Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ድርቅ ርሃብና ችጋር ምንና ምን ናቸው? ኢትዮጵያስ ለምን የርሀብ ሀገር ሆነች? |ፈቃደ ሸዋቀና

0
0

ሀገራችን መሬት ላይ እንድ ሌላ ግዙፍ የርሀብና የችጋር ዳመና እያንዣበበ ነው። አንዳንድ ቦታም ግዳይ መጣል መጀመሩን እየሰማን ነው። ይህ ችግር በሰብዓዊ ዕውቀትና ሀይል የሚፈታ ሆኖ ለምንድነው እንዲህ እየተመላለሰ የሚጎበኘን? ሌሎች ሀገሮች ተመሳሳይ የአየር ሁኔታ ችግር እየገጠማቸው እንደኛ ለአዋራጅ ጉስቁልናና ልመና አልተዳረጉም። እኛ ጋ ምን የተሰወረብን ነገር አለ? የአፍሪካ የውሀ ሰገነት የምትባልና ከማንም የማይተናነስ የተፈጥሮ ጸጋ ያላት ሀገር ይዘን ለምን እንደዚህ አይነት ሕዝብ ሆንን? በጅጉ የሚደንቅ ነገር ብቻ ሳይሆን በንዴት የሚያቃጥል ነገር ነው። እንደሚመስለኝ ችግሩን የልፈታንበት አንዱ ምክንያት ተገቢና የበሰለ ውይይት የማናካሂድ ህዝብ መሆናችንና ይህንንም ለማድረግ የመወያያና መፍትሄ ፍለጋ ሁኔታ እንዳይፈጠር መንግስታቱ ተጠያቂነትን ለማምለጥ ሲሉ የሚፈጥሩት እንቅፋትነት ይመስለኛል። እስከመቼ በዚህ ውርደት እንደምንቀጥል ባሰብኩ ቁጥር የሚያመኝን ህመም ችዬ ነው ይህን ለውይይት የሚሆን ጽሁፍ የጻፍኩት። 

fekade shewakena

ከላይ በርዕሱ ላይ ያነሳኋቸውን ቃላት ብዙ ሰዎች በተለዋዋጭነት ሲጠቀሙባቸው መስማት ያልተለመደ ነገር አይደለም። ችጋርን ወይም ሰፊ መጠን ያለውን የሀገራችንን ርሀብ ድርቅ እያሉ የሚጠሩ ሰዎች ብዙ ናቸው። ርሀብና ችጋርንም እንደዚሁ የሚያደበላልቁ ሰዎች ብዙ ናቸው። ዝቅ ብዬ ለማሳየት እንደምሞክረው ድርቅ የምንለው የአየር ባህርይ ርሀብና ችጋር ብለን ከምንጠራቸው ነገሮች ጋር በመሰረቱ የመንስዔና የውጤትም ሆነ ሌላ የተፈጥሮ (structural) ተዛምዶ የለውም። ይህንን በቅጡ ለመረዳት የቃሎቹን ቀጥተኛና ቴክኒካል ትርጉም የያዙትንም ጽንሰ ሀሳብ በቅጡ መለየት ያስፈልጋል። በዚህ ላይ ይህን የሚያረጋግጡ በርካታ የአለማችንን ተመክሮ መመልከት ይጠቅማል።

ድርቅ (Drought) ባንድ አካባቢና ባንድ ወቅት ባልተለመደ ሁኔታ የሚደርስን የዝናብ መጥፋት ወይም መጠን መዛባት የሚገልጽ ቃል ነው። ከሰው ቁጥጥር ውጭ የሆነ የአየር ሁኔታንና የአየር ሁኔታን ብቻ የሚገልጽ ሀሳብ ነው ማለት ነው። ርሀብ (Hunger) በምግብ አለመብቃት ምክንያት ሰዎች የምግብ ፍላጎታቸው ሳይሟላ ቀርቶ ውሎ ለማደር ብቻ ምግብ የሚያገኙበት አልፎ አልፎም በምግብ ችግር ምክንያት ለሞት የሚዳረጉበት ሁኔታ ነው። ችጋር (Famine) ሰዎች የሚላስ የሚቀመስ ምግብና ውሀ በማጣት አካላቸው እያለቀ ሄዶ በብዙ ቁጥር (mass) ለዕልቂት የሚዳረጉበት ሁኔታ ነው። ድርቅ በመሰረቱ ከርሀብም ሆነ ከችጋር ጋር ተፈጥሮአዊ ዝምድና  የለውም ብያለሁ።  በሌላ አነጋገር ድርቅ የርሀብም የችጋርም የተፈጥሮ ምክንያት አይደለም።  በምግብ ራስን ለመቻልና በችጋርም ሆነ በርሀብ ላለመጠቃት የግድ እህል አምራች ሀገር መሆንም ላያስፈልግ ይችላል። ሌላ ነገር ሰርተው ምግባቸውን ከውጭ ገዝተው የሚኖሩ ሀገሮች እሉ። ስለዚህ ድርቅና ኤል ኒኖ የርሀብ ምንጭ ነው የሚለው ልፈፋ ሌላ የጎላ ስሕተትና የችግሩን ዕውነተኛ መንስዔ መሸፈኛ ሆኖ እያገለገለ ነው።  እንዲያ ቢሆን ኤል ኒኖና ድርቅ አገር እየመረጡ ችጋርና ርሀብ አያመጡም ነበር።

ድርቅ የተፈጥሮ ሁኔታ ስለሆነ ለመከላከልም አይቻልም።  ችጋርና ርሀብ ሰው በጥረቱ ሊከላከላቸውና ሊያጠፋቸው የሚችሉ ነገሮች ናቸው። ብዙ ሀገሮች ይህን በማድረጋቸው ከኛ የበለጠ ድርቅ እየመታቸው እንኳን ችጋርም ርሀብም አይነካቸውም። እድግመዋለሁ ድርቅ የርሀብና የችጋር የተፈጥሮ ምክንያት አይደለም። ይህን የሚሉ ሰዎች ወይ አውቀው እውነተኛውን ችግር መሸፈን የሚፈልጉ ወይ አገላብጦ ማየት የተሳናቸው የዋሆች ናቸው። አንድ ሰው ናላው እስኪዞር ድረስ አልኮል ጠጥቶ ሰክሮ መኪና ሲነዳ ተጋጭቶ ወይም ገደል ገብቶ ቢሞት የሞቱን ምክንያት በደፈናው የመኪና አድጋ ነው ብሎ መሸፋፈን እውነት እንዳልሆነ ሁሉ በኛም ሀገር እየተደጋገመ የሚደርሰውን ርሀብና ችጋር በኤል ኒኖና በድርቅ ማመካኘት ዕውነት አይደለም። ሌላው ቀርቶ ችጋርንና አደገኛ ርሀብን በጊዜ በመለመን ማስቀረት ይቻላል።    በሀገራችን የስከዛሬዎቹን ችጋሮች ጥፋት መቀነስ ወይም ማስወገድ ያልተቻለው መንግስታቱ ክብራቸው ወይም ሊፈጥሩ የፈለጉት ገጽታ የተበላሸ እየመሰላቸው ችግሩን በመደበቃቸውም  ነው። ባሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣኖች ለርዳታ ሰጭዎች የሚያቀርቡትን አንዴ ራሳችንን ስለቻልን ራሳችን እንወጣዋለን ሌላ ጊዜ ደግሞ ርዳታ ስጡን የሚሉ የተምታቱ መልዕክቶችን አሁን ሀገሪቱ ውስጥ ግዳይ መጣል ከጀመረው ርሀብ ጋር ስናስተያየው ከዚሁ በባዶ ቤት የአክብሩኝ ባይነት የመግደርደርና የመደባበቅ ተግባር ብዙ አለመራቃችንን ያሳያል። የኢትዮጵያ ሹማምንት ነጋ ጠባ በሚቲዮር ፍጥነት ኢኮኖሚ አሳደግን ሲሉን የነበረው ፕሮፓጋንዳና ኢኮኖሚው አንድ የድርቅ ወቅት የሚያሻግር አቅም የሌለው  ሆኖ መገኘት እንዳሳፈራቸው በግልጽ ይታያል። ይህ እንዳይሆን ቀድሞ ነበር ስታቲስቲክሱን አልሞ መደቆስ የነበረባቸው።  ለመሆኑ አንድ አስርት ሙሉ በሚያስጎመጅና አለም እይቶት በማያውቅ መጠን ሲያድግ የነበረ ግብርና እንዴት ያንድ በልግና መኸር ዝናብ ችግር መሻገር ኣቃተው? አለም ለዚህ ጥያቄ መልስ እየፈለገ ይመስለኛል። እስካሁን ለዚህ ጥያቄ መልስ የሰጠ ሹም ግን አላየሁም።

ችጋር በድርቅ ሳይሆን ሰዎች በተለይም መንግስታት አስበው መስራት ያለባቸውን ስራ በዕውቀትና በትጋት ባለመስራታቸው ወይም በተለያየ ምክንያት ትክክለኛ ፖሊሲ ለመከተል ባለመፈለጋቸው  የሚመጣ አደጋ ነው።  እዚህ ላይ ከባህል ጋር የተያያዙ ሌሎች ሊለወጡ የሚገባቸውና የሚችሉ ምክንያቶችን መጨመር ይቻል ይሆናል። በአለም ዙሪያ በብዙ መጠንና በተደጋጋሚ ማየት እንደምንችለው ሰዎች  ምግባቸውን ባግባቡ የማያሟሉባቸው ሀገሮች  የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚገፉ ወይም አፈናና አድሎ የበዛባቸው ፣ ማናለብኝነትና አምባገነናዊ ፖለቲካ ስርዓት የሰፈነባቸው ፣ ማህበራዊ ግጭቶችን በውይይት ከመፍታት ይልቅ መጨፍለቅ በሚያበዙ ወይም ሙስና በሚፈጥረው ቀውስና ብልሹ አስተዳደር የተበከሉ የህግ ልዕልና የሌለባቸው ናቸው። እውሮፓና አሜሪካ ውስጥ ብዙ ጊዜ ትልልቅ ድርቅ ይከሰት እንጂ  ሰው ተርቦ ሞተ ሲባል የማንሰማው ዴሞክራሲያዊና ግልጽነት የሰፈነበት ስርዓት ስላላቸውና መንግስት ልሒቃኑና  ተቋማቱ ከነፖለቲካ ልዩነታቸው ካለምንም ይሉኝታና መፎጋገር ስለመጭው ዘመን ተጨንቀው ስለሚያስቡ ስለሚወያዩና ስለሚያቅዱ ነው።

የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች የቀድሞዎቹም ያሁኖችም ድርቅን የርሀብና የችጋር ምክንያት አድርገው ራሳቸውን ነጻ ለማድረግ በሚያደርጉት ሀሰተኛ  ጥረት በጣም ይመሳሰላሉ።  የቀድሞዎቹን መንግስታት ህዝብ በማስራብና ለችጋር በመዳረግ የሚከሱት የዛሬዎቹ መሪዎች አሁን ሀገሪቱን የገጠማትን የርሃብና የችጋር አደጋ ልክ እንደቀድሞዎቹ በድርቅ በተለይ በፈረደበት ኤል ኒኖ ማመካኘቱን ተያይዘውታል። ኤል ኒኖ ከችጋር ጋር ዝምድና ያለው ስራቸውን ባግባቡ ባልሰሩ ሀገሮች እንደሆነ እንድናውቅ አይፈልጉም። በነሱ ቤት አንድም የፖሊሲም ሆነ የሀገር አስተዳደር ምክንያት የለበትም። የችግሩ መንስዔ የግብርና ፖሊሲ ፣ ያጠቃላይ የኢኮኖሚ ወይም የመሬት ይዞታ ፖሊሲ ወይስ የዴሞክራሲ ችግር  ብሎ ሰው እንዲጠይቅና መልስ እንዲፈልግ አይፈልጉም።

አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ አንድ የዲያስፖራዎች (ይህ ዲያስፖራ የሚል ቃል ሲያስጠላኝ) ነው በተባለ ስብሰባ ላይ በድርቅ ምክንያት ካሊፎርኒያና አውስትራሊያም እየተሰቃዩ ነው ሲሉ ወዶ አይስቁ ሳቅ እየሳኩ ስምቻቸዋለሁ። እኛ ሀገር ላይ የተለየ ነገር አልመጣም እያሉ መዋሸታቸው ነበር። እኝህ ሰውዬ እንዴት ምስክር አይኖርም ብለው እንደገመቱ በጣም ነው የገረመኝ። እኔ ራሴ  ድርቁ በገነነበት ባለፈው ስፕሪንግ ካሊፎርኒያ  ሳን  ፍራንሲስኮ ኦክላንድና ሳን ሆዜ አካባቢ ነበርኩ።  ጆግራፈር ስለሆንኩ ለንደዚህ አይነት ጆግራፊያዊ ክስተት መመልከቻ ትልቅ አይን አለኝ። ሁኔታውን  ስራዬ ብዬ ነበር ለማየት የሞከርኩት። ብዙ የደረቀ ሳርና ቅጠል ብዙ ቦታ አይቻለሁ።  አፈሩም ብዙ ርጥበት እንዳልነበረው አይቻለሁ።  አቶ ሀይለማሪያም የሚያወሩት ስቃይ ግን በቦታው አልነበረም። ለመኪና ማጠቢያ ውሀ አራርቆ መጠቀምን ፥ የጓሮ አትከልት ዉሀ ቆጥቦ ማጠጣትን ፥ ቧንቧ የሚያወርደው ውሀ ቀጠን እንዲል ማድረግንና ሌሎች የውሀ ቁጠባ ስራዎችን ሰቃይ ነው ካላሉ በስተቀር ስቃይ አልነበረም። ብዙ ያካበቢው ነዋሪ ድርቅ መኖሩን እንኩዋን የማያውቅ አለ። ካለኝ መረጃ አውስትራሊያም  ስቃይ ሊባል የሚችል ነገር አልነበረም። በነገራችን ላይ አቶ ሀይለማሪያም ስለ ካሊፎርኒያና አውስትራሊያም በድርቅ መሰቃየት ሲናገሩ ያጨበጨቡት ዲያስፖራዎች በጅጉ አስገርመውኛል። ጭብጨባቸውን ስሰማ አቅለሽልሾኝ ነበር ብዬ ዕውነቱን ልናገር መሰለኝ። ቪዲዮውን ያላያችሁ እዩትና የገባችሁ ካላችሁ የጭብጨባውን ትርጉም ንገሩኝ። የድርቅ ስቃያችን ከካሊፎርኒያና ከአውስትራሊያ ጋር ይመሳሰላል ስለተባለ ሀገራችን እኩል ሆነች ብለው መደሰታቸው ይሆን? ቁጥሩ ይህን የሚያህል ገልቱ ዲያስፖራ ያለ አይመስለኝም ነበር።

ወደተነሳሁበት ነገር ልመለስ። ድርቅ የምክንያት ርሀብና ችጋር  የውጤት ግንኙነት እንዳላቸው እያደረግን የምንለፍፈው ወሬ ከደረቅ ውሸትነቱ አለፎ ለስንፍና የሚዳርግ አደገኛ  ነገርም ነው። ተፈጥሮን (ድርቅን) መቆጣጠር ስለማንችል ድርቅ በመጣ ቁጥር ለሚመጣው ርሐብና ችጋር እጅ እየሰጠንና እየለመንን ከመኖር ሌላ ምርጫ የለንም ወደሚል አደገኛ ድምዳሜ ይወስደናል። ለሀገሩ የሚቆረቆር ማንኛውም ቅን ኢትዮጵያዊ የሀገራችን የርሀብ ምንጭ ድርቅና ኤል ኒኖ ነው  የሚለውን ሀሰት የማታለያ ፕሮፓጋንዳ መቀበል ቀርቶ ለመስማት ፈቃደኛ ሊሆን አይገባም። ባለስልጣናትም ይህን ውሸት በመደጋገም ካለባቸው ሀላፊነት እንዲሸሹ ልንፈቅድላቸው አይገባም። ይህ የችግሩ መፍቻ የመጀመሪያ ርማጃ ይመስላኛል።

ግጥጥ ያለው ዕውነት ግን እንዲህ ነው። የኖቤል ሎሬቱን አመርትያ ሴንን የመሳሰሉ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች እንደሚነግሩን ዴሞክራሲ ባለበት ቦታ ሁሉ ርሀብና ችጋር የለም። ችጋርና ሰፊ ህዝብ የሚሸፍን ርሀብ በአንድ ሀገር ውስጥ የዴሞክራሲና ነጻ ማህበረሰብ አለመኖር ውጤት ናቸው። ዴሞክራሲ ባለበት ሀገር እንደልብ በሚካሄድ ክርክር የሀሳብ አማራጮች ይፈልቃሉ። አምባገነኖች ህዝብ የሚጠቅምና ርሀብ ጭራሽ የሚያስወግድም ቢሆን እንኳን ስልጣናቸውን የሚፈታተን ከሆነ ርሃብና ችጋሩን ይመርጣሉ። ነጻ ውይይትና ክርክር ስልጣንና ፖሊሲ የሚጠይቅ ስለሆነ ይህንን እንድንወያይ አይፈልጉም። በኢትዮጵያ የመሬት ይዞታን ፖሊሲ ህዝብ አይከራከርበትም። ሀገሬውን የመንግስት ጭሰኛ ያደረገ ፖሊሲ በኔ እምነት ርሀብተኛ ሀገር ለመሆናችን አንድ ምክንያት ይመስለኛል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ይህ ነገር ከተቀየረ የሚቀየረው በመቃብራችን ላይ ነው ነበር ያሉት። የገበሬው የይዞታ ባለቤትነት ርግጠኝነት አለመኖር ፣ የግለሰብ ይዞታዎች ከጊዜ ጊዜ እየተቆራረሱ ማነስ ፣ በርሻ መሬት ላይ ያለውን የሰው ብዛትና ግፊት ለመቀነስ የሚያስችል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ባግባቡ አለመዘርጋት ከብዙ ጥቂቶቹ የሀገራችን የርሀብና የችጋር ምክንያቶች ይመስሉኛል። ተገቢና ስራ ላይ ባግባቡ መዋል የነበረበትን የብሔረሰቦች የእኩልነት ጥያቄ ወደ በለጠ ልዩነትና ሰዎችና ካፒታል ብሄረሰብ ሳይመርጡ እንዳይዘዋወሩ የሚያደርገው ፖለቲካ ሁኔታ ችጋር ይፈለፍል እንደሆነ እንጂ ብልጽግና አያመጣም። አነስተኛ ገበሬዎችን በገፍ እያፈናቀሉ ለውጭ ሀገር ቱጃር መሬት መሸንሸን ችግርና ርሀብ ያፈላ እንደሆን እንጂ የማንንም ችግር ሲያስወግድ አልታየም። ሀገርን ለዜጎቿ ሳይሆን ለባዕዳን መስሕብ በማድረግ የዳበረና ችግር ያስወገደ ሀገር የለም። ይህን ማረም የማይችል መንግስት ርሃባችንን በኤል ኒኖ ሲያመካኝ ማፈር አለበት።  በነዚህና እነዚህን በመሳሰሉ ማነቆዎች ላይ በግልጽና በቅንነት ተወያይተን መፍትሄ ካላበጀን ርሀብና ችጋር በየጊዜው የሚጎበኙን የውርደት ሀገር ሆነን መኖራችን ይቀጥላል።

የሀገራችንን ባለስልጣኖች አስመልክቶ በጣም የሚያስተዛዝበው የርሀቡ ደረጃ ለምን ባደባባይ ተዘገበ በማለት ባለማቀፍ ሚዲያዎች ላይ  የሚያካሂዱት ቡራ ከረዩ ነው።  የሚዲያው የርሀቡን አስከፊነት በስፋት መዘገብ ልመና ለማቀላጠፍ ይረዳ እንደሆን እንጂ ጉዳት የለውም። ቡራ ከረዩው ሀገርና ህዝብ ተጎዳ በሚል ሳይሆን በብዙ  ቅባት ያሳመርነው ገጽታ ለምን ይነካል ነው።  ሰሞኑን ቢቢሲ ያቀረበውን ዘገባ አስመልክቶ የመንግስት ሹሞችና ደጋፊዎች የሚያደርጉት ያዙኝ ልቀቁኝ በጣም አስገራሚም አስተዛዛቢም ነው። በካሜራ ላይ ሰለባዎች እየተናገሩ ያካሄዱትን ዘገባ በምን ምክንያት ነው የምናወግዘው? ለንደን ያለው ኤምባሲ የሚለው ቢያጣ የርሀቡን አስከፊነት አስመልክቶ ቢቢሲ ባቀረበው ዘገባ ላይ በሰጠው የተቃውሞ መልስ ቢቢሲ ርሀቡን ያመጣው ኤል ኒኖ ነው የሚለውን የመንግስት ውሸት ደግሞ ባለማለቱ አጥብቆ ይከሳል። እንዲህ ይላል። “The report also failed to give perspective on the drought situation currently unfolding in Ethiopia and around the world and how it is triggered by the El Nino phenomenon”. የዚች አረፍተ ነገር ቁም ነገር ችግሩን ያመጣብን ኤል ኔኖ ስለሆነ ምንግስታችን አይጠየቅም የምትል ነች። ተጠያቂነትን ማምለጫ ብልጠት መሆኗ ነው። ኤል ኒኖ ሀገር እየለየ ነው እንዴ ጥቃት የሚያደርሰው? አስር ዐመት ሙሉ ግብርና ከሁለት ዲጂት በላይ ያደገባትን ሀገር ከቀርፋፋዎቹ እንዴት እድርጎ እንደመረጣት ግራ የገባው ታዛቢ ታዲያ ምን ይበል?

በኔ አመለካከት ከዚህ በአለም ፊት በተደጋጋሚ ካዋረደንና እያዋረደን ካለ ርሀብና ችጋር መገላገል የምንችለው በችግሩ ዙሪያ በግልጽ በመወያየት ነው። የስካሁኑን ተመክሯችንና መረጃዎቻችንን ይዘን በግልጽ እንወያይ። ይህ የወገንተኛ ፖለቲካ ጉዳይ አይደለም። የህልውና ጉዳይ ነው። ወደ ዝርዝር ምክንያቱ እንግባ ካልን በመንግስት ላይ ብቻ በማመካኘት የምንገላገለውም አይደለም። እንደ ህዝብ ያሉብንም ባህላችን ውስጥ የተዋቀሩና ለችግሩ የዳረጉን ብዙ ችግሮች አሉ። በሀገራችን ይህን ሁላችንም የምንወያይበት ዴሞክራሲያዊ መድረክ ያስፈልገናል። ለመፍትሄውም ፍለጋ ሆነ ያገኘነውን የመፍትሔ ሀሳብ ስራ ላይ ለማዋል ዲሞክራሲ የግድ እንደሚያስፈልገን ግን ብዙ መከራከር ያለብን አይመስለኝም። ይህን ማድረግ ካልቻልን የሚቀጥለው ቸነፈር ጊዜም ይህንኑ እያወራን በውርደታችን ለመቀጠል ተስማምተናል ማለት ነው።

The post ድርቅ ርሃብና ችጋር ምንና ምን ናቸው? ኢትዮጵያስ ለምን የርሀብ ሀገር ሆነች? | ፈቃደ ሸዋቀና appeared first on Zehabesha Amharic.


በዘመናችን የተራቡ ዜጎችን መደበቅ እንደ ገጽታ ግንባታ የሚቆጥሩ ሰዎችን ከባለሻሽ ሌቦች ለይቼ ኣላያቸውም |ከበእውቀቱ ስዩም

0
0

beweketuባገራችን ኣብዛኛው ዜጋ ለቀን ጉርስና ላመት ልብስ ሲታገል የሚኖር ነው፡፡ ጌቶች ደግሞ ኣማርጠው ይበላሉ፡፡ ኣማርጠው ይለብሳሉ፤በለስ ሲቀናቸው ደግሞ የሃያ ኣምስት ሚሊዮን ብር ቪላ ይቀልሳሉ፡፡ እንዲያም ሆኖ ደግሞ መከበርና መደነቅ ይፈልጋሉ፡፡ ሰው ምንም በስጋው ቢመቸው በሌላው ተመዝኖ እንደቀለለ ሲሰማው ደስተኛ ኣይሆንም፡፡ ስለዚህ ጌቶች ያስንቀናል ብለው የሚያስቡትን ነገር በሙሉ ጠምድው ይይዙታል፡፡ ይዋጉታል፡፡ ኢትዮጵያ- ጌቶች ለኩራታቸው፤ ዜጎች ለራታቸው የሚታገሉባት መድረክ ናት፡፡

ብዙ ጊዜ ረሀብ ሲከሰት ጌቶች ራብተኛውን ሁሉ ሰብስበው ጎተራ ውስጥ ሊደብቁት ይቃጣቸዋል፡፡ የድሆች የተራቆተ ሰውነት የገጠጠ ኣጥንት፤ የጌቶችን የመከበር ፍላጎት ያከሽፈዋል፡፡ ባንድ ወቅት በቦሌ መዳኒያለም ዳርቻ ስራመድ ኣካባቢው ኣለወትሮው በለማኞች ኣለመሞላቱን ታዝቤ ተገረምሁ፡፡ያዲሳባ ኣስተዳደር ፤ ለማኞችን“ በጥቃቅንና ኣነስተኛ ” ኣደራጅቶ ያሳለፈላቸው መስሎኝ ነበር፡፡ እንደተሳሳትሁ ለመረዳት ጥቂት ደቂቃ በቦታው መቆም ነበረብኝ፡፡ ኣንዲት ተመጽዋች ሴት ልጇን ይዛ ከቅጽሩ ስር ለመቀመጥ ስታነጥፍ ፖሊስ በቆረጣ ገብቶ “ዞር በይ ነግሬሻለሁ” እያለ ሲያዋክባት ተመለከትሁ ፡፡ የደነገጠ ልጇን እየጎተተች ተወገደች፡፡ ከዚያ ወዲያ ከኣቡነ ጳውሎስ ሃውልት በቀር ባካባቢው ደፍሮ የቆመ ኣልነበረም፡ ፡ ወደ ቤቴ ከመሄዴ በፊት ያቡኑን ወፍራም ሀውልት ዞር ብየ ሾፍኩት፡፡ እጁን እንደ ራሱ ሀይሉ ሙርጥ ገትሮ ከፊትለፊት ያለውን “ ሬድዋን ህንጻ ” ሲባርክ ነበር፡፡

“ገጽታ ግንባታ?”

በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን የፍርድ ምኒስተር የነበሩት ኣፈንጉስ ነሲቡ የሌባ ብዛት ቢያስቸግራቸው ኣንድ መላ መቱ፡፡ ሲሰርቅ የተገኘ ወሮበላ ግንባሩ ላይ በጋለ ስለት ምልክት እንዲደረግበት ደነገጉ፡፡ ታድያ ሌቦች የዋዛ ስላልነበሩ ሻሽ በመጠምጠም የግንባራቸውን ጠባሳ ሊሰውሩት ሞክረዋል፡፡ በጊዜው ደግሞ ሻሽ መጠምጠም ካክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ የወረደ የነገስታቱና የመሳፍንቱ ወግ ነበር፡፡ ጮሌ ሌቦች ውርደታቸውን ከመሸፈን ኣልፈው የንጉስ ገጽታ ተላብሰው ብቅ ኣሉ፡፡

ethiopian famaine

በዘመናችን የተራቡ ዜጎችን መደበቅ እንደ ገጽታ ግንባታ የሚቆጥሩ ሰዎችን ከባለሻሽ ሌቦች ለይቼ ኣላያቸውም፡፡
በነገራችን ላይ፤ ብርቱካን ኣሊ ግለሂስ ያደረገችበትን ዘገባ ካየሁ በኋላ ለጊዜው ለመናደድ እንኳ ቸግሮኝ ነበር፡፡ ዘገባውን የሠራው ጋዜጠኛ እንዲህ ኣይነቱን ካንድ ድንጋይ የተጠረበ ደደብነት ተሸክሞ የመኖር ችሎታው በጣም ኣስደነቀኝ፡፡ በዚህ በሰላቢው ቀን ይቅርና፤ በደህናው ቀን እንኳ የባላገሩን ራብና መከራ ከጉያው የበቀልን ልጆቹ እናውቀዋለን ፡፡ ኣስራ ኣምስት ሚሊዮን ህዝብ መደበቅ ሰማይን በመዳፍ ለመሸሸግ እንደ መሞከር ይቆጠራል፡፡ መመፍትሄው በተቸገሩ ሰዎች ጫማ ቆሞ ነገሮችን መመልከት ነው፡፡ ለነገሩ ችግርን ያልቀመሰ ሰው ለችግረኛ መራራት እንዴት ይቻለዋል?

ኣብን ተውትና ፤ንገሩት ለወልድ
ተገርፏል ተሰቅሏል ፤ እሱ ያውቃል ፍርድ
እንዲል ባላገር፡፡

The post በዘመናችን የተራቡ ዜጎችን መደበቅ እንደ ገጽታ ግንባታ የሚቆጥሩ ሰዎችን ከባለሻሽ ሌቦች ለይቼ ኣላያቸውም | ከበእውቀቱ ስዩም appeared first on Zehabesha Amharic.

ሳይኮሎጂ |ለራሳችን መንገር የሌለብን 4 ነገሮች

0
0

Confident የተለያዩ ችግሮች ውስጥ የምታልፉበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለችግሮቹም ራሣችሁን ተጠያቂ ታደርጉ ይሆናል፡፡ በየትኛውም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑም ግን ደካማነታችሁን የሚያጎሉና ከሠዎች በታች ሆናችሁ እንድትታዩ የሚያደርጉ ቃላትን መጠቀም የለባችሁም በማለት የሥነ-ልቦና ምሁራን ይመክራሉ፡፡ እነኚህ ቃላት አስተሳሰባችን ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የመፍጠር አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡ ፡ ለራሳችን የምንናገራቸው አሉታዊ ቃላት ከፍተኛ ጉዳት እንዳላቸው ከሕይወት ልምዴ ተገንዝቤያለሁ የሚሉት የሥነ-ልቦና ባለሙያው ማይክ ቡንድራንት በተለይ የሚከተሉትን ቃላት ለራሳችሁ ፈፅሞ መንገር የለባችሁም ይላሉ፡፡

  1. የማልረባ ነኝ

ይህ በራስ መተማመናችሁን በቀጥታ የሚገድል አነጋገር ነው፡፡ የማትረቡ ወይም አንዳች ዋጋ የሌላችሁ መሆኑን ለራሳችሁ መንገር አሉታዊ አስተሳሰብ በአእምሯችሁ እንዲሰርፅ የማድረግ ኃይል ስላለው ቃሉን መጠቀም ተገቢ አይደለም፡፡

2. አልችልም

አንዳንድ ነገሮችን በምትፈልጉት ደረጃ መስራት የማትችሉባቸው ሁኔታዎች በሚፈጠሩበት ጊዜ አቅማችሁን ልትጠራጠሩ ትችላላችሁ፡ ፡ የምታደርጉት ነገር ጥቅም እንደ ሌለው ለራሳችሁ መንገር ለሥራ ያላችሁን የተነሳሽነት ስሜት ይቀንሠዋል፤ አቅማችሁን ያሣጣችኋል፡፡ ይህ አነጋገር እውነታውን ከመግለፅ በላይ ራሳችሁን መልሶ የማጥቃት አቅም አለው፡፡ አንድ ነገር ከመሥራታችሁ በፊት እወድቃለሁ/ አይሣካልኝም ከማለት ይልቅ ደጋግሞ በመሞከር ለውጤት መብቃት እንደምትችሉ ማመን አለባችሁ፡፡

3. ሠዎች አይወዱኝም

ሠዎች አይወዱኝም የሚለውን ስሜት በአእምሯችን ማስረፅ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ እንደሆኑ እንድናስብና ለራሳችን ጥረት ተገቢ ውጤት እንዳንሠጥ ያደርገናል፡፡ በሌሎች ያለመወደድ ስሜት ከተሠማን ደግሞ ለራሳችን የምንሠጠው ክብርም ይቀንሳል::

4. ለውጥ ማምጣት አልችልም

አንድን ነገር ለመለወጥ አቅማችሁ ካልፈቀደ ራሣችሁን አታስገድዱት፡፡ ፍፁም መሆንንም ከራሣችሁ አትጠብቁ፡፡ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የምትሠጧቸው ሀሳቦች የራሳቸው አዎንታዊ ተፅእኖ አላቸው፡፡ ስለዚህ ‹ለውጥ ማምጣት አልችልም›› የሚለው ቃል ለራሳችሁ መንገር ከሌለባችሁ አሉታዊ ቃላት መካከል አንዱ ነው፡፡

በአጠቃላይ ስሜታችሁን የሚጎዱ እንዲህ ዓይነት ቃላትንና አነጋገሮችን መጠቀም ትታችሁ አንደበታችሁን በመጠበቅ በየዕለቱ ለምታከናውኗቸው ተግባራት ትኩረት በመስጠት ውጤታማ መሆን ትችላላችሁ፡፡

ምንጭ፡- Psychcentral.com

The post ሳይኮሎጂ | ለራሳችን መንገር የሌለብን 4 ነገሮች appeared first on Zehabesha Amharic.

“ሙስሊሙ ማህበረሰብ የወገኖቹን ህይወት ለመታደግ የመረባረብ ዜግነታዊ ብቻ ሳይሆን ሀይማኖታዊ ግዳጅም አለበት!”ድምፃችን ይሰማ

0
0

በሀገራችን የተከሰተውን ረሀብ አስመልክቶ ከ‹‹ ድምፃችን ይሰማ›› የተሰጠ መግለጫ

ረሀቡ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ተሳትፏችን ሊጎላ ይገባል!!!
ሰኞ ህዳር 6/2008

ሙእሚን ህያው የሆነ፣ ልስልስና አዛኝ ልቦና ባለቤት ነው፡፡ በዚህ ህያው ልቡ ሌሎችን ከማወክ ይርቃል፤ ከወንጀል ይቆጠባል፤ በመልካም ያዛል፤ ከመጥፎ ይከለክላል፡፡ በዙሪያው ላሉ ፍጡራን ባጠቃላይ የበጎ ነገራት እና የሰላም ምንጭ ነው፡፡ ይህንን የሙእሚን ስነ-ምግባር ቁርዓን እንዲህ ይገልፀዋል፡-
‹‹በትዕግስትና (እርስ በእርስ) በመተዛዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች መሆን ነው፡፡›› (አል በለድ፡ 17)

ethiopian famaine
አንዱ ለአንዱ የመተዛዘን ታላቅ ስነ-ምግባር በሙእሚኖች የእርስ በእርስ ማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ ተፅእኖ በማሳደር ማህበረሰባቸው በእዝነትና በርህራሄ፣ በበጎና በፅድቅ የተሞሉ የተቀደሱ ስሜቶች መፍለቂያ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ይህ መተዛዘን ከሰው ልጅ አልፎ ለእንስሳትም ጭምር የሚተርፍ ሊሆንም ይገባል፡፡ ኢስላም ለሰው ልጅ ክብርና ልቅናን ችሮታል፡፡ ምድር ፍላጎቱን እንድታሟላ እንደተገራችለት ያስተምራል፡፡ ‹‹የተፈጥሮ ሀብቶች ውስን ናቸው›› ከሚሉ ስግብግብነትን መፍጠር ከሚሹ ርዕዮተ ዓለሞች በተቃራኒ ለመተጋገዝ፣ መተሳሰብና መተዛዘን ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ በተለይም የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎት የሆኑት ምግብና መጠለያ በነፍስ ወከፍ ይዳረሱ ዘንድ ከመስበክና ማበረታታት ባለፈ የተራበን ማብላትን በተለያዩ አምልኮአዊ ስነ-ስርዐቶች ላይ ለሚፈጠሩ ጉድለቶች ማካካሻ (ከፋራ) እንዲሆን አድርጎታል፡፡
የኢስላም የመረዳዳት ፅንሰ ሀሳብ ከአቅም ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ አቅም ያለው በእርዳታ ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ከማበረታትና ማስጠንቀቅ ባሻገር አቅም የሌላቸውም በማስተባበሩ ረገድ መሳተፍ የሚችሉበት ማዕቀፍ እንዳለ አመላክቷል፡፡ አቅም የለኝም ብሎ እርዳታን ከማስተባበር መዘናጋትን በሚከተለው መልኩ የእኩያንን ባህሪ ሲገልጽ እንደጉድለት በማንሳት በፅኑ አውግዞታል፡-
‹‹ድሀን በማብላት ላይም የማያግባባው ሰው ነው፡፡›› (ሱረቱል ማዑን፡ 3)
በተለይም ቁርአን ‹‹የረሀብ ባለቤት›› ሲል በሚጠራው ክፉ ቀን የተራቡን አለማብላት ለሰው ልጅ ከተሰጡት ሃላፊነቶች ውስጥ አንዱን እንዳለመፈፀም ይቆጥረዋል፡፡
‹‹ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡ ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ? ….. ወይም የረሀብ ባለቤት በሆነ ቀን ማብላት (ነው)›› (አል በለድ፡ 12-14)
በሀገራችን የተከሰተውን ረሀብ ተከትሎ ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የወገኖቹን ህይወት ለመታደግ የመረባረብ ዜግነታዊ ብቻ ሳይሆን ሀይማኖታዊ ግዳጅም አለበት፡፡ በእርግጥ ህዝበ ሙስሊሙን የሚወክል ተቋም ቢኖር በዚህ ወቅት ህዝብን በማስተባበር ለወገኖች በቀላሉ መድረስ በተቻለ ነበር፡፡ የእርዳታ መስመሩም ቀላል በሆነ ነበር፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለዚህ ባለመታደላችንና በመንግስት በተመረጡ ካድሬዎች የተሞላው ተቋማችን ህዝብ ሙስሊሙን መጨቆኛ ሽፋን ከመሆን ባለፈ ይህ ነው የሚባል የረባ ፋይዳ ሊያበረክት የሚያስችለውን መዋቅራዊም ሆነ አስተዳደራዊ ቁመና የተላበሰ ባለመሆኑ መሰል ሀላፊነቶች በግል በምናደርጋቸው ጥረቶች ላይ የተመረኮዙ ናቸው፡፡
ረሀቡ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ የጎላ ሊሆን ይገባል፡፡ ከሌሎች ጋር በአጋርነት በሚደረጉ የእርዳታ ተግባራት ላይ መሳተፍ፣ እድርና መሰል ማህበራዊ መዋቅሮችን በመጠቀም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ፣ ከዚህ በፊት በፈጠርናቸው የተለያዩ አደረጃጀቶች በመጠቀምም የአቅማችን ሳንሰስት በመለገስ ለወገኖቻችን አጋርነታችን ልናሳይና ሀገራዊና ሀይማኖታዊ ሀላፊነቶቻችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ይህን መከራን እንዲያነሳልንና ይዞት ከሚመጣው ጉዳት ህዝባችንን ይታደገው ዘንድ ያለመሰልቸት ወደ አላህ (ሱ.ወ) ተደጋጋሚ ዱዐ በማድረግ ሰደቃዎቻችን በረሀብ ለተጎዱ ወገኖች የሚደርሱበትን መንገድ ማመቻቸት የነፍስ ወከፍ ግዴታችን ነው፡፡
ሁላችንም ወገንን ለማዳን እንረባረብ!!!!
ብሄራዊ ጭቆናን አንቀበልም! ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!

The post “ሙስሊሙ ማህበረሰብ የወገኖቹን ህይወት ለመታደግ የመረባረብ ዜግነታዊ ብቻ ሳይሆን ሀይማኖታዊ ግዳጅም አለበት!” ድምፃችን ይሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

እነሃብታሙ አያሌው ላይ የተጠየቀው ይግባኝ “ያስቀርባል”ተባለ * ፍርድ ቤት ቀርበው ሊከራከሩ ነው

0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
አቃቤ ህግ የሽብርተኝነት ክስ መስርቶባቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ተበይኖላቸው በነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ላይ አቃቤ ህግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የጠየቀው ይግባኝ ያስቀርባል ተባለ፡፡

habitamu
ዛሬ ህዳር 6/2008 ዓ.ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ የተጠየቀውን ይግባኝ መዝገቡን መመርመሩን በመግለጽ ዝርዝር ሁኔታውን በንባብ ሳያሰማ በአጭሩ፣ ‹‹ይግባኙ ያስቀርባል ብለናል›› ብሏል፡፡
በመሆኑም ይግባኝ የተጠየቀባቸው ተከሳሾች ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሺ እና አብርሃም ሰለሞን በቀረበባቸው ይግባኝ ላይ በአካል ቀርበው የቃል ክርክር ለማድረግ ለህዳር 29/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡
የስር ፍርድ ቤት በነጻ እንዲሰናበቱ ቢበይንም፣ ሁሉም ተከሳሾች አሁንም ድረስ በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

The post እነሃብታሙ አያሌው ላይ የተጠየቀው ይግባኝ “ያስቀርባል” ተባለ * ፍርድ ቤት ቀርበው ሊከራከሩ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

“አክሱም እና ላሊበላ በቅድስት ከተማነት ቢሰየሙ; የኢትዮጵያን ታላቅነት ያሳያሉ.. ትልቅ ሃብትም ያስገኛሉ”ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ

Next: Hiber Radio ፡በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ከተፈጥሮ ችግር ባሻገር የመልካም አስተዳደር እጦት ውጤት ጭምር መሆኑን ምሁራኖች ገለጹ፣ የኢትዮጵያው አገዛዝ ስኳር ለውጭ ገበያ ላቀርብ ነው ማለቱ አነጋጋሪ ሆነ፣ የግብጽ የጸጥታ ሀይሎች የበርካታ ስደተኞችን አስከሬን ከበረሃ ውስጥ ወድቆ ማግኘታቸውን ገለጹ ፣ በረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ላይ በኢትዮጵያ የተከፈተበት ክስ እንዲቋረጥ ወንድሙ ጠየቀ ፣ በአገር ቤት ዜጎች በርሃብ የሚሞቱ ወገኖቻቸውን ለመርዳት በግላቸው ቤዛ እንሁን ሲሉ ኮሚቴ አቋቁመው እንቅስቃሴ ጀመሩ ፣ለርሀቡ ትኩረት አልተሰጠም በመቀሌ ለብአዴን 35ኛ ዓመት ታላቅ የሙዚቃ ድግስ ተደረገ ፣ የታክሲና ሊሞ አሽከርካሪዎች ሁበርን ጨምሮ ለሌላ ኩባንያ እንዳያሽከረክሩ የሚከለክል ሕግ የለም ፣የታክሲ ኩባንያዎች ሊዝ ለመስጠት ለመስተት የሚያስችላቸው የሕግ ረቂቅ ላይ ውይይት ሊደረግ ነው እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራ ጋር እና ሌሎችም አሉን
0
0


SBS Amharic Radio: ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ፤ ስለ የሳባዋ ንግሥት (ንግሥት ማክዳ) ከሃይማኖት አንጻር ይናገራሉ።
ዳዓማት የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሥርወ መንግሥት ነው።

ephrem yisak

The post “አክሱም እና ላሊበላ በቅድስት ከተማነት ቢሰየሙ; የኢትዮጵያን ታላቅነት ያሳያሉ.. ትልቅ ሃብትም ያስገኛሉ” ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio ፡በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ከተፈጥሮ ችግር ባሻገር የመልካም አስተዳደር እጦት ውጤት ጭምር መሆኑን ምሁራኖች ገለጹ፣ የኢትዮጵያው አገዛዝ ስኳር ለውጭ ገበያ ላቀርብ ነው ማለቱ አነጋጋሪ ሆነ፣ የግብጽ የጸጥታ ሀይሎች የበርካታ ስደተኞችን አስከሬን ከበረሃ ውስጥ ወድቆ ማግኘታቸውን ገለጹ ፣ በረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ላይ በኢትዮጵያ የተከፈተበት ክስ እንዲቋረጥ ወንድሙ ጠየቀ ፣ በአገር ቤት ዜጎች በርሃብ የሚሞቱ ወገኖቻቸውን ለመርዳት በግላቸው ቤዛ እንሁን ሲሉ ኮሚቴ አቋቁመው እንቅስቃሴ ጀመሩ ፣ለርሀቡ ትኩረት አልተሰጠም በመቀሌ ለብአዴን 35ኛ ዓመት ታላቅ የሙዚቃ ድግስ ተደረገ ፣ የታክሲና ሊሞ አሽከርካሪዎች ሁበርን ጨምሮ ለሌላ ኩባንያ እንዳያሽከረክሩ የሚከለክል ሕግ የለም ፣የታክሲ ኩባንያዎች ሊዝ ለመስጠት ለመስተት የሚያስችላቸው የሕግ ረቂቅ ላይ ውይይት ሊደረግ ነው እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራ ጋር እና ሌሎችም አሉን

0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ህዳር 5 ቀን 2008 ፕሮግራም

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የወቅቱን ረሃብና የስርዓቱን ሁኔታ በማስመልከት ካደረግንላቸው ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

ብለን የዕርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አቐቁመናል። ይህን ለማድረግ የመንግስት ፈቃድ አያስፈልገንም ። መንግስት ከአገርና ከወገን በላይ ሊሆን አይገባም ።ማንም ሰው በረሃብ እየሞተ ላለ ወገኑ መድረስ አለበት።ኢህ ካልሆነ ግን…>>

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የ ለድርቁ ተጎጂዎች ለመድረስ የተቋቋመው ኮሚቴ ሊቀመንበር ጋር የተደረገ ቆይታ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የኔቫዳ ትርንስፖርት ባለስልጣን ለህብር ሬዲዮ ጥያቄዎች ሰጠው ምላሽ (ልዩ ጥንቅር )

የፈረንሳዩ የአሸባሪዎች መጠነ ሰፊና የተቀናጀ ጥቃት ከ130 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ህይወት ቀጥፏል።ከሁለት መቶ በላይ ቆስለዋል።ፓሪስ እምዴት ሰነበተች? የዐይን እማኞች፣የጥቃቱ አራማጆች እና የዓለም መሪዎች ምን ይላሉ(ልዩ ጥንቅር)

በቻርሎቴ የተደረገው የአርበኞች ግንቦት ሰባት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት (ቃለ መጠይቅ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ከተፈጥሮ ችግር ባሻገር የመልካም አስተዳደር እጦት ውጤት ጭምር መሆኑን ምሁራኖች ገለጹ

የኢትዮጵያው አገዛዝ ስኳር ለውጭ ገበያ ላቀርብ ነው ማለቱ አነጋጋሪ ሆነ

የግብጽ የጸጥታ ሀይሎች የበርካታ ስደተኞችን አስከሬን ከበረሃ ውስጥ ወድቆ ማግኘታቸውን ገለጹ

በረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ላይ በኢትዮጵያ የተከፈተበት ክስ እንዲቋረጥ ወንድሙ ጠየቀ

በአገር ቤት ዜጎች በድርቅ ሳቢያ በርሃብ የሚሞቱ ወገኖቻቸውን ለመርዳት በግላቸው ቤዛ እንሁን ሲሉ ኮሚቴ አቋቁመው እንቅስቃሴ ጀመሩ

ለርሀቡ ትኩረት አልተሰጠም በመቀሌ ለብአዴን 35ኛ ዓመት ታላቅ የሙዚቃ ድግስ ተደረገ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ራስ ተፈሪያውያን አገሪቷ የጠበቋት የተስፋይቷ ምድር አልሆነችልንም ሲሊ አገዛዙን አማረሩ

የታክሲና ሊሞ አሽከርካሪዎች ሁበርን ጨምሮ ለሌላ ኩባንያ እንዳያሽከረክሩ የሚከለክል ሕግ የለም

የታክሲ ኩባንያዎች ሊዝ ለመስጠት ለመስተት የሚያስችላቸው የሕግ ረቂቅ ላይ ውይይት ሊደረግ ነው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio ፡በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ከተፈጥሮ ችግር ባሻገር የመልካም አስተዳደር እጦት ውጤት ጭምር መሆኑን ምሁራኖች ገለጹ፣ የኢትዮጵያው አገዛዝ ስኳር ለውጭ ገበያ ላቀርብ ነው ማለቱ አነጋጋሪ ሆነ፣ የግብጽ የጸጥታ ሀይሎች የበርካታ ስደተኞችን አስከሬን ከበረሃ ውስጥ ወድቆ ማግኘታቸውን ገለጹ ፣ በረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ላይ በኢትዮጵያ የተከፈተበት ክስ እንዲቋረጥ ወንድሙ ጠየቀ ፣ በአገር ቤት ዜጎች በርሃብ የሚሞቱ ወገኖቻቸውን ለመርዳት በግላቸው ቤዛ እንሁን ሲሉ ኮሚቴ አቋቁመው እንቅስቃሴ ጀመሩ ፣ለርሀቡ ትኩረት አልተሰጠም በመቀሌ ለብአዴን 35ኛ ዓመት ታላቅ የሙዚቃ ድግስ ተደረገ ፣ የታክሲና ሊሞ አሽከርካሪዎች ሁበርን ጨምሮ ለሌላ ኩባንያ እንዳያሽከረክሩ የሚከለክል ሕግ የለም ፣የታክሲ ኩባንያዎች ሊዝ ለመስጠት ለመስተት የሚያስችላቸው የሕግ ረቂቅ ላይ ውይይት ሊደረግ ነው እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራ ጋር እና ሌሎችም አሉን appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያና የኤርትራ የትላንት፣ የዛሬና የነገ ግንኙነቶች – የአዲስ ድምጽ ራዲዮ ውይይት

Previous: Hiber Radio ፡በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ከተፈጥሮ ችግር ባሻገር የመልካም አስተዳደር እጦት ውጤት ጭምር መሆኑን ምሁራኖች ገለጹ፣ የኢትዮጵያው አገዛዝ ስኳር ለውጭ ገበያ ላቀርብ ነው ማለቱ አነጋጋሪ ሆነ፣ የግብጽ የጸጥታ ሀይሎች የበርካታ ስደተኞችን አስከሬን ከበረሃ ውስጥ ወድቆ ማግኘታቸውን ገለጹ ፣ በረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ላይ በኢትዮጵያ የተከፈተበት ክስ እንዲቋረጥ ወንድሙ ጠየቀ ፣ በአገር ቤት ዜጎች በርሃብ የሚሞቱ ወገኖቻቸውን ለመርዳት በግላቸው ቤዛ እንሁን ሲሉ ኮሚቴ አቋቁመው እንቅስቃሴ ጀመሩ ፣ለርሀቡ ትኩረት አልተሰጠም በመቀሌ ለብአዴን 35ኛ ዓመት ታላቅ የሙዚቃ ድግስ ተደረገ ፣ የታክሲና ሊሞ አሽከርካሪዎች ሁበርን ጨምሮ ለሌላ ኩባንያ እንዳያሽከረክሩ የሚከለክል ሕግ የለም ፣የታክሲ ኩባንያዎች ሊዝ ለመስጠት ለመስተት የሚያስችላቸው የሕግ ረቂቅ ላይ ውይይት ሊደረግ ነው እና ቃለ መጠይቅ ከዶ/ር አክሎግ ቢራራ ጋር እና ሌሎችም አሉን
0
0

የኢትዮጵያና የኤርትራ የትላንት፣ የዛሬና የነገ ግንኙነቶች በሚል ርእስ ዙሪያ ቭዥን ኢትዮጵያ (Vision Ethiopia) የተባለ ድርጅት በዋሽንግተን ዲሲ ውይይት ማካሄዹ ይታወሳል:: ውይይቱ ነጻ ሳይሆን አንድን ወገን – በተለይም የአቶ የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂን ስብእና ከፍ ለማድረግ የታቀደ ነው ሲሉ በርካታ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ተወላጆች እየተቹት ይገኛሉ:: አዲስ ድምጽ ራዲዮ አራት ተወያዮችን (ሁለት ከኢትዮጵያ እና ሁለት ከኤርትራ) አቅርቦ አነጋግሯል;; ውይይቱን ያድምጡ::


addis-dimts-panel

The post የኢትዮጵያና የኤርትራ የትላንት፣ የዛሬና የነገ ግንኙነቶች – የአዲስ ድምጽ ራዲዮ ውይይት appeared first on Zehabesha Amharic.


“በቀን 2 ህፃናት በረሃቡ እየሞቱ ነው እየተባለ የእኛ በረሃቡ ላይ መረባረብ በመንግስት በኩል ለምን ችግር እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም”–ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

0
0

በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ዛሬም ረሃቡን ለመደበቅ ሬሳ እስከመግረፍ ይሄዳል። ረሃብ ቀን አይሰጥም ለወገናችን እንድረስ ያሉ በአገር ቤት የሚገኙ አስራ ሶስት ግለሰቦች ብዙዎቼ ጋዜጠኞች ናቸው ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል ኮሚቴ አቋቁመው ቤዛ እንሁን!ብለው ተነስተዋል።የባንክ ሒሳብ ከፍተው ጥሪ አቅርበዋል።በረሃብ ለሚሞተውና በዚህ ሰቀቀንና ሰቆቃ ውስጥ ላለው ወገን ከመድረስ ይልቅ ስለ ረሃቡ መጋለጥ የሚአስጨንቀው ስርዓት አስፈሪውን አደጋ ለመከላከል የበኩላችንን እናድርግ ያሉት እነዚህን ወጣቶች ያሰራቸዋል? ከኮሚቴው ሊቀመንበር ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል። የኮሚቴው የባንክ ቁጥር እነሆ፤-Commercial Bank of Ethiopia Arada Ghiorgis Branch
Account No – 1000143645987
Swift Code – CBETETAA “ቤዛ እንሁን!”

“በቀን 2 ህፃናት በረሃቡ እየሞቱ ነው እየተባለ የእኛ በረሃቡ ላይ መረባረብ በመንግስት በኩል ለምን ችግር እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም” – ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

The post “በቀን 2 ህፃናት በረሃቡ እየሞቱ ነው እየተባለ የእኛ በረሃቡ ላይ መረባረብ በመንግስት በኩል ለምን ችግር እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም” – ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያዊው በቨርጂኒያ የሚነዳውን አውቶቡስ ለማንሳት ሲሄድ በመኪና ተገጭቶ ሕይወቱ አለፈ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) አሜሪካ – በፕሪንስ ዊሊያም ካውንቲ ቨርንጂኒያ ነዋሪ የሆነው ኢትዮጵያዊው ግርማ ገነሞ በድንገተኛ መኪና አደጋ ሕይወቱ ማለፉን ኤቢሲ 7 የተባለው የቴሌቭዥን ጣቢያ ዘገበ::
ethiopian

ethiopian2

እንደ ቴሌቭዥን ጣቢያው ዘገባ የ64 ዓመት ዕድሜ ያለው ግርማ መኪና አደጋ የደረሰበት በጌንስቪል ቨርጂኒያ የሚነዳውን አውቶቡስ ለማንሳት፣ ከቤቱ ቅርብ ርቀት ወደሚገኘውና አውቶቡሱን ወዳቆመበት ሜቶዲስት ቤተክርስቲያን በማምራት ላይ ሳለ ነው::

ባለፈው ሃሙስ ኖቬምበር 12, 2015 በመኪና ተገጭቶ ሕይወቱን ያጣው አቶ ግርማ የሁለት ልጆች አባት ሲሆን፣ የልጅ ልጅም ማየቱ ተዘግቧል::

አቶ ግርማ በሕይወት ዘመኑ ሁለት ጊዜ የልብ ቀዶ ጥገና አድርጎ የነበረ መሆኑን የጠቀሰው ቴሌቭዥን ጣቢያው በቢኤል ኤም የሊሞ ኩባንያ ውስጥ በአውቶቡስ ሹፌርነት ይሰራ እንደነበር ዘገቧል::

The post ኢትዮጵያዊው በቨርጂኒያ የሚነዳውን አውቶቡስ ለማንሳት ሲሄድ በመኪና ተገጭቶ ሕይወቱ አለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

ስለ ርኀብ ገና ብዙ እናወራለን – (ሜሮን አ. እና ዐቢይ ተክለ ማርያም)

0
0

ከ7 ኪሎ መጽሔት የተገኘ

በ1987 ዓ.ም የባንድ ኤይድ ዐሥረኛ ዓመት ሲከበር የሮይተርሱ ጋዜጠኛ በጊዜው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን አቶ መለስ ዜናዊን ታላላቅ ሙዚቀኞች በዚያ ክፉ የርኀብ ጊዜ የሰጡትን ምላሽ በተመለከተ ጠይቋቸው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአቀንቃኞቹን ሰብዓዊነት እና ርኅራኄ ካደነቁ በኋላ ፍርጥም ብለው ታሪኩ ተመልሶ እንደማይደገም ለጋዜጠኛው ነገሩት። ርኀቡ የመንግሥት አስተዳደር እና የጋራ ማኅበረሰብ ታላቅ ውድቀት እንደ ኾነ በማብራራት የመጻዒዋ ኢትዮጵያ ልጆች የሚድኑት በሙዚቃ አቀንቃኞች ርዳታ ሳይኾን ራሳቸው በስኬት በሚያራምዱት ልማት እንደሚኾን ተስፋቸውን ገለጹ።
Ethiopia12
ጉም አዘጋኝ ተስፋ . . .

አቶ መለስ ተስፋ መቋጠራቸው አይገርምም። 1987 ዓ.ም ለኢሕአዴግ ጥሩ ዓመት ነበር። እንደ ኢኮኖሚስቶች ኢትዮጵያ “የጦርነት ፍጻሜ የድርሻ ክፍያ” (End of war dividend) ማግኘት ጀምራለች። ረጅም ጊዜ የቆዩ ጦርነቶች ሲያበቁ ያለ ሥራ ታምቀው የተቀመጡ ኃብቶች በጥቂቱም ቢኾን ለምርት ስለሚውሉ ምርታማነት በፍጥነት ይጨምራል። ይህ ግን ብዙ ጊዜ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው። ነገር ግን አቶ መለስ የረጅም ጊዜ ሊኾን ይችላል ብለው እንዲያስቡ የሚያደርጓቸው ሌሎች ምክንያቶች ነበሩ። የፓርቲያቸው ዋነኛ ተቀናቃኝ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የኹከት እና አስገዳጅ ኀይሉ በ1986 መጨረሻ በጣም ተዳክሟል። በከተሞች ተነስቶ የነበረው የመምህራን እና የሠራተኞች ማኅበራት ጨቅላ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በአጭሩ ተቀጭተዋል። በኢሕአዴግ ውስጥም መረጋጋት ሰፍኗል። እነዚህ አቶ መለስ የሚፈልጉትን የተረጋጋ አምባገነንነት (stable authoritarianism) ለመመሥረት ጠንካራ የማዕዘን ድንጋዮች ነበሩ። ስለዚህ ከጦርነቱ መቆም የተገኘው ዲቪደንድ በአጭር ጊዜ አይቆምም የሚል ግምት ቢወስዱ ኢ-ምክንያታዊ አይደለም። በተጨማሪ አቶ መለስ ለሚያልሙት የምሥራቅ እስያ አገሮች ዐይነት ፈጣን ልማት ማምጣት የተረጋጋ አምባገነንነት መሠረት እንደ ኾነ እስኪሞቱ ድረስ ሙጭጭ ብለው የያዙት እምነት ነበር።ነገር ግን ይህን ተስፋቸውን የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አንኮታኮተው።

በ1992 ዓ.ም በተለይ በአፋር አካባቢ ከፍተኛ ርኀብ ተከሰተ። አቶ መለስ በዚህ ዓመት ተደጋጋሞ የተነሳባቸው “ለምን?” የሚል ጥያቄ ነበር። ከ1987 መልሳቸው የምንረዳው ርኀብን የማጥፋት ‘እንቁላላቸውን’ በሙሉ የኢኮኖሚ ዕድገት ቅርጫት ውስጥ እንዳስቀመጡት ነበር። በ1992 ዕድገቱ የለም። የአቶ መለስ መልስም ይኼን ታሳቢ የሚያደርግ ነበር። በአንድ ቃለ ምልልስ- ፖሊሲዎቻቸው ልማት ላይ እንዳተኮሩ በመጥቀስ ረኀብ ማጥፋትን ዓላማው ያደረገ በራሱ የሚቆም የፖሊሲ ግብ እንደሚቀርጹ አስረዱ፤ ዕድገት ላይ ያልተንጠለጠለ ማለታቸው ነው። በጊዜው አገሪቱ ከጦርነት መውጣቷ ስለነበር ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ለአቶ መለስ ርኅራኄ ነበረው። የብርታኒያው ዘ-ኢኮኖሚስት መጽሔት “Drought, death and taxes” በሚል እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 2 ቀን 2002 ባወጣው ጽሑፉ “የአሁኑ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ አለፈው ማርክሲስታዊ አምባገነን ሥርዐት ወይም እንደ ዚምባቡዌ አስተዳደር ለዜጎቹ ሥቃይ ደንታቢስ አይደለም” ሲል ይኼንኑ ርኅራኄ አስተጋብቷል።

ውሃ ያልቋጠረው የርኅራኄ ዳመና . . .

በ2001 ዓ.ም ሌላ ርኀብ ሲከሰት ግን የኢትዮጵያን መንግሥት ይቅር ለማለት አስቸጋሪ ነበር። ይኼኛው ርኀብ 14 ሚልዮን ዜጎችን ያጠቃ ነበር። ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለት ማምለጫዎች ነበሩት። በአንድ በኩል በርካታ የረኀቡ ተጠቂ የኾኑ ኢትዮጵያውያን በኦጋዴን አካባቢ የነበሩ በመኾናቸው በቦታው በነበረው ጦርነት ምክንያት ከሥፍራው የሚወጡ ሪፖርቶች እጅግ የተገደቡ ነበሩ። እነዚህን ጥቂት ሪፖርቶች የሚያጎላ የተጠናከረ የሶሻል ሚዲያ ድምጽም አልነበረም። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ “እንደ ጀት ለመብረር እያኮበኮበ ነው” የሚለው መልዕክት ተቀባይነት ማግኘት ጀምሯል። ልክ እንደ 1987 የተጀመረው ዕድገት የርኀብ አደጋን ቀስ በቀስ ያጠፋል የሚለው ተስፋ እያንሰራራ ነው፤ በተለይ በርዳታ ሰጪዎች ዘንድ።

ይኹንና አሁንም የርኀብ ክፉ መንፈስ ለ12 ዓመታት ሳያቋርጥ አድጓል ተብሎ ብዙ የተደሰኮረለትን ኢኮኖሚ ክፉኛ ተጠናውቶታል። የአሁኑ የርኀብ አደጋ የመንግሥትን ሁለቱን የርኀብ ማጥፋት ተረኮች (narratives) ይፈታተናል። “ልማት የረኀብ አደጋን ያጠፋል” (መለስ፣ 1987)፣ “ራሱን የቻለ በራሱ የሚቆም ከልማት ጋራ ያልተቆራኘ የረኀብ ማጥፋት ፖሊሲ ያስፈልገናል” (መለስ፣ 1992)! እነዚህን ተረኮች መንዘር አድርገን ስንመለከት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ይፋዊ (ኦፊሴልያዊ) መረጃዎች ላይ እና የኢኮኖሚ መዋቅር ላይ ጣምራ ጥያቄዎች እንድንሰነዝር ያደርገናል።

ከጥያቄዎች ኹሉ ቀዳሚው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መንግሥት በሚለው ፍጥነት ካደገ እንዲህ ያለው መጠነ ሰፊ የረኀብ አደጋ እንዴት ሊያዳግም፥ ሊያሳልስም ቻለ? የሚል ነው።የዚህ ጥያቄ መነሻ በችጋር እና በጂዲፒ ፐር ካፒታ (ፒፒፒ) መካካል ያለው የጠበቀ ቁርኝት ነው። የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ በመግዛት አቅም ሲሳላ 1500 ዶላር አካባቢ ደርሷል። ይህን የመግዛት አቅም መለኪያ ከሌሎች መለኪያዎች በተሻለ የጂዲፒን እና የችጋርን ዝምድና ለማጥናት የምንጠቀምበት ምክንያት ኢኮኖሚስቶች የመጠነ ሰፊ ርኀብን ክስተት ከንጽጽራዊ ዋጋ (በተለይ የምግብ ዋጋ) ለውጥ መጠን ጋራ ስለሚያገናኙት ነው። ኢትዮጵያ አሁን በይፋ ደርሳበታለች የሚባልበት የግል ገቢ መጠን ላይ ደርሰው በዚህ ደረጃ – 17 በመቶ የሚኾነው የአገሪቱን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ እህል ርዳታ የሚፈልግበት ኹኔታ- የርኀብ ስጋት የገጠማቸው አገራትን በባትሪ እንኳ ፈልጎ ማግኘት ያስቸግራል። ለአሁኑ የኢትዮጵያ ኹኔታ ቀረብ የሚል ለማግኘት ብንቧጥጥ ተጎትተን የምናርፈው በ1920ዎቹ ሩስያ ውስጥ ወደ ተፈጠረው ኹነት ነው። እውን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሚባልበት ፍጥነት እያደገ ነው? እያደገ ከኾነ እንዲህ ዐይነት ታሪካዊ ችግር ያጋጠመው ሥር የሰደደ መዋቅራዊ ብልሽት ስላለበት ይኾን?

ሌላው ጥያቄ አገሪቱ በቅርቡ ድኽነትን በመቀነስ ካገኘችው ዓለም አቀፍ ዝና ጋራ የተገናኘ ነው። በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ኮንፈረንሶች ኢትዮጵያ ከኢኮኖሚ እድገት በሚገኘው ኀብት ድኽነት ለመቀነስ በመጠቀም እና የሚሌኒየሙን የልማት ግቦች በፍጥነት በማሳካት እንደ ምሳሌ የምትጠቀስ አገር ነች። አንዳንድ ኢኮኖሚስቶች “ቆይ – ቆይ – ቆይ . . . ከኢትዮጵያ መንግሥት የሚገኘው ዳታ ስንክሳሩ የበዛ ነው” ቢሉም በፕሮፖጋንዳ መንጋ ተዳምጠዋል። አንድ ኢኮኖሚስት እንዲያውም ከአምስት ወራት በፊት ኢትዮጵያ “ከችጋር ወደ ምግብ ድግስ” የሚል ጽሑፍ አስነብቦ ነበር። የሰሞኑን ዜና ተመልክተን “ጅል” ልንለው እንችላለን። ነገር ግን ኢኮኖሚስቱ ያገኛቸው የዓለም አቀፍ ተቋማት ማኅተም ያረፈባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ይፋዊ መረጃዎች እንዲህ ዐይነቱ መደምደሚያ ላይ ቢያደርሱት አያስገርምም። ታዲያ ኢትዮጵያ ድኽነት በመቀነስ ለዓለም ድኻ አገሮች ተምሳሌት ከኾነች እንዴት 17 በመቶ የኾነው ሕዝቧ እጅግ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ አስፈለገው? ወይስ የድኽነት ቅነሳ ለልጄ እና ለእንጀራ ልጄ በሚል መርኾ የሚፈጸም ኢ-እኩልነት በሰፊው የተንሰራፋበት ተግባር ነው? እነዚህ እና ሌሎች ጥያቄዎች ኢኮኖሚውን በቀላሉ የሚለቁት አይመስልም።

ምሑራዊ ትሕትናን ያስታበየ የተሳካ ማርኬቲንግ

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ስምንት ዓመታት በአገር ውስጥ እና በውጭ “የልማት መንግሥት ነኝ፣ ፈጣን ልማት እያስመዘገብኩ ነው” የሚል ስኬታማ ማርኬቲንግ እና መጠነ ሰፊ ፕሮሞሽን ሠርቷል። የዚህ ወንጌል ሰባኪዎች የመንግሥቱ ካድሬዎች ብቻ ሳይኾኑ ሃንስ ሮስሊንግን የመሳሰሉ ስመ ጥሩ የጸረ- ድኽነት እና ጤንነት ተሟጋች ኢኮኖሚስቶች ጭምር ናቸው። በዚህ ጉዳይ ከዚህ ጽሑፍ ጸሐፊዎች መካከል የአንዳቸውን የግል ተመክሮ እናንሳ። ከሁለት ዓመታት በፊት ከሃንስ ሮስሊንግ ጋር የኢትዮጵያን የጤና ዳታ በሚመለከት የኢ-ሜይል ልውውጥ ተደረገ። ዳታው ላይ አንዳንድ ጥያቄዎች በማንሳት ከተዘጋጁ ግራፎች ጋር ተያይዞ ተላከላቸው። በትሕትናቸው የሚታወቁት ሮስሊንግ የሰጡት መልስ በትዕቢት የተመላ ነበር። ግራፎቹንም ኾነ ጥያቄዎቹን ለሰከንዶች እንኳ የተመለከቷቸው አይመስልም። በአንደኛው ደብዳቤያቸው “ሌላ የዴታ ምንጭ ይጠቀሙ!” ብለው የጠቆሙት የዳታ ምንጭ አስቀድሞ ከተላከላቸው ጋራ ተመሳሳይ ነበሩ። ሃንስ ሮስሊንግ የኢትዮጵያ መንግሥት ቅጥረኛ አይደሉም፤ እንዲህ ዐይነት ጠንካራ ድጋፍ የሚሰጡበት ምክንያት በማርኬቲንጉ መልዕክት ስላመኑ ነው። የሰሞኑ ዜና እና ከዚያ ጋር ተያይዘው የተነሱ ውዝግቦች እርሳቸውን እንኳን ባይኾን እርሳቸውን መሰል የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ መረጃ ያለ ብዙ ጥያቄ የተቀበሉ ታዋቂ ኢኮኖሚስቶች እና አክቲቪስቶች አስፈላጊ ወደ ኾነ ምሑራዊ ተጠራጣሪነት (intellectual skepticism) የሚወስድ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ይኽን ኢኮኖሚውን የተጠናወተ ክፉ መንፈስ ስያሜ ላይ የሚያቀርበው ሙግት ለኢኮኖሚክስ ትምህርት ሴሚናር አግባብነት ያለው ቢኾንም በአደባባይ መድረክ ግን ኀዘኔታ የሚያስገኝለት አይደለም። 15 ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ቢያንስ ከርኀብ ጋር ተፋጠዋል፤ በምግብ ማጣት ሕጻናት እየሞቱ ነው፤ ዋናው ነጥብ ይህ ነው፤ ሌላው የግርጌ ማስታወሻ ነው።

የርኀቡ መከሰት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በተመለከተ ካስነሳቸው ጥያቄዎች ሌላ ላለፉት ስድሳ ዓመታት በኢኮኖሚስቶች እና በፖሊሲ ነዳፊዎች ዘንድ የችግሩን መፍትሔ ለማመላከት ሲደረጉ የነበሩ ክርክሮችን እንደገና እንድንከልስ የሚያስገድደን ነው። በእነዚህ ዓመታት ሦስት ታላላቅ የመፍትሔ ሐሳቦች ገነው ወጥተዋል፤ ቴክኖክራሲያዊ ጣልቃ ገብነት፣ ዴሞክራሲያዊ ተጠያቂነት፣ እና የኢኮኖሚ መዋቅር (structure) ለውጥ።

ቴክኖክራሲያዊ ጣልቃ ገብነት

የቴክኖክራሲያዊ ጣልቃ ገብነት ደጋፊዎች ርኀብ የሚጠፋው በጥንቃቄ በተሰላ እና በተጠና የቴክኖክራቶች ርምጃ መኾኑን ያወሳሉ። ባለፉት አንድ መቶ ዓመት ኢኮኖሚስቶች እና ሶሲዮሎጂስቶች የርኀብ መንስዔን አጥንተዋል፤ መርምረዋል። ከእነዚህ ጥናቶች ሁለት ዋነኛ የመንስዔ ማብራሪያዎች ተገኝተዋል። አንደኛው ርኀብ የሚከሰተው በከፍተኛ የምግብ እጥረት (food availability decline) ምክንያት እንደ ኾነ ያትታል። የዚህ ሰበብ ድርቅ፤ የተፈጥሮ ኃብት መጎሳቆል፣ ወይም ዴሞግራፊያዊ የመዋቅር ችግር ሊኾን ይችላል። ሌላኛው ለርኀብ ዋነኛ ምንጭ ተደርጎ የሚቀርበው የመብት ቅንብርብርታ (entitlement system) ክሽፈት ነው። “ርኀብን የሚያስከትለው ድርቅ ሳይኾን ሰዎች ለግል ጥቅም የሚኾን የኃብት እና ንብረት አቅማቸው እጅግ ተዳክሞ መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ማሟላት ሲያቅታቸው ነው” ይላል። የቴክኖክራሲያዊ ጣልቃ ገብነት አቀንቃኞች “ እነዚህን መንስዔዎች ስለምናውቅ ከፖለቲካ ገለልተኛ በኾኑ ቴክኖክራቶች አማካኝነት መፍትሔዎች ማዘጋጀት እና ማስፈጸም እንችላለን” ብለው ይፈክራሉ። የአደጋ ግምገማ፣ የቀዳሚ ማስጠንቀቂያ ሥርዐት፣ የንብረት መብት ሪፎርም፣ የገበያ ማረጋጊያ ፖሊሲዎች ወዘተ ቴክኖክራሲያዊ መፍትሔዎች ናቸው።

ዴሞክራሲያዊ ተጠያቂነት

የዴሞክራሲያዊ ተጠያቂነት አቀንቃኞች የቴክኖክራሲያዊ ጣልቃ ገብነት ብቻውን መፍትሔ እንደማይኾን ይተነትናሉ። የትንታኔው ሁለት ማረፊያዎች ‘የኢንሴንቲቭ ክርክር’ እና ‘የኢንፎርሜሽን ችግር’ ናቸው። እንደ ኢንሴንቲቭ ክርክር በርካታ መንግሥታት በሚያስከትልባቸው የፖለቲካ ችግር ምክንያት ዜጎቻቸው ስለተጋረጠባቸው የርኀብ አደጋ መናገር አይፈልጉም። ማትጊያቸው (ኢንሴንቲቫቸው) ዜናውን መቅበር ነው። በዚህ ብልሹ ማትጊያ (perverse incentive) ምክንያት የቴክኖክራቶች ርምጃ ከመንግሥት ግፊት እና ጫና ውጪ ሊኾን አይችልም። ለዴሞክራሲያዊ ተጠያቂነት ደጋፊዎች ለዚህ የኢንሴንቲቭ ችግር መፍትሔው የርኀብ አደጋን የፖለቲካ ሙግት አካል (politicization of hunger) ማድረግ ነው። ይኼን ለማድረግ ደግሞ በነጻ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ መንግሥትን ለመተቸት የማያቅማማ ፕሬስ፣ ብርቱ የአደባባይ መድረክ ያስፈልጋል። መንግሥት የርኀብ ፖለቲካ ካስፈራው እና ኢንፎርሜሽን በማፈን እንደማያመልጠው ካወቀ ኢንሴንቲቩ አደጋው ሳይጠናከር መፍትሔ ለመስጠት መሯሯጥ ነው።

የዴሞክራሲያዊ ተጠያቂነት ትንታኔ ሁለተኛ ማረፊያ ኢኮኖሚስቶች የኢንፎርሜሽን ችግር የሚሉት ነው። በአምባገነን ሥርዐቶች የቀዬ ፖለቲከኞች እና አስተዳዳሪዎች ሹመት እና ማዕረግ ለማግኘት ወይም ከቁጣ ለማምለጥ ለበላዮቻቸው ስለ አካባቢያቸው ሰብስበው የሚልኩት መረጃ በአብዛኛው አዎንታዊ ነው። አሉታዊ መረጃን ይቀብራሉ። በቻይና ታላላቅ ርኀቦች ላይ የተደረጉ ጥናቶች ይኼን የኢንፎርሜሽን ችግር ቁልጭ፣ ግልጽ አድርገው ያሳያሉ። “ማዖ ይቆጣል” በሚል በየአካባቢያቸው በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በርኀብ ሲረግፉ እየተመለከቱ መረጃን ለበላይ ያላስተላለፉ/ የደበቁ በርካታ የቀዬ ፖለቲከኞች ነበሩ። ይኽን የኢንፎርሜሽን ችግር ለመቅረፍ የአካባቢ መሪዎች እና ፖለቲከኞችን ለዴሞክራሲያዊ ፉክክር እና ተጠያቂነት ማጋለጥ እንደ መፍትሔ ይጠቀሳል።

በርግጥ በቅርቡ በዚህ በዴሞክራሲያዊ ተጠያቂነት ክርክር ላይ የተሠሩ ጥናቶች ሐሳቡ በግርድፉ ምሉዕ አለመኾኑን ያሳያሉ። የሐሳቡ ታላቅ አቀንቃኝ ኢኮኖሚስቱ አማርትያ ሴን በተለይ በህንድ ርኀብ ዙርያ የሠሯቸው ጥናቶች የዘነጉት አንድ ቁም ነገር አለ፤ እርሳቸው ባጠኗቸው አካባቢዎች መካከል ርኀብን በማጥፋት በኩል የፍጥነት ልዩነት ይታያል። ልዩነቱን የመረመሩ ጥናቶች ያስተዋሉት በእነዚህ ቦታዎች መካከል ያለውን የፕሬስ ባህርይ እና ትኩረት መለያየት ነው። ለድኾች የሚቆረቆር የአካባቢ ፕሬስ (pro-poor press) ያለባቸው ቦታዎች እንዲህ ያለው ፕሬስ ከሌለባቸው ቦታዎች በተሻለ ፍጥነት ርኀብን ማጥፋት ችለዋል። ለምን? ድኻ ተኮር ፕሬስ የርኀብ አደጋን ገና በእንጭጩ አሽትቶ ሪፖርት ያደርጋል። ሌሎች ፕሬሶች ብዙ ጊዜ የርኀብ ሪፖርት የሚያደርጉት ችግሩ ከጎላ፣ ከገነነም (salient) በኋላ ነው። ስለዚህ አዲሱ ትውልድ የዴሞክራሲ ተጠያቂነት ሊትሬቸር ርኀብን በፍጥነት ለማጥፋት ነጻ ፕሬስ ብቻ ሳይኾን ነጻ ድኻ ተኮር ፕሬስ አስፈላጊ መኾኑን ያትታል፤ ለድኾች ድምጽ የሚሰጥ ዴሞክራሲ። በርካታ የዚኽኛው መፍትሔ ተቺዎች ዴሞክራሲ በባለጠጎች እና በልኂቃን ለራስ ሲባል እንደሚጠመጠም (gamed democracy) እና በልዩ ጥቅም ቡድኖች (special interests) እንደሚሸረብ (captured democracy) በማውሳት ይኼን የአዲስ ትውልድ ሊትሬቸር “ላም አለኝ በሰማይ” ይሉታል። ትችቱ በውስጡ እውነት ያዘለ ቢኾንም እጅግ የተጋነነ ነው። በተለይ ዳን ባኒክ የሠሯቸው ጥናቶች እንደሚያሳዩት ድኻ ተኮር ፕሬስ በሌለባቸው ቦታዎች ሳይቀር ፕሬሱ በተለይ የኢንሴንቲቭ ችግርን ለመቀነስ ያለው አስተዋጽዖ የጎላ መኾኑን ነው።

የኢኮኖሚ መዋቅር (structure) ለውጥ

ስትራክቸራሊስቶች ግን ሁለቱም መፍትሔዎች አይጥሟቸውም። የርኀብ አደጋ ዘለቄታዊ መፍትሔ ለተፈጥሮ ችግሮች ከተጋለጠው እና ጉልበት ከተትረፈረፈበት የግብርና ኢኮኖሚ ራስን ማላቀቅ እንደ ኾነ ያስቀምጣሉ። ዜጎቻቸው በገጠር ችምችም ብለው ይኖሩባቸው የነበሩ ብዙ የምሥራቅ እስያ አገሮች ከቋሚ ታላላቅ የርኀብ አደጋዎች ነጻ የኾኑት ፈጣን ኢንደስትሪያላይዜሽን በማካሄድ ነው። የግብርና ምርትን ማሻሻል ለአጭር ጊዜ ርኀብን ሊቀንስ ወይም ሊያጠፋው ይችላል፤ ነገር ግን የረጅም ጊዜ መፍትሔ ሊኾን አይችልም። “ጂኒየስ” ቴክኖክራቶችም ይኹኑ ጠንካራ ዴሞክራሲ ያለ ኢኮኖሚ መዋቅር ለውጥ ከርኀብ አደጋ ጋራ ያላቸውን ትንቅንቅ በዝረራ ማሸነፍ አይቻላቸውም- እንደ ስትራክቸረሊስቶች።

የሦስቱም ቡድኖች አቋሞች በቲዮሪዎችና በኢምፔሪካል ማስረጃዎች ላይ የታነጹ ናቸው። ሦስቱም የተለያዩ አገሮችን ጥልቅ ተሞክሮዎችን ያነሳሉ። አንዳንድ ጊዜ የተመሳሳይ አገሮችን ታሪክ በተለያየ መንገድ ይተረጉማሉ። ምናልባትም ለርኀብ አደጋ አመርቂ መፍትሔ የሚገኘው ሦስቱን ሐሳቦች በመቀየጥ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ከባለሥልጣናቱም ይኹን ከደጋፊዎቻቸው እንደምንስማው የሚመርጠው ሐሳብ ቴክኖክራሲያዊ ጣልቃ ገብነትን ነው። መንግሥት ለርኀቡ አደጋ ምላሽ ለመስጠት ያሳየው ዘገምተኝነት እና በኋላም ጉዳዩ የአደባባይ ውዝግብ ማዕከል ሲኾን በቃላት ጫዎታ እና በፕሮፖጋንዳ የአሳሳቢነቱን ደረጃ አዳክሞ ለማቅረብ ያደረገው ጥረት የዴሞክራሲያዊ ተጠያቂነት አቀንቃኞች የሚያነሱትን የኢንሴንቲቭ ክርከር ጉልበተኝነት ያሳየ ነው። ላለፉት ዐሥር ዓመታት የፖለቲካ ቅቡልነቱን (ሌጂትሜሲውን) በሙሉ ልማትን በማቅረብ ላይ ያሳለፈው ኢሕአዴግ ከስድስት ዜጎቹ አንዱ እጅግ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ መፈለጋቸው ይፋ እንዲኾንበት አይፈልግም፤ ተክለ አስተዳደሩን ስለሚያናጋ። ልክ እንደ ብዙ አምባገነን መንግሥታት ከችግሩ ጋራ ሲጋፈጥ ኢንፎርሜሽን በማፈን ለማምለጥ መንፈራገጡ አይቀርም። አምባገነንነት ይህ የተንሻፈፈ፣ የተንሸዋረረ፣ ብልሹ የፖለቲካ ኢንሴንቲቭ ጎጂ ውጤት እንዲወለድ ያደርጋል። ይልቁንስ የመንግሥትን ችግር ነቅሰው በማውጣት እና ለሕዝብ በማሳየት ትርፍ የሚያገኙ ጠንካራ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ነጻ ፕሬስ (በተለይ ደሃ ተኮር ፕሬስ) ባለበት መንግሥት በርኀብ አደጋ ተክለ አስተዳደሩ እንዳይናጋ ርኀብ ሳይስፋፋ በፍጥነት መልስ ለመስጠት ይሞክራል። ይኹንና ስትራክቸራሊስቶች እንደሚከራከሩት ይኼ ኹሉ የእሳት አደጋ መከላለከል (fire-fighting) ነው። ግሩም ቴክኖክራሲያዊ መፍትሔዎች ከዴሞክራሲያዊ ተጠያቂነት ጋራ ሲቀየጡ ብርቱ የእሳት አደጋ መከላከያ አቅም ሊፈጥሩ ይችላሉ፤ ነገር ግን የአደጋውን ዕድል ወደ ዜሮ እንዲቀርብ አያደርጉም። ለዕድሉ መጥበብ የኢኮኖሚ መዋቅራችንን መለወጥ አለብን። ነገር ግን በሰባት ኪሎ መጽሔት የመጀመርያ ዕትም ላይ እንደጻፍነው የኢትዮጵያ ኢንደስትሪያላይዜሽን ያለፉት ኻያ ዓመታት የዕድገት ጉዞ ከዚያ በፊት ከነበሩት 40 ዓመታት የተለየ አይደለም፤ ኢሕአዴግ የኢንደስትሪያላይዜሽን ሞተር ማስነሳት አቅቶታል።

ያለ ዴሞክራሲ፣ ያለ ኢንደስትሪያላይዜሽን ከርኀብ አደጋ ጋር መተናነቅ ሞኝነት ነው፤ ይኼን ስናጤን የ2008 ዓ.ም የርኀብ ዜና እና እርሱን ተከትሎ የሚመጣው የሕዝብ ቁጣ ማክተሚያ እንደማይኖረው እንረዳለን።

The post ስለ ርኀብ ገና ብዙ እናወራለን – (ሜሮን አ. እና ዐቢይ ተክለ ማርያም) appeared first on Zehabesha Amharic.

በውጭ ሃገር ያሉ ኢትዮጵያውያን የተራቡ ኢትዮጵያውያንን እንዳይረዱ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች በየሃገራቱ መግለጫ እያወጡ ነው (ይዘናቸዋል)

0
0

(ዘ-ሐበሻ) 15 ሚልዮን ሕዝብን ለረሃብ የዳረገው የድርቅ አደጋ በየቀኑ የሰው ሕይወትን እየቀጠፈ መሆኑን የተረዱ ኢትዮጵያውያን በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች የሚያደርጉትን እንስቅቃሴ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ሕገወጥ ነው በሚል መግለጫ በማውጣት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን እንዳይረዱ በማከላከል ላይ እንደሚገኙ ታወቀ::

ዘ-ሐበሻ ከትናንት በስቲያ ባቀረበችው ሰበር መረጃ መሠረት መንግስት በድርቁና ረሃቡ የተነሳ መልካም ስሜ እየጠፋ ነው በሚል “ረሃብ አልተከሰተም… የሞተ ሰውም የለም” በሚል እያስተባበለ ይገኛል:: የመንግስት ሚዲያዎችና ኢምባሲዎች እንዲሁም ከፍተኛ ባለስልጣናት ከጠ/ሚ/ር ጽሕፈት ቤት; የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና የመንግስት ኮምዩኒኬሽን መስሪያ ቤት በተላለፈላቸው ት ዕዛዝ መሰረት ይህንኑ ረሃብ የለም የሞተም የለም ዘገባ በሰፊው እያሰራጩት ይገኛሉ::

ኢምባሲዎች በሚገኙበት ሃገራት ኢትዮጵያውያን ማንኛውንም የገንዘብ ማሰባሰብ እንዳያደረጉ በማከላከል ሥራ ላይ እንዲሰማሩ በወረደላቸው ት ዕዛዝ መሰረት “ሕዝቡ ገንዘብ እንዳያዋጣና ረሃብም አልተከሰተም; መንግስት ጉዳዩን ተቆጣጥሮታል” በሚል ደብዳቤ እየበተኑ ይገኛሉ::

በሳዑዲ አረቢያ; በዱባይ; በአቡዳቢ የሚገኙ ቆንስላዎች እና ኢምባሲዎች በረሃቡ ስም ሕዝቡ ገንዘብ እንዳያዋጣ ቢያከላክሉም ሕዝቡ ግን ገንዘቡን ለመንግስት ባንሰጥም በውጭ ድርጅቶች በኩል ለሕዝቡ እንዲደርስ እናደርጋለን በሚል በከፍተኛ ሁኔታ ገንዘብ እየሰበሰበ ይገኛል:: መንግስት በውጭ ሃገር የሚደረጉ የገንዘብ ማሰባሰቦች “ገጽታዬን” ያበላሸዋል በሚል ረሃቡን ለመደበቅ የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደማይኖር የነገሩን የዘ-ሐበሻ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ይህ ረሃብ ስርዓቱን በወዳጆቹ ሃገራት ፊት እንዲዋረድ አድርጎታል ብለውናል::

ዘ-ሐበሻ ቀድማ በዘገበችው መሠረት በቢቢሲ ላይ ቀርባ ልጇ በርሃብ እንደሞተባት የገለጸችው ብርቱካን በደህነቶች አስገዳጅነት ልጄ የሞተው በበሽታ ነው ብላ እንድትናገርና በቲቭ እንድትቀርብ የተደረገውም ይኸው ገጽታን በማስተካከል ሰበብ ነው ተብሏል::

የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች ከበተኗቸው ደብዳቤዎች መካከል የተወሰኑትን እነሆ::
dubai

abudabi
Saudi Arabia

The post በውጭ ሃገር ያሉ ኢትዮጵያውያን የተራቡ ኢትዮጵያውያንን እንዳይረዱ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች በየሃገራቱ መግለጫ እያወጡ ነው (ይዘናቸዋል) appeared first on Zehabesha Amharic.

ረሐብና የድርቅ መከራ በኢትዮጵያ |ዛሬ ህወሃት ሲክደው እኛም ዝም ያልንበት ትራጄዲ እንዳይሆን |ህወሃት ከክደት መነሳቱ ጭካኔውንና ግዴለሽነቱን ያሳያል

0
0

ቢላል አበጋዝ
ዋሽግተን ዲ ሲ
ሰኞ ፣ ኖቬምበር 16 ቀን 2015

በ1984/85ቱ የራብና መከረኛ ወቅት ዓለም ለኢትዮጵያ እጅግ አዝኖ ነበር።እንዲህ እንደዛሬው የፈረንጅ ገና ሰሞን “ገና መድረሱን ያውቃሉ ወይ?” ተብሎ የዓለም ዘፋኞች በሀዘን አጎርጉረውልን ነበር።ያኔ እንደዛሬው በሚሊዮን ቁጥር አልተሰደድንም ነበር።ዛሬ በተለይ በዳያስፖራ ያለነውን አላፊነታችንን አክብዶት ከፊታችን የገጠሩ ኢትዮጵያ መከራ ግልጥ ብሎ እየታየ ነው። ህወሃት “ከብት እንጂ ሰው አልሞተም” በሚል ክደት ጀመረ።ምንም ዝግጅት ያላደረገው ህወሃት በእንግሊዝ ኤምባሲው ይባስ ብሎ ራብ የለም ብሎ ካደ። ከሰላሳ ዓመታት በኋላ 15 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ዜጎች በ2016 ለራብ እንደሚዳረጉ የተባበሩት መንግስታት እየገለጠ ህወሃት ይክዳል።

File Photo

File Photo


የራቡ የተፈጥሮ ምክንያት ከሰው ሰራሹ መለየት አለበት።ህወሃት ራቡን መካድ ብቻ ሳይሆን ድርቅ በሌሎች አገሮችም መከሰቱን ይናገራል። በዓለም የመጣ ነው ለማለት።የተፈጥሮው ምክንያት ማንንም አገር ሃብታም ደሃ ብሎ አይለይም።ድርቅ ድርቅ ነው።ሃብታም አገሮች ይቋቋሙታል።ደሃ ህዝቦች መከራቸው የጠና ይሆናል።ብልሹ መንግስት፤ ብልሹ አስተዳደር ባለበት ይብሳል።የአገራችን እንዲህ ያለ ነው።በዝናቡ መቅረት የጠፋው ቡቃያ የአሁኑን አደጋ ከ1984 የከፋ እንደሚያደርገው ደሃው አርሶ አደር አውቆታል።ተጨንቋል።

ኢኮኖሚስ መጽሄት በ2011 እአአ “ተንባይ የማይሻው የብራ ምዝገብ” ብሎ ባቀረበው አፍሪካ ቀንድ ተኮር ጽሁፍ ራቡን ሁኔታ መግለጥ ብቻ ሳይሆን የራቡ ሁኔታ ሊክዱ የሚችሉትንም ተናግሮ ነበር።የሱማሌ የእክራሪ እስልምና ድርጅት ባንድ ወገን ህወሃት መሩን መንግስት ከጎን አብሮ አቅርቧል።ክ1984/85 ራብ አንስቶ ምንም አለማድረጉን የሚያውቀው ህወሃት መካድ እንጂ ሌላ እንደማያደርግ ቀድሞውን የተነገረ ነው ለማለት ነው።እጅግ የሚያጋልጠው በመሆኑ መረጃ ለማፈን የማያደርገው ነገር አይኖርም።እኛም የወገኖቻችን አላፊነት፤ ያለናቸውም አለኝቶች እኛው በመሆናችን ዓለም እንዲያውቀው ማድረግ ዛሬ ግዴታችን ነው።
ከላይ በዳያስፖራ ያለነውን አላፊነት ጠቅሻለሁ።የታሪክ አጋጣሚ በሉት ፍርጃ ዛሬ ካለንበት ጥሎናል።መሰረታችን ኢትዮጵያ በመሆንዋ ለወገን ብለን ለመጮህ ህሊናችን ይፈርዳል።ከዚህ ያፈራናቸው ልጆችም አብረዋችው የሚማሩት ያገሬው ልጆች ሲጠይቋቸው ማዘን ብቻ ሳይሆን ቁጭታችንን አሳይተን እንርዳ ብንል እንጂ ሌላ መልስ የምንሰጣቸው አይሆንም።ስለዓለም ያየር ንብረት መበከል አያውቁም ዘበት ነው።የራብን ታሪክ ብንደብቅ አፍታ ኢንተርኔት ላይ ያገኙታል። ብልሹ አስተዳደር ያከፋው ራብ እንደ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነው ብለን እውነቱን ብናስጨብጣቸው እነሱ ዝርዝሩን እነሱ ያገኙታል።

የኢትዮጵያ ህዝብ መብቱን ነጻነቱን ዜጋዊ ክብሩን አገሩን ሃይማኖቱን ተቀምቶ እየኖረ ሁለት አስርት ዓመታት አልፈው ይሄው ቀጥለናል።ህወሃት እየሰራ ያለው ግፍ ከመብዛቱ ጥዋው ሞልቶ ከመፍሰሱ የተነሳ ከፖለቲካ ድርጅት ውጪ እንዲው በምሬት ብረት ይዞ ዱር የሚገባበትን ሁኔታ ሲዘገብ እንሰማለን።ከዚህ የበለጠ የህወሃት መሩን መንግስት እድሜ ማጠር የሚያሳይ ምልክት የለም ብዬ ስከራከር “ስለመንግስት ለውጥ ስታነሳ ራቡን አስብ” እያለ ህሊናዬ አላስቀምጥ አለኝ። ዛሬ ከፖለቲካ የዘለለ እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ መምጣቱንየዓለም ሚዲያ ሲዘግበው የህወሀትን “የሙስና ድራማ ተዋናዮቹ አነ አባይ ጸሃዬና ደብረ ጽዮን ሲጫወቱ ማየት ብቻ ሳይሆን “ይሄው ሙስናን ሲዋጉ” ለማለትም የዳዳው አለ። የህወሃት መሩ መንግስት ለምእራቡ ዓለም ያዘጋጀው ድራማ መሆኑን ያልገባው ሁሉም ነገር አምልጦታል እላለሁ።ይህን ትተን ስለ ገጠሩ የኢትዮጵያ ህዝብ ስቃይ እንቀጥል።ድርቅ አይደለም ተወቃሹ በኢትዮጵያ ያለው ስርአት ብልሹነት ነው የኢትዮጵያን ችግር እየከፋ የሚያስኬደው።

ህወሃት መሩ መንግስት መሬት ካርሶ አደር ቀምቶ ለውጭ ከበርቴ ሲቸበችብ፡አርሶ አደሩን በማዳበሪያ እዳ መነቆ ሲያስገባ፡እርሻ በውል የሚስፋፋበትን መንገድ አንዳችም ሳይከተል ይሄው ዛሬ ትልቁ መከራ፤ ቀን የማይሰጠው ፈተና አስራ አምስት ሚሊዮን ህዝብን ለመከራ ዳረገ።ህወሃት መሩ መንግስት ልክ የዘውዱን ስርዓት ስተት ሲፈጽም የምናይ እንዴት እንዴት አሳዛኝ በሆነ መንገድ ታሪክ እራሱን ሲደግም እያስተዋልን ነው።በአንጻሩ ብዙ በህወሃት የተወነጀለው ደርግ በ1984 እአአ ተከስቶ የነበረውን ራብ አልደበቀም ነበር።ዛሬ ህወሃት ራብን ሌላ ስም ሊሰጠው ብሎም ሲክደው እናያለን።የ1984 ቱን ራብ ባትራፊነት የተጠቀመበት የነመለስ ህወሃት ዛሬ ይህን ቢያደር “ወይ ጉድ!” ማለት ምን ትርፍ አለው? ወደሰላሳ ዓመታት ሊጠጋ ያለን ግፍ እዲህ ያለው መከራ ሲጨመርበት አስተባብሮን ከገጠር እስተ ከተማ የትም የዓለም ጫፍ የምንገኝ፤ ከአንዳች የሚለያይ ምክንያት ባሻገር ለደሃው ኢትዮጵያ ገበሬ ብለን እነዚህ እብሪተኛ፤ሙሰኛ፤ዳፋሮች ላይ ካልተነሳን በዚህም በዚያም “አይዟችሁ ግፉበት” እንዳልናቸው አይቆጠርም ? ከፖለቲካ በዘለል ትልቁ ጉዳይ ይህ ነው። የአርሶ አደሩ መራብ።

የራቡ ሁኔታ ግፈኛው፡ሙሰኛው፡ደፋሩ ህወሃት መሩን መንግስት እንቅልፍ ነስቶታል። እርዳታ ሰጭ አገሮች ላዓመታት ሲተነብዩ የነበሩት ጭለማ ዛሬ ኢትዮጵያን ዳግመኛ እየጋረዳት መጥቷል።አካላቸው የመነመነ ራብ በምጸቱ ሆዳችውን የወጠረው ህጻናትን ምስል እያየን ነው።እኔ በእድሜዬ ይህን ሶስቴ በዓይኔ ላይ ነው።እንደ 1970 ቀድሞው የእግሊዝ ጋዜጠኛ ዛሬም እንደገና ልጇን ራብ የቀማትን እናት ሲያናግር አደመጥን።አንዳንዱ ራብ “አዋረደን” ይላል።የራባቸውን ጠይቃቸው እላለሁ።ለነሱ ራብ ስቃይ ነው።ሞት ነው።ህወሃት መሩ መንግስት ለምንቃወም ህሊና ላለን ደግሞ የህይወታችን ትልቁ ፈተና ነው።ውርደትንማ ህወሃት ነክሮ አልብሶናል። የዛሬው የህወሃትን ግፍ ሊበቀል የመጣ የኢትዮጵያ ደሃ ገበሬ አምላክ ያዘዘው ቁጣ ይመስላል።የአላህ ፍርዱ ምስጥር አለው።ህወሃቶች ሁሉ ሞልቶ! ምን ጠፍቶ !ልማቱ ደምቆ!ገበሬው ሚሊዮነር ሆነ ሲሉ በምእራቡ ያለው ፈረጅ አሽቃባጭ ደግሞ ኢኮኖሚው ተመነደገ ሲል ከዜህ አሳዛኝ ጊዜ ደረስን።

የኢትዮጵያን የመሬት ስሪት ጠንቅቀው የሚያቁት ለዘመናት የተከሰተውን ራብ ያጠኑት የ1984/85 እአ አቆጣጠርን ራብ ትልቁ ገጠር ኢትዮጵያን የበደለ አሳዛኝ ሆኖ የማያውቅ ድራማ ብለወታል አቶ ደሳለኝ ራህመቶ።በጊዜው ከነበረው የጦርነት ሁኔታ ጋር ተደምሮ የፈተና ጊዜ የነበረ ቢሆንም ህወሃት በአረመኔነት ነግዶበታል።በጎ አድራጊ ድርጅቶችም ተሞኝተውለት ነበር። ዛሬ በሚነገረው ቁጥር በስደት በየፈረንጁ አገር ሆነን ምንም ላንል ይሆን ? ልክ እንደርግ ህወሃትም ከራቡ ይልቅ “ያዘው መጣሁብህ” የሚለው ተቃዋሚ ላይ አተኩሯል።ደርግ በዚያን የራብ ወቅት የመከላከያ በጀቱ ከኢኮኖሚ አጠቃላይ ምርቱ 46% ነበር።ዛሬ በተራው ህወሃት መሩ መንግስት ይብሳል እንጂ የተለየ አይደለም።

ምእራባውያ በጎ አድራጎቶች ዛሬ ሳየሆን 2005 እአአ ጀምሮ ሲናገሩ ነበር።እንዲያው የ1984/85 ቱ ራብ እንዳለፈ ራቡን ሳይከሰት መተንበያ ዘዴ ፈጥረው(Famine Early Warning System network (FEWS NET))ይከታተላሉ።ኤን ቢ ሲ (NBC) የደቡብ ኢትዮጵያን መራብ ዘግቧልከእርዳታ ለጋሾቹም አንዱ ድርጅት ኦክስ ፋም (OXFAM) በ2009 እአአ ከሰማንያ አራቱ የራብ እልቂት በኋላ የተደረገው እርዳታ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም በሏል።ህወሃቶች ስለ አስራሃድን እጅ የኢኮኖሚ እድገት ሲያወሩን እኛም አዲስ አበባን ጎብኝተን ህንጻና መንገዱን ስናይ ይሄው የገጠሩ ወገናችን ለመከራ ሲዳረግ ዛሬ ለመመልከት በቃን። ህወሃት ከክደት መነሳቱ ጭካኔውንና ግዴለሽነቱን ያሳያል።

የ ኢኮኖሚስ መጽሄት በ2011 እአአ “ተንባይ የማይሻው የራብ ምዝገብ ብሎ ባቀረበው ጽሁፍ ራብ ማስረጃዊ አገላለጥ አለው።ካሉ ህጻናት ቊጥር 30 % በምግብ እጦት ከተጎዱ፤20 % ከህዝቡ ቁጥር ከተራበ፤ከ10000 አቅመ አዳም እድሜ ካለው ሁለቱ ለሞት ከተዳረገ፤ከህጻናትም ከ10000 አራቱ እየሞቱ ከሆነ፡ ወዘተ ዋናው ነገር ስለ ብልሹ አስተዳደር ስለሙስና እንደሚዋሸው ለህወሃት ቀላል አይደለም።ሁቆ መሳፍር መረጃ የሚሰበስበው ሳቴላይት የህወሃት ቀበኛ ነው።ህወሃት የራቡን ክደቱ አንገትዋን ብቻ አሸዋ ውስጥ ቀብራ ተደበቅሁ እንዳለችው ወፍ ያስመስለዋል። እንደ ቢ ቢ ሲ ባንዱ ክልል በቀን ሁለት ህጻናት እየሞቱ ነው። አደጋው ተከስቷል። እንተባበር። ሌላውን ትተን ለወገን እንጩህ።ለፈጣሪም ለሚረዳ ሁሉ ተናግረን የወገኖቻችንን ህይወት እናትርፍ።
የፖለቲካ ሽኩቻ ሳይሆን የወገን፤የህሊና የፍርድ ጥያቄ ነው። ለርዳታ ለጋሾች የሞራል አላፊነት አሁን ከዓለም አቀፉ ፍልሰትአንጻር የብሄራዊ ደህንነታቸው ጉዳይ ነው::ለኛ ኢትዮጵያውያን ከሁሉም በላይ ብሄራዊ ግዴታ የወገን ዋይታ ነው።እንቅልፍ የሚነሳን። ከመቼም በላይ ዋሾና እብሪተኞች ላይ አንድ ሆኖ ተባብሮ መስራት ዛሬ ነው።እኛም ዝም ያልንበት ትራጄዲ እንዳይሆን
ለደሃው የኢትዮጵያ አርሶ አደር አለኝቶቹ ዛሬ በዳያስፖራ የምንገኝ ነን!

መብቱን ነጻነቱን ያጣ ህዝብ ደግሞ በራብ ሲጠበስ ግፈኞች ሲክዱ ሊከፋን ይገባል!
ኢትዮጵያን ከክፉ መከራ አላህ የሰውራት! ሁላችንም እየጸለይን እንታገል!

The post ረሐብና የድርቅ መከራ በኢትዮጵያ | ዛሬ ህወሃት ሲክደው እኛም ዝም ያልንበት ትራጄዲ እንዳይሆን | ህወሃት ከክደት መነሳቱ ጭካኔውንና ግዴለሽነቱን ያሳያል appeared first on Zehabesha Amharic.

በቺካጎ ኤርትራዊው የ42 ዓመት ጎልማሳ ራሱን ዛፍ ላይ ሰቅሎ መሞቱ ተዘገበ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን አሜሪካ በኢሊኒዩስ ግዛት በቺካጎ ከተማ ነዋሪ እንደሆነ የሚነገርለት ኤርትራዊው የ42 ዓመት ጎልማሳ አብደላ ሃጊቶ ራሱን የመንገድ ዳር ዛፍ ላይ ሰቅሎ መገደሉ ተዘገበ::

chicago

የቺካጎ ከተማ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ፖሊስ አብደላ ራሱን እንደገደለ እንጂ ሰዎች ሰቅለው እንደገደሉት እንደማያምን ነው:: ፖሊስ በምርመራ ላይ እንደለ የጠቀሱት የመረጃ ምንጮቹ ከአስመራ ከተማ ተሰዶ በቺካጎ ከተማ የመጣው ይኸው ጎልማሳ ራሱን ያጠፋው ባለፈው ሰኞ ኖቬምበር 16 ቀን ነው::

በጣም ውኪቢያ በበዛበትና በርካታ መኪኖች በሚተላለፉበት መንገድ ዳር ዛፍ ላይ ራሱን ሰቅሎ የተገኘው አብደላ ኢንቲሳም እና ሃና የተባሉ የሁለት ሴት ልጆች አባት ሲሆን፣ ከአስመራ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀ እንደነበርም የዜና ምንጮቹ ጠቁመው ራሱን የማጥፋቱ ሚስጥር ገና እየተመረመረ ይገኛል::

The post በቺካጎ ኤርትራዊው የ42 ዓመት ጎልማሳ ራሱን ዛፍ ላይ ሰቅሎ መሞቱ ተዘገበ appeared first on Zehabesha Amharic.

በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በርኀብ የተጎዱትን ወገኖቹን ጉዳይ በቁጭት ሰማ፣ቀጥሎስ |የጉዳያችን ለውይይት የቀረበ ጥያቄ

0
0

በኢትዮጵያ የተከሰተው ርኀብ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ዘገባ ከሆነ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ ያልታየ ነው።ዓለም አቀፍ የዜና ወኪሎች፣የተባበሩት መንስታት የምግብና እርሻ ድርጅት፣ከርኀቡ ስፍራ በስልክ ቃላቸውን ለኢሣት ራድዮ እና ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛው አገልግሎት የሰጡ የችግሩ ተጠቂዎች ሁሉ ያረጋገጡት የሰው ልጅ መሞት እንደጀመረ ነው።
ፎቶ ፋይል

ፎቶ ፋይል

በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በአንድ በኩል ከገዢው ፓርቲ የሚሰጠው ርኀቡን ተቆጣጥረነዋል የሚለው ዲስኩር እና በሌላ በኩል ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚቀርበው የልመና ጥሪ እየሰማ በከፍተኛ ቁጭት ላይ ነው።በአገር ቤት የሚኖረውም በተመሳሳይ ስሜት እና ይብሱን ነገ ይዞ የሚመጣውን ባለማወቅ በስጋት ላይ ይገኛል።ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ስርዓቱ ዛሬም ከፍተኛ ገንዘብ እያወጣ ለቀጣይ የጎጥ ድርጅቶች በመቶ ሚልዮን ብሮች እያወጣ ድግስ እያሳመረ ነው።
በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ችግሩን ከመስማት እና ከመቆጨት ባለፈ ለወገኖቹ የሚደርስበትን አንድ አይነት መንገድ ማመቻቸት አለበት። በተለይ በተበጣጠሰ መልክ በየቦታው የማሰባሰብ ሥራ እንዳይሰራ መጠንቀቅ እና ለአንዳንድ በወገናቸው ስም ለሚነግዱ ስርዓት አልበኞች እንዳይጋለጥ በህብረት አንድ ዓለማቀፋዊ በሆነ መልክ ማስተባበር ተገቢ ነው።ለምሳሌ በሳውዲ፣በየመን፣በሊብያ እና በደቡብ አፍሪካ ወገኖቻችን ላይ ችግር ሲደርስ የአቅሙን ጥረት ያደረገው በአክትቪስት ታማኝ እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን የሚስተባበረው ”ግሎባል አልያንስ” ትልቅ ሥራ መስራት ይችላል።ይህ ተግባር በእራሱ በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ለወገኖቹ ከመድረሱ በላይ ህብረቱን የሚያጠነክር አንዱ  አይነተኛ አጋጣሚ ነው።ለወደፊቱም እንደ አገር ለሚገጥሙን  ችግሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ አቅማችንን የምናዳብርበት ሌላው መንገድም ነው። ለኢትዮጵያ ማንም ከየትም አይመጣላትም እኛው ኃላፊነት ያለብን።በአገር ቤት በሕዝብ ንብረት እና ሀብት ላይ የሚቀልደው ስርዓት የተዋጣውን ገንዘብ ወይንም የተገዛውን እህል በትክክል ለወገኖቻችን መድረሱን የማረጋገጥ እና ሂደቱን በዓለም አቀፍ ድርጅቶች በኩል ማድረግ አሁንም የዓለም አቀፍ እንቅስቃሴው ኃላፊነት ይሆናል።
ምክንያቱም የብዙዎች ስጋት በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት በኩል መላክ ያለው አሉታዊ ማለትም ለፖለቲካ ጥቅም ሊጠቀመበት ይቻላል የሚል ነው።ይህ ደግሞ የማይካድ ሀቅ ነው።ሆኖም ግን ኢትዮጵያውያን በአንድነት ግልፅነት ባለው መልክ እርዳታውን ያሰባስቡ እንጂ የሚላክበትን መንገድ በሥርዓት እና በመልኩ እንዲሆን የማድረግ እንዲሁም የማስገደድ አቅም ይኖራል። ገንዘብ ሲያዝ የመደመጥም ሆነ ተፅኖ የመፍጠር አቅሙም በእዛው መጠን ይጨምራል።አሁን ጥያቄው በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በርኀብ የተጎዱትን ወገኖቹን  ከቁጭት ባለፈ እንዴት ይርዳ? የሚለው ነው። ቁጭት፣ሃዘን እና ብስጭት የሰሞኑ ከራሞታችን ሆኗል።ቀጥሎስ? በእዚህን ያህል ደረጃ ኢትዮጵያ ተርባ ዝም እንበል? ይህ ፈፅሞ ሊሆን አይችልም።በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የገንዘብ አቅሙን ማሳየቱ ለወገኖቹ ፈጥኖ ከመድረሱ ባለፈ  አምባገነኑን ስርዓት የመገዳደር አቅሙንም ማሳያ አንዱ መንገድም ነው እና ችላ አይባል።

The post በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በርኀብ የተጎዱትን ወገኖቹን ጉዳይ በቁጭት ሰማ፣ቀጥሎስ | የጉዳያችን ለውይይት የቀረበ ጥያቄ appeared first on Zehabesha Amharic.


“15 ሚሊዮን ህዝብ መደበቅ ሰማይን በመዳፍ ለመሸሸግ እንደ መሞከር ይቆጠራል” በ እውቀቱ ስዩም

0
0

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen)

በእውቀቱ ስዩም

ባገራችን ኣብዛኛው ዜጋ ለቀን ጉርስና ላመት ልብስ ሲታገል የሚኖር ነው፡፡ ጌቶች ደግሞ ኣማርጠው ይበላሉ፡፡ ኣማርጠው ይለብሳሉ፤በለስ ሲቀናቸው ደግሞ የሃያ ኣምስት ሚሊዮን ብር ቪላ ይቀልሳሉ፡፡ እንዲያም ሆኖ ደግሞ መከበርና መደነቅ ይፈልጋሉ፡፡ ሰው ምንም በስጋው ቢመቸው በሌላው ተመዝኖ እንደቀለለ ሲሰማው ደስተኛ ኣይሆንም፡፡ ስለዚህ ጌቶች ያስንቀናል ብለው የሚያስቡትን ነገር በሙሉ ጠምድው ይይዙታል፡፡ ይዋጉታል፡፡ ኢትዮጵያ- ጌቶች ለኩራታቸው፤ ዜጎች ለራታቸው የሚታገሉባት መድረክ ናት፡፡Ethiopian author and poet, Bewketu Seyoum

ብዙ ጊዜ ረሀብ ሲከሰት ጌቶች ራብተኛውን ሁሉ ሰብስበው ጎተራ ውስጥ ሊደብቁት ይቃጣቸዋል፡፡ የድሆች የተራቆተ ሰውነት የገጠጠ ኣጥንት፤ የጌቶችን የመከበር ፍላጎት ያከሽፈዋል፡፡ ባንድ ወቅት በቦሌ መዳኒያለም ዳርቻ ስራመድ ኣካባቢው ኣለወትሮው በለማኞች ኣለመሞላቱን ታዝቤ ተገረምሁ፡፡ያዲሳባ ኣስተዳደር ፤ ለማኞችን“ በጥቃቅንና ኣነስተኛ ” ኣደራጅቶ ያሳለፈላቸው መስሎኝ ነበር፡፡ እንደተሳሳትሁ ለመረዳት ጥቂት ደቂቃ በቦታው መቆም ነበረብኝ፡፡ ኣንዲት ተመጽዋች ሴት ልጇን ይዛ ከቅጽሩ ስር ለመቀመጥ ስታነጥፍ ፖሊስ በቆረጣ ገብቶ “ዞር በይ ነግሬሻለሁ” እያለ ሲያዋክባት ተመለከትሁ ፡፡ የደነገጠ ልጇን እየጎተተች ተወገደች፡፡ ከዚያ ወዲያ ከኣቡነ ጳውሎስ ሃውልት በቀር ባካባቢው ደፍሮ የቆመ ኣልነበረም፡ ፡ ወደ ቤቴ ከመሄዴ በፊት ያቡኑን ወፍራም ሀውልት ዞር ብየ ሾፍኩት፡፡ እጁን እንደ ራሱ ሀይሉ ሙርጥ ገትሮ ከፊትለፊት ያለውን “ሬድዋን ህንጻ” ሲባርክ ነበር፡፡

“ገጽታ ግንባታ?”

በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን የፍርድ ምኒስተር የነበሩት ኣፈንጉስ ነሲቡ የሌባ ብዛት ቢያስቸግራቸው ኣንድ መላ መቱ፡፡ ሲሰርቅ የተገኘ ወሮበላ ግንባሩ ላይ በጋለ ስለት ምልክት እንዲደረግበት ደነገጉ፡፡ ታድያ ሌቦች የዋዛ ስላልነበሩ ሻሽ በመጠምጠም የግንባራቸውን ጠባሳ ሊሰውሩት ሞክረዋል፡፡ በጊዜው ደግሞ ሻሽ መጠምጠም ካክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ የወረደ የነገስታቱና የመሳፍንቱ ወግ ነበር፡፡ ጮሌ ሌቦች ውርደታቸውን ከመሸፈን ኣልፈው የንጉስ ገጽታ ተላብሰው ብቅ ኣሉ፡፡

በዘመናችን የተራቡ ዜጎችን መደበቅ እንደ ገጽታ ግንባታ የሚቆጥሩ ሰዎችን ከባለሻሽ ሌቦች ለይቼ ኣላያቸውም፡፡

በነገራችን ላይ፤ ብርቱካን ኣሊ ግለሂስ ያደረገችበትን ዘገባ ካየሁ በኋላ ለጊዜው ለመናደድ እንኳ ቸግሮኝ ነበር፡፡ ዘገባውን የሠራው ጋዜጠኛ እንዲህ ኣይነቱን ካንድ ድንጋይ የተጠረበ ደደብነት ተሸክሞ የመኖር ችሎታው በጣም ኣስደነቀኝ፡፡ በዚህ በሰላቢው ቀን ይቅርና፤ በደህናው ቀን እንኳ የባላገሩን ራብና መከራ ከጉያው የበቀልን ልጆቹ እናውቀዋለን ፡፡ ኣስራ ኣምስት ሚሊዮን ህዝብ መደበቅ ሰማይን በመዳፍ ለመሸሸግ እንደ መሞከር ይቆጠራል፡፡ መመፍትሄው በተቸገሩ ሰዎች ጫማ ቆሞ ነገሮችን መመልከት ነው፡፡ ለነገሩ ችግርን ያልቀመሰ ሰው ለችግረኛ መራራት እንዴት ይቻለዋል?

ኣብን ተውትና ፤ንገሩት ለወልድ

ተገርፏል ተሰቅሏል ፤ እሱ ያውቃል ፍርድ

እንዲል ባላገር፡፡

The post “15 ሚሊዮን ህዝብ መደበቅ ሰማይን በመዳፍ ለመሸሸግ እንደ መሞከር ይቆጠራል” በ እውቀቱ ስዩም appeared first on Zehabesha Amharic.

የዞን 9 ጦማሪው ዘላለም ክብረት ከሃገር እንዳይወጣ ታገደ

0
0

zelalem Kibret
(ዘ-ሐበሻ) የባራክ ኦባማን የኢትዮጵያ ጉብኝት ተከትሎ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ከተከሰሰበት የሽብር ክስ በነፃ የተሰናበተው የዞን 9 ጦማሪው ዘላለም ክብረት ከሃገር እንዳይወጣ በደህንነቶች ፓስፖርቱን ተቀምቶ መመለሱ ተሰማ::

ዘገባዎች እንደሚሉት ጦማሪው ዘላለም ክብረት ድንበር የለሽ የዘጋቢዎች ተቋም (Reporters Without Borders) በፈረንሳይ ሃገር ሊሸልመው የጠራው ቢሆንም ወደዚያው ለመጓዝ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ቢደርስም ፓስፖርቱን ተቀመቶ እንዲመለስ ተደርጓል::

የዞን ዘጠኝ ጦማሪው ዘላለም ክብረት ፓስፖርቱን ቀምተው ወደ ውጭ እንዳይወጣ የከለከሉት የደህነነት አባሎች ምክንያታቸውን ያልገለጹለት ሲሆን በፍርድ ቤትም ክሱ ተቋርጦ እንደወጣ ምንም ዓይነት ከሃገር እንዳይወጣ እግድም ሆነ ገደብ እንዳልተሰጠው የዘ-ሐበሻ ምንጮች ለማወቅ ችለዋል::

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ካለፍርድ ቤት ት ዕዛዝ የትኛው የመንግስት አካል እንደሆነ ባልታወቀ ሁኔታ ስውሩ መንግስት የሚፈልጋቸውን ሰዎች ከሃገር እንዳይወጡ በማሰቃየት እንዲሁም በማህበራዊ ሕይወቶቻቸው ውስጥ ጣልቃ በመግባት እንደሚያሰቃይዋቸው ይታወሳል:: ከነዚህም መካከል አንዱ ድምፃዊው ቴዲ አፍሮ ነው:: ቴዲ አፍሮ ከዚህ ቀደም ፓስፖርቱን ተቀምቶ ከአንድ ጊዜ በላይ የውጭ ሃገር ኮንሰርቶቹን ለመሰረዝ መገደዱ ይታወሳል::

The post የዞን 9 ጦማሪው ዘላለም ክብረት ከሃገር እንዳይወጣ ታገደ appeared first on Zehabesha Amharic.

“በኢትዮጵያ የስርዓት ለውጥ ካልመጣ ረሃብ ነገም ተመልሶ ይመጣል”–ዶ/ር አክሎግ ቢራራ

0
0

Dr Aklog Birara

በኢትዮጵያ ያለው ረሃብ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ውጤት ነው የሚል ሙግት ይቀርባል።ድርቅ እአለ ረሃብ የማይከሰትባቸው አገሮች በርካታ ናቸው። የአፍሪካ የዳቦ ቅርጫት በሚል በአንድ ወቅት የምትታወቀው አገራችን ኢትዮጵያ የረሃብ ምሳሌ መሆን ከጀመረች ውሎ አድሯል። ዶ/ር አክሎግ ቢራራ ይህ ስርዓት ስልጣን ከያዘ እንኳ አምስት ረሀብን አስተናግደናል ስርዓቱ ካልተለወጠ ረሃብ ነገም አይቀርልንም ይላሉ። ወገንን መርዳቱ የማይታለፍ የወቅቱ ጉዳይ ኒሆንም ለምን ተራብን? የሚለውን ጥያቄ ካልመለስን ነገም ተመልሰን መራባችን አይቀርም ይላሉ።በወቅታዊው ጉዳይ ላይ የሰጡንን ቃለ መጠይቅ አድምጡት።

The post “በኢትዮጵያ የስርዓት ለውጥ ካልመጣ ረሃብ ነገም ተመልሶ ይመጣል” – ዶ/ር አክሎግ ቢራራ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሳይኮሎጂ |ወንዶች በመጀመሪያ የፍቅር ቀጠሮ የሴቷን ልብ ለመማረክ ብዙ ምግብ ይበላሉ? (የድምጽ ትንታኔ)

0
0

በአዲስ አበባ የሚሰራጨው ብስራት ራድዮ ባቀረበው የስነልቡና ዘገባ ወንዶች በመጀመሪያው የፍቅር ቀጠሮ ብዙ ምግብ እንደሚመገቡ ይተነትናል:: ያድምጡና አስተያየትዎን ያስፍሩ::

dinner

The post ሳይኮሎጂ | ወንዶች በመጀመሪያ የፍቅር ቀጠሮ የሴቷን ልብ ለመማረክ ብዙ ምግብ ይበላሉ? (የድምጽ ትንታኔ) appeared first on Zehabesha Amharic.

አቶ በረከት ስምዖን “ኢሕአፓ ትልቅ አቅም ይዞ ተነስቶ ያንን ያባከነ ድርጅት ነው”አሉ

0
0

Bereket Simon
15 ሚሊዮን ሕዝብ ተርቦ በሚሊዮኖች ብሮች እየፈሰሰ እየተከበረ በሚገኘው የብአዴን (ብዙዎች “በድን” ይሉታል) 35ኛ ዓመት በዓለን አስመልክቶ ሽር ጉዱ እንደቀጠለ ነው:: ፍርፋሪ እየተወረወረላቸው ወይም በተስፋ የሚሰሩት መንግስታዊ ጋዜጠኞች የተለያዩ ባለስልጣናትን ቃለምልልስ እያደረጉ በማቅረብ ላይ ናቸው:: ከነዚህም መካከል በቅርቡ ሞተዋል ተብሎ የተዘገበላቸውና በኋላም አልሞቱም ተብሎ የተወራላቸው አቶ በረከት ስምዖን (ብዙዎች በቁማቸውና በሕዝብ ልብ ውስጥ ከሞቱ ቆዩ ይሏቸዋል) ቃለምልልስ ተደርጎላቸዋል:: በአማራ ክልል ቴሌቭዥን ላይ የቀረቡት አቶ በረከት በአብዛኛው ለማውራት የፈለጉት ስለኢሕ አፓ ነው:: “ኢሕአፓ ትልቅ አቅም ይዞ ተነስቶ ያንን ያባከነ ድርጅት ነው” ያሉት የአቶ በረከትን ቃለምልልስ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ዘ-ሐበሻ እንደወረደ አስተናግዳዋለች::

ጋዜጠኛው አቶ በረከትን ሲያስተዋውቅ እንዲህ ይላቸዋል “በጐንደር ከተማ አስተዳደር አባጃሌ ተብሎ በሚታወቀው ቀበሌ ውስጥ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዚያው በጐንደር ከተማ ተምረዋል፡፡ ከ1967 እስከ 1968 ዓ.ም እድገት በህብረት ዘመቻ አዲርቃይ ከተማ ተመድበው አገልግለዋል፡፡ ከሀምሌ 1968 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ /ኢሕአፓ/ ተቀላቅለዋል፡፡ ኢሕአፓ ሲፈራርስ ከኢሕአፓ ወጥተው ኢሕዴንን ከመሰረቱት ነባር ታጋዮች አንዱ ናቸው፡፡”

ቃለምልልሱን እንደወረደ እነሆ:-

ወደ ኢህአፓ እንዴት ተቀላቀሉ?

የ1960ዎቹ መጀመሪያ የኢትዮጵያ አብዮት ንቅናቄ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ወቅት ነበር:: በወቅቱ የነበሩት ተማሪዎች በጣም ብስለት ያላቸው ሀሣቦች እያነሱ አገሪቱን ይመራ የነበረውን ዘውዳዊ አስተዳደር ይሞግቱ፣ ይታገሉ ነበር:: ትግሉ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው ደግሞ ያኔ በነበሩት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አማካኝነት ነው:: ይህ ግን በእነሱ ብቻ የታጠረ አልነበረም:: ብዙም ሳይቆይ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተዛወረ:: ዘውዳዊውን አገዛዝ በመቃውም የዴሞክራሲ ስርዓት እንዲገነባ፣ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የአርሶ አደሩ የመሬት ባለቤትነት እንዲረጋገጥ፣ ሙሰኝነት እንዲወገድ፣ የብሔሮች እኩልነት እንዲከበር ትግል ይካሄድ ነበር:: በ1960ዎቹ መጀመሪያ በተለይም ከ1963 ዓ.ም ጀምሮ እኛም ወደ ተማሪዎች ነቅናቄ መቀላቀል ጀመርን:: ሁኔታው ከዚያ በፊት የነበሩት ትልልቅ ተማሪዎች የሚያነሷቸውን በጣም ብስለት የተሞላባቸው ሀሣቦች እንድንሰማ፣ ለፖለቲካ እንድንጋለጥ ሠፊ እድል ሰጦን ነበር::

በዚህ መሠረት እኛም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሆነን ትግሉን ተቀላቅለናል:: ቀስ በቀስ የህዝቡ ትግል እየተጠናከረ ሂዶ በ1966 ዓ.ም መላው ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ንጉሳዊውን አስተዳደር መታገል ይጀምራል::ትግሉ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ሲደርስ የተማሪዎች ንቅናቄ ያንን ትግል ወደ ፖለቲካዊ ስልጣን ለማምጣት የሚያስችል ብልሀት ጐድሎት ተገኘ:: ይህን ጉድለት ለመሙላት የፖለቲካ ፓርቲ መመስረት በጣም አስፈላጊ ሆኖ መጣ:: ይህን ተከትሎ ብዙ ድርጅቶች ተመሰረቱ::

ኢህአፓ፣ መኢሶን፣ ህወኃት፣ ኢኮፖ/ኢትዮጵያ ኮሚኒስት ፓርቲ/ የመሳሰሉ በርካታ ድርጅቶች መመስረት ቻሉ:: ከተመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በወቅቱ በመሀል ሀገር ሰፊ ተቀባይነት የነበረው ድርጅት ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ/ ኢሕአፓ/ ነበር:: ስለዚህ እኛም እ ን ደ ማ ን ኛ ው ም የድርጅት ጥማት እ ን ደ ነ በ ረ ው ወጣት ኢሕአፓን ለመቀላቀል ቻልን::

ስለዚህ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ ኢሕአፓን በአባልነት ለመቀላቀል በቃሁ:: ስለኢሕአፓ ምን ይላሉ? ኢሕአፓ ሲጀመር ዴሞክራሲያዊ የትግል ፕሮግራም ይዞ የተነሳ ድርጅት ነው:: በኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት በህብረተቡም ፣ በወጣቱ ትውልድም የነበረውን ከፍተኛ ጉጉትና ፍላጐት ተንተርሶ ፕሮግራሙን የቀረፀ ድርጅት ነው:: ስለዚህ በመጀመሪያዎቹ ወቅቶች ላይ ብዙ ሊሻሻሉ የሚችሉ ችግሮች እንዳሉት ሆኖ ኢሕአፓ የሚያታግል ድርጅት ነበር::

በማንኛውም የድርጅት ፕሮግራም ሲጀምር ባለቀለት መልኩ ምንም መሻሻል በማይፈቅድ መልኩ አይደለም የሚዘጋጀው::በሂደት ሊሻሻል የሚችልበት እድል እንደተጠበቀ ሆኖ ለመነሻ ያህል ግን አስፈላጊዎችን የትግል አላማዎች በትክክል የያዘ፣ የትግሉን ስትራቴጅዎች በወሳኝነት የሚያመለክት ሆኖ ከተዘጋጀ ብቁ የትግል መሣሪያ ሆኖ ሊወሰድ የሚችል ነበር:: ኢህአፓም የዚህ አይነት ፕሮግራም ነው የነበረው:: ህውኃትም በወቅቱ የነበረው ፕሮግራም፣ ሌሎች ፓርቲዎችም የነበራቸው ፕሮግራም በሂደት ነው እየተሻሻለና እየጠራ የመጣው::

ስለዚህ ድርጅቱ ለሁላችንንም ሊያታግል የሚችል ፕሮግራም ይዞ የተነሳ ነበር:: በሂደት ፓርቲው ይህን ፕሮግራም ተከትሎ በጽናት መታገልና ይበልጥ እያሻሻለው የሚሄድ እድል ቢኖረውም ይህን ግን ሳይጠቀምበት ቀረ::

1966/1967 ዓ.ም በኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ በጣም ብዙ ድርጊቶች የተፈፀመበት ወቅት ነበር:: ደርግ ወደ ሥልጣን መጣ:: ደርግ ወደ ሥልጣን እንደመጣ የአርሶ አደሩን ትግል ለመግታት መሬት ከፌውዳሎች መንጠቅ የጀመሩ አርሶ አደሮችን አረፋችሁ ተቀመጡ፣ ፊውዳሎችን እንዳትነኳቸው ማለት ጀመረ:: ነገር ግን ደርግ የአርሶ አደሩን ትግልሊያቆመው አልቻለም:: አርሶ አደሩ በጉልበት መሬት መንጠቁን በተለይ በኦሮሚያና በደቡብ በሰፊው ቀጠለ:: በዚህ የተነሳ የመሬት አዋጅ ለማወጅና ትግሉን ለማቀዝቀዝ የተገደደበት ሁኔታ ተፈጠረ:: የመሬት አዋጅ ሲታወጅ ኢሕአፓ ላይ ትልቅ ፈተና መጣ::
Berekey simon

ኢሕአፓም የመሬት አዋጅ የአርሶ አደሩን ጥያቄ መልሶለታል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰ:: ነገር ግን “አርሶ አደሩ መሬት ቢያገኝም ዴሞክራሲን አላገኘም፣ መሬት ቢያገኝም ስልጣን አላገኘም፣ መሬት ቢያገኝም የብሔር ጥያቄው አልተመለሰትም ነበር:: እነዚህ ምክንያቶች ቢኖሩም ኢሕአፓ አርሶ አደሩ ለትግል የተመቸ አይደለም” ወደሚል መደምደሚያ ላይ ደረሰ:: ስለዚህ ትኩረቱ ሁሉ በከተሞች ወደሚካሄድ ትግል አዘነበለ:: በከተሞች ደግሞ ደርግ የተከማቸ አቅም ይዞ የተቀመጠበት ሁኔታ ነበር:: ወታደሩ፣ የትራንስፖርት አቅሙ፣ የጦር መሣሪያው፣ የእዝ ሠንሰለቱ፣ የኮሙኒኬሽን መሳሪያው በሙሉ የተከማቸው ከተማ ላይ ነው::
ስለዚህ ኢሕአፓ በከተሞች የትጥቅ ትግል ደርግን እጥላለሁ ማለት ሲጀምር ያልተመጣጠነ ግጥሚያ ውስጥ መግባት እንደማይቀርለት የታወቀ ነበር:: የምትገጥመው ተቀናቃኝህ ሀይሉን በሚያከማችበት ቦታ ላይ ሂደህ የምትገጥም ከሆነ ከውድቀት በስተቀር ሌላ እድል የለህም:: የሽምቅ ውጊያ ህግ የሚለው የጠላትን/የተቀናቃኝህን/ ስስ ብልቶች እያየህ ማጥቃት አለብህ ነው:: ኢሕአፓ ግን የጠነከረውን ብልት፣ የጠነከረውን የደርግ አቅም መርጦ መፋለም ጀመረ:: ከዚህ በኋላ ብዙ ነገር ከእጁ እየወጣ እየተበላሸ ሄደ::
ኢሕአፓ በከተማ የትጥቅ ትግል ላይ ሲያተኩር፣ በመፈንቅለ መንግስት ሥልጣን እይዛለሁ ብሎ ሲያስብ በረሀ ላይ ያቋቋመውን ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ወደ መዘንጋት ሄደ:: በዚህ የተነሳ ለሰራዊቱ ብቁ አመራር ለመስጠት የሚያስችላውን እንቅስቃሴ ማካሄድ አቆመ:: ከዚያ በረሀ የነበረው ሀይልም እውነተኛ ተዋጊ ሀይል ሆኖ ሊገነባ አልቻለም:: ከዚህ ይልቅ እንደማቆያ ምናልባትም በከተማ ያለው ትግል ከተሳካ ያንን ደግፎ ኢሕአፓ የማታ ማታ መጠቀሚያ ሊያደርገው የሚችል ሠራዊት ከመሆን በዘለለ እውነተኛ ተዋጊ እንዲሆን ለማድረግ የተደረገ ትግል አልነበረም:: ይህ ሠራዊቱ ውስጥ የነበሩና ለትግል የተዘጋጁ ብዙ ወጣቶችን ሞራል በከፍተኛ ደረጃ የሚጐዳ ሆኖ ነበር::

ወጣቶቹ “የእንዋጋ” ጥያቄ ያቀረቡት ገና ከጠዋቱ ነበር:: በ1968 ዓ.ም ወደ ትግሉ ተቀላቅየ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ “ለምንድን ነው ወደ ጦርነት የማንሄደው? ለምንድን ነው የማታዋጉን” የሚል ጥያቄ እስከመነሳት ደርሶ ነበር:: 25 የማይማሉት የፀለምት ታጋዮች ይህን መሠል ጥያቄ ያቀረቡ ነበር:: ይህን ለመሰለው ታጋይ ግን ብቃት ያለው አመራር
አልተሰጠውም ነበር::

ይህ በሰራዊቱ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች እንዲነሱ በር ከፍቷል:: የከተማውን የትጥቅ ትግል ፋይዳ፣ ብስለት አስመልክቶ መጠየቅ ተጀመረ:: ኢሕአፓ ግን ለጥያቄዎች መልስ ከመስጠት ይልቅ ጥያቄ ያነሱ ታጋዮችን በአንጀኝነትና በፀረ ድርጅትነት እየፈረጀ ማሰር፣ መምታት ጀመረ:: የታጋዮች መታሰርና መመታት እንደገና ሌላ ጥያቄ መቀስቀስ ጀመረ:: ውስጠ ዴሞክራሲው ክፍተት እንዳለበትና ብዙ መሻሻል ያለበት ነገር እንዳለ በፓርቲው አባላት ዘንድ ጥያቄ ሆኖ ተነሳ :: አልፎ ተርፎም ከሌሎች ብሔራዊ የትግል ድርጅቶች ጋር ውጊያ ውስጥ የገባበት ሁኔታ ስለነበር ይህም ትክክል አይደለም “ለምንድን ነው ከትግል ድርጅቶች ጋር የምንዋጋው?” የሚል ጠንከር ያለ ጥያቄ በአባላቱ ዘንድ በስፋት መነሳት ጀመረ::

ስለዚህ ኢሕአፓ ጥሩ ጀምሮ፣ ሊሻሻል የሚችል ብዙ ነገር ነበረው:: ነገር ግን አመራሩ ይህንን በብቃት መምራት ባለመቻሉ ምክንያት ነገሮች ከእጁ እየወጡ ድርጅቱን በስኬትሳ ይ ሆ ን በውድቀት ጐዳና እንዲራመድ አድርጐታል:: ሌላ የፖለቲካ ድርጅት ከመመስረት ይልቅ ኢህአፓን አጠናክሮ መስቀጠል አይቻልም ነበር ወይ? ኢህአፓን አጠናክሮ እንደገና እንዲደራጅ ማድረግ አይቻልም ወይም ይቻላል ያከራክራል:: ለምን አልተሞከረም? ለሚለው ጥያቄ ግን መልሱ ሞክረናል ነው:: ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄው የመጀመሪያ አላማ አድርጐ የያዘው ኢሕአፓን ማቅናት ነበር::

ኢሕአፓ ብዙ መስዋዕት የተከፈለበት ድርጅት ነው:: ይህ ድርጅት ያሰባሰበው ቀላል የማይባል የሠው ሀይል ነው:: በኢትዮጵያ በመሀል ሀገር ከነበረው ወጣት ምርጥ የሚባለውን ሀይል አሰባስቦ ይታገል የነበረው ድርጅት ነው:: ስለዚህ ይህንን ሀይል ከማፋረስ ወይም በሌላ ከመተካት ይልቅ አስተካክሎ ወደ ተሻለ ብቃት ለመምራት የሚቻልበት ሁኔታ ቢኖር ኑሮ ተመራጭ ይሆን ነበር:: በመጀመሪያ የተደረገው ሙከራ ይሄ ነበር:: ይህ ሙከራ እንዲሳካ ለማድረግ ጥረት የተደረገው መሪዎችን በመቀየር ጭምር አይደለም:: ለምሳሌ ኢሕአፓ በ1972 ዓ.ም ሊካሄድ የታሰበው ጉባኤ ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን፣ አመራሩም ተስተካክሎና ታርሞ እንዲቀጥል ማድረግ ይገባናል ብለን ነበር:: አመራሩ እንዲስተካከል ለማድረግ ደግሞ የታጋዮቹ ወኪል የሆነ ኃይል በአመራሩ ውስጥ መግባት አለበት፣ ከታች አመራሩን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ሠዎች ሁሉ ማስገባት አለብን የሚል ንቅናቄ ማካሄድጀምረን ነበር::

ስለዚህ ኢሕአፓን አስተካክሎ መቀጠልየመጀመሪያው ፍላጐት ነበር:: ነገር ግን የኢሕአፓ መሪዎች በነበራቸው ግትርነት ለዴሞክራሲያዊ ሀሣቦችና ጥያቄዎች በነበራቸው ጥላቻና ፍርሀት ምክንያት ሊሳካ አልቻለም:: ኢህአፓ ሀሣቡን ተቀብሎ ከማስተካከል ይልቅ ወደ ማሰር አመራ:: ልዩነቱ በቀላሉ እንዳይታረቅና በቀላሉ እንዳይጠገን የሚያደርግ ግፊት አደረጉ:: ይህ ግፊት በዋነኛነት ለታጋዮች ጥያቄዎች ቀና ምላሽ ባለመስጠት የሚገልጽ ነበር:: አንደኛው ችግር ይሄ ነው:: ሁለተኛው ተጨባጭ ችግር በለሳ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት ጠገዴና አርማጭሆ በሚባሉ ሪጅኖች /ክልሎች/ ላይ የነበረ ነው:: እነዚህን ሪጅኖች/ ክልሎች/ እንደ አንድ አካል ማግኘት ከባድ ነበር::

ስለዚህ መጨረሻ ላይ እያዳንዱ ሪጅን/ክልል/ ለራሱ መቆም የጀመረበት ሁኔታ ተፈጠረ:: አርማጭሆ፣ ጠገዴ፣ ወልቃይት የነበሩት ወደ ሱዳን በቀላሉ ወጡ ወደ ኤርትራ ደርግም በብዛት የገቡበት፣ በለሳ ላይ የነበርነው ደግሞ ለመታገል ሞክረን ሁኔታው አስቸጋሪ ሲሆን ወደ ትግራይ መሄድ የመረጥንበት ሁኔታ ተፈጠረ::

ኢ ሕ አ ፓ ን ለ ማ ቅ ና ት ና አ ስ ተ ካ ክ ሎ ለ ማ ስ ቀ ጠ ል ጥ ረ ት ተ ደ ር ጓ ል : : ነገር ግን በ ኢ ህ አ ፓ አ መ ራ ር እ ም ቢ ታ ና በሁኔታዎች አስገዳጅነት የታሰበው ሊሳካ ባለመቻሉ አዲስ ድርጅት ወደ መመስረት አምርተናል:: ወደ ትግራይ የመሄዱ ሀሣብ እንዴት መጣ?

መጀመሪያ ወደ ትግራይ ከመሄዳችን በፊት 1971 ዓ.ም ህዳርና ታህሳስ አካባቢ ኢሕአፓና ህወኃት ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ ዙር ጦርነት ወልቃይት አካባቢ ይጀምራሉ:: በፊት አካባቢ ጦርነት ሲጀመር በለሳ የነበረው ንቅናቄ አንድ የተጠናከረ ደረጃ ላይ ደርሷል:: በኢሕአፓ ላይም ሙሉ ግምገማ አድርጐ ኢሕአፓ ችግር ያለበት ድርጅት ነው ወደ ሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል:: ኢሕአፓ መስተካከል አለበት የሚል አቋምም ይዟል:: ይህን አቋም ይዞ የነበረው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ኢሕአፓን በመታገል ሂደት እያለ “ ጦርነት ውስጥ ግቡ” ተባልን::

ከብሔራዊ የትግል ድርጅቶች ጋር የሚካሄድ ጦርነት ትክክል አይደለም፤ አንደግፈውም፤ የበለሳው ንቅናቄም ለጦርነቱ አስተዋጽኦ አያደርግም እስከማለት ተደረሰ :: ያም ሆኖ ጦርነቱ ተካሄደና ኢሕአፓ ተሸነፈ:: በዚህ ሁኔታ እያለን ኢሕአፓ ውስጥ የነበረው ቀውስ እየተባባሰ መጣ:: ታጋዩ በብዙ ጉዳዮች ላይ ግራ ተጋባ:: የሚይዝ የሚጨብጠውን አጣ:: በዚህ ምክንያት ግማሹ ወደ ደርግ መሄድ ጀመረ:: ግማሹ በተናጠል ወደ ቤቱ ተመለሰ:: ግማሹ ወደ ሱዳን ተበተነ::

ይህ ሁኔታ እየጠነከረ ሲሄድ “ምን እናድርግ?” የሚል ጥያቄ አነሳን:: በለሳ ውስጥ ለመቆየት በጣም አስቸጋሪ እየሆነ መጣ:: ደርግ ብዙ ሠራዊት መበተኑን ሲያይ ወታደራዊ ዘመቻዎቹን በተደጋጋሚና በቅርበት መፈፀም ጀመረ:: ሠራዊቱ መዋጋት የማይችልበት ሁኔታ ተፈጠረ፣ አርሶ አደሩ ደግሞ ደርግ የሀልይ ሚዛን ብልጫ እንደወሰደ መመልከት ሲጀምር ኢሕአፓንና ሠራዊቱን ገሸሽ የማድረግ አዝማሚያ እያሳየ መጣ:: ስለዚህ ሁኔታው አስቸጋሪ መሆን ጀመረ::

በዚህ ሁኔታ ንቅናቄው ከዚያ አካባቢ የመቆየት እድሉ ጠባብ ሆነ:: በዚህ ጊዜ “ወደ ትግራይ ብንሄድ ይሻላል” የሚል አቅጣጫ ማውጠንጠን ተጀመረ:: ከመከላከላችን ወደ አርማጭሆ እንሂድ የሚል ሀሣብም ተነስቶ ነበር::

ወደ አርማጭሆ የምንሄደው በደርግ ግዛት አቋርጠን ነው:: የታጠቀ ሠራዊት ይዘን፣ ደርግ የሚቆጣጠረውን ግዛት አቋርጠን ወደ አርማጭሆ መሄድ አደጋው ከፍተኛ ነው:: ሙሉ በሙሉ መጥፋትም ይመጣል:: አርሶ አደሩም የሀይል ሚዛን ብልጫውን ተመልክቶ ወደ ደርግ ያዘነበለበትና እኛን ጠቁሞ መሾሚያ ማድረግ የሚፈልግበት ጊዜ ነበር:: ስለዚህ ያኔ ነጭ መሬት/ነጻ መሬት/ በምንለው በኩል አልፈን መሄድን አንደ መልካም አማራጭ ወስደነው:: ለዚህ ደግሞ የተሻለው አማራጭ ትግራይ መሄድ ነው የሚል ነው:: ከህውሓት ጦርነት ገጥመን የነበረ ቢሆንም አሁን ወደሱ ብንሄድ ኢሕአፓ እንደሚነግረን ላይሆን ይቻላል:: እንደማንኛውም ታጋይ ድርጅት የትግል ፍላጐት ይኖረዋል:: ሲሆን አንድንደራጅ ይተባበረናል:: ካልሆነ ደግሞ ወደ ሱዳን ማለፊያ መንገድ ይሠጠናል:: ገብተን ተደራጅተን ተመለስን በአንዱ የአማራ አካባቢ እንደገና ትግል እንሞክራለን በሚል ሀሣብ ነው ወደ ትግራይ የሄድነው::

ሕወሓት ጋ ምን ጠበቃችሁ?

ትግራይ ስንሄድ ብዙ ነገር ነው ያገኘነው:: ብዙ ነገሮችን ነው የተመለከትነው:: ከሁሉ በፊት እኛ ከቆየንበት ከበለሳ አካባቢ የተለዩ ሁለት ትልልቅ ነገሮችን አግኝተናል:: አንደኛ የትግራይ ህዝብ ሁኔታ ነው:: ሁለተኛ የህውሓት ድርጅትና ሠራዊቱ ሁኔታ ነው:: እነዚህ ሁለቱ ትልልቅ ነገሮች ነበሩ:: በዚያን ወቅት የትግራይ ህዝብ በጣም ከፍተኛ የሆነ የ ት ግ ል መ ነ ሳ ሳ ት እንደነበረው ታዝበናል:: መ ሀ ል ሀገር ያለው ሁኔታ ትግሉ ተቀዛቅዟል:: ደርግ በቀይ ሽብር በወሰደው እርምጃ በጣም ብዙ ወጣቶች ተጨፍጭፈዋል:: የትግል ድርጅቶች ተበታትነዋል:: የህዝቡ የትግል መነሳሳትም ተቀዛቅዟል:: ከዚያ አልፎ ከባድ የሞራል ውድቅት ተከስቷል:: የደርግ መንግስት ባካሄደው ጭፍጨፋ ህዝቡ ከልክ በላይ ስለተቀጣ የተሸማቀቀበትና ግራ የተጋባባት ሁኔታ ነበር::

ትግራይ ላይ ሥንገባ ያየነው ሁኔታ ከዚህ ለየት ይላል:: ህዝቡ በህወሓት እየተመራ የተለያዩ ድሎችን እየተጐናፀፈ ነው:: የተራዘመ የገጠር ትጥቅ ትግል የሚባለው አቅጣጫና ስትራቴጂ በትክክል ተግባራዊ ተደርጐ ውጤት ማምጣት ጀምሯል:: ደርግም በትግራይ ተከታታይ ግዙፍ ዘመቻዎች ያካሄደ ቢሆንም ህወሓትና የትግራይ ህዝብ በጋራ ሆነው ባደረጉት ትግል በብቃት መክተው መልሰውታል:: በትግራይ ነጻ መሬቱ ሠፍቶ ህዝቡ ለሌላ አዲስ ትግል የሚነሳሳበት ሁኔታ ተፈጥሯል:: ስለዚህ በሄድንበት ሁሉ የትግል ወኔን ይበልጥ የሚቀሳቀስ፣ ከታገሉ ይህን የመሰለ ሁኔታ መፍጠር ይቻላል የሚል አስተሳስብ እንድንይዝ የሚያደርግ ተጨባጭ ሁኔታ መመልከት ቻልን::

ህወሓትም ኢሕአፓ ውስጥ እያለን አንስማው ከነበረው የተለየ ነው:: ስንገናኝ በትጥቅ ትግል
አካሄድና በገነቡት ሠራዊት ጥንካሬ በጣም የሚያስቀና ደረጃ ላይ ደርሰው ነበር:: ገና ተፈላጊው የአንድነት ደረጃ ላይ አልደረሱም እንጂ ጠንካራ የሚባል ብቃት ያለው፣ በአግባቡ የተደራጀ፣ በጥሩ ሁኔታ የሚመራ ሠራዊት ገንብተው ነበር:: ተዋግቶ፣ ድል አድርጐ የራሱን ነፃ መሬት ገንብቶ መከላከል የሚችል ሀይል ፈጥረው ነበር:: ይህም ከታገልክ ጥሩ አመራር ማግኘት፣ እንዲህ አይነት የትግል ሠራዊት መገንባት ይቻላል የሚል ትምህርት እንድንወስድ በር የከፈተ ነበር::

በሌላ በኩል ህወሓት ጋ ስንገባ ያገኘነው ሌላው ነገር የአስተሳሰብ ብስለትናግልጽነት ነው:: እኛም ኢሕአፓ ውስጥ ሆነን ስናነሳቸው የነበሩ ጥያቄዎች በህውሓት ደረጃ ተነሳተው ውይይት ተደርጐባቸው የተሻለ አቅጣጫና ግልጽነት ተይዞባቸዋል:: ስለዚህ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄው ትግራይ ሲገባ ከሞላ ጐደል በጣም የተመቸ ሁኔታ ገጥሞናል:: “መታገል አለብን!”
ብለን መወሰናችን ትክክል እንደነበር የሚያረጋግጥ፣ ወደ መደራጀት እንድናመራ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ
ነበር ::
ረጅም ጊዜ ወስደን በብዙ ነገሮች ላይ ከህወሐት ጋር ለመወያየትና ለመከራከር እንዲሁም በሚያስማሙን መስማማት፣ በሚያለያዩን ነገሮች መለያየት የምንችልባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ማረጋገጥ የጀመርንበት ሁኔታ ተፈጥሯል::

ወደ ትግራይ ከገባችሁበት ጊዜ ኢህዴን እስከ ተመሰረተበት ድረስ ያለው ወቅት ምን ይመስል ነበር?

ያ ስዓት ብዙ ነገሮች የነበሩበት ነው:: መሀል ሀገር ላይ የኃይል ሚዛኑ ተገለባብጧል:: የሀይል ብልጫ ሚዛኑን ደርግ ወስዷል:: በመሀል ሀገር ብቻ አይደለም:: ትግራይ ላይ በተነፃፃሪ የተሻለ ሁኔታ ቢፈጠርም 1969 እስከ 1975 ዓ.ም የቀይ ኮከብ ዘመቻ ድረስ በነበሩት ዓመታት ደርግ የበላይነቱን ያረጋገጠበት ዘመን ነበር::

በዚህ ዘመን መደራጀት አለብን ብለን ስንነሳ መጀመሪያ ያደረግነው ልክ ትግራይ እንደገባን የእርማት እንቅስቃሴ ብለን ራሳችን ንቅናቄው የፈፀማቸው ስህተቶች ካሉ እነዚህን ማረም ጀመርን:: አዲሱ ትግል ከኢሕአፓ ሥህተቶች በፀዳ መንገድ ብቻ ሣይሆን ከራሳችንም ሥህተቶች በፀዳ መንገድ መካሄድ አለበት የሚል አቋም ወሰደን ወደ እርማት እንቅስቃሴ አምርተናል::
የእርማት እንቅስቃሴው ተካሄደ:: የራሳችንን ድክመቶች ሙሉ በሙሉ ወስደን እናስተካክላለን አልን:: አዲሱ መተዳደሪያ ደንባችን ዴሞክራሲያዊ ይሆናል ብለን ያንን በመተዳደሪያ ደንባችን ቀርጽነው:: ይህን ከጨረስን በኋላ የፖለቲካ ፕሮግራማችንን የመንደፍ ሀሣብ ይዘን ተንቀሳቀስን:: የፖለቲካ ፕሮግራማችን በራሳችን ለመንደፍ ጥናቶች ወደ ማድረግ ፣ መከራከርና ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር መስማማት አለበት የሚል አቋም ያዝን::በዚህ ዝግጅት በአብዛኛው ከህወሓት ጋር የሚመሳሰል ግን በተወሰኑ ሁኔታዎች ደግሞ ከህወሓት የተለየና እኛ በምናምንባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የተዋቀረ ፕሮግራም ይዘን ወጣን:: ሦስተኛውና የመጨረሻው የመደራጀት እንቅስቃሴ ነው:: በዚያን ጊዜ በነበርንበት ሁኔታ ይብዛም ይነስም ፕሮግራም ማዘጋጀት፣ የአደረጃጀት መመሪያዎቻችንን ማጠቃለልና ለጉባኤ ዝግጅት የማድረግ ሥራ የምንሰራበት ወቅት ነበር::

የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ኢህዴን/ የተመሰረተበትን ቀን እንዴት ያስታውሱታል?

ለእኔ ትልቅ ቀን ነበር:: ብዙ ጊዜ በትግል በቆየሁባቸው አመታት ውስጥ አንዳንድ ለራሴ የያዝኳቸው ግቦች ተሳክተው ካየሁ በኋላ በትግሉ የሚያጋጥም መስዋእት ቢያጋጥምም ግድ የለኝም የምልባቸው ነገሮች ነበሩ:: ገና ኢሕአፓ እያልን ከኢሕአፓ ወጥተን የራሳችንን ድርጅት አቋቁመን ለትግል የምንነሳሳበትን ሁኔታ አይቼ ብሞት የሚል ሀሣብ ነበረኝ:: ስለዚህ ኢሕዴንን ለመመስረት የነበረው እንቅስቃሴ በጥሩ ሁኔታ ተሳክቶ መጨረሻ ላይ አዲስ ድርጅት በምንፈጥርበት ጊዜ ሁላችንም የተስማን ስሜት በጣም ትልቅ እፎይታ የፈጠረ ነበር:: ድርጅት ምን ያህል አቅም እንደሆነ እናውቃለን::

ኢሕአፓ ትልቅ አቅም ይዞ ተነስቶ ያንን ያባከነ ድርጅት ነው:: እኛ ትንሽ ሆነን ተነስተን ወደ መደራጀት በማምራት ላይ የነበረን ነን:: ህውሓት እንዲህ ትንሽ ሆኖ ጀምሮ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሰ፣ ትግራይን ነፃ በማውጣት፣ ለኢትዮጰያ ህዝቦች ትግልም የበኩሉን ማበረከት የሚችልበት ብቃት እየተጐናፀፈ መሄድ የቻለ ድርጅት ነው:: ድርጅት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ምን ያህል ትልቅ የለውጥመሣሪያ እንደሆነ እንረዳ ነበር::

The post አቶ በረከት ስምዖን “ኢሕአፓ ትልቅ አቅም ይዞ ተነስቶ ያንን ያባከነ ድርጅት ነው” አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live