Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Sport |ኬቪን ደብሩኒ የሲቲዎች አዲሱ አለኝታ

$
0
0

 

ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽል አማካዩ ኬቪን ደብሩኒ በቀድሞው ክለቡ ዎልስበርግ ቆይታው ያለፈው ሲዝንን ያጠናቀቀው በባየር ሙኒክ ስኳድ የሚገኙ በርካታ ወርልድ ክላስ ፉትቦለሮችን በመብለጥ የጀርመን ቡንደስሊጋ ውድድር ኮከብ ተጨዋች በመባል መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ከሁለት ዓመታት በፊት በቼልሲ ቆይታው ሌላው ቀርቶ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ መደበኛ ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን የሚያስችለውን አስተማማኝ ብቃትን ለመያዝ መቸገሩን ከግንዛቤ በማስገባት አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ የ24 ዓመቱ ቤልጅየማዊ ኢንተርናሽልን በእጃቸው ያስገቡበት ውሳኔያቸው ፍሬያማ መሆን መቻሉን ተጠራጥረውት ነበር፡፡ በተለይም በበርካታዎች ዘንድ ከዚህ በፊት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተሳትፎው ስኬታማ ለመሆን አለመቻሉን ከግንዛቤ በማስገባት ማንችስተር ሲቲ በታሪኩ አቻ በማይገኝለት ከፍተኛ የግዢ ሂሳብን ማለትም 54 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ ለዎልስበርግ መክፈሉ ለደብሩኒ ብቃት የሚበዛበት ዋጋ ነው የሚል አመለካከታቸውን ሲገልፁ ተደምጠዋል፡፡

Manchester City v West Ham United - Premier League

ሆኖም ግን ደብሩኒ ለማንችስተር ሲቲ በእስካሁኑ ሲዝን በመስጠት ላይ ያለው ግልጋሎት እጅግ ከፍተኛ ሆኖ መገኘት ፔሌግሬኒ ያወጡበት ከፍተኛ የግዢ ሂሳብን በሜዳ ላይ ባለው ውጤታማ ፉትቦሉ በአግባቡ ለመክፈል እንደሚችል የጠቆመ ሆኗል፡፡ ይህንን በማመንም የባየር ሙኒኩ አሰልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ በያዝነው ሳምንት ውስጥ በሰጠው መግለጫው ‹‹በአሁኑ ወቅት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በመሳተፍ ላይ ካሉት ተጨዋቾች በምርጥ ብቃቱ የቅድሚያው አድናቆት የምገልፅለት ተጨዋች ኬቪን ደብሩኒ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ለዎልስበርግ በተሰለፈባቸው 18 ወራት በሜዳ ላይ ሁሉንም አይነት ስኬታማ ተግባሮን በመፈፀም ሲያስገርመኝ ዘልቋል፡፡ ለማንችስተር ሲቲም በዘንድሮው ሲዝን ይህንን ውጤታማ ፉትቦሉን በተሟላ ሁኔታ ሲደግመው ማየቴ በደብሩኒ አስገራሚ ብቃቶች መገረሜን እንድቀጥል ምክንያት ሆኖኛል፡፡ በእኔ አመለካከትም የዘንድሮው ሲዝን ከጀመረበት ያማረ ታላቅ ፐርፎርንሱ አንፃር ለማንችስተር ሲቲ የተሰለፈበት የመጀመሪያውን ሲዝን የሚያጠናቅቀው በእንግሊዝ ፉትቦል ያሉትን ሁሉንም አይነት የኮከብ ተጨዋችነት ስያሜዎችን በማግኘት ይሆናል፡፡ ዎልስበርግ ደብሩኒን በመሸጡ ደግሞ ምትክ የማያገኝለት ቁልፍ ተጨዋቹን ለማጣት ተገድዷል፡፡ በዛኑ መጠን ግን የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሬኒ እውነተኛ የማሸነፊያ መሳሪያቸውን በእጃቸው ለማስገባት ችለዋል፡፡›› ብሏል፡፡

በእርግጥም ደብሩኒ ከማንችስተር ሲቲ የጨዋታ ስታይል ጋር በፍጥነት በመዋሃድ ለአዲሱ ክለቡ በተሰለፈባቸው በእስካሁኑ ግጥሚያዎች 5 ወሳኝ ጎሎችን ከማስቆጠር አልፎ አራት የጎል አሲስቶችን በስሙ ማስመዝገቡ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በሚገኙት ተጨዋቾች ምርጥ ብቃቱ አቻ የማይገኝለት በሚል በብዙዎች ዘንድ እንዲወደስ ምክንያት ሆኖታል፡፡

ደብሩኒ ከዚህ በፊት ለዎልስበርግ በአብዛኛው የሚሰለፈው የ10 ቁጥር ሚናን በመያዝ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ለማንችስተር ሲቲ ከፈረመ ወዲህ የተጫዋቹ ሁለገብ ብቃት ባለቤትነትን በመገንዘብ ቺሊያዊው አሰልጣኝ በተደራቢ አጥቂነት ብቻ ሳይሆን በግራና በቀኝ ክንፎች በኩልን በመጠቀም የቡድናቸው አጠቃላዩ የማጥቃት እንቅስቃሴን ከፍተኛ ኃይልን እንዲያስገኝለት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ማንችስተር ሲቲ በኢትሃድ ስቴዲየም የስፔኑ ኬቪያን 2ለ1 በሆነ ውጤት በረታበት የቻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ውስጥ በፊት አጥቂ ሚና ተጠቅመውበታል፡፡

kevin de brunye

ይህ ቡድናቸው ወሳኙ የማሸነፊያ ጎልን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረትን በማድረግ ላይ ባለበት ወቅት በግጥሚያው ሂደት የፈፀሙት ታክቲካል ውሳኔያቸው ፍሬያማ ሆኖላቸውም ደብሩኒ የማንችስተር ሲቲ የዘንድሮ ሲዝን የቻምፒዮንስ ሊግ ዘመቻ ወደ ትክክለኛው መስመር ያስገባላቸውን ወሳኙ የማሸነፊያ ጎልን በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ከመረብ ለማሳረፍ ችሏል፡፡ በዚህም በማንችስተር ሲቲ ስኳድ የሚገኙት ተጨዋቾን የቡድናቸው የዘንድሮ ሲዝን አጠቃላዩ ዘመቻ የሚወሰነው ከኬቪን ደብሩኒ ጥሩ ብቃት ጋር በተያያዘ ምክንያት እስከማለት በመድረስ ላይ ናቸው፡፡ ይህንን እምነትን በማሳደር በተለይም እንግሊዛዊያን የቡድኑ ግብ ጠባቂ ጆ ሀርት በሰጠው መግለጫው ኬቪን ደብሩኒን ‹‹የቡድናችን የስኬት መሳሪያ›› በማለት ገልፆታል፡፡ ማንችስተር ሲቲ በአሁኑ ወቅት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ዋነኛ ተቀናቃኙ አርሰናልን በጎል ክፍያ በልጦ በመሪነት ስፍራ ላይ ለመቀመጥ እንዲችልና ከእስካሁኑ ሶስት የቻምፒዮንስ ሊግ ምድብ ማጣሪያ ግጥሚያዎቹ ሁለቱን ድል እንዲቀናው ግንባር ቀደሙን አስተዋፅኦን ካበረከቱለት ተጨዋች ግንባር ቀደሙ ደብሩኒ መሆኑን በማመን ሀርት አስተያየቱን ሲቀጥል፡- ‹‹… በእኔ አመለካከት ኬቨን ደብሩኒ ከክለባችንም አልፎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የእስካሁኑ እጅግ ምርጡ ተጨዋች ለመሆኑ አጠራጣሪ አይደለም፡፡ በእርግጥ ስኳዳችን ሌሎችንም በርካታ ብቃታቸው አስተማማኝ የሆኑ ተጨዋቾችን ይዟል፡፡ በተለይም ሌሎቹ አዲስ ፈራሚዎችን ከሆኑት ውስጥ ራሂም ስተርሊንግና ኒኮላስ አታሜንዴ ለቡድናችን የጨዋታ ስታይል ጋር በፍጥነት ለመዋሃድ ችለው የቡድናችንን ጥንካሬን ወደ ትልቅ ደረጃ ለማሸጋገር የቻሉበት አስተዋፅኦን እያከረክቱልን ይገኛሉ፡፡ ከሁሉም ግን ኬቨን ደብሩኒ እጅግ የተለየ አይነት ተጨዋች ሆኖብኛል፡፡ በእያንዳንዱ ግጥሚያዎች ለቡድናችን ከፍተኛ ወሳኝነት ያለው ጎልን በማስቆጠር ወይም ወሳኝ የጎል አሲስትን በስሙ በማስመዝገብ ማሳለፉን የተለመደ ባህሉ ማድረጉ በከፍተኛ ደረጃ እንድገረምበት ምክንያት ሆኖኛል፡፡ ባለፈው ሲዝን የጀርመን ቡንደስሊጋ ውድድር ኮከብ ተጨዋችነት ስያሜን ማግኘቱን ባወቅም የያዘው ብቃት ግን እንደ አሁኑ ሁሉ ፍፁም እንከን የማይወጣለት ይሆናል በሚል ግምት ግን በጭራሽ እንዳልነበረኝ ከማመን አልቆጠብም›› በማለት ተናግሯል፡፡

ከማንችስተር ሲቲ ቁልፍ ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ ሆኖ የዘንድሮውን ሲዝንን የጀመረው እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ በሌሎች ጉዳዮችም ዙሪያ አስተያየቱን ሰሞኑን ሰጥቷል፡፡ በተለይም በግሉ በያዘው ባህሪን በማስመልከት ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን የሰጠው ‹‹…የተሰጠኝን ኃላፊነት በአግባቡ ለመፈፀም ሁሉንም አይነት ከፍተኛ ጥረቶችን የማደርግበት ባህሪ እንዳለኝ አምናለሁ፡፡ ይህ ባህሪዬ በሜዳ ላይ ላለው ፉትቦሌ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በህይወቴ በማደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ላይ ጭምር ሲደገም መታየቱ የተለመደ መሆኑን እኔን በቅርበት የሚያውቁኝ ሰዎች ምስክርነታቸውን ይሰጡኛል፡፡ ለእያንዳንዱ ግጥሚያዎች አስቀድሜ ከፍተኛ ትኩረትን በመስጠት በተጠናከረ ሁኔታ ልምምድን በመስራት ባህል አለኝ፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ሰሞን የስፔኑ ኬቪያን ባስተናገድንበት የቻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ ከፍተኛ ወሳኝነት ያለውን ድልን ለመቀዳጀት ችለናል፡፡ ሆኖም ግን እኔ በድሉ ከመኩራራት ይልቅ በሳምንቱ መጨረሻ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ለማናደርገው ግጥሚያ በሙሉ ትኩረትን መስጠት የጀመርኩት ሐሙስ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ አንስቶ ነው›› በማለት ነው፡፡

Kevin and sterling

ሀርት በዚሁ መግለጫው ላይ ቡድናቸው የዘንድሮው ሲዝን አጀማመሩን በመዳሰስ አስተያየቱን የሰነዘረው ‹‹የዛሬ ዓመት ከነበረን አጀማመር አንፃር የዘንድሮው ሲዝን አጀማመራችን በመልካም ጎኑ ሊጠቀስ የሚገባው ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህንን ስል ግን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት በአሁኑ ወቅት ያለን አቀማመጥ በሰፊው ሲዝን የሚፈጠረው ሁኔታን የመወሰን ኃይል እንደማይኖረው በማመን ነው፡፡ በእኔ አመለካከትም የዘንድሮ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ፉክክር እስከመጨረሻው ጥቂት ሳምንታት ድረስ የተካረረ ፉክክር የሚያስተናግድበት ይሆናል፡፡ ይህንን ለመቋቋም የምንችለው ደግሞ ከሃያላን ክለቦች ጋር ለምናደርጋቸው ግጥሚያዎች ብቻ ሳይሆን በሊጉ ከሚገኙት እያንዳንዱ ክለቦች ጋር የሚጠብቀን ግጥሚያዎችን በሙሉ ትኩረትን በመስጠት ወደ ሜዳ ለመግባት ስንችል መሆኑን አምናለሁ፡፡ ለምሳሌ የእሁዱ የማንቸስተር ደርቢን የጀመርነው ከፍተኛ የሆነ ትኩረት ሳይለየን ነው፡፡ ይህንን በቀጣይ የሊጉ ግጥሚያዎችም በተሟላ ሁኔታ የመድገም ኃላፊነት አለብን፡፡ ይህንን በአግባቡ ለመፈፀም ስንችል በቀጣዮቹ አምስትና ስድስት ወራት የሚጠብቀን የተጠናከረ ፉክክርን በመቋቋም ማንቸስተር ሲቲን ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር የማገናኘት አላማችንን በአግባቡ ለመፈፀም እንችላለን›› በማለት ነው፡፡

ሀርት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መሳተፍ የጀመረው ገና የ19 ዓመት ወጣት እያለ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ዕድሜው 28 በመድረሱ በዛ ጊዜ ከነበረው አንፃር በአሁኑ ወቅት የተሟላ ብቃት ያለው ግብ ጠባቂ መሆን መቻሉን በማመን በመቀጠልም አስተያየቱን የሰነዘረው ‹‹የግብ ጠባቂዎች ብቃት የሚለካው የሚቃጣባቸው የጎል ማስቆጠር ሙከራዎችን ለማዳን ተሰጥኦአቸው አኳያ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ግብ ጠባቂዎች ከኋላ ሆነው በሚያስተላልፉት መመሪያቸው የቡድናቸው የተከላካይ መስመርን የማደራጀትና የማነቃቃት ኃላፊነት ጭምር አለባቸው፡፡ ይህንን ኃላፊነትን ከአንዱ ዓመት ወደ ሌላው በተሸጋገርኩ ቁጥር ያሳደኩት ተሰጥኦም ከኋላ ሆኜ ለቡድናችን በምሰጠው መመሪያዎች እንዲነቃቁ የማስቻል ተሰጥኦን ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ዕድሜዬ እያደገ ሲሄድ አጠቃላዩ የግጥሚያችን እንቅስቃሴን በአግባቡ የማነብበት ብቃቴም በማዳኑ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንና ለማንችስተር ሲቲ በምሰለፍባቸው ግጥሚያዎች ላይ በፊቴ ከሚገኙት የተከላካይ መስመር ተጨዋቾች ጋር የበለጠ ባማረ ሁኔታ የመግባባት ደረጃዬ ሊያድግልኝ ችሏል ለማለት እችላለሁ›› ብሏል፡፡ የማንችስተር ሲቲው ቁጥር አንድ በአሁኑ ወቅት የዓለም ፉትቦል ከሚገኙት ግብ ጠባቂዎች በምርጥ ብቃታቸው ሶስቱን እንዲጠቅስ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን የሰጠው የባየር ሙኒኩ ማኑኤል ኢዬር፣ የማንቸስተር ዩናይትዱ ዳቪድ ዳሂአና የጁቬንቱሱ ጂያን ሉዊስ ቡፎንን የመጀመሪያዎቹ ሶስቱ ምርጥ ግብ ጠባቂዎች በማድረግ ነው፡፡

The post Sport | ኬቪን ደብሩኒ የሲቲዎች አዲሱ አለኝታ appeared first on Zehabesha Amharic.


ይናገራል ፎቶ

$
0
0

የአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ታምራት ገብረጊዮርጊስ በፌስቡክ ገጹ ላይ የሚከተለውን ፎቶ ለጥፏል:: ፎቶው የአዲስ አበባ አውቶቡስ ሲሆን የተለጠፈው ማስታወቂያ ደግሞ ሹፌሩ ሕግን የማይከተል ሹፌር (በጥንቃቄ የማይነዳ) ከሆነ በተለጠፈው ስልክ ቁጥር እንዲደውሉ ይጠይቃል:: የስልክ ቁጥሩ ግን የኢትዮጵያ ስልክ አይደለም:: ዘ-ሐበሻ ባደረገችው ማጣራት የተለጠፈው ስልክ በተባበሩት አረብ ኤመሬትስ ውስጥ አጅማን በተባለችው ግዛት ውስጥ የሚገኝ የአንድ የአውቶቡስ እና ሹፌር ማከራያ ድርጅት ንብረት ነው::

የኢትዮጵያ ሕዝብ በ”ሕገወጡ” ሹፌር ላይ አስተያየት ለመጥተት የሚደውሉት አጅማን (የተባበሩት ኤመሬትስ ነው?)

tamrat

The post ይናገራል ፎቶ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: በሊቢያ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እጁ ያለበት ያሸባሪዎች መሪ አሜሪካ በወሰደችው ጥቃት ሳይገደል እንዳልቀረ ተገለጸ |የሎስ አንጀለስ ፖሊስ አንድ የቀድሞ የኢትዮጵያን መኮንን አፋልጉኝ አለ |ዶ/ር ኑሩ ደደፎ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ይናገራሉ |የአርበኞች ግንቦት 7 በሳን ሆሴ የተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ለነጻነት ትግሉ የኢትዮጵያውያን ምላሽ |የኢትዮ-ኬኒያ ድንበር ወታደራዊ ውጥረት አይሏል፣ኢትዮጵያ የድንበር ኬላዎቿን ዘጋች…ሌሎችም ዜናዎች አሉ

$
0
0
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ህዳር 12 ቀን 2008 ፕሮግራም

 <…ወያኔ በጉልበት ያለፈው ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ የሞከረውንና ያልተሳካለትን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ዛሬ በህግ ስም የኦሮሚያ ከተሞች አስተዳደር ሕግ በሚል የኦሮሚያ ም/ቤት እንዲያወጣ አድርጎ ለወያኔና ለአባሎቹ የኦሮሞን መሬት ለመንጠቅ ነው። ይሄ ደግሞ …የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከስርዓቱ ጋር እንጂ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ችግር የለበትም ።የወያኔ ስርዓት ለመኖር የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ።ሕዝቦችን ከሕዝቦች ጋር ለማጋጨት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ይሞክራል ራሱ አጣልቶ ገላጋይ ልሁን ይሆናል።ለዚህ ሕዝቦች መጠንቀቅ አለባቸው…>   ዶ/ር ኑሩ ደደፎ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የውጭ ጉዳይ ሀላፊ በቅርቡ የኦሮሞ ድርጅቶች አድርገውት የነበረውን ውይይት አስመልክቶ ካደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

<…ሁበር ከሁለት ዓመት በላይ ሰርቻለሁ። እንዲህ አይነት አደጋ ያጋጥመኛል ብዬ አላሰብኩም። ሰውዬውን ጭኜ ወደመኖሪያው ነበር የወሰድኩት በመንገድ ላይም ስናወራ የነበረው ወሬ ያው የተለመደ አይነት ነበር ቦታው ሲደር ግን ያልጠበኩትን ንግግር መናገር ጀመረ።ሙስሊም መስዬው እንደሆነ ነገር ግን ሙስሊም ባልሆንም ሁሉም ሙስሊም ለዚአ ተጠያቂ እንዳልሆነ በጽሞና ለማስረዳት ለማረጋጋት ሞከርኩ። ሀይለ ቃል መናገር እንደውም ከመኪና እንድወርድ መጠየቅ ጀመረ .. በወቅቱ ሲያደርግ የነበረው እኔን ለማናደድና በግጭት ውስጥ ለማስገባት ነበር።እንዲህ ሲሆን መታገስና ሁኔታውን ለማረጋጋት ሞክሬያለሁ በሁዋላ ግን አልወርድም ብሎ ወደፊት ለመሄድ ስሞክር ደጋግሞ ጭንቅላቴ ላኢ መታኝ…> አቶ ዳንኤል ወ/ሚካኤል ከቻርሎቴ ኖርዝ ካሮላይና ሁበር ሲያሽከረክር በጥላቻ ከተሞላ ተሳፋሪ ጋር የገጠመውን ጥቃት በተመለከተስለ ሁኔታው ከሰጠን ማብራሪአ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የኢትዮጵያው አገዛዝን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አምባገነኖች ከዓለም አቀፉ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ለማምለጥ የሚያደርጉት ሙከራ (ልዩ ጥንቅር)

በቬጋስ በሁበርና ሊፍት አሽከርካሪዎች ላይ ጫና ለመፍጠር የሚደረግ የከተማዋ አስተዳደሮች ሩጫ እና የቀድሞ የፍሪያስ አሽከርካሪዎች የስራ አጥ ኢንሹራንስ ክርክር ለግልግል ዳኝነት የተሰጠውን ቀጠሮ አስመልክቶ የተደረገ ውይይት(ሙሉውን ያዳምጡ)

የአርበኞች ግንቦት 7 በሳን ሆሴ የተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ለነጻነት ትግሉ የኢትዮጵያውያን ምላሽ  (ቃለ መጠይቅ ከዝግጅቱ አስተባባሪዎች ጋር)

ሌሎችም 

ዜናዎቻችን

በሊቢያ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እጁ ያለበት ያሸባሪዎች መሪ አሜሪካ በወሰደችው ጥቃት ሳይገደል እንዳልቀረ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የተከሰተውን አስፈሪ የረሃብ አደጋን ስፋት አገዛዙ ለመደበቅ መሞከሩ ተዘገበ

የኢትዮ-ኬኒያ ድንበር ወታደራዊ ውጥረት አይሏል፣ኢትዮጵያ የድንበር ኬላዎቿን ዘጋች

3 የኢትዮጵያ 4 የኬኒያ ወታደሮች መሞታቸውን የኬኒያ ጋዜጣ ዘገበ

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ህመም ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑና ዛሬም ሕክምና እንዳልተፈቀደለት ተገለጸ

በረሃቡ ሳቢያ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉና በጎዳና ለልመና የተጋለጡ አርሶ አደር ኢትዮጵያውያን  አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ቁጥራቸው እያደገ ነው 

የመኢአድ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አብርሃም ጌጡን ጨምሮ በተለያዩ እስር ቤቶች ቁጥራቸው በርካታ የድርጅቱ አባላት በእስር ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለጸ

የሎስ አንጀለስ ፖሊስ አንድ የቀድሞ የኢትዮጵያን መኮንን አፋልጉኝ አለ 

 ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: በሊቢያ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እጁ ያለበት ያሸባሪዎች መሪ አሜሪካ በወሰደችው ጥቃት ሳይገደል እንዳልቀረ ተገለጸ | የሎስ አንጀለስ ፖሊስ አንድ የቀድሞ የኢትዮጵያን መኮንን አፋልጉኝ አለ | ዶ/ር ኑሩ ደደፎ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ይናገራሉ | የአርበኞች ግንቦት 7 በሳን ሆሴ የተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ለነጻነት ትግሉ የኢትዮጵያውያን ምላሽ | የኢትዮ-ኬኒያ ድንበር ወታደራዊ ውጥረት አይሏል፣ኢትዮጵያ የድንበር ኬላዎቿን ዘጋች… ሌሎችም ዜናዎች አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

አንተም ደመቀ መኮንን |ይድረስ ለማውቅህና ለማታውቀኝ የኢትዮጵያ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን |ከአንተነህ መርዕድ

$
0
0

ኅዳር 2007 ዓ ም
ይድረስ ለማውቅህና ለማታውቀኝ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን።

የኢትዮጵያ ህዝብ እስከአሁን መሪዎቹን መርጦ አያውቅም። ሁሉም በጉልበት ትክሻው ላይ ተፈራርቀው ወጥተውበታል፤ እየተካኩም አሁን ላለበት ከዓለም የመጨረሻነትና የርሃብ ተምሳሌትነት አድርሰውታል፤ አድርሳችሁታል። ያለፈ ታሪክ እየቆፈርን ማን ምን ሠራ እያሉ ለመዘባነን በአሁኑ ወቅት ህሊና ላለው አንገብጋቢ ጥያቄ አይመስለኝም። በእጃችን ላይ ያለውን ዐይኑን አፍጥጦ የመጣውንና የብዙ ሺዎችን ህይወት ለመቅጠፍ “ሀ’’ ብሎ የጀመረውን ርሃብ ለመግታት ደመኛ ጠላቶችም ቢሆኑ የሚተባበሩበት ወቅት ነውና። ከየትም ወገን ይምጣ ርሃብን ለፖለቲካ ፍጆታ የመጠቀምን ያህል ጭካኔ ከቶ የለም።
demeke Mekonnen
ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር! ሰሞኑን መንግስትህን ወክለህ ስለርሃቡ የሰጠኸው መግለጫ አጥንቴ ድረስ ተሰምቶኛል። ማንነትህንና ምንነትህን አጥርቼ የማውቅ ቢሆንም ይህን ያህል ወርድህ በርሃብተኛው ትሳለቃለህ ብዬ አልጠበቅሁም ነበር። በኃይለስላሴ የመጨረሻ ዘመን ርሃብ በጨካኝ እጁ ሰሜን ኢትዮጵያን ሲገርፍ፤ የቻለ ቤተሰብና የቀረች ንብረቱን፣ ያልቻለም ውሃ መጠጫ ቅሉን አንጠልጥሎ በመላ ኢትዮጵያ ነፍሱን ለማዳን ተሯሩጧል። ገና ልጅ ሁኜ ርሃብና መንገድ ያደከማቸው አዛውንት፣ አሮጊት፣ ጎልማሶችና ህፃናት ጎጃም ውስጥ መተከል አውራጃ ለመስፈር ሲሄዱ የነበራቸውን ድካምና እንግልት ዐይቻለሁ። የሚያልፉት በአካባቢዬ ነበርና ትዝታዬ ህያው ነው። እነዚህ ምስኪኖች ድክሟቸው ባረፉበት ሄጄ ከእኩዮቼ ጋር የተጫወትሁት አሁንም ድረስ አይጠፋኝም።

ውድ ደመቀ መኮንን! እኒያ ርሃቡ ካደከማቸውና ጣመኑ ከመታቸው በመንደሬ ተስተናግደው ካለፉት ጎልማሶች አባትህ አቶ መኮንንና ቀሪው ቤተሰብህ እንዳሉበት በእርግጠኝነት እናገራለሁ። ከወሎ መተከል ቻግኒ ያለውን ርቀት ዛሬ በምትንፈላሰስበት ላንድ ክሩዘር ፍጥነት አትለካው። ቤተሰብህ ያንን ሁሉ መንገድ ለሳምንታት በመጓዝ አቋርጠው መተከል መንታወሃ አካባቢ ጫካ መንጥረው በመስፈር፤ በለሙ መሬት ሰርተው፤ ርሃባቸውን አስታግሰው፣ የአካባቢውን ገበያም አጥግበዋል። እየቆዩም በመደላደል ቤተሰቦቻቸውን አምጥተዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ነገሩ ሁሉ አልጋ በአልጋ አልነበረም። ዛሬ አንተና አለቆችህ አይዞህ እያላችሁ በዘረኝነት የቀሰቀሳችኋቸው አዲሶቹ ዘረኛ ካድሬዎች ሠርቶ የሚበላውን ተፈናቃይ ሃያና ሰማንያ እየገደሉ መቅበራቸውን ሰሞኑን በዜና እንደሰማነው ሁሉ፤ በጊዜው አጠራር ሻንቅላ አሁን ደግሞ ጉምዝ የሚባለው አዳኝ ህብረተሰብ በዚያን ጊዜም ሰፋሪዎችን ሳያስቡ ዘምቶባቸው ብዙዎችን በጥይት፣ በቀስትና በገጀራ ጨፈጨፋቸው።

ርሃቡ ያጠቃቸው የወሎ ተሰዳጆች ወደ መተከል ሲሄዱ ሰውነታቸው ቢደክምም በተስፋ ነበር። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ጭፍጨፋ ሲፈፀምባቸው ለማምለጥ የቻሉት ሰፈራችን ሲደርሱ ግን ስለሞቱ ቤተሰቦቻቸው እያለቀሱ ይናገሩ የነበረው አሁንም ልቤ ውስጥ ህያው ሆኖ ይኖራል። እነዚያ አብሬ የተጫወትሁት እኩዮቼና አዛውንቱ ማምለጥ አልቻሉም። ደርግ፣ ወያኔ ሆነ ቀሪው ህዝብ ያወግዛቸው የነበሩት ንጉሥ ፈጥኖ ደራሽ ሰራዊት በመላክ፣ አመፀኞችን በመቅጣት፣ ሰፋሪዎች ተመልሰው ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ አስችለዋል። አንተም የዚያ ስቃይና በኋላም የተፈጠረው መረጋጋት ውጤት ነበርህ።

አቶ ደመቀ መኮንን ይህንን ሁሉ የምዘረዝረው ቀሪው ኢትዮጵያዊ እንዲያውቀው እንጂ አንተማ አታውቀውም ብዬ አይደለም። ይህንን እውነት ለማወቅ ከፈለግህ መተከል መንታውሃ ውረድና በህይወት ያሉትን አባትህን፣ አጎቶችህንንና አክስቶችህን ከዚያ መራራ ትዝታ ጋር እንዴት እንደኖሩ ጠይቃቸው። በዝርዝር ይነግሩሃል። አንተማ ምን ህሊና ኖሮህ ታስታውሰዋለህ! ርሃብን በተመለከተ፣ ድርቅንና ስደትን ከእሱም ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ጨካኝ ሞት በተመለከተ ህያው ምስክር ትሆናልህ ብለው ሲያስቡ፤ በርሃብ ማትረፍና መዝረፍ የለመደው ስርዓት ጠበቃ ሆነህ ሲያዩህ አባትህ አቶ መኮንን፣ መላው ዘመዶችህ፣ እነ አያ ሙሄ፣ እነ ዘይነባ ምን ያህል ያፍሩብህ?

ደመቀ እባክህ ህወሃትን በተለይም መለስ ዜናዊን የማደንቅበትን ብቸኛ ነገር ላካፍልህ። እቃ ፈልጎ የማግኘትን ችሎታ የት እንደተካኑት ጠይቀኻቸዋል? ይህንን ብቃታቸውን ያስመሰከሩበትን ልዘርዝርልህ። ሲጀምሩ ታንምራት ላይኔን፣ ተፈራ ዋልዋን፣ አዲሱ ለገሰን፣ አባዱላ ገመዳን፣ኩማ ደመቅሳን፣ ካሱ ኢላላን ቆይቶ ክፍሌ ወዳጆን፣ ዳዊት ዮሃንስን፣ ገነት ዘውዴን ወዘተ…ፈልገው በማግኘት አስከፊውን ወንጀል ሁሉ ለመስራት ተጠቅመውባቸዋል። እቃ እቃ ነው፤ ያረጃል ያፈጃል።ስለሆነም ህወሃት ሲሰፋና ሲደረጅ ሌላ እቃ ቀየረ፤ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ደመቀ መኮንን፣ አለምነው መኮንን፣ ሺፈራው ሽጉጤ፣ ሬድዋን ሁሴን….ስንቱን የቤት እቃ ልቁጠርልህ?

ትልቁ እውነት ወያኔ እቃ መምረጥ መቻሉ ነው። አንተን ፈልገው ሲያገኙህ ተገርሜአለሁ። ከርሱን ለመሙላት ብቻ ሲል የትኛውንም ሃጢያት የሚሰራላቸው ሰው ያልሆነ ሰው ፈልጎ ማግኘት ችሎታቸው የሚሰነቅ ነው። ገና ደጋ ዳሞት አስተማሪ ሳለህ ለቢራና ለምግብ ስትል አያትህን ከሚያክሉ የቡናቤት ባለቤቶች የፈፀምከውን አስነዋሪና አፀያፊ ምግባር አደባባይ ባውለው አንተ ባታፍርበትም ለቤተሰቦችህ ስል እተወዋለሁ።

ይህ ህሊና ቢስነትህ ነው ወያኔ በመብራት ፈልጎ እንዲያገኝህ ያደረገው። የአማራው ክልል ባለስልጣን ሆነህ መሬቱን ለሱዳን እንዲሰጥ በፈረምክ በጥቂት ጊዜ ሚኒስትር አደረጉህ። ምንም ነገር የሚሞሉብህ ባዶ እቃ መሆንህን የበለጠ ባወቁህ ጊዜ ስልጣን አልለውም ለሌላ አገልግሎት ከፍ አደረጉህ። ነገ እንደሌሎች እስኪወረውሩህ። ደመቀ ዝናቡ እንዳይዘንብ አደረጋችሁ ብሎ የሚያወግዛችሁ የለም። ድርቅ የትም ያለ ነው። ርሃብ ግን የጨቋኝ አገዛዝ ውጤት ነው። በቴሌቪዥን ፊት ወጥቶ ርሃቡን ማስተባበል ምን ሊፈይደው ነው። የኃይለስላሴ ሆነ የደርግ አገዛዝ ርሃቡን ሊሸፍኑት አልቻሉም። እንዳለመታደል ሆኖ የእናንተ ጊዜ ደግሞ የበለጠ አስቸጋሪ ነው። ሶሻል ሚድያው፣ የውጭ የዜና አውታሮች፣ ኢሳትና አገር ውስጥ ያሉ ቆራጥ ኢትዮጵያውያን እስካሉ የማይጋለጥ የኢህአዴግ ወንጀል አይኖርም።

በዚህ ቀውጢ ወቅት፣ አንዲት ጠብታ ውሃና ቁራሽ ዳቦ ህይወት ለመታደግ በምትፈለግበት ሰዓት ለህወሃት ባርነት የተገዛችሁበትን ሰላሳ አምስተኛ ዓመት በሶስት መቶ ሚሊዮን ብር ድግስ ለማክበር መነሳታችሁ ብቻ የጭካኔአችሁን መጠን፣ ሆዳምነታችሁንና ህሊናቢስነታችሁን ፍያ አውጥቶባችኋል። ኃይለስላሴ ሰማንያኛ ዓምመታቸውን ለማክበር፣ ደርግ አስረኛውን የአብዮት በዓል ለማስታወስ፤ ያንን ሁሉ ወጪ ማውጣታቸውን በአወገዛችሁበት አንደበት የህወሃትን የ1977 ማሌሊት ምስረታ፣ የህወሃትን አርባኛ ዓመት፣ የብአዴንን ሰላሳ አምስተኛ ዓመት ከረሃብ ጋር እየተያያዘ መምጣትና የእናንተንም አቅል ማጣት በምን ታስተባብሉታላችሁ? በዚች ቅፅበት የወያኔ አገልጋዮችና አለቆቻችሁ ባህርዳር ከተማ ቁንጣን እስኪይዛችሁ ስትበሉ፤ እስከ አጥንቱ የዘረፋችሁት በመላው ዋግ ህምራ፣ በጎንደርና በጎጃም ቆላማ ቀበሌዎች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህፃናት ደረቁን የእናታቸውን ጡት እየመጠጡ ለዘለዓለሙ በማሸለብ ላይ ናቸው። ወላጆቻቸው አገር ይቀልብ የነበረ ፈርጣማ ክንዳቸው ዝሎና ሟሙቶ፣ ተፈጥሮ ፊቷን አዙራባቸው፣ የልጆቻቸውን ስቃይ ከማየት የማይቀረውን ሞት እየተሳሉ ነውና በምን የሞራል ብቃት ነው እናንተ እየገደላችሁ ላለው አማራ ወኪል የምትሆኑት?

በሶስት መቶ ሚሊዮን ብር ድግስ ህሊናችሁን ልታደነዝዙት ብትታገሉም፣ የአምስት ዓመት ልጇ በርሃብ የሞተባትን ብርቱካን አሊን ከምትኖርበት ሃብሩ ወረዳ ስልሳ ኪሎ ሜትር እርቃ መጥታ ለምለሙ ተሁለደሬ ወረዳ ለጎ ሃይቅ እንድታስተባብል ብታደርጉም፣ መዳ ወላቡ በርሃብ የደከሙ ህፃናትን ብትደባብቁም፣ የአበርግሌውን የእንስሳት እልቂትና የሰውን ህትወት መቀጠፍ መጀመሩን ብትሸፋፍኑም፤ ሥራችሁ የበለጠ እናንተን ከማጋለጥ ሌላ አልጠቀማችሁም። ያለውን እውነት ተቀብሎ ህይወትን ለማዳን ከማንም ጋር መተባበር ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ነበራችሁ። ነገር ግን ምርጫችሁ መውደቂያችሁን ማፋጠን ሁኗል። የሁሉም አምባገነን ባህሪይ ነውና፤ መልካም እድል ለቁልቁለቱ ጉዟችሁ እላለሁ።

ደርግን በመሰለ አምባገነን ስርዓትም ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስና አቶ ሽመልስ አዱኛ በየምዕራቡ አገር እንባ አውጥተው ለምነው የሚሊዮኖችን ህይወት አትርፈዋል። ዛሬ እነሱም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው አንገታቸውን ቀና አድርገው በህዝቡ መካከል በክብር ይንቀሳቀሳሉ። የፀሃይ ሙቀት ሲዋጀው እንደሚጠፋ ጤዛ ስርዓት በተቀየረ ቁጥር እንደምትጠፉት እንደናንተ እንደካድሬዎች አልነበሩም። አይደሉምም።

ደመቀ! ህወሃት ተጠቅሞብህ የመወርወሩ ጉዳይ ቀኑን አታውቀው እንደሆነ እንጂ የማይቀር ለመሆኑ ከጓደኞችህ እጣ ተረዳ። ሌላ ሌላውን ወንጀል ብትሠራላቸውም፤ በድርቅ በተጎዱ ወገኖች አንተ ስትቀልድና ስታስተባብል ግን ሁላችንን ያመናል። አንተም ደመቀ! ብዬ የፃፍሁልህ ለዚህ ነው። ያንን ሁሉ ስቃይ አልፈው በመጨረሻው የህይወት ዘመናቸው ላይ ያሉትን ዘመዶችህን በክፉ ሥራህ አታሳዝናቸው። ምንም ብታገለግላቸው የአንዱን መሃይም ወያኔ አባል ያክል ክብር ከህወሃት አታገኝም። እቃ እቃ ነው።እቃን ባለቤቱ ይገለገልበታል እንጂ አያከብረውም። ወያኔዎች አንተንና ጓደኞችህን እንደ እቃ እንጂ እንደሌላ እንደማያዩአችሁ ልቦናህ ያውቀዋል።

ለቀሪው ኢትዮጵያውያንም መልዕክት አለኝ። ከክርስቶስ ልደት አራት መቶ ዓመት ቀደም ብሎ የኖረው ታላቁ ግሪካዊ ፈላስፋ ፕሌቶ “one of the penalties for refusing to participate in politics, is that you end up being governed by your inferiors” “በፖለቲካ አልሳተፍም የማለትህ አንዱ ቅጣት፤ በሁለመናቸው የበታቾችህ በሆኑ ስትገዛ መኖርህ ነው” ብሏል። ሁሉንም ነገር ፖለቲካ ነው የምንልና የምንሸሽ ጅሎች እነዚህን በመሰሉ ትንንሾች የመገዛታችን ንግርት በፕላቶ ተነግሮን በተግባር እያየነው ነው።ጥፋቱ የትንንሾቹ ሳይሆን እንዲገዙን የፈቀድንላቸው የእኛ ነው። ደመቀ፣ ኃይለማርያም፣ በረከት፣ ሬድዋን፣ አባይ ወልዱ ሆነ ቴዎድሮስ አድሃኖም ወገኖቻችንን በርሃብ ሲገርፉ፣ ሲዘርፉ የመኖራቸው ምክንያት የእኛው ድክመት ነው።

ድርቁ የምግብ ብቻ አይደለም። ለራስ ነፃነት ለመታገል አለመቁረጣችንም ነው። ይህንን ለመለወጥ እስካልተነሳን ለትንንሾች ስንገዛ፣ አገሪቱም ስትዋረድ ትኖራለች።
መጥኔ በሁለመናው ለተራብነው!!

The post አንተም ደመቀ መኮንን | ይድረስ ለማውቅህና ለማታውቀኝ የኢትዮጵያ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን | ከአንተነህ መርዕድ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፤ የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚደንት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የመልካም አስተዳደርና ሙስና ችግሮች ይናገራሉ | Audio

“በአዛዙ የአፈና መዋቅር የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነትና የእኩልነት ትግል አይቀለበስም”–ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

semayawi
ህወሓት/ኢህአዴግ በህገ መንግስቱና በሌሎች ራሱ ባወጣቸው ህጎች በርካታ መብቶችን ለይስሙላ ቢደነግግብ ቅሉ፤ በተግባር ግን እነዚህን መብቶች ሆነ ብሎ ባደራጀው የአፈና መዋቅሩ እየደፈቃቸው ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን አገዛዙ የመደራጀት መብትን በወረቀት ቢያሰፍርም ‹‹እግር እስኪያወጡ እንጠብቃለን፤ እግር ሲያወጡ ግን እንቆርጣለን›› በሚል መርህ ፓርቲዎችን በዚሁ የአፈና መዋቅሩ በገሃድ እያፈረሰ ቀጥሏል፡፡ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ፈቅጃለሁ ቢልም ጋዜጠኞችን በማሰር፣ በማሳደድና ሚዲያዎችን በመዝጋት አማራጭ ሀሳብ እንዳይራመድ አድርጓል፡፡ የመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን ወረቀት ላይ ቢደነግግም በአስተዳደራዊ መዋቅሩ መሰረት ክርችም አድርጎ ዘግቶታል፡፡ የዜጎችን የመዘዋወር መብት ቢደነግግም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፓስፖርት በመንጠቅ ጉዟቸውን በማተጓጎል ላይ ይገኛል፡፡ የመንግስት አሰራር ግልፅና ተጠያቂነት አለበት ተብሎ ተደንግጓል፤ ነገር ግን በየ መስርያ ቤቱ ያለ እጅ-መንሻ ዜጎች አገልግሎት ማግኘት አይቻልም፡፡ ይህ ሁሉ አፈና ሆነ ተብሎ ታስቦበት፣ የአገዛዙን ስልጣን ለማራዘም የሚደረግ መዋቅራዊ ጫና መሆኑን ፓርቲያችን በጽኑ ያምናል፡፡
ዛሬ በሀገራችን ከፍተኛ ርሃብ፣ ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ስራ አጥነት፤ ስደት እና ሌሎችም ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውሶች በሰፊው ተንሰራፍተው ይገኛሉ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እነዚህን ወቅታዊ ጉዳዮች ከህዝብ ጋር ተወያይቶ አቋም ለመውሰድና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለመሰንዘር ህዳር 18 ቀን 2008 ዓ.ም ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርግ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የእውቅና ደብዳቤ ለማስገባት በተደጋጋሚ ጥረት ያደረግን ቢሆንም የአፈና መዋቅሩ የእውቅና ደብዳቤውን መቀበል ባለ መፈለጉ ለ5 ጊዜ ተጉላልተን በ6ኛው በሪኮመንዴ(በፖስታ) ለመላክ ተገደናል፡፡

የእውቅና ደብዳቤው በሪኮመንዴ የደረሰው አስተዳደሩ ህዳር 6 ቀን 2008 ዓ.ም ላይ ሆኖ ‹‹ህዳር 18/2008 ዓ.ም አልፏል›› በሚል ለተጨማሪ ጊዜ ደብዳቤውን ሳያስተናግድ ቀርቷል፡፡ ህዳር 18 ያላለፈ መሆኑን ካስረዳን በኋላ ለሶስት ቀናት በተደጋጋሚ ብንመላለስም ‹‹ከደህንነትና ፖሊስ ጋር ካልተመካከርኩ እውቅና አልሰጥም›› ሲል እምቢታውን ገልጾአል፡፡ በዚህም ምክንያት ከአባላትና ደጋፊዎቻችን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ልናደርገው የነበረው ውይይት ሊደናቀፍ ችሏል፡፡

ከዓለም የነጻነት የትግል ታሪክ እንደምንገነዘበው በአገዛዝ አፈና የተገታ የህዝብ ጥያቄ ኖሮ አያውቅም፡፡ አፈናው የነጻነትን ጊዜ ቢያዘገይ እንጅ ፈጽሞ ሊያስቀርም አይችልም፡፡ ስለሆነም ጭቆናው ወደ ነፃነት የሚያስኬደውን ጉዞ እልህ አስጨራሽ ከማድረግ በቀር ዘላቂነት ኖሯቸው የነጻነት ጥያቄውን ፈጽሞ ማዳፈን እንደማይችሉ አገዛዙ ሊረዳ ይገባል፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብ ለማይቀረው የነፃነት ትግል ቆርጦ እንዲነሳና ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ህዳር 14 ቀን 2008 ዓ.ም
አዲስ አበባ

The post “በአዛዙ የአፈና መዋቅር የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነትና የእኩልነት ትግል አይቀለበስም” – ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ አገዛዝ ዋና ዋና ባለስልጣናትን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች ሲሰሩት ከኖሩት የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማምለጥ ሩጫ ላይ ናቸው

$
0
0

የኢትዮጵያ አገዛዝ ዋና ዋና ባለስልጣናትን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች ሲሰሩት ከኖሩት የዘር ማጥፋት፣ በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ዓለም አቀፍ ወንጀል ለማምለጥ ሩጫ ላይ ናቸው:: ዓለም አቀፉን የወንጀለኛ ፍርድ ቤት በማውገዝ ተጠምደዋል – ይለናል የጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ ዘገባ።

ጋዜጠኛ ታምሩ ለሕብር ራድዮ ያዘጋጀውን ትንታኔ ያድምጡ::

የኢትዮጵያ አገዛዝ ዋና ዋና ባለስልጣናትን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች ሲሰሩት ከኖሩት የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማምለጥ ሩጫ ላይ ናቸው

The post የኢትዮጵያ አገዛዝ ዋና ዋና ባለስልጣናትን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች ሲሰሩት ከኖሩት የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማምለጥ ሩጫ ላይ ናቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ‹‹የምኖረውና የማስበው ስለ አሁኑ ብቻ ነው›› ሜሲ – (አዲስ ቃለምልልስ ከያሁ ስፖርት ጋር)

$
0
0

የትናንት ምሽቱን የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ሳይጨምር ለአራት ጊዜው የዓለም ኮከቡ ሊዮኔል ሜሲ የዘንድሮ ሲዝን በመልካም ጎኑ የሚጠቀስለት አይደለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ከጥቂት ሳምንታት በፊት በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ ከሜዳ ለመራቅ ከመገደዱም አልፎ በጥሩ ጤንነት ሆኖ ግጥሚያዎችን የሚያደርግበት ጊዜ መች እንደሚሆን እርግጠኛ ሆኖ የማያውቀው ነገር የለውም፡፡ የ28 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ኢንተርናሽል በአሁኑ ወቅት ከጉዳቱ ለማገገም በተጠናከረ ሁኔታ ጥረትን በማድረግ ላይ ባለበት ሁኔታ ስሙን ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሃያላን ክለቦች ዝውውር ጋር በስፋት የሚያያዙት ዘገባዎች በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡
mesi2
ከዚህ በፊትም የሜሲ ስም ቼልሲ፣ ማንችስተር ሲቲና ማንችስተር ዩናይትድን ከመሳሰሉት የእንግሊዝ ሃያላን ክለቦች ዝውውር ጭምጭምታ ጋር አብሮ መነሳቱ የተለመደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የእስካሁኑ የፉትቦል ህይወቱን በባርሴሎና ማሊያ ያሳለፈው ሜሲ አስተያየቱን ከመስጠት ተቆጥቦ መዝለቁ ይታወቃል፡፡ በያዝነው ሳምንት ውስጥ ከያሆ ስፖርት ድረገፅ ጋር ባደረገው ሰፊ ቃል ምልልሱ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ ‹‹ወደፊት ከስፔን ውጪ በሌላ ሀገር ትልቅ የሊግ ውድድር የመሳተፍ ፍላጎት ይኖርሃል›› በሚል ለቀረበለት ጥያቄ ሜሲ ምላሹን የሰጠው ‹‹ወደፊት ስለሚፈጠረው ጉዳይ አስቀድሜ የማስብ ባህል የለኝም፡፡ ምክንያቱም ሁልጊዜም የምኖረውና የማስበው የአሁኑ ህይወቴን ብቻ ነው፡፡ የማውቀው ለበርካታ ዓመታት ከባርሴሎና ባለመለየት ያማረ ህይወትን አሳልፌያለሁ፡፡ በአሁኑ ወቅት በባርሴሎና ባለኝ የተረጋጋ ህይወት ሙሉ ለሙሉ ደስተኛ ነኝ ከሁለት ልጆና ከአጠቃላዩ ቤተሰቦቼ ጋር በአሁኑ ወቅት አስደሳች ህይወትን በመኖር ላይ ነኝ፡፡ ተስፋ የማደርገውም ይህ ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥልልኝ ብዬ ነው፡፡››
ይህንን የሜሲ መግለጫን ተከትሎም የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ማሪያ ባርቶሚ በሰነዘሩት አስተያየት የቡድናቸው ቁልፍ ተጨዋች ‹‹በየጊዜው ስሙ ከተለያዩ ሃያላን ክለቦች ዝውውር ጭምጭምታዎች ጋር ሲያያዝ መስማት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሰለች ሆኖብኛል›› የሚል መግለጫቸውን ሰጥተዋል፡፡ በተለይም ባለፈው ሳምንት ውስጥ አብዛኛዎቹ የስፔን ሚዲያዎች ሊዮኔል ሜሲ በጉልበቱ ላይ ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም እያደረገው ከሚገኘው ጥረት በተጓዳኝ ባርሴሎናን በዘንድሮ ሲዝን መጠናቀቅ በኋላ የመልቀቅ ሃሳቡን ከመያዝም አልፎ ቀጣዩ ክለቡ ማን መሆን አለበት የሚለውን ጉዳይ ልዩ ትኩረትን ሰጥቶበት በማመዛዘን ላይ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የመሳተፍ ፍላጎቱ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እያደገ ሄዷል በሚል የቀረበው ዘገባ ለባርሴሎናው ፕሬዝዳንት የሚያበሳጭ ሆኖባቸዋል፡፡

ባርቶሜ በአንርጀንቲናዊው ኮከብ ዙሪያ እንደዚሁም አይነቱ ጭምጭምታዎች መሰማታቸውን የሚጠሉበት ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ የጭምጭምታዎቹ መሰማት ከጉዳቱ በማገገም ጥረቱ ሙሉ ትኩረትን ከመስጠት እንዲቆጠብ የበኩሉን ስነ ልቦናዊ መረበሽን ይፈጥርበታል በሚል ስጋት ስላላቸው መሆኑን ከመጠቆምም አልተቆጠቡም፡፡

ባርቶሜ በጉዳዩ ዙሪያ በያዝነው ሳምንት ኤይቲ ቲቪ ለተባለው ቻናል መግለጫቸውን የሰጡት ‹‹ሊዮኔል ሜሲ ባርሴሎናን የመልቀቅ ፍላጎት ይኖረዋል ብለው የሚያስቡት ሰዎች ራሳቸውን ላልተፈለገ የግራ መጋባት መንፈስ ያጋለጡት ብቻ ናቸው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ምክንያቱም ራሱ ሜሲ ብቻ ሳይሆን ወላጅ አባቱ በተደጋጋሚ የሚናገሩት ባርሴሎናን የመልቀቅ ሃሳብ በጭራሽ ሊኖረው እንደማይችል ነው፡፡ ከባርሴሎና ጋር ያለው ወዳጅነት እንዳለፉት በርካታ ዓመታት ሁሉ እጅግ ያማረና የተዋበ ሆኖ ዘልቋል፡፡ ከሜሲ ባሻገር የቤተሰቡ አባላት በጠቅላላ ከክለባችን ጋር እርስ በርስ የተዛመዱ ናቸው ለማለት እችላለሁ፡፡ በአሁኑ ወቅት ከባርሴሎና ጋር ያለው ኮንትራት የሚጠናቀቀው ከሶስት ዓመታት በኋላ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ለሜሲ አዲስ ኮንትራት ለመፍቀድ የምንጣደፍበት ምንም አይነት ምክንያት አይኖረንም፡፡

በአሁኑ ወቅት ግን በታክስ ጉዳይ ከስፔን መንግሥት የተነሳበትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ብቻ ተጨባጭነት የሌላቸው ዘገባዎች እየቀረቡበት መሆኑ የክለባችን አባላት የሚያበሳጭ ሆኖብናል፡፡ ምክንያቱም እንደዚህ አይነቱ ከሃቅ የራቀ ጭምጭምታ ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም በሚያደርገው ጥረት ላይ ሙሉ ትኩረት እንዳይኖረው የሃሳብ መበታተን ችግር እንዳይፈጥርበት ስጋትን ያሳደረብን ሆኖናል›› በማለት ነው፡፡

mesi

የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት በዚሁ መግለጫው ላይ በሌላው የቡድናቸው ተጨዋች ማለትም ብራዚላዊው ኢንተርናሽል ኔይማር ኮንትራት ሁኔታ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሻቸውን የሰጡት ‹‹የኔይማር ጉዳይ ከሜሲ አንፃር በብዙ መልኩ የተለየ በመሆኑ በዘንድሮው ዓመት አዲስ የኮንትራት ማራዘሚያ ውልን ልናቀርብለት አቅደናል፡፡ አስቀድመን ለኔይማር ቃል በገባንለት መሰረት ከወዲሁ የኮንትራት ማራዘሚያ ድርድሩ የመጀመሪያው ምዕራፍ ተግባራዊ በመሆን ላይ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው የኔይማር ተጨመሪ በርካታ ዓመታት ከክለባችን መሰለፍን እንዲቀጥል ከፍተኛ ጉጉትን አሳድረን መዝለቃችንን ነው፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት ከቡድናችን እጅግ ቁልፍ ተጨዋቾች ውስጥ መሆኑን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከያዘው አጠቃላይ አስተማማኝ አቋሙ በቀላል ለመረዳት የምንቸገር አይሆንም በማለት ነው፡፡

‹‹በእርግጥ ኔይማር በቅርብ ሳምንታት ወዲህ ባርሴሎና በተከታታይ ግጥሚያዎች ድልን ለማስመዝገብ እንዲችል ከፍተኛ አስተዋፅኦን እያበረከተለት ይገኛል፡፡ የቀድሞው የሳንቶ ክለብ ስታር ባለፉት ዓመት የባርሴሎና ግጥሚያዎቹ አምስት ጎሎችን በስሙ ለማስመዝገብ መቻሉ ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ባለፉት ስድስት የባርሴሎና የሁሉም ውድድሮች ግጥሚያዎች ላይ በአጠቃላይ 5 የጎል አሲስቶችን በስሙ ለማስመዝገብ ችሏል፡፡ ይህ የሚያሳየው ሊዮኔል ሜሲ በጉዳት ከሜዳ ከራቀ ወዲህ ለባርሴሎና ውጤታማ ተግባርን በመፈፀም የ23 ዓመቱ ብራዚላዊው ኢንተርናሽናል ግንባር ቀደሙ ስፍራን ለመያዝ መቻሉን ነው፡፡ ከኔይማር ባሻገር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባርሴሎና አይበርን 3ለ1 በፈታበት የስፓኒሽ ላሊጋ ግጥሚያው ሀትሪክ የሰራው ኡራጓዊው አጥቂ ሉዊስ ስዋሬዝ በጥሩ አቋም መገኘት የካታላያኑ ክለብ ደጋፊዎች የሜሲ ጉዳት ከሜዳ መራቅ በቡድናቸው ውጤታማነት ላይ ያስከተለው ያንን ያህል ጎልቶ የሚጠቀስ ችግር አለመኖሩን እንዲገነዘቡት የረዳቸው ቢሆንም የአብዛኛዎቹ የባርሴሎና ደጋፊዎች ከፍተኛ ጉጉት ግን ቡድናቸው በቀጣዩ ወር ከሪያል ማድሪድ ጋር ለሚያደርገው የዘንድሮ ሲዝን የመጀመሪያው ኤልክላሲኮ ፍልሚያ የሜሲ በጥሩ ጤንነት ሆኖ መድረስ መቻልን ማየት ነው፡፡ ሜሲ በሰሞኑ ቃለ ምልልሱ ግን ከጉዳቱ አገግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰለፍበት ግጥሚያ የትኛው እንደሚሆን ለመገመት መቸገሩን ተናግሯል፡፡ በአሁኑ ወቅት ቲያጎና ማቲዬ የሚል መጠሪያ ያላቸው ሁለት ልጆችን ያፈራው ሜሲን በቃለ ምልልሱ ላይ ከተነሱለት ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ ሁለት ልጆች አባት መሆኑ በሜዳ ላይ ላለው ፉትቦሉ ዙሪያ ያስከተለበት ለውጥ አለ የሚለው ይገኝበታል፡፡ ለጥያቄው ምላሹን የሰጠው እንደማንኛውም አባት ሁሉ ልጆቼን የማሳድግበት ተጨማሪ ኃላፊነት ያሸከመኝ ሆኗል፡፡ ይህ ግን በሜዳ ላይ ላለው ፉትቦሌ እንደወትሮው ሁሉ የማደርገው ሙሉ ትኩረትን የቀነሰብኝ አልሆነም›› በማለት ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጨዋታው ሚና ስለመቀየሩና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ላደረገው ቃለ ምልልስ ይህንን ይመስላል፡፡

ጥያቄ፡-ስለ አሁኑ የጨዋታ ሚናህ ምን አስተያየት አለህ?
መልስ፡- በእያንዳንዱ ግጥሚያዎች ከቡድናችን ከፍተኛ ጠቀሜታን ለማስገኘት ይችላል ብለን ባመንበት መልኩ የጨዋታ እንቅስቃሴዎችን የማድረግ ባህል አለን፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ ጊዜ ወደ ኋላ ተመልሼ ኳስ የማዘጋጀት ተግባርን የምፈፅምበት እንዲሁም ጎሎችን በማስቆጥርበት ቦታ ላይ የመገኘት ኃላፊነቱን የምፈፅምበት አጋጣሚዎችም አሉኝ፡፡ እንደዚህ አይነቱ በበርካታ ተግባሮች ላይ በመሳተፍ የጨዋታ እንቅስቃሴን ማድረግ የባርሴሎና የተለመደ ባህል በመሆኑ አዲስ ተቀይሯል የምለው የጨዋታ ስታይል ለውጥ ያንን ያህል የለም ለማለት እደፍራለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሚጫወትበት የእግርኳስ ትውድል አብረህ መጫወት ላይ መሆንህ ችሎታህን ወደ ትልቅ ደረጃ ለማሸጋገር እንድትችል ያደረገልህ ድጋፍ አለ?
መልስ፡- እንደዚህ አይነት አመለካከት በሰዎች ዘንድ መኖሩ ያስገርመኛል፡፡ ምክንያቱም እኔ በግሌ ራሴን ከክርስቲያኖ ሮንልዶ ጋር ፉክክርን በማድረግ ላይ ነኝ በሚል የቆጠርኩበት ወቅት የለኝም፡፡ በእኔ ግምትም እሱም (ክርስቲያኖ ሮናልዶን) ከእኔ ጋር ፉክክር በማድረግ ላይ ነኝ የሚል አመለካከትን መያዙን እጠራጠራለሁ፡፡ የእኔ ሙሉ ትኩረት ለምሰለፍበት ቡድን ውጤታማነት በተቻለኝ አቅም ሁሉ ጥረትን ማድረግ መቻል ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱ መንፈሴን ወደፊትም ቢሆን ልቀይረው እንደማልሻ ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ከአገርህ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያለህ ግንኙነት ምን ይመስላል? ሰዎች እንደሚናገሩት ሁሉ በበርካታ ውጣ ውረዶች የተሞላ ነው?
መልስ፡- አጀርንቲናዊያን በአብዛኛው ከፍተኛ የሆነ የእግርኳስ ፍቅር ያላቸው በመሆናቸው የአገራችንን ብሔራዊ ቡድንን በትልቅ ኢንተርናሽናል ውድድር ደረጃ በመወከል ለምንጫወተው ተጨዋቾች ከፍተኛ የሆነ ክብርን የሚሰጡበት አመለካከትን ተላብሰዋል ለማለት እችላለሁ፡፡ በዚሁ መልኩ ግን በጣም ጥቂቶች ለአገራችን ብራዊ ቡድን ስኬታማነት በሜዳ ላይ የተቻለንን ሁሉ ጥረትን በምናደርግበት ወቅት ጩኸትን በማሰማት ሊሰድቡን የሚሞክሩ አሉ፡፡ሆኖም ግን እኔ በግሌ ሁሌም የአገራችንን የፉትቦል አፍቃሪዎች በእኩል አይን የመመልከት ባህል አለኝ፡፡

ጥያቄ፡- በአመጋገብ ስርዓትህ ላይ መጠነኛ ለውጥን አምጥተሃል ስለሚባለው ነገር የምትነግረን ይኖርሃል?
መልስ፡- ጠንካራ ሰውነት እንዲኖረኝ ምንም አይነት ጠቀሜታን የማይሰጡን አንዳንድ የምግብ አይነቶችን ከመቀነስ በስተቀር በአመጋገብ ስርዓቴ ላይ ያመጣሁት አጠቃላይ ለውጥ የለም፡፡ ከሌሎች ፕሮፌሽናል ፉትቦለሮች በዚህ ጉዳይ እለያለሁ የሚል እምነት የለኝም፡፡

ጥያቄ፡- በሌላ አገር የሊግ ውድድር ለመሳተፍ የምትችልበት አጋጣሚ ይኖርሃል?
መልስ፡- ወደፊት ስለሚፈጠረው ነገር ከወዲሁ አስቀድሜ በማሰብ አስተያየቴን ለመስጠት አልሻም፡፡ የምኖረውና የማስበው በአሁኑ ወቅት ስላለኝ ህይወት ብቻ ነው፡፡ ይህ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በስፓኒሽ ላ ሊጋ ውድድር ተሳትፎና በባርሴሎና ክለብ መገኘቴን ብቻ ነው የማውቀው፡፡ የማስበው በቅር ስለሚፈጠሩ አውነታዎች ብቻ መሆኑን በድጋ ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ከዚህ በፊት የግል ህይወትህን የያዘው መፅሐፍን ማንበብህን መጀመርህ ተነግሮን ነበር፤ አሁንስ መፅሐፍን አንበብህ ጨርሰኸዋል?
መልስ፡- ስለ እውነቱ ለመናገር መፅሐፉን አንብቤ አልጨረስኩትም፡፡ ምክንያቱም ባለፈው ታሪክም ሆነ ወደፊት ከበርካታ ዓመታት በኋላ ስለሚፈጠረው ነገር ማሰብን አልወድም፡፡

ጥያቄ፡- በሜዳ ላይ በምታደርገው ፉትቦልን ይበልጥ እንዲደሰት የምትጓጓው እነማን ነው የምትሰለፍበት ቡድን ደጋፊዎችን ወይስ ቤተሰቦችህን?
መልስ፡- ወደ ሜዳ የምገባው በውጤታማ ፉትቦሌ የማስደስተው ሰው እንዲኖረኝ መመኘትን ዋነኛ አላማዬ በማድረግ አይደለም፡፡ እግርኳስን በከፍተኛ ደረጃ ስለምወደው እጫወታለሁ፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ወደ ሜዳ ይዤው የምገባው ዋነኛ አላማ ለምሰለፍበት ቡድን ስኬታማ ተግባርን ለመፈፀም የተቻለኝን ሁሉ ጥረትን ማድረግ መቻል ነው፡፡

ጥያቄ፡- በቅርቡ ጉዳት ሲደርስብህ ለመጀመሪያ ጊዜ በውስጥህ ያሳደርከው ስሜት ምንድነው?
መልስ፡- ከዚህ በፊት ጉዳት ሲደርስብኝ ከነበረኝ ሁኔታ በተለየ ለየት ያለ ስሜትን አሳድሬያለሁ፡፡ ምክንያቱም ጉዳቱ አንድ መደበኛ ግጭት አለመሆኑንና አስከፊነት ያለው መሆኑን ያወቅኩት ገና ከዛኑ ጊዜ አንስቶ ነው ለጉዳት መጋለጥ ለማንኛውም ፕሮፌሽናል ስፖርታዊ ትልቁ ሃዘንን የሚፈጥር ጉዳይ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን በጠንካራ ስነ ልቦና ሆኜ በፍጥነት ለማገገም የሚረዳኝን እንቅስቃሴዎችን ላይ በመሆኔ ጥረቴ ፍሬያማ እንደሚሆንብኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ጥያቄ፡- ከሪያል ማድሪድ ጋር ለሚረገው የዘንድሮው ሲዝን የመጀመሪያው ኤልክላሲኮ እደርሳለሁ የሚል ግምት አለህ?
መልስ፡- በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እርግጠኛ ሆኜ አስተያየትን መስጠት ይከብደኛል፡፡ ሙሉ ትኩረት የህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡንን መመሪያን በማክበር ሁሉንም አይት የማገገም ጥረቶችን በማድረጉ ተግባር ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን በጥሩ ጤንነት የምገኝበት ወቅትን በትክክል ለመገመት የሚችሉት በማገገም ጥረቴ ከጎኔ ሳይለዩ ድጋፍን እየሰጡን በሚገኙት የህክምና ባለሙያዎች እንጂ እኔ ልሆን አልችልም፡፡

ጥያቄ፡- ባርሴሎና ያለፈው ሲዝንን የሶስት ትላልቅ ውድድር ዋንጫዎች ድሎችን ዘንድሮ ይደግመዋል የሚል እምነት አለህ?

መልስ፡- የውድድር ዘመኑ ገና የመጀመሪያው ሶስት ወራት ያላለቀ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ከወዲሁ እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም የሲዝኑ ሰፊው አካል ያለው ከፊታችን ያለው ስድስት ሰባት ወራት ውስጥ ነው፡፡ ካለፈው ሲዝን በትሪፕል ዊነርነት(ሶስት ዋንጫ) ድል ለማጠናቀቅ የቻሉት አብዛኛዎቹ የቡድናችን ተሰላፊዎች እስካሁንም ድረስ በስኳዳችን የሚገኙ በመሆናቸው ግን በተሳተፍንባቸው እያንዳንዱ ውድድሮች የዋንጫ ሽልማቶችን ለማግኘት እንችላለን የሚል ሙሉ እምነትን ለማሳደር የምንቆጠብበት ምክንያት አይኖረንም፡፡

የውድድር ዘመኑን የጀመርነውም በጥሩ አቋም ሆነን መሆኑን አምናለሁ፡፡ ከመጀመሪያዎቹ ዘጠን የስፓኒሽ ላ ሊጋ ግጥሚያዎች በኋላ በደረጃው ሰንጠረዥ ከዋነኛ ተቀናቃኞቹ ሪያል ማድሪድ እኩል 21 ነጥቦችን መያዛችን ከግንዛቤ ሲገባም የዛሬ ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ከነበረን የነጥብ ድምር አንፃር የዘንድሮው የተሻለ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ያለፈው ሲዝን እስኪጋመስ ድረስ በቡድናችን ላይ የታየው የአቋም አለመረጋጋት ችግር ዘንድሮ ሲደገም አልታየም፡፡ ከዚህ አንፃር የዘንድሮ ሲዝንን ለሌላ የትሪፕል ዊነርነት ድል ለመብቃት በማለም የማናካሂድበት ምክንያት አይኖርም፡፡

The post Sport: ‹‹የምኖረውና የማስበው ስለ አሁኑ ብቻ ነው›› ሜሲ – (አዲስ ቃለምልልስ ከያሁ ስፖርት ጋር) appeared first on Zehabesha Amharic.


ኢትዮጵያዊው ፍቅር ሲመነዘር ፊልም እና የጣሊያኑ Ti va di pagare? (Priceless) ፊልም

$
0
0

ኢትዮጵያዊው ፍቅር ሲመነዘር ፊልም እና የጣሊያኑ Ti va di pagare? (Priceless) ፊልም

የፍቅር ሲመነዘር ፊልም ደራሲና አዘጋጅ ፊልሙን ሲጽፈው መነሻ ታሪኩ የተወሰደው ከዚሁ ከጣሊያኑ Ti va di pagare (Priceless) ፊልም መሆኑን ቢገልጽም ሙሉ በሙሉ ነው ሊባል በሚያስችል ሁኔታ ነው ኮፒ ያደረገው:: የተወሰነውን ክፍል ቆራርጠን አቅርበናል ይመልከቱት::

The post ኢትዮጵያዊው ፍቅር ሲመነዘር ፊልም እና የጣሊያኑ Ti va di pagare? (Priceless) ፊልም appeared first on Zehabesha Amharic.

ማለዳ ወግ |የሳውዲው ባለሃብት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ቅሬታ ማሰማት ጀመሩ | * “በኢትዮጵያ በደልና ዘረፋ ተፈጸመብን !”ባለሃብቱ

$
0
0

=========================================
* “በኢትዮጵያ በደልና ዘረፋ ተፈጸመብን !” ባለሃብቱ!
* ” ቅሬታ ውንጀላው መሰረት ቢስ ነው ” የኢትዮጵያ ዲፕሎማት

ህዳር 15 ቀን 2008 ዓም በወጣው ታዋቂው የሳውዲ ጋዜጣ አረብ ኒውስ የኢትዮጵያ መንግስት አንዳንድ ባለስላጣኖች መሬታቸውን እየተቀሙ በደልና ዘረፋ እየተፈጸመባቸው መሆኑን ሞሀመድ አልሸህሪ የተባሉ ባለሃብት ለአረብ ኒውስ አስታውቀዋል። እኒሁ ባለሃብቶችን መርተው ወደ አፍሪካና ወደ ኢትዮጵያ ከአመታት በፊት ወደ የዘለቁት ባለሃብት አንዳንድ የመንግስት ኃላፊዎች በኢንቨስትመንት ፈቃድ ወደ ሀገሪቱ ያስገቡትን ንብረቶች ለመውረስ በእርሳቸውና በጓደኞቻቸው ላይ የወንጀል ክስ አንደተመሰረተባቸው ማስታወቃቸውን አረብ ኒውስ ዘግቧል ። ቅሬታ አቅራቢው ሳውዲ ባለሃብት ሞሃመድ አልሸህሪ ለአረብ ኒውስ ጋዜጣ እንዳስታወቁት ሙስናው የከፋ እየሆነ መምጣቱን በመጠቆምሳውዲ ባለሃብቶች በማመሳሰል ( Forgery) ወንጀል ሳይቀር ተወንጅለው ለስራ ያስገቧቸውን እቃዎች መመለስ እንዳልቻሉ አስረድተዋል ።
agriculture_in_ethiopia

Ethiopia-rice-farming-008
ከስድስት አመት በፊት ጀምሮ በእርሻ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሳውዲ ባለሃብቶች በመንግስት የተገባላቸው ቃል በተግባር ባለመፈጸሙ 50 % እጅ ያህሉ ባለሃብት ከኢትዮጵያ ለቀው መውጣታቸውን እኒሁ ቅሬታ አቅራቢ ሳውዲ ባለሃብት ተናግረዋል ። በደረሰባቸው በደል ተማረው ሀገሪቱን ለቀዋል ስላሏቸው ባለሃብቶች ሲያስረዱም ያቻሉት ሸጠው መውጣታቸውን አልደበቁም። መሸጥ ያልቻሉትና ያልቻሉት እቃቸውን ትተው የወጡት ግን ተመልሰው እቃቸውን ቢጠይቁ ” በማናውቀው ወንጀል እንያዛለን !” በሚል ስጋት ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ላይ ወረታቸውን በትነው መቅረታቸውን ሞሃመድ አልሸህሪ ለአረብ ኒውስ አስታውቀዋል ።

ከዚህ ቀደም ተሰምቶ የማይታወቀውን የሳውዲ ባለሃብቶች ቅሬታና ብሶት ለታዋቂው የሳውዲ ጋዜጣ ለአረብ ኒውስ በአደባባይ ያጋለጡት ባለሃብቱ ሞሃመድ አልሻህሪ ቅሬታቸውን ለሁለቱም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቢያቀርቡም እስካሁን ምነም አይነት ምልሽ እንዳላገኙ ጠቁመዋል !

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዜናውን ማስፈንጠሪያ በፊስ ቡል የፊት ገጼ ላይ እንደለጠፍኩ ” እንዴት ይህን ያልተጨበጠ መረጃ ሊንክ Link ይዘህ ትለጥፋለህ? ” በማለት የጅዳ ቆንስል ዲፕሎማት ቆንስል ሸሪፍ በስልክ ቅሬታቸውን ግልጸውልኛል ። ለሚሊዮኖች በአለም ዙሪያ የተሰራጨውን መረጃ ማስተላለፊን በአግራሞት የተመለከቱትና በጅዳ ቆንስል የኢኮኖሚ ኋላፊ አቶ ሸሪፍ ኼሪ በዜናው ዙሪያ ዘርዘር ባለ መልኩ አነጋግረውኛል ። እኔም ያቀረብኩት መረጃ ከአረብ ኒውስ ማግኘቴን ደግሜ በማስረዳት ማሰተባበያ ማቅረብ እንጅ የወጣውን መረጃ አታሰራጩ ፣ አለያም አትለጥፉ ማለት እንደ ሚከብድ አሳውቄቸዋለሁ !

ቆንስል ሸሪፍ በመጨረሻም ” አረብ ኒውስ ጋዜጣ ዛሬ ያወጣው መረጃ የተዛባ በመሆኑ አስፈላጊው ሁሉ እርምጃ ይወሰዳል ” በማለት “ፍጹም መሰረተ ቢስ ነው ! ” ላሉትን የተሰራጨ መረጃ ምላሽ ለመስጠት በሪያድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ በኩል አስፈላጊ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸውልኛል !

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 15 ቀን 2008 ዓም

The post ማለዳ ወግ | የሳውዲው ባለሃብት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ቅሬታ ማሰማት ጀመሩ | * “በኢትዮጵያ በደልና ዘረፋ ተፈጸመብን !” ባለሃብቱ appeared first on Zehabesha Amharic.

ገሃዱ አሰቃቂ ረሃብ እና የማወናበጃው «የልማት ዕድገት» በኢትዮጵያ |ሞረሽ ወገኔ

$
0
0

ሞረሽ ወገኔ በወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ያወጣው ጽሁፍ

 

በያዝነው ዓመት በአገራችን በኢትዮጵያ አስከፊ ርሃብ አደጋ እንደተስፋፋ ከተለያዩ የዜና አውታሮች ይደመጣል። በተቃራኒው ደግሞ የትግሬ-ወያኔ የሚቆጣጠራቸው የመገናኛ ብዙሃን በአገዛዙ ጥረት ስለተገኘው የልማት ትሩፋት ይለፍፋሉ። በአንድ አገር በአንድ ጊዜ ሁለት እጅግ ተቃራኒ ሁኔታን የሚያንጸባርቁ ዜናዎች ሲደመጡ እውነቱን አንጥሮ ማሣዬት ተገቢ ነው። ስለሆነም በዚህ መግለጫ ዕውነቱ የትኛው እንደሆነ ብቻ ሣይሆን የመፍትሔ ኃሣቦችንም ለማመልከት ተሞክሯል። 

አገራችን ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ጊዜያት ከፍተኛ ርሃብ አደጋዎች ከስተዋል። በዚሁ ሳቢያ በሚኖች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን አልቀዋል፤ አሁንም እያለቁ ነው። ለአብነት ያህል በንጉሡ ዘመን በ1958ዓ.ም. እና በ1965-66 ዓ.ም. እንዲሁም በደርግ ጊዜ በ1977 ዓ.ም. የተከሰቱት የርሃብ አደጋዎች በአስከፊነታቸው እና በሕዝብ ጨራሽነታቸው የሚጠቀሱ ናቸው። በትግሬ-ወያኔ የአገዛዝ ዘመን ርሃብ አልፎ አልፎ የሚመጣ ሣይሆን በየዓመቱ ከ7 እስከ 25 ሚሊዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያንን ለችጋር ማጋለጡ እና የሰው እጅ ተመልካች እንዳደረጋቸው ይታወቃል። ይህም ሆኖ እንደ ዘንድሮው እጅግ የከፋ አልነበረም። በመሆኑም በዚህ ዘመን ርሃብ በኢትዮጵያውያን ላይ ቤቱን ሠርቷል ለማለት ያስደፍራል። ስለሆነም ሦሥቱም ተከታታይ አገዛዞች አንዱ ካለ ገዢ ስህተት ሊማር ባለመቻሉ ችግሩ እየተባባሰ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም። 

Ethiopia12

በሦሥቱም የአገዛዝ ዘመኖች ለርሃቡ መንስኤ ተደርጎ የሚቀርበው ድርቅ ነው። ከፍተኛ ዝናብ እጥረት ሲከሰት ድርቅ ይፈጠራል። ስለዚህ ድርቅ የተፈጥሮ ክስተት በመሆኑ ምንጊዜም የአየር ንብረት አካል ነው። ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወንዞች ና ሐይቆች ያሏት፣ በተፈጥሮ ብት የታደለች አገር ናት። ስለሆነም ሕዝብን የሚል እና ሕዝባዊ ተሳትፎ ያለው ሥርዓት ካለ፤ ድርቁን ተፅዕኖ ለመቋቋም ቻላል። ይኽውም፥ ወንዞችን በመገደብ እና ሐይቆችን ውኃ በመጠቀም ከፍተኛ የመስኖ እርሻ ማፋፋት ይቻላል። እንደሚታወቀው ከ85% የማያነሰው የአገራችን ሕዝብ ከእጅ-ወደ-አፍ በሆነ የግብርና ኢኮኖሚ ዘርፍ የተሰማራ ነው። ይኽ የአገራችን ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው ዘርፍ እስካሁን ድረስ የሚዘወረው ከጥንት ጀምሮ ባልተቀየረ ኋላቀር የበሬ እርሻ ነው። «ይህ ኋላቀር የእርሻ ዘይቤ ሣይቀየር አገሪቱ እንዴት በልማት ትሩፋት ልተምነሸነሽ ትችላለች?» ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል።

አሁን በአስከፊ ሁኔታ የተከሰተው ርሃብ በሥልጣን ላይ ያለው ፀረ-ሕዝቡ ና ፋሽስቱ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የፈጠረው ነው። እንዴትስ ፈጠረው? ምክንያቶቹ፥

·         ኢትዮጵያ መሬት ብቸኛ ባለቤት የሆነው የትግሬ-ወያኔ ገዥ ኃይል ገበሬውን እጅግ አነስተኛ በሆነ የእርሻ መሬት ስለወሰነው፣ ገበሬው በቂ ምርት ማምረት አልቻለም

·         ገበሬው ተበላሸ እና ጊዜው ያለፈበት ማዳበሪያ በግድ እንዲገዛ በመደረጉ መሬቱ ተጎድቷል፣ ለምቱም ቀንሷል።

·         ገበሬው በቀላሉ ገንዘብ የሚገኝበት ሰብል (cash crop)፥ እንደ ጫት፣ አበባ ወዘተርፈ …. እዲያመርት በሥዓቱ በመገፋፋቱ ምግብ ል ምርት አሽቆልቁሏል።

·         በወያኔ የዘር ማጽዳት ፖሊሲ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ገበሬ፣ በተለይም ዐማሮች፣ ከነቤተሰቦቻቸው ከቀያቸው መፈናቀላቸው ክንያት አምራቾች ሣይሆኑ የዕለት ምግብ የሚመፀወቱ ምንዱባን ሆነዋል።

·         ፍጥነት እያደገ የመጣው የሕዝብ ብዛት የእርሻ መሬት ጥበት በማስከተሉ፣ ሥራ ለመፈለግ ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሰውን ገበሬ ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል። ይህም በእርሻው ኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ድቀት አስከትሏል።

·         የትግሬ-ወያኔ ሆን ሎ ከፍተኛ የደን ክምችት ያላቸው ቦታዎች በየጊዜው በእሳት ማጋየቱ ምክንያት አገራችንን የተፈጥሮ ሚዛን ና የአካባቢ አየር ንብረት በማዛነፉ ድርቅ በተደጋጋሚ እንዲከሰት አድርጓል

·         የትግሬ-ወያኔ ከፍተኛ ለምነት ያላቸውን የእርሻ መሬቶች እስከ መቶ ዓመት በሚደርስ የጊዜ ገደብ በሊዝ መልክ ቸብችቧል። መሬት በሊዝ የሚገዙት ራሱ የፈጠራቸው የአገር ውስጥ ከበርቴዎች እንዲሁምየውጭ አገር ከበርቴ ግለሰቦች ና ኩባንያዎች ናቸው። እነዚህም ከበርቴዎች ና ኩባንያዎች የሚያመርቷቸውን ምርቶች የሚያቀርቡት ለአገር ውስጥ ፍጆታ ሳይሆን በቀጥታ ውጭ አገሮች ገበያ እና ሸማች ይልካሉስለሆነም ኢትዮጵያውያን በእጅ-አዙር ቅኝ አገዛዝ ሥር ወድቀው የበይ ተመልካቾች በመሆናቸው እና በአገራቸው ውስጥ የሥራ እድል ሊያገኙ ስለአልቻሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣት አምራች ኃይሎች ለሥራ እድል ፍለጋ ወደ አረብ አገሮች ለመሰደድ ተገድደዋል።

·         ለተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ብሎ በእርዳታ እና በብድር መልክ ከውጭ የሚገባው ብዙ ቢሊዮን ዶላር፤ እንዲሁም የአገራችን አንጡራ ኃብት በትግሬ-ወያኔዎች ያለማቋረጥ ይዘረፋል። ይህም ድህነት እንዲሠራፋ አድርጓል።

·         የድርቅን አደጋ ተቋቁሞ ርሃብን በዘላቂነት ለመግታት ሠፋፊ የመሠረተ-ልማት ግንባታዎች ማከናወን ወሣኝ ነው። ሆኖም ባለፉ አገዛዞች ከነበረው አዝጋሚ የመሠረተ-ልማት ግንባታ በከፋ ሁኔታ በዘረኝነት መንፈስ የትግራይ ክልል የተባለው ብቻ ተጠቃሚ እንዲሆን ይደረጋል። ከዚህ በተጨማሪም የአገዛዙ ሥርዓት ዕድሜውን ለማራዘም ከአገሪቱ በጀት ከግማሽ የማያንሰውን ለስለላ ሥራ ያውላል። ስለዚህ በርሃብ ወቅት ሕዝቡን ከአደጋ ለመታደግ የሚያስችሉ ከፍተ የእህል ጎተራዎች አልተሠሩም፤ ጤና ለመጠበቅ የሚያስችሉ ተቋሞች አልተገነቡም፣ እንዲሁም ወደ ገጠሩ እንደልብ ለመግባት ሚያስችሉ የገጠር መንገዶች አልተዘረጉም።

·         የትግሬ-ወያኔ በሚከተለው የከፋፍለህ-ግዛው ፖሊሲ ምክንያት ሕዝባችንን በዘር፣ በጎሣ እና በኃይማኖት እየለያየ ያጫርሳል።  የእርስ በርስ ግጭቶች እ ጦርነቶች  በተለያዩ አካባቢዎች በመከሰት ላይ ናቸው። ለአብነት ያህል፥ በጎንደር፣ በወሎ፣ በሸዋ፣ በጎጃም፣ በአርሲ፣ በወለጋ፣ በባሌ፣ በኦጋዴን፣ በጋምቤላ፣ በሲዳሞ፣ በጋሙ-ጎፋ፣ በከፋ፣ ወዘተርፈ …. በተደጋጋሚ ጊዜያት ሕዝብ እርስ በእርሱ እንዲጫረስ ተደርጓል። ይህም የአምራቹን ኃይል ቁጥር የሚያመናምን፣ በተቃራኒው ለርሃብ አደጋ የሚጋለጠውን ዜጋ የሚያበዛ ነው።

ርሃብ እና ችጋር እንደ ደራሽ ጎርፍ በድንገት አይመጡም። በመጀመሪያ ድርቅ ሲከሰት ሰብሎች ይጠወልጋሉ፣ ምርትም አይገኝም፤ ይህ በትንሹ ከሦሥት ወራት ያላነሰ ጊዜ ይወስዳል። በድርቅ ጊዜ ከብቶች በግጦሽ ሣር እና በውኃ እጦት ይኮሰምናሉ፣ ከዚያም በገፍ ያልቃሉ። ይህ ሁሉ በአንድ ቀን ጊዜ አይከሰትም። ስለዚህ ከድርቅ ጋር የተያያዘን ችጋር ለመቋቋም በአንድ አገር የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ እና የዝግጁነት ሥርዓት ካለ ሕዝብ ለርሃብ አይጋለጥም። ይህ ተሞክሮ ረሃብን ታሪክ ለማድረግ በበቁ አገሮች በተግባር ታይቷል። በእኛም አገር ለአጭር ጊዜም ቢሆን ምልክቱ ታይቶ ነበር። በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ግን የሚደረገው ሆን ተብሎ የዚህ ተቃራኒ ነው። በአፄ ኃይለሥላሤ ዘመን «የድርቅ ኮሚሽን» በመባል የተቋቋመው መሥሪያቤት በደርግ ዘመን እጅግ ጎልብቶ የአገሪቱን ሕዝብ ከከፍተኛ የርሃብ መቅሰፍት ለመታደግ የሚያስችል ተቋም ለመሆን በቅቶ ነበር። በተደጋጋሚ በርሃብ ሲጠቁ የነበሩ ዜጎችን ለም እና ለኑሮ ተስማሚ የሆነ የአየር ንብረት ባላቸው አካባቢዎች በማስፈር ከተረጂነት ወደተትረፈረፈ ምርት አምራችነት ለመቀየር ተችሎ ነበር። ዛሬ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ከገጠር እስከ ከተማ፣ በሁሉም ሥፍራ የዕርዳታ እህል የማይሠፈርለት ዜጋ በቁጥር ነው። ያም ቢሆን ውጭ አገር ያሉ ዘመዶቹ ገንዘብ የሚልኩለት፤ አልያም የወያኔ ሹመኛ ከሆነ ብቻ ነው። በተለይ ደግሞ ዐማራውን ለይተው ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በዘር ማጽዳት ዘመቻ በማፈናቀል በርሃብ እና በችጋር ይፈጁታል። «ለወያኔ አገዛዝ አንንበረከክም» ያሉትን አፋሮችን እና ሶማሌዎችን በርሃብ ይቆላሉ። በአጠቃላይ ለርሃብ እና ለችጋር የሚያጋልጠው ብል ና ኃላፊነት የጎደላቸው አገዛዞች የሚፈጥሩት ችግር እንጂ ድርቅ ብቻውን ሊሆን አይችልም። ድርቅ ብቻውን ርሃብ የሚያመጣ ቢሆን ኖሮ የዝናብ ጠብታ የማያውቁ አገሮች ዜጎች ገና ጥንት ከምድረ-ገፅ ይጠፉ ነበር።

አንዳንድ ጸሐፊዎች «ፖለቲካ እና ሰብዓዊነት መያያዝ የለበትም» የሚለውን ኃይለ-ቃል ደጋግመው ይናገራሉ። ሆኖም ይህን የሚናገሩት በአፄ ኃይለሥላሤም ሆነ በደርግ የአገዛዝ ዘመኖች ለተከሰቱት የርሃብ ችግሮች ምንጮቹ የአገዛዝ ሥርዓቶቹ መሆናቸውን ሲያስተጋቡ የኖሩት ናቸው። ዛሬ ታዲያ ካለፉት ሁለት የአገዛዝ ሥርዓቶች እጅግ በከፋ ሁኔታ ኢትዮጵያውያንን ለማያባራ የርሃብ ችግር የዳረጋቸው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ሆኖ ሳለ ከዚህ ፍርድ እንዴት ሊያመልጥ ይችላል? የትግሬ-ወያኔዎች ኢትዮጵያውያንን በርሃብ እያቆራመዱ ዶላር ለመሰብሰብ የበሰለ ምግብ ወደ ውጪ አገሮች ይልካሉ። በአገር ቤት ግን ዜጎች የሚጣል የምግብ ትርፍራፊ በጉርሻ መልክ እየገዙ ሕይዎታቸውን ለማቆየት ይፍገመገማሉ። በየዓመቱ በርሃብተኛው ስም በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ በዕርዳታ መልክ ከውጪ የሚለገሣቸው ወያኔዎች ገንዘቡን ወደ ውጪ አገሮች መልሰው እያሸሹ እነርሱ ቢሊዬኔሮች ሆነዋል፤ አሁንም ግን በርሃብተኛው ስም ከውጪ ዕርዳታ ይለመናል። ስለዚህ ኢትዮጵያውያን በማንኛውም የአገር ውስጥም ሆነ ዓለም-አቀፍ ድርጅት አማካይነት በርሃብተኞች ስም የሚደረገውን ዕርዳታ ፋይዳው ምን እንደሆነ ቆም ብለን ልናስብብት ይገባናል። ለወገን ደራሹ ወገን ነውና ለርሃብተኛ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ካለማንም ጣልቃ ገብነት በቀጥታ የዕርዳታ እጃችንን እንዘርጋላቸው። ሞረሽ-ወገኔም ለዚህ የተቀደሰ ተግባር አስፈላጊውን መሠናዶ ያደረገ ስለሆነ ዕርዳታችሁን በተገቢው ሁኔታ ለማድረስ ዝግጁዎች ነን፤ በአድራሻችን ጠይቁን። ሆኖም ምንጊዜም ማስታወስ ያለብን ዘለቄታዊ መፍትሔ የሚመጣበትን መንገድ ነው። የትግሬ-ወያኔ ካለ፣ ርሃብ እና ችጋር ይቀጥላል። ስለሆነም ለዚህ ዓይነቱ ሁኔታ የዳረገን የችግራችን ሁሉ ምንጭ የሆነው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ መወገድ አለበት። ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ በአንድነት ተንቀሳቅሰን የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ የሆነውን የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ለማስወገድ ቆርጠን እንነሣ።

ርሃብን ታሪክ ለማድረግ ቆርጠን እንነሣ!

የትግሬ-ወያኔን አገዛዝ በተባበረ ክንድ እናስወግድ!

The post ገሃዱ አሰቃቂ ረሃብ እና የማወናበጃው «የልማት ዕድገት» በኢትዮጵያ | ሞረሽ ወገኔ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፊታችን ማክሰኞ በአውሮፓ ፓርላማ ንግግር ያደርጋሉ ተባለ

$
0
0

Birhanu Nega

(ዘ-ሐበሻ) የትጥቅ ትግሉን መንገድ መርጠው ታግዬ አታግላለው ብለው አስመራ የወረዱት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፊታችን ማክሰኞ ዲሴምበር 2 በአውሮፓ ፓርላማ ንግግር እንዲያደርጉ መጋበዛቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ::

ከአስመራ ወደ ብራሰልስ እንደበረሩ የሚነገርላቸው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለሕዝብ ክፍት በሆነው በዚሁ የአውሮፓ ፓርላማ ላይ ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት በወ/ሮ አና ጎሜዝ ነው ተብሏል:: በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ መገኘት ለሚፈልጉ – የአውሮፓ ነዋሪዎች በምርጫ 97 ወቅት የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ለነበሩት ወ/ሮ አና ጎሜዝ ደብዳቤ
ፕሮግራሙ ለሕዝብ ክፍትና ነፃ በመሆኑ አስቀድማችሁ:-

  • ስማችሁን
  • የተወለዳችሁበትን ቀን/ ወር/ ዓ.ም
  • ዜግነታችሁን
  • እና የፓስፓርት ቁጥራችሁን በ Anamaria.gomes@europarl.europa.eu በመላክ መመዝገብ እንደሚቻል የደረሰን መረጃ ጠቁሟል::

euro

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሚገኙበት በዚሁ የአውሮፓ ፓርላማ ላይ ለመገኘት ምዝገባው እስከፊታችን አርብ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን በፓርላማው ላይ ማክሰኞ የሚገኙ ሰዎች ፓስፖርት ወይም ሕጋዊ ወረቀት መያዝ እንደሚኖርባቸው ተጠቁሟል::

የኢትዮጵያ አገዛዝ ፕሮፌሰር ብርሃኑን አሸባሪ እንዲባሉለት የየሃገራቱን መሪዎች በሚለምንበት በዚህ ወቅት ፕሮፌሰሩ በአውሮፓ ፓርላማ መጋበዛቸው ለስርዓቱ ትልቅ የፖለቲካ ኪሳራ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ::

The post ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፊታችን ማክሰኞ በአውሮፓ ፓርላማ ንግግር ያደርጋሉ ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.

በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ አደባባይ የወጣ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲሰማ ዋለ * ህዝቡ ጎማ እያቃጠለ ነበር

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በምእራብ እና በመካከለኛው የኦሮሚያ ክልሎች ዛሬ ሙሉ ቀን ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ሲያሰማ መዋሉ ተዘገበ:: የዘ-ሐበሻ የመረጃ ምንጮች እንደዘገቡት በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ በተደረገው ከፍተኛ ተቃውሞ ሕዝቡ በአደባባይ ጎማዎችን ጭምር በማቀጥል መሪር ተቃውሞውን አሰምቷል::

ፎቶዎች የተገኙት ከጃዋር መሀመድ ፌስቡክ ገጽ ነው::

ፎቶዎች የተገኙት ከጃዋር መሀመድ ፌስቡክ ገጽ ነው::

 

Photo Jawar
ይህ በመንዲ ከተማ የተጀመረው ተቃውሞ ወደ መካከለኛው ና ም ዕራብ ወለጋ ከተሞች እየተዛመተ መሆኑ የተሰማ ሲሆን በአካባቢው ከፍተኛ የፌደራል ፖሊሶች መስፈራቸውንም የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ::

በመንዲ ከተማ ሲቀጣጠል የዋለው ተቃውሞ መነሻ በአዲስ አበባ አዲሱ ማስተር ፕላን ዙሪያ መሆኑ ተሰምቷል:: በዚሁ በአዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ዙሪያ ከአንድ ዓመት በፊት በተደረገ ተቃውሞ በአምቦ በስልጣን ላይ ያለው የሕወሓት መንግስት በርካታ ተማሪዎችን መግደሉ ይታወሳል::

የሕወሓቱ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ አባይ ጸሐዬ ከዚህ ቀደም በርካታ ወጣቶች በተቃውሞ ከተገደሉ በኋላ በአንድ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ስብሰባ “የአዲስ አበባን አዲሱን ማስተር ፕላን ተግባራዊ እናደርጋለን… የሚቃወሙትንም ልክ እናስገባለን” ሲሉ መፎከራቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

oromia 2

በቅርቡ በኦሮሚያ የሚነሱ ተቃውሞዎችን ለማርገብ በአንዳንድ የኦህዴድ ባለስልጣናት አማካኝነት ለሕዝቡ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አይካሄድም በሚል ሲነገረው የቆየ ሲሆን ከበስተጀርባ ሌሎች ባለስልጣናት ማስተር ፕላኑን ለማስፈጸም እየተንቅሳቀሱ መሆኑ በኦሮሚያ የተለያዩ ክልሎች እንደገና አደባባይ የወጡ ተቃውሞዎች መታየት ጀምረዋል::

በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን ለማቅረብ ዝግጁ ነን::

The post በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ አደባባይ የወጣ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲሰማ ዋለ * ህዝቡ ጎማ እያቃጠለ ነበር appeared first on Zehabesha Amharic.

“የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ማሻሻያ የኦሮሞን መሬት ለመንጠቅ እንጂ ለልማት ታስቦ አይደለም”ዶ/ር ኑሩ ደደፎ |የኦነግ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ

$
0
0

The post “የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ማሻሻያ የኦሮሞን መሬት ለመንጠቅ እንጂ ለልማት ታስቦ አይደለም” ዶ/ር ኑሩ ደደፎ | የኦነግ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ appeared first on Zehabesha Amharic.

የእውቁ ከያኒ ደበበ እሸቱ ‘ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል’መጽሐፍ ምርቃት በቶረንቶ ካናዳ |የጥሪ ማስታወቂያ

$
0
0


የጊዜውን የቅኝ ገዢዎች መላ ፍንትው ብሎ ያመላከተውንና በዘረኛው ጠበቃ በሮማን ፕሮቻዝካ በ1985 (እ.አ.አ) መግቢያ ላይ በጀርመንኛ ቋንቋ ተደርሶ በኦስትሪያ; የዓመቱ መጨረሻ ላይ በለንደን ከተማ በ እንግሊዙ ዓለም አቀፍ የዜና አገልግሎት በ እንግሊዘኛ ቋንቋ የታተመው ይህ መጽሐፍ በ እውቁ ከያኒ ደበበ እሸቱ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተመልሶ ለንባብ በቅቷል:: ይህ ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል የተሰኘው መጽሐፍ የፊታችን እሁድ ከያኒ ደበበ እሸቱ በሚገኝበት ልክ ከዚህ ቀደም በዋሽንግተን ዲሲ እንደተመረቀው ሁሉ በቶረንቶ ካናዳም ይመረቃል:: በአካባቢው የምትኖሩ ሁሉ እንዳትቀሩ ተጋብዛችኋል – የመጥሪያው በራሪ ወረቀት የሚከተለው ነው::Debebe Eshetu Book Signing Poster

The post የእውቁ ከያኒ ደበበ እሸቱ ‘ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል’ መጽሐፍ ምርቃት በቶረንቶ ካናዳ | የጥሪ ማስታወቂያ appeared first on Zehabesha Amharic.


ሙፍቲ ሙሐመድ ሲራጅ አል አኒይ በመጨረሻም የአሏህን ጥሪ ተቀብለው አረፉ |ሳዲቅ አህመድ

$
0
0

Sheik

እኛም ካንተ፥ እኛም ወዳንተ ተመላሾች ነን!

የሰሜን አሜሪካ ኢስላማዊ ተቋማትን በመመስረት የመንፈስ አባት በመሆን ለአያሌ አመታት አግልግሎት የሰጡት አባታችን ሙፍቲ ሙሐመድ ሲራጅ አል አኒይ በመጨረሻም የ አሏህን ጥሪ ተቀብለው አረፉ። ሳዲቅ አህመድ በወርሃ ሜይ/2008 ከርሳቸዉ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር። አጠር ባለ መልኩ የተዘጋጀዉን ቃለ መጠይቅ ከታች ያንብቡ።ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሒ ራጂኡን እኛም ካንተ፥ እኛም ወዳንተ ተመላሾች ነን።

 

ሶላተል ጀናዛ (ለሙታን የሚደረግ ጸሎት) የሚከናወነው በነገዉ እለት ዳረል ሒጅራ መስጊድ ዉስጥ ከሁለተኛዉ የጁመዓ (የአርብ) ሶላት በሗላ ነዉ። አድራሻ: 3159 Row St, Falls Church, VA 22044

 

የቀብር ቦታ:National Memorial Park

7482 Lee Hwy, Falls Church, VA 22042

 

ቆይታ ከሼህ ሙሐመድ ሲራጅ ሷል ጋር

 

እንደ ከዋክብት የደመቁ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ መንገድን አመላካች  ብርሃን የሆኑ አገርንና  ህዝብን ያቀኑ ህይወታቸውን በመማርና በማስተማር ሂደት ውስጥ ያሳለፉ አያሌ ኡለሞች (የሐይማኖት-ሊቃዉንት) በምድረ ሐበሻ መፈጠራቸው አሌ አይባልም።

 

ለዚህ  ሰናይ  ምግባር  እማኝ  ይሆን  ዘንድ  ፈርስት ሂጅራን ብሎም በድርን (የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ድርጅቶች) በመመስረት  የመንፈስ አባት ከሆኑት ከልጅነት እስከ አረጋዊነት ህዝብን እና አገርን ካገለገሉት  ሼህ  ሙሐመድ  ጋር አጭር ቆይታ አድርገን አንኳር የህይወት ተሞክሮአቸውን ጠየቅናቸው።መርሐባ በማለት የሚከተለውን አጫወቱን፦

 

ሳዲቅ፡በቅድሚያ የቤተሰብዎን ታሪክ ቢነግሩን?

ሼክ ሙሀመድ ሲራጅ: ቤታችን በይተል-ኢልም (የእውቀት ቤት) ነበር። ዓሊም ከነበሩት አባቴ ነው ብዙውን የተማርኩት። ሃብትም ነበራቸው። ብዙ የቀንድ ከብትና ግመሎች ነበሩን። አባታችን  ብዙ ደረሳወችን (የሀይማኖት ተማሪዎችን) ይቀልቡ ነበር።

 

ሳዲቅ፡ ዒልሙ (ሐይማኖታዊ ትምርት) የጀመረው ከርሶ  አባት ብቻ  ነው ወይስ አያት-ቅድመ-አያቶችዎም ዓሊም ነበሩ?

ሼክ   ሙሀመድ፡ የአባቴ  አባት ሳይሆን  አያታቸው

አሊም ነበሩ የአባቴ አባትም ቢሆኑ ሙእሚንና ፈጣሪን የሚፈሩ ነበሩ።

 

ሳዲቅ፡ የት ነው የተወለዱት?

ሼክ ሙሃመድ፡ የተወለድኩት ራያ ነው አውራጃው ማይጨው ራያ አዘቦ  ሲሆን  ወረዳውም ሙኸኒ ይባላል።

 

ሳዲቅ፡ መቼ ተወለዱ?

ሼክ   ሙሃመድ፡ የተወለድኩት ጃንዋሪ 15/1930 እንደ  አሮጳውያኑ አቆጣጠር ነው።

 

ሳዲቅ፡የመጀመሪያ  ልጅ ነዎት? እህትና ወንድም ነበሮትን?

ሼክ    ሙሃመድ፡  የአባቴ   የመጀመሪያ  ልጃቸው አብደላህ  ይባል ነበር። እኔ ሁለተኛ  ልጅ ነኝ። ከኔ በኋላ አሊ፤ ኢብራሂም፤ሙሃመድ፤ጁሃር እና ሃሺም የሚባሉ ወንድሞች ነበሩኝ በህይወት ያለው አሊ ብቻ ነው።

 

ሳዲቅ፡ ከርሶ ሌላ በዒልም  ውስጥ የገባ  ወንድም ነበሮት?

ሼክ   ሙሃመድ፡ቁርዓን  የቀሩ  ቢሆን እንጂ ዒልም እምብዛም የገቡ አልነበሩም።

 

ሳዲቅ፡ እድገትዎ  የት ነበር?  ዒልሙን የት በመሄድ አካበቱት?

ሼክ ሙሃመድ፡ ቁርዓንን ከአባቴ ራያ ተምሬአለሁ ወደ ደቡብ ወሎ እና ወደ የመን በመሄድም ተምሬAለሁ።

 

ሳዲቅ፡ ወደ የመን ሲሄዱ ስንት ዓመት ይሆኖት ነበር? የመንንስ እንዴት አገኟት?   የቋንቋስ ችግር ገጥሞት ነበርን?

ሼክ ሙሃመድ፡ ሃያ አራት ወይም ሃያ አምስት ዓመት ይሆነኝ ነበር የየመን  ሰዎች በጣም ጥሩዎች ነበሩ ተግባቢና ሰውን የሚረዱ ነበሩ በስራ ላይ ትጉህ ከመሆናቸው  ሌላ በጣም የተለየ ጥሩ ፀባይ ያላቸው ነበሩ። የቋንቋ ችግር አልነበረ ብኝም ገና አገሬ  ሳለሁ አረብኛን አውቅ ነበርና።

 

ሳዲቅ፡ ከየመንስ ሲመለሱ ወዴት ሔዱ?

ሼክ  ሙሃመድ፡ አባቴ አረፉ ልጆቻቸውን ትተው ሄዱ ወንድሞቼን ማሳደግና መቆጣጠር ስለነበረብኝ ወደ ስራ ዓለም ገባሁ። እርሻ እና ንግድን መከታተል ጀመርኩ።በከብት እርባታችን ውስጥ እስከ ሶስት መቶ የሚደርሱ ከብቶች ነበሩን። የልጆቹ እድሜ እስኪፀና ድረስ ለሰባት   መታት     መቆጣጠር ነበረብኝ።

 

ሳዲቅ፡ የቤተሰብን ሀላፊነት ከመወጣት ባሻገር ምን ያደርጉ ነበር?አ

ሼክ ሙሃመድ፡ አስተምርም ነበር ቢሆንም ከኔ በላይ ዒልምየነበራቸው ዓሊሞች በአከባቢያችን  ስለነበሩ እማርም ነበር።

ሳዲቅ፡ወንድሞቾ ካደጉ በኋላ የነበረው  ህይወቶ እንዴት ነበር?

ሼክ ሙሃመድ፡ የአገር ምርጫ ስለመጣ በአከባቢው ህብረተሰብ ለፓርላማ ተመርጬ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1954 ወደ አዲስ አበባ  ሔድኩኝ።

 

ሳዲቅ፡የፓርላማ ህይወቶ እንዴት ነበር?

 

ሼክ ሙሃመድ፡አላህ  አጅሩን  ይቁጠርልን  እንጂ ግዜው  በጣም አስቸጋሪ  ነበር።  አንዳንዶቹ ደካሞች ነበሩ ፓርላማ የመጡት  በባላባትነት እንጂ በእውቀት ባለመሆኑ፤  የሆነው  ቢሆንም አላህ ከኛ ጋር  ነበር። ቁርዓን በሬዲዮ እንዲቀራና ጁመዓን ለመስገድ እንዲፈቀድልን ጥያቄ ለንጉሱ አመራር ብናቀርብም ጁመዓ ከጉባዔ ወጥተን እንድንሰግድ፤በሮመዳን መንዙማና ዱዓ ከፉጡር በኋላ እንዲተላለፍ ተፈቀ ደልን። ከፓርላማው ስራም ጎን ለጎን የህግ ትምህርት ጀመርኩ በመጀመሪያ ሰርተፊኬት አግኝቼ በመቀጠልም በዲፕሎማ ለመመረቅ በቃሁ።

 

ሳዲቅ፡ ከዚያስ ፓርላማ ማገልገሉን ቀጠሉ ወይስ ወደ ዒልሙ ተመለሱ?

ሼክ ሙሃመድ፡ ወደ ፓርላማ አልተመለስኩም የአምባሳደርነት ሹመት Aግኝቼ ወደ የመን ሄድኩኝ።

 

ሳዲቅ፡ እንዴት አምባሳደር እንደተደረጉ ያው ቃሉ? ሼክ      ሙሃመድ፡ እኔ ምንም   የማውቀው ነገር አልነበረም አንድ  ቀን አንዋር መስጊድ ተሰባስበን የሀጅ ኮሚቴን እያቋቋምን ሳለን ከቤተ-መንግስት የተላከ ሻምበል እበርላይ ቆሞ  ጠራኝና  ከቤተ- መንግስት  እንደምፈለግ ነግሮኝ  በመኪናው  ይዞኝ ሄደ።  እንደ እኔ የተጠሩ    አምስትሰዎች     ነበሩ ሁላችንም ለምን ይሆን የተጠራነው ብለን መጨነቅ ጀመርን     የንጉሱ ተላላኪ              መጥቶ አይዞአችሁ የተጠራችሁት  ለደግ ነገር ነው ብሎ አጽናናን ከዚያ አንድ በአንድ እየተጠራን ማዕረግ ተሰጠን።

 

ሳዲቅ፡የመን በአምባሳደርነት ሲያገለግሉ ሁለቱን አገሮች በማቀራረብ ረገድ ምን ያደረጉት ነገር ነበር?

 

ሼክ  ሙሃመድ፡ በኢትዮጵያና በየመን መካካል ግኑኝነት ነበር ቢሆንም እኔ ከሄድኩ በኋላ  ያደረግሁት ነገር ቢኖር ግልጽ ያልነበረዉን የባህር ሀብታችንን ማካፈል ነው። በተጨማሪም ወንጀለኛን መለዋወጥ ማለትም የየመን ወንጀለኛ ኢትዮጵያ  እንዳይቀመጥ የኢትዮጵያ  ወንጀለኛ የመን ውስጥ እንዳይቀመጥ። ሌላው ብዙ ነው ትዝ አይለኝም።

 

ሳዲቅ፡ከየመን ሌላ በአምባሳደርነት የሰሩበት አገር አለ?

ሼክ መሃመድ፡ ስምንት ዓመት ከሰራሁ በኋላ   ወደ ካይሮ ግብፅ እንድዛወር ተወስኖ ሳለ ስራ ከመጀመሬ በፊት  የመንግስት   ለውጥ  መጣ። በደርግ ጥሪ ተደርጎልኝ ጓዜን ጠቅልዬ ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩ በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዉስጥ የመካከለኛዉ ምስራቅ አገሮችን  እንዳነጋግርና  የመንግስትን  ፖለቲካ እንዳሰራጭ ስራ ተሰጠኝ።  ይህ በተጽዕኖ የመጣው የኮሚኒስት  ስርዓት  ለኢትዮጵያ አይመችም    ብዬ ኢትዮጵ ያን ለቅቄ ወደ የመን ሄድኩኝ ከዚያም ወደ ሳውዲ አረቢያ በመሄድ ለ13  ዓመታት ከተቀመጥኩ በኋላ  በስራ ምክንያት ወደ አሜሪካ መጣሁ።

 

ሳዲቅ፡ ወደ አሜሪካ እንዴት መጡ?

ሼክ ሙሃመድ፡መካ ያለው ራቢጠተል አለመል ኢስላሚያ (Muslim World League)   የተሰኘው ድርጅት ኒውዮርክ ባለው ቅርንጫፍ ቢሮው ስራ ሰጥቶኝ ነው የመጣሁት።

 

ሳዲቅ፡ ራቢጣ በሚሰሩበት ወቅት  ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሚጠቅም ምን ያደረጉት ነገር አለ?

ሼክ  መሃመድ፡ የኢትዮጵያን ሙስሊሞች የሚመሩ ኡለሞች ክፍያ አልነበራቸውም በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ያሉ ኢማሞች ደሞዝ ሲኖራቸው የኢትዮጵያ ኡለሞች ደሞዝ የላቸውም። ለብዙዎቹ ደሞዝ እንዲከፈላቸው አድርጌአለሁ። ትምህርት ቤቶች እንዲሰሩ ጥያቄ  አቅርቤ ነበር ግን አልተፈጸመም። የራቢጣ ስራዬን በ1997 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር) ስጨርስ በብዙ ወንድምና እህቶች ጥያቄ ወደ ዋሺንግተን  ዲሲ መጣሁ። የኔው ከሆኑት ሙስሊሞች ጋር በመገናኘት ደዕዋ (ሰበካ) ማድረግ ጀመርኩኝ። በዓመት በዓል ካልሆነ የማይገናኙትን ሙስሊሞች መገናኘት በመጀመራቸው ቤት ተከራይተን ትምህርታችንን ቀጠልን።  ዛሬ  አለሀምዲልላህ  የራሳችን  መስጂድ ብሎም የራሳችንን ሬዲዮ ፕሮግራም ለማስተላለፍ በቅተናል።

 

ሳዲቅ፡ ስንት ልጅና የልጅ ልጆች አሎት?

ሼክ ሙሃመድ፡ አስራ አራት ልጆች አሉኝ።  ስምንት ወንድ ሰባት ሴቶች አስራ ስምንት የልጅ ልጆች አሉኝ።

ሳዲቅ፡ለመላው ኢትዮጵያውያን  የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ?

 

ሼክ ሙሃመድ፡ መልዕክቴም አደራችሁን አደራችሁንዲናችሁን(ሐይማኖታችሁን) አጥብቃችሁ ያዙ፤ እንደ ማዕበል ወደላይና ወደታች የሚማታ ነገር መጥቷል። ሃይማኖቱ አንድ ነው ቁራአንና ሃዲስን ቀጥ ብላችሁ ያዙ።በዘመናችን ወጣቱን ግራ የሚያጋቡ ሰዎች አሉ፤ ወጣቱ የሰራው መጥፎ ስራ የለም። ተጠንቅቃችሁ ቁርዓንና ሐዲስን ይዛችሁ እንድትራመዱ፤ እውነትን እንድትይዙ፤ ለሸይጣን እጃችሁን እንዳትሰጡ። ሀቅ በጣም መሪር ናት ጀግንነት ያለው ሰው እንጅ ሌላ አይወጣትም፤ ስለዚህ አደራ የምላችሁ ዲናችሁን አጥብቃችሁ ያዙ፤ ሞት አይቀርም፤ ይህች ታልፋለች።

 

The post ሙፍቲ ሙሐመድ ሲራጅ አል አኒይ በመጨረሻም የአሏህን ጥሪ ተቀብለው አረፉ | ሳዲቅ አህመድ appeared first on Zehabesha Amharic.

የመኢአድ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበረው አቶ አብርሃም ጌጡ ይግባኝ ተጠየቀበት

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በአቶ ማሙሸት አማረ ካቢኔ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበረው አቶ አብርሃም ጌጡ ህዳር 14/2008 ዓ.ም አራዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት (ሰባራ ባቡር) ቀርቦ ይግባኝ ተጠይቆበታል፡፡ የአራዳ ምድብ ችሎት ለህዳር 11/2008 ዓ.ም ቀጥሮበት የነበር ቢሆንም ህዳር 7/2008 ዓ.ም ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዲለቀቅ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

abreham getu

አቶ አብርሃም ጌጡ ሰኔ 12/2008 ዓ.ም ቤቱ ተበርብሮ ከታሰረ በኋላ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ቆይቷል፡፡ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተዛውሮ ከቆየ በኋላ ከሀምሌ 12/2008 ዓ.ም ጀምሮ ማዕከላዊ ታስሮ ይገኛል፡፡ አቶ አብርሃም ጌጡ ‹‹በሽብር ወንጀል›› ለ6ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ መዝገቦችና በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ለ11ኛ ጊዜ መቅረቡን ጠበቃው ገልፀዋል፡፡

አቶ አብርሃም ጌጡ ወደ ማዕከላዊ ተዛውሮ ለሶስት ወራት በማዕከላዊ የቆየው ‹‹በሽብር ወንጀል›› ነው ተብሎ የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የተከሰሰው በሽብር ሳይሆን በሀሰት ወሬ በማውራት በመሆኑ፣ ይህም ዋስትና እንደማያስከለክል፣ ለዚህ ክስም በቂ ዋስትና አስይዞ እንዲለቀቅ ወስኖ ነበር፡፡ ይሁንና አቶ አብርሃም ጌጡ ከእስር እንዲለቀቅ ፍርድ ቤቱ ከወሰነ በኋላም በማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ እንዲቆይ ተደርጎ ከሰባት ቀናት በኋላ ህዳር 14/2008 ዓ.ም ይግባኝ ተጠይቆበታል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ህዳር 16/2008 ዓ.ም ድረስ ‹‹የሀሰት ወሬ በማውራት›› በሚል ክስ ቀርቦበት እንዲፈታ የተወሰነለት አቶ አብርሃም ጌጡ በማዕከላዊ ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

The post የመኢአድ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበረው አቶ አብርሃም ጌጡ ይግባኝ ተጠየቀበት appeared first on Zehabesha Amharic.

ልብ አንጠልጣዩ ‘ሞጋቾች’ድራማ ምዕራፍ 3 የዘገየበት ምክንያት ታወቀ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ልብ አንጠልጣዩና በርካታ ተከታዮችን ያፈራው ሞጋቾች የኢቢኤስና ዩቱዩብ ቴሌቭዥን ድራማ ምዕራፍ ሁለት ድንገት እንዲያልቅ የተደረገበት እና ም ዕራፍ 3ትም ቶሎ ያልጀመረበት ምክንያት ታወቀ:: ከደራሲው ኃይሉ ጸጋዬና ከፕሮዲውሰሯ መቅደስ ጸጋዬ የቅርብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው የድራማውን 3ኛ ክፍል የሚጽፈው ሌላ ደራሲ ይሆናል::

Hailu Tsegaye

Hailu Tsegaye

በፕሮዲውሰሯ መቅደስ ፀጋዬ (በድራማው የዶ/ር ኮከብን ገጸ ባህርይ ተላብሳ የምትጫወተው ) እና በደራሲው ኃይሉ ጸጋዬ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት የተነሳ ደራሲው ካሁን በኋላ ድራማውን አልጽፍም በማለቱ ድራማው ሊዘገይ መቻሉን ያስታወቁት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ም ዕራፍ 3ን (ከክፍል 49) በኋላ ያለውን ውድነህ ክፍሌ የተባለው ደራሲ እንደሚጽፈው አስታውቀዋል::

ደራሲ ኃይሉ ጸጋዬ ድራማውን ካሁን በኋላ አልጽፍም ያለበትን ምክንያት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ሲያስረዱ “ፕሮዲውሰሯ (መቅደስ) በሥራዬ ውስጥ ጣልቃ እየገባች አስቸግራኛለች” በሚል ምክንያት ነው::

Mekedes Tsegaye

Mekedes Tsegaye

የማዕበል ዋናተኞች የራድዮ ድራማን ለረዥም ጊዜ በመጻፍ የሚታወቀው ደራሲ ሃይሉ ጸጋዬ ለ እረፍት የመጣ ፍቅር የተሰኘውን የኮሜዲ ትያትር ጨምሮ በርካታ የቴሌቭዥን; የራድዮ እና የመድረክ ድራማዎችን ጽፏል::

ሞጋቾች ድራማ ክፍል 49 (ምዕራፍ 3) በቅርቡ እንደገና ወደ ዕይታ ይመለሳል ይባል እንጂ መቼ እንደሚመለስ የታወቀ ነገር የለም::

ሞጋቾች ድራማ የመጨረሻው ክፍል 48 ከታየ አንድ ወር አልፎታል::

The post ልብ አንጠልጣዩ ‘ሞጋቾች’ ድራማ ምዕራፍ 3 የዘገየበት ምክንያት ታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከአስመራ ወደ ብራሰልስ መጠራት |ዜና ትንታኔ

$
0
0

nega berehanu

ፕሮፌሰሩ ለረቡዕ ህዳር 22 ቀን 2008 ዓ.ም. (December 2, 2015) ከአስመራ ወደ ቤልጄየም ብራሰልስ የተጠሩት በሀገራችን ኢትዮጵያ ድርቅን ተከትሎ በተከሰተው ፖለቲካዊ የፖሊሲ ውድቀት ወለድ ርሃብ ጉዳይ ላይ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ንግግር፣ ምክክር እና ውይይት ለማድረግ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የኢህአዴግ የ11 በመቶ የቁጥር ኢኮኒሚ ዕድገት ጋጋታ ገደል የከተተውና በምግብ ራሳችንን ችለናል መዝሙር ከአዳራሹ ነፋስ እንደወሰደው የሚያሳብቀው ከ15 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በርሃብ አለነጋ ከመገረፍ አልፎ አስቸኳይ የምግብ ርዳት እንደሚያስፈልገው የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተራድዖ ድርጅቶች እና የተባበሩት መንግሥታት ይፋ አድርገዋል፡፡

ይሄንን እውነታ ለመደበቅ መንግሥት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ለማስተባበልና በርሃቡ ወደተጎ ዜጎች አካባቢ ሚዲያ ድርሽ እንዳይል እና እንዳይዘገብ በውስጥ መመሪያ መተላለፉንም ከሰማን ሰነበትን፡፡

 

ይሄ ሁሉ የራስን የጥፋት ገመና ለመሸፈን ሲባል ህዝብ ርሃቡ ከእኛ ቁጥጥር ውጭ አይደለም ሲባል ለሀገሬው ዜጋ በቋንቋው ሲነገር፤ ለዓለም አቀፍ ለጋሽ ሀገሮች ደግሞ በእንግሊዘኛ በሀገሪቱ ከፍተኛ የርሃብ አደጋ መከሰቱን እና በሀገሪቱ የእርዳታ ማስተባበሪያ የጠገኘው እህል ከአንድ ወር እንደማያልፍ በመግለፅ ተማፅኖውን ማሰማቱን ቀጥሏል፡፡ ይህንን ስንሰማ የኢህአዴግ መንግሥት አስተዳደር ኃላፊነቱ ለነጮች ነው ወይስ ለኢትዮጵያውያን የሚል ጥያቄ ቢያጭርም ከተለመድ የተለየ ነገር ግን የለም፡፡ ለዓመታት የተለመደ የመረጃ (ዳታ) ጋገራ መግለጫና ፕሮፖጋንዳ በተጨማሪ በግልፅ መረጃ ለማፈን ከፍተኛ በጀት መድቦ መንቀሳቀስ ከጀመረ እነሆ ከ10 ዓመታት በላይ ሆኖታል፡፡ ልዕለ ኃያሏ አሜሪካም ብትሆን ከስርዓቱ ያላትን የፀጥታ ጉዳይ ትብብር (ወታደሮችን ለአላስፈላጊ እልቂት ማገዳ ካላት ስምምነት) አኳይ እንደ ጥሩ አጋር ብትቆጥርም የስርዓቱን አምባገነንነት፣ ዘረኛ አገዛዝ፣ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት አለመኖር፣ የፍትህ እጦት፣ ሙስና እና ተጠያቂነት የሌለው አሰራር የሚከተለው ስርዓት እንደሆነ ልትሸሽገው አልቻለችም፡፡
ይሁን እንጂ የአውሮፓ ህብረት የተለመደ ሰብዓዊ እርዳታውን በስሱም ቢሆን መለገሱን ባያቆምም የምንጊዜም የስርዓቱ ቀኝ እጅ የሆኑት እንግሊዝ፣ ጣሊያን እና አየርላንድ እንደድሮ ለስርዓቱ ሰዎች ፊት መስጠቱን የቀነሱ ይመስላሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያን በሚመለከት በአውሮፓ ህብረት አሊያም በአውሮፓ ኢኮኖሚ ቅንጅት የጋራ አባል ሀገሮች በኩል ውሳኔ እንዲያልፍ እየተደረገ መሆኑን እየታዘብን ነው፡፡ ወቅታዊውን ርሃብ ለማስታገስና ለተጎዱ ወገኖች የሚደረው ሰብዓዊ እርዳታ እንኳ እንደቀድሞ በቀጥታ ለመንግሥት ከመስጠት ይልቅ በእርዳታ መልክ የተሰጠው ገንዘብ በሌሎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች በኩል በቀጥታ ለተጎጂዎች እንዲደርስ የሚያስችል አሰራር እየተከተሉ እንደሆነ የስርዓቱ አጋር አሜሪካ እና በቅርቡም ስውድን የወሰደችው እርምጃ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ስርዓቱ በተለያዩ ለጋሽ ሀገሮች እንኳ እምነት እንደታጣበት እና የተለመደው የመረጃ ጋገራ ሪፖርትና ጋጋታ ፋይዳቢስ መሆኑን የተገነዘቡ ይመስላል፡፡
እነሆ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያውን ርሃብ በተመለከተ ህዝባዊ ዓመኔታና ቅቡልነት ባይኖረው ኃላፊነት ያለበት መንግሥት እያለ ስርዓቱን ለመገርሰስ ከሚታገሉት መካከል ተዓማኒና ትክክለኛ መረጃና ትንታኔ ይሰጣሉ ተብለው ከታመኑት መካከል በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አማካኝነት ከአስመራ የትግል ሜዳ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተጋብዘዋል፡፡ በርግጥ ፕሮፌሰሩ ካላቸው የፖለቲካ ስብዕና በተጨማሪ በሙያቸው ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት ባለሙያና ተመራማሪ እንደመሆናቸው መጠን በስፍራው መጋበዛቸው የህብረቱ ትክክለኛ ምርጫ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ይሄ ደግሞ የስርዓቱን ሰዎች የበለጠ ምክንያታዊ መሸሸጊያ የሚያሳጣ ወቅታዊ የመረጃ ጉዳይ ሆኗል፡፡ የሚገርመው በኢትዮጵያ ስም ስርዓቱን ወክሎ በቤልጀየም ከፍተኛ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እያሉ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ መረጃና ትንታኔ እንዲሰጡ ከበረሃ የትግል ሜዳ የፕሮፌሰሩ መጋበዝ ለስርዓቱ ትልቅ ራስምታት ነው፡፡ ምክንያቱም ፕሮፌሰሩን እና የሚመሩትን የፖለቲካ ድርጅትና አባላት በሽብርተኝነት ለማስፈረጅ ለዓመታት በተለመደ የመረጃ ጋገራ ቢሞከርም በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ተቀባይነት አላገኘምና፡፡

Birhanu nega photo
በተለይ በመረጃ እና ሐሳቡን ለመግለፅ ለታፈነው የኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ አጋጣሚ ሲሆን፤ ለፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ለሚመሩት ድርጅት እንደ አንድእመረታ ሊታይ ይችላል፡፡ እንደ አንዳንድ የስርዓት ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጥቆማ ከሆነ መንግሥት ርሃቡን ከሀገሬው ሰው በመደበቅ ለጋሽ ሀገራት በተማፅኞ በማጨናነቅ ዕርዳታቸውን በጥሬ ገንዘብ ወይም ዶላር እንዲሆን እየሰራ እንዳለ እና ለዚህም ያቀረበው ምክንያት ገንዘቡ ከተሰጠኝ ከሀገር ውስጥ ነጋዴዎች እህሉን ራሴ ገዝቼ በማከፋፈል ጊዜና ጉልበት መቆጠብ እችላለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡

ይህ ለተጎጂዎች ታስቦ ሳይሆን መንግሥት በሀገሪቱ ከደረሰበት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ አጋጣሚውንም እንደ ጥሩ ዕድል ሊጠቀምበት እንዳሰበና እስካሁንም እንዳልተሳካለት ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተጠቁሟል፡፡ በአሁን ወቅት ከአስከፊው ርሃብ በተጨማሪ በሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመከሰቱ የተለያዩ አስመጪዎች እና ኢንዱስትሪዎች ለአብነትም ቴክኖ ሞባይል የስልክ መገጣጠሚያን የመሳሰሉት ስራ ማቆማቸውም መነገር ከተጀመረ ሰነባብቷል፡፡ በዚህ ሁሉ የስርዓቱ አጣብቂኝ ውስጥ ፕሮፌሰሩ የበለጠ ተዓማኒነትና ተቀባይነት አግኝነተው በአውሮፓ ህብረት መጋበዛቸው በቀጣይ ምን ሊያሳየን ይሆን የሚለውን ወደፊት አብረን የምናየው ነው ሚሆነው፡፡

 

ቸር ወሬ ያሰማን፡፡

 

ማሳሰቢያ:

የዚህ ዜና ትንታኔ ባለቤት netsanetlegna.wordpress.com ነው::

The post የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከአስመራ ወደ ብራሰልስ መጠራት | ዜና ትንታኔ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሴም ዘር ማን ነው? የኩሽ ዘርስ የቱ ነው? ሐበሻ የሚባሉትስ  እነማን ናቸው? |ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

ኢትዮጵያ ውስጥ አንዱ ከአንዱ የተለያየን አድርጎ ማቅረብ አሁን አሁን በሰፊው እየተሰማ ነው። ኢትዮጵያ ብዙ የሚባሉ የታሪክ ሙሁራን ቢኖራትም ሙህራኑ በአገር ጉዳይ በያገባኛል መንፈስ በአንድነት ተሰባስበው ከመመካከር እና ከማስተማር ይልቅ ዝምታን መርጠዋል። የኢትዮጵያን እውነተኛውን ታሪክ ለህዝባቸው ከማሳወቅ ችልተኝነት ማሳየታቸው ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ እየሰራ ያለው ወያኔ ያስደስት ይሆናል። ወያኔ አሁን አሁን እየተከተለ ያለው የአረብ አብዮትን ነው። አረቦች ጥያቄአቸው እንዲመለስላቸው የሚፈልጉት በሁከት ነው። ግዛታቸውንም ማስከበር  የሚፈልጉት በሁከት ነው። ሃሳባቸውን ሌላው እንዲቀበላቸው የሚፈልጉት በማስፈራራት እና በሁከት ነው። እየገደሉ ሞተብን ብለው ይጮሃሉ እያፈነዱ አፈነዱብን ብለው ይናገራሉ በሁሉ ነገር በደል ፈጻሚ ቀዳሚዎቹ እነሱ ሆነው ሳለ ምላሽ የሚሰጣቸውን አገር አረብን ሊያጠፋ ነው ብለው ሁሉም እንዲነሱላቸው ማሳደም መቀስቀስ ይጀምራሉ አንድ ችግር ሲያጋጥማቸው ይሄንን ያደረሱብን እንደዚህ የምትባል አገር  እና እንደዚህ የተባሉ  አገር ናቸው ብለው በራሳቸው የተፈጠረውን ጥፋት ከማመን ይልቅ ወደሌላ አገር ላይ በመለጠፍ አረብ አገር በሙሉ እና ወዳጅ አገሮታቸውን ጥላቻ እንዲቀረጽባቸው አድርጎ  መመረዝ ነው። ወያኔም እየሄደበት ያለው አካሄድ ይሄንኑ ነው።

ethiopia

ኢትዮጵያ መሽቶ በነጋ ቁጥር አዳዲስ ነገሮችን የሚሰማባት አገር ሆናለች። እድሜ ለወያኔ በዘር ፐውዞ ፐውዞ አንተ አበሻ ነው እኔ አበሻ አይደለሁም። አንተ ሴም ነህ እኔ ኩሽ ነኝ። አንተ እንደዚህ ነህ እኔ እንደዚ አይደለሁም። አንተ ከገሌ ወገን ነህ እኔ ከእገሌ ወገን አይደለሁም  የሚል ጫጫታ በስፋት እየተሰማ ይገኛል። ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት የተማረው እና ታሪክ ጠንቅቀው የሚያውቁት ሙህራኖች በአንድላይ ተሰባስበው ስለ አገር በማሰብ የተለያዩ  መድረኮችን በመፍጠር  እውነተኛውን ታሪካችንን  ከማስተማር እና ከማሳወቅ ይልቅ ዝምታን በመምረጣቸው የተነሳ ወያኔ እና መድረኩን የፈቀደላቸው  የማያውቁትን ታሪክ  የየራሳቸውን ሃሳብ በማንጸባረቅ በተደጋጋሚ እየተነገረ  እና በመጽሃፍም ጭምር እውነትነት የሌለው ታሪክ አስመስለው እየተጻፉ በመሆኑ እንደዚህ የተዛቡ ታሪኮች ሲነገር በአጉል ተስፋ ሰዎችን ስለሚሞላቸው የኢትዮጵያን ታርክ የኛ ታሪክ አይደለም ብለው እስከማመን እያደረሳቸው ነው። በዚህ የተነሳ የኛ ታሪክ ወድቋል፣ ጠፍቷል፣ ተሰርዟል፣ ተረግጧል…… ሌላም ሌላም እየተባለ ስለሆነ  እውነተኛ ታሪክን እያፋለሱ ያሉትን ሰዎች ወደ ሚዲያው በማውጣት ከታሪክ ሙሁራኑ ጋር ፊት ለፊት በማገናኘትና   በማነጋገር ኢትዮጵያን የማዳኑን ስራ ትሰሩ ዘንድ ጋዜጠኞች ትልቅ ድርሻም አደራም አለባችሁ።

ሴም ወይንም ሴሜቲክ ማን ነው? ኩሽ ወይንም ኩሸቲክ ማን ነው? ሐበሻ የሚባሉትስ እነማን ናቸው? የሚለውን እንመልከት

ኖህ፡- ሴም፣ ካም፣ እና ያፌትን ወለደ ዘፍጥረት ፲+ ፩-፴፪ (10+1-32)

ሴም፡- ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሎድ፣ አራም፣ ቃይናን ወለደ።

ካም፡- ኩሽ፣ ምስራይም፣ ፍጥ፣ ከነዓን ወለደ።

ያፌት፡- ጋሜል፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያህያን፣ ያልሳ፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቴራስን ወለደ።

ከላይ የዘረዝርኳቸው የኖህ ልጆች እና የኖህ የልጅ ልጆች የሆኑ ናቸው።

ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በሆነ የዘር መጠላለፍ የሚታየው ይሄንን እውነት ካለመረዳት ነው። ሴም በሉት ሴመቲክ ኩሽ በሉት ኩሸቲክ ለሴም አባቱ ለኩሽ አያቱ የሆነው ኖህ ነው። ታዲያ የአንድ ዘር ግንድ የሆንን ወንድማማቾች ይሄንን ያህል መጠላላት እና መለያየት ለምን አስፈለገ? ዛሬ ሴሜቲክ ነን እያልን የምንፎክር ዛሬ ኩሸቲክ ነን ብለን የምንፎክር አባታችን አንድ እንደሆነ  ሲነገረን መደምደሚያችን ኖህ እንደሆነ ስናውቅ ምን ይሆን መልሳችን። ከየት ተነስተን ወደ የት ነው የምንሄደው? ወዴየትስ ነው መሄድ የምንፈልገው? ከማንስ ተፈጥረን ነው የሌላ ነን የምንለው ዛሬ እኛ ሴም ነን እኛ ኩሽ ነን ብለን የምንናገረው የተፈጥሮ  ዑደታችን እውነቱ ይሄ ነው። ለዚህ ነው ብንጣላ የማንኮራረፈው ብንሰዳደብ የማንራራቀው የአንድ ቤተሰብ ልጆች ስለሆንን ነው። ነገሮችን ጠለቅ ብለን ስናውቅ ማንነታችንን እናውቀዋለን ማንነታችንን ስናውቅ ታሪካችንን እንወዳለን ታሪካችንን ስንወድ አገራችንን እንገነባለን አገራችንን ስንገነባ ለአለም ሁሉ የፍቅር፣ የሰላም የአንድነት የስልጣኔ መሰረት ሆነን እንታያለን።

ሌላው ሐበሻ ሴሜቲክ ናቸው እንጂ ኩሸቲክ አይደሉም ይሉናል። ከመነሻው እንዳየነው ሴም ለኩሽ አጎቱ ነው የኩሽ አባት እና ሴም  ወንድማማቾች ናቸው ማለት ነው። በቃ የኛ አመጣጥ እዚህ ጋር በአራት ነጥብ ተዘግቷል። ኩሸቲክ እና ሴመቲክ የአንድ ዘር ልጆች ነን። ታዲያ ሐበሻ የሚለው ቃል የመጣው ከየት ነው? ከተባለ መልሱ ከአረቦች ነው።

ነብዩ መሃመድ ከቆሬሾች ጋር ከፍተኛ ችግር ውስጥ በነበረበት ወቅት በጃፋር መሪነት የነብዩ  የቅርብ ሰዎች የነበሩትን  ወደ ኢትዮጵያ ሲልኩ የተናገሩትን ቃል እጠቅሳለው ቃሉ ቃል በቃል ከቁርአን ነው የተወሰደው << ሐበሻ (ኢትዮጵያ) የእውነት አገር ናት በውስጧም ሰውን የማይበድል እርሱም ዘንድ አንድም የማይበደል ንጉስ አለና ወደዚያ ብትሄዱ መልካም ነው>> ይላል። ነብዩ መሃመድ በእስልምና እምነት አማኞች ዘንድ ትልቅ ቦታ ያላቸው ሰው  ናቸው። ሐበሻ የሚለውን ስም እስካሁንም ድረስ አረቦች ይጠቀሙበታል። ታዲያ በነብዩ  መሃመድ እንዲህ የተገለጹት ደግ በደልን የማያደርጉ ህዝብን የማይበድሉ መሪ ኢትዮጵያ ነበራት። እኚህ መሪ የሴምም የኩሽም ልጅ የሴምና የኩሽ ሃረግ የነበራቸው መሪ ናቸው እንጂ ዛሬ ዛሬ እንደሚነገረው የወያኔ ፖለቲካ እና የወያኔ አካሄድ የሚከተሉ እንደሚሉት ሐበሻ ስለተባሉ የሴም ወገን ናቸው ተብሎ መነገሩ የራስን ታሪክ ጠንቅቆ ካለመረዳት እና የፖለቲካን ትርፍ ለማግኘት ተብሎ ታሪክን በገዛ ፍቃድ እንደመጣል ይቆጠራል። ለኢትዮጵያ የሚሰጥ የታሪክ፣ የጀግንነት፣ የስልጣኔ፣ የሃይማኖት፣ የስነ ፈጠራ፣ የባህል፣ የቋንቋ፣ ድርሻ የሴምም የኩሽም እኩል ታሪክ ነው። ማንም ከማንም የተነጠለ ታሪክ የለንም። ማንም ከማንም የሚለያይ ስራም የለንም። ወያኔ ለአገዛዙ ማቆያ ለስልጣኑም ማራዘሚያ በማሰብ መጀመሪያ እና መሃል የሌለው ጫፍ ብቻ ያለው ታሪክ ይነግረናል። ጫፉ ላይ ወጥተን ከማንነታችን ውጪ ግዜአዊ የፖለቲካ ትርፍ ፍለጋ ማንነታችንን እና አገራችንን አደጋ ላይ መጣል ተገቢ አይደለም ነገም ታሪክ ይጠይቀናል ማንም ከተጠያቂነት አያመልጥም። ስለዚህ ወደ እውነተኛው ማንነታችን መመለስ ያስፈልገናል።

እንደ ማሳሰቢያ መናገር የምፈልገው አንድ ሰው የተለየ ሃሳብ ለምን አመጣ ተብሎ አይከለከልም ማንም የፈለገውን ሃሳብ ማምጣት ይችላል ያንን ሃሳብ ግን በማስረጃ ሊያቀርብ ያስፈልጋል። በነጻ ሚዲያ ዘርፍ የተሰማራችሁ ጋዜጠኞች በታሪክ ዙሪያ የተለየ ሃሳብ ያለው ሰው ካለ ወደሚዲያው በመጋበዝ ከታሪክ ሙሁራኑ ጋር ግልጽ ትንታኔ ከሁለቱም ወገን እንዲሰጡበት በማድረግ እና ጥያቄአቸውን በማስረጃ እንዲመልሱ በማድረግ እውነታውን ህዝቡ እንዲያውቀው የማድረጉን ስራ ቢሰራ በህዝቡ ዘንድ የሚኖሩትን ብዥታዎች ያጠራዋል። ህዝብን በመከፋፈል ዙሪያ ወያኔ የሚጠቀምበትን መንገድ አንድ አንዶችም በመከተል ላይ ስለሆኑ የፈረሰውን በመገንባት የሃሰት ታሪካዊ ወሬዎችን እውነተኛ በሆነው ታሪክ በማነጽ ያስፈልጋል። ጥያቄ አንሺውን እና ሙሁራኑን በማገናኘት በየግዜው ትንታኔ እንዲሰጥበት በማድረግ  በጋዜጠኝነት ሙያውስጥ ያላችሁ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለአገራችሁ ታሪክ ስሩ።  ኢትዮጵያን ወደ ሰላሟ እና ወደ እረፍቷ የሚያመጣት መልካም መንገድ ነውና።

ከተማ ዋቅጅራ

26.11.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

 

The post የሴም ዘር ማን ነው? የኩሽ ዘርስ የቱ ነው? ሐበሻ የሚባሉትስ  እነማን ናቸው? | ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live