Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

“እውነትን ተጋፈጧት”–ጀዋር መሐመድ ለመንግስት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ የሰጠው ምላሽ

$
0
0

Jawar and Getachew Reda
በወያኔው ቃላቀባይ ጌታቸው ረዳ የተሰጠውን መግለጫ ኣነበብኩት።

በኣጋዚ ሃይል ላይ የተወሰደው ጥቃት በታጠቀ ቡድን የተከናወነ መሆኑን ይናገራሉ። ይህ በከፊል እውነት ነው። ነገር ግን ማነው ያ የታጠቀ ቡድን? ለመሸሸግ የተሞከረው ሃቅ እንዲህ ነው። የፌዴራል ፖሊስና የኣጋዚ ወታደሮች በክልሉ የሚሊሻና የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ (ፈጥኖ ደራሽ) የተቀናጀ ሃይል ተገድለዋል። ለዚህ ማስረጃው ደግሞ የኣጋዚ ሃይሎች በርካታ የኦሮምያ ልዩ ፖሊስ መኮንኖችን መግደላቸው ነው። በኣጋዚ ከተገደሉት የኦሮምያ ፖሊስ መኮንኖች መካከል ሙስጠፋ ሃሰን (የኣካባቢው ተወላጅና ነዋሪ) እና ረመዳን ኣብደላ (ከምስራቅ ሃረርጌ) ናቸው። እነዚህ ሁለቱ ግለሰቦች በተሳሳተ መልኩ በሲቪል ሰርቫንትነት ተገልጸዋል። (ምንጩ ሲናገር ‘ለመንግስት የሚሰሩ’ በማለት ሲገልፅ ኣኛ ደግሞ በሲቪል ሰርቫንትነት ወስደነው ነው።)

1. ሁለቱን ሰላማዊ ሰልፈኞች የገደሉትን የመጀመሪያዎቹን የኣጋዚ ቡድን ኣባላት ትጥቅ ያስፈቱት የኦሮምያ የፀጥታ ሃይሎች (ሚሊሻና ፖሊስ) ናቸው። ተጨማሪ የፌዴራል ጦር ሃይል ደርሶ የተማረኩትን ሁለቱን የኣጋዚ ጦር ኣባላትን ለማስለቀቅ ጥቃት ሲፈፅም የኦሮምያ ፖሊስ ለኣንዳንድ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የጦር መሳሪያ በማቀበል ባደረገው የኣፀፋ ጥቃት 11 የኣጋዚ ወታደሮች ተገደሉ። ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ መኮንኖች ህዝቡ ኣስከሬናቸውን ተመልክቶ መለየት የቻለው ብቻ ናቸው። ከሁለቱም ወገኖች የተገደሉትና የቆሰሉት ወደ ኣዋሳና ፍንፊኔ ሆስፒታሎች ተወስደዋል። እነዚህ ‘የታጠቁ ቡድኖች’ የተባሉት ከሩቅ የመጡ ባእዳን ኣማፂዎች ሳይሆኑ በራሱ በስርኣቱ መሪዎች የታጠቁና የተሰማሩ የደህንነት ኣካላት ናቸው።

2. ቃላቀባዩ ኣክለውም ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የመንግስት እርሻ እንዳወደሙ ተናግረዋል። ልክ ነው ሰላማዊ ሰልፈኞቹ እርሻና ሌሎች ንብረቶችን ኣውድመዋል። እነዚህ እርሻዎች ቀደም ሲል የመንግስት የነበሩ ቢሆኑም ሁዋላ ላይ ግን ለውጭና ለህወሃት ኩባንያዎች ተሽጠዋል። እናም ሰልፈኞቹ ‘መሬታችንን ቀምታችሁኣል፣ እኛ ስንራብ የስንዴውን ምርት ወደ ሌላ ቦታ ጭናችሁታል!’ እያሉ መፈክር ሲያስተጋቡ ተሰምተዋል። በነገራችን ላይ ምእራብ ኣርሲ/ምስራቅ ሸዋ በረሃቡ ክፉኛ ከተጎዱት ኣካባቢዎች መካከል ይጠቀሳሉ። 40% የሚሆነው የኣካባቢው ህዝብ ኣስቸኩዋይ የምግብ እርዳታ ፈላጊ ነው።

3. የስርኣቱ ቃላቀባይ በመቀጠልም ለግጭቱ መንስኤ ሃይማኖታዊ እንደምታ ሰጥተውታል። ይህ ጨርሶ ውሸት ነው። ኣንድም የኣካባቢው መስጊድም ሆነ ቤተክርስቲያን ጥቃት ኣልተፈፀመበትም። በኣካባቢው ምንም ኣይነት ሃይማኖታዊ ኣለመግባባት ኣልነበረም። የኛ ስጋት የነበረው ኣካባቢው ከደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጋር ስለሚዋሰን የሰርኣቱ ወኪሎች የብሄር ግጭት ይጭሩ ይሆናል የሚል ነበረ። ያ ራሱ ኣልተከሰተም።

ለስርኣቱና ለውጭ ደጋፊዎቹ የምለግሰው ምክር ኣለ። ከእውነት ጋር ተጋፈጡ። ከውጭ የመጡ ግጭት ቀስቃሾችን ኣይደለም እየተዋጋችሁ ያላችሁት። ህወሃት በሚያደርገው ወሰን የሌለው ጣልቃ ገብነት ሳቢያ በኦሮምያ የኣስተዳደርና የደህንነት ሁኔታው ሙሉ በሙሉ ዘቅጧል።

1. ህወሃት ወያኔ የክልሉን ፕሬዝዳንት ከስልጣን ካነሳው ወር ያለፈው ሲሆን ፕሬዝዳንቱ እስካሁን የት እንዳለ ኣልታወቀም። በሌላም ኣልተተካም። ክልሉ በዋና ስራ ኣስፈፃሚ እየተመራ ኣይደለም።

2. የኦሮሚያ ካቢኔ ላለፉት ሁለት ወራት ተሰብስቦ ኣያውቅም። በክልሉ ምንም ኣይነት የጋራ ስራ ኣስፈጻሚነት ውሳኔ እየተደረገ ኣይደለም። ትእዛዞች በቀጥታ እየተላለፉ ያሉት ከህወሃት ደህንነት ቢሮ ነው።

3. የኦህዴድ ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ሁለቱንም ማለትም መደበኛና ኣስቸኩዋይ ስብሰባዎችን እንዳያደርግ ታግዷል።
4. የህወሃት ደህንነት ሃይል የኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላትን፣ የድፓርትመንት ሃላፊዎችንና የዞን ኣስተዳዳሪዎችን እንዳሻው ያዋክባል፣ ይደበድባል፣ ስማቸውን ያጠቁራል። ይህም ክልሉን የማስተዳደርን ስራ ኣስቸጋሪ ኣድርጎታል።

5. ጨፌ ኦሮምያ ላለፉት 4 ወራትና ከዛ በላይ ተሰባስቦ ኣያውቅም። በርካታ የጨፌው ኣባላት ወይ ታስረዋል ኣልያም የገቡበት ኣልታወቀም። ዳኞች፣ ኣስተዳዳሪዎችና የድፓርትመንት ሃላፊዎች ያለ ህጋዊ ኣካሄድ ከስራቸው ተወግደዋል።

6. ህወሃት የኦህዴድ ማ/ኮሚቴ ባለፈው የመጨረሻው ጉባኤው (ጃኑዋሪ 10-13?) ያቀረበውን ባለ 15 ነጥብ ጥያቄ ውድቅ ኣድርጎበታል። እነዚህ የቀረቡት ጥያቄዎች የፌዴራል ሃይሎች ከኦሮምያ እንዲወጡ፣ ኮማንድ ፖስት እንዲፈርስና ሌሎች (በሚቀጥሉት ቀናት እዚሁ ላይ የምናነሳቸውን) በርካታ ፖሊሲ ነክ ጥያቄዎችን ያካተቱ ነበረ።
ስለሆነም የህወሃት ኣመራሮችና የውጭ ደጋፊዎቻቸው በጥብቅ የሚመከሩት ጉዳይ ኣይናቸውን ከፍተው እውነታውን እንዲመለከቱ ነው። በኦሮሞ ተቃዋሚዎች፣ ተማሪዎች ወይም ዳያስፖራው ላይ ብቻ ሳይህን ባገር ቤትና በውጭ የሚገኘውን መላው የኦሮሞን ህዝብ ኢላማቸው ኣድርገዋል። ‘የታጠቀ ቡድን’ በማለት ከሩቅ የመጣ ኣማፂ ቡድን ኣስመስለው ለማቅረብ የሚሞክሩት ሃይል የገዛ የደህንነታቸው ኣካል ነው። እንዲሁም በእስላማዊ ኣክራሪነት ለመፈረጅ የሞከሩት የምስራቅ ሸዋ/ምእራብ ኣርሲ ወረዳዎች በኣመዛኙ የኣድቬንቲስት ክርስትና ተከታዮች ናቸው። ስለሆነም ፍረጃው ከእውነት የራቀ፣ ኢ-ሎጂካዊና ኣደጋም የሚያስከትል ነው።

ከዚህ ቀውስ ለመላቀቅ ኣንድ ብቸኛ መንገድ ነው ያለው። የተቃዋሚው ጎራና የመንግስቱ ኣካል የሆኑ የኦሮሞ ኣመራሮችን ኣድምጧቸው። የፌዴራል ፖሊስን ከኦሮምያ በማስወጣትና የኮማንድ ፖስት መዋቅሩን በማፍረስ መጀመር ትችላላችሁ። ከዚያም ሙሉ ስልጣን ለክልሉ መንግስት መልሱ። ከዚሁ ጎን ለጎን የጋራ መፍትሄ ለማፈላለግ ከኦሮሞና ሌሎችም ኣመራሮች ጋር ቁጭ ብላችሁ ተወያዩ።

ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ኣለመሆን በስርኣቱ፣ በቀንዱ ቀጣናና በማህበረሰቡ ላይ ኣደገኛ ውጤቶችን መጋበዝ ይሆናል። የኦሮሞ ህዝብ በኣገሪቷና በቀጣናው ኣስተማማኝ ሰላምና መረጋጋትን የማስፈን መብትና ፍላጎት ኣለው። ይሁንና በተጫነበት የጭቆናና የብዝበዛ ኣገዛዝ እንዲሁም በገዛ ኣገሩ ላይ ክብር በመነፈጉ ተዳክሞ ቆይቷል። ኣሁን ግን የሚገባውን ክብር ለማስመለስ በቁርጠኝነት ተነስቷል!!

ጀዋር በ እንግሊዘኛ የጻፈውን ጽሁፍ የተረጎመው ያያ በሽር ነው::

The post “እውነትን ተጋፈጧት” – ጀዋር መሐመድ ለመንግስት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ የሰጠው ምላሽ appeared first on Zehabesha Amharic.


የድርቁ ገፅታ –ከአምዶም ገ/ስላሴ

$
0
0

drought 23በሃገራችን ኣጋጥሞ ባለው የድርቅ ኣደጋ 15 ሚልዮን ህዝብ ለረሃብ ተዳርጓል።

መንግስት የተባበሩት መንግስታት ኣስከትሎ እርዳታ ቢለምንም በቂ እርዳታ ኣልተገኘም።

የሚመጣው ጥቂት የእርዳታ እህልም ከከፍተኛ ባለስልጣን እስከ የቀበሌ ካድሬዎች እየዘረፉ ስላባከኑት ወደ ተጠቂው ህዝብ ሊደርስ ኣልቻለም።

እንደ ውጤቱም የሰውና የእንስሳት ሂወት በረሃብ እያለፈ ይገኛል።

እርዳታው ያልደረሳቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከገጠር ወደ ከተማ እየጎረፉ ይገኛሉ።

ኣረጋውያን፣ ህፃናት፣ እናቶችና ወጣቶች መቐለ እያጨናነቅዋት ይገኛሉ። የመቐለ ገፅታም እየተቀየረ ነው።

ህዝቡ ራስበራሱ ካልተረዳዳ በስተቀር ይሄ በሌቦች የተሞላ መንግስ ህዝቡ ከኣደጋ ሊታደግ ኣይችልም።

ይሄ ምስል መቐለ 16 ቀበሌ ትራፊ ለምነው የሚበሉ ኣባትና ልጅ ናቸው።

‪#‎ክፉ_ቀን‬

‪#‎Ethiopian_Famine‬

ነፃነታችን በእጃችን ነው።
it is so.

The post የድርቁ ገፅታ – ከአምዶም ገ/ስላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

ቤልጂየም ከግዛቷ ያባረረቻቸው ኤርትራዊው ሰደተኛ በ አ/አው የ ቦሌ አርፖርት ውስጥ “እየተሰቃዩ”ነው

$
0
0

“እባካችሁ ወላጅ አባቴን ከመከራ እና ከ ሰቃይ ታደጉልኝ” የ ሴት ልጃቸው የተማጽኖ ጥሪ ከኖሮዊይ

ከታምሩ ገዳ

እ ኤ አ በውርሃ ጥቅምት 2015 ከ ጎረቢት ከ ደቡብ ሱዳን ወደ ምእራብ አውሮፓዊቷ ቤልጂየም በመጓዝ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቁት ኤርትራዊው አቶ ተስፋ ገብር ሃይሌ ደስታ የጠበቁት እና የሰነቁት የጥገኝነት ጥያቄ መልካም ዜና ይዞ አልመጣም ነበር።

addis ababa airport

“ኤሪ ጋዜት” የተባለ ድህረ ገጽ ሰሞኑን እንደ ዘገበው ከሆነ ቤልጂየም/ብራስልስ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ እንደደረሱ የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የሆነባቸው የ 52 አመቱ አቶ ተስፋ ገብር ይዘውት የነበረው መጠኑ ለጊዜው ያልተገለጸ ገንዘብ እና ንብረት በቤልጂየም የኢምግሬሽን እና የደህነነት ሃላፊዎች ከመነጠቅ አልፎ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸው “ወደ መጣህበት ወደ ደ/ሱዳን እንባርሃለን “በሚል ስሜት ያለ ውዴታ በግዴታ እ ኤ አ በየካቲት 2 /2016 እጃቸው በካቲና ተጠፍሮ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነ አውሮፕላን ከተጫኑ በሁዋላ አ/አ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደረሱ ወደ ቤልጂየም ከማቅናታቸው በፊት የነበሩባት አገር (ደ/ሱዳን ) ለመመለስ ሀጋዊ የጉዞ ሰነድ አልባ በመሆናቸው ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግለሰቡን ወደ ሌላ አገር ለማሸጋገር ውክልና ስለ ሌለው ፣ ወደ ትውልድ አገራቸው ወደ ኤርትራም እንዳይመለሱ ቤልጂየም ከምእራባዊያን ጎረቤቶቿ ሊደረሰባት የሚችለው ብርቱ የሰበዊ መብት ጥሰት ተቃውሞን በመሰጋት አና ዋስትና ባለማግኘታቸው በአ/አ የ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ በ ከብረት ከተሰራ ወንበር ላይ ያለ ብርድ ልብስ በብርድ እና በሙቀት እየተቀጡ መሆናቸው ተገልጿል።

በኖሮዊይ የሚገኙ የአቶ ተስፋ ገብር ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ ያደረገው ዜና ዘገባው አቶ ተስፋ ግብር በቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ቆይታቸው ለየተለያዩ የሰነልቦና ችግሮች ከመጋለጣቸው ባሻገር ወደ ኤርትራ ወይም ወደ ደ/ሱዳን ካለሆነ ደግሞ ወደ ኡጋንዳ ሊባረሩ እንደሚችሉ የሚገልጹ ማሰፈራሪያዎችም እንደገጠሟቸው ተነግሯል ። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ቢሆን የቤልጄየም መንግስትን ፍላጎት ለማርካት ሲል ብቻ የሰብ አዊ መብት ረገጣን ሸሽተው አውሮፓን መዳረሻ በማድረግ የተሰደዱት የአቶ ተስፋ ገብር እና መሰል ሰደተኞችን የምርጫ እና የጥገኝነት ፍላጎትን በመጣረስ የተፈጸመ በመሆኑ አየር መንገዱም ቢሆን ለከፋ ትችት የተዳረገ ሲሆን የወላጅ አባቷ የሰብእዊ መብት መጣስ ያሰጋት በኖሮዊይ አገር የምትኖረው የአቶ ተሰፋገብር ሴት ልጅ የ ኢትዮጵያ መንገድ የፈጸማቸው ድርጊቶችን በመኮነን ወላጅ አባቷ ቢቻል የፖለቲካ ጥገኝነት ወደ ጠየቁባት ወደ ቤልጂየም እንዲመለሱላት አሊያም በ አ/አ ለሚገኘው ለአለማቀፉ የሰደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR)ተላልፈው እንዲሰጡላት ተማጽናለች። አለም አቀፍ ዝና እና ክብር ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግለሰቡ ላይ ስርቶታል ሰለ ተባለው የሰበዊ መብት ጥሰት ሆነ በአሁኑ ወቅት በርካታ አለማቀፍ አየርመንገዶች ከምእራብ አውሮፓ በገፍ የሚባረሩትን ሕገ ወጥ ሰደተኞችን “ ለመንገደኞቻችን ደህንነት ሲባል እንጭንም “የሚል አቋሟቸውን በሚያሰሙበት በአሁኑ ወቅት የኛው አየር መንገድ ለምን ይህንን መሰሉን አደጋ በራሱ እና በደምበኞቹ ላይ ለመጋበዝ እነደ ፈለገ እሰከ አሁን ድረስ የሰጠው ማብራሪያ ፣ ማስተባበያም ሆነ ይሁንታዊ ምላሽ አለተገኘም።

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ቤልጂየም ከዚህ ቀደም በአንድ ኢትዮጵያዊ የደህንነት አባል ላይ ተመሳሳያ ኢሰብ አዊ የመብት ረገጣ ያደረገች መሆኑ የሚታውስ ሲሆን ፍሬ ሃሳቡም በአጭሩ እንደሚከተለው ነው። አለም ሰገድ ተካ የተባለ አገዛዙን በመቃወም እ ኤ አ በወረሃ ጥር 27 / 2001 በእቃ መጫኛ አውሮፕላን ውስጥ በመደበቅ ወደ አውሮፓ ለመሰደድ ሲጥር አውሮፕላኑ ግብጽ ላይ ነዳጅ ለመሙላት ሲቆም አለምሰገድም አውሮፓ የደርሰ መስሎት ከአውሮፕላኑ ጉያ ብቅ ይላል። የ 28 አመቱ የደህንነት ሰራተኛው አቶ አለም ሰገድ ሁኔታን በድንጋጤ የተመለከቱት ፕይለቶቹ ለራሳቸውም ደህነነት በመፍራታቸው አቶ አለም ሰገድ ካይሮ ላይ እጁን ለግብጽ ኢሚግሬሽን ባለሰልጣናት እንዲሰጥ ለማግባባት ቢሞክሩም የግብጽ የደህንነት ባለሰልጣናት ግን ኢትዮጵያዊው የደህንነት ሰራተኛው ካይሮ ላይ እጁን መሰጠት አይችልም (አሻፈረን )በማለታቸው ሳቢያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፓይለቶቹም የአየር መንገዱ የደህንነት ክፍል አባሉ አቶ አለም ስገድን ሳይወዱ በግድ ወደ ቤልጂየም ይዘውት ይጓዛሉ።

ቤልጂየም/ብራስለስ አንደ ደረሱም በዘመኑ የኢ ሕ አዲጋዊ አጠራር የክልል ሶስት ተወላጅ በመሆኑ ብቻ በአገዛዙ ሹማምንቶች የተለያዩ በደሎች አንደሚደርሱበት ፣ ለህይወቱም እንደሚሰጋ ፣የደህነነት ሰራተኛ መሆኑን የሚያሳይ መታወቂያ በማሳየት በብራስልስ/ቤልጂም የፖለቲካ ጥገኝነት ያቀርባል። የአቶ አለምሰገድ ጉዳይን በግርድፉ የተመለከቱት የቤልጂየም የኢሚግሬሽን ሃላፊዎች የጥገኛ ጠያቂዎን ጉዳይ በአንክሮ ሳይመለከቱ የአቶ አለም ሰገድ ን መታወቂያ በመያዝ “በደል አደርሱብኝ “ወደ አላቸው የኢሕ አዲግ የ ደህንነት ሹማምንቶች ፋክስ በማድረግ የማብራሪያ ጥያቄ ያቀርባሉ። ከ አ/አ ገዢዎች በኩል “ የምትሉት ግለሰብ የእኛ አባል አይደለም፣ አሸባሪ ሊሆን ይችላል …ወዘተ ” የሚል ምላሽ በማግኘታቸው አቶ አለምሰገድ ተደብቆ ወደ ቤልጂየም ለመኮብለል በሞከረበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቤልጂየም የደህንነት እና የኢሚግሬሽን ሰራተኞች በግዴታ ተጭኖ ወደ አ/አ ለመመለስ ይገደዳል።
አቶ አለምሰገድ ከቦሌው አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርስም የጠበቁት ዘወትር የሚወዱት ቤተሰቦቹ ሳይሆኑ ፣ “በደል አደርሱብኝ “በማለት ጥሏቸው የሄደው የኢ ሕ አ ዲግ የደህነነት ሹማምንቶች ነበሩ። አቶ አለም ሰገድ ቦሌ እንደደረሰ ብዙም ሳይቆይ ወደ ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ የወሰዳል። በዚህ ወቅት ነበር የቀድሞ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ (ኢነጋማ ) የስራ አስፈጻሚ ኮሜተ አባላት ፣መብረቅ/መብሩክ ለተባሉት ጋዜጦች እና ለተለያዩ የነጻ ፕሬስ ውጤቶች ይሰሩ የነበሩት ፣በአሁኑ ወቅት ደግሞ በስድት አለም ከምድረ አሜሪካ ከላስ ቬጋስ ከተማ ዘውትር እሁድ በአካባቢው ሰአት አቆጣጠር 6፡30 pm (በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 12፡30) በአማሪኛ ቋንቋ የሚተላለፈው እና በራሱ ድህረ ገጽ hiber radio .com እንዲሁም በመላው አለም ተደራሽነት እና ታዋቂነት ባላት በ ዘ ሃበሻ ድህረ ገጽ አማካኝነት መረጃ ለሚናፍቀው ህዝባችን የወቅታዊ መረጃዎች ምንጭ የሆነው የሕብር ራዲዮ መሰራቾች እና ዋና አዘጋጆች ለሁኔታው ልዩ ትኩረት በመስጠት ፣ የምርመራ ጋዜጠኝነት ክህሎታቸውን (ኢንቨስቲጊቲቭ ጆርናሊዝም ሪፖርቲንግ ) በመጠቀም ፣ጉዳዩንም ከሰብ አዊ መብት ጥሰት ጋር የተያያዘ መሆኑን በመገንዘብ እና ጉዳዩን ለአለማቀፉ ማህበረሰብ በተለይ ለዲፕሎማቲኩ ማህበረሰብ በፍጥነት ያሳውቃሉ ።
የቤልጂየም የደህንነት እና የኢሚግሪሽን ሃላፊዎች ከኢሕ አዲግ የደህንነት ሹማምንቶች ጋር በመሆን በአቶ አለምሰገድ ላይ የፈጸሙት የሰበዊ መብት ረገጣዎችን የተመለከቱት በፓሪስ/ፈረንሳይ እና በጀርመን/በርሊን የሚገኙ የአውሮፓ የዲፕሎማቲክ አባላት በቤልጂየም ሕገወጥ እርምጃ በመደናገጥ ቤልጄየም የወሰደችው የተቻኮለ ፣ የተሳሳታ እና ግዴለሽነት የተላበሰው እርምጃዋን በአጽነኦት በመኮነናቸው የተነሳ የብራስልስ ም ባለሰልጣናት በሰሩት ሰህተተ በመጸጸት ሁኔታውን ለኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር እና የደህነነት ሹማምንቶች አበከረው በማስጠንቀቅ እና በመማጸን በአቶ አለምሰገድ ላይ ምንም አይነት የአካላዊ እና የስነልቦናዊ ተጽኖ እንዳይደርስበት በማሰገንዘባቸው አቶ አልምሰገድ ከታሰረበት የማእከላዊ እስር ቤት ብዙም ሳይቆይ እንዲፈታ፣ ቤልጂየምም በሰራቸው ትልቅ ስህተት አቶ አለምሰገድን በግልጽ ይቅርታ በመጠየቅ ፣ ለአቶ አለም ሰገድምም የሞራል ማካካሻ የሚሆን መጠነኛ የገንዘብ ጉርሻ መሰጠቱን የቀደሞዎቹ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ አባላቱ እና የአሁኖቹ የህብር ራዲዮን አዘጋጆቹ ኢህአዲግ ዘውትር ነጻው ፕሬስን “የተቃዋሚዎች ልሳናት “አደርጎ ለመፈረጅ ቢሞክርም ፣ ነጻ ፕሬስ መኖር ለአገዛዙ ሰዎች ሳይቀር በጭንቀት ቀን እንደሚጠቅማቸው የአቶ አለም ሰገድ ገጠመኝን በናሙናነት በመጥቀስ በትውስታ መነጽራቸው. ይመለከቱታል ።

The post ቤልጂየም ከግዛቷ ያባረረቻቸው ኤርትራዊው ሰደተኛ በ አ/አው የ ቦሌ አርፖርት ውስጥ “እየተሰቃዩ” ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

በምዕራብ አርሲ በኮፋሌ መንገዶች ተዘጋጉ –በዋቤ ከተማ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው

$
0
0

Kofale 2 Kofale

(ዘ-ሐበሻ) ምዕራብ አርሲ በተለያዩ ከተሞች የተቀጣጠለው የሕዝብ አመጽ ዛሬ በኮፋሌ እና በዋቤ ከተሞች ቀጥሎ መዋሉ ተሰማ::

በተለይ በኮፋን ከሌሎች ከተሞች ጋር የሚያገናኘውና ሌሎች መንገዶች ሙሉ በሙሉ በሰልፈኞች የተዘጋ ሲሆን የፌደራል ፖሊስም በሰልፈኞቹ ላይ እርምጃ ቢወስድም ተቃውሞውን ሊያስቆመው እንዳልቻለ የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች አስታውቀዋል::

የድንጋይ መከላከያ የለበሱና ጠመንጃ የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት የኮፋሌ ከተማን ቢወሯትም የህዝቡን ቁጣ ማቆም ተስኗቸዋል::

በተመሳሳይ በቡሌ ሁራም እንዲሁ የህዝቡ ተቃውሞ ቀጥሏል::

የፌደራል መንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ትናንት በቴሌቭዥን ወጥተው በኦሮሚያ የተነሳውን የሕዝብ ተቃውሞ ተቆጣጥረን አስቁመነዋል ቢሉም ዛሬም በተለያዩ ከተሞች የሕዝቡ ቁጣ አይሎ ውሏል::

The post በምዕራብ አርሲ በኮፋሌ መንገዶች ተዘጋጉ – በዋቤ ከተማ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

“ብሔራዊ ጭቆናው የትግላችን መዘውር ሆኖ ይቀጥላል! ”–ድምጻችን ይሰማ

$
0
0

muslim a

ረቡእ የካቲት 9/2008

ኢትዮጵያዊው ሙስሊም እየደረሰበት የሚገኘውን ብሔራዊ ጭቆና ከጫንቃው ላይ ለማራገፍ ላለፉት አራት አመታት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየታገለ ይገኛል። ይህ እልህ አስጨራሽ ትግል የተለያዩ እርከኖችን ሲሻገር ሰላማዊነቱን እንደጠበቀ መሆኑ ብዙዎችን አስደምሟል፡፡ ለአንዳንዶችም ትምህርት መሆኑ አልቀረም። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ትግልን እንደ ህይወት መንገድ፣ ድልን ደግሞ በመንገዱ ላይ እንደሚገኝ ፍሬ አድርጎ ስለተመለከተው ከመንግስት በኩል የሚደርሱበት አሳዛኝ በደሎች ሳይበግሩት ትግሉን ጠብቆ ማቆየት ችሏል። ወትሮውንም ቢሆን ለፍትህ በሚደረግ ሰላማዊ ትግል የሙስሊሙ ድርሻ መታገል፣ ድሉን ማሳካት ደግሞ የፈጣሪው ድርሻ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ይሁንና ሰላማዊውን ትግል ለማደፍረስ ሳር ቅጠል የሚበጥሰው መንግስት መልክና ቅርጹን እየለዋወጠ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከትግሉ ለማደናቀፍ እየሞከረ ይገኛል። ከዚህ ቀደም በተለያዩ ልሳኖቹ ብቅ እያለ ሰላማዊውን ትግል ከማጠልሸት አንስቶ ንጹሀን ኮሚቴዎቻችንን በሀሰት እንደወነጀለው ሁሉ አሁንም ከእውነት ፍጹም የራቁ መረጃዎችን በህብረተሰቡ ዘንድ እየረጨ ነው። ‹‹የታጠቀ ሰራዊት በወሬ ይፈታል›› እንዲሉ መንግስት በጉልበት አልገታ ያለውን የሙስሊሙን የመብት ጥያቄ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ ለማድቀቅ የከፈተውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ቀጥሎበታል።

ሰሞኑን ትግሉን በሚመለከት በ‹‹ኢትዮ ቻናል›› ጋዜጣ ታትሞ ለንባብ የበቃው ዘገባም የሚያሳየው ይህንኑ ተጨባጭ ነው። መንግስት በቆርጦ ቀጥል የቅንብር መርሁ መሰረት የውድ ኮሚቴዎቻችንን ሰነድ ከሚፈልገው ዘገባ ጋር በማዛመድ ‹‹በሬ ወለደ›› አይነት ዜና አውጇል። ከዚህ ቀደምም ቢሆን ‹‹ጂሀዳዊ ሀረካት›› ብሎ በሰየመው ‹‹ልብ ወለድ›› ዘገባው ላይ የኡስታዝ አቡበከርን ንግግር ቆራርጦ ‹‹ለጂሀድ አነሳስተናል›› የሚል አይነት ወሬ ለመፍጠር ያደረገውን ጥረት የምንዘነጋው አይደለም። ይሁንና ሙስሊሙ ህብረተሰብ በእንዲህ አይነቱ ደባ ከመሸወድ ይልቅ አንድነቱንና የመረጃ አሰባሰብ ክህሎቱን አጠናክሮ መቀጠሉ መንግስትንና የሀሰት ልሳኖቹን ማክሰሩ ተስተውሏል። ጋዜጣው ‹‹የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መንግስትን ይቅርታ ለመጠየቅ እየተማጸኑ ናቸው›› ሲል ያሰራጨው ዘገባ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ሞራል ለመሸርሸር እና እንድነቱን ለማዳከም ታቅዶ የተዘጋጀ ጥንቅር እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። ለመረጃነት አባሪ ተደርጎ የቀረበው የኮሚቴዎቻችን ፊርማም ከጽሁፉ ጋር ምንም አይነት ተዛምዶ የሌለው ነው። ይልቁንም ኮሚቴው ላለፉት አራት አመታት ሰላማዊነቱን ጠብቆ እንደተጓዘው ሁሉ አሁንም ቢሆን ሰላማዊ አማራጮችን በሙሉ እስከ መጨረሻው ድረስ አሟጦ እንደሚጠቀም፣ መንግስትም ከማያዋጣ እብሪተኝነቱ በመታቀብ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ያወጀውን ብሄራዊ ጭቆና ለማቆም ዝግቹ እስከሆነ ድረስ ኮሚቴው ሰላማዊ መፍሄን መሻት ስቃይ እና መከራ ያማያዛንፈው አቋሙ መሆኑን በፊርማው ያረጋገጠበት ልዩ ሰነድ እንጂ ‹‹ይቅርታ ለመጠየቅ የተደረገ ተማጽኖ›› አይደለም፡፡ (የትግላችንን ሰላማዊነት በተመለከት በግንዛቤ ማስጨበጫ ትንታኔዎችን ወደፊት በአላህ ፈቃድ የምንመለስባቸው ይሆናል፡፡)

ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያነሳቸው ጥያቄዎችም ሆኑ ጥያቄዎቹን ለማስመለስ ኮሚቴውና አጠቃላይ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የሄደባቸው መንገዶች ሰላማዊ፣ ህጋዊ እና ፍትሃዊ ስለሆኑ ይቅርታ የምንጠይቅበት አንዳችም ነገር ያለመኖሩን ያክል ኮሚቴው በማንኛውም አካል በኩል ይቅርታ እንዲጠየቅለት የሚፈልግበት ሁኔታም አይኖርም። በእስር ላይ የሚገኙ የኮሚቴው አባላት እና የሙስሊሙ ህጋዊ መሪዎቻችንም ሆኑ ከትግላችን ጋር በተያያዘ በአገሪቱ የተለያዩ እስር ቤቶች እየተሰቃዩ የሚገኙ ሙስሊሞች ኢፍትሃዊ የሆነ ስርዓት ሰለባ እንጂ የትኛውንም ህግ የተላለፉ ጥፋተኞች አይደሉም።

መንግስት የሙስሊሙን ትግል ለማዳከም፣ ብሎም ለማጥፋት ባሳለፍናቸው አራት የጽናት አመታት ውስጥ ያልፈነቀለው ድንጋይ እንደሌለ ሁሉ ዛሬም ነገም ይህንን አላማውን ለማሳካት ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለአፍታ የምንዘነጋው አይሆንም። በተለያየ ጊዜ ያወጣቸው የቴሊቪዥን ድራማዎችም ይሁኑ በጋዜጣው የሚያወጣቸው ተረት ተረቶች ለዚሁ ዓላማ የታቀዱ መሆናቸው ምንም የሚያጠራጥር አይደለም። እስካሁን ያልተሳካለት እና ወደፊትም ፍጹም የማይሳካለት ጉዳይ የሙስሊሙን አንድነት እና ለትግሉ ያለውን ሞራል መስበር ቢሆንም ይህ ግን የእኛን የዘወትር ጥረት እና ጥንቁቅነት ይፈልጋል። የመንግስት ሴራ ሰለባ ከመሆን ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል። ብሄራዊ ጭቆናን በቋሚነት ለማስወገድ የምናካሂደው ትግላችን ብዙሃኑን አሳታፊ ሆኖ የሚቀጥል ሲሆን ሁላችንም ከግል ፍላጎቶች በመራቅ ራሳችንን ለወጣው የትግል መርህ ተገዥ በማድረግ እና ይህንንም መርህ ብቻ በመከተል ከድል የምንደርስበትን ቀን ልናፋጥን ይገባል። ይህንን ማድረጋችን አንዳችን ለአንዳችን ተደጋጋፊ ሲያደርገን ሁላችንንም ሰለባ በሚያደርግ የመንግስት ሴራ ውስጥ ገብተን ከመነታረክም እንዲሁ ይጠብቀናል። ትግሉን ለመደገፍ የሚደረጉ ጥረቶች ተኣማኒነት እና ተቀባይነት የሚኖራቸውም የትግሉን መርህ ብቻ ተከትለን ስንንቀሳቀስ ብቻ ይሆናል፡፡ (የትግላችንን ብዙሃኑን አሳታፊነት በተመለከተ በግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎቻችን በሰፊው የምንመለስበት ይሆናል።) በመሆኑም መንግስት ይዞልን የቀረበውን ተረት ተረት ተከትሎ በግልም በቡድንም የሚደረግ የትኛውም አይነት ውዝግብ እንዳይኖር አጥብቀን እየጠየቅን ውዝግቡ ትርፉ የመንግስትን አላማ ከግብ ማድረስ ብቻ እንደሚሆን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ስለትግሉ በሚኖሩን መሰረታዊ መረጃዎች ዙሪያ ጥንቃቄ ማድረግም እንዲሁ አስፈላጊ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይለናል፦ ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡›› (ሱረቱል ሁጁራት 43፡6) በዚህ መለኮታዊ ትእዛዝ መሰረት መረጃን ሳያጣሩ ድምዳሜ ላይ መድረስና እርምጃ መውሰድ ለጥፋት የሚያጋልጥ ጠንቅ ነው፡፡ በመሆኑም ምንጊዜም የሚደርሱንን መረጃዎች በጥንቃቄ መመርመር እና ለሌላ ሰው ከማስተላለፋችን ወይም ለራሳችን እውነት ነው ብለን ከመቀበላችን በፊት ተአማኒነቱን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ልንዘነጋ አይገባም፡፡ ትግላችንን እና ሂደቱን፣ እንዲሁም አቅጣጫውን በተመለከቱ ጉዳዮችም ምንጊዜም ትክክለኛውን መረጃ ከ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› ገጽ ብቻ መውሰድ እንዳለብንም በአንክሮ ለመግለጽ እንወዳለን። ትግላችን ብሔራዊ ጭቆናው እስካልተወገደ ድረስ ተጠናክሮ የሚቀጥል እና በየትኛውም አይነት ሴራ ሊገታ በማይችልበት ህዝባዊ መሰረት ላይ ያረፈ መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ ለማስታወቅ እንወዳለን።

ብሄራዊ ጭቆናን አንሸከምም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!

The post “ብሔራዊ ጭቆናው የትግላችን መዘውር ሆኖ ይቀጥላል! ” – ድምጻችን ይሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

“ሳልሰማ ከሰደበኝ የነገረኝ አሳመመኝ” –ተስፋዬ ገ/አብና የሶሻል ሚዲያዎቻችን ነገር 

$
0
0

ይችን ሁለትና ሶስት ወራት የማስተር ፕላኑን ግርግር ተገን በማድረግ ኤርትራዊዉ የሻብያ ሰላይ ተስፋየ ገ/አብ መርዛማ ሀሳቦችን ዳግም ሊያዘንብብን ሲወራጭ እያየን ነው።እነ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻና አለማየሁ ከቀበሩበት መቃብር ዉስጥ ድንጋዮችን እየፈነቃቀለ፣ ያለበሱትን አፈር እየጠራረገ ወደ ሚዲያዉ ለመግባትና እኩይ ስራዉን ለመቀጠል ተፍ ተፍ እያለ ይገኛል። ይህ ግለሰብ ማንም እንደሚረዳዉ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ለምትባል ሀገር በተለይ ደግሞ ለአማራ ሕዝብ የመረረ ጥላቻ ያለው ሰዉ ነው።ይህንንም ጥላቻውን በገሀድ የሚናገርና ከዚህም ቀደም በሰራቸው ስራዎቹ ከባድ የሚባል ጉዳት ያደረሰ የሀገርና የሕዝብ ጠላት ነዉ።

(ተስፋዬ ገብረአብ)

(ተስፋዬ ገብረአብ)

እስኪ እንደመግቢያ ጥላቻ (Hatred) ምንድን ነዉ ?? ብለን እንደርደር።

ጥላቻ ማላት በጣም በመረረና ከመጠን ባለፈ ሁኔታ አንድን ነገር ያለመዉደድ ስሜት (deep and emotional extreme dislike) ነዉ ። በአጠቃላይ ሲታይ የጥላቻ መሰረታዊ ምንጮች ሁለት ናቸው። የመጀመሪያዉ አንደ ግለሰብ ላይ አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ የሆነ ከባድ በደል ሲፈፀም ፤ ለምሳሌ ጥረዉ ግርዉ ያፈሩትን ሀብትና ንብረት መዘረፍ ፣ በግዴታ መደፈር፣ በጣም የሚወዱትንና የሚሳሱለትን ሰው ላይ የግድያ ወንጀል ሲፈፀም የሚፈጠር ጥላቻ ነዉ። ሁለተኛው ነጮች Learned hatred የሚሉት በአስተምሮት የሚወረስ ጥላቻ ነዉ። ይህ አይነቱ ጥላቻ መሰረቱ እዉነት ወይንም ዉሸትም ሊሆን ይችላል።አባቶች በዘመናቸዉ የተፈፀመ ግፍ ነዉ የሚሉትን ፣ ወይንም በአባቶቻቸዉ ዘመን ተፈ ፅሞ ነበር ተብለዉ በዉርስ የተቀበሉትንና መወራረድ አለበት ብለዉ የሚያስቡትን ግፍ ለልጆቻቸዉ በትምህርት ያወርሳሉ።ልጆችም ከሚወዶቸዉ ወላጆቻቸዉ የወረሱትን የጥላቻ ዉርስ ከቻሉ በእነሱ እድሜ ለማወራረድ ይሞክራሉ ካልተቻለ ደግሞ እነሱም ለሚወልዶቸዉና ለሚወዶቸዉ ልጆቻቸዉ አዉርሰው ያልፋሉ።

ሌላዉ ጥላቻ (Hatred) አድማሱም ይለያያል። ለምሳሌ አንድ ግሰብ የሚጠላዉ ግለሰብን፣ ቡድንን ወይንም ቡድኖችን፣ ዘር (ነገድን)፣ ሀገር ሊሆን ይችላል።አንዳንዴ ደግሞ ቁሳዊ አካል ፣ባሕሪን ፣አመለካከትን እና የመሳሰሉትን አምሮ ጠልቶ መከራዉን የሚያይ ሰዉም ይኖራል። ከላይ በተዘረዘሩት በአንዱም ሆነ በሌላ ምክንያት የሚፈጠር የመረረ ጥላቻ በሽታ ነው። ከመጠን ያለፈ ጥላቻ ብስጭት፣ፍርሀትና ጭንቀት ይፈጥርና የሰው ተፈጥሮአዊ በሽታ የመከላከል አቅም በማዳከም ከፍ ሲሊም ጨርሶ በማጥፋት የበሽታዎች ቁንጮ ለሆነዉ ካንሰር (cancer) ለተባለዉ ገዳይ በሽታ መፈጠርና በአጭር ግዜ መስፋፋት ምክንያል ሊሆኑ ይችላሉ ይላሉ በመስኩ ያሉ ጠበብት። ለገሰ ዜናዊ የዚህ ተጠቂ ነበር።ለካንሰሩ መፈጠር አማራ ላይ የነበረዉ እጅግ የመረረ ጥላቻ ፣ ካንሰሩ በአጭር ግዜ (በአንድ ወር ዉስጥ ብቻ) የመጨረሻው ደረጃ ላይ እንዲደርስ ደግሞ አበበ ገላው በዓለም ፊት ያደረሰበት ማሸማቀቅ ከፍተኛ ሚና ነበረው።

ጥላቻ አመለካከትን የማዛባት አቅም አለው። በተፈጥሮ የአንድ ጤነኛ ሰዉ ጭንቅላቅ ዲዛይን(design) የተደረገዉ ጠንካራና አሳማኝ በሆኑ መረጃዎች ላይ እየተመሰረተ ጠቃሚና ችግር ፈቺ የሆኑ ሀሳቦችን እንዲያፈልቅና ዉሳኔዎችን እንዲያሳልፍ ነዉ።ችግሩ ይህንን የተፈጥሮ ሀብታችንን በመልካም ስነምግባርና በትምህርት ተንከባክቦ ፣ ኮትኩቶ የሚያበለፅገው ሀላፊነት የሚሰማው ቤተሰብ፣ማሕበረሰብና ተቋማት ያስፈልጉታል።ያ ሳይሆን ቀርቶ ህሌናን በዘር ከአባት ከሚወረስ ወይ ደግሞ ለአንድ የተወሰነ አላማ ሲባል ብቻ በሚፈጠር የውሸት ድርሰትን አንብቦ ጭንቅላትን በክፋትና በተንኮልን ሞልተን ካሳደግነዉ በጥላቻ ይታወራል። ጥላቻ አመለካከትን ያንሸዋርራል ። ከፍ ሲልም ደግሞ ከነ አካቴዉ ያጠፋና ጭንቅላት ግልብና ግብታዊ የሆኑ ድርጊቶች ላይ እንዲተጋ ይሆናል።

ወደ ዋናው ሀሳብ ልመለስ። አንድ ሰው ለአቅመ አዳም/ሔዋን ሲደርስ ለእርሱንም ሆነ ለቤተሰቡን ቀለብ መስፈሪያ ስራ መስራት ግድ ይለዋል።ጎልማሳው ተስፋዮ ገ/አብም እንደ ማንኛዉም ሰዉ ስራ አለው።ተቀጣሪነቱ ለአባት ሀገር ኤርትራ የደንነት ቢሮ ዉስጥ ሲሆን የስራ ድርሻዎቹ ሁለት ናቸዉ።

>> የመጀመሪያ ግዳጅ ለኦነግ ሰዎችና ደጋፊዎች መታገያ የሚሆን የፈጠራ ድርሰት እየደረሰ በሕዝቦች መካከል ጠላትነትን ማንገስ ነዉ። ከዛም አባት ሀገር ኤርትራ በምስራቅ አፍሪካ ጎልታ ትታይ ዘንድ ትናንሽና ደካማ ጎረቤት ሀገራት እንዲፈጠሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ።ይህንን ተልኮዉን ባብዛኛው አጥጋቢ በሚባል መልኩ ያገባደደዉ ይመስላል ። ይህ መርዘኛ እባብ በኢትዮጵያዊነትና በደራሲነት ዉስጥ ተደብቆ፤ በሀገርና በሕዝብ ላይ የሸረባቸዉ ሴራወቹ ነፍስና ስጋ ነስተዉ በአካል በመካከላችን ሜንጫቸዉን እያወናጨፉብን ነዉ። እነዚሁ ክፉ ቡድኖች “ሰዉ እና እንጨት ተሰባሪ ነዉ” በማለትም ከግለሰቦችም እድሜ በላይ ይኖሩ ዘንድ ቆሚ የጥላቻ ሀዉልት ተክለዋል።

>> ሁለተኛዉ ግዳጅ ዛሬ ዛሬ እንደ ዋና ሙያ አድርጎ የያዘ ስራ ደግሞ በተገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ አማራንና የአማራ የሆነዉን ሁሉ መዝለፍ፣ማሳነስና ማጥላላት ነዉ። ይህ ከይሲ የአማራ ጠላት በትምባሆና በአልኮል ከገለማ ሳምባዉ ዉስጥ የሚወጣዉን ፀያፍና መርዛማ ጠረኑን አማራን እንዲሸተዉ አድርጎ ነዉ የሚተነፍሰዉ። ይህንን ፀያፍ ጠረኑን ደግሞ ንፋስ ሆነው ተሸክመው በመላዉ ዓለም ለሚገኙ አማራ ወገኖችና ለአማራ ጠላቶች የሚያደሱለት ሚዲያዎች ሰሞኑን ተበራክተዋል።

ሚዲያን ካነሳሁ ዘንድ አንድ ትዝብቴን ልግለፅ። በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያንን መሰረት አድርገው የሚንቀሳቀሱ የአንዳንድ ሶሻል ሚዲያዎች ነገር ግርም ነው የሚለኝ። መችም እያንዳንዱ ሶሻል ሚዲያ ከቢዝነስነት ያለፈ አንዳች ዕራይና ግብ አለዉ ብየ ነዉ የማስበዉ። ዕራይና ግብ ደግሞ እንደየ ሶሻል ሚዲያ ባለቤቱ የተለያየ ሊሆን እንደሚችል እሙን ነዉ። ለምሳሌ የፓርቲ/የቡድን/ የድርጅት ልሳን ከሆኑ የፓርቲውን/የቡድኑን/ የድርጅቱን ዕራይ በሚያሳካ መልኩ ነዉ የሚንቀሳቀሰዉ ። ከየትኛውም ቡድን/ፖርቲ/ድርጅት ውጭ ሆነዉ ሀገራዊ አጀንዳ ካለዉ ደግሞ ለሀገር መፃሂ እድል ይጠቅማል በሚል ማእቀፍ ዉስጥ ሆኖ ይሰራል። ይህንን መሰል ሚዲያዎች በሕብረተሰቡ ዘንድ ያሉ የተለያዩ አስተሳሰቦችን በማንሸራሸር ትዉልዱ ጠቃሚ መረጃዎችን እንዲያገኝ የሚል ሰፉ ያለ ዕራዮ ይዘዉ ይንቀሳቀሳሉ። የሚዲያዉ ኤዲቶሪያ ቦርድም ስራዉ የሚሆነዉ በሚዲያዉ የሚተላለፈዉን መልክት በተቀመጠለት አቅጣጫ መሆኑን ለመከታተል ይሆናል ማለት ነዉ። ከዚህ አንፃር ስናየዉ አንድ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ ዘመን ሊሻገር የሚችል ከባድ ደባ የፈፀመን ግለሰብ ሊያስተናግድ የሚችል ኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ስም የሚንቀሳቀስ ሚዲያ ማየት እጅግ የሚደንቅ ነገር ነዉ።

እርግጥ ነዉ የዚህን መርዝ ግለሰብ ሀሳቦች ማስተናገድ “ሀሳብን በነፃነትና ያለገደብ መግለፅ” ከሚላዉ ዋና (basic) ከሚባሉት የሰዉ መብቶች ጋር እያነፃፀሩ የሚሞግቱ እንደሚኖሩ እገምታለሁ። አዎ ማንም ሰው በነፃነትና ያለ ገደብ ሀሳቡን የመግለፅ ሰባዊ መብት አለዉም ይገባልም። ነገር ግን አንድ መገደፍ የሌለበት ሀቅ አለ።ከአንዳንድ ከባድ ወንጀለኞች ላይ ሀሳባቸን የሚገልፁበትን መብት ብቻ ሳይሆን ሕይወታቸዉንም የመንጠቅ የሕግ አግባብ መኖሩን መርሳት አይገባም። በዓለም ላይ ባሉ አብዛኛ ሀገራት ዉስ እንደ ከባድ ወንጀል የሚወሰድና የወንጀለኛውን ሕይዎት እስከመንጠቅ የሚደርሱ ጥፋቶች መካከል አንዱና ዋናዉ በሀገር ላይ ክህደትን መፈፀም ነጮች treason የሚሉት ነዉ። ከፍተኛ ክህደት (High treason) ዉስጥ ከሚካተቱ ወንጀሎች አንዱና ዋናዉ ደግሞ የሚኖሩበትን ሀገር በመሰለል(spying) መረጃዎችን ለሌላ አካል ማቀበል የሚለዉ ነዉ። እንግዲህ ይህ ግለሰብ ይህንን ወንጀል መፈፀሙ በማያሻማ መረጃ እጅ ከፍንድ ( red hand) የተያዘ ወንጀለኛ ነዉ።ዛሬ ግለሰቡ በሚስጥር ሲሰራዉ የነበረዉን ሀገር የማጥፋት፣ ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ስራ በብርቱ ዜጎች ማንነቱ ተጋለጦ ፀሀይ የሞቀዉ ጉዳይ ሆኖል። የሀገርና የሕዝብ ፀር መሆኑ ተረጋግጦል። ይህ በሆነበት ሁኔታ የዚህን ግለሰቡ መርዛማ ሀሳቦቹን ለሕዝብ ጆሮ በማድረስ እየተባበሩት ያሉት ሶሻል ሚዲያዎች አላማቸው ምንድን ሊሆን ይችላል?? ብየ እራሴን ደጋግሜ ጠይቄ መልስ ማግኘት እቸገራለሁ።

እንደገናንወደ ዋናው ሀሳብ። የዚህ ግለሰብ ጥላቻ ከማንና ለምን የሚሉትን ሁለት ጥያቄዎች እንፈትሽ። ይህ ግለሰብ ከማን ጋር ነዉ ብለን ስናይ እንደ ሀገር ከኢትዮጵያና እንደ ሕዝብ ደግሞ አምርሮ የሚጠላዉ የአማራዉን ብሔር ነዉ። በመሰረቱ አንድን ሕዝብን ብሔር መጥላት ጤነኛ ጭንቅላት ካለው አካል ሰው የሚጠበቅ ነገር አይደለም። ጅልነትም ነዉ። አንድ ግለሰብ በተለያዩ ምክንያት ሌላዉ ሰው ወይን ቡድን ሊጠላ ይችላል። ቡድን ሊፈርስና ሊጠፋ የሚችል ነገር በመሆኑ ጥላቻዉም አብሮ ሊጠፋ ይችላል ተብሎ ይታሰባል። ግለሰብም ከሆነ ከአካባቢዉ ርቆ ሲሄድ ወይ ደግሞ በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ምክንያት ከጠይዉ በፊት ቀድሞ ካለፈ ጥላቻዉም አብሮ ይጠፋል። ጥላቻ ግን ከአንድ ብሔር ጋር ሲሆን እብደት ነዉ። ጠይዉ እንደ ግለሰብ የሚያደርሰዉ ጉዳት አይኖርም ባይባልም ሕዝብን ግን በጥላቻ ሆነ በሌላ ሀይል ማሸነፍ አይቻልም።

ሕዝብን በመጥላት ተስፋየ የመጀመሪያ ሰው አይደለም። ሂትለር በወቅቱ የነበሩ ወገኖችን አስተባብሮ በርካታ ሐይሁዶችን ገሏል ። ግለሰቡ አዳፋ ታሪኩን ለትዉልዶቹ አዉርሶ ሲሞት እስራኤላዊያን ግን ትላንትም እንደነበሩ ዛሬም በሰፊዉ አሉ ነገም ይኖራሉ። የኛ ሂትለር ለገሰ ዜናዊም በአላማ የሚመስሉትን አስተባብሮ ቀላል የማይባል አማራ ወገኖችን ጨፍጭፎል። እርሱም እንደ ብጤዎቹ አዳፋዉን ታሪኩን ትቶልን ለአማራ የነበረው ጥላቻ ነቀርሳ ሆኖ ታሪክ አድርጎታል።የአማራ ሕዝብ ግን ትላንት እንደነበረ በመከራ ዉስጥም ሆኖ ቢሆን ዛሬም አለ። ነገ ደግሞ የቀድሞዉ ሀያልነቱንና ክብርኑ አስመልሶ ይኖራል።

በመቀጠል እስኪ ይህ ግለሰብ ይህን ያህል የመረረ ጥላቻ የቆጠረዉ ለምንድን ነው?? ብለን ስንጠይቅ እኔ እስከማዉቀው ግለሰቡ በግሉ እንደ ሀገር በኢትዮጵያ ስምም ሆነ እንደ ሕዝብ በአማራ ደረሰብኝ የሚለው አንዳች በደለ ሲያሰማ አይታይም። ምናልባት በዚህ ዙሪያ የጠቀሰው ነገር ካለም የጋዜጠኛ ማስታዎሻ በሚለው መፀሀፉ ዉስጥ በጎጃሜዉ ሙሉጌታ ሉሌ የነበረዉንላይ የነበረዉን የተዛባ አመለካከት ነዉ። በአንድ ወቅት ታዋቂዉ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በሚመራ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዉስጥ ስራ ለመቀጠር ማመልከቻ በአካል አስገብቶ እንደነበር ፣ በሐሜት ደረጃ ያ ሊሰራበት የሚመኘው ቢሮ የጎጃሜዎች ቤት ነው የሚል የተሳሳታ ግምት እንደነበረዉ ፣ በኋላም ቢሮዉን ለመምራት አጋጣሚዉን አግኝቶ ሐሜቱ ውሸት መሆኑን ማረጋገጡን ማንበቤን አስታውሳለሁ።ከዚህ ዉጪ ከአማራ ጋር ያገናኘው የግል ታሪኩን በግሌ አላዉቅም። ያደገው ደግሞ በኦሮሞው ማሕበርሰብ አካባቢ በመሆኑና ዛሬም ድርስ እያጭበረበር ያለው ለኦሮሞዉን ማሕበረሰብ ተቆርቆሪ ነኝ በሚል ስሌት በበመሆኑ ያደገበትም ማሕበረሰብ የበደለው ነገር የለም ማለት ነው።

ሌላው ማህቀፍ ደግሞ እሱና ፀረ አማራዉ ኦነግ እንደሚሉት “ኦሮሞው በአማራው በመጨቆኑ” ለኦሮሞ ተቆርቆሪ በመሆኑ ይሆን እንዴ?? ብለን እንዳናስብ በነ አለማየሁእና ወልደሚካኤል መሸሻ የወጣው መረጃ የሚያሳየው ሌላ ነዉ። የግለሰቡ ዋናው አጀንዳው የኦሮሞዉ ማሕበረሰብ ጉዳይ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ይህንን ማሕበረሰብ የሚጠቀምበት በአባት ሀገር ኤርትራ ለተሰጠው ሀገር የማፍረስ አጀንዳዉ ብቻ መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ እንደውም ለኦሮሞው ማህበረሰብ ያለዉን ንቀት ነው የሚያሳየው።ስለዚህ የዚህ ግለሰብ ጥላቻው ከየት መጣ?? ለሚለው ሀሳብ መልስ ሊሆነን የሚችለዉ በህዉሃትና ሻብያ ደደቢት እና ሳህል በረሀ ዉስጥ ከተደረሰው ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ የውሸት ድርሳናት ውስጥ ብቻ ሆኖ እናገኛለን።ስለዚህ ግለሰቡ ውሸት ላይ ተመስርቶ ፤የፅሑፍ ክህሎቱን በመጠቀም ሀገር ዉስጥ በነበረበት ውቅት በህዉሃት እየታገዘ ከሀገር ከተባረረ በኋላ ደግሞ በኦሮሞው ኢሊቶች አይዞህ ባይነት ሀገር እንዲያፈርስና አማራን እንዲሰድብ መድረክ ተመቻችቶለት ሲንቀሳቀስ ቆይቶል። በመጨረሻም ከላይ በተጠቀሱት ግለሰቦች ብርቱ ጥረት የቁም ሞት እንዲሞት ተደርገ።ለበርካታ ወራቶች ምላሱን እንዲሰበስብና ከሚዲያዎች እንዲርቅ ሆነ ።ይኸዉ ይችን ሰሞን የታጠፈ ምላሱ ተዘርግቶ፣ የነጠፈው ብዕሩን ዳግም አንሰራርቶ መርዛማ ቅርሻቱን በአማራ ሕዝብ ላይ እያቀረሸ ነዉ።

ይህንን ሀሳብ እንዳነሳ ያደረገኝ በቅርቡ ግለሰቡ የበዕውቀቱ ስዩም ወጎች በሚል እርህስ በዘ አበሻ ላይ የለጠፈዉንና የበዉቀቱ ቀደምት ስራዎቹን ከኦሮሞ ማንነቱ ጋር ያያያዘበትን መጣጥፍ በመታዘቤ ነዉ። እዛ መጣጥፍ ዉስጥ የተወሰኑ የበውቀቱን ግጥሞች መርጦ አማራን ማንቆሸሽ በሚችልበት መልኩ ትንታኔዉን አስቀምጦል። አንዱን ግጥምና ትንታኔዉን እንደተቀመጠ ልቅዳ።

“በዕውቀቱ አያቱን ከተሸሸጉበት አውጥቶ ለነፃነት ከማብቃቱ በፊት በዚሁ ቁጭት የፃፋቸው የሚመስሉ ስንኞችን ማስተዋል ችዬ ነበር። ለአብነት በአንድ ግጥሙ ኦሮሞ – አማራንና ትግሬን በገፀባህርይነት ያመጣና እንዲህ ሲል ያላግጣል፣
በታሪክ ሜዳ ላይ
አሉላ ጎበና
ወንዱን አስከትለው – ሲገድሉ ሲሞቱ
አባ ገብረሃና
እርስዎ ባይኖሩ – ምን ይውጠው ሴቱ፧
ጨመረልኹ መሰል – ባባ ነፍሶ ፈንታ
እንደ አንደበትዎ – እንትንዎ መንታ
አንዱ ለቀን ሲሆን – አንደኛው ለማታ
“ባባ ነፍሶ ፈንታ” ማለቱ ባልቻ አባነፍሶ ስልብ ነበሩ ስለሚባል ሲሆን፤ “እንትንዎ መንታ” ማለቱ ደግሞ አለቃ ገብረሃናን እንደ ምላስዎ መሾል (የቀጣፊነት ችሎታ) ሁለት ብልት ይዘዋል ማለቱ ነው። ሌሎች ጦር ሜዳ ሲሞቱ እርስዎ ውሎና አዳርዎ ከሴት ጋር መዳራት ነው ማለቱ ነው። በዕውቀቱ እንዲህ በመረረ ሁኔታ ሊሳለቅ የቻለው ምን ተሰምቶት እንደሆን ባውቅ በጣም ደስ ባለኝ ነበር። በተለይ ገዢዎች ላይ ቅሬታና ቂም እየያዘ እንደመጣ የሚጠቁሙ ከጥቂት በላይ ስንኞቹን ታዝቤያለሁ። ”

ሁለት ነገሮችን ብዮ ሀሳቤን ልሰብስብ። የመጀመሪያዉ ይህ ከላይ የተቀመጠው ግጥምና የተሰጠዉ ማብራሪያ እዉነት ነዉ፣ የደራሲዉን ሀሳብ ይገልፃል ብለን መደምደም አንችልም ። ለምን ደራሲውን በዛሬዉ አይን አይተነው ባለማዎቃችንና ከአንደበቱ ባለመስማታችን። በሌላው ጎን ደግሞ አይ ይሄ የዚህ ከይሲ ሀሳብ እንጂ የገጣሚው ሊሆን አይችልም ብለንም መደምደም አንችልም። ለምን በእናትና በአባቱ እቅፍላይ ያደገ፣ በስነፅሁፍ ዉስጥ በርካታ አመታትን ያሳለፈና ለተዋቂነትም የበቃ፣ ከሶስት ሺህ በላይ የእድሜ ባለቤት የሆነችን ሀገር ታሪክ እበረብራለሁ ብሎ የደፈረ ሰዉ ፤ አንድም በህፃንነቱ ጎዳና ላይ ተጥሎ በማደጎነት እንዳደገ ፣ አንድም መመርመርና መመራመር እንደማይችል መሀይም ሰዉ ኦሮሞው ማንነቱን ፈልጎ ያገኘዉ ዛሬ በ 40 ዓመቱ ነው የሚለውን ቀልድ መቀበሉ ይከብዳልና ነዉ።

ሁለተኛዉ ነጥብ በግጥሙ ላይ የተቀመጠዉ ንፅፅር በራሱ ትርጉም የሚሰጥ አይደለም። ግለሰቡ እንደሚነግረን ገጣሚዉ ኦሮሞ አማራንና ትግሬን አወዳደር ብለን እንኮ ብንወስደዉ ፤ አሉላ ጎበናና ባልቻ የሚታወቁት የጦርሜዳ መኮነን በመሆን ሲሆን አለቃ ገብረሃና የሚታወቁት በቤተክርስቲያን ሊቅነታቸው፣ እንደ ገጣሚው በተረታ ተረታቸዉ ፣ በጨዋታ አዋቂነታቸዉ፣ በባለቅኔነታቸው በአጠቃለይ በደፍተራነታቸው ነዉ። ስለዚህ ዉድድሩ ሲጀመር አቻ ለአቻ አይደለም። በጦርሜዳዉ ግንባር አማራን ለመወከል ቢፈለግ ከላይ ንጉሱን ጨምሮ ከበርካታ አማራ የጦርሜዳ ጀግኖች አንዱን መምርጥ በተቻለ ነበር። እንደዉም በአግባቡ ለማስቀመጥ ከተፈለገ በዚህ ማህቀፍ ማወዳደሩ ከመጣ ከሌላዉ ወገን ከተጠቀሱት ዉጭ ፈልጎ ማግኘቱ ነዉ ከባዱ።

ማጠቃለያ
“መጥፎ ቁራኛ ያለ መቃብር አይለቅም” እንዲሉ አበዉ ይህ ግለሰብ ለአማራና ለኢትዮጵያ ያለዉ ጥላቻ ካንሰር ሆኖ እንደ መለሰ ዜናዊ እስኪወስድልን ድረስ ከኢትዮጵያም ሆነ ከአማራ ራስ ላይ እንደማይወርድ የታወቀ ነው። እስከዛች ሰሀት ድረስ ግን ቢያስ ሀሳቡን እንዳይሰራጭና ጥላቻው ብቻውን እንዲበላው ማድረግ የሚዲያዎች ሀላፊነት ነዉ ብየ ነዉ የማስበዉ። ከንደዚህ አይነት ክፋ ጭንቅላቶች የሚረጩ መርዞችን ወደ ሌላዉ ወገን ማዛመት በራሱ ሀላፊነት የጎለዉ ስራ ነዉ።

ግዜነዉ ደም መላሽ

 

The post “ሳልሰማ ከሰደበኝ የነገረኝ አሳመመኝ” – ተስፋዬ ገ/አብና የሶሻል ሚዲያዎቻችን ነገር  appeared first on Zehabesha Amharic.

በምስራቅ ሐረርጌ ፌደራል ፖሊስ ሁለት አርሶ አደሮችን ገደለ –በጉራዋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ተቃጠለ

$
0
0

east harerege

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት የ60 ዓመት አዛውንት በተገደሉበእት የምስራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ወረዳ ዛሬ ደግሞ 2 ገበሬዎች በፌደራል ፖሊሶች መገደላቸው ተዘገበ::

የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች እንዳሉት ማሃዲ ሳኒ እና ሳፊ ኢብሮ የተባሉት አርሶ አደሮች በፌደራል ፖሊሶች የተገደሉት ዛሬ በከተማዋ በተደረገ ህዝባዊ ተቃውሞ ነው::

በምስራቅ ሐረርጌ በተከሰተ ሕዝባዊ ተቃውሞ በርካታ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን አብዛኞች በህክምና ላይ እንደሚገኙ ታውቋል:: በዚሁ በጉራዋ ወረዳ ፌደራል ፖሊስ ትናንት እና ዛሬ የፈጸመውን ግድያ የተቃወሞ የአካባቢው ነዋሪዎች የፖሊስ ጽህፈት ቤትን ማቃጠላቸው ተሰምቷል:: ሰለፈኞቹ ፖሊስ ጣቢያውን ካቃጠሉ በኋላ እስረኞችን ለማስመለጥ መሞከራቸው ሲገለጽ እስረኞች ያምልጡ አያምልጡ ዘ-ሐበሻ ለማጣራት ያደረገችው ጥረት አልተሳካም::

በሌላ ዜና በም ዕራብ አርሲ የተነሳው የሕዝብ ተቃውሞ በኢዶ ከተማ ቀጥሎ ሕዝቡ ከፌደራል ፖሊስ ጋር ተፋጦ ይገኛል:: በተለይ የም ዕራብ አርሲ ግጭትን ወደ ዘር ግጭት ለማስፋት አንዳንድ ወገኖች ተቃውሞውን በመጠቀም እያደረጉት ያለውን ጥረት ይህን ትግል የሚመሩ ሰዎች ሊያስቡበት ይገባል የሚሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አሉ::

The post በምስራቅ ሐረርጌ ፌደራል ፖሊስ ሁለት አርሶ አደሮችን ገደለ – በጉራዋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ተቃጠለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የህወሓትን‬ አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ሄሊኮፕተር ይዘው ከሀገር የወጡት እነ ሳሙኤል ግደይ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው

$
0
0

ginbot 7

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ) ሳሙኤል ግደይ፣ ፀጋ ዘአብ ግደይ እና ቢልልኝ መኮንን የህወሓትን አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር በማብረር ከምስራቅ አየር ምድብ ድሬዳዋ በውሎ የጠፉት በ2007 ዓ.ም ሲሆን የህወሓት አገዛዝ የጦር ፍርድ ቤት የካቲት 4 2008 ዓ.ም በሌሉበት በሞትና እድሜ ልክ እስራት ቀጥቷቸዋል፡፡

የሄሊኮፕተሯ ዋና አብራሪ ሳሙኤል ግደይ በሞት ሲቀጣ ፀጋ ዘአብ ግደይ እና ቢልልኝ መኮንን የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸዋል፡፡
ከእነ ሳሙኤል ግደይ በፊትም በ1993 ዓ.ም ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ ኤል-39 ተዋጊ ጀት እያበረረ ከመቀሌ ተነስቶ ኤርትራ መግባቱ፤ መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬ እና መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ ኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር እያበረሩ ጅቡቲ ማረፋቸው የሚታወስ ነው፡፡ መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬና አብዮት ማንጉዳይ በጅቡቲ መንግስት ለህወሓት ተላልፈው ተሰጥተው የእድሜ ልክ እስራት እና የ15 አመት እስር ተፈርዶባቸው መቶ አለቃ አብዮት የእስር ጊዜውን ጨርሶ በመፈታቱ በአሁኑ ጊዜ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅሎ ኤርትራ በረሃ እንደሚገኝ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

የኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አዛዥ እና የበረራ አሰተማሪ የነበረው ሻለቃ አክሊሉ መዘነም ከአመታት በፊት ስርዓቱን በመቃወም ወደ ኤርትራ መጥቶ አርበኞች ግንቦት 7ን በመቀላቀል ትግል ላይ ይገኛል፡፡

The post የህወሓትን‬ አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ሄሊኮፕተር ይዘው ከሀገር የወጡት እነ ሳሙኤል ግደይ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው appeared first on Zehabesha Amharic.


ሰልፈኞች በቡልቡላ ከተማ የአላሙዲ ንብረት የሆነው የነዳጅ ታንከር አቃጠሉ

$
0
0

 

tank Trank 1

(ዘ-ሐበሻ) ንብረትነቱ የአላሙዲን የሆነው ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ንብረት የሆነው የነዳጅ ታንከር በኦሮሚያ ክልል በቡልቡላ ከተማ ተቃጠለ::

እንደምንጮች ገለጻ በኦሮሚያ የወርቅ ማዕድኖችን እና የተለያዩ የሕዝብ ንብረቶችን ወደራሱ አስገብቷል ተብሎ ተቃውሞ የቀረበበት የአላሙዲን ንብረት በሆነው ሜድሮክ ኢትዮጱያና በሕወሓት አስተዳደር ሥር ያሉትን ንብረቶች ሁሉ ሕዝቡ እንዳይጠቀምና ከአካባቢውም ጠራርጎ እንዲያስወጣቸው በቀረበው ጥሪ መሠረት በተለያዩ ቦታዎች እርምጃ ሲወሰዱ ቆይተዋል::

በትናንትናው ዕለትም እንዲሁ ንብረትነቱ የትራንስ ኢትዮጵያ የሆነ ቦቴ የተቃጠለ ሲሆን በዚያው ምሽት በቡልቡላ ከተማ ሰልፈኞች የአላሙዲን የነዳጅ ታንከር መቃጠሉን የተሰራጩት ዜናዎች አስታወቀዋል::

በኦሮሚያ የሚገኙ የሕወሓት የንግድ ተቋማትና እንዲሁም የሼህ መሀመድ አላሙዲ ንብረት የሆኑ ድርጅቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ከስር ዓቱ የደህንነት ተቋማት ት ዕዛዝ እንደደረሳቸው የሚያስታውቁት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በተለይም በአሁኑ ወቅት መንግስት ለአላሙዲ ድርጅቶች በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል::

The post ሰልፈኞች በቡልቡላ ከተማ የአላሙዲ ንብረት የሆነው የነዳጅ ታንከር አቃጠሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሞጋቾች ተከታታይ ድራማ ክፍል 59…

ከአነጋገር ይፈረዳል ከአያያዝ ይቀደዳል –ጥላሁን ዛጋ

$
0
0

ጥላሁን ዛጋ /fikireyohanis@yahoo.com

የአደባባይ ሰው የሚባለው፣ በአንድም በሌላም መልኩ ራሱን ለማህበረሰብ እይታ ገሃድ ያወጣ አኗኗሩ፣ አዋዋሉና አነጋገሩ በማህበረሰቡ ዘንድ በአዎንታዊም ይሁን አሉታዊ መንገድ ተጽእኖ ሊፈጥር የሚችል ግለሰብ ማለት ነው። አንድን ሰው የተለያዩ  ኩነቶች አደባባይ ያወጡታል፣ ከነዚህም ጥቂቶቹና ዋናዎቹ ሊባሉ የሚችሉት ኪነ ጥበብ፣ ፖለቲካና የቴክኖሎጂ ፈጠራ /ሌሎች ካሉ ጨምሩባቸው/ ናቸው። በነዚህና በመሳሰሉት ዘርፎች በማህበረሰቡ ዘንድ ውስንም ይሁን ጉልህ ድርሻ ያላቸው ሰዎች፣ እንዲህና እንዲያ ብለዋል እየተባለ ንግግራቸውና አባባላቸው ለሌሎች ማጣቀሻ እየሆነ ይቀርባል፤ ሌላው ቀርቶ የሚበሉትና የሚጠጡት እየተነገረ፣ እነሱን መከተል ልማድ ነው።

አንድ ወቅት ግሩም ኤርሚያስ የተባለ አርቲስት “በጭስ ተደብቄ“ የሚለውን ወጥ ሲኒማ በዋና ገጸ ባህሪ ለመስራት የሄደበት መንገድ ለብዙዎች መነጋገሪያ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። አርቲስቱ የአደንዛዥ እጽ ሱሰኛ የሆነውን ገጸ ባህሪ ለመጫወት እጹን ከሚወስዱ ሰዎች ጋር ብዙ ጊዜ እንዳሳለፈና እጹንም እንደሞካከረ ሲነገር፣ አድናቂዎቹን እዚህና እዚያ ከፍሎ ለወራት ሲያነታርክ እንደነበር አስታውሳለሁ።

ይህ አደንዛዥ እጽ አሁን አሁን በተለይ በመዲናዋ አዲስ አበባ እንደፋሽን ከተያዙ ጎጂና አውዳሚ ልምዶች እንደአንዱ ሆኖ በሱሱ ተጀንጅነው በየመንገዱ የምናያቸው በርካታ ወጣቶች ቢኖሩም እንደዚያን ሰሞን መነጋገሪያ የሆነበትን ጊዜ ግን አላስታውስም። የሆነ ሆኖ አርቲስቱ እንዲህ አደረገ የተባለው ዜና ግን ባደባባይ ብዙዎችን አነታርኳል፣ ምክንያቱም በኪነ ጥበቡ ዘርፍ የራሱ የሆኑ አድናቂና ተከታዮችን በማፍራት ራሱን ለአደባባይ በማብቃቱ ነው።

የዛሬ ስንት ዓመት ግድም እንደሆነ አላስታውስም፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በዋልታ ኢንፎርሜሽን ስቱዲዮ Exclusive ቀርቦ ስለቤተሰብ ህይወቱ ተጠይቆ የሰጠውን መልስ እዚህ ላይ ማምጣቴ የላይኛውን ሃሳብ ያበረታዋል፣ ከጋዜጠኛው ጋር ሌሎች ብዙ ነገሮችን አንስተው ከጣሉ በኋላ ሃዘን፣ ሰርግና የመሳሰሉት ማህበራዊ መስተጋብሮቹን በተመለከተ ሲጠየቅ እምብዛም እንደሆነና፣   እንዲህ ያሉት መስተጋብሮች በጥቂት በተለይም በቅርብ ጓደኞችና ቤተሰቦች ብቻ የተወሰነ እንደሆነ ተናግሮ፣ በነዚህ አካባቢዎች ላይ በሚነሱ ጨዋታዎችና ወጎች እንደልብ እንደማያወጋና “ቀልድ እንኳ ቢያምረኝ . . . አምሮኝ ይቀራል እንጂ . . . መቀለድ አልችልም“ ምክንያቱም እንዲህና እንዲያ ብሎአል እየተባለ በህዝቡ ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ ቀላል አይሆንም፣ አንዳንዴም ልቅሶ ቤት ያወራከው እንደድርጅት አቋም ተደርጎ ሲወራ ዞሮ ይደርስሃል፣ ብሎ ሲናገር ሰምቻለሁ።

አንድ ሌላ ምሳሌ ልጨምርና በቀጥታ ወደዛሬው የጽሁፌ ዓላማ ላምራ . . .  ወቅቱ እኤአ በ1950ዎቹ ነበር፣ ከሮዛሪዮ አርጀንቲና ተነስቶ ወደሰሜናዊ ላቲን አሜሪካ ሃገራት በማቅናት በቺሊ፣ ቦሊቪያ፣ ጓቲማላና ኩባ ህዝቦች ላይ የካፒታሊስቱ በዝባዦች የሚሰሩትን ኢኮኖሚያዊ ሸፍጥ የታዘበው፣ ጀብደኛው አብዮተኛ ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ . . . ከወጣበት ሳይመለስ ነበር ሜክሲኮ ድንበር ላይ ተሰባስበው፣ በካፒታሊስቶቹ ምእራባውያን የሚደገፈውንና ለብዝበዛቸው ህጋዊ ከለላ የሚሰጣቸውን የኩባ አምባገነናዊ አገዛዝ ፉልጌንቾ ባቲስታን ስርወ – አገዛዝ ለመገርሰስ በቁጥር 80 ከሚሆኑና በፊደል ካስትሮ ከሚመሩት የጉሬላ ተዋጊዎች ጋር የተቀላቀለው።

በጀብደኝነቱ፣ በአንባቢነቱ፣ በአብዮተኛነቱና በጸሃፊነቱ በብዙዎች ዘንድ ስሙ የናኘው ቼ . . . እሱ በሚመራቸው የጉሬላ ግንባሮች ላይ የሚፈጽማቸው ጀብዱዎችና ሌሎች ወጣ ያሉ ተግባራት፣ ካስገኙለት እውቅና አንጻር እሱን ለመምሰልና እንደሱ ለመሆን የሚጥሩ በርካታ ሰዎችን በየጎዳናው ላይ ማየት የተለመደ ሆኖ ነበር። የሱን ዓይነት ኮፍያ፣ እንደሱ ዓይነት ቄንጠኛ የሲጋራ አያያዝ፣ እንዲሁም እንደሱ ዓይነት አንባቢና ጸሃፊ ለመሆን የሚሞክሩ “የቼ ደቀመዛሙርት“ የሚባሉ ፋኖዎች ነበሩት።

ቼ ጉቬራ በተለይ ከባቲስታ ደህንነት ቢሮ በሚስጥር ለሚላኩ ሰላዮች አንዳች ርህራሄ ያልነበረው ፍጹም ጨካኝ እንደሆነ ይታወቃል፣ የቼ ደቀመዛሙርትም እንዲሁ ከመንፈስ አባታቸው ያዩትንና የሰሙትን ለመድገም ሲታትሩ ማየት የተለመደ ዓይነት /Fashion/ ነበር። እጅግ ብዙ ቁጥር ባላቸውና ከዋለበት ውለው ካደረበት አድረው የህይወቱን ልምድ ከቀሰሙት ደቀመዛሙርቱ ባሻገር ሌሎች በብዙ ሚሊዮን በሚቆጠሩ ወጣት ጀብደኞች ላይ ያሳደረው ተጽእኖ ቀላል አልነበረም፣ የቼ ቄንጠኛ የሲጋራ አያያዝ፣ የኮፍያ አደራረግና፣ ቄንጠኛ ሞሎቶቭ ኮክቴል ቦምብ አጣጣልን በወቅቱ የነበሩ ወጣቶች በየአካባቢው ሲለማመዱት ማየት የተለመደ ነገር ነበር።

እንግዲህ እሳቸው እንዳሉት ብለን ወደቀደመው ነገራችን ስንመለስ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት . . . አዎንታዊም ይሁን አሉታዊ ተጽእኖ ያላቸው በተለይም የአደባባይ ሰዎች ናቸው የሚባሉት ግለሰቦች ተግባራቸውና ንግግራቸው ማህበረሰቦች ላይ ተጽእኖ ማሳረፉ ሃቅ ነው፣ ልክ የዛሬ ሁለት ዓመት ግድም እንደተከሰተችው “የሜንጫ“ ታሪክ ማለት ነው።

አሁን አሁን የሃገሪቱ ስስ ብልት ሆኖ አስታምመው ካልያዙት  እንደምርቅዝ ቁስል እዚም እዚያም በሚለበልበው የፖለቲካችን ዓውድ፣ ባልተገራ አንደበታችን የምንናገራቸው ቃላትና ዓረፍተ ነገሮች ሲውል ሲያድር ቆምንለት ለምንለው ስብስብ ብቻ ሳይሆን እኛንም /ተናጋሪዎቹን/ ጭምር ዋጋ እንዳያስከፍለን መጠንቀቅ ብልህነት ብቻም ሳይሆን ከሚመጣው አደጋ ማምለጫ መንገድም ጭምር ነው።

“አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል“ እንዲሉ . . . ንግግራችን የእኛነታችን ነጸብራቅ፣ የአስተሳሰባችንም ውጤት ነው፣ በተለይም በፖለቲካው ንፍቅ ላይ ታች የምትሉ ወገኖች የአንደበቶቻችሁ ቃላቶች በአንድም በሌላ፣ በጥቂቱም ይሁን በብዙሃኑ ላይ አርፈው በበጎም ይሁን በክፉ ጫና መፍጠራቸው እሙን ነው፣ ስሜት ለመቀስቀስ ብለን በስሜት በምንናገራቸው ንግግሮች እንዳይፈረድብን፣ ከአያያዛችን ደካማነት የተነሳም እንዳይቀደድብን ጥንቃቄ ማድረጉ የነገ ሳይሆን የዛሬ ይልቁንም የአሁኗ ሰዓት ስራችን መሆን አለበት። እኔ ያለሁበት አካባቢ 100% እንደዚ ነው፣ እኔ ያለሁበት ደግሞ 80% እንደዚያ እያሉ፣ አጓጉል የሆኑና ምናልባትም ውለው አድረው ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጠንቅ የሚያመጡ እሰጥ-አገባዎች ሜዳ ላይ መገኘቱ፣ ምርኮውን ለገዢዎች ዳረጎት ከማቅረብ የዘለለ ፋይዳ የለውም።

ሰሞኑን እዚም እዚያም ተቃጠሉ የተባሉት አብያተ-እምነቶች ጉዳይ የሜንጫዋ ግብዝ ታሪክ ድግምት ላለመሆኑ አስረጂ የለንም፣ በተለይ ደግሞ ትናንትናና ከትናንት በስቲያ በአርሲና መሰል የኦሮሚያ አካባቢ የሆነው፣ አድጦንም ይሁን ሆን ብለን የተናገርነውን ውጤት እያየን እንደሆንስ ማን ያውቃል ? ? ? ፖለቲከኞች ነን ካልን፣ ይህንና ያኛውን ማህበረሰብ እንወክላለን ካልን፣ ጥቂትም ይሁን ብዙዎችን ወክለን ከፊት መስመር /ከፊት ለፊት/  ቆመናል ካልን፣ ለራሳችንም ይሁን ቆመንለታል ላልነው ማህበረሰብ ስንል ንግግራችን የታረመ፣ ተግባራችን ሃላፊነት ያለበት ሊሆን ይገባዋል፣ አልያ ግን  “አንደበት እሳት ነው“ እንደተባለው፣ ወላፈኑ ለእኛም /ለተናጋሪዎቹ/ ለሌሎችም መትረፉ አይቀርም . . .  “ከአነጋገር ይፈረዳል፣ ከአያያዝ ይቀደዳል“  . . . ነውና።

comment pic

 

The post ከአነጋገር ይፈረዳል ከአያያዝ ይቀደዳል – ጥላሁን ዛጋ appeared first on Zehabesha Amharic.

ብሔራዊ ጭቆና የትግላችን መዘዉር ሆኖ ይቀጥላል! |የሳዲቅ አህመድ የቪዲዮ ዘገባ

$
0
0

ህወሃት መራሹ መንግስት ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማሳሳትና ለማከፋፈል፤ጥቅሙን አስከባሪ በሆነ ጋዜጣ ላይ ያወጣዉን የሐሰት መረጃ አስመልክቶ ድምፃችን ይሰማ ያወጣዉ መግለጫ በድምጽና በቪድዮ ቢቢኤን እስቱዲዮ ዉስጥ ተቀናብሯል። መረጃዉን በማየት፣በማዳመጥና ለሌሎችም በመላክ ሐላፊነቶን ይወጡ።


ብሔራዊ ጭቆና የትግላችን መዘዉር ሆኖ ይቀጥላል! | የሳዲቅ አህመድ የቪዲዮ ዘገባ

The post ብሔራዊ ጭቆና የትግላችን መዘዉር ሆኖ ይቀጥላል! | የሳዲቅ አህመድ የቪዲዮ ዘገባ appeared first on Zehabesha Amharic.

የካሩቱሪ ቁጣና የህንድ ሃያልነት በኢትዮጵያ – ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የጸሐፊው ማስታወሻ፡ ይህንን ትችት የጻፍኩት በካሩቱሪ እና በዘ-ህወሀት መካከል በጋምቤላ የመሬት ስምምነት ውዝግብ ላይ እየተካሄደ ያለው የሕግ ጉዳይ የሚያሳስበኝ በመሆኑ ምክንያት አይደለም፡፡ ወሮበላ ዘራፊዎች እና ከወሮበላ ዘራፊዎች ጋር የሚነግዱ አካሎች የገቡበትን ው

ዝግብ በሰላማዊ መንገድ ቢፈቱት ወይም ደግሞ ባይፈቱት ጉዳዬ አይደለም፡፡

ሆኖም ግን በካራቱሪ-ዘ-ህወሀት የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አጋጣሚ እንደምታ የደረሰው የውድቀት ቀውስ ጥልቅ በሆነ መንገድ ያሳስበኛል፡፡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች የካሩቱሪ ፕሮጀክት በጋምቤላ ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን በሚል ስሌት ከመሬታቸው በኃይል ተፈናቅለዋል፣ እንዲሰፍሩ እና በ”መንደር”  እንዲሰባሰቡ ተደርገዋል፡፡ እራሳቸውን የቻሉት አነስተኛ አምራች ገበሬዎች እና የአርብቶ አደሩ ማህበረሰቦች ከይዞታቸው እንዲነቀሉ እና ወደ አስከፊ ድህነት ውስጥ እንዲገቡ ከተደረጉ በኋላ የምግብ እርዳታ ተመጽዋች  በመሆን ኑሯቸውን እንዲገፉ ተገደዋል (ለማኝ እንዲሆኑ ማለት) ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የካሩቱሪ ፕሮጀክት በመውደቁ እና የማይቀጥል መሆኑ በመታመኑ ከጋምቤላ ዘለቄታዊ በሆነ መልኩ እንዲባረሩ ተደርገው የነበሩት ዜጎች በአሁኑ ጊዜ ያላቸው ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው? በካሩቱሪ ፕሮጀክት ምክንያት ከይዞታ መሬታቸው በኃይል ተፈናቅለው ለነበሩት ዜጎች ምን ዓይነት የመፍትሄ እርምጃዎች ይወሰዳሉ፣ ወይም ደግሞ እነዚህ ሰዎች እና የስነ ምህዳር ውድመት የደረሰበት አካባቢ እንደገና እንዲያገግም ለማድረግ ምን የተወሰዱ እርምጃዎች እና የታቀዱ ነገሮች አሉ? ለወደፊት በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለሚያፈስሱ የውጭ ባለሀብቶች የከሰረው እና በቀውስ ባህር ውስጥ ዋኝቶ የወጣው የካሩቱሪ ፕሮጀክት ምን ዓይነት አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ሊያስከትል ይችላል?

በዚህ ትችት በጋምቤላ የቁማር ጨዋታ ላይ ካሩቱሪ እና ዘ-ህወሀት ባጣመሙት እና በገመዱት የሕግ መረብ ላይ ከበርካታ ጉዳዮች መካከል ጥቂቶችን ብቻ አመላክታለሁ፡፡

“እስኪ ትንሽ ንካኝ፣ ከዚያ በኋላ የሕንድን ኃያልነት ታያለህ”

The Wrath of Karuturi and the “Power of India” in Ethiopiaበቅርቡ ለሳይ ራማክሪሽና ካሩቱሪ በተደረገለት ቃለ መጠይቅ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን(ህወሀት) በቀጥታ በሚገዳደር መልኩ በንዴት በገነፈለ ስሜት “እስኪ ትንሽ ንካኝ ከዚያ በኋላ የሕንድን ኃያልነት ታያለህ” በማት አውጇል፡፡ ይኸ የወሮበላ ንግግር ትንሽ ብትነካኝ ግንባርህን ነድዬ እጥልሀለሁ ማለቱ ነውን? የማፊያ ዓይነት ስሜትን የሚያንጸባርቅ ንግግር ነው፡፡

ሳይ ራማክሪሽና ካሩቱሪ የካሩቱሪ ግሎባል ኃላፊነቱ የተወሰነ (Karuturi Global Ltd.) እና እራሱን የዓለም የጽጌረዳ አበባ ንጉስ አድርጎ የሰየመው እንዲሁም “የጋምቤላ አንበሳ” ነኝ የሚለው ድርጅት መስራች እና ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር እንዲህ በማለት አምባርቋል፣ “በኢትዮጵያ የንግድ እርሻ/commercial farming ፈጥሪያለሁ እንዲታወቅም አድርጊያለሁ…በውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች የሚከናወን የንግድ እርሻ የወደፊት ታላቅ የኢንቨስትመንት አማራጭ ተደርጎ አይታሰብም ነበር፡፡ ሆኖም ግን ካሩቱሪ ይህንን ተግባራዊ ሲያደርግ የመጀመሪያው ነው፡፡“

ወይ ጉድ! ካሩቱሪ እንደ አቡጀዲ እየተቀደደ ነው ወይም ደግሞ ጥንቃቄ የተመላበት ንግግር እያደረገ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ በንጉሱ ዘመን ጊዜ የንግድ እርሻዎቸ/commercial farms ይካሄዱ ነበር፡፡

ፕሮፌሰር ኤድመንድ ኬለር፣ “አብዮታዊት ኢትዮጵያ፡ ከአገዛዝ ወደ ሕዝባዊ ሬፐብሊክ“ በሚል ርዕስ በጻፉት መጽሐፋቸው ውስጥ ገጽ 127 ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አስፍረዋል፡

“አጼ ኃይለ ሥላሴ የልማት ሂደትን ከላይ ለመጀመር በማሰብ ዘርፈ ብዙ የሆኑ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን በመንደፍ በስራ ላይ አውለው ነበር፡፡ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች/manufacturing industries እና ለንግድ እርሻዎች/commercial agriculture የተለዬ ትኩረት በመስጠት በተለይ ከውጭ ሀገር የሚመጡትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በሀገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት/import substitution ዓላማ በማድረግ ምርትን ለማሳደግ ጥረት አድርገዋል…የአጼ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ የንግድ እርሻውን ከፊውዳሉ የምርት ግንኙነት እና መዋቅር ውጭ በማድረግ ለውጥ ለማምጣት አልነበረም ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት፣ ሆኖም ግን በአርሶ አደሩ ላይ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ጉዳት እና አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ እውነት ነው፡፡ የፊውዳሉ ስርዓት ለለውጥ እንቅፋት ስለነበረ ንጉሱ የመጣው ይምጣ በማለት ለንግድ እርሻው ስኬታማነት እስከ መጨረሻው ገፍተውበታል፡፡ ንጉሱ ከዚያ ማግኘት የነበረባቸውን አግኝተዋል፡፡ ምናልባትም ያንን ለማስፈጸም ቀናት አጥረውባቸዋል፣ ችግሩን በአንድ ምት ለመምታት ዝግጁነቱ አልነበራቸውም፡፡“

ስለሆነም የንግድ እርሻን በተመለከተ ዘ-ህወሀትም ሆነ ካሩቱሪ ከአጼ ኃይለ ሥላሴ ጋር ምንም መፎካከር አይችሉም፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች በእነዚህ ታሪኮች ላይ እውነተኛ እና የማያወዛግብ እውነታን እንዲይዙ እፈልጋለሁ፡፡

እጅግ በጣም በተጋነነ እና ሳቢነት ባለው ዝቅተኛ “የመሬት ኪራይ ስምምነት” በግብርና እና በገጠር ልማት ሚኒስቴር እና በካሩቱሪ የግብርና ምርቶች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት/Karuturi Agro Products Plc መካከል በተደረገ የመሬት ኪራይ ስምምነት መሰረት ካሩቱሪ በረዥም ዕቅድ የመሬት ሊዝ (ኪራይ) ሌላ መጠባበቂያ 200,000 ሄክታርን ታሳቢ በማድረግ 100,000 ሄክታር ተረከበ፡፡ ተግባራዊ ሆኗልን?

በዘ-ህወሀት እና በካሩቱሪ መካከል በጋምቤላ ባደረጉት የመሬት ኪራይ ስምምነት መሰረት በአሁኑ ጊዜ አወዛጋቢ የሆነ የሕግ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ካሩቱሪ እየተከራከረ ያለው በውስጠ ተዋቂነት ስምምነቱ ዋጋ ያለው ከመሆኑ ጋር ባለው ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ከዚህም በተጨማሪ ስምምነታቸውን መተርጎም ስለሚችሉት የህግ መሳሪያዎች ባህሪ በማንሳት ዘ-ህወሀትን በመሞገት ላይ ይገኛል፡፡

ካሩቱሪ ከዘ-ህወሀት ጋር የሊዝ ስምምነት እንዳለው ይናገራል፡፡ የዘ-ህወሀት ሰነድ በበኩሉ ካሩቱሪ “የመሬት ኪራይ” ስምምነት አለው ይላል፡፡

ሸፍጡ የበለጠ እየተወሳሰበ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ እንደ ካሩቱሪ ከሆነ ሁለት የተለያዩ ዓይነት የሊዝ ስምምነቶች አሉ፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) ካሩቱሪ ከጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ጋር 300 ሺ ሄክታር መሬት እንደሚረከብ የሚገልጸው እናት ሰነድ ስምምነት ሲሆን፣

2ኛ) ሁለተኛው እና ሌላው ስምምነት ደግሞ “100 ሺ ሄክታር መሬት ለማረስ እረከባለሁ፡፡ ከዚያም 100 ሺ ሄክታሩን መሬት አርሸ የምጨርስ ከሆነ እና ከፈለግሁ ሌላ 200 ሺ ሄክታር ተጨማሪ ማግኘት እችላለሁ“

ካሩቱሪ እናት ሰነዱ የጋምቤላ ስምምነት እንጅ የግብርና ሚኒስቴር (ከላይ የተጠቀሰው የመሬት ኪራይ ስምምነት) ቅጅ አይደለም ይላል፡፡

መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉንም መሬት ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡ (ግን የመንግስትነቱን ስልጣን ተቆጣጥሮ የሚገኘው ማን ነው? ማለቴ ለመሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘውን መሬት በሙሉ ጠቅልሎ በመያዝ የመሬት ከበርቴ ሆኖ የሚገኘው ማን ነው? በኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስትነቱን ስልጣን ተቆጣጥሮ የሚገኘው ማንም ቢሆን ኢትዮጵያንም በባለቤትነት መያዝ ይችላል ማለት ነውን?

በአሁኑ ጊዜ ባለው ውዝግብ በዘ-ህወሀት የበላይ ተቆጣጣሪነት የሚመራው መንግስት እና የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት በአንድ ጊዜ የመሬት ባለቤትነቱ የእኔ ነው የእኔ ነው በማለት ሁሉቱም የመሬት ባለቤትነት የይገባኛል ጥያቄ በማቅረብ አንዱን ዓይነት መሬት ለካሩቱሪ ሰጥቻለሁ በማለት ላይ ናቸው፡፡ ከህገ መንግስቱ እና ከኮንትራት ስምምነት አንጻር የትኛው የመሬት ስምምነት ነው በሕግ ተቀባይነት የሚኖረው?

ካሩቱሪ ከዘ-ህወሀት ያገኘው የመሬት ኪራይ ከሆነ ዘ-ህወሀት የመሬት ከበርቴ ነው ማለት ነው? ካሩቱሪ እንዳለው ከጋምቤላ ክልላዊ መንግስት የሊዝ ስምምነት ካለው የሕግ ጥያቄ በማስነሳት የሊዝ ስምምነት ሰጭ እና የሊዝ ስምምነት ተቀባይ የሆኑት ተዋንያን ፍጹም የሆነ ልዩ ልዩ ዓይነት ግዴታዎች፣ ጥቅሞች እና ክልከላዎች ይኖሯቸዋል ማለት ነው፡፡

የካሩቱሪን መብት እና ግዴታዎች ለመቆጣጠር የሚያስችሉት የመቆጣጠሪያ ህጎች የዘ-ህወሀት ወይም ደግሞ የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ስምምነት ሁለቱም ናቸውን? ወይስ የትኛው?

ዘ-ህወሀት የመሬት ኪራይ ስምምነት በመጀመሪያው አንቀጽ በመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር ላይ የሰፈረው እንዲህ በማለት ይገልጻል፣ “ይህ የመሬት ሊዝ ስምምነት ተደረገ…ሆኖም ግን “የመሬት ኪራይ ስምምነቱ” እንዲህ ተከፋፍሏል “የመሬት ኪራይ ኮንትራክቸሯል ስምምነት…“

ዘ-ህወሀት ያረቀቀው “በግብርና እና በገጠር ልማት ሚኒስቴር እና በካሩቱሪ አግሮ ኢንዱስትሪ ፕሮዳክትስ ፒኤልሲ መካከል የተደረገ የመሬት ኪራይ ኮንትራክቸሯል ስምምነት ወይስ ደግሞ የመሬት ኪራይ ኮንትራት ነው?“

ያም ሆነ ይህ በመጨረሻ ላይ ጉዳዩ ነጻ ወደሆነ የፍትህ አካል ሲቀርብ  ስምምነቱ ሊዝ ወይም ደግሞ የመሬት ኪራይ የሚሉት ነገሮች በካሩቱሪ እና በዘ-ህወሀት መካከል ላለው ውዝግብ ዋና ወሳኝ ነገሮች ሆነው የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

የጎሳ ፌዴራሊዝም መዋቅር (ማጭበርበር አላልኩም) እየተባለ እንደሚጠራው የፌዴራል መንግስት ወይም ደግሞ ክልላዊ መንግስታት በክልላዊ መንግስት ስር ያለን መሬትን የመያዝ ቅድሚያ የመብት ተጠቃሚነት ዕድል ይኖራቸዋልን?

ካሩቱሪ በቀጣይነት እንዲህ የሚል ጥያቄ አቅርቧል፣ “ስምምነቱ እየተረቀቀ በነበረበት ጊዜ 300 ሺ ሄክታር እንዳይሆን ስለምናቸው ነበር፣ ሆኖም ግን በማስገደድ የተጠቀሰውን ብዛት እንዲሰፍር አደረጉ፡፡“

ካሩቱሪ ከዚህም በተጨማሪ 300 ሺ ሄክታር ሳይሆን 10 ሺ ሄክታር ብቻ ይፈልግ  እንደነበር ግልጽ አድርጎ ነበር፡፡

ካሩቱሪ የመሬት ኪራይ ስምምነቱን ፈርሞታል ወይስ ደግሞ ኃይልን በመጠቀም ሊዝ እንዲፈርም ተደርጓል?

የዘ-ህወሀት-ካሩቱሪን የመሬት ኪራይ ወይም የሊዝ ስምምነቱ ሰነድ በአንክሮ ሲታይ ወጥነት የሌለው፣ የተወሳሰበ እና የተጣመመ የሕግ ግንኙነት እንዳለው ያሳያል፡፡

ዘ-ህወሀት ከካሩቱሪ ጋር የፈረመውን ስምምነት ሰረዘው ምክንያቱም ካሩቱሪ ከሚጠበቀው በታች 1200 ሄክታር ብቻ ነው ያለማው፡፡ የዘ-ህወሀት የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር የሆነው ጌታቸው ረዳ ዘ-ህወሀት ለካሩቱሪ ለረዥም ጊዜ ሲያራዝምለት ቆይቷል ብሏል፡፡

ረዳ የስምምነቱን መሰረዝ በሚከላከል መልኩ በካሩቱሪ ላይ በመሳለቅ እንዲህ ብሏል፣ “የሕግ አማራጭ አለው ብሎ የሚያስብ ከሆነ ይሞክረው፡፡“ (ረዳ በካሩቱሪ ላይ በመሳለቅ የሕግ አማራጭ አለው ብሎ የሚያስብ ከሆነ ይሞክረው ሲል ካሩቱሪ ወደ ይስሙላው የዘህወሀት የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ይዞ የሚሄድ መስሎት ከሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ የዘ-ህወሀት ስምምነቱን የመሰረዝ ትረካ ትንሹንም መስፈርት የሚያሟላ አይደለም፡፡ ዘ-ህወሀትን ከማመኔ በፊት ፒኖክዮን አምናለሁ፡፡ እኔ እስከማስበው ድረስ ”TPLF   “ በሚለው አህጽሮተ ቃል  “LF“ የሚሉት ሁለት ፊደሎች Lie Factory/የውሸት ፋብሪካ የሚለውን ትርጉም ይሰጣሉ፡፡ ተወደደም ተጠላም እኔ እንዳለ እውነታውን እናገራለሁ!

ስድስት ዓመታት ወይም ደግሞ ከዚህ ባነሰ ጊዜ ውስጥ የዌልስን ሀገር ያህል መጠን ያለውን ሰፊ ቦታ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ እና አካባቢያዊ ሁኔታ መመንጠር እና የንግድ እርሻ ለማድረግ ማልማት ይቻላልን?

መሬቱን ለማልማት ምን ያህል ጊዜ ሊወስድበት ይችላል ተብሎ ሲጠየቅ ካሩቱሪ ወዲያውኑ እንዲህ የሚል ጥያቄ በዘ-ህወሀት ላይ ያቀርባል፣ “በግልገል ጊቤ 3 ግድብ ቁፋሮ ላይ የፈላ ምንጭ በተገኘ ጊዜ የኤሌክትሪክ ምርት ለማምረት ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል በማለት ልትነግረኝ ትችል ነበር ወይ? ንገረኝ፡፡ ጀነሬተር በመያዝ ከቤቴ ተቀምጨ እሰራ ነበር፣ ምክንያቱም ለሁለት ዓመታት ያህል ምንም ዓይነት በቂ ኃይል አልነበረም፡፡ ዘ-ህወሀት የጊቤ 3ን የግድብ ግንባታ ስራ የጀመረው እ.ኤ.አ በ2008 ነበር፡፡ እናም  እስከ አሁንም ድረስ ትርጉም ያለው እና ሊለካ የሚችል የኤሌክትሪክ ኃይል ማምረት አልቻለም፡፡ በሀሳብ ደረጃ እ.ኤ.አ ጥቅምት 2015 በድረ ገጽ ላይ ተለቋል፡፡“

በዘ-ህወሀት የመሬት ኪራይ ስምምነት የአፈጻጸም መርሀ ግብር ወይም ደግሞ መገኘት ያለባቸው የስራ ውጤቶች በእርግጠኝነት የሉም፡፡ ስራውን ለመገምገም የሚያስችል የመነሻ መረጃ ቁጥር ወይም ደግሞ ሜትሪክስ በ9 ገጽ የመሬት ኪራይ ስምምነት ላይ የሌለ ከመሆኑም በላይ በካሩቱሪ በኩል የአፈጻጸም አለመኖርን ያመላክታል፡፡ በመሬት ኪራይ ስምምነቱ ውስጥ ካሩቱሪ ስኬታማ መሆኑ ወይም ደግሞ መውደቁን ለመወሰን የሚያስችል ምንም ዓይነት የተጻፈ ነገር የለም፡፡

የረዳ ለረዥም ጊዜ የማራዘም ጥያቄ በመሬት ኪራይ ስምምነቱ ላይ ምንም ነገር የማያመጣ የሕግ ትርጉም የለሽነትን የሚያመላክት ነው፡፡

ዘ-ህወሀት ፕሮጀክቱ የተሰረዘ መሆኑን ለካሩቱሪ ባሳወቀበት ጊዜ ተከላካዩ ካሩቱሪ እንዲህ አለ፣ “ለዚህ ስረዛ ዕውቅና አልሰጥም፡፡ የማቋረጡ ሁኔታ በህገ ወጥ መንገድ ንብረትን እንደመዝረፍ ያህል ነው፡፡ እናም በሁለትዮሽ የመዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ስምምነት በሚደረግበት ጊዜ በጊዜው የገበያ ዋጋ ታስቦ ካሳ መከፈል አለበት ይላል፡፡“

ካሩቱሪ ከኢትዮጵያ ወይም ደግሞ ከህዝቡ ጋር ምንም ዓይነት ችግር የለበትም፡፡ ለኢትዮጵያ ያለውን ፍቅር በይፋ ግልጽ አድርጓል፡፡ “ኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ኃይማኖት አጥባቂ ሀገር ናት፡፡ በጣም ጠንካራ የሆኑ እሴቶች፣ የእራሳቸው ደካማ እና ጠንካራ ጎኖች ያሏቸው በጣም ጠንካራ የሆኑ ባህል  አሏት፡፡ እኔ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነኝ፡፡ እዚህ መጣሁ ምክንያቱም ይህችን ሀገር እወዳታለሁ፡፡ ቦታውን እወደዋለሁ እናም በርካታ የሆነ የእራሴን ገንዘብ በማውጣት በዚህ ሀገር ውስጥ አፈሰስኩ፡፡” በእርሱ ተማዕኒነት ላይ ጥርጥር የለኝም ሆኖም ግን ከመኖሪያ ቦታቸው በጅምላ ተፈናቅለው እና በመንደር ማሰባሰብ በሚል ፈሊጥ በአስር ሺዎች የሚሆኑ ዜጎች ለአስከፊ ድህነት ሲዳረጉ እያየ ዝም የሚል እንዴት ለህዝቡ ፍቅር አለኝ ሊል ይችላል?

ኢትዮጵያን ስለመውደድ ሁኔታ ከተነሳ ዘንድ አንድም የዘህወሀት አመራር በይፋ ኢትዮጵያን እወዳለሁ ወይም ደግሞበአንደበቱ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነኝ የሚል ሰምቸ አላውቅም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማንም ቢሆን ለማስተባበል የሚሞክር ካለ የእርኩም ስጋ ለመብላት ዝግጁ ነኝ፡፡ ይኸ በአትክልት ተመጋቢዎች ከባድ አነጋገር ነው!

የካሩቱሪ ችግር ዘ-ህወሀት እራሱ ነው፡፡ በበርካታ በዘ-ህወሀት ቃላት የተሞኙ የተጭበረበሩ መሆኑን ይናገራል፡፡ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ መስመር በመስመር በማንበብ ካሩቱሪ የተሞኘ መሆኑን በመጮህ ይናገራል፡፡ ካሩቱሪ ተታሏል ተጭበርብሯል፣ ተሞኝቷል፣ እናም ተጃጅሏል! በዘ-ህወሀት፡፡

ዘ-ህወሀት ካሩቱሪን ሙልጭ አርጎ በልቶ በወንዝ ላይ ላከው ፡፡

ካሩቱሪ በእርግጠኝነት በአታላይ ዘ-ህወሀት ጌቶቹ ትብብር ተነፍጓል፣ ተታሏል፣ ተጭበርብሯል?

እ.ኤ.አ በ2016 ካሩቱሪ በዝቅተኛ ማዕበል ብቻ አይደለም ክልከላ የተደረገለት ሆኖም ግን በጋምቤላ ቁማር ደሙ እስከደርቅ ድረስ መከራውን አይቷል፡፡

ለካሩቱሪ ቀደም ሲል እንዲህ በማለት ነግሬዋለሁነጻ መሬትን የሰጠ እጅ በነጻ የሚወስድ እጅ ነው…“

ካሩቱሪ የፈረመው ሊዝ  (ከዘ-ህወት ወይም ከጋምቤላ መንግስት ጋር ማለቴ ነው) ቀለሙ ከመድረቁ በፊት ሊቀማ እንደሚችል አውቃለሁ፡፡

በመጨረሻ ላይ ካሩቱሪ እየገለጸ ያለው ነገር በእርግጠኝነት በጣም መጥፎ ነገር ነው፡፡ ቃለ መጠይቅ በተደረገለት ጊዜ ካሩቱሪ እንዲህ ብሏል፣ “ በአፍረካ ውስጥ ውድቀት ከደረሰብህ አለቀልህ፡፡ ከወደቅህ ጆቢራዎቹ ይመጡና መሞትህን ይጠባበቃሉ፣ ከዚያም እየዘነጠሉ በሚገባ ይበሉሀል፡፡“

ደህና፣ ካሩቱሪ የዘ-ህወሀት ጆቢራዎች 100 ሺ ሄክታር ከእይታ ውጭ የሆነ መሬት ሲሰጡት በፍጥነት ከበው በመያዝ ሊዘነጥሉት እንደሚችሉ ሊያውቅ በተገባ ነበር፡፡ ይኸ ነገር በዩናይትድ ስቴትስ በፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ እና በ1970ዎቹ ሲደረግ እንደነበረው ዓይነት ነው፡፡

ካሩቱሪ ልዩ በሆነ መልኩ በእይታ ካልተጠበቀ በስተቀር ስምምነት እያደረገ ያለው ከዳክየዎች ጋር ሳይሆን ከጆቢራዎች ጋር ነበር፡፡ ካሩቱሪ አጥንቱ እስኪቀር ግጠው ሊበሉት ስለሚችሉት ጆቢራዎች በአሁኑ ጊዜ ስሞታ እያሰማ የመሆኑ ጉዳይ በጣም የዘገዬ አይደለምን?

በእርግጥ እኔ ቀደም ሲል አውቄዋለሁ፡፡ በእርግጥ ካሩቱሪ ወደ ወንጀለኞቹ ሲሄድ ገና በመጀመሪያው ዕለት ምን ሊሆን እንደሚችል አውቅ ነበር፡፡ የካሩቱሪ ፕሮጀክት እንዴት ወደ መቀመቅ ሊወርድ እንደሚችል በእርግጠኝነት አውቂያለሁ፡፡

እ.ኤ.አ መጋቢት 2011 “ኢትዮጵያ፡ ለሽያጭ የቀረበች ሀገር“ በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችቴ ነጻ ስጦታ የያዙትን ማለትም ነጻ መሬት የሚያቀርቡትን ተጠንቀቅ በማለት ለካሩቱሪ ነግሬው ነበር፡፡

እነዚህ ነጻ መሬት ሰጭ ፍጡሮች እንዴት እንደሚያታልሉ፣ እንዴት በሸፍጥ የተሞሉ እንደሆኑ፣ አጭበርባሪዎች እና አታላዮች እንደሆኑ ለካሩቱሪ ተናግሬ ነበር፡፡ ይህን ነገር አታድርገው ወይም ብታደርገው እንኳ ኋላ ትጸጸታለህ በማለት ነገሬው ነበር! ነጻ መሬት የሰጡህ ሰዎች በገብጋባ ሰዎች ልብ እና አዕምሮ ውስጥ ያለውን የገብጋባዎችን ኃያልነት ይገነዘባሉ በማለት ነግሬው ነበር፡፡

ተስፋ የለሽ በመሆን እራስን በማግለል ካሩቱሪ በዘ-ህወሀት ሸፍጥ ተጠልፎ እንዳይወድቅ አስቀድሜ በማወቅ እንዲህ በማለት አስጠንቅቄው ነበር፡

“ካሩቱሪ ስለ ነጻ ምሳ፣ ነጻ ገንዘብ እና ነጻ መሬት በህልመኝነት ተነሳስቶ ከመቅጽበት እራሱን ለመዶል ነጻ ነበር፡፡ ነጻ ምሳ እንደሌለ ሁሉ ነጻ መሬትም እንዲሁ በነጻ አይገኝም፡፡ ካሩቱሪ ደኑን ለመመንጠር በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ካጠፋ በኋላ በጣም ውድ የሆኑ የግብርና መሳሪያዎችን አመጣ፣ እንደዚሁም ሁሉ መሰረተ ልማቶችን መገንባት እና እርሻውን በአስቸኳይ መጀመር ነበር፡፡ ሆኖም ግን ነገሮች ሁሉ እንዲህ ቀላል ሆነው አልተገኙም፡፡  ካሩቱሪ በጋምቤላ አንድ ቀን ከእንቅልፉ ሲነቃ የእርሱ ኩባንያ በነጻ ያገኘው መሬት ከሁሉም በላይ ነጻ አይደለም፡፡ ካሩቱሪ ይህን ወይም ያን ለማግኘት ወይም ደግሞ የ50 ዓመት ሊዙን ህግ በመጣስ ወድቋል፡፡ ይህንን ትምህርት ቤት ወይም ደግሞ ያንን ክሊኒክ አልገነባም፡፡ የገነባቸውም ቢሆኑ በቂዎች አይደሉም ወይም ደግሞ ጥሩዎች አይደሉም፡፡ በትክክለኛው መንገድ ይህንን መንገድ ወይም ያንን ከተማ አልገነባም፡፡ እናም የገነባቸው በቂዎች አይደሉም፣ እንዲሁም ገና ብዙ መገንባት ይኖርባቸዋል፡፡ ካሩቱሪ በሚሊዮኖች ሄክታር ነጻ መሬት ያሰጣቸው የውጭ መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ ሕጉ ነጻ መሬት የሰጡት አካሎች ምን እንደሚፈልጉ መተርጎም አለበት… በመጨረሻም ነጻ መሬት የሰጠ እጅ በደንብ የለማውን ነጻ የእርሻ መሬት በነጻ የሚወስድ እጅ እንደሆነ ካሩቱሪ ይደርስበታል!…በመጨረሻ ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ሁሉንም ነገር ያጣሉ፡፡ በመጨረሻ ነጻ መሬት አዳዮች መልሰው ይወስዱታል፡፡ ባለፉት አስርት ዓመታት ከአንጎላ እስከ ዙምባብዌ ለባዶ ዓይነት ሸፍጦች ነጻ መሬቶችን አይተናል፡፡“

ካሩቱሪ ከቅርብ ጊዜ በፊት በተደረገለት ቃለ መጠይቅ ይህንን ነገር ማድረግ እንደሌለበት ወዳጆች ነግረውት እንደነበር አመነ፡፡ እንዲህ ነበር ያለው፣ “ጥቂት ኢትዮጵዊ የሆኑ ወዳጆቼ ጋምቤላ የመሄዴን ጉዳይ እብደት እንደሆነ ነግረውኝ ነበር፡፡“ ሆኖም ግን እወጣዋለሁ የሚል መልስ በመስጠት ለስጋታቸው አመስግኛቸው ነበር፡፡ ሆኖም ግን በዚህች ሀገር ውስጥ የምግብ ምርትን ለመጨመር በሚል ዓላማ ወደ ጋምቤላ ሄጃለሁ፡፡ ግን ያ ከመቼ ጀምሮ ወንጀል እንደሆነ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ገንዘቤን አፍስሻለሁ እናም እርሻዬን አልምቻለሁ፡፡

ጋምቤላ መሄድ እብድነት አይደለም፡፡ ይልቁንም እብድነቱ የዘ-ሀወሀትን ቃልኪዳን ከማመኑ ላይ ነው፡፡ የዘ-ህወሀት ቃልኪዳን ከማታለል ቃልኪዳን የዘለለ ጠቀሜታ የለውም፡፡ ካሩቱሪ እጅግ ዘግይቶም ቢሆን ትምህርት የወሰደበት አጋጣሚ ነው፡፡

ስለሆነም እ.ኤ.አ ጥር 2016 ሁሉም ትንበያዎቼ እውነት ሆኑ፡፡

ይህንን ማለት ያስጠላኛል፣ እናም ይህንን ከማለት የማገኘው ደስታ የለም፡፡ ሆኖም ግን እለዋለሁ፡፡ ስለካሩቱሪ ሲደረግ ስለነበረው የስምምነት ጉዳይ ትክክል ነበርኩ፡፡ ከመጀመሪያው ጀምሮ ትክክል ነበርኩ፡፡ የዘ-ህወሀት ስምምነት ምን እንደነበረ አስቀድሜ ደምድሚያለሁ፡፡ ሌላ ምንም ሳይሆን ሸፍጥ!

ካሩቱሪ ለውድቀት ነበር የተዘጋጀው?

ካሩቱሪ የገዥ ጥፋተኝነትን በመያዝ በአሁኑ ጊዜ ጆቢራዎቹ በፍጥነት እየተሰባሰቡ እየሞተ ያለውን ፕሮጀክት ለመጋጥ አሰፍስፈው እንደሚጠባበቁ የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም፡፡

ካሩቱሪ ከዘ-ህሀወት ጋር ስምምነቱን ሲፈራረም ምን እያሰበ ነበር? (ይኸ ግልፅ ጥያቄ ነው፡፡ መልሱ አያስብም ነበር ነው ፡፡)

ምናልባትም “የዓለም የጽጌረዳዎቸ ንጉስ” ከዘ-ህወሀት ጋር ስምምነቱን ሲፈራረም ጽጌረዳ ዓይነት መነጽር አድርጎ ነበር፡፡ ጽጌረዳን በሌላ በማንኛውም ስም ብንሰይማትም ያው ጫፋጭ ሽታዋ አይቀየርም፡፡ ሆኖም ግን “የመሬት ኪራይ ስምምነት” በሌላ በማንኛውም ስም “ሊዝ” ነውን?

ካሩቱሪ 10 ሺ ሄክታር መሬት ብቻ ነበር የጠየቀው ምክንያቱም ለጊዜው ሊያለማው የሚችለው መጠን ይህን ያህል ነበር፡፡ ሆኖም ግን ከፍላጎቱ እና ከአቅሙ ወጭ በግዳጅ 100 ሺ ሄክታር እንዲቀበል ተደረገ፡፡ እንዲወድቅ የተደረገ ድርጊት ነበርን? ይህንንም ድርጊት በተመሳስሎ ለመግለጽ አንድ ሰው አንድ እንጀራ (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዳቦ) ለመብላት ብቻ ቢችል እና አምስት እንጀራዎች ተሰጥተውት እንዲበላ ቢገደድ ቀሪዎቹን አራቱን እንጀራዎች ሳይበላ በመቅረቱ ሊወቀስ ይችላልን? ካሩቱሪ አሁን ነጥቡን አግኝቶታል፡፡

ዘ-ህወሀት የክርክራቸውን መጨረሻ በመያዝ እንደሚቀጥሉ በእርግጠኝነት ካሩቱሪ እምነት አለውን? አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ እና የእርሱ ዘ-ህወሀት በጋምቤላ እንዲያሸንፍ ቢፈቅዱለት የለየለት ሞኝ ነው፡፡

ካሩቱሪ ገዥ ተጠንቀቅ የሚለውን መርህ በእራሱ የአደጋ ተጋላጭነት እንዳለ ትቶታል፡፡

አምባገነኑ መለስ እና የእርሱ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሆነው ዘ-ህወሀት አንድ ጨዋታ ብቻ እንዴት እንደሚጫወት ያውቃል፡፡ የዜሮ ድምር፡፡ ይህም ማለት ሁልጊዜ መቶ በመቶ ያሸንፋሉ፡፡ ሌላው እያንዳንዱ ሰው ሁልጊዜ መቶ በመቶ ይሸነፋል፡፡

እኔን ልታምነኝ አትችልምን? ከዚያም እንዲህ የሚለውን ይህንን ጥያቄ መልስ፡  “ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ ግንቦት 2005 የተካሄደውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በስንት መቶኛ ነው ያሸነፈው? ደህና! አንተን ልሰማህ አልችልም፡፡ እኮ በስንት መቶኛ?!“

እንዲህ የሚል ቀላል ጥያቄ እነሆ፡ ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ በ2010 የተካሄደውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በስንት መቶኛ ነው ያሸነፈው? (ፍንጭ፡ 99.6%::)

ጉዳዬን ላጠቃለው!

ካሩቱሪ እና አምባገነኑ መለስ በመጨረሻ አንዱ አንዳቸውን ለማታለል በመተንበይ ነበር እንዴ ይህንን ስምምነት የተፈራረሙት?

በተኩላዎች መካከል መከባበር ይኖራልን? የሚለው ሌላኛው የጥያቄ መንገድ ነው፡፡

በእርግጠኝነት አላውቀውም፣ ሆኖም ግን  የትኛው የማድረግ ብቃት እንዳለው መናገር አልችልም፡፡

ሆኖም ግን ካሩቱሪ በእራሱ በኩል ያለውን ታሪክ ያቀረበበት መንገድ አሁን በህይወት በሌለው በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ እየተባለ በሚጠራው በታናሽ ታላቅ ሰው እና ታላቅ ቦታ በያዘው የአጭበርባሪዎች ጌታ ጋር ባደረገው ስምምነት ሙሉ በሙሉ መታለሉን የማያውቀው መሆኑን በግልጽ ያሳያል፡፡

ካሩቱሪ ስምምነቱን እንዲፈርም ሲጨቀጨቅ የነበረበትን ዕድለቢስ ቀን እንዲህ በማለት በሀዘን ያስታውሳል፡፡

“አንድ ቀን ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው እና በመንግስቱ ላይ ታላቅ የስልጣን ቦታ ከያዘ ሰው ጋር ተገናኘሁ፡፡ ከእርሱ ጋር ቀጠሮ ነበረኝ፡፡ በቀጠሮው መሰረት ወደዚያው በመሄድ በእንግዳ መቀበያ ማረፊያ ቦታው ላይ ተቀምጨ በነበረበት ጊዜ ‘ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ 70 ሺ ቶን ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ ታስገባለች‘ የሚል ጽሑፍ በጋዜጣ ላይ አየሁ፡፡ ከዚያ በኋላ የንግድ ስምምነቴን ከፈጸምኩ በኋላ ከ80 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ያላት፣ በቂ ዝናብ እና ዓመቱን ሙሉ የማያቋርጥ የጸሐይ ብርሀን ሀገር እና የ80 ሚሊዮን ህዝብ ባለቤት የሆነችው የተገላቢጦሽ በሆነ መንገድ ምግብ ከደቡብ አፍሪካ ስታስገባ በማየቴ ስሜቴን ጎዳው አልኩ፡፡ እኔ ማንም አይደለሁም፡፡ የዓለም ባንክ አይደለሁም፡፡ ሆኖም ግን ጎዳኝ፡፡”

ስም የለሹ ታላቅ መሪ ተብዬ (ካሩቱሪ ኪም ጆንጊል የ ሰሜን ኮርያ ነበር አላለም) ካሩቱሪን እንዲህ በማለት ጠየቀው፡

“በግብርና ላይ መዋለ ንዋይ ለማፍሰስ መሰረተ ሀሳቡ የለኝም፡፡ እኔ የማውቀው የአበባ ንግድን ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በኩል በ260 ኪ/ሜ ርቀት አካባቢ ላይ በምትገኘው ከባኮ ከተማ መሬት ተሰጠሁ፡፡ እዚያ ላይ እርሻውን ማረስ ጀመርኩ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት እኔን ለማየት ፈለገ፡፡ ኤምባሲው የት እንዳለ ጠየቅሁ፡፡ በቃላቴ ላይ ምልክት በማድረግ ጋምቤላ ሌላ ሀገር እንደሆነች አድርጌ አሰብኩ፡፡ ድንቁርናዬን ደገምኩት፡፡ እርሱ ከቢሮዬ ድረስ በመምጣት እንደሚጎበኘኝ ተነገረኝ፡፡ ከዚህ ይልቅ በግዮን ሆቴል ተገናኘን እና ጋምቤላ ውስጥ መሬት እንደሚሰጡኝ ተናገረ፡፡ ስለሆነም በፕሬዚዳንቱ እና በጋምቤላ መንግስት ግብዣ መሰረት ጋምቤላ ሄድን፡፡ 10 ሺ ሄክታር መሬት እንዲሰጡን ጠየቅን…መላው የጋምቤላ መንግስት ካቢኔት በስብሰባ ላይ ነበር፣ እናም 300 ሺ ሄክታር መሬት መውሰድ አለብህ አሉ፡፡ ሆኖም ግን እኔ መውሰድ የምችለው 10 ሺ ሄክታር መሬት ብቻ ነው ምክንያቱም አቅሜ ያንን ያህል ነው አልኩ፡፡ ምንም ዓይነት ምርጫ አልሰጡኝም፡፡ ከስብሰባው በኋላ ሰዎቹ ጠሩኝ እና 300 ሺ ሄክታር መሬት እንሰጥሀለን አሉኝ፡፡ አመሰግናለሁ ሆኖም ግን 10 ሺ ሄክታር ብቻ ነው ማልማት የምችለው አልኩ፡፡ እነርሱ ግን 300 ሺ ሄክታር መሬት እንድወስድ ማግባባት ጀመሩ፡፡ እናም ስምምነቱን አደርጋለሁ ግን እነርሱ ግን በዚህ መሬት እንደማይስማሙ ገለጹልኝ፡፡ መንግስት ይህን የሚያህል ግዙፍ መሬት በጣም ርካሽ በሆነ ዋጋ በመስጠቱ ምክንያት ከሁሉም ማዕዘን ትችት ይጎርፍበት ጀመር፡፡ እኔ ግን አልወሰድኩትም፡፡ በአንድ ጊዜ አንድ እንጀራ ነው መብላት የምትችለው፡፡ ሆኖም ግን አምስት እንጀራ አቀረቡልኝና ብላው አሉኝ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ተመለስኩ እና ለምን መጨረስ እንዳልቻልኩ ወቀሳ ማድረግ ጀመሩ፡፡ ከዚህ በስተጀርባ ምን ዓይነት አመክንዮ ነው ያለው?“

እ.ኤ.አ መስከረም 2010 አምባገነኑ መለስ በካሩቱሪ ስምምነት ላይ በመመካት እራሱን ከፍ ከፍ በማድረግ እንዲህ በማለት አወጀ፣ “ትርፍ ምርት ማምረት የሚያስችለንን እ.ኤ.አ በ2015 ምንም ዓይነት የውጭ እርዳታ ሳይስፈልገን እራሳችንን መመገብ የሚያስችል ዕቅድ ነድፈናል፡፡“ (እ.ኤ.አ በ2016 ግን እራስን መመገብ መቻል ሳይሆን 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ለረሀብ መጋለጣቸውን ልብ ይሏል፡፡)

ካሩቱሪ እንዲህ ይላል፣ “ መንግስት የእህል ምርት ወደ ውጭ እንዳይወጣ ክልከላ የሚጥል አዋጅ በማወጅ እና 180 ሚሊዮን ዶላር ለዚሁ ተግባር የተመደበውን በማገድ የስምምነቱን የመጨረሻ ካርታ አልሰጠንም፡፡ እንደዚሁም ከብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እ.ኤ.አ በ2014 በጦርነት ከተበጣጠሰችው ከደቡብ ሱዳን የቅርብ ጎረቤት ወደሆነችው ወደ ጋምቤላ የዲዝል ነዳጅ እንዳይገባ ከለከለ፡፡“ እንዲህ ይላል፣ “100 ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ የማስፈጸም ጥረቶች እና ዓመታዊ የጎርፍ አደጋን በመቀልበስ መንግስት እያካሄደው ያለው  ዕድገት በቂ ማስረጃ ነው፡፡“

የካሩቱሪ ታሪክ ቀላል እና በዋናነት አሳማኝ ነው፡፡ እኔ ዳኝነት እየሰጠሁ እና ዘ-ህወሀትን እየወቀስኩ አይደለም (ይህንን መገመት የማትችሉ ከሆነ)፡፡ ሆኖም ግን በቀረበው መረጃ መሰረት የካሩቱሪ ታሪክ በእውነታ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የካሩቱሪን ፕሮጀክት በቅርብ ስከታተል ቆይቻለሁ፡፡ በፕሮጀክቱ ላይ ያሉ የሕግ ሰነዶችን በካሩቱሪ እና በዘ-ህወሀት ባለስልጣኖች ሲሰጡ የነበሩትን መግለጫዎች ሳነብ እና ስመረምር ቆይቻለሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የካሩቱሪ ፕሮጀክት በጋምቤላ ላይ ስለሚያስከትለው ተጽዕኖ በአበዳሪ እና በለጋሽ ድርጅቶች የወጡ ሰነዶችን እና ህትመቶችን እንደዚሁም ነጻ ጥናቶችን እና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን እና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ሲሰጡ የነበሩትን ትችቶች እና መግለጫዎች ሁሉ ስመረምር ቆይቻለሁ፡፡

በእኔ መደምደሚያ ካሩቱሪ እንዲወድቅ አልነበረም የጀመረው፡፡ ሆኖም ግን የውድቀት ዕድል እንዲገጥመው ተደርጓል፡፡

ዘ-ህወሀት ከካሩቱሪ ስምምነት ጋር በተያያዘ መልኩ በእኔ አመለካከት ለመጨረሻው የፍልሚያ ጨዋታ ሁለት ስትራቴጂዎችን ነድፏል፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) ካሩቱሪ ግዙፍ የሆነ የንግድ እርሻ ድርጅትን በማቋቋም መሬቱን ከማልማት አንጻር ስኬታማ ሆኗል፡፡ ስለሆነም ሁሉንም ነገር እነርሱ በመበዝበዝ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለግብረ አበሮቻቸው፣ ለጓደኞቻቸው እና ለደጋፊዎቻቸው ለማከፋፈል የሚያስችል መንገድ ይፈልጋሉ፡፡

2ኛ) ካሩቱሪ እየወደቀ ነው፡፡ ስለሆነም ሁሉንም የእርሱን የእርሻ መሳሪያዎችን እና የፈሰሰውን መዋለ ንዋይ በመያዝ ካሩቱሪንን ድራሹን አጥፍቶ ከሀገር ማባረር ነው፡፡ በሁለቱም መንገዶች ዘ-ህወሀት ያሸንፋል! በአሁኑ ጊዜ ለዘ-ህወሀት ጆቢራዎች የእራት ጊዜ መሆኑን ካሩቱሪ አሳምሮ ያውቃል!

በእርግጥ ዘ-ህወሀት በካሩቱሪ ላይ ያደረገው ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ እርሱ የተለየ ሰለባ እንደሆነ አድርጎ የማሰብ ስሜት ሊኖረው አይገባም፡፡ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ መዋለ ንዋይ ማፍሰስ እና የማጭበርበር የሸፍጥ ስራ በመስራት በርካታ ዕኩይ ተግባራትን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

ካሩቱሪ ስምምነቱን ከመፈረሙ በፊት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ቢያደርግ ኖሮ ብዙ ነገር ይማር ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይህንን ነገር አላደረገም፡፡

እ.ኤ.አ መጋቢት 2011 ወደኋላ መለስ ብለን ስናየው በኢትዮጵያ የካሩቱሪ ፕሮጀክት ማናጀር የነበረው ካርምጅት ሴክሆን በጋምቤላ ውስጥ ያለውን መሬት እንዴት እንዳገኙት እጅግ በደስታ ስሜት ፍንድቅድቅ ባለ ሁኔታ እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው፡ “መሬቱን ፍጹም አይተነው አናውቅም፡፡ እነርሱ ሰጡን እኛ ደግሞ ተቀበልናቸው፡፡ በእውነት ይህንን ነው ያደረግነው፡፡ መሬቱን እንኳ አላየነውም፡፡ (በድል አድራጊነት ሳቁን ለቀቀው፡፡) እነርሱ ሰጡን፡፡ ይኸው ነው፡፡ በጣም ጥሩ መሬት ነው፡፡“

“የዓለም የጽጌረዳው ንጉስ” የንግድ ስምምነቶችን ሲያካሂድ ጽጌረዳ ዓይነት መነጽር አድርጎ ነው እዴ ሄዶ የነበረው? እሪ ብሎ በመጮህ አንድ በዓለም ላይ ያለ የንግድ ድርጅት እንዴት ባላየው መሬት ላይ የ10 ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ ያፈስሳል?

የካሩቱሪ-ዘ-ህወሀት ስምምነት በዓለም የቅጥፈት ዓለም ውስጥ የፑፍን ታምራዊ ድራጎን እና የሳንዲን የቀይ እና ሰማያዊ ላሞች እና ቀይ ዝሆኖችን ሁልጊዜ ያዩ እንደነበር የሚተርተውን ተረት እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡

በእርግጥ ካሩቱሪ ስምምነቱን ከመፈረሙ በፊት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ቢያደርግ ኖሮ በዘ-ህወሀት የቢዝነስ ፕላናቸውን ይዘው እንዲመጡ ሲጠየቁ እና እንዲጸድቅላቸው ለበርካታ ወራት ጠብቁ እየተባሉ ሲጠብቁ ቆይተው ባልታሰበ እና በድንገት የዘ-ህወሀት ግብረ አበሮች በቢዝነስ ፕላናቸው ላይ ዲያስፖራዎቹ ያቀረቡትን ፕላን እንዳለ በመውሰድ እነርሱ ሲሰሩበት የነበረበትን እና በርካታ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ለክስረት የዳረገበትን ሁኔታ መረዳት አይችሉም ነበርን?

ካሩቱሪ ስምምነቱን ከመፈረሙ በፊት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ቢያደርግ ኖሮ የዲያስፖራ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ከፍተኛ በሆነ ግብር እንዲደቆሱ ተደርገው ውጤታማ ከነበረው ቢዝነሳቸው ከተባረሩ በኋላ ያቋቋሟቸው የንግድ ስራዎች ለዘ-ህወሀት ግበረ አበሮች እና ደጋፊዎች በጨረታ እየተቸበቸቡ መሰጠታቸውን በማየት ትምህርት ይሆናቸው ነበር፡፡

ካሩቱሪ ስምምነቱን ከመፈረሙ በፊት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ቢያደርግ ኖሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ እና በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ህጋዊ የቢዝነስ ሰዎች የቢዝነስ ስራዎቻቸው በዘ-ህወሀት መሪዎች ወይም ደግሞ በቤተሰብ አባሎቻቸው፣ በግብረ አበሮቻቸው እና በጓደኞቻቸው እየተነጠቁ ሲወሰዱባቸው ከነበረው ሁኔታ በመማር ከኪሳራው ይድን ነበር፡፡

ካሩቱሪ ስምምነቱን ከመፈረሙ በፊት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ቢያደርግ ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ እና በውጭ ሀገር ያሉ በርካታ ህጋዊ የቢዝነስ ሰዎች ቢዝነሶቻቸውን ከዘ-ህወሀት እና ከእነርሱ ግብረ አበሮች ጋር በድብቅ የእነርሱን እውነተኛ ማንነት በመደበቅ ለዘ-ህወሀት ባለቤቶች ያስረክቡ እንደነበር ትምህርት በመውሰድ ከእንደዚህ ያለው ኪሳራ እራሳቸውን ያድኑ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ/Global Financial Integrity የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2000 እና በ2009 በህገወጥ መልኩ የተገኘ 11.7 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ወደ ውጭ በማስወጣት እንድታጣ ተደርጓል፡፡“ የበለጠ የሚያስገርመው ነገር ደግሞ የዚያ ዓይነት ገንዘብ ያለው ማን ነው፣ እናም እንዴት አድርጎ ነው በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ውስጥ እንዲወጣ የተደረገው? የሚለው ነው፡፡

ዘ-ህወሀት በካሩቱሪ ላይ ያደረገው ነገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲጫወቱት የቆዩት ጨዋታ ነው፡፡ የቆየው የማታል ድርጊት ነው፡፡

አንድ እንግዳ የሆነ ነገር ግን አግኝቻለሁ፡፡ ዘ-ህወሀት ጥቂት ቁራጭ መሬት ከመስጠቱ በፊት ጥቂት መዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ ሰዎችንም ቢሆን ሁልጊዜ የቢዝነስ ፕላንን ለማየት ይጠይቃል፡፡ ታዲያ እውነታው ይኸ ከሆነ ዘ-ህወሀት በእግሩ ላልረገጠው እና መሬቱን ላላየው ለውጭ ሀገር ሰው 100 ሺ ሄክታር መሬት እንዴት ሊሰጥ ቻለ?

እውነት ለመናገር ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ውስጥ በፊውዳሉ ስርዓት ሲያደርጉት ከነበረው እጅግ በከፋ መልኩ መሬትን በዓይነ ገመድ የመስጠት ሁኔታ ነው፡፡

በእርግጥ ይህ ነገር በጣም አውሬነት፣ አዕምሮን የሚበጠብጥ እና በቀላሉ ሊታመን የማይችል ነገር ነው!

እኔን ታማኝነት የሌለው፣ ከካሩቱሪ ጋር የወገነ፣ ዘ-ህወሀትን የሚጠላ ወዘተ፣ ወዘተ በማለት የሚከሱኝ ጥቂት ሰዎች እንደሚኖሩ እርግጠኛ ነኝ… ማለት የምችለው ነገር እንደዚህ ነው!

ማለት የምችለው እ.ኤ.አ መጋቢት 2011 የሰጠሁት ትንታኔ እና ትንበያ ትክክለኛ እና እውነተኛ ነገር መሆኑን ነው፡፡ መካድ አይቻልም !

በማይበገረውየጋምቤላ አንበሳእናበዘህወሀት ጅቦችመካከል ያለ ጦርነት፣

እራሱን “የጋምቤላ አንበሳ” አድርጎ የሚጠራው ካሩቱሪ ጥፋተኛ ያለመሆኑን በጽናት እንደሚያስመሰክር አውጇል፡፡

ዘ-ህወሀት የግል ለማድረግ እያደረገው ያለው ስረዛ የሁለትዮሽ የጋራ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ስምምነት እንደሚለው የገበያ ዋጋን መሰረት ባደረገ መልኩ በካሳ መደገፍ አለበት፡፡

ካሩቱሪ በመከላከል ተግባሩ ከዚህም በበለጠ ዘልቆ የሚሄድበት ይሆናል፡፡ መሬቴን የሚነካ ማንኛውንም ባለስልጣን እሟገታለሁ ብሏል፡፡ ከዚያ በኋላ ውጤቱን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የሚያዩት ይሆናል፡፡ እኔ ግማሽ ኢትዮጵያዊ ብቻ ነኝ፡፡ የህይወቴን አስር ዓመታት ያህል እዚህ አሳልፊያለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ የሆነ የፖለቲካ ክርክር እንድናደርግ እጠይቃለሁ፡፡ ከዚህ በላይ የመናገር መብት የለኝም ምክንያቱም የኢትዮጵያዊነት ዜግነት የለኝምና፡፡ እኔ ለዚህች ሀገር እንግዳ ነኝ፡፡

እንደ ግማሽ ኢትዮጵያዊነቱ ካሩቱሪ ለጠብ አይጋበዝም፡፡

ካሩቱሪ እንዲህ ይላል፣ “እኔ ወደ ጋምቤላ የሄድኩ አንበሳ ነኝ፡፡ ምናልባትም የቆሰልኩ፣ ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን ያው አንበሳ ነኝ፡፡ እያምባረቅሁ ወይም ደግሞ እራሴን ከፍ ከፍ እያደረግሁ አይደለም፡፡“

ምንጊዜም ካሩቱሪንን እንደ ቢዝነስ ሰው ሳስበው ካሩቱሪ በጽናት የተሞላ ጀግና ሰው ነው፡፡

ካሩቱሪ በዘ-ህወሀት ወሮበሎች ፊት በመቅረብ የእርሱን መሬት ሊዘርፉት እንደማይችሉ እና ይህንን ሙከራ የሚያደርጉ ከሆነም ትልቅ አቧራ ሊያስነሳ እንደሚችል ይነግራቸዋል፡፡

ሚስተር ካሩቱሪንን አክብሩት! በዘራፊ ወሮበሎች ገንዘብህን ልታጣ እንደማትችል መጠራጠር የለብህም፣ ሆኖም ግን ለመብትህ የቆምክበትን መንገድ እወደዋለሁ፡፡ ጉዳቶችን አስወግድ! በሙሉ ፍጥነት ወደፊት ቀጥል፡፡

ካሩቱሪ ለንብረቱ እና ለመብቱ መታጋሉን እቀጥላለሁ ሲል ጉዳት ለማድረስ መሆን አለመሆኑን የማውቀው ነገር የለም፡፡ ረዳ የህግ ምርጫውን መሞከር ይችላል ብሏል፡፡

ይኸ የሚሆነው በዘ-ህወሀት የይሰሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ነውን?

ስለዚህ ጉዳይ እርሱት!

በቆሰለ አንበሳ እና በሚስከመከሙ ጅቦች እና በሚንጋጉ ዞቢራዎቸ መካከል የሚደረገውን ጦርነት ለማየት መቆየት አልችልም፡፡

በጋምቤላ ክልል ውስጥ በአንበሶች እና በጅቦች መካከል በመደበኛነት የአጭር ጊዜ ጦርነት እንደሚካሄድ እውነት ነው፡፡

ብቸኛ ጥያቄ ሆኖ ሊቀርብ የሚችለው ጉዳይ በቆሰለ አንበሳ እና በሚስከመከሙ ጅቦች እና በተራቡ ጆቢራዎች መካከል የሚደረገው ጦርነት ውጤት ነው፡፡ ህይወትን ከዱር አራዊት ጋር ማመሳሰል ምን ዓይነት አስገራሚ ነገር ነው?

ካሩቱሪ በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ የመዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ሁኔታ እራሱን ከጥቂት ቀልደኞች ለመከላከል በማሰብ አንዳንድ ሀሳቦችን ለመፈንጠቅ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ “ይኸ ማስፈራራት ነው ምክንያቱም በቃ በቃ ነው” በማለት ሲናገር ቃላትን ለማሳመር አይደለም፡፡ እራሴን መከላከል አለብኝ፡፡ መሬቴን የሚነካ ማንኛውንም ባለስልጣን እሟገታለሁ፡፡ (እንደ አበደ ውሻ ነው! ካሩቱሪ በመንፈሰ ጠንካራነት እና በጽናት ቆሟል፡፡)

በሁሉም በህንድ የሁለትዮሽ ኢንቨስትመንት አጠባበቅ ስምምነት አወዛጋቢ የሆኑ ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት የሚከተሉትን እንደ ቅደም ተከተላቸው ይቀርባሉ፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) ስምምነት፣

2ኛ) ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ካልተፈቱ ግጭቱ ወደ ፍትህ አካል ይቀርባል፣

3ኛ) ግጭቱ የተከሰተባቸው ፓርቲዎች በአስታራቂዎቸ አማካይነት መታረቅ ካልቻሉ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አስፈላጊዎቹን ቀጠሮዎች ያዘጋጃል፡፡ የአስታራቂ ፍርድ ቤቱ የእራሱን የአሰራር ስርዓት እንዲወስን ስልጣኑ ተሰጥቶታል፡፡

ካሩቱሪ ከዘ-ህወሀት ጋር ያለውን ግጭት በእርቅ መፍታት እንደሚያስፈልግ ሀሳብ አቅርቧል፡፡ (የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች የሁለትዮሽ ኢንቨስትመንት አጠባበቅ ስምምነትን እርቅ ወይም ደግሞ የህግ እና የፖለቲካ ጠቀሜታ ያውቁታልን?)

የመሬት ማከራየት ስምምነት አንቀጽ 12 የሚከተለውን መብት እንደሚያጎናጽፍ ማስተዋል ጠቃሚ ነው፣ “ በዚህ ስምምነት መሰረት ስለአፈጻጸም ህጉ በኢትዮጵያ ህግ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል“ ይላል፡፡

በእኔ ትንታኔ መሰረት ግጭትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ለዘ-ህወሀት ጥሩ ነገር አይመስልም፡፡

ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ በ2002 ለመጨረሻ ጊዜ የግጭት መፍቻ ስምምነት በቀረበላቸው ጊዜ በኢትዮ-ኤርትራ የወሰን ድንበር ላይ የምትገኘውን ባድሜን እንዲለቁ ታዝዘው ነበር፡፡ (እኔ እንደዚህ ያለውን ነገር ለመግለጽ ይከብደኛል፡ አንድ ሀገር አንጸባራቂ በሆነ መልኩ ድልን ተቀዳጅታ ጠላቷን ካሸነፈች በኋላ እና በጦር ሜዳ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ህይወት በመገበር ድንበሩን ካስከበረ በኋላ ተመልሶ ይህንኑ ግዛቱን ለወራሪው ኃይል በግጭት ማስወገድ ስምምነት መሰረት ለመስጠት እንዴት ስምምነት ያደርጋል?

ይኸ ነገር አጠቃላይ ግራ የተጋባ ነገር እኮ ነው!)

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን የዘ-ህወሀት “የመሬት ኪራይ ስምምነት” ደካማ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ የሕግ መሳሪያ ከወንፊት በላይ ቀዳዳ ያለው ነው፡፡ ለግጭት ፈች አስማሚዎች አስቂኝ የሆነ እና ችግሮችን ለመፍታትም አስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጥር ነው፡፡

የመሬት ማከራየት ስምምነቱን ያረቀቁት ሰዎች የአቅም ክፍተት የሚታይባቸው እና ደንቆሮዎች በመሆናቸው በእራሱ/በእራሷ ሊያፍር/ልታፍር ይገባቸዋል እላለሁ፡፡

እጅግ ሰፊ የሆነ የኢትዮጵያዬ ግዛት የህግ መሳሪያዎችን ከዓለም አቀፍ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ልውውጦች አንጻር ምን እንደምታ እንደሚኖራቸው በማያውቁ እና ምንም ዓይነት ሀሳብ በሌላቸው በወሮበላ ዘራፊ የደናቁርት ስብስብ በድንገት ለሌላ ሀገር አሳልፈው ሲሰጡ ማየት አዕምሮን የሚበጠብጥ እና የሚያሳብድ ነገር ነው፡፡

ምን ዓይነት የሚያናድድ ነገር ነው!

(ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያን አንጡራ ግዛት እየቆረጠ ለሱዳን ለመስጠት በሚስጥር ያደረገውን ስምምነት ወይም ደግሞ ከዓባይ ግድብ ጋር በተያያዘ መልኩ ከግብጽ ጋር እየተደረገ ያለውን አግባብነት የሌለው ስምምነት በማስብበት ጊዜ ያንቀጠቅጠኛል፡፡ ስለመጋዝኑ ማንም ጉዳዩ አይደለም፡፡ ስለሀገሪቱ ማለቴ ነው፡፡)

ያም ሆነ ይህ ግልጽነት ከሌለ ወይም ደግሞ ስለትርጉም አሰጣጥ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች አጠቃላይ የህግ መስፈርቱ ግልጽ ያለመሆኑ እና በጥርጣሬ የተሞላ መሆኑ ስምምነቱን ያረቀቁት ክፍት ለሆነ ትርጉም እንዲጋለጥ አድርጓል፡፡

የዘ-ህወሀት የህግ ባለሙያዎች እጆቻቸውን በአየር ላይ እያወዛወዙ እና ግልጽ ያልሆነ ትርጉም ያላቸውን ቃላት እየወሰዱ በመለጠፍ ስለመሬት ኪራይ ስምምነት አዘጋጅተው እንዳቀረቡ አስባለሁ፡፡

የካሩቱሪ የህግ ባለሙያዎች ቃላቱ ከወረቀቱ ላይ እስከሚጠፉ ድረስ ስምምነቱን እየቆረጡ እና እየቆራረጡ የሚመረምሩት ይሆናል፡፡

ከመሬት ከራይ ስምምነቱ ጋር በተያያዘ መልኩ በርካታ የቴክኒክ እና የትርጉም ችግሮች ያሉበት ቢሆንም መቁጠሩን አቁሚያለሁ፡፡

በካሩቱሪ እና በዘ-ህወሀት/በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት መካከል በስምምነቱ ላይ መጥፎ አሻራ ሊያሳርፉ እንደሚችሉ ከዚህ በታች ጥቂት ቀላል፣ ግልጽ የሆኑ የመለኪያ ጉዳዮች ይቀርባል፡፡

1ኛ) ስለጋምቤላ ፕሮጀክት ጉዳይ ስንት ስምምነቶች ይኖራሉ? ካሩቱሪ ከጋምቤላ ክልላዊ መንግስት እና ሌላ ደግሞ ከዘ-ህወሀት ጋር በግዳጅ እንዲፈረም ለተደረገው ለ300 ሺ ሄክታር መሬት አንድ ስምምነት አለ ይላል፡፡ ከግዳጅ ሕግ አንጻር ትክክለኛው ስምምነት የትኛው ነው?

2ኛ) በእርግጠኝነት መሬቱን በባለቤትነት የያዘው ለማከራየት ስልጣኑ ያለው ወይም በኮንትራት ለመስጠት የሚችለው ማን ነው? በክልሎች ውስጥ የሚገኝን መሬት በሊዝ ማከራየት ወይም ደግሞ በኮንትራት ለመስጠት ስልጣኑ ለፌዴራሉ መንግስት ነው ወይስ ደግሞ በክልሎች? በክልል መንግስታት ስር የሚገኝን መሬት የፌዴራል መንግስት የክልሎችን ስልጣን በመጣስ እጅግ ግዙፍ የሆኑ መሬቶችን ለሌለ ሀገር እየሰጠ ከመሆኑ አንጻር የፌዴራላዊ መንግስት ሕገ መንግስታዊ ስልጣን ምንድን ነው? የክልል መንግስታትም ሆኑ የፌዴራሉ መንግስት ስምምነት ለማድረግ መቻላቸው ህገ መንግስታዊ አይደለምን?

3ኛ) የመሬት ኪራይ ስምምነቱ የመሬት ሊዝ ኪራይ ነውን? የመሬት ኪራይ ስምምነት ሁለቱን ሀረጎች በተለዋዋጭነት ይጠቀማል፡፡ ካሩቱሪ የረዥም ጊዜ የሊዝ ስምምነት ፈረምኩ ይላል፡፡

4ኛ) የመሬት ኪራይ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ግልጽ አይደለም፣ እናም በበርካታ ክፍሎች ስለሁለቱ አጋሮች ዓላማ ግልጽ የሆነ ነገር የለም፡፡ ከካሩቱሪ ቃለመጠይቅ መግለጫ መገንዘብ እንደሚቻለው ከጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ጋር በርካታ መብቶችን እና ጥቅሞችን በማካተት የሊዝ ስምምነት ለመዋዋል ዓላማ ነበረው፡፡ የዘ-ህወሀት የመሬት ኪራይ ስምምነት ካሩቱሪን እንደ አንድ ተራ ጭሰኛ ተከራይ አድርጎ የሚያስተናግድ ሲሆን በትንሽ ማስታወቂያ ማባረርም ይችላል፡፡ የተዋዋይ አጋሮቹ ዓላማ ከስምምነት ሰነዱ ላይ ያልተወሰነ ከሆነ እነዚህ ስምምነቶች በአጋሮቹ መካከል የህጋዊ የተፈጻሚነት ግዴታ አለባቸውን?

5ኛ) ካሩቱሪ ከእርሱ አቅም በላይ የሆነ መሬት በግዳጅ እንዲወስድ የተገደደ መሆኑን ግልጽ አድርጓል፡፡ ስለሆነም አንድ ወይም ሁለት ዓይነት ስምምነቶችን ከፈቃዱ ውጭ በግዳጅ እንዲፈርም የተደረገ መሆኑን ግልጽ አድርጓል፡፡ ካሩቱሪ በህገ ወጥ መልኩ፣ ተገዶ ወይም ደግሞ በጎ ያልሆነ ተጽዕኖ ተደርጎበት የሊዝ ስምምነቱን ወይም ደግሞ የመሬት ኪራይ ስምምነቱን ነው የፈረመው? ይህ ከሆነ አንዱን ወይም ሁለቱንም ለማስወገድ ህጋዊ ድጋፍ ያለው እና ከዘ-ህወሀት እና ከጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ለደረሰበት ጉዳት በህግ መጠየቅ ይችላልን?

6ኛ) ስምምነቱ በሚረቀቅበት ወይም ደግሞ በሚፈረምበት ጊዜ የጋራ ስህተት ነበርን? ለምሳሌ ዘ-ህወሀት እነርሱ የመሬት ከራይ ስምምነት የገቡ ሲል ካሩቱሪ ደግሞ በሊዝ የኪራይ ውል ስምምነት እንደገባ ያምናል፡፡ ሁሉቱም ወገኖች የተሳሳቱበት ስምምነት የግዳጅ ተፈጻሚነት ሊኖረው ይችላልን?

7ኛ) በዋናዎቹ ስምምነቶች ሁለቱም አካሎች መካከል የማቴሪያል አለመግባባት ችግር ነበርን? ለምሳሌ ካሩቱሪ ያለመግባባት ግጭቶች በመጨረሻ በድርድር ይፈታሉ ብሎ ሲያምን ዘ-ህወሀት ደግሞ የአካባቢ ፍርድ ቤቶች የተለየ ስልጣን እንደሚኖራቸው ያምናል፡፡

8ኛ) የህግ ግጭቶች በሚኖሩበት ጊዜ (አሁን በእጅ ላለው ጉዳይ የትኛው ህግ ነው መተግበር የሚኖርበት? መፈጸሙ ምናልባትም የማይቀር እንደመሆኑ በማን እና እንዴት ነው ግጭቱ መፈታት የሚችለው?

9ኛ) በሁለትዮሹ ስምምነት መሰረት ዘ-ህወሀት የቀረበለትን የግጭት ማስወገጃ ዕርቅ አልቀበለም በማለት ቢቃወም (እኔ እንደምገምተው መንግስት በሲቪል ፍርድ ቤት አልዳኝም በማለት የሕግ ከለላ የሉዓላዊነት ጥያቄ እንደሚያቀርብ ስለምገምት) ካሩቱሪ ነጻ ዳኝነት ሊያገኝ ይችላልን? (ዘ-ህወሀት በሁለትዮሹ ስምምነት መሰረት የግጭት ማስወገጃ ድርድር አላደርግም ብሎ ቢቃወም ወደፊት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረግ ኢንቨስትመንት ላለማድረግ ቻው በማለት ምክንያቱም በዓለም ላይ በግጭት ማስወገጃ ስምምነቱ መሰረት አልገዛም የሚል ማንም አካል መኖር ስለማይችል እና ሁሉንም የኮንትራት ግጭቶችን ለመጨረሻ ውሳኔ ለሀገር ውስጥ ፍርድ ቤቶች የሚቀርብ ይሆናል፡፡ (የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት አላልኩም፡፡)

አስረኛውን ጉዳይ እዚህ ላይ አልገልጸውም ምክንያቱም ለብዙ ጊዜ ለተደረገ ትንተና እና ስምምነት ይኸ ጉዳይ ሌሎችን ጉዳዮች ሁሉ ዋጋቢስ እንደሚያደርጋቸው አምናለሁ፡፡ እናም በነጠላ በስምምነት ጉዳዩን በመጣስ የህግ አሸናፊነት እንዲወሰን ወይም ደግሞ አንዳቸው ወይም ሁለታቸውም እንዲያሸንፉ ያደርጋል፡፡ ይህንን አባባል የማቀርበው በሰለጠነ ሁኔታ ነው፡፡

ስለካሩቱሪ- ዘ-ህወሀት የሕግ ውጤት ጉዳይ ደንታ የለኝም ስል ስለቆየሁ እና ግጭቱ በአሁኑ ጊዜ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን ለመግለጽ ለእኔ የማስመሰል ስራ ሆኖ ነው የሚታየኝ፡፡

የሕንድ ኃያልነት፣

የካሩቱሪ የፖለቲካ የመጫወቻ ካርድ የህንድ ኃያልነት ነው፡፡

ካሩቱሪ ግራ ለተጋበው ለእርሱ ክፍያ መፈጸም ኃጢያት ነው ይላል፡፡ እኔን ልታስፈራራኝ እንደምትችል ታስፈራራኛለህን? ሂድ እና ከሌላ ቦታ ሞክረው፡፡ ህጉ እስከቀረበ ድረስ መገደድ እንደሌለብኝ መብት አለኝ፣ ሆኖም ግን በጥቂት ፌዘኞች ተታልያለሁ፡፡ በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የሁለትዮሹ የክልከላ ስምምነት እኔን ይጠብቀኛል፡፡ እስኪ ትንሽ ንካኝ፣ከዚያ በኋላ የህንድን ኃያልነት ታያለህ፡፡  ይኸ ማስፈራራት ነው ምክንያቱም በቃ በቃ ነው፡፡ እራሴን መከላክል ይኖርብኛል፡፡

ህንድ እና ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ሀምሌ 5/2007 የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

እንደ አንድ የዘ-ህወሀት ይፋ የሆነ ሰነድ ህንድ በኢትዮጵያ 4.8 ቢሊዮን ዶላር በማፍሰስ ሁለተኛዋ ታላቅ የውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ ሀገር ናት፡፡ በሁለትዮሹ ሀገሮች የጋራ የንግድ ስምምነት መሰረት እ.ኤ.አ በ2013 1.082 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ ከዚህ ውስጥ 1.053 ቢሊዮን ዶላር ህንድ ወደ ኢትዮጵያ የምትልከው ንግድ ነበር፡፡ ህንድ 28.210 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያለው በግማሽ የከበሩ ድንጋዮች፣ ቆዳ፣ ጥጥ እና ሌሎች ሸቀጦችን ያካተተ ነበር፡፡ እንደዚሁ የመረጃ ሰነድ ኢትዮጵያ ከአፍረካ ብቸኛዋ ትልቅ የህንድ ብድር ተቀባይ ሀገር ናት፡፡ ይህም ማለት 65 ሚሊዮን ዶላር ለገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ለኃይል ማሰራጭ እና ማከፋፈያ፣ 640 ሚሊዮን ዶላር ለ3 የስኳር ፋብሪካዎች ልማት እና 300 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ለባቡር ሀዲድ ዝርጋታ ፕሮጀክት (ከአሳኢታ ኢትዮጵያ እስከ ታጁራ ጅቡቲ ወደብ) ሰጥታለች፡፡

ገንዘብ ይናገራል ይላሉ፡፡ የቀረበውን የመረጃ ዳታ በመያዝ ካሩቱሪ “ እስቲ ትንሽ ንካኝ፣ እናም የህንድን ኃያልነት ታያለህ“ ሲል የተሳሳተ እንዳልሆነ አምናለሁ፡፡

የህንድ መንግስት ከውጭ ዜጎቹ መካከል አንዱ በውጭ ሀገር መዋዕለ ንዋይ አፍስሶ በጠራራ ጸሐይ የማፍስስ ስራዋን በማስፋፋት ላይ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 የህንድ ኩባንያዎች በዓለም ላይ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር አፍስሰዋል፡፡ የህንድ መንግስት የካሩቱሪን ጉዳይ ወደ ጎን የሚለው ከሆነ በዓለም በተለይም በአፍረካ ላይ ባሉ የህንድ ኢንቨስትመንቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳርፋል፡፡ በሁለትዮሹ ስምምነት መሰረት የህንድ መንግስት የካሩቱሪን መብት በሚያስጠብቅ መልኩ መንቀሳቀስ አመክኖያዊነት ያለው ይመስላል፡፡ በተለዋጩ በህንድ በኩል የማድረግ ውድቀት ከቀጠለ በሌሎች ሀገሮች ላይ ባሉት መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ስሜትን እንዲይዙ ያደርጋቸዋል፡፡

በትክክል ለማስቀመጥ ዘ-ህወሀት ካሩቱሪን እንደተነቃነቀ ጥርስ በመምታት ያጎረሰውን እጅ ይነክሳል፡፡ ሆኖም ግን የደናቁርት ስብስብ የሆነው የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች የህንድን ኃያልነት የሙቀት መለኪያ ያለጥርጥር ይለካሉ፡፡

ካሩቱሪ በጆቢራዎች እና በቀልደኞች መካከል ተጣብቋልን?

ካራቱሪ ዘ-ህወሀትን እንደ ጆቢራዎች እና ቀልደኞች አድርጎ መቁጠሩ የሚያስደስተኝ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡

ይህ ድርጊት “በመካከል ከእራስህ ጋር ተጣበቅ“ የሚለውን የግጥም ስንኝ አስታወሰኝ፡፡ ደህና፣ ዛሬ ማታ ወደዚህ ለምን እንደመጣሁ አላውቅም፡፡ አንድ ነገር ትክክል እንዳልሆነ የሚሰማኝ ስሜት አለ፡፡ አስቂኝ ኮሚኮች ከግራ ጎኔ ቀልደኞች ደግሞ ከቀኝ ጎኔ፣ እኔ ደግሞ እዚህ አለሁ፡፡ ከአንተ ጋር በመካከል ተጣብቂያለሁ፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ካሩቱሪ በአሁኑ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ለምን እንደመጣ ያስገርማል፡፡ ከአጋሩ ከዘ-ህወሀት ጋር ከፈጸመው ስምምነት ጋር ትክክል ያልሆነ ነገር እንዳለ የሚሰማው ስሜት አለ፡፡ አዝናለሁ! እርሱ በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት ቀልደኞች እና አስቂኝ ኮሚኮች መካከል ተጣብቀዋል፡፡ በእነርሱ ላይ እየሳቁባቸው ነው፡፡ (እንደሚስከመከሙ ጅቦች አላልኩም፡፡)

ካሩቱሪንን ሊጠብቀው የሚችለው ብቸኛው ነገር የህንድ ኃያልነት ነው፡፡ ያ ምን ማለት እንደሆነም በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር የለም፡፡ ሆኖም ግን የህንድ መንግስት በካሩቱሪ ላይ ለተፈጸመበት ማጭበርበር በዘ-ህወሀት ላይ የብቀላ እርምጃ ይወስዳል፡፡ የዘ-ህወሀት መሪዎች ስለዚህ ጉዳይ ደንታቸው አይደለም፡፡

ህዝባዊ አመጽ በጠቅላላ በሀገሪቱ ውስጥ ተስፋፍቶ ባለበት ሁኔታ የእራሳቸውን የፍጻሜ ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡

ከሰይጣን እና ከሸፍጠኛ ጋር ስምምነት ማድረግ፣

ቀደም ሲል እንዳልኩተ ሁሉ ካሩቱሪ ለውድቀት የተዘጋጀ አልነበረም፡፡ ስምምነቱን ከዘ-ህወሀት ጋር ባደረገበት ጊዜ መጥፎ ዕድል ገጥሞት ወድቋል፡፡

ከሰይጣን ጋር ስምምነት ስታደርግ ሊከሰት የሚችለው ነገር ይኸው ነው፡፡ ሁልጊዜ ታጣለህ፡፡

በሌላ አባባል ግልጽ ለማድረግ ካሩቱሪ ቤቱን በላስ ቬጋስ ውስጥ ገነባ እናም አጣ፡፡

እንደገና እለዋለሁ፡፡ በዘራፊ ወሮበሎች እና ከዘራፊ ወሮበሎች ጋር ቢዝነስ በሚሰሩ ሰዎች መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም፡፡ ካሩቱሪ እና ዘ-ህወሀት እያንዳንዳቸው ምን እንዳደረጉ ለእኔ ጉዳየየ አይደለም፡፡ እውነታው አልጋቸውን በአንድ ላይ አደረጉ፣ እናም በአሁኑ ጊዜ በአንድ ላይ ይተኙበታል፡፡

ከዘ-ህወሀት ጋር ስምምነት ለማድረግ የጎቴ ፋውስትን ቀስቃሽ ቃላት በመጠቀም መግለጽ ይቻላል፡፡ (በእርግጥ እ.ኤ.አ በ2006 ባዘጋጀሁት ቀዳሚ ትችቴ ላይ የፋውስትን ተመሳስሎ ለማንሳት ሞክሪያለሁ፡፡ ፋውስት ከሰይጣን ጋር ስምምነት አደረገ፡፡ እንደዚሁም ነብሱን ወሰን ለሌለው እውነት እና ከልብ የሆነ ደስታ ማግኘት ነው፡፡ ፋውስት የሚፈልገውን ነገር አገኘ፡፡ ሰይጣን ነብሱን አገኘ፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻ ፋውስት በታላቅ ክብር ተጠበቀ፡፡

ካሩቱሪ በጋምቤላ ላለ ለሁሉም መሬት ነብሱን ሸጧል፡፡ መሬቱን አግኝቷል፡፡ ለአስር ዓመታት ያህል ከዘ-ህወሀት ጋር በጥንካሬ ለሰራው አሁን ነብሱን መቀየር አለበት፡፡ በህንድ ኃያልነት ሊጠበቅ ይችላልን?

ካረሩቱሪ በአሁኑ ጊዜ ሙዚቃውን መስማት አለበት፡፡ የዘ-ህወሀት ጆቢራዎች ላገኛቸው እና ላላገኛቸው ለእያንዳንዷ ሳንቲም ኪሱን ያነሳሉ፡፡ ከዘ-ህወሀት ኢትዮጵያ ባዶ እጁን ይዞ ይሄድ ይሆን?

የቆሰለው የጋምቤላው አንበሳ በጅቦች መመገቢያ ሳህን ውስጥ ይጠናቀቃልን? (ይቅርታ ጆቢራዎች ለማለት ነው፡፡)

የቀረው ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡

ካሩቱሪ ህይወት ፍትሀዊ ያለመሆኑን ማሰብ አለበት፣ አይደል? ምናልባትም የካሩቱሪ ፕሮጀክት ተግባራዊ እንዲደረግ እና የመንደር ምስረታ በሚል በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ ጋምቤላውያንን ጥያቄ ማንሳት የተሻለ ነው፡፡

ካሩቱሪ መጥፎ ሰው ነው ብዬ አላስብም፡፡ ሆኖም ግን የዓለም የጽጌረዳው ንጉስ በእንደዚህ ያለ ማጭበርበር ሊወድቅ ይችላል፡፡ በአንድ በቃለ መጠይቁ ወቅት ካሩቱሪ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ደደብ መሆን ነበረብኝ፡፡“ እንደዚህ አላስብም፡፡ በእርግጥ ትንሽ ገብጋባ ነገር ነው፡፡ መለስ እና ግበረ አበሮቹ 100 ሺ ሄክታር በትንሽ ገንዘብ በሸጡለት ጊዜ በምራቅ መሞላበት አለበት፡፡

ስግብግብበት አውዳሚ ነገር ነው፡፡ ሁሉንም ነገር ያወድማል፡፡ ካሩቱሪ ዘግይቶ የተማረው ነገር ይኸው ነው፡፡ ፡፡

ካሩቱሪ በተለይም በአፍሪካ እንደማንኛውም እንደዚህ ያለ ታላቅ የንግድ ኩባንያ እንዳለው ሰው ሁሉ በመዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ተግባሩ ላይ ጉዳዮች ነበሩት፡፡ ካራቱሪ አጭበርባሪ ሰው አይደለም ብዬ አምናለሁ፡፡ ሆኖም ግን የማይፈልገውን በመቶ ሺዎች ሄክታር የሚቆጠር መሬትን በ5 ወይም በ6 ዓመታት እንዲያለማ እንደሚጠበቅ በማለት መሬቱን እንዲቀበል ከመደረጉ ጋር በተያያዘ መልኩ ተታሏል ብዬ አምናለሁ፡፡

ካሩቱሪ የቢዝነስ ሰው ነው፣ እናም እንደሌሎች የቢዝነስ ሰዎች ሁሉ ትርፍ ማትረፍን ይፈልጋል፡፡ እኔ በዚህ ነገር ላይ ካሩቱሪንን አልወቅስም፡፡ እውን፣ እውን… የተራቡ የኢትዮጵያ ህዝቦችን እና ሌሎችን ለመመገብ ይፈልጋል?

ሆኖም ግን ከሁሉም በላይ ሊካድ የማይችለው ነገር ካሩቱሪ የእራሱን በ10 ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በመመደብ የጋምቤላ ፕሮጀክት እውን እንዲሆን ወጭ አድርጓል፡፡ ፕሮጀክቱን የወሰደው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ለመክሰር አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን አሁንም ሊካድ የማይችለው ነገር ወደ ኢትዮጵያ የመጣው አንዱ እና የመጀመሪያወ ነገር ትርፍ ለማግኘት ነው፡፡

ካሩቱሪ “ኢትዮጵያን እወዳለሁ“ ብሎ ሲናገር ለማስመሰል ነው ብዬ ለማመን ምንም ዓይነት አመክንዮ አይኖረኝም፡፡ ወይም ደግሞ ይህንን ያለው እራሱን ከህዝቡ ጋር ለማግባባት ነው፡፡ ካሩቱሪ ማለት የፈለገውን ይላል እናም የሚለውን ይላል ብዬ አስባለሁ፡፡ የተናገረው ነገር በፖለቲካ እይታ ትክክል ቢሆንም እንኳ ደንታ የለኝም፡፡

በእርግጥ ካሩቱሪ በጋምቤላ ውስጥ መሬቱን ለማግኘት የሄደበት መንገድ ላይ ግዙፍ የሆኑ ችግሮች አሉኝ፡፡

ካሩቱሪ ወገኖቼን በጋምቤላ ባስተናገደበት፣ ባፈናቀለበት መንገድ ላይ እና በገባው ቃል መሰረት ለወገኖቼ ትምህርት እና የመሰረተ ልማት ባለማቅረቡ ምክንያት ግዙፍ የሆኑ ችግሮች አሉብኝ፡፡ ስለጋምቤላ ህዝቦች ምንም ዓይነት ደንታ የሌለው ሰው በመሆኑ በጥልቅ አዝኛለሁ፡፡

ባለፉት ትችቶቼ እንዳቀረብኩት ካሩቱሪ ፕሮጀክቱን ለማልማት ከጋምቤላ ህዝቦች ጋር መነጋገር ቢችል ኖሮ፣ እነርሱ የሚሉትን ቢሰማ ኖሮ፣ የእነርሱን ችግሮች እና ፍላጎቶች ለማሟላት ግማሽ መንገድ በመጓዝ በጥሩ መንፈስ እና እምነት ጥረት ቢያደርግ ኖሮ ቀላል እና ምቹ ጊዜ ይኖረው ነበር፡፡ ካሩቱሪ ከጋምቤላ ህዝብ ጋር ቢሰራ ኖሮ (ከሌባው ከዘ-ህወሀት ጭፍሮች ጋር ሳይሆን) ስኬታማ ይሆን ነበር፡፡ ሆኖም ግን የጋምቤላን ህዝቦች ዝቅ አድርጎ በማየት፣ ችላ በማለት እና እምነቱን በዘ-ወሀት ላይ በማድረግ ለመዝለቅ ሞክሯል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እራሱን ታስሮ አግኝቶታል፡፡

ካሩቱሪ ከዘ-ህወሀት ጋር ስምምነት ለማድረግ ሲወስን ደፋር ሰይጣን ነበር፡፡ አሁን ግን ሰይጣንን ከደፈርክ፣ ከሰይጣን ጋር አብረህ ብይ የምትጫወት ከሆነ ሁልጊዜም ቢሆን ታጣለህ፣ ትሸነፋለህ የሚለውን ትምህርት ተምሯል!

ካሩቱሪ እንዲህ በሚለው የመልአክት ትምህርት የአዕምሮ ጭንቀት ሰላም ያገኛል፡ “ማንም ጠንክሮ የሚሰራ እና በጥንካሬ የሚኖር ሁሉ አሁንም የልፋቱን ዋጋ ያገኛል፡፡“

ካሩቱሪ በጋምቤላ ለ10 ዓመታት ያህል ላቡን ያፈሰሰበትን አምላካዊ ካሳ ላያገኝ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን በህንድ ኃያልነት ካሳ ሊያገኝ ይችላል፡፡

ስለፈሰሱ እንባዎች ከተነሳ ዘንድ በጋምቤላ በእርሱ ፕሮጀክት ምክንያት ለተፈናቀሉ እና ወደ ድህነት አዘቅት ውስጥ እንዲዘፈቁ ለተደረጉ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች አሁን ሀዘን እንደሚሰማው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በጉዳዩ ላይ በጨዋታው የመጨረሻ ደረጃ ላይ ምንም ዓይነት ምርጫ ሊያኖረው የማይችል ቢሆንም የጉዳቱ ሰለባ የሆኑትን ሰዎች በጋምቤላ የጎርፍ መተኛ ቦታዎች ላይ በዝረራ እንደማይጥላቸው (ቀልድ አይደለም) ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ፋውስት ከሜፊስቶፌለስ ጋር ያደረገውን ስምምነት ካጣ በኋላ በመጨረሻ መኖር እና ማደግ ጀመረ፡፡

ስለሆነም ካሩቱሪም እንደዚሁ ይሆናል!

የደስታ ምንጭ በመሆን ይጠቅም ይሆን በሚል እሳቤ በጌታ ክሪሽና እና በተዋጊው አርጁና መካከል በሂንዱ ቅዱስ መጽሐፍ ያደረጉት ንግግር እንዲህ ይቀርባል፡

“በዚህ ዓለም ላይ ስራን ስራ፡፡ አርጁና እንደ ሰው ምንም ዓይነት ስግብግብነትን ሳያስከትል እራሱን መሰረት አደረገ፡፡ እናም ተመሳሳይ ነገር በማድረግ ስኬታማ ሆነ እና ድል ተቀዳጀ፡፡“

በዘ-ህወሀት ጨዋታ ባልተጠበቀ መልኩ መለያ ካናቴራቸውን ያወለቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጉዳት ሰለባዎች ማን እንደሆኑ ያውቃሉ፡፡ ጥቂቶች አታላይን ልታታልለው አትችልም በማለት ግኝታቸውን ከባድ በሆነ መልኩ ያስቀምጣሉ፡፡

ካሩቱሪ ለ10 ዓመታት ያህል በጋምቤላ የንግድ እርሻ ልማቱን ለማካሄድ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በ10 ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንዲያጣ ሆኗል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ነገሮች ወደተሳሳተ አቅጣጫ ይሄዳሉ፣ እናም እጅግ በጣም ምርጥ የተባሉት የአይጦች እና የሰው ዕቅዶች አብዛኛውን ጊዜ ከዕቅድ ውጭ ይሆናሉ፡፡ አመንኩ ገበርኩ!

ካሩቱሪ የኢትዮጵያን ህዝቦች ከመውደድ የበለጠ ገንዘብን በመውደድ መዋዕለ ንዋዩን እንዳፈሰሰ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አንድን ነገር ለማግኘት አንድ ነገር ለመስራት ፍቅር ክሪሽማ ለአርጁና የሰጠው ምክር መገለጫ ባህሪ እንደሆነ አምናሁ፡፡ ካሩቱሪ ምንም ዓይነት ስግብግብበነት ሳያስከትል እና የኢትዮጵያን ህዝብ ከማፍቀር አንጻር የሰራውን የሰራ መሆኑን የሚያምን ከሆነ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አጥቷል፡፡ ሆኖም ግን የመጨረሻውን ሽልማት ለማግኘት በጽናት ይቆማል፡፡ በዘላለማዊ እውነታ ሰነዱ ላይ የወደፊቱን ሁኔታ የሚወስኑ ነገሮችን ፈልጎ ማግኘት ይኖርበት ነበር፡፡“

ድህረ ጽሑፍ፡

በካሩቱሪ -ዘ-ህወሀት በጩኸት የታጀበ ደስታ ይህ ግጭት ወደፊት በኢትዮጵያ ውስጥ የውጭ መዋዕለ ንዋይ የመጨረሻ ፋይዳ ሊኖረው እንደሚችል ማንም ሊረሳው አይገባም፡፡

ካሩቱሪ ዘ-ህወሀት ማንኛውንም የውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ ከሀገር ውስጥ እያባረረ ነው ይላል…

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!         

የካቲት 9 ቀን 2008 .

The post የካሩቱሪ ቁጣና የህንድ ሃያልነት በኢትዮጵያ – ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም appeared first on Zehabesha Amharic.

ጎግል ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ- ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ትርጉም ጀመረ

$
0
0

Amharic Translation
(ዘ-ሐበሻ) እስካሁን በ104 ቋንቋዎች የትርጉም አገልግሎት የሚሰጠው ጎግል የኢንተርኔት ትርጉም አገልግሎት (https://translate.google.com) 105ኛውን የቋንቋ ትርጉም አማርኛ እንዲሆን በማድረግ የአማርኛ ትርጉም መጀመሩ ታወቀ::

ከአፍሪካ የዙሉን; ስዋህሊን የሱማሊኛን ቋንቋዎች ወደ እንግሊዘኛ ሲተረጉም የቆየው ጎግል በዓለም ላይ የራሷ ፊደል ብቻ ያላትን የኢትዮጵያን የአማርኛ ቋንቋዎች ወደ መተርጎሙ መሸጋገሩ በርካቶችን አስደስቷል:: የጎግል ከ እንግሊዘኛ ወደ አማርኛ ትርጉም አንዳንድ የአረፍተ ነገር ችግሮች ቢታዩም ጅምሩ ግን በጣም መልካም ነው:: የጎግል ትርጉም አገልግሎት እንግሊዘኛን ወደ አማርኛ የመተርጎሙን ሥራ ከመጀመሩም በላይ ስፓኒሽ; ፈረንሳይኛ; አረብኛ ቋንቋዎችን ጨምሮ ወደ 104 ቋንቋዎችን ወደ አማርኛና ከአማርኛ ይተረጉማል::

በአሁኑ ወቅት በጎግል ትርጉም ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ; ከ እንግሊዘኛ ወደ አማርኛ መተርጎም ይቻላል:: እንኳን ደስ ያለን::

The post ጎግል ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ- ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ ትርጉም ጀመረ appeared first on Zehabesha Amharic.

በወለጋ ሆሮጉድሩ ጃራቴ ወረዳና በምዕራብ አርሲ ዋዴና ኤዶ ከተሞች መንገዶች ተዘጋግተው ተቃውሞው ቀጥሏል

$
0
0

Horo Gudru
(ዘ-ሐበሻ) መንግስት በቁጥጥር ሥር አውዬዋለሁ በሚለውና በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ተባብሶ በቀጠለው የሕዝብ አመጽ ዛሬ በወለጋ ሆሮጉድሩ በተለይም ጃራቴ ወረዳ አሊቦ ከተማ ተቃውሞ እየተሰማ ነው::

በዚሁ ሆሮጉድሩ ከተማዋን ከተለያዩ ከተሞች ጋር የሚያገናኟት መንገዶች በሰልፈኞች የተዘጋ መሆኑ ሲታወቅ ይህ የመንገድ መዝጋቱ ተቃውሞም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እየቀጠለ መሆኑ ተሰምቷል;:

በሆሮ ጉድሩ እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ መንገዶች በመዘጋጋታቸው ወደ ሌላ ከተማ ለመዘዋወር የሚፈልጉት ላይ መስተጓጎል እንደተፈጠረ ታውቋል:: የፌደራል ፖሊሶች አካባቢውን ከበው ከሕዝቡ ጋር የተፋጠጡ ሲሆን በወጣቶች እና በገበሬዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውም ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች ያሳያሉ::

በሌላ በኩል በም ዕራብ አርሲም አለመረጋጋቱ እንዳለ መሆኑ ተሰማ:: ዛሬ በዋዴ እና ኤዶ በተሰኙ ከተሞች ተቃውሞዎች የነበሩ ሲሆን ሙሉ በሙሉ በሰልፈኞች መንገዶች መዘጋታቸውና በነዚያ መንገዶችም መኪኖች ማቋረጥ እንደማይችሉ ተሰምቷል:: ሕዝቡ መንገዶችን በመዝጋት ላይ የሚገኘው ዛፎችን በመቁረጥና በትላልቅ ድንጋዮች ነው::

የአሜሪካ; የፊላንድ; የኖርዌይና የተለያዩ ሃገሮች ዜጎቻቸው ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዳይሄዱ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውም ጨምሮ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል::

The post በወለጋ ሆሮጉድሩ ጃራቴ ወረዳና በምዕራብ አርሲ ዋዴና ኤዶ ከተሞች መንገዶች ተዘጋግተው ተቃውሞው ቀጥሏል appeared first on Zehabesha Amharic.


ወደ ጉደር እና አምቦ የሚያደርሱ በርካታ መንገዶች በሰልፈኞች ተዘጋግተዋል |በአምቦ አፈሳ ተጀምሯል

$
0
0

Gudar ambo gudar

(ዘ-ሐበሻ) እየተጋጋለ የመጣው የኦሮሚያ ክልል የሕዝብ አመጽ ወደ መንገዶች መዘጋጋት ተሸጋግሯል:: በዚህ ተቃውሞ አሁንም በርካታ አንድን ከተማ ከአንድ ከተማ የሚያገናኙ መንገዶችን በመዝጋት የቀጠለ ሲሆን በደርሰን መረጃ መሰረት ወደ ጉደር እና አምቦ የሚያደርሱ መንገዶች ሙሉ በሙሉ ተዘጋግተዋል::

ሰልፈኞች በፌደራል ፖሊስ ወታደሮች የሚደርሰባቸውን የጥይት እና የዱላ ድብደባ ሳይበግራቸው አሁንም ይህንኑ የመንገድ መዝጋቱን ተቃውሞ በተለያዩ ከተሞችም እንደሚያደርጉት እየተጠበቀ ነው:: ወደ ጉደር እና አምቦ ከሚያደርሱ መንገዶች በተጨማሪ በወለጋ ሆሮጉድሩ ጃራቴ ወረዳና በምዕራብ አርሲ ዋዴና ኤዶ ከተሞች; በጉራዋ ምስራቅ ሐረርጌ መንገዶች በሰልፈኞች ተዘጋግተዋል::

በምስራቅ ሐረርጌ ጉራዋ ከተማ በተደረገ ተቃውሞ የፌደራል ፖሊስ ኢብሳ ጀማል መሐመድ የተባለን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ክፉኛ ማቁሰሉ ታውቋል::

በሌላ ዜና በአምቦ አፈሳ መጀመሩ ታውቋል:: የፌደራል ፖሊሶች በከተማ በቶዮታ ፒካፕ ላንድክሩዘር መኪና እየተዟዟሩ ለዓይናቸው ያላማራቸውን እና አመጽ ሊቀሰቅስ ይችላል ብለው ያሰቡትን ሰው ሁሉ እያፈሱ በመሄድ ላይ መሆናቸውን ለዘ-ሐበሻ መል ዕክታቸውን ያስተላለፉ ወገኖች ገልጸዋል::

The post ወደ ጉደር እና አምቦ የሚያደርሱ በርካታ መንገዶች በሰልፈኞች ተዘጋግተዋል | በአምቦ አፈሳ ተጀምሯል appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ወሲብ ብጉርን ካጠፋ ለምን በማስተርቤሽን አይጠፋም? |የዶክተሩን ምላሽ ያንብቡ

$
0
0

እኔ የ22 ዓመትና የአንደኛ ዓመት ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወጣት ስሆን እስካሁን ድረስ የሴት ጓደኛ የለኝም፡፡ ወሲብ የማድረግ ፍላጎ አለኝ፡፡ ግን አላደርግም፡፡ ለምን መሰላችሁ ዘመኑን ፈርቼ ነው፡፡ በተኛሁበትም ዝም ብሎ የዘር ፍሬዬ ይፈሳል፡፡ ምን ይሄ ብቻ እኔም ሴጋ እየተጠቀምኩ በሳምንት ለጌ አፈሳለሁ፡፡ ሴት ልጅ ስመለከት ደግሞ ስሜቴ ወዲያውኑ ይቀሰቀሳል፡፡ ከምንም አይነት ሴት ጋር ልቅ የሆነ ወሲብ አላደርግም፡፡ ፊቴ በጣም ብጉር ይበዛበታል፡፡ ‹‹ይህ ፊትህ ወሲብ ትፈፅም ጥርት ይልልህ ነበር›› ይሉኛል፡፡ እኔ ግን ከማንም ጋር ወሲብ ከማድረግ ሴጋ መጠቀም መርጫለሁ፡፡ ስለዚህ ከእናንተ የምፈልገው ሐኪማዊ ምክርም እውነት ወሲብ ብጉርን ያጠፋል? የብጉር ዋና መንስኤው ምንድነው? ይህ የሴጋ ሥራ በወደፊት ህይወቴ የሚያመጣው ችግር አለ? ውለታ ከፋይ ያድርገኝና የዚህን ጥያቄ መልስ ወደ ኋላ ላታደርጉ ቅድሚያ ሰጥታችሁ እንድታስተናግዱኝ ከወዲሁ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

ከቤ ነኝ

ask your doctor zehabesha

ውድ ከቤ፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ የአንተ ጥያቄ ቀላል ግምት የምንሰጠው ሆኖ አላገኘነውም፡፡ በበርካታ ታዳጊ ወጣቶቻችን በተደጋጋሚ የሚጠየቅና በህሊናቸውም የሚጉላላ ከመሆኑ አንፃር ደብዳቤህን ስናስተናግደው በታላቅ አክብሮትና ደስታ ነው፡፡

ብጉር በማንኛውም ሰው ላይ በየትኛውም ዕድሜው ሊከሰት የሚችል ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ የሚታየው ግን ዕድሜያቸው ለአቅመ አዳማ ወይም ለአቅመ ሔዋን በደረሱ በአስራዎቹ ውስጥ በሚገኙ ጎረምሶች እና አልፎ አልፎ ደግሞ በሃያዎቹ ውስጥ በሚገኙ ወጣቶች ላይ ነው፡፡

ብጉር እንዲህ ባለ ሁኔታ ከጉርምስና ዕድሜ ጋር በቀጥታ ሊያያዝ የቻለው የራሱ የሆነ ምክንያት አለው፡፡ በዚህ የዕድሜ ክልል ላይ በሚገኝ ሰው አካል ውስጥ የሚከሰቱ ለየት ያሉ ለውጦች ያሉ ሲሆን በተለይም አካላዊ ለውጦች በጉልህ የሚታዩ ናቸው፡፡ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ የሰውነት ቁመት ይረዝማል፡፡ በወንዶች ዘንድ ትከሻ ሰፋ ሰፋ ብሎ የደረትና የእግር እጅ ጡንቻዎች ይፈረጣጥሉ፡፡ ድምፅም እንዲሁ በመጀመሪያ መቆራረጥ፣ ቀጥሎ ደግሞ ይጎረንናል፡፡ ሴቶችም በፋንታቸው ለአቅመ ሄዋ መድረሳቸውን የሚያመላክቱት እንደ ቁመት መጨመር፣ የቆዳ መለስለስ፣ የሰውነት ቅርፅ መዳበርና የጉሮሮ ድምፅ መቅጠን ከዚህ የጉርምስና ለውጥ ውስጥ የሚከተቱ ናቸው፡፡

እነዚህ ሁሉ ለውጦች የሚመጡት ዕድሜን ተከትለው መሆኑ ታውቋል፡፡ ዕድሜን ተከትሎ የሚመጣው ሌላው ለውጥ ደግሞ ሆርሞን እየተባሉ የሚጠሩ ኬሚካሎች መጠን መጨመር ነው፡፡ በጉርምስና ዕድሜ ወቅት ሆርሞኖች በሰውነታችን ውስጥ ያላቸው መጠን ይለወጣል፡፡ በተለይም የፆታ ሆርሞኖች በደም ውስጥ ያላቸው መጠን ከበፊቱ ጋር ሲነፃፀር በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ በጉርምስና ወቅት ለሚከሰቱ አካላዊ ለውጦች ቀጥተኛ ተጠያቂዎቹም ሌላ ነገር ሳይሆን እነዚህ የፆታ ሆርሞኖች ብቻ ናቸው፡፡

እነዚህ ልዩ የፆታ ሆርሞኖች የጉርምስና ዕድሜን ብቻ ጠብቀው እንዲህ አለቅጥ መብዛታቸው የተፈጥሮን አላማ ለማሳካት በሚል ሲሆን፣ በእዚህ ዕድሜ የሚከሰቱ አካላዊ ለውጦች ወንዱን ለዘር ፈሳሽ አመንጭነት፣ ሴቷን ደግሞ ፅንስን ተሸክማ ለመውለድ መንገድ የሚጠርጉ ናቸው፡፡ ትውልድ ትውልድን እየተካ የሰው ዘር ዝርያውን ከምድረ ገፅ ሳያጠፋ እንዲቀጥል የማድረግ ኃላፊነቱ የተጣለው በእነዚህ የፆታ ሆርሞኖች መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

በጉርምስና ወቅት የወንድና የሴት ልጆች ባህሪም ይቀየራል፡፡ ወንዶች ወደ ሴቶች መመልከትና የሴቶችን ውበት ማድነቅ ይጀምራሉ፡፡ ሴቶችም እንዲሁ፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ አስተሳሰብ ተቃራኒ ፆታዎችን እርስ በእርሳቸው አቀራርቦ ተራክቦ እንዲፈፅሙና ብሎም ዘር እንዲያፈሩ የሚያደርግ ነው፡፡ እንግዲህ ሰዎች ለአካለ መጠን ሲደርሱ አካላዊና ስነልቦናዊ ለውጥ እንዲያመጡና በእነዚህ ለውጦች ተገፋፍተውም ተራክቦ እንዲያደርጉ ያዘዘችው ተፈጥሮ ነች፡፡ ይህን ትልሟን በማስፈፀምም የፆታ ሆርሞኖችን በብዛት እንዲመነጩ ታደርጋለች፡፡

ከእነዚህ የፆታ ሆርሞኖች መካከል በተለይም ቴስቴስትሮን በመባል የሚታወቀው ንጥረ ነገር በቆዳ ላይ አንዳንድ ለውጦችን ያስከትላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ብጉር ነው፡፡

በጉርምስና ዕድሜ የዚህ ልዩ ሆርሞን መጠን መጨመሩ ስለማይቀር ብጉር መፈጠሩ የማይቀር ነው፡፡ ሁሉም ሰዎች ይህን የጉርምስና ጊዜ ብጉር ማውጣትን አሳልፈው ነው ወደ ወጣትነት እና ጎልማሳነት የዕድገት ደረጃ የሚዘልቁት፡፡

ሆኖም የአንዳንድ ሰዎች ብጉር ግን ለየት ያለ ነው፡፡ በብዛት አንፃር በጣም ብዙ ነው የሚበቅሉት፡፡ የብጉር እባጮችም ትላልቅና የፊትን ውበት ሊያበላሹ የሚችሉ ናቸው፡፡ ብጉር እንዲህ አለቅጥ እንዲስፋፋ በሚያደርጉት ከሆርሞን በተጨማሪ ማለት ነው ሌሎች ምክንያቶችም እንዳሉ ታውቋል፡፡

ከእነዚህ መንስኤዎች መካከል አንዱ የህሊና ውጥረት ነው፡፡ ማንኛውም ለውጥ አዲስ ሁኔታን ይዞ ይመጣል፡፡ ያለመዱት ነገር ደግሞ እስኪለማመዱት ድረስ ጭንቀት ማስከተሉ አይቀርም፡፡ ጉርምስናም እንደ ለውጥነቱ ሰዎችን ያስጨንቃል፡፡ ሰውነት በአንዴ ሲመዘዝ፣ ጡንቻ ሲፈረጥም ድምፅ ሲዘበራረቅ እና የፊት ቆዳም በሽፍታዎች ሲዋጥ በእርግጥም ማስበርገጉ አይቀርም፡፡

እንግዲህ በተዘዋዋሪ መንገድ የዚህ ጭንቀት መሰረቱ የፆታ ሆርሞን ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ የማህበረሰቡ አመለካከትም ተጨማሪ የጭንቀት መንስኤ ነው፡፡ ማህበረሰቡ በጉርምስና ወቅት ስለሚከሰቱ ለውጦች አስመልክቶ የሚያራምደው እምነት ከእውነታው የራቀ ሲሆን በሚከሰተው የተሳሳተ ግንዛቤ ሳቢያ የሚመጣ ችግርም ነው፡፡

በእርግጥም በጉርምስና ወቅት የሚከሰቱ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ለውጦች ሁሉ አላማቸው የፆታ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ሆኖም ይህ ፍላጎት የመነጨው በጎረምሳው ወይም በኮረዳዋ ፍላጎት ሳይሆን በውስጣቸው በሚዘዋወረው ሆርሞን አማካኝነት መሆኑ ግን ግልፅ ሲሆን አይታይም፡፡

በጉርምስና ወቅት ከሚከሰቱት አካላዊ ለውጦች መካከል ወሲባዊ ግንኑነትንም እምብዛም አስተዋፅኦ የሚያበረክተው ብጉር ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ከሌሎች ለውጦች ጋር አብሮ ስለተከሰተ ብቻ ብጉር ያለበት ሰው ወሲብ እንደሚያስፈልገው ተደርጎ ሲተረጎም ይታያል፡፡ ይህ ግን የተሳሳተ ትርጓሜ ብቻ ነው፡፡

ብጉርን ያመጣው የፆታ ሆርሞን ነው፡፡ የወሲብ ፍላጎትን ያመጣው የፆታ ሆርሞን ነው፡፡ የፆታ ሆርሞንን ለመቀነስ ቢቻል ብጉር ይጠፋል፣ የወሲብ ፍላጎቱም ይቀንሳል፡፡ ወሲብ ግን ብጉርን ሊቀንስ አይችልም፡፡

ይህን የመሳሰሉ በማህበረሰቡ የሚናፈሱ አመለካከቶች በጉርምስና ዕድሜ ላይ ያሉ ልጆች ላይ ከፍ ያለ ጫና ያመጡባቸዋል፡፡ የብጉር ሽፍታው የጨመረባቸውም ስለወሲብ ስላሰቡ ስለሚመስላቸውና ይህ ያላሰቡት ሐሳብም አደባባይ የወጣ ስለሚመስላቸው ይሸማቀቃሉ፣ ይጨነቃሉ፡፡

ይህ ጭንቀት ግን ቀድሞውንም ከማህበረሰቡ ዘንድ የመጣባቸው እንጂ ወሲብ ባለመፈፀማቸው አለመሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡ ለብጉር ብለው የሚፈፅሙት ወሲብም የማያስፈልግ ከመሆኑም በላይ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ጨምሮ ሌሎች የአባላዘር ህመሞችንና ስላልተፈለገ እርግዝና ያጋልጣቸዋል፡፡

ውድ ኬቢ፡- ብጉር በወሲብ የሚጠፋ ቢሆን ኖሮ አንተ የምታዘወትረው ማስተርቤሽን (ሴጋ) የሚባለው ወሲብ አይነት ድራሹን ባጠፋልህ ነበር፣ ከእንስት ጋር የምታደርገው ግንኙነትም የተለየ ውጤት አያስገኝምና፣ ስለዚህ የሚወራውን ወሬ አትመን፣ በመታቀብህም ፅናበት፡፡

በተረፈ ግን

1. ብጉርን በጣትህ ለማፍረጥ ፍፁም አትሞክር፡፡ ወደ ጠባሳነት ይቀየርብሃል፡፡

2. ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ይህ ብጉርህ ይከስምልሃል፡፡

3. አለቅጥ የበዛውን ብጉርህን ሊያስወግዱ የሚችሉ እንደ Doxycycline ያሉ መድሃኒቶች ስላሉ በሐኪም ትዕዛዝና ገዝተህ መጠቀም ትችላለህ፡፡

4. የጉርምስና ለውጥ ከሰው ሰው ይለያያል፡፡ አንዳንዱ ድምፅ በጣም ይጎረንናል፡፡ አንዳንዱ ቁመቱ በጣም ይረዝማል፣ አንዳንዱ ጡንቻው በጣም ይፈረጥማል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ የፊት ላይ ብጉር ይበዛበታል፡፡ ስለዚህም አትጨነቅ እንልሃለን፡፡ መልካም የፊት ውበት!!

The post Health: ወሲብ ብጉርን ካጠፋ ለምን በማስተርቤሽን አይጠፋም? | የዶክተሩን ምላሽ ያንብቡ appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ብርቋ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ትናንት በስዊድን ሪከርድ የሰበረችበት ቪዲዮ

በቶረንቶ ካናዳና አካባቢው ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የቀረበ ጥሪ

የበይነመረብ ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ

$
0
0

የበይነመረብ ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ

የዘመቻው ርዕስ፦ የኅሊና እስረኞች ይፈቱ!
የዘመቻው ቀናት፦ የካቲት 16-17, 2008
የዘመቻው ዓላማ፦
1ኛ) በግፍ የታሰሩ ጓደኞቻችን እንዲሁም ሁሉም የኅሊና እስረኞች (በምርመራ ቀጠሮ ላይ ያሉ፣ ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት የሚመላለሱ እና የተፈረደባቸው) ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ መንግሥትን ለመጠየቅ እና ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሚሠሩ አካላትም ተፅዕኖ እንዲያደርጉ ለመጠየቅ፤
2ኛ) በየእስርቤቱ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ያሉበትን ሁኔታ ለሕዝብ ማሳወቅ፤
3ኛ) ስለመረጃና የመናገር ነፃነት፤ ስለፍትሕ፣ ስለመንቀሳቀስ መብት፤ እና መሰል ሰብኣዊ መብቶች ግንዛቤ ማስጨበጥ እና መንግሥት እነዚህን መሠረታዊ መብቶች እንዲያከብር ዜጎች እስከጥግ ስለመብታቸው በመጠየቅ የድርሻቸውን እነወዲወጡ ማበረታታት።
የዘመቻው ቦታ፦ ዘመቻው በዋነኛነት የሚካሄደው ‹‹ፌስቡክ›› እና ‹‹ትዊተርን›› በመጠቀም ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ጦማሪዎችና የዜና አውታሮች በየጦማሮቻቸው ላይ በመጻፍ ዘመቻውን መቀላቀል ይችላሉ።
የዘመቻው ዋና፣ ዋና ሃሽታጎች፦ #FreeAllPoliticalPrisoners #ሁሉም_የኅሊና_እስረኞ_ችይፈቱ #FreeZelalem #ዘላለም_ይፈታ #FreeEthiopia #ኢትዮጵያ_ትፈታ #FreeAllBloggersAndJournalists #ጋዜጠኞችና_ጦማሪዎች_ይፈቱ #FreeJournalists #ጋዜጠኞች_ይፈቱ

Ze2-340x340
የዘመቻው ተሳታፊዎች፦ ያገባናል የሚሉ ሁሉ!
ዘመቻው ላይ መሳተፍ የሚቻልባቸው መንገዶች፦
1ኛ) በዘመቻው ወቅት ዘማቾች ፕሮፋይል ፎቶዎቻቸውን እና የከቨር ምስሎቻቸውን ለዘመቻው በተዘጋጁ የፖለቲካ እስረኞች ፎቶዎች (ወይም ራሳቸው ባዘጋጁት ምስል) እነወዲሁም አባባሎች በማስዋብ መቀየር፣
2ኛ) በየዕለቱ የተለያዩ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ፣ በፖለቲካ እስረኞች አያያዝ፣ በፍርድ ቤት ቤት ሒደት እና መሰል ጉዳዮች ላይ የሚያውቁትን መረጃ በመጻፍ እና የተጻፉትንም በማጋራት፣
3ኛ) ስለሚያውቁት የፖለቲካ እስረኛ ማንነት እና ስለእስሩ ዝርዝር መረጃዎችን በማጋራት፣
4ኛ) መጠየቅ የሚፈቀድላቸው የፖለቲካ እስረኞችን በመጠየቅ አሰተያየቶቻቸውን እና ያሉበትን ሁኔታ መልሶ ለሕዝብ በማድረስ፣
5ኛ) ከፖለቲካ እስረኛ ቤተሰቦች ጋር በመነጋገር ያሉበትን ጥቅል ሁኔታ ይፋ በማድረግ… እና ወዘተ።
ze3-340x340
——
ዘላለም ወርቃገኘሁ ደ ብርሃን ብሎግ ላይ አጋር ጦማሪ ሆኖ ሰርቷል። በታሰረበት ወቅት ሃምሌ ሁለትሺ ስድስት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ዲግሪ ተማሪ ነበር። ከአራት ወራት በሁዋላ ሲከሰስ የግንቦት ፯ አባል በመሆን፤ በዓረቡ አገር የተከሰተው ሽብር በኢትዮጵያም ተከስቶ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመጽ ለመጣል ሰዎች መልምሏል ፣ ለዚህም የሚጠቀምበት አሥር ሺሕ ብር ተልኮለታል ተብሎ ተከሷል። በተጨማሪም ማኅበራዊ ድረ ገጽ በመክፈት፣ በአንድ አገር በአመጽና በግጭት ማኅበራዊ ለውጥ የሚመጣበትን ማብራሪያ የሚጠይቅ መልዕክት ተላልኳልም ተብሎ ተከሶ ነበር:: ይሄ ብቻ አደለም ስለጎንደር ዩንቨርሲቲ ረብሻ በፈረንጆች አቆጣጠር ፳፩፩ መፃፉና ይህም በውጭ አገር ባሉ ድህረ ገፆች ላይ መውጣቱ፣ ሃገር ቤት ውስጥ ካሉ ጓደኞቹ ጋራ ስለፖለቲካ መወያየቱ መምከሩ ሁሉ በክሱ ወስጥ ተጠቅሰዋል። ከዘላለም ጋራ ሌሎች ሁለት ጓደኞቹ ታስረዋል፥ ዮናታን ወልዴና ባህሩ ደጉ፣ ጥፋታቸው ደሞ አንድ አሜሪካን አገር ያለ ኢትዮጲያውዊ ጋዜጠኛ አለ ባለው የኢንተርኔት ስልጠና ላይ ለመካፈል በማመልከታቸው። ክሱ ግን የሽብር ስልጠና ነው ይለዋል።
ze11-415x153
ከስድስት ወር በፊት ፍርድ ቤቱ ብዙዎቹን ክሶች ውድቅ አድርጎ አባላት ለመመልመል መሞከርና የኢንተርኔት ስልጠናውን ማመቻቸት በሚሉት ላይ እንዲከላከሉ ወሥኖ ነበር። በዚህም መሠረት ሁሉም የመከላከያ ምስክሮች የተሰሙ ሲሆን (ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ)፤ በየካቲት 16 የመጨረሻው የመከላከያ ምስክር አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲሰሙ ቀጠሮ ተይዟል። ዘላለም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መከላከያ ምስክር አድርጎ የጠራው በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ተገናኝተህ ነበር የሚል ክሱ ውስጥ ስለተካተተ ነው።
ደብርሃን ብሎግና ወዳጆቻችን የሁለት ቀን የበይነ መረብ ዘመቻ አዘጋጅተናል። በዚህ ዘመቻ ላይ በመሳተፍ እነዘላለምንና እነሱን የመሳሰሉ ሰዎች ከእስር እንዲፈቱ፤ ይህን አይነትም ኢፍትሃዊነት እንዲበቃ በጋራ እንድንጠይቅ ጋብዘናችሗል።
ስለ ተከሳሾቹ ወይም ስለክሶቹ ጠለቅ ያለ መረጃንማግኘት ይህን: ይህን: ይህን: ይህን ወይም ይህን ማስፈንጠሪያ ወይም ሊንኮች ይጠቀሙ።

ze4-340x340
ze5-340x340

The post የበይነመረብ ዘመቻ ጋዜጣዊ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live