Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በእስራኤል ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን የቀረበ ጥሪ

↧

↧

እርቅ፤ የሚነገር –የማይተገበር |ይገረም አለሙ

$
0
0

በአቶ ኦባንግ ሜቶ በሚመራው ድርጅት አዘጋጅነት በተጠራ ጉባኤ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያዉያን ስብሰባቸውን ያጠናቀቁት በሀገራችን እርቅ አስፈላጊ መሆኑ ላይ በመተማመንና ለዚህም ተግባራዊነት እርቅን ከራስ መጀመር እንደሚገባ አጽንኦት በመሰጠት መሆኑን ሰምተናል፡፡ የእስከዛረሬው ተሞክሮአችን ተግባራዊነቱን አንድንጠራጠር ቢያደርገንም የአሰባሳቢዎቹ ተግባርም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የደረሱበት ድምዳሜ የሚደነቅ ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊነቱ ድጋፍ ሊቸረው የሚገባ ነው፡፡
Ethiopia
የእርቅ ተቃራኒ ጸብ ነው፡፡ ከሁለቱ ደግሞ የትኛው ቀላል እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡እርቅ ብዙ መንገድ መሄድ፣ ብዙ ተግባር መከወንን ያሻል ብዙ መስዋዕትነትም ይጠይቃል፡፡ ለዚህም ነው ሲነገር እንጂ ሲተገበር የማንሰማው፣ሲወጠን አንጂ ከግብ ሲደርስ የማናየው፡፡ ጸብ ግን ማሰብና መጨነቅ፣ ማመዛዘንና ረጋ ብሎ መወሰን የማይጠይቅ በደቂቃ ውስጥ ሊከውኑት የሚችል ነው፡፡

ቢያንስ ባለፉት ሀያ ዓመታት የእርቅን አጀንዳ በየግዜው ቢነሳም ከንግግር ማድሚቂያነት አልፎ ተግባራዊነቱ ሊታይ አልቻለም፡፡ የሚናገሩትን መተግበር ያልቻሉቱ የፖለቲካው ተዋናዮች የሚያቀርቡት ምክንያት ደግሞ አንድና የተለመደ ከቁም ነገር ሊገባ የማይችል ነው፡፡ ኮ/ል መንግሥቱ ስለ እርቅ ሲጠየቁ የሀገር ጉዳይ ነው የባልና ሚስት ጸብ አይደለም ማለታቸውን የሰሙና መጨረሻ የሆኑትን ያዩ ወያኔዎች ከዚህ ባለመማር እነርሱ ደግሞ በተራቸው እርቅ ሲባሉ ማን ከማ ጋር ተጣላና ነው በማለት ይሳለቃሉ፡፡በአንጻሩ አንዴ ብሔራዊ እርቅ ሌላ ግዜ ሀገራዊ መግባባት ወይንም ብሔራዊ መግባባት ያስፈልጋል እያለ የሚጮኸው ተቃዋሚ ለነገሩ ተግባራዊ አለመሆን የወያኔን እምቢተኝነት በምክንያት እያቀረበ ለአመታት ዘልቋል፡፡

እርቅን የማይፈልጉ ከጸብ የሚያተርፉ መሆናቸው እሙን ነው፡፡ ወያኔ አጣልቶ እንጂ አስማምቶና ተስማምቶ፤ አለያይቶ አንጂ አንድነትን አጠናክሮ በስልጣኑ ሊቆይ አንደማይችል ስጋት ስላለው እርቅን ቢጠላ መግባባትን በሩቁ ቢል ከዓላማው የመነጨ ነው፡፡ ተቀዋሚዎቹ ግን ሀያ አራት አመታት ስለ እርቅ ሲጠይቁ አንጂ የሚችሉትን ሲያደርጉ አለመታየታቸው ለምን ይሆን የሚል ጥያቄ ያነሳል፡፡ ለዚህ መልሱ የወያኔ አምቢተኝነት ነው የሚባል ከሆነ ራስን ማታለል ይሆናል፡፡

እርቅ የሚጠይቁት ፖለቲከኞች ርስ በርሳቸው አይደለም መጀመሪያ ከራሳቸው መች ታረቁ፤ብሄራዊ መግባባት ሲሉ የሚደመጡት እነርሱ በተቃዋሚነት ደረጃ ፓርቲ ከፓርቲ አይደለም በአንድ ፓርቲ ውስጥ ግለሰቦች አንኳን መች መግባባት አላቸው፡፡ ብዙ ተባዙ የተባሉ ይመስል የተግባር ሳይሆን የቁጥር ፓርቲ በውጪም በውስጥም የሞላው በዚሁ ምክንያት አይደለምን፡ ከወያኔ ጋር ውይይት እንሻለን የሚሉት እነርሱ መች ለውይይት አንድ ላይ መቀመጥ የሚችሉ ናቸው፡፡ በአንድ ብሄር ስም አራት አምስት ድርጅት የመሰረቱ ስለ አንድነት እያወሩ መለያየየትን የሚተገብሩ፣ ሀገራዊ መግባባት እየጠየቁ ድርጅታዊ መናቆር የሚያካሂዱ አይደሉምን፡፡

ወያኔ ተቀዋሚዎቹ እርቅ ብለው የሚጮሆት በምርጫ ያጡትን ሥልጣን በአቋራጭ እናገኛለን ብለው በማለም ነው ብሎ እያሰጋ የሥልጣን ነገር ደግሞ ለርሱ የነበር ጅራ ሆኖበት ማስተዋል ነስቶት እንጂ እኔ ከዚህ ሁሉ ድርጅት ተብየ ጋር ውይይት መቀመጥ አልችልም መጀመሪያ ራሳችሁ ታረቁና፣ አለያም በመካከላችሁ መግባባት ፍጠሩና ከዛ በኋላ ጠበብ ባለ ቁጥርና በተወሰነ አጀንዳ መነጋገር አንችላለን ቢል ተቀዋሚዎቹ ይህን ፈተና ማለፍ ይችላሉ ብሎ በርግጠኝነትመናገር አይቻልም፡፡

መጀመሪያ ከራሳችን አንታረቅ የሚለው የእነ አቶ ኦባንግ ስብሰባ ውጤት ተግባራዊ ቢሆን ይህን ችግር ይቀርፍ ነበር፤ መጀመሪያ ግለሰቦች ከራሳቸው ጋር፣ ቀጥሎ በአንድ ፓርቲ ወስጥ ያሉት ርስ በርሳቸው ከዛም በመቀጠል ፓርቲ ከፓርቲ እየተባለ እርቁም ይን መግባባቱ ቢፈጠር ፓርቲዎቹ ቁጥራቸው የተወሰነ ከወያኔ ጋር አንነጋገርበታለን የሚሉት አጀንዳ የተመጠነ ሀይላቸው የጠነከረ ይሆናል፡ ያኔ ወያኔ በእምቢተኝነቱ ቢጸና የማስገደድ አቅም ይኖራቸዋል፡፡አሁን ባሉበት ደረጃ ሆኖ ስለ እርቅ አስፈላጊነትና ስለ ወያኔ አምቢተኝት ማውራት ከምር እርቅ ፈላጊነትን አያሳይም፡፡ የዓለም አቀፉ ማህበረስብ አካላትና የሀያላኑ መንግሥታት ተወካዮች በአንዲት ሀገር ኢትዮጵያ ጉዳይ ከስንቱ ጋር እንደሚነጋገሩ እየቸገራቸው እባካችሁ አንድ ሆናችሁ ኑ ማለታቸውን በተደጋጋሚ ራሳቸው ፖለቲከኞቹ አንደነገሩን አንዘነጋውም፡፡

የእርቅ አስፈላጊነትንና ጠቀሜታን የማይረዳ ሰው ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ችግሩ ሁሉም የሚያሰበው እርቅ ለሀገሪቱ ስለሚያስገኘው ጠቀሜታና ለትውልድ ስለሚያቆየው በረከት ሳይሆን እሱ ስለሚያጣውና ስለሚያገኘው ግለሰባዊ ጥቅም ( ፕ/ር መስፍን በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጭንቅላት ላይ አለ የሚሉት ዘውድ ሊሆን ይችላል) በመሆኑ እርቅ የሚናገሩት አንጂ የማይተገብሩት አጀንዳ ሆኖ አመታት ያስቆጠረው፡፡

ዛሬ የተነሳው እርቅን ከራስ የመጀመር ጉዳይ በተለያየ ግዜ በግለሰቦችም በድርጅቶችም የተባለና ከመባል ያላለፈ ነው፡፡ ከፖለቲካው መድረክ ውጪም ያሉ በጽሁፍም በንግግርም ሀሳብ የሰጡበት ነው፡፡ ምንግዜም በኢትጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ በቀዳሚነት የሚወሳው ቅንጅት በምርጫ 97 ማንፌስቶው ውስጥ “በሐገሪቱ ታሪክ ውስጥ እንደ መጥፎ ገጽታ የሚታዩ የእርስ በእርስ ግጭቶችም ደም ያፋሰሱ ጦርነቶችና እልቂቶችም በተለያዩ ምክንያቶች ተከስተዋል፡፡በሀገራችን የሚመሰረተው ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት በማይናወጥ ዴሞክራሲያዊ መሰረት ላይ መገንባት ካለበት የእስካሁኑ የጥላቻ የበቀልና ያለመተማመን ምዕራፍ ተዘግቶ ለተከታይ ትውልድ የሚዘልቅ አዲስ ምዕራፍ መከፈት ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዳችን ከራሳችን ፤ሕዝብ ከሕዝብ መንግሥት ከሕዝብ የፖለቲካ ፓርቲ ከፖለቲካ ፓርቲ ለመግባባት የሚችሉበት ብሔራዊ ዕርቀ ሰላም ከሁሉ በፊት መቅድም አለበት ብሎ ቅንጅት ይምናል፡ በማት ነበር የገለጸው፡፡

ይህን የጻፉት ሰዎች ግን ራሳቸውም አብረው መዝለቅ ሳይችሉ ቀርተው የማይሆን ሆነ፡፡ እርቅ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን በወያኔ አባባል ለመጠቀም የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም ሀያ አራት አመት የተነገረው ይብቃና አሁን ከምር ወደ ተግባር ይገባ፡፡ ለዚህ ደግሞ ሁሉም ከራሱ ከቤቱ ከጎረቤቱ የሚጀምርበት ሁኔታ ይፈጠር፡፡ በተመሳሳይ ስም ( በአንድ ብሄር) እየተጠሩ አንድ አይነት አላማ እየተናገሩ አራት አምስት ሆነው የቆሙ ውደ አንድ ይምጡ፤የሚችሉ የታረቁ፣የማይችሉ የአንድ ሀገር ልጅነት መግባባት ይፍጠሩ፤ ይህም የማይሆንላቸው ወያኔ ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ መነሳት ያለበት በመሆኑና በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ይግባቡ፡፡ ይህን ማድረግ ከተቻለ የወያኔ ምርጫ ተገዶ ወደ እርቅ መምጣት አለያም በተባበረ ሀይል ተገፍቶ ሥልጣኑን ማጣት ይሆናል፡፡ ከወያኔ በኋላ ስልጣን በሚይዝ ሀይል ፖለቲካዊ የበቀል ርምጃ የማይጠበቅ ቢሆንም ተገዶ ከስልጣን መውረድ ብዙ ነገር ስለሚያከትል ሁለተኛውን መንገድ ወያኔዎች ባይመርጡት ይመከራል፡፡

እኔም ለማለት ያህል አልኩት አንጂ ተቀዋሚው ወገን ካለፈው ተምሮ ፣በወያኔ እብሪትና እኩይ ድርጊት ተማሮ ስለ እርቅ ከማውራት አለፍ ብሎ እርቅን ከየራሱ በመጀመር በተቀዋሞው ጎራ ሀገራዊ መግባባት ሊፈጠር ይችላል ብሎ ማሰቡ ራሱ ይከብዳል፡፡ በተቃውሞው ጎራ ይህ አንደ ተአምር የሚፈጠር ነገር ተግባራዊ ሆኖ ጠንካራ የተባበረ ሀይል መፍጠር ቢቻል ወያኔን ለእርቅ ማስገደድ ካላሆነም ከሥልጣን ለማስወገድ የሚገድ አይሆን ነበር፡፡

ወያኔ ንቀቱ የበረታው ጥፋቱ የከፋውና የሚፎክር የሚደነፋው የተቃውሞው ጎራ ምንነትና ማንነት አንደማያሰጋው ስላረጋገጠ ነው፡፡ አንባገነን ያሉትን ሀይል ያስገድዱታል አንጂ እንታረቅ እያሉ አይለምኑትም፡፡ ወያኔ ልመና አይሰማ ተቀዋሚው ለማስገደድ አይበቃ፣በዚህ መሀል ህዝብ አሻፈረኝ ብሎ ተነስቶ በየቀኑ የጥይት ሰለባ እየሆነ ነው፡፡የሚያሳዝነው ይህ የዜጎች እልቂት ለወያኔ ከቁብ ያልተቆጠረ ለተቀዋሚው ያላስመረረ መሆኑ ነው፡፡

The post እርቅ፤ የሚነገር – የማይተገበር | ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ተክደናል!!!

$
0
0

tekedenal

እሁድ እረፋድ | ታሪኩ ደሳለኝ

አባት ከ 7 አመት ልጁና ከ3 አመት ሴት ልጁ ጋር ግቢ ውስጥ እየተጫወተ ነው በዚህ መሀል የግቢው በር ይንኳኳል ሴት ልጁን አቅፎ ወደ በሩ ሲያመራ ወንድ ልጁ ሱሪውን ይዞ ተከተለው። በሩን ሲከፍት መሳሪያ የደቀኑ ወታደሮች ከቀበሌው ሊቀመንበር ጋር ቆመው አገኛቸው። አባት ሴት ልጁን ጠበቀ አድርጎ እያቀፈ ወንዱን ልጅ ወደ ኃላ ሸሸት አደረገው። አንደኛው ወታደር ያያዘውን ወረቀት ሰጠው በስጋት ተቀብሎ ተመለከተው “ሀገር የመክዳት ወንጀል የፈፀመ” ይላል ። ወታደሩ በመሳሪያው ጫፎ ወደ ቆመው ፓትሮል መኪና እንዲሄድ መልክት አሳየው ልጆቹን በሩ ላይ ጥሎ ወደ መኪናው ገባ ። መኪናው ሞተሩን አስጩሆ ሲሄድ ጎልቶ የሚሰማው የሞተሩ ድምፅ ሳይሆን የልጆቹ የለቅሶ ድምፅ ነው።

ይህ ክስተት የተፈፀመው ከ 5 ወራት በፊት በጎንደር ከተማ ነበር።

ሐሙስ ከሰዓት

በአካባቢው ሰው የተወደደ ጉልማሳ ነው። የራሱን ሚኒባስ መኪና ነው የሚያሽከረክረው።የተጣላን አስታራቄ ለተቸገረ ቀድሞ ደራሽ ። በሱ ሚኒባስ የተሳፈሩ እናቶችና አባቶች አቅመ ደካሞች አይከፍሉም ማለት የቻላል። ሀሙስ ከሰአት ገቢያተኞችን ጭኖ እንደወትሮው እየሳቀና እየተጫወተ ሲሄድ የትራፊክ ፖሊስ እንዲቆም ምልከት አሳየው። መኪናው ዳራ እያሲያዞ እያቆመ በውስጥ መስታወት ትርፍ ሰው አለመጫኑን ከረጋገጠ በኃላ ከነፍገግታው ከመኪናው ወረዳ። በአካባቢው ቁጥቋጦ ውስጥ ተሸሽገው የነበሩት ወታደሮች ጠመንጃቸውን እንደ ወደሩ ከበቡት። ግራ ተጋባ ሽፎቶቸ ናቸው እንዳይል ትራፊክ ፖሊሱን ለ3 አመታታት ያህል ያቀዋል። አንደኛው ወታደር የያዘውን ወረቀት ሰጠው ተቀብሎ ተመለከተው “ሀገር የመክዳት ወንጀል የፈፀመ” ይላል። እጁን እረጋ ብሎ ሰጣቸው። ከፊት አስቀድመውት ሲሄዱ ሚኒባስ ውስጥ ያሉት ተሳፋሪዎች የሚደረገውን ነገር በቁጣ እየተመለከቱ ነበር።
ይህ ድርጊት የተፈፀመው ከአንቦ ወደቶኪ በሚወስደው መንግድ ላይ ከ 2 ወራት በፊት ነው።

ለማሳያ ያህል ከላይ ስለገለፅኳቸው ሰዎች ጉዳይ መንግስት ሲናገር “አሰልጥኜ፣ ቃል ኪዳን አስገብቼ መሳሪያ ያስታጠኳቸው ወታደሮች ነበሩ ሆኖም ለሀገር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰው መሳሪያቸውን ጥለው ማንነታቸውን ለውጠው ግዲታቸውን ሳይፈፅሙ የከዱ ወታደሮች ናቸው” ይላል። የከዱ የተባሉት ወታደሮች ደግሞ ይህን ያላሉ “ለሀገራችን የደምም የአጥንትም መሳዋትነት ከፍለናል፣ የበረሃው ሀሩር ሳይበግራን የወይን አደጋው በርድ ሳያሸንፈን በዱር በግድሉ በየ ግንባሩ ተፋልመናል። ሆኖም በሚገባን ጊዜ ማረግ ልናገኝ ይቀርና ባለ ማአረግ ይጎትተናል፣ የውል አበላችንም ሆነ ደሞዛችን በወራት ነው ይምናገኘው፣ የሠላም ማስከበር ስራ ለመስራት ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሄድ በሁሉም መስፈርት ብቁ ብንሆንም ከመሀላችን ተመርጠው ነው ሌሎች የሚሄዱት በዚህ ላይ የሀገር ወታደር እንደሆንን እንዲሰማን አያደርጉንም። ታዲያ ማነው የተከዳው?” ይላሉ።

የሆነው ሆኖ መንግስት ከ2005ዓ.ም ጀምሮ የ1990 ዓ.ም ዘማቾችን፣ የ1994ዓ.ም ዘማችን እና ከዛ በኃላ ውትድርናን ተቀላቅለው ከድተውኛል የሚላቸውን እያፈሰ በፌደራሉ የሸዋ ሮቢት እስርቤት ማጉር ከጀመራ ሦስት አመት ሆኖታል።
ይበልጥም ህዝባዊ እንቢተኝነት በኦሮሚያና በጎንደር መታየት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አሰሳውና አፈሳው ተጠናክሮል።

እንዚህ መንግስት ከድቷናል የሚሉ ወገኖች መሳሪያ መተኮሱንና ማስተኮስ የሚችሉ፣ ጥቃትን እንዴት ይፈፀማል ጥቃትንስ እንዴት መመከት ይቻላል የሚሉትን ነገሮች ጠንቅቀው የሚያውቁ በዚህ ላይ ከመሀበረሰቡ ጋር ተግባብተው የሚኖሩ መሆናቸው በአሁን ሰዐት የመንግስት ትልቁ እራስ ምታት እንዲሆኑ አስችሎቸዋል። ለዚህ ነው መንግስት አይኑንም እጁንም እነሱ ላይ ያደረገው። በብዛት በመሀበረሰቡ ውስጥ የሚገኙት ተክደናል የሚሉት ወገኖች ህዝባዊ እንቢተኝነትን ከተቀላቀሉ ምን ይከሰት ይሆን?
(በሸዋ ሮቢት የፌደራሉ እስር ቤት ከሚገኙ ተማኝ እስረኞች ከሚባሉት ጋር የተደረገ ወግ)

The post ተክደናል!!! appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በሰሜን ጎንደር ዳባት ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተቀሰቀሰ |ወደ መቀሌና ሽሬ የሚወስዱ መንገዶች ተዘጋግተዋል

$
0
0

Breaking News zehabesha

(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን ጎንደር ዳባት ሕዝባዊ እምቢተኝነት መቀስቀሱን ከአካባቢው የሚመጡ መረጃዎች አስታወቁ:: ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንደሚገልጹት ወደ መቀሌና ሽሬ የሚወስዱ ወይም ከዚያ ወደ ዳባት የሚያመጡ መንገዶች ተቃውሞውን ባነሳው ሕዝብ በድንጋይ እና በ እንጨት መዘጋጋቱ ተሰምቷል::

በዳባት ከተማ ሕዝቡ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ያነሳው ከወልቃይት መሬት እና ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ እንደሆነ ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች ጠቁመው ሕዝባዊ ቁጣው እስከ እኩለሊት ድረስ እንደቀጠለ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::

ይህን ጉዳይ ተከታትለን እንዘግባለን::

በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች አሁንም ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ መቀጠሉ የሚታወስ ነው::

The post በሰሜን ጎንደር ዳባት ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተቀሰቀሰ | ወደ መቀሌና ሽሬ የሚወስዱ መንገዶች ተዘጋግተዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የአድዋ ድል በዓል ልዩ ዝግጅት ከአድማስ ራድዮ ጋር |ሊያደምጡት የሚገባ ታሪካዊ ቃለምልልስ

$
0
0


የአድዋ ድል በዓል ልዩ ዝግጅት ከአድማስ ራድዮ ጋር | ሊያደምጡት የሚገባ ታሪካዊ ቃለምልልስ
ADWA4-600x310

The post የአድዋ ድል በዓል ልዩ ዝግጅት ከአድማስ ራድዮ ጋር | ሊያደምጡት የሚገባ ታሪካዊ ቃለምልልስ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ፍቅር እስከ…

$
0
0

Love and Crime in Ethiopia

መርማሪ ፖሊሱ ፊት ለፊቱ የተቀመጠውን የ24 ዓመት ወጣት አተኩሮ ያየዋል፡፡ በአንድ መስታወቱ የተሰበረ የእንጨት መስኮት ውስጥ የገባው ብርሃን ጠባቡን የምርመራ ክፍል ጨለማ በመጠኑ ገፍፎታል፡፡ አሮጌ የድሮ ጠረጴዛ ላይ ከተቆለሉት ፋይሎች ጀርባ ካኪ ሸሚዝ ለብሶ ጎመን የመሰለ ጃኬት በላዩ ላይ የደረበው ወፈር ያለ መርማሪ ፖሊስ በእጁ የሚያፍተለትለውን ስክሪፕቶ ይዞ የወጣቱን ቃል ይጠብቃል፡፡ አዳፋ ጃኬት የለበሰውና ከውስጥ የነተበ ሸሚዝ ያደረገው ወጣት ፂም የወረረውን አንገትና ጉንጩን በእጁ እያሻሸ መሬት መሬት ያያል፡፡ ያደረገው ጂንስ ሱሪ በቆሻሻ ቀለሙን ለውጧል፡፡ አሮጌ ስኒከር ጫማ አድርጓል፡፡ 

‹‹ሰውየውን የገደልከው አንተ ነህ አይደል?››

መርማሪ ፖሊሱ የሚጠብቀው መልስ አለ፡፡ ይህቺን ጥያቄ ሰንዝሮ ከወጣቱ የሚመጣውን ምላሽ ወረቀቱ ላይ ለማስፈር ተዘጋጅቷል፡፡ ወጣቱ ዝም አለ፡፡ 

‹‹ተናገር እንጂ! ዓለምሰገድን የገደልከው አንተ ነህ አይደለህም?››

ወጣቱ ቀና አለና የሚጠይቀውን ፖሊስ አየ፡፡

‹‹ምን አድርጎኝ የምገድለው ይመስልሃል?›› መለሰ፡፡ መርማሪ ፖሊሱ በዚህ ልጅ ተደጋጋሚ ቃል የተሰላቸ ይመስላል፡፡ በፍርድ ቤት የተሰጠውን የ21 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሊያጠናቅቅ የቀረው 3 ቀን ብቻ ነው፡፡ ዓለምሰገድን ይህ ወጣት ለመግደሉ የተለያዩ ማስረጃዎች ቀርበዋል፡፡ በተለይም ከወጣቱ ጋር አብሮ የታሰረው አስመላሽ በምን ሁኔታ ሟችን እንደገደሉት አብራርቶ ተናግሯል፡፡ ፖሊሱ አሁን ማጣራት የፈለገው ይህ ተከሳሽ ሟችን በጩቤ ደረቱ ላይ ወግቶታል ወይስ አልወጋውም የሚለውን ብቻ ነው፡፡ 

‹‹ተደባደብን፡፡ በያዘው ድንጋይ ደረቴን ሲመታኝ ወደቅሁ፡፡ አስመላሽ ከኋላ ሲይዘው ተነሳሁና በእርግጫ ሆዱን መታሁት፡፡ በፊቱ ወደቀ፡፡ ከዚያም በእርግጫ ወገቡ ላይ መታሁት፡፡ ሮጬ ሄድኩ፡፡ አስመላሽ ጥቂት ቆይቶ ተከተለኝ፡፡ በኋላ ከልጁ የደረት ኪስ ውስጥ ያገኘውን ቆዳ የኪስ ቦርሳ (ዋሌት) አሳየኝና በውስጡ 400 ብር እና 2 የአሜሪካ ዶላር አውጥቶ እንካፈል አለኝ፡፡ ሁለት መቶ ሁለት መቶ ብር ተከፋፈልንና የቀረችውን ሁለት ዶላርም አንድ አንድ ወስደን ቦርሳው ውስጥ ያገኘናትን 5 ብር ለአንድ ትልቅ ሽማግሌ ሰጠናቸው፡፡ በዚያ ብር ካዛንቺስ ሄደን ስንጠጠያ ቆየንና ሌሊት አራት ኪሎ ሄደን ከሴት ጋር አደርን፡፡ በማግስቱ ብራችን ያለቀው ምሳ ሰዓት ላይ ነው፡፡ ማታ በተኛንበት ቦታ ፖሊሶች መጥተው ያዙን›› አለ፡፡ መርማሪ ፖሊሱ ይህንን ቃል ደጋግሞ ስለሰማው መልሶ አልፃፈውም፡፡ እስኪጨርስ ጠበቀና በድጋሚ ጠየቀው፡፡ 

‹‹ስማ አዲስ፤ ዝም ብለህ ትለፋለህ እንጂ ሟችን የገደልከው አንተ ነህ፡፡ ሁለታችሁም በሰው መግደል ወንጀል ተከሳችሁ ለምን እሱ ሲናገር አንተ ትደብቃለህ?›› አለው፡፡ 

ይህ ቃል አሮጌ የእንጨት ወንበር ላይ በተቀመጠው ወጣት ላይ የሚያመጣው አንዳች ለውጥ እንደሚኖር መርማሪው አልተጠራጠረም፡፡ ወጣቱ ዝም ብሏል፡፡ ፖሊሱ በግራ በኩል ያለውን መሳቢያ ከፈተና አንድ እጀታው ብረት የሆነ የእህል መሰቅሰቂያ ስለት ያለው ክፍት ቧንቧ ነገር አወጣ፡፡

‹‹ይሄ መሰቅሰቂያ ያንተ አይደለም?›› አለው የአዲስን ዓይን ዓይን እያየ፡፡ 

አቀርቅሮ የነበረው ወጣት ቀና አለና በመርማሪ ፖሊሱ እጅ ላይ የተንጠለጠለውን ባለስለት ብረት አየ፡፡ ፊቱ ተለዋወጠ፡፡ ፖሊሱ እያስተዋለው ነው፡፡ 

‹‹አስመላሽ ነው የአዲስ ነው ያለህ?›› አለና ፖሊሱን ጠየቀው፡፡ ፖሊሱ መልስ መስጠት አልፈለገም፡፡ አዲስ በተራው በትዝብት የሚቃኙትን የፖሊሱን ዓይኖች በፍርሃት አያቸው፡፡

‹‹ይህን ጩቤ የሰጠኝ አስመላሽ ራሱነው›› አለ ዝምታ ሲበዛበት እንደ መደናገጥ ብሎ፡፡ ፖሊሱ አሁንም ምንም አልተናገረም፡፡ አዲስ ቀጠለ፡፡ 

‹‹አንድ ወቅት ወፍጮ ቤት ተቀጥሬ እሰራ ነበር፡፡ ሚዛን የሚሰራው ልጅ ሲያስቸግረኝ በዚህ ቂጡን ወግቼው ጠፋሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እዚያ ሰፈር ደርሼ አላውቅም ብሎ የነገረኝ ራሱ ነው፡፡ ይህንን ጩቤ ብዙ ጊዜ ራሱ ጋር አስቀምጦት ነው የኖረው፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ደግሞ አንተ ጋር ይሁንልኝ ብሎ የምተኛበት ላስቲክ ቤት ውስጥ ፍራሼ ስር አስቀምጦታል፡፡› አለና ዝም አለ፡፡ መርማሪ ፖሊሱ አሁን ቀና አለ፡፡ 

‹‹በመጨረሻ ቀን ዓለምሰገድን ልትደብድቡ ስትሄዱ እሱ ይህንን ጩቤ አልያዘውም ነበር፡፡ የነበረው አንተ ጋር ነው፡፡ ወገብህ ውስጥ ደብቀኸው ነበር፡፡ ሟች በድንጋይ ሲመታህ አውጥተህ አንተ ደግሞ በጩቤው ደረቱን ወጋኸው፡፡ ከዚያ አስመላሽ ደሙ እየፈሰሰ የወደቀውን ዓለምሰገድን ቀና አድርጎ ሲያየው ‹‹አሻራህ ዓይኑ ላይ ይቀራል ተው›› ብለኸው ከከሲ ውስጥ ዋሌቱን ሰርቃችሁ ተሰወራችሁ፡፡ ልክ ነው ልክ አይደለም?››

መርማሪው አሁን ድምፁ ጠንከር ብሏል፡፡ አዲስ ከዚህ በላይ ሰውየውን ለመግደሉ መረጃ አይፈልግም፡፡ ነገር ግን ማመን አለበት፡፡ በፖሊስ ምርመራ ወንጀል የፈፀመው ሰው ድርጊቱ በማስረጃ ከተረጋገጠበት ስለወንጀል ማመን አለማመኑ የሚያመጣው አንዳች ለውጥ የለም፡፡ ነገር ግን የምርመራውን ስራ ለማቃለልና የወንጀል ፈፃሚውን ማንነት አጠራጣሪ ላለማድረግ ሲባል የዕምነት ቃል ተጠርጣሪው ቢሰጥ ጥሩ ማጠናከሪያ ይሆናል፡፡

‹‹ይኸውልህ… አስመላሽ እኔን ገዳይ አድርጎ ራሱ ነፃ እንዲወጣ ፈልጎ ከሆነ ይገርመኛል፡፡ ወንጀሉን የፈፀምነው አብረን ነው፡፡ ዓለምሰገድን የገደልነውም አብረን ነው፡፡ ሸቤ ከገባንም አብረን እንበሰብሳታለን እንጂ እኔን አጋፍጦ መ    ሸወድ አይችልም›› አለ አዲስ፡፡ 

ፊቱ ላይ ቁጣ ይነበባል፡፡ መርማሪው የጠየቀው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም፡፡ ዋናው ወንጀል ፈፃሚው ከሁለቱ የትኛው ነው? ተባባሪውስ?

‹‹ለመሆኑ ከሟች ጋር ፀብ ያለው ማነው?›› አለ ፖሊሱ ለጊዜው የመጀመሪያ ጥያቄውን ተወት አድርጎ፡፡ 

‹‹ሁለታችንም አዲስ ነበር፡፡››

‹‹ወርቅነሽ የማን ሚስት ናት?›› መርማሪው ራሳቸው ወጣቶቹ በሚጠቀሙበት ቃል መጠቀምን መርጧል፡፡ 

‹‹የኔ ሚስት ነበረች፡፡ ዓለምሰገድ እንደኔ ጎዳና ተዳዳሪ ስላልሆነና ስራ ስላለው ቀማኝ፡፡››

‹‹እና ከአንተና ከአስመላሽ ለዓለም ሰገድ ጥላቻ የሚኖረው ማነው?››

‹‹አስመላሽ እኮ ለኔ የልብ ጓደኛዬ ነው›› 

‹‹ቢሆንም የፀባችሁ መንስኤ ልጅቱ ከሆነች ዓለምሰገድን የምትጠላው አንተ ነህ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ማንም ሰው ቢጠየቅ ለዚህ ልጅ መሞት ምክንያቱ ያንተ እሱን በጩቤ መውጋት ነው የሚሆነው አይደል?››ርማሪ ፖሊሱ የአዲስ ፊት ሲቀያየር አየው፡፡

‹ወርቅነሽን ጠርቼ አናግሬያት ነበር፡፡››

የአዲስ ፊት በጉጉትና በጥርጣሬ ተለዋወጠ፡፡ ዓይኑን ወደ መርማሪው ልኮ ቀጣዩን መጠበቅ ጀመረ፡፡ 

‹እኔ አልፈልግህም… ተወኝ… ከጎዳና ህይወት ያወጣኝን ሰው አትንካብኝ ብዬ ደጋግሜ ነግሬው ነበር፡፡ እሱ ግን ታያለሽ… እገድለዋለሁ አንቺም ውሻ ስለሆንሽ ባልሽ የቱ እንደሆነ አታውቂም፡፡ አብሬ እደፋሻለሁ ብሎኛል፡፡ ጩቤውም ሁል ጊዜ ማታ ማታ ከእጁ አይለየውም፡፡ የራሱ ነው ብላኛለች፡፡›› 

አለ መርማሪው፡፡ አዲስ በተስፋ መቁረጥ ፈገግ አለ፡፡ ከጥቂት ዝምታ በኋላ መናገር ጀመረ፡፡ 

‹‹እኔ እኮ ለሷ ብዬ ነው፡፡ እወዳት ነበር፡፡ ሁሉም ጓደኞቼ የሚያውቁት እሷ የኔ ሚስት መሆኗን ነው፡፡ የትም ብትሄድ የሚነካት የለም፡፡ የአዲስ ሚስት ነች ከተባለ ዝንቧን እሽ የሚል ሰው የለም፡፡ እኔ መዓት ሴቶች እየከበቡኝ ከርሷ በቀር ሌላ ሴት አልፈልግም ነበር፡፡ ለሷ ብዬ ባደረኩት ደግሞ እኔ ላይ መሰከረችብኝ?›› አለና እግሩን አነባብሮ ተቀመጠ፡፡ ‹‹ጩቤው በእርግጥ የኔ አይደለም የአስመላሽ ነው፡፡ የዚያን እለት ግን ጠጥቼ ስለነበር ዓለምሰገድ አንተ የጎዳና ልጅ ብሎ ሲሰድበኝ ስለተናደድኩ…››

መርማሪ ፖሊሱ ፊት ለፊቱ የተቀመጠው ወጣት የነገረውን ነገር በምርመራ መዝገቡ ላይ አሰፈረና አስፈረመው፡፡ መዝገቡን እንደዘረጋ አንዳንድ ነገሮችን ፃፈና አዲስን ይዞ ከጠቧቧ ክፍል ወጣ፡፡ ወደ እስር ቤቱ እየወሰደው ነው፡፡ ለአዲስ የጎዳና ህይወት… አስፓልት ዳር መተኛት… በብርድና በፀሐይ መንከራተት ከዚህ እስር ቤት የተሻለ ነው፡፡ እዚህ ንፁህ ክፍሎች… የመተኛ ሰሌን ወይም ምንጣፍ… የሚበላ ነገር… ንፅህና መጠበቂያ ሻወር አለ፡፡ ነፃነት ግን የለም፡፡ ገንዘብ ማግኘት ቢገኝም መጠጥ ገዝቶ መጠጣት የለም፡፡ የፈለጉበት ቦታ መሄድ አይቻልም፡፡ ሰክሮ መጮህ መበጥበጥ የውጪውን ዓለም አየር መሳብ አይሞከርም፡፡ በአንዱ በተዘጋ ግቢ ውስጥ በብረት ፍርግርግ በታጠረ የብሎኬት ቤት አስር፣ አስራ አምስት፣ ሃያ ሆኖ ተፋፍጎ መተኛት ብቻ… ነጋ ግንብና ሰማይ… መሸ… ግድግዳና ጣራ፡፡ የእስር ቤት ህይወት አሰልቺ ነው… ለአዲስ፡፡ ለመርማሪው የሰጠው ቃል ተጠናቋል፡፡ አሁን የሚጠብቀው ከጠባቡ እስር ቤት ወደ ሰፊው ማረሚያ ቤት የሚዘዋወርበትን ዕለት ብቻ ነው፡፡ እስር ቤት ውስጥ ‹‹መርማሪው የሚጠይቅህን አትመንለት… ምንም ነገር ቢሆን ካድ›› ተብሎ የተነገረውን ተግባራዊ ለማድረግ ሞከረ፡፡ በመጨረሻ ላይ ግን ከራሱ ጋር መጣላት አልቻለም፡፡ ‹‹ለዚህ ሁሉ የዳረገችኝ እሷ ናት›› ብሎ አስቧል፡፡ እሷና የርሷ ፍቅር ወርቅነሽ ለአዲስ የህይወቱ መብራት ነበረች፡፡ ወርቅነሽን ካጣ የትም ቢገባ አይደንቀውም ቢሞትም ጭምር፡፡ እሷ የሌለችበት ዓለም እንዴት ይገፋል? በፍቅር ያሳለፉትን ጊዜ መሽቶ በነጋ ቁጥር ከአዕምሮው አይፍቀውም፡፡ 

1989 

አዲስ አበባ

እኩለ ሌሊት አልፏል፡፡ አዲስና ሌሎች ሁለት ጓደኞቹ ከሚያድሩበት ለገሀር አካባቢ ያለ አንድ በረንዳ ላይ ተነስተው ቀን ‹‹ሲሸቅሉበት›› በዋሉበት ሣንቲም አረቄ ወደ ሚጠጡበት ቤት መጡ- ናዝሬት ፔንሲዮን አካባቢ የቀድሞው ወረደ 21 ቀበሌ 01 ክልል ውስጥ፡፡ 

አዲስ ወደ ጎዳና ከወጣ አራት ዓመታት አልፎታል፡፡ የ16 ዓመት ልጅ ሳለ በዘበኝነት ስድስት ልጆቻቸውን ያሳድጉ የነበሩት የቀድሞ አስር አለቃ አባቱ በህመም ሲሰቃዩ ኖረው ሞቱ፡፡ የሳቸው ሞት በቋፍ ቆሞ የነበረውን ጎጆ ናደው፡፡ እናቱ የመጨረሻ ልጃቸውን ይዘው ልመና ወጡ፡፡ ታላላቆቹ ወንድሞቹ በባቡር ተሳፍረው ወደ ድሬዳዋ ከሄዱ በኋላ ተመልሰው አልመጡም፡፡ አንድ ሰው ግን ድሬዳዋ ባቡር ጣቢያ አካባቢ ጎዳና ላይ ከሚያድሩ ልጆች ጋር ተቀላቅለው እንዳያቸው ለሰው ሲናገር ሰምቷል፡፡ አዲስ ቤት ተቀምጦ በረሃብ መቆላቱ ሲሰለቸው ወጣ ብሎ ከጎዳና ልጆች ጋር መለመን ጀመረ፡፡ ቀስ በቀስም በዚያው ማደር አመጣ፡፡ ተጠቃልሎ ወደ ጎዳና የገባው በአጭር ጊዜ ውስጥ ነበር፡፡ የነ አዲስ ቤት ከስድስት ልጆች ሶስቱ ሴቶች ብቻ ቀሩበት፡፡ ከእናታቸው ጋር፡፡ 

የአዲስ ታናሽ ሰፈራቸው ውስጥ ተከራይተው የሚኖሩ ሴተኛ አዳሪዎች ቤት በመላላክ የዕለት ጉርሷን ታገኛለች፡፡ አንድ ቀን ግን እዚያ ቤት ይመላለስ የነበረ ደላላ ለአንድ ወንድ በገንዘብ ‹‹ሸጧት›› እንደ ተደፈረችና በዚያው ሴተኛ አዳሪ ሆና እንደቀረች ሰምቷል፡፡ እናትየው አሁንም ጨርቆስ አካባቢ ይለምናሉ፡፡

የዚያን ዕለት ናዝሬት ፔንሲዮን አካባቢ ያለችው አረቄ ቤት በጎዳና ልጆችና በሌሎች የቀን ሙያተኞች ተጨናንቃለች፡፡ አዲስ ከተቀመጠበት በር ጥግ ላይ አንዲት ዓይኖቿ ትልልቅ የሆኑ፣ ወፈር ያለች ልጅ ይዟት የመጣውን ወጣት እንሂድ እያለች ትጨቀጭቀዋለች፡፡ ልጁ በጣም ሰክሯል፡፡ ሁለቱም ጎዳና ተዳዳሪዎች ናቸው፡፡ በመጨረሻ ልጅቷ ለመሄድ ተነሳች፡፡ አዲስ የት እንደምትሄድ ጠየቃት፡፡ ካዛንቺስ አካባቢ እንደምታድር ነገረችው፡፡ እኛ እንሸኝሻለን ቁጭ በይ አላት፡፡ እነርሱን አምና ተቀመጠች፡፡ ልጁ ምኗም እንዳልሆነ ነግራቸዋለች፡፡ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ሲሆን ከአረቄ ቤቱ ተያይዘው ወጡ፡፡ አዲስ… ልጅቷ ሁለት ጓደኞቹ፡፡ 

በዚህ አጋጣሚ የተጀመረ ትውውቅ ወዲያው ነበር ወደ ፍቅረኝነት የተሸጋገረው፡፡ ወርቅነሽ እናትም አባትም የላትም- ሁለቱም ሞተዋል፡፡ የ17 ዓመት ወጣት ናት፡፡ ጎዳና ላይ ከወጣች ከሰባት ዓመት በላይ ሆኗታል፡፡ ከመርካቶ እስከ ሰንጋተራ… ከፒያሳ እስከ ካዛንቺስ ኖራለች፡፡ የማታውቀው የሰፈር ስም የለም፡፡ አሁን በቅርቡ የተዋወቀቻቸውን ሁለት ጓደኞቿን ተከትላ ካሳንቺስ መጥታለች፡፡ ኦሜድላ ሆቴል አካባቢ ነው የምታድረው፡፡ ብዙ ጊዜ የምትተዳደረው ከሰከሩ ሰዎች ጋር በርካሽ ዋጋ ‹‹በመውጣት›› ነው፡፡ አልፎ አልፎ ደግሞ ፊንፊኔ ሆቴል አካባቢ እየቆመች ‹‹ቢዝነስ›› ትሰራለች፡፡ 

አዲስ ይህችን ልጅ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ መኖር ፈለገ፡፡ ህይወት ጣመችው፡፡ ከወርቅነሽ ጋር ፍቅር የያዘው በፍጥነት ነበር፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እሷን ለማግኘት ካዛንቺስ አካባቢ ያጠመደ አላጣው አለ፡፡ ከጊዜ በኋላም ከወርቅነሽ ጋር አብረው መኖር ጀመሩ፡፡ 

ከለገሀር እየተማለለሰ የሚያመሽበት ፍልውሃና አካባቢ ጎዳና ልጆች ለመዱት፡፡ ኃይለኛ፣ ደግ፣ ቆንጆና አንዳንዴም ባህሪውን ለማወቅ የሚያስቸግር ልጅ በመሆኑ ከወንዶቹ ይልቅ ሴቶቹ ይቀርቡት ነበር፡፡ አዲስ የሚታወቀው በእልኸኝነቱ ነው፡፡ የትኛውም ሰው ቢሆን አዲስን ተተናኩሎ በሰላም መኖር አይችልም፡፡ በጣም ቂመኛ ስለሆነ ተከታትሎ ያለበት ድረስ ሄዶ ካላጠቃው ልቡ አያርፍም፡፡ በዚህ ባህሪው የተነሳ ሁሉም ይፈሩታል፡፡ በተለይ ሴቶቹን የሚነካቸው ሰው ስለማይወድ ከርሱ አጠገብ የምትርቅ ሴት የለችም፡፡ አንድ ዲኤክስ መኪና የያዙ ትልቅ ሰው ፊንፊኔ ሆቴል በር ላይ አንዲት የጎዳና ተዳዳሪን ‹‹ሸርሙጣ›› ብለው በመሳደብ ምራቃቸውን ሲተፉባት በማየቱ በድንጋይ የመኪናቸውን የኋላ መስተዋት አድቅቆ በፖሊስ ተይዞ 2 ወር ሙሉ ታስሮ ያውቃል፡፡ በዚያን ጊዜ ሁሉ የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ያገኙትን እየያዙ ታስሮ የነበረበት ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ ሄደው ይጠይቁት ነበር፡፡ 

በጎዳና ህይወት ውስጥ መከባበርና መተሳሰብ አለ፡፡ የአዲስን ‹‹ሚስት›› አንድም ሰው ጫፏን ነክቷት አያውቅም፡፡ አዲስ ሲታሰር ጓደኛው አስመላሽ የዚህችን ልጅ አደራ ተረክቦ ነው የቆየው፡፡ አዲስ ከእስር ሲፈታ ከዚያ አካባቢ መቀየር ፈልጎ የነበረ ቢሆንም ወርቅነሽ ግን ‹‹መተዳደሪያዋ›› ቦታ ስለነበር ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡ 

አዲስ ወርቅነሽ በምትሰራው ነገር ደስተኛ አይደለም፡፡ ሁል ጊዜም ቢሆን ራቅ ብሎ ቆሞ መኪና ሲያልፍ እየጮኸችና እየሮጠች ስትከተል ሲያያት አይወድም፡፡ አልፎ አልፎ ወጣቶች ወይም በዕድሜ የገፉ ሰዎች በመኪና አልያም በእግር ይዘዋት ሲሄዱ ደሙ ይንተከተካል፡፡ ነገር ግን ብዙዎች ጓደኞቹ ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ ‹‹ሚስቶች›› ስሏሏቸው ላለመናገር አፉን ይይዛል፡፡ ወርቅነሽ ብዙውን ጊዜ ፍልውሃ ይዘዋት የሚገቡ ደንበኞች ስላሏት እነዚያ ክፍሎች ውስጥ የፍቃዳቸውን ፈፅማላቸው ገንዘብ ካገኘች በኋላ ተመልሳ አስፓልት ላይ አትቆምም፡፡ በተቻላት መጠን የምታገኘውን ገንዘብ ከአዲስ ጋር ታጠፋዋለች፡፡ በተለይ በክረምት ጊዜ ያገኘችውን ጥቂት ብር አልጋ እየተከራየች እንዲያድሩበት በማድረግ አስቸጋሪውን የጎዳና ልጆች ጠላት የሆነ የክረምት ወር ታወጣዋለች፡፡ ትወደዋለች፡፡ ለርሷ የሚያስብላት መሆኑን ታውቃለች፡፡ እሷም ከሱ መለየትን አትፈልግም፡፡ 

1993

ሁለቱ ጥንዶች ከተዋወቁ አራት ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ እሱ የ24 እሷ የ21 ዓመት ወጣቶች ሆነዋል፡፡ የ20 እና የ17 ዓመት ወጣቶች ሳሉ የጀመሩት ፍቅር አሁንም አብሯቸው አለ፡፡ ሠርግ ባይሰረግም… ወዳጅ ዘምድ ተሰብስቦ ሙሽርዬ ብሎ ባይዘፍንም… መዘጋጃ ሄደው ባይፈራረሙም ቅሉ እነዚህ ወጣቶች ጎዳና አስተዋውቋቸው ጎዳና ያገባቸው ናቸው፡፡ ድህነት መጠለያ አልባ አድርጎ ሲያንከራትታቸው የተገናኙ… ምድርን ወለላቸው… ሰማይን ጣራቸው አድርገው የሚኖሩ… ከፍቅራቸው በቀር የኔ የሚሉት ምንም ነገር የሌላቸው ወጣቶች ናቸው፡፡ ድህነት በተጫነው ህይወት ውስጥ ሆነው የሚተሳሰቡ የማይካካዱ… አንዳቸው ለአንዳቸው ህይወት የሚጨነቁና ለምቾቶቻቸው የሚጠነቀቁ ናቸው፡፡ የወርቅነሽ ዘወትር በሚወስዷት ሰዎች መሰቃየትና የማትፈልገውን ዓይነት ወሲብ እንድትፈፅም መገደድ አዲስን አሳስቦታል፡፡ ስራውን እንድትተወው ይፈልጋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እሷ ይህንን ሴተኛ አዳሪነት ትታው ለሷ የሚሆን ገንዘብ ከየት አግኝቶ ሊያስተዳድራት እንደሚችል ሲያስብ ይጨነቃል፡፡ እንደ ጓደኞቹ የሰራችበትን ገንዘብ እየተቀበለ ለራሱ አይወስድም… በፍፁም፡፡ ይልቅስ ለራሷ ልብስ እንድትገዛ… የሚያስደስታትን ነገር እንድታደርግ ነው የሚገፋፋት፡፡ ይህ ባህሪው ከዚህ ቀደም ከምታውቃቸው ሰዎች የተለየ መሆኑን አሳይቷታል፡፡ ወርቅነሽ ከርሱ መለየትን ፈፅም አትፈልገውም፡፡ 

አሁን ግን የአስፓልት ላይ ሕይወት መርሯታል፡፡ በዕድሜ እኩዮቿ የሆኑ ወጣት ሴቶችን ታያለች፡፡ ቆንጆ ናት፡፡ ቀይ ናት፡፡ ፀሐይና ውርጭ ስለጠበሰው ነው እንጂ ከማንም የማያንስ ውበት አላት፡፡ ፀጉሯን በስርዓቱ ከጠበቀችው ያምራል፡፡ ሰውነቷ በልኩ የተፈጠረ በመሆኑ ልብስ በተለይም ሱሪ ያምርባታል፡፡ ከድህነት በቀር በሴትነቷ የሚጎድላት ነገር የለም፡፡ ይህን ሴትነቷን ያየውና ውበቷ በልቡ የገባው አንድ ወጣት አለ ዓለምሰገድ፡፡

ዓለምሰገድ መካኒክ ነው፡፡ የሚሰራበት ጋራዥ የለውም፡፡ ነገር ግን ካዛንቺስ ቶታል አካባቢ በጎሚስታ ስራ ከሚሰሩ ሰዎች ጋር እየተቀመጠ የተበላሸ መኪና ሲመጣ ይጠግናል፡፡ ‹‹ዱርዬ መካኒክ›› ይሉታል አንዳንዶች፡፡ በስራው ጎበዝ ነው፡፡ ተያዥ የሌለው መሆኑና አልፎ አልፎም የሚያምነው ሰው ስለሚያጣ ጋራዥ ተቀጥሮ ለመስራት የሞከራቸው ሙከራዎች በሙሉ ፍሬ አልባ ሆነውበታል፡፡ ቀስ በቀስ እየገዛ ያጠራቀማቸውን የመኪና መፍቻና የመካኒክ ዕቃዎችን በሻንጣ ይዞ በየቦታው እየዞረ የተበላሹ መኪኖችን ይገጠግናል፡፡ ሰው ይወደዋል፡፡ ጉርሻ የሚሰጡት… መኪና ሲበላሽባቸው በቀላል ገንዘብ ስለሚጠግናቸው ወደ እርሱ የሚመጡት ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ቀስ በቀስ ጥሩ ገቢ የሚያገኝ ሰው ሆነ፡፡ ምሽት ላይ ግን በጊዜ ቤቱ ሄዶ በቀዝቃዛ አልጋ ላይ መጠቅለል ስለሚሰለቸው ካዛንቺስ አካባቢ ሲጠጣ ያመሻል፡፡ እስከ እኩለ ሌሊት ይቆይና ነው ወደ አሸዋ ተራ አካባቢ የተከራያት አንዲት ክፍል የጭቃ ቤት ውስጥ ሄዶ የሚያድረው፡፡ 

ዓለምሰገድ ከወርቅነሽ ጋር የተዋወቀው በአንድ ምሽት ነው፡፡ ከኦሜድላ ሆቴል ሲወጣ በር ላይ ከጓደኛዋ ጋር ቆማ አገኛት፡፡ ጠራት፡፡ መጣች ከርሱ ጋር ወደቤት መሄድ ትፈልግ እንደሆነ ጠየቃት፡፡ አላመነታችም፡፡ ዋጋ ጠየቃት ‹‹አስበህ ክፈለኝ›› አለችው፡፡ ይዟት ሄዶ አደሩ፡፡ ጠዋት ላይ ሲነሳ አያት፡፡ የጎዳና ተዳዳሪ መሆኗን አውቋል፡፡ ግን ከዚህ በፊት ከሚያውቃቸው ሴቶች የተለየ ውበትና ንፁህነት አላት፡፡ ያለምንም ሜክአፕ በተፈጥሮ ውበት ብቻ ቆንጆ መሆኗን አወቀ፡ የዚያን ዕለት 50 ብር ሰጥቶ ሸኛት፡፡ ይህ ብር ለወርቅነሽ ብዙ ነበር፡፡ በደስታ ተቀበለችው፡፡ በዚያኑ ዕለት ማታ እንገናኝ ተባብለው ተለያዩ፡፡ 

ከዚያን ቀን ጀምሮ ጓደኛሞች ሆኑ፡፡ ዘወትር ይገናኛሉ፡፡ የህይወቷን ታሪክ ነግራው አዝኖላታል፡፡ እሱም ብቸኝነቱ አንገፍግፎታል፡፡ አብራው እንድትኖር ጠየቃት፡፡ አላመነታችም፡፡ አንድ ቀን እንደሚያልፍላት ታስብ ነበርና እንደ መሰሎቿ ከጎዳና መውጣትን ትመኛለች፡፡ በተቻላት ሁሉ ቤቱን በማፅዳት፣ ልብሱን በማጠብ… ዕቃዎቹን በመሰብሰብና መልክ መልክ በማስያዝ ቤቱን ሞቅ ሞቅ አደረገችለት፡፡ አልፎ አልፎ በምትችለው ሙያ ምግብ ቤት ውስጥ መስራት ጀመረች፡፡ ቡናም ታፈላ ጀመር፡፡ የዓለምሰገድ ህይወት ተለወጠ፡፡ በጊዜ ወደ ቤቱ መግባት ገንዘብ ማጠራቀም ጀመረ፡፡ ሰው ሆነ፡፡ ወርቅነሽ የቤቱ ጌጥ ሆነችለት፡፡ ሊያገባት ቆረጠ፡፡ ነገራት፡፡ አላቅማማችም፡፡ 

አዲስ የወርቅነሽ እየሄዱ ቀልጦ መቅረት አሳስቦታል፡፡ ተከታተላት፡፡ ከብዙ ጊዜ ክትትል በኋላ በተደጋጋሚ አብራው የምትታየው ወንድ ዓለምሰገድ መሆኑን አወቀ፡፡ እንድትተወውና ወደርሱ ተመልሳ እንድትመጣ ጠየቃት፡፡ ወርቅነሽ ሁሉንም ነገር ዘርዝራ ነገረችው፡፡ ‹‹ብቻዬን ጎዳና ላይ ጥለሽኝ?›› አላት፡፡ ቀድሞም ጎዳና ላይ መተዋወቃቸውንና አሁን ግን ከርሱ ይልቅ የሷ ጎዳና ላይ መቆየት እንደሚጎዳት ነገረችው፡፡ ቂም ያዘ፡፡ ከዳችኝ ብሎ አሰበ፡፡ ‹‹ገንዘብ ስለሌለኝ ናቀችኝ›› አለና ተናደደ፡፡ በመሰረቱ የተቆጣው በዓለምሰገድ ነበር አንድ ቀን ዓለምሰገድን ስራ ቦታው ድረስ ሄዶ አናገረው፡፡ ዓለምሰገድ የልጅቷን ህይወት እንደሚያውቅና ያገባትም ወስኖ መሆኑን ነገሮት ካንተ ጋር ጉዳይ የለኝም ብሎ መለሰለት፡፡ በዚያ ቂም ሊደበድበው ዕቅድ ያዘና ቀን መጠበቅ ጀመረ፡፡ 

ታህሳስ 4 ቀን 1993 ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት

አዲስና አስመላሽ ሲዘጋጁ የቆዩበትን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ተነሱ፡፡ የዓለምሰገድን መውጫ መግቢያ ሲያጠኑ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ዕለት ዓለምሰገድ ኦሜድላ ሆቴል ገብቶ ጠጥቶ እስከሚወጣ ድረስ ጠበቁት፡፡ ከአንድ ልጅ ጋር ብቅ አለ፡፡ ተስፋ አልቆረጡም ተከታተሉት፡፡ አብሮት የነበረው ልጅ አጂፕ አካባቢ ሲደርስ ተገንጥሎ ወደ አቧሬ የሚወስደውን መንገድ ያዘ፡፡ ዓለምሰገድ ወደ አሸዋ ተራ የሚወስደውን መንገድ ተከትሎ ወደ ጨለማው ገባ፡፡ ወደ ቤቱ እየሄደ ነበር ድንገት ከኋላው የደረሰው አዲስ በያዘው ድንጋይ ጀርባውን መታው፡፡ ዓለምሰገድ በርከክ እንደማለት አለና ተነስቶ ቆመ፡፡ ፊት ለፊቱ የሚያያቸውን ሁለት ልጆች ለመጋፈጥ እጁን ሰብስቦ ድብድብ ተጀመረ፡፡ ዓለምሰገድ ከመሬት ያነሳውን ድንጋይ ፊት ለፊቱ ወደነበረው ልጅ ወረወረ፡፡ አዲስ ነበር የተመታው ወደኋላው ወደቀ፡፡ ይሄኔ አስመላሽ ዓለም ሰገድን ከኋላ ያዘው፡፡ አዲስ ከወደቀበት በንዴት ተነስቶ ከኋላው ሽጦት የነበረውን ስለት አወጣና ደረቱን ወጋው ወደኋላ ሲወድቅ ኪሱ ውስጡ ያለውን ቦርሳ ይዘው በቅፅበት ተሰወሩ፡፡ አስመላሽ ይህ ድርጊቱ አደገኛ እንደነበር ደጋግሞ ቢነግረውም አዲስ ግን ‹‹ማንም ሰው ደፍሮኝ አያውቅም በሚስቴ እኮ ነው የመጣው ወርቅነሽን አስመልሳለሁ›› አለው፡፡ 

በማግስቱ ፖሊስ በጀመረው ክትትል ኦሜድላ ሆቴል አካባቢ ምሽቱን ሁሉ የታዩት ሁለት የጎዳና ልጆች እንዲሁም አንደኛው ከሟች ጋር ያለውን ፀብ የሚያውቁ ሰዎች የሰጡት መረጃ እነ አዲስን ተፈላጊ ቀለበት ውስጥ ከተታቸው፡፡ እነሱን ለማግኘት ብዙ መልፋት አላስፈለጋቸውም፡፡ ሲመሽ ያሉበት ቦታ ድረስ ሄደው በተኙበት በቁጥጥር ስር አዋሏቸው፡፡ በተለይ ዕለቱንና ምሽቱን ብዙ ገንዘብ ይዘው መታየታቸውና የዓለምሰገድ ቦርሳ መጥፋቱ ለፖሊሶች ጥርጣሬ ትክክለኛነት ማረጋገጫ ነበር፡፡

የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ዓለምሰገድና አስመላሽ በዋነኛነት ተባባሪ የሰው መግደል ወንጀል ተዋናይነት ሁለቱንም ከስሶ ተዘጋ፡፡ ሰፊው ወህኒ ቤት ውስጥ ገብተው ከመሰሎቻቸው ጋር ተቀላቀሉ ሁለቱም፡፡ ወርቅነሽስ የት ሄዳ ይሆን?

The post ፍቅር እስከ… appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በአዲስ አበባ የታክሲዎችን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ የትራንስፖርት ችግር ተከሰቷል

≫ Next: Hiber Radio: ኦነግ ወያኔ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ዘር ማጥፋት ለመቃወም የሰራዊቱ አባላትና ሰራተኛውን ጨምሮ ልዩ ልዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተቃውሞውን እንዲቀላቀሉ አዲስ ጥሪ አስተላለፈ፣የኤርትራ መንግስት በኦሮሚያ ተቃውሞ እጄ የለበትም የወያኔ ውሸት የተለመደ ነው ሲል መግለጫ አወጣ ፣ የእስራኤል መንግስት ከኢትዮጵያ ሊወስዳቸው የነበሩ ቤተ እስራላዊያን ጉዞን አቋጠ፣ የአድዋ ድል በማርች ወር እንዲታወስ የሜሪላንድ ሞንቲጎመሪ ካውንቲ በአዋጅ ወሰነ፣በኦሮሚያ ክልል በተነሳው ተቃውሞ የኤርትራ እጅ አለበት ማለት ሕዝቡን እንደመሳደብ ይቆጠራል ሲሉ ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ገለጹ፣በሱዳን አማላጅነት ወደ ኤርትራ ታፍነው ከተወሰዱት 32ቱ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተገለጸ፣ፕ/ር መረራ ጉዲና በኦሮሞ ሕዝባዊ እንቀሰቃሴ ጋር የኤርትራ እጅ አለበት በሚለው የአገዛዙ ውንጀላ ዙሪያ ምላሽ ሰጡ፣ የአውሮፓ ህብረት ለሰላም አሰከባሪው ጦር የሚላከው የገንዘብ ደጎማን በ20 በመቶ እንደሚቀነስ አስታወቀ
$
0
0

በአዲስ አበባ የሚገኙ የታክሲ ሹፌሮች የወያኔ አገዛዝ ያወጣውን የትራንስፖርት እና መንጃ ፍቃድ ሕግ በመቃወም የጠሩት የስራ ማቆም አድማ በዛሬው እለት የአዲስ አበባን መንገዶች ከትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ውጪ በማድረጋቸው ተገልጋዩ በትራትስፖርት ችግር ሲገጥመው ተስተውሏል::

የአዲስ አበባን የታክሲ ሹፌሮች ከስራ ውጪ ለማድረግ እና ስራ ፈት ዜጎችን ለመፍጠር ታስቦ በወያኔ የወጣው አዲስ ሕግ ማንኛውም ሹፌር 21 ጊዜ ጥፋት ካለበት መንጃ ፈቃዱ ተነጥቆ ከሹፌርነት ለመጨረሻ ጊዜ የሚያግድ ሲሆን የታክሲ ሹፌሮችን ሆን ብሎ በማጥቃት ከስራ ውጪ በማድረግ የደህንነት አካላት የሆኑ አዳዲስ እየሰለጠኑ የሚገኙ የሕወሓት አባላትን የታክሲ ባለቤቶች ላይ ጫና በመፍጠር በሹፌርነት ለማሰማራት የታቀደ እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ::

የወያኔው አገዛዝ በተለያዩ በዝባዥ እና ሕዝብን በሚበድሉ ሕጎች ኢትዮጵያውያንን እያሰቃየ ሲሆን ይህም ከፍተኛ የሆነ ብሶት አደባባይ ላይ መሰማቱ ሲቀጥል የስራ ማቆም አድማውም የዚሁ ብሶት አካል መሆኑ ታውቋል::በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ተገልጋዮች በተለያዩ መንገዶች ትራንስፖርት ለማግኘት ቢሞክሩም እንዳልቻሉ ታይተዋል::የወያኔ አገዛዝ ለሶስት ወር አራዘምኩት ይሕጉን ተግባራዊነት የሚል መግለጫ ቢሰጥም ተቀባይነት አጥቶ የስራ ማቆም አድማው ተደርጓል::ሕዝቡ ብሶቱን በተለያየ መንገድ በመግለጽ ስርኣቱ እንዲወገድ ትግሉን ቀጥሏል::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.

 

 

 

The post በአዲስ አበባ የታክሲዎችን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ የትራንስፖርት ችግር ተከሰቷል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Hiber Radio: ኦነግ ወያኔ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ዘር ማጥፋት ለመቃወም የሰራዊቱ አባላትና ሰራተኛውን ጨምሮ ልዩ ልዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተቃውሞውን እንዲቀላቀሉ አዲስ ጥሪ አስተላለፈ፣የኤርትራ መንግስት በኦሮሚያ ተቃውሞ እጄ የለበትም የወያኔ ውሸት የተለመደ ነው ሲል መግለጫ አወጣ ፣ የእስራኤል መንግስት ከኢትዮጵያ ሊወስዳቸው የነበሩ ቤተ እስራላዊያን ጉዞን አቋጠ፣ የአድዋ ድል በማርች ወር እንዲታወስ የሜሪላንድ ሞንቲጎመሪ ካውንቲ በአዋጅ ወሰነ፣በኦሮሚያ ክልል በተነሳው ተቃውሞ የኤርትራ እጅ አለበት ማለት ሕዝቡን እንደመሳደብ ይቆጠራል ሲሉ ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ገለጹ፣በሱዳን አማላጅነት ወደ ኤርትራ ታፍነው ከተወሰዱት 32ቱ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተገለጸ፣ፕ/ር መረራ ጉዲና በኦሮሞ ሕዝባዊ እንቀሰቃሴ ጋር የኤርትራ እጅ አለበት በሚለው የአገዛዙ ውንጀላ ዙሪያ ምላሽ ሰጡ፣ የአውሮፓ ህብረት ለሰላም አሰከባሪው ጦር የሚላከው የገንዘብ ደጎማን በ20 በመቶ እንደሚቀነስ አስታወቀ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የካቲት 20 ቀን 2008 ፕሮግራም
እንኳን ለአድዋ ድል 120ኛ ዓመት በዓል አደረሳችሁ!

<... ...> አባ ጫላ ለታ የኦነግ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ስለ አዲሱ የኦነግ ጥሪና የኦሮሚያ ክልል በወታደራዊ ዕዝ ስር ስለመውደቁ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

አጠር ያለ ቃለ መጠይቅ ከጋዜጠኛ ርዮት ኣለሙ ጋር በወቅቱ የኦሮሞ ሕዝብ የተቃውሞ እንቅስቃሴ፣በእስር ላይ ስለሚገኙት ሌሎች የህሊና እስረኞችና ተያያዥ ጉዳዮች(ሙሉውን ያዳምጡት)

ታሪክ ተራኪው ኤድዋርዶ ባይኖሮ የአድዋን ድል 120ኛ ኣመት አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

በቬጋስ ለጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ የተካሄደው የአክብሮት ምሽትን በተመለከተ ( አጭር ቆይታ ከበኣሉ አዘጋጅ ኮሚቴ አንዱ ጋር )

የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ቅሌት ላይ የሚደረግ የሕዝብ አስተያየት ማሰባሰብና የታክሲ አሽከርካሪዎች ቅሬታ (ቃለ መጠይቅ ከተሳታፊዎች አንዱ ጋር)

በግዙፉ የቴክኖሎጂ ድርጅት አፕል እና በአሜሪካው የፌዴራል ምርመራ ተቋም ( FBI) መካከል ሰሞኑን የተከሰተው የመረጃ ብርበራ ጥያቄ እና ውጤቱ ሲዳሰስ

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ኦነግ ወያኔ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ዘር ማጥፋት ለመቃወም የሰራዊቱ አባላትና ሰራተኛውን ጨምሮ ልዩ ልዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተቃውሞውን እንዲቀላቀሉ አዲስ ጥሪ አስተላለፈ

የኤርትራ መንግስት በኦሮሚያ ተቃውሞ እጄ የለበትም የወያኔ ውሸት የተለመደ ነው ሲል መግለጫ አወጣ

በኦሮሚያ ክልል በተነሳው ተቃውሞ የኤርትራ እጅ አለበት ማለት ሕዝቡን እንደመሳደብ ይቆጠራል ሲሊ ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ገለጹ

በአዲስ አበባ የተጠራውን የታክሲዎች አድማ የአገዛዙን ማስፈራሪያ አልፎ ውጤታማ ከሆነ ለውጡን ያፋጥናል ተብሏል

የአድዋ ድል በማርች ወር እንዲታወስ የሜሪላንድ ሞንቲጎመሪ ካውንቲ በአዋጅ ወሰነ

የእስራኤል መንግስት ከኢትዮጵያ ሊወስዳቸው የነበሩ ቤተ እስራላዊያን ጉዞን አቋጠ

በሱዳን አማላጅነት ወደ ኤርትራ ታፍነው ከተወሰዱት 32ቱ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተገለጸ

የአገዛዙ ራዲዮ ሙሉ ለሙሉ ተመለሱ ሲል መዋሰቱ ተገለጸ

ፕ/ር መረራ ጉዲና በኦሮሞ ሕዝባዊ እንቀሰቃሴ ጋር የኤርትራ እጅ አለበት በሚለው የአገዛዙ ውንጀላ ዙሪያ ምላሽ ሰጡ

አንድ ግብጻዊ ቱጃር እና የ ሕዘብ እንደራሴ በሕዳሴው ግድብ ውዝግብ ዙሪያ የ እስራኤልን ጣልቃ ገብነትን መሻታቸውን አስታወቁ

የሰብኣዊና የሴቶች መብት ተሟጋቿ ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው አረፉ

በኤርትራ ጉዳይ አንድ አፍቃሪ የሕወሓት ድህ ረገጽ ሐይለማሪያም ደሳልኝን ክፉኛ አብጠለጠላቸው

በሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በአገሪቱ ህዝብ ዘንድ የተጠላ መሆኑን ምሁራኖች ገለጹ

የአውሮፓ ህብረት ለሰላም አሰከባሪው ጦር የሚላከው የገንዘብ ደጎማን በ20% እንደሚቀነስ አስታወቀ

የዙምባቤው ፕ/ት ሮበርት ሙጋቤ ለአፍሪካ ሕብረት መርጃ ሲሉ በርካት የቀንድ ከብቶችን ለገሱ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: ኦነግ ወያኔ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ዘር ማጥፋት ለመቃወም የሰራዊቱ አባላትና ሰራተኛውን ጨምሮ ልዩ ልዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተቃውሞውን እንዲቀላቀሉ አዲስ ጥሪ አስተላለፈ፣የኤርትራ መንግስት በኦሮሚያ ተቃውሞ እጄ የለበትም የወያኔ ውሸት የተለመደ ነው ሲል መግለጫ አወጣ ፣ የእስራኤል መንግስት ከኢትዮጵያ ሊወስዳቸው የነበሩ ቤተ እስራላዊያን ጉዞን አቋጠ፣ የአድዋ ድል በማርች ወር እንዲታወስ የሜሪላንድ ሞንቲጎመሪ ካውንቲ በአዋጅ ወሰነ፣በኦሮሚያ ክልል በተነሳው ተቃውሞ የኤርትራ እጅ አለበት ማለት ሕዝቡን እንደመሳደብ ይቆጠራል ሲሉ ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ገለጹ፣በሱዳን አማላጅነት ወደ ኤርትራ ታፍነው ከተወሰዱት 32ቱ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተገለጸ፣ፕ/ር መረራ ጉዲና በኦሮሞ ሕዝባዊ እንቀሰቃሴ ጋር የኤርትራ እጅ አለበት በሚለው የአገዛዙ ውንጀላ ዙሪያ ምላሽ ሰጡ፣ የአውሮፓ ህብረት ለሰላም አሰከባሪው ጦር የሚላከው የገንዘብ ደጎማን በ20 በመቶ እንደሚቀነስ አስታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ማኅበረ ቅዱሳን ለፓትርያርኩ መምሪያ ምላሽ ሰጠ፤ የስምዐ ጽድቅ ጽሑፍ የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ የማሳወቅ ግዴታችን አካል ነው፤ ደብዳቤውም መድረክ ስለተነፈገንና ፍትሕ ስለተጓደለብን ነው

≪ Previous: Hiber Radio: ኦነግ ወያኔ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ዘር ማጥፋት ለመቃወም የሰራዊቱ አባላትና ሰራተኛውን ጨምሮ ልዩ ልዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተቃውሞውን እንዲቀላቀሉ አዲስ ጥሪ አስተላለፈ፣የኤርትራ መንግስት በኦሮሚያ ተቃውሞ እጄ የለበትም የወያኔ ውሸት የተለመደ ነው ሲል መግለጫ አወጣ ፣ የእስራኤል መንግስት ከኢትዮጵያ ሊወስዳቸው የነበሩ ቤተ እስራላዊያን ጉዞን አቋጠ፣ የአድዋ ድል በማርች ወር እንዲታወስ የሜሪላንድ ሞንቲጎመሪ ካውንቲ በአዋጅ ወሰነ፣በኦሮሚያ ክልል በተነሳው ተቃውሞ የኤርትራ እጅ አለበት ማለት ሕዝቡን እንደመሳደብ ይቆጠራል ሲሉ ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ገለጹ፣በሱዳን አማላጅነት ወደ ኤርትራ ታፍነው ከተወሰዱት 32ቱ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተገለጸ፣ፕ/ር መረራ ጉዲና በኦሮሞ ሕዝባዊ እንቀሰቃሴ ጋር የኤርትራ እጅ አለበት በሚለው የአገዛዙ ውንጀላ ዙሪያ ምላሽ ሰጡ፣ የአውሮፓ ህብረት ለሰላም አሰከባሪው ጦር የሚላከው የገንዘብ ደጎማን በ20 በመቶ እንደሚቀነስ አስታወቀ
$
0
0
  • የጋዜጣው ጽሑፎች፣ “መንፈሳዊ ኮሌጆቹ በአጠቃላይ የመናፍቃን መፈልፈያ ናቸው» አይሉም
  • በጋዜጣው አጻጻፍ አንዳንድ የቃላት አጠቃቀሞች ላይ ቅሬታ ካለ ለመወያየት ዝግጁዎች ነን
  • ጉዳዮቹን እንድናስረዳና የተፈጠረውንም ችግር ለመረዳት የውይይት መድረክ ይዘጋጅልን
  • በተለያየ መንገድ እንደጠየቅነው፣ በአካል የመወያያ ዕድል ማጣታችን በእጅጉ ያሳዝነናል
  • ለሚታረም ነገር እርምት መውሰድና ስናጠፋም ይቅርታ መጠየቅ የአገልግሎታችን መርሕ ነው

* * *

  • ሰዎች እንደመኾናችንና ልንሳሳት ስለምንችል፣ በማንኛውም ደረጃ ተወያይተን የሚታረም ነገር ካለ አስፈላጊውን እርምት መውሰድ እና በትክክል ጥፋት እንዳጠፋንም ስንረዳ ይቅርታ መጠየቅ አንዱና ዋነኛው የአገልግሎታችን መርሕ ነው፡፡
  • በሀገራችን የተከሠቱትን ማኅበራዊ ችግሮች ለመፍታት ኹሉም አካል በየዘርፉ በሚረባረብበት በዚኽ ወቅት፣ ትልቅሓላፊነት ያለባት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አባትና ልጆች እንዲህ ዓይነት ደብዳቤዎችን በመጻጻፍ መጠመዳችን እጅግያሳዘነን መኾኑን ሳንገልጸው አናልፍም፡፡
  • ሕግ አውጥቶ፣ ሥርዓት ሠርቶ የሰጠን የቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ፣በማኅበሩ አገልግሎቶች ላይ አኹንም እየተፈጠሩ ያሉት ዕንቅፋቶች እንዲታዩልንና አስፈላጊው እርምት እንዲደረግልንበታላቅ ትሕትናና አክብሮት እንጠይቃለን፡፡ (የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ከዚኽ በታች ይመልከቱ)

008009

Source:: haratewahido

The post ማኅበረ ቅዱሳን ለፓትርያርኩ መምሪያ ምላሽ ሰጠ፤ የስምዐ ጽድቅ ጽሑፍ የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ የማሳወቅ ግዴታችን አካል ነው፤ ደብዳቤውም መድረክ ስለተነፈገንና ፍትሕ ስለተጓደለብን ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ የክተት ዘመቻ

$
0
0

ነፃነት ዘለቀ

በሁሉም የሀገራችን ግዛቶች ውስጥ በወያኔ ቅልብ ጦር የጭካኔ እርምጃ ሕይወታቸውን ያጡና አሁንም ድረስ እያጡ ያሉ ወገኖቻችን ነፍሳቸውን ፈጣሪ ተቀብሎ ከፃድቃን አጠገብ እንዲያስቀምጥልን መልካም ፈቃዱ ይሁንልን፤ በየማጎሪያ ቤቶች የሚገኙ ወገኖቻችንንም ጽናቱን ይስጥልን፡፡ የመከራችንን ደብዳቤም እንዲቀድልን ሁላችን ተግተን እንጸልይ፡፡ በዘር፣ በጎሣና በሃይማኖት  ሳንከፋፈል በአንድ ላይ ጸንተን ከቆምን የወያኔ ዕድሜ ከአንድ ደቂቃም ያጠረ ነው፡፡ ነገር ግን አንድ እንዳንሆን ወያኔ የሚጥልብን ደንቃራ ቀስፎ ስለያዘን ይህን ሁኔታ በእስካሁኑ አካሄድ መቀየር አልቻልንም፡፡ ስለዚህ በመከባበር መደማመጥ እንደሚኖርብን እንረዳ፡፡ መጪው ጊዜ ብዙ ደም የማይፈስበትና በተቻለ መጠን በትንሽ መስዋዕትነት ታላቅ ሀገራዊ የነፃነት ድል የምንቀዳጅበት የትግል ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡  

ethiopian flag

በቅድሚያ እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ እኔ መሰንበት ከተባለ ደህና ሰንብቻለሁ፡፡ የሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ እየተንተከተከ ያለ ይመስላል፡፡ እነወያኔዎችም ሰይጣን ይሁን እግዚአብሔር የፈቀደላቸውን ሀገርንና ሕዝብን እንደእባብ የመቀጥቀጥ ሥራ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ በአዲስ አበባ ታክሲዎች ሥራ አቁመው ሠራተኛውና ጥቃቅኑ ነጋዴ ከማለዳው ጀምሮ እየተቸገረ ነው፤ በእግሩም እየኳተነ ይታያል፡፡ የደኅንነትና የትግሬዎች ታክሲዎች ግን እየሠሩ እንደሆነ በግልጽ ይታያል፡፡ ከሕንጻውና ከንግዱ በተጓዳኝ አብዛኛው የትራንስፖርት መስክ በትግሬዎች በመያዙ ይህ ዐድማ ብዙም ፋይዳ ያለው አይመስልም፡፡ እነሱ ያልያዙትና ያልተቆጣጠሩት ነገር የለም – ዕድሩም፣ ዕቁቡም፣ ሰንበቴውም፣ መረዳጃ ማኅበሩም፣ ምኑም ምናምኑም በነሱው ቁጥጥር ሥር ነው – የጽዳትና ጥበቃ ኃላፊውንና የቆሻሻ ገንዳ ጠባቂውን ሣይቀር ብትመለከት ከአሥር ዘጠኙ ትግሬ ነው፡፡ አሥርን ካነሳሁ አይቀር ከአሥር ሕንፃ ዘጠኙ፣ ከአሥር ሠርግ ዘጠኙ፣ ከአሥር አውቶሞቢሎች ዘጠኙ፣ ከአሥር ሱቆች ዘጠኙ፣ ከአሥር ሱፐርማርኬቶች ዘጠኙ፣ ከአሥር ኢንቬስተሮች ዘጠኙ፣ ከአሥር ኮንዶሚኒዮሞች ዘጠኙ፣ ከአሥር የመንግሥትና የመያድ ባለሥልጣናት ዘጠኙ፣ ከአሥር … ዘጠኙ ሀብት ንብረቱ የወያኔ ትግሬዎች ሀብትና ንብረት ነው – ሰዎቹም እነሱው ናቸው፡፡ በመያድ ለመቀጠር ትግሬ መሆን አለብህ፤ በመንግሥት ለመቀጠር ትግሬ መሆን አለብህ፡፡ በደርግ ዘመን “ምርጥ ምርጡ ለሕጻናት” የሚል (የውሸት) መፈክር በየግድግዳው ይጻፍ እንደነበር አስታውሳለሁ፤ ዛሬ ደግሞ “ምርጥ ምርጡ ለትግሬ ወያኔ “ የሚል በህቡዕ የሚሠራጭ (የእውነት) መፈክር ሀገር ምድሩን ሞልቶት አለ – ዘይገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈሌ ማለት አሁን ነበር፡፡ ፡ ኢትዮጵያ ከአሥሩ ዘጠኟ — አይ … ዘጠኝ ብቻ? … ከአሥሩ ዘጠኝ ነጥብ ዘጠኟ የወያny ጥገት ላም ናት፡፡ ሌላው በድርቅ እያለቀ ነው፡፡ ወያኔ እየተንደላቀቀና እየተምነሸነሸ ሌloch በጠኔ እየተንጠራወዙ ናቸው – ዕድል ቀንቷቸው ከተገደሉት ውጪ ማለተይ ነው፡፡ ቧይ! ፈጁን እኮ!

በአዲስ አበባ በረንዳ አዳሪውና እሥር ቤቱን የሞላው ማን ነው? ዐማራውና ሌላው ነው፡፡ … በየዝጉብኝ ዊስኪና ቮድካ ሲጨልጥ፣ ጮማ ሲቆርጥ የሚያመሽና የሚያረው ማን ነው? በየጥሩ ት/ቤቶች የሚማሩ ልጆች የነማን ናቸው? በጫት ገረባ ሰክረው በየበረንዳው እጅብ ብለው የሚውሉና የሚያድሩተ ልጆችስ የነማን ናቸው? አሁን ማን ነው እየኖረ ያለው? ማንስ ነው እያጣጣረ ሞትን በመናፈቅ ላይ የሚገኘው? የሀገሪቱን ሀብትና ንብረት በግል ተቆጣጥረው እየተዘማነኑባት ያሉት ወያኔዎች ብቻ ናቸው፡፡ አዲስ አበባንና ዐይ ዐይን ቦታዎቿን ካለ ገልማጭና ቆንጣጭ የተቆጣጠሩት ትግሬዎች ናቸው – ብልጣብልጥ ወያኔ ትግሬዎች፡፡ ጉራጌ ከማርካቶ ተፈናቅላ ትግሬ ተቆጣጥሮታል፡፡ ሌሎችነን በግብርና በኪራይ ፈነቃቅለው ለስደትና ለራስን ማጥፋት ክፍት የሥራ ቦታ አጋልጠው እነሱ የሁሉም አዛዥ ናዛዥ ሆነዋል – ይህን የሰው ልጅ ቅለት እያየሁ ከምኖር በበኩሌና ማን ከለከለህ እንዳትሉኝ እንጂ ሞቴን ብመርጥ ይሻለኛል፡፡ በወያኔ ትግሬዎች ምክንያት የሰው ልጅ ኅሊናዊና ሰብዓዊ ዕድገት እንዳለ ጥያቄ ውስጥ እንደገባ ይሰማኛል፡፡ “እነዚህ ‹ሰዎች› በርግጥም ሰዎች ይሆኑ እንዴ?” እያልኩ ብዙ ጊዜ እጨነቃለሁ፡፡ በአጥንትና ደም አነፍናፊነታቸው ከእንስሳትም በታች ይወርዳሉ፡፡

እኔም ዛሬ ታክሲ አጥቼ በመኪና ነው ወደመሥሪያ ቤቴ የሄድኩት – ማለቴ በልመና መኪና፡፡

ሲያልቅ አያምር ይባላል፡፡ የኛ ይሁን የነሱ ማለቂያ የደረሰ ይመስላል፡፡ በዚህ መልክ የምንጓዝበት ዘመን ማክተሚያው የተቃረበ ለመሆኑ ብዙ ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡ አንድ ቄስና አንድ ሼህ ያንጀት ጓደኛሞች ነበሩ አሉ፡፡ ሼሁ “መምሩዋ ለመሆኑ እስቲ በነቢ ይሁንብዎና ሃቂቃውን ይንገሩኝ – ከእስላምና ከዐማራ(ከክርስቲያን ማለታቸው ነው) ማንኛቸው ይጠድቃሉ?” ብለው ቄሱን ይጠይቃሉ አሉ ዱሮ በደጉ ዘመን፡፡ መምሩም መለሱና “ኧረ በእግዝትነይቱ እንዴት ያለ ጥያቄ ጠየቁኝ ሸኽዬ – መቼስ ከሁለት አንድኛቸው እንታናቸውን ሳይበሉ አይቀሩም!” ብለው መለሱ አሉ፡፡  የዚህን ወግ ጭብጣዊ መልእክት  ወደወያኔ አምጡልኝ፡፡ እንጂ ከጽድቅና ኩነኔ አኳያ ብንነጋገር እኔ በበኩሌ ተቋማዊ መዳን እንደሌለ ወይም ቢያንስ ሊኖር እንደማይገባ ማመን ከጀመርኩ ቆይቻለሁ፡፡ የመዳን መንገድ አንዲት ብቻ ስለመሆንዋ ደግሞ ብዙም አላውቅም፡፡ መዳኛውን አንድዬ ብቻ ያውቃል – “ሁሉም የየራሱን ሲያደንቅ እሰማለሁ፣ የኔም ለኔ ዕንቁ ናት እኮራባታለሁ.…” የምትል የቆየች የንዋይ ደበበ ዘፈን አሁን በጆሮየ ውልብ አለችብኝ – በዚህ አጋጣሚ ነፍስ ይማር ንዋይ ደበበና ኃይሌ ገ/ሥላሤና ሠራዊት ፍቅሬና መስፍን በዙና ሙሉጌታ አሥራተ ካሣና ገነት ዘውዴና … ኦ! የክፉ ቀን ምርጥ ምርጥ ዜጎቻችንን ዘርዝሬ አልጨርሳቸውም – አንድዬ ግን የሚሣነው ነገር የለምና እርሱ ይጨርስልኝ፡፡ ወደገደለው ልሂድ እባካችሁ፡፡ ቀልድና መጠጥ ቤት ያጠፋል፡፡

ሰሞኑን ወደ ትግራይ ሄጄ ነበር – ከምር፡፡ ትግራይ ውስጥ ወንድ ልጀ ያለ አይመስልም፡፡ ሁሉም ተነቅሎ ለማያዳግም አጠቃላይ ክተታዊ የወረራ ዘመቻ ወደተቀረችዋ ኢትዮጵያ የተበገሰ ይመስላል፡፡ በተለይ በገጠር ቤቶች – ብዙዎቹ የድንጋይ ቤቶች – ተንሻፈው ተንጋደውና ፈርሰው ካለሰው ብቻቸውን ይታያሉ፡፡ አንዳንዶች ተዘግተዋል፤ አንዳንዶች ክፉኛ ፈራርሰዋል፡፡ ብዙዎቹ የገጠር ከተሞች የተወረሩ ይመስላሉ፤ የሚገርመው ግን ያን ሁሉ በረሃና የድንጋይ ጫካ እያቆራረጠ በየርሻውና በየፈፋው ብቅ እያለ የሚታይ ንጹሕ የመጠጥ ውኃ ቧምቧ አለ፤ ኦ! ትግራይ ታስቀናለች፤ ልጆቿ ክሰዋታል፡፡ ሥልኩ፣ ውኃው፣ መንገዱ፣ ት/ቤቱ፣… ሁሉም ከሞላ ጎደል ተሟልቶ ይታያል – እንደሚባለው አይደለም፤ በተንጣለለው ገደላማ ኹዳድ እንደዘንዶ ተጋድሞ የሚታየውን ወፍራም የውኃ ቧምቧ ስታዩ “ምነው ይህን መሰል ነገር በጎጃምና በጎንደር ገጠሮች ማየት በቻልኩ?” ሳትሉ አትቀሩም እንደኔ በ“ዐማራነት ልክፍት ከተነደፋችሁ”፤ ወይ ወያኔ ለካንስ ይህን ያህል ቀንድ ማነው ዐይን አውጣዎች ኖረዋል? ችግሩ ግን እነዚያ የገጠር ሥፍራዎች ሰው አይኖርባቸውም – ትግሬ ያለውስ አዲስ አበባ ላይ ነው ወንድሞቼ፡፡ ቅናት አይደለም – ከሆነም በመንፈስ ቀናሁ ልበላችሁ፡፡ እንዲህ የሚያኮራ ውድብ ቢኖረኝ ብዬ ከመዓንጣየ – ካንጀተቴ – ቀናሁ፡፡ በፈርሳሙ ብአዴንም ኮራሁ፤ ኧረ በዐማራው በረከት ስምዖንም አምርሬ ቀናሁ! በስድብ ባቦነነኝ በአረምነው መኮንንም ቀናሁ፡፡  በዐማራው አካባቢም ስላለፍኩ ብአዴን ስላልሠራቸው የልማት ንድፎች ክፉኛ ኮራሁ፡፡ ቀንደኛው ድርጅታችን ባልሠራልን ነገር ካልኮራን በምን እንኩራ? ብቻ በየገጠሩ ያሉ ብዙ ትግሬዎች  ተለቃቅመው “ሪፓብሊኳ”ን በመተው ወደምድረ ገነት ወደ “ኢትዮጵያ” ሄደዋል፡፡ ከሞላ ጎደል ሕይወት ያላት የምትመስለው መቀሌ ማለትም መቐለ እንጂ ሌሎቹ ኦና ናቸው፡፡ ምሥጢሩ ታዲያ ወዲህ ነው፡፡…

ዛሬ ለዚህች ማስታወሻ መጻፍ ምክንያት የሆነኝ ነገር አለ፡፡ በመጣሁበት መኪና ውስጥ ሰዎች ሲያወሩ የሰማሁት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ሕወሓት ያመጣባትን ዳፋ ትግራይ ከፍላ ለመጨረሽ በሺዎች የሚቆጠሩ ዓመታትም አይበቋትም፡፡ ወያኔ ትግራይን በሰው ደም፣ በሰው አጥንት፣ በሰው ላብና ወዝ፣ በሰው ሀብት፣ በሀገር ንብረትና ወደር በሌለው ግፍ አጨቅይቷት  -እንደ እግዚአብሐየር ፈቃድ – ኢንሻአላህ – በጣም በቅርቡ መሰናበቱ ስለማይቀር ወዮ ለትግራይና ሕዝቧ!!! ለማንም ፈርቼ በማላውቀው ሁኔታ ፈራሁላት፡፡ ትዕቢትና ዕብሪት ጥፋትንና ውርደትን ቀድማ ትመጣለችና እነኚህ የዲያብሎስ ሽንቶች ሒሣባቸውን የሚያወራርዱበት ዘመን በፍጥነት ሲመጣ ይታየኛል፡፡ የኛ መጥፎ ሥራ እነሱን እንዳመጣብን ሁሉ የነሱ ግፍና በደል ደግሞ እነሱ ቀርተው ትግራይ ልትሸከመው የማትችለውን የመከራ ዶፍ እንደሚያመጣ የእግዜሩን ትተን ታሪክን ብቻ በማጣቀስ መረዳት ይቻላል፡፡ መተት ይረክሳል፤ ደንቃራ ይከሽፋል፡፡ የላላ ይጠብቃል፤ የጠበቀ ይላላል፡፡ የተራቡ አልቅቶችና መዥገሮች ወፍረውና አብጠው ይፈነዳሉ፡፡ ከብቶችም ያኔ ነፃ ይወጣሉ፡፡ የመዥገሮችና የአልቅቶች ዘመን ሲገባደድ የከብቶችና የደገኛ እንስሳት ዘመን ይብታል፡፡ ያኔን ለማየት ዕድሜና ጤና ብቻ ይስጠን፡፡

ታዲያ ሰው የሚያስፈልገን አሁን ነው፤ ትልቅ ሽማግሌ ትግሬ፣ ትልቅ ሽማግሌ ዐማራ፣ ትልቅ ሽማግሌ ኦሮሞ የሚያስፈልገን አሁንና አሁን ብቻ ነው፡፡ ከደፈረሰ በኋላ ማቄን ጨርቄን ቢሉ ዋጋ ዘይብሉ ከምዝብሃል ኢዩ ሀወይ፡፡ ሦርያንና “ታላቋን” ሶማሊያ ያዬ በእሳት አይጫወትም፡፡ እርግጥ ነው ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ እንዲባል የነዚህ መሬት የጠበበቻቸው ዐይነ ሥውራን ትግሬ ገዢዎቻችን አይተውት ቀርቶ አስበውት የማያውቁት እርዚቅ ውስጥ በታሪካዊ ጠላቶቻችን ሁልአቀፍ ዕርዳታ ታግዘው ሲነከሩበት ጊዜ ቀን የማይገለበጥ መስሏቸው ከሰማይ በታች የማይሠሩት የበደል ዓይነት ጠፋ – በአንድ በኩል እነሱም ያሳዝኑኛል ታዲያ፡፡ ሰው በእርኩስ መንፈስ ካልተሞላ በስተቀር መቼም እነሱ የሚሠሩትን ዘግናኝ ነገር በሰውኛ ተፈጥሮ መሥራት የሚሞከር አይመስለኝም፡፡ ለይቶላቸው ዐበዱ እኮ! ምድራዊ ንዋይና ሥልጣን እስከዚህ ያሳብዳል? እንዴ፣ እንደዚያ እንደፈረንሣዩ አንድ ንጉሥ ‘after me the deluge’ (እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል …) እንዳለው ይሉኝታና ሀፍረት በጭራሽ አጥተው የለየላቸው ጅቦችና ዓሣሞች ሆኑ እኮ፡፡ እኔ እምለው ከዚህኛው ወገን ባይገኝ ወይም ለመስማት ፈቃደኛ ባይኑ ከነሱ በኩል “ኧረ ይ ነገር አያዛልቅም!” ብሎ የሚመክራቸው ሃይ ባይ ምራቅ የዋጠ ሰው እንዴት ይጥፋ? ለነገሩ በምን ጆሮ ይሰማሉና! ጆሯቸው በበቀልና በጥላቻ እንዲሁም በሀብት አራራ ያበደ ፍላታቸውን እንጂ ሌላ ነገር መች ያዳምጥና? …

እንዲህ ሲሉ ሰማሁ አብሬያቸው የመጣሁት ሰዎች፡፡ በ2004 ዓ.ም አካባቢ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ አካባቢ ጥቂት ሰዎች የጨረቃ ቤት ይሠራሉ፡፡ ጥቂት ጊዜ ቆይቶ ግን ቀበሌና ክፍለ ከተማው መጥተው ያፈርሱባቸዋል፡፡ ከነዚያ ከፈረሰባቸው ሰዎች ውስጥ ብዙዎቹ ትግሬዎች ነበሩ፡፡ እነዚያ ትግሬዎች ወደ ክፍለ ከተማ ይሄዱና አብዚሎ ቅብዚሎ ይላሉ፡፡ የቀሪዎቹ (ባጋጣሚ ሆኖ ዐማሮች ናቸው) ጩኸት የቁራ ጩኸት ሆኖ ሲቀር እነዚያኞቹ – የመጀመሪያ ደረጃ ዜጎቹ “አይዟችሁ፡፡ …” የለም ይህን ነገር በትግርኛ ልበለው – “አጆሃትኩም አህዋትና! ወዲተጋሩ ኮይንኹምስ ዝትንክፈኩም የለን፡፡ ውፅዔት ቃልሲኩም ስለዝሆነ ንኣሃትኩም ዝከውን ነገር በቅልጡፍ ተመኻኺርና ገለ ነገር ክንግብረልኩምኢና ቃል ንኣቱ… ብትዕግስቲ ክትፀብዩና ይግብኣኩም ድማ … ንኣሃትኩም ዘይኮነ ነገር …” አሉና እነዚያን ዐማሮች አመናጭቀው ካባረሩ በኋላ – እንዲህ ጭምልቅል ያለ ነገር ስናገርና ስጽፍ ተገድጄ የወረድኩት መውረድ እእየታየኝ ራሴን በራሴ እንዴት እንደምጸየፈው አትጠይቁኝ – ለትግሬዎቹ ሌላ መንገድ ፈለጉና አሁን እነዚያ ትግሬዎች ቢጠሯቸው የደነቆሩ ሚሊዮነሮች ሆነዋል – “ሀ” ራስህን አድን ለጫማው በኋላ ይታሰብበታል እንደተባለው ማስታወቂያ ነው ነገሩ፡፡ ከጨረቃ ቤት ባዶ ሕይወት ወደሚሊዮነርነት፡፡ እንደትግሬ ወያኔ ያለ ደደብና ደንቆሮ ቀትረ ቀላል ቡድን በዓለም ታይቶም ሆነ ተሰምቶ አያውቅም፡፡ በነገራችን ላይ እነዚያ ዐማሮችም ከተፈረደባቸው የዘር ማጽዳትና ጭፍጨፋ ማምለጣቸውና ጨረቃ ቤት በማጣት ብቻ መታለፋቸው ትልቅ ነገር ነው፡፡ ዓለመኛ ዳቦ ቅቤ ቀቡኝ ይላል እንዲሉ ሆኖ እነዚያ ምስኪኖች አዲስ አበባ ላይ በመገኘታቸው እንጂ ሌላ ቦታ ቢሆን ጠገባችሁ ተብለው ይረሸኑ ነበር፡፡ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ እኮ እኮ ደም አፍልቶና አንተክትኮ ወደ ጋዝነት የሚለውጥ ነው፡፡

እነፕሮፌሰር መስፍን ግን እንዳይቆጡኝ እፈራለሁ፡፡ እርሳቸው አንዲት አፓርትማ ውስጥ ተወሽቀው የኛን የተራ ዜጎችን እንግልትና የትግሬዎችን የዱባ ጥጋብ ማየት ስላልቻሉ በፍርደ ገምድል ብይናቸው እነሱም እንደኛው አልተጠቀሙም ይላሉ፡፡ ማለቴ እኛ በትግሬ አገዛዝ እንዳልተጠቀምን ሁሉ እነሱም አልተጠቀሙም ባይ ናቸው፡፡ ሰው መቼም መስማትና ማየት የሚፈልገውን ብቻ እሰማለሁና አያለሁ ብሎ ከቆረጠ  ከዚህ ዓይነቱ ሞገደኛና ሸውራራ አመለካከቱ ፈጣሪ ነፃ እንዲያወጣውና እውነቱን እንዲያመላክተው ከመጸለይ በስተቀር ምን ማድግ ይቻላል? ሆ! ትግሬ አልተጠቀመም? ድራማዊ አስቂኝ ዐረፍተ ነገር፡፡

የባዳ ልጆች ጉድ ሠርተውናል፡፡ የተሰባበርነው ሁሉ እንዴትና መቼሰ እንደሚጠገን ሳስበው ይጨንቀኛል፡፡ ኢትዮጵያ የሌሎቹም ያልሆነች ያህል ሌሎች እንዲህ ባይተዋር ሆነው ስታዩ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንደጪስ በንና ጠፋች ወይ ትላላችሁ፡፡ በርግጥም ኢትዮጵያ አሁን የለችም፡፡ ሌላው ሁሉ የትግሬ አሽከርና ገረድ ሆኖ ትግሬዎች የጠገቡ ጌቶች ሆነዋል፡፡ ጥጋብን የማያውቅ ሰው ደግሞ አይግጠምህ፡፡ የተሸናፊ አሸናፊ አይግጠምህ፡፡ ከአፍ እስካፍንጫው ማሰብ የማይችል “አሸናፊ ጀግና” አይግጠምህ፡፡ ብሃጺሩ ቀን አይጉደልብህ፡፡ ምን ዓይነት ጉዶች ናቸው በል? መጥኔ ለጤናማ ትግሬዎች! ሀፍረቱን እንዴት ይችሉት ይሆን? የ16 ዓመት ታዳጊ ከትግራይ ገጠር አዲስ አበባ መጥቶ በሣምንት ውስጥ ሚሊዮነር ሲሆን የሚታዘብ ጤናማ ትግሬ በሀፍረት እንደሚሸማቀቅ መቼም ግልጽ ነው፡፡ አይ… እኔ እንኳንስ በግማሽ ብቻ ትግሬ ሆንኩ! ሙሉ በሙሉ ብሆን ኖሮ ነገን በማሰብ ከአሁኑ ነበር አንገቴን ደፍቼ በሰቀቀን የምሞተው፡፡ ውይ ወያኔዎች ሲያሳፍሩ! ሱቅ እንደገባ ሕጻን ዓይነት ሁሉንም ለራሳቸው አፍሰው ሌላውን ባዶ ሲያስቀሩ ስታዩ እነዚህ ሰዎች ምን እንደነካቸው በማሰብ ታዝኑላቸዋላችሁ፡፡ ደግሞም እምብርት የሚባል ነገር አልፈጠረባቸውም፡፡ እንዴ – አንድ ሰው እኮ በልቶ ይጠግባል፤ ጠጥቶ ይረካል፡፡ ሲያመነዥኩና ሲጋቱ መዋል የጤንነት ምልክት አይደለም፡፡ ለከት የሚባል ነገር አለ፡፡ የሁሉም ነገር ዳር ድንበር አለው፡፡ ለፍቅርም ለጥላቻም ወሰን አለው፡፡

መጨረሻቸው ሦስት ክንድ ለሆነው ቦታ እነሱ 50 እና 60 ቦታ ይዘው አይረኩም፡፡ ከአንድ እንጀራ የማያልፍ ሆድ ይዘው በሚሊዮኖችና በቢሊዮን የሚገመት ገንዘብ በደቂቃዎች ውስጥ ሲያገለባብጡ በዚህም አይረኩም፡፡ ከምን ተፈጠሩ? ገድለው የማይረኩ፣ በልተውና ጠጥተው የማይረኩ፣ አሥረውና ደብድበው የማይረኩ፣ በሕይወት ያለን ገድለውም ስለማይረኩ ዐፅምን ሣይቀር ከመቃብር አውጥተው የሚቀጠቅጡና በዚያም ዕርካታን የማያገኙ፣ ህግን መሬት ላይ ጥለው በመደፍጠጥ መጫወቻ እስሚያደርጓት ድረስ ቢዘልቁም በዚያም የማይረኩ፣ ዐማራን ጨፍጭፈው የማይረኩ፣ ቂምን ከ40 ዓመታት በላይ በልባቸው ቋጥረው በመያዝ እየታደሰ በሚሄድ በቀልና ጥላቻ ሀገርንና ሕዝብን በታትነው የማይረኩ፣ድንበርንና መሬትን ለባዕዳን ሸጠው በሚያገኙት ሥፍር ቁጥር የሌለው ገንዘብ የማይጠግቡ፣ ዓለምን በማታለል ወደር ያልተገኘላቸው እነዚህን የሲዖል ትሎች ፈጣሪ ከየት ላከብን? ለመሆኑ እነዚህን መሰል የእሳት ጅራፎች በሺህ ወይ በሁለት ሺህ ዓመታት ስንቴ ይሆን ወደ አንድ ሕዝብ ለቅጣት የሚላኩት? ይህ ዓይነቱስ ቅጣት አመክሮ የለውምን?

እነፕሮፍ አንዴ ስሙኝማ – ለታሪክ ምሥክርነት ትሆኑ ዘንድ መከላከያን፣ ደኅንነትን፣ ውጭ ጉዳይን፣ ፖሊስን፣ ጉምሩክን፣አየር መንገድን፣ አየር ኃይልን፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤችን፣ ንግድ ቤቶችን፣የከተማ ቦታዎችን፣ ሕንፃዎችን፣ የትምህርት ተቋማትን፣የንግድ ማዕከላትን፣ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን፣…. ለጥቂት ጊዜ ጎብኙ፡፡ ከዚያ እውነትም ለአካለ ዘረፋ የደረሰ ወጣት ወያኔ ትግራይ ውስጥ እንደሌለ ያኔ ትረዳላችሁ፡፡ መጥኔ ለወደፊቷ ትግራይ! ኹልና ጥዑይ ውልቀሰባት ተጋሩ ህጅ እዩ ብዙህ ማሰብ ዜድልየና፡፡ እዚዮም አሻታት ንኣዲና ከምዘሃሰቡ መሲሎምሲ ከመይ ገይሮም ከምዝቀተልዋ ህጅ እዩ ምህሳብን ምጭናቅን፡፡ ጊዜ ካለፈ በኋላ የፈሰሰ አይታፈስምና በነዚህ ወራዳ የባንዳ ልጆች ምክንያት ትግራይ መከራና ስቃይ ስትዝቅ ይታየኛል – አሁን ትግራይ ያለች የመሰለችው በባንዳዎቹ ልች ጥንካሬ ሣይን በፈጣ ቸርነት ብቻ ነው – ነገር ግን ይህ ትዕይንት እንዳለ እስከመጨረሻው አይቀጥልም – ሁልጊዜ ፋሲካ ደግሞ ኖሮ አያውቅም፡፡ ፈጣሪ ክፉዎቹም ደጋጎቹም ሁሉም ልጆቹ ስለሆኑ ለክፉዎቹም ለደጋጎቹም እኩል ዕድልን እንደሚሰጥ መረዳት ይገባል፡፡

እኔ ግን በኅሊና ሠሌዳየ አሁን የሚታየኝ ክፉ ነገር ሲፈጸም ከማየቴ በፊት አሁኑኑ ብሞት ሞትኩ አልልም – በርግጥም ዐረፍኩ እንጂ፡፡ ሰው ሰውነቱን ለምን ይነጠቃል? ሰው በመግደልና በማሰር፣ በመዋሸትና በመቅጠፍ፣ በመዝረፍና ሁከትን በመፍጠር እንዴት ይደሰታል? አንድ ጭቅላ ሕጻን ዐማራ የሚል ወያኔያዊ ታርጋ ስለለጠፉበት ብቻ ካለምርጫው በተወለደበት ዘውግ ምክንያት ከነሕይወቱ በበደኖ ገደል የሚለቀቀው ገዳዩና አስገዳዩ ስንት ሺህ ዓመት ሊኖሩ ነው? ወደኅሊናችን እንመለስና ራሳችንን እንመርምር – አሁኑኑ!!

በሌላ አቅጣጫ ጅሎችና ነሁላሎች ኢትዮጵያውያን በሌለች ሀገር ሲጨቃጩ መስማት የሚገርም ነው፡፡ ጠላት ባቆመላቸው የጡት ቁራጭ ሀውልት፣ በፈጠራ ተደርሶ ዘወትር በሚነበነብ ስብከት ፣ በጠላት ሠርጎ ገቦች መሠሪ ውትወታ፣ በሆድ አዳሪዎች የኅሊናቢሶች ሸርና ተንኮል… የጋራ ትግሎች እየመከኑ የተናጠል ትግሎችም እየተውተበተቡ እህት ነፃነት ከአድማስ ባሻገር ቆማ በምናብ ስትታይ መታዘብ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠርን እስከወዲያኛው ያስረግማል፡፡ ሥልጣን በሬኮማንዴ ውጪ ሀገር ይሄድ ይመስል መቶና ሁለት መቶ ድርጅት በውጪ ሀገራት መመሥረቱ ደግሞ ጥቅም እንደሌለው ከታወቀ ቆይቷል፡፡ በዚህ የተበላ ዕቁብ የሚጃጃሉ ወገኖች ቁጥርም ቀላል አይደለም፡ አየ ኢትዮጵያ! የዕንቆቅልሽ ሀገር፡፡

The post በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ የክተት ዘመቻ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በዳባት የሕዝብ ቁጣ አይሏል –የወያኔ ሥርዓት በቃን፤ ወልቃይት ወደ ቀድሞ ማንነቱ ይመለስ እያሉ ነው

$
0
0

Breaking News zehabesha

(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ዳባት የተነሳው ሕዝባዊ ቁጣ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉ ተሰማ:: ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት መንገድ የዘጋጉት የአካባቢው ነዋሪዎች ጥያቄያቸው የወያኔ መንግስት በቃን ወደሚል ተሸጋግሯል::

ከወልቃይትና መልካም አስተዳደር ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተነሳው በዚህ ሕዝባዊ ተቃውሞ ሕዝቡ ያሳየው እምቢተኝነት ተጠናክሮ አሁን ጥያቄው ስር ዓቱ ይውረድ; የወልቃይት ጠገዴ ሕዝቦች ወደ ቀድሞው ማንነታቸው ይመለሱ የሚል ሆኗል:: በተለይ ሕዝቡ እያሰማ በሚገኘው ተቃውሞ አካባቢውን የሚመሩት ባለስልጣናት መሃይሞችና ያልተማሩ በመሆኑ በነዚህ ሰዎች መመራቱ አንገሽግሾናል እያለ ነው::

በዳባት ትናንት ማምሻውን ከትግራይ ጋር የሚያገናኙ መንገዶች በሕዝባዊ እምቢተኝነቱ በተሳተፉ ሰልፈኞች መዘጋጋቱን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

The post በዳባት የሕዝብ ቁጣ አይሏል – የወያኔ ሥርዓት በቃን፤ ወልቃይት ወደ ቀድሞ ማንነቱ ይመለስ እያሉ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Breaking: በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ ዙሪያውን በእሳት እየነደደ ነው

$
0
0

weliso campus

(ዘ-ሐበሻ) በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካሞፓስ ዛሬ ማምሻውን የ እሳት ቃጠሎ ተነስቶ በወሊሶ ካምፓስ በ እሳት እየነደደ መሆኑ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አስታወቀ::

እንደመረጃው ከሆነ በወሊሶ ካምፓስ የተነሳው የ እሳት ቃጠሎን ማን እንዳስነሳውና እንዴት እንደተነሳ ለጊዜው ባይታወቅም እስካሁን የተማሪዎች መኝታ ቤት እና አስተዳደር ጽህፈት ቤት እንዳልደረሰ የአይን እማኞች ገልጸዋል::

የአካባቢው ነዋሪዎች እሳቱን ለማጥፋት እየተረባረቡ ይገኛሉ::

ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሷት ይዛ ትመለሳለች::

The post Breaking: በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ ዙሪያውን በእሳት እየነደደ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

“ኦሮሞ እየሞተ ያሸንፋል፤ ወያኔ እየገደለ ይሞታል”|የድምጽ ትንታኔ

↧
↧

‘ፎር ጉድ’ብሎ ወደ ሃገር ቤት የገባ ዲያስፖራ ወይ ጉድ እያለ ወደመጣበት እየተመለሰ ነው

$
0
0

addis ababa
(ዘ-ሐበሻ) በውጭ ሃገር 2 ሥራ ጭምር እየሰራ ያጠራቀመውን ጥሪት አሟጦ በሃገሬ ላይ ሰርቼ እለወጣለው በሚል ሕልም ወደኢትዮጵያ ጠቅልለው የገቡ ዲያስፖራዎች በምሬት ወደመጡበት ሃገር እየተመለሱ መሆኑ ተሰማ::

ዘ-ሐበሻ ያነጋገረቻቸውና ወደኢትዮጵያ ጠቅልለው ገብተው የነበሩ ዲያስፖራዎች በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ሰርቶ መለወጥ የማይታሰብ ነገር ነው ይላሉ::

አቶ በሪሁን ገብሬ የተሰኙና በሰሜን አሜሪካ ለ24 ዓመታት ኖረው በኋላም በሃገሪቱ ውስጥ እድገት አለ የሚለውን ወሬ ሰምተው ወደ ኢትዮጵያ ቤተሰባቸውን ይዘው የገቡት ባለሃብት ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ተመልሰው ከመጡ በኋላ ለዘ-ሐበሻ በሰጡት አስተያየት “የውጭ ንግድ ላይ ለመሰማራት ሞክሬ ነበር:: ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት አይቻለልም:: ሌተር ኦፍ ክሬዲት (ኤልሲ) ለማግኘት ከ24 ወራት በላይ ለመጠበቅ ከመቸገሬም በላይ የሚያሰራ ሁኔታ በሃገሪቱ ውስጥ የለም” ብለዋል::

በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጠረው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሌተር ኦፍ ክሬዲት (ኤል ሲ) ማግኘት ከተቸገሩ ዲያስፖራዎች መካከል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉና በአሁኑ ወቅት በጅቡቲ ወደብ ያስመጧቸው የኮንስትራክሽን እቃዎች ተይዞባቸው የሚገኙት አንድ ነጋዴ ለዘ-ሐበሻ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በሰጡት አስተያየት “አሁን ወደ አሜሪካ የመጣሁት ቤተሰቦቼን ለማድረስ ነው:: ኢትዮጵያ ተመልሼ ሄጄ የኮንስራክሽን እቃዎቹን ከሸጥኩ በኋላ እኔም ኑሮዬን እዚሁ አሜሪካ ለማድረግ ወስኛለሁ” ብለውናል:: እንደ እኚሁ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ነጋዴ ገለጻ “በሃገሪቱ ውስጥ በተንሰራፋው የአንድ ቡድን የበላይነት የውጭ ምንዛሬውን እንኳን ለማግኘት የዛ ቡድን አባል መሆን ያስፈልጋል:: እነዚህ የኮንስትራክሽን እቃዎቼ ጅቡቲ ወደብ ከመቀመጣቸውም በላይ እየበሰበሱ ሲሆን በክራይ እና በአንዳንድ ሰበባሰበብ የሚወጣው ገንዘብ የግል ንብረቴን እያራቆተው ይገኛል:: እንደውም ካሁን በኋላ እነዚህን የኮንስትራክሽ እቃዎች ምንዛሬው ተገኝቶ አውጥቼ ብሸጣቸው እንኳ ዋናዬን የማገኝ አመስለኝም” ሲሉ አምርረዋል::

በኢትዮጵያ ውስጥ የውጭ ምንዛሬው እጥረት በውጭ ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎችን እጅጉን እያከሰራቸው እንደሚገኙ የሚገልጹት ሌላዋ ዲያስፖራ ወይዘሮ እሌኒ ማንያህልሃል “ከ4 ዓመት በፊት ነበር ኢትዮጵያ ጠቅልዬ የገባሁት:: በኪሳራ ምንክያት ወደመጣሁበት አሜሪካ ለመመለስ ተገድጃለሁ” ብለውናል::

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የዲያስፖራ ነጋዴዎች ስም የወጣላቸው ሲሆን “ፎር ጉድ” ብለው ወደ ሃገር ቤት የገቡ ወገኖች “ወይጉድ” እያሉ እየተመለሱ ነው እየተባለም ይቀለድባቸዋል::

The post ‘ፎር ጉድ’ ብሎ ወደ ሃገር ቤት የገባ ዲያስፖራ ወይ ጉድ እያለ ወደመጣበት እየተመለሰ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በኦህዴድ ውስጥ ፕወዛው ተጀመረ |በከር ሻሌ (ኦቦ ገብረመድህን) የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ ተሾመ |ዳባ ደበሌ ትልቁን ስልጣን አጡ

$
0
0
በከር ሻሌ (ኦቦ ገብረመድህን)

በከር ሻሌ (ኦቦ ገብረመድህን)

(ዘ-ሐበሻ) ለሕወሃት አስተዳደር ራስ ምታት የሆነበትን የኦህዴድ አመራሮችን የመበወዙ ሥራ በይፋ ተጀመረ:: ከሳምንታት በፊት በዘ-ሐበሻ ድረገጽ የኦሮሞ ህዝብ በተለያዩ ከተሞች ያነሳውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ የኦህዴድ አመራሮች ጥርስ እንደተነከሰባቸውና በ ህወሓቶች እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ምንጮቿን ጠቅሳ መዘገቧ ይታወሳል::

የኦሮሞ ሕዝብ ያነሳውን ጥያቄ ተከትሎ በሕወሓት መንግስት የኦሮሞን ህዝብ እንዲያረጋጉ ተልከው በየሚዲያው እየወጡ ሲያስተባብሉ የከረሙት የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኦቦ ዳባ ደበሌ ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ኦሮሚያ የትምህርት ቢሮ ተዘዋውረዋል:: በርሳቸው ቦታ ላይም በሕወሓት መንግስት ተላላኪነታቸው “ኦቦ ገብረመድህን” የሚል ስም የተሰጠው አቶ በከር ሻሌ ይህን ቁልፍ ስልጣን መረከቡን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

አቶ በከር ሻሌ ከዚህ ቀደም የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ከመሆኑ በፊት በሚኒስትር ዴኤታነት የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆኖ ለወራት የሰራ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ተነስቶ ወደ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ተዛውሮ እንዲሰራ ተደርጎ የነበረው አቶ በከር፣ በጽሕፈት ቤቱ ለተወሰኑ ወራት በሚኒስትር ዴኤታነት ካገለገለ በኋላ የአዳማ ከተማ ከንቲባ ሆኖ መሾሙ ይታወሳል::

ዳባ ደበሌ

ዳባ ደበሌ

ከግንቦት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ በሙስና ወንጀል በሕወሐት ተከሰው የታሰሩትን አቶ መላኩ ፈንታን ተክቶ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዳይሬክተር የተደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በተመሣሣይ ሁኔታ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ባላወቀበት ሁኔታ የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆኖ በቀጭን ደብዳቤ ተሹሟል::

በቀጣይም ልክ እንደ ዳባ ደበሌ ሁሉ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ከየስልጣናቸው እየተነሱ ወደ ሌላ ቦታ እንደሚዘዋወሩ ምንጮቻችን ገልጸው ተረኞች ተራቸውን እየጠበቁ ሕወሓት ማድባቱን ተያይዞታል ብለውናል::

The post በኦህዴድ ውስጥ ፕወዛው ተጀመረ | በከር ሻሌ (ኦቦ ገብረመድህን) የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ ተሾመ | ዳባ ደበሌ ትልቁን ስልጣን አጡ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Breaking: ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐረፉ

$
0
0

abune natnaiel

(ዘ-ሐበሻ) አቡነ ጳውሎስ በአረፉ ጊዜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አቃቤ መንበር ፓትርያርክ ሆነው ተሹመው የነበሩት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ::

የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የኾኑት የቀድሞው ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል አቡነ ጳውሎስ ካረፉ በኋላ የዋናው ፓትርያርክ ምርጫ እስከሚከናወን ድረስ ከቋሚ ሲኖዶስ ጋራ እየመከሩ በአቃቤ ፓትሪያርክነት በማገልገል አዲስ የተሾሙት አቡነ ማቲያስ ቦታቸውን እስኪይዙ ድረስ ቤተክርቲያኒቱን በአቃቤ ፓትሪያርክነት መርተዋል::

ለዘ-ሐበሻ እንደደረሰው መረጃ ከሆነ ብፁዕነታቸው በ1971 ዓ.ም በሦስተኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ ከተሾሙትና ዛሬ ሕይወታቸው እስካለፈነት ጊዜ ድረስ በአገልግሎት ላይ ከሚገኙት 16 አንጋፋ ብፁዓን አባቶች መካከል አንዱ ነበሩ::

አቡነ ናትናኤል በአባይ ጸሐዬ የመሰማትን እድል አያግኙ እንጂ የሃገር ቤቱን እና የውጩን ሲኖዶስ ለማስታረቅ በጣም ሲጥሩ ከነበሩ አባቶች መካከል አንዱ እንደነበሩና በተለይም አቡነ ጳውሎስ ካረፉ በኋላ ከሕጋዊው ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆርዮስ ጋር በስልክ ጭምር በማውራት ለማስማማት ቢጥሩም በአባይ ጸሐዬ አማካኝነት ይህ ህልማቸው ሳይሳካ መቅረቱ በታሪክ ይጠቀስላቸዋል::

The post Breaking: ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐረፉ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ኢትዮጵያ፤ ሙስናና በእምቢተኝነት ቅሬታ የሚያሰሙት ንብረት ማቃጠላቸው። ድርጊቱን እናውግዝ ወይስን ይበል እንበል? ተጠያቂው ማነው?

$
0
0

በፕሮፌሰር ሰዒድ ሃሰን፣ መሪ ስቴት ዪኒቨርሲቲ፤

( ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ አንዱዓለም ተፈራ እንደተረጎመው )

ቅዳሜ፣ የካቲት ፭ ቀን፣ ፳ ፻ ፰ ዓመተ ምህረት

መግቢያ

Seid Hassen - 346

ፕሮፌሰር ሰዒድ ሃሰን፣ መሪ ስቴት ዪኒቨርሲቲ

ትርጉም ከማይሠጠው በእምቢተኝነት ቅሬታቸውን ለማሰማት በተነሳሱት ላይ የገዥው ፓርቲ ከፈጸማቸው ግድያዎች በተጨማሪ፤ አሁን በቅርብ የወጡት ቁንፅል የቪዲዮ ቅንብሮችና የዜና ዘገባዎች፤ እኒሁ በኦሮሚያ አካባቢ በእምቢታ ቅሬታቸውን ለማሰማት የተነሱት፤ ንብረትና ተቋሞችን ወደ ማጥፋት/ማቃጠል እንዳመሩ ያመለክታል። በዚህ ቀውስ ዙሪያ፤ በውጪ ሀገራትና በሀገር ውስጥ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መካከል፤ የጎደራ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው። በውጪ ሀገር በሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን መካከል የሚገኙ ጥቂቶቹ፤ የማቃጠሉን/ማውደሙን ተግባር፤ በገዥው ፓርቲ ከሚፈጸሙት ጽንፍ የለሽ አረመኔያዊ ምግባርና ሥር ከሰደደው ሙስናቸው ጋር (በዚህ ረገድ በትክክል) ያዛምዱታል። ለኒህ በውጪ ላሉት ኢትዮጵያዊያን፤ ተግባሩን ይበል ለማለታቸው መሠረት የሚመስለው፤ አያሌዎቹ የወደሙት ንብረቶች፤ ባለቤቶቻቸው በሥልጣናቸው የባለጉ ልሂቆችና የውጪ ሀገር ኩባንያዎች መሆናቸው ነው። የኒህ ንብረቶችና ሕንፃዎች ባለቤቶች፤ የዘሩትን ነው እያጨዱ ያሉ በማለት አቋማቸውን ያቀርባሉ። ይሄን ግንዛቤ የሚያስተጋቡ ወገኖች፤ በእምቢተኝነት ቅሬታን ለማሰማት መነሳሳት፤ ለለከት የለሽ ምዝበራና ግድ ብሎ የመጣ አደገኛ ክፋት፤ ማሻሪያ ነው ብለው ይወስዱታል። ሌሎች፤ በተለይም ራሳቸውን የሰላማዊ ትግሉ ዘበኛ ብለው የሚቆጥሩ፤ በእምቢተኝነት ቅሬታቸውን በማሰማት የተሳተፉትንና ዝግጅቱን ያቀናበሩትን የሚያካትት ክፍል፤ የንብረት ማቃጠሉንና ማውደሙን በመቃወም ይከራከራሉ። የታየው ውድመትና ቃጠሎ፤ የሰላማዊ ትግሉና በሰላማዊ ታጋዮች ላይ የገዥው ፓርቲ እያደረሰ ላለው አጥር ዘለል አረመኔያዊ ተግባር የተከተለውን አጸፋ በማይወዱ ተንኮለኛ ጠምጣሚዎች፤ የተከናወነ ነው ይላሉ። ውድመቱና ቃጠሎው ቁጥራቸው በዛ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን፤ አወዛጋቢና የከረረ አጣብቂኝ ውስጥ የከተታቸው ይመስላል። ምርጫ የለሽ አረንቋ ውስጥ የገቡ በሚመስል ሁኔታ ተጠምደዋል – (ማለትም ጥፋቱን ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም በማይችሉበት ወጥመድ ውስጥ መገኘታቸው)።

እንደ የሰላማዊ እምቢተኝነት ዘበኝነቴ አግባብ ደግሞ፤ የተስተዋለውን ቃጠሎና ውድመት ይበል አልልም። ከምኞታችን በተጻራሪ ግን፤ በጣም የከፋ ቃጠሎና ውድመት ተግባራዊ የመሆን ችሎታ አይቀሬ ሀቁን፤ አውቃለሁ፤ አሳስቦኛልም። እንደ እውነቱ ከሆነ፤ ይህ ቀውስ እንደሚከተል ቀደም አድርጌ፤ ተገንዝቤ ነበር። እናም፤ ከጓደኞቼ ከነፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ፣ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደና ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግሥቱ ጋር በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ሙስና ከንካኝ ባህሪ ባነሳንባቸው ወቅቶች ሁሉ፤ የዚህ መከሰት ችሎታ እንዳለ ጠቁሜያለሁ። በኢትዮጵያ ያለውን የሙስና ክፋትና ክብደት ስንወያይ፤ ሚዛኑ ይኼ ነው በማይባል ደረጃ ሊከተል የሚችለውን ጥልቀቱ የማይደረስበት ጥፋት በማሰብ፤ ልክ ጭንቅላቶቻችን የተውገረገሩ፣ ድምፆቻችን የተሽመደመዱ መሰሉ። ለምንድን ነው ኢትዮጵያዊያን በመንግሥት የተደገፉ መዋዕለ ተቋማትና ንብረቶች፤ የነሱ ያልሆኑና በተቃራኒው “የውጭ” ዕሴቶችና አልፎ ተርፎም የመበዝበዣና የመጨቆኛ መሳሪያዎች አድርገው የሚወስዷቸው?

እንግዲህ፤ ለምን የውጭ ቀጥተኛ መዋዕለ ንዋይ (ውቀመን) ብልጽግናን እንደሚያስከትል በእምቢተኝነት ቅሬታቸውን ለማሰማት የተነሳሱት ሊረዱት እንዳልቻሉ፣ ነገር ግን በግልባጩ እነሱ ከዚያ አልፎ “የሀገር በቀል” (ማለትም በፖለቲካ ፓርቲና በልሂቃን ባለቤትነት የተያዙት) “መዋዕለ ንዋይ” እንኳ የማይጨበጥ/የውጭ ባለቤትነት ያለው ንብረት ብለው መወሰዳቸው፣ ለምን የውጭ ቀጥተኛ መዋዕለ ንዋይ (ውቀመን) “የስርቆት ማንቆለጳጰሻ ቃል” እና የከፋ በዝባዥና ለመጥፎ ምግባር አባሪ በር ከፋች ተደርጎ እንደተወሰደ . . . ወዘተ. እናም እነሱ እኒህን ሁሉ ለማውደም ለምን እንዳቀኑ መረዳት ከፈለጉ፣ ንባብዎን እንዲቀጥሉ አበረታታዎታለሁ። በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ሙስና ሁለተናዊ ባህሪ፣ የሚያስከትለውን ጉዳት፣ እንዴት የሀገሪቱን ተቋማዊ መስተሳሰሮች ተመልሶ በማይጠገን ሁኔታ እየጎዳ እንደነበርና አሁንም እንደቀጠለ መረዳት  የሚፈልጉ ከሆነ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ፤ ይህን ተግባር ለመዋጋት ዕቅድ ለማውጣት ማሰብ በዕውነት የምትፈልጉ ከሆነና ልክ የለሽ የማጥፋት አደጋውን ለማዘግየት በዕውነት የምትሹ ከሆነ፤ እባክዎን ለማብራራት ይፍቀዱልኝ።

ይህ ሐተታ የተሰናዳው፤ እርስዎ (አንባቢው) በኢትዮጵያ የነገሰውን ሙስና አልገታ ባይ ባህሪይ ተረድተው፤ ከዚያ በኋላ ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉ “መፍትሔዎችን” እንዲያስቡባቸው ለመማጸን ነው። ይህ እንዲሆን የተደረገበት ምክንያት፤ ዕቅዶችን መቀየስና “መፍትሔዎችን” መሻት፤ በታሰበበት ሀገር፤ እዚህ ላይ ኢትዮጵያ፤ የሚገኘውን ሙስና ዓይነትና ምንነት በደንብ አድርጎ መረዳት ስለሚጠይቅ ነው።

የገዥዎች ንጥቂያ፤ የታላቅ ሙስና ቅርጽ የያዘው የችግሩ መሠረታዊ መንስዔነቱ

ከዚህ በፊት በተለያዩ ወቅቶች እንዳሳየሁት፤ በኢትዮጵያ ነግሦ እየተገነዘብን ያለነው፤ የገዥዎች ንጥቂያ ተብሎ የሚታወቅ፤ ከሙስናዎች ሁሉ በጣም ሰርሳሪና የማይገታ ዓይነቱ ነው። የዚህ ዓይነቱ ሙስና፤ በሙስና ስነ-ጽሑፍ ውስጥ የአስተዳደር (መዋቅራዊ ውጣ ውረድ – ቢሮክራሲያዊ) ሙስና ከሚባለው ተለይቶ መታወቅ አለበት። የገዥዎች ንጥቂያ፤ በተለምዶ ሁኔታ፤ ከሞላ ጎደል ሁሉም ሀገሮች፤ ድኅረ-ኮምኒስት (የሽግግር) ሀገሮችን በመተው፤ የተመዘገበውና የተስተዋለበት ዓይነት ሙስና ነው። አስተዳዳራዊ (መዋቅራዊ ውጣ ውረድ) ሙስና በተለይ፤ ጉቦ ከፋዩ፤ በሀገሩ ያሉ ሕጎችን፣ ደንቦችን፣ እና መተዳደሪያዎችን በመለጠጥ፤ ለራሱ ሚዛናቸው እንዲደፋ በማድረግ ማካሄድ ነው። ባጠቃላይ የአስተዳደር (መዋቅራዊ ውጣ ውረድ) ሙስና፤ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች መዋቅራዊ ውጣ ውረድ ተግባራዊ ሂደቱ ላይ የሚፈጸም ሲሆን፤ የፖለቲካ ( ታላቁ ) ሙስናው የሚካሄደው፤ ከፍተኛውን መንግሥታዊ ሥልጣን በያዙት ደረጃ ነው። የተለያዩ የአስተዳደራዊ ሙስና ምሳሌዎች ሊሆኑ ከሚችሉት መካከል ለመጥቀስ፤ የተወሰነ ብያኔን እንዳይተገበር የማደናቀፍ፣ መዝገቦችን የማጥፋት፣ ወይንም መዝገቦችን አስመስሎ የመቅዳት ተግባር ተባባሪ መሆን፤ በከፍተኛ ደረጃ ሕጋዊ የሆኑ (እንዲተገበሩ የተመሩትን) የማስተጓጎል ወይንም/እናም እንዲዘገዩ የማድረግ፣ የተመደቡበትን የመሥሪያ ቤት የሥራ ሰዓት ለግል ጥቅም ማከናወኛ ሰዓት የማድረግ፣ ያልያዙትን ሥልጣን እንደያዙ በማስመሰል የመቅረብ፣ ጣልቃ የመግባትና ለዘመድ ጥቅምን የማስገኘት (የሥልጣን ብልግና)፣ የሕዝብን ንብረት ያላግባብ የመጠቀም፣ ከሥራ ምድብ ቦታ ያለመገኘት፣ ለልማት ከሚውሉ የአገልግሎት ዝግጅቶች መላሾ መውሰድ ላይ የመጠመድ፣ የሕግ ስነ-ሥርዓቱ ላይ ድጋፍ ለመሥጠት ገንዘብ የመቀበል፣ የሕዝብን ንብረት ወደ ግል መጠቀሚያነት የመምራት፣ ሕገ-ወጥ የሆኑ ተግባራትን እንዳላዩ ዓይቶ የማለፍ፣ ተራ ሌብነትና ንብረት የማባከን፣ ከዋጋ በላይ የመጫን፣ ሕልውና የሌላቸውን የሥራ ዝግጅቶች የማካሄድ፣ ቀረጥ የመሰብሰብ፣ የቀረጥ ፍተሻ ማወናበጃ የማድረግ፣ …ወዘተ።

ምንም እንኳ ከሥሩ መንግሎ ማጥፋት ባይቻልም፤ ደግነቱ፤ መንግሥታት የአስተዳደር (መዋቅራዊ ውጣ ውረድ) ሙስና የሚያደርሰውን ጉዳት፤ መንግሥታዊ ተግባራትን በታወቀ ይፋ መዋቅራዊ ሂደት፣ በተጠያቂነት እና በግልጽነት ሊያሳንሱት ይችላሉ። ይህ የሚሆነው፤ ለምሳሌ የሚከተሉትን በማድረግ፤

ሀ)  ከመንግሥታዊ መዋቅሩ ውጪ ሥልጣን ያለው አካል በማቋቋም

ለ)  ነፃ የምርጫ ቦርዶችን በማቋቋምና ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመፍቀድና በማሳደግ

ሐ) ነፃ የዜና ሥርጭት ተቋማትን በመጠቀም፣ ይህ ደግሞ በተራው ተቆርቋሪ ቡድኖችን፣ የኅብረተሰቡ የትብብር ማኅበሮችን፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችንና፣ … ወዘተ እየረዳ

መ) የፓርላማውን የምርመራ ሥልጣን በመጠቀም

ሠ)  ነፃ የሆኑ ፀረ-ሙስና ቦርዶችን እና የተልዕኮ አካሎችን መፍጠር

ረ)  ነፃ የሆነውን የፍትህ ሥርዓት በመጠቀም

ይሁንና፤ በኢትዮጵያ የተገነዘብነው የገዥዎች ነጠቃ በመባል የሚታወቀው፣ በሽግግር ባሉ (በፊት ሶሺያሊስት የነበሩ) ሀገሮች የተከሰተው ነው። ይህ፤ ጉልበተኛ ቡድኖች፤ ተቋሞችና መመሪያዎች፣ ሕጎችና ማዘዣዎች በሚያመቻቸው መንገድ እንዲገነቡላቸው ተገቢ ያልሆነና የተበላሽ ተጽዕኗቸውን በመጫን፤ ለሕዝቡ በጎ ተግባር ከማዋል ይልቅ፤ ለራሳቸው ጥቅም የሚያስጠብቁበት ክስተት ነው። የገዥዎች ነጠቃ በተለያየ መንገድ ሊነሳና ሊተገበር ይችላል፤ ማለትም ጉልበተኛ ግለሰቦች፣ ቡድኖች ወይንም የጥቅም ትስስር ያላቸው ስብስቦች፤ ባንድ በኩል ሚስጢራዊ የሆኑ መንገዶችን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሕጋዊና ተገቢ መዋቅሮችን በመጠቀም፤ ተፎካካሪዎቻቸው በኃላፊነት የተቀመጡትን ባለሥልጣኖችን እንዳይገናኙና የአገልግሎት በሮች እንዳይከፈቱላቸው በማገድ የሚከሰት ነው። የተለዩ ቡድኖችና የመንግሥት ባለሥልጣናት፤ “የመንግሥት ባለሥልጣናትን የፖለቲካ ኃላፊነትና የግል የንግድ ፍላጎት የደበዘዘ መለያያ አጥር” በመለጠጥ አሸዋረው፤ ከኅብረተሰቡ ይልቅ ለራሳቸው የጋራ ጥቅም በማዋላቸው ሊነሳ ይችላል (ከሄልማን፤ 1998፡3  የተወሰደ አስተሳሰብ)። እንደ የብሮድማን እና ሬካናቲኒ (2001) አስተሳሰብ)፤ የገዥዎች ነጠቃ፤ ለተለዩ ቡድኖችና የንግድ ጥቅሞች የሚረዱ መመሪያዎችና ደንቦች ማስፈጸሚያ በመቀየስ፤ ጠቅላላ የፖለቲካ ሂደቱን ድምጥማጡን የሚያጠፋ ጎጂ ሙስና ነው።

የገዥዎች ንጥቂያ ከሀገር ሀገር ሊለያይ ይችላል። በአንዳንድ ሀገሮች፤ የገዥዎች ንጥቂያ፤ በብልግና የላሸቀ ምግባር ተብሎ በሚታወቀው ስር የሰደደ መሰሪ ካፒታሊስታዊ ግዛት፤ አንድ ገጹ ሆኖ ሊታይ ይችላል። በዚህ ክት፤ ጉልበተኛ ቡድኖች፣ ግለሰቦች እና በጣት የሚቆጠሩ ገዥዎች ባሉበት ሀገር፤ እኒሁ ገዥዎች አዳዲስ መንግሥታዊ መመሪያዎች ሲወጡ፤ ሆን ብለው በመጠምዘዝና ቅርጹን በማሳመር “የጨዋታ ሕጎችን” ለራሳቸው እንዲያጋድል የሚያደርጉበት ነው። ይህን፤ በኃላፊነት የተቀመጡ ባለሥልጣናት፤ የተደራጁ የንግድ ቡድኖች፣ ጥቂቶቹ ገዥዎች ወይንም ጉልበተኛ ግለሰቦች እንዲጠቀሙ፤ ድንጋጌዎችን ሲያውጁ እና/ወይም በሚወጡ ሕጎች ላይ ድምጻቸውን ሲሠጡ መገንዘብ ይቻላል። በተጨማሪ ደግሞ ግዙፍ የሆነ “የምጣኔ ሀብት ሥምሪትና የፖለቲካ ሥልጣን በአንድነት በአንድ ክፍል መያዝ” እና ጥቅም አሳዳጆች በሀገሪቱ የግዛት ልጓምና በሀገሪቱ ሀብት የበላይነቱን መጨበጥ በሚከተለው የሀብት አለመመጣጠን ይታያል። የገዥዎች ንጥቂያ ክስተት፤ በኃይለኛ መሪዎች (ማለትም የአካባቢ ወይንም የሀገር አቀፍ የሆኑ)፣ ሚኒስትሮች፣ ሕግ መወሰኛና የፍትኅ ሚኒስትር ሥራ አስኪያጆች፣ የመንግሥታዊ ተቋማትና/ትልልቅ ድርጅቶች፣ የገዥው ፓርቲ ባለቤትነት ያለባቸው ኩባንያዎች ሥራ አስኪያጆች በሚያደርጉት ድብቅ ሻጥር ሊታይ ይችላል። በአንዳንድ በኩል የገዥዎች ንጥቂያ፤ የሕጋዊና የፖለቲካ ተቋማት መዳከም ውጤት ነው። በሌሎች አንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ፤ ነጣቂዎቹ፤ ለንጥቂያቸውና ለብዝበዛቸው እንዲያመችላቸው የሀገሪቱን ሕጋዊና ፖለቲካዊ ተቋማት ሆን ብለው ያዳክሟቸዋል። በተጨማሪም፤ በምጣኔ ሀብት ሥምሪቱ እደሳ መክሸፍ እና ጉልበተኛ ግለሰቦች ወይንም የተደራጁ ቡድኖች፤ ከ“መንግሥት ይዞታ ወደ ግለሰብ ባለቤትነት” የሚደረገውን የሽግግር ሂደት በመጠቀም፤ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለውን የሕዝብ ንብረት፤ በመመንተፋቸው ይከሰታል። በአንዳንድ ሁኔታዎች የገዥዎች ንጥቂያ፤ የተደራጁ ቡድኖች፤ እነሱ የፈለጉትን ያደርጉ ዘንድ፤ ግዛታዊ መዋቅሩን፣ ፍርድ ቤቶችን፣ መረጃ ክፍሉን፣ ጦር ሰራዊቱን፣ ሕዝብ መገናኛ መስመሮችን ጭምር፤ ተጽዕኖ ለማድረግ በሚስጥር፤ በግዛቱ ውስጥ የድብቅ ግዛት (“ጎድናዊ ግዛት”) ሲፈጥሩ ሊታይ ይችላል። የገዥዎች ንጥቂያ በነገሰባቸው አንዳንድ ሀገሮች፤ የመንግሥት በሆነውና የግለሰብ በሆነው፣ ይፋ በሆነውና ይፋ ባልሆነው፤ የግዛት ክፍልና የገበያ ክፍል በሆነው መካከል ያለው የመለያያ መስመር አካቶ ድብዝዟል። ከላይ በተሠጠው ገለጻ እንደምትረዱት፤ በገዥዎች ንጥቂያ ሥር፤ የአንድ ሀገር ሕጎች፣ ደንቦች፣ ሕጋዊነቶች እናም በመጨረሻም አጠቃሎ ተቋማቱ እንዳሉ የሙስናው አካል ናቸው። እኒህን የመሰሉ የሙስና ገጾች፤ ቀደም ብሎ ከላይ ከተገለጸው አስተዳደራዊ/መዋቅራዊ ውጣ ውረድ ሙስና ፍጹም የተለዩ ናቸው።

በአንዳንድ ኢትዮጵያን በመሰሉ ሀገሮች፤ (ሃሰን፤ 2013) (በተወሰነ ደረጃ ደግሞ፤ እንደ ዩጋንዳ እና ሩዋንዳ የመሳሰሉ ሀገሮች) ጠቅላላ የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሀብት ሥምሪቱ፣ ሕጋዊና ወታደራዊ መዋቅሮች በሙሉ እንዳሉ በጉልበተኛ የተቧደኑ ክፍሎች ወይንም በትውልድ ሐረግ የተሰባሰቡ ቡድኖች እጅ ገብቷል። ይኼን የመሰለው ሙስና፤ አደገኛና መርዛማ ነው። ምክንያቱም፤ እኒሁ የተዋቀሩ ቡድኖች፤ ከታላላቅ ድርጅቶች ባለቤቶች እና/ወይም በጣት የሚቆጠሩ ገዥዎች ጋር በመተባበር፤ የሁሉም ተቋማትን ወሳኝ የሆነ የደም ሥር (የምጣኔ ሀብት ሥምሪት፣ የኅብረተሰቡ ትስስር፣ የጦር ሰራዊት) እየተቆጣጠሩ በመገኘታቸው ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች፤ እንደ ሩስያ በ1990ዎቹ እና በአንዳንድ የአፍሪቃ ሀገሮች፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ እንደታየው፤ የንጥቂያው ተግባራዊነት፤ በጣም የተደራጀና ዘሎ ገባ ገፋፊ ነው። ነጣቂዎቹ፤ አመጽና ማስፈራራት፤ ከሌሎች መገልገያ መሣሪያዎቻቸው መካከል እንደተጠቀሙ ታውቀዋል። የሀገሪቱን የምጣኔ ሀብት ሥምሪት ሥርዓት ወሳኝ የደም ሥር በበላይነት ለመቆጣጠር፤ የራሳቸውን ሁሉን ከላይ አንቆ ያዥ የንግድ ተቋም (ሞኖፖሊ/ ኦሊጋርኪ) እና ወሳኝ የተጣመረ የንግድ ቡድን (ካርቴል) በማቋቋም፤ እግረ መንገዳቸውን በሥራ ላይ እየዋለ ያለውን የገበያ ማሻሻያ ሂደት ባንድ በኩል በማሰናከል ታውቀዋል። ባጭሩ፤ ይኼን የመሰለው ሙስና፤ የአዲሱ ዘመናችን የተደራጀ የወንጀል ምግባር ይመስላል።

የያንዳንዱ ሀገር ልዩ የሆነ የሙስና ባህርያት

የነጣቂዎች ብልሹ ተግባራት በሁሉም ዘንድ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ናቸው። ነገር ግን፤ ከሀገር ሀገር ወይም የንጥቂያው አጀማመር እና የነጣቂዎች ዓይነት ሊለያይ ይችላል። በድኅረ-ኮምኒስት ሀገሮች፤ ሄልማን እና ተባባሪዎቹ እንዳሉት፤ (2003) በየግል “ነጣቂ ድርጅቶች (ማለትም ለባለሥልጣናት የጨዋታውን ሕግ እንዲመቻችለት የግል ክፍያ የሚያካሂድ) እና በተደማጭ ድርጅቶች (ማለትም ለባለሥልጣናት ክፍያ ሳይቸገር፤ በሕጎቹ ላይ ተደማጭነት ያላቸው ድርጅቶች)” መካከል ልዩነት ያደርጋሉ። በጥቅሉ ነጣቂዎቹ፤ ስርዎ ስሙ የተሠጠው (ኖሜንክላቱራ)፤ በቀድሞው የሶቪየት ሥርዓትና የምሥራቅ አውሮፓ ፈርጅ ሀገሮች ሥር፤ መንግሥት ይቆጣጠራቸው በነበሩት የምርትና የንግድ ድርጅቶች፤ የቀድሞ ሥራ አስኪያጆችና በመዋቅሩ ተሰግስገው የነበሩ ኃላፊዎች ቡድን፣ (ቁጥራቸው በግምት ከሕዝቡ ከመቶ አንድ ነጥብ አምስት የሚሆኑ) ናቸው። እኒህ “ከሌሎች በተለየ የተከበሩ ባለመብት ሆነው፤ ፍጹማዊ የሥልጣን ልጓሙን ጨብጠው፤ እርስ በርሳቸው የማያልቅ የፖለቲካ ቁማር በመጫወት ተጠምደው” ነበር። በተጨማሪም “የተሠጣቸውን የኃላፊነት ቦታ በመጠቀም፤ የንግድ ተቋሞችን ነጣቂ” ባለሥልጣናት ሊሆኑ ይችላሉ። አለያም የተሰባሰቡ የፓርላማ አባላት፣ ዋና ሥራ አስኪያጆች፣ ሚኒስትሮች፣ ዳኞች በመተባበር ሊሆኑ ይችላሉ (የራሱ የገዥው ፓርቲ መሪዎች፣ ከሳሽ፣ ዳኛና ጠበቃ በመሆን)። የገዥዎች ንጥቂያ በሁሉም ቦታ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ሆኖ፤ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ውስጥ፤ በድኅረ-ኮምኒስት ካሉት ሀገሮች በአንዳንድ ወሳኝ ጉዳዮች ይለያያሉ።

አንድ ሲሉ፤ እኒህ የኢትዮጵያ ነጣቂዎች፤ እንደ ሩሲያዊያን እና የምሥራቅ አውሮፓ አጓዳኞቻቸው ስርዎ ስሙ በተሠጠው (ኖሜንክላቱራ)(የኮምኒስት ፓርቲው ከፍተኛ ባለሥልጣናት) አባል አይደሉም። ከኒህ ከኛዎቹ፤ ብዙው አባሎቻቸው ሥልጣን ለመውሰድና ራሳቸውን ለማበልጸግ ብጥስጣሽ ልብሶቻቸውን ጣጥፈው ለብሰው ከበርሃ የመጡ ሽምቅ ተዋጊዎች ነበሩና።

ሁለተኛ ደግሞ፤ እንደ ኢትዮጵያ በመሰሉ ሀገሮች፤ የገዥዎች ንጥቂያ ክስተት፤ በተፈጥሮው በጣም ውስን ነው (ባላባታዊ አስተዳደር ቀመስ እና በጎሳ ትስስር የተያዘ)። አለመታደል ሆኖ፤ በትስስር ተቀፍድዶ የተያዘው የኢትዮጵያ ሙስና፤ ለቅናትና መቻቻል አመቺ ይሆናል። ሙስናው የረዳቸው የአንድ ወገን ሊሂቃን ሀብታቸውን ሲያበዙ፤ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍል ያሉት ቅናት ይይዛቸዋል። በተገላቢጦሹ፤ በገዥው ቡድን ወገኖች በኩል፤ ይኼን መርዛማ ተግባር ችላ ብሎ የማለፉ አቀቤታ ሊከሰት ይችላል። ይህ ዝንባሌ የኬንያን ኅብረተሰብ ሠርጾ መግባቱ ታውቋል (የሚሸላ ሮንግን,የ 2009. “አሁን መብላቱ የኛ ተራ ነው።” የሚለውን መጽሐፍ ይመልከቱ።) የመጨረሻው ውጤት፤ እያንዳንዱ (በአብዛኛው ኃይለኛ) የጎሳ ቡድን ተራቸውን እየተቀባበሉ ሌሎችን በመጠቅጠቅ ራሳቸውን በሀብት የሚያደልቡበት እሾካማ ተናካሽ የሙስና እሽክርክሪት ነው። በነዚህ ሀገሮች (በተለይም ኢትዮጵያ) አንድ ሽንጡን ገትሮ የሚያደባ ጠንካራ መዘዝ እንዳለ ይታዘቧል – ይሄውም ለሙስና የደንበኝነት እና የዘመናዊ – ወራሽነት ባህሪ ነው።

በሶስተኛ ደረጃ፤ የቀድሞ አንቆ ያዥ ገዥዎች ከፖለቲካ ሥልጣናቸው ከተወገዱበት ከአንዳንድ የድኅረ-ኮምኒስት ሀገሮች፤ ለምሳሌ እንደ ምሥራቅ አውሮፓ በተጻራሪነት መልኩ፤ የኢትዮጵያ ነጣቂዎች የፖለቲካውንም የምጣኔ ሀብት ሥርጭቱንም ጠቅልለው ይዘውታል። የሩስያ እፍኝ ገዥ ባለጸጎች፤ ሀብት ያግበሰበሱት፤ ከዚያም ከዚህም በማምታታት እና ሁሉንም ዓይነት የሀብት ማጠራቀም ወንጀሎችን በማካሄድ፤ የሀገራቸውን ንብረት በጣም በርካሽ ዋጋ በማግበስበስ ጭምር ነበር (የኢትዮጵያ አጓዳኞቻቸውም ይሄኑ ተግብረዋል)። አቶ ፑቲን ታዲያ የአንዳንዶቹን የሥልጣን ጥመኝነት አልወደደውም ነበርና የመንጥር ዘመቻውን አካሄደና አንዳንዶቹን ወደ ዘብጥያ አወረደ። አንዳንዶቹን ደግሞ ለስደት ዳረጋቸው። ይሄን ሲያደርግ በጎን ንብረታቸውን ጋፍፎ ባዶ አስቀርቶ ነው (ለሱ የፖለቲካ ተቀናቃኝ ለመሆን ያልቃጣቸውን ትቶ)። የምሥራቅና የመካከለኛው አውሮፓ ነጣቂዎች፤ በከፊል እነዚህ ሀገሮች የአውሮፓ ኅብረትን መቀላቀል ስለፈለጉና ስለጣሩ፤ እናም የአውሮፓው ኅብረት ያስቀመጠውን ቅድመ-ሁኔታ ማሟላት ስለነበረባቸው፤ ኅብረቱም የገዥዎችን ነጣቃ በመታገልና በማጥፋት ስለረዳቸው፤ ቀስ በቀስ የፖለቲካ ተደማጭነታቸውን አጡ።

በአራተኛ ደረጃ፤ ኢትዮጵያን በመሰሉ ሀገሮች፤ የገዥዎች ነጠቃ አቻ የለውም፤ ማለትም በሌሎች ሀገሮች ከሚገኘው በተለየ መንገድ ጠንካራ ነው። ይህም፤ ሁሉን የፖለቲካ ሂደቱን ማከናወኛ መስሪያ ቤቶችና የሀገሪቱን የምጣኔ ሀብት ሥርጭት ቁንጮ ያጠቃለለ መሆኑ ነው። እዚህ ላይ ንጥቂያው የጦር ሠራዊቱን፣ የጸጥታ ክፍሉን፣ የውጭ ጉዳይ መመሪያውን፣ እና የፍትኅ ሥርዓቱን አልፎ ተርፎም የሕዝብ ግንኙነት መስመሮችን በሙሉ ያካትታል። በኢትዮጵያ፤ የጉልበተኛ ዘራፊዎቹ የሀገሪቱን የምጣኔ ሀብት ሥርጭት ቁንጮ አንቀው መያዛቸው፣ የሀብት ምንጩን ያላግባብ መውሰድ፣ በዘረጉት የፖለቲካ ሥልጣን ትስስር ተጠቅመው ሀብት ማካበት አልጠግብ ባይነት፤ በደሃና በሀብታሞች መካከል ያለውን የአጥር ልዩነት ከመቼውም በላይ እያሰፋ፤ አሁንም ያለምንም ገደብ እየጎደራ ነው። የልሂቃኑ ዝርፊያ እንዲያው በደፈናው፤ ራሱን መንግሥታዊ ሥርዓቱን በወንጀል የተጨማለቀ ስላደረገው፤ አልፎ አልፎ የተደራጀ ወንጀለኛ ቡድን (ማፊያ) የሚያከናውናቸው ድርጊቶች ብቅ ይላሉ። የገዥዎች ንጥቂያ በኢትዮጵያ ሌላው የተለየ መገለጫው፤ በጣም የከፋ የአንድ ጎሳ ወገንተኝነት ተፈጥሮው ነው። በዚህም የተነሳ፤ የመንግሥት የሚባለውና የግል የሚባለው፤ መለያ መስመራቸው ደብዝዟል፤ ፓርቲው ከመንግሥቱ ተለይቶ የማይታይ አካል ሆኗል። ለዚህም ነው ብዙዎቹ፤ የኢትዮጵያን የሙስና ቅንብር፤ በጣም የጋለ ዝርፊያ ነው ወደ ማለት የተፈታተኑት። እኒሁ ወገኖች፤ በዚህ የተነሳ፤ ይህ የተነጠቀ የምጣኔ ሀብት ሥምሪት በክፉ አዟሪት ውስጥ በመጠመዱ፤ ማንኛውም የአስተዳደሩን ሂደት ለማሻሻል የተወጠነ መመሪያ፤ ከወዲሁ ለውድቀት ተዳርጓል ይላሉ። ከመንግሥት አካል ውጪ ሆነው በሚንቀሳቀሱት እና በመንግሥቱ ውስጥ ባሉ ጉልበተኛ ቡድኖች መካከል የማያቋርጥ ፍጥጫና ግጭትን ያያሉ።

በኢትዮጵያ ምን ተፈጠረ?

በኢትዮጵያ የተከሰተው ከሀገሪቱ የንግድ ማከናወኛ ደንብ በተጻራሪ፤ የባዶ ቀፎ ኩባንያዎች መቋቋም ነው። እነዚህ ባዶ ቀፎ ኩባንያዎች የተቋቋሙት፤ ከሁለት እስከ አምስት የሚሆኑ “የአክሲዮኑ ተቋሯጮች”፤ እኒህ “የአክሲዮኑ ተቋሯጮች” የፖርቲ መሪዎች ሆነው፤ በመሰየም ነው። ገነት መርሻ እንደገለጹት፤ የፖለቲካ ፓርቲ የሆኑ የንግድ ክፍሎች በሀገሪቱ የንግድ ሥምሪት ሂደት ጎን ለጎን መሰለፍ፤ ለ ሀ) “የጥሬ ገንዘብ ተጋፎ ወደ ውጪ በመንጎዱ የሀገሪቱ የብልጽግና ምንጭ ሊሆን የሚችለው መንጠፉ፤ ለ) የፍቃድ አሠጣጡን እና ማምታታቱ ሐ) የመንገድ ሥራን፣ የሕንፃዎች መቆምን፣ እና ሌሎች የእነፃ ተቋራጭነትን በሚመለከት ለሚወጡ የመንግሥት ጨረታዎች፤ የውስጥ መረጃን በሚመለከት የቅድሚያ ጥቆማን ማግኘት፤ መ) የተወዳዳሪዎች እጥረት እና የመጨረሻው ደግሞ ሠ) የንግድ ሥምሪቱንና ባለሙያተኞችን በሰላ የአድልዖ ዘዴ የማግለል መንገድ ከፍቷል።

የታዘብነው፤ “የመንግሥት ንብረት የሆኑ የንግድ ድርጅቶችን ለግለሰቦች ለመሸጥ በተቋቋሙ አስፈጻሚ ክፍሎች፤ አድልዖና በጥቅም የተቆራኙ ቡድኖች ፈጠራ ሲፋፋም ነው (ሚንጋ ነጋሽ)። የኢትዮጵያ ሕዝብ የታዘበው፤ የመንግሥት ንብረት የሆኑ የንግድ ድርጅቶችን፤ ለግለሰቦች ለመሸጥ የተደረገው ሂደት፤ በትክክል አለመካሄዱ ነበር ((የገነት መርሻን፤ 2010)፣ የያንግን (1998)፣ የቬስታልን (2009)፣ እና የሚንጋ ነጋሽን (2010) ጥናቶችና ጽሑፎች ይመልከቱ)። ኢትዮጵያዊያን የታዘቡት፤ ፈጥርቀው በሚይዙ የፖለቲካ ፓርቲ ኩባንያዎች (“የችሮታ ተቋሞች”) እንደ የትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ችሮታ – ትመማች (ኢፈርት – በእንግሊዝኛ፤ ትእምት – በትግርኛ ) እና በሥሩ በተጠቃለሉ ከመጠን በላይ የበዙ ኩባንያዎች፤ ከአጥናፍ አጥናፍ ተዘርግቶ የተዋቀረ የገዥዎች ንጥቂያ ነበር። የተረዳነው፤ የገዥው ሤረኛ ቡድን አባላት፤ የሽምቅ ተዋጊዎች በነበሩበት ወቅት የዘረፉትን የሀገር ሀብት ለመመለስ፤ እምቢተኝነታቸው ነው። የምናውቀው፤ “በፓርቲያቸውና  በመንግሥት የንግድ ድርጅቶች፤ ባንኮችን ጨምሮ፤” አጥር ዘለል የፓርቲ አባሎቻቸው “በከፍተኛ ደረጃ ባሉ ቦርዶች በበላይነት” መቀመጣቸውና፤ በአካባቢያቸው ላሉ የፓርቲ ኩባንያዎች፤ በቀላሉ የባንክ ብድር ማንዶልዶላቸው ነው። የሥራ ተቋራጭ ጨረታውን፤ “ሌሎች” የተባሉ ኢትዮጵያዊያንን በማግለል፤ ከፓርቲው ጋር ትስስር ላላቸው መሥጠቱና ውድድር ማምከኑ፤ ልክ በሕንጻ ግንባታ ውስጥ በጣም አይሎ እንዳለው፤ ወገንተኝነቱ፤ (የዓለም ባንክ ሙስናን በኢትዮጵያ ምርመራ፤ ምዕራፍ 6ን ይመልከቱ) ተቀጣጠለ። ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታትና አሁንም በመቀጠል፤ ዕለት ተዕለት እየታዘብን ያለነው፤ ለኒሁ ግዙፍ የተጠራቀሙ የንግድ ድርጅቶች ኅብረቶችና ካድሬዎቻቸው ለያዟቸውና የሚወዷቸው ኩባንያዎች ውለታ ማመቻቸቱ ነው። የዚህ ውጤት፤ የውድድር ሂደቱን ማምታታትና የውድድር የገበያ ሁኔታውን ባዶ ማስቀረት ሆኗል። የታዘብነው፤ ልክ በሶቪየት ኅብረት ጥላ ሥር እንደነበሩት ሀገሮች፤ የገንዘብ ነክ ጉዳይ በሙሉ፤ በተወሰነ ቡድን መያዙና በቁጥጥር ሥር መዋሉ ነው። በኢትዮጵያ እየታዘብን ያለነው፤ አዲስ የዜና ማሰራጨትን እና ፀረ-ሽብር በሚባሉ የይስሙላ ሕጎች ታንቆ መያዝን ነው። በኢትዮጵያ የተመከትነው፤ የአዳዲስ ሕጎች – ልክ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከውጪ ሀገሮች እርዳታ እንዳያገኙ የሚያግደው ሕግ ዓይነት፤ በዚያኑ ወቅት የገዥው ፓርቲ በሕጉ ሳይታሰር፤ ከውጪ በሚያገኘው እርዳታ ያለ ልክ በመጠቀም ላይ እያለ፤  – መረቀቃቸውና መታወጃቸው ነው። ያደገው፤ ጀሯችን ዳባ ይልበስ ያሉ ጉልበተኛ መሪዎች “አጉል ግትር፣ እብሪተኛና ከሀቁ የራቁ” የዜሮ ድምር አስተሳሰብ ባህላቸው ነው። ኢትዮጵያዊያን የታዘቡት፤ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በማያቋርጥ ሁኔታ ሲጨፈጨፉና ድራሻቸው ሲጠፋ፣ የሀገሪቱ ተቋማትን፤ ነፃ የኅብረተሰቡ ማህበራትን በመበጣጠስም ሆነ የትምህርቱን ጥራት በማላሸቅ፣ በየጊዜው ራሳቸው ያወጧቸውን ሕጎችን በመጣስ፤ … ወዘተ. ሲያዳክሟቸው ነው። እየተገነዘበ ያለው፤ የውጪ እርዳታ ሠጪ መንግሥታትን ለመሸወድ፤ (ድርጅቱ እራሱ በሙስና የተነከረ መሆኑ የሚታማው) የተኮላሸ የፀረ-ሙስና መርማሪ ኮሚሽን መቋቋሙና፤ ይኼንኑ ሙስናን ለመዋጋት የሚደረግ ጥረት፤ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት እስከመጠቀም ድረስ መጥለፋቸው ነው። ልክ እንደ ሩስያና ሌሎች ቦታዎች፤ የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ፤ የሕግ አውጪውን፣ ሕግ አስፈጻሚውን፣ የፍትኅና ሁሉን የሕግ ማውጫና ማስከበሪያ መንግሥታዊ ክፍሎችን ነጥቆ ይዟል። እኒህ፤ “ለዝርፊያ መቀራመት የተመራ (ለኪራይ ሰብሳቢነት)” ከሁሉም በላይ በጣም የከፋው ሙስና፤ የገዥዎች ንጥቂያ ሙሉ ገጸ-ባህሪ ማሳያ ምስሎች ናቸው።

እኒህ ጥቂቶቹ ናቸው፤

የተከተለው ውጤት፤

የገዥዎች ንጥቂያ (የማፊያን ተግባር ዓይነቱ) እና ወንጀለኛው ገዢ ቡድን፣ ከማይታመን እብሪትና ጭቆና ጋር ተዳብሎ፤ በሀገሪቱ ውስጥ የጠለቀ ጨለምተኝነትን፣ ሁሉም ለራሱ ብቻ የሚስገበገብበትና፣ ጥግ ጥጉን ይዞ ተከፋፍሎ የተፋጠጠበትን ሀቅ አስከትሏል። ይህም በአንድ ምሽት፤ በፈጠራ ችሎታቸውም ሆነ ይኼ ነው በሚባል ጥሩ ነገር የማይታወቁ የትናንት ቁምጣ ለባሽ የሽምቅ ተዋጊዎችና ደሃ ታክሲ ነጅዎች፤ በማይታሰብ ደረጃ የተለጠጡ ቱጃሮች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ይህ፤ ያገሬው ትንንሽ ባለሀብቶች፤ የጥፋቱን አቦል የተቋደሱበት የንብረትን መጋየት አስከትሏል። ግብታዊ መነሳሳት ግብታዊ አይደለም – ማለትም፤ ያለ ምክንያት ከመሬት ተነስቶ የሚካሄድ አይደለም። ምክንያቶቹ፤ በገዥው ፓርቲ በኩል ያለው የሚያቅለሸልሸው ስግብግብነት፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ባለሀገር ነዋሪዎቹ፤ ለዘመናት ቀደምቶቻቸው ከኖሩበት ባድማቸው መፈናቀላቸውና፣ ይሄ ነው በማይባል ወይንም ያለምንም ማካካሻ፤ እኒሁ የተነጠቁ መሬቶች፤ የገዥው ፓርቲ ንብረት ለሆኑት ኩባንያዎች፣ ለገዥው ፓርቲ ልሂቃንና፣ ለውጪ ሀገር ሰዎች፤ ባለቤትነታቸው መዘዋወሩና መሠጠታቸው ነው። የግብታዊ መነሳሳቶች ምክንያቶች፤ ያለምንም ጥርጥር፤ የገዥው ክፍል መሪዎች ጭፍን ወገንተኝነትና በዚሁ ክፍል ልሂቃን በኩል የተደራጀ የቡድን ወንጀል መፈጸሙ ናቸው። ሙስና የጋለበበት የመሬት ልውውጡ፤ የሀገሪቱን የብልጽግና ምንጮች ባለቤትነት፤ ከተራው ሕዝብ ወደ በጣም ጥቂት ግለሰቦች እንዲዛወር አድርጓል። መሬታቸው በግዳጅ ተነጥቆ የተፈናቀሉትና የተጨቆኑት፤ ግፉ መጋቱ በቃን ያሉበት ሁኔታ ታየ። እንደ የምጣኔ ሀብት ሥምሪት ባለሙያነቴ፤ የገዥው ሤረኛ ቡድን ያልተገራ ቁንጠጣ (አስገድዶ ማፈናቀል፣) እብሪት፣ የማይረካ ስግብግብነት፣ አፍኖ ያዡ ሙስና ) የማያባራ የሚነቅዝ ቁርሾ ትቶ ማለፉ ይታየኛል። ለገዥው ያልተገራ ቁንጠጣና ለፓርቲው ልሂቃን ወንጀለኛ ተግባር ምስጋና ይግባውና፤ አሁን የውጭ ቀጥተኛ መዋዕለ ንዋይ፤ ለማጭበርበርና ለምዝበራ የጌጥ ስም ሆኖ ተወስዷል። በርግጥ፤ ሕዝብን ማዕከል የሚያደረጉና በትክክል ድጎማቸው የሚካሄዱ የከተማ ልማት ውጥኖች፤ ሁሉንም ባለጉዳዮች በአቸናፊነት የሚያስቀምጡ በሆኑ ነበር። መሬት ቀመስ ለሆነው ለከት አልባ ሙስና ምስጋና ይግባውና፤ የገዥው ሤረኛ ቡድን የገማ ተንኮል ሽረባ፤ የወደፊት ሕጋዊ የልማት ውጥኖችን የመካሄድ ዕድልን ሽርሽሮታል። ያለ ጥርጥር እኒህ ያልተገሩ የገዥው ሤረኛ ቡድን ቁንጠጣዎች፤ ለወደፊት ልማት ከፍተኛ ደንቃራ ይሆናሉ።

በሻጥር የገማውንና በዝርፊያ የተለወሰውን፤ ብዙ አለመረጋጋቶችን ያቀጣጠለውን የመሬት ነጠቃ ትንሽ ጨምሬ እንዳብራራ ይፍቀዱልኝ። ልክ እንደ ቻይናና ሰሜን ኮርያ፤ መሬት የኢትዮጵያ መንግሥት ንብረት ነው። ይህ በተራው፤ መሬትን ያለምንም ማካካሻ ለመንጠቅ ሩጫን፣ ባገኙበት ለማግበስበስና ለአድልዎ የተመቸ ሁኔታን ፈጠረ። ከሚሽጎደጎደው የማያልቅ የመሬት አዋጆች ጥቂቶቹን መገልገያ መሣሪያቸው አድርገው በመጠቀም፤ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና መሬት ነጣቂዎች፤ የቻይናን አስገድዶ መሬትን መውረሱን ቀድተውት ይሆናል። የኢትዮጵያ መሬት ነጣቂዎች፤ ከእንዲህ ዓይነቱ ተግባር ጋር የተያያዙትን ችግሮች መረዳት የተሳናቸው ይመስላል።

አንደኛ፤ በማስገደድ ማፈናቀሉ፤ የሰብዓዊ መብቶችን ረገጣና ቻይና የፈረመችውን አስገድዶ ከመሬት የማፈናቀል ዓለም አቀፍ ውልን ድፍረቶች ማስከተል ብቻ ሳይሆን፤ የተንኮል ጥንሰሳው፤ እያደገ ለመጣው የገቢ ልዩነት ማሻቀብ አስተዋጽዖ አድርጓል። እያደገ የሚሄድ የኑሮ ልዩነት የሚያስከትለው ጣጣ እንዳለ፤ የኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ ገዥዎች መረዳት ነበረባቸው።

ሁለተኛ፤ በቻይና፤ አብዛኛው የመፈናቀሉ ተግባር የተፈጸመው፤ ከማዕከላዊው መንግሥት ፍላጎት ውጪ፤ በአብላጫው በአካባቢው ባሉ የክልል ባለሥልጣናት ነበር። በኢትዮጵያ፤ ሁለቱም መሬት የማካለሉ እቅድና በሥራ ላይ መዋል የተከናወኑት፤ በማዕከላዊው መንግሥት ባለሥልጣናት ዕዝና መመሪያዎች ነው። ይህም ላደጉት ቁርሾዎች አስተዋፅዖ አድርጓል።

ሶስተኛ፤ ሁለቱም የቻይና ማዕከላዊና የአካባቢ መንግሥታዊ አካሎች፤ ለብዙኀን የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች በር የከፈተ የፋብሪካ የሥራ ቦታዎችን መፍጠር ችለዋል። በዚህም በተዘዋዋሪ መንገድ ንብረታቸውን ላጡና ለተፈናቀሉ ሰዎች፤ የፋብሪካ ሥራው፤ ከፊል ማካካሻ እንዲሆንላቸው አድርጓል።

አራተኛ፤ በኢትዮጵያ በስፋት ከተስተዋለው በተጻራሪ፤ ምንም እንኳ የተሠጣቸው ማካካሻ መሬታቸው በወቅቱ ሊያስገኝ ከሚችለው ዋጋ ፍጹም የማይስተካከል ቢሆንም፤ የቻይና የአካባቢ ባለሥልጣናትና አልሚዎቹ፤ የተፈናቀሉትን የካሷቸው ይመስላል።

አምስተኛ፤ በኢትዮጵያው ሁኔታ፤ ከመሬት ጋር የተያያዘው ሙስና ተጠቃሚዎቹ (በማስገደድ ማፈናቀሉንና የንብረት መውደሙን በሚያካትተው) የገዥው ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሆነው ተገኝተዋል።

ስድስተኛ፤ ከቻይናው በተለየ ሁኔታ፤ የራሱ የገዥው መመሪያዎች ክፍፍሉን እያባባሱት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ በጎሳ መስመሮች የተከፋፈለ ነው። በዚህም የተለሳ፤ ዘውገ-ነኩ የሙስና ነቀዛው ግጭቱንና ብጥብጡን ያባብሰዋል።

በመጨረሻም፤ ከኢትዮጵያ መሬት ነጣቂዎች በተለየ መልክ፤ የቻይና በለሥልጣናት፤ መሬታቸው ያለአግባብ በተነጠቁ ሰላማዊ ተቃውሞ አሰሚዎች ላይ የጥይት ውርጅብኝ አላሰፈሩም። ለዚህ ይሆናል ሌሎች በኢትዮጵያ የሚገኙ ጎሳዎች፤ በተለይም ኦሮሞዎች፤ የፌዴራል ፖሊሱን (በተደጋጋሚ ተማሪዎችን አረመኔያዊ በሆነ መንገድ ሲደበድብ የተስተዋለው) እና የጦር ሠራዊቱን፤ ንብረትነቱና መጠቀሚያነቱ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አጥፊ ጦር-ቀመስ የታጠቀ የሕዝብ መጨፍጨፊያ ቡድን አድርገው የሚወስዱት። የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ገዥው ፓርቲ ለፈጸማቸው ግፎች ተጠያቂነት እንደሌለው፤ በተደጋጋሚ አስተውለዋል። በጥቂቱ ለመጠቆም፤ በ 1995፣ 2005/6፣ 2014፣ አና አሁን 2015/6 ገዥው ክፍል እያደረሰ ያለውን ስቃይ፣ ግለስቦችን ከምድረ-ገጽ መሰወሩን፣ ጋፎ ማሰሩን፣ እና መጨፍጨፉን፤ በ2003 በአኝዎክ ወገኖቻችን ላይ ያደረሰውን የሕዝብ ዕልቂት፣ በ2001 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን መግደሉን ያስተውሏል። የኢትዮጵያን ሕዝብ የማያልቀው ግፍ አንገሽግሾታል። እኒህና ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሌሎች ስቃዮች ናቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ፤ በሥልጣን ላይ ያለው የነሱ መንግሥት እንዳልሆነ እንዲያስቡ ያደረጋቸው። የሕዝብ ብልጽግና ምንጮቹን ጥቂቶቹ መቀራመታቸውና የኒህ ጥቂቶች ለከት የለሽ የሙስና ተግባር ነው የኢትዮጵያን ሕዝብ፤ ንብረቶቹና መዋዕለ ንዋዮቹ ከነሱ የማይወግነው የመዥገሩ ቡድን ናቸው፤ ብሎ እንዲያስብ ያደረገው። እናም ከዚህ ተከትሎ፣ “ከሌሎች” የሚመነጨውን ሙስና መገመቱ ከባድ አይደለም (በብዙዎች እንደወራሪ የተወሰዱ) በብዙ ሁኔታዎች ላይም፤ አንድን ጎሳ እንወክላለን በሚሉት እየተራገበ – በከፍተኛ ቅናትና ቁጣ እየተስተዋለ እያደረገ፤ ብሎም ተከፋፍሎ፤ ሁሉም ወደ ጥጉ መፈርጠጡን እያከረረው ሄደ።

የገዥዎች ንጥቂያ፤ ከጭቆናው፣ ከእብሪቱና፣ ከአረመኔ ተግባሩ ጋር ተዳምሮ፤ ሀገሪቱን እየተመነደገ ለሄደ የኅብረተሰብ-የፖለቲካ-የምጣኔ ሀብት ሥምሪት ምስቅልቅል በሩን ፍንትው አድርጎ ከፍቶ፤ ለወደፊቱ የጎሳ/የጠባብ ወገንተኝነት ግጭቶች መካሄድ በማመቻቸት፤ እየበሰበሰ የመጣው ሥርዓት ወደ የሚጋለጥበትና የሚፍረከረክበት ሁኔታ አምርቷል። አለመታደል ሆኖ፤ እየሟሸሸ በመሄድ ላይ ያለው ሥርዓት፤ የአጓዳኝና የንጹኀን ሰለባዎች ይኖሩታል።

“መፍትሔዎች”፤ አሁን ካለንበት ወዴት እንሄዳለን?

ከላይ እንዳመለከትኩት፤ ለገዥዎች ንጥቂያ፤ መሻሻል ማድረግ ዕርሙ ነው። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ፤ በየጊዜው፤ በሕግ የመተዳደር ሥርዓት፤ በከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዳሻቸው ሲለሚሽከረከር፤ የሕግ የበላይነትን የሚያስከብር ነፃ የሆነ የፍትኅ ሥርዓትን አስከባሪ አካል የለም። በተለያዩት የመንግሥት አካሎችም ምንም ዓይነት የሥልጣን ድርሻ ክፍፍል፣ መከባበርና መጠባበቅ የለም። ያለን ነገር ቢኖር፤ የተሽመደመደ ፋይዳ ቢስ ፓርላማ ነው። አለን ብለን የምንቆጥረው፤ በአጥንት የለሽነትና ደካማነት ታስሮ የተያዘ፤ ሥልጣን አልባው የፀረ-ሙስናው ድርጅት ነው። ከሞላ ጎደል ሁሉም የነፃና በግል ባለቤትነት የተያዙ ጋዜጦች ተገደው ድምጥማጣቸው ጠፍቷል፤ ብዙዎቹ ጋዜጠኞችም ታስረዋል፤ አለያም ተሰደዋል። እኒህ አረመኔያዊ እርምጃዎች፤ ሀገሪቱ (ራሱ የገዥው ሤረኛ ቡድንም) ነፃ የዜና አገልግሎትን በመጠቀም፤ ሥር የሰደደውን ሙስና የማጋለጥ ችሎታውን ነፍጓታል። በሀገሪቱ ያሉ የኅብረተሰቡ ድርጅቶች፤ አንድም ድርሻቸው ጠፍቷል አልያም የገዥዎቹ መገልገያ እንዲሆኑ ተደርገዋል። ያለን፤ የመርማሪ መሥሪያ ቤቱ ሙስናን እና የቢሊየን ብሮች መሰወርን ሲያጋልጥ፤ የምርመራ ሹሞቹን አሽቀንጥሮ የሚያባርር የሀገራችን ዋና የሥራ አስኪያጅ አካል ነው። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ፤ እያንዳንዱ የቁጥጥር ድርጅት፤ አልፎ ተርፎ መሥራች፣ አቋቋሚ ፈትፋቹና አሁን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ቁንጮው ላይ በክብር የተቀመጡት አቶ ስብሃት ነጋ፤ በድፍረትና ያለዕፍረት፤ ሙስና በኢትዮጵያ ቅጥ አጥቶ ከመስፋፋቱ የተነሳ፤ የሃይማኖት ተቋማትን ሳይቀር ሰርፆ ገብቶባቸዋል እስኪሉ ድረስ፤ የገዥዎቹ ሤረኛ ቡድን መገልገያ ነው። የኢትዮጵያ ሤረኛ ገዥ ቡድን፤ የፀረ-ሙስና አለቃ ሆኖ የማይስተካከል ሥልጣኑንና ማኪያቬሊያዊ ስልቱን በመጠቀም፤ የሚያስቸግሩትን ለማጥመድና ጭጭ ለማሰኘትና ከተቻለም የሤራ ግዛታቸውን ሕይወት ለማርዘም የሚያገለግል ቭላድሚር ፑትንን (ማለትም መለስ ዜናዊን) የመሰለ አጥቷል። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መሪዎችና ግብረ አበሮቻቸው፤ (ወይም ባጠቃላይ መላ ሀገሪቱ) (የአሜሪካን ዘራፊ ባላባቶችን የተቋቋመ) ስግብግብ የሤረኛ ገዥ ቡድኑን የሚገታ ወይም የሚያፈራርስ፤ ቴዎድሮስ ሮዝቬልት የላቸውም፤ የኢትዮጵያ ሤረኛ ገዥ ቡድን ከኢትዮጵያ መንግሥት ተለይቶ መታየት አይችልምና። ሄዶ ሄዶ፤ በኦሮሞዎች ላይ የሤረኛ ገዥ ቡድን የተወሰዳቸው የድንብርብርና አይምሬ የጭካኔ እርምጃዎች በግልጽ የሚያመለክቱት፤ የገዥው ክፍል አንድ ፈላጭ ቆራጭ ቁንጮ መሪ ማጣቱን ብቻ ሳይሆን፤ ሀገር አቀፍ ማዕከላዊ ዕዝና ቁጥጥር እንዳነስው ጭምር ያመለክታል።

የቀሩልን፤ ሶስት በንፅፅር ሲታዩ ጠናካራ የሚባሉ ቡድኖች ሲሆኑ፤ እኒህ ቡድኖች፤ ሀገሪቱን ሁሉ ያበሻቀጠው ሙስና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ስቆቃ ሊያረግቡት ሲችሉ፤ የሚወስዷቸውት እርምጃዎች፤ እግረ መንገዳቸውን፤ ያልተገራ ዘራፊውን ገዥ መንግሥት ዕድሜ የማርዘም ዕድል አላቸው። ምንም እንኳ እኒህ ሶስት ቡድኖች የሤረኛ ቡድኑን መንግሥት የፖለቲካ ሕልውና ማርዘም ቢችሉም፤ በዚህ ደረጃ ያለ ሙስና በባለቤቶቹ ሊድን ስለማይችል፤ ከአይቀሬው ውድቀቱ  ሊያተርፉት አይችሉም። እኔ በማቅማማት ላይ ያለሁት፤ ሀ) አህጉራት አቀፍ ተቋማት፤ ለማሳሌ እንደ አይ. ኤም. ኤፍ፣ የዓለም ባንክ፣ እና ሌሎችም፤ ለ) ዕርዳታ ሠጪ ሀገሮች፤ ዩናይትድ ስቴትስ ኦቭ አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት (በተለይም እንግሊዝ) እና ሐ) የገዥው አካል የሆኑና ከገዥው አካል ጋር ቅርበት ያላቸው ጉዳዩ የሚያገባቸው፤ ማለትም፤ “ላለው ሥርዓት ጥብቅና ቆመው የሚጠብቁት”ን (ብርሃኑ መንግሥቱ, 2016 – “ለፖለቲካ ሠፈሩ ምልጃ . . .”) በማጤን ነው። የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ፤ በመንግሥቱ ላይ ከባድ ጫና ማድረግ የሚችል ፈርጠም ያለ ጉልበት አላቸው። እኒህ ተቋማትና ዕርዳታ ሠጪ ሀገሮች፤ ይህ መንግሥት ምን ያህል የዕርዳታ ጥገኛ – ዕልም ብሎ የዕርዳታ ጥገኛነቱ “[ልክ] በሕመም ማስተገሻ ከኒና እንደተለከፈ በሺተኛ፣” እንደሆነ ያውቃሉ። በተለይ ዩናይትድ ስቴትስ ኦቭ አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገሮች፣ ዩናይትድ ኪንግደም፤ ከርዳታ ሠጪ ተቋሞች ጋር በመሆን፤ የሚሠጡት ዕርዳታ፤ ገዥዎቹ ለኒሁ  ክፍያ የሚያደርጉላቸው፣ በግዳጅ ሰውን ወደ አንድ አካባቢ የሚያሰፍሩበት ወይንም በሌሎች መንገዶች የሚያፈሱት፤ የሙስናው ምንጫቸው መሆኑን ግጥም አድርገው ያውቃሉ። ሌሎች ቦታዎች ላይ እንዳሳየሁት፤ ዕርዳታ ሠጪ መንግሥታት፤ የፓርቲው ስብስብ የተዋቀሩ ግዙፍ የንግድ ድርጅቶች መነሻ ገንዘባቸው፤ የሚሠጡት ዕርዳታ መሆኑን ያውቃሉ። እኒህ ዕርዳታ ሠጪ መንግሥታት ከፈለጉ፤ የትግሬዎች ነጫ አውጪ ግንባር መሪዎችን፤ ከውጪ የተሠጠን ዕርዳታ ማባከንና ገንዘቡን ያለአግባብ ወዳልተገባ ቦታ ማዛወር በሚል ክስ መስርተው፤ አንገታቸውን ሊያስደፏቸው ይችላሉ። ሶስተኛውን ቡድን በተመለከተ፤ ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግሥቱ (2016) እንዳቀረበው፤ “ላለው ሥርዓት ጥብቅና ቆመው የሚጠብቁት” የሚሳካላቸው፤ “ከመካከላቸው ጥቂት አክራሪ የሆኑ ባለጉዳዮችን”፤ ለውጡ ለነሱ ዘላቂ ፍላጎት በጣም ጠቅሚነቱን በማግባባትና፤ ለውጡንም ተቀብለው በመምራትም ነው። እዚህ ላይ ትክክለኛ ጥያቄ ማስቀመጥ ይቻላል። እኒህ የሥርዓቱ ዘብ ቋሚዎች፤ ከላይ እስከታች ሁሉም የፓርቲ አባላት በሚገማ መልኩ ሙስኞች ሆነው፤ የራሳቸውን ስግብግብነትና ግለኝነት መቆጣጠር ይችላሉ ወይ? የሚለውን ነው። ታዲያማ ይኼን ካላደረጉ፤ እስካሁን ያካበቱትን ሁሉ ያጣሏ!

እሺ፤ ታዲያ በእምቢተኝነት ተቃውሟቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማሰማት የተነሱት ኦሮሞዎች ንብረቶችን እና የመዋዕለ ንዋይ ሕንጻዎችን ለምን አቃጠሉ? ይኼማ ባንድ ሌሊት እልም ያሉ ቱጃሮች ያደረጋቸውን የራሳቸው ያልሆነን መሬት፤ እንዳሻቸው በሚዘርፉ ሁሉን ለኔ የፓርቲ ልሂቃን ላይ፤ ሥር የሰደደው ምሬት ያስከተለው ነው። ሕዝቡ ያየው፤ ጥሮ ግሮ ሀብት ማግኘት፤ ወይንም በአያት የቅድመ አያት ባድማ ላይ ለማረስ ቅድሚያን ማግኘት ሳይሆን፤ ሀብት ማካበቱ፤ ቅጥ ያጣ ሙስናን፤ አፍቃሪ ፓርቲ መሆንን፣ የደም ትስስርን ተከትሎ ሲነጉድ ነው። በእምቢተኝነት ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት የተነሱት፤ ከትውልድ ቦታቸው ላይ በአስገዳጅ መፈናቀላቸው ብቻ ሳይሆን፤ ሥራ የላቸውም፤ ገንዘብ የላቸውም፣ ተስፋውም እንኳ የላቸውም። የኒህ ተነሳሺዎች የተለዩ ይዞታዎችን እየለዩ ማጥቃቱ እንደሚያመለከተው፤ ማቃጠሉ/ ማውደሙ እና የእምቢታ ዕቀባው ያተኮረ የሚመስለው፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርና የደጋፊዎቹ በሆኑት ላይ ነው። አለመታደል ሆኖ፤ እኒህን የመሰሉ ቅሬታዎች፤ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍል ነዋሪዎች ዘንድ ተረግዟል። ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ብዙ የሚቃጠልና የሚጠፋ የሀብት ምንጭ ባይኖራትም፤ በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ ድርጊት ሊደገም ይችላል።

አለመታደል ሆኖ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የምጣኔ ሀብት ሥምሪት አጉራ ዘለል ጉልበተኝነት እና መንግሥት የሚመራው የስቃይ ናዳ፤ አንጀቱ ቆስሏል። ያንጀት መቁሰል ወደ ተስፋብሲነት፣ አክራሪ ቁጠኝነት፣ እና የዛለ መንፈስ መያዝ ያመራል። ከዚያም በላይ ራስን ጎጂ እስከመሆን ያደርሳል። ስለዚህ፤ የንብረት ቃጠሎዎች፤ ኦሮሞዎች ከደረሰባቸው በደል የተነሳ ያንጀታቸው መቁሰል ተከታይ ውጤቶች ናቸው። አንድ ቀን እኒህን የመሰሉ ጥፋቶች፤ ምንአልባትም በከፋ ሁኔታ፤ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ይደገሙ ይሆናል የሚል የሚቀነቅን ፍርሃት አለኝ። በላያችን ያንዣበበውን አደጋ እንዳይከሰት የሚያደርጉ ተገቢ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ብለን ፀሎትና ተስፋ እናደርግ።

 

ጸሐፊው፣ ሰዒድ ሃሰን፣ በመሪ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ሥምሪት (ኢኮኖሚክስ) ፕሮፌሰር ናቸው። ሊያገኟቸው ከፈለጉ፤የኢሜል አድራሻቸው፤ shassan@murraystate.edu ነው።

The post ኢትዮጵያ፤ ሙስናና በእምቢተኝነት ቅሬታ የሚያሰሙት ንብረት ማቃጠላቸው። ድርጊቱን እናውግዝ ወይስን ይበል እንበል? ተጠያቂው ማነው? appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ለዲ/ን ኒቆዲሞስ፦ በውቀቱ ስዩም፣ ጓደኛው ተመስገንን “ከሚወዳት ልጅ ጋር አንሶላ ሲጋፈፍ ማደር …”  እንዳለበት አልመከረም! ውሸት ነው!

$
0
0

አሊ ጓንጉል

aliguangul@gmail.com

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen)ዲ/ን ኒቆዲሞስ፣ በውቀቱ ጓደኛው ተመስገንን “..ከሚወዳት ልጅ ጋር አንሶላ ሲጋፈፍ ማደር …” እንዳለበት መክሯል የሚሉትን ከየትኛው ገጽ ላይ እንዳገኘኸው አላውቅም። “አንሶላ”፣ “ሲጋፈፍ” እና “ማደር” የሚሉት፣ እንኳን ቃላቶቹ ራሳቸው፣ የግስ እርባታቸውም በምዕራፉ ውስጥ የለም። ለነገሩ ግን “መጽሃፉም” እንኳን ቢሆን፣ “ብዙ ተባዙ” ሲል አንሶላ ሳይጋፈፉ መባዛት የለም። በውቀቱ ያለው “አለምን መቅጨት…” ማለት ደግሞ፣ እንዳለ በጽሁፋዊ (Literal) ትርጉሙ በየትኛው መ/ቃላት “አንሶላ መጋፈፍ..” ማለት እንደሆነ ዲ/ን እና ዲ/ን ኒቆዲሞስ ብቻ መሆን አለበት የሚያውቀው። ስለዚህ ዲያቆኑ ዋሽቷል።

 

ለመሆኑ ፍሮዳይኒዝም  “…የሚያስተምረው ራስን ያለ ልክ መውደድን ነው። ሃይማኖትን አለመከተል፣ እግዚአብሔርን አለመቀበል፣ ባህልን አለመጠበቅ፣ ወሲብን ለእርካታ ብቻ መጠቀም፣ የገዛ እናትን ለወሲብ መመኘት የገዛ ወላጅ አባት እንዲሞት በጥልቅ መሻት የመሳሰሉት እሳቤዎች የፍሮይድ አስተምህሮ የማዕዘን ድንጋይ ናቸው። ለፍሮዳዊያን ወሲብ እንቅልፍ ማምጫ እንጂ ከአብሮ መቆየት፣ ከቅዱስነት፣ ዘርን ከማስቀጠል፣ ሓላፊነት ከመውሰድ ጋር ፈፅሞ አይገናኝም…” ያልከው ከየትኛው መጽሃፍ ላይ ነው ያገኘኸው? ለምን መጽሃፉን ከነገጹ ጠቅሰህ አትነግረንም?  እኔ “ሲግመንድ የሚታወቅባቸው ነገሮች” ብየ ጎግል አድርጌ፣ በጎግል የመጀመሪያ ረድፍ ላይ ያገኘሁት ይኸን ነው፦ “… Freud has been influential in two related, but distinct ways. He simultaneously developed a theory of the human mind and human behavior, and a clinical technique for helping unhappy (i.e. neurotic) people. በግርድፉ እንዲህ ይተረጎማል፦

ሲግመንድ ፍሪውድ በተለያየ መንገድም ቢሆን በሁለት [እርስ በርስ] በተገናኙ ጉዳዩች ለውጥ አምጪ ሆኗል–ደስታ ቢስ የሆኑ ስዎችን መርዳት የሚያስችል የህክምና ቴክኒክ ፈጥሯል፣ የሰው ልጅን ባህርይ (behavior)  እና አይምሮ (mind) በተመለከተም ቲዩሪ ነድፏል።

ሲግመንድ በስራዎቹ ውስጥ ስለወሲብ እና ውስብና መጻፉ እርግጥ ነው። እግዚአብሄርን አለመቀበል ደግሞ ከሶቅራጢስ ጀምሮ ያለ፣ በዚህ ዘመንም ትልቅ ሃይማኖት እየሆነ ነው። ነገር ግን ታላቅ የክ/ዘመኑ ሊቅ ከሆነው ከሲግመንድ ፍሩይድ ታላላቅ ስራዎች ውስጥ “ወሲብ፣ ባህልን አለመጠበቅ፣ ወዘተ…” የመሳሰሉትን ኢምንት የሆኑትን ጉዳዩች ብቻ በመጥቀስ፣ እንዲህ በሙያው የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጠውን ሳይንቲስት “ሰይጣን” አድርጎ መቀባት፣ የራስን “ቅዱስነት ለማጉላት” [ምናልባትም ምንም ቅዱስ ነገር ሳይሰሩ] ካልሆነ ምን ይባላል?

መግቢያየ ላይ እንደጠቀስኩት ዲ/ን ኒቆዲሞስ ያልተባለውን “ተብሏል” ብሏልና ዋሽቷል። “ከአንድ የሃይማኖት ሰባኪ እንደዚህ ያለ ውሸት አይጠበቅም…” እንዳልል፣ በውቀቱ ካሁን ቀደም “…የዲሲ ቄስ በበኩሉ ሙዳየ ምጽዋት አፍሶ፤… የንስሃ ልጁን ጡት ተንተርሶ፤ በቴስታ ተከሳክሶ ይኖራል የሚል ሀሜት አለ…” እንዳለው፣ የአብዛኛውን የሃይማኖት መሪዎችን በሞራል የመዝቀጥ ነገር ሳስበው “በርካታ እውነት የሚናገሩ የሃይማኖት መሪዎች አሉ” የሚል እንድምታ ያስከትልብኛል። እናም በደፈናው ዲ/ን ኒቆዲሞስ እንዲህ ያለተጻፈ ነገር እንደተጻፈ አስመስሎ የመጻፉ ነገር ብዙም አይገርመኝም።

 

እኔ ዲ/ን ኒቆዲሞስን ብሆን ኖሮ፣ ብዕሬን የማነጣጥረው፣ ከዋሽንግቶን ዲሲ እስተ ሎንዶን ከተሞች ሳይቀር የምዕራቡን አለም ከተሞች እስኪቀውጥ ድረስ በኡኡታ አገር ሲያምሱ እና ሲያተራምሱ፤ “በቴስታ ሲከሳከሱ…” የሚውሉትን እና በቅርቤ ያሉትን ሰዎች መተቸት እና መፍትሄ መፈለግ ላይ ነበር የምሰራው። “እሱ ብሎ ቄስ፣ እሱ ብሎ ጳጳስ፣ ዲያቆን ማንትስ ይኼን ያህል ገንዘብ አጎደለ፣ የወያኔ ተላላኪ ነው…ወዘተ…” የሚል ጽሁፍ እና የቪዲዩ ንትርክ ሳናይ ውለን የምናድርበት ቀን አለ እንዴ?

 

አንድ በአገሪቱ የስነ-ጽሁፍ ታሪክ አንቱ የተባለ ያገሬን ሰው “ለኢትዮጵያ ምን ትመኛለህ” ብለው “…ላንድ ሰከንድ የነብይነት ስልጣን ባገኝ፣ ኢትዮጵያዊ እንዳይዋሽ አደርገው ነበር” ያለኝን ሳስታውስ፣ እና እንዲህ ከሃይማኖት መሪዎች የሚታየው ማስመሰል፣ ቅጥፈት እና ሸፍጥ፣ ኢ-ሞራላዊ መሆን…ወዘተ ያመጣብን ይሆን? እላለሁ።

 

ስለ ዲሲ ቄስ “ሙዳየ ምጽዋት ማፈስ”፦ አንዲት በጣም የምግባባት እና በሰዓት $7.00 እያገኘች፣ ተሰኞ እስተ ሰኞ ያለ እረፍት እየሰራች፣ ሜሪላንድ የምትኖር ያገሬ ሴት “… የስለቴን ለቤተስኪያን $1000.00 አገባሁ…” ብትለኝ “አብደሻል እንዴ! አሊቤርጎ የመሰለ ቤት ተከራይቶ ለሚሰብክ አጭበርባሪ ሁላ እንዴት እንዲህ የደከምሽበትን ገንዘብ ትስጫለሽ?” ስላት “…በቃ! ደስ ያለኝን ነገር ስላገኘሁ፣ ደስ ያለኝን ነገር አደረግሁ” ካለችኝ ወዲህ፣ እውነትም የያንዳንዳችን የደስታ ማግኛችን መንገድ የተለያየ ነው። ይቺም እህቴ፣ ደስታ እስተሰጣት ድረስ፣ ገንዘቧን ወንዝ ውስጥ ብትበትነውስ ምን አገባኝ?” ከዚያ ወዲህ አንስቼባት አላውቅም።

 

ስለ ዲሲ ቄስ “የንስሃ ልጁን ጡት ተንተርሶ ማደር”፦ በውቀቱ “ ሃሜት አለ…” ነው ያለው። እኔ ደግሞ በእርግጥ የሆነውን እና የግለሰቧን ማንነት ማውጣት ባይሆንብኝ ኖሮ፣ ለንስሃ አባቷ ሃጥያቷን ልትናዘዝ የሄደች ሴት እንዴት በአባቷ ልትደፈር እንደነበር ከነቤተስኪያኑ እና ከነቄሱ እዚህ በተናገርኩ ነበር። ምን ላተርፍ? የጉዳዩ ባለቤት የሆነችውን ሴት ራሷን፣ ዛሬም እየሄደች የአባቷን ስብከት እንደምትሰማ ስትነግረኝ “እኔ አንቺን ብሆን ኖሮ አንደኛ አጋልጠው ነበር፣ ሁለተኛ እሱ ያለበት ቦታ ድርሽ አልልም ነበር…” ስላት “… እሳቸውን ለመስማት ብዬ ብቻ አይደለም የምሄደው፣ ለቦታው ነው…” ታለችኝ ወዲህ፣ እንዲህ ያለ ክርክር አቆምሁ። እኔ የማውቀው፣ ሲጀምር ቦታውን (መስበኪያውን ቦታ/ቤተስኪያኑን) ያቆሙት እሳቸው (አባቷ) እና አባቷን መሰሎቹ ተጥራርተው ነው። እዚሃር/ሚካየል ራሱ ወርዶ ጎልላት ሲሰቅል አላየሁም።

 

አሁን አሁንማ በየፈረንጅ አገሩ ያለ ያበሻ ቄስ ሁላ “እልል በቅምጤ[1]” ሆኖለታል። የፈረንጅ ቸርች ሁላ ምእመን እያጣ እየተዘጋ ነው። ያበሻ ቄስ እና ደብተራው ሁላ እየተጠራራ ይገዛዋል። አንድ ወቅት፣ እንዲያው ለቤተሰብ ብዬ (እድሜ ለ66ቱ አብዩት፣ እኔም ተሃይማኖት ተተፋታሁ 35 ዓመት አለፈኝ) አንድ አዲስ የተከፈተ ቤተስኪያን “ግራንድ ኦፐኒንግ” (በውቀቱ “ሙዳየ መጽዋቱን እያፈሰ” አለ? ቀላል ቢዝነስ ነው እንዴ!) ላይ ተገኝቼ ነበር። ጸሎተ ቡራኬ ተሰጥቶ እንዲያው ታ’ቀረቀርኩበት ቀና ተ’ማለቴ ቀድሞ ያላየሁት አንድ ፈረንጅ ታ’ጠገቤ ቆሟል። መቸም ኢትዬጵያ የኖረ፣ ቅባ ቅዱስ አግኝቶ፣ ከርስትና የተነሳ፣ የተጠመቀም ይሆናል … እያልኩ ሳስብ፣ ራሱ ወሬ ጀመረኝ–በሹክሹክታ፦

 

“…ኢትዮጵያዊ ነህ፣ አይደል?”

“አዎን”

“አይ ኖው”

“ኧረ! እንዴት አወቅህ በል?”

“ዌል…ይኼ ቤተስኪያን የኛ ነበር፣ የሸጥነው ለኢትዮጵያዊያን ነው እና…”

ጆሮዬ ቆመ። “እናንት እነማን ናችሁ? ማለቴ የማን ቤተስኪያን?”

“የግሪክ…” አለና ፈገግ ብሎ ቀጠለ “…የማስተዳደሪያ ገንዘብ (በሙዳየ ምጽዋት የሚገኘው) መግባት አቆመ፣ ምዕመኑ ተመናመነ። ሳር ማሳጨጃ እና ማጽጃ ባጀት ሁሉ ጠፋ። እናም ተዘጋ፤ ይኼው እናንተ ገዛችሁት” አለኝ።

 

ለነገሩ የዲ/ን ኒቆዲሞስ ትኩረት በመሰረቱ፣ በንግስት ሣባ ርዕሰ ጉዳይ አስታኮ፣ የበውቀቱን በአደባባይ “ከሃይማኖት ጋር መፋታት…” (ኢ-አማኒነት) ለማጋለጥ እና ኢ-አማኒነትን ለመዋጋት ያደረገው ይመስለኛል። ኢ-ሃይማኖተኛነት እየገነነ/እየገዘፈ የመጣ “ሃይማኖት” እንደሆነ ዲ/ን ኒቆዲሞስ ሳያውቁ ቀርተው አይመስለኝም። ያ ብቻ’ማይደል፣  እንዲህ “ኩላሊት እያወጡ ይወስዳሉ፤ አሳ ነባሪ በላቸው፣ አይሲስ አረዳቸው…” እየተባልን ሁሉ እንዲህ አይናችንን እየጨፈንን የምንመጣበት የምዕራባዊያኑ አገር፣ ስለ እዝጌሩም ሆነ ሰይጣኑ፣ ስለ ሳባም ሆነ ሰለሞን፣ ስለ ወሲብም ሆነ “አንሶላ መጋፈፍ” ወዘተ… በነጻነት ለመወያየት፣ ለመጻፍ፣ ለመናገር ወዘተ የሚያስችል ዲሞክራሲያዊ መብት ያላቸው በመሆኑ ያቆሙት እና እንዲህ ያደረጁት/ያለሙት አገር መሆኑን ዲ/ን ረስቶት አይመስለኝም። የእሱም የንጀራ  ነገር ቢሆንበት ይመስለኛል።

 

የምዕራባዊያኑ በነጻነት የመሰብሰብ፣ ሃሳብን የመናገር፣ የመጻፍ ወዘተ ሲፈቅድ፣ ኢ-አማኒያኑንም የሚሞግት ነጻነትንም ያካተተ ነውና፣ ዲ/ን ኒሞዲቆስ መከራከር መብቱ ነው። ግንሳ መዋሸት ባልተገባ ነበር። ደሞ’ስ የደራሲ በውቀቱ ጽሁፍ መጥፎ መሆኑን የታየውን ያህል፣ እንዲያውም መጽሃፉ ውስጥ የሌለውን እና “… እግረ ሙቅ ለሚጠብቀው ወዳጁ እንደ መልካም ወዳጅ በደጁ ከሚጠብቀው መከራ…  ያንዣበበበትን የመከራ መርግ ለጊዜውም “…አንሶላ ሲጋፈፍ ማደር…” ብሎ ስለመምከሩ በምናብም ቢሆን የታየውን ያህል፤ የተመስገን ደሳለኝ መልካም ሰብዕና፣ እና “… እንደምታሰር …ሰምቻለሁ… ልጆቹን ይዤ የመጣሁት ለዛ ነው። ከምሳ በኋላ እነሱን ሳዝናና ለመዋል አስቤያለሁ። የዛሬው ቀን የነሱ ነው…” (ገጽ 78)፣ የማለቱ እና ተመስገን ያለችውን ግማሽ ቀን፣ በጉዲፈቻ የሚያሳድጋቸው ልጆቹን ለማዝናናት የማሰቡ እና የማድረጉ መልካም ሰብዕና ለምን አልታየህም? ምነው የበውቀቱ አጉል/መጥፎ ሰብእና ብቻ ታየህ? የሌላውን ሰው መጥፎ ስራ (አንዳንዴ የሌለ ጥፋትን በመፍጠር፣  እና ምንም አይነት መልካም ስራ ሳንሰራ) አጎልቶ በማውጣት፣ የራስን መልካምነት ለማሳየት ከመሞከር የምንወጣው መቼ ነው?

 

‹‹… ወዳጄ እንግዲህ የፈራኸው የመከራ ቀን ኮተተት እያለ እየመጣ እንደሆነ ሳይገለጽልህ እንዳልቀረ እገምታለኹ እናም አብዮተኛው ወንድሜ …” የሚል ጽሁፍ ያለው የትኛው ገጽ ላይ ነው? መጀመሪያ ነገር እያንዳንዱን በመጽሃፉ ውስጥ ተጻፈ ያልከውን ነገር አንድም ቦታ ላይ ገጽ በመጥቀስ ያሳየኸው ነገር የለም። ሲመስለኝ እንዲሁ አድበስብሶ እና አስመስሎ ደራሲውን ለማስጠቆር የተጻፈ ነው የሚመስል።

 

“… በጠራራ ፀሐይ ወሲብ እንደ ሸቀጥ በሚቸረቸርባት በአሜሪካዋ በላስቬጋስ ከተማ ቆይታው በኋላ ይህችን ከተማ ‹‹አትጠገብም፣ ትጣፍጣለች›› በሚሉ ውብ ቃላት ነው ሊገልጽልን የሞከረው። እንዲህ ዓይነቱ ከሃይማኖታችን፣ ከኢትዮጵያዊ ባህላችንና ትውፊታችን ያፈነገጠ የበዕውቀቱ ለወሲብ ያለው ይሄ አፈንጋጭ አመለካከቱ እንዴት በልቡ ሊሰርጽ እንደቻለም እንዲህ ሲል ያወጋናል…” በሚልም በዕውቀቱን ሊተቸው ይሞክራል። ለመሆኑ የትኛው ባህላችን? ይኼ የ10 እና 11 አመት ህጻናት በቦሌ እና መርካቶ፣ በሃገሪቱ ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች… በየአደባባዩ ተኮልኩለው፣ ይበሉ ይቀምሱት አጥተው እያየን፣ ት/ቤት በመሄጃ እድሜያቸው ገላቸውን ሸጠው የሚኖሩ ህጻናት የፈሉበትን ኢትዮጵያዊ ባህላችንን፣ ትውፊታችንን እና ሃይማኖታችንን ነው?

 

ባንድ ወቅት አገር-ቤት ሆኜ፣ ለኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ ፕሮጄክት ለመስራት፣ እየዞርኩ ቃለ መጠይቅ አደርግ ነበር። መርካቶ ውስጥ፣ በጎዳና/ሴትኛ አዳሪነት የምታድር አንዲት የ13 አመት ልጅ “…ኮንዶም ትጠቀሚያለሽ?” ስል ጠየቅኋት። “…እሞክራለሁ። ካልፈለጉ ግን አላስገድዳቸውም” አለችኝ። “…ኮንዶም አለመጠቀም፣  ለኤድስ እና አባለዘር በሽታ ያጋልጣል…” ከማለቴ “ተወኝ ባክህ! ኤድስም፣ አባለዘርም በሽታ ነው። ቀን ይሰጣል። አንተ ምግብ ሳትበላ ስንት ቀን መቆየት ትችላለህ? በሽተኛ እናቴ እና ሁለት ታናናሽ ውንድሞቼ የሚጠብቁት የኔን እጅ ነው። ጊዜ የለኝም..” ብላ፣ እዚያው ትታኝ፣ የመርካቶ ጽልመት ውስጥ ገባች።

 

እኔ እስከማውቀው ድረስ፣ ጠቅላላ አሜሪካ፣ ቬጋስም ሆነ ሎስ አንጀለስ፣ 18 አመት ያልሞላቸው ልጆች፣ ለወሲብ ባደባባይ የማይታዩበት እና በዚህ እድሜ ክልል ካሉ ልጆች ጋር ወሲብ መፈጸም፣ በህግም ሆነ በሞራል የሚያስጠይቅበት አገር መሆኑን ነው! ሃያ አንድ አመት ያልሞላው ሰው መጠጥ ገዝቶ የማይጠጣበት፣ ሲጠጣ ቢገኝ፣ ሻጩም ጭምር የሚቀጣበት ህግ እና የሞራል መሰረት ያለው አገር እና ህዝብ መሆኑን ነው የማውቀው።

[1] “እልል በቅምጤ”= ደስታ በ“እልል”ታ ይገለጻል። ዋናው ደስታ ግን እንዲያው ተነስተህ ቆመህ፣ ጉልበትህ እየተንቀጠቀጠ አይደለም። ተሆነ አይቀር በ“ቅምጥህ እልል” ያልክ እንደሆን የደስታ ሁሉ ደስታ ሆነ ማለት ነው።

 

The post ለዲ/ን ኒቆዲሞስ፦ በውቀቱ ስዩም፣ ጓደኛው ተመስገንን “ከሚወዳት ልጅ ጋር አንሶላ ሲጋፈፍ ማደር …”  እንዳለበት አልመከረም! ውሸት ነው! appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ያልተጠናቀቀ ጦርነት፣ያልተቋጨ ትግል! –አገሬ አዲስ

$
0
0

Unfinished w arየዛሬ መቶ ሃያ ዓመት አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት የወጠኑት ሴራ የከሸፈበት፣በምድረ ኢትዮጵያ በአድዋ ጦር ሜዳ የጣሊያን ወራሪ ሃይል ድባቅ ተመቶ ያገራችን ነጻነት የተከበረበት የድል ቀን በመሆኑ በየዓመቱ እናከብረዋለን።የአድዋ ጦርነትና የተገኘው ድል የመጀመሪያ ሳይሆን የመጨረሻው እንደሆነ ታሪክ ይዘግባል። ሆኖም ግን የጦርነትና የወረራ መጨረሻ አልሆነም።

ከአድዋው ጦርነትና ድል በዃላ የወራሪው የጣሊያን ሃይል ሙሉ ለሙሉ ከኢትዮጵያ መሬት ሳይወጣ በኤርትራ ክፍለሃገር ለአርባ ዓመት ተንሰራፍቶ ለመኖር ሲችል ይህም ለሁለተኛው ጊዜ የወረራ እቅድ የመዘጋጃ ዕድል ፈጥሮለታል።የአድዋውን ጦር መርተው ለድል ያበቁት አጼ ሚኒሊክ በገጠማቸው የትጥቅና ስንቅ እጥረት፣በድርቅና በበሽታ መከሰት የብዙ ሕዝብ ሕይወት በማለፉና ወታደራቸውም ቀጣይ ጦርነት ለማካሄድ አቅም ስለተሳነው፣በተጨማሪም በምስራቅና ደቡብ የኢትዮጵያ ድንበርና  እንዲሁም በመሃል አገር በተፈጠረው የጠላት ሰርጎ ገብ አደጋ ምክንያት በችግር ላይ ችግር ስለተከሰተባቸው ጠላታቸውን ሙልጭ አድርገው ከቀይ ባሕር ወዲያ ሳያሶጡ  ፊታቸውን ወደ መሃል አገር ለመመለስ ተገደዋል።

ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የጠላት ወራሪ ሃይል ለዳግመኛ ወረራ የመዘጋጃ ዕድል ከፈተለት። ለአርባ ዓመታት ሲዘጋጅ ቆይቶ በአጼ ሃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ተመልሶ መላ አገሪቱን ለመውረር መንቀሳቀስ ጀመረ።በዚህ ጊዜ ቀድሞ ከነበረው ዝግጅት የላቀ አዲስ የጦር ሃይል በአየር ሃይልና ዘመናዊ መሳሪያ፣በመርዝ ጭስና ቦምብ የታገዘ ብዛት ያለው ወታደር ከአገሩ ብቻ ሳይሆን በቅኝ ግዛት ከያዛቸው አገሮች ጭምር፣ከኤርትራ፣ከሶማሊያ፣ከሊቢያ የመለመላቸውን ባንዳ ሰራዊት አሰልፎ ተንቀሳቅሶ በተለያዩ አቅጣጫዎች ጦርነት ገጠመ።ከአምላኩና ከአንድነቱ በስተቀር ዘመናዊ መሳሪያ ያልታጠቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቂት የሰለጠኑ ወታደሮችና በጣት የሚቆጠሩ ዘመናዊ ከባድ መሳሪያዎችን ይዞ ወረራውን ለመቋቋም ከመሪዎቹ ጎን ተሰለፈ።

የጠላት ሃይል እንደ እባብ እየተሳበ የተከዜን ወንዝ ተሻግሮ ትግራይ መሬት እንደገባ ንጉስ ሃይለሥላሴ እንደ ቀድሞው የአድዋ የድል ባለቤት እንደ አጼ ምኒሊክ ወታደራቸውን መርተው ማይጨው ላይ ጦርነት ገጠሙ።ብዙ ትንቅንቅና የጨበጣ ውጊያ ሳይቀር አካሂደው የጠላት ጦር በመሬት ሳይሆን በአየር ላይ ባለው የበላይነት፣  ከሚያወርደው የቦምብና የመርዝ ጭስ ጉዳቱ ስለበዛ ለመቋቋም ሳይቻል ብዙ መስዋእት ተከፍሎ የኢትዮጵያ ወታደር ለመበታተንና ለማፈግፈግ ተገደደ፤ንጉሱም ባገራቸውና በሕዝባቸው ላይ የደረሰውን በደል ለዓለም ፍርድ ለማቅረብ ለመሰደድ ተገደዱ።ያፈገፈገው የኢትዮጵያ ተዋጊና የጦር አለቆቹ የጠላትን የበላይነት አምነው ባለመቀበል የውጊያ ስልታቸውን በመቀየር በዱር በገደል የሽምቅ ውጊያ ለማካሄድ ወስነው ጫካ ገቡ።ለአምስት ዓመት በዚህ የአርበኝነት ትግል ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ  ጠላትን እንቅልፍ ነሱት። በመጨረሻም የዓለም ሁኔታ ተለዋወጠና በወራሪ የአውሮፓ መንግስታት መካከል የጥቅም ግጭት በመነሳቱ እርስ በርሳቸው መባላት ሲጀምሩ ለኢትዮጵያኑ አርበኞች ትግል ስኬታማ ውጤት አመጣላቸው።አገራቸውን ከጠላት መንጋጋ አላቀቁ።ይህም ለኢትዮጵያኑ በጣልያን ወራሪ ሃይል ላይ ሁለተኛ ድል ሆነ።

የአውሮፓ ወራሪ ሃይሎች በኢትዮጵያ ባይሳካላቸውም በሌላው የአፍሪካ፣፤የደቡብ አሜሪካ፣የኤሽያና የካሪቢያን አገሮች ላይ የዘረጉት የቅኝ አገዛዝ መረብ ሳይበጠስ ለመቆየት ችሏል።የኢትዮጵያውያን ትግልና ድል ለነዚህ አገር ሕዝቦች እንደምሳሌ በመሆን ለነጻነታቸው የሚያደርጉትን ትግል እንዲቀጥሉበት ያደፋፈራቸው ሲሆን ለማይቀረው ነጻነትም አብቅቷቸዋል።

በአድዋና በማይጨው ጦር ሜዳ የተካሄደው የነጻነት ትግልና ድልም ሆነ በየአገሩ የተካሄደው የነጻነት ትግል ዘላቂ ነጻነት አስገኝቷል ማለት አይቻልም።ምንም እንኳን አገሮች የራሳቸውን ባንዲራ ለመስቀል ቢችሉም በወራሪ የቅኝ ገዥዎች እግር የተተኩት አገር በቀል መሪዎቹ ከወራሪዎቹ የባሱ የጥቁር ፈረንሳዮች፣እንግሊዞች፣ጣሊያኖች፣ደቾች፣ ቤልጅጎች፣…ወዘተ ሆኑና አረፉት።ቃንቋቸው፣ባሕላቸው፣ ስማቸው ሳይቀር  አስተዳደራቸው ሁሉ የወራሪዎቹ  አይነት ሆነ።ሕዝብ በገዛ አገሩ ተወላጆች መከራውን ማየት ጀመረ።በቀጥታ ወረው ለመበዝበዝ ያልቻሉት አውሮፓውያን የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዛቸውን በመዘርጋት የጥቅም አጋር የሚሆኗቸውን አገር በቀል ከሃዲዎች ስልጣን ላይ እንዲወጡ  አደረጉ።በቀጥታ ወታደራቸውን በጦርነት ከማሰለፍና ከማስጨረስ ይልቅ ዓይን የጣሉበት አገር ሕዝብ በራሱ ወገኖች እየተገደለ፣አገር ወዳድ መሪዎች ከስልጣን እየተወገዱና ወደ ስልጣንም እንዳይጠጉ በማድረግ ልዩ ልዩ ዘዴ በመፍጠር  ጥቅማቸው እንዲከበር አደረጉ።በየጊዜው የማሳሳቻ እቅድ እያወጡ ሕዝቡን አወናበዱት።በዘመናችን አሁን ሰፍኖ የሚታየው የግሎባላይዜሽን(globalization) ቅምርም የዚህ የብዝበዛ ስልት አካል ነው።በህወሃት/ኢሕአዴግ የሚመራውም ስርዓት የዚሁ የወረራና የብዝበዛ አካልና የአንድ ሳንቲም ገጽ ነው።

በየአገራቱ የሚታየው ትርምስ፣ጦርነት፣ስደት፣ ድህነት ሁሉ የዚሁ የእጃዙር ቅኝ አገዛዝ  ከይሲ አስተሳሰብ የወለደው መከራ ነው።አገራት ሙሉ ለሙሉ ነጻ ሊሆኑ የሚችሉት እኛም ኢትዮጵያውያን ሙሉ በሙሉ ነጻ ሆነን መኖር የምንችለው በአገራችን ጉዳይ ላይ  ለመወሰን ስንችል፤ነጻ አገራዊ ኤኮኖሚና ፖለቲካ አመለካከት ስንከተል፤ከውጭ ተጽእኖ ስንላቀቅ፣ከሌሎች አገራት እርዳታና ዳረጎት ስንገላገል፣ያለንን የተፈጥሮ ሃብትና ጸጋ ፣ተፈጥሮ ያደለንን ለም መሬትና ወንዞች ተጠቅመን ድህነትን፣እርሃብን ድል ስንመታ ብቻ ነው ዘለቄታ ያለው ድልና ነጻነት ተጎናጽፈናል ብለን ለመናገር የምንችለው።ያ እስካልሆነ ድረስ ባንዲራ ብቻ ስላውለበለብን ነጻ ነን ማለት አይቻልም።ለዘላቂው ነጻነት በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ጠላቶች ማንበርከክ ይኖርብናል፤ያም ሊሳካ የሚችለው እንደ አደዋው ጊዜ ተባብረን፣በአንድነት ስንታገልና የተጋረጠብንን አደጋና ጠላት ስናስወግድ ነው።ያ ሲሆን ብቻ ነው አፍን ሞልቶ ነጻ ሕዝብ ነን ማለት የምንችለው።

አሁን በየአቅጣጫው የተቀጣጠለው የሕዝብ መነሳሳትና እንቅስቃሴ በጠላቶቻችንና በእጅ አዙር ቅኝ ገዢዎች ሳይጠመዘዝ በእውነተኛ ሰብአዊና አገር ወዳድ ትግል አቅጣጫ እንዲቀጥልና ለድል እንዲበቃ ነጻነትና እኩልነት አፍቃሪው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚችለውን ማበርከት ይኖርበታል።ወራሪዎችና አገልጋዮቻቸው ሕዝቡን በክልል፣በቋንቋ በሃይማኖት ለመከፋፈልና ለማዳከም የሚያደርጉትን ጥረትና ሙከራ በህብረት ተቋቁመን አሳፍረን ልንመልሳቸው ይገባናል።አለበለዚያ አገረ ቢስ ሆነን፣ከአገር ይልቅ የመንደር ነዋሪዎች ሆነን፣ እጣ ፈንታችን ከትልቅነት ትንሽነት ይሆናል።የዓለምም መሳቂያ መሳለቂያ ሆነን እንቀራለን። ከዚህ አይነቱ አደጋ ለመታደግና እንደ አደዋው ድላችን ለሌሎቹ ምሳሌ ለመሆን የዘመናችንን፣የራሳችንን አደዋ መድገም ይኖርብናል። የአባቶቻችን ታሪክ እንደምሳሌ መውሰድ እንጂ እጃችንን አጣጥፈን  እያወደሱ ብቻ መኖር ጥቅም የለውም። ሌላው በሰራው ጀግንነት መመጻደቅና መኩራትም ተገቢና ትክክል አይደለም።የሃይማኖት አባቶችም ከአቡነ ጴጥሮስ ተጋድሎ ትምህርት ሊቀስሙ ይገባል፤ ክርስቶስ ያልተሰቀለበትን የወርቅ መስቀል አንዠርግጎ በስጋዊ ድሎትና ጥቅም እየተነታረኩና አገር አጥፊ ለሆነ ስርዓት እየጸለዩ መኖር ምድራዊ ሃጢያት መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል።ወደ ህሊናቸው ተመልሰው ሌላው ቢቀር “አትግደል” “አትስረቅ” የሚለውን አምላካዊ ትእዛዝ የሚጥሰውን መንግስት ሊያወግዙት ይገባል።የእስልምና ሃይማኖት ተከታይም እግሩን ኢትዮጵያ ላይ ተክሎ ልቡን  ወደ ሳውዲ ማድረጉ የሚጎዳው መሆኑን አውቆ ትኩረቱ ለተወለደባትና መስጊድ ባቋቋመባት አገር ላይ ሰላምና መከባበር የሚኖርበትን መንገድ ቢከተል እራሱን አድኖ ሌላውንም ማዳን ይሆናል።ከአገር በላይ አገር የለምና ክርስቲያኑም ሆነ እስላሙ ከሃይማኖት በፊት ለኖረችና ወደፊትም ለምትኖር አገሩ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።መስጊድም ሆነ ቤተክርስቲያን ሊገነባ የሚችለው አገር ሲኖር ነው።ለክርስቲያኑ እየሩሳሌሙ፣ ለሙስሊሙም መካው ኢትዮጵያ አገሩ መሆን ይኖርባታል።

በምሁር ደረጃም የሚገኘው ወገን ትክክለኛ የምሁርነትን ምነነት በሚገልጸው አመለካከትና ተግባር ላይ ቢሰማራ፣ሕዝብን ከመከፋፈል ይልቅ ስለመቻቻል፣አብሮነትና አንድነት ጥቅም፣ስለደግነት በማስተማር ግንባር ቀደም ቢሆኑ አደራቸውን ተወጡት ማለት ነው።የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችም የሚያነጣጥሩት በምንም መንገድ፣በውጭ እርዳታም ቢሆን ስልጣን ላይ የሚወጡበትን ሳይሆን በሕዝብ ድጋፍና ምርጫ በስልጣን ላይ ተከብረውና ሕዝብ ወዶና ተቀብሏቸው የሚኖሩበትን ቀና አስተዳደር የሚመርጡ ቢሆን ከአድዋው ጀግኖች ባላነሰ ደረጃ ሕዝብ ሊኮራባቸውና በታሪክ ሊያስታውሳቸው እንደሚችል አውቀው አስተሳሰብና አካሄዳቸውን ሊያስተካክሉ ይገባል።ነጋዴና ሃብታም የድካሙን ውጤት በሰላም ደስ ብሎት ሊጠቀም የሚችለው ሰላም የሰፈነበት፣ሕዝብ ተስማምቶና ተደስቶ የሚኖርበት ስርዓት ሲኖር ብቻ እንደሆነ ሊያውቁት ይገባል። መሪዎች ከሕዝብ እየዘረፉ በውጭ አገር ባንክ የሚያጠራቅሙት ገንዘብ የዃላዃላ የባንኮቹ ባለንብረቶች ሲሳይ እንደሚሆን ከነሞቡቱ ሴሴሴኮ፣ከቦካሳ፣ከፊሊፒንሱ ፈርዲናንድ ማርቆስ…ወዘተ ትምህርት ሊቀስሙ ይገባል።ወይም ሕዝብ ስልጣኑን ሲረከብ በሕጋዊ መንገድ የሚያሰመልሰው እንደሚሆን በቅድሚያ ተረድተው ከአድራጎታቸው ቢቆጠቡ ለእነሱም ለቤተሰባቸውም የተሻለ ይሆናል።

ለዳግመኛ የዘመናችን፣የእኛ ለሆነው የየካቲት ድል ተባብረን እንታገል!

የጋራ ቤታችንን፣ኢትዮጵያን ከመፍረስ አደጋ እናድናት!

አገሬ አዲስ

The post ያልተጠናቀቀ ጦርነት፣ያልተቋጨ ትግል! – አገሬ አዲስ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተላለፈ የአደራ መልዕክት –“ከታሪክ ተጠያቂነት ለመዳን ከኛ የሚጠበቁ 4 ነገሮች”

$
0
0

addis-ababa-university

ይች ሀገር የኛናት የምንል ወጣቶች በሙሉ ይመለክታል:-

እኛ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ተረካቢዎች ለሀገራቸ ባእድ መሆናችን እስክመቼ?በተለይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመሆን ባአሁኑ ወቅት ከቤተሰብ እርቀን የምንገኝ ወይም ከቤተሰብ ጋ በምኖር ትምርታችን በመከታተል ላይ ያለን በሙሉ ሀገራችን ከመቸዉም በላይ የኛን ተሳትፎ የምትሻበት ወቅት መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ሰንበትበት ብሏል::

በተለይም እጃቸውን አቆላልፈው ሰልፍ በወጡ ወንድሞቻችን ላይ የደረሰዉን (እየደረሰ ያለው )ሲቃ ከኛ የተደበቀ አይደለም
ሌላዉ የአለም አቀፉ ህ/ስብ ያለዉን ርሀብ እንዲያውቅና ለሰብአዊ ዕርዳታ እንዲነሳ ሲደረግ ተሯሩጠው ማስተባበያ በመበከያ መሳሪያቸው EBC ብለዉ በሚጠሩት በሚሳፍር ሁናቴ ድራማቸዉን ሰርተው ህዝቡ መጥገቡን አበሰሩን ::

ኢትዮጵያ አድጋለች እንባላለ እድገቱ በምን ነዉ ሚመዘነዉ?በጦር መሳሪያ ክምችት ?በዎታደር ብዛት? ወይስ የህ/ሰብ ነሮ መሻሻል፣የተማረ ሰዉን ተገቢዉን ግልጋሎት እንዲሰጥና እንዲያገኝ በማድረግ?መልሱ ግልጽ ነዉ::

ለሀገር ለማሰብ የግድ የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪ መሆን አይጠበቅብንም ይለቅ አገር ዎዳድ መሆን የግድ ይጠበቅበናል እነማርታ ምሳሌ ሊሆኑን ይገባል (ማርታ የጤና ሳይንስ ተማሪ ነበረች)

ተቃውሞን የታክሲ አሽከርካሪዎችና ባለንበረቶ ጀምረዉታል እየደረሰባቸዉ ያለዉ ብሶት ጫና ከቁጥጥር ውጭ ሲሆንባቸው

ክኛ ምን ይጠበቃል ክታሪክ ተጠያቂነት ለመዳን

  1. ካሁን ጀምሮ ለሚደርሱ ማንኛዉም ሰብባዊ ጥፋት አጋርነታችንን መግለጥ
  2. የርሀብ አድማ መምታት ባላት ጨምሮ( ባማከለ ሁኔታ) ከሀገር በላይ ምንም ጉዳይ እንደሌለን በማዎቅ በተለይም በየይንቨርስቲዎች የምንገኝ የተማሪ ፖሊሶች ይህንን ጉዳይ ከግብ ይደርስ ዘንድ ጠቀሜታዉን ማስገንዘብ (መገንዘብ)
  3. በየምንኖርበት አካባቢ እውነታዉን ለማህበረሰቡ ማሳወቅ ብጅታ የተፈጠረበት ካለ መጻፍቶችን ማንበብ ምሳሌ (የመለስ አምልኮ ተመስገን ደሳለኝ) ፣(የይስማእክ ዎርቁ ተከታታይ መጻህፍትን)(የፕሮፌሰር መስፍን የታሪክ መጻህፍትን)ና የመሳሰሉትን በማየት ብጅታዎ ማስዎገድ ይችላል::
  4. በዪኒቨርስቲዎች ዉስጥ አዲስ መታወቂያ አንድን ጎሳ ከቡድን ፖሊሶች ጥቃት ለመታደግ እየተሯሯጡ ይገኛሉ በመሆኑም ይህን ጉዳይ በትኩረት እንድትከታተሉ እና ራሳችሁ እንድትጠብቁ፣መታዎቂያሰራችሁትም ብትሆኑ ጉዳዩ የተሰሳተ ጽንፍ መያዙ አዉቃችሁ ተድርጊቱ ይታቀቡዘንድ አስረዱ ተቃዎሙ ጉዳዩ የሀገር ጉዳይ ነዉ እና::

ይህን አላማ ለማስፈጸም ላንድ ወገን ወይም ማህበር የተተወ አደለም:: ይልቅ የሃገር ወዳድ ተማሪዎች እና ወጣቶች መለገጫ እንጂ:: በዚህ ዙርያ ሁሉም ሀገር ወዳድ ሃሳቡን ያስቀምጥ; ለጉደኞቹ ያጋራ (share) ያድርግ::

 

The post ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተላለፈ የአደራ መልዕክት – “ከታሪክ ተጠያቂነት ለመዳን ከኛ የሚጠበቁ 4 ነገሮች” appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live