Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

 ከአድዋ ድል ብቻ ሳይሆን ከክፉ ቀን ድልም እንማር!!  –ከ ይሁኔ አየለ

$
0
0

 

Adwavictoryድህነት ዋናው የምግብ ዋስትና አለመኖር ምክንያት ቢሆንም ብቸኛ ግን አይደለም፡፡ ሌላም ብዙ ምክንያቶች ይኖራሉ፡፡ አፍቅሮተ-ቁስ (Materialis) አንዱ ነው፡፡ አፍቅሮተ-ቁስ የሥነ-አዕምሮና የምግብ አጠቃቀም አጥኝዎች አልጠግብባይነት የሚል ፍች ይሰጡታል፡፡ ዳውሰን የተባሉ የመስኩ ተመራማሪ ሀብትን በመሰብሰብ የደስታ ምንጭና የስኬት መለኪያ ከዚያም አልፎ የመኖር ዋስትና አድረጎ መውሰድ በአፍቅሮተ- ነዋይ ለተለከፉ ሰዎች መለያ ባህርያት ናቸው ይላሉ፡፡

የስግብግብነት ምንጩ ብዙ ነው፡፡ ዋና ዋና የተባሉት፤ በህጻንነት በቂ መሰረታዊ ነገሮችን(በተለይ ምግብና ልብስ) አለማግኘት፣ የቤተሰብ መበታተን፣ ጥራት ያለው ጥምህረት አለማግኘት፣ በወጣትነት ጊዜ የሚከሰት የማንነት ችግር፣ የሕይወት አጋር ስለ አፍቅሮት ነዋይ ያለው ግንዛቤ፣ ወላጅና ሌላም ሊጨምር እንደሚችል አጥኝዎች የተስማሙበት ይመስላል፡፡ ስለ አልጠግብ ባይነት ይህን ካልሁ ወደ ዋናው አጀንዳ ልለፍ፡፡

 

በኢትዮጵያ ከ 1880- 1884 ዓ.ም (ለአምስት አመታት)  ክፉ አመታት ነበሩ፤ ይህ ጊዜ በህዝቡም ክፉ ቀን በመባል ይታወቃል፡፡ እነዚህ ዓመታት በተለያቱ የሀገሪቱ ክፈሎች ታላቅ ፍጅት አስከትለው አልፈዋል፡፡ አንድ ጸሐፊ ወደ አንድ ሶስተኛው የሀገሪቱ ህዝብ በረሃብና በተያያዥ ምክንቶሞች እንዳለቀ በመጽሐፋቸው አስፈረዋል፡፡ የችግሩ ሰለባ የሆኑ ሰዎች በወቅቱ የማይበሉ እንስሳትን ከመብላት አልፈው ሰውም እንደበሉ ተጽፎ አንብበናል፡፡

 

የዚያን ጊዜው የረኃቡ ምክንት ኢሊኖይስ አልነበረም፡፡ ምክንያቱ ፈረንጅ አመጣው ተብሎ በሚገመት የቀንድ ከብት በሽታ ባስከተለው የከብት እልቂት ነበር፡፡ ዋናው መንስኤ የከብቶች ማለቅ ቢሆንም አልጠግብ ባይነት (ስግብግብነትም) የራሱን ሚና ሳይጫወት አልቀረም፡፡ እስኪ በ 2002 ዓ.ም በታተመውና የኢትዮጵያ ታሪክ በአለቃ ተክለ ኢየሱስ፤ ሐተታ በዶክተር ሥርገው ገላው ከሚለው መጽሐፍ ከተጻፈው ሐተታ እንጨልፍ፤

ያን ወራት የሽዋ አራሽ ጉዛም እህሉን በጉርጓድ እየከተተ ለመንድሙ፣ ለእኅቱ፣ ለዘመዱ እህል አየነፈገ በገበያ እህል ታጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ዳግማዊ ምኒልክ በየጉዛሙ ቤት ወታደር ሰደደ፡፡ ለባለ እህሉ የአንድ አንድ ዓመት ቀለብ እየተወለት ትርፉን በደብዳቤ አግብቶ ተበድሮ ለድሀ ናኘው፡፡ ከዚህ በኋላ ወታደር ከሚዘርፍን ገበያ ብንሸጠው ያሻለናል እያለ ገበያ አወጣው፡፡ ያን ጊዜ እህል በገበያ ተረፈ፡፡

 

ይህ አንዱ የምንማረው የአጼ ምኒልክ የአመራር ጥበብ ይመስለኛል፡፡ ይህ እርምጃ የህዝቡን ሕይወት ያተረፈ፤ ስግብግቡንም ያልጎዳ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን ስኳር የደበቁ ስግብግቦች ይህን እድል ያገኙ አልመሰለኝም፡፡ ይህ ከዛሬ 120 ዓመት በፊት የሆነ ድርጊት ነው፡፡ ለስግብግቡ የአንድ አመት ቀለብ እየተወ ትርፉን በደብዳቤ አግብቶ ተበድሮ ለተቸገረው በነጻ ሰጠው፡፡ ሕይወትም አተረፈ፤ ገበያውንም አጠገበ፡፡ ለእኔ፤ ህዝባዊነት ማለት ይህ ነው፡፡

 

በዚሁ መጽሐፍ ላይ ሌላም ያስደነቀኝ ነገር ልጨምር፡፡ “ዳግማዊ ምኒልክም ለህዝቡ ትጋትና ትሕትና አስተማረ፡፡ መጥረቢያ አበጅቶ ካንቻ መታ፡፡ መቆፈሪያ አበጅቶ ዳገት ቆፈረ” ይላል፡፡ በወቅቱ የንጉሱን አርአያነት መበከትል ከከፍተኛ ሹማምነት እስከ ቤትሰራተኛው አይረባ ኩራቱን እየተወ መሬቱን አየመነጠረና እየቆፈረ ከረሃብና ከችግሩ ወጣ፡፡ ድህነቱን በስራው ድል መታው፡፡

 

በዚህ ወቅት ከንጉሱ ድርጊት የምንማረው አይኖር ይሆን? መቸ ይሆን ከልመና (ምጽዋት) የስነ ልቦና ጫና የምንወጣው?

 

The post  ከአድዋ ድል ብቻ ሳይሆን ከክፉ ቀን ድልም እንማር!!  – ከ ይሁኔ አየለ appeared first on Zehabesha Amharic.


ወግ ከርዕዮት አይበገሬዋ ጋር –ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የጸሐፊው ማስታወሻ፡ በኢትየጵያ ውስጥ የፕሬስ ነጻነት እንዲከበር ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ካለችው ከአይበገሬዋ ርዕዮት ዓለሙ አስደናቂ ታሪክ ጋር በተያያዘ መልኩ ለማቀርበው ተከታታይ ውይይት ይህ የመጀመሪያው ክፍል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዴሞክራሲ፣ በህግ የበላይነት፣ በሰብአዊ መብት ጥበቃ እና በተጠያቂነት ጠንካራ መሰረት ላይ ለምትገነባው በኢዲሲቷ ኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ልዩ የሆነ ጥረት በማድረግ ላይ ከሚገኙት በላስ ቬጋስ ከሚኖሩ ወጣት ኢትዮጵያውያን ጋር የሚደረግ ውይይት የሚቀርብበት ነው፡፡

ርዕዮትን እንዴት እንዳገኘኋት፣

Reeyot Eskedar pix 30ርዕዮት አሁን በህይወት በሌለው እና የአለቆች ሁሉ አለቃ በነበረው በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የግል ትዕዛዝ እ.ኤ.አ ሰኔ 2011 በቁጥጥር ስር ከዋለች እና ወደ ማጎሪያው እስር ቤት እንድትወረወር በተደረገችበት ጊዜ አቅልን በሚያሳጣ መልኩ እጅግ በጣም ተበሳጭቼ ነበር፣ ሆኖም ግን የተለመደው የዘረኛው ቡድን ሸፍጥ ስለነበር በሁኔታው እምብዛም አልተደነቅሁም ነበር፡፡ ስለእርሷ ማንነት ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ ስሟንም እንኳ በፍጹም ሰምቼ አላውቅም ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2005 በኢትዮጵያ ተድርጎ የነበረውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ውዝግብ እርሱን እንደ መልዓክ የማያመልኩትን እና የማይኮፍሱትን እያንዳንዱን ጋዜጠኛ እንደ አበደ ውሻ እየሮጠ እና እየተክለፈለፈ መንከስ ጀመረ፡፡ የእኔ ግላዊ መርህ በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ እና በእርሱ ዘ-ህወሀት ጥቃት የሚደርስበትን ማንኛውንም ጋዜጠኛ መከላከል ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ነው ርዕዮትን ለማግኘት የቻልኩት፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ለይስሙላው ፓርላማ ተብየው ርዕዮት በዓለም የመጀመሪያ ደረጃን የያዘች እና ስሙ በማይታወቅ ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን እና የኢትዮጵያ ጎረቤት በሆነችው በኤርትራ ድጋፍ አማካይነት መሰረተ ልማቶችን፣ የቴሌኮሙኒኬሽን እና የኃይል መስመሮችን ለማውደም ዕቅድ ነድፋ ስትንቀሳቀስ የነበረች አሸባሪ ናት በማለት የእዩልኝ እመኑልኝ ንግግሩን ካደረገ በኋላ የርዕዮት ቁጥር አንድ አድናቂ እና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሀሳብ ዳኝነት ፍርድ ቤት ፊት በመቆም ለእርሷ እራሴን ጠበቃ አድርጌ ቆምኩ፡፡ ዓይኑን በጨው አጥቦ በድርቅና እንዲህ አለ፣ “ርዕዮት የአሸባሪዎች ተላላኪ ናት“  ወዘተ፣ ወዘተ ወዘተ…

በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ውንጀላ ላይ ከት ብዬ ሳቅሁ፣ ምክንያቱም የእርሱ መሰረተቢስ ውንጀላዎች የሚያስቁ ብቻ አልነበሩም ሆኖም ግን ከምንም ጥርጣሬ በላይ ተራ ቅጥፈት እና ነጭ ውሸት ነበሩና፡፡

አምባገነኑ መለስ ውንጀላውን እየሰጠ በነበረበት ጊዜ የዘህወሀት (የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድንስብስብ) አገዛዝ የቴሌኮሙኒኬሽን ተቋማትን በእርግጠኝነት አውድሞ ነበር፡፡

አሌክሳንደር ግራህም ቤል በመሳሪያ የድምጽ ግንኙት መሳርያ ከፈጠሩ በኋላ ንጉስ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የቴሌፎን እና የቴሌግራፍ አገልግሎትን እ.ኤ.አ በ1889 በአፍሪካ አህጉር ያስተዋወቁ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ መሆናቸው የታሪክ እውነታ ነው፡፡ በጭንቀት ላይ የነበሩት መኳንንቶቻቸውና ቀሳዉስት ይህ የሰይጣን ስራ ነው እናም መወገድ አለበት በማለት ለዳግማዊ አጼ ምኒልክ በነገሯቸው ጊዜ አጼ ምኒልክ ይህንን ለስልጣኔ ጸር የሆነውን አባባል ወደ ጎን በመጣል የኢትዮጵያን የቴሌኮሙኒኬሽን መሰረተ ልማት ግንባታ በቆራጥነት አስጀመሩ፡፡ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በስራ ላይ ማዋል በአውሮፓ ኃያላን ላይ እንደ ሀገር ጠንካራ ሆነን ለመኖር የሚያስችለን እና የተማሩ ሰዎችን ለማግኘት ያለንን ፍላጎት የሚያሳካልን ነው በማለት አጽንኦ ሰጥተው ተንቀሳቅሰዋል፡፡

ከ127 ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ በ2016 ኢትዮጵያ ከዓለም በአስከፊነቱ የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘ የቴሌኮሙኒኬሽን መሰረተ ልማትን ይዛ ትገኛለች፡፡

ሁሉም ነገሮች በዚያው ይቀጥላሉ ብለን ብናስብ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ1889 የነበረችበት የቴሌኮሙኒኬሽን መሰረተ ልማት ግንባታ አሁን በ2016 ካለበት ሁኔታ የተሻለ ነበር ማለት አስደናቂ ሊሆን አይችልምን? ምን ዓይነት የወረደ እና አሳፋሪ ነገር ነው እባካችሁ! ይኸ ጉዳይ‘ወደ ታች ነው እንጅ ውኃ አወራረዱ ሽቅብ ሽቅብ አለኝ እኔንስ ለጉዱ’ ማለት አይደለምን?

እ.ኤ.አ በ2013 ፍሪደም ሀውስ/Freedom House የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “እጅግ በጣም አናሳ የሆነ የመሰረተ ልማትን በመያዝ፣ መንግስት የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፉን በብቸኝነት ጠቅልሎ በያዘበት ሁኔታ እና ችግር ፈጣሪ የቴሌኮም ፖሊሲዎች እየተነደፉ በስራ ላይ እየዋሉ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ በኢንተርኔት እና በተንቀሳቃሽ ስልክ አጠቃቀም መጣኔ መስፈርት ከዓለም በመጨረሻው ደረጃ ላይ ከሚገኙ ሀገሮች አንደኛዋ ሆና ትገኛለች…“

እ.ኤ.አ በ2014 ዎል ስትሬት ጆርናል/Wall Street Journal የተባለው መጽሄት የኢትዮጵያ ገበሬዎች የተንቀሳቃሽ ስልኮች ያሏቸው ቢሆንም ትልቁ ችግር የተሻለ የግንኙነት መስመር ለማግኘት በርካታ ኪሎ ማይሎችን መጓዝ ይኖርባቸዋል በማለት ዘግቧል፡፡ ኢትዮጵያ በኢንተርኔት አጠቃቀም አስከፊነት ከአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ እንደ ፍሪደም ሀውስ ዘገባ ከሆነ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በኩል በ450 ማይሎች ርቀት ላይ የምትገኘው ኬንያ በኢንተርኔት አጠቃቀም ፍጥነት እ.ኤ.አ በ2012 ከጋና ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች በማለት ዘግቧል፡፡ እ.ኤ.አ በ2016 የኬንያ የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ እድገት “ምንም ዓይነት የቴክኖሎጂ እድገት ያልተጓደለበት ምሉዕ“ እየተባለ ይጠቀሳል፡፡

እንግዲህ እንደዚህ ያለውን እና በአፍሪካ በአስከፊነቱ የሚታወቀውን የቴሌኮሙኒኬሽን ስርዓትን ነው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ርዕዮት ልታወድመው ዕቅድ ነድፋ ተነስታለች በማለት ውንጀላ ያቀረበው! አዬ ጉድ! መለስ “ባለራዕይው መሪ”!

ያም ሆነ ይህ የርዕዮትን በቁጥጥር ስር መዋል ተከትሎ በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት (አንዳንድ ጊዜ ቃሊቲ የማጎሪያ እስር ቤት እየተባለ በሚጠቀሰው) ስለእርሷ ሁኔታ የተሟላ መረጃ ይደርሰኝ እንደነበር በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡

በዚህ ተከታታይነት ባለው ውይይት ላይ የርዕዮትን ወይም ደግሞ የእርሷን ልዩ ወላጆች (ርዕዮትን እና እህቷን እስከዳርን የሰጡንን ወላጆች ልዑል አምላክ ይባርካቸውና) ታሪክ ለመዘገብ አይደለም ዋናው ትኩረቴ፡፡ ሆኖም ግን የርዕዮት ጽናት ያለው እውነታ፣ ድፍረት፣ አርበኝነት፣ መስዋዕትነት፣ ክብረ ሞገስ፣ ታማኝነት፣ የሞራል ልዕልና እና ሰብአዊነት ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ለነጻነት የሚያነቃቃ እና ለእምነታቸው በጽናት እንዲቆሙ የሚያደርግ በፍቅር የተሞላ ተስፋ ፍንትው እና ወለል ብሎ ስለሚታየኝ ነው፡፡ በእርግጠኝነት እርሷ እኔን የበለጠ እንድነሳሳ አድርጋኛለች፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ውይይቴን ከርዕዮት ታሪክ ጋር እቀጥላለሁ፣ ስለሆነም በእርሷ ላይ የተፈጸመውን ሰብአዊ ወንጀል እና በሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰብአዊ ወንጀል የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በእርሷ መነጽር ለማየት እንዲችል በማሰብ ነው፡፡ በርዕዮት ላይ የተፈጸመው ሰብአዊ ወንጀል ሁሉ በእያንዳንዱ የፖለቲካ እስረኛ ኢትዮጵያዊ ላይ ይፈጸማል፡፡ ርዕዮት እራሷን በዘ-ህወሀት ሰብአዊ ወንጀል የተፈጸመባት አንድ ልዩ የጥቃት ሰለባ አድርጋ አትቆጥርም፡፡ ይልቁንም በዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ ዘብጥያ ተጥለው ከሚገኙ በብዙ ሺዎች ከሚቆጠሩ ከታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች መካከል እራሷን አንዷ አድርጋ ታቀርባለች፡፡ የእርሷ ትግል ለእርሷ ነጻነት አይደለም፣ የእርሷ ትግል ይልቁንም ከጎሳ፣ ከኃይማኖት፣ ከቋንቋ፣ ከክልላዊነት እና መንደርተኝነት፣ ከጾታ፣ ወዘተ የጸዳ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ነጻነት ማቀዳጀት ነው፡፡

ርዕዮትን መግለጽ እንዲህ ቀላል ነገር አይደለም፡፡

ርዕዮት በበርካታ መንገድ ከህይወት ተምሳሌት በላይ ናት፡፡ ገና የ31 ዓመት እድሜ እንደነበራት አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ወደ ማጎሪያው እስር ቤት ወረወራት፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በግንባር በአካል ባገኘኋት ጊዜ ሳስበው ከነበረው እና ከምንም ነገር በላይ ሆና ነው ያገኘኋት፡፡

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ስለእርሷ ጉዳይ ለይስሙላው ፓርላማ እዩልኝ እመኑልኝ የውንጀላ ዲስኩር ባቀረበበት ጊዜ አንድ አስፈሪ የሆነ ሰው፣ እሳት የሚተነፍስ፣ አስፈሪ እና የፍሀት ማዕበልን የሚረጭ ነገር እንደገጠመው ነበር የጠበቅሁት፡፡ አስፈሪውን ተምሳሌት እንደሚጋፈጥ ነበር የጠበቅሁት፡፡ (ምናልባትም አስፈሪ የሚለውን ቃል በዚህ ጽሁፍ ማቅረብ ስህተት ሊሆን ይችላል)፡፡

ርዕዮት ባለ ትንሽጠርዝ ወጣት ሴት ናት፡፡

ገና በመጀመሪያ ዓይን ለዓይን በተገናኘንበት ጊዜ ለእርሷ ያቀረብኳቸው ቃላት እንዲህ የሚሉ ነበሩ፣ “አንች ርዕዮት ነሽን?! ምንም አታስፈሪም!“ በሳቅ ፈነዳች፡፡

በእርግጥ እየቀለድኩ አይደለም፡፡ በእርግጥ ቃላትን በስሜታዊነት እየወረወርኩ ነው፡፡

የእርሷ ቀለል ሆኖ የመቅረብ ሁኔታ ርዕዮትን ለመግለጽ ከባድ አድርጎታል፡፡

ርዕዮት ልክ እንደ አልማዝ ናት፡፡ ፊለፊት ሲመለከቷት ታንጸባርቃለች፣ እናም የብርሀን ፍንጣቂ ትረጫለች፡፡

ከእርሷ ጋር ለጥቂት ደቂቃዎች መነጋገር መቻል ማለት ሌላውን የአልማዝነቷን ጥራት መመልከት ማለት ነው፡፡ የአረብ ብረት ነርቭ የተጎናጸፈች፣ አንጸባራቂ የብረት የማድረግ ኃይል ያላት እና የሲልቨር ብረት ጽናትን የተላበሰች አይበገሬ ጀግኒት ናት፡፡

ርዕዮት ግልጽ የሆነ እና ወገናዊ ፍቅርን የተላበሰ ስብዕና ያላት ጀግኒት ናት፡፡ እንዲህ የሚለውን የህይወቷን ተልዕኮ ሚስጥር አድርጋ አትይዘውም፣ “እኔ በኢትዮጵያ ለነጻነት እና ለዴሞክራሲ ካልቆምኩ ሌላ ማን ሊያደርገው ይችላል?“

እኔ ለእራሴ እንዲህ በማለት አጉረመረምኩ፣ “ወይ ጉድ!!! አምላኬ! መለስ ዜናዊ እና የእርሱ ወሮበላ የዘራፊዎች ስብስብ ምንድን አይነት ሰው የፈጠሩት!?“

(ወደ ኋላ መለስ ብዬ ስመለከት በእያንዳንዷ ቀን ለአስር ዓመታት ያህል ለመሳሳይ ጥያቄ በጽናት በመቆም ስታገል ቆይቻለሁ በማለት መናገር እችላለሁ፡፡ ስለሆነም የርዕዮትን የህይወት ተልዕኮ ለመገንዘብ ችግር አይኖርብኝም፡፡ በእርግጥ የእኔን ትንሽ ጥረቶች ከርዕዮት መስዋዕትነት ወይም ከእርሷ ወሰን ከሌለው ድፍረቷ ጋር ላነጻጽረው አልችልም፡፡)

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ርዕዮትን ወደ ማጎሪያው እስር ቤት ከመወርወሩ በፊት አንድ ተራ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርት፣ ጋዜጠኛ እና በየሳምንቱ እየታተመ የሚወጣው የፍትህ ጋዜጣ ዓምድ ጸሀፊ ነበረች፡፡ (የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው አይበገሬው ተመስገን ደሳለኝ በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር ቤት ታስሮ ይገኛል፡፡)

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ አንዷን ተራ መምህርት እና ጋዜጠኛ አምባገነናዊ እና ጨቋኝ ስርዓትን ወደምትገዳደር እና ወደምትፋለም ደፋር ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነጻነት ታጋይነት አሸጋገራት፡፡

አውነት እላችህዋለሁ፡ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ርዕዮት እንድትፈጠር ስላደረገ አመሰግነዋለሁ፣ ምክንያቱም እንደ አረብ ብረት በጠነከረው ጽናታቸው፣ በአይበገሬው ድፍረታቸው እና በመርህ ላይ በተመሰረተው ትግላቸው የኢትዮጵያ ወጣቶች አስከፊው የጭቆና አገዛዝ ከጉልበታቸው ስር ወድቆ እንዲማጸን የሚያስችላቸው ሁኔታ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡

ሆኖም ግን ስለአምባገነኑ መለስ ዜናዊ በአእምሮዬ ጭንቅላት ውስጥ እየተብላላ ያለ አንድ ጥያቄ አለ፡፡ እርሱም፣ “በእርግጥ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ርዕዮት አሸባሪ ሆና እስከ አፍንጫዋ ቦምብ ታጥቃ የቴሌኮሙኒኬሽን መሰረተ ልማትን ዒላማ በማድረግ ለማውደም ከወዲያ ወዲህ በማለት ስትቅበዘበዝ ነበር ብሎ በእርግጠኝነት ያምናልን?“ ያንን የሚያምን ከሆነ የምስክር ወረቀት የተሰጠው የአዕምሮ በሽተኛ ነው ወይም ደግሞ የለየለት ቦቅቧቃ ፈሪ አለያም ሁለቱን ነው፡፡

ስለበርካታ ጉዳዮች ለሰዓታት ተነጋገርን፡፡ ውይይቶቻችን ሙሉ በሙሉ ነጻነትን የተላበሱ ነበሩ፡፡ የወጣት አፈታሪኮች እንደሚሉት “በጥሩ ሁኔታ አወጋን፡“

ስለዘ-ህወሀት ዕንጭጫዊ አጭበርባሪነት፣ ስለድድብናቸው እና ባዶነታቸው፣ ስለድንቁርናቸው እና እብሪታቸው፣ ስለአቅመቢስነታቸው እና ስለጨካኝነታቸው፣ ስለጥላቻቸው እና ጥልቅ ጥላቻቸው፣ ስለአውሬነታቸው እና ኢሰብአዊነታቸው፣ ስለዘራፈ ወሮበላነታቸው እና እርባናቢስ ባህሪያቸው፣ ስለቅጥፈታቸው፣ ስለአታላይነታቸው እና ስለመረጃ አፋላሽነታቸው፣ ስለሙሰኛነታቸው፣ ስለአድሏዊ እና ወገንተኝነታቸው በስፋት እያነሳን በቆየንባቸው ጊዚያት በሙሉ ሳቅን፡፡ ሳቅን፣ እናም እንደገና ሳቅን…

ሪዮትን ለማግኘት ሲሄድ ሃሳቤ በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ ሆና ሲደርስባት የነበረውን ኢሰብአዊ ወንጀል ለማስተዛዘን ነበር::  ስለእርሷ እስራት እና ስለሌላውም ነገር ሁሉ የሆድ ቁርጠት እና የእራስ ምታት ይሆንበኝ እንደነበር ልነግራት እንደምፈልግ ነገርኳት፡፡

በመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ ሆና እንዴት እንዳሳለፈችው እንድትነግረኝ እየተዘጋጀሁ ባለሁበት ሁኔታ ከመቅጽበት ሳቋን ለቀቀችው፡፡ ተደናገርኩ፡፡

ይልቁንም ለአራት ዓመታት በእስር ቤት ውስጥ በማማቀቅ መንፈሳዊ ጥንካሬዋን ለመስበር ሲያደርጉት በነበረው ያልተሳካ ሙከራ የሆድ ቁርጠት እና የእራስ ምታት የሆነባቸው የእራሱ የዘ-ህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አባላት ናቸው፡፡ ምናልባትም ለእነርሱ ላዝንላቸው እችላለሁን?

ልንገራችሁ ርዕዮት በጣም ቧልት ታውቃለች ፡፡

ያም ሆነ ይህ ዘ-ህወሀት በእርሷ ላይ ምን እንደሰራ እንድትነግረኝ ጠይቂያት ስለዘ-ህወሀት ያለውን ሁሉ ኢሰብአዊ ወንጀል አንድ በአንድ ልቅም አድርጋ ከነገረችኝ በኋላ ሆድን በሚያፈርስ ሳቅ ከት ብላ ስቃ ደመደመችው፡፡ እነዚህ ሰዎች ዉነት የሚአሰብ አምሮ አላቸው ብዬ ራሴን ጠየኩ::

አንደዚያ ዘህዋሃት ላይ ስንስቅ ርዕዮት የመለስ ዜናዊ እስር ቤት ተደላደላ ትኖር ነበር ማለቴ አይደለም:: ርዕዮት የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ሰለባ የነበረች ስለሆነ ጠንካራ የሆነ ስሜታዊነት አይንጸባረቅባትም እያልኩ አይደለም፡፡ ርዕዮት እኔ በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ ተሰቃይታለች፡፡

እጅግ በጣም አስፈሪ የሆኑ ገጠመኞችን አሳልፋለች፡፡

ለምሳሌ በስም ሀሳን ሽፋ  የሚባል አፈ ጤቀኛ ወሮበላ ዘራፊ የፖሊስ ኮሚሽነር ተብዬው ለመናገር የሚዘገንን፣ አስፈሪ እና እንደተራራ የተቆለለ የስድብ ናዳ ያወረደባትን ስታስብ በጥልቅ ታዝናለች፡፡

ያን ስሰማ እንዲህ በማለት ልነግራት ፈለግሁ፣ “ወሮበላ ዘራፊዎችን ከጫካ በማስወጣት እርካሽ ልብስ በማልበስ የባለስልጣን ስም መስጠት ይቻላል፣ ሆኖም ግን ጫካውን ከወሮበሎች ውስጥ ነጥሎ ማውጣት በፍፁም አይቻልም፡፡ ወሮበላ ዘራፊ ምንጊዜም ዘራፊ ነውና፡፡“ ይህንን በሚገባ ታውቀዋለች፣ መድገም ለምን አስፈለገ!

ርዕዮት በዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር ቤት በወሮበሎች በየዕለቱ ይደርስባት በነበረው ማሸማቀቅ እና ዘለፋ ሁልጊዜ ትበሳጭ ነበር፡፡

ርዕዮት በዘ-ህወሀት የማጎሪያ እስር ቤት በመታሰሯ ምክንያት በእናቷ፣ በአባቷ እና በእህቷ ይደርስ በነበረው ሊነገር በማይችለው ስቃይ እጅግ በጣም ታዝን ነበር፡፡

ርዕዮት እህቷ እስከዳር በዘ-ህወሀት ወሮበሎች ኃላፊነት በጎደለው መልኩ በተደበደበችበት እና በእራስ ቅሏ ላይ በደረሰው ስብራት ምንክንያት ለአንድ ሳምንት ጊዜ ሆስፒታል ስትታከም መቆየቷን ባወቅች ጊዜ ከቁጥጥሯ ውጭ በሆነ መልኩ አልቅሳለች፡፡

ርዕዮት በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በምትሰቃይበት ወቅት ቤተቦቿ በሙሉ መለስ ዜናዊ በፈጠረው እና በኢትዮጵያ ክፍት የሆነ እስር ቤት እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት ውስጥ ይሰቃዩ እንደነበር የምታውቀው ጉዳይ ነው፡፡

ርዕዮት ለዘ-ህወሀት ተባባሪ እንድትሆን እና ሌሎችንም በመወንጀል ተባባሪ እንድትሆን ተጠይቃ ፈቃደኛ ባለመሆኗ ምክንያት የጡት ካንሰር ኦፕሬሽን ክትትሉን እንዳታደርግ ተከልክላ በነበረበት ወቅት ተስፋ ቆርጣ ነበር፡፡ ህይወትን በሚፈታተን አደገኛ ቁስል ትጨነቅ ነበር፡፡

ርዕዮት በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ የስነ ልቦና ዶክተር ነኝ የሚለው ደደብ በስም ዶ/ር ዓለሙ የሚባል የእርሷ ችግር የጡት ካንሰር ሳይሆን የስነ ልቦና ችግር ነው በማለት ሲነግራት ጆሮዋን አላመነችውም ነበር፡፡ ዓለሙ ከጡት ጋር በተያያዘ መልኩ ለሚመጡ በሽታዎች ባለሙያ ነኝ በማለት ከነገራት በኋላ የህክምና ስነምግባሩ ከሚፈቅደው ውጭ ጡቷን ይነካካ ይጫን ነበር፡፡ የዓለሙ የህክምና ውጤት እንዲህ የሚል ነበር፡ ርዕዮት እየተሰቃየች ያለችው በመንፈስ ጭንቀት ነው፡፡ ያ እርባናቢስ የሆነው ዶ/ር ተብዬው ዓለሙ የእርሷ ችግር ያለው ከጭንቅላቷ ነው በማለት ነገራት፡፡ ምንም ዓይነት የጡት ካንሰር የለባትም! አለ፡፡ ባለሙያ አሰዳቢ !

ርዕዮት ሀሰን ሽፋ እና ሌላው በስም ለይኩ ገብረ እግዚአብሔር በሚባል ወሮበላ ዘራፊ የዓቃቤ ሕግ ኃላፊ በሁለት በተለያዩ አጋጣሚዎች በኤሊያስ ክፍሌ ላይ የሀሰት ምስክርነት እንድትሰጥ ያለዚያ ከሞት ቅጣት እንደማታመልጥ ሲዝትባት በነበረው ሰው መሳይ ሰይጣን ላይ በጥልቅ አዝና ነበር፡፡

ሀሰን ሽፋ እና ለይኩ ገብረእግዚአብሔር ሁለቱም የሞት ቅጣት ባይፈጸምባትም እንኳ ያለምንም ጥርጥር የእድሜ ልክ እስራት ይበየንባት እንደነበር ያስፈራሯት ነበር፡፡ እድሜዋ ስንት እንደሆነ እና ከእስር ቤት ስትወጣ ስንት ሊሆናት እንደሚችል የቁጥር ስሌት ሲሰሩ ነበር፡፡ ከእስር ቤት የምትወጣበት ጊዜ 20 ወይም 25 ዓመታት እንደሚሆኑ ነግረዋት ነበር፡፡ ከዚያ ጊዜም በኋላ ጋብቻ ልትፈጽም እንደማትችል፣ ልጆች እንደማይኖሯት እና ምንም ዓይነት ሙያ እንደማይኖራት ነግረዋት ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ እርሷ ምንም ነገር እንዳልሆነች ዋጋ እንደሌላት አድርገው ነግረዋት ነበር፡፡

ርዕዮት እራሷን በማረጋጋት ቆየች፡፡ የዘ-ህወሀት ፕሬዚዳንት የሞት ቅጣትን መፈረም እንደማይወድ የሰማች መሆኗን ነገረችው፡፡ ሆኖም ግን የሞት ቅጣቱን የሚፈርመው ከሆነ ርዕዮት ለወሮበላ ዘራፊው እንዲህ በማለት ነገረችው፡ “ያ ምንም ዓይነት ችግር የለውም፡፡“

እንዴ? ምን አይነት አነጋገር ነው!?  (ችግር የለም? በጣም ችግር አለ አንጂ ብዬ ከራሴ ተሟገትኩ::)

አዎ፣ ርዕዮት በዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊ ፊት በመቅረብ የሞት ቅጣቱ ለእርሷ ምንም ዓይነት ችግር የሌለው መሆኑን ነግራዋለች!

ወይ ርዕዮት! የእኔ! የእኔ፣ የእኔ ርዕዮት!!!

ለዚህም ነው እርሷን አይበገሬዋ (የማትንበረከከዋ ርዕዮት) ርዕዮት እያልኩ የምጠራት፡፡

የዘ-ህወሀትን ሰይጣን ዓይኖች ተመለከተች እና እንዲህ በማለት ነገረችው፣ “አሁን ልትገለኝ ተችላለሀ፣ ሆኖም ግን ገሀነም አስድጄ አስገባሃለሁ!“

ወሮበላ ዘራፊው ጭንቅላቱን ተመታ፡፡ እንደተቆጣ ግመር ዝንጀሮ የሚይዝ የሚጨብጠውን አጣ፡፡ ሆኖም ግን ርዕዮት ከዓላማዋ ስንዝር ያህል ፍንክች አላለችም፡፡ ስለዚሁ ጉዳይ እንድታስብበት የሶስት ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ሰጣት፡፡ ከዚያ በኋላ ተመልሳ በመሄድ ለዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ሁሉ ምላሽ ለማግኘት ሲጠባበቁ እንዲህ አለቻቸው፡ መልሴን  ለማግኘት ቀጥታ ገሀነም ሂዱ አለቻቸው ፡፡

ስለርዕዮት በርካታ አስደማሚ የሆኑ ነገሮች አሉ፡፡ እናም በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ ሲፈጸሙ የቆዩትን ተሞክሮዎች በተከታታይ በማቀርባቸው ጽሁፎች የሚዳሰሱ ይሆናል፡፡ የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ምን ያህል ጨካኞች እና ኢሰብአዊ ፍጡር እንደሆኑ ለመናገር ከማሰብ አድማሳችን ውጭ ነው፡፡ እንዴት የሰው ዘር የሆኑ ሰዎችሰይጣንን ይሆናሉ? (በዘ-ህወሀት ባንዲራ መካከል ላይ ያለውን የኮከብ ምስል (የጨለማውን ልዑል የሚከተሉትን ዓለም አቀፍ ምስሎች) ናቸው አላልኩም፡፡)

ዘ-ህወሀት ርዕዮትን በብቻ እስር ቤት ውስጥ ለማጎር የተለየ መሰረት የሌለው ትንሽ የቆርቆሮ እስር ቤት ገነባ፡፡ ርዕዮት የምትናገረውን እና የምታደርገውን ሁሉ በየዕለቱ ዘገባ የሚያቀርቡ በዚያ መሰረት በሌለው እስር ቤት ውስጥ ከሶስት ሰላዮች ጋር እንድትቀመጥ አደረጉ፡፡

ለምንድነው ከላይ እስከታች ያሉት የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች፣ ሲቪሎች፣ ወታደሮች፣ ፖሊስ ሁሉም በርዕዮት ፍርሀት ያደረባቸው?

ሆኖም ግን አንድ ነገር አለ፣ አንድ ነገር እንደ መብረቅ የሚመታኝ፡፡ ርዕዮትን እንዲህ ልዩ እንድትሆን የሚያደርጋት አንድ ነገር አለ፡፡

ለበርካታ ሰዓት ተቀምጠን ውይይት ባደረግንበት ጊዜ በዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ላይ ምንም ዓይነት የጥላቻ፣ የፍርሀት እና የጥልቅ ጥላቻ ምልክት አላሳየችም፡፡

ፈፅሞ ሊገባኝ አልቻለም ፡፡ እንደዚያ ያለ ኢሰብአዊነት ድርጊት የተፈጸመበት፣ የተዋረደ ከህግ አግባብ ውጭ የተያዘ እና በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ውስጥ የተዋረደ ሰው እንዴት እንደዚህ ያለ ጨዋ እና የመርህ ሰው ለመሆን የመቻል ነገር የሚያስደንቅ ነገር ነው፡፡

ዘ-ህወሀት ርዕዮትን በቁጥጥር ስር ባዋላት ጊዜ ምን ዓይነት ሰውን እያስተናገዱ እንደነበር ምንም ዓይነት ሀሳብ አልነበራቸውም፡፡ ርዕዮት የእርሷ ሙያ የሆነው ጋዜጠኝነት ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ ዉጤት በሚገባ ተገንዝባ የገባችበት ነበር፡፡ አንድ ቀን በቁጥጥር ስር ውላ ወደማጎሪያው እስር ቤት እንደምትጣል ለአዕምሮዋ ምንም ዓይነት ጥያቄ እንደሌለው ታውቅ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ሰኔ 21/2012 የሆነው ታላቁ አስደናቂ የሆነባት ነገር ያ አንድ ቀን እየተባለ ይታሰብ የነበረው በጣም በተፋጠነ መልኩ የመድረሱ ሁኔታ ነው፡፡

የእርሷ አመለካከት ኢትዮጵያ በጥላቻ ነጻ ልትሆን አትችልም የሚል ነው፡፡ በጥላቻ ምንም ዓይነት የወደፊት ህይወት ሊኖር አይችልም፡፡ ሰይጣናዊውን ድርጊት ጥሉ እንጅ ሰውን አትጥሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ አመለካከት በአብዛኛው በተራው ህዝብ ዘንድ ሊተገበር የማይችል እና ጥላቻን ኃይማኖታቸው ባደረጉ የሚፈጸም አስቸጋሪ የሆነ ነገር ነው፡፡

ኔልሰን ማንዴላ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ጥላቻ ማለት መርዝን እንደመጠጣት እና ጠላቶቼን ይገድልልኛል ብሎ ተስፋ እንደማድረግ ያህል ነው፡፡“

በመካከለኛ አድሜዬ ላይ የበለጠ ተጠራጣሪ ሆኛለሁ፡፡ “ለወያኔ ወሮበላ ዘራፊዎች አዝናለሁ፡፡ ወሮበላ ዘራፊዎች ሁልጊዜ ያው ወሮበላ ዘራፊዎች ናቸው፡፡ ዥንጉርጉር የሆነው ጅብ የቆዳ ቀለሙን ሊቀይር ይችላልን?“ይህ ነው ዘህውሃት ማለት ::

በሲኦል ገሀነም ውስጥ ቆይታ የወጣችው ርዕዮት ዓለሙ በሰይጣኖቹ ላይ ጥላቻ ሳይኖርባት በሰይጣዊ ድርጊቱ ላይ ብቻ መዝመት እንደሚያስፈልግ በጽናት እቆማለሁ በማለቷ ኩራት ይሰማኛል፡፡ ሆኖም አስተሳሰቧ ይደንቀኛል::

እንግዲህ ለሰዓታት ያወጋህዋት ርዕዮት ማለት ይህች ናት፡፡ በፈገግታ የተሞላች እና አዲሲቷን ኢትዮጵያ የምታልም ህልመኛ፡፡

ከርዕዮት ጋር ከተነጋገርን በኋላ ከምንጊዜውም በላይ ኢትዮጵያ ተስፋ ያላት  ሀገር እንደሆነች እና የተሻለ ጊዜ እየመጣ እንደሆነ እንዲሁም የኢትዮጵያ ወጣቶች ለዓላማው ስኬታማነት በጽናት መታገል እንዳለባቸው ግንዛቤ ወስጃለሁ!

በዘህወሀት ገሀነም ውስጥ ተጋድሎ በማድረግ በድል አድራጊነት የወጣች ወጣት ሴት፣

በገሀነም ውስጥ ገብተው ሳይጎዱ፣ ሳይቃጠሉ ሳይነዱ ሳይፈርሙ፣ ምንም ዓይነት ችግር ሳያጋጥማቸው የሚወጡ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው!

በገሀነም ውስጥ ገብተው ሰይጣኑ ላይ ተፍተው ከዚያም ወጥተው ታሪካቸውን የሚናገሩ በጣም ጥቂት ሰዎቸ ብቻ ናቸው፡፡

ከሁሉም በላይ ታላቁ ኔልሰን ማንዴላ አንዱ ሰው ነበሩ፡፡

ማንዴላ ለ27 ዓመታት ያህል የአፓርታይድን ሰይጣን ፊት ለፊት በመጋፈጥ በእያንዳንዷ ዕለት ወደ ገሀነም እንዲሄዱ ይነግሯቸው ነበር፡፡

ማንዴላ ከቨረስቴር እስር ቤት የገሀነም በር ሲደርሱ እና የመጨረሻዎቹን 14 ወራት የእስራት ዘመናቸውን አጠናቅቀው እ.ኤ.አ የካቲት 11/1990 ሲደርሱ ፈገግታ ይነበብባቸው ነበር፡፡

በኋላ ላይ ማንዴላ እንዲህ ነበር ያሉት፣ “ነጻነቴን ወደሚያስገኘው ወደ ዋናው የመውጫ በር እየተጠጋሁ በሄድኩ ጊዜ ቀደም ሲል የነበረኝን ምሬት እና ጥላቻ እዚያው ውስጥ ጥየው የማልወጣ ከሆነ እዚያው እስር ቤቱ ውስጥ መቆየት እንዳለብኝ አውቃለሁ፡፡

ማንዴላ በመሬት ላይ ለ27 ዓመታት በገሀነም ውስጥ አስገብተው ስቃይ ሲያሳዩአቸው ለቆዩት ጠላቶቻቸው ይቅርታ ማድረጋቸው ታላቅ ሰው መሆን አለባቸው ብለው ለነገሯቸው ሰዎች ቀስ ብለው በመሳቅ እንዲህ ነበር ያሉት፣ “እኔ መልዓክ አይደለሁም፣ መልዓክ እንደሆንኩ አድርጋችሁ የምታስቡኝ እስካልሆነ ድረስ ደግሜ ደጋግሜ በመሞከር ላይ ያለሁ ኃጢያተኛ ሰው ነኝ፡፡“

ማንዴላ በእራሳቸው ጨዋታ የአፓርታይድን ሰይጣን በድል አድራጊነት ተወጡት! ለመውደድ ተማር፣ ለጥላቻ አትማር በሚሉት በማንዴላ መርሆዎች፣ “በቆዳ ቀለሙ ልዩነት፣ ወይም ደግሞ በታሪካዊ አመጣጡ ወይም ደግሞ በሚከተለው ኃይማት ምክንያት ማንም ሰው ቢሆን ሌላውን ሰው ለመጥላት አልተወለደም፡፡ ህዝቦች ለመጥላት መማር አለባቸው፣ እናም ለመጥላት የሚማሩ ከሆነ ፍቅርንም መማር ይችላሉ፣ ፍቅር በተፈጥሮ በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ከተቃቀራኒው ይልቅ ቀድሞ ይመጣልና፡፡“

ወጣቷ ኢትዮጵያዊት የፕሬስ ነጻነት ቀንዲል ርዕዮት ዓለሙ የዘመናዊውን የጥቁር ህዝቦች የዘ-ህወሀት ቀንዳም አፓርቲድ  ሰይጣን ለ1500 ቀናት እና ሌሊቶች ያህል ፊት ለፊት ተጋፍጣ ከቆየች በኋላ እርሱ እራሱ ወደ ገሀነም፣ ገሀነም፣ ገሀነም እንዲገባ በግልጽ ነገረችው!!!

ርዕዮት እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2015 ከአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት በምትወጣበት ጊዜ እንደማንዴላ ሁሉ የጥላቻ መንፈስን አላሳየችም፡፡

ለዘ-ህወሀት አፓርታይድ ሰይጣን እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት እንዲህ በማለት ነበር የተናገረችው፣ “በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እና ፍትህ ሰፍነው ለህዝቦች ጥሩ መኖሪያ እስከምትሆን ድረስ ባለኝ አቅም ሁሉ ሙሉ በሙሉ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡  እንደዚህ ዓይነት ኢትዮጵያውያንን እስከማይበት ድረስ ትግሌን እቀጥላለሁ፡፡“

ርዕዮት እንደማንዴላ ሁሉ በዘ-ህወሀት ጨዋታ ላይ እርሷ ሙሉ በሙሉ ድልን እንደምትቀዳጅ ግልጽ አድርጋለች፡፡ የርዕዮትመርህ፡ ትግሉ ይቀጥላል! የሚል ነው፡፡

ማንዴላ እ.ኤ.አ በ1962 የአፓርታይድ የጥቂት ነጮች የበላይ አገዛዝ የእድሜ ልክ እስራት በበየነባቸው ጊዜ የ44 ዓመት ጎልማሳ ነበሩ፡፡

ርዕዮት ዓለሙ በኢትዮጵያ የስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ በሚገኘው በዘ-ህወሀት አፓርታይድ አገዛዝ በቁጥጥር ስር ስትውል የ31 ዓመት ወጣት ነበረች፡፡

ርዕዮት በመጀመሪያ በዘ-ህወሀት የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት የ14 ዓመት እስራት ተበየነባት፡፡ ብይኑ በተሰጠበት ዕለት በሌሎች ንጹሀን ዜጎች ላይ የሀሰት ምስክርነት የምትሰጥ ከሆነ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወዲያውኑ እንደሚፈታት ግልጽ አደረገ፡፡ ሆኖም ግን ዘ-ህወሀትን ወደ… እንዲሄድ ነገረችው፡፡

የዘ-ህወሀት የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ብይኑን ወደ አምስት ዓመታት ዝቅ አደረገው፡፡ ይሀ በእንዲህ እንዳለ ከዕለታት በአንዱ ቀን ከማጎሪያው እስር ቤት “ውጭ” ብሎ ነገራት፡፡ ምንም ዓይነት ስነስርዓት አልነበረም፡፡ ምንም ዓይነት ማብራሪያ እና ገለጻ አልነበረም፡፡ ምንም ነገር አልነበረም፡፡ ብቻ “ውጭ” የሚል ነበር!

የርዕዮት የፍርድ ሂደት እና መከራ በዘህወሀት አውሬዎች ሆድ ውስጥ፣

አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በእራሱ ትዕዛዝ ርዕዮት በቀጥጥር ስር እንድትውል ማድረጉ እውነት ነው፡፡

ሆኖም ግን የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ርዕዮትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሄዱበት አካሄድ አስቂኝ ነበር፡፡ ይህ ክስተት በፖሊስ አካዳሚ ወይም ደግሞ በኪስቶን ወታደራዊ ፊልም የሚባለው ሲንማን  ያስታዉሰኛል፡፡ ርዕዮት በቁጥጥር ስር በዋለችበት ጊዜ የፌዴራል ፖሊስ እና የጸረ ሽብር ግብረ ኃይል እየተባሉ የሚጠሩ የጨካኞች፣ የመገንዘብ ብቃት የሌላቸው እና ብቃት የለሽ የወታደር ስብስቦች በዓለም ላይ የመጀመሪያ ደረጃ አሸባሪ እያሉ የሚጠሯትን ርእዮት ዓለሙን የመያዝ ዕቅድ ነድፈው አወጡ፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 21/2011 ከሰዓት በፊት በቁጥጥር ስር ከማዋላቸው በፊት በእርሷ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥረ ግቢ ውስጥ የመምህራን ስብሰባ ላይ ከርዕሰ መምህሩ ጋር አብራ ትካፈል ነበር፡፡ በትምህርት ቤት ግቢው ውስጥ ተማሪዎች አልነበሩም፡፡ መምህራን የመጨረሻ ወሰነ ትምህርት ውጤት ማጠናቀር ስራ ላይ ነበሩ፡፡

ስብሰባው ከተጀመረ ከ20 ደቂቃ አካባቢ በኋላ የትምህርት ቤቱ ድረክቶር ያለመረጋገት እና ጭንቀት ይታይበት ነበር፡፡ ተንቀሳቃሽ ስልኩ መጮህ ጀመረ፡፡ በእያንዳንዱ የድወላ ጊዜ ይወጣ እና ጥቂት ደቂቃዎችን ከቆየ በኋላ እንደገና ወደ ስብሰባው ይገባ ነበር፡፡ ርዕሰ መምህሩ ከርዕዮት ጋር መቀለድ ጀመረ፡፡ “ለምንድ ነው ከጀርባ የተቀመጥሽው?“ በማለት እራሷን ለመደበቅ የተቀመጠች በማስመሰል መልኩ መቀለድ ሞከረ፡፡

ከስብሰባው ለበርካታ ጊዚያት ሲወጣ እና ሲገባ ከቆየ በኋላ ርዕሰ ድረክቶሩ ከውጭ ዘመድ እንደሚፈልጋት ነገራት፡፡ እርሷም እውነት መስሏት መንጠቅ ብላ ስትወጣ የሲቪል ልብስ የለበሱ አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ሁለት ሰዎች ሰላምታ አቀረቡላት፡፡ እንዲህ በማለት ነገሯት፣ “ኦ፣ ዘመድ ይፈልግሻል፡፡“

ርዕዮት ግራ ተጋባች፣ ሆኖም ግን ልዩ የሆነ ጥርጣሬ አላደረባትም፡፡ ምናልባትም በቤተሰብ ላይ የደረሰ አደጋ ነገር ሊኖር ይችላል የሚል ሀሳብ አሰበች፡፡

ሁለቱ ግለሰቦች እንደህ በማለት አረጋገጡላት፣ “ኦ፣ አሁን ከዚህ በምትወጭበት ጊዜ ዘመድሽን ታያለሽ፣ አይዞሽ አትጨነቂ…ምስጢሩን ታያለሽ ፡፡“

ርዕዮት ወደ ትምህርት ቤቱ በር ለመሄድ በደረጃዎች ላይ አብራ ወረደች፡፡

ወደ ትምህርት ቤቱ በር ስትቃረብ ርዕዮት እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ እና 4 የፖሊስ ተሽከርካሪዎችን የያዙ የፌዴራል ፖሊሶችን ስብስብ ተመለከተች (በግምት ወደ 9 የሚሆኑ ዩኒፎርም የለበሱ ፖሊሶች እንደሆኑ ትገምታለች፡፡)

ከዚህም በተጨማሪ የሲቪል ልብስ የለበሱ ሌሎች ሰዎች እና መለያ የሌላቸው መኪኖች በአካባቢው ቆመዋል፡፡ እንግዲህ ከእርሷ እይታ አንጻር በአካባቢው ሄሊኮፕተሮች እና ወታደሮችን የያዙ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች አልነበሩም፡፡ ርዕዮት እያሽካኩ ባሉ እና ለሀጫቸውን እያዝረበረቡ በሚቋምጡ የጅብ መንጋዎች መካከል እንዳለ አጋዘን እና (ወይም ደግሞ እንደ አነር ነብር) ዓይነት ስሜት ተሰማት፡፡

ወደ በሩ እየቀረበች በመጣች ጊዜ ተመልሳ ወደ ት/ቤቱ ለመሄድ ሞከረች፡፡ ሆኖም ግን እርሷን አጅበው ያመጧት ሁለቱ ሲቪል የለበሱ ሰዎች አልፈቀዱም፡፡ በዚህ ጊዜ ርዕዮት ተመልሳ የተማሪዎችን ውጤት መሙላቱን ለማጠናቀቅ ተመልሳ መሄድ እንዳለባት ለመንገር ሙከራ አደረገች፡፡ ወደ በሩ አጅቧት የመጣው ሰው ምንም ነገር ማድረግ አትችይም አላት፡፡

ከትምህርት ቤቱ በር መውጣት እንደማትችል ለመገዳደር ሞከረች፡፡ በዚያን ጊዜ በርካታ የፌዴራል ፖሊሶች በድንገት ተረባረቡቧት፡፡ እርሷን ለመያዝ ሁሉም ነገር ነጻ ነበር፡፡ ከመካከላቸው አንዱ በእጇ ላይ የብረት ካቴና አስገባ፣ ሌላው እጇን ይዞ ጎተታት፣ ሌሎቹ ደግሞ ሌሎችን የአካል ክፍሎቿን ሁሉ ያዙ፡፡ የጅብ መንጋዎች አጋዘንን በሁሉም አቅጣጫ በመውረር እንደሚያጠቁት እንደሚቀራመቱት አድርጋችሁ አስቡ፡፡

እርሷ ግን እንዲህ በማለት ተቃወመች፣ “ለምንድን ነው በቁጥጥር ስር የምውለው?” እርሷን ከስብሰባው ቦታ ጀምሮ አጅቧት የመጣው ሰው እንዲህ በማለት አምባረቃባት፣ “በሽብርተኝነት ስለተጠረጠርሽ ትፈለጊያለሽ“ ብሎ ተቆታት ፡፡ እርሷን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል የማዘዣ ደብዳቤ አልነበረም፣ ወይም ደግሞ ለእርሷ በቁጥጥር ስር መዋል ሊያስረዳ የሚችል ምንም ዓይነት ህጋዊ ሰነድ አልነበረም፡፡

በእጇ ላይ ካቴና ካስገቡ በኋላ እርሷን አጅቧት የመጣው የሲቪል ልብስ የለበሰ ሰው ጎትቶ በመሳብ እንደ ቁራጭ ቡትቶ ወደ ፖሊስ መኪና ውስጥ ወረወራት፡፡

ርዕዮትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተላኩት ፖሊሶች አንዲትን ሰላማዊ ወጣት መምህርት እና ጋዜጠኛ ሴት ለመያዝ የመጡ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ የሽብር ጥቃት አቀናባሪ እና ዋና መሪ የነበረውን ኦሳማ ቢን ላደንን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተላኩ ኮማንዶዎች ይመስሉ ነበር፡፡ (እርሷን በቁጥጥር ስር ለማድረግ የተላኩት ወሮበላ ዘራፊዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ የምትፈለገውን ርዕዮት ዓለምን በቁጥጥር ስር በማዋላቸው ምክንያት በደስታ ተውጠው በእጅ መዳፎቻቸው በኃይል እየተመታቱ የደስታ ስሜቶቻቸውን ለመግለጻቸው ግልጽ የሆነ ነገር የለም፡፡)

በእርግጥ የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ርዕዮት በመንገድ ላይ ስትሄድ ወይም ደግሞ በመኗሪያ ቤቷ ማታ በሯን ስትዘጋ በቀላሉ በመያዝ በኃይል ሊወስዷት ይችሉ ነበር፡፡ እንዲህ ያለውን ድርጊት ሁልጊዜ የሚፈጽሙት ድርጊት ነው፡፡ ሰላማዊ ዜጎችን ያፍኑ እና የደረሱበት እንዳይታወቅ በመሰወር ደብዛቸውን ያጠፋሉ፡፡

ስለዚህ ያ ሁሉ የትምህርት ቤት ተውኔት እንዲተወን የተፈለገው ለምንድን ነው?

እኔ የማውቀው ነገር የለም፣ ሆኖም ግን የዘ-ህወሀት የጸረ ሽብር ግብረ ኃይል እንደ ኪስቶን ወታደሮች የተንከባለለው በዚህ ዓይነት መልኩ ነው፡፡

ዘ-ህወሀት ርዕዮትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ያደረገው የትምህርት ቤት ተውኔት የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች እንደ ኪስቶን ወታደሮች እ.ኤ.አ በ1914 በወሮበሎች መዳፍ ስር እንደዋለው ክስተት አድርጌ እቆጥረዋለሁ፡፡

የዘ-ህወሀት ወሮበሎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁጥር አንድ የሆነችውን አሸባሪ ርዕዮት ዓለሙን በቁጥጥር ስር በማድረግ በመማረካቸው እና ወደ ማዕከላዊ የፖሊስ ምርመራ እንዲሁም የስቃይ ማዕከል ወደሚባለው የሰቆቃ ቦታ በመውሰድ እንኳን ደስ ያለህ በማለት እርስ በእርስ ሲጨባበጡ ነበር፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እ.ኤ.አ በ2013: “የእምነት ቃል እንዲሰጡ መፈለግ፡ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ የፖሊስ ምርመራ ጣቢያ ማሰቃየት እና ደካማ የሰብአዊ መብት አያያዝ“ በሚል ርዕስ በማዕከላዊ ምርመራ በርካታ የሆኑ ማሰቃየቶች የተፈጸሙ መሆናቸውን በዘገባው አካትቷል፡፡

እንግዲህ ዘ-ህወሀት ርዕዮትን ያንን ያልታቀደ ጉብኝት እንድትጎበኘው ነው ወደ ማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራ የወሰዳት፡፡

(ይቀጥላል አንቺ ርዕዮት ዓለሙ ነሽን? ብሎ ሀሰን ሽፋ በንቀት ደነፋባት) 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

የካቲት 22 ቀን 2008 .

The post ወግ ከርዕዮት አይበገሬዋ ጋር – ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም appeared first on Zehabesha Amharic.

ማሳሰቢያ –ከአባቢያ የባለሀገር ንቅናቄ

$
0
0
Oromo የኢትዮጵያ ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው:: ሲባል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ማለትም የኦሮሞ ሕዝብ: የአማራ ሕዝብ: ጉራጌ ሕዝብ: የአፋር ሕዝብ: የሶማሌ ሕዝብ: የወላይታ ሕዝብ የካንባታ ሕዝብ: የሲዳማ ሕዝብ: የአገው ሕዝብ እና የትግሬ ሕዝብ ጭምር  ማለት ነው:: ሁሉም ሕዝብ በያለበት ቦታ ሆኖ የአገር ባለቤት ነው ::
 ዛሬ ይህ የአገር ባለቤትነት መብት በጦር ጠማሽ ድርጅት ማለትም በወንበዴ አንጃ አማካይነት ተጥሶአል::የአገር ባለቤት መሆን ካልተቻለ ደግሞ  ዜጋ መሆን አይቻልም::  ለዚህም ነው ጦር ጠማሹ ድርጅት እንደ ጠላ እንኩሮ እያነኮረ ሕዝብን የሚያሰቃየው:: እንደሚታወቀው  በአሁኑ ሰዓት የኦሮሞ ሕዝብ የመረረ ተቃውሞ በማድረግ ላይ ነው::
ይህ የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ የተነሳው በእራሱ  አገር ቤት በሚኖረውና የወያኔ ግፍ ያስመረረው ሕዝብ ነው:: ሃሳቡም ዓላምውም  ግቡም የእራሱ ነው:: አባ ቢያ የባለአገር  ንቅናቄ እስከሚያውቀው ድረስ መሠረታቸው ውጭ የሆነ  በግንባር እና በሌላ ሌላ ስያሜ የሚታወቁ  በኦሮሞ ሕዝብ ጉዳይ ላይ የተመሠረቱ በኦሮሞ መሬት ላይ የሌሉ  ዴርጅቶች አማካይነት የተፈጠረም ሆነ የሚመራ እንዳልሆነ ነው:: የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ኦሮሞ ውስጥ እያለ የኦሮሞን ሕዝብ መከራ እና ሥቃይ እየተቀበለ: እየታሠረ: እየተገረፈ:  ቶርች እየተደረገ:  እየተሰለለ: ለቁም እስር እየተዳረገ  ታፍኖ እየተወሰደ:  ታድኖ እየተገደለ እንኩዋን ንቅናቄው የኦሮሞ ሕዝብ መሆኑን በማረጋገጥ የሕዝብን ጥያቄ በአጽናዖት ሲያከብር እና ሲያስከብር ይስተዋላል:: የሚያሳዝነው ግን በውጭ የሚገኙ የኦሮሞ ተቃዋሚ ድርጅቶች እና አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች  የኦሮሞን ንቅናቄ ለመደገፍ በሚል መነሻ ሃሳብ የራሳቸውን ሰንደቅ ዓላማ  ሲያውለበልቡ: የራሳቸውን አጀንዳ ሲያራምዱ:  በሚዲያ እና በሶሻል ድረገጾች ላይ በለው ሲሉ ይደመጣሉ::  ይስተዋላሉም:: የሚገርም ነገር ደግሞ ወያኔ ገና ከመነሻው የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ ለማጣመም የተለመደ ብረታዊ እርምጃ ለመውሰድ እንዲቀናው: ኦነግ በሌለበት አለ ለማስባል ኦነግ ባልዋለበት ዋለ እያለ  ሕዝብን ለመምታት ዘዴ እንደሚዘይድ የታወቀ ነው:: ዛሬ በወያኔ እስር ቤት የሚማቅቁ እልፍ አእላፍ ኦሮሞዎች የታሠሩበት ምክንያት እኮ በኦነግ ስም ነው:: ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ እንዴት ኦነግና የኦነግ መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ለኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ  ማራገቢያና  ማውለብለቢያ ሊሆን ይችላል?
  ወያኔ የሚሠራውን ሤራ እራሱ በተቃዋሚ ፓርቲ ሲሠራ ለወያኔ ደስታ ነው::  የጦር ሠራዊት ቢያሰፍርበት  ጦሩን ለመቃወም  እንዴት ያስችላል? በኃይል መብቴን አስከብራለሁ ያለ ድርጅት በትጥቅ ትግል የሚያምን ድርጅት ከሠላማዊ ንቅናቄው ጋራ  ከተዳበለ ሁኔታውን የባሰ አስቸጋሪ ያደርጋል:: ለዲፕሎማሲያዊ ድጋፍም አወሳሳቢ ይሆናል:: ይህም የኦሮሞን ሕዝብ ከመጥቀም ወይም የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ከማገዝ ይልቅ ለበለጠ ጉዳት  ይዳርጋል::  ሠላማዊ እና ያልታጠቀን ሲቪል ሕብረተሰብ ከጨካኝ የወያኔ ነፍሰ ገዳይ  ወታደር ጋራ ግንባር ለግንባር እንዲገጥም መገፋፋት   እራሱን የቻለ  ጭካኔ ነው::  ዛሬ በ21ኛው ክፍለዘመን  ሁከት አልባ ንቅናቄ የብዙዎችን አምባገነን መሪዎችን ሲጥል እየታየ  ሁከት አልባ ትግል መስፈርቶቹ መመዘኛዎቹ እና ባህርያቶቹ ዓለምአቀፋዊ ናቸው:: ማየት መመርመር ያስፈልጋል::  ከዚህ ከዓለም ተሞክሮ በመነሳትም ሕዝባዊ ንቅናቄን ሁከት አልባ በማድረግ ዘዴ ለውጥ ማምጣት ይቻላል:: በሌላ በኩል የፖለቲካ ድርጅት ያልሆኑ ክፍሎች ሚና ግልጽ መሆን የሚገባው ነው:: ለምሳሌ የሚዲያ ተቁዋማት አስተዋጽኦ ገሀድ ነው::  ሳይንቲፊክ ነው::  የሚዲያ ጀግኖች አሉ::  እውነትን በማውጣት ድብቅን በማጋለጥ ስውሩን  ይፋ በማድረግ   ረገድ የሚዲያ ድርሻ ይታወቃል:: ነገር ግን ከሚዲያ ተፈጥሮ አፈንግጦ   በሚዲያ ላይ አንባገነን ሆኖ እንደፈጣሪ በሁሉም ቦታ   በአንድ ሰዓት  ለሁሉም ጉዳይ እኔ  በሚል ከተተካ  ሚዲያው ሃይጃክድ ሆኖአል ማለት ነው:: ከኤድቶሪያል ሥነ-ሥርዓት ያፈነገጠ  ታዛዥ የሆኑ ጥቂት ግለሰቦችን ብቻ ይዞ  መንቀሳቀስ የሚዲያ ህግን መጻረር ነው:: ወይም ተገቢ ያልሆነን ቁዋንቁዋ መጠቀምም ሕዝብን ወደአልተፈለገ አቅጣጫ ይወስዳል :: ላልተፈለገ ግምትም ያሰጣል ::
 በግልጽ እስከሚታወቀው ድረስ  የሚዲያ ተቃዋሚ የለም::  የሚዲያ ጦረኛ የለም::   ሚዲያ ሚዲያ ነው:: በቃ:: ወደ አንድ  ፓርቲ መጻነፍ: ወደ አንድ የፖለቲካ አመለካከት ማጋደል ከአንድ ሚዲያ የሚጠበቅ ሙያ አይደለም::  በመሆኑም  የኦሮሞን ሕዝብ ተቃውሞ እና የወያኔን ነፍሰ-ገዳይነት እያጋለጠ  የሚዲያ አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ የኦሮሞን ሕዝብ ንቅናቄ በመጥለፍ የመሪነትን: የአዛዥነትን ሚና እጫወታለሁ ብሎ ራስን መሰየም የሚገርም አካሄድ ሆኖ ተገኝቶአል::  በአሁኑ ሰዓት ዋና ጠላት እያለ  የእርስ በእርስ ጉዳይ ማንሳት ጥሩ አይሆንም በሚል ሰበብ  ሰፊ ትዕግስት ሲሰጠው በአንዳንድ ግለሰቦች ጭንቅላት ብቻ የሚደረገው አካሄድ አጠቃላይ ትግሉን ውኃ ያሰበለዋል እና ዝም ማለት ኃላፊነት የጎደለው አስተሳሰብ ይሆናል:: ሳይተራረሙ: ሳይነጋገሩ: ሳይወያዩ:  ሳይተቻቹ ትግል የለም:: ካለም ውጤቱ ሕዝብን  ማስጨረስ ነው::  ግልጽ ለማድረግ ያህል አብነት ወስዶ የሚዲያ ስም ጠቅሶ የፈላጭ ቆራጭ  ኃላፊዎችንም  ተሰጥኦ ስም ነቅሶ  መናገር ይቻላል:: የኤድቶሪያል ቦርዳቸው ቀጥታ መስመር የተጋረደባቸው  ለሚዲያ የሚላከው መረጃ በግለሰብ እጅ እየገባ በሌላ አተረጉዋጎም የሚሰራጨው  መረጃ   የሚያስከትለው ኃላፊነት ከባድ ነው::  እንዲህ ዓይነቶቹ  ግለሰቦች አደገኞች ናቸው:: በዓለም ላይ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ  ተነስተው የወደቁ አያሌዎች ናቸው:: ካስፈለገም ይዘረዘራሉ::  የአንድን ሚዲያ  መሠረታዊ መርሆንና ዓላማን  ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ሲሆን ደግሞ ትርጉዋሜውም ውጤቱም የዚያኑ ያህል የከፋ ይሆናል::  ዛሬ አገራችን ባለችበት  ሁኔታ    እንድህ ዓይነት ባህርይ ማሳየት ተገቢ አይደለም:: ሕዝብን ይጎዳል::  ጎድቶአል:: እየጎዳም ነው::በሕዝብ ደምና ሕይወት ላይ የራስን ዝና ለማትረፍ መፍጨርጨር  ውጤቱ ውርደት ብቻ  ሳይሆን በወንጀልም ያስጠይቃል::
  አባቢያ የባለአገር ንቅናቄ  ለኦሮሞ ተቃዋሚ ድርጅቶችና ለሎችም ታጣቂ ታጋዮች ማሳሰብ የሚፈልገው ነገር ቢኖር  የሕዝብን ንቅናቄ  መንጠቅ: ጩኸቱን መቀማት  ሳይሆን አጋር መሆን: ደጋፊ: ተባባሪ  መሆን እንጂ ደርሶ ሠላማዊ ትግሉን መምራት አለብኝ ብሎ ማለት ለሥልጣን ሩጫ ራስን ለማዘጋጀት መጣር  አይሆንም::   የተቃዋሚ ስሞች  ሕዝብ ላይ ከተለጠፈ  በተለይም  በጦርነት ሥርዓቱን እቀይራለሁ የሚሉ   የትግል መስመራቸውን በቀይ ቀለም  ያሰመሩ  ድርጅቶች  በዚህ ላይ  የወያኔ መንግስት አሸባሪ ብሎ በፓርላማ አዋጅ አውጆ ምን ዓይነት ቅጣት እንድሚያስከትል እየታወቀ ሕዝብ ከዚህ ድርጅት ጋራ ቢሠራ ትግሉ ወዴት እንደሚተረጎም ለመረዳት የግድ  በሀርቫርድ በር መውጣትና መግባትን አይጠይቅም::  ማንም ሰው የሚገምተው ነው::  በሕዝቦች መካከል ቅራኔ በሚፈጥር:  ቂም በሚያበቅል: ጥላቻን  በሚዘራ:  ሕዝብ ለሕዝብ እንዳይገናኝ የሚያደርግ: የሚያቀያይም: የማያቀባብር:  የማያረዳዳ: የማያተባብር  ንግግሮችን ማድረግ  አደገኛ ሁኔታ ነው::  የራስን መብትና ነጻነት ለማስከበር በሚደረገው ትግል የሌላን መብት መጣስ ተገቢ አይሆንም:: በሌሎች ህልውና  ላይ የሥጋት ዳመና መጣል  አስፈላጊ አይደለም:: ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትም አያገኝም::   በተለይ  በውጭ አገር እየተኖረ: በሌላ ሕዝብ ምድር ላይ ሕይወትን መለወጥ በሚቻልበት:  ከየትም ና  ምንም ዓይነት ቀለም ይኑር  እንደሰው ተክብሮ ከአገሬው ጋራ  እኩል መታየትን  በተግባር ያረጋገጠ ሰው:  እንዴት ላገር ቤቱ ሰው ጠባብነትን ያስተምራል:: እንዴት በቁዋንቁዋ ላይ ጥላቻን ያሳድራል:: ይኸ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ለሰብዓዊ መብት መረጋገጥ ሳይሆን እየተደረገ ያለው ትግል ይህንን የተበደለ ሕዝብ ተጠግቶ ይህንን የከፋው ሕዝብን ተገን አድርጎ የራስን ወያኔያዊ ፍላጎት ለማሳካት መጣር ነው:: ወይም እንደጩቤ በሁለቱም ጎን እየቆረጠ ለመብላት ሲል የሚጥር አደገኛ ባህርይ ያለው ሰው ነው::
    ስለዚህ የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ኃይሎች  መብታቸው ነው::  ሕዝብ የሚለካቸው በውጤታቸው ነው:: ማለትም በያዙት  ነጻ መሬት  መመዘን አለባቸው:: በሕዝብ ላይ የሚደርሰው ሰብዓዊ ጥቃቶችን መቃውም ይችላሉ::  ሕዝብን መርዳት ይችላሉ::  ነገር ግን  ከተግባራቸውና ከሥራቸው ቀድሞ  ስማቸውና ባንዲራቸው  በአገር ላይ እንዲውለበለብ መፍቀድና ማበረታታት  ሕዝብ ላይ ስለሚደርሰው ጉዳት አለማሰብ ነው:: አለመጨነቅም ነው::
 ማናቸውም የፖለቲካ ድርጅቶች በሕዝብ ትግል መነገድ የለባቸውም::በሕዝብ ሞትና ደም ማትረፍ የለባቸውም::  የሚሰቃዩት እያሉ: የሚገረፉት እያሉ:የሚደበደቡት እያሉ:     በዳያስፖራ ሕይወት ውስጥ ሆኖ የመሪ ታጋዮችን  ክሬዲት ለራስ ማድረግ  ድፍረት ነው:: ጥንቃቄ ይፈልጋል::  ይህን ለምን ተባልን የሚሉ ኃይሎች እንዳሉ አባቢያ ያውቃል::   ዘራፍ የሚሉ ካሉ ብቅ ብለው መነጋገር ይችላሉ::በባህላዊ በማህበራዊ በኢኮኖሚያዊ በፖለቲካዊ እና  በየትኛውም ሳይንሳዊ መልክ  መከራከር ይችላሉ   :: ንግግሩም ሆነ  ምክክሩ የሚፈለግ ነው:: ሃሳቦች ይጸነሳሉ  :: ይወለዳሉ:: ያድጋሉ:: እናም ይፈለጋል::

The post ማሳሰቢያ – ከአባቢያ የባለሀገር ንቅናቄ appeared first on Zehabesha Amharic.

የወተት አብዮት በኦሮሚያ እና በጎንደር |ከአብርሃም ታዬ

$
0
0

የወተት አብዮት ምንድን ነው?

ወተት በመጀመሪያ ትርጉሙ ለሰውነት ገንቢ የሆነ የምግብ አይነት ውስጥ የሚመደብ ብቻ ሳይሆን የንጹህነት፣ የደግነት  ምሳሌ ነው። ሁለት ጡት ቢኖረንም ወተት ግን አንድ ነው ያው ነጭ ነው። ከኦሮሚያ ምድርም ይገኝ ወይ ከአማራ ክልል ወተት ምግብ ነው።ወተት በጨዋነቱ በንጹህነቱ በደግነቱ  የሚታወቀው የኢትዮጵያ ህዝብ መገለጫ ነው።

Milk

በሁለተኛ ትርጓሜው ደግሞ ዶክተር ታደሰ የተባሉ ታጋይ እንደተነተቱት ወተት ማለት ወቅታዊ ተግባራዊ ትግል የሚለው ቃል ምሕጻረ ቃል ነው።ጨጓራችን ውስጥ አሲድ በዝቶ ሲለበልበን ወተት እፎይታን ስለሚሰጥ አገራችንም እኛም ህወሓት በተሰኘ ዘረኛ አሲድ እየተቃጠልን ነውና በአስቸኳይ ወተት ያስፈልገናል።

የወያኔ የግፍ አገዛዝ ገደቡን አልፎ እየፈሰሰ መሬታችንን እያረሰ ያጎረሰውን እጅ እየነከሰን ሰለሆነ ለመከላከል ጊዜውን የወቅታዊ ተግባራዊ ትግል/ የወተት/ አብዮት አድርገነዋል።ወተቱን መጠጣት እንጂ ለማለብ ማቀድ፣መዘጋጀት የሚባሉትን ደረጃዎች አልፈናል።በወተት ውስጥ በቀጥታ ተግባር የምንጀምርበት ነው።

በመላው የኦሮሚያ ክልል ከሶስት ወር ወዲህ በተለየ ሁኔታ የተነሳው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ወያኔን እንቅልፍ ነስቶታል። የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላንንን በማስፋት ገበሬዎችን ከቀዬኣቸው የማፈናቀሉን ዕቅድ ትቼአለው ቢልም የመንግስት ይውረድ ጥያቀው ተባብሶ ቀጥሏል።ወያኔ ‚ታላቋን ትግራይ‛ ተብላ የምትጠራ አገር ለመመስረት ሲል የጎንደርና የወሎ መሬትን ቆርሶ ለራሱ ትግራይ ክልል ለማስገባት የፈጸመውንና አሁንም በጋምቤላም እየፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት(Genocide) ፥ ህዝብን የማፈናቀል (Ethnic cleansing ) ወንጀሎች በየፊናው እየተሞገተ ይገኛል። እነደነ ሚስተር ኦባንግ ሜቶ ያሉ አክቲቪስቶች በወጪው አለማት የሚያጋልጡትን ጉዳይ በጠቅላላው የዲፕሎማሲ ስራ በውጪ ያሉ ተቃዋሚዎችን የቤት ስራ ሳንዘነጋ ወቅታዊ ተግባራዊ ትግላችን በአገር ቤት ይህን ይመስላል።እንዲህም ሊሆን ይገባዋል።

ወተት 1:-  መንገድ መዝጋት

ወደ ሃረር ወደ ጅማ ፥የሚወስዱ መንገዶችን በመዝጋት የወያኔ ቅልብ ወታደሮች እንደልብ እንዳይነቀሳቀሱ እንደተደረገው ሁሉ በሰሜን ጎንደር ዳባት ህዝባዊ እምቢተኝነት ተቀስቅሷል። የከተማዋ ወጣቶች ከዳባት ወደ መቀሌና ሽሬ የሚወስዱ መንገዶችን ዘግተዋል። የሰሞኑ በአዲስ አበባ የታክሲዎች አድማ የትራንስፖርት ዕጥረትን ብቻ ሳይሆን የወያኔው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት 120ኛ የ አድዋ ድል በዓል ቀን ለማካሄድ የያዘውን የፖናል ውይይት ከአ/አ ታክሲዎች አመጽ ጋር በተያያዘ ለመሰረዝ ተገዷል።

ድንጋይ፥ እንጨት፥ ቆሻሻዎችን  በመንገድ ላይ በመከመር  ሲቀጥልም ድልድዮችን በመስበር ሊገድለን የሚመጣውን የ ፌዴራል ወታደር ማዘግየት ይቻላል።

ያም ሆኖ ለሰው ምንም ሀዘኔታ የሌለው መንግስት፥ደንቆሮ የአግኣዚ ጦር እና ሆዳም ካድሬዎች በውስጣችን ሰርገው መግባታቸው ስለማይቀር የነሱን ያህል  የአጸፋ ምላሽ በመስጠት ትግሉን እናክርረው። በኦሮሚያ ከተማሪ እስከ መምህራን ከልጆች እስከወላጆች  ያሳዩት ወኔ እልክ እጅግ የሚደነቅ መሆኑ የሚደገፍ ቢሆንም  መንግስት በታንክና መትረየስ እየረፈረፈን በየቀኑ ዱላ ብቻ ይዞ መሰልፍ የዋህነት ነው። በበኩሌ ወያኔ ሕጻናት ተማሪዎችን የገደለበትን ፎቶ ሳይ እርጉዟን ከነልጇ ጨፍልቆ ሲያፈርጣት ሳይ የተሰማኝ ጥልቅ ሀዘን ለብቀላ አነሳሳኝ።ምን ላድርግ ብዬ ስጎረጉር ባዶ ጠርሙስ በጋዝ ሞልቶ በጨርቅ በመድፈን ኣቃጥሎ ነፍሰ ገዳዩ ወያኔ ላይ  መወርመር እንደሚቻል ተረዳው በቀላሉ። በሕጻናት ወይም በእናቶች ሞት ለመቆርቆር የግድ ኦሮሞ ወይ አማራ መሆን አይጠበቅብንም።

pastedGraphic.png

ወተት 2: – የወያኔ ንብረቶችን ማቃጠል

ወቅታዊው ተግባራዊ ትግል ወተት ውስጥ ካየነው አንዱ የህወሃት መኪኖች ፣የነዳጅ ቦቴዎች  ላይ አደጋ ማድረስ አንዱ ነው።የወተትን አብዮት በሰፋት ተግባራዊ ለማድረግ በየሰፈራችን የሚገኙ የወያኔ ካድሬች፥ የነሱ መኖሪያዎች፥ቢሮዎች፥የቤት መኪኖች ውስጥ እሳት በመለኮስ ማቃጠል በምርጫ 1997 እንደሞከርነው ቀጥሎ የሚዘረዘረውን የኮክቴል ቦምብ ሰርተን ተሽከርካሪውች ስር ማስቀመጥ አያቅተንም።በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወቅት ናዚን ይቃወሙ በነበሩ ሲቪሎች የኮክቴል ቦምብ በስፋት ጥቅም ላይ ዉሎ እንደነበር ይነገራል፡፡ ይህን ቦምብ ለማዘጋጀት ቀላል ከመሆኑም በተጨማሪ የሚስፈልጉት ቁሳቁሶችን ለማግኝት አዳጋች አይደለም፡፡

የኮክቴል ቦምብ አሰራር

1) በመጀመሪያ መጠኑ ተለቅ ያለ (ቢያንስ 30 ሲንቲ ሜትር እርዝማኔ ያለዉ) ጠርሙስ ያስፈልጋል፡፡ አብዛኛዉ የወይን ጠርሙስ ለዚህ አላማ ተስማሚ ነዉ፡፡ ጠርሙሱን በማንኛዉም አይነት ተቀጣጣይ ፈሳሽ ለምሳሌ በጋዝ በዘይት ወይም በአልኮል መሞላት አለበት፡፡

2) የጠርሙሱ 3/4ኛ በተቀጣጣይ ፈሳሹ ከተሞላ በኋላ በደንብ ሊገጥመዉ የሚችል ክዳን ፈልጎ ክዳኑን የጨርቅ ትልታይ ወይም የጧፍ ምድጃ ክር እንዲያስገባ አድርጎ በድሪል ወይም በወፍራም ሚስማር መብሳት ፡፡

3) ከ2 እስከ ሶስት እጅ የሚሆነዉን ያህል የጨርቅ ትልታይ ወይም የጧፍ ምድጃ ክር ተቀጣጣይ ፈስሽ የተሞላዉ ጠርሙስ ዉስጥ በመክተት ክዳኑን ግጥም አድርጎ መዝጋት፡፡ ለማቀጣጠል እና ለመወርወር ያህል በቂ ጊዜ የሚሰጥ የጨርቁ ትልታይ ከጠርሙሱ ክዳን ዉጪ እንደተረፈ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነዉ፡፡

4) አሁን ኮክቴል ቦንቡ ጥቅም ላይ ለመዋል ዝግጁ ነዉ

ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች

ከላይ የተጠቀሱት የአዘገጃጀት ሂደቶች ከተጠናቀቁ በኋላ የቀረዉ ጉዳይ የጨርቁን የዉጪኛዉን ጫፍ ከለኮሱ በኋላ ወደሚፈለገዉ ኢላማ መወርወር ነዉ፡፡ ሆኖም ግን የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ ማለት በጣም አስፈላጊ ነዉ፡፡

1) ጠርሙሱን ከመወርወር በፊት የተለኮሰዉ (እየነደደ ያለዉ) የጨርቅ ትልታይ ክፍል በበቂ ሁኔታ ወደ ተቀጣጣይ ፈሳሹ እየቀረበ መምጣቱን ማረጋገጥ፡፡

2) በጣም ፈጥኖ መወርውር ተገቢ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እየነደደ ያለዉ የጨርቅ ትልታይ ክፍል ወደጠርሙሱ ከመድረሱ በፊት ጠርሙሱ ከኢላማዉ ጋር ተጋጭቶ ወይም መሬት ላይ ወድቆ ሊሰበር ይችላል፡፡ ይህም መሆኑ ተቀጣጣይ ፈሳሹ ሊፈስና ተፈላጊዉ ፍንዳታ እንዳይከሰት ያደርገዋል፡፡

3) በእራስ ላይ አካላዊ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ጨርቁን ከለኮሱ በኋላ ጠርሙሱን ሳይወረወሩ ብዙ መቆየት ፈጽሞ አግባብ አይደለም፡፡

ወተት3-  ትግሉን መላ ሀገራዊ ማድረግ

ዛሬ ይህን ያህል ኦሮሞ ሞተ ከማለት ይህን ያህል ሰው በኢትዮጵያ ሞተ ተብሎ ቢዘገብ: በተለይም ኦሮሞ ፕሮቴስት አምጽ #Oromo Protest ከማለት ኢትዮጵያ ፕሮቴስት  #Ethiopia_Protest    ቢባል የሁላችንም ትኩረት ይስባል። በተለይ ህወሃት የመሬት ቅርምቱን አቁም #Stop Ethiopia land grab የሚል  ዘመቻ ከመነሻው ቢጀመር ኖሮ ሁሉም  የህብረተሰብ ክፍል ይነሳሳ ነበረ።ምክንያቱም የ አዲስ አበባ ማስተር ፕላን ብቻ ሳይሆን በጋምበላም፥በ ጎንደርም፥በአፋርም ባጠቃላይ ሁሉም የህብረተስብ ክፍል የመፈናቀል ኣደጋ ስለተጋረጠበት በአንድነት ያቆመናል። አሁንም ቢሆን ወተት የሰውም ይሁን የላሞች ዞሮ ዞሮ ገንቢ ነውና ሁላችንም ለትግሉ ግብ መምታት እኩል መነሳሳት ይኖርብናል።ባለፈው ዓመት ላንድ ወቅት የብር ኖቶች ላይ Graphity ቅስቀሳ ማድረግ ብሎም ሳንቲሞችን ሰብስቦ የህወሃትን ካዝና ማዳከም የድምጻችን ይሰማ ወተት ነው ብለን እነሱ ብቻ እንዲያደርጉ የወሰንን መስሎ ኣለፈ።  ሌላው ቀርቶ በሶሻል ሚዲያ ለምሳሌ በፌስቡክ  የፕሮፋይል ፎቶ በዘመቻ መልክ መቀየርን ጨምሮ  ለመላው አለም ልንገልጽ የሚገባን ኢትዮጵያውያን በገፍ እየተገደልን #killings_in_Ethiopia መሆኑን ነው።በወር ብቻ ከ300 በላይ ወገኖቻችን እንደቅጠል ረግፈው ፥ምንም የማያውቁ ሕጻናት እየተሳቀቁ ከጎናቸው  እምባቸውን ካላበስን ደማቸውን ካልመለስን ወይ በዚህ መልኩ ሌላው አለም ግፉን እንዲያውቅልን ካላደረግን መቼ ልናደርግ ነው።?

ጽሁፉን በተለያየ የሃገራቸን ቋንቋ በመተርጎም በማሰራጨት የወተት አብዮትን ያራምዱ።

አብርሃም ታዬ

Zeabraham tye

The post የወተት አብዮት በኦሮሚያ እና በጎንደር | ከአብርሃም ታዬ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአፕል እና በFBI መካከል ሰሞኑን የተከሰተው የመረጃ ብርበራ ጥያቄ እና ውጤቱ ሲዳሰስ | Audio

በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ ወያኔያዊ የክተት ዘመቻ (ነፃነት ዘለቀ)

$
0
0

tplfበሁሉም የሀገራችን ግዛቶች ውስጥ በወያኔ ቅልብ ጦር የጭካኔ እርምጃ ሕይወታቸውን ያጡና አሁንም ድረስ እያጡ ያሉ ወገኖቻችን ነፍሳቸውን ፈጣሪ ተቀብሎ ከፃድቃን አጠገብ እንዲያስቀምጥልን መልካም ፈቃዱ ይሁንልን፤ በየማጎሪያ ቤቶች የሚገኙ ወገኖቻችንንም ጽናቱን ይስጥልን፡፡ የመከራችንን ደብዳቤም እንዲቀድልን ሁላችን ተግተን እንጸልይ፡፡ በዘር፣ በጎሣና በሃይማኖት  ሳንከፋፈል በአንድ ላይ ጸንተን ከቆምን የወያኔ ዕድሜ ከአንድ ደቂቃም ያጠረ ነው፡፡ ነገር ግን አንድ እንዳንሆን ወያኔ የሚጥልብን ደንቃራ ቀስፎ ስለያዘን ይህን ሁኔታ በእስካሁኑ አካሄድ መቀየር አልቻልንም፡፡ ስለዚህ በመከባበር መደማመጥ እንደሚኖርብን እንረዳ፡፡ መጪው ጊዜ ብዙ ደም የማይፈስበትና በተቻለ መጠን በትንሽ መስዋዕትነት ታላቅ ሀገራዊ የነፃነት ድል የምንቀዳጅበት የትግል ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡  

በቅድሚያ እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ እኔ መሰንበት ከተባለ ደህና ሰንብቻለሁ፡፡ የሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ እየተንተከተከ ያለ ይመስላል፡፡ እነወያኔዎችም ሰይጣን ይሁን እግዚአብሔር የፈቀደላቸውን ሀገርንና ሕዝብን እንደእባብ የመቀጥቀጥ ሥራ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ በአዲስ አበባ ታክሲዎች ሥራ አቁመው ሠራተኛውና ጥቃቅኑ ነጋዴ ከማለዳው ጀምሮ እየተቸገረ ነው፤ በእግሩም እየኳተነ ይታያል፡፡(የካቲት 21 ቀን 2008ዓ.ም) የደኅንነትና የአንዳንድ ትግሬዎች ታክሲዎች ግን- የአድርባዮቹም ጭምር – እየሠሩ እንደሆነ በግልጽ ይታያል፡፡ ከሕንጻውና ከንግዱ በተጓዳኝ አብዛኛው የትራንስፖርት መስክ በትግሬዎች በመያዙ ይህ ዐድማ ትልቅ ለውጥ ከማምጣት አንጻር ብዙም ፋይዳ ያለው አይመስልም፡፡ እነሱ ያልያዙትና ያልተቆጣጠሩት ነገር የለም – ዕድሩም፣ ዕቁቡም፣ ሰንበቴውም፣ መረዳጃ ማኅበሩም፣ ምኑም ምናምኑም በነሱው ቁጥጥር ሥር ነው – የጽዳትና ጥበቃ ኃላፊውንና የቆሻሻ ገንዳ ጠባቂውን ሣይቀር ብትመለከት ከአሥር ዘጠኙ ትግሬ ነው፡፡ አሥርን ካነሳሁ አይቀር በተለይ በአዲስ አበባና አካባቢዋ ከአሥር ሕንፃ ዘጠኙ፣ ከአሥር ሠርግ ዘጠኙ፣ ከአሥር አውቶሞቢሎች ዘጠኙ፣ ከአሥር ሱቆች ዘጠኙ፣ ከአሥር ሱፐር ማርኬቶች ዘጠኙ፣ ከአሥር ኢንቬስተሮች ዘጠኙ፣ ከአሥር ኮንዶሚኒዮሞች ዘጠኙ፣ ከአሥር የመንግሥትና የመያድ ባለሥልጣናት ዘጠኙ፣ አብረው ከሚጓዙ አሥር ሰዎች መካከል ዘጠኙ፣ በወታደራዊ ተሸከርካሪዎች ተሣፍረው ከሚጓዙ አሥር ወታደሮች ወይም መለዮ ለባሾች ዘጠኙ፣ ምን አለፋችሁ ከማንኛውም ነገር ከአሥር … ዘጠኙ ሀብት ንብረቱ የወያኔ ትግሬዎች ሀብትና ንብረት ሲሆን – ሰዎችም ከሆኑ እነሱው ናቸው( ክርስቶስ “ሁለት ባላችሁበት ሦስተኛ እኔ አለሁ” እንዳለ ወያኔዎችም “አንድ ሆናችሁ በቆማችሁበት ዘጠኝ ሆኜ አጅባችኋለሁ” ሣይል የቀረ አይመስለኝም፡፡) በኃላፊነትና በጥሩ ደሞዝ በመያድ ውስጥ ለመቀጠር ትግሬ መሆን አለብህ፤ በኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለመቀጠር ትግሬ ሆነህ መፈጠር አለብህ፤ በመንግሥት መ/ቤቶች በተለይ በኃላፊነትና ጥቅማጥቅም ባለበት ቦታ ላይ ለመቀጠር ትግሬ መሆን አለብህ፡፡ በደርግ ዘመን “ምርጥ ምርጡ ለሕጻናት” የሚል (የውሸት) መፈክር በየግድግዳው ይጻፍ እንደነበር አስታውሳለሁ፤ ዛሬ ደግሞ “ምርጥ ምርጡ ለትግሬ ወያኔ “ የሚል በህቡዕ የሚሠራጭ (የእውነት) መፈክር ሀገር ምድሩን ሞልቶት አለ – ዘይገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈሌ ማለት አሁን ነበር፡፡ ፡ ኢትዮጵያ ከአሥሩ ዘጠኟ — አይ … ዘጠኝ ብቻ? … ከአሥሩ ዘጠኝ ነጥብ ዘጠኟ የወያኔ ጥገት ላም ናት፡፡ ሌላው በድርቅ እያለቀ ነው፡፡ ወያኔ እየተንደላቀቀና እየተምነሸነሸ ሌሎች በጠኔ እየተንጠራወዙ ናቸው – ዕድል ቀንቷቸው ከተገደሉት ውጪ ማለተይ ነው፡፡ ቧይ! ፎጁን እኮ!

በአዲስ አበባ በረንዳ አዳሪውና እሥር ቤቱን የሞላው ማን ነው? ዐማራውና በገዛ የጋ ሀገሩ ባይተዋርና ከርታታ የሆነ ሌላው ዜጋ ነው፡፡ … በየዝጉብኝ ቤቱ የእንግሊዝ ዊስኪና የስዊድን/የራሽያ ቮድካ ሲጨልጥ፣ ጮማ ሲቆርጥ የሚያመሽና የሚያድረው ማን እንደሆነ ዜጎች ብቻ ሣይሆኑ አየሩና መሬቱም ያውቃሉ፡፡ በየጥሩ ት/ቤቶች የሚማሩ ልጆች የትግሬዎችና የአድርባይ ነጋዴዎችና ባለሥልጣን ተብዬዎች ልጆች መሆናቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡ በጫት ገረባ ደምብሸውና በቁንድፍት ሰክረው በየበረንዳው እጅብ ብለው የሚውሉና የሚያድሩት የነማን እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ አሁን ማን ነው እየኖረ ያለው? ማንስ ነው እያኗኗረና እያጣጣረ ሞትን በመናፈቅ ላይ የሚገኘው? የሀገሪቱን ሀብትና ንብረት በግል ተቆጣጥረው እየተዘማነኑባት ያሉት ወያኔዎች ብቻ ናቸው፡፡ አዲስ አበባን ጨምሮ የሀገሪቷን ዐይን ዐይን ቦታዎች ካለ ገልማጭና ቆንጣጭ የተቆጣጠሩት ትግሬዎች ናቸው – የዋሃኑና ለዘብተኞቹ ሣይሆኑ ብልጣብልጥ ወያኔ ትግሬዎች፡፡ ማርካቶን ያቀናች ምድረ ጉራጌ ከአዲስ አበባ እምብርት ተፈናቅላ የገበያ ማዕከላትን ብቻ ሣይሆን መላ ከተማዋን ትግሬ ተቆጣጥሯታል፡፡ ሌሎችነን በግብርና በኪራይ ፈነቃቅለው ለስደትና ለራስን ማጥፋት ክፍት የሥራ ቦታ አጋልጠው እነሱ የሁሉም አዛዥ ናዛዥ ሆነዋል – ይህን የሰው ልጅ ቅለት እያየሁ ከምኖር በበኩሌና ማን ከለከለህ እንዳትሉኝ እንጂ ሞቴን ብመርጥ ይሻለኛል፡፡ በወያኔ ትግሬዎች ምክንያት የሰው ልጅ ኅሊናዊና ሰብዓዊ ዕድገት እንዳለ ጥያቄ ውስጥ እንደገባ ይሰማኛል፡፡ “እነዚህ ‹ሰዎች› በርግጥም ሰዎች ይሆኑ እንዴ?” እያልኩ ብዙ ጊዜ እጨነቃለሁ፡፡ በአጥንትና ደም አነፍናፊነታቸው ከእንስሳትም በታች ይወርዳሉ፡፡

እኔም ዛሬ ታክሲ አጥቼ በመኪና ነው ወደመሥሪያ ቤቴ የሄድኩት – ማለቴ በልመና መኪና፡፡

ሲያልቅ አያምር ይባላል፡፡ የኛ ይሁን የነሱ ማለቂያ የደረሰ ይመስላል፡፡ ከሁለት አንድኛችን በቅርቡ አሣራችንን ማየታችን አይቀርም ብዬ እገምታለሁ፡፡ በዚህ መልክ የምንጓዝበት ዘመን ማክተሚያው የተቃረበ ለመሆኑ ብዙ ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡ አንድ ቄስና አንድ ሼህ ያንጀት ጓደኛሞች ነበሩ አሉ፡፡ ሼሁ “መምሩዋ ለመሆኑ እስቲ በነቢ ይሁንብዎና ሃቂቃውን ይንገሩኝ – ከእስላምና ከዐማራ(ከክርስቲያን ማለታቸው ነው) ማንኛቸው ይጠድቃሉ?” ብለው ቄሱን ይጠይቃሉ አሉ ዱሮ በደጉ ዘመን፡፡ መምሩም መለሱና “ኧረ በእግዝትነይቱ እንዴት ያለ ጥያቄ ጠየቁኝ ሸኽዬ – መቼስ ከሁለት አንድኛቸው እንታናቸውን ሳይበሉ አይቀሩም!” ብለው መለሱ አሉ፡፡  የዚህን ወግ ጭብጣዊ መልእክት  ወደወያኔ አምጡልኝ፡፡ እንጂ ከጽድቅና ከኩነኔ አኳያ ብንነጋገር እኔ በበኩሌ ተቋማዊ መዳን እንደሌለ ወይም ቢያንስ ሊኖር እንደማይገባ ማመን ከጀመርኩ ቆይቻለሁ፡፡ የመዳን መንገድ አንዲት ብቻ ስለመሆንዋ ደግሞ ብዙም አላውቅም፡፡ መዳኛውን አንድዬ ብቻ ያውቃል – “ሁሉም የየራሱን ሲያደንቅ እሰማለሁ፣ የኔም ለኔ ዕንቁ ናት እኮራባታለሁ.…” የምትል የቆየች የንዋይ ደበበ ዘፈን አሁን በጆሮየ ውልብ አለችብኝ – በዚህ አጋጣሚ ነፍስ ይማር ንዋይ ደበበና ኃይሌ ገ/ሥላሤ፣ ነፍስ ይማር ሠራዊት ፍቅሬና መስፍን በዙ፣ ነፍስ ይማር ሙሉጌታ አሥራተ ካሣና ገነት ዘውዴ፣ … ኦ! የክፉ ቀን ምርጥ ምርጥ ዜጎቻችንን ዘርዝሬ አልጨርሳቸውም – አንድዬ ግን የሚሣነው ነገር የለምና እርሱ ይጨርስልኝ፡፡ ወደገደለው ልሂድ እባካችሁ፡፡ ቀልድና መጠጥ ቤት ያጠፋል፡፡

ሰሞኑን ወደ ትግራይ ሄጄ ነበር – ከምር፡፡ ትግራይ ውስጥ ወንድ ልጀ ያለ አይመስልም፡፡ ሁሉም ተነቅሎ ለማያዳግም አጠቃላይ ክተታዊ የወረራ ዘመቻ ወደተቀረችዋ ኢትዮጵያ የተበገሰ ይመስላል፡፡ በተለይ በገጠር ቤቶች – ብዙዎቹ የድንጋይ ቤቶች – ተንሻፈው ተንጋደውና ፈርሰው ካለሰው ብቻቸውን ይታያሉ፡፡ አንዳንዶች ተዘግተዋል፤ አንዳንዶች ክፉኛ ፈራርሰው ወደጢሻነት ተለውጠዋል – የነማን ቤቶች እንደሆኑ ወዲያውኑ ትገምታላችሁ፤ የነዚያ ቤቶች ጌቶች አዲስ አበባ ላይ በልዩ ሊሞዚን ሲምነሸነሹ በምናባችሁ ይታዩኣችኋል – ከዚያች እልም ያለች በረሃማ የገጠር መንደር ወጥተው ከአዲስ አበባም አልፈው በቅጽበት ውስጥ እልም ወዳለ የኒዮርከና ላስቬጋስ ከተማ ሲሻገሩ ይታያሁ!  እንዲህ የሚያርገው ደግሞ ባላጋሩ ያልተማረ ትግሬ ነው፡፡ ብዙዎቹ የገጠር ከተሞች የተወረሩ ይመስላሉ፤ የሚገርመው ግን ያን ሁሉ በረሃና የድንጋይ ጫካ እያቆራረጠ በየርሻውና በየፈፋው ብቅ ጥልቅ እያለ የሚታይ ንጹሕ የመጠጥ ውኃ ቧምቧ አለ፤ ኦ! ትግራይ ታስቀናለች፤ ልጆቿ ክሰዋታል፡፡ ሥልኩ፣ ውኃው፣ መንገዱ፣ ት/ቤቱ፣… ሁሉም ከሞላ ጎደል ተሟልቶ ይታያል – እንደሚባለው አይደለም፤ በተንጣለለው ገደላማ ኹዳድ እንደዘንዶ ተጋድሞ የሚታየውን ወፍራም የውኃ ቧምቧ ስታዩ “ምነው ይህን መሰል ነገር በጎጃምና በጎንደር ገጠሮች ማየት በቻልኩ?” ሳትሉ አትቀሩም እንደኔ በ“ዐማራነት ልክፍት ከተነደፋችሁ”፤ ወይ ወያኔ ለካንስ ይህን ያህል ቀንድ ማነው ዐይን አውጣዎች ኖረዋል? ችግሩ ግን እነዚያ የገጠር ሥፍራዎች ሰው አይኖርባቸውም – ትግሬ ያለውስ አዲስ አበባ ላይ ነው ወንድሞቼ፡፡ አዲ አበባ ውስጥ በየትም ሥፍራ ስትንቀሳቀስ  በትግርኛ ቋንቋ የሚያወራው የሕዝብ ቁጥር ከሀገሪቱ የሕዝብ ቆጠራ ተመጣጥኖ ጋር ስታወዳድር ትግርኛ ተናጋሪው እጅግ ብዙ ነው፡፡ ወያኔ ቆሜለታለሁ ለሚለው ወገን ብዙ ደክሟል በውነቱ፡፡ ቅናት አይደለም – ከሆነም በመንፈስ ቀናሁ ልበላችሁ፡፡ እንዲህ የሚያኮራ ውድብ ቢኖረኝ ብዬ ካብ መዓንጣየ – ካንጀተቴ – ቀናሁ፡፡ በፈርሳሙ ብአዴንም በኩራት ተኮፈስኩ፤ ኧረ በዐማራው በረከት ስምዖንም አምርሬ ቀናሁ! በስድብ ባቦነነኝ በአረምነው መኮንንም ቀናሁ፡፡  በዐማራው አካባቢም ስላለፍኩ ብአዴን ስላልሠራቸው የልማት ንድፎች ክፉኛ ኮራሁ፡፡ ቀንደኛው ድርጅታችን ባልሠራልን ነገር ካልተጀነንን በምን እንጀነን? ብቻ በየገጠሩ ያሉ ብዙ ትግሬዎች  ተለቃቅመው “ሪፓብሊኳ”ን በመተው ወደምድረ ገነት ወደ “ኢትዮጵያ” ሄደዋል ማለት ይቻላል – “የነብርን ጅራት አይዙም፣ ከያዙም አይለቁም” ብለው ያመረሩ ይመስላሉ፡፡ ከሞላ ጎደል ሕይወት ያላት የምትመስለው መቀሌ ማለትም መቐለ እንጂ ሌሎቹ ኦና ናቸው፡፡ ምሥጢሩ ታዲያ ወዲህ ነው፡፡ እመለስታለሁ …

ዛሬ ለዚህች ማስታወሻ መጻፍ ምክንያት የሆነኝ ነገር አለ፡፡ በመጣሁበት መኪና ውስጥ ሰዎች ሲያወሩ የሰማሁት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ሕወሓት ያመጣባትን ዳፋ ትግራይ ከፍላ ለመጨረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዓመታትም አይበቋትም፡፡ ወያኔ ትግራይን በሰው ደም፣ በሰው አጥንት፣ በሰው ላብና ወዝ፣ በሰው ሀብት፣ በሀገር ንብረትና ወደር በሌለው ግፍ አጨቅይቷት  -እንደ እግዚአብሐየር ፈቃድ – ኢንሻአላህ – በጣም በቅርቡ መሰናበቱ ስለማይቀር ወዮ ለትግራይና ሕዝቧ!!! ለማንም ፈርቼ በማላውቀው ሁኔታ ፈራሁላት፡፡ ትዕቢትና ዕብሪት ጥፋትንና ውርደትን ቀድመው ይመጣሉና እነኚህ የዲያብሎስ ሽንቶች ሒሣባቸውን የሚያወራርዱበት ዘመን በፍጥነት ሲመጣ ይታየኛል፡፡ የኛ መጥፎ ሥራ እነሱን እንዳመጣብን ሁሉ የነሱ ግፍና በደል ደግሞ እነሱ ቀርተው ትግራይ ልትሸከመው የማትችለውን የመከራ ዶፍ እንደሚያመጣ የእግዜሩን ትተን ታሪክን ብቻ በማጣቀስ መረዳት ይቻላል፡፡ መተት ይረክሳል፤ ደንቃራ ይከሽፋል፡፡ የላላ ይጠብቃል፤ የጠበቀ ይላላል፡፡ የተራቡ አልቅቶችና መዥገሮች ወፍረውና አብጠው ይፈነዳሉ፡፡ ከብቶችም ያኔ ነፃ ይወጣሉ፡፡ የመዥገሮችና የአልቅቶች ዘመን ሲገባደድ የከብቶችና የደገኛ እንስሳት ዘመን ይብታል፡፡ ያኔን ለማየት ዕድሜና ጤና መለመን ብቻ ነው፡፡

ታዲያ ሰው የሚያስፈልገን አሁን ነው፤ ትልቅ ሽማግሌ ትግሬ፣ ትልቅ ሽማግሌ ዐማራ፣ ትልቅ ሽማግሌ ኦሮሞ የሚያስፈልገን አሁንና አሁን ብቻ ነው፡፡ ከደፈረሰ በኋላ ማቄን ጨርቄን ቢሉ ዋጋ ዘይብሉ ከምዝብሃል ኢዩ ሀወይ፡፡ ሦርያንና “ታላቋን” ሶማሊያ ያዬ በእሳት አይጫወትም እህቶቼ፡፡ እርግጥ ነው “ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ” እንዲባል የነዚህ መሬት የጠበበቻቸው ዐይነ ሥውራን ትግሬ ገዢዎቻችን አይተውት ቀርቶ አስበውት የማያውቁት እርዚቅ ውስጥ በታሪካዊ ጠላቶቻችን ሁልአቀፍ ዕርዳታ ታግዘው ሲነከሩበት ጊዜ ቀን የማይገለበጥ መስሏቸው ከሰማይ በታች የማይሠሩት የበደል ዓይነት ጠፋ – በአንድ በኩል እነሱም ያሳዝኑኛል ታዲያ፡፡ ሰው በእርኩስ መንፈስ ካልተሞላ በስተቀር መቼም እነሱ የሚሠሩትን ዘግናኝ ነገር በሰውኛ ተፈጥሮ መሥራት የሚከብድ ይመስለኛል፡፡ ለይቶላቸው ዐበዱ እኮ! ምድራዊ ንዋይና ሥልጣን እስከዚህ ያሳብዳል? እንዴ፣ እንደዚያ እንደፈረንሣዩ አንድ ንጉሥ ‘after me the deluge’ (እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል …) እንዳለው ይሉኝታና ሀፍረት በጭራሽ አጥተው የለየላቸው ጅቦችና ዓሣሞች ሆኑ እኮ፡፡ እኔ እምለው ከዚህኛው ወገን ባይገኝ ወይም ለመስማት ፈቃደኛ ባይሆኑ ከነሱ በኩል “ኧረ ይሄ ነገር አያዛልቅም!” ብሎ የሚመክራቸው ሃይ ባይ ምራቅ የዋጠ ሰው እንዴት ይጥፋ? ለነገሩ በምን ጆሮ ይሰማሉና! ጆሯቸው በበቀልና በጥላቻ እንዲሁም በሀብት አራራ ያበደ ፍላታቸውን እንጂ ሌላ ነገር መች ያዳምጥና? …

እንዲህ ሲሉ ሰማሁ አብሬያቸው የመጣሁት ሰዎች፡፡ በ2004 ዓ.ም አካባቢ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ አካባቢ ጥቂት ሰዎች የጨረቃ ቤት ይሠራሉ፡፡ ጥቂት ጊዜ ቆይቶ ግን ቀበሌና ክፍለ ከተማው መጥተው ያፈርሱባቸዋል፡፡ ከነዚያ ከፈረሰባቸው ሰዎች ውስጥ ብዙዎቹ ትግሬዎች ነበሩ፡፡ እነዚያ ትግሬዎች ወደ ክፍለ ከተማ ይሄዱና አብዚሎ ቅብዚሎ ይላሉ፡፡ የቀሪዎቹ (ባጋጣሚ ሆኖ ዐማሮች ናቸው) ጩኸት የቁራ ጩኸት ሆኖ ሲቀር እነዚያኞቹ – የመጀመሪያ ደረጃ ዜጎቹ “አይዟችሁ፡፡ …” የለም ይህን ነገር በትግርኛ ልበለው – “አጆሃትኩም አህዋትና! ወዲተጋሩ ኮይንኹምስ ዝትንክፈኩም የለን፡፡ ውፅዔት ቃልሲኩም ስለዝሆነ ንኣሃትኩም ዝከውን ነገር ብቅልጡፍ ተመኻኺርና ገለ ነገር ክንግብረልኩምኢና ቃል ንኣቱ… ብትዕግስቲ ክትፀብዩና ይግብኣኩም ድማ … ንኣሃትኩም ዘይኮነ ነገር …” አሉና እነዚያን ዐማሮች አመናጭቀው ካባረሩ በኋላ – እንዲህ ጭምልቅልቅ ያለ ነገር ስናገርና ስጽፍ ተገድጄ የወረድኩት መውረድ እየታየኝ ራሴን በራሴ እንዴት እንደምጸየፈው አትጠይቁኝ – ለትግሬዎቹ ሌላ መንገድ ፈለጉና አሁን እነዚያ ትግሬዎች ቢጠሯቸው የደነቆሩ ሚሊዮነሮች ሆነዋል -አሁን እነሱ የሚይዙት መኪና በትንሹ በ500 እና 600 ሺህ ብር የሚገመት ነው፤ “ሀ” ራስህን አድን ለጫማው በኋላ ይታሰብበታል እንደተባለው ማስታወቂያ ነው ነገሩ፡፡ ከጨረቃ ቤት ባዶ ሕይወት ሁለትና ሦስት ዓመታት ውስጥ ወደሚሊዮነርነት፡፡ እንደትግሬ ወያኔ ያለ ደደብና ደንቆሮ ቀትረ ቀላል ቡድን በዓለም ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አያውቅም፡፡ በነገራችን ላይ እነዚያ ዐማሮችም ከተፈረደባቸው የዘር ማጽዳትና ጭፍጨፋ ማምለጣቸውና ጨረቃ ቤት በማጣት ብቻ መታለፋቸው ብቻውን ትልቅ ጠጋ ነው፡፡ ዓለመኛ ዳቦ ቅቤ ቀቡኝ ይላል እንዲሉ ሆኖ እነዚያ ምስኪኖች አዲስ አበባ ላይ “መዘባነናቸው” በጃቸው እንጂ ሌላ ቦታ ቢሆን ኖሮ ጠገባችሁ ተብለው በአጋዚ ይረሸኑ ነበር፡፡ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ እኮ እኮ ደም አፍልቶና አንተክትኮ ወደ ጋዝነት የሚለውጥ ነው፡፡

እነፕሮፌሰር መስፍን ግን እንዳይቆጡኝ እፈራለሁ፡፡ እርሳቸው አንዲት አፓርትማ ውስጥ መሽገው የኛን የተራ ዜጎችን እንግልትና የትግሬዎችን የዱባ ጥጋብ ማየት ስላልቻሉ በፍርደ ገምድል ብይናቸው እነሱም እንደኛው አልተጠቀሙም ይላሉ፡፡ ማለቴ እኛ በትግሬ አገዛዝ እንዳልተጠቀምን ሁሉ እነሱም አልተጠቀሙም ባይ ናቸው፡፡ ሰው መቼም መስማትና ማየት የሚፈልገውን ብቻ እሰማለሁና አያለሁ ብሎ ከቆረጠ  ከዚህ ዓይነቱ ሞገደኛና ሸውራራ አመለካከቱ ፈጣሪ ነፃ እንዲያወጣውና እውነቱን እንዲያመላክተው ከመጸለይ በስተቀር ምን ማድግ ይቻላል? ሆ! ትግሬ አልተጠቀመም? ድራማዊ አስቂኝ ዐረፍተ ነገር፡፡

የባንዳ ልጆች ጉድ ሠርተውናል፡፡ የተሰባበርነው ሁሉ እንዴትና መቼ እንደሚጠገን ሳስበው ይጨንቀኛል፡፡ ኢትዮጵያ የሌሎቹም ያልሆነች ያህል ሌሎች እንዲህ ባይተዋር ሆነው ስታዩ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንደጪስ በንና ጠፋች ወይ ትላላችሁ፡፡ በርግጥም ኢትዮጵያ አሁን የለችም፡፡ ሌላው ሁሉ የትግሬ አሽከርና ገረድ ሆኖ ትግሬዎች የጠገቡ ጌቶች ሆነዋል – ማይምነት ደግሞ ትልቅና መድኃኒት የሌለው በሽታ ነው፤ ከሞላ ጎደል ሁሉም ወያኔዎች ምናልባት ከማንበብና ከመጻፍ ውጪ ብዙም ያላለፉ ፍጹም ማይማን ናቸው፡፡ በዚያ ላይ ጥጋብ አይችሉም፡፡ ጥጋብ ይሆኑትን አሳጥቷቸዋል፡፡

ጥጋብን የማያውቅ ሰው ደግሞ አይግጠምህ፡፡ አስተሳሰበ ድውይ ደካማ አሸናፊ አይግጠምህ፡፡ ከአፍ እስካፍንጫው ማሰብ የማይችል “አሸናፊ ጀግና” አይግጠምህ፡፡ ብሃጺሩ ቀን አይጉደልብህ፡፡ ወያኔ ትግሬዎች ምን ዓይነት ጉዶች ናቸው በል? መጥኔ ለጤናማ ትግሬዎች! ሀፍረቱን እንዴት ይችሉት ይሆን? የ17 ዓመት ታዳጊ ከትግራይ ገጠር አዲስ አበባ መጥቶ በሣምንታት ጊዜ ውስጥ ሚሊዮነር ሲሆን የሚታዘብ ጤናማ ትግሬ በሀፍረት እንደሚሸማቀቅ መቼም ግልጽ ነው፡፡ አይ… እኔ እንኳንስ በግማሽ ብቻ ትግሬ ሆንኩ! ሙሉ በሙሉ ብሆን ኖሮ ነገን በማሰብ ከአሁኑ ነበር አንገቴን ደፍቼ በሰቀቀን የምሞተው፡፡ ውይ ወያኔዎች ሲያሳፍሩ! ሱቅ እንደገባ ሕጻን ዓይነት ሁሉንም ለራሳቸው አፍሰው ሌላውን ባዶ ሲያስቀሩ ስታዩ እነዚህ ሰዎች ምን እንደነካቸው በማሰብ ለነሱም ሣይቀር ታዝኑላቸዋላችሁ፡፡ ደግሞም እምብርት የሚባል ነገር አልፈጠረባቸውም፡፡ እንዴ – አንድ ሰው እኮ በልቶ ይጠግባል፤ ጠጥቶ ይረካል፡፡ ሲያመነዥኩና ሲጋቱ መዋል የጤንነት ምልክት አይደለም፡፡ ለከት የሚባል ነገር አለ፡፡ የሁሉም ነገር ዳር ድንበር አለው፡፡ ለፍቅርም ለጥላቻም ወሰን አለው፡፡

መጨረሻቸው ሦስት ክንድ ለሆነው ቦታ እነሱ 50 እና 60 ቦታ ይዘው አይረኩም – በዚያ ላይ ያልጠገቡ በመሰላቸው መስክ ማታውኑ ዐዋጅ ያወጡና ይደነግጋሉ – ትንሽ ቆይተው ደግሞ ያወጡትን ዐዋጅ በአነስተኛ ቁራጭ ወረቀት ወይም በሥልክ ቀጭን ትዕዛዝ ይሽሩታል፡፡ ለምሳሌ መሬት ከፈለጉ መሬት መውሰድ እንደሚቻል እነሱ ወስደው እስኪጨርሱ ድረስ ዐዋጅ ያውጃሉ፤ የሚፈልጉትን ያህል መሬት በየውሻቸው ስም ሣይቀር ይዘርፉና ያን ዐዋጅ ይሰርዙታል፡፡ ለነገሩ ዐዋጁ ለነሱ ብቻ እንጂ ቀድሞም ቢሆን ለሌላው አይሠራም፡፡ ዕብድና ዘመናይ እንደልቡ ነው – እነሱም፡፡

ከአንድ እንጀራ የማያልፍ ሆድ ይዘው በሚሊዮኖችና በቢሊዮን የሚገመት ገንዘብ በደቂቃዎች ውስጥ ሲያገለባብጡ በዚህም አይረኩም፡፡ ከምን ተፈጠሩ? ገድለው የማይረኩ፣ በልተውና ጠጥተው የማይረኩ፣ አሥረው፣ ደብድበውና አሰቃይተው የማይረኩ፣ በሕይወት ያለን ገድለውም ስለማይረኩ ዐፅምን ሣይቀር ከመቃብር አውጥተው የሚቀጠቅጡና በዚያም ዕርካታን የማያገኙ፣ ህግን መሬት ላይ ጥለው በመደፍጠጥ መጫወቻ እስሚያደርጓት ድረስ ቢዘልቁም በዚያም የማይረኩ፣ ዐማራን ጨፍጭፈው የማይረኩ፣ ቂምን ከ40 ዓመታት በላይ በልባቸው ቋጥረው በመያዝ እየታደሰ በሚሄድ በቀልና ጥላቻ ሀገርንና ሕዝብን በታትነው የማይረኩ፣ድንበርንና መሬትን ለባዕዳን ሸጠው በሚያገኙት ሥፍር ቁጥር የሌለው ገንዘብ የማይጠግቡ፣ ዓለምን በማታለል ወደር ያልተገኘላቸው እነዚህን የሲዖል ትሎች ፈጣሪ ከየት ላከብን? ለመሆኑ እነዚህን መሰል የእሳት ጅራፎች በሺህ ወይ በሁለት ሺህ ዓመታት ስንቴ ይሆን ፈጣሪ ወደ አንድ ሕዝብ ለቅጣት የሚልካቸው? ይህ ዓይነቱስ ቅጣት አመክሮ የለውምን?

እነፕሮፍ አንዴ ስሙኝማ – ለታሪክ ምሥክርነት ትሆኑ ዘንድ መከላከያን፣ ደኅንነትን፣ ውጭ ጉዳይን፣ ፖሊስን፣ ጉምሩክን፣አየር መንገድን፣ አየር ኃይልን፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤችን፣ ንግድ ቤቶችን፣የከተማ ቦታዎችን፣ ሕንፃዎችን፣ የትምህርት ተቋማትን፣የንግድ ማዕከላትን፣ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን፣…. ለጥቂት ጊዜ ጎብኙ፡፡ ከዚያ እውነትም ለአካለ ዘረፋ የደረሰ ወጣት ወያኔ ትግራይ ውስጥ እንደሌለ ያኔ ትረዳላችሁ፡፡ መጥኔ ለወደፊቷ ትግራይ! ኹልና ጥዑይ ውልቀሰባት ተጋሩ ህጅ እዩ ብዙህ ማሰብ ዜድልየና፡፡ እዚዮም አሻታት ንኣዲና ከምዘሃሰቡ መሲሎምሲ ከመይ ገይሮም ከምዝቀተልዋ ህጅ እዩ ምህሳብን ምጭናቅን፡፡ ጊዜ ካለፈ በኋላ የፈሰሰ አይታፈስምና በነዚህ ወራዳ የባንዳ ልጆች ምክንያት ትግራይ መከራና ስቃይ ስትዝቅ ይታየኛል – አሁን ትግራይ ያለች የመሰለችው በባንዳዎቹ ልጆች ጥንካሬ ሣይሆን በፈጣሪ ቸርነት ብቻ ነው – ነገር ግን ይህ ትዕይንት እንዳለ እስከመጨረሻው አይቀጥልም – ሁልጊዜ ፋሲካ ደግሞ ኖሮ አያውቅም፡፡ ፈጣሪ ክፉዎቹም ደጋጎቹም ሁሉም ልጆቹ ስለሆኑ ለክፉዎቹም ለደጋጎቹም እኩል ዕድልን እንደሚሰጥ መረዳት ይገባል – ወያኔዎች “ደግ ናቸው” ብለን ብናምንም እንኳን “ለሁሉም ጊዜ አለው” ለማለት እንደፈለግሁም በታሳቢነት ይያዝልኝ፡፡ እናም “ክፉዎቹ ዐማሮችና ሌሎች ጭቁኖች” ተራቸውን የሚረከቡበት ዘመን በርግጠኝነት መምጣቱ አይቀርምና ከአሁኑ ሲታይ ለፍርድ የሚያስቸግር በሚመስለው የወያኔዎች ጥጋብ ትግራይና ተጋሩ እንዳይጎዱብን ከአሁኑ እንጠንቀቅ የሚል አስተያየት አለኝ፡፡ የፈሩት መድረሱ የጠሉት መውረሱ ደግሞ ያለ ነው፡፡

እንደኔ ከሆነ በኅሊና ሠሌዳየ አሁን የሚታየኝ ክፉ ነገር ሲፈጸም ከማየቴ በፊት አሁኑኑ ብሞት ሞትኩ አልልም – በርግጥም ዐረፍኩ እንጂ፡፡ ሰው ሰውነቱን ለምን ይነጠቃል? ሰው በመግደልና በማሰር፣ በመዋሸትና በመቅጠፍ፣ በመዝረፍና ሁከትን በመፍጠር እንዴት ይደሰታል? ለአብነት አንድ ጭቅላ ሕጻን፣ “ዐማራ” የሚል ወያኔያዊ ታርጋ ስለተለጠፈበት ብቻ ካለምርጫው በተወለደበት ዘውግ ምክንያት ከነሕይወቱ በበደኖ ገደል የሚለቀቀው ገዳዩና አስገዳዩ ስንት ሺህ ዓመት ሊኖሩ ነው? ሌባ ጣታችንን ወደሰው ከመቀሰር ይልቅ ውስጣችንን መመርመሩም ክፋት የለውም፡፡ ባለፉት 25 ዓመታት ዐማሮች ላይ የደረሰው ግፍና ሰቆቃ የትኛውም በምናብ የተፈጠረ በሌሎች ማኅበረሰቦች ላይ ደረሰ የተባለ ግፍና ሰቆቃ አይወዳደረውም፡፡ ዱሮ ግፍ ተፈጽሞ ቢሆን አሁን በሚፈጸም ግፍ ሥርየት አያገኝም፡፡ ክፋትን በክፋት መመለስ መፍትሔ ሣይሆን ችግርን ማባዛት ነው የሚሆነው፡፡ ይህ ዓይነት ወያኔያዊ አካሄድ ደግሞ ለሀገራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች መፍትሔ አይሆንም፡፡ ከሁሉም የሚበልጠው ወደኅሊናችን መመለስና ራሳችንን መመርመር ነው – አሁኑኑ!!

በሌላ አቅጣጫ ጅሎችና ነሁላሎች ኢትዮጵያውያን በሌለች ሀገር ሲጨቃጩ መስማት የሚገርም ነው፡፡ ጠላት ባቆመላቸው የጡት ቁራጭ ሀውልት፣ በፈጠራ ተደርሶ ዘወትር በሚነበነብ ስብከት ፣ በጠላት ሠርጎ ገቦች መሠሪ ውትወታ፣ በሆድ አዳሪዎች የኅሊናቢሶች ሸርና ተንኮል… የጋራ ትግሎች እየመከኑ የተናጠል ትግሎችም ከድጥ ወደማጥ እየገቡ እህት ነፃነት ከአድማስ ባሻገር ቆማ በምናብ ስትታይ መታዘብ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠርን እስከወዲያኛው ያስረግማል፡፡ ሥልጣን በሬኮማንዴ ውጪ ሀገር ይሄድ ይመስል መቶና ሁለት መቶ ድርጅቶችን በውጪ ሀገራት ነጋ ጠባና አንዳቸውን በአንዳቸው ላይ መመሥረቱ ደግሞ ጥቅም እንደሌለው ከታወቀ ቆይቷል፡፡ በዚህ የተበላ ዕቁብ የሚጃጃሉ ወገኖች ቁጥርም ቀላል አይደለም፡ አየ ኢትዮጵያ! የዕንቆቅልሽ ሀገር፡፡

The post በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ ወያኔያዊ የክተት ዘመቻ (ነፃነት ዘለቀ) appeared first on Zehabesha Amharic.

በኦሮሚያ ክልል ሹምሽር ተካሄደ |ተጨማሪ ባለስልጣናት ከቦታቸው ተነሱ

$
0
0

ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው የኦህዴድ የከተሞች ዘርፍ የፖለቲካ የድርጅት ኃላፊ አቶ ለሲሳ ሃዩ ተነስተው በምትካቸው የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በነበሩት ሳዳ ነሻ ተተክተዋል።
OPDO 5

እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ የነበሩት አቶ በዙ ዋቅቢሳ የኦሮሚያ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ዘርፍ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ በዚህ ቦታ ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ሰለሞን ከቹማ የፕሬዝዳንቱ አማካሪ በመሆን ተመድበዋል።

በኦሮሚያ ክልል ኦህዴድ ያካሄደው ሹምሽር ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር በተያያዘ የተደረገውን ግምገማ ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ምንጫችን ጨምሮ ገልጿል።

የኦህዴድ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው የተመደቡት አቶ በከር ሻሌ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ትላንት ከሰዓት በኋላ ድረስ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መ/ቤት ሥራቸው ላይ የነበሩ ሲሆን በእርሳቸውም ቦታ እስካሁን የተተካ አዲስ ሰው አለመኖሩ ታውቋል።

አቶ በከር በሙስና ወንጀል የተከሰሱትን አቶ መላኩ ፈንታን ተክተው ወደ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ተሹመው ከመምጣታቸው በፊት የአዳማ ከተማ ከንቲባ ነበሩ። ከዚያም ቀደም ብሎ የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ማኀበር ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆንም አገልግለዋል።

The post በኦሮሚያ ክልል ሹምሽር ተካሄደ | ተጨማሪ ባለስልጣናት ከቦታቸው ተነሱ appeared first on Zehabesha Amharic.

መልስ ለኃይሉ የሺወንድም፤ በወልቃይት ፀገዴ ባህልና ማንነት ጥያቄ እኔም ቅሬታ አለኝ!

$
0
0

ከዚህ በታች ያለው ፅሑፍ የአቶ ኃይሉ የሺወንድም የመጀመሪያ 8 ገፅ ፅሑፍ እንደወጣ የተዘጋጀ ነበር። ሆኖም በጊዜ ዕጥረት ምክንያት ትየባውንና የፊደል ለቀማውን ሳልጨርሰው ሁለተኛውን “መልስ ለጀለሶቼ” በሚል 15 ገፅ ፅሁፍ ተከተለ። ታዲያ ፅሁፌን የማቀርበው መጀመሪያ በተዘጋጀው መሠረት ምንም ሳይቀየር አቶ ኃይሉ ካቀረበው 15 ገፅ ፅሑፍ አንድ አራት ነጥቦች ብየ መጀመሪያ ወደተዘጋጀው ፅሑፌ እወስዳችኋለሁ።
በመሠረቱ እውነቱን ምን እንደሆነ እየታወቀ ተከራክሮ አሸናፊ ሆኖ ለመገኘት ብቻ እውነትን እየካዱ እርስ በርስ መወነጃጀሉ ለማንም አይበጅም፤ ምክንያቱም እውነትና ንጋት እያደረ ይጠራልና። እኔ እስከማውቀው እነ አቶ ጎሹ ገብሩ፤ አቶ ቻላቸው አባይ፤ አቶ አባይ መንግሥቱና መሰሎቻቸው ሠፊው የወልቃይት ፀገዴ ህዝብና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቃቸው የህዝብ ልጆች መሆናቸውን ነው። ይህን ስል ደግሞ ዝም ብዬ ሳይሆን በሥራቸው ነው። ለምሳሌ “ልሳነ ግፉአን”በሚል የሲቪክ ድርጅት መሥርተው ከዛሬ 4ና 5 ዓመት በፊት በኢሳት ቴሌቪዥንና የአርበኞች ግንቦት 7 ሬዲዮ ቀርበው የወልቃይት ፀገዴ ህዝብ ችግር ሲያጋልጡ ለዓለም ህብረተሰብ ሲያሳውቁ የምናውቃቸው ጀግኖቻችን ናቸው።
አንተ ግን በሥም ማጥፋት ወንጀል ትከሳቸዋለህ። ነገሩ ከአነጋገር ይፈረዳል፤ ከአያያዝ ይቀደዳል ነው። እነሱ አንተ ያልሆንከውንና ያላደርገክውን አልፃፉም። የፈረደ የሺወንድም ወንድም፤ የአዜብ መስፍን ያክስት ልጅ መሆንህንና ወያኔ ያወጣውን የመሬት ቅርምት ፖሊሲ ለመተግበር ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ኢንቨስት ልታደርግ እንደገባህ አንተም አልካድክም። ታዲያ ከዚህ የበለጠ ወያኔን መደገፍ ምን ሊመጣ ነው? እኛ ወያኔዎችን -የወልቃይት ፀገዴ ህዝብ እያሰሩ እየገደሉ መሬታችን ወሰዱ – ብለን ከተቃወምን አንተ የጋምቤላ ወገኖቻችንን አፈናቅለህ መሬት ከተቀበልክ ከወያኔ በምን ተለየህ? የራስህ እንዳይበቃ ደግሞ የወልቃይት ፀገዴ ወጣቶችን የጋምቤላን መሬት እንዲቀራመቱ ታበረታታለህ። አንተ ራስህ ባመንከው መሠረት ማለት ነው።
ሌላው ነገር ከድርጅት ድርጅት ይቀያይራሉ ብለህ እንደምሳሌ ያቀረብከው ከኢሕአፓ ወደ ግንቦት 7 እና ወደ የወቃይት ፀገዴ የአማራ ማንነት ነው። እነዚህ ሁሉም እኮ ህብረብሔር ድርጅቶች ናቸው። ከቤትህ ወደቤትህ እንደመሔድ ነው የሚቆጠረው። ለውጥ የሚባለው ከህብረብሔር ወደጠባብ የዘር ድርጅት ለሚሔድ ነው። በኢሕአፓ ያልታቀፈ ግለሰብ እንዳልነበር ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው ነገር ነው። ምን አዲስ ነገር አለው?
በመቀጠልም “ዕውቀት የላቸው፤ ሃብት የላቸው፤ ባዶ ባዶ ናቸው” ብለሃል። መቼም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሰር ወይም ሳይንቲስት ይሁን ካልተባለ በቀር ያላቸው ዕውቀት በቂ ነው። አንተ ሰውን የምትለካው በምንድን ነው? በሀብት ነው እንዴ? በሀብት ከሆነማ፤ ዛሬ ሀብታሞቹ እነ ሳሞራ ዩኑስ፤ ስብሀት ነጋ፤ አባይ ፀሀየ፤ ሼክ አላሙዲን የመሳሰሉ ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝብማ ሁሉም ደሃ ነው። እኔ እስከማውቀው እነ አቶ ጎሹ ገብሩ፤ አቶ አባይ መንግሥቱ፤ አቶ ቻላቸው አባይና መሰሎቻቸው በጣም ስኬታማ ሰዎች ናቸው፤ ሁሉም ጥሩ ጥሩ ቤተሰብ መስርተው ልጆቻቸውን በሥነሥርዓት ያሳደጉ፤ የኳሉ፤ የዳሩና ለወግ ለማዕረግ ያበቁ አባወራዎች ናቸው። ለኔ ከዚህ በላይ ሥኬት የለም።
ሌላው በአፄ ፋሲል ዘመን ጎንደር ውስጥ ከትግሬ ይልቅ በብዛት ኦሮሞች ይኖሩ እንደነበር እየገለፅክ፤ በአፄ ምንሊክ ዘመን ደግሞ ኦሮሞዎች እንደባሪያ ሲሸጡ ሲለወጡ እንደነበሩ ትገልፃለህ። የወያኔ ውሸት እንዳይበቃን! ታዲያ በ17ኛው ክፍለዘመን ኦሮሞች ጎንደር ከነበሩ ወረራውን ቀድሞ የጀመረ ማን ነው? ኦሮሞች ወደጎንደር ሲመጡ ዕቅፍ አበባ ይዘው ነበር እንዴ የመጡት? ፈረስ፤ ጋሻና ጦር መስሎኝ! ምነው? ሁሉም ወገኖችህ ናቸው። ለምን ታደላለህ? ፅሁፍህ የመረረ የአማራ ጥላቻ እንዳለህ ያመለክታል። ወያኔዎች እስኪበቃን የነገሩን በቂ ነበርኮ! የመረረ የአማራ ጥላቻ እንዳለህ የሚያመላክት ሦስት ምሳሌዎች ልጥቀስ!
አማራው ገዢ ስለነበር የበታችነት አይሰማውም ብለሃል። እውነቱ ግን የተውጣጡ ገዢ መደቦች ኢትዮጵያን ይገዙ ነበር እንጂ የአማራው ማህበረሰብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጭቁን ነበር። ለዚህ ነው የአማራ ወጣቶች ለውጥን ፍለጋ መሥዋዕትነት ሲከፍሉ የነበሩት፤ ያሉትም።
2. በወልቃይት ፀገዴ ውስጥ በወያኔ የደረሰውን በደል ተከድኖ ይብሰል እያልክ፤ ተራ ለሆነው “የአማራ ገዢዎች” አደረሱት የምትለውን በደል በዝርዝር አንድ ሳታስቀር ፅፈሃል።
3. ወያኔዎች “አፄ ምንሊክ ጡት ቆረጡ” እያሉ ነበር የሚከሷቸው። አንተ ደግሞ ጨምረህ “ኦሮሞዎችን ሸጡ፤ ለወጡ” እያልክ በ17ኛው ክፍለ ዘመን ኦርሞዎች ጎንደርን ሲወርሩ ስላደረሱት በደል ግን ያልከው ነገር የለም። እንግዲህ ይህን ካልኩኝ ቀደም ብሎ ወደተዘጋጀው ፅሁፌ ልመልሳችሁ።
በቅርቡ “የወልቃይት ፀገዴ ባህልና የማንነት ጥያቄ” በሚል ርእስ ኢትዮሚዲያ ላይ የወጣውን ፅሑፍ አይቼዋለሁ። የምስማማባቸውና የማልስማማባቸው ነገሮች ቢኖሩም አንተ የወገኔ ጉዳይ ያገባኛል፤ ይመለከተኛል ብለህ መስሎ በታየህ ሃሳብ ላይ ውድ ጊዜህን ሠውተህ የድርሻህን ማበርከት በመቻልህ ከልብ አመሰግናለሁ። ቢሆንም ግን የምስማማባቸው ነገሮች እንዳሉ ሆነው በማልስማማባቸው ጉዳዮች ብቻ አስተየየቴን እሰጣለሁ። ይህ ማለት ግን ያንተ ተቃዋሚ ሆኜ ሳይሆን እንደወንድም ሃሳቤን ላጋራህ ስለፈለኩና በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከአንተ ዕይታ ውጭ ስለሆኑ ነገሮች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያህል ነው። እኔ በበኩሌ እንኳን አንተን ቀርቶ ህሊናቸውን በጥቅም ደልለው ጠላት ለሆነው ወያኔ እያገለገሉ ላሉ ወገኖችም ቢሆን ወደህሊናቸው ተመልሰው የበደሉትንና ያደሙትን ወገናቸውን ይቅርታ እንዲጠይቁና እንዲክሱ ከማበረታታት በስተቀር በፍፁም በጠላት ዓይን ተመልክቻቸው አላውቅም። ምክንያቱም በመሃላችን ክፍተት ፈጥረን እሳት በተወራወርን ቁጥር የኛን መኖር የማይፈልጉ እየተወራወርን ባለው እሳት ላይ ቤንዚን ለማርከፍከፍ ተዘጋጅተው የሚጠባበቁ የጋራ ጠላቶች እንዳሉ ስለምገነዘብ ነው። እንግዲህ ለመግቢያ ያህል ይህን ካልኩኝ ወደዋናው ቁምነገር ልመለስ፦
1ኛ. የመጀመሪያው ቅሬታዬ እኛ የወቃይት ፀገዴ ተወላጆች የአካባቢያችንም ሆነ የአገራችንን ጉዳይ በተመለከተ ስንወያይ ሆነ ስንፅፍ ወልቃይት ፀገዴ ብለን እንጂ ወልቃይትና ፀገዴን ለያይተን አንስተን አናውቅም። አንተ ግን 8 ገፅ ሙሉ ፅሑፍ ስታዘጋጅ በስህተት አንድ ጊዜ እንኳ ወልቃይት ፀገዴ ብለህ አልፃፍክም። ወልቃይቴ ሆኖ ከፀገዴ የማይወለድ፤ ፀገዴ ሆኖ ከወልቃይት የማይወለድ ፈፅሞ አይገኝም። አንተ ግን ወልቃይትና ትግራይ የሌለ ትውልድ ፈልገህ እያዛመድክ አንድ የሆነውን የወልቃይት ፀገዴ ህዝብ ግን ለየይተህ ትፅፋለህ። ጭራሽ አርበኛ ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንንን ወልቃይት ዘምተው በወልቃይት ህዝብ ላይ ወረራ እንደፈፀሙ በመግለፅ አንድ በሆነው ይወልቃይት ፀገዴ ህዝብ መካከል ጥላቻ ትዘራለህ። ይህ ነገር ለማን እንዲመቸው አስበህ ነው? አስተዋዩ የወልቃይት ፀገዴ ህዝብ በወዳጅ ዓይን የሚያይህ ይመስልሃል? ይልቅ አስፍቶና አርቆ በማሰብ እንደእኛ በዘረኛው የትግራይ ወያኔ ስለሚሰቃዩት ስለጠለምት ህዝብ ጭምር መፃፍ ነበረብህ። ካልሆነ ግን ወልቃይት ፀገዴን ባትከፋፍል መልካም ነበር።

2ኛ. የወቃይት ፀገዴ አማራነት ጥያቄ ውስጥ አስገብተኸዋል። የወልቃይት ፀገዴ አማራነት ለመገንዘብ እኮ ብዙ አያዳግትም። ለምሳሌ አንተ በግልህ አማራ ነኝ ብለህ ባታምን እንኳ ጎንደሬ ለመሆንህ ግን እርግጠኛ ነኝ መቶ በመቶ ታምናለህ። ስለዚህ የጎንደር የሆነ ግዑዝ አካል ወይም ሰብአዊ ፍጡር ሊቀርብ የሚችለው ለአማራነት እንጂ ለትግሬነት ወይም ለአፋርነት ሊሆን እንደማይችል ግልፅ ነው – ኢትዮጵያ ዘርን መሰረት ባደረገ አከላለል እስከተካለለች ድረስ። መቼም በአንድ ነገር እንደምንስማማ እርግጠኛ ነኝ። የወልቃይት ፀገዴ ህዝብ አመጣጥ ሊሆን የሚችለው ከአማራው ወይም ከትግሬው አልያም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ብሔረሰቦች ከአንዱ እንጂ ከሰማይ ዱብ እንደማይል ግልፅ ነው። እኛ የወልቃይት ፀገዴ ተወላጆች ከአሁን በፊት በአገራችን ኢትዮጵያ ዘርን መሰረት ያደረገ ክልላዊ መስተዳድር ስላልነበረ ዘራችን ከየት ነው የሚለውጉዳይ አሳስቦን አያውቅም ነበር። አሁን ግን ሳንፈልገው ኢትዮጵያን በዘርና ቋንቋ ከፋፍለው የወልቃይት ፀገዴ ህዝብ በጉልበት የትግራይ አካል ነው ብለው ህልውናችን የሚፈታተኑ ኃይሎች ስለመጡ “እኛ ማን ነን? አመጣጣችንስ ከየት ነው?” ብለን እንድንመረምር ተገደናል። ሆኖም ከዚህ አንፃር ማንነታችንን ለማወቅ ብዙ ሩቅ መሔድ አያስፈልገንም።
የወልቃይት ፀገዴ ሕዝብ በኢትዮጵያ የ3 ሺህ ዘመን ታሪክ አንድ ቀን እንኳ ከትግራይ ጋር ተዳድሮ አያውቅም። በመቀጠልም ለረጅም ጊዜ ወልቃይት ፀገዴ ቤጌምድር እየተባለ ሲጠራ ቆይቶ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በደርግ ዘመን ጎንደር ተባለና ከተማውም ክ/ሀገሩም ጎንደር ተባለ። አሁን ደግሞ የዘር ልክፍት የያዘው መንግሥት መጣና ጎንደር የነበረው አማራ ክልል ሲባል እንደጂኦግራፊአዊ አቀማመጣችን አማራ የማንባልበት ምክንያት የለም? እኛ ብቻ ሳንሆን ወሎዬ ወሎዬነቱ እየከሰመ አማራ፤ ጎጃሜ ጎጃሜነቱ እየከሰመ አማራ፤ ሸዋ ሸዋነቱ እየከሰመ አማራ ሲባል እኛ ደግሞ እንድወንድሞቻችን ጎንደሬነታችን እየከሰመ አማራ ልንባል ይገባል ነው። በሰበብ አስባቡ የወልቃይት ፀገዴ ሕዝብ ስሙ ይቀያየር እንጂ ለ3 ሺህ ዘመን የነበረበት ማንነቱ ማንም ሊቀይረው አይችልም። እንደዛሬ ተከዜን የምንሻገርበት ድልድይ ሳይሠራ የወልቃይት ፀገዴ ህዝብና የትግራይ ህዝብ በዓመት 6 ወር ብቻ ሲገናኝ – ተከዜ ከግንቦት ወር እስከ ጥቅምት ስለሚሞላ ማለት ነው – የወልቃይት ፀገዴና የአማራው ማህበረሰብ ግን ዓመቱን ሙሉ ከመገናኘት የሚያግደው ነገር የለም። ስለዚህ የኢትዮጵያ የ3 ሺህ ዘመን ታሪክ ሲሰላ የወልቃይት ፀገዴና የትግራይ ህዝብ ለ1500 ዓመታት ብቻ ሲገናኝ የወልቃይት ፀገዴና የአማራው ማህበረሰብ ግን ለ3 ሺህ ዘመናት አብረው ኑረዋል፤ ተዋልደዋል፤ ተዛምደዋል። ይህን ስል ግን ከትግራይና ከኤርትራ ጋር አልተዋለዱም ለማለት አይደለም። ግን ከመቶ አሥራ አምስት እጅ (15%) አይበልጥም። ከአማራው ማህበረሰብ ግን ቢያንስ ከመቶ ሰማንያ አምስት እጅ (85%) ያህል ተዋልደናል። ለዚህ ማስረጃ ካስፈለገ ደግሞ አብዛኛው የወልቃይት ፀገዴ የዘር ሐረግ ሲቆጠር የአማርኛ ስሞች እንጂ የትግርኛ ስሞች እጅግ ጥቂቶች ናቸው። ለምሳሌ ያንተ የራስህን እንኳ ብንወስድ ኃይሉ የሺወንድም – የሺወንድም ናደው – ናደው ብሬ – ብሬ ማሩ -እያለ ይቀጥላል። በእናትህ ወገን ስናይ ኃይሉ እንጉዳይ – እንጉዳይ ጎላ – ጎላ ጎሹ እያለ ይቀጥላል።

ለምሳሌ አንድ ሰው ስሙ መሃመድ፤ የአባቱ ስም አብደላ፤ የአያቱ ስም ኦስማን እያለ ከቀጠለ እስላምነቱ አያጠራጥርም፤ ወይም ስሙ ወ/ሚካኤል፤ ያባቱ ስም ፍቅረየሱስ፤ ያያቱ ስም ሣህለስላሤ ከሆነ ክርስቲያንነቱ አያጠራጥርም። ለምሳሌ ወደደቡብ ኢትዮጵያ ስንሄድ ስሙ በቀለ፤ ያባቱ ስም ተስፋየ ያያቱ ጌታቸው ይልና ቅድመአያቱ ፈይሳ ወይም አብዲሳ ይሆናል እና የዘር ሐረጉ ለማወቅ ከባድ አይሆንም። የአፄ ኃ/ሥላሴ እንኳ ብንወስድ ተፈሪ መኮንን – መኮንን ወ/ሚካኤል ብሎ ወ/ሚካኤል ጉዲሳ ይሆናል። ስለዚህ በከፊል የአፄ ኃ/ሥላሴን የዘር ሓረግ ለማወቅ አይከብድም። ስለዚህ ከሰማይ ዱብ እንደማንል ከተማመንን ቤጌምድር ተባልን ጎንደሬ፤ አማርኛ ዘፍነን ትግርኛ ተናገርን የዘር ሐረጋችን እንድሚያመለክተን ወደድንም ጠላንም አማሮች ነን።

ሌላው የትግራይ አካል ላለመሆናችን ማስረጃ ደግሞ በትግራይ ወያኔ እየተወሰደብን ያለው የጭካኔ እርምጃ ነው። ወገኖቻችን ናቸው ብለው ቢያምኑ ኖሮ እንደዚህ ባልጨከኑብን ነበር። እንዳውም ጭካኔያቸው የንጉስ ሰለሞንን ፍርድ ያስታውሰኛል። “ሁለት እናቶች አንድን ህፃን የኔ ነው የኔ ነው ተባብለው ተጣሉና ለፍርድ ይቀርባሉ። ህፃኑ ለሁለት ተቆርጦ ግማሽ ግማሽ እንዲከፋፈሉ በተወሰነ ጊዜ ያልወለደችዋ ህፃኑ ለሁለት እንዲቆረጥ ስትስማማ፤ የማትጨክነዋ ወላጅ እናት ግን እያለቀሰች ‘ለሁለት ከሚቆረጥ በቃ እሷው ትውሰደው’አለች። ታዲያ ጠቢቡ ንጉሥ ሰለሞን ግን የጨካኟን ሴት ቅጥፈትና ጭካኔ ተረድቶ ህፃኑን ለእውነተኛዋ እናት እንደሰጣት” ይነገራል። መቼም ምን ለማለት እንደፈለኩ ግልፅ ይመስለኛል።
3ኛ. የወልቃይት ፀገዴ ትክክለኛ ማንነት በህዝበ ውሳኔ ሊፈታ ይገባዋል፤ አማራ ለመሆን ወይም ከትግራይ ጋር ለመጠቃለል አልያም እንደወልቃይት ፀገዴነቱ ለብቻው ቢፈልግ ትላለህ። ይህ በጣም ትልቅ ስህተት ነው። አንተ ስለ አንድ የህብረተሰብ ክፍል ስትፅፍ እኮ ቢያንስ በመጠኑም ቢሆን የአካባቢውን ሠዎች እንዲሁም የአካባቢው የዕድሜ ባለፀጎች ልታማክር ይገባል። ዝም ብለህ አንተ በመሰለህ ልትፅፍ አይገባም። የወልቃይት ፀገዴ ህዝብ ከጎንደሬነት ወይም ከአማራነት ሌላ ምርጫ ሊቀርብለት አይገባም። ይህ ማለት እኮ ከትግራይ አውራጃዎች አድዋን ወይም አክሱምን ወስዶ “የጎንደር ነው ወይስ የትግራይ ነው?” ብሎ ህዝበ ውሳኔ እንደማድረግ ነው። ምክንያቱም የትግራይ መሆኑ ግልፅ ሆኖ እያለ የወልቃይት ፀገዴ ጉዳይም ከዚሁ ፈፅሞ የተለየ አይደለም። እርግጥ ነው ከኤርትራና ትግራይ ወጥተው ወልቃይት ፀገዴ የተወለዱ የሉም ማለቴ አይደለም። ቢሆንም ግን እነሱ የወልቃይት ፀገዴ ተወላጆች ይሆናሉ እንጂ ወልቃይት ፀገዴን ትግራይ ማድረግ አይችሉም። የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች አብዛኛዎቹ የአማራ ዝርያ ያላቸው ናቸው። ነገር ግን መቀሌ በመወለዳቸው መቀሌዎች ይሆናል እንጂ መቀሌን ጎጃም ወይም ጎንደር ማድረግ ግን አይችሉም። የአድዋ ሰዎችም በብዛት ከኤርትራ ጋር የተዋለዱ ናቸው። ለዚህ ነው አንዳንድ የአድዋ ተወላጆች የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ከኢትዮጵያ ይልቅ ለኤርትራ የሚቆረቆሩት። ቢሆንም ግን አድዋ ስለተወለዱ አድዋ ይሆናሉ እንጂ አድዋን ኤርትራ ማድረግ አይችሉም። የወልቃይት ፀገዴ ህዝብም ከዚህ የተለየ ዕጣ ፈንታ ሊገጥመው አይገባም።

ሌላው ወልቃይት ፀገዴ ለብቻው የሚለውን ቅዠት ነው። ይህች ይህች እንኳ የወያኔ ቡራኬ የዘመኑ በሽታ ትመስላለች። ለመሆኑ ከየት አመጣኸው? ከአባትህ? ከአያትህ ወይንስ ከቅድመ አያትህ? በየትኛው ዘመን ነው ወልቃይት ፀገዴ ለብቻችን ሆነን የምናውቀው? ይህ ለኔ በጣም እንግዳ ነገር ነው የሆነብኝ። ወያኔዎችን የምንቃወመው በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሆኖ የማያውቀውን – ወልቃይት የትግራይ አካል ነው – ስላሉን እኮ ነው። አዲስ ነገር ስላመጡብን ነው። አንተ ደግሞ በታሪካችን ያልነበረ የሌለ አዲስ ነገር ስታመጣብን ከነሱ በምን ተለየህ። ለመሆኑ ለብቻ መሆን ጥቅሙ ምንድነው? የወልቃይት ፀገዴ ህዝብን አጋር ማሳጣት? ወገን አልባ ማስቀረት? በሁለት በኩል እንደጠላት እንዲታይ ለማድረግ? “መሃል ሰፋሪ በሁለት ጥይት ይመታል” ሲባል እንደነበር በሁለት እሳት መካከል ልትጠብሰን?
ደግሞ አማራና የወልቃይት ፀገዴ ህዝብ አጎራባች ብሔረሰብ ታደጋቸዋለህ። በርግጥ ትግሬና ኤርትራ የወልቃይት ፀገዴ አጎራባች ብሔረሰብ እንደሆኑ ግልፅ ነው። ጎንደሬ ወይም የአማራው ማህበረሰብ ግን እንዴት ሆኖ ጎረቤት ይሆናል? የአማራው ወይም የጎንደሬው አካል እንጂ? ምናልባት አንዳንድ ሰዎች አማራ ነን ባይሉም ጎንደሬነታቸው መቶ በመቶ ያምኑበታል። ታዲያ ጎንደሬና አማራ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ማለት ናቸው። ስለዚህ የወልቃይት ፀገዴና የአማራው ማህበረሰብ ሲወርድ ሲዋረድ በደም በሥጋና በአጥንት የተሳሰረ አንድ አካል እንጂ ጎረቤት ሊሆን አይችልም። በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሥጋ ዘመዶች ቤተሰብ እንጂ ጎረቤት ሊባሉ አይችሉም። አንተ ለወልቃይት ፀገዴ ህዝብ ከልብ ብታስብ ኖሮ እንኳን ለጎንደሬነታችን ለአማራነታችን ብዙ ማስረጃ እያለን ከኤኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አንፃር እንኳ ሲታይ ከአማራ ጋር ብንሆን አማራው ለራሱ ቀርቶ ለሌላ የሚተርፍ ሰፊና ለም መሬት አለው። ከኛ ምንም ነገር አይፈልግም። ያውም የዋህነቱ፤ ቅን አመለካከቱ፤ አርቆ አስተዋይነቱና ርህራሔው ሳይጨመርበት ማለት ነው። ከትግራይ ጋር ብንሆን ግን እነሱ ከኛ የሚያገኙት ጥቅም እንጂ እኛ ከነሱ የምናገኘው ጥቅም ፈፅሞ የለም። ለዚህም ነው 800 000 ያህል ህዝብና ሰራዊት እላያችን ላይ አምጥተው ያፈሰሱብን። ያውም የወልቃይት ፀገዴ ህዝብ እያጠፉና ባዶ ስድስት ከሚባል ከመሬት በታች እስር ቤት እያጎሩ። ይህን ስል ግን ወያኔና የወያኔ ደጋፊዎችን እንጂ ድፍን የትግራይ ህዝብ ለማለት እንዳልሆነ እያሳሰብኩ ማለት ነው።
4ኛ. “የአማራ ገዢዎች ወልቃይት ፀገዴን ሲያስተዳድሩ ከፖለቲካ ባሻገር ባህል የመለወጥ ይሁን ኤኮኖሚያዊ አጀንዳ ስላልነበራቸው በሰላም ተስማምተው ኑረዋል። ባህል አስመልክቶ ግን የወልቃይት ፀገዴ ተወላጆች ትግርኛ ተናጋሪዎች በመሆናቸው ቋንቋቸው በቀላሉ ሊቀይሩት አልቻሉም፤ ትግሬዎች ግን በቋንቋ ስለሚመሳሰሉ በቀላሉ ሊቀይሩት ይችላሉ” ትላለህ። ለመሆኑ ጥናት አድርገህ ነው ወይስ በግምት ነው የምትናገረው? እኔ ደግሞ አማርኛ ተናጋሪ ገዢዎች ወልቃይት ፀገዴን ያልቀየሩ ባህሉ በጣም ስለተመሳሰለባቸው እንጂ ቋንቋው ስለጠጠረባቸው ነው የሚል እምነት የለኝም። ምክንያቱም አማርኛ ተናጋሪ ገዢዎች ወደ ወልቃይት ፀገዴ ሲመጡ እንደሌላው አካባቢ እንደትግራይ፤ እንደ ኤርትራ ወይም እንደደቡብ ኢትዮጵያ አስተርጓሚ አያስፈልጋቸውም። ህዝቡ አሳምሮ አማርኛ መስማትና መናገር ይችላል። ገዢዎቹ ወደ የወልቃይት ፀገዴ ስብሰባ ሲመጡ ስብሰባው የሚካሔደው በአማርኛ ነው። ወደ ሠርግ ቢኬድ የሚዘፈነው አማርኛ እስክስታውም አማርኛ ነው። ሀዘን ሊያሰተዛዝኑ ሲሄዱ አስለቃሽ ምሾ የሚያወርደው በአማርኛ ነው። ቤተክርስቲያን ሲሄዱ የሚሰበከው በአማርኛ ነው። ጠላት ያርበደበደ ወይ አንበሳ የገደለ የወልቃይት ፀገዴ ጀግና ገዢዎች ፊት ቀርቦ ቢፎክር በአማርኛ ነው። ሥነ ፅሑፍ ፅፎ ቢያቀርብ በአማርኛ ነው። ታዲያ ምኑን ነው የሚቀይሩት? ያልቀየሩት የሚቀየር ነገር ስላጡ እንጂ ቋንቋው ጠጥሮባቸው አይደለም። እንዳውም ባይተዋር የሚሆኑት ከትግራይ የሚመጥ ሰዎች ናቸው። አንዳንዴ “እንዳው ይች ትግርኛ በየት በኩል ሾልካ ገባች” የምልበት አጋጣሚ አለ። የመሃል አገር ገዢዎች የምትላቸው እንኳን በጣም የሚቀራረብ አማርኛና ትግርኛ ቋንቋ ቀርቶ ከአማርኛ ቋንቋ ጋር ፈፅሞ የማይመሳሰሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ቋንቋዎች ላይ ተፅዕኖ አሳድሮ ከ50 ብሔረሰቦች በላይ አማርኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ እንዲያውቁት አስችለዋል። ደግሞ ታውቃለህ በወልቃይት ፀገዴ ባህል አማርኛ ቋንቋ አውቆ መገኘት የትልቅነት ምልክት መመዘኛ ነው። ህዝቡ አማርኛ የሚለምደው በፍላጎት እንጂ በግዴታ አይደለም። በማህበረሰቡ ዘንድ አማርኛ የማያውቅ ክርስቲያን ሆኖ ዳዊት ያልደገመና (እስላም ሆኖ ቁራን ያልቀራ) እንደሙሉ ሰው አይቆጠርም። ጠቅለል ባለ መልኩ የወልቃይት ፀገዴ ህዝብ አማርኛ ቋንቋ ለክት ትግርኛ ለዘወትር ነው የሚጠቀምበት ለማለት ይቻላል። በአገራችን ባህል ምርጥ ልብስና ነጫጭ ሸማ የክት ሆኖ ለሰርግ ለስብሰባ ለቤተክርስቲያን ለመስጊድ እንዲሁም ለመሥሪያ ቤት ለሩቅ ዘመድ ጥየቃ ተጠቅሞ ለቤት ሥራ ሲሆን የዘወትር ልብስ እንደሚለበስ ማለት ነው።
ወልቃይት ፀገዴም ለሰርግ፤ ለስብሰባ፤ ለቤተክርስቲያን፤ ለፍከራ ለጀግንነት መግለጫና ለመስሪያ ቤት አማርኛን ተጠቅሞ ለዘወትር ሲሆን ትግርኛ ይጠቀማል። ይህ ለማጋነን ሳይሆን ትክክለኛ የህዝቡን ባህል ነው የምገልፅልህ። ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ ነገር አይደለም። ለምሳሌ በፊት ለሁሉም ነገር የግዕዝ ቋንቋ እንጠቀም ነበር፤ ከጊዜ በኋላ ግን ቀደምት አባቶች በግዕዝ ቋንቋ ቃለ እግዚአብሔር እያስተማርን፤ እየቀደስን፤ ቅኔ እየዘረፍን፤ ማህሌት እየወረድን አምላካችንን በምናመሰግንበት ቋንቋ ተመልሰን ክፉ ቃል ልንናገርበት አይገባምና ግዕዝ ለቤተክርስቲያን ብቻ ትተን ለዓላማዊ ነገር ሌላ ቋንቋ ሊኖረን ይገባል ብለው አማርኛም ትግርኛም እንደፈጠሩ ይነገራል። ስለዚህ ግዕዝ የቤተክርስቲያን ቋንቋ ሆኖ ስለቀረ የኢትዮጵያ ቋንቋ አይደለም እንደማይባል ሁሉ የወልቃይት ፀገዴ ህዝብም አማርኛ ቋንቋን ለዘወትር ተግባራት ባለመጠቀሙ አማርኛ ተናጋሪ አይደለም ማለት ፈፅሞ የተሳሳተ አመለካከት ነው።

5ኛ. “የትግራይና የወልቃይት ፀገዴ ህዝብ አንድ ዓይነት ቋንቋ በመናገራቸው አብረው በሰላም የመኖር ዕድላቸው ከፍ ያደርገዋል። ከባላባት እስከ ተራ ሰዎች ለዘመናት በጋብቻ ተሳስረውና ተዛምደው ኖረዋል ” ትላለህ። ይህ አንተ ነህ የምትለው፤ እነሱ ግን ተዋልደናል ተዘምደናል አይሉም – መሬታችንንና ንብረታችንን ከመዝረፍ በስተቀር። ደግሞ አንድ ህዝብ በሰላም የሚኖረው ወስጣዊ የአንድነት እምነትና ነባራዊ የሥነልቦና ትስስር ሲኖረው እንጂ አንድ ዓይነት ቋንቋ ስለተናገረ አይደለም። አንድ ዓይነት ቋንቋ መናገር በሰላም የማኖር ዕድል ቢፈጥር ኖሮ ለሶማሌዎች፤ ለየመናዊያን፤ ለሶሪያዊያን፤ ለኢራቃዊያንና ለሊቢያዊያን በሰላም ማኖር በቻለ ነበር። በዓለማችን ላይ በከፋ መልኩ የሰላም ዕጦት ያለባቸው ሀገሮች አንድ ዓይነት ቋንቋ የሚናገሩ ህዝቦች የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ናቸው። ስለዚህ ነገሮችን በዙሪያ ገብ (360 ዲግሪ) የዕይታ ስፋት ልትመለከታቸው ይገባል!

6ኛ. “የዘመናችን የትግራይ ገዢዎች የፈፀሙት የወልቃይት ፀገዴን ህዝብ ሰብአዊ ክብር የሚያዋርዱ ጥሰቶችን በዚህ መድረክ ላይ መግለፅ በህዝቦች መካከል አላስፈላጊ ቁርሾ ስለሚፈጥር እዛው ተከድኖ ይብሰል” እያልክ እንዳንተ አባባል የአማራ ገዢዎች በወልቃይት ፀገዴ ህዝብ ላይ አደረሱት የምትለውን ግፍ ግን አንድ ሳታስቀር ዝክዝክ አድርገህ ፅፈኸዋል። ታዲያ በወልቃይት ፀገዴና በአማራው ማህበረሰብ መካከልስ የሚፈጠረው አላስፈላጊ ቁርሾ አያሳስብህም? ያውም ተራ ነገር ከደምቢያ የሔዱ፤ ከወገራ የሔዱ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ምግብ በሉ ጠላ ጠጡ እያልክ ትንንሿን ነገር እያጋነንክ ሁለት ቤተሰብ ማጋጨት ከንፁህ ህሊና የሚጠበቅ አይደለም። እርግጥ ነው ኢትዮጵያ በወቅቱ በበጀት የታገዘ ዘመናዊ የሆነ መንግሥታዊ መዋቅር ስላልዘረጋች ገዢዎች በሚሄዱበት አካባቢ ማረፊያና ቀለባቸው የሚያዘጋጅላቸው ህዝቡ ነበር – በመንግሥት የሚመደብላቸው በጀት ባለመኖሩ! የወልቃይት ፀገዴ የአካባቢ ገዢዎችም ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ ማረፊያቸውና ቀለባቸውን የሚጎበኙት ህዝብ ነበር የሚችላቸው።
ታዲያ ደሞዝ የላቸው! ገንዘብ እንኳ ቢይዙ የሚስተናገዱበት ሆቴል የለ! የት ይሒዱ? እንኳን ይህ ቀላል የሚበላና የሚጠጣ ማቅረብ ይቅርና የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት መጣ በተባለ ቁጥር ከመንግሥት ምንም ውለታ ሳይጠብቅ በራሱ ስንቅና ትጥቅ ከጠላ ጋር ሲዋጋ የኖረ ህዝብ ነው። አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን ለብዙ ዓመታት ሲያስተዳድሩ ሠራዊታቸውን እኮ የሚቀልብላቸው የአማራው ማህበረሰብ ነበር። ይህ ደግሞ እንድብዝበዛ ወይም እንደበደል የሚቆጠር ሳይሆን ጊዜው የሚጠይቀው ያ ስለነበር ነው። ስለዚህ ትናንትን በዛሬ ሚዛን፤ ዛሬን ደግሞ በትናንት ሚዛን መለካት ተገቢ አይደለም። ትናንትን በትናንት፤ ዛሬን በዛሬ እንጂ!

እንዲያውም ምን እንደታወሰኝ ታውቃለህ? ወያኔዎች የኦሮሞን ህዝብና የአማራ ህዝብ ለማጋጨት ከ150 ዓመት በፊት የተደረጉትን መጥፎ ትዝታዎች ብቻ እየቀሰቀሱ – አፄ ምኒልክ የኦሮሞ ሴቶች ጡት ቆርጠዋል – እያሉ በህዝቦች መካከል ቁርሾ ለመፍጠር የተቆረጡ ጡቶች የያዙ እጆች ሐውልት አሰርተዋል። ሴቶች ጡታቸውን ተቆርጠው እኮ በህይወት መኖር ይችላሉ – ይህን ስል ጡት መቁረጥ ወንጀል አይደለም ማለቴ እንዳመስልህ! ወያኔዎች በአንድ ጀምበር 150 ሰው እየገደሉ፤ ከ5000 ሰዎች በላይ እስር ቤት እያጎሩ፤ ከ150 ዓመት በፊት ለተቆረጡ ጡቶች ሐውልት ያሰራሉ – ያውም እኮ ወንጀሉ ተፈፅሞ ከሆነ ነው?
የድሮ ገዢዎች መጀመሪያ ሲገቡ የአካባቢ ህዝብ ፈርቶ እንዲገዛላቸው የጭካኔ ርምጃ ይወስዳሉ እንጂ አንዴ ወደ ህዝቡ ከቀረቡ በኋላ ሩህሩሆች ነበሩ። ወያኔዎች ግን ሲገቡ ጀምረው መግደል ማጋደል፤ ማሰርና መዝረፍ የጀመሩ 25 ዓመት ሙሉ ቀጥለውበውት እስካሁን አላቆሙም። ስለአፄ ምንሊክ ካነሳሁ አንድ ነገር ልበልና ላብቃ! የእምዬ ምንሊክን ስም ማጥፋት የሚፈልጉ ሰዎች “አፄ ምንሊክ ሰው እንዳይሞት ጋላም (ኦሮሞም)ቢሆን” ብለዋል። ስለዚህ ኦሮሞን እንደሰው አይቆጥሩም ነበር እየተባለ ይወራል። እውነታው ግን ይህ አልነበረም። አጼ ምንሊክ በጊዜው ከደቡብ ኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ኦሮሞች ነበሩ ጠንከር ብለው ይዋጓቸው የነበሩና ደቡብ አካባቢ በቁጥጥራቸው ስር እያዋሉ ሲሔዱ ህዝቡን እየሰበሰቡ “ሰው እንዳይሞት! እየተዋጉኝ ያሉ ኦሮሞዎችም ቢሆን በሰላም እጃቸውን ከሰጡ እንዳትገድሉዋቸው” ለማለት ነው! ሰዎች አይደሉም ለማለት አይደለም። ለምሳሌ ደርግ ወያኔዎችን አሸንፎ የትግራይ አካባቢ ቢቆጣጠር ከተማ ከያዘ በኋላ “አንድ ሰላማዊ ሰው እንዳይሞት! ወያኔም ቢሆን” ሊል እንደሚችል ማለት ነው። እንኳን ሰላማዊ ሰዎች እየተዋጉኝ ያሉ ወያኔዎች በሰላም እጃቸው ከሰጡ አትግደሉዋቸው ለማለት እንጂ ወያኔዎች ሰዎች አይደሉም ለማለት አይደለም። ወያኔዎችም በተራቸው ኢትዮጵያን ሲቆጣጠሩ – አንድ ሰው እንዳይሞት፤ ኢሠፓም ቢሆን – ሊሉ እንደሚችሉ ማለት ነው። እውነት ለመናገር አፄ ምንሊክ ኦሮሞን እንደሰው እማይቆጥሩ እሳቸው ምን ቢሆኑ ነው?
7ኛ. ሌላው የመጨረሻ አስተያየቴ “አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሥርዓት በበጎ ጎኑ የሚታወቀው በኢትዮጵያ ውስጥና ሰላም ባልሰፈነባቸው የአካባቢያችን ቀጠናዎች ሰላምንና መረጋጋትን በማምጣቱ ነው፤ ከዚያም በተጨማሪ የብሔረሰቦችን ጥያቄ ምላሽ ለማምጣት የተደረገው ሙከራ አዎንታዊ ይዘት አለው” የሚለው አባባልህ ላይ ነው። ይህ አባባል በውነቱ የወያኔ የከፋፍለህ ግዛና ዘረኛ ፖሊሲ ተልዕኮ ለማስፈፀም ራሳቸውን ለጥቅም በመሸጥ ህሊናቸው የማይፈቅደውን የሐሰት መልዕክት ከሚያስተላልፉ ግብዞች የሚተናነስ አይደለም። በምንም መመዘኛ ወያኔዎች ችግርን ከማባባስና የራሳቸውን ጥቅም ከማሳደድ በስተቀር አንድም ችግር አልፈቱም፤ ለወደፊቱም አይፈቱም። ይህን የምለው በጣም እርግጠኛ ሆኜ ነው። ንቦች ማር ለመሥራት አበባ መቅሰም እንዳለባቸው ሁሉ ወያኔዎችም ትርፍ የሚያገኙት ችግር በመፍጠርና ሌላውን ክፍል በመጉዳት ስለመሆኑ የታወቀ ነው። ስለዚህ ወያኔዎች ችግር ፈቱ ማለት ኪሣራ ላይ ወደቁ ማለት ነው።
እንደሚታወቀው እንደ እስስት መቀያየር የማይቸግራቸው ወያኔዎች የደርግ መውደቅ ተከትሎ ኢትዮጵያን ለመዝረፍ ኢትዮጵያዊ መልክ ተላብሰው ኢትዮጵያዊ ይምሰሉ እንጂ ሲጀመር ፀረ-ኢትዮጵያ አጀንዳ ቀርፀው የተንቀሳቀሱ ኃይሎች ናቸው። አንግበውት የተነሱ ዓላማ እኮ ትግራይ የራሷ ሪፐብሊክ ሊታወጅላት፤ ኤርትራ በቅኝ ግዛት የተያዘች እንጂ የኢትዮጵያ አካል አይደለችም፤ አማራ የትግራይ አዝብ ጠላት ነው፤ የኢትዮጵያ ህልውና የ አንድ መቶ ዓመት ታሪክ ነው፤ ባንዲራ ጨርቅ ነው እያሉ ለራሳቸው ተሳስተው ኩሩ ኢትዮጵያዊው የትግራይ ህዝብን ያሳሳቱ (በአሁኑ ሰዓት ያለው የትግራይ ህዝብ ወያኔዎች በፈርሃ እግዚአብሔርና በሃገር ፍቅር ስሜት የነደዱ ቀደምት የትግራይ አባቶችና እናቶች ገድለው ጨርሰው ብሬይን ዋሽ የተደረጉ በልጅነት አዕምሮዋቸው በአምሳላቸው ቀርፀው ያሳደጓቸው ነው ያሉት። ለዚህ ነው ተዉ የሚል ሰው የጠፋው። ሠርቀው ትግራይ ቢገነቡ እሰየው፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ቢጨፈጭፉ እሰየው፤ የሰው መሬት ቀምተው ቢሰጡአቸው እሰየው፤ የኢትዮጵያ መሬት ለውጭ ባለሀብት ቢሰጥ መሬታቸው አይመስላቸው፤ የሀገር ድንበር ተቆርሶ ለጎረቤት አገር ቢሰጥ የሀገራቸው ድንበር አይመስላቸው፤ የትግራይን ወጣት አደንዝዘው የነሱ የጥፋት ተባባሪ አድርገውታል። እና ወገናችን የትግራይ ህዝብ ሳያውቀው በጠላት እጅ ወድቋል። ስለዚህ ነፃ መውጣት ካለ በቅድሚያ ነፃ መውጣት ያለበት የትግራይ ህዝብ ነው) እነዚህ ኢትዮጵያዊ ሥጋ ደም ተላብሰው ኢትዮጵያን ለማጥፋት የመጡ የውጭ ጠላት ተልዕኮ አስፈፃሚዎች በምን መልኩ ነው ከነዚህ ጥሩ ነገር ይመጣል ብለህ ምስክርነትህ የምትሰጠው? ዘርን መሰረት ካደረገው የወያኔ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ እንዴት በጎ ነግር ትጠብቃለህ? የብሔረሰቦች ችግር መፍታት ማለት ለዘመናት ተዋልዶና ተዛምዶ ለኖረ ህዝብ ብዙ መልካምና መጥፎ ትዝታዎች አብሮ ያሳለፈ ህዝብ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የተሰሩ መጥፎ ትዝታዎች ብቻ እየመዘዙ ብሔር ከብሔር ማጋጨት ይህ ነው መፍትሔ? አገሪቷን በ10 የቋንቋ ክልል ከፋፍሎ፤ አስር ባንዲራ ሰጥቶ፤ አንቀፅ 39 ፈጥሮ መገነጣጠል ትችላላችሁ ማለት ነው የብሔረሰብ ችግርን መፍታት? ወይስ ህዝብ የማያወቃቸው፤ ፈቅዶ ያልመረጣቸው፤ ብሔሩን የማይወክሉ የወያኔ ተላላኪዎችና የተባሉትን ፈፃሚዎች የአሻንጉሊት ፌዴራሊዝም ፈጥሮ የ95 ሚሊዮን ህዝብ ድርሻ ለአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ብቻ እየዘረፉ ማጋዝ ነው ፍትህ? ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ገንብተናል ብለው ምርጫውን መቶ በመቶ አሸነፍን የሚሉ?
በወያኔ ያልተሰቃየ ብሔረሰብ ማን ነው? ኦሮሞ፤ አማራ፤ አፋር፤ ጉራጌ፤ ሶማሌ፤ አኝዋክ ወዘተ ማን ነው የደም እንባ ያላነባ? በንጉሡ ዘመንና በወታደራዊው መንግሥት ይታይ የነበረው የየመሥሪያ ቤቱ የብሔር ተዋፅኦ ስብጥር እኮ ዛሬ ያለ ይሉኝታ በአንድ ብሔር መተካቱ ፍትህ ነው? መከላከያ፤ ፖሊስ ሠራዊት፤ ደህንነት፤ ቁልፍ ቁልፍ የሃገሪቷ የሥልጣን ተዋረድ በአንድ ብሔረሰብ መያዙ መፍትሔ ነው?
ይህ ነው የብሔረሰቦችን ችግር መፍታት ማለት? በኔ በኩል ይበልጥ አወሳሰቡት እንጂ ምንም መፍትሔ አላመጡም፤ እስከመጨረሻም አያመጡም። አስር የማይሞሉ ፊውዳሎች የደሃ ገበሬ መሬት ወሰዱ ብለን “መሬት ላራሹ” እያልን እንዳልሞትንና እንዳልቆሰልን ሁሉ ዛሬ ዓይናችን እያየ ለህንድ፤ ለአረብ፤ ለአውሮፓዊያንና ለመላው የዓለም ባለሀብቶች የድሀውን ገበሬ መሬት በውስጥ ለውስጥ ገበያ በገፍ እየተቸበቸበ ያለበት ዘመን እኮ ነው ያለነው! ለአጭር ጊዜ በሥልጣን ለመቆየት ሲባል ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን መስዋዕትነት ከፍለው ያቆዩልንን ዳር ድንበራችን እንደኬክ እየተቆረሰ ለአጎራባች አገሮች የሚታደልበት ዘመን ደርሰን መፍትሔ አመጡ ትለናለህ። ከትግራይ በስተቀር ሌላው ኢትዮጵያዊ እንደወገናቸው የማይቆጥሩ፤ አግዘው የማይደክሙ፤ ዘርፈው የማይጠግቡ ይሉኝታ ቢሶች! አንድ ህንፃ ሊገነቡ 1000 አባወራ፤ አንድ ኪሎ ሜትር መንገድ ሊሰሩ 10000 አባወራ የሚያፈናቅሉ ጨካኞች! ሥልጣን ላይ ከወጡ በ25 ዓመት ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም በዕርዳታ 45 ቢሊዮን ዶላር፤ በብድር 30 ቢሊዮን ዶላር በድምሩ 75 ቢሊዮን ዶላር ተረክበው 65 ቢሊዮኑን ወደኪሳቸው ከተው በ10 ቢሊዮን ዶላር ልማት አለማን እያሉ የሚመፃደቁ አጭበርባሪዎች! ደርግኮ በ17 ዓመቱ የሥልጣን ዘመኑ 3.7 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነበር በዕርዳታ ያገኘው። ይታይህ እንግዲህ!
በል ወዳጄ! የነዚህ ጉድ እንኳን በ9 ገፅ በ9 መጻህፍት ተፅፎ አያልቅምና በዚሁ ልሰናበት!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ግዛት ተገኘ
ለማንኛውም አስተያየት gizat.tesfaye@gmail.com ይጠቀሙ

The post መልስ ለኃይሉ የሺወንድም፤ በወልቃይት ፀገዴ ባህልና ማንነት ጥያቄ እኔም ቅሬታ አለኝ! appeared first on Zehabesha Amharic.


ህወሓት “ከቡና ጠጡ” ወደ “መርዝ ጠጡ” ከታደሰ ብሩ

$
0
0

የአዲስ አበባ ታክሲ ሾፌሮችና ባለንብረቶች ለሁለት ቀናት ያካሄዱት የሥራ ማቆም አድማ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ትምህርት ሊገኝበት የሚገባ ነው። ስታሊናዊ አፈና በሰፈነባት አዲስ አበባ ውስጥ እንዲህ ዓይነቱ አድማ መሞከሩ ብቻውን የሚያስደንቅ ሳለ ተግባራዊ ሆኖ ከተማዋን ለሁለት ቀናት ማስተኛቱ የታክሲዎችን ጉልበት፤ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ውጤታማነት እና የተባበረ እርምጃ ስኬታማነት በተግባር አሳይቷል።
አገዛዙ የአወዛጋቢውን አዋጅ ተፈፃሚነት ለሶስት ወራት ማራዘሙን ተናግሯል። ይህ ማራዘምም ከቅርብ ጊዜዓት ወዲህ ካስተዋልናቸው የማፈግፈግ እርምጃዎች አንዱ ሆኗል። የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እና የሆሳዕና የትራንስፓርት ህግ ተፈፃሚነት መዘግየት ሌሎቹ ማፈግፈጎች ናቸው።
እዚህ ላይ ሁለት ነጥቦችን ማንሳት ተገቢ ነው።
አንደኛ – ጠላት ማፈግፈግ ሲጀምር ማጥቃት መቀጠል አለበት። የአምባገነን ሥርዓቶች ውድቀት ለማፋጠን ትናንሽ ድሎችን እየሰበሰብን ለበለጡ ድሎች የሚደረገውን ትግል ማጠናከር የዘወርት ሥራችን አካል መሆን ይኖርበታል። ስለሆነም አገዛዙ የተጠየቀውን በአርኪ ሁኔታ መልሶት ቢሆን ኖሮም ሌሎች ጥያቄዎች መነሳታቸው አይቀርም ነበር።
ሁለተኛ – ለአዲስ አበባ ታክሲ ሾፌሮችና ባለንብረቶች ጥያቄ አገዛዙ የሰጠው ምላሽ የማፈግፈግ ምልክት ቢሆንም አርኪ ምላሽ ሊሆን ቀርቶ ግማሽ ምላሽ እንኳን አይደለም። ፓርላማ ያወጣውን አዋጅ አስፈፃሚው በየትኛው ሥልጣኑ ሊያዘገየው እንደቻለ አጠያያቂ ነው። ይህ ህገ አልባነታቸው ለምንም ነገር እንዳይታመኑ ያደርጋቸዋል። አዋጁን በአፋቸው ተራዝሟል እያሉ በተግባር ግን ተፈፃሚ እያደረጉት ስለአለመሆኑ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ አለን? ምንም። ስለዚህም የታክሲ ሾፌሮችና ባለንብረቶች ጥያቄዎች እንኳንስ ሙሉ ግማሽም ምላሽ አላገኙም ብለን መደምደም እንችላለን። ይህ ደግሞ በተራው የሥራ ማቆም አድማው ወደፊትም ሊደገም ይችላል የሚለውን መላምት ያጠናክርልናል።
የአዲስ አበባ ታክሲ ሾፌሮችና ባለንብረቶች የሥራ ማቆም አድማ መልሶ መጀመር ስለሚቻልበት ሁኔታ መምከር እና አድማው ወደ ሌሎች የሥራ መስኮችና አካባቢዎችም እንዲዛመት መሥራት የሁላችንም ኃላፊነት ነው።
በዚህ ወቅት ህወሓትስ ምን እያሰበ ነው ብሎ መጠየቅም ብልህነት ነው።
እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት የህወሓት ጆሮ ጠቢዎች የአድማው አደራጆችን የመለየት ሥራ ውስጥ ተጠምደው ሰንብተዋል። በተወሰነ መጠን መረጃ ያላቸው ቢሆንም የለመዱትን የጉልበት እርምጃ ለመውሰድ ድፍረት ያጡበት አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል። የኦሮሚያ እና የሙስሊም ወገኖቻችን ንቅናቄ እኚህን እኩያን ጆሮ ጠቢዎች አደብ እንዲገዙ አስገድዷቸዋል። በምትኩም “ለስላሳ መንገድ” ያሉትን መፍትሄ መርጠዋል።
ለስላሳው መንገድ “ቡና እንጠጣ” ብለውታል። እንደ እቅዳቸው በየሰፈሩ ብዙ የቡና እንጠጣ ኢመደበኛ ማኅበራትን ያቋቁማሉ። እያንዳንዱ ካድሬም ጥቂት የሰፈሩን ሰው ቡና እየጋበዘ “ስለ ሰላምና ልማት” እንዲሰብክ ይደረጋል። ልዩ ትኩረት ለባለታክሲዎች፣ ሾፌሮች፣ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሰጥ ተወስኗል። “ቡና” የተባለውም እንደ ሁኔታው ወደ ቢራና አልኮል እንዲያድግም በጀት እንዲመደብ ጠይቀዋል።
“ቡና እንጠጣ” ከቀድሞው 1 ለ 5 በመጠኑ ይለያል። 1 ለ 5 ጥርነፋ ሲሆን “ቡና እንጠጣ” ፍርሀት የወለደው ማባበያ ነው። የአሁኑ “ቡና እንጠጣ” በምርጫ 97 ዋዜዋ የነበረው የአርከበ እቁባይ ተለማማጭነትን ያስታውሰኛል። አርከበ በምርጫው በፊት የነበረው “ደግነት” ሁሉ ከምርጫው በኋላ ወደ አውሬነት መቀየሩ አይዘነጋም።
ህወሓቶች የዛሬው “ቡና ማጠጣት” ከተሳካላቸው ነገ ወደ “መርዝ ማጠጣት” እንደሚቀይሩት በበኩሌ እርግጠኛ ነኝ። ስለሆነም “ለቡና እንጠጣ” የምንሰጠው ምላሽ “እንቢ” መሆን ይኖርበታል ብዬ አምናለሁ።

The post ህወሓት “ከቡና ጠጡ” ወደ “መርዝ ጠጡ” ከታደሰ ብሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ቆየት ካሉ ግጥሞቼ አንዱን እነሆ ፦ከቴዲ አፍሮ

$
0
0

ጎራው ያለ እደሆን ባራምባራስ ደስታ
ዛራፍ ያለ እንደሆን ባራምባራስ ደስታ
ጠላት ይጠፋዋል መደበቂያ ቦታ።
ፊት አውራሪ ፍላቴ
ግራ አዝማች በሃፍቴ
አዛዥ ለጥ ይበሉ
ቀኝ አዝማች በአካሉ
ዣንጥራር ባያለው
ደጃዝማች እንዳለው
እንዲህ ነው ካልቀረ አንጀት አርስ ሹመት
ለድል የሚያበቃ ጦር ይዞ ቢዘመት።
የጣልያን ጄኔራል ኮኮቡን ደርድሮ
በሊጋባሞ ዜር ስንት አሳሩን ቆጥሮ
ድል አድርጎት የኛ ሰው ፎክረን በኩራት እንደተመለስን
ስልጣኔ መስሎን የሱን ስም ወረስን።
ማቹ ጄኔራል ነው ገዳይ ፊት አውራሪ
ስም እንዴት ይዋሳል ደፋር ሰው ከፈሪ
በጠላት ሬሳ ላይ ቆመን እያቅራራን
በድላችን ማግስት የኛን ሹመት ንቀን ከ ሆንን ኔተራል
ባናውቀው ነው እንጂ የዛን ቀን ሙተናል።
ኮኔሬል አይበሉን ያገሩን አርበኛ
ጄኔራል አይበሉን ያገሩን አርበኛ
ፈረንጅ አደለንም ሀበሻ ነን እኛ።
የሞች ስም አደለም የገዳይ ሰው ምሱ
በደም ተበላሽተዋል ባለ ኮከብ ልብሱ
ገድየው ሳበቃ ባስታጠቁኝ ወኔ
በሱ ስም አይጥሩኝ ቆሞ እንዲሄድ በኔ
ጄኔራል ድል ሆኖ ስላለፈች ነፍሱ
ይበሉ ጃንሆይ ሹመቴን መልሱ።
ፊት አውራሪ ካታካምቦ
ሊጋባ ዴሊቦ
አዛዥ ለጥ ይበሉ
ቀኝ አዝማች አካሉ
ዣንጥራር አበጋዝ
እንዲህ ነው አንጀት አርስ ሹመት
ለድል የሚያበቃ ጦር ይዞ ቢዘመት
ፍቃድዎ ከሆነ ግርማዊ ተፈሪ
እንዳገሬ ሹመት በሉኝ ፊት አውራሪ
በሞች ከመጠራት ስለ ሚሻል እሱ
ይበሉ ጃንሆይ ሹመቴን መልሱ።

12792233_689477834525197_1099353148366092921_o

The post ቆየት ካሉ ግጥሞቼ አንዱን እነሆ ፦ከቴዲ አፍሮ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአድዋ ድል፦ የዘመኑ ኢትዮጵያዊ ትውልድ የማንነት ፈተና –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             ረቡዕ የካቲት ፳፫ ቀን ፪ሺህ፰  ..            ቅፅ ቁጥር

moreshነፃነት-ወዳድ ለሆነው የዓለም ጥቁር ሕዝብ በሙሉ መመኪያ የሆነው የአድዋ ድል ለ፻፳ኛ (ለአንድ መቶ ሃያኛ) ጊዜ ዛሬ ተከብሮ ይውላል። ይህንን ቀን ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው በድሉ ትክክለኛ የነፃነት መንፈስ ለማክበር ያልታደሉባቸው ዘመኖች፦ በፋሽስት ጣሊያን ወረራ ከ፲፱፻፳፰ እስከ ፲፱፻፳፱ ዓም በነበሩት ፭(አምሥት) ዓመታት፣ እንዲሁም ከ፲፱፻፹፫ ዓም ወዲህ ለ፳፭(ለሃያ አምሥት) ዓመታት በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ነው። የአድዋ ድል ሲነሣ ምንጊዜም ተነጥሎ የማይቀረው የኢትዮጵያን አርበኞች እየመሩ ጦርነቱን በድል የተወጡት ታላቁ ንጉሠ-ነገሥታችን ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል፥ ብርሃን-ዘኢትዮጵያ ናቸው። በእኒህ ታላላቅ ኢትዮጵያውያን መሪዎች ሥር ቁጥራቸው በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ አርበኞች በየጦር መሪዎቻቸው ሥር ተሰልፈው ለውዲቷ አገራቸው ሕይዎታቸውን ገብረዋል፣ ደማቸውን አፍስሰዋል፣ አጥንታቸውን ከስክሰዋል። ስለዚህ የአድዋን ድል የምናከብረው እኒህን ለአገራችን ባለውለታ የሆኑ ታላላቅ አርበኞቻችንን ለመዘከር፣ እንዲሁም እኛም በዘመናችን የበኩላችንን የትውልድ አደራችንን እንድንወጣ ቃልኪዳን ለመግባት መሆን ይገባዋል። ነገር ግን ባለፉት ፳፭(ሃያ አምሥት) በነበረው ጊዜ ለአድዋ ድል አከባበር ኢትዮጵያውያን ያደረጉት እንቅስቃሴ የተዘበራረቀ ምሥል ይታይበታል።

ከሦሥት ዓመታት በፊት «ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት» ፻፲፯ኛውን የአድዋ ድል በዓል በሕዝባዊ ስብሰባ ለመዘከር በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ጥሪ ሲያደርግ በዝግጅቱ ላይ ለመካፈል የተገኙት ታዳሚዎች ከ፶ አይበልጡም ነበር። በተመሣሣይ ቀን እና ሰዓት «የኢትዮጵያዊነት ውርስ እና ቅርስ ማኅበረሰብ በሰሜን አሜሪካ» በጠራውም ዝግጅት የተገኙት ታዳሚዎች ጥቂት መቶ ነበሩ። በዋሽንግተን ዲሲ እና በአካባቢዋ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ይታወቃል። በመሆኑም ይህ ማኅበረሰብ የራሱን የድል በዓል ለመዘከር ቸልታ ያሣየበትን ምክንያት በጥልቀት ካልመረመርነው እንቆቅልሽ ሊሆንብን ይችላል። ነገር ግን በወቅቱ «አለን አለን» የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ልሂቃን በታላቁ ኢትዮጵያዊ ንጉሠነገሥት በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ላይ ያወርዱ የነበረው የተቀነባበረ የማጥላላት ፕሮፓጋንዳ አንዱ አብይ ምክንያት እንደነበረ መታወቅ አለበት። እኒህ ድርጅቶች እና ልሂቃን አሁንም ከዚሁ አቋማቸው ፈቀቅ አላሉም። ሌሎችም በኢትዮጵያ ስም የተደራጁ የፖለቲካ እና የሲቪክ ድርጅቶች በአድዋ ድል እና ለድሉም መገኘት የመሪነቱን ሚና በተጫወቱት በታላቁ ንጉሠነገሥታችን በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ላይ ያላቸውን ግልፅ አቋም በይፋ ለሕዝብ አላሣወቁም፣ ወይም ለሕዝባዊ ስብሰባ ሲጠሩ «የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ» ዓይነት አልባሌ ምክንያት እየደረደሩ ተወካዮቻቸውን ሣይልኩ የሚቀሩ ናቸው። ስለዚህ እኛ ኢትዮጵያውያን በጠቅላላ እኒህን የፖለቲካ እና የሲቪክ ድርጅቶች እንዲሁም «ልሂቃን» በዚህ የኢትዮጵያዊነት መለኪያ በሆነ አብይ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋም እንዲገልፁ ፊት ለፊት ተጋፍጠን መጠየቅ ይገባናል። ይህ የዜግነት እና የትውልድ ግዴታችን ነው።

«ሣይደግስ አይጣላም» ይባላል። የአድዋ ድል በዓል አከባበር በአገራችን በኢትዮጵያ የደበዘዘውን ያህል፣ በውጪ አገሮች በስደት በሚኖረው ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ በኩል የሚታየው እንቅስቃሴ ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደትክክለኛው መሥመር የመምጣት አዝማሚያ ይታይበታል። በዚህ ረገድ በውጪ አገር ኃላፊነቱን ወስደው በዓሉ በትክክለኛ ገፅታው እንዲከበር የሚያደርጉት የሲቪክ ድርጅቶች ሊመሠገኑ ይገባል። ሆኖም ኃላፊነታችን በዚህ አያቆምም፣ ሊቆምም አይገባውም። በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለን እኛ ኢትዮጵያውያን፣ የአድዋ ድል በትክክለኛው የድሉ በዓል መንፈስ እንዲከበር በመጀመሪያ በየማኅበረሰባችን ይህ በዓል በየዓመቱ በጋራ ከምናከብራቸው በዓሎች አንዱ ሆኖ እንዲቆጠር ማድረግ አለብን። ለዚህም በኢትዮጵያ ስም የተደራጁ የሲቪክ እና የፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ ኃላፊነቱን እንዲወስዱ ማስገደድ ይገባናል። ከዚያ ባሻገር ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ ለዚህ በዓል ያለው ግንዛቤ እንዲጎለብት ከፍተኛ የማስተዋወቅ ሥራ ማራመድ ተገቢ ነው። ይህንን ካደረግን ትውልዳችን ካሉበት ብሔራዊ ግዴታዎች ቢያንስ አንዱን ለመወጣት እንደሞከረ ታሣቢ ይሆንለታል። ይህንን ሣናደርግ ከቀረን ግን ለተተኪው ኢትዮጵያዊ ትውልድ የምናወርሰው «ለነፃነቴ አልበገርም» ባይነትን ሣይሆን በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ማፈርን መሆኑን ለቅፅበትም ያህል መዘንጋት አይገባንም።

 

የአድዋ ድል የመላው ጥቁር ሕዝብ መመኪያ ነው!

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጇቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

The post የአድዋ ድል፦ የዘመኑ ኢትዮጵያዊ ትውልድ የማንነት ፈተና – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የአፍ ጠረን (Halitosis) እና ምላስ |የአፍ ጠረን ያለባቸው ሰዎች ለ7 ችግሮች የተጋለጡ ናቸው

$
0
0

ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል::

መጥፎ ነገሮችን ማየትና መስማት ለረጅም ሰዓት ስሜትን የሚረብሽ ቢሆንም መጥፎ ነገርን ማሽተት ግን ሙድን ከሚረብሹ ነገሮች በቅድሚያ ይመደባል፡፡ በተለይ ከአፍ የሚወጣ መጥፎ ሽታ እጅግ ያስቀይማል፡፡ በመሆኑም ለዛሬ መጥፎ የአፍ ጠረን (Halitosis) መንስኤዎችና መፍትሄዎችን በተመለከተ እንመካከራለን፡፡ ያልተለመደ ወይም ጠረን ያለው ሽታ አብዛኛው ከ80 ፐርሰንት በላይ መነሻ ከአፋችን ሲሆን የተቀረው ከአፍንጫችን ከጎሮሯችን አካባቢ በሚከሰት ምክንያት ነው፡፡ በቅርቡ ከታዩ የጥናት ጽሑፎች ዘገባ በተለየ መልኩ መንስኤዎችን ዘርዝሯል፡፡

Bad Breath Amharic

1. ምላስ ይዛ የምትገኛቸው ባክቴሪያዎች

እንደ ኤክስፐርቶች ዘገባ፣ ዋነኛና ቀዳሚ ምክንያት ምላስ ተሸክማ የምትኖራቸው የባክቴሪያ ክምችት ሲሆን እነዚህም ባክቴሪያዎች የሚያመነጩት (VSC) የሚባል ወይም ሰልፈር የተባለ ኬሚካል የያዘ የሚተን ሽታ ሲሆን ሽታውም ከተበላሸ የዕንቁላል ሽታ ጋር ይመሳሰላል፡፡ ባክቴሪያዎችም በምላስ ላይ ቢበዙም፣ በጥርስና በድድ ላይ ለሚለጠፉ ቆሻሻ (Plaque) ላይም ይገኛሉ፡፡ ሽታውም በራሱ የድድና የጥርስ ህመም ያስከትላል፡፡

የምላሳችን ሻካራነትና ምግብ ወደ ጉሮሮ ሲያልፍ የሚቀሩ ምግቦች ምላስ ላይ መለጠፍ ምላስ ላይ ሽፋን ይፈጥራል፡፡ በዚህም ሽፋን ውስጥ ባክቴሪያዎች በመደበቅ ለኑሯቸው አመቺ ቦታ ይፈጥራሉ፡፡ ባክቴሪያዎቹም በተፈጥሯቸው ኦክስጅን የማይጠቀሙ ስለሆነ እና ኦክስጅንም ስለሚገላቸው በሽፋን ውስጥ መኖር ይመቻቸዋል፡፡

2. የአፍ መድረቅ

የአፍ መድረቅ ሌላኛው ለአፍ መሽተት ምክንያትና ለምላስ ላይ ለሚገኙ ባክቴሪያዎች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ ስለሚቀንስና የአፋችንን እንቅስቃሴ ስለሚገታ ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነሳ ከአፋችን ጊዜያዊ መጥፎ ጠረን ያወጣል፡፡ ምግብ ስንመገብ ወይም አፋችንን ካፀዳን በኋላ የሚጠፋ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በፆም ወራት ከውሃና ከምግብ ስለምንርቅ፣ ጥርሳችን የማናፀዳ ከሆነ ለረጅም ሰዓታት አፋችን እንደሚሸት ይገለፃል፡፡ በሽተኞች በሚወስዱት መድሃኒትና በበሽታ ምክንያት የአፍ መድረቅ ይከሰትባቸዋል፡፡

3. በጭንቅላታችን እንዳለብን ማመን

(Halitophobia) የመጥፎ አፍ ጠረን ፍራቻ የብዙ ሰው ችግር ነው፡፡ ይህም ባለቤቱ ራሱን የመጥፎ የአፍ ጠረን ተጋላጭ እንደሆነ በማሰብ የሚከሰት ሲሆን እነዚህ ሰዎች መጥፎ የአፍ ጠረን ሊኖርባቸው ይችላል፡፡ እንደምክንያት ራሳቸውን የመጥፎ ሽታ ባለቤት የሚያደርጉ ሰዎች፣ አብዛኛው ጊዜ አይናፋሮችና ራሳቸውን ዝቅተኛ ደረጃ አድርገው የሚመድቡ በህብረተሰቡ የተገለሉ ሰዎች ናቸው፡፡

4. የአመጋገብ ሁኔታ

አንዳንድ ምግቦችና መጠጦች ለጊዜያዊ የሆነ መጥፎ በሽታ ያጋልጣሉ፡፡ እነዚህም ውስጥ ነጭ ሽንኩርትና አልኮል መጠጦች ይመደባሉ፡፡

እንዴት መጥፎ ሽታ እንዳለብን እናውቃለን

1. የራስ የአፍ ሽታን ለማወቅ ከሚረዱ ዘዴዎች አንዱ የቅርብ ጓደኛ ቤተሰብ ወይም ፍቅረኛ ነው፡፡ በግልፅ ስለአፍጠረን መጠየቅ ራስን ከማወቅ በተጨማሪ በግልጽ ስለመጥፎ የአፍ ጠረን መወያየትን ያዳብራል፡፡

2. ራሳችን የምንመረምርበት ዘዴዎች፡- መዳፋችንን በእጅና በአፍንጫችን መካከል በማድረግ፣ ወደ ውጭ በመተንፈስ የማሽተት ዘዴ ነው፡፡ በዚህ ዘዴ ጊዜያዊ ሽታዎችን ለማሽተትና ለመጠንቀቁ ይረዳናል፡፡

3. ዋናው መንስኤ የሆነውን፣ የምላሳችንን የኋለኛው ክፍል በአመልካች ጣት በመቧጠጥ ከዚያም የማሽተት ዘዴ ሲሆን ሌላው ደግሞ፣ በስቴክኒ ወይም በተዘጋጀ እንጨቶች በጥርስ መካከል የቆሸሸ ካለ በማሽት የሚታወቅ ዘዴ ነው፡፡

መድሃኒቱ

ጥርስን መቦረሽ ጥሩ የአፍ ንፅህና ቢያስጠብቅም፣ ለመጥፎ የአፍ ሽታ ለብቻው መፍትሄ አይሆንም፡፡

1. ለሽታ መንስኤ የሆነውን ምላስ ማፅዳት ዋነኛው መፍትሄ ነው፡፡ ስለዚህ ምላሳችንን በተገቢው መልክ ማፅዳት ሽታን ለመከላከል ዋነኛ መፍትሄ ነው፡፡

2. በአፍ መድረቅ ለሚከስ የአፍ ሽታ መጀመሪያ የአፍ መድረቅን ለሚያስከትሉ ችግሮች ህክምና መውሰድ፡፡ በዛ ያለህ ውሃ መጠጣት፣ ከስኳር ነፃ የሆነ ማስቲካዎችን ማኘክ የአፍ ድርቀትን ይከላከላል፡፡

የመጥፎ የአፍ ጠረን ፍራቻ ያለባቸው ሰዎች፣ መጀመሪያ ወደ ሳይኮሎጂስት ከመሄድ ምክር ማግኘት ይገባቸዋል፡፡

የጥርስ የድድ በሽታ፣ በማንኛውም ሰው ላይ በየትኛውም የዕድሜ ክልል ሊከሰት የሚችል ቢሆንም ነገር ግን በአብዛኛው በከተማና ዘመናዊ የኑሮ ህይወት በሚኖር የምግብ ይዞታቸው ከጣፋጭ ምግቦችና መጠጦች ጋር የተዛመዱ ሰዎችና በተለያዩ በሽታዎች የተጋለጡ ሰዎች የበለጠ ተጠቂዎች ናቸው፡፡ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች፣ በደማቸው ውስጥ የስኳር መጠን መዛባት ጋር በተያያዘ የሰውነት አካላቸው ላይ የሚመጣውን ችግር፣ የስኳርን ህመም አስቸጋሪና በየጊዜው መረጃና ጥናት እንዲያስፈልገው አድርጎታል፡፡

የስኳር በሽታ የሰውነት አካላት የሆኑትን ልብ፣ የደም ስር ዓይንና ኩላሊት ከመጉዳቱ በተጨማሪ በዋነኝነት በጥርስና አካባቢ ያሉትን አካላት ይጎዳል፣ የቀረበ ግንኙነትም አለው፡፡ ይህም በደም ውስጥ ያለ ስኳር በቀጥታ ከጥርስ መቦርቦርና ከድድ ህመም ጋር ይገናኛል፡፡ የስኳር በሽታ ያለባቸው በሽተኞች በሽታው ከሌለባቸው ሰዎች የበለጠ ለአፍ አካባቢ ችግሮች የተጋለጡ ናቸው፡፡

እነዚህም ችግሮች

1. የድድ መቁሰል

2. የአፋችን አካባ ቁስሎች ቶሎ አለመዳን

3. የጥርስ መቦርቦር

4. የምራቅ መጠን መቀነስና አፍና ምላስ ማቃጠል

5. የአፍ ድርቀት

6. በፈንገስ የሚመጡ በአፍና በምላስ አካባቢ ቁስለቶች መጋለጥ

7. ጣዕም ለመለየት መቸገር

የድድ መቁሰል ወይም በድድ ላይ የሚከሰቱ ችግሮች፣ የስኳር መጠን በደም ስር መዛባት በአፍ ውስጥ ለሚገኙ ባክቴሪያዎች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር፣ በድድና በጥርስ መካከል ያለውን ግንኙነት አሻክረው የጥርስ መነቃነቅና ሲብስም ያለጊዜው እንዲነቀል ያደርጋሉ፡፡ በተቃራኒ የድድ በሽታ ያለበት ሰው ከሌለበት ሰው የበለጠ በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን መቆጣጠር ያቅተዋል፡፡

በስኳር ህመምተኛ በተለይ የሚከሰተው የአፍ መድረቅ ወይም የምራቅ መጠን መቀነስ በምራቅ አማካኝነት የምናገኘው የባክቴሪያዎች ማጽዳት፣ በባክቴሪያ የሚዘጋጀውን አሲድ ማምከን ያሰጣል፡፡ ለዚህም ምክንያት ጥርሳችን ባልተጠበቀ መጠን መቦርቦርና መበስበስ ያስከትላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአፍ መድረቅ አፋችን፣ ምላሳችንን ማቃጠልና ምግቦችንና መጠጦችን ጣዕም እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ይህ የአፍ መድረቅ ለአፍ ሽታ መከሰት አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

ጥንቃቄ

አመጋገብን ማስተካከል

ለስኳር ህመምተኞች ብዙም የማይመከረው የጣፋጭ መጠን፣ በተለየ መልኩ መቀነስ በምግቦች መካከል የሚወሰዱት እነዚህ ጣፋጭ መጠጥና ምግቦች ለምሳሌ ለስላሳ መጠጦች ሻይ፣ ቡና፣ ስኳር፣ ኩኩሶች እንዲሁም ሌሎች በጥርስ ስር መቦርቦር የአሲድነት ያላቸው ምግቦችና መጠጦች መቀነስ ያስፈልጋል፡፡

የስኳር በሽተኛ በሽታው ከሌለበት ሰው በተሻለ የጥርስ ህክምና ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ይህም ማንኛውም የተለየ ምልክት በአፍ አካባቢ ሲታይ ለምሳሌ ጥርሳችን በምናፀዳበት ወይም ድዳችን ሲነካ የሚደማና የሚያመን ከሆነ እብጠት ካለው፣ አላስፈላጊ ፈሳሽ በድዳችን ሲነካ የሚደማና የሚያመን ከሆነ እብጠት ካለው፣ አላስፈላጊ ፈሳሽ በድዳችንና በጥርሶቻችን መካከል ሲወጣ፣ መጥፎ የአፍ ጠረን ካለ በአፋጣኝ ወደ ጥርስ ህክምና ቦታ በመሄድ ክትትል ያስፈልጋል፡፡

በመጨረሻ የስኳር በሽተኞች በቤታቸው ውስጥ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

1. በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በመቆጣጠር በተለያዩ አካላት ላይ የሚመጣውን ችግር በመከላከል ጠንካራ ጥርስና ድድ መፍጠር፤

2. ቢያንስ በቀን ሁለቴ ጥርስን ፍሎራይድ የተባለውን ንጥረ ነገር በያዘ የጥርስ ሳሙና ማጽዳት፤

3. በየጊዜው የጥርስ ሐኪም በመጎብኘት ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

The post Health: የአፍ ጠረን (Halitosis) እና ምላስ | የአፍ ጠረን ያለባቸው ሰዎች ለ7 ችግሮች የተጋለጡ ናቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ናቾ ሞንሪያል –የመድፈኞቹ እጅግ ተፈቃሪው ተጨዋች

$
0
0

 

arsenal Nocho

ስፔናዊው ግራ ተመላላሽ ናቾ ሞንሪል በጃንዋሪው 2013 በአርሰናሉ አርሴን ቬንገር ከማላጋ ክለብ የተገዛው በቡድናቸው የግራ ተመላላሽ ሚና የመጀመሪያው ተመራጭ ለነበረው ኬራን ጊብስ ትክክለኛው ሽፋንን ለመስጠት የሚችልበት ብቃትን ተላብሷል በሚል ታምኖበት ነበር፡፡ በአርሰናል የፈረመበት የመጀመሪያው ዓመትን ያጠናቀቀው ከእንግሊዝ ፉትቦል የጨዋታ ስታይል ጋር በአግባቡ ለመላመድ ጥረትን ለማድረግ ተገድቦ ቢሆንም ቀስ በቀስ አርሰናል የመጀመሪያ ተመራጭ ተጨዋች መሆን ችሏል፡፡

የሞንሪል የአርሰናል መፈረምን ተከትሎም የሰሜን ለንደኑ ክለብ ደጋፊዎች በድፍን ዘጠኝ ዓመታት የዘለቀው የዋንጫ ሽልማት ጉጉታቸውን ለመቅረፍ ያለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት የኤፍ.ኤ ካፕ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት አርሰናል የዘንድሮው ሲዝንን ከ3ኛ ጊዜ በተከታታይ የኤፍ.ኤ.ካፕ የዋንጫ ድልን በመቀዳጀት በውድድሩ ታሪክ ብቸኛው ክለብ የመሆን ታሪክን ለመስራት ከመጓጓት አልፎ ከ2004 የዘለቀው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ናፍቆቱን የመቅረፍ አላማን እንዲይዝ በዋነኝነት የሚጠቀስ ምክንያት የሆነ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት ላይ ከሚገኙለት ተጨዋቾችም ውስጥ አንዱ ናቾ ሞንሪል ነው፡፡

ምክንያቱም በዘንድሮው ሲዝን በእያንዳንዱ የአርሰናል ግጥሚያዎች ላይ በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት በመጫወት የቡድኑ የግራ መስመር እጅግ ጠንካራ ሆኖ እንዲዘልቅ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ አስተዋፅኦን ለማበርከት ችሏል፡፡ ይህንን ከግንዛቤ በማስገባትም አርሴን ቬንገር ሰሞኑን ለሞንሪል ከክለባቸው ጋር ለተጨማሪ ዓመታት የሚዘልቅበትን አዲስ ኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ፈቅደውለታል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ፈረንሳዊው አሰልጣኝ በያዝነው ሳምንት ውስጥ በሰነዘሩት አስተያየትም ናቾ ሞንሪልን በስኳዳቸው በሚያገኙት በእያንዳንዱ የቡድናቸው ተጨዋቾች በከፍተኛ ደረጃ የሚፈቀር ተጨዋች ነው በማለት ገልፀውታል፡፡

Nocho2

ሞንሪል በአሁኑ ወቅት በስኳዳችን ከሚገኙትና ከቡድናችን እጅግ ከፍተኛ ወሳኝነት ካላቸው ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ መሆኑን መጠራጠር በፍፁም አያሻም፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ያካበተው ሰፊ ልምድን መሰረት በማድረግ እያንዳንዱ የቡድናችን ተጨዋቾች እንደ ትልቅ አርአያቸው የሚቆጥሩና በከፍተኛ ደረጃ የሚፈቀሩት ተጨዋች መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ›› በማለት በስፔናዊው ግራ ተመላላሽ ዙሪያ መግለጫቸውን መስጠት የጀመሩት አርሴን ቬንገር በመቀጠልም ‹‹በቡድናችን በዘንድሮው ሲዝን በግራ መስመሩ ካለፉት ዓመታት በብዙ መልኩ የተሻለ የተረጋጋ ጥሩ አቋም እንዲኖው ግንባር ቀደሙን አስተዋፅኦን ያበረከተው በመሆኑ የተፈቀደለት አዲስ የኮንትራት ማራዘሚያን ውል በትክክልም በሚመጥነው መሆኑን አምናለሁ›› የሚል አስተያየታቸውን አክለዋል፡፡

ሞንሪል በእስካሁኑ ሲዝን የያዘው የማይዋዥቅ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ከአርሰናል መደበኛ ቋሚ ተሰላፊዎች ውስጥ የያዛቸው ብቃት አስፈላጊው ከበሬታን ያላገኘለት ተጨዋች ነው በማለት ላይ ናቸው፡፡ በዚህ አመለካከት ዙሪያ አርሴን ቬንገር አስተያየታቸውን የሰነዘሩት ‹‹እኔ እስከሚገባኝ ድረስ የሌሎቹ ተቀናቃኞቻችን ክለቦች አባላትም የሞንሪል የተዋጣለት የግራ መስመር ተመላላሽ ሚና ባለቤት መሆንን በአግባ የተረዱበት የውድድር ዘመን ላይ እንገኛለን፡፡ ማንኛውም አስተያየት ሰጪ ቢሆን ሞንሪልን ፍፁም እንከን የማይወጣለት ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት ባህሉ ያደረገበት የውድድር ዘመንን በማሳለፍ ላይ መሆኑን ሊመሰክርለት ይችላል፡፡ ከግራ ተመላላሽ ሚና ባሻገር አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት በመሀል ተከላካይ ክፍል በመሰለፍ ለቡድናችን ተጨማሪ ትልቅ ኃላፊነትን የሚፈፅምልን ተጨዋች ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በእያንዳንዱ ግጥሚያ የሚሰጠውን ኃላፊነትን ለመፈፀም 100 ፐርሰንት ጥረትን የማድረግ ባህሉ ለሌሎች የቡድናችን ተጨዋቾች በትልቅ አርአያነት የሚጠቀስለት ባህሉ ነው፡፡

 

በአቡኑ ወቅት ቡድናችን በሞንሪልና በኬራን ጊብስ አማካይነት ሁለት ወርልድ ክላስ የግራ ተመላላሽ ሚና ባለቤቶችን መያዙም እድለኛ እንደሀነ ያህል ይሰማኛል፡፡ ምክንያቱም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሚገኙት አብዛኛዎቹ ክለቦች ከዚህ ቦታ ላይ መሰረታዊና ያለው የመሳሳት ችግር በግልፅ በመታየት ላይ ነው፡፡ ከዚህ መልካም አጋጣሚያችን በአግባቡ ተጠቃሚ በመሆን የዘንድሮው ሲዝንን በምንሳተፍባቸው ውድድሮች ሁሉ መልካም ውጤቶችን በማስመዝገብ ለማጠናቀቅ የማናልምበት ምክንያት አይኖርም ብለዋል፡፡

ስፔናዊው ኢንተርናሽናል ግራ ተመላላሽ በበኩሉ አርሰናል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጠንካራ አቋምን በመያዝ በአሁኑ ወቅት የፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥን በመምራት ላይ ካለው ሊስተር ሲቲ የሁለት ነጥቦች ልዩነት በማነስ የሻምፒዮንነት ፉክክሩ ዋነኛ ተዋናይ የሆነው አብዛኛዎቹ ተጨዋቾች ሳይበታተኑ አብረው ብዛት ባላቸው ግጥሚያዎች ላይ የመሰለፍ እድልን ማግኘታቸው መሆኑን ያመነበት መግለጫን ከትናንት በስቲያ ሰጥቷል፡፡

አርሴን ቬንገር ባለፉት ሁለት ተከታታይ የዝውውር መስኮቶች ከአርሰናል አዲስ ያስፈረሟቸው ተጨዋቾች ፒተር ቺክና መሐመድ አልኔኒይ ብቻ መሆናቸውን በማስገንዘብ ሞንሪል መግለጫውን የሰጠው ‹‹በእኔ አመለካከት በስኳዳችን የሚገኙት አብዛኛዎቹ ተጨዋቾች ከሁለትና ከሶስት ዓመታት በላይ በበርካታ ግጥሚያዎች ላይ አብረው የመሰለፍ እድልን ያገኙ መሆናቸው በመሃላቸው እጅግ ተደናቂ ህብረት እንዲፈጠር የበኩሉን ትልቅ አስተዋፅኦን አበርክተውልኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት በመሃላችን ያለው ህብረትም እጅግ ጠንካራ ነው፡፡ በሜዳ ላይ ብቻ ሳይሆን ከሜዳው ውጪም አብዛኛውን ጊዜያችንን አብረን ማሳለፋችን በመሀላችን ያለው የእርስ በርስ መፈቃቀር ከፍተኛነትን የማያንፀባርቅ ነው፡፡

Arsenal v Stoke City - Barclays Premier League

ለአንድ ቡድን የዋንጫ ሽልማቶችን ለማግኘት እንዲችል ትልቅ አስተዋፅኦን የሚያበረክትለት ጉዳይ ደግሞ በቡድኑ ካምፕ የሚኖረው ህብረት ያማረ መሆን ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ይህንን ከፍተኛ ወሳኝነት ያለው ክራይቴሪያን በተሟላ ሁኔታ ለመያዝ ችለናል የሚል እምነት አለኝ›› በማለት ነው፡፡ የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር በእያንዳንዱ የዝውውር መስኮት ከአንድ ወይም ከሁለት የማይበልጡ አዲስ ተጨዋቾችን ማስፈረምን በቅርቡ ዓመታት ውስጥ የተለመደ ባህላቸው ማድረጋቸው የበኩሉን ትልቅ አስተዋፅኦን እንዳበረከተላቸው በማመን ሞንሪል በመቀጠል የሰጠው መግለጫ ‹‹…አርሰናል በ11 ተጨዋቾች ክለብ በቻ አይደለም በዋናው ቡድናችን ስኳድ የሚገኙት ሁለት 24 ተጨዋቾች አንዳንድ ህብረትን በመፍጠር ተደናቂ ስኬቶችን ለማስመዝገብ የተቻላቸውን ሁሉ ጥረትን የሚያደርጉበት ህብረቱና አጠቃላዩ ቅንጅቱ ያማረ ክለብ ነው፡፡ ለዚህ የረዳን ደግሞ በእያንዳንዱ የዝውውር መስኮት ከአንድ የማይበልጥ አዲስ ተጨዋቾችን ማስፈረማችንን የተለመደ ባህላችንን ማድረጋችን መሆኑን አምናለሁ፡፡ ለዚህ ክለብ ከመጣሁበት ጊዜ አንስቶም በስኳዳችን ያለው ህብረትን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ ለመምጣት ምስክርነቱን መስጠት እችላለሁ፡፡ አብዛኛዎቹ የቡድናችን ተሰላፊዎች ከሁለት ዓመታት በላይ አብረን የመጫወት እድልን በማግኘታችንም በመሃላችን ያለው አጠቃላዩ ቅንጅትና የጨዋታ እንቅስቃሴ መናበብ ይበልጥ እያማረ ሊሄድልን ይችላል›› በማለት ነው፡፡

 

The post Sport: ናቾ ሞንሪያል – የመድፈኞቹ እጅግ ተፈቃሪው ተጨዋች appeared first on Zehabesha Amharic.

ከአድዋ ድል ብቻ ሳይሆን ከክፉ ቀን ድልም እንማር!! 

$
0
0

    (ከ ይሁኔ አየለ)

ድህነት ዋናው የምግብ ዋስትና አለመኖር ምክንያት ቢሆንም ብቸኛ ግን አይደለም፡፡ ሌላም ብዙ ምክንያቶች ይኖራሉ፡፡ አፍቅሮተ-ቁስ (Materialis) አንዱ ነው፡፡ አፍቅሮተ-ቁስ የሥነ-አዕምሮና የምግብ አጠቃቀም አጥኝዎች አልጠግብባይነት የሚል ፍች ይሰጡታል፡፡ ዳውሰን የተባሉ የመስኩ ተመራማሪ ሀብትን በመሰብሰብ የደስታ ምንጭና የስኬት መለኪያ ከዚያም አልፎ የመኖር ዋስትና አድረጎ መውሰድ በአፍቅሮተ- ነዋይ ለተለከፉ ሰዎች መለያ ባህርያት ናቸው ይላሉ፡፡

የስግብግብነት ምንጩ ብዙ ነው፡፡ ዋና ዋና የተባሉት፤ በህጻንነት በቂ መሰረታዊ ነገሮችን(በተለይ ምግብና ልብስ) አለማግኘት፣ የቤተሰብ መበታተን፣ ጥራት ያለው ጥምህረት አለማግኘት፣ በወጣትነት ጊዜ የሚከሰት የማንነት ችግር፣ የሕይወት አጋር ስለ አፍቅሮት ነዋይ ያለው ግንዛቤ፣ ወላጅና ሌላም ሊጨምር እንደሚችል አጥኝዎች የተስማሙበት ይመስላል፡፡ ስለ አልጠግብ ባይነት ይህን ካልሁ ወደ ዋናው አጀንዳ ልለፍ፡፡

በኢትዮጵያ ከ 1880- 1884 ዓ.ም (ለአምስት አመታት)  ክፉ አመታት ነበሩ፤ ይህ ጊዜ በህዝቡም ክፉ ቀን በመባል ይታወቃል፡፡ እነዚህ ዓመታት በተለያቱ የሀገሪቱ ክፈሎች ታላቅ ፍጅት አስከትለው አልፈዋል፡፡ አንድ ጸሐፊ ወደ አንድ ሶስተኛው የሀገሪቱ ህዝብ በረሃብና በተያያዥ ምክንቶሞች እንዳለቀ በመጽሐፋቸው አስፈረዋል፡፡ የችግሩ ሰለባ የሆኑ ሰዎች በወቅቱ የማይበሉ እንስሳትን ከመብላት አልፈው ሰውም እንደበሉ ተጽፎ አንብበናል፡፡

Battle of Adwa1

የዚያን ጊዜው የረኃቡ ምክንት ኢሊኖይስ አልነበረም፡፡ ምክንያቱ ፈረንጅ አመጣው ተብሎ በሚገመት የቀንድ ከብት በሽታ ባስከተለው የከብት እልቂት ነበር፡፡ ዋናው መንስኤ የከብቶች ማለቅ ቢሆንም አልጠግብ ባይነት (ስግብግብነትም) የራሱን ሚና ሳይጫወት አልቀረም፡፡ እስኪ በ 2002 ዓ.ም በታተመውና የኢትዮጵያ ታሪክ በአለቃ ተክለ ኢየሱስ፤ ሐተታ በዶክተር ሥርገው ገላው ከሚለው መጽሐፍ ከተጻፈው ሐተታ እንጨልፍ፤

ያን ወራት የሽዋ አራሽ ጉዛም እህሉን በጉርጓድ እየከተተ ለመንድሙ፣ ለእኅቱ፣ ለዘመዱ እህል አየነፈገ በገበያ እህል ታጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ዳግማዊ ምኒልክ በየጉዛሙ ቤት ወታደር ሰደደ፡፡ ለባለ እህሉ የአንድ አንድ ዓመት ቀለብ እየተወለት ትርፉን በደብዳቤ አግብቶ ተበድሮ ለድሀ ናኘው፡፡ ከዚህ በኋላ ወታደር ከሚዘርፍን ገበያ ብንሸጠው ያሻለናል እያለ ገበያ አወጣው፡፡ ያን ጊዜ እህል በገበያ ተረፈ፡፡

ይህ አንዱ የምንማረው የአጼ ምኒልክ የአመራር ጥበብ ይመስለኛል፡፡ ይህ እርምጃ የህዝቡን ሕይወት ያተረፈ፤ ስግብግቡንም ያልጎዳ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን ስኳር የደበቁ ስግብግቦች ይህን እድል ያገኙ አልመሰለኝም፡፡ ይህ ከዛሬ 120 ዓመት በፊት የሆነ ድርጊት ነው፡፡ ለስግብግቡ የአንድ አመት ቀለብ እየተወ ትርፉን በደብዳቤ አግብቶ ተበድሮ ለተቸገረው በነጻ ሰጠው፡፡ ሕይወትም አተረፈ፤ ገበያውንም አጠገበ፡፡ ለእኔ፤ ህዝባዊነት ማለት ይህ ነው፡፡

በዚሁ መጽሐፍ ላይ ሌላም ያስደነቀኝ ነገር ልጨምር፡፡ “ዳግማዊ ምኒልክም ለህዝቡ ትጋትና ትሕትና አስተማረ፡፡ መጥረቢያ አበጅቶ ካንቻ መታ፡፡ መቆፈሪያ አበጅቶ ዳገት ቆፈረ” ይላል፡፡ በወቅቱ የንጉሱን አርአያነት መበከትል ከከፍተኛ ሹማምነት እስከ ቤትሰራተኛው አይረባ ኩራቱን እየተወ መሬቱን አየመነጠረና እየቆፈረ ከረሃብና ከችግሩ ወጣ፡፡ ድህነቱን በስራው ድል መታው፡፡

በዚህ ወቅት ከንጉሱ ድርጊት የምንማረው አይኖር ይሆን? መቸ ይሆን ከልመና (ምጽዋት) የስነ ልቦና ጫና የምንወጣው?

The post ከአድዋ ድል ብቻ ሳይሆን ከክፉ ቀን ድልም እንማር!!  appeared first on Zehabesha Amharic.

“ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ወንድሙ ሲገደል ሌላው ቆሞ ካየ ውርደት ነው”ሕብር ራድዮ ልዩ ቃለምልልስ ከፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ጋር

$
0
0

ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም የሕግ ባለሙያ ብቻ ሳይሆኑ የበለጠ የሚታወቁት ባለፉት አስር ዓመታት ሳይሰለቹ በአደባባይ የዚህን ስርዓት ግፍ በመቃወም በብዕራቸው ስለ ሰብኣዊ መብት መከበር፣ስለ ሕሊና እስረኞች እንግልት፣አገሪቱን አፍኞ ሕዝቡን ረግቶ ስለሚያሰቃው ዘረና አገዛዝ ብዙ ወቅታዊና ትኩረት ሊያገኚ የሚገባቸውን ጉዳዮች በጥልቅ በየሳምንቱ  ሲጽፉ ኖረዋል።ዛሬም ይጽፋሉ።በወቅታዊው የኦሮሚአ ሕዝባዊ ተቃውሞ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከህብር ሬዲዮ ጋር ተወያይተዋል።

  • ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ወንድሙ ሲገደል ሌላው ቆሞ ካየ ውርደት ነው ከዚህ ለመውጣት የተበደለው ሁሉ በብሄር ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቱ ለመብቱና ለነጻነቱ በአንድ ላይ መነሳት አለበት
  • የኦሮሞ ተቃውሞ አይደለም.. የተበደሉ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ነው.. ያልተበደለ የለም
  • ሕወሃት የሚፈልገው ወደሁዋላ እንድናይ ነው ወጣቱ ትውልድ ነው መጠየቅ ያለበት ወደፊት ነው መሔድ የምንፈልገው ወይስ እነሱ እንደፈለጉት ወደሁዋላ እያዩ በትላንት ታሪክ ስንጋጭ መኖር? ይሄን በአግባቡ መመለስ ያስፈልጋል
  • ሕወሓት በኦሮሚያ ያን ሁሉ የወገኖቻችን ደም እያፈሰሰ በራሴ እንባ ጠባቂ አጣራለሁ ማለት ቀልድ እና ተቀባይነት የለውም
  •  በኦሮሚያ ለተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ የኤርትራ እጅ አለበት ማለት የተበደለው የኦሮሞ ሕዝብ ለመብቱ አውቆ አይነሳም ብሎ መሳደብ ነው

almariam

The post “ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ወንድሙ ሲገደል ሌላው ቆሞ ካየ ውርደት ነው” ሕብር ራድዮ ልዩ ቃለምልልስ ከፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ጋር appeared first on Zehabesha Amharic.


በሚኒሶታ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍን የሚያሳይ ቪድዮ

ቁም ነገር መጽሄት – ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆኜ እየኖርኩ ነው

$
0
0

ቁም ነገር መጽሄት – ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆኜ እየኖርኩ ነው

አትሌት መቶ አለቃ ታደሠ
አትሌት መቶ አለቃ ታደሠ ሰጥ አርጋቸው እድሜያቸው ገፍቷል፡፡ 78ኛ አመታቸውን ይዘዋል፡፡ ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ የሩጫ ውድድሮች ላይ ተሳትፈዋል፡፡ መሳተፍ ብቻ ሳይሆን ከወርቅ እስከ ነሐስ ሜዳልያዎች አምጥተዋል፡፡ በወጣትነት ዘመናቸው ለሃገራቸው ክብርን አስገኝተዋል፡፡ ዋሚ ቢራቱ፣ ማሞ ወልዴ፣ ምሩጽ ይፍጠር፣ የትነበርክ በለጠ፣ ደምሴ ወልዴ፣ ከበደ ባልቻ፣ መገርሳ ቱሉና መሃመድ ከድርን ከመሳሰሉት ጋር ከ1960ዎቹ መጀመሪያ እስከ 1970ዎቹ መጨረሻ ድረስ በተለያዩ ርቀቶች ሲሮጡ ነበር፡፡

የመከላከያ ስፖርት ክለብ (የቀድሞው መቻል) አትሌት የነበሩት መቶ አለቃ ታደሰ ሰጥ አርጋቸው በጉብዝና ወራታቸው ላባቸውን ጠብ አድርገው የሃገራቸውን ባንዲራ በአለም ፊት ከፍ ቢያደርጉም አሁን በስተርጅና ጊዜያቸው፣ ጉልበታቸው ሲደክም ዞር ብሎ እንኳ የሚያያቸው ሰው አጥተዋል፡፡ የ500 ብር ጡረተኛው መቶ አለቃ ታደሠ 550 ብር ከሚከፍሉባት፣ ለማድቤት እንኳ በማትመጥን ጠባብ ቤት ውስጥ ይኖራሉ፡፡ ልጆቻቸውን ማሳደግ የሚችሉበት አቅም ስለሌላቸው ሁለቱን በየዘመድ አዝማዱ በትነዋቸዋል፡፡

አሁን ያላቸው ሃብት በየሃገራቱ ተወዳድረው የሰበሰቧቸው ሜዳሊያዎች ብቻ ናቸው፡፡ በስፖርት የጠበቁት ተክለ ሰውነታቸው በኑሮ ሸክም ምክንያት መጉበጥ ጀምሯል፡፡ ‹‹ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆኜ እየኖርኩ ነው›› ይላሉ፡፡ ቃለ ምልልሱን ሳደርግላቸው በየመሃሉ እምባና ሳግ እየተናነቃቸው ሃሳባቸውን በአግባቡ መቋጨት እንኳን ይቸገሩ ነበር፡፡

ቁም ነገር፡- በውጭ ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ የሮጡት መቼ ነበር?
መቶ አለቃ ታደሠ፡- መጀመሪያ የተሳተፍኩት 53 የአፍሪካ ሀገራትን ወክዬ በሜክሲኮ በተደረገው ውድድር ነበር፡፡ ከ20 ቀን በላይ የፈጀና እንደኦሎምፒክ ያለ ውድድር ነው፡፡ አፍሪካ ራሱን ችሎ፣ አውሮፓ ራሱን ችሎ፣ ሌላውም አህጉር ራሱን ችሎ ነበር የሚሳተፈው፡፡ በዚያ ውድድር በማራቶን አንደኛ ሆኜ ነው ያሸነፍኩት፡፡ የመጨረሻውን 21 ኪሎ ሜትር ብቻዬን ከሞተር ጋር ነበር የሮጥኩት፡፡
ቁም ነገር፡- በምን ያህል ሰአት ነበር ውድድሩን የጨረሱት ሰዓቱን ያስታውሱታል?
መቶ አለቃ ታደሠ፡- ሁለት ሰዓት ከአስራ አምስት ደቂቃ ከ25 ሰከንድ ነበር የፈጀብኝ፡፡
ቁም ነገር፡- በመቼ አመተ ምህረት ነው?
መቶ አለቃ ታደሠ፡- በ1966 አካባቢ ነው፡፡
ቁም ነገር፡- በኦሎምፒክ ውድድርስ ተሳትፈው ያውቃሉ?
መቶ አለቃ ታደሠ፡- ለኦሎምፒክ ውድድር ሰአት ያሟላሁት በ1976 በፈረንጆቹ ለተደረገው የሞንትሪያል ኦሎምፒክ ነበር፡፡ እዚህ መጽሔት ላይ እንደምታየው (በሞንትሪያል ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትሌቶችንና ልዑካን ቡድኑን ዝርዝርና ፎቶ የያዘውን መጽሔት እያሳዩኝ) ወደ ካናዳ ሞንትሪያል ሄደን ነበር፡፡ ለ15 ቀናት ያህልም ቆይተናል፡፡
ቁም ነገር፡- በውድድሩ ግን አልተሳተፋችሁም ነበር?
መቶ አለቃ ታደሠ፡- ከተዘጋጀን በኋላ አቶ ይድነቃቸው በውድድሩ አንሳተፍም አሉን፡፡
ቁም ነገር፡- ምንድ ነበር ምክንያቱ?
መቶ አለቃ ታደሠ፡- በዘረኝነት ጉዳይ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ የነበረውን ዘረኝነት በመቃወም ብዙዎቹ የአፍሪካ ሃገራት አንሳተፍም ብለው ውድድሩን አቋርጠው ነበር፡፡ እኛም ወደሃገራችን ተመለስን፡፡ የሚገርመው ነገር ለሞንትሪያል ኦሎምፒክ ሲባል ለአንድ አመት ያህል ሆቴል ውስጥ ሆነን ነው ልምምድ ስንሰራ የቆየነው፡፡
ቁም ነገር፡- ሌሎች የተሳተፉባቸው ውድድሮችስ የትኞቹ ናቸው? የሚያስታውሷቸውን ይንገሩኝ?
መቶ አለቃ ታደሠ፡- በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ፖርቶሪኮ የሚባል ሃገር ሄጄ ተወዳድሬ ነበር፡፡ የቡድን ጨዋታ ነበር፡፡ 6 ሆነን ነው የተሳተፍነው፡፡ ሻምበል ምሩፅ፣ እኔ፣ መሃመድ ከድር፣ ሾላና ሌሎች ሁለት ሰዎች ነበሩ፡፡ በጣም አስቸጋሪ ውድድር ነበር፡፡ ዳገትና ቁልቁለት አለው፡፡ ሻምበል ምሩፅ በውድድሩ አንደኛ ሲሆን እኔ ሁለተኛ ሆኜ ነው የጨረስኩት፡፡ የተዘጋጀውን ዋንጫ በእኛ እጅ አስገባነውና ለፌዴሬሽን አምጥተን አስረከብን፡፡ የ21 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ነበር፡፡ ጅቡቲም የግማሽ ማራቶን ሩጫ ተወዳድረን ነበር፡፡ በጫማ ቀለም እየተደበደብን ነው ውድድሩን የጨረስነው፡፡ አልጄሪያ በተደረገው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ላይም ተወዳድሬ ነበር፡፡ በማራቶን ዛንዚባር ላይ ሮጠን ገብሬ ጉርሙ አንደኛ ሲሆን እኔ ሁለተኛ ሆኜ ጨርሻለሁ፡፡ አቴንስ ላይ ደግሞ ደረጀ ነጂ አንደኛ እኔ ሁለተኛ ከበደ ባልቻ (አሁን ካናዳ ነው ያለው) ደግሞ ሶስተኛ በመሆን አሸንፈናል፡፡ ሌሎች ብዙ ሃገራትም ሮጫለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- በማራቶን ብቻ ነበር የሚወዳደሩት?

tadsse
መቶ አለቃ ታደሠ፡- በማራቶን ብቻ ሳይሆን በግማሽ ማራቶንና በ12 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድርም እሳተፋለሁ፡፡ 9 ኪሎ ሜትርም እሮጥ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ከነባር የማራቶን ሯጮች እኔ ብቻ ነው ያለሁት፡፡
ቁም ነገር፡- አሁንም በተለያዩ ውድድሮች ታላቁ ሩጫን ጨምሮ ይሮጣሉ… በዚህ እድሜዎም ከስፖርቱ አልራቁም ማለት ነው?
መቶ አለቃ ታደሠ፡- አዎ እሮጣለሁ፤ በደንብ ነው የምሮጠው፡፡ በእኔ እድሜ ያለ ሰው ሮጦ አይቀድመኝም፡፡
ቁም ነገር፡- የኑሮ ሁኔታዎስ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
መቶ አለቃ ታደሠ፡- እኔ መውደቂያ የለኝ፣ መጠለያ የለኝ፣ ብዙ ችግር ላይ ነው ያለሁት፡፡ ቁሜ መሄዴን አትይ፡፡ ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆኜ ነው ያለሁት፡፡
ሰርቻለሁ፣ ደክሜያለሁ፣ ለኢትዮጵያ ባንዲራ በስነስርአት አገልግያለሁኝ ግን እንዳገለገልኩት አላገኘሁም፡፡ ዝም ብዬ ወድቄ ነው የቀረሁት፡፡ ምናልባት ሃገር ወዳድ ሰው አለ፣ ስፖርት አፍቃሪም አለ፤ ያለሁበትን አይተው ድጎማ ሊያደርጉልኝ፣ ሊደግፉኝ ይችላሉ ብዬ አስባለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- ስንት ልጆች አሉዎት?
መቶ አለቃ ታደሠ፡- አራት ልጆች ናቸው ያሉኝ፤ ሁለቱን አቅሜ ስላልቻለ ወደ ዘመድ ላኳቸው፡፡ አሁን እኔ ጋር ያሉት ሁለቱ ብቻ ናቸው፡፡ ሁሉንም ልጆቼን አንድ ላይ አድርጌ እንዳላሳድግ ምን ላይ ይኖራሉ፤ምን ላይ ይተኛሉ፤ ምን ይበላሉ፡፡ አልቻልኩም፡፡ ብዙ ችግር ላይ ነው ያለሁት፡፡ ሌላው ይቅር የአንገት ማስገቢያ መጠለያ ካገኘሁ ልጆቼን ሰብስቤ ከጎኔ ሆነው እንዲማሩ አደርግ ነበር፡፡ ግን በየፊናው ተበትነው በቃ እኔም ከሞትኩ አንገናኛም (እያለቀሱ)
ቁም ነገር፡- በተለያዩ ውጭ ሀገራት ተዘዋውረው ሲሮጡ እዚያው ለመቅረት አስበው አያውቁም ነበር?
መቶ አለቃ ታደሠ፡- ብዙ ጊዜ እዚያ እንድንቀር ይለምኑ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ከሻምበል ማሞ ወልዴ ጋር ስፔን ሃገር ሄደን የመኪና ቁልፍ እንስጣችሁ… ቤት እንስጣችሁ አትሂዱ ሲሉን ነበር፡፡ታዲያ ሻምበል ማሞ ጎበዝ ነው… ቆራጥ ነው፡፡ አልፈልግም… ሃገሬን ጥዬ አልሄድም ይል ነበር፡፡ እኔም ዘወር በሉ ነው የምላቸው፡፡
የትኛውም ቦታ ስንሄድ እንድንቀር ይጠይቁናል፡፡ እዚህ ስራ እናሰጥሃለን ይላሉ፡፡ ግን ሃገሬን ጥዬ አልኖርም፡፡ የምታበላኝ የምታጠጣኝን ሃገር ጥዬ አልሄድም፣ ሞቴንም ምኔንም ሃገሬ ላይ ነው የሚሻለኝ ብየ እምቢ እያልኩ ነው እንጅ በጣም ይለምኑን ነበር፡፡ አቅም ባለን፣ ጉልበት ባለን ጊዜ ማለት ነው፡፡ ግን ያሳደገችኝን ሃገር ከድቶ መሄዱም ይከብዳል፤ ጥሩ አይደለም፤ አይቀናም፡፡
ቁም ነገር፡- በናንተ ጊዜ ሲሮጡ ከነበሩ አትሌቶች መካከል የሚያገኟቸው አሉ?
መቶ አለቃ ታደሠ፡- ብዙዎቹ አሁን በሕይወት የሉም፡፡ ጥቂት አትሌቶች ናቸው፡፡፡ አልፎ አልፎ አገኛቸዋለሁ፡፡ እና እንዲያውም አንዳንዶቹ ሲያገኙኝ ‹‹ታዴ አለህ… አልሞትክም›› ይሉኛል፡፡ እንድሞት ነው ወይ የምትፈልጉት እላቸዋለሁ፡፡ እግዚአብሔር አለ የሚወስነው እሱ ነው እላቸዋለሁ፡፡
ቁም ነገር፡- አመሠግናለሁ፡፡
ከአዘጋጁ፡- አትሌት መቶ አለቃ ታደሰ ሰጥ አርጋቸውን መርዳት የምትፈልጉ በስልክ ቁጥር 0943108106 ልትደውሉላቸው ትችላላችሁ፡፡
ወገኖቼ ከኝህ አባት ጎን እንቁም አምላክ ብድራቱን ይከፍላችሃል

The post ቁም ነገር መጽሄት – ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆኜ እየኖርኩ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

በጂዳ ኢትዮጵያዊቷ አሰሪዋን ገደለች ተብላ ታሰረች

$
0
0
File Photo

File Photo

(ሳተናው) ባሳለፍነው ማክሰኞ በጂዳ አል ካፍጂ አካባቢ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ አሮጌቷን ቀጣሪዋን ደጋግማ በመደብደብ ከገደለቻት በኋላ ቤቱን ዘግታባት ወጥታለች በሚል ፖሊስ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሏን አረብ ኒውስ ለንባብ አበቃ::
የአል ካፍጂ የምስራቅ ወረዳ የፖሊስ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ዛያድ አል ራካቲ ‹‹ማክሰኞ ከቀኑ አስር ሰዓት ለፖሊስ ከማህበረሰብ የደህንነት ጥበቃ አካላት ከቤት ሰራተኛዋ ጋር ትኖር የነበረችን የአንዲት አሮጊት ሴት መኖሪያ ቤት እንዲከፍት ጥያቄ ይቀርብለታል፡፡በጥያቄው መሰረትም የግለሰቧ መኖሪያ ቤት ሲከፈት አሮጌቷ ብዙ ቦታ ላይ ተፈነካክታ ሞታ አግኝተዋታል››ብለዋል፡፡

የቤት ሰራተኛዋ እስክትገኝ ድረስ ፈጣንና ጥልቅ ሆነ ምርመራ በአካባቢው ጭምር ማድረግ በመቻሉ ገዳይዋ በቅርብ ቦታ ተደብቃ ተገኝታለች የሚሉት ቃል አቀባዩ ‹‹በእርሷና በአሰሪዋ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ አሰሪዋን በመደብደብ እንደገደለቻት ተናግራለች››ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አሰሪዎቻቸውን ገደሉ እየተባሉ እስከ ስቅላት ለሚደርስ ቅጣት ይቀጣሉ፡፡የዚህችን ምስኪን እህታችንን ጉዳይ በመከታተል እውነተኛ ፍትህ እንድታገኝ የሚረዳት መንግስት ታገኝ ይሆን?

ምንጭ አረብ ኒውስ

The post በጂዳ ኢትዮጵያዊቷ አሰሪዋን ገደለች ተብላ ታሰረች appeared first on Zehabesha Amharic.

የካቶሊኩ ቄስ በመቂ ተቃጠለ ስለተባለው ቤተክርስቲያን አስረዱ

$
0
0

meki

ባለፈው ወር በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን መቂ ከተማ የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስትን ለመቃወም ወደ አደባባይ በወጡበት ወቅት የሰው ህይወት መጥፋቱ፣ የሰዎች መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያንና የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ክሊኒክ መዘረፋቸውንና መቃጠላቸውን መነገሩ አይዘነጋም፡፡ የተዘረፈችው ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ቄስ አብርሃም ደስታ ድርጊቱ መፈጸሙን በማረጋገጥ ስለጉዳዩ ተናግረዋል፡፡
ቄስ አብርሃም ደስታ ለአለም አቀፉ የካቶሊክ የእርዳታ ድርጅት በጻፉት ደብዳቤና ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ

‹‹በመቂ የሚገኘው የጥንቱና ትልቁ ቤተክርስቲያን ጥቃት ደርሶበታል፣ ጥቃቱ የደረሰበትም በምናገለግላቸው፣አብረውን በሚሰሩና ለስራችን በጣም ቅርብ በሆኑ ሰዎች ነው››ብለዋል፡፡

የመቂው ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ቄሱ የጥቃት አድራሾቹን ሁኔታ ሲያብራሩም ‹‹ልጆች፣ወጣቶች፣ሽማግሌዎችና ሴቶች ድንጋዩችን በመወርወር በመጀመሪያ የቤተክርስቲያኑን ንብረት አጠፉ፣ የዲያቆናትና የመጋቢዎች ማዕከልን፣ለአካል ጉዳተኞች ህክምና ርዳታ የሚሰጥ ክሊኒክም ዝርፊያ ተፈጽሞባቸዋል››ይላሉ፡፡

በቤተክርስቲያኑ ላይ ጥቃቱ ሲሰነዘር 55 የሚደርሱ ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ ካቶሊካዊያን በመጋቢዎች ማዕከል ይሰጥ የነበረውን የነርሶች ትምህርት በመከታተል ላይ ይገኙ እንደነበር ያስታወሱት ቄሱ እንግዶቹ አደጋ ሳይደርስባቸው ለመቂ ቅርብ ወደሆነችው ሻሸመኔ መወሰዳቸውን በማውሳት ‹‹በክሊኒኩ የሚሰሩ ነርሶች ግን ህመምተኞቻቸውን ለአደጋ በማጋለጥ ጥለዋቸው ሊሄዱ ባለመፍቀዳቸው አብረዋቸው ቆይተዋል፡፡የክሊኒኩን ንብረት በሙሉ ሌላው ቀርቶ በነርሶቹ ፊት ለፊት የግል ልብሳቸውን ሳይቀር ሰዎቹ ጠራርገው ከወሰዱ በኋላ ህንጻውን በእሳት አወደሙት››ብለዋል፡፡

ነርሶቹን አንድም ሰው ሊረዳቸው አለመፈለጉን በምሬት የሚገልጹት ቄስ አብርሃም ‹‹በእግዚአብሄር ርዳታ ህመምተኞቹን በመያዝ በቅርባቸው ወዳገኙት የሻሸመኔ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በመግባት ምሽቱን በዚያ ማሳለፍ ችለዋል፡፡እነርሱ ሁሉን ነገር አጥተዋል፣ እጃቸው ላይ የቀረው ከእግዚአብሄር በነጻ ያገኙት የዘላለም ህይወት ብቻ ነው፣ ይህንን ሊወስዱባቸው አልቻሉም››፡፡
የተዘረፉ ንብረቶችን በዝርዝር ያስቀመጡት ቄሱ ‹‹250 አልጋዎች፣700 ብርድ ልብሶች፣የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ቴሌቭዥኖች፣ጀነሬተሮች፣የኮፒ ማሽኖች፣ኮምፒውተሮች፣በሮችና መስኮቶች ሳይቀሩ ተነቃቅለው ተወስደዋል››ይላሉ፡፡
ማዕከሉ ለአንድ ዓመት ያከማቸውን (በእርዳታ ያከፋፍለው የነበረ) 26.455 ፓውንድ ጥሬ እህል ሩዝ፣ስንዴ፣ ፓስታ፣ ላሞችና ዶሮዎች መወሰዳቸውን በመጥቀስ ዝርፊያ ያልተፈጸመው በትምህርት ቤቱ ላይ ብቻ ነበር ብለዋል፡፡
በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ጥቃት ለመፈጸሙ ምክንያቱ ምን ነበር የተባሉት ቄሱ ምክንያቱን አሁን ለመናገር ባይፈቅዱም ‹‹በአእምሯችንና በልባችን ጥያቄ አለብን፣ጌታ ሆይ ለምን ?ግን ለምን እንዲህ ሆነ ?››በማለት ምላሽ ከአምላካቸው ለማግኘት ጥያቄያቸውን ሲያገለግሉት ለቆዩት ጌታ አቅርበዋል፡፡

The post የካቶሊኩ ቄስ በመቂ ተቃጠለ ስለተባለው ቤተክርስቲያን አስረዱ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከሞላ አስገዶም ጋር ከአስመራ የተመለሱ የተባሉ ወታደሮች በዩናይትድ ኔሽን እንደኤርትራ ስደተኛ እየተመዘገቡ መሆኑ ተሰማ

$
0
0

Mola asgedom

(ዘ-ሐበሻ) ከሞላ አስገዶም ጋር የትህዴን ወታደሮች ናቸው በሚል ለኢትዮጵያ መንግስት እጃቸውን እንደሰጡ ተደርገው ሲነገርላቸው የነበሩት ‘ወታደሮች’ በኢትዮጵያ በሚገኘው ዩናይትድ ኔሽን ልክ እንደኤርትራ ስደተኛ ራሳቸውን በማስመዝገብ ላይ መሆናቸው ተሰማ::

በተለይ እነዚህ ከሞላ አስገዶም ጋር ተመለሱ የተባሉት የትህዴን ወታደሮች በአዳማ ማረፊያ ተሰጥቷቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የሕወሓት ሚድያዎች ሲዘግቡ የቆዩ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አብዛኞቹ ወደ ትግራይ ክልል በማቅናት በሽሬ የተለያዩ የስደተኞች ካምፖች ውስጥ ልክ እንደኤርትራ ስደተኛ ተመዝግበው እንደሚገኙ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አጋልጠዋል::

በማይ ዓይኒ ወረዳ በሚገኘው የስደተኞች ካምፕ እንዲሁም ሽሬ አካባቢ በሚገኘው አዲ ሃሪሽ የስደተኞች ካምፕ ከሞላ አስገዶም ጋር ተመለሱ የተባሉት ወታደሮች ራሳቸውን እንደኤርትራ ስደተኛ አስመዝግበው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ተናግረዋል::

በማይ ዓይኒ እና በአዲ ሃሪሽ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች በኛ ስም ሌሎች ወደ3ኛ ሃገራት እየተሻገሩ ነው በሚል በተደጋጋሚ ጸብ ያነሱ እንደነበር በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል::

ከሞላ አስገዶም ጋር ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ራሳቸውን እንደኤርትራዊና አብዛኞቹም ከኤርትራም የፕሮቴስታንት ሃይማኖታቸውን ለማምለክ ስለሚከለከሉ እንደተሰደዱ አድርገው ለዩናይትድ ኔሽን የስደተኛ ማመልከቻ አቅርበው እየተጠባበቁ እንደሚገኙም ለዘ-ሐበሻ ጨምሮ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል::

The post ከሞላ አስገዶም ጋር ከአስመራ የተመለሱ የተባሉ ወታደሮች በዩናይትድ ኔሽን እንደኤርትራ ስደተኛ እየተመዘገቡ መሆኑ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live