Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Breaking: የኤፍኤም 97.1 ራድዮ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሥርዓቱን ከድተው ለንደን ሄደው በዛው ቀሩ

$
0
0

Breaking News zehabesha

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኤፍ ኤም ራድዮ የሆነው fm97.1 ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አንድነት ለንደን ለስራ ተልከው በዛው መቅረታቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አጋለጡ::

በገዢው መንግስት ቁጥጥር ሥር የሆነው በዚሁ ኤፍ ኤም ራድዮ ላይ የሚተላለፉ ለከት የሌላቸው የመንግስት ፕሮፓጋንዳዎች እና የሚታፈኑ የሕዝብ ድምጾች እንዳበሳጫቸው የሚገለጽላቸው አቶ አንድነት ስርዓቱን በመክዳት ለንደን ቀርተዋል::

የኢትዮጵያ መንግስትን በመቃወም ሥር ዓቱን የሚከዱ አባላት ቁጥር እየጨመረ ይገኛል:: በቅርቡ በርካታ ፌደራል ፖሊሶች ከነትጥቃቸው ሥር ዓቱን ከድተው ወደ ኤርትራ መግባታቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

The post Breaking: የኤፍኤም 97.1 ራድዮ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሥርዓቱን ከድተው ለንደን ሄደው በዛው ቀሩ appeared first on Zehabesha Amharic.


Breaking: የኢቢሲ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ስርዓቱን ከድተው አሜሪካ ቀሩ

$
0
0

Breaking News zehabesha

(ዘ-ሐበሻ) በመንግስት 100% ቁጥጥር ሥር የሆነው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጨምቤሳ አሜሪካ ለሥራ መጥተው በዚሁ መቅረታቸው ታወቀ::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት በአሁኑ ወቅት ሥርዓቱን በመክዳት በሁለት ዲጂት የሚቆጠሩ ባለስልጣናት እና ወታደሮች ወደ ተለያዩ ሃገራት በመኮብለል ላይ ይገኛሉ::

የኢቢሲ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ጨምቤሳ አሜሪካ ከመጡ በኋላ በአሁኑ ወቅት ሚኒሶታ በተሰኘችው ግዛት ውስጥ እንደሚገኙ ጨምሮ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያሳያል::

The post Breaking: የኢቢሲ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ስርዓቱን ከድተው አሜሪካ ቀሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ወያኔ፤ አንድም በብልሀት -አንድም በጉልበት (ይገረም አለሙ)

$
0
0

Abay Tsehayeወያኔዎች ለትግል በርሀ ገባን  የሚሉበት ግዜ  የንጉሡ ሥርዓ ፈርሶ ኢትዮጵያ ወዴት አንደምትሄድ አይደለም የት ላይ እንደቆመች እንካን ብቅጡ ያልየበት ወቅት ስለነበር ለብሶት ዳርጎ ወደ ጫካ የሚያስኬድ ቀርቶ ከተማ ተቀምጦ ለማኩረፍ የሚያበቃ በደል ነበር ለማለት አይቻልም፡፡ ስለሆነም ወያኔዎች በዛን ወቅት ለትግል የተነሱት የአጼ ዮሐንስን ቤተ መንግሥት ይዘው  የትግራይን መንግሥት የመመስረት ህልማቸውን ለማሳካት መንግሥት አልባው ወቅት ምቹ ሆኖ ስለታያቸው ነበር፡፡ ቢዘገይም ካሰቡት በላይ ተሳክቶላቸዋል፡፡

 

ወያኔዎች ሀ ብለው ትግል ሲጀምሩ በሰነድ ያሰፈሩት ዓላማቸውም  ሆነ ፤አመሰረራታቸውን፣ እድገትና ሂደታቸውን በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች የሚሰጡት ምስክርነት ከሁሉም በላይ ደግሞ  ኢትዮጵያን በጥቅል እየገዙ ነጻ አውጪ የሚለውን ስማቸውን መለወጥ አለመቻላቸውና ተግባራቸው ሁሉ  ጫካ የገቡበትን ዓላማም ሆነ የረዥም ግዜ ዘላቂ ግባቸውን ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ፡፡

 

ንጉሳዊው ሥርዓት ፈርሶ የመጪው ምንነትና እንዴትነት ባልለየበት ሰዐት አጋጣማዊ በአጭር ግዜ ዓላማችንን ለማሳካት ያስችለናል በማለት ከከተማ ተጠራርተው በረሀ ቢወርዱም የአጭር ግዜ ዓላማቸውን ለማሳካትም ሆነ  ወደ ረዥሙ ግዜ ግባቸው የሚያደርሳቸውን መንገድ ለማመቻት በጥልቀት አስበውና  አቅደው  የተነሱ ለመሆናቸው በብልሀትም በጉልበትም የፈጸሙዋቸው ተግባሮችና አሁንም ቀሪ ዓላማቸውን ለማሳካት እየሄዱበት ያለው መንገድ ይመሰክራል፡፡ሀያ አራት አመት አናሳዎቹ ብዙኃኑን ረግጠው እየገዙ ለመዝለቅ መቻላቸውም  በራሱ ከመነሻው በጠንካራ መሰረት ላይ መቆማቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

 

ምንም እሰጥ አገባ የማያስከትለውና እነርሱም ሊክዱት የማይችሉት አነሳሳቸው ለትግራይ መንግስትነት ነበር፡፡ ነገር ግን  አጋጣሚው ለኢትዮጵያ መንግሥትነት አበቃቸው፡፡ እነርሱ ግን መነሻ ዓላማቸውም ሆነ መድረሻ ግባቸው ይህ አይደለምና  ሀያ አራት አመት በሥልጣን ላይ ሆነውም የኢትዮጵያ መንግሥት ለመሆን አልቻሉም፡፡ የኢትዮጵያን መንግስትነት በመያዛቸው ምክንያት የዘገየው ግን ሊተውት ያልቻሉትና መቼ ተግባራዊ እንደሚሆን እነርሱም ርግጠኛ ያልሆኑበትን ዓላማቸውን ማመቻቸቱን ግን አንድም ቀን ችላ ብለውት አያውቁም፡፡

 

ያ የደደቢት ጽንስ ዓላማቸው  በአስተማማኝ ተግባራዊ እንዲሆን  ሁለት አበይት ነገሮችን ይፈልጋል፡፡ አንድ ለሚመሰረተው የትግራይ መንግሥት ዘላቂነትና መረጋጋት ኢትዮጵያዊነት የሚባለው የእንድነት አስተሳሰብ መጥፋትና ኢትዮጵያ የተዳከመችና የተበታተነች ሀገር መሆን፡፡ ሁለት አዲሲቱ ሀገር  በሁለንተናዊ መልኳ ራሱን እንድትችል  የቆዳ ስፋቷን ማስፋት፤ መሰረተ ልማቷን ማስፋፋት የህዝቡን ስነ ልቦና መለወጥ፡፡ ወያኔዎች ይህንን በብልሀትም ሆነ በጉልበት ተግባራዊ ማድረግ የጀመሩት ትግሉን ሀ ብለው ሲጀምሩ ነው፡፡

 

ገና ትግላቸው ሳይጠነክርና አቅማቸው ሳይደረጅ ሀገራዊ ዓላማና አደረጃጀት የነበራቸውን ድርጅቶች ዒላማ ማድረጋቸው በኢትዮጵያዊነት ላይ ላላቸው አመለካከት አንዱና ዋናው ማሳያ ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ በቀላሉ በኢህአፓና ኢዲዩ ላይ የፈጸሙትን ማስታወስ ይበቃል፡፡ ከዛም ከኢህአፓ በወጡ እንበለው በከዱ ወይንም ለወያኔ እጅ በሰጡ  ሰዎች የተመሰረተውና የኢትዮጵያ ህዝቦች  ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ይባል የነበረውን ፓርቲ  ዓላማና ስም አስለውጠው ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እንዲባል ሲያደርጉት ሀገራዊ አሰተሳሰብ ፈጽሞ አንዲጠፋ ታጥቀው የሚሰሩ ለመሆናቸው በቂ ማረጋገጫ ነበር፡፡ ልብ ያለው ብዙም አልነበረም እንጂ፡፡

 

ብሄር ብሄረሰቦች በአለፉት ሥርዓታት የተነፈጉትን የራስን እድል በራስ የመወሰን  መብት ለማጎናጸፍ በሚል ልብ አማላይ ስብከት በየደረሱበት ምርኮኛውንም ወዶ ገቡንም እየሰበሰቡ  አባልም አጋርም ያሉዋቸውን የጎሳ ድርጅቶች በመመስረት ለዓላማቸው ስኬት አንቅፋት ይሆናል ያሉትን  ኢትዮጵያዊ አመለካከት የሚያጠፉበትን መንገድ  ሲያመቻቹ  ዓላማቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁና የመሪዎቹን እኩይ ተግባር የተረዱ ሰዎች  ሊከተል የሚችለውን ጥፋት ለማመላከት ቢሞክሩም ብዙም ከቁብ የቆጠራቸው አልነበረም፡፡

 

ይልቁንም በየጎሳችሁ ተደራጁና የሽግግር መንግሥቱ አካል ሁኑ የሚለውን ጥሪ ተቀብለው አያሌ ኢትዮጵያውያን   በአጭር ግዜ በርካታ የብሔር ብሄረሰብ /የጎሳ ድርጅቶች  በመመስረት እያወቁም ይሁን ሳያውቁ የወያኔዎቹን መንገድ አመቻቹላቸው፡፡ (በደቡብ ብቻ በአንድ ግዜ ከ15 በላይ ድርጅቶች መፈጠራቸውን እናስታውሳለን፡፡)  አስገራሚ የነበረው ነገር  በብሄራዊ ስሜት አቀንቃኝነት በሀገራዊ መፈክር አንጋቢነት ከዛም በላይ በአለም አቀፋዊ አጀንዳ አራማጅነት ይታወቁ የነበሩ  ትላልቅ የተባሉ ሰዎች ሳይቀሩ  የጎሳ ድርጅት መስርተው  የሽግግሩ ፓርላማ ውስጥ ለመታየት መብቃታቸው ነበር፡፡

 

ይህ የኢትዮጵያዊነትን ብሎኮ እየገፈፉ  የየጎሳውን ነጠላ እያለበሱ የማስጨፈር መላው በብዙ መልኩ የሰመረለት ወያኔ የሚዘፍኑትን ዘፈን ግጥምና ዜማ ሳይቀር እየሰጠ  ሁሉንም በተናጠል ማዘፈን ቻለ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም  ያለፈ ታሪክ እየመዘዘ ለእያንዳንዱ የቤት ስራ በመስጠት የኢትዮጵያ ልጆች ርስ በርስ አንዲወጋገዙና ሆድና ጀርባ እንዲሆኑ ለማድረግ ቻለ፡፡

ወያኔዎች ይህን በማድረግ ፖለቲካዊ ዓላማቸውን ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ መሰረታቸውን ለማጠናከር ያስቻላቸውን ኢኮኖሚያዊ እቅዳቸውንም አሳክተዋል፡፡  በድርጅት ከህውኃት በክልል ከትግራይ በስተቀር  ሌሎቹ  በተሰጣቸው አጀንዳ  ተጠምደው በጎሳ ፖለቲካ ሰክረው  እንወክለዋለን የሚሉትን  አካባቢ እንኳን በንቃት ማየት ባለመቻላቸው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የነበሩና የወያኔን ቀልብ ያማለሉ ንብረቶች  ያለምንም ተቃውሞና ሀይ ባይ   የተቻለው  በቀን በጠራራ ጸሀይ ሌላው  በለሊት መብራት እያጠፋ ተጓጓዘ፡፡

 

በወያኔ የራስን እድል በራስ መወሰን ልብ አማላይ  ስብከት ተታለውም ይሁን ከመጀመሪያው በውስጣቸው የነበረው የጎሰኝነት ስሜት አመች ግዜ ሲያገኝ ፈንቅሎአቸው ይሁን ባይታወቅም ድርጅት እየመሰረቱ በወያኔ  የጎሰኝነት መስመር የገቡ ሰዎች እንዳንዶቹ ብዙም ሳይቆዩ ከሰሙ፤ እስከዛሬ የዘለቁትም ቢሆኑ ለወያኔ ከመጥቀማቸው ባሻገር ይህ ነው የሚባል ያስገኙት ፋይዳ የለም፡፡

 

ምንም ተባለ ምንም ተደረገ ግን  ኢትዮጵያዊነት እንዲህ አንደ ዋዛ የሚጠፋ ባለመሆኑ ወያኔ አጠፋሁት ብሎ እፎይ ማለት በጀመረ ማግስት መልሶ እያንሰራራ ይሄው እስከ ዛሬ እንቅልፍ እንደነሳው  ይገኛል፡፡ ወያኔ ከደደቢት  ሲነሳ ካነገበውና ሀያ አራት አመታትም ለተግባራዊነቱ እየሰራ ካለው ዘላቂና የረዥም ግዜ ግቡ አንጻር ከኢትዮጵያዊነት ጋር ሊታረቅ የሚችል  አይደለም፡፡ ኢትዮጵዊነትም በየዘመናቱ ከውስጥም ከውጪም የተቃጣበትን አደጋ ሁሉ ተቋቁሞ ለመዝለቅ የቻለ መቼም ሆነ በማን የሚጠፋ አይደለ እንደመሆኑ መቼም ሆነ በማን የሚጠፋ አይደለም፡፡ ይህም ሆኖ ወያኔ  በበርሀ ታጋይነቱም ሆነ በከተማ መንግሥትነቱ ዘመን የፈጸማቸው  ተግባራት ሁሉ ኢትጵያዊነትን ማጥፋት እንዳላስቻሉት  ከራሱ ተሞክሮ ትምህርት አግኝቶ ከእኩይ ተግባሩ ሊገታ አልቻለም፡፡  በመሆኑም  ግዜ እየጠበቀ ለደደቢቱ ዓላማው ስኬት ሲል በብልሀትም በጉልበትም በሚፈጸመው ተግባር   ሕዝብ እየተጎዳ ነው፡፡ ከዚህ የማያባራ ጉዳት ለመዳን የ ህዝቡ ምርጫ የሌለው አማራጭ አንድ ነው፡፡  እሱም ከወያኔ አገዛዝ መገላገል አለያም  ወያኔ መቼም በምንም ሊያጠፋው የማይችለውን  ኢትዮጵያዊነት ለማጥፋት በየግዜው በሚፈጽማቸው ኢ- ሰብአዊ ተግባራት እየታሰሩ እየተደበደቡ እየተገደሉ  በአንዱ ሲደርስ ሌላው እያለቀሰ ተራውን እየጠበቀ መኖር፡፡  ሁለተኛው  የሚመረጥ ኣራች አይመስለኝም፡፡

 

ለኢትዮጵያ መንግስትነት መብቃቱ  የደደቢት  ዓላማውን ሊያስተወው  ያልቻለው ወያኔ  በኢትዮጵያ መንግሥትነት ስም የያዘውን  ሥልጣን የተነሳበትን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችለውን ምቹ ሁኔታ ለማመቻቸት መጠቀሚያ ማድረግ  የጀመረው ገና ወንበሩ ሳይደላደል እንደነበረ አሌ የሚባል አይደለም፡፡ ይህንንም የቻለውን በብልሀት በዚህ መንገድ ያልሆነለትን ደግሞ በጉልበት ተግባራዊ እያደረገ ከዛሬ ደርሷል፡፡ አሁንም ቀጥሏል፡፡

 

ወያኔ የደደቢት ውጥኑን ለማሳካት ከተጠቀመባቸው ብልሀቶች አንዱና ዋናው  በማር የተለወሰ መርዝ የሆነው ፌዴራላዊ አወቃቀር ነው፡፡  የፌዴራል  የመንግሥት ሥርዓትም ሆነ የመሬት አከላለል የአሀዳዊ ሥርዓት ደጋፊ ከሆኑ ሰዎች በስተቀር በአብዛኛው ሰው የሚደገፍ  በመሆኑ ወያኔ ከላይ ሲታይ ለሀገርና ለሕዝብ በማሰብ የመረጠው በሚመስል ሁኔታ በኢትዮጵያ ተግባራዊ አንዲሆን በህገ መንግስት እንዲሰፍር ያደረገው ብዙም ተቃውሞ ሳይገጥመው ነበር፡፡ ፌዴራል አወቃቀርን የፈለገው የተነሳበትን ዓላማ ገቢራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማሟያነት ብሎም ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በማለም አንጂ ለሀገርና ለሕዝብ አስቦ ባለመሆኑ አከላለሉ በቋንቋንና በብሄረሰብ /በጎሳ ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚከናወን እንዲሆን  የሚያደርግ ሕገ መንግሥት አጸደቀ፡፡   ይህ አዋቃቀር የወያኔን ፍላጎት የሚያሳካ አንጂ በኢትዮጵያ ተግባራዊ የማይሆን ለመሆኑ የደቡብ ክልል የሚባለውን ማየት ብቻ ይበቃል፡፡ ፌዴራላዊ መንግስትነትን ደግፈው ቋንቋና ብሄርን መስፈርት ያደረገውን አወቃቀር የተቃወሙ የመኖራቸውን ያህል ደጋፊዎችም ስላልታጡ የፌዴራል አወቃቀሩን በህገ መንግሥት ለማስፈርም ሆነ ተግባራዊ  ለማድረግ ወያኔ ብዙ አልተቸገረም፡

 

በመሆኑም በፋኖነት ዘመኑ የትግራይን የቆዳ ስፋት ለማስፋት በሀይል የያዛቸውን  የጎንደርና የወሎ ቦታዎች በዚህ የህገ መንግስቱ አንቀጽ መሰረት   ከማጽናቱ በተጨማሪ  ሲጎመዥባቸው የነበሩ ለም መሬቶችን በሙሉ የትግራይ ክልል ብሎ ወደሰየመው ለመጠቅለል ቻለ፡፡ እንዲህ በብልሀት በህገ መንግሥት ሽፋን  ወደ ትግራይ የተከለሉ ዜጎች እኛ ጎንደሬ /አማራ አንጂ ትግሬ አይደለንም ብለው ትግሬ ናችሁ ለመባላቸው የተጠቀሰባቸውን ህገ መንግስት ራሱኑ ለመከራከሪያነት ጠቅሰው ይህን መሰል ጉዳይ የማየት ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን ለተሰጠው የፌዴሪሽን ምክር ቤት አቤት እስከ ማለት ቢደርሱም ጩኸታቸው በተኩላ አደባባይ የበግ አቤቱታ አንዲሉ ሆኗል፡፡ ሕገ መንግሥቱ ወያኔ ሲጠቀምበትና ህዝብ ጥያቄ ሲያነሳ  አፈጻጸሙ የተለያየ በመሆኑ  ሕግ አለ ብለው በህግ ተማምነው ከጎንደር አዲስ አበባ ዘልቀው አቤት ላሉ ወገኖች ለጥያቄአቸው መልስ ሊያገኝላቸው ቀርቶ ከጥቃት ሊታደጋቸው ባለመቻሉ ዓላማ ፍላጎቱን  በብልሀት ካልሆነም  በጉልበት ተግባራዊ በሚያደርገው ወያኔ እየታደኑ ነው፡፡ ህገ መንግሥቱ በተግባር የተጻፈበትን ወረቀትና ቀለም ያህል አንኳን ዋጋ የለውም የተባለውም አንዲህ በመሆኑ ነው፡፡

 

ወያኔ ዓላማውን ተፈጻሚ ለማድረግ አስቀድሞ በብልሀት ብልሀቱ ካላዋጣ  በጉልበት ይሄ አልሆን ካለ ደግሞ  በህግ መሳሪያነት ጉልበት ከሥርዓት ይሉት ዘዴ የሚጠቀም በመሆኑ ከመነሻው ነገሮችን ለዚሁ ያመቻቻል፡፡  በመሆኑም ወደ ትግራይ ሊጠቀልላቸው ያሰባቸውን ቦታዎች አስመልክቶ  በብልሀትም በጉልበትም ምን ማድረግ እንዳለበት ገና ደደቢት ሳለ ነው ያሰበው ያቀደውና የተዘጋጀው፡፡ ይህ እቅዱንም  ነው  በፋኖነት ዘመኑም ሆነ በመንግሥትነት ግዜው ተግባራዊ ያደረገውና አሁንም እያደረገ ያለው፡፡

ከእነዚህ ስራዎች  አንዱና ዋናው ከላይ የተጠቀሰው ቋንቋና ብሄርን መሰረት ያደረገው የፌዴራል አዋቃቀር ሲሆን ሌላው ተቀናሽ ያላቸውን ታጋይ ተጋዳላዮች ቦታው ላይ ማስፈር ነው፡፡ እነዚህ እነ መለስን ቤተመንግስት በማድረስ ተልእኮአቸው የተጠናቀቀና ከታጋይነት ወደ ቀደሞ አራሽነታቸው አንዲመለሱ የተደረጉ  ዜጎች በቦታው የሰፈሩት ከነ ጠመንጃቸው በመሆኑ የተሰጣቸውን  ለም መሬት አርሰው ከሚያገኙት ጥቅም በላይ ለወያኔ የሚሰጡት ጥቅም ብዙ ነው፡፡ ወሰናችን ተከዜ ነው በማለት የሚያስቸግሩትን  እያስፈራሩ ጸጥ ማሰኘት፤ በፍራቻ ለማይበገሩት ደግሞ  ጠመንጃቸውን ስራ ላይ ማዋል፡፡ ይህን ደግሞ ሰሞኑን በተካሄደ ሰልፍ ላይ የተሰሙት ታውቁናላችሁ እናሳያችኋላን ወዘተ መፈክሮች በቂ ገላጮች ናቸው፡፡   ሌላው የወያኔ ርምጃ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ሰዎችን በመውሰድ በወረራ በየዘው መሬት ላይ ማስፈሩ ነው፡፡ ተቃውሞ በርትቶ ትግሉ ገፍቶ በብልሀትም በጉልበትም የማይገታ ከሆነና ወያኔ በመጠባቢቂያነት ወደሚያስበውና አስቀድሞ የተዘጋጀበት ወደሚመስለው  ህዝበ ውሳኔ ቢያመራ የተጋዳላዮቹም ሆነ  የሰፋሪዎቹ ውሳኔ ምን እንደሚሆን የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡

 

ከሀገር ጥቅም አንጻር ሳይሆን ከራሱ ዓላማ ስኬት አንጻር አርቆ የሚያስበውና የሚሰራው ወያኔ ልብ አማላዩን የፌዴራል ስርዓት   ለራሱ ዓላማ ማመቻቻ የተጠቀመበት በመሬት አከላል ብቻም አይደለም፡፡ አንድ ቀን  መንግሥት ሊሆንባት የሚያዘጋጃትን ክልል በቀሪው የኢትዮጵያ ሀብት በሁለንተናዊ መልክ ለማሳደግም ተጠቅሞበታል፡፡ የፌዴራል ስርዓት በሚፈቅደውና በህገ መንግስቱም ውስጥ በተጻፈው መሰረት ክልሎች ሙሉ ነጻነት ቢኖራቸው  እቅዱን ገቢራዊ ማድረግ እንደማይችል ቀድሞውንም የተረዳውና  የዘየደው ወያኔ በአደባባይ  የብሄር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች  ራስን የማስተዳደር መብት እስከ መገንጠል ህገ መንግሥታዊ እውቅና እንዳገኘ እየለፈፈ  በተግባር ግን  የየክልሎቹ ሹማምንት ስሙንና ወንበሩን  ከመያዝ የለፈ ሥልጣንም  ነጻነትም እንዳይኖራቸው አድርጎ ያልተጻፈ አሀዳዊ  ስርዐት እያራመደ የሁሉም ጠቅላይ ገዥ ራሱን አድርጎ ይሾማል ይሽራል ሀብት ይዘርፋል ፡፡

ወያኔ ፍላጎቱን በብልሀት ለመፈጸም እንዲያስችለው በማር የተለወሰ መርዝ ሲያቀርብልን መርዙን በለማየት ለእኩይ አላማው ስኬት ብዙዎች ተባባሪ ሆነዋል ብዙዎችም በዝምታ ተመልክተዋል፡፡ ነገሮች ካለፉ በኋላ መርዙን በማየት የሚሰሙ ጩኸቶችም ሆኑ የሚደረጉ ትግሎች  በብልሀት ያሳካውን በጉልበት ለማስጠበቅ በሚወስደው ርምጃ መስዋእትነት እንጂ ድል ሊያስገኙ አልቻሉም፡፡

ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የተለየ የሚመስል ነገር ይታያል፡፡ ወያኔ በማስተር ፕላን ስም በብልሀት ያሰበው የመሬት ወረራ የገጠመውን ተቃውሞ በጉልበት ሰጥ ለማድረግ ኢሰብአዊ ተግባር ፈጽሞ  አልሳካ ሲለው የለመደውን በህግ ሽፋን ጉልበት ከሥርዓት የመጠቀም አካሄድም ሞክሮ ውጤት ባለማግኘቱ ማስተር ፕላኑን ሰርዣለሁ ብሏል፡፡ ይህን ብሎ ግን በባልስልጣኖች አንደበት የሚነገረውም ሆነ በነብሰ ገዳዮቻቸው የሚፈጸመው ድርጊት እንዲሁም ኦህዴድን በወያኔ ታማኞች ለማጠናከር የተያዘው ርምጃ  ወያኔዎች እንዴት ያሰብነውን ማሳካት ያቅተናል በሚል አልህ ውስጥ ያሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ታክሲ አሽከርካሪዎች ባካሄዱት የአንድ ቀን ስራ ማቆም መንገድ ትራንስፖርት ያወጣውን ደንብ ለሶሰስት ወር አዘግይተነዋል የሚል ምላሽ ተሰምቷል፡፡

ጫካ ሆኖም ሆነ ቤተመንግሥት ተቀምጦ የደደቢት ህልሙን በብልሀትም በጉልበትም ተግባራዊ ሲያደርግ ለኖረው ወያኔ ማስተር ፕላኑን ሰርዣለሁ ማለቱ የመንገድ ሥነ ሥርዓት ደንቡንም ተግባራዊነት ለሶስት ወር አራዝሜአለሁ ማለቱ የህዝብ ትግል ውጤት መሆኑ ባይካድም  ወያኔ የባህርይ ለውጥ አምጥቶ ነው ማለት ግን አይቻልም፡፡ እንዲህ በማሰብ መዘናጋት ከተፈጠረ ይህን ውጤት ያስገኘውን ትግል ማክሸፍ ታጋዮችንም ማስበላት ይሆናል፡፡

ወያኔ ከዓላማው ፍንክች ያለበት ግዜ የለም፡፡ቅንጅቶችን ከጸሀይ በታች ባለ ማናቸውም ጉዳይ ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ ብሎ ትጥቃቸውን  (የህዝብ ሀይል ) ካስፈታ በኋላ እኔ በመረጥኩት አጀንዳና በምለው መንገድ ብቻ ነው መነጋገር የሚቻለው ማለቱ የሚዘነጋ አይመስለኝም፡፡ ስለሆነም በብልሀትም በጉልበትም ያሰበውን ከማሳካት ወደ ኋላ የማይለው ወያኔ ሸብረክ ያለ የሚመስለው ግዜ ለመግዛት ሁኔታዎችን ለማመቻቸትና ወጥመዱን ለማጥበቅ እንደሆነ በመረዳት በማስመሰያ ድርጊቶች ሳይታለሉና ሳይዘናጉ ለተጨባጭ ለውጥ መታገል ያስፈልጋል፡፡

ወያኔ የደደቢት ህልሙን ለማሳካት ብልሀትን ጉልበትን ጉልበት ከሥርዓትን እንደ ሁኔታው እያማረጠም እያደባለቀም አንደሚጠቀመው ሁሉ በለውጥ ሀይሉ በኩል ለትግሉ ከግብ መድረስ አንድና አንድ መንገድና አማራጭ ብቻ የሚጠቀም ሳይሆን መስዋዕትነቱን ቀላል ድሉን ቅርብ ሊያደርጉ የሚችሉ ግንባር ቀደም ታጋይ አታጋዮችን ከአደጋ የሚከልሉ  ወያኔ ጉያ ውስጥ እሳት ማቀጣጠል የሚያስችሉ አማራጭ ስልቶችንና ተግባራዊ የማድረጊያ መንገዶችን  መተለም ያስፈልጋል፡፡ በወያኔ ብልሀት መበለጥ፤ በጉልበት ለሚያደርገው መንበርከክ፤ በህግ ሽፋን በሚፈጽመው ውንብድና መታለል እንግዲህ ያበቃ ይመስላል፡፡ቢሆንም ግን ወያኔ እስካሁን ካጠፋው ይልቅ ወደፊት ሊያጠፋው የሚችለው ለበለጠ ተጠያቂነት እንደሚዳርገው ተረድቶ  እርቅ  የሚፈልግ፤ አድራጎቴን ህዝብ አልወደደውም ብሎ ከደደቢት ህልሙ የሚላቀቅ ሳይሆን ሸብረክ ያለ እየመሰለ የህዝብን ጥያቄ ተቀብያለሁ እያለ  በብልሀትም በጉልበትም ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ ከጥፋት የማይመለስ በመሆኑ  ከነጻነት ወዲህ ማዶ የሚኖር መዘናጋት ተራ በተራ መበላትን ያስከትላል ፡፡

The post ወያኔ፤ አንድም በብልሀት -አንድም በጉልበት (ይገረም አለሙ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ህወሓት የወልቃይትን ህዝብ ጉሮሮ ፈጥርቆ እስትንፋሱን ሊያቋርጠው ተግቶ እየሰራ ነው –ከትግራይ ህዝብ አጓጉዞሊያሰፍር ዝግጅቱን አጠናቋል

$
0
0

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)  “ህወሓት መሬታችንን እንጂ እኛን አይፈልገንም…” የሚሉት የወልቃይት ነዋሪዎች ዛሬ ዛሬ የሚፈፀምባቸው መከራ ከመቸውም ጊዜ በላይ በርትቷል፡፡ ግፍና በደሉ ምድሪቷን አጥለቅልቋል፡፡ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሰዎች በህወሓት ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች እየታፈኑ ደብዛቸው እየጠፋ ነው፡፡ በስውር እየተገደሉ ነው፡፡ የህወሓቶች ሰፋፊ እስር ቤቶች በወልቃይት ነዋሪዎች ተጨናንቀዋል፡፡

Wolqite News

የወልቃይት ህዝብ ይህ ሁሉ መከራ፣ ግፍና ሰቆቃ እየተፈፀመበት የሚገኘው “ትግሬ አይደለሁም አማራ ነኝ” በማለቱ ብቻ ነው፡፡ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ተደራድሮ ለመፍታት ያቋቋመው ኮሚቴ አባላት በህወሓት እየተሳደዱ ነው፡፡ አቶ በለጠ ታደሰ እና አቶ ማሩ ሽፋ የተባሉት የኮሚቴው አባላት የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም በደህንነቶች ታፍነው “የህዝቡን ሃሳብ አስቀይራችሁ ትግሬ ነኝ እንዲል ካላደረጋችሁ በስተቀር በምድር ላይ አትኖሩም…” የሚል ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው በኋላ ተለቀዋል፡፡ ከየካቲት 29 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ሁለቱ ኮሚቴዎች የት እንደተወሰዱ ሳይታወቅ ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡

የወልቃይትን ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ለማፈን የህወሓት ቡድን ከግድያው፣ አፈና እና እስሩ ባሻገር የተለያዩ ሸፍጦችን እየፈፀመ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ከትግራይ አጓጉዞ በወልቃይት ምድር ላይ በአራት ሰፈራ ጣቢያዎች ለማስፈር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በሁመራ እና በሌሎች የወልቃይት ከተሞች የሚገኙትን ሆቴሎች፣ ህንፃዎችና የንግድ ቦታዎች የስርዓቱ ታማኝ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች እንዲከራዩዋቸው እየተደረገ ነው፡፡

በመሆኑም ወልቃይቶች ተዕግስታቸው እንደተሟጠጠና ጠብመንጃቸውን በመወልወል ላይ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡ “በግንቦትና ሰኔ አንዱ ይለያል” በማለት ቆርጠው መነሳታቸው ተሰምቷል፡፡

The post ህወሓት የወልቃይትን ህዝብ ጉሮሮ ፈጥርቆ እስትንፋሱን ሊያቋርጠው ተግቶ እየሰራ ነው – ከትግራይ ህዝብ አጓጉዞሊያሰፍር ዝግጅቱን አጠናቋል appeared first on Zehabesha Amharic.

በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ተከስቷል

የባለቤቴ ፖርን (የወሲብ ፊልም) ማየት ልማድ ወደማልፈልገው ፍቺ እየመራኝ ነው |የዶክተሩን ምላሽ ከነመፍትሄው ያንብቡ

$
0
0

ask your doctor zehabesha

‹‹ባለቤቴን እጅግ እወደዋለሁ፡፡ አሁን ላይ ለእርሱ ያለኝ ስሜት ከ7 ዓመት በፊት ከነበረኝ ስሜት ጋር ሲነፃፀር ቢጨምር እንጂ ቅንጣት ያህል አልቀነሰም›› የሁለት ልጆቼ አባት የሆነው ባለቤቴ የወሲብ ቪዲዮዎችን እና ምስሎችን በስልኩ አማካኝነት ዘወትር እንደሚመለከት ደርሼበታለሁ፡፡ በእጅጉ ተቀይሮብኛል ወሲባዊ ግንኙነት እንደማልፈልግ ስነግረው ምንም ሳያነጋግረኝ እሺታውን ይሰጠኛል፡፡ ነገር ግን ለወትሮው እኔ እስክስማማ ድረስ እጅግ ይጎተጉተኝ ነበር፡፡ ያ ነገር አሁን የለም፡፡ ስልኩን ልጠቀምበት እንዲሰጠኝ ስጠይቀው ፈቃደኛ አይደለም፡፡ በአንድ አጋጣሚ እጄ ላይ ሲገባ በስልኩ ውስጥ በርካታ የወሲብ ፊልሞች እንደጫነ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጊዜ በአካባቢያችን በሚገኝ የኢንተርኔት ካፌ ውስጥ እስከ ምሽቱ 4 እና 5 ሰዓት ድረስ ቆይቶ ይመጣል፡፡ ባህሪውን (ማምሸቱን እና እኔን ትኩረት መንፈጉ) እንዲያስተካክል ብነግረውም ወደምጠላው ግጭት ከመግባት የዘለለ ውጤት ማምጣት አልቻልኩም፡፡ ባለቤቴ ለእኔ ያለው ፍቅር በፍፁም ቀንሷል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ከእኔ ጋር ለመሆን ከቤተሰቦቹ ጭምር ለመለያየት ወደ ኋላ ያላለ ጀግናዬ ነው፡፡ ነገር ግን በይፋ እንኳን ለመወያየት ሞራሌ ከማይፈቅደው ድርጊት እንዴት ላወጣው እችል ይሆን? ስል ራሴን እጠይቃለሁ፡፡

በሌላ መልኩ ወጣትነቴ በማፈልገው መስመር እንዲያልፍ ምክንያት የሆነኝን የወሲብ ቪዲዮ እና የባለቤቴ ባህሪ የበታችነት እና የመከዳት ስሜት ውስጥ እንደከተተኝ ሳስብ ስለዚህ ግንኙነት ቆም ብዬ እንዳስብ እገደዳለሁ፡፡ ለማንም ያላዋየሁትንና ምክር እጠይቅበት ዘንድ ድፍረት ያሳጣኝ የባለቤቴ ልማድ ወደማልፈልገው ፍቺ እየመራኝ ነው››
ወ/ሮ ስሜ አይጠቀስ

መልስ፡-
በ2014 (እ.ኤ.አ) ትኩረቱን በመላው ዓለም ያደረገ ጥናት በእንግሊዛውያን የጥናት ባለሙያዎች ተደርጎ ነበር፡፡ በርካታ ወንድ እና ሴት በጎ ፈቃደኞችን ያሰባሰበው ፕሮጀክት ‹‹Sex›› የሚለው ቃል በስፋት በኢንተርኔት የሚፈለግ ቃል መሆኑን አረጋግጧል፡፡

የቅርቡ የአሜሪካውያን ጥናት ደግሞ 68 ፐርሰንት የሚሆኑት ጎረምሶች እና 18 ፐርሰንት የሚገመቱት ሴት ኮረዶች በትንሹ በሳምንት አንድ ቀን የኮምፒዩተር መስኮት ላይ የሚገኙት የወሲብ ቪዲዮዎችን እና ምስሎች ለመመልከት እንደሆነ አሳይቷል፡፡

ያለንበት ወቅት ታዲያ የወሲብ እና የግንኙነት ቴራፒስቶች የወሲብ ቪዲዮዎች እና ምስሎችን መመልከት ሰዎች በመኝታ ክፍላቸው ከጓደኞቻቸው ጋር ምን እንዲያጋጥማቸው ያደርጋል በሚለው ላይ በይበልጥ ትኩረት አድርገው መስራት የመረጡበት ነው፡፡

የወሲብ ቪዲዮዎችና ምስሎችን መመልከት የወቅቱ መሰረታዊ ጉዳይ ሆኗል፡፡ የዚህ ችግር ሰለባዎችም ቁጥራቸው ከፍተኛ ሆኗል፡፡ በተለይ ወጣት ወንዶች እና በከፍተኛ መጠን ቁጥራቸው እያደጉ የመጡት ሴቶች ለኢንተርኔት እጅ የሰጡ ሆነዋል፡፡

ችግሩ በወንዶች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ግን አሁንም ጫን ያለ ነው፡፡ በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የወሲብ ቪዲዮና ምስሎችን ማየት የጀመሩ ወንዶች በኋላ ላይ በግንኙነት (በትዳር) መታሰራቸው ነፃ የሚያወጣቸው ሰዎች ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ አዕምሮን የሚቆጣጠር ከባድ ልማድ ይሆናል ነው የስፔን የካታላን ዩኒቨርሲቲ የስነልቦና ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ሮድሪገዝ የምትለው፡፡ በርካታ ሚስቶች በመሰል ችግር ውስጥ የሚገኙት ባሎቻቸው ለትዳራቸው ያልታመኑ ያህል ሊቆጥሯቸው ይችላሉ የሚሉት ባለሙያዎች የመፍትሄ ጥረቶቻቸው ውጤታማ ላይሆን ይችላል፡፡

ፓርኖግራፊዎች የወንዶችን አዕምሮ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ከሚደረግ ወሲብ ይልቅ የወሲብ ቪዲዮ እና ምስሎች እርካታ ሊሰጡ እንደሚችሉ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡
ለመሰል ወንዶች አንድም ሴት ከምታስገኝለት እርካታ በላይ ይሄ ሱስ በብዙ የተሻለ እንደሆነ እንዲያስብ በጊዜ ርዝመት በውስጡ የተሰራጨውና ቫሶፕሬሲን የተሰኘው ኬሚካል ያስገድደዋል፡፡

ባለሙያዎቹ መሰል ቪዲዮ እና ምስሎችን በድብቅም ሆነ በጋራ መመልከቱ በራስም ሆነ በትዳር አጋር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ይስማማሉ፡፡ መደበኛ እና ትክክል የሆነ ባህሪ አይደለም፡፡ በግንኙነት ውስጥ ሲደረግ ደግሞ ለጓደኛ ክብር አለመስጠት እና ማዋረድ እንዲሁም ማመንዘር ወይም ለትዳር ታማኝ አለመሆን እንደሆነ ዶ/ር ሮድሪገዝ ይናገራሉ፡፡ በመሰል ሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች አጋሮቻቸው ራሳቸውን መልከጥፉ፣ የተካዱና የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ከማድረግ ባለፈ ልባቸው እና እምነታቸውን ይሰብራል፡፡ በርካታ ጥንዶች በሌላ መልኩ ድርጊቱን በወሲባዊ ህይወታቸው ላይ የሚጨምርላቸው ተግባር እንዳለ በማሰብ የህይወታቸው አካል ያደርጉታል፡፡ ከPom ብዙ እንደሚማሩ በማሰብም በጋራ ቪዲዮውን ምስሎችን መመልከት ያዘወትራሉ፡፡ ይሄኛው እርምጃ ቢያንስ አንዱ የሌለውን እምነት እንዲያጣና የሚሰብርም ልብ እንዳይኖር የተሻለው አማራጭ ይመስላል፡፡

ፓርን ምን አይነት ጉዳት ሊያስከትል ይችላል?
የወሲብ ቪዲዮ እና ምስሎች አቅርቦት እንደ ልብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የጎንዮሽ ጉዳትም በዛው መጠን አግዝፎታል፡፡ ጉዳቱም በየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል የሚገኝን አካል የሚመለከት ነው፡፡

ሙሉ ለሙሉ ከዚህ ልማድ ለመላቀቅ ወስነናል ያሉ በርካቶች ከማረጋገጫቸው ባሻገር በዛው ሱሳቸው ውስጥ የመዝለቅ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡
ሚስቶች ባሎቻቸው አዘውትረው ወሲባዊ ቪዲዮ እና ምስሎችን የሚመለከቱ መሰል ይዘት ያላቸውን ፅሑፎችም እንደሚያነቡ መረጃው ቢኖራቸው እንኳን  ርዕሰ ጉዳዩን አንስተው መወያየቱን አይመርጡም፡፡ ይሄም በሂደት በጥንዶች መሀከል የነበረው ግንኙነት እንዲሻክር ምክንያት ይሆናል፡፡

ሚስቶቻቸውን ስለማፍቀራቸው ማረጋገጫ የሚሰጡት እነዚህ አካላት ለልማዳቸውም ባሪያ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ባንዴ ሁለት ግንኙነትን ማስቀጠል ማለት ነው፡፡ ያለ ውጤታማ የባለሙያ እርዳታ እና የግል ቁርጠኝነት በስተቀር መሀላና መገዘት የቱንም ያህል የመጨረሻ መፍትሄ ሊሆን አይችልም፡፡

የፓርን ሱሰኝነት መገለጫዎች ምንድናቸው?
1. ባሎች በወሲብ ላይ የነበራቸው ፍላጎት ይቀንሳል
ብዙዎቹ የዚህ ችግር ተጠቂዎች ሱሳቸውን ለማስቀጠል ራስን በራስ ማርካትን ደጋግመው ሊፈፅሙ ስለሚችሉ ከጓደኞቻቸው ጋር መደበኛው ወሲብ ላይ የነበራቸው ፍላጎት ይቀንሳል ለሌሎች የእርካታ አይነቶችም መደንዘዝም ይታይባቸዋል፡፡
2. ወንዶች በወሲብ ጊዜ የብልት መቆም ችግር ሊገጥማቸው ይችላል

የፓርን ሱሰኞች ከብልት መቆም ችግር ጋር መጋፈጣቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ በእነዚህ ሰዎች ችግሩ በኦርጋናቸው ውስጥ ሳይሆን በአእምሮአቸው ውስጥ የሚፈጠር ነው፡፡ አዕምሯቸውን ለዚህ እርካታ ለማነቃቃት የወሲብ ቪዲዮ እና ምስሎችን መመልከት የግድ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡

3. ወንዶች ቀድሞ ከወሲብ ያገኙት የነበረው እርካታ ይቀየራል

ከትዳር አጋር ጋር ወይ ከፍቅረኛ ጋር ይደረግ የነበረው ፆታዊ ግንኙነት በፓርን አማካኝነት ሌላ ቅርፅ ሊይዝ ይችላል፡፡ ቪዲዮ እና ምስሎችን በመመልከት የተለያዩ የወሲብ ድርጊቶችን በተለይ ወንዱ የተመግበር ፍላጎት ሊያሳድር ይችላል፡፡ ሁኔታው ታዲያ የሴቷን ምቾት ከመንሳት ባለፈ በራስ መተማመኗን ሊያሳጣት ይችላል፡፡
4. ወንዶች ረጅሙን ጊዜያቸውን በኮምፒዩተር ላይ ማሳለፍ ይጀምራሉ

የፓርን ሱሰኞች ብዙ ጊዜ ከቴክኖሎጂዎች ጋር የተለየ ቁርኝት ይፈጥራሉ፡፡ ለብቻቸው ከኮምፒውተራቸው ስክሪን ላይ እንዳፈጠጡ ለሰዓታት ሊቆዩ ይችላሉ፡፡

5. በስሜት ከጓደኛ እና ቤተሰብ መነጠል ይታይባቸዋል
ወንዶች ይበልጥ በፓርን ሱስ ሲተበተቡ ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከሚስት እና ከልጆች ጋር እንዲሁም ከእውነተኛው ዓለም ጋር የነበራቸውን ግንኙነት እያጡ ይመጣሉ፡፡
እርዳታዎቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ::

Pom ከመመልከት ግለሰብን የሚታደግ አንዳችም መድሃኒት የለም፡፡ ብቸኛው አማራጭም ራስን እንደ ወሲብ ሱሰኛ ቆጥሮ ለዚህ ችግር የሚደረገውን የስነ ልቦና ህክምናን በቁርጠኝነት መከታተል ይሆናል አማራጩ፡፡ ይሄኛው መፍትሄ ችግሩ በግለሰቡ ላይ ስር የሰደደ እና ጥልቅ ጉዳይ መሆኑ ከታመነበት የሚገባበት ነው፡፡
በባለሙያዎች ሁለቱም ወገኖች ማለትም ወንዱ እና ሴቷ ግንኙነታቸውን ጤናማ ማድረጋቸው እና በችግሩ ላይ አብሮ ለመስራት ያላቸው ተነሳሽነት መሰረታዊ ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ወሲባዊ ቪዲዮዎች እና ምስሎች አልፎ አልፎ መጠቀሙ ካለፉት ዓመታት አንፃር በዚህ ዘመን የተለመደ ተግባር ሆኗል፡፡ በባለሙያዎቹም ጤናማ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

አስተማሪ እና መረጃ ለማግኘት የተለያዩ ቪዲዮዎች እና የኢንተርኔት ሳይቶች ግንኙነት የሚደገፉ መሳሪያዎች ሆነው እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ከመደበኛ የህይወት ዑደት የሚነጥል እና በቀላል ሊገላገሉት ያለመሆኑ ደግሞ የጎንዮሽ ጉዳት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

The post የባለቤቴ ፖርን (የወሲብ ፊልም) ማየት ልማድ ወደማልፈልገው ፍቺ እየመራኝ ነው | የዶክተሩን ምላሽ ከነመፍትሄው ያንብቡ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአዲስ አበባ በከባድ የመኪና አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

$
0
0

semit
(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 10  በተለምዶው ሰሚት  በሚባለው አካባቢ በደረሰ አሰቃቂ የመኪና አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ::

የአካባቢው ነዋሪዎች በፎቶ ግራፍ አስደግፈው ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው ሰሚት የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ አካባቢ በሚገኝ መስቀለኛ መንገድ ላይ ሲኖ ትራክ መንገድ ስቶ ከመንገድ ጋር ሲጋጭ ግንብ በመፍረሱ በአቅራቢያው ሰው አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ባጃጅ መኪና ላይ በመውደቁ አሽከርካሪውን ጨምሮ ተሳፋሪዎች ሕይወታቸው አልፏል::  ከሟቾች መካከል ሁለቱ ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል::: ፖሊስ የአደጋውን ሁኔታ እያጣራ ይገኛል:: በዚህ አደጋም በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው ተሰምቷል::

ተጨማሪ መረጃዎች ከደረሱን ለማቅረብ እንሞክራለን::

The post በአዲስ አበባ በከባድ የመኪና አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

የቢዮንሴ አምላኪዎች ሃይማኖት “ቤይዝም”|“እብደትም ቀልድም አይደለም”–የሃይማኖቱ መስራች

$
0
0



beyonce
(ዘ-ሐበሻ) የቢዮንሴ አምላኪዎች ሃይማኖት የሚለውን ርዕስ ስትመለከቱት ቀልድ ሊመስላችሁ ይችላል:: እብደትም ነው:: ይህን ሃይማኖት ላቋቋመው ፓውሊን ጆን አንድሪው ግን ቀልድ አይደለም:: “12 ሆነን የጀመርነው ሃይማኖት በአሁኑ ወቅት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችን አፍርቶልናል” ይላል::

beyonce 3

በየሳምንቱ እሁድ እየተገናኙ ክርስቲያኖች እንደሚዘምሩትና መጽሐፍ ቅዱስን እንደሚያነቡት ሁሉ የቤይዝም ሃይማኖት ተከታዮችም የቢዮንሴን ዘፈን ይዘፍናሉ እንዲሁም ቤይብል (the Beyble) የተሰኘውን መጽሐፋቸውን በማውጣት ጥቅሶችን እየጠቀሱ ይሰብካሉ ያመልካሉ::

beyonce 2

የዚህ ሃይማኖት መስራች እንደሚለው “ከጓደኞቹ ጋር ሞስካቶ እየጠጣና ማሪዋና እያጨሰ የቢዮንሴን አንድ ዘፈን ካደመጡ በኋላ ዘፈኗ መለኮታዊ ሃይል እንዳለው ስለተረዱ ከዚያም በኋላ በሷ ማምለክ መጀመራቸውን” ነው:: “የዘፈኖቿ መል ዕክቶች ሃይል አላቸው” የሚለው አንድሪው ወደፊት ሚሊዮኖች የሚከተሉት ሃይማኖት ይሆናል ይለናል::

አትላንታ ውስጥ በሚገኘው የዚህ የቢዮንሴ ሃይማኖት ተከታዮች የማምለኪያ ስፍራ ክርስቲያኖች የሚጠቀሙበትን የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕል በቢዮንሴ ቀይረው ሰርተውታል:: በርሷ ፎቶ ስርም ሻማ በማብራት ይጸልያሉ::

beyonce 4

በአሜሪካ ውስጥ ማንም ሰው የፈለገውን ሃይማኖት ማራመድ ይችላል:: ለምን እንዲህ አመለኩ ብሎ መተቸትም በሕግ ሊያስጠይቅ ይችላል:: ግን ምን አስተያየት አላችሁ?

The post የቢዮንሴ አምላኪዎች ሃይማኖት “ቤይዝም” | “እብደትም ቀልድም አይደለም” – የሃይማኖቱ መስራች appeared first on Zehabesha Amharic.


ግልጽ ደብዳቤ ለአቡነ ማቲያስ |በኢየሩሳሌም የሚገኙ የኢትዮጵያ ገዳማት ስለጎደለውን ገንዘብና ተያያዥ ጉዳዮች

በእኛ ዝምታ እነሱ ጀገኑ!!

$
0
0
ምን ብዬት መጀመር ግራ አገባኝ……. የቱን አንስቼ የቱን ልተው…… ምንስ ብፅፍ የውስጤን ቁጭት ይገልፀዋል……!! በህዝባችን ላይ እለት ተዕለት  እየተፈፀመ ያለውን ግፍና ሰቆቃ እየሰማንና እያየን እስከመቼ…..በዝምታ እንኖራለን ግፉ ፅዋ ሞልቶ ፈሷል። ዜጎች በራሳቸው ሀገር፣ በራሳቸው መንደር፣ በራሳቸው ማንነት እንዳይኖሩ የሚደረግበት ሀገር ኢትዮጵያ!!
Kalkidan
ትናንት በኦሮሞና በጋምቤላው ወገናችን ላየ በደረሰው ኢሰብዓዊ ድርጊት ምን ያህልን ውስጣችን ስንቃጠል እንደከረምን ከሁላችን የማንረሳው ነው። ይባስ ዛሬ ደግሞ የገደሉትን ገለው፣ያሰሩትን አስረው ፣ይህ አለበቃ ሲላቸው የሰው ልጅ ከሰው ጋር አስሮ ማሰቃየት ላይ ደርሰዋል። ይህን እኩይ ተግባር ማየቱንም ሆን መስማቱ እንዴት እንዴት ያማል…..!! “በእኛ ዝምታ እነሱ ጀገኑ!!”
ስማኝ ልንገርህ ወገኔ ዛሬ ሱርማ ወገናች ላይ የተፈፀመው እኩይ ተግባር ነገ በእኔና በአንተ የገዛ ቤታችን ውስጥ መተው እንደሚያድርጉት አትጠራጠር። 21 ክፍለ ዘመን ላይ እየኖረን ኑሮቻች እና ስቃያችን 18 ክፍለ ዘመን ሆኖል። ይህን ግፍና ሰቆቆ እስከመቼ በዝምታ እንደምንገልፀው!!
ጥቂቶች መብታቸውን ተከብሮ ነገር ግን ብዙሃኑ መብቱን እና ነፃነቱን ተነፍጎ የሚኖርባት ሀገር ኢትዮጵያ እየሆን ያለው በህዝባችን ላይ በእውነቱ ዝም የሚያስብል አይደለም። አሁን አሁንማ መብት ሲጠየቅ ምላሹ በመሳሪያ ሆኖል።  “በእኛ ዝምታ እነሱ ጀገኑ!!”
ይህን ግፍና መከራ እየሰማን፣ እየተመለከትን ስለምን ዝም አልን፣ ስለምን ዝምታን መረጥን፣ ስለምን በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ስቃይና መከራ ለማውገዝ አቅም አጣን፣ ስለምን የወገናችንን ሞት ሞታችን ማድረግ አቃተን፣ ስለምን መንገድ ዳር ስለሚገድሉብን ልጆች፣ እናቶች፣ ወጣቶች እንዲሁም አዛውንቶች እየሰማንና እያየን ዝምታን መረጥን!!
የእኛን ዝምታ እነሱን ካጀገነ ችግሩ እነሱ ጋር ሳይሆን እኛው ጋር ነው። ስለዚህ ስማኝ ልንገርህ ወገኔ ህወሓትን ከስልጣን ለማወረድ የእኛ ዝምታችን ሰባብረን በአንድነት ስንጮህ ነው። ተደራጅ፣ ተሰባሰብ፣ ተወያይ………..”የሀገር ጉዳይ ነውና” እንክፈል ጊዜችን፣ እንክፈል ገንዘባችን፣ እንክፈል ህይወታችን………ነፃነት ዋጋ ታስከፍላለችና ያለ መሰዋትነት ድል የለምና መከፈል ላለበት መክፈል አለበት……… “ኢትዮጵያ ደምና አጥንት የተከፈለባት ሀገር ናት” አሁንም ልንከፍል ግድ ነው!! “በእኛ ዝምታ እነሱ ጀገኑ!!”
በህዝቡ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እንቢተኝነት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በህዝባዊ እንቢተኝነቱን እንዲሳተፍ የየበኩላችን ጥረት እናድርግ ኢትዮጵያና ህዝቦቾን ከዚህ ፋሽስት ስርዓት እንታደግ!!
“ህወሓት እስካለ ተቃውሞ አለ”
ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር!!
ድል ለጭቁኑ ህዝብ!!
ቃልኪዳን ካሳሁን   (ከኖርዌ)

The post በእኛ ዝምታ እነሱ ጀገኑ!! appeared first on Zehabesha Amharic.

ፍርሃትም ይሸነፋል |ከተስፋዬ ገ/አብ

$
0
0

ዝነኛው አሸማጋይ ፕሮፌሰር ይስሃቅ ኤፍሬም መሰንበቻቸውን ስራ እንደበዛባቸው ተሰምቷል። የኦሮሞን ህዝብ አመፅና ጥያቄ በሰላም ለመጨረስ እዚህም እዚያም እየደዋወሉ ልብ የሚነኩ እግዚአብሄራዊ ቃላት ተናግረዋል። የፕሮፌሰሩ ጥረት በደፈናው የሚነቀፍ ባይሆንም አይሳካላቸውም። የሽማግሌው የእርቅ መንገድ ጥሎ ማለፍ ይዘት እንዳለው ካለፈ ድርጊታቸው ትምህርት ተገኝቷል። በተጨማሪ ድርድር ወይም እርቅ ሲታሰብ መላ የኢትዮጵያን ህዝብ የመብት ጥያቄዎች ታሳቢ በማድረግ እንጂ፤ ጉልበት ካገኘው  ሃይል ጋር ብቻ የመደራደር ዝንባሌ ያለፈውን ስህተት መድገም ይሆናል። በመሰረቱ ወያኔ በስውር ሽማግሌ መላክ መጀመሩ ጊዜ ለመግዛት ካልሆነ ከልብ እርቅና መደራደር ፈልጎ እንደማይሆን ይገመታል። ከፋፍሎ የማዳከም የህወሃት አካሄድ ገና ድሮ ተባኖበታል።

TPLF

 

ህወሃት ምንም እንኳ ላይ ላዩን የተረጋጋ ለመምሰል ቢሞክርም ውስጡ መበጥበጡ ይሰማል። አለመግባባት ባንዣበባቸው ስብሰባዎች እየታመሰ ከርሞአል። ይህን ስፅፍ ስብሰባዎቹ ገና አልተቋጩም። ቀደም ሲል በኢህአዴግ ስብሰባዎች ላይ የOLFን ወይም የግንቦት7ን ስም በበጎ ማንሳት የማይታሰብ ነበር። አሁን ተለምዶአል። የህወሃት ሰዎች አጋር እና አባል ድርጅቶችን ወደ ማባበል ደረጃ ዝቅ ብለዋል። ይህን እውነት የገመገሙ የወያኔ ወዳጆች ህወሓት ከገጠመው ቀውስ እንዲያገግም ተግተው እየሰሩ ነው። የህወሃትን ውስጣዊ ቀውስ የሚጠቁሙ መረጃዎች ከጥቂት በላይ ናቸው። ለአብነት የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ኮምፕዩተሮች የመዘረፍ ምክንያት ተራ ጉዳይ አይደለም። በሳሞራ የኑስ የሚመራው የመከላከያ ካውንስል ኦሮሚያን ማስተዳደር መጀመሩ ትልቅ ርእሰ ጉዳይ ነው። የተከሰተውን የረሃብ ችግር ለመፍታት በሚል ስም አሜሪካኖች በገፍ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ሾላ በድፍን ነው። “የኦሮሚያ አመፅ” የሚለው አባባል “የኢትዮጵያ አመፅ” ወደሚል ማደጉ የመሳሰሉት ርእሰ ጉዳዮች ህወሃት የመኖር ግዳጁን እንደፈፀመ፤ ነዳጁን እንደጨረሰ የሚጠቁሙ ሆነዋል።

በርግጥ ወያኔ ለመውደቅ አንድ ሃሙስ ብቻ እንደቀረው ከብዙ አመታት በፊት ጀምሮ ሲፃፍ ነበር። ዛሬም እየፃፍን ነው። ወያኔ ግን ሳይወድቅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሃሙሶች እንደዋዛ አልፈዋል። ትንበያዎቹ የተሳሳቱ ነበሩ ወይስ ሌላ ምክንያት አለ? ሳስበው ጉዳዩ የትንበያዎች ስህተት አይመስለኝም። የወያኔ ስርአት አፈናውን እንዲያቆም ማስገደድ የሚቻልባቸው ጥቂት እድሎች በተለያዩ ሰንካላ ምክንያቶች አምልጠዋል። ወያኔም፣ “በስብሰናል! ከሞት አፋፍ ላይ ቆመናል!” ብሎ ራሱን የገመገመባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ። ካልተገፋ ግን የበሰበሰ ግድግዳ እንደቆመ ይቆያል። አሁን እነሆ ጊዜው ደረሰ። “ቻዎ TPLF” የሚሉ ስንብቶች ከየአቅጣጫው እየተሰሙ ነው። ሃሰን ሁሴን ከሚኒሶታ ህወሃትን የተሰናበተው በምርጥ የአማርኛ ግጥም ነበር። የቀዌሳ የልጅ ልጅ ሎሬት ፀጋዬ ትዝ እስኪለኝ ሃሰን ሁሴን በአማርኛ ቋንቋ ተቀኘ። በረጅም ግጥሙ ውስጥ እንዲህ የሚሉ ስንኞች ነበሩበት፣

ገናናነቱ መስሎት የዘላለም – የዘወትር

ኮትኮቶ ያፈራው ፍራቻ

አቻውን የማያገኝ መስሎት – በሞት

ሞትም ተበራክቶ – መካን ሞትም ሳያመክን

ሃያል ቁጣን ወለደና – ጊዜ አይቀር የለና

ሳይታሰብ እንደ ደራሽ – የበጋ ጎርፍ – ከተፍ ብሎ ደረሰና

ክምሩም ካናት ቁልቁል መናድ ጀመረና…

 

የኦሮሚያ አመፅ ቀጥሎአል። ተዳፍኖ ሊቆም እንደሚችል ይገመት የነበረበት ጊዜ አልፎአል። ‘አመፁ ይቆማል’ ብሎ ከመጠርጠር ይልቅ፤ አመፁ ወደ ሌሎች ክልሎች ሊስፋፋ እንደሚችል መናገሩ ወደ እውነት የቀረበ ሆኖአል። በርግጥ የወያኔ አመራር ይህን እውነት በአደባባይ ባያምንም ኦሮሚያ በመከላከያ ካውንስል እንድትመራ ለጄኔራል ሳሞራ ትእዛዝ መስጠቱ ጉዳዩ ከቁጥጥራቸው ውጭ እንደሄደባቸው የሚጠቁም ነው።

oromia

ኦሮሚያን አገላብጦ እንዲጠብስ ሃላፊነት ከተሰጠው የመከላከያ ካውንስል መካከል አንድ ኦሮሞ እንኳ አልተጨመረም። በንጉሱም ሆነ በደርግ ዘመናት ኦሮሞ በጦር አዛዥነት ችሎታው አይታማም ነበር። ‘ተሰጥኦቸው ነው’ እስኪባል ድረስ ጄኔራልነት የኦሮሞዎች ነበር። ከታደሰ ብሩ አንስቶ እስከ ረጋሳ ጅማ፤ ከቁሲ ዲነግዴ እስከ መርእድ ንጉሴ፤ ከገበየሁ ጉርሙ እስከ ደምሴ ቡልቶ፣ ከጃጋማ ኬሎ እስከ አበራ አበበ ከሁለት ደርዘን በላይ ሙያውን የሚያውቁ ኦሮሞ ጄኔራል መኮንኖችን መጥራት ይቻላል። ዛሬ ተገላቢጦሽ ሆኗል። ሌሎች ከኮሎኔልነት በላይ ከፍ ማለት አቀበት ሆኖባቸዋል። በወያኔ መከላከያ ውስጥ የሚገኙ አማራና ኦሮሞ ከፍተኛ መኮንኖች አጫዋችና በሶ በጥባጭ ሆነው ቀርተዋል። የመከላከያ ካውንስሉን ከሚመሩት አስራ አንድ ጄኔራሎች ዘጠኙ የህወሃት አባላት ሲሆኑ፤ እነርሱም ሳሞራ የኑስ፣ ዮሃንስ ገ/መስቀል፣ ሰአረ መኮንን፣ ገብረ አድሃኖም፣ ኢብራሂም አብዱል ጀሊል፣ መሃሪ ዘውዴ፣ አብርሃ ወ/ማርያም፣ ፍስሃ ኪዳኑ እና ዮሃንስ ገ/ሚካኤል ናቸው። ቀሪዎች ሁለቱ አማራና አገው ናቸው። እነሱም አደም መሃመድና ገብራት አየለ ናቸው። ሳሞራ ባለፈው ሳምንት ከተጠቀሱት ጄኔራል መኮንኖች መካከል የህወሃት አባል የሆኑ ስድስቱን (ስታፍ ጄኔራል መኮንኖች) ሰብስቦ በኦሮሚያ ጉዳይ ላይ አነጋግሯቸዋል። ሳሞራ በስብሰባው ላይ፣

“እያንዳንዳችሁ የምታደርጉት ውጊያ ለራሳችሁ ለህልውናችሁ መሆኑን ተረዱ። አመፁን ማክሸፍ ካልቻልን የመጀመሪያው የጥቃት ኢላማ እኛ ነን። አደጋ ላይ ነን!” ሲል በግልፅ እንደነገራቸው ተሰምቷል።

እነዚህ ጄኔራል መኮንኖችም በመቀጠል የሳሞራን ቃል እየጠቀሱ ማስጠንቀቂያውን በጠባብ ክልል ወደታች አውርደውታል። ሳሞራ አልተሳሳተም። እውነት ብሏል። የትግራይ ህዝብ ሳይሆን፤ የህወሃት መሪዎች አደጋ ላይ ናቸው። ካልታጠቀ ህዝብ ጋር ከመዋጋት፤ ከለየለት ታንከኛና መድፈኛ ሰራዊት ጋር መዋጋት በእጅጉ የቀለለ ነው። ወያኔ በለመደው የውጊያ ስልት እየተዋጋ አይደለም። በወታደራዊ አነጋገር ልጠቀምና የኦሮሞ ህዝብ ራሱ በመረጠው ስልት፣ ራሱ በመረጠው ጊዜ እና ራሱ በመረጠው ሜዳ ላይ ከወያኔ ሰራዊት ጋር እየተፋለመ ነው። ይህ ለኦሮሞ ህዝብ ድል ነው። OPDO ፈርሶ በምትኩ ኦሮሚያን በህወሃት ጄኔራሎች እዝ ስር እንዲያስገቡ ማስገደዳቸው በእውነቱ ትልቅ ድል ነው። ለወያኔ በአንፃሩ የፍፃሜው መጀመሪያ ነው።

ህወሃት ከምስረታው ጀምሮ በታሪክ ጎዳና ላይ እየሮጠ ነው። እየወደቀ እየተነሳ ሲሮጥ 42 አመታት ሞልቶታል። መቸም አንበሳና ሚዳቋም በማለዳ ተነስተው ሁለቱም ይሮጣሉ። ምክንያቱም ህይወት ከመሮጥ እና ራስን ከመተካት ያለፈ ሌላ ልዩ ተልእኮ የላትም። ወያኔ መሮጡንስ ሮጧል። አሁን እየጣረ ያለው ራሱን ተክቶ ለማለፍ ነው። በመሆኑም ካጋጠመው መውደቅ ለመነሳት ማንኛውንም ርምጃ ይወስዳል። ለአብነት ለሃያላን አገራት ራሱን መሸጥ ቀደም ሲል ከፈፀማቸው የነፍስ አድን ርምጃዎች አንዱ ነበር። ከአምስት ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ሶማሊያ ወስዶ ሲሰዋ አለቆቹ ለስልጣኑ ዋስትና እንዲሰጡት እንጂ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም አልነበረም። “ወደድንም ጠላንም አሜሪካኖች ጌቶቻችን ናቸው” የሚለውን አባባል መለስ ዜናዊ በማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎች በግልፅ የሚናገረው ነበር። እና አሁንም በጌቶች እርዳታም ቢሆን የኦሮሞን ህዝብ የቁጣ ማእበል ለማፈን ጥረት ማድረግ የማይቀር ነው።

ወያኔ እንደ አጤ ሃይለስላሴ፣ “እንግዲህ ኢትዮጵያን ለመምራት ተራችን ነው ካላችሁ፤ አደራ አገራችሁን ጠብቋት!” ብሎ አልጋውን ለተቃዋሚዎቹ በመተው ከመድረኩ ዘወር ይላል ተብሎ አይጠበቅም። እንደ ደርግ ስርአት፣ “አንድ ጥይት እስኪቀረን እንገድላለን” ቢሉ ግን በትክክል ራሳቸውን ይገልፃቸዋል። የወያኔ ሰዎች እስከተቻላቸው በስልጣን ለመቆየትና በመጨረሻ ራሳቸውን ለመተካት ይጥራሉ እንጂ፤ አገሪቱ የጋራ አገር ናት በሚል እንደ መፍትሄ የሚቀርብላቸውን ለሁሉም ወገን የሚበጅ በጎ ምክር ለመስማት ዝግጁ አይደሉም። ግትርነታቸው ግን መሆን ያለበትን ከመሆን አያስቀረውም። እንደምናየው ህዝባዊ አመፁ ቀጥሎ ከመጨረሻው ጠርዝ ላይ እየደረሰ ነው። እየተስፋፋ አገራዊ መልክ እየያዘ ነው።

የህወሃት ፖለቲካ በማታለል መንገድ ተጉዞ እዚህ ደርሶአል። አዲስ ክረምት ዞሮ በመጣ ቁጥር በምግብ ራስን ስለመቻል መናገር ቋሚ ልማዳቸው ነበር። ሟቹ ሰውዬ “በቀን ሶስት ጊዜ ስለመመገብ” ከመፈላሰም አንስቶ “ትርፍ እህል ለአለም ገበያ በሽያጭ ስለማቅረብ” ጭምር በልበ ሙሉነት ሲገልፅ ደጋግመን ሰምተነው ነበር። ጥቂት የዝናብ መዛባት ሲያጋጥም ግን ለአንድ አመት የሚበቃ መጠባበቂያ ምግብ እንኳ አለመያዛቸው ይጋለጣል። ከአፍሪቃ በውሃ ጎተራነቷ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠች ሃብታም አገር እየመሩ ምግብ መለመን በእውነቱ ማሳፈር ነበረበት። ተለማመዱትና ሳያፍሩ ቀሩ። አየር ባየር የመሬት ንገድ ለመዱና እንደ መንግስት ማድረግ ያለባቸውን ቀዳሚ ስራ ማከናወን ረሱ።

በ2015 ምርጫ 100% የህዝብ ድምፅ እንዳገኙ ለአለም ባወጁ በጥቂት ወራት ልዩነት 100% የኦሮሞ ህዝብ ሲያምፅባቸው፤ ቁጥሩ በትክክል ባይታወቅም ከ50% በላይ ሌላው ህዝብ በተመሳሳይ ቅሬታውን ሲገልፅ የህወሃት ሰዎች አልተሳቀቁም። ከመብት ጠያቂው በሚሊዮን የሚገመት ህዝብ ጀርባ ላይ፣ “የግብፅና የኤርትራ ተላላኪ” የሚል ታርጋ ሲለጥፉ ወለም አላላቸውም። የማያስነቃ ውሸት መደባለቅ በፖለቲካ ውስጥ የተለመደ ሊሆን ይችላል። በተደጋጋሚ ገገማ ውሸት መስማት ግን ያስተክዛል። ከዚህ ሁሉ የተተራመሰና የባከነ ጉዞ በሁዋላ ታዲያ ኢትዮጵያ በህዝባዊ አመፅ ተንጣ መጪ እድሏን ለመተንበይ ያስቸገረች አገር ለመሆን በቅታለች። አሳዛኙ ነገር ህዝቡ በምርጫ ላይ እምነት ማጣቱ ነው። ይህን እምነት ማጣት ለማስተካከል፤ ይህን በምርጫ የማጭበርበርን ልማድ ለማስወገድ እንደገና ሌላ ጊዜና ጉልበት መጠየቁ የማይቀር ነው። በምርጫ ጉዳይ ህዝብን ተስፋ ከማስቆረጥና እምነት ከማሳጣት እንደ ሃይሌ ገብረስላሴ “የኢትዮጵያ ህዝብ ዴሞክራሲ አያስፈልገውም” ብለው ቁርጡን ቢናገሩ በተሻለ። ህዝቡም በውሸት ምርጫ ጊዜውን ከማቃጠል፤ በቀጣይ ማድረግ ያለበትን በወሰነ።

ወቅታዊው ሁኔታ “የኦሮሚያ አመፅ ቀጥሎአል” ከሚለው ዜና “የኢትዮጵያ ህዝብ አመፅ ቀጥሎአል” ወደሚል ደረጃ ማደጉ እየታየ ነው። ከኦሮሞ ህዝብ ያላቋረጠ ተቃውሞ ባሻገር በወልቃይት የተቀሰቀሰው፣ “ትግሬ አይደለንም” ጥያቄ አልተዳፈነም። ባለፉት ጥቂት ቀናት ሰሜን ጎንደር ዳባት ላይ አማራ አማፅያን መንገድ ዘግተው መዋላቸው የአመፁ መስፋፋት ተቀጥያ ነው። ጎጃም ከመሬት መጥበብ ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለው። ትናንት የአዲሳባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች “አሸባሪዎች አይደለንም” የሚል ተቃውሞ ይዘው ከስድስት ኪሎ ወደ አሜሪካ ኤምባሲ በመጓዛቸው ድብደባና እስራት ገጥሟቸዋል። በደቡብ በተለይም ሙርሲ ብሄረሰብ፤ በሃመርና በኦሞ ሸለቆ አካባቢ ህዝብና ፖሊስ መጋጨታቸው ተሰምቷል። ፖሊሶች ልብስ መልበስ ያልጀመሩ ዜጎችን አንገታቸውን እንደ ጉሬዛ በገመድ እያሰሩ ሲያንገላቱ ምስሉ በማህበራዊ ድረገፆች ይፋ ሆኖአል። የግጭቱ መነሻ አሁንም መሬት ነው። በጋምቤላና በቤኒሻንጉልም ተመሳሳይ የአመፅ እንቅስቃሴዎች ቀጥለው ከርመዋል። የሃዲያ ሽማግሌዎች በባህላዊው መንገድ ስብሰባ አድርገው ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ያላቸውን ወገናዊነት መግለፃቸው ባለፈው ሳምንት ከተሰሙ ትኩረት ሳቢ ዜናዎች መካከል አንዱ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የደቡብና የኦሮሚያ ህዝቦች መቀራረብ እየጠነከረ መሄዱ የመጪውን ዘመን የፖለቲካ የሃይል አሰላለፍ የሚጠቁም ነው። እንዲህ ያለ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ መቀራረብ በኦሮሞና በአማራ ህዝቦች መካከል ቀደም ብሎ ቢጀመር ኖሮ የመከራው ዘመን ገና ድሮ ባበቃ ነበር።

Taxiiየአዲስአበባ ታክሲዎች የአንድ ቀን የስራ ማቆም አድማም የወያኔን ደም ስር የነካ ክስተት ሆኖ አልፎአል። በር ከፋች ምልክት ነው። መሞከሪያ ነበር። የትልቁ ምስል ማሳያ ነበር። በትክክልም ውጤቱ ታይቷል። ወያኔ ያለ ልማዱ ለታክሲ አሽከርካሪዎች ጥያቄ 24 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ምላሽ መስጠቱ በኦሮሚያ የተጀመረው አመፅ ወደ ሌሎች ክልሎችም እንዳይስፋፋ መስጋቱን ይጠቁማል። የህወሃት ደጋፊ ነጋዴዎች ከኦሮሚያ እና ከደቡብ ኢትዮጵያ እጃቸውን እየሰበሰቡ አዲስአበባ ተከማችተዋል። ገንዘባቸውን ወደ ውጭ ምንዛሪ በመለወጥ ስራ መጠመዳቸውም የከረመ ወሬ ነበር። ይህ ሂደት አላቋረጠም። አላሙዲ በተመሳሳይ የጥቃት ኢላማ ሆኖአል። የቦረና የከብት እርባታው ላይ ከደረሰ አደጋ በሁዋላ ይህን እየፃፍኩ ሳለ እንኳ የጎሞሮ የሻይ እርሻው ላይ ተመሳሳይ የእሳት አደጋ ደርሶበታል።

የትግራይ ህዝብ ይህ ጊዜ እንደሚመጣ ቀድሞ ተንብዮአል። መስፍን ወልደማርያም በትክክል እንደገለፁት የህወሃት ዘራፊዎች መቐለ ላይ የገነቧቸውን ቪላዎች ህዝቡ “የአፓርታይድ መንደር” ብሎ ሲሰይም “እኔ የለሁበትም” እያለ ነበር። ከደሙ ንፁህ መሆኑን እያወጀ ነበር። በአማርኛ ቋንቋ የልጆች ተረት ውስጥ አንድ የማይረሳኝ ድንቅ ታሪክ አለ። አንድ ጅብ ከሁለት ልጆቹ ጋር ተባብሮ አህያ ይጥላል። ከዚያም ልጆቹን አባሮ ብቻውን ይበላል። ሊነጋ ሲል የአህያው ባለቤት ጦር ይዞ መጣ። ልጆቹ ጥለውት ሲሸሹ አባት፣ “አድነኝ ልጄ መዝሩጥ?” ሲል ተጣራ። ልጁም፣ “አባቴ ሆይ! እንደበላህ እሩጥ” ሲል ምላሽ ሰጠ። ይህ ተረት ለህወሃት ደጋፊ ሙሰኞች ጥሩ ምሳሌ ነው። የትግራይ ህዝብ በስሙ በሚነግዱ ጥቂት ከበርቴዎች ምክንያት ሊወገዝም ሆነ ሊወቀስ አይችልም። ትግራይ ላይ ተገነቡ የሚባሉ መንገዶችና ጥቂት ፋብሪካዎች ከሚገባው በላይ አይደሉም። ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ካለ በመላ ኢትዮጵያ ከዚያም በላይ ማድረግ በተቻለ።

በኢትዮጵያ ላጋጠመው የአስር ሚሊዮን ህዝብ የረሃብ አደጋ እርዳታ ለመስጠት በብዛት ወደ አዲስአበባ እየገቡ ያሉት አሜሪካኖች ከፊል አላማቸው ሌላ ስለመሆኑ ጥርጣሬ አለ። ርግጥ ነው፤ የወያኔ ስርአት የሚፈርስ ከሆነ አሜሪካኖች ሌላ አማራጭ ለመፈለግ ከወዲሁ ሰዎቻቸውን ልከው ሁኔታውን ማጥናት እንዳለባቸው ያውቃሉ። ወያኔ በአሜሪካኖች በኩል ድርድር ለማድረግ ሽማግሌ መመልመላቸው ወቅታዊ ነው። የህወሃት አመራር በስልጣን ላይ ሳለ ለፈፀመው ወንጀል በማይጠየቅበት መንገድ፤ የደጋፊዎቹ ሃብትና ንብረት በማይነካበት መንገድ የሽግግር መንግስት ለመመስረት ከተስማሙ ኮርተው ያዋጣቸዋል። አሜሪካኖችም ከደከመው ጋር ከሚዳከሙ ከታጣቂም ሆነ ከባዶ እጅ ተቃዋሚዎች፣ እንዲሁም በስደት ከሚገኙ ታዋቂ ግለሰቦች አዛንቀው አንድ ጊዜያዊ መንግስት ለማቋቋም ከቻሉ ለወያኔም ቢሆን ምንም አይላቸው። በመጨረሻ ከማይቀርላቸው ተገፍቶ መውደቅ ይሻላቸዋል። ሙሰኛ ደጋፊዎቻቸውን ከበቀል ዱላ ማዳን ይቻላቸዋል። በርግጥ እንዲህ ያሉ ወጎች ጊዜው ደርሶ ሰበር ዜና እስኪሆኑ ሹክሹክታ ሆነው ይቆያሉ።

ከዚሁ ሹክሹክታ ጋር በተያያዘ በቅርቡ የፌደሬሽን ምክር ቤት ኮምፕዩተሮች የመዘረፋቸው ክስተት አቅጣጫ ጠቋሚ ነው። ኮምፕዩተሮቹን የዘረፉት ያለምንም ጥርጣሬ የጌታቸው አሰፋ ልጆች እንጂ ተራ ሌቦች ሊሆኑ አይችሉም። ተራ ሌባ ፌዴሬሽን ምክርቤት ገብቶ ኮምፕዩተሮችን የመስረቅ ችሎታ ሊኖረው አይችልም። እንዲህ ያለ ድርጊት ከዚህ ቀደምም ተፈፅሞ ነበር። “ጥረት” የተባለው በሙስና የሚታማ የብአዴን የንግድ ድርጅት ምስጢሮቹን ለመደበቅ የሂሳብ ክፍሉን በእሳት አጋይቷል። ከብሄራዊ ባንክ የተሰረቀው ወርቅ እና የሼኽ መሃመድ አልአሙዲ ንብረት ጉዳይም እንዲሁ ምላሽ ያላገኙ እንቆቅልሽ ናቸው። በአሰራር ደረጃ የደህንነት መስሪያቤቱ በህጋዊ መንገድ ማግኘት የሚያስቸግረውን ሰነድም ሆነ ንብረት በሌቦች የማስመንተፍ ልምድ እንዳለው የሚታወቅ ነው። ለአብነት በክንፈ ገብረመድህን የደህንነት ስልጣን ዘመን የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን የእጅ ቦርሳ በሌባ ማስነጠቃቸው የሚታወስ ነው። የመለስ ዜናዊን አስከሬን ጄኔራል ሳሞራ በሄሊኮፕተር አድዋ አድርሶ ሲያበቃ፤ አዲስአበባ ላይ ባዶ ሳጥን መቅበራቸው የአንድ ሰሞን ሹክሹክታ ሆኖ አልፎአል። ይህ በርግጥ ያስቃል እንጂ አያናድድም። ለአዲስአበባ የመለስ ራእይ እንጂ አስከሬኑ ምንም አያደርግላት። የፌዴሬሽን ምክርቤቱ ኮምፕዩተሮች ስርቆት ጉዳይ በተመሳሳይ አላማ ያለው መሆኑን የአካባቢው ሹክሹክታ ይጠቁማል።

ከፀጥታው መስሪያ ቤት ቀጥሎ ወያኔ ሊደብቃቸው የሚፈልጋቸው ሰነዶች የሚገኙት በካሳ ተክለብርሃን ስር በሚገኘው የፌዴሬሽን ምክርቤት ኮምፕዩተሮች ውስጥ ነው። በህዝብ ብዛት መጠን የሚሰፈረው የክልሎች በጀት ጉዳይ፣ የክልሎች ድንበርና የክልሎች ካርታ ጉዳይ፣ የብሄረሰቦች አቤቱታዎች፣ የተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይና ውሳኔዎች ሁሉ ወደዚሁ ወደ ፌደሬሽን ምክርቤት ሲጎርፉና ሲከማቹ ኖረዋል። የወያኔ አመራር ስርአታቸው እንደሚፈርስ ካወቁ በቅድሚያ ማስወገድ ያለባቸው በዚህ ቢሮ ውስጥ የተከማቸውን ሰነድ መሆኑ ግልፅ ነበር። አድርገውት ከሆነ ጥሩ ዘይደዋል።

በጥቅሉ ላለፉት አራት ወራት የተካሄደውን ህዝባዊ አመፅ መታዘብ እንደሚቻለው የቄሮ ወጣቶች ሞትን ንቀውታል። የፍርሃቱን ዘመን ተሻግረውታል። የዝምታውን የብረት በር በርግደውታል። የፖለቲካ ቁማሩን ተረድተውታል። ብዛትና ብርታታቸው ከሚታወቀው በላይ በመሆኑ ጉዳዩ የነብር ጭራ ላይ እንደተተረተው አይነት እየሆነ ነው። Dances with Wolves በተሰኘው የKevin Costner ዝነኛ ፊልም ላይ እንዳየነው ትረካ የቄሮ አመጣጥ ልክ እንደ ከዋክብት ነው። ማለትም ብልጭታዎች ጥቁሩን ሰማይ ሸፍነውታል። የከዋክብቱን ብርሃን ከጥቁሩ ሰማይ ላይ ማስወገድ የሚቻል አይደለም።  የበረዶው ወቅት አልፎ ፀሃይ ስትወጣ የሞቱ መስለው የነበሩ እፅዋትና አዝርእት ምድሩን እንደሚያለብሱት አይነት ናቸው። በሌላ አገላለፅ ከጊቤ ወንዝ ዳርቻ አንድ የተኛ አዞ አለ። አዞው ውሃ ልትጠጣ የመጣችውን ሚዳቋ ቀጨም ከማድረጉ በፊት ህይወት ያለው አይመስልም ነበር። የኦሮሚያ አመፅ እንዲያ ሆኖአል። የኦሮሞ ህዝብ ወደ መጨረሻ ግቡ እየተጓዘ ነው። እንደ ግመል በጥንካሬ ወደፊት እየገፋ ነው። ይህን ለመረዳት የፖለቲካ አዋቂ ወይም ኦሮሞ መሆን ግድ አይደለም።

በመጨረሻ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ በቅርቡ “Ethiopia at the Eleventh Hour of Peaceful Change” በሚል ርእስ ካስነበበው ቀንጭቤ ላብቃ፣

“…በሁኔታዎች ግራ ለተጋቡት አንዳንድ የህወሃት ደጋፊዎች ስለአዲሱ ክስተት ላስታውሳቸው እወዳለሁ። በመጨረሻ የኦሮሞ ህዝብ ፍርሃትን ማስወገድ ችሎአል። ታሪክ በተደጋጋሚ እንዳሳየን ፍርሃቱን ያሸነፈ ህዝብን ማቆም አይቻልም። with the added fact that the recovery of courage is a contagious phenomenon. Such a movement can be temporarily blocked, ነገር ግን ጨርሶ ማዳፈን አይቻልም።”

The post ፍርሃትም ይሸነፋል | ከተስፋዬ ገ/አብ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከአዲስ አበባ ወደ ወልዲያና ወደ መቀሌ የሚጓዙ አውቶቡሶች ላይ ጥቃት ደረሰ

$
0
0

sky bus

(ዘ-ሐበሻ) አንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ በስርዓቱ የተማረረ የተባለ ኢትዮጵያዊ በወሎ ሰንበቴ በተባለ ቦታ በሁለት የሕወሓት ባለስልጣናት ንብረት በሆኑ አውቶቡሶች ላይ በድንጋይ ጥቃት አደረሰ:: የአውቶቡሶቹን መስታወትም በድንጋይ መሰባበሩ ተሰማ::

አ.አ ወልዲያ በሚጓዝ ሰላም ባስ ና ከአ.አ ወደ መቀሌ በሚጓዝ ስካይ ባስ በመጋቢት 29/08 ተከታትለው ሲጓዙ በነበሩ ሁለቱም ባሶች ላይ በአንድ ለግዜው ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ ወሎ ሰንበቴ በተባለ አካባቢ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ጥቃት ያደረሰው ግለሰብ መታሰሩ ተሰምቷል::

የዓይን እማኞች በፎቶ ግራፍ ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ መሠረት ስካይ ባስ ከፊት ስለነበረ በሰባት ድንጋይ የግንባር መስተዋቱ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።

ከ3,400 በላይ ሼር ሆልደሮች አሉኝ የሚለው ስካይ ባስ በቀጥታ በሕወሓት ሰዎች የሚመራና አብዛኛው ሼርም በነርሱ የተያዘ መሆኑን የቅርብ ሰዎች ይናገራሉ::

The post ከአዲስ አበባ ወደ ወልዲያና ወደ መቀሌ የሚጓዙ አውቶቡሶች ላይ ጥቃት ደረሰ appeared first on Zehabesha Amharic.

አገርን እንደ እናት ያለመቀበል አደጋ እና የብሄራዊ መግባባት አስፈላጊነት |አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

$
0
0

Dr Aklog Birara

አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

ባለፈው ትንተናየ እንዳሳየሁት፤ የኢትዮጵያ እናቶች ልጆቻቸውን ወልደው በለጋቸው ሲቀብሩ ኖረዋል። የኢትዮጵያ ረዢም ታሪክ የተመሰረተው ያፈራቻቸው ልጆቿ ተቆርቁረው በህይወታቸውና በንብረታቸው ዋጋ ስለከፈሉ ነው። ከጀርባቸው ሆነው ስንቅ የሚያቀርቡላቸውና የመንፈስ ድጋፍ የሚሰጧቸው እናቶች ናቸው። እናት አገርና ወላጅ እናት ከዋጋና ከህይወት በላይ ናቸው፤ አይነገድባቸውም የምለው ለዚህ ነው። ከኢትዮጵያ መንግሥት ውጭ፤ ማንም የአፍሪካ መንግሥት እናት አገሩን ጠበቃ ሆኖ እንድትፈራርስ አያመቻችም። ከኢትዮጵያ ውጭ ማንም የአፍሪካ መንግሥት በወጣቱ ትውልድ ላይ ጭካኔ አያካሂድም፤ እናቶችን ለለቅሶ አይዳርግም። ዛሬ እንደሚታየው በጎሳና በቋንቋ ልዩነቶች ላይ የተመሰረተው የህወሓት/ኢህአዴግ ሕገመንግሥት ውጤት ቀስ በቀስ አገርን እንደሚያፈራርስ ከመንስኤው ያነጋግር ነበር። ለምሳሌ ምን የድብቅ ስትራተጅ ቢኖረው ነው ህወሓት ተከታታይ መንግሥታት ብሄራዊ ያደረጉትን፤ ከሁሉም ብሄረሰቦች የተወጣጣውን አገር ወዳድ የመከላከያ ሰራዊት አፍርሶ በአንድ ብሄረሰብ እዝ የበላይነት የተዋቀረ የፌደራልና ልዩ ፖሊስ፤ የስለላ መረጃና መከላከያ ተቋም የፈጠረው? መልሱን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቀዋል። የመከላከያ ተቋም ዋና ሚና የአገርን ግዛታዊ አንድነት፤ ነጻነትና ሉዐላዊነት ማስከበር ነው። የአንድ አናሳ ጎሳ አውራ ፓርቲን ስልጣንን መታደግና ማንኛውንም ዘዴ ተጠቅሞ ማቆየት አይደለም።

የዚህ ሃተታ መሰረተ ሃሳብ ኢትዮጵያ ከፍተኛ አደጋ ላይ መውደቋን ለማሳየትና አደጋውን ለመከላከል አማራጭ ለማቅረብ ነው። ህወሓት/ኢህአዴግ ጨካኝና አምባገነን ቢሆንም አገራችን የሚያስፈልጋት የመንግሥት ለውጥ ብቻ አይደለም። “ጉልቻ ቢቀየር ወጥ አያሳምርም” እንዲሉ አንዱን አምባገነን በሌላ መቀየሩ መሰረታዊ ለውጥ አያመጣም። አስፈላጊው የስርዓት ለውጥ ነው። የስርዓት ለውጥ መሰረታዊ ስለሆነ በማያዳግም መልኩ ሁሉን ሕዝብ ማሳተፍ አለበት። ሁሉም የተሳተፈበት ስርነቀል ለውጥ ዘላቂነት ይኖረዋል። ለእድገት አስፈላጊ ነው። ካለፈው የምንማረው የንጉሰነገሥቱን መንግሥት ለውጠን የተካነው የወታዳራዊ አምባገነን መንግሥት ነው። የወታደራዊውን መንግሥት አስወግደን የተካነው የባሰውን የጎሳኞች ልሂቃን የበላይነትን ነው። የእነዚህ ውጤት ሕዝብን የስልጣኑ ባለቤት ያላደረጉ ተከታታይ መንግሥታትን መተካት ሆኗል። የችግሩ እምብርት ስርዓቱ አለመለወጡ ነው።

የስርዓት ለውጥ ስኬታማ የሚሆነው አገር ሲኖረን ነው። የመጀመሪያው ትርኩርት ኢትዮጵያን ተባብሮ ከአደጋ ማዳን ይሆናል። አገሪቱን ለማዳን የሕዝብ መተባበርን፤ ከቡድን፤ ጎሳና ጥቅም በላይ ለአገሪቱ ማሰብን ይጠይቃል። ሁላችንም በየፊናችን ነጻነት፤ ሰብአዊ መብቶች፤ ዲሞክራሲ፤ ልማት ወዘተ አስፈላጊ ናቸው እንላለን። እነዚህን ማንም አይቃወምም። የኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅሞች፤ ብሄራዊ አንድነትና ሉዐላዊነት፤ የሕዝቧ እኩልነትና ህብረት አስተማማኝ ካልሆኑ ዲሞክራሲና እድገት አይታሰብም። ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለምንቆረቆር የማቀርበው ሃሳብ መጀመሪያ መቀበል ያለብን ኢትዮጵያ የጋራ አገራችን መሆኗን እንቀበል የሚል ነው። የጋራ እናት አገር ከሆነች አገሪቱን ከመፈራረስ ማዳን ያለብን ሁላችንም ነን። በጎጠኛነት አስተዳደር የተቀነባበረው የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት (Ethnic federalism) ስርዓት ከዚህ በፊት ተደርጎ በማይታወቅ ደረጃ የብሄረሰቦችን እኩልነት፤ ተከባብሮና ተደጋግፎ መኖር ስኬታማ ያደርጋል ተብሎ ነበር። የጎሳ ወይንም የክልል ፌደራል አገዛዝ ያስከተለው መለያየትን፤ ጥላቻን፤ የመገንጠል ዝንባሌን፤ የሽብርተኞችንና የአክራሪዎችን መጠናከር ነው። የውጭ ጠላቶ ደስ እንዳላቸው ማመን ያስፈልጋል።

ህወሓት በአማራው ብሄረሰብ ላይ የጥላቻና የማግለል መርህ ስለተከተለ ከአማራው ክልልና ከአዲስ አበባ ውጭ በአብዛኛው ኢትዮጵያ ማህል አገር የሚኖረውን የአማራ ሕዝብ እንዲወገድ፤ ቤቱና ንብረቱ እንዲወድም፤ ህልውናው ወደ አደጋ እንዲሸጋገር አድርጎታል። የወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ ማንነቱ ተነጥቆ የትግራይ ክልል አካል እንዲሆን ተገዷል። መሬቱን ተነጥቋል። በጋምቤላ፤ አኟኩና ሌላው ነዋሪ መሬቱ እንዲነጠቅ አድርጓል፤ በሕዝቡ ላይ ግድያ አካሂዶበታል። የኦጋዴን ሶማሌዎች የሚዘገንን ጭካኔና ግድያ ተካጅሂዶባቸዋል። በኦሮሞው ወጣት ትውልድ ላይ የሚካሄደው ጭካኔ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ እንዲወጣ አድርጎታል። ዛሬ ዜጎችን መግደል፤ ማፈን፤ እንዲሰወሩ ማድረግ፤ ዘር ማጥፋትና አሰገድዶ ከቀያችው ማስወገድ፤ ማንነታቸው እንዲጠፋ ማድረግ ወዘተ ለአገሪቱ ህልውና አደገኛ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። ለዚህ በታሪክና በተከታታይ ትውልድ የሚጠየቀው የአገሪቱን ፖለቲካ አመራርና ኃብት በበለይነት የያዘው ህወሓት ነው። ስርዓቱ ይለወጥ የምልበት መሰረታዊ ምክንያት ይኼው ነው። ስርዓቱን ለመለወጥ የሚቻለው ለአንድ አገርና ለአንድ ሕዝብ አብሮና ተባብሮ መስራት ሲቻል ብቻ ነው። ጥሩና አስተዋይ የመንግሥት አመራር አለ ሊባል የሚቻለው ባለሥልጣናት የሚሰጡት ቅድሚያ ለራስና ለቡድን ሳይሆን ለአገርና ለመላው ሕዝብ ሲሆን ብቻ ነው። አሁን ያለው አደጋ የሚያሳየው ከጎሳ ወደ አገር አቀፍ መሰብሰብና ፍትህ መሸጋገር ወሳኝ መሆኑን ነው።

የችግሩን መንስኤ የሚክድ አገዛዝ

ድጋፍ ይስጥ እንጂ ችግሩን የፈጠረው የውጭ ጠላት አይደለም፤ የውጭ ጠላት መግቢያ ቀዳዳ ማግኘቱ አይካድም። ለምሳሌ፤ የቀይ ባህር ሙሉ በሙሉ የአረቦች ኃይቅ እየሆነ ነው። በዘላቂነቱ ሲታይ ማን ይጎዳል? የሚጎዳው መላው ወንድማማቹ የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ሁለቱ ሕዝቦች ከሚለያያቸው ይልቅ የሚጋሯቸው ትሥስሮች ያመዝናሉ–ባህል፤ ታሪክ፤ ኃይማኖት፤ጋብቻ፤ የኢኮኖሚ መደጋገፍ፤ ብሄራዊ ደህንነት አስፈላጊነትና የወደፊት እድገት ወዘተ። የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደገና መተባበሩ የማይቀር ነው። ለራሱ ማንነት፤ ክብርና ህይወት ሲል። ሆኖም፤ ሁለቱም አገሮች ቅንነት፤ አርቆ አስተዋይነት፤ ሕዝብን የፖለቲካ የበላይ ያደረገ አመራርና መንግሥት ያስፈልጋቸዋል። እራሳችን እንጠይቅ፤ ጥላቻውን፤ መገንጠሉን፤ ጦርነቱን፤ መጠላለፉን ማን አመቻቸው? መልሱ ግልጽ ነው። መለስ ዜናዊ የበላይ ባለሥልጣን በነበረበት ወቅት በራሱ ፈቃደኛነት ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ የሽግግሩ የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራን መገንጠል ይደግፋል ብሎ ነው።

ኤርትራን ካስገነጠለ በኋላ ብዙ ሽህ ወገኖቻችን የሞቱበትን ጦርነት አካሄደ፤ አሰብን ሳያስመልስ ተመለሰ። የመለስ ዜናዊ ቅርስ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን ሕዝቧን በጎሳና በቋንቋ መከፋፈሉ ጭምር ነው። ዛሬ በየትኛውም ቦታ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎሳ ፖለቲካ እየታመሰ ነው። በሰሜን ጎንደር፤ በኦሮሚያ፤ በኦጋዴን፤ በጋምቤላና ሌሎች ቦታወች ገዢው ፓርቲ ተወጥሯል። መወጠሩ ብቻ ሳይሆን፤ ለችግሮቹ አጥጋቢና አግባብ ያለው መልስ ለመስጠት አልቻለም። በሕዝብ የተነሳውን አምቢትኛነት ሁሉ በሌሎች ያመካኛል፤ አመካኝቶ ይቀጣል። የሕዝብ ዐመጽ ሲኖር ሌሎች፤ አመጸኞችን ጨምሮ፤ የምስጢር አጀንዳዎችን ለመጠቀም እንደሚሞክሩ አምናለሁ። ለምሳሌ፤ አል ጀዚራ ዶሃ ስለ ኢትዮጵያ እድገታዊ መንግሥት በምርምር የተደገፈ ጥናት አቅርብ ብሎ ጋብዞኝ የሰማሁትና የተከራከርኩት “የኢትዮጵያ ሕዝብ በሃይማኖት እንደተከፋፈለ፤ ኢትዮጵያ አረቦችን ለመጉዳት የዓባይን የተሃድሶ ግድብ እንደምትገድብ” ወዘተ ይነገር ነበር። ከእኔና ከባለቤቴ በስተቀር ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም የተከራከረ የለም። ከወሓት/ኢህ አዴግ ስልጣን በፊት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በመከባበር፤ በመተሳሰብ፤ በአንድ ላይ የኖረ ሕዝብ መሆኑን ለማስረዳት ሞከርኩ። በግልጽ የሚታየው አረቦች ስለኢትዮጵያና ስለ ሕዝቧ ያላቸው አመለካከት የተለየ መሆኑን ነው። ኢትዮጵያ ወንዞቿን የመጠቀም መብት እንዳላት ለማስረዳት ሞክረናል። ይኼን ሳደርግ የማይደገፍ መንግሥት መደገፌ አይደለም። የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም የደገፍኩት ዋና ምክንያት ስለማምንበት ነው።

ገዢው ፓርቲ መሰረታዊ የፖሊሲና የአስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አይችልም

ችግርን ለመፍታት የችግሩን መነሻ ማወቅ ያስፈልጋል። ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በገዢው ፓርቲ፤ በተለይ በህወሓት የበላይነት ብልቂያጥ/ብልቃጥ የተሞላው የብሄረሰቦች ልዩነትና ጥላቻ መርዝ የአገሪቱን ማህበረሰባዊ ግንኙነቶችና የአገሪቱን ዘላቂ ጥቅም መርዟቸዋል፤ በክሎታል። የመንግሥት ተቋማትን ተጠቅሞ ሕዝብን ከሕዝብ በመለያየት ቆይታውን የሚያመቻቸው ህወሓት አሁንም አደጋውን አላየውም። ትኩረቱ ከበላይነት ላይ ነው። ተከታታይ ችግሮችን ለመፍታት የሚሞክረው በሌሎች በማመካኘት ነው። ችግሩን ራሱ ፈጥሮ በሌሎች ማመካኘት እሰከመቸ ያዋጣል? ለምሳሌ፤ ሕገመንግሥቱ ማንም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም ኢትዮጵያ መሬት፤ ንብረት፤ ቤት ወዘተ ሊይዝ ይችላል፤ ይኼን መብት የሚቀማው የለም ይላል። በአፈጻጸም ሲታይ ይኼ አልሰራም። ካልሰራ ሕገመንግሥቱም አልሰራም ማለት ነው። ሕገመንግሥቱ ካልሰራ መለወጥ አለበት ማለት ነው። የፌደራሉ መንግሥት ሚና ሕጎችን ማስከበር ከሆነ ለምን የኢትዮጵያዊያንን መብቶች ለማስከበር አልቻለም? ካልቻለ ስልጣኑን ለምን ለሌሎች ለመስጠት ወይንም ከሌሎች ጋር ለመጋራት አይፈልግም? ብለን መጠየቅ ብሄራዊ ግዴታችን ነው።

ብዙ የአገር ውስጥና የውጭ ታዛቢዎች እንደሚሉት፤ ህወሓት አደጋውንም ቢያየው፤ የመረጃ፤ የስለላ፤ የልዩ ፖሊስና የመከላከያ እዙንና ኃይሉን በበላይነት ስለሚቆጣጠረው ሕዝቡን በመሳሪያ ኃይል ታዛዥ አደርገዋለሁ የሚል እምነት አለው። አገሪቱ ከቁጥጥር ውጭ ብትሆንስ? የሚል ጥያቄ ቢቀርብስ። ለዚህ አንቀጽ 39 መሳሪያ ይሆናል የሚሉ ብዙ ተመልካቾች አሉ። ህወሓት ስልጣን ከያዘብት ጀምሮ የትግራይን ድንበር ከሱዳን ጋር እስከሚዋሰን ድረስ አስፋፍቷል። የውስጥ መስፋፋት ችግር የለበትም የሚሉና የሌለ ታሪክ የሚፈጥሩ እንዳሉ አውቃለሁ። ድንበሩን በኃይል ለውጦ አንዱን ብሄረሰብ ከመሬቱና ከኑሮው ማስወገድ ጸረ-ዲሞክራሲና ኢ-ስብአዊ ከመሆኑም በላይ አብሮ ለመኖር አያስችልም። ለተከታታይ ትውልዶች ጥላቻንና ግጭትን ይፈጥራል። የሕዝብ ግጭት ተከታታይ ሲሆን አገር ይፈርሳል። ለዚህ ነው፤ አገር ወዳዶች አንዱን ዜጋ አስወግዶ ሌላውን መተካት ጸረ-ኢትዮጵያ አቋም ነው የሚሉት። ይኼ በግልጽ የተካሄደና የሚካሄድ የአገር ውስጥ የመሬት ነጠቃ፤ ቅርሚትና የፖለቲካ ንግድ ተከታታይ የጋራ ታሪክ ላለውና በአንድ አገር አብሮ ለሚኖር ሕዝብ ለምን አስፈለገ? ብለን ብንጠይቅ መልሱን ለማሰብ አያስቸግርም። በአጭሩ፤ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ ቢወጡ ለመገንጠል ያስችላል። መገንጠል ግን ሰላምን አያመጣም።

የኢትዮጵያ የመከላከያ ተቋም እንደዱሮው ብሄራዊ ቢሆን ኖሮ ከማንም ጎራ የሚመጣን መገንጠልና የሕዝብ እልቂት ይከላከለው ነበር። ህወሓት ይኼን የሚያኮራ ታሪክ ያለው ተቋም አፈራርሶ ኤርትራን እንድትገነጠል አድርጓል። የባህር በሯን ዘግቷል። የዛሬው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የበላይ እዝ ጎሳዊ በመሆኑ የሚከተለው ፖሊሲና ተግባር ህወሓት የሚያዘውን ነው። ዘጠና ሰባት በመቶ የሚሆነው የበላይ እዝ የትግራይ ብሄረሰብ አባልትን ያካተተ ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ አይወክልም ማለት ነው።ዘመናዊውኑን የኢኮኖሚ የበላይነት የያዙት የህወሓት አባላት፤ ቤተሰቦችና ደጋፊዎች ናቸው። ህወሓት ተጠልቶ የትግራይን ሕዝብ የሚያስጠላው ለዚህ ነው። የመከላከያ እዙ የኢኮኖሚ የበላዩ አካልና ተጠቃሚ ሆኗል። የራሱ ጥቅም ከህወሓት ባለሥልጣናትና ተባባሪዎች አይለይም። ተጠቃሚ ስለሆነ እዙ በሙሉ የሚወክልው ህወሓትን ነው። ታዛዢነቱ ለህወሓት ነው። የህወሓት የበላዮች በኦሮሚያ የተከሰተውን ሊቆም የማይችል የሕዝብ ዓመጽ በብሄራዊ መግባባት፤ በውይይት፤ በድርድር፤ በእርቅና በሰላም ለመፍታት በመሞከር ፋንታ የህወሓትን ጀኔራሎች በሕዝቡ ላይ ጭነውበታል። ይህ የክልል መፈንቅለ መንግሥት መሰረታዊውን የፖሊሲና የመጥፎ አስተዳደር ችግር ሊፈታው አይችልም። ተመሳሳይ ሕዝባዊ አመጾች በሌሎች ክልሎች ቢከሰቱ፤ ለምሳሌ በጎንደር የሚካሄደው ተመሳሳይ ሕዝባዊ አመጽ፤ ተመሳሳይ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሊካሄድ ነው? መፈንቅለ መንግሥቱ የት ላይ ያቆማል? የህወሓት ጀኔራሎች አገሪቱን በሙሉ በበላይነት ከያዙ ኢህአዴግ የሚባለው የፓርቲ መርህና አገዛዝ አከተመለት ማለት ይሆናል። ኦሮሞዎች አክትሞለታል ቢሉ አልደነቅም። ጎንደሬዎችም መንግሥት የለም ሲሉ ቆይተዋል፤ የሚሰማቸውና የሚተባበራቸው አላገኙም።

በየትኛውም ቦታ ይሁን በሕዝብ ላይ የሚካሄድ ጭካኔ ለተከታታይ ዓመታት የሚያስከትለውን አደጋ ለመገመት ይቻላል።

አንድ፤ ሕዝቡ በመንግሥቱ ላይ ያለው ጥላቻና እምቢተኛነት እየጠነከረ ይሄዳል፤

ሁለት፤ መግባባትን ያመጣል፤ ዲሞክራሲን ያጠናከራል ተብሎ የተመሰረተው በቋንቋና በጎሳ የተዋቀረው የጎሳ ፌደራሊዝም እንዳልሰራ ያሳያል፤

ሶስት፤ የኑሮ ውድነት፤ የስራ አጥነት እየተባባሰ ሄዷል።

በቁጥሩ አንጋፋ የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ያልተቀበለውን ፌደራሊዝም ማን ይቀበለዋል? የአማራው፤ የአፋሩ፤ የጋምቤላው፤ የትግራዩ ወዘተ ሕዝብ ይቀበለው አይቀበለው በምን ሊረጋገጥ ይችላል። በእኔ ግምት ብቻ ሳይሆን ጥናት፤ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የአሁኑን ሕገመንግሥት አይቀበልም። የማይቀበልበትን ምክንያቶች በሌሎች የፖለቲካ ኢኮኖሚ ትንተናዎቸ አቅርቤአለሁ። በአጭሩ ሕገመንግስቱ የአንድ ብሄረሰብ፤ ማለትም የህወሓት መጠቀሚያና መቆያ መሳሪያ ሆኗል። ሕገመንግሥቱ ሁሉን የሚያገለግል፤ ለሁሉም ዜጎች መብቶች የቆመና ሕገመንግሥቱ የሚለውን የበላይ ባለሥልጣኖች ወደ ስራ ቢተረጉሙት ኖሮ የስልጣን መፈራረስ፤ መሽጋሸግና መድክም (Rapid dedgradation of Federal government authority in the entire country) አይኖርም ነበር።ላስምርበት የምፈልገው መሰረተ ሃሳብ፤ የፖለቲካ አመራሩ ሊፈታው ያልቻለውን ቀውስ የመከላከያ ኃይሉ ሊፈታው አይችልም። የመከላከያ ተቋሙ ገዢው ፓርቲ የፈጠረውንና ሊፈታው ያልቻለውን ችግር እንዴት ሊፈታው ይችላል? ሊፈታው አይችልም። የደርግ አገዛዝ የወደቀበት ዋና ምክንያት የሕዝቡን መብትና ስልጣን የራሱ ስላደረገና ችግሮችን በመሳሪያ ኃይል እፈታለሁ ወደሚል ውዥንብር ስለገባ ነው።

ሆኖም፤ አገሪቱ እንዳትፈራርስ ከተፈለገ የመከላከያ ኃይሉ ብሄራዊ ግዴታውን መወጣት አለበት። ብሄራዊ ግዴታውን ሊወጣ የሚችለው ራሱን ከፓርቲው በላይ ለማድረግና ኢትዮጵያዊ ለመሆን ሲችል ነው። በዘላቂነት ሲታይ ገዢውም ፓርቲ ሆነ ተቃዋሚዎች ሕገመንግሥቱ፤ ማለትም ስርዓቱ ለምን እንዳልሰራ ደፍረውና ቆርጠው መነጋገር አለባቸው። መነጋገር ስል በአንድ በኩል በገዢው ፓርቲና ደጋፊዎቹ፤ በሌላ በኩል በተቃዋሚዎች፤ አገር ወዳድ ታዋቂ ግለሰቦች፤ በሕዝቡና በሌሎች በሚያገባቸው ስብስቦች መካከል ማለቴ ነው። ኢትዮጵያዊያን ከአሁኑ አስከፊ ሁኔታ መጥቀን ለመውጣት ከፈለገን መነጋገር፤ መወያየትና መደራደር መቻል አለብን።

እውነተኛ እኩልነትና የሕግ የበላይነት መርህ ይሁን

የኦሮሞ ሆነ የአፋር፤ የትግራይ ሆነ የአማራ ወዘተ ሕዝብ ከሁሉም በላይ የሚፈልገውና የሚመመኘው መብቱና ነጻነቱ እንዲከበርለት ነው። ሕዝቡ ነጻነት ቢኖረው በሰላም አብሮ መኖርንና አብሮ ማደግን ይመርጣል። አብሮ ለመኖርና አብሮ ለማደግ ፍትህ፤ እውነተኛ እኩልነት፤ የሕግ የበላይነትና ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ወሳኝ ናቸው። እነዚህ ሁኔታዎች እስከተመቻቹ ድረስ የኢትዮጵያ ዘላቂነትና ደህንነት ዋስትና ይኖራቸዋል። ይኼን የሚወስነው ሕዝብ እንጅ የፖለቲካ ልሂቃን መሆን የለባቸውም። ሕዝብን እያሰቃዩና እየለያዩ እርጋታ፤ ሰላም፤ እድገት፤ ደህንነትና ዘላቂነት ሊኖር አይችልም። እድገት አለ ተብሎ የሚለፈፈው መፈተሽ ያለበት ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኑሮ መሻሻል አንጻር ነው።

በቅርቡ ኢኮኖሚስት የተባለው መጽሄት የጥቁር አፍሪካን የእድገት እንቅስቃሴ ሲዘግብ እንዲህ ብሏል። “ውጣ ውረድ፤ የአስተዳደር ችግር፤ ሙስናና አምባገነን አገዛዝ ቢኖሩም ከሳሃራ በታች ከሚገኙ 49 መንግሥታት መካከል ከአረብ አገሮች ጋር ሲነጻጸሩ በአገዛዝና በእድገት በኩል ጥቁር አፍሪካ የተሻለ ውጤት እያሳየች ነው…ከእነዚህ መካከል ለሕዝባቸው ህይወትና ኑሮ መሻሻል የተሻለ ውጤት የሚያሳዩት ነጻነት ያላቸውና ዴሞክራሳዊ የሆኑ አገሮች ናቸው–እንደ ናይጀሪያ፤ ጋና፤ ኬንያ፤ ታንዛኒያ፤ ዛምቢያ፤ ደቡብ አፍሪካ፤ ናሚቢያ፤ ቦትስዋና ያሉት። እነዚህ ሙሉ በሙሉ ነጻ ሆነው ብሄራዊ ተቋማትን አጠናክረዋል።” በሌላ በኩል እንደ “ሰሜንና ደቡብ ሱዳን፤ አንጎላ፤ የመካከለኛው አፍሪካ፤ ዚምባብዌ፤ ዩጋንዳ፤ የኮንጎ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ፤ ሶማሊያ፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ ምንም ነጻነት፤ ፍትህና ዲሞክራሳዊ አገዛዝ የሌለባቸው፤ በውስጥ የጎሳ ግጭት የተበከሉና ለሕዝባቸው የኑሮ መሻሻል የሚዳሰስና የሚታይ ነገር የማያሳዩ ናቸው” ይላል (The Economist, The World in 2016: A Revolution from Below and Continental Drift).

ዘገባው የፖለቲካ ነጻነትና ዲሞክራሳዊ አገዛዝ፤ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው እድገት ቀጥታ የሆነ ግንኙነት እንዳላቸው ያሳያል። ይኼን መሰረተ ሃሳብ ሙሉ በሙሉ እጋራለሁ። የአፍሪካ ልማት ባንክ የዛሬ ዓመስት ዓመት ያካሄደውን ጥልቀት ያለው የእድገት መስፈርቶችና በቅርቡ የደቡብ አፍሪካው ስታንደርድ ባንክ ያካሄደውን ሰፊ ጥናት መሰረት በማድረግ በአማካይ ሲታይ አፍሪካ ባለፉት 15 ዓመታት በአመት 5 በመቶ የሚገመት እድገት አሳይታለች። የኢትዮጵያ እድገት ከዚህ ከፍ ይላል የሚለውን ለመቀበል አስቸጋሪ ነው። ከፍም ዝቅም ቢል ቁም ነገሩ ይኼ ከመቸውም ጊዜ ከፍ ያለ የእድገት መጠን ምን ውጤት አሳየ? የሚለው ነው። በአፍሪካ ልማት ባንክ ስሌት የአፍሪካ መካከለኛ መደብ 300 ሚሊየን ሕዝብ ደርሷል ይል ነበር። ግዙፍ መሆኑ ነው። ልክ ዓለም ባንክ እንደሚያደርገው ስህተት፤ ባንኩ ቀረብ ብሎ ያላየው ጉዳይ አለ። ይኼውም፤ ልክ እንደ ኢትዮጵያ በሌሎች ታዳጊ የአፍሪካ አገሮች የእድገቱ ውጤት ለጥቂቶች ገቢ፤ ኃብትና የድሎት ኑሮ ማስገኘቱ ነው። ምንም እንኳን ከድህነት ነጻ ለመውጣት የነፍስ ወከፍ ገቢ ዓለም ባንክ ለኑሮ አስፈላጊ ነው ከሚለው በቀን ከሁለት ዶላር በላይ የሚያገኙ አፍሪካዊያን ቁጥር አድጓል ቢባልም ይኼ ገቢ ምን እንደሚገዛ አልተብራራም። የአቅርቦት እጥረት ባለበት አገር የዋጋ ግሽበት የተለመደ ነው። በእኔ ግምት ጠቅላላ የአገር ገቢና የነፈስ ወከፍ ገቢው ብቻ የኑሮ መሻሻልን አያመለክትም፤ ዋናው የመግዛት አቅምና የግለሰቦች ኑሮ መሻሻል ነው። በቀን ገቢው ሁለት ዶላር ወይንም ከዚህ በታች የሆነውን ወደጎን እንተወውና በመግዛት አቅም ገቢው በቀን ከሁለት ዶላር በላይ ቢሆንስ ብንል በስታንዳርድ ባንክ ዘገባ የመካከለኛው መደብ ሕዝብ ቁጥር ግማሽ ይሆናል።

የእድገትን መረጃዎች ማስመሰል

በቀን ሁለት ዶላር እንኳን ቴሌቪዢን፤ ዘመናዊ ቤትና ሌላ ለመግዛት የእለት የምግብ ፍላጎትን ለማሟላት አይችልም። በስታንዳርድ ባንክ ጥናት መሰረት ቴሌቪዢንና ሌሎች የቅንጦት እቃዎች ለመግዛት የሚችለው አፍሪካዊ መካከለኛ መደብ ብዛት ከ 15 ሚሊየን አይበልጥም። “የዚህ አንድ ሶስተኛው የሚኖረው ናይጀሪያ ነው፤ ሌሎቹ በአስር የአፍሪካ አገሮች ይኖራሉ፤ አብዛኛዎቹ ነጻና ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ያላቸው ናቸው። ነጻነትና ዲሞክራሳዊ መንግሥት ያላቸው ሃብታም ይሆናሉ፤ የዚህ ክፍተት ያለባቸው ደሃ ሆነው ይቆያሉ ወይንም የባሰ ደሃ ይሆናሉ ማለት ነው። የእርስ በርስ ግጭት ድህነትን ያባብሳል ማለት ነው። “There are just 15 million middle-class people in 11 sub-Saharan Africa’s biggest economies. Almost a third of these live in Nigeria; hardly any are in Ethiopia.” በኢትዮጵያ መስፈርቱን የሚያሟላ የመካከለኛ መደብ አባል የለም። ይህ በሚባልበት ጊዜ የማይበሳጭ የትግራይ፤ የአማራ፤ የአፋር፤ የኦሮሞ፤ የወላይታ ወዘተ ሕዝብ ሊኖር አይችልም። እድገት ቢኖርም የእድገቱ ውጤት የጥቂቶችን ኪስ ሞልቷል ማለት ነው። የወደፊቱን ወጣት ትውልድ እድል የሚወስኑት የእነዚህ የጥቂት የህወሓት ቤተሰቦች ልጆች ይሆናሉ ማለት ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በጋራ ሆኖ ትኩረት መስጠት ያለበት ለመልካም አስተዳደር፤ ለፍትህ፤ ለእውነተኛ እኩልነትና ሕዝብን መዓከልና የበላይ ለሚያደርግ ዲሞክራሳዊ አማራጭ መሆን አለበት እያልኩ የምክራከረው ለዚህ ነው። ደሃ፤ ጥገኛና ኋላ ቀር ሆነን እንድቀጥል ከፈለግን የህወሓትን የበላይነትና የእርስ በርስ ግጭቱን መቀበል አግባብ አለው።

ከዚህ አሰቃቂ ሁኔታ መላቀቅ ግዴታችን ነው ካልን ግን በብሄራዊ ደረጃ፤ በአንድነት ለለውጥ መታገል አለብን ማልት ነው። በእኔ ግምት፤ አንዱ ነጻ ሆኖ ሌላው ታፍኖ ሊኖርና ከድህነት ነጻ ሊወጣ አይችልም። ሌላው በኢትዮጵያ በገሃድ የሚታይ ሁኔታ የመካከለኛው መደብ አለማደግና የኢትዮጵያን ስብጥር ሕዝብ ስርጭት አለማንጸባረቅ በመተባበርና በመተሳሰብ ለፍትህ፤ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ሕዝባዊ አመጽ በመጠኑም ቢሆን ይገታዋል። ጥቂት ኃብት ያገኘው ስርዓቱ ምን አደረገ ማለት ጀምሯል። ችግሩ የተቃዋሚውና የአመጸኞች ነው ወደሚል የተሳሳተ ግንዛቤ አምርቶታል። ገዢው ፓርቲ የሚጠቅምበት የፖለቲካ ዘዴ ስርዓቱ የፈጠራቸውን ጥቂት ባለሃብቶችና በረሃብ የሚሰቃየውንና ኩራዝ መብራት የሚጠቀመውን ሕዝብ ጥገኛ አድርጎና በጎሳ ከፋፍሎ በአንድነት እንዳይነሳ ጫናዎች በማደረግ ነው።

የውሸት የእድገት መስፈርቶች ጉዳት

አገራቸውን በፍጥነት በማሳደግ ላይ ያሉ አገር ወዳድና ዲሞክራሳዊ የአፍሪካ አገሮች ለአገራቸው አንድነትና ዘላቂነት ያልተቆጠበ ጥረት ያደርጋሉ። ሕዝባቸው ከድህነት ነጻ እየወጣ ወደ መካከለኛው መደብ ሲሸጋገር በሕዝብ መካከል የቆየው የጎሳ ልዩነት እየጠፋ እንደሚሄድ በተግባር እያሳዩ ነው። ቦትስዋና ከጎሳ በላይ ናት። ናይጀሪያ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ አካሂዳ የእስልምና ተከታይ ጀኔራል ፕሬዝደንት እንዲሆኑ መርጣለች። እኒህ የጸረ-ሙስና አባት ሊባሉ የሚችሉ መሪ አገር ወዳድ ከመሆናቸውም በላይ ሽብርተኞችን በማያወላውል ደረጃ እየተዋጉ ነው። የተዘረፈው ኃብት እንዲመለስ ጥረት እያደረጉ ነው። ናይጀሪያ በኢንዱስትሪ እንድታድግ እያደረጉ ነው። የግሉ ክፍል በናይጀሪያኖች የበላይነትና ቁጥጥር ስር እንዲውል አመቻች ሁኔታዎች እየፈጠሩ ነው። ለክልሎቻችንና ለጎሳዎቻችን የተለየ ትኩረት ከምንሰጥ ይልቅ ሁሉም ለሚጋራት ለአገር እንክብካቤ እንስጥ ስል ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ልምድ በመማርና ኢትዮጵያዊያን የሚያኮራ ታሪክና የተፈጥሮ ኃብታችን ባለቤትነት ልምድ እንዳለን በመቀበል ነው። እናስብ፤ በጎሳ ተከፋፍላ የነበረችው ናይጀሪያ ( ቢያፈራ) አንድ ስትሆን በአንድነቷ የታወቀችው ኢትዮጵያ እንዴት ወደኋላ ወደሚወስድ፤ መከፋፈልና መበታተን ወደሚያስከትል ስርዓት ተሸጋገረች? ብሎ መጠየቅና መልሱን መስጠት አግባብ አለው። ሌሎች ተቆርቋሪ አፍሪካዊያን የሚጠይቁት ይኼን ነው።

በአገር ደረጃ የሚያስብ ትውልድ እንከባከብና እንደገና እንዲያብብ እናድርግ

ማንኛውም አገር፤ ጎሳ ወይንም ኃይማኖት ተተኪ ትውልድ ያስፈልገዋል። ይህ ተተኪ ትውልድ ጠንካራ የሚሆነው በመለያየትና በጥላቻ፤ በጉራ፤ በትምክኸተኛነት፤ በእርስ በርስ እልቂት፤ አንዱ ሌላውን በማዋረድ፤ በኪራይ ሰብሳቢነት ባህልና ልምድ አይደለም፤ አብሮና ተከባብሮ በመኖርና በማደግ ነው። ታንዛኒያ በአስደናቂና በማይለወጥ ደረጃ የሰጠችው ትኩረት ለብሄራዊ መግባባት፤ ለሕዝቧ አንድነትና እኩልነት ነው። እንደ ታንዛኒያና ናይጀሪያ፤ ጋናና ዛምቢያ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው ለውጥ የሚያሳዩ አፍሪካዊ አገሮች በአስተሳሰብ እየቀደሙን ነው፤ ይኼን አንካድ። የሚያስቡትና የሚሰሩት ለዘላቂ አገርና ትውልድ ነው። አሁን በኢትዮጵያ የሚታየው የአብሮና ተቻችሎ የመኖር ታሪክ ወደ መፈራረስ እያመራ መሆኑ ለሌሎች አፍሪካዊያን አሳፋሪ እየሆነባቸው ነው። የኢትዮጵያ መንግሥታት ለጥቁር አፍሪካ ነጻነት የአቅማቸውን አድርገዋል። ዛሬ የአገራችን ሕዝብ እየታፈነና አገራችን እየፈረሰች ወደ ሌሎች፤ በተለይ ዲሞክራሳዊ ወደሆኑ የጥቁር አፍሪካ አገሮች እንሰደዳለን። በመታገል ፋንታ፤ ከችግሩ እየሸሸን ማለት ነው። በአገር ቤትም ያለው ችግሩን ይሸሻል። ለምን ትሰደዳላችሁ ብለው ሲጠይቁን ምን መልስ እንደምንሰጥ አይታወቅም፤ እነሱ ግን ያውቁታል። ረሃብና የምግብ እጥረት እንዳለ፤ የስራ እድል እንደሌለ፤ ነጻነት እንደሌለ፤ የብሄረሰቦች ግጭት እንዳለ ወዘተ ያውቁታል።

ኢትዮጵያን የሚያውቁ አፍሪካዊያን ሁሉም ቦታ ስርዓቱ የፈጠረው የጎሳ ግጭትና መናጋት እንዳለና ሰላም እንደሌለ ያውቃሉ። በራሳቸው ልምድ እንዳዩት ሁሉ፤ ሰላምና ደህንነት ሲበከሉ ኑሮም አብሮ እንደሚበከል ያውቃሉ። በተለየ ደረጃ የሚጎዱት ሴቶች፤ ህጻናት፤ ሽማግሌዎች፤ ጡረተኞች መሆናቸውን ያውቃሉ። ብዙዎቹ ኢትዮጵያዊያን የሚሰደዱት ወደ ኬንያ፤ ታንዛኒያ፤ ዛምቢያ፤ ናሚቢያ፤ ደቡብ አፍሪካ ነው። ይኼ ተከታታይ ሁኔታ ለምን አያሳፍረንም? ለምን አያስተባብረንም? ለምን አያስማማንም? የሚሰደዱት ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፤ እናቶች፤ እህቶች/ዎንድሞች/ ዘመዶች ወዘተ አሏቸው። የሚሰደዱበት ምክንያት ግልጽ ቢሆንም እናቶች በተናጠል ይጨነቃሉ። የትግራይ ደሃ አናት ከአማራ ድሃ እናት ጋር አትነጋገርም። እናቶችን የሚያስተባብራቸው ተቆርቋሪ ቡድን የለም። አገራችን ምን ሆኗ ነው ለልጆቻችን ህይወት የማትቆረቆረው ብለው ራሳቸውን ይጠይቃሉ። ጥያቄውን የሚመልስ ባለቤት ወይንም ባለሥልጣን ወይንም ተቃዋሚ ክፍል ፈልጎ ለማግኘት አይቻልም። በተመሳሳይ ኢትዮጵያን ለማዳን የሚቆረቆሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ቢኖሩም በአንድነት ሆነው ለአገሪቱ ዘላቂነት ሃላፊነት ወስደው ባለቤት አልሆኑም። እንተባበር የሚለው የሚሰለች ብሂል ተደጋጋሚ ሆኖ ትርጉም-የለሽ ሆኗል። አገሪቱ የወላድ መካን ሆናለች የሚያስብል ሁኔታ እንዳለ መካድ አይቻልም።

የአገርን ጤናማነት ከሕዝብ ህይወትና ኑሮ ለይቶ ለማየት አይቻልም። የናይጀሪያ ኢኮኖሚ አደገ ሲባል የመካከለኛው መደብ እያደገ ሄደ ማለት መሆኑን ከላይ አሳይቻለሁ። በሶማሊያ እንዳየነው አገር ስትጎዳና ስትወድቅ አብሮ የሚጎዳውና የሚወድቀው ሕዝብም ነው። አገር ስትጠነክር ሕዝብም ይጠነክራል። እናቶች በተደጋጋሚ የተጎዱት ከሁለት አንጻር ነው።

አንድ፤ ልጆቻቸው የአገራቸውን ነጻነትና ግዛታዊ አንድነት ሲታደጉ መሞታቸውና መቁሰላቸው። ለምሳሌ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተካሄደው ትርጉም የለሽ ጦርነት ከሁለቱም ሕዝቦች ከሰባ ሽህ በላይ ሰው ሞቷል፤ አብዛኛው ወጣት። በቅርቡ በኦሮሚያ እንደሆነውና እንደሚሆነው ወጣቶች ለፍትህ፤ ለእኩልነትና ለእድገት ሲታገሉ እነደወጡ መቅረታቸው፤ መሰወራቸውና በገፍ መሰደዳቸው ተከታታይ ሆኗል። በአገር ደረጃ ብናየው፤ በደርግ ዘመን ብቻ ኢትዮጵያ አንድ የተማረ ወጣት ትውልድ አጥታለች። ይኼ ትውልድ የተማረው በደሃው ሕዝብ ኃብት ነው። ደሃው የባከነውን ወጣቱን ትውልድ ከፍሎ ያስተማረው ለእልቂትና ለስደት አልነበረም፤ ራሱን ከድህነት ነጻ አውጥቶ አገሩንና ሕዝቡን እንዲያገለግል ነው። የአሁኑ አገዛዝ ብሷል። ብዙ ሚሊየን የተማረ የሰው ኃይል በስደት ይኖራል፤ አሁንም ይሰደዳል። የየመን መንግሥት 400,000 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በየመን ብቻ እንደሚኖሩ ዘግቦ ነበር። በሳውዲ አረቢያ፤ በኩዌይት፤ በተብበሩት የአረብ ኤምሬቶች፤ በሌባኖን፤ በካታርና ሌሎች የአረብ አገሮች ሰብአዊ መብታቸው ታፍኖ፤ በእስር ቤት ታጉረው የሚኖሩትን ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም ብዙ እንደሆኑ አውቃለሁ። የአገራቸው መንግሥት መብታቸውን ለማስከበር የወሰደው አንድም እርምጃ የለም። እንዲያውም በስደቱ ይነግድበታል። ኢትዮጵያ ግዙፍ የተማረ የሰው ኃብት አላት፤ የሚኖረው በውጭ ነው። ይኼን ግዙፍ የሰው ኃብት ወደ አገሩ ገብቶ፤ መብቱ ተከብሮ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዲያገለግል የጠየቀው የመንግሥት ባለሥልጣን የለም።

ሁለት፤ ምንም እንኳን መንገድና ሌላ መሰረተ ልማት ቢስፋፋም ሴቶችና አብዛኛው የተማረው ክፍል የእድገቱ ውጤት ተካፋይ አይደሉም። ነጻነት፤ ፍትህ፤ የሕግ የበላይነትና እውነተኛ ዲሞክራሳዊ መንግሥት እስካልተቋቋመ ድረስ ሁኔታው አይለወጥም። በሃያ አምሥት ዓመታት የእድገት ታሪክ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የመካከለኛ-ገቢ መደብ ለመፍጠር ያልቻለና ረሃብን ለመቅረፍ ፍላጎትና አቅም የሌለው ስርዓት በሚቀጥሉት 25 ዓመታት የተለየ ውጤት ያስገኛል ብሎ መገመት ራስን ማታለል ነው። አይቻልም። ለማጠናከር የምፍልገው ሃሳብ የእናቶችና የወጣቶች ጤናማነትና የአገር ደህንነት የተያያዙ መሆናቸውን ነው። ጤናማ አገር ጤናማ እናቶችና ተከታታይ ትውልድ ይኖሯታል። ወጣቶች ለፍትህ ሲታገሉ ማፈንና መጨፍጨፍ ጤናማነት አያሳይም። የባሰውን ህወሓት/እህአዴግ በአገራቸው ተፍጨርጭረው ራሳቸውን እንዲችሉና አገራቸውን ዘመናዊ እንዲያደርጉ አመቻች ሁኔታን ከልክሏል።

ብሄራዊ መግባባት፤ እርቅና ሰላም አስቸኳይ ሆኗል

ምን መፍትሄ አለ? ይሔን ጽሁፍ ለማጠቃለል፤ አፓርታይዷ ደቡብ አፍሪካ በዘር ጥላቻ የተመረዘች አገር ነበረች። የጥቁሩን ሕዝብ በጭካኔ ትጨፈጭፍ፤ ታስር፤ ታጉርና ታሳድድ ነበር። ለብዙ አስርት ዓመታት የደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚ፤ ለጥቂት ነጮች አይተውት የማያውቁት ገቢና የድሎት ኑሮ ከማመቻቸቱ ባሻገር ለማምረት፤ ለብዙሃኑ የጥቁር ሕዝብ የስራ እድል ለመፍጠር ያልቻለበት ዋና ምክንያት የስርዓቱ ትኩረት ሕዝብን አፍኖና ቀጥቅጦ በመግዛት ላይ ስለሆነ ነው። በጥቂት ነጮች የበላይነት ይተዳደር የነበረው ስርዓት ለስለላ፤ ለአፈናና ሌላ የሚያወጣው ኃብት ብዙ ፋብሪካዎች ሊያሰራና የስራ እድል ሊፈጥር ይችል ነበር። ኔልሰን ማንዴላ አፈናውና ግድያው የማያዋጣ መሆኑን ካሳሰቡ በኋላ አማራጭ አቅርበው የስርዓት ለውጥ አምጥተው ነበር። ይኼም አማራጭ ሁሉን አቀፍ የሆነ ዲሞክራሳዊ መንግሥት እንዲቋቋም ማድረግ ነበር። አስተዋይ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ መሪዎችና አባቶች፤ በተለይ ማንዴላና ዴስሞንድ ቱቱ ለሃገራቸውና ለሕዝባቸው በመቆርቆር ስርዓቱ ከስሩ መለወጥና እንደገና መመስረት አለበት የሚል መርህ ተከተሉ። ብሄራዊ መግባባት፤ እርቅና ሰላም እንዲካሄድ አድርገው የሰላም መሰረት ጣሉ። ዛሬ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ገዢውን ፓርቲ፤ ሁሉንም የፖለቲካና የማህበረሰብ ስብስቦችና ተቋሞች፤ መንፈሳዊ መሪዎችና አባቶች፤ እውቅና ያላቸው ግለሰቦች የሚያካትት የብሄራዊ መግባባት፤ ውይይት፤ የፖለቲካ ድርድር፤ እርቅና ሰላም ጉባኤና ስብሰባ ማካሄድ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብና ልሂቃን ፊት ለፊት ሆነው ለመነጋገር ካልተቻሉ አደጋው እየተባባሰ ይሄዳል። ስለሆነም ይኼ ጉዳይ ጊዜ የሚሰጥ አይመስለኝም፤ በአስቸኳይ መካሄድ አለበት።

 

The post አገርን እንደ እናት ያለመቀበል አደጋ እና የብሄራዊ መግባባት አስፈላጊነት | አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር) appeared first on Zehabesha Amharic.

ይድረስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጉልበት ላላችሁ ሁሉ |ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

$
0
0

Pro Mesfin

ልጆች ሆነን ታላላቆቻችን ጉልበት አለን ብለው በደል ሲፈጽሙ ‹እግዚአብሔር በቀዳዳ ይየው!› እንል ነበር፤ ለመርገምም እየፈራን አንዲያው ድርጊቱ እንዲመዘገብልን ማሳሰባችን ይመስለኛል፤ አሁንም እንደዚያ ለማለት ይቃጣኛል፤ ግን አግዚአብሔር በሰማይ ላይ መኖሩን፣ በእያንዳንዳችን ውስጥ መኖሩን የቤተ ሃይማኖት ሰዎች እንኳን ማመናቸው በሚያጠራጥርበት ዘመን ለዓለማዊ ባለሥልጣኖች የእግዚአብሔርን ስም ማንሣት ፋይዳ ይኖረዋል ብዬ አልገምትም፤ ሆኖም እኔ ስለማምንበት የራሴን አሳውቃለሁ፤ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር አገር ነች፤ ኢትዮጵያን ጎድቶ የተጎዳ እንጂ የተጠቀመ የለም፤ ኢትዮጵያን አዳክሞ የደከመ እንጂ የበረታ የለም፤ ኢትዮጵያን አደህይቶ የደኸየ እንጂ የበለጸገ የለም፤ ኢትዮጵያን አዋርዶ የተዋረደ እንጂ የተከበረ የለም፤ ይህ የታሪክ ሐቅ ነው፡፡

የኢትዮጵ ባለሥልጣኖች ዓላማችሁ ምንድን ነው? እስከዛሬ ድረስ በየትም አገር በሰማይ ጠቀስ መቃብር ውስጥ የተጋደመ ባለሥልጣን የለም፤ ደግሞስ ሰማይ ጠቀስ መቃብር ካስፈለገ ለአንድ ባለሥልጣን ከነቤተሰቡ ስንት ሰማይ ጠቀስ ፎቆች፣ ስንት ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ያስፈልጉታል? ከዚህ በፊት ምጽዓት በሚል ግጥም የሚከተለውን አመልክቼ ነበር፡፡

ከራስ በላይ ነፋስ ትልቁ ሃይማኖት፤
ዘረፋን ሲያውጀው ቂም ሲያስረግዝ ጥቃት፤
ዓይን አያይም አሉ፤ ጆሮም አያዳምጥ፤
ተለጉሞ አንደበት ሁሉም ይዞታል ምጥ!
በቁንጣን፣ በስካር ጥቂቶች ሲንሩ፣
ብዙዎቹ ደግሞ በረሀብ መንምነው በቁንጫ ሲያርሩ፣
የደሀ እንባ ሲጎርፍ መሬቱ ሲሸበር፣
ዝብርቅርቁ ወጣ፤
ሕይወት ትርጉም አጣ፤

ኧረ የት ነው ጉዞው ዓላማው ምንድን ነው?
ቀድመው የሄዱትን ምነው አናያቸው?

የት ገቡ? የት ጠፉ? ፋና እንኳን አይታይ፤
ብልጭ የሚል የለ ከመሬት ከሰማይ!
መንገዱ ጠበበ፤ ትርምስምሱ በዛ፤
እሪታው ኡኡታው ቀለጠ እንደዋዛ!
መሬቱም ዓየሩም በክፋት ጠነዛ!
ጥላቻና ቂሙ በሰፊው ተነዛ፡፡

እምቢልታው ሲጣራ ነጋሪት ሲያገሳ፣
የአለው ሁሉ ሞቶ የሞተው ሲነሣ፣
ምጽዓት መድረሱ ነው ሊስተካከል ነው ፍርድ፤
በግና ፍየሉ ሊለዩ በገሃድ!

እንደሚመስለኝ በአሁኑ ጊዜ ይህንን አቅጣጫ ማየት የሚያዳግተው ሰው በራሱ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በቤተሰቡና በአገሩ ሕዝብ ላይ መቅሠፍትን የሚጠራ ነው፤ እየተማረርን ነው፤ የርኅራኄ ወዛችን እየደረቀብን ነው፤ መጨካከን እንደጀግንነት እየተቆጠረ ነው፡፡

በሌላ ሞት ማለት በሚል ግጥም፡–

ሞት ማለት፡-
አለመናገር ነው፤ ጭው ያለ ዝምታ፣
የመቃብር ሰላም የሬሳ ጸጥታ፤
ደሀ በሰሌኑ ሣጥን ገብቶ ጌታ፤
የውሸት ልዩነት ተጋድሞ በተርታ!

እኔ እንደምገምተው ጉልበተኞች የሆናችሁ ሁሉ ዓላማችሁ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዓላማ የተለየና በቅራኔ ላይ ያለ አይመስለኝም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብልጽግና፣ እድገትና ክብር የናንተም ነው፤ በየትም አገር ስትሄዱ የሚነጠፍላችሁና የሚጨበጨብላችሁ የኢትዮጵያን ሕዝብ በመወከላችሁ ነው፤ ዛሬ በአውሮፓና በአሜሪካ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለው ክብርና በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ሕዝብ የነበረው ክብር በጣም የተለየ ነው፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ ያገኙትን ክብር ከሳቸው በኋላ የመጡት አላገኙትም፤ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ አዋርዶ ከየትም ክብርን ማግኘት አይቻልም፤ የራስን ሕዝብ ንቆ መከበር አይቻልም፤ የራስን ሕዝብ አንገቱን አስደፍቶ ቀና ብሎ መሄድ አይቻልም፡፡

እስር ቤቶችን ሁሉ ዝጉ፤ የዘጋችሁትን አንደበት ሁሉ ልቀቁ፤ ያፈናችሁትን አእምሮ ሁሉ ለነጻነት አብቁት፤ ጭካኔን በርኅራኄ፣ ጉልበትን በእውቀት፣ ዱላን በክርክር፣ ቁጣን በፍትሐዊነት እየለወጣችሁና እያበረዳችሁ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ታረቁ፤ በተለይ ከኢትዮጵያ ወጣት ጋር ልብ ለልብ ተገናኙ፤ ነገ የወጣቱ ነው፡፡

አይተናል፤ አንበሶች ነን የሚሉ ቀሚስ ለብሰው ሲሸሹ! አይተናል፤ አለኛ ማን? እያሉ ሲወጠሩ የነበሩ እንዳይጥ በጓሮ ተደብቀው የሙጢኝ ሲሉ! አይተናል፤ ጀግኖች ነን ብለው ሲያቅራሩ የነበሩ በየፈረንጅ አገሩ አንገታቸውን አቀርቅረው ትሕትና ሲማሩ! አይተናል፤ የዘረፉትን ሁሉ ሳይበሉ፣ ሳያጌጡበት ሲቸገሩ! አይተናል! ሰምተናል አይደለም አይተናል!

ሌላ ዙር ግፍ ቂምን እየወለደ፣ ቂም በቀልን እየወለደ፣ በቀል አዲስ ግፍን የሚወልድበት ሁኔታ ሲፈጠር ለማየት አንፈልግም፤ በቃን ግፍ! በቃን ቂምና በቀል! በቃን እየተዋረደ የሚያዋርደንን ማየት! በቃን መንፈሳዊ ወኔ በሌላቸው ጉልበተኞች መነዳት! በቃን ጠመንጃቸውን ሲነጠቁ አይጥ የሚሆኑ አሻንጉሊቶች! በቃን በደሀ ጉልበት ጉልበተኞች፣ በደሀ ሀብት ሀብታሞች መስለው የሚታዩ ኅሊና-ቢሶችን መሸከም! እስቲ እኛ ደካማዎቹ ሰዎች እንሁን! አስቲ እናንተም ጉልበተኞች ሰዎች ሁኑልን! እንደሰዎች በሰላም እንድንነጋገር ድፍረቱን፣ መንፈሳዊ ወኔውን ከቅን መንፈስ ጋር እንዲሰጠን እግዚአብሔርን እንለምነው! ክፋትን እንሻረው! ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለው ‹‹ለክፉዎች ሰላም የላቸውም፤ ይላል እግዚአብሔር፤›› እንዳይሆንብን!

The post ይድረስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጉልበት ላላችሁ ሁሉ | ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም appeared first on Zehabesha Amharic.

በዛሬው እለት በበኒ ኑር መስጅድ ታላቅ ተቃውሞ ተደረገ

$
0
0

muslim 3 muslim muslim2

መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ብሄራዊ ጭቆና አንሸከምም በማለት  ሙስሊሙ ማህበረሰብ በዛሬው እለት በኑር መስጅድ ውጭ ላይ ተቃውሞ ማካሄዱን ቢቢኤን ራድዮ ዘገበ፡፡

ብሄራዊ ጭቆናን አንሸከምም፤ ነጻነት እንፈልጋለን የሚሉ ጽሁፎች ታይተዋል፡፡ ተቃውሞው ከተካሄደ በሁላ በሁኔታው የተደናገጡት ፖሊሶች በሙስሊሙ ላይ ትንኮሳ ማካሄዳቸውም ታውቋል፡፡
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ3 ሳምንት በፊት በአንዋር መስጊድ; ባለፈው አርብም በተጨማሪ በበኒ መስጊድ ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ማሰማታቸው ይታወሳል::

The post በዛሬው እለት በበኒ ኑር መስጅድ ታላቅ ተቃውሞ ተደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.


መንግስታችን ለመጪው ግንቦት ሃያ አብዮት ይጠራ ይሆን? |ግርማ ሠይፉ ማሩ

$
0
0
Girma Seifu Maru

Girma Seifu Maru

የካቲት 21 2008 በኢትዮጵያ ታሪክ ተመዝግቦ አልፏል፡፡ ቀጣዩ ታሪካዊ ቀን ደግሞ የሚመጣው ግንቦት 20 2008 ነው፡፡ የግንቦት 20 ማግሰት ምን አዲስ ነገር እንደሚመጣ ግን ማንም የሚያውቅ የለም፡፡ መገመት ግን ይቻላል፡፡ የመጪው ግንቦት ሃያ ቀደም ብለን እንድንነጋገርበት ያሳሰበኝ በቅርቡ የአዲስ አበባ የትራንሰፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ያደረጉት የሰለማዊ ተቃውሞ/የስራ ማቆም አድማ ነው፡፡ እንደሚታወቀው በአዲስ አበባ አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች መደዳ ቁጥር ሰላሣ ሺ የደረሰ ሲሆን በእርግጠኝነት በስራ ላይ የሚገኙት ግን ከግማሽ የሚበልጡ አይደለም፡፡ በተጨማሪ አገልግሎት የሚሰጡትን ታክሲ ያልሆኑ ሚኒባሶች ሲጨመሩ ሃያ ሺ የሚሆኑ መኪኖች በአግልግሎት ውስጥ ናቸው የሚል ታሳቢ መውሰድ ይቻላል፡፡ እነዚህ የትራንሰፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በሰራቸው የሚተዳደረውን በመቶ ሺ የሚቆጠረ ቤተሰብ አባል ችግር ላይ ሊጥል የሚችል እርምጃ በመውሰድ መንግሰትን የተጋፈጡ ሲሆን፣ በማህበራቸው በኩል ተደረገ በተባለ ድርድር ለተቃውሞ መነሻ የሆነው መመሪያ ለሶሰት ወር ተግባራዊ እንዳይሆን ከስምምነት በመደረሱ ተቃውሞ ተቋርጦዋል፡፡ ሶሰት ወር የሚሞላው ደግሞ ግንቦት 20 2008 ነው፡፡ ከዚህ አንፃር መነሳት ያለበት ጥያቄ ከሶሰት ወር በኋላስ? የሚለው ነው፡፡ በተለይ ጥያቄውን ከአሸከርካሪዎች አንፃር የተወሰኑ መሰረታዊ ነጥቦችን በማንሳት እንመልከተው፤

parlament

 የመጫኛ እና ማውረጃ ቦታ በቂ ያለመሆን

እንደሚታወቀው ለታክሲ ማቆሚያና ማውረጃ በቂ ቦታዎች በከተማው ውስጥ የለም፡፡ በዚህ ምክንያት ታክሲዎች ባመቻቸው ቦታ ይጭናሉ ያወርዳሉ፡፡ ተሳፈሪውም በየአስር ሜትሩ ወራጅ አለ ብሎ መውረድ ይፈልጋል፡፡ ተሳፋሪን በየቦታው ለማውረድ ብቻ ሳይሆን ለመጫንም ይቆማሉ፡፡ በዚህ ጊዜ በመንገድ ዳር የቆሙ መኪኖችን ደርበው መጫንና ማውረድ መደበኛ የታክሲ ስራ አካል ነው፡፡ ይህ ድርጊት አሁን በወጣው መመሪያ መሰረት ከፍተኛ ቅጣት የሚያስጥል ነው፡፡ ሰለዚህ በሚቀጥለው ሶሰት ወር ውስጥ  መንግሰት ይህን ችግር ለመፍታት እና መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል አቅምም ፍላጎትም የለውም፡፡ አማራጩ ደርቦ መጫንና ማውረድ ትክክለኛ ተግባር ተደርጎ እንዲወሰድ ማድረግ አንዱ ነው፡፡ ሌላው አማራጭ ደግሞ ለታክሲ ማቆሚያ ሲባል በመንገድ ላይ መኪና ማቆም መከልከል ነው፡፡ ይህ ደግሞ መንገድ ተከትለው የተሰሩት ህንፃዎች እና የተከፈቱ የንግድ ተቋማት ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ ይህ የፊት ለፊቱ ችግር ሲሆን መንገድ ላይ ፓርክ ማድረግ መከልከል ከዚህ የከፋ ሌላም ችግር እንደሚኖረወ መዘርዘር ይቻላል፡፡ ለማነኛውም መንግሰት ይህን ችግር እንደማይፈታው ታውቆ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡

የትራፊኮች የሰነ ምግባር ጉዳይ

የትራፊኮች የስነ ምግባር ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ሁሉም ይረዳዋል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት መንግሰት መፍትሔ ብሎ ያሰቀመጠው አቅጣጫ ግን ከህግም ከሞራልም አንፃር ተገቢ አይደለም፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ትራፊክ ላይ ከጠቆመ ትራፊኩ ከስራ ይባረራል፡፡ ምን ማለት ነው? የትራፊኮች የሰነ ምግባር ችግር በሌሎች ዜጎች የሌለ ይመስል ሌሎችን አምኖ እርምጃ መውሰድ የህግ መሰረት የለውም፡፡ ትራፊክ ያለጥፋት ሊቀጣን ይችላል የሚል ስጋት ሲቀርብ ትራፊኩን ያለጥፋቱ የሚያስቀጣ አስራር ይፈጠር ማለት አይደለም፡፡ አንድ ትራፊክም ቢሆን ያለጥፋቱ ጉዳት ሊደርስበት አይገባም ለምንል ሰዎች ግን ይህ ህገወጥ ነገር ግን በአደባባይ እየተነገረ ያለ የእርምጃ ዓይነት ዜጎችን አሸማቃቂ ነው፡፡ ለማነኛውም ዋነኛው ችግር ግን ትራፊኮች በዚህ ዓይነት ህግ ውስጥ ምን ያህል ሊቆዩ ይችላሉ? የሚለው ሲሆን የትራፊኮች የስራ ማቆም አድማ መንገድ ከመዝጋት አልፎ የተለየ ነገር ያመጣል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ይህ እርምጃ ሰዎች በትራፊኮች ላይ ጥቆማ ከማድረግ ይልቅ ትራፊክና አሸከርካሪ ተጣምረው ለበለጠ ውስብስብ ችግር የሚዳርግ ነው የሚሆነው፡፡ ልብ ማለት ያለብን ትራፊኮቹም ቢሆኑ የማህበረሰቡ አካል መሆናቸው እና ለትራፊክነት ፍላጎት ያላቸው ከሰራ ፍቅር ወይም ከደሞዙ አማላይነት የተነሳ አይደለም፡፡ በአንድ ወቅት ሪፖርት ጋዜጣ ያወጣው ዜና ትዝ የሚለኝ ዲግሪ ያላቸው ወጣቶች በጉምሩክ ለፈታሽነት ስራ በሺዎች መመዝገባቸው የስራ ፍቅር እንዳልሆነ ግልጥ ከመሆን አልፈን ወጣቶቻችን የደረሱበትን የገንዘብ ማግኛ ፍላጎት መስመር የሚያጋልጥ ነው፡፡ ሃሳቤ ግልፅ ይመስለኛል፡፡ ዲግሪ ይዞ ኬላ ላይ ፈታሽ መሆን መመኘት የጤና አይመስለኝም፡፡

የቅጣቶች ተደራራቢነት

ቅጣቶች ተደራራቢ ከመሆናቸው አንፃር አንድ የቤት መኪና አሸከርካሪ ሰድስት ወር ወይም ሁለት ዓመት ቢቀጣ በትራንስፖርት መሄድ አማራጭ ሲሆን አቅም ካለው ደግሞ በሾፌር መሄድ ይችላል፡፡ በአሸከርካሪነት የሚኖር ለመደበኛ አሸከርካሪ በስራው ፀባይ የተነሳ ደንብ ለመተላለፍ የተጋለጠ አሸከርካሪ ግን ዲግሪውን ነው የሚቀማው፡፡ ለምሳሌ እኔ ዲግሪ ብቀማ የምሰራውን ስራ የሚከለክለኝ ነገር ስለሌለ ተቀጥሬ መስራት ብቻ ነው የሚቀርብኝ፡፡ አንድ አሸከርካሪ ግን መንጃ ፍቃዱ ከተቀማ ከሰራ መስኩ ነው የሚባረረው፡፡ ለስድስት ወር ለሁለት ዓመት ምን እየበላ እንዲኖር እና ቤተሰቡን እንዴት እንዲያስተዳደር እንደታሰበ መመሪያው አይገልፅም፡፡ በትራፊክ አደጋ ሰው እንዳይሞት በረሃብ ግን ይሙት የሚል ይመስላል፡፡ አንድ ቀደም ሲል በህገወጥ ተግባር ሲሰማራ የነበረ፣ ነገር ግን ፀባዩን አርቆ ስርዓት ይዞ የታክሲ ረዳት ከዚያም ሁለተኛ፣ ሶሰተኛ ብሎ መንጃ ፍቃድ አውጥቶ በስራ ላይ ያለ አሸከርካሪ ቃል በቃል አለ የተባለው “ችግር የሌም ተመልሼ ወደ ቀድሞ ስራዬ እገባለሁ” ነው፡፡ ማጅራት እየመታ ሰው ገድሎ እንዲኖር ማለት ነው፡፡ ሌሎች ሀገሮች የዚህ ዓይነት ህግ ሲተገብሩ በሀገራቸው ስራ የሌለው ሰው የማህበራዊ ዋስትና የሚባል ክፍያ የሚያገኝ በመሆኑ ስራ አጥቼ ምን ልሁን አይልም፡፡ ይህን ስናስብ ህጎችን ስንቀዳ በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ማድረግ ይኖርብናል፡፡ አሁንም መነሳት ያለበት ጥያቄ የዛሬ ሶሰት ወር መንጃ ፍቃዱን  የተቀማ አሽከርካሪ ምን ይሁን? ፈቃድ የማይጠይቁ ስራዎች ገቢ የሚያስገኙ አማራጭ ካሉም ይነገረን፡፡ አንዱ የገዢው ፓርቲ አባልነት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ከአባልነት በመለስ ማለቴ ነው፡፡

ገዢው ፓርቲ ካለው የድርድር ባህሪ አንፃር ለማሳያ ከላይ የተዘረዘሩትን ችግሮች ሊፈታቸው አይችልም፡፡ በአሁኑ ወቅት ሊያደርግ የሚችለው ብዙ ቢሆንም ከልምድ ግን የተወሰኑትን ማንሳት ይቻላል፡፡ አንደኛ ይህን ተቃውሞ ሲመሩ የነበሩትን በተለያየ መንገድ በመደለል የተደረገውን የስራ ማቆም አድማ በድጋሚ ሊጠራ የማይችልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው፡፡ ለዚህም  እነዚሁኑ ሰዎች የአገልግሎት ሰጪ ሾፌሮችና ረዳቶችን በመከፋፈል ባቀደው መሰረት ከሶሰት ወር በኋላ መመሪያውን በማን አለብኝነት ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ይህም ሲሆን ከዚህ ቀደም የተደረገውን ድርጊት እንዲያወግዙ ጭምር በማድረግ ሞራላቸውን ማኮላሸት ዋናው ግብ ይሆናል ማለት ነው፡፡ በንግድ ባንክ ሰራተኞች ላይ የተወሰደውን እርምጃ ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡

በቀጣይ ደግሞ ተጨማሪ ታክሲዎች በመንግስት ድጋፍ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ወይም ይገባሉ እያሉ በማስወራት አሁን ያሉትን አገልግሎት ሰጪዎች ከጫወታ ሊያሰወጣን ነው ወደሚል የሰነ ልቦና ጦርነት መፍጠርና ማሰጨነቅ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከዚህ ቀደምም ተሞክሮ የሰራ ሲሆን በቀጣይ በተመሳሳይ መልኩ ስራ ላይ አይውልም አይባልም፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው ከዚህ ቀደም በባለ ታክሲዎች የተደረጉ የስራ ማቆም አድማዎች ናቸው፡፡

እኔ ከዚህ የስራ ማቆም አድማ በግሌ ብዙ ነገር ተምሬያለሁ ዋነኛው ነገር ህዝቡ ከተባበረ ማንኛውም መብቱ የተነካ ስብስብ መብቱን ማስከበር እንደሚቻል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የታክሲ ሾፌሮች ዘወትር በተለያዩ ሚዲያዎች ከሚደርስባቸው ዘለፋ አዘል አስተያየቶች በተቃራኒው የእነርሱ መኖር በሁሉም እንቅስቃሴ ውስጥ ሞተር መሆኑን ለዘነጋው ዜጋ ትምህርት አስተላልፈዋል ብዬም አምናለሁ፡፡ በቀጣይ ሁሉም በጋራ የማይቆሙ ቢሆን እንኳን ጉዳዩ የበለጠ የከነከናቸው አሸከርካሪዎች በተናጥል መኪናውን ለባለቤቱ አስረክበው ዋነኛ የሰራ ሰርተፊኬት ከማሰረከብ ይህ ህግ እስኪሻሻል በሾፌርነት ላለመስራት ቢወስኑ ባለንብረቶች መኪናው በፈረስ ስለማያሰጎትቱት መንግሰትም ባለቤቶቹን ለማስገደድ አቅም አይኖረውም፡፡ ሰለዚህ ጫናውን ማስቀጠል ይቻላል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ሌላው መንገድ ደግሞ ሾፌሮች ሰራቸውን ለመስራት አሁን ከሚከፈላቸው በላይ የሚመጣውን የወደፊት አደጋ ለመቋቋም የሚያስችል ደሞዝ እና የቀን አባል ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ ታሪፍ ሲሻሻል እና ገቢው ሲጨምር ብቻ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አዲሱ ተግባራዊ የሚሆነው መመሪያ ወደ ህዝቡ የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪ ይጠራል ማለት ነው፡፡ ህዝቡ ደግሞ አሁንም ያለው ዋጋ መሸከም አልቻለም እና በሌሎች ዕቃዎችም ላይ የዋጋ ንረት ሊጠራ ይችላል፡፡ እነዚህ ሲደመሩ ደግሞ ሌላ ጦስ ላለመጥራታቸው ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡

የዛሬ ሶስተ ወር አጭር ጊዜ ነው፡፡ አሸከርካሪ፣ የመኪና ባለቤቶች፣ ተጠቃሚው ህዝብ፣ በተለይም መንግስት ከፍተኛ የቤት ስራ ይጠብቃቸዋል፡፡ ግንቦት 20 2008 በሚያበቃው ሶሰት ወር መንግሰት ምን ይዞ እንደሚመጣ በጉጉት እንጠብቃለን፡፡ መንግሰታችን ለመጪው ግንቦት ሃያ አብዮት ይጠራ ይሆን?

ቸር ይግጠመን

 

The post መንግስታችን ለመጪው ግንቦት ሃያ አብዮት ይጠራ ይሆን? | ግርማ ሠይፉ ማሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሕወሓቱ ኤፈርት (ማረት) ሾፌሮች በኦሮሚያ ክልል መኪና ማሽከርከር ለሕይወታቸው እንደሚያሰጋቸው ገለጹ

$
0
0
በኮፋሌ ሰልፈኞች አቃጥለው አወደሙት የተባለው የትራንስ ኢትዮጵያ የጭነት መኪና

በኮፋሌ ሰልፈኞች አቃጥለው አወደሙት የተባለው የትራንስ ኢትዮጵያ የጭነት መኪና

አምዶም ገብረሥላሴ እንደዘገበው

በኤፈርት ስር የሚገኘው የትራንስ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሰራተኞች የሆኑ ከ200 በላይ የከባድ ጭነት መኪና ሹፌሮች “በኦሮምያ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር ለህይወታችን አስጊ በመሆኑና በፌደራል ፖሊስ እየተጠበቅን መስራት ስላስጨነቀን ችግሩ እስኪፈታ ድረስ ስራ እናቆማለን” የሚል መልእክት ያለው ደብዳቤ መቐለ ለሚገኘው ለትራንስ ኢትዮጵያ መስርያ ቤት በማስገባት ግልባጩን ለትግራይ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ኣባይ ወልዱ ለመላክ እየተዘጋጁ መሆኑን የአረና ፓርቲ አመራር የሆነው አምዶም ገ/እግዚአብሄር በማህበራዊ ድረ ገጹ አስፍሯል።

የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ ሹፌሮቹ “እኛ አገራችን እያገለገልን ሳለ በኦሮምያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ለህይወታችን አ ስጊ ሆኖብናል፣በፌደራል ፖሊስ እየታጀብን መንቀሳቀስም ሰልችቶናል። መንግስት ፀጥታውን በአስተማማኝ ሁኔታ ሲያስከብር ወደ ስራችን እንመለሳለን” በማለት ውሳኔያቸውን አስታውቀዋል።
የኤፈርት ሃብት በትግራይ ህዝብ ስም የተከፈተ ኢንደውመንት ቢሆንም እስካሁን ከ10 በማይበልጡ የህወሓት መሪዎች ብቻ የሚሽከረከርና ኦዲት ተደርጎ የማያውቅ ግዙፍ ካፒታል የሚያንቀሳቅስ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል።
የኢህአዴግ መንግስት በኦሮሚያ ክልል የተነሳበትን ተቃውሞ በቁጥጥር ስር ማዋሉን በመግለጽ ተቃውሞ ይደረግባቸው በነበሩ ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ትምህርት በቤቶችና የንግድ እንቅስቃሴዎች ወደመደበኛ ተግባራቸው መመለሳቸውን ቢገልጽም የትራንስ ኢትዮጵያ የከባድ ጭነት መኪና ሹፌሮች የወሰዱት የስራ ማቆም አድማ አካባቢው መንግስት እንደሚለው ወደመደበኛ ሰላማዊ ሁኔታው ላለመመለሱ አይነተኛ ማሳያ ይሆናል፡፡

The post የሕወሓቱ ኤፈርት (ማረት) ሾፌሮች በኦሮሚያ ክልል መኪና ማሽከርከር ለሕይወታቸው እንደሚያሰጋቸው ገለጹ appeared first on Zehabesha Amharic.

“የዕድገት በኅብረት ዘመቻ ምናልባትም በኢትዮጵያ የመጀመሪያው  የሴቶች የነፃነት ቀን ተብሎ ሊታሰብ የሚችል ነው።” –አሰፋ ጫቦ

ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳና አቶ ጃዋር መሐመድ ይናገራሉ

ነገሮች አዲስ የሚሆኑት ፣ በእኛ ትናንትን መርሳት |ይገረም አለሙ 

$
0
0

12801147_966036103443554_4958790932868175941_n

ሰሞኑን  በደቡብ ኢትዮጵያ በሚኖሩ ዜጎች ላይ የተፈጸመን የባሪያ ፍንገላን ዘመን የሚያስታውስ  ኢሰብአዊ ድርጊት  የሚያሳይ ፎቶ  በማህበራዊ ድረ-ገጽ ተሰራጭቶ አጀኢብ ጉድ ብለናል፡፡ ነገሩ ትናንትን እየረሳን ዛሬ ለሚያጋጥመን ነገር አዲስ እየሆንን ጉድ ጉድ ለምንለው  ለእኛ ነው እንጂ አዲስነቱ ለወያኔ ከበርሀ ጀምሮ አብሮት የኖረ ተግባሩ ነው፡፡

አይደለም ሥልጣኑን ሊነጥቁት በተቃውሞ የተሰለፉ፣  እኩይ ድርጊቱን እያጋለጡ ማንነቱን ጸሀይ የሚያሞቁ ፣ ሀሳብ እቅዱን እየተቃወሙ ጉዞውን የሚያደናቅፉ ቀርቶ የህውሀት አባል ሆነው ስህተት የጠቆሙ የዓላማቸውን መስመር መሳት የገለጹ የመሪዎቹን እኩይ ተግባር የነቀፉ ወዘተ ምን እንደተፈጸመባቸው የአይን ምስክር የሆኑ ሰዎች ሲናገሩ ሰምተናል ጽፈው አንብበናል፡፡ ባዶ ምንትስ ይባሉ በነበሩት እስር ቤቶች በውልደታቸው ትግሬ በድርጅታቸው ህውኃት የነበሩ ዜጎች ሳይቀሩ ምን አይነት ኢሰብአዊ ድርጊት አንደተፈጸመባቸው እነ ገብረ መድህን አርአያ ደጋግመው የነገሩን ነው፡፡ ዛሬም በተለያየ የሥልጣን ስም ተቀምጠው አረመኔያዊውን ድርጊት የሚፈጽሙ የሚያስፈጽሙት እነዛ የበርሀው ሲኦል እስር ቤቶች ሀላፊዎች የነበሩቱ ናቸው፡፡

ለሥልጣናቸው የሚያሰጋ፣ ያሰቡ ያቀዱትን ተፈጻሚ እንዳያደርጉ አንቅፋት የሚሆን፣ ማንም ሆነ ከየትም  ከማጥፋት የማይመለሱት ወያኔዎች (በተለይም አቶ መለስ) ዘር ሀይማኖት ሳይለዩ አስሮ ማሰቃየቱን አፍኖ መሰወሩን ገድሎ መጣሉን ብሎም ርስ በርስ ማገዳደሉን አብይ ተግባራቸው አድርገው የኖሩ ለመሆናቸው  ብዙ እጅግ ብዙ ማረጃዎችን መዘርዘር ይቻላል፡፡

የህውኃት ቀኝ እጅ የነበረው የደህንነቱ ሹም ክንፈየአግልግሎት ግዜው ሲያበቃ እንዴት እንዳስገደሉትና የግድያ ትዕዛዙን በፈጸመው የዋህ ታዛዥ ላይ ያደረጉትን የምናውቅ  በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ የሚፈጽሙት አረመኔያዊ ተግባር ለምን አዲስ አንደሚሆንብንና እንደሚገርመን  ራሱ የሚገርም ነው፡፡ ለህይወታቸው መድህን ለሥልጣናቸው ዘብ ሆነው የኖሩ ሰዎቻቸውን ለማጥፋት የማይመለሱ ሰዎች አንገዛም ባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽሙት ኢሰብአዊ ድርጊት ሁሌም አዲስ የሚሆንብን እኛ ትናንትን በመርሳት በሽታ በመለከፋችን  አለያም ሞኝ የሰማ/ያየ እለት እንደሚባለው እየሆነብን እንጂ ድርጊቱ ለወያኔ አዲሰ  አይደለም፡፡ እንደውም  ትናትን የመርሳት ችግራችን ከእባብ አንቁላል ርግብ አይጠበቅም የሚለውን አባባል  አስረስቶን የተቃውሞአችን እንዴትነትና  የጩኸታችን ምንነት  ከወያኔ የባህሪው ያልሆነ ነገር የምንጠብቅ ያስመስለናል፡፡

መቅረጸ ድምጽም ሆነ ምስል ያልደረሰባቸው የአይን ምስክርም ተገኝቶ ይፋ ያላደረጋቸው ብዙ አጅግ ብዙ ዘግናኝ አረመኔያዊ ድርጊቶች በወያኔ ለመፈጸማቸው በመረጃ ከተረጋገጡት ድርጊቶቹ ተነስቶ መገመት ይቻላል፡፡እነዚህ ሰዎች ለሥልጣን የበቁት የመረጃ ማስተላለፊያው ጥበብ እንዲህ ባለልተስፋፋበትና ባልተራቀቀበት ዘመን ቢሆን ምን ያደርጉ ነበር ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ፡፡የሚሰሩት ብቻ ሳይሆን በር ዘግተው በምስጢር የሚነጋገሩት ድምጽ ከምስል እየሾለከ ለአለም ህዝብ አይንና ጆሮ ሲበቃ የማያስደነግጣቸው፣ የማያሳፍራቸውና የማያስፈራቸው (ለነገሩ ማን ሰው ብለው) ወያኔዎች በድብቅ የሚሰሩት ሁሉ ተደብቆ የሚቀር ቢሆን የአረመኔነታቸው መጠን የክፋታቸው ደረጃ  የአገዛዛቸው ግዞት እስከምን ይደርስ አንደነበር መገመት አይገድም፡፡

ጎምቱ ጋዜጠኞች ውሻ ሰው ነከሰ ዜና አይሆንም ሰው ውሻ ቢነክስ ግን ትልቅ ዜና ነው ይላሉ፡፡ የአባባሉ ምንነት ግልጽ ነው፡፡ ውሻ ሰው መንከሱ የተፈጥሮው፣ የባህሪው፣ የሚጠበቅበት ተግባሩም ስለሆነ  ነው ዜና የማይሆነው፡፡ ሰው ግን ውሻ ቢነክስ  ያልተለመደ ብቻ ሳይሆን የማይጠበቅና የማይገመት አዲስ አስገራሚ ክስተት  በመሆኑ ነው ትልቅ ዜና የሚሆነው፡፡

ወያኔም ማሰሩ፣ መግደሉ፣ ማሰቃየቱ፣ መዋሸቱ ፣ማታለሉ ሰው በሀሰት መወንጀሉ ወዘተ  ለሥልጣን የበቃበትና ሀያ አራት ዓመታትም ለመግዛት የቻለበት የተፈጥሮ ባህሪይው እና ተግባሩ  በመሆኑ በዚህ መልክ የሚፈጽማቸው ድርጊቶች ለጋዜጠኞች ዜና ሊሆኑ ቢችሉ አንኳን ለእኛ ለኢትዮጵያውያን  አዲስ ክስተት የሆኑ ያህል ሊያስገርሙን ሊያስደንቁንም ሆነ ሊያስደደነግጡን  አይገባም ነበር፡፡ ምነው ቢሉ እየረሳናቸው ካልሆነ በቀር አብረውን ያሉ ናቸውና፡፡

ይልቁንስ ከወያኔ አንጻር ለመገናኝ ብዙኃን ትልቅ ዜና ሊሆን ከኢትዮጵያውያን አልፎ የኢትዮጵያን ጉዳይ (ለራሳቸውም ዓላማም ሆነ ለህዝቡ ጥቅም ሲሉ) በቅርብ ለሚከታተሉ አለም አቀፍ ግለሰቦች ቡድኖችና መንግሥትታ አስገራሚ ክስተት ሊሆን የሚችለው፡፡

  • ሀያ አራት አመት የተጓዝንበት መንገድ  ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ እየወሰደን እንዳልሆነ ስለተገነዘብን  መሰረታዊ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ቢባል፤
  • ለዘመናት አብረውን የዘለቁ ሀገራዊ ችግሮችን እየቆፈሩ  አዳዲስ ልዩነቶችን መፍጠር የዛሬ መንገዳችንንም ሆነ  የነገ ግባችንን ከማሰናከሉም በላይ ኢትዮጵያን አንደ ሀገር ለማቆየት አስጋቸሪ የሚያደርጉ በመሆናቸው በእርቅ እልባት ሰጥቶ ሀገራዊ መግባባት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝበናል ቢባል፤
  • የገደለ ያስገደለ፣ የሰረቀ የተባበረ፣ በህዝብ ሀብት የከበረ፣ ከህግ በላይ ያደረ፣ወዘተ ለፍትህ ቀርቦ የህግ የበላይነትን በተግባር ለማረጋገጥ የሚያስችሉ  ርምጃዎች መታየት ቢጀመሩ፣
  • የመገናኛ ብዙሀን ሰራተኞች አፋሽ አጎንባሽ መሆናቸው ቀርቶ እውነትን አነፍናፊ፣ የባለሥልጣናትን ፊት እያዩና ትንፋሽ እያዳመጡ የሚሰሩ ሳይሆን የሙያቸውን ነጻነት አክብረው ለህሊናቸው ታማኝ ሆነው መስራት የሚችሉበትን አሰራር ተግባራዊ  የማድረግ ጅምር ቢታይ፤
  • ክልሎች በህገ መንግሥቱ የሰፈረው ሙሉ ነጻነታቸው ተጠብቆ ከህውኃት የሞግዚት አስተዳደር ተላቀው ራስን በራስ የማስተዳደር መብታቸውን በተግባር የሚያረጋግጥ ጅማሮ ቢታይ ፤
  • አባልም ሆነ አጋር የሚባሉት በህውኃት ተፈጥረው በህውኃት የሚዘወሩት ድርጅቶች የአገልጋይነት ዘመናቸውን ፈጽመዋል ተብሎ  በራሳቸው መቆም የሚያስችላቸው እንቅስቃሴ ቢጀመር፡፡
  • በድርጅት ታጥሮ በታማኝነት  ተወስኖ ሀገር መምራት አንዳማይቻል የሀያ አራት አመት ልምዳችን አስተምሮናል፣ ስለሆነም ከዚህ በኋላ ሀገር መምራት በእውቀትና ሁሉን አሳታፊ በማድረግ  መሆን እንለበት ተገንዝበናል  ተብሎ ይህንኑ ገቢራዊ ማድረግ የሚያስችል ተግባራዊ ርምጃ  ቢታይ፡፡ ሌላም ሌላም ተመሳሳይ ነገር ከወያኔ ሰፈር ቢታይ ቢሰማ ትልቅ አስገራሚና ማራኪ ድንቅ ዜና ይሆናል፡፡ከዚህ ውጪ መልካም አስተዳደር የፍትህ መጓደል እያሉ ማላዘንም ሆነ  ይቅርታ እንጠይቃለን ማለት ሸብረክ ያሉ መስሎ ግዜ መግዣ የወያኔ የባህሪው  ተግባር ነውና ሊደንቀን አይገባም፡፡

ነገር ግን ወያኔ ያልፈጠረበትን በምክርም በመከራም ሊቀበለው ያልቻለውን ይህን ቅዱስ ተግባር በምን ተአምር ፈጽሞት ይህ  እውነት ሆኖ ለመስማት እንበቃለን! አይታሰብም፡፡ ወያኔዎች ይህን ለማድረግ አንደገና መፈጠር ይኖርባቸዋል፡፡ እኛስ ትናንትን እየረሳን በየግዜው የሚገጥሙንን የወያኔን የባህርይ ድርጊቶች  እንደ አዲስ  ከማየት ለመላቀቅ እና ትግሉን በምሬትና በወኔ ለማጥበቅ  እንደገና መፈጠር ይጠይቀን ይሆን?

ትናትን እየረሱ የእለት የእለቱን አዲስ እያደረጉ መጮኹ በትግሉ ላይ ትልቅ አሉታዊ ተጽእኖ ያለው ለመሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ የበደል ሸክሙ የሚከብደን፣ የጥቃቱ ምሬት የሚመረን፣አንባገነናዊ አገዛዙ የሚያንገሸግሸን ከ እስከ አሁን ያለውን ስናስታውስ ነው፡፡ የዛሬው ሲያስለቅሰን ሲያስቆጣን ብቻ ሳይሆን የትናቱም ሲቆጠቆጠን ነው፡፡  የትናንቱን እየረሳን ለዛሬው አንድ ሳምንት እየጮኸን ከዛም ሌላ አዲስ ነገር እስኪመጣ ይህን እየረሳን  እኩል መብሰል ባለመቻላችን (ጥሬ  ብስልና የአረረ) ነው ሀያ አራት አመት ሙሉ ትግል እንጂ ለውጥ ማስመዝገብ ቀርቶ አዳዲስ ጥቃቶችን ማስቀረት፤ ተጨማሪ ጥፋት እንዳይፈጸም ማስቆም ወያኔን ከደደቢት ህልሙ ስንዝር መግታት  ያልቻልነው፡፡  እውቁ የጽሁፍ ሰው አቶ ከበደ ሚካኤል ልጆች ሆነን ባነበብነው አንድ ጽሁፋቸው ፤

ያለፈው ሲረሳኝ መጪውን ሳላውቀው

እኔ መቼ ይሆን የምጠነቀቀው፤  ብለው የነበረው  ከላይ ለተገለጸው  ለእኛ እኛነት  በቂ ገላጭ አይሆንም ትላላችሁ?

 

The post ነገሮች አዲስ የሚሆኑት ፣ በእኛ ትናንትን መርሳት | ይገረም አለሙ  appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live