Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባቀረቡት ጥሪ ኢትዮጵያ ውሰጥ ያለው የአርበኞች ግንቦት 7 መዋቅር ቅድሚያ ሰጥቶ ሊተገብራቸው የሚገቡ ስድስት ተግባራት

0
0

አርበኞች ግንቦት 7

በሚከተሉት ስድስት ነጥቦች ዙርያ የተቀናጀ ትግል እንዲካሄድ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ጥሪ ያደርጋል።

Ginbot arbegnoch1. በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች እየተካሄደ ያለው ትግል ከአሁኑ በተሻለ ተጠናክሮ እንዲቀጥል! ለዚህም በነኝህ አካባቢዎች ያለው የነኝህ ማህበረሰብ አባላት ብቻ ሳይሆን ባካባቢዎቹ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ትግሉን በስፋት እንዲቀላቀሉ እንጠይቃለን! በትግሉ ሂደትም በአሮሞና በአማራ ሕዝብ መካከል የትግል አጋርነትና የግብ ተመሳሳይነት መኖሩን ማጉላት ይገባናል። በአሁኑ ሰዓት ግፉና ስቃዩ እጅግ ለበረታበት የኦሮሞ ሕዝብ “አለንልህ፣ ከጎንህ ነን” ማለትና በርግጥም ከጎኑ ተሰልፎ መገኘት ይኖርብናል።
2. በሌሎች ክልሎች ያሉ ኢትዮጵያውያን ትግሉን በያሉበት ባስቸኳይ እንዲቀላቀሉ ጥሪ እናደርጋለን! ሌሎች ክልሎችና አካባቢዎች የሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች በየአካባቢያቸው ባሉ የአስተዳደር በደሎችና የነጻነት ፍላጎት ላይ ያተኮሩ እንዲሆን ማድረግ ይገባል፤ ሆኖም ግን ለአካባቢያዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት የሚቻለው የአገራችን የፓለቲካ ሥርዓቱ ሲለወጥ ብቻ መሆኑ በትግሉ ሂደት ማሳየት ይጠበቅብናል!
3. የኢትዮጵያ መከላከያና ፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም በያካባቢው ስርዓቱን እንዲያገለግሉ የተመለመሉ ሚሊሺያዎች ከኢትዮጵያ ህዝብ አብራክ የወጡ፤ ራሳቸውም የወያኔ አገዛዝ ሰላባ የሆኑ መሆኑን ሁሌም ማስታወስ ይገባል። አርበኞች ግንቦት 7 ይህ የኢትዮጵያ ሰራዊት በወንድሞቹ፣ እህቶቹና ወላጆቹ ላይ እንይተኩስ ይልቁንም አፈሙዙን በዚህ እኩይ ስርዓት ላይ እንዲያዞር በደተደጋጋሚ ጥሪ አድርጓል፤ አሁንም በዚህ ባስራ አንደኛው ሰዓት ይህንን ህዝባዊ ጥሪ በድጋሚ እናደርጋለን! በትግሉ ውስጥ የምትሳተፉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህንን ጥሪ በየትግሉ አደባባይ ማስተጋባት፤ በጎናችን ለምናገኘው ጎረቤታችን፤ ዘመዳችን ወይንም ጓደኛችን ለሆነ የዚህ ያፈና መዋቅር አባል ሁሉ በተደጋጋሚ መንገር አንርሳ!
4. ለኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደህዴድና ህወሓት መካከለኛና አነስተኛ ካድሬዎች እንዲሁም ዝቅተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለሆናችሁ ሁሉ! እናንተ ዛሬ ከሕዝብ ትግል ጎን ቆማችሁ ራሳቸሁንም ሆነ አገራችሁን መታደግ የምትችሉበት ወቅት መሆኑን እወቁ። ዛሬ የሕዝብን ጥሪ ሳትሰሙ ሥርዓቱን ለመታደግ ግፍ መፈፀማቸሁን ከቀጠላችሁ ነገ ዘራፊ አለቆቻቸሁ የዘረፉትን ለመብላት ሲሮጡ እናንተን የማያስጥሏችሁ መሆኑን መረዳት ለራሳችሁም ሆነ ለቤተሰባችሁ ዘለቄታዊ ጥቅም ይበጃል። አሁኑኑ ሰልፋችሁን አሳምሩ! ነገ አብሮአችሁ ከሚኖረው ህዝብ ጋር አትጣሉ! በትግሉ ውስጥ የምትሳተፉ ኢትዮጵያውያንም ከሕዝብ ትግል ጎን ለመቆም ለሚፈልጉ ለነኝህ ወገኖች መንገዱን አመቻቹላቸው!
5. ደም እየበዛ ሲሄድ ሀሞት እየመረረ እንደሚሄድ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጊዜው ሳይመሽ ቢገነዘቡት ይበጃቸዋል! የኢህአዴግ ባለሥልጣናት አገራችን መመለሻ የሌለው ቀውስ ውስጥ ከመግባቷ በፊት እና የዘረፉትን ንብረት በሰላም ለመብላት በፍጹም የማይችሉበት ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት እየሄዱበት ያለውን የእውር ድንብር መንገዳቸውን ቆም ብለው እንዲያስቡ እንመክራቸዋለን! ለሀገራችን ችግሮች ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚያሻግር ሁሉንም ያሳተፈ ድርድር አሁኑኑ ቢጀምሩ ለራሳቸውም ላገሪቱም እንደሚበጅ ልናሳስባቸው እንወዳለን! ይህን ለማድረግ ደግሞ በቅድሚያ ሰላማዊ ሰዎች መግደልና ማፈንን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ፤ የፓለቲካ እስረኞችን በሙሉ ባስቸኳይ እንዲፈቱና አፋኝ ህጎችን በመሰረዝ ለእንዲህ አይነት ሰላማዊ ሽግግር ዝግጁ መሆናቸውን በተግባር እንዲያሳዩ እንጠይቃቸዋለን!
6. በመጨረሻም በመሳሪያም ሆነ በሌላ መንገድ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚታገሉ ኃይሎች ሁሉ እንዲሰባሰቡና ይህን ስርዓት ለማንበርከክም ሆነ በይበልጥም ከዚህ ስርዓት ባሻገር የጋራ ቤታችን የሆነችውን ኢትዮጵያ አገራችንን በእውነተኛ እኩልነት፤ በፍትህና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደገና የምትታነጽበትን መንገድ በጋራ ለመተለም ባስቸኳይ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ እናደርጋለን!

The post ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባቀረቡት ጥሪ ኢትዮጵያ ውሰጥ ያለው የአርበኞች ግንቦት 7 መዋቅር ቅድሚያ ሰጥቶ ሊተገብራቸው የሚገቡ ስድስት ተግባራት appeared first on Zehabesha Amharic.


የአቡነ እንጦስ በኖርዌይ ቆይታ ሃይማኖታዊ ወይንስ ፖለቲካዊ ተልዕኮ?

0
0

” በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው” ዮሐ ምዕ 10፣1

Abune Eበለንደን በማበጣበጥ የተባረሩት አቡነ እንጦስ ኖርዌይ ምእመንን ለመከፋፈል ገብተዋል ፤አስቸካይ እርምጃ የሚጠይቅ ጉዳይ ነውና አንብበው በንቃት ተሳተፉ!!!

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ10፣ቁጥር 1 ላይ ”እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው” ዮሐ ምዕ 10፣1 ብሎ አስተምሮናል።ይህ ቃል የሚያስተምረን ትልቅ ቁም ነገር አለ።በሃይማኖታዊ ተግባር ላይ የተሰማሩ የሚመስሉ ነገር ግን ተግባራቸው የቆሙለትን የዘር ዘውግ ወይንም የንዋይ ጥማት ለማርካት ብቻ የሚፈልጉ አባት ያልሆኑ ነገር ግን በአባትነት ስም ቤተ ክርስቲያንን የሚያምሱ እንደሚነሱ ሲነግረን እነኝህ ሌባ ወንበዴ እንደሚባሉ እራሱ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል።

[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

 

Download (PDF, 261KB)

 

 

 

The post የአቡነ እንጦስ በኖርዌይ ቆይታ ሃይማኖታዊ ወይንስ ፖለቲካዊ ተልዕኮ? appeared first on Zehabesha Amharic.

በስደት የሚገኘው ሕጋዊው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለኦሮሞ ተቃዉሞ ድጋፉን ገለጸ

የዲሞክራሲ መብት መሳሳት ጭምር ነው!!! –ግርማ ሠይፉ ማሩ

0
0

girmaseifu32@yahoo.com; www.girmaseifu.blogspot.com

Girma Siefuሰሞኑን በሀገራቸን ያለው ትኩሳት በኦሮሚያ ክልል የተከሰተው በአብዛኛው ተማሪውን ያሳተፈው “እንቢ የተቀናጀ ማስተር ፕላን” በሚል የተነሳው ንቅናቄ ነው፡፡ ለዚህ ንቅናቂ መንሰዔ ናቸው በሚል የኦሮሚያ ክልል እና የፌዴራል መንግስቱ ከፍተኛ የኦህዴድ ሾሞች መግለጫ እየሰጡ ይገኛል፡፡ በእነሱ መግለጫ መሰረት ደግሞ ጥያቄው ከዚህም አልፎ የመልካም አሰተዳደር ጭምር መሆኑን አምነዋል፡፡ ሁላችንም እንደምናሰተውለው ኦህዴድ ውስጥ የሚታየው ከፍተኛ የተማረ የሰው ኃይል እጥረት ከተወሰኑ ሰዎች ውጭ ለማየት እድል አልሰጠንም፡፡ ይህ ባጠቃላይ በኢህአዴግ ውስጥ ያለ ችግር ነው፡፡ የዚህ ችግር ምንጭ ገዢው ፓርቲ የሚከተለው መስመር ለተማረ ቀርቶ ለሚያመዛዝን ሰው እንኳን ምቾት የሚሰጥ አለመሆኑ ነው፡፡ ኤርሚያ ለገሠ የሚባለው የቀድሞ ኢሕዴግ ሹም ሂሣብ ተምረህ እንዴት ኢህአዴግ ሆንክ? የሚል ጥያቄ እንደቀረበለት ሰምቻለሁ፡፡ ይህን ለዛሬ እንለፈው፡፡

ሰሞኑን በተፈጠረው ንቅናቄ ሁለት ጎራ ተፈጥሮዋል፡፡ አንዱ መንግስት ያወጣውን የተቀናጀ ፕላን እንደወረደ ደጋፊ ሲሆን ሌላው ደግሞ እንደወረደ ተቃዋሚ፡፡ ከዚህ ውጭ ሃሳብ መያዝ በሁለቱም መስመር “ፀረ ህዝብ” በሚል ያስፈርጃል፡፡ ይህ ፅንፍ ግን ፀረ ኃሳብ በመሆኑ፣ በእኔ እምነት ተቀባይነት የለውም፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የግሌን ሃሳብ ላክፍላችሁ የወደድኩት እዚህም እዚያም በፌስ ቡክ የሰጠሁትን ሃሳብ ለማጠናከር ጭምር ነው፡፡ በእኔ እምነት አሁን የተፈጠረው ችግር የኢህአዴግ እና በሽግግር ጊዜ ጀምሮ ኢህአዴግ ህገመንግሰቱን ሲያረቅ አባሪ ተባባሪ የነበሩ ቡድኖች የተከተሉት የፖለቲካ መስመር ችግር ውጤት ነው፡፡ ማለትም አሁን መንግሰት እተገብረዋለሁ የሚለው ዕቅድ ለማሳረፍ የሚፈልግበት የመሬት ፖሊስ አሁን እየተቃወመ የሚገኘው ኦነግ በዋነኝነት የተሳተፈበት የሽግግር ወቅት ሃሣብ ነው፡፡ የመድረክ አባል ድርጅቶች በሙሉ (የቀድሞ አንድነትን ሳይጨምር) የዚህ ፖሊሲ ደጋፊዎች ናቸው፡፡ አሁንም በፊት አውራሪነት የሚቃወመው የዶክተር መረራ ጉዲና ኦፌኮ ጭምር መሬት የመንግሰት መሆኑን ከምር ይደግፋል፡፡ በቅንፍ ውስጥ ኦሮሞው መሬት እንጂ ገንዘብ ስለሌለው እንዳይፈናቀል በሚል የተሳሳተ ታሳቢ ማለት ነው፡፡

የኦሮሚያ ርዕሰ መሰተዳድር እንዲሁም አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ በተከታታይ በሰጡት መግለጫ ህዝበ ካልተሰማማ “ይህ የተቀናጀ ማስተር ፕላን” ተግባራዊ አይሆንም የሚል ቃል ሰጥተዋል፡፡ ይህን ቃል ሲሰጡ በተለይ ለአባዱላ ጋዜጠኛው ተገዳችሁ ነው ወይ? ስትላቸው አዎ የመረጠን ህዝብ ቢያስገድደን ምን አለበት ብለው መልስ ሰጥተዋል፡፡ ይህን መልስ ወድጄዋለሁ፡፡ በፌስ ቡንክ ቋንቋ ላይክ አድርጌዋለሁ፡፡ ከአሁን በኋላ ታዲያ ይህን ማሰገደድ በመቀጠል አንድ ደረጃ ከፍ በማድረግ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ የኦሮሚያ ልጆች ገበሬ ሆነው እንዳይቀሩ፤ ከከተሜነት ትሩፋት እንዲቋደሱ መሬታቸው አሁን ከሚባለው የመጠቀም መብት ከፍ እንዲል የመሸጥና መለወጥ መብት እንዲጨምር የፖሊሲ/ህገ መንግሰታዊ ማሻሻያ/ እንዲደረግ መጠየቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ በለገጣፎ አካባቢ አንድ ካሬ ሜትር ቦታ ከስምንት ሺ ብር በላይ መንግሰት መሸጡን ሰምተናል፤ ሰለዚህ መንግሰት ቢያንስ ከገበሬው በአንድ ሺ ብር ለመግዛት መዘጋጀት ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ ካልሆነም መንግሰት ማስተር ፕላኑን ሰርቶ መሰረተ ልማቱን ይዘርጋ ለማልምታ የሚፈልግ ደግሞ ከገበሬው ጋር ተደራድሮ ይግዛ፡፡ መቼም ይህቺ የኒዎ ሊብራል አስተሳስብ የምትዋጥ አትመስለኝም፡፡ ጉዳዩ ግን ይህው ነው፡፡ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የሚቃወሙ ወገኖች በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ አርሶ አደሮች ባሉበት ሁኔታ እንዲቆዮ ከሆነ በእርግጥ የአስተሳሰብ በሸታ ያለበት መሆን አለበት፡፡

ሌላው  መነሳት ያለበት ጉዳይ እና ለገዢው ፓርቲም ግልፅ መደረግ ያለበት “ውይይት ተደርጎ ህዝቡ ካመነ ብቻ ነው የሚተገበረው” የሚለው የርዕሰ መስተዳድሩ ፈራ ተባ እያሉ የሰጡት መግለጫ እና አፈ ጉባዔው በተመሳሳይ ፈራ ተባ ሲሉ የገለፁት ጉዳይ ነው፡፡ በኢቲቪ የርዕሰ መሰተዳድሩን መግለጫ ተከትሎ በተያያዘ ዜና በሚል የኢህአዴግ ዝቅተኛ ሹሞች “ይህ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ለአርሶ አደሩ ጠቃሚ ነው” በሚል መንፈስ በተቃውሞ የቆሙ ፀረ -ሰለም እና ፀረ-ህዝብ መሆናቸውን ሲገልፁ ነበር፡፡ ኦህዴድ/ኢህአዴግ ከዚህ በፊት ባለው ታሪካቸው አቶ አባዱላ እንደሚሉት አሳምነው ሳይሆን አስገድደው በመስራት ነው የሚታወቁት፡፡ አስገድደው እንደተመረጡም ረስተውት በተደጋጋሚ የመረጠን ህዝብ ሲሉ ሰው ይታዘበናል ማለት የተዉ ይመስላል፡፡ ሰለዚህ ህዝቡን ለማሳማን ኢህአዴግ ያመነበትን ማስተር ፕላን ይጠቅምሃል ተቀብል ሳይሆን፤ ውይይት ሲባል ለማሳመን ብቻ ሳይሆን ለማመንም ተዘጋጅቶ መሄድን ይጠይቃል፡፡ በነገራችን ላይ በብዙ መስፈርት ጠቃሚ መሆኑ ግንዛቢ ኖሮ ቢሆን እንኳን በማነኛውም ተራ ምክንያት አልቀበልም ካለ ይህን ለመቀበል ኢህአዴግ መዘጋጀት ያስፈልገዋል፡፡ ዲሞክራሲ ማለት መሳሳት ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ የተቀናጀ ማሰተር ፕላኑ በግልፅ ባልታወቀ ይዘቱ ጠቃሚ መሆኑ ቢታመን እንኳን አሁን ባለው የመሬት ፖሊሲ ቢተገበር የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርገው ከመሬቱ ከሚፈናቀለው አርሶ አደር ይልቅ ሌላውን ክፍል ነው የሚል አስተሳሰብ በፍፁም ውድቅ ሊደረግ የሚችል ምልከታ አይደለም፡፡ ለዚህም ነው አሁን የተፈጠረው ችግር መሰረታዊው መንሰዔው ህገ መንግሰታዊ መሰረት የያዘው የዜጎችን ንብረት ማፍራት መብት የሚፃረራ የመሬት ባለቤትነት መብት ነው የምለው፡፡ ሰለዚህ ትግላችን መሆን ያለበት ዜጎችን ባለሀገር የሚያደርግ የመሬት ፖሊስ እንዲኖረን በሚያስችል ሁኔታ ህገ መንግሰታዊ ማሻሻያ መጠየቅ ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ በዚሁ ጥያቄ መነሻነት አብዮት እንዲነሳ የሚፈልጉ መኖራቸው አንዱ የሚታወቅ ነገር ነው፡፡ ይህ መንግሰት በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እየተሳነው መሆኑን እረዳለሁ፡፡ ይህ ማለት ግን ኢህአድጋዊያንን ሊጠርግ የሚመጣ አብዮት ሰለማዊውን ዜጋ እንደማይበላ ማረጋገጫ ሰለሌለኝ አብዮትን አልወዳትም፡፡ በቅርቡ የታተመውን የቀድሞ የደርግ ከፍተኛ ሹም የነበሩት ፍስሃ ደስታ “አብዮቱና ትዝታዬ” በሚል የፃፉትን መፅሃፍ እያነበብኩ አብዮቱ እንዴት አድርጎ ዜጎችን ሲቀረጥፍ እንደነበር ሳነብ ዳግም አብዮት የሚያሰኝ ነገር አልታየኝም፡፡ ገዢው ፓርቲ መሪዎች ይህን የሚያክል ጥራዝ ለማንበብ ጊዜም ሆነ ሞራል ባይኖራቸው እንኳን የዚህን መፅሃፍ መጨረሻ ክፍል ማጠቃለያውን አንብበው ለብሔራዊ ዕርቅ ግንባር ቀደም ሚና እንዲጫወቱ እፈልጋለሁ፡፡ እዚሁ መፅኃፍ ላይ አንባገነኑ መንግሰቱ የሚሰጠወን መክር አልሰማ ብሎ በመጨረሻ ደቂቃ ላይ ቢወራጭም መፍትሔ ሊያመጣ እንዳልቻልም፡፡ ኢህአዴግም እድሉን ቢጠቀምበት ጥሩ ይመስለኛል፡፡

በሀገራችን ያሉ ተቃዋሚዎች አብዛኞቹ በሚያሳዝን ሁኔታ የሚገኙ መሆናቸው የሚያጋልጠው የሰሞኑን ክስተት አስመልክተው የሚሰጡት መግለጫ በፍፁም ፓርቲያቸው ቆሜለታለሁ ከሚለው መርዕ ጋር የሚሄድ አለመሆኑ ነው፡፡ እነዚህን ፓርቲዎች ይህን አስታካው ህዝቡን ወደ ለውጥ እንዲመሩ አንድ አንድ ግለሰቦች/ቡድኖች ጥሪ እስከ ማቅረብ ደርሰዋል፡፡ እንኳን ሊመሩ መሪ የሚያስፈልጋቸው ደንባሮች እንደሆኑ ግን መግንዘብ ያልቻሉት ጥሪ አቅራቢዎቹ ናቸው፡፡ ለማነኛውም አብዮት እንደ ቱኒዚያው ቡሃዚዝ አይነቱ በሚጭሩት ትንሽ ጉዳይ ነገር ግን ሁሉም በሚሳተፍበት ሁኔታ ሊነሳ እንደሚችል ባምንም፤ አሁን ባለው ያልተቀናጀ ሁኔታ ባልጠራ መንገድ እብዮት መጥራት ሀገርን አደጋ ላይ ሊጥል ይቸላል የሚል የግል እምነት አለኝ፡፡ ይህ ግን በፍፁም አንባገነኖችን እሺ ብለን  እንገዛ ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ የሰሞኑ ጥያቄ በመሰረታዊነት በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ በኦሮሚያ አርሶ አደሮች መፈናቀል የለባቸውም የሚል ነው፡፡ በተመሳሳይ በከተማ ያለም ነዋሪ ተገቢ ካሳ ሳይከፈለው በልማት ሰም መነሳት የለበትም ማለት ይኖርብናል፡፡ በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች በከተማ ማሰፋፋት ስም እየተነሱ ያሉ ሰዎች ተገቢ ካሳ ሊያገኙ ይገባል ማለት ይኖርብናል፡፡ በዚህ መንፈስ ጥያቄው ከተነሳ በከተማም በገጠርም ያለነው በጋራ ለመቆም እድል ይስጠናል፡፡

በመጨረሻ በመላው ሀገሪቱ ጥያቄያቸውን በተለያየ መንገድ ያቀረቡ ወጣቶች ህይወት በአንባገነኖች ጥይት እንዲቀሰፍ እርምጃ የወሰደው መንግሰት ከሃያ ዓመት በኋላም ግጭቶችን በጉልበት እንጂ በሰላማዊ መንገድ ለመቆጣጠር አቅም እንደሌለው ማሳያ ነው፡፡ እነዚህ ግድያዎች ደግሞ በፍፁም የሚረሱና የሚተዉ አይደሉም፡፡ የሞቱት ሁሉ በኢትዮጵያ ለለውጥ የተሰዉ ሰማዕታት ናቸው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ገዢው ፓርቲና መንግሰት ዜጎች ጥያቄ የማቅረብ መብታቸውን በመጋፋት በቁጥጥር ስር ውሎዋል የሚለው ቀረርቶ እና በምናብ ከሚስላቸው ፀረ-ህዝብና ፀረ-ሰላም ጋር የሚፈጥረው ምናባዊ ቁርኝት ድክመቱን ከማጋለጥ ውጭ ማንንም ግርታ ውስጥ እንደማይከት ማወቅ አለበት፡፡ አሁን በሚዲያ የምናያቸው የህዝብ አደረጃጀት ብሎ የሚሰበሰባቸው የፎረም አባለት የሚነግሩትን ከመስማት መታቀብ እና ትክክለኛውን የችግር ምንጭ ተቃዋሚ ከሚላቸው ቢያዳምጥ ይሻለዋል፡፡

ቸር ይግጠመን!!

The post የዲሞክራሲ መብት መሳሳት ጭምር ነው!!! – ግርማ ሠይፉ ማሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

በቅርቡ የምንሰማው ዜና በጥምር ተቀናጅተው ኦነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ወደፊት እየገሰገሱ ወያኔን መቆሚያ እያሳጡት ነው የሚለው ይሆናል።   –መርጋ ደጀኔ (ከኖርዌይ)

0
0

Tenesuምከረው ምከረው እንቢ ካለ መከራ ይምክረው እንደሚሉት አበው 25 ዓመት ሙሉ ሲመከር ሲለመን ሲዘከር ምክርን እንደ ስድብ ልመናን እንደ ፍራቻ ዝክርን እንደ ማታለል አድርጎ በመቁጠር ዝም በሉ ዝም ካላላችሁ ዝም አደርጋችሃለሁ ረግጫችሁ እገዛችኋል አማራና ኦሮሞን አጋጭቶ በመሃል እኔ ስልጣኔን እያደላደልኩኝ 100 ዓመት እገዛለሁ ብሎ የቀየሰው ስልት ዛሬ በእርግጠኝነት መናገር ወደሚቻልበት ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ  በመግባቱ ታውቋል። ኦነግና  አርበኞች ግንቦት 7 የተቀናጀ ድምጽ አሰምተውን ኦነግ በአሶሳ ፤በሀረር ፤በቦረና ወያኔን እየደመሰሰ ወደ ፊት እየመጣ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 በጎንደር፤ በጎጃም ፤በደቦብ በድሬደዋና በመላው ኢትዮጵያ ብሎም በአዲስ አበባ ትግሉን በማቀጣጠል ወያኔን መቆሚያና መቀመጫ እያሳጡት ነው የሚለውን ዜና እንሰማለን።

ማንም ታጋይ መኖሪያውን በረሃ ላይ እንዲሆን የሚፈልግ የለም፡ ማንም ታጋይ ከሚወደው ቤተሰቡ እና ህዝቡ ተነጥሎ በበረሃ ላይ ከባዱን ኑሮ የሚፈቅድ ያለ አይመስለንም ፡ ማንም ታጋይ በአገሩና በህዝቡ ላይ ጥፋትና ጥቃት ሲፈጸም እያየ ዝም የሚል የለም በረሃ ወርደው አገርን ነጻ ለማውጣት የህብንም ጭቆናና መከራ  ደምሦሶ ለማጥፋት ብረት ያነሱት አርበኞች ግንቦት 7 እና ኦነግ አንድ የሆኑበትን የጋራ መግለጫ አውጥቶተው እንደሚቀሳቅሱ ተስፋ አደርጋለሁ።

ህዝብን ነጻ ለማውጣት ለህዝብ እኩልነት ለማምጣት ለሚያስቡ እና የሚታገል ታጋይ ከዚህ የበለጠ ትልቅ አጋጣሚ ከወድየትም አይገኝም ።

እናም ታጋዮቻችን አንዱን ጥለን ሌላ ችግር ሊፈጥር የሚችረስ ውጭ እታገልለታለው ለሚለው ህዝብ ደግሞ የበለጠ መከራና ስቃይን እንዲገፋ የማድረግ መብት ለበዳዩ ወያኔ መፍቀድ እንዳይሆንብን አሁን ሰዓት ላይ ነንና በዜና አውታር በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ የኢትዮጵያን ህዝብ ከወያኔ ነጻ ለማውጣት ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር የጋራ ጥምረት ፈጥረው በወያኔ ላይ የተቀናጀ ጥቃት ለመፈጸም እና ወያኔን ህዝባችን ላይ የበለጠ ጥፋትና ጥቃት ሳያደርስ ለምንወደውና ለምንታገልለት ህዝባችን ለመድረስ ደቂቃዋና ሰዓቷ አሁን ነውና ጥምረታችሁን በይፋ ለህዝብ ንገሩና ወያኔን መግቢያና መውጫ ምድረ ካድሬን ደግሞ የሚናገረውን እንዲያጣ በማድረግ ህዝባችንን እየገደለ እና ንብረታቸውን እያቃጠለ አማራውን ይሄንን ያደረገብህ ኦነግ ነው ብለው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እንዲነሳ የኦሮሞ ህዝብ እየገደለ እና ንብረቱንም እያቃጠለ ያለውን አማራ ነው ብለው የኦሮሞን ህዝብ አማራው ላይ እያነሳሳ የከሰረ 25 ዓመት ሲሰራበት የነበረውን ህዝብን ከህዝብ እያጣሉና እያፋጀ ስልጣኑን የማራዘም ስራ ሁሉም ህብረተሰብ በይፋ እንዲያውቀው ፖለቲካውን በበላይ የሚመሩት አካሎች ትልቅ ድርሻ አላቸው በተለይም ደግሞ ብረት አንስተው ስለህዝባቸው እና ስለ ሃገራቸው የሚታገሉት የፖለቲካ አመራሮች ለህዝቡ ነጻነት የናንተንም የበረሃ ላይ ትግል በአጭር ግዜ ወደ አሸናፊነት የሚያመጣችሁ አንድነት ሲኖራቸው ነውና የአንድነት ዜናዎችን በቅርቡ እንደምታሰሙን ተስፋ አለኝ።

ወያኔ አሁን እየተንቀሳቀሰ ያለው በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ያሉትን በተለይ ሁለቱን ብሄሮች የማጣላት ስራን ለመስራት ማንንም ሳያሳትፉ የሕወአት ሰዎች ብቻ ተሰብስበው መመሪያ አስተላልፈዋል። ከተላለፉት መመሪያ ውስጥ አደገኛውና በህዝባችን ጥፋት ላይ ያነጣጠረው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ አማራ ያልሆኑ፡ ነገር ግን አማርኛ ተናጋሪዎችን በማስፈራራት አማረነታቸውን እየገለጹ  በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጥላቻ እንዳላቸው እየተናገሩ ህዝቡን እንዲገሉ በማድረግ እና  የኦሮሞ ህዝብ በአማራው ላይ እንዲነሳ ..በአማራው ክልል ውስጥ የኦሮሞኛ ቃንቃ የሚናገሩ ነገር ግን ኦሮሞ ያልሆኑትን የመከላከያ ሰራዊት በማሰለፍ የአማራን ህዝብ በመጨፍጨፍ አማራን እንደሚጠሉ በመንገር በኦሮሞ ህዝብ ላይ እንዲነሱ የማድረግ ስራ ሰርተው ህዝባችንን ለመጨፍጨፍ ወያኔ የመጨረሻውን የመፍጨርጨር የሞት ሽረት ትግል ለማድረግ ቆርጦ ተነስታል።

እዚህ ላይ ወያኔ እኔ ህዝብን በህዝብ የኦሮሞ ህዝብ እና የአማራን ህዝብ አጣልቶ እርስ በርስ ሲጨፋጨፉ ያኔ የኔ ስልጣን ለሁል ግዜ ይጸናል ሁለቱ ካልተጣሉ ግና ስልጣኔ ያበቃል ብሎ ከመነሻው ሲሰራ የነበረው የወያኔ ሴራ በመጨረሻዋ ህዝባችንን አጣልቶ እና አፋጅቶ አላማው እንዳይሳካለት የፖለቲካ አመራሮች በዚህ ሰዓት ግልጽ መልዕክት መግለጫ ማውጣት አለባቸው ኦነግና አርበኞች ግንቦት 7 ተዋህደው ወያኔን ለመደምሰስ አንድነታቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ አስታውቁ  በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሁሉም አንድ በመሆን ገዢው ፓርቲ በህዝብ መግለጫ ሰው ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድ መሆናችን ማንኛውም ህዝብ የትኛውም ህዝብ ጠላት ሳይሆን ጠላታቸው ወያኔ ስለሆነ ሁሉም በህብረት ወያኔን ለእታገል በህብረት እንነሳ የሚል መልዕክት በማስተላለፍ ህዝባችንን የትግል ችቦ በመለኮስ ሁሉም ጋር እንዲዳረስ ማድረግ በፖለቲካው አመራር ላይ ያሉት ሰዎች ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ ይሄ ሲሆን ወያኔ ሊሰራ ያቀዳቸውን እቅዶች ሁሉ በህዝባችን መሃል ለስልጣን ብሎ የመጠፋፋት ስራን ሊሰራ ያሰበውን ዜሮ በማስገባት ሁሉም ህዝብ ሃሳቡን ወደ አንድ አቅጣጫ በማድረግ ወያኔን በአጭር ግዜ ውስት ሆ ብሎ በመነሳት ድል ማምጣት ይቻላል።

ትግሉ ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ ወደ አንድነት መጥቶ ወያኔን መቆሚያ  እና መቀመጫ ማሳጣት ያለብን ግዜ ላይ ነን። ትላንትና ከፋፍዬአቸዋለው በትኛቸዋለው የቤት ስራዬንም በደንብ ሰርቼአለው ብሎ  ሲኩራራ የነበረው ከእንግዲህ ወዲያ ሁሉም ስለተከፋፈሉ እየነጣጠልክ ማጥፋት ስለምችል ስልጣኔን ማስቀጠል እችላለው በማለት ሰይጣናዊ ስራን እየሰራን የነበረው ወያኔ ዛሬ በሁሉም አቅጣጫ አልተለያየንም ሁላችንም አንድ ነን በማለት አንድነትን እየፈጠሩ ሲመጡ ሲያያቸው ግራ  በመጋባት ከላይ እስከ ታች በወያኔ መንደር ትርምስ ተፈጥሯል። የሞት ሽረት ትግልም እያደረጉ ይገኛሉ በየግዜው ሕወአት ለብቻቸው በድብቅ እየተሰባሰቡ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ቢሰበሰቡም ያለ ምንም ውጤት ይለያያሉ። ከሌላውም ግዜ በከፋ እንደውም እስከ መጠፋፋት የሚያደርሳቸው መከፋፈል በመካከላቸው እንደተከሰተ ከውስጣቸው ባሉት አካላት በሰፊው እየተነገረ  ነው።

ብረት ሳያነሱ የኢትዮጵያ ፖለቲካን ትግሉን በከፍተኛ ሁኔታ ወያኔን በመታገል ላይ ያሉት ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ ወያኔ እየሰራ ያለውን መከፋፈል ሰብረውት ከአሁን በኋላ  በኢትዮጵያ  ጉዳይ ተነጣጥሎ  ለወያኔ መመቸት የለም ሁላችን አንድ ነን ስለ አንድ ኢትዮጵያ በአንድነት ሆነን ለመታገል ከመቼውም ግዜ  በላይ ተቀናጅተን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ግፍና በደል እየሰራ ያለውን ወያኔን ለመታገል ውህደት መፍጠራቸው ብራቮ ኢንጅነር ይላቃል ጌትነት ብራቮ ዶክተር መራራ ጉዲና ብራቮ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በማለት በዚህ ወሳኝ ሰአት ወያኔ  ኢትዮጵያን  ሊያጠፋት የመጣ ኃይል መሆኑን አውቀው ሁሉም ኢትዮጵያዊ የአንድነቱን ድምጽ በመስማት በአንድነት ህዝባችን ጫንቃ ላይ ያለውን ወያኔ ላይ የምንነሳበት ሰዓት አሁን መሆኑን አሳይተውናል።

ሌላው የቀድሞ የኦነግ መስራች የሁኑት አሁን ደግሞ የኦዴግ አመራር የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታ በኢሳት ቴሌቭዝን ቀርበው ያቀረቡት ንግግር ሳዳምጣቸው ነበር። ፖለቲካ ማለት ከግዜው ጋር የሚቀያየር እንደሆነ እና የህዝብን ፍላጎት ያካተተ ትግል ወደ አሸናፊነት ብሎም ወደ ፍጹም ነጻነት የሚያስጉዝ መሆኑን ተረድተው ትግላችን ኢትዮጵያ በአንድነት የሚያስጉዝ ህዝቡንም ለኢትዮጵያ ሰላም እና  ነጻነት በአንድነት የሚያስነሳ  አላማ  ያዘለ  በመሆኑ ፖለቲካውን በአግባቡ የተረዱት አቶ  ሌንጮ ለታ  ትክክለኛ የፖለቲካ  ሰው እንደሆኑ አስመስክረዋል። ትግሉ የዘር ጉዳይ አይደለም ትግሉ የሃይማኖት ጉዳይ አይደለም ትግሉ የኢትዮጵያን የማዳን ትግል ነው። ለኢትዮጵያ  በጋራ ስንታገል ዘር ሃይማኖት ባህል የመሳሰሉት በመሉ በአንድነት ይከበራሉ። አንድነት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ  ወደ አሸናፊነት እና  ዲሞክራሳዊ መንግስት መመስረት ነው።

በመጨረሻም በረሃ ወርዳችሁ በድልና በክብር ወደምትወዱት ህዝብ በአጭር ግዜ በመምጣት የሚቻለው ኦነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 የአንድነት ድምጻችሁን አሰምታችሁ ለህዝባችን አሳውቁን በውጭ እና በአገር ቤት የምትኖሩ ሙሁራኑ እና የፖለቲካ ሰዎች እናንተንም በአንድነት የሚያስተሳስራችሁን አዋጅ አውጃችሁ ለህዝባችን ንገሩት ያኔ ወያኔ ውሃ ውስጥ የገባች አይጥ ይሆናል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝቦች !!

መርጋ ደጀኔ (ከኖርዌይ)

20.12. 2015

Email- mergadejene50th@gmail.com

The post በቅርቡ የምንሰማው ዜና በጥምር ተቀናጅተው ኦነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ወደፊት እየገሰገሱ ወያኔን መቆሚያ እያሳጡት ነው የሚለው ይሆናል።   – መርጋ ደጀኔ (ከኖርዌይ) appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: ኦነግ የሕዝቡን የለውጥ ጥያቄ የማይመልስ ከወያኔ ጋር የሚደረግ የጓዳ ድርድር ጥያቄ እንደማይቀበል ገለጸ ፣ሕዝቡ በወያኔ ሴራ ሳይከፋፈል ለነጻነቱ በጋራ መቆሙምን እንዲቀጥል ጠየቀ፣አና ጎሜዝ የወያኔ ባለስልጣናት ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋርና ከግንቦት ሰባት መሪዎች ጋር እንዳስታርቃቸው ጠይቀውኝ ነበር ሲሉ ገለጹ

0
0

Habtamu Asefa
የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 10 ቀን 2008 ፕሮግራም

የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቃሲም አባነሻ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን የቀድሞው የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር ሊቀመንበር በወቅቱ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

አቶ ንጉስ ሰለሞን በቺካጎ የ24/7 የታክሲ ኩባንያ ባለቤትና ዋና ስራ አስፈጻሚ ስለታክሲ ሊዝ አሰራር ተጠይቀው ከሰጡት ምላሽ (ሙሉውን ያድምጡት)

በብሩንዲ ውስጥ ያንጃበበው የእርሰበርሰ ግጭት ስጋት መንሴዎቹ እና የዓለማቀፉ ማህበረሰብ ሰሞነኛ ምላሽ ሲቃኝ (ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ኦነግ የሕዝቡን የለውጥ ጥያቄ የማይመልስ ከወያኔ ጋር የሚደረግ የጓዳ ድርድር ጥያቄ እንደማይቀበል ገለጸ

ሕዝቡ በወያኔ ሴራ ሳይከፋፈል ለነጻነቱ በጋራ መቆሙም እንዲቀጥል ጠየቀ

አና ጎሜዝ የወያኔ ባለስልጣናት ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋርና ከግንቦት ሰባት መሪዎች ጋር እንዳስታርቃቸው ጠይቀውኝ ነበር ሲሉ ገለጹ

በኦሮሚያ ክልል በርካታ ንጹሃን የተገደሉበትን ጭፍጨፋ የአገዛዙ ሸሪኮችን ጭምር አስቆጣ

ሐርማን ኮህን አገዛዙ በሰላማዊ በዜጎች ላይ እየወሰደ ያለውን የጭካኔ እርምጃ ተቃወሙ

ሰሞኑን በጎንደር የመከላከያ ሰራዊቱ በተቃዋሚው ሕዝብ ላይ ጦርነት የገጠመው ከግብጽ ሰራዊት ጋር ተዋጉ በሚል ማታለያ መሆኑን ቁስለኛ ወታደር ገለጸ

በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ተቃውሞውን በተመሳሳይ ሰዓት በመጮህ እንዲገልጽ ተጠየቀ

የሰራዊቱ አባላት ድንበር ጠብቁ ብላችሁ ቤተሰቦቻችንን ትገላላችሁ ሉ መጠየቃቸው ተነገረ

ጥያቄ በመጠየቃቸውታፍነው የተወሰዱ አሉ ተባለ

በግብጽ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጋራ አገዛዙ በኦሮሚያ በወገኖቻቸው ላይ የፈጸመውን ግድያ በተቃውሞ ሰልፍ አወገዙ

ኤርትራዊው ጥገኝነት ጠያቂ ወጣት ጣሊያን ውስጥ ከሆስፒታል ፎቅ ተንጠልጥሎ ለመውረድ ሲሞክር ሕይወቱ አለፈች

በባህር ዳር እስር ቤት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በእግር ብረት ታስረው እንደሚገኙ ታወቀ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: ኦነግ የሕዝቡን የለውጥ ጥያቄ የማይመልስ ከወያኔ ጋር የሚደረግ የጓዳ ድርድር ጥያቄ እንደማይቀበል ገለጸ ፣ሕዝቡ በወያኔ ሴራ ሳይከፋፈል ለነጻነቱ በጋራ መቆሙምን እንዲቀጥል ጠየቀ፣አና ጎሜዝ የወያኔ ባለስልጣናት ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋርና ከግንቦት ሰባት መሪዎች ጋር እንዳስታርቃቸው ጠይቀውኝ ነበር ሲሉ ገለጹ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ አዲስ አበባ ላይ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ

0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) ሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አዲስ አበባ ላይ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው የሚታወስ ሲሆን እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም በጋራ ሰልፍ መጥራታቸውን አቶ ነገሰ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

File Photo

File Photo


ሰማያዊ ፓርቲና መድረክ የጠሩት ሰልፍ በዋነኛነት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ መንግስት እየወሰደው ያለውን እርምጃ፤ እንዲሁም መንግስት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ያቀደውን መሬቱ እንዳይሰጥ ለመቃወም ያለመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰልፉ ላይ በሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ መንግስት እየወሰደው ያለውን እፈና እና እርጃዎቸ እንደሚያወግዙ ምክትል ሊቀመንበሩ ተገልፆአል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በጋራ የሚያደርጉት ሰልፍ መነሻውን ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ አድርጎ፣ በቸርቺል አደባባይ የሚያልፍ ሲሆን መዳረሻው ኢትዮ-ኩባ አደባባይ መሆኑን ታውቋል፡፡ መንግስት እየወሰዳቸው ባሉ የተሳሳቱ እርምጃዎች ሀገራችን አጣብቂኝ ውስጥ መሆኗን የገለፁት አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ሀገራችን ካለችበት ችግር ለማውጣት ኢትዮጵያውያን በጋራ እንዲቆሙና በሰልፉም እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ሰልፉ እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ ላይ እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል፡፡

The post ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ አዲስ አበባ ላይ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ብሩህ ኢትዮጵያ ንቅናቄ መግለጫ አወጣ –“የመሬት ነጠቃና ሕዝብን ከሕዝብ ማጋጨት ይቁም”


በሰሜን በጌምድር (ጎንደር) ወልቃይት ፀገዴ፣ ፀለምት በአማራው ላይ ተስፋፊው ተሓህት/ህወሓት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጄል (ገብረመድህን አርአያ)

0
0

ይህ ታሪካዊ መረጃ በተቀነባበረ መልኩ የሚጀምረው ገና ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ሲፈጠር ጀምሮ አስቀድሞ ለማጥፋት ያነጣጠረው በአማራው ህዝብ ላይ እንደሆነ በማስገንዘብ ነው።

(ገብረመድህን አረአያ ከፐርዝ አውስትራሊያ)

(ገብረመድህን አረአያ ከፐርዝ አውስትራሊያ)


ከዚህ በመነሳት የተሓህት ፕሮግራም ገና ከ1967 ጀምሮ የረቀቀው በዲማ ኮንፈረንስ በየካቲት ወር 1968 ከ150 ያነሱ የተሓህት ታጋዮችን በማሰባሰብ ሕጋዊ ሆነ ተብሎ ቢነገርም፣ ሁሉም ታጋዮች ግን አልተቀበሉትም። በመጥፎ መልኩ የተዘጋጀውና አማራውን በማውገዝና ጠላት ብሎ የፈረጀ ነው። በኢትዮጵያና በህዝቧ፣ 1ኛ፣ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አውዳሚ፣ 2ኛ፣ አንድነቱን ጠብቆ ለዘመናት አብሮ የኖረውን የኢትዮጵያ ህዝብ በጎሳ በዘር ለመበታተን ተደምሮና ተቀንሶ የተቀነባበረ አደገኛ ፕሮግራም በማለት አውግዘውት ነበር። ከነዚህ ካወገዙት መካከል ለምሳሌ ለመጥቀስ፤ አስገደ ገብረሥላሴ፣ ካህሳይ በርሄ (ዶ/ር ግንጽል)፣ ተሾመ ጉዶ፣ ሲሆኑ እነዚህ በህይወት ያሉ ሲሆን፣ እቁባዝጊ በየነ፣ አሰፋ ገብረዋእድ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ ዘርኡ ገሰሰ (አጋአዚ) ገሰሰው አየለ፣ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ፣ ዘወንጀል በየነ፣ መሃረ ተክሌ ወዘተ እነዚህ ፕሮግራሙን በጠነከረ አቋም ስለተቃወሙ የተገደሉ ናቸው።

Read Full Story in PDF

The post በሰሜን በጌምድር (ጎንደር) ወልቃይት ፀገዴ፣ ፀለምት በአማራው ላይ ተስፋፊው ተሓህት/ህወሓት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጄል (ገብረመድህን አርአያ) appeared first on Zehabesha Amharic.

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአርማጭሆ ሙሴ ባምብ ከተማ ውርደትን ተከናንበው ተመለሱ

0
0

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) “አማራ ክልል” እየተባለ የሚጠራው ሹም እና የህወሓት ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው ገዱ አንዳርጋቸው በዛሬው ዕለት ወደ አርማጭሆ ሙሴ ባምብ ከተማ አምርቶ የአካባቢውን ህዝብ ለማወያየት ሞክሮ ያለምንም ውጤት በውርደት ተመለሰ፡፡

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው


የህወሓቱ አሽከር ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ጠዋት በከፍተኛ ወታደራዊ አጀብ ከባህር ዳር አርማጭሆ ሙሴ ባምብ ገብቶ የአካባቢውን ህዝብ በሦስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለማነጋገር ሞክሯል፡፡
በስብሰባው ላይ የተነሱት ሦስቱ የመወያያ አጀንዳዎች፦
1. በጎንደር የተከሰተው የእርስበርስ ግጭት
2. የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ እና
3. የኢትዮ-ሱዳን ድንበርን በሚመለከት ናቸው፡፡
ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች የብአዴን ካድሬዎች በመሩት ስብሰባ ላይ የተገኘው የአርማጭሆ ህዝብ በጎንደር የተከሰተውን የእርስበርስ ግጭት ህወሓት እንደጠነሰሰው እና የእሱ ዲቃላ የሆነው ብአዴን እጁ እንዳለበት ገልጿል፡፡ ብአዴን የአህያ ባል ሆኖ ህወሓት ለተባለ የቀን ጅብ አሳልፎ ሰጥቶ የወልቃይትን ህዝብ እያስበላው እንደሚገኝም ህዝቡ ጨምሮ ተናገሯል፡፡
ድንበሩን በሚመለከት ደግሞ
“እናንተም ሆናችሁ ህወሓት የአገሪቱን ዳር ድንበር ማስከበር ስላልቻላችሁ፣ ህዝቡንም መምራት ስለተሳናችሁ ስልጣናችሁን ልቀቁ አርበኞች ግንቦት 7 ይምራን…” በማለት ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ በአንድነት ጠይቋል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ለሱዳን ተቆርሳ የምትሰጥ አንድ ጋት መሬት እንኳን ብትኖር ህዝቡ ከውስጥም ከውጭም በአንድነት ለመዋጋት ቆርጦ እንደተነሳና ህወሓት ከባድ ዋጋ እንደሚከፍል ማስጠንቀቂያ ጭምር አስተላልፏል፤ ጀግናው የአርማጭሆ ህዝብ፡፡
በአጠቃላይ በአርማጭሆ ሙሴ ባምብ በህወሓት አሽከር ገዱ አንዳርካቸው እና በህዝቡ መካከል በዛሬው ዕለት የተካሄደው ውይይት ከፍተኛ ንትርክና እሰጥ አገባ እንዲሁም የከረረ ቁጣና ተቃውሞ የተሞላበት ሲሆን ከቀኑ 9፡30 ላይ ያለምንም ውጤት በአገዛዙ ውርደት የተላበሰ ሽንፈት ብቻ ተቋጭቷል፡፡

The post አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአርማጭሆ ሙሴ ባምብ ከተማ ውርደትን ተከናንበው ተመለሱ appeared first on Zehabesha Amharic.

ዛሬ ምን ማድረግ አለብን ? – 2 ዋና ዋና ጉዳዮች

0
0

oromo
ቁምላቸው መኩሪያ

በአሁኑ ሰዓት የኦሮሚያ ልጆች ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ ድረስ የታጠቀውን የዐጋዚ(ህ ወ ሐ ት) ወታደር በባዶ እጃቸው እዬተፈለሙት ይገኛሉ። ይህ የነፃነት ፍልሚያ ግን ከኦሮሞ ጎሳ(ብሔር) በስተቀር በሌላ ጎሳዎች(ብሔሮች) በኩል ሲከናወን አይተይም። ለምን ?። በእኔ እይታ ይህ የሆነበት በሁለት አንኳር ምክንያቶች ይመስለኛል። እናሱም፦
የኦሮሞ ወጣቶችን ንቅናቄ በጥርጣሬ ዐይን መመልከት።
ህወሐት/ ኢህአዴግ የሚወረውረውን የጎሳ ቅስቃሳ(ፕሮፓጋንዳ) መስማት። የሚሉ ናቸው እላለሁ።

1፡ የኦሮሞ ወጣቶችን ንቅናቄ በጥርጣሬ ዐይን የመመልከት ጉደይ፦

በርግጥ የትግራይ ነፃ አውጪ ቡድን በትረ ሥልጣኑን ከጨበጠ በሆላ ለራሱ ሥልጣን ማረዘሚያ ሲል የብሔሮችን ቋንቋ ፤ የብሔሮችን ማንነት፤ የብሔሮችን መብት ማስጠበቅ እና የብሔሮችን እኩልነት ማስጠበቅ በሚል በመርዝ በተለወሱ ማር ቃላት እና በወቅቱ የተራማጅ ዘዬ ነው ይባል በተባለው በዋላልኝ መኮነን ይሰበክ በነበረው ጨቅላ የፖላቲካ ምህዋር ማለትም ”የእራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል” በሚል ፍልስፍና የኦሮሞ ጎሳዎችን ቀልብ በመስብ አሌ የማይበል ዕኩይ ተግበር በኢትዮጵያ ህዝብ ለይ ፈፅሞል። ጥቂትም ቢሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ይህንን ጥሪ ተቀብሎ አለስተጋባም ማለት ጋሃዱን መሸሽ ነው።
ነገር ግን“ንጋት እና ዕውነት እዬቆዬ ይጠራል” እንደ ሚባለው ብዙ የኦሮሞ የነፃነት ፓርቲዎች ይህንን አንቀጽ 39 የሚለውን ፈሊጥ በመተው “ኦ ነ ግ” የሚለውን ምህጸረ ቃል ወደ “ኦ ዴ ግ”በመቀየር ለአንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመታግል ገሚሱ ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ቀሪው በኤርትራ ምድርና በአገር ቤት በመሆን የአንድነት እና የነፃነት ትግሉን ከትግራይ ነፃ አውጪ ቡድን እጅ ፈልቅቆ ለመውሰደ በፍልሚያ ለይ ነው።
አሁን ትግሉ መሆን ያለበት “ከህወሀት” ውጅንብር ወጦ የኦሮሞ ልጆችን ተቀላቅሎ ኢትዮጵያን ከባርነት ማውጣት ነው። ” ኦሮማይ” !!!

2፡ ህወሐት/ኢህአዴግ የሚወረውረውን የጎሳ ቅስቃሳ(ፕሮፓጋንዳ) መስማት፦

አሁን ኢትዮጵያን እዬገደለና ንብራቷንም እዬዘረፈ መሬቷንም ለባዕድ ሀገር እዪናኘ ያለው የትግራይ ነፃ አውጪ ቡድን ልክ እንደ አመንምኒት(ኤይድስ) በሽታ ብዙ ገጸበህርያት አለው።
ይኸውም ምንጩ ከሆነው ትግራይ ክ/ሀ ሲደርስ” ህወሐት” ይሆናል። ጎጃም፡ ጎንደር፡ ወሎ እና ከፊል ሸዋ ክ/ሀገሮች ሲደርስ “ብአዴን” ይሆናል። ኢሉባቦር፡ ባሌ፡ ወለጋ፡ካፋ ፡ አሩሲ፡ ከፊል ሓረር እና ከፊል ሸዋ ክ/ሀገሮች ሲደርስ “ኦህዴድ” ይሆናል። ሲደሞ እና ጋሞጎፋ ክ/ሀገሮች ሲደርስ “ደህዴን” ይሆናል። ሐረር ሲደርስ “አዴን” ይሆናል። አፈር ሲደር “አዴግ” ይሆናል። ጋምቤላ ሲደርስ “ጋዴድ” ይሆናል። አሶሳ ሲደርስ “ቤጉዴድ” ይሆናል። (ብቻ ምን አለፋችሁ የጎሣውን ስም እዬጠረ ከሆለው “ዴ”ን (ዴሞክራሲን)ወይም “ድ”ን(ድርጅትን) መሽለም ነው።
እናዚህ ሁሉ ከላይ የተዘረዘሩት የህወሐት ሎሌዎች ደግሞ በሥሮቻቸው ሊግ፤ፎራም፤ወጣት ማህበር፤የፓርቲ አባል የሚባሉ ግልገል ሎሌዎች አሎቸው። የሁሉም ታግባር ግን የህወሐትን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም አንዱን ጎሳ ከሌላው ጎሣ አንዱን ሀይማኖት ከሌላው ሀይማኖት ማጋጨት እና ደም ማፋሰስ ነው።
በተለይ ጎላ ያሉትን የአማራውን ጎሳ ከኦሮሞው ጎሣ፡ የከርስትያኑን ማህበረስብ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ለማጋጫት እና ደም ለማፋሰስ በራሱም ሆነ በሎሌዎች አማካኝእነት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። ይህንንም አድራጎት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአርምሞ የሚረደው ይመስለኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ጊዜ ጀግኖች ወንድሞቻችን የኦሮሞ ልጆች ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጸጉሩ ድረስ ዘመነዊ መሰሪያ ታጥቆ የመጠውን የአጋዚ(የህወሀት) ጧር በባዶ እጃቸው ጕሮሮ ለጉሮሮ ታናንቀው ዓረፋ እየስደፈቁት ይገኛሉ።
ስለዚህ ፦ወንድም እና እህት፡ እናት እና አባት የሆነው ሌላው የኢትጵያ ጎሣ(ብሄረስብ) በወየኔ እና በሎሌዎቹ ፕሮፓጋንዳ ሳይፈታ ከኦሮሞ ወንድሞቹ ጎን በመቆም ወንድሞቹን ከሞት ኢትዮጵዮጵያ ከመከራ ሊታደጋት ይገባል።

“ኢትዮጵያ ከእነ ክብሮ ለዘላአለም ትኑር !!!!!”

The post ዛሬ ምን ማድረግ አለብን ? – 2 ዋና ዋና ጉዳዮች appeared first on Zehabesha Amharic.

“እንቢ” ማስተር ፕላኑን! –“ጥያቄው የመሬት ይዞታ ብቻ ሣይሆን፣ የሰብዓዊና የዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ነው፡፡”

0
0

abebe Gelawይድነቃቸው ከበደ

“የኦሮሚያ ክልል፤ የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ ከተማ በኦሮሚያ ክልል መሀል የሚገኝ በመሆኑ፣ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል፤ ከዚህ በተጨማሪም የኦሮሚያን ጥቅም ለማስከበር ዝርዝር ጉዳዮች በሕግ እንሚወሰኑ ያስረዳል፡፡” ይህ ቃል ሰፍሮ የሚገኘው በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 49 ንዑስ ቁጥር 5 ላይ ነው፡፡

“ከቃላት ድምቀት በላፈ ሕገ-መንግሥቱ ለ “እኛ” ኢትዮጵያዊያን ምንም ነው !” ምንም ስለመሆኑ ከዚህ በፊት ሃሳቤን በገለጽኩባቸው መንገዱች ሁሉ ለማስረዳት ሞክሬያለሁ፡፡አሁንም በሙከራዬ እቀጥላለሁ ፡፡

“የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን” የሚል ስያሜ የተሰጠው በእኔ አረዳድ፣ “የመሬት ነጠቃ እና ወራር ያስከትላል” ብዬ የማስበው መንግሥታዊ ድርጊት፤ ከባለፈው ሁለት ዓመት ጀምሮ በአገራችን አለመረጋጋትን ፈጥሯል፤መተኪያ የሌለው የሰው ልጅ ሕይወት እንዲጠፋ፣ የንብረት ውድመትና ኪሳራ እንዲደርስ ምክንያት ሆኗል፡፡

ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው መንግሥት ነው ! የህውሓት/ኢሕአዴግ ክፉ ባሕርይ “እኔ አውቅልሃለው” ብቻ በማለት፣ የአገዛዙን ሥርዓትና የሥርዓቱን ደጋፊ የሆነውን ብቻ፣ ታሳቢ ያደረገ ልማት ያልሆነ ፤የልማት ስያሜ የሚሰጠው እንቅስቃሴ ማድረግ ዋና መገለጫ ነው፡፡

የፌደራል መንግሥትም ነኝ ባዩ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል አስተዳዳር “የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን”ን አስመልክቶ ከጉዳዮ ቀጥተኛ ባለቤት ከሆነው የአካባቢ አርሶ አደሮች፣ ከክልሉ ነዋሪዎችና ከሚመለከታቸው ጋር በግልፅ ከመወያየት ይልቅ፣የቀበሌ ካድሬ ሰብስቦ ለእነርሱ “እነርሱን” ተጠቃሚ ያደረገ ውሳኔ እያሳለፉ ሀገር እየታመሰ ይገኛል ፣ወደ ፊትም ይቀጥላል!

በሕገ-መንግሥቱ ላይ የሚገኘውን ድንጋጌ የበለጠ ሊያሰፋ የሚችል፤ የኦሮሚያ ክልልን ጥቅማ ጥቅሞች የሚጠብቅ የትኛውም ዓይነት አዋጅ ሆነ መመሪያ እስካሁን እኔ በላኝ መረጃ አልወጣም፤ በዚህም ምክንያት የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ስለምታገኘው ጥቅማ ጥቅም አስመልክቶ በሕግ መፍትሄ የተሰጠው ነገር የለም፡፡ “ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ” እንደሚባለው ጥቅማ ጥቅሞች ቀርተው የክልሉን መሬት ዘረፋና ንጥቂያ በአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን የሚል ሽፋን በመስጠት ለመፈጸም የታሰበው የመንግሥት የመሬት ወረራ ነው፡፡

እንደሚባለው ከሆነ ተግባራዊ ለማድረግ የታሰበው ማስተር ፕላን አዲስ በአዲስ አበባ ዙሪያ፤እንደ አዲስ የሚዋቀር የኦሮሚያ ልዩ ዞን እንዲያቅፍ ይደረጋል፡፡በልዩ ዞኑ ስር ስድስት ከተሞችና ስምንት የገጠር ወረዳዎች የሚገኙ ሲሆኑ፣ እነዚህ ከተሞችና የገጠር ወረዳዎች ከአዲስ አበባ ጋር የሚያስተሳስር ማስተር ፕላን ይኖረዋል፡፡ማስተር ፕላኑ ተግባራዊ ሲሆን ኦሮሚያ ተጠቃሚ ስለመሆንዋ ምን አይነት ማረጋገጫ የለም! ይሄን ለማለት የሚያስደፍረው፤ጠቀሜታውን አስመልክቶ ከላይ እንደተገለጸው ህበረተሰቡን ያማከል ምን ዓይነት ውይይት አልተካሄደም፡፡

ይህ ማስተር ፕላን ከምንም በላይ ፤ለማስተር ፕላን ቁማርተኞች ሰፊ እድል እንደሚሰጥ የባለፉት ተሞክሮ እማኝ ይሆናል፡፡ባሁን ወቅት በአገራችን ትልልቅ ኢንቬስተሮች እነማን እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው፡፡በኢንቬስትመንት ስም በቡራዩ፣ በላጋ ጣፎ፣ በገላን፣ በሱሉልታና የመሳሰሉ ከተሞች ፤መሬት ዘረፋ ተፈጽሞል ካዛም አልፎ አርሶ አደሮችን ተገቢ ባልሆነ ካሳ ከእርሻ መሬታቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል፡፡በዚህም ምክንያት አርሶ አደሩ ለስደትና ለችግር ተጋልጦል፡፡
ይህም በመሆኑ የአካባቢዊ ነዋሪዎችና እና የችግሩ ተጋላጭ የሆኑ፣እንዲሁም የመሬት ነጠቃና ወረራ የሚቃወሙ የተለያዩ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሞቸውን በአደባባይ እየገለፁ ይገኛሉ፡፡ መንግሥት ከህዝቡ የገጠመውን ግልጽ ተቃውሞ ወደ-ጎን በመተው፤ ሠላማዊ እና ሕጋዊ ተቃውሞ መልኩን እየቀየረ እንዲሄድ በር ከፍቷል ብሎ መረዳት ቻላል፡፡

የመሬት ጥያቄ ለአርሶ አደሩ የኅልውና ጉዳይ ነው፤ከዚያም አልፎ አሁን ላይ ሕዝባዊ ተቃውሞ የሰብዓዊና የዲሞክራሲ ጥያቄ ያካተተ ሆኗአል፡፡ሰላማዊ ተቃውሞ በገዢው መንግሥት የተሰጠው ምላሽ እና እሱን ተከትሎ የመጣው፣ የሕዝብ የመረረ ቁጣ መጠኑ እየሰፋ መጥቷል፡፡ይህ ሐቀ ለማንም ግልጽ በሆነበት ሰዓት እንኳን እኔ አውቅልሀለሁ ባዮ መንግሥት ፤የእርሱ ልዕሳን በሆኑ የመገናኛ ብዙሃን በመቅርብ ፤እንደ አቶ አባዱላ ገመዳ ዓይነቱ ለሕዝባዊ ጥያቄ እየሰጡት ያለው ምላሽ ንቀትን ያዘለ ነው፡፡

“የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ መሪ እቅድ የሚተገበረው በህብረተሰቡ ተቀባይነት ሲያገኝ ነው” በማላት አቶ አባ ዱላ በድፍረት የሚናገሩትና ያህል ለተግባራዊነቱ እሳቸው እና የእሳቸው መንግሥት ቅንጣት ያህል ግድ አይሰጣቸውም ፡፡እነሱ እንደሚሉት ከሆነ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ መሪ እቅድ ህበረተሰቡ ላለፉት ሁለት ዓመታት በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ ተቃውሞውን እየገለጸ ይገኛል፡፡

በመሆኑም እቅዱ ተቀባይነት እንደሌለው ከዚህ በላይ ምን ማሳያ ይኖራል ? ምንም ! ይሁን እንጂ ዕቅዱ ሕብረተሰቡ እንደማይፈልገው በግልጽ እየታወቀ የማስተር ፕላን ቁማርተኞች ፤ዕቅዳቸውን ገብራዊ ለማድረግ እዚህም እዚያ ሲንደፋደፉ እየታየ ነው፡፡ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አሁን ላይ ደግሞ የ “ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት” አፈ-ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ በኦሮሚያ ክልል የመሬት ዝርፊያና ሽያጭ እሳቸው እና መሰሎቻቸው በፊት አውራሪነት እጃቸው እንዳለበት ይገለፃል፡፡

እውነታው ይሄ ሆኖ እያለ አሁን ላይ ቀድሞ የበደሉትን ሕብረተብ ሣይክሱ፤በድፍረት ለተጨማሪ የመሬት ወረራ እና ንጥቂያ ውስጥ፣ በማን-አለብኝነት ሰተት ብለው ለመግባት ሲሞክሩ፣ የእነሱ ልክ ያጣ ድፍረት የሕብረተሰብ ደግሞ የመረረ ተቃውሞ ፊት-ለፊት ገጥሞል፡፡ምንም ይሁን ምን፣ ሕዝብ ሁሌም አሸናፊ ነው፡፡ ከላይ በመጠኑ ለመግለጽ እንደ ሞከርኩት፣ አሁን ጥያቄው የመሬት ይዙታ ብቻ ሣይሆን የሰብዓዊና የዲሞክራሲያዊ ጭምር ነው፡፡

አሁን ላይ የሕዝብ ጥያቄና ተቃውሞ መጠኑ እየሰፋ ሲሄድ፤ተጨማሪ ስሕተት መንግሥት ነኝ ባዮ እየፈፀመ ይገኛል፡፡ የሕዝብን ጥያቄ በተለመደው ረብ-በሌለው መንገድ፣ የቀበሌ ካድሬዎችን በመሰብሰብ “የፀረ ሰለማ ይሎች እንቅስቃሴ እናወግዛለን ፣ከጀመርነው ልማት ወደ-ኋላ አንልም፣ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ መሪ እቅድ እንደግፋን፣….”እና የመሳሰሉትን “ልማታዊ” መፍክር እያቀነቁ፤ በጉዳዮ ዙሪያ ከሕብረተሰብ ጋር ተወያይን ይላሉ፡፡ቀጥሎም የመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን “ሕብረተሰቡ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በመመለስ ልማቱ ላይ እንዲያተኩር፣ አንድ-አንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች አሳሰቡ” በማላት ያበቃል፡፡
የህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት የሕዝብ ጥያቄ ቢቻል አድበስብሶ ማለፍ፣ካልተቻለ በመሳሪያ ሃይል በመጠቀመ አፍኑ ለማስቀረት ጥረት ማድረግ የአገዛዙ ሥርዓት መገለጫ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነቱ አፈና እና ጭቆና የተዳፈነ እሳት ከመሆኑ ባሻገር ለሕጋዊና ሰላማዊ ተቃውሞ መተኪያ የማይገኝለት ፤የአንድነት መገለጫ ብርታትን ይሰጣል፡፡ከምንም በላይ ደግሞ ድል ናፋቂ ያድርጋል !የሚናፉቁቱን ለማግኘት መሆን ያለበት ሁሉ ይሆናል !!!

The post “እንቢ” ማስተር ፕላኑን! – “ጥያቄው የመሬት ይዞታ ብቻ ሣይሆን፣ የሰብዓዊና የዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ነው፡፡” appeared first on Zehabesha Amharic.

ሳተላይት ዲሽን ንቀሉ፥ የሳተላይት ዲሽን ትከሉ  “በአንድ ሳምንት ሁለት ግራ አጋቢ ትእዛዝ!”–ቢቢኤን ሬዲዮ

0
0
 የሱሉልታ ነዋሪዎች
Sadik Ahemed Journalistበአንድ ሳምንት ዉስጥ የመንግስት ሁለት አስገዳጅ ዘመቻ ተከናወነ።በሱሉልታዉስጥ ብዙ የሳተላይት ዲሾች ከየጣራዉ ላይ በታጣቂ የፌደራል ፖሊሶች ተነቅለዋል። በአይሱዙ የጭነት መኪና ዲሾቹ ተጭነዉ መወሰዳቸዉን የሱልልታ ነዋሪዎች ያስረዳሉ። ሳምንት ባልሞላ ግዜ ዉስጥ የፌዴራል ፖሊሶች የሱልልታ ነዋሪዎች የሳተላይት ዲሽን መልሰዉ እንዲተክሉ ትእዛዝ እየሰጡ ነዉ። የፌዴራል ፖሊሶች ስለተወሰደዉ የሳተላይት ዲሽ የምናዉቀዉ ነገር የለም በማለት ለነዋሪዎቹ እንደሚመልሱና ነዋሪዎቹ ለገንዘብ ኪሳራ መዳረጋቸዉ ታዉቋል። ሳዲቅ አህመድ ሱልልታ ድረስ በመደወል የነዋሪዎቹን ወኪል አናግሯል።

 

The post ሳተላይት ዲሽን ንቀሉ፥ የሳተላይት ዲሽን ትከሉ  “በአንድ ሳምንት ሁለት ግራ አጋቢ ትእዛዝ!” – ቢቢኤን ሬዲዮ appeared first on Zehabesha Amharic.

VOA_“ሰብዓዊ መብቶች ገደብ የላቸውም”ከሕግ ባለሞያ አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ጋር የተደረገ ቃል ምልልስ (ክፍል ሁለት) –ጽዮን ግርማ

0
0

ረቡዕ, ታህሳስ 23, 2015

ዋሽንግተን ዲሲ—

Tsion Girma

ጽዮን ግርማ

አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምሕርት ክፍል የቀድሞ መምሕር ነበሩ። በተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት የሰብዓዊ መብትና መልካም አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ኾነው ሠርተዋል።አሁን ደግሞ በአውስትራሊያ ሜልበርን ከተማ፤ በሜልበርን የሕግ ትምሕርት ቤት “በሕገ-መንግሥት ሕግ” የዶክሬት ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል።

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሰሞኑን እየታየ ያለውን ያለመረጋጋት የቀሰቀሰው ተቃውሞ የሽብር አድራጎት ሳይሆን በሃገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ሕግጋት የተፈቀደ፣ መዘዞቹ ደግሞ በሕግ አግባብ ሊታዩ የሚችል የተቃውሞ አቀራረብና መብትም ነው ሲሉ የሕግ አስተማሪና ተመራማሪው አቶ ፀጋዬ ረጋሳ አራርሳ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡ ጽዮን ግርማ አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳን አነጋግራቸዋለች፡፡አርብ ምሽት የዝግጅቱ የመጀመሪያ ክፍል ተላልፏል፡፡ የመጨረሻው ክፍል ቀጥሎ ይቀርባል፡፡

ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

The post VOA_“ሰብዓዊ መብቶች ገደብ የላቸውም” ከሕግ ባለሞያ አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ጋር የተደረገ ቃል ምልልስ (ክፍል ሁለት) – ጽዮን ግርማ appeared first on Zehabesha Amharic.

“…ድርድር የሚባል ነገር የለም”–ኦቦ ቃሲም አባነሻ የኦነግ ቃል አቀባይ |ሊደመጥ የሚገባ ቃለምልልስ

0
0

ኦቦ ቃሲም አባነሻ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባይ ናቸው። በወቅቱ አገር ቤት በኦሮሚያ ክልል በከፍተኛ ደረጃ የተስፋፋውን እንዲሁም በሰሜን ጎንደር የታየውን ሰላማዊ የህዝብ ተቃውሞና ቁጣ የአገዛዙ ታጣቂዎች በመሳሪያ ለማፈን በወሰዱት የጭካኔ እርምጃ ከ80 በላይ ንጹሃን ተገለዋል። የህወሃት ገዢዎች ያሳሰባቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ መተኮሳቸው ሳይሆን በእነሱ ሂሳብ አራርቀነዋል ያሉት የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ እንዳሰቡት አለመጋጨቱ አስደንግቷቸዋል።በኦሮሞያ አመያ ላይ አማሮች ባሉዋቸው ላይ በተቀነባበረ ሁኔታ ጥቃት እንዲፈጸም አድርገዋል።አምስት ሰዎች ሞተዋል። ይህ የተቃዋሚዎቹ ጥያቄና እርምጃን የማይወክል ድርጊት ነው። በሚኒሶታ ላይና ዋሽንግተን፣ ካይሮና ሌሎችም ከተሞች በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵአውያን በግፍ የተገደሉ ንጹሃን ላይ የተወሰደውን ግፍ አውግዘው የኦሮሞ ተማሪዎች ያነሱትን የፍትህ ጥያቄ ደግፈው ቆመዋል። አገዛዙ በአንድ በኩል በጥይት፣በአጥፊው ቅስቀሳ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማብረድ ይሞክራል በሌላ በኩል ተቃዋሚዎችን ለመከፋፈል በአደባባይ አሸባሪዎች ያላቸውን ጭምር በጓሮ በር እንደራደር በሚለው ባህሪው ይታወቃል።ዛሬስ ይህንና ሌሎችን ወቅታዊ ጉዳዮችን አንስተን ቃል አቀባዩ ምላሽ ሰጥተዋል።

“…ድርድር የሚባል ነገር የለም” – ኦቦ ቃሲም አባነሻ የኦነግ ቃል አቀባይ  | ሊደመጥ የሚገባ ቃለምልልስ

The post “…ድርድር የሚባል ነገር የለም” – ኦቦ ቃሲም አባነሻ የኦነግ ቃል አቀባይ | ሊደመጥ የሚገባ ቃለምልልስ appeared first on Zehabesha Amharic.


“በኢትዮጵያ የተነሳው ተቃውሞ የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የሲዳማ እና ሌሎችም ተብሎ የሚከለል አይደለም”–ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን | Audio

0
0

በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት የተነሳው ተቃውሞ የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የሲዳማ እና ሌሎችም ተብሎ የሚከለል አይደለም ባይ ናቸው የዛሬ እንግዳችን ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን በቬጋስ የተመሰረተው የቀድሞ የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር ሊቀመንበር። በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን በኦሮሞ ተማሪዎች የተጀመረውን ነጻነት ጥያቄ ለወያኔ ዘረኛ ከፋፋይነት ቦታ ሳይሰጡ በጋራ መደገፍ አንድ ላይ መቆም ይገባል ይላሉ።በወቅታዊው ጉዳይ ያደረግነውን አጠር ያለ ውይይት ያድምጡ።ለበለጠ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ።


“በኢትዮጵያ የተነሳው ተቃውሞ የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የሲዳማ እና ሌሎችም ተብሎ የሚከለል አይደለም” – ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን  | Audio

The post “በኢትዮጵያ የተነሳው ተቃውሞ የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የሲዳማ እና ሌሎችም ተብሎ የሚከለል አይደለም” – ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን | Audio appeared first on Zehabesha Amharic.

በብሩንዲ ውስጥ ያንጃበበው የእርስ በርስ ግጭት ስጋት መንሴዎቹ እና የዓለማቀፉ ማህበረሰብ ሰሞነኛ ምላሽ ሲቃኝ (ልዩ ጥንቅር) |ሊደመጥ የሚገባ

0
0

በብሩንዲ ውስጥ ያንጃበበው የእርስ በርስ ግጭት ስጋት መንሴዎቹ እና የዓለማቀፉ ማህበረሰብ ሰሞነኛ ምላሽ ሲቃኝ (ልዩ ጥንቅር) | ሊደመጥ የሚገባ ትንታኔ በታምሩ ገዳ

The post በብሩንዲ ውስጥ ያንጃበበው የእርስ በርስ ግጭት ስጋት መንሴዎቹ እና የዓለማቀፉ ማህበረሰብ ሰሞነኛ ምላሽ ሲቃኝ (ልዩ ጥንቅር) | ሊደመጥ የሚገባ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በርገን ቅርጫፍ ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ አደረገ

0
0

norway
በሃገራችን ኢትዮጵያ ለሚደረገው መራር ትግል የዘወትር ድጋፉን እና ድምጹን በማሰማት ላይ የሚገኘው ድርጅታችን እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በአሁኑ ጊዜም አፋኙ የወያኔ ቡድን በሰላማዊ ጥያቄን በጠየቁ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ቆመጥና ጥይት ሆኗል መልሱ በተጨማሪም አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ያቆዩልንን ዳር ድንበራችንን በምዕራብ ኢትዮጵያ በጎንደር ክልል ህዝቡን በማፈናቀል በመግደል በማሰደድ 1600 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ወደ ጎን ከ 30 እስከ 60 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ቦታን ለሱዳን አሳልፎ ለመሰጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል ::

ይህን በመቃወም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አራቱም ትላልቅ ከተሞች ሰለፍ ያዘጋጀ ሲሆን በዛሬው እለት ማለትም በ22.12.2015 በኖርዌይ በርገን ከተማ በተዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ ሰው የተገኘ ሲሆን በወገኖቻችን ላይ አምባገነኑ ወያኔ እያደረሰ የሚገኘውን እስር አፈና ግድያና ድብደባ በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል::

ሰላማዊ ሰልፉ በኖርዌይ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 14:00 ጀምሮ እስከ 16:00 የተደረገ ሲሆን በጣም አስቸጋሪውን የበርገንን የአየር ጸባይ በመቋቋም የወያኔን መንግስት የሚያወግዙ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ እና በማሰማት ወደ ከተማዋ ከንቲባ ጽ/ቤት ተጉዘዋል በሰልፉ ላይ ሰልፈኞቹ ያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል :-ጥያቄያችን የነጻነት የመብት የፍትህ ጥያቄ ነው ፣ ህዝብን በማጣላት ህዝብን በማጋጨት ሃገር መምራት አይቻልም ፣ እኛም የትግሉ አጋር ነን ፣ ጠላታችን ወያኔ ወያኔ ብቻ ነው ፣ አባቶቻችን በደማቸው በአጥንታቸው ያቆዩልንን ድንበር ቆርሶ ለባእዳን መስጠት ህዝብን መናቅ ታሪክን ማጥፋት ነው ኢትዮጲያዊነት ፣ አንድነት ነው የሚሉ ይገኙበታል

የበርገን ከተማ ከንቲባ ማርተንስ ሚዮ ፐርሸን / Martens Mjøs Persen, Ordfører i Bergen / የሰላማዊ ሰልፈኞቹን በበርገን ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ እንዲገቡ በመጋበዝ ስለመጡበት ጉዳይ እንዲያስረዱ የጠየቁ ሲሆን በሃገራችን ላይ የሚፈጸሙትን ግድያዎች አፈናዎች ድብደባዎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሰፊ ማብራሪያ የተሰጣቸው ሲሆን : ኖርዌይ ለአባገነኑ የወያኔ መንግስት የምታደርገውን እርዳታ እንድታቆምም አሳስበዋል በመጨረሻም የዚህም ድርጊት ፈጻሚ አንባገነኖች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ በመጠየቅ የድርጅቱን የአቋም መልክት ደብዳቤ ያስረከቡ ሲሆን የከተማዋ ከንቲባ ማርተንስ ሚዮ ፐርሸንም ከሰፊው ህዝብ ጋር አብረው እንደሚቆሙ ጥያቄያችሁም ለሚመለከተው አካል እንደሚያደርሱ ቃል ገብተዋል

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ !!
በርገን ቅርጫፍ

The post የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በርገን ቅርጫፍ ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ አደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.

ታሪክ አይፈራም –ጌታቸው ኃይሌ

0
0
getachew

ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

“አማራ የሚባል ዘመድ አለ ወይስ የለም? ለመሆኑ አማራ ማነው?” የሚል ውይይት ተነሥቶ ሳይ፥ ታሪክን መሠረት በማድረግ የማውቀውን በጽሑፍ አቅርቤ ነበረ። ድርሰቴን ያነበበው ሁሉ አስተያየቴን ቢቀበለውም፥ “ደመ ንጹሕ አማራ ነን” የሚል እምነት ያላቸው አንዳንድ ሰዎች አንዳንድ ቅሬታ ያዘለ አስተያየት አንሥተዋል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ታሪክ ያነበቡ አይመስለኝም። ባያነቡም በግምት እንዲደርሱበት አንድ ነገር በማንሣት ልጋብዛቸው። –[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]——

The post ታሪክ አይፈራም – ጌታቸው ኃይሌ appeared first on Zehabesha Amharic.

የህንዱ ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረውን 55.8 ሚሊዮን ብር አልከፍልም ተሰማ

0
0

481154_550780071735675_4995213108371569437_nየህንዱ ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረውን 55.8 ሚሊዮን ብር አልከፍልም ስላለ የወሰደውን 100 ሺሕ ሔክታር፣ መጋዘን፣ የሠራተኞች ተገጣጣሚ ቤትን ለጨረታ ቢያቀርብም እስካሁን በሃራጅ ተሽጦ ባንኩ ሊያገኘው የቻለው 2.6 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው። የካሩቱሪ ዳይሬክተር ራማክሪሽና ካሩቱሪ ለ100 ሺህ ሔክታር ሊዝ መሬት አንድ ጊዜ የሚከፈል 5.6 ሚሊዮን ዶላር በባንክ እንዳይከፍል ታዞ በጥሬ ገንዘብ ጉዳዩ ለሚመለከተው ግለሰብ መክፈሉን መናገሩ ይታወሳል። መንግስትን የሚወክለው ግለሰብ መጀመሪያ 5.6 ሚሊዮን ዶላር ተቀብሎ በኋላ ካሩቱሪ መክፈል የማይችለውን 55.8 ሚሊዮን ብር እንዲበደር ፈቅዶለታል።

The post የህንዱ ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረውን 55.8 ሚሊዮን ብር አልከፍልም ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live