Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ወይኔዎች በአዳማ ተሰብስበዋል –የሚሊዮኖች ድምጽ

$
0
0

ሕወሃት በኦሮሚያ ክልል የተነሱ ተቃዉሞዎችን ለመቆጣጠር በአዳማ ሚስጥራዊ ስብሰባ የጠራ ሲሆን የክልሉ የሕወሃት አገልጋይ ኦህደድ ሃላፊዎችም እንዲገኙ ተደርጓል። የስብሰባው ሚስጥር በኦዲዮ በሚስጠር እንዳይወጣ የኦሮሚያ ፕሬዘዳነት አቶ ሙክታር ከድርን ጨመሮ፣ እምነት ሰለማይጣልባቸው ስልካቸውም ዉጭ አስቀምጠው ወደ ስብሰባው የገቡት።
በተያያዘ ዜና፣ የሚነሱ ተቃዎሞዎችን ለመቀነስም፣ ህወሃት ማስተር ፕላኑን ለጊዜው ለማስተላለፍ እንደወሰነም ዘገባዎች ይጠቁማሉ።
ማስተር ፕላኑ ለጊዜውተላለፈ ቢባልም፣ መሰረታዊ የስርዓት ለዉጥ ካልመጣ፣ ገበሬው የመሬት ባለቤት ካልሆነ፣ የሚለወጥ ነገር የለም። በመሆኑም ሕወሃቶች በሚያደርጉት የተለያየ ታክቲካል ማዘናጊያ ሳንወናበድ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለሕዝብ የቆመና ሕዝብን በትክክል የሚያገለገል ስርዓት ለመዘርጋት ሁላችንም መንቀሳቀስ ይኖርብናል።

12311083_1039823142706259_3308051653654062719_n

The post ወይኔዎች በአዳማ ተሰብስበዋል – የሚሊዮኖች ድምጽ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

↧

በአዋሣ ሪፈራል ሆስፒታል መብራት በመቋረጡ 3 ህሙማን ህይወታቸው አለፈ

$
0
0

draping-ESS-Awasaa-300x200በአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ መብራት ለሀያ ሰዓታት ያህል በመቋረጡ ምክንያት በፅኑ ህክምና ክፍል (ICU) ውስጥ የነበሩ ሦስት ህሙማን ለሞት ተዳረጉ፡፡
ህዳር 20 ምሽት ላይ ለ20 ሰዓታት መብራት ተቋርጦ በመቆየቱና የሆስፒታሉ ጀነሬተር ተበላሽቶ በመቀመጡ የተነሳ በፅኑ ህክምና ክፍል የነበሩ አንዲት ወላድ እናትና ሁለት ሌሎች ህሙማን ህይወታቸው እንዳለፈ ምንጮች ገልፀዋል፡፡
ከይርጋለም ከተማ ወደ ሆስፒታሉ ሪፈር ተደርጋ የመጣችውና ከእርግዝና ጋር በተያያዘ የደም ግፊት ህመም ሳቢያ ወደ ፅኑ ህክምና ክፍል የገባችው እናትና ሁለቱ በፅኑ ህክምና ክፍል ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩት ህሙማን በራሳቸው መተንፈስ የማይችሉ በመሆኑ፣ በመሳሪያዎች እገዛ ድጋፍ እየተደረገላቸው ህክምናቸውን ሲከታተሉ ነበር፡፡ ሆኖም ድንገት መብራት ተቋርጦ በመቅረቱ ህሙማኑ ህይወታቸው አልፏል፡፡ የሆስፒታሉ ጄነሬተር ተበላሽቶ ስለነበር መተካት አልተቻለም ተብሏል፡፡ መብራት መጥፋቱን ተከትሎ የቀዶ ህክምና ሊደረግላቸው የነበሩ ህሙማን ቀጠሮአቸው ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፡፡
በዕለቱ የተከሰተውን ችግር አስመልክቶ መረጃ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የሆስፒታሉ ዋና ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ክንፈ ለማን ወክለው ሆስፒታሉን በማስተዳደር ላይ የሚገኙት ዶ/ር አብይ ሚካኤል፤ ስለሁኔታው ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
በአካባቢው በትልቅነቱ የሚታወቀው የአዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል በአሁኑ ወቅት በርካታ የአሰራር ችግሮች እንዳሉበት ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የሆስፒታሉ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዎች ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው ህዝቡን እያገለገሉ አይደለም ያሉት ምንጮች፤ በጥብቅ (ጥኑ) ህሙማን ክፍል ውስጥ ያሉትን ጨምሮ በተለያዩ ከባድ የጤና ችግሮች የተያዙ ህሙማን ክትትል የሚደረግላቸው በነርሶችና በተማሪ ሀኪሞች እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

Source:: Addisadmass News

The post በአዋሣ ሪፈራል ሆስፒታል መብራት በመቋረጡ 3 ህሙማን ህይወታቸው አለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የፕሮፌሰር እዝቄል ጋቢሳ እና የጃዋር መሐመድ አስታራቂ ሃሳብ በቪዲዮ ይመልከቱ

$
0
0

በኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ የቀረቡት ፕሮፌሰር እዝቄል ጋቢሳ እና ጃዋር መሐመድ በኦሮሚያ ክልል ሰሞኑን የተነሱትን የመብት ጥያቄዎችን ተንትነው ከሌላው ኢትዮጵያዊ ምን ይጠበቃል? በተለይ ያለውን ክፍተት እንዴት መድፈን ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ አስታራቂ ሃሳብ ሰጥተዋል:: የሚከተለውን ቪዲዮ ይመልከቱ::

Jawar Mohamed and Ezkiel

The post የፕሮፌሰር እዝቄል ጋቢሳ እና የጃዋር መሐመድ አስታራቂ ሃሳብ በቪዲዮ ይመልከቱ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ሽግግር ከየት ወዴት? –የኤፍሬም ማዴቦ ንግግር በቪዲዮ

$
0
0

የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራርና በአሁኑ ወቅት አስመራ የሚገኙት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ባለፈው ግንቦት ላይ ስለ ሽግግር መንግስት ንግግር አድርገው ነበር:: ንግግሩ አመት ሊሞላው ቢሆንም በሚዲያ ስላልተለቀቀ ቪዲዮውን ስላገኘነው እንደ አዲስ ለግንዛቤዎ ይረዳ ዘንድ አቅርበነዋል::

ሽግግር ከየት ወዴት? – የኤፍሬም ማዴቦ ንግግር በቪዲዮ

The post ሽግግር ከየት ወዴት? – የኤፍሬም ማዴቦ ንግግር በቪዲዮ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አማራ የሚባል ዘመድ አለ ወይስ የለም? |ጌታቸው ኃይሌ

$
0
0

Getachew Haile
መግቢያ፤

መጀመሪያ ለመግቢያ ያህል፥ “ዘመድ” የሚለውን ቃል እንዴትና ለምን እንደተጠቀምኩበት ላስረዳ። “ዘመድ” ማለት “ወገን” ማለት ነው። በእንግሊዝኛ “kin, family, tribe” ማለት ነው። በየሊቃቸው የሚመሩ የተለያዩ የመላእክት ሠራዊት “ዘመድ” ወይም “ነገድ” ነው የሚባሉት”–ዘመደ መላእክት፣ ነገደ መላእክት። ሌሎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው መጠሪያዎች “ቤት” (ቤተ አምሐራ)፣ “ጎሳ” (የጉጂ ጎሳ)፣ “ዘር” ናቸው። ዛሬ ደግሞ “ ብሔረ ሰብ” የሚለው መጠሪያ ነግሧል። ከነዚህ ስሞች ውስጥ አንዳንዶቹን የሚጠሏቸው ሰዎች አሉ። “ዘመድ” የሚለውን መጠሪያ የመረጥሁት ዝምድና ስለሚያስተሳስብና አምላክ የሰውን ልጅ ከመላእክት ደረጃ መመደቡን ለማስታወስ ነው። ቅዱስ ዳዊትም ጌታን “የሰውን ልጅ ከመላእክትህ ብዙ አላሳነስከውም” ይለዋል። ሰው እንደ መላእክት ክቡር ነው። መላእክት የተፈጠሩት እግዚአብሔርንና ሰውን ለማገልገል ነው። ዓለም ራሷና በውስጧ ያሉት ሁሉ የተፈጠሩት የአዳምን ልጆች ለማገልገል ነው። ክርስትና እንደሚያስተምረን አምላክ ሰው ሁኖ ለስቅላት የደረሰው የሰውን ልጅ ከጥፋት ለማዳን ነው።

የመላእክት ሠራዊት የተለያዩ ቢሆኑም፥ ፍጥረታቸውና ደረጃቸው እኩል ነው። የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠራዊት ከሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሠራዊት አይበልጡም አያንሱም። ዘመደ መላእክት ይተባበራሉ እንጂ አይጣሉም። አንዱ ሊቅ ልብለጣችሁ ቢል ከነሠራዊቱ ተሽቆልቁሎ እንጦርጦስ ወርዷል። ዘመደ ኢትዮጵያውያንም አይበላለጡም አይተናነሱም። የሚያበላልጠን ካለ የኛም የእግዚአብሔርም ጠላት፥ የሳጥናኤል ወዳጅ ነው። የሰውን ልጅ በሚነካ ጉዳይ ላይ በዋልን ቍጥር፥ በተለየ ልግዛ የሚሉ ባለጡንቻዎች፣ ማንን እንደሚነኩ ያስተውሉ። የሰው ልጅ የሚያንከባክቡት እንጂ የሚደፍሩት አይደለም።

የሞኞች ወይስ የአላዋቂዎች ጥያቄ፤

“አማራ የሚባል ዘመድ አለ ወይስ የለም?” የሚለው ጥያቄ የሞኞች ነው። ሞኝ የሚባለው ዓይን እያለው፥ ሰው ሁሉ የሚያየውን ግዙፍ ነገር የማያይ፥ ሰው ሁሉ የሚያውቀው የወልና የጋራ ዕውቀት እንግዳ የሚሆንበት ነው። ሞኝ ዛሬ የተወለደ ይመስል የሚያጋጥመውን ነገር ሁሉ ሰው ሳይጠይቅ በራሱ አይደርስበትም። እውነት እንዲህ ያለ ሰው አለ? “አማራ የሚባል ዘመድ አለ ወይስ የለም?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ካለ እሱ አንዱ ነው።

ቃል ያንድ ነገር መጠሪያ ነው። ለምሳሌ፥ “ዛፍ”፣ “ድመት”፣ “ቤት” የምንለው በነዚህ ቃላት የሚጠሩ ነገሮች ቢኖሩ ነው። ባይኖሩ ኖሮ ቃላቱም አይኖሩም ነበር። አንዳንድ ቋንቋዎች ውስጥ ያሉ ቃላት እሌላው ቋንቋ ውስጥ የማይኖሩት በእነዚያ ቃላት የሚጠባቸው ነገሮች የዚያ ቋንቋ ተናጋሪዎች ዘንድ ስለሌሉ ነው። ለምሳሌ bird በአማርኛ “ወፍ” ነው። ወፍ የተባለችው ፍጥረት ኢትዮጵያ ስላለች “ወፍ” የሚለው መጠሪያ ወጣላት። ለ kangaroo ግን አማርኛ የለንም። የሌለን kangaroo የሚባል ፍጥረት በሀገራችን ስለሌለ ነው። በአንጻሩ፥ መዝገበ ቃላት ውስጥ ያሉ ቃላት በሞላ ላለ እና ለታወቀ ነገር መጠሪያ የተፈጠሩ ናቸው። በመፈጠር የቅደም ተከተል ሂደት፥ የሚጠራው ነገር ይቀድማል፤ መጠሪያው ስም ይከተላል። ውይይቱን ሰፋ ለማድረግ፥ መጽሐፋችን እንደሚለው፥ አባታችን አዳም ፍጡራኑን በዕብራይስጥ ላም፣ በሬ፣ ርግብ፣ ዋኖስ፣ ዝሆን፣ አንበሳ፣ ነምር፣ በሬ፣ ግስላ፤ ንስር፣ ወፍ ብሎ የጠራቸው ተፈጥረው ስላገኛቸው ነው።

የሌለ ነገር ስም ስለማይወጣለት መጠሪያ ስም ከሚጠራው ነገር ቀድሞ ተፈጥሮ አያውቅም። “ምናልባት አንዳንድ ነገሮች የተፈጠሩ ወይም ድንገት የተገኙ እንደሆን መጥሪያ ይሆናሉ” ተብለው የተከተቱ ቃላት ወይም ስሞች የሉም። እርግጥ አንዳንድ ሰዎች “ወንድ ልጅ የወለድኩ እንደሆነ እገሌ (አሰፋ)፣ ሴት ልጅ የመለድኩ እንደሆነ እገሊት (አልማዝ) እላታለሁ” ይሉ ይሆናል። እነዚህም ስሞች ቢሆኑ፥ ለታሰቡት ልጆች በመጠሪያነት የሚያገለግሉት መጀመሪያ ልጆቹ ከተወለዱ በኋላ ነው። ልጆቹ ካልተወለዱ ላልተወለዱት ልጆች ስሞች አይሆኑም። በአጭሩ በአንድ ቋንቋ ውስጥ ያሉ ቃላት ሁሉ ላሉ ነገሮች መጠሪያ ናቸው፤ ቃል ካለ ነገር አለ።
አማራ አለ፤ እንዲህ ከሆነና “አማራ” የሚል መጠሪያ ቃል ካለ ተጠሪ አለ ማለት ነው። ተጠሪው ዘመደ አማራ ነው። “አማራ የሚባል ዘመድ የለም” ከተባለ ስሙ የተፈጠረው ማን እንዲጠራበት ነው? አማራ የሚባል ዘመድ ለመኖሩ ዋናው ማስረጃ መጠሪያ ስሙ መኖሩ ነው። አማሮች እንደ አግዓዝያን፣ እንደ ሐርላ ስማቸውን ትተውልን ሊጠፉ ይችላሉ፤ አሁን ግን አሉ።

ለአማሮች መኖር ሁለተኛው ማስረጃ፥ አማራ ነን የሚሉ ሰዎች መኖራቸው ነው። ቍጥራቸውም ቀላል አይደለም። አማራውን “አማራ ነኝ ካልክ የለህም (You do not exist)” አይሉትም። ቢሉትም ይኖራል።

ለአማሮች መኖር ሦስተኛው ማስረጃ አማራው የገዢ ዘመድ ነው እየተባለ ከመንግሥቱ ኃይለ ማርያም እስከ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባለው የጨለማ ዘመንና የጨለማ ግዛት መጠቃቱ ነው። ይህን ጽፉፍ በማረቅበት በአሁኑ ሰዓት ሳይቀር በኢትዮጵያ መንግሥት አበረታችነት አማራው ተለይቶ እየተመታ ነው–ያለውን እንዳይኖር ለማድረግ፤ የሚያስፋፋውን ኢትዮጵያዊነት ለማቆም።

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የብዙ አዝማድ አባል ነው–የጾታ፣ የቋንቋ፣ የትውልድ። አባልነቱ በራሱ ምርጫ የመጣ ስላይደለ ሊክደውም ሊያፍርበትም አይገባም። ለምሳሌ፣ ሴት ወይም ወንድ መሆን ሊካድ አይቻልም፤ ሊታፈርበትም የማይገባው እግዚአብሔር የመረጠው ጾታ ስለሆነ ነው። ዘመድም እንደዚያ ነው። የጾታ ባሕርይ አለው፤ አማራነት፣ ጉራጌነት፣ ዶርዜነት የማይደበቅ፥ የማይካድና የማይታፈርበት ነው።

ግን ጾታና ዘመድ ትልቅ የሚለያዩበትም ባሕርይ አላቸው። ጾታ ለብዙ ከፍተኛ ጉዳይ መመዝገብ ሲኖርበት ዘመድን በተለይ በመንግሥት ደረጃ መመዝገብ ለተንኮል ነው። ጾታን ለይቶ ማሳወቅ ግን ለጥቅም ነው፤ ለሐኪም ቤት፥ ለመጸዳጃ ቤት፣ ለጋብቻ፥ ለልብስ ሰፊ፥ ወዘተ. በመታወቂያ ወረቀት ላይ ሳይቀር በወል ሊታወቅ ያስፈልጋል። ልብስ ለመግዛት ወደ ልብስ ተራ ስንሄድ “የወንዶች”፣ “የሴቶች”፣“የሕፃናት” ክፍል እናገኛለን። ዘመድና ሃይማኖት ግን የግል ናቸው። በልብስ ሱቅ ውስጥ “የአማራ”፣ “የቱለማ” ፣ “የጉራጌ” . . . ክፍል አናይበትም። አንድ ኢትዮጵያዊ የየትኛው ዘመድ እንደሆነ እንኳን በመታወቂያ ወረቀት ላይ መስፈር ቀርቶ በተራ ውይይትም ቢሆን ለባህል ካልሆነ በቀር ሌላ ጥቅም የለውም። በባህል ረገድም ቢሆን፣ የአማራን ዘፈን ትግሬው ይዘፍነዋል፤ የከረዩንና የጉራጌውን ጭፈራ መንዜው ያሳምረዋል። ግን ሴት ያለ ተፈጥሮዋ ወንድ መሆን፣ አትችልም ወንዱም ሴት መሆን አይችልም።

የኢትዮጵያዊ መታወቂያ(ዎች)፤

“አማራ አለ ወይስ የለም? አማራ ማነው?” ስለሚለው ጥያቄ አንድ ነገር ማወቅ ይኖርብናል። ዕውቀቱ ምናልባት ሞኙን ጠያቂ ከሞኝነት ያድነው ይሆናል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሁለት የባህል መታወቂያ (identity) ሲኖረው አማራው በተለየ መታወቂያው አንድ ብቻ ነው። ባለሁለት መታወቂያዎች አንዱ መታወቂያቸው የጎሳቸው ባህል ሲሆን ሁለተኛው መታወቂያቸው የመንግሥቱ ባህል ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በተስፋፋበት ጊዜ፥ ባህሉ (ሥርዓቱና አስተዳደሩ) በታሪክ አጋጣሚ በአስፋፊዎቹ ቋንቋ (በአማርኛ) ተገልጿል። የመንግሥቱና የተከታዮቹ መታወቂያ አማርኛ ሆኗል። የአንድ መንግሥት ባህል በአንድ ቋንቋ መገለጽ በየትኛውም ታሪካዊ ሀገር የተፈጸመ ነው። በኢትዮጵያና በሌሎችም ሀገሮች እንዴት እንዲህ እንደሆነ ታሪኩን እናውቀዋለን፤ እዚህ እንዳንተቸው ንባብ ሰልቺ ያበዛል።

የጎሳ ወይም የዘመድ ባህል ከቤተ ሰብ ይወረሳል፤ የመንግሥት ባህል ከቤተ መንግሥት ይወጣል። ሁለቱንም የሚጐናጸፉ ኢትዮጵያውያን ባለሁለት መታወቂያዎች ናቸው። የመንግሥቱ ባህል መገለጫ ወይም መታወቂያ አማርኛ ነው ብያለሁ። የጎሳን (የዘመድን) ቋንቋና የመንግሥቱን ቋንቋ (አማርኛን) የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን/ት ባለሁለት መታወቂያዎች ናቸው (ጉራግኛ-አማርኛ፤ ትግርኛ-አማርኛ፤ ሱማልኛ-አማርኛ፤ ወዘተ.)። የመንግሥቱን ባህል ብቻ ይዘው የሚጓዙ መታወቂያቸው አንድ ብቻ ሆኗል (አማርኛ ተናጋሪዎች)። የታሪካችንን ሂደት ለተመለከተው አማርኛ ተናገሪዎች ሁለት ዓይነት ናቸው፤ (ሀ) “xxx-አማርኛ”፤ (ለ) “አማርኛ-አማርኛ” ልንላቸው እንችላለን። (ሀ) “xx-አማርኛ” የምላቸው አማራነታቸው “ከጉራግኛ-አማርኛ”፣ ወይም “ከትግርኛ-አማርኛ”፣ ወይም “ከወላይታኛ-አማርኛ” ወዘተ. የሆኑትን ነው። ጥንቱ ግንዳቸው ጉራግኛ፥ ትግርኛ፥ ወላይትኛ፥ ወዘተ. ነበር፤ አሁን ግን አማሮች ሆነዋል ለማለት ነው። (ለ) “አማርኛ-አማርኛ” የምላቸው ጥንቱን በግንዳቸው አማሮች የነበሩትንና መንግሥቱን ለመከተል አዲስ ቋንቋ ማወቅ ያላስፈለጋቸውን ነው። ዛሬ እነዚህ ሁሉም (ሀ እና ለ) እኩል አማሮች ይባላሉ፤ (ሀ) የቤተ ሰብ ቋንቋ ያልወረሱ አማሮችና (ለ) የወረሱ አማሮች ።
በይበልጥ ለማብራራት፥ ዛሬ አማርኛ ብቻ የሚናገሩ ባለአንድ መታወቂያዎች ናቸው። ከእነሱ ውስጥ ብዙዎቹ እንደ ሌሎቹ ሁሉ ባለሁለት መታወቂያዎች ነበሩ (ሀ)። በታሪክ ሂደትና በዘመን ብዛት የጎሳቸውን መታወቂያ እየተዉ የመንግሥቱን መታወቂያ ብቻ ይዘው ቀሩ፤ ከባለአንድ መታወቂያዎች ጋር አንድ ሆኑ። መንግሥት አማርኛን መታወቂያው ከማድረጉ በፊት የጎሳ መታወቂያቸው አማርኛ የነበረ ኢትዮጵያውያን ነበሩ (ለ)። እነዚህ ኢትዮጵያውያን አማርኛ የመንግሥቱ መታወቂያ ስለሆነ በጎሳ መታወቂያቸው ላይ የመንግሥት መያወቂያ ባህል አልተጨመረባቸውም። ቍጥራቸውም ቀላል አልነበረም። መጀመሪያውኑ ባህላቸውን የመንግሥቱ ባህል ያደረገው የቍጥራቸው ትልቅነት ነው። ባለሁለት መታወቂያዎች የነበሩም የጎሳ መታወቂያቸውን እየተዉ የመንግሥቱን ባህል መታወቂያቸው ያደረጉም (ሀ) ጥቂቶች አይደሉም። እነዚህ በታሪክ ሂደት የመንግሥቱን ባህል መታወቂያቸው ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ዘመዶቻቸው ባለሁለት መታወቂያ የነበረ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

እነዚህን የጎሳ መታወቂያቸውን ትተው የመንግሥቱን ባህል ብቻ መታወቂያቸው ያደረጉትን ኢትዮጵያውያን በዘመድ፣ በቤት፣ በብሔር ረገድ ማን እንበላቸው? ከጥንት ተነሥተን አማሮች እንዳንላቸው ጥንታቸው አማራ አይደለም። “አማራ የለም” የሚሉ ሰዎች ዋናው ምክንያታቸው ይህ ነው። የአማርኛ መስፋፋትና የመንግሥቱ ጥንካሬ አማራ ያደረጋቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው። መንግሥቱን በማቀፍ አማራ ያልነበረው ሕዝብ አማራ ሆነ። ዛሬ በትውልድ ከአማራው ቤተሰብ በመጡ አማሮችና ከሌላ ቤተሰብ በመጡ አማሮች መካክል ምንም ልዩነት የለም። ማን ከየትኛው ጥንት (origin) እንደመጣ እንኳን አይታወቅም። ሁሉም ከየመጡበት መጥተው የመንግሥቱን መታወቂያ እኩል መታወቂያቸው አድርገዋል።

ዘመድ መለወጥ ወደ አማራነት መዛወር ብቻ አይደለም፤ ከረዩ ያልነበሩ ብዙ ኢቱዎች ከረዩ ሆነዋል። አግዓዝያንና ሐርላዎች ጠፍተዋል፤ ጠፉ የምንለው ስለጠፉ ሳይሆን አጠገባቸው ወዳለው ጎሳ ስለተዛወሩ ነው። ግን በሁለቱ የለውጥ ዓይነቶች መካከል ያለው ልዩነት ትልቅ ነው። አንዱ ለውጥ የኢትዮጵያ መንግሥት (የአገር-አቀፍ) አባል ለመሆን
ሲሆን፥ ሁለተኛው ለውጥ የጎሳ (የአካባቢ-አቀፍ) አባል ለመሆን ነው። የመንግሥቱ መታወቂያ አማርኛ የሆነው የአፄ ይኩኖ አምላክ ቤተ ሰብ የመንግሥቱን ሥልጣን በትልቁ ሕዝብ (ቋንቋው አማርኛ በሆነው) ላይ ስለመሠረተ ነው።

የወያኔ መንግሥት የመንግሥቱ ቋንቋ እንዳይስፋፋ ብዙ ጥረት ሲያደርግ ይታያል። የቋንቋ አገልግሎት መግባቢያ ከሆነና አማርኛ ያንን አገልግሎት ለአፍሪቃ ቀንድ ሲሰጥ ዘመናት ከአለፉ በኋላ ዛሬ አገልግሎቱን መግታት ምን ጥቅም ለማግኘት ነው? በአማሮቹ ቀንተው እንደሆነ፥ የቋንቋ ባለቤት ተናጋሪው ግለሰብ ነው፤ ባለቤቱ ጎሳው መሆኑ ከቀረ ዘመናት አልፈዋል። ማለት፥ የአማርኛ ባለቤት የጥንቶቹ አማሮች ብቻ ከሆኑ ታሪክ ሆኖ ከቀረ ዘመናት አልፈዋል። አማሮች አሉ፤ ግን አማራ የሚባል የአማርኛ ባለቤት ከግንዱ ወጥቶ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ጥንታዊ ጎሳ ግን የለም። ያለው የመንግሥትን ባህል (ኢትዮጵያዊነትን) ብቻ ባህሉ ያደረገ “አማራ” የተባለ ዘመድ ነው።
ባይታሰብበትና ክፋት ስለሌለበት ነው እንጂ የዛሬዎቹ አማሮች “አማራ” መባልም አልነበረባቸውም። ባይገርመን ጎጃም፥ ጎንደር፥ ሸዋ፥ ወሎ በከፊል በመሠረቱ አማራ አይባሉም ነበር። “አማራ” (አምሐራ) እንደ ጎጃም፥ እንደ ጎንደር፥ እንደ ሼዋ የክፍለ ሀገር ስም ነበር። የነዚህ ክፍለ ሀገር ነዋሪዎች ሁሉ እንዴት አማራ እንደተባሉ የሚገመት እንጂ በማስረጃ የተደገፈ ዕውቀት የለንም።

ዛሬ ሁሉም ማኵረፊያ (ሌላ መታወቂያ) ሲኖራቸው፥ አማሮች ሁሉን ትተው ከተከተሉት ከመንግሥቱ (ከኢትዮጵያዊነት) በቀር ሌላ መታወቂያ የላቸውም። ወያኔዎች አንድ ቦታ ከለሏቸው እንጂ የነሱ ክልል የኢትዮጵያ መንግሥት የተዘረጋበት ነው። ኢትዮጵያ እንዳትበታተን የሚፈልጉት ክልላቸውና መታወቂያቸው ስለሆነች፥ ራሳቸውንና አባቶቻቸው የመሠረቷትን ኢትዮጵያ ከመጥፋት ለማዳን ነው። መታወቂያቸው መላዋ ኢትዮጵያ ብቻ ስለሆነች፥ በክልል መወሰንን ባለሁለት መታወቂያ ኢትዮጵያውያን ሲቀበሉት አማሮች አይቀበሉትም። የወያኔ መንግሥት የዛሬዎቹን አማሮች የሚያጠቃው ኢትዮጵያን በጎሳ ለመበታተን የሚያደርገውን ጥረት አንቀበልም በማለት እንቅፋት ስለሆኑበት ነው። የአማራው ቍጥር እንዲቀነስ፥ የተረፈው ለሀገር አንድነት ድርና ማግ መሆኑ እንዲያቆም ከየቦታው እያሶጡ አንድ ቦታ እንዲታጎር፥ ሙሉ ዘመቻ ዘምተውበታል።

የወያኔ የሐሰት ክስ፤

ወያኔዎች አማሮችን፥ “ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያዊነት የምትሉት የመንግሥቱ ባህል የናንተን ባህል ስለያዘ ነው” ይሏቸዋል። የዚህ ወቀሳ ምንጩ ታሪክ ከአለማወቅ የመጣ ወይም አንገት ለማስደፋት የታቀደ ተንኮል ነው። የሆነው ግን ወያኔዎቹ እንደሚሉት ብቻ ሳይሆን፣የተገላቢጦሽ ሂደትም አለበት። አማሮች (ሀ) ናቸው የመንግሥቱን ባህል ወስደው አማራ የሆኑ እንጂ የጥንቱ መንግሥት ባህል የአማሮች ባህል አልነበረም። መንግሥቱ ሲቋቋም የራሱ ባህል ነበረው፤ ቋንቋውም ግዕዝ ሳይሆን አይቀርም። ከላይ እንደገለጥኩት መንግሥት አማርኛን ቋንቋው ያደረገው የአማርኛ ተናጋሪው ቍጥር ትልቅ ስለነበረ ነው። እርግጥ መንግሥቱ አማርኛን ቋንቋው ማድረጉ ለአማርኛ መስፋፋት ረድቷል፤ ግን አማርኛ የተስፋፋው የመንግሥት ቋንቋ በመሆኑ ብቻ አይደለም። የመንግሥቱ እጅ እማይደርስበት ቦታ ሁሉ አማርኛ ይነገርበት ነበር። ደግሞስ መንግሥት ያቋቋሙት አማሮች ከሆኑ ያስከብራቸዋል እንጂ አያስወቅሳቸውም። እማን ላይ ቆመው በአማራው ያማርራሉ!

ወያኔዎችና አማሮች አይግባቡም፤

ወያኔዎችና አማሮች ከማይግባቡባቸው ጉዳዮች ዋናው፥ ወያኔዎች “በጎሳ ተከፋፈሉ” (አገሪቷ ትበታተን) ሲል አማሮች “አሻፈረን” ማለታቸው ነው። ከጎሳዎች ውስጥ አንዳንዶች መከፋፈሉን ይደግፋሉ። አማሮች የኢትዮጵያን በጎሳ መከፋፈል የሚቃወሙት የጎሳዎች መብት መከበርን ለመቃወም ይመስላቸዋል። ግን ሁለቱ ግንኙነት የላቸውም። እርግጥ የጎሳ ቋንቋዎች መጻፊያ እንዳይሆኑ መንግሥት የከለከለበት ጊዜ ነበረ። አንደኛ፥ ለዚያ ተጠያቂው አማሮች አይደሉም፤ ሁለተኛ፥ የጎሳዎች መብት ባይከበር አማሮች ምንም የሚያገኙት ጥቅም የለም። ጥቅም ካላገኙበት ለምን ይቃወማሉ? ሦስተኛ፥ አሁን ያ ከአለፉት ጋር አብሮ አልፏል፤ አራተኛ፥ አማርኛ ተናጋሪዎች “ባህል ይጨቆን” አይሉም፤ “የሚሉት ባህልን ማስከበር የሚቻለው ሰላምንና የሀገርን ጥንካሬ በሚያመጣ ስልት እንጂ የግድ መለያየትን፣ መበታተንን፥ በሚያስከትል መንገድ መሆን የለበትም” ነው።

አራተኛውን ነጥብ ለማብራራት፥ የጎሳውን ቋንቋና የአካባቢውን ታሪክ ከኢትዮጵያ ታሪክና ከብሔራዊ ቋንቋ ጋር ጎን ለጎን ማስተማር አማራጭ ሊኖረው የማይገባ ዘዴ ነው። መንግሥት የሚቋቋመው የሀገር ዳር ድምበር ለማስከበር፥ የሕዝብን ሰላም ለመጠበቅ፣ ሕዝቡ ኢኮኖሚውን እንዲያዳብር መንገዱን ለመጥረግ፣ ክፍትና ሰላማዊ ለማድረግ ነው። ወያኔዎች የመጡት ግን ይህን ሁሉ ለመቃረን ስለሆነ ይኸን አማራጭ ዞር ብለው እንደማያዩት በሥራ አሳይተውናል። አንድነትን ጠብቀን በምርጫ ጊዜ ለኢኮኖሚው እድገት የጎሳየ ሰው ይጠቅመኛል የሚል እሱን መምረጥ ይችላል።

የሀገርን ኢኮኖሚ ከማዳበር የተለየ የፖለቲካ ዓላማ ያለው ዜጋ ካለ ሌላው ሞኝ ነው። ደንቆሮም ክፉም ልንለው እንችላለን። የሀገር ኢኮኖሚ ሊዳብር የሚችለው ሕዝብ የሚቆጣጠረው መንግሥት ሲኖር ብቻ ነው። በተገላቢጦሽ እንደወያኔ የሕዝብን ሕይወት የሚቆጣጠርና ዳር ድምበር የማያስከብር መንግሥት ለኢኮኖሚው መዳበርና ለሀገሪቱ ጥቅም ማሰብ አይችልም፤ ዘበት ነው። ይህ ነቀፌታ ከብዙዎች የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሊቃውንት በተነሣ ቍጥር የወያኔዎችና የደጋፊዎቻቸው መልስ፥ “በሀገራችን የምንገነባውን አታዩም ወይ? ኢትዮጵያን ለውጠናታል” የሚል ነው። ኢኮኖሚስቶች እንደሚነግሩን መጀመሪያ መገንቢያው ገንዘብ አገር በቀል አይደለም፤ ከውጪ የመጣ ነው። እርግጥ ከውጪ ገንዘብ ማምጣት መንግሥታት ሁሉ የሚመኙት ነው። ግን ገለልተኛ ተቆጣጣሪ ከሌለ ገንዘቡ ለታሰበው ሥራ መዋሉ በምን ይታወቃል? ፎቅ ቤቶች የሚያሳዩን “ከውጪ የመጣውን ገንዘብ ሁሉንም አልጠጣንበትም፥ ሁሉንም የግል ግምብ ቤት አልሠራንበትም፥ ሁሉንም የግል ንግድ አላቋቋምንበትም፥ ሁሉንም እውጭ አገር ባንክ በየስማችን አልሸሸግነውም” ለማለት አይደለም?

ወያኔዎችና አማሮች ከማይግባቡባቸው ሌላው ዋና ጉዳይ የዲሞክራሲና የነፃነት ነገር ነው። ወያኔዎች ለዲሞክራሲ ዋጋ እንደማይሰጡት አስመስክረዋል። በዚህም ትልቋን ኢትዮጵያ አዋርደዋታል። ውርደቱን አለመቀበላችንን በቃል ሳይሆን በሥራ ማሳየት ይኖርብናል። የአንድ ሀገር ዜጋ ለዲሞክራሲ አስተዳደር ቅድሚያ ካልሰጠ ኋላ ቀር ደንቆሮ ነው። ለዲሞክራሲ አስተዳደር በመታገል ፈንታ መገዛትን ከተቀበለ፥ ደረጃውና ክፍሉ ከመላእክት ደረጃ ወርዶ ከእንስሳት ጋር ይሆናል፤ ይነዳል፤ እንደ አጋሰስ ጭነት ያጓጕዛል። በዚያው አንጻር የሕዝብን የዲሞክራሲ ጥያቄ የሚጨቁን ገዢ የዲያብሎስ መልክተኛ ነው።

መደምደሚያ፤
ድርሰቴን በተነሣሁበት ለማጠቃለል፥ በዘር ሲታይ የአማራ ጎሳ የለም። በመንግሥት ባህል ሲታይ አለ። ወያኔዎች ስለኢትዮጵያ አንድነት የሚቆረቆረውን ሁሉ ሲያጠፉ አማራውን ለምን ተቀዳሚ ዓላማቸው እንዳደረጉት ሊገባንና በግላጭ ልንቋቋመው ይገባናል። ዓላማቸው “የኢትዮጵያ አንድነት የለም” ለማለት ነው። በሥራ “እምቢ አሻፈረኝ” እንበል። የሚገርመው አማራው የሚመታው የኢትዮጵያን አንድነት ያነገበና የአንድነት ባንዲራ የሚያውለበልብ መሆኑ እየታወቀ፥ “ኢትዮጵያ አንድ ናት” ከሚለው ወገን ውስጥ የደረሰለት ቍጥሩ ኢምንት ነው። ይኸ ብቻ አይደለም፤ አማራው ራሱ “ለአማራው ብቆረቆር ጎሰኛ እሆናለሁ/እባላለሁ፤ ለአማራው እየተቆረቆርኩ ለጎሳው የሚቆረቆረውን እንዴት እነቅፋለሁ?” በማለት ጭጭ ብሎ ራሱን ደፍቶ መርዶውን ያዳምጣል። በሞኝነት ከወያኔ ወጥመድ ገብቷል። “ኢትዮጵያ አንድ ነች፤ አትከፋፈልም” በማለቱ ለሚያጠቁት የአንድነት ወገን መድረስ ኢትዮጵያዊነት እንጂ ጎሰኝነት አይደለም። ወያኔዎች አማራውን የሚመቱት የአንድነት ኃይልን ለማዛል መሆኑ የገባቸው በቍጥር ናቸው። ግን የአማራውን ሕዝብ መሠረት ያላደረገ የአንድነትና የነፃነት ትግል አለት ድንጋይ እያለለት ቤቱን አሸዋ ላይ እንደመሠረተ ሞኝ ሰው፥ ወይም መድፉን ከካዝና ቈልፎበት በሽጉጥ እንደዘመተ ሠራዊት ይቈጠራል።

The post አማራ የሚባል ዘመድ አለ ወይስ የለም? | ጌታቸው ኃይሌ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

የፊታችን ሐሙስ በሚኒሶታ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ተጠየቀ

$
0
0

st paul Ethiopia
(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ የሚገኘው የኦሮሞ ማህበረሰብ የፊታችን ሐሙስ ዴሴምበር 10, 2015 ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ:: በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ማንኛውም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ እንዲገኝ ተጋብዟል::

አዲሱን የአዲስ አበባን ማስተር ፕላንና ሰሞኑን በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም የተጠራው ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ሴንት ፖል በሚገኘው ስቴት ካፒቶል ሐሙስ ዴሴምበር 10 ከቀኑ ከ12 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ታውቋል::

ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በማውገዝ እንዲሁም በቅርቡ ለሱዳን የሚሰጠውን የኢትዮጵያ ሰፊ መሬትንና በሌሎች አካባቢዎች እየተፈጸመው ያለውን የመሬት ነጠቃ አካተው ለማውግዝ በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንዲገኙ በሚኒሶታ የሚገኙት ኢትዮጵያ ወጣቶች ንቅናቄ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::

በሚኒሶታ የሚገኙት የኢትዮጵያ ወጣቶች ንቅናቄ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም በሚኒሶታ የተደረጉ በርካታ የሕወሓት መንግስ ስብሰባዎችን እንዳኮላሹት ሁሉ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ኦሮሚያን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች እየተደረጉ ያሉ ግድያዎችን እና መሬት ነጠቃዎችን በማውገዝ ይህን የተቃውሞ ሰልፍ ይቀላቀላሉ:

The post የፊታችን ሐሙስ በሚኒሶታ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ተጠየቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ለታዋቂዋ የትግርኛ ሙዚቃ ድምጻዊት የህክምና ወጪ የሚውል የገቢ ማሰባሰብ በዋሽንግተን ዲሲ ተዘጋጀ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ የትግርኛ ሙዚቃ ስልት ታዋቂ ከሆኑት አንፋ ድምፃዊት የሆነችው አርቲስት ንግስቲ ሃየሎም መታመሟ ተሰማ:: በዋሽንግተን ዲሲም ለአርቲስቷ የህክምና ወጪ የሚሆን የገቢ ማሰባሰብ ወዳዶቿ ማዘጋጀታቸውን ለዘ-ሐበሻ የተላከው መረጃ አመልክቷል::

ለድምጻዊቷ የህክምና ወጪ መሸፈኛ የሚውለው የገቢ ማሰባሰብ የሚደረገው በዋሽንግተን ዲሲ በኩዊን ኦፍ ሼባ ሬስቶራንት ዲሴምበር 20, 2015 ከቀኑ 4 ሰዓት ጀምሮ መሆኑ ታውቋል::

ሕዝብ ተገኝቶ አርቲስቷን በህክምና ወጪ እንዲጋራ ጥሪ የቀረበበት በራሪ ወረቀት እንደሚከተለው ተስተናግዷል::
Nigisti Hayelom

The post ለታዋቂዋ የትግርኛ ሙዚቃ ድምጻዊት የህክምና ወጪ የሚውል የገቢ ማሰባሰብ በዋሽንግተን ዲሲ ተዘጋጀ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የቅማንት የራስ አስተዳደር ቢቋቋም የየትኛዉ ህዝብ ጥቅም ይነካል? (በጥላሁን ጀምበር)

$
0
0

wpid-img_5725580438707በአገር ዉስጥም ሆነ ከአገር ዉጭ የሚገኘዉ ተቃዋሚ ኃይል የግል ፍላጎትን ተመርኩዞ የቅማንት ብሄረሰብ የራስ አስተዳደር ጎንደር ላይ ቢቋቋም የሰፊዉ አማራ ህዝብ ጥቅም በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጎዳ በመጥቀስ ህዝቡን በተሳሳተ መንገድ እንዲያስብና ከቅማንት ህዝብ ጋር አላስፈላጊ ጦርነቶች እንዲካሄዱ የሚያደርጉ የዉሸት ቅስቀሳዎች (propagandas) ሌት ተቀን እያካሄዱ እንደሆነ እናዉቃለን፡፡ ስለሆነም ለእነዚህ የዉሸት ቅስቀሳዎች መልሳችን የሚከተለዉን ሊመስል ይገባዋል ባይ ነኝ፡-

  1. በመጀመሪያ ደረጃ የቅማንት ብሄረሰብ የጠየቀዉ የራስ አስተዳደር ጥያቄ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የሚገዛበትን ወይም የሚተዳደርበትን ህገ-መንግስት (የህጎች ሁሉ የበላይ በሆነዉ ህግ) መሰረት የቀረበ እንጅ እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ በግለሰቦች ወይም በቡድኖች ፍላጎት ላይ ተመስርቶ አይደለም፡፡ የምንገዛበት ህገ-መንግስት ወይም ሌሎች ህጎች ሁሉ የሁሉንም ህዝቦች ጥቅም ባከበሩና ባቻቻሉ መንገድ የሚቀረፁና የሚተገበሩ እንጅ የአንዱን ህዝብ ጥቅም ብቻ በሚያስከብር ሁኔታ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለሆነም የቅማንት ብሄረሰብ የራስ አስተዳደር በሚቋቋምበት ወቅት የቅማንትና የአማራን ህዝቦች ጥቅሞች ባከበረ ወይም ባቻቻለ መንገድ መሆኑ የማይቀር ነዉ፡፡
  2. የቅማንት ብሄረሰብ የራስ አስተዳደር የሚዋቀረዉ የቅማንት ህዝብ በኩታ-ገጠም ሰፍሮ በሚገኝባቸዉ ቀበሌዎች እና ጎጦች እንጅ ተቃዋሚዎች እንደሚያስወሩት ቅማንት ያልሆነዉን አማራ ሁሉ በጉልበት በቅማንት አስተዳደር ዉስጥ እንዲገባ በማድረግ አካሄድ አይደለም፡፡ ካሁን በፊት የክልላችንና የፌዴራል መንግስቶቻችን የቅማንት ህዝብ ከጠየቃቸዉ 126 ቀበሌዎች መካከል ያፀደቋቸዉ 42 የቅማንት ቀበሌዎች ፍፁም ኩታ-ገጠም መሆናቸዉ ሃቅ ነዉ፡፡ ይሁን እንጅ ሌሎች በርካታ ቀበሌዎችና ጎጦች አሁንም ፍፁም ኩታ-ገጠም ሆነዉ ሳለ በቅማንት አስተዳደር ስር ሳይካተቱ መዘለላቸዉ እና የ42 ቀበሌዎች ብቻ ዉሳኔ አላስፈላጊ የሆነ ደም አፋሷል፡፡ ይህን ተከትሎም መንግስት የቅማንት የራስ አስተዳደር የሚፈታዉ በጠበንጃና በኃይል ሳይሆን በህዝብ ፍላጎትና ቀጥተኛ ተሳትፎ እንደሚሆን አቋም ወስዷል፡፡ የቅማንት ህዝብ ብቻ ሰፍሮ የሚገኝባቸዉና ፍፁም ኩታ-ገጠም የሆኑ ቀበሌዎችንና ጎጦች በተመለከተ በቅማንት ህዝብ ቀጥታ ተሳትፎ የሚወሰኑ ሲሆን ከአማራ ህዝብ ጋር እንደመጠኑ ብዛት ተቀላቅለዉ የሚገኙትን ቀበሌዎችና ጎጦች በሚመከለት ግን ሁለቱም ህዝቦች በነፃነት ይወስናሉ፡፡ በህዝበ-ዉሳኔ (referendum) ስርዓት ሁለቱም ህዝቦች ማንም ሳያስገድዳቸዉ ድምፅ በሚሰጡበት አካሄድ ተፈፃሚ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
  3. የሁለቱን ህዝቦች ፍላጎት ባጣጣመ መንገድ በቅማንት አስተዳደር ስር የሚካተቱት ቀበሌዎችና ጎጦች በግልፅ ከታወቁ በኋላ ቀጥሎ የሚመጣዉ ጉዳይ የቅማንትን አስተዳደር በልዩ ወረዳ ደረጃ ሳይሆን በዞን ደረጃ ማደራጀት ይሆናል፡፡ ምክኒያቱ ደግሞ ግልፅና ግልፅ ነዉ ፡ በቅማንት አስተዳደር ስር የሚካተቱት ቀበሌዎችና ጎጦች ቁጥር ብዙ ከመሆናቸዉ አንፃር የቅማንትን ህዝብ በልዩ ወረዳ አጭቆ ወይም ጨፍልቆ ማስተዳደር የባሰ የመልካም አስተዳደር ችግር መፍጠር ይሆናል፡፡ በአገሪቱም ሆነ በክልል 3 ዉስጥ ያሉት የአስተዳደር መዋቅሮችም በተሞክሮ የሚያሳዩት ይህንን ነዉ፡፡ ይህ ማለት የአሁኑ ሰ/ጎንደር ዞን በጥቅሉ ከሁለት ተከፍሎ ሁለት የዞን አስተዳደሮች ይኖሩታል፡-

1)የቅማንት ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር 2) ሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር፡፡ ለሁለቱም የዞን አስተዳደሮች የዞን መስሪያ ቤቶች (መምሪያዎች፣ የዞን ፍ/ቤቶች) መቀመጫ በታሪካዊቷ ከተማ ጎንደር ይሆናል፡፡ በእርግጥ ጎንደር ከተማ ልዩ አስተዳደር ሆና ከቋቋመች ቆይቷል፡፡ ስለሆነም ርዕሰ መዲና እንደመሆኗ መጠን የሁለቱ ህዝቦች የዞን አስተዳደሮች መቀመጫ ብቻ ሳይሆን የከተማዉ ልዩ አስተዳደር መቀመጫም ሆና ጎንደር ከተማ ማገልገሏ የማይቀር ነዉ፡፡

  1. ይህ ከሆነ በኋላ ቅማንቶችም ሆነ አማሮች የራሳቸዉን ክልል ያለማሉ፤ጎንደር ከተማን ከሌሎች ብሄር-ብሄረሰቦች ጋር በመሆን በጋራ ያለማሉ፤ ጎንደር ከተማ ከሚገኘዉ ጥቅምም እኩል ተጠቃሚ ይሆናሉ እንጅ ድሮዉንም ጎንደር ከተማ የተቋቋመበት መሬት የቅማንቶች ስለነበር አሁንም ከጎንደር ከተማ ዉጭ እንሆናለን የሚል ምክኒያታዊ ያልሆነ ስጋት ሊፈጠር አይገባዉም፡፡ የቅማንት ህዝብም የራሱን ጥቅም አስከብሮ የሌሎችን ህዝቦች ጥቅም ያለአግባብ ሳይነካ ጥቅምን አቻችሎ አብሮ እንዴት መኖር እንዳለበት ጠንቅቆ የሚያዉቅ አስተዋይ ህዝብ እንደሆነ ታሪክ የሚመሰክረዉ እዉነታ ስለሆነ በግለሰቦች ወይም ቡድኖች የግል ፍላጎት ብቻ አቅጣጫዉን ስቶ ደጉ የቅማትም ሆነ የአማራ ህዝብ በወሬ ተነድቶ ወደ አላስፈላጊ ጥልቻና ግጭት እንደማይገባ እርግጠበኛ መሆን ይገባናል፡፡
  2. ከዚህ በላይ በተገለፀዉ አግባብ የቅማንት አስተዳደር የህዝብን ፍላጎት መሰረት አድርጎ ቢቋቋም በጎረቤት አማራ ወንድሞች በኩል አንድም አይነት ጉዳት አያመጣም፡፡ ይልቁንስ በብዙ መንገዶች የጋራ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ጎጃም ዉስጥ የአዊ አገዎች ልማት ለሌሎች አማራ ወንድሞች እንዴት እንደጠቀመ ጠንቅቀን እናዉቃለን፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የሰ/ጎንደር አማሮችና ቅማንቶች ማንነታቸዉን መሰረት አድርገዉ የራሳቸዉን የቤት ስራ ለመስራት የአስተዳደር ክልላቸዉን ተከፋፈሉ እንጅ ጭራሽ ላይገናኙ ሊፈራረሙ አይችሉም፡፡ አንዱ ካንዱ የሚወስደዉ መልካም ተሞክሮ ቀላል አይሆንም፡፡ ስለሆነም የቅማንት አስተዳደር ከተፈቀደ ቅማንት ብቻ ይለማል፤ አማራ በድህነት ይራቆታል የሚለዉ ከንቱ ወሬ ቦታ አይኖረዉም ማለት ነዉ፡፡
  3. ሌላዉ ትልቁ ቅማንትና አማራ አብረዉ እንዳይሄዱ እንደስጋት የሚነዛዉ ወሬ ወደፊት ደንበር ለይተዉ ካንዱ አካባቢ ወደ ሌላዉ አካባቢ ሄደዉ መስራት ስለማይችሉ ፍፁም በኢኮኖሚም፣በማህበራዊና በሌሎች ጉዳዮች ይለያያሉ የሚለዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ ይህ ስጋት ከከንቱ ስጋትነት ያመልጥም፡፡ ምክኒያቱም በክልል 3 ዉስጥ የስራ ቋንቋ አማርኛ እንደሆነ የክልሉ ህገ-መንግስት ደንግጓልና፡፡ ቅማንትኛ ቋንቋ አደገም አላደገም የክልሉ ህገ-መንግስት እስካልተሻሻለ ድረስ የሁለቱም ህዝቦች የመግባቢያና የስራ ቋንቋ አማርኛ ሆኖ መቀጠሉ የማይቀር ጉዳይ ነዉ፡፡ ስለሆነም ቅማንትም ሆነ አማራ በማንነቱ ሳይገለልና ሳይጨቆን በየትኛዉም ክልል ዉስጥ ተንቀሳቅሶ መስራትና መኖር እንደሚችል የፌዴራሉ ህገ-መንግስት በአንቀፅ 41 ስር ጭምር ደንግጎት የሚገኝ ጉዳይ ነዉ፡፡ ነገሩ የሚሆነዉ የእዉቀትና አመለካከት ጉዳይ ብቻ ይሆናል፡፡ ቀጥሎም የአፈፃፀም ጉዳይ ይሆናል እንጅ የስጋት ምንጭ ሆኖ አገር የሚያናጋ ጉዳይ በፍፁም ሊሆን አይችልም፡፡
  4. በመጨረሻም፡-
    7.1. ቅማንትና አማራ በማንነታቸዉ ምክኒያት ማለትም አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ወይም ቅማንት በመሆናቸዉ ብቻ እስካልተጨቆኑ ድረስ፣
    7.2. የጋራ መግባቢያና የስራ ቋንቋ (አማርኛ) እስካላቸዉ ድረስ፣
    7.3. ከቅማንት ህዝብና ሰ/ጎንደር አማራዎች ዉጭ ሌላ ሶስተኛ ወገን በጉዳያችን ዉስጥ ገብቶ እንዳይፈተፍት ማድረግ እስከቻልን ድረስ፣
    7.4. በቅማንትም ሆነ አማራ በኩል ፅንፈኛ የሆነ አቋም ይዘዉ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን ወይም ቡድኖችን (Like ESAT journalist Messay Mekonnen) ማስተካከል እስከቻልን ድረስና፣
    7.5. የቅማንት ህዝብና ሰ/ጎንደር አማራዎች ጎንደር ከተማን በጋራ እስከተጠቀሙ ድረስ አብረዉ በልማት ጎዳና የማይገሰግሱበት ምክኒያት ምንድነዉ?

ህዳር 23፣2008

The post የቅማንት የራስ አስተዳደር ቢቋቋም የየትኛዉ ህዝብ ጥቅም ይነካል? (በጥላሁን ጀምበር) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

“በገዛ አፈ-ሙዙ መቃብሩን የሚቆፍር የሽንፈትን ጽዋ ይጎነጫል !”ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

semayawi
ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማንና ዙሪያን ለማከለል ከወጣው የማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ፤ ገቢራዊነትና ሃሳቡን የተቃወሙ የኦሮሞ ተወላጆች እና የዕቅዱ ተቃዋሚዎች፣ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሌጆች እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲሁም የየከተማዎቹ ነዋሪዎች ላይ የኃይል እርምጃ እየተወሰደ እንዳለ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡

ዜጎች እያሰሙት ያለውን ተቃውሞና የሃሳብ ልዩነት በኃይልና በጠብ-መንጃ ለመመለስ የተደረገውም አግባብነትና ኃላፊነት የጎደለው ጭፍን ተግባር እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት በጽኑ ያምናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፣ መቶ-በመቶ ሁሉንም ተቋማትና መንግሥታዊ መዋቅሮች በጠቅላላ እንደልቡ የሚያዘውና ያሻውን የሚፈጽመው የኢህአዲግ መራሹ ኃይል፣ ልማትንና እድገትን በኃይልና በጉልበት እፈጽማለሁ እንዲሁም አስፈጽማለሁ ብሎ መነሳቱም መሠረታዊ የእብሪት ተግባር መሆኑም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳምሮ ያውቀዋል፡፡

በተለይም ደግሞ፣ ኢህአዲግ መራሹ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር ላይና በኢትዮጵያውያን ላይ የተከለው የጎሳ ፌዴራሊዝም ችግር ምን ያህል አስከፊ እንደሆነና ውጤቱም የዜጎችን ሞት፣ እስራት፣ ስደት፣ የንብረት ውድመትና የትምህርት መስተጓጎል ማስከተል እንደሆነ ታይቶበታል፡፡ በመሆኑም፣ የአዲስ አበባ ዙሪያ ነዋሪዎችም ሆኑ በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉት ልማትም ሆነ እድገት በ“እኔ አውቅልሃለሁ” ባዩ የኢህአዲግ አንባገነናዊ ልማትና የጎሳ ፌዴራሊዝም ሳይሆን፣ በሕዝብ-ለሕዝብ-ከሕዝብ ፍላጎትና ስምምነት ላይ የተመሠረተን ልማትና እድገት ብቻ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡

ከዚህ ዓላማና ግብ ውጪ የሚተገበር ማንኛውም የልማት ዕቅድና የከተማ ማካለልም ሁሉ የኢህአዲግ መራሹ መንግሥት አንባገነናዊ አስተዳደር ሁነኛ መገለጫ በመሆኑ አጥብቀን እንቃወመዋለን፡፡ በተከሰተው ብሔራዊ ቀውስና ችግር ዙሪያም በቀጥታ ለችግሩ ተጋላጭ ከሆኑት ዜጎች ጋር ሆነ ችግሩ በዋነኛነት ከሚያሳስባቸው የአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያ ነዋሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት ተማሪዎች ጋር ባስቸኳይ ውይይትና ንግግር እንዲደረግ እያሳሰብን፤ አንባገነኑ የኢህአዲግ መንግሥት እየተከተለው ያለውን የዜጎችን ጥያቄ በኃይልና በጉልበት ለማፈን ከሚያደርገው ፀረ-ዲሞክራሲያዊ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን፡፡

በተመሳሳይ መልኩም፣ በጎንደር ከተማ በሚገኘው ማረሚያ ቤት ላይ ተከስቶ የነበረውን የእሳት ቃጠሎን ተከትሎ ኢህአዲግ መራሹ መንግሥት የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ በማጥፋት፤ በሕግ ቁጥጥር ሥር የሚገኙትን ዜጎች ሕይወትና ደሕንነት ለመታደግ መሯሯጥ ሲገባው፣ ሕይወታቸውን ከቃጠሎው ለማዳንና ለሞከሩት ዜጎች የጥይት እሩምታ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ከዚህ መንግሥታዊ ተግባርና ቸልተኝነት ተነስተን እንደምንረዳው ከሆነ፣ አገዛዙ ለማንኛውም ዜጋና አገራዊ ጉዳይ የሚሰጠው ምላሽ ከጠብ-መንዣና ከጉልበት የማይዘል መሆኑን በግልጽ አስመስክሯል፡፡ ይህንንም መሰሉን ኢ-ሰብአዊና ኢ-መንግሥታዊ ተግባር የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት በቸልታ እንደማይመለከተው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመግለጽ ይገደዳል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤትም መንግሥት የሚፈጽማቸውን ኃላፊነት የጎደላቸው ተገባራት እስኪያቆሙ ድረስ፣ አንባገነናዊው ሥርዓት የሚፈጸመው የሕገ-አራዊት ተግባራት እስካለቆሙ ድረስ፣ ሕጋዊና ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

ከዚህም በተጨማሪ፣ ኢህአዲግ መራሹ መንግሥት የአዲስ አበባ ዙሪያ ማስተር ፕላንን በኃይል ለመተግበር ሲባል ስለሞቱት፣ ስለታፈሱት፣ ስለተሰደዱትና ስለተሰወሩት ዜጎች ጉዳይ የሚያጣራና በጎንደርም ከተማ በሚገኘው ማረሚያ ቤት ስለተከሰተው የእሳት ቃጠሎና ከርሱም ጋር ተያይዞም ስለተፈፀመው የጅምላ-ፍጅት ጉዳይ የሚያጣሩ ገለልተኛ የሆኑ አጣሪና አካል ተቋቁመው ስለተፈጠረው ዘግናኝና ኢ-ሰብአዊ ተግባር መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትክክለኛውን መረጃ እንዲያገኝ እና ወንጀለኞችም ለፍረድ እንዲቀርቡ መደረግ አለበት፡፡

ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ ኢህአዲግ መራሹ መንግሥት በያዘው የእብሪት መንገድ የሚገፋ ከሆነ የገዛ መቃብሩን በገዛ አፈ-ሙዙ እየቆፈረ እንደሆነም እየገለጽን፤ አጥፍቶ-ጠፊው ኢህአዲግም ሆነ ኢህአዲግአውያን አጀንዳቸውን በኃይል እናስፈጽማለን ብለው የቁም ሕልም ሲያልሙ፣ በቁማቸውም እንደሚቀበሩ ሊያውቁት ይገባል፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር !!!
ኀዳር 27 ቀን 2008 ዓ.ም

The post “በገዛ አፈ-ሙዙ መቃብሩን የሚቆፍር የሽንፈትን ጽዋ ይጎነጫል !” ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

የተማሪዎቹ ቁጣ ዛሬም በተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል –በአዳማ፣ አምቦ፣ ሱሉልታ፣ ወለጋና ቡሌ ሆራ ውጥረት አለ |በሃሮማያ አንድ ተማሪ ተገደለ

≫ Next: Hiber Radio: ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው ድርድር ይራዘምልኝ ስትል ጠየቀች፣ ኢትዮ-ኬኒያ በጋራ ድንበሮቻቸው ላይ የጸጥታ እና ውጥረት የማብረድ ስራ ሊሰሩ መሆናቸውን አሳወቁ፣ አገዛዙ በኦሮሚያ በማስተር ፕላን ስም የጀመረው የመብት ረገጣ የድርቁን አደጋ ትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየርና ሕዝቡን ለመከፋፈል ሊጠቀምበት እየሞከረ መሆኑ ተገለጸ ፣ ቃለ መጠይቅ ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ እና ከፓርቲው ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሰብሳቢ አቶ ነጌሳ ኦዶ ጋር በወቅታዊው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞና የተወሰደው የግፍ እርምጃ ላይ ወቅታዊ ዘገባና ሌሎችም አሉን
$
0
0
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በፌደራል ፖሊስ ተወሮ

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በፌደራል ፖሊስ ተወሮ

ሙገር

ሙገር

ሱሉልታ

ሱሉልታ

ሱሉልታ

ሱሉልታ

(ዘ-ሐበሻ) 2ኛ ሳምንቱን የያዘው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ በአዳዲስ ከተሞችም ቀጥሎ መዋሉ ተሰማ:: በአዲስ አበባ እና በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የተገደሉ ተማሪዎችን ለማሰብ ተማሪዎች ተሰብስበው የነበረ መሆኑ ታውቋል::

በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎቹ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሎ በዚያው አካባቢ የነበረ አንድ የ9ኛ ክፍል ተማሪ በፌደራል ፖሊስ መገደሉ ተሰምቷል:: እየተደረገ ያለው ተቃውሞ ከዩኒቨርሲቲዎች ወርዶ እስከ መለስተኛ ሁለተኛ ትምህርት ቤቶች ደርሷል:: በቡራዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎቹ ማስተር ፕላኑን እና የተፈጸመውን ግድያ ሲያወግዙ የዋሉ ሲሆን አሁንም አካባቢው በፌደራል ፖሊስ ተወጥሮ እንደሚገኝ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል::

ይህ የተማሪዎች ተቃውሞ በአዳማ ዩኒቨርሲቲም የተሰማ ሲሆን ፌደራል ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን የሃይል እርምጃዎችን ሲወስድ እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል::

በሱሉልታም እንዲሁ የመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከነዩኒፎርማቸው አደባባይ የዋሉ ሲሆን ማስተር ፕላኑን አጥብቀው ሲያወግዙት ውለዋል::

በአምቦ ዩኒቨርሲት በነበረው ተቃውሞ በርካታ ተማሪዎች በደረሰባቸው ድብደባ ቢጎዱም ይህ የባሰ ውጥረቱን እንዳባባሰው መረጃዎች ጠቁመው ተማሪዎቹ አሁንም አምርረው በመቃውም ላይ መሆናቸው ታውቋል::

በሙገር የተደረገው ተቃውሞ ከተማሪዎች አልፎ ገበሬዎችን እና የመንግስት ሠራተኞችንም ጭምር ያካተተ እንደነበር ሲሰማ ውጥረቱ አሁንም እንዳለ መሆኑ ተሰምቷል::

የአዲስ አበባ አዲሱ ማስተር ፕላን ገበሬዎችን የሚያፈናቅልና በስፍራው የሚኖረውን አርሶ አደር ተጠቃሚ የሚያደርግ ሳይሆን የመሬት ቅሚያ ነው በሚል በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተነሳው ተቃውሞ ማብረጃው ማስተር ፕላኑን መሰረዝ ብቻ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ:: መንግስት ይህን ካላደረገ ወይም ሰብስቦ ካላነጋገረ ይህ ተቃውሞ ወደ ህዝባዊ አመጽ ሊሸጋገር እንደሚችል ይገመታል::

The post የተማሪዎቹ ቁጣ ዛሬም በተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል – በአዳማ፣ አምቦ፣ ሱሉልታ፣ ወለጋና ቡሌ ሆራ ውጥረት አለ | በሃሮማያ አንድ ተማሪ ተገደለ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Hiber Radio: ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው ድርድር ይራዘምልኝ ስትል ጠየቀች፣ ኢትዮ-ኬኒያ በጋራ ድንበሮቻቸው ላይ የጸጥታ እና ውጥረት የማብረድ ስራ ሊሰሩ መሆናቸውን አሳወቁ፣ አገዛዙ በኦሮሚያ በማስተር ፕላን ስም የጀመረው የመብት ረገጣ የድርቁን አደጋ ትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየርና ሕዝቡን ለመከፋፈል ሊጠቀምበት እየሞከረ መሆኑ ተገለጸ ፣ ቃለ መጠይቅ ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ እና ከፓርቲው ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሰብሳቢ አቶ ነጌሳ ኦዶ ጋር በወቅታዊው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞና የተወሰደው የግፍ እርምጃ ላይ ወቅታዊ ዘገባና ሌሎችም አሉን

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ህዳር 26 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…የተማሪዎቹ ጥያቄ የዴሞክራሲ ጥያቄ ነው።የመብት ጥያቄ ነው። ተማሪዎቹ ቤተሰቦቻቸው ሲቸገሩ ሲፈናቀሉ ከመሬታቸው ሲነሱና ሲቸገሩ ያዩ ናቸው።ብሶት ነው ያስነሳቸው።በምንም መንገድ በዚህ አካባቢ ሌላው አይኑር አይደለም።የኦሮሞ ሕዝብ ከሌላው ጋር አብሮ በሰላም የኖረ ወደፊትም የሚኖር ነው።እነሱ በየጊዜው ስንት ነገር ለማቀጣቀጠል ሕዝቡን ከሕዝብ ለማጋጨት ሞክረው አልተሳካላቸውም።ሕዝቡ አብሮ የኖረ ይሄን የተረዳ ሕዝብ ነው…ዓለም ገና ላይ በማይክራፎን የሌላ ብሄር ተወላጅ የሆናችሁ ስብሰባ ውጡ ብለው ኦሮሞ ሊያጠፋችሁ ነው የሚል ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር ይሄ የዚህ ስርዓት ውሸትና ፕሮፖጋንዳ ነው…>
አቶ በቀለ ነጋ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ(ኦፌኮ) ዋና ጸሐፊ በኦሮሚያ ክልል የአገዛዙን ማስተር ፕላን ማሻሻያ በመቃወም ሰልፍ ወጥተው ስድስት ተማሪዎች የተገደሉበትን የተቃውሞ እንቅስቃሴና የአገዛዙን ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት ያሰበ ቅስቀሳ በተመለከተ ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
Hiber Radio
<…በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን የግፍ ግድያ በመቃወም የተጠራው የሐሙሱ ሰላማዊ ሰልፍ በሚኒሶታ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ከተሞች ይደረጋል። የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ብቻ ሳይሆን ሰው ሁሉ የሆነ ሁሉም በአንድ ላይ እንዲቃወመው በተማሪዎቹ ላይ የተወሰደው የጭካኔ እርምጃ እንዲያወግዘው ያስፈልጋል ። …ብሄርን ከብሄር ለማጋጨት የሚሞክሩት የሚያወሩት ላይ ትኩረት ማድረግ አያስፈልግም በአንድ ላይ ተቃውሞን ማሰማት ያስፈልጋል…>

አቶ ነጌሳ ኦዶ የኦፌኮ ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሰብሳቢ በመጪው ሐሙስ በተለያዩ ከተሞች ስለተጠራው በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም ሊካሄድ ስለታቀደው ሰላማዊ ሰልፍና ተያያዥ ጉዳዮች ከሰጡትን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…ሁበር ሲያሽከረክዩ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ችላ ማለት ነጥብ ላይ የሚያመታው ተጽጨዕኖ አለ። ያንን መረዳት ያስፈልጋል። ነጥቡ ዝቅ ሲል ተመልሲ መውጣት የሚችለው ሌላ የተሻለ ነጥብ መስጠት የሚችል ተሳፋሪ በሚሰጠው አስተያየት ወይም ነጥብ ነው። ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ግን አሉ…አሌክስ አበራ በሳንፍራንሲስኮ በሁበር ብላክ ላይ የተሰማራ ሁበር በማሽከርከር ላይ የገጠሙትን ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በተመለከተ ከሰተው አስተያየት(ሙሉውን አዳምጡ

<…በቬጋስ ሰላሳ ሁለት ዓመት ኖሬያለሁ። አንድ ቀን ቁማር ተጫውቼ አላውቅም። ያኔ ስመጣ ግርማ ጂሚ ስለ ቁማር የነገረኝ አይረሳኝም። ተመልከተው ይሄኛውን ቁማር ይጫወታል ቤቱ ቴሌቬዥን የለውም ፣ይሄኛው ማደሪያ እንኳን የለውም ይሄኛው ቤቱ ቴሌቬዥን አለው አለኝ።ያኔ ቴሌቪዥን እንደ ትልቅ ነገር ነበር ለኛ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ቁማር እስካሁን አልተጫወትኩም…በእኛ ጊዜ መንገድ የሚያሳየን ጠፍቶ ነው።ወጣቶች ታክሲ ላይ ሳያቸው እናለሁ።ስራው የትም አይሄድም ትምህርት ቤት መሄድና መማር አለባቸው…>

አቶ ገዛኸኝ ተፈራ በቬጋስ የረጅም ጊዜ ነዋሪና 27 ዓመት ታክሲ ያሽከረከሩ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ መጠይቅ ሁለተኛ ክፍል(ሙሉውን ያዳምጡት)

በአሜሪካው የካሊፎርኒያ ግዛት ሰሞኑን ሁለት ባልና ሚስት አሸባሪዎችበወሰዱት እርምጃ አንድ ሐበሻን ጨምሮ የ14 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል። እርምጃውን የወሰዱት አሸባሪዎች ማንነት እና አሳዛኙ ድርጊት ሂደትን በስፋት ዳሰነዋል (ልዩ ጥንቅር)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን

– የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰዱት የሀይል እርምጃ ዓለም አቀፍ ውግዘት ገጠመው
– ዕቅዱን ጀምረነዋል እንጨርሰዋለን ሲሉ ዝተዋል
– ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው ድርድር ይራዘምልኝ ስትል ጠየቀች
– ኢትዮ-ኬኒያ በጋራ ድንበሮቻቸው ላይ የጸጥታ እና ውጥረት የማብረድ ስራ ሊሰሩ መሆናቸውን አሳወቁ
– አገዛዙ በኦሮሚያ በማስተር ፕላን ስም የጀመረው የመብት ረገጣ የድርቁን አደጋ ትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየርና ሕዝቡን ለመከፋፈል ሊጠቀምበት እየሞከረ መሆኑ ተገለጸ

The post Hiber Radio: ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው ድርድር ይራዘምልኝ ስትል ጠየቀች፣ ኢትዮ-ኬኒያ በጋራ ድንበሮቻቸው ላይ የጸጥታ እና ውጥረት የማብረድ ስራ ሊሰሩ መሆናቸውን አሳወቁ፣ አገዛዙ በኦሮሚያ በማስተር ፕላን ስም የጀመረው የመብት ረገጣ የድርቁን አደጋ ትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየርና ሕዝቡን ለመከፋፈል ሊጠቀምበት እየሞከረ መሆኑ ተገለጸ ፣ ቃለ መጠይቅ ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ እና ከፓርቲው ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሰብሳቢ አቶ ነጌሳ ኦዶ ጋር በወቅታዊው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞና የተወሰደው የግፍ እርምጃ ላይ ወቅታዊ ዘገባና ሌሎችም አሉን appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አሰቃቂ አደጋ ኮልፌ ልኳንዳ አካባቢ ተከሰተ –ሚኒባስ ሙሉ ህፃናት ሕይወታቸው ማለፉ እየተነገረ ነው

≪ Previous: Hiber Radio: ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው ሕዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረው ድርድር ይራዘምልኝ ስትል ጠየቀች፣ ኢትዮ-ኬኒያ በጋራ ድንበሮቻቸው ላይ የጸጥታ እና ውጥረት የማብረድ ስራ ሊሰሩ መሆናቸውን አሳወቁ፣ አገዛዙ በኦሮሚያ በማስተር ፕላን ስም የጀመረው የመብት ረገጣ የድርቁን አደጋ ትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየርና ሕዝቡን ለመከፋፈል ሊጠቀምበት እየሞከረ መሆኑ ተገለጸ ፣ ቃለ መጠይቅ ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ እና ከፓርቲው ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን ሰብሳቢ አቶ ነጌሳ ኦዶ ጋር በወቅታዊው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞና የተወሰደው የግፍ እርምጃ ላይ ወቅታዊ ዘገባና ሌሎችም አሉን
$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በየቀኑ እየደረሰ ያለው የመኪና አደጋ አስከፊነቱና አሳዛኝነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጨመረ መጥቷል:: የዚህ ዜና ዘጋቢ የዘ-ሐበሻ ከፍተኛ ሪፖርተር በአንድ ወር ውስጥ 2 ጓደኞቹን ሕይወት በመኪና አደጋ አጥቷል:: ይህ የሚያሳየው ምን ያህል የመኪና አደጋ የሃገሪቱ ከፍተኛ ገዳይ ችግር መሆኑን ነው::

ዛሬ ከአዲስ አበባ ኮልፌ አካባቢ በፎቶ ግራፍ ተደግፎ በደረሰን መረጃ መሰረት የተፈጠረው አደጋ የህፃናትን ነብስ የቀጠፈ ሆኗል:: ፖሊስ ትክክለኛውን መረጃ አይስጥ እንጂ የዓይን እማኞች እንደሚገልጹት የሞቱት አንድ ሚኒባስ ሙሉ ህፃናት ናቸው::

ዛሬ ኮልፌ ልኳንዳ አቃቂ ድልድይ አካባቢ ከትምህርት ቤት ሲመለሱ የነበሩ ህጻናት ላይ አንድ አይሱዚ መኪና የሚሄዱበትን ሚኒባስ ታክሲ በመግጨቱ በደረሰው ከፍተኛ አደጋ በሚኒባሱ ውስጥ የሚጓዙት ህፃናትን ነብስ እንደቀጠፈ የአይን እማኞች ተናግረዋል::

ፖሊስ የሟቾችን ቁጥር ይፋ እንደሚያደርግ ሲገለጽ በምርመራ ላይ እንዳለም ታውቋል:: የአደጋውን ፎቶዎች ይመልከቱ::

ኮልፌና አካባቢዋ በለቅሶ ላይ ስትሆን አካባቢው ያለው ሕዝብ በከፍተኛ ሃዘን ላይ ይገኛል::

በዚህ አደጋ ስለ ቆሰሉት እና ስለሞቱት ወገኖች ተጨማሪ መረጃዎችን አጣርተን ይዘን እንመለሳለን::

mini

mini bus 2 Mini bus selman siraj 2 selman siraj

The post አሰቃቂ አደጋ ኮልፌ ልኳንዳ አካባቢ ተከሰተ – ሚኒባስ ሙሉ ህፃናት ሕይወታቸው ማለፉ እየተነገረ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ጅብ የሚጮኸው መብላት ሲፈልግ ነው። –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

tplf-rotten-apple-245x300ወያኔ የጅብ ባህሪውን በግልጽ ማውጣት ጀምሯል።መብላት ሲፈልግ ይጮሃል ያጯጯሁ ሁኔታ በየግዜው የተለያዩ  ናቸው። ከዚህ ቀደም የወያኔ ጩኸቶችን በትንሹ ጠቋሚ የምላቸውን ሃሳቦች በማንሳት  ለመግለጽ ሞክሬአለው ዛሬ ደግሞ ስለ ሰሞኑ የወያኔ ጩኸት ኢትዮጵያኖችን ለመብላት ጅቦችን እየጠራ እንደሆነ እናያለን። የጅቦች ነብስ በከንቱ የሚቀሩ ድምጻቸውም በህይወት እስካሉ ድረስ ብቻ የሚሰማ ነው። ኢትዮጵያኖች ሆይ ሰው እንሁን ሰው የሆንን ለታ ነብሳችን በክብር ያርፋል ድምጻችንም ዘመን ተሻጋሪ ይሆናል።

የሰሞኑ የወያኔ ጩኸት በወደ ጎንደር እና በወደ አዲስ አበባ ዙሪያ እየጮኸ ይገኛል። በግፍ ሃብት ንብረቱ ለሚነጠቅ የኢትዮጵያ መሬቱ ተቆርሶ  ለሱዳን አይሰጥም የሚለው የጎንደር ገበሬ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚደረገውን የገበሬዎችን መፈናቀል ይቁም ብለው ሰላማዊ ሰልፍ በወጡት የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ በግፍ ለሚሞተው ኢትዮጵያዊ ወገኔ ልቤ እየደማ አይኖቼ እንባን እያዘነበ መሬት መሬቱን እየጫርኩኝ ግፈኞች እና በደል አድራሾች በቆፈሩት የግፍ ጉድጓድ እራሳቸው ይግቡ እያልኩኝ ሃዘኔን እገልጻለው። በደል ለሚያደርሱት በደላቸውን እንዲተዉ ምህረትን አውርድላቸው ወደ ልቦናቸው ተመልሰው መልካም እንዲያደርጉ ብዬ እንዳልጸልይ ሰይጣን ሆኑብኝ ሰይጣን ደግሞ ምህረትን አይፈልግም ወደ ምህረትም መምጣትም አይፈልግም። የወያኔ ሰዎችም ወደ ምህረት አንዱም አይመጡም መምጣትም አይፈልጉም። ሰይጣንም የሚወጣው በጸበል ኃይል ወያኔም በግድ አስገድዶ ካልሆነ በቀር ከስህተቱ ይማራሉ ብሎ ማሰብ ከንቱነት ነው።

ወያኔ (ህውሓት) ነጭ ጅብ ሆኖ ማለትም የጅቦቹ ንጉስ ሆኖ  ለመብላት ሲፈልግ ጮኾ የሚጠራቸው ጅቦች አሉት። ብአዴን፣ ኦፒዲዮ፣ እና ደህዴን ይባላሉ። እነዚህ ጅቦች ወያኔ ካልጮኸ የማይጮኹ ወያኔ ካልበላ የማይበሉ በራሳቸው ምንም ማድረግ የማይችሉ ብቻ ሁሉንም በዘር ከፋፍሎ እንደ መዶሻ በመጠቀም አማራውን በብአዴን ኦሮሞውን በኦፒዲኦ ደቡቡን በደህዴን ለመምታት የሚጠቀምባቸው የግፍ በትሮቹ ናቸው። ወያኔ በራሳችሁ ሰዎች እና በመረጣችሁት ነው የምትመሩት በሚል ቁማር ሁሉንም በተናጠል እየሄደ መብላት ጀምሯል። ልዩነታችንን ትተን አንድ ሆነን በአንድነት እስካልታገልን ድረስ ኦሮሞውን በኦፒዲኦ አማራውን በብአዴን ደቡቡን በደህዴን ተመስሎ ወያኔ እያንዳንዳችንን እንደሚጨርሰን የታወቀ ነው። ለዚህም የሚሆነውን እና የሚሰራውን ስራ እያየን ነው። ኦሮሞ ለኦሮሞ የሚለውን ትተን አማራ ለአማራ የሚለውን ትተን ደቡብ ለደቡብ የሚለውን ትተን እጅ ለእጅ ተያይዘን አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ሲዳማ፣ ሱማሌ፣ ትግሬ፣ አፋር፣ ጋንቤላ፣ ሁላችን አንድ ነን ሁላችን ኢትዮጵያዊ ነን ብለን በመነሳት ከመጥፋታችን እና ከመጠፋፋታችን በፊት ቀድመን አስበን አገርን ከጥፋት ህዝባችንንም ከመከራ መታደግ ያለበት ወሳኝ ግዜ ላይ ነን። ተነጣጥለን በወያኔ ተበልተን ከማለቃችን በፊት ለግል ፖለቲካዊ ጥቅም በማሰብ በመለያየት ስራ ውስጥ ያሉት ሃይሎች ከግል ጥቅማቸው ይልቅ አገራዊ ጥቅምን በማስበለጥ ከግላዊ ክብራቸው ይልቅ ለህዝብ ክብር ቅድሚያ በመስጠት በአንድነት ሆነን በአንድነት ቆመን ጠላትን ማሳፈር አንባገነኖችን ማጥፋት የሚያስፈልግበት ግዜ ላይ ነን። ካለበለዛ ግን ከዚህ እስከዚህ የምንለው ክልል ጠቦብን ከዚህ እስከዚያ  የምንለው ግቢ አጥተን ለመቀበሪያ የሚሆነንንም ጉድጓድ  እንዳናጣ እሰጋለው። በፍቅር በአንድነት ሆነን መታገል አቅቶን ለቁጥጥር እንዳያመች አድርገን ነገሮችን አስፍተን በትነናቸው መሰብሰብ አቅቶን መከራችንን ለልጆቻችን እንዳናተርፍ በትግሉ ጎራ ያላችሁ ፖለቲከኞች ወደ አንድ አላማ በመምጣት ኢትዮጵያን ለሁል ግዜ የሰላም ቀጠና እና የፍቅር አገር የማድረግ ሃላፊነት አለባችሁ። ህዝቡም እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በጥንቃቄ ሊከታተላቸው ይገባል።

በጎንደር ብአዴን የተባለው የወያኔ ቅጥር  የጎንደርን ሃብቱን እና መሬቱን ለሱዳን ለመስጠት ብአዴን የተባለውን ጅብ ፈርሞ  እንዲያስረክብ ወያኔ እየተሯሯጠ ነው። ምን ጎንደርን ብቻ ከወለጋን ከጋንቤላንም ጭምር እንጂ። ወያኔ ቀጥታ  እንዳይፈጽመው ህዝቡ ከተነሳ ማብረድ ስለማይችል ይሄንን እየሰራ ያለው እናተው የመረጣችሁት ብአዴን ነው ለማስባል ነው። ወያኔ በደል ሰሪ  ሆኖ ነገር ግን ነገሮቹ ከከፉ አስታራቂ መስሎ  በመግባት እራሱን በአፈር ውስጥ እንደሚቀብር እባብ በመምሰል በፈጠራቸው ድርጅቶች ውስጥ እራሱን ቀብሮ  በተመቸው ግዜ እየወጣ ህዝባችን ላይና አገራችን ላይ መርዙን በመርጨት እያጠፋ እና እየገደለ ነው።

ወያኔ በአዲስ አበባ ዙሪያ በማስተር ፕላን አማካኝነት የምስኪኑን ኢትዮጵያዊ ገበሬ መሬት ለመብላት በኦፕዲኦ አማካኝነት መጥቷል። ሌሎቹ እንደ ብአዴን እና ደህዴን ያሉት እዚህ ጋር ምንም አይመለከታቸውም ሁሉም ቦታ የሚመለከተው ወያኔ ብቻ ነው። በኦፕዲኦ ውስጥ ተሰውረው እራሳችሁ የመረጣችኋቸው መሪዎቻችሁ ናቸው በሚል ሰበብ ገበሬዎች አይፈናቀሉ በሚል በወጡት ሰላማዊ ሰልፈኖች ላይ ጥይት በማዝነብ በግፍ የንጹሃንን የሰው ክቡር ህይወትን እያጠፉ ይገኛል።

ወያኔ ዛሬ ኦሮሚያ ክልል፣ አማራ ክልል፣ ደቡብ ክልል፣ ሱማሌ ክልል፣ ትግራይ ክልል፣ አፋር ክልል፣ ጋንቤላ ክልል፣ እያለ ከፋፍሎ የሰጠውን ካርታ አይተን የኛ ግዛት እዚህ ድረስ ነው ግዛታችን ይሄንን ያክላል ብለን የምንናገር ነገ ወያኔ ይሄ የተከለለው ክልል የናተ አይደለም እናተ የሚገባችሁ እዚህ ድረስ ነው ብሎ ማሳነስ እንደማይችል ምን ያህል እርግጠኖች ነን። እናተ ምን አገባችሁ ለሁሉም ክልሎች አጥር አጥሬ የሰጠኋችሁ እኔ ነኝ እንደውም ከአሁን በኋላ የናተ ግዛት እንደዚ አይደለም እንደዚህም የሚባል ክልል አከላለል የለም ብለው የሚከለክል አዋጅ እንደሚያወጣ ምን ዋስትና አለን። በየግዜው አዲስ ነገር ሲከሰት አዳዲስ ህጎችን በማውጣት እራሱን እንደ እስስት እየቀያየረ የሚቀርበው ወያኔ ክልል የሚባል የለም እንደማይል ምን ያህል እርግጠኛ ሆነን ነው የኔ ክልል ይሄ ነው ብለን የወያኔን የመከፋፈል ግዛ ስራን እየሰራልነት የምንገኘው ድል የምናደርገው ወያኔ ባስቀመጠልን መንገድ ስንጓዝ ሳይሆነ በፍቅር እና በአንድነት ለኢትዮጵያ ስንቆም ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰአት ሰጪም ከልካይም አሳሪም ፈቺም አቁሳይም ገዳይም ሁሉንም አድራጊ ሆኖ ማን ከኔ በላይ ማን ወንድ እያለ ነው። እኛ ደግሞ ለዚህ አላማው መንገድ ላይ በመገኘት ስለምንድነው ለጥፋት እና ለመጠፋፋት የምንጋለጠው? ለምንድነው ባዘጋጀልን የጥፋት ፈረስ ላይ የምንጋልበው? ነገ የሰጠንን የክልል ካርታ አግባብ አይደለም ብለው ቢያነሱት እኛ ምንድነው የምንለው? ይሄ ካርታስ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም ሊያኖረን ይችል ይሆንን? በአገራችን በሰላም እንድንኖር ገበሬዎቻችን ያለ አግባብ እንዳይፈናቀሉብን መሬታችን ለሱዳን እንዳይሰጥብን ፖለቲከኖች ያለ አግባብ እንዳይታሰሩብን ወጣቱ ያለ አግባብ እንዳይገደልብን ጋዜጠኞች በነጻነት እንዲዘግቡልን በአጥር ተከፋፍለን አጥር ውስጥ ላለው ብቻ መጮህ ሳይሆን ከአጥር ውስጥ በመውጣት ወደ ትልቁ አገር ኢትዮጵያ  በሚለው ሁላችንም በአንድነት አገራችንን ነጻ ለማውጣት በጋራ መታገል ይኖርብናል።

ህዝባችንን እና አገራችንን ከወደድን ኦሮሞን ለኦሮሞ አማራን ለአማራ የሚለውን ተረት ትተን በአንድነት ለአንዲት ኢትዮጵያ መቆም አለብን። ዛሬ እየተገደልን ያለው ስለተለያየን ነው ዛሬ አገር እየተዘረፈች ያለችው ተከፋፍለን ስላለን ነው ተከፋፍለን የምናደርገው የግል ትግል አሸናፊው እና ተሸናፊው ወደማይታወቅበት አዘቅት ውስጥ የሚከተን በመሆኑ እና ለወያኔም አመቺ ስለሆነ አንደነታችንን በግልጽ አውጀን ኢትዮጵያኖች እንደማንለያይ አንድ እንደሆንን አውጀን  እውነተኛ ነጻነት ለማምጣት በጋራ እንታገል። አንድነት አሸናፊ ነው፣ አንድነት ፍቅር ነው፣ አንድነት ነጻነት ነው፣ አንድነት ኃይል ነው። አንድነት አንድነት አንድነት ለኢትዮጵያዊነት።

ከተማ ዋቅጅራ

07.12.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

The post ጅብ የሚጮኸው መብላት ሲፈልግ ነው። – ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ ኦቦ በቀለ ነጋ ስለወቅታዊው የኦሮሞ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ያብራራሉ |ሊደመጥ የሚገባ

$
0
0

የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ማሻሻያ የሚለው በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ማንንም ሳያማክር ያወጣው ዕቅድ  ከዚህ ቀደም ጠንከራ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር። ተቃውሞውን ተከትሎ በግፍ የተገደሉ፣ የታሰሩና የተፈረደባቸው አሉ። አዲሱ ዕቅድ መልኩን ለውጦ በጥድፊያ መምጣቱን በመቃወም ሰሞኑን በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የተነሳው ሰላማዊ የተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም ምላሹ ጥይት ሆኗል። ቢያንስ ስድስት ተማሪዎች በተለያዩ ቦታዎች ተገለዋል።ተቃውሞውም ተጠናክሮ ቀጥሏል። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ ከሆኑት አቶ በቀለ ነጋ ጋር በወቅታዊው የተማሪዎቹ ጥያቄ፣ የአገዛዙ ምላሽና ዘርን መሰረት ያደረጉ ቅስቀሳዎች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው ከህብር ራድዮ ጋር ተወያይተዋል::


የኦፌኮ ከፍተኛ አመራር ኦቦ በቀለ ነጋ ስለወቅታዊው የኦሮሞ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ያብራራሉ | ሊደመጥ የሚገባ

The post የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ ኦቦ በቀለ ነጋ ስለወቅታዊው የኦሮሞ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ያብራራሉ | ሊደመጥ የሚገባ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አቶ ነጌሳ ኦዶ የፊታችን ሐሙስ “ሁላችንም ያለንን አጋርነት ማሳየት አለብን”ይላሉ –ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል

$
0
0

አቶ ነጌሳ ኦዶ የፊታችን ሐሙስ ሚኒሶታን ጨምሮ በመላው ዓለም ስለሚደረገው የኦሮሞ ተማሪዎችን ስለሚደግፈው ሰላማዊ ሰልፍ ለህብር ራድዮ ይናገራሉ

negesssa copy

The post አቶ ነጌሳ ኦዶ የፊታችን ሐሙስ “ሁላችንም ያለንን አጋርነት ማሳየት አለብን” ይላሉ – ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የዘመናችን ሙሴ (ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ)

$
0
0

Birhanu Nega
«ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ» ዕብ 11-24
ታዬ ብርሃኑ ከቨርጂንያ

በመጽሐፍ ቅዱስ ካሉ የቅዱሳን ታሪኮች ውስጥ የሙሴን ታሪክ አብዛኛው ኢትዮጲያዊ እንዳነበበው ስለማምን የሙሴን ታሪክ በዚህ ጽሁፍ ላይ መተረኩ አያስፈልገኝም። ሆኖም የዕብራውያን መልእክት ዕምነት ምን ማለት እንደሆነ የሚያስተምርበትን 11ኛው ምእራፍ ላይ ሌሎች ቅዱሳንን ጨምሮ የሙሴን ታላቅ እምነት ይጠቅሳል። ሙሴ በግብጽ ፈርዖን ቤተ መንግስት
ውስጥ ጮማ እየቆረጠ፣ ጠጁን እየተጎነጨ፤ በወርቅና በገንዘብ ተከቦ መኖርን ትቶ በባርነት ከሚሰቃዩት ወገኖቹ ጋር መከራ መቀበልን እንደመረጠ ይተርካል። የንጉሱን ቁጣ ሳይፈራ በጊዜዋ ልዕለ ኃያል ሃገር የነበረችውን የግብፅን አገር ኑሮ ትቶ ከወገኖቹ ጋር የኤርትራን ባህር ተሻግሮ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመሄድ የወሰነው በእምነት ነበር። እምነት ማለት የማይታየውን እንደሚታይ አድርጎ በተስፋ መነጽር ማየት ነው።

nega

ባለፉት አራት አስርት ዓመታት የሀገራቸን ኢትዮጵያ ጉዳይ በሁሉም ዘርፍ ከድጡ ወደ ማጡ እንደሆነ የዓይን ምስክር ነን። ሞት፣ ርሃብ፣ ስደት፣ ጎጠኝነትና የፍትህ እጦት የዘመናችን ታሪክ ነው። ወደድንም ጠላንም በየትኛውም ጎራ ብንቆምም፤ በፍትህ እጦት እየተገደሉ መንገድ ላይ ሬሳቸው ይጣል የነበሩት ወጣቶች፣ ተረሽነው በአንድ ጉድጓድ ውስጥ የተቀበሩት 60 ሚኔስትሮች፣ አገርን የባህር በር ማሳጣት፣ ድምጻቸው እንዲከበር ሊጠይቁ አደባባይ ሲወጡ በአጋዚ አልሞ ተኳሾች የተገደሉት የእነ ህጻን ነቢዩ ታሪክ የዚህ ትውልድ ታሪክ ነው። በአማራው፣ በኦጋዴንና በአኝዋኩ ላይ የተካሄደው የዘር ማጥፋት ዘመቻም የኛ ታሪክ ነው። ለአገር ለምድር እንደ ታቦት የሚከብዱና እድሜ ልካቸውን ቤተክርስቲያናቸውን እና አገራቸውን ያገለገሉት የኦርቶዶክስ ቤ/ክ አባቶች ስደትም የዚህ ትውልድ ታሪክ ነው።

ይሄ ትውልድ ይህንን ታሪክ ፈቅዶ አይደለም የሰራው። ጠብመንጃን መከታ ባረጉት በገዢው መንግስት ጫና ምክንያት ነው። ዝምም ብሎ አላየም። ይህንን ታሪክ ለመቀየር ከፕሮፌሰር አስራት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሁሉም በሚችለው ሞክሯል። አብዛኛው የመታሰር፣ ሌላውም የስደትና የሞት ጽዋ ደርሶታል። እስከ አሁን ድረስ የተከፈለው መስዋዕትነት ዘረኛውን የወያኔ መንግስት ሊገረስሰው አልቻለም። ምናልባትም የትግሉ ስልት ሁሉን አቀፍ ወይም ሁሉንም የትግል ተልዕኮ ያላካተተ ስለ ነበር ይሆናል። አሁን ግን ከምስራቁ የአሜሪካ ክፍል የኢትዮጵያውያንን የትግል ተልእኮ በአንድ ላይ አካትቶ፣ የኤርትራን ባህር አሻግሮ፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር በመውሰድ የዚህን ትውልድ ታሪክ የሚቀይር ልባምና አስተዋይ መሪ የዘመናችን ሙሴ አግኝተናል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በተመቻቸ ህይወት ይኖርባት ከነበረው ምድረ አሜሪካ፣ የደለበ ደሞዝ የሚያገኝበትን የፕሮፌሰርነትን ስራ ትቶ በወያኔ የአፓርታይድ መንግስት የሚሰቃዩት ወገኖቹ ነጻ ይወጡ ዘንድ መከራን መረጠ። ከሁሉም በላይ ሞትን ሳይፈራ እንደ ዓይን ብሌን የሚሳሳላቸው ቤተሰቦቹን ትቶ ምትክ የማይገኝለት ህይወቱን ለኢትዮጵያ ሀገሩ ሊሰዋ ወስኖ ወደ ትግል ሜዳ ሄደ። አስከፊ ታሪክ ያለው የዚህ ዘመን ትውልድ የሚያስደስትም ታሪክ አለው። የዘመናችን ሙሴ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የዚህ ትውልድ ታሪክ ነውና። ፕሮፌሰር ብርሃኑ እና የትግል አጋሮቹ ነጻነትን እምነት አርገው የድል ተስፋን ሰንቀው ዱር ቤቴ ብለዋል። እኛስ ምን እያደረግን ነው?

ይህችን አጭር ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ሰሞኑን የወያኔዎችን ደም ያንተከተከው የፕሮፌሰር ብርሃኑ ለአውሮፓ ፓርላማ የሰጠው የምስክርነት ቃል ነው። ሁላችን እንዳያነውና እንዳነበብነው በርቱዕ አንደበቱ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ኢትዮጵያው ውስጥ ያለውን ችግር ነቅሶ በማውጣት አቅርቦታል። በዚህ ትንታኔው ውስጥ የኔን ትኩረት የሳበውን ኃይለ ሃሳብ መጥቀስ እወዳለሁ። ፕሮፌስር ብርሃኑ ወያኔ በቤተ እምነት ውስጥ ጣልቃ እንደሚገባ አስረድቶ በኦርቶዶክስ ቤ/ክ አባቶች ላይ እስከ መሰደድ ያደረሰውን የወያኔ ጥፋት በአለም አደባባይ ይፋ አርጎታል። በተቃዋሚ የትግል ጎራ ያሉ መሪዎች ስለተሰደደችው ቤ/ክ እና አባቶች ከዚህ በፊት ሲያነሱት አለመስማቴ ሁሌም ያሳዝነኝ ነበር። የተሰደደችው ቤ/ክ ወይም ህጋዊ ሲኖዶስ ሰብዓዊ መብት፣ የህግ የበላይነት እና ፍትህ በምድረ ኢትዮጵያ እንዲከበር ከአውደ ምህረትም እሰክ ዓለም በአደባባይ ድምጻቸውን እያሰሙ የትግሉ አካል ተደርገው አለመወሰዳቸው ይገርመኝ ነበር። ሽማግሌ በሀገሪቷ ስለጠፋ እንጂ ከልጅነት እስከ ሽምግልና ቤተክርስቲያንን ያገለገሉ አባቶች በባእድ አገር ሲሰደዱ እንዴት ዝም ይባላል? ዳሩ ሽምግልና የእንጨት ሽበት የሆነበት
ďżź
ዘመን ላይ ደርሰናል። እነዚህ አባቶች ስደታቸውን ባርኮ በስደት ያለውን ህዝብ ቢሰበስቡም አያሌ አብያተ ክርስቲያናትን ቢመሰርቱም በየአውሮፕላን ጣቢያ በሽምግልና እድሜአቸው ሻንጣ እየተሸከሙ ህዝባቸውን ለማገልገል ቀና ደፋ ሲሉ ማየት ያቆስላል። የዮሴፍን ስደት የባረከ አምላክ የእነርሱንም ባርኳል። ፕሮፌስር ብርሃኑ ያገኘውን በረከት ቀድሞ የቅንጅት አሁን ደግሞ ህብረ ብሔር ፓርቲ የሆኑት አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች አላገኙትም። ወደፊት የወያኔ መንግስት በሌሎች ቤተ እምነቶች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ሲያወግዙ ወያኔ በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ላይ የፈጸመውን የቀኖና መደፍጠጥ፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የተሾመን መንበር ለስደት ማብቃቱን ማውገዝ ይገባቸዋል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለሌሎች ታጋዮች ተምሳሌት ሆኗል።

በአንጻሩ በስደት የሚገኙትን አባቶች በተሰደዱበት የባእድ አገር እንኳን በሰላም እንዳይኖሩ ማኃበረ ቅዱሳን የተሃድሶ ታርጋ በመለጠፍ አገልግሎታቸው ላይ እንቅፋት የፈጸመው አፍራሽ ተልዕኮ ያስተዛዝባል። ራሱን የቅዱሳን ማኃበር እያለ የሚያሞካሸው ስብስብ ዳንኤል ክብረት የሚባል የጎበዝ አለቃ ከኢትዮጵያ እየላከ አባ መላኩ ጋር እያረፈ ከአቡነ ማትያስ ጋር በመላው ሰሜን አሜሪካ እየዞረ ህዝቡ ህጋዊውን ሲኖዶስ እንዳይቀበል ያረገው ሙከራ ሊሳካ አልቻለም። ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያናን ለመፈተን ከሰማይ ወደ ምድር ወንድሞችን እና አባቶችን ሊከስ የተወረወረው ዘንዶ ነው። ይሄ አውሬ አሁን በስደት ላይ በምትገኘው ቤተክርስቲያን ስኬት እንደገና ተቆጥቶ ስልቱን ቀይሮ በአዲስ መልክ የስም ማጥፋት ዘመቻውን አጠናክሯል። በፊት ከውጭ ሆኖ ነበር አሁን ግን በህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ካድሬዎቹን አስርገው በማስገባት ምእመናን ለዓመታት በስደት ያገለገሉትን አባቶች በተሃድሶ አራማጅነት እንዲጠራጠር በማድረግ ትጥቁን የማስፈታት ዘመቻ በከፍተኛ ደረጃ እያካሄደ ነው። የማህበረ ቅዱሳን ክፍተኛ አመራር የነበሩት ጠቅልለው ወደ ምድረ አሜሪካን መጥተው የጥፋት ዘመቻውን በግንባር እየመሩት ነው። በስደተኛው ሲኖዶስ ስር የሚገቡት ካህን መስል ጮሌ ካድሬዎች መስቀል ጨብጠው ቀሚሱን አንዘርፍፈው ነው የሚገቡት። በዲሲ ገብርኤል፣ በአትላንታ ቅድስት ማርያምና በቶሮንቶ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ የገቡት ካድሬዎች ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው። ውሎአቸው ከማህበረ ቅዱሳን ከፍተኛ አመራርና ከአባ መላኩ ጋር ነው። የአትላንታው መነኩሴ (አባ ኃይለሚካኤል) የጥፋት ስራቸው አልሳካ ስላላቸው እዚህ ቨርጂንያ መጥተው ከማኅበረ ቅዱሳን አባላት ጋር በመሆን የቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ብለው በአባ መላኩ ባራኪነት ከፍተው ነበር። ለአንድ ወር ያህል ሞክረው ስላልተሳካላቸው እንደ ኪዮስክ ዘግተውት ተሰናብተው ወደ መጡበት አትላንታ ማርያም ሄደው ዘው ብለው ገብተዋል። ይህ የሚያመላክተው ማኃበረ ቅዱሳን ካድሬ ካህናትን ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ሆዳም የቦርድ አባላትን አቅፈው እንደሚንቀሳቀሱ ነው። የአትላንታ ማርያም የባጣህ ቆየኝ አማራጭ ስትሆን ዝም ብሎ የሚያይ የቦርድ አባል ሃላፊነት የማይሰማው ነው።

ፕሮፌሰር ብርሃኑና የትግል አጋሮቹ እንደ ሙሴ የተመቻቸ ህይወታቸው ትተው፤ ስለ ፍትህ ስለ ነጻነት በእምነት እምቢ ብለው የድል ተስፋን ሰንቀው የሚመጣውን መከራ ከህዝባቸው ጋር ለመቀበል መርጠዋል። በእግዚአብሔር ድጋፍ ምኒልክ ቤተመንግስት ከተቀመጠው የዘመናችን ፈርዖን ህዝባቸውን ነጻ ለማውጣት የኤርትራን ባህር ሰንጥቀው ሰብዓዊ መብት በሚከበርባት፣ የህግ የበላይነት ወደሚኖርባትና እኩልነት ወደ ሰፈነባት ወደ ተስፋይቱ ምድር ያደርሱታል። በአሁኑ ሰዓት ፕሮፌሰር ብርሃኑ የመረጠውን የትግል ስልት ለመተቸት ማንም የሞራል ልእልና የለውም፤ ቢቻል ይከተለው አለዚያም እጁን በአፉ ላይ ያስቀምጥ። ፕሮፌስር ብርሃኑ ይህን ትግል ስልት የመረጠው ወዶ አይደለም። የሰላሙን ትግል ሞክሮና አይቶ ነው። በእስር ቤት ሆኖ እንኳ አሳሪዎቹ ላይ ጥላቻ እንዳይኖረን የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት የመሰለ መጽሃፍ ነበር የጻፈልን። ወያኔን ደህና አርጎ ስለሚያውቃቸው፤ በሚያቁት ቋንቋ ሊያናግራቸው እነርሱን አዝሎ የሚኒልክ ቤተመንግስትን ወደ አሳያቸው አካል ጋር ግንኙነት ፈጥሮ ሊገጥማቸው ሄዷል።

በመጨረሻም የአርበኞች ግንቦት 7ትን ትግልን ለሚደግፉ አካላት በሙሉ ፕሮፌስር ብርሃኑ መልእክት አስተላላፏል። ወያኔን በደንብ ስለሚያውቅ፤ የወያኔ ዘመቻ በፓሊቲካ ሜዳ ላይ ብቻ ሳይሆን በቤተ እምነትና በማህበራዊ ህይወትም ውስጥ እንደሆነ ጠቁሞናል። እምነትና ፖሊቲካን እንለይ ለምትሉ የዋሆች ወያኔ በሁሉም ዘርፍ እንደገጠመን ከፕሮፌስሩ ትንተና እንማራለን። ወያኔን እየተቃወማችሁ ከእነ አባ መላኩ ጋር አትሞዳመዱ። ቀኖና ጥሶ በጠብመንጃ ኃይል የተሰበሰበ ሲኖዶስ፤ በመንፈስ ቅዱስ ሳይሆን በወያኔ ርእዮተ ዓለም የሚመራ ቅድስና የሌለውን ሲኖዶስ እንዴት መቀበል ይቻላል?

የአባቶቻቸን አምላክ ስሙ እግዚአብሔር ነው እርሱም ተዋጊ ነው እርሱም ድል አድራጊ ነው! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
የአባቶቻችን አምላክ የተመሰገነ ይሁን

The post የዘመናችን ሙሴ (ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

እኛ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት አባላት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ በኦሮሞ ወጣት ተማሪዎችና በጎንደር ሕዝብ ላይ ያደረሰውን ግድያ በጥብቅ እናዋግዛለን!

$
0
0
DCESON

DCESON

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የአቋም መግለጫ ታህሳስ 16, 2008 ኖርዌይ!!

እኛ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት አባላት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ በኦሮሞ ወጣት ተማሪዎችና በጎንደር ሕዝብ ላይ ያደረሰውን ግድያ በጥብቅ እናዋግዛለን!

ሰሞኑን በሃገራችን የተለያዩ  ግዛቶች በኢትዮጵያዉያን ላይ እየደርሰ ያለዉ ጥቃት ከመቼዉም ጊዜ በላይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሶአል።ሕዝባችን ይኸዉ ከወያኔ የሚደርስበትን ጥቃት በመቋቋም ተቃዉሞዉንና አልገዛም ባይነቱን በገሃድ በተለይ በመላዉ ኦሮሚያና  በጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች እያሳየ ይገኛል።

ይህ የወገኖቻችን የአልገዛም ባይነትና የዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብት ጥያቄዎችን ህወሃት/ወያኔ በተለመደዉ የእብሪተኛ ድርጊቱ የሕዝቡን ድምጽ ለማፈን ተማሪዎች በሚማሩበት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶችና ዩንቨርስቲዎች ድረስ ዘልቆ በመግባት በመግደል፤በመደብደብና በማሰር የሕዝቡን ቁጣና ብሶት በሃይል ለማፈን ቢሞክርም ዉጤት ሳያገኝ ማፈን ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶአል።ተቃዉሞዉም ከእለት ወደ እለት እየተባባሰ የሄደ ሲሆን የወያኔም ጥቃት ከእለተ ወደ እለት አስከፊ ደረጃ ላይ እየደረሰ ይገኛል።

የአዲስ አበባን ከተማን ለማስፋት በሚል ህወሃት/ወያኔ ድብቅ አጀንዳዉን ከአንድ ዓመት በፊት ባቀደዉ የማስተር ፕላን በርካታ ወገኖቻችን ለሞት፤ እንግልትና እስር ምክንያት በመሆን ሂደቱ ቢጠናቀቅም በእብሪት የተሞሉት የህወሃ/ወያኔ ዘረኛ ቡድን እናስተዳድርሃለን በሚሉትና በኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ነዉ የተመረጥነዉ የሚለዉን ሕዝብ ምርጫዉ ባለቀ ማግስት የዘረኛ መሪዎቹ ቁንጮ በማን አለብኝነት ማስተር ፕላኑን የሚቃወሙትን ልክ እናስገባችኋለን በማለት በአደባባይ ለሕዝባችን ያላቸዉን ጥላቻና ንቀት በግልጽ አሳይተዋል።

እብሪተኛዉ የህወሃት/ወያኔ ቡድን ይህን ማስተር ፕላን የሚለዉን እቅድ ከመነሻዉ የቀደዉና የነደፈዉ እዉነት የከተማዋ መስፋት አስፈላጊነት ለሕዝቡ የሚሰጠዉ ጥቅምና ጉዳቱ ሕዝብ ተወያይቶበትና መክሮበት ሳይሆን በሙስናና ብልሹ አሰራር ለተዘፈቁት የህወሃት ሹመኞችና የእነሱ ቡችሎች በከተማዋ በሕገወጥ መንገድ ከያዙት ንብረት በተጨማሪ ሌላ ንብረት ለማስገኘት ሆን ተብሎ ታስቦ የተሸረበ ድብቅ ሴራ እንደሆነ ድርጅታችን ያምናል። ህወሃት/ወያኔ ትላንት በአቃቂ በሚገኙት የአቡ ጨፌ፤ገላን፤ቂሊንጦና ቀርሳ እንዲሁም በቦሌ ቡልቡላ የረር በርና ጎላ ሰፈር የነበሩትን ወገኖቻችንን በማፈናቀል የፈጸሙት በደልና የዘር ማጥፋት ድርጊት ቁስላችን ሳይሽር በድጋሚ ይህንኑ ለመፈጸም የሚደረገዉን ሕገ ወጥ ድርጊት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በፅኑ ሊያወግዘዉ ይገባል።

በሌላ በኩል በዘረኛነትና  የተለከፈዉ ሥልጣን በሃይል የያዘዉ የህዋሃት/ወያኔ ቡድን በሕግ ጥላ ስር በጎንደር እስር ቤት ታስረዉ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ በእስር ቤቱ ላይ በተነሳዉ የእሳት ቃጠሎ እስረኛዉ የታሰረበትን ክፍል በመቆለፍ በእሳት ያስፈጃቸዉ ሲሆን ከእስር ቤቱ ሕይወታቸዉን ለማትረፍ የሚወጡ እስረኞችን ዙሪያዉን ከቦ በጥይት ፈጅቷቸዋል። ይህ የወያኔ ድርጊት በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወቅት ፋሺስቶች እንኳን ያልፈጸሙትን ይህ ዘረኛ ቡድን በወገኖቻችን ላይ ይህን አሰቃቂና የጭካኔ ድርጊት ፈጽሞአል።

ህወሃት/ወያኔ በዉልደቱ ጊዜ የነበረዉን በመርዝ የተለወሰ ጥላቻ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዉያን ላይ ከመቼዉም ጊዜ በላይ እየረጨ የሚገኝ ሲሆን ይህ እኩይ ቡድን ሃገሪቷን ለመገነጣጠልና ታላቋን ትግራይ ለመመስረት ያለዉን የቀን ቅዠት ለመፈጸ ሲል የመጨረሻዉን ካርድ በመሳብ በወልቃይትና ጠገዴ ሕዝብ ላይ ጦርነት የከፈተና የቅማንትን የማንነት ጥያቄ አስከትሎ  ግዙፍና ለም የሆነዉን የሃገሪቷን ዳር ድንበር ለባዕዳን/ለሱዳን አሳልፎ  ለመስጠ ዝግጅቱን አጠናቆ  በዚህ በያዝነዉ ወር ለማስረከብ ቃል ገብቷል።የሃገራችን ዳር ድንበር ጉዳይ እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ሊያሳስበዉና ሊያስጨንቀዉ የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ድርጅታችን ያምናል።

ዉድ ኢትዮጵያዉያን ዛሬ በኦሮሚያ በአማራና በተለያዩ  የሃገሪቷ ክልሎች በህወሃት/ወያኔ የሚፈጸምብንን ጭካኔ የተሞላበት እኩይ ድርጊት በጋራ ልንቃወመዉና ልናወግዘዉ የሚገባንና የተደገሰልንን ሃገርንና ሕዝብን የማፈራረስና የመበታተን አደጋ ማስወገድ የምንችለዉ ሆ!ብለን በአንድነት መነሳት ስንችል ብቻ ነዉ።በኦሮሞዉ ላይ የሚፈጸመዉ የእስር፤ድብደባና እንግልት አማራዉን፤ትግሬዉን ፤ከንባታዉን፤ ሐረሪዉን፤ጋንቤላዉን፤ወላይታዉን የሚመለከት ሲሆን እንዲሁም በአማራዉና በሌሎቹ ብሄረሰቦች ላይ የሚደርሰዉ ጥቃት የእኔም ጥቃት ነዉ በሚል በአንድነት መነሳት ያለብንና የተደቀነብንን ጥቃት በጋራ መመከቻዉ ጊዜ አሁን ነዉ ብሎ  ድርጅታችን በጽኑ ያምናል።

የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን ችግር ህወሃት/ወያኔ ሲወገድ ችግሩም አብሮ እንደሚወገድና አንድነታችን ቀድሞ ወደነበረዉ ቦታ የሚመለሰዉና የቀደመዉ ገናና ስማችንና እኛነታችን እንዲሁም አንድነታችንን የምናስመልስበት ጊዜዉ እሩቅ እንደማይሆን ድርጅታችን ዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት በኖርዌይ እምነቱ የጸና ሲሆን ይኸዉ ህልማችን እዉን ይሆን ዘንድ ሁሉም ብሄር በአንድነት መቆምና መተባበር ጊዜ የሚጠይቀዉ ሃገራዊ ጥሪ ነዉ።

ስለዚህ ኢትዮጵያዉያን በሃገራቸዉ ዳር ድንበርና በመላዉ ሕዝባችን ላይ የሚቃጣዉን ማናቸዉም ጥቃት በጋራ መክቶና ተከላክሎ ጠላትን አሳፍሮ አንገት በማስደፋት መመለስ የሚችል ሕዝብ መሆኑን ታሪኩ የሚያስተምረን ሲሆን ይህን የትላንቱን አንድነታችንን በበለጠ በማጠናከር የሃገራችንንና የሕዝቦቿን ጠላት የሆነዉን ወያኔን ለማስወገድ የሚደረገዉን ትግል አጠናክረን እንድንቀጥልና ትግሉን በመቀላቀል የሃገራችንን ትንሳኤ እዉን ይሆን ዘንድ ድርጅታችን ጥሪዉን ያቀርባል።

ወያኔ በማስወገድ የሃገራችንን አንድነትና ዳር ድንበር እናስከብር!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ !!

The post እኛ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት አባላት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ በኦሮሞ ወጣት ተማሪዎችና በጎንደር ሕዝብ ላይ ያደረሰውን ግድያ በጥብቅ እናዋግዛለን! appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ወያኔ ህዝብ ለሕዝብ የሚያግጫ ስለሆነ እንጠቀቅ ይላሉ ዶር በያን

$
0
0

Beyanዶር በያን የቀድሞ የኦነግ አመራር አባል ነበሩ። አሁን ደግሞ በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ከፍተኛ አመራር አባል ናቸው።ሰሞኑን በኦሮሞ ተማሪዎችና በጎንደር በተነሳው ሰላማዊ ተቃዉሞ ዙሪያ ፣ ለኢሳት በሰጡት ቃለ ምልልስ ሁሉም ካልተባበረ፣ በተናጥል የሚደረግ ዉጤት እንደማያመጣ ገልጸዋል።
“እምቢተኝነት፣ ተቃዉሞ በመላው ኢትዮጵያ መካሄድ አለበት። የኦሮሞ ተማሪዎች ሲያመጹ ሌላው ቁጭ ብሎ ካየ፣ ወይንም በጎንደር ወይም በየአገሪቷ ያለ ማህበረሰብ ሲያምጽ ፣ ኦሮሞው ወይንም ሌላው ቁጭ ብሎ ችግር ነው” ያሊት ዶር በያን አሰቦ፣ በዘር በኃይማኖት ኢትዮጵያውያን ሳይከፋፈሉ በጋራ ለመበት፣ ለዲሞክራሲና ለነጻነት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

“ሕዝቡ ፍትህ ጠምቶታል፤ በአገሩ በሰላም መኖር ጠምቶታል” ያሉት ዶር በያን፣ “ህዝብ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ በአራቱም ማእዘናት ተባብሮ፣ ለሚደረገው የዴሞክራሲና የነጻነት የፍትህ ጥያቄዎች በጋራ መቆም አለበት” ብለዋል።

ወያኔ ላለፉት 24 አመታት ህዝብ ለሕዝብ እያጋጫ፣ ያለፉ ታሪኮች አጣሞ እያቀረበ፣ በተለይም በኦሮሞው እና በሌሎች ኢትዮጵያዊያን መካከል መግባባትና መቀባበል እንዳይኖር ሲያደርግ እንደነበረ ይታወቃል። በአንድ በኩል ፣ ለኦሮሞው ሌሎች በተለይም አማርኛ ተናግሪዎች “ከዚህ በፊት የጨቆኑህ ናቸው፣ የገደሉህ ናቸው፣ ነፍጠኞች ናቸው ..” እያሉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለሌሎች ደግሞ “ኦሮሞው ስልጣን ካገኝ ይጨርሳል፤ እኛ ነን የምንጠብቅህ” በማለት ህዝብን ከሕዝብ በመከፋፈላቸው፣ የተጠናከረ ሁሉን ያቀፈ ትግል ማድረግ አልተቻለም ነበር።

ዶር በያን ይህ አይነቱ ሕዝብብ ከህዝብ የመከፋፈል እኩት ተግባራትን ገዢው ፓርቲ አሁንም ሲስተማቲክ በሆነ የሚቀጥልበት እንደሆነ በመገጽል ትክቅ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
“ሕዝብ ለሕዝብ እያጋጫ ስልጣኑን ለማራዘም እንደሚሞክር መጠበቅ አለበት። ተደርጓል ከዚህ በፊትም። ወደፊትም የሚጠበቅ ነው። ስለዚህ ንቅናቄው (በኦሮሞ ተማሪዎችና በጎንደር የተጀመረው) ፣ ሕዝቡ against the regime ተነስቶ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ተባብሮ የሚቃወምበት መሆን አለበት እንጂ፣ ህዝብ ለሕዝብ እንዳይጋጭ፣ ሕዝቡ ለሕዝብ በምንም አይነት ተቃዉሞ ዉስጥ እንዳይገባ፣ መጠንቀቅ ያስፈልጋል” ሲሉ በአራቱም ማ፤እዘን ለሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ አደርገዋል። የሚሊዮኖች ድምጽ

The post ወያኔ ህዝብ ለሕዝብ የሚያግጫ ስለሆነ እንጠቀቅ ይላሉ ዶር በያን appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በምዕራብ ሸዋ ሙገር ከተማ ትናንት የተደረገው የተማሪዎች ተቃውሞ ቪድዮ

$
0
0

በምዕራብ ሸዋ ሙገር ከተማ ትናንት የተደረገው የተማሪዎች ተቃውሞ ቪድዮ
Zehabesha News

The post በምዕራብ ሸዋ ሙገር ከተማ ትናንት የተደረገው የተማሪዎች ተቃውሞ ቪድዮ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በበጋው ወቅት መጀመሩ ነውን? |ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

$
0
0

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የአረቡ ዓለም የጸደይ አብዮት እ.ኤ.አ ታህሳስ18/2010 የቱኒስያን አብዮት በማቀጣጠል ይጀምራልብሎ የገመተ ማንም ሰው አልነበረም፡፡ መሐመድ ቡአዚዚ የሚባል በመንገድ ላይ እየተንቀሳቀሰለዕለት ኑሮው መደጎሚያ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘትጥቃቅን ሸቀጦችን የሚሸጥ ወጣት በከተማው ማዘጋጃ ቤትእና በፖሊሶች ኃላፊነት የጎደለው አሰራር መሰረት በዜጎችላይ እየተፈጸመ ያለውን የማሸማቀቅ፣ ከሕግ አግባብ ውጭስልጣንን የመጠቀም እና የማዋረድ ዕኩይ ድርጊቶችንበመቃወም በእራሱ ላይ እሳት በመለኮስ እራሱን በማቀጣጠል በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ሀገሮች ላይየአብዮት ማዕበልን ያስከትላል ብሎ የገመተ ማንም ሰው አልነበረም፡፡
oromia

ለህዝቦች ነጻነት ሲል እራሱን በእሳት ያቀጣጠለው ዜጋ ዚን ኤል አቢዲን ቤን አሊን በቱኒስያ፣ ሆስኒ ሙባረክን በግብጽ፣ሙአመር ጋዳፊን በሊቢያ፣ አሊ ሳለህን በየመን እና ሌሎችንም በእሳት ተቃጥለው ዶግ አመድ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡

ሶቭየት ህብረት በብርሀን ፍጥነት እና ከመቅጽበት ፍርክስክሷ ይወጣል ብሎ የገመተ ማንም አልነበረም፡፡ እ.ኤ.አ ታህሳስ25/1991 ሚካኤል ጎርባቾቭ እራሳቸውን ከፕሬዚዳንትነት ያገለሉ መሆናቸውን በማወጅ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብየገና ስጦታ አድርገው አቅርበዋል፡፡ ጎርባቾቭ ለሰባት አስርት ዓመታት ያህል በሶቭየት ህብረት ውስጥ ነግሶ የቆየውንየኮሙኒስት አገዛዝ ገመድ ውጤታማ በሆነ መልኩ ስበው በጥሰው በመጣል ለዓለም ህዝብ አስደናቂነታቸውን በተግባርአስመስክረዋል፡፡

ትላንት ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት “በኢትዮጵያሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እንደገና ሌላ ደም አፋሳሽ የኃይል ጥቃት“ በሚል ርዕስ በድረ ገጹ ላይ በመልቀቅ ህዝብእንዲያውቀው አድርጓል፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፣ “የተማሪዎች ተቃውሞ በኦሮሚያ ክልል በሁሉም አካባቢዎችውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በመሰራጨት ላይ ይገኛል… የማህበራዊ ድረ ገጾች በደም በተነከሩ እና በተጨማለቁ ሰላማዊሰዎች ፍቶግራፎች ተሞልተዋል፡፡ በበርካታ ቦታዎች ላይ በርካታ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ቁስለኞች እና በቁጥጥር ስርየዋሉ በርካታ ሰዎች የሚገኙ መሆኑን ታማዕኒነት ያላቸው ምንጮች ዘግበዋል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የአካባቢ ፖሊሶችእስከ አሁን ድረስ ሶስት ተማሪዎች መሞታቸውን ይፋ አድርጓል፡፡“

ሂዩማን ራይትስ ዎች በአሁኑ ጊዜ በተማሪዎች እየተካሄዱ ላሉት ሰላማዊ ሰልፎች አንቀሳቃሽ ምክንያቶች ናቸውያላቸውን ጉዳዮች እንደሚከተለው አቅርቧቸዋል፡

“ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች እውነትነት ያለው በሚመስል መልኩ እና ሆኖም ግን ከጥርጣሬ ውስጥ በሚጥል መልኩየአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ወሰን ከድንበሩ አልፎ ወደ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ እየተስፋፋ በመሆኑ እና የኦሮሞን አርሶአደሮች ከመሬታቸው የሚያፈናቅል መሆኑን ከመፍራት አንጻር ነው፡፡ በርካታ ኦሮሞዎች በኢትዮጵያ ላይ ስልጣን በያዙተከታታይ ነገስታት የማግለል አድልኦ እንደተፈጸመባቸው አድርገው ይሰማቸዋል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ በኢትዮጵያተከታታይ መንግስታት ሁልጊዜ በመንግስት ፖሊሲዎች ላይ ተሳትፎ ማድረግ እንደማይችሉ እና ድምጽ እንዳይኖራቸውአድርገዋል የሚል እምነት አላቸው፡፡”
oromia
በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ–ህወሀት)እንደዚህ ያለ መጥፎ ዜናን የሚያሰራጩ ዜናዎችን ወዲያውኑ ማጥፋት ተቃውሞዎችን ጸጥ ማድረግ በሚለው ስልታቸውላይ ሁልጊዜ ትክክል እና ውጤታማ እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ፡፡ ሆኖም ግን ዜጎች በሰላማዊ መንገድተቃውሞዎቻቸውን በሰላማዊ ሰልፍ መግለጽ እንዳይችሉ ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ ማለት ነገሮችን ከማወሳሰብ ባለፈመልኩ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ወገኖች በተደጋጋሚ ለአካባቢያቸው ማህበረሰቦች ሲሉ ወደ አደባባይ በመውጣትየሚፈጽሙት እና የማያቋርጥ ትግል ስለሆነ በአንድ ወቅት እውነታው ቁልጭ ብሎ ሊወጣ ይችላል፡፡

ጥያቄው እውነታው ፍንትው ብሎ የሚወጣው መቼ ነው የሚለው ብቻ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ጥያቄ ሆኖ የሚቀርበውዘ–ህወሀት እውነታን መያዝ ይችላል ወይ? የሚለው ነው፡፡

በእርግጠኝነት እውነታው ምንድን ነው?

እውነታው ሁሉም ሊመልሰው በሚችልበት መልኩ እንዲህ በሚሉ ጥያቄዎች ዓይነት ሊቀርብ ይችላል፡

1ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት ከ100 ሚሊዮን በላይ ቁጥር ያለውን ህዝብ የመሬት ላይ ባሮች በማድረግ እንደ ሰም አቅልጦእንደ ብረት ቀጥቅጦ የሚገዛው እስከመቼ ድረስ ነው?

2ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት እራሳቸው ጌታ እና እያንዳንዱ ዜጋ ደግሞ ገባር በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ የመሬት ማሳ ላይጢሰኛ ባሮች አድርገው የሚቆዩት እስከምን ያህል ጊዜ ነው?

3ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት አርሶ አደሮችን ከእራሳቸው መሬት ላይ በማፈናቀል በድህነት አረንቋ ማዕበል ውስጥ እየዘፈቁበችጋር ሲያሰቃዩአቸው የሚኖሩት እስከ መቼ ድረስ ነው?

4ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት የመኖሪያ ቤት ያላቸውን ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው እያፈናቀሉ፣ የንግድ ስራ ባለቤቶችንከንግድ ስራዎቻቸው በግፍ እየነቀሉ እና እያባረሩ በእራሳቸው፣ በደጋፊዎቻቸው እየተኩ እና የተቀደሱትን የእምነትማደሪያ የሆኑትን ቤተክርስቲያኖችን እና መስጊዶችን እያረከሱ እና መሬቶቻቸውን እየነጠቁ የእነርሱን የማይሞላኪሳቸውን በገንዘብ ሲያጭቁ የሚኖሩት እስከ መቸ ድረስ ነው?

5ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት ከአያት ቅድመ አያቶቻቸው ጀምሮ የኢትዮጵያውያን የነበረውን በርካታ መጠን ያለውንመሬት እየነጠቁ እና እየዘረፉ ለቻይኖች፣ ለህንዶች፣ ለሳውዲዎች፣ ለቱርኮች እና ለሌሎችም የጥቅም ተጋሪዎቻቸውበቁርጥራጭ ሳንቲም እየቸበቸቡ ኪሳቸውን ሲሞሉ የሚኖሩት እስከ መቼ ድረስ ነው?

6ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ህገመንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀም ተቃውሟቸውንበሚገልጹበት ጊዜ በጥይት እየተደበደቡ የሚገደሉበት ጊዜ የሚዘልው እስከ መቼ ድረስ ነው?

7ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት የ100 ሚሊዮኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጽ አፍኖ ጸጥ ረጭ በማድረግ በድንቁርና አገዛዙየሚቀጥልበት እስከ መቼ ድረስ ነው?

8ኛ) ለመሆኑ ዘ–ህወሀት የ100 ሚሊዮን ህዝቦችን አንገት እረግጦ የያዘውን ጫማውን ዘለቄታዊ እንዲሆን በማድረግቀጥቅጦ የሚገዛው እስከ መቼ ድረስ ነው?

እኮ እስከ መቼ?

ሩቅ አይሆንም እላለሁ!

ሩቅ አይሆንም!

አሁን እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 ላይ ሆኘ ዘ–ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ መቼ እንደሚወድቅ ለመተንበይ አልችልም፡፡

ሆኖም ግን የውድቀት የእጅ ጽሁፉ በግድግዳው ላይ ነው፡፡

የዘ–ህወሀት አድራጊ እና ፈጣሪ ዘዋሪ የነበረው ከስልጣን ኮርቻው ላይ እ.ኤ.አ ነሐሴ (?) ተሽቀንጥሮ ለዘላለሙይጠፋል ብሎ ያሰበ ማንም አልነበረም፡፡

አሁንም በስልጣን ኮርቻ ዙፋኑ ላይ ተጣብቆ የሚገኘው ዘ–ህወሀት ይወድቃል፡፡ ብን ብሎም ይጠፋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ መቅረብ ያለበት ጥያቄ ዘ–ህወሀት ይወድቃል ወይ የሚለው ሳይሆን መቼ ነው የሚወድቀው የሚለውነው፡፡

ይኸ አስደማሚ እና አሳሳቢ የሆነው የዘ–ህወሀት ረዥሙ የጨለማ ጉዞ የአገዛዝ ጥቄያ በጀግኖቹ ኢትዮጵያውያንእየተብላላ እና እየተሰለቀ ቆይቶ ተገቢውን ምላሽ የሚያገኘው መቼ ነው? ይህንን ጉዳይ አንድን ህጻን በዛፍ ጫፍ ላይበተሰራለት የመኝታ አልጋ ላይ መተኛት እንዲችል እንድናባብለው ከሚደረግ የዋህ ድርጊት ጋር በማመሳሰል እስቲ በዚህየግጥም ስንኝ እንቃኘው፡፡

ህጻኑን አባብለው ከዛፍ ጫፍ ይተኛ፣

በተሰራው አልጋ ለሷም ሳይሆን ለኛ፣

መጠበቅ አትችልም ከነፋስ ቀበኛ፣

ከማት ልታድነው ከኃይል ሞገደኛ፡፡

ነፋስ በሰዓቱ በነፈሰ ጊዜ፣

ቢነቃም ባይነቃም ከያዘው አባዜ፣

ወድቆ መንኮታኮት በደረሰ ጊዜ፣

ሁሉም መልክ ይይዛል የልጁ ኑዛዜ፡፡

የዛፉ ቅርንጫፍ ዘንበል ያለ እንደሆን፣

የህጻን መኝታው እንዳይሆን እንዳይሆን፣

ከመሬት ተላትሞ አፈር ትቢያ ሊሆን፣

ከማይቀረው ዓለም ምንም ጊዜ ቢሆን፣

ህጻን ተሸክሞ ያያታል ሲኦልን፡፡

አይ የህጻኑ አልጋ በዛፍ ላይ ያለኸው፣

ይህንን ሞኘ ህጻን አታለህ የያዝኸው፣

ምቹ በማስመሰል እንዲተኛ አርገኸው፣

ትንሽ እንደተኛ እውነት አልጋ መስሎት፣

ከመቅጽበት ወድቆ ከዛፉ ስር አለት፣

ሳይበቃ ቀረ አሉ ለኑዛዜ ስርየት፡፡

አወይ በሬ ሞኙ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ፣

እልም ካለው ገደል ወድቀህ ቀረኽ ወይ፣

የሚባለው ተርት ይህ አይደለም ወይ?

የህዝቡን ደስታ ያራቀ፣ ከፍተኛ የሆነ ቁጡነት እና ብስጭትን የተላበሰ ህዝባዊ ማዕበል በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እየነፈሰነው፡፡

ይህንን ህዝባዊ ማዕበል በመጋፈጥ የዘ–ህወሀት ዛፍ ታላቁ ቅርንጫፍ መቋቋም አቅቶት ተቆርጦ የሚወድቀው መቼነው?

አሁን ይህ ነው ለማለት አልችልም፡፡ ሆኖም ግን ቅርንጫፉ ተገንድሶ የመውደቂያ ጊዜው እየደረሰ ነው ለማለትእችላለሁ፡፡

ታላቁ ቅርንጫፍ ተገንድሶ ሲወድቅ ምን ይከተላል የሚለውን ጥያቄ መመለስ ቀላል ነገር ነው!

የዘ–ህወሀት ታላቁ ቅርንጫፍ ተዘንጥሎ ሲወድቅ የሙስና አገዛዝ ከነጉግ ማንጉጉ ተንኮታኩቶ ይወድቃል፣ ሰይጣናዊውአገዛዝ እና አልጋውም ሁሉም ነገር ተንኮታኩቶ ወድቆ አፈር ድሜ ይበላል፡፡

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 ነገሮች ሁሉ ሲታዩ ሚስጥራዊ የሆነ ብሩህ ቁስ አካል በሰማይ ጨለማውን ሰንጥቆ የሚሄድመስሎ ይታያል፡፡ ምልክቱን ማየት ቀላል ነገር ነው፣ ሆኖም ግን ሁኔታውን ለማወቅ እና ግንዛቤ ለመውሰድ በጣም ከባድነገር ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት የዘ–ህወሀት የኃይል እርምጃ እና የቁጣ መንስኤ የሆኑት እና የሚይዝ የሚጨብጠውን ያሳጣው አመጹንየቀሰቀሱት የተማሪዎች ጉዳይ ብቻ አልነበረም፡፡

በአንድ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ከፍል በአንድ እስር ቤት ላይ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ከአደጋው ለማምለጥ በሚንቀሳቀሱ የህግእስረኞች ላይ የዘ–ህወሀት ታማኝ የሆኑ ፖሊሶች ተኩስ በመክፈት ግድያዎችን እንደፈጸሙ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛውአገልግሎት ይፋ አድርጓል፡፡ (የቪዲዮ ምስሉን ለማየት እዚህ ጋ ይጫኑ፡፡)

ይኸ ዕኩይ የአረመኔዎች ድርጊት እ.ኤ.አ ህዳር 2/2005 በቃሊቲ እስር ቤት ግቢ ውስጥ አሁን በህይወት በሌለውበአምባገነኑ በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ታጣቂዎች ተኩስ በመከፍት በርካታ እስረኞች እንዲሞቱ እና ብርካታዎቹ ደግሞቁስለኛ እንዲሆኑ የተደረገበትን ዘግናኝ ክስተት አስታወሰኝ፡፡ (እልቂቱ የተፈጸመባቸውን እስረኞች ስም ዝርዝር ለማየትእዚህ ጋ ይጫኑ፡፡)

እ.ኤ.አ ህዳር 1983 የዩኤስ አሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ኸርበርት ኢ. ሜየርየዩኤስኤስአርን/USSR መንኮታኮት ዋና ዋና ምክንያቶችን አስቀድመው በማወቅ ያቀረቡት ምልከታ እ.ኤ.አ ታህሳስ2015 እየተከሰተ ካለው እውነታ ጋር ልዩ የሆነ መስተጋብር እና ጠቀሜታ አለው የሚል እምነት አለኝ፡፡

ሜየር ሁሉም ነገር በራሽያ የቁጥጥር አስተዳደር ምክንያት አንድም ብሄራዊ የሆነ ድርጅት ደስ ተሰኝቶ በማይኖርበትሁኔታ ዩኤስኤስአር ፍጹም በሆነ መልኩ ተንኮታኩታ ትወድቃለች የሚል ጽሁፍ በማዘጋጀት የክርክር ጭብጣቸውንአቅርበው ነበር፡፡

በ21ኛው ክፍለ ዘመን ተስማሚ የሆነ የምጣኔ ሀብት እና የስነ ተዋልዶ ሁኔታዎች በሌሉበት እና በማይኖሩበት መንገድየዓለም የመጨረሻዋ ግዛት የሆነችው ሀገር ህልውና ሊኖራት እንደማይችል አረጋግጠዋል፡፡

ሜየር እንዲህ በማለት አውጀው ነበር፣ “የሶቭየት የምጣኔ ሀብት ወደ አደገኛ የቀውስ ቅርቃር ውስጥ ገብቷል፡፡“ ከዚህምበተጨማሪ እንዲህ ብለው ነበር፣ “የሶቭየት ዩኒየን የስነ ተዋልዶ ቅዠት ነው፡፡“

ሜየር እንዲህ የሚል የማጠቃለያ ሀሳብ ሰጥተው ነበር፣ “የሶቭየት አመራር አስፈላጊ የሆኑትን ለውጦች ለማምጣትወይም ደግሞ እነዚህን ሁኔታዎች ለመመለስ የሚያስችል ወይም መፍትሄ በመስጠት ከነገሮች ጋር አብሮ ለመሄድየሚያስችል ድርጊት ሊያከናውን አይችልም፡፡“

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 እኔም እንደዚሁ በኢትዮጵያ ላይ ተመሳሳይ የሆነ የክርክር ጭብጤን አቀርባለሁ፡፡

ኢትዮጵያ በፖለቲካ ቀውስ ቅርቃር ውስጥ ገብታለች፣

ኢትዮጵያ በዘ–ህወሀት የአገዛዝ ስርዓት ውስጥ እንደ ሀገር የመቀጠሏ ሁኔታ ፍጹም በሆነ መልኩ ወድቆ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ዘ–ህወሀት በብችኝነት ህዝቡን በጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት ውስጥ እጅ ከወርች በመጠፍነግተቆጣጥሮ ይዞት ባለበት ሁኔታ የትኛውም ትልቅ ብሄራዊ የሆነ የፖለቲካ ቡድን ደስ ብሎት ሊኖር አይችልም፡፡

ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ የዘ–ህወሀት የእራሱን የአገዛዝ ስርዓት እና ስልጣን ለማጠናከር ሲል የጎሳ ፌዴራሊዝም አባዜንእና በፖለቲካ የከፋፍለህ ግዛን ፖሊሲ በማራመድ ተግባራት ላይ ሲውተረተር ይገኛል፡፡ ዘ–ህወሀት በስልጣን እርካብላይ ተፈናጥጦ ለመኖር እንዲመቸው የፍርሀት፣ የጥልቅ ጥላቻ እና በኢትዮጵያ ውስጥ አንዱን ጎሳ ከሌላው ጋር በማናቆርዕኩይ እስትራቴጂ ነድፎ በመተግበር ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ የዘ–ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ ውስጥ ታሪካዊ የፖለቲካ ቅሬታላላቸው ቡድኖች እና ግለሰቦች በትክክለኛው የፌዴራሊዝም አወቃቀር መስፈርት መሰረት እራሳቸውን በእራሳቸውማስተዳደር እንዲችሉ የፈቀደ በማስመሰል የህዝብ ንብረት የሆነውን መሬቱን ለባዕዳን እየሸጠ እና ሌላውንም የሀገሪቱንአንጡራ ሀብት እየመዘበረ ኪሱን በዶላር በማጨቅ ላይ ይገኛል፡፡

የዘ–ህወሀት ተልዕኮ አስፈጻሚዎች በኢትዮጵያ ተገልለው ለቆዩት ብሄረሰቦች የጎሳ ፌዴራሊዝም ሀውልት በማቆምበአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ የጎሳ ፌዴራሊዝም ሰፍኗል በማለት ዘ–ህወሀት እራሱን የበላይ ጠባቂ አድርጎ አስቀምጧል፡፡ፍጹም የሆነ ሸፍጥ!

ላለፈው ሩብ ምዕተ ዓመት ዘ–ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም የመጫወቻ ኳስ በማዘጋጀት አንዱን የጎሳ ቡድን ከሌላኛውየጎሳ ቡድን ጋር እያጋጨ ሀገሪቱን በትክክል ባልታሰበበት ሁኔታ ከፍሎ እና ሸንሽኖ ህዝቦችን በኃይማኖት እየለያየእያጋጨ እያተራመሰ ከፋፍሎ በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡

ላለፈው ሩብ ምዕት ዓመት ዘ–ህወሀት ለጥቅም የሚገዙ የይስሙላ የፖቲካ ፓርቲዎችን በማቋቋም አስመሳይነት የሸፍጥጨዋታ ሲጫወት ቆይቷል፡፡ እራሱን የኢትዮጵይያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ብሎበመጥራት የዘ–ህወሀትን የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች (ጅቦች አላልኩም) የኢትዮጵያን ህዝብ የሚጠብቁ በመምሰልእየገደሉት እና እያሰቃዩት ይገኛሉ፡፡

ዘ–ህወሀት የጎሳ ታማኝነትን እያዘጋጀ እና የጎሳ ፍርሀትን እና ጥልቅ ጥላቻን እያራመደ ሲያካሂድ የነበረው የሸፍጥጨዋታ ከእንግዲህ ወዲያ የሚቀጥል አይሆንም፡፡

በአሁኑ ጊዜ ያለው እውነታ ዘ–ህወሀት በኢትዮጵያ በሚገኝ በእያንዳንዱ የጎሳ ቡድን እየተጣለ ነው ያለው፣ ምንም ደጋፊየለውም!

የማስመሰል ጨዋታው ተጠናቅቋል፣ እናም ይህንን ጉዳይ ዘ–ህወሀት በሚገባ ተገንዝቦታል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ከሩብ ምዕተ ዓመታት በኋላ በዘ–ህወሀት አማካይነት ለእራሱ የተፈጠረለትን የጎሳ ክፍፍልእያንዳንዳቸውን ምንም ዓይነት ጥቅም የማያገኙበት እና በዘለቄታዊነት ዘ–ህወሀት ብቻ አሸናፊ ሆኖ ተጠቃሚየሆነበትን ስርዓት አንድ በአንድ ተገንዝበውታል፡፡

ዘ–ህወሀት የእራሱን ፍላጎት ፍጹም በሆነ መልኩ በህዝቦች ጫንቃ ላይ እየጣለ ያለው ሁኔታ ሊያሰኬደው እንዳልቻለከጊዜ ወደ ጊዜ እየተገነዘበው መጥቷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ተማሪዎች እና ወጣቶች ለሀገሪቱ ጥቅም እና ነጻነታቸውን ለማስከበር ወደፊት ገፍተው በመሄድ ላይ ናቸው፡፡

ሆኖም ግን እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ከዋናው የግድብ ውኃ አንዲት ጠብታ ብቻ ናቸው፡፡ ዘ–ህወሀት የሌባ ጣቱንወደ ንጹሀን ዜጎች ላይ በመቀሰር እና የተማሪዎችን ተቃውሞ በግድያ በመጨፍለቅ ሊያስቆመው እንደሚችል አድርጎያስባል፡፡

ዘ–ህወሀት ያልተገነዘበው ጉዳይ ቢኖር እያንዳንዷ የተማሪዎች ቅሬታ ተሰባስባ ህዝባዊ በሆነ ቁጣ፣ ማዕበል፣ ጥላቻ እናመቃቃርን ፈጥራ ወደ ግብዓተ መሬቱ የሚያደርሰው መሆኑን ነው፡፡

የዘ–ህወሀት ትልቁ ቅርንጫፍ በሚገነደስበት ጊዜ የጎሳ ፌዴራሊዝም አልጋ ተንኮታኩቶ ይወድቃል፣ እናም ዘ–ህወሀትወደ ታሪክ ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ውስጥ ይወረወራል፡፡

የዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋች የስራ ጌቶች ዘ–ህወሀት እ.ኤአ. ግንቦት 2015 ምርጫውን መቶ በመቶአሸነፊያለሁ ብሎ ካወጀ በኋላ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ጎዳና ላይ በመገስገስ ላይ ናት በማለት እየነገሩን ይገኛሉ፡፡

ባራክ ኦባም ቢሆን የአእምሮ ክህሎታችንን በሚፈታተን መልኩ በመዘለፍ ይህንን ቡድን እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015ተቀላቅሏል፡፡ አስመሳዩ ፕሬዚዳንት ተብዬ እንዲህ ብሏል፣ “እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 በተካሄደው ምርጫ ዘ–ህወሀትመቶ በመቶ ያሸነፈበት ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ነው፡፡“ ባራክ ኦባማ ስለኢትዮጵያ እውነት እንዲናገር ነግሬው ነበር፡፡ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ስለኢራቅ የጦር እልቂት አምጭ መሳሪያዎች የፈጠጠ ውሸት ዋሽቷል፡፡ ባራክ ኦባማ ስለዘ–ህወሀትሀሳብን የማስቀየሻ የውሸት የምርጫ ውጤት ሙልጭ አድርጎ ዋሽቷል፡፡

ኢትዮጵያ በማህበራዊ የቀውስ ቅርቃር ውስጥ ወድቃለች፣

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አንገብጋቢው ጥያቄ ረኃብ ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ.ኤ.አበ2016 የመጀመሪያው ግማሽ በኢትዮጵያ ቢያንስ 15 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ለረኃብ እንደሚጋለጡ ይፋ አድርጓል፡፡

ዘ–ህወሀት ከዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋቾች እና ከአበዳሪ እና ለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመሆኑ በአሁኑ ጊዜበሀገሪቱ ውስጥ ተከስቶ ህዝቡን በችጋር እየጠበሰ እና እልቂትን እየፈጸመ ያለውን የረሀብ ቀውስ ከምንም ባለመቁጠርረኃብ በሀገሪቱ ውስጥ በፍጹም የለም፣ አለ እንኳ ቢባል የሚኖረው የምግብ ዋስትና እጦት እና የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገርእጥረት እጦት ነው እያሉ የሚጠሩት ነው በማለት የፕሬስ መግለጫዎችን ሁሉ አጨናንቀው ይገኛሉ፡፡

ዘ–ህወሀት የሚጠቀምበት አዲሱ ፋሽን ደግሞ ረኃቡን ያመጣው ኤል ኒኖ እየተባለ የሚጠራው ፍጡር ነው በማለትከደሙ ንጹህ ነን በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ ረኃቡን በየጊዜው የሚያመጣው እና የሚፈጥረው ብልሹ አስተዳደራቸው እናየማይለወጠው ገታራው ፖሊሲያቸው መሆኑን ለአምዲትም ሰከንድ ቢሆን ማመን አይፈልጉም፡፡ ምክንያቱ የተግምባርድሁሮች መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በምሁራን እና በባለሙያዎች የሚሰጥን ማንኛውንም ዓይነት አዎንታዊ ምክረ ሀሳብአእምሯው ሊቀበል አይችልምና ነው፡፡ ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውም የሚባለው ዓይነት ነገር መሆኑ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት የቪኦኤ ሬዲዮ የአማርኛው አገልግሎት በድርቅ በተመቱ አካባቢዎች በመገኘት ለአርሶ አደሮች ቃለመጠይቆችን በማካሄድ የሚከተሉትን ዘገባዎች በመግለጫ መልክ አቅርቧል፡

“ሰዎች ስለረኃቡ እና ስላለባቸው መከራ እንዲናገሩ አይፈቀድም፡፡ እነርሱ (ዘ–ህወሀት ማለታቸው ነው) ስለረኃቡያለውን መረጃ ሁሉ ይደብቃሉ፡፡ ስለዚህ ነገር አንድም ነገር መናገር አይፈልጉም፡፡ ስለረኃቡ ሲናገር የተገኘ ሰው የነፍስማጥፋት ወንጀል እንደፈጸመ ወንጀለኛ እኩል ጥፋተኛ ተብሎ ይፈረጃል፡፡ ስለረኃቡ መናገር ወንጀል ነው፡፡ ስለረኃቡየሚናገሩ ሰዎችን ያስራሉ፡፡ ሰዎችን ይደበድባሉ፡፡ ሰዎችን ያስፈራራሉ፡፡ ሰዎች ተርበዋል፡፡ በእርግጠኝነት ተርበዋል፡፡በርካታ የሆኑ ሰዎች ምንም ዓይነት የሚላስም ሆነ የሚቀመስ ነገር የላቸውም፡፡ ከ4-5 የሚሆኑ የበቆሎ ራሶች 10 ብርያወጣሉ…“

ዘ–ህወሀት እና ዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋቾች የረኃቡን እውነተኛ ገጽታ ለመደበቅ ከሚል ዕኩይ ምግባር ባዶየፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማራመድ ስራ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ እናም እስከ ጥርሳቸው ድረስ በዋሹ ቁጥር በሚሊዮኖችየሚቆጠሩ ወገኖቻችን በረኃብ የሞት ነጣቂ ተኩላ ይነጠቃሉ፡፡

ዘ–ህወሀት “ረ“ ሀብ የምትለዋን ፊደል በፍጹም መጠቀም አይፈልግም፡፡

እ.ኤ.አ ነሐሴ 2008 አሁን በህይወት የሌለው የዘ–ህወሀት አድራጊ ፈጣሪ አምባገነን መሪ ለታይም መጽሔት እንዲህየሚል ቃለ ምልልስ ሰጥቶ ነበር፣ “በኢትዮጵያ የረኃብ አደጋ ለበርካታ ጊዚያት ሲከሰት ቆይቷል፡፡ እንዲህ ዓይነት አደጋሲከሰት ለጉዳዩ ትኩረት የማያደርግ ደደብ ነው፡፡ ሆኖም ግን በእኛ ሁኔታ ምንም ዓይነት ረኃብ የለም – የአስቸኳይ ጊዜብቻ ነው፡፡ ረኃብ በፍጹም የለም…በአንዳንድ አካባቢዎች በአንዳንድ ኪስ ቦታዎች የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረትብቻ ነው ያለው“ በማለት በድፍረት በቅጥፈት ተናግሯል፡፡

ዘ–ህወሀት እና የዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋቾች 15 ሚሊዮን የሚሆነውን ህዝብ የረኃብ ሰለባ ያደረገውንየረኃብ አደጋ እንደዚህ ባለ አሳፋሪ የቃላት እና የሀረጎች አጠቃቀም በመሸፋፈን ያለው የምግብ እጥረት፣ የምግብክፍተት፣ የአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጥረት፣ የምግብ ዋስትና እጦት እና በኤል ኒኖ ድርቅ ምክንያት የተከሰተ የግብርናምርት እጥረት እና በመሳሰሉት ነው በማለት የቅጥፈት ልብስ ለማልበስ ይሞክራሉ፡፡

አሁን በቅርብ ጊዜ ያለው ጥረት ደግሞ የኢትዮጵያን ረኃብ “የስነ ምግብ ቀውስ” እያሉ የሚጠሩበት አካሄድ ነው፡፡ አዎ፣“የስነምግብ ቀውስ”ይሉታል ፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 2015 የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ጽ/ቤት እንዲህ በማለት አስጠንቅቋል፣“በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተጠናከረ ምላሽ እስካልቀረበ ድረስ ከፍተኛ የሆነ የምግብ ዋስትና እጦት እና የስነምግብቀውስ ሊከሰት ይችላል፡፡“

ዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋቾች “ረ“/”F) የምትለዋን ፊደል ለማስወገድ ሲባል የእንግሊዝኛን ቋንቋ እያሰቃዩእንዳሉ ስነገነዘብ ምን ያህል የወረዱ ፍጡሮች እንደሆኑ እንገነዘባለን! ያም ሆነ ይህ ምን ዓይነት የውሸት የማጭበርበርአነጋገር ነው እባካችሁ?

በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦችን ለሞት፣ ለአካል ጉዳተኝነት እና በሚሊዮኖች ለሚሆኑ ሰዎች ደግሞለመፈናቀል የሚያበቁነው የመሬት መንቀጥቀጥ እና ሱናሜን ጨምሮ “የተፈጥሮ አደጋ” ሲባል ሰምቻለሁ፡፡

ምግብ በማያገኙ ሰዎች ላይ የሚከሰተው “የስነምግብ ቀውስ” አደጋ በተመሳሳይ መልኩ እንደ ተፈጥሮ አደጋ እኩልተደርጎ ሊቆጠር ይችላል ለማለት ነዉን?

ወደኋላ መለስ ብለን ስንመለከተው “የስነምግብ ቀውስ” አደጋ ረኃብ ተብሎ የሚጠራውን ነገር ለመጥራትየሚጠቀሙበት ሐረግ ነው፡፡

ቢቢሲ ብቻ ነው ረኃበን ረኃብ ብሎ በመጥራት ድፍረት ያለው፡፡

ኢትዮጵያ ወደ ምጣኔ ሀብት ቀውስ ቅርቃር ውስጥ ገብታለች፣

ውሸቶች፣ ተራ ቅጥፈቶች እና የሀሰት የቁጥር ድርደራ ጨዋታዎች በዓለም ባንክ፣ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እናበዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ እና በሁሉም የአውሮፓ እና አበዳሪ እና ለጋሽ ድርጅቶችአማካይነት የኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት 11 በመቶ (ይቅርታ የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ ህዳር 2014 ባወጣው ዘገባውየኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ዕድገት 10.9 በመቶ ይል ነበር) የምጣኔ ሀብት ዕድገት ባለፉት አስር ዓመታት ዕድገትአስመዝግቧል በማለት የሚዘግቡ ቢሆንም የምጣኔ ሀብቱ በአሁኑ ጊዜ በአስከፊ የቀውስ ቅርቃር ውስጥ ገብቶ ይገኛል፡፡

ዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋቾች ሁሉም ኢትዮጵያውን ከአለት በበለጠ መልኩ የደደቡ ናቸው ብለውእራሳቸውን የሚያሳምኑበትን እውነታ እገነዘባለሁ፡፡

የኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት በፍጥነት እያደገ ያለ እና በዓለም ፈጣን የምጣኔ ሀብት ዕድገትን ከሚያስመዘግቡ ሀገሮችመካከል አንዱ ነው በማለት ሌት ከቀን እንደበቀቀን እየደጋገሙ ውሸትን በመዋሸት የኢትዮጵን ህዝብ እና የዓለም አቀፉንማህበረሰብ ለማሳመን ቅጥፈትን ከቶ ሲያራምዱ የሚውሉት ለምንድን ነው?

ላለፉት አምስት ዓመታት የኦክስፎርድ የድህነት እና የሰው ኃይል ልማት ተነሳሽነት ዘርፈ ብዙ የድህነት አመልካቾች/Oxford Poverty and Human Development Initiative (OPHDI) Multidimensional Poverty Index ባወጣው የድህነት እና የሰው ኃይል ልማት መለኪያ መስፈርትመሰረት ባለፉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ በፕላኔቷ ውስጥ ካሉ ሀገሮች በሙሉ በድህነት በሁለተኛ ደረጃላይ የተቀመጠች መሆኗን ይፋ አድርጓል፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የዓለም ባንክ ባወጣው ዘገባ መሰረት በአጠቃላይ በአገልግሎት እና በግብርና ዘርፉ ላይ ትኩረትባደረገ መልኩ ኢትዮጵያ አስደናቂ የሆነ ፈጣን የምጣኔ ሀብት ዕድገት እያስመዘገበች መሆኗን እንዲህ በማለት ይፋአድርጓል፡

“የግብርና የምርት ውጤቶች ዕድገት ሊመዘገብ የቻለው የግብርናውን ምርታማነት በማሳደግ እና ሊታረስ የሚችለውንየመሬት መጠን በመጨመር ነው፡፡ ለግብርናው ምርት ማደግ እንደ ዋና ዋና ነገሮች ሊቆጠሩ የሚችሉት የኤክስቴንሽንአገልግሎት እና ለአርሶ አደሮች ስልጠና መሰጠት በመቻሉ ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ እየተመዘገበ ያለው የግብርና ምርት ዕድገትበዋናነት መንግስት በኤክስቴንሽን አገልግሎት፣ በመንገዶች ግንባታ እና በትምህርት ላይ ከፍተኛ የሆነ መዋዕለ ንዋይበማፍሰሱ እንደዚሁም ደግሞ ምቹ የሆኑ የዋጋ ማበረታቻዎችን ማድረግ በመቻሉ ነው“ ብሏል፡፡

አንግዲህ እግዚአብሔር ያሳያችሁ የግብርናውን ምርታማነት በማሳደግ እና ሊታረስ የሚችለውን የመሬት መጠንበመጨመር መንግስት እያደረገ ባለው ከፍተኛ ጥረት እ.ኤ.አ በ2015 የግብርና ምርት ዕድገትን ሳይሆን ረኃብንለማምረት ቻለ ማለት ነው፡፡ የሚታየው እውነታ ይኸ እና ይኸ ብቻ ነው መቀነስም መጨመርም የሚቻል ነገር ሊሆንአይችልም፡፡

የዘ–ህወሀት መሪዎች ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓ ህብረት እና ከቻይና እርጥባን በመለመን እና ለማኝ መንግስት በመሆንእራሳቸውን በስልጣን ላይ እንደ መዥገር አጣብቀው መቆየት እንደሚችሉ አድርገው ያስባሉ፡፡

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን ከለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች በምጽዋት ከሚያገኘው እርጥባን ውጭ ለአንድምቀን ቢሆን በስልጣን ላይ ሊቆይ አይችልም፡፡

ታዋቂ የሆነችው አፍሪካዊት የምጣኔ ሀብት ባለሙያ እና የሙት እርዳታ/Dead Aid መጽሐፍ ደራሲ ዳምቢሳ ሞዮየኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት ሁኔታ በማስመልከት እንዲህ ብላለች፣ “በኢትዮጵያ 97 በመቶ የሚሆነው ግዙፍየመንግስት በጀት የሚገኘው ከውጭ እርዳታ ነው፡፡“ በእርዳታ እና በብድር እስትንፋስ ህይወት ዘርቶ ስለሚንቀሳቀስአገዛዝ ከዚህ በላይ ምን ማለት ይቻላል?

በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀባይነት ሊኖረው የሚገባውን ጠቃሚ ነገር ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ የተባለው ዓለም አቀፍድርጅት እንዲህ በማለት አስቀምጦታል፣ “የኢትዮጵያ ህዝቦች አጥንታቸው እስኪቀር ድረስ ተግጠዋል፡፡ ፍጹም ከሆነእጦት እና ድህነት አረንቋ ውስጥ ለመውጣት በከፍተኛ ሁኔታ ትግል የሚያደርጉ ቢሆንም ቅሉ በሕገ ወጥ የገንዘብዝውውር ምክንያት በወንዙ ውስጥ ወደ ላይ በመዋኘት ላይ ይገኛሉ“ በማለት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ እንግዲህ የዘ–ህወሀት ጉድ “ወደ ታች ነው እንጅ ውኃ አወራረዱ ሽቅብ ሽቅብ አለኝ እኔንስ ለጉዱ” እንደሚባለው መሆኑ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በስነ ህዝብ የቀውስ ቅርቃር ውስጥ ገብታለች፣

የዘ–ህወሀት መሪዎች ባለፈው አስርት ዓመታት ውስጥ 10.9 በመቶ ዓማካይ አመታዊ የምጣኔ ሀብት ዕድገትአስመዝግባለች በማለት ሁልጊዜ ያናፋሉ፡፡ (እንደ አህያ “ያናፋሉ” አላልኩም።)

ሆኖም ግን የዘ–ህወሀት መሪዎች ለመናገር የሚጠሉት 3 በመቶን ሊዘል ትንሽ ስለሚቀረው እና የኢትዮጵን ህዝቦችህልውና ስለሚፈታተነው ልቅ የተደረገ የስነ ህዝብ መጣኔ ጉዳይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕድገት ለበርካታ አስርት ዓመታት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ አገዛዙ እንደ አንድኃላፊነት እንደሚሰማው ቡድን እንኳ ስለ ስነህዝቡ ሁኔታ አንድም ትንፍሽ የሚለው ነገር የለም፡፡ በሙስና መብከት እናመበስበስ እንጅ ይህ ነገር ለእርሱ ጉዳዩ አይደለምና፡፡

እ.ኤ.አ በ1967 የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 23.5 ሚሊዮን ነበር፡፡

አ.ኤ.አ በ1990 ወደ 51 ሚሊዮን ከፍ አለ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ እ.ኤ.አ በ2003 68 ሚሊዮን ደረሰ፡፡

እ.ኤ.አ በ2008 የህዝቡ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እያደገ በመምጣት 80 ሚሊዮን ደረሰ፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 የዩኤስ አሜሪካ የስነ ህዝብ ቆጠራ ቢሮ በሰጠው ግምት መሰረት የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 91 ሚሊዮንደረሰ፡፡

እ.ኤ.አ ከ1995 ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ አማካይ ዓመታዊ የህዝብ ዕድገት መጣኔ ከ3 በመቶ በላይ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ይኸ ነገር እንዴት ነው የሚል እና ኃላፊነት የሚሰማው አካል ጠፍቷል፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 የዩኤስ አሜሪካ የስነ ህዝብ ቆጠራ ቢሮ ስለኢትዮያ ህዝብ ብዛት በጣም አስፈሪ የሆነ ትንበያ በመስጠትእ.ኤ.አ በ2050 በወቅቱ ካለበት የህዝብ ቁጥር በሶስት ጊዜ እጥፍ በማደግ 278 ሚሊዮን ይደርሳል ብሏል፡፡

እ.ኤ.አ በ2025 ማለትም ከዛሬ አስር ዓመታት በኋላ የዩኤስ አሜሪካ የስነ ህዝብ ቆጠራ ቢሮው በሰጠው ትንበያመሰረት የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 131 ሚሊዮን ይደርሳል ብሏል፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ 99 ሚሊዮን የሚደርስ ህዝብ መመገብ አትችልም፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 ደግሞ 87 ሚሊዮን ህዝብ መመገብ አትችልም ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2006 78 ሚሊዮን ህዝብ መመገብ አትችልም ነበር፡፡

እንደዚሁም ሁሉ እ.ኤ.አ በ1984 40 ሚሊዮን ህዝብ መመገብ አትችልም ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ1974 32 ሚሊዮን ህዝብ መመገብ አትችልም ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2025 ኢትዮጵያ 131 ሚሊዮን ህዝቦቿን ለመመገብ ምን ያህል ገሀነም እንደሚሆንባት ልናስበውእንችላለን?

ኢትዮጵያ ወደፊት የምግቡ ደረጃ ካለበት የእድገት መጠን ጋር ሊሄድ የሚችል የስነ ህዝብ ዕድገት እንዲኖራት ለማስቻልየህዝቡን የዕድገት ሁኔታ ከምጣኔ ሀብት ዕድገቱ ጋር ለማመጣን እንዲቻል የማልተስ እልቂት ወደሚባለው የተቃወሰየህልወት እርምጃ (ማለትም በሽታ፣ ረኃብ፣ ጦርነት፣ ወዘተ የመሳሰሉት ነገሮች የህዝቡን ቁጥር ይቀንሱታል) በማለትዝም ብሎ በግዴለሽነት የማየት ሁኔታ የሚታይ ይመስላል፡፡

በአንድ ወቅት አሁን በህይወት ለሌለው ለአምባገነኑ የዘ–ህወሀት መሪ በይስሙላ ፓርላማ ተብየው የስነ ህዝብ ጉዳይንየሚመለከት ጥያቄ ቀርቦለት የሚወለደው ሰው ሆድ ብቻ ሳይሆን የሚሰሩ እጆች ጭምር ይዞ ነው የሚመጣው የሚልምላሽ በመስጠት ተሳልቆ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ እንግዲህ ይኸ የሚያሳየው ሰውየው ስለ ስነህዝብ ጉዳይ ምንነትምንም ነገር እወቀቱ የሌለው መሆኑን እና እርሱ የሚመራው መንግስት ስለዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ምንም ዓይነት እርምጃለመውሰድ ክህሎቱ የሌለው መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያመላክታል፡፡ እንደ እርሱ አባባል ቢታይ እንኳ የኢትዮጵያ ህዝብበየጊዜው ለረኃብ ሰለባ የሚጋለጠው የሚወለዱት ህጻነት ሆድ ብቻ ይዘው የሚመጡ እንጅ የሚሰሩ እጆች የሌሏቸውስለሆኑ ይሆን?

እ.ኤ.አ መስከረም 2010 አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ የዘ–ህወሀት መሪ መለስ ዜናዊ እራሱን ከፍ ከፍበሚያደርግ መልኩ እንዲህ በማለት አውጆ ነበር፣ “ትርፍ ምርት ለማምረት የሚያስችለንን ስትራቴጂ ቀይሰናል፣ እናምእ.ኤ.አ በ2015 ከውጭ ምንም ዓይነት የምግብ እርዳታ ሳይደረግልን እራሳችንን መመገብ እንችላለን“ ብሎ ነበር፡፡ከዚህም በተጨማሪ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ከተባበሩት መንግስታት የሚሊኒየም የልማት ግቦች ጋር በሚመሳሰል መልኩእ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ፍጹም ድህነት በ50 በመቶ ከአልሚ ምግብ ንጥረ ነገር እጦት ጋር ይቀንሳል“ ብሎ ነበር፡፡ምን ዓይነት ዲያብሎሳዊ ውሸት ነው!

ዘ–ህወሀት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን ኢትዮጵያን ህዝብ ዕድገት ለመቆጣጠር የሚያስችል እና 15 ሚሊዮኑንህዝብ ከአሰቃቂ ረኃብ ለማዳን ወይም ደግሞ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ምንም ዓይነት ዕቅድም ሆነ ፕሮግራምየለውም፡፡

ዘ–ህወሀት እራሱ ወደ ቀውስ ቅርቃር ውስጥ እየገባ ነው፣

ዘ–ህወሀት አስተማማኝ የሆነ ወታደራዊ ኃይል አለኝ፣ በውሸት ላይ የተፈበረከ የምጣኔ ሀብት ስኬት አለኝ፣ በሀገሪቱውስጥ አስተማማኝ የፖለቲካ መረጋጋት አለ፣ ወዘተ በማለት በእራሱ የቅጥፈት ትረካ እራሱን ሕጋዊ አስመስሎ ለማቅረብሙከራ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ዘ–ህወሀት እና ዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ወትዋች ግብረ አበሮቹ መልካም እና ጥሩ ስም ያለው እያስመሰሉበማቅረብ ስለምጣኔ ሀብቱ ዕድገት የሀሰት የቁጥር አሀዞችን በመደርደር የነቀዘ እና የበከተ ገጽታውን ለመደበቅ በመሞከርላይ ይገኛሉ፡፡

ዘ–ህወሀት የኃይል እና የጭቆና አገዛዙን ለማስቀጠል የመጨረሻውን አቅሙን አሟጦ በመጠቀም ለህዝብ ለማሳየትበዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ሆኖም ግን ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ከዚህ በኋላ “አንዲት ጋት ወደ ኋላ አናፈገፍግም” በማለት በጽናት የተሞላስሜቱን በማሳየት ላይ ይገኛል!

እውነታውን ሙልጭ አድርጎ መካድ የአምባገነኖች ሁሉ መለያ ባህሪ ነው፡፡ ዘ–ህወሀት ለዚህ የተለዬ ብችኛ ሊሆንአይችልም፡፡

ለሁሉም አምባገነኖች የማይቀየሩ ዘላለማዊ እውነታዎች አሉ የምንል ከሆነ እምባገነኖች ሆን ብለው እያወቁ ደንቆሮዎች፣እውሮች እና ዱዳዎች ናቸው፡፡

ለህዝቦች ጩኸቶች እና እንባዎች ሆን ብለው ጆሮ ዳባ ልበስ የሚል ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

ስለደኃ ህዝቦች መሰቃየት፣ ለድርቅ አደጋ ሰለባ ለሆኑ እና አቅም ለሌላቸው ሁሉ አላየሁም በማለት አድፍጠውይቀመጣሉ፡፡

መከራን የሚገፉ ህዝቦችን ለይቶ በማውጣት አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ከችግሮቻቸው ለማውጣት ባለመቻልዱዳ ሆነው በመቀመጥ ይመለከታሉ፡፡

ህዝቡ እነርሱን የሚወዳቸው ለመሆኑ ሌላ ማንንም ሶስተኛ ወገን ሳያስፈልጋቸው እራሳቸውን በእራሳቸው ያሳምናሉ፡፡

በማስመሰያው የቅርጫ ምርጫ ከህዝቡ መቶ በመቶ ድምጽ ያገኙ በመሆናቸው እና በዚህም መሰረት ስልጣን እንደያዙአድርገው የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳመን ይሞክራሉ፡፡

እነርሱ እብዶች ናቸው፡፡ ልክ እንዳበደ ቀበሮ፣ እውነታው ይኸው ነው፡፡

እ.ኤ.አ የካቲት 2011 የሊቢያ ህዝባዊ አብዮት እየተቀጣጠለ ባለበት ሁኔታ አምባገነኑ ሙአማር ጋዳፊ ለዓለም አቀፉማህበረሰብ እንዲህ የሚል ቱልቱላውን ነፍቶ ነበር፣ “ህዝቡ እኔን ይወደኛል፡፡ ሁሉም ህዝቦች ከእኔ ጋር ናቸው፣ እናምይወዱኛል፡፡ የእኔ ህዝቦች እኔን ለመጠበቅ ሲሉ ይሞቱልኛል“ ነበር ያለው፡፡

እርሱን ከስልጣኑ ላይ ለማስወገድ የሚታገሉ የነጻነት ኃይሎችን “አይጦች እና በረሮዎች” በማለት ነበር የጠራቸው፡፡እራሱን የንጉሶች ሁሉ ንጉስ በማድረግ በቆሻሻ መውረጃ ፉካ ውስጥ የህይወቱ እስትንፋስ እስከምታልፍ ድረስ ሊቢያንእስከሚሞት ድረስ የመግዛት መብት እንዳለው አድርጎ ነበር የሚያምነው፡፡ በሊቢያ ውስጥ እራሱን ለ42 ዓመታት ያህልአምላክ አድርጎ የሚቆጥር አምባገነን በወሮበላ የዘራፊ ዓይነት አሟሟት ዓይነት ወደማይቀረው ዓለም በውርደትተሰናበተ፡፡

በመጨራሻዋ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የተቃራኒው ዕጣ ፈንታ አሸናፊ ሆኖ የገዳፊ ዕድል በምታዘቀዝቅበት ጊዜ ጋዳፊ ተቃዋሚታጋዮቹ ምህረት እንዲያደርጉለት ፍትህን ጠየቀ፡፡ እንደ ቆሻሻ አይጥ ተስቦ እና እንደበረሮ በኃይል ተደልዞ ምህረትእየጠየቀ ከፉካው ውስጥ በመውጣት እንዲህ አለ፡ “አትግደሉኝ!“

ከአምባገነኑ ሳዳም ሁሴን በፊት የጣሊያን ፋሽሽት መሪ የነበረው ቤኒቶ ሙሶሊኒ እንዲህ በማለት ጉራውን ቸርችሮ ነበር፣“በእያንዳንዷ የልቤ ምት ሁሉ ለጣሊያን ህዝብ አገልግሎት እሰጣለሁ፡፡ በመሆኑም ሁሉም ጣሊያናዊ እኔንእንደሚወደኝ እና እንደሚረዳኝ ይሰማኛል፡፡“

የኡጋንዳ ህዝብ አራጅ የሆነው ኢዲ አሚን ዳዳ እንዲህ የሚል አነስተኛ የሆነ ስሜታዊነትን አንጸባርቆ ነበር፣ “ህዝቦችመሪያቸውን መውደድ አለባቸው!“ ይህንን የማያደርጉ ከሆነ መሪያቸውን እንዲወዱ የሚያደርግባቸው ጠንካራ የሆኑየእራሱ መሳሪያዎች በመጠቀም ስራውን ይሰራል፡፡

የዛየሩ ሞቡቱ ሴሴ ሴኮ በጸጥታ ቀስ ብሎ በመሳቅ ለውጭ ግንነት አድራጊዎቹ ሲናገር ህዝብ እርሱን ስለሚወደው ህዝቡእርሱን መውደድ ብቻ አይደለም እንዲያውም በስልጣኑ ላይ እንዲቆይ ይፈልጋል በማለት ባዶ ጉዳውን ሲቸረችርነበር፡፡

ደም መጣጩ ወታደራዊ አምባገነን መንግስቱ ኃይለማርያም ከአርበኝነት እና ከሀገር ወዳድነት የይስሙላ ማታለያተልዕኮው አንጻር ህዝቡን እንደ ሰም አቅልጦ እንደ ብረት ቀጥቅጦ የመግዛት ዓላማ ነበረው፡፡ እርግጥ ነው መንግስቱለድፍን 17 ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውንን በገፍ እንደ ቄራ ሰንጋ እያረደ ሲገድል የቆየ ስለነበር እንደእርሱ እምነት ያለምንም ጥርጥር ሀገር ወዳድ ነው፡፡

እ.ኤ.አ ግንቦት 2010 አሁን በህይወት የሌለው የአፍሪካው ልዩ የሆነው ወሮባለ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያህዝብ የእርሱን ወሮበላ ፓርቲ እና በውስጠ ታዋቂነት ደግሞ የእርሱን የፓርቲ መሪነት በመውደዱ ምክንያት 99.6በመቶ የህዝብ ደጋፍ በማግኘት ምርጫውን አሸንፈናል በማለት የሸፍጥ እና የቅጥፈት ቱሪናፋውን ዘረገፈ፡፡ ህዝቡእነርሱን እና ኢህዴግን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው እናም ምንም ዓይነት ኃይል የእርሱን ድርጅትሊነቀንቀው እንደማይችል በእብሪት አፉን ሞልቶ ተናግሯል፡፡ ህዝቡ የእርሱን ፓርቲ በመምረጥ ላሳየው መልካም የህሊናዳኝነት እና ፍትሀዊነት ከልብ እንደሚያመሰግን እና የህዝቡን ይሁንታ በካርዳቸው እንደሰጡት በማድረግ የድርቅናቅጥፈቱን በአደባባይ አሰራጭቷል፡፡

በመጨረሻም የዘ–ህወሀት ችግር በነብሩ ጀርባ ላይ ወጥቶ እንደሚጋልበው ነብር ጋላቢ ሁሉ ለመውረድ አስፈሪ ሆኖየመገኘቱ ሁኔታ እየተባለ እንደሚነገረው ተረት ነው፡፡ ለድፍን 25 ዓመታት ዘ–ህወሀት የነብሩን ጭራ ይዞ ለመልቀቅእየፈራ በመወራጨት ላይ ያለ የዕኩዮች ስብስብ ነው፡፡

መሄድ እንዲችሉ ልቀቋቸው፡፡ ለመሄድ እንዲችሉ ፍቀዱላቸው፡፡

ነብር ጋላቢው ለበርካታ ጊዜ በመጋለቡ ምክንያት ታምሟል እናም በጣም ድካም ይዞታል፡፡ ዘ–ህወሀት ከስልጣን እርካብላይ እንዲወርድ በሚገደድበት ጊዜ በፈጣጣዎቹ ዓይኑ አፍጥጦ ይመለከታል፣ ጥርሶቹን ያንገጫግጫል፣ እናምየተንጨፈረሩ ጥፍሮቹን ይሰነዝራል!

በጋንዲ የተነገሩትን እንዲህ የሚሉትን ዘላለማዊ እውነታዎች ዘ–ህወሀት እንዲያስብበት እነግረዋለሁ፡ “በታሪክ ሂደትሁሉም የእውነት እና የፍቅር መንገዶች ያሸንፋሉ፡፡ አምባገነኖች እና ገዳዮች ለጊዜው የማይበገሩ አሸናፊዎች መስለውይታያሉ፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻ ሁልጊዜ ይወድቃሉ፡፡ ይህንን ነገር አስቡት ። ሁልጊዜ ይወድቃሉ፡፡“

ዘ–ህወሀት ከዚህ ዘላለማዊ እውነታ ሊያመልጥ አይችልም፡፡

የድሀረ ዘ–ህወሀት ኢትዮጵያ፣

በዘ–ህወሀት ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ እና ከምንም አድልኦ በጸዳ መልኩ፣ በሰለጠነ አኳኋን፣ በጓዳዊነት፣ ቅንነትንበተላበሰ መልኩ የእራሴን ምልከታ ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡

እውነቱን እንዳየሁት፣ አብሬው እንደኖርኩት፣ እንደሚሰማኝ፣ እንዳሰብኩት፣ እንደተገነዘብኩት አድርጌ አቀርባለሁ፡፡

ለኢትዮጵያውያን ድምጽ የለሾች፣ ኃይል የለሾች እና ለተስፋ የለሾቸ እናገርላቸዋለሁ፡፡ አዎ፣ እራሴን በእራሴ ሾሚያለሁ፣ሆኖም ግን ጥልቅ በሆነ መከባበር እና አገልግሎት ላይ በተመሰረተ መልኩ ነው፡፡

በኢትዮጵያ በዘ–ህወሀት ከተፈጠረው የሌሊት ቅዠት ሊወጣ የሚቻልበት መንገድ ይኖራል፡፡

ዘ–ህወሀት ያንን መንገድ አይጠቀምበትም፡፡

የዘ–ህወሀት አመራር እንደሞተው የሶቪዬት አመራር ሁሉ ያሉትን የጥፋት አደጋዎች ወይም ባሉበት መፍትሄ ለመስጠትእና ለውጥ ለማምጣት ሊሰራ አይችልም፡፡

ሆኖም ግን የመውጫ መንገዱ አለ፡፡

ስለውይይት መድረክ ነው፣ ስለጽኑ አርበኝነት መንገድ ነው፣ ስለማህበረሰቡ የማሰብ መንገድ ነው፣ ስለ መንፈሳዊህይወት የማሰብ መንገድ ነው፡፡

ወደ ብርሀን ወይም ደግሞ ቀጣይነት ወዳለው ጨለማ ውስጥ ስለመግባት መንገድ ነው፡፡

ስለሆነም ለእኛ በመስታወቱ ላይ የተጻፈልን ጥያቄ እና ለዘ–ህወሀት፣ ለደጋፊዎቹ እና ለግብረ አበሮቹ በግድግዳው ላይየተጻፈላቸው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነው፡ “ዘ–ህወሀት በሚወድቅበት ጊዜ ምን መደረግ አለበት?“

ለዘ–ህወሀት መልሱ ቀላል ነው፡፡ ተመትተው፣ እየጮኹ እና እያከኩ ወደ ታሪክ የቆሻሻ ማስቀመጫቸው ይሄዳሉ፡፡

ለእኔ የድህረ ዘ–ህወሀት ኢትዮጵያ የሸክስፒርን ጣያቄዎች ያቀርባል፡፡

ለጋራ ዕድል መተባበር ወይም አለመተባበር ያ ነው ጥያቄው፡፡

በዘ–ህወሀት የጋህነም መንገድ ላይ መጓዝ መቀጠል እና እራስን ወደ ገደል አፋፍ ላይ ወስዶ መጣል የሚለው ሌላውጥያቄ ነው፡፡

እኔ በዘ–ህወሀት ወዳጅ አይደለሁም ፡፡ (እሺ፣ ለቧልት ያህል ነው ያልኩት፡፡)

ዘ–ህወሀት እራሱን ከመጥፋት ለማዳን ቀደም ሲል ያወደማትን ኢትዮጵያን መጠበቅ መቻል ይኖርበታል የሚል እምነትአለኝ፡፡

እራሱን ለማዳን ዘ–ህወሀት እስከ ዛሬ ድረስ በመላ ኢትዮጵያ በጎሳ ፌዴራሊዝም ስም ሲገነባው የቆየውን የጥላቻንግድግዳ የግርዶሽ ግንብ መናድ አለበት፡፡

ዘ–ህወሀት ለዓመታት የገነባው የጥላቻ ግንብ በእራሱ ላይ ከመደርመሱ በፊት የጥላቻን ግንብ ቀድሞ ማፍረስ እናማስወገድ ይኖርበታል እላለሁ፡፡

ዘ–ህወሀት ከጀርባ የእናንተ አመራር፣ ግብረ አበሮች እና ደጋፊዎች ያሉበትን በግድግዳው ላይ የተጻፈውን የእጅ ጽሁፍማንበብ ይኖርባችኋል እላለሁ፡፡

ዘ–ህወሀት ኢትዮጵያውንን እንደ በረት ከብት በነገድ፣ በጎሳ፣ በኃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በመደብ ወዘተ በመከፋፈልበገነባችሁት የክልል ግንብ ላይ የተጻፈውን የእጅ ጽሁፍ ማንሳት ይኖርባችኋል እላለሁ፡፡

ዘ–ህወሀት ከቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዳትገናኙ ከቪላችሁ ጀርባ የገነባችሁትን ግንብ እና እስር ቤት ላይየጻፋችሁትን የእጅ ጽሁፍ አንብቡት እላችኋለሁ፡፡

ዘ–ህወሀት ላለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በገነባችሁት የጥላቻ ግንብ ላይየጻፋችሁትን የእጅ ጽሁፍ አንብቡት እላችኋለሁ፡፡

የዘ–ህወሀት አመራሮች የጥላቻ ግንብ በእራሳችሁ ላይ ከመናዱ በፊት እራሱን የጥላቻን ግንብ አስቀድማችሁ ናዱትእላችኋለሁ፡፡

ምናልባትም በመጽሐፍ ቅዱስ የአቀራረብ ዘይቤ ዘ–ህወሀትን (አሕዛቦቹን አላልኩም) ለመስበክ እችላለሁ፡፡

የኢያሪኮ ከተማ ግንቦች በጣም ጠንካሮች፣ ኃይለኛ ምሽጎች እና ለመስበርም የማይሞከሩ ነበሩ፡፡ የኢያሪኮን ግንብ መስበርየሚችል ምንም ዓይነት ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል አልነበረም፡፡

ሆኖም ግን ህዝቡ የኢያሪኮን ግንብ ለመስበር የወታደር ኃይል አላስተባበረም ነበር፡፡ ህዝቡ ጸጥታን በተላበሰ መልኩ ቀስብሎ ለስድስት ቀናት በመጓዝ ወደ ግንቡ ተቃረበ፡፡ በሰባተኛው ቀን ህዝቡ ኾ ብሎ ጮኸ፡፡ የኢያሪኮ ግንብ ወዲያውኑፈረሰ፡፡

የዘ–ህወሀት ግንብ በወታደራዊ ኃይል አይፈርስም፡፡ የጦር እና አውዳሚ መሳሪያዎችን በገፍ እና በብዙ ቁጥር በህዝብሀብት እየገዛ አከማችቷል፡፡ የአውዳሚ እና የጦር መሳሪያዎችን ከቻይና፣ ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓ ወይም ኬሎችምከሚፈልጋቸው ሀገሮች ወሰን በሌለው መጠን አከማችቷል፡፡

ህዝቡ አንድ ሆኖ ከሰሜን እስከ ደቡብ እና ከምስራቅ እስከ ምዕራብ “አምባገነናዊ አገዛዝ በቃን! ስልጣንን ከሕግ አግባብውጭ መጠቀም ይብቃ! ሙስና ይብቃ! የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ይቁም! በቃ በቃ ነው!“ በማለት በአንድ ድምጽሲጮህ የዘ–ህወሀት ግንብ እሳት እንዳልነካው ሸክላ ፍርክስክስ ብሎ ይወድቃል፡፡

የዘ–ህወሀት ግንብ ህዝቦች ስለ ዘ–ህወሀት ስያቅለሸላቸው አና ሲያስታዉካቸው ዘ–ህወሀት ይወድቃል ይደረመሳል፡፡

ዘ–ህወሀት ይወድቃል ምክንያቱም ዘ–ህወሀት የኢትዮጵያን ህዝቦች አእምሮ እና ልብ ሊቆጣጠር አልቻለምና፡፡

በወታደራዊ ኃይል ማቋረጫ የሌለው ጽናት ሊኖር አይችልም፡፡ ለረዥም ጊዜ ለጭቆና ተዳርጎ የቆየን የህዝብ ቁጣ እናብስጭት እንደዚሁም ሁሉ በየዕለቱ ክብሩን አጥቶ በውርደት ተዘፍቆ ኑሮን በመግፋት ላይ ያለን ህዝብ ማቆምየሚያስችል በምንም ዓይነት መንገድ በመሬት ላይ የሚገኝ ምድራዊ ወታደራዊ ኃይል ሊኖር አይችልም፡፡

የአንድ ሀገር እውነተኛ ጥንካሬዋ፣ የአንድ ሀገር መንግስት እውነተኛ ጥንካሬው የሚለካው የአንድን ሀገር ህዝብ አእምሮእና ልብ መቆጣጠር ሲችል ነው፡፡

የወደፊቷ ኢትዮጵያ አሁን በሚደረጉ ድርጊቶች፣ በማይደረጉ ድርጊቶች ወይም ደግሞ በዘ–ህወሀት ምላሾች ወይምበእርሱ ግብረ አበሮች ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡

የወደፊቷ ኢትዮጵያ መሰረት የምታደርገው የወጣት ህዝቧን አእምሮ እና ልብ በመቆጣጠር እና ለሀገራቸው ባላቸውፍቅር፣ በህዝቡ፣ ህዝቡ እራሱን ለማሻሻል በሚያደርገው ጥረት፣ ወንድሞቹን እና እህቶቹን ከገቡበት አዘቅት ውስጥመንጥቆ የማውጣት ፍላጎት ሲኖረው እና ከድህነት ብቻ ሳይሆን ከሞራል ስብዕና ኪሳራ ጭምር ነጻ ማድረግ ሲችልነው፡፡

ዘ–ህወሀት ይህንን ያልኩትን ሁሉ ማድረግ ከቻለ የሚፈራውን ቀውስ ማስወገድ ይችላል፡፡

እኩልነትን በማረጋገጥ፣ አንድነትን በማራመድ፣ ወንድማማችነትን በማጠናከር፣ የስልጡንነት አካሄዶችን በመተግበር እናጨካኝነትን በማስወገድ፣ አረመኔያዊነትን እና ጭራቃዊነትን በማጥፋት የጥፋት ቀውስን ማስወገድ እችላለሁ፡፡

ዘ–ህወሀት ፍትህን በማስፈን፣ ፍትሀዊነትን በማስተማር፣ እውነተኛው ነገር እንዲሰራ በማደፋፈር፣ በተጠያቂነት ላይአጠንክሮ በመስራት፣ የጭካኔ ድርጊቶችን ከመፈጸም ይልቅ አዲስ የፈጠራ ባህልን በማዳበር እና በመጠቀም፣ ችግሮችንሰላማዊ በሆነ መንገድበመፍታት፣ ፍቅርን በማሳየት፣ ልግስናን በመውደድ፣ በሰለጠነ መልኩ በመንቀሳቀስ፣ ቅዱስ የሆኑሀሳቦችን በመከተል፣ በታማኝነት እና ክብርን በጠበቀ መልኩ በመራመድ የህዝቦችን አእምሮ እና ልብ መቆጣጠርይችላል፡፡

ሆኖም ግን ዘ–ህወሀት የኢትዮጵያን ወጣቶች አእምሮ እና ልብ ለመያዝ እና ለማሸነፍ ያለችው ጊዜ በጣም ትንሽ ናት፡፡(70 በመቶ የሚሸፍነውን በኢትዮጵያ ወጣቶች ላይ ትኩረት በማድረጌ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡)

ምናልባትም ዘ–ህወሀት ከተለያዩ ዘመናት በርካታ የሆኑ ሰብአዊ መከራዎችን ከተቀበለው እና የእነርሱ ቅርብ ጓደኛእንዲህ በማለት የጠቀሰው መልዕክት የበለጠ ግልጽ ሊያደርግላቸው ይችላል፡ “አስቀድሞ ወጣቱን የያዘ የወደፊቱንመጻኢ ዕድል ይቆጣጠራል፡፡“

ይቀጥላል…

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ህዳር 28 ቀን 2008 ዓ.ም

The post የኢትዮጵያውያን የጸደይ አብዮት በበጋው ወቅት መጀመሩ ነውን? | ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live