Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የጅማ ህዝብ ተነሳ –በቀለም ወለጋ ሕዝብ በጩኸት አጋዚ በጥይት እየታገሉ ነው * 4 ሰልፈኞች ተሰውተዋል

0
0

(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት መንግስት ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ የመንግስት ጋዜጠኞችን ሰብሰበው በኦሮሚያ ክልል ሰልፍ የወጡ ነጹሃንን ካላረፉ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ቢያስፈራሩም በኦሮሚያ ክልል ግን ይህን የርሳቸውን ቃል የሚሰማ እንደሌለ በየከተማው እየተደረጉ ያሉ ተቃውሞዎች አሳይተዋል::

Jima

በቀለም ወለጋ በጊዳሚ ወረዳ በቡሪ መንደር ዛሬ በተደረገ ከፍተኛ ተቃውሞ የአጋዚ ጦር በሕዝቡ ላይ ጥይት አንዝንቦ ከ40 በላይ ሰዎችን ሲያቆስል 4 ሰዎችን እንደገደለ ለዘ-ሐበሻ የመጡ መረጃዎች አሳይተዋል:: ሕዝቡ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄው እንዲመለስ መንግስትም እንዲለቅ እየጠየቀ ባለበት ወቅት በተለይም ከቤንሻንጉል እና ከጋምቤላ አካባቢ የመጡ የአጋዚ ጦር አባላትይ ሕዝቡ ላይ ተኩሰዋል:: እነዚህ የቤንሻንጉል እና የጋምቤላ የአጋዚ ጦር አባላት አማርኛም ሆነ ኦሮሚኛ የማይነገሩ በመሆኑ የኦሮሞ ሕዝብ ምን እያለ እንደሚጮህ እንኳ የሚረዱ አይደሉም የሚሉ በስፍራው ያሉ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ሕወሓት መንግስት በምርጫ 97 ማግስት በሕዝብ ላይ የተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ወታደሮችን ከሌላ ክልል በማስመጣት የፈጸመውን ተመሳሳይ ፍጅት በኦሮሚያም እየደገመው ነው ብለዋል::

የኦሮሞ ሕዝብ ተቃሞ በጉጂም በረካ ሕዝብ በአደባባይ ወጥትቶ ዛሬም ተቃውሞውን ሲያሰማ ነው የዋለውም:: በተለም በቀንቻ ከተማ ከህፅአነት እስከ አዋቂ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያሰማ የኦሮሚያ ፖሊስ ከሕዝብ ጋር በመሆን ያለውን አጋርነት አሳይቷል:: በተለይ በዛሬው ተቃውሞ የኦሮሚያ ፖሊስ የጉጂን ሕዝብ አጅቦ እንደነበርና ከጥቃትም ሲከላከል እንደነበር የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::

tekawemo

በጅማ እስካሁን የኦሮሞ ህዝብ እንቅስቃሴ ከተጀመረ በኋላ አሳይቶት የነበረውን ዝምታ በመስበር ዛሬ በ ሻቤ ሶዶ ከተማ በዓይነቱ ልዩ የነበረ ት ዕይንተ ህዝብ ታይቷል:: በጅማ ከሕፃናት እስከ አዋቂ አደባባይ በመውጣት በስር ዓቱ ላይ ያለውን ጥላቻ ገልጾ የሕወሃት መንግስት አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ሲጠይቅ እንደነበር ምንጮቻችን አስታውቀዋል::

west welega

በሌላ በኩል በምስራቅ ወጋ ቆዶላ ከተማም እንዲሁ ሕዝቡ አደባባይ ነበር የዋለው:: እንደ ሪፖርቶች ገለጻ በምስራቅ ወለጋ በቆዳላ ከተማ በነበረው ተቃውሞ አጋዚ ሠራዊት ሕዝቡ ላይ እንዲሁ ሲተኩስ ነበር:: እነዚሁ ዱላ የያዙትና በዝማሬና የተከለከሉ የኦሮሚኛ ዘፈኖችን በመዝፈን የወጡት ተቃዋሚዎች ትግላቸው እስከሞት ድረስ እንደሆነ ሲገልጹ ነበር::

The post የጅማ ህዝብ ተነሳ – በቀለም ወለጋ ሕዝብ በጩኸት አጋዚ በጥይት እየታገሉ ነው * 4 ሰልፈኞች ተሰውተዋል appeared first on Zehabesha Amharic.


አክብሮት ለርዮት |ሳዲቅ አህመድ የላቀ ክብር የሚገባትን መምህርትና ጋዜጠኛ ርዮት አለሙን አስመልክቶ ያዘጋጀዉ ልዩ ፕሮግራም |ቢቢኤን ሬድዮ

ለኢትዮጵያ አቦ ሸማኔዎች ትውልድ ልዩ መልዕክት፡ ነጻ ሆናችሁ እንደተወለዳችሁ ሁሉ ነጻ ሆናችሁ ኑሩ!

0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም     

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

(የተመደበ፡ ለኢትየጵያ አቦ ሸማኔዎች ዓይን ብቻ)   

 2013 ወዲህ የመጀመሪያ መልዕክቴ፣

zehabesha

ይህ በሶስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔ ትውልድ ማለትም ለኢትዮጵያ ወጣቶች ለሁለተኛ ጊዜ ያቀረብኩት ልዩ መልዕክት  ነው፡፡

እ.ኤ.አ ጥር 2013 ዓመቱ የኢትዮጵያ አቦ ሸማኔ ወጣት ትውልድ ዓመት እንደሚሆን የአዲስ ዓመት መልዕክቴን ጽፌ አስተላልፌ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ “ምርጦቹ እና የብሩህ አዕምሮ ባለቤት” የሆኑትን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁትን እና ባለሙያዎችን ብቻ ያካተተ ሳይሆን በነጻነት ለመተንፈስ ተጋድሎ እያደረጉ ያሉትን ሁሉንም በአንድነት የሚቆሙ የወጣቶች ስብስብን ያቀፈ  ነው በማለት ገልጨ ነበር፡፡

የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ህወሀት) አድሎአዊ አሰራር፣ የጓደኝነት ስራ፣ ሙስና እና የሰብአዊ መብቶች ረገጣ ሰለባ ለሆኑት ለሁሉም በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩት ወጣቶች የክርክር መድረክ እንዲፈጠር ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡

እንደዚሁም ሁሉ ለኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ እና የዘ-ህወሀት የፖለቲካ እስረኞች ማለትም እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ውብሸት ታዬ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ እና ሌሎችም እንደ እነርሱ ያሉት በርካታዎቹ የሞራል መሪዎች ከማጎሪያው እስር እንዲፈቱ ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2013 አቅርቤው በነበረው መልዕክቴ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ ሀገሪቱን ከዘ-ህወሀት የጭካኔ እና አምባገነናዊ የግፍ አገዛዝ የብረት መዳፍ አደጋ ውስጥ ፈልቅቆ ሊያወጣት የሚችል ብቸኛው ትውልድ ነው በማለት አውጀ ነበር፡፡ ይህ ወጣት ትውልድ ኢትዮጵያን ከጨካኝ አምባገነኖች የእባብ መርዝ አደጋ ውስጥ ሽራ እንድትወጣ ማድረግ የሚችል ብቸኛው እና በቅጥፈት እና በሙስና ላይ የተገነባውን ይህንን የበሰበሰ እና በወታደር ኃይል የቆመ ምንም ዓይነት ኃላፊነት የማይሰማው የበከተ መንግስት አሽቀንጥሮ በመጣል ወደታሪከ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ የሚጥለው ይኸው ወጣት ትውልድ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ ይፋ ያልሆኑ የክርክር መድረኮችን በእራሳቸው መካከል ማካሄድ መጀመር እና የእራሳቸው ብሄራዊ ዕርቅ መወሰን እንዳለባቸው ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡

እንዲሁም ወጣቶች እራሳቸውን እንዲያጠናክሩ እና የእራሳቸውን የፖለቲካ ምህዳር እንዲፈጥሩ እና በጎሳ፣ በኃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በጾታ፣ በክልል እና በመደብ መስመሮች ላይ አንድ በአንድ እያነሱ እንዲነጋገሩባቸው ተማዕጽኖዬን አቅርቤ ነበር፡፡

የጾታ ልዩነቱን በመዝጋት እና የወጣት ሴቶችን ተሳትፎ ከምንጊዜውም በላይ በማሳደግ በብሄራዊ ዕርቅ ንግግሩ ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አስምሬበት ነበር፡፡ ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ወደ ስምምነት፣ እርቅ እና ግጭትን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ረገድ በእጅጉ ከወንዶች እንደሚልቁ በማህበራዊ ሳይንሳዊ መረጃዎች በተደገፈ መልኩ ለማቅረብ ሞክሬ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ውይይት እርስ በእርስ መነጋገርን ብቻ የሚያካትት አይደለም፣ ሆኖም ግን  እርስ በእርስ መደማመጥ አስፈላጊ እንደሆነ ምክሬን ለግሸ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ ብዝሀነታቸውን እንደ ጥንካሬ በመጠቀም እና በተጻራሪው ብዝሀነታቸውን ለከፋፍለህ ግዛ እና ለሽንፈት ለሚያበቃቸው እኩይ ምግባር በፍጹም ቀዳዳ እንዳይከፍቱ ተማዕጽኖ አቅርቤ ነበር፡፡

ለመሆኑ ባለፉት ሶስት ዓመታት ምን ተከናወነ?

የኢትዮጵያ አቦ ሸማኔ ወጣት ትውልድ ሙሉ በሙሉ የነቃ ለመሆኑ አምናለሁ፡፡ ጥቂት የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ በአሁኑ ጊዜ እንደምናየው በንዴት በመነሳት በአይበይገሬነት ዘ-ህወሀትን በመገዳደር እና ጉሮሮ ለጉሮሮ በመተናነቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በመንሾካሾክ እና በማጉተምተም ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ ደስተኛ አይደሉም፡፡ ለዚህም ነው በመላ ሀገሪቱ ጅቦቹን በመጋፈጥ በማጉተምተም ላይ ያሉት፡፡

ለኢትዮጵያ አቦሸማኔ ወጣት ትውልድ የእኔ አዲሱ የመገዳደር መልዕክቴ፣

የኢትዮጵያ የጉማሬው ትውልድ (በእርግጠኝነት በምርጫም ባይሆን እኔም አባል የሆንኩበት) የጨነገፈው የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔ ትውልድ እንደሆነ አምናለሁ፡፡

ጆርጅ አይቴ የአፍሪካን የጉማሬ ትውልድ እንዲህ በማለት በትክክል ገልጸውታል፣ “በምሁራዊ ጨለምተኝነት የታጠሩ እና አመክንዮአዊነት በራቀው የቅኝ ገዥዎቻቸው የተለጣጠፈ የትምህርት ዘይቤ ላይ እንደ መዥገር የተጣበቁ“ በማለት ገልጸዋቸዋል፡፡ ነጮች በጥቁሮች ላይ የሚያደርጉትን የኢፍትሀዊነት ደባ በጭልፊት ዓይን ግልጽ በሆነ መልኩ ገና ከሩቅ ያዩታል፡፡ ሆኖም ግን እነርሱ በእራሳቸው ጥቁር ዜጎች ላይ ለሚያደርጉት የበለጠ ሰይጣናዊ ለሆነው ተስፋ በሌለው መልኩ እውር ይሆናሉ…”

እኛ ኢትዮጵያውያን የጉማሬው ትውልድ አባላት በጎሰኝነት፣ በኃይማኖት ጽንፈኝነት፣ በፍርሀት እና በጥላቻ በመታወር አመክንዮአዊ በጎደለው የትምህርት ዘይቤ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀን ህሊናን በሳተ መልኩ አውዳሚ የሆነውን የፖለተካ ጎማ በማሽከርከር ላይ እንገኛለን፡፡

አሁን ለተወሰነ ጊዜ በፖለቲካ ኮማ (መንፈስ መደንዘዝ) ደረጃ ውስጥ በመግባት በድን ሆነን እንገኛለን፡፡ ያንኑ የዱሮውን ያፈጀውን እና ያረጀውን እንዲሁም ተደጋግሞ የሚነገረውን እና አሰልችውን አንድ ዓይነት መዝሙር በመዘመር ያለፉትን ሀሳቦች በመኮነን አንድ ዓይነት ነገርን በማነብነብ እናወጣለን፡፡ በማንኛውም ነገር ላይ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ከዘ-ህወሀት አሻሻ ገዳሜ ዳንስ ጋር በመሰለፍ አብረን እንሾራለን፡፡ በአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ ላይ የምናሳርፈው ተጽዕኖ ጎታች፣ ከአድራጊነት ስሜት የሚገታ፣ ራዕይ የለሽ የሚያድርግ እና ሙሉ በሙሉ ከፈጠራ ስራ የሚያኮላሽ ነው፡፡

እኛ የጉማሬው ትውልድ አባላት ለአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ ያተረፍንለት ነገር ቢኖር የውድቀት ትሩፋት፣ ተጠራጣሪነት፣ ያለመተማመን፣ ህብረት የለሽነት፣ ጥላቻ፣ የደስታ እጦት፣ ወኔቢስነት፣ ፍላጎት የለሽነት፣ ተምኔታዊነት እና በእራስ አለመተማመንን ነው፡፡

እስቲ ትንሽ እናፍታታው!

ይኸ እየተሰጠ ያለው ማብራሪያ እያንዳንዱን የኢትዮጵያን የጉማሬ ትውልድ አባላት በመውቀስ በጅምላ እራሱን በእራሱ የሚከስ የጉማሬው ትውልድ አባል ይመስላል፡፡ በእርግጥ ይህ የአንድ የጉማሬው ትውልድ አባል ግላዊ እምነት ነው፡፡ የእኔን አመልካች ጣት በሌሎቹ ላይ በምቀስርበት ጊዜ ሶስቱ ጣቶቼ ወደ እራሴ እንደሚያነጣጥሩ እየመረረኝም ቢሆን እገነዘባለሁ፡፡

በተወሰኑ ልማዶች ጥፋትን ማመን ብዙውን ጊዜ ንስሀ የመግባት ድርጊትን ያስከትላል፡፡ ይህም ማለት በቀደሙ ጊዜ የተሰራን መጥፎ ድርጊት በመልካም ነገር ለመካስ ሲባል ስህተት መሆኑን በማመን ሀጢአትን መናዘዝ እና መልካም ነገርን ለመስራት ቃል ኪዳን መግባት ማለት ነው፡፡

እንግዲህ ይህ የእራሴን ኃጢአት በመናዘዝ በቀጥታ ከኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ ጋር በመቀላቀል ለለውጥ እንዲነሱ እና የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን እንዲወስኑ ማድረግ ነው፡፡ (ኃጢያቴን በመናዘዙ ረገድ የተጋነነ የሞራል ልዕልናን እንዳሳየሁ እና ስብከት መሳይ ነገርን ያደርግሁ እንደሚመስል አምናለሁ፡፡ ሆኖም ግን እራሴን በመሻሻል ላይ ያለሁ አድርጌ እቆጥራለሁ፡፡ በጊዜ ሂደት አሻሽላለሁ፡፡)

በዚህ ዓመት በማስተላልፈው መልዕክት የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔ ትውልድ አዕምሯቸውን ክፍት በማድረግ እና ለእራሳቸው በማሰብ፣ ትክክለኛ እና ጠጣር ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንዲሁም እንደ ነጻ ወንዶች እና ሴቶች ሆነው ለህሊናዎቻቸው እንዲኖሩ ለማድረግ መገዳደር ነው፡፡

እነዚህን መገዳደሮች ለመቀመር አልበርት አነስታይን በአንድ ወቅት እንደተመለከቱት እና እንዲህ በሚለው በጣም እመሰጣለሁ፣ “አንድን ችግር ለመቅረፍ የአንድ ሰዓት ጊዜ የሚኖረኝ ከሆነ 55 ደቂቃውን ስለችግሩ በማሰብ አጠፋለሁ፡፡ በ5ቷ ደቂቃ ውስጥ ደግሞ ስለመፍትሄው አስባለሁ፡፡“ ብለዋል፡፡

አነስታይን ያስተላለፉት ዋናው መልዕክት አንድ ሰው ችግሩን ለመገንዘብ በርካታ ጊዜ የሚያጠፋ ከሆነ ለችግሩ በጣም ውጤታማ የሆነ መፍትሄን እና ውሳኔን የማምጣት ዕድሉ ከፍተኛ ይሆናል ለማለት እንደሆነ አስባለሁ፡፡ አብዛኞቻችን (ከእራሴ ጀምሮ) አምባገነኖችን ከማስወገድ እና ድህነትን ከስሩ መንግሎ በመጣል ሁሉንም የኢትዮጵያን ችግሮች ለማጥፋት መፍትሄዎች እንዳሉን የእራሴ ምልከታ አለኝ፡፡ አብዛኞቹ መፍትሄዎቻችን በግማሽ የተጋገሩ፣ ቅርብ ዕይታን የያዙ፣ የመከኑ እና በድክመት የታሰቡ ናቸው ማለት እችላለሁ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አነስታይን እንዲህ የሚል ምልከታን አድርገዋል፣ “ማሰብ ከእውቀት የበለጠ ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ እውቀት ለሁሉም ውሱን እንደመሆኑ መጠን አሁን ልናውቅ እንችላለን እናም ልንገነዘብ እንችላለን፡፡ ማሰብ ግን ዓለምን በሙሉ ያቅፋል፣ እናም ሁሉም ነገር ለማወቅ እና ለመገንዘብ ይሆናል፡፡“ ጆርጅ በርናርድ ሻው የበለጠ ውበትን በተላበሰ መልኩ እንዲህ ብለዋል፣ “ነገሮችን ታያለህ፣ እናም እንዲህ ትላለህ፣ ‘ለምን?‘ ሆኖም ግን ስላልነበሩ ነገሮች አልማለሁ፣ እናም እንዲህ እላለሁ፣ ‘ለምን አይሆንም?’“ እንግዲህ እየተናገርኩ ያለሁት ስለእንደዚህ ዓይነቱ ማሰብ ነው፡፡

አነስታይን ማለት ፈልገው የነበረው የሰው የወደፊት አቅም እና ዕድል በእርግጠኝነት በምናውቀው ነገር የሚወሰን አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ከዚህም በተጨማሪ ልናስበው በምንችለው ነገር ነው የሚወሰነው፡፡ እንዲህ የሚለውን ታላቅ ቆንጆ የማሰብ ጥያቄን ጠይቀው የነበሩት አነስታይን ናቸው፣ “በህዋ ላይ በብርሀን ፍንጣቂ እየጋለብኩ ብሄድ ምን ይፈጠራል?“ ይህንን ነገር እስቲ አስቡ!!!

የኢትዮጵያን የአቦ ሸማኔ ወጣት ትውልድ በህዋ ላይ አቋርጦ በሚሄድ የብርሀን ፍንጣቂ እንዲጋልቡ አልማጸንም፡፡

በእርግጠኝነት እንዲበሩ ነው የምፈልገው፡፡ በባርነት ውስጥ ከሚዘፍቅ የጎሳ ፖለቲካ በርረው እንዲያመልጡ ነው የምፈልገው፡፡ ከአምባገነንነት በነጻነት ብረሩ፡፡ ከሙስና እና ከሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ነጻ ሁኑ፡፡

ብዙም ሳይርቅ ዘ ኢኮኖሚስት የተባለው መጽሔት ለበርካታ ዓመታት በአዕምሮየ ውስጥ ሲብላላ የቆየውን ጥያቄ ጠየቀ፡፡ እንዲህ የሚለው ያ ጥያቄ እንደ መብረቅ መታኝ፣ “ኢትዮጵያውያን በእርግጠኝነት ነጻ ቢሆኑ ኖሮምንድን ይሆን ነበር?

ዘ ኢኮኖሚስት እራሱ የጠየቀውን ጥያቄ እራሱ እንዲህ በማለት መለሰው፡ “መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብበነጻነት እንዲተነፍስ ቢያደርግ ኖሮ ይበሩ ነበር፡፡“

የኢትዮጵያን ህዝቦች በነጻነት ለመተንፈስ ያለመቻል ችግር ለ55 ደቂቃዎች ያህል አሰብኩ፡፡ ከዚያም ስለመፍትሄው በማሰብ 5 ደቂቃዎችን አጠፋሁ፡፡

“ብረሪ ኢትዮጵያ፣ ብረሪ…የአቦ ሸማኔ ወጣት ትውልድ ብረሩ፣ ወደ ሰማይ ከፍ ብላችሁ ብረሩ…“ በሚለው ትችቴ ላይ የሀሳብ በረራን አከናውኛለሁ፡፡

ኢትዮጵያውያን መብረር የሚችሉ ቢሆን ኖሮ ለመሞት ወደ ባህር አቅዋርጠው አይሄዱም ነበር እላለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ባሮች ለመሆን ወደ መካከለኛው የአረብ ሀገሮች አይሄዱም ነበር፡፡ ደም ለጠማቸው አሸባሪዎች ሰለባ ለመሆን በረሀዎችን አቋርጠው አይሄዱም ነበር፡፡ ወደ ስደት ሀገር አይሄዱም ነበር፡፡ የሚበሩ ቢሆን ኖሮ እንደ አፍሪካ ተሙለጭላጭ አሳ እንደ ባህር ወፍ አይገለባበጡም ነበር፡፡ ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው ወደ ሰማይ ከፍ አድርገው ያነሳሉ፣ እናም ይበራሉ፡፡ እንደ ዘማሪዎቹ ትንሽየ ወፎች ክንፎቻቸውን በፍጥነት ያርገፈግፋሉ፡፡

ለዚህም ነው በዚህ ዓመት ከኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ ጋር ቀጣይነት ባለው መልኩ ለመቀላቀል እና አብሮ ለመጓዝ ዓላማ አድርጌ የተነሳሁት፡፡

በክንፎቻቸው ወደ ላይ ወደ ሰማይ ከፍ ብለው እንዲበሩ እፈልጋለሁ፡፡ ሁሉንም ትክክለኛ እና ጠንካራ ጥያቄዎችን ኢትዮጵያን ስለገጠሟት ህልቆ መሳፍርት ለሌላቸው ችግሮች ከብዙ አቅጣጫ ጥያቄዎችን እንደጠይቁ እፈልጋለሁ፡፡ በሀሳቦቻቸው በረራ እንዲያደርጉ እፈልጋለሁ፡፡ ከጎሳ ፖለተካ፣ ከኃይማኖት ጽንፈኝነት እና ከጥላቻ ነጻ የሆነች አዲሲቷን የእራሳቸው ፍጡር ኢትዮጵያን እንዲያስቡ ግፊት አደርጋለሁ፡፡ የእራሷ እና የጎረቤቶቿ ሰላም የተጠበቀ ኢትዮጵያን እንዲያስቡ እፈልጋለሁ፡፡ ከጭቆና እና ከወሮበላ ዘራፊነት ነጻ የሆነች ኢትዮጵያን እፈልጋለሁ፡፡ ተምኔታዊት ኢትዮጵያን እንዲያስቡ እፈልጋለሁ፡፡

እያንዳንዱ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ “የኢትዮጵያ ጥልቅ አሳቢ” –መሀንዲስ፣ ዕቅድ ነዳፊ፣ ፈጣሪ፣ ለኪ መሀንዲስ፣ ህንጻ ገንቢ እና ዜጎቿ ስለጎሳ ማንነታቸው ሳይሆን ስለእያንዳንዳቸው ሰው የመሆን እውነታነት፣ ዕኩል ዕድል ስላለባት ኢትዮጵያ፣ ከሙስና፣ ከጭቆና እና ከወሮበላ ዘራፊነት ነጻ ስለሆነች ኢትዮጵያ እንዲሟገቱ ጥረት እንዲያደርጉ እፈልጋለሁ፡፡

“በጠርሙስ ውስጥ ያለ መልዕክት” የሚለውን ተመሳስሎ በመጠቀም የእኔን መልዕክት (ትችቴን) በጠርሙስ ውስጥ ከትቸ ኢንተርኔት እየተባለ በሚጠራው ባህር ውስጥ እንዲለቀቅ በማድረግ ሁሉም የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ በአጋጣሚ እንዲያገኘው እና የጠርሙሱን ክዳን በመክፈት እንዲያነበው አደርጋለሁ፡፡

የእኔን መልዕክት ለማንበብ ስንቶቹ እንደሚያገኙት አላውቅም፡፡ በርካታዎቹ እንደሚያነቡት ግን ተስፋ አለኝ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ጥቂቶች ከእኔ ጋር ይስማማሉ፣ ሌሎች ግን አይስማሙም፡፡ ስምምነት ወይም ደግሞ አለመስማማትን አልፈልግም፡፡ የእኔ መልዕክት ዋናው ዓላማው የኢትዮጵያ ወጣቶች ትክክለኛ ጥያቄዎችንእንዲጠይቁ፣ እውነታውን (የእራሳቸውን እውነታለማወቅ እንዲደፍሩ እና አዲስ ሀገር እንዲያስቡየኢትዮጵያን ወጣቶች ማደፋፈር ነው፡፡

የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔ ወጣት ትውልድ፡ ነጻ ሆናችሁ ተወልዳችኋል፣ ሆኖም ግን ነጻ ሆኖ ለመኖር ከጎሳፌዴራሊዝም እግረ ሙቆች አዕምሯችሁን ነጻ ማድረግ አለባችሁ፡፡ 

ጥያቄው፡ የጎሳ ፌዴራሊዝም ምንድን ነው?

የዘ-ህወሀት ህገ መንግስት መግቢያው እንዲህ የሚል ለዚህ የተዘጋጀ መልስ አለው፡ “እኛ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና የኢትዮጵያ ህዝቦች…“ የሚከተሉትን ለመፈጸም ህገመንግስቱን አርቅቀን ጽፈናል፡

1ኛ) ብሄር ብሄረሰቦች የእራሳቸውን መብት መወሰን እስከ መገንጠል ለማስከበር፣

2ኛ) የብሄር ብሄረሰቦችን የግዛት ልዩነት ለማረጋገጥ፣ ስለሆነም ከእራሳችን ከበለጸገ እና የሚያኮራ የባህል ውርስ ጋር አብረው ለመኖር፣

3ኛ) ለዘመናት ፍትሀዊ ያልሆነ ግንኙነቶችን ለማስተካከል፣ እና

4ኛ) እንደ አንደ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለማሳለጥ፡፡ (ከዚህም በተጨማሪ አንቀጽ 39ን ይመልከቱ፡፡)

የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ የዘ-ህወሀትን የጎሳ ፌዴራሊዝም ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ስላለበት ሁኔታ ተጨባጭ መረጃ እና አባባሌን ሊደግፍ የሚችል ማስረጃ በማቅረብ የክርክር ጭብጤን አቀርባለሁ፡፡

የክርክር ጭብጤ ፍሬ ነገር ማጠቃለያ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡ “የጎሳ ፌዴራሊዝም የኋህ እና አስመሳይ የሚመስል ስያሜን በመያዝ በ21ኛው ክፍለ ዘመን አፍሪካ አዲስ እና የተሻሻለ የጥቂት የነጮች የበላይነት የተንጸበረቀበት የአፓርታይድ ቅጅ ነው፡፡ የዘ-ህወሀት ክልል በዘር ላይ ለተመሰረተው የአፓርታይድ ባንቱስታን ዘመናዊ ትርጉም ነው፡፡ የጥቂት የነጮች የአፓርታይድ መንግስት በደቡብ አፍሪካ ባንቱስታንስን የፈጠረ ሲሆን ዋናው ዓላማቸው በዘር፣ በቋንቋ፣ በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ፣ በጎሳ፣ በባህል፣ ወዘተ ላይ መሰረት ባደረገ መልኩ ለደቡብ አፍሪካ ጥቁር ህዝቦች እራሳቸውን በእራሳቸው እንዲያስተዳድሩ በማለት የተዘጋጀ ነበር፡፡ የመጨረሻው ዋናው ዓላማ ባንቱስታንስ አንድ ቀን የእራሳቸው ሀገር እንደሚኖራቸው እና (የእራስን ዕድል በእራስ የመወሰን) ነጮችም እንደዚሁ የእራሳቸው ሀገር እንደሚኖራቸው በሚያስገርም ሁኔታ በሀገሪቱ ውስጥ አሉ የተባሉትን ምርጥ ለም መሬቶች ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረው ነበር፡፡“

ክልል የሚለው የአማርኛው ቃል ከጎሳ ፌዴራሊዝም ትርጉም አንጻር በአንድ አካባቢ ያለን መሬት የሚገልጽ እና ለልዩ ጠቀሜታ እና የቡድን አባላትን አስተዳደር ለማሳለጥ ተመሳሳይ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ባህል፣ወዘተ የሚጋሩ ህዝቦችን የያዘ ነው፡፡ ክልል የታጠረ፣ የተወሰነ ወሰን፣ ግዛት እና የመሬት ስፋት ያለው መሆኑን ይገልጻል፡፡ ዘ-ህወሀት የማያቋርጥ የመልክዓ ምድር ልዩነትን ለመፍጠር እና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ልዩነትን በመፍጠር ህዝቦችን ብሄሮች እና ብሄረሰቦች በሚል ፈሊጥ እንደ ከብት መንጋ በአንድ በረት ውስጥ ለማጎር ዋና ዓላማው አድርጎ በመነሳት የጎሳ ፌዴራሊዝሙን ቀየሰ፣ ነደፈ፣ ፈጠረ፣ አዋቀረ እናም ረቂቅ ካርታውን ሰርቶ አወጣ፡፡

የኢትዮጵያን ህዝቦች በቡድን፣ በቋንቋ፣ በባህል እና በክልላዊ ቡድኖች በህገ መንግስታዊ ማዕቀፍ በመከፋፈል ዘ-ህወሀት ለዘላለም እና ሊመለስ በማይችል መልኩ የማህበራዊ ትስስሮችን ለማጥፋት እና የመቻቻልን፣ የፍቅርን እና የመግባባትን ክሮች ለመበጣጠስ እና ለዘመናት አንድ ሆኖ የኖረውን የኢትዮጵያን ህዝብ ለመከፋፈል የተሰራ የሸፍጠኞች ዕኩይ ምግባር ነው፡፡

አንቀጽ 39 እየተባለ በሚጠራው ስር የዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም የመጨረሻ ዓላማው ኢትዮጵያን በጎሳ ለመከፋፈል እና በግንብ ላይ በቋፍ ላይ የተቀመጠች እና በቀላሉ የምትወድቅ የሚለውን ተረት ሆኖ ይታያል፡፡ ሁሉም የንጉሱ ፈረሶች እና የንጉሱ ሰዎች አጭሩን ፍጡር እንደገና አንድ ሊያደርጉት አይችሉም፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ኢትዮጵያ ከክልል ህንጸ ላይ በምትወድቅበት ጊዜ ዘ-ህወሀት ይፈጠራል፣ የንጉሱ ፈረሶች እና ሰዎች ጀርባዋን አንድ ለማድረግ የሚጥሩት አይደሉም፡፡ ይህንን የሚያደርጉት በአምላክ ፈቃድ የተነሳሱት የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ አባላት ናቸው!

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በጣም ከባድ የሆነው የህልውና ጥያቄ ችግር (በኢትዮጵያ ውስጥ የሁሉምማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እናት የሆነውያለምንም ጥያቄ የጎሳ ፌዴራሊዝምእንደሆነ አምናለሁ፡፡

በእጅ ላይ ያሉት አምስት የተለያዩ ጣቶች በአንድ ላይ ተሰባስበው ወደ መዳፋችን መሀል በመምጣት ጭብጥ ሲሰሩ እና ቡጢን ሲመሰርቱ ጣቶቹ ብቻ ተነጣጥለው ለየብቻ ሲሆኑ የነበረበት ሁኔታ ከቡጢው በጣም ያነሰ ኃይል ብቻ እንደሚኖራቸው ዘ-ህወሀት ተገንዝቦታል፡፡ ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያ አምስት ጣቶች በአንድነት እንዳይሰለፉ እና በዘ-ህወሀት ፊት ጠንካራውን ቡጢን እንዳይመሰርቱ እና ጣቶችን ለየብቻ በታትኖ ለብቻው ሀገሪቱን እንደብረት ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ ሲገዛ ለመኖር እንዲመቸው የጎሳ ፌዴራሊዝምን ህገመንግስታዊ አድርጎታል፡፡

የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ የዘ-ህወሀትን የጎሳ ፌዴራሊዝምን ለመቀበል ከመፈለጋቸው በፊት ስለስርዓቱ ምንነት በጥሞና መገንዘብ፣ መገምገም እና መወሰን አለባቸው፡፡

ከምንም በላይ በመጀመሪያ ደረጃ የአቦ ሸማኔው ትውልድ ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ላይ ስላለው የመሰረት ድንጋይ ታሳቢዎች ላይ መስማማት አለመስማማታቸውን ማወጅ እንዳለባቸው ለመጠየቅ እፈልጋለሁ፡፡

ታሳቢ ቁጥር 1 የኢትዮጵያውያን ብሄራዊ የሚባል ነገር የለም ምክንያቱም ኢትዮጵያ የብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ስብስብ ናት፡፡ ዘ-ህወሀት ኢትዮጵያ እየተባለች በምትጠራ ምትሀታዊ መሬት ላይ በመቆየት ወቅቱን ጠብቆ ወደ ጎሳ መበታተን ላይ የሚወስድ አደገኛ የጥፋት ስርዓት በመዘርጋት በወጥመድ ውስጥ አስሮ በመያዝ የውሸት የእዩልኝ እመኑልኝ የብሄሮች እና የብሄረሰቦች ኮንፌዴሬሽን መስርቶ በማጭበርበር ላይ ይገኛል፡፡ ሁሉም በአጠቃላይ ሲታይ ከእያንዳንዱ ድምር ውጤት አይበልጥም፣ ምክንያቱም ክፍልፋዮቹ ዋናውን ትልቁን በፍጹም አይሆኑምና፡፡

የዘ-ህወሀት ህገመንግስት ታሪካዊ ኢፍትሀዊነቶችን ትክክለኛ አድርጎ በማቅረብ እራሱን መሳሪያ አድርጎ አቅርቧል፡፡ ብሄሮችን እና ብረሰቦችን የእራስን እድል በእራስ መወሰን በሚል ታሪካዊ ኢፍትሀዊነትን በማካተት መሳሪያ አድርጎ አቅርቧል፡፡ ብሀሮች እና ብሄረሰቦች ለእያንዳንዳቸው የፈንጅ ሳጥን በመስጠት ለብዙሀን እልቂት እራሳቸውን የኒኩሊየር መሳሪያ አስታጥቋል፡፡ እናም መላዋን ሀገሪቱን ወደ ትናንሽ ቁርጥራጭ አገዛዞች በመከፋፈል በተግባር እያበጡ ይገኛሉ፡፡

ታሳቢ ቁጥር 2 የኢትዮጵያ ባህል ፍጹም የለም፡፡ በእራሱ የቆመ እና ምንም ዓይነት የጋራነት በሌለው መልኩ የብዙህን ባህሎች አሉ፡፡ በዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም ፍልስፍና መሰረት የአንድነት በልዩነት አጠቃላይ መሰረተ ሀሳብ ብዝሀነትን በልዩነት፣ በጥላቻ እና ዘገምተኛ ምላሽን በመስጠት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

ታሳቢ ቁጥር 3 የኢትዮጵያ ታሪክ የሚባል ነገር የለም፡፡ ታሪክ የሌለው ህዝብ ያለፈ ህዝብ እና ወደፊትም የሚኖር ህዝብ እንደሌለ ዓይነት ነው፡፡ የዘ-ህወሀት ጭንቅላት የነበረው እና አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በ1993 በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ እንዲህ ብሎ ነበር፡ “ኢትዮጵያ የ100 ዓመት እድሜ ብቻ ነው ያላት፡፡ ከዚህ በተለየ መልክ የሚያቀርቡ ሰዎች ካሉ እራሳቸውን በትረካ ውስጥ የዶሉ ናቸው፡፡“ እንደ ዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም የብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ታሪክ ብቻ ነው ያለው፡፡

ታሳቢ ቁጥር 4 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ማንነት የለም፡፡ ብሄራዊ ማንነት አንድ ሰው ለአንድ መንግስት ወይም ደግሞ ለአንድ ብሄር የእኔነት ስሜት የሚንጸባረቅበት ሁኔታ ነው፡፡ ብሄራዊነት እንደ አያያዥ ጠቅላይ ሆኖ፣ ይህም መገለጫው ልዩ በሆኑ ልማዶች፣ ባህል፣ ቋንቋ እና ፖለቲካ የሚገለጽ ነው፡፡

እኔ እስከማውቀው ድረስ ኢትዮጵያውያን ጎሳቸውን ለአገዛዙ ባለስልጣኖች እንዲያሳውቁ በህግ የተገደበባቸው ህዝቦች ኢትዮጵያውያን ብቻ ናቸው፡፡ የህዝብ አገልግሎትን ለማግኘት ሲባል አንድ ሰው ጎሳውን እንዲናገር የሚገደድበት ሁኔታ ታላቅ ስድብ፣ ታላቅ ውርደት ሊሆን አይችልምን?

የእንግሊዝ ዜጎች የእንግሊዞችን ስሜት እንደሚያንጸባርቁ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ የፈረንሳይ ህዝቦች የፈረንሳዮች ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ለብራዚላውያን፣ ለህንዳውያን፣ ለግብጻውያን እና ወዘተ አንድ አይነት ነው፡

የአሜሪካ ህዝቦች የአፍሪካ እና የአሜሪካ፣ የፖላንድ፣ የአሜሪካን፣ የጃፓን አሜሪካን እና የመሳሰሉትን ስሜት ከመያዛቸው በፊት አሜሪካውያንነት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡

በደፍጣጮቹ የዘ-ህወሀት ጫማ ስር ሆኖ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የኢትዮጵያዊነት ስሜት ሊሰማቸው ይችላልን?

እንዲያው ሌላው ቢቀር ኦሮሞ ኢትዮጵያውያን፣ አማራ ኢትዮጵያውያን፣ ትግራይ ኢትዮጵያውያን፣ ወዘተ የሚል ስሜት ሊሰማቸው ይችላልን?

ወይም ደግሞ ከብሄራዊነታቸው ውጭ፣ ሰው ከመሆናቸው ውጭ ስለ ጎሳቸው ሊያስቡ ይችላሉን?

ታሳቢ ቁጥር 5 ለብሄራዊ ማንነት ምልክትነት፣ ለክብር እና ለአርብኝነት ሊውል የሚችል የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የለም፡፡ ከባንዲራ ጋር በተያያዘ መልኩ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ በአንድ ወቅት ዘ-ህወሀት በባንዲራ ላይ ስላለው አቋም ተጠይቆ እንዲህ የሚል ተደጋጋሚ ምላሽ ሰጥቶ ነበር፣ “የኢትዮጵያ ባንዲራ ጨርቅ ነው፡፡“

አብዛኞቹ አሜሪካውያን ለባንዲራቸው ክብር እና ኩራት ይሰጣሉ፡፡ ባንዲራቸውን የጥንት ዝና የሚል ቅጽል ስም ሰጥተዋል፡፡ በአብዛኛው በህዝብ፣ በስፖርት እና በአርበኝነት አጋጣሚዎች የጥንት ዝናቸውን ለማሳየት “በጠቃጠቆ ኳክብት ውበት ያማርሽው“ እያሉ ይዘምራሉ፡፡ በመጨረሻዎቹ ሶስት የግጥም ስንኞች ላይ እንዲህ እያሉ ይዘምራሉ፡ “ የእኛ ዓላማ ይህ መሆን አለበት-እግዚአብሄር የእኛ ታማኝ አምላክ ነው፡፡ ባንዲራዋ በነጻው መሬት እና በጀግኖቹ ቤት በኳክብት ጠቃጠቆ በመዋብ በድል አድራጊነት ትውለበለባለች፡፡“ ይኸ ነው እንግዲህ በዋናነት ለአብዛኞቹ አሜሪካውያን ከየትኛው የዓለም ማዕዘን ቢመጣም ወይም ደግሞ ጥንታውያን ቀደምቶቻቸው ከየትም ይምጡ አሜሪካውያን ቁብ አይሰጡትም፡፡

በተመሳሳይ መልኩ አረንጓዴ፣ ብጫ እና ቀይ እንዲሁም በመካከሏ ላይ ሰማያዊ መደብ ባላት ሀገር ውስጥ ኢትዮጵያውያን አንድ ዓይነት ስሜት ሊኖራቸወ ይችላልን? ኢትዮጵያ ለምንድን ነው የነጻነት መሬት እና የጀግኖች መጠለያ የማትሆነው? በዚህ ጉዳይ ላይ አሜሪካኖች ብቻ ነው የጠቅላይነት መብት ያላቸው? ኢትዮጵያ እኮ የጀግና አገር ነበረች!

ዘ-ህወሀት በባንዲራቸው መካከል ላይ ኮከብ ያስቀምጣሉ፡፡ የኮከብ ምልክትነት አስፈላጊ የሆነ የዓለም መልክት ነው፡፡ የኮከብ ምልክቱ በውስጡ ያለበት ባንዲራ በየትኛውም ሀገር አይገኝም፡፡ ለነገሩ የነሱ የባንዲራ ኮከብ በዓለም የሚታወቀው የጭለማው ንጉስ (ዳቢሎስ) ተከታዮች ብቻ ነው:: ወይ ጉድ!

ታሳቢ ቁጥር 6 የኢትዮጵያ ህልም የሚባል ነገር የለም፡፡ ያለው የዘ-ህወሀት የሌሊት ቅዠት ብቻ ነው፡፡ ዘ-ህወሀት ኢኮኖሚውን፣ ፖለቲካውን እና ማህበረሰቡን ተቆጣጥሮታል፡፡ ማንም ቢሆን አየር መተንፈስ አንክዋን ያለ ዘ-ህወሀት ፈቃድ አይችልም፡፡ ማንም በቅዠት ህልም ሊያልም አይችልም!

የዘ-ህወሀትን የጎሳ ፌዴራሊዝም በአሁኑ ጊዜ እንደ ዘመናዊ አፓርታይድ ለመገንዘብ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ የአፓርታይድን ህጎች ማጥናት እና ባንቱስታንስ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንዴት እንደመጡ መገንዘብ አለበት፡፡ ዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝምን ከአፓርታይድ የጨዋታ መጽሀፍ የተኮረጀ ነው፡፡ በእርግጥ የጎሳ ፌዴራሊዝም የደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ መንግስት መገለጫ ነው፡፡

በዚህ ጽሁፍ ላይ የእኔ ዓላማ በአፓርታይድ ህጎች ላይ እና በዘ-ህወሀት አዋጆች መካከል ያሉትን ተመሳሳይነቶች እና ልዩነቶችን ነቅሶ በማውጣት ለማሳየት አይደለም፡፡ አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ በቀላሉ እና በደስታ ማድረግ እችላለሁ፡፡ ሆኖም ግን ልክ አሁን ዘ-ህወሀት በአትዮጵያ ውስጥ ፍጹም በሆነ መልኩ የሀገሪቱን መሬቱ ተቆጣጥሮት እንደሚገኘው ሁሉ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የጥቂት ነጮች መንግስት የደቡብ አፍሪካን ብዙሀን ጥቁር ህዝብ በቁጥጥሩ ስር በማድረግ እና ፍጹም በሆነ መልኩ አኮኖሚውን በቁጥጥሩ ስር በማድረግ የተጠኑ እርምጃዎችን ይወስድ እንደነበር ቀላል የሆነውን ነጥብ ለማሳየት ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ1995 የጸደቀው የዘ-ህወሀት ህገ መንግስት እንዲህ በማለት ያውጃል፣ “የገጠር እና የከተማን መሬት እንዲሁም ሁሉንም የተፈጥሮ ሀብቶች የመያዝ መብት ብቸኛ ለኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝቦች የተተወነ ነው፡፡ መሬት የብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የጋራ ሀብት ነው፡፡ ስለሆነም አይሸጥም፣ አይለወጥም፡፡ (አንቀጽ 40 (3)፡፡)“

መንግስት የገጠር እና የከተማን መሬት በብቸኝነት የመያዝ መብት ካለው ግልጽ የሆነው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነው፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛ የመንግስትነቱን ስልጣን ተቆጣጥሮት የሚገኘው ማን ነው?

ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስትነቱን ስልጣን በብቸኝነት በመያዝ እየዘወረው ያለው ማን ነው?

እ.ኤ.አ በባንቱ የ1993 ድንጋጌ (የመጀመሪያው የኗሪዎች የመሬት ድንጋጌ [የ1913 ድንጋጌ ቁጥር 27] የነጭ ሰፋሪዎች ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ እንደምታ የሚያስከትለውን የደቡብ አፍሪካን ብዙሀን ጥቁር ህዝቦች የመሬት ባለቤትነት መብትን በመንፈግ የገባርነት የመሬት ስርዓትን ፈጥሮ ነበር፡፡ የባንቱ የመሬት አዋጅ በአፓርታይድ ስር የአካባቢ መንግስት እና አስተዳደር በመፍጠር የተለየ ልማትን በመዘርጋት የደቡብ አፍረካን መንግስት ለተለያዩ ኗሪዎች በመከፋፈል የጭቆና አገዛዙን ቀጠለ…አዋጁ ብዙሀኑን የደቡብ አፍሪካን ጥቁር ህዝብ መሬት የመያዝ መብት ሙሉ በሙሉ ነጠቀ፡፡

የባንቱ ባለስልጣኖች የ1951 ድንጋጌ (የጥቁሮች ባለስልጣኖች የ1951 ድንጋጌ) ጥቁር ህዝቦችን ወደተከለሉላቸው አካባቢዎች እንዲጣሉ በማድረግ የጎሳ፣ የክልል እና የግዛት ባለስልጣኖችን ፈጠረ፡፡ ይህ ድንጋጌ በተከታይነት የባንቱ ዜጎች የመኖሪያ ቦታን ድንጋጌ እ.ኤ.አ በ1970 በማዘጋጀት (የጥቁር መንግስታት ዜጎች ድንጋጌ እና የብሄራዊ መንግስታት ድንጋጌ 1970) የባንቱ ኗሪዎችን የህግ ደረጃ የሚለውጠውን እና የባንቱስታንቶችን የዜግነት ተጠቃሚነት እንደ ደቡብ አፍሪካዊነት ፍጹም በሆነ መልኩ በመከልከል የተዘጋጀ ነበር፡፡ እነዚህ ህጎች በጥቁር የደቡብ አፍሪካ ህዝቦች ንቅናቄ ላይ አሳሪ የሆኑ የክልከላ ህጎችን ጣሉ፡፡ እነዚህ ህጎች ከዚህም በተጨማሪ ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን የአፍሪካን ብዙሀን ህዝብ በመወከል ድምጽ የመስጠት መበት እና የመንግስትን እንቅስቃሴ በአጠቃላይ በብቸኝነት በመያዝ ማረጋገጥ ፈለጉ፡፡

እ.ኤ.አ የ1950 የቡድን የአካባቢ ድንጋጌዎች (እ.ኤ.አ በ1966 እንደገና የጸደቁት ድንጋጌዎች) ደቡብ አፍሪካን ለነጮች እና ለጥቁሮች በማለት ወደተለያዩ አካባቢዎች በመከፋፈል መንግስት ለጎሳ እና ለዘር ቡድኖች ሲባል ካልተመደቡባቸው አካባቢዎች በኃይል ማበረር ጀመረ፡፡ በዚህ ድንጋጌ ስር ማንም በተሳሳተ ቦታ ሲኖርየተገኘ ሰው ወደ ቡድናዊ መኖሪያ ቦታው/ቦታዋ ይወሰዳል/ትወሰዳለች፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ህጉ በደቡብ አፍሪካ በማንኛውም ቦታ አፍሪካውያንን ከመሬት ባለቤትነት እና የፖለቲካ መብቶች ሁሉ ይከለክላል፡፡ በዚህ ህግ አማካይነት ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ህዝቦች ለጉዳት ተዳርገዋል፣ እንደዚሁም ደግሞ በኃይል እዲጋዙ እና በባንቱስታንስ ቡድኖች እንደ ከብት መንጋ በአንድ በረት እንዲታጎሩ ተደርገዋል፡፡

የክልላዊነት ፍልስፍና የአፓርታይድን ባንቱስታኒዝም በርካታ መገለጫዎች ይጋራል፡፡

በአንቀጽ 39 እና በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ የይስሙላ ፓርላማ በጸደቁት ሌሎች ህጎች መለስ ልክ አፓርታይድ በደቡብ አፍሪካ የባንቱ (ጥቁሮች) ባለስልጣኖች ድንጋጌን እ.ኤ.አ በ1951 እንደመሰረተ ሁሉ እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ የጎሳ መንደሮችን መሰረተ፡፡ አንቀጽ 39 እንዲህ ይላል፣ “ብሄሮች ብሄረሰቦች ወይም ህዝቦች በዚህ ህገ መንግስት የጋራ ባህል ወይም ደግሞ ተመሳሳይ ልማዶች፣ የጋራ ቋንቋዎች የጋራ እምነቶች ወይም ተመሳሳይ ማንነቶች እና ማን በከፍተኛ ሁኔታ በግዛቱ ላይ የመቆጣጠር ኃይል እንደሚኖረው በግልጽ ያስቀምጣል፡፡“ ሁሉቱም ፍልስፍናዎች በተከለሉት የጎሳ ቡድኖች ላይ ትኩረት በማድረግ አንድ ዓይነት ቋንቋ ያላቸው ህዝቦች የራስ ገዝ አስተዳደሮች በሚል ፈሊጥ በአንድ አካባቢ እንዲሰፍሩ አደረጉ፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2012 “አረንጓዴ ፍትህ ወይም የጎሳ ኢፍትሀዊነት“ በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት የጎሳ ፌዴራሊዝም ዋና ቀማሪ እና አድራጊ ፈጣሪ መሀንዲስ የነበረው እና አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በእራሱ ቃላት ዘመናዊ የአፓርታይድ ስርዓትን እያራመደ መሆኑን ግልጽ አድርጓል በማለት በማስረገጥ ተናግሬ  ነበር፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2012 አምባገነኑ መለስ እራሱ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎችን ከደቡብ ኢትዮጵያ እንደባረሩ እና እንዲጋዙ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ የእራሱን ዕኩይ ድርጊቶች ምክንያታዊ ለማድረግ “ከአማራ ከምስራቅ ጎጃም የመጡ አማራ ሰፋሪዎች“ እና በወንጀለኝነት ደን እየመነጠሩ የሚኖሩ መሬት ተቀራማቾች ናቸው ነበር ያለው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖርን ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ በህገወጥ መልክ መሬትን የያዘ ብሎ በመፈረጅ በዘረኝነት ለማጥቃት ሲሞከር ያቅለሸልሸኛል፡፡ (የመለስ ዜናዊን ቨዲዮ ለመመልከት እዚህ ጋ ይጫኑ)፡፡

…በታሪክ አጋጣሚ ባለፉት አስር ዓመታት ከምስራቅ ጎጃም የመጡ በርካታ ህዝቦች-ወደ 30,000 የሚሆኑ ሰፋሪዎች (ህገወጥ) በደቡብ ኢትዮጵያ በቤንች ማጂ ዞን ሰፍረው ነበር፡፡ በጉራ ፈርዳ ውስጥ 24,000 ሰፋሪዎች ነበሩ፡፡ አካባቢው በደን የተሸፈነ በመሆኑ ምክንያት በርካታ ህዝብ በዚያ አካባቢ አይኖርም፡፡ ሆን ተብሎ ለዓላማቸው ማስፈጸሚያ በሚመች መልኩ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ጉራ ፈርዳን ትንሿ ምሽራቅ ጎጃም እያሉ ይጠሯት ነበር፡፡ ያ ምንም ዓይነት ችግር የለውም፡፡ በቤንች ማጂ ዞን ሊታረስ የሚችል መሬት አለ፣ እናም ይህንን ስራ ሊሰሩ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ፡፡ እያንዳንዱ አሸናፊ ነው፣ ማንም ተሸናፊ አይሆንም፡፡ አንድ ችግር ብቻ አለ፡፡ ህገወጥ ሰፋሪዎች ስራውን እየሰሩ ያሉት በተበታተነ መልኩ ነው፡፡ ህገወጥ ሰፋሪዎች በግል እና በዘፈቀደ እንዲሁም አካባቢውን ሊያወድም በሚችል መልኩ ነው የሰፈሩት፡፡ የሰፈሩበት ቦታ የደን ውድመትን ሊያስከትል እንደሚችል የአካባቢ የስነ ምህዳር ጥናት አልተደረገበትም፡፡ በአካባቢው ያለው ብርቅዬ ደን መጠበቅ አለበት፡፡ ህገወጥ ሰፋሪዎች በቀላሉ ሊለማ የሚችል የሚታረስ መሬት ይፈልጋሉ፡፡ ደን ሆነ አልሆነ ደንታቸው አይደለም፡፡

ደኑን ይቸፈጭፋሉ እናም ከሰል ያከስላሉ፡፡ ይህም በመሆኑ መጠነ ሰፊ የሆነ የአካባቢ ውድመት ተፈጥሯል…ሰፋሪዎች ወደ አካባቢው በመሄድ ደኑን ለመኖሪያነት ሊያወድሙ አይችሉም፡፡ ይህ ህገወጥ ነገር ነው፣ እናም መቆም አለበት፡፡ ይህንን ነገር አዛብተው የሚያቀርቡ ኃላፊነት የጎደላቸው ናቸው፡፡ እውነታውን ማጣራት ተገቢ ነገር ነው፡፡ የኢትዮጵያውያን መብቶች ሁሉ በእኩልነት መጠበቅ አለባቸው፡፡ አማራዎች እየተሰቃዩ እና ከቦታቸው እየተፈናቀሉ ነው እያሉ የሚያራግቡ ኃይሎች ኃላፊነት የጎደላቸው እና ለምንም የማይጠቅም ነገር ነው…

ይኸ ዓይነት ነገር ነው እንግዲህ በአፓርታይ ዘረኛ የጥቂት ነጮች የበላይነት አገዛዝ በደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች ላይ የተፈጸመው፡፡ ህገወጥ ሰፋሪዎች ተብለው ይፈረጁ ነበር እናም ከሚኖሩበት አካባቢ በኃይል ይባረሩ ነበር…

የኢትዮጵያን የአቦ ሸማኔ ወጣት ትውልድ ከነጻነት ብልጭታ ጋር ከእኔ ጋር እንዲበሩ እጠይቃለሁ፡፡ ነጻ ሆናችሁ ተወልዳችኋል፡፡ አሁን በነጻነት መኖር አለባችሁ ምክንያቱም ያ አምላካዊ ዕጣ ፈንታችሁ ነውና፡፡

አክባሪያችሁ፣

የእናንተው “የአቦ ሸማኔጉማሬ” ጓደኛችሁ!

መልዕክቱ ይቀጥላል

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!             

የካቲት 15 ቀን 2008 .

The post ለኢትዮጵያ አቦ ሸማኔዎች ትውልድ ልዩ መልዕክት፡ ነጻ ሆናችሁ እንደተወለዳችሁ ሁሉ ነጻ ሆናችሁ ኑሩ! appeared first on Zehabesha Amharic.

ኃይለማርያም ደሳለኝ በቴሌቭዥን ቀርቦ በሕዝቡ ላይ ዛተ

0
0

harar

ከግርማ ካሳ

ሕዝቡ መሰረታዊ የመብት ጥያቄ ነው ያቀረበው። ሕገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት፣ ህዝቡ በሰላም ድምጹን አሰማ። ዜጎች ባነሱት ጥያቄ ልንስማማ፣ ላንስማማ እንችላለን ። ሆኖም ማንም ዜጋ የመሰለውን መናገርና መቃወም ይችላል። ህዝቡ ያደረገውም ይሄንኑ ነው።

ሆኖም የአጋዚ ጦር ሕዝቡን ጨፈጨፈ። ሕጻናት፣ አረጋዉያን ሴቶች፣ ወንዶች፣ ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች ሁሉም እንደ ቅጠል በጥይት ረገፉ።

አጋዚ የፈጸመው ወንጀል የተደበቀ አይደለም። ፎቶዎችንና ቪዲዮዎች እያየን ነው። የሟች ቤተሰቦችን ድምጽ እየሰማን ነው። መረጃው፣ ሁሉም ነገር አለ።

ሆኖም ሃይለማርያም ደሳለኝ የሕዝቡን ጥያቄ አራክሶ፣ “የማይደገም ትምህርት እንሰጣለን” እያለ በመዛት ለሕዝብ ያለውን እጅግ በጣም ትልቅ ንቀት ማሳየቱን መርጧል። ከሕዝቡ ጎን ከመቆም፣ለህዝብ ከመቆርቆር፣ እነ ሳሞራን አሁን በቃቹህ ከማለት፣ እነ ሳሞራ ለፈጸሙት ወንጀል የክብር ሜዳሊያ እያጠለቀላቸው ነው። “ጎሽ ጥሩ አደረጋችሁ” እያላቸው ነው።

ኃይለማሪያም አይኖቹ የሚያዩ፣ አይምሮ የሚያስብ ከሆነ ፣ ትንሽ በሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ ይመረመር ዘንድ፣ ተቃዉሞ የተነሳባቸውን ቦታዎች እንደሚከተለው ላቀርብለት ወደድኩ። እንቅስቃሴ የተደረገባቸው ቦታዎችን በቀይ ተከበዋል። (ካገኘሁት መጠነኛ መረጃ በመነሳር)

በኦሮሚያ ወደ 20 ዞኖች አሉ። የጂማ ልዩ ዞን፣ የጂማ ዞን፣ የኢሊባቡር ዞን፣ የቀለም ወለጋ ዞን፣ የምእራብ ወለጋ ዞን፣ የምስራቅ ወለጋ ዞን፣ የሁሩ ጉዱሩ ዞን፣ የአዳማ ልዩ ዞን፣ የቡራዪ ልዩ ዞን፣ የምስራቅ ሸዋ ዞን፣ የሰሜን ሸዋ ዞን፣ የደቡብ ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ የምእራብ ሸዋ ዞን፣ የአርሲ ዞን፣ የምእራብ አርሲ ዞን፣ የምስራቅ ሃረርጌ ዞን፣ የምእራብ ሃረርጌ ዞን፣ የባሌ ዞን፣ የጉጂ ዞንን የቦረና ዞን ናቸው።

• በጉጂ ፣ በምእራብ ሃረርጌ ፣ በምእራብ አርሲ፣ በምእራብ ወለጋ፣ በምስራቅ ወለጋ ፣ በቀለም ወለጋ ፣ በአጠቃላይ በስድስት ዞኖች ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል ተቃዉሞ ተነስቷል።

• በምስራቅ ሃረርጌ፣ ከሃረር በስተምእራብ ባለው ቦታ፣ በአርሲ ወደ ታች ወረድ ብሎ፣ በጂማ ዞን በስተምእራብ ደቡብ በሸቤ ሳምቦ፣ በምስራቅ ሸዋ ዞን ወደ ታች ወርዶ ምእራብ አርሲ ዞን አዋሳኝ ላይ በሚገኙት በቡልቡላና አዳሚ ቱሉ አካባቢ፣ ምእራብ ሸዋ ዞንን በሚያዋስኑ የሰሜን ሸዋ አንዳንድ አካባቢዎች፣ ወሊሶን ጨምሮ ግማሽ በሚሆነው የደቡብ ምስራቅ ሸዋ ዞን ፣ ባጠቃላይ በጥቂት ይሁን በከፊል በሌሎች አራት ዞኖች ተቃውሞ ተነስቷል።

• እርግጥ ነው ከቡልቡላ፣ አዳሜ ቱሉ በስተቀር፣ በኦሮሚያ አሉ ከሚባሉት ትላልቅ ከተሞች ከአንድ እስከ አምስት ከሚጠቀሱት ዉስጥ ( አዳማና ቢሾፍቱ) በሚገኙባቸው የአዳማ ልዩ ዛን እና በምስራቅ ሸዋ ዞን ብዙ እንቅስቃሴ አልታየም። እንደ ጂማ፣ አሰላ ባሉ ከተሞችም እንደዚሁ። በኢሊባቡር ዞን እንደ ሌሎች ዞኖች ብዙ የሚታይ እንቅስቃሴ የለም። ሆኖም እንቅስቃሴው የመዛመት ባህሪ ስላለው ተቃዉሞ በሌለባቸው ቦታዎች ያለው ህዝብም መብቱን ነጻነቱ የተነፈገ በመሆኑ፣ በማንኛውም ጊዜ ሊንቀሳቀስም ይችላል። ይንቀሳቀሳልም።

እንግዲህ ኃይለማሪያም ይሄንን በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅን የሕዝብን እምቢተኝነት ነው፣ በሚቆጣጠረው ሜዲያ እያሳነሰ ያቀረበው።

የሚያዙት ሕወሃቶች ነገ ያስጡልኛል፣ ወይንም ሸሽተው ወደ ትግራይ ሲሄዱ እዚያ ያስጠልሉኛል ብሎ አስቦ ከሆነ በጣም ተሳስቷል። ተጠቅመዉበት እንደ ታኘከ ማስቲካ ነው የሚተፉት። በአደባባይ ለተናገራቸውም ነዋራ ንግግሮች ምላሽ በሕዝብ ፊት ይሰጣል።

ያመረረና በቃኝ ያለ ህዝብ የሚፈለገውን ካለገኘ ወደኋላ አይልም። እነ ኃይለማርያም የሚበጃቸው ሰላምን መፈለግ ነበር። የሚበጃቸው የሕዝብን ጥያቄ አክብሮ ብሄራው እርቅ እንዲመጣ ነገሮች ማመቻቸት ነበር። እንግዲህ እንደ እንስሳ ማሰብ ከፈለጉና ከሕዝብ ጋር መላተም ከመረጡ መንገዱን ጭርቅ ያድርግላችው ከማለት ውጭ የምንለው የለንም። እኛ መክረናል። አስጠንቅቀናል። እንደ ጲላጦስ እጆቻችንንም ታጥበናል።

The post ኃይለማርያም ደሳለኝ በቴሌቭዥን ቀርቦ በሕዝቡ ላይ ዛተ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዕለቱ ምርጥ ካርቱን |ኮማ ውስጥ የገባው ወያኔ

“የአዲስ አበባን የወደፊት እጣ የሚወስነው ሕዝቡ ነው”|ቃለምልልስ የኦነግ ከፍተኛ አመራር አቶ ኦዳ ጣሴ ጋር

0
0

የሕብር ራድዮ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑትን አቶ ኦዳ ጣሴን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ወሳኝ ጥያቄዎችን በማንሳት አወያይቷቸዋል:: ቃለምልልሱ ቢደመጥ አያስቆጭም::

“ሕዝቡ እየተንቀሳቀሰ ነው.. መንግስት ቢወርድ ሃገሪቱን የመምራት ብቃት አላችሁ ወይ?”

“የኦሮሞ ሕዝብ ትግል የማንንም ሕዝብ የሚነካ አይደለም… የኦሮሞ ሕዝብ የሌላውን ሕዝብም ትግል ይደግፋል”

“የኦሮሞ ሕዝብ ግንባር እና የኦሮሞ ሕዝብ ካለምንም ገደብ የሁሉም ብሔር ብሄረሰብ መብት እንዲከበር ነው የሚታገለው”
“ሕዝቡ ሞኝ አይደለም… ወያኔ ከወረደ ሃገሪቱ ትበጠበጣለች የሚለው አይሰራም; ትግላችን ከወያኔ እንጂ ከሌላው ሕዝብ ጋር አይደለም”
“ይህ እንቅስቃሴ ከመጀመሩ በፊት ያሰብነበት ጉዳይ ነው.. ወያኔ እንዲህ ያለውን ሴራ እንደሚሸርብ:: የኦሮሞ ህዝብ ሙስሊምም ክርስቲያንም ነው:: መስጊድም ሆነ ክርስቲያን የማቃጠል ፍላጎት የለውም”
“ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር ጉባኤ እናደርጋለን ለጊዜው ግን ትግሉን ማፋፋም ላይ ነው ትኩረታችን”
“የአዲስ አበባ እጣ ምንድን ነው የሚሆነው?”

 

The post “የአዲስ አበባን የወደፊት እጣ የሚወስነው ሕዝቡ ነው” | ቃለምልልስ የኦነግ ከፍተኛ አመራር አቶ ኦዳ ጣሴ ጋር appeared first on Zehabesha Amharic.

የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አጣሪ ኮሚቴዎች ከያሉበት ተለቃቅመው እንዲታሰሩ የትግራይ ነፃ አውጭ (ሕወሓት) ሥራ አስፈጻሚዎች ወስነዋል

0
0

welkayet - satenaw

የልዑል ዓለሜ ዘገባ

የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አጣሪ ኮሚቴዎች ከያሉበት ተለቅመዉ እንዲታሰሩ የወያኔ ብሔራዊ መረጃን ተንተርሶ የትግራዩ ነጻ አዉጭ ቡድን ስራ አስፈጻሚዎች በትናንትናዉ እለት ወስነዋል።

” የወልቃይት ህዝብ ሙሉ ለሙሉ በትግሬነቱ አምኖ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል ” በማለት ሪፖርት ለብሔራዊ መረጃ ያቀረበዉ የትግራዩ መስተዳድር ደህንነት ክፍል… የህዝቦችን የእርስ በእርስ መጨራረስ በሚፈልጉ የአርበኞች ግንቦት 7 እና መሰል የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ሴራ ምክንያት የተሰማሩ ቀንደኛ ተቀናቃኞች! ይላቸዋል… የወልቃይት ጠገዴን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች።
ወልቃይት ጠገዼ ላይ የሰፈሩ ወራሪዎቹ የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ደጋፊዎች እንዲሁም ከትግራይ ክልል ይተወሰዱ ሰላማዊ ሰልፈኞች ወልቃይቶች ትግሬዎች ነን ብለዋልና ወልቃይት አማራ ነዉ በሚል የሚንቀሳቀስ ማንኛዉም ሐይል ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የመረጃ ዉሳኔዉ ተላልፏል ።
በመላዉ ሐገሪቱ ላይ በተለይም በኦሮሚያ የተነሳዉን ህዝባዊ እንቢተኝነት ምክንያት ባደረገ መልኩ በተለያዩ ክልሎች የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ወደ ቅርብ ከተማ ክልል እንዲሸጋገሩ የተላለፈዉን ዉስጣዊ ትእዛዝ ተከትሎ አዲስ አበባና መሰል ከተማዎች የፈለሱ የትግሬ ተወላጆችን እያስተናገዱ ሲሆን በየእለቱ በልዩ ወጪ ወደ ሁለት መለስተኛ አዉሮፕላኖች እና የእረጅም እረቀት ተጓዥ ባሶች ተዘጋጅተዉ ወደ ትግራይ ሽሽቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል..ሆኖም መረጃዎቻችን እንደሚገልጹት ወልቃይትን ከትግራይ መስፋፋት አናጻር የመጠቅለሉ ሂደት ግድ ይላል በሚል የሞት ሽረቱ ተጀምሯል!!
በመላዉ ኢትዮጵያ የምትገኙ ወገኖቻችን በሙሉ በሐገራችን ላይ የትግራይ ነጻ አዉጭ የተባለ ወራሪ ሐይል እንዳሻዉ እየገደለና እየዘረፈ መሬትህን እየነጠቀ እየወሰደና ለለሎች ሐገሮች እየሸጠ ክብርህን እንዳሻዉ እየዋረደ ሊቀጠቅጥህ የተሰየመዉን ጠላትህን ህወሃት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተባብረህ ታንበረክከዉ ዘንድ ጊዜዉ አሁን ነዉ!!

ወርደት ወይም ነጻነት ! !
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

The post የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አጣሪ ኮሚቴዎች ከያሉበት ተለቃቅመው እንዲታሰሩ የትግራይ ነፃ አውጭ (ሕወሓት) ሥራ አስፈጻሚዎች ወስነዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

ወልቃይት የትግራይ ከሆነች ኢትዮጵያ የቻይና የማትሆንበት ምክንያት የለም ቀጣይ ደግሞ ሚስቶቻችን የማን እንደሚሆኑ ማየት ነው


የአሜሪካ በጥቅሟ ላይ የተመሰረተው የውጭ ፖሊሲ እና ከአፍሪካውያን አምባገነኖች ጋር ቀን እስኪጎድልባቸው የምትፈጥረው ወዳጅነት በቆዩት ዲፕሎማቶቿ ሪፖርት ውስጥ ሲፈተሽ

0
0

የአሜሪካ በጥቅሟ ላይ የተመሰረተው የውጭ ፖሊሲ እና ከአፍሪካውያን አምባገነኖች ጋር ቀን እስኪጎድልባቸው የምትፈጥረው ወዳጅነት በቆዩት ዲፕሎማቶቿ ሪፖርት ውስጥ ሲፈተሽ (ልዩ ዘገባ -ሁለተኛ ክፍል)

The post የአሜሪካ በጥቅሟ ላይ የተመሰረተው የውጭ ፖሊሲ እና ከአፍሪካውያን አምባገነኖች ጋር ቀን እስኪጎድልባቸው የምትፈጥረው ወዳጅነት በቆዩት ዲፕሎማቶቿ ሪፖርት ውስጥ ሲፈተሽ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኦሮሞ ሕዝብ ተቋውሞ ትሩፋቶችና የአማራ ሕዝብ ለተቋውሞው ያሳየው ዝምታ … (ግዜነው ደም መላሽ)

0
0

 

unityእንደመነሻ ሰሞኑን በኦሮሞ ወጣቶች እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ ትክክለኛው መንስሄ ምንድን ነው? ብለን እንነሳ።እንደሚታወቀው  በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ የነገሰው ጭቆናና ግፍ ሞልቶ መፍሰስ አንዱና ዋናዉ ነገር ነዉ። ቢሆንም ግን ይችን ቅፅበት  የሞት የሽረት ያደረጋት ነገር ምን ይሆን? ብሎ መጠየቅ ይገባልና የኔ ግምገማ ሁለት ኩነቶች ላይ ይወድቃል። እንቅስቃሴውን ባነሱት ወገኖች ዘንድ ላለፉት ሁለት ተከታታይ አመታት   “ማስተር ፕላንኑ መሬት ላይ ከዋለ  አርሶ አደር ኦሮሞዎች ካለ በቂ ካሳ ያፈናቅልና ለችግር ያጋልጣቸዋል”   የሚል መፈክር ከፊት  አንግቦ   ከጀርባ  ደግሞ  “ማስተር ፕላኑ የኦሮሞ ሕዝቦችን አፈናቅሎ በሌላ ሕዝብ በመተካት የአካባቢዉን Demography (የሕዝቦች ስብጥር) ይቀይረዋል።ይህ ደግሞ ኦሮሚያን ምህራብና ምስራቅ ኦሮሜያ በማድርግ ለሁለት አስተዳደር ስለሚከፍላት ለነገዋ ነፃ የኦሮሞ ሀገር ምስረታችን እንቅፉት ይፈጥርብናል” በሚል  ኦህዴድን ፣ ኦነግን ፣ እንዲሁም ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶችን በአንድ መስመር ያሰለፈው  የኦሮሚያን ኢንተግሪቲ(አንድነት) የማስቀጠሉ አጀንዳ ። ሁለተኛውና ማስተር ፕላኑን የቀረፀው የህዉሃቱ ቡድን ደግሞ  ላለፉት ዓመታት በአዲስ አበባም ሆና ከትግራይ ውጭ ባሉ ክልሎች ሲያደርግ እንደነበረው  “በልማትና በከተማ ማስፉፉት” ስም ነባር ባለ እርስቶችን እየነቀለ አንድም መሬቱን ቸብችቦ ዶላሩን ወደ ግለሰቦች ኪስና ወደ ወገኖቹ ለማሸሽ ፣ አንድም ዘሮቹንና ደጋፊዎችን ፌደራል ከተማዋ አካባቢ በማስፈር ከላይ የተጠቀሰውን የሕዝቦችን ስብጥር በመቀየር የፖለቲካ የበላይነቱን ለማስጠበቅ የወጠነው ተንኮል ዉጤት ነው። እንግዲህ በርህሱ የተነሱ ሀሳቦችን እነዚህ እውነታዎች ላይ ቁመን ነው የኦሮሞ ወጣቶች መሰዋት የሆኑበትን ትግል ዉጤትና “ አማራዉ ለምን ዝም አለ? እየተባለ የሚሰነዘረውን  ሀሳብ የምንቃኘው።

ከመጀመሪያው ነጥብ ስንነሳ ፦ ላለፉት ወደ አራት ለሚጠጉ ወራቶች በኦሮሞ ሕዝብ እየተካሄደ ያለው ደም አፋሳሽ ተቋውሞ የበርካታ ንፁህ ዜጎችን ሕይዎት የቀጠፈ፣ ብዙዎችን አካለ ጎዶሎ ያደረገ፣የእምነት ቦታዎች ላይ አደጋ ያስከተለ፣እንዲሁም አንዳንድ አካባቢ ደግሞ መጤ ናቸው የሚባሉትን አማራ ወገኖች ንብረት ያወደመ ክስተት ነው። ትግል መሰዋትነትን ይጠይቃልና ይህንን መሰል ነገሮች ይጠበቃሉ። ሆኖም ግን ልጆቻቸውን ባጡ ወላጆችና ወዳጆቻቸው ፣ አካላቸው የጎደለ ወንድም እህቶች ፣ በሕይዎት ያፈሩትን ሀብትና ንብረት የወደመባቸው ወገኖች ጫማ ዉስጥ ሆኖ ለሚያየው ሰዉ እንዲህ በሩቁ “ትግል መሰዋትነትን ይጠይቃል” ብሎ እንደማለፉ ቀላል አይደለም። በተለይ ልጆቻቸውን ላጡት ወላጆችና ወዳጆቻቸው ክስተቱ አጥንትን ዘልቆ የሚሰማ ሀዘንን፣ከሕሌና የማይፋቅ ፀፀትን፣ ተስፋ የሚያስቆርጥ የልብ ስብራትን የሚፈጥር ከባድ ነገር ነዉና የሚያመልኩት አምላክ ለወላጅና ለዘመዶቻቸው መፅናናትን፣ ለሟቾችም ምህረትን እንዲሰጥ ከልብ እመኛለሁ ። እፀልያለሁም።

ይህንን ካልኩ ዘንድ እንቅስቃሴውን ማን ነው የሚመራው? አላማ ምንድን ነው? እንዴት ይቆጫል? እና መሰል መላምቶችን በይደር ትተን ፣  በነዚህ ወጣቶች መሰዋትነት በኔ ግምገማ እስካሁን ተገኙ የምላቸውንና ለሁሉም ዜጋ ጠቃሚ በረከቶች ናቸው የምለዉን ብቻ ላንሳ።

ህውሃት ባሳለፍናቸው 25 የመከራ  ዓመታት ውስጥ እንደ ዘንድሮው ተፈትኖ አያውቅም።ይሄ “የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን” የተባለው ዝነኛና መዘዘኛ ፕሮጀክት የህዉሃትን አልጋ ያነቃነቀ፣ በሻብያ ተሰፍቶ የተሰጠውና ለአለፉት 25 ዓመታት በፕሮፖጋንዳ ጋጋታ ሲጎትተው የከረመው ሱሪዉ መዉለቅ መጀመሩን ያሳበቀ ወርቅ አጋጣሚ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚስማማበት ህውሃት እንደ ድርጅት አንድ ፕሮጀክት ቀርፆ ለመተግበር  የሕዝብን ይሁንታ ጠይቆ አያዉቅም። በትግበራ ወቅት ተቋዉሞ ቢገጥመውም በሕዝብ ግፊት ቀልብሶት የሚያቀው  ፕሮጀክት የለም። ስለዚህ የዚህ የኦሮሞ ሕዝብ ተቋውሞ ይህንን የህውሃት  ትቢት የሰበረና ለዚህም ጣፋጭ የትግል ፍሬው ላቅ ያለ አክብሮት ይገባዋል።  ሌላው በ 97 የምረጡኝ ዘመቻ ወቅት እነ ዶ/ር ብረሀኑ ነጋ  የህውሃት ሰዎች  በሚለብሶቸው ውድና ዘመናዊ ሱፎች የተሸፈነውን ገመናቸውን ገላልጦ ድንቁርናቸውን አጋልጦ ነበር። ይህ የአሁኑ የኦሮሞወች ተቃውሞ ደግሞ የትቢታቸውን ልክ እንድናውቀው እረድቶናል። እንደ ስዩም መስፍን ፣ ስብሐት ነጋ ፣ አባይ ፀሀየ፣ ጌታቸው እረዳ እና መሰል   የህዉሃት ጋንግስተሮች  በርካታ ሕዝብ በተሳተፈባቸው ስብሰባዎች እየተገኙ፣ በትላልቅ ሚዲያዎች  ላይ  እየቀረቡ  በትቢትና  በማን አለብኝነት  ሕዝብ ላይ ፀያፍ ቃላቶችን  ሲሰነዝሩ እንጂ ሕዝብ ይቀየመናል በማለት በይፋ ሲያስተባብሉና ይቅርታ ሲጠይቁ አይቃወቅም ነበር። ዛሬ እንደ ውሻ የተፉትን መልሰው ሲዉጡ ፣ በአደባባይ በሕዝብ እግር ስር ወድቀው ሲንደባለሉ ማየት የሕዝብን ሀያልነትና ሁሌም አሸናፊነት እንዲሁን  የህውሃትን መፍረክረክ የሚያሳይ  አንድ አበይት ክስተት ነዉ።ይበል የሚያሰኝና ልምዱም በሌሎች ወገኖች እንደየ አስፈላጊነቱ መቀሰምና መተግበር ያለበት ነገር ነው።

ሌላውና ወሳኙ ነጥብ ደግሞ  የኙ የማሸማቀቂያ ፕሮፖጋንዳ አዲሱን ትውልድ ላይ ምንም ተፅህኖ እንዳልፈጠረ የታዘብንበት አጋጣሚ ነው። “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” እንዲሉ  ህውሃት  “ደርግን ያህል እስከ አፍንጫው የታጠቀ ሰራዊት አሸንፌለሁ”ና ምን ይሳነኛል የሚለው ላለፉት 25 ዓመታት ትዉልዱ በፍርሀት ለማሸማቀቅ የተቸረቸረው ቱልቱላ የጀግንነት ታሪክ   “ጨፈቃ” በታጠቁ  ወጣቶች ተፈተነና ልቦለድነቱ ፀሀይ ሞቀዉ።በርግጥ ከታሪኩ ቅርበት አንፃር ህ.ው.ሃ.ት የጀግንነት ተክለ ሰውነቱን የቀረፀበት “በምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ ሀይል የነበረውን ደርግን አሸነፍኩ” የሚለው ትርክት ብዙም ሚስጥር ያልሆነና ጉልምስናና ከዛ ከፍ ባሉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የሚታወቅ ነገር ነዉ።። ደርግ ይከተለዉ በነበረው የፖለቲካ ፍልስፍና ከምህራቡ ሀያላን ሀገራት ጋር ጠላትነትን ፈጥሮ ነበር። እንደ ዘርን አማክሎ ባይሆንም  የሚገዛውን ሕዝብ በግድያ ፣ በአፈናና በእስር አሳሩን ያሳይ ስለነበር በሕዝቡና በገነባው ሰራዊቱ ሳይቀር አይንህን ላፈር ከተባለ ሰነባብቶ ነበር። በመጨረሻም ይህንን አጋጣሚ በተጠቀመዉ እንደ ሶሪያ፣ ቱርክ ፣ ኢራቅ እና መሰል አረብ ሀገራት  ከፍተኛ እርዳታ ይጎርፍለት በነበረው ሻብያ ተገፍፈታትሮ ፈራረሰ። እንግዲህ ይህ የታሪክ ክፍተት  እስከ 70ዎቹ መጨረሻ ድረስ  በደርግ ሆነ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ድልድዮችን ከመስበር፣ ቤተ እምነቶችን ከመዝረፍ ፣ አንዳንድ ሰላማዊ ሰዎችን ከመግደል ባጠቃላይ ከሽፍታነት ያለፈ ቦታ ያልነበረዉና  እምብዛም  የማይታወቀው ህውሃት የተበታተነውን የደርጉን ወታደር ከሻብያ ጎን ተሰልፍ እያባረረ አራት ኪሎ ፊጥ አለ።እግዲህ ብዙ የተባለለትና እየተባለለት ያለዉ የ 17 ዓመቱ የህዉሃት የጫካ ቆይታ ከዚህ የዘለለ  አልነበረም። ህዉሃትን በአግባቡ የሚገልፀው ትላንት ያልነበረና በፕሮፖጋንዳ ሊያሳምነን የሚውተረተረው የጀግንነት የጦርሜዳ ዉሎው ሳይሆን በሀገር ላይ የፈፀመው ክህደትና ዛሬ በንፁሀን ዜጎች ላይ እየወሰደ ያለው ዘግናኝ ጨፍጫፊነቱ ነው። ጀግና እንኮን ሰላማዊ ዜጋን  እጅ የሰጠዉን ጠላቱ ላይ ሰይፉን አይመዝምና።የኦሮሞ ወጣቶች የተቋውሞ ፍሬ ይህንን ያስረገጠ ነውና አድናቆት ይገባዋል።በኦሮሞ ሕዝብ የተቋውሞ እንቅስቃሴ የተመዘገቡትን ድሎች በዚህ ልግታና “ አማራዉ ለምን ዝም አለ”የሚለውን ሀሳብ ላንሳ።

አማራው ለምን የተቋዉሞው አካል አልሆነም ?

አማራው ለምን የተቋዉሞው አካል አልሆነም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በሃያ አምስ አመት የህውሃት አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመውን ግፍ በስማ በለው መስማት ብቻ ሳይሆን  አማራ ሆኖ መገኘትና ስሜቱን  መረዳትን ይፈልጋል። ጉዳዩን በሦስት ከፍየ ለማየት ልሞክር።

መጀመሪያውና ቀላሉ መልስ የሚሆነው አማራ በህውሃትና በአጋሮቹ  ከአያት ቅድመ አያቶቹ መሬት ሀብት ንብረቱን እየተቀማና ከእርስቱ እየተነቀላ ይሄ የአንተ ሀገርህ አይደለምና ወደ አማራ ክልል ሂድ ሲባል ፣ በጅምላ ሲጨፈጨፍ፣ከፖለቲካ ፣ከማህበራዊ፣ ከኢኮኖሚው መድረክ አድልሆ እየተፈፀመበት  ሲገለልና ሲሰቃይ  ለአማራ ሕዝብ ወገናዊነቱን ያሳየ አካል አለመኖሩ እንደ አንድ ምክንያት ሊወሰድ የሚችል ነው።

ሁለተኛው ምክንያት የሚሆነው ደግሞ ከመነሻው ለመግለፅ እንደተሞከረው የኦሮሞ  ሕዝብ እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ አላማው ግልፅና አሳታፊ  አለመሆኑ ነው። “ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ህዝቦች ኦሮሚያ ውስጥ እንደ አንድ ቻይናዊና ኬንያዊ መኖር ነው የሚችሉት” ፣ “ኦሮሚያ የኦሮሞ ብቻ” የሚልና ኦሮሚያን እንድንገነጥል ተባበሩን አይነት እንቅስቃሴ ሌሎች ሕዝቦች እንዲደግፋ መፈለግ ስህተት ነው። ይህ አቆም የሁሉም ኦሮሞ ሕዝብ አቆም ነው ለማለት የሚያስችል ሁኔታ ባይኖርም ተቋውሞውን እየመራን ነው የሚሉት ግለሰቦች ግን ደጋግመው ሲያነሱት እየተሰማ ነውና በሌላው ሕዝብ ዘንድ ጥርጣሬው ቢኖር የሚጠበቅ ነገር ነው። አንድ በወፍራሙ ሊሰመርበት የሚገባ ነጥብ አለ። የአማራ ሕዝብ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ሲባል ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ከፊት መስመር ተሰልፎ  ከትላንት በስቲያ የአባቶቹን ዙፋን አፍርሶል፣   ትላንት ደግሞ “ከደርግ የባሰስ ጨቋኝና አረመኔ አገዛዝ አይኖርም” በሚል ስሜት ለደርጉ ጀርባውን በመስጠት ህዉሃትን አይነት የሀገርና የሕዝብ ነቀርሳ አጅቦ አራት ኪሎ የተከለ ለዛም ውለታው ዛሬ አሳሩን እያየ ያለ ሕዝብ መሆኑን ነው። ስለዚህ የአሁን ነገሮችን በቅርብና በትግስት መታዘብ አንዳንድ ደፋሮች “አማራ ተኝቶል” ፣ “አማራ አከካሪው ተሰብሮል” እንደሚሉት ወይንም በታሪክ ተደጋግሞ በተከሰተው ውድቀት ተሰላችቶ ሳይሆን የማሕበረሰቡን በፖለቲካ መብሰል የሚያሳይ ነው።ዳግመኛ ተመሳሳይ ስህተት ላለመፈፀና  ለችግሮች ቆሚና የማያዳግም መፍትሄ ከመሻት የተወሰደ እርምጃ ነው።

ለአማራ እንደ ሕዝብ ህውሃትን የሚስተካከል ጠላት ገጥሞት አያውቅም ። በአጠቃላይ ሲታይ ህዉሃቶች ላለፉት 25 ዓመታት በሕዝብና በሀገር ላይ በርካታ ግፎችን ፈፅሞል።ነባር ሕዝብን ከርስቱ እየነቀሉ የኛ የሚሉትን ሕዝብ ተክለዋል። ከትግራይ ክልል አጎራባች መሬቶች አይናቸው ያየዉንና ቀልባቸው የወደደውን አካባቢ እየቆረሱ ወደ ታላቋ ትግራይ ቀላቅለዋል።  ከትግራይ ክልል ጋር ኩታ ገጠም ያልሆኑትን  ደግሞ  ቀድሞውንም ለዚሁ አላማ ተመልምለው ስልጣን እንዲይዙ በተደረጉ የየአካባዉ አድር ባይ ባለስልጣናትን በመጠቀም ያሻቸዉንና አቅማቸው የቻለውን መሬት ነጥቀው ሲያርሱ ፣ ከነሱ ከተረፈ ደግሞ በዝቅተኛ ዋጋ ለ”ኢንቨስተር” ቸብችበው ኪሳቸውን አድልበዋል። እንደ ሕዝብ ከታየ ደግሞ በህዉሃት የአማራን  ያህል በደል የደረሰበት ሕዝብ የለም።ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚረዳው፣ ህዉሃቶችና አጋሮቹም ደጋግመው እንደገለፁልን ዋናው ጠላታቸው የአማራ ሕዝብ ነዉ። አነሳሳቸውም “በአማራው መቃብር ላይ ታላቆን ትግራይ መመስረት” ነበረና በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማራ ወገኖችን አጥፍተዋል፣ ከርስታቸው እየተነቀሉ እንዲሰደዱ አድርገዋል፣ አስርዋል፣ ገርፈዋል ፣ገለዋል። ይህንን እኩይ ድርጊታቸውን ለመተግበርይረዳቸው ዘንድ አማራና የአማራ የሆኑ ባህሎችና ወጎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ሰርተው አንዳን ወገኖችን ከጎናቸው ለማሰለፍ ችለዋል። ከነዚህ ወገኖች ግምባር ቀደሙ ደግሞ ዛሬ ባለተራ የሆነዉን የኦሮሞውን ማሕበረሰብ እወክላለው የሚለው ኦነገ  ዋናው ሲሆን ዛሬ ለምንገኝበት አጣብቂኝ ቀላል የማይባል ሚና ተጫውቶል። ደርግ በወደቀ ማግስት  ኦነግ  ኢትዮጵያን የሚያፈርሰዉንና አማራን እርስት አልባ የሚያደርገውን ቻርተር ከመቅረፅ ጀምሮ በትግበራ ላይም ቀጥታ ተሳታፊ በመሆን በርካታ አማራ ወገኖችን አርዶል።በአጠቃላይ ሲታይ  ኦነግ እንደ ቡድን ከተሰባሰበበት ግዜ ጀምሮ በሕዝቦች መካከል ቆሚ ጥላቻ እንዲፈጠር ከፍተኛ ደባ የፈፀመ ፣ ለኢትዮጵያዊያን በአጠቃላይም ሆነ የአማራ ሕዝብ ዛሬ ለሚገኝበት ነባራዊው ሁኔታ  ከህዋትና ሻብያ ያልተናነሰ ተጠያቂነት ያለበት ቡድን ነው።እንግዲህ ይህ በዚህ ቡድን የተዘራው የፈጠራና  የጥላቻ ታሪክ  ሲደመር በህውሃት ጋባዥነትና አይዞህ ባይነት በአማራ ወገኖች ላይ የወሰዳቸው አሳዛኝና ዘግናኝ ድርጊቶች  በሁለቱ ታላላቅ ሕዝቦች መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠርና ተባብረው እንዳይቆሙ እንቅፋት መፍጠሩን ማንም አይስተውም።

በሶስተኝነት መጠቀስ ያለበት ነጥብ ደግሞ የተቋውሞው አላም ግልፅና አሳታፊ ሆኖ ቢሆን ኖሮ እንኮን አማራን አማራ በብሔር አለመሰባሰብና አለመደራጀቱ ለንደዚህ አይነት ወሳኝ ወቅት አፋጣኝና የተቀናጀ መልስ ለመስጠት አመች አይሆንም። ያልተደራጀ ሕዝብ መንግስት አይደለም ድንጋይ መፈንቀል አይችልም።ያልተደራጀ ሕዝብ  ሌሎች ሲጠቁ ፈጥኖ ደርሶ አለኝታ መሆን ይቅርና እራሱን መከላከል አይችልም። መንግስት በጥላቻ፣ በትችትና በስድብ ወድቆ አያውቅም። በግለሰብ ደረጃ እዚህም እዛም  የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መንግስትን መስደብና መተቸቱ ዝናብ ሰዉን ለግዜው እንደሚያበሰብና ፀሀይ ሲመጣ ወዳይው የራሰው እንደሚደርቅ አይነት ነው።የዝናብ ጠብታ ተሰባስቦ ጅረት ፣ ጅረቶች ተሰባስቦ ታላላቅ ወንዞችን፣ወንዝ ተገድቦና በእንዲት ጠባብ ክፍተት እንዲወጣ ተደርጎ ተርባይን ዘውሮ ለሀገር ብርሀን የሚሰጥ ሀይል እንደሚፈጥር ሁሉ ሕዝብ በአንድ አላማ ዙሪያ ተሰባስቦና ተደራጅቶ በአንድ እዝ ስር ከዋለ የሚያቆመው ምድራዊ ሀይል  አይኖርም።እንግዲህ አማራ ተሰባስቦና ተደራጅቶ ሰይፍ የመዘዘበትን ጠላቱ ህውሃት እንዳይመክትና የሰሞኑን አይነት አጋጣሚ ተጠቅሞ አብሮ ህዉሃትን እንዳያሶግድ በህውሃትና በአንዳንድ ምሁራን ከፍተኛ ደባ ተፈፅሞበታል።

የአማራን መሰባሰብ አጥብቀው የሚዋጉት ቡድኖች ሁለት ናቸው። የመጀመሪያውና ዋናው ህውሃት ነው።እንደሚታዎቀው ህውሃት፣ ሻብያና ኦነግ የትግል ማህቀፍ አድርገው ይንቀሳቀሱ የነበረው አማራን በጠላትነት በመፈረጅ ነበር። ይህንን አቆም ለመያዝ ያስቻላቸው ደግሞ አማራ እንደ ሕዝብ ተደራጅቶ እነሱ እንወክለዋለን በሚሉት ማሕበረሰብ ዘንድ የፈፀመው ግፍ ስለነበረ አይደለም። ይህንን የሚያሳይ አንዳች የታሪክ ምህራፍ የለምና። እንደዉም በታሪክ አማራ በአማራነት ተደራጅቶ ስልጣን የያዘበትና ሌሎችን በዘር ከፋፍሎ ያጠቃበት ግዜ የለም።ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱት ቡድኖች አማራ ጠል አቆም ለመያዛቸው ምክንያት ያደረጉት የኢትዮጵያን አንድነትና ጥንካሬ ከአማራና አማራዊ አስተሳሰብ ጋር ስለሚተነትኑት ነው።የቡድኖቹ አላማ ኢትዮጵያን አፈራርሰው የየራሳቸው ጎጆ ለመቀለስ ስለሆን ይህ አላማቸው ግቡን የሚመታው ደግሞ ከላይ እንደተጠቀሰው አማራውንና አማራዊ አስተሳሰብን በማጥፋ ነው ብለው አቆም በመውሰዳቸው ነው ጫካ በነበሩበትም ወቅት ሆነ ዛሬ ቤተመንግስቱን ተቆጣጥረው የአማራ ሕዝብ ላይ ግፍ እየፈፀሙ የሚገኙት።ይህንንም  በቀላሉ ለመረዳት ህዉሃት ስልጣን ከጨበጠ ባኋላ የወሰዳቸውን እርምጃዎች ማየተ በቂ ነው። ህውሃት ኤርትራን ባርኮ ከሸኘ በኋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሰፈነው ቋንቋን መሰረታ ያደረገው አስተዳደር በብሔር መሰባሰብና መደራጀትን የሚደግፍ ነው።ለዚህም ከአማራ ብሔር ውጭ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉት ሁሉም ብሔሮች በብሔራቸው ተደራጅተው በአንፃራዊነት በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ ተደርጎል። ይህ ሕግ ግን አማራ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን አይታሰብም። በተለያየ ግዜ ከህውሃት ደንነት ቢሮ አምልጠው የወጡት መረጃዎች የሚሳዩት የአማራ ሕዝብ በአንድ እዝ ውስ መደራጀት ይቀርና አማራዎች ሁለትና ከዛ በላይ ተሰባስበው ሻይ መጠጣት  ለህውሃት ሰዎች ትልቅ እራስ ምታት መሆኑን ነው። በነ ፕ/ር አስራት ወልደየሱስ ተመስርቶ የነበረው ብቸኛው የአማራ ድርጅትን መአድ ህውሃት መሪውን ገሎ አባላቱን በመብራት እየለቀመ እንዴት እንዳጠፋቸው ሁሉም የሚያውቀው ነገር ነው።

የአማራን በብሔር መሰባሰብ የማይፈልገው ሁለተኛው አካል ደግሞ በግለሰብ ደረጃ በየተሰማሩበት ሙያ አንቱታን ያገኙ ሙሁሮችንና ከአማራው አብራክ የተገኙ ቀላል የማይባሉ ኢሊቶችን ያቀፈው ቡድን ነው። እነዚህ ወገኖች “አማራ ኢትዮጵያን እንደ ድርና ማግ  አሰባስቦ የያዘው ሕዝብ ስለሆነ የአማራ በብሔር መሰባሰብ ኢትዮጵያን ያፈርሳል” የሚል ትንተና ሲሰጡ ይሰማል። ድንቅ ነው መቸም ።ህውሀትና አጋሮቹ አማራና የአማራ አመለካከት ከጠነከር ኢትዮጵያን ማፍርስ አይቻልም ብለው አማራን ሊያጠፋ ሲታትሩ ምሁራኑ ደግሞ በተቃራኒው ይቆሙና አማራ ተደራጅቶና ጠንክሮ ከወጣ ኢትዮጵያ ፈረሰች የሚል አስቂኝና ግልብ ትንታኔ እየሰጡ ለህውሃት መሳሪያ ሆነው እናያለን።ለዚህም አላማቸው የአማራን ህልዉና እስከመካድ ድርስ ሄደው ሲዘባርቁ ታዝበናል። መቸም እነዚህ ቡድኖች በአማራ ሕዝብ ላይ እንደሰሩት ሴራ  የሚገርመኝና እንደግለሰብም የሚያበሳጨኝ ነገር የለም።ህዉሃትና አጋሮቹ የአማራን መጠንከር ከኢትዮጵያ ክብርና ዳር ድንበር መከበር ጋር ማገናኘቱ ታሪካዊ መሰረት ስላለው “አማራ ጠንክሮ የወጣባትን ሀገር ለማፍርስ ከባይ ይሆናል” ብሎ መስጋቱ እውነትና የሚጠበቅ ነገር ነው።የ”አማራን መጠንከር ከኢትዮጵያ መፍርስና መበታተን” ጋር የሚያያይዘው የሙሁራኑ ትንታኔ ግን ከየትኛው የታሪክ አንጎ ላይ እንደተመዘዘ እነሱ ብቻ ናቸው የሚያውቁት።

የኢትዮጵያ የታሪክ  ፀሀፊ የሆኑት አቶ ይልማ ዴሬሳ በፃፉት “የኢትዮጵያ የታሪክ በአሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን”  በሚለው መፀሐፋቸው የሚነግሩን ከላይ የተገለፁት ወገኖች ከሚያቀርቡት ትንታኔ በተቃራኒው ነው።  ከአማራው አካባቢ የተነሱ ነገስታት ሀገሪቶን በመሩባቸው ወቅቶች ሁሉ በተለያየ ምክንያት ቀደምቶቻቸው ያጦቸውን እርስቶች ለመመለስና ግዛታቸውን ለማስፋት ሲተጉ እንጂ ሀገር ሲያፈርሲ ታሪክ መዝግቦ አያውቅም።  ለምሳሌ የአክሱም መንግስት ከወደቀና ንግስናው የዛጉዬ ወገኖች በተያዘበት ወቅት የኢትዮጵያ ድንበር ከሰሜን እስከ ደቡብ እንደ መቀነት በቀጭኑ የተዘረጋ ነበር። በዮዲት ወርራ እንዲህ ተሸማቆ የነበረውን የኢትዮጵያ ድንበር በ1284ዓ.ም ከዛጉዌዉ የመጨረሻ ነጋሲ ከንዋይ ክርስቶስ ከተረከበዉ ከይኩኖ አምላክ  ጀምሮ በዮዲት ወረራ ወቅት የተበታተኑ እርስቶች የተመለሱበት፣የስነፅሁፍና የኪነ ጥበብ ስራዎች እድገት ያሳዩበት፣  ገዳማትና አድባራት የተስፋፉበት ወቅት እንደነበረ ነው።እነ አምደ ጽዮን ፣እነ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ፣እነ አጼ ናዖድ አይነት ታላላቅ ነገስታት የኢትዮጵያን  የጥንት እርስት እያስመለሱ ከአክሱም ነገስታት በደረሱበት ስልጣኔ ደረጃ የደረሱበት፣ አክሱሞች እንኮን ያልደረሱበት ድንበር ተሻግሮ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በህንድ ዉቅያኖስ ማዉለብለብ የቻሉበት ዘመን ነበር።ይህ የኢትዮጵያ ታላቅነት እስከ  አጼ ልብነ ድንግል  ድርስ የተራዘመ ነበር። በዛን ዘመን የቱርኮች አቶማኑ ኢምባየር ጉልበቱ የፈረጠመበት ወቅት በመሆኑና በክርስቲያን ሀገራት “እስልምናን በጎራዴ” የሚለው  ጅሐድ የታወጀበት ወቅ ነበር። በዚህ ወቅት  የሐረሩ አህመድ ቢን ኢብራሂም ኤልጋዚ (ግራኝ) ከቱርኮች በዘነበለት የነፍስ ወከፍ መሳሪያ፣ መድፍና የሰው ሀይል በመታገዝ አጼ ልብነ ድንግልን አሸንፎ ኢትዮጵያን እንዳልነበረች አድርጎ ሀብትና ቅርጾቾን ዘርፎ በእሳት አጋየ።በመጨረሻው ግራኝ በአጼ ገላውዲዮስ ተሸንፎ ቢገደልም የክርስቲያን መንግስት በመዳከሙና በነ ሚካሄል ስውል ሸር ኢትዮጵያ የዛሬው አይነት መበታተን ደርሶባት የነበር ቢሆንም ከዛ በኋላ የተነሱት  በነ አፄ ቴዎድሮስ፣ በነ አፄ ምኒሊክ፣ በነ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ መልሳ ማንሰራራትና መጠናከር ጀምራ እንደነበር የቅርብ ግዜ ታሪክ ነው። ይህን የሚያሳየን ከአማራው አካባቢ የሚነሱ ነገስታት በየዘመናቸው የሚተቹበት ነገር ባይጠፋም የሀገርን ልዋላዊነት በተመለከት ግን አንዳች የሚነሳ እፀፅ አለመኖሩን ነው።

ሌላው እነዚህ ግለሰብና ቡድኖች  “አማራ በብሔር ከተደራጀ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች”  ከሚለውን አስተምሮት ጎን ለጎን አማራ አሁን ባለበት ነባራዊዉ ሁናቴ እንዴት አድርጎ የኢትዮጵያን መፍርስ እኅደሚታደግ ሲያስረዱ አይታይም። መችም ህውሃት በሚዘዉራት ኢትዮጵያ ውስጥ ባሳለፍናቸው 25 ዓመታት በአማራው ላይ ያልደረሰ የግፍ አይነት አለመኖሩን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚረዳው ጉዳይ ነዉ። ሲጀመር አማራው ባልተወከለበትና ሀሳቡን ባላዋጣበት “ዋና ጠላታች አማራ ነው” ብለው ሰነድ አዘጋጅተውና ጦር መዘው ደርግን በተኩ ጠላቶቹ በሆኑ በነ ህዉሃት፣ ሻብያና ኦነግ በተረቀቀ ሕገ መንግስት ስር የሚተዳደር ፣ ከፖለቲካዉ ፣ከማህበራዊዉ፣ ከኢኮኖሚው እና ከመሳሰሉት ዘርፎች ዉስጥ የተገለለ ሕዝብ መሆን ይታወቃል። ሌላው ቀርቶ በአንድነት ስም የሚሰባሰቡ ድርጅቶች በህዉሃት እንዲበታተኑ የሚደረገው የአማራ ጅርጅቶች ናቸው የሚል ታፔላ እየተለጠፈባቸው ነው።ይባስ ብሎ ዛሬ ዛሬ ደግሞ ከኢትዮጵያ ዉጭ እንኮን እየተደራጁ ባሉት እንደ ግንቦት ሰባት አርበኞች ግንባር አይነት ድርጅቶት “በአማራነት እንዳንታማ” በሚል አመራራቸውን ከአማራው ሲያፀዱ እየታዘብን ነው። እና አማራ እንዲህ በተገለለባት ሀገረ ኢትዮጵያ አማራ እንደ ዛሬው ተበታትኖ እራሱን በማያድንበት ደረጃ መገኘት እንዴትና በምን አስማት ለኢትዮጵያ አለኝታ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል??ብሎ ለሚሞግት አካል ምላሽ የሚሰጥ አይኖርም።

ለማጠቃለል ይህን ሀሳብ እያራመዱ ያሉ ወገኖች የህዉትን አማራንና የአማራን አመለካከት የማዳከም አጀንዳ እያራገቡ ነዉ። አማራዉን ተበታትኖ እንዲጠቃና ጨርሶም እንዲጠፋ ድንጋይ እያቀበሉ ነዉ። እነዚህ ግለሰቦችና ቡድኖች ሌላ የተደበቀ አጀንዳ ከሌላቸው የያዙት አቋም ስህተት ነው ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል ።  ልብ ገዝተውና አቆማቸውን አስተካክለው አማራን እያሰባሰቡ ለሚገኙት እንደ ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት (ሞረሽ)  አይነት ሲቪክ ማህበራትንና እንደ የቤተ አማራ ንቅናቄ(ቤአን) ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን ቢደግፋ የመከራ ቀኖችን ማሳጠር ይቻላል ብየ አምናለሁ።

ቸር እንሰንብት!!

 

The post የኦሮሞ ሕዝብ ተቋውሞ ትሩፋቶችና የአማራ ሕዝብ ለተቋውሞው ያሳየው ዝምታ … (ግዜነው ደም መላሽ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የጭቆናው ምክንያት   አንባገነናዊ ሥርዓት  ወይንስ የብሄር  ልዩነት ይገረም አለሙ

0
0

Woyanes shoud face justiceወያኔ በተናጠልም ሆነ በቡድን  በዜጎች ላይ የሚፈጽማቸውን  ድርጊቶች አስመልክቶ  የበደሉ ተጠቂዎችም ሆኑ ለተጠቁት ድምጽ የሚያሰሙ ወገኖች  በደሉ የተፈጸመው  አማራ ስለሆን/ኑ ነው ኦሮሞ ስለሆን/ኑ ነው ወዘተ በማለት በደሉን በብሄራቸው ምክንያት  የተፈጸመ አድርገው  ሲገልጹ ይሰማል፡፡ የሚፈጸሙት የግፍ ድርጊቶች  በተጠቂዎቹ ላይ የሚፈጥሩት ስሜት እንዲህ ሊያናግሩ ይችላሉ፡፡ በምክንያት ወደ ውጤት የሚጓዙ ሳይሆን በስሜት ህዝብ ማነሳሳት ላይ ለሚያተኩሩ ወገኖችም  ይህ አገላለጽ ቀላል መሳሪያ ነው፡፡ ዜጎች በብሄራቸው አስተሳሰብ ታጥረው የእርስ በርስ ልዩነታቸው ሲሰፋ ተጠቃሚ የሚሆኑ ወገኖችም  ይህን አገላለጽ ይፈልጉታል፤ያራቡታል፡፡ ነገር ግን ሰከን ብለን ካየነው አገላለጹ የነገሩን ትክክለኛ ገጽታ የሚያሳይ  ለመፍትሄም የሚበጅ አይደለም፡፡

ጠለቅ ያለ  መመርመር ሳያስፈልግ በቅርብ ያሉና በግልጽ የሚታዩ ነገሮችን ብቻ በጥሞና መመልከት ብንችል እኔ ወይንም አኛ እንዲህ የሆነው ይሄ ይሄ በደል የተፈጸመብን በብሄራችን ምክንያት ነው ( አማራ ኦሮሞ ጉራጌ ወዘተ በመሆናችን ነው) ሲባል ይህ በደል ያልነካቸው  የብሄሩ አባላትን መዘንጋት ይሆናል፡፡ የጥቃቱ መነሻ ምክንያቱም ሆነ መድረሻ ግቡ ብሄር ተኮር ከሆነ ከተዘመተበት ብር መካከል መስፈርት እያወጣ የሚመርጠው አይኖርም፡፡ በእኛ ዘንድ የሚታየው አጥቂዎቹም ተጠቂዎቹም ከሁሉም ብሄር መሆናቸው ነው፡፡

ከየብሄሩ ከወያኔ በላይ ወያኔ ለመሆን የሚዳዳቸውና በብሄራቸው አባላት ላይ በደል የሚፈጽሙ፤በእኔ ካልደረሰ በማለት ካለው  ተስማምተው የሚኖሩ፤ጎመን በጤና ብለው ህሊናቸው እየቆሰለ ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል አይነት የሚኖሩ ወዘተ ብዙ አጅግ ብዙ አሉ፡፡ ታዲያ የተበደልነው  አማራ/ኦሮሞ ወዘተ በመሆናችን  ነው ብለን ጅምላ ካደረግነው  የእነዚህ ወገኖች ጉዳይ  ምን ሊባል ነው፡፡ መቼም የብሄር ማንነነታቸውን መካድም መንሳትም አይቻልም፡፡ በመሆኑም ይህን ብቻ በማየት የበደል ጥቃቱ መሰረተ ምክንያት   የብሄረሰብ ማንነት  ሳይሆን የገዢዎች ጸረ ዴሞክራሲያዊነትና  የተጠቂው ዴሞክራሲ ናፋቂነት ነው ማለት ይቻላል፡፡

ስለዚህ የበደሉ ምክንያት የዚህ ወይንም የዛኛው ብሄረሰብ አባል መሆን ሳይሆን  እኔ ሰው  ነኝ ማለት  ነው፤  እኔ ሰው ነኝ የሚል ሰው  ሎሌነትን  ይጸየፋል ፤ ነጻነቱን ይሻል፤ በጠመንጃ ሳይሆን በህግ መተዳደርን ይፈልጋል፤ በድምጹ የሚመርጠውን መንግሥት ማየት ወዘተ ይመኛል፡፡ እነዚህ ሁሉ  ቢሟሉ ደግሞ  አንባገነኖች በሥልጣን ላይ ውለው ማደር አንደማይችሉ ስለሚያውቁ  ተግባራዊ አየደርጓቸውም፡፡ እንደውም ሰው ነኝ የሚል ሰው የሚያቀርባቸው ጥያቄዎቸም ሆኑ ምኞት ፍላጎቶች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መሆናቸው ይቀርና  የስልጣን ጥያቄ ተደርገው በአንባገነኖች እየተተረጎሙ  ለጥቃት ምክንያት ይሆናሉ፡፡ ሁሉም ዜጋ እኔ ሰው ነኝ ማለቱንና ሰው በመሆኑ ሊኖሩት የሚገቡትን መብቶቹን  ትቶና ረስቶ አቤት ወዴት ብሎ ቢያድር ወያኔን ከነምናምኑ ተቀብሎ ቢኖር  የሚፈጸም ጥቃት ቀርቶ በደል አይኖርም፡፡ ስለሆነም እንግዲህ በዜጎችና በገዢዎች መካከል ያለው  መሰረታዊ ልዩነትም ሆነ  የጥቃት በደሉ ምክንያት የብሄር ማንነት ሳይሆን አንበገነናዊ አገዛዝ  ነው ማለት ይቻላል፡

ከላይ በተገለጸው የዜጎችና የአንባገነኖች መሰረታዊ ልዩነትና የበደል ጥቃት ምክንያት መስማማት ከቻልን የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ብቻ ሊኖረው የሚገባው ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች  በብሄረሰብ ልዩነት ምክንያት የሚለያዩ አይደሉም፡፡ አንዱ ብሄረሰብ ከሌላው ተለይቶ ለእኔ ብቻ የሚገባኝ ብሎ ሊያነሳቸው የሚችሉ ጥያቄዎችም ሆኑ የሚሻቸው ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ያሉ አይመስለኝም፡፡ሰለሆነም ልዩነቱ አንባገነንነትና አልገዛም ባይነት ነው፡፡መፍትሄው ደግሞ የአንባገነኖችን በደል በብሄረስብ እየሸነሸንን የየራሳችንን መልክና ቅርጽ እየሰጠን ከመከፋፈል ተላቀን  ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመስረት መቻል ነው፡፡

ኢትዮጵያችንን በዴሞክራሲያዊ ጽኑ መሰረት ላይ የቆመ መንግስት ባለቤት ማድረግ ቢቻል  የሁሉም  ልጆቿ የሰው ልጆች ሰው በመሆናቸው ብቻ የሚኖራቸው  ከልካይ አንጂ ሰጪ  የሌለው  መብታቸው፣ የዜግነት ክብራቸው፣የብሄር ማንነታቸው፣ እምነት አመለካከታቸው ወዘተ በእኩልነት የረጋገጣል፡፡ እነዚህ መብቶች ሥልጣን ላይ ያለው ፓርቲ አባል በመሆን አለመሆን በመደገፍ በመቃወም ወዘተ ልዩነት ሳይደረግ በህዝብ ንቁ ተሳትፎና ይሁንታ ተግባራዊ የሚሆነውን ህገ መንግሥት አክብረው ለሚኖሩ ዜጎች ሁሉ በእኩል ተፈጻሚ ስለሚሆኑ በዜጎችና በመንግሥት መካከል የሚፈጠር መሰራታዊ ልዩነት አይኖርም፡፡ አበው ሰው በሀገሩ ቢበላ ሳር ቢበላ መቅመቆ ይከበር የለም ውይ ሰውነቱ ታውቆ ይሉት የነበረውም ያኔ እውን ይሆናል፡፡

አንድ ሁለት ተጨባጭ ጉዳዮቸን በመጠኑ አንመልከት

አማራው በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሀገሬ ብሎ ሲኖር ለጥቃት ተጋልጧል በክልሉም በወያኔ ጥቃት እየደረሰበት ነው ስለዚህ መደራጀት አለበት ሲባል አንሰማለን፡ የተደራጁም አሉ፡፡በተለያዩ ክልሎች ይኖሩ በነበሩ ወገኖቻችን ላይ ጥቃት የተፈጸመው አማራ በመሆናቸው ነው ብሎ ለመቀበል የሚቸግረው እነዚህ ወገኖቻችን በዛ አካባቢ መኖር የጀመሩት ከብዙ አመታት በፊት በመሆኑ ጉዳዩ አማራነታቸው ከሆነ እስከ ዛሬ አንዴት በሰላም ኖሩ የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ነው፡፡ መኖር ብቻ ሳይሆን በአካባቢው ከሚኖሩ ሌሎች ብሄረሰቦች ጋር ተጋብተዋል ተዋልደዋል በተለያዩ ማህበራዊ ግንኑነቶች ተሳስረዋል፡፡

ስለሆነም ነገሩን በወገኖቻችን ለይ የደረሰው በደል ከፈጠረብን ስሜት ሰከን ብለን ካየነው ችግሩ አማራነታቸው ሳይሆን የአንባገነኖች እርስ በእርስ እያጋጩ የሥልጣን ዘመንን የማራዘም እኩይ ሴራ ውጤት ነው፡፡  እነዚህ ወገኖች እኔ ሰው ነኝ ሳይሉ ተገዢነትን አሜን ብለው በወያኔ አገልጋዮች በኩል ለወያኔ እየገበሩ መስለው ተመሳስለው ቢኖሩ እንደማይነኩ ይገመታል፡፡ ስለሆነም ችግሩ የተፈጠረው በአማራነታችን/ቸው ነው ሲባል ይህን የወያኔ እኩይ ተግባር ማለምለም ይሆናል፡፡

አማራው በሚኖርበት ክልልም እየተበደለ መሆኑ አነጋጋሪ አይደለም፡፡ ይህም  አንደኛ ከላይ ለማየት አንደተሞከረው እኔ ሰው ነኝ በሚሉት ላይ አንጂ በሁሉም አማራ ላይ ባለመሆኑ፤ በወያኔ አገዛዝ ስር ባሉ ሁሉም ክልሎች የሚፈጸም በመሆኑ  እንዲሁም የበደሉ ፈጻሚዎች የወያኔ አገልጋይ አማሮች በመሆናቸው የበደሉ ምክንያት አማራነት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡

በኦሮሞዎችም ላይ የሚፈጸመው በደል የዚሁ ተመሳሳይ ነው፡፡ ለሰሞነኛው ያላባራው ተቃውሞ ምክንያት የሆነውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ብንመለከት ኦሮሞን ለማፈናቀል ባህሉን ቋንቋውን ላማጥፋት በኦሮሞ ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው የሚለው ትክክል አይመስለኝም፡ ምክንያቱም አንደኛ  አጋጣሚ ሆኖ አዲስ አበባ በኦሮምያ ክልል መገኘቷ አንጂ በአንድ ወይንም ከዛ በላይ በሆነ አቅጣጫ ሌላ ተጎራባች ክልል ቢኖር ማስተር ፕላኑ ሁሉንም ነበር የሚነካው፤ ስለሆነም ጉዳዩ  የወያኔ የመስፋፋትና መሬት የመቀራመት  እንጂ በተለየ ኦሮሞን የማጥቃት አይደለም፡፡ ሁለተኛም  እስካሁን በአዲስ አበባም ሆነ በአካባቢው  የተፈጸመው ማፈናቀል የቦታውን መፈለግ አንጂ በቦታው ላይ  የሚገኙ ዜጎችን ብሄረሰብ ማንነት መሰረት ያደረገ አይደለም፡፡ በሶስተኛ ደረጃም የድርጊቱ ዋና አስፈጻሚዎች ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ ኦሮሞ በኦሮሞ ላይ የሚፈጽመው ጥቃት ብሄርን ምክንያት ያደረገ ሊባል አይችልም፡፡

ስለሆነም የችግሩ  ምንነትም  ሆነ የጥቃቱ ምክንያት አንበገነናዊ ሥርአት አንጂ የተጠቂዎች ብሄር ማንነት አይደለም፡፡ መፍትሄውም ጥቃቱን በየብሄር እየለያዩ መለያየት ሳይሆን በጋራ ትግል ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መብቃት ነው፡፡

The post የጭቆናው ምክንያት   አንባገነናዊ ሥርዓት  ወይንስ የብሄር  ልዩነት ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአባይ ወልዱ በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም የህይወት ዋጋ ያስከፍላል! |ጎንደር ህብረት

0
0

abay weldu

ጎንደር ህብረት

የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ብሎ እራሱን የሚጠራዉ ድርጅት መሪ አቶ አባ ወልዱ እና የክልሉ የፀጥታና የአስተዳደር ኃላፊ አቶ ሐድስ ዘነበ ከዘራፊ ካድሬወቻቸው ጋር በመሰባሰብ፤ በወልቃይት፤ በጠገዴ እና በጠለምት ህዝብ ላይ የማያዳግም ጦርነት ለማካሄድ የጦር ነጋሪት እየደለቁ በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ። ጦርነቱን በሚፈልጉት መንገድ በድል ለመወጣት እየተጠቀሙበት ያለው የሞራል መምቻ ደግሞ፤ ህብረተሰቡን፤ በገብያ፤ በቤተክርስቲያን እና ቤት ለቤት በማደን እያስፈራሩ ወደፖሊስ ጣቢ እየወሰዱ፤ ወልቃይት የትግራይ ክልል እንደሆነች እንድትቀጥል እንደሚፈልጉ በማሥመሰል በማሥገደድ እያስፈረሙ ናቸው።

Gondor Hibret

ሌላ የዚህ ሳምንት አስገራሚዉ የወያኔ ቲያትር ደግሞ፤ ከስህተት ላይ ሥተት በመደራረብ ህዝብና ህዝብን ለማጋጨት የትግራይ ተወላጆችን ስልፍ አሰልፎ በጉልበት ይዞት የቆየዉን መሬት የትግራ ነዉ እያለ ማስጨፈሩ ነዉ። ወያኔ በመላዉ ኢትዮጵያ ሰልፍ ከልክሎ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በታንክና መትረየስ እዬጨፈጨፈ፤ ጎንድር መሪ የሌለዉ መሆኑን የተረዳዉ ወያኔ ወገራ አዉራጃ ላይ የትግራይ ተወላጆችን ከጎንደር ህዝብ ጋር ቂም ለመትከል የዉሸት ሰልፉን አቀነባብሮ ያስጨፍራል። የተቃዉሞ ስሜትን በአደባባይ መግለጽ ከሆነማ ይህ አይነቱ ወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ብሎም ለመላዉ ጎንደር/ አማራ ህዝብ መፈቀድ የግድ ይላል።

ጦረኛ ቡድን በአሁኑ ሰዓት ሌላ ወንጀል እና ደባ ከመፈጸም ይልቅ፤ መደረግ የነበረበት፤ የወልቃይት፤ የጠገዴ እና የጠለምትን ህዝብ ባለፉት 25 ዓመታት በተፈጸመበት ግፍና በደል ይቅርታ መጠየቅ ነበር እንጂ አድሮ ጥጃ የሆነዉ የትግራይ ነፃ አዉጭ ግንባር የአማራን መሬት በሰፊዉ ለመቆጣጠር የጦርነት ክተት አዋጅ ነጋሪት መደለቅ እና በቴለቭዥን መስኮት ውሸት መርጨት አልነበረበትም። ይህ ድርጊት ታሪክ ይቅር የማይለው አሳዛኝ ተግባር ነው። ለዚህ ሰይጣናዊ ስራው የሚገጥመዉ ምላሽም በጣም የከፋ ሊሆን ስለሚችል ለጥፋት ብቻ ትግራይ መሬት ላይ የተቀመጠዉ አቶ አባይ ወልዱ በጊዜው የያዘውን ሥልጣን እና ያስታጠቀውን ሚሊሺያ ሌላ ሊበግረው የሚችል ሃይል መሥሎት በትቢት ወይም በድንቁርና ከአንድ ጥፋት ወደ ሌላ ጥፋት መሸጋገሩ ትልቅ አደጋ ነዉ። በመላው አገሪቱ በዜግነታቸው ኮርተው፤ የሚኖሩበትን ህብረተሰብ አምነው እና ተዋደው የሚኖሩትን የትግራይ ተወላጆች በወልቃይት ጠገዴ የግፍ እሳት ላለማቃጠል ቆም ብሎ እንዲያስብ እጅግ እናሳስባለን።

ላለፉት 30 ዓመታት የቃፍቲያ ሁመራ፤ ወልቃይት ጠገዴ/ጠለምት ህዝብ የአማራ ምንነቱን ተነጥቆ፤ አማራም ጎንደሬም አይደለህም ተብሎ፤ የዘር ማጽዳት ድርጊት ተፈጽሞበታል። ለዘመናት ከኖረበት መሬት ተፈናቅሎ ብዙ ትዉልድ ለስደት ተዳርጓል። ላለመሰደድ በቀየው መሞትን የመረጠ ተወላጅ፤ እጣ ፈንታው ለዘመናት ፀሐይን እንዳያይ ተወስኖበት እስር የሚማቅቀዉን ብዛት፤ የትግራ እስር ቤቶች ይቁጥሩት። በጀምላ የተቀበረዉን ደግሞ፤ ጊዜ እያወጣዉ ነዉ፤ ክቡር ገረመድን አራያ ይናገራሉ።

የዚህን አካባቢ ህዝብ ከገደለ እና ካፈናቀለ በኋላ፤ ብዛት ያላቸውን የትግራይ ተወላጅ የወያኔ ደጋፊዎቹን ተከዜን አሻግሮ አስፍሯል። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ይህን ሁሉ ግፍ እና በደል ከፈጸመ በኃላ፤ በአካባቢው ለህዝበ ውሳኔ ለማቅረብ የማጥቂያ ስልት ነድፎ ተነስቷል። በቂ የወልቃይት ተወላጆች የሉምና እኔ ያሰፈርኳቸውና አንዳንድ ሆዳሞች በድምጽ ብልጫ ለኔ ድምጽ ሊሰጡ ይችላሉ ብሎ በማመን፤ የዘወትር ዉሸትና ብልጥነቱን በማጠናከር እራሱ ፌደራል ብሎ በሰየመዉ ምክር ቤት ህዝቡ ተጠይቆ ምክር ቤት ይወስናል የሚል አጀንዳ ይዞ ብቅ ለማለት እየተዘጋጀ ነዉ። ከአሁን በኋላ፤ የወልቃይት አማራም፤ ጎንደሬም የመሆን ውሳኔ የሚጸናው፤ በወልቃይት መሬት በሰፈሩ ተከዜ ተሻጋሪ የትግራይ ተወላጆች ሳይሆን፤ የመላው ጎንደር ሕዝብ ውሳኔ ነው።

ይህ የማንነት ውሳኔ ደግሞ፤ በወያኔ መሪዎች በነ አባይ ወልዱ ችሮታ የሚለገስ ሳይሆን፤ በቆራጥነት፤ እነሱ የረገጡትን ጀግንነታችን አሥመስክረን በምንጎናፀፈው ነፃነት ብቻ ነዉ።። በዚህ መልክ ቆርጠን ስንነሳ ነው፤ የጎንደር ታሪካዊ መሬት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወደነበረዉ ወደጥንቱ ጎንደር ክፍለ ሃገር በአስቸኳይ ሊመለስ የሚችለው ብሎ የጎንደር ሕብረት አጥብቆ ያምናል። ይህ እንደሚመጣ ወያኔ አስቀድሞ በማወቁ፤ መላ የትግራይን ወንድ ልጅ ከመንግሥት ካዝና እየዘረፈ ሙሉ በሙሉ አስታጥቋል። ይን ለመመከት፤ ካሁን በፊት ደግመን ደጋግመን እንዳስጠነቀቅነው፤ ዛሬም እንዳለፈው፤ ለአቅመ አዳም የደረሰ ጎንደሬ በሙሉ መታጠቅ አለበት። የወልቃይት ጉዳይ፤ ከአዲስ አበባው ማስተር ፕላን በላይ በዜጎች ማንነት ላይ እዬተፈጸመ ያለ አስከፊ በደል ነው። በመሆኑም በቆራጥነት መስዋዕትነትን መክፈል፤ የማንነትም፤ የተወላጅ ባለቤትነትም፤ የዜግነት ግዴታ ነው።

ከዚያም በላይ! በጎንደር ህብረት አቋም እና እምነት ደግሞ፤ ይህ በጎንደር ህዝብ ላይ፤ ብሎም በሰፊዉ አማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የወያኔ ቱባ መሪ አባይ ወልዱ የክተት አዋጅ ወያኔ እራሱን እንደማነቅ ሲሆን፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍኖ የሚመራዉ ስርዓትም የመጨረሻዉ የሞት ጣር እና ኑዛዜ ከመሆን እንደማያልፍ እርግጠኛ ሁነን እንናገራለን። ታላቁን የአማራ እና የትግራይን ህዝብ ለማዳማት በፈጸሙት የአርባ አመታት የጭፈጨፋ እና የጥላቻ ዘመቻ በኪሳራ ስሌት እየገፋ የሁለቱ ማህበረሰብ እስከ አሁኑ ድረስ ችግርም ሆነ ደስታዉን የወያኔን ከፋፋይ መርዝ ተቋቁሞ በጋራ ህይወቱን እየገፋ ይገኛል። ይህ እንዳይደፈረስ ከታሰበ፤ “የትግራይ ህዝብ የጎንደርን መሬት በጉልበት እንድንገዛ ድጋፍ ሰቶናል” እያሉ የሥራዓቱ ሙስና እጃቸዉ የነካ ግለሰቦችን በማናገር በቴሌቢዥን መስኮት የሚያካሂዱት ቅስቀሳ በአስቸኳይ መቆም አለበት።

ሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብም የአቶ አባይ ወልዱን የእርስ በእርስ ጦርነት አዋጅን በመቃወም በጎንደር ሕዝብ ላይ የተቃጣዉን ጥቃት ለመጋፈጥ አጋርነታችሁን እንድታሳዩ በአክብሮት እንጠይቃለን። እንዲሁም የብሔረ አማራ ዲሞክራሲ ንቅናቄ (ብአዴን)ብሎ የሚጠራዉ፤ የአማራን ህዝ እወክላለሁ የሚለዉ የወያኔ አጋር ድርጅት፤ የወያኔ መጠቀሚያ መሳሪያ የመሆን የባዶ ጨዋታ ዘመን አክትሞ የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር የሚያካሂደዉን የመስፋፋት ዘመቻ እንቅስቃሴ ህዝቡ ተቃዉሞዉን በመግለጽ ምላሽ ለመስጠት በሚዘጋጅበት ሁኔታ ሁሉ ጣልቃ ገብቶ ተጽዕኖ ከማድረግ እንዲቆጠብ በጥብቅ እናሳስባለን።

በመጨረሻም፤ ከህዝብ አብራክ የወጣዉ ሰራዊትም የአገሩን ዳር ድንበር ከማስከበር ዉጭ የወያኔ ታዛዥ ሁኖ በዘረኛ መንግስት የተበደለ ወገኑን ተኩሶ ከመግድል እንዲቆጠብ እናሳስባለን።፤ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን አረመኒያዊ የግፍ ሥራዓት ሊሸከም ባለመቻሉ፤ በእምቢተኝነት እየተነሳሳ ያለውን ወገንህን፤ በተለይም በሽዋ፤ በወለጋ፤ በአርሲ፤ በሃረር በጋምቤላ፤ የሚያካሄደዉን ጭፍጨፋ በአስቸኳይ እንዲቆም ወገናዊ ጥሪያችን እናስተላልፋለን። እንዲሁም፤ የወያኔ መንግስትም ብዙ ደም ሳይፈስ ስልጣን ለቆ አገሪቱን የሚያድን፤ ህዝቡን የሚያረጋጋ፤ ሁሉን ያካተተ በሕዝብ የተመረጥ መንግስት በአስቸኳይ እንዲቋቋም በጥብቅ እናሳስባለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ጎንደር ህብረት።

The post የአባይ ወልዱ በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም የህይወት ዋጋ ያስከፍላል! | ጎንደር ህብረት appeared first on Zehabesha Amharic.

የዕለቱ ምርጥ ካርቱን |ሚሚ ስብሃቱ

የኦባማን እምባ ለእነዚህ በኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ የተነሳ በአጋዚ ሰራዊት ለተገደሉት ሕጻናት እንዋሰው |ቪዲዮ

የካቲት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነጻነቱ የታገለበትና መስዋዕት የከፈለበት ታሪካዊ ወር –ሸንጎ

0
0

የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ.ም.

shengoየካቲት በኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ የያዘ ወር ነው።ጣሊያን አገራችንን በወረረበት ጊዜ  ዜጎች በአንድ ቀን ጀንበር በየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ከ30000ሺ ሰው በላይ በአዲስ አበባና አካባቢዋ ብቻ በጠላት መትረየስ የታጨዱበት በአካፋ የተጨፈጨፉበት መስዋእት በመሆን ደማቸውን ያፈሰሱበት  ዕለት በመሆኑ ሊታሰብና ሊከበር ይገባዋል።በዚያን ዕለት ጣልያኖች እርምጃውን ሲወስዱ ሕዝብ ፈርቶ ያድርልኛል፣ይገዛልኛል በሚል እምነት ነበር።ውጤቱ ግን የብዙ ወጣቶችን ልብ የቀሰቀሰና ለትግል እንዲሰለፉ ያደፋፈረ ሆነ።

በዚያ ዓይን ያወጣ የጭካኔ እርምጃ የተጨፈጨፉት ዜጎች ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተወለዱና ከልዩ ልዩ ያገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው።የጣሊያን ወራሪ ሃይል ጠቅላይ አዛዥ የሆነው ግራዚያኒ ሕዝቡን ሰብስቦ  በሱ የሚመራውን የወራሪውን አስተዳደር እንዲቀበልና ባወጣው ሕግ እንዲተዳደር ለማድረግ ብሎም የጣሊያን መንግስት ለኢትዮጵያ እድገትና መሻሻል  እንጂ  ለመጉዳት የመጣ አለመሆኑን ለማሳመንና ለድሆች እርዳታ እሰጣለሁ በሚል የማታለያ ሰበብ ስብሰባ ጠራ።

ሕዝቡን ለመሰብሰብ ያስገደደው ዋናው  ምክንያት በየአቅጣጫው በዱር በገደል ተሰማርቶ ለአገሩ ነጻነት የሚታገለው አርበኛ ቁጥርና በጠላት ላይ የሚያደርሰው አደጋ እየጨመረ በመምጣቱ፣በከተማም ውስጥ ያለው ጫካ ባይገባም ልቡ ሸፍቶ ለጠላት አልገዛም ባይነት ስሜቱ እያደገ በውስጥ አርበኝነት ተግባር ላይ ተሰማርቶ ለአርበኞቹ የስንቅና የመረጃ ምንጭ በመሆኑ ይህን ሕዝብ በማታለልና በማስፈራራት በቁጥጥር  ስር ማድረግ እንዳለባቸው በመገንዘብ ነበር።

ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በጠላት ጦር አዛዦችና ሹማምንቱ ላይ በተለይም በግራዚያኒ ላይ አደጋ ለመጣል ምክርና ዝግጅት አድርገው በተግባር የገለጹት በኤርትራ  ክፍለ ሃገር የተወለዱት አገር ወዳድ ወጣቶች  አብርሃ ደቦጭና  ሞገስ አስገዶም ነበሩ።

ወጣቶቹ ግራዚያኒ በሰገነቱ ላይ ቆሞ ንግግር ለማድረግ ሲዘጋጅ ከመሃል ሳይታሰብ ፎክረው በመውጣት ያዘጋጁትን ሰባት  ቦምብ አከታትለው ወረወሩ።እንዳጋጣሚ ሆኖ የተወረወረበት ግራዚያኒና ከሃምሳ ሁለት በላይ አጃቢ ሹማምንቶቹ  የመቁሰል  አደጋ ሲደርስባቸው የሞሰለኒ አማች የነበረው አንድ ዓይኑ ጠፍቶ አንድ እግሩ ተቆርጦ ተዘረረ። ስብሰባው በሽብር ተናወጠ፤ በሁኔታው የተደናገጡትና የተበሳጩት ጣሊያኖችና  ባንዳዎቻቸው በእጃቸው ባለ ጠመንጃና ሌላም መሳሪያ ሕጻን፣ወጣት፣ ሽማግሌና አሮጊት ሳይለዩ በአደባባይ የተሰበሰበውን  ረፈረፉት።በማከታተልም የቤት ለቤት  ፍተሻ አድርገው የጠረጠሩትን ሁሉ አፍሰው ረሸኑት። የነዚያ የንጹሃን ደም በገዛ አገራቸው መሬት ላይ በውጭ ወራሪዎች እጅ ፈሰሰ። ያ ቀን  የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም.የጣልያኖችን ግፍና  ጭካኔ የኢትዮጵያኑን ድፍረትና ቆራጥነት በድጋሚ  ያረጋገጠ ዕለት ነበር።

የኢትዮጵያኖቹ አልገዛም ባይነት ባገራቸው ብቻ ተወስኖ አልቀረም በጣልያኖቹ ከተማ በሮማ አደባባይ ሳይቀር የኤርትራው ክ/ሃገር ተወላጅ ዘርአይ ደረስም ያገሩ ሰንደቅ ዓላማ አረንጓዴ ቢጫና ቀይ መሬት ላይ ተነጥፎ ጠላቶች ጫማቸውን እየጠረጉበትና እየረገጡት ሲሄዱና ሲያፌዙበት  ማየቱ አላስችል ብሎት እምቢ ላገሬ!፣እምቢ ለክብሬ!እምቢ ለባንዲራዬ !ብሎ ከጣልያኖች ጋር ግብግብ ገጥሞ የሚችለውን ያህል ጉዳት አድርሶ ህይወቱን ሰጥቷል።

በአደዋና በማይጨው ጦር ሜዳና ከዚያም በዃላ በተደረገው የአምስት ዓመት ትግል በዱር በገደል ተሰማርተው ደማቸውን ያፈሰሱት፣የቆሰሉትና ለድል ቀን የበቁት እኛም በነጻ አገር ተወልደን እንድንኖር  ያበቁን ከአንድ የህብረተሰብ ክፍል የተወለዱና ከአንድ አከባቢ ብቻ የመጡ ሳይሆን ከመላ የአገሪቱ ክፍል፣ ከጫፍ እስከጫፍ  ከሚኖሩት የተለያዬ  ቋንቋ የሚናገሩና በአንድ አገር ልጅነታቸው በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑና የሚኮሩ ጀግኖች ነበሩ።ምንም እንኳን ጥቂቶቹ ደካሞች ለጥቃቅን ጥቅምና የጠላትን መሰሪ ዓላማ ካለመረዳት በባንዳነት ያገለገሉ መኖራቸው ባይካድም አብዛኛዎቹ ለአገራቸው ክብር ነጻነትና ዳር ድንበር በየጊዜው ከመጣ ጠላት ጋር እየተዋጉ አስከብረው የኖሩ ናቸው።የነዚያን ደፋርና ጀግኖች ውለታ ለመክፈል ያስከበሩትን የአገር ነጻነትና አንድነት ማስከበር የአሁኑ ትውልድ አላፊነት ነው።የአሁኑ ትውልድ ከትናንቱ ትውልድ አገር ወዳድነትን፣ጀግንነትን ሊወርስ ይገባዋል።ለተተኪውም ትውልድ የማውረስ አላፊነትም አለበት።ይህን ለማድረግ ታሪካዊ ዕለቶችን እያስታወሱ መዘከር አንዱ ነው።የኢትዮጵያ ጠላቶችና ተባባሪዎቻቸው ኢትዮጵያውያን ያደረጉትን ተጋድሎና ያረጋገጡትን ድል እያጥላሉ  ለመጭው ትውልድ ምሳሌ እንዳይሆን በልዩ ልዩ ዘዴዎች እንዲረሳ በማድረግ ላይ ቢሆኑም  ምኞትና ፍላጎታቸው እንዲሳካ መፍቀድ የለብንም።የማንነታችን አንዱ መግለጫ ነውና ልንዘናጋ አይገባም።በታሪካችን ላይ ዘመቻ ሲካሄድ  በዝምታ ማለፍ  የለብንም።አክብረን ማስከበር አለብን።

በዚሁ የካቲት ወር 1888 ዓ.ም. ኢትዮጵያዊ አባቶቻችንና እናቶቻችን ይህንኑ የጣሊያን ወራሪ ሃይል ለመጀመሪያ ጊዜ  ቅጣት ሰጥተው የመለሱበትን፣ለሌላው የቅኝ አገዛዝ ሰለባ ለሆነው በተለይም ለአፍሪካ ሕዝብ የነጻነት ትግል ደወል የሆነውን የአድዋን ድል እናከብራለን።የአድዋ ድል ኢትዮጵያውያኖች ብቻ ሳንሆን የሌላውም አገር ጥቁር ሕዝብ ለነጻነቱ እንደ አርማ አድርጎ የሚወሰደው የታሪክ አምድ ነው።በዚህም የነጻነት ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ በጋራ ጎሳና ቋንቋ ሃይማኖት ሳይለየው  በአድዋ ጦር ሜዳ ተሰልፎ ለነጻነቱ መስዋእት ሆኗል። የዛሬ መቶ ሃያ ዓመት  የቀድሞዎቹ በከፈሉት የህይወት ዋጋ  የእኛ ትውልድ የሚኮራበትን የድል ውጤትና ነጻ አገር አስረክበውን አልፈዋል።ያንንም በሚገባ መዘከርና ታሪኩ ከትውልድ ትውልድ እንዲሸጋገር የማድረግ ሃላፊነት አለብን።

ኢትዮጵያውያን በጣልያን ላይ ያደረሱት ውርደት ለአውሮፓውያን ቅኝ ገዥወች ቅሌትን ያከናነበ ፣ ለሌሎቹም የቅኝ ግዛት አስተዳደር ለሰፈነባቸው አገር ሕዝቦች የነጻነት ምሳሌ በመሆኑ ለመበቀል ኢትዮጵያ የምትባል አገርና ሕዝብ እንዳይኖሩ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ ኖረዋል፤በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ የሕዝቡን አንድነት በመቦርቦር  የእርስ በርስ ግጭት እንዲኖር ያልሞከሩበት ወቅት የለም።እንደ አብርሃ ደቦጭ፣ሞገስ አስገዶምና ዘርአይ ደረስ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑና የሚኮሩ ሌሎች ኤርትራውያን እንዳይበቅሉ፣ እንደ አሉላ አባ ነጋ ያለ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ የጦር መሪ ፣ በስለላ የጣሊያኖችን ጦር መቀመቅ የከተተው  እንደ አውዓለም በትግራይ መሬት ዳግመኛ እንዳይወለድ፣እንደ ጎበና ዳጬ፣እንደ ጃጋማ ኬሎ፣ ደረሱ ዱኪ፣አብዲሳ አጋ ፣ይልማ ደሬሳ ያሉ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን የኦሮሞ ልጆች እንዳይፈጠሩ፣እንደ ሃብተጊዮርጊስ፣እንደ ወልደሥላሴ በረካና ሌሎቹም  ያሉ የጉራጌ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን የጦር አበጋዞች ዳግም እንዳይወለዱ፣ እንደ መኮንን ጉዲሳ( ሃ/ሚካኤል) እምሩ ሃይለሥላሴ፣ደስታ ዳምጠው፣በላይ ዘለቀ፣አሞራው ውብነህ፣መስፍን ስለሽ፣አበበ አረጋይ፣ ሃይለማርያም ማሞ፣አክሊሉ ሃብተወልድንና  ሌሎቹንም የመሰሉ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ፣ እንደ ተፈሪ፣ምኒሊክ፣ ዩሃንስና ቴዎድሮስ ያሉ  ለጠላት  ያላጎበደዱ መሪዎች፣ ከሴቶችም ጣይቱ ብጡል፣መነን አስፋው፣ ጸሃይ ሃይለሥላሴ፣ሸዋረገድ ገድሌ፣ስንዱ ገብሩ፣ጽጌ መንገሻ፣ከበደች ስዩም፣ቀለመወርቅ ጥላሁን፣ላቀች ደምሰው፣ ቆንጅት አብነትንና ሌሎቹንም የመሰለ  አርበኞችና የጦር መሪዎች ዳግመኛ እንዳይነሱ ለማድረግና ኢትዮጵያዊነትን ለማደብዘዝ የቆዬ ፍላጎታቸውን  እውን ለማድረግ ለዘመናት ሲያውጠነጥኑት የቆዬ ሴራ ነው። ይህን ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ በቀጥታ እራሳቸውን ለዳግመኛ ውርደት ከማቅረብ ይልቅ አገር በቀል ተባባሪዎቻቸውን በማደራጀትና በመርዳት አሁን በስልጣን ላይ በሚገኘው ጸረ ኢትዮጵያ ቡድን አማካኝነት   በታሪክ ና በሁሉም መልክ ተሳስሮ የኖረውን የኤርትራ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን እንዲክድና እንዲረሳ፣የባህር በሯን ለመንፈግ ኤርትራን አስገንጥለው ሌላውንም እንዲሁ ለማስገንጠል ሌት ተቀን በመስራት ላይ ይገኛሉ።  የህወሃት/ኢሕአዴግ ስብስብ የሕዝቡን መብትና እኩልነት ለማረጋገጥ የሚሰራ ሳይሆን አንድነቱን አናግቶ አንድ ጠንካራ አገር እንዳይኖረው ፣በተበጣጠሰ ክልል ውስጥ በበረት ውስጥ ተቀፍድዶ እንደሚያድር እንስሳ እንዲኖር ለማድረግ  የሚሠራ የጥፋት መልእክተኛ ቡድን ነው።መሆኑንም በየቀኑ ከሚያካሂዳቸው አገር አጥፊ ክንውኖቹ ለመገንዘብ ይቻላል።  በቋንቋ፣በሃይማኖት፣በክልል ሳቢያ ልዩነት እየፈጠረና ጥላቻ እያሰራጨ  ሕዝብ እርስ በርሱ እንዳይተማመን አልፎ አልፎም እንዲዋጋ አድርጎታል።በፌዴራሊዝም ስም ዜጋ ከኢትዮጵያ(ከአገር) ባለቤትነት ወጥቶ በደባልነት እንዲኖር፣ሐሀገራዊ ሲሜቱና የጋራ እሴቱም እንዲሸረሸር ማድረግ እውነት ለእድገት የሚጠቅም ነውን?ሕዝቡን ከድህነት፣ከዃላቀርነት፣ያድነዋልን? ይህ ታዲያ ከጣሊያኖቹ ከፋፋይ ተግባር በምን ተለዬ?

ካለፉት ትግሎችና ከተከፈለው መስዋእት የምንወስደው ጠቃሚ ትምህርት ለአገር ክብር መዋጋት ማለት፣ለእራስ ክብርና ነጻነት መዋጋት እንደሆነና ያም በተናጠል ትግል የሚገኝ እንዳልሆነ ነው።ስለዚህም አገራችን ከገባችበት ቀውስና አደጋ ለመከላከል፣ነጻነቷንና አንድነቷን ጠብቆ ለተተኪው ትውልድ ለማውረስ የተጣለብን የታሪክ አደራ ነውና እንደ ቀድሞ ትውልድ  እጅ ለእጅ ተያይዘን የተጋረጠብንን አደጋ በጋራ ልናሶግደው ይገባናል።

የዛሬ አርባ ሁለት ዓመት በ1966 ዓ.ም.የካቲት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ከዳር እስከዳር  ለመብቱ የተነሳበትና ትግል የተቀጣጠለበት ወር በመሆኑ በታሪክ መዝገብ ውስጥ ሰፍሯል።በአሁኑም በያዝነው የየካቲት ወር 2008 ዓ.ም.የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች ለመብቱና ለአንድነቱ መስዋእት እየከፈለ የሚገኝበት የትግል ወቅት ነው።ካለፉት የካቲቶች ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ትግሉ በአንድነት ዙሪያ ገና ያልተቀናጀና ከአገራዊ ገጽ ይልቅ የአከባቢና የተከፋፈለ ስሜት የሚንጸባረቅበት መሆኑ ነው።ይህንን ክፍተት በአስቸኳይ በመሙላት እና  ብሔራዊ ስሜት ሳይላላ፣የአገር አንድነት አደጋ ላይ ሳይወድቅ  ሕዝብ ተባብሮ ሙሉ ነጻነቱና እኩልነቱ የተረጋገጠባት የዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ባለቤት የሚያደርገውን ትግል ከግብ ለማድረስ እጅ ለእጅ ተያይዞ ዳግም የካቲትን እውን ማድረግ የወቅቱ ዋና ጥያቄ ነው። የተናጠል ትግል  ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል።ከትንሽነት ትልቅነት፣ በትንሽ ክልል ነዋሪነት ከመታጠር ይልቅ የትልቅ አገር ዜጋ ሆኖ በፈለጉበት ቦታ የመኖርና የመስራት መብት፣የብዙ ሃብትና ዕድል ባለቤት መሆን ይሻላልና  የመነጣጠልን ጎጂ አዝማሚያና  መሰረታዊ አገራዊ ለውጥ እኩልነትና ነጻነት ፈላጊ የሆነ ሁሉ ሊታገለው ይገባል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ለየካቲት አስራ ሁለት 1929 ዓ.ም. ሰማእታትና ለየካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ለአድዋ ድል ባለቤት ለሆኑት ኢትዮጵያውያን ትልቅ ክብር አለው። በደማቸው ያስረከቡንን ነጻ አገርና የህዝቡን መብት ለማስከበር ከሁሉም   አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ለመስራትና  ለመታገል ቁርጠኝነቱን አሁንም ይገልጻል። በዚህ አጋጣሚም ለቀሩት ኢትዮጵያውያን እንደ ጥንቶቹ የአገር ፍቅርና የአንድነት መንፈስ እንዲኖረን ፣ለማንኛውም ከፋፋይ ተግባር ቦታና ዕድል ሳንሰጥ አገራችንና ሕዝባችን  ከገጠማቸውና ሊገጥማቸው ከሚችለው ግፍ በደልና አደጋ ተባብረን እናድናት ይላል።

የአድዋውን ድል በመዘከር ምሳሌነቱንም በመቅሰም ልዩነታችንን አቻችለን በዘመናችን ባለው የውስጥና የውጭ ጠላት ላይ ዘምተን ድል ማድረግ ይጠበቅብናል። አባቶቻችን የነበሩበትን የየካቲት ወር ለቁምነገር ስራ እንደተጠቀሙበት ሁሉ የእኛንም የዘመናችንን የካቲት ወር የቁም ነገር መስሪያ አድርገን በታሪክ የያዘውን ቦታ እንድንደግመው ሸንጎ ያሳስባል። ለዳግማዊ የካቲት በጋራ እንነሳ!

አንድነትና ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁን!

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ

 

The post የካቲት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነጻነቱ የታገለበትና መስዋዕት የከፈለበት ታሪካዊ ወር – ሸንጎ appeared first on Zehabesha Amharic.


የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ለመንግሥትና ለምዕመናን የሰላም ጥሪ አቀረበ

0
0

front1651‹‹ሽማግሌዎች የሌሉበት አገር የሚባልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል›› ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ማክሰኞ የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤቱ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሱት ተቃውሞችና አለመረጋጋቶች አስመልክቶ ባወጣው የአቋም መግለጫና ሃይማኖታዊ ጥሪ፣ መንግሥትንና ምዕመንናን ለሰላማዊ መድረክ እንዲተጉ ጥሪ አቀረበ፡፡
የሰባቱም የሃይማኖት ተቋማት ተጠሪዎች፣ የጉባዔው የቦርድ አባላትና የበላይ ጠባቂዎች በተሰየሙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ ኡመር አሚንና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል፣ በአገሪቱ እየታየ ያለው አለመረጋጋት ከፍተኛ ሥጋት እንዳሳደረባቸው ገልጸዋል፡፡
ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ በኦሮሚያ፣ በአማራና በጋምቤላ ክልሎች የተቀሰቀሱና አሁንም ያልበረዱ ግጭቶች አገሪቱን ወደ ኋላ የሚመልሱና እየታየ ያለውን ለውጥ የሚያጠለሹ እንደሆነ በመጠቆም፣ መንግሥትና ሕዝብ ለሰላማዊ መድረክ ትኩረት እንዲሰጡና አለመግባባትን በማርገብ ለዘለቄታዊ መፍትሔ እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በግጭቶቹ ምክንያት የሚጠፋው የሰው ክቡር ሕይወት፣ የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት ያሳዝናል በማለት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ፣ ‹‹ለዘመናት የተመሰከረልን አብሮ የመኖርና የሃይማኖት መቻቻልን ጥላሸት የሚቀቡ አጋጣሚዎችን በመጥቀስ፣ ሽማግሌዎች የሌሉበት አገር የሚባልበት ጊዜ ላይ ተደርሷል፤›› በማለት ማንኛውንም ግጭትና አለመግባባት ለመፍታት ውጤታማ የሆነውና ባህላዊው የሽምግልና ሥርዓት መዳከም እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በምዕራብ አርሲ በቅርቡ በተፈጠረው ግጭት የሞቱትን ወገኖችና የወደሙ የልማት ተቋማትና መሠረት ልማቶችን በመጥቀስ በጥፋተኝነት የሚወነጀሉ አካላት ሁሉ ለፍርድ መቅረብ እንደሚገባቸው ያሳወቀው የሃይማኖት ተቋማቱ ጉባዔ፣ በቀጣይ መንግሥትና ምዕመናኑ ለሰላም የሚተጉበት ጊዜ እንዲሆን በሁሉም ቤተ እምነቶች ጾምና ጸሎቱ እንዲጠናከርም ጥሪ አድርገዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባስተላለፉት መልዕክት በእምነት ተቋማት ላይ እየደረሰ ያለው ውድመት መቆም እንዳለበት፣ ምዕመናን በየቤተ እምነታቻው የፈጣሪያቸውን ምሕረት በመለመን ለአገርና ለወገን ሰላምን፣ ፍቅርንና መቻቻልን እንዲያበዛ በጸሎት መትጋት እንዳለባቸው አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከስድስት ዓመታት በፊት በሰባት የእምነት ተቋማት መሪዎች የተመሠረተ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያንና የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት በአባልነት ያቀፈ ነው፡፡ ተቋሙ በአገሪቱ ለረዥም ዓመታት ፀንቶ የቆየውን መቻቻልንና ሰላምን በማጠናከር፣ ለሕዝብ አንድነትና ለአገር ብልፅግና የሚሠራ መሆኑን የሃይማኖት መሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር

The post የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ለመንግሥትና ለምዕመናን የሰላም ጥሪ አቀረበ appeared first on Zehabesha Amharic.

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስተር በአንዳርጋቸው እና በሌሎችም ጉዳዮች ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ ሊያቀኑ ነው

0
0

(ዘ-ሐበሻ) የመን ላይ በሕወሓት መንግስት ተጠልፈው በአዲስ አበባ ባልታወቀ ቦታ ታስረው እየተሰቃዩ የሚገኙት ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ እንዲፈቱ ያሳዩት ባህሪ ለዘብተኛ ነው በሚል የብሪታኒያ ታዋቂ ግለሰቦችና የፓርላማ አባላት ያካተተ የ135ሺ ፌርማዎችን ለጠቅላይ ሚንስትሩ ዴቭድ ካሜሮን ካስገቡ በኋላ ጠቅላይ ሚንስትሩ በቅርቡ ለጉብኝት ወደ አዲስ አበባ እንደሚሄዱ የሃገሪቱ ሚድያዎች ዘገቡ::
Andargachew Tsige David Cameron

ዴቭድ ካሜሮን በቅርቡ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት በተመለከተ የብሪታኒያ የኢሚግሬሽንና ዜጎች እንዲሁም ተጓዳኝ ጉዳዮችን የሚከታተለው ሆም ኦፊስ ምክትል ቋሚ ፅሃፊ የሆኑት ኦሊቨር ሮቢንስ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በመዲናችን አዲስ አበባ እየተወያዩ እንደሚገኙ ምንጮች አስታውቀዋል::

ዴቭድ ካሜሮን ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ የአቶ አንዳርጋቸውን መለቀቅ እንደ አንድ አጀንዳ እንደሚያነሱት የሚጠበቅ ሲሆን ይህም በዚህ ጉዳይ ለዘብተኝነት አሳይተዋል በሚል ለደረሰባቸው ወቀሳ ምላሽ ለመስጠት ነው የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች አሉ::

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢትዮጵያ የት ታስረው እንደሚገኙ ባይታወቅም በቅርቡ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ “በአባታቸው እየተጎበኙ” እንደሚገኙ መረጃ አለን ብለዋል:: አቶ አንዳርጋቸውም በቅርቡ ከ እስር ካልተለቀቁ የአ እ ምሮአቸው ሁኔታ አስጊ እንደሆነ የ እንግሊዝ ዲፕሎማቶች መግለጻቸውን ዘ-ሐበሻ መዘግቧ አይዘነጋም::

The post የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስተር በአንዳርጋቸው እና በሌሎችም ጉዳዮች ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ ሊያቀኑ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

የ1884 ዓመተ እግዚእ የበርሊን ኮንፈረንስ እና የ1882 ዓመተ ምሕረት የዲማ ኮንፈረንስ ተመሳሳይነት |ጌታቸው ኃይሌ

0
0

Getachew Haile
በ1884 ዓመተ እግዚእ አፍሪካ ለቅርጫ መሥዋዕት ላይ የቀረበችበት ጉባኤ በርሊን ላይ ተካሂዶ ነበር። ጉባኤውን የጠራችው ፖርቱጋል ስትሆን፥ አዘጋጁ የጀርመኑ ካንስለር ኦቶ ፎን ቢስማርክ ነበር። የጉባኤው ዓላማ የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ሲሻሙ ግጪት እንዳይፈጠር የሺሚያ ሕግ ለማውጣት ነበር። ተስማምተው General Act of the Berlin Conference በሚል ስም የታወቀውን ውል አጸደቁ። ኮንፈረንሱ የጎሳ መሪዎች ንግድም፥ ጉቦም እያሳዩ የያዙትን ውሉ አጸደቀላቸው፤ ያልያዙትንም “ሕግ አክብረው” የሚይዙበትን ሥርዓት አወጣላቸው። አፍሪካውያን ሳይሰሙ አገራቸውን አውሮፓውያን ተከፋፈሉት፤(ከኢትዮጵያና ከላይበሪያ በቀር የቀሩትን)። ጉባኤውን ታሪክ The Scramble for Africa “ አፍሪካን ሽሚያ” በሚል ስም መዝግቦታል።

ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

The post የ1884 ዓመተ እግዚእ የበርሊን ኮንፈረንስ እና የ1882 ዓመተ ምሕረት የዲማ ኮንፈረንስ ተመሳሳይነት | ጌታቸው ኃይሌ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሚኒሶታና አካባቢው ለምትገኙ |የአቶ ብርሃኑ በየነ አልማው የለቅሶ መድረሻ እና የቀብር አፈጸጸም መረጃ

0
0

Funeral

አቶ ብርሃኑ በየነ አልማው በአደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ 69 አመቱ እኤአ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

በታህሳስ 1 ቀን 1950 እኤአ በጎጃም ክፍለ ሃገር በደብረማርቆስ ከተማ ተወለደ፤ ትምህርቱንም በዚያው ከተማ ከተማረ በሗላ፤ የመጀመሪያ ስራዉን ጎንደር ክ/ሃገር በሴቲቱ ሁመራ የአንድ የእርሻ ጣቢያ ሃላፊ ሆኖ በማገልገል ላይ እያለ በሃገሪቱ ዉስጥ የፖለቲካና የመንግስት ለዉጥ በመደረጉ ፤ አርሱም ወደ መንግስት ስራ ተዛዉሮ በጎንደር ክ|ሃገር በተለያዩ ኣዉራጃዎች ተዘዋዉሮ በተለያዩ የኣስተዳደር ሃላፊነት ዉስጥ የሰራ ከመሆኑም በላይ፤ ቤኤርትራ ጥያቄ ካለበ1992 በተፈጠረዉ የመንግስት ለዉጥ የሚወዳትን ሃገሩንና የሚወዳቸዉን ቤተሰቡን ትቶ ወደ ጎረቤት ኬኒያ ተሰደደ::

በ2004 ወደ ሃገረ አሜሪካን መጥቶ እስክ ታህሳስ 31 2015 ጡረታ ወጣበት ድረስ በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚነሶታ ዉስጥ ሲሰራ ቆይቷል::

አቶ ብርሃኑ በየነ አልማው የ 7 ልጆች ኣባት ነዉ።

በሃገር ዉስጥም ሆነ በዉጪ ሃገር ለሚኖሩ ቤተሰቦቹ፤ ወዳጆቹና ጏደኞቹ ሁሉ ቸሩ ዓምላካችን መፅናናትን ይስጥልን::

የለቅሶዉና የስርአተ ቀብሩ ፕሮርጋም እንደሚከተለዉ ነዉ።

ካረፈበት ግዜ ጀምሮ በእየ እለቱ ከቀኑ 4 pm ሰኣት ጀምሮ በ 2718 E Franklyn Ave. Minneapolis MN 55406 ለቅሶ መድረስ ይቻላል

ስርአተ ቀብሩ ቅዳሜ ፌብ. 27/ 2016

12:00 pm ስርዓተ ፍታት በ ርዕሠ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ስላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን። 2601 Minnehaha Ave. Minneapolis, MN 55406.

ከቀብር በጏላ ፀበልን ፃዲቅ በ ርዕሠ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ስላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን። 2601 Minnehaha Ave. Minneapolis, MN 55406.

ጥያቄ ካለ 612 644 7665

እግዚአብሔር የአቶ ብርሃኑን ነብስ ይማርልን!

2pm ስርዓተ ቀብር Hillside Cemetery & Funeral Home

,2600 19th Ave NE, Minneapolis, MN 55418

The post በሚኒሶታና አካባቢው ለምትገኙ | የአቶ ብርሃኑ በየነ አልማው የለቅሶ መድረሻ እና የቀብር አፈጸጸም መረጃ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለውድ ወያኔ ወንድሞቼ እና እህቶቼ! እባካችሁን ከባንዲራው ታረቁ |ከታምራት ነገራ

0
0

ለውድ ወያኔ ወንድሞቼ እና እህቶቼ!

ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ

ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ

የእስከአሁኑ ጉዟችሁ በየትኛውም አጋጣሚ ከኢትዮጵያ ብሔርተኞች የሚመጣውን ማንኛውንም ምክር በጥሞና እንደምትሰሙ አያሳይም፡፡ ምክር ስንሰጣችሁ ፤ ምክሩን ከሰማችሁም በኋላ ከምክሩ የሚጠቅመውን እና የሚጎዳውን ሃሳብ ለመለየት እንደምትጥሩ፤ ይጠቅማል እና ይጎዳል ብላችሁ የለያችሁትን ሃሳብም መልሳችሁ ከኢትዮጵያ ብሔርተኞች ጋር እንደምትወያይዩበት የሚያሳይ ምንም መረጃ የለም፡፡

ይልቁንም ያለው መረጃ የሚያሳየው ከቀን ወደቀን የኢትዮጵያ ብሔርተኞችን ድምጽ ከየትኛውም ድምጽ እንደምትጸየፉ ነው፡፡ የኢትዮጵያን መንበር ከተቆነጣጣችሁበት ቀን ጀምሮ እኛ የኢትዮጵያ ብሔርተኞች ስልጣን መያዛችሁ ካልቀረ ኢትዮጵያን እና ሆነ የአፍሪካ ቀንድን ከእናንተ ቀድመን እንደማቅናታችን፤ ያለንን ልምድ እና እውቀት ለማካፈል አልታከትንም፡፡

በእኛ እና በእናንተ መካከል ያለው የፖለቲካ ልዩነት እኛ ለአገራችን ለባንዲራችን፤ ለሉአላዊነታችን፤ ለአንድነታችን እና ለዳርድንበራችን ክብር ካለብን ተጠያቂነት ስለማይበልጥብን ከእናንተ ጋር ያለንን ልዩነት ሁሉ ችላ ብለን አብረናችሁ ልንሰራ ፈቃደኛነታችንን ሁሌም ከመግለጽ ተቆጥበን አናውቅም፡፡

ይህን ትናንት ያደረግነውም ሆነ ዛሬም የምናደርገው አሽከር መሆን ስለምንመርጥ፤ አንገታችንን አይደለም በኩራት በእብሪት ቀና አድርጎ የሚስኬድ አከርካሪ ስለሌለን አይደለም፡፡ ለኢትዮጵያ ሲሆን የምንሳሳው ምንም ነገር ስለሌለን እንደሆነ እናንተም ጠላቶቻችንም ያውቃሉ፡፡ የሚኒልክን ክቡር እና ምርጥ መንበር ስትቆናጠጡ የሽንፈት ቁስላችን ደሙ ሳይደርቅ ነበር ከሱዳን ፤ ኤርትራ እና የተለያዩ ፀረ-ኢትዮጵያ አገራት ጋር የያዛችሁት ግኑኝነት እንደማያዛልቅ ማስጠንቀቂያ የሰጠነው፡፡

Bandiraw

አያያዛችሁ ኢትዮጵያን ለመሰለ በሺ ዓመታት የሚቆጠር የተገለፀ፤ የብሔራዊ ደሕንነት ፍላጎት፤ ጥቅም፤ እውቀት እና ልምድ ላላት አገር የማይመጥን የማይጠቅም እና የማያዛልቅ እንደሆነ ከላይ ከታች የጮኅነው፡፡ በአዲስ መልክ ቆራርሳችሁ የቀረፃችሁት የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ምንኛ ቢያሳዝነን የእናንተ ስልጣን እነደተጠበቀ፤ ከነሽንፈታችን ፤ አንገታችን ደፍተን የእናንተን የበላይነት ሳንቀናነቅ፤ አዲሱን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለመጠበቅ እንድትፈቅዱልን ከማንም ቀድመን ወደ ምድብ ዘባችን እንድትመልሱን ማመልከቻ ያስገባነው እኛ እንደሆንን የተመዘገበ ማስረጃ በአደባባይ አለ፡፡

ከዚህ ይልቅ የሰጣችሁን መልስ እስርቤት እና መበታተን እና መባረር ነበር፡፡ አብሮ አደጋችሁ ሻዕቢያ ቀን ጠብቆ ጦርነት ሲያውጅ የተማመነው አንድ ነገር ነበር፡፡ እኛ ዳር ቆመን እንደምናይ፡፡ የተወረረው ትግራይ ነው እንጂ ኢትዮጵያ አይደለም ብለን ጥግ የምንቆም የመሰለውን ሁሉ በሚያሳፍር መልኩ ትዳራችን በትነን ለዳርድንበራችን እንደገና መጣን፡፡

ከውጊያው በኋላ ለኢትዮጵያ ብሔርተኞች ውለታ የሰጣችሁት ምላሽ ምን ያህል አሳፋሪ እንደነበር እንደገና ማንሳት አያስፈልግም፡፡ ጥሎብን ኢትዮጵያን የምንወዳት ለምትከፍለን ውለታ አይደለም፡፡ ተረግመን ይሁን ተባርከን ለዳርድንበር የምንሰለፈው የደሞዙን መጠን አይተን አይደለም፡፡ ለኢትዮጵያ ያለን ታማኝነት ከምን እንደሚመነጭ ፤ የአገር ነገር እንዲህ ለምን እንደሚያንዘረዝረን አይደለም – ለእናንተ ለእኛ ለእራሳችን በቂ እና አሳማኝ ምክንያት የለንም፡፡

በዚህ አላበቃችሁም፡፡ ከዘውድ ዘመን ጀምሮ ከአገሪቷ ጥጋ ጥግ በቆላ ሆነ በደጋ ይሄ ነው የሚባል የጡረታ መብትም ሆነ ለልጅ እንኳን የማይወረስ ደሞዝ እየተሰጠው አገሩን ሲያገለገል የነበረውን አገር ወዳድ መምር ሆነ፤ መሃንዲስ፤ ሹፌር ሆነ ተራ የቢሮ ፀሀፊ አንድ በአንድ አፈናቀላችሁት፡፡ ሲቪል ሰርቪሱን አገሩን በሚወደው ሳይሆን በሆዳሙ እና በ መንደሬ ብሔርተኛው አጨቃችሁት፡፡

ለነገሩ ይሄ አሰራራችሁ የመነጨው ኢትዮጵያን ከአንድ አገርነት ወደ ትናንሽ ብሔሮች፤ ህዝብ፤ ጎበዞች፤ ጋጦች ምናምን ስብስብ ካዘቀጣት ህገመንግስት እንጂ በድንገት ከሰማይ አልወረደም፡፡ ኢትዮጵያን እንዲህ ከፋፍሎ ማስቀመጥ እና ዜጎችን እርስ በእርስ ማጣለት ለኢትዮጵያ ዘላቂነት እንደማይከጅል ከመጀመሪያው አሳሰብን፡፡ እሱ ባይታያችሁ ለገዛ ስልጣናችሁ ዘላቂነት እንደማያዋጣ መከርን፡፡ መልሳችሁ አሁንም ብስለት የታየበት ሳሆን አሳፋሪ ነበር፡፡

እናንተ አዲስ አበባ ስትገቡ ዳዴ ይሉ የነበሩ ልጆችን እናንተን የሚጠቅም መስሏችሁ በተገቢው የኢትዮጵያዊነት ሲቪክ ሃሳብ ሳይሆን በትንንሽ መንደሬነት ኮትኩታችሁ አሳደጋችኋቸው፡፡ ይሄው የዘራችሁት ለምልሞ መጣ፡፡ በኮተኮታችሁት ጠባብነት ከምድር ከሰማይ የዘረፋችሁትን እንኳን በሰላም የማትበሉበት ቀን ከተፍ አለ፡፡
እኛ የኢትዮጵያ ብሔርተኞች አሁንም አገሪቷ ላይ የተጋረጠውን አደጋ እንደቀልድ አናየውም፡፡ አሁንም ከእናንተ ጋር ካለን ቅራኔ ይልቅ ለአገራችን ያለን ፍቅር እና ታማኝነት ሺ ቢሊዮን እጥፍ ይንተገተጋል፡፡ ይህ ትንታግ ኃይል ዛሬም በመቅጽፈት ኢትዮጵያን ከማንኛውም አደጋ ለመታደግ ዝግጁ ነው፡፡

ይህን አገልግሎታችን ለማቅረብ ስልጣናችሁን አንጠይቅም፡፡ ከእናንተ ጋርም ሆነ ለእናንተ ለማገልገል ከዘረፋችሁትም ሆነ ነገ ከምትዘርፉት 5 ሳንቲም አንጠይቅም፡፡ አገልግሎታችን ነፃ ነው ማለት ፍላጎት የለንም ማለት ግን አይደለም፡፡ ፍላጎታችን በአንድ ቃል ሊጠቃለል ይችላል፡፡ ከባንዲራው ጋር ታረቁ፡፡ በቃ!!

ከኢትዮጵያ ባንዲራ ጋር በያዛችሁት ውሸታም የባንዲራ ቀን መሰል ቀልድ ሳይሆ እውነተኛ ተሃድሶ መልክ ስትታረቁ የእኛን አካል ብቻ ሳይሆን ነብሳችን ታገኙታላችሁ፡፡ ከባንዲራው ጋር መታረቃችሁን በቲቪ አውጃችሁ ሳይሆን በተግባር መታየት ይጀምራል፡፡ ቢያንስ በእነዚህ በሚከተሉት ርእሰ ጉዳዮች ላይ ከእኛ ጋር በተገቢው መልኩ በይፋ መነጋገር እና መግባባት ትጀምራላችሁ፡፡

የዳር ድንበራችን ነገር

ከሱዳን እና ኤርትራ ጋር በዳር ደንበራችን ላይ የምታደርጉትን ሽንሸና አሁኑኑ ታቆማላችሁ፡፡ የሄደው ሄዷል የቀረውን እንዴት እናርግ የሚባልም ከሆነ የትኛውን ለዛሬ የትኛውን ለነገ እንደምናሳድር እንነጋገር፡፡

የብሔር ብሔረሰቦች ነገር

ብሔር ብሔረሰቦች በቋንቋቸው መናገራቸው፤ ተገቢ መጠን ያለው ቋንቋ የፌደራል ቋንቋ መሆኑ፤ ብሄሮች የፈለጉትን ልብስ መልበሳቸው፤ በፈለጋቸው ቀን እና ስፍራ መጨፈራቸው፤ ማጓራታቸው ፤ መዝለላቸው እናም ሌላም ሌላም ባህላቸው የሚያዛቸውን ነገር ማድረጋቸው ከፍቶን አያውቅም፡፡ የእናንተን ዘመን ልዩ የሚያደርገው አስራ ሁለት የማይሞሉትም ሆነ በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩት አገር የመሆን ምኞት ከነ መዋቅሩ፤ ባዲራው፤ ሰራዊቱ አስረክቦ ጥግ ቆሞ ማየቱ ላይ ነው፡፡

ይህን ውሸታም እና እርባና ትዕቢት በህገመንግስት ፤ በክልሎች አወቃቀር፤ በትምህርት ፖሊሲ፤ በበጀት ሁሉ አጅባችሁ ያሳደጋችሁት እናንተ እንጂ እኛ አይደለንም፡፡ አሁንም የምታሳዩት እርምጃ ለጥያቄው በተገቢው መንገድ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መልሶችን መስጠት ሳይሆን እሳቱን የበለጠ በሚያፋፍም ጭፍን ግድያ ብቻ ነው፡፡

ከላይ ባቀረብናቸው ጉዳዮች ከእኛ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኞች ሁኑ እንጂ አገሪቷን በጦርነትም፤ በጭፍጨፋም፤ በንግድም ፤ በጋብቻም በጭንገረድም በገበያም በጠላም፤ በጠጅም ያቀናናት እና የሰፋናት እኛው ነን እና ማን ላይ የትጋር እንዴት ምን አይነት እርምጃ እንደምትወስዱ እንደ አባይ ከረዘመው ታሪካችን እናጫውታችኋለን፡፡
እንደገና ይህን ምክር ሌላው ቢቀር የዘረፋችሁትን በሰላም የምትበሉበት እና በመቀጠልም የምትዘርፉት አገር እንዲኖራችሁ ስትሉ እንኳን አድምጡት፡፡ ውድ የአገር ልጅ ጥልሽ እንዳለው

ሳቅ ፈገግታ ደስታ ሁሌ የምናየው፤ ሀገር በነፃነት ኮርታ ስትኖር ነው
ጥሩ ልብስ ለብሰን፤ አምሮብን ተውበን የምንታየው
ሰዎች እንረዳ ቢገባን ትርጉሙ ሁሉም ባገር ነው

እና አንደገና እላለሁ ከባንዲራው ታረቁ፡፡ ከባንዲራው ከታረቃችሁ ሌላው ሁሉ ተከታይ እና ዝርዝር ነው፡፡
አሜን!

 

* ታምራት ነገራ የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ እና በአሁኑ ወቅት ደግሞ የ7 ኪሎ መጽሔት ጋዜጠኛ ነው::

The post ለውድ ወያኔ ወንድሞቼ እና እህቶቼ! እባካችሁን ከባንዲራው ታረቁ | ከታምራት ነገራ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live