Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኢሳት የሳምንቱ እንግዳ- ጋዜጠኛና መምህር ሪዮት አለሙ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋር


የዕምነት ቤቶች ምን እየአደረጉ ናቸው? |ቁምላችው መኩሪያ

0
0
 
      የዕምነት አባቶች በዕኩይ መሪዎች ምክንያት  ፍትህ ሲጓደል፤ ድሀ ሲበደል እና መንገጋው ሲበትን ብሎም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ፍጡር ሲገድል፤ ሲሰደድ እና በረሃብ አለንጋ ሲገረፍ  በዳዩን የመገሠፅ  የሞራልም ሆነ የዕምነት ግዴታ አለባቸው።
prayer
አሁን ግን በዕምነት ቤቶች አከባቢ ይህ ሴደረግ አይተይም። ይባስ ብሎም ስለ ተበደለ ህዝብ መነገር ፖላቲካ ነው  ወይም ከዕምነት አሥተምህሮት ውጪ ነው አሊያም ሁለቱንም ናቸው በማለት ውኃ የማይቆጥር  ምክንያቶች ሲደረድሩይ ይደመጠሉ። 
በትልቁ መጽሐፈችን በመጽሐፍ ቅዱስ ግን (እርግጠኛ ነኝ በቅዱስ ቁራኑም ቢሆን ሰለ ፍትህ እና ስለ ሰው ልጆች ደህንነት ሳያወሳ አቀይርም  ብዬ አምናለሁ)  የሚከተሉት ተፅፈዋል በዕምነተት ቤቶችም ተሰብካዋል።

 

    • ሙሴ፡ ፋርዖንን ገስፆል ህዝብንም ከባርነት አውጥቷል።

 

    • ነብዩ ናታን፡   ንጉሥ ደዊትን ግስጾል፡ ደዊትም ዕንባ አውጥቶ አልቅሶል።

 

    • ቅዱስ ዮሐንስ፡ ሔሮዶስን ገሥጾል።

 

    • የመይሞተው እየሱስ ክርስቶስ የሞተው የሰውን ልጅ ከባርነት እና ከመካራ ለመታደግ ነው።ምሣሌነቱም የሰው ልጅ በአርዕየ ክርስቶሰ ለተፈጠረው ወንድሙ  በመካራ ቀን ከጎኑ ቁሞ መስዋዕት መክፈል እንደአለበት ለማሳየት ነው።

 

    • አባታችን ብፁ ወቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ መንገውን ሊበትን የመጠን ወራሪ በጎቼን አትንካብኝ ብለው ደረታቸውን ለአሩር ስጠዎል።አሁን ግን አባቶቻችን ያቋሙላቸው ሀውልት የትም ሲጣል ዝምታን መርጠናል።

 

 አባቶቼ ሆይ!!፦ እንደ እናተ አሰተሳሰብ ቢሆን እኒህ ሁሉ ከለይ የተዘረዘሩት ፖላቲካኞች ናቸው ማለት ነው ? የሠሩት ሥራስ ከዕምነት አሥተምህሮ ውጪ ነው ማለት ነው? ለእናንተ ፖላቲካ ማለት ምን ማለት ይሆን? ፖላቲካኞች እኳ እያሉ ያሉት፦ ፍትህ ተጓደለ፡ ድሃ ተበደለ፡ ሀገር በዘውግ ተሸነሸነ፡ ህዝብ በራሃብ አለንጋ ተገረፈ። ወገን ተሰደደ ነው። ይህ የዕምነት ቤቶች ሥራ ከልሆነ ሥራችሁ ንግድ እና ውትድርና  ነው ማለት ነው?
  
የዕምነት አስተምህሮትስ ቢሆን ጥሬ ቃሉ  እኳ የሚለው  ድሓ ሲበደል ጩህ፡ ባልንጃራህን እንደ ራስህ ውደድ ነው። ታዲያ ሀገራችን  ኢትዮጵያ እንዲህ ስታናባ ህዝቦቾ በጥይት እና በራሃብ ሲቆሉ ካላአዘነችሁ ችግራቸውን ካልተነገረችሁ እራኝነቱ እና ባልንጀራን እንድ ራስ መውደድ ምኑ ላይ ነው?  በዚህ አጋጣሚ በስደት ለይ ያለውን የኢትዮጵያ ህጋዊ ሲናዶስ እና ወሺንግተን ዲሲ ያለውን ፈርስት ሂጅራን የኢትዮጵያ እስልምና ምህበርን    አመሰግናለሁ። በሥሩ የሚገኙት አድባራት እና ካህናት እንዲሁም አጥባቂ ምዕመናን ግን ዝምታቸውን መሥበር አለባቸው እላለሁ። የእስልምናውም ቢሆን እንዲሁ።
 
   በርግጥ ሀገርን በዬፊነው የሚያገለግሎ አራት በአዘውንት ዘንድ “ቀአነተ” በሚል ምህፀረ ቃል የሚተውቁ መሰረተዊ አውታሮች ማለትም” ቀዳሽ(ኃይማኖት)፡ አራሽ(አምራች)፡ ነጋሽ(አስታዳዳሪ)፡ ተኮሽ(ወተደር)”   የስፈልጓታል። ይህ ማለት ግን መነኩሴውም ሆኑ ጰጰሱ፡ ሼኪውም ሆኑ ቄሱ፡  ዘመሪውም ሆኑ ፓስተሩ ሀጂውም ሆነ ደብታራው በፖላቲካ እና  በእስተምህሮ ቆፈን ተሸብበው በዝምታ ይቆዝሙ ማለት አይደለም።  ኃይማኖት መልኩን ሲቀይር ሀገርም ደብዛው ሲጠፋ ህሊናቸውን ሊጎሽማቸው ይገባል።
  ሌላው አሳዛኙ “ሀገራችን በሰማይ ነው ስለ ምድር አተስቡ” የሚባለው መፈክር ነው። በርግጥ ስለ ሰማይ ቤተችን ማሰቡ ጥሩ ነው ። ዕውነተኝውን የሰማይ ቤት የምናገኘው እኳ በምድር ለይ ሆነን በሰረነው በጎ ሥራ ነው። በምድር ለይ ሆነን  የወገንን ሥቃይ ለመታደግ  ለባረከትነው  ልቅሶነው።በምድር ለይ ሆነን ወገንን ከባርነት እና  ከሞት ለመታደግ ለደረግነው መልካም ሥራ ነው። 
  ይህንን ምድር ሆነን ካልሰረን የትኘው ሰማይ ነው ሀገራችን የሚሆነው?
    ያ የሰማዩ መንግሥት(ቦታ) እኳ  እንደ ወየኔ መንግሥት በዘመድ ወይም በአገር ልጅነት ወይም እንደ ኮንደሚኒያም በማጎብደድ አይተደልም። እባካችሁ ወገኖቼ ዕምነትን በትክክል እንተርጉም።
  ወገኖቼ ሆይ!!፦ ሀገር በመንታ መንገድ ለይ ነት። ወየኔ በፈጠርው ጧስ ወገን በጥይት እና በራሃብ አላንጋ እዬተገረፈ ነው። መሬት እዬተቆረሰ ለሱደን፤ ለሰውዲ ዓረቢያ፧ ለቻይና፤ ለህንድ፤ ለግብፅ፤ ለኴያት እና ለቤልጂያም እዬተደለ ነው። ሀገሬቷን የዘር ፖላቲካ እዬአናዋጣት ነው።ኢትዮጵያን የመሰለች ትልቅ ሀገር ወደብ አልባ ሆናለች። ውርደት እና ራሃብ መለዮችን ሆናዋል። ዝም ብለን ከአየናቸው እነዚህ የጣሊያን ቡችሎች ሀገረችንን በጥቂት ጊዜ ውስጥ ያጠፎታል።  ስሞንም ይቀይሮታሎ።
 የትግራይ ወጣቶች ሆይ!!  ከሌሎች ኢትዮጵያውኖች ጎን ቁሙ። ራሳችሁን ከታሪክ ተጠየቂነት አድኑ። የትግራይ አባት እና እናቶች ሆይ!! ልጆቻችሁን ሀይ በሎቸው። ከአብራካችሁ የወጡ ልጆቻችሁ ሀገር አያጥፉ፡ ወገንም አይጨርሱ ነው።
 
አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ!!!
“ኢትዮጵያ ታበፅህ እደዊሃ ሀበ ኢግዚአብሔር”!!!!!!

The post የዕምነት ቤቶች ምን እየአደረጉ ናቸው? | ቁምላችው መኩሪያ appeared first on Zehabesha Amharic.

ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማሪያም ደሳለኝ (በዛልኝ ፀጋው ) -አዲስ አበባ

0
0

ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ይህን ደብዳቤ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዋናው ምክንያት በአሁን ጊዜ በብዙ ኢትዮጲያዊያን ላይ የሚፈጸመውን ግድያ፣ ግፍ፣ መከራና ሰቆቃ በመመልከት ከምንም ነገር በላይ የአገራችን የኢትዮጲያ ቀጣይ ሁኔታ ስላስጨነቀኝ ነው። አቶ ኃይለማሪያም፣ እርስዎ ወደስልጣን ሲወጡ አገራችን የተሻለ አስተዳደር ታገኛለች ብለው ብዙ ተስፋ አድርገው ከነበሩት ኢትዮጲያዊያን መካከል አንዱ ነኝ። ለዚህም ምክንያቶች ነበሩኝ። አንደኛ እርሰዎ እግዚአብሄርን የሚፈሩ ሰው ነዎት ሲባል በመስማቴ፣ ሁለተኛ በትምህርት ባገኙት ችሎታዎ በራሰዎ የሚተማመኑና የሚያምኑበትን ለመናገር ወደኋላ አይሉም ብየ በማሰቤ፣ ሶስተኛ በትምህርት ቤት በነበሩበት ዘመንዎ ያዩት የነበረው የተማሪወች እንቅስቃሴ ለአጠቃላይ ህዝብ መብት መከበር እንጅ በዘር ላይ ያልተመሰረተ ስለነበር፣ እርሰወም የዘር ፖለቲካን እንደዋና መርህ አይቀበሉም ብየ መገመቴ፣ አራተኛ እነ አቶ መለስ የሚቃወሟቸውን ሁሉ፣ የረሳቸውን ጓደኞች ሳይቀር፣ እያጠፉ ለሰው ህይወት ብዙም ሳይጨነቁ ወደ ስልጣን ሲመጡ፣ እርሰዎ ግን ወደ ስልጣን አመጣጠዎ የተለየ ነው ብየ በመገመቴ ነው። ይህ አመለካከቴ ከመጠን በላይ በጎ ነገር ከመጠበቅ የተነሳ መሆኑን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተረዳሁ መጣሁ። እኔ ተስፋ ሳደርግ፤ ብዙ ኢትዮጲያዊያን ግን የእርሰዎ ጠቅላይ ሚንስቴር መሆን፣ ስልጣኑንና፣ ጦሩን፣ የስለላ ድርጅቱንና ኢኮኖሚውን ህውሃት እስከተቆጣጠረው ድረስ፣ ለውጥ እንደማያመጡ ሲናገሩ ነበር። በትክክልም እርሰዎ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንዳሉ መገንዘብ ቻልኩ። ሆኖም ግን አሁንም አገሪቱን ወደ ከፋና የማትወጣበት ችግር ወስጥ ከመግባቷ በፊት፣ በታሪክም ተወቃሽ እንዳይሆኑ፣ ህዝቡን ይዘው ማድረግ የሚችሉትን መጠቆም እወዳለሁ። የወያኔ መንግስት ባመጣው በዘር ከፋፍሎ አስተዳደር፣ በገዥው መንግስት መሪነት፣ በህዝቡ መካከል ይዘራ የነበረው የዘርና የጥላቻ ፖለቲካ፣ ከሃያ አራት አመታት በላይ በዘለቀው ገደብ የሌሌው የመብት ረገጣና የንጹሃን ግድያ ጋር ባንድ ላይ ሆኖ በፈጠረው ብሶት፣ የህዝብ አመጽ ገንፍሎ እየመጣ ነው። ይህም የአገራችንን የወደፊት እጣ ምን ሊሆን እንደሚችል ማወቅ አስቸጋሪ አድርጎታል። እርስወ በዘር ፖለቲካና ትእቢት በተሞሉና፣ የህዝብ ሃብት በሚዘርፉ ወያኔወች ተተብትበው በመታሰርዎ ኢትዮጲያን በዲሞክራሲያዊ መንገድ መምራት እንደማይችሉ ኢትዮጲያዊ ሁሉ ያውቃል። ሆኖም ግን አገራችንን ከከፋ ጥፋት ለማዳን አሁንም ማድረግ የሚችሏቸው ነገሮች አሉ፣ 1. የህዝቡን ስቃይና መከራ ለማየት ህሊናዎን ይክፈቱ፣ 2. የመብት ጥያቄ የሚያነሱትን ኢትዮጲያዊያን ጠላት አድርጎ መመልከትዎን አቁመው ለአገራቸው እንደሚያሰቡና በአገራቸው ጉዳይ እኩል ባለድርሻ መሆናቸውን ይቀበሉ፣ 3. የመንግስት ሃይል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚያደርገውን ዘግናኝ ግድያ ባስቸኳይ ያስቁሙ፣ 4. የታሰሩትን የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች በመፍታት፣ ሁሉንም ለአገሪቱ ባለድርሻ የሆኑትን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት መሪወች፣ የዜጎች ወይም ማህበራዊ ድርጅቶች መሪዎችና ያአገር ሽማግሌወች የሚካፈሉበት አገር አቀፍ ጉባኤ በመጥራት፣ ጉልበት ሳይሆን የህግ የበላይነት የሚመራበት ሁሉን ኢትዮጲያዊ የሚወክል መንግስት እንዲቋቋም ይርዱ፣ 5. ይህን ማድረግ የማያስችለወት ሁኔታ ካለ ግን፣ ለኢትዮጲያ ህዝብ ችግረዎን በግልጽ አሳውቀው ስልጣንወን ይልቀቁ። ይህን በማድረግ ለእግዚአብሄር፣ ለኢትዮጲያና ለኢትዮጲያ ህዝብ መታመነዎን ያሳያሉ። ይህን መልዕክቴን በቀና ልቦና እንደሚያዩልኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

The post ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማሪያም ደሳለኝ (በዛልኝ ፀጋው ) -አዲስ አበባ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኤርሚያስ አመልጋ የተገባላቸው ቃል ታጥፎ ለእስር ተዳረጉ

0
0

ዘጋቢ ዳዊት ሰለሞን

ተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች መስራችና የአክሰስ ሪል ስቴት ባለቤት የነበሩት ኢንተርፕርነሩ ኤርሚያስ አመልጋ በኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሰራተኞች መታሰራቸው ተሰምቷል፡፡በአሜሪካ የነበሩት ባለሐብቱ ከመንግስት ጋር በተደረገ ረዘም ያለ ጊዜ የወሰደ ድርድር እንደማይታሰሩና ያሉባቸውን ዕዳዎች ሰርተው እንደሚከፍሉ በመስማማታቸው በየካቲት ወር ወደ አገር ለመመለስ መብቃታቸው አይዘነጋም፡፡
የኢትዩጵያ ቴሌቭዥን እንደዘገበው ከሆነ የታሰሩት ኤርሚያስ ኪሳራ አጋጥሞታል ስለሚሉት አክሰስ ሪል ስቴትና መኖሪያ ቤቶችን ለማግኘት ቃል ተግብቶላቸው ክፍያ ስለተፈጸመባቸው ቤቶች ምርመራ ይደረጋል ፡፡
ባለፈው ዓመት ሪፖርተር ጋዜጣ የፍትህ ሚንስትር ምንጮችን በመጥቀስ አስፍሮት በነበረ ዘገባ ‹‹በኤርሚያስና በድርጅታቸው ላይ የቀረቡባቸው 81 ክሶች ለአንድ ዓመት ሳይንቀሳቀሱ እንደሚታገዱ፣ ያሉባቸውን ዕዳዎች እስከሚከፍሉና ቤቶቹን በተመለከተ የተፈጠረውን ውዝግብ እስኪፈቱ ለአንድ ዓመት የህግ ከለላ እንደሚያገኙ ››ጠቅሶ ነበር፡፡
Ermias-Amelga
በ2004 ኦዲተሮች ባቀረቡት ሪፖርት አክሰስ ሪል ስቴት ለቤት ገዢዎቹ ለማስተላለፍ ቃል በመግባት የተለያዩ ክፍያዎችን የተቀበለባቸውን ቤቶች የማቅረብ አቅም እንደሌለው አስታውቀው ነበር፡፡ሪፖርቱ በወጣ በአመቱ ኤርሚያስ ወደ ጎረቤት አገር ከዚያም ወደ አሜሪካ አቀኑ፡፡ባለሐብቱ በአሜሪካ ቆይታቸው የደምበኞቻቸውን ገንዘብ መብላት እንደማይፈልጉ በመጥቀስ ከእስር በመለስ እዳቸውን ለመክፈል የሚያስችሏቸው ሁኔታዎች እንዲፈጠሩላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡
ነገር ግን ኤርሚያስ በአሁኑ ወቅት ወደ አገር ለመመለስ ያስቻላቸው የተስፋ ቃል እንደጉም በኖባቸው አንዱን ዓመት ሳያገኙ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል፡፡ኤርሚያስ ወደ አሜሪካ ከማቅናታቸው ጥቂት ቀደም ብለው ከቼክ ጋር በተያያዘ ታስረው የነበሩ መሆኑ አይዘነጋም፡፡
በአሜሪካ ትምህርታቸውን ያከናወኑት ኤርሚያስ በአገሪቱ በፋይናንስ ኢንደስትሪ ውስጥ ለዓመታት ሰርተዋል፡፡በ1989 አካባቢ ወደ አገራቸው የራሳቸውን ካምፓኒዎች በመፍጠር ሰርተዋል፡፡ባለሐብቱ አዳዲስ ሐሳቦችን በማፍለቅ ፣ካምፓኒዎችን በመመስረትና በገንዘብ በመደገፍ ተለይተው ይታወቃሉ፡፡
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የታሸገ ውሃ አምራች ካምፓኒ ሐይላንድ ውሃ፣ አክሰስ ካፒታል፣አክሰስ ባንክና ጃኖ ባንድን በመመስረት ስማቸውን አስተዋውቀዋል፡፡የኤርሚያስ የመጀመሪያ ካምፓኒ ሮያል ክራውን የተፈጥሮ ውሃ ፋብሪካ በተመሰረተ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ እንዲዘጋ መደረጉ አይዘነጋም፡፡

The post ኤርሚያስ አመልጋ የተገባላቸው ቃል ታጥፎ ለእስር ተዳረጉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ህዝብ ሃዘን ላይ ነው መሪዎቻችን ሰርግ ላይ ናቸው። አልተገናኘንም!!! ከተማ ዋቅጅራ

0
0

አንድ አርበኛ ጣሊያን ኢትዮጵያን ልትወር በመጣችበት ግዜ በትግል ላይ እያለ የእናቱ ሞት ይነገረዋል አጠገቡ ያሉትም አርበኞች የእናት ሞት ከባድ ነውና ትንሽ ሃዘንህ ቀለል እስኪልልህ ድረስ አንተ እዚህ ሁንና አረፍ በል እኛ ጠላትን እንፋለማለን ብለው ይነግሩታል። አርበኛውም እንዲ በማለት መለሰላቸው፡- የእናት ሞት በጣም ከባድ ነው። እናቴ የሞተችው በእናት አገሯ ላይ ነው። አገር ስላላት በክብር የሚቀብሯት ብዙ ወገን አሏት። ጠላት አገራችንን ሊያሳጣን ጦርነት ከፍቶብናል ሞተህ በክብር የምትቀበርበት ቀርቶ በህይወት እያለህ የሞት ሞትን ሞተህ የምትኖርበትን አገር ሊያደርግብን ነው። እኔ ለልጄ እና ለልጅ ልጄ ማውረስ የምፈልገው በክብር በነጻነት የሚኖሩባትን አገር የማስረከብ ሃላፊነት ስላለብኝ የናቴ ሞት ከአገሬ ክብር እና ከነጻነት በላይ አይሆንም የተሰጠኝ አደራ በመከራ ግዜ ወደኋላ ብዬ የሚያስቀር ሳይሆን እስከህይወት ፍጻሜ በጽናት ጠላቴን ለመታገል ነው። ስለዘህ ከአላማዬ የሚያስቀር ወደኋላም የሚያስብለኝ የለም እኔ ከእናቴ ብገኝም አሁን ግን የአገር አደራ ስለተቀበልኩኝ የህዝብ ነኝ ለህዝቤ ባርነትን አላወርሰውም፤ በማለት የእናቱ ሃዘን ሳያዝን ወደ ትግሉ ጎራ ሄዷል። እንኳን ሰርግን ቀርቶ የእናት ሞትንም ለህዝብ እና ለአገር ክብር ሲሉ የሚያሳልፉ ጀግኖች ነበሩን።የዛሬዎቹ አገርን እንመራለን የሚሉት የኢትዮጵያ ህዝቡ በከፍተኛ ሃዘን ላይ ባለበት አገር አደጋ ውስት ሆና ባልተረጋጋችበት ሰዓት ልጃቸውን እየዳሩ የሰርጋቸው ታዳሚ እንድንሆን ይነግሩናል።

haile1
እንደ ኃይለማርያም ትልቅ ቦታ ያለው ያውም የአገር መሪ የሚል ስም ይዘው ህዝብና ወገን በአጋዚ በጥይት እየተገደለ ህጻን፣ ነፍሰ ጡር፣ አዛውንት፣ ወጣት፤ ያለርህራሄ እየተጨፈጨፉበት ባለበት ሰዓት በቤተ መንግስት የተቀመጡት ልጄን ድሬአለው ብለው መናገራቸው ደስታው ወደ ሃዘን ይቀየራል ሃዘንም ወደ ደስታ ይለወጣል የሚለውን የመጽሃፍ ቅዱስን ቃል ላስታውሳቸው እወዳለው። ህጻናት የተገደሉባቸው እናቶች እያለቀሱ ባለበት ሰዓት፣ ነብሰ ጡር ስትገደል ሁሉም እያለቀሰበት ባለበት ሰዓት፣ የይኑቨርስቲ ተማሪዎች፣ 2ተኛና 1ኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ገበሬዎች፣ ሰራተኞች፣ ሲገደሉ ኢትዮጵያኑ ሁሉ ሃዘን ላይ በሆኑበት ሰዓት፣ እንባችን ሳይደርቅ፣ ሃዘናችንም ሳንጨርስ፣ የመብት ጥያቄአችን ሳይመለስልን፣ ገዳዮች እና በዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ እያለ ህዝቡ ተቃውሞውን በመግለጽ ላይ እያለ፤ አገር እመራለው፣ ህዝቡን በትክክል አስተዳድራለው ከሚሉት አካል 100% በህዝብ ተመርጬ ነው ስልጣኑን የያዝነው ተብሎ በሚናገሩት ዘንድ በየግዜው ለህዝብ የሚያሳዩት ጭካኔ ለስልጣናቸው እና ለጥቅማቸው የሚያሳዩት ስግብግብነት ያሳዝናል ህዝብ ሲያዝን እነሱ ይደሰታሉ ህዝባችን የሃዘን ድንኳኑን ሲደኩን እነሱ የሰርግ ዳሳቸውን ይጥላሉ። ሃዘንተኛው ሃዘኑን ሳይረሳ የሃዘን ድንኳንም ሳይፈርስ መሪ ተብዬው በአዳራሽ ውስጥ ልጃቸውን ይድራሉ። ህዝቡ ቤት ሃዘን… ቤተ መንግስት ሰርግ… የሚነገርባት አገር የሆነች ኢትዮጵያ ናት። ህዝባችንን እየገደሉ እያስለቀሱ ለማኖር ገዢዎቻችን ደግሞ እየሰረጉ እየተጋቡ የህዝቡ ሃዘን ለኛ ሰርጋችን ነው እያሉ ይገኛሉ። እናንተ ስትሞቱ እኛ እንባዛለን በማለት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የቅኝ አገዛዝ አዋጅ አውጀውብን ህዝባችንን ነጻነቱን ነፍገው እያሰቃዩት ነው። የህዝብ ሃዘን የህዝብ እንጂ የኛ አይደለም የህዝብ ሞት የህዝብ እንጂ ለኛ ሞት አይደለም ያሉ ይመስለኛል።

እዚህ ጋር አንድ ተራ ሰው ቢያደርገው ብዙም የሚደንቅ ነገር ላይሆን ይችላል። የአገር መሪ ግን ህዝቡ መረጠኝ የህዝቡን መብት አስከብራለው ብሎ ቃል ገብቶ በፖለቲካው ስልጣኑ ላይ ያሉት አካላት ግን እንደዚህ አይነት ነገር ሲያደርጉ ሊያስተላልፉ የሚፈልጉት መልዕክት አለው። እኛ ሰላም ላይ ነን ችግር የለብንም የሚሞትም ሆነ የተጎዳም ሰው የለም የተነሳም ተቃውሞ እንዲሁም የተወጣ ሰልፍ የለም የሚለውን መልእክት ለማስተላለፍ መሪ ተብዬው የልጃቸውን ሰርግ አድርገዋል። ይሄ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ችግር የሚባል የለም ችግር ቢኖር እንዴት ጠቅላይ ሚንስትሩ ልጃቸውን ይድራሉ ብለው የተለመደውን የማይቀየረው ስልታቸውን ለውጪ መንግስታት ለማቅረብ የሚያደርጉት የከሰረ ፖለቲካ አካሄዳቸው ነው።

ሌላው በመንግስት ደረጃ ያሉት አካሎች ያለ ህዝብ ፍላጎት ስልጣኑን እንደያዙት ያውቃሉ። የተነሳውንም የህዝብ ጥያቄ በአፈ ሙዝ አፍነው እንደያዙት ያውቃሉ። ህዝቡ እንደማይወዳቸው ብቻ ሳይሆን እንደማይፈልጋቸው ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ጠቅላይ ሚንስትሩ ልጃቸውን በዚህ ሰዓት ህዝቡ ከፍተኛ ሃዘን ላይ ሆኖ ሳለ ስልጣን ላይ ያሉት ፖለቲካውን በበላይ የሚመሩት እኛ ሰርግ ላይ ነን ደስታ ላይ ነን የሚል አንድምታን ይሰጠናል። የህዝባችን ሃዘን ለነሱ ደስታ ነውና። እንግዲ ምን እንላለን የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን በእጁ እስከሚያስገባ መከራና ሃዘን ሁሌም ቤቱ ውስጥ እንዳሉ ያውቃል። ዛሬ የመሸ የሚመስለው ነገ ለተጨቆነው ህዝብ ብርሃኑን ሲያበራው ለገዚዎቻችን ይጨልማል። ዛሬ ያዘናችሁ ተጽናኑ ነገ ትደሰታላችሁና። ዛሬ የተደሰታችሁ ነገ ታዝናላችሁና የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘን ግድ ነው ቃሉ የሰው ሳይሆን የፈጠሪ ስለሆነ። ጥቂት እንሰንብት ሁሉንም አብረን እናየዋለን።

ከተማ ዋቅጅራ
13.01.2015
Email- waqjirak@yahoo.com

The post ህዝብ ሃዘን ላይ ነው መሪዎቻችን ሰርግ ላይ ናቸው። አልተገናኘንም!!! ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከ6 ነጋዴዎች ጎማ አስነግዳችኋለሁ በሚል ብር ተቀብሎ ተሰውሯል የተባለው አርቲስት ሚኪያስ መሐመድን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ ጥረት ተጀመረ |የደረቅ ቼክ ማስረጃውን ይዘናል

0
0

Mikiyas ahmed

(ዘ-ሐበሻ)  ከ6 ሰዎች ገንዘብ ተቀብሎ ስንቅ የሌለው ቼክ በመስጠት ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ዕዳ አለበት ተበሎ የተከሰሰው አርቲስት ሚኪያስ መሀመድ(ባለታክሲው) ከተደበቀበት ለማስመጣት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተሰማ:: የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደገለፁልን አርቲስቱ በቼክ ማጭበርበር በጷግሜ ወር ውስጥ በአዲስ አበባ ቦሌ ፖሊስ መምሪያ ታስሮ የነበረ ቢሆንም ከከሳሽ ጋር በሽማግሌ በተደረገ ድርድር ተለቆ ሊፈታ ችሏል፡፡ በቦሌ ደህንነቶች የተለቀቀውም የሕወሓት መንግስት ደጋፊ በመሆኑና በየሕወሓት በአል ላይ በመገኘት ለስርዓቱ ታማኝ መሆኑን በማሳየቱ መሆኑም ምንጮች ይናገራሉ::

ሚኪያስ መሐመድ አጭበረበበት የተባለው ደረቅ ቼክ

ሚኪያስ መሐመድ አጭበረበበት የተባለው ደረቅ ቼክ

ከእስር ከተፈታ በኋላም እጁ ላይ የነበረውን የአሜሪካ ቪዛ በመጠቀም ወደ አሜሪካ  ካሊፎኒያ ግዛት ገብቶ ተደብቋል ተብሎ ገንዘባችን ተወሰደብን በሚሉ ወገኖች እየተወገዘ ይገኛል::

በአርቲስት ሚኪያስ መሀመድ ገንዘባቸውን ከተበሉ ሰዎች መካከል ድምፃዊ ታደለ ሮባ አንዱ ሲሆን፤ ታደለ አርቲስቱን ለመፈለግ ከሰሞኑ ወደአሜሪካ ማቅናቱ ታውቋል፡፡

ድምፃዊ ታደለ ለአርቲስቱ የሰጠው 1.7 ሚሊዮን ብር እንደነበርም ለማወቅ ችለናል፡፡ አርቲስት ሚኪያስ መሀመድ ገንዘባችንን ወስዶ ባዶ ቼክ ሰጥቶናል ያሉ ወደ 6 ያህል ሰዎች አቤቱታ እያሰሙ ሲሆን ከነዚህም መካከል የኪንግ ሲልቨር ባለቤት እንደሚገኝበት ታውቋል:: ጉዳያቸው በሽምግልና ተይዞ ይገኛል፡፡ በዚህ ሽምግልና ውስጥም አቶ ኤፍሬም የተባሉ ግለሰብ፤ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬና ዮናስ ቬጋስ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡ በተለይም ዮናስ ቬጋስ በተጣለበት ሽምግልና አርቲስቱን ይዞ ወደኢትዮጵያ የማምጣት አላማ ሰንቆ ወደአሜሪካ እንደሄደም ምንጮቻችን ነግረውናል፡፡

ሚኪያስ መሀመድ ብአዴን

ሚኪያስ መሐመድ አጭበረበበት የተባለው ደረቅ ቼክ

ስልኩን የዘጋውና በቫይበርም ቢሆን ከዮናስ ቬጋስ ውጭ ለማንም መልስ የማይሰጠው አርቲስት ሚኪያስ መሀመድ አሁን ለሽማግሌዎቹም ትልቅ ራስ ምታት ሆኗል፡፡ ምክንያቱም ዮናስ ቬጋስ አሜሪካ ከገባ በኋላ አርቲስቱ የእሱንም ስልክ መመለስ(በቫይበር) አቁሟል፡፡ አርቲስት ሚኪያስ መሀመድ ከበርካታ ግለሰቦችና ታዋቂ ሰዎች ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ይዞ ወደአሜሪካ ለመሰወር የቻለው የጎማና የሲሚንቶ ንግድ በጋራ እንስራ በማለት ነበር፡፡ ይህ ከላይ ያቀረብነው ቼክ አርቲስት ሚኪያስ መሀመድ ከሰጣቸው ባዶ ቼኮች አንዱ ሲሆን የከሰሱትና አሳስረውት የነበሩትም እኚሁ ግለሰብ ናቸው፡፡ እኚህ አቶ ሰይፍ ዳሳ የተባሉት ግለሰብ በላስ ቬጋስ ሎተሪ ደርሷቸው ወደኢትዮጵያ በመጡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከአርቲስት ሚኪያስ መሀመድ ጋር ተገናኝተው 2 ሚሊዮን ብር ለጎማ ኢንቨስትመንት በሚል የሰጡ ነበሩ፡፡

 

ከአርቲስት ሮማን በፈቃዱ ሁለት ልጆችን የወለደው አርቲስት ሚኪያስ መሀመድ አሁን በኢቢኤስ እየተላለፈ ባለው ‹‹ዳና›› ድራማ ወሳኝ ገጸ ባህርይ ያለው መሆኑ ይታወቃል፡፡ የ‹‹ዳና›› ድራማ ምንጮቻችን እንደገለፁልን አርቲስቱ በጥቅምት ወር ውስጥ እንደሚመለስ በመናገሩ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ከአገር መጥፋቱ ስለተረጋገጠ ደራሲዎቹ እሱ የሌለበት ሌላ ታሪክ ለመፃፍ ተገደዋል፡፡

adhanom

አርቲስት ሚኪያስን አሜሪካን ሃገር ይዞታል በተባለው በስልክ ቁጥሩ ደውለን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም:: እንዳገኘነው የርሱንም ምላሽ ይዘን እንቀርባለን::

ተጨማሪ ወሬዎችን እየተከታተልን እናቀርባለን፡፡

The post ከ6 ነጋዴዎች ጎማ አስነግዳችኋለሁ በሚል ብር ተቀብሎ ተሰውሯል የተባለው አርቲስት ሚኪያስ መሐመድን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ ጥረት ተጀመረ | የደረቅ ቼክ ማስረጃውን ይዘናል appeared first on Zehabesha Amharic.

ህዝብ ሃዘን ላይ ነው መሪዎቻችን ሰርግ ላይ ናቸው። አልተገናኘንም!!!  –ከተማ ዋቅጅራ

0
0

mushirawአንድ አርበኛ ጣሊያን ኢትዮጵያን ልትወር በመጣችበት ግዜ በትግል ላይ እያለ የእናቱ ሞት ይነገረዋል አጠገቡ ያሉትም አርበኞች የእናት ሞት ከባድ ነውና ትንሽ ሃዘንህ ቀለል እስኪልልህ ድረስ አንተ እዚህ ሁንና አረፍ በል እኛ ጠላትን እንፋለማለን ብለው ይነግሩታል። አርበኛውም እንዲ በማለት መለሰላቸው፡- የእናት ሞት በጣም ከባድ ነው። እናቴ የሞተችው በእናት አገሯ ላይ ነው። አገር ስላላት በክብር የሚቀብሯት ብዙ  ወገን አሏት። ጠላት አገራችንን ሊያሳጣን ጦርነት ከፍቶብናል ሞተህ በክብር የምትቀበርበት ቀርቶ  በህይወት እያለህ የሞት ሞትን ሞተህ የምትኖርበትን አገር ሊያደርግብን ነው።  እኔ ለልጄ እና ለልጅ ልጄ ማውረስ የምፈልገው በክብር በነጻነት የሚኖሩባትን አገር የማስረከብ ሃላፊነት ስላለብኝ የናቴ ሞት ከአገሬ ክብር እና ከነጻነት በላይ አይሆንም የተሰጠኝ አደራ በመከራ ግዜ ወደኋላ ብዬ የሚያስቀር ሳይሆን እስከህይወት ፍጻሜ በጽናት ጠላቴን ለመታገል ነው። ስለዘህ ከአላማዬ የሚያስቀር ወደኋላም የሚያስብለኝ የለም እኔ ከእናቴ ብገኝም አሁን ግን የአገር አደራ ስለተቀበልኩኝ የህዝብ ነኝ ለህዝቤ ባርነትን አላወርሰውም፤ በማለት የእናቱ ሃዘን ሳያዝን ወደ ትግሉ ጎራ ሄዷል። እንኳን ሰርግን ቀርቶ የእናት ሞትንም ለህዝብ እና ለአገር ክብር ሲሉ የሚያሳልፉ ጀግኖች ነበሩን።የዛሬዎቹ አገርን እንመራለን የሚሉት የኢትዮጵያ ህዝቡ በከፍተኛ ሃዘን ላይ ባለበት አገር አደጋ ውስት ሆና ባልተረጋጋችበት ሰዓት ልጃቸውን እየዳሩ የሰርጋቸው ታዳሚ እንድንሆን ይነግሩናል።

 

እንደ ኃይለማርያም ትልቅ ቦታ ያለው ያውም የአገር መሪ የሚል ስም ይዘው ህዝብና ወገን በአጋዚ በጥይት እየተገደለ ህጻን፣ ነፍሰ ጡር፣ አዛውንት፣ ወጣት፤ ያለርህራሄ  እየተጨፈጨፉበት ባለበት ሰዓት በቤተ መንግስት የተቀመጡት ልጄን ድሬአለው ብለው መናገራቸው ደስታው ወደ ሃዘን ይቀየራል ሃዘንም ወደ ደስታ ይለወጣል የሚለውን የመጽሃፍ ቅዱስን ቃል ላስታውሳቸው እወዳለው። ህጻናት የተገደሉባቸው  እናቶች እያለቀሱ ባለበት ሰዓት፣ ነብሰ ጡር ስትገደል ሁሉም እያለቀሰበት ባለበት ሰዓት፣ የይኑቨርስቲ ተማሪዎች፣ 2ተኛና  1ኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ገበሬዎች፣ ሰራተኞች፣ ሲገደሉ ኢትዮጵያኑ ሁሉ ሃዘን ላይ በሆኑበት ሰዓት፣  እንባችን ሳይደርቅ፣ ሃዘናችንም ሳንጨርስ፣ የመብት ጥያቄአችን ሳይመለስልን፣ ገዳዮች እና በዳዮች ለፍርድ  ይቅረቡ እያለ ህዝቡ ተቃውሞውን በመግለጽ ላይ እያለ፤ አገር እመራለው፣ ህዝቡን በትክክል አስተዳድራለው ከሚሉት አካል 100% በህዝብ ተመርጬ ነው ስልጣኑን የያዝነው ተብሎ በሚናገሩት ዘንድ በየግዜው ለህዝብ የሚያሳዩት ጭካኔ ለስልጣናቸው እና ለጥቅማቸው የሚያሳዩት ስግብግብነት ያሳዝናል ህዝብ ሲያዝን እነሱ ይደሰታሉ ህዝባችን የሃዘን ድንኳኑን ሲደኩን እነሱ የሰርግ ዳሳቸውን ይጥላሉ።  ሃዘንተኛው ሃዘኑን ሳይረሳ የሃዘን ድንኳንም ሳይፈርስ መሪ ተብዬው  በአዳራሽ ውስጥ ልጃቸውን ይድራሉ። ህዝቡ ቤት ሃዘን… ቤተ መንግስት ሰርግ… የሚነገርባት አገር የሆነች ኢትዮጵያ ናት። ህዝባችንን እየገደሉ እያስለቀሱ ለማኖር ገዢዎቻችን ደግሞ እየሰረጉ እየተጋቡ የህዝቡ ሃዘን ለኛ ሰርጋችን ነው እያሉ ይገኛሉ።  እናንተ ስትሞቱ እኛ እንባዛለን በማለት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የቅኝ አገዛዝ አዋጅ አውጀውብን ህዝባችንን ነጻነቱን ነፍገው እያሰቃዩት ነው። የህዝብ ሃዘን የህዝብ እንጂ የኛ አይደለም የህዝብ ሞት የህዝብ እንጂ ለኛ ሞት አይደለም ያሉ ይመስለኛል።

 

እዚህ ጋር አንድ ተራ ሰው ቢያደርገው ብዙም የሚደንቅ ነገር ላይሆን ይችላል። የአገር መሪ ግን ህዝቡ መረጠኝ የህዝቡን መብት አስከብራለው ብሎ ቃል ገብቶ በፖለቲካው ስልጣኑ ላይ ያሉት አካላት ግን እንደዚህ አይነት ነገር ሲያደርጉ ሊያስተላልፉ የሚፈልጉት መልዕክት አለው። እኛ ሰላም ላይ ነን ችግር የለብንም የሚሞትም ሆነ የተጎዳም ሰው የለም የተነሳም ተቃውሞ እንዲሁም የተወጣ ሰልፍ የለም የሚለውን መልእክት ለማስተላለፍ መሪ ተብዬው የልጃቸውን ሰርግ አድርገዋል። ይሄ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ችግር የሚባል የለም ችግር ቢኖር እንዴት ጠቅላይ ሚንስትሩ ልጃቸውን ይድራሉ ብለው የተለመደውን የማይቀየረው ስልታቸውን  ለውጪ መንግስታት ለማቅረብ የሚያደርጉት የከሰረ ፖለቲካ አካሄዳቸው ነው።

 

ሌላው በመንግስት ደረጃ ያሉት አካሎች ያለ ህዝብ ፍላጎት ስልጣኑን እንደያዙት ያውቃሉ። የተነሳውንም የህዝብ ጥያቄ በአፈ ሙዝ አፍነው እንደያዙት ያውቃሉ። ህዝቡ እንደማይወዳቸው ብቻ ሳይሆን እንደማይፈልጋቸው ጠንቅቀው ስለሚያውቁ  ጠቅላይ ሚንስትሩ ልጃቸውን በዚህ ሰዓት ህዝቡ ከፍተኛ ሃዘን ላይ ሆኖ ሳለ ስልጣን ላይ ያሉት ፖለቲካውን በበላይ የሚመሩት እኛ ሰርግ ላይ ነን ደስታ ላይ ነን የሚል አንድምታን ይሰጠናል። የህዝባችን ሃዘን ለነሱ ደስታ ነውና። እንግዲ ምን እንላለን የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን በእጁ እስከሚያስገባ መከራና ሃዘን ሁሌም ቤቱ ውስጥ እንዳሉ ያውቃል። ዛሬ የመሸ የሚመስለው ነገ ለተጨቆነው ህዝብ ብርሃኑን ሲያበራው ለገዚዎቻችን ይጨልማል። ዛሬ ያዘናችሁ ተጽናኑ ነገ ትደሰታላችሁና። ዛሬ የተደሰታችሁ ነገ ታዝናላችሁና የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘን ግድ ነው ቃሉ የሰው ሳይሆን የፈጠሪ ስለሆነ። ጥቂት እንሰንብት ሁሉንም አብረን እናየዋለን።

ከተማ ዋቅጅራ

13.01.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

 

The post ህዝብ ሃዘን ላይ ነው መሪዎቻችን ሰርግ ላይ ናቸው። አልተገናኘንም!!!  – ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.

በኦሮሚያ በሚገኙ የክፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ባሉ የአማራ ልጆች ጉዳይ ከቤተ አማራ የተሰጠ ማሳሰቢያ

0
0

The post በኦሮሚያ በሚገኙ የክፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ባሉ የአማራ ልጆች ጉዳይ ከቤተ አማራ የተሰጠ ማሳሰቢያ appeared first on Zehabesha Amharic.


ለተስፋኪሮስ ኣረፈ የተሰጠ አስተያየት –አቻምየለህ ታምሩ

0
0

woyaneተስፋኪሮስ «ሃገራችንን በዲፕሎማሲው መስክ ዋጋ እያስከፈሏት ያሉ የኢህኣዴግ ጭንጋፍ ኣስተሳሰቦች» በሚል ርዕስ በጻፈው አርቲክል ላይ አስተያየት እንድሰጥ ጋብዦኝ ነበር። ሙሉውን የተስፋኪሮስ አርቲክል ከዚህ ጽሁፍ ግርጌ ካለው የአስተያየት መስጫ ሳጥን ላይ ማንበብ ይቻላል። አርቲክሉን በሚመለከት ያሉኝን ሰፋ ያሉ አስተያየቶች ግን እነሆ!

አይተ ተስፋኪሮስ ያንተን ጽሁፍ ሁልጊዜ የሚያነብ ሰው አንተ ከተነሳህበት ሐሳብ ይልቅ ጎልቶ የሚታየው አንድ ነገር አለ። ይህም ከዋናው ጽሁፍህ ጭብጥ በላይ አትኩሮት በመስጠት ወያኔን «ከደሙ ነጻ ለማድረግ» ወይንም የወያኔን ኃጢዓት ለማቅለል በህይወት ያለውን ወያኔን ከሞቱት መንግስታትና መሪዎች «ክፋት» ጋር እያነጻጸርህ ወያኔን አጉልተህና አሳብጠህ የምታቀርበው ነገር ግፍዝ ነስቶ መታየቱ ነው። ይሄን ዘዴህን ብዙ ሰው ነቄ ያለው ይመስለኛል። ምናልባት እስካሁን ከምትታወቅበት ዘዴ ውጭ ወያኔን የምትታደግበት አዲስ ችሎታ ካለህ ሌላ ነገር ሞክር።

ለምሳሌ የጽሁፍህ ርዕስ « ኢትዮጵያን ዋጋ እያስከፈሏት ያሉ የኢህኣዴግ ጭንጋፍ ኣስተሳሰቦች» ብለህ በጻፍከው ጽሁፍ ውስጥ «ኢህአዴግ» የሚለውን ስም አስራ አምስት ጊዜ በበጎና በተለሳለሰ ትችት ስጠቅስ «ኣፄ ምኒልክ» የሚለውን ስም ግን በጠጠረ ጥላቻና ትችት አስራ ስምንት ጊዜ ጠቅሰሀል። አንተ ለአጼ ሚንልክ ከዋናው የጽሁፍህ ርዕስ ትኩረት የላቀ ትኩረት የሚሰጥ ከሆነ ለምን የጽሁፍህን ርዕስ « ኢትዮጵያን ዋጋ እያስከፈሏት ያሉ የኣፄ ምኒልክ ኣስተሳሰቦች» ብለህ አትቀይረውም ነበር? ይገርማል! ከዚህ በላይ ወያኔን እንዴት ትከላከለው? የቀበሮ ለምዱን አውልቆ በሰብዓ ቆዳው ወያኔን አደግድጎ ሌት ቀን የሚያገለግለው ዳንኤል ብርሀነ እንኳ ያንተን ያህል ወያኔን ከሞቱ ከመቶ አመታት በላይ ከሆናቸው መንግስታት ጋር እያነጻጸረ አያንቆለጻጽሰውም።

ለማንኛውም ለኔ አጼ ዮሀንስ ሰፊ አስተሳሰብ የነበራቸው ላገራቸው የወደቁ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ናቸው። አጼ ሚንልክ ደግሞ የአባቶቻቸውን የአጼ ቴወድሮስንና የአጼ ዮሀንስን ራዕይ ከግብ በማድረስ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያን ስልጣኔ መሰረት የጣሉ ታላቅና ብልህ መሪ ናቸው። ለዚህ ከገብረሕይወት ባይከዳኝ በላይ ምስክር የለም። አጼ ዮሀንስና ንጉስ ሚንልክ በጋብቻ የተዛመዱ፤ ልብ ለልብ የተሳሰሩ፤ ለኢትዮጵያ አንድነት አብረው የተሰለፉ፤ ሰፊ የጋራ ራዕይ የነበራቸው ኋለኛው የቀዳሚውን ራዕይ ተቀብሎ በማስፈጸም የአንድ አገር ነገስታት መሆናችውን ያስመሰከሩ እንጂ ከደርግ በኋላ እንደመጣው ወያኔ ያለፈውን ሁሉ እንዳፈረሰውና የጠላት አገር እንደተረከቡ የሚያስቡ አንተና መሰል የወያኔ ሎሌዎች በምታቀርቡት ደረጃ የሚደባቡ ጠላቶች አልነበሩም። እድል አግኝተው ሚንልክና ዮኃንስ ተመልሰው ቢመጡና አንተና ሌሎች መሰሎችህ ያከማቻችሁትን የሁለቱን ጠላትነት ቢያዩ እንዴት ይታዘቧችሁ?

ሆኖም አንተ ያልከው «ከአፄ ዮሃንስ ወዲህ ግን ሃገራችን ኢትዮጵያ የተሟላ ሉኣላዊነትና ኣንድነቷ ኣጣጥማ ኣታውቅም።»ተራ ስህተትና የወረደ ወገንተኝነት ነው። ለምሳሌ [ለአክሊሉ ኃብተወልድና ለጓዶቹ ክብር ይግባቸውና] አጼ ዮሀንስ በዘመናቸው የኢትዮጵያ አካል ያላደረጉት የዛሬው ኤርትራ መሬት ሙሉ በሙሉ በአጼ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ ግዛት ነበር። እንደ አብነትም በአጼ ዮሀንስ ዘመነ መንግስት ምዕዋ የኢትዮጵያ አካል አልነበረችም፤ በአጼ ኃይለ ስላሴና በደርግ ግን የኢትዮጵያ አካል ነበረች። ጋምቤላና ሞያሌ፤ ኦጋዴንና አፋምቦ በአጼ ዮሀንስ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ አካል አልነበሩም፤ በአክሊሉ የረቀቀ ዲፕሎማሲ ጥረት ግን በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመን የኢትዮጵያ አካል ሊሆኑ ችለዋል።

ሌላው «በኣፄ ምኒልክ ወቅት ኤርትራን ለጣሊያን ኣሳልፋ በመስጠት ሉኣላዊነትና ኣንድነቷ ገብራለች» ያልከው የወያኔ ፕሮፓጋንዳና ነጭ ውሸት ነው። ከፍ ብዬ ጠቆም እንዳደረግሁት በአጼ ዮኃንስ ዘመነ መንግስት የማይናቅ የኤርትራ መሬት የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት አካል አልነበረም። ለምንድን ነው ዛሬ ኤርትራ ተብሎ የሚታወቀው መሬት ሙሉ በሙሉ የአጼ ዮኃንስ ኢትዮጵያ አካል እንደነበር ተደርጎ የሚቀርበው? ታሪክ የሚያውቅ የለም ለማለት ነው? በአጼ ዮሀንስ ዘመን ጣሊያን ከቆላው የኤርትራ ክፍል አልፋ ወደ ደጋው በመውጣት ሰፊ የኤርትራን መሬት በንጉሰ ነገስቱ ፈቃድ ይዛ ነበር። አጼ ዮሀንስ ጀግናው አሉላን ሳይቀር «ለምን ጥሊያንን ወጋህ?» ብለው ሲቀጡት፤ ጣልያን የልብ ልብ አግኝታ በመደሰት የመስፋፋት ምኞቷ እያየለ መጥቶ ብዙ ደጋማ የኤርትራ መሬቶችን መያዟ በአጼ ዮሀንስ ዘመን የነበረ እውነታ ነው። ለምን ይህንን አታነሳውም?

ከዚያም አልፎ የትግራይ መሳፍንትና መኳንንት አጼ ዮኃንስ ወራሽ አድርገው የመረጧቸውን ራስ መንገሻን አንቀበልም ብለው መንገሻን ለመጉዳት ወደ ጣሊያን መግባታቸውንና ለጥሊያን የመሬት ገጸ በረከት በማቅረብ የአስመራና አካባቢዋን መሬት ለጥሊያን ያስረከቡትን ደጃች ደበብን፣ የአካለ ጉዛይን መሬት ለጥሊያን የሰጡትን ደጃች ባህታ ሐጎስን፣ ከረንንና ቦጎስን ለኢጣሊያ መንግስት እጅ መንሻ ያቀረቡትን ባላምባራስ ክፍለ እየሱስን ለምን አታነሳም? ነው ንጉስ ሚንልክ ሳይነግሱ የትግራይ መኳንንቶችና መሳፍንቶች ለጣሊያን ያስረከቧቸው አስመራንና አካባቢዋ፣ አካለ ጉዛይ፣ ከረንና ቦጎስን የኤርትራ አካል አልነበሩም?

ንጉስ ሚኒንልክ በደብዳቤ «የአገር ጥቅም አሳልፎ ሰጥቷል» እያልህ አጼ ዮኃንስን ከፍ ለማድረግ ስትጥር በደብዳቤ ሳይሆን ፊት ለፊት ተሰልፈው ቀለብ እየሰፈሩ፤ መንገድ እያሳዩ፤ ታማኝነታቸውን እያስረገጡ መቅደላ ድረስ ሰተት አድርገው የአጼ ቴዎድሮስን ገዳዮች የመሩትን የካሳ ምርጫን ጉዳይ ግን ማንሳት አትፈልግም። የንጉስ ሚንልክን ከአጼ ዮሀንስ በስተጀርባ መሄድ ሳታስተባብልና ሲባል ከሰማከውም ጨምረህ ስትናገር ፤ የካሳ ምርጫን ከአጼ ቴዎድሮስ ጀርባ መሰለፍ ማስተባበል ለምን አስፈለገህ? ለትውስታ እንኳ ያለፉትን መሪዎች ህጸጽ ስታነሳ ካሳ ምርጫ ለስልጣናቸው ሲሉ የሰሩትን ይህንን ትልቅ ስህተት መዝለሉ ጥፋታቸውን እንደማስተባበል አይቆጠርምን? በእውነቱ እንደዚህ አይነቱ አቀራረብ አይን ያወጣ ወገንተኝነት ነው። እኔ አጼ ዮሀንስም ሆነ አጼ ሚንልክን የማያቸው በእኩል አይን ነው፤ ሁለቱም ታሪካዊ መሪዎቼ ሲሆኑ በዘመናቸው የሰሩትን ጎደሎ ነገር ሳላዳላ በታሪክነቱ ብቻ ትምህርት ወስጀበት የማልፈው ጉዳይ እንጂ የኔን ስህተት ለማስተባበል የነሱን ስህተት ያለዘመኑ የማነሳባቸው የጠላት አገር መሪዎች አይደሉም። ሁለቱም ክብር ይገባቸዋል።

እንዳንተ አቀራረብ ከሆነ ግን ታሪክን ከኔ ምኞችና ፍላጎት አኳያ ብቻ እየተመለከትሁ፤ ጎጃምን ያጠፉትን አጼ ዮሀንስንና ንጉስ ተክለኃይመኖትን ጮመን ረግረግ በመክተት ኢምባቦ ላይ የረቱትን ንጉስ ሚንልክን በአገር ክዳት እየከሰስሁ ሳርውኃ ላይ ቤተሰቦቻቸውን ሳይቀር መስዕዋት ስላደረጉ አገር ወዳድ ንጉስ ተክለሀይማኖት ብቻ ናቸው ማለት ሊኖርብኝ ነው ማለት ነው። በፍጽም! እኔ እንዳንተ የኢትዮጵያን ታሪክ ከተወለድሁነት አካባቢ ፍላጎትና ምኞች አንጻር ብቻ እያየሁ ትልቁን ምስል በመሳት የተንሸዋረረ እይታ እንዲኖረኝ አልሻም።

«አፄ ሃይለስላሴ ከጨርጨር (ማይጨው ኣልደረሱም) ፈርጥጠው ከኣገር በመኮብለል ሃገራችን ለኣምስት ኣመታት በጣሊያን ቁጥጥር ስር ውላለች፣» ያልከው ቀይ ውሸትና የደርግና የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ነው። የዘውዴ ረታን በማስረጃ የታጨቀ «የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት» መጽሀፍ ያነበበ አንድ ሰው ይህንን ቀይ ውሸት ወይንም አደገኛ ውሸት አይዋሽም። ይህንን ቀይ ውሸትህን ለኛ መጽሀፍ ለምናነበው ሳይሆን ትግራይ ላሉ ህጻናት ንገርና በጥላቻ ቀስቅስበት። Otherwise, it is an insult to our intelligence.

«ፕሬዚደንት መንግስቱ ሃይለማሪያም እንደ ኣፄ ሃይለስላሴ ፈርጥጠው ከኣገር በመኮብለላቸው ኤርትራ በህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (EPLF) እጅ ሙሉ በሙሉ ልትወድቅ በመቻሏ የኣፄ ሃይለስላሴን የዲፕሎማሲ ጥረት ኣፍር ድሜ ኣብልቶት ኤርትራ ዳግም ልትነጠል ችላለች።» ብለሀል ጥሩ፤ መንግስቱ ኤርትራን ለሻዕብያ ጥሎ ሲፈረጥጥ ወያኔ ኤርትራን ለኢትዮጵያ ለማድረግ ያደረገው ጥረት ምንድን ነው? ዛሬ ድረስ ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ናት ብለው አይደለም እንዴ ስለኤርትራ ነጻነት አንደራደርም የሚሉን ወያኔዎች? ለምን መንግስቱ ስህተት ላይ ብቻ ቆመህ ወያኔን ከደሙ ንጹህ ታደርገዋለህ? እይታህ ወገናዊ ስለሆነ ላንተ የሚታይህና መሆን ያለበት አንድ ነገር ብቻ ነው፡- ይህም የታሪካዊ ስህተታችች ሁሉ ምንጮች ከትግራይ ውጭ የሆኑ መሪዎቻችን ብቻ ናቸው የሚለ ነው። ያንተ መነሻም መድረሻም ይህ ነው። መነሻውም መድረሻውም ለሚታወቅ አንድ አይነት «ትንተና» እንዳዲስ ነገር ለምን ትደጋግመዋለህ?

ሌላው ያንተ የተለመደ ነገር ደግሞ አጼ ሚንልክንና ወያኔን የምታወዳድረው ነገር ነው። ያንተ «ትንተና» አይን ያወጣ ወገንተኛነት የሚታይበት መሆኑን አንድ ማሳያ ልጨምርልህ። በዛሬው ጽሁፍህ «አጼ ሚንልክና ኢህአዴግ አንድና ተመሳሳይ ናቸው፤ የሚለያቸው ነገር የለም» ብለኸናል። ጥሩ! ታዲያ ይህን ነግረኸን ስታበቃ «ከትግራይ አይደሉም» ብለህ የምታስባቸውን አጼ ሚንልክን በጠላትነት ፈርጀህ በጥላቻ አፌር ድሜ ስታስግጣቸው በወያኔ የበላይነት የሚዘወረውን ኢህአዴግን ግን «እሱ ከስልጣን ከወደረ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች» እያልህ ለምን ጥብቅና ትቆምለታለህ? አጼ ሚንልክና ኢህአዴግ ላንተ አንድ ከሆኑ ለምን በሁለቱም ላይ የምታሳየው ፍቅርና ነቀፌታ እኩል አይሆንም? ለምን አጼ ሚንልክን አምርረህ እየጠላህ ኢህአዴግን አጣፍጠህ ታፈቅራለህ? ለዚህ ምክንያቱ አጼ ሚንልክ ወያኔ ጠላት ብሎ ሊፋለመው በረሀ ከወረደ ከየሸዋ አማራ በመሆናቸው ላንተም «ጠላትህ» ሆነው ስትዘምትባቸው ፤ ወያኔ ደግሞ አንተ ከበቀልህበት ከትግራይ በመሆኑ ነጻ አውጭህ ስለሆነ ብቻ የመጣ ከልሆነ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?

አሁን አጼ ሚንልክንና ወያኔን «እኩል አጥፍተዋል» ብለህ ሁለቱም «ይመሳሰላሉ» ወዳስባሉህ የውጫሌና የአዲስ አበባ ስምምነቶች ልመለስ። ሁለቱንም ስምምነቶች ያነበበ ሁሉ እንደሚያውቀው ጣሊያን በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት በማወጇ የተነሳ ፈርሰውና ሞተው የተቀበሩቱ የአዲስ አበባና የውጫሌ ስምምነቶች ጥሊያን ከኤርትራ ስትለቅ ኤርትራ ወደ እናት አገሯ ኢትዮጵያ እንደምትመለስ እንጂ ነጻ አገር እንደምትሆን አይደነግጉም። ላንተ አጼ ሚንልክና ወያኔ ወይንም ባንተ አገላለጽ ኢህአዴግ በአጥፊነታቸው «አንድ አይነት ከሆኑ» ለምን በውጫሌና በአዲስ አበባ ስምምነት መሰረት አጼ ሚንልክ ጣሊያን ከኤርትራ ስትወጣ ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ትመለሳለች ብለው እንደተስማሙትና እንደተደራደሩት ሁሉ ወያኔም ከሻዕብያ ጋር ተደራድሮ ኤርትራን ወደ እናት አገሯ አላስመለሰም? የአጼ ሚንልክ ስምምነቶችኮ [ ልብ በል፡ የውጫሌ ስምምነት በአድዋ ጦርነት ምክንያት፤ የአዲስ አበባ ስምምነት በሙሶሎኒ ወረራ የተነሳ ፈርሰው NULL AND VOID ሆነዋል] ጥሊያን ከኤርትራ ስትወጣ ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ የሚያስመልሱ እንጂ ነጻ አገር እንድትሆን የሚያደርጉ አይደሉም። እና እንዴት ሆኖ ነው ጥሊያን ከኤርትራን ከወጣች በኋላ ነጻ አገር እንድትሆን ያደረገውን ወያኔንና ጥሊያን ከኤርትራ ከወጣች በኋላ ኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ እንደምትመለስ አድርገው ስምምነት የፈረሙትን አጼ ሚንልክን አንድ የምታደርጋቸው?

«የኣፄ ምኒልክ ኣድናቂ ሆኖ ኢህኣዴግን መውቀስ በDouble Standardነት ያስከስሳል/ያስገምታል» ያልከውም ሎጂክ የሌለው ባዶ ነው። እንዳንተ እይታ «አጼ ሚንልክ የሰሩትን ተመሳሳይ ስህተት» ወያኔ ሲደግመው ሁለቱንም እኩል ተሳስተዋል ማለት ከሆነ ይህ ሊሆን የሚችለው አንድም ታሪክ በሌለበት ሁኔታ ነው ሁለትም የታሪክን ትምህርት ጥቅም ካለመገንዘብ የሚመነጭ ወገናዊ አስተያየት ብቻ ነው የሚሆነው። የአጼ ሚንልክ ስህተት ለወያኔ ጥፋት ማስተባበያ ተደርጎ ሊቀርብ አይችልም። ወያኔኮ የተረከበው አገር እንጂ የጠላት ምድር አይደለም። አገር ከተረከበ ደግሞ ያለፈው ስህተት ማረም እንጂ ዛሬ ሊደግመው አይገባም። የተረከበውን አገር የጠላት መሬት አድርጎ ከቆጠረው ግን ያለፈውን ስህተት ዛሬ ለምንፈጽመው ጥፋት ማጽጃ በማድረግ የምንመዘው መጫዎቻ ካርድ ይሆናል። ለማንኛውም ወያኔ ስልጣን ሲይዝ የጠላት አገር የተረከበ ባይመስለው ኖሮ የአጼ ሚንልክ «ስህተቶች» ያልካቸው በሙሉ በወያኔ ሊታረሙ ይችሉ ነበር።

ከሁሉ በላይ ግን እናንተ ወያኔዎች ላገር ጉዳይ ሲባል እንኳ እንዲገባችሁ የማትፈልጉትና እንዲገለጥላችሁ የማትፈልጉት ነገር ለሁላችንም ግልፅ የሆነ አንድ ነገር አለ። አጼ ሚንልክ «ተሳስተው ተዋዋሏቸው» የሚባሉ ስምምነቶች በሙሉ በስምምነቱ ፈራሚ በሆነው በሌላኛው ወገን ወይንም በጥሊያን ጦረኛነት ስምምነቶቹ ተሽረው ሙሉ በሙሉ NULL AND VOID ሆነዋል። አጼ ሚንልክን ለማጥቃትና ኢትዮጵያን ለመጉዳት ታስቦ ካልሆነ በስተቀር በአድዋ ጦርነትና በሙሶሎኒ ዳግም ወረራ ወደ መቃብር የገቡ የአጼ ሚንልክ ስምምነቶች ህይወት እንዳላቸው ሰነዶች ለክርከር የሚቀርቡ አይደሉም። አንድ የኢትዮጵያ መንግስት ነኝ የሚል አካል የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ እና NULL AND VOID የሆነ ስምምነት እየጠቀሰ የኢትዮጵያን ጉዳይ ለጠላት እኩል አይመለከትም። ወያኔ ያደረገው በዚያው በአጼ ሚንልክ ዘመን NULL AND VOID የሆኑ ስምምነቶችን ነፍስ ሰጥቷቸው ኢትዮጵያ እንድትጎዳ ማድረግ ነው። ልብ በል! ያጼ ሚንልክ ስህተት ስምምነቶች NULL AND VOID በዚያው በራሳቸው በአጼ ሚንልክ ዘመን ነው። የተወሰኑት ስምምነቶች ደግሞ ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን በድጋሜ ሲወርር በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን መንግስት ፈርሰዋል። እነ አክሊሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተከራክረው ኤርትራን ሲያስመልሱ ባደረጉት ክርክር ወቅት ጥሊያን NULL AND VOID የሆኑ ስምምነቶችን አልጠቀሰችም፤ እንደማይጠቀሱ ታውቃለችና፤ ከጦርነት በኋላ ከጦርነት በፊት የነበረ ስምምነት NULL AND VOID እንደሆነ ያውቃሉና።

እና አንተ ዛሬ ሚንልክ «ይሄን አድርጎ» እያልህ የምትከሰው የወገንተኛ ክስ ባጠቃላይ NULL AND VOID የሆነና ለወያኔ ጥፋት ማጣፊያ በምንም መልኩ እንደ ምክንያት ሊጠቀስ የሚችል አይደለም። NULL AND VOID ሆኖ ወደ መቃብር የወረደን የአጼ ሚንልክና የጥሊያን ስምምነት ወደ ጠረጼዛ ዙሪያ መመለስ ማለት ኢትዮጵያን ለመጉዳት ከመፈለግ ውጭ በምንም መልኩ በተለይ በኢትዮጵያ በኩል ባለ ወገን እንደመከራከሪያ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም። ሆኖም ግን የወያኔ የጥላቻ ሀመም ተሻካሚ ስለሆንህ ደንቆሮዎቹ ወያኔዎች የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈው ለመስጠት ከመቃብር ቆፍረው ያወጡትን NULL AND VOID የሆነ የአጼ ሚንልክ-ጥሊያን ስምምነቶች ህይወት እንዳላቸው ሁሉ በማስረጃ እየጠቀስህ ወያኔን ለመከላከል ትከራከርባቸዋለህ! ይህን አይነቱን በሞተ ኃሳብ የሚደረግና ትርጉም የሌለው ፖለቲካ ጨዋታ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ «የሙታን ፖለቲካ» ይለዋል። አንተም የዚህ የሙታን ፖለቲካ ተጋሪ ነህ። ባትሆን ኖሮ NULL AND VOID የሆነ የኢትዮጵ ጥሊያን ስምምነት እያነሳህ «ጣሊያን በውጫሌ ውል ያገኘችው ኣልበቃ ብሏት እየተንፏቀቀች ተጨማሪ መሬቶችን መያዝ ጀመረች፡፡ ኣፄ ምኒልክም ዝም በሏቸው እያሉ ከውሉ ውጪ የተያዙ መሬቶች በኋላ የውጫሌ ውል በጣሊያን ኣገር ሲፈረም በጊዜያዊነት በውሉ ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል ( እነዚህ የውሉ ኣካል ያልሆኑና በጊዜያዊነት የተቀጠሉት ኢህኣዴግ በድርድሩ እንዴት እንዳስተናገዳቸው ኣይታወቅም-» በማለት ቁም ነገር የሰራህ አይመስልህም ነበር።

እስቲ ማን ይሙት በአድዋ ጦርነት NULL AND VOID የሆነው የውጫሌ ስምምነት ኤርትራን ነጻ ለማውጣትና የኤርትራ መሬት ለመስጠት ሲባል ከመቃብር ተቆፍሮ ኢትዮጵያዊ የሆነ ወገን ይወጣል? ያውም ስምምነቱ ጣሊያን ኤርትራን ለቅቃ ስትወጣ ኤርትራ ወደ እናት ወደ ኢትዮጵያ ትመለሳለች እያለ? እስቲ የትኛውን የውጫሌ ስምምነት አንቀጽ ጠቅሶ ነው ወያኔ ጥሊያን ከኤርትራ ለቅቃ ስትወጣ ኤርትራ ነጻ መውጣት አለባት ብሎ ከኢትዮጵያ ለማስገንጠል ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደብዳብ የጻፈው? የውጫሌ ስምምነትኮ አነ አክሊሉ ኃብተወልድና ወልደ አብወልደ ማሪያም በተባበሩት መንግስታት ፊት ቆመው ክርክር ሲያደጉ አልተነሳም፤ ምክንያቱም በአድዋ ጦርነት ምክንያት ስምምነቱ NULL AND VOID እንደሆነ ይታወቃልና።

ለምን ሲባል ነው NULL AND VOID የሆነ ስምምነት ከመቃብር ተቆፍሮ አክሊሉና ወልደአብ ለክርክር ሳያቀርቡት መለስና ኢሳያስ ለድርድር ያቀረቡት? ኢትዮጵያን ለመጥቀም ነው? ይህ በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመው ታሪካዊ በደል መለስም ኢሳያስም ኤርትራዊ ሆነው ካልቀረቡ በስተቀር በኢትዮጵያ በኩል NULL AND VOID የሆነ ስምምነት ከመቃብር ተቆድሮ በመውጣት የኤርትራን ህልውና ለማስጠበቅ ሲባል ብቻ ጥቅም ላይ አይውልም። ይህንን ወያኔ ከቃብር አውጥቶ ነፍስ የዘራበትን የውጫሌ ስምምነት ነው እንግዲህ አጼ ሚንልክ በአድዋ ጦርነት ወደ መቃብር ካወረዱት ጋር እኩል ዋጋ ሰጥተህ አጼ ሚንልክንና ወያኔን የምታመሳስላቸውና ሞቶ የተቀበረውን ስምምነት ነፍ እንዳለው ቆጥረህ በስምምነቱ ውስጥ «ኤርትራ ከጥሊያን በኋላ ነጻ አገር ትሁን» የሚል አንቀጽ ያለው ይመስል ወያኔ ኤርትራ ነጻ አገር እንድትሆን መወሰኑን ያጼ ሚንልክ ጥፋት ነው እያልህ የምትከራከረው። እስቲ አጼ ሚንልክ ተሳሳቱት የምትለውን ኤርትራን የጥሊያን የመስጠት ጥፋት ወያኔ ለማረምና ኤርትራን ወደ እናት አገሯ ለመመለስ ያደረገው አንድ ጥረት ንገረኝ ?

በመጨረሻ « ኣፄ ምኒልክ ኣባይን ላለመገደብ ተስማምተዋል» ያልከውም ያው የለመድነው የፈጠራ ክስና በሬ ወለደ ሲሆን ወያኔ ባለፈው ሳምንት ከግብጽና ሱዳን ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ወደፊት የአባይን ውሀ ግድቡን ላለመሙላት ሰበብ ሲፈልግ «የቀድሞው መሪዎች በተስማሙት ስምምነት የተነሳ ነው ግድቡ የማይሞላው» የሚለውን ካርድ ለመምዘዝ የታለመ ስለሆነ ጊዜው ሲደርስና ስበቡ ሲጎነጎን እመለስበታለሁ።

The post ለተስፋኪሮስ ኣረፈ የተሰጠ አስተያየት – አቻምየለህ ታምሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፓትርያሪክ አቡነ ማቲያስ “እስከምሞት እዋጋዋለኹ፤ እጅ እግሩን አስረዋለኹ” ሲሉ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዛቱ

0
0

የሐራ ተዋሕዶ ዘገባ እንደወረደ

holy-synod-tik07-on-protestant-reformation

ቅዱስ ሲኖዶስ፡-

  • በምልመላ፥ የደቀ መዛሙርቱ የሃይማኖት ጥንካሬ እንዲታይ አህጉረ ስብከትን አስጠንቅቋል
  • በቅበላና በትምህርት ዝግጅትም፥ ጥራቱና የመምህራኑ ሃይማኖት እንዲፈተሽ ኮሌጆቹን አሳስቧል
  • አህጉረ ስብከቱ ጤናማ ተማሪ ቢልኩም፣ ተመርቀው ሲወጡ “ሌላ ሰው ኾነውና መስለው ነው”
  • በጤና የተላኩ ልጆች መናፍቃን ኾነው ሲመለሱ እያንዳንዱን ኮሌጅ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባዋል
  • እነማን እንደሚማሩባቸው፣ መምህራኑ እነማን እንደኾኑና መጻሕፍታቸው ሊመረመሩ ይገባል

*          *           *

ማኅበረ ቅዱሳን፡-

  • በየኮሌጆቹ፥ የተሐድሶ ኑፋቄን አስከፊ ደረጃ የሚያትቱ ጽሑፎችን በሚዲያዎቹ አስነብቧል
  • ከተማሪ ምልመላ ጀምሮ የአመራር፣ የክትትልና አያያዝ ድክመቶች በመንሥኤነት ተጠቅሰዋል
  • የኑፋቄው ተጽዕኖ ስለማየሉ የቀረቡት ገለጻዎች፣ በበቂ ማስረጃ መደገፋቸው ተገልጧል
  • ማስረጃዎቹ፥ በ1991 እና በ2004 በቅ/ሲኖዶስ በተላለፉ ውግዘቶች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል
  • በመተዳደርያ ደንቡ፣ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ትውፊትን የማስጠበቅ ተልእኮ ተሰጥቶታል

*          *           *


ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፡-

  • ማኅበሩን በፀረ ተሐድሶ እንቅስቃሴው ከሚከሡ የኮሌጆቹ ተቃዋሚዎቹጋ ትላንት ተወያይተዋል
  • ማኅበሩ እያስቸገረን ነው፤ በሚል “ከመንግሥት ጋር ተረዳድተን መጣል አለብን” ሲሉ አሳሰበዋል
  • በአሜሪካ ጉብኝታቸው፣ ቤተ ክርስቲያንን ሊረከብ ትንሽ እንደቀረው መረዳታቸውን ገልጸዋል
  • “ወይ ማኅበሩ ይረከበናል፤ ወይ እኛ እንወርሳቸዋለን” ሲሉ የኮሌጅ ተቃዋሚዎቹን አበረታተዋል
  • ማኅበሩን፣ ደንብ አልባ እንዳደረጉት ጠቅሰው በቀጣይም፣ “የሚኾነውን እናደርጋለን” ብለዋል
  • ቅ/ሲኖዶሱን ለተጋፉ የኮሌጆቹ አካላት፣ አባቶችን በአድመኝነት በማማት እገዛ እጠይቀዋል

*          *           *

በኮሌጆቹ ስም የሚንቀሳቀሱት ሓላፊዎች እና ደቀ መዛሙርት፡-

  • ማኅበሩን፥ በፖሊቲከኛነት፣ በአሸባሪነት፣ በዘረኝነት፣ በደም አፍሳሽነት እና በኑፋቄም ከሠዋል
  • በቅ/ሲኖዶስ የተሰጠው ዕውቅና ተነስቶት በአሸባሪነትና በስም አጥፊነት እንዲከሠሥ ጠይቀዋል
  • የማኅበሩን፥ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስኮላርሽፕ“ኮሌጆቹን ለማዘጋት ያቀደበት ነው፤” ብለዋል
  • ያስመረቃቸውም ደቀ መዛሙርት፥ “ሙስሊሞች ይኹኑ አሸባሪዎች አይታወቁም” ሲሉ አፊዘዋል

Birhane Gebra tsadikan

ብዙዎች፥ በአካዳሚያዊ አቅሙና በማስተማር ክሂሉ “የኮሌጁ ኀፍረት” ነው፤ ይሉታል፡፡ በሓላፊነት ከተቀመጡ ሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያኑን እያደራጀ፣ በቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ግፍ እየፈጸመ ይገኛል – በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የማታ መርሐ ግብር ሓላፊውብርሃኔ ገብረ ፃድቃን

በተለይ፣ አስተምረበታለኹ የሚለውን ማስታወሻ ጭምር በተማሪዎቹ እገዛ የሚያዘጋጀው አቅመ ቢሱ እና ቀንደኛ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያኑ አስተባባሪ ብርሃኔ ገብረ ፃድቃን፡-

  • “ከማኅበሩ ይከፈላቸዋል፤ ሙዝ ይገባላቸዋል” እያለ ብፁዓን አባቶችን ሲዘልፍ አምሽቷል

በጽሑፍ ባዘጋጀው መግለጫው፥ በአንድ በኩል ማኅበረ ቅዱሳንዕውቅናው ይነሳው እያለ በሌላ በኩል ደግሞ ማኅበሩን በፖሊቲከኛነት እየከሠሠ ለአባላቱ እና ለመንግሥት መልእክት ሲያስተላልፍ የነበረው የቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ ዲኑ ተስፋይ ሃደራ፡-

  • “ቅዱስነትዎ፥ በሲኖዶስ ስብሰባዎች አጋዥ እያጡ ነው፤ እኔ 150 ተማሪ ይዤ መምጣት እችላለኹ፤” ብሏል፡፡

*           *           *

abune-matyas

የኮሌጆቹ ታዛቢ ሓላፊዎች እና ብዙኃን ደቀ መዛሙርት፡-

  • ካልፈረማችኹና ካልተሰልፋችኹ በሚል በግዴታ ወደ ፓትርያርኩ ቢሮ እንዲገቡ ተደርገዋል፤
  • ለምሩቃን የደመወዝ ጭማሪ እንጠይቅ በሚል የፈረሙበት አቤቱታ ተለውጦ ለሌላ ቀርብዋል፤
  • ፓትርያርኩ ከከሣሾቹ ይልቅ፥ “የዐቅሜን ታግየዋለኹ፤ የሚሰማኝ አጣኹ” ሲሉ አቤቱተኛ ነበሩ፤
  • “በቅ/ሲኖዶስ የወሰኑበትን የተሐድሶ ኑፋቄን አሳሰቢነትና የደመወዙን ጉዳይ እንኳ አልጠየቁም፤”
  • “ሌሎችም አሉ፤ እነርሱንም ላነጋግራቸው አላሉም፤ ውይይት ሳይደረግ በአንድ ጊዜ ዳኛ ኾኑ፤”
  • ማኅበረ ቅዱሳን፥ ለቤተ ክርስቲያን እንደማያስፈልግ፣ ያለጥናት እንደተመሠረተና ዕውቅናም እንደሌለው ተናገሩ፤
  • ሊቃነ ጳጳሳቱንም፥ “በያንዳንዱ ይሔዱበታል፤ ያስጠኗቸዋል፤ አንድ ኹነው አድመው ይመጣሉ፤ እዚኽ አንድ አጀንዳ ሳነሣ ይንጫጫሉ፤ ራሴ ላይ ይወጡብኛል፤” በማለት አምተዋቸዋል፤
  • “አቋም ካላችኹ፣ ቆርጣችኹ ከተነሣችኹ እኔ ማኅበሩን እስከ ሞት ድረስ ነው የምታገለው፤ እስከምሞት ድረስ እዋጋዋለኹ፤ እጅ እግሩን አስረዋለኹ፤” ሲሉ እነብርሃኔ አስጨበጨቡ፤
  • ትግሉም ከፍተኛ መሥዋዕትነት እንደሚጠይቅና ከፍተኛ ጦርነትም እንደሚከፈት አስገነዘቡ፤
  • “ወሳኝ አካላት ናችኹ፤ የሌላችኹበት አገር የለም” ብለው ከሣሾችን በማበረታታት በቀጣዩ የሲኖዶስ ስብሰባ፣ “ልታስረዱን ትችላላችኹ፤ ከመንግሥት ጋር ተረዳድተን መጣል አለብን፤” ሲሉ አሳሰቡ፤
  • የትግሉ ውጤት እና ፍጻሜም፥ “ወይ እነርሱ ይወርሱናል፤ ወይ እኛ እንወርሳቸዋለን፤ ወይ እርሱ ተረክቦ እንዲመራ ይደረጋል፤ ወይ እኛ እንመራለን፤” መኾኑን አስታወቁ፤
  • ‘ታጥቃችኹ ውጡ፤ እንጋደላለን’ እያሏቸው እኮ ነው፤ ጭፍን ጥላቻ ነው ያላቸው፤ በእውነቱ ለእርሳቸው ይታዘንላቸዋል፤ እኛም ሐሳብ ልንሰጥ ተነጋግረን እንዴት ብለን እንስጥ!
  • ደጋጎች በተቀመጡበት መንበር እንዲኽ ያሉ የወረዱ አባት ስናይ እርሳቸውን ነው፤ ምንም አይጠይቁም፤ አቋም የላቸውም፤ አስቀድሞ የተነገራቸውን ብቻ ነው መልሰው የሚያስተጋቡት፤ ተራ ንግግራቸው መልሶ የሚያስንቃቸው ራሳቸውን ነው፤ ቤተ ክርስቲያኗ ምን ዕዳ ነው የጣለባት??? በጣም አዝነንና ንቀናቸው ነው የወጣነው!!!

The post ፓትርያሪክ አቡነ ማቲያስ “እስከምሞት እዋጋዋለኹ፤ እጅ እግሩን አስረዋለኹ” ሲሉ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዛቱ appeared first on Zehabesha Amharic.

ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስቴር  ኃይለማሪያም ደሳለኝ በዛልኝ ፀጋው (አዲስ አበባ)

0
0

ታህሳስ 29፣ 2008

ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣

ይህን ደብዳቤ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዋናው ምክንያት በአሁን ጊዜ በብዙ ኢትዮጲያዊያን ላይ የሚፈጸመውን ግድያ፣ ግፍ፣ መከራና ሰቆቃ በመመልከት ከምንም ነገር በላይ የአገራችን የኢትዮጲያ ቀጣይ  ሁኔታ ስላስጨነቀኝ ነው።

Hailemariam-PM1-300x282አቶ ኃይለማሪያም፣ እርስዎ ወደስልጣን  ሲወጡ አገራችን የተሻለ አስተዳደር ታገኛለች ብለው ብዙ ተስፋ አድርገው ከነበሩት ኢትዮጲያዊያን መካከል አንዱ ነኝ። ለዚህም ምክንያቶች ነበሩኝ። አንደኛ እርሰዎ እግዚአብሄርን የሚፈሩ ሰው ነዎት ሲባል በመስማቴ፣ ሁለተኛ በትምህርት ባገኙት ችሎታዎ በራሰዎ የሚተማመኑና የሚያምኑበትን ለመናገር ወደኋላ አይሉም ብየ በማሰቤ፣ ሶስተኛ በትምህርት ቤት በነበሩበት ዘመንዎ ያዩት የነበረው የተማሪወች እንቅስቃሴ ለአጠቃላይ ህዝብ መብት መከበር እንጅ በዘር ላይ ያልተመሰረተ ስለነበር፣ እርሰወም የዘር ፖለቲካን እንደዋና መርህ አይቀበሉም ብየ መገመቴ፣ አራተኛ እነ አቶ መለስ የሚቃወሟቸውን ሁሉ፣ የረሳቸውን ጓደኞች ሳይቀር፣ እያጠፉ ለሰው ህይወት ብዙም ሳይጨነቁ ወደ ስልጣን ሲመጡ፣ እርሰዎ ግን ወደ ስልጣን አመጣጠዎ የተለየ ነው ብየ በመገመቴ ነው። ይህ አመለካከቴ ከመጠን በላይ በጎ ነገር ከመጠበቅ የተነሳ መሆኑን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተረዳሁ መጣሁ።

እኔ ተስፋ ሳደርግ፤ ብዙ ኢትዮጲያዊያን ግን የእርሰዎ ጠቅላይ ሚንስቴር መሆን፣ ስልጣኑንና፣ ጦሩን፣ የስለላ ድርጅቱንና  ኢኮኖሚውን ህውሃት እስከተቆጣጠረው ድረስ፣ ለውጥ እንደማያመጡ ሲናገሩ ነበር። በትክክልም እርሰዎ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንዳሉ መገንዘብ ቻልኩ። ሆኖም ግን አሁንም አገሪቱን ወደ ከፋና የማትወጣበት ችግር ወስጥ ከመግባቷ በፊት፣ በታሪክም ተወቃሽ እንዳይሆኑ፣ ህዝቡን ይዘው ማድረግ የሚችሉትን መጠቆም እወዳለሁ።

የወያኔ መንግስት ባመጣው በዘር ከፋፍሎ አስተዳደር፣ በገዥው መንግስት መሪነት፣  በህዝቡ መካከል ይዘራ የነበረው የዘርና የጥላቻ ፖለቲካ፣  ከሃያ አራት አመታት በላይ በዘለቀው ገደብ የሌሌው የመብት ረገጣና የንጹሃን ግድያ ጋር ባንድ ላይ ሆኖ  በፈጠረው ብሶት፣ የህዝብ አመጽ ገንፍሎ እየመጣ ነው። ይህም የአገራችንን የወደፊት እጣ ምን ሊሆን እንደሚችል ማወቅ አስቸጋሪ አድርጎታል። እርስወ በዘር ፖለቲካና ትእቢት በተሞሉና፣ የህዝብ ሃብት በሚዘርፉ ወያኔወች ተተብትበው በመታሰርዎ ኢትዮጲያን በዲሞክራሲያዊ መንገድ መምራት እንደማይችሉ ኢትዮጲያዊ ሁሉ ያውቃል። ሆኖም ግን አገራችንን ከከፋ ጥፋት ለማዳን አሁንም ማድረግ የሚችሏቸው ነገሮች አሉ፣

  1. የህዝቡን ስቃይና መከራ ለማየት ህሊናዎን ይክፈቱ፣
  2. የመብት ጥያቄ የሚያነሱትን ኢትዮጲያዊያን ጠላት አድርጎ መመልከትዎን አቁመው ለአገራቸው እንደሚያሰቡና በአገራቸው ጉዳይ እኩል ባለድርሻ መሆናቸውን ይቀበሉ፣
  3. የመንግስት ሃይል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚያደርገውን ዘግናኝ ግድያ ባስቸኳይ ያስቁሙ፣
  4. የታሰሩትን የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች በመፍታት፣ ሁሉንም ለአገሪቱ ባለድርሻ የሆኑትን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት መሪወች፣ የዜጎች ወይም ማህበራዊ ድርጅቶች መሪዎችና ያአገር ሽማግሌወች የሚካፈሉበት አገር አቀፍ ጉባኤ በመጥራት፣ ጉልበት ሳይሆን የህግ የበላይነት የሚመራበት ሁሉን ኢትዮጲያዊ የሚወክል መንግስት እንዲቋቋም ይርዱ፣
  5. ይህን ማድረግ የማያስችለወት ሁኔታ ካለ ግን፣ ለኢትዮጲያ ህዝብ ችግረዎን በግልጽ አሳውቀው ስልጣንወን ይልቀቁ። ይህን በማድረግ ለእግዚአብሄር፣ ለኢትዮጲያና ለኢትዮጲያ ህዝብ መታመነዎን ያሳያሉ።

ይህን መልዕክቴን በቀና ልቦና እንደሚያዩልኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

 

በዛልኝ ፀጋው

አዲስ አበባ

The post ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስቴር  ኃይለማሪያም ደሳለኝ በዛልኝ ፀጋው (አዲስ አበባ) appeared first on Zehabesha Amharic.

መምህር ግርማ ወንድሙ ከ76 ቀናት እስር በኋላ ተፈቱ –በ4 ክሶች 240 ሺህ ብር ዋስ አስይዘዋል

0
0

girma wendimu

(ዘ-ሐበሻ) በተለያዩ ክሶች ተከሰው ላለፉት 76 ቀናት በ እስር ላይ የነበሩት ታዋቂው አጥማቂና መምህር ግርማ ወንድሙ ከእስር መፈታታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታወቁ::

መምህር ግርማ በማታለል ወንጀል; ካለፈቃድ የቤተክርስቲያንን ስም ተጠቅመው አጥምቀዋል እንዲሁም ከሰው ሕይወት መጥፋት ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ክሶች ተመስርተውባቸው ፍርድ ቤት ሲመላለሱ መቆየታቸውን ጉዳዩን እየተከታተለች ስትዘግብ የነበረችው ዘ-ሐበሻ ማስታወቋ ይታወሳል::

መምህር ግርማ በተከሰሱበት ክሶች ሁሉ በተደጋጋሚ በዋስ ሲለቀቁ እንደገና ፖሊስ አዳዲስ ክሶችን እያመጣ እስከዛሬዋ ድረስ መቆየታቸው ይታወሳል::

ዛሬ ጃንዋሪ 13, 2015 (ጥር 4) በዋለው ችሎት መል አከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ላይ ፖሊስ ለአራተኛ ጊዜ አቅርቦት ከነበረው አንደኛ በጸበል አፍነው ሰው ገድለዋል በሚለው ክስ ፍርድ ቤቱ በ100 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፈቅዷል::

መምህር ግርማ በ800 ሺህ ብር የማጭበርበር ክስ – በ40 ሺህ ብር ዋስ ተለቀው ነበር:: እንዲሁም በቤተክህነት ክስ 50 ሺህ ብር; እንዲሁም አዲስ በተከሰሱበት ክስ 50 ሺህ ብር ዋስ ያስያዙ ሲሆን በ76 ቀናት እስር ቆይታቸው መምህሩ ለዋስ 240 ሺህ የኢትዮጵያ ብር በድምሩ አውጥተዋል::

The post መምህር ግርማ ወንድሙ ከ76 ቀናት እስር በኋላ ተፈቱ – በ4 ክሶች 240 ሺህ ብር ዋስ አስይዘዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

ሙስሊሞችን የሚሳደቡ ፖለቲከኞች ለአሜሪካ ሰላምና ደህንነት ጠንቅ ናቸዉ ሲሉ ኦባማ አስጠነቀቁ

0
0
160112213514-06-sotu-2016-large-169
ፃዲቅ አህመድ
ለዚያም ነዉ ማንኛዉንም ዘርና ሐይማኖት ላይ ያነጣጠረን ፖለቲካ የምቃወመዉ። ይህ የፖለቲካዊ ተዓርሞ ጉዳይ አይደለም።ጠንካራ የሚያደርገን ግንዛቤ ቢሆን እንጂ። አለም የሚያከብረን ለጦራችን ብቻ አይደለም። የሚያከብረን ለአመለካከት ልዩነታችንና ለሁሉም እምነቶች አክብሮት ለመስጠት ላለን መንገድና ግልጽነታችን ነዉ። ብጹእ ወቅዱስ (የሮማዉ ሊቃነ-ጳጳስ) አቡነ ፍስራንሲስ፤ ልክ በዛሬዉ ምሽት የቆምኩበት ቦታ በመሆን፤እዚህ ላለዉ አካል ተናግረዉ ነበር “ጥላቻን፣የጨቋኞችን ሁከትና ግድያን መኮረጅ የነርሱን ቦታ ለመዉሰድ ምርጥ መንገድ ነዉ!”…ፖለቲከኞች ሙስሊሞችን ሲሳስደቡ (ባህር ማዶም ይሁን የኛን ዜጎች)መስጊድ ላይ ጥቃት ሲደርስ፣ህጻናትን ማብሸቅ…ይህ ሰላም ደህንነታችንን አያስጠብቅልንም።ይህ ስህተት ነዉ።ይህ በአለም ፊት ያሳጣናል።አላማችንን ከግብ ለማድረስ መሰናክል ይሆናል።…እናም…ይህ እንደ አገር ማንነታችንን መክዳት ነዉ።
ለዚያም ነዉ የጓንታናሞ እስር ቤት ለመዝጋት መስራቴን የምቀጥለዉ።አስፈላጊ አይደለም።ለጠላቶቻችን የምልመላ ተግባር የሚዉል ነዉ። 
 
ኦባማ 

The post ሙስሊሞችን የሚሳደቡ ፖለቲከኞች ለአሜሪካ ሰላምና ደህንነት ጠንቅ ናቸዉ ሲሉ ኦባማ አስጠነቀቁ appeared first on Zehabesha Amharic.

በዕውቀቱ ስዩም እና ዮሐንስ ጦና የፊታችን እሁድ በሚኒሶታ “ብዕር እና ዜማ”በሚል ርዕስ የጥበብ ምሽት ደግሰዋል

0
0

ለመጀመሪያ ጊዜ በአይነቱ ልዩ የሆነ የሥነጽሑፍ እና የሙዚቃ ምሽት እንደሚሆንም ይጠበቃል።

(ዘ-ሐበሻ)  በሚኒሶታ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር (ESA) ጋር በመተባበር ዝግጅቱን ያሰናዱ ሲሆን ዝግጅቱም የፊታችን እሁድ ጃንዋሪ 17, 2016 ቀን ከ3:00 ሰዐት ጀምሮ እንደሚደረግ የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

ESA

 

ከዝግጅቱ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ወጣት ቃልኪዳን ዓለማየሁ ለዘ-ሐበሻ በሰጠው መረጃ “ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዝግጅት በሚኒሶታ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲዘጋጅ ተጋባዥ እንግዶች ሆነው የሚመጡት ተወዳጁ ደራሲና ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም እንዲሁም ታዋቂው ቤዚስት ዮሐንስ ጦና ናቸው” ብሏል::

በብዙዎች ዘንድ በአስገራሚ ምልከታው እና በለዛ ቀመስ አጻጻፉ ተወዳጅነትን ያተረፈው በዕውቀቱ ስዩም የፊታችን እሁድ በሚኒሶታ በተዘጋጀው የሥነጽሑፍና የሙዚቃ ምሽት ላይ እስካሁን ያልተሰሙ ተወዳጅ ሥራዎቹን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል:: በተጨማሪም በጃዝ ሙዚቃዎቹ በተለያዩ ትልልቅ መድረኮች መልካም ስምና ዝናን ያተረፈው ዮሐንስ ጦና ከነሙሉ ባንዱ ተወዳጅና ጣዕም ያላቸው ስራዎቹን እንደሚያቀርብ የወጣው መርሃ ግብር ያስረዳል::

በሚኒያፖሊስ Mcnamara Alumni Center በተዘጋጀው በዚሁ የስነጽሁፍና የጃዝ ሙዚቃ ዝግጅት ላይ ለህፃናት የተለየ ፕሮግራም መዘጋጀቱን አስተባባሪው ወጣት ቃልኪዳን ለዘ-ሐበሻ ገልጾ ወላጆች ይህን ዝግጅት ለመታደም ሲመጡ ልጆቼን የት አደርጋለሁ? ብለው ማሰብ እንደሌለባቸው አስታውቋል:: “ለዚሁ ፕሮግራም መሳካት በማሰብ ለልጆች ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችን ለብቻቸው ከጠባቂዎች ጋር አዘጋጅተናል… ሁሉም ተሰብስቦ እንዲመጣና ይህንን ታሪካዊ ምሽት እንዲታደም ጥሪዬን አቀርባለሁ” ያለው ቃልኪዳን አክሎም ዝግጅቱ የሚደረግበት ማክናማራ አልሙኒ ሴንተር በቂ የመኪና ማቆሚያ እንዳለውም አስታውቋል::

ይህን ምሽት ለመታደም መግቢያው $20 ብቻ ነው:: ዝግጅቱ የሚደረግበት አድራሻም የሚከተለው ነው::

MCNAMARA ALUMNI CENTER
University of Minnesota
200 Oak Street S.E.,
Minneapolis, MN 55455

ስለዝግጅቱ በቂ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 612-423- 3495 / 605-951-8233 መደወል ወይም በESA@umn.edu መልክት መላክ ይችላሉ::

The post በዕውቀቱ ስዩም እና ዮሐንስ ጦና የፊታችን እሁድ በሚኒሶታ “ብዕር እና ዜማ” በሚል ርዕስ የጥበብ ምሽት ደግሰዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

ኮለኔል ደረሰ ተክሌ “ሠራዊቱ ከሕዝቡ ጎን በመቆም ጠመንጃውን ወደ ዘረኛው አመራር ማዞር አለበት”አሉ |ሊደመጥ የሚገባ

0
0

hiber

በኢትዮጵያ በየጊዜው የሚነሱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ጦር እያዘመተ በመግደል፣ በማሰር፣ በማሰቃየት ተጨማሪ የአፈና ዕድሜ ለማራዘም ይሞክራል። ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞ የተሰጠው ምላሽ ከ140 በላይ ንጹሃንን ሕይወት ቀጥፏል። ሺዎች ተግዘው በየእስር ቤቱ እየማቀቁ ነው። እስሩም ሆነ ግድያው አላበቃም። አገዛዙ ለአፈና የሚጠቀምበት ሰራዊት ሙሉ ለሙሉ በሕወሃት ቁጥጥር ስር ያለ አመራር ቢኖረውም ይህን ሁሉ ጭፍጨፋ አላየሁም አልሰማሁም ማለት ይችላል? ሰራዊቱ በትክክል ከማን ጋር ነው የሚቆመው? በእዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ኮ/ል ደረሰ ተክሌ የሰራዊቱ ዕቅድና ምርምር መምሪያ ሀላፊ ከነበሩ ጋር የሕብር ራድዮ ዋና ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ ተወያይቷል:: ያድምጡት::

The post ኮለኔል ደረሰ ተክሌ “ሠራዊቱ ከሕዝቡ ጎን በመቆም ጠመንጃውን ወደ ዘረኛው አመራር ማዞር አለበት” አሉ | ሊደመጥ የሚገባ appeared first on Zehabesha Amharic.


 ዳሪና ቀባሪ (ወለላዬ ከስዊድን)         

0
0

weddingd23 -satenaw ዳሪ

ወዳጄ እንደምነህ  – ውዱ  ጎረቤቴ

ባለህበት ቦታ – ይድረስህ መልክቴ

የልጄ ሰርግና – የሟች ልጅህ ቀብር

አንድ ላይ መሆኑ  – ፈጥሮብኛል ችግር

መቼም ይገባሃል – ግልጽ ነው ነገሩ

ብዙ ነው ማዕረጉ –  የሠርገኛ ክብሩ

ስለዚህ አደራ – የልጄን ታላቅ ሠርግ

በደስታ በሆታ – እንዳሳልፍ በወግ

በዛ ቀን ተነስተህ – ልጅህን ስትቀብር

ስዎችን ሰብስበህ – አታብዛ ግርግር

እንደውም ጨርሶ – ከሞት ላታድናት

በሳቅ በደስታ – በ`ልልታ ቅበራት

ለለቅሶኛው ሁሉ – ይኼን ንገርልኝ

ነገ ማታ ድረስ – መልስህን ላክልኝ

      ቀባሪ

ክቡር አስተዳደር- የላኩልኝ መልዕክት

እጅግ አስገራሚ  – ድንቅ ነው በእውነት

ታስራ ተገንዛ  –  ልጅ ልትቀበር

ተሞሸረች አሉኝ – የርስዎ ልትዳር

ለክብርዎ ሲባል – ለርስዎ ወግ ማዕረግ

እንድስቅ አዘዋል – ለቅሶዬን በመንፈግ

እንደዚህ አድርጎ – ቀኑ ከከበደ

በርስዎ አስተዳደር – ታምር ከወረደ

ሀዘንና ደስታ – መውጣቱ መውረዱ

አንድ ስለሆነ – ሁለቱም መንገዱ

መቼም ምን ይደረግ – በእልልታ ልቅበራት

እርስዎም ልጅዎን –  በለቅሶ ይዳሯት

ወይም ደስታ ሀዘን – እንዳይቀያየጥ

ስምምነት አ’ርገን – ቤት እንለዋወጥ

እግረ – መንገዱንም –  በዚህ – አዲስ መንገድ

መከራን ይቅመሱ – እኔም ደስታ ልልመድ

 

The post  ዳሪና ቀባሪ (ወለላዬ ከስዊድን)          appeared first on Zehabesha Amharic.

“ተማሪን ተማሪ ገደለው ሲባል ሰምቼ አላውቅም …” –የሟች ሣሙዔል ከተማ አባት

0
0
ሟች ሣሙዔል ከተማ(ከማኅበራዊ ሚድያ የተገነ ፎቶ)

ሟች ሣሙዔል ከተማ(ከማኅበራዊ ሚድያ የተገነ ፎቶ)

(ቪኦኤ) “በማንኛውም ትግል ውስጥ ተማሪን ተማሪ ገደለው ሲባል ሰምቼ አላውቅም” ሲሉ ሰሞኑን በሮቤው መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተገደለው ተማሪ ሣሙዔል አባት አቶ ከተማ በቀለ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተናግረዋል፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ —
በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና “… ገዥው ፓርቲ ለአንዱ እነ እንትና ናቸው እንደዚህ ያደረጉት፣ ለዚህኛው ደግሞ እንደዚያ ነው እነዚያ ናቸው እንደዚህ ያደረጉት እያሉ የግጭት ሁኔታን ለመፍጠር ከፈለገ ያስቸግራል” ብለዋል፡፡
የተገደለው ሣሙዔል ከተማ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በተወለደባት ድሬዳዋ ከተማ አጠናቅቆ ለዩኒቨርሲቲ ትምህርቱ ሮቤ ከተማ ወደሚገኘው መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ እንደሄደና የመጀመሪያ ዲግሪውን ለመቀበል የወራት ዕድሜ የቀረው እንደነበር ወላጅ አባቱ አቶ ከተማ በቀለ ገልፀዋል፡፡
ልጃቸው እርሣቸው ጋ ደርሶ ከተመለሰ አንድ ወር እንደማይሞላው ወላጅ አባቱ ነግረውናል፡፡
ጽዮን ግርማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡት፡፡

The post “ተማሪን ተማሪ ገደለው ሲባል ሰምቼ አላውቅም …” – የሟች ሣሙዔል ከተማ አባት appeared first on Zehabesha Amharic.

የዕለቱ ምርጥ ካርቱን –አባይ ጸሐዬ እና ሙክታር ከድር

የበዕውቀቱ ሥዩም አዲስ መጽሐፍ “ከአሜን ባሻገር”ምርቃት divider

0
0

beiwketu syum- sat

“ከአሜን ባሻገር” በድሮና በዘንድሮ ይመላለሳል። የዘመናችንን ዐበይት ጉዳዮች ይዳስሳል።

“ከአሜን ባሻገር” ሃያ ምናብ አሳሽ፥ልብ ዳሳሽ፥ አዕምሮ ፈታሽ፥ ዋዘኛ እና ምፀተኛ ድርሰቶችን ይዟል።

ድርሰቶቹ ጉዞ ቀመስ፥ ፖለቲካ ለበስ፥ ታሪክ ጠቀስ ናቸው።

በጉዞ ቀመስ ተረኮቹ ዕይታው የቀሰቀሰበትን ሐሳቦች ያወጋናል።

የፖለቲካ ለበስ መጣጥፎቹም “…የእንጉርጉሮ እና የልግጫ ድብልቅ…” ናቸው ይለናል።

በታሪክ ጠቀስ መጣጥፎቹ  የታላላቅ ኢትዮጵያውያንን ገድል ያወሳልናል።

 

እሁድ ጃንዋሪ 24 ቀን 2016 ከ4:00pm -7:00pm የበዕውቀቱ ሥዩም “ከአሜን ባሻገር” በዋሽንግተን ዲሲ ሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ

በድምቀት ይመረቃል።

 

የምረቃ በዐሉ አይጠገብ የኮሜዲ ቡፌ የሚቀርብበት፥ ከራሱ ከበዕውቀቱ ጋራ ቃለምልልስ የሚደረግበት፥ ውብ ሙዚቃ እንደ ጅረት የሚፈስበትይኾናል።

መጽሐፉን አሁኑኑ ከትኬትዎ ጋር ገዝተው በምርቃቱ ቀን ይውሰዱ። በምርቃቱ ቀን መገኘት ካልቻሉ፣ መጽሐፉን ከmeshcart.com አሁኑኑ አዘው ከምርቃቱ በኋላ እቤትዎ ድረስ ይመጣልዎታል።

 

ከአሜን ባሻገር Team

The post የበዕውቀቱ ሥዩም አዲስ መጽሐፍ “ከአሜን ባሻገር” ምርቃት divider appeared first on Zehabesha Amharic.

“ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ይላል፤ ተቃዋሚ ኃይሎች መተባበር አለባቸው።” –ጽጌረዳ ሙሉጌታ

0
0

ወ/ሮ ጽጌረዳ ሙሉጌታ፤ የኢትዮጵያ መድኅን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲና የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ምክትል ሊቀመንበር፤ ስለ ሸንጎው ወቅታዊ ሚናና የኢትዮጵያ ሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎን አስመልክቶ ይናገራሉ። (SBS Radio Amharic)

“ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ይላል፤ ተቃዋሚ ኃይሎች መተባበር አለባቸው።” – ጽጌረዳ ሙሉጌታ

The post “ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ይላል፤ ተቃዋሚ ኃይሎች መተባበር አለባቸው።” – ጽጌረዳ ሙሉጌታ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live