Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ነቀምት በጥይት ተኩስ እየታመሰች ነው |በምስራቅ ሃረርጌና በቀለም ወለጋ ሕዝባዊ ተቃውሞው ቀጥሏል |በበደኖ የኦነግ ባንዲራ በአደባባይ ተውለበለበ

$
0
0

bedeno

(ዘ-ሐበሻ) በነቀምት ከተማ የአጋዚ ሰራዊት ለ3 ተከታታይ ቀናት በሕዝብ ላይ እየተኮሰ ነው:: እንደ ምንጮቻችን ገለጻ በዛሬው ዕለት በከተማው የሚሰማው የጥይት ጩኸት በርትቷል:: በዚህም ከተማዋ እጅጉን ታምሳለች::

በነቀምት ከትናንት ምሽት ጀምሮ በአጋዚ ሰራዊት በተተኮሰባቸው ጥይት በርካታ ወጣቶች የቆሰሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል የስድስቱ ማንነት ታውቋል:: 2 ሰዎችም እንደሞቱ እየተነገረ ሲሆን ዘ-ሐበሻ ይህን ለማረጋገጥ እየጣረች ነው::

በቀለም ወለጋም እንዲሁ መረር ያለ ተቃውሞ እየተደረገ ሲሆን ሕዝቡ ዱላ በመያዝ አደባባይ በመውጣት እየተቃወመ ይገኛል:: በተለይም በቀለም ወለጋ ሕዝቡ ስለነፃነት እየጠየቀ ሕወሓት አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ በመጠየቅ ላይ ይገኛል::

በምስራቅ በምስራቅ ሐረርጌ ቃንጫ ከተማ  ባለው ተቃውሞ ሕዝቡ መንገዶችን ሁሉ በድንጋይ እና በእንጨቶች በመዘጋጋት በአካባቢው የሚደረግን የመንገድ ትራንፖስርት አግዷል:: የአጋዚ ሠራዊት ድንጋይ እና እንጨት ማፈሻ መሣሪያዎችን በመጠቀም መንገዶችን ለመክፈት ቢሞክርም ሰልፈኞቹ በድጋሚ በመዘጋጋት እንደገና ተቃውሟቸውን ቀጥለዋል::

OLF Flag

እንደዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ገለጻ በምስራቅ ሐረርጌ በበደኖ ሰልፈኞች በየመንደሩ እየገቡ ሕዝቡን እንዲነሳ በመቀስቀስ በርካታ የአካባቢው ነዋሪ እንዲቀላቀላቸው በማድረግ ለአጋዚ ሠራዊት ራስ ምታት ሆነውበታል::

በተለይም በበደኖ እየተደረገ ባለው ሰፊ ተቃውሞ ሕዝቡ በአደባባይ የኦነግን ባንዲራዎች በመስቀል በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት አትመራኝም ሲል መል ዕክቱን አስተላልፏል::

The post ነቀምት በጥይት ተኩስ እየታመሰች ነው | በምስራቅ ሃረርጌና በቀለም ወለጋ ሕዝባዊ ተቃውሞው ቀጥሏል | በበደኖ የኦነግ ባንዲራ በአደባባይ ተውለበለበ appeared first on Zehabesha Amharic.


በኦሮምያ ክልል የተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄና የሃገራችን መጻሒ ሁኔታ! |ከኃይለገብርኤ አያሌው

$
0
0

ሃገራችን በረጅም ዘመን ታሪኳ አያሌ ግጭትና ጦርነቶችን እስተናግዳለች ። በተደጋጋሚ ሕልውናዋን ሊያጠፉት የተቃረቡትን የውጭና የውስጥ አደጋዎች ተቋቁማ ዛሬ የደረስንበት ዘመን ላይ ደርሳለች። በነዚህ ዘመናት ውስጥ የገጠሟትን ችግሮች ፤ ዘር ሃይማኖት የቋንቋ ልዩነት ሳይገድባቸው ቆራጥና አስተዋይ ልጆቿ በሕብረት በከፈሉት ወደር የለሽ ተጋድሎ ሕልውናዋን እስጠብቃ ኖራለች። ሃገራችን ከዓለም ቀድምት ከሆኑት የስልጣኔና ፈር ቀዳጅ ጥቂት ሃገራት ተርታ የሚቆጠር አኩሪ ታሪክ ያላት ፡ በምድር የከበረች በሰማይም የተመሰገነች ፤ የቅዱሳን መሸሸጊያ የነጻነት ተምሳሌት ሆና ታፍራና ተከብራ   መኖሯ እርግጥ ነው።

Oromia

ኢትዮጵያ ዙሪያዋን በከበቧት እረፍት የለሽ የቅርብና የሩቅ ጂዖ ፖለቲካዊ ስትራቴጂካዊና ታሪካዊ ጠላቶቿ ሴራ በተራዘመ የግጭት አዙሪት ውስጥ ወድቃ እንድትኖር የቀበሩት ግዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ በተደጋጋሚ ጉዳት ሲያደርስብን ቆይቷል። እነዚሁ ከራሳችን ሊወርዱ የማይሹት ባላንጣዎቻችን የተንኮል ሴራ ፍላጎታቸውን  ሊያስፈጽሙ የሚችሉ ሃገር በቀል  እንደ ሕውሃት ያለ ቅጥረኛ ባንዳዎች ያልተቋረጠ ድጋፍ ሲሰጡ ቆይተዋል። በዚህም  ትላንት በቀጥታ ያልቻሉትን በገዛ ወንድሞቻችን ጀርባ ተረማምደው የሃገራችንን ሕልውና በማፍረስ ሃገሪቱን በእጅ አዙር ለመቆጣጠር ብዙ ግዜ ሞክረው ያልተሳካላቸው ፖሊሲ ይህው በ 21 ክ/ዘ ተሳክቶላቸው በባህል በሃይማኖት በጋብቻና  በዕለት ተዕለት ሕይወት ተቆራኝቶ ተስማምቶ ለዘመናት የኖረውን ሕዝባችንን በዘውግ  ፖለቲካ ተከፋፍሎ፤  ያለፈ ታሪክ ማጥ ውስጥ ጥለውን እርስ በዕርስ እንድንጠፋፋ ሲያመቻቹን ከርመዋል። ሕወሃትና ሸሪኮቹ  ሃገራችንን እየቀሙን በስደት የባዕዳን አሽከር በሃገራችንም ሁለትኛ ዜጋ ሆነን ተነጣጥለን እንድንቆም ማድረግ በመቻላቸው ብሶትና መከራችን የጋራ መሆኑ ቀርቶ ክልልን የማይሻገር በጎጥ የታጠረ የተናጥል እንዲሆን ተድርጎ ቆይቷል።

በተለይም አውሮፓውያን አፍሪካን እንደ ቅርጫ ስጋ ተከፋፍለው ባካሄዱት ሕገወጥ የጭካኔ ወረራ ድፍን አፍሪካን ተቀራምተው ፍላጎታቸውን ለማሳካት ሲበቁ ፤ እንቢኝ አሻፋረኝ ብለው ለቅጥሯ ዘብ ሆነው ወራሪዎችን አይቀጡ ቅጣት እየቀጡ የሃገራችንን ሕልውና ለማስጠበቅ አባቶቻችን ቢችሉም ፥ ይህ ሽንፈት ያልተዋጠላቸው  ምዕራባዊ ተስፋፊ ሃይሎች ከገዛ ልጆቿ ማህል በመለመሏቸው ባንዳና ሹንባሾች ፤ በብሔሮች መካከል ጸንቶ የኖረውን ውህዳዊ የአብሮነት ኑሮ ለመበረዝ ጨቋኝና ተጨቋኝ ፤ ቅኝ ገዥና ተገዢ የሆነ ሃገር በቀልና ብሔርን መሰረት ያደረገ አስተዳደር  እንዳለና እንደነበር  አድርገው የረጩት ፕሮፓጋንዳና ያቀዱት የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ ዘመን ተሻግሮም ቢሆን ሊሰምርላቸው ችሏል።

በዚህ ባለንበት የ21ኟው ክፍለ ዘመን ዓለም በቴክኖሎጂ መንጥቆ የመገናኛ ዘዴዎችን ባቀለለበት የህዝቦች የባህል ፤ የኢኮኖሚና የጸጥታ ጉዳዮችን  በቀላሉ ከአንዱ ወደ ሌላው ክፍለ ዓለም በሰከንድ መረጃ በሚያደርስበት ግሎባላይዜሽን በሚዘመርበት የሃሳብ የበላይነት ገኖ በወጣበት በዚህ ባለንበት ዘመን ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ብሎ የሚጠራው ፤ ከቅኝ  ገዥዎች  መቃብር ላይ የበቀለ የጥፋትና የዘረፋ ቡድን ዘመን የሻረውን ሗላ ቀርና  በታኝ የከፋፍለህ ግዛው ፍልስፍና በሃገራችን ላይ አንብሮ  በተንኮልና በአሻጥር ሲያተራምሰን  ቆይቷል።

ይህ ከዘመኑ አስተሳሰብ የተጣላ የዕውቀት ጠር ጨካኝና አረመኔ አገዛዝ ባለፉት 25 አመታት ሃይማኖትን በሃይማኖት ፤ ብሄርን ፤ ከብሄር የሚያጋጭ ክፉ ፖለቲካ ሲያራምድ ቆይቷል። እንደዚህ ፋሽስታዊ ቡድን ቅስቀሳና ፍላጎት ምንም ሕዝባችን ወደ አጠቃላይ ግጭት ባያመራም ፤ ነገር ግን ጸንቶ የኖረውን የሕዝባችንን አብሮነት በማወክ ለጋራ ሃገራዊ አላማዎች  የጋራ ሕብረት እንዳይኖረው ማድረግ የሚያስችል መሰሪ ዕቅዱ ለረጅም ግዜ ተግባራዊ ሆኖ ቆይቷል። ዛሬም ቀጥሏል ።  ለነገም ይህን እኩይ ሴራ ነቅቶ  ማክሸፍ የማይቻል ወገን ካለ መከራውም ይረዝማል ፥ ልዩነቱም ይሰፋል ፤ ባርነቱም ፤ ይቀጥላል!!

ለዘመናት በአንድነት የኖረው ሕዝባችንን አንድነቱን አላልቶ በቅራኔ አፋጦ ባለፈ የታሪክ ጠባሳ ላይ ስንታገል ሕወሓት ግን አፓርታይዳዊ ዘረኛና ዘራፊ አገዛዙን በላያችን ጭኖ ያሻውን ሲያደርግና ሲፈጽምብን ቆይቷል።  የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት  ይህው የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ እስከግዜውም ቢሆንም ተሳክቶለት ፤ አማራው ሲጠቃ ፤ ኦሮሞው ቆሞ እንዲያይ ፤ ኦሮሞው ሲጎዳ አማራው በጸጥታ ሲያልፈው ፤ እንዲሁም ክርስቲያኑ ችግር ሲገጥመው ሙስሊሙ ዝም ሲል ፤ ሙስሊሙን ጉዳት ሲገጥመው የክርስቲያኑ ጸጥታ እስከ ተወሰነ ግዜ ገዥዎችን ሲጠቅም ቆይቷል። በነዚህ ዘመናት የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት እያፈራረቀ በተለያየ አጀንዳና ግንባር የሚፈልገውን እየደፈጠጠ አገዛዙን በሕዝብና በሃገር ላይ አጽንቶ ልክ እያስገባን ይገኛል።• ።

የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት የረጨው የጥላቻና የመለያየት መርዝ ነቅቶ በግዜ በማርከስ ሕዝብን ማቀራረብ የነበረባቸው የአማራውና የኦሮሞ  ምሁራን መካከል ተካሮ የቆየው ልዩነት ለዘረኛው አገዛዝ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠሩም በላይ ሁለት ግንባር በአንዴ ከማጥቃት ተቆጥቦ ስልታዊና ታክቲካዊ ሽግሽግ በማድረግ የግዜና የሁኔታዎችን አመቺነት እያሰላ ፤ በተከታታይ እንደታየው የተነሳበትን ሕዝባዊ ተቃውሞና የአመጽ እንቅስቃሴ ለማዳፈን አንዱን በሌላው ላይ እየቀሰቀሰ ከጎኑ ለማሰለፍ ሲችልና ሲያደርግ ቆይቷል ፤ አሁንም ያንኑ ስልቱን በመቀመር በከፋና ምንአልባትም ሃገሪቷን ሊበታትን የሚችል የዘር ግጭት ለመቅስቀስ እየተንቅሳቅስ ለመሆኑ ከሚወጡት መረጃዎች መረዳት ይቻላል።

በተለይም ባልፉት አራት አስዕርተ አመታት ውስጥ በአንዳንድ የኦሮሞ ምሁራን ተላላነት በጥቂት ሆድ አድሮችና በእንዳንድ ጽንፈኞች ቅንብር እና በትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት አዝማችነት በተሳሳተ ፕሮፓጋንዳና በተንሸዋረረ የማንነት ውዥንብር  የኦሮሞን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት ማዕከል ለመነጠል ያልተቋረጠ ሴራ ሲራመድ ቆይቷል። የዚህም ሴራ ዋና አላማ  እንዱ  የኦሮሞ ማሕበረሰብ ዙሪያውን ካሉት ሌሎች ብሄሮችና ከእንድነት ሃይሎች ጋር ያልተቋረጥ ቅራኔ ውስጥ  ከቶ ፋታ በመንሳት በተፈጥሮ ሃብት የበለጸገውን የኦሮምያ ምድር በምስለኔዎቹ ተረማምዶ ለዘመናት ትቆጣጥሮ ያለ ከልካይ ሲመዘብር ለመኖር ካለው ሕልም የተንሳ ነው።

በዚህም የሴራ ቅመራ ባለፉት አመታት እንደሆነውና እንደታየው ፥ በተለይ የአማራ ተወላጆችን ከኦሮሞ ማህበረሰብ ፍላጎትና ፈቃድ ውጪ የጥላቻ ቅስቀሳ በማድረግ በካድሬዎቹ አዝማችነት ተወልደው ካደጉበት ፤ ለፍተው ያፈሩትን ሃብትና ንብረት እየቀሙ ከክልሉ በገፍ እንዲባረሩ ሁን ተብሎ  በትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት በተቀነባበረ ሴራ በብዙ ሺህ በሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የጅምላ ግድያና ፥ የዘር ማጥፋት ወንጀል በኦሮሞ ነገድ ስም ሲፈጸም   ቆይቷል። ዛሬም ይህው ሴራ  ቀጥሏል ፥ ነገም በጋራ ካልቆምን ካሁን ቀደሙም የከፋ የእርስ በዕርስ መተላለቅ ሊከሰት እንደሚችል ለመረዳት ነብይ መሆን አይጠይቅ።

ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነው ፤ ኢትዮጵያም የኦሮሞ ናት! ይህን ሊፍቅና ሊያስቀር የሚችል ምንም ውሃ የሚቋጥር ምክንያት የለም። የኦሮሞ ልጆች ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነትና ለወሰኗ ክብርና ለሉዓላዊነቷ ወደር የሌለው መስውዕትነት ሲከፍሉ ኖረዋል። ይህንን የክብርና የኩራት ታሪክ ንደው የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ከሃገራዊውና ከአህጉራዊው ተምሳሌታዊ ሕዝብነት አርቀው የባርነትንና የተገዥነትን የሃሰት ማቅ ሊያለብሱት በጠባብ ብሔረተኝነትና በጨለምተኛ የስሜት ፖለቲካቸው እሳት ውስጥ ትውልዱን ሊጥሉት የሚራወጡ ጽንፈኞች የሚያራምዱት ኦሮሚያ ለኦሮሞ የሚል ከፋፋይና አፍራሽ እንቅስቃሴ ለማንም የማይጠቅም ዘመኑን ያልዋጀ መፈክር ነው።

እርግጥ ነው ፥ መላው ሕዝባችን በየግዜው በተፈራረቁት መንግስታት ሲበዘበዝና ሲጨቆን የመኖሩን ሃቅ ሊዘነጋ የማይችልና ጠባሳውም ያልጠፋ ነው። ነገርግን ትላንትም ሆነ ዛሬ ጥቂት መሳፍንት ባላባትና ኤሊቶች ፥ ከአንዱ ወይ ከሌላው ብሄር በቁጥር ልቀውና የስልጣን ወንበር ይዘው ቆይተው ሊሆን ይችላል። አንድ ብሄረሰብ አጠቃላይ ተጠቃሚና የበላይ ሌላው ጎሳና ነገድ ተገዥ የሆነበት የመንግስት መዋቅር ፥  አልነበረም  ፥ የለምም ።

ምናልባት ዛሬ የትግሬዎች የበላይነት አለ የሚል  ክርክር ሊነሳ ይችላል። እርግጥ ነው በሃገራችን ታሪክ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ በማይታወቅ ደረጃ የሃገሪቱን የስልጣን ፥ የኢኮኖሚ ፥ ወታደራዊና ፥ ማህበራዊ ሴክተሮች ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ በትግራይ ተወላጆች ተይዞ ለመገኘቱ አይን የሚያየው ሃቅ ነው።  ይህም ሆኖ ግን በስመ ትግሬነት ሁሉንም የብሄሩን ተወላጆች ከስልጣኑም ከዘረፋውም እንጥፍጣፊው ያልደረሳቸውን ጨምሮ በአንድ  ቅርጫት ከቶ የመፈረጁ አተያይ ተገቢም አስፈላጊም አይሆንም። ዛሬ ሕዝባችንን አለያይቶ የዘረፋ አገዛዙን ያነበረው የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ፥ ለዚህ አሁን ለደረሰበት ልዕልና ያበቃውን የትግራይ አርሶ አደር ክዶ ብዙ ሺዎች የከፈሉትን የሕይወትና የአካል መስዋዕተነት  ረስቶ  ቁንጮ መሪዎቹና አጫፋሪዎቻቸው በሃብት ላይ ሃብት ሲያካብቱ ፥ የራሳችውን መደብ ለይተው በቅንጡ ቪላ ሲምነሸነሹ ያስተዋልው የትግራይ ሕዝብ አፓርታይድ መንደር ሲል ብሶቱን መግለጹ ይታወሳል።

ዛሬ ለደረስንበ ሃገራዊ ውድቀት አያሌ ምክንያቶች መጥቀስ ይቻላል ነገር ግን እንደ አንድ የዚህ የጥበብና የግሎባልይዜሽን አለም ውስጥ እንዳለ እንድ ሕብረተሰብ ዛሬም በዛው እንዲያውም በባሰ ደረጃ ተዳክመን ለመገኘታችን ተጠያቂው ማን ነው። ሃገራችንን በብረት ክንዱ ደቁሶ የከፋፍልህ ግዛው ያረጀና ያፈጀ ሃገር በታኝና ትውልድ እውዳሚ የጥላቻና የጎሳ አስተሳስብ እየገዛ ያለው የህውሃት ቡድን በዋናነት ሊጠቀስ የሚችል ቢሆንም ፤ ይህ እኩይ ሴራ  በአንድም ሆን በሌላ ምክንያት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ተቀብለን ፤ ዘውገኛ   አመለካከትን ያራባንው ፤  በጠባብና ግትር አመለካክት ተካርን ለዘመናት ተዋልዶና ትጋብቶ በፍቅርና በአብሮነት የኖረውን ሕዝባችንን ጠላቶቻችን  ዘር መሰረት ያደረገ ግንብ ሲያጥሩልን ድንጋይ ያቀብልነው ፤ አጥፊነቱን እያወቅን በዝምታ ያለፍንው ፤ ጊዚያዊ ጥቅምና ጎጠኘነት አይሎብን ጸጥታን የመረጥንው ፤ ሁላችንም የተጠያቂንቱን ድርሻ ማንሳት ይኖርብናል ።

ታሪክ ሠሪው ሠፊው ሕዝብ ነው አዋቂዎች እንዲሉ ፤ የትላንት ገናናነታችን የዛሬው ውድቀታችን ተመስጋኙም ሆነ ተወቃሹ በዘምኑ ያለ ትውልድ  ነው። ቀደምት አባቶቻችን ዘርና ሃይማኖት ቋንቋና ነገድ ሳይሉ ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ቢያንስ በዓለም አደባባይ አንገታችንን ቀና አድርገን እንድንሄድ ታላቅ የስነልቦና ውርስ ትተውልን አልፈዋል።

ዛሬም ያለነው ትውልዶች ከቀደሙት አባቶቻችን መልካሙንና በጎውን ባህልና ፥ እሴት ጠብቀን አሮጌውን ጥለን እንደ ግዜያችን ዘመን የዋጀው ህይወት እንዲኖረን ፤ ለመብትና ነጻነታችን ዋጋ ሰጥተን ራሳችንን አስከብረን ሌሎችንም አክብረን ለመኖር የሚያስችል አስተዳደራዊ ስርዕት በሃገራችን እንዲኖር ፤ አሮጌ አስተሳሰቦችንና የጭቆና መዋቅሮችን እጅ ለእጅ ተያየዘን አፍርሰን የሕዝቦችን መብት የሚያከብር መንግስታዊ ስርዓት ልንመሰርት የሚያስችለንን ትግል በጋራ ልናደርግ ይገባል ።

በአሁኑ ወቅት ሃግራችንን የገጠማት የህልውና አደጋ ከምን ግዜውም የከፋ ሆኖ ይታያል ። የሕወሃት መራሹ ዘረኛና አፓርታይዳዊ አገዛዝ ባለፉት ሁለት አስዕርተ ዓመታት ሲከተለው በቆየው የጥቂት ወገኖችን ፍላጎት ማዕከል ያደረገ የአገዛዝ መዋቅርና የኢኮኖሚ ፖሊሲ የፈጠረው የጭቆናና የችጋር ወጀብ ሃገራችንንና ሕዝባችንን ውድቀት አፋፍ አድርሶዓታል። ይህ ሃገራዊ አደጋ እንዳይከሰት አስቀድመው ድምጻቸውን ያሰሙ የፖለቲካ መሪዎች  የኢኮኖሚ ባለሙያዎችና አክቲቪስቶች የተለያየ ስንካላ ምክንያትና የፈጠራ ወንጀል እየከሰሰ ከሃገራዊ ጉዳይ እንዲገለሉ ሲያደርግ ቆይቷል።

ሕወሃት ላለፉት 25 አመታት ቁልፍ የስልጣን ቦታዎችን ያለተቀናቃኝ ይዞ በመቆየቱ በሕዝባችን ላይ የፈለገውን ሲያደርግ ሊገድበው የሚችል ሳይኖር ቆይቷል። የዚህ የግፍና የጭካኔ ሰለባ የሆነው መላው ህዝባችንን በየግዜው ከማሃሉ ብሶቱን ብሶቴ ብለው በአደባባይ የታገሉትን ፖለቲከኞችን ጋዜጠኞችና የመብት ተከራካሪዎች ሲገልና ሲያስር የቀሩትንም ያለፍላጎታቸው ሃገር ለቀው እንዲሰደዱ አድርጓል።

ሕዝባችን ሕወሃት ባነበረበት አስከፊ የድህነት ሕይወት የሚካሄድበትን ጭቆና በጋራ መከላከያ እንዳይቻል በእለታዊ ኑሮው እንዲጠመድ ሁን ተብሎ ከመደረጉም በላይ አንዳንዴም ገንፍሎ ሲወጣ የተወሰደበት ምህረት የለሽ ጭፍጨፋ አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር አስገድዶት ቆይቷል።  የአገዛዙን ግፈኛ እርምጃ በትግዕስት ችሎና በፍርሃት ተሽብቦ መቀመጡ ይበልጥ ልባቸው እንዲደነድን የሆኑት የህወሃት መሪዎች የከተማውን ሕዝብ በግፍና በገፍ አፈናቅለው ራሳቸው ለፈጠሯቸው የጠፍ ጨረቃ ከበርቴዎች አከፋፍለዋል። በከተማ የጀመሩትን  የመሬት ዝርፊያና ቅርምት  አልበቃ ብሎዐቸው የገጠሩን አርሶ አደር ያለ ተመጣጣኝ ካሳ ከመሬቱ እያፈናቀሉ ለድህነትና ለጎዳና አዳሪነት አድርገውታል።

በኦሮሚያ ከአመት በፊት ይህንን ግፍና በደል ያስተዋሉ የምስኪን ገበሬዎች ዋይታና እንባ ያስቆጫቸው ተማሪዎች በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመቃወም አደባባይ በወጡ ተማሪዎች ላይ እብሪተኛው የሕወሃት አገዛዝ የለመደውን ጭፍጨፋ በማካሄድ ተቃውሞውን ለማርገብ የቻለ መስሎት ቆይቷል

ብሶት ጭቆናና ፥ የመብት ረገጣ እስካለ ድረስ ትግል መኖሩ እይቀርም ። በኦሮምያ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን መሰረት በማድረግ ዳግም ሌሎች በደሎች ገፊ ምክንያት ታክሎበት የፈነዳው አመጽ ከመጀመሪያው በይዘትም በመጠንም ሆነ  በአይነት የተለየ ከመሆንም በላይ ሕወሃትን በጣም የተገዳደረ ፥ ተምሳሌትነቱ ለመላው የሃገራችን ሕዝቦች የሆነ ፥ የጸረ አፈና ትግልን መረብ በጣጥሶ ፤ ሕዝባዊ እንቢተኝነትን ያሳየ ፥ ጠንካራ የለውጥ ሃይል የታየበት ፥ የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት  መግደል እስከ ቻለ ድረስ ለመሞት የቆረጠ የማይፈራ ትውልድ በየአደባባዩ ለፍትህ የተሰዋበት ፥ ወጣት ህጻን አዋቂው በጋራ በሰው በላው የወያኔ አጋዓዚ ወታደሮች  አፈሙዛቸው ስር በድፍረት በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞዎች ሲያሰማ በየማህበራዊ ሚድያዎች ተመልክተናል ።

በኦሮምያ በተለያዩ ቦታዎች ላለፉት ተከታታ ወራት ሲካሄድ የቆየውና አሁንም እንደቀጠለ ያለው ሕዝባዊ ትግል ከዚህ ሁሉ መስዋዕትነት በሗላ እንዳይቀለበስ የፖለቲካ ሃይሎች ና ሲቪክ ተቋማት በመሰብሰብ ፥ ከዘውገኝነት ከፍ ያለ ሃገራዊነት የተላበስ ፤ በፋሽስታዊው የሕወሃት አገዛዝ የተማረረውን መላውን ሕዝባችንን ያሳተፈ የተቀናጀና ፥ በስልት የታጀበ ሕዝባዊ ትግሉ እንዲፋፋምና ለውጤት እንዲበቃ አመራር ለመስጠት በሚያስችላቸው ደረጃ ልዩነታቸውን ወደ ጎን በማድረግ በዚህ ቀውጢ ወቅት ለሕዝብ ያላቸውን አጋርነትን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።

ይህ በኦሮምያ ክልል ያሉ ትንታግ ወጣቶች የተጀመረው መሬት አንቀጥቅጥ የሰላማዊ ትግል ሕዝባዊ ንቅናቄ የሃገራችንን መጻሒ እድል ሊወስን የሚችል እንቅስቃሴ በመሆኑ ፤ ወደ ሌሎችም ክልሎች ተዳርሶ በእንድ የጋራ አጀንዳና መፈክር ስር ታጅቦ ለስር ነቀል ለውጥ ትግሉን ለማብቃት ሁሉም ወገን በየአካባቢው መንቀሳቀስ ይኖርበታል። ህዝባችን የወያኔ አገዛዝ ሰልችቶታል ፥ ከጥቂት የዘረፋው ተቋዳሾች ውጪ ይህንን መንግስት እንዲለወጥ የማይፈልግ ወገን የለም ።ይህንን የሚሊዮኖች የጋራ ብሶት አንቀሳቅሶ ወደ ሕዝባዊ እንቢተኝነት ለመለወጥ የሁሉም ወገን የጋራ ጥረትን ይጠይቃል። ይህም ሲባል ለጥቂት የፖለቲካ ሃይሎች ብቻ የሚተው ሳይሆን ሁሉም ያገባኛል የሚል ዜጋ በያለብት በሚችለውና ባለው እቅም ተሳትፎ የማድርግን ሃላፊንትን በመወጣት የተጀመርው ሕዝባዊ እንቢተኝነት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ የሁኑንም ወገን ጥረት ይጠይቃ ።

እግዚያብሔር ኢትዮጵያን ይባርክል ! !

The post በኦሮምያ ክልል የተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄና የሃገራችን መጻሒ ሁኔታ! | ከኃይለገብርኤ አያሌው appeared first on Zehabesha Amharic.

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ቁልቁል የመንሸራተት አንድምታ!

$
0
0
dagna tegene
ኢትዮጵያ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ማለት፤ የአገሪቱ የህግ ማስፈጸሚያ የመጨረሻው ችሎት ነው። ከዚህም በተጨማሪ፤ የአገሪቱ ፕሬዘዳንትም ሆነ ጠቅላይ ሚንስትርእንዲሁም የፓርላማ አባላት ስራቸውን ከመጀመራቸው በፊት፤ ቃለ መሃላ የሚያስፈጽመው የዚህ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት መሆናቸው ይታወቃል። የህገ መንግስት ወይም የህግ ትርጉም የሚሰጠው የመጨረሻ አካል ነው – ጠቅላይ ፍርድ ቤት። ከዚህ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በላይ ደግሞ፤ ፕሬዘዳንታቸው አለ። እስከቅርብ ግዜ ድረስ ፕሬዘዳንቱ አቶ ተገኔ ጌታነህ ነበር። እናም በቅርቡ “ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ፤ ስልጣኑን በገዛ ፍቃዱ ለቀቀ ሲባል፤እንደማንኛውም ዜና ሰምተን ዝም የምንለው ሊሆን አይገባም።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ወይም ቃልአቀባዮች መግለጫ ባለመስጠታቸው የተፈጠረ ክፍተት አለ። ይህን ክፍተት በመጠቀም እኛም የራሳችንን መላ ምት እንሰጣለን። ከዚያ በፊት ግን ስለዳኛ ተገኔ የየራሱን ትንሽ ትንሽ ማለቱ አይቀርም። እኔ ከትንሽም ባነሰ መልኩ… በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ችሎት የቀኝ ዳኛ በነበረበት ወቅት ነው፤ ከጥቂት በታች በጥቂቱም ቢሆን ሰብዕናውን ለማወቅ የቻልኩት።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት 
ቁልቁል የመንሸራተት አንድምታ!
 
ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ)
 
በፐሬስ ክስ ጉዳይ ስከሰስ… ለመጀመሪያ ግዜ የቀረብኩት፤ ዳኛ ተገኔ ጌታነህ ቀኝ ረዳት በነበረበት  1ኛ ችሎት ነበር። ከሁሉም የከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ 1 ችሎት ትንሽ ቀለል ያለ ነበር። ለንፅፅር እንዲረዳን ከጎኑ ወዳለው 2 ችሎት ልውሰዳቹህ።
 
2ኛ ችሎት ውስጥ የግራ እና ቀኝ ዳኞች ቢኖሩም፤ ጎልቶ የሚታወቀው – ሃጎስ ወልዱ የሚባለው ከሰይጣን ቁራጭ የተሰራ የሚመስለው ቀይ ሰውዬ ነው። በተለይ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች ካጋጠመው፤ በቁጣ እና በስድብ ያንቀረቅባቸዋል። እነፕሮ/ር አስራት ወልደየስ፣ እነዶ/ር ታዬ ወልደሰማያት፣ ታምራት ላይኔ እና በሌሎች ታዋቂ ሰዎች ላይ ምንም ቅም ሳይለው ስድብ አቅምሶ፤ ፍርዱን በፖለቲካ ጭቃ ለውሶ ፈርዶባቸዋል።
 
 በደርግ ዘመን የአዲስ አበባ ከተማ ዳኛ የነበረው ግለሰብ፤ ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ… በአንድ ግዜ ተስፈንጥሮ የፌዴራሉ /ቤት መሃል ዳኛ እስከመሆን የደረሰው፤ በችሎታ ሳይሆን በፖለቲካ ሹመት በመሆኑ አብረው የሚሰሩት ጭምር ይፈሩታል። ችሎቱ በታጠቁ ፖሊሶች የሚጠበቅ ቢሆንም፤ ዳኛ ሃጎስ ወልዱ ግን የራሱን ሽጉጥ ታጥቆ ነበር ችሎት የሚሰየመው። በዚያ ላይ ስድብ እና ጩኸቱ አይጣል ነው። ከድሮ ጋዜጠኞች መካከል አበራ ወጊ፣ አክሊሉ ታደሰ፣ ተፈራ አስማረ፣ ዘገየ ሃይሌ፣ እስክንድር ነጋ እና ሲሳይአጌና ላይ ያለምንም ግርግር እስር እንደፈረደባቸው አስታውሳለሁ። 
 
በ2ኛ ችሎት ከታዩት ክሶቹ መካከል አበራ ወጊ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ጦርነት ሊጀመር መሆኑን በመዘገቡ፣ አክሊሉ በሰሜን ሸዋ ስለነበረው ወታደራዊ እንቅቃሴ በመጻፉ፣ እክንድር የኤርትራውን ፕሬዘዳንት በካርቱን እባብ አስመስሎ በመሳሉ “የፕሬዘዳንቱን ክብር ነክተሃል” ተብሎ… ብቻ በትንሽ እና በትንሹ ሰበብ ሁሉ ዳኛ ሃጎስ ወልዱ የስርአቱ ‘አፋሽ አጎንባሽ’ ሆኖ ንጹሃንን በእስር ቀጥቷል። እናም 2 ችሎቱን ሃጎስ ወልዱ የሚያውቅ ሰው እሱ ፊት አለመቅረቡ በራሱ ደስ ያሰኘዋል።
 
በመጨረሻም በዚህች ቀልድ መሰል የፍርድ ቤት ገጠመኝ ሁለተኛ ችሎትን እንሰናበት። አንድ ተከሳሽ በችሎት ቆሞ ዳኛው ሃሳቡን እንዲረዱለት በተደጋጋሚ ክቡርፍርድ ቤት! ክቡር ፍርድ ቤት!” እያለ አቤቱታውን ያሰማል፡፡
በዚህ የተናደደው ዳኛ ሃጎስ ወልዱ፤ “አስሬ ክቡር ፍርድ ቤት

The post የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ቁልቁል የመንሸራተት አንድምታ! appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን (EBC) በኦሮሚያ በተለይም በምዕራብ አርሲ ስለተነሳው የሕዝብ አመጽ የሚከተለውን ዘገቧል | Video

የኢህአዴግ የተበሉበት 7 ሙዶች

$
0
0

eprdf
ከአቡ ባይሳ

1. በኢትዮጵያ፣ ህዝብ ጥቅሙን የሚጎዳ ነገር አልቀበልም በማለት ተቃውሞ ካነሳ ትምክተኛ ሲባል፤ ኢህአዴግ የህዝብ ጥቅም የሚጎዳ ነገር በግድ ካልተቀበላችሁ ብሎ ሙጭጭ ካለ ግን የዓላማ ፅናት ነው::

2. በኢትዮጵያ፣ ህዝብ በኢህአዴግ ላይ ቁጣ ሲያስነሳ ሽፍታ ሲባል፤ ኢህአዴግ ቁጣውን ለማብረድ ንፁሃንን ሲገድል ግን የማያዳግም እርምጃ ነው።

3. በኢትዮጵያ፣ ጋዜጠኛ ሆኖ ኢህአዴግን ከተቸ ወይም ከተቃወመ አሸባሪ ሲባል፤ ጋዜጠኛ ሆኖ ኢህአዴግን ከደገፈ ግን ልማታዊ ጋዜጠኛ ነው::

4. በኢትዮጵያ፣ ኦሮሞ ሆኖ ኢህአዴግን ከተቃወመ ኦነግ፣ አማራ ሆኖ ኢህአዴግን ከተቃወመ ደግሞ ግንቦት ሰባት ሲባል፤ ኢህአዴግ ህዝቡን ሲቃወም ግን መንግስት ነው::

5. በኢትዮጵያ፣ ህዝብ የኢህአዴግን ወታደር ሲገድል ሽፍታ ጋኔን ሲባል፤ የኢህአዴግ ወታደሮች ህዝቡን ሲገድሉ ግን ፀጥታ ለማስፈን ነው::

6. በኢትዮጵያ፣ ጥፋተኞች ተብለው ነገርግን ያለምንም ጥፋት ከኢህአዴግ ጋር ፍርድ ቤት የቆሙ በሙሉ ሲፈረድባቸው፤ ኢህአዴግ ግን ጥፋተኛም ሆኖ ይፈረድለታል
በኢትዮጵያ፣ ህዝብ “ዴሞክራሲ መሰረታዊ ነገር ነው” ሲል፤ ኢህአዴግ ግን ” ዴሞክራሲ ቅንጦት ነው::

7. በኢትዮጵያ፣ ህዝብ ሲሳሳት ኢህዴግ ለምን ተሳሳተ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል ፤ ኢህአዴግ ሲሳሳት ግን ” ከኢህአዴግ ስተት ከብረት ዝገት አይጠፋም……… ” በማለት የተበላበት ሙድ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለመያዝ ይሞክራል………………።

The post የኢህአዴግ የተበሉበት 7 ሙዶች appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ጊዜም ገንዘብም በማጣቴ ፍቅረኛ ልይዝ አልቻልኩም!!ምን አድርግ ትሉኛላችሁ?

$
0
0

የ26 ዓመት ወጣት ስሆን በአንድ ድርጅት ውስጥ ቋሚ ሠራተኛ ነኝ፡፡ የስራው ባህሪ ስለሆነ ጠዋት ሥራ የገባሁ 11፡00 ሰዓት ነው የምወጣው፡፡ ምሳ እንኳ እዛው ነው የምበላው፡፡ ከሥራ እንደወጣሁ የማታ ትምህርት እማራለሁ፡፡ ቅዳሜና እሁድም ትምህርት እማራለሁ፡፡ ከትምህርት ቤት መልስ ደግሞ ያለኝን ጊዜ በማጥናት አሳልፋለሁ፡፡ ከሚፈለኝ ደመወዝ እንደ ምንም አብቃቅቼ ለትምህርት እከፍላለሁ፡፡ ይህንን ሁኔታዬን ቆም ብዬ ሳየው እጨነቃለሁ፡፡ ጊዜ የሚባል ነገር የለኝም፡፡ ሁልጊዜም ቢዚ ነኝ፡፡ እንደ እኩዮቼ ፍቅረኛ ይዤ የመኖር ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረኝም በየትኛው ጊዜዬ ሴት ልቅረብ፡፡ የሚከፈለኝ ደመወዝም ተርፎ ሴት ለመጋበዝ አይበቃም ብዬ አስባለሁ፡፡ ከጊዜ በኋላ ደግሞ ለምንድነው እንዲህ ተጨናንቄ የምኖረው ብዬ አስብና በህይወቴ እርካታ አጣለሁኝ፡፡ የህይወት ትርጉሙ ይጠፋብኛል፡፡ ምን አድርግ ትሉኛላችሁ?

M ነኝ

ask your doctor zehabesha

ውድ ጠያቂያችን ኤም ከፅሑፍህ መረዳት እንደቻልነው ሁሌም በስራና ትምህርት እንደተወጠርክና ጊዜ እንደሌለህ፤ ይህም ፍቅረኛ የመያዝ ፍላጎትህን እንዳሰናከለብህና ለጭንቀት እንደዳረገህ ብሎም በህይወትህ እርካታን አሳጥቷል፡፡ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ሁለት ዓይነት አካሄዶች አሉ፡፡ አንደኛው እያንዳንዱን ችግር አንድ በአንድ እየፈቱ መሄድ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በህይወት ላይ መሰረታዊ ለውጥ በማምጣት ችግሮችን ቀድሞ የመከላከል መንገድ ነው፡፡ የመጀመሪያው መንገድ አብይ ችግር፣ አንድን ችግር ስትፈታ ሌላው ሲመጣ፣ እሱን ስትፈታ ሌላ ሲመጣ፣ ስትፈታ ሁሌም በችግር አዙሪት ውስጥ እንድትኖር ያደርጋል፡፡ የሁለተኛው መንገድ አብይ ችግር ደግሞ፣ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ስትንቀሳቀስ ቀደምት ችግሮች እንቅፋት ይሆኑብሃል፡፡ በመሰረቱ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ሁለተኛውን መንገድ የተሻለና አዋጭ መንገድ ይሉታል፡፡ ስለሆነም ይህንን መንገድ እንዴት  ተግባራዊ እንደምታደርግ እጠቁምሃለሁ፡፡ ይህንን መንገድ ተግባራዊ ስታደርግ እንቅፋት ሊሆንብህ የሚችል ችግር ደግሞ ጭንቀት ሊሆን ስለሚችል፣ በስተመጨረሻ የጭንቀት ማቅለያ መንገዶችን እጠቁምሃለሁ፡፡

መሰረታዊ ለውጥ

ብዙዎቻችን ጊዜያችንን አልባሌ በሆኑ ተግባራት እናሳልፍና፣ በህይወታችን ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን የምንከውንበት ጊዜ እናጣለን፡፡ አንዳንዶቻችን ደግሞ ህይወት ያመጣችውንና አሁኑኑ መስራት ያለብንን ነገሮች ከመከወን ራሳችንን ቢዚ እናደርጋለን፡፡ ሌሎቻችን ደግሞ እቅድ አውጥተን፣ ያቀድነውን እንጂ ሌላ ነገር አንፈፅምም በማለት በህይወታችን ላይ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ተግባራትን ሳንሰራቸው፣ ዝም ብለን በማየት ህይወታችንን እንገፋለን፡፡ በጣም ጥቂቶቹ ግን ትኩረታቸውን ውጤታማ የሆኑ ነገሮች ላይ በማድረግ በህይወታቸው እርካታን ይጎናፀፋሉ፡፡ የእነዚህ ሰዎች ትልቅ ምስጢር ደግሞ ጊዜያቸውን በአግባቡ ለአስፈላጊና ውጤታማ ተግባራት ማዋላቸው ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ እቅድ ከማውጣታቸው በፊትና በኋላ የሚተገብሯቸው ተግባራት አሉ፡፡ እስኪ የእነዚህን ተግባራት ሂደት በቅደም ተከተል  እንመለከታቸውና አንተም ተግብረሃቸው እርካታን ተጎናጸፍ፡፡

ሀ. ባለ ራዕይ መሆን

በዚህ ሂደት ውስጥ የመጀመሪያው ተግባር ራዕይ መዘጋጀት ነው፡፡ ራዕይ ማለት መሆን የምፈልገው ምንድን ነው፣ ማድረግ የምሻው ምንድን ነው እና መድረስ የምፈልገው የት ነው፣ ለሚሉ ጥያቄዎች መልስ ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡ በዚህች ዓለም ስትኖር ማድረግ የምትፈልጋቸውን እና መሆን የምትፈልጋቸውን እንደ ራዕይ ቀርፀህ አስቀምጣቸው፡፡ ጊዜ ውሰድና ምን መሆን፣ ምን ማድረግ፣ የት መድረስ እንደምትፈልግ ብሎም በህይወት የመኖርህ ትርጉም ምን እንደሆነ ለይና ራዕዮችህን ነጥረህ አውጣ፡፡ በመሆኑም ራዕይህ የእርካታህ ምንጭ ይሆናል፡፡ ተግባሮችህ ወደ ራዕዮችህ ሲወስዱህ ትደሰታለህ፤ ትረካለህ፡፡  ያ ሳይሆን ሲቀር ደግሞ እርካታ ታጣለህ፡፡ በመሆኑም ራዕይ ማዘጋጀትን የመጀመሪያው ተግባርህ አድርግ፡፡ ይህ እንግዲህ ያንተ አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓስ ነው ማለት ነው፡፡

ለ. ሚናዎችን መለየት

አንድ ግለሰብ በህይወት ሲኖር ሊጫወታቸው የሚገቡ የተለያዩ ሚናዎች አሉት፡፡ ግለሰቡ ውጤታማ እንዲሆን ከፈለገ ደግሞ ሚናዎቹን ለይቶ ማውጣት ይጠበቅበታል፡፡ አንተ ለምሳሌ ሠራተኛ ነህ፣ ተማሪ ነህ፣ ወጣት ነህ፣ ወዘተ…፡፡ እንደ ተማሪ የምትጫወተው ሚና አለህ፣ እንደ ሠራተኛ የምትጫወተው ሚና አለህ፣ እንደ ወጣት የምትጫወተው ሚና አለህ፣ ምናልባትም እንደ ልጅ፣ እንደ ወንድም፣ ወዘተ…፡፡

እንደ ተማሪ የምትጫወተው ሚና አለህ፤ እንደ ሠራተኛ የምትጫወተው ሚና አለህ፣ እንደ ወጣት የምትጫወተው ሚና አለህ፣ ምናልባትም እንደ ልጅ፣ እንደ ወንድም፣ ወዘተ… የምትጫወታቸው ሚናዎች አሉህ፡፡ በመሆኑም እነዚህንና ሌሎች ሚናዎችህን ለይተህ አውጣቸው፡፡

ሐ. ተግባራትን መዘርዘር እና ግቦችን ማስቀመጥ

አንድን ሚና ውጤታማ ለማድረግ፣ የተለያዩ መንገዶችን ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን፡፡ ከእነዚህ መንገዶች ውስጥ ውጤታማ የሆኑትን መለየት ደግ የእኛ ተግባር ነው፡፡ በመቀጠል ሚናዎችህን ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉ ተግባራትን በዝርዝር ፃፍ፡፡ ምን ብታደርግ እላይ የዘረዘርካቸውን ሚናዎች ማሳካት እንደምትችል በዝርዝር ፃፋቸው፡፡ እነዚህንም ተግባራት እንደ ግብ አስቀምጣቸው፡፡ ለምሳሌ ተማሪ የሚል ሚና ካስቀመጥክ በኋላ፣ በስሩ እንደ ተማሪ ውጤታማ ሊያደርጉህ የሚችሉ ተግባራትን ዘርዝርና እንደ ግብ አስቀምጣቸው፡፡ ለምሳሌ ሁሌ ክፍል መግባት፣ ትምህርት ቤት በሰዓቱ መገኘት፣ በሚገባ ማጥናት፣ ፈተና ላይ በተረጋጋ መንፈስ መስራት፣ ወዘተ… የሚሉ ተግባራትን እንደ ግብ አስቀምጥ፡፡

መ. እቅድ ማውጣት

እያንዳንዱ ሚናዎችህን ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዙህን ግቦች ካስቀመጥክ በኋላ ሳምንታዊ እቅድ አውጣ፡፡ ሳምንታዊ የጊዜ ሰሌዳ ለማዘጋጀት ደግሞ፣ ራዕይህን ለማሳካት በዝርዝር ያስቀምጥካቸውን ተግባራት በሳምንቱ ውስጥ መቼ፣ መቼ መተግበር እንዳለብህ በሰንጠረዡ ላይ ታሰፍራለህ፡፡ ይህንን ካደረክ በኋላ ሰንጠረዥህን ስትመለከተው ክፍት የሆኑ ቦታዎችን/ሰዓታትን ታገኛለህ፡፡ እነሱንም ክፍት እንደሆኑ ትተዋቸዋለህ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ነገር ልጠቁምህ፡፡ መከወን አለብኝ ብለህ የዘረዘርካቸውን ተግባራት በሙሉ በሳምንታዊ የጊዜ ሰሌዳ ስታዘጋጅ ከተግባራቱ ውስጥ የትኞቹ ናቸው፡፡ በጣም ጠቃሚዎችና በዚህ ሳምንት ልተገብራቸው የምችላቸው ብለህ መመዘን ይኖርብሃል፡፡ ለዚህም እንዲያግዝህ ጠቃሚ ናቸው የምትላቸውን፣ በቅደም ተከተል አስፍረህ /Prioritization/ በሳምንቱ መከወን የምትችላቸውን ያህል ብቻ አስፍር፡፡

ሠ. ዕቅድን መተግበር

እቅድ ማውጣት በራሱ ስኬት አይደለም፡፡ ይልቁንም ያወጣነውን እቅድ መተግበሩ ነው ስኬት ማለት፡፡ በመሆኑም በመጀመሪያ ዕቅድህን በተግባር ለማዋል ቁርጠኛ አቋም ያዝ፡፡ ከዛም ወደ ትግበራው እንቅስቃሴ መሄድ ትችላለህ፡፡ ወደ ትግበራ ስትመጣ አንድ ያቀድከው ተግባር በተለያዩ ምክንያቶች ያልተገበርከው እንደሆነ ወደ ክፍት ሰዓታት በማዞር ያለምንም መጨናነቅ መከወን ትችላለህ፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ እቅድህን ገምግመው፡፡ በዚህ ጊዜም ውጤታማ የሆኑትን ለያቸው፡፡ በመቀጠልም ያልከወንካቸውን ተግባራት ለይተህ አውጣ፡፡ ለምን እንዳልከወንካቸው ለይና ትምህርት ወስደህባቸው የሚቀጥለው ሳምንት እቅድ ውስጥ አካታቸው፡፡ ሚናዎችህን ለማሳካት ከዘረዘርካቸው ተግባራት ውስጥ፣ አሁንም የተወሰኑትን ምረጥና የቀጣይ ሳምንት እቅድህ ውስጥ አካታቸው፡፡ በዚህ መልኩ ለተከታታይ ሳምንታት እቅዶችን በማውጣት ለመተግበር ሙከራ ስታደርግ፣ እየለመድከው ትመጣና በስተመጨረሻ በራዕይ የሚመራ ግለሰብ ትሆናለህ፡፡

እላይ የጠቀስኳቸውን ተግባራት በትክክል ከተረዳሃቸውና በተግባርም ካዋልካቸው፣ ጊዜህን በአግባቡ የምትጠቀም ብሎም በራዕይ የምትመራ ስለምትሆን በህይወትህ እርካታን ትጎናፀፋለህ፡፡ ይህንን ስታደርግ ደግሞ ከዚህ ቀደም የነበረብህ የመጨነቅ አባዜ እንቅፋት ሊሆንብህ ይችላል፡፡ ስለሆነም ቀጥዬ ጭንቀትን መቀነሻ ስልቶችን ልጠቋቁምህ፡፡

ጭንቀትን የመቀነሻ ስልቶች

ውድ ኤም መጠነኛ ጭንቀት ጠቃሚና አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም መጠነኛ ጭንቀት፣ ነገሮችን ለመከወን ወይም ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ኃይልን ይሰጠናል፡፡ ነገር ግን ጭንቀቱ የቀን ተቀን ህይወትህን የሚያስተጓጉል ከሆነ መቀነስ አለበት፡፡ በጭንቀት ዙሪያ ያለው አስደሳች ዜና ደግሞ፣ ጭንቀት ሲበዛብን በቀላሉ መፍታትን መማር እንችላለን፡፡ ያ ማለት አዕምሯችንን ጭንቀትን እንዴት እንደሚያቃልል ማሰልጠን እንችላለን፡፡ ስለሆነም ውድ ጠያቂያችን ጭንቀትህ መሰረታዊ የለውጥ ሂደትህን የሚያስተጓጉልብህ ከሆነ የሚከተሉትን ተግባራት ከውን፡፡

1. በቀን ውስጥ ብቻህን የምትሆንበትን 20 ወይም 30 ደቂቃ ወስን፡፡ በቀን ውሎህ የሚያስጨንቅህ ነገር ሲገጥምህ ጉዳዩን ወረቀት ላይ ፃፈው፡፡ ስትፅፍ የዋልካቸውን ጉዳዮ በመደብከው ሰዓት ተመልከታቸውና በተረጋጋ መንፈስ ቃኛቸው፡፡ ይህንንም ተግባር በተደጋጋሚ በመፈፀም አዕምሮህን ጭንቀትን ማስተላለፍ ታስተምረዋለህ፡፡

2. ጭንቀት ሲሰማህ ልታወያያቸው የሚችሉ ሰዎችን ለይና ጠበቅ ያለ ግንኙነት ፍጠር፡፡ በጨነቀህ ሰዓት ከእነዚህ ሰዎች አንዱን አግኝና ስለሁኔታው አወያየው፡፡ የሚጨንቅህን ጉዳይ አካፍለውና ድጋፍ ጠይቀው፡፡

3. ቀኑን ቁርስ በመብላት ጀምር፡፡ ከዛም ትንሽ ቆየት ብለህ ትንሽ ነገር ቀማምስ፡፡ አሁንም አሁንም ትንንሽ ነገራትን በመቀማመስ የረሃብ ስሜት ሳይሰማህ የሚውልበትን ሁኔታ አመቻች፡፡ የረሃብ ስሜት ሲሰማን፣ ሰውነታችን ያለው የስኳር መጠን ስለሚቀንስ ለድብቅና ጭንቀት የመጋለጥ ሁኔታችን ይጨምራል፡፡ ስለሆነም ጥራጥሬ፣ ፍራፍሬ እና ቅጠላ ቅጠል በመመገብ ጭንቀትን መቀነስ ትችላለህ፡፡

4. ካፌን ያለባቸውን መጠጦች ማለትም ሶዳ፣ ቡና፣ ሻይ፣ ወዘተ… መጠጦችን አትጠጣ፡፡ ምክንያቱም እነዚህ መጠጦች እንቅልፍ ስለሚነሱ ለጭንቀት ያጋልጣሉ ወይም ጭንቀትህን ያባብሳሉ፡፡ በተመሳሳይ ስኳር የበዛባቸውን ምግቦችም አትጠቀም፡፡ ምክንያቱም የዚህ አይነት ምግቦች የሰውነታችንን የስኳር መጠን ከፍ አድርገው ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዝቅ ስለሚያደርጉት ለጭንቀት ያጋልጣሉ፡፡

5. አካላዊ እንቅስቃሴዎች በተፈጥሯቸው ፀረ ጭንቀት ናቸው፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴ አድርገህ፤ ሰውነትህ ሲፍታታ አዕምሮህ አብሮ ይፍታታል፡፡ በተለይ ደግሞ የኤሮቢክስ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ጭንቀትን ለማስወገድ ፍቱን መፍትሄ ነው፡፡

6. አልኮልና ሲጋራ፣ ጭንቀትን ለጊዜው እንድንረሳ የሚያደርጉ ቢሀንም በስተመጨረሻ ግን ጭንቀትን የሚያባብሱ እንደሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በመሆኑም የምታጨስና የምትጠጣ ከሆነ አቁም፡፡

7. በቂ እንቅልፍ አለማግኘት ጭንቀትን ያባብሳልና ቢያንስ ከችግሮችህ ወጥተህ መሰረታዊ ለውጥ እስክታመጣ ድረስ በቂ እንቅልፍ አግኝ፡፡

8. ጭንቅ ሲልህ አየር በጥልቀት ሳብና ተንፍስ፡፡ አየሩን በረጅሙ ሳብና በረጅሙ ተንፍስ፡፡ ይህ ተግባር ሰውነትህንም ሆነ አዕምሮህን ያፍታታዋል ብሎም ጭንቀትህን ይቀንሰዋል፡፡

በአጠቃላይም፣ ቀደም ብዬ የጠቀስኳቸውንና ህይወትህን በተግባር ለመለወጥ የሚያስችሉህን ተግባር በመከወን፣ ችግሮችህን መለወጥ ብሎም ጭንቀት ሲስቸግርህ እነዚህን ስልቶች እየተጠቀምክ ለውጥህን ማፋጠንና ችግሮችህን ማስወገድ ትችላለህ፡፡ ምላሼን ከማጠናቀቄ በፊት ሁለት ነገሮችን ማለት እፈልጋለሁ፡፡ የመጀመሪያው አዕምሯችን የመርካታችንና ያለመርካታችን ምንጭ ነውማ፣ በተቻለህ አቅም ነገሮችን በበጎ መልኩ በመመልከት፣ ትኩረትህን ያሉህ ነገራት ላይ አድርግ፡፡ ለምሳሌ በጽሑፍህ ላይ ስራ ስትሰራ ውለህ፣ ምሽን ደግሞ ትምህርት ቤት ማሳለፍህን በአሉታዊ ሁኔታ ነው የተመለከትከው፡፡ በተቃራኒው ግን ስንት ባንተ ዕድ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ስራ አጥተው አልባሌ ቦታ ያሳልፋሉ፡፡ አንተ ሥራ አለህ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንተ የምታገኘውን ብር አብቃቅተህ፣ ለትምህርት የምትከፍለው ብር አለህ፤ ሌሎች ደግሞ ስራ እየሰሩ የሚከፈላቸው ብር ስለማይተርፋቸው መማር እየፈለጉ አልቻሉም፡፡ በአጠቃላይም ነገሮችን በአዎንታዊ አተያይ መመልከትን ቀስ በቀስ አዳብር ባይ ነኝ፡፡ ሌላው ጉዳይ ደግሞ ፍቅረኛን የተመለከተ ያነሳኸው ጉዳይ ነው፡፡ በመጀመሪያ ራስህን በአሁኑ ሰዓት ፍቅረኛ ያስፈልገኛል ወይ ብለህ ጠይቀው፡፡ አንዳንዶቻችን ሌሎች ፍቅረኛ ስለያዙ ብቻ ፍቅረኛ መያዝ አለብኝ ብለን እናስባለን፡፡ ሌሎቻችን ደግሞ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ፍቅረኛ መያዝ አለብህ ስላሉን ብቻ መያዝ አለብን ብለን እናምናለን፡፡ ነገር ግን ይህን ውሳኔ መመራት ያለበት በውስጣዊ ስሜታችን ነው፡፡ ውስህ አዎ የሚልህ ከሆነ ደግሞ አካባቢህን ቃኝ፡፡ ትምህርት ቤት አካባቢ፣ ስራ ቦታ አካባቢ፣ መኖሪያህ አካባ ያሉ ሴቶችን አጢናቸው፡፡ እኔ ጋር የተሻለ ትስስር መፍጠር ትችላለች የምትላትም ላይ ትኩረት በማድረግ ጥናት አድርግ፡፡ በተመሳሳይም በዙሪያ ያሉ ሰዎችን አማክርና እንዲጠቁምህ አድርግ፡፡ ነገር ግን የመጨረሻውን ውሳኔ መስጠት ያለብህ አንተ እንጂ ባንተ ህይወት ሌሎች ውሳኔ መስጠት የለባቸውምና፡፡ በመሰረቱ የምትንህን ፍቅረኛ ለማግኘት አስፈላጊ ነገሮች ፍላጎት፣ ድፍረትና ግልፅነት ናቸው፡፡ በስተመጨረሻም እላይ የጠቆምኩህን የመፍትህ አቅጣጫዎች ተግብረህ፣ በህይወትህ ለውጥ እንድታመጣና ከችግሮችህ እንድትላቀቅ መልካሙን ሁሉ እየተመኘሁልህ በዚሁ እሰናበትሃለሁ፡፡

The post Health: ጊዜም ገንዘብም በማጣቴ ፍቅረኛ ልይዝ አልቻልኩም!!ምን አድርግ ትሉኛላችሁ? appeared first on Zehabesha Amharic.

በሪሞት ኮንትሮል ትግል መምራት አለመቻልና ሕብረት በዲያስፖራ –ጣስው አሰፋ

$
0
0

የአዲስ ድምጽ ሬዲዎ ጃንዋሪ 17.2016  3 ሰዎችን፤- 1ኛ. ዶ/ር አረጋዊ በረሄን የትግራዮች ለደሞክራሲያዊ ትብብር ሊቀ መንበር፤  2ኛ. ዶ/ር በያን አሶቦን ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር  3ኛ/ አቶ ተክሌ የሻውን ከሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት  አቅርቦ በኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታ ላይ አወያይቷቸው ነበር። በቅድሚያ አቶ አበበ የተዋንያኑ አመራረጥ የተዋጣለት ስለ  መሆኑ ያለኝን አድናቆት ልገልጽለት እወዳለሁ፤ እነሱም ለዚህ መልካም ተግባር ዝግጁ ሆነው መገኘታ

“…የዲያሰፖራው ሃይል፤ ውጭ ያለው ሃይል ውጭ ነው ያለው  እንግዲህ ምከንያቱን የመለየቱ ጉዳይ የሚጠበቅብን ነው። እንዴት ነው? አሁን ደጋፊ ነን? መሪ ነን? የሚለው ጉዳይ እንግዲህ አገር ውስጥ ያለውን ትግል የሚመራው እዚያ ያለ ሃይል ነው፤ እዚያ ያለ ሕዝብ መሆን አለበት። እኛ ወይ ገብተን እዚያ መታገል አለብን ወይ ደግሞ ከፍተኛ የድጋፍ አስተወ ጽኦዋችንን መቀጠል አለብን። በሪ ሞት ኮንትሮል ትግል መምራት እንደማይቻልም ታይቷል እሱን ባን ቃጣም…” ስርዝ የኔ

                   ዶ/ር በያን አሶቦ

ቸው የሚያስመሰግን ነው።

እኔ ታዲያ ያንን ሰፊ ውይይት ለመተቸት የተነሳሁ አይደለሁም፤ ሀሳብ ልሰጥበት በርዕሰ ስላስቀመጥኩት ጉዳይ መዳረሻ የሚሆነኝን ያህል ብቻ ቀንጨብ አድርጌ  ለመያዝ ነው።

አስተናጋጁ  ለሁሉም ያቀረበው የጋራ ጥያቄ ፤ “ባሁኑ ሰዓት ብዙዎቻችንን እያበሳጨ ያለው በጣም በየጊዜው የተደረገ ነገር ነው፤ አዲስ ነገር አይደለም፤ ነገር ግን አሁን ለሁለትና ለሶስት ወር የቆየ ሊቆም  ያልቻለ ማባሪያ የሌለው ግድያ ባገዛዙ በተለይ በኦሮሞ ክፍለሃገር የተለያየ አካባቢ ወገኖቻችን እየተገደሉ፤ እየታሰሩ፤ እየተፈናቀሉ ነው የሚገኙትና እንዴት ነው የተከታተላችሁትና የህብረተሰቡስ ጥያቄ፤ ያለውን ሁኔታ በእናንተ ዕይታ እንዴት ነው ያያችሁት?”  የሚል ሲሆን፤ ተጠያቂዎቹን ተራ በማስያዝ መልስ እንዲሰጡ አደረገ። ዶ/ር በያን ጀመሩ፤ ዶ/ር አረጋዊ ቀጠሉ አቶ ተክሌ የሻው አሳረጉ።

ተጠያቂዎች የቀረበላቸውን ጥያቄ ሲያስተናግዱ የኔ ከሚሏቸው የየግል የልብ ቁስሎች እየቆነጣጠሩ የጨመሯቸው ብዙ ነጥቦች ቢኖሩም፤ በጊዜው የኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ተማሪ ወጣቶች ላነሱት ጥያቄ  የማስተር ፐላኑ እንደምክንያት ሆነ እንጂ፤ የወያኔ አገዛዝ ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ሲፈጽም የኖረው የተከማቸ በደል ብሶት ጋኑ ሞልቶ መፍሰሱን የሚያሳይ ምልክት ነው ነው በማለት ነበር ሶስቱም ባንድ ቃል ያሰመሩበት። ከዚህ በሁዋላም በኦሮሚያ ክፍለ-ሃገር – ክፍለ ሃገር የምለው እኔ ነኝ፤ ምከንያቱም በልጅነቴ በከብት ጥበቃ (እረኝነት) ስራ ተሰማርቼ ስሰራ  ክልል የሚለውን ቃል ሲጠቀሙበት የማውቀው ለከብት ግጦሽ የሚውል የሳር መሬት ሲከለልበት ስለነበር፤ ዛሬ ወያኔ በከብት ምትክ ሰውን መከለያ ማድረጉ ስላልተመቸኝ ነው። – በሰፈነው እንቅስቃሴ ላይ ብዙ አልቆዩበትም። ከዚያ ይልቅ በመልስ አሰጣጡ ሂደት ጊዜ  በአቶ ተክሌ የሻው ለመድረኩ እንግዳ የሚመስል “እንቅስቃሴውን ኢትዮጵያዊ መልክ እንስጠው” የሚል  ሃሳብ ተነስቶ ስለነበር፤ እሱን የመልሱ አካል ሆኖ እንዲዋሃድ ለማለማመድ  የተደረገው ውይይት ሰፋ አለና ተሳታፊዎቹን ባላሰቡት ጊዜና ፍጥነት ወደሌላ የውይይት ነጥብ ማለትም የሃገሪቱ መከራና ስቃይ ምንጭ የሆነው አጥፊ የወያኔ ሥርዓትን  አደብ ማስያዝ ስለሚቻልበት የትግል ጥያቄ ጉዳይ አሸጋገራቸውና በዚያ ላይ ላደረጉት ውይይት ሰፊውን ጊዜ ሰጡት።

 

ብሎም ይህ ጸረ-ወያኔውን ትግል ማዕከል ያደረገው ውይይት በመጠናቀቂያው አካባቢ፤ ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ፤ ሃቻምና፤ አምና፤ ዘንደሮ፤ ተናትም ዛሬም፤ እየተነሳ የሚጣለው የህብረት ትግል አስፈላጊነት  በተለይ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው! ማለት ብቻ ሳይሆን፤ ጉዳዩን ለማፋጠን ድርጅት ከድርጅት ጋር ለምሳሌ ኦዴኤፍ ከሸንጎ ጋር፤ ሞረሽ ወገኔ እንዲሁ ከሸንጎ ጋር ውይይት እያደረገ እንደሚገኝ ተበስሯል። በዚህ መሃል ግን  ዶ/ር በያን – መድረኩ ሳይበርም ቢሆን፤ ልብ ብላችሁ ቨዲዎውን አዳምጡት ልክ ዲያስፖራውን ዞር ዞር ብለው የሚቃኙ ይመስላል – ለመሆኑ እኛ ማንነን? የትና ምንስ ለማድረግ ነው ሕብረት የምንፈጥረው በሚል መንፈስ የቃኙትንና የኔንም ቀልብ የሳበውን  ከዚህ ጽሁፍ አናት አካባቢ በአራት ማዕዘን ማዕቀፍ ውሰጥ ያስቀመጥኳትን ሃሳብ የወረወሩት፤ ሌሎቹ ተሳታፊዎች ልብ ብለዋት ይሁን አይሁን ለጊዜው መረጃ ባይኖረኝም፤ ሃሳቧ ወደፊት በሚፈጠረው ሕብረት ሂደት ውስጥ ትልቅ ሚና ትጫወታለች ብዬ አስባለሁ፤ መጫወትም አለባት፤  የዚያን ጊዜ እንጠብቃት፤

 

ሶስቱም የውይይት ተሳታፊዎች አበክረው የዘከሩለት የትግል ዓይነት የሰላማዊ ትግል/ሕዝባዊ እምቢተኛነት መሆኑ ግልጽ የሆነውን ያህል፤ ይህ ህዝባዊ እምቢትኝት እንዴት ነው የሚገለጠው? የትስ ነው የሚካሄደው? ሲሉ በያን ያነሱትን ጥያቄ ለማጠናከር ዕውነትም ብለን፤ ለናሙና ያህል ጥቂቶቹን ብናነሳ፤- ስትራይክ፤ ቦይኮት፤ ያልተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፤ አግባብ የልሆኑ ህጎችን አለመቀበል የመሳሰሉትንና ባሁኑ ጊዜም ዛሬ በኦረሚያ ክፍለሃር፤ በጎንደር አካባቢ  የሚጫጫሰውን ዓይነት  መሪ የሌለውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ መስመር አሲዞ፤ በእቅድና በጥበብ እንዲራመድ ለማድረግ፤ እንደገና በያን እንዳሉት በሪሞት ኮንተሮል  እንደማይቻል ማን ነው አሌ የሚል?

 

ትብብር  ትብብር! ትብብር! ትብብር! ይህ ቃል የወሬ ወፈጮዋችን እሰኪሟልጥ ከርትፈነዋል፤ ሰልቀነዋል፤ አልመነዋል ማለት ብቻ ሳይሆን፤ ባህል ሆኖናል ብል የተሳሳተ ግምት አይሆንብኝም። ከፍ ብሎ በተደረገው ውይይት ላይም ተነስቶ ሲወራ ቀደም ሲል ተደርገው ስለነበሩ ህብረቶችም በዶ/ር አረጋዊ በርሄ “የተሞከሩ ህብረቶች ነበሩ” በሚል መነሳታቸውን  አዳምጫለሁ። ይህንን እኔም አረጋግጣለሁ፤ ነበሩ። ነገር ግን ታዲያ እንዲሁ ነበሩ ብሎ ማለፉ ስላልተመቸኝ የሚከተለውን ላክልበት ሞክሬአለሁ፤

 

ካልተሳሳትኩ ወያኔ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ ብቻ በተቃዋሚነት የተፈጠሩትንና ነበሩ የተባሉትን ትብብሮች በዝርዝር ላስቀምጣቸው፤ የመጀመሪያው የአማራጭ ሃይሎች ምክር ቤት፤ ሁለተኛው/ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ሕብረት (ኢተፖድህ)፤ ሶስተኛው/ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ሕብረት (ኢድሃህ)፤ አራተኛው/ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ (ቅንጅት)፤ የሚባሉት ናቸው። ስለያንዳንዳቸው የሚክተልውን ላስታወስ፤

 

አማራጭ ሃይሎች ምክር ቤት፤- ይህ ምከር ቤት የተቋቋመው ከጅምሩ ለማቋቋም ታስቦ ሳይሆን፤ በሀገርቤትና እውጭ ባሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች ትብብር ኢህአዴግን ጨምሮ በሃገር ቤት እንዲደረግ  የተዘጋጀ የሰላምና እርቅ ጉባኤ  ወያኔ አሻፈረኝ ቢልም ጉባዔው ተደርጎ ሲጠናቀቅ በአጋጣሚ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ወያኔው የሱ በጉባዔው አለመሰታፍ ብቻ ሳይሆን፤ በጉባዔው ለመካፈል  ከውጭ ሰዎች እንዲገቡ ከፈቀደ በኋላ ሀገር ሲደርሱ ማሰር ጀመረ፤ በመንገድ ላይ የነበርው ጉዞወን አቋርጦ ተመለሰ፤ ይህ የወያኔ ድርጊት በሃገር ቤቱና በውጭው ባለው ሃይል በኩል ጉባኤው እኛ ካልተካፈልንበት መደረግ የለበትም የሚል ሃሳብ ተነሳና ካከራከረ በዃላ በወግ የተጣሉና እርቅ የሚሹ ሰዎች ባለመገኘታቸው ጉባኤው የእርቅና የሰላም መሆኑ ቀርቶ ድርጅት ማቋቋሚያ ሆነና አማራጭ ሃይሎች ምክር ቤትን አምጦ ወለደ። ከዚያ በኋላ በውጭውና በሃገር ቤት የነበረው ግንኙነት ሻከረና ቀልብ ያለው ግንኙነት ሳይሰፍን ሰነባበተና፤ በመሃሉ ሌላ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ሕብረት (ኢተፖድህ) የሚለው ድርጅት የማቋቋም ሂደት ተጀመረ።

 

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ሕብረት (ኢተፖድህ)፦ ይህ ስብስብ ልዩ የሚያደርጉት ሁለት ጥሩ ነገሮች ነበሩት፤ አንደኛ/ እስከዚህ ጊዜ ድርስ አንዱ ወያኔ እንደምክንያት እያደርገ ነገር ያቆረፍድበት የነበረ ጉዳይ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በመካክላቸው ጦረኞች አሉባችው፤ ሰላማዊ አይድሉም እያለ የሚወነጅለብት ምክንያት ጦረኞቹ ለሰላም ባላቸው ፍቅር ከወያኔ ጋር ያግባባን ነበር የሚሉትን የመሳሪያ ቋንቋ እርግፍ አድርገው የተውበትና ለወያኔ የሰላም እጃቸውን የዘረጉበት ጊዜ ሲሆን፤ በሌላው በኩል ደግሞ ይህ ስብስብ አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረውና የት ይደርሳል የተባለም ነበር። ታዲያ ምን ይሆናል ይህም ስብስብ “የማያድግ ልጅ … እንትን ይበዛዋል” እንዲሉ፤ ችግር የገጠመው ምስረታው በተጠናቀቀ በማግስቱ ነበር። የተፈጸሙት ነገሮች አስገራሚም፤ አሳፋሪም ነበሩ፤ መጥፎ ሽታ ስላላቸው እዚህ አይነሱም እንጂ፤ ሆኖም ይህ ስብስብ ከተቋቋመ በኋላ ያንን ጉባኤ አዝጋጅቶ በነበረው “ሰላም ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ የምርምርና የተግባር ቡድን” (Research and Action Group for Peace in Ethiopia and Horn of Africa)” በተባለው ደርጅት ድጋፍ አማካይነት ወደሃገር ቤት የሚተላለፍ ቀስተዳመና የሚል ራዲዎ ፕሮግራም ነበር። ይህም ሊሆን የቻለው ቀደም ብዬ እንደጠቆምኩት ስብስቡ ክነበረው ዓለም አቀፋዊ ድጋፍ የተነሳ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።

 

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ሕብረት (ኢድሃህ)፤  ይህ ስብስብ 15 የፖለቲካ ድርጅቶችን አቅፎ የተቋቋመ ሲሆን፤ ከነዚህ 15 ድርጅቶች ውስጥ 10ሩ ከውጭ፤ 5ቱ ከሃገር ቤት የነበሩ፤ የዚያን ያህል ብዛት ያለው የፖለቲካ ድርጅት አሰባስቦ የያዘ ስብስብ እስከዛሬ ታይቶ አይታወቅም። እዚህ ስብስብ ላይ ጥኢት ልቆይበት፤ የስብስቡ አመራር ሃገር ቤት የተደረገ ሲሆን፤ ይኸው አመራር በውጭ የሚገኙት አባል ድርጅቶቹ  በሃገር ውስጥ ተቋቁመው እንደማንኛቸውም በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች በህጋዊነት ተመዝግበው እንዲንቀሳቀሱ የሚችሉበትን ሁኔታ ከመንግስት ጋር በመነጋገር እንዲያመቻች ይደረጋል፤ በዚህም መሰረት ሁኔታው በመንግሥት በኩል አዎንታዊ መልስ ያገኘ መሆኑን ገልጾ፤ በውጭ ያሉት አባል ድርጅቶቹ ወደሃገርቤት ገብተው ህጋዊ ሰውነት አግኝተው አብረው በህብረት እንዲነቀሳቀሱ መልክት ያደርሳል፤ የውጭየዎች „ፍንከች ያባ ቢላዎ ልጅ“  አሉ። ምናልባት እውጭ ካሉት በአመራር ላይ የሚገኙና በመነግስት በኩል በቂ መተማመኛ የሌላቸው ቢሆኑ እንኳን፤ የግድ የነሱን ወደሃገር መግበት ሳያስፈልግ፤ ሃገር ውስጥ ባሉ አባሎቻቸው አማካይነት ሊመዘገቡ እንደሚችሉ ሁሉ ከሃገር ቤቱ በኩል ሃሳብ ይቀርብ ነበር። ቆየና ከሃገር ቤቱ ሃይል ውስጥ ካ5ቱ ሁለቱ ህብረቱን ትተው ወጥተው ቅንጅትን ይፈጥራሉ፤ እንዲያ እንዲያ እያለ የግንቦት 1997 ዓ.ምህረቱ የአቶ መለስ „ዕንከን የለሽ“ – በዃላ ላይ „ዕውር ሲቀናጣ በትሩን ጥሎ ፍለጋ ይሄዳል“ እንደሚባለው የሆነበት –  ምርጫ ይደርስና፤ ምርጫው ይደረግና፤ ወያኔ በምርጫ ይሸነፍና፤ አሸናፊዎቹ በአሸናፊነት ወንጀል ተከሰው በተሸናፊ ወያኔ ፊት ለፍርድ ይቀርቡና፤ የተሰጣቸው ፍርድ ከአንገት መድፋት ወይም አንገት ቀና አድርጎ ቃሊቲ ከመግባት መምረጥ ነበር፤ – እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባ ነገር የተሰጠው አማራጭ ነጻና ፍትሃዊ አይሁን እንጂ ዴሞክራቲክ ነበር – ከፍርድ በሁዋላ ስለሆነው መቀጠል  አሰልቺ ስለሚሆን፤ እሱን አልፌ ከዘረዘርኳቸው ስብስቦች ሂደቶች ምን እንማራለን ወደሚለው ተሻግሬ ጠቅለል ያለ ሃሳቤን ላስፍር፤

 

ምን እንማራለ? የማወራው ለውጭው ሃይል እንደሆነ አይዘንጋ፤ ምንም እንኳን አንዱ ከሌላው ለየት የሚልበት የራሱ ገጽታ ቢኖርም፤ ሁሉም ከሃገር ቤቱ ሃይል ጋር ከሞላ ጎደል ግለጽ በሆነ መነገድ በመገናኘት  በጋራ ይሰሩ ነበር። ሁሉም የዲያሰፖራው ድጋፍ ነበራቸው፤ በወጤትም በኩል ቢሆን፤ የሚመዘነው ወያኔን ከቤተ-መንግስት አውጥቶ በመጣል ብቻ ነው ካልተባለ በስተቀር፤ በ1997 ምርጫ ከቅንጅት ቀጥሎ ብዙ መቀመጫዎችን ያገኘው ህብረቱ እንደነበረ አይዘነጋም። ያም ሆኖ ደግሞ የውጭው ሃይል ህብረቱ በተቋቋመ ጊዜ አመችውን ሁኔታ ተጠቅሞ ወደሀገር ገብቶ/በሀገር ውስጥ ተተክሎ ትግሉን አለመቀላቀሉ ትልቅ ጥቁር ነጥብ መሆኑን መዘንጋት አይገባም፤ ለምን ለሚለውም ጥያቄ አንድም መልስ የሰጠ የለም። ሕዝብም „እንግዳ ሳይመጣ ሁሉ ሴት“ እንዲሉ በውጭ ያሉት የራሳችን የሚሉት በሀገር ውስጥ መሰረት የሌላቸው፤ ወይም ቢኖራቸውም ውጭ ባለውና አገር ውስጥ ባለው ሃይላቸው መካከል መተማመን ባለመኖር ይሆናል የሚል መላ ምቱን አዚሞ ነው የቀረው። እድሉ ግን አምልጧል። አንባቢ የራሱን ሃሳብ ይስጥበት፤ እንደኔ ግን  ወደፊት  በውጭ  ያሉ ድርጅቶች ከሁኔታዎቹ ብዙ ሊማሩባቸው የሚችሉ ነገሮች ስላሉ ነገ እኔን አንዱ ወይም ሌላው ሁኔታ ቢገጥመኝ እንዴት ነው የማስተናግደው ብሎ ለማሰብ ይረዳዋል ብዬ አምናለሁ። በመጨረሻም ታዲያ ከዚህ በላይ ያመላከትኳቸው በውጭና በግቢ መካከል የነበሩ ግንኙነቶች ከ1997 በዃላ ተቋርጠው ቀርተዋል፤ ለምን? ለዚህ ጥያቄ የዚያን ጊዜ በኢትዮጵያ  የነበረውን ሁኔታ ከዚያ ወዲህ ካለው ጋር ማገናዘብ ለሚችል ሁሉ በቀላሉ መልሱን ማግኘት የችላል። ከሁሉም እጅ ይጠበቃል፤ ይህንን እዚህ ላይ ሸብ ላድርግና በአዲስ ድምጽ ራዲዎ በሶስቱ የድርጅት ተወካዮች ቀን የማይሰጠው ተግባር በመባል ውይይት ወተደረገበት፤ ከአድማጭ ጋር በተደረገ ጥያቄና መልስ ዳብሮ፤ የተግባራዊነቱን ከፍተኛ ሃላፊነትም አዋያዩንና ተዋያዮቹን ተሸካሚ አድርጎ፤ ወደተጠናቀቀውና የብዙዎችን የልብ ትርታ ወዳናረው፤ የአጣዳፊው ትብብር ጥያቄ ልለፍ፤

 

በውይይቱ ተሳታፊዎች የተነሳው አጣዳፊው ትብብር፤- ይህ ትብብር ተቃዋሚዎች የሚቃወሙትን ሃይል በሚገባ አውቀው የሚያቅዱት፤ የሚተልሙት፤ የሚቋጠሩት የሚፈቱት እርምጃ ሁሉ በዚያ ሃይል ላይ እንጥፍጣፊም እንኳን ቢሆን ተጽእኖ ለማሳደር የሚችል መሆን አለመሆኑኑን በማመዛዘን የተቀናጀ መሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል። ሌላው  ከዚህ ተለይቶ የማይታየው ጉዳይ ደግሞ፤ የሚፈጠረው ትብብር ምንም ያህል ቅንጅቱ ቢያምር፤ መተማመን ከሌለ፤ ጊዜው የሚባክነው በውስጥ ፍትጊያ ስለሚሆን፤ አመርቂ ስራ ለመፈጸም አይቻልም። ለመተማመን ደግሞ ልዩነት ይታይባቸዋል የሚባሉ ጉዳዮች ላይ ትልቅ ትንሽ ሳይሉ አፍረጥርጦ በማውጣት፤ በማይፈልጉትና በሚፈልጉት ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ አለመኖሩን ማረጋገጥ ይገባል፤ ለዚህ አሰራር ጠቃሚ ይሆናሉ በማለት ካለኝ ልምድ ተነስቼ  በቅድሚያ ሊጤኑ ይገባል የምላቸውን አካሄዶች እንደሚቀጥለው ለማቅረብ ሞክሬአለሁ፤ የትግሉ መነሻ በደልን መቃ

ወም ነው። በደል ደግሞ አድራጊና ፈጣሪ አለው። ዛሬ በሃገራችን በደል ፈጻሚ ነው የተባለውና ሕዝብ የሚማረርበት አንድ መጥፎ ስርዓት አለ። ታዲያም ይህ ሥርአት የሚጠራበት ስም ብቻ ሳይሆን፤ የሥርዓቱ አራማጅም ስም ሳይቀር አደናቃፊ ሚና ይኖራቸዋል የምላቸውን እንደሚከተለው አቅርቤያቸዋለሁ፤

 

1ኛ/ የሥርዓቱ መጠሪያ፤- አንዱ አፋኝ አምባ ገነን ሥርዓት ነው  ሲለው፤ ሌላኛው  ዘረኛ ሥርዓት ነው  ይለዋል። በጉዳዩ ብዙ የማይጨነቅ ሰው ታዲያ፤ ኤዲያ! ያንንም አልከው ያንን ሁሉም ጸረ-ዴሞክራሲ ነው ተወኝ በማለት ሊሸኘው ይሞክራል። ነገሩ ግን እንደሱ አይደለም። በሁለቱ መካከል ትልቅ ልዩነት አለና።

 

ካጭሩ እንጀምር፤- – ዘረኛ ሥርዓት በተፈጥሮው  ጸረ-ዴሞክራቲክ ነው።

– ጸረ-ዴሞክራቲክ ሥርዓት ሁሉ ግን ዘረኛ አይደለም። ይህ ዋናና የመጀመሪያው ልዩነት ሆኖ፤ ከሁለቱ ስርዓቶች ጋር የሚደረገውም የትግል ግብ-ግብ የተለያየ ነው። አጠር አጠር እያደረግሁ ሌሎች ልዩነቶችንም ላመላክት፤

 

ድርድረ፤- በአምባገንን ስርዓቶቸና በተቃዋሚዎቻቸው መካከል የሚደረገው ትንቅንቅ ከሁለቱ አንዳቸውንም            በአሸናፊነት የሚያወጣቸው ሆኖ ሲያገኙትና መውጫ ሲያጡ፤ ወይም በሌላ ምክንያት ወደርድር መጥተው ጉዳዩ መፍትሄ እንዲያገኝ ይሆናል። ድርድር አድራጊዎቹ ማንኛቸውም ቢሆኑ የሚያገኙት ድርድሩ ያስገኘላቸውን እንጂ፤ የሚፈልጉትን እንደማያገኙ አውቀውም ነው ወደድርድር የሚመጡት፤ በተለመደው አነጋገርም ሰጥቶ መቀበል በሚለው መርህ መመራትም ማለት ነው።

 

ከዘረኛ ስርዓት ጋር ግን ለመደራደር እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም ከላይ እንዳልኩት ድርድር ሰጥቶ መቀበልን ስለሚጠይቅ፤ ዘረኝነት ይሕንን መርህ በስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል አይደለም። ከዘረኝነቱ ይህን ያህሉን ልተውልህ ይህን ያህሉን ተውልኝ አይባልም። ምክንያቱም ዘረኝነት ወደር የማይገኘለት አገርና ሕዝብ የሚያጠፋ በሽታ በመሆኑ ከምድረ ገጽ መጥፋት ያለበት ስለሆነ ነው – መናለባት ተግደዶ ይደራደር ይሆናል ቢባል እንኩዋን፤ የሚሰጠው እንጂ ምንም የሚቀበለው ነገር ስለማይኖር፤ ትልቅ የባልሞት ባይ ተጋዳይነት ጥፋት ከማድረስ ስለማይቆጠብ አስቸጋሪነቱን ልመገመት የሚቻል አይደለም። – ለድርድር አይመችም የምለው፤ አንድ ዘረኛ ድረጅት መቆሚያውና የጀርባ አጥንቱ ዘረኝነቱ ነው። ያ ከተነካበት ፈረሰ ማለት ነው። ስለዚህም ነው መለስ ዜናዊ  በ2002ቱ ምርጫ ጊዜ የራሱን ጋዜጠኞች ሰብስቦ ጠይቁኝ በማለት ባደረገው ድራማ ላይ እንዴት ነው ስልጣን መካፈል ስለሚባለው ምን አስተያየት አለህ ተብሎ ሲጠየቅ “ይህ ማለት እኮ የኔ ፐሮግራም ስራ ላይ እንዳይውል መደናቀፍ ማለት ነው። እኔ እንደዚሕ ያለውን አላደርግም። ከተሸነፍኩ ጥየ መሄድ ብቻ ነው።” ሲል መልስ የሰጠው። ከሰወየው ሳልርቅ የኢትዮጵያ ገዢ ሆኖ እያለ እሱ አላኮራውም። “ትግሬ ወርቅ ነው ከዚህ ዘር በመወለዴ እኮራለሁ” ነበር ያለው። ይህን  ማነው የጤና ነው ብሎ የሚወስደው? ይህ ሰው እኮ ለምሳሌ እናቱ ወይም አባቱ አንደኛቸው ከወላይታው፤ ከኦሮሞው፤ ወይም ከጉራጌው ወዘተ… – ከአማራው መቸም አይሞከርም – ቢሆኑ ኖሮ አጋም ስር እንደበቀለ ቁልቋል ሲያለቅስ የኖረ ይሆን ነበር ማለት ነው።  እዚህ ላይ መጠንቀቅ ያለብን “ወርቅ” የሚሏት ቃል በጌጥነቷ ብቻ ሳይሆን እንደተጠቃሚው ሌላም  የምትታወቅበት ሙያ ስላላት ግጭት እነዳትፈጥረ ነው። በመጨረሻም እንግዲህ ከሁለቱ ስሞች በየትኛው ስም የሚጠራውን ነው የምንታገለው የሚለውን ማሰብ ግድ ይላል፤ ስለ ሥርዓቱ መጠሪያ ጉዳይ በዚህ ላብቃና ወደስርዐቱ አራማጅ መጠሪያዎች ልሻገር፤

 

ስለገዥው ፓርቲ መጠሪያ

 

ሀ. ወያኔ                   በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጥቅም ላይ የሚውል። ተቃዋሚ የትግራይ ተወላጆች የማይጠቀሙበት፤ ሌሎችም

ሲጠቀሙበት ባይሰሙ ፈቃዳቸው የሚሆን፤ አንዳንዶቹ በአጼ ሃይለስላሴ መንግሰት ጊዜ  አምጾ የነበረውን ገራገሩን ወያኔ ካሁኑ ከፉው ወያኔ ጋር መቀላቀል ይሆናል የሚል ስጋት እነዳላቸውም የሚጠቁሙ አሉ፤ አብዛኛው የሚጠቀምበት ግን ይህን ያህል የይዘት ልዩነት ያመጣል አያመጣም ብሎ ሳይሆን፤ በጣም የተለመደና ቀላልም በመሆኑ ብቻ ነው፤     

 

ለ. ኢሕአዴግ   በሃገር ቤት የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጀቶች፤ በገዢው ፓርቲና አገልጋዮቹ ጥቅም ላይ የሚውል፤ ከላይ የጠቀስኳቸው ተቃዋሚ የትግራይ ተወላጆችም የሚፈቅዱት፤

                  

ሐ. ወያኔ/ኢሕአዴግ፤  የወያኔ የበላይነት የጎላበት  ሆኖ ሌሎቹም ተለጣፊዎቹ  ሚና እንዳላቸው ለማሳየት በሚፈልጉ፤ ወይም

                    ደግሞ ከሁለቱ ባንዱ ቢጠራ ለውጥ የለውም ለማለት በሚፈልጉ፤                                      

        መ. የትግሬ ሕዝበ ነጻነት ግንባር/ ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሃርነት ትግራይ፤ በውጭ የሚገኙ የፖለቲካ                                    ድርጅቶች/ግለሰቦች በማለዋወጥ ስራ ላይ የሚውል፤ ህዝባዊ ወያኔ የሚለው አልፎ አልፎ ካልሆነ፤ ብዙ                            አይሰማም። የትግራይ ሕዝብ ነጻነት ከማለት ይልቅ በእንግሊዝኛው ቲፒ ኤል ኤፍ ቢባል ደስ የሚላቸው                           የትግራይ ተወላጆችመ አሉ።

 

ማሳሰቢያ.- ከዚህ በላይ ስለ አጠራሩ ያቀረብኩት እንዲሁ ከመሬት ተነስቼ ሳይሆን፤ አንዳንድ ካጋጠሙኝ ሁኔታዎች ተነስቼ ነው። በዚህ በስም አጠራር ምክንያት ዱላ ቀረሽ ጭቅጭቅ ሲስተናገድ አይቻለሁ፤ እራሴም ብሆን ወያኔ ከሚለው አልፎ አልፎም የትግሬ ሕዝብ ነጻነት ግንባር ከሚለው በስተቀር ሌላ ባፌ ስለማይዞር ካንዳንድ ወዳጆቼ የትግራይ ተወላጆች በንግግራችን መሃል  እንዲያው እንዲህ ከምትል እንዲህ ብትለው ይሻላል የሚል ጥቆማ ያጋጥመኛል። የትግራይ ወንደሞቼን ችግራቸውን አልረዳም ማለቴ እንዳልሆነ ግን  ተረዱልኝ፤ ትግሬ የሚለው ቃል ከክፉ አድራጊዎች ጋር ተቀላቅሎ መነገሩ ስለሚያሰቆጫቸው እንደሆነ እረዳለሁ፤ አኔም በነሱ ቦታ ብሆን ከዚያ የተለየ አቋም ላይኖረኝ እንደማይችል ዋስትና አልሰጥም። እዚህ ያነሳሁበት ምክንያት ግን በህበረት ትግል ሂደቶች ውስጥ ላለመተማመን በመጠኑም ቢሆን ምክንያቶች እንደሚሆኑ ስለምገነዘብ ነው። ስለሆነም ተነጋግሮ ለስርዓቱም ሆነ ለስርዓቱ አራማጆች በጋራ  ስምምነት የተደረሰበትን ስም  የህብረቱ የጋራ ቋንቋ ይዞ መሄድ የመለያያ ምክንያቶችን ማጥበቢያ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። እነዚህን ሁለት ከስም አጠራር ጋር የተያያዙ ሃሳቦችን ከዳሰስኩ   በዃላ ወደዋነው ጉዳይ ስመለስ በተለይ ሥርዓቱን በተመለከተ የትኛውን ዓይነት ሥርዓት ነው የምንታገለው የሚለውን ጥያቄ አንስቶ በሱ ላይ ስምምነት ኖሮ ግልጽ አቋም ሳይደወሰድ በተሸፋፈነ መልክ አንዱ ዘረኛ ሌላው አምባገነን እያለ አብሮ በህብረት መስራት እንደማይቻል፤ ግልጽ ነው። ነገር ግን ሁለቱም በየግላቸው ሊታገሉ ይችላሉ ወደዲያሰፖራው ተመልሰን የሚፈጠረውን አጣዳፊ ሕብረት እንየው፤

 

ትግሉ ሰላማዊ ነው እስከተባለ ድረስ፤ ዶ/ር በያን ያነሱት በሀገር ቤት ተተክሎ እዚያ ስለሚፈጠር ሕብረት ወይም እዚሁ በዲያስፖራው ስለሚመሰረት የድጋፍ ድርጀት ሕብረት የሚለውን ጥያቄ በቅድሚያ መልስ እንዲያገኝ ማድረጉ አላስፈላጊ የሆኑ ውጣ ውረዶችን ያስወግዳል። ሌላው ከዚሁ ጋር እየተነሳ ያለው  „ሁሉን ያቀፈ“ የሚባለው ሃሳብ ነው። ይህ ነገር ለመረዳት ከሚያስቸግሩኝ ሚሊዎን ነገሮች አንዱ ነው። ሁሉን ያቀፈን ጽንሰ ሃሳብ የሚያራምዱት ወገኖች  አንዴም አብራርተው ሲያስቀምጡት አላየሁምና ነው። ያ ማለት ግን፤ እራሴን በራሴ ለመርዳት ሙከራ አላደረግሁም ማለት አይደለም።

 

ስለሆነም፤ የመጀመሪያው ግንዛቤዬ እንዲታቀፉ/እንዲተቃቀፉ የሚፈለጉት በየሜዳው፤ በየተራራው፤ በየሸንተረሩ፤ በጓዳ በጎድጓዳው ተበታትነው የሚገኙትን የተደራጁ ሃይሎች በወረንጦ ለቅሞ ይዞ አስተባብሮ/ተባብሮ ሕብረት መፍጠር ማለት ይመስለኛል። እዚህ ላይ ግን፤ አንተኛው ማተብህን በጥሰህ፤ አንተኛው ደግሞ ክርስትና ተነስትህ ነው ለዕቅፍ የምትበቃው  የሚሉ ገደቦች እነዳሉም አለመዘንጋቴን ዕወቁልኝ፤ ወደዃለም እመለስበታለሁ። በወረንጦ መልቀሙ ከተቻለ መጥፎ አይደለም። መቻሉን ግን እጠራጠራለሁ። ሌላው የሚታየኝ አማራጭ ደግሞ፤ ሁሉንም ለቅሞ መያዝ ሳያስፈልግ አንድም፤ ሁለትም፤ ሶስትም ጠንከረከር ያሉ ሃይሎች ተሰባስበው፤ እነሱ ለህዝብ የሚመኙለትን ሳይሆን፤ ሕዝቡ ምን ይፈልጋል? ምን እያለ ነው? የሚለውን ጥያቄ አንስቶ፤ የህብረተሰቡን ስሜት ተከታትሎ በመረዳት፤ ዛሬ ምን ይዘን ብንቀርብ ነው ህዝብ ለማዳመጥ ጆሮውን የሚሰጠን? የሚለውን ጥያቄ  መልሶ፤ ለዚህ የህዝብ ስሜት ቀራቢ የሆነና ሁሉንም ያሰባስባል የሚል ፐሮግራም ዘርግቶ፤ ማስተዋወቅ፤ ሁሉም እስኪሰባሰብ ሳይጠብቁ እጅ ላይ ባለው ሃይል ሥራ መጀመር፤ ዱሮ ለቡሄ ስንጨፍር „እዚያ ማዶ ጭስ ይጨሳል አጋፋሪ ይደግሳል“ እንደምንለው የስራ ጭስ ሲጨስ ያየ፤ ቀድሞ ጥሪውን ያልሰማው ጭምር፤ እዚያ ማዶ ምን አለ ሲል  ጆሮውን ይቀስራል፤  ይህ የኔ እምነት ብቻ ሳይሆን፤ በልምድ ያገኘሁትና፤ አሁንም የሚታይ ነው።

 

ሰለማተብ መበጠስና ስለክርስትና መነሳት ባነሳሁት ላይ እመለስበታለሁ እንዳልኩት ተመልሻለሁ፤ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያ አንድነት የሚሏቸው አነጋገሮች በተወሰኑ የየዘውጋቸውን መብት እናስጠብቃለን በሚል ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ አካባቢ ጉሮሮ የመከርከር ጠባይ ያላቸው መሆናቸውን  አሌ ማለት ይከብደኛል።     – አንድ ትዝ የሚለኝ ነገር፤ ዶ/ር መርራ ጉዲና ጀርመን ሃገር አንድ ማህበራዊ ስብሰባ ላይ ስለ ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታ ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዣቸው ንግግሩን ካደረጉ በሁዋላ፤ ስላደረጉት ንግግርና ሌላም ሌላም ለብቻችን ቁጭ ብለን ስንጨዋወት፤  የኢትዮጵያዊነቱና የተያያዙ ጉዳዮች ተነስተው ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ፤ ወዘተ … እያልኩ ስንጫጫባቸው ይመስለኛል፤ እንደመሰልቸት ብለው፤ „እናንተ ( እናንተ የሚለው የተቀየረ ስም ነው) እኮ የኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያ አንድነት ችግር የለባችሁም፤ እኛ ሰፈር ግን ችግር አለ።“ ያሉኝን አስታውሳለሁ። – ከእነዚህ ንቅናቄዎች ውስጥ ደግሞ  „እንገነጠላለን“ ይላሉ የሚልም አለ። ሕብረት እንፍጠር ብለው ለሚነሱ ሌሎች ወገኖች እንዲህ ያለ ጥያቄ የሚያነሳን ዓይኑን አያሳየኝ  ይሉና ለመተባበር መጀመሪያ ይህንን አላማሕን ሰርዘህ፤ ያንን አቋምህን ትተህ ነው ካንተ ጋር የምነጋገረው ይላሉ፤ በበኩሌ የዚህ ዓይነቱን ጥያቄ ማቅረብ ማለት በተዘዋዋሪ እራስህን አጥፋ እንደማለት አድርጌ ነው የምወስደው፤ ምክንያቱም ድርጀቱ ያለአላማ፤  አላማው ደግሞ ያለድርጅቱ ህልውና ሊኖራቸው  ስለማይችሉ ጥያቄው ፉርሽ ነው ማለት ነው።

 

እንደኔ ከነጻ አውጭዎቹ የሚጠበቀው እንዲሁ አየር ላይ የተነሳፈፉ ሳይሆኑ፤ የሚኖሩት እዚቺው  ኢትዮጵያ በምትባለው ጥላ ስር መሆናቸውን፤ በዚህ ጥላ ስር የተጠለሉት እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ሚሊዎኖችም እነደሆኑ፤ በዚያውም ልክ ሕይወታቸው ከሌላው ጋር በብዙ ድር የተሳሰረ መሆኑን፤ ባሁኑ ሰዓት ሀገሪቱና ሕዝቧ  ላይ ተንሰራፍቶ በሚገኘው ዘረኛ ስርዓት ስር የሚማቅቁ መሆናቸውን፤ እነሱም የዚህ የአጥፍቶ አጥፊ ሥርዓት ሰለባ መሆናቸውን                   – ይሄኛውን እያረጋገጡጥ እንዳሉ ግልጽ ነው – መቀበል፤ በወዲህ በኩል ደግሞ ልገንጠል ብሎ ጥያቄ ማንሳት ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሰብአዊ መብትም ጥያቄ መሆኑ ታውቆ፤ የዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ደግሞ በዴሞክራሲ መፈታት ስለሚገባውና ስለሚቻልም „ተገንጣዮች“ ችግራቸው በዴሞክራሲ የሚፈታ መሆኑን በማስረዳት ለጋራ ትግሉ ተባባሪ እንዲሆኑ መጋበዝ፤ በዘውግ ንቅናቄ ውስጥ ያሉ ዴሞክራቶች ይህንን አይቀበሉትም የሚል እምነት የለኝም። ይቻላል ብዬም  አምናለሁ። ጥያቄው እንዴት የሚለው እንደሆነም ግልጽ ነው። በኔ እምነት ብዙ የሚከብድ አይደለም። የሚጠይቀው ዋና ጉዳይ ቢኖር በሁለቱም ወገን  የዴሞክራሲ አርበኛ ሆኖ መገኘትን ብቻ ነው። በስርዟ ላይ እመለስባታለሁ፤  ወደሚከተለው ላግድም፤

 

ዴሞክራሲ በተግባር – ይህቺ ቋንቋ  ከቪኦኤ በትውስት የተገኘች ነች – ዴሞክረሲያዊ ጥያቄን በዴሞክራሲ ለመፍታት በመጀመሪያ ዴሞክራሲ እራሱ ረጋ ብሎ የሚኖርበት  መቀመጫ ቦታ ያስፈልገዋል። ዛሬ ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ ሁሉ ታጥሮበት፤ መተናፈሻ አጥቶ እንደሚገኝ እናውቃለን፤ እንዲህ ከሆነ ታዲያ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄያችንን በዴሞክራሲ  ለመፍታት ከተስማማን፤ ዛሬ ነገ ሳንል ያሉንን ጥያቄዎች(ፐሮግራሞች) ጉዳት እንዳይደርሰባቸው በጠንካራ ካርቶን አሽገን አስቀምጠን፤ ዛሬ ወያኔን ዙሪያውን ከብበን ወደየራሳችን መጎተቱን አቁመን፤ ወደ አንድ አቅጣጫ ጎትተን ጥለን ቦታውን ከወያኔ ጉጀሌ መፈንጫነት የዴሞክራሲ መናኸሪያ ማድረግና ተደራጅተው ወያኔውን በማስወገድ የተሳተፉት ብቻ ሳይሆኑ፤ ሌሎች ስፍር ቁጥር የሌላቸው የህብረተሰብ ተወካዮችን  አካትቶ በሚቋቋም የሽግግር መንግሰት አማካይነት  ወያኔ በሱ ሽንጥ ልክ የሰፋውን ሕገ-መንግሥት በሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሽንጥ ልክ በተሰፋ ሕገመንግስት ተክቶ፤ በሱ መተዳደር መጀመር፤ እዚህ ከተደረሰ ስለሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ገብቼ ላሰለቻችሁ አልፈልግም። ምክንያቱም ያሰመርኩበት ደረጃ እስከሚደረስ ድረስ በሚደረገው ጉዞ በዙ ዳገትና ቁልቁለት ተወጥቶ ተወርዷልና፤ በዚያወም ልክ ብዙ ጉዳዮች ቀደም ብለው ፍጻሜ ስለማግኘታቸው ጥርጥር አይኖርም።

 

የዴሞክራሲ አርበኛ ሆኖ መገኘትን አመለስባታለሁ እንዳልኩት፤ የምለውን ልበልና ከዚህ ሰፈር ልውጣ፤  ግንዛቤዬ፤- „ተገንጣይ ሃይል“ በሚለው ትይዩ የቆመው „የአንድነት ሃይል“ ነው። በነዚህ ሁለት ሃይሎች ዘንድ ዴሞክራሲ የሚፈራበት („ፈ“ ን አጥብቃችሁ አንብቡ) ጉዳይ አለ። የአንድነት ሃይሉ „አንድነት“ ወደመንግስተሰማያት የሚያስገባው መንገድ እሱ ብቻ ነው የሚል የማይነቃነቅ ዕምነት ስለያዘ፤ በዴሞክራሲ አማካይነትስ ቢሆን፤ እገዜሩ/አላሁ የሚሰሩት ስለማይተወቅ፤ መገንጠል ቢመጣ ምን ይውጠኛል የሚል ስጋት አለው። „ተገንጣይ ሃይል“ ደግሞ  የዚያች እጁ የሚያደረጋት  ቀበሌ  ገዥ ሆኖ በዓለም አቀፍ መድረክ ብቅ ማለት ቅሪት በውስጡ ሰለሚኖር፤ ይህ ምኞት ደግሞ በዴሞክራሲ መንገድ ስለመሟላቱ እርግጠኛ ያለመሆን ስጋት አለው። እዚህ ላይ ነው እንግዲህ „የዴሞክራሲ አርበኝነት“ ያስፈልጋል የምለው፤ ባጭር ቋንቋ፤ በዴሞክራሲ የተገኙ ውጤቶችን ለመቀበል በቁርጠኝነት መቆም ማለት ነው። ምክር፤- ለ“ተገንጣይ“ ታጋይ! ዛሬ ለመገንጠል ብለህ ብረት አንግበህ በረሃ ለበረሃ መንከራተትህ፤ እንደ አውሬ መታደንህ፤ ይቀርና፤ ዴሞክረሲ በሰፈነባት ኢትዮጵያ ውስጥ ከመገንጠሉ ፖለቲካ ትግልህ ጎን ለጎን  በህዝብህ መሃል ሆነህ፤ አገርህን፤ ሰፈርህን፤ መንደርህን እያለማህ አንተም እየለማህ፤ እየወለድክ እየከበድከ የምታደርገው ትግል ስለሆነና፤ ይህ የሰለጠነ አካሄድም እንደሆነ መገንዘብ አስቸጋሪ ሳይሆንብህ፤ ቀደም ብዬ እንደጠቆምኩት፤ ዛሬ ያነገብካትን ፕሮግራም አመቺ በሆነ ቦታ አሽገህ አስቀምጠህ፤  ነገ ዛሬ ሳትል ዛሬውኑ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን በማስፈኑ ስራ ተሳተፍ!  „የአንድነት“ ሃይልም የዜጎች ሃይል እንደመሆንህ  ከአንድ የዘውግ ስብስብ የከበደ ሃላፊነት እንዳለብህ ተገንዝበህ ያህንን ሃላፊነት የመወጣት ብቃት እንዳለህ ማሳየት ሊቸግርህ አይገባም።

 

እስከዚህ ድረስ ሕብረትን በተመለከተ ካለፉ ትብብሮች በክፉም ሆን በደጉ ምን መማር እንደሚቻል፤ ተቃዋሚዎች ለትብብር ሲዘጋጁ ቢያጤኗቸው ይጠቅማል የሚሉ ጉዳዮችን በመጠቆም፤ ትብብሩ ሁሉንም ያቀፈ ይሆናል ለሚለውም አማራጭ አካሄዶችን ለማመላከት ሙከራ በማድረግ፤ ከኢትዮጵያ ሁኔታ በመነሳት ለህብረት የሚሰባሰቡ ሃይሎች ሰለዴሞክራሲ ሚና ሰለሚኖራቸው ዕይታና ተመሳሳይ ነጥቦች ላይ ያለኝን ግንዛቤን ነማንሸራሸር ሞክሬአለሁ። እነዚህ በህብረት ለመሰባሰብ ጠቃሚ ናቸው ያልኳቸውን ሃሳቦች ግንዛቤ በማስገባት በዲያስፖራ የሚቀናጀው አጣዳፊው የትብብረ ሃይል በሚከተለው መልክ ቢቀናጅ ፍሬአማ ስራ ሊሰራ ይችላል የሚል እምነት አለኝ።

 

የወያኔን የባርነት አገዛዝ ለማስወገድ የሚደራጅ ሃይል በርግጥም ታግሎ ለማታገል የወሰነ ከሆነ፤ በሃገር ውስጥ ሕልውናውን አሳውቆ ከሕዝብ መሃል በመገኘት ትግሉን መምራት፤  „በሪሞት ኮነትሮል እመራለሁ ብሎ አለመቃጣት፤  ይህ የማይሳከ ከሆነ ደግሞ፤ ተሳክቶለት በሃገር ውስጥ ታግሎ በማታገል  የባርነቱ አገዛዝ እንዲያበቃ ለማድረግ ደፋ ቀና የሚለውን ሃቀኛ ታጋይ ሃይል አጢኖ በስንቅ፤ በትጥቅና በሌላ ሌላም አቅጣጨ በሚደረጉ ድጋፎች ትግሉን ለማጠናከር ተደራጅቶ መንቀሳቀስ። እዚህ ላይም አንድ ምልከታ አለኝ። በተለይ ሁለተኛውን አቅጣጫ በተመለከተ፤ ቅኝቱ ከወያኔው ባህርይ አቅጣቻ መሆን ስላለበት፤ ከሁሉ አስቀድሞ  ከሀገር ቤቱ ሃይል ጋር በሚያስማማ ቋንቋ መግባባትን መፍጠር፤ (ወያኔን የሚያሸብሩ ቋንቋዎች አለመጠቀም)፤ ከማንኛውም መሳሪያ አንጋች ጋር ብቻ ሳይሆን፤ ተመሳሳይ ሃሳብ የሚያወጣ የሚያወርድ ነው ተብሎ ከሚጠረጠር ጋር ጭምር ንክኪ እንደይኖር ጥንቃቄ እንደይኖር ማድረግ፤  ይህንን የምለው ያለምክንያት አይደለም። ወያኔን እንደምንታዘበው፤ የራሱም ጥላ ጭምር ስለሚያስሸብረው፤ ተሸብሮ እንዳያሸብርና በሃገር ቤቱና በዲያስፖራው መካከል ያለውን ግንኙነት እንዳያደናቅፍ ለማለት ነው። ጸረ-ሽብር ሕጉ „የንጉሡን ጠላት የራቀውን በመድፍ የቀረበውን በሰይፍ“ እንደሚሉት በቅርብም በሩቅም አገልግሎት ላይ ስለሚውል፤ ስህተት እንዳይፈጸም ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው። በመጨረሻም ጥያቄ አለኝ።

 

ትግል የሚደረገው ምን ለመድረስ ነው?  እስከዛሬ በነበረው አካሄድ ሰላማዊና ሕጋዊ ታጋዮች – የምርጫ ፓረቲዎች – ጥርሳቸውን ነከሰው በያአምስት አመቱ በሚደረገው የምርጫ ግርግር ተሳትፈው የወያኔ የዘውድ በዓል ከተከበረ በዃላ በዚህም በዚያም በምርጫው ላይ የተፈጸመ ደባዎችን መዝግበን፤ ለምርጫ ቦረድ አቅርበን፤ ተወዳዳሪዎቻችን ተደብድበውብን፤ ታስረውብን፤ ታዘቢዎቻችን ተበርረውብን ወዘተ … የበደሉ ዓይነት ተዘርዝሮ አያለቅም፤ እያሉ ይተርኩልናል፤ ዱሮውንም ቢሆን፤ ምረጫው ውስጥ የገባነው ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ ይሆናል ብለን ሳይሆን፤ አንዱ የውጭ መንግስታት ጽንፈኞች የሉናል ብለን ነው፤ ሲል ሌላው ደግሞ ምርጫ ሰው እንደሚለው መወዳደሪያ ሳይሆን፤ መታገያ ስለሆነ ነው የገባነው፤ አንድ ጊዜ ደግሞ የሰማነው፤ ከዚሁ ከምረጫ ጋር የተያያዘ ፊረማ ተፈርሞ የፈረምነው የውጭ መንግስቶች ኮረኩመውን ነው የሚል ሮሮ ሁሉ ሰምተናል። ከምርጫው በሁዋላ ደግሞ – ምርጫውን አያሸንፉ እንጂ የመረጣቸው ምንም ሰው የለም ማለት ግን አይደለምና – እኛን የመረጡ ደጋፊዎቻችንን ገዠው ፓረቲ እኔን ለምን አልመረጣችሁም እያለ ያሰቃያቸዋል፤ ከመሬታቸው ያፈናቅላቸዋል፤ – ምርጫ አለማሸነፋቸው አንሶ ለመራጮቻቸው ጦስ የመሆን ጣጣ ሁሉ አለባቸው። – መቼም ላይችል አይሰጠው ማለት ነው እንጂ መከራው ብዙ ነው። በመጨረሻው ምርጫ ይልቅ በጣም ስለመረራቸው መሰለኝ ቁርጥ አድረገው ምርጫውን አንቀበለውም አሉና “አፈር አስበሉት።” አልፎ አልፎም ምርጫው ነጻና ፍታዊ ቢሆን ያለጥርጥረ እናሸንፍ ነበር የሚሉትም ነገር አለ። እዚህ ላይ ጥሩ ነገር መጣ። „ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ ቢሆን“ የሚለው ነገር፤ ይህን በተመለከተ አጠቃላይ ሕዝብን አንድ ያደረገ  ድምዳሜ አለ። ይኸውም በኢትዮጵያ ውስጥ የብዙሃን ፓረቲ ስርዓት የሚስተናገድበትን  አካሄድ ተከትሎ ዛሬ ባለው የገዥ ፓርቲ አዘጋጅነት ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ መካሄድ ይችላል ብሎ ማሰብ „የህልም እንጀራ“ ነው የሚለው ነው።  ይሄ ወዴት ነው የሚወስደን? ካልን፤ በወያኔ አገዛዝ ስር በምትገኘው ኢትዮጵያ የሚደረገው ፋይዳቢስ የመረጫ  ውጣ ውረድ ቀርቶ፤ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ ለሚያስችል ነጻነት መታገልን አስፈላጊ ነው ወደሚለው ይሆናል። ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ ለሚያስችል ነጻነት ስንል ምን ማለታችን ነው?  መልስ፤-  መራጩ ነጻ መሆን አለበት ማለት ነው። እንደዚያ ካልን ታዲያ ደግሞ የመራጮች ሁሉ ትግል የሚሆነው የነጻነት ትግል ነው ማለት ነው። ለዛሬ እዚች ላይ ላብቃ፤ ነገ በዚሁ የነጻነት ትግል ላይ አቅሜ በፈቀደው ያለኝን ሁሉ  አሟጥጬ ይዤ እቀርባለሁ፤ የዚያው ሰው ይበለን።

 

ጣስው አሰፋ

tassat@t-online.de

Comment

 

 

The post በሪሞት ኮንትሮል ትግል መምራት አለመቻልና ሕብረት በዲያስፖራ – ጣስው አሰፋ appeared first on Zehabesha Amharic.

በዕውቀቱ የተቀመጠበት ሸፋፋ ሚዛን (ዳዊት ግርማ)

$
0
0

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen)

በዕውቀቱ ስዩም ሰሞኑን “ከአሜን ባሻገር” የሚል ርዕስ ያለው መጽሐፍ አውጥቷል፡፡ ከ“መግባትና መውጣት” በኋላ ብዙ ጊዜ መታገሱን ልብ ይሏል፡፡ በመካከል ባለው ረጅም ክፍት ጊዜ በሕትመትና ማሕበራዊ መገናኛ ብዙሃንና በሚያወጣቸው መጣጥፎች ነበር የታደምነው፡፡ በውቀቱን የምናውቀው በቁምነገር አዘል ሸንቋጭ ጽሑፎቹና በሳል ቅኔዎቹ ነው፡፡ ስለልጁ የጽሑፍ ባለጸጋነት መተንተን ጊዜን ባጉል ማጥፋት ነው የሚሆነው፡፡ የተሰጥኦው ነገር “ሀ”ና“ለ” የለውም፡፡ ማንም የሚምልለት ነው በተለይ ግጥሞቹ፤ ነገሮችን የሚያይበትና የሚያቀርብበት መንገድ፡፡ የሰሞኑ “ከአሜን ባሻገር” መጽሐፉ ከወትሮዎቹ በተለዬ ቁም ነገር ይበዛበታል፡፡ የአቀራረብ ሁኔታው ከፍታ ላይ ነው አሁንም፡፡ በተለይ የዳሰሳቸው ታሪካዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች “ፕሮፌሰር” ያክል የማዕረግ ማማ ላይ ተቀምጠው፣ የዕውቀት ጥግ ላይ አለን ብለው የሚኮፈሱ የአገራችን ልሂቃን “በልጄን ላሳድግበት” ልማድ ያልደፈሩትንና ያልዳሰሱትን ጉዳዮች “ይበል” በሚያሰኝ የአቀራረብ፣ የንባብ፣ የመረጃና የምክንያታዊነት ርቀ’ት ሲተነትን እናገኘዋለን፡፡ መጽሐፉ በጥቅሉ ግሩም ቢሆንም ቅሉ አንዳንድ ስንኩል እይታዎችን ታዝቤበታለሁ፡፡ እነሱን መዳሰስ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ነው፡፡
ዘመናዊነትን ፈጥኖና በቀላሉ መቀበል፣ ዘመናዊነት በሃገር እንዳይሰርፅ ማነቆ የሆኑትን መንቀፍ መልካምነት አለው፡፡ ይህን ሁኔታ ሲነቅፍ በተደጋጋሚ እናስተውላለን፡፡ መንቀፉ ባልከፋ፤ የበውቀቱ ነቀፋ መነሻውና መድረሻው እዛው ድሮና የድሮው ማኅበረሰብ ላይ መሆኑን ነው የማያስማማኝ፡፡ በራሱ አገላለፅ“በዘመኑ መንፈስ” ንፅፅሩ ቢሰራ መልካምነቱ ይጎላል ባይ ነኝ፡፡ ያለፈው ማኅበረሰብ ላይ የሚሰነዘር ታሪክ ቀመስ ትችት ግቡ ያሁኑን ማኅበረሰብ ለማደስ እንጂ ያለፈውን የቀድሞውን ነቅፎ በዚያው ለመርካት መሆን የለበትም፡፡
ስለ አፄ ቴዎድሮስ የዘመናዊነት ምኞት፣ የቴክኖሎጂና ዘመናዊነት ትውውቅ፣ አንድነት፣ ለዚያም ስለከፈለው መስዋዕትነት ከቧልት በዘለለ አንዳች ቁምነገር ለማለት ያልደፈረ፤ ስለቴዎድሮስ “እጅ ቆረጣ” ዲስኩር ለማውራት ግን ብዕሩ ይሰላል፡፡ የአሁኑን ስርዓት አምባገነንነት ለመግለጽ የስርዓቱ አምባገነንነት በራሱ በቂ ነው፤ የግድ ወደአጼዎቹ ዘመን ወደኋላ መንደርደር ያለበት አይመስለኝም፡፡ በቴዎድሮስ ዘመን’ኮ አብዛኛው የዓለም መንግሥት በፈላጭ ቆራጭ የፊውዳል ስርዓት ስር ነበር፡፡ የኛዎቹን ነገሥታትነጥሎ መወረፍ አይጠበቅበትም፡፡
ስለ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ሐውልት የመጎብኘት ነገር ሲያወሳ “ባጋጣሚ ከንጉስ ከመወለዱ ውጭ” ምን ሠራ? ብሎ ይጠይቃል፡፡ ልዑል ማለት በደምሳሳው የንጉሥ ልጅ ነው፡፡ የየትኛውም ሃገር ንጉሥ ልጅ ዝናው ናኝቶ ነው የምናውቀው፡፡ የሚናኘውም ምንም ስላደረገ ሳይሆን የንጉሥ ልጅ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡ የኦስትርያው ንጉሥ ልጅ መቃብር የሚጎበኘው ለምንድነው? ባጋጣሚ የንጉሥ ልጅ ከመሆኑ ውጭ የሰራው ነገር የለም፡፡ በርግጥ ለሁለተኛ የዓለም ጦርነት መጀመር የልዑሉ መገደል ፊሽካ ነበር፡፡ ቢሆንስ በሴራ ተገደለ እንጂ ምን አስደናቂ ስራ ሰራ? እንቀጥል፡፡ የእንግሊዝ ልዑላን በእንግሊዛውያን ዘንድ ታዋቂና ተከባሪ ናቸው፡፡ ሹመታቸውና ጋብቻቸው ታላቅ ግርግርታና ሽፋን አለው፡፡ ታዲያ እኒህ የእንግሊዝ ልዑላን በትዕዛዝ ነው እንዴ የተወለዱት?
የበዕውቀቱ ሸፋፋ ዕይታ ባብዛኛው የሚመነጨው ለሃይማኖት ካለው ግንዛቤ ነው፡፡ የልጁ የብዕር ሰይፍ ብዙውን ግዜ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ይወረወራል፡፡ ብዙ ጊዜ መሠረታዊ ያልሆነ ትችጭ ይሰነዝራል፡፡ ለትችቱ መሸሸጊያ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ያለው ለማስመሰል ይጥራል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዳለው የሚያሳይ አሳማኝ ምልክት አላይበትም፡፡ ያደገበት ባህል ለቤተ ክርስቲያን ጉልህ ቅርበት ስላለው ጠቅሞት ይሆናል፡፡ ከዚያ የዘለለ ድፍረት ግን “አወቅሁሽ ናቅሁሽ ነው” ይመስላል፡፡ ብዙው ሰው ከቤተ ክርስቲያን ታዛ “ዘኬ” አነፍንፏል፤ ይህን ግ የእውቀት እማኝ አድርጎ መውሰድ ያስታል፡፡ ልጁ ከአንዴም ሁለቴ “ኢ-አማኒ” ነኝ ብሎ ድምጹን ከፍ አድርጎ ይናገራል፡፡ ራሱን ኢ-አማኒ ያደረገ ሰው የሉላውን ሰው እምነትና ሃይማኖት መጎንተል ዘላንነት፣ ወንጀልም ነው፡፡ በተለይ ካህናትን በሸንቋጭ ቋንቋ የመዝለፍ ልማድ አለው፡፡ ነገር ግን ከኢ-አማኒ ወደአማኒ የሚሰነዘር ማንኛውም ሃይማኖት ነክ ጉንተላ ምክንያታዊ አይደለም፡፡

መቼ ነበር ይህ ልጅ እስልምናን ወይምፈረንጅ ጠቀስ አመጣሽ ቤተ እምነቶችን የሸነቆረው? ይህ ልጅ አቡነ ተክለ ኃይማኖትን በተቸበት አግባብ መሃመድን ቢነካ በእውኑ የበዕውቀቱን አንገት ከተቀረው ሰውነቱ ላይ ተሰክቶ ማግኘት የማይታሰብ ሊሆን ይችል ነበር፡፡ እስልምናም ሆነ ሌሎች የክርስትና ቅርንጫፎች በዚች ሃገር ታሪክ ውስጥ ጎታች ምዕራፍ አልነበራቸውም?

ልጅ በውቄ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን ሳይንስ-ጠል ሊያደርግ ሲዳክር በ“ከአሜን….” መጽሐፉ ታዝበነዋል፡፡ ስለ “ መሬት መዞር” አንድ ፈረንጅ ለሊቃንቱ ሲናገር እንዳልተቀበሉትና አለቃ ለምለም ወደሚባሉ የላቁ ሊቅ ፈረንጁን እንደመሩት ይነግረንና አለቃ ለምለምም ጉዳዩን ሰምተው ከነጩ ጋር ጠጅ ጠጥተው ሲዞርባቸው “ያገሬ መሬት አሁን ዞረች” ብለው ሳይንስን ላለመቀበል ከፌዝ ጋር እንዳቅማሙ ከትልቅ ነቀፋ ጋር ይተርክልናል፡፡ ይህን የሚለው ከማን ጋር አነፃፅሮ ነው? እኔ እስኪ ይኼን እውነት ከፈረንጆች ጋር ላነፃፅር፡፡ መቼም ከእውነቱ ጋር እንጂ ከፈረንጅ ጋር አታነፃፅር እንደማይለኝ ተስፋ አለኝ፡፡ ምክንያቱም ለርሱም ሆነ ለሌሎች “ዘመናዊ ትምህርት” ቀመስ ነቃፊዎች መነፅራቸው ምዕራባውያኑ ናቸውና፤ ይልቁንም ልጅ በዕውቀቱን ራሱ እንደነገረን “በአንድ ሃባ መፅሐፍ” የልጅነት ማኅተቡን አስበጥሰው ሃይማኖትን ያስተውት ሐዋሪያዎቹ ናቸውና፡፡ “የመሬት መሸከርከር” ነገር ሲነሳ የሳይንሱ መገኛ ምዕራብ አውሮፓውያን ራሳቸው በእልልታ አልተቀበሉትም ነበር፡፡ በተለይም የሮማካቶሊክ ልሂቃን፡፡ ስሙን የዘነጋሁት ተመራማሪ “መሬት እንደምትዞር” አረጋገጥኩ አለ፡፡ የዘመኑ ፈላጭ ቆራጭ ፓፓዎች ንስሃ ግባ አሊያ አንገትህ ይከላል ብለው አስፈራሩት፡፡ “ሰይጣን አሳስቶኝ ነው” ብሎ “ተፀፀተ”፡፡ ቀጥሎ እውቁ የግኝት ሊቅ ጋሊሊዮ ጋሊሊ “አውነቱን” አገኘሁት አለ፡፡ “ሰይጣን አሳሳተኝ” በል ተባለ ፓፓዎች ዘንድ ቀርቦ፡፡ ፈቃደኛ ሊሆን ባለመቻሉ አንገቱን ሊቀላ ችሏል፡፡የልጁን ክፍተት እዚህ ላይ በሰፊው ማየት እንችላለን፡፡ ይህ እንግዳ ግኝት ለሳይንስና ፈጠራ ቅርብ በሆኑትን ነጮች እንኳ በቀላሉ ቅቡል አልነበረም፡፡ የሮም ቤተክርስቲያን ፓፓዎች አውሮፖ ውስጥ ብዙ ግኝት ያመጡ የሳይንስ ሊቆችንና የተለየ ሃይማኖታዊ አቋም ያራመዱ ሊቃውንትን በእሳት አቃጥለው መጨረሳቸው ታሪክ ያወራው ሃቅ ነው፡፡ ጉዳዩ ወደ እኛ ሃገር እና ቤተ ክርስቲያን ሲመጣ ነው እንዴ ለበዕውቀቱ ለአቅመ- ወሬነት የሚበቃለት? የእኛዋቹ ሊቃውንት መልሳቸው ሁለት ነው፡፡ አንደኛው አንቀበልም፤ ሁለተኛው ደግሞበቀላል ፌዝ አዘል “ቤተ-ሙከራ” “ሰክረህ ሲዞርብህ” መሬት ትዞራለች አትበል! የሚል ነው፡፡ እንደ ሮማዎቹ ከዶግማ ጋር አላያያዙትም፡፡ ሌላው ቀርቶ ወደ ዛቻና ማስፈራሪያ አላደገም፡፡ አውሮፓውያኑ ግን “የሰይጣን ሃሣብ” ነው፡፡“ትምህርተ-ሃይማኖት” አፋለሰ ብለው ሰው ሰቅለዋል፡፡

በአዲሱ መጽሐፉ ገፅ 91 ላይ “አንድ ፍሬሽንብራ የሚያክል ቄስ በአንዲት ቃል’አሰርሁ ፈታሁ’ እያለ ሃገር ሊያምስ ይችላል” ይላል፡፡ ምን ማለት ነው? “አንድ ፍሬ ሸንብራ” የሚለው ሃረግ የስድብ ቃና ነው ያለው፡፡ እንዲህ ብሎ አንድን ክብር ያለው የሃይማኖት አባት መዝለፍ ተከታዩን ከማሳዘኑ አልፎ የፀሐፊውን ደረጃም ያወርዳል፡፡

እዛው ገፅ ላይ ሌላ ሸንቋጭ ገለፃ አለ፡፡ “መንፈሳዊ ባለስልጣኖች ከዓለማዊ ባለስልጣኖች የሚበልጥ እንጂ የማያንስ ጉልበት ነበራቸው” የሚል፡፡ ከዚህ ዓረፍተ ነገር፤ ሁለት ህፀፆችን መንቀስ እንችላለን፡፡ የመጀመሪያው“መንፈሳዊ ባለስልጣኖች” በሚል ድፍረት በተቀላቀለበት ገለፃ መንፈሳዊ አባቶችን ይወርፋል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ትውፊትና በአማኞቹ ዘንድ ክብር ባለው አጠራር ነው የሃይማኖቱ አባቶች የሚጠሩት፡፡ በስድ ውከላ ቤተ ክርስቲያኗን ማንኳሰስ አላማው ስለሆነ እንጂ የዛሬዎቹን “ጥቂት” ፖለቲካ መር የኃይማኖትመሪዎች ቢተች ጥቅሙ ለራሷ ለቤተ ክርስቲያኗም በሆነ ነበር፡፡ ሁለተኛው የመንፈሳዊ አባቶችን ስልጣን /power/ ሊያሳይ የሞከረበት ነው፡፡ አሁንም በንፅፅር ነው የማሳየው፡፡ ከየትኛው ቤተ እምነት ራሶች ጋር ተወዳድረው ነው የኛዎቹ “ባለጉልበት” የሆኑት፡፡ እስልምና አረብ አገራት ላይ ራሱ መንግስት ነው፡፡ አባቶችም አድራጊ ፈጣሪ መሆናቸው ግልፅ ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ በዓለም አብያተ-እምነት ታሪክ እንደ ሮማ ካቶሊክ ፓፓዎች ጉልበተ ብርቱ መንፈሳዊ መሪ ተከስቶ የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ እኒህ ፓፓዎች ታላቁን የሮም መንግስት በትረ ስልጣን ይዘውሩ ነበር፡፡ በጉባኤ ኬልቄዶን ለአንዷ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሁለት መከፈል፣ በ16 መ/ክ/ዘመን ፕሮቴስታንቲዝም ለተባለው እንቅስቃሴ መጀመርና ለቤተ ክርስቲያን ወደ ሶስት ቅርንጫፍ ማደግ፣ ቤተ ክርስቲያን ወደ አንድነቷ እንድትመለስ በተጠሩ የተለያዩ ጉባኤዎች ላይ እንቅፋት በመሆን የሮማ ፓፓዎች ጡንቻ ከባድ ድርሻ ነበረው፡፡

የላሊበላን አብያተ ክርስቲያናት “አዳራሾች” (ገጽ 25፣26፣28፣31) ብሎ ከእምነትም ከሥነ ውበትም ጎራ ገፍቶ ያወርዳቸዋል፡፡ የላሊበላ ቤተ መቅደሶችየተሰሩትም፣የሰራቸው ቅዱስም መንፈሳዊና ለመንፈሳዊ ዓላማ ነው፡፡ ከታሪክና ሥነ-ህንፃ ፋይዳቸው፣ ከቅርስነታቸውም ጎን ለጎን አምልኮ የሚፈፀምባቸው መንፈሳዊ መካናት ናቸው፡፡ አዳራሽ ብሎ መንፈሳዊና ቅርሳዊ ይዘትና ልዕልናቸውን ያንቋሸሸበት ምክንያት ግልፅ አልሆነልኝም፡፡

በሌላ መልኩ በገፅ 162 ላይ እንዲህ ይላል፡ “ብዙ ያገራችን ገዳሞችና ጥንታዊ ህንፃዎች በሰላሙ ቀን ለቤትነት የሚያገለግሉ ምሽጎች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡” አሁን ይኼ ምን ማለት ነው? ዓረፍተ ነገሩም ይዘቱም ግራ አጋቢ ነው፡፡ ገዳማት በሰላም ቀን መኖሪያ ቤቶች ናቸው ማለት ምንድነው?“አምልኮ ቦታን የሙጢኝ የሚል እምነት እንደሚወገድ” (ገፅ 171) ሲተነብይ እናገኘዋለን፡፡ አሁንም ቢሆን በዚህ አባባሉ ከዚች መከራ የበዛበት ቤተክርስቲያን ራስ ላይ ሊወርድ አልፈለገም፡፡

ቤተክርስቲያንን ለመጐንተል ቀልቡ የማያርፈውን ያህል ስለሰራችው መልካም ትሩፋት ለመዘከር ብዕሩ ይዶለዱምበታል፡፡ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት የቀመሙትን ቅኔ ሲነጥቅ እንጂ ሲያሞግስ አንብበን አናውቅም፡፡ ስለ ሊቃውንቱ የዘመን አቆጣጠር (Calendar) ጥበብ /ግኝነት፣ ስለ ሥነ-ፈለክ ምርምራቸው፣ ሒሣብ፣ ፍልስፍና፣ ታሪክ፣ ሥነ-ህንፃ፣ ሥነ-ፅሑፍ፣ ፊደል፣ አሃዝ፣ ብራና ፍቀው ቀለም በጥብጠው እውቀት ስለማቆየታቸው በስህተት እንኳ ለማውራት ወይ ለመፃፍ ሲደፍር አላየሁትም፡፡ ለመንቀፍ፣ ለማንኳሰስና ለማላገጥ ግን ከብርሃን ፈጥኖ ይደርሳል፡፡

ሌላ ቦታ ላይልጅ በዕውቀቱ “ኡ ኡ” ብሎ ጮኾ ኢ-አማኒነቴን እወቁልኝ ሲል እናገኘዋለን፡፡ ኢ-አማኒነትን ለመግለጽ ሁለት ጊዜ ቃል በቃል አንድ ቦታ ላይ ደግሞ በአገባብ ሞክሯል- በ“ከአሜን ባሻገር” ላይ፡፡ ይህን ለማሳወቅ መጽሐፍ መፃፍ አይጠበቅም በህይወት ፍልስፍናውና በእለት-ተለት የኑሮ ዘይቤው ሊገልፀው ይችል ነበር፡፡ ምናልባት አማኒው ክፍል ከተከፋ ብሎ ይመስላል አንድ ቦታ ላይ ደግሞ “ለፋሲካ በዓል ማንኩስ” ሄጄ ይላል፡፡ ይህን የማመጣጠን ፓለቲካውን አልወደድኩለትም፡፡ በ“ማመጣጠንፓለቲካ” ብዙ ገፆች ላይ ሲዋዥቅ ይዤዋለሁ፣ በተለይ ታሪክንና ማንነትን በተነተነባቸው ክፍሎች፡፡ ኢ-አማኒ መሆን መብቱ ነው፤ በነጋሪትም አሳወጀ በህይወት ዘይቤው፡፡ ግን በእሱ ኢ-አማኒነት ውስጥ የሌላውን አማኒነት አንኳሶ መሳል ተንኳሽነት ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ቂም ሊጋባ ይችላል፣ በህይወት መንገዱም ላትመቸውት ችላለች፡፡ ቤተ ክርስቲያኗን በሰበብ አስባቡ መጎንተል ግን የተከታዩን ግለሰባዊ መብት እንደመፃረር ነው፡፡ በልጅነቱ በቁንጥጫ የመዘለጉትን ቄስ ሲጠላ አድጎበት፣ የኢትዮጵያን ቄስ በጅምላ ሊጠላ አይገባውም፡፡ የእሱ የጥላቻ አገላለፅ አዕላፋት የሚሆኑ የቄሱን ልጆች ያሳዝናልና፡፡

ከዚህ ወጣ ስንል፣ “ጉግስ፣ ጊጤ፣ ሰንጠረዥ አካዱራ፣ ገና የተባሉት ጨዋታዎች የጦርነት ቃና ነበራቸው” ይለናል፡፡ (ገፅ 162)፡፡ የየትኛውም ሃገር ጨዋታዎች (Games) በሁለት ተቃራኒ ቡድኖች መካከል የሚካሄዱና አንዱ ቡድን ወይም ግለሰብ ሌላኛውን ቡድን ወይም ግለሰብ ለማሸነፍ የሚደረግ ግብ ግብ ነው፡፡ እሱ ካልሆነማ የጨዋታው አጓጊነት አይኖርም፡፡ አሁን ያሉ ዘመናዊ ስፖርታዊ ጨዋታዎችን ስንወስድም በዚህ መንፈስ የተቃኙ ናቸው፡፡አሸናፊነት ግባቸው ይሆንና ያልቻለ ተሸናፊ ይሆናል፡፡ በዚህ ግብግብ ውስጥ መጎዳዳት አልፎ ተርፎምመገዳደል ሊኖር ይችላል፡፡ በዘመናዊ ስፖርት እንደ American football ጦርነት አካል ጨዋታ የለም፡፡ የኛን ጨዋታዎች የጦርነት ታሪካችን መግፍኤና ቆስቋሽ ሊያረጋቸው ይዳዳል፡፡ ጨዋታዎች እርሱ እንዳለው የጦርነት ቀደምት ሽሎች ሊሆኑም ላይሆኑም ይችላሉ፡፡ በጥናት እስካልተረጋገጠ ድረስ ከግለሰብ ግምት ያለፈ እውነታ አይኖረንም፡፡

ስለጡት ቆረጣ ባወራበት አንቀፅ ዮዲት ጉዲት ወደ አክሱም ወርዳ “በሴተኛ አዳሪነት” እንደተሰማራች ይነግረናል፡፡ “የቄስ ሚስት አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት…” የሚለው ብሒል የሚሰራው እዚህ ጋር ነው፡፡ ከሚገባው በላይ ተጨብጭቦልህ ማማ ላይ ከወጣህ መውረጃው ነው የሚጠፋህ፤ ወጥም ትረግጣለህ፡፡ ሴተኛ አዳሪነት የተጀመረው ከሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ጋር ተያይዞ እንደሆነ ነው በስፋት የሚታወቀው፡፡ ሴተኛ አዳሪነት /Prostitution/ እንደ ስራ ዘርፍና መተዳደሪያ ነው፡፡ በየት በየት አድርጎ ነው ከዛሬ 1100 ዓመት በፊት ኢትዮጵያ (አክሱም) ውስጥ ሴተኛ አዳሪነት አለ የሚለን? ምን አልባት ዘማዊነትን ሴተኛ አዳሪነት ብሎ ተረድቶት ከሆነ በትልቁ ስቷል፡፡ ሴተኛ አዳሪነት ነጮቹ commercial sex የሚሉት ነው፡፡ እሱም ገንዘብ ማግኛና ኑሮን ማሸነፊያ መንገድ ነው፡፡ ይህ ስራ ከሺ ዓመታት በፊት አገራችን ውስጥ ነበር ማለት ጸሐፊውንም ሆነ ምንጩን ከስህተት አያድናቸውም፡፡

የጉዞ ማስታወሻ “ጊዜ አልፎበታል” ይለናል ልጅ በውቀቱ፡፡ ገጣሚው የሚያስገርመኝ ጠባዩ እርሱ በግሉ ያመነበትን ጉዳይ ነባራዊ እውነታ አድርጎ መሳሉ ነው፡፡ “የጉዞ ማስታወሻ”ን Google Earth ተክቶታል አይነት ስብከት ያስቀምጣል፡፡ “የጉዞ ማስታወሻ” ሲባል “ደብረ ብርሃን ከአ/አ በስተሰሜን አቅጣጫ 130 ኪ.ሜ ርቀት ላይ፣ ከባህር ጠለል በላይ ምንትስ ጫማ ከፍታ…” ምናምን አይደለም`ኮ፡፡ የሕዝቡን ባህል፣ ወግ፣ ተረት፣ መልክዓ ምድር፣ የኑሮ ዘይቤ፣ የስልጣኔ ባህል፣ ትምህርት፣ ፍልስፍና፣ ፍቅር፣ ጥላቻ፣ ሐዘን፣ ደስታ፣ ሌሎችም ይገለጹበታል፡፡ የ“ገለጻ” ችሎታ በራሱ አንድ የሥነ ጽሑፍ ስልት ነው፡፡ እስኪ ዛል አንበሳን ከመሐመድ ሰልማን “ፒያሳ…” ልቆ የሚከስትልን ድረ ገጽ ይጠቁመን፡፡ እስኪ በሞቴ ስለአርማጭሆ በቂ መረጃና ምስል የትኛው ድረ ገፅ ላይ ነው ያለው?

ታሪክ ቀመስ ትንተና ከሰጠባቸው ምዕራፎች ባንዱ “ስምና ማንነት” በተሰኘው ጥግ ስር ጎጃም ኦሮሞ ልትሆን ለጥቂት ነበር የተረፈችው፡፡ እውነት ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በርሱ የተጋባ ነው፡፡ ይህን ማሳወቅም በጎ፡፡ ግን ይህን እውነታ ለመግለጽ ቀይረውበት ነው እንጂ አያቴኮ “ከበደ” ሳይሆን “በዳዳ” ነበር አይነት ዲስኩርን ምን አመጣው? እዚህ ድረስ መሄድስ ለምን አስፈለገ? ስለምኒልክና የሃገር አንድነት ዘመቻው ያቀረበው ትንታኔ እጅግ ግሩም ነው፡፡ እውነትና በታማኝ ዋቢዎች የተጣቀሰ ነው፡፡ እውነት ነው ዳግማዊ ምኒልክ በዘመቻው የአንድ ንጹህ ሰው ጡት አላስቆረጠም፡፡ ይህን እውነት በእውነትነቱ ብቻ ማስረዳት የምሁርነትም የጀግንነትም ምልክት ነው፡፡ በዕውቀቱ የዲግሪ መዓት የቆለለ “የታሪክ ምሁር” ነኝ ባይ ያልደፈረውን ነው የደፈረው፡፡ ለዚያውም በፍቱን ምክንያታዊነትና ማስረጃ ከግሩም ጥናት ጋር- ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ይህን ለ“ማመጣጠን” ግን “የጎጃም ነገሥታት ኦሮሞ ናቸው”፤ “ነገሥታቱ ከኦሮሞ ሲጋቡ ነው ክብራቸው የሚጨምረው”፤ “የጎጃም አካባቢዎች ‘ኦሮሞ-ወረስ’ ናቸው”፤ ሌላው ቀርቶ “ከኦሮሞ ያልተቀላቀለ ጎጃሜ ክብሩ ያነሰ ነው” የሚለው ዲስኩር ግነት አከል አዎ-ኦሮሞ አገላለጽ ነው፡፡ የአካባቢውን ባህል የሚያውቅ ሰው ደግሞ ገለጻው ከእውነታ ምን ያክል እንደጎነ አያጣውም፡፡ ያለፈ የታሪክ ስህተት የሁላችንም ቀደምቶች መፈጸማቸው እሙን ነው፡፡ እሱን ለእነሱው ትተን እኛ የጸዳ ዛሬና ነገን ለመገንባት መትጋት አዋጪው ነገር ነው፡፡

ስለራስ ጎበና የሰጠው ታሪካዊ ትንታኔ ግሩም ነው፡፡ ራስ ጎበናን ለማክበር ግን “ንጉሥ ምኒልክ ‘አንቱ’ ብሎ ጎበናን ይጠራዋል” ማለት፣ አልፎም “የጎበና ንብረት ከምኒልክ ይበልጣል” ብሎ መቀኘት በእውኑ አጓጉል ግነትና ኢ-ምክንያታዊ ነው፡፡ አንድነታችን እንፈልገዋለን፤ ለዚያ የሚያሻውን መስዋዕትነት እስከመክፈል፡፡ ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያዊነት ውሁድ፣ ቅልቅል እየሆነ መጥቷል፡፡ ይኼን ለማሳየት የሄደበት መንገድ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ግን አበበንም እንዳይከፋው ጫላንም እንዳይከፋው “በማመጣጠን” የሚቀርብ ነገር ሁሌም በጎ አይሆንም፣ ሕጸጽ ሊያስከትል ይችላልና፡፡ እንደውም ይሄን ክፉ ነገር የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሳናስበው ያሰረፁብን ይመስለኛል፡፡ እውነት በማመጣጠን አትቀርብም፣ እውነት ያው ራሷ እውነት ናት፡፡

በታሪክ የተከሰተን ድክመት ተምረንበት ለዛሬ በጎነት ትርፍ ማግኘት መልካም ድርጊት ነው፡፡ በሌላው ዓለም ወተትና ማር የመዝነብ ታሪክ እንደተመዘገበ ሁሉ በእኛ ላይ መሳለቅ ግን ደግ አይመስለኝም፡፡ “በታሪክ ውስጥ ያሉ ቁልፍ ቃላቶች (ቃላት?) ‘ታሠረ፣… ነገሠ… ዘመተ… ተሰቀለ’ የሚሉ ብቻ…” (ገጽ 80) ይለናል፡፡ የዓለም ታሪክም ከዚህ የተለዬ ዘገባ የለውም፡፡ የታላቋን አውሮፓ ታሪክ እንኳ ብንወስድ “ወረረ፣ አስገበረ፣ ቅኝ አደረገ፣ በዘር አገለለ፣ ገደለ….” እና መሰል ትርክቶች የዘለለ አይደለም፡፡ ዛሬ በዘር ማግለላቸውን በአንጻሩ ከማስቀጠላቸው በቀር ከታሪካቸው ተምረው አሁን የዓለማችን ቁንጮዎች ሊሆኑ ችለዋል፡፡ የዓለም ታሪክም እንዲሁ ነበር የእኛ የተለዬ አይደለም የሚለው አይደለም የእኔ መከራከሪያ፡፡ እርግጥ ነው ዓለም ከሰራው የተለዬ የእኛ ቀደምት አልሰሩም፡፡ ግን ግን የቀደሙትን በመተቸት ላይ ብቻ በዕውቀቱ ለምን ረክቶ ይቀራል ነው የእኔ መነሻ፡፡ የታሪክ ክስተቶችን የአሁኑን ለማስተማርና ለመገሰጽ ይጠቀምበት እንጂ የቀደሙትን ብቻ ዘልፎ አይቁም ነው፡፡ በዚህ ዘመን የታሪክ ደካማ ጎኖችን በማስቀጠል ለማትረፍ ደፋ ቀና የሚሉ ልሂቃንን መተቸት በአንጻሩ የበለጠ ጠቃሚ ይሆን ነበር፡፡ ታሪክን በዘመኑ አውድ ስንመዝነው በዓለም መድረክ ከተከሰተው ውጭ በእኛ ሃገር ብቻ ተለይቶ የተከሰተ ነገር የለም፡፡ የተከሰተውንም በ“ዘመኑ መንፈስ” ስናጤነው መጥፎም ቢሆን ቅሉ ጭራቅ ጎኑ ብቻ ገኖ ሊወጣ አይገባም፡፡ አሁን ያለውን ነባራዊ እውነታ መተቸቱ ግን የበለጠ ሃገራዊ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡

በዕውቀቱ ስዩም ከዚህ ሁሉ ያልፍና አንድ ዘለላ የፈረንጅ መጽሐፍ አንብቦ ‘ኃይማት ለምኔ’ ማለቱን ይነግረናል፡፡ እስኪ አብረን እንከታተለው፤ “The Future of an Illusion የሚል የፍሮይድን መጽሐፍ ካነበብኩ በኋላ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከሃይማኖት ጋር ፍቺ ፈጸምኩ” ይለናል፡፡ ለስንት የጠበቅነው ግሩም ልጅ ለአንድ ባህር አቋርጦ ለመጣ መጽሐፍ እጅ ወደላይ ብሎ ማንነቱን ሲሰጥ እናየዋለን፡፡ ከራሱ አንደበት ሲወጣማ አብሶ በጣም ያስደነግጣል፡፡ እንዲህ ብሎን በሕዝብ ጭብጨባ ከወጣበት ማማ ላይ ወርዶ ሲከሰከስ እናየዋለን፡፡ የበዕውቀቱ ጠንካራ መንፈስ በአንድ የፈረንጅ መጽሐፍ የሚፈረካከስ አይመስለኝም ነበር፡፡

ወደ ሃይማኖት ቀመስ ጉዳዩ አንዴ ልመለስና በገጽ 216 ላይ “ክርስትና በጥንታዊ ቁመናው… ሌሎችን የሚችልበት…” ትዕግስት እንዳልነበረው ይነግረናል፡፡ ከክርስትና በዓለም መሰበክ በኋላ ኃይማኖቱ በአገራችን ገናናና ብሄራዊ ሆነ፡፡ በማይካድ ሁኔታ ከሰሜን እስከ ደቡብ ጫፍ ቢሄዱ ክርስትና በአገራችን ባህልና አስተሳሰብ ላይ ከባድ አሻራ ማኖሩን ይገነዘቧል፡፡ ሌሎችን የማሳነስ ነገር እንኳ ቢኖር የሃይማኖቱ አስተምህሮ ሳይሆን የግለሰቦች ዘዬ መሆኑ እርግጥ ሆኖ በየዘመኑ ደግሞ ሁሉም ኃይማኖቶችና የኃይማኖት መሪዎች ይፈጽሙት የነበረ ነው፡፡ ምስራቃውያኑ በተለይ ጃፓን በሕግ ለክርስትና በራቸው ዝግ ነበር፡፡ እስልምና በአረብ አካባቢ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም የዓለም ጥግ አብላጫውን ይዞታ በተቀናጀበት ግዛት ሁሉ ‘የእኔ ብቻ’ አምባገነንነትን አብዝቶ ይተገብረዋል፡፡ የሮማ ካቶሊክ በግዛቷ ሌላውን የምትሰማበት ጊዜ አልነበራትም፡፡ ሌላው ቀርቶ በኃይማኖቶች ታሪክ ቅርብ ክስተት የሆነው ፕሮቴስታንቲዝም እንኳ በመካከለኛው ዘመን በርካታ ተከታዮች ባፈራባቸው የአውሮፓ ግዛቶች እንዳቅሙ ጉንተላና ማስፈራሪያ ይፈጽም ነበር፡፡ በዕውቀቱ ከታሪክ መዘዝኩ ብሎ ነው የኢትዮጵያን ክርስትና ከመጭራቅ የሚከሰው፡፡ ባለንበት ዘመን እስልምና ሳዑዲ ውስጥ ክርስትና እንዲገባ አይፈቅድም ብዬ የሞኝ መከራከሪያ አላቀርብም፤ ይልቁንም ኢትዮጵያ ውስጥ እስልምና በብዛት በሰፈነባቸው ግዛቶች ውስጥ በክርስቲያኑ ማኅበረሰብ ላይ ግፍ አልፈጸመም? ካቶሊኮች በመካከለኛው ዘመን በነፔድሮ ፓኤዝ፣ አልፎንሱ ሜንዴዝና ቤርሙዴዝ ጊዜ በተለይ ሱስንዮስን ከቀየሩ በኋላ ከጉንተላና ስራ ማስፈታት አልፈው ወደ16 ሺህ ገደማ የላስታና ጎንደር ንጹሃን ሰዎች መገደል ምክንያት አልነበሩም? ፕሮቴስታንቲዝም ዛሬ የኢትዮጵያን ክርስትና “ድንጋይ ከመሳም” ጋር አመሳስሎ አይወርፍም? የቅዱሳንን ገድል “ገደል” ብሎ መጽሐፍ አይጽፍም? ከዚህ የበለጠ የሌላውን ባህልና እምነት ያለማክበር ምን አለ? ፍትሃዊ ይሁን’ጂ እይታችን ጎበዝ! ገና ለገና ‘እኔን’ ባይ የለም ብሎ ምሳር ማብዛት ምንድነው?፡፡ ይህን የምለው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ሆኜ አሊያም የቤተ ክርስቲያኗ አባላትም መሰል ድርጊቶችን አይፈጽሙም ከሚል ጭፍንነት ላይ ቆሜም አይደለም፡፡ እንደየድክመቱ ሁሉም ይነቀፍ ዘንድ የተገባ ነው፡፡ ለአብሮነታችን የሚበጀውም እርሱ ነውና፡፡ ነገር ግን ልጅ በውቀቱ ሌላ ሌላውን አይዳስስም፣ አዚችኛዋ ላይ ግን ሳይበላው ያካል፡፡ ፍርደ-ገምድል ሆነብኝ፡፡ ሌላው ሌላውን ሁሉ እንተወውና እስልምና አሁን ላለው ተክለ ቁመና ለመብቃቱ ያኔ በተጀመረበት ዘመን የመጀመሪያዎቹ አማኞች ሲሰደዱ፣ አሳዳጆቹን አሳፍሮ መልሶ ተከታዮቹን ያስጠለላቸው እኮ በፍጹም ክርስቲያናዊ ባህልና እምነት የበለጸገው ንጉሥና ሕዝብ ነው፡፡ ይህን ይህንም መጥቀስ ይገባው ነበር፡፡ በቅርበት የሚያውቀውን ባህልና ቤተ እምነት በ“አወቅሁሽ ናቅሁሽ” ስልት ለርካሽ መስዋዕትነት ማቅረብ አጉራ-ዘለልነት ነው፡፡

በሌላ ጎኑ በጽሑፉ ውስጥ ለሥነ ጽሑፋዊ ውበት ሆን ተብሎ የተደረገ ማፈንገጥ በማይባል መልኩ እንደ “ምሽት” እና “ቢስማር” አይነት ቀበልኛ ቃላት መጽሐፉ ውስጥ ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

እንደመውጫ፡- ስለዳግማዊ አጼ ምኒልክና የዘመቻው ትርክት የተከራከረበት መንገድና ቀረበው በፍጹም ማስረጃ የታሸ እውነነታ፣ ፍትሃዊነትና ምክንያታዊነት በእውነት የደራሲውን ከፍታ አሁንም የመሰከረ ነው፡፡ በማር ስለተለወሰው አደገኛ መርዝ፣ ጸረ-ኢትዮጵያዊው ተስፋዬ ገ/አብን ተንኮሎችና ውሸቶች ፉርሽ ያደረገበት መንገድ እጅግ ግሩም ነው፡፡ እንዲሁም ሌሎች ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ቧልታይ (Satiric) ወጎቹ በበጎ ጎን የሚነሱ ናቸው፡፡ በ“ከአሜን ባሻገር” ላይ የብዕሩን ከፍታ ማዬት ችለናል፤ ነገር ግን በእስከአሁን ቀይታው (ማለትም “መግባትና መውጣትን” ከጻፈ በኋላ ባገኘው የእፎይታ ጊዜ)፣ ካለው የሥነ-ጽሑፍ ተሰጥኦ፣ በነ“እንቅልፍ እና ዕድሜ” ካሳየን አቅም አንጻር ስንመዝነው ግን ከዚህ የተሸለ ነገር ይዞልን ሊመጣም በተገባው ነበር፡፡

 

The post በዕውቀቱ የተቀመጠበት ሸፋፋ ሚዛን (ዳዊት ግርማ) appeared first on Zehabesha Amharic.


“የኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር በቀጥታ ከግብጽ ነው የመጣው።” –ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ – SBS Radio

ኦሮሞዎቹ፣አማሮቹ፣ትግሬዎቹ ወዘተ መባባል እስካለ ድረስ ነጻነት የለም! (ሰርጸ ደስታ)

$
0
0

ይህ የእኔ የግል እምነቴ ነው ብል ይሻለኛል፡፡ ምክነያቱም ብዙ ነጻ ነን የሚሉ ሰዎች እንኳን ምንም ሳይከብዳቸው ኦሮሞዎች፣ አማሮች፣ ትግሬዎች ወዘተ ሲሉ እሰማለሁ፡፡ ልብ በሏቸው ቃላቶቹ ምንን እንደሚያመለክቱ፡፡ ኦሮሞዎቹ ወይም አማሮቹ ወይም ሌላ ሲል አንድ ሰው ለእኔ እኔ የለሁበትም እያለ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ በኋላ አንድነት የለም፡፡ አንድነት ቢባልም ለይስሙላ ነው የሚመስለኝ፡፡ እንዲህ ያለ አነጋገር ደግሞ ሕዝብ እያደነቃቸው ካሉ የፖለቲካ መሪዎችም ሲወጣ ይደመጣል፡፡ ለእኔ በጣም የሚሻክሩ ቃላቶች ናቸው፡፡ ብዙ ሰው የማያሰተውለው ነገር ማንነቱን እንኳን ጠንቅቆ ሳያውቅ ራሱን የሆነ ብሔረሰብ አባል አድርጎ ሌላውን እንትናዎቹ ማለትን ይጀምራል፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ደግሞ አክራሪ ኦሮሞ ነኝ የሚለው ጎጃሜ ሆኖ ሊገኝ ይችላል አክራሪ አማራ ነኝ የሚለው በተቃራኒው ሜጫ ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙዎች ራሳችንን መርመመርመር ስንጀምር ታሪካችን የሚያበቃው እንደዛ ነው፡፡ አንድ ደብረማርቆስ ተወልዶ ያደገ የገዛ ጓደኛዬ ቅልጥ ያለው ጎጃሜ ሆኖ ራሱን አማራ አደርጓል፡፡ የሚገርመው ግን የቤተሰቡን የዘር ሀረግ ከጉደር አካባቢ ከሚኖሩ ኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ እንደሆነ ያውቃል፡፡ አክራሪ አማራ ነገር ስለነበር ምን ሆነህ ነው ታዲያ እንደዚህ አክራሪ አማራ ነገር የምትሆነው ስለው በራሱ ተገርሞ የሰጠኝ መልስ እውነት ምን ሆኜ ነው የምል ነበር፡፡ እሱስ ስለሚያውቀው እውነት ምን ሆኜ ነው አለ፡፡ ሌሎች ደግሞ ከእነ አካቴው ራሳቸውን ጠንቅቀው ሳያውቁ ዋና የሆነ ብሔረሰብ አሳቢና ተቆርቋሪ ሆነው ይገኛሉ፡፡

ብዙ ጊዜ እኔ ኦሮምኛ ተናጋሪ፣ አማራ የሚባለው ምናምን እያልኩ የምጽፈው ወድጄ አደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከቋንቋና እራስን የሆነ ብሔር አድርጎ ከማሳመን ያለፈ በቂ መረጃ ኖሮት በእርግጠኝነት እኔ የዚህ ብሔረሰብ አባል ነኝ ሊል የሚችል ሰው ካለ አንድ ከመቶ አይሆንም፡፡ ሁሉም ብቻ በስሜትና በወከባ ራሱን የሆነ ጎሳ አባል አድርጓል፡፡ ይህ ደግሞ ከ25 ዓመት ወዲህ አደገኛ ልክፍት ሆኗል፡፡ በእርግጠኝነት የምናውቀው ግን አንድ ዘር ሀረግ ያለው አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ ምናምን የሚባል ሕዝብ እንደሌለ ነው፡፡ ኦሮሞ የሚባለውን ሕዝብ ባለፈው አንስቼ ነበር፡፡ በጠቂቱ ለማስታወስ ላንሳ፡፡ ዛሬ የኦሮምኛ ተናጋሪ ሕዝብ የሆነው የተለያየ ዘር ሀረግ ያለውና የኦሮሞ እንቅስቃሴ ከሚባለው ከዛሬ 450ዓመት በኋላ ብዙ የተልያዩ ሕዝቦች ወደ ኦሮምኛ ተናጋሪነት በመቀየራቸው የተፈጠረ ሕዝብ ነው፡፡ ለዚህ በዝዋይ ሀይቅ የሚኖረው የዜይ ሕዝብ በኦሮምኛ ተናጋሪዎች ተጽኖ ብዙም ስላልነበረበት ለምልክት ይሆነን ዘንድ ዛሬም ድረስ እንዳለ እናሰተውል፡፡ ከ450 ዓመት በፊት ዛሬ ኦሮምኛ በሚነገርባቸው አካባቢዎች ሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ነበር፡፡ አማራን ስናይ ብዙ ቦታዎች በተለይ በሰሜን አማርኛ የመሳፍንት ቋንቋ ስለነበር ብዙ ሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች አማርኛ ተናጋሪ ሆነው ዛሬ አማራ በሚል ተጨፍለቀዋል፡፡ ዛሬ ጎንደር አካባቢ ቅማንት ነን የሚሉት ሕዝቦችም የዚሁ አንዱ መገለጫ ናቸው፡፡ እኛ እንኳን ስናውቅ ወይጦ የሚባል ሕዝብ በጎጃም ይኖር ነበር፡፡ አሁን ያ ሕዝብ ፍጹም ተቀይሮ አማራ ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ የታሪክ ባለቤት የሆነው አገው ሳይቀር አፋፍ ላይ ነው ያለው፡፡ ትግርኛንም ስናይ ወልቃይቶች ትግርኛ ተናጋሪ እንጂ በዘር ከተከዜ ማዶ ካሉት አይገናኙም፡፡ አላማጣ ቆቦ ራያ ድሮ ኦሮምኛ ተናጋሪ እንደነበሩ ይነገራል፡፡ ዛሬም ለምልክት አለ፡፡ ወሎ የጁ፣ ቦረና ኦሮምኛ ተናጋሪ ነበር ዛሬ አማራ ነው፡፡ እነዚህን ሶስት ብሔረሰቦች ለምሳሌ ነው ያነሳሁት፡፡ ሌላውም እንደዛው ነው፡፡

ዘር ከተባለ ኢትዮጵያ ከጥንትም ጀምሮ ሰዎች ተደበላልቀው የሚኖሩባት፣ የሚዋለዱባት፣ አበሻ (ሐበሻ) ተብለው በአንድነት የሚጠሩባት ሕዝቦች አገር ነች፡፡ ዛሬም ቢሆን ይህ የጋብቻና የዘር ቅልቅሉ እንኳንስ ቋንቋን እምነትን (ሀይማኖትን) እንኳን ጥሶ አንዱ ከሌላው ሲጋባና ሲዋለድ ሌላ ትውልድ ሲፈጥር እናያለን፡፡ ለዚህ ማስተዋል ዝግ የሆንን እኛ ዛሬ ራሳችንን መነዘርንና ማንነታችንንም፣ ነጻነታችንንም የጠላቶቻችን መገልገያ አደርገን ሰጠን፡፡ ያሳዝናል፡፡ ኢትዮጵያ የአለም ሕዝቦች ሁሉ ዘር ሀረግ ያለባት አገር እንደሆነች ዛሬ ሳይንስ ሳይቀር እየመሰከረ ነው፡፡ በቅርቡ ታዋቂው ሳይንስ የተባለው የሳይንስ ምርምር የሚቀርብበት መጽሔት ይሄንኑ ነው የሚያረጋግጠው፡፡ በተመሳሳይ ሌላ ተናጥል እትም የሳይንስዊ መጽሔት ጥንታውያኑ ግብጾች ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ይመሰክራል፡፡ ዓለም በሰው ዘር ዝርያ ሀረግ ምርምር ኢትዮጵያ ውስጥ ይርመሰመሳል፡፡ የእኛ ሳይንቲስት ተብዬዎች በጎሳ ልክፍት መክነው ስልቀበሌ ያወራሉ፡፡ http://science.sciencemag.org/content/350/6262/820   እንድታነቡት ከምጋብዛችሁ አንዱ ነው፡፡ ብዙ ነው፡፡ የሐበሻ ምድር የሚባለው በእርግጥ የዛሬዋን ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ሱዳንን፣ ኤርትራን፣ ሶማሌን፣ የመንን የሚጨምር ነው፡፡ አስኳሏ ግን ኢትዮጵያ ነች፡፡ እውነታው ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ብቻ ሳይሆኑ በእነዚህ አገራት ሁሉ የሚኖሩ የዘር ሀረግ መጠላልፍ አለ፡፡ በቋንቋ የሚለያዩ በድንበር የሚዋሰኑ የኢትዮጵያ ዛሬ ብሔረሰብ የምንላቸው ሕዝቦች የዘር ቅርርብ ከምናስበው በላይ ነው፡፡ እውነትን መናገር ግድ ስለሆነብኝ እንጂ አንድነት የሚባለውን ለመስበክ አይደለም፡፡ አሁን አሁን እንደውም ተለያይትን ብንሞክረው እያልኩ ነኝ፡፡ ለምሳሌ ኦሮምኛ ተናጋሪው ከኢትዮጵያ ውጭ ለዓመት አብሮ መኖር የማይችል ዘጠኝ ትንንሽ የሚሆን ሕዝብ ነው፡፡ አይደለም ባሌና ወለጋ ሐረቶና ሻመቡ ተለያይተው ነው የምናገኛቸው፡፡ አማራም እንደዛው፣ ትግሬም ተብዬው እንደዛው፡፡ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያዊነት እንጂ አንድ የሆኑት በብሔረሰብ እንዳልሆነ መጀመሪያ እንወቅ፡፡ ማስተዋል የጎደለው ትውልድ ሆነናል፡፡ አስናለሁ! ለእኛ ዛሬ ላለንው ትውልድ የሚከተለውን ግጥም ጋብዣችኋለሁ፡፡

የነጠፈው የኢትዮጵያ ማህጸን!?

ሀ ብሎ ሲጀምር ጥበብን የጠራ፣

አክሱም ላሊበላን በእጆቹ የሠራ፣

ያንን ምጡቅ ትውልድ ሲያፈራ የኖረ፣

ወላድን በድባብ ከድኖ ያከበረ፣

ምን ሆኖ ደረቀ/ነጠፈ ያ ለምለም ማህፀን፣

ምክነያቱ ጠፋኝ ግራ ገባኝ እኔን፡፡

በእግዚአብሔር አምላክ ፊት ሲቦርቅ አይተሽው፣

ምን አልባት ዳዊትን በልብሽ ንቀሽው፣

የሳዖል ልጅ ሜልኮል የደረሳት ዕጣ፣

ያ የእግዚአብሔር በትር ያ የእግዚአብሔር ቁጣ፣

ዘላለም እንዳትወልጅ ዳግም በአንቺ መጣ?

ነገሩን ሳስበው የአንቺ ከእሷ ባሰ፣

መዘጋት መድረቁ ደግሞ ባላነሰ፣

አራሙቻ አብቅሎ አገር አረከሰ፡፡

ምንኛ ቢከፋ ታዲያ የአንቺ ኃጥያት፣

እንዳልተባለልሽ የጠቢባን እናት፣

ያ ለም ማህጸንሽ የተዘመረለት፣

መንጠፉ ሳያንሰው አረም በቀለበት!?

ኃጥያትሽ በዝቶ እንደሁ ተስፋ ሳትቆርጪ፣

አጥቦ ያፀዳሽ ዘንድ እምባሽን አመንጪ፣

በአፍኝሽ ሙይና እርጪው ወደ ሰማይ፣

መስዋዕት ይሁንሽ በአምላክሽ ፊት ይታይ፡፡

በፀፀትሽ ብዛት አስቦ ታሪክሽን፣

ዳግም እንድከፍተው ለምለም ማህፀንሽን፡፡

ስቃይዋ ቢበዛ ብታጣ ልጆቿን፣

መጽናናት ቢሳናት ልቧ ገብቶ ሐዘን፣

ስቅስቅ ብላ አልቅሳ አውጥታ የአንጀቷን፣

ብሶቷን አሳፍራ ብትልክ አምባዋን፣

እግዚአብሔር ስለእሷ ሕዝቡን መመልከቱን፣

ያቺን የሐዘን እናት አስቢ ራሄልን!!!

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ! አሜን!

comment_stage_5

The post ኦሮሞዎቹ፣አማሮቹ፣ትግሬዎቹ ወዘተ መባባል እስካለ ድረስ ነጻነት የለም! (ሰርጸ ደስታ) appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: ኦነግ ትግሉ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል ሌሎችም የነጻነቱን ትግል ይቀላቀሉ ሲል ጥሪውን በድጋሚ አቀረበ |የአዲስ አበባ ጉዳይ በሕዝቡ ወደፊት የሚወሰን ይሆናል |ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገው የጥናት ውጤት አይገዛኝም ማለቱዋ ተዘገበ |የሕወሓት ወታደራዊና የደህነት ባለስልጣናት በኦሮሚያ ያለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማፈን ተጨማሪ ወታደሮች ተሰማርተው አፈናው እንዲቀጥል ወሰኑ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የካቲት 13 ቀን 2008 ፕሮግራም

<...> አቶ ኦዳ ጣሴ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) በውጭ የድርጅትና የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

ታሪክ ተራኪው ኤድዋርዶ ባይኖሮ የየካቲት 12 ሰማእታት አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

የጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ የአክብሮት ምሽት በቬጋስ መካሄድን አስመልክቶ ከአዘጋጆቹ አንዱ ጋር ቆይታ

የኔቫዳ የዲሞክራቲክ ካከስ ምርቻ የሂላር አሸናፊነትና የሴናተር በርኒ ሳንደርስ መራጮች ( አጭር ቆይታ ከመራጮች ጋር )

የዓለማችን የኢኮኖሚ እስትንፋስ እና የራስ ምታት የሆነው የነዳጅ ምርት አቅርቦት እና የአምራች አገሮች ስጋቶች ከመጪው እቅዳቸው ጋር ሲቃኝ(ልዩ ወቅታዊ ዳሰሳ)

የአሜሪካ በጥቅሟ ላይ የተመሰረተው የውጭ ፖሊሲ እና ከአፍሪካውያን አምባገነኖች ጋር ቀን እስኪጎድልባቸው የምትፈጥረው ወዳጅነት በቆዩት ዲፕሎማቶቿ ሪፖርት ውስጥ ሲፈተሽ(ልዩ ዘገባ-ሁለተኛ ክፍል)

ዜናዎቻችን

ኦነግ ትግሉ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል ሌሎችም የነጻነቱን ትግል ይቀላቀሉ ሲል ጥሪውን በድጋሚ አቀረበ

የአዲስ አበባ ጉዳይ በሕዝቡ ወደፊት የሚወሰን ይሆናል

ወያኔ ቢወድቅ አገሪቱ ትበታተናለች የሚለው የስርዓቱ ቅዠት መሆኑን ገለጸ

በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሃብ ለመቋቋም የገንዘብና የሎጀስቲክ ችግሮች መከሰታቸው ስጋት ፈጠረ

ኬኒያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያወዛግባትን ቁልፍ በማዕድን የበለጸገ መሬት በድርድር ለመውሰድ ዘመቻ ጀመረች

ዶ/ር መረራ ጊዲና የሚመሩት ኦፌኮ ቢሮ በወታደሮች ቁጥጥር ስር ወደቀ በስፍራው የነበሩ ተደብድበው ታሰሩ

ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገው የጥናት ውጤት አይገዛኝም ማለቱዋ ተዘገበ

የሕወሓት ወታደራዊና የደህነት ባለስልጣናት በኦሮሚያ ያለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማፈን ተጨማሪ ወታደሮች ተሰማርተው አፈናው እንዲቀጥል ወሰኑ

የተቃውሞው አመራሮች ጊዜው ሲደርስ ራሳቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ተገለጸ

የህቡው መሪዎች የስትራቴጂ ለውጥ ያደርጋሉ ተብሎ ተጠብቋል

የኤርትራ ጦር ሃይል የደምብ ልብስን የለበሱ ታጣቂዎች በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ላይ ከ80 በላይ ወጣት ኢትዮጵአውያንን አፍነው ወሰዱ

ስለ ጉዳዩ የአዲስ አበባም ሆነ የአስመራ ባለስልጣናት ያሉት የለም

ሒላሪ ክሊንተን በኔቫዳ ከዲሞክራት መራጮች የበለጠ ድጋፍ አግኝተው በርኒ ሳንደርስን አሸነፉ

የኡጋንዳውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዩዌሪ ሙሲቪኒ አሸነፉ መባሉ በአገሪቱ ውጥረት አነገሰ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: ኦነግ ትግሉ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል ሌሎችም የነጻነቱን ትግል ይቀላቀሉ ሲል ጥሪውን በድጋሚ አቀረበ | የአዲስ አበባ ጉዳይ በሕዝቡ ወደፊት የሚወሰን ይሆናል | ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገው የጥናት ውጤት አይገዛኝም ማለቱዋ ተዘገበ | የሕወሓት ወታደራዊና የደህነት ባለስልጣናት በኦሮሚያ ያለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማፈን ተጨማሪ ወታደሮች ተሰማርተው አፈናው እንዲቀጥል ወሰኑ appeared first on Zehabesha Amharic.

አሜሪካ ለትምህርት የመጡ ሁለት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በሰካራም ሹፌር ተገጭተው ሕይወታቸው አለፈ

$
0
0

Manchester Un
(ዘ-ሐበሻ) በኢንዲያና ግዛት በማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ የሚማሩት 2 ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በመኪና አደጋ ሕይወታቸው አለፈ:: አብራቸው የነበረችው ናይጄሪያዊትም እንዲሁ በመኪናው አደጋ ሕይወቷ ጠፍቷል::

በኢንዲያና 69ኛው መንገድ ላይ አንድ ሰክሮ የሚያሽከረክር የነበረው ግለሰብ እነዚሁ ኢትዮጵያውያኑ የነበሩበትን መኪና በመምታቱ ሌሎች ወጣቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል::

እንደ ከተማው ቴሌቭዥን ዘገባ ከሆነ ብሩክ ዳኘው እና ኪሩቤል ዓለማየሁ ሃይሉ የነበሩበት መኪና መንገዱ ዳር ላይ ጎማ ተንፍሶበት ቆሞ ነበር:: በዚህም ወቅት ይኸው ሰካራም ሹፌር መጥቶ መኪናቸውን በመግጨቱ ሕይወታቸው ሊያልፍ ችሏል:: ከነዚህ 3 ወጣት ተማሪዎች በተጨማሪ እስራኤል ሰለሞን የተባለው ኢትዮጵያዊም በአደጋው ጉዳት ደርሶበት ህክምና ላይ ይገኛል:: የካውንቲው ፖሊስ በሰጠው አስተያየትም ይህ ወጣት በጣም በመጎዳቱ ቀዶ ህክምና ሳያስፈልገው አይቀርም::

ሰካራሙ ሹፌር እነዚህን ከኢትዮጵያ ለትምህርት የመጡትን ኢትዮጵያውያን እና አንዲት ናይጄራዊትን ሕይወት ካጠፋ ራሱ ላይም የደረሰበትን መጠነኛ ጉዳት ከታከመ በኋላ ወደ እስር ቤት ተልኳል::

የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ ለነዚህ ሟች ተማሪዎች መታሰቢያ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀ መሆኑን በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል:: 2ቱ ሟች ተማሪዎች በአዲስ አበባ ሴንት ጆሴፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነበሩ::

The post አሜሪካ ለትምህርት የመጡ ሁለት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በሰካራም ሹፌር ተገጭተው ሕይወታቸው አለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

መንግስት ከብሄራዊ ባንክ ተበድሮ ያልመለሰው ገንዘብ 92 ቢሊዮን ብር ድርሷል ተባለ

$
0
0

TPLF Police Found Millions of Birr, Dollars and Euros in Ato Gebrewahid Wolde Giorgis Houseኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2008)  አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለመንግስት የሚሰጠውን ቀጥተኛ ብድር እንዲያቆም ቢያሳስቡም ባንኩ ለመንግስት እያበደረ ያለው ገንዘብ በመጨመር ላይ መሆኑ ተገለጠ።
ባንኩ ለፌዴራል በጀት መሸፈኛ ካበደረው ገንዘብ ውስጥ ያልተመለሰለት ገንዘብ ከ92 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች በበኩላቸው የመንግስት ብድር እየጨመረ መሄድ ለሃገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ማደግ አስተዋጽዖ ማድረጉን በመገለጽ ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑን አስረድተዋል።
የብሄራዊ ባንክ ለመንግስት አበድሮ ካለተመለሰለት 92.1 ቢሊዮን ብር ውስጥም 9.7 በመቶ የሚሆነው በቦንድ ተበድሮ ያልተመለሰ መሆኑም ታውቋል።
የአለም አቀፍ ሞኒተሪ ፈንድ (አይ ኤም ኤፍ) እና የተለያዩ አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የኢትዮጵያ መንግስት ከብሄራዊ ባንክ በሚበደረው ገንዘብ ላይ ማስተካከያን እንዲያደር ሲያሳስቡ መቆየታቸው ይታወሳል።
ይሁንና መንግስት ከብሄራዊ ባንክ የሚወስደው ብድር እየጨመረ በመምጣቱና ያልተከፈለ ብድርም በመኖሩ ምክንያት የዋጋ ግሽበቱ እያደገ መምጣቱን የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ገልጸዋል።
የተያዘው ወር የአሃገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 10.2 በመቶ የደረሰ ሲሆን፣ ቁጥሩ እድገትን እያሳየ ሊሄድ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።
በተመሳሳይ ሁኔታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያበደረው ገንዘብ 23.3 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ቁጥሩም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ15.3 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተገልጿል።

The post መንግስት ከብሄራዊ ባንክ ተበድሮ ያልመለሰው ገንዘብ 92 ቢሊዮን ብር ድርሷል ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.

ገራፊዬን አየኹት ፡ (አቤል ዋበላ)

$
0
0

ገራፊዬን አየኹት ፡ (አቤል ዋበላ)
.

ጦማሪ አቤል ዋበላ

ጦማሪ አቤል ዋበላ

ቀልድ ያለፈበት ጨዋታ ሆኗል፡፡ አሁን ዘውጉ ተቀይሯል፡፡ ፍጥጥ ግጥጥ ያለ ዕውናዊ ድርሰትን መመልከት ይዘናል፡፡አይን አያየው የለም፡፡ አሁን ደግሞ ገራፊዬን አሳየኝ፡፡ በኮምፒዩተር የኤሌክትሪክ ገመድ ጀርባዬ እስኪቀደድ የገረፈኝን፣ በመጥረጊያ እንጨት ውስጥ እግሬን ያነደደኝን፣ እጄ በካቴና ታስሮ ወለል ላይ ያንከባለለኝን፣ ጨለማ ቤት ውስጥ አስገብቶ ከየት እንደመጣ በማላውቀው ጅራፍ አሳሬን ያበላኝን፣ እናቴን ከመቃብር ጠርቼ “አንቺ እናቴ ለምን ጥሩ ሁን ብለሽ አሳደግሽኝ? ብዙ ክፉ ሰዎች እንዳሉ ለምን አልመከርሽኝም?” ብዬ እንድወቅሳት ያደረገኝን፣ ወንድ፣ የወንዶች ቁና በካቴና የታሰረን ሰው በዕኩለ ሌሊት ጠርቶ አፉ ውስጥ ጨርቅ ወትፎ የሚደበድብ በአይኔ በብረቱ አየኹት፡፡

ዮናታን ተስፋዬ ለጊዜያዊ ቀነ ቀጠሮ አራዳ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ሰምቼ ነው ወደዚያ የሄድኩት፡፡ ይህችን የተለመደች ሰርከስ ሁሉም የፖለቲካ እስረኛ ይወዛወዛታል፡፡በማዕከላዊ ይጀመራል ከዚያ አራዳ ፍርድ ቤት ይቀጥላል፡፡ የማዕከላዊ ደብዳቢዎች በጨለማ የሚያሰቃዩትን እስረኛ በቀን ሰው መስለው (ወገኞች ናቸው አንዳንዴማ ዩኒፎርምም ያጠልቃሉ) ፍርድ ቤት ያቀርቡታል፡፡ ውሸት ውሸቱን ይቀባጥራሉ፡፡ “ግበረ አበሮቹን በኢንተርፖል እያሳደድን ነው፣ ክቡር ዳኛ በዋስ ከተለለቀቁ ልማታችንን ያደናቅፋሉ፡፡ ወህኒ ሰብረው እስረኛ ያስፈታሉ” የመሳሰሉትን በጠራራ ጸሐይ ይቀባጥራሉ፡፡ እየቀለድኩኝ አይደልም የምሬን ነው እንዲህ አይነት በሬ ወለደ ምክንያት በጆሮዬ ሰምቻለው፡፡ ዳኛውም አብሮ ይተውናል፡፡ የፈለጉትን ቀን ያህል ያራዝማል፡፡

ገራፊዬንም ያየሁት እኔንና ጓደኞቼን እንደነዳው እንዲሁ ተረኛውን ገፈት ቀማሽ ሲያመጣ ነው፡፡ ላንዳፍታ አይኖቻችን ተጋጩ፡፡ አስተውሎኝ ይሁን አይሁን አላውቅም በፍርድ ቤቱ ቢሮዎች መሐል ገብቶ ተሰወረ፡፡ እኔ ግን በእርግጠኝነት ለይቸዋለው፡፡ ውስጤ ዳግም ተቆጣ፡፡ እስር ቤት ብቻዬን ደጋግሜ ባሰብኩት ቁጥር እንደአዲስ የልቤ ቁስል ያመረቅዝ ነበር፡፡ ቂም ስቋጥር እና ስፈታ ከአመት በላይ ቆይቻለው፡፡ ቂም ይዣለው በውድም ሆነ በግድ ኢትዮጵያዊ በሆነ ሁሉ ላይ ቂም ይዣለው፡፡ እንዴት ሰው በሀገሩ ይህንን ጉድ ተሸክሞ ይኖራል? እንዴት እንደዚህ አይነት ተቋም በመዲናይቱ እምብርት ላይ አስቀምጦ ዝም ይላል? ይህን ባርቤሪዝም ጌጡ ካደረገ ማኀበረሰብ ጋር በቀላሉ የማይበርድ ግጭት ውስጥ ነኝ፡፡ ስለዚህ በመንገድ ስታገኙኝ ፊቴ ጥቁር ብሎ ብታገኙኝ “ምን ሆነህ ነው?” አትበሉኝ፡፡ ቂም ይዤ ነው፡፡ ተራ ማኩረፍ አድርጋችኹ አትውሰዱት ስር የሰደደ ከነፍስ የሚቀዳ ጸብ ነው፡፡

በግርፋት የተሰነጠቀውን ጀርባዬ በቅባት ላሹኝ ዕድሜ ለእነ ኤባ ቁስሉ እዛው ማዕከላዊ ነው የዳነው፡፡ የልቤ ስንጥቅ ግን አልዳነም ፡፡ ያ ዘላለም ክብረት “ምድር ብዙ ክፋት የሚፈጸምባት ቦታ ናት በእኛ ላይ የደረሰውም አዲስ ነገር አይደለም” እያለ ብዙ እንዳላዝን ቢመክረኝም ያቄመው ልቤን ሊያሸንፈው አልቻለም ነበር፡፡ የተገኘሁበት፣ ያሳደገኝ ማኀበረሰብ ላይ እንዳቄምኩኝ ከእስር ወጣኹኝ፡፡ ባለፉት አራት ወራት በአንጻራዊ ነጻነት ማሳለፌ ግን ትንሽ እንዳዘናጋኝ የገባኝ ግን በቀደም ገራፊዬን ያየኹት ቀን ነው፡፡ወይ ጊዜ ስንቱን ያስረሳል አልኩኝ፡፡ አሁን ከእስር መፈታት ብርቅ የሆነበት ጊዜ አልፏል፡፡ ቁስሌ ዳግም አመርቅዟል፡፡ ገራፊዬን እና አለቆቹን የያዘው ህንጻ ካልፈረሰ አልያም ሙዚየም ካልሆነ ዕርቅ የማይታሰብ ነው፡፡ ድሮ እስር ቤት ሳለኹኝ በእስረኛ ማጓጓዣ መኪና ወደ ፍርድ ቤት ስንመላለስ በመስኮት ስመለከተው የዕለት ጉርሱን ለማብሰል የሚራኮተው አዳሜ አሁንም ውስጡ ሁኜ ስመለከተው ከሆዱ በቀር የኔ ቁስል ግድ የሰጠው አይመስልም፡፡ ስለዚህ ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ ብዬ ይቅር እላለው? ውስጤ የበለጠ ስለሻከረ እምቢኝ ብያለው፡፡ ይህ የአንዲት ነጠላ ነፍስ መብት ነው፡፡ በገዛ ነፍሴ ጥላቻን ማርገዝ መብቴ ነው፡፡ ከፈለጋችኹ ለዐቃቤ ሕግ ንገሩትና በፊት ‘የማኀበረሰቡን ጤና እና ደህንነት ለአደጋ በማጋለጥ’ እንደ ከሰሰኝ አሁን ደግም ‘በማኀበረሰቡ ላይ ስር የሰደደ ጥላቻና ቂም በመቋጠር’ ይክሰሰኝ፡፡

እነ ኤቢሳ አካላዊ ቁስሌን እንደሳምራዊው ሰው በቅባት እንዳሹልኝ አሁን ደግሞ ዘመዶቻቸው የተሰበረ መንፈሴን የቆሰለ እኔነቴን ሊጥገኑ ተነስተዋል፡፡ የእነኤቢሳ፣ የእነቶፊቅ እና የእነ ቶላ ዘመዶች እኔን ከህመሜ ሊያድኑኝ ደማቸውን እየከፈሉ መሆናቸውን ድፍን ፌስቡክ እየተመለከተው ነው፡፡ አዲስ አበቤ “አገር ሊያፈርሱ ነው ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አትኖርም” ቅብርጥሴ ቅብርጥሴ ቢልም እኔ ግን ከሚፈርሰው አገር ከፒያሳ ከፍ ብሎ ያለው ማዕከላዊ ጎልቶ ይታየኛል፡፡ ስለዚህ በመሬት ላይ ዋጋ እየከፈሉ ያሉትን ወገኖቼን ይቅር ብያለው፡፡ ከነዚህ በቀር ሌላው ማኀበረሰብ “እርሱ” አይደለም “እኔ” ራሱ ይቅርታን አያገኛትም፡፡ አራዳ ፍርድ ቤት መሄዴ አይቀርም፡፡ በማዕከላዊ በርም አልፋለው፡፡ በየጊዜው እየሄደኩኝ ከገራፊዎቼ አንዱን እያየው ጥላቻዬን እያደስኩኝ እመጣለው፡፡ ቁስሉ ይበልጥ እንዲቆጠቁጠኝ ወደገራፊዬ ተጠግቼ አይኖቹን በአይኖቼ አድናለው፡፡ አይገርምም ግን ………….…ገራፊዬ እስካሁን እዚያው ነው፡፡

The post ገራፊዬን አየኹት ፡ (አቤል ዋበላ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ከአሜን ባሻገር በበዕውቀቱ ስዩም –ከዳንኤል አበራ (ኖርዌይ)

$
0
0
ከአሜን ባሻገር በ19 ምዕራፎች የተቀነበበች246 ገጽ የሆነች ተነባቢ መፅሃፍ ነች። የዞን ዘጠኙ በፍቃዱ እንደነገረን ከሆነ አብዛኛዎቹ ምእራፎች በመጽሄትም በጋዜጣም የወጡ ስለነበሩ አዲስ አይደሉም ብሏል። በመጽሄትና በጋዜጣ የሚወጡ መጣጥፎች ማጣቀሻ ዋቢ ስለማያክሉ ከጊዜ ብዛትም ጸሀፊውም ስለሚረሳቸው የይድረስ ይድረስ ነገር ሻጥ ሻጥ ይደረጋሉ። የበዕውቀቱ ከአሜን ባሻገር በዚህ ረገድ ጉልህ ጎደሎነት አሳይቷል። ከቤተ አማራ ፖለቲካ አቀንቃኞችንም ጋር እሰጥ አገባ ያስገባው ይሄ የመጽሃፉ ደካማ ጎን ለምንጭ ለዋቢ የሚሰጠው ግምትና ቦታ። በሁለተኛው እትም ይስተካከላሉ የሚል ግምት አለኝ።
bewketu
ስለ 19ኞቹ መጣጥፎች በዕውቀቱ በ13 ቃላት በሁለት አረፍተ ነገር ሲገልጽ “መጣጥፎቼ የእንጉርጉሮና የልግጫ ድብልቅ ናቸው። የሐሳብ አርአያዎቼ አንጎራጓሪ ሴቶች እንጂ ፕሮፌሽናል ፖለቲከኞች አይደሉም።”
ከአሜን ባሻገር ተስፋ መቁረጥና ንዴት ይታይበታል። ለዚህ ተስፋ መቁረጥና ንዴት የመፅሃፉ ጀርባ ጽሁፍ ጥሩ ገላጭ ይመስለኛል። ከአሜን ባሻገር በዚህ ስሜት ቢነበብ ለመረዳት አያስቸግርም።
በዕውቀቱ ሲጀምር እንዲህ ይላል። “የዘመኔ ጀግና እንዲህ የሚል ይመስለኛል”
“በኔ ዘመንና በጥንት አቴናውያን የቸነፈር ዘመን መካከል መሰረታዊ መመሳሰል አለ።
በሁለቱም ዘመኖች ውስጥ ለነገ ተስፋ ማድረግ የሚባል ነገር የለም።
ለፍቼ የሰራሁት ቤቴን ባቡር ይሁን ሰርጓጅ መርከብ በውል ያልታወቀ ነገር ጥሶት የሚያልፍ ከሆነ ቤት ለመስራት እንዴት ላቅድ እችላለሁ?
ሰባት መቶ ሺህ ብር የገዛሁትን ቤቴን በክረምት አፍርሶ ደርዘን ጃንጥላ የማይገዛ ፍራንክ ሸጎጥ አድርጎ፣ ቤተ መቅደስ እንደገባች ውሻ አካልቦ የሚያባርረኝ ባለስልጣን ባለበት ሀገር ውስጥ ጎጆ ለምን እቀልሳለሁ።
ጌቶች ለችግር ቀኔ ያጠራቀምኩትን ብር በጥጋብ ዘመናቸው የሚወርሱብኝ ከሆነ የባንክ ደብተር የማወጣው ለምንድነው?
ልጄ በሕይወት እያለሁ እጓለማውታ ሊሆን እንደሚችል እያወቅሁ፣ “የዛሬ ዓመት የማሙሽ ልደት” እያልሁ የምዘፍንበት ምክንያት ምንድነው?
“ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” ከሚለው መፈክር በስተቀር ኢትዮጵያን ለዘላለም የሚያኖራት መሰረት መፍረሱን እያወቅሁ ለሚቀጥለው አመት እንዴት ላቅድ እችላለሁ?
ተው ባክህ! እኔም እንደጥንቱ አቴናውያን የሞት ፍርድ እንደተፈረደበት ሰው እኖራለሁ። የመሰቀያው ገመድ አንገቴ ውስጥ እንደተፈረደበት ሰው እኖራለሁ። የመሰቀያው ገመድ አንገቴ ውሰጥ እስቲገባ ድረስ የጥንቱ ባላገር ግጥም በቃሌ እወጣለሁ።”
ይህን ይመስላል የበዕውቀቱ ስዩም ከአሜን ባሻገር የተጻፈበት መንፈስ። አብዛኞቹ የመፅሃፉ ምእራፋት ባንድም ሆነ በሌላው በኩል የኦሮሞዎችን ላገር ግንባታ ያደረጉት አስተዋፆ ተንታኝ ነው። የኦሮሞ ታሪክ ሲነሳ ምኒልክም መነሳታቸው ስለማይቀር አንድ ሁለት ምእራፍ ምኒልክም ተችሯቸዋል። ዳያስፖራውም አንድ ምዕራፍ ደርሶታል። የኦሮሞ ታሪክ ሲነሳ ራስ ጎበናም ስለተነሱ አንድ ማስተካከያና አንድ ሀሳብ ልጨምር።
1) “ይታመሳል አሉ ከፋና ቦረና
አማን አይደሉም ወይ እነ ራስ ጎበና” (ገፅ 70)
በዕውቀቱ ይህንን ግጥም አንተርሶ ጎበና አማን (ሰሜን ሸዋ) በተባለ ቦታ ተወልዷል ይለናል። የግጥሙ አማን ሚዛን ቴጲ የሚገኘው ሲሆን ጎበና ደቡብ ሄደው የጎበና መልክተኛ ድምፅ በመጥፋቱ የተገጠመ ነው።
2) በዕውቀቱ “የጎበናን ቅኝት” ምዕራፍ የጀመረው በዮፍታሄ ግጥም ነው
አጥንቱን ልልቀመው መቃብር ቆፍሬ
ጎበናን ተሸዋ፤ አሉላን ተትግሬ
አሉላን ለጥይት፤ ጎበናን ለጭሬ
አሉላ ሴት ልጁን፤ ጥይት ሲያስተኩስ
ጎበና ሴት ልጁን፤ ሲያስተምር ፈረስ
አገሬ ተባብራ፤ ካረገጠች እርካብ
ነገራችን ሁሉ፤ የእምቧይ ካብ የእምቧይ ካብ…
መነሳት የነበረበት ግን በዕውቀቱ ያላነሳው የጎበና ሴት ልጅ ማናት ነው (በዕውቀቱ ያነሳው የጎበናን ወንድ ልጅ ወዳጆን ስለሆነ) ግን ደግሞ በዕውቀቱ ላነሳው ትርክት አጋዥ እሷ ትሆነው ነበር። አስካለ ማርያም ትባላለች የራስ አበበ አረጋይ እናትም ነች። እንዲህም ተብሎላቸዋል።
“በለው በዱባይ በለው በዱባይ
የአስካለ ማርያም ልጅ አበበ አረጋይ”
በዕውቀቱ ስለ ውጫሌው ውል በሌላው ምዕራፉ ሲያትት ገብርኤል ጎበና የተባለ አስተርጓሚ እንደነበር ያትታል። በዚህ ትርክቱ ግራዝማች ዮሴፍ ሲካተቱ አፅመ ጊዮርጊስ ተዘለዋል። በሁለተኛው ከአሜን ባሻገር እትም የሶስቱን ሚና ይልይልናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
በዕውቀቱ ስለ ሀሰን አንጃሞ ሲፅፍ ሀሰን ወንጃቦ ብሎታል አስተካክላችሁ አንብቡለት።
በሌላው ገፅ (224) እንዲሁ የኦሮሞዎችን ላገር ግንባታ አስተዋፅኦ ሲያጎላ በስህተት የዳውሮውን ተወላጅ የኦሮሞ ተወላጅ ብሎታል።
እራሮት ቢበዛበትም ከአሜን ባሻገር ተነባቢ ፅሁፍ ነው። እንድታነቡት እጋብዛለሁ።
መልካም ንባብ

The post ከአሜን ባሻገር በበዕውቀቱ ስዩም – ከዳንኤል አበራ (ኖርዌይ) appeared first on Zehabesha Amharic.


Health: አጠቃላይ የጤና ምርመራ(ሜዲካል ቼክአፕ) መቼና ለምን እናድርግ? |‹‹ሴቶችም ወንዶችም ሊያውቁት የሚገባ የሜዲካል ቼክ አፕ ካሌንደር አለ››

$
0
0

medical-checkup

(ከዶክተሩ ጋር ቃለምልልስ)

‹‹ሴቶችም ወንዶችም ሊያውቁት የሚገባ የሜዲካል ቼክ አፕ ካሌንደር አለ›› የሚሉን የዛሬ እንግዳችን ናቸው፡፡

በሀገራችን ‹‹ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ›› እንደሚባለው፣ ከመታመም በፊት ተላላፊም ሆነ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ 4 ዋና ዋና መንገዶች አሉ፡፡ እነሱም፡-

– ክትባት

-መድሃኒት መውሰድ

– የባህሪ (የአኗኗር ዘይቤ) ለውጥ ማምጣትና

– በየጊዜው አጠቃላይ የጤና ምርመራ (ሜዲካል ቼካፕ) ማድረግ፤

እንደየሁኔታው እነዚህን ዘዴዎች በመጠቀም፣ በሽታዎች ሳይከሰቱ መከላከል ወይም ደግሞ ከተከሰቱም ስር ሳይሰዱ በፍጥነት መፍትሄ ማግኘት ይቻላል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን በሽታዎችን አስቀድሞ የመከላከል ዘዴዎች ወደፊት እንደ ሁኔታው በዝርዝር ለማየት እንሞክራለን፡፡ ለዛሬ ግን በየጊዜው አጠቃላይ የጤና ምርመራ (ሜዲካል ቼካፕ) ማድረግ ምንነቱን፣ የሚያስገኘውን ጥቅም፣ ለየትኞቹ በሽታዎች እነማን መቼ መመርመር እንደሚገባቸውና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ፣ የውስጥ ደዌ በሽታዎች ላይ ትኩረት ያደረጉትን የህክምና ዶክተር እንግዳችን በማድረግ አነጋግረንልዎታል፡፡

ጥያቄ፡- አጠቃላይ የጤና ምርመራ ሲባል ምን ማለት ነው?

ዶ/ር፡- ሰዎች ገና ከመታመማቸውና አልጋ ይዘው ከመተኛታቸው እና በዚህም ምክንያት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት፣ በሽታዎችን በመመርመር የተወሳሰበ የጤና ችግር ከመድረሱ አስቀድሞ ለማወቅ የሚደረግ ምርመራ ነው፡፡ በተጨማሪም የግለሰቡን ለተለያዩ በሽታዎች የተጋላጭነት ደረጃውን ለመለየት የሚያገለግል ምርመራ ማለት ነው፡፡

 

ጥያቄ፡- ከመታመም አስቀድሞ ቅድመ ምርመራ ማድረግ የሚያስገኘው ጠቀሜታ ምንድነው?

ዶ/ር፡- ሰዎች ከመታመማቸው አስቀድሞ የሚያደርጉት አጠቃላይ ምርመራ የሚሰጠው ጠቀሜታ በግለሰብና በሀገር ደረጃ የሚታይ ነው፡፡ ግለሰቦች ከመታመማቸው አስቀድሞ የጤና ሁኔታቸው በምን ደረጃ እንዳለ ማወቅ ይችላሉ፡፡ የጤና ችግር ካለ ህመሙ ስር ሳይሰድና የከፋ ጉዳት ሳያስከትል ተገቢውን ህክምና በማድረግ ፈጣን መፍትሄ ማግኘት የሚችሉበትን ዕድል ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም የአመጋገብና የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ በማድረግ ረጅም ዕድሜ መኖር ይችላሉ፡፡ እነዚህ ጥቅሞች የሚገኙት በአነስተኛ ወጭ መሆኑ ሲታይ ደግሞ አስቀድሞ በሚደረግ ምርመራ፣ የጤና ሁኔታን በየጊዜው መከተል ጠቀሜታው በምንም ሊተካ የማይችል መሆኑን በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የተሟላ ጤና፣ ጠንካራና በራሱ የሚተማመን ማህበረሰብ መፍጠር ያስችላል፡፡ በሌላ በኩል ጠቀሜታው ከሀገር አንፃር ሲታይ፣ ማህበረሰቡ አስቀድሞ የመመርመር ባህሉን ቢያዳብር፣ በቀላሉ ምርመራ ህመምተኛውን በመለየት በወቅቱ የማከም ዕድልን ስለሚፈጥር በጤና ተቋማት ላይ የሚታየውን የህክምና ፈላጊ ጫና ይቀንሳል፡፡ ህሙማን በሽታው ከተባባሰባቸው በኋላ በመምጣት ለከፍተኛ ወጭና እንግልት የመዳረጋቸው ጉዳይ ይቀንሳል፡፡ ሀገሪቱ በጤናው ዘርፍ አክሞ ለማዳን የምታወጣውን ወጭ ለመቀነስ ያግዛል፡፡

 

ጥያቄ፡- የግድ ቅድመ ምርመራ ሊደረግባቸው ከሚገቡ የጤና ችግሮች ዋና ዋና የሚባሉትን ቢገልፁልኝ?

ዶ/ር፡- ሰዎች ከመታመማቸው አስቀድሞ በየጊዜው ቅድመ ምርመራ ሊያደርጉባቸው የሚገቡ የጤና ችግሮች በርካታ ናቸው፡፡ ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ አንፃር የበለጠ ትኩረት የሚሹ በሽታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ የማህፀን፣ የጡት ካንሰር፣ የፊኛ፣ የዘር ፍሬ፣ የአንጀትና የጨጓራ ካንሰር፣ ስኳር፣ ደም ግፊት፣ ኮሌስትሮልና ኤች.አይ.ቪ፣ የልብና ከልብ ጋር ተያያዥነት ላላቸው ህመሞች ትኩረት ሰጥቶ ቅድመ ምርመራ ማድረግ ይገባል፡፡ ከእነዚህ የጤና ችግሮች በተጨማሪ ለዓይን፣ ለጥርስ፣ ለጆሮ፣ ለውፍረትና በደም ውስጥ የስብ መጠን መብዛትን ተከትሎ ለሚከሰቱ የጤና ችግሮች ምርመራ በማድረግ፣ የጤናችን ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በየጊዜው ክትትል ማድረግ ተገቢ ብቻ ሳይሆን ስልጣኔም ጭምር ነው፡፡ ለቅድመ ምርመራ ጉዳይ ሁሉም ሰው የተለየ ትኩረት እንዲሰጥ የሚያስገድዱ ሳይንሳዊ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ የሞት መጠን ለመቀነስ፣ የአካል ጉዳትን ለመከላከል፣ ደስታ ማጣትን ለማስቀረት፣ በምንም ነገር ላይ ያለመርካት ስሜትን ለመለወጥ፣ ምቾት አለመሰማት ካለ ችግሩን ለይቶ መፍትሄ ለመስጠት፣ ድህነትንና በማህበረሰብ ደረጃ የሚከሰቱ ጫናዎችን ለመቀነስ እንደዚሁም በሽታው ሳይባባስ ከተገኘ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ይረዳል፡፡

ጥያቄ፡- ከሌላው ዓለም በተለየ ሁኔታ፣ በቅድመ ምርመራ ወቅት በሀገራችን ትኩረት የሚሰጣቸው በሽታዎች አሉ?

ዶ/ር፡- ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በተመለከተ፣ በሀገራችን የሚደረገው ቅድመ ምርመራ ከየትኛውም ሀገር ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ነገር ግን በሀገራችን ተላላፊ ለሆኑ በሽታዎች ትኩረት ስለሚሰጥ በዚህ በኩል በሀገራችን የተለየ ሁኔታ አለ፡፡

ጥያቄ፡- ከቅድመ ምርመራ ባህል አንፃር፣ የዓለማቀፉና የሀገራችን ሁኔታ በምን ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው?

ዶ/ር፡- በዓለማቀፍ ደረጃ በተለይም በምዕራቡ ዓለም፣ ሁሉም ሰው የጤናውን ሁኔታ አስቀድሞ የመከታተል ባህሉ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካን ብንወስድ ለማህፀን፣ ለጡትና ለአንጀት ካንሰር የሚረገው ቅድመ ምርመራ ከ50 እስከ 70 በመቶ ደርሷል፡፡ በአገራችን ያለው ሁኔታ እዚህ ግባ ተብሎ የሚነገርለት አይደለም፡፡ በጣም ብዙ መስራትን ይጠይቃል፡፡

ጥያቄ፡- በአጠቃላይ ምርመራ ወቅት የሚካሄዱ ዋና ዋና ምርመራዎች የትኞቹ ናቸው?

ዶ/ር፡- በመጀመሪያ ደረጃ የሚደረገው ምርመራ፣ የተመርማሪውን ታሪክ ጠይቆ መረዳትና እሱን ተከትሎ ደግሞ አካላዊ ምርመራ ይደረጋል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ እንደ አስፈላጊነቱ የሽንት፣ የደምና የሰገራ ምርመራን ጨምሮ የላቦራቶሪና በተለያዩ የመሳሪያ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የተለያዩ ምርመራዎች ይደረጋሉ፡፡

 

ጥያቄ፡- ከምርመራ በኋላ የሚገኘውን ውጤት በተወሰኑ ምሳሌዎች ቢያብራሩልኝ?

ዶ/ር፡- የመጀመሪያው ነገር 2 ሰዎች አጠቃላይ ምርመራ ቢያደርጉ፣ የመጀመሪያው ውጤት ሁለቱም ከየትኛውም በሽታ ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጣቸው ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላኛው ገፅታ ደግሞ ከሁለት ተመርማሪዎች አንዱ፣ በውስጡ ያለው በሽታ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ቀድሞ እንዲታወቅለት መደረጉ ሌላ የውጤት ማሳያ ነው፡፡ ለምሳሌ አንዲት ሴት፣ የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ አድርጋ በሽታው በጊዜው ከታወቀላት በሚደረግላት ህክምና ለ25 ዓመታት ዕድሜዋን ማራዘም ትችላለች፡፡ ለልብ ህመም ተጋላጭ የነበረ የሲጋራ ሱሰኛና በደም ውስጥ ቅባቶች መጠን ከፍ ያሉበት ሰው፣ የህመም ስሜቶች ባይሰሙትም፣ የቅድሚያ ጤና ምርመራ ማድረግ ልምድ ካለው በወቅቱ ችግሩ ተገኝቶለት ሊታከምና ሊፈወስ ይችላል፡፡

 

ጥያቄ፡- በየጊዜው አጠቃላይ የጤና ምርመራ በማድረግ፣ የጤና ሁኔታን አለመከታተል የሚያስከትለው ጉዳት ምንድን ነው?

ዶ/ር፡- የህመም ምልክቶች አለመታየት ማለት አለመታመም ማለት አይደለም፡፡ በሽታዎች ምንም አይነት ምልክት ሳያሳዩ ለረጅም ጊዜ በውስጣችን ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ በቅድመ ምርመራ የጤና ደረጃችንን ባለማወቃችን፣ በሽታዎች ስር እንዲሰዱና እንዲሰራጩ በማድረግ የተለያዩ የአካል ክፍሎችን በማይድኑበት ሁኔታ እንዲጎዱ ጊዜና ዕድል እንሰጣቸዋለን፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ያጋጠመው የጤና ችግር ከ3 ዓመት በኋላ ቢታወቅለት በቀላሉ መዳን የሚችልበት ሁኔታ የለም፡፡ ወይም ደግሞ አንዱን አካሉን መልሶ ሊያገኘው በማይችለው መንገድ ሊያጣው ይችላል፡፡ ስለዚህ ቀድሞ የጤናን ሁኔታ ማወቅ ከተወሳሰቡ ችግሮች ያድናል፡፡

ጥያቄ፡- አጠቃላይ የጤና ምርመራ ባህልን እንዴት ማሳደግ ይቻላል?

ዶ/ር፡- ኅብረተሰቡ ስለጤናው ሁኔታ ያለው ግንዛቤ እንዲያድግ የማስተማር ስራው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ በማህበረሰቡ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ተደማጭነት ያላቸው ግለሰቦች፣ በየጊዜው አጠቃላይ ምርመራ እንዲያደርጉና በተለያዩ መንገዶች አርአያ ሁነው ህብረተሰቡን እንዲያስተምሩ ማድረግ፣ በሌላም በኩል የምርመራ አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ፣ ደረጃ በደረጃ በህብረተሰቡ ውስጥ የጤና ሁኔታን የመከታተል ባህል እየዳበረ የሚመጣበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡

The post Health: አጠቃላይ የጤና ምርመራ(ሜዲካል ቼክአፕ) መቼና ለምን እናድርግ? | ‹‹ሴቶችም ወንዶችም ሊያውቁት የሚገባ የሜዲካል ቼክ አፕ ካሌንደር አለ›› appeared first on Zehabesha Amharic.

ሕወሓቶች የወልቃይት ጸገዴን ሕዝብ መስለው ሰልፍ ወጡ 

$
0
0

welkait

(ዘ-ሐበሻ) “በመላዋ ኢትዮጵያ ሰልፍ መውጣት ወንጀል በሆነበት በዚህ ወቅት በትግራይ ክልል ግን ይፈቀዳል:: የሕዝብ እኩልነት ይህ አይደል?! ከሁለት ሳምንት በፊት የወልቃይት ጸገዴን ማንነት ለማስረዳት ወደ አዲስ አበባ የመጡት ተወካዮች መታሰራችው ይታወሳል::” ያሉን አንድ አስተያየት ሰጪ የሕወሓት መንግስት ዛሬ በጸገዴ ወረዳ አስደረጉት ስላለው ሰላማዊ ሰልፍ ሲያስረዱ “የጸገዴ ሕዝብ የአማራ ህዝብ መሆኑን ያውቃል; አውቆም ተቀብሎታል.. ዛሬ የራሱን የሕወሓት አባላትን ከየቦታው ሰብሰቦ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የብሄርን ግጭት ከማባባስ የባሰ ምንም ፋይዳ የለውም” ይላሉ::

መንግስታዊው ራድዮ ፋና “በትግራይ ክልል የፀገዴ ወረዳ ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄያችን ተመልሷል አሁን ላይ ይህን የሚያነሱ እኛን አይወክሉም በማለት ሰልፍ ወጡ” ሲል ያስነበበው ዜና መነጋገሪያ ሆኗል:: የወልቃይት ጸገዴ ማንነት ጥያቄን የሚያነሱትን እና እኛ አማራ ነን በግድ ወደ ትግራይ ክልል እንድንጠቃለል ተደርገናል በሚል ተቃውሞ ሲያነሱ የነበሩትንም እንደተለመደው ሰልፈኞቹ “የጸረሰላም ሃይሎች ናቸው” ብለዋቸዋል ይለናል::

በጸገዴ ሕዝብ ስም ዛሬ ሰልፍ የወጡት የሕወሓት አባላት ይህን ሰልፍ የጠሩት አንድም የገቡበትን ውጥረት ለማብረድ በሌላ በኩልም ሕዝብን ለማናከስ እንደሆነ ማንም ያውቃል:: እንደፋና ዘገባ እነዚህ ሰልፈኞች “የፀረ ሰላም ሃይሎች የጀመሩት ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት ዓላማ በጥብቅ እንደሚቃወሙ ሰልፈኞቹ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ ከዓመታት በፊት የተመለሰውን የህዝብ የማንነት ጥያቄ እና አብሮና ተስማምቶ የሚኖርን ህዝብ ለማጋጨት በአሁኑ ወቅት እንደ አዲስ እያነሱ የሚገኙትን የፀረ ሰላም ሃይሎች እንቅስቃሴን በጥብቅ እንደሚቃወሙም ነው ዛሬ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ የገለፁት።”

የሕወሓት መንግስት ለሌላው ኢትዮጵያዊ የከለከለውን ሰላማዊ ሰልፍ የመውጣትና ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በጸገዴ ሕዝብ ስም ለወጡት አባላት መፍቀዱ የሚያስደንቅ ባይሆንም ይህ ሰልፍ እንዲህ ባለው ሁኔታ መደረጉ ይበልጥ የወልቃይት ጸገዴን ሕዝብ እንደሚያነሳሳው አስተያየት ሰጪዎች በማህበራዊ ድረገጾች ሃሳባቸውን እየገለጹ ነው::

The post ሕወሓቶች የወልቃይት ጸገዴን ሕዝብ መስለው ሰልፍ ወጡ  appeared first on Zehabesha Amharic.

የአድዋን 120ኛ የድል በዓል በጋራ ለማክበር የአዘጋጀነውን የግብዣ –በሆላንድ የኢትዮጵያዊያን ማሕበር

$
0
0

 

የአድዋን 120ኛ የድል በዓል በጋራ ለማክበር የአዘጋጀነውን የግብዣ

በሆላንድ የኢትዮጵያዊያን ማሕበር
የበዓል አዘጋጅ ኮሚቴ
አምስተርዳም
ማሳሰቢያ፦ 
የእለቱን ዝግጅት መዘገብ ለሚፈልጉ የመገኛ ብዙሃን፣ በሚቀጥለው የስልክና የኢሜይል አድራሻ ሊያነጋግሩልን ይችላሉ።
ስልክ ቁጥር ፦ +31619928621፣ +31641221184፣ +31619683890
ኢሜይል ፦ info.venholland@gmail.com
5dec3d24-6dfe-4af5-952e-2ca1d3667f2d

The post የአድዋን 120ኛ የድል በዓል በጋራ ለማክበር የአዘጋጀነውን የግብዣ – በሆላንድ የኢትዮጵያዊያን ማሕበር appeared first on Zehabesha Amharic.

አቶ ዮናታን ተስፋዬ ተጨማሪ 28 ቀን የምርመራ ጊዜ ተሰጠበት

$
0
0

yonatan Tesfayeበነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በሽብር ተጠርጥሮ ላለፉት ሁለት ወራት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በእስር ላይ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ተጨማሪ የ28 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተሰጥቶበታል፡፡
ዛሬ የካቲት 15/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት ለ3ኛ ጊዜ የቀረበው ዮናታን ተስፋየ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ በዚህም በቀጣይ መጋቢት 13/2008 ዓ.ም ለ4ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡
እስካሁን የተከሳሽነት ቃሉን እንዳልሰጠ ለችሎት የገለጸው ዮናታን በእስር በሚገኝበት ማዕከላዊ ከጠበቃው ጋር እንዲነጋገር እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ከታሰረ ጊዜ ጀምሮ አንድም ቀን ጠበቃውን አግኝቶ ለማነጋገር እንዳልቻለ የተገለጸ ሲሆን፣ አሁንም ከጠበቃው ጋር ሳይመካከር ቃሉን ለመስጠት እንደማይፈልግ ለችሎት አስረድቷል፡፡
የአቶ ዮናታንን ችሎት ለመከታተል በስፍራው የተገኙ ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ፣ ጋዜጠኞችና የዲፕሎማቲክ ኮሚኒቲ ተወካዮች ችሎቱ በዝግ በመታየቱ ችሎቱን መከታተል አለመቻላቸው ታውቋል፡፡

The post አቶ ዮናታን ተስፋዬ ተጨማሪ 28 ቀን የምርመራ ጊዜ ተሰጠበት appeared first on Zehabesha Amharic.

ለአውሮፓ ፓርላሜንት፤ –ከሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

Moreshሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

8221 Georgia Avenue, Silver Spring, MD. 20910

Tel: (202) 230-9423 www.moreshwegenie.org

ቀን : የካቲት ፲ ፩/፪ሺህ፰ ዓም

ቁጥር : ሞወዐድዉጪ-0020-2008

MW-EXT-0020-2016

ለአውሮፓ ፓርላሜንት፤

ጉዳዩ፦ የአውሮፓ ፓርላማ በቁጥር

2016/2520/RSP ያሳለፈውን ውሣኔ ይመለከታል።

በቅድሚያ ለአውሮፓ ፓርላማ አባላትና ለዓለም ሕዝብ አምላካችን፣ ሰላም፣ ጤና፣ ዕድገትና ብልጽግና እንዲቸረን እንመኛለን። ለተከበረው የአውሮፓ ፓርላማ ፣ ይህን አቤቱታ የሚያቀርበው ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተሰኘ፣ መሠረቱን የተባበሩት የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ ሜሪላድ ግዛት ያደረ፣ በሕጋዊነት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ሲቪክ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በመላው ዓለም በሚገኙ ከተሞች መሠረቱን ጥሎ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ድምፅ አልባ ለሆነው የዐማራ ነገድ ድምፅ በመሆን እየሠራ ያለ ሲቪክ ድርጅት ነው። የተቋቋመበት መሠረታዊ ዓላማም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሩት ነገዶች በቁጥር ከፍተኛ ከሆኑት በመጀመሪያው ረድፍ የሚሰለፈው የዐማራ ነገድ፣

«ትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር» በሚመራው «የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራስያዊ ግንባር(ኢሕአዴግለሚፈጸምበት የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ድምፅ በመሆን፣ ከሚፈጸምበት የሕይዎት፣ የኢኮኖሚና የመብት ነጠቃ መታደግ የሚችልበትን ዘዴ ማፈላለግ ነው። ዐማራው ከፈጽሞ ጥፋት እንዲድን ጉዳዩን ለዓለም ማኅበረሰብና ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ማሰማት ነው።

ድርጅቱ ከተቋቋመ ሦስት ዓመታት አስቆጥሯል። በነዚህ ዓመታት የትግሬ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር በዐማራው ነገድ ላይ እየፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች የሚያሳዩ ከ

80 በላይ መግለጫዎችን በማውጣት የሚመለከታቸው ወገኖች እንዲያውቁት ጥረት አድርጓል። ከሁሉም በላይ ባለፉት 25 ዓመታት የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር በዐማራው ነገድ ላይ ያደረሰውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል በተጨባጭ የሚያሳዩ፣ የሰነድ፣ የድምፅ፣ የቦታ፣ የቃል፣ የፎቶ ግራፍ፣ የቪዲዮና መሰል መረጃዎችን አሰባስቦ ለሚመለከታቸው ሁሉ ለማሰራጨት በዝግጅት ላይ ይገኛል።

የተከበረው የአውሮፓ ፓርላማ፣ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ መዝኖ፣ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ፣ ዝምታውን ሰብሮ፣

«የኢሕአዴግ መንግሥት በገዛ ሕዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ግድያ፣ እስራት፣ ድብደባና አፈና ምን ያህል የከፋና የሰፋ መሆኑን ተረድቶ፣ ከዚያ አድርጎቱ እንዲቆጠብ ያሳለፈው ይህ ውሣኔ፣ ፓርላማው ለሕዝቦች መብት መከበር የቆመ እንደሆነ ያሳየበት አንዱ አጋጣሚ እንደሆነ እንገነዘባለን። ይህም የአውሮፓ መንግሥታት ከታሪካዊቷ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ገንብቶት ለኖረው የመንግሥታትና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በተሻለ መልኩ መቀጠል የራሱን በጎ ሚናይ ይጫዎታል ብለን እናምናለን። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተከበረው የአውሮፓ ፓርላማ ለዚህ ዓይነቱ ውሣኔ እንዲደርስ ጥረት ያደረጉትን ወገኖች ሊያመሰግን ይወዳል።

ሆኖም፣ ከእያንዳንዱ መልካም ነገር፣ ይብዛም ይነስም የራሱ የሆኑ ችግሮች ወይም ሕፀፆች አጣያም። በመሆኑም ከላይ በጉዳዩ ሥር የተጠቀሰው የፓርላማው ውሣኔ፣ በፊደል ተራ

«E» ሥር የተገለጸው ማለትም «ኢትዮጵያ በሃይማኖት 2

እና በባህል የተለያየ ማኅበረሰብ የሚኖርባት አገር ሆና፣ታላቆቹ ነገዶች ፤በተለይም ኦሮሞ እና የኦጋዴን ሶማሊዎች፣ በአማራውና በትግሬው ወደ ዳር ተገፍተዋል፣ በፖለቲካ ያላቸው የውክልና ተሳትፎ ትንሽ ነው

»

«E. whereas Ethiopia is a highly diverse country in terms of religious beliefs and cultures; whereas some of the largest ethnic communities, particularly the Oromo and the Somali (Ogaden), have been marginalized in favour of the Amhara and the Tigray, with little participation in political representation»

ሲል የደረሰበት መደምደሚያ ከዕውነት የራቀ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ፍጹም ስሕተት ስለሆነ፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማር ድርጅት ይህ እንዲታረም ለማስገንዘብ ይህን ደብዳቤ ለመጻፍ ግድ ብሎናል። ነገሩ እንዲህ ነው

!

ባለፉት

25 ዓመታት የኦሮሞ እና የሶማሊያ ፖለቲካ ድርጅቶች ከትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር ጋር አብረው፣ በዐማራው ነገድ ላይ የዘር መጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጽመውበታል። ሀብት ንብረቱን ነጥቀውታል። ከፍተኛ የሆነ የሥነልቦና ሰላባ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፍተውበታል። እንደ እንስሳ ታርዷል። ተሰልቧል። በገፍ ለዘመናት ከኖረበት አካባቢ ተባሯል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነባራዊ ዕውነታ ይህ ሆኖ እያለ፣ «ዐማራው ከትግሬ ጋር አብሮ ኦሮሞቹንና ሶማሌዎቹን ከፖለቲካ ተሳትፎ አግሎ፣ ወደ ዳር ገፍቷቸዋል» የሚለው ውንጀላ ወይም ክስ መሠረት የሌለው ነው።

ይህ በዐማራው ነገድ ላይ የተሰነዘረ መሠረተ ቢስ ውንጀላ፣ ፓርላማው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ለማስተካከል ይረዳል ብሎ ላቀደው ዓላማ መሣካት የሚረዳው አይሆንም። የዐማራው ነገድ የአገዛዙና የአጋሮቹ የጥቃት ሰላባ እንጂ፣ አጥቂ ባለመሆኑ፣ የችግሩ ምንጭ አይደለም። የችግሩ ምንጭ ካልታወቀ ደግሞ መፍትሄውን ለማግኘት ያስቸግራል። የአውሮፓ ፓርላማ ከላይ በተጠቀሰው አንቀጽ የደረሰበት ድምዳሜ በተሎ ካልታረመ፣ የዐማራውን ነገድ ለበለጠ ጥቃት የሚያግልጠው ከመሆኑም በላይ፣ ከነገዶቹ ጋር ለሚኖረው የወደፊት ግንኙነት አራፍሽ ሚና የሚጫወት ነው። የዐማራው ነገድ በደረሰበት የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል፣ፓርላማው ድምፅ እንኳን ባይሆነው፣ አጥፊ ነው ብሎ ይፈርጀዋል የሚል ግምትም ሆነ አስተሳሰብ አልነበረንም።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የአውሮፓ ፓርላማ የደረሰበትን ይህን ድምዳሜ በአንክሮ ሲያምሰለስለው ይህ አባባል ከሁለት የተሳሳቱ መነሻዎች ሊነሳ እንደሚችል አሰብን።

አንደኛ፣

እኤአ በ1935 «ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል» በሚል ርዕስ የተጻፈ መጽሐፍ ፣«የኢትዮጵያ ሕዝቦችና ነገዶች በዘር፣ በቋንቋ፣ በባህል ከኢትዮጵያ ገዥዎች ጋር የሚጋሩት ነገር የለም፤ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ተሰጥቷቸው ቢሆን ኖሮ፣ ገና ድሮ የኢትዮጵያዊነትን አስኳል ከውስጣቸው አውጥተው በጣሉ ነበር።» ሲል የፋሽስቱ መሶሎኒ ሰላይ የነበረው ሮማን ፕሮቻዝካ የጻፈው ቅጅ ሆኖ በማግኘታችን፤

ሁለተኛ፣

ዮሓን ክራፍ የተባለው ጀርመናዊ ሰላይ በ1837 ዓም ኢትዮጵያ በቆየበት ጊዜ፣ መካከለኛውን አፍሪካ በጀርመን ቅኝ ግዛት ሥር ለማዋል ባደረገው ጥናት፣ «በሸዋ ቆይታየ ለጋሎች(ኦሮሞዎች) የተለየ ትኩረት ያደረኩት በእግዚአብሔር ፀጋ ፕሮቴስታንትነትን ከተቀበሉ በኋላ የሠራዊት ጌታ ለጀርመኖች በአውሮፓ ላሳየው የተልዕኮ መሳካት የተመረጡ እንደሚሆኑ በመገመት ነው።» ሲል የደረሰበት ድምዳሜና አያይዞም « የሮማ ካቶሊክ ሚስዮናዊ ሽንን“(ቻይናን) ስጡንና እስያ የእኛ ትሆናለች» እንዳለው ሁሉ ክራፍም«ጋሎችን(ኦሮሞዎችን) ስጡንና ማዕከላዊ አፍሪካ የእኛ(የጀርመኖች) ይሆናል» (J.Lewis; Travler,and Missionery Lavour During an eight years resident—London: 1968, 2nd ed p.72) በማለት ለጀርመን መንግሥት ያሳሰበው በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለዘመን ተግባራዊ ለማድረግ ታልሞ ይሆን? ብለን እንድንጠይቅ አድርጎናል።

 

The post ለአውሮፓ ፓርላሜንት፤ – ከሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live