Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በኦሮሚያ ተቃውሞው ቀጥሏል (VOA)

$
0
0

ሕዳር ሁለት ቀን የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ቀጥሏል። በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች፤ ዞኖችና ወረዳዎች ተቃውሞው ስለመቀጠሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አስተያየት ሲሰጡ ይደመጣል። ዛሬም ሰዎች ይሞታሉ፣ይታሠራሉ እንዲሁም ይደበደባሉ የሚሉ አስተያየቶች ይነገራሉ። የዘገባዎቹን ዝርዝር ጽዮን ግርማ ይዛለች።

ሕዳር ሁለት ቀን የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ቀጥሏል። በተለያዩ  የኦሮሚያ ከተሞች፤ ዞኖችና ወረዳዎች ተቃውሞው ስለመቀጠሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አስተያየት ሲሰጡ ይደመጣል። ዛሬም ሰዎች ይሞታሉ፣ይታሠራሉ  እንዲሁም ይደበደባሉ የሚሉ አስተያየቶች ይነገራሉ።

የዞንና የወረዳ ባለሥልጣኖች “የሚደርሳችሁ መረጃ የተሳሳት ነው” ይላሉ፡፡ የዛሬውን የቦረና ዞንና የሰሞኑን  የሻኪሶ ወረዳ ከራሞት በተመለከተ ጽዮን ግርማ ነዋሪዎችን አነጋግራ የሚመለከተውን ዘገባ ሠርታለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

 

4FF3E8DC-8B4B-4195-A5DC-B9836539BEC7_w640_r1_s

 

The post በኦሮሚያ ተቃውሞው ቀጥሏል (VOA) appeared first on Zehabesha Amharic.


23 ዓመቷን ኩዌታዊ ገድላ ራሷን አቆሰለች የተባለችው ኢትዮጵያዊት ማምሻውን አረፈች

$
0
0

Kuwait

ነቢዩ ሲራክ 

በኩዌት “ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ የ23 ዓመቷን ፋጢማ የተባለችን ኩዌታዊ የአሰሪዋን ልጅ ገድላና ራሷን አቁስላለች ” በሚል በፖሊስ ጥበቃ ላለፉት ሳምንታት ሳባ በሚባል ሆስፒታል ህክምና ላይ የነበረችው ኢትዮጵያዊት ዛሬ ሐሙስ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካበቢ ማረፏን አረጋግጫለሁ ። ሆስፒታል ከገባች ጀምሮ በኩዌት ኤንባሲ ስትጠየቅ የሰነበተችው እህት ከቀናት በፊት በተሻለ ጤንነት ላይ እንደነበረች ተጠቁሟል ። በአካል ያዩዋት ወገኖች በተለይ በአንገቷ ላይ ተተክሎ የነበረው ቱቦ ተነስቶላት እንደነበርና ለመናገር ሙከራ ታደርግ እንደ ነበር አጫውተውኛል ።

በተመሳሳይ ሁኔታ ከሳምንት በፊት የተለቀቁት መረጃዎች ይህችው እህት ከጉዳቷ እንዳገገመች ተነግሮ ነበር ። ይሁን እንጅ የዛሬ ምሽት ” አሟሟቷ ከልብ ህመም ጋር በተገናኘ ነው ” የሚል መልስ በሆስፒታሉ እየተሰጠ እንደሆነ ጉዳዩን የሚከታተሉት ወገኖች መረጃውን አጋርተውኛል ! አንዳንድ መረጃውን የሰሙ ወገኖች በበኩላቸው ” በግድያው ወቅት ያን ያህል ደሟን ፈሷ ልቧ ሰከክ ሳይል እንዴት በልብ ህመም ህይዎቷ አለፈ ይባል ? ” በማለት ያጠይቃሉ!

ነፍስ ይማር !

ነቢዩ ሲራክ
የካቲት 25 ቀን 2008 ዓም

The post 23 ዓመቷን ኩዌታዊ ገድላ ራሷን አቆሰለች የተባለችው ኢትዮጵያዊት ማምሻውን አረፈች appeared first on Zehabesha Amharic.

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የላውሪዮስ ሽልማት የ2016 ምርጥ አትሌት እጩ ሆና ተመረጠች

$
0
0

genzebe 1

በሴቶች የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ በዕጩነት የተካተቱት ኢትዮጵያዊቷ ገንዘቤ ዲባባ፣ ጃማይካዊቷ የአጭር እርቀት አትሌት ፍሬስር ፕራይስ፣ አሜሪካዊቷ የቴኒስ ተጨዋች ሴሪና ዋሊያምስ፣ አሜሪካዊቷ እግር ኳስ ተጨዋች ካርሊ ሊሎይድ፣ኦስትሪያዊቷ አና ፌኒንገር እና አሜሪካዊቷ ዋናተኛ ኬቲ ናቸው፡፡

ገንዘቤ በቤጅንግ የዓለም ሻምፒዮና ማሸነፏ 2 ክብረወሰኖችን ማሻሻሏ ከሌሎቹ በተሻለ ትመረጣለች የሚል ግምት ተሰጥቷታል፡፡
ገንዘቤ ዲባባ ዓለም አቀፍ እውቅና ባለው የላውሪዮስ ሽልማት በ2015 ዓመት ምርጥ ስፖርተኛ ተብላ መሸለሟ የሚታወስ ሲሆን በወንዶች ጃማይካዊው የአጭር እርቀት አትሌት ዩዜን ቦልት፣ ሰርቢያዊው የቴኒስ ተጨዋች ኖቫክ ጆኮቪች፣ እንግሊዛዊው የመኪና ተወዳዳሪ ሊዌስ ሀማልተን ፣አርጀንቲናዊው እግር ኳስ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ፣ አሜሪካዊው ቅርጫት ኳስ ተጨዋች ስቴቨን ኬሪ በዕጩነት ቀርበዋል፡፡


የላውሪዮስ ሽልማት አሸናፊ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሚያዚያ 18ቀን 2016 በበርሊን ይፋ ይሆናል::

World champions Usain Bolt, Shelly-Ann Fraser-Pryce and Genzebe Dibaba are among the nominations for the 2016 Laureus world sportsman and sportswoman of the year awards.

Bolt, a three-time winner of the Laureus sportsman of the year award, successfully defended his world titles in the 100m, 200m and 4x100m at the IAAF World Championships Beijing 2015.

Fraser-Pryce did likewise in the 100m and 4x100m, while Dibaba – the 2015 Laureus world sportswoman of the year and IAAF world female athlete of the year – won the world 1500m title in Beijing, having broken the world record for the distance earlier in the year.

Outside of athletics, the other male nominees are (in alphabetical order): US basketball player Stephen Curry, Serbian tennis player Novak Djokovic, British racing driver Lewis Hamilton, Argentinian footballer Lionel Messi and US golfer Jordan Spieth.

Dibaba and Fraser-Pryce are joined on the list of female nominees by Austrian skier Anna Fenninger, US swimmer Katie Ledecky, US soccer player Carli Lloyd and US tennis player Serena Williams.

World champions Jessica Ennis-Hill and David Rudisha have been nominated in the ‘comeback of the year’ category.

Ennis-Hill won the world heptathlon title in Beijing, one year after giving birth to her first child and having battled an achilles injury. Rudisha bounced back from two years of injury problems to win the world 800m title in Beijing.

Cuba’s visually impaired sprinter Omara Durand has been nominated in the disability category. At last year’s IPC World Championships in Doha, Durand won the 100m, 200m and 400m, setting world records of 11.48, 23.03 and 53.05 respectively.

The winners will be announced at the Laureus World Sports Awards ceremony in Berlin on 18 April.

The post አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የላውሪዮስ ሽልማት የ2016 ምርጥ አትሌት እጩ ሆና ተመረጠች appeared first on Zehabesha Amharic.

በወልቃይት ጉዳይ አረና እንደ ህወሓት 

$
0
0

arena

ከዳዊት ሰለሞን
አረና እንደ ኢህአዴግ ያላልኩት እንደ ህወሓት ሁሉ በትግራይ የሚገኝና በወልቃይት ጉዳይ ከህወሓት ተመሳሳይ አቋም በመያዙ ነው ።
አረና ህወሓትን በአምባገነንነት፣ ለሌሎች ሀሳብ ዕድል ባለመስጠት፣ላወጣው ህገ መንግስት የማይገዛ ፣ አባላቱን ከላይ ወደ ታች በሚወርድ ትዕዛዝ የሚመራ ፣በብዙሃንነት ሽፋን ጥቂቶችን የሚያፍንና ተቃዋሚዎቹን ደርግ፣የነፍጠኛው ስርዓት ተላላኪ በማለት የሚወነጅል በማለት ይገልፀዋል ።መቼም ህወሓት ይህ ስያሜው የሚያንሰው እንጂ የሚበዛበት አለመሆኑን የምንስማማበት በመሆኑ ያለመከራከሪያ እንደወረደ እንቀበለው ።
አረናዎችን በወልቃይት ጉዳይ ሚዛን ላይ ሳስቀምጣቸው በህወሓት ጫማ ውስጥ ያገኘኋቸው መሰለኝና የማከብራቸውን ሰላማዊ ታጋዮች ለመተቸት ተነሳሁ።


ወልቃይቴ በግድ ትግራዋይነት ተጭኖበታል ያሉ ወገኖች ኮሚቴ አቋቁመው ህዝብ እየሰበሰቡ ጥያቄያቸውን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ።ህወሓት ደግሞ ለአረና የከለከለችውን ሰልፍ ለወልቃይት ትግራይ ነው ቡድን ፈቅዳ ኮሚቴዎቹን ህገወጦች ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች ነው ።
አረናዎች እንወክለዋለን የሚሉት የትግራይን ህዝብ በመሆኑ ለትግራይ ጥቅም መቆማቸው የሚጠበቅ ሊሆን ይችላል ።ነገር ግን የትግራይ ህዝብ ወይም የክልሉ መብት ሌሎች ላይ በሚጫን አፈና እንዲከበር ማድረግ በየትኛውም መመዘኛ ከአንድ ዴሞክራሲያዊ ወይም ፖለቲካሊ ኮሬክት መሆን ከሚፈልግ ፓርቲ የሚጠበቅ አይደለም ።


በህገመንግስቱ የማንነት ጥያቄ ማቅረብ መብት ተደርጎ ተጠቅሷል ።ትግራይ አይደለንም ያሉ ሰዎችም ያነሱት ጥያቄ በህገመንግስቱ መሰረት ተገቢ በመሆኑ ህገመንግስታዊ ምላሽ ማግኘት ይኖርበታል ።ከዚህ በፊት እኛ ስልጤ እንጂ ጉራጌ አይደለንም ላሉ ወገኖች ጥያቄ ቀና ምላሽ ተሰጥቶ በግድ ተጫነብን ተጫነብን ያሉት ጉራጌነት ከላያቸው እንዲወልቅ መደረጉ አይዘነጋም ።


ህወሓትን በኢህገመንግስታዊነት የሚከስ ድርጅት በደፈናው እየተነሳ የሚገኝን የህዝብ ጥያቄ በህወሓት መንገድ መመለስ ከሚከሱት ድርጅት ጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅ መሆን ነው ።


ጥያቄውን ያነሱ ሰዎችንም ከቀድሞው ስርዓት ጋር ማቆራኘት ሌላኛው የህወሓት መንትያ መሆንን ማሳያ ነው ።


በቅርቡ የአረናው ሊቀመንበር ወልቃይትን በተመለከተ በሶሻል ሚዲያ ለቀዋል ።ግለሰቡ ፅሁፉን በግላቸው የፃፉት ቢሆንም የፓርቲያቸው አቋም በማድረግ ለብደውታል።የተወሰኑ የፓርቲው ሰዎችም ፅሁፉን ሼር በማድረግ እኛ እንዲህ ነን ብለዋል ።


ግን እንዴት ነው ከላይ ወደ ታች በወረደ አስተሳሰብ ህወሓት አባላቱን ይመራል በማለት እየከሰሱት በዚያው ጅረት የሚፈሱት?
እንበልና የተወሰኑ አባላት የሊቀመንበሩን ድምዳሜ ባይጋሩትስ? አረናዎች ከመድረክ ጋር የወልቃይት ጉዳይ በህገመንግሥቱ መሰረት መልስ ማግኘት አለበት በማለት መግለጫ ከሰጡ በኋላ ጥያቄውን በህወሓት መንገድ የሚያዩት እንዴት ነው ?


በሉ ከህወሓት መለየታችሁን ለሌሎችም መብት ባለመደራደር ጭምር አሳዩን ።

The post በወልቃይት ጉዳይ አረና እንደ ህወሓት  appeared first on Zehabesha Amharic.

በነቀምት መምህራን ኮሌጅ የአጋዚ ሠራዊት አንድ ወጣት ገደለ |በነቀምት ዛሬ ታክሲ የለም

$
0
0

nekemte

(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች እና ወረዳዎች የተነሳው የሕዝብ ማዕበል የሚበርድ አልሆነም:: ኦሮሚያን በ8 ዞኖች ከፋፍሎ የሚመራው ወታደራዊው አስተዳደር የሕዝቡን ቁጣ ለማብረድ ምላሹ ጥይት ከሆነ ሰነባብቷል::

ዛሬ በነቀምት መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ የአጋዚ ሠራዊት የተማሪዎችን ክፍል ሰባብሮ በመግባት ከ16 ተማሪዎች በላይን ሲያቆስል የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱም እየተዘገበ ነው::

ለዘ-ሐበሻ በደረሰው መረጃ በአጋዚ ጥይት ዛሬ ሞተ የተባለው ወጣት መሰረት ምስጋናው ይሰኛል:: የዚህ ተማሪ ፎቶግራፍም እንዲሁ በተለያዩ የማህበራዊ ሚድያዎች እየተሰራጨ ይገኛል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በነቀምት ዛሬ ታክሲ አለመኖሩ ታወቀ:: በተለይ ከሰዓት በኋላ በነቀምት ከተማዋ በታክሲዎች የሥራ ማቆም አድማ ጭር ብላ መዋሏ ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

The post በነቀምት መምህራን ኮሌጅ የአጋዚ ሠራዊት አንድ ወጣት ገደለ | በነቀምት ዛሬ ታክሲ የለም appeared first on Zehabesha Amharic.

በአዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስ በቋሚ ሲኖዶሱ አማካኝነት ድንገተኛ ስብሰባ ተቀመጠ |በፓትሪያርኩና በማህበረ ቅዱሳን ዙሪያ ይመክራል

$
0
0

Holy sinod addis ababa

 የሐራ ተዋሕዶ ዘገባ እንደወረደ 

  • ድንገተኛ ልዩ ስብሰባው የተጠራው በቋሚ ሲኖዶሱ ነው
  • በፓትርያርኩና በማኅበረ ቅዱሳን ውዝግብ ላይ ይወያያል
  • በዐቢይ ጾም የጸሎተ ምሕላ ጉዳይም ውሳኔ ያሳልፋል

 

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ዛሬ የካቲት ፳፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ጀምሮ ድንገተኛ ልዩ ስብሰባ መቀመጡ ተገለጸ፡፡

ድንገተኛ ልዩ ስብሰባውን የሚያካሒዱት፣ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሞተ ዕረፍትና ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በዓለ ሢመት በመዲናይቱ አዲስ አበባ የተሰበሰቡ ከ25 ያላነሱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ናቸው፡፡

ስብሰባው እንደሚካሔድ የታወቀው፣ ፓትርያርኩ በመጪው ሰኞ የሚጀመረውን ዐቢይ ጾም በማስመልከት ዛሬ ረፋድ ላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ በተገኙበት በቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው እንዳበቁ ሲኾን አስቀድሞ መረጃው እንዳልነበራቸው ተገልጧል፡፡

ፓትርያርኩ መግለጫውን በንባብ ካሰሙ በኋላ ከአዳራሹ ለመውጣት ተነሥተው እንደቆሙ፤ በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጥያቄ ተመልሰው እንዲመቀጡ መደረጉን የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ፓትርያርኩ ተመልሰው እንደተቀመጡ፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቡነ ማቴዎስ፣ ማእከላዊ አሠራርን ባለመጠበቅ እየተከሠቱ ስለሚገኙና እልባት ለመስጠት ስላዳገቱ ችግሮች በስፋት አስረድተዋል፡፡ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በበላይነት የሚመራው ጠቅላይ ጽ/ቤታቸው ሳያውቀው ከቅዱስነታቸው ልዩ ጽ/ቤት ለአስፈጻሚ አካላትና ተቋማት የሚወጡ ደብዳቤዎችን ብፁዕነታቸው በማሳያነት አቅርበዋል፡፡ ይህም በሥራ ግንኙነቶች ላይ ቀውስ እንደፈጠረና አለመግባባቱ በውጭ አካላት ዘንድ ሳይቀር ትዝብት ላይ እየጣለን በመኾኑ ቅዱስ ሲኖዶሱ አንድ መፍትሔ እንዲሰጠው ብፁዕነታቸው ጠይቀዋል፡፡

ማዕከላዊነቱን ስላልጠበቀ የአሠራር ችግር በማብራራት ተጨማሪ አጽንዖት የሰጡት የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ በኦሮሚያ ክልልና በአንዳንድ የአገራችን ክፍሎች ስላጋጠመው የሰላም ቀውስና ስለ ተቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ሲጠይቁ መቆየታቸውን ጠቅሰው፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዚኹ መልካም አጋጣሚ በእነዚኽና ሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች  ተወያይቶ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ጠይቀዋል፡፡

የብፁዕ ዋና ጸሐፊውንና የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን መግለጫ ያዳመጠው ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ጉዳዩ በአጀንዳ ተቀርጾ እንዲቀርብለት፤ ከኹለቱ ብፁዓን አባቶች ጋር ብፁዕ አቡነ ሕዝኤልን፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስንና ብፁዕ አቡነ ያሬድን በመጨመር በአርቃቂነት ከሠየመ በኋላ ተዘጋጅቶ በቀረበለት መሠረት ከቀትር በኋላ ስብሰባውን መጀመሩ ታውቋል፡፡

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ድንገተኛ ልዩ ስብሰባው እንደቀጠለ ሲኾን በአርእስተ ጉዳይ ደረጃም፡-

  • ስለ ሰላም እና ስለ ተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት፤
  • በድርቁ ምክንያት ለተጎዱት ወገኖች እየተደረገ ስላለው ርዳታና ጸሎተ ምሕላ፤
  • ማዕከላዊነትን ስላልጠበቁ አሠራሮችና ስላስከተሏቸው ችግሮች፤
  • ከልዩ ጽ/ቤት ስለሚወጡ ደብዳቤዎችና መጻጻፎች በተመለከተ፤
  • ሐዋርያዊ ጉዞን(የፓትርያርኩን የውጭ ጉዞዎች) በተመለከተ፤ 

የሚሉ መነጋገርያዎች እንደሚገኙበት ተመልክቷል፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት፣ በዓመት ኹለት ጊዜ ከሚደረገው የምልዓተ ጉባኤው መደበኛ ስብሰባዎች በተለየ፣ አስቸኳይና ድንገተኛ ጉዳይ ሲያጋጥም ቋሚ ሲኖዶሱ በብፁዕ ዋና ጸሐፊው አማካይነት ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ከጠቅላላ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከግማሽ በላይ ጉባኤ እንዲደረግ በጠየቁ ጊዜ ጥሪ ሊደረግና ስብሰባው ሊካሔድ ይችላል፡፡

በስብሰባው፣ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ለሚመለከቱ አጀንዳዎች ከአባላት ከሦስቱ እጅ ኹለቱ እጅ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይኾናል፤ በአስተዳደር ጉዳዮች ውሳኔዎች ሲተላለፉም ከግማሽ በላይ በኾነ ድምፅ የተደገፈው ሐሳብ ያልፋል፡፡

The post በአዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስ በቋሚ ሲኖዶሱ አማካኝነት ድንገተኛ ስብሰባ ተቀመጠ | በፓትሪያርኩና በማህበረ ቅዱሳን ዙሪያ ይመክራል appeared first on Zehabesha Amharic.

በአዲስ አበባ በኒ መስጅድ ከፍተኛ ፍተሻና ወከባ ሲደረግ ዋለ

$
0
0

mesgid

(የቢቢኤን ራድዮ ዘገባ) የሙስሊሞችን የእምነት ነፃነት መብት በሃይል እና በአፈ ሙዝ ረግጦ እየቀማ ያለው ኢሓዴግ መራሹ መንግስት በዛሬው እለት በአዲስ አበባው በኒ መስጅድ ተቃውሞ ሊደረግ ይችላል በሚል ስጋት እና ጥርጣሬ በመስጅዱ መግቢያና አካባቢ በርካታ ፓሊሶች እና ደህንነቶችን አሰማርቶ ሙስሊሞችን በፍተሻ እያዋከበ እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል ።
እንደምንጮቻችን ተጨማሪ ገለፃ መሰረትም ባለፉት ግዜያት በአንዋር እና ፍልውሃ መስጅዶች በተደረገው ከፍተኛ ተቃውሞ ድንጋጤ ያደረበት መንግስት ይሄው ተቃውሞ ዛሬ በበኒ መስጅድ ሊደገም ይችላል በማለት እና በመስጋት ፓሊሶች እና ደህንነቶችን አሰማርቶ በሙስሊሙ ላይ ለየት ያለ ፍተሻና ወከባ መፈፀሙ ታውቆ በተለይም መስጅዱ ሞልቶባቸው ውጭ ላይ መስገጃ አንጥፈው ለመስገድ የሞከሩ ሙስሊሞችን ውጭ ላይ አንጥፋችሁ መስገድ አይችሉም በማለት ፓሊሶችና ካድሬዎች ወከባ ሲፈፅሙ እንደነበር ተዘግቧል

ይህ በእንዲህ እንዳለም በዛሬው ጅሙዓ የአንዋር መስጅዱ ኢማም ኮማንደር ጡሃ ሃገራችን ሰላም ናት መንግሥታችንም ጥሩ ነው በአራቱም አቅጣጫ ምንም ችግር የለም ፣ ሀገራችን በኢኮኖሚውም አድጋለች የህዝቦች መብት ተከብሯል በማለት በግልፅ የፓለቲካ ቅስቀሳ ተልዕኮውን መፈፀሙ የታወቀ ሲሆን በተለይም የመብት ጠያቂዎችን ” ነውጠኞች ” እና “የሃገር ሰላም የማይፈልጉ “በማለት እና በመፈረጅ መናገሩን ምንጮች ለቢቢኤን ገልፀዋል
ከዚህም በተጨማሪ ኮማንደር ጡሃ በዛሬው ንግግሩ የመጅሊስ አካላት በከፍተኛ የሙስና ተግባር ውስጥ ተዘፍቀዋል የህዝቡን ገንዘብ እየዘረፉት ነው በማለት የተናገረ ሲሆን በተመሳሳይም የአንዋር መስጅድ አስተዳደር የሆነው አቶ ሸምሱ የመስጅዱን ገንዘብ ዘርፎ እየጨረሰው መሆኑን በይፋ አጋልጧል ።

The post በአዲስ አበባ በኒ መስጅድ ከፍተኛ ፍተሻና ወከባ ሲደረግ ዋለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የፈረንሳይ ፖሊሶች የኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች ጎጆዎችን በአሳት አጋዩ |ታንዛኒያ ኢትዮጵያዊያን “ማፊያዊችን”በቁጥጥር ስር አደረግሁ አለች 

$
0
0

 

ከታምሩ ገዳ

በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ምድረ አውሮፓ በተለይ ደግሞ ወደ እንግሊዝ የመሰደድ ህልማቸውን ለማሳካት በጉዞ ላይ ያሉ እና በፈረንሳይ መዲና አቅራቢያ ጢሻዎች ውስጥ እጅግ ዘግናኝ በሆነ የስነልቦና እና አካላዊ ችግሮች ውስጥ የወደቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ አትዮጵያዊኖች ጊዜያዊ መጠለያ ጎጆዎቻቸው በፈረንሳይ የአድማ በታኝ እና አፈራሽ ግበረሃይሎች ባለፈው ሰኞ አለት በአሳት አንዲጋዪ እና በቡልደዘሮች እንዲጠራረጉ ተደረገዋል። በሁኔታውም የተቆጡ ሰደተኞቹ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ተጋጭተዋል።የታሰሩም አሉ ተብሏል።

France 3


እንደ ሚድል ኢስት አይ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ሰደተኞቹን መጠለያዎች ለማፈራረስ ወደ ሰፍራው የተንቀሳቀሱ ሁለት ቡልደዘር መኪኖች እና ከሃያ በላይ አፈራሽ ገብረ ሃይሎች ተሰፋ ከቆረጡ ሰደተኞችጋር ግብግብ ውስጥ የገቡ ሲሆን ፖሊሶችም አስለቃሽ ጢስ በመጠቀም ሰድተኞቹን ከሰፍራው በማባረር ጎጆዎቻቸውን በእሳት አጋይተዋቸውል ሁኔታውንም የተቃወሙ አንድ ሰደተኛ እና “ድንበር ይለሽ” የተባለ አንድ የግበረ ሰናይ ሰራተኛ በ ፖሊስ ቁጥጥር ውለዋል። በአሁኑ ወቀት ከኢትዮጵያ ፣ ከ ኢራቅ ፣ ከ ሱዳን ፣ከኤርትራ ፣ ከሶሪያ ከ አፍጋኒስታን አና ከመሳሰሉት አገሮች የሚደርባቸውን የሰብ አዊ መብት ጥሰት ሸሸትው በ ፈረንሳዩ “ጃንግል” (ቁጥቋጦ) የተጠለሉት 4000 የሚጠጉ ሰደተኞች እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ የሚኖሩ ሲሆን ሰሞኑን ከድንኳናቸው /ጎጆዎች ውስጥ ገሚሶቹ እንዳይፈርሱ ለፍርድ ቤት ሰሞኑን የቀረበው ተማጽኖ ውደቅ መሆኑን ተከትሎ ነበር የሰኞው እለቱ የማፍረስ እና የማቃጠል እርምጃ የተወሰደው። እንዳንድ ሰደተኞች ፖሊስ ጎጇቸውን እንዳያጋየው ለመከላከል ሲሉ ከጣሪያው ላይ በመወጣት ለመከላከል ጥረት አድርገው ነበር ። ብርቱው የአውሮፓ ክረምት ሲመጣ የሰደተኞቹ የመከራ ወቅት ይበረታል ተብሎ ተሰግቷል።

france


ሊ ሞንድ የተባለው የፈረንሳዩ ጋዜጣ ሰሞነኛው የማፍርስ ዘመቻው መሰረታዊ ተቋማት የሆኑት ት/ቤቶች ፣ መሰጊድ እና ቤተክርስቲያናት እንደማይፈርሱ ፍ/ቤት መወሰኑን ዘግቧል። ይሁን እና የፈረንሳይ ሕዝብ በተለይ ደግሞ ግራ ዘመም እክራሪዎች ሰደተኞቹ ተጠራርገው መሔድ አለባቸው የሚል አቋም እያሰሙ በመሆናቸው ውጥርቱ ከመቼውም ጊዜ በከፋ እየከረረ መጥቷል ተብሏል። 


በተያያዘ የሰደተኞች ነክ ዜና በተለያዩ ጊዜያት በርካ ታኢትዮጵያዊያኖችን በታንዛኒያ በኩል ወደ ደ/አፍሪካ እና ወደ አውሮፓ እናሻግራችሁለን በማለት በማማለል ፣ ለእሰራት ለእካል ጉዳት እና ሕይወታቸውን ኣንዲያጡ እሰከ ማድረግ የደረሱ በረካታ ማፊያዎችን (ኢትዮጵያዊያን፣ሶማሊያዊያን፣ ታንዛኒያዊያን እና ደ/አፈሪካዊያን )የሕገወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎችን ሰሞኑን ታንዛኒያ ውስጥ በቁጥጥር ሰር መዋላቸውን እና “ማፊያ” ሰነሰለቱ መበጣጠሱን ተቀዳሚ የኢሚግሬሽን ሃላፊ የሆኑት ጆሲፍ ሙሉንቡ ሰሞኑን ለዜና ሰዎች የገለጹ ሲሆን ይህ ከወራት በፊት ከ 23 በላይ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኖች መታሰራቸውን ተከተሎ የተ ካሔደው ህገወጥ የሰዎች አሸጋጋሪዎችን የማደኑ ዘመቻ ተጠናክሮ ኣንደሚቀጥል እና ሕዝቡም ከፖሊስ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅረበዋል። 

France2


የምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ፣ታንዛኒያ ፣ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአገራቸው ሰርተው ለመኖር ተስፋ የቆረጡ በርካት ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች መሸጋጋሪያነት የሚጠቀሙባት ስትሆን ቀደም በሉት ጊዜያት (አኤአ በሰኔ 27/2012) ከ45 በላይ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በእቃ መጫኛ (ኮንቴይነር) ውስጥ ተጭነው ሲጓጓዙ ምግብ፣ወሃ እና አየር በማጣት እጀግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ መሞታቸው የበረካታ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ልብን ክፉኛ የሰበረ እና አለማቀፋዊ የ ዜና መወያያ ርእስ እንደነበር አይዘነጋም።

The post የፈረንሳይ ፖሊሶች የኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች ጎጆዎችን በአሳት አጋዩ | ታንዛኒያ ኢትዮጵያዊያን “ማፊያዊችን”በቁጥጥር ስር አደረግሁ አለች  appeared first on Zehabesha Amharic.


እውነት ህወሓት በሻዕብያ ይጨክናልን…?

$
0
0

12804896_996830047075318_509225686992572769_n

Amdom Gebreslasie

ዛሬ በፌስቡክ ገፆች ላይ የኢትዮጵያ የኣየር ሃይል በኤርትራ ሁለት ቦታዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰደ እየተባለ ነው።

ኣንዳንድ ሰዎች ደግሞ የኔ ስም እየጠቀሱ “የማያዳግም እርምጃ ውሃ በላው ያልከው ይኸው በተቃራኒው ሆነ” ሲሉ እየገለፁ ነው።

እኔ ግን ኣንድ ጥርጣራ ኣለኝ። እውን ህወሓት/ኢህኣዴግ በሻዕብያ ጨክኖ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ወኔው ኣለው ወይ የሚል ነው?

የማያዳግም እርምጃ ሲባል ደግሞ ሁለት ጀቶች በሁለት ቦታዎች ቦምብ ጥለው መመለስ ኣይደለም። ኣሁንም ህወሓት በሻዕብያ የማያዳግም እርምጃ በሚባል ደረጃ ጥቃት ይፈፅማል የሚል እምነት የለኝም።

በኣሁኑ ሰዓት ወደ ከፍተኛ ጦርነት መግባት ልክ እንደ ሻዕብያ ለህወሓት/ኢህኣዴግ ህልውናም ኣደገኛ ነው።

በኢትዮጵያ 15 ሚልዮን ህዝብ ተርቦ ፣ የኦሮሞ ህዝባዊ ተቃውሞ፣ በየክልሉ ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ፣ የመልካም ኣስተዳደር እጦት፣ በሰለማዊ መንገድ ለማንቀሳቀሱተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወሰድ ዓፈናና እስር እያለ ወደ ታላቅ ጦርነት መግባት ታላቅ ኪሳራ የሚያስከፍልና ጅልነትም ጭምር ነው።

እና ማ የኢህኣዴግ መንግስት በወዳጁ ሻዕብያ “የማያዳግም እርምጃ” በሚባል ደረጃ የሚወሰድ ጥቃት ይኖራል ብየ ኣላስብም።
ደግሞ ዕጣፈንታቸው ተመሳሳይ ይመስለኛል።

ሻዕብያ እንኳን የማያዳግም እርምጃ ጠንከር ያሉ ጥቃቶች ቢወሰድበት ደስ ይለኛል።

ጥቃቱ በኣስር ሺ የሚቆጠሩ በኤርትራ ይኖሩ የነበሩና ከድንበር ኣከባቢዎች ታግተው የተወሰዱ ኢትዮጵያ በባርነት የሚያሰራቸው ዜጎቻችን ነፃ እስኪወጡ ጥቃቱ ቢቀጥል ግሩም ነበር። ግን የሚሆን ኣይመስለኝም።

ኣባሯው ጨሰ …… የምትሉ ሰዎች ተረጋጉ እንጂ…! መከላከልያችን እኮ በጀግንነቱ የሚታማ ኣይደለም።

ችግሩ ቁርጠኛ ፖለቲካዊ ኣመራር ሊሰጥ የሚችል ጠንካራ የሃገር ፍቅር ያለው መሪና መንግስት ነው ያጣነው።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

it is so.

The post እውነት ህወሓት በሻዕብያ ይጨክናልን…? appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: አስፕሪን ‹‹ተአምረኛው›› ክኒን

$
0
0

 

AM4CCD Aspirin tablet close up

አብዛኞቻችን አስፕሪን ከራስ ምታት ክኒንነት ያለፈ ተግባር ያለው አይመስለንም፡፡ ተከታዩ ፅሑፍ እንደሚያስረዳው ግን አስፕሪን ከራስ ምታት እስከ ስትሮክ እና ልብ ህመም ህክምና ድረስ የሚዘልቅ ከፍተኛ አገልግሎት አለው፡፡ ይህ ‹‹ተአምራዊ›› ክኒን እየተባለ የሚጠራውን መድሃኒት ሰፊ አገልግሎቶች፣ በጨጓራ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ከሚመከሩት የጥንቃቄ መልዕክቶቹ ጋር የተለያዩ የመረጃ ምንጮች እና ባለሞያዎችን ዋቢ አድርገን እነሆ ብለናል፡፡

የ51 ዓመቱ አቶ ሰለሞን ግርማ (ስም የተቀየረ)፣ ራሱን ሙሉ ጤነኛ አድርጎ የሚወስድና ዘወትር ስራውን በትጋት የሚሰራ፣ ከጠዋት እስከ ምሽትም ከቢሮው የማይታጣ ጠንካራ ሰው ነው፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት በቢሮው የሆነው ግን ይህን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነበር፡፡ ባላሰበው ሁኔታ እዚያው ቢሮው ውስጥ ራሱን ስቶ ወደቀ፡፡ ባልደረቦቹ ተረባርበው ወደ ሆስፒታል በፍጥነት ባያደርሱት ዕድሜ ልኩን በጉት ይኖር እንደነበር አቶ ሰለሞን ያስታውሳል፡፡

አቶ ሰለሞን የገጠመው ችግር ስትሮክ ነበር፡፡ በጭንቅላት ውስጥ የደም መርጋት ወይም የደም አቅርቦት ወደ ጭንቅላት መድረስ ሲያቅተው የሚፈጠረው ይህ ችግር ብዙውን ጊዜ በግልፅ የሚታይ ምልክት ስለማይኖረው ብዙዎች ይዘናጋሉ፡፡ ታዲያ አቶ ሰለሞን በህክምና ሰዎች ከተሰጡት መድሃኒቶች አንዱ አስፕሪን ነበር፡፡ አስፕሪን ለረጅም ጊዜ እንዲወሰድ መታዘዙ ግራ ያጋባው አቶ ሰለሞን፣ የራስ ምታትና ትኩሳት እንደሌለው አንስቶ ማብራሪያ ሲጠይቅ ነበር የአስፕሪን ዘርፈ ብዙ የመድሃኒትነት ጥቅሞች የተብራሩለት፡፡ አስፕሪን እንደ አቶ አሰለሞን ላሉ ለሚሊዮኖች መድን የሆነ ዘመናትን አብሮን የኖረ መድሃኒት ነው፡፡ ጥቅሞቹ በየጊዜው እየጎሉና እየጨመሩ መምጣታቸውን ያዩ ባለሙያዎች፣ አስፕሪንን ለብዙ ችግሮች ማዘዛቸው ግን የጎንዮሽ ጉዳትን ማምጣቱ አልቀረም፡፡ ለዚህም ይመስላል የመድሃኒቱን ተአምራዊነት የሚዘረዝሩ ጥናቶች የማስጠንቀቂያ መልዕክቶችንም አብረው የሚያነሱት፡፡

የአስፕሪን መነሻ

የሰው ልጆች፣ የአስፕሪን ዋነኛ ውሁድ የሆነውን ሳሊሲሌት የተሰኘ ቅመም፣ ከተለያዩ ለባህላዊ ህክምና ከሚውሉ ዛፎች ቅርፊት ላይ በመቀመም፣ ለህመም ማስታገሻነት ሲያውሉት ከ4 ሺ በላይ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ የዘመናዊ ህክምና አባት የሚባለው ሂፓክራተስ ለትኩሳት እና የህመም ስሜት ለመቀነስ፣ ሳሊሲሌት የያዘ የዛፍ ቅርፊትን እንዲያኝኩ ይመክር ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በወሊድ ወቅት የምጥ ህመምን ለማስታገስ ከቅርፊቱ የተፈላ ሻይ ሴቶች እንዲወስዱትም ይደረግ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ብዙ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ በርካታ ጥረቶችና ምርምሮች ሲደረጉ ከቆዩ በኋላ በ1900 አስፕሪን በክኒን መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀረበ፡፡ ይህ የሆነው ባየር የተባለው የመድሃኒት አምራች ኩባንያ፣ በርካታ ጥናቶች ካካሄደ እና አስፕሪን የተሰኘውን የንግድ ስም ከሰጠው በኋላ ነበር፡፡ ይህም መድሃኒቱ በባለሞያዎች በደንብ እንዲታወቅ አጋጣሚዎችን የፈጠረ ሲሆን ከ15 ዓመታት በኋላ ደግሞ ያለ ሐኪም ትዕዛዝ እንዲሸጥ ሲወሰን አብዛኛው ሰው፣ በቤቱ የሚያውቀውና የሚያስቀምጠው ዝነኛ ህመም አስታጋሽ ሆነ፡፡ ከህመም ማስታገስ ተግባሩ ውጪ ያሉ ዝርዝሮች እጅግም የማይታወቁ የነበረ በመሆኑ፣ በዚህ ዙሪያ ዝርዝር ጥናት የሰሩ እንግሊዛዊው የፋርማሲ ባለሞያ ሮበርት ቬን እና ሳሙኤልሰን በ1982 አስፕሪንን ለዓለም እነሆ በማለታቸው የኖቤል ሽልማትን አግኝተውበታል፡፡

የአስፕሪን ሰፊ ጥቅሞች

አስፕሪን መነሻውን ከተፈጥሮ ተክሎችን ያደረገ፣ በሰውነት ውስጥ የህመም ስሜትን የሚፈጥሩ ኬሚካሎችንና ንጥረ ነገሮችን ከስርዓታችን በማገድ የእረፍት ስሜትን ይሰጣሉ፡፡ ህፃናት የህመም ስሜቶቻቸው እንዲቃለል በአነስተኛ ምጣኔ ሲሰጣቸው፣ አዋቂዎችም እንደየልካቸው ይህን የህመም ማስታገሻ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት ህመምን በውጤታማነት ያስታግሳሉ፡፡

አስፕሪን ከሚሰጠው የህመም አስታጋሸነት በተጨማሪ በዋናነት የሚጠቅመው፣ የደም መርጋትን በመከላከሉ ነው፡፡ የደም መርጋት በዋናነት ስራቸውን የሚያናጋባቸው አካላት ደግሞ ልብ እና አንጎል ሲሆኑ፣ የልብ ድካም እና ስትሮክ ለገጠማቸው ሰዎች ከሚሰጡ ህክምናዎች አንዱ አስፕሪን በየቀኑ እንዲወሰዱ ማድረግ ነው፡፡ አስፕሪን እነዚህን ህመሞች ለመከላከልና ለማከም የሚረዳው፣ የደም መርጋትን የሚቆጣጠሩትን ፕላትሌት የተባሉትን የደም አርጊ ንጥረ ነገሮችን ተሰባስቦ ችግር የመፍጠር ስራ በማዘግየት ነው፡፡ ፕላትሌቶች አደጋ በሚገጥማቸው እና የደም መፍሰስ በሚኖርበት ወቅት፣ እርስ በእርሳቸው በመተሳሰር ግድግዳ ይፈጥሩና የደም መፍሰስን ያቆማሉ፡፡

ነገር ግን ይህ የደም ማርጋት ስራ አንዳንድ ጊዜ ከልክ ያልፍና ወሳኝ የሆኑ የደም ቧንቧዎች ላይ ሲከወን ደም እንደልቡ ወደ ወሳኝ አካላት መድረሱን ያቆማል፡፡ በዚህም ደም ወደ አንጎል መድረስ ያቆማል፣ ስትሮክም ይከሰታል፡፡ በደም ውስጥ ከፍተኛ የቅባት ክምችት መኖር በራሱ የደም ቧንቧዎችን የማጥበብ ሚና ስላለው፣ ይህ ሁኔታ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን በደማቸው ያሉ ሰዎች ላይ ከፍቶ ይታያል፡፡

አስፕሪን በሐኪም ትዕዛዝ ስትሮክ ለገጠማቸውና፣ የልብ ድካም ላለባቸው ሰዎች ከመታዘዙ በተጨማሪ፣ በቅርቡ በወጡ ጥናቶች ከካንሰር የመታደግ አቅም ሊኖራቸው እንደሚችልም እየተገለፀ ይገኛል፡፡ አንዳንድ ባለሞያዎች ግን እነዚህን ተጨማሪ ጥቅሞች እጅግም አይደግፏቸውም፡፡ የእነዚህ ባለሙያዎች ሙግት፣ አስፕሪን አሁንም ብዙ ጥቅሞችን እየሰጠ ያለ በመሆኑና፣ ለብዙ ተጨማሪ ችግሮች የማዘዝ ነገር ሲለመድ ውስብስብ የጎንዮሽ ሂደቶችን ሊያመጣ ስለሚችል ጥንቃቄን ይሻል ባይ ናቸው፡፡

አስፕሪን የእግር እና እጅ መገጣጠሚያዎች ላይ የሚከሰቱ ህመሞችን በመቀነስ በኩልም ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ባለሞያዎች ያስረዳሉ፡፡

አስፕሪንን በብልሃት

የአስፕሪንን ለብዙ ወሳኝነት ያላቸው የጤና ችግሮች ጥቅም ላይ መዋል ያዩ ባለሞያዎች፣ የመድሃኒቱን የጎንዮሽ ጉዳቶች ታካሚዎች ብቻ ሳይሆን፣ የህክምና ባለሞያዎችም ጭምር ሊያውቋቸው እንደሚገባ ማሳሰቢያዎች እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡ የአስፕሪን ዋነኛ የጎንዮሽ ጉዳት በዋናነት ጨጓራና አንጀት ላይ የሚያደርሱት የመቆጥቆጥና የማድማት አደጋ ነው፡፡ ቀድሞውኑም የጨጓራ ችግር ያለባቸው ሰዎች ላይ ጉቱ ይከፋል የሚሉት ባለሞያዎች ተከታዮቹን ዋና ዋና የጥንቃቄ እርምጃዎች ይመክራሉ፡፡

– ማንም ሰው አስፕሪንን ለህመም ማስታገሻነት ከአንድ ቀን በላይ መውሰድ የለበትም፡፡ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ የአስፕሪን ትዕዛዝ፣ ከሐኪም ሲመጣ ብቻ የሚወሰድ መሆን አለበት፡፡

– የልብ ህመም እና ስትሮክ ተጋላጭ የሆኑና፣ ከዚህ ሰዎችም ቢሆኑ የሚወስዱት የክኒን መጠን በሐኪም ክትትል የሚደረግበት ሊሆን ይገባል፡፡

– አልኮል መጠጦች የአንጀትን የመቆጥቆጥ ተፈጥሮ ስላላቸው፣ ከአስፕሪን ጋር ተደምረው ጉትን ስለሚያከፋ፣ አስፕሪንን በህክምናነት የሚወስዱ ሰዎች አልኮል መጠጦችን ባይዳፈሩ ይመከራል፡፡

– አስፕሪን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው መድሃኒት ቢሆንም፣ ያለባለሞያ ትዕዛዝ ከአጭር ጊዜ የህመም ማስታገሻነት ውጪ ያለ አጠቃቀም በሙሉ በባለሞያ ትዕዛዝና ምክር መደረግ አለበት፡፡

The post Sport: አስፕሪን ‹‹ተአምረኛው›› ክኒን appeared first on Zehabesha Amharic.

እውን ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ጥቁር አይደለንም ይላሉ? |ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ

አድዋ የድል አምባ (ተፈራ ድንበሩ)

$
0
0

 

አውሮፓ አርግዞ ለመውለድ ፋሽት

ሲሰላ ዘመኑ ሲያምጥ የቆየበት

12 ዓመቱ በሰማኒያ ስምንት።

ጣልያን ቢቀላውጥ ከምኒልክ ቤት

እቴጌ ጣይቱ ፊት ነሥተውት

ውሀ አጠጥተው አፈር አስበሉት።

ፒያትሮ ቶሴሊ እና ባራቴሪ

ባለጥቁር ሸሚዝ ምንደኛ አስካሪ

ሊደፍሩሽ አልቻሉም አገራችን ኩሪ

የድል አምባ አድዋ ዘለዓለም ክበሪ።

ሐዲያ፣ ሲዳማ፣ ቦረና  ኮንሶው

ወላይታ፣ ቤንች፣ ጉጂና ዶርዜው

አማራ፣ ኦሮሞ፣  ሽናሻ፣  ጉራጌው

ሶማሊ፣  አፋር፣  ጉሙዝ፣  ጋምቤላው

ከምባታ፣ አደሬ፣  አርጎባ፣ አገው

ኧረ ማንስ ቀርቷል ደም ያላፈሰሰው?

ከፋ፣ ኩሎ ኮንታ፣ ጌዲዮ ቡርጂው

በአጥንታቸው ማገር ጊድጊዳ ሠርተው

ባንድ ላይ ተባብረው ምሰሶ አቁመው

ኢትዮጵያን ያቆዩን ሁሉም በኅብረት ነው።

ያፄ ካሌብ አገር የነአምደጽዮን

ያፄ ዘርዓ ያዕቆብ የቴዎድሮስን

የዶጋሊ አርበኛች የነአሉላን

የመተማው ሰማዕት ያፄ ዮሐንስን

የጣይቱ ብጡል ያፄ ምኒልክን

የአቡነ ሚካኤል ያቡነ ጴጥሮስን

የጎበናን አገር የነገበየሁን

የበቀለ ወያ የአብዲሳ አጋን

የዳንኤል አበበ የአሞራው ውብነህን

ሸዋረገድ ገድሌ የነአብቹን

የባልቻ አባነፍሶ የገረሱ ዱኪን

የኃይለማርያም ማሞ የበላይ ዘለቀን

የነአበበ አረጋይ የጃጋማ ኪሎን

የመንሥቱ ንዋይ የሙሉጌታ ቡሊን

ባንዳ አያጠፋውም በደም የቆየውን።

በደም ያለሙትን እነ ባሐታ ሐጎስ

እንክርዳዱን ዘርተው እነ ባሻ አስረስ

ይፈታተኑናል እስከዛሬው ድረስ።

የአድዋ ገበሬ ጀግና አገር ወዳድ

በቅሎበት አይቀርም በማሳው እንክርዳድ

ነቃቅሎ ያርማል ያጠፋል ከሁዳድ።

በቋንቋ በቀለም አገር መከለል

በነፃ እንዳንኖር በመቀላቀል

ተፈጥሮን ለማገት እድገት መከልከል

ኅብረትን ማጥፋት ነው እንዳንደግም ድል።

አገር ሲጠባበቅ ለወረት በተርታ

በወንድማማቾች የቁማር ጨዋታ

በእህትማማቾች የካርታ ጨዋታ

አሸናፊ አይኖርም ማንም ማን ቢረታ።

ብዙ እምነት ቢኖርን ቢለያይ ቋንቋችን

አንድ ቤተሰብ ነን ተዋህዷል ደማችን

እንኮራባታለን በጋራ እናታችን።

የአድዋ ባለቤት መላው ሕዝብ ነው

ምንም ቢዥጎረጎር እምነት የማይለየው

ተወራራሽ ቋንቋ ያስተሳሠረው

ባህሉን በመካፈል ያወራረሰው

በዘር ተቀያይጦ የተዋለደው

መለያው ኢትዮጵያ ማንም አይደፍረው።

አድዋ አንቺ ነሽ ክብሬ

እቆምልሻለሁ ከጎሬ

ወለጋ፣  ጎጃም፣ ጎንደሬ

ከፋ፣  ሲዳማ፣  አደሬ

ከባሌ፣ ከፋ፣ ሐረር፣ ትግሬ

ከ ወንድም እህቶቼ ተባብሬ

ጅረት፣  ተራሮች ተሻግሬ

እደርስልሻለሁ በየትም ዞሬ

ባንቺ ነው ከቶ መታፈሬ

እናት ኢትዮጵያ አገሬ።

Minilik

 

 

 

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የካሜሮን አቻቸውን ይገጥማሉ

$
0
0

Lucy
(ኢትዮ ኪክ) ለ2016 ካሜሩን በምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ የቶጎን ብሔራዊ ቡድን አልካፈለም ማለቱን ተከትለው ዳግም የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያው እድል ያገኙት ሉሲዎች ነገ ከአልጄሪያቻቸው የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በኦማር Hamadi ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሉሲዎቹ ትላንት በአልጄሪያ ልምምድ አድርገዋል። የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን 8 በውጭ የሚጫወቱ ፕሮፌሽናል እንስት ተጨዋቾቹን አካቶ ሉሲዎችን ይገጥማል። የሁለቱ አገሮች የመልስ ጨዋታ ከሁለት ሳምንት በኃላ አዲስ አበባ ላይ ይደረጋል።

የአርባ ምንጭ – ጂንካ መንገድ ተዘጋ

$
0
0

ESAT Breaking News May 13 2013 Ethiopia

(ኢሳት) ዛሬ የካቲት 25/08 በኮንሶ ከተማ የመከላከያ ኃይል ከህዝቡ ጋር በፈጠረው ግጭት የኮንሶ ልዩ ወረዳ ዋና ከተማ ካራት ውስጥ የጥይት ድምጽ እየተሰማ ነው፡፡ ወደከተማዋ ደውለን ባገኘነው መረጃ መሰረት ግጭቱ የተነሳው እስከ ፌዴሬሽን ም/ቤት የደረሰውን የአካባቢው ህዝብ ያቀረበው ህገመንግስታዊ የአከላለል ጥያቄ ለማፈን የሄደውና ለወራት በአካባቢው ሰፍሮ የሚገኘው የደቡብ ልዩ ኃይል በአካባቢው የህዝብ ጥያቄውን ለመንግስት እንዲያቀርቡ የተወከሉት የአገር ሽማግሌዎች/ ተወካዮች ሰብሳቢ አቶ ገዛሃኝ ገላ ቤት በመሄድ አስገድደው ይዘው ሲወጡ ህዝቡ ባሰማው ተቃውሞ ነው፡፡
ይሁን እንጂ ህዝቡ ለማስለቀቅ ቢሞክርም ታጣቂ ኃይሉ ጥይት ወደ ህዝቡ በመተኮስ ከበተኑ በኋላ አቶ ገዛሃኝን ይዘው በመሄዳቸው ህዝቡ በተቃውሞው ቀጥሎበታል፡፡ ይህንኑ ግጭት ተከትሎ ተጨማሪ ታጣቂ ኃይል በ11 ሰዓት ደቡብ ፖሊስ በሚሉ መኪናዎች ከተማዋ እንደደረሰ ተረጋግቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ታጣቂ ኃይሉ ህዝቡን ለማስፈራራት ጥያቄውንም ከተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ እየሞከረ ሲሆን በዚህ መሰረት በምርጫ 2007 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የነበሩት አቶ አክሊሉ ቤታቸውን እንደተከበበ እርሳቸውም ቤታቸው ሆነው የሚመጣውን ለመጠበቅ እንደተገደዱ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
የተኩስ ድምጽ የሰሙ በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ የገጠር ነዋሪዎች የከተማውን ህዝብ ተቀላቅለዋል፡፡ ከዚሁ ግጭት በተያያያዘ ከተማዋን አቋርጦ የሚያልፈው የአርባ ምንጭ–ጂንካ መንገድ የተዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ከየቱም አቅጣጫ ወደ ከተማዋ የሚመጡ መኪናዎች ፊታቸውን እያዞሩ ወደመጡበት ለመመለስ ተገደዋል::

በኢትዮጵያ የረሃብ አደጋ፣ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ለአገሪቱ ፀጥታ ጠንቅ እንዳይሆን የአሜሪካ መንግስት ሰጋ

$
0
0

• ከለጋሾች ገንዘብ ካልተገኘ፣ በግንቦት ወር የእርዳታ እህል ይሟጠጣል” ተመድ
• እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው የዓለም ሀገሮች፣ ኢትዮጵያ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች

efaበኢትዮጵያ ድርቅ ያስከተለው ከባድ የረሃብ አደጋ፣ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ለአገሪቱ ፀጥታ ጠንቅ እንዳይሆን የአሜሪካ መንግስት እንደሰጋ የዘገበው ሲኤንኤን፣ ሃያ የረድኤት ባለሙያዎችን ለመላክ እንደወሰነ ገለፀ፡፡ የተመድ የእርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበኩሉ፣ ለግንቦትና ለሰኔ ወር የሚደርስ የእርዳታ እህል ለመግዛት ለጋሾች በፍጥነት ገንዘብ መስጠት እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡

በአለማቀፍ የፀረ ሽብር ዘመቻ ኢትዮጵያ የአሜሪካ አጋር መሆኗን ሲኤንኤን ጠቅሶ፣ ሀገሪቱ የክፍለ ዘመኑ ከባድ ድርቅ እንደገጠማትና በተለይ የአፋር አካባቢ ክፉኛ እንደተጐዳ ገልጿል – ትናንት ባሰራጨው ዘገባ፡፡ በአፋር ክልልና በሰሜን የአገሪቱ ክፍል፣ በድርቅ የተከሰተው የምግብ እጥረት አዝማሚያው  አደገኛ እንደሆነ በባለሙያዎች ጥናት መረጋገጡን ሲኤንኤን ገልጿል፡፡ አደጋው ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ለአገሪቱ ፀጥታ ጠንቅን እንዳይሆን የአሜሪካ መንግስት ይሰጋል፤ ይህንንም ለመከላከል እርዳታ እየሰጠ ነው ብሏል – ሲኤንኤን፡፡ የድርቁ አደጋ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን አሜሪካ ድጋፍ ተደርጋለች ብሏል፡፡

የአሜሪካ መንግስት የረድኤት ተቋም (ዩኤስኤይድ)፣ 20 የእርዳታ ባለሙያዎችን በተለይ ወደ አፋር ክልል ልኳል፡፡ ባለሙያዎቹ የድርቁን ጉዳት፣ የእርዳታውን ስርጭት የሚያሻሽል የቴክኒክ ምክር ይሰጣሉ ብሏል – ሲኤንኤን፡፡  ድርቅን መቋቋም የሚችሉና ቶሎ የሚደርሱ የእህል ዝርያዎችን ለማልማትም የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ 4 ሚ. ዶላር በጀት መድበናል ያሉት የዩኤስኤይድ ዳሬክተር፣ በዚህም ሩብ ሚሊዮን አባወራዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

ባለሙያዎቹ፣ ሃይቲና ጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ባጋጠማቸው ወቅት የቴክኒክ ድጋፍ ለመስጠት ተሰማርተው የነበሩ መሆናቸውን ሲኤንኤን ጠቅሶ፣ ኢቦላን ለመከላከል በምዕራብ አፍሪካ አገራት እርዳታ ያበረከቱ አንጋፋ ባለሙያዎች ናቸው ብሏል፡፡ ሲኤንኤን የ4 ሚ. ዶላርና የ20 ባለሙያዎችን እርዳታ አጉልቶ ቢዘግብም፤ አሜሪካ በአንድ አመት ከመንፈቅ ጊዜ ውስጥ፣ ለድርቅ ተጎጂዎች ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ እርዳታ ሰጥታለች፡፡ ከጥቅምት ወር ወዲህ ባሉት ወራት ብቻ፣ 230 ሚሊዮን ዶላር ለግሳለች፡፡ እንዲያም ሆኖ የተረጂዎች ቁጥር ብዙ ስለሆነ፣ ተጨማሪ እርዳታ እንደሚያስፈልግ የገለፀው የተባበሩት መንግስታት፤ ለጋሾች በፍጥነት ገንዘብ ካልሰጡ፣ ከግንቦት በኋላ የእርዳታ እህል ሊሟጠጥ ይችላል ብሏል፡፡

በሌላ በኩል፤ የበአለ ሲመታቸውን 3ኛ አመት ከትናንት በስቲያ ያከበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ፤ ለበአሉ አከባበር ተመድቦ የነበረውን ግማሽ ሚሊዮን ብር ለድርቁ ተጐጂዎች እንዲውል ወስነዋል፡፡

Addis Admass


ወይ ኦሮሚያ የበሕዝብ የሚቆምሩ መፈንጫ!!! –ሰርፀ ደስታ

$
0
0

Oromoእባብ ሞኝን ሁለት ጊዜ ነደፈው ይባላል፡፡ አንዴ ሳያየው ድንገት ነደፈው፡፡ በስንት ሕክምና ዳነና ሌላ ጊዜ ደግሞ ከጓደኛው ጋር መንገድ ሲሄድ መንገድ ላይ ተጠቅሎ ሲያየው ለጓደኛው ባለፈው የነደፈኝ ነገር ይሄውልህ ብሎ በጣቱ ሲነካው እንደገና ነደፈው፡፡ እስከመቼ ማንም እየሸወደንና እያደማን እንደምንኖር አላውቅም፡፡ ዛሬም ምን ያህሎቻችን እንደገባን አላውቅም፡፡ በሁሉም የአገራችን ክልሎች የየራሳቸው ችግር ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ዛሬ ኦሮሚያ እየተባለ የሚጠራው ክልል ሁኔታ ግን ከሁሉም አሳዛኝ ነው፡፡ ይህ ክልል ለኢትዮጵያና ኢተዮጵያውያን ጠላቶች ለሆኑ አደገኛ ሴረኞች መፈንጫ ሆኗል ብል እያጋነንኩ አይደለም፡፡ ዛሬ በሥልጣን ላይ ያለው ገዥ ከመጣ ጀምሮ ይሄ ክልል ለሴረኞቹ እንዲመቻች ተደርጎ ሲሰራበት ቆይቷል፡፡ አሁን የሕዝብ ልጆች ለገዛ ጠላቶቻቸው መሳሪያ እየሆኑ ያሉት፡፡ ታላላቆቻቸውንና (እውነተኛዎቹን) እና ጀግኖቻቸውን ማሰብ አልቻሉም፡፡ ለመሆኑ ሴረኞቹ እነማን ናቸው፡፡

ኦነግና ኦነጋውያን (የሚኒሶታዎቹን ጨምሮ)

ኦነግና ኦነጋውያን የኦሮሞ ሕዝብ ተቆርቋሪ በመምሰል ሕዝብን ለራሳቸው ሴራ ተገዢ እንዲሆንላቸው ሲሰሩ ከነበሩት ሴረኞች አንዱ ናቸው፡፡ ብዙ ኦሮሞ ነኝ የሚለው የዛሬው ትውልድ ኦነግና ኦነጋውያን ባሪያቸው እንዲሆን እንደቀረጹት አይረዳም፡፡ ኦነግና ኦነጋውያን ዓላማቸው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ማጥፋት  እንጂ ኦሮሞ ብለው የሚጠሩት ሕዝብ ነጻነት ምናቸውም እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ ይልቁንም ይህን ሕዝብ እንደ መሣሪያ ለሞትና ለስቃይ እያጋፈጡ እነሱ በሕዝቡ ሰቆቃ የሚዝናኑ መሆኑን አሳምረን እናውቀዋለን፡፡ አናስታውሳለን የሕዝብን ልጆች ለሞትና እንግልት ዳርገው እነሱ ወደሚመቻቸው አገር በሰላም በአውሮፕላን እንደተሸኙ አንረሳም፡፡ ዛሬ በስልጣን ላይ ያሉት ባለስልጣኖች ኦነግን እንደ አሸባሪ ለሕዝብ እየነገሩን የኦሮምኛ ተናጋሪውንም ሆነ ሌላውን ሕዝብ ለማጥቃት ግን ዋና አጋራቸው ኦነግና ኦነጋውያን እንደሆኑም እንረዳለን፡፡ የኦነግ ባለስልጣኖች አሁን በስልጣን ላይ ካሉት ባለስልጣኖች ጋር ሚስጢራዊ ግንኙነት እንዳላቸው ተረድተናል፡፡ ኦነግና ኦነጋዊያን የኦሮምኛ ተናጋሪውን ሕዝብ ኢትዮጵያዊነቱን በማሳጣት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር እንዳይተባበርና እንዲነጠል በማድረግ አሁን ላለው ገዥ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻቹ ተረድተናል፡፡ አሁንም ያላዝኑብናል፡፡ እባብ ሞኝን ሁለት ጊዜ ነደፈው…….ነው፡፡ እኛ ጅሎች ሆነናል፡፡ ብዙ ጊዜ እንነደፋለን፡፡ ጠላቶቻችን እኛን እየገደሉ እነሱ ይኖራሉ፡፡ ከዚህ ሞኝነት መውጣት ግድ ካልሆነብን ሞታችንና መከራችን አያበቃም፡፡

በቅርቡ በአንድ ድህረ ገጽ እንዳነበብኩት የኦነግ ባለስልጣኖች ለጋራ ትግል በሚል እየጋበዙ የአዲስ አበባ ጉዳይ በኋላ በሕዝብ እንደሚታይ ይነግሩናል፡፡ ሕዝብ ሊሉ የፈለጉት እንሱ ኦሮሞ የሚሉትን መሆኑ ነው፡፡ እኛ አድስ አበባም ሆነ ሌላ ቦታ ላይ ያለን ጥያቄ የፍትሐዊነት እንጂ የጎሰኝነት አይደለም፡፡ በቅርቡ የተከሰተው ተቃውሞም ይዘቱን የጎሰኛ እንዲሆን ባይደረግ መልካምና ውጤታማ በሆነ ነበር፡፡ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የዚሁ ተቃውሞ አካል በሆኑ ነበር፡፡ ሁኔታው ግን ሌሎች ኢትዮጵያውያን የበለጠ እንዲያስቡበትና ዛሬም የኦነግና ኦነጋውያን ሴራ ደጃፋቸው ላይ እንዳለ ያስተዋሉበት ነበር፡፡ ይሕዝብ ልጆች አሁንም ባላወቁት ነገር የሞታሉተ ለስቃይ ይዳረጋሉ፡፡ ኦነግና ኦነጋውያን ግን ከሩቅ ሆነው በሕዝብ እልቂት እየተዝናኑ በለው ይላሉ፡፡

ኦነግና ኦነጋውያን በተለይም በምስራቁ የአገራችን ክልሎች በተለይ ደግሞ በአርሲ፣ ሐረርና ባሌ የሙስሊም ጽንፈኝነት እንዲስፋፋ ከውጭ ሀይሎች ጋር ጭምር እንደሚሰሩም አናያለን፡፡ እነዚህ የጠቀስኳቸው ክልሎች ከእምነት የቅርብ ጊዜ ታሪክ ቁስል እንዳለ የምናውቀው እናውቃለን፡፡ ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ይህንን አይረዱም፡፡ ለጊዜው ስለዚህ ታሪክ ለሚዲያም ስለማይመች እዘለዋለሁ፡፡ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ግን አብዛኞቹ ኦነግና ኦነጋውያን ከእነዚህ ክልሎች እንደሆኑ አስተውሉ፡፡ ሕልማቸውና ምኞታቸው እስላማዊ አክራሪነትን የምትከተል ኦሮሚያን መፍጠር ነው፡፡ ክርስቲያን ዜጎችን በሜጫ ማረድ፣ ወይም ማስለም ነው፡፡ ይሄ በተደጋጋሚ ተሞክሯል:: ዛሬ በእነዚህ ቦታዎች የሚኖረው ሕዝብ በደንብ ያውቃቸዋል፡፡  በበጎ ካልሆነ የግለሰቦችን ሥም መጥራት አስፈላጊ አይደለም ብዬ ስለማምን ነው እከሌ የማልለው፡፡ በየቧህነትና ባለማወቅ የእነዚህ ሴረኞች ደጋፊ የሆናቸው እራሳችሁን ከእነዚህ በሕዝብ ደም ከሚታጠቡ  ራሳችሁን አርቁ፡፡

 

የኢሕአዴግ ባለስልጣናት

ከላይ እንደገለጽኩት ኢሕአዴግና ኦነግ አብረው የሚሰሩ አጋሮች እንጂ በሚዲያ እንደምንሰማው ጠላቶች አይደሉም ሆነውም አያውቁም የሚል እምነት አለኝ፡፡ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት የኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ከሆነ አይደለም አዲስ አበባ ድሮ የተነሱበትም ደደቢት እድል እንደሌላቸው ያውቁታል፡፡ ስለዚህ ከኦነግ ጋር መጀመሪያ የቀረጹት ፕሮጄክት ኦሮምኛ ተናጋሪውን ሕዝብ ከኢትዮጵያነቱ ማምከን ነበር፡፡ ከሞላጎደል ዛሬ 25 ዓመት የሆነውን በዘረኝነት የተለከፈ የአባቶቹን ታሪክና ደም ያቃለለ ትውልድ በማፍራታቸው ተሳክቶላቸዋል፡፡ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት ከሁሉም ክልል በላይ ዛሬ ኦሮሚያ የሚባለው ክልል ሕዝብ ያስፈራቸዋል፡፡ ይህን ደግሞ ከታሪክም ያውቁታል፡፡ ይህ ሕዝብ የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ መሥራቾች አባቶቹ እንደሆኑ ካወቀና ከተረዳ ለኢሕአዴግ ባለስልጣናት አደጋ እንደሆነ ተረድተውታል፡፡ ሥለዚህ ይህን ሕዝብ ከታሪክና ከማንነቱ በማምከን የገዛ አባቶቹነ ታሪክ እየረገመ በመከራ የሚኖር የባዘነ ሕዝብ ማደረግ ነበረባቸው፡፡ ኦነግና ኦነጋውያን የዚህ ሴራ አጋር ተዋናዮች ናቸው፡፡ ዛሬ ኦሮምያ ከሚባለውን ሰፊ ክልል የሚያስተዳደር መሪ እንኳን ጠፍቶ ማየታችን ስለፈዘዘን ማስተዋል ባንችልም ሒደቱ እንዲህ ነበር፡፡ እስከዛሬ ይህንን ክልል የመሩት እነማን ናቸው; ቢባል ዘርዝሩ፡፡ እውነተኛ የሕዝብ ልጆች እንዳይደመጡ ተደርገዋል፣ ታስረዋል፣ ተሰደዋል፡፡

 


አሸን የሆኑት የኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት ታጋይ ነን የሚሉትና እውነተኞቹ የሕዝብ ልጆች

የዘር ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ መሪ ከሆነ ጀምሮ የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ አውጭ ነን እንደሚሉ ድርጅቶች የበዛ ያለ አይመስለኝም፡፡ አብዛኞቹ የሚመሰረቱትና የሚመሩት ከላይ የጠቀስኳቸው ኦነግና የኦነግ አስተሳሰብ ባለቸው ነው፡፡ አላማቸውም የሕዝብ ነጻነት ሳይሆን የግል ፍላጎታቸው ስለሆነ እድሜም የላቸውም፡፡ መሥራች ተብዮዎቹም የሚፈልጉት የግል ጥቅም እነዳልተሳካ ሲያውቁ፡፡ ወይ ሌላ ጥቅም የሚያስገኝላቸው ይቀላቀላሉ ወይም ይተውታል፡፡ ሆኖም ግን ጥቂት የሚባሉ የሕዝብን ጉዳይ ጉዳዬ ያሉ አልታጡም፡፡ እነዚህ የሕዝብን ጉዳይ በትክክል ዓላማችን ያሉ ግን በሌሎቹ አስመሳዮች ስለሚደበዝዝ አልፎም ስለሚጥላላና ከገዥዎቹም ባለስልጣን ጥብቅ ክትትል ስለሚደረግባቸው ውጤታማ መሆን አልቻሉም፡፡ ከዚህ አንጻር ታዋቂው የፖለቲካ ምሁሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና (በበጎ ስለሆነ ሥማቸውን መጥቀስ መልካም ስለሆነ ነው)  እነዚሕን ትክክለኛ የሕዝብን ጉዳይ ዓላማዬ ያሉ ድርጅቶችን ለመመስረትና ተጽኖ ፈጣሪ ለመሆን ብዙ ጥረው ነበር፡፡ አሁንም እየጣሩ ነው ያሉት፡፡ የሚያሳዝነው ግን እኚህ ሰው የሚመሰርቷቸውን ድርጅቶች አባል ነን ብለው በሚገቡና በኢሕዴግ ዳረጎት በሚታለሉ ወይም ሌላ ድብቅ ሴራ ባላቸው ግለሰቦች ብዙ ጊዜ ሲፈርስ እናያለን፡፡ ዛሬ በዘር የተለከፈው የኦነግና ኦነጋውያነ ሥሪት የሆነውም ትውልድ ብስለት ያላቸውን እንደነ መረራ ያሉትን የምሁራንን ድምጽ ሳይሆን የሚሰማው በፌስቡክ ጥግ ሆነው ሴራቸውን የሚነዙለትን ተራ ግለሰቦችን ነው፡፡  ብዙ ጊዜ መርዘኞቹ ነድፈውናል ከአሁን በኋላም ቢሆን ብንነቃ መታደል ነበር፡፡ የትክክለኛና ኃላፊነት የሚሰማቸውን የምሁሮቻችንን ቃል መስማት እምቢ ብለን ተጎድተናል፡፡ አባቶቻችን በደምና በአጥንት ያቶዩልንን አገርና ማንነት ረስተን ጠላቶች በሰበኩን የዘር ልክፍት ተይዘን እንባዝናለን፡፡

ኦሮሞን ነጻ እናወጣለን የሚሉ እነሱ ሞት እንዳያገኛቸው ተጠንቅቀው እኛን በፌስ ቡክ ወሬ ለሞት እንድንማገድ ያደርጉናል፡፡

ኦሮሚያ የሚባለው ክልል በዚህ ከቀጠለ አደጋው ለሁሉም ይተርፋል፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት ክልሉ በአሻንጉሊቶች ተመራ፡፡ በዘር ልክፍት ያደገው ትውልድ በታሪክ ማማ የነበሩትን የቀደሙትን አባቶች ውለታ አርክሶ ባርነትን ፈለገ፡፡ አኖሌ ሀውልትን ሲያቆሙለት ጨፈረ፡፡ ጥላቻን እንደ ድል ቆጠረ፡፡ ሀውልቱ 25 ዓመት እንዲመክን የተሰራበትን ማረጋገጫ መሆኑን አላወቀም፡፡ ለማያውቀውና ላልተጻፈ ታሪክ የራሱን ነጻነት ሰጠ፡፡ የሚነግሩትን አልቀበል አለ፡፡ ከአጎራባቾቹ ጋር ሁሉ ተናከሰ፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት ኦሮምያ የሚባለው ክልል ከሚያጎራብታቸው ከሁሉም ጋር ተናቆረ፡፡ ችግር ሲደርስበትና ብሶቱን ሲያሰማም ሌሎች ከእሱ ጋር መተባበርን እንዳልፈለጉ አየን፡፡ ምን እንደሚፈልግ እንኳን የማይረዳ በዘረኝነት የተለከፈ ዓላማ የሌለው የባዘነ ትውልድ ሆነ፡፡ በመሆኑም እንደልባቸው ለሚዘውሩት ሴረኞች ተመቻቸ፡፡ አሁን ክልሉ የለየለት የቁማርተኞቹ መፈንጫ ሆነ፡፡ ትውልዱ ግን መስማት ያለበትን ለመስማት አሁንም ፍላጎት የለውም፡፡

 

አዝናለሁ!

“ኢትዮጵያ ውስጥ የብዙኃን አስተሳሰብ ተጨፍልቋል” የልደቱ አያሌው

$
0
0

 

12512262_10208531169267480_8685710729599944735_n

ልደቱ አያሌው

ባለፉት 4 ወራት በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረውን ተቃውሞና ግጭት እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ
አካባቢዎች የተከሰቱ ብጥብጦችን አስመልክቶ አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው፤ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሚከተለውን ትንታኔ ሰጥተዋል

አዲስ አድማሱ- ዘንድሮ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለምን ተቃውሞና ግጭቶች የበዙ ይመስልዎታል?

የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመርን አንስቶ፣ ስርአቱ እንደ ስርአት ያለው አቅጣጫ ልዩነት ላይ የሚያተኩር ስለሆነ፣ በሂደት የህዝብን ትስስርና አብሮ የመኖር ሁኔታ እየሸረሸረ፣ ግጭቶችን እንደሚያባብስ ስንገልፅ ነበር፡፡ በአንፃሩ ኢህአዴግ የያዝኩት መንገድ ይበልጥ የህዝቡን አንድነት የሚያጠናክር ነው የሚል አቋም ላለፉት 25 አመታት ይዞ ቀጥሏል፡፡ ነገር ግን በእነዚህ ጊዜያት የሰላም ኮንፈረንስ ሲያካሂድ ነው የኖረው፡፡ ሰላም የሰፈነበት ሁኔታ አልታየም፡፡ አሁን ደግሞ በመጠኑም ሆነ በይዘቱ አቅጣጫውን የቀየረ አስቸጋሪ ሁኔታ በሀገሪቱ እየተፈጠረ መሆኑን እያየን ነው፡፡ ከአሁን በፊት ግጭት ብቅ ይላል፤ ብዙም ሳይታይ ይዳፈናል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ብቅ ይላል፡፡ አሁን ግን ቀጣይ ግጭቶችና አለመግባባቶችን በብዙ አካባቢዎች እያየን ነው፡፡ ኢህአዴግ በአጠቃላይ በህዝቦች አንድነት ላይ ሳይሆን ለልዩነት ትኩረት ሰጥቶ የሚያራምደው ፕሮፓጋንዳ፣በሂደት ውጤቱ ምን እንደሆነ እየታየ ነው፡፡ ይሄ እንግዲህ በቀጥታ ከፌደራል ስርአት አደረጃጀቱ ጋር ይያያዛል፤ቋንቋና ብሄርን መሰረት አድርገው ከተደራጁ ፓርቲዎች አጠቃላይ ሁኔታም ጋር ይገናኛል፡፡

አዲስ አድማሱ- በአሁኑ ወቅት ችግሮቹ ለምን እየተባባሱ መጡ?

አንዱና ዋናው ጉዳይ ህብረተሰቡ በሰላማዊ መንገድ ሃሳቡን የሚገልፅበት እድል እየጠበበ መምጣቱ ነው፡፡ ስርአቱ በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ የበላይነት ብቻ የሚመራ መሆኑና የህብረተሰቡ አስተሳሰብና ጥቅሞች የሚወከሉበት ም/ቤት ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ፓርላማ መጥፋቱ ሌላው ነው፡፡ ኢህአዴግ ስለ ዲሞክራሲ ሲያወራ ትርጉም የሌለው የታይታ ዲሞክራሲ እንደሆነ፣ የተለያዩ ሃሳቦችም ተቀባይነት እንደሌላቸው ህብረተሰቡ እየተረዳ ነው የመጣው፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከቀበሌ እስከ ፓርላማ ም/ቤቶች ጥርግርግ ብለው መውጣታቸው ህዝቡ ብሶቱን የሚተነፍስበት መድረክ አሳጥቶታል። ህዝቡ መድረኩን ሲያጣ ሊከተል የሚችለው አማራጭ አመፅንና ተቃውሞን ነው፡፡

ቀደም ሲል ይሄ አልታየም፤ ምክንያቱም ቢያንስ በርከት ያሉ ፕሬሶች ነበሩ፡፡ ተቃዋሚዎች በፓርላማ ነበሩ፡፡ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ክርክሮች ይካሄዱ ነበር፡፡ ህዝባዊ ስብሰባዎችም ይደረጋሉ። በአጠቃላይ የተለያዩ የህብረተሰቡ ቅራኔዎችና ሃሳቦች የሚስተናገዱበት እድል ነበረ፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ ወደ አመፅና ግጭት የመሄድ እድሉ እምብዛም ነበር፡፡ አሁን በሂደት ይሄ እየጠፋና መድረኩ እየጠበበ በመምጣቱና ፍፁማዊ የአንድ ፓርቲ የበላይነት በመንገሱ ለአመፅና ግጭቶች በር ከፍቷል፡፡ መንግስት ሰላማዊ ትግልንም ፈርቶ፣ የትጥቅ ትግልንም ፈርቶ መኖር አይችልም፡፡ አንዱን መምረጥ አለበት፡፡ የፖለቲካና የአመለካከት ልዩነት የሚስተናገድበት መድረክ ከሌለ፣ አመፅና የትጥቅ ትግል ምቹ መደላድል እያገኘ እንደሚሄድ መታወቅ አለበት፡፡ የተፈጠረው ችግርም የዚህ ሁሉ መግለጫ ነው፡፡

አዲስ አድማሱ – አመፅና ግጭቶቹ የመብት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የብሄር አክራሪነት የታከለባቸው ናቸው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?

ህብረተሰቡ በታሪኩ አብሮ የኖረ ህብረተሰብ ነው፡፡ በልዩነት የመኖሩን ያህል ብዙ የአንድነት መገለጫ የሆኑ እሴቶች አሉት፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት ግን ሲሰበክ የኖረው ልዩነቱ ነው እንጂ አንድነቱ አልነበረም፡፡ በዚህ ህብረተሰቡ “እኛና እነሱ” የሚል አመለካከት እንዲያዳብር ነው የተደረገው። ይሄ ሂደት ወደ ጠባብነትና ዘረኝነት የሚያመራ አደጋ እንደሚፈጥር ግልፅ ነው፡፡ አሁን እያየን ያለነው ይሄን ነው፡፡ አሁን እያየን ያለነው ሃገራዊ ራዕይ ሳይሆን አካባቢያዊ ሁኔታን ነው፡፡ እኛ ብሎ “እነሱ” የሚባሉትን የሚጠላ ኃይል ነው እየተፈጠረ ያለው፡፡ በኔ ሀብት ማንም ሊጠቀም አይገባም ብሎ የሚያምን ህብረተሰብ ነው እየተፈጠረ ያለው፡፡

ጤናማ ያልሆነ ጥላቻ የታከለበት ፉክክር ነው እየዳበረ የመጣው፡፡ ስርአቱምኮ የጠባብነት ችግር እንዳለበት ይናገራል፡፡ ግን ይሄን የጠባብነት አመለካከት ወደዚህ ደረጃ ያጎለበተው ማን ሆነና ነው ዛሬ እሱ ወቃሽ የሆነው? አሁን እያጨድን ያለነው የዚህን ፍሬ ነው፡፡፡ ይሄ ሀገር ወዴት እየሄደ ነው ተብሎ ተገምግሞ መሰረታዊ ማሻሻያ መወሰድ ካልተቻለ አደገኛ ነው፡፡ በተሃድሶ ላይ በር የዘጋ ስርአት አመፅና አብዮት ነው የሚያስተናግደው፣ ይሄ በታሪክ የተረጋገጠ ነው፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ ሰላማዊና ህጋዊ መንገዱን ባጠበበ ቁጥር ሊያስተናግድ የሚገደደው አመፅና አብዮት ነው፡፡

ኢህአዴግ ያለፈውን ምርጫ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ሲል አደጋው ሊታየው ይገባ ነበር። ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የብዙሃን አስተሳሰብ ተጨፍልቋል፡፡ አንድ አስተሳሰብ ብቻ የህብረተሰቡን ህይወት እየወሰነ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ የብዙሃን አስተሳሰብና ፓርቲ ስርአት አስፍነናል ማለት በህዝብ ላይ መቀለድ ነው፡፡ ኢህአዴግ በሌሎች ላይ ጣት መቀሰሩ የትም አያደርሰውም፤ ራሱን ነው መመርመር ያለበት፡፡ ተቀናቃኙም ሃይል ቢሆን አመፅና ግጭት ይህቺን ሀገር ወዴት ሊወስዳት እንደሚችል ቆም ብሎ ማሰብ አለበት፡፡ ህጋዊና ሰላማዊ መንገድ መከተል ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያለው ብጥብጥ ኢትዮጵያን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ሊወስዳት ይችላል፡፡

አዲስ አድማሱ-መንግስት ችግሩን እያስተናገደ ያለበት ሁኔታ ያዋጣል ብለው ያስባሉ?

እንግዲህ ችግሩን ከህብረተሰቡ ጋር እየተወያየሁ እየፈታሁ ነው ይላል፡፡ በኛ ግምገማ ግን መንግስት በቀጥታ ከጉዳዩ ባለቤት ጋር ሲወያይ አይደለም የምናየው፤ የራሱን ካድሬዎች እየሰበሰበ ነው እያወያየ ያለው፡፡ የራሱን ካድሬዎች ያወያያል፤ በቴሌቭዥንና በሬዲዮ ይቀረፃል፤ ያ ለህዝብ ይቀርባል፡፡ ይሄ መሬት ላይ ካለው እውነት ጋር አይሄድም፡፡ ህዝቡ የመንግስት ሚዲያዎችን በዚህ የተነሳ ማየት አይፈለግም፤ ሌሎች የውጭ አማራጮችን ይሻል። 25 ዓመት ሙሉ በሚዲያዎች እየተሰራ ያለው ፕሮፓጋንዳ፣ ስርአቱን በህዝብ ዘንድ አመኔታ እንዲያጣ አድርጎታል፡፡ ህዝብና መንግስትን ሆድና ጀርባ አድርጎታል፡፡ አሁን መንግስትን የሚያምን ህዝብ የለም፡፡ በዚህ ምክንያት ነው አመፅና የትጥቅ እንቅስቃሴዎች ካለፈው ጊዜ በተሻለ እድል እያገኙ የመጡት፡፡

አዲስ አድማሱ -ባለፉት 4 ወራት በተከሰቱ ግጭቶች የበርካቶች ህይወት መጥፋቱ ተገልጿል፡፡ እልባቱ ምንድን ነው ብለው ያስባሉ?

በዚህ ጉዳይ ብዙ ድርድር ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡ እነ ቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ሶርያ… አሁን ያሉበት ችግር ውስጥ የገቡት ተሃድሶ ማካሄድ አቅቷቸው ነው፡፡ ስርአቶቹ ቆም ብለው ራሳቸውን ገምግመው፣ ተሃድሶ ማድረግ አቅቷቸው ነው አብዮት ተቀስቅሶ ለራሳቸውም ለህዝባቸውም የማይጠቅም ሁኔታ ውስጥ የገቡት፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም ቆም ብሎ ተሃድሶ የማያደርግ ከሆነ፣ እነሱ የደረሰባቸው እጣ ፈንታ በሱም ላይ የማይደርስበት ምክንያት የለም፡፡ ችግሩ ግን በመንግስት ላይ ደርሶ የሚቆም አይደለም፡፡ ለሀገርና ለህዝብ የሚተርፍ ነው፡፡ በተለይ በሀገሪቱ ባለው የፖለቲካ ቅራኔና የልዩነት ስፋት እንዲሁም ሲሰብክ ከኖረው የጠባብነት አስተሳሰብ አንፃር፣ በግብፅና በሊቢያ የተፈጠረው አይነት እዚህ ቢያጋጥም፣ የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ውስጥ የሚከት ነው የሚሆነው፡፡ ችግሩ ቢከሰት የአደጋው ተጠቂ የሚሆነው መንግስት ብቻ ነው ብሎ ማሰብ ተገቢ አይሆንም፡፡ መንግስት ይሄን አደጋ በሚገባ ተገንዝቦ ራሱን ለተሃድሶ ዝግጁ ማድረግ አለበት፡፡

አዲስ አድማሱ – ለተሃድሶ ዝግጁ መሆን አለበት ሲሉ ምን ማለት ነው?

ለዚህ ሀገር የታይታ ሳይሆን እውነተኛ ዲሞክራሲ እንዲመጣ ጥረት ማድረግ አለበት፡፡ የህብረተሰቡ የተለያዩ አመለካከቶች የሚወከሉበት መድረክ መፍጠር መቻል አለበት፣ ፓርቲዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው፣ ልዩነታቸውንና ሃሳባቸውን የሚያራምዱበት ሁኔታ መኖር ይገባዋል፡፡ በየ5 ዓመቱ የሚካሄዱ ምርጫዎችም ይሄን የህብረተሰቡን የሀሳብ ልዩነት የሚያስተናግዱ መሆን አለባቸው፤ ለታይታ ብቻ መሆን የለባቸውም፡፡ ግጭቱን በሃይል ለተወሰነ ጊዜ ማስቆም ይቻል ይሆናል፤ በዘላቂነት ግን ማስቆም አይቻልም፡፡ ዘላቂው መፍትሄ ከተፈለገ፣ ሃቀኛ የሆነ ተሃድሶ መምጣት አለበት፡፡

አዲስ አድማሱ – ሰሞኑን የታክሲ ሾፌሮች አዲሱን የመንገድ ደህንነት ደንብ በመቃወም የሥራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር፡፡ አድማው ተገቢ ነው ይላሉ?

የታክሲ ሹፌሮች ህይወታቸው የተመሰረተበት ስራ ስለሆነ ህጉ ሊያመጣባቸው የሚችለው ችግር ሊያሳስባቸው ይችላል፡፡ ሲያሳስባቸው ተቃውሞአቸውን ማቅረብ መብታቸው ነው፡፡ ይህን ማንም ሰው መቃወም ያለበት አይመስለኝም፡፡ ተቃውሞአቸውን ያቀረቡት በሰላማዊ መንገድ ነው። ስራ ማቆም አንድ የሰላማዊ ተቃውሞ መንገድ ነው። ታክሲዎች ሲቆሙ ዞሮ ዞሮ ህብረተሰቡ ይጎዳል፡፡ ስለዚህ ሹፌሮችና መንግስት ተወያይተው መፍትሄ ማበጀት አለባቸው፡፡ ግን በአጠቃላይ በኦሮሚያም ሆነ በአማራ ክልል ወይም በሌሎች አካባቢዎች የሚነሱት ተቃውሞዎች መነሻ ምክንያቶች ይኑራቸው እንጂ ጥያቄዎቹ ብዙ ናቸው፡፡ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የተከሰተውም ይሄ ነው፡፡ አንዳንድ ጥያቄዎች መነሻ እንጂ ዋነኛ ጥያቄዎች አይደሉም። በኦሮሚያ ያለው የማስተር ፕላን ጥያቄ ብቻ ነው ብሎ የሚያስብ ካለ ተሳስቷል፤ስረ መሰረቱን በደንብ መመርመር ያስፈልጋል፡፡

አዲስ አድማሱ – ለነዚህ ሁሉ የሀገሪቱ ችግሮች ምንድነው መፍትሄው ይላሉ ትሄ ያበጁለታል?

ህዝብና መንግስት እየተራራቁ እንደሆነ መንግስት ተገንዝቦ፣ ህዝቡ በአግባቡ ብሶቱንና ተቃውሞውን የሚያሰማበት መድረክ መፍቀድ አለበት፡፡ በአጠቃላይ በሀገሪቱ የሚካሄዱ ምርጫዎች እድል የሚሰጡ መሆን አለባቸው፡፡ አንዱ መፍትሄ ሰላማዊና ህጋዊ መንገዱን ማስፋት ነው፡፡ የብዙሃን ፓርቲ አሰራር ሰፍኖ ልዩነት፣ ብሶት፣ ተቃውሞ… የሚደመጥበት መድረክ ያስፈልጋል፣ አሁን ግን ይሄ የለም፤ የአንድ ፓርቲ ብቸኛ የበላይነትና ቁጥጥር ያለበት ሀገር ነው፡፡

ሁለተኛው ህገ-መንግስታችንን መመርመር ያስፈልጋል፡፡ በተለይ የፌደራል አደረጃጀቱን በተመለከተ አደረጃጀቱ 25 ዓመት ውስጥ አንድነታችን እያጠናከረ መጣ ወይ? በህብረተሰቦች ዘንድ መተማመንን መፈቃቀርን ነው ወይ ያመጣው? የሚለውን መመርመር ያስፈልጋል፡፡ መሻሻል ካለበት መሻሻል አለበት፡፡ አሁን የሚደረገው ወታደራዊ እርምጃ ለጊዜው ችግሩን ሊያስታግሰው ይችላል ግን ያዳፍነዋል እንጂ አያጠፋውም፤መልሶ መፈንዳቱ አይቀርም፡፡

የህወሃት መከላከያ ሠራዊት ወደ ኤርትራ መጠጋት እውን ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም ወይስ በኤርትራ የሚገኙ አማጽያን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ለማድረግ?

$
0
0

አንተነህ ገብርየ


mmmአጭር መግቢያ፦ከ1998 እስክ 2000 የዘለቀው ጦርነት ከሁለቱም ወገን ከፍተኛ የሰው ሕይወትና የሀገር ሀብት ማውደሙ ይታወቃል።ያኔ ህወሃት ጨርቅ ነው ሲለው የነበረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ በማውለብለብ መላ ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲሰለፉ ጥሪ ማቅረቡ፤እንደ አሮጌ ቁና የጣለውንና የበተነውን የቀድሞ ሠራዊት መማጸኑም ይታወቃል ማንም አላቅማማም ሁሉም ጥሪውን ተቀብሎ ዘመተ ዘመቻው ቀጥሎ ወደ አሥመራ ብቅ ሲል የኢትዮጵያው ጦር እንዲያፈገፍግ ተደረገ የኢትዮጵያን መሬት ለኤርትራ በማስረከብ የተጠናቀቀው ጦርነት የኢትዮጵያ ድል ተብሎ በቅጥፈት ታወጀ።ያነገር አሁንም እልባት አላገኘም ገዥው የህወሃት ቡድን የንጹሐንን ደም በማጉረፍ ተኪ አይገኝለትምና ይህንም እንዲህ አድርጎት ፀጥ አለ።

ያኔ የቀድሞው ጦርም ሆነ ሕዝቡ ህወሃትን የተቀላቀለው የህወሃትን ውስጣዊ ማንነትና ግብ ባለመረዳት ሲሆን ከዚያ ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ባለው ጊዜ ውስጥ ህወሃት ምን ያህል አረመኔያዊ ተቋም እንደ ሆነ በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ራሱን በተግባር አስተዋወቀ ብዙ የተቃዋሚ ኃይሎች አበቡ በርከት ያሉ ጋዜጠኞች ጦማሪያን የሥርዓቱን ጭራቅነትና ዝርክርክነት በስፋት አጋለጡት በነዚህ ጥረቶች ህወሃት እንደ እባብ ገላ ከሕዝብ ሾልኮ እርቃኑን ቀረ።ሕዝብና ህወሃት ዳግም ላይገናኙ ሕዝብ ሥርዓቱን በማስወገድ ጎዳና ብቻ መብቱን ማስከበር እንዳለበት አመነ።አሁን ከላይ እንደገለጽኩት ኤርትራና የህወሃት መከላከያ ኃይል ወደ ጦርነት ቢገቡ ምን ሊከሰት ይችላል የሚል ነጥብ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ያነጋገረ ጉዳይ መሆኑና እያነጋገረ እንዳለ ግልጽ ነው እንደ እኔ የግል አስተያየት ህወሃት ከጉራና ማስፈራራቱ አልፎ ጠብ ቢጭር የህወሃት ፋሽስታዊ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ትካሻ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያከትምለታል እንጅ የሚያገኘው ትርፍ አይኖርም(አዲዮስ ህወሃት)።

በመግቢያ ያስቀመጥኳቸውን መሠረታዊ ሀሳቦች በዝርዝር ለመመልከት እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።

ህወሃት ጦሩን አስጠጋ የሚባለው በኦማሐጀርና ተሰነይ ነው ይህ እንግዲህ በሱዳን በኩል በገዳሪፍና በከሰላ መሆኑ ነው ይህ ደግሞ ሱዳን ደፍራ ከፈጸመችው በሱዳንና በኤርትራ ሊያስነሳ የሚችለው አደጋ ቀላል አይሆንም ። ኤርትራ እንደ ህወሃት ከሱዳን ጋር በጥቅም የተሳሰረች አይደለችም ስለዚህ ኤርትራ በሱዳን ላይ የምትወስደው ርምጃ ሱዳንን የሚጎዳ ይሆናል።ህወሃት እውን ኤርትራን ለመግጠም የሚያስችል መሠረታዊ ምክንያት አላት ወይ? ያላት ሠራዊትስ ብቃት አለው ወይ?ምንም አይነት ምክንያት ማስረጃ ሳይኖር ጦርነት እገጥማለሁ ማለትና ጦር ማስጠጋት በራሱ እንደ ጦር አጫሪነት አያስቆጥርም ወይ? የሚሉ ጉዳዮችን ማንሳታችን የማይቀር ነው።እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ በኔ እይታና አመለካከት የሚከተለውን አይነት አንድምታ አስቀምጣለሁ።

1ኛ/ የህወሃትን አነሳስና አሁን ላይ ያደረሰውን ጉዞ ስንመለከት፦

ህወሃት መጀመርያ አንድ ሁለት እያለ ራሱን ወደ ድርጅትነት አሳድጎ ሲነሳ መሠረታዊ ጥያቄው የክፍለ ሐገሩን ምርታማ አለመሆንና በኢኮኖሚ በኩል ትግራይ ውስጥ ያለውን ድኸነት ለመቅረፍ ሲባል ለም የሆኑ የአጎራባች ክፍለ ሐገሮችን በኃይል በመንጠቅ ትግራይን ገንጥሎ ሌላ አገር ለመፍጥር መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው።ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ መጀመርያ ሁለት ነገሮችን አስቀድሞ ማጽዳት የግድ ይል ነበር።ይኸውም አማራን ከምድረ ኢትዮጵያ ማጽዳትና ዘሩን ማጥፋት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሐዶ እምነትን ህወሃት የሚቆጣጠረው ውስጡ የተዳከመ ተቋም ማድረግ ነበረበት።ለምን?ብለን ጥያቄ ልናነሳ እንችል ይሆናል? መልሱ የሚሆነው አማራው ለዚህ አመለካከት ፈቃደኛ ሊሆን ስለማይችል የመረረ ርምጃ መውሰድ ነበረባቸው እነሆ በወሰዱት ርምጃ ከ5ሚሊዮን በላይ የሚሆን የአማራ ነገድ ሕዝብ ደብዛው ጠፍቶ ዛሬ በሞረሽ ወገኔ ከፍተኛ ጥረት ጥናት ተካሂዶ የጥናቱ ከፊል በአንዳንድ ድረ-ገጾች በይፋ ለአንባብያን ቀርቦ ኢትዮጵያውያን እየተነጋገሩበትና በጣም አስደንጋጭ አሳዛኝና እልህ የሚያስይዝ ሆኖ ተገንቷል።የዚህ አካል የሆነው አንዱ ገጽታ በጠለምት፤ጠገዴና ወልቃይት ነዋሪ ሕዝብ በኃይል ተገደህ ትግሬ ትሆናለህ የሚለው የመሬት ነጠቃ አባዜ ነገር አጭሮ ነብስ ዘርቶ የህወሃትን የመብት ረገጣና አፈና ሰብሮ ጢም ብሎ በሞላ አዳራሽ ውስጥ እነማን መቼ የት እንደተገደሉ በሕይወት ተርፈው የተገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች የምስክርነት ቃላቸውን እየሰጡበት ይገኛል።

በኅይማኖታችን ጣልቃ በመግባት መንግሥታዊ (ህወሃታዊ ኃይማኖት)እምነት እንዲኖረን ህወሃት ካድሬዎቹን በቤተክርስቲናችን ውስጥ አስርጎ በማስገባት ለዘመናት ተከብሮ የኖረው ሲኖዶስ ተጥሶ በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ እንደፖለቲካው ሁሉ የህይማኖቱ ሹመትም ከአንድ አናሳ ጐሣ የተወለዱት እንዲቆጣጠሩት ተደርጎ ሕዝበ ክርስቲያኑ በውጭና በውስጥ በሚባል ሲኖዶስ ተከፍሎ በመሀሉ የመከፋፈልና አለመተማመን ብርድ ገብቶ ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉኡላዊነት ለዳር ድንበሯ መከበር ትልቁ ጋሻና ጦር ሆኖ ሲያገለግል የኖረው ቤተክርስቲያናችን በዘመነ ህወሃት ተደፍሮ እኛም ማዶ ለማዶ ቆመን እንድንተያይ አድርጓል።ይህ አሁን ህወሃት እተገብረዋለሁ ለሚለው ከኤርትራ ጋር ጦር የመማዘዝ ጉዳይ ህወሃትን በፍጥነት አደጋ ውስጥ የሚከት ነው።ይህን ህወሃቶች ጠንቅቀው ያውቁታል እንዲያው በአዋጅና በጉራ በከንቱ ድንፋታ ስነ-ልቦናዊ ጫና ለመፍጠር እንጅ የህወሃት አቅም ዳገት እንደማያወጣ መገመት ወይም እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል።ይህ አሁን ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ እየተቀጣጠለ የመጣው የኢትዮጵያውያን አልገዛም ባይነትም የህወሃትን አቅም ወይም ሕዝብ ለመምራትና ለማስተዳደር የሞራል ይሁን የአካላዊ ብቃት እንደሌላቸው ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ምልከታ ነው።እስኪ ማን ይሙት የህወሃት የመከላከያ ሠራዊት ከህወሃት ካድሬ ልቆ ነው እንዴ በኦሮሞ ክልል ሠራዊቱ ወደ አስተዳዳሪነት የገባው?

2ኛ/ እራሱን የመከላከያ ሠራዊቱን ቁመናና ተክለ ሠውነት እንመልከት፦

የህወሃት የመከላከያ ሠራዊት ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅር የሚመራው በአንድ አናሳ ጎሳ ከትግራይ ሲሆኑ በአብዛኛው ኢትዮጵያ በክልል ወይም በአዲሱ መሳፍንታዊ አገዛዝ እጅ እንደገባች አስታውሳለሁ የመከላከያ ኃይሉ በክልሎች የህዝብ ብዛት ስብጥር እንዲኖረው ሲደረግ ከህወሃት የሚቀነሰው ኃይል ብዙ በመሆኑ አማርኛ መናገር የሚችለው የአማራውን የሠራዊት ኮታ እንዲሸፍን የተደረገ ሲሆን ከሌላው ብሔርና ብሔረሰብ ከመጣው የመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ያለው ግንኙነት የሻከረ ሊበጠስ ትንሽ ምክንያት ብቻ የሚፈልግ በመሆኑ እና ይህ ከታች እስከ ላይ ያለው በመከላከያ ኃይሉ ውስጥ በመሪነት የሚገኘው አካል የተደራጀ በዝርፊያ ሀብት ያፈራ ባለ ሰፊ እርሻ ባለትልቅ ፎቅና ቱጃር ነጋዴ ስለሆነ ጦሩ ከሰገባው ሲወጣ ሞትን መርጦ ደፍሮ ይገባል ብሎ ማሰብ ከንቱነት ነው። የጥይት ማብረጃና የጦርነት ገፈት ቀማሹን ከድሃ ቤተሰብ የመጣውን  የሠራዊቱ አባላት ማን መርቶ ወደ ጦርነቱ ይከተዋል ለሚለው ጥያቄ መልሱ ቀላል ነው።አማራውን ከአማራ ኦሮሞውን ከኦሮምው ወንድሞቹ ጋር እያባሉ የመጡ አይደሉ በቀላሉ ሹመት መስጠት እርስ በርሱ እንዲተላለቅ ማድረግ የተካኑበት ሴራ ስለሆነ ይህን ማድረግ ይችላሉ ወደፊት መግፋት እንዲችል ደግሞ ከኋላው ሆኖ ጀርባውን የሚመታ ከግንባሩ የተጻራሪው ወገን የጥይት አረር እንዲበላው ማድረግ የተለመደ ነው።

ይህ ጉዳይ ከጉራነት አልፎ ወደ ተግባር ከተቀየረ ሊሆን ይችላል ያልኩትን ከፍ ብየ ሳስቀምጥ እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ ሲፈጠር የመከላከያ ሠራዊቱ ከእሥር ሊወጣ የሚችልባቸው ብዙ እድሎች ሊፈጠሩለት ይችላሉ ትጥቁ ይዞ ወይም ትጥቁን ደብቆ ከፊት ለሚገጥመው ወይም ወደ ሌላ አቅጣጫ ከድቶ መጥፋት ይችላል።እንደ እምሰማውና እንዳለኝ መረጃ ኤርትራ ውስጥ ቢያንስ ከ12 የማያንሱ ህወሃትን በነፍጥ እናስወግዳለን ብለው የተደራጁ የተቃዋሚ ኃይሎች ስለሚኖሩ ወደ እነሱ የመሄድ ወይም እነዚህ ኃይሎችን በቀላሉ ማግኘት የሚችሉበት መንገድ ከተመቻቸ ህወሃት ወሽመጡ የሚሰበርበት ሌላኛው መንገድ ነው።እንዲህ አይነቱን መንገድ መከተልና መጠቀም በአንድ አውደ ውጊያ ከሚገኘው የጦርነት ድል የበለጠ ይሆናል።

3ኛ/ ኤርትራ ውስጥ የሚገኙትን የህወሃት ተቃዋሚ ኃይሎች እንዳይወጡ እንዳይገቡ ለመዝጋት ታስቦ ከሆነ ለሚለው፦

ህወሃት የማይፈነቅለው ድንጋይ የማይቆፍረው መሬት የለም አጥር አጥሮ በር ዘግቶ የግዛት ዘመንን ለማራዘም ያስባል ይሁን እንጅ ይህ ከቅጀት የዘለለ ሊሆን አይችልም።ምክንያቱም እነሱም በአንጻራዊነት የህወሃት ሠራዊት የታጠቀውን ነፍጥ የታጠቁ ስለሆነ እንኳን ያን ያህል ሰፊ የመሬት ቆዳ ሊሸፍን የሚችል ኃይል የሌለውን ቢኖረውም የተቃዋሚ ኃይሎች ቁልፍ በሆነና ገዥ በሆነ ቦታ ከኤርትራ ለመግባትም ሆነ ለመውጣት ካሰቡ ደፈጣ በመጣል ሰብሮ መውጣት ወይም መግባት ይችላሉ።ከዚህ ባሻገር ሊሆን የሚችለው ከየአቅጣጫው ጦርነት በመክፈትና ኃይሉን በመከፋፈል አቅሙን ደካማ ማድረግና የፖለቲካ ሥራ በመስራት ወደ እነርሱ እየሄደ እጁን እንዲሰጥ የሚያደርግ አጋጣሚ ነው የሚኖረው።

4ኛ/ የኤርትራ ሠራዊትና ሕዝቡ ወይም ሠራዊቱ ለመንግሥት ያለው ታማኝነት፦

በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ እውቀት ባይኖረኝም የምገምተውን ማስቀመጥ እችላለሁ።አገዛዙ ወይም የኢሳይያስ አፈወርቂ መንግሥት አምባገነን ፈላጭ ቆራጭ ሕዝቡን ያስመረረ እየተባለ እንደሚተች፤ጋዜጠኞችን የሚቃወሙትን ፖለቲከኞች እንደሚያስር እንደሚገርፍ ከራሳቸው ከኤርትራውያን እሰማለሁ።መሠራዊቱ በኩል ግን አቅሙን ባላውቅም እንደኢትዮጵያው አይነት እንደ ህወሃት ሠራዊት ውስጡ እንዳለቀ ጨርቅ የተበጣጠሰ አለመሆኑን በድፍረት መናገር ይቻላል።ከሁለቱ ማንኛው በከፋ ጫፍ ላይ ይገኛል ሲባል ግን ህወሃት ግማሽ አካሉ መቃብር ውስጥ ያለ ያም በመከላከያ ሠራዊቱና በደህንነቱ በፖሊስ መዳፍ እጅ ያለ ስለሆነ የተቃዋሚ ኃይሎች እርስ በርስ ከመሰረጃጀት አልፈው ወሬያቸውን ከምንሰማ እንዲህ አይነቱን ለህወሃት የጀርባ አጥንት ሆኖ በሚገኘው ኃይል ላይ የማፍረስ ጨርሶም የመናድ ተግባር ላይ ቢያጠምዱ በለሱ እንደሚቀናቸው ተስፋ ሰጭ ሁኔታዎች እያመለከቱ ይገኛሉ።

 

                      ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

                     አንድነታችን ጥንካሬያችን ነው!!

                                         «አንተነህ ገብርየ»

 

ከቤተ አማራ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ 

$
0
0
1098476_965417466839011_4517603872310760613_nቤተ አማራ የአማራን ዘር በእየለቱ እየደረሰበት ካለው ጥቃት እና ከተደገሰለት ጥፋት ለመታደግ ብሎም ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በትጋት በመንቀሳቅሰ ላይ ይገኛል። በሂደትም ለህዝባቸው ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ለመስዋዕትነት ያቀረቡ ጠንካራ አመራሮቸን ለመፍጠር ተችሏል፡፡ ዲሞክራሲያዊ አሰራርንም በአመራሩ ውስጥ አስፍኗል፡፡ ነግር ግን የድርጂቱ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ መለክ ሀራ ከማዕከላዊ ኮሚቴው እውቅና ውጭ ለብቻቸው የሚሊዮኖች ተስፋ የሆነችውን ቤተ አማራን በድንገት ከሌላ ድርጀት ጋር አብሮ የመስራት ብሎም የማዋሀድ ስምምንት መፈፀማቸውን እና ከዚህ ጋር ተያይዞም የፖለቲካ ክፍል ዋና ሀላፊ የሆነ ጓዳችን ማባረራቸውን ለህዝብ ይፋ ማድረጋቸውን አሳውቀዋል፡፡ ይህን ዜና እንደማንኛውም ከድርጂቱ ውጭ እንዳለ ሰው የሰማው ማዕከላዊ ኮሚቴ ነገሩን በርጋታ ለብዙ ቀናት ሲመረምር ቆይቷል፡፡
ወደ ኋላም በመሄድ የአቶ መለክን ባህሪ እና ተግባር በጥልቀት መርምሯል፡፡በመጨረሻው ቀን አቶ መለክን እንዲሁም ወደ ቤተ አማራ ገባ ወጣ ሲሉ ቆይተው ለከፍተኛ አመራርነት የበቁትን እና ተፈፀመ ለተባለው ውህደት እንደ ተላላኪ በመሆን ህገወጥ ግን ደግሞ እውነት ያልሆነ ስራ ሲሰሩ የቆዩትን አቶ ሙሉጌታ ሀይሉን ባካተተ መልኩ ግምገማ ተካሂዷል፡፡ የግምገማው ውጤት ሲጠቃለል ሁለቱ ግለሰቦች በድርጅቱ ላይ እጂግ ከባድ በደል እንዳደረሱ አረጋግጧል፡፡
በተጨማሪም አቶ መለክ በማዕከላዊ ኮሚቴው መካከል ስር የሰደደ አለመተማመን እንዲኖር፤ አመራር አባላቱም ሙሉ አቅማቸውን አውጥተው ድርጂቱን ወደፊት እንዳያራምዱ ከፍተኛ እንቅፋት ፈጥረው ቆይተዋል፡፡ ሁለቱ ግለሰቦች የተለያዩ የጋራ ሶሻል ሜዲያ አካውንቶችን በመክፈት ቤተ አማራን ሲያወናብዱ እና የአቶ መልክን ስም ሲያጃግኑ የቆዩ መሆኑን የቤተ አማራ ደህንነትና ጸጥታ ክፍል የደረሰበት በመሆኑና እነርሱም በማመናቸው ነገር ግን በሰሩት ጥፋት ምንም አይነት የመፀፀት ስሜት ያልታየባቸው መሆኑን በማስመር ማዕከላዊ ኮሚቴው ጥፋተኛ ሆነው አግኝቶአቸዋል። ስለሆነም በስብሰባው ካልተገኙ ሶስት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሰተቀር በሙሉ ድምፅ አቶ መለክ ሀራ እና አቶ ሙሉጌታ ሀይሉ ከያዙት ሀላፊነት እስከፍፃሜው ተሰናብተዋል፡፡
አቶ መለክ ሀራም ሆኑ አቶ ሙሉጌታ ሀይሉ ከዚህ ቀን ጀምሮ በቤተ አማራ ስም ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ይህንን ውሳኔ ተላልፈው ቤተ አማራንም ሆነ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን እና ሌሎች አባላትን የሚጎዳ ነገር ፈፅመው ቢገኙ ግን ማንኛውም አይነት ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድባቸው መሆኑን ጨምረን እናስጠነቅቃለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ቤተ አማራ ለአማራ ነጻነት እና ክብር ከሚታገሉ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ምንጊዜም ፈቃደኛ መሆኑን እየገለጸ ትብብርም ሆነ ውህደት ሊፈጸም የሚችለው ግን መላ አባላቱ በየደረጃው ተወያይተውብት ሲጸድቅ ብቻ መሆኑን ሊገልጽ ይወዳል። የቤተ አማራ እና የትግሉ ባላቤት ህዝቡ እንጅ ግለሰቦች ሊሆኑ አይችሉም።
ስለሆነም ድርጅታችን ቤተ አማራ ለሰርጎ ገቦችም ሆነ ለግለሰባዊ አምባገነኖች ፈጽሞ የማይመች ሆኖ እንዲቀጥል በዲሞክራሲያዊ አመራር መርሆ መሰረት በየጊዜው ራሳችን እየፍተሸን እና እያጠራን እንደምንሄድ ለህዝባችን ቃል እንገባለን። ቆራጥ እና እጂግ የተማሩ የአማራ ውጣቶች ትግሉን በብዛት እና በየጊዜው እየተቀላቀሉ በመሆናቸው ድርጅቱ በፍጥነት እያደገ መሆኑን እያበሰርን የተከበራችሁ የአማራ ልጆች ይህን የህዝብ ድርጅት በፍጥነት እንድትቀላቀሉ ጥሪያችን ጨምረን እናስተላልፋለን።
ድል ለሰፊው የአማራ ህዝብ!
ቤተ አማራ ወደፊት!

ይድረስ ለአቶ ልደቱ አያሌው፦ ያዬ አበበ

$
0
0
ከማከብራቸው ፓለቲከኞች አንዱ እርሶ ነዎት። የአገራችን እንጭጭ ፓለቲካን ፊት ለፊት ከተጋፈጡትና ብዙ መስዋዕትነት ከከፈሉ ግለሰቦችም አንዱ እርሶ ነዎት። ሰላማዊ ትግል መንገድ ላይ ያለዎትን አቋምና ፅናት አደንቃለሁ።
ሆኖም በአዲስ አድማስ ላይ የሰጡት ምልልስ* ላይ ስለኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄ ያነሷቸው ሃሳቦች ህፀፅዊ (fallacious) ናቸው። ትችቴን ነጥብ በነጥብ እነሆ።
=========
12512262_10208531169267480_8685710729599944735_nአዲስ አድማስ፦ አመፅና ግጭቶቹ የመብት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የብሄር አክራሪነት የታከለባቸው ናቸው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
አቶ ልደቱ፦ ህብረተሰቡ በታሪኩ አብሮ የኖረ ህብረተሰብ ነው፡፡ በልዩነት የመኖሩን ያህል ብዙ የአንድነት መገለጫ የሆኑ እሴቶች አሉት፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት ግን ሲሰበክ የኖረው ልዩነቱ ነው እንጂ አንድነቱ አልነበረም፡፡ በዚህ ህብረተሰቡ “እኛና እነሱ” የሚል አመለካከት እንዲያዳብር ነው የተደረገው። ይሄ ሂደት ወደ ጠባብነትና ዘረኝነት የሚያመራ አደጋ እንደሚፈጥር ግልፅ ነው፡፡ አሁን እያየን ያለነው ይሄን ነው፡፡ አሁን እያየን ያለነው ሃገራዊ ራዕይ ሳይሆን አካባቢያዊ ሁኔታን ነው፡፡ እኛ ብሎ “እነሱ” የሚባሉትን የሚጠላ ኃይል ነው እየተፈጠረ ያለው፡፡ በኔ ሀብት ማንም ሊጠቀም አይገባም ብሎ የሚያምን ህብረተሰብ ነው እየተፈጠረ ያለው፡፡

==========

1. “ህብረተሰቡ በታሪኩ አብሮ የኖረ ህብረተሰብ ነው፡፡”
– አብሮ መኖር ትርጉም የለውም። ተከባብሮ መኖር እንጂ። ወሳኙ ምን አይነት አኗኗር ነው? የሚለው ጉዳይ ነው። በበረት ውስጥ መኖር ወይም በእስር ቤት መኖር በራሱ ዋጋ የለውም። ዋጋ ሚሰጠው የግንኙነቱ አይነትና ጥራት ነው።
2. “በልዩነት የመኖሩን ያህል ብዙ የአንድነት መገለጫ የሆኑ እሴቶች አሉት፡፡”
– እዚህ ላይ “አንድነት” የሚለው ቃል የተሳሳተ ነው። ‘አንድ አይነት’ ማለትዎ ይመስላል። የምንመሳሰልባቸው እሴቶች አሉ። መመሳሰል ግን የእኩልነት ምልክት አይደለም። እኩልነት ሚለካና ሚሰፈር ነው። ዘመናዊት ኢትዮጵያ የእኩልነት ተምሳሌት አልነበረችም።
3. “ባለፉት 25 ዓመታት ግን ሲሰበክ የኖረው ልዩነቱ ነው እንጂ አንድነቱ አልነበረም፡፡”
ባለፉት 25 ዓመታት የማንነት ግንባታ (identity empowerment) ነው የተደረግው። እኔ ዐማራ ነኝ። ዐማራ ነኝ ማለት ፀረ-“አንድነት” መሆን ነውን? ሌሎች ወገኖች “ትግራዋይ ነን” ማለታቸው፤ “ኦሮሞ ነን” ማለታቸው…ፀረ-“አንድነት” ነውን? ሊረዱት ሚገባው አሃዳዊት ኢትዮጵያ በረት እንደነበረች ነው። በግ፥ ፈየል፥ ፈረስ፥ በቅሎ፥ በሬ፥ ላም፥ ዶሮ … አንድ በረት ውስጥ ስለታጎሩ “አንድነት” አላቸው ማለት አይቻልም። ሁሉም እንደ ማንነቱና ምንነቱ የሚኖርበት ሰፊና ምቹ አገር ለመፍጠር ያለፉት 25 ዓመታት ከፍተኛ ሚና ተጫወተዋል። ዛሬ የኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄ የሚያመለክተው ዜጎች የብሔር ማንነታቸው ተገንብቶ ሳለ፥ ሕገመንግስታዊ መብታቸው በግፍና በሰፊው መናዱን ነው። ያ ነው ጉዳዩ።
4. “በዚህ ህብረተሰቡ “እኛና እነሱ” የሚል አመለካከት እንዲያዳብር ነው የተደረገው።”
“እኛና እነሱ” ባለፉት 25 ዓመታት የተፈጠረም ሆነ የዳበረ ነገር አይደለም። ዘመናዊት ኢትዮጵያ በወረራ ከተፈጠረችበት ጊዜ አንስቶ “እኛና እነሱ” ሲባል ነው የኖረው። ሁለት ማስረጃ ላቅረብ፦ ዳግማዊ ምኒሊክ አርሲን ለመውረር አምስት አመት ወስዶባቸዋል። ያ ለምን ይመስልዎታል? “እኛና እነሱ” ስለነበር ነዋ! ወላይታን ለመውረር ዳ.ሚ. 8 አመት ወስዶባቸዋል። ንጉስ ጦና ያን ሁሉ ጊዜ እምቢ ብሎ የተፋለመው “እኛና እነሱ” ሰለነበረ ነው። “እኛና እነሱ” መኖሩ “አንድነት” ለመፍጠር እንቅፋት አድርገው ለማቅረብ ከሆነ እጅጉን ተሳስተዋል። የአገር አንድነት ሚከበረው “እኛንም” “እነሱንም” በእኩልነት ሚያስተናግድ አገር ሲኖር ብቻ ነው። ሌላ መንገድ የለም። እርሶ የልቅ-ዴሞክራሲ ርዮት (liberal democracy) አቀንቃኝ ሆነው እንዴት የበዝሃነት (plurality, diversity) ፅንስን ዘነጉት?!
5. “ይሄ ሂደት ወደ ጠባብነትና ዘረኝነት የሚያመራ አደጋ እንደሚፈጥር ግልፅ ነው፡፡”
ኦሮሞ “ኦሮሞ ነኝ” ስላለ፥ ታሪኩን፣ ወጉን፣ ባህሉን፣ አመለካከቱን (mythology) ከፍ አድርጎ ስላነገበ እንዴት ወደ “ጠባብነት” ይመራዋል? እንዴትስ ወደ “ዘረኝነት” ይመራዋል? በማንነት መኩራት እንዴት ወደ “ጠባብነትና ዘረኛነት” ያመራል? ማንነትን በግልፅ ማንገብና መላበስ ጤ-ነ-ኝ-ነ-ት እንጂ “ጠባብነት” አይደለም። በዳበሩ ልቅ ዴሞክራሲያዊ አገሮች እንኳንስ የብሔር ማንነትን ማስተናገድ አይደለም … የጋብቻ መብትም ለተመሳሳይ ፆታ ይሰጥ ብለው የርሶ ምዕራባዊያን የርዕዮት ጓዶች በሚታገሉበት ወቅት (እርሶ ያንን ይደግፉሉ ማለቴ አይደለም፥ አላውቅምና)፥ እርሶ የብሔር ማንነት ግንባታ እንደ አደጋ ፈጣሪ ሲያመለክቱ አልገባኝም። ወይ ርዮቱ አልገባዎትም ወይ የጓዳ ትምክህተኛ ነዎት። እኔ እንዲያውም ልቅ ዴሞክራሲ አራማጆች የብሔር ማንነትን ግንባታ ከብሔር ድርጅቶች በላይ ልትንከባከቡት ይገባል ባይ ነኝ።
6. “አሁን እያየን ያለነው ይሄን ነው፡፡”
አሁን እያየን ያለነው ከመቶ አመታት በፊት የኦሮሞን መሬት በጉልበት ሲቀራመት ለኖረውንና ዛሬም ለቀጠለው ንጥቂያ ኦሮሞ ወጣቶች እምቢ ማለታቸውን ነው። እምቢተኝነቱ ከሌሎች እምቅ ብሶቶች ጋር ተደምሮ የማያባራ ታሪካዊ ሕዝባዊ ንቅናቄ Nov 12 ላይ ፈነዳ! ፍንዳታው በኢትዮጵያ ታሪክ ተከስቶ የማያቅ በ-ኦሮሞ፣ ለ-ኦሮሞ፣ ከ-ኦሮሞ የተከወነ ነው። ኦሮሞ ባንኗል። ይሄንን ታላቅ ሕዝብ ከእንቅልፉ እንደባነነ አንበሳ ጋሜውን አሻሽተን ማረጋጋት እንጂ “ጠባብ ዘረኛ” ማለቱ አደጋ ነው። ኸረ ሲያገሳስ ምን ሊሉ ይሆን?!
7. “አሁን እያየን ያለነው ሃገራዊ ራዕይ ሳይሆን አካባቢያዊ ሁኔታን ነው፡፡”
ኤዲያ! ፓለቲካ እኮ ሁልጊዜ አካባቢያዊ ነው። (Politics is always local) አገራዊ ሲሉ ለመሆኑ ኦሮሞ አድዋ ላይ ለኢትዮጵያ አጥንቱ መከመሩን ረስተዉት ነው? ለራሱ መብትና ጥቅም የሚታገል በሚሊዮን ሚቆጠሩ ቁቤ የቆጠሩ (‘ፊደል የቆጠሩ’ ካልኩ ኦሮሞ ወዳጆቼ አይለቁኝም) ብሩህ ኦሮሞ ወጣቶች የኦሮሞን ሕዝብ ጥቅም ለይተው በማወቃቸውና ለፓለቲካ ትግል አቅመ ዓዳምና ሄዋን መድረሳቸውን እያየን ያለነው። ይሄ አገራዊ ራዕይ ነው!!! ኦሮሞ ለመብቱ መሞቱ አገራዊ ራዕይ ነው! ቅድመ አያቶቹ አድዋ ላይ ሲሞቱ ብቻ ነው አገራዊ ራዕይ ሚባለውን? ኦሮሞ ለኦሮሚያ ጥቅም ሲሞትም አገራዊ ነው፤ ምክንያቱም ኢትዮጵያንና ኦሮሚያን ለይቶ ማየት እንዴት ይቻላል? አይቻልም።
8. “እኛ ብሎ “እነሱ” የሚባሉትን የሚጠላ ኃይል ነው እየተፈጠረ ያለው፡፡”
በመጀመሪያ ፓለቲካ ጥቅም ማስከበሪያ ሂደት ነው። ሌላው ጉዳይ ፓለቲካ አንገት ላይ የታሰረ ቃጭል ነው። ኦሮሞ ሁለቱን እጆቹን አንስቶ፥ ግንባሩ ላይ አድርጎ፥ ደሙን ማፍሰሱና ለጥቅሙ መሞቱ እንዴት በጥላቻ ይታያል? “እነሱ” ያሉትስ ወርቁና ሰሙ ምንድን ነው? የልቅ ዴሞክራዲ አቀንቃኝ ከሆኑ ድብቅ አቀራረብ አይመጥንዎትም። ግልፅ ይሁኑ።
9. “በኔ ሀብት ማንም ሊጠቀም አይገባም ብሎ የሚያምን ህብረተሰብ ነው እየተፈጠረ ያለው፡፡”
ስህተት! የተፈጠረው ‘የአያት ቅድመ አያቶቼ መሬትን ነጥቆ እኔን ኩሊ፣ ሚስቴን ኩሊ፣ ልጆቼን ስደተኛ፣ ሱሰኛ፣ የወሲብ ሰራተኛ ማድረግን አላምንም፣ አልቀበልም” የሚል ትውልድ ነው። ፓለቲካ ጥቅም ማስከበሪያ መንገድ ነው። ጥቅም፣ ጥቅም፣ ጥቅም! ሌላው ቃጭል ነው … ኪል ኪል ኪል። የኦሮሞ ወጣት ይኼ ገብቶታል። እርሶስ?
ከአክብሮት ጋር!
ያዬ አበበ
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live