Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

እስከመቼ ዝም ብለን –ከስቶክሆልም

$
0
0

Andinet Party Demoሰላም ያገር ልጅ መቼም በሃገራችን ሰላምና ዲሞክራሲ ሰፍኖ ፣መንግስታት በሰላማዊ መንገድ ሲለወጡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሳዊ መብቱ ተከብሮ በሃገሩ ላይ ሁሉም እንደ አንድ ዜጋ መታየትና በጋራ የምናስብበት መድረክ ተፈጥሮ ማየትን የሚጠላ ዜጋ አለ ለማለት አስቸጋሪ ነው በርግጥም በተለያየ ጥቅማ ጥቅምና በዘረኝነት በሽታ ተለክፈው ያሉትን ማስብ አይቀርም እነሱም ቢሆን ከሰውነት ተራ የወረዱ በቁማቸው የበሸቀጡና ህሊና የሚባል ያልተፈጠረባቸው ስለሆኑ እነሱን ይሄ አይመለከታቸውም ።እኛ የፈጣሪ አምሳልና እንደሰው ማሰብ የምንችለው ግን ለዚህ ለቆምንበት ሃገራችን ሊኖራት ስለሚገባት ሰላምና ዲሞክራሲ አርቀን ልናስብ ይገባል ለዚህም ነው አደራው ቀላል እንዳይደለ በተለያዩ መንገዶች የሚገለጸው በዚህ አጋጣሚ ለመጥቀስ ያህል በቅርቡ በፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም አዳፍኔ መጽሃፍ በገጽ 79 “ከትናንቱ ታሪክ መማር የማይችል ሕዝብ ክስሕተቱ አይማርምና ስህተቱን እንደ እንስሳ እየደጋገመ ይኖራል ።

ትናንት በሌሎች ላይ ሲፈፀም ያየነውን ግፍ ዛሬም እንዲቀጥል ተባባሪ መሆን ለራስ ሳይሆን ለልጅና ለልጅ ልጅ ፍዳን ማውረስ ነው ። ይህም ያው እንደ እንስሳ መሆን ነው” ብለውናል። ታዲያ ከዚህ በመነሳት ለወደፊትዋ ኢትዮጵያ የሚበጅ ለህሊናችንም ጠባሳ የማይተው እንደ እንስሳም የማያስቆጥረን እያንዳንዳችን ማድረግ በምንችለው እቅም ብቻ ማድረግ የምንችለው ብዙ ነገር አለ። በእርግጥ ኢትዮጵያዊነት ለያንዳንዳችን ሊሰበክልን የማይገባ ነገር ግን አንዳንድ ግዜ በተለያየ ሁኔታ ችላ የምንለው እየሆነ ይታያል። ታዲያ ይህ ችላ ባይነት እንደ እንስሳ እንዳያስቆጥረን ስጋት አለኝ ።

ሆኖም ግን አሁን አሁን ችላ የማያስብሉ ጠንካራና በአይን የሚታዩ ስራዎች እየተሰሩ እናያለን ነገር ግን እነዚህ ስራዎች እንዲያብቡ እና መንገዱ ጥርጊያ ይሆን ዘንድ እያንዳንዳችን እጃችንን እንዘረጋ ዘንድ ግድ ይለናል እጅ መዘርጋቱን በስንቲም ብቻ አትዩት አንድ ነገር አለ ስለ እውነት እኛ እጅ ለእጅ ከተያያዝን ብታምኑም ባታምኑም በርግጠኝነት የኢትዮጵያ ጠላቶች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ። ታዲያ ይህን ለማድረግ ማንንም መጠየቅ አያስፈልገንም ብቻ ቅንነትና ወደ ህሊናችን መመለስ ያስፈልገናል እና ደግሞ አትዮጵያዊነታችን ወደ ቦታው ይመለስ አቅምና ጉልበት ያለው ወደ ትግሉ ሜዳ እየወረደ እንደሆነ አይተናል አቅሙ የሌለን ደግሞ እጃችንን እንዘርጋ ። ኢትዮጵያዊነት ለሚያስፈልገው ተግባራዊ ጥሪ እንተባበር። ድል ለአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች!!

ethiofri@gmail.com
ከስቶክሆልም

The post እስከመቼ ዝም ብለን – ከስቶክሆልም appeared first on Zehabesha Amharic.


ካለፉት ድርጊቶች መማር ያልቻለ ትውልድ፣ ለገጠሙት ችግሮች መፍሔ ማግኘት  አይቻለውም! –አበበ ተድላ

$
0
0


Commentየአንድ አገር ችግሮች የዛሬ ሁኔታዎች የፈጠሩዋቸው ብቻ አይደሉም።  እንዳውም የአብዛኞቹ ችግሮች መነሻ መሠረታቸው ዛሬ ሳይሆን፣ ትናንትና ከትናንት ወዲያ ነው። የወቅቱን ችግሮቹ አስቸጋሪና ውስብስም የሚያደርጋቸውም ይኸው ምንጫቸው ካለፉ ትውልዶች ተያይዘው መምጣታቸው ነው። የዛሬውን የአገራችን ፖለቲከኞች አብሮ ለመሥራት ቀርቶ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ማሰብ ያቃታቸው የለውጥ አራማጅ ነኝ የሚለው ትውልድ ዘርቶት የሄደው «ኢትዮጵያ አገር አይደለችም፤ እንዳውም የብሔረሰቦች እስር ቤት ናት፤» የሚለው አስተሳሰብ ተሸካሚ በመሆኑ ነው።  በመሆኑም ዛሬ ትውልዱ  ለገጠመው ሁለንተናዊ ችግር መፍትሔ ለመሻት ከልቡ ካሰበና ለዚህም ቆርጦ ከተነሳ፣ ያለፉት ትውልዶች የተከተሉትን ሕዝብን በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በማንነት የመከፋፈል አስተሳሰብና አመለካከት አውልቆ መጣልና ኢትዮጵያዊ ማንነትን መቀበል ይጠበቅበታል። ያ ትውልድ በተከተለው «እኔ ያልኩት ብቻ ትክክል ነው»፣ «እነ እገሌን የተከተልክ የአባት ጠላት ነህ»፣ «ይህኛው አመለካከት ወይም ቃላት፣ ከዚህኛው የበለጠ ነው»፣ «ይኸኛው ነገድ ጠላትህ ነው» ከሚሉት አስተሳሰቦች ራሱን ማጽዳት አለበት። ሃይማኖትና ርዕዮተዓለም-ወለድ ከሆኑ የጠላትነት ስሜቶችና አመለካከቶች መራቅ አለበት። ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያ ያሰኙ አባቶቻችን እና እናቶቻችን የተከተሉትን የአንድነትና የኢትዮጵያዊነት ዜግነት ስሜትና እምነት አድሶ መላበስ አለበት። አሁን አገራችን ከገጠሟት ችግሮች መላቀቅ እንድትችል ዓለም ከምትከተለው የአንድነትና የመቀራረብ ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ኢትዮጵያዊ አመለካከትና አስተሳሰብ ትውልዱ፣ በተለይም ፖለቲከኞቹና ልሂቃኑ ሊጨብጡ ይገባል።

በኢትዮጵያ በተቀናጀ ትግል ትሕነግን* (ወያኔን) ከሥልጣን ለማስወገድ እንዳይቻል ካደረጉ ምክንያቶች ዋንኛው፣ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እና ልሂቃን የዘለቄታ መፍትሄ ለማምጣት ሳይሆን፣ እንደኑሮ የፊት የፊቱን ብቻ መኖራቸው እና  ካለፉ ድርጊቶችና ክስተቶች ትምህርት መቅሰም አለመቻላቸው ነው። በሌላ አባባል፣ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችና ልሂቃን ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ ሳይሆኑ፣ ሁኔታዎችን የሚከተሉ ናቸው። ካለፉ ስሕተቶች የሚማሩ ሳይሆኑ፣ በስሕተት ላይ ስሕተትን የሚደራርቡ ናቸው። ሂደውበት ውጤት ባላገኙበት ጎዳና ደጋግመው የሚመላለሱ ናቸው። ዛሬ በዐይናቸው ሥር የሚሠራውን ወንጀል ሳይመለከቱ፣ ባልነበሩበትና ስለአፈጻጸሙም ምን ዓይነት ትክክለኛ መረጃ በሌላቸው፣ ባለፉት አገዛዞች «ተፈጸሙ» በሚባሉ ጀሮጠገብ አሉሽ አሉሾች የተጠመዱ ናቸው።  ይህ ዓይነት ጉዞ ችግር ፈቺ ሳይሆን፣ ችግር ቀፍቃፊ ነው። አንድነት ፈጣሪ ሳይሆን፣ ልዩነትን አራጋቢ ነው።

የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖቶች “የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ” የሚለው የዘወትር ፀሎት፣ ትውልዱ የዛሬን ብቻ እንዲያስብ ተጽዕኖ ያሳደረብን ይመስላል። ዓለም ላይ እስካለን እና በተለይም ራስ ወዳድ በሆኑ ሰዎች በተሞላች ዓለም ላይ እስከኖርን ድረስ ግን፣ ከአጭር ጊዜ ሕልምና ምኞት ባሻገር፣ የረዥም ጊዜ ዕቅድ ነድፈን ያን ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር እያጣጣምን ተግባራዊ ለማድረግ ካልጣርን፣ አገራችን ለገጠሟትና ሊገጥሟት ከሚችሉ ሁለንተናዊ ችግሮች ልንታደጋት አለመቻላችን የምንገኝበት ሁኔታ ያሳያል። ከዚህ መውጫው ብቸኛው አማራጭ ትናንትን መሠረትና እርሾ አድርገን፣ ለዛሬና ለነገ የሚጠቅም ሥራ በዕቅድ መሥራት ስንችል ነው።   በዕለት ሁኔታዎች መገፋት፣ ዛሬን እንጂ፣ ነገን አለማሰብ፣ ለዛሬ ከጠቀመ የትናቱን ወርቅ መዳብ ነው ማለት፣ በፖለቲካው መስክ ብቻ ሳይሆን፣ በሁሉም የሙያ ዘርፎች ይታያል። ለምሳሌ መኃንዲሶቻችንን እና አርኪቴክቶቻችን እንመልከት፤ የከተሞችን ፕላን ሲያወጡ፣ የዛሬ 50 እና 100 ዓመት የሕዝቡ ብዛት የቱን ያህል እንደሚሆን፣ ምን ዓይነት አገልግሎቶች ሊጨመሩ እንደሚችሉ፣ ከተሞቹ የቱን ያህል ሊሠፉ እንደሚችሉ አስበው ከዚያ ጋር በሚጣጣም መልኩ ሳይሆን፣ የዕለት የዕለቱና የዛሬውን ብቻ አስበው ስለሚሠሩ ከተሞቻችንን  በየጊዜው ሲፈርሱና ሲገነቡ ይታያሉ። ይህ አስቦና አቅዶ ያለመሥራት አባዜ በዕድገታችንና በማኅበራዊ ሕዎታችን ላይ ተከታታይነትን በማሳጣት ሁልጊዜ ጀማሪዎች እንድንሆን አድርጎናል።

ለዚህ ዓይነቱ ስሕተት የዳረገንም፣ ልሂቃኖቻችን እና ፖለቲከኞቻችን ትናንትን ያላገናዘበ፤ ነገን ግምት ውስጥ ያላስገባ፣ ለባህላችንና ታሪካችን ተገቢ ትኩረት ያልሰጠ፣ ግብታዊ ውሣኔዎችን ላለፉት 50 እና 60 ዓመታት ሲወስኑ በመኖራቸው ይኸውና ደሀውን ኢትዮጵያዊ  አገር አልባ ካደረገው ሁኔታ ላይ ጥሎት ይገኛል። ይህን በምሳሌ እንይ፤

  1. 1. «በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም፤»

ባለፉት የዘመነ ትህነግ (ወያኔ) አገዛዝ ዓመታት በአንድነት ኃይሎች ለአገሪቱ ኅልውና መጠበቅ ጥያቄዎች ሲነሱ «ነፍጠኛ ሊመጣብህ ነው» እየተባለ የአንድ ኅብረተሰብ ወገን «መስጊድ» እንደገባች ውሻ ሲካለብ፣ ሲገደልና ሲፈናቀል ብሔርተኛ ፖለቲከኞችና ቆምንለት የሚሉት ነገዶች ምንም ነገር እንዳልተፈጸመ በቸልታ ያዩ እንደነበር እናስታውሳለን። እነሆ! አሁን ደግሞ በተራው ብሔርተኛው በብሔርተኛውና ዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ላይ አምፆ ሲነሳ፣ «ኦነግ ሊመጣብህ ነው፣ ሊያርድህ ነው፣ ሊያጠፋህ ነው፣» ተብሎ «ዝመቱበት» የሚል ጥሪ ከወያኔ ሠፈር ሲዘመርና ልምጭ ባልያዙ ልጆች ላይ መትረየስ ሲያዘንብ፣ በተመሣሣይ ሁኔታ የአንድነት ጎራውና መሰል የኅብረተሰቡ ክፍል በተራው እንዳለፉት የጥፋቱ ተባባሪ ባይሆንም፣ ዝምታን መርጧል። «በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም» ማለት ይኽ ነው። የተለያየ የፖለቲካ አቋም ያላቸው የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በየተራ ወያኔ ነጣጥሎ ብቻ ሳይሆን፣ አንዱን የሌላው የአባት ደመኛ አድርጎ እየሳለ ርስ በርሳቸው እንዲጠፋፉና በየተራ ቁና ሰፋሪዎች እንዲሆኑ ማድረጉን እያየን ነው። በሁለቱም አመፆች የደሃ ልጅ ደም በከንቱ ፈሰሰ። መቼም መነጋገር እና መደማመጥ የማይፈልጉት ልሂቃን እና ፖለቲከኞች ዛሬም የደሀው ልጆች ደም እንደጎርፍ ሲፈስ እያዩ፣ ነገሮችን ቁጭ ብለው ተወያይተው አዋጭ የሆነ የጋራ ራዕይና ተልዕኮ ይዘው ለመውጣት ሲጥሩ አይታዩም። አሁንም ነገሮችን አቻችለው ወደ ሰላም ከመምጣት ይልቅ፣ «እኔ ያልኩት ብቻ ነው ልክ» በሚል በተለያየ ጎራ እንደቀጠሉ ናቸው። በመሃል ተጠቃሚው ደግሞ ትሕነግ(ወያኔ) እና አጋሮቹ ናቸው። ሌሎቹ እርስ በእርስ ሲጋጩ ትሕነግ በሥልጣን ላይ ቆይቶ የመዝረፍያ ዕድሜውን  ያራዝማል። በሌላ በኩል የተቃውሞው ጎራ አንድነትና ኅብረት በማጣቱ የተነሳ፣ ሥሩ የነገለውን፣ ቅርንጫፉ የተኮማተረውንና የሚይዘውና የሚጨብጠው ጠፍቶት እንደገበታ ውኃ የሚዋልለውን ወያኔን የሚገፋው አጥቶ የአጥፍቶ መጥፋት ፖሊሲውን በማን አለብኝነት ሲገፋበት እያዬን ነው።

በቅጡ ሳይደራጁና የተቀናጀ የትግል ሥልት ሳይነድፉ፣ ሕዝብን ለአማጽ ማነሳሳት የቱን ያህል ዋጋ አስከፋይና በሕዝብ ሥነ-ልቦና ላይ ጥሎት የሚያልፈው የተሸናፊነት ስሜት ምን ያህል ጥልቅ መሆኑን ካለፉት ስሕተቶቻችን ተምረን፣ ቀጣዩን አካሄድ መስመር ለማስያዝ ቅድመ-ዝግጅት አለማድረጋችንን ትውልዱ ካለፉት ስሕተቶች ያለመማሩን ነቃሽ ነው። እንግዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ በያካባቢው የሚነሱትን ትንንሽ ተቃውሞዎችን ለጊዜው እንተወውና፣ እስቲ በየአሥር ዓመታቱ የተካሄዱትን እና በርካታ የደሀ ልጆች ደም አፍስሰው ያለፉትን የ1997 ዓ.ም. እና የ2008 ዓ.ም.ን ሕዝባዊ አመፆች እንመልከት።

ከ1997 ዓ.ም. ብሔራዊ ምርጫ በኋላ እንዳስተዋልነው፣ ትሕነግ(ወያኔ) ሥልጣን በምርጫ አልለቅም ብሎ ሕዝባዊ አመጽ መቀስቀሱ ይታወሳል። ያኔ ሁሉም ድርጅቶች ቀድመው መክረው ቢሆን ኖሮ፣ ትሕነግ ዕድሜው ባጠረ ነበረ፤ ሆኖም ግን የውስጥ ባንዳዎችን እነ ልደቱ አያሌውን እንተውና፣ ዶ/ር መራራም ይሁን ዶ/ር በየነ እነኚህ «የድሮ ሥርዓት ሊያመጡብን ነው» ብለው ከትሕነግ ጋር በመወገናቸው ወያኔ ለከፈተው ፕሮፓጋንዳ ሠፊ ቦታ እንዲያገኝ ስላደረጉት፣ ምዕራቡና ደቡቡ ኢትዮጵያ ባብዛኛው ቦታ ዝምታን መረጠ። መሃሉ፣ ሰሜኑ እና አብዛኛው ትልልቅ ከተሞች ቢንቀሳቀሱም አጋዥ አልነበረውም። በዚህም ምክንያት ትሕነግ ሁለት የተከፋፈለ ጎራን ስላገኘ አጋጣሚውን ተጠቅሞ አመፁን እንዲኮላሽ አደረገ። የሚያሳዝነው ትንሽ ቆይቶ ስለ መጀመሪያው «ድምፅ ተጭበርብሯል፣ አልተጭበረበረም፣» የሚለው ቀርቶ፣ «ስንት ሰው  ሞተ? ስንት ታሰረ?» ወደሚለው ክርክር ተገባ። «የታሰሩት እስረኞች ይለቀቁ» የሚለው ዋናው ጉዳይ ሆኖ ቀረበ። ያኔ ለምን ይሄ ክፍፍል ተፈጠረ? ይህ ዓይነት ክፍፍል ወደፊት እንዳይከሰት ምን ማድረግ አለብን? ትሕነግ ሥልጣኑን እንዲለቅ በምን መልክ ማስገደድ ይቻላል? ተብሎ ሳይመከር፣ አገር አቀፍ ምክክር ሳይደረግና ስምምነት ሳይኖር ይህ የሰሞኑ ሠፊ አመጽ ተከሰተ። አለመስማማት አንድ ነገር ነው። ግን ሁሉም ያልተስማማበትንና ለመስማማትም ያላስቻሏቸውን ነገሮች በግልጽ ለሕዝቡ በማሳወቅ፣ ሕዝቡ የችግሩ ብቻ ሳይሆን፣ የመፍትሔውም አካል እንዲሆን ማድረግ ይጠብቅባቸው ነበር። ይህ ሳይሆን፣ በነባራዊ ሁኔታዎች ግፊት ሕዝቡ በራሱ ብሶት አዲስ አመጽ ሲነሳ፣ ግልፅ ባልሆነ መልኩ «አብረን ለመሥራት ተስማምተናል» የሚል ማጭበርበሪያ መግለጫ ማውጣት ለትግሉም ሆነ ለታጋዩ የሚጠቅም አይደለም። የማይስማሙ ከሆነ አይስማሙም፤ ሁሉም ባፈተተው ይቀጥል፤ ሕዝብ «የተሻለ ነው» ላለው ድጋፉን ይስጥ፣ የሕዝብ ድጋፍና አመኔታ ያለው ምንጊዜም አሸናፊ መሆኑ ዕውነት ነው።

በ2008 ዓ.ም. ደግሞ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም የኦሮሞ ተወላጆችና «የኦሮሞ ክልል» ተብሎ በተከለለው በሚገኙ የትምህርት ተቋሞች የሚማሩ ተማሪዎች፣ በፖለቲካ ድርጅቶች አነሳሽነት ሕዝባዊ ሊባል የሚችል አመጽ ቀሰቀሱ። ተቃውሞው ካለፉት ሁሉ የተለየና በጣም የተቀናጀ ተቃውም ታይቷል። ነገሩ እሰየው የሚያስብል ነው። ሁሉንም የሚያሰባስብ ቢሆን ኖሮ ደግሞ የበለጠ የተዋጣለት በሆነ ነበር። ምክንያቱም አንድነት ኃይልና ጥንካሬ በመሆኑ፣ ዋናውን የችግራችን አውራ፣ ወያኔን አሽቀንጥሮ ለመጣል ያስችለን ነበርና ነው። ነገር ግን እኔንም ጨምሮ እንደሚሰማኝ አመፁ “ኦሮሚያ” ብለው ከትሕነግ ጋር የከለልነው “የኦሮሞ ብቻ ነው” የሚል ድምዳሜ ያለው አመጽ ስለሆነ እና ለሌላው ኢትዮጵያዊ ሥጋትን አመልካች በመሆኑ፣ በ1997 ዓ.ም. ለአማጽ የተነሳው ሕዝብ የአመጹ ተካፋይነቱን ትቶ በተራው እንቅስቃሴውን በልዩ አትኩሮት መከታተልን መረጠ። ይህ ደግሞ ለወያኔ መልካም አጋጣሚ ፈጠረ። ወያኔ እንኳን ሕዝቡ ራሱ ተከፋፍሎለት፣ ዓላማው መከፋፈል ነውና ሁኔታውን ራሱን በሚጠቅም መልኩ አመፁን ወደ ማስቆም ደረጃ እየገፋው እንዳለ እናያለን። የሚያሳዝነው ዛሬም የአመጹ ታላቁ ግብ ወያኔን ማስወገድ መሆኑ ይዘነጋና ክርክሩ በታሰሩት እና በሞቱት ሰዎች ቁጥር ማነስና መብዛት፣ እንዲሁም «የሞተው የገሌ ነገድ ነው የገሌ» ወደሚለው እንዳይዞር እሰጋለሁ። ከዋናው ጉዳይ ወጥተን፣ አመጹ የተነሳበት ጉዳይ ይድበሰበስና የታሰሩት ይፈቱ ወደሚል ክርክር እንዳንዘቅጥ አፈራለሁ። የፍራቻየ ምንጩ፣ በተለያዩ ቡድኖች ውስጥ ያሉ ፖለቲከኞች እና ልሂቃኖች ለመደራደር ዝግጁ ሳይሆኑ፣ ዛሬም የራሳቸውን እና የደጋፊዋቻቸውን ድምፅ ብቻ እንደገደል ማሚቶ እየሰሙ ነገሩ ሁሉ ባለህበት ሂድ እየሆነ በማየቴ ነው። ለዘላቂ መፍትሔ የሚሆን አመርቂ ሥራ እስካሁን ሲሠራ አላየሁምና።  እያንዳንዱ ሕዝባዊ አመጽ ግቡ የደሃ ልጅ ማስጨረስ ሳይሆን፣ የአገርና የሕዝብ ጠላት የሆነውን ወያኔ የጨበጠውን የፖለቲካ ሥልጣን ፈልቅቆ የሕዝብ ማድረግ መሆን አለበት። ከዚህ ባለፈ እንዳለፉት ሁሉ የደሀ ልጆችን አስጨፍጭፎ ሁኔታዎች ወደነበሩበት ስኩዬር አንድ ተመልሶ ዜሮ ወደ ሆነ የፖለቲካ ጨዋታ ልንወጣ ግድ ይለናል።

ታዲያ መቼ ነው ከጥፋታችን የምንማረው እና አንድነታችን መልሰን የምንጨብጠው? የተለየ የፖለቲካ አስተሳሰብ ያላቸውን ዜጎች እስከ መቼ ነው በጠላትነት ፈርጀን የምናቆማቸው? እየጨቆኑን ብቻ ሳይሆን፣ እያጠፉን ያሉትን፣ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው የሚያጠራጥሩ ዘረኞችን እስከ መቼ ነው ተሸክመን የምንኖረው? እንዴትና በምንስ ሁኔታ ነው ወደፊት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት እና በሰላም በአገሩ መኖር የሚቻለው? ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ብዙ ምርምር የሚጠይቁ አይደሉም። የሚጠይቁት የፖለቲከኞቻችንና የልሂቃኑን ቅን ልቦናና ኢትዮጵያዊ ሆኖ ማሰብን ብቻ ነው። ምክንያቱም ሕዝባችን ለዘመናት ድንበር ሳይኖረው፣ ማነህ? የት ትሄዳለህ? ዘርህ ምንድን ነው? ሳይባል ተቀላቅሎ፣ ተዋልዶና ተዋዶ የኖረ ነው። ለዚህ ሕዝብ የቋንቋ ድንበር አበጃለሁ ማለት ውኃና ወተትን ቀላቅየ እለያለሁ እንደማለት ነው። ትንሽ ጊዜ ጣልያን ከኢትዮጵያ ለይቶ የገዛት ድንበር አለኝ የምትለው «ኤርትራ» እንኳን በተነሳው የድንበር ግጭት ስንት ደም እንደፈሰሰ ቤቱ ይቁጠረው። ወደፊትም በአሁኑ ወያኔ-ሠራሽ በሆነው የቋንቋ ድንበር ሕዝባችን እንዲከለል ከፈቀድን የደሃ ልጅ ደም እንደጎርፍ በማያባራ መልኩ የሚፈስ መሆኑን መናገር ክፉ አሳቢነት አይሆንም።

  1. «ካልደፈረሰ አይጠራም»

አንዳንድ ድርጅቶች ትብብር፣ ኅብረት፣ ቅንጅት፣ ጥምረት፣ ግንባር፣ ውኅደትና አንድነት የሚሉትን ጽንሰ ሀሳቦች ትርጉምና በእያንዳንዳቸው የግንኙነት ቅርጾች ውስጥ ሊሠሩ የሚገባቸው ጉዳዮች ምን ምን እንደሆኑ ለይተው ሳያውቁ፣ ስለ ስምምነትና በአንድነት ስለመሥራት አስፈላጊነት ሲሰብኩ ይሰማሉ። ልንስማማባቸው ስለሚችሉ ጉዳዮች፣ ስለመስማማቱ አስፈላጊነት በግልፅ ንግግር ተደርጎ ሁሉንም አስገዳጅ ወደ ሆነ ውልና ግዴታ ሳይገባ፤ በጣም ወሳኝ በሆኑ አቋሞች ማለትም በመንግሥት ቅርጽ፣ በቋንቋ አጠቃቀም፣ በነገዶች ጥቅምና መብት፣ ስለ ዕኩልነትና ነፃነት፣ ታሪክ፣ ባህልና ሃይማኖት አጠቃቀም ላይ የወል ስምምነት ሳይኖር፣ በምን መልኩ አገሪቱን ለማስተዳደር እንደሚያስቡ ለተከታዮቻቸውም ለሕዝቡም ሳያሳውቁ «ጨቋኙን አገዛዝ ለመጣል እንተባበር» የሚለው ጥሪ «እባብ ያዬ በልጥ በረየ» ነውና ከትህነግና ከኦነግ ትብብር ትምህርት የወሰድን አይመስልም።

“ጨቋኙም”፤ “ተጨቋኙም” ሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ዕውነት ነው። ታዲያ ይህን ዘረኛ አገዛዝ በምን ዓይነት መንገድ አስወግደን፣ ኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዐላዊነቷን፣ ታሪኳን፣ ባህሏን፣ የነፃነትና ተጋድሎዋን ሊያስጠብቅና ሊያስከብር በሚችል መልካም አስተዳደር እና አብሮ መኖር የሚቻልበት ሁኔታ ምክክር ተደርጎ ከጋራ ስምምነት ላይ ሳይደረስ፣ በጋራ እንታገላለን ማለት «ተጨፈኑ ላሞኛችሁ» ዓይነት ጥሪ ነው የሚመስለው። ነገዳቸውን እንደ አንድ ሠራዊት አሰልፈው፣ ባንድ ጠቅላይ አዛዥ እንዲመራ ያደረጉ ወገኖች፣ ያልተደራጁትንና የተበታተኑትን «የሥልጣን መወጣጫ እርካብ ሁኑን፣ የናንተን ዕጣ ፈንታ ኋላ እንወስናለን» የሚሉ ወገኖች «ከወያኔና ከኦነግ ትብብር» ትምህርት ያልቀሰሙ የዋሆች ይመስላሉ። የሰው ልጅ ሊሞኝ ወይም ሊታለል የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። አንድ ሰው ካንድ ጊዜ በላይ ከተታለለ ሰው ሳይሆን ከብት ነው። በዚህ ጉዳይ ዐማራው ከበቂ በላይ ተሞኝቷል። የተተኪውን ማንነትና ምንነት በውል ሳያውቅና ሳይደራጅ፣ «ደርግ ይውደቅ እንጂ የፈለገው ይሁን» ለሚሉ ብልጣብልጦች ተበልጦ ችግሩ ከእሣት ወደ እረመጥ ኑሮ፣ ከመቸገር አልፎ መኖሪያ ቦታ የማጣት፣ የመኖሪያ ቦታ ከማጣት እንደሰው የመቆጠር መብት ካጣበትና በሕይዎት የመኖር ሰብአዊ መብቱን ከተገፈፈበት ደረጃ ላይ ደርሶ እያየን ነው። ስለሆነም አስቀድሞ ግቡና ዓላማው ላልታወቀ የ«እንተባበር»ና የ«አንድ እንሁን» ጥሪ፣ ዐማራው ለጥሪው ያለው አቋም አዎንታዊ ቢሆንም፣ ነገን አሻግሮ ማየት የሚችልበት የአኗኗርና የአስተዳደር ሁኔታ ምን መልክ እንዳለው ሳያውቅ፣ ሂደቱን በአንክሮ ከመከታተል ውጪ የጥሪው ግንባር ቀደም ተሰላፊ ሊሆን ያለፉት ድርጊቶች የሚጋብዙት አለመሆናቸው በቅጡ ሊታወቁ ይገባል። «ግድ የለም፣ ሰላም ይመጣል፣» በሚል «ልጆቻችሁን በሰላም ታሳድጋላችሁ» ተብሎ ገበሬው የተሻለ ነገር የሚመጣ አስመስለው ለባሰ እልቂት የተዳረገው የአማራ ህዝብ ምን ያህል ከዚህ በኋላ ነፃ እናወጣሃለን የሚሉትን ድርጅቶች በጥርጣሬ ዓይን እንደሚመለከታቸው ማስታወስ ተገቢ ነው።

አገር አጥፊው የኤህነግ (ሻዕቢያ) ቡድን በአንድነት ኃይሉ መከፋፈል፣ በምዕራባዊያን የቆየ ሤራ ተዳክሞ፣ ኤርትራ ከእናት ሀገሯ መገንጠሏ የዘመናችን አሳፋሪው ድርጊት መሆኑ ዕውነት ነው።  ይህን አሳፋሪ ድርጊት እንደ ጀግንነት በመቁጠር፣ «ኤህነግን (ሻዕቢያን) አትንኩብን»፣ «ጥፋቱን አታንሱብን» የሚሉ ፖለቲከኞች በጣም ይገርሙኛል። «የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም» እና የኢትዮጵያ ችግር በተነሳ ቁጥር ሻዕቢያ መነሳቱ የማይቀር መሆኑን እነዚህ ፖለቲከኞች ሊያውቁት ይገባል። የችግሮቻችን ቋጠሮ ሁሉ ኤህነግ ነውና! የትህነግ (ወያኔ) ፈጣሪ ማን ሆኖ፣ ኤህነግ (ሻዕቢያ) ለኢትዮጵያ፣ ከሁሉም በላይ ለዐማራ ቅን ነገር ያስባል ብሎ ማን ያምናል?

አሁን ሌላ ብዙ የቤት ሥራ ስላለብን፣ ቅድሚያ የምንሰጣቸው ባይሆኑም፣ ይሄንን የቤት ሥራ እንዲኖረን ያደረገን ሻዕቢያ ነውና፣ አሁንም ሆነ ነገ፣ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ሰላም ሆና ማየት ከማይፈልጉት መካከል፣ እንደ ግብፅ ወይንም የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ሻዕቢያ አንዱና ቀንደኛ ጠላታችን መሆናቸውን ዐማራ ነኝ የሚለው ሁሉ ማወቅ ያለበት ጉዳይ ነው። ዐማራ የሆኑ የቀድሞ ወታደሮችን ለይተው መረሸናቸውን፤ «ዐማራ ነው ለዚህ ሁሉ ጦርነት ተጠያቂ» ብለው ባንዳ አማራዎችን አስመልምለው ይቅርታ ማስጠየቃቸውን ወዘተ ዐማራ ነን የምንል ሁሉ እንደማንረሳ ለኅሊናችን ቃል ልንገባ ይገባል። ለዘር ጥፋትና ለዘር ጽዳት የዳረገን አውራ ጠላታችን ኤህነግ (ሻዕቢያ) ነው።

ሌላው ሰዎችን ለማሞኘት ከሚደረጉ ጥረቶች መካከል አንዱ፣ ሰሞኑን “ኦሮሞ ክልል” ተብሎ የተከለለው ክልል «የኦሮሞ ብቻ ነው» ከሚሉ ጋር ተሰለፉ የሚሉ የዋሆች መበራከት ነው። እሺ የተነሳሁበትም ስለሆነ እና ተነጋግረን መፍትሄ መፈለግ አለብን ብዬ ስለማምን አዎን ከሁሉም ፖለቲከኞች ጋር መነጋገር አለብን። ነገር ግን ጃዋር ትናንት “Ethiopia out of Oromia”፤ “ኢትዮጵያ ከ”ኦሮሚያ” ትውጣ” እንዳላለ ማስተባበያ እንኳን ሳይሰጥ፣ የሀሳብ ለውጥ ሳያደርግ፣ ይህንም በይፋ ሳያሳውቅ፣ እርሱና መሰሎቹ ለሚመሩት አመጽ «ኢትዮጵያዊያን በትግላችን ውስጥ ተቀላቀሉ ብለዋልና እንተባበር» እያሉ አታሞ የሚመቱ ቡድኖችና ግለሰቦች «ተጨፈኑ እናሞኛችሁ» የሚሉ ዓይነቶች ሆነው ታይተውኛል። በተመሳሳይ ወንጀለኛው ሌንጮ ለታም ድሮውኑ በዐማራ ደም የተጨማለቀው እጁን በንስሃ ሳያጸዳና ይቅርታም ሳይጠይቅ፣ እንዲሁ የአገራችን አውራ ችግር የሆነው ሕገ-መንግሥት «እኔ ያልኩት ትንሽ ማስተካከያ ተደርጎበት ነው የፀደቀው» እያለ ስላሰመረው የአፓርታይድ ክልል ሳይጠየቅ፣ ሌሎች ባልተወከሉበት «ጸደቀ» የተባለውን ሕገመንግሥት «መሻር አለበት» ሳይል፣ ያንኑ ተቀብለን ትህነግን (ወያኔን) ብቻ አጣጥሉን ለሚለው ጥሪው ምን ዓይነት ኅሊና ያለው ሰው አቤት ሊለው ይችላል? እንዴትስ ሌላው እንዲቀበል ይጠብቃሉ? ሳይበደሉ በደላችሁን ብለው የትህነግ እጄታና ዛብ ሆነው የጥፋት ዘመቻ ከከፈቱብን ቡድኖች ጋር «በደላችሁን በሆዳችሁ ይዛችሁ፣ ችግሩንንና በደሉን ረስታችሁ፣ የነሌንጮ ለታን ጥሪ ተቀበሉ» የሚሉን ወገኖች «በቁስላችሁ ላይ ጨው እንነስንስበት» ያሉንን ያህል የሚሰማን መሆኑን ሊያውቁት ይገባል። ሕዝባችን ግን የሚበጀውን ከማወቅ አልፎ ጨዋና አስተዋይ ከመሆኑ የተነሳ፣ ድርጊቱን በጥንቃቄ ከመከታተል ውጭ የጥፋቱ ተባባሪ አልሆነም። ያውም ኦሮሞዎቹ «አስነሳነውና መራነው» በሚሉት አመጽ ዋና ተጎጂ ሆኖ እያለ፣ የዛሬውንም የትናንቱንም ድርጊቶች እያወቀ፣ በኦሮሞ ስም የተደራጁ ድርጅቶች ከትህነግ ጋር ወግነው የገደሉት፣ያሠሩት፣ የዘረፉት፣ ካገር ያባረሩትን ቂም ሳይዝ፣ የትናንቱ ወዳጃቸው ወያኔ በነርሱ ላይ የጥፋት እጁን ሲያነሳ፣ ዐማራው ተባባሪ ሆኖ አለመቆሙ የታላቅነቱ ምልክት ነው። ዐማራው አርቆ ተመልካች፣ ለትውልድና ለነገ የሚያስብ መሆኑ ከዚህ የተሻላ ማሳያ የለም።

  1. «ጉድ አንድ ሰሞን ነው» አልለቅ አለን!!!

እስቲ በቅርብ አመታት ብቻ በተለይ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ያነሳቸውንና ጉድ አንድ ሰሞን ነው የሚባለው አይነት ነገር ሆኖ ደግመን የማናነሳቸውን ሁኔታዎች እንመልከት።

በመጀመሪያ ከላይ እንዳልኩት ስንቶች ሕይወታቸውን እስኪያጡ ድረስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሳይወከል በቋንቋ መስፈርትነት ብቻ የተሰመረ የድንብሮች አከላል አይሠራም ተብሎ ተጮኸ። የሚያሳዝነው፣ ያንን ባደባባይ የተቃወሙ ሰዎችና ድርጅቶች «ይሄ ማለት እኮ በቃ ካንዱ ወዳንዱ “ክልል” ስንሄድ ፓስፖርት አምጡ ልንባል ነው፣» ያሉ ሰዎች ጭምር ምንም እንዳልተናገሩ የተቃወሙትንና የተፉትን መልሶ እንደመዋጥ በሚያስቆጥር መልኩ፣ “አማራ ክልል”፤ “ኦሮሞ ክልል”፤ “ትግሬ ክልል” ወዘተ እያሉ ሲጠሩና ሲጽፉ እናያለን። ይህ ያሳዝናል፤ ያስተዛዝባልም። ልቡና ይስጣቸው ከማለት ውጪ ምን ማለትስ ይቻላል? ወደ ትፋቱ የሚመለስ ውሻ እንጂ፣ ሰው አለመሆኑ ይታወቃል።

ስለኤርትራና ስለ ሻቢዕቢያ ስንት እንዳልተባለ፤ ጠላትነታቸውን ያደረሱብንን በደል በግልፅ ያየነውን ደጋግመው እንዳልነገሩን ሁሉ፣ “ኤርትራ” የተባለችው የኢትዮጵያ ግዛት/አካል መገንጠልዋ አልበቃ ብሎ፣ በኢትዮጵያ ላይ ስንት ሸፍጥ እንደተሠራ እያወቅን፤ የድርጅቱን መሪ ሲያሞካሹልን፤ ትግላቸው ትክክል እንደነበር ሌላም ሌላም ሲነገረን መስማት ያማል። ኤህነግ (ሻዕቢያ) እና ትህነግ (ወያኔ) ዛሬ የሰረቁትን ሲከፋፈሉ ቢጣሉም፣ የአንድ ሳንቲም ግልባጭ መሆናቸውን እያወቅን፣ ኤህነግ የትህነግ ፈጣሪ እንደሆነ እያወቅን፣ በቅሎ ወለደች፤ ሸንበቆ አፈራ፤ ዝንብ ማር ጋገረች እያሉ ያወሩናል። እንግዲህ እነሱስ እሺ ኅሊናቸውን ይሳቱ፤ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ነገሮችን አያስተውልም ብለው ላሞኝህ ማለታቸው ግን ትልቅ ስሕተት ነው። ጠላቶቻችንን እናውቃለን፤ በቅደም ተከተልም አንደኛ ሁለተኛ ሶስተኛ እያልን ማን እንደሆኑ በደንብ እናውቃለን እና ልታሞኙን ብትሞክሩ ሞኞቹ እናንተ እንጂ፣ እኛ ለዳግም ሞኝነት አልተዘጋጀንምና አትልፉ ልንላችሁ እንወዳለን። ከንቱ ልፋታችሁ ያሳዝነናል!

እስቲ ደሞ ወደ «እስረኞች ይፈቱልን» ጩኸት ልመለስ። ይሄንን በተመለከተማ የታሰሩትን ሳስብ ያመኛል። ልቤ ይደማል። ትህነግም ድክመታችንን ስለሚያውቅ በየቀኑ አዲስ የቤት ሥራ እየሰጠ፣ በፊት የነበሩ አንገብጋቢ እና ወሳኝ ጉዳዮችን ያስረሳናል። እስቲ እነ እስክንድር ነጋን፣ እነ አንዱአለም አራጌን ወይንም ሌሎች በእስር ቤት ያሉ ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞች አስቡዋቸው። አንድ ሰሞን ይፈቱ! ይፈቱ! የሚል ጩኸት ነበር። ይህ ጩኸት ሲበረክት ትህነግ ሌላ አጀንዳ ሰጠን። እኛም የጨበጥነውን ለቀን፣ አዲስ በተሰጠን ሌላ አጀንዳ እንጮኻለን። እንደዚህ እያለ የጨበጥነውን እየለቀቅን፣ ትህነግ በሚሰጠን አጀንዳ ላይ ለፍሬ ያልበቃ ጩኸት ስንጮህ ይኸውና 25 ዓመታት ተቆጠረ። መቼ ነው በራሳችን አጀንዳ መጮህና ለፍሬ የምናበቃው? መቼ ነው የቀደመውንና  የአሁኑን አቀናጅተን በአንድ ላይ መጮህና መታገል የምንጀመረው? እስቲ «አንዳርጋቸው ፅጌ ይፈታ» በሚል አንድ ሰሞን በዓለም ዙሪያ የነበረውን አስቡትና አሁን ደግሞ ስሙም የተረሳ በሚመስል መልኩ የይፈታው ጩኸት ደብዛው በመጥፋት ላይ ነው። ይህ የሚያሳየው ፖለቲከኞቻችን የራሳቸው አጀንዳ የሌላቸው፣ ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ ሳይሆኑ፣ ሁኔታዎች የሚገዙዋቸው፣ አልፎ አልፎም ወረት የተጠናወታቸው ይመስላል። ሕዝቡም ለእሱ ብለው ሕይዎታቸውን የሰዉትን ብቻ ሳይሆን፣  በሕይዎት  በእስር እየማቀቁ ያሉትንም ዘንግቶ የዕለት ተዕለት ጉዳዮችን ብቻ በማንሳት ዘላቂ ነገር ሳያመጣ ንፁሃንን እያስበላ ማለፍን ባህሉ እያደረገው መምጣቱን የሚሳይ ነው። እንዲህ የተዘነጉ ክስተቶችን እና በከንቱ ደማቸው ፈሶ የቀረውን ኢትዮጵያዊያን  ዘርዝሬ አልጨርሰውም። ሆኖም ግን ምንም የተቀናጀ ነገር እንደሌለን ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው። ይህን አባባል ኦስካር ዴቭስ እንዲህ ይገልጸዋል፤

“While in prison, your greater fear is being forgotten by those whom you have fought for and gave up your own freedom to defend their right” by Oscar Daves.

ሌላው ቢቀር አሁን በረሃብ እየተጠበሱና እያለቁ ስላሉ ወገኖቻችን እንኳን ለራባቸው ልንደርስ፣ ችግራቸውን ለማሰማት የተባበረ ጥረት ስናደርግ አይታይም።  በቃ እነ ትህነግ በየጊዜው ትኩስ ዜና እየፈጠሩልን ስለ አዲስ ክስተቱ ብቻ እየተወዛገብን በፊት የተከሰተውን አሁን ካለው ሁኔታ ጋር አገናኝቶ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ማሰብ ተስኖናል። ይሄ ነገር ሳይቀየር፣ አገር ሰላም ሆና እኩልነት የሰፈነባት ሀገር ይኖረናል ማለት ዘበት ነው። ሰከን ባለ አእምሮ አስበን፤ የተቀናጀ ዘላቂ መፍትሄ ሰንቀን ትህነግን (ወያኔን) ለማውረድ ቁርጠኛ አቋም ይዘን በተደራጀ መልክ መንቀሳቀስ ካልጀመርን በስተቀር፤ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አውራ ጠላት የሆነው ትህነግ (ወያኔ)፣ ለረጅም ጊዜ የተውጠነጠነ ድክመታችንን ግምት ውስጥ ያስገባ እቅድ አንግቦ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ፣ እየፈራነው ያለው የአገራችን ከመኖር ወደ አለመኖር የቁልቁለት ጉዞ እኛው ራሳችን እያፋጠነው መሆኑ መታወቅ አለበት።

  1. «የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግርግዳው ሰንበሌጥ»

ሁላችንም እንደምንገነዘበው፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ኢሕአፓ ከፍተኛ የሆነውን ሕዝብ ስሜት ተቆጣጥሮ እንደነበር እናስታውሳለን። ለድል ግን ሲበቃ አላየንም። ለዚህም ያበቃው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን በሚመለከት የጠራና በሐቅ ላይ የተመሠረት ዓላማ አለመያዝ፣ የኢትዮጵያ ጠላቶች መሣሪያ መሆኑንና ኢትዮጵያን እንደአገር ሳይሆን፣ «የብሔረሰቦች እስር ቤት ናት» ብሎ ማመኑና  በእስር ላይ የሚገኙት ነገዶች ባፈተታቸው መንገድ የታሰሩበትን ቤት አፍርሰው የየራሳቸውን ጎጆ እንዲቀልሱ የሰጠው ዕውቅና አንዱና ዋናው ነው። ከዚህ በተጨማሪ በቂ የትጥቅ ትግል አራማጅ ኃይል ሳያዘጋጅ፤ አመራሩ ወጥ አመለካከት ሳይገነባ፣ በጨበጣ የፖለቲካ ሥልጣን ለመጨበጥ የወሰደው የከተማ ውስጥ ትጥቅ ትግል «ጠላቴ ናቸው» ባላቸው ኃይሎች የተሰነዘረበትን የመልስ ምት መመከት አለመቻሉ እንደሆነ ይታወቃል። በአጠቃላይ ሁለንተናዊ አቅም ሳይገነባ፣ «በቶሎ ጥይት ተኩሳችሁ አሳዩን ወይንም ልንተኩስ ነው፣ ዝግጅት ጨርሰናል ባጭር ጊዜ ውስጥ ሥልጣን እንረከባለን» የሚል ተስፋን በወጣቱ ኅሊና ውሰጥ በክራር በተቀነባበረ ቅስቀሳ በማሰራጨት፣ ያሉትን አምኖ በርሃ ለገባው ወጣትና ጎልማስ ያሉትን ሆነው አለመገኘት፣ ለድርጅቱ በትግል ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ መፍጠሩ ሐቅ ነው። ድርጅቶች መወጣት የማይችሉትን ቃል መግባት እና ያን ቃል ሳይፈጽሙ መቅረት በሕዝቡ ሥነልቦና ውስጥ በቀላሉ ሊሽር የማይችል የተስፋ መቁረጥ ስሜት ሊከት መቻሉን፣ ሕዝባችን የሚገኝበት ተበታትኖ ለጠላት ምት የተጋለጠበት ሁኔታ ያሳያል።

እስቲ ግንቦት 7ን አስቡት። «በቃ 6 ወር ነው፣ ዓመት ነው፣ ተደራጅተናል ወያኔን እንጥላለን» ሲሉን አመታት አለፉ። «ይሄንን ያህል ሠራዊት አሰልጥነን፣ ዝግጅት ጨርሰናል፣ ውጊያ ጀምረናል» እያሉ በተቆጣጠሩት ራዲዮና ቴሌቪዥን ይነግሩናል። በተጨባጭ ግን የምናየው አለን የሚሉት «ሠራዊት» ከነመሪው ለትህነግ(ወያኔ) እጁን ሲሰጥ ነው። የዚህ ሁሉ ውድቀት ምክንያቱ እታገላለሁ የሚለው ኃይል በተቀናጀና በተጠና፣ የአብዛኛውን ለውጥ ፈላጊ ፍላጎትን እምነት ያማከለ ሥራ አለመሠራት ውጤት ነው። አስቦ፣ ጊዜ ወስዶ፣ ተጨንቆና ተማክሮ ከመስራት ይልቅ፣ የይድረስ ይድረስ፣ በአቋራጭ ለድል ለመብቃት በተወሰኑ ሰዎች ፍላጎት ላይ በመንጠልጠል ርቆ የተሰቀለውን ዳቦ ያለመሰላል ለማውረድ ስለምንጣደፍ ነው። ድርጅቶች እንደዚህ ወደተጣደፈ ተግባር የሚገቡትም ወደው እንዳልሆነ ይታወቃል። ደጋፊዎቻቸው እንዲህ እንዲሠሩ ይገፋፉዋቸዋል። የሕዝቡንና የደጋፊዎቻቸውን ስሜት ለመጠበቅ ሲሉ፣ የማይችሉትን ቃል በመግባት፣ ለጊዜውም ቢሆን ደጋፊዎቻቸን ከጎናቸው ለማሰለፍ ለተወሰነ ወቅት ጫጫታ ከጎናቸው ያቆማሉ።  ይህ ደግሞ ለትህነግ የመከፋፈል ዓላማ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር «ተቃዋሚ ነኝ» ያለውን ራሱን በራሱ እያናካሱ እንዲገዙ ዕድል ሰጥቷቸዋል። ምክንያቱም  ድርጅቱ ሳይጠናከር፣ በስሜት ብቻ የተቀላቀሉትን ለይቶ ለማጥቃት ይመቻልና ነው። እስቲ ወደ ኋላ ዞር ብለን እናስብ፤ በዕውነት ከምር አስቡት፤ በግልጽ መሬት ይዞ፣ እዚህ ቦታ ውጊያ አካሄደ ሳንባል፣ ኃይል እጠቀማለው ስላለ ብቻ፣ የግንቦት 7 አሸባሪ አባላት ተብለው ስንቶቹ የአሸባሪ ታፔላ ተለጥፎባቸው ተገደሉ? ለዕድሜ ልክ እስር ቤት ተዳረጉ። ስለዚህ ምናለ፣ መጀመሪያ ሕዝቡን አንድ ባይሆን እንኳን፣ አብዛኛውን የሚያቀራርብ ሃሳብ ላይ ተመሥርቶና ተመክሮ ወደሚያስማው ሃሳብ የማይመጡትም በግልጽ አቋማቸውን አሳውቀው በራሳቸው መንገድ እንዲጓዙ መፍቀድ። በአብዛኛው የሚያሰባስበውን ሀሳብ የሚያራምዱ የትግሉ ተመክሮ፣ የዓላማ ጽናት፣ ሐቀኝነትና ታታሪነት ያላቸውን ሰዎች ወደፊት አውጥቶ፣ ቀሪው በነርሱ ዙሪያ እንዲሰባሰብና የሚችለውን እንደአቅሙና ችሎታው ለትግሉ አስተዋጽዖ የሚያደርግበትን ስልት ነድፎ መንቀሳቀስ ይደር የሚባል መሆን የለበትም ባይ ነኝ።  ይገባኛል፣ ለትህነግ(ወያኔ) አንድም ቀን መጨመር የኢትዮጵያን ጥፋት ከድጡ ወደማጡ እንደሚያስኬድ፤ ግን በችኮላ የተጓዝንባቸው ጉዞዎች ለፍሬ ስላላበቁን ፣ ቸኩለንም የምናመጣው ለውጥ ይኖራል ተብሎ ስለማይጠበቅ፣ ካለፉት ስሕተቶቻችን ትምህርት ቀስመን፣ ችግሮቻችን አበጥረን አውቀን፣ ለመፍትሔዎቹ በጋራ የምንሠራበት ሁኔታ መፈጠር ይኖርበታል እላለሁ።

የችኩሎችን ምሳሌ ላስረዳ። ዶ/ር ፍሥሓ እሸቱ ወደ ፖለቲካው መድረክ ዘው ብለው ገብተው፣ በ6 ወር ውስጥ መንግስት መለወጥ ይቻላል ብለው፣ አጀብ! አጀብ! ተባለ። ከዚያም ጊዜው ሲያልፍ ምን ላይ እንዳሉ ባላውቅም ድምፃቸው ጠፋ። ዐወጋን የሚባሉ ዐማራዎች ተደራጅተው ወያኔ ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው ተብሎ ፕሮፓጋንዳ ተናፈሰ፣ ኢሣትም አራገበው፤ ወዲያው ተለቃቅመው ተያዙ መሰል ወሬያቸው ጠፋ። አርበኞች ግንባር ከፍተኛ ጥቃት እያደረሰ ነው ተባልን። አሁን ግን ስለነሱ ጥቃት ማድረስ ብዙም አንሰማም። ሌላም ሌላም ምሳሌ ማቅረብ ይቻላል። መቼ ነው ሰከን ብለን ሕዝባዊ መሠረት ያለው፣ በብሔርተኝነት እስከመገንጠል የሚያምኑትንም ይሁን፣ ብሔር ተጠርቶም ይሁን፣ ሳይጠራ፣ ባንድነት እንኑር የሚሉትን ሁሉንም ድርጅቶች አሰባስቦ፣ ሁሉንም ባያስደስት እንኳን፣ ጠርዝ የያዙትን ወደ መሀል ስቦ፣ አብዛኛውን አስማምቶ ማኖር የሚችል የፖለቲካ አስተሳሰብ መጨበጥና ከዚህ በመለስ ያሉትን፤ ልዩነቶች በሂደት ደረጃ በደረጃ ለሁሉም አስማሚ የሆነ የጋራ መፍትሔ በማመንጨት፣ ልዩነቶቻችን ምን እንደሆኑ፣ ለሕዝብ አሳውቀን ሕዝቡ ራሱ ሊዳኘን ወደሚችልበት የፖለቲካ አስተሳሰብ መግባት የምንችለው? ይህ ለእኔ የምናፍቀው ጉዳይ ነው።

እዚህ ጋር የግል ሀሳቤን እና የታዘብኩትን ልጨምር። በኢትዮጵያዊነት በጽኑ አምናለሁ፤ ሁላችንም እኩል የሆንባት ሀገር እንድትኖረን እመኛለሁ። ሆኖም፣ ሁሉ በኢትዮጵያዊነት የሚያምኑት የዐማራውን በትህነግ(ወያኔ) መበደል የማይቀበሉና ይህን ገሸሽ እያደረጉ ሌሎችን ለማስደሰት የሚጥሩና በዐማራው ደምና ጥፋት ኢትዮጵያ እንድትገነባ የሚያደርጉትን እቃወማለሁ። በተመሳሳይ መልኩ የብሔር ድርጅቶች «መብታችን ይከበር» ሲሉ የሌሎችንም መብት እነርሱ ማክበር ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው። «ባህላችን ይከበር፣» ብለው መልሰው የዐማራን ባህል ወስደው ዐማራውን አዲስ ባህል እንዲሰጡት አልፈቅድም። «ድሮ ሳንፈልግ በአማርኛ ተናገርን» ብለው፣ ዛሬ ዐማራውን በግድ የራሱ ያልሆነ ቋንቋ እንዲናገር ሲያስገድዱት ማየት አልፈቅድም። ስለሆነም በኢትዮጵያዊነት የተደራጁት ዐማራን ካገለሉ፣ በብሔር የተደራጁትም ዐማራውን በአውራ ጠላትነት ፈርጀው ኅልውናውን ከተፈታተኑት፤ ዐማራው ራሱን እንደ ዐማራ አደራጅቶ፣ ቢቻል ከሌላው ጋር ዕኩል ሆኖ አብሮ የመኖር መብቱን ማስከበር፤ ካልተቻለ ደግሞ ጠባቦቹ ዐማራን ለማጥፋት በያዙት መንገድ ከቀጠሉ፣ ዐማራውም ራሱን በዐማራነት አደራጅቶ  ከሚፈጸምበት ጥቃት መከላከል ተገዶ የሚገባበት መንገድ በመሆኑ ማንም ይህን ሊከለክለው አይገባም ባይነኝ። ምክንያቱም እንደ ሲቪክ ድርጅት ዐማራውን አንቅቶ በአንድነት ጎራ ሥር ያሉትን ዐማሮች፣ የዐማራ መብቶች እንደተነጠቁና እንደተገፈፉ ተረድቶ፣ ባለበት ድርጅት ልክ የሌላው ኢትዮጵያዊ መብት ሲከበር የዐማራውም መብት መከበር እንዳለበት ጠንክረው እንዲሠሩ ማስተማርና ማንቃት ይችላል። ነገሩ ገፍቶ ደግሞ ብሔርተኞቹም ከገነኑ፣ ዐማራው ወገኖቹን አሰባስቦ፣ «መጀመሪያ ዐማራን ላድን» የሚሉ የዐማራ ፖለቲካ ድርጅቶች ከውስጡ ይወለዳሉ። በዚህም ምክንያት ሞረሽ የዐማራ ድርጅት የሚባል መቋቋሙን ከሚደግፉ አንዱ ነኝ። ይህም በእኔ አመለካከት አንድ ሕዝብ እጅህን አጣጥፈህ ሞትን በፀጋ ተቀበል የሚል የሃይማኖትም ሆነ የሌላ ሕግ ስለሌለ የሚደገፍ ነው። ይህ ዐማራ እንደ ዐማራ ብቻውን ሌሎችን የሚገጥመው ግን፣ የመጀመሪያው አማራጭ በአብሮነትና በዕኩልነት እንኑር የሚለው ሰሚ ካጣ ነው። ዐማራውን ጠላታችን ነው ብለው ያመኑና  ለዚሁ ተግባር ነገዳቸውን በዙሪያቸው ያደራጁ ቡድኖች፣ ሲያጠፉት፣ ሌላው ኢትዮጵያዊ እንደ ዜጋ ከጥፋት ሊያድነው ካልቻለና ከጎኑ ካልቆመ፣ ዐማራው ዝም ብሎ ጥፋትን መቀበል የለበትም። ከጥፋት ራሱን መከላከል ተፈጥሮአዊ መብቱ ነውና ማንም ሊከለክለው የሚችል አይሆንም።

በአገራችን የፖለቲካ ጉዞ ያስተዋልኩት ሌላ አንድ ነገር አለ። «ለምን ተብሎ፣ እንዴትስ ተደርጎ የዐማራ ድርጅት ይቋቋማል?» የሚሉ ወገኖች አሉ። ይህን ጥያቄአቸውን ወደ ሌሎች ሲያዞሩት አይታዩም። ትግሬው፣ ኦሮሞም፣ ጉራጌው፣ ሶማሌው፣ አፋሩ፣ ወዘተ በነገዱ ተደራጅቷል። «እነዚህ ለምን ተደራጁ?» ተብሎ ሲጠየቅ አይሰማም። ዐማራ ጊዜ ወስዶ፣ አስቦና ሁኔታዎችን ገምግሞ «ነገዱን ከፈጽሞ ጥፋት ለመከላከል ያለው ብቸኛና ተገዶ የገባበት መንገድ ተደራጅቶ ራሱን ከጥፋት መከላከል ነው፤» ብሎ ዝግጅት ሲጀምር ለምን? እንዴት? የሚሉ ድምፆች ከዚህም ከዚያም ይደመጣሉ። እነዚህ ድምፆች ዐማራውን እንዲጠፋ ተያይዞም ኢትዮጵያ እንድትጠፋ ምኞት ያላቸው ድምፆች እንጂ፣ ለዐማራው ማንነትና ለኢትዮጵያዊነት ዳብሮ መቀጠል ከሚመኙ ወገኖች እንዳልሆኑ መገንዘብ አይገድም።

በሌላ በኩል «የዐማራው መደራጀት ተገቢ ነው፣ በሀሳብ እንደግፈዋለን ወይንም አንቃወምም» የሚሉ ድምፆች ቢኖሩም፣ ጠጋ ብለው የመደራጀቱ ሂደት ተፋጥኖ በነገዱ ላይ ተጨማሪ ጥፋት ሳይጠፋ፣ የኢትዮጵያዊነት አያያዥ ክሮች ሳይበጠሱ ሁኔታዎችን ወደ ነበሩበት ጤናማ ሕይዎት ለመመለስ ለሚደረገው ትግል ምንም አይነት አስተዋፅኦ ሲያደርጉ አይታዩም። በተለያየ ምክንያት ከዳር ሆነው ሲመለከቱ ነው የሚታዩት። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርት ድርጅቱ ተመሥርቶ 3 ዓመት ከተጓዘ በኋ፣ አንዳንድ ሰዎች «እንዴት ናችሁ? ምን እየሠራችሁ ነው? ለተጎጂው ዐማራ ምን አደረጋችሁ?» የሚሉ ድምፆችን ያሰማሉ። እነርሱ ግን «እኛ ምን አደረግን? ከእኛ ምን ይጠበቃል?» ብለው ራሳቸውን አልጠየቁም። ይህን ቢጠይቁ ምን እንደተሠራና ምን እንደቀረ መልሱን ራሳቸው ያገኙት ነበር። ሞረሽ ወገኔ በዚህ የሦስት ዓመት ጉዞው ማንም ሊሠሩ ይችላሉ ብሎ ሊያምን ቀርቶ ሊያስባቸው የማይችሉ መሠረታዊ የመረጃ ማሰባሰብ፣ የማደራጀትና ዐማራውን የማንቃት ሥራዎች ሠርቷል። የሞረሽ ምሥክሩ ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን፣ ተግባር ስለሆነ ተግባሩ ኅያው ሆኖ የሚቀጥልበት መሠረቱ ተጥሏል። በዚህ ረገድ ሞረሽ ወገኔን የመሠረቱና በሂደት የተቀላቀሉ ወገኖች «ለወገን ችግር ፈጥኖ ደራሹ ወገን ነው» የሚለውን አባባል በተግባር ያሳዩ በመሆኑ በነገዱ ታሪክ ውስጥ የጎላ ቦታ የሚይዙ እንደሚሆን መጠራጠር አይቻልም።

እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን ድራሻ ሳይወጣ፣ ሌሎችን «ምን ሠራችሁ?» ብሎ መጠየቅ አግባብነቱ ባይታየኝም፣ ምንም ሳያደርጉ «የታለ ሞረሽ? ምን ሠራ?» ብሎ ድርጅቱን ማጣጣል እና አማራ በአማራነቱ መደራጀቱ ጥቅም እንደሌለው ማሰብ፣ ዐማራውን ለጠላቶቹ የጥፋት እልቂት ተመቻችቶ ጥፋቱን በፀጋ እንዲቀበል የጥፋት መልክተኛ ከመሆን ውጭ የሚታይ በጎ አመለካከት አይደለም። ይሄ እኮ ነው ችግራችን። ምንም ሣንሠራ ለውጥ እንፈልጋለን። ሰዎች በአቅማቸው የሠሩትን ማመስገን ሳይሆን፣ ያልሠሩትን ማብጠልጠል እንሻለን። ስለዚህም በቃ ፖለቲካ ድርጅቶች ካቅማቸው በላይ እንዲህ ልናደርግ ነው እንዲሉ ያስገድዳቸዋል። «አይነጋ መስልዋት ከቋት ምን አለች» እንዲሉ ይሄኛውን አጣጥለው አዲስ የሚመጡትም አዲስ ድርጅት ቢያቋቁሙም ለዘላቂ መፍትሄ እስካልሠሩ ልፋታቸው እንዳለፉት ሁሉ ከንቱ ሆኖ እንደሚቀር መናገር መጥፎ ምልኪ አሳቢነት አይሆንም። እናም ያልዘሩት ማጨድ አይቻልምና ዘርተን ለማጨድ እንጣር!

  1. 5. በለስ ከቀናው ጋር ተስማምቶ የድርሻን ለማግኘት ጥረት ማድረግ እንጂ ግልጽ አቋም አለመያዝ፣

ከላይ በተወሰነ መልኩ ለማንሳት እንደሞከርኩት፣ ዋናው ችግራችን በውስጣችን ስለ ግላቸው ስብዕና ወይንም ስለ ጥቅማቸው ብቻ እንጂ፣ ስለ ኅብረተሰቡ ወይንም ለሀገሪቱ የማያስቡ ብዙ ሰዎች በፖለቲካው መድረክ ውስጥ መኖራቸው ነው። ይህን ስል ራሴን ነፃ ለማድረግ አልፈልግም። የራሴን የግል ዓላማ ለማሳካት እስካሁን በግል ሕይዎቴ ዙሪያ ብቻ ስለተጠመድኩ፣ ለወገኔ ማበርከት የሚገባኝን እንዳላበረከትኩ ይሰማኛል። «አንተስ?» የሚል ጥያቄ ከመጠየቄ በፊት ግዴታየን አለመወጣቴን እንደማውቅ ተረዱልኝ።

ዋናው ግን በቃ! ጣልያን ሲመጣ በባንዳነት፣ ሲወጣም በውስጥ አርበኝነት በሚሉ ስሞች ሌሎች ዕውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች በከፈሉት የሕይዎት፣ የአጥንትና የደም ዋጋ ምቾታቸውን ያስጠበቁ ብዙ ባንዳዎች እንደነበሩ ሁሉ፣ ዛሬም  በዚህ ዘመን ውስጥ በከፋና በሠፋ መልኩ አሉ። ወደፊትም ይኖራሉ። ኅብረተሰብ እንደ ወራጅ ውኃ ነውና ይህ የሚቋረጥ አይሆንም። ማቋራጫው ዕውነተኛ ታሪክን ለትውልድ በማስተማር ባንዶቹ እንዳለፈውና እንዳሁኑ የቀረው ቢቀር «እንምራችሁ» እንዳይሉን የእያንዳንዱን ፖለቲከኛ ማንነት ማወቅ ተገቢ ነው እላለሁ። ያለፈውን ታሪካችን አሳዛኝ የሚያደርገው ባንዳዎቹ በሥልጣን ማማ ላይ ተቀምጠው ልጆቻቸውን በራሳቸው አምሳል ከመቅረጽ አልፈው፣ ይህን ውርስ በትምህርት ዘመናዊነት እንዲላበስ አድርገው የባንዳዎቹ ልጆች ዛሬ የት እንዳሉ የምናውቀው ነው።

የአርበኞቹ ልጆች ወላጆቻቸው ያስተማሩዋቸው ያገር ፍቅር፣ አርበኝነት እንጂ፣ ዘመናዊ ትምህርት የሚያስተምሩበት አጋጣሚውም ዕድሉም ስላልነበራቸው የአርበኝነቱንና የአገር ፍቅሩ ብቻ በልባቸው ቀረ። የዘመናዊ ትምህርቱ ባይተዋሮች በመሆናቸው፤ ይኸውና በባንዳ ልጆች ከመገዛት አልፈው፣ አባቶቻቸው ሞተው ያስጠበቋትን አገር ከማጣት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።  በዚህም ምክንያት ዛሬ ሀገሪቱ  የምትመራው በባንዳ ልጆች ነው። በተቃዋሚው ጎራም ያሉት ብዙዎቹ የባንዳ ልጆች ናቸው። ሁለቱም ስለ ግለሰብ ስብዕናቸው ወይንም ስለሚያካብቱት ሀብት እንጂ፣ ስለ ኅብረተሰቡ ሲጨነቁ አይታዩም። አሁንም እየታየ ያለው የደሀን ልጅ አስገድለው የነርሱንና የልጆቻቸውን ሕይዎት የተደላደለ ለማድረግ ነው።

ለዚህም ነው «ቶሎ ተኩሶ ቶሎ ለውጥ አምጡ፣ አለበለዚያ ካለው ጋር እንሠራለን» የሚሉን። «ቶሎ ተኩስ» የሚሉት ደግሞ በሚገርም ሁኔታ እንኳንስ ጥይት ሊተኩስ የሚችል የሰው ኃይል ቀርቶ፣ በሰማይ ሊንሳፈፍ የሚችል ባሉን (ፊኛ) ያዘጋጁ አይደሉም። ለዚህም ነው ግልጽ የሆነ አቋም ሳይያዝ፣ የማይቀላቀሉ ዘይት እና ውኃ «ትህነግን ብቻ እንጣል እንጂ፣ እኛ እንስማማለን» የሚሉን። አትሳሳት ወገኔ እንዲህ ያለ የችኮላ አካሄድ አይሠራም። ይህ ትልቅ ማጭበርበር እና በሌላ ሰው ደም የሥልጣን ባለቤቶች ለመሆን የሚፈልጉ የባንዳዎች ሀሳብ ነው። መስማማት አንድነት ያስፈልጋል፣ አዎ! ያስፈልጋል። ግን በደፈናው ስምምነትና አንድነት የለም። የአንድነቱና የስምምነቱ መሠረታዊ ጉዳዮች በግልጽ ለሕዝብ ይፋ መሆን አለበት። አንድነቱና ስምምነቱ የኢትዮጵያን አገራዊነትና አንድነት መሠረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል። አገር ለማፍረስና ለመበታተን ስምምነት አያሻም። አገር ለማፍረስ የሚያሻው እንደ ትህነግ (ወያኔ) ጉልበት ብቻ ነው።

  1. ከኔ ሀሳብ ውጪ ያላ ሀሳብ ላሣር ነው፣

እንደምናውቀው ከሶሻሊዝም አብዮት የተጠናወተን ከፉ ልክፍት፣ «ከኔ ሀሳብ ውጪ ያለ ሁሉ መጥፎ ነው። ያን የሚያራምድ ሁሉ ጠላቴ ነው» የሚለው ነው። «ከእኔ የተለየ ሀሳብ የሚያቀነቅነውን ሰው ወይም ቡድን ላጥፋው» ከሚለው አስተሳሰብ እስካልተላቀቅን ድረስ፣ ዲሞክራሲ፣ መቻቻል፣ መከባበር፣ መደማመጥ፣ ልዩነቶችን አውቆና ተቀብሎ የአንድነቱ ምሰሶዎች የማድረግ አመለካከት እስካልቀረጽን ድረስ፣ አብሮ መኖር የሚባል ነገር አይታሰብም። በእርግጥ በኢኮኖሚ ዕቅዳቸው ምክንያት ግራ ዘመም፤ ቀኝ ዘመም፣ መሀል፣ አጥባቂ ፣ ለዘብተኛ ወዘተ ተባብለው በመሠረታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ግን ተስማምቶ መኖር የተለመደና ዴሞክራሲያዊ ነው። ምክንያቱም ይህ የሕዝቡን መብት የሚነካና የሚጫን ሳይሆን፣ ልዩነታቸው የተመሠረተው በቋንቋ፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣ ወዘተ ሳይሆን፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካ መርሕ ላይ ነው። አንደኛው ወገን፣ «አንዷን ጥንታዊ  ሀገር በብሔር ከፋፍለን፣ አንድ የነበረን ሕዝብ ልዩነቱን በምን መልኩ ልናጠበውና የመጨረሻ ዕልባት ልንሰጠው በማንችልበት የብጥብጥና የመጋደል አዙሪት ውስጥ አስገብተን፣ ከኢኮኖሚ ውጪ በሰዎች ኅሊና ውስጥ ያለ ስስ ስሜትን በማዳበር አብሮ መኖርን እስከ ወዲያኛው የማይቀበለው ትክክል ነው» ሲል፣ ሌላው ደግሞ «የለም፣ በብሔር ድንበር ሳይከፋፈል፣ የሁሉም መብት ተከብሮ፣ በጋራ የምንኖርበት አገር ይኑረን፣» የሚል ነው። እነኚህ ሀሳቦች ፈጽሞ የማይስማሙ ሀሳቦች ስለሆኑ፣ ሁለቱ ሀሳቦች አብረው እንዲኖሩ ማድረግ ከባድ ነገር ነው። እንደዚህም ሆኖ ሳለ ግን፣ ሁሉም ሀሳቡን አንጥሮ አውጥቶ፣ አንዱ አስተሳሰብ የሌላውን ሥጋት በምን መልኩ እንደሚመልስ በግልጽ አስቀምጦ፣ ልንመራበትና አብሮ ሊያኖረን የሚችለውን ቀመር ሕዝብ እንዲወስንበት ማድረግ ብልኅነት ብቻ ሳይሆን ለሕዝብ ድምፅ መገዛትም ነው። ይህ ደግሞ «ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት ነው፤ ባለሥልጣኖች የሕዝብ ወኪሎችና እንደራሴዎች ናቸው፣» የሚለውን የዲሞክራሲ መርሕ የሚያራምድ በመሆኑ አስማሚ ነው። ችግሩ አንዱ የሌላውን ሀሳብ ማዳመጥ አይፈልግም፤ ሕዝቡ እንዲወስን ሳይሆን፣ እርሱ የፈለገውን በጉልበት በሥራ ላይ እንዲውል የመፈለጉ ጉዳይ የፖለቲከኞቻችን ያልተለወጥ ቅኝት መሆን ነው።

ሌላኛው ትዝብቴ ደሞ ከላይ እንዳነሳሁት ኢትዮጵያው ውስጥ በብሔር እና በሀገር ደረጃ ያለው አደረጃጀት በተመለከተ የሚሰጡ አስተያየቶች ይለያያሉ። የልዩነቱ መሠረት ጉልበት ከሆነ አላውቅም። ለምሳሌ ትግሬ ወይንም ኦሮሞ ወዘተ በኢትዮጵያዊነት ሲሰባሰብ እሰየው ይባላል፣ ይበረታታልም። ትግሬ ወይንም ኦሮሞ በብሔር ሲደራጁ ጉልበት አላቸው፣ ተደራጅተዋል በሚል እንደሆነ አላውቅም ሀሳባቸውን በግልጽ ከመቃወም እንቆጠብና፣ በነገድ መደራጀታቸው የሚያስከትለውን ችግር ከማስረዳት ይልቅ፣ እነሱን ወደ ማባበል እንዞራለን። ዐማራ ሲደራጅ ግን፣ ራሱ ዐማራን ጨምሮ፣ ያለው ተቃውሞ ለየት ያለ ነው። ሲጀመር ዐማራ «በኢትዮጵያዊነት ልደራጅ» ሲል «የድሮ ሥርዓት ናፋቂ» ይባላል። ከዚህ ሁሉ አጣብቂኝ ለመውጣትና ዘሩን ከጥፋት ለመከላከል፣ «እንግዲህ ምን ላድርግ? በዚህም በዚያም ቦታ ካሳጣችሁኝ፣ እንደዐማራ ልደራጅ» ሲል፣ አንዱ «ዐማራ የለም» ይላል። ሌላው ደግሞ «እንዴት ዐማራ ይጠባል? ቢያልቅም፣ ከጥፋት የሚያድነው ቢያጣም፣ በዐማራነት ከሚደራጅ ጭራሹኑ ቢጠፋ ይሻለዋል» ይላል። እንግዲህ ያለውን አመለካከት ልዩነት አስቡት። በዚህ ብቻ አያበቃም። ራሳቸው ዐማራዎቹ በአንድነት ጎራ ሥር ያሉት እና አሁን አሁን እያቆጠቆጡ የመጡት «ዐማራ በዐማራነት መደራጀት አለበት» ከሚሉት ከዋና ጠላቶቻቸው ይልቅ የእርስ በእርስ ጠላትነታቸው ገኖ የሚወጣበት ይበልጣል።  ይሄም «እኔ ካልኩት ሀሳብ ውጪ ሌላው ሁሉ ስሕተት ነው፣ የተለየ ሀሳብ ያላቸው መጥፋት አለባቸው» ከሚለው የቆየ አስተሳሰብ የሚቀዳ መሆኑ ጥርጥር የለውም።

መሆን የነበረበት፣ ሌሎች ስሕተትም ይሁኑ ልክ፣ በብሔርም ሆነ በአንድነት ድርጅት ውስጥ ተወካይ እንዳላቸው እና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የብሔራቸውን መብት እንደሚያስከብሩ ሁሉ፣ ዐማራውም በአንድነት ድርጅት ውስጥም ይሁን በዐማራነት የተደራጁትን በሚያስማማቸው፣ «ዐማራን ከጥፋት መታደግ» በሚለው አብረው እየሠሩ ልዩነታቸውን ለሕዝቡ እየገለጹ በሂደት የትኛው ድርጅት እንደሚስማማው ሕዝቡ እየመዘነ የራሱን ውሳኔ እንዲሰጥ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነበር ያለባቸው። አይደለም፣ የዐማራ የፖለቲካ ድርጅት ይቅርና! ሕዝብን ለማሰባሰብ እና ለመርዳት የተቋቋመ የሲቪክ ድርጅትን «የዐማራ ሲሆን አንቀበልም» ማለት የቱን ያህል እኛ ካልነው ውጪ ለመስማት ችግር እንዳለብን ያሳያል። ሜጫና ቱለማን ያልተቃወመ ሰው ወይንም ድርጅት ለምን እና እንዴት ሞረሽን ይቃወማል? ኦነግን ያውም እጁ በደም የተጨማለቀን ድርጅት ያልተቃወመ ገና አየር ላይ ያለ ቤተ-አማራን ድርጅት እንዴት ያጥላላል? እስቲ ነገሮችን ሰፋ አድርገን እንይ? አንድን የፖለቲካ ሃሳብ መቃወም መብታችን ነው ግን ከተቃወምንም ሁሉንም እንጂ፣ የአንዱን ነገድ ድርጅቶች ብቻ ለይተን አንቃወም። ሰው መጥቶ አይንካህ እንጂ፣ የፈለገውን ሀሳብ ያራምድ። ድንበር ተሻግሮ ከነካህ መልስ ምት ያስፈልጋል። መደራጀትህም ለዛ ነው። ግን መቻቻልና መደማመጥ ከሌላ የትም አይደረስም።

መፍትሔው

በሀገሪቱ አሉ የተባሉ የፖለቲካ፤ የሲቪክ፤ የሃይማኖት ድርጅቶች ተሰባስበው የሁሉንም ሀሳብ አዳምጠው፤ እያንዳንዱ ለሚለው ሀሳብ ማጠናከሪያውን መረጃ አቅርቦ፤ እንዲሁም ላቀረበው ሀሳብ በመረጃ የተደገፈ የተቃውሞ ሀሳቦችን አዳምጦ፤ ሁሉንም እንኳን ባያስደስት አብዛኛውን በተወሰነ መልኩ አስማምቶ፣ በሰላምና በእኩልነት የምንኖርባትን ሀገር እንድትኖረን ለነገ ሳይባል ዛሬ ማካሄድ ግድ የሚለን ይመስለኛል። እዚህ ጋር የሚቀርበው መፍትሔ በሀገሪቱ ትልቁን ቁጥር የሚይዙትን ዐማራን እና ኦሮሞን የሚያቀራርብ ሀሳብ ማቅረብ የግድ ነው። ነገር ግን ይህ ሀሳብ በፍፁም ቁጥራቸው አነስተኛ በሆኑት ሌሎች ነገዶች ላይም ይሁን የተቀላቀሉ ነገዶች ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚኖረውና መብቶቻቸውን የሚያስከብር መሆኑን ከወዲሁ እርግጠኛ መሆን አለበት። ከምንም በላይ ለችግራችን ሁሉ መነሻ የሆነው አንድን የኢትዮጵያ አካባቢ ለአንድ ብሔር ሰጥቶ የተቀሩትን በዛ አካባቢ 2ኛ ዜጋ ያደረገው በባንቱስታን ሥልት የተዘረጋውን የብሔር አከላለልና የዚሁ መሠረት የሆነው ሕገመንግሥት መናድ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። የሁሉም ባህል፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ ተከብሮ የሚኖርባት ሃገር እንዲኖረን ማድረግ ያስፈልጋል። (ልብ በሉ ይህ መብት ዐማራንም ይጨምራል። አዲስ በቻይና ልብስ አዲስ ባህላዊ አለባበስ ለዐማራው መስጠት መቆም አለበት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ባህል ይከበር እስካልን ድረስ)። ሕዝቡ በድምፅ ብልጫ እስከወሰነ ድረስ በሀገሪቱ ሁለትና ከዚያም በላይ ብሔራዊ ቋንቋ ቢኖር መበልጸግን እንጂ፣ መደህየትን ስለማያመለክት ክፋት አለው ብየ አላምንም። ለጉዳዩ ግን ባለቤቱ ሕዝቡ ዓላማውና ግቡ ተብራርቶ ቀርቦለት ጥቅሙንና ጉዳቱን መዝኖ በድምፁ የሚወስነው መሆን ይኖርበታል።

«ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልምና» እኔ ሀሳቤን አካፍያለሁ። በደፈናው ሰውን ማብጠልጠል ሳይሆን፣ ሀሳብን በሀሳብ በመሞገት የተሻለ የምትሉትን ሀሳብ እያቀረባችሁ የሕዝባችንን የመከራ ቀናት ለማሳጠር እንሥራ። መፍትሔውን በተመለከተ ብዙ ዝርዝር ሀሳቦች የምላቸውን ወደፊት ይዤ እቀርባለሁ።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይታረቃት!!!

ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች!!!

*በስነፅሁፍ ህግ መሰረት በአማርኛ ስፅፍ አማርኛ ቓንቓ ብቻ መጠቀም ስላለብኝ ትህነግ (የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር) የሚለውን እንጂ በትግርኛ የሆነውን ህወሃት (ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ) የሚለውን አልጠቀምም። በተለምዶ ወያኔ ስለሚባሉ አልፎ አልፎ እጠቀማለው። ሻዕቢያም እንዲሁ በአማርኛ ሲሆን ኤህነግ ነው። በውንግሊዝኛ ሲሆን TPLF, EPLF ወዘተ ተብሎ ይፃፋል። በአማርኛ ሲሆን ኦነግ የምል ሲሆን በኦሮምኛ ከፃፍኩ/ከተናገርኩ አባኦ (አደ ቢሊሱማ ኦሮሞ) ብዬ ነው።

አበበ ተድላ (abetedla2011@gmail.com)

ታህሳስ 2008

The post ካለፉት ድርጊቶች መማር ያልቻለ ትውልድ፣ ለገጠሙት ችግሮች መፍሔ ማግኘት  አይቻለውም! – አበበ ተድላ appeared first on Zehabesha Amharic.

ይድረስ ለ ኢህአዴግዬ! ጉዳዩ፤ እየመሸ መሆኑን ስለማሳወቅ! –አቤ ቶኪቻው

$
0
0

(ይህ ጽሁፍ ለአዲስ ገጽ መጽሄት ተብሎ የተጻፈ ነው! ባለፈው ቅዳሜ ከታተመ በኋላ መጽሄቷን በቅርብ የማያገኙ ወዳጆች አጋራን ባሉኝ መሰረት እነሆ… ብያለሁ!)

Abe-Tokchaw-Satenawይሄንን ደብዳቤ ልጽፍልሽ ከመጀመሬ በፊት አንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራም እየተመለከትኩ ነበር። ያዲሳባ ሴቶች መደዳውን ተደርድረው አንድ ጎረምሳ በፍቅር ያጫቸው ዘንድ በዜማ እና በሌሎችም ጥቅማጥቅሞች ሲለማመጡት እና እኔ እሻል እኔ ሲፎካከሩበት አየሁ… አጀብ ያገሬ ቴሊቪዥን ጣቢያዎች ስንት ርዕሰ ጉዳዮች ባሉባት ሃገር ለቆነጃጅት ጎረምሳ በመምረጥ መጠመዳቸው ስልጣኔው እንዴት ዘልቆ ቢገባቸው ነው… ስል አደነኳቸው።

ይህ አይነቱ የቴሌቪዥን መሰናዶ እዚህ እኛ የምንኖርበት ሃገርም አለ… እነ አሜሪካም ያደርጉታል፤ ልክ ባለፈው ጊዜ አቶ ሃይለማሪያም ‘’ድርቅ ብርቅ አይደለም ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ካሊፎርኒያም በአሁኑ ሰዓት በድርቅ እየተሰቃየ ነው’’ እንዳሉት በይው! ታድያ ግዜው የግሎባላይዜሽን ነውና፤ እዚህ እኔ ያለሁበት እንግሊዝ እና አማሪካ ያለው ነገር ሁሉ ኢትዮጵያ መኖሩም ብዙም ባይደንቅም፤ ነገር ግን ‘እነርሱጋ ለምን ኖረ እኛጋስ ለምን ያስፈልጋል ብሎ መገምገም የቴሌቪዥን ዝግጅት አቅራቢዎቹ ስራ ነበር። እነ ድርቁንስ እግዜሩ ከላይ አከፋፍሎን ነው… ድርቅናውን ግን ራሳችን እንዳመጣልን ከነርሱ የኮረጅነው ነው። ልብ አድርጊልኝ ኢህአዴግዬ፤ ቆነጃጅት መድረክ ላይ ተኮልኩለው ‘’ቁርስህን እንቁላል ፍርፍር ራትህን ቋንጣ ፍርፍር እንዳበላህ፣ በዘፈን እያሞካሸው እንዳባብልህ እኔን ውሰደኝ እኔን ውሰደኝ’’ ሲሉ ማየት ከባድ ድርቅና አይደለም ትያለሽ…? እነ አማሪካ እና እንግሊዝ እንዲህ ያለውን ዝግጅት በየቴሌቪዥናቸው የሚያቀርቡት ማህበረሰቡ ርስ በርሱ በቅጡ የማይቀራረብ ሁሉም የየራሱን ክበብ ከቦ አትደረስብኝ አልደርስብህም ያሰመረ አይነት ስለሆነ የመገናኛ መድረክ ለመፍጠር አስበው ነው… እኛ ሃገር አውቶብስ ፌርማታው… ታክሲ ግፊያው ወፍጮ ቤቱ ሳይቀር የፍቅር መድረክ በሆነበት ቆነጃጅት በቴሌቪዥን መስኮት አደባባይ ወጥተው አንዱን ወንድ እኔን ውሰደኝ እኔን… ሲሻሙበት ማየት በእውኑ እንግዳ ነገር ነው!

አንዳንድ ወዳጆች እማ እንደሚጠረጥሩት ‘’ይሄ አይነቱ ዝግጅት ኢህአዴግዬ ጎረምሳውን ሁሉ አስራ፣ አስራ ሃገሩ ላይ የወንዶች እጥረት እንዲከሰት በማድረጓ የመጣ ነው’’ ቢሉ… የለም… በዚህ እንኳ እኔ አልስማማም፤ ነውር አይደለም እንዴ ኢህአዴግዬ እንዲህ አይነት አድሎ አታውቅም። የጾታ እኩልነት በተረጋገጠበት በዚህ ወቅት ወንድ ወንዱን ለይታ አታስርም ይሄ ስም ማጥፋት ነው ሁሉንም ነው የምታስረው እንጂ ‘ወንድ ወንዱን ለቅማ አስራ የወንድ እጥረት ተከሰተ’ ብሎ ማለት ተራ ስም ማጥፋት ነው ብዬ ተከራከርኩልሽ!

ነገርን ነገር ያነሳዋል አፈር ስሆን በዘጠና ሰባት ዓመተ ምህረት የሆነውን ልንገርሽ…. ምነው እንኳ ያኔ ‘’ከንግዲህ ጣቱን የቀሰረ ጣቱ ይቆረጣል’’ አዋጅ የታወጀ ጊዜ… አንቺኮ ትረሻለሽ! ደግነቱ እኛ አለንልሽ መዝግበን የያዝን ሰዎች እናስታውስሻለን! እናልሽ ያኔ ጎረምሳው ሁሉ በአደገኛ ቦዘኔ አዋጅ ተለቅሞ እስር ቤት ሲገባ አንዱ ‘’አደገኛ ቦዘኔ’’ ወዳጃችን በዛ በቀውጢ ሰዓት አንዷን አፍቅሮልሽ ጠየቃት፤ የፍቅር አጋሬ ሁኚ … ብሎ ቢላት ጊዜ ምን አለችው መሰለሽ… ‘’የኔ ጌታ በዚህ ሰዓት ካንተጋ ፍቅር ጀምሬ ካሁን አሁን ታሰረ አልታሰረ እያልኩ የምጨነቅበት እና የምሳቀቅበት ምክንያት የለም! ግርግሩ ሲያልፍ ካለህ ያኔ ጠይቀኝ’’ አለችው።
የኔ ነገር… ይሄንን ሁሉ ያነሳሁት በምን መሰለሽ… ላንቺ ይሄንን ደብዳቤ ከመጻፌ በፊት አየሁት ባልኩሽ ፕሮግራም ላይ፤ አንዷ ኮረዳ በግድግዳ ተከልሎ ላላየችው ጎረምሳ የዘፈነችለትን ዘፈን፤ እኔ ላየኋት ላጣጣምኳት ኢህአዴግዬ ለምን አልዘፍንላትም ስል ባስብ ጊዜ ዝግጅቱ ትውስ ብሎኝ ይሄንን ሁሉ መዘብዘቤ፤ ‘እስቲ ልቤን አትስቀለው ቶሎ ዝፈንልኝ…’ ብለሽ ችኩል ስትይ ታየኝ። አንቺ እኮ ችኩል ነሽ እንደው ጥድፍ ጥድፍ ማለት ትወጃለሽ ‘ችኩል ብላ ካደረገች በኋላ እንዴት ላድርገው ብላ የምታማክር፤ ከገደለች በኋላ ቁም! ብላ የምታስጠነቅቅ ችኩል’ እያለ ሃገሩ ሲያማሽ መቼም ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እና አልሰማሽም፤ እኔ አለሁልሽ አይደል እንዴ ታድያ ይሄው ነገርኩሽ (ማስታወሻሽን ያዢ ብቻ አንቺ) እና አዚምላት አዚምላት ያለኝ ምን የሚለውን ዘፈን መሰለሽ…

’ገዳይ ነሽ ገዳይ ነሽ በፍቅር ገዳይ ነሽ…
ገዳይ ነሽ ገዳይ ነሽ በመውደድ ገዳይ ነሽ’’
ምነው ሳቅሽ መጣ እወነቴን ነው ገዳይ ነሽኮ… ካላመንሽኝ ያለፉትን ሳምንታት ዜናዎች ዘወር ብለሽ ተመልከቺ… (በቅንፍም፤ ‘’ዞሮ መመልከት ብችል መቼ ገዳይ እሆን ነበር’’ ካልሽኝ አደንቅሻለሁ!) ሰው አንድ ይገድላል ሁለትም እሺ ይሁን ሴጣን ካሳሳተው ምን ይደረጋል፤ አንቺኮ በአንድ ሳምንት ብቻ አንድም ሳይሆን አስርም ሳይሆን መቶ ገዳይ መሆንሽን አለም የመዘገበልሽ ተዓምረኛ ነሽ! ደፍተር ያለው በደፍተሩ ልብ ያለው በልቡ ሁሉንም ጥፎልሻል….
ሰይጣን ብል ጊዜ ምን ትዝ አለኝ… (ስል መቼም ራስሽው ‘’ሚኒስቴር ጌታቸው ረዳ!’’ ሳትይኝ አትቀሪም።) በትክክል መልሰሻል! እኔ የምልሽ ኢህአዴግዬ እንደው እንዴት እንዴት አይነቱን ታበቅይ ጀመር ባክሽ…? የኛ ሀገር ሰው ለራሱ እንኳንስ እንዲህ በቀጥታ ሰድበሽው እና እንዲሁም ምን ለማለት ፈልጋ ነው… ብሎ ይጠምድሻል ጭራሽ ባለስልጣኖችሽ የገዛ ህዝብሽን ‘’ሰይጣኖች አጋንንቶች ጠንቋዮች…’’ እያሉ ሲሳደቡ ዝም ትያለሽ እንዴ! እንዴ…. ማህበረሰቡ እኮ ‘’ድሮም ሰው የውሎውን ነው የሚያወቀው’’ ብሎ በሌላ በሌላ እየጠረተረሽ ነው…!

ኢህአዴግዬ… ለመሆኑ እንዴት አለሽልኝ… ጤና እንዴት ይዞሻል… ጤና መንሳት እንዴት ይዞሻል አልልሽም… የገዛ ጤናሽን ነው የምጠይቅሽ፤ ስብሰባው ግምገማው እንዴት እያደረገሽ ነው፤ እውነቴን ነው የምልሽ እንዳንቺ ብርቱ የለም እኮ፤ ትዝ ይልሻል ከአስር ይሁን አስራ ምናምን አመት በፊት የመበስበስ አደጋ አጋጠማት ተብለሽ… ምነው እንኳ የገዛ አባትሽ አቶ መለስ ዜናዊ ነበሩ እኮ ‘’ኢህአዴግ የመበስበስ አደጋ ላይ ናት’’ ብለው ባደባባይ የተናገሩት… ከዛ የመበስበስ አደጋ ድነሽ ስንቱን ለአደጋ ዳረግሽው… ልልሽ ነበር እንዲህ አይባለም!

ይሄው ዛሬም ቃል በቃል መበስበስ ባይባልም ትልቅ የሆነ የመልካም አስተዳደር ችግር ውስጥ እንድለሽ ቱባ ቱባ ባለልጣኖችሽ ተሰባስበው ሲናገሩ ሰማን። እኔ የምልሽ አንዳንዴ እኮ አስማተኛ ነው የምትመስይኝ… በዘረፈ ብዙ ችግር ውስጥ ሆነሽ አለቀላት በቃ! ስትባይ አንቺቴ አፈርሽን ረገፍ ረገፍ አድርገሽ ተነስተሽ ነፍስ ዘርተሽ ዳግም አናታችን ላይ ጉብ ስትይ… የምርም አስማት የምትችዪ ነው የሚመስለኝ…
የሆነስ ሆነና ኢህአዴግዬ ዛሬ ዋናው ደብዳቤ ልጽፍለሽ ያነሳሳኝ ጉዳይ እየመሸ መሆኑን ልነግርሽ ፈልጌ ነው…
ጊዜው እንዴት እንደሚሮጥ ልብ ብለሻል። እንደ ዋዛ ሃያ አምስት አመት ሞላሽ እኮ… ትዝ ይለኛል አስራ አስራ ስምንት አመት የሞላሽ ጊዜ ‘’ኢህአዴግ እስካሁን ላጠፋችው ልጅነት ይዟት ነው ብለን እንምራታለን ከንግዲህ ግን አስራ ስምንት አመት ሞልቷታል እና ሃላፊነቱን ትወስዳለች’’ ብለን ከጓደኞቻችን ጋር ስናወራ ነበር… ይሄው ዛሬ ይሄንን ደብዳቤ ስጽፍልሽ ሩብ ምዕተ አመት ሆኖሻል… ይሄ እድሜ ታድያ ምራቅ ዋጥ የምታደርጊበት ብቻ ሳይሆን ያጠፋሽው የበደልሽውንም ተናዘሽ ሂስሽን ዋጥ የምታደርጊበት እድሜ ይመስለኛል!
እውነቴን ነው የምለሽ ኢህአዴግዬ እየመሸብሽ ነው… እንደው ዝም ብሎ ደመና ነው ብለሽ እንዳትታለዪ… ደምመና ሆኖ አይቀርም… (ብዬ ልቀኝብሽ እንዴ….) የምሬን ነው እየመሸ ነው… ልብ ብለሽ ብትመለከቺ ሰማዩ ጠቁሯል። ግዜው እየመሸብሽ ነው…
እና ምን ይጠበስ….? ያልሽኝ እነደሆነ ግን እንደሚከተለው እነግርሻለሁ…
እኔ እንደሌላው መሽቶብሻል እና ወደምትሄጂበት ሂጂ አልልሽም። እኔ እንደማምነው አንቺም ሌላ ሃገር፣ ሌላ ቤት የለሽም። የትም የምትሄጂበት አይኖርሽም… እና ዝም ብለሽ እረፍት አድርጊ…. ጋደም በዬ ኢህአዴግዬ! አረፍ በይ…! ቆመሽ አታቁሚን… ጋደም በይ እና አረፈሽ አሳርፊን እንጂ!
ዘንድሮ ምን ልብ አለኝ እንዳትይኝ እንጂ ልብ ብለሽ እንደሆነ፤ ቀድሞ ሰላማዊ ታጋይ የነበሩ ሁሉ በሰላማዊ ትግሉ ተስፋ ቆርጠው የትጥቅ ትግል አማራጭን መጠቀማቸው የመምሸቱ ምልክት ነው… በየቦታው የህዝቡ ሆድ ብሶት አደባባይ መውጣቱ በኦሮሚያ እና በጎንደር እንደሚታየው የሚሆነው ሁሉ የመምሸቱ ምልክት ነው…. አንቺም ብትሆኚ ለየጥያቄዎቹ ሁሉ ደምሽ ቱግ ቱግ እያለ ተኩሽ ተኩሽ የሚያሰኝሽ የመምሸቱ ምልክት ነው… እና ግዴየለሽም መሽቶ ሳይመሽ በፊት አረፍ በይ!
ታድያ እንዲያም ስልሽ እንደ ንጉስ ሚካኤል ስዑል ተኝተሽ ምሪን አይደለም። ‘’መሪውን ተረከቡኝ ልተኛበት… ልረፍበት’’ ብለሽ ጥሪ አድርጊ! አንቺስ ብትሆኝ ምን በወጣሽ ሃያ አምስት አመት ሙሉ ስትመሪ እና ስታማርሪ ትኖሪያለሽ! አለበለዛ ምሽቱ እየገፋ አንቺም እርጅናው እየተጫጫነሽ መጥቶ በድቅድቁ ጨለማ የወደቅሽ እንደሆነ ለመጠገን ከባድ ነው…. እና መሽቶ ሳይመሽ ጨለማው ሳይበረታ አረፍ በይ ኢህአዴግዬ!

አሳቢሽ
ከሰላምታ ጋር!

The post ይድረስ ለ ኢህአዴግዬ! ጉዳዩ፤ እየመሸ መሆኑን ስለማሳወቅ! – አቤ ቶኪቻው appeared first on Zehabesha Amharic.

እውን ኢትዮጵያ የአሜሪካ ገዳይ አውሮፕላኖችን ከግዛቷ ተጠራርገው እንዲወጡ አደረገች? –ታምሩ ገዳ

$
0
0

አሜሪካ ገዳይ ጥያራዎቿን ሰብሰባ ወጣች ፣ቱርክ ወታደራዊ ጓዟን ጠቅልላ ከጎረቤታችን ገባች
Tamiru-Geda-article-Satenawበ ወቅቱ የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት ኢሕ አዲግ አና በ አሜሪካ መንግስት መካከል ያለው ስትራቴጂካዊ ቁርኝት የጠበቀ እንደሆነ በሚነገረበት በአሁኑ ወቅት አሜሪካ እስከ ዛሬ ድረስ ይፋ ያላደረገችው ፣ነገር ግን በበርካት የስለላ እና የመገናኛ ተቋማት ዘንድ ከ አ/አ 450 ኬ ሜ ርቀት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ አርባ ምንጭ ውስጥ ከዛሬ አምስት አመት በፊት (2011) እንደቆረቆረችው የሚነገረው የ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ማእከሏን(ቢዝ) መዘጋቷን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ይፋ አደርጋለች።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ለዜና ሰዎች ባቀበለው መልእክቱ” በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መንግስታት መካከል በተደረሰው የጋራ ሰምምንት በአርባ ምንጭ የሚገኘው የሰው አልባ አውሮፕላኖች(ድሮንስ) ማእከል ከዚህ በሁዋላ ስራውን አቁሟል” ይላል የመግለጫው መንፈስ። ታዲይ ይህ ባለፈው ሳምንት ለዜና ሰዎች ግባት የተገለጸው ነገር ግን እንደ ብዙዎች እምነት ካለፈው መሰከረም ወር ጀምሮ ሰራው አንደተቋረጠ የሚታመነው የአርባ ምንጩ የ አሜሪካኖቹ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጦር ካምፕ ጉዳይን እና መግለጫውን ተከተለው የሚወጡ ዘገባዎች የተለያዩ እንደምታዎችን እና ጥርጣሪዎችን ይዘው ብቅ እያሉ ናቸው።
አንደ ዜና ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የአርባ ምንጩ የሰው አልባ አውሮፕላኖች (ጥያራዎች) እንዲዘጉ “ከ ኢትዮጵያ መንግስት በኩል በቅድሚያ ጥያቄ በመቅረቡ ነው” ሲሉ የአገዛዙ አፈቀላጤ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል ብሏል። በአቶ ጌታቸው አምነት የአርባ ምንጩ የአሜሪካኖች የሰው አልባ አውሮፕላኖች ካምፕ ለናሙና የተቆረቆረ እንጂ ለ ዘለቄታ ተብሎ አይደለም የሚል አንድምታ አለው። አቶ ጌታቸው ሆኑ የአሜሪካ ባለ ስልጣናት ሰለ ጦር ካምፑ መዘጋት ይናገሩ አንጂ እንደ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ዘገባ ከወራት በፊት የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የመከላከያ ባለሰልጣናት 6.7 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያለው ፣ ለ 130 ጥያራ አበራሪዎች የ ሶስት አመት አዲስ የማሻሻያ ኮንትራት ተፈራርመውበት የነበረው እና የሰምመነቱ ቀለም ሳይደርቅ ባለተጠበቀ ሁኔታ እና በፍጥነት ሰለ ተቋረጠው ሰለፕሮጀክቱ አውንታዊ ይሁን አሉታዊ ውጤት ለጊዜው የገለጹት ነገር የለም። ይሁን እና ፒተር ፓሃም የተባሉ በአትላንቲክ ጉባኤ የአፍሪካ ጉዳይ ተመራማሪ “የአሜሪካ ሰው አልባዎቹ አውሮፕላኖቹ አልሽባብ ግስጋሴን በመግታት እና ቀንደኛ የተባሉ የቡድኑ መሪዋቹን በ መግደል በኩል ውጤታማ ነበሩ “ሲሉ ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ተናግረዋል።ከኢትዮጵያ ምድር እየተነሱ በሶማሊያ የአየር ግዛት ላይ የሚሳይል እና የቦምብ ናዳዏችን ሲያዘንቡ የቆዩት የአሜሪካ ድሮኖች ከዚህ ቀደም ስራውን ወደ አቁረጠው እና እድሳት ወደ ተደረገለት በጎረቤት ጅቡቲ ወደ ሚገኘው የአሜሪካ የጦር ካምፕ ይዛወራሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን ለሎች ምንጮች በበኩላቸው ሰው አልባዎቹ ጥያራዎች ወደ መካከለኛው ምስራቆቹ ሶሪያ እና ኢራቅ እና ወደ ማሊ እና ሊቢያ (እስላማዊ መንግስት ነኝ ባዩን ለመዋጋት) ፣ወደ ምእራብ አፍሪካ ዎቹ ናይጄሪያ እና ካሜሮን (ቦኮ ሃራምን ለመፋለም) ሳይዛወሩ አየቀርም የሚል ጭምጭምታም አልጠፋም።

በጆርጅ ማሶን ዩኒቨርስቲ ተባባሪ ፕሮፊሰር የሆኑት ተመራማሪው ትሪያንስ ለዮንስ የወጪ ፖሊሲ (ፎርያን ፖሊሲ) ለተባለው መጽሄት ሰሞኑን በሰጡት አስተያየት “የዋሽንግተን ባለሰልጣናት ከ አ/አ ገዢዎች ጋር የማይግባቡባቸው ጉዳዮች አሉ። ኢትዮጵያ ከመሬቷ እየተነሱ በጎረቤቶቿ በሚገኙ በሙስሊም ወገኖች ላይ የግድያ እርምጃ የሚወሰዱት ሰው አልባ አውሮፕላኖቹ ጉዳይ ጠጠር ያለ ችግር ሳይፈጥርባት አልቀረም።”ሲ ሉ ጥርጣሪያቸውን ሰንዝረዋል። በሌላ ጎኑ አሜሪካ ለ ሰው አልባዎቹ አውሮፕላኖቹ አብራሪዎች(ባለሙያዎች) የምተከፍለው ከፈተኛ የሆነው ውሎ አበል እና ጉርሻ(ቦነስ) ወገቧን እያጎበጠው በመሆኑ ፒንታጎን ኢትዮጵያ ውስጥ የነበራት ጓዟን ጠቅልላ ፣ወጪዎቿንም ሰብሰብ አድርጋ የአክራሪዎች ጥቃቶች ወደ በረቱባቸው ወደ መካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ለማዛወር ተገዳለች የሚሉ ዘገባዎች ተደምጠዋል።
ሰው አልባዎቹ አውሮፕላኖች በሚሰማሩባቸው ምርጥ ኢላማዎች እና አካባቢዎች ተፈላጊ እና ቁልፍ የሆኑ አሸባሪዎችን እያነፈነፉ የመግደላቸውን ያህል ፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ከሸብር ተግባራት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት በሌላቸው ንጹሃን እና ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚያደርሷቸው ተደጋጋሚ ግድያዎች በሰበዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰተናገዱ አልቀረም።”ወደ ግጭቶች አካባቢ ወታድሮቼን በጭራሽ አልክም” የምትለው አሜሪካ ግን ምንም ይባል ምን፣ ምንም ይሁን ምን ከ ሰው አልባዎቹ አውሮፕላኖችን ከመጠቀም ውጪ ሌላ ጊዜያዊ አማራጭ የለኝም ያለች ትመሰላለች።

በሌላ ወታደራዊ እና አካባቢያዊ ነክ ዜና አሜሪካ በኢትዮጵያ የነበራት የሰው አልባ አውሮፕላኖቿ ካምፕ መዝጋቷን ሰትገልጽ ሌላኛዋ የ ሰሜን አትላንቲክ የቃል ኪዳን (ኔቶ )አባል አገር የሆነችው ቱርክ በጎረቤታቸን ሶማሊያ ውስጥ “ከሶማሊያ አልፎ ለአጠቃላዩ የአፍሪካ አገራት ጥቅም የሚሰጥ” ዘመናዊ የጦር ሃይል ት/ቤት እና ማሰልጠኛ ማእከል ለመቆርቆር በሂደት ላይ መሆኗን አስታውቃለች ።ካለፈው 2010 አኤአ ጀምሮ ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ግንኑነቷን ያጠናቀረችው አንካራ(ቱርክ) ከተለያዩ ወዳጅ እና ለጋሽ አገራት በተዋጣ የወታደራዊ የደንብ ልብሶች እና ጫማዎች የሚነቀሳቀስው የሶማሊያ የ መከላከያ ጦርን አንድ ወጥ በሆነ የደንብ ልብስ ለመተካት ማቀዷን በሶማሊያ ጉዳይ በቱርክ የወጪ ጉዳይ ሚንስተር ከፍተኛ ሃላፊ የሆኑት ኢሚል ቲኪን ሰሞኑን ለዜና ሰዎች ገልጸዋል። ቱርክ በቅርቡ ግምቱ ከ 400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወታደራዊ እርዳታ ለሶማሊያ መንግስት መርዳቷ ታውቋል ።

The post እውን ኢትዮጵያ የአሜሪካ ገዳይ አውሮፕላኖችን ከግዛቷ ተጠራርገው እንዲወጡ አደረገች? – ታምሩ ገዳ appeared first on Zehabesha Amharic.

ክፉ ቀን ይምጣ ቶሎ ይመልስ፣  ያስተዛዝባል እስካዛው ድረስ  –ይገረም አለሙ

$
0
0

ይህ በርእስነት የተጠቀምኩበት የአበው አባባል መልእክቱ ግልጽ ይመስለኛል፡፡የሰው ልጅ የተደበቀ ማንነት የሚጋለጠው፣ ቃልና ተግባሩ ሀራምባን ቆቦ መሆኑ የሚረጋገጠው፣ ወዳጅነቱ የአፍ ይሁን የልብ የሚለየው፣ ሀገርና ህዝብ አፍቃሪነቱ የሚታወቀው፣ ወዘተ ከተለመደው ለየት ያለ ነገር ሲያጋጥም መሆኑን ነው የሚያሳየው፡፡

ገና ከጅምሩ ታላላቅ ሰዎችን የነጠቀን 2008 ሩብ እድሜ ሳያስቆጥር ብዙ ሀገራዊ ጉዳዮችን አሳይቶናል እያሳየንም ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የርሀብ አደጋ፣ የወልቃይት አካባቢ ነዋሪዎች በግድ ትግሬ ሁኑ ተብለናል የሚለው ተቃውሞ፤ ቅማንትና አማራ በሚል የተፈጠረው ክፍፍል፤ የጎንደር እስር ቤት መቃጠልና የዜጎች ዕልቂት፤ በኦሮምያ አካባቢ  የተቀሰቀሰውና እስካሁን ያልቆመው ተቃውሞ፤ በድንበር ማካለል ስም ለሱዳን ለም መሬት ለመስጠት እየተካሄደ ያለው የድብብቆሽ ጨዋታ ዋናዎቹ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉም በየራሳቸው  ጥሩም መጥፎም ነገር እንድንታዘብ አድርገውናል፡፡ እያደረጉንም ነው፡፡  እስቲ የሁለቱን ትዝብት እንቃኝ፡፡

welkayet - satenaw

1-ከቀን ወደ ቀን እየከፋ ያለው ረሀብ፤ ይህ ረሀብ ወያኔ ተከታታይና ፈጣን  ባለ ሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገብኩ ነው እያለ በሚፎክርበት ወቅት የተከሰተ በመሆኑ አለም የወያኔን ዋሾነት እንዲታዘብ  ያደረገ ነው፡፡ በአንጻሩም የሚባለው እድገት የፈጠራ ቁጥር አንጂ በተጨባጭ መሬት ላይ ያለ አይደለም ሲሉ የነበሩ ወገኖች ተአማኒነት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ስለሚናገሩት ነገር ቅንጣት የማወቅ ሙከራ ሳያደርጉ በሉ የተባሉትን እንደወረደ እየተናገሩ ርሳቸው ባያፍሩም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ማፈሪያ እየሆኑ ያሉት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በምግብ እህል ራሳችንን ችለናል ብለው በአደባባይ ተናግረወው ሶስት ወር ባለሞላ ግዜ ይፋ የሆነ ረሀብ በመሆኑ ወትሮም ባለሥልጣኖቹ በሚናገሩት ነገር ላይ እምነት የሌለው ህዝብ ይበልጥ አንዲታዘባቸው ይበልጥ እንዲንቃቸው አድርጓል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሊደበቅ የማይችልን ረሀብ ለመደበቅ ያሳዩት መቀለማመድ፣ በራሳችን እንቋቋመዋለን ባሉ ማግስት ርዳታ ሲለምኑ መሰማት የአንዱ ባለሥልጣን ንግግር ከአንዱ አለመግጠም ወዘተ የመንግስት ባለሥልጣንነታቸውን አይደለም ሰው መሆናቸውን እንድንታዘብ አድርጎናል፡፡

በጥቅሉ የተከሰተው ረሀብ  በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት እስካልተቻለ ድረስ ከረሀብ ተጠቂነት መላቃቅ አይቻለም የሚለውን አስተሳሰብ ትክክለኛት ያረጋገጠና በወያኔ አገዛዝ ስር ሆኖ ህዝብን እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ ሀገራዊ እድገት ማምጣት አይደለም  ከረሀብ መላቀቅ የማይቻል መሆኑን ያሳየ  ነው፡፡ በመሆኑም ለለዴሞክራሲ የሚደረገውን ትግል አስተባብሮና አጠናክሮ ከመቀጠል ውጪ አማራጭ አንደሌለ የሚያስተምር ነው፡፡

2–በኦሮምያ አካባቢ የተከሰተውና እስካሁን ያልበረደው ተቃውሞ ፤  ጊንጪ አካባቢ በሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቀስቅሶ መላ ኦሮምያን ያደረሰው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ብዙ ነገር እንድንታዘብ አስችሎናል፡፡ ከትዝብት አልፎም የሚማር ካለ ትልቅ ትምህርት የሚገኝበት ነው፡፡

  • የህዝቡ ብሶትና የለውጥ ፍላጎት በሀይል ታፍኖ የተዳፈነ እንጂ ጨርሶ ያልጠፋ መሆኑን ያሳየው ይህ እንቅስቃሴ የህዝብ ብሶት የመዳፈኑ መጠኑ ከቦታ ቦታ የሚለያይና ለመቀጣጠልም የሚጠይቀው ሙቀት ከአካባቢ አካባቢ የሚለያይ መሆኑን ያሳየነ ነው፡፡ይህም የአካባቢ ሁኔታዎችን ማጥናት የህዝቡን ሥነ -ልቦና መረዳትና ተስማማሚ የትግል ስልት መንደፍ አስፈላጊ መሆኑን ያመለክታል፡፡
  • ወያኔ ዓላማውን ከዳር ለማድረስና ፍላጎቱን ለማሳካት ማናቸውንም ርምጃ ከመውሰድ ወደ ኋላ የማይል የሰው ህይወትና የሀገር ሀብት ደንታ የማይሰጠው መሆኑን ቀደም ብሎም የምናውቅ ቢሆንም የሰሞኑ አረመኔያዊ ድርጊቱ በሂደት ያልተማረና ፈጽሞ የማይለወጥ መሆኑን አረጋግጦልናል፡፡ይህም አንድም ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ከማውረድ ውጪ ሌካ አማራጭ የሌለ መሆኑንና የሚካሄደው ትግል ከድሉ መስዋእትነቱ እንዳይከብድ የሚያስችል የትግል ስትራቴጂ መቀየስን አስፈላጊነት የሳያል፡፡
  • የኦህዴዶች የወያኔ ገባርነት እስከምን ድረስ እንደሆነም ለመታዘብ አስችሎናል፡፡ በኦሮምያ የህውኃት ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር እወክለዋለሁ የሚሉትን የኦሮሞ ወጣት የገደሉ የወያኔ ነፍሰ ገዳዮችን  ሲያመሰግኑ የተመለከትነው የሰው ልጅ ህሊናውን ሸጦ አካሉን ለሎሌነት ሲያስገዛ ሊሆን የሚችለውን የመጨረሻ ደረሻ ያሳየ ነው፡፡ በጥቅሉ ወያኔዎች በኦህዴዶች ላይ ያላቸው የበላይነት ከጌታና ሎሌም ግንኙነት የላቀ መሆኑን ከሰሞኑ ድርጊት ታዝበናል፡፡ ሎሌ ነገር ሲበዛበት ጭቆናው ሲብስበት ሌላ ማድረግ ባይችል ይኮበልላል ከጌታም ጌታ አማርጦ የተሻለ ወደ መሰለው ጌታ ይጠጋል፡፡ ኦህዴዶች ግን….. ይህ ደግሞ ለወያኔ የደሩትን ሰዎች ለወያኔ ከማደራቸው በፊት ሰው መሆናቸውን እንዲያስቡና ወደ ሰውነት እንዲመለሱ የማድረግ፣ከውስጣቸው ስንዴና እንክርዳዱን የመለየት፣ ወዘተ ስራ እንደሚያፈልግ ይናገራል፡፡

AbyssiniaPeople

  • የተቀዋሚነትን ስም ይዘው ነገር አለሙን ረስተው የተኙ ፖለቲከኞችን ይህ የህዝብ እንቅስቃሴ ከእንቅልፋቸው ቀስቅሶአቸው ኢሰብአዊውን ድርጊት በማውገዝና  የተባብሮ መስራትን አስፈላጊነትና ወቅታዊነት በመግለጽ መግለጫ ሲያወጡም ታዝበናል፡፡  ያለፈው አስቆጭቶአቸው በወያኔ መበለጣቸው አስቆጥቶአቸው በዚሁ በተናቃቃ መንፈስ ይቀጥላሉ ብለን ተስፋ አድርገንም ነበር፡፡ ነገር ግን ዜጎች በእየለቱ እየሞቱ ባሉበት በዚህ ወቅት ከእንቅልፋቸው መንቃታቸውን  በመግለጫቸው ያሳዩን ፖለቲከኞች ከመግለጫ አልፈው  ቢያንስ በመግለጫቸው ያነሱዋቸውን ጉዳዮች ተግባራዊ ለማድረግ  የሚያስችል ጅምር ርምጃ አላማሳያታቸው  መቼም የማይማሩ ከሥልጣን በላይ አሸጋግረው ማየት የማይችሉ ቃልና ተግባራቸው የማይዛመድ ወዘተ ለሚል ትዝብት የሚዳርጋቸው ሆኗል፡፡ ይህም ዋናው ነገር ቁጥር ሳይሆን ተግባር፣ ስም ሳይሆን ሆኖ መገኘት መሆኑን በማጤን ፓርቲዎችንም ሆነ መሪዎቻቸውን በዚሁ እየፈተኑ ድጋፍ መስጠትም ሆነ መንሳት እንደሚገባ የሚጠቁም ነው፡፡
  • የፖለቲካ ፓርቲ ስም ይዘው ሌላው ቢቀር ግድያውን ለማውገዝ ፈቀደኝነቱም ሆነ ድፍረቱ ያልታየባቸው ፓርቲዎችንም ታዝበናል፡፡ በርግጥ እነዚህን ስመ ፓርቲዎች ማንነትና ምንነት ህዝቡ አሰቀድሞ አውቆ አንቅሮ የተፋቸው ቢሆንም ተቃውሞአቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ በተነሳሱ ወጣቶች ለይ የተፈጸመውን ግድያ ማውገዝ አለመቻላቸው እንደ ፖለቲከኛ ብቻ ሳይሆን እንደ ዜጋ በህብረተሰቡ ውስጥ ምንም ቦታ ሊያገኙ አንደማይገባ የሚጠቁም ነው፡፡
  • በኦሮምያ የታየው የህዝብ የተቃውሞ እንቅስቃሴና ተቃውሞውን ለመጨፍለቅ ወያኔ የወሰደው አረመኔያዊ ተግባር መልካም ነገር እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑንም ታዝበናል፡፡ ሁሉንም በእኩል እየበደለ ያለውን የዛሬውን አገዛዝ በጋራ ትግል አስወግዶ  የነገውን መልካም መንገድ ከማሳመር በትናንት ታሪክ መወነጃጀልና መካሰስን ምርጫቸው አድርገው ለሚቃወሙት ወያኔ እድሜ መርዘም አስተዋጽኦ ሲያደርጉ የነበሩ ወገኖች ቆም ብለው ፈጥነው እንዲያስቡ አብቅቶአቸዋል፡፡ በዚህም  ከመጡበት መንገድ ወጥተው ከያዙት አላስፈላጊ አስተሳሰብ ተላቀው በኢትዮጵያዊነት ተባብረን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረትን ግባችን አድርገን በአንድነት እንታገል ወደሚል ተገቢና ቅዱስ አስተሳሰብ መምጣቸውን በአድናቆት ታዝበናል፡፡ በጋራ መጮህ መቻላቸውንና እጅ ለእጅ ተያይዘው ሰልፍ መውጣታቸውንም አይተንና ሰምተንም እሰየው ብለናል፤ከእንግዲህ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ እንዳትሉ በማለትም አደራ ብለናል፡፡

ይህም በቁጥር በዝተው በተግባር የሌሉት፣በስም ተለያይተው እዛና እዚህ የቆሙት የበዛወውን ቁጥር ይቀንሱት የሰፋውንም ልዩነት ያጠቡት ዘንድ የየድርጅቶቹ አባላትም ደጋፊም ፣ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ናፋቂም ግፊት ማድረግ ተጽእኖ መፍጠር እንደሚገባው  ያሳየ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ወያኔን ለማውገዝ በአንድነት ሰልፍ በሚወጡበትም ሆነ ጩኸት በሚያሰሙበት ወቅት ተቃዋሚዎችም መተባበርን ከቃል ወደ ተግባር እንዲቀይሩት ሊጠይቁ ሊወተውቱ እንደሚገባ ያመላከተ ይመስለኛል፤

  • ይሄ መስዋዕትነት እየተከፈለበት ያለው የህዝብ እንቅስቃሴ የሀይማኖት አባቶችንም እንድንታዘብ አብቅቶናል፡፡ በሁሉም እምነት አምላክ በአምሳሉ የፈጠረውን ክቡር የሰው ልጅ መግደል ወጉዝ እንደመሆኑ በየእምነቱ መሪነት ቦታ ላይ የተቀመጡ የሀይማኖት አባቶች ገዳዮችን ሊያወግዙ ግድያውን ሊኮንኑና ግድያ ይቁም ብለው ጥሪ ሊያስተላልፉ የተቀመጡበት ቦታና እንፈጽመዋለን የሚሉት የፈጣሪ ትዕዛዝ  ግድ ይላቸው ነበር፡፡ ግን ከአንዳቸውም ይህን ለመስማት አልቻልንም፡፡( ይህ ትዝብት ከሀገር ውጪ የሚገኙ የሀይማኖት አባቶችን አይመለከትም)

ደፈር ብለው ተቃውሞ ለማሰማት ወደ እምነቱ መሪነት ቦታ የመጡበት ሁኔታ የማይፈቅድላቸው ከሆነ (ማለትም ለቦታው የበቁት በፖለቲከኞቹ ምርጫና ይሁንታ ከሆነ) ወይንም ከፈጣሪያቸው ይልቅ ጠመንጃ አንጋቾችን የሚፈሩና ከነፍሳቸው ይልቅ ለስጋቸው የሚሳሱ ከሆነ ደግሞ መንግስት ከሚሰጠው መግለጫ ጋር ራሳቸውን አመሳስለው ከህዝቡ ግልጽ ጥያቄ ጀርባ ስውር አላማቸውን ለማሳካት የተንሳቀሱ ኃይሎች በፈጠሩት ሁከት ምክንያት ለሞቱ ንጹሀን ዜጎች እናዝናለን ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይማር ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን አንዲሰጥ እንጸልያለን ማለት እንደምን ገደዳቸው፡፡ የሚጠበቅባቸውን ማድረግ ካቃታቸው  ዜጎች በግፍና በገፍ ተገድለው ዝም ከማለት ከበጣም መጥፎ መጥፎውን መምረጥ ብለው ሁለተኛውን መፈጸም ይችሉ ነበር፡፡ ግና አንዱንም አላደረጉትምና ታዘብናቸው፡፡ ታዲያ ለፈጣሪ ትዕዛዛት ሳይሆን ለጠመንጃ የሚያጎበድዱና ክቡር በሆነው የሰው ልጅ ላይ የሚፈጸም ኢሰብአዊ ግድያ ስሜት የማይሰጣቸው የሀይማኖት መሪዎችን እንዴት አድርገን በአባትነት መቀበል ይቻለናል፡፡

ይህም ለሀይማኖት ነጻነት መረጋገጥ የወያኔን መወገድ ግድ የሚል መሆኑን ያሳየ በተናጠል ስለ ሀይማኖት ነጻነት የሚታገሉ ወገኖች የትግላቸውን ደረጃ ከፍ አድርገው አላማቸውንም ለዴሞክራሲ ወደሚል ቀይረው ለነጻነት እንዲታገሉ ያመላከተ ይመስለኛል፡፡

 

በአጠቃላይ የሰሞኑ ክስተት ካሳየን ትዝብት ፖለቲከኞቹ ትምህርት በመውሰድ ከእንግዲህ በወያኔ መበለጥ በነገሮች ክስተትም መቀደም የለም ብለው ደጋመው በአንደበታቸው የሚናገሩትንና ሰሞኑንም አጠንክረው የጮሁበትን መተባበር በተግባር ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በአንጻሩም ትግሉን በእምነትና በቁርጠኝነት ከምር የያዙትና አስመሳዮቹ፣ አላጋጮችንና ነጋዴዎቹ ይለዩ፡፡

ለተቃውሞ ሰለፍ በአንድነት ለመውጣት ፈቃደኝነታችውን የሳዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እንኳን በጣም ብዙ ናቸውና  በስምም በፕሮግራምም በአደረጃጀትም ተመሳሳይነት ያላችው በፍጥነት ለውይይት ተቀመጠው  መቀራረብ አይደለም ውህደት በመፍጠር አንድ ይሁኑ፤ ከዛም  በዚህ መልኩ ቁጥሩ ከተቀነሰ በኋላ ሌላ ዙር ውይይት ሌላ ዙር መቀራረብ ይፈጠርና መሰረታዊ የሆነ የጎላ የኣላ ልዩነት የሌላቸው ወደ አንድ እንዲመጡ ይደረግ፤ ቀጥሎም ሁሉም በሚግባቡበት ተግባብተው በማይግባቡበት ላለመግባባት ተግባብተው  በኢትዮጵያዊነት መንፈስ  ለዴሞክራሲያዊ ስርአት እውን መሆን  በጋራና በትብብር ለመታገል የሚያስችላችውን የጋራ አጀንዳ ያዘጋጁ ግባቸውን  በግልጽ ያስቀምጡ ወደ ግባችው የሚያድርሳቸው መንገድ ላይም ይስማሙ ከወያኔ በኋላ እውን ሆና ሊያዩት በሚመኙዋት ኢትዮጵያ እንዴትነት ላይም መግባባት ይፍጠሩ ከዛ በቆራጥነት  በተቀናጀ  ትግል ጉዞ  ወደ ድል፡፡

ስራው ብዙ፣ ሀላፊነቱ ከባድ ጊዜው እየመሸ ህዝብ እየቀደመ ነው፡፡ ብዙ አመታት አለአግባብ ባክነዋልና እንኳን ተዘናግቶ ሮጦና ሀያ አራት ሰአት ተሰርቶም የሚካካስ አይደለም፡፡ ስለሆነም የህዝብ እልቂት ይቁም የወያኔ አገዛዝ ያብቃ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት እውን ይሁን የምንለው በስሜት ሳይሆን በእምነት ከሆነ ይህ ወቅት የመጨረሻው መጀመሪያ መሆንአለበት፡፡ ግዜ የለም፡፡

The post ክፉ ቀን ይምጣ ቶሎ ይመልስ፣  ያስተዛዝባል እስካዛው ድረስ  – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

ወገንን የማዳን ጥሪ በአትላንታ

ኃይለማርያም ልጃቸውን ከመዳራቸው አንድ ቀን አስቀድሞ ሙሽራው በፌደራል ፖሊስ ጥይት ተደብድቧል

$
0
0

ታሪክ ራሱን ሲደግም! የሌላውን ሰው ልጅ ደስታ አበላሽቶ በራስ ልጅ ሰርግ መደሰት…!

 ከብስራት ወልደሚካኤል

በምርጫ 1997 ዓ.ም. ወቅት የኢህአዴግን መሸነፍ ተከትሎ ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ በሰጡት ቀጥተኛ ትዕዛዝ በአዲስ አበባ የ14 ዓመት ዕድሜ የነበራቸው ሴትና ወንድን በመንገድ ላይ እያሉ ገደሏቸው፡፡ በዛው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ሰኔ 1997 ዓ.ም. መጨረሻ ህፃናት ያስገደሉት አቶ መለስ፤ ልጃቸው ሰመሃል መለስ የ2ኛ ደረጃ ትምህርቷን በማጠናቀቋ በሸራተን አዲስ የእንኳን ደስ ያለሽ የእራት ግብዣ አድርገው ተደሰቱ፡፡ ከነበረው ተቃውሞ ጋ ምንም ንኪኪም ሆነ ግንኙነት ያልነበራቸው ሌሎችኢትዮጵያውያን ህፃናትን በአደባባይ አስገድለው የራሳቸውን ልጅ እንኳን ደስ ያለሽ ብለው ከተዝናኑ ባለፈው ሰኔ 10 ዓመታት አለፈው፡፡

mushiraw

ዛሬ ደግሞ ተረኛው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንት ወዲያ አርብ በኢሉባቦር መቱ ሌላ አሳዛኝና የማይረሳ ታሪክ ሰሩ፡፡ ይኸውም በመቱ ወረዳ መምህር ፍፁም አባተ መኮንን በነጋታው ትናንት ቅዳሜ ታህሣሥ 30 ቀን 2008ዓ.ም. ከፍቅረኛው ፍሬህይወት በለጠ ጋ የጋብቻ ስነስርዓታቸውን ለመፈፀም ወዳጅ ዘመድ ጠርተው በዋዜማው እንደ ሀገርኛው ባህል ቤተሰብና ጓደኛ ስራ ጨርሰው በቤታቸው እየተዝናኑና እየጨፈሩ ሳለ፤ ፌደራል ፖሊስ በር በርግዶ በመግባት ፊትለፊት የተገኘውን ጫጉላ/ሙሽራ መምህር ፍፁምን በጥይት ደበደቡት፡፡ 

በወቅቱ ከሙሽራው በተጨማሪ ሌሎችም የተጎዱ እንዳሉ ተሰምቷል፡፡ ሙሽራው በዕለተ ሰርጉ በነ ኃይለማርያም ደሳለኝ ትዕዛዝ ንፁሃን ዜጎችን ለመግደል በታዘዙ የህወሓት ወታደሮች ክፉኛ በጥይት ተመቶ ሆስፒታል እያሳለፈ ይገኛል፡፡ የወዳጅ ዘመድና የአካባው ማኀበረሰብ የሰር ደስታም ወደ ሀዘን ተቀይሮ የተሰናዳው የሰር ዝግጅት ሁሉ አብሮ ከንቱ እንዲሆን ተፈርዶበታል፡፡

ዛሬ እሁድ ጥር 1 ቀን 2008 ዓ.ም. አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የመምህር ፍፁም አባተን እና የወ/ት ፍሬህይወት በለጠን ሰርግና ህይወት አበላሽተው ልጃቸው በሞቀ ሰርግና ምላሽ በቤተመንግስት ድረዋል፡፡ መምህር ፍፁም እንዳቅሙ በቤቱና ባካባቢው ሰርጉን እንዳያሳልፍ የፈረዱበት አቶ ኃይለማርያምና ግብርአበሮቻቸው የመጀመሪያ ልጃቸውን ዶ/ር ሶስና ኃይለማርያምና የልጃቸውን እጮኛ አቶ አቤል አየለን በሞቀ ሰርግ በቤተ መንግሥት ተምነሽንሸዋል፡፡ ይሄ ነው የታሪክ ድግግሞሹ! በሰው ልጅ ስቃይ የራስ ደስታን ማጣጣም፡፡

haile1

እዚህ ላይ የልጃውን ማግባትና ሰርግ መሰረግ ላይ ተቃውሞ ባይኖረኝም፣ የሰውን ልጅ ህይወት፣ ሰርግና ደስታ አበላሽቶ ልጁን በመዳር መደሰት ምን ዓይነት አዕምሮ ያለው ወላጅ አስተሳሰብ ይሆን? እንደው ለነገሩ ለንፅፅር የወረዳ ዘንድ ሙሽራውን ጠቀስኩ እንጂ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሰላማዊ ተቃውሞ እያካሄዱ የነበሩ ከ7 ዓመት ህፃን እስከ 78 ዓመት አዛውንት፣ ከ7 ወር ነፍሰ ጡር አዛውንት እናትን ከነልጅ፣ ከመምህር እስከ ገበሬ፣ እንዲሁም የ4 ልጆች እናት ሱቅ ዕቃ ልትገዛ ስትሄድ በጥይት መንገድ ላይ የገደሏትን ጨምሮ ከ140 በላይ ሰላማዊ ዜጎችን ህይወት በግፍ ቀጥፎ ለራስ ልጅ ሰርግ ሽር ጉድ ብሎ ድሮ መደሰት ምን ዓይነት ስብዕና እና ሞራል ኖሮ ይሆን?
ይብላኝ ለልጆቻቸውና ለቤተሰቦቻቸው፡፡ ነገ እነሱስ ምን ይደርስባቸው እንደሆን ማን ያውቃል?

ብቻ፤ መልካሙን ያምጣልን እንጂ…

The post ኃይለማርያም ልጃቸውን ከመዳራቸው አንድ ቀን አስቀድሞ ሙሽራው በፌደራል ፖሊስ ጥይት ተደብድቧል appeared first on Zehabesha Amharic.

ፌደራል ፖሊስ በባሌ ሮቤ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በጥይት ቆላ |የሞቱ ተማሪዎች አሉ እየተባለ ነው

$
0
0

medwelabu

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት ማምሻውን በባሌ ሮቤ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የፌደራል ፖሊስ ሰላማዊ ተማሪዎች ላይ ጥይት ሲያዘንብ ማምሸቱ ተሰማ:: ከ100 በላይ ተማሪዎች ታፍነው መወሰዳቸውንም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቆመ::

በሰላማዊ መንገድ ተማሪዎቹ የመብት ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውን ተከትሎ ግቢውን የወረረው ሕወሓት የሚመራው ሰራዊት ወደ ተማሪዎች ላይ የተኮሰ ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቀ በርካታ ተማሪዎች መቁሰላቸው ተሰምቷል:: በፌደራል ፖሊስ ጥይት የተገደሉ ተማሪዎች እንዳሉ መረጃዎች ቢወጡም ዘ-ሐበሻ ለማረጋገጥ ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም::

ያነጋገርናቸው ተማሪዎች እንደገለጹልን ፌደራል ፖሊሶች የሴቶችን መኝታ ክፍሎች በመስበር አስገድዶ መድፈር አድርሰውባቸዋል:: መኝታ ክፍሎችን እየሰበሩ በመግባትም ከ100 በላይ ተማሪዎችን ወስደው ማሰራቸውን እነዚሁ ተማሪዎች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

በባሌ ሮቤ መደውላቡ ዩኒቨርሲቲ ፖሊስ በይት ተማሪዎችን ሲቆላ መብራት አጥፍቶ እንደነበርም እነዚሁ ተማሪዎች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

The post ፌደራል ፖሊስ በባሌ ሮቤ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በጥይት ቆላ | የሞቱ ተማሪዎች አሉ እየተባለ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን ተቃውሞ እና የፌደራል ፖሊስን የጠመንጃ ተኩስ የሚያሰማ ቪዲዮ | Video

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርር ያለ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ አመሹ:: ሕወሓት የሚመራው መንግስት ወታደሮች በጥይት አካባቢውን ሲረብሹ አምሽተው ከ300 በላይ ተማሪዎችን አፍሰው እንደወሰዱ ተሰምቷል:: በጅማ ዩኒቨርሲቲ ማምሻውን የተማሪዎቹን ተቃውሞ እና የፌደራል ፖሊሶችን ተኩስ የሚያሰማውን ቪዲዮ ይመልከቱ::

Zehabesha News

The post ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን ተቃውሞ እና የፌደራል ፖሊስን የጠመንጃ ተኩስ የሚያሰማ ቪዲዮ | Video appeared first on Zehabesha Amharic.

በምዕራብ ሐረርጌ መኢሶ ወረዳ ህፃናት ወታደሮችን ለማባረር ጎማ እያቃጠሉ መሆኑ ተሰማ

$
0
0

meiso
(ዘ-ሐበሻ) የአዲስ አበባን አዲሱን ማስተር ፕላን መነሻ አድርጎ በኦሮሚያ ክልል የተነሳው የሕዝብ ቁጣ እንደአዲስ ከተቀጣጠለ በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች አለመረጋጋቱ እንዳየለ ምንጮች ዘገቡ::

ሕወሓት የሚመራው መንግስት ወታደሮች በየከተማው ትግሉን ያቀጣጠላሉ ብለው ያሰቧቸውን ሰዎች እያሰሩ በሚገኙበት በዚሁ ወቅት በምዕራብ ሀረርጌ ዞን መኢሶ ወረዳ የሕዝቡ ቁጣ እንዳየለ ምንጮች ዘግበዋል:: እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገባ ከሆነ በመኢሶ ወረዳ በርካታ ወጣቶች እና አዛውንቶች በመታሰራቸው የተነሳ ትግሉን እያቀጣጠሉት የሚገኙት ህፃናት ናቸው::

እነዚሁ ህፃናት ወረዳዋን ያጠሩትን ፖሊሶች ከአካባቢው ለማባረር በከተማዋ አውራ ጎዳናዎች ላይ ጎማዎችን ሲያቃጥሉ መዋላቸውን ምንጮች ዘግበዋል:: በመኢሶ ወረዳ ካለማቋረጥ የሕዝብ ቁጣ እየተስተጋባባት ይገኛል::

The post በምዕራብ ሐረርጌ መኢሶ ወረዳ ህፃናት ወታደሮችን ለማባረር ጎማ እያቃጠሉ መሆኑ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

“የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ኢሕአዴግ በጠራው ስብሰባ ቀድመው የተቃወሙት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው”–ኤርሚያስ ለገሰ በኦሮሞ ተማሪዎች ቁጣ ዙሪያ ይናገራል

$
0
0


“የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ኢሕአዴግ በጠራው ስብሰባ ቀድመው የተቃወሙት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው” – ኤርሚያስ ለገሰ በኦሮሞ ተማሪዎች ቁጣ ዙሪያ ይናገራል
Ermiasssss

The post “የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ኢሕአዴግ በጠራው ስብሰባ ቀድመው የተቃወሙት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ናቸው” – ኤርሚያስ ለገሰ በኦሮሞ ተማሪዎች ቁጣ ዙሪያ ይናገራል appeared first on Zehabesha Amharic.

“ኢትዮጵያ የሚለውን ማንንነት እንዲቆም ያደረጉት አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ናቸው።” –ዶ/ር ደረሰ አየናቸው

$
0
0

ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፣ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ዲፓርትመንት መምህርና የድኅረ ምረቃ ዲን፤ ስለ ንጉሥ አምደ ጽዮንና ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ ሥጣንና እልፈት።

“ኢትዮጵያ የሚለውን ማንንነት እንዲቆም ያደረጉት አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ናቸው።” –  ዶ/ር ደረሰ አየናቸው

The post “ኢትዮጵያ የሚለውን ማንንነት እንዲቆም ያደረጉት አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ናቸው።” – ዶ/ር ደረሰ አየናቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

ፋንታሁን ሸዋንቆጨው፣ ጸጋዬ እሸቱ፣ ሃቻሉ ሁንዴሳና ቫሂ ቲልቢያን ስለ ሙዚቃ ሕይወታቸው ይናገራሉ

ሰምሃል መለስ ዜናዊ ትናገራለች ”ሃይለማርያምን ለዚህ ስልጣን ያበቃው ኣባቴ አንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኣይደለም”

$
0
0

ከምኒልክ ሳልሳዊ

ከቅርቤ ቤተሰቤ ኣንዱ ኣሪፍ ባልንጀራዋ ነው፤ሰምሃል መለስ የኣቶ መለስ ዜናዊ ልጅ ናት፥የኣባቷ የመጀመሪያ ለእናቷ ሁለተኛ ልጅ ስትሆን የኣባቷን ሁለመና የጎሳ ፖለቲካ ኣስተምሮቱን ሳይቀር ወርሳለች ፥የኢሕአዴግ ሊቀመንበር የመሆን ሕልም ኣላት። ኣብዛኛውን ጊዜ ኤርትራዊ አንደሆነች ቢሰማትም በኣዲስ ኣበባ መኖሯ ኢትዮጵያዊ የሚል ፓስፖርት እንዲኖራት ኣድርጓታል፥ ስታናግርህ ቅን ልጅ ናት ከእናቷ ደሞ ቅንነቷን የሚበርዝ መርዝ አንደሚሰጣት ሳትደብቅ ትናገራለች።ስክር ስትል መጀመሪያ እናቷን መሳደብ ደስ ይላታል፤ብዙ ከመብላት ይልቅ ብዙ ኣልኮል መጠጣት ይቀናታል፥ለዛም ነው ከምሽት ራስ መሳት አስከ ቀን ድብርት አና ጭንቀት የሚደራረቡባት፥ ፈታ በተን ዘና ካለች ግን አንደቤተሰቦቿ ጨካኝ እና በጥላቻ የተሞላች ሳትሆን ቀና አና ርሁሩህ ነች።ቅንጅት የሚባል ቃል እና ኣበበ ገላውን ስትጠላ የቴዲ ኣፍሮ አና የታማኝ በየነ ምርጥ ኣድናቂ ናት።ከመጋረጃ ጀርባ ኣብራ የምትውላቸው ሰዎች ኣስታውጾ ኣላቸው።
semhal meles

ሰምሃል መለስ ስለ ሃይለማርያም እና ስለ መለስ ፋውንዴሽን የገንዘብ ስጦታ ስትናገር መጀመሪያ ደረጃ ሃይለማርያምን ለዚህ ስልጣን ያበቃው ኣባቴ አንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኣይደለም ስለዚህ ገንዘቡ በስጦታ መሰጠት ያለበት ለፋውንዴሽኑ እንጂ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ኣይደለም።ፋውንዴሽኑ ኣስፈላጊ ሆኖ ከተሰማው በድርቅ ለተጎዳ ወገን ያስተላልፋል።የሃይለማርያም ቤተሰብ የሶስናን ሰርግ ውጪ ግን ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘቡን መስጠቱ ቤተሰቡ ላለበት ማእረግ ያበቃው መለስ ስለሆነ እንደ ውለታ መመለስ እንጂ እንደ ስጦታ ኣይቆጠርም።ማናችንም የማንክደው እውነት ነው። ለሰርግ ውጪ የተባለው ኣንድ ሚሊዮን ከፈረስ በረት ቢሮ ኣውጥቶ ለቤተመንግስት ላበቃው መለስ ሲያንስ ነው።ብላለች ሰምሃል የተንጨባረረ ጸጉሯን አያመቻቸች።

The post ሰምሃል መለስ ዜናዊ ትናገራለች ” ሃይለማርያምን ለዚህ ስልጣን ያበቃው ኣባቴ አንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኣይደለም” appeared first on Zehabesha Amharic.

የመቀሌ የባጃጅ አሽከርካሪዎች መስተዳደሩን አንበረከኩት |‘የኦሮሞ ተማሪዎች ስልፎች የሕወሓት አስተዳደር በሹፌሮቹ እንዲንበረከክ ተፅእኖ አድርጎታል’–አምዶም ገብረሥላሴ

Next: Hiber Radio ፡ ስምንት ሺህ የሰራዊቱ አባላት በአንድ ዓመት ብቻ በአገዛዙ ዘረኛ አመራር ተማረው ከሰራዊቱ ከድተዋል፣በአመራሩ ላይ እርምጃ የወሰዱ ወታደሮች አሉ፣ሰራዊቱና ሕዝቡ በአንድ ላይ ሲቆሙ ጠመንጃው ወደ ዘረኛው ስርዓት መሪዎች ላይ ይዞራል፣ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊቷን አንገቷን ቀልታ መግደሏ ይፋ ሆነ፣የመን የሴት ቀሚስ ያጠለቁ አራት ኢትዮጵያውያን ወንዶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉዋን ገለጸች፣ግብጽና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከይሮ ላይ ኢትዮጵያን ያገለለ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ፣ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ የቀረበላትን ማሻሻያ ሀሳብ ውድቅ አደረገች፣ዶ/ር መረራና ኢ/ር ይልቃል በጋራ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በውጭ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተው ለሕዝቡ ጥሪ አቀረቡ፣ ቃለ መጠይቅ ከኮ/ል ደረሰ ተክሌ፣ ከአቶ ኦባንግ ሜቶ እና ሌሎችም አሉን
$
0
0

mekele
የአረና ፓርቲ አመራር አባል አቶ አምዶም ገበረሥላሴ በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን መረጃ አስፍሯል::

የባለ ባጃጆች እምቢታ በመቐለ
=*=*=*=*=*=*

የመቐለ ወጣት ባለ ባጃጆች መስተዳድሩን ኣንበረከኩት። ( ‪#‎Bajaj_Protest‬ እንደ ማለት ነው)

የኢህኣዴግ መንግስት ዓይኑን ጨፍኖ የሚያወጣቸው ኣዋጆች፣ እቅድና ኣሰራሮች ህዝቡን ኣማርሮ ለዓመፅ እየገፋፋው ነው።
ሰሞኑ የመቐለ መስተዳድር በከተማዋ የሚገኙ ከ2500 በላይ ባለ ባጃጆች የሚመለከት ያወጣውና “ባጃጆች በታፔላና በሚወጣላቸው መስመር ብቻ እንዲሰሩ” የሚያስገድድ ኣሰራር ከፍተኛ ተቃውሞ ኣጋጥሞታል።

መስተዳድሩ “ባጃጆች እንደ ታክሲ ታፔላ ተለጥፎባቹ፣ በተመደባቹ መስመር ብቻ መሰራት ኣለባቹ፣ ማንኛውም ኮንትራት መስራት ኣይፈቀድም፤ ይሄ ኣሰራር ፀጥታችን ኣስተማማኝ እንዲሆንና የሽብር ጥቃቶች ለመቆጣጠር ይረዳል ተብሎ የወጣ ስለሆነ የማይቀለበስ መመርያ ነው” የሚል ኣምባገነናዊ መመርያ ኣውርደዋል።
ይህ መመርያ ለባለ ባጃጆቹ ” ካሁን በኋላ በመቐለ ከተማ ሰርታቹ መኖር ኣትችሉም ” የሚል ግልፅ ኣምባገነናዊና ትእቢተኝነት የወለደው ክልከላ ነው ብለው ገልፀውታል።
ሃላፊዎቹ ኣዋጃቸው ለመተግበር ባለ ባጃጆች ለስብሰባ ወደ ማዘጋጃ ቤት ተጠሩ።

የስብሰባው መሪዎች መሓሪና ወዲ ሓየሎም የሚባሉ የመንገድ ትራንስፖርት ሓላፊዎች ሲሆኑ “ይሄ መመርያ በውድና በግድ መቀበል ኣለባቹ እምቢ የሚል ባለ ባጃጅ ካለ ግን የማያዳግም እርምጃ ይወሰድበታል” ሲሉ ዝተዋል።

ወጣቶቹ… “ይሄ ኣሰራር መተግበር ማለት ከደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ተበድረው፣ የቤተሰባቸው የቤት ፕላን ኣስይዘው፣ ንብረት ሽጠው፣ ቤተሰብ ኣስቸግረው የገዟት ባጃጅ ሳትሰራ በኪሳራ ኣስቀምጧትና በእዳ ተዘፈቁ፤ ስራ ኣጥ ሁናቹ እየሰረቃቹ፣ እየዘረፋቹና ወደ ሱስ ገብታቹ እርባና ቢስ ሁኑ፤ ከዚህ በተረፈ ደግሞ ኣገር በመተው እግራቹ ወደ መራቹ እየተሰደዳቹ እንደ ሌሎች ወንድም እህቶቻቹ በበረሃ ሃሩር፣ ኣውሬ፣ ሙቀት፣ በባህር ዓሳ፣ በኣሸባሪዎችና በኩላሊት ነጋዴዎች ተበልታቹ ጥፉ ማለታቹ ነው”… ሲሉ በመግለፅ መስተዳድሩ ኣምርረው ኮንነዋል።

“ይሄ ኣሰራር ይተግበር ያለ ኣካል በወጣቶች ሞት እየፈረደ መሆኑ ሊያውቀው ይገባል” ሲሉ ኣሳውቀዋል።
ባለ ባጃጆቹ መመርያው ወደ ትግበራ እንዳይገባ የሚያሳስብ ደብዳቤ ፅፈው ለትግራይ ክልል ኣስተዳዳሪ ኣቶ ኣባይ ወልዱ፣ ለክልሉ ምክርቤት፣ መንገድ ትራንስፖርት፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ህወሓት ቢሮ ኣስገብተዋል።
ደብዳቤው
” * መንግስት ይሄ በትእቢት የወጣ መመርያ በቀጥታ ይሰርዝ።
* መንግስት ባጃጆቻቸን ይግዛንና ራሱ ሹፌር ቀጥሮ በመስመር ብቻ ያንቀሳቅሳቸው።
* መንግስት ኣልረከብም የሚይል ከሆነም እስከ 14/04/2008 ዓ/ ም ያሳውቀን።
* ካላሳወቀንና ትራፊክ ፖሊስ ታርጋ ለመፍታት ቢሞክር እስከ ድብደባ የሚደርስ ጥቃት እናደርሳለን።
* ለትግበራው ቢንቀሳቀስና በፖሊስ ሃይል ሊቆጣጠረን ቢሞክርና ለ16ና 17 /04 /2008 ዓ/ም ሰለማዊ ስልፍ እንደምናካሂድ ሊያውቀው ይገባል።
* ሰለማዊ ስልፍ ኣካሂደን ሊመለስልን ካልቻለ ባጃጆቹ በሙሉ ሰብስበን በጎዳናዎች ኣቃጥለን ወደ ምትመኝሉን ስደት እንሄድላቹሃለን። ” የሚል ነው።
የመቐለ ወጣቶች በዚህ መልኩ ቁርጠኝነታቸው በማሳየታቸው መስተዳድሩ ሳይወድ በግድ በትእቢት ተወጥሮ ያረቀቀው መመርያው እንዲተው፣ ካልሆነም እንዲያዘገይ ተገድደዋል።
የመቐለ ባለ ባጃጅ ወጣቶች እምቢታና ዓመፅ በድርቅናውና ህዝብ ባለ መስማት የሚታወቀው የህወሓት መንግስት ኣንበርክከውታል።
‪#‎Oromo_protest‬ ለዚህ የህወሓት መንበርከክና ሳይወድ ወጣቶቹ እንዲያዳምጥ የራሱ ኣወንታዊ ተፅእኖ ኣበርክተዋል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
it is so.

The post የመቀሌ የባጃጅ አሽከርካሪዎች መስተዳደሩን አንበረከኩት | ‘የኦሮሞ ተማሪዎች ስልፎች የሕወሓት አስተዳደር በሹፌሮቹ እንዲንበረከክ ተፅእኖ አድርጎታል’ – አምዶም ገብረሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.


Hiber Radio ፡ ስምንት ሺህ የሰራዊቱ አባላት በአንድ ዓመት ብቻ በአገዛዙ ዘረኛ አመራር ተማረው ከሰራዊቱ ከድተዋል፣በአመራሩ ላይ እርምጃ የወሰዱ ወታደሮች አሉ፣ሰራዊቱና ሕዝቡ በአንድ ላይ ሲቆሙ ጠመንጃው ወደ ዘረኛው ስርዓት መሪዎች ላይ ይዞራል፣ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊቷን አንገቷን ቀልታ መግደሏ ይፋ ሆነ፣የመን የሴት ቀሚስ ያጠለቁ አራት ኢትዮጵያውያን ወንዶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉዋን ገለጸች፣ግብጽና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከይሮ ላይ ኢትዮጵያን ያገለለ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ፣ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ የቀረበላትን ማሻሻያ ሀሳብ ውድቅ አደረገች፣ዶ/ር መረራና ኢ/ር ይልቃል በጋራ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በውጭ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተው ለሕዝቡ ጥሪ አቀረቡ፣ ቃለ መጠይቅ ከኮ/ል ደረሰ ተክሌ፣ ከአቶ ኦባንግ ሜቶ እና ሌሎችም አሉን

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ፣ከላይ አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ኮ/ል ደረሰ ተክሌ፣የአይኤሬስና የታክሲና ቴክኖሎጂ ኩባንያዎቹ ሎጎ፣ሰራዊቱ አባላት ዩኒፎርም ሲቃተል፣የአጋዚ ጦር ለአፈና ተሰማርተው፣የኢራኖች ተቃውሞ በሳውዲ ግድያ ላይ

የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ሀብታሙ አሰፋ፣ከላይ አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ኮ/ል ደረሰ ተክሌ፣የአይኤሬስና የታክሲና ቴክኖሎጂ ኩባንያዎቹ ሎጎ፣ሰራዊቱ አባላት ዩኒፎርም ሲቃተል፣የአጋዚ ጦር ለአፈና ተሰማርተው፣የኢራኖች ተቃውሞ በሳውዲ ግድያ ላይ


የህብር ሬዲዮ ጥር 1 ቀን 2008 ፕሮግራም

<...> አቶ ከባዱ በላቸው የሰማያዊ ፓርቲ በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳይ ላይ በአገር ውስጥና ከውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስላደረጉት የጋራ ውይይት እና የሰማያዊና የመድረክና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ተገኝተው ስለሰጡት ማብራሪያ አስመልክቶ ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)
<...>
አቶ ኦባንግ ሜቶ የትብብር ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን አዳምጡት)
<...> ኮ/ል ደረሰ ተክሌ የመከላከያ የዕቅድና ምርምር ሀላፊ የነበሩ ሰራዊቱ በኦሮሚያ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ በተመለከተ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ( ቃለ መጠይቁን ያዳምጡ)
<...> አቶ ተካ ከለለ ከአትላንታ የቲኬ ሾው አዘጋጅ ስለወቅቱ የታክስ ጉዳይ ካነሱት ጥያቄ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)

ሳውዲ አረቢያ ታዋቂው የሺያት ሙስሊም የሃይማኖት መሪ ሼክ ኒሚር አል ኒምርን ጨምሮ 47 ስዎችን መግደሏን ተከተሎ በኢራን እና በሳውዲ አረቢያ መካከል ሰሞኑን የተጋጋመው አካባቢያዊ እና ዓለማቀፋዊ የደፕሎማሲያዊ ቁርቋሶ(ልዩ ጥንቅር) ሌሎችም
ዜናዎቻችን
ስምንት ሺህ የሰራዊቱ አባላት በአንድ ዓመት ብቻ በአገዛዙ ዘረኛ አመራር ተማረው ከሰራዊቱ ከድተዋል
በአመራሩ ላይ እርምጃ የወሰዱ ወታደሮች አሉ
ሰራዊቱና ሕዝቡ በአንድ ላይ ሲቆሙ ጠመንጃው ወደ ዘረኛው ስርዓት መሪዎች ላይ ይዞራል
ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊቷን አንገቷን ቀልታ መግደሏ ይፋ ሆነ
የመን የሴት ቀሚስ ያጠለቁ አራት ኢትዮጵያውያን ወንዶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉዋን ገለጸች
ግብጽና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከይሮ ላይ ኢትዮጵያን ያገለለ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ
ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ የቀረበላትን ማሻሻያ ሀሳብ ውድቅ አደረገች
ዶ/ር መረራና ኢ/ር ይልቃል በጋራ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በውጭ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተው ለሕዝቡ ጥሪ አቀረቡ

ኤርትራ 400 ወታደሮቿን ወደ የመን ልካ ጦርነቱን መቀላቀሏ አነጋጋሪ ሆኗል
በኦሮሚያ የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተማጋቾችና በሚዲያው ትኩረት እያገኘ መጣ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio ፡ ስምንት ሺህ የሰራዊቱ አባላት በአንድ ዓመት ብቻ በአገዛዙ ዘረኛ አመራር ተማረው ከሰራዊቱ ከድተዋል፣በአመራሩ ላይ እርምጃ የወሰዱ ወታደሮች አሉ፣ሰራዊቱና ሕዝቡ በአንድ ላይ ሲቆሙ ጠመንጃው ወደ ዘረኛው ስርዓት መሪዎች ላይ ይዞራል፣ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊቷን አንገቷን ቀልታ መግደሏ ይፋ ሆነ፣የመን የሴት ቀሚስ ያጠለቁ አራት ኢትዮጵያውያን ወንዶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉዋን ገለጸች፣ግብጽና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከይሮ ላይ ኢትዮጵያን ያገለለ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ፣ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ የቀረበላትን ማሻሻያ ሀሳብ ውድቅ አደረገች፣ዶ/ር መረራና ኢ/ር ይልቃል በጋራ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በውጭ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተው ለሕዝቡ ጥሪ አቀረቡ፣ ቃለ መጠይቅ ከኮ/ል ደረሰ ተክሌ፣ ከአቶ ኦባንግ ሜቶ እና ሌሎችም አሉን appeared first on Zehabesha Amharic.

ጃሉድ ጸልዩልኝ አለ

Previous: Hiber Radio ፡ ስምንት ሺህ የሰራዊቱ አባላት በአንድ ዓመት ብቻ በአገዛዙ ዘረኛ አመራር ተማረው ከሰራዊቱ ከድተዋል፣በአመራሩ ላይ እርምጃ የወሰዱ ወታደሮች አሉ፣ሰራዊቱና ሕዝቡ በአንድ ላይ ሲቆሙ ጠመንጃው ወደ ዘረኛው ስርዓት መሪዎች ላይ ይዞራል፣ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊቷን አንገቷን ቀልታ መግደሏ ይፋ ሆነ፣የመን የሴት ቀሚስ ያጠለቁ አራት ኢትዮጵያውያን ወንዶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉዋን ገለጸች፣ግብጽና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከይሮ ላይ ኢትዮጵያን ያገለለ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ፣ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ የቀረበላትን ማሻሻያ ሀሳብ ውድቅ አደረገች፣ዶ/ር መረራና ኢ/ር ይልቃል በጋራ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በውጭ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተው ለሕዝቡ ጥሪ አቀረቡ፣ ቃለ መጠይቅ ከኮ/ል ደረሰ ተክሌ፣ ከአቶ ኦባንግ ሜቶ እና ሌሎችም አሉን

ህብረት ህብረት ህብረት አሁንም ህብረት |ገለታው ዘለቀ

$
0
0

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግፍና የፍትህ መጥፋት ስለበዛ ህዝባዊ አመጽ በሁለት መንገድ ሊነሳ ይችላል ሲሉ ቆይተዋል አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች። አንደኛው ህዝብ ራሱ ድንገት የሚያነሳውና የሚመራው (spontaneous አመጽ) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በፖለቲካ ወይም በሲቪክ በተደራጁ ሃይላት ታቅዶ የሚመራ በቅስቀሳና በጥሪ የሚነሳ ሊሆን ነው። ከወር በላይ የሆነውና በኦሮሞ ክልል ውስጥ በሰፊው የተነሳው ተቃውሞ የአዲስ አበባውን ማስተር ፕላን ተከትሎ የተፈጸመውን ማፈናቀል እንደ ማቀጣጠያ አድርጎ የተነሳ በህዝብ የተመራ ህዝባዊ አመጽ ሆኖ ብዙ ሰው በሚገባ እንደተረዳው የህዝቡ ጥያቄ የመንግስት ለውጥ ጥያቄ ነው። ለብዙ ዓመታት ታምቆ የቆየ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እጦት፣ የመሬት ነጠቃው ጉዳይ ናቸው ዛሬ ይህን ህዝብ አስመርረው- አስመርረው ጎዳና ላይ ያወጡት። ህዝቡ በየቦታው ሲጨፍርና መፈክር ሲያሰማ በአብዛኛው ይል የነበረው በመረጥነው እንተዳደር፣ ፍትህ ፣ነጻነት፣ የመሬት ነጠቃው ይቁም፣ መሬታችን የኛ፣ የመሳሰሉትን ነው። ይህ የሚያሳየው የህዝቡ ጥያቄ የስር ነቀል ለውጥ ጥያቄን ያዘለ መሆኑን ነው። ይህ ጥያቄ በርግጥ የሁሉ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው። ዛሬ በኦሮምያ ጠንከር ያለ ተቃውሞ እየተሰማ በሌሎች አካባቢዎች ተቃውሞው እምብዛም ያልሆነበት አንዱ ምክንያት የአዲስ አበባውን ማስተር ፕላን ተከትሎ የህዝብ ቁጣ ሲገነፍል የኦሮሞ ወጣቶች በተወሰኑ አካባቢዎች የህዝብ ግንኙነት ስራ መስራታቸውና ወጣቶች ማህበራዊ ድረ ገጾችን እየተጠቀሙ ትግሉን በማቀጣጠላቸው ነው። በሌሎች አካባቢዎች የውስጥ ለውስጥ ስራዎች እምብዛም አልተሰሩምና ተቃውሞውን ማቀጣጠል አልተቻለም እንጂ በደል በሁሉም ክልሎች እስከ ጥግ ድረስ አለ።

unity
በዚህች አጭር ጽሁፍ ስር አስተያየት ለመስጠት ያነሳሳኝ ነገር ግን ይህ አይደለም። ለአስተያየት ያነሳሳኝ ጉዳይ ትግሉ ምን ላይ እንዳለና ፍጻሜው ምን ሊሆን እንደሚችል ትንሽ አሳብ ለማካፈል ነው። አሁን በስፋት በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞና በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በአነስተኛ ሁኔታ የተነሳው የተናጠል ተቃውሞ አንደኛ ምን መጨረሻ ሊኖረው ይችላል? ብሎ መወያየት በጣም አስፈላጊ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ውጤታማ ለውጥ ለማምጣት ምን ማድረግ እንደሚያስፈልግ መወያየት ወሳኝ ነገር ነው። የኦሮሞ ኢትዮጵያውያንን ተቃውሞ ስናይ እጅግ አስደናቂና የተናበበ ነው። ምን አልባትም በአገራችን የሰላማዊ አመጽ ትግል ውስጥ ከፍተኛውን ደረጃ የሚይዝ ነው። ይህ ትግል አሁንም በተጠናከረ መንገድ መቀጠል ያለበት ሲሆን ነገር ግን ይህ ህዝባዊ አመጽ ወደ ፍጻሜ ደርሶ ተፈላጊውን ለውጥ ለማምጣት በሌሎች ብሄሮች መደገፍ አለበት። አሁን ያለውን የኦሮሞ ህዝብ ተቃውሞ ስናይ ወዴት ነው የሚሄደው፣ እስከምን ደረጃ የመድረስ አቅም ይኖረዋል፣ ምን አይነት ለውጦችን ያመጣል፣ ብለን ስናጤን ትግሉ በዚሁ ክልል ታጥሮ ከቆየና ሌሎች አካባቢዎችም ካልፈነዳ የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ አይመልስም። የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ ቢሰረዝ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ተመለሰ ማለት አይደለም። ከፍ ሲል እንዳልነው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ የሆነ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ጥያቄ ነው። ምን አልባትም መንግስት ሲጨንቀው ኦህዴድን አስገድዶ ይሰበስብና ተለውጠናል በሉ፣ ህዝቡን ይቅርታ ጠይቁና አረጋጉ በማለት ለማስቀየስ ይሞክራል። ትግሉ አሁንም ከገፋና በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ በክልሉ አዲስ ምርጫ ይካሄድ ኦሮሚያ በመረጠችው ትተዳደር ሊል ይችላል። የኦሮሞ ህዝብ በጥያቄው ከገፋ፣ መንገድ እየዘጋ ካስቸገረ፣ ካመጸ፣ የመጨረሻው ርምጃ ይህ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በህወሃት ኢህአዴግ ጥላ ስር ባለ እጅግ ጠንካራ ፌደራል ስርዓት ውስጥ ኦሮምያ ውስጥ እንደገና ምርጫ ቢካሄድም ጥያቄው አይፈታም። የኦሮሞ ህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄም ሆነ ነጻ የሆነ የክልል መንግስት ምስረታ በወያኔ መራሹ ፌደራል መንግስት ስር ፈጽሞ እውን አይሆንም። “የጉልቻ መለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም” እንደሚባለው አዲስ የሚመረጡትም ቢሆኑ ከላይ ያለው መንግስት እስካልተለወጠ ድረስ ለኦሮምያ መሰረታዊ ለውጥ አይመጣም። ከፍተኛው ስልጣን ያለውና የሃገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መዘውር የያዘው ፌደራል መንግስት ስለሆነ ክልሉ አዲስ ምርጫ ቢያካሂድም ከዚህ አምባገነን ስርዓት አይላቀቅም። በመሆኑም ሰፋ አድርገን ካየነው የአሁኑ የኦሮሚያ ህዝብ ጥያቄ በዋናነት የፌደራል መንግስት ለውጥ ጥያቄ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ፌደራል አካባቢ ያለው ዘረኛ መንግስት የሚያሽከረክራቸው የኦህዴድ አመራር አባላትንም ይመለከታል። ታዲያ የኦሮሚያ ጥያቄ ከላይ ከቁንጮው አካባቢ መስተካከል አለበት ብሎ ከተነሳ ይህ ጥያቄ ደግሞ የመላው የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው የሚሆነው። ፌደራል መንግስቱን በሃቀኛ ፌደራል ስርዓት አዋቅሮ የክልል መንግስታትትን በሃቀኛ ስርዓት ለመምራት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግል መደባለቅ አለበት።

በመሆኑም ኦሮምያ ብቻውን ታግሎ የራሱንም ሆነ የኢትዮጵያን ጥያቄ እንዲፈታ ሃላፊነት ሊጫንበት አይገባም። ኦሮሞ እየታገለ ያለው ለሃቀኛ ፌደራሊዝም እንደመሆኑ ትግሉን ልንደግፈውና የትግሉን መሪ ቃል ከፍ አድርገን የጋራ አድርገን ልንነሳ ይገባል ።

ስለሆነም በአሁኑ ሰዓት የኦሮምያን አካባቢ ህዝብ እያነቃቁ ያሉ ጀግና የኢትዮጵያ ልጆች ትግሉ ወደ ፍጻሜ ይሄድ ዘንድና የመንግስት ለውጥ አምጥቶ የተሻለ ስርዓት ለመገንባት እንዲቻል ትግሉ ሁሉን አቀፍ እንደሆነ ማሳየት አለባቸው። በአንጻሩ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ የኦሮሞ ወገኖቻችን ያነሱት ጥያቄ የኛም ነው። እኔም ኦሮሞ ነኝ በማለት ህብረትን በማሳየት ነው ትግሉ ጫፍ ደርሶ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣው። ትግሉን በተለያየ ማህበራዊ ድረ ገጽ የሚያቀጣጥሉ የኦሮሞ ወጣቶችም የለውጥ ጥያቄን ከፍ አድርገው ማንሳት ሲጀምሩ ይህ መሪ ቃል ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ወደ ጎን መተሳሰር (link) ይፈጥራል። ትግሉ የአካባቢን የመልካም አስተዳደር ችግር መሰረት አድርጎ ከፍ ያለው ጥያቄ ደግሞ የለውጥ ጥያቄ መሆኑን ማሳየት ተገቢ ነው። ይህ ሲሆን በስፋት የኦሮሞ ወገኖች የጀመሩትን ትግል ሁሉም ይቀላቀልና የጋራውን የችግር ቤት አፍርሰው እንደገና ጥሩ አድርገው ይሰሩታል። በሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የፖለቲካ ድባብ የተነሳ የተናጠል ትግል ውጤት አያመጣም ብቻ ሳይሆን ሆኖለት አሸንፎ የፌደራል መንግስትን ስልጣን ቢይዝም ለኢትዮጵያ ጥሩ አይደለም። ከገባንበት የቡድነኝነት ክብ አንወጣም። አሁን ያለውን በከፍተኛ ሁኔታ በኦሮምያ አካባቢ ታጥሮ ያለውን ተቃውሞ ስናይ ሄዶ ሄዶ ምን ይሆናል? ስንል። ሄዶ ሄዶ ህብረትን ነው የሚጠራው። ለዚህ ነው ሌሎቻችንም የኦሮሞው ጥያቄ የኔም ነው ብለን የጋራ ጥያቄ አድርገን ልንነሳ ይገባል የሚያስብለን።

አሁን ያለው የኦሮሞ ህዝብ ትግል ሲጠናከርና ሌላው ህዝብም ሲቀላቀለው ጥያቄው አድጎ የለውጥ ጥያቄ ሲሆን ትግሉ ወዴት ነው የሚሄደው ልንል እንችላለን። በአዳንድ አገሮች እንዲህ አይነት ቀውስ ሲነሳ በገዢው ፓርቲ አካባቢ መፍረክረክ ይነሳና ለለውጥ ይዘጋጃሉ። አንዳንድ አገር ደግሞ መፈንቅለ መንግስት ይነሳና የሽግግር መንግስት ሊነሳ ይችላል። አንዳንድ አገር ደግሞ መሪዎች እየፈረጠጡ ጥለው ይጠፉና ማእከላዊ መንግስት ሲዳከም ወደ ውይይት ሊመጡና መላ ሊፈጥሩ ይችላሉ። የሃገራችንን ጉዳይ ስናይ ለምሳሌ መፈንቅለ መንግስት የመነሳቱ እድል በጣም ጠባብ ነው። በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ከአንድ ብሄር በወጡ መኮንኖች የሚመራ ሰራዊት ወደዚህ ያመራል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ማን ላይስ ነው መፈንቅለ መንግስት የሚያደርገው? ሃይለማርያም ላይ እንዳይባል ሰውየው የነዚሁ መኮንንኖች አሻንጉሊት በመሆናቸው የመፈንቅለ መንግስት እድሉን ተስፋ ያሳጣዋል። በሌላ በኩል በፓርቲው ውስጥ የመሰንጠቅና ለለውጥ ክፍት የመሆን አዝማሚያ ይኖር ይሆን ወይ? ብለን ስናስብ ከመፈንቅለ መንግስቱ የተሻለ እድል ሊኖረው ቢችልም ይህ ሁኔታ የሚወሰነው በቤተሰቦቻቸው የግፊት መጠንና በራሱ ህወሃት አካባቢ ባሉ ሰዎች የመለወጥ ልብ ላይ የተመረኮዘ ነው። ። ቢያንስ ስለ ህዝቡ ብለው ባይሆንም ስለራሳቸው ፍጻሜ ብለው ተቃውሞ በረታና እንለወጥ የሚል ነገር ያነሱ እንደሆን ብለን ስናስብ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ይህ ተስፋ የለም። ህወሃት ይራራል፣ ይለወጣል ብለው የሚያስቡባቸው ጊዚያት አልፈዋል። ተቃውሞው ሲበረታና መንግስት መውጫ መግቢያ ሲያጣ፣ መንገዶች ሲዘጉ ምን አልባትም አንዳንዶች የኦሮሞውን ጥያቄ ወደ ብሄርተኛና የመገንጠል ጥያቄ አውርደው፣ የራሳቸውን ካድሬዎች እያነሳሱ ኦሮሞ የመገንጠል ጥያቄ አስነሳ በማለት አገር አፍርሰው ትግራይን በመገንጠል እንገላገል የሚል ነገርም ያነሱ ይሆናል። ወያኔ አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ ላይ ሙጭጭ ያለው ለክፉ ቀን ትሆነኛለች እስከዚያው ልዝረፍ ብሎ የሚኖር ነው የሚመስለውና እንዲህም ልንጠረጥር እንችላለን። ::

እንግዲህ ኦሮምያ አካባቢ ያለው ተቃውሞ ሲከር ውሎ ቢያድር ተጽእኖው እስከ ምን ነው፣ የሚለውን ስናይ ከፍተኛ ነው። ይሁን እንጂ ቤተመንግስት ሄዶ ወታደሩን ተጋፍቶ መንግስት ይለውጣል ወይ? ብለን ስናስብ በኢትዮጵያ ሁኔታ ከባድ ነው ብዙ ዋጋ ያስከፍላል። ይሁን እንጂ በአራቱም ማእዘናት ያሉ ህዝቦች ሲያምጹ ግን መንግስትን ቤተ መንግስት ብቻ ያስቀራሉና ተፈላጊ ለውጥ መምጣቱ አይቀርም።

ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሲነሱ በተቃውሞው ጊዜ ብዙ የሰራዊቱን አባላት በየመንገዱ ይማርካሉ፣ የሚማረከው የሰራዊት አባል ደግሞ ለስርዓቱ መውደቅ በጣም ጉልህ አስተዋጾ አለው። ስለዚህ የኦሮሞ ወገኖቻችን የራሳቸውንም ሆነ የሌላውን አካባቢያዊ ጥያቄዎችና አገራዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ዛሬ የእንተባበር ጥያቄ እያሰሙ ነውና ሁሉም ብሄሮች ድጋፍ ሊያሳዩ ይገባል። የኦሮሞ አክቲቪስቶች ለውጥ ለኢትዮጵያ አገራችን ሲሉ፣ ሌላው ኢትዮጵያዊ ደግሞ እኔም ኦሮሞ ነኝ፣ የኦሮሞ ትግል የኔ ነው ስንል የመንፈስ አንድነትን እናዳብራለን። ይህ አገራዊ አንድነት የባህል ማንነታችንን የሚጻረር አይደለም። ጥያቄው ከላይ ቁንጮው አካባቢ የተበላሸውን አስተዳደር ለውጠን ለሁሉም ብሄሮች የምትሆን የተባበረች ኢትዮጵያ እንገንባ በመሆኑ ባህላዊ ማንነታችንን አክብረንና ጠብቀን ለተሻለ ፌደራል ስርዓት እንታገላለን።

በሌላ በኩል መዘንጋት የሌለብን ነገር ይህ መንግስት የሚወድቀው ከትግሉ እጅግ ሰፊውን ሽፋን በሚይዝ ሰላማዊ አመጽ ሲሆን ነገር ግን የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ወገኖች ደግሞ ሽፋን ሊሰጡት ይገባል። ህዝቡ አምጾ ሲያበቃ ወታደሩ ምን ይሆናል? ብዙ ጊዜ በህዝባዊ አመጽ ጊዜ በጣም ተደራጅቶና ሃይለኛ ሆኖ የሚወጣው ወታደሩ ነውና በኢትዮጵያ ሁኔታ ህዝባዊ አመጹ እጅግ ሲከርር ወታደሩ ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ያሰፈልጋል። በዚህ ዙሪያ ኢትዮጵያውያን ምሁራን መወያየት አለባቸው። ዝም ብሎ ዛሬ እዚህ ከተማ ተቃውሞ ነበር ብቻ ሳይሆን ትግሉን ወደ ፍጻሜ ለማድረስ ያሉትን ተለዋዋጮች (Variables) በማጤን ትግሉን መምራት ያስፈልጋል። በህዝብ የተነሳው ይህ አመጽ አሁን አመራር የሚፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷልና።

በሌላ በኩል ትግሉ እየገፋ ሳለ አንዱ መደረግ ያለበት ነገርና አንድ የትግል ስልት ተደርጎ መያዝ ያለበት የታጠቀውን ማለትም ፖሊስንና ወታደሩን የማግባባት ስራ ዜጎች ሁሉ እንዲካፈሉት ማድረግ ነው። በዚህ በኩል ሚዲያዎችና ትግሉን በማህበራዊ ድረ ገጾች የሚያስተባብሩ ወጣቶች ትልቅ ስራ ይጠበቅባቸዋል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወይ ልጁ፣ ወይ ወንድሙ፣ ወይ ጓደኛው፣ ወይ ዘመዱ ወታደር ወይ ፖሊስ ሊሆን ይችላል። ወታደር ወይም ፖሊስ ባል ያላቸው ሴቶች አሉ። እነዚህ ወገኖች በግለሰብ ደረጃ ይህን የታጠቀ ሃይል በወገኑ ላይ እንዳይተኩስ ብቻ ሳይሆን ከለውጥ ጎን እንዲቆምላቸው ሊያግባቡና ሊማጸኑ ይገባል። እንዲህ ሲሆን ወታደሩን መማረክ ይቻላል።

በአረብ ስፕሪንግ ጊዜ ግብጽ ውስጥ የታየው ነገር ይገርም ነበር። የግብጽ ወታደር ጸጥታ አስከብር ተብሎ ሲመደብ ለህዝብ ወገንተኛነቱን አሳይቷል። ገለልተኛ ተቋም ስለነበር ያልታጠቀው ህዝብ መንግስትን መለወጥ ችሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ግን የተለየ ነው። የወታደሩ አመራሮች ድሮ ጫካ የነበሩ የህወሃት አመራሮች ናቸው። ሃያ አምስት አመት ሙሉ ሰው አላፈሩምና ሙሉ በሙሉ ከፍተኛውን ስልጣን የአንድ ብሄር ሰዎች ይዘውታል። ስለዚህ ህዝባዊ አመጽ ጫፍ ሲደርስ ወታደሩ ወደ ህዝብ ወግኖ ወይም ገለልተኛ ሆኖ ይመለከታል ማለት አይቻልም። ለዚህ ነው ከስር ከስሩ ኢትዮጵያውያን የወታደሩን አባል እየማረኩ ይህ ተቋም ለለውጥ እንቅፋት እንዳይሆን ማድረግ የሚቻለው።

ይህ ህዝብ የቀሰቀሰው አመጽ መንግስትን ለመጣል ከሚኖረው ጉልህ ሚና ባሻገር የሽግግር መንግስት ለመመስረት የወታደሩ ሚና ወሳኝ ነው። በሌላ በኩል አንድ በጣም ትኩረት ሊያገኝ የሚገባው ነገር የተጠቁ ተቃዋሚዎች ጉዳይ ነው። እነዚህ ተቃዋሚዎች (ሃቀኛ ተቃዋሚዎችን ማለቴ ነው) ከመቼውም ጊዜ በላይ በተጠናከረ መንገድና በህብረት ሊቆሙ ይገባል። እንደ ኦነግ፣ ግንቦት ሰባት አርበኞች፣ ትህዴን ወዘተ የመሳሰሉት ወደ ውህደት ማምራት አለባቸው።

ስር ነቀል ለውጥ ይመጣ ዘንድ የግድ የታጠቁ ሃይሎችም የህዝቡን ሰላማዊ አመጽ ደግፈው ለውጡን ካላመጡ የትግሉ ፍጻሜ ተፈላጊውን ለውጥ ላያመጣ ይችላል። ነገር ግን መንግስትን ለመለወጥና አዲስ ለሁሉም የምትሆን ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ትግል ውስጥ ትልቁ ትግል ህዝባዊ አመጹ ነው። ያም ሆኖ ግን ህዝቡ መንግስትን ገዝግዞ ሲያዳክም እነዚህ የታጠቁ ሃይሎችም በታክቲክ አግዘው ለውጡን ካላመጡ በህዝባዊ አመጽ መንግስት ቢፈርስ የሆነ የሃይል ክፍተት አገሪቱን እንዳይመታትና በዚህ መሃል ደግሞ አንዳንድ አክራሪ የብሄር ኢንተርፕሩነርስ ገብተው አገሪቱን እንዳይበጠብጡና አንድነታችን አደጋ ላይ እንዳይወድቅ እነዚህ የታጠቁ ሃይላት የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት የማረጋጋት ስራ ሊሰሩ ይችላሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ የተደራጁ የፖለቲካ ሃይሎች አንድ ጉዳይ ላይ መስማማት አለባቸው። ይህ ማለት አንድ ርእዮት ይኑራቸው ማለት አይደለም። የተለያየ ርእዮት ይዘው ይሆናል። ይሄን ተራራ ለጊዜው አልፈው በኢትዮጵያ ውስጥ የተውጣጣ የሽግግር መንግስት ለመመስረት መስማማት የግድ አለባቸው። ልዮነቶች ሁሉ በሽግ ግሩ ወቅት ሊነሱና ወደ ህዝብ ቀርበው ህዝብ የመረጠው ሊሆን ይችላል። በአሁኑ ሰዓት የሚኖረው ትግል የአይዲዮሎጂ ሳይሆን አገሪቱ ወደ ዴሞክራሲ መስመር እንድትገባና የፖለቲካው ምህዳር ሰፍቶ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት በመድረክ የሚከራከሩበትን ሁኔታ መፍጠር ነው። በዚህ ጥላ ስር ሁሉም የፖለቲካ ተቋማት ሊሰባሰቡ ይችላሉ። ይህ ሲሆን ትግሉ አመራር ያገኛል። ለውጡ ወደ ቤተ መንግስት ሲደርስና መንግስት ተፈረካክሶ ሲወድቅ እነዚህ የተደራጁ ሃይላት በቀጥታ የሃይል ክፍተት ሞልተው የሽግግር መንግስቱን በማቋቋም ሊቀጥሉ ይችላሉ።

እዚህ ላይ አንድ ኢትዮጵያውያንን ያሰለቸ ጉዳይ ማንሳት ተገቢ ነው። ህዝቡ ተባበሩ፣ ተባበሩ፣ ተባበሩ….. እያለ ሲጮህ ይታያል። ይሁን እንጂ ስለምን መተባበር አቃተን እንላለን። አንዳንዱ አገር ወዳድ የሆነና በተቃዋሚዎች አለመተባበር ውስጡ የበገነ ሰው በቃ እኛ ኢትዮጵያውያን የመተባበር ችግር አለብን ይላል። አይደለም። እንደ ህዝብ እኛ ኢትዮጵያውያን የመተባበር ችግር የለብንም። እንዴውም ከሌላው ህዝብ በተሻለ አብሮ የመብላት፣ ችግርን የመካፈል ባህል አለን። ይሁን እንጂ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዳይተባበሩ ካደረጋቸው ጉዳይ መካከል አንዱ የመንግስት ሰርጎ ገብነት ባህርይ ነው። የሚገርማችሁ ነገር ተቃዋሚ ፓርቲ የተባሉ ድርጅቶች ሁሉ ተቃዋሚ አይደሉም። አንዳንዶቹ በራሱ በህወሃት የተቋቋሙ ናቸው። የውስጥ አርበኞች ሆነው የሚያገለግሉ የተቃዋሚውን ጎራ በተከላካይነትና በአጥቂነት የሚያዳክሙ መሳሪያዎች ናቸው። በሌላ በኩል በእውነተኛ ተቃዋሚ ድርጅቶች መካከል ደግሞ እንዲሁ እስከ አመራር ሾልከው የሚገቡ አባላትን ስለሚመለምል በሃገራችን ተቃዋሚዎች እንዳያብሩ ትልቅ መሰናክል ፈጥሯል። ሌሎች የምንጠረጥራቸው ምክንያቶች ሁሉ ያላቸው አስተዋጾ በጣም አናሳ ነው። ትልቁ ያለመተባበር ምክንያት የወያኔ ሰርጎ ገብነት ባህርይ ነው። ታዲያ ችግሩ ይህ ከሆነ ዘንዳ ሃቀኛ ተቃዋሚዎች አሳቾችን ከስራቸው የመለየት ስራ መስራት አለባቸው። ከፍ ሲል እንዳልኩት በሽግግር መንግስት ምስረታው ዙሪያ ለመስማማት አሳብ አቅርቦ በዚያ ላይ አልሳተፍ ያሉትን የመንግስት ደጋፊ ናችሁ ብሎ አፋጦና ጨክኖ የሚይዝ የሚያጋልጥ አመራር እስካላገኘን ድረስ መቼም ህብረት አይኖርም። የግድ ሚና የመለየት ስራ መሰራት አለበት። ሚዲያዎችና የቆረጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተደጋግፈው እነዚህን ህብረት የማይፈልጉና ህብረትን የሚያደናቅፉ ሃይሎችን የማጋለጥ ስራ መሰራት አለበት። በዚህ ደረጃ ጨካኝ ሆነን ነው ህብረትን የምንመሰርተው። በአንድ ቀን ወርክሾፕና ሰሚናር ወይም በራሪ የጥሪ ወረቀት ህብረትን መመስረት አይቻለም። ስንዴውን ከእንክርዳዱ ካለየንና ጨክነን የማውገዝ ስራ ካልሰራን ወያኔ በዚህ ታክቲኩ ሊቆይ ይፈልጋል። የወያኔ ትልቁ ጉልበት ወታደሩ ሳይሆን የተቃዋሚው ወገን መፈረካከስ ነውና ይህንን ጎራ መምታት አንድ የትግል ስትራተጂ ተደርጎ በሃቀኛ ታጋዮች ዘንድ መታወቅ አለበት።

ሌላው በታጠቁ ሃሎች ዘንድ ያለው ጉዳይ ደግሞ በጣም ሊታሰብበት የሚገባ ነው። በብሄር ላይ ቆሞ የታጠቀ ሃይል ኢትዮጵያን ነጻ ያወጣል እያሉ መጃጃል መቆም አለበት። ውህደት ያስፈልጋል። ካልሆነ ደግሞ ራስን ችሎ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል እንጂ በማይሆን አጠማመድ መግባት አስፈላጊ አይደለም። ጥበብም አይደለም። ይህን በግልጽ መወያየት ያስፈልጋል። ከዚህ በፊት በትህዴንና በግንቦት ሰባት አርበኞች በኩል የተጀመረው ጥምረትና ውህደት ቶሎ መግፋት አለበት። አንዳንዶች በትህዴን ላይ ያላቸው ጥያቄ የሚመለሰው ትህዴን ለውህደት በሚያሳየው ቁርጠኝነት ነው። በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ታሪክ ውስጥ እንደ ትህዴን ግራ የሚያጋባ ሽምቅ ተዋጊ ያለ አይመስለኝም። ይህን የምልበት ምክንያት። አንደኛ ይህ ድርጅት ከተቋቋመ ረጅም ዓመታትን አስቆጥሯል። የሚገርመው ቁጥሩ ደግሞ ከሃያ ሽህ በላይ (> 20,000) ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በትግራይ ተወላጆች ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ አለው ይባላል። የሚገርመው ግን ይህን ያህል ግዙፍ ሰራዊት ይዞ ይሄ ነው የሚባል ውጊያ እንኳን አርጎ አያውቅም። አንድ ወረዳ ቀርቶ ቀበሌ አልያዘም።ትግሉን ኣገር ቤት ኣላስገባም። ህወሃት ወደ ጫካ ሲገባ ሰባት ሆነው ሲሆን በስድስተኛ ወራቸው ትግራይ መሬት ውስጥ ጦርነት ጀምረዋል። ትህዴን በትግራይ ህዝብ ከተደገፈ መደበቂያ አለው ማለት ነው። ሰርጎ እየገባ ወታደራዊ ጥቃት በማድረግ መንግስትን አስጨንቆ ብዙ ሊሰራ ብዙ ሊማርክ የሚችል ሃይል ይዞ ነገር ግን ኪነትና ስፓርት እየሰራ ቁጭ ካለ ያስጠረጥራል። አገር ወዳዶች ይሄ ቡድን ድንገት አገር ሲበጠበጥ (ልክ አሁን የኦሮሞ ህዝብ ያነሳውን ትግል አይነት ሲፈጠርና መንግስት ሲፈረካከስ) እንደተጠባባቂ ሆኖ በጦርነት ስም አዲስ አበባን ተቆጣጥሮ ሌላ ህወሃት ሊሆን ይችላል ብለው ሰዎች ቢሰጉ አይፈረድም። ወይም ይህ ቡድን በዚያ በኤርትራ አካባቢ ያሉ የታጠቁ ታጋዮችን ትግል እያሳነፈ የህወሃትን እድሜ ያራዝማል ተብሎ ሊጠረጠር ቢችል ትህዴን እባክህ አትቆጣ። ለሽምቅ ውጊያ መቶዎች በቂ ናቸው። ሃያ ሺህ ስንት ክፍለ ጦር ስንት ብርጌድ ነው? በደርግ ጊዜ ህወሃት ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ ህዝቡ ማን ነህ ምንድነህ አላለም። እያገዘ ነው አዲስ አበባ ያስገባቸው። አሁን ግን በተፈጠረው ዘረኛ ስርዓት ምክንያት ህዝቡ የሚመጡ ታጋዮችን ማን ነህ ምንድን ነህ ማለት ጀምሯል። ስለዚህ ወንድሜ ትህዴን ሆይ በጋራ አርማ ለጋራዋ አገራችን ተዋሃድ። እንዴውም ለመዋሃድ ሌሎቹን ቀስቅስ።

ግንቦት ሰባት አርበኞችና ሌሎች ብሄራዊ አጀንዳ ያላቸው ይህን ድርጅት መምከርና ህብረት መሻሉን አሳይቶ ወደ ጋራ ግንባር መምጣት አስፈላጊ ነው። ዖነግ የኦሮሞን ህዝብ ልብ ማሳየት አለበት። ኢትዮጵያ ብዙው አካሏ ኦሮሞ ነው። ኦሮሞ ነች ኢትዮጵያ። የፈለገውን ያህል ጥሩና መጥፎ ታሪክ እናሳልፍ የኦሮሞ ህዝብ ግን አገሩን የሚወድና የአገሩ ተቆርቋሪ በመሆኑ ቶሎ ብሎ ህብረ ብሄራዊ ትግል ውስጥ መግባት አለበት። ወያኔ በብሄር ተኮር ትግሎች አይደነግጥም። እንዴውም ያበረታታል። የሚገርመው በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያ ውስጥ ባለው ተቃውሞ ውስጥ አንዳንድ የኦነግን ባንዲራ የሚይዙ ሰዎች የራሱ የወያኔ ደጋፊና ካድሬዎች ናቸው። ይሄ የሚያሳየው መንግስት ኦነግን ስለወደደ ሳይሆን ብሄርተኛ ትግሉ ከብሄራዊ ትግሉ ይሻለኛል ብሎ ስለሚያምን፣ የኦርሞን ህዝብ ከሌላው ነጥሎ ለማሳየትና ድጋፍ ከሌላው ወገኑ እንዳያገኝ ለማድረግ ነበር። እንዲህ ዓይነት መሰሪዎችን ተቃዋሚው ሊነቃባቸው ይገባል።

በሌላ በኩል የትጥቅ ትግሉ አንድ ቦታ ብቻ በጣም ጥገኛ መሆን የለበትም። ለምን ኤርትራ ውስጥ ስልጠና ይካሄዳል፣ ለምን ከኤርታራ ድጋፍ ታገናላችሁ ማለት ተገቢ አይደለም። የማግኘት የመሰልጠን መብት አላቸው። ከዚህ አልፎ ግን እጅግ ሲበዛ በዚያ አካባቢ ብቻ ጥገኛ መሆኑ ከትግሉ ባህርይና ከሚያስከፍለው መስዋእትነት አንጻር ተገቢ አይደለም። ሁል ጊዜ አዳቫንቴጅ እንዳለ ሁሉ ዲስ አድቫንቴጆች ስላሉ ሌሎች አማራጮችንም መጠቀምና በምስጢር መያዝ ተገቢ ነው። ከሁሉ በላይ ግን ትግሉ የግድ አገር ቤት መግባት አለበት። እንዲህ ህዝቡ ሲያምጽ የታጠቁ አካላት ብዙ ክፍተት ስለሚያገኙ በሽምቅ ውጊያዎች መንግስትን ወጥረው ሊይዙና ለውጡን ሊያፋጥኑ ይችላሉ። በመሰረቱ ነጻ አውጪ ታጋይ በህይወት የሚቆየውና ትግሉ እየበረታ ሰራዊቱ እየጠነከረ የሚሄደው ትግል ሲያደርግ ነው። ስልጠና ብቻ አይደለም። ስንት ሰራዊት ሲሰለጥን ነው ትግል የሚጀመረው?:: አይደለም። የነጻነት የትጥቅ ትግል የሚጀመረው በጥቂት ተዋጊዎች ነው። እነዚህ አካላት እንደ መንግስት የማይነጥፍ ባጀት የላቸውም። ህይወታቸው የሚመሰረተው ህዝቡ በሚያቀብላቸው ስንቅ፣ እየማረኩ በሚያገኙት መሳሪያ ነው። የሚማርኳቸው ወታደሮች እየሰለጠኑ ቁጥሩን እያበዙ ይሄዳሉ። ዋናው የገቢ ምንጩና ወታደራዊ አቅሙ የሚደገፈው ራሱን ትግሉን ነው። የሽምቅ ተዋጊና የነጻ ኣውጪ ዋና የገቢ ምንጭ ምርኮና የህዝ ድጋፍ ነው። ለረጅም ጊዜ ስልጠና እያደረገ ከቆየ ብዙ ሺህ እስኪሆን ከጠበቀ ወጪው ከባድ መሆኑ ብቻ ሳይሆን አይቀጥልም። የዚህ ሰራዊት ህይወት ሁል ጊዜም በትግል ውስጥ ነው። ትግል ካቆመ ኣይኖርም። ስለዚህ የታጠቁ ሃይሎች ሜጀር የሆኑ ኦፕሬሽኖች ማካሄድ ባይችሉ የሽምቅ ውጊያዎችን በማድረግ የመማረክና በሁለንተናዊ መልኩ ራስን የማብቃት ስራ መስራት ያለባቸው ይመስለኛል። የበለጠውን እነሱ ያውቃሉ።

በአሁኑ ሰአት ታጋይ ኤርትራ ገባ፣ ወጣቶች ኤርታራ ገቡ መባሉ ግማሽ ትርጉም ቢኖረውም ትልቁ ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ በረሃ የገባ ሰው ነው ትግል ገባ የሚባለው። የቴፒ ወጣቶች በጣም ጥቂት ሆነው ከግንቦት ሰባትና አርበኛች ከትህዴን የበለጠ ሲሰሩ ታይተዋል። ብዙ ስልጠና የወሰዱ፣ ትንሽ አቅም ያላቸው የታጠቁ ሃይላት ደግሞ ከዚህ የተሻለ ሊያደርጉ ህዝቡ ይጠብቃል። ስለዚህ ህዝባዊ አመጽ የመጨረሻ ውጤት እንዲያመጣ የግድ የህብረት ትግል ውስጥ መግባት አለብን። ህብረቱ በህዝቦች ደረጃና በፓርቲዎች ደረጃ መሆን አለበት። በህዝቦች መካከል የሚኖረው ትብብር በመረዳዳት (understanding each other) ላይ ያተኮረ፣ በፍቅርና በአንድነት ላይ ያተኮረ ቢሆን ጥሩ ሲሆን ፓርቲዎች ደግሞ አገሪቱን በሽግግር ጊዜ ውስጥ አሳልፎ ወደ ዴሞክራሲ ለማቅናት በሚያስችል ጠቅላላ አሳብ ላይ መስማማት ጥሩ ነው።

ጀግናው የኦሮሞ ህዝብም አሁን የጀመረውን ትግል ከፍጻሜ አድርሶ፣ የመንግስት ለውጥ መጥቶ አገራችን የተሻለ ስርዓት ውስጥ የምትገባው ህብረት በተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ህብረት በታጠቁ አካላት ዘንድ፣ ህብረት በሰፊው ህዝብ ዘንድ ሲያይል ነው። ህብረት ሲባል ሁላችን አንድ እንሁን አይደለም። አንዳንድ ከህብረት የተጣሉ ሁል ጊዜም ይኖራሉ። የኛ መከፋፈል ግን በዛ። ስለዚህ ይህን የበዛ ክፍፍል እናጥብና በተወሰነ ደረጃ ሰፋ ያለውን ማህበረሰብ ልብ የሚያሳርፍ ህብረት እንፍጠር ነው።ህብረት ህብረት ህብረት አስሬ…… የሚያሰኘን አገራችን ራሷ የህብረት አገር በመሆኗ ነው። ተፈጥሮአችን ይህ በመሆኑ ትግላችንም ሆነ ድላችን በህብረት ላይ መመስረት አለበት።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

geletawZeleke@gmail.com

The post ህብረት ህብረት ህብረት አሁንም ህብረት | ገለታው ዘለቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

የደህንነት ኃይሎች በአዳማ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ያወደመውን የእሳት አደጋ ከተቃዋሚዎች ጋር ለማያያዝ እየሰሩ መሆኑ ተጋለጠ

$
0
0

Zehabesha News
(ዘ-ሐበሻ) ከትናንት በስቲያ በአዳማ ከተማ ቀበሌ 10 (ፖስታ ቤትና በከልቻ) በሚባለው አካባቢ ስድስት የመኖሪያ ቤቶች፣ አንድ ሱቅና አንድ የከባድ ጭነት መኪና ተሳቢ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ተከትሎ ስርዓቱ አደጋውን ከተቃዋሚዎ ጋር ለማያያዝ እየሞከረ መሆኑ ተሰማ::

ፖሊስ አደጋው በደረሰበት ወቅት የአደጋውን መን ስኤ እያጣራሁ ነው በሚል ይህን ጉዳይ አድበስብሶት ካለፈ በኋላ የደህንነት ኃይሎች ቃጠሎው የደረሰበት አካባቢ በመሄድ ቭዲዮዎችን በመቅረጽ እንዲሁም የተጎዱትን ሰዎችም ለማነጋገርና አደጋው የደረሰው በተቃዋሚ ሃይሎች በንጹሃን ንብረት ላይ የተወሰደ ለማስባል እየሰሩ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አጋልጠዋል::

የደህንነት ኃይሎች የራሳቸውን ሰዎች በማዘጋጀት ንብረቱ በቃጠሎ የደረሰበት ቦታን ከጀርባ እያሳዩ ሰዎችን ቃለምልልስ እያደረጉ ሲቀርጹ መታየታቸውንም ምንጮች አጋልጠዋል::

በተለይ የኦሮሞ ተማሪዎች ሰላማዊ ጥያቄ በተለያዩ ከተሞች መቀጠሉን ተያይዞ ሕወሓት የሚመራው መንግስት ይህን ሰላማዊ ጥያቄን ከሃገርና የንጹሃንን ንብረት ከማፈራረስ ጋር በማያያዝ ለማቅረብ እየተጋ ባለበት በዚህ ወቅት እንዲህ ያሉ አደጋዎች መፈጠራቸው የሚያስገርም አይደለም የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች 4 ሚሊዮን ብር የወደመበትን ይህን አደጋ ከፖለቲካ ጋር ለማያያዝ መሞከሩ ግን ያሳፍራል ብለዋል::

በዚሁ በአዳማ ከተማ በደረሰው የ እሳት ቃጠሎ 2 ሰዎች መጎዳታቸውን መንግስታዊ ሚድያዎች መዘገባቸው አይዘነጋም::

በአደጋው የሰው ህይወት አለማለፉንና የቃጠሎው መንስኤም እየተጣራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

The post የደህንነት ኃይሎች በአዳማ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ያወደመውን የእሳት አደጋ ከተቃዋሚዎች ጋር ለማያያዝ እየሰሩ መሆኑ ተጋለጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የእጅ ቦምብ ተወረወረ | 33 ተማሪዎች ተጎድተዋል | 2 ተማሪዎች በሞት አፋፍ ላይ ናቸው

$
0
0
File Photo

File Photo

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት ማምሻውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ባለበት ወቅት በተወረወረ የእጅ ቦምብ በ33 ተማሪዎች ላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰ ተዘገበ::

የ እጅ ቦምቡን ወደ ተማሪዎቹ ላይ ማን እንደወረወረው ባይገለጽም ከሕወሃት ወታደሮች ና ቅጥረኞች ውጭ የሚያደርገው እንደሌለ ተማሪዎች በመግለጽ ላይ ናቸው:: በትናንቱ የ እጅ ቦምብ አደጋ በ33ቱም ተማሪዎች ላይ በተለያዩ የሰውነታቸው አካል ክፍል ላይ ጉዳት መድረሱን ያስታወቁት እነዚሁ የዜና ምንጮች ሁለቱ ወጣት ተማሪዎች ግን ሕይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ላይ እንዳለ ገልጸዋል::

የኦሮሞ ተማሪዎች ሰላማዊ ጥያቄ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በሁለት አሃዝ የሚቆጠሩ ወጣቶች በስ ር ዓቱ መገደላቸው የሚታወስ ነው:: በተጨማሪም ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተቃውሞ ካለማቋረጥ ከሚሰማባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ ነው::

ዘ-ሐበሻ በዚህ ተማሪዎች ላይ በተወረወረውና ለ33 ተማሪዎች አካል መጎዳት ምክንያት ስለሆነው የ እጅ ቦምብ አደጋ ተጨማሪ መረጃዎችን እያሰባሰበች ነው::

The post በጅማ ዩኒቨርሲቲ የእጅ ቦምብ ተወረወረ | 33 ተማሪዎች ተጎድተዋል | 2 ተማሪዎች በሞት አፋፍ ላይ ናቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live