የሚወዱት አይመስለኝም።

 

(7) ስለማዊ ትግላችን ከግብታዊነት ነፃ መሆን አለበት። ግብታዊ ሰላማዊ ትግል በትግላችን ሂደት ውስጥ ለምንወስዳቸው እርምጃዎች አምባገነኖች ሊሰጡ የሚችሉትን አረመኔያዊ ምላሽ በቅድሚያ የመገመት እና የመዘጋጀት እድል ስለማይሰጠን ግብታዊነትን በትግላችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።  ግብታዊ ሰላማዊ ትግል ሊገጥሙት የሚችሉትን ወሳኝነት ያላቸው እንቅፋቶች በቅድሚያ አንስቶ ተመራምሮ ተገቢ ፕላን ስለማያሰላ ውጤቱ ውድመት ሊሆን ስለሚችል ግብታዊነት ሊወገድ ይገባል። ግብታዊ ሰላማዊ ትግል በስልጣን ላይ የሚገኘውን አምባገነን መንግስት ማውረድ ቢችልም ቀደም ብሎ የተሰላ ህዝብን የመንግስት ስልጣን ባለቤት የሚያደርግ የዴሞክራሲ ሽሽግር ፕላን ስለማይኖረው የሰላማዊው ትግል ፍሬ በሽግግር ወቅት ሊከሰት በሚችል በመፈንቅለ መንግስት ወይንም በራሱ ከስልጣን በወረደው ቡድን ሊነጠቅ ይችላል። ግብታዊትግል በስልጣን ላይ የሚገኘውን መንግስት ማውረድ ቢችልም ግባታዊው ትግል ቅልበሳን የሚከላከል ፕላን ስላማይኖረው አገሪቱን ወደ ነፃ ምርጫ እና ወደ ዲሞክራሲ ማሸጋገር ሊሳነው ይችላል። ህዝብን የድል ባለቤት ማድረግ አይችልም። አዲስ አምባገነን ወይንም ነባሩ አምባገነን ቡድን የድል ፍሬ ሰብሳቢ ሊሆን ይችላል።

 

(8) የሰላማዊ ትግላችን መሪዎች ደሞዝ የከፈለ ማዘዝ ይችላል የሚለው አባባል በፖለቲካም እንደሚሰራ ማስተዋል አለባቸው። ስለዚህ ሰላማዊ ትግሉን ከፍ በማድረግ በአገር ውስጥ ከንብረት ባለቤትነት፣ ከመሬት ባለቤትነት፣ ከንግድ፣ ከሰራተኛ ደሞዝ የሚያሰባስበውን ግብር እና በኢትዮጵያ ስም ከለጋሾች የሚፈስለትን የገንዘብ መጠን ከምንጩ ማድረቅ ያስፈልጋል። ይህ የኢኮኖሚ ትብብር መንፈግ የሚባለው ነው። ሰላማዊ ትግሉን ከፍ በማድረግ ከጅቡቲ፣ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሸቀጦችን ማቆም ይቻላል። መንገዶችን በተለያዩ ከተሞች ላይ በመዝጋት ከውጭ ወደ አዲስ አበባ እና ሊሎች ከተሞች የሚገባ ነዳጅ እና በርካታ ሸቀጦችን ማስተጓጎል ይቻላል። በዚህ አይነት የመንግስትን ኪስ መዳበስ ይቻላል። የኪሱ እብጠት ሲቀንስ እንደቀድሞው ደሞዝ የመክፈል አቅሙ ስለሚዳከም ሰላማዊ ተቃውሞ በማድረጋቸው ብቻ ህጻናትንን እና ወጣቶችን እንዲገድሉ የሚያዛቸውን ደህንነቶች እና ፖሊሶች እንደልቡ ማዘዝ ይሳነዋል። ሰራዊቱም ሰለማይከፈለው በተቃዋሚው ሁሉን አቀፍ ህብረት ለሚደረግለት “ለህገ-መንግስተ ተገዛ” እና “ሰላማዊውን ለውጥ ተቀላቀል” ጥሪ የሚሰጠው ምላሽ ከጊዜ ወደ ጊዜ አዎንታዊ እየሆነ እንደሚሄድ መጠራጠር የለብንም።

 

(9) የህዝቡ ጥያቄ በቅርቡ፥ “በ100% አሸናፊነት የተፈጠሩት መሳቂያ የፌዲራል እና የክልል ፓርላሞች ይፍረሱ፣ ጊዚያዊ መንግስት ይቋቋም፣ አዲስ ምርጫ ይደረግ” ከሚል ደረጃ እንደሚደርስ ጥርጥር የለኝም። ስለዚህ አርጅቶ በመበስበስ ላይ የሚገኘው የህውሃት/ኢህአዴግ መንግስት አንዴ “ስለ ይቅርታ” ሌላ ጊዜ “ስለመልካም አስተዳደር እጦት” በስውር ደግሞ “ስለ ወታደራዊ ዕዝ አስተዳደር“ ማውራቱን አቁሞ ከህዝብ ቢታረቅ እና የተጀመረውን የፖለቲካ ስርዓት ለውጥ ብሎም የነፃነት እና የዴሞክራሲ ሽግግር ሂደት ቢቀላቀል የሚሻለው ይመስለኛ። ቢያንስ በህወሃት/ኢህአዴግ ውስጥ የሚገኙ ተራማጅ ሰዎች ይህን አይነት እርምጃ ቢወስዱ ለራሳቸውም ለአገሪቱም ጠቃሚ ይመስለኛል። የአገር ሽማግሊዎች እና ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሁሉን አቀፍ ጉባኤ መጥራት የሚያስችል ስራ መስራት መጀመር ያለባችሁ ይመስለኛል። እርግጥ ለውጥ ነገ ይመጣል ማለት አይደለም።  ስራው ግን ቢጀመር ጥሩ ነው።

 

ሰላማዊ አቤቱታ እና ተቃውሞ በማንሳታቸው ብቻ ወጣት ልጆቿን የምትገድል፣ የምታስር፣ የምታዋክብ ኢትዮጵያ ማብቃት አለባት። ዜጎቿን በነፃነት እና በዴሞክራሲ ማስተዳደር ወደ ምትችል ኢትዮጵያ መሸጋገር አለብን። የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ተገቢውን ትብብር ካገኘ እንደሚሳካ ጥርጥር የለኝም።!

 

ከሰላምታ ጋር

ግርማ ሞገስ

 

The post ኢትዮጵያ ወዴት? – ግርማ ሞገስ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሀይገር አውቶብስ ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ ተገልብጦ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ 13 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

0
0

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬ ማምሻውን 11 ሰዓት ተኩል አካባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ 03 46206 አዲስ አበባ የሆነ ሀይገር አውቶብስ ከፒያሳ ወደ ለገሃር ሲያቀና ቴዎድሮስ አደባባይ ጋር ሲደርስ ተገልብጧል።
a8e80f5539fda3cfcc7ab42f76c04110_XL
ከእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር ባለስልጣን የህዘብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደገለፁት፥ በአደጋው 13 ሰዎች ከባድ አደጋ ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

የባለስልጣኑ አምስት አምቡላንስ ተሽከርካሪዎችም የተጎዱትን ወደ ህክምና ተቋማት አድርሰዋል።

እሰካሁን በአደጋው የአንድ እግረኛ ህይወት ማለፉንም ጠቅሰዋል።

The post ሀይገር አውቶብስ ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ ተገልብጦ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ 13 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል appeared first on Zehabesha Amharic.


የሰማያዊ ሊቀመንበር መቀመጫቸውን አ.አ ላደረጉ 21 የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ተወካዮች ገለጻ አደረጉ

0
0

1044212_856562327802760_3735872674734306429_n

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ 21 የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ተወካዮች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ማድረጋቸውን ገለጹ፡፡

ሊቀመንበሩ ዛሬ መጋቢት 6/2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ የአውሮፓ ህብረት ጋባዥነት በተለያዩ የሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ በተለይ በኦሮሚያ፣ ጋንቤላ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ እና ወልቃይት አካባቢዎች ስለተከሰቱ ህዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ለተወካዮቹ ገለጻ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ምክትል ኃላፊ ተርሂ ሌተነን በመሩት ገለጻ ላይ ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል በኢትዮጵያ ስላለው የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ቀውሶች ላይ ማብራሪያ መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት 18 ሚሊዮን ዜጎች ለርሃብ መዳረጋቸውን፣ የኑሮ ውድነት መጨመሩን፣ ሙስና መንሰራፋቱን፣ የገቢ አለመመጣጠን መጉላቱን እና የስራ አጥነት ችግር እየከፋ መሄዱን ለተወካዮች መግለጻቸውን ተናግረዋል፡፡

በፖለቲካው መስክም ኢትዮጵያ ውስጥ መድብለ ፓርቲ ፖለቲካ ጨርሶ መዘጋቱን፣ ፓርቲዎች በጸረ-ሰላምነት ተፈርጀው በመንግስት እየተሰለሉ መሆናቸውን በፍርድ ቤት የቀረበ ማስራጃ ማረጋገጡን፣ የሰማያዊ እና መድረክ ፓርቲዎች አባላት በግፍ እስር ላይ መሆናቸውን እንዳብራሩ ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ህዝቡ መብቱን ለመጠየቅ ለተቃውሞ መውጣቱን ተከትሎ በአራት ወራት ጊዜ ብቻ በመንግስት ከ260 ሰዎች በላይ መገደላቸውን በዝርዝር እንዳስረዱ ሊቀመንበሩ ገልጸዋል፡፡ በወልቃይት የማንነት ጥያቄ አለን በሚል ለትግራይ ክልል እና ለፌደሬሽን ም/ቤት ህጉን ተከትለው ጥያቄ ያነሱ ዜጎች መታሰራቸውንና በመንግስት ሚዲያዎች ግጭት ቀስቃሽ ዘገባ እየቀረበ እንደሆነ መታዘባቸውን፣ ይሄም እንደሚያሳስባቸው ለተወካዮች ማብራራታውን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ችግሮች ከኢህአዴግ በላይ በመሆናቸው መንግስት ሁሉም ፓርቲዎች፣ የማህበራት ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች የሚሳተፉበት አካታች ውይይት እንዲደረግ እንዲፈቅድ ጥሪ ማቅረባቸውንና የህብረቱ ሀገራትም ይህ እንዲሆን አስፈላጊውን ግፊት እንዲያደርጉ ማሳሰባቸውን አስረድተዋል፡፡

The post የሰማያዊ ሊቀመንበር መቀመጫቸውን አ.አ ላደረጉ 21 የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ተወካዮች ገለጻ አደረጉ appeared first on Zehabesha Amharic.

በርሀብ የሚገድል መንግሥት እንዴት በሥልጣን ላይ ይቆይ? –ገለታው ዘለቀ   

0
0

 

ginbot7-supporters-blame-woyaneታላላቅ ረሀቦች ተብለው በዓለም ታሪክ ከሚዘከሩት ውስጥ የቻይናውያን ረሀብ ኣይዘነጋም። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1958-1961  ድረስ ቻይና ውስጥ ከፍተኛ ረሀብ ተከስቶ ወደ ሰላሳ ሚሊዮን ህዝብ ረግፏል። ብዙ ምሁራን እንደሚሉት ለዚህ አስከፊና ቻይናውያን ሊረሱት ለማይችሉት ረሀብ አንደኛ ተጠያቂ ማዖ ዚዳንግን ነው።  የኮሙኒስት ፓርቲ መሪ የነበረው ማዖ ዚዳንግ በሶቪየት ህብረት በነጆሴፍ ስታሊን አብዩት ፍቅር የከነፈ ሲሆን ቻይናን በአምስት ዓመታት ውስጥ ከሁዋላ ቀር ግብርና አውጥቼ ወደ ኢንዱስትሪ እለውጣታለሁ በማለት Great Leap Forward ታላቁ የግስጋሴ ርምጃ የተሰኘ የአምስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ ነድፎ አመጣ። እቅዱ የግል የመሬት ባለቤትነትን የሚጻረርና የወል እርሻን የሚያራምድ ነበር። በዚሁ እቅድ መሰረት ቻይናውያን በፍጥነት እየተደራጁ የወል እርሻ ሥራን ጀምረው ነበር። ይሁን እንጂ እቅዱ እንደተቋመጠለት ሳይሳካ ቀርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተገላቢጦሽ ችግር አመጣና ቻይናውያንን አስርቦ ቁጭ አለ። ዛሬ ላይ ያን ረሀብ የ Great Leap Forward ረሀብ ይሉታል።

በማዖ ዚዳንግ ጊዜ ቻይናውያን በጋራ እርሻ ከጀመርን ነው የምናድገው ተብለው የግል እርሻ በሰፊው ማካሄድ ተከልክሎ ስለነበር አልፎ አልፎ ጓሮ አካባቢ ትንሽ አትልክት ቢጤ ከማሳደግ ውጭ መሬት ሁሉ የጋራ ሆኖ በጋራ ማረስ ተጀመረ። ከፍተኛ የሰው ኃይል ደግሞ ከግብርናው ተቀንሶ ወደ ብረት ማቅለጥ ሥራ እንዲሄድ ታዞ የብረት ማቅለጥ ሥራ ተጀምሮ ነበር። ይሁን እንጂ እቅዱ ቀቢጸ ተስፋ የሞላውና የግል መብቶችን የጣሰና የግል ንብረት ባለቤትነትን የሰበረ በመሆኑ ከፍተኛ ሶሺዮ ኢኮኖሚክ ኪሳራን አመጣና ወዲያው ከሸፈ።  እንደታሰበው ምርታማነትን ሳያሳድግ ቀርቶና በተቃራኒው ሄዶ ብዙ ሰው ጨረሰባቸው። ታዲያ ቻይናውያን እድለኛ ሆነው የድህረ ማዖ መሪዎች ለዛች ኣገር የኢኮኖሚ እድገት የተሻለ ፖሊሲ አምጥተው ማደግ ችለዋል። እነሆ ዛሬ ቻይና ድህነትን ለመቀነስ ባደረገችው ጥረት ከዓለም አንደኛ ናት። በዓለማችን ታሪክ ውስጥ መጠናቸው ይብዛም ይነስም ከፓሊሲና ከመልካም ኣስተዳደር ብልሹነት የተነሳ ሰዎች በረሀብ አልቀዋል።

ዩክሬን ውስጥ ከ 1932-1933  ድረስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በርሀብ ያለቁት ጆሴፍ ስታሊን ባወጣው የኣምስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ እንደሆነ ብዙ ምሁራን ይስማማሉ። ከ 1932-1933  ጊዜ ውስጥ፣ በዚህች ኣጭር ጊዜ  ወደ ኣስር ሚሊዮን የሚጠጉ ዮክሬናውያን በረሀብ ኣልቀዋል። ህጻናት ዋይ ዋይ እያሉ፣ አረጋውያን እያቃሰቱ በሳይቤሪያ በረሀ ሳይቀር በየሜዳ የቀሩበትን ይህን ክፉ ጊዜ ዮክሬናውያን በቋንቋቸው ሆሎዶሞር (Holodomor) ሲሉ ይዘክሩታል። በአማርኛ  በረሀብ መግደል ወይም ሰውን በችጋር መጨረስ እንደ ማለት ነው። ረሀቡ ሰው ሰራሽ ነው፣ የስታሊን የአምስት ዓመት ትራስንስፎርሜሽን እቅድ ውጤት ነው ብለው የዩክሬን ሰዎች ኣምርረው ኮንነውታል። በርግጥም ዮክሬናውያን ይህን ለማለት ይገባቸዋል። በጣም የከፋው ነገር ደግሞ ከፖሊሲው መክሸፍ ባሻገር ረሀብ በተከሰተበት ወቅት ስታሊን የውጭ ርዳታ እንኳን እንዳያገኙ በተለያየ መንገድ ተጽእኖ ፈጥሮ ነበር። ረሀብ ያለባቸው አካባቢዎችም ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ እንዳይዘዋወሩ በመከልከሉ የጉዳቱን መጠን ኣስፍቶታል።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ፔትሮ ፕሮሸንኮ በርሀብ የሞቱትን ሰዎች በመታሰቢያ ሀውልቱ ስር ሲያስቡ።

 

በርግጥ ይህ አሁን የምናወራው ረሀብ ከብዙ ዓመታት በፊት ያለ ነው። ዛሬ የሰው ልጅ አይራብም። ቢያንስ እጅግ ብዙው ዓለም በምግብ ኣይቸገረም። ወደኛው ቤት ስንመለስ ግን በሃያ ኣንደኛው ክፍለ ዘመን እንደነ ስታሊንና ማዖ ዚዳንግ የኢትዮጵያ መንግሥት ያመጣው የአምስት ዓመት ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተባለው በመጨረሻ ይሄውና ኣስር ሚሊዮን ህዝብ ለረሀብ ኣጋልጦ ቁጭ ብሏል። ዩክሬናውያን ስታሊን በችጋር ገደለን ሲሉ ሆሎዶሞር እንዳሉት እኛም የመንግሥት ትራንስፎርሜሽን እቅድ ኢትዮጵያውያንን ኣስርቦ እየገደለብን ነው።

ለዚህ ረሀብ ምክንያቱ ምንድን ነው? ሲባል የኢትዮጵያ መንግሥት ሮጦ ድርቅ እኮ ኣውስትራሊናያ ካሊፎርኒያም ገባ….. አልሰማችሁም እንዴ?….. ይላል። የውቅያኖስ ውኃ ሙቀት መጨመርን ተከትሎ የመጣ የኣየር ንብረት ችግር ኤሊኖ የተባለ የአየር  መዛባት ያመጣው ችግር  ነው ብለው ያብራሩልናል። ኤሊኖ ሆኖብን ነው እንጂ የኣምስቱ ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅዳችን ኣገራችንን ትራንስፎርም ኣድርጓል ይሉናል። ብንራብም በጥንድ ቁጥር እያደግን ነው ሲሉን ደግሞ ግራ የተጋባው ዜጋ እነዚህ ሰዎች የሚያወሩት ስለ ሌላ ሀገር ይሆን? እያለ ይደመማል። ወይስ እኔ የምኖርባትን ይህቺን ኢትዮጵያን የሚመለከት ነው? እያለ ይገረማል።

 

ኣስር ሚሊዮን ህዝብ ረሀብ ላይ ወድቆ ስናይ ማንን ነው የምንወቅሰው? ተፈጥሮን ነው? በርግጥ ኢትዮጵያ አፈርና ውኃ የላትም ወይ? የሚል ጥያቄ እናነሳለን። በመሰረቱ የአገራችን ረሀብ መቶ እጅ ከፖሊሲ ችግር የመጣ ነው። ከአመራር ችግር የመጣ ነው። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ደረጃ ከምሥራቅ ኣፍሪካ ሀገራት የውኃ ገንዳ የምትባል አገር ናት። ውኃ ሞልቷታል እየተባለች በሌሎች ኣፍሪቃ ሀገራት ይቀናባታል። በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ ከሀገሪቱ ሆድ ሞልቶ የሚተርፍ ነገር ማምረት የሚያስችል ለም መሬትም አላት። ይሁን እንጂ ድሮም ቢሆን የብዙ ገበሬዎችን ህይወት ካበላሸው  የመሬት ፖሊሲ ጀምሮ ያለንን የከርሰ ምድር ውኃና ወንዞች በአግባቡ መጠቀም ባለመቻላችን እነሆ ዝናብ ጸጥ ሲል ለረሀብ ተጋልጠን ቁጭ እንላለን።  አፈርና ውኃ እያለን መራባችንን ስናይ በርግጥ የኛ ሀገር ረሀብ ከአመራር ችግር ጋር ብቻ መያያዙን በሚገባ ያሳየናል።

አሁን ያለንበት ዘመን የሰው ልጅ የሚራብበት ዘመን አይደለም። ቴክኖሎጂ አድጎ ረሀብን ጉልበቱን ሰብሮታል። የከርሰ ምድርን ውኃን አየሳቡ፣ መስኖ እያለሙ፣ የተለያዩ የእርሻ ግብዓቶችን እየተጠቀሙ አገሮች የምግብ ዋስትናቸው ከቶ ኣሳሳቢ የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ኣሁን ይህ ዘመን ስለ ምግብ ሳይሆን ስለ ቴክኖሎጂ፣ ስለ የተሻለ ህይወት፣ ስለሌሎች ፕላኔቶች የሚታሰብበት ዘመን ነው። በዚህ ዘመን የሚራብ ህዝብ መንግሥት የሌለውና በጦርነት ምክንያት ህዝቡ ማምረት ካቆመ ነው።  መንግሥት ያለበት አገር አይራብም። ለምሳሌ ያህል ሶርያን ብናይ ፕሬዚደንት ኣሳድ ወደ ሰማኒያ በመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱን ክፍል መቆጣጠር ኣልቻለም ነበር። ይህ ሰፊ የሀገሪቱ ክፍል ከኣሳድ እዝ ውጭ ቢሆንም ኣሳድ ደማስቆ ላይ ቁጭ ብሎ ግድ የለውም። ኣንዳንድ ከተሞች እርዳታ እንኳን እንዳይደርስላቸው የጦርነት ቀጣና ሆነው ብዙ ሰው በአጥንቱ እስኪቀር ተርቧል። ኣሳድ ሰማኒያ በመቶ የሶሪያን ግዛት ኣጥቶ፣  በሶሪያውያን ስደት በተባበሩት መንግሥታትት ድርጅት የስደተኞች ድርጅት ፣ ኣውሮፓውያን፣ ዓለም ባጠቃላይ ተጨንቀው ስደተኛውን ምን እናድርገው? እያሉ ኣስሬ ስብሰባ ሲጠሩ፣ ዓለም በሶሪያ ስደት ስትናወጥ ኣሳድ ደማስቆ ቤተመንግሥቱ ቁጭ ብሏል። ይገርማል። ዲክቴተርስ ምን ያህል ግድ የለሽ እንደሆኑ ከግል ጥቅም ባሻገር ለብዙሀኑ እንደማያስቡ ያሳይል።

ወደ ሀገራችን ስንመለስ ያለፈው ትራንስፎርሜሽን እቅድ በአገሪቱ ውስጥ በመስኖ ሊለማ ከሚችለው ኣምስት በመቶ እንኳን ሳያለማ ገበሬውን እንደ ጥንታዊ ዘመኑ የዝናብ ጥገኛ ኣድርጎ ለኪሳራ መዳረጉ ሳይበቃው እንደገና ሁለተኛ የትራንስፎርሜሽን እቅድ ተብሎ መጣ። እቅዱ የገበረውን የመሬት ችግር የማይፈታ ሆኖ ይታያል። የኣምስቱ ዓመት ትራንስፎርሜሽን እቅድ ልክ እነስታሊን የወደቁበትን ይመስል በኢትዮጵያም በውጤቱ ኣገሪቱን ወደ ተሻለ ህይወት ከመምራት ወደ ርሀብ ሲወስዳት ይታያል። ረሀቡ ደግሞ የእለት እንጀራ ብቻ ሳይሆን የሚጠጣ ውኃንም ይጨምራል። የከርሰ ምድር ውኃችንን ለእርሻ ልማት መጠቀም አለመቻላችን ብቻ ሳይሆን እቅዱ የመጠጥ ውኃ እንኳን ኣሳጣን። ይሄ ተሀድሶ ሊባል አይችለም። ዛሬ አንዳንድ ቦታዎች የሚታየው የጀሪካን ሰልፍ መንግሥትን ኣያሳፍረውም። ይህ ረሀብና በምግብ ራስን አለመቻል የተከሰተው ከመንግሥት የፖሊሲ ችግር ጋር የተያያዘ ነው የሚያስብለን ዋነኛ ምክንያት ኣንደኛ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ገበሬ ውስጥ ወደ ሰማኒያ በመቶ የሚሆነው ገበሬ ከፍ ያሉ ቦታዎች የሚኖር ሲሆን ይህ ገበሬ የመሬት ባለቤትነት የሌለው ከመሆኑም ባሻገር የበሬ ግንባር የምታክልን መሬት እያረሰ ይኖራል። በአማካይ አንድ ሄክታር መሬት ነው የሚያርሰው። መንግሥት ይህንን ሰፊ ህዝብ በዚህ መልኩ እንዳይንቀሳቀስ ኣፍኖ ይዞ በሌላ በኩል ደግሞ በዝቅታ ቦታዎች አካባቢ ያለውን ለም መሬት ለመሬት ቅርምት ዳርጓል። እነዚህ ሁለት መሰረታዊ የግብርናው ችግሮች ያለንን ሪሶርስ ተጠቅመን ረሀብን እንዳናሸንፍ ኣድርጎናል። ለረሀብ ኣጋልጦናል። በሌላ በኩል መንግሥት የምከተለው የእድገት ኣቅጣጫ ግብርና መር ነው ይበል እንጂ በተግባር ግን በብልጭልጭ (glitz economy) እድገት የተለከፈ ነው። ለታይታ የሚሆኑ ነገሮችን ሰርቶ “በጥንድ እያደግን ነው” አጨብጭቡ ማለት ለስልጣን እድሜ ይቀጥላልድ ክመትን ይሸፍናል ብሎ ያምናል።

በመሰረቱ አገሮች ሁሉ የዝናብ ሁኔታ ስለተመቻቸላቸው ኣይደለም ከርሀብ ያረፉትና ዜጎቻቸውን ያላሥራቡት። ለምሳሌ ግብጽን ብንወስድ ይህቺ ኣገር በዝናብ ኣትደገፍም። የሷ ድጋፍ መስኖ ነው። ከሀገሪቱ መሬት  ዘጠና እጅ የሚሆነው በረሀ ነው። ለምንም ኣይሆንም። ለእርሻ ከሚሆነው ጥቂት መሬቷ ውስጥ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆነው በመስኖ የሚለማ መስኖን የተደገፈ ነው። በመሆኑም በየዓመቱ አንጋጣ የምትጠብቀው የለምና ያለ ኣሳብ ከመስኖ ልማቶቿ ቀለቧን ታፍሳለች። ራሷን ከመቻል ኣልፋም እነሆ ዛሬ ለእኛ ለርሀብ ማስታገሻ የሚሆን ወደ ኣንድ ሚሊዮን ዶላር ለገሰች።

የኢትዮጵያ መንግሥት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛው ግብርና መር ፖሊሲ ኣለኝ በሚል ነው። ግብርናን ተገን ኣድርገን ነው ወደ ኢንዱስትሪ የምናድገውና ጥርመሳ ውስጥ የምንገባው ይሉናል። በመርህ ደረጀ ብዙ ሰው ይስማማል። በርግጥም በኛ ሁኔታ ግብርና መር የልማት ስትራተጂ ነው የሚያስፈልገን። ታዲያ በተግባር ግብርና መር ማለት ቢያንስ ቢያንስ በዚህ ሩብ ምእተ ዓመት የስልጣን ዘመን በመስኖ ሊለማ የሚችለውን መሬት ጥርግ ኣርጎ መጠቀም ሲቻል ነበር። እስካሁን የለማው ኣምስት በመቶ ኣለመሙላቱ የሚያሳየው ግብርናው ላይ ትኩረት ኣለመደረጉ ነው። ወሎ ውስጥ በመስኖ ሊለማ የሚችል በብዙ ሺህ ሄክታር የሚለካ መሬት እያለ  ዝናብ ሲጠፋ ረሀብ ከተፍ ኣለ። በጣም በቂ የሆነ የከርሰ ምድር ውኃ እያለን ያንን እየጎተቱ ኣውጥቶ ኣካባቢን ኣረንጓዴ ማድረግና ቢያንስ ረሀብን ማጥፋት ሲቻል ግብርናው መር መንግሥት ኣልሞከረውም። ውኃ ያዘለ መሬት ላይ ቆመን በውኃ ጥምና በርሀብ አለቅን::

በጣም የሚገርመው ደግሞ በተለይ በአሁኑ ሰዓት እንዲህ ይህ ሁሉ ሕዝብ በፖሊሲ ችግር ተርቦ እያለ መንግሥት ኣለመደንገጡ ነው። ይሄ ኣሳዝኖኛል:: ልክ ስታሊን የዩክሬንን ህዝብ ኣፍኖ እንደጨረሰው መንግሥትም የቁጥር ጨዋታ ይዟል። ረሀቡን ለመሸፈን ይሞክራል። ኣንዳንዴም ረሀቡ በቁጥጥሬ ስር ነው ይላል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣  ኣሜሪካ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ ረሀቡ ኣሳሰበን የሚለገሰው እርዳታም በቂ ኣይደለም እያሉ ኣሳብ ይዟቸዋል። እንዴውም በቅርቡ የተባበረችው ኣሜሪካ ድርቁ ለሰኪዩሪቲዋ ኣሳስቦኛል ብላለች። በርግጥ ኣርቆ ኣሳቢ መሪዎች ስላሉ ነው። ድርቅና ረሀብ ኣገርን ሊፈታ ይችላል። እየተባባሰ የመጣው ሥራ ኣጥነትና ስደት ሲደመር ርሀብ የአገርን ሉዓላዊነት የሚደፍሩ ኣገርን የሚያፈርሱ እምቅ ችግሮች ናቸው። ይህንን ጦማር እየጻፍኩ ባለሁበት ሰዓት እንኳን ሁለቱ የዓለማችን ታላላቅ መሪዎች ማለተም ፕሬዚደንት ኦባማና የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ አሜሪካ ውስጥ በተሰበሰቡበት ወቅት ፕሬዚደንት ኦባማ እንዲህ አሉ፣ “ከሀምሳ ዓመታት ወዲህ የከፋ ነው የሚባለው ድርቅ በኢትዮጵያ ያስከተለውን የምግብ እጥረት ለመርዳት አስቸካይ ርምጃ ወስደናል::”

በዚህ ደረጃ ትኩረት ያገኘና ዓለምን ያሳሰበ ድርቅ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ኣሳሳቢ ኣይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግብርና መር የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ኣለኝ የሚለው መንግሥት በሁለተኛው ዙር ላይ ኣስር ሚሊዮን ህዝብ ሲያስርብ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምን እንደሚያደርጉ ኣላውቅም። ለህዝባዊ ተቃውሞ ኣንዱ ትልቁ መነሻ የድህነት መጨመር ሲሆን በተለይ በረሀብ ሰዎች ከተጎዱ ደግሞ ከበድ ያለ የለውጥ ትግል መኖር ኣለበት። ኣሜሪካም ሆነች ካናዳና እንግሊሊዝ፣ ስዊድን፣ አውስትራሊያ፣ ኖርዌይ፣ ጀርመንና ሌሎች ለጋሽ አገሮች ድርቁና ረሀቡ ያሳሰባቸውን ያህል እንዴት የኛው መንግሥት ኣላሳሰበውም የሚለው ነገር እንደገና እጅግ ገራሚ ነው።

ለማናቸውም ዋናው የአገራችን ረሀብ ችግር ያለንን ውኃ ስቦ እያወጡ ማልማት ኣለመቻል ጋር የተያያዘ ነው። የተራብነውም ውኃ ወይ ከመሬት ውስጥ  ወይ ከወንዞቻችን ስበን ማልማት ባለመቻላችን መሬታችንን ለመሬት ነጣቂ በማስረከባችን፣ የመሬት ላራሹ ጥያቄ ባለመመለሱ ሲሆን ይህም በቀጥታ የመንግሥት ችግር ነው። ከፍታ ቦታዎች ላይ ያለው ድሀ ገበሬ መሬቱን በከርሰ ምድርና በመስኖ ውኃ እያለማ እንዳይጠቀም ካለመታገዙም በላይ የመሬት ላራሹ ጥያቄ ሀምሳ ዓመት ሙሉ ቆይቶ እነሆ ሰማኒያ በመቶ የሚሆን ገበሬ በበሬ ግንባር በምታህል መሬት ላይ ታስሮ ይገኛል። ኢትዮጵያ  ታሪካዊ ኣገር እንደመሆኑዋ ለጋሽ ኣገራት በቀና ልብ እርዳታውን ቢያጎርፉትም ግብርናው ከጥንቱ ኑሮው ንቅንቅ ኣላለም። ገበሬው ወገናችን ዛሬም የዛሬ ሶስት ሺህ ዓመት ያርስ እንደነበረው ያርሳል፣ በሳር ቤቶች ውስጥ ይኖራል፣ ሁለ ገብ እርሻን ተጠቅሞ ኣነሰችም በዛች ያችኑ ከጓዳው እያገኘ ለመኖር ይጥራል እንጂ የገበያ ሰው ኣልሆነም፣ የዛሬ መቶ ሁለት መቶ ዓመት የነበረው ግብርና ሲስተም ዛሬም ይኖራል። በእግሩ ይሄዳል፣ በቤቱ ውስጥ የሚጠቀምባቸው መሳሪያዎች አያቱ ይጠቀምባችው ከነበሩት አይለይም። የታየው ለውጥ ህዝብ ብዛት ሲጨምር የመሬት ጥበት ካልሆነ ግብርናውና ገበሬው ኣልተለወጡም። ተጀምሮ የነበረ መሰረተ ትምህርት የደርግ በመሆኑ  በታጋዮች ተደመሰሰና ስሙን መጻፍ ጀምሮ የነበረው ገበሬ ወደ ጥንቱ ማይምነቱ ተመለሰ።

ለዚህ  ረሀብ የዳረጉን ጉዳዮች በዓጠቃላይ ኣንደኛ የመሬት ፖሊሲውና ርዳታን በአግባቡ አለመጠቀም ናቸው። በኣሥራ ዘጠኝ ስልሳዎቹ ተነስቶ የነበረው የመሬት ላራሹ ጥያቄ መነሳት ኣለበት የሚያስብለን ይሄ ነው። ርሀባችን ሰው ሰራሽ በመሆኑ የመንግሥት ለውጥ የግድ ያስፈልገናል። ኢትዮጵያ ከሰሀራ በታች ካሉ ኣገራት በእርዳታ መቀበል ከፍተኛውን ቦታ ይዛለች። ብዙ እርዳታ እናገኛለን። የኢትዮጵያ መንግሥት ዓመታዊ ባጀት ከሀምሳ እስከ ስልሳ በመቶ የሚሆነው ከለጋሾች በሚገኝ ርዳታ የቆመ ነው። ይህቺ ኣገር በዚህ ልክ ርዳታን ተገን ኣድርጋ የምትኖርበት ጊዜ  በታሪክ ኣልነበረም። አጼ ኃይለ ሥላሴ እርዳታ ያደርጉ እንደነበር ይነገራል። ደርግ ሲመጣ በተወሰነ ደረጃ ርዳታ መቀበል የጀመርን ሲሆን ኣሁን ስልሳ በመቶ ባጀታችን በእርዳታ የቆመ ሆኖ ቁጭ ብሏል። እርዳታ ለጋሾቹ የሚረዱት ኢትዮጵያ ራሷን እንድትችል ነበር። ይህ ሁሉ እርዳታም እየተገኘ ግብርናው ፈቀቅ አለማለቱ ያሳዝናል ሳይሆን ያስቆጣል። በዚህ ያልተቆጣን በምን ልንቆጣ። ዛሬ በኦሮሚያ፣ ጋምቤላና አማራ አካባቢ ያሉ ተቃውሞዎች በርግጥ ፍትሀዊ ናቸው ብቻ ሳይሆን  በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ሊደገፉ ይገባል። በዚያ በድሀ ገበሬ ስም የሚመጣው እርዳታ ብዙ መስኖ ልማቶችን ሊሰራ ሲችል ተዘርፎ ይሸሻል። የኢትዮጵያ ኣንዱ ትልቅ ችግር ገንዘቡ መዘረፉ ብቻ ሳይሆን የተዘረፈው ገንዘብ መሰወሩ ነው። ዓለም ባንክ ውስጥ ከፍተኛ ኤክስፐርት የነበሩት ዶክተር አክሎግ  ቢራራ ሲናገሩ ሙስና ኢንዶኔሽያም ውስጥ ነበር ይላሉ። ኢንዶኔሽያም ውስጥ ከፍተኛ ሙስና ይታይ የነበር ቢሆንም ዘራፊዎቹ ገንዘቡን ዘርፈው ሲያበቁ እዚያው ኣገራቸው ውስጥ የንግድ ተቋማት ነው የሚከፍቱበት የነበረው። ኣንዳንዶቹ ሆስፒታል፣ ኣንዳንዶቹ ሆቴል፣ ኣንዳንዶቹ የግብርና ሥራ ይሰሩበት ነበር ኣሉ። ይሄ መቼም ሳይሻል ኣይቀርም። የኢትዮጵያን ጉዳይ ስናይ ኣንደኛ ፖለቲካው ራሱ የብሔር በመሆኑ እነ ኤፈርት የሕዝብን ንብረት ወስደው ምን እንደሚያደርጉት ኣይታወቅም። ኦዲት ተደርጎ ለህዝብ ይፋም ኣይሆንም። የኢትዮጵያውያን ሁሉ ሀብትም ኣይደለም ተብሏል። ሕወሓት በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ከትግሉ ጎን ለጎን እየነገድኩ ያደለብኩት ነውና ንብረትነቱ የትግራይ ሕዝብ ነው ይላል። ይህንን ሲል አያስጠላውም። የሚገርመው ደግሞ ይሄንን የግሌ ነው ብሎ በአንድ እጁ ይዞ በጉጂ ኦሮሚያ አካባቢ ያለውን ወርቅ ደግሞ የጋራችን ነው ብሎ በሌላ እጁ ይዝቃል። ይህን ሲያደርግ አያስጠላውም። ጉጂዎች የሚጠጣ ንጹህ ውኃ እንኳን ኣያገኙም። ስለዚህ በእንዲህ ዓይነት የመንግሥት  እምነቶች ግብርናው ኣያድግም። ርሀብም ይህ መንግሥት አስካለ ይቀጥላልና ድሮ መሬት ላራሹ ብለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደታገሉ የዛሬው የአለማያ የግብርና ሳይንስ ተማሪ፣ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ፣ የጅማ፣ የዲላ፣ የጎንደር ወዘተ….. ሊነሱና የገበሬውን ኣባታቸውን የመሬት ፖሊሲ ጥያቄ ሊያስመልሱ ይገባል። ዛሬም መሬት ላርሹ ብለን ለውጥን ማምጣት አለብን። አለበለዚያ የተባበረችው አሜሪካ እንዳሳሰበችው ይህቺን አገር ረሀብና ስደት ሊፈታት ይችላል። ለለውጥ መነሳትና መታገል አለብን። ውኃና አፈር እያለን፣ እርዳታ እያገኘን ሕዝባችንን ያሥራበ መንግሥት ላይ ጥያቄ ካላነሳን በታሪክ ተጠያቂ እንሆናለን። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ።

 

 

The post በርሀብ የሚገድል መንግሥት እንዴት በሥልጣን ላይ ይቆይ? – ገለታው ዘለቀ    appeared first on Zehabesha Amharic.

ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ታላቅ ተቃውሞ ሰልፍ ኢትዮጵያውያን አድርገዋል (ቪዲዮ)

“ሳውዲስታርስ የሩዝ እርሻ”በፋይናንሺያል ታይምስ |ዘገባ በጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ

በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ የታቀደው ድቡቁ የህወሓት ሴራ ሲጋለጥ |ምስጢራዊ መረጃ

0
0

ከዚህ በታች የምታነቡት በትግረኛ ተጽፎ የህወሓት ባለስልጣናት የተወያዩበትና የተስማሙበት ድብቅ መረጃ ነው። ይህ ረቂቅ ዶኩመንት በወያኔም ባለስልጣናት ተቀባይነት አግኝቶና ጸድቆ በተግባር በአስቸኳይ በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ በተግባር ላይ እንዲውል ስምምነት ተደርሶበታል።
ይህ በትግረኛ የተዘጋጀውና ወደ አማርኛ የተተረጎመው ሰንድ የተዘጋጀውና በህወሃት ባለስልጣናት እንዲተገበር ያቀረበው በብዕር ስሙ ዘጽኣት አናንያ በሚል ስም የሚታወቅ እውነትኛ ስሙ ግን ጎይቶኦም የማነ ገብረኣናንያ የተባለ ቀንደኛ የህወሃት ስውር ፊታውራሪ ነው።
ከትግረኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመውን ከዚህ ቀጥሎ ያንብቡ። በትግረኛ የተጻፈው በመጨረሻዎቹ ገጾች ላይ ማንበብ ይቻላል።

ባለፉት 15 ኣመታት በትንሽ ግለሰቦች ሲነሳ የቆየ ባሳለፍናቸው ትንሽ ኣመታት ደግሞ የተቃውሞ ቅርፅ እየያዘ እየመጣ ያለው በምዕራባዊ ዞን ወረዳ ጠለምትና ግላዊ ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለሰቦች በኣሜሪካ በሚገኙት የሰሜን ጎንደር ወልቃይት ጠገዴ እድርና በጎንደር ህብረት በሚባሉ የስምሪት ኣሰላለፍ እየተረዱ ይመለከተናል በሚሉት የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ኣካባቢ እጆጃቸው ለኣንዳችም የልማት ስራ እንኳ ሳያነሱ ለነዚያ የግል ቅሬታ ያለባቸው ሰዎች በማሰባብሰብ የገንዘብ፣ የሞራልና ሓሳብ ምክር ሙሉ ድጋፍ በመስጠት ለኣራቱም የትግራይ ወረዳዎች ነዋሪዎች የኣማራ ማንነት ጥያቄ እንዳላቸውና በማንነታቸው ወደ ሚመስላቸው የኣማራ ማንነት ሊመለሱ እንደሚፈልጉ በማስመሰል ህዝብ ያልጠየቀው ጥያቄ በመያዝ ከህግ ውጭ የማንነት ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ፌደረሽን ምክር ቤት፣ የኣማራ ክልል ርዕሰ ኣስተዳደርና ሌሎች የፌደራል ኣካላቶች እንደደረሳቸው በተለያየ መልክ ተሰራጭቷል።

ይህ ጉዳይ ሕጋዊ ለማስመሰልና ለማሰራጨት ሰንደቅ ጋዜጣ በ28 ቀን 2008 ዓ/ም ዕትም ኣድምቆ ለማቅረብ ሞክሯል። ከዚህ በተጨማሪ በትምክህተኞች ሃይል የሚመሩ ሚዲያዎች እየተሰራጨና እየተስፋፋ መጥቷል ፤ እየመጣም ነው። ከዚህ በመሻገር ደግሞ በውጭ ከሚገኙ ሚሊዮን ዶላሮች ለዚህ ኣላማ ለማዋጣት ዝግጁነታቸው በማጠናቀቅ ለጦርነት እስከ የማነሳሳት ስራ ለመስራትና ከጎጃምና ኣብዛኞቹ የጎንደር ወረዳዎች የገንዘብ እርዳታ የሚደረግላቸው በቀን ሰራተኛነት ስም ወደ ምዕራባዊው የትግራይ ዞን (ወልቃይት፣ጠገዴ፣ ቃብቲያና ሁመራ) በብዛት በማስገባት ኗሪ ለማድረግ በተዘጋጁብት ግዜ እና ከኣማራ ክልል ኗሪ ለዚህ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ከጎናቸው በቆሙበት ስኣትና በትንሽ የብኣዴን ኣመራር ካድሬዎች ኣይዟችሁ እያሉ ባሉበት ስኣት ትግሬዎች እንደትግሬነታችን ተነሳስተናል ወይ የሚል ጥያቄ እንድታነሳ ያድርጋል። የዚህ ምልክት በዚህ ሳምንት በፌስቡክ የተለቀቀው የ13 ደቂቃ የቅስቀሳ ቪድዮ በቋራ ይካሔድ ወይንስ በኣርማጭሆ ብዙ ሰው በተገኘበት ዳስ ተጥሎ የመብልና የመጠጥ ግብዣ ተደርጎ ቅስቀሳ ሲደረግ ከላይ ያለውም ሆነ ታችኛው የብአዴን ኣመራር ኣያውቅም ማለት የዋህነት ነው።

ስለሆነ በትግራይስ እንደ ህወሓት ምንና ምን ስራዎች እየተሰሩ ነው የሚል የብዙ ትግሬዎች ጥያቄ እንኳን ቢሆንም በሚስጥር እየተሰራ ከሆነ ጥሩ ሆኖ ሳለ ህወሓት በመሬት ጉዳይ ተዝናንታ ስትቆይና በድረስ ድረስ ባለቀ ስኣት ብትሯሯጥ ግብ ሳይመቱ የመቅረት የነበሩዋት ክፍተቶች ኣሁንም እንዳይከሰት እንድትጠራጠር ያደርግሃል። ይህ በኢትዮጵያ የመንግስት ሽግግር ግዜ የኣማራና ትግራይ ክልል ሲከለሉ የነበረው የህወሓት ቅንነት ግን ደግሞ የብአዴን ተንኮል ታይቷል። ለምሳሌ፦ ግልፅ በሆኑ ኣከባቢዎች በግልፅ የሚወሰድ ሲሆን በእነዛ የሁለቱም ብሔረሰቦች የሚገኙበት ኣካባቢ ማለትም የትግርኛ ተናጋሪዎችና የኣገዉኛ ተናጋሪዎችም ተደበላልቀው የሚኖሩበት ከሰቆጣ እስከ ኣበርገሌ ፊናርዋ የትግርኛ ተናጋሪ ነህ ወይስ የኣገውኛ እየተባሉ በሚጠየቁበት ግዜ በብአዴን የተሸረበ ተንኮል ለሁለቱም ቋንቋ እኩል የሚችላቸውን ህዝብ ትግርኛ ትችላለህ ሆይ ተብሎ ሲጠየቅ ኣልችልም የሚል ጭንቅላቱ ነቅንቆ ምልክት ሲያሳይ በተቃራኒው ደግሞ ኣገዉኛ ትችላለህ ሆይ ተብሎ ሲጠየቅ ኣዎ ብሎ መልስ እንዲሰጥ ውስጥ ለውስጥ ተሰርቶበት በኣብዛኛዎቹ ድል ሲቀናቸው በተወሰኑ የፊናርዋ ኣካባቢና በግማሽ የኣበርገሌ ኣካባቢ ተደናቅፈው በዚህ ምክንያት ፊናርዋ ከፊል የኣበርገሌ ወደ ትግራይ ሲሆኑ እነዛ ብዙዎቹ ቀበሌዎች ግን ወደ ኣማራ እንዲከለል ተደርጓል፤ ይህ የክልሎች መነሻ ክለላ ስለነበረ ብዙ ጥያቄዎችን ኣላስነሳም። ከክልላችን ውጭ ባሉ ስንመለከት ደግሞ ከ1998 እስከ 2008 ዓ/ም የይገባኛል ጥያቄዎች የሶማሊ ክልል ከኦሮሚያ ክልል ፤ የደቡብ ክልል ከኦሮሚያ ክልል በሁለቱም በኩል ጥያቄ የተነሳበት ኣከባቢዎች በፌደረሽን ምክር ቤት ወደ ሪፈረንደም እንዲቀርብ በማድረግ ልክ ይሁን ኣይሁን እልባት ተደርጎበታል። ለምሳሌ፦ በሶማሊና ኦሮሚያ ክልል የተነሳው የይገብኛል ጥያቄ ከመኢሶና ኣዋሽ ወንዝ ጥግ እስከ የኬንያ ኣዋሳኝ የሚዘልቅ ብዙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ያቀፈ ነበር። በዚህ ሁኔታ ሁለቱም ክልሎች ኮሚቴ ኣቋቁመው የሪፈረንደም ቀን የሚያደርስ የስብከትና ብዙ ሚሊዮን ብር በጣም ብዙ ሺ ኩንታል ስንዴ እና ሩዝ እንዲሁም ዘይት ለህዝቡ በዋነኝነት ለጎሳ መሪዎችና የኣገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ተሰሚነት ላላቸው ወገኖች ሲሰጡ ከቆዩ ብሗላ የቋንቋቸው ተናጋሪዎች እንደስጦታቸው መጠን፣እንደ ስብከታቸው፣ ተንኮላቸውና ቅልጥፍናቸው መጠን ወረዳዎችና ቀበሌዎች ኣግኝተዋል። በኦጋዴን ሰራዊት መከላከል ምክንያት ደካማ ውስጣዊ ኣሰራር የነበረውን የሶማሊ ክልል የተሻለ የኮሚቴዎች ኣወቃቀር፣ ብር፣ ስንዴና ሩዝ የነበረው የኦሮሚያ ክልል በጣም በበለጠ ሁኔታ ድል ሊቀናው ችሏል። በኣሁኑ ስኣት ኣብዛኞቹ የሶማሊ የነበሩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በማጉረምረም ላይ ናቸው። ተታለን ወደ ኦሮሚያ ሔደን ኣሁን ልጆቻችን ቋንቋቸውን ትተው በኦሮምኛ በግድ እየተማሩ ነው፤ ያለ ቋንቋችንና ኣስተዳደራችን እየተዳደርን ነው ይላሉ። ይሁን እንጂ የማይመለስ ንስሓ መሆኑ ግን በሚገባ ተረድተዋል።
ይህ ከላይ የተገለፀው በእኛ ላይ እንዳይደገም እኛ ትግሬዎች ምን ብናደርግ ነው የሚሻለው?

የወልቃይት ጠገዴና ኣካባቢዎቹ የታወቁ የናይዝጊ ልጆች መሆናቸው ያ መሰረቱ የማይጠፋው የናይዝጊ ቤተ መንግስትና የትግርኛ ታናጋሪዎች መሆናቸውን የሚያጠያይቅ ስላልሆነ የፅሑፍ ሓተታ ኣያሰፈልገንም። ታዲያ ለምን? ቢሉ ከፊላችን እያወቅን ከፊላችን ደግሞ በየዋህነት እንዳንዘናጋ ወይ ደግሞ ብአዴን ያን ውስጣዊ የክልላዊ ስልጣን ተቀባይነቱ ለማናር ብሎ ብአዴን ህዝብ እየጠዬቀ ነው በሚል በግልፅ ጥያቄው ለፌደረሽን ምክር ቤት ሊያቀርብ ስለሚችል ሳንታለል ተዘጋጅተን መቆየት ስልያስፈልገን ነው። ይህ የተንኮል ምልክት በታየባቸው የምዕራባዊ ዞን ኣካባቢዎች ብቻ ሰርተን የምንተኛ ሳይሆን በራያ ኣንዳንድ ኣካባቢዎችም በልዩ ሁኔታ ደግሞ ራያ ኣላማጣ፣ ኦፍላ፣ በኮረም ከተማና ኣላማጣ ከተማ ጭምርም ሊሰራበት ይገባል። ለዚህ ደግሞ በግልፅና በውስጣዊ ኣሰራር ሊተገበሩ የሚገቡ ኣንገብጋቢ መርሃ ግብሮች ኣሉ።
እነዚህም፦

ሀ. በግልፅ ሊሰራባቸው የተገቡ መርሃ ግብሮች

የህወሓት ፓርቲ ገዢዎችና በትግራይ ክልል ብቻ የተመሰረቱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከመወነጃጀል ስራ ነፃ ሆነው በትግራይ የበላይነት ኣላማ ኣምነው የዚህ ክልልና ሃገር እድገት ለማረጋገጥ የኣቋምና የመተማመን የምናይበት ግዜ እየናፈቀን ነው። ይህ ኣሁን ያለንበት ግዜ ደግሞ ይሔን ጉዳይ ኣጥብቆ የሚፈልግበት ሁኔታ መሆኑ ማስተዋል ይጠይቃል። በኦሮሚያ ያሉ ተቃዋሚዎችና ገዢው ኦህዴድን ብናይ በሉኣላዊነትና የህዝብ የድህንነት መብትና ተጠቃሚነት የተዋሃዱና የተናበቡ ሆነው ይታያሉ።

በወረዳዎች ያለው የመልካም ኣስተዳደር እጦትና በሕብረተሰቡ መሰላቸትና ማጉረምረም ስለሚፈጥር ለእነዚህ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች የሚበቅሉበት በማዳበሪያ የተዘጋጀ ለም መሬት በራሳችን እየፈጠርንላቸው ስላለን በኣፋጣኝ የሚታረምበትና ስርኣትና መልክ የሚይዙበት ሁኔታ መፈጠር ኣለበት። ወደ ምዕራባዊው የትግራይ ዞን (ወልቃይትና ጠገዴ) የሚላኩት የተሾሙ የዞንና የወረዳ ኣመራሮች፣ የፍትህ ኣካላት በደጋማው የትግራይ ኣካባቢዎች ደካማ የስራ ኣፈፃፀም ያላቸውና ጥፋትም ያላቸው በቅጣት መልክ ወደ ኣካባቢው እንዲላኩ መደረጉ፤ መምህራን፣ የጤና ባላሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች ደግሞ ለስራቸው መጀምሪያ ልምድ እንዲያገኙበት እንዲሆን ተደርጎ የተፈረደበት ኣካባቢ ነው። ይህ ደግሞ በኣካባቢው ልማትና መልካም ኣስተዳደር ትልቅ ኣሉታዊ ተፅእኖ ኣለው።

የመፍትሔ ሓሳብ፦

ያ ኣካባቢ በልማት ተጠቃሚ የሚሆንበትን በተጠቃሚነቱ በጎረቤቱ ከሚገኙት የኣማራ ክልል ወረዳዎች የተሻለ የልማት ተጠቃሚ ሆኖ በሚያይበት ግዜ ትግሬነቱ ኣጠናክሮ የሚቀጥልበትና ለሚመጡ የትግሬነቱ ጠላቶች በጣም ኣጠንክሮ የሚዋጋበት ሁኔታ ስለሚፈጥር በዚህ ጉዳይ በጣም ተጠናክሮ ቢሰራበት ዘላቂ መፍትሔ ያስገኛል። በተጨማሪ ከምዕራባዊው የትግራይ ዞን ውጭ ብንመለከት እንኳን በደርቅ የተጠቁ የኣማራ ክልል ወረዳዎች ዋግሀምራና ራያ ቆቦን በቂ የሰውና እንሰሳ ምግብና የመጠጥ ዉሃ ሲቀርብላቸው በኣንፃሩ ደግሞ በእነዚህ ኣከባቢ የሚገኙ የኣማራ ክልል ኣዋሳኝ የሆኑ የትግራይ ወረዳዎች እንደ ጣንቋ ኣበርገሌ፤ ሰሓርቲ ሳምረና ራያ ለሰዉና እንሰሳ የሚያስፈልግ ምግብና የመጠጥ ውሃ ከጅምር በዘለለ የሚታይ ስራ ኣለ የሚያስብል ኣይደለም። ራያ ቆቦ ከከርሰ ምድር በሚገኝ ውሃ በመስኖ ሲለማ በኣንፃሩ ደግሞ ቀድሞ የተጀመረው የራያ መስኖ ስራ በትግራይ ስላልተሰራበት የራያ ትግራይ ህዝብ ለልማት ተጠቃሚነት ሲል ወደ ኣማራ ክልል ከሔድን እንደራያ ቆቦ እንለማለን የሚል መንፈስ ፈጥሮ ችግር እስከሚፈጠር ድረስ እንዲያድግ ሰለማያስፈልግ በፍጥነት መፍትሔ ቢደርግለት ኣሁንም ጠቀሜታን ያስገኛል።

ሀ. በውስጣዊ ኣሰራር ሊተገበሩ የሚገባቸው መርሃ ግብሮች

1. ለእነዛ ከህግ ውጭ ኮሚቴ ኣቋቁመው በኣካባቢውና በውጭ (በኣሜሪክ ኣውሮፓና ሌሎች ኣግሮች) እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ኮሚቴና ኣባላቶቹ ጉዟቸው የሚደናቀፍበትና በተጓዙበት ሁሉ እንቅፋት እንዲያጋጥማቸውና ተስፋ እንዲቆርጡ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል። ይሔም በዛ በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ባሉ ትግሬዎችና የትግራይን ጣዕም በሚገባ የሚያውቁ ኣካላት በሚስጥር ሊሰራና ሊከናወን ይችላል።

እነዚያ ኣባላቶቹ ጉዟቸው የሚያቋርጡበትና ከሕብረተሰቡ እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጫና እንዲያድርባቸው መስራት ያስፈልጋል። በዚህ የማይመለሱ ከሆነ ደግሞ ከሕብረተሰባቸውና ቤተሰቦቻቸው የሚለዩበት ስራዎች መስራት የግድ ይለናል። ለዚህ ሃሳብ የሚያንቀሳቅሱ ኣባላት፣ ኮሚቴውና ተባባሪዎቻቸው ከማህበራዊ ኣገልግሎት እንዲገለሉ መስራት፤ሆቴል ፣ መኪና ወዘተርፈ እንዲጠቀሙ በሚቀርቡበት ግዜ ለባለንብረቶቹና ኣግልግሎት ሰጪዎቹ የማንቂያ ሰራ በመስራት እነርሱ የሚፈልጉትን ኣገልግሎት እንዳያገኙ በማድረግ ባለንብረቶቹ ግዴታዎቻቸው እንዲወጡ መስራት ያስፈልጋል።

2. ይህ የትግራይ የቆላ ኣካባቢ ህዝብ (ምዕራባዊው ዞን)በደጋ ከሚኖረው የትግራይ ህዝብ ጋር ስነ-ልቦናዊና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲደለደል ማድረግ። የወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ወረዳዎች ካለፉት መንግስታት ጀምሮ እስከ ኣሁን ድረስ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቱና ማዕከሉ የጎንደር ከተማ ብቻ እንዲሆን ነው የተፈረደበት። የንግድ ሸቀጣ ሸቀጦች ከፋብሪካ ውጤቶች እስከ ኣትክልቶችና ፍራፍሬዎች የሚቀርብለት ከጎንደር ብቻ ነው። ለተጨማሪ የግል ትምህርት ልጆቹ የሚጓዙት ወደ ጎንደር ነው፤የሱዳን ሸቀጣ ሸቀጦች የሚገኝበት በመተማ በኩል ነው፤ በትግራይ ምዕራባዊው ዞን (በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ) እንደምንም ተጠጋግቶ ተጣቦ ኣርሶ ብር ያጠራቀመ ሰው ሲኖር ህንፃና የንግድ ቤቶች የሚሰራበትና የሚከትምበት ጎንደር ወዘተርፈ…ይህ በጣም ሓይለኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ጫና ፈጥሮ ስለሚገኝ ይሔን ችግር ለመቀልበስ ደግሞ ደረሰኝ የሌላቸው ሸቀጣ ሸቀጦች ከጎንደር እንዳይመጡ የክልከላ ጫና ሰለባ እንዲሆን በማድረግ በተቃራኒው ከደጋማው የትግራይ ኣካባቢ ጋር ግንኙነት ለማጠናከር ደግሞ በሽሬና መቀሌ የሚገኙ ታላላቅ ነጋዴዎች በልዩ ሁኔት በማናገር በኣከፋፋዮች ደረጃ ከሁሉም ዓይነት የንግድ ዉጤቶችና ሸቀጣሸቀጦች ከጎንደር ከሚመጣው ንብረት ሁሉ በጣም በቀነሰ የዋጋ መጠን ቢያንስ ግን ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ሙሉ ብሙሉ የሚሸፈንበት መንገድ በኣጭር ግዜ ውስጥ መፈጠር ኣለበት። ከሽሬ ጀምሮ በሉግዲ በኩል የተዘረጋው ጥርጊያ (ሱዳንና ትግራይ የሚያገናኘው የጥርጊያ መስመር) በጣም ተጠናክሮ በፍጥነት እንዲሰራበትና ይህ የጥርጊያ መስመር እንዲጠናከር በጣም ጠንክሮ መስራትና ማገዝ፤ በዚህ ጉዳይ ከሱዳን ጋር በጥልቅትና በፍጥነት መወያየት ያስፈልጋል።

የትግራይ ኪነ-ጥበብ በተለይ የትግርኛ ዘፈኖች ብናያቸው በሁሉም ዘፈኖቹ ሲጠሩ የምንሰማቸው የኣካባቢ ስሞች ትግራይ ማለት ከሽሬ የሚመለስ እንደሆነ የሚሰብኩ ናቸው። ይህን ችግር ከመሰረቱ በማረም ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሁመራ ያካተተ እንዲሆን የትግራይ ጥበበኞች እንዲያስቡበት ማድረግ፤ ምክንያቱም በኣማርኛ ቋንቋ የሚዘፈኑ የጎንደር ኣካባቢ ስም የሚያነሱ ዘፈኖች ሁሉ ብንመለከት ኣሁንም ያልተዋቸው በሽታ የእነዚህ ኣካባቢ (ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰሜን፣ኣርማጭሆ፣ጠለምትና ሁመራ) ስም ሳይጠሩ ኣያልፉም። ስለሆነም የጥበብ ድርሻ በሰው ልጅ ስነ-ልቦና ከፍተኛ ተፅእኖ ስላለው የትግራይ ጥበበኞች ልንሰራበት ይገባል። የቆላው የትግራይ ተወላጅ (ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሁመራ፣ ቃብቲያና ጠለምት) ከጎንደር ታሪክ በላይ በኣክሱምና ይሓ ታሪክ ኩራት እንዲሰማዉና የእኔነት ስሜት እንዲያድርበት ማድረግ የግድ ያስፈልጋል። ከኣጤ ቴድሮስ ታሪክ በላይ የኢትዮጵያን ዳርድንበርን ለማስከበር ላይ እና ታች እያለ ሳለ የሞተውን የኣጤ ዮሃንስ ኣራተኛ ጀግንነት ኣውቆ እንዲኮራበትና እንዲመካበት ቢደረግ የትምክህተኞቹ የኣማራዎቹ ተግባር ማለትም ከድሮ ጀምሮ በተዋረድ የመጣውን ክፋታቸውና ዉሸታቸው እንዲሁም የትግራዋይን ስም የማጥፋትና በወሬ በማስተጋባት ብልግና እንደሰሩ በማስተማር በተቃራኒው ደግሞ የትግራይና ትግራዎትን የበላይነትንና ብሔርተኝነትን ከፍ በማድረግ በውስጣዊ ስብከት እንዲያስተጋባ በማድረግ ጫና መፍጠር።

3. የሐይማኖት ኣባቶች ግዴታዎች፦
በኣካባቢው ኣብዛኛው የኦርቶዶክስ ሐይማኖት እምነት ተከታይና የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆኑ በኣብያተ-ክርስቲያናት ላይ የሚደረጉት ስብከቶችና ኣገልግሎቶች ከኣማርኛ ሙሉ በሙሉ ነፃ እንዲሆኑ በማድረግ በትግርኛ እንዲገለገሉ ማድረግ። በኣከባቢው ወደ ሚገኙ ኣብያተ-ክርስቲያናት የሚመደቡ ገበዝ፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ከኣካባቢ ሰዎች እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ ትግርኛ ብቻ የሚናገሩ ኣገልጋዮች ከሁሉም የደጋው የትግራይ ኣካበቢ የሚመደቡበት ሁኔታ በማመቻቸት የመስበኪያ ቋንቋ ትግርኛ እንዲቆጣጠረው ማድረግ። ይህም ማለት ያ ኣሁን ያለው የኣካባቢው የኣብያተ-ክርስቲያናት ኣገልግሎት የኣማርኛ ቋንቋ የበላይነት የሚያራምዱ የጎንደሬዎችና የጎጃሞች ቋንቋ ለትግርኛ ቋንቋ የሚቆጣጠረው ስለሆነ ነው።

4. የኣካባቢው ተወላጅ የሆኑ ተሰሚነት ያላቸው የኣገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት መሪዎችና ሃብታሞች ትግሬነታቸው እንዲኮሩበትና ለእነዛ በመሓል ስሜት ያሉ ሰዎች ሰብከው የሚያመጡበት ሁኔታዎች ለመፍጠር መነጋገርና መግባባት በመፍጠር እንዲሰሩበት ማድረግና በልዩ እንክብካቤ መያዝ ያስፈልጋል።

5. የኣካባቢው ኗሪ ተወላጆች በመንግስት ስራዎችና በግል ስራዎች በሁሉም የትግራይ ደጋማው ኣካባቢ ከሚኖሩብት የተሻለ ስራ እንዲሰሩ ማድረግና ከትግራይ ነጋዴዎች ጋር ጥብቅ ሁኔታዎችና ግንኙነት እንዲኖር መፍጠር። በተቃራኒው ደግሞ ወደ ትግራይ ምዕራባዊው ዞን የደጋማው የትግራይ ህዝብ በብዛት በማምጣት ቋሚ ኑሮ የሚኖርበትና የሚመራበት ሁኔታዎች በመፍጠር ይህ መርሃ ግብር በፍጥነት እውን እንዲሆን ማድረግ ኣስፈላጊ ነው።

6. ኣዳዲስ የሰፈራ ማዕከሎችን በማቋቋም በሸራሮና ሁመራ የጥርጊያ መስመር ፈቃደኛ የወልቃይትና የጠገዴ ተወላጆች በዛ ኣድርገን ከሌላ ኣካባቢዎች ኣደባልቆ በሰፈራ ማዕከሎች ማስፈር። በኣማራ ክልል ድንበር የሚገኙ ኣዋሳኝ የወልቃይትና የጠገዴ ቀበሌዎች ላይ ከትግራይ በሚመጡ ሰፋሪዎች በቋሚነት እንዲሰፍሩና በእርሻና ንግድ በጣም ፈጣንና ጠንካራ እንዲሆኑ በማድረግ የተለያዩ የብድር ኣገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ እንዲሁም ግብር እንዳይከፍሉ በማድረግ በቋሚነት የሚኖሩበት ሁኔታ ማመቻቸት።

7. በባላባት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆችና ለስራ ከደጋው የትግራይ ኣካባቢበሔዱትና በሚሔዱት የትግራይ ተወላጆች መካከል በትዳር በሰፊው እንዲገናኙ በማድረግ የትግራይ ልጆች ኣንድነት እንዲጠነክር መስራት ያስፈልጋል። በመጨረሻ እነዚህ የመሳሰሉትን የሚነሱ ጥያቄዎች የሚከታተል ውስጣዊና ሚስጥራዊ ኮሚቴ በማቋቋም መፍትሔዎችን ያፈላልጋል፤ በትምክህተኛ የኣማራ ሓይል በኩል የሚደረጉ ዉስጣዊና ዉጫዊ እንቅስቃሴዎች በትኩረት መከታተል ያስፈልጋል።
wolqit1

wolqite 3

wolqite2

The post በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ የታቀደው ድቡቁ የህወሓት ሴራ ሲጋለጥ | ምስጢራዊ መረጃ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live