Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የባሌ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲቃወሙ አመሹ * በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የፌደራል ፖሊስ የፈጸመውን ግድያ አወገዙ

0
0
ፎቶ ከፋይል

ፎቶ ከፋይል

(ዘ-ሐበሻ) የአዲስ አበባን አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም የተነሳው የሕዝብ ቁጣ ወደ ተለያዩ ከተሞች እየተዛመተ ሲሆን የመንግስት ሚድያዎች በበኩላቸው ምንም እንዳልተፈጠረ መረጃዎቹን በማፈን ስለ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እያወሩ ይገኛሉ::

በሃሮማያ ዪኒቨርሲቲ የተማሪዎቹን ሰላማዊ ጥያቄ ፖሊስ በኃይል ለመበተን ባደረገው ጥረት ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸውን ዘ-ሐበሻ ቀደም ብላ መዘገቧ የሚታወስ ሲሆን ይህን ተከትሎም በባሌ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ አመሻሹ ላይ ተማሪዎች ቁጣቸውን መግለጻቸው ተሰምቷል::

በመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ቁጣቸውን ከገለጹ በኋላ ወደ መኝታቸው እንደሄዱ የገለጹት ምንጮቻችን በተለይ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ በመንግስት ኃይሎች የተወሰደውን እርምጃ ተቃውመዋል::

መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚገኝ የሚገልጹት ምንጮች አካባቢው በፖሊስ መወረሩም ተዘግቧል::

The post የባሌ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲቃወሙ አመሹ * በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የፌደራል ፖሊስ የፈጸመውን ግድያ አወገዙ appeared first on Zehabesha Amharic.


የኢትዮጵያዊቷ “ባለህ ነገር አመስግን”ባለች ከቀናት በኋላ በሜሪላንድ ሕይወቷ አለፈ

0
0

 

 

ethiopia yesew lik

(አድማስ ራድዮ) ሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ ነዋሪ የሆነችው የሰውልክ እንዲህ ነው፣ ህይወቷ ያለፈው ትናንት ሰኞ፣ ኖቬምበር 30 ቀን ሌሊት 3 ሰአት ላይ ነው። የዜና አውታሮች እንደዘገቡት፣ እሷና አብሯት ያለ ሰው ቼሪ ሂል የተባለ መንገድ መታጠፊያ ላይ ሲደርሱ፣ ትልቅ የፖስታ ቤት ትራክ ከሌላ አቅጣጫ በመምጣቱ ሊጋጩና ትራኩም የነ የሰውልክ ኢንፊኒቲ መኪና ላይ በመውደቁ ነው። አብሯት የነበረውና ስሙ ያልተገለጸው ወጣት ፣ እንዲሁም የፖስታ ቤቱ ትራክ ሾፌር ተጎድተው ሆስፒታል ናቸው።

የሰውልክ እንዲህነው፣ ባለፈው ዓመት ከሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ በጤና ትምህርት ተመራቂ ነበረች። ከመሞቷ ከሁለት ቀን በፊት የመጨረሻዋ የነበረው የፌስ ቡክ ገጿ ጽሁፍ “ባለህ ሁሉ አመስግን፣ መልካም የምስጋና ቀን” የሚል ነበር።

በደጀን ከተማ የመጀመሪያው ዘመናዊ ሆቴል ባለቤት ልጅ ናት:: የሰውልክ እንዲህነው ትዝአለ የ24 ዓመት ወጣትና ከ6 ወር በፊት ከሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ በዲግሪ የተመረቀች ነበረች።

በዚህች ወጣት ሕይወት ማለፍ የተሰማቸውን ሃዘን ከገለጹት መካከል አንዱ አርቲስት መስፍን በቀለ ይገኝበታል:: መስፍን በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን መል ዕክት አስተላልፏል::

እኔ ይህንን አምኖ ለመቀበል አልቻልኩም። የሰው ልክ እንደ ስምሽ የሰዋችን ልክ የምታውቂ፣ አንድ ሰው ህይወቱ ሲያልፍ መባል ስላለበት ብቻ ሳይሆን መናገር የምፈልገው እንደው ስላንቺ እንደ ሰው ከብዙዎቹ በጥቂቱ…..በህይወት በዚህች ምድር ላይ በቆይሽባቸው ዘመኖችም ሆነ ከኔም ጋር እስከተዋወቅንባቸው ዓመታት ድረስ በጣም የሚደንቅ እና እጅግ የሚወደድ በሀሪ ያላትና፣ሰው የምትወድ፣ የምታከብር፣ እጅግ ሲበዛ ሀይማኖተኛ፣ቤተሰቦን አክባሪ፣እንዲህ ነው ተብሎ ተነግሮ የማያልቅ ዓላማና በ ዓይን የሚታይ ተስፍ ያለት፣ለ ጎደኝነት ትልቅ ቦታ የምትሰጥ፣ ከፀብ ይልቅ ፍቅርን የምታስቀድም፣እንደ ስሟ የኖረች፣” የሰውልክ” ትናንትን ያልጥገበች፣መሽቶ እሲኪነጋ ብዙ ስራዎችን ለመስራት የምትጎጏ ነበረች። ከእንግዲህ ወድያ ነች እያልን ሳይሆን: ነበረች እያልን: ልንመሰክርላት: በደረሰባት ከባድ ድንገተኛ የመኪና አደጋ አተንናታል። ይህ ባይሆን መልካም ነብር.!!! እግዚአብሔር ግን በባህሪው ስተት የሌለበት አምላክ ነውና። ይህ ለምን ሆነ ተብሎ እሱን መውቀስ አይቻልም እና። አንተ ባለህ ጥበብ ባለህ ፀጋ ቤተሰቦቾንም ወዳጅ ዘመዶቾንም ታፅናናልን እና ታበረታልን ዘንድ የ እህታችንንም ነብስ በገነትህ ታኖርልን ዘንድ እንለምንሀለን አሜን።።።

The post የኢትዮጵያዊቷ “ባለህ ነገር አመስግን” ባለች ከቀናት በኋላ በሜሪላንድ ሕይወቷ አለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

በጎንደር እስር ቤት ተቃጠለ * እስረኞች እያመለጡ ነው * የሞቱም የተጎዱም አሉ ተብሏል

0
0

gonder
(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ከተማ የሚገኘው ትልቁ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የ እሳት ቃጠሎ ተነስቶ እስረኞች እያመለጡ
መሆኑ ተሰማ:: የዘ-ሐበሻ የጎንደር ምንጮች እንደዘገቡት በከተማዋ ከፍተኛ የጥይት ድምጽ ይሰማል::

በጎንደር ከተማ የሚገኘው ባህታ የተሰኘው ወህኒ ቤት የተነሳው የ እሳት ቃጠሎ መነሻ ያልታወቀ ሲሆን ቃጠሎው በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ በርካታ እስረኞችን እንዲያመልጡ ምክንያት ሆኗቸዋል:: በተለይ ከግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተፈርዶባቸው የነበሩ እስረኞች ማምለጣቸው በተለይ በቂም በቀል በሚፈላለጉ ቤተሰቦች ላይ ትልቅ የሆነ ፍራቻን እንደሚፈጥር አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::

ፖሊስ እያመለጠ የሚገኘውን እስረኛ ለማስቆም በሚተኩሰው ጥይት ከተማዋ በከፍተኛ ሁኔታ መረበሿን የሚጠቁሙት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች እስካሁን ወደ 380 የሚጠጉ እስረኞች ማምለጣቸውን ገምተዋል:: ፖሊስ በሚተኩሰው ጥይት የተጎዱ እስረኞች በአካባቢው በሚገኙ የጤና ጣቢያዎች ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቁ እስረኞችም ሊያመልጡ ሲሉ መገደላቸው ተሰምቷል:

በሌላ በኩል በእሳት ቃጠሎው ምክንያት ከእስር ክፍላቸው መውጣት ያልቻሉ እስረኞች የቃጠሎ ጉዳት እንደደረሰባቸው ምንጮቻችን ገልጸዋል::

The post በጎንደር እስር ቤት ተቃጠለ * እስረኞች እያመለጡ ነው * የሞቱም የተጎዱም አሉ ተብሏል appeared first on Zehabesha Amharic.

(ይናገራል ፎቶ) የፌደራል ፖሊስ ወረራ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ

0
0

የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያነሱትን ሰላማዊ ጥያቄ ፖሊስ በሃይል ለመግታት በመሞከሩ 3 ሰዎች መሞታቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ዘ-ሐበሻ ትናንት መዘገቧ አይዘነጋም:: ፖሊስ በዩኒቨሪስቲው ውስጥ ያደረገውን ወረራ የሚያሳዩ ምስሎች ተለቀዋል – ለግንዛቤ እነሆ::
haromaya 2 haromaya jawar

The post (ይናገራል ፎቶ) የፌደራል ፖሊስ ወረራ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ appeared first on Zehabesha Amharic.

(ይናገራል ፎቶ) በጎንደር ቤቱ ከተቃጠለ በኋላ አካባቢው በፌደራል ፖሊስ ታጥሯል

0
0

(ዘ-ሐበሻ) ከሰዓታት በፊት ጎንደር ከተማ ውስጥ ባታ የተሰኘው እስር ቤት ተቃጥሎ በርካታ እስረኞች ማምለጣቸውን እና የቆሰሉና የሞቱ ሰዎች እንዳሉ ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል:: ከጎንደር አካባቢ ለዘ-ሐበሻ የተላኩ ፎቶዎች እንደሚያሳዩት ፌደራል ፖሊስ ከተማዋን እያሸበረው ይገኛል:: በየቦታው ፖሊስ ሰፍሮ አካባቢውን በማሰስ ላይ ሲሆን ያመለጡ እስረኞችን ለመያዝም የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ:: ዘ-ሐበሻ የሟቹቹን ቁጥር ለማጣራት እየሞከረች ነው:: እስከዚያው የጎንደር ከተማን የዛሬውን ውሎዋን የሚያሳዩ 3 ፎቶዎች ይመልከቱ::

gonder 2 gonder 4 gonder

The post (ይናገራል ፎቶ) በጎንደር ቤቱ ከተቃጠለ በኋላ አካባቢው በፌደራል ፖሊስ ታጥሯል appeared first on Zehabesha Amharic.

አርበኞች ግንቦት 7 ዛሬ ዋልድባ ላይ መዋጋቱንና ጉዳት ማድረሱን ገለጸ * 29 ወታደሮችን ገደልኩ አለ

0
0

birhanu nega

(ዘ-ሐበሻ) መነሻውን ኤርትራ ያደረገው አርበኞች ግንቦት 7 ከቀናት በፊት በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር አካባቢ በሚገኙ ከተሞች በምሽት ቀስቃሽ ወረቀቶችን ሲበትን መክረሙን ከገለጸ በኋላ ዛሬ በለቀቀው መረጃ ዋልድባ ላይ ከመንግስት ኃይሎች ጋር መዋጋቱን ገለጸ::

ዘ-ሐበሻ ከአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ያገኘችው መረጃ እንደሚጠቁመው ሰራዊቱ ዛሬ ዲሴምበር 1, 2015 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ከመንግስት መከላከያ ሰራዊት እና ልዩ ጦር ጋር ተዋግቶ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ነው:: ከመንግስት በኩል ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ስለመዋጋቱ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተሰጠ መግለጫ የለም::

የአርበኞች ግንቦት 7 በራድዮው በኩል እንዳሰራጨው መረጃ በድንገት በከፈትኩት ጥቃት ዋልድባ ላይ ለሰዓታት ያህል ሰራዊቴ ሲዋጋ ውሎ በትሹ 29 ወታደሮችን ገድያለው እንዲሁም ከ40 በላይ ደግሞ አቁስያለሁ ብሏል::

The post አርበኞች ግንቦት 7 ዛሬ ዋልድባ ላይ መዋጋቱንና ጉዳት ማድረሱን ገለጸ * 29 ወታደሮችን ገደልኩ አለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የዛሬዉ የአዉሮፓ ሕብረት ንግግራቸዉ – VOA

0
0

nega
(VOA Amharic) የአርበኞት ግንቦት ሰባት መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ብረስልስ ቤልጄም በሚገኘዉ የአዉሮፓ ፓርላማ በኢትዮጽያ ስለተከሰተዉ ድርቅና ረሃብ ማብራሪያ መስጠታቸዉ ታዉቋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያን መንግሥት በትጥቅ ከሥልጣን የማዉረድ ዓላማ ያነገበዉን ግንቦት ሰባት በመምራት በጎሬቤት ኤርትራ እንደሚገኙ የሚታወቀዉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ስብሰባዉን ባዘጋጁት የፓርላማዉ አባላት እንደተጋበዙ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ አሁን በድርቅ ምክንያት ስለተከሰተዉ የምግብ እጥረት ያደረጉት ንግግርም ድርቅ ተፈጥሮአዊ ክስተት፣ ረሃብ ግን የመንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ዉድቀት መሆኑን የሚያመለክት ነዉ ብለዋል።

“ከኢትዮጵያ ረሃብን ማስወገድ ከባድ አይደለም” ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ፤ መንግሥት ሁሉን ነገር የመቆጣጠር አባዜ ይዞታል፣ገበሬዉን መፈናፈኛ አሳጥቶ ከእለት ጉርስ ያለፈ የኢኮኖሚ ሕይወት እንዳይኖረዉ አድጓል” ብለዋል፡፡ አያይዘውም እየጨመረ የሄደዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛትና እንዲሁም ፤ ኬሚካል ማዳበሪያ እየፈጠረ ያለዉ ችግር እንደ ምግብ እጥረት ምክንያትነት ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የአሁኑን ድርቅ ኢልኒኖ የተባለዉ የአየር መዛባት እንዳስከተለዉና እስካሁን ድርቁ ባሰከተለዉ ረሃብ የሞተ ሰዉ እንደሌለ ለአስቸኳይ ጊዜ የመደበዉን ርዳታም ድርቅ ላጠቃዉ ሕዝብ እያደለ መሆኑን ይናገራል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የዛሬዉ የአዉሮፓ ሕብረት ንግግራቸዉ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፓለቲካ ጉዳዮችም ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ለለዉጥ አሻፈረኝ በማለት ተቃዋሚዎች ጋር የገባዉ ፍጥጫ ለአዉሮፓ ሕብረት አሳሳቢ በመሆኑ አባላቱ ሰለ ወቅታዊ የአገሪቱ የፓለቲካ ሁኔታም እንደተወያዩ ተናግረዋል።

ቃለ-ምልልሱን ለመስማት የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

The post የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የዛሬዉ የአዉሮፓ ሕብረት ንግግራቸዉ – VOA appeared first on Zehabesha Amharic.

የመምህር ግርማ ወንድሙ አዲሱ የግድያ ወንጀል መጠርጠር ክስ ከየት መጣ? |የጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ ትንታኔ በድምጽ

0
0

በመንፈሳዊ አባትነታቸውና አጥማቂነታቸው የሚታወቁት መምህር ግርማ ወንድሙ ላይ ከዚህ ቀደም የስምንት መቶ ሺህ ብር አጭበርብረዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው የነበረ ሲሆን ፖሊስ ክሱን በበቂ ሁኔታ ሊያሳምን ባለመቻሉ በዋስ እንዲለቀቁ ተወስኖ ነበር። ከመጀመሪያም በመምህሩ መያዝ ላይ አንዳች ጥርጣሬ ያደረባቸው አንዱ ክስ ሲወድቅ ሌላ መምጣቱ የበለጠ ጥርጣሬያቸውን አጠናክሯል። በተለይም አስቀድሞ በዘሐበሻ እንደተዘገበው የተደበቀው በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ ማሰብ – ይፋ ሆኗል። አዲሱ ክስ ከየት መጣ!? ወቅታዊ ጉዳዩን ጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ በሕብር ራድዮ ዳሶታል – ያድምጡት::

The post የመምህር ግርማ ወንድሙ አዲሱ የግድያ ወንጀል መጠርጠር ክስ ከየት መጣ? | የጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ ትንታኔ በድምጽ appeared first on Zehabesha Amharic.


Sport: በቼልሲ ዙሪያ የተዘጋጀ ልዩ ዘገባ |ጉስ ሂድኒክ የቼልሲ ስራን ለመያዝ ተዘጋጅተዋል

0
0

ቼልሲ ያለፈውን የውድድር አመት ያጠናቀቀው ሁለት የዋንጫ ሽልማቶችን በማግኘት ማለትም ለፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር በመብቃትና የካፒታል ዋን ውድድር ድልን በመቀዳጀት ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን በእነዚህ ሁለት ውድድሮች የዋንጫ ሽልማቶችን የማግኘት ተስፋው ዝቅተኛ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም ከስቶክ ሲቲ በመለያ ምት ተሸንፎ የካፒታል ዋን ውድድር ዘመቻውን ወደ ሩብ ፍፃሜው ደረጃ ለማሸጋገር ሳይችል ቀርቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከሊጉ መሪዎች ማንችስተር ሲቲና አርሰናል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት 11 በመሆኑም የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ክብሩን የማስከበሩ ተስፋ ዝቅተኛ ሆኗል፡፡
chealsea

ይህንን እውነታን ከግንዛቤ በማስገባትም በፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ምትክ የቼልሲ ስራን ለመረከብ በግንባር ቀደምትነት ሆላንዳዊው ጉስ ሂድንኪና ጣሊያናዊው ካርሎ አንቾሎቲ ታጭተዋል፡፡ የእነዚህ ሁለት ባለሙያዎች ስም ከቼልሲ ስራ ላይ እንዲያያዝ በዋነኝነት የሚጠቀሰው ምክንያት ሁለቱም በአሁኑ ወቅት ካለስራ መቀመጣቸው ነው፡፡ በተለይም ከዚህ በፊት ቼልሲን ለአጭር ጊዜ በተጠባባቂ ዋና አሰልጣኝነት የመሩት ጉስ ሂድኒክ ከሰሞኑ በሰጡት አንድ መግለጫቸው በሞውሪንሆ ምትክ የቼልሲ አዲሱ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ለመሾም ዝግጁ መሆናቸውን የሚጠቁም ሆኗል፡፡

ሂድንኪ የፊታችን ሰኔ ወር በፈረንሳይ አዘጋጅነት ለሚካሄደው ዩሮ 2016 ውድድር የሆላንድ ብሔራዊ ቡድንን ተሳታፊ የማድረግ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለመፈፀም ስለተሳናቸው ከአሰልጣኝነት ራሳቸውን ማግለላቸው ይታወቃል፡፡ በሰሞኑ መግለጫቸው ለ2ኛ ጊዜ ሊመሩት መመኘታቸውን የጠቆሙት ቼልሲን በ2009 ለስድስት ወራት ያህል በተጠባባቂ ዋና አሰልጣኝነት በመምራት ለኤፍ.ኤ.ካፕ ድል ያበቁት ከመሆኑም ባሻገር በፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ፉክክሩ እስከመጨረሻዎቹ ጥቂት ሳምንታት ድረስ በጠንካራ አቋም ሆኖ ለመዝለቅ እንዲችል ረድተውት ነበር፡፡

ያንን መልካም ጊዜቸውን መለስ ብለው በማስታወስ ሂድኒክ ደግሞ የቼልሲ ስራን ለመያዝ መመኘታቸውን የጠቆሙበት መግለጫን ሲሰጡ ተደምጠዋል፡፡ ‹‹ፉትቦል ኢንተርናሽናል›› የተባለው የሆላንድ ጋዜጣ ከሰሞኑ ‹‹ከስድስት ዓመታት በኋላ ወደ ቼልሲ በመመለስ በዋና አሰልጣኝነት የመስራት ፍላጎቱን አሳድረዋል በሚል ላቀረበላቸው ጥያቄ ሂድኒክ ምላሻቸውን ሲሰጡ የተደመጡት ‹‹በትልቅ ደረጃ በሚደረግ ውድድር የሚሳተፍ ትልቅ ክለብን በዋና አሰልጣኝት የመምራት ፍላጎትን የማሳደር ባህል አለኝ፡፡ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በርካታ ጥሪዎችንም ቀርበውልኛል፡፡ የቀረበልኝ ጥሪዎችን ሳልቀበላቸው የቀረሁት የትልቅ ክለብ ሥራን ለመያዝ በመመኘት ነው፡፡ ለምሳሌ እንደ ቼልሲ አይነቱ ትልቅ ክለብ ጥያቄ የሚያቀርብልኝ ከሆነ ካለምንም ማመንታት መልሴን የምሰጠው እንደሚሆን አልደብቅም፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ቀጣዩ ሥራዬ ምን እንደሚሆን እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ጉዳይ የለኝም›› በማለት ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት ዕድሜያቸው 68 የደረሰው ሂድኒክ ከዚህ በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ የቼልሲ ስራን በፌብርዋሪ 2009 የተረከቡት የብራዚሉ አሰልጣኝ ሉዊስ ፍሊፕ ስኮላሪ ለሰባት ወራት ከዘለቁበት የስታምፎርድብሪጅ ስራ መነሳትን ተከትሎ ነበር፡፡ ሃዲንኪ ስታምፎርድ ብሪጅ እንደደረሱም ቼልሲ እስከሲዝኑ መጋመስ ድረስ የነበረው የአቋም አለመረጋጋት የ2008-09 ሲዝን ዘመቻውን በፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ በ3ኛ ስፍራ ላይ ተቀምጦ እንዲጨርስ አስችለውታል፡፡

የቻምፒዮንስ ሊግ ዘመቻውን እስከ ግማሽ ፍፃሜው ደረጃ ድረስ ለመዝለቅ እንዲችልም አድርገውታል፡፡ በወቅቱ በቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የደርሶ መልስ ግጥሚያ ቡድናቸው በባርሴሎና በአጠቃላይ ውጤት ተሸንፎ በሮም ከተማ ከተደረገው የውድድሩ ፋይናል የቀረውን ግልፅ የሆኑ የዳኝነት በደሎች ተፈጽሞበት እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ሂድኒክ ያንን ፀፀታቸውን ግን በሜይ 2009 በዌምብሊ ስቴዲየም ከኤቨርተን ጋር የተደረገው የኤፍ.ኤ.ካፕ ፋይናልን 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫውን ሽልማትን በማግኘት በመጠኑም ቢሆን ሊረሱት ችለዋል፡፡ ይህ የሚያሳየው ሂድኒክ ቼልሲን ለአጭር ጊዜ በተጠባባቂ አሰልጣኝነት በመሩበት ግማሽ ሲዝን ለቡድኑ ጠንካራ አቋምን አስገኝተውለት እንደነበር ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የቼልሲው ባለቤት ሮማን ኢብራሞቪች በሚጠበቀው መልኩ ጆሴ ሞውሪኖን ከስራቸው ካነሷቸው ጉስ ሂድኒክን አዲሱ የክለባቸው ዋና አሰልጣኝ አድርገው መቅጠርን በቅድሚያ ምርጫቸው ቢያደርጉት አስገራሚ ሊሆን አይችልም፡፡
mourinho

ሂድኒክ የ2008-09 ሲዝን ከተጋመሰ ወዲህ የቼልሲን ስራ ተረክበው የቡድኑ ያልተረጋጋ አቋምን በፍጥነት ለማረም የቻሉበትን ያንን ተደናቂ ተግባራቸውን በማስታወስ በርካታ የፉትቦል ተንታኞች በዘንድሮ ሲዝን የቼልሲ የእስካሁን ችግሮች ትክክለኛው የመፍትሄ እርምጃን ሊያበጁለት የሚችሉበት ተደናቂ ተሰጥኦን ተላብሰዋል የሚል እምነት አሳድረውባቸዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር ለበርካታ ዓመታት በዘለቀው የአሰልጣኝነት ሙያቸው በርካታ ክለቦችና የተለያዩ አገሮችን ብሔራዊ ቡድኖችን በዋና አሰልጣኝነት የመሩት ሂድኒክ በቼልሲ ደጋፊዎችና በክለቡ አባላት በጠቅላላ እስካሁንም ድረስ ከፍተኛ የሆነ ከበሬታን አሳድረው ዘልቀዋል፡፡

‹‹እንደ ቼልሲ ያለው ትልቅ ውድቀትን በሌላ ክለብ አላስታውስም››
አለን ሽረር
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆሴ ሞውሪኖ ባለፈው ሲዝን ቼልሲ ከፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ጋር ያገናኙት ሙሉው ሲዝንን በደረጃው ሰንጠረዥ አናት ላይ በማስቀመጥና የቅርብ ተቀናቃኙ ማንችስተር ሲቲን በስምንት ነጥቦች በልጦት እንዲጨርስ በማስቻል ነው፡፡ በዘንድሮው ሲዝን ግን ገና የመጀመሪያዎቹ 10 የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች ከመደረጋቸው ከሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ በ11 ነጥቦችና በአስር ደረጃዎች ላይ ተቀምጦ ይገኛል፡፡
ከእስካሁኑ 10 የሊጉ ግጥሚያዎች 15 ጎሎችን አስቆጥሮ መረቡን በ19 ጎሎች ማስደፈሩም ሌላው የቼልሲ አስደንጋጭ የአቋም መውረድ ችግር እንዲከሰትበት የሚያሳይ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ አንዱ ምክንያት አብዛኛዎቹ የቡድኑ ተሰላፊዎች አቋም ወርዶ መገኘት ነው፡፡ ባለፈው ሲዝን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ድሪም ቲም ምርጫ ከተካተቱት 11 ተጨዋቾች ውስጥ ስድስቱ የቼልሲ ተጨዋቾች ነበሩ፡፡ በዘንድሮ ሲዝን ግን አንድም በጥሩ አቋም ሊጠቀስ የሚችል ተጨዋች እስከመጥፋት ደረጃ ደርሷል፡፡

እነዚህ እውነታዎችን በመተንራስ የቀድሞው የኒውካስል ዩናይትዱ ስታር አለን ሽረር ሰሞኑን በሰነዘረው አስተያየቱ የቼልሲ በፍጥነት የአቋም መውረድን ‹‹ከዚህ በፊት በሌላ ክለብ ያልታየ አስደንጋጭ አጋጣሚ›› በማለት ገልፆታል፡፡ የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ የአጥቂ መስመር ተጨዋች በመቀጠልም ‹‹እኔ እስከማስታውሰው ድረስ እንደ ቼልሲ ሁሉ በጥቂት ወራት ውስጥ ከነበረበት ትልቅ አቋም በፍጥነት ሙሉ ለሙሉ ወደ ታች የወረደ ክለብ በእንግሊዝ ክለብ አልታየም፡፡ የቼልሲ በአስደንጋጭ ሁኔታ ወርዶ መገኘት በክለቡ ውስጥ አንድ ግልፅ ያልታየ ከፍተኛ ችግር ተፈጥሯል የሚል ጥርጣሬን እንዳሳድር አስገድዶኛል፡፡ ከእነዚህ ችግሮች ውስጥ ምናልባትም አንዱ ሞውሪንሆ በስኳዳቸው የሚመኙት ትክክለኛዎቹ ተጨዋቾች አለማግኘታቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ማንኛውም የፉትቦል አፍቃሪና አስተያየት ሰጪ ቢሆን በዘንድሮው ሲዝን በቼልሲ ላይ የተፈጠረውን መሰረታዊ ችግሮች ምንነትን በትክክል ይረዳዋል የሚል እምነት በጭራሽ የለኝም›› የሚል አስተያየት ሰጥቷል፡፡

የስፖርትስ ሜይል የፉትቦል ተንታኞች በበኩላቸው ጆሴ ሞውሪኖ በኦገስት ወር በቼልሲ የዘንድሮ ሲዝን የመጀመሪያው ከስዋንሲ ሲቲ ጋር 2ለ2 ሲለያይ ለክለባቸው ዶክተር ኢቫ ካርኔሮ ጋር ግጭትን ከፈጠሩ ወዲህ ቡድናቸው ካደረጋቸው ግጥሚያዎች ግማሽ ያህሉን መሸነፉን ከግንዛቤ በማስገባት ከዛ ወዲህ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ላይ የተፈጠሩትን ችግሮችን ከዚህ በታች ባለው መልኩ ዘርዝረዋቸዋል፡፡

ኦገስት 8፡-
ጆሴ ሞውሪኖ የክለባቸው ዶክተር ኢቫ ካርኔሮና ረዳቷን ጆን ፍርንን የሚተች መግለጫን በመስጠት በክለባቸው ችግር እንዲቀሰቀስ በር ከፋች ሆነዋል፡፡ በሞውሪኖና በህክምና ባለሙያዎቹ መካከል ተፈጠረው ግጭት ተካርሮ በመዝለቁ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ በእንግሊዝ ፉትቦል ማህበር እስከመከሰስ ደረጃ ደርሰዋል፡፡ ሆኖም ግን ካርኔሮን በብልግና ቃላት ሰድበዋል በሚል ከቀረበባቸው ክስ ካለምንም ቅጣት አምልጠዋል፡፡ በዚህ በመበሳጨት የህክምና ዶክተሯ በቼልሲ የነበራትን ስራ በራሷ ፈቃድ ለመልቀቅ ወስናለች፡፡

ኦገስት 16
ቼልሲ በኢትሃድ ስቴዲየም በማንችስተር ሲቲ 3ለ0 በተረታበት የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያው ወቅት ጆሴ ሞውሪኖ ባልተለመደ መልኩ የቡድናቸው አምበል ጆን ቴሪን ቀይረው አስወጥተውታል፡፡ ከዛ በኋላ ባሉት ጥቂት ግጥሚያዎች ላይም ቴሪን በመደበኛ ቋሚ አሰላለፋቸው ውጪ በማድረግ የክለባቸው ደጋፊዎችን ቅር አሰኝተዋቸዋል፡፡ ቼልሲ የፕሪሚየር ሊግ ውድድር የመጀመሪያዎቹ ሁለት ግጥሚያዎችን ለማሸነፍ ሲሳነው ዘንድሮ ከድፍን 17 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

ኦገስት 29
ሞውሪኖ ቼልሲን በስታምፎርድ ብሪጅ የመሩበት 100ኛው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያው በሽንፈት ተደምድሟል፡፡ በክሪስታል ፓላስ 2ለ1 የተሸነፈበትን ጨምሮ ሞውሪኖ በራሳቸው ሜዳ ባደረጓቸው 100 የፕሪምየር ሊግ ግጥሚያዎች ሽንፈት ሲደርስባቸው ያ ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ በዛ ግጥሚያ ኮሎምቢያዊው ኢንተርናሽናል ራዳሜል ፉልካኦ ለቼልሲ በውሰት ውል ከፈረመ ወዲህ የመጀመሪያውን ጎሉን ለማስቆጠር ቢችልም በስሙ ያስመዘገባት ጎል ግን ቼልሲን ከሽንፈት ሳታድነው ቀርታለች፡፡

ሴፕቴምበር 13
የሞውሪኖ ቡድን የጉድሰን ፓርክ ስቴዲየም ከኤቨርተን ጋር ያደረገው የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያውን 3ለ1 በሆነ ውጤት በሽንፈት ለማጠናቀቅ ተገድዷል፡፡ በዛ ግጥሚያ የኤቨርተን አጥቂ ስቴቨን ሃይስሚዝ ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ሃትሪክ የሰራው የቼልሲው የተከላካይ መስመር ከተሰለፉት ጆን ቴሪና ለፈረንሳዊው ወጣት ተከላካይ ኩርትዙማ ከአቅማቸው በላይ የሆነ እጅግ ውጤታማ የማጥቃት እንቅሰቃሴን በማድረግ ነው፡፡ እስከዛ ደረጃ ድረስም ቼልሲ በመጀመሪያዎቹ 5 የሊጉ ግጥሚያዎቹ በእያንዳንዱ ላይ ቢያንስ ሁለት ጎሎች ተቆጥረውበታል፡፡ ከአምስቱ ግጥሚያዎች በአጠቃላይ ያገኘው ነጥብ አራት ብቻ ነበር፡፡

ሴፕቴምበር 19
ቼልሲ አርሰናልን 2ለ0 በረታበት የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ ወቅት የቡድኑ የፊት አጥቂ ዲያጎ ኮስታ ከሎረን ኮስኒሌይ ጋር በፈጠረው ግጭት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በእንግሊዝ ፉትቦል ማህበር የሶስት ተከታታይ ግጥሚያዎች የእገዳ ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡ እስከዚህ ጨዋታ ድረስ ኮስታ ከአንድ የፕሪሚየር ሊግ ጎል በስተቀር ለማስቆጠር አልቻለም፡፡ ሆኖም ግን ሞውሪኖ ኮስታ ለሶስት ግጥሚያዎች የታገደበት ውሳኔን በመተቸት በእንግሊዝ ፉትቦል ማህበር ላይ የሰላ ትችትን ሲሰነዝሩ ተደምጠዋል፡፡

ሴፕቴምበር 29
ጆሴ ሞውሪኖ በ2004 ለአውሮፓ ሻምፒዮንነት ክብር ወደመሩት ፖርቶ ሜዳ ተመልሰው ባደረጉት የቻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ ቡድናቸው 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ በዛ ግጥሚያ ሞውሪኖ ኤደን ሃዛርድና ኔማኒያ ማቲችን ለቡድናቸው መደበኛ ቋሚ አሰላለፍ ውጪ ያደረጉበት ተግባር ስህተት የፈፀሙበት ተደርጎ ተቆጥሯል፡፡ ከፖርቶ ጎሎች ለአንዷ መገኘት ጥፋትን የፈፀመው ኩርት ዙማን በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት በማስጀመር ጆን ቴሪን በተጠባባቂ ወንበር ላይ ያስቀመጡበት ተግባራቸውን ለቡድናቸው ሽንፈት ተወቃሽ የሆኑበት ሌላው ጉዳይ ሆኗል፡፡

ኦክቶበር 3
ቼልሲ በሳውዝአምፕተን 3ለ1 በተረታበት የዘንድሮ ሲዝን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር 4ኛው ሽንፈቱ በኋላ ለሞውሪኖ ኃላፊነት ለትልቅ አደጋ ተጋልጧል፡፡ ከግጥሚያው ሶስት ቀናት በኋላ የቼልሲ ቦርድ ባወጣው ይፋዊ መግለጫው ግን ለሞውሪኖ ሙሉ ድጋፍን መስጠትን ምርጫው አድርጎታል፡፡ ሞውሪኖ በሳውዝአምፕተን የተረቱበት ግጥሚያ የመሩት አርቢትር ሮቤርቶ ማድሌይን በይፋ በመተቸታቸው በእንግሊዝ ፉትቦል ማህበር 50 ሺ ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል፡፡

ኦክቶበር 17
ያለፈው ሲዝን የፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጨዋች የሆነው ኤደን ሃዛርድ ቡድናቸው አስቶንቪላን 2ለ0 በረታበት የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ ከመደበኛ ቋሚ አሰላለፋቸው ውጪ አድርገውታል፡፡ በኋላ ላይ በሰጡት መግለጫም የቤልጂየሙ ኢንተርናሽናል የዘንድሮው ሲዝን አቋሙን ከወትሮ በብዙ መልኩ የወረደ በማለት ተችተውታል፡፡

The post Sport: በቼልሲ ዙሪያ የተዘጋጀ ልዩ ዘገባ | ጉስ ሂድኒክ የቼልሲ ስራን ለመያዝ ተዘጋጅተዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የውብ ወገብ ባለቤት የሚደርጉሽ 7 ምስጢሮች

0
0

by Lili Moges

ሴት ከሆንሽ የፋሽን ኢንዱስትሪው በየጊዜው ከሚያቀርባቸው አልባሳት ጋር ለመዋሃድ አካልሽን በሚገባ አስተካክለሽ መጠበቅ ሳያስፈልግሽ አልቀረም፡፡ ለፋሽን ፍላጎቱ ሳይኖርሽ በተገኘው ተሸፋፍኖ መውጣቱን ምርጫሽ ካላደረግሽ በቀር፡፡ ያልተስተካከለው አካላዊ ቅርፃችንን ሲሸፍኑልን ብዙ ምዕተ ዓመታትን ያሻገሩን የባህል ልብሶቻችንም ቢሆኑ እኮ፣ ዛሬ ላይ በፋሽን ኢንዱስትሪው ተመዝግበው ወዝወዝ ለሚሉት ቆነጃጅት እየተዘጋጁ በስፋት እየቀረቡ ነው፡፡ አንቺ የባህል ልብሳችን እንደነበሩ መቆየት አለባቸው ለውጥ ባህላዊነታቸውን ያሳጣቸዋል ከሚሉት ጎራ ከሆንሽና ተቆርቋሪነትሽ ከልብሽ ከሆነ የእኔም ድጋፍ እንዳለሽ እንዳትዘነጊ ነገር ግን ክርክርሽ ከባህሉ ባሻገር ከሆነው ችግሩ፡፡ ተመራማሪዎች ውለው ይግቡና ለችግሮቻችን መፍትሄ የሚሉትን በየጊዜው ያቀርቡልናል፡፡ ለዛሬም የሆድ ቅርፃችንን በመሰረታዊነት ከሚያስተካክሉልን ቀላል ከሚሆኑ መንገዶች ጋር እንተዋወቃለን፡፡
no soda
1.እያወራሽ ተራመጂ

ከጓደኞቻችን ጋር በምግብ እና መጠጥ ክፍለ ጊዜ ብቻ ከመገናኘት የእንቅስቃሴ ወዳጅነት እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ወቅት የግድ ቁም ነገር ያዘሉ ወሬዎችን መወያየት ላይጠበቅብን ይችላል፡፡ የባጥ የቆጡንም እያወራን የእግር መንገድ ብናደርግ የሆዳችን ጡንቻ መስራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ካለን በ10 ፐርሰንት በሰውነታችን የጥንካሬ ላይ ለውጥ እናመጣለን፡፡ እያወሩ የመራመድ እንቅስቃሴን ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ማድረግ በፍፁም መዘንጋት የለበትም፡፡

2. በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ጨምረሽ ተመገቢ፡-
በቀን ቢያንስ 10 ግራም ፋይበር ወደ ሰውነትሽ ብታስገቢ ሆድሽ ከ4 ፐርሰንት በታች ብቻ ፋት ነው የሚሸከመው የፋይበር ክምችትሽን በቀን ውስጥ ሁለት የአፕል ፍሬዎችን፣ ግማሽ ኩባያ ባቄላ ወይም ሁለት ኩባያ አበባ ጎመን በመመገብ የሆድ ቅርፅሽን የሚያስተካክል 10 ግራም ፋይበር ታገኛለሽ፡፡

3. በቃኝን አስቀድሚ፡-

በምግብ ቤቶች ከሴት ጓደኞችሽ ጋር ጠረጴዛ ሞልታችሁ ስትቀመጡና አስተናጋጅ መጥቶ ተጨማሪ የምግብ ክምችት ያመጣ እንደሁ ሲጠይቅ ምንጊዜም ዝቅተኛ ፍላጎት ይኑርሽ፤ ራስሽን የምታውቂው አንቺው እንደመሆንሽ ግዴታ ካልሆነብሽ መመገቡ በቃኝ ማለቱንም እወቂበት፡፡ በቅርብ የወጡ ጥናቶች እንዳመለከቱት መካከለኛ ክብደት ያላቸው ሴቶች ከወፍራም ሴቶች ይልቅ የቀጭን ሴቶችን የአመጋገብ ባህል የመቅዳት ዝንባሌ አላቸው፡፡
4. የምንጠቀመውን የጨው መጠን በተመለከተ እንደገና እናስብ
ከፍተኛ መጠን ያለው ጨው በተጠቀምን መጠን በዛው ልክ ፈሳሽ እንድንወስድ እንገደዳለን፡፡ ይሄም ለበለጠ ሰውነት እና ተጨማሪ ውሃ አምጪ ክብደት የተጋለጥን ያደርገናል፡፡

5. የመቅለብ ስፖርትን አዳብሪ

ጉልበትሽ ወደላይ በማጠፍ መሬት ላይ ተኚ፡- ጀርባሽ የተስተካከለ መሆኑን ስታረጋግጪ አንገትሽ ከተኛሽበት መሬት ላይ ቀና አድርጊ፡፡ የመጫወቻ ኳስ ቆሞ የሚወረውርልሽ ሰው ካዘጋጀሽ በኋላ የሚወረወርልሽን ኳስ አንገትሽና ጉልበትሽን በነበሩበት ሆነው ወገብሽ አንዴ ወደ ግራ ሌላ ጊዜ ወደ ቀኝ በማንቀሳቀስ የመቅለብ እና መልሶ የመወርወር እንቅስቃሴን ምቾትሽ እስካልተጓደለ ድረስ ደጋግመሽ አከናውኚ፡፡ የእንቅስቃሴውን ድግግሞሽ በየሳምንቱ እያሳደግሽ ፈጣኑን ለውጥ መጠበቅ ነው፡፡

6. ከሶዳ መጠጦች ራቂ፡-
የምትጠጪያቸው በሶዳ ኬሚካል የበለፀጉ መጠጦችን በተቻለ መጠን ቀንሺ አደገኛ ኬሚካል በውስጣቸው ያለመጠጦች በመጨረሻ ማረፊያቸው የት ይመስልሻል? ሆድሽ ላይ ነው፡፡ ደንደን ያለ ቦርጭ ባለቤት ያደርጉሻል፡፡ እነዚህን መጠጦች ሳትወስጂ በውሃ መተካት ይኖርብሻል፡፡
7. አልኮል ሌላው በሆድ ላይ ለሚመጣ ውፍረት (ቦርጭ) ምክንያት ነው
ከምግብ ጋር የሚቀርበው ብርጭቆ ወይን ብቻውን የለበሽው ሱሪ እንዲያጣብቅሽ ሊያደርግሽ ይችላል፡፡ የአልኮል ፍጆታችን ከፍ ማለት ወደ ሆዳችን በቀጥታ ፋታ የሚያሰራጨውን የብርቲሶል ሆርሞን መጠንን የሚያሳድግ በመሆኑ ከአልኮል መጠጦች እንራቅ አልያም እንቅስቃሴ እናድርግ፡፡

The post Health: የውብ ወገብ ባለቤት የሚደርጉሽ 7 ምስጢሮች appeared first on Zehabesha Amharic.

ወያኔዎች ይገድላሉ ያገዳድላሉ |ይገረም ዓለሙ

0
0

ኢትዮጵያዉያን በፍቅር በሰላምና በአንድነት ከኖርን በኢትዮጵያ ሥልጣነ መንበር ላይ መቆየት አንደማይችሉ ገና ሀ ብለው ትግል ሲጀምሩ የተረዱት ወያኔዎች ለዚህ መላ ዘይደው እቅድ ነድፈው ነው የተነሱት፡፡ በሀይማኖት በቋንቋ በጎሳ በአካባቢ ወዘተ በማለያየት በኢትዮጵያውያን መካከል ፍቅር ሰላምና አንድነት እንዳይኖር ማድረግ የዚሁ እቅዳቸው አንዱና ዋናው ክፍል መሆኑን ላለፉት ሀያ አራት ዓመታት የፈጸሙትና አሁንም የቀጠሉበት ተግባራቸው በቂ ምስክር ነው፡፡ የጥላቻ መርዝ እየረጩ ርስ በርስ ያናክሳሉ፣ አጀንዳ እየሰጡ በሰላምና በፍቅር አብረው የኖሩ ዜጎች በጥርጣሬ አንዲተያዩ ያደርጋሉ፤ ከዚህ አልፎም ራሳቸው የሚገድሉት አልበቃና አላረካ ሲላቸው ለአመታት አብረው የኖሩ ርስ በርስ እንዲገዳደሉ ያደርጋሉ፡፡

TPLF leaders
ይህ በ1984 ዓም በበደኖ ወተር አርባ ጉጉ ወዘተ ተጀምሮ ጊዜና ሁኔታ እየጠበቀ በበብዙዎቹ የሀገራችን አካባቢዎች ተግባራዊ ሲደረግ የኖረ የወያኔ እቅድ ሰሞኑን ደግሞ ጎንደርን ወር ተረኛው አድርጓል፡፡ በስፍራው የተፈጸመውና በማህበራዊ ድረ ገጾች ተሰራጭቶ የተመለከትነው ግድያ እጅግ ሰቅጣጭ ነው፡፡ ለምንም ዓላማ ይሁን በማንም ይፈጸም አንዲህ አይነቱ የግፍ አገዳደል ለዛሬ የሚወገዝ ቀን ሲወጣ ደግሞ ለፍርድ የሚያስቀርብ ነው፡፡ ለነገሩ እኛ ነን እንጂ ሁሌ አዲስ የምንሆን ወያኔዎች ለደደቢቱ ዓላማቸው ስኬት ማናቸውንም ነገር ከመፈጸም ወደ ኋላ እንደማይሉ በሀያ አራት ዓመታት የአገዛዝ ዘመናቸው ያቀዱትንና የቻሉትን ሁሉንም ነገር አድርገው አሳይተውናል፡፡አሁንም እያሳዩን ነው፡፡ ለወያኔ ከምንም ነገር ቀዳሚው በሥልጣን መቆየት ነውና፡፡

ሀገር ቆርሰው ሰጥተዋል፤ አሁንም መሬት ለመስጠት እየተዘጋጁ ነው፤ዜጎችን ገድለዋል፤አገዳድለዋል፤አስረዋል አሰቃይተዋል፤ንብረት ዘርፈዋል ሌላም ሌላም፡፡ ሥነ ልቦናችንን ተረድተዋል ደካማ ጎናችንን አውቀዋልና፡ በየግዜው አዳዲስ ነገር እየፈጠሩ ሲግቱን እየተቀበልን ርስ በርስ ከመጠላላት አልፎ ይሄው ሰሞኑን ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ እንደተፈጸመው ርስ በርሳችን አንገዳደላልን፡፡ በዚህ አድራጎታችንም የወያኔን የደደቢት ትልም በዘላቂነት አንዲሳካ መሳረያ በመሆን ምቹ ሁኔታ አንፈጥራለን፡፡

በግልጽ የሚታወቀው እስከዛሬ ያልተለወጠው ስማቸውም የሚያረጋግጠው የወያኔ የደደቢት ትልም የትግራይ መንግሥት መሆን ነው፡፡ ኢትዮጵያን በሙሉ የመያዝ በለስ ሲቀናቸው አንድም ሁሉን መያዝ ከቻልን ለምን በጠባብ እንወሰናለን ብለው ሁለትም ኢትዮጵያን ጎጆ መውጫና መበልጸጊያ ብሎም የዘላቂ ዓላማቸው ማደላደያ ለማድረግ እንጂ የተነሱበትን ዓላማ የሻሩ ላለመሆናቸው ድርጊቶቻቸው በቂ ማስረጃዎች ናቸው፡፡

የሚያሳዝነው ወያኔዎች ለከፋፍለህ ግዛው ስልታቸው ማስፈጸሚያ የፈጠሩዋቸውን ስመ ድርጅቶች የሚመሩ ሰዎች ራሳቸውን ከመጥቀም የዘለለ ምንም ዓላማና ግብ ሳይኖራቸው ለወያኔ የደደቢት ህልም አስፈጻሚ ሆነው መሰለፋቸው ነው፡፡ ሌላው ወያኔን በመቃወም የተሰለፈው ደግሞ ጠንክሮ በመታል ወያኔን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ማንሳት መቻሉ ቢቀር የወያኔን ጥፋት ለመግታት የሚያስችል እንቅስቃሴ ከማድረግ በወያኔ ከፋፋይ መርዝ ተመርዞ ሆድና ጀርባ ሆኖ በመኖር የሚቃወመውን ሀይል እድሜ የሚያራዝም ተግባር ይፈጽማል፡፡አንዳንዱም ለወያኔ የማገዳደል እቅድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአስፈጻሚነት ያገለግላል፡፡

ወያኔዎች ገና ደደቢት እያሉ ያወጡትን እቅድ ደረጃ በደረጃ ግዜ እየጠበቁና የእኛን ሙቀት እየለኩ ተግባራዊ ሲያደርጉ በፈጻሚነት የምንሰለፈው እኛው ነን፡፡የሕዝቦችን ራስ በራስ የማስተዳደር መብት ከወረቀት ጌጥነትና ከፕሮፓጋንዳ መሳሪያነት ተሻግሮ ተግባራዊ አለማድረጉን ሀያ አራት አመታት በተግባር ያየነው ነው፡፡ ከህውኃት ውጪ ያሉት የኢህአዴግ አባል የሚባሉት ድርጅቶች ብአዴን ኦህዴድ ደአህዴንም ሆኑ አጋር የሚሰኙት ድርጅቶች የያዙዋቸውን ክልሎች በነጻነት እንደማያስተዳድሩ በግልጽ ይታወቃል፡፡በዚህ ሁኔታ በይስሙላ ፌዴራሊዝም ሀገሪቱን እየገዛ ያለ አንድ ፓርቲ ለአመታት መለስ ያላገኘን የቅማንት ጥያቄ ዛሬ ድንገት ተነስቶ ጥያቄአችሁ ተቀባይነት አግኝቷል ራሳችሁን በራሳችሁ ታስተዳድሩ ዘንድ ተፈቅዷል ሲል ጎንደሬው “ጠርጥር ከገንፎም አለ ስንጥር” በአንድ ክልል ውስጥ ከዞንም ያነሰ አካባቢ የራስ አስተዳደር መብት ተጎናጽፎ ከወያኔ ፍላጎትና አመራር ውጪ ራሱን ማስተዳደር ይችላል ተብሎ ታምኖ ለዘመናት አብረው በኖሩ ተጋብተው ተዋልደው ክፉንም ደጉንም አብረው እያሳለፉ የአንድ አካባቢ ነዋሪዎች መካከል አለመግባባት መፍጠሩ፤ አለመግባባቱንም ለዘመናት በዘለቀው አካባቢያዊ ዘየ ለመፍታት ከመሞከር መሳሪያ ወደ መማዘዝ ተኪዶ ዘግናኝ ግድያ መፈጸሙ ወያኔ ለዓላማው ስኬት ምን ያህል እኩይ ተግባር አንደሚፈጽም ያሳየ ነው፡፡ በአንጻሩም መለስ ብለው የኋላውን ማስታወስ ቀና ብለውም የዛሬውን ማሰብ የማይችሉ ሰዎችን ወያኔ በመብራ እየፈለገ እንዴት እንደሚጠቀምባቸው አሳይቶናል፡፡

የውድቀታችን ክፋት የመክሸፋችን ስፋት በወያኔ እኩይ ሴራ ትናንትም ሆነ ዛሬ የሰው ልጅ የገዛ ወገኑን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገድል ጠብ የሚያበርድ ሽማግሌ፣ እርቅ የሚፈጥር የሀይማኖት አባት መጥፋቱ ነው፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ሕገ ወጥና ኢሰብአዊ ድርጊት ማውገዝ ቢያቅታቸው፣ መንግሥትን ለእርቅና ለሰላም መጠየቅ ቢያስፈራቸው ወዘተ እንዴት ታች ቀበሌና ወረዳ ላይ የሚፈጸሙ እጅግ ዘግናኝ የሆኑ አረመኔያዊ ድርጊቶችን ማውገዝና ጸብ አብርደው እርቅ ለማውረድ መንቀሳቀስ ይቸግራቸዋል፡፡ እነርሱም እንደኛ የነገሩ ወጣኝ ወያኔ መሆኑን ተረድተው የነገሩን ጫፍ ይዘን ሀረጉን ቢመዙት ከወያኔ እጅ ላይ እንደሚወድቁ ገብቷቸው ይሆን፡፡ አሳዛኝ፡፡ ከዚህ የባሰ ምን መክሸፍ አለ፤ ከዚህ በላይስ ምን የሀገር ሞት ይኖራል፡፡

ወያኔ በሥልጣን ላይ እስካለ አንድም ለጥቅም እያደሩ፤ሁለትም በወያኔ ፕሮፓጋንዳ እየሰከሩ ለጥፋት የሚሰለፉ መኖራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ወያኔ ለደደቢት ትልሙ ተግባራዊነት እነዚህን በመሳሪያነት በመጠቀም ጊዜና ሁኔታ እየጠበቀ በሚፈጽማቸው ተግባራት ልዩነታችን አሁን ካለውም እየበሳ በመንደር ደረጃ ሊወርድ የመቻሉን ምልክት ነው ያየነው፡፡አማራ ኦሮሞ ትግሬ ሲዳማ ጉራጌ ወዘተ የሚለው ክፍፍል አላንስ ብሎ ትናንት ስልጤ ጉራጌ አይደለሁም ብሎ ተለየ፡፡ ይህን በማሳካት ግንባር ቀደሙን ሚና የተጫወቱት አቶ ሬዲዋን ሁሴን ከተቀዋሚ ፓቲ መሪነት የመንግሥት ባለሥልጣንነትን አገኙ፡፡ ይሄው ዛሬ ደግሞ ቅማንት ከአማራ ልለይ እያለ ነው፡፡ ወያኔ እስካለ ነገም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ይሄው መለያየትና መናቆር ይቀጥላል፡፡

ወያኔዎች የማይወዱትንና ለሥልጣናቸው ጠንቀቅ አድርው የሚያዩትን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን በአንድ ግዜ ለማጥፋት ብዙ ሞክረው አልተሳካላቸውም፡፡ ስለሆነም ለህዝብ ግልጽ ሆኖ በማይታይና ፈጥኖ በማይታወቅ መንገድ ቀስ በቀስ የማመንመንና የማክሰም ስራ እየሰሩ ነው፡፡ እነርሱ የሀገር መሪነቱን ሥልጣን ባጡ ማግስት ኢትዮጵያ አስራ ምናምን ብጥስጣሽ እንድትሆን እየሰሩ ስለመሆኑ እንደ ቅኝ ገዢዎች በየቦታው የሚቀብሩዋቸው ግዜ ጠብቀው የሚፈነዱ ፈንጂዎች እያሳዩን ነው፡፡

ወያኔን ለመገላገል ከሚደረገው ትግል ባልተናነሰ ይህ ሴራ ከዚህ በላይ ሰፍቶና ከፍቶ አንዳይሄድ በጽኑ መስራት ያስፈልጋል፡፡ስለሆነም ጎንደር ውስጥ ያለውን ውጥረት በቅጡ ሳይረዱ የጠቀሙ መስሏቸው ያልሆነ መልእክት በማስተላለፍ “የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል” አይነት ተግባር የፈጸሙና አሁንም በመፈጸም ላይ ያሉ ወገኖች ቆም ብለው በማሰብ ጠብ እንዲበርድ ውጥረት አንዲተነፍስ በሚያስችል ተግባር ላይ ሊሰማሩ ይገባል፡፡ በጉዳይ ላይ የጠለቀ እውቀት ያላቸውና ነገሩን ከመሰረቱ የሚያውቁም የአካባቢው ሕዝብ እውነቱን ተረድቶ ከወያኔ ሴራ በማምለጥ ለጉዳዩን ራሱ ሰላማዊ መፍትሄ የሚያገኝበትን መንግድ ማመላከት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከተለያየ ጥቅምና ፍላጎት አንጻር ነገሩ እንዲከር የሚያደርጉ ሰዎች ካሉም ተለይተው መታወቅና መጋለጥ ይኖርባቸዋል፡፡

ወያኔ ራሱ የጫረውን እሳት ራሱ መልሶ አጥፊ መስሎ የሚቀርበው ነዳጅ እየጨመረ ይበልጥ ለማቀጣጠል ነውና በተለይ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች በጥንቃቄና በንቃት ሊከታተሉት ይገባል፡፡ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ጠያቂው ስለፈለገ ብቻ የሚያገኘው ሌላው ስለተቃወመውም የሚያስቀረው አይደለም፡፡ እንዴት ለምንና በምን ሁኔታ እንደሚጠየቅና ተግባራዊም አንደሚሆን በህግ የሚታወቅ በመሆኑ ባለሙያዎች ይህን ያብራሩ ያስረዱ፡፡

ራስን በራስ የማስተዳደር ቀልብ አማላይ ጥያቄ ትናንት የኢትዮጵያ ተማሪዎችን አማልሎ በውስጥ የተጠነሰሰውን ሴራ ሳይረዱና ከጀርባ ያለው ተልእኮ ሳይገባቸው ለኤርትራ መገንጠል አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ እንዳባቃቸው ሁሉ ዛሬም ብዙዎች ከቅማንት የማንነት ጥያቄ በስተጀርባ ሊኖር የሚችለውን የወያኔ ስውር ደባ ሳያውቁ ለወያኔ ዓላማ ማስፈጸሚያ መሳሪያ አንዳይሆኑ ማንቃት ማትጋትና ከዚህ የሚያልፉትን ማጋለጥ ይገባል፡፡ ሰሞኑን ያየነው ዘግናኝ ግድያ እንዳይቀጥልም ሁሉም በሚችለው መጣር ይኖርበታል፡ስሙን እንጂ ግብሩን ላልያዙት የሁልም እምነት አባቶችም እስቲ በዚህ ግዜ አንኳን ድምጻችሁ ይስማ የአስታራቂነት ግብራችሁ ይታይ አንበላቸው፡፡

The post ወያኔዎች ይገድላሉ ያገዳድላሉ | ይገረም ዓለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተነሳው ተቃውሞ ወደ ቱሎ ቦሎና ወሊሶ አካባቢ ተዳረሰ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም እንደገና በምዕራብ ወለጋ የተቀሰቀሰው የተማሪዎች ቁጣ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች እየተዛመተ ይገኛል:: የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች እንደሚሉት በተለይ ፖሊስ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ ግድያ ከፈጸመና ካቆሰለ በኋላ ይበልጥ ቁጣው እየናረ መጥቷል::
Zehabesha News

በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች እየተዳረሰ የሚገኘው ተቃውሞ ዛሬ በቱሉ ቦሎና በወሊሶ አንዳንድ አካባቢዎች ደርሷል:: በነዚህ አካባቢዎች አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም ወጣቶች ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል::

በባሌና በወለጋ አካባቢዎች አሁንም ውጥረቱ እንዳለ የሚጠቁሙት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጉዳዩ አፋጣኝ እልባት ካላገኘ ወደ አስከፊ ደረጃ ሊደርስ እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ጨምረው ገልጸዋል:: በተለይም እስከ ትናንት ድረስ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሞቱት ተማሪዎች ቁጥር 3 የነበረ መሆኑና አሁን ደግሞ ወደ 4 ከፍ ማለቱ ጉዳዩን አጡዞት ይገኛል::

ይህ በ እንዲህ እንዳለም ዛሬም በ ም ዕራብ ወለጋ ጉሊሶ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ሲካሄድ መዋሉም ተዘግቧል:: አካባቢውን የፌደራል ፖሊስ ቢወረውም ሕዝቡ ተቃውሞውን በአደባባይ እየገለጸ አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እየተቃወመ ነው::

The post የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተነሳው ተቃውሞ ወደ ቱሎ ቦሎና ወሊሶ አካባቢ ተዳረሰ appeared first on Zehabesha Amharic.

መንግስት በጎንደር የ17 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን አመነ * አንዱን የገደልኩት እኔ ነኝ ብሏል

0
0

gonder

(ዘ-ሐበሻ) በትናንትናው የዘ-ሐበሻ የዜና እወጃ በጎንደር በ እስር ቤት ላይ በደረሰ ቃጠሎ የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ዘግበን ነበር:: መንግስት አንድ ሰው መግደሉን ሲያምን ሌሎቹ 16 ሰዎች ህይወት የጠፋው በቃጠሎው ወቅት ከ እስር ቤቱ ለማምለጥ ሲጋፉ ነው አለ::

የአማራ ክልል ፖሊስ ለመንግስት ሚድያዎች በሰጠው መግለጫው ትናንት ህዳር 21፣ 2008 በጎንደር ማረሚያ ቤት ከቀኑ 7፡30 አካባቢ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ከማረሚያ ቤቱ ለመውጣት በተደረገው ግፊያ የ16 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰው ሊያመልጥ ሲል ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ገልጿል::

እንደ አይን እማኞች ገለጻ ከሆነ ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር ከ30 በላይ ቢሆንም መንግስት ቁጥሩን ማሳነሱንና በ እጁ የጠፉትን ቁጥር ወደ አንድ ብቻ ማሳነሱ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል:: እንደ እማኞች ገለጻ አብዛኛው እስረኛ በመንግስት እጅ የተገደለ እንጂ ከ እስር ቤት ከ እሳት ለማምለጥና ለመውጣት ሲጋፉ አይደለም::

The post መንግስት በጎንደር የ17 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን አመነ * አንዱን የገደልኩት እኔ ነኝ ብሏል appeared first on Zehabesha Amharic.

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት መገኘት ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ሀይሎች የጋራ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው |ከዚህ ወዲያ አፍ እንዳመጣ “ሽብርተኛ” ማለት የህወሃት መሩ መንግስት እብደት ሆነ!

0
0

ቢላል አበጋዝ  ዋሽግተን ዲ ሲ

ረቡዕ ፣ ዲሴምበር 2 ቀን 2015

ዛሬ ኢትዮጵያ ለህወሃት መሩ መንግስት ተንፈራጦ መግዛት የምትመች አለመሆንዋን ማንም ዜና መከታተል ለሚፈልግ ግልጽ ነው።የህወሃት ባለስልጣናትም ከወትሮው በተለየ መልኩ እርስ በርስ እየተናቆሩ ነው።ተስፋ የቆረጡት ደግሞ ንብረት እያሸሹ ይገኛሉ።በቀይ ባህር አካባቢ አፍሪካ ቀንድን ሊያምስ የሚችል ደመናም ጥሏል ማለት ይቻላል።ሀብታም አረቦችም ልክ እንደ ህወሃት በስጋት ተወጥረዋል።ኢትዮጵያን ማተራመስ ቅር ሳይላቸው ማንኛውንም ድርጊት የሚፈጽሙ ለመሆናቸው የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ይመሰክራል።

birhanu nega

ከላይ የጠቀስኩት አደጋ ማንጃበቡ ሳያንስ ዛሬ አስራ አምስት ሚሊዮን ወገናችን ለራብ ተዳርጓል።ይህን መከራ በመካድ የጀመረው ህወሃት ህይወት ለማትረፍ የሚጥር አይደለም።በኢትዮጵያ በያለበት እስራትና ግድያው በርትቷል።የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት ስለ ኢትዮጵያ እንዲናገር መጋበዙ ያቀረብኩትን የኢትዮጵያ ሁኔታ ለመንግስታቱ ተወካዮች መግለጽ ብቻ ሳይሆን አጣዳፊ ሁኔታ መፈጠሩንም የማስስጨበጥ ሁኗል። ኢትዮጵያን የፋሺት ኢጣሊያ መንጋጋ ሲያኝካት የተሰደዱ አርበኞች በዓለም መድረክ ጮሆውላት ነበር። ዛሬም በህወሃት መንጋጋ ስትታኘክ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢትዮጵያውያ ወገኖቹ ጋር ሆኖ ድምጹን ከፍ አድርጎ አሰምቶላታል።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህን የፈጸመው በግንባር ሆነው ህወሃት መሩን መንግስት ብርክ እያስያዙ ያሉትን የኢትዮጵያን ጀግኖች ከበረሃ ተለይቶ ነው።

የኢትዮጵያ ሁኔታ ጊዜ የማይሰጥ ነው።ህወሃት መሩ መንግስት በመለስ ዜናዊና ጀሌዎቹ አማካይነት ያፈላው የጥላቻ ጥንስስ ድንገት ሳይፈነዳ አደጋውን ሊገታ የሚችል ዝግጅት ማድረግን ይጠይቃል።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሁሉም የሚወከልበት ጊዜያዊ መንግስት ካልቆመ ወያኔ ፈጽሞ የመግዛት ሀይሉን ሊያጣ የሚችልበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም።ህዝቡ በቃኝ ለማለቱ ምልክቶቹ መበራከታቸው ይህን አመላካች ነው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ሃይማኖትን ተቋማት ጣልቃ በመግባት አዳክሟል።የእስልምና ሃይማኖት ተቋማትን ደፍሮ መሪዎችን ለእስር ዳርጓል።ነጻነትና ዜግነት በየፈጁ ተደፍሯል።

የዓለም መንግስታት በተለይ ሃያላን የኢትዮጵያን ጉዳይ ወደጎን በመተው ህወሃት መሩን መንግስት መወንጀል ሳይሆን በስመ ሽብርተኝነትን መቋቋም አብረውት እየሰሩ ነው።በታሪካችንም የፋሺት ኢጣሊያውን ሙሶሊኒንም አይዞህ ያሉት ነበሩ።ሁሉም ለየራሱ ጥቅም በዓለም ዲፕሎማሲ ሰልፉን ያስተካክላል።በየጊዜውም ይለውጣል።ኢትዮጵያን የምንል አንድ መሆን የግድ የሚለን ጊዜ አሁን ነው።ህወሃት መሩ መንግስትማ ለሙግት፡ለመልስ እንኳን ያቆመው ቅጥረኛ የውጭ አገር ተላላኪን ነው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዋለበት መድረክ።የህወሃት ድንቁርና አንድ መገለጫ ምልክት ነው።የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት መግለጫ መስጠት ህወሃት መሩን መንግስት ለሚቃወሙና ለተራበው ከተሜ ገጠሬ ወገናችን ትልቅ ግምት የሚሰጠው ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው።ኢትዮጵያ በዚህ የመከራ ዘመን ለታደጓትን አላህ ለነሱም ይመስክርላቸው።

 

ድል ለዲሞክራሲያዊ  ሀይሎች ሁሉ!

ኢትዮጵያ በአንድነትዋ በነጻነት ለዘለዓለም ትኑር!

አላህ ኢትዮጵያ ይጠብቃት!

 

 

 

The post የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት መገኘት ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ሀይሎች የጋራ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው | ከዚህ ወዲያ አፍ እንዳመጣ “ሽብርተኛ” ማለት የህወሃት መሩ መንግስት እብደት ሆነ! appeared first on Zehabesha Amharic.

ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ምስክር ሆነው እንዳይቀርቡ ያቀረበውን ይግባኝ ዛሬ ህዳር 23/2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውድቅ አደርጎታል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ተጠይቆ የነበር ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ በተደጋጋሚ ሳያቀርባቸው ቀርቷል፡፡

andargachew Tisge

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ምስክርነት በተጠሩበት ወቅት የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ እና በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መዝገብ ላይ ክስ ቀርቦባቸው በእድሜ ልክና በሞት እንዲቀጡ ተወስኖባቸው የህዝባዊ መብታቸው የተሻረ በመሆኑ በምስክርነት ሊቀርቡ እንደማይችሉ መቃወሚያ አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይሁንና ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡላቸው የጠየቁት ለዋስት አሊያም ልዩ አዋቂ ምስክር ሆነው ሳይሆን ነበሩበት የተባለውን ጉዳይ ለመናገር በመሆኑ ለምስክርነት ሊቀርቡ ይገባል በሚል የፌደራል አቃቤ ህግ ያቀረበውን ተቃውሞ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

የልደታ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም ቀርበው ምስክርነት እንዲሰጡ ከወሰነ በኋላ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ‹‹ትዕዛዝ አልደረሰኝም፣ የተፃፈው ለቃሊቲ ሳይሆን ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የሚል ነው›› እና ሌሎችም ምክንያቶች በማቅረብ በተደጋጋሚ አቶ አንዳርጋቸውን ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡ በስተመጨረሻም ጥቅምት 12/2008 ዓ.ም ማረሚያ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ቃሊቲ እንደሌሉ በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ከተከሰሱት መካከል አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) ውጭ ያሉት የፍትህ ሂደቱ እየተጓተተባባቸው በመሆኑ የአንዳርጋቸው ፅጌ ምስክርነት ቀርቶ በሌሎች መረጃዎች ውሳኔ እንዲሰጥላቸው ሲጠይቁ ሁለቱ ተከሳሾች ግን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሊመሰክሩላቸው እንደሚገባ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበው ነበር፡፡

በዚህም መሰረት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለፀረ ሽብር ግብረ ኃይልና አቶ አንዳርጋቸውን ጠይቀውታል ለተባሉት የብሪታኒያ አምባሳደር ደብዳቤ መፃፋቸው ይታወቃል፡፡ ይሁንና ተከሳሾቹ ለሶስቱ አካላት ደብዳቤውን በፃፉበት ማግስት የፌደራል አቃቤ ህግ ከወራት በፊት ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መመስከር አይገባቸውም ብሎ አቅርቦት የነበረውን መከራከሪያ መሰረት በማድረግ አቶ አንዳርጋቸው ምስክር እንዳይሆኑ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ነበር፡፡
የአቃቤ ህግን ይግባኝ ያየው ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ዛሬ ህዳር 23/2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት ‹‹አንድ ሰው ለምስክርነት ይቅረብ አይቅረብ በሚል ይግባኝ ሊጠየቅበት አይገባም፡፡ ካስፈለገ ግለሰቡ የሰጡት ምስክረነት መረጃው ተመዝኖ የሚሰጠው ፍርድ ላይ ይግባኝ ሊባል ይችላል፡፡ እኛም ጉዳዩን ለማጣራት ምስክርነቱ እንዲቋረጥ አድርገን የነበር ቢሆንም አሁን ግን እንዲቀጥል ወስነናል፡፡ የአቃቤ ህግን ይግባኝም አልተቀበልነውም›› ሲል ይግባኙን ውድቅ አድርጓል፡፡ አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ምስክር መሆን የለባቸውም ብሎ ያቀረበው ክርክር በፍርድ ቤት ውድቅ ሲሆንበት ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡

በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከተከሰሱት በተጨማሪ በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል 1ኛ ተከሳሽ አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት ጠርቷቸዋል፡፡ በሌሎች የክስ መዝገቦች ከአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር ተገናኝታችኋል የተባሉ ተከሳሾችም አቶ አንዳርጋቸውን የመከላከያ ምስክር አድርገው ሊጠሯቸው እንደሚችሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡

The post ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.


በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች ተቃውሞው ቀጥሏል

0
0


(ዘ-ሐበሻ) አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች መቀጠሉ ተሰማ::

Hospital tekawemo

እንደ ዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ገለጻ በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች በሚገኙ ከፍተኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተቀጣጠለው ተቃውሞን ለመበተን ፖሊስ ሃይል ቢጠቀመምም የሕዝቡ ቁጣ አሁንም እንዳየለ ተገልጿል::

በበደኖ አደባባይ የወጣው ተቃውሞን ፖሊስ ለመበተን በወሰደው እርምጃ በርካታ ተማሪዎች መጎዳታቸውን የደረሰን መረጃ ሲያመለክት በተመሳሳይም በነጆ እና በነቀምቴም ፖሊስ ተማሪዎቹን ለመበተን በወሰደው እርምጃ መጎዳታቸውም ተሰምቷል::

በሆለታም እንዲሁም በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተነሳው ተቃውሞ ወጣት ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል:: ተቃውሞው ከፍተኛ እንደነበር የሚገልጹት ዘገባዎችም በርካታ ተማሪዎች በፖሊስ ቆመጥ መቀጥቀጣቸውን አስታውቀዋል::

የተማሪዎቹ ጥያቄ ከማስተርፕላኑ በተጨማሪ ፌደራል ፖሊስ እየፈጸመ ያለውን ግድያ እንዲያቆም የሚጠይቅም ሆኗል::

በሌላ በኩል በደቡብ ኦሮሚያ ቡሌ ሆራ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተነሳው ተቃውሞን ለማብረድ የተማሪዎች ተወካዮች እና የከተማው አስተዳደሮች ስብሰባ ቢቀመጡም ሊስማሙ አለመቻላቸው ታውቋል::

በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች አለመረጋጋቱ እንደቀጠለ ነው::

The post በወሊሶ፣ በሆለታ፣ በበደኖ፣ በሙገር፣ በነጆ እና በነቀምቴ ከተሞች ተቃውሞው ቀጥሏል appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: የዮሃንስ ‹‹ግትርነት›› እስከመቼ ይቀጥላል? |ኡጋንዳ ከሩዋንዳ ለዋንጫ ይጫወታሉ

0
0

ከግሩም ሰይፉ

38ኛው የዲኤስቲቪ ሴካፋ ሲነዬርስ ቻሌንጅ ካፕ ቅዳሜ ሲጠናቀቅ ለዋንጫ ጨዋታ ኡጋንዳ ከሩዋንዳ ሲገናኙ፤ አዘጋጇ ኢትዮጰያ እና ሱዳን ለደረጃ ይጫወታሉ፡፡ ኡጋንዳ እና ሩዋንዳ በሴካፋ የዋንጫ ጨዋታ ሲገናኙ የቅዳሜው ፍልሚያ በታሪክ ለ4ኛ ጊዜ ነው፡፡ ባለፉት ሶስት የዋንጫ ጨዋታዎች ኡጋንዳ አሸንፋለች፡፡ለ37ኛ ጊዜ በሴካፋ ሻምፒዮና በመሳተፍ ግንባር ቀደም የሆነችው ኡጋንዳ 13 ጊዜ ሻምፒዮን ስትሆን ፤ ለ17ኛ ጊዜ በሴካፋ ሻምፒዮና የተሳተፈችው ሩዋንዳ 1 ጊዜ ብቻ ዋንጫውን ማግኘት ችላለች፡፡

File Photo

File Photo


በ38ኛው የዲኤስቲቪ ሴካፋ ሲነዬርስ ቻሌንጅ ካፕ በዮሃንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጰያ ብሄራዊ ቡድን የመጀመርያውን ጨዋታ በሩዋንዳ 1ለ0 ተሸነፈ፤ እንደምንም በሁለተኛ ጨዋታ ሶማሊያን 2ለ0 አሸነፈ፤ ከዚያም ከታንዛኒያ ጋር 1ለ1 አቻ ተለያይቶ በምርጥ ሶስተኛ የማለፍ እድል የመጨረሻውን እጣ አግኝቶ ወደ ሩብ ፍፃሜ ገባ፡፡ በሩብ ፍፃሜ በድጋሚ የተገናኘው ከታንዛኒያ ጋር የነበረ ሲሆን በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 አቻ ከተለያዩ በኋላ በመለያ ምቶች 4ለ3 ዋልያዎቹ አሸንፈው ግማሽ ፍፃሜ ገቡ፡፡ በግማሽ ፍፃሜ ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት ከተሰጠው የኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ተገናኙ፡፡ የተጫወቱት መቶ ሃያ ደቂቃቃዎች ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት አበቃ፡፡ በመለያ ምቶች ከዋልያዎቹ አምበሉ ጋቶች ፓኖም ሳተ፤ ኡጋንዳዎች ደግሞ ሁሉንም የፍፁም ቅጣት ምቶች አገቡ፡፡ አዘጋጇ አገር ወደቀች፤ ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት የተሰጣች ኡጋንዳ ለፍፃሜ አለፈች፡፡ በሌላ ጨዋታ ሩዋንዳ ለዋንጫ ያለፈችው ሱዳንን በመለያ ምቶች በመርታት ነበር፡፡
Yohanes sahele
የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑና ዋና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የተፈራረሙት የቅጥር ውል 8 ወራት ሆኖታል፡፡ ከተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ጋር በወር 75ሺ ብር እየተከፈላቸው የሚሰሩት ዋና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ሲቀጠሩ በወቅቱ በይፋ ተገልፆ በነበረው የውል ስምምነት መሰረት በ2017 ጋቦን በምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ዋሊያዎቹ ወደ ዋናው ውድድር ለማለፍ የሚያስላቸውን ነጥብ በማግኘት የ31ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ተሳታፊነታቸውን ማረጋጋጥ ዋና ዓላማ ነው መባሉ አይዘነጋም፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ የዮሃንስ እና የዋልያዎቹ እድል ላይ ከወዲሁ አስተያየት መስጠት የሚከብድ ይሆናል፡፡ ምናልባትም አሰልጣኙ ከተሳካላቸው ፌደሬሽኑ ኮንትራታቸውን እንደሚያራዝምም ቃል ገብቷል፡፡ ግን በሌሎቹ የቅጥር ዓላማዎች ዋልያዎቹ በቻን 2016 እና በሴካፋ አህጉራዊና ክፍለ አህጉራዊ ውድድሮችም አመርቂ ውጤት እንደሚጠበቅባቸው ተመልክቶ ነበር፡፡ በእርግጥ ሩዋንዳ ለምታስተናግደው የቻን ውድድር ዋልያዎቹ ማለፋቸው በዮሃንስ ሳህሌ የተመዘገበው ጉልህ ስኬት ማለት ይቻላል፡፡ መርቂ ውጤት በቻን ላይ ማስመዝገብ አለማስመዝገባቸውን ሲደርስ የምንታዘበው ይሆናል፡፡ ዋልያዎቹ አዘጋጅ ሆነው በተሳተፉበት የሴካፋ ሻምፒዮና ግን የተጠበቀው አመርቂ ውጤት ሳይመዘገብብት ቀርቷል፡፡ ዮሃንስ ሳህሌ ውድድሩ ተጀምሮ እስኪያልቅ የዋንጫ ተፎካካሪ የሚያደርጋቸውን አስተያየት፤ አቀም እና ቡድን የመምራት ባህርይ አሳይተዋል ማለት ይከብዳል፡፡ ከጅምሩ የቡድናቸውን ተሳትፎ ልምድ ለማግኘት፤ አዲስ ብሄራዊ ቡድን ለመገንባት፤ ለወጣቶች እድል ለመስጠት እያሉ ቆይተዋል፡፡ ግማሽ ፍፃሜ ላይ ሩጫው ሲያበቃም ይሄ ግትርነታቸው ተስተውሏል፡፡

ከኡጋንዳው ሚቾ ጋር በሰጡት መግለጫ ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው አንድ ጥያቄ ነበር፡፡

The post Sport: የዮሃንስ ‹‹ግትርነት›› እስከመቼ ይቀጥላል? | ኡጋንዳ ከሩዋንዳ ለዋንጫ ይጫወታሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

በኦሮሚያ የተማሪዎችን የተቃውሞ ሰልፍ ለመበተን የመጣው የፀጥታ ሃይል ከህዝቡ ሸሽቶ ሲሮጥ የሚያሳይ ቪዲዮ

ውል አልባው ተቃውሞ |ይገረም ዓለሙ

0
0

ወያኔ ለሥልጣን ከበቃበት ግዜ አንስቶ ከተቃውሞ ነጻ የሆነበት ግዜ የለም፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ድርጅቱንም ሆነ በአመራር ላይ የነበሩና ያሉ ግለሰቦችን በመጥላት ሳይሆን ለዮሐንስ ቤተ መንግሥት ታግሎ ለምንይልህ ቤተ መንግሥት ሲበቃ፤ ከፋኖነት ወደ መንግስትነት ሲለወጥ የዓላማም ሆነ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማድረግ ባለመቻሉና ኢትዮጵያን በማጥፋት እቅዱ በመቀጠሉ ነው፡፡
sululta
የሚካሄደው ተቃውሞ ግን መልክና ቅርጽ የሌለው ቀጣይና ተደጋጋፊ ያልሆነ ውል አልባ በመሆኑ መስዋዕትነት የሚያስከፍል እንጂ የወያኔን ሥልጣን የሚነቀንቅ ለመሆን አልቻለም፡፡ በየትኛውም የህብረተሰብ ክፍልና በማናቸውም የሀገሪቱ አካባቢ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምክንያቱ ወያኔ ሆኖ እያለ ጥቃቱ የደረሰበት ወይንም ቀድሞ በመንቃት ጥቃቱን ለመከላከል አንዱ አካባቢ ወይንም የህብረተሰብ ክፍል ተቃውሞ ሲያሰማና የጥይት ምላሽ ሲለገሰው ሌላው አካባቢ ወይንም የህብረተስብ ክፍል በእኔ ካልደረሰ የሚል በሚመስል ሁኔታ በዝምታ ይመለከታል፡፡እሱ ተረኛ ሲሆን ደግሞ ሌላኛው ለእኔ ግዜ ልትረዳኝ ቀርቶ ቢያንስ መች ጮህክልኝ በሚል አይነት በል ብቻህን ተወጣው ብሎ በዝምታ ያያል ያዳምጣል፡፡ ይህ መልክ አልባ ተቃውሞም ወያኔ በየተራ በተናጠል ዜጎችን በማሰር በማሰደድ በመግደል ከጨዋታ ውጪ እያደረገ ተደላድሎ ለመኖር አስችሎታል፡፡

ሌላው ቢቀር የጥያቄው ምንነትና የጠያቂዎቹ ማንነት ሳይታይ ወያኔ ለጥያቄው የሚሰጠው ኢ- ሰብአዊ ኢ- ሕጋዊና ኢ- ዴሞክራሲያዊ ምላሽ የወያኔን አገዛዝ የማይቀበሉትን በሙሉ (የተደራጁም ሆኑ ያልተደራጁ) በአንድ ድምጽ እንዲጮሁና በአንድ መስመር እንዲሰለፉ ባበቃቸው ነበር፡፡አንድ የህብረተሰብ ክፍል የሚያነሳውን ጥያቄ ሌላው ላይደግፈው ይችላል፡፡ የአንድ አካባቢ ነዋሪዎች ጥያቄ በሌላ አካባቢ ለሚኖሩ የሚጎረብጥ ሊሆን ይችላል፤አንዱ የፖለቲካ ድርጅት የሚያራምደው አቋም ለሌላው የማይጥመው ሊሆን ይችላል፡፡ስለሆነም ለጥያቄው መልስ ማግኘት ለአቋሙ ግብ መምታት ላይተባበር ይችላል፡፡ እንደውም አለመተባበር ብቻ ሳይሆን ጥያቄውን ሊቃወም አቋሙን ሊያወግዝ ይችላል፡፡

ነገር ግን የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ መብት በሆነውና ወያኔም በህገ መንስቱ ውስጥ ባሰፈረው ሀሳብን የመግለጽ፤ተቃውሞን በሰላማዊ መንገድ የመግለጽ፤ ያለማንም ጣልቃ ገብነት በነጻነት የመደራጀት ወዘተ መብቶቹን ተጠቅሞ ግለሰብም ይሁን ህብረተሰብ በነጠላም ይሁን በቡድን ጥያቄዎችን ሲያቀርብ አቋሙን ሲያራምድ ተቃውሞውን ሲያሰማ የሚሰጠው ምላሽና ጥይትና ዱላ ሲሆን ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን መሆንና ለሰብአዊ መብቶች መከበር እታገላለሁ የሚል ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በእኔ ካደረሰ ብሎ የዳር ተመልካች በመሆን በዝምታ ሊያልፈው የሚገባ አይደለም፡፡
የእኛ የሀያ አራት አመታት ተቃውሞ ግን መልክ የለሽ ውል አልባ በመሆኑ ሁሉ በየራሱ አጥር ዙሪያ የእኔ በሚላቸው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ በመመርኮዝ በተናጠል ከመጮህ ሊያልፍ አልቻለም፡፡ እንዲህም በመሆኑ በየጊዜው የሚነሱ ተቃውሞዎች እስር ድብደባና ሞት ከማስከተል አልፈው ውጤት ማስመዝገብ አልቻሉም፡፡ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በወያኔ ላይ የሚያካሂዱዋቸው ተቃውሞዎች በእውቀት ላይ ተመስርተው ዘላቂ ዓላማ አንግበው በእቅድ የሚመሩ ሳይሆን በወቅታዊ ትኩሳት የሚቀሰቀሱና በስሜት የሚካሄዱ ነው የሚመስለው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙ ህገ ወጥ ድርጊቶች ቢያንስ በሁለት ምክንያት ከፈጻሚው ወገን ውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ የሚመለከቱና በአንድ ድምጽ እንዲጮህ የሚያደርጉት ነበሩ፡፡ ግን ትናንትም አልሆነም ዛሬም የለም፤ወደፊትም የሚሆን አይመስልም፡፡አንደኛ ድርጊቱ ህገወጥና ኢሰብአዊ በመሆኑ፤ሁለት ወያኔ ሌሎችን ለመወንጀያነት የሚጠቀምበትን ሕገ መንግሥት የሚጥስ በመሆኑ ሶስተኛ እንጨምር ካልን የድርጊቱ ፈጻሚ ሁሉም የሚቃወሙት ወያኔ በመሆኑና ጥቃቱ አይነትና ዘዴውን እየቀያየረ በሁሉም ላይ የሚፈጸም በመሆኑ ነግ በእኔ በማለት በየትኛውም አካባቢ በማናቸውም ዜጋ ላይ ሲፈጸም የፖለቲካ አመለካከት የአደረጃት ልዩነት ሀይማኖትም ሆነ ጎሳ ሳይለይ ሁሉም መቃወም ነበረበት፣ ግን የለም፡፡

በርግጥ የተቃውሞአችን መሰረቱ የህግ የበላይነት መረጋገጥ፣የሰብአዊት መብት መከበር በጥቅሉ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን መሆን ከሆነ ኢሰብአዊና ሕገ ወጥ ድርጊት የተፈጸመበት ግለሰብም ይሁን ቡድን የምንወደወው ይሁን የማንወደው ዓላማ ድርጊቱን የምንደግፈው ይሁን የምንቃወመው የተፈጸመበትን ድርጊት ከማውገዝና ከመቃወም የሚያግደን ሊሆን አይገባም፡፡ ለድርጊቱ መፈጸም ሰበብ/ ምክንያት የሆነው ጉዳይ ምንነትም ጥያቄ ባነሱና ተቃውሞ ባሰሙ ግለሰቦችም ይሁን ቡድኖች ላይ የተፈጸመን ህገ ወጥና ኢ-ሰብአዊና ድርጊት ከማውገዝና ከመቃወም ለመቆጠብ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ ትግላችን ትናናሽ ፍጎቶቻንን ለማሳካት ካልሆነ በስተቀር ማንም ይፈጽመው በማንም ላይም ይፈጸም ሕገ ወጥ የሆኑ ኢ-ሰበአዊና ኢ- ዴሞክራሲያዊ ድርጊቶችን ልናወግዝና ልንቃወም ዳግም እንዳይፈጸምም በተባበረ ኃይል ልንታገለው ነው የሚገባው፡፡

በህብረተሰብ ደረጃ ቀርቶ ፕሮግራም ነድፈው ድርጅት መስርተው መንግስት መሆንን አልመው የሚታገሉት ፖለቲከኞችም (ብዙዎቹ በቁጥር ብቻ ነው ያሉት)አንዳቸው በሌላው ላይ የሚፈጸምን ሕገ ወጥ ድርጊት ሲያወግዙም ሲቃወሙም አይሰሙ፡፡ ከተግባራቸው አንደምናየው እነርሱን ለተቃውሞ የሚያነሳሳቸው የተፈጸመው ድርጊት ሕገ ወጥነትና ኢሰብአዊነት ሳይሆን የተፈጸመበት ግለሰብ፣ ቡድን ወይንም አካባቢ ለእነርሱ ያለው ቅርበት ወይንም ግንኑነት ነው፡፡ የአንደኛው ፓርቲ አባል ሲገደል ሌሎቹ ዝም፤የአንደኛው ፓርቲ አመራር ሲታሰር ሌሎቹ ዝም፣ ጥቃቱ ግን ሁሉንም በየተራ ያዳርሳል፡፡( ለወያኔ ካደሩት በስተቀር፡)

ፖለቲከኞቻችን የሚታገሉት ቢሳካላቸው ቤተ መንግሥት ለመግባት ብቻ ሳይሆን ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ ለሰብአዊ መብት መከበር ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን መሆን ካልሆነ ነገራችን ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ ይሉት ይሆናል፡፡ ከሆነ ደግሞ የሚቃወሙት ኃይል በሌላ ተቀዋሚ ላይ፣እነርሱ እንወክለዋለን ከሚሉት የሀገሪቱ ክፍል ውጪ በሚኖሩ ዜጎች ላይ በጥቅሉ በሀገሪቱ ውስጥ የሚፈጽማቸውን ሕገ ወጥ ተግባራት በሙሉ መቃወም ብሎም መታገል ይኖርባቸዋል፡፡ እንደውም ይህ ብቻ አይደለም ወያኔ በራሱ አባሎችም ላይ ሕገ ወጥና ኢ-ሰብአዊ የሆነ ድርጊት ከፈጸመ መቃወምና ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምክንያቱም የተቃውሞአቸው መሰረት የማውገዛቸውም ምክንያት የሚሆነው የፈጻሚውም ሆነ የተፈጸመበት ግለሰብ ወይንም ቡድን ማንነት ሳይሆን የተፈጸመው ድርጊት ህገ ወጥነትና ኢሰብአዊነት ነውና፡፡
ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ኦሮምያን እያጥለቀለቀ ያለ የተማሪዎች ተቃውሞ እያየን እየሰማን ነው፡፡ ለተማሪዎቹ እንቅስቃሴ ከወያኔ በኩል የተሰጠው ምላሽ ያው የሚታወቀው የወያኔ ተግባር የሆነው በየግቢያቸው ውስጥ አያፈኑ መደብደብ ማሰርና መግደል ነው፡፡ ይህን የተማሪዎች ተቃውሞና የተሰጣቸውን ምላሽ ልዩ የሚያደርገው ጠቅላይ ምኒስትር ሀይለማሪያምደሳለኝ ኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ተቃውሞን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ የሚቻልባት ሀገር በመሆኗ ብረት ያነሱ ሀይሎች ብረታውን ጥለው ተቃውሞአቸውን በሰላማዊ መንገድ ቢያራምዱ ይበጃቸዋል በማለት ምክር መለገሳቸውን በሰማን ማግስት መሆኑ ነው፡፡

ፈጣሪ ያሳያችሁ፣አዲስ አበባን ለማስፋፋት የታለመውን ማስተር ፕላን ተቃውመው ሰለፍ ለማድረግ ባሰቡ ተማሪዎች ላይ ጥይት የሚተኩሰውና የሚገድለው የህውኃት አገዛዝ ስልጣን የሚቀናቀኑትን ፖለቲከኞች በሰላማዊ መንገድ ሲያስተናግድ ፡፡ (በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ሀምሳ ምናን ፓርዎች አሉ አይደለም ወይ እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ) አቶ ሀይለማሪም በወያኔዎች እየተገፉ ያልሆነና የማይሆን ነገር ይናገራሉ፣ ውሉ ሳያድር ይጋለጣሉ፣ አንዴ ገብተውበታልና ከአፈርኩ አይመልሰኝ በማለትም ደግሞ ሌላ ውሸት ይናገራሉ፡አይ አለመታደል፡ነገ ደግሞ ምን ይሉን ይሆን!
ለመሆኑ የኦሮምያ መስተዳድር መቀመጫ አዲስ አበባ ይሁን ብለው የጠየቁ ሰዎችን ያሰረ ያንገላታ፣ (የሚጫና ቱለማ ማህበር አመራሮችን ያስታውሷል) በምርጫ 97 ቅንጅት አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ ሲያሸንፍ ተጣድፎ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነች የሚል ሕግ ያወጣ፣ ቅንጅቶችን ለተመረጡበት መንግሥትነት ሳይሆን ለቃሊቲ ወህኒ ቤት ከዳረገ በኋላ ሕጉን ሽሮ ኦህዴድን ከአዲስ አበባ ያባረረ፣ ወያኔ ለአዲስ አበባም ሆነ ለኦሮምያ የሚጠቅም ነገር ያስባል ማለት አዙሮ ማየት አለመቻል ነው፡፡
ነገርን ነገር ያነሳዋል አንዲሉ ሆኖ ሌላ ጉዳይ ውስጥ ገባሁ፡፡ተማሪዎቹ ያነሱትን ተቃውሞ መደገፍ አለመደገፍ ብሎም መቃወም አንድ ነገር ነው፡፡ በተማሪዎቹ ላይ የተፈጸመውን ህገ ወጥና ኢሰብአዊ ድርጊት በዝምታ ማለፍ ግን ከማንም ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ አይደለም፡ ድርጊቱን በማውገዝ መግለጫ ያወጣው በፕ/ር መረራ የሚመራው ፓርቲ ብቻ ነው፡፡ ፓርቲው ስሙም ዓላማውም በኦሮምያ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ጉዳዩ በቀጥታ ያገባዋልና በተማሪዎቹ ላይ የተፈጸመውን ሕገ ወጥ ድርጊት በማውገዝ ብቻ ሳይወሰን ማስተር ፕላኑንም በመቃወም ነው መግለጫ ያወጣው፡፡
ሌሎች ግን ኦፌኮ አባል የሆነበትን መድረክ ጨምሮ ማስተር ፕላኑን ማውገዝ ባይጠበቅባቸውም ተቃውሞአቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ የተነሱ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ህገ ወጥና ኢሰብአዊ ድርጊት ማውገዝ ነበረባቸው፡፡ በየግዜው ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ህይወት ሰዋዊ ባህርይ በራቃቸው አረመኔዎች እንደ አልባሌ በየሜዳው ሲወድቅ ለጉዳዩ ቅርበት አለን የሚሉ ወገኖች/ ድርጅቶች ድምጽ ብቻ ነው የሚሰማው፡፡ ኢትዮጵያውያን ላይ በተፈጸመ ድርጊት ኢትዮጵያውያን ዝም ብለው አኣለም አቀፍ ድርጅቶች ተቃውሞ ሲያሰሙ መስማት አያሳፍርም ጥያቄ ላይስ አይጥልም፤ ምን ጉዶች ነን፡፡ የእስካሁኑ አልፏል አሁን ግን በዚህ አንድ ተብሎ ሕገ ወጥና ኢሰብአዊ ድርጊትን ሁሉም የማውገዝና የመታገል ጅማሮ ቢያሳዩ አንድ ርምጃ ነበር ፡፡ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ ለይስሙላ ታውመናል አውግዘናል ለማለት ሳይሆን ከልብ አምነውበት ሊሆን ይገባል፡፡

በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም ማስተር ፕላኑን በሚመለከት ያላቸው የሀሳብ አንድነትም ሆነ ልዩነት ጥያቄ ውስጥ ሳይገባ በመሰሎቻቸው ላይ የተፈጸመውን ኢሰብአዊና ሕገ ወጥ ድርጊት ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ነገ እነርሱም ለተቃውሞ የሚያስወጣ የእኔ የሚሉት ጉዳይ ገጥሞአቸው ( የምግብ ጉዳይ፤የመማር ማስተማሩ ጉዳይ ወዘተ ሊሆን ይችላል) ለተቃውሞ ቢንቀሳቀሱ የሚገጥማቸው በተመሳሳይ ዱላና ጥይት መሆኑን በማሰብ ሌላ ሌላው ቢቀር ነግ በእኔ በሚል መንፈስ ዛሬ በኦሮምያ ክልል በሚገኙ ዮኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ሕገ ወጥ ድርጊት ማውገዝና የታሰሩ እንዲፈቱ፤ የተገደሉ እንዲታወቁና ገዳዮች ለፍርድ አንዲቀርቡ መጠየቅ ይኖርባቸዋል፡፡

ተቃውሞው እንዲህ መደጋገፍ መልክ መያዝና ውል ማበጀት ካልቻለ ሁሉም የእኔ የሚለውን ጉዳይ አንጠልጥሎ ለተቃውሞ ሲነሳ ድብደባ እስርና ሞትን እያሰተናገደ ይቀጥላል፡፡ይህ ደግሞ የወያኔ የከፋፍሎ መግዛት እቅድ ውጤት በመሆኑ በወያኔ መበለጣችንንና ለግዞት የተመቻችን መሆናችንን ያሳያል፡፡ በአንዱ የሀገራችን ክፍል ወያኔ ያሻውን ሲፈጽም ሌላው የእኔ ጉዳይ አይደልም ካለ፤በአንድ ብሄረሰብ ላይ ጥቃት ሲፈጸም ሌሎች ብሄረሰቦች የሱ ጉዳይ ለእኛ ምናችን ነው ካሉ፤የኦሮምያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግድያ ለሌላው ኢትዮጵያዊ የማያስቆጣ ከሆነ፤ጎንደር ላይ የተፈጸመው እስረኞች ከእሳት ሲሸሹ በጥይት መፍጀት የሚያስቆጣው አማራውን ብቻ ከሆነ፤ ወዘተ የመከፋፈሉ ሊቅ አቶ መለስ የአክሱም ሀውልት ለወላይታው ምኑ ነው በማለት የዘሩት ፍሬ በሚገባ አፍርቷል ማለት ነው፡፡

The post ውል አልባው ተቃውሞ | ይገረም ዓለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኦሮሞ ወጣቶችን ተቃውሞ በመጠቀም ገዢው መንግስት የኦሮሞን ሕዝብ ከሌላው ሕዝብ ለማጋጨት የሚያደርገውን ሴራ ሕዝቡ በንቃት እንዲመለከት ተጠየቀ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች እስከ ሰው ህይወት ማለፍን ያስተከተለ ተቃውሞ በመካሄድ ላይ መሆኑን ተክትሎ ገዢው መንግስት የተማሪዎቹን ጥያቄ የሃገር አንድነትን ከመበታተን ጋር በማያያዝ በብሔር ለመከፋፈል የሚያደርገውን ሴራ ሕዝቡ በንቃት እንዲከታተለው ተጠየቀ::

nekemt

በተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎች ላይ በተለይም የኦሮሞ ሕዝብ ደጋፊና ተቆርቋሪ በመምሰል ሰሞኑን ተማሪዎቹ እያደረጉ ያሉትን ተቃውሞ በመደግፍ ሌላውን ብሔር የመሳደብ እና የማጥላላት ዘመቻ መጀመሩን ተከትሎ ይህን የሚያደርጉት መንግስት ያሰማራቸው ካድሬዎች በመሆናቸው ሕዝቡ በንቃት እንዲከታተለው ተጠይቋል::

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ እነዚሁ መንግስት ያሰማራቸው የሶሻል ሚዲያ ካድሬዎች ጥያቄው ወደ ሌላ ብሄር ጥላቻ እንዲሸጋገር በማደረግ ከፍተኛ ሥራ ላይ እንደተሰማሩ የታወቀ ሲሆን ይህም እንዲደረግ የተወሰነበት ምክንያት የኦሮሞ ተማሪዎች ጥያቄ የማስተር ፕላን ጥያቄ ሳይሆን የሌላ ብሄረሰብ ጥላቻ እንደሆነ ተደርጎ እንዲወሰድ ነው ተብሏል::

መንግስት የራሱ ን ካድሬዎች በማሰማራት በኦሮሞ ተወላጆች ስም ሆን ብሎ ሌላውን ብሄረሰብ በመሳደብ የተማሪዎቹን ጥያቄ ለማፈን የሚያደርገው ጥረት ከዚህ ቀደምም የተሞከረ እንደነበር ያስታወሱት የፖለቲካ ተንታኞች ባለፈው ዓመት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ የአማራ ተወላጅ ንብረት የሆነ ቤትን በማቃጠል እነዚሁ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች እንዳቃጠሉት በማስመሰል ለፕሮፓጋንዳና ለብሔር ግጭት የሚጋብዝ ሴራ ቢጠነሰስም ሕዝቡ የገዢው መንግስት ሴራ መሆኑን በመረዳት ማክሸፉ ይታወሳል::

በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልሎች ተማሪዎቹ ሰላማዊ ጥያቄ ሲያቀርቡ በመሃላቸው መንግስት ያሰማራቸው ካድሬዎች ሕዝቡ ጋር በመመሳሰል ሌላውን ብሄር የሚሳደቡ መል ዕክቶችን አብረው እንዲናገሩ በማድረግ ሴራ ላይም የተሰማሩ እንዳሉ የጠቆሙት ተንታኞች ተማሪዎቹ ከእንደዚህ ያሉ ተኩላዎች መጠቀሚያ ሳይሆኑ በሰላማዊ መንገድ ሌላውን ሳይነኩ ጥያቄያቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሎ የፖለቲካ ተንታኞች ምክራቸውን ይለግሳሉ::

ከኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መስሪያ ቤት በሶሻል ሚድያዎች በተለይም በፌስቡክ በኦሮሞ ተወላጆች ስም ህዝብን ከሕዝብ የሚያቃቅሩ መል ዕክተኞች የተሰማሩ መሆኑን የሚጠቁሙት ምንጮች እነዚህ ሰዎች የሚያስተላልፏቸውንና ብሄርን ከብሄር ሊያጋጩ የሚችሉ መል ዕክቶችን በንቃት እንዲከታተሏቸው ተጠይቋል::

The post የኦሮሞ ወጣቶችን ተቃውሞ በመጠቀም ገዢው መንግስት የኦሮሞን ሕዝብ ከሌላው ሕዝብ ለማጋጨት የሚያደርገውን ሴራ ሕዝቡ በንቃት እንዲመለከት ተጠየቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live