Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Health: በሰውነታችን የኮሌስትሮል መብዛት እንዴት እናውቃለን?

$
0
0

ኮሌስትሮል በሰውነታችን ውስጥ ስላለው ጥቅምና ጉዳት ከመነጋገራችን አስቀድሞ ስለምንነቱ የተወሰነ ነገር እናንሳ፡፡

ኮሌስትሮል ቅባታማ ተፈጥሮ ያለው፣ ከሰው ልጆች በተጨማሪ በሁሉም እንስሳት ሰውነት ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ነው፡፡ ይህ ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ላሉት የተለያዩ ሴሎችና ሆርሞኖች የተፈጥሮ አካላቸው ነው፡፡ ኮሌስትሮል በተፈጥሮ ቅባታማ ስለሆነ ከደም ጋር በቀላሉ ተዋህዶ መዘዋወር አይችልም፡፡ ስለዚህ በደማችን ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ኮሌስትሮል ተሸካሚ የሚባሉትን ይጠቀማል፡፡ በእነዚህ ተሸካሚዎች አማካኝነት የሚዘዋወረው፣ ኮሌስትሮል መጠን ጤናማ ከሚባለው በላይ ሲሆን በተለያዩ የደም ስሮች ውስጥ በመጠራቀም፣ በልባችንና በደም ቧንቧዎቻችን ብሎም በአጠቃላይ ጤንነታችን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳርፋል፡፡

cholestorl

በሰውነታችን የኮሌስትሮል ተሸካሚ በመሆን በብዛት የሚታወቁት Low Density Lipoprotein (LDL) እና High Density Lipoprotein (HDL) ናቸው፡፡ LDL የሚባሉት ኮሌስትሮልን ይዘው ደም ውስጥ የሚዘዋወሩ ሲሆኑ፣ HDL ደግሞ ኮሌስትሮልን ወደ ጉበታችን የሚመልሰው ነው፡፡ እናም በሰውነታችን ውስጥ ያለው ኮሌስትሮል ሁሉም ጎጂ ነው ብሎ ማሰቡ የተሳሳተ ነው፡፡ ምክንያቱም ከላይ ካየናቸው ውስጥ HDL የተባለው የኮሌስትሮል አይነት፣ ሰውነታችንን ለልብና ደም ቧንቧዎች በሽታ ተጋላጭነት የሚቀንስ/ተከላካይ ኮሌስትሮል ሲሆን፣ LDL ግን በተቃራኒው ለተለያዩ በሽታዎች አጋላጭ ወይም አምጪ የኮሌስትሮል አይነት ነው፡፡ ስለዚህ LDL ጎጂ ኮሌስትሮል በመባል ይታወቃል፡፡

ኮሌስትሮል ለሰውነታችን ጥቅም አለው?

ከላይ ለማብራራት እንደተሞከረው ኮሌስትሮል ሙሉ ለሙሉ ለሰውነታችን አላስፈላጊ ሳይሆን በጤናማው መጠን አስፈላጊ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለተለያዩ ሆርሞኖች፣ ቫይታሚን ዲ እንዲሁም ምግብ እንዲፈጭ የሚያግዙ ኢንዛይሞችን ለመስራት እንደሚያገለግል መረዳት ነው፡፡

ነገር ግን መጠኑ ከፍ ባለ በደም ቧንቧዎቻችን በመከማቸትና፣ አቴሮስከለሮስስ እንዲፈጠር በማድረግ የደም ዝውውርን ያዛባል፡፡ በዚህም ምክንያት እንደ ልብ፣ አንጎልና ኩላሊት የመሳሰሉት የሰውነት ክፍሎቻችን የሚያስፈልጋቸውን የደም መጠን ካለማግኘታቸው የተነሳ ጤናማ አሰራራቸው ይስተጓጎላል፤  በዚህም ምክንያት፡-

– በልባችን ላይ የኮረናሪ ደም ቧንቧ በሽታ

– ስትሮክ (የግማሽ ሰውነት መድከም ወይም ፓራላይዝድ መሆን)

– የኩላሊት መድከም (Renal Failure) እና የመሳሰሉትን ሊያመጣ ይችላል፡፡ በተጨማሪም የኮሌስትሮል መጠን መጨመር ለሽንት ቧንቧ ዕጢ ካንሰር (prostactic cancer) የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራል፡፡

ሰውነታችን የማይፈለግ የኮሌስትሮል መጠን የሚጨምረው እንዴት ነው?

1. የምንበላው ምግብ፡- አላስፈላጊ ኮሌስትሮሎችን LDL ሊያበዙ የሚችሉ ምግቦች የሚባሉት እና ኮሌስትሮል ናቸው፡፡ እነዚህ ሳቹሬትድ ፋትና ኮሌስትሮል በብዛት የሚገኙት ደግሞ የእንስሳት ተዋፅኦ በሆኑ እንደ ስጋ፣ ዕንቁላል፣ ወተትና አይብ በመሳሰሉ ምግቦች ውስጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡

2. የሰውነት ክብደት፡- ከመጠን ያለፈ ክብደት በሰውነታችን ውስጥ አደገኛ የሆኑ ኮሌስትሮሎችን ያበዛል፡፡ የክብደት ጤናማነት የሚለካው በቦዲ ማስ ኢንዴክስ ሲሆን ክብደታችንን ለቁመታችን ስኩዬር በማካፈል ማወቅ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ፡- 1 ሜትር ከ70 ሴ.ሜ እና 70 ኪ.ግራም የሆነ ሰው ቦዲ ማስ ኢንዴክሱ

=70Kg (1.7m)2= 24.2 ይሆናል

ጤናማ የሚባለው ከ18.5 እስከ 24.9 ያለው ሲሆን፣ በ24.9 በላይ ጤናማ ያልሆነ ክብደት ነው፡፡ እንደተለያዩ ጥናቶችና የዓለም የጤና ድርጅት አገላለፅ፣ የአንድን ሰው ክብደትና አላስፈላጊ ቅባቶች ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ችግር አመላካች ቦርጭ ነው፡፡ እናም የአንድን ሰው የሆድ ውፍረት ጤናማነት ለመለካት፣ የወገብን ስፋት ብቻውን ወይም የወገብ ስፋትን ለዳሌ ስፋት ብቻውን ወይም የወገብ ስፋትን ለዳሌ ስፋት አካፍለን መለካት እንችላለን፡፡ ይህ ልኬት በተለይ በሴቶች ላይ ከላይ ካስቀመጥነው BMI ይልቅ በተሻለ ሁኔታ ችግር አምጪ የውፍረት መጠን ሊጠቁም ይችላል ተብሏል፡፡ የሆ ውፍረት ልኬት በፆታና በዕድሜ እንዲሁም በዘር (ማለትም በተለያዩ አህጉራት ባሉት ህዝቦች) ሊለያይ ሲችል እኛ መጠቀም የምንችለው፡-

– የወገብ ስፋት ጤናማ አይደለም የምንለው ለወንድ ከ102 ሴ.ሜ በላይ ከሆነና ለሴት ከ88 ሴ.ሜ በላይ ከሆነ

– የወገብ ስፋትን ለዳሌ ስፋት ስናካፍል ጤናማ አይደለም የምንለው ደግሞ ለወንድ ከ0.9 በላይ ከሆነና ለሴት ከ0.85 በላይ ከሆነ ነው፡፡

3. የሰውነት እንቅስቃሴ መጠን፡- መደበኛ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ክብደታችንና ብሎም ጎጂ ኮሌስትሮሎችን ከሰውነታችን ውስጥ ይቀንሳል፡፡

4. ከቤተሰብና በዘር የሚወረስ፡- ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን ከቤተሰብና በዘር ሊተላለፍ እንደሚችል ነው፡፡ በዚህ መንገድ የኮሌስትሮል መብዛት ያጋጠመው ሰው፣ ከተወለደ በኋላ ችግሩ ከተከሰተበት ሰው ይልቅ ቀደም ባለ /በለጋ/ ዕድሜ ለልብ ችግር ሊጋለጥ ይችላል፡፡

5. ዕድሜና ፆታ፡- ዕድሜ በጨመረ መጠን፣ በሰውነታችን ውስጥ የጎጂ ኮሌስትሮል መጠንም እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ታዲያ ሴቶች በወጣትነታቸው ከወንዶች ያነሰ ጎጂ ኮሌስትሮል ቢኖራቸውም፣ ከ55 ዕድሜያቸው በኋላ የጎጂ ኮሌስትሮል መጠናቸው እንደሚበዛ ነው፡፡

በሰውነታችን የኮሌስትሮል መብዛት እንዴት እናውቃለን?

በሰውነታችን ውስጥ የኮሌስትሮል መብዛት በራሱ ምንም ምልክት አያሳይም፡፡ ስለዚህ ማንም ዕድሜው ከ20 በላይ የሆነ ሰው፣ ቢያንስ በዓመት አንዴ የደም ውስጥ ኮሌስትሮልን መጠኑን መለካት አለበት፡፡

እንደ ሲዲሲ በአሜሪካ ዕድሜያቸው፣ ከ20 ዓመት በላይ ከሆኑ ሰዎች ሃያ በመቶ /20 በመቶ/ የሚሆኑት ከፍተኛ የደም ውስጥ ኮሌስትሮል መጠን አላቸው፡፡ ከእነዚህም ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ከ65 እስከ 74 ዕድሜ ያላቸው ሴቶች ናቸው፡፡

የተለያዩ የኮሌስትሮል ዓይነቶች በሰውነታችን ውስጥ ያላቸውን ጤናማ መጠን ስናይ

– አጠቃላይ ኮሌስትሮል ከ200 mg/dl (decilitre) ያነሰ፤

– LDL (ጎጂ) የሚባለው ኮሌስትሮል ከ100 mg/dle ያነሰ

– HDL (ጠቃሚ) ኮሌስትሮል ከ40 mg/dle የበለጠ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡

ኮሌስትሮል ብዛት ያለበት ሰው ምን ማድረግ አለበት

– ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት መከተል- የሰውነት ክብደት መቀነስ

– መደበኛ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ

– በሐኪም ትዕዛዝ ኮሌስትሮልን የሚቀንሱ መድሃኒቶችን መጠቀም ቀዳሚዎቹ መፍትሄዎች ናቸው፡፡

The post Health: በሰውነታችን የኮሌስትሮል መብዛት እንዴት እናውቃለን? appeared first on Zehabesha Amharic.


በደላስና ፎርትወርዝ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዳላስና ፎርትወርዝ የኢትዮጵያውያን ፎረም የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ!

$
0
0

ኢትዮጵያ በአፓርታይዱ የወያኔ/ኢህአዴግ መሰሪ ስርዓት የተሳሳተ ፖሊሲና የመልካም አስተዳደር ችግር ምክንያት ምን ላይ እንዳለች ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ግልፅ ነው። ይህን የተገነዘበው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያዩ ጊዜያት ለስርዓቱ ያለው ጥላቻ ቢያሳይም የወያኔ/ኢህአዴግ ቱባ ባለስልጣናትና ካድሬዎች ጭቆናቸውን ገፍተውበታል። ዛሬ ኢትዮጵያ ሃገራችንና ህዝባችን በስርዓቱ ዋልጌነት የተነሳ ትልቅ የታሪክ ዝቅጠት ውስጥ ይገኛሉ።

IMG_022511-1 (1)

ዛሬም፦

  1. 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን እሚበላ እሚቀመስ አጥተው የእርዳታ እህል እየጠበቁ ይገኛሉ። በተከሰተው ድርቅና ረሃብ ምክንያት የሰው ህይወት እየተቀጠፈ ነው።
  2. በአዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የተነሳ የመሬቱ ይዞታ የሆኑ ገበሬዎች የሚደርስባቸውን ግፍ በመቃወም አደባባይ የወጡ ንፁሃን ዜጎች በአጋዚ ጦር እየተረሸኑ ነው። በተለይ በኦሮሚያ ክልል ድርጊቱን የተቃወሙ ከኤለመንታሪ እስከ ከፍተኛ ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎች ከስርዓቱ የሚያገኙት ምላሽ ሰላማዊ ከመሆን ይልቅ ድብደባ፣ እስራት፣ ግድያ ሆኗል።
  3. ጎንደር በሚገኘው የስርዓቱ እስር ቤት እሳት በመነሳቱ ምክንያት ከእሳቱ ሲሸሹ በነበሩ እስረኞች ላይ ፌደራል ፖሊስ በወሰደው ህገ-ወጥ እርምጃ የአያሌ እስረኞች ነፍስ ጠፍቷል።
  4. ኢትዮጵያውያን ሁሉ በገዛ ሃገራችን የስርዓቱ እስረኞች ሆነናል። ያለ ምንም ጥፋታቸው የውሸት ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ቤት እየማቀቁ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማርያን፣ ደራሲያን፣ የሃይማኖት መሪዎችና አባቶች…. ዛሬም ፍትህ ይሻሉ። ለፍትህ ይጮሃሉ። ህዝብ እንዲጮህላቸው ይማፀናሉ።
  5. ከተለያዩ የሃገራችን ክልሎች አማራ ናችሁ በሚል የተፈናቀሉት ወገኖቻችን የምንረሳው አይደለም።
  6. በኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ፣ ቤንሻንጉል፣ አማራና ሌሎችም የሃገራችን ክፍሎች ላይ በስርዓቱ እየተፈፀመ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻና ከዚህ በፊት የተፈፀመው በመገንዘብ ህዝባችን ከዚህ ሰው በላ ከሆነ አውሬ ስርዓት ልንታደገው ይገባል።
  7. ከዚህ በፊት በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተር በጎንደር በኩል ለሱዳን የተሰጠውን መሬት የማካለል ስራ በዚህ ወር ለመቀጠል ቀጠሮ ተቆርጦአል።

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትንና ተዘርዝሮ የማያልቅ በደል በህዝባችንና በሃገራችን እያደረሱ ተሰደን የምንኖርበት ሃገር ድረስ በመምጣት የውሸት ዲስኩራቸውን ለመለፈፍ ይፈልጋሉ። ይህ ደግሞ እንዳይሳካላቸው ማድረግ በዲያስፖራ ያለው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሃላፊነትና ግዴታ ነው። ይህ ደግሞ ለረጅም ጊዜ በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የወያኔ/ኢህአዴግ ቁንጮ ባለስልጣናትን በማሳፈርና በማሳቀቅ እንዲሁም ያቀዱትን ስብሰባ በመበተን ድምፁ ለተነፈገው ህዝባችን ልሳን በመሆን ወገንተኝነቱን አስመስክሮአል።

አሁን ደግሞ ተራው የዳላስ ነው። በዳላስ በሚገኙት የወያኔ/ኢህአዴግ ካድሬዎች(እንደነሱ የዳላስ ህዳሴ ምክር ቤት) አማካኝነት ለSaturday December 5th 2015 ህዝባዊ ስብሰባ በ Intercontinental Dallas, 15201 Dallas Parkway Addison, Tx, 75001 @ 3 PM. ህዝባዊ ስብሰባ ተጠርቷል። ስለዚህ በእለቱ ከላይ የተጠቀሰው ስፍራ በመገኘት በዳስላስና አካባቢው የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድምፁ ለታፈነው ህዝባችን ድምፃችሁ በአንድ ላይ እንድታሰሙ በዳላስና ፎርትወርዝ የኢትዮጵያውያን ፎረም ጥሪውን ያስተላልፋል።

በቀጥሮው ስዓትና ቦታ በመገኘት ለህዝባችንና ለሃገራችን ያለን ወግንተኝነትና ቁርጠኝነት እናሳይ!

ድለ ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

The post በደላስና ፎርትወርዝ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዳላስና ፎርትወርዝ የኢትዮጵያውያን ፎረም የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ! appeared first on Zehabesha Amharic.

የብአዴንን ህዝባዊ ወገንተኝነት ያያችሁ? – (ከጠረፈኛው የፍትህ ርሃብተኛ፤ ቂልንጦ ማጎሪያ ቤት)

$
0
0

ANDM 3

ህዝባዊ ነኝ ብሎ የሚያወራ ወይም የሚመኝ ሁሉ ህዝባዊ ሊሆን አይችልም፡፡ በተግባር መሬት ላይ ላለው ህዝብ ጠብ የሚል ህዝባዊነትን የሚሸት ተግባራትን ካልፈፀመ፡፡ በእኔ እይታ የብአዴንን ህዝባዊነትና አድርባይነቱን፣ አፋዊና ተግባራዊነቱን መዝኜ ስመለከተው ህዝባዊነቱና ተግባራዊነቱ ቀልሎ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም ብአዴን አድርባይ አፋዊ እና ጥገኛ ፓርቲ እንጂ የራሱን ማንነት ጠብቆ ህዝባዊነቱን ያስቀጠለ ድርጅት አይደለም፡፡ በብአዴን እየተሠራ ያለው ሆድ አደርነት፣ አድርባይነት፣ ግላዊነት፣ የግለሰብ ኪስ አድላቢነትና ማን አለብኝነትን እንጂ በማንኛውም መልኩ ካመጣቸው ለውጦች ይልቅ ያጠፋቸው ታሪካዊ ስህተቶች እና ውድቀቶች ለውጥ የሚለውን ቃል አፈርድሜ አብልተውታል፡፡

 

ANDM 2
ህዝባዊነት ሲባል ለህዝብ ሲሉ እንደ ሻማ ቀልጠው ብርሃን መስጠትን፣ ለህዝብ ሲሉ የግል ጥቅም ማጣትን /መተውን/፣ ለህዝብ ተገቢውን መስዋዕትነት መክፈልን፣ ኃላፊነትን በአግባቡ መውጣትን፣ የህዝብ ሀብትና ንብትን በአግባቡ መጠበቅና መንከባከብን፣ ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ መስጠትን አካባቢውን ወደ ተሻለ የዕድገት ጎዳና መለወጥን፣ በኢኮኖሚያዊ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተራማጅ አስተሳሰቦችን ማምጣትን ይጠይቃል፡፡ በሀሳብና በህግ የበላይነት ማመንን፣ ስለ እውነትና ታሪክ ወግና ባህል መከበር ዘብ መቆምን፣ ድህነትን ድንቁርናና ጦርነትን በማስወገድ የሠላምና የፀጥታ የሠብአዊነት የዲሞክራሲያዊ መብት፣ የእኩልነት የፍትህ፣ የመልካም አስተዳደርና የፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በማድረግ፤ ከህዝብ ፊት ሆኖ መሠናክሎችን በአሳታፊነት፣ በመቻቻልና በውይይት በመፍታት ዋጋ መክፈልን ይጠይቃል፡፡ ህዝባዊነት!
ህዝባዊነት አስፈላጊ ብቻ መሆን አይችልም! መፈለግ አንዱ ቅድመ ሁኔታ ቢሆንም ዋነኛው ነገር በተግባር ማሳየት ነው፡፡ ስለዚህ በቅድሚያ ራስን ማሸነፍ ይጠይቃል፤ ከራስ ጋር መታረቅን ይጠይቃል፡፡ እንዲሁም መቅደም ያለበትን ለይቶ ማስቀደምንና መከተል ያለበትን ማስከተልን ይጠይቃል፡፡
ህዝባዊነት ርዕስ አድርጌ የወሰድኩበት ዋነኛ ምክንያት ኢህዴን – ብአዴን ከሠሞኑ 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በከፍተኛ ድግስ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የተመረጡ ቦታዎችና እስከ ጎረቤት ሀገር ጅቡቲም ድረስ በመሄድ “እወቁልኝ፣ የመናገር መብቴ በ35 ዓመት በወያኔ ተፈቀደልኝ፣ ብሉ ጠጡልኝ፣ ድሌ ዛሬ ነው፣ ሠርጌ ዛሬ ነው ይህ የመጨረሻዬ ነው” በሚመስል መልኩ እያከበረ መሆኑ ነው፡፡ ዋናው መፈክሩም ‹‹የብአዴን ህዝባዊነት›› ላይ ያተኮረ በመሆኑ ጭምር ነው ርዕሴ ያደረኩት፡፡ የዘንድሮው በዓል ብአዴን ‹‹ለሠርጌ ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ›› በሚል ከወያኔ ነፃ የወጣ ይመስል፤ ለዚህ ለማይደገመው ሠርጌ ያልሆነ ገንዘብ ለምን ሊሆነኝ ነው በማለት በሩጫ፣ በኳስ ጨዋታ፣ በእስክስታ፣ በስነ-ፁሁፍ በ‹‹መስክ ጉብኝነት››፣ በ‹‹ፓናል ውይይት››፣ በጥያቄና መልስ፣ በውዝዋዜው፣ በከፍተኛ ወጭ ሽልማትና የመጠጥ የምግብ ዝግጅት ‹‹ታጥቄ እንደታገልኩት ታጥቄ እጠጣለሁ እጨፍራለሁ፣ በውስኪና በሻምፓኝ እረጫለሁ›› ሲል ተመልክተናል፡፡

 

ANDM
ታጥቄ እስክስታ እመታለሁ፤ ሠልፍ እወጣለሁ፣ ሁሉንም የቴሌቭዥን ጣቢያዎች እቆጣጠራለሁ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ቲሸርቶችን፣ ፓንፕሌቶችን፣ ጋዜጦችን፣ መፅሄቶችንና መፅሀፍቶችን አሳትሜ እየቸበቸብኩ ነው ብሎናል፡፡ ይሄን ነው እንግዲህ ለብአዴን ህዝባዊነት ማለት፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ባሉበት፣ ህፃናት እየሞቱ በሚገኙበት፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች በስደት ላይ ኩላሊታቸውን እየተነጠቁ የባህር አሳዎችና አዞዎች እጣፈንታ እየሆኑ፣ የመኪና አደጋ ሠለባዎች፣ የበርሃ ሲሳዮችና አንገታቸውን እንደ በግ እየታረዱ ባለት አሳዛኝና አሠቃቂ ጊዜ ላይ ይህ ሁሉ ድግስ ህዝባዊነትን ያሳይል? በቁስለኛው ህዝብ ላይ ተጨማሪ ቁስል ማፍራት ሀገር ቀምቶ በማሣደድ፣ ማሣረድ በሀሳብ ልዩነት የተነሣ በየ እስርቤቱ አሸባሪ የሚል ታርጋ በመለጠፍ እያጎሩ ማሰቃየት፣ ማኮላሸት በአካል በሞራሉ በስነ-ልቦናው ጫና መፍጠር ህዝባዊነት ነው ፀረ ህዝብነት?
ከሥራ እያፈናቀሉ፣ የሀሰት/የፈጠራ ወንጀልን እየፈጠሩ፣ በሀሰት አስገድደው እያስመሰከሩ፣ ወጣቱን በአካልና በአዕምኖ እየቀጠቀጡ ማደንዘዝ፣ ያለፍትህ ማጎር ነው የብአዴን ህዝባዊነት የሚባው የተቃርኖ ዓለም፡፡ በእርግጥ የቀጥተኛ አለቃው ወያኔ የተቃርኖ ዓለምም ተመሳሳይ ነው፡፡ በጣም የሚገርመው የአማራን ህዝብና ኦርቶዶክስን ፈርጀው ‹‹አከርካሪውን እንሰብራለን›› ብለው በጫካ ዕቅድ የተነሱት እነ ጄነራል ሳሞራ የኑስ እና አባይ ፀሃዬ ስለ ህዝብ አስተያየት መጠመዳቸው ነው፡፡ ምን የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ?
ይህ ብአዴን ነው በሀገራችን ከ15 ሚሊዮን ህዝብ በላይ በድርቅና በረሃብ ላይ ባለበት ሁኔታ የ35 ዓመት የአሮጊት (ጋለሞታ) ድሮ ውስኪና ሻምፓኝ የሚራጨው፡፡ ሀገሪቱ አላዋቂ ሰዎች ሞልተውባታል፡፡ ብአዴንም ሆነ መሰል ድርጅቶች በአጉል ድንቁርና፣ ትዕቢትና እብሪት ተወጥረው በአስተሳሰብ ድህነት /ደዌ/ ተይዘው ወደፊት መንቀሳቀስ አቅቷቸው፣ መቆም ተስኗቸው ወደ ኋላ በማፈግፈግ ላይ ናቸው፡፡
ደም የገበሩትን አባቶቻችንና እናቶቻችንን ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ ግን የምንፈልገው አላማቸውን አስቀጥሎ የኢትዮጵያንና ክልሉን ህዝብ ከድህነት አረንቋ የሚያላቅቅ መሬት ላራሹ ጥያቄን የሚመልስ፣ ፍትህና እኩልነት የሚያሰፍን ነፃነትና ክብርን ሀገርን የማይቀማ፣ መንደርተኛ ያልሆነ፣ ኢትዮጵዊነት ያሠፈረ ድርጅትና አመራር ነበር፡፡ ግን አለመታደል ሆኖ በተቃራኒው ሆነ! ስለመበታተን የሚሰብክ፣ እወክለዋለሁ የሚለውን ህዝብ የሚያስጨፈጭፍ ሆነ! ብአዴን የህዝብ ወኪል ነኝ እያለ ከጥቃት ህዝብን ከመታደግ ይልቅ አላዳንኩሽምን ይዘምራል! የስቃይ ድምፅ እየቀረፀ ያዳምጣል፡፡
በአማራ ክልል ብዙ አሣፋሪና አሳዛኝ ድርጊቶችን እየተሰሩ ነው፡፡ ምሳሌዎችን እንመልከት፡-
በክልሉ ውስጥ ሰዎች በአልሞ ተኳሽ ወታደሮች ተገድለው በመኪና ሲጉተቱ፣ ፀጉራቸው ከእንጨት ጋር ታስሮ በአስፓልት ላይ በህዝብ ፊት ሲጎተቱ አይተናል! አይቀበሩም (በቤተክርስቲያን ስርዓት) ተብሏል፤ ቤተሰብ እንዳያለቅስ የተከለከለ መሆኑን አይተናል (ምሳሌ በታች አርማጭዎ ሳንጃ ከተማ – እነ ሽንኩ ካፌና ዳኛው ይህ አረመኔያዊ ድርጊት ተፈፅሟል) ታዲያ ይህ ህዝባዊነት ወይስ ፀረ-ሕዝባዊነት?)
ሰዎችን ከእስር ቤት አስወጥተው ሲገድሉ አይተናል:: በፍ/ቤት ተከሰው ከ4 በላይ ሰዎች የምስክርነት ቃላቸውን ቢሰጡም ገዳዩ በሙስና በነፃ ተለቋል፡፡ (ታች አርማጭ ወረዳ ወጣት ጎሹ እያዩ ሲገደል፡፡) በሀሳብ ልዩነት መጠፋፋት የለብንም ይላል የብአዴን መፈክር፡፡ ግን ብአዴን በመቃወማችንና ባለመደገፋቸው የተነሳ የመኖር መብታቸው ተገፎ (ጭቆና ግፍና በደል) በዝቶባቸው ኑሯቸውን፣ የሞቀ ቤታቸውን፣ ሚስታቸውንና ልጃቸውን ትተው ኑሯቸውን ጫካ ያደረጉ ወገኖች እንዳሉ ታዝበናል! የሽፍታ ቤተሰብ /ወገን/ በመሆናቸው ብቻ ‹‹ገደላችህ አስክሬን አምጡ!›› እየተባሉ ልጆቻቸው ለመግደል ፈቃደኛ ባመሆናቸው የተነሳ መሬታቸውን የተነጠቁ፣ እርሻ ቦታቸውን ወደ ከተማ እንዲገቡ የተገደዱ በኑሮ ውድነትና በእስር እየተሰቃዩ ያሉ ሰዎችን አየን፡፡
የህግ የበላይነት ተጥሶ የግለሰብ የበላይነት ሰፍኖ በቂም በቀልና በስነ-ልቦና ሰዎች ተሰቃይተዋል፡፡ የዘር ማጥፋት ድርጊት የተፈፀመባቸውን የወልቃት አርማጭሆ ነዋሪዎችን አይተናል፡፡ በብሎክ የህዝብ መሬትን በመሸንሸን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጥቅመኛ ባለሀብቶች ሲሸጡ አይተናል፡፡ የመኖገር፣ የማሰብ፣ ያለመሰቃየት መብት አላችሁ እየተባለ በተቃራኒው ግለሰቦች በጉባኤ በመናገራቸው በጅምላና በጭፍን ፍርጃ ፀረ-ሠላም፣ ፀረ-ዴሞክራሲ፣ አሸባሪ እያሉ በማሰባቸውም እየታሰሩ ነው፡፡ ሀሰት ነግሶ፣ እውነት ተገርስሶ፣ በውሸት ሪፖርት፣ በፈጠራ ክስ ኑሮአቸውን ያደረጉ ወገኖችን አይተናል፡፡
ብአዴን ጥገኛ ሲሆን ወያኔ በበላይነት አገሪቱንም ድርጅቶች ሲያስከብር ኖሯል፡፡ ዛሬ ብአዴን በ35 ኣመቷ ዳሩኝ ማለቷ የሀገራችን ባህል ወይም ስርኣትን የጣሰ ነው፡፡ ‹‹የጋለሞታ/ የአሮጌቶች›› ጋብቻ ነው! ስካሁን ድረስ ወያኔ ባሪያ አድርጓት ከቆየ በኋላ ትንፍሽ ብላ የማታውቀ ለመጨፈር አስፈቅዳለች፤ ጎጠኝነት አስተምሯት ቅማንት አማራና አገው ብቻ ሳይሆን በጎጥ እየተከፋፈለ የቀን ሠራኛው ሲገደል አይተናል፡፡ የክልሉ ዜጎች ሲፈናቀሉ ምላሽ መስጠት ሲሳናት አይተናል፡፡ የኮንትሮባንድ ንግድ በመኪና እየነገደች ቲሸርትና ኦሞ የያዘን ድሃ ትወርሳለች፡፡ ታዲያ የብአዴን ዲሞክራሲያዊነትና ህዝባዊነት የት ላይ ነው?

The post የብአዴንን ህዝባዊ ወገንተኝነት ያያችሁ? – (ከጠረፈኛው የፍትህ ርሃብተኛ፤ ቂልንጦ ማጎሪያ ቤት) appeared first on Zehabesha Amharic.

‹‹ጉራጌ ሲሰርቅና ሲያጭበረብር እንጂ ሲታገል አያምርበትም እየተባልኩ እደበደብ ነበር›› 9ኛ ተከሳሽ

$
0
0

እነ ዘላለም ወርቃገኘሁ ተጨማሪ መከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰሙ
‹‹ጉራጌ ሲሰርቅና ሲያጭበረብር እንጂ ሲታገል አያምርበትም እየተባልኩ እደበደብ ነበር›› 9ኛ ተከሳሽ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በፌደራል አቃቤ ህግ የሽብርተኝነት ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው እየታየ የሚገኙት እነ ዘላለም ወርቃገኘሁ ተጨማሪ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ዛሬ ህዳር 24/2008 ዓ.ም አስደምጠዋል፡፡

zelalem
በዚህ መዝገብ 9ኛ ተከሳሽ የሆነው አቶ ባህሩ ደጉ 3 መከላከያ ምስክሮቹን ያስደመጠ ሲሆን፣ የተከሳሽነት ቃሉንም ለፍርድ ቤቱ ሰጥቷል፡፡ አቶ ባህሩ በተከሳሽነት ቃሉ ላይ እንደጠቀሰው ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞበታል፤ ቃሉንም በግዳጅ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡
አቶ ባህሩ ደጉ ለፍርድ ቤቱ እነዳስረዳው ማዕከላዊ እያለ ራቁቱን ተደብድቧል፤ ከድብደባ ብዛት ሽንቱን መቆጣጠር ተስኖት እንደነበር በማውሳት የገዛ ሽንቱን እንዲጠጣ ተገድዷል፡፡ በተጨማሪም አቶ ባህሩ ‹‹የግንቦት ሰባት መሪ ብርሃኑ ነጋ ምንህ ነው? ከአንዳርጋቸው ጽጌስ ምን አለህ? ብርሃኑ ዘመድህ ነው?›› የሚሉ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እየቀረቡለት በማያውቀው ነገር ሲሰቃይ እንደነበር ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
አቶ ባህሩ ደጉ በማንነቱ ምክንያትም ስቃይ እንዳሳለፈ በማውሳት፣ ‹‹ከጉራጌ መወለድ ወንጀል ነው እንዴ?›› ሲል በችሎት ፊት ጠይቋል፡፡ ‹‹ጉራጌ ሲሰርቅና ሲያጭበረብር እንጂ ሲታገል አያምርበትም እየተባልኩ እደበደብ ነበር›› ያለው አቶ ባህሩ፣ ‹‹የደም ስርህን በጥሰን እንገልሃለን፤ ፖሊሱ፣ አቃቤ ህጉ፣ ፍርድ ቤቱ፣ ደህንነቱ…ሁሉም የኛ ነው፤ አንተን 20 አመት እናስርሃለን›› እየተባለ ስቃይ እንደተፈጸመበት በማስረዳት በምርመራ ወቀት የሰጠው ቃል ተገድዶ የሰጠው መሆኑን ፍርድ ቤቱ እንዲረዳለት አሳስቧል፡፡
9ኛ ተከሳሽ ባህሩ ደጉ የተከሳሽነት ቃሉን ከሰጠ በኋላ ሦስት መከላከያ ምስክሮችን አሰምቷል፡፡ ከምስክሮቹ መካከል በዚሁ መዝገብ 1ኛ ተከሳሽ ዛላለም ወርቃገኘሁ እና ሌላኛው ምስክር ጦማሪ ዘላለም ክብረት ተከሳሹ ‹‹ለሽብር ወንጀል ስልጠና ሊወስድ ነበር›› በሚል ስለቀረበበት ክስ የስልጠናውን አይነትና የአሰልጣኞችን ማንነት በማብራራት ስልጠናው ለሽብርተኝነት ድርጊት ሳይሆን በታወቁ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የሚሰጥ ግልጽ ስልጠና እንደነበር አስረድተዋል፡፡ 3ኛ ምስክር በበኩላቸው ተከሳሹ ማዕከላዊ ወንጀል ምረመራ በነበረበት ወቅት አብረው ታስረው እንደነበር በመግለጽ ይፈጸምበት የነበረውን አሰቃቂ ምርመራ በተመለከተ የሚያወቁትን መስክረዋል፡፡ እኒህ ምስክር ተከሳሹ ሌሊት ለምርመራ በሚል እየተጠራ ድብደባ ይፈጸምበት እንደነበር አስረድተዋል፡፡
በዚሁ መዝገብ 1ኛ ተከሳሽ በምስክርነት የጠሯቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ እና ዳንኤል ሺበሽ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ ትዕዛዝ ከፍርድ ቤቱ ቢሰጥም እስካሁን አለመቅረባቸው ታውቋል፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቱ ዛሬም ሌላ ትዕዛዝ በመስጠት ማረሚያ ቤቱ እስካሁን ያላቀረበበትን ምክንያት ገልጾ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርባቸው ታዝዟል፡፡

The post ‹‹ጉራጌ ሲሰርቅና ሲያጭበረብር እንጂ ሲታገል አያምርበትም እየተባልኩ እደበደብ ነበር›› 9ኛ ተከሳሽ appeared first on Zehabesha Amharic.

‎በእሳት‬ በጋየው የጎንደሩ ግዙፍ ወህኒ ቤት ውስጥ በህወሓት ጦር የተጨፈጨፉት እስረኞች ማንነት በመታወቅ ላይ ነው

$
0
0

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ህዳር 21 2008 ዓ.ም በጎንደር ከተማ በሚገኘው ግዙፍ ወህኒ ከባድ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን ተከትሎ የህወሓት ሰራዊት በርካታ እስረኞችን በግፍ መጨፍጨፉና ዙሪያውን በእሩምታ ተኩስ አጥሮ ማህሉንም ዳሩንም እሳት በእሳት በማድረግ መሽሎኪያ ቀዳዳ በማሳጣት ብዙዎቹን ማጋየቱ ይታወቃል፡፡

shimeles abuay

በመሆኑም በግፈኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ ሰራዊት ከተጨፈጨፉት እስረኞች መካከል የተወሰኑት ማንነታቸው ተለይቶ በየትውልድ ቀዬዎቻቸው በመቀበር ላይ ናቸው፡፡
አቶ አለቤ ኃይሌ የተባሉትና ከመታሰራቸው በፊት በጥበቃ ስራ ይተዳደሩት የነበሩት ሰው ትናንት በወገራ ወረዳ ጉንትር ቀበሌ አቦ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟ፡፡ በተጨማሪም የዚሁ ወገራ ወረዳ ጉንትር ቀበሌ ነዋሪ የሆነው የ17 ዓመቱ ታዳጊ መላክ ችሎት በወህኒ ቤቱ ውስጥ በጥይት ተደብድቦ ከባድ ጉዳት ደርሶበት በህክምና ላይ ይገኛል፡፡

ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው በቅርቡ በህወሓት ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች ታፍነው ከደልጊ ወደ ጎንደር ከተወሰዱት ከ10 በላይ ሰዎች መካከል እስካሁን አቶ አሰፋ ገዳሙ የተባሉት አዛውንት መገደላቸው ተረጋግጧል፡፡ በአርማጭሆ የሽመለ ጋራ ቀበሌ አስተዳዳሪ የነበረው ነውጥ ብቃለ የተባለው ግለሰብም መገደሉ ጭምር ታውቋል፡፡

አድራሻቸውና የአባታቸው ስም ገና በመጣራት ላይ ከሚገኙት እጅግ በርካታ የተጨፈጨፉ እስረኞች መካከል ደግሞ ቀናው፣ እሸቴ፣ ጤናው፣ ማስረሻ፣ አዱኛ… የተባሉት ይገኙበታል፡፡
ሽመልስ አቡሃይ የተባለው እስረኛ ያልነበረ ሰላማዊ ወጣት ደግሞ ትናንትና በተነሳው ግርግር በግፍ ተገድሎ ዛሬ በጎንደር ደብረ ብርሃን ስላሴ ቤተክርስቲያን ተቀብሯል፡፡

The post ‎በእሳት‬ በጋየው የጎንደሩ ግዙፍ ወህኒ ቤት ውስጥ በህወሓት ጦር የተጨፈጨፉት እስረኞች ማንነት በመታወቅ ላይ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

የአጋዚ ሰራዊት ቡሌ ሃራ ዩኒቨርሲቲን ጥሶ በመግባት በርካታ ተማሪዎችን በድብደባ አቆሰለ

$
0
0

federal police bule hora federal Police

(ዘ-ሐበሻ) አንደኛ ሳምንቱን የያዘውና በድጋሚ የተነሳው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ በተለያዩ ከተሞች የቀጠለ ሲሆን ዛሬ ጠዋት የአጋዚ (ፌደራል ፖሊስ) ሠራዊት አባላት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲን ጥሰው በመግባት በርካታ ተማሪዎችን በድብደባ አቆሰሉ::

የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች እንደሚሉት በቀድሞዋ ሃገረ ማርያም ወረዳ ስር በነበረችው ቡሌ ሃራ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተማሪዎች አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ሲያሰሙ የዋሉ ሲሆን ሄልሜትና ድንጋይ መከላከያ የታጠቁ ፌደራል ፖሊስ ግቢውን ጥሰው በመግባት ክፍተኛ ቅጥቀጣ አድርገውባቸዋል::

በተማሪዎቹ ላይ ፖሊስ እየፈጸመ ያለውን ግድያና ዱላ እንዲያቆም ተቃዋሚዎቹ ሲጠይቁ የዋሉ ቢሆንም ሰሚ አላገኙም:: ለዘ-ሐበሻ እንደደረሰው መረጃ በቡሌ ሃራ ዩኒቨርሲቲ ከተማሪዎቹ በተጨማሪ በአስተማሪዎች ላይም ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሷል::

እስካሁን ድረስ በቡሌ ሃራ ዩኒቨርሲቲ ፌደራል ፖሊስ ባደረሰው ከባድ ጉዳት የሞተ ተማሪ እንዳልተመዘገበ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል::

The post የአጋዚ ሰራዊት ቡሌ ሃራ ዩኒቨርሲቲን ጥሶ በመግባት በርካታ ተማሪዎችን በድብደባ አቆሰለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የብአዴንን ህዝባዊ ወገንተኝነት ያያችህ?(ከጠረፈኛው የፍትህ ርሃብተኛ፤ ቂልንጦ ማጎሪያ ቤት)

$
0
0

ህዝባዊ ነኝ ብሎ የሚያወራ ወይም የሚመኝ ሁሉ ህዝባዊ ሊሆን አይችልም፡፡ በተግባር መሬት ላይ ላለው ህዝብ ጠብ የሚል ህዝባዊነትን የሚሸት ተግባራትን ካልፈፀመ፡፡ በእኔ እይታ የብአዴንን ህዝባዊነትና አድርባይነቱን፣ አፋዊና ተግባራዊነቱን መዝኜ ስመለከተው ህዝባዊነቱና ተግባራዊነቱ ቀልሎ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም ብአዴን አድርባይ አፋዊ እና ጥገኛ ፓርቲ እንጂ የራሱን ማንነት ጠብቆ ህዝባዊነቱን ያስቀጠለ ድርጅት አይደለም፡፡ በብአዴን እየተሠራ ያለው ሆድ አደርነት፣ አድርባይነት፣ ግላዊነት፣ የግለሰብ ኪስ አድላቢነትና ማን አለብኝነትን እንጂ በማንኛውም መልኩ ካመጣቸው ለውጦች ይልቅ ያጠፋቸው ታሪካዊ ስህተቶች እና ውድቀቶች ለውጥ የሚለውን ቃል አፈርድሜ አብልተውታል፡፡

12294786_803134063145587_7039710926777056167_n
ህዝባዊነት ሲባል ለህዝብ ሲሉ እንደ ሻማ ቀልጠው ብርሃን መስጠትን፣ ለህዝብ ሲሉ የግል ጥቅም ማጣትን /መተውን/፣ ለህዝብ ተገቢውን መስዋዕትነት መክፈልን፣ ኃላፊነትን በአግባቡ መውጣትን፣ የህዝብ ሀብትና ንብትን በአግባቡ መጠበቅና መንከባከብን፣ ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ መስጠትን አካባቢውን ወደ ተሻለ የዕድገት ጎዳና መለወጥን፣ በኢኮኖሚያዊ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተራማጅ አስተሳሰቦችን ማምጣትን ይጠይቃል፡፡ በሀሳብና በህግ የበላይነት ማመንን፣ ስለ እውነትና ታሪክ ወግና ባህል መከበር ዘብ መቆምን፣ ድህነትን ድንቁርናና ጦርነትን በማስወገድ የሠላምና የፀጥታ የሠብአዊነት የዲሞክራሲያዊ መብት፣ የእኩልነት የፍትህ፣ የመልካም አስተዳደርና የፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በማድረግ፤ ከህዝብ ፊት ሆኖ መሠናክሎችን በአሳታፊነት፣ በመቻቻልና በውይይት በመፍታት ዋጋ መክፈልን ይጠይቃል፡፡ ህዝባዊነት!
ህዝባዊነት አስፈላጊ ብቻ መሆን አይችልም! መፈለግ አንዱ ቅድመ ሁኔታ ቢሆንም ዋነኛው ነገር በተግባር ማሳየት ነው፡፡ ስለዚህ በቅድሚያ ራስን ማሸነፍ ይጠይቃል፤ ከራስ ጋር መታረቅን ይጠይቃል፡፡ እንዲሁም መቅደም ያለበትን ለይቶ ማስቀደምንና መከተል ያለበትን ማስከተልን ይጠይቃል፡፡
ህዝባዊነት ርዕስ አድርጌ የወሰድኩበት ዋነኛ ምክንያት ኢህዴን – ብአዴን ከሠሞኑ 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በከፍተኛ ድግስ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የተመረጡ ቦታዎችና እስከ ጎረቤት ሀገር ጅቡቲም ድረስ በመሄድ “እወቁልኝ፣ የመናገር መብቴ በ35 ዓመት በወያኔ ተፈቀደልኝ፣ ብሉ ጠጡልኝ፣ ድሌ ዛሬ ነው፣ ሠርጌ ዛሬ ነው ይህ የመጨረሻዬ ነው” በሚመስል መልኩ እያከበረ መሆኑ ነው፡፡ ዋናው መፈክሩም ‹‹የብአዴን ህዝባዊነት›› ላይ ያተኮረ በመሆኑ ጭምር ነው ርዕሴ ያደረኩት፡፡ የዘንድሮው በዓል ብአዴን ‹‹ለሠርጌ ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ›› በሚል ከወያኔ ነፃ የወጣ ይመስል፤ ለዚህ ለማይደገመው ሠርጌ ያልሆነ ገንዘብ ለምን ሊሆነኝ ነው በማለት በሩጫ፣ በኳስ ጨዋታ፣ በእስክስታ፣ በስነ-ፁሁፍ በ‹‹መስክ ጉብኝነት››፣ በ‹‹ፓናል ውይይት››፣ በጥያቄና መልስ፣ በውዝዋዜው፣ በከፍተኛ ወጭ ሽልማትና የመጠጥ የምግብ ዝግጅት ‹‹ታጥቄ እንደታገልኩት ታጥቄ እጠጣለሁ እጨፍራለሁ፣ በውስኪና በሻምፓኝ እረጫለሁ›› ሲል ተመልክተናል፡፡
ታጥቄ እስክስታ እመታለሁ፤ ሠልፍ እወጣለሁ፣ ሁሉንም የቴሌቭዥን ጣቢያዎች እቆጣጠራለሁ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ቲሸርቶችን፣ ፓንፕሌቶችን፣ ጋዜጦችን፣ መፅሄቶችንና መፅሀፍቶችን አሳትሜ እየቸበቸብኩ ነው ብሎናል፡፡ ይሄን ነው እንግዲህ ለብአዴን ህዝባዊነት ማለት፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ባሉበት፣ ህፃናት እየሞቱ በሚገኙበት፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች በስደት ላይ ኩላሊታቸውን እየተነጠቁ የባህር አሳዎችና አዞዎች እጣፈንታ እየሆኑ፣ የመኪና አደጋ ሠለባዎች፣ የበርሃ ሲሳዮችና አንገታቸውን እንደ በግ እየታረዱ ባለት አሳዛኝና አሠቃቂ ጊዜ ላይ ይህ ሁሉ ድግስ ህዝባዊነትን ያሳይል? በቁስለኛው ህዝብ ላይ ተጨማሪ ቁስል ማፍራት ሀገር ቀምቶ በማሣደድ፣ ማሣረድ በሀሳብ ልዩነት የተነሣ በየ እስርቤቱ አሸባሪ የሚል ታርጋ በመለጠፍ እያጎሩ ማሰቃየት፣ ማኮላሸት በአካል በሞራሉ በስነ-ልቦናው ጫና መፍጠር ህዝባዊነት ነው ፀረ ህዝብነት?
ከሥራ እያፈናቀሉ፣ የሀሰት/የፈጠራ ወንጀልን እየፈጠሩ፣ በሀሰት አስገድደው እያስመሰከሩ፣ ወጣቱን በአካልና በአዕምኖ እየቀጠቀጡ ማደንዘዝ፣ ያለፍትህ ማጎር ነው የብአዴን ህዝባዊነት የሚባው የተቃርኖ ዓለም፡፡ በእርግጥ የቀጥተኛ አለቃው ወያኔ የተቃርኖ ዓለምም ተመሳሳይ ነው፡፡ በጣም የሚገርመው የአማራን ህዝብና ኦርቶዶክስን ፈርጀው ‹‹አከርካሪውን እንሰብራለን›› ብለው በጫካ ዕቅድ የተነሱት እነ ጄነራል ሳሞራ የኑስ እና አባይ ፀሃዬ ስለ ህዝብ አስተያየት መጠመዳቸው ነው፡፡ ምን የተፈጠረ አዲስ ነገር አለ?
ይህ ብአዴን ነው በሀገራችን ከ15 ሚሊዮን ህዝብ በላይ በድርቅና በረሃብ ላይ ባለበት ሁኔታ የ35 ዓመት የአሮጊት (ጋለሞታ) ድሮ ውስኪና ሻምፓኝ የሚራጨው፡፡ ሀገሪቱ አላዋቂ ሰዎች ሞልተውባታል፡፡ ብአዴንም ሆነ መሰል ድርጅቶች በአጉል ድንቁርና፣ ትዕቢትና እብሪት ተወጥረው በአስተሳሰብ ድህነት /ደዌ/ ተይዘው ወደፊት መንቀሳቀስ አቅቷቸው፣ መቆም ተስኗቸው ወደ ኋላ በማፈግፈግ ላይ ናቸው፡፡
ደም የገበሩትን አባቶቻችንና እናቶቻችንን ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ ግን የምንፈልገው አላማቸውን አስቀጥሎ የኢትዮጵያንና ክልሉን ህዝብ ከድህነት አረንቋ የሚያላቅቅ መሬት ላራሹ ጥያቄን የሚመልስ፣ ፍትህና እኩልነት የሚያሰፍን ነፃነትና ክብርን ሀገርን የማይቀማ፣ መንደርተኛ ያልሆነ፣ ኢትዮጵዊነት ያሠፈረ ድርጅትና አመራር ነበር፡፡ ግን አለመታደል ሆኖ በተቃራኒው ሆነ! ስለመበታተን የሚሰብክ፣ እወክለዋለሁ የሚለውን ህዝብ የሚያስጨፈጭፍ ሆነ! ብአዴን የህዝብ ወኪል ነኝ እያለ ከጥቃት ህዝብን ከመታደግ ይልቅ አላዳንኩሽምን ይዘምራል! የስቃይ ድምፅ እየቀረፀ ያዳምጣል፡፡
በአማራ ክልል ብዙ አሣፋሪና አሳዛኝ ድርጊቶችን እየተሰሩ ነው፡፡ ምሳሌዎችን እንመልከት፡-
በክልሉ ውስጥ ሰዎች በአልሞ ተኳሽ ወታደሮች ተገድለው በመኪና ሲጉተቱ፣ ፀጉራቸው ከእንጨት ጋር ታስሮ በአስፓልት ላይ በህዝብ ፊት ሲጎተቱ አይተናል! አይቀበሩም (በቤተክርስቲያን ስርዓት) ተብሏል፤ ቤተሰብ እንዳያለቅስ የተከለከለ መሆኑን አይተናል (ምሳሌ በታች አርማጭዎ ሳንጃ ከተማ – እነ ሽንኩ ካፌና ዳኛው ይህ አረመኔያዊ ድርጊት ተፈፅሟል) ታዲያ ይህ ህዝባዊነት ወይስ ፀረ-ሕዝባዊነት?)
ሰዎችን ከእስር ቤት አስወጥተው ሲገድሉ አይተናል:: በፍ/ቤት ተከሰው ከ4 በላይ ሰዎች የምስክርነት ቃላቸውን ቢሰጡም ገዳዩ በሙስና በነፃ ተለቋል፡፡ (ታች አርማጭ ወረዳ ወጣት ጎሹ እያዩ ሲገደል፡፡) በሀሳብ ልዩነት መጠፋፋት የለብንም ይላል የብአዴን መፈክር፡፡ ግን ብአዴን በመቃወማችንና ባለመደገፋቸው የተነሳ የመኖር መብታቸው ተገፎ (ጭቆና ግፍና በደል) በዝቶባቸው ኑሯቸውን፣ የሞቀ ቤታቸውን፣ ሚስታቸውንና ልጃቸውን ትተው ኑሯቸውን ጫካ ያደረጉ ወገኖች እንዳሉ ታዝበናል! የሽፍታ ቤተሰብ /ወገን/ በመሆናቸው ብቻ ‹‹ገደላችህ አስክሬን አምጡ!›› እየተባሉ ልጆቻቸው ለመግደል ፈቃደኛ ባመሆናቸው የተነሳ መሬታቸውን የተነጠቁ፣ እርሻ ቦታቸውን ወደ ከተማ እንዲገቡ የተገደዱ በኑሮ ውድነትና በእስር እየተሰቃዩ ያሉ ሰዎችን አየን፡፡
የህግ የበላይነት ተጥሶ የግለሰብ የበላይነት ሰፍኖ በቂም በቀልና በስነ-ልቦና ሰዎች ተሰቃይተዋል፡፡ የዘር ማጥፋት ድርጊት የተፈፀመባቸውን የወልቃት አርማጭሆ ነዋሪዎችን አይተናል፡፡ በብሎክ የህዝብ መሬትን በመሸንሸን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጥቅመኛ ባለሀብቶች ሲሸጡ አይተናል፡፡ የመኖገር፣ የማሰብ፣ ያለመሰቃየት መብት አላችሁ እየተባለ በተቃራኒው ግለሰቦች በጉባኤ በመናገራቸው በጅምላና በጭፍን ፍርጃ ፀረ-ሠላም፣ ፀረ-ዴሞክራሲ፣ አሸባሪ እያሉ በማሰባቸውም እየታሰሩ ነው፡፡ ሀሰት ነግሶ፣ እውነት ተገርስሶ፣ በውሸት ሪፖርት፣ በፈጠራ ክስ ኑሮአቸውን ያደረጉ ወገኖችን አይተናል፡፡
ብአዴን ጥገኛ ሲሆን ወያኔ በበላይነት አገሪቱንም ድርጅቶች ሲያስከብር ኖሯል፡፡ ዛሬ ብአዴን በ35 ኣመቷ ዳሩኝ ማለቷ የሀገራችን ባህል ወይም ስርኣትን የጣሰ ነው፡፡ ‹‹የጋለሞታ/ የአሮጌቶች›› ጋብቻ ነው! ስካሁን ድረስ ወያኔ ባሪያ አድርጓት ከቆየ በኋላ ትንፍሽ ብላ የማታውቀ ለመጨፈር አስፈቅዳለች፤ ጎጠኝነት አስተምሯት ቅማንት አማራና አገው ብቻ ሳይሆን በጎጥ እየተከፋፈለ የቀን ሠራኛው ሲገደል አይተናል፡፡ የክልሉ ዜጎች ሲፈናቀሉ ምላሽ መስጠት ሲሳናት አይተናል፡፡ የኮንትሮባንድ ንግድ በመኪና እየነገደች ቲሸርትና ኦሞ የያዘን ድሃ ትወርሳለች፡፡ ታዲያ የብአዴን ዲሞክራሲያዊነትና ህዝባዊነት የት ላይ ነው?

 

ምንጭ:- ነገረ-ኢትዮጵያ

The post የብአዴንን ህዝባዊ ወገንተኝነት ያያችህ?(ከጠረፈኛው የፍትህ ርሃብተኛ፤ ቂልንጦ ማጎሪያ ቤት) appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ሪህ (Gout Arthritis)

$
0
0

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

የሪህ ሕመም የሚከሰተዉ ዩሪክ አሲድ የተባለው ኬሚካል በአጥንት መገጣጠሚያዎች ውስጥ በሚከማችበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ዩሪክ አሲድ የተባለው ኬሚካል የሚገኘው ፕሮቲንን በዉስጣቸዉ ከያዙ ምግቦች ነው፡፡ የሪህ ችግር አንድ ጊዜ ከጀመረ በኋላ የመከላከያ ዕርምጃዎችን ካልወሰድን የመመላለስ ባህርይም አለዉ፡፡
rih
የአጥንት መገጣጠሚያዎች በተለይም በእግራችን የአውራ ጣት፣ በቁርጭምጭሚት፣በጉልበት፣በእጃችን የክንድ እና የእጅ መገጣጠሚያዎች ላይ ተከማችቶ ይገኛል፡፡

✔ የሪህ ህመም ስሜት ቀስቃሽ ሁኔታዎች
• ዉስጣዊ የሆኑ ህመሞች
• አልኮል መጠጦችን ማዘዉተር
• ፕሮቲን የበዛባቸው የምግብ ዓይነቶችን መመገብ (ስጋ፣ሽሮ የመሳሰሉት)
• የሰዉነት ቁስለት
• ድካም
• ጭንቀት
• በሃኪም የታዘዘን የሪህ መድኃኒት ማቆም ናቸዉ፡፡

✔ የሪህ ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸዉ፡፡
• ከአንድ ወይንም ከዛ በላይ በሆኑ መገጣጠሚያዎች ላይ የሚኖር ኃይለኛ የሕመም ስሜት፡፡
• የመገጣጠሚዎች ማበጥ፣ መቅላት እና የሙቀት መጠን መጨመር
• ትኩሳት መኖር
• ብርድ ብርድ ማለት ናቸዉ

✔ ሪህ ተደጋግሞ እንዳይመጣ ምን ማድረግ ይገባል
• ፕሮቲን ያላቸውን ምግቦች በተለይም ቀይ የበሬ ሥጋ፣አሳ፣እንቁላል፣የመሳሰሉት ምግቦች መቀነስ ወይንም ለጊዜው ማስወገድ፣
• ውሃ በብዛት መውሰድ፣
• የአልኮል መጠጦችን አለመጠጣት፣
ከላይ የተጠቀሱት የሕመም ስሜቶች ሲሰማዎትም ሐኪምዎን ማማከር የኖርቦታል፡፡
ጤና ይስጥልኝ

The post Health: ሪህ (Gout Arthritis) appeared first on Zehabesha Amharic.


መንግሥት፣ ማስተር ፕላኑን ካልሰረዘ፣ ሰላማዊ ሰልፍ እጠራለሁ” –የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)

$
0
0

addis admass

“ማስተር ፕላኑ ልማትን ያሻሽላል፤ በረብሻ የተሳተፉ ይከሰሳሉ” – መንግሥት

“የአዲስ አበባና የፊኒፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን” ላይ፣ ሰሞኑን በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች  በተቀሰቀሰው ተቃውሞ፣ ከፖሊስ ጋር ግጭት ተፈጥሮ፣ ሶስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፤ መንግስትን ተጠያቂ አድርጓል፡፡ የክልሉ ፖሊስ በበኩሉ፤ በረብሻው የተሳተፉ ሰዎች ይከሰሳሉ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እጅ አለበት ብሏል፡፡

አምና ተመሳሳይ ግጭትና ተቃውሞ ተፈጥሮ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን፤ “ማስተር ፕላኑ የአዲስ አበባ አስተዳደር፤ በዙሪያው የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞችን እንዲጠቀለል የሚያደርግ ነው፤” የሚለው ተቃውሞ ከሰሞኑ እንደገና ተሰንዝሯል፡፡ “የከተሞቹ የአስተዳደር መዋቅር በማስተር ፕላኑ አይቀየርም” የሚለው መንግስት በበኩሉ፤ መሰረተ ልማትን በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል ነው ሲል ቆይቷል፡፡

“የአዲስ አበባ አስተዳደር፤ በዙሪያው ወዳሉ የኦሮሚያ አካባቢዎች እየሰፋ መጥቷል” በማለት የሚከራከረው ኦፌኮ፤ “ማስተር ፕላኑን አንቀበልም፤ መሬታችን አጥንታችን ነው፤ አንነቀልም” በማለት መግለጫ አውጥቷል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች (ግንጪ፣ ደንቢዶሎ፣ ዲላላ፣ ወሊሶ፣ መደወላቡ፣ ሀረማያ፣ አይራ ጉይሶና በሌሎችም) ለተነሳው የተማሪዎች  ተቃውሞ፤ መንግስት ሰላማዊ ምላሽ መስጠት አለበት የሚለው ኦፌኮ፤ እየደረሰ ላለው ጉዳት መንግስት ኃላፊነቱን ይወስዳል ብሏል፡፡

እስር፣ ድብደባና ግድያ እየተፈጸመ፣ መሆኑን በማውገዝ፤ መንግሥት ይህን ድርጊት በአስቸኳይ ማቆም አለበት ብሏል- ኦፌኮ፡፡ “የአዲስ አበባ ወሰን፤ ከ1987 ዓ.ም በፊት  ወደነበረበት መመለስ አለበት፤ ከወሰን አልፈው የተከናወኑ ግንባታዎች በሙሉ በኦሮሚያ ክልል ስር መተዳደር አለባቸው” ሲልም ፓርቲው ጠይቋል፡፡ የከተሞች ፕላን የፌደራል መንግስት ጉዳይ አይደለም ያለው ኦፌኮ፤ ማስተር ፕላኑ ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን ይጻረራል ብሏል፡፡

ለልማት ተብሎ ከመሬታቸው የሚነሱ ገበሬዎች የህንፃዎች ጠባቂ እየሆኑ ነው ያሉት የኦፌኮ አመራር ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ ገበሬዎቹ የባለሀብትነት ድርሻ ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ዓለም ባንክ ማስተር ፕላኑን መደገፍ የለበትም ያለው ኦፌኮ፤ ባንኩ እጁን ያንሳ ሲል ጠይቋል፡፡ የፈረንሳይዋ ሊዮን ከተማ አስተዳደር ለማስተር ፕላኑ ድጋፍ በመስጠትም አሁን ለተፈጠረው ችግር አስተዋጽኦ ስላደረገ ይቅርታ መጠየቅ ይኖርበታል ብሏል – ኦፌኮ፡፡

የመንግስት በደልና ግፍ ካልቆመ፣ የአገሪቱን ሰላምና አንድነት ስጋት ላይ ይጥላል ያሉት ዶ/ር መረራ፤ መንግስት ለህዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንደሚገደድ ተናግረዋል፡

“በአዲስ አበባ ዙሪያ፣  በኦሮሚያ ላይ ሰፊ የመሬት እና የባህል ወረራ ተካሂዷል  ያሉት ዶ/ር መረራ፤ ከ25 ዓመት በፊት በአዲስ አበባ አካባቢ የነበሩ 28  የገበሬ ማህበራት ዛሬ የሉም ብለዋል፡፡ መንግስት በርካሽ የካሳ ክፍያ ከገበሬዎች መሬት እየወሰደ  በሚሊዮን ብሮች በጨረታ ይሸጣል ያሉት ዶ/ር መረራ፤ ሱሉልታ አካባቢ ገበሬዎች በ50 ሺህ ብር ካሳ ይፈናቀላል ብለዋል፡፡

ሰኞ እለት በሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከፖሊስ ጋር በተነሳ ግጭት በርካታ ተማሪዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ትምህርት ተስተጓጉሎ ሰንብቷል፡፡  ዩኒቨርስቲው በበኩሉ፣  በተቃውሞ ምክንያት ትምህርት ሙሉ ለሙሉ እንዳልተቋረጠና የግቢው ሁኔታ እንደተረጋጋ ገልጿል፡፡

ተቃውሞው በበርካታ ከተሞች በሚገኙ ዩንቨርስቲዎችና ት/ቤቶች የተስፋፋ ሲሆን ፣ በአንዳንዶቹ  አካባቢዎችም  ነዋሪዎች እንደተሣተፉበት ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር በበኩሉ፤ በረብሻው የሰው ህይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን በመግለፅ ተቃዋሚዎችን ተጠያቂ አድርጓል፡፡ ማስተር ፕላኑ የፌደራል ስርአቱን አይጥስም ያለው መስተዳድሩ፤ የኦሮሚያ መሬትንም ቆርሶ ለሌላ አካል አይሰጥም ብሏል፡፡  ሁከት የሚሹ ሃይሎች፤ ለማስተር ፕላኑ የተሣሳተ ትርጉም ሰጥተውታል፣ በዚህም ለጠፋው ህይወትና ለወደመው ንብረት ተጠያቂ ናቸው ብሏል መስተዳድሩ ፡፡

ባለፈው አመት በዩንቨርስቲዎችና በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ማስተር ፕላኑን ተመሳሳይ ተቃውሞ ተቀስቅሶ፤ ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት 10 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡

The post መንግሥት፣ ማስተር ፕላኑን ካልሰረዘ፣ ሰላማዊ ሰልፍ እጠራለሁ” – የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የቀድሞው የፖለቲካ እስረኛ ኦቦ ደበላ ታፋ ታፍነው ተወስደው አስከሬናቸው ተጥሎ መገኘቱ ተዘገበ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ከ6 ዓመታት እስር በኋላ የተፈቱት ኦቦ ደበላ ታፋ ሮቢ ባልታወቁ የስርዓቱ ሰዎች ታፍነው ተወስደው መገደላቸውን አክቲቭስት ጃዋር መሐመድ በፌስቡክ ገጹ ዘገበ::

Zehabesha News

አክቲቭስቱ ከሟች ቤተሰብ አገኘሁት ባለው መረጃ ኦቦ ደበላ ታፍኖ የተወሰደው ፍቼ አካባቢ ከቀናት በፊት ዲሴምበር 2, 2015 ነበር:: ከአንድ ቀን በኋላም ከጫንጮ አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዲች ከተማ ተገድሎ ተገኝቷል::

ሕወሓት የሚመራው የኢሕ አዴግ መንግስት የሚፈልጋቸውን ተቃዋሚዎች በአሸባሪነት ከመክሰስና ከማሰር በተጨማሪ በስውር እያፈነ በመውሰድ በመግደል ሲከሰስ መቆየቱ ይታወሳል::

The post የቀድሞው የፖለቲካ እስረኛ ኦቦ ደበላ ታፋ ታፍነው ተወስደው አስከሬናቸው ተጥሎ መገኘቱ ተዘገበ appeared first on Zehabesha Amharic.

‘ልክ አታስገቡንም’ያሉት የኦሮሞ ወጣቶች በየከተማው ዛሬም ተቃውሟቸውን ቀጥለዋል * በርካታ ወጣቶች እየታሰሩ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የአዲስ አበባ አዲሱ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዳይሆን ሲሉ የኦሮሞ ወጣቶች ሲጠይቁ የኢሕ አዴግ መንግስት ከመጋረጃው በስተጀርባ መሪ አባይ ጸሃዬ ይህን ጥያቄ የሚያቀርቡትን ልክ እናስገባቸዋለን ሲሉ ቢዝቱም የኦሮሞ ተማሪዎች ‘ልክ አታስገቡንም… ማስተር ፕላኑም ተግባራዊ የሚሆነው በኛ ሬሳ ላይ ነው” በሚል ትግላቸውን በየከተማው ቀጥለዋል::

say no

አንደኛ ሳምንቱን በያዘው በዚሁ የተማሪዎቹ ተቃውሞ ዛሬም በተለያዩ ከተሞች ቀጥሎ በቡራዩ ገፈርሳ; በምስራቅ ሃረርጌ ፉርዳ አካባቢ እንዲሁም በድሬደዋና በደምቢ ዶሎ ቀጥሎ መዋሉ ተዘግቧል::

አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም የጀመረው ይኸው ተቃውሞ መንግስት በሃይል በወሰደው እርምጃ የተነሳ ጥያቄው ወደ አትግደሉን ተሻግሯል:: አንደኛ ሳምንቱን በያዘው በዚሁ ተቃውሞ በርካታ ተማሪዎች ደም የፈሰሰ ሲሆን መንግስት በጨለማ ተማሪዎችን እያፈነ በማሰር ላይ እንደሚገኝም ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች ያመለክታሉ::

በድሬደዋ; በሐሮማያ; በጅማ; በወለጋ በርካታ ተማሪዎች በማታ እየታፈኑ መታሰራቸው ሲዘገብ እስካሁን የት እንደታሰሩ እንኳ ቤተሰብ ማወቅ እንዳልቻለ የደረሱን መረጃዎች ጠቁመዋል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ሕወሓት የሚመራው የኢ ህ አዴግ አገዛዝ ጥያቄ ካነሱ ወገኖች ጋር በሰላም ከመነጋገር ይልቅ ትግሉን በማፈን እየተደረገ ያለውን ትግል ተቆጣጥሬዋለሁ በሚል ለማዳፈን መሞከሩ ጉዳዩን ከማክረር ውጭ እርባና ቢስ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ:: እንደፖለቲካ ተንታኞች ገለፃ መንግስት በአስቸኳይ ቆም ብሎ ካላሰበ በየከተማው የተቀጣጠለው የሕዝብ ድምጽ እንደጎርፍ ይዞት ሊሄድ ይችላል::

The post ‘ልክ አታስገቡንም’ ያሉት የኦሮሞ ወጣቶች በየከተማው ዛሬም ተቃውሟቸውን ቀጥለዋል * በርካታ ወጣቶች እየታሰሩ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: በዱካክ ተሰቃየሁኝ፣ ምን መፍትሄ አላችሁ?

$
0
0

ask your doctor zehabesha

ዕድሜዬ 17 ዓመት ሲሆን በ10+3 ፕሮግራም የኮሌጅ ትምህርቴን ከጀመርኩ ወራትን አስቆጥሬያለሁ፡፡ ከዚህ በላይ ግን በትምህርቴ መግፋት የምችል አይመስለኝም፡፡ የደረሰብኝ ችግር ትምህርቴን ማስተጓጎል ብቻ ሳይሆን አጠቃላዩ ኑሮዬንም ምስቅልቅሉን እያወጣው ነው፡፡ 

እንደሚታወቀው ክላስ ገብቼ ትምህርት መማር የምችለው ቀን ቀን ነው፡፡ ከአንድ ወር ገደማ በፊት ይመስለኛል ክፍል ውስጥ እንቅልፍ እየወሰደኝ ተቸግሬያለሁ፡፡ ከአየሩ መቃትነት የተነሳ ደግሞ ታግዬ እንኳን የምቆጣጠረው አልሆነልኝም፡፡ ይህ ችግሬ በአሁኑ ጊዜ በጣም እያሳፈረኝ ነው፡፡ ችግሬን እንደ ችግር ቆጥሮ የሚያዝንልኝ ሰው እንኳን የለም፡፡ በስርዓት ተቀምጬ አስተማሪ በምከታተልበት ሳላስበው ዥው ያለ እንቅልፍ ይወስደኛል፡፡ ግንባሬን ከዴስኩ ጋር የማጋጭበት ጊዜም ብዙ ነው፡፡

ይህን ችግሬን ያወቁ ልጆች ወደ ኋላ አካባቢ እንድቀመጥ መከሩኝና ያሉትን አደረግሁ፡፡ እኔ ስተኛ ግን ክላሱ እስኪያልቅ ድረስ የሚቀሰቅሰኝ ሰው የለም፡፡ ይህስ ባልከፋ፣ ሆኖም ወዲያው እንቅልፍ እንደወሰደኝ የሚያሳቅቅ ነገር ይደርስብኛል፡፡ ምን መሰላችሁ ይሄ እንደ ዱካክ ነገር ደረቴን ፈጥርቆ ይዞ እንዳልንቀሳቀስ ያሳስረኝና ሳላስበው ቀጭን ጩኸት አሰማለሁ፡፡ በዚህ ጊዜ ነው መምህሩ መተኛቴን የሚያውቁት፡፡ ተቀስቅሼ ስነቃ ደግሞ ተማሪው ሁሉ እየሳቀብኝ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ሁኔታ እንዴት አድርጌ ነው የምማረው? ይኸው ትምህርት ካቋረጥኩ ሁለት ሳምንት ሆኖኛል፡፡ 

ይህ ዱካክ እና በቀን የመተኛት አባዜ መፍትሄ አለው ትላላችሁ? ማብራሪያችሁን በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡ 

የእናንተው ጢኖ

መልስ፡- ውድ ጢኖ ለጥያቄህ ልባዊ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን፡፡ ሳይታሰብ እና ሳፈለግ የሚመጣ የቀን እንቅልፍ በአጠቃላይ ህይወት ላይ የሚያመጣው ምስቅልቅ እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑ ቅድሚያ ሰጥተነዋል፡፡

ምናልባት ለትምህርትህ ከምትሰጠው ላቅ ያለ ግምት አንፃር ክፍል ውስጥ ተቀምጠህ የማንቀላፋቱን ነገር የበለጠ ትኩረት ሰጠኸው እንጂ ህመሙስ ከዚህ የባሰም ፈተና ሊያስከትልብህ ይችላል፡፡ ሳይፈልጉ በቀን መተኛት በጣም መጥፎ ክስተት ነው፡፡ ህመሙ በህክምናው ዓለም ‹‹Narcolepsy›› ተብሎ ይጠራል፡፡

‹‹Narcolepsy›› የእንቅልፍ መዛባት ቢሆንም ከሌሎች ተያያዥነት ካላቸው የእንቅልፍ መዛባት ችግርህ ለየት የሚያደርገው ቁጥራቸው በጣም ውስን በሆኑ ሰዎች ላይ የሚከሰት ህመም በመሆኑ ሳቢያ ነው፡፡ አልጋ ላይ ተጋድመው አይናቸውን ቢጨፍኑም እስከ ውድቅት ሌሊት ወይም እስከ ንጋት ድረስ እንቅልፍ አልወስድ ብሏቸው ሲገላበጡ የሚያድሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርጋቸውም ግማሽ ሰዓት ወይም አንድ ሁለት ሰዓት ብቻ ከቆዩ በኋላ ተመልሰው የሚነቁና የቀረውን የሌሊት ክፍል ፈጠው የሚያድሩም ጥቂት አይደሉም፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ጠዋት ከእንቅልፋቸው መንቃት ተስኗቸው ተጋድመው ያረፍዳሉ፡፡ ከዚህ አንፃር ‹‹Narcolepsy›› የጥቂቶች ብቻ ችግር ነው፡፡

‹‹Narcolepsy›› በጣም አደገኛ ህመም ነው፡፡ የዕለት ስራን በወጉ ለማከናወን፣ ለመብላት፣ ለመዝናናት፣ ወዲያ ወዲህ ብሎ ለመንቀሳቀስ የህሊና ንቃት ያስፈልጋል፡፡ በተለይም የመኪና መንገድ ለማቋረጥ፣ ማሽን ላይ ለመስራት ወይም መኪና ለማሽከርከር ብሩህ የአዕምሮ ንቃት ማስፈለጉ የግድ ይላል፡፡

በእርግጥ ይህ ህመም ያለባቸው ሰዎች ተረጋግተው ክፍል ውስጥ መማር ይከብዳቸዋል፡፡ ከዚህ ህመም ጋር በተያያዘ መልኩ የሚከሰት አንድ ሌላ ችግር አለ፤ ይህም በተለምዶ ‹‹ዱካክ›› እየተባለ የሚጠራውና በእንቅልፍ ዓለም ውስጥ ሆነው መሰቃየት ሲሆን በጣም የሚያስጨንቅ ጉዳይ ነው፡፡

ይህ ሁኔታ ‹‹Sleep paralysis›› ተብሎ ይጠራል፤ ዱካክ እንደማለት ነው፡፡ በእርግጥ ከቀን እንቅልፍ ‹‹Narcolepsy›› ጋር ባልተያያዘ ሁኔታም ሊከሰት ይችላል፡፡ በተለይም ታዳጊ ህፃናት እና ጎረምሶች ናቸው በዚህ ችግር የሚጠቁት፡፡

ህመሙ ህክምና ያስፈልገዋል፡፡ አለበለዚያ ግን በሽተኛውን ለአደጋ ወይም ለሞት የሚዳርግ ክስተት ያስከትልበታል፡፡

ውድ ጠያቂያችን የስነ አዕምሮ ሐኪሞች ክትትል የግዴታ ያስፈልጋል፡፡ የሚታዘዙልህ መድሃኒቶች ጥንቃቄ ካልታከለባቸው በጣም አደገኞች በመሆናቸውም ሁኔታህ እየታየ የመድሃኒቶቹ መጠን ያስተካክልም ዘንድ መጠቆም እንወዳለን፡፡

The post Health: በዱካክ ተሰቃየሁኝ፣ ምን መፍትሄ አላችሁ? appeared first on Zehabesha Amharic.

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሰላም አስመራ መግባታቸው ተሰማ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ የነበራቸውን የአንድ ሳምንት ቆይታ አጠናቀው በሰላም አስመራ መግባታቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጹ::

Dr Birhanu Nega

በአውሮፓ ፓርላማ መጠራታቸውን እና ብራሰልስ መግባታቸውንም ዘ-ሐበሻ ቀድማ መዘገቧ አይዘነጋም::

ፕሮፌሰሩ በአውሮፓ ፓርላማ ባለፈው ማክሰኞ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ረሃብ እና የመልካም አስተዳደር እጦት ንግግር ያደረጉ ሲሆን የተጋበዙትም በፖርቱጋላዊቷ ሚስ አና ጎሜዝ እንደነበር ታውቋል::

ፕሮፌሰሩ በአውሮፓ ፓርላማ ንግግር ካደረጉ በኋላ ለሁለት ቀናት ከተለያዩ ሃገራት ተወካዮች ጋር መነጋገራቸውንም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያስረዳል::

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስመራ ገብተው እዚያው የሚገኘው ጦራቸው የተቀላቀሉት ትናንት ማምሻውን እንደሆነ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

The post ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሰላም አስመራ መግባታቸው ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

በምርጫ 2007 ለፓርላማ የተወዳደረው ታጋይ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቀለ

$
0
0

arbegnch G7

(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ እንደዘገበው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል የሆነው ወጣት በርሃ ወርዶ ብረት ያነሳውን ሰራዊት ተቀላቀለ::

በሰላማዊ መንገድ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ሲታገል የቆየውና ይህም የማይታሰብ መሆኑን የተረዳው የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ወጣት እንደግ አዳነ የሟቹ ሳሙኤል አወቀ የቅርብ ጓደኛ እንዲሁም የትግል አጋር እንደነበር ራድዮው ዘግቧል::

አርበኞች ግንቦት 7ን የተቀላቀለው እንደግ አዳነ በ2007 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ሞጣ ወረዳ ላይ ለተወካዮች ምክር ቤት የተወዳደረ ሲሆን አሁን ደግሞ የህወሓትን አገዛዝ ፈፅሞ በሰላማዊ ትግል መለወጥ እንደማይቻል አምኖ ጫካ ገብቶ ብረት አንስቷል ሲል የዘገበው ራድዮው “ሰላማዊ ትግል አብቅቶለታል!” ሲልም ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮመናገሩን ገልጿል::

G 7

አርበኞች ግንቦት 7ን የተቀላቀለው እንደግ አዳነ በ2007 ዓ.ም የሞጣ ወረዳን ወክሎ ለምርጫ በተወዳደረበት ወቅት የህወሓት አገዛዝ ማዳበሪያ በመከልከልና ሌላም የበቀል እርምጃ በመውሰድ በገበሬ ቤተሰቦቹ ላይ በደል እንዳደረሰ ለራድዮው ገልጿል፡፡ በምርጫው ማግስት የሞጣ ህዝብ የሰጠውን ድምፅ በጠብመንጃ ከመነጠቁ በላይ የህወሓት ደህንነቶች አፍነውት ልብሶቹን አስወልቀው መለመላውን ብርድ ላይ አቁመው በማሳደር ሰቆቃ እንደፈጸሙበትም አስረድቷል::

አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅሎ አሁን በረሃ ውስጥ የሚገኘው ወጣት እንደግ አዳነ “ከንቱ መሰዋዕትነት ከመክፈልና ጊዜ ከመፍጀት ውጭ ፈፅሞ ለውጥ ማምጣት ስለማይቻል ከተማ የቀራችሁ የሰላማዊ ትግል ጓዶቼ በሙሉ ፈጥናችሁ የእኔን ፈለግ እንድትከተሉና ትክክለኛውን የትግል አማራጭ እንድትይዙ፡፡” ሲል ጥሪውን ማስተላለፉን የንቅናቄው ራድዮ ዘግቧል::

The post በምርጫ 2007 ለፓርላማ የተወዳደረው ታጋይ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቀለ appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: 15ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ –አርሰናል አሸነፈ –ሲቲ ተሸነፈ –ማን.ዩናይትድ ጎል ማግባት ተስኖት ነጥብ ጣለ

$
0
0

arsenal

Updated – (ዘ-ሐበሻ) 15ኛው ሳምንት የ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከደቂቃዎች በፊት ተካሂዷል::  በዛሬው ጨዋታ አርሰናል እና የዘንድሮው አስደናቂ ቡድን ሌስተር ሲቲ ድል ቀንቷቸዋል:: በሌላ በኩል ዘግየት ብሎ የተጫወተው ቸልሲ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት በርንማውዝን አስተናግዶ 1ለ0 ተሸንፎ በአሰልጣን ሆዜ ሞሪንሆ ላይ ጫናው እንዲበረታ አድርጓል::

ፕሪምየር ሊጉን በ32 ነጥብ የሚመራው ሌስተር ሲቲ ስዋንሳን 3ለ0 አሸንፎታል:: የሊጉ 2ኛ የሆነው አርሰናል ሰንደርላንድ 3ለ1 አሸንፎ ነጥቡን 30 አድርሶ ሌስተር ሲቲን ይከተላል::

ማንቸስተር ዩናይትድ አሁንም ጎል ማግባት ተስኖት ከዌስትሃም ጋር 0ለ0 ተለያይቷል:: ማንቸስተር ሩኒን እና ማርሻልን በጉዳት ምክንያት ያጣ ሲሆን ቡድን የፕሪምየር ሊጉ ደባሪ ቡድን እስከሚባል ድረስ የጎል እጥረት ተከስቶበታል::

ሌላው አስገራሚ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ በስቶክ 2ለ0 ተሸንፏል:: ሲቲ ደረጃው ወደ 3 ዝቅ ያለ ሲሆን ከማን.ዩናይትድ ጋር በኩል 29 ነጥብ ቢቀመጥም በጎል ብልጫ ነው 3ኛ የሆነው::

የሌሎች ጨዋታዎች ውጤቶች:-
ዋትፎርድ ኖርዊችን 2ለ0
ሳውዛምተን እና አስቶን ቭላ 1ለ1
ዋትፎርድ ኖርዊችን 2ለ0 ሆኗል::

The post Sport: 15ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ – አርሰናል አሸነፈ – ሲቲ ተሸነፈ – ማን.ዩናይትድ ጎል ማግባት ተስኖት ነጥብ ጣለ appeared first on Zehabesha Amharic.


በኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ህጻናት በመንግስት ሃይሎች ደማቸው ሲፈስ እየታዬ ዝምታን የሚመርጥ ኣንጀት ሊኖር ኣይገባም።

$
0
0

Oromo

በበቀለ ጅራታ* | (የኦፌዴን የቀድሞ ዋና ፀሐፊ)

 

ኦቦ በቀለ ጅራታ

ኦቦ በቀለ ጅራታ

ይህ የኣሁኑ መንግስት ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ያለ ሟቋረጥ የበርካታ ዜጎችን ህይዎት ኣጠፍቷል። በተለይም በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የተፈጽሙት ግዲያዎች፣ የጅምላ እስርና ማሰቃየት ተነግሮና ተጽፎ የሚያልቅ ኣይደለም። ይህ መንግስት የኦሮሞን ህዝብ በተለዬ ሁኔታ ሆን ቢሎ ነገር እየፈለገ በሰላም እንዳይኖር በማድረግ በገዛ ሃገሩ ግፍ እየፈጸመበት ይገኛል። የዛሬ ኣስራ ኣምስት ኣመት ኣካባቢ ሆን ቢሎ የክልሉን መንግስት ዋና ከተማ ከኣዲስ ኣበባ ወደ ኣዳማ እንዲቀየር በማለት በማናለብኝነት የወሰነውን ውሳኔ በሰላማዊ መንገድ በመቃወማቸው በርካታ የክልሉ ተማሪዎችን በግፍ ጨፈጨፈ።

በሺዎች የሚቆጠሩትን በተለያዩ እስር ቤቶች በማጎር በድብደባና በህክምና እጦት በርካቶች በእስር ቤቶች ውስጥ እንዲሞቱ ተደረገ። ከዚያም ጊዜ ወዲህም ምክንያት እየተፈለገ በርካቶች በእስር ቤቶች እየታጎሩ የበደሎች በደል ሲፈጸምባቸው ኖረዋል።

ከቅርብ ኣመታት ወዲህ ደግሞ በልማት ስም የገበሬውን መሬት ለውጪ ባለሃብቶች በመሸጥ ከኖሩበት በማፈናቀል ለከፋ ችግርና መከራ ሲዳርግ ቆይቷል። ይህንን ህገወጥ ድርጊት የተቃወሙትንም በእስር ሲያንገላታ ኖሯል። ካለፉት ሁለት ኣመታት ወዲህ ደግሞ ኣዲስ ኣበባን ለማስፋት የሚል ኣዲስ ምክንያት በመፍጠር በኣዲስ ኣበባ ከተማ ዙሪያ ያሉትን የገበሬውን መሬቶች ወደ ከተማው ለመቀላቀል የወጠነውን የማስተር ፕላን እቅድ በሰላማዊ መንገድ የተቃወሙትን ህጻናት ሳይቀሩ ያለሟቋረጥ በጭካኔ በመፍጀት ላይ ይገኛል። የኦሮሞ ተማሪዎችም ሆኑ መላው የኦሮሞ ህዝብ የሚቃወሙት በማስተር ፕላን ሰበብ ነባሩ ነዋሪ ህዝብ መፈናቀል ኣይገባውም፣ የሃገር ልማት ህዝቡን ለዘመናት ከኖረበት ቄዬ በማፈናቀል ሳይሆን መከናውንያለበት ህዝቡን ጭምር የሚያለማና ኑሮውን ወደተሻለ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆን ኣለበት በሚል ነው እንጂ ልማትን በመቃወም ኣይደለም።

ኣዲስ ኣበባ መሃሉ ገና ምንም ባልለማበት ሁኔታ ላይ እያለ ከዚያ ውጭ ብዙ ኪሎሜትሮች በመሄድ የኣርሶ ኣደሩን ህይዎት ለማናጋትና ከገዛ መሬቱ ለማፈናቀል የተፈገበት ምክንያት እንደተለመደው ለውጭ ባለሃብቶች ለመሸጥና ለመክበር ካልሆነ ሌላ እንዳልሆነ ማንም ያውቃል። በዚህ ማስተር ፕላን ሰበብ የኦሮሞ ህጻናትን በመፍጀት “ታላቁ መሪያቸው” ያስቀመጠውን “ብዙሃንን ኣናሳ ማደረግ ይቻላል” የሚለውን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ናቸው። ይህ መንግሥት ባለፈው ኣመት በኣምቦ፣ በኣዳማ፣ በባሌ ሮቤ ወዘተ የበርካታ የኦሮሞ ተማሪዎችን ያለ ርህራሄ ፈጃቸው። ይሄው ዘንድሮም ካለፉት ጊዜያት በከፋ መልኩ የኣንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን በእናቶቻቸዉ ፊት ሳይቀር በሳንጃ እየቀደዳቸው ሬሳቸውን በየሜዳው በትኖ በማሳየት ላይ ነው። እንደዚህ ኣይነት ድርጊት የሃገሪቷ መንግስት ነኝ ከሚል ኣካል ቀርቶ ከውጭ በመጣ ጠላትም ኣይፈጸምም። እድሜ ለዘመኑ ቴክኖሎጂ ይህንን የግፍ ኣገዳደል ለመደበቅ ቢሞክርም ፈጽሞ ኣይችልም። ሁሉ ነገሩ ገዳዮቹ በቦታው ላይ ጭፍጨፋ ሲያካሄዱ ለኢትዮዽያ ህዝቦችና ለኣለም ህብረተሰብ እየደረሰ ይገኛል።

ይህ መንግስት ከላይ እንዳልኩት ባለፉት ሃያ ኣምስት ኣመታት ያለሟቋረጥ በማን ኣለብኝነት ሃገሪቷን ሰላም እየነሳ እዚህ ደርሷል። ሆኖም የሃገሪቷ ህዝቦች ተባብረው በቃህ ልሉ ኣልቻሉም። ምንም የማያውቁ ህጽናት በግፍ መንግስት ባሰማራቸው ገዳዮች ሬሳ በየሜዳው ወድቆ ማየትን የሚያክል ኣሳዛኝ ነገር ይኖራል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ይህ ኣሰቃቂ የግፍ ግዲያ የማንንም እናትና ኣባት ኣንጀት ያቆስላል። ሆኖም እስካሁን ድረስ ከኦሮሞ እናቶችና ኣባቶች በስተቀር ድምጻቸውን ያሰሙ ኣልታዩም። በተለይም በሃገሪቷ ይህን መንግስት እንቃወማለን የሚሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኣንዳችም ድምጽ ኣለማሰማታቸው ይገርማል፣ ያሳዝናልም። ሁላችንም ይህን መንግስት በማስወገድ ፍትሕ ሰላምና እኩልነት በሃገሪቷ እንዲሰፍን እንፈልጋለን። ነገር ግን መሰረታዊ የሰዎች ልጆች መብት ላይ እንኳን ለመስማማትና ለመተባበር ኣልቻልንም። ይህም ተደጋግሞ እንደተነገረው ለኣፋኙና ጸረ-ዲሞክራሲ ለሆነው ቡድን ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። ይህ መንግስት ሊወገድ የማይችለው በጥንካሬው ሳይሆን በእኛ በተለይም ፖለቲከኞች ኣለመስማማት ነው። ቢያንስ ቢያንስ ኣምባገነኑ መንግስት ህጻናትን በጠራራ ጸሃይ መርዝ እየረጨባቸው ተንገዳግደው ሲወድቁ በጥይት በሚጨርሳቸው ጊዜ እንኳን ኣለመቃወም ማለት የተቃዋሚነት ትርጉሙ ምን እንደሆነ ለመረዳት ያዳግታል። ይህ በኣዲስ ኣበባ ዙሪያ በሚኖሩ የኦሮሞ ገበሬዎችን ከተማ ለማስፋት ተብሎ የሚወሰደው የማፈናቀል እርምጃን መቃወም ሁሉንም የሚመለከት ጉዳይ ነው። ምክንያቱም በዚህ ኣካባቢ የሚኖሩት ሌሎች ኣማራ፣ ወላታ፣ ከምባታ፣ ሲዳማ ወይም ሌሎች ቢሆኑ ተመሳሳይ ግፍ ስለሆነ የሚፈጸምባቸው ለመብታቸው መቆማቸው ኣይቀርም ነበር። ስለዚህ ኦሮሞ ይህንን ህገወጥ ወረራ መቃወሙ ማንኛውም ሰባዊ ፍጡር የሚያደርገው የመብት ማስከበር ጥያቄ ነው እንጂ የሌሎችን ጥቅም የሚጎዳ ተደርጎ ሊታይ ኣይገባም።

የኦሮሞ ህዝብ በገዛ ሃገሩ ላይ በሰላም መኖር ካልቻለ በምንም መልኩ ሌሎች በሰላም ሊኖሩ ኣይችሉም። ስለዚህ ኣምባገነኖችንና ጸረ ሰላም የሆኑትን ገዢዎች ከኦሮሞ ህዝብ ጎን ቆመን ካልተቃወምነውና ካላስወግደነው ሰላምም ሆነ እድገት ለሁላችንም ኣይመጣም። ምናልባት ገዢው መንግስት ኣሁን ባለው የወታደር ብዛትና መሳሪያ ተመክቶ የህዝባችንን ተቃውሞ የሚያቆም ሊመስለው ይችላል። የህዝቦችን ሃይል በወታደር ብዛትና መሳሪያ ለማቆም እንደማይቻል ኣሁን ያለው ገዢው መንግስት በሚገባ ያውቃል። መተማመኛው ሃይል ሳታሰብ ኣንድቀን ይከደዋል። ያኔ ሁሉም ነገር ከቁጥጥር ውጭ ሲሆን የኢትዮዽያ ኣንድነትም የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫው ላይ እንዳስጠነቀቀው ኣደጋ ላይ ይወድቃል። ምናልባትም ታሪክ ሆኖ ይቀር ይሆናል። ስለዚህ ስለ የኢትዮዽያ ኣንድነት ብቻ የሚጨነቁ ወገኖች በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈጸሙ ጭቆናዎች እንዲቆምና ይህ ሰላማዊ ህዝብ በተፈጠረበት ምድር ላይ ሙሉ መብቱ ተጠብቆለት ከሌሎች የሃገሪቷ ህዝቦች ጋር በሰላም እንዲኖር መደገፍና ከጎኑ መቆም ተገቢ ብቻ ሳይሆን ኣስፈላጊም ነው።

በመሆኑም በሃገሪቷ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ይግፍ ኣገዛዝ ወደት ሊያመራ እንደሚችል ቆም ብሎ የማሰቢያ ጊዜ ኣሁን ነው። የኦሮሞ ህዝብ ለተፈጥሮና ህጋዊ መብቶቹ መከበር መታገሉን ያቆማል ብለው የሚያስቡ ካሉ ተሳስተዋል። ገዢው መንግስትም በሃይል ኣስቆማለሁ በማለት ህጻናትን እየፈጀ ይገኛል። ግን ፈጽሞ ሊያቆመው ኣይችልም። የማን ህዝብ የመብት ትግል እንደቆመ የኦሮሞ ትግል ይቆማል? ስለዚህ ሁላችንም ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለራሳችንም ጭምር ስንል ይህን ኣምባገነን መንግስት በለጋ ህጻናት ላይ የሚያካሄደውን ጭፍጨፋ ማውገዝ ኣለብን የሚል እምነት ኣለኝ። የሁላችንም መብት መከበርና እንደ የኣለም ህዝቦች በነጻነት፣ በእኩልነትና በመከባበር መኖር የሚንችለው ተባብረን ይህን ኣምባገነን መንግስት ሲናስወግድና ዳግም ለኣምባገነኖች ላለመገዛት ሲንወስን ብቻ መሆኑን ተገንዝበን፣ የፖለቲካን ትርፍና ኪሳራ ማስላት ትተን ለዘመናት በሁዋላ ቀር ኣገዛዞች ምክንያት ለም ሃገር እያለ በረሃብ ኣለንጋ ሲገረፉ ለኖሩትና እየ የኖሩ ላሉት ህዝቦች ስንል ግፍን ለማስወገድ መተባበር የውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው።

ከደብተራቸውና ኣሬንጓዴ ቅጠል ሌላ ነገር ባልያዙት ህጻናት ተማሪዎች ላይ መንግስት ባሰማራቸው ገዳዮች ጭፍጨፋ ሲካሄድ እያዬ ዝምታን የሚመርጥ አንጀት ሊኖር ኣይችልም፣ ኣይገባም።

* በቀለ ጅራታ (የኦፌዴን የቀድሞ ዋና ፀሐፊ) – ከስዊድን

The post በኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ህጻናት በመንግስት ሃይሎች ደማቸው ሲፈስ እየታዬ ዝምታን የሚመርጥ ኣንጀት ሊኖር ኣይገባም። appeared first on Zehabesha Amharic.

ሕወሓት የሚመራው የኢሕአዴግ መንግስት በዳላስ ያዘጋጀውን ስብሰባ ኢትዮጵያውያን ሲያውኩት የሚያሳይ ቪዲዮ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ገዢው የሕወሓት መንግስት የበርካታ ንጹሃንን ባፈሰሰ አንድ ሳምንት ሳይሞላው ዛሬ ዳላስ ላይ ስለ ልማት ለመነጋገር ሕዝባዊ ስብሰባ ጠርቶ ነበር:: በዳላስ የሚገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ይህን ስብሰባ እንዲህ አውከውታል:: ቪድዮውን ይመልከቱት:: ተጨማሪ ቪድዮዎች እየጠበቅን ነው እንደደረሱን እንመለሳለን::
በስብሰባው ላይ የተገኙት በ አሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ግርማ ብሩ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል።

Zehabesha News

The post ሕወሓት የሚመራው የኢሕአዴግ መንግስት በዳላስ ያዘጋጀውን ስብሰባ ኢትዮጵያውያን ሲያውኩት የሚያሳይ ቪዲዮ appeared first on Zehabesha Amharic.

ማስተር ፕላኑና ተቃውሞው፡- የፖሊሲ ግድፈቶችና የመፍትሄ ሀሳብ!

$
0
0

በአብዱረዛቅ ሑሴን
.
የሰሞኑ ርህራሄ የጎደለው የመንግስት እርምጃን የሚያሳዩ ዜናዎችና ምስሎችን ማየት እጅጉን ያማል፡፡ ገዢዎቻችን የህዝብን ቅሬታ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት የሚባል ነገር ከራቃቸው ሰነባብተዋል፡፡ በውይይት ከያዙት አቅዋም የተመለሱበት ጊዜያት ጥቂት ቢሆንም፣ ከህዝብ ተቃውሞ ሲነሳ ተወካዮችን በማስመደብ እና ሽምማግሌዎችን በመላክ ድርድሮችና ውይይቶች ይደረጉ የነበሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በመንግስትም ላይ ሆነ በስሩ በሚያስተዳድራቸው ተቋማት ላይ ለሚነሱ ማንኛውም አይነት ተቃውሞዎች ዘግናኝ እርምጃዎች መውሰድን እንደ ብቸኛ አማራጭ ተያይዞታል፡፡ ከሰሞኑም በአዲስ አበባው ማስተር ፕላን ዙሪያ ለተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድረስ እየተወሰደ ያለው ዘግኛኝ እርምጃ የስርአቱን ማን አለብኝነትና የአመራሩን ጭካኔ በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡
oromia
.
የተቃውሞው መንስኤ የሆነው የአዲስ አበባ አዲስ ማስተር ፕላን ይህን ያህል ደም ማፍሰሱና ለብዙ አካልና ንብረት መጉደል ምክንያት መሆኑ ያሳዝናል፡፡ ይህንኑ ፕላን ከአመት በፊት የትግበራ እንቅስቃሴውን በመቃወም በተነሳው ተቃውሞ በመንግስት ፀጥታ ሃይሎች በተወሰደ እርምጃ የብዙ ንፁሃን ህይወት ተቀጥፏል፡፡ በማስተር ፕላኑ ስር የተካተተው የኦሮሚያ አጎራባች ከተሞችን በአዲስ አበባ ስር የማካተት እቅድና በቦታው ላይ ሰፍሮ የሚገኘው ህዝብ እጣ ፈንታ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡ እንደዚህ አይነት እቅድ ህገ መንግስቱ ያፀደቀውን የፌደራሊዝምን መርህ ጥያቄ ውስጥ ከማስገባቱም በላይ ሀገሪቱ የምትከተለው የከተማ ልማት ፖሊሲ ግድፈቶች ማሳያም ጭምር ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ የፖሊሲ ግድፈቶቹንና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በአጭሩ ለመቃኘት ተሞክሯል፡፡
.
ያልተመጣጠነ የከተማዎች እድገት
.
አዲስ አበባ የሃገሪቱ ዋና ከተማ እና የትላለቅ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ እንደመሆኗ ከሌሎች ከተሞች በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴም ይሁን በአገልግሎት አቅርቦቷ የተሻለች እንደምትሆን ቢጠበቅም አሁን እንደሚስተዋለው ከሌሎች ከተሞች አንፃር የተጋነነ ልዩነት መኖሩ የሃገሪቱን የከተማ ልማት ፖሊሲ ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል፡፡ ኢትዮጵያ ማለት አዲስ አበባ ማለት እስኪመስል ድረስ (ምናልባትም ከተወሰኑ የቱሪስት ከተማዎች ውጪ) የመንግስትም የህዝብም ንብረት፣ እውቀትና ገንዘብ አዲስ አበባ ላይ እየፈሰሰ ይታያል፡፡ ከሌሎች ከተሞች ጋር ያላት ልዩነትም እያደር በተጋነነ መልኩ እየሰፋ ይገኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዲስ አበባ እጅግ የተጨናነቀች ከተማ ሆናለች፡፡ የከተማዋ ኢንፍራስትራክቸር መሸከም ከሚችለው በላይ ህዝብ እያስተናገደ እንደሆነ የትናስፖርት፣ የገበያ፣ የጤና ተቅዋማት በመሳሰሉ የህብረተሰብ አገልግሎቶች መስጫ ቦታዎች ላይ የሚስተዋለውን ከመጠን ያለፈ ትርምስ እንደምሳሌ መውሰድ ይቻላል፡፡ ይሁንና የተሻለ የስራ እድል፣ የተሻለ አገልግሎቶች እና የተሻለ ብሩህ ተስፋ ይኖራል ተብሎ እስከታሰበ ድረስ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ስደትም፣ ትርምስና መጨናነቁም ይቀጥላል፡፡
.
አንድ ሀገር እድገትን ማስመዝገብ ሲጀምር ከተማዎች ላይ የሚኖረው የህዝብ ቁጥር እየጨመረ ይመጣል፡፡ ስለዚህም የከተማዎች ማደግና መስፋፋት የአንድ ህዝብና ሀገር ተፈጥሮአዊ ሂደት ይሆናሉ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ግን ሚዛናዊ የሆነ የከተማ እድገት ፖሊሲ እስካልተከተልን ድረስ በተለይ እንደኛ ፌደራላዊ ስርአትን እከተላለው በምትል ሀገር ላይ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ችግሮችን መፍጠሩ አይቀሬ ነው፡፡ አሁን የተከሰተው ተቃውሞም የዚህ ማሳያ ነው፡፡ ሌሎች ተወዳዳሪና አማራጭ ከተሞች እንዲመሰረቱ እና እንዲያብቡ፣ ላሉትም በቂ ድጋፍና ማበረታቻዎችን በማድረግ ማሳደግ እስካልተቻለ ድረስ ያልተመጣጠነ የከተማዎች እድገት በተወሰኑት ላይ ጫና በመፍጠር የቀውስ መንስኤ ከመሆን አይወገድም፡፡ መሪዎቻችን የአዲስ አበባ መስፋት የእድገታችን ትሩፋት መሆኑን ሲነግሩን ያልተመጣጠነ የከተማዎች እድገት ያስከተለው ፖሊሲያቸው ደግሞ ሀገሪቱ በታቀደ እና በተጠና መንገድ እየሄደች እንዳልሆነ እንደሚያሳብቅባቸው ልንነግራቸው ይገባል፡፡
.
ህዝብን ያላማከለ ከተሜነት
.
አንድ ገጠራማ የሆነ አካባቢ ወደ ከተማነት ለመቀየር የቦታው ባለቤት የሆኑትን ገበሬዎችንና የመሬት ባለቤቶችን ማፈናቀሉ አይቀሬ ነው፡፡ አዲሱ ማስተር ፕላንም በአዲስ አበባ አካባቢ ያሉ የኦሮሚያ ክልሎችን በስሩ ለማካተት ሲያቅድ ተመሳሳይ ነገር እንዲተገብር ይገደዳል፡፡ ሀብት ንብረቱን የሚያጣው የአካባቢው ነዋሪ በቂ ካሳ ሳይከፈለው ሲቀር ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገባል፡፡ በግብርና ለብዙ ትውልድ ሲተዳደር ለነበረ የህብረተሰብ ክፍል የንብረቱን ተመጣጣኝ የገንዘብ ካሳ ቢሰጠውም እንኳን ህይወቱን ሊለውጥ ይቅርና ባለበት ለማስቀጠል የሚያስችል ከግብርና ውጪ የስራ ክህሎት ይኖረዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ይህም ከተሜነቱ ሀብት ንብረቱን በማሳጣት የኑሮ ደረጃውን ወደታች የማሽቆልቆሉ እድል ሰፊ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህም አይደለም እንደኛ ሀገር በቂ የንብረት ካሳ በማይሰጥበት ሀገር ይቅርና በቂ ካሳ ቢሰጥም እንኳን የገበሬውን ህይወት በነበረበት ለማስቀጠል ተጨማሪ መንግስታዊ ድጋፎችን ይሻል፡፡
.
ለዚህ አዋጭ የሆነው አማራጭ ካሳን በአግባብ ከመክፈል ባለፈ ህብረተሰቡ ሊደረግ በሚታቀደው ልማት ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል ነው፡፡ የለውጡ መሪም፣ ተግባሪም፣ ተጠቃሚም መንግስትና በአካባቢው ያሉ አጃቢዎቹ ሲሆኑ ህብረተሰቡ የሚሰራው ልማት ለእሱ ጥፋት እንደሆነ ቢሰማው ተወቃሽ አይሆንም፡፡ የከተማዎች ግንባታ እንደሚታየው በወረራና በጅምላ በማፈናቀል ሳይሆን ከካሳ ክፍያው በተጨማሪ ህብረተሰቡን ጊዜ ሰጥቶና እድሎችን አመቻችቶ የመታዳደሪያ ምንጩን ከግብርና ወደ ሌላ አማራጮች እንዲቀይር በትምህርት፣ በስልጠና እና በፖሊሲ በመደገፍም መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ሲሆን የከተሜነቱን ሂደት ቀድሞ የነበረውን ነዋሪ ያካተተ በማድረግ ጤናማ የሆነን ኢኮኖሚና ማህበረሰብን ለመገንባት ያግዛል፡፡
.
ህገ-መንግስታዊ እክል

.
ሀገራችን በፌደራላዊ ስርአት በተግባርም ባይሆን መተዳደር ከጀመረች ሃያ አምስት አመት ሊሞላት ነው፡፡ ፌደራላዊ ስርአት ሲባል የተለያዩ ራስ ገዝ የሆኑ አስተዳደሮች/ክልሎች በበጎ ፈቃድ አንድ ላይ ብንሆን የተሻልን እንሆናለን ብለው በማመን በጋራ ስምምነት ላይ የተመሰረተ የራስ ገዝ ግዛቶች ስብስብ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባለው ህገ መንግስት ደግሞ ከብዙ ሀገራት በተለየ መልኩ የመገንጠልን ነፃነት መጨመሩ ክልሎችን የራስ ገዝ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል፡፡ በክልሎች መካከልም ያለው ወሰን በሀገራት መካከል እንዳለ ወሰን ጠንካራ ያደርገዋል፡፡ በዚህ አግባብ ውስጥ የአዲስ አበባ አስተዳደርን የኦሮሚያ አዋሳኝ ከተሞችን በስሩ ለማካተት ማሰቡ በመርህ ደረጃ የሌለ ሀገርን ግዛቶች ከመውረር ጋር ተመሳሳይ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ አይደለም ገበሬዎችን ከይዞታቸው ያፈናቅላል፣ ገንዘብ ንብረት አልባ አድርጎ ወደ ድህነት ይወረውራቸዋል፣ በቂ ካሳ አይሰጣቸውም የሚሉ ክርክሮች የፕላኑ አተገባበር ፍትሃዊ በማድረግ ሊቀረፉ ይችላሉ፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ህገ-መንግስታዊ እክል ግን በመርህ ደረጃ አዲስ አበባ እንደዚህ አይነት እቅድም ማውጣት እንደማትችል ያሳየናል፡፡
.
የመፍትሄ አቅጣጫ
.
አዲስ አበባ ታቅዶም ይሆን ሳይታቀድ እያደገችና እየሰፋች ያለች ከተማ መሆኗ ግልፅ ነው፡፡ የከተማዋ አጎራባች ከተሞችም ከከተማዋ ተርፎ እየፈሰሰ ያለው ከተሜነት በከፍተኛ ፍጥነት እየወረራቸው ይገኛል፡፡ ይህንን መስፋፋት መስመር በያዘና በታቀደ መልኩ እንዲፈስ ማድረጉ አስፈላጊነቱ አያጠራጥርም፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ግን ያለው የአገሪቱ ፌደራላዊ አወቃቀርና ከዚህ በፊት የነበሩ የተመሳሳይ እቅዶች አፈፃፀም የነበራቸው መጥፎ አሻራዎች ከፍተኛ እክል ሆኖበት ይገኛል፡፡ በሀገሪቱ ለሁለተኛ ጊዜ የተቀሰቀሰውም ተቃውሞ በትክክልም ህገ መንግሳታዊ እና ሞራላዊ መሰረት እንዳለው ከዚህ አንፃር በግልፅ ማየት ይቻላል፡፡ የእንደዚህ አይነት ሁለት ፌደራላዊ ግዛቶችን የሚያካትት እቅድ በሁለቱ ከተሞች ህዝቦችና አስተዳደሮቻቸው ስምምነት እና ትብብር መተግበራቸው የግድ ይላል፡፡
.
ሁለቱ ክልሎች ተባብረውና ተናበው እስከሰሩ ድረስ የአዲስ አበባ አጎራባች ከተሞች የግድ አዲስ አበባ ውስጥ መካተት አለባቸው ማለት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ከመናዱም በላይ አላስፈላጊ ግትርነት ነው፡፡ የአካባቢዎቹን ልማት በኦሮሚያ ውስጥ ማድረጉ የሀገሪቱን የከተማዎች ስብጥር የተሻለ እንዲሆን የሚያደርገው ሲሆን አተገባበርም ላይ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌን እንዳይጥስ ያደርገዋል፡፡ ከተሜነቱን ተከትሎ የሚገኘውም ገቢ በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ በክልሉ ውስጥ ለሌላ ልማታዊ ስራዎች ጥሩ የገቢ ምንጭ ይሆናል፡፡ ከዚህ መሰረታዊ ለውጥ በተጨማሪ በከተማ መስፋፋቱ ለሚፈናቀሉ ገበሬዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች በቂ ጊዜ በመስጠት ህይወታቸው መስተጓገል ሳይደርስበት ወደ አዲሱ ህይወት እንዲሸጋገሩ ማገዙ ግድ ይላል፡፡ ልማት ህግን አክብሮ እና ህዝብን ተጠቃሚ አድርጎ ሲመሰረት ዘላቂነቱም ቅቡልነቱም ሰፊ ይሆናል፡፡

The post ማስተር ፕላኑና ተቃውሞው፡- የፖሊሲ ግድፈቶችና የመፍትሄ ሀሳብ! appeared first on Zehabesha Amharic.

በማረሚያ ቤት አለመኖራቸው በተገለጸው አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ

$
0
0
Andargachew

ንዳርጋቸው ጽጌ

በሽብር ድርጊት ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ተመሥርቶባቸው ማረሚያ ቤት በሚገኙት በእነ ዘመኑ ካሴ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት በተቆጠሩት የግንቦት ሰባት አመራር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣

በመከላከያ ምስክርነት እንዳይቀርቡ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ይግባኝ ኅዳር 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ውድቅ ተደረገ፡፡

ተከሳሾቹ ከተመሠረተባቸው ክስ አንዱ የግንቦት ሰባት አመራር ከነበሩትና ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ከየመን ወደ አስመራ ሊሄዱ ሲሉ ከሰንዓ አውሮፕላን ማረፊያ ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ከተሰጡት አቶ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተው መመርያ መቀበላቸውን የሚመለከት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም አቶ አንዳርጋቸው በፌዴራል ማረሚያ ቤት ስለሚገኙ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው፣ ክሱን እየመረመረ ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት አመልክተው ፍርድ ቤቱም ተቀብሏቸዋል፡፡

የተከሳሾቹን አቤቱታ በመቃወም ለፍርድ ቤቱ ያመለከተው ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ፣ አቶ አንዳርጋቸው በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብና በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የክስ መዝገብ የዕድሜ ልክና ሞት ፍርደኛ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ምስክርነት ለመስጠት እንደማይችሉና መብታቸው የተገፈፈ መሆኑን አስረድቶ ተቃውሞ ነበር፡፡ ነገር ግን ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን አቶ አንዳርጋቸው መብታቸው የተገፈፈው ስለራሳቸው እንጂ ስለሌሎች ምስክርነት መስጠት ስላልሆነ ሊመሰክሩ እንደሚገባ ገልጾ፣ የዓቃቤ ሕግን ማመልከቻ ውድቅ በማድረግ ቀርበው እንዲሰሙ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡

አቶ አንዳርጋቸውን በመከላከያ ምስክርነት እንዲያቀርብ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ታዞ የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠት ሳያቀርባቸው ቢቆይም፣ ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ደብዳቤ ግን ‹‹አቶ አንዳርጋቸው ማረሚያ ቤት የሉም፤›› ብሎ መግለጹ ይታወሳል፡፡

ተከሳሾቹ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ በመቃወም አቶ አንዳርጋቸው አገር ውስጥ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉና በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር እንደሚያውቁ በመጠቆም፣ ለእነሱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ተመካክሮ እንደሚያሳውቃቸው ገልጾ በቀጠሮ ላይ እንዳሉ፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ አቶ አንዳርጋቸው በመከላከያ ምስክርነት ሊቀርቡ እንደማይገባ ለሥር ፍርድ ቤት ያመለከተበትን ምክንያት ጠቅሶ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ መርምሮ በሰጠው ብይን በፍርድ ቤት እንዲቀርብ የታዘዘ ምስክር ‹‹ይቅረብ አይቅረብ›› ተብሎ ይግባኝ ሊባል እንደማይቻል በመግለጽ፣ የዓቃቤ ሕግን ይግባኝ እንዳልተቀበለው አስታውቋል፡፡
የጠቅላይ ፍርድ ቤትን ውሳኔ የተቃወመው ዓቃቤ ሕግ፣ መሠረታዊ የሕግ ጥሰት መፈጸሙን በመጥቀስ ለሰበር ሰሚ ችሎት ማመልከቻ ማቅረቡን ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post በማረሚያ ቤት አለመኖራቸው በተገለጸው አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረው ሱዳናዊ ተከሰሰ

$
0
0

ETከቻድ ዋና ከተማ እንጃሚና ወደ አዲስ አበባ መንገደኞችን አሳፍሮ ይበር በነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ፣ ተጓዦችን በመደብደብ ወንጀል የተጠረጠረው የሱዳን ዜጋ ክስ ተመሠረተበት፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተበት ሱዳናዊው አህመድ አልሼክ እድሪስ የ19 ዓመት ወጣት ሲሆን፣ ጥቅምት 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በበረራ ላይ በነበረው የበረራ ቁጥሩ ኢት-938 የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ፣ ሆን ብሎ ሚስተር አርክ ምርዶቻይን የተባሉ የእስራኤል ዜጋን መደብደቡን ዓቃቤ ሕግ የመሠረተው ክስ ያስረዳል፡፡

ወጣቱ ሱዳናዊ ሆን ብሎና የኃይል ድርጊት ለመፈጸም አስቦ ባደረገው የድብድብ ድርጊት፣ ተሳፋሪው ከመጐዳታቸውም በተጨማሪ ሌሎች መንገደኞችን ከፍተኛ ሥጋት ውስጥ ከቶ እንደነበር ክሱ ይገልጻል፡፡

በወቅቱ በበረራ ላይ የነበረው አውሮፕላን ውስጥ ችግር ይፈጠራል የሚል ሥጋት በሁሉም መንገደኞች ውስጥ የተፈጠረ ቢሆንም፣ በመንገደኞቹ ዕርዳታና በተደብዳቢው ግለሰብ ትዕግሥት አውሮፕላኑ በሰላም ማረፉ ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ግለሰቡ በፈጠረው የሚበር አውሮፕላንን ሥጋት ውስጥ የመጣል ወንጀል መከሰሱን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡ ተከሳሹ ዋስትና ተከልክሎ በማረሚያ ቤት ሆኖ ክሱን እንዲከታተል ፍርድ ቤቱ በማዘዝ፣ ለየካቲት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረው ሱዳናዊ ተከሰሰ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live