Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም “አንዳርጋቸው ሞኝ ነው.. ዶ/ር ብርሃኑም ከንቲባነቱን ውሰድ ተብሎ እምቢ ብሏል”አሉ

0
0

በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ቀርበው ከሕዝብ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በድጋሚ በ እስር ላይ የሚገኙት የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ መጽሐፍ እየጻፉ መሆኑን እና ልማታችንን እየጎበኙ ነው አሉ:: አቶ አንዳርጋቸው መቼ ነው እስር ቤት የሚለቀቁት? እርስዎ መጽሐፍ እየጻፉ ነው እያሉ እርሳቸው ግን የተያዝኩበት ሁኔታ መጥፎ ነው በእንግሊዝ ሃገር ቅበሩኝ ብለዋል የሚሉና ተመሳሳይ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል:: ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳርጋቸው አንዳርጋቸው ይቅርታ አድርጉልኝ ማለት ካለ ጉዳዩ ሊታይለት ይችላልም ሲሉ ተናግረዋል::

ቃለ ምልልሱን ያድምጡት::

Adargachew Tsegie

The post ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም “አንዳርጋቸው ሞኝ ነው.. ዶ/ር ብርሃኑም ከንቲባነቱን ውሰድ ተብሎ እምቢ ብሏል” አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

↧

Sport: የአሮጊት ፉትቦል…..የሴት ጨዋታ –ከገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)

0
0

genene Mekuria
የብሄረዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሰሞኑን በሬድዮ ሲናገር እንደሰማሁት‹‹እኔ የአሮጊት ፉትቦል መጫወት አልፈልግም››አለ፡፡አሰልጣኙ አሁን እየተኬደበት የምትትሮሽ ጨዋታ ይልቅ ልጆቹን መነሻ ባደረገ በኩል እንዲሰራ ሀሳብ ሲቀርብለት ያንን ለመቃወም የተናገረው ነው‹‹እኔ ቶሎ ባለጋራ ሜዳ የሚገባ ቡድን ነው የምፈለወገው ››አሉ፡፡ባለጋራ ሜዳ ቶሎ መግባት ጥሩ ነው ግን በምንድነው ባለጋራ ሜዳ የሚገባው? ፡፡ቶሎ ባለጋራ ሜዳ የሚገባውተጠልዞ ነው በዚህ መንገድ ደግሞ ከእኛና ባለጋራ ማን እንደተሻለ ብዙ ግዜ ታይቷል፡የእኛ ተጨዋቾች በተለይ ከምእራብ አፍሪካ ቡድን ጋር ሚዛን ላይ ተቀምጠው በምንድነው መቋቋም የሚችሉት ቢባል ያለን ነገር በቴክኒክ በኩል ነው፡፡ይሄ ቴክኒክ መገለጫው በመቀባበል ነው፡፡መቀባበሉ ደግሞ በመረዳዳት ባለጋራን ለመቋቋም ያስችላል፡፡ ቶሎ ወደፊት ኳሱ ሲጣል የእኛ ተጨዋች ተሻምቶ ነው የሚያገኘው(ያውም ካገኘ) ኳስ ሲያገኝ የሚረዳው ስለሌለ በግል ይሞክራል፡፡ በግል ደግሞ እነርሱ በፍጥነትም ጉልበት ይበልጡናል ፡፡እንደሚበልጡንም ለረጅም አመት አይተነዋል፡፡ስለዚህ በግል ተገኝቶ በጉልበት ከተበለጥን ኳስ የያዘ ሰው ረዳት ተበጅቶለት እየተቀባበሉ ባለጋራ ሜዳ ቢገቡ ያዋጣል እንጂ አይጎዳም፡፡

መረዳዳቱን(መቀባበሉን)የአሮጊት ፉትቦል ከተባለ የአሮጊት ባልሆነው ፉትቦል አሰልጣኙ መብለጫ መንገድ ሊያሳዩን ይገባል፡፡ከዮሀንስ በፊት የነበሩት አሰልጣኝ ባሪቶ ሀዋሳ በልምምድ ጌም ተጨዋቾቹ ሲቀባበሉ‹‹ እኔ የሴት ፉትቦል አልፈልግም፡፡ ቶሎ ኳሱን ለአጥቂው ወደፊት ጣሉት››ብለው ትእዛዝ ሰጡ ፡፡ቶሎ ለአጥቂው የሚጥልላቸውን ተጨዋች ቀይረው አስገቡ፡፡ እዚህ በሜዳችን ከአልጀርያ ጋር ቶሎ ለአጥቂው እየተጣለ ምን እንደደረሰብን አይተነዋል ፡፡ ቶሎ ለአጥቂው መጣል ‹‹የወንድ›› መቀባል ደግሞ ‹‹የሴት›› ከሆነ እናም በመቀባበሉ የምንበልጥ ከሆነ አዋጪው የሴት የተባለው ነው፡፡ዮሀንስም እንደባሪቶ ቶሎ ባለጋራሜዳ ለመግባት ወደፊት እየጣለ ያለረዳት ለመጫወት መሞከሩ የባሪቶን ነገር ሊደግምልን ነው፡፡ተጫዋቾቹ የሚችሉት ነገር አለ፡፡በሚችሉት ነገር ላይ እንዲጫወቱ መፍቀድ በሜዳ ላይ ብልጫ እንዲይዙ ማደረግ ነው፡፡የልጆቹን መብለጫ ‹‹የአሮጊት ፉትቦል ነው አልፈልግም….የሴት ፉትቦል ነው አልፈቅድም››በሚል ማጣጣሉ የት እንዳረሰን አይተነዋል፡፡ የሚገርመው አሰልጣኞቹ ያዋጣል በሚሉት ነገር ሊያሳዩን አልቻሉም ፡፡አማራጩንም(የአሮጊት፤ የሴት )በሚል ማጣጣል ስያሜ እየሰጡ እነርሱ በሚሰሩት ነገር እየተዋረዱ እዚህ አድርሰውናል፡፡ያሁኑ አሰልጣኝ ለለውጥ አልመጣም፡፡ ሌሌቹ ትተው የሄዱትን የውድቀት አጨዋወት ሊያስቀጥል ነው፡፡

…የሆንስ መረዳዳቱን ወይም ልጆቹ በሚችሉት በሚያውቁት መንገድ መጫወቱን የአሮጊት ፉትቦል ካለ የአሮጊት ባልሆነው ነገር ባለጋራን መብለጥ እንዳልቻለ አይተነዋል ነገም ይሄንኑ ነገር ያሳየናል፡፡የዮሀንስ ስትራቴጄ ደጋግሞ እንዳወራው ቶሎ ባለጋራ ግብ ጋር መድረስ ነው፡፡

እንዴት ነው የሚደረሰው የሚለው ጉዳይ ነው አስቸጋሪ የሆነው፡፡አሁን እንደታየው ግብ ጋር የሚደረሰው(በተለይ ከሜዳ ውጭ) በሚጣል ኳስ ነው፡የሚጣለውን ኳስ አጥቂዎቹ ለማግኘት ይቸገራል፡፡ቢያገኙም ረዳት ስሌሌለ ቶሎ ይነጠቃሉ፡ምክኒያቱም ብቻለ ብቻ ጉልበት ስለሚጠይቅ የእኛዎቹ በጉልበት የመቋቋም ችግር ስላለባቸው እያስረከቡ ይመጣሉ ቶሎ ግብ ጋር እንዲደርስ የተጣለው ኳስ ቶሎ ባለጋራ እጅ ገብቶ እኛ ላይ የጥቃት ጫናው ይጠነክራል፡፡ቶሎ ግብ ጋር ለመድረስ ሲባል እንቅስቃሴው በግል ነው የሚሆነው፡፡ በግል ጉልበት ስለሚጠይቅ አስቸጋሪ መሆኑን ከዮሀንስ የተሻለ ሰው አስረጅ ሊሆን አይችልም፡በ1975 ዮሀነስ ለብሄራዊ ቡድን ተመርጦ ነበር፡፡በዚያን ግዜ የነበሩት ተጫዋቾቻን በፊዚካል አሁን ካሉት በብዙ እጥፍ ይሻላሉ፡፡ እነርሱ እንኳን በዚህ አጨዋወት ሊቋቋሙ አልቻሉም፡፡ በጉልበት በፍጥነትም ቶጎን የነዮሀንስ ቡድን እንዳልቻለ ሁሉ ያሁን ቡድን ከዚህ አጨዋወት ማስወጣትሲገባው እሱ ያልቻለበትን መነገድ ተጨዋቾችን እንዲተገብሩ ማድረግ ተገቢ አይደለም፡፡ እሱም ያውቃል፡፡ቶሎ ቶሎ ባለጋራሜዳ እየጣሉ መግባቱ ለሌሎች አሰልጣኞችም እንዳላዋጣ ታይቷል፡፡ ዮሀንስ ሌሎች አሰልጣኞች አሁን እሱ እየሄደበት ባለው ነገር ውስጥ ተግብረው ወድቀት ውስጥ ገብተው እንደነበር መማር ይገባዋል፡፡ከአሰልጣኞቹ መማር ብቻ ሳይሆን እራሱም በኢንተርናሽናል ፉትቦል ካገኘው ተሞክሮ ትምህርት መወሰድ ነበረበት፡፡በ1975 ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከቶጎ ሲጫወቱ 4ለ2ተሸንፈው ነው የወደቁት፡፡በተለይ ቶጎ በሜዳው 3ለ0 ሲየያሸንፍ ከሜዳ አላስወጣቸውም ፡፡ከተከላካዪቹ አንዱ ዮሀንስ ከግራ በኩል ለአጥቂዎቹ በረጅሙ እየጣለ ነበር የሚሰጣቸው (ቶሎ እዲያገቡ) እሱ የሚጠልዛቸው ኳሶች በርግጥ ባለጋራ ሜዳ ደርሰዋል ግን የእኛ አልነበሩም፡፡ ዮሀንስ ወደ ባለጋራ ግብ ያሻገራቸው ኳሶች ቶጎ በር ላይ ደርሰዋል ነገር ግን ቶጎ እነዚህን ኳሶች እየተቀበለ በማጥቃት እኛ ላይ ብዙ ጫና ፈጥረውብን 3ለ0 ተሸነፍን፡፡ቶጎ በጣም ነው የበለጠን፡የተበለጥነው እኛ ይዘንለት የገባነው ነገር ለእነርሱ ስለተመቸ ነው፡ በዚያ አጨዋወት ብሄራዊ ቡድኑ ባለጋራን መግጠሙ አዋጪ እንዳልሆነ ይልቅ አክሳሪ እንደሆነ ራሱ ተጫውቶ አይቶታል፡፡፡እሱ ተጫውቶ ያላዋጣውን ነገር ያሁኑ ተጨዋቾች እንዲተገብሩ ማድረጉ ጉዳት ነው፡፡ ያ ቡድን ከቶጎ በፊት ሞሪሸስን ገጥሞ ነው ያለፈው ሞሪሸስን ሲያሸንፉ አጨዋወቱ ትክክል ነው ብለው አመኑ፡፡ ቶጎ ላይ ሞሪሸስ የሰጣቸውን ክፈተት ማግኘት አልቻሉም(ልክ አሁን ብሩንዲን ሲያሸንፉ ትክክል እንደመሰላቸው) ቶጎ በፍጥነት አና ጉልበት ከሞሪሸስ የተለየ በመሆኑ አልቻሉትም፡፡ ይሄ ከሆነ 33 አመት ሆነው ፡፡ዮሀንስ 33 አመት ሙሉ አልተማረም ፤አልገባውም፡፡ቢገባው ኖሮ እኔ ብሄራዊ ቡድን በነበርኩበት ግዜ በሀይል አጨዋወት ስላስቸገሩን በዚህ መንገድ አስቸጋሪ ስለሆነ አሁን በአሰልጣኝነት ግዜ ይሄን መንገድ መቀየር አለብኝ ማለት ሲገባቸው ተመልሰው ባልተቻለበት መንገድ መግባቱ አስገራሚ ነው፡፡በዚያ ላይ በተክለሰውነት የነ ዮሀንስ ቡድን ካሁኑ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች በእጅጉ የገዘፉና ጠንካራ ናቸው ግን እነርሱም(የነዮሀነስ ብሄራዊ ቡድን) በዚያ ሰውነታቸው መብለጥና መቋቋም አልቻሉም(የሰውነት አቀማቸውን ለማነጻጸር እንዲመቻችሁ ያሁን ብሄራዊ ቡድን እና ቶጎን በ1975 የገጠመውን ቡድን ፎቶ አቀርቤላችኋለሁ ፡፡ዮሀንስ ከቆሙት ከግራ ሁለተኛው ነው )እናም ዮሀንስ ተጫውቶ ያልቻለበትን ነገር እንዴት ያሁኑ ትወልድ ሊተገብረው ይችላል፡፡

…………አሁን ይሄ ቡድን በዚህ አጨዋወት ለአፍሪካ ዋንጫ በሆነ ምኪኒያት ቢያልፍ የሚቋቋም ይመስላችኋል?፡፡ ብናልፍም እንኳን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ሳይሆን አልፈን ምንድነው የምንሰራው?የሚለው ነው መታየት ያለበት፡፡ባለፈው አፍሪካ ዋንጫ የገባው ቡድን አንድ አግብቶ ሰባት ገብቶበት ውራ ሆኖ መጣ ፡፡ጥሩ ነው የተባለለነት ነገር ቀጣይነት አልነበረውም፡፡ጀግና የተባለው ቡድናችን ገብቶ ውራ ሲሆን ጀግንነታቸችን ለውራ ከሆነ ምን ያደርግልናል፡፡በዚያ የአፍሪካ ዋንጫ የውጭ ጋዜጠኖች የእኛን ቡድን ኳስ ጥሩ ናቸው አሉን፡፡ ግን ኳስ የሚጫወት ቡድን ሰርተን አይደለም የገባነው፡፡ በተፈጥሮ ያለን ነገር ይሄ በመሆኑ በዚህ የተወሰኑ ልጆች በግል የሆነ ነገር ስላሳዩ ኳስ ጥሩ ናችሁ አሉን፡፡ታዲያ ለምን ጥሩ ናችሁ የተባልንበትን ነገር(አሁን የአሮጊት የተባለውን) በስልጠና ብናሳድግ እንጠቀማለን፡፡ጋዜጠኞቹ የእኛን ቡድን በጉልበት ጥሩ ናችሁ አላሉንም፡፡ በንጽርር ከሌሎች ቡድን ጋር አስተያይተውን እንደማንበልጥ ስላዩን በጉልበት ጥሩ ናችሁ አላሉም ፡፡እኛ ግን አሁን እየሰራን ያለነው በጉልበት ነው፡፡ይሄ ደግሞ አዋጪ እንዳልሆነ ነው ለብዙ ግዜ የታየው፡፡ዮሀነስ እስካሁን አለቆቻችን የሆኑትን ምእራብና ሰሜን አፍሪካ ቡድኖችን አላገኘም፡በርግጥ ደደቢትን ይዞ የናጀርያን ቡድን ገጥሞ ተበልጦ ነው ከውድድር የወጣው እዚያ 2ለ0 ሲሸነፍ ከነብልጫው ነው፡፡ከዚህ ጨዋታ እንኳን መማር አልቻለም፡፡(በቅርቡ ካደረገው)ከምእራብ ቡድኖች ጋር ወደ ፊት ቶሎ ቶሎ የጣሉ ባለጋራ ሜዳ መግባት እንዳላዋጣ ተጫውቶም አሰልጥኖም ካየው ሌላ አማራጭ መፈለግ ነበረበት ፡፡ግን አማራጩና ጠቃሚውን የአሮጊት ፉትቦል ካለ ከእነርሱ ጋር ሲገናኝ ዳግም አሰቃቂ ነገር ነው የሚታው፡፡ያን ግዜ ሰበብ ደርድሮ ቆይታን ለማስቀጠል ካልሆነ ለውጥ ከእዚህ ቡድን ምንም አይጠበቅም ፡፡
የምእራብ አፍሪካ ቡድኖች የበለጡን በጉልበት ነው፡፡፡እነርሱ በዚህ አጨዋወት የበለጡን እኛም በጉልበት ስለገባን ነው፡፡በዚህ እንቅስቃሴ ለረጅም አመት እየበለጡን ነው፡፡ዛሬም ለረጅም አመት የተበለጥንበትን ነገር አንለቅም ብለን የለውጡን መንገድ‹‹የአሮጊት ነው››በሚል በነበረበት(በተዋረድንበት) ለመቀጠል መዘጋጀት አስገራሚ ነው፡፡መቼ ነው ታዲያ ማመዛዘን የሚችል አሰልጣኝ የምናገኘው? ያስብላል፡፡ ግን ለማመዛዘን የቸገራቸው ምንድነው፡፡ልጆቹ ያላቸው ችሎታ የታወቀ ነው ፡፡ያንን በስልጠና አዳብሮ በሚችሉት መንገድ እንዲጫወቱ ቢደረግ የተሻለ ነው፡፡አሁን ግን በማይችሉበት መንገድ እንዲጫወቱ ተደርገው በዚያ ላይ ተጠያቂ መደረጋቸው ጉዳት ነው ፡፡
– የሚሰጡት ስልጠና ጨዋታን የሚወከል አይደለም፡፡ ስልጠናው በረኛ ይለጋል፤ ሲለጋል ተሻምታችሁ አግኙ ነው፡፡ማሻማት ማሰልጠን አይደለም ይሄን ማን ያቅተዋል?…..መለጋት፤መልስ ምት፤እጅ ውርወራ፤ኮርና፤ክሮስ እነዚህ ሁሉ ማሻማት ናቸው፡፡ በማሻማት ወስጥ ከእኛ ይልቅ የውጭ ቡድናች ተጠቃሚ ናቸው፡፡ከማሻማት ውጭ ያለው ነገር ኳስ ይዞ ተረራድቶ መጫወት እውቀት ነው፡፡ በእወቀት ማሰልጠን ብልህነት ነው፡፡ግን በእወቀት ማሰልጠን አስቸጋሪ ሲሆንባቸው ባለጋራ ሜዳ እየጠለዙ በመግባት ነው የመረጡት፡፡በእወቀት ማሰልጠንና መጫወትን ግን ‹‹የአሮጊት›› ይሉታል
–እነርሱ በመረጡት አጨዋወት መቋቋም እንዳማይችሉ አሰልጣኞቹም ያውቃሉ፡፡ባለጋራን መብለጥ የምንችልበት አጨዋወት ፈልጎ መተግበር ሳይሆን እንዴት ሰበብ እየፈለጉ መቆየት ሚችሉበትን ነገር ነው የሚያስቡት

እከዛሬ የሰሩት አሰልጣኞች እግር ኳሱን ለመለወጥ ሳይሆን ደሞዝ በልተው የሚሄዱ ብቻ ነው ያየነው፡፡ያሁኑም አሰልጣኝ እንደበፊቶቹ በእግር ኳሱ ላይ የምንናፍቀውን ለውጥ የሚያሳየን እንዳልሆነነ ከአየያዙ መረዳት ይቻላል

– አሰልጣኞች ያመኑበትንና ያወጣል ያሉትን አጫወወት ሀላፊነት ሲወስዱ አይታዩም፡፡ይሄነገር ያወጣናል ካሉ በዚህ ለሚመጣው ነገር ሀላፊነት ወስደው ሲሸነፍም እኔ ነኝ የምጠየቀው ብለው መናገር አለባቸው፡፡ይሄ ማለት የመረጡት ነገር ስህተት ከሆነ ወደ ተሻለና ወደሚያዋጣ ነገር እንዲመጡ ያደርጋል፡፡አሁንግን ሀላፊነት ስላማይወሰዱ ከተሳሳተው ነገር መውጣት አይችሉም፡፡ስለማይወጡም በተሸነፉ ቁጥር ሰበብ እየደረደሩ የሚፈለገው ለውጥ ሊመጣ አልቻለም፡፡
–
– – አንዳንዴ ቡድኑ ሲያሸንፍ አሰልጣኞቹ ያሸነፉበትን መንገድ እንኳን አያውቁም፡፡እንዴት እንዳሸነፈ ስለማያውቁ ሲሸነፍ ሰበብ ይደረድራሉ፡፡ያሸነፈበትን ነገር ካላወቁ ሲሸነፍ ስህተቱ የቱ ጋር እንዳለ አይረዱም፡፡ለዚህም ነው ከማስተካከል ይልቅ ሰበብ የሚደረድሩት፡፡ለአፍሪካ ዋንጫ የገባው ቡድን ባለጋራውን(እነ ቡርኪናን) መቋቋም ያቃተው ማጣሪያውን ሲያልፍ እንዴት እንዳሸነፈ ስለማያውቅ ነው፡፡ውጤት የሚባለው አንድ ጨዋታ አሸንፎ መፎለል ሳይሆን ቀጣይነት ባለው መንገድ ብልጫ ይዞ ማሸነፍ የሚችል ቡድን ሲገኝ ነው፡ትናንትም ዛሬም ቀየጣይነት ያለው ነገር ይዞ የሚሄድ ቡድን አላገኘንም፡፡ቀጣይነት ያለው ሰበብ ብቻ ነው ከአሰልጣኞቹ ያገኘነው፡፡አሰልጣኙ ባመኑበት፤ ያዋጣል ብሎ በመረጠው ነገር ለውጥ ካላመጣ በአማራጩ ሀሳብ መሞከር አለበት
– እኛ ሀገር ለውጥ እንዲመጣ ሚዲያው ትልቅ ስራ መስራት አለበ ፡፡ከማሸነፍና መሸነፍ ውጭ በእወቀት ቢዘግቡ አሰልጣኞችን ወደ እውነተኛው ነገር ሊያመጧቸው ይችላሉ፡፡ቡድኑ ሲያሸንፍ ጉሮ ወሸባ ይላሉ፡፡ያሸነፈበትን ነገር መነሻችን ነው ወይ ብለው አየይመረምሩም ፡ብሩንዲን ያሸነፍንበት የጨዋታ እንቅስቃሴ ሌሎች ቡድኖች ለረጅም አመት ሲጨፈጭፉን የነረበት እንቅስቃሴ መሆኑ ታውቆ ከጉሮ ወሸባዬ ነገር ወጥተን ይሄ ነገር ከሌሎች ጋር አላዋጣንም(ከሰሜንና ምእራቡ) ብሩንዲው ውጤት አሳሳች ነው ቢሉ አሰልጣኞችም ወደ ትክክለኛው ነገር ሊመጡ ይችላሉ፡፡ለወደፊቱ ይሄ ቢስተካከል አሰልጣኞቹን ማረም ይቻላል ፡፡

ያሁኑ አሰልጣኝ በቅርብ ከሀላፊነት ይነሳል፡፡ግን አሰልጣኙን በምን እናስታውሰዋለን፡፡ምኪኒያቱም ምንም የሰራልንና ያስቀመጠልን ነገር የለም፡፡ሌሎች አሰልጣኞች ያልቻሉበትን መንገድ እያስቀጠለ ነው፡፡በአምስተኛው አፍሪካ ዋንጫ ቡድኑን ያሳለፉት አሰልጣኝ ሽፈራው በሴኔጋል 5ለ1 በቱኒዝያ 4ለ0 ተሸንፈው ከምድቡ ከአጠቃላይም ውራ ሆነው ተመለሱ፡፡ ለሰባተኛውም ያሳለፉት አሰልጣኝ በአይቮሪኮስት 6ለ1 በሱዳን 3ለ0 ተሸንፈው ከምድቡም ከአጠቃላዩም ውራ ነው የወጡት፡፡መንግስቱ ወርቁ ለ13ተኛው አፍሪካ ዋንጫ ቡድኑ እንዲያልፍ አደረገ፡፡ ነገር ግን አንድም ጨወታ ሳያሸንፍ ቡድኑ በሶስቱም ጨዋታተበልጦ ከምድቡም ከአጠቃላዩም ውራ ነው የወጣው(ከስምንት ቡድን ስምንተኛ) ከሊቢያወው ቀጥሎ በ29ነኛ አፍሪካ ዋንጫ በ2005 አለፍን በማለፋችን እግር ኳሱ እንደተለወጠ ተወራ፡፡ይሄኛውም እንደሌሎቹ ከምድቡም ከአጠቃላዩም ውራ ነው የወጣው፡፡ባለጋራን መብለጥ ቀርቶ መቋቋም አልቻለም አንድ ግብ አስቆጥሮ ሰባት ገብቶበት ነው የተመለው፡፡እነዚህን ለአፍሪካ ዋንጫ ያሳለፉትን አሰልጣኞች በምን አንስታውሳቸው ምክኒያቱም ምንም ያስቀመጡልን ነገር የለም፡፡ የምእራብ አፍሪካን ቡድኖች መቋቋም አቅቷቸው ነው የወጡት፡፡እነዚህን አሰልጣኞች የማናስታውሳቸው እኛ በምንበልጥበት ሳይሆን በተበለጥንበት ይዘውን ስለገቡና ስላስጨፈጨፉን ነው፡፡እነዚህ ለአፍሪካ ዋንጫ አሳልፈው ምንም ሳይሰሩ ውራ ወጥተው ተበልጠው የተረሱ ናቸው፡፡ ሌሎች አሰልጣኞችም ምንም ሳያሳዩን ከሀላፊነት ተነስተዋል የሆንስም ከእነኚህ አንዱ ነው ምንም ሳያሳየን ወደ ለውጥ ሳይወስደን ችግሩን ሳይፈታ ከሀላፊነት ይነሳል እናም በዚው ይረሳል፡፡ከሌሎች አሰልጣኞች ይልቅ በአሁን ሰዓት የካሳዬ ስም የሚነሳው ትንሽ የለውጥ መንገድ ስላሳየና ስላስቀመጠ ነው፡፡ለሌሎች ከተከተሉበት መንገድ ወጣ ስላለ ነው፡፡ፍንጭ ለማሳየት በመሞከሩ ነው፡፡ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ በራሱ ምንም ነገር የለውም….ማለፉችን ከእድገት ጋር ቢሆን ከለውጥ ጋር ቢሆን ጥሩ ነው፡፡፡ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋችን እድገታችንን ሳይሆን ውድቀታችንን ነው የሚየሳየው(በብዙ ግብ እየተሸነፍን ውራ ሆነን ስለምንወጣ)፣፡እከዛሬ የታየው ተስፋ የሌለውና በባለጋራ በእቅስቀሴና በውጤት ተበልጠን ነው የታየው፡፡ዛሬም ሀላፊነቱን የያዙት ከሌሎች ሳይማሩ ለሌሎች ያሳዩትን ደካማ ነገር ለመድገም ነው፡፡ገና አንድ ጨዋታ ሲሸነፉ‹‹የኢትየዮጵያ እግር ኳስ ችግር አለው፤አጥቂ የለም፤በረኛ የለም››ይላሉ ሲረከቡ እኮ ይሄን አውቀው ነው ፡፡ሲቀጠሩ ለአፍሪካ ዋንጫ እናሳልፋለን ይሉና ሲሸነፉ የቅድሙን ችግሮች ያነሳሉ
– አንድ ነገር ደግሞ አለ፡፡ወደ ለውጥ የሚወስድ ቡድን መስራት ሲያቅታቸው እንትናን ወደ ብሄራዊ ቡድን ያመጣሁት እኔ ነኝ በሚል ክሬዲት በዚህ እንዲያዝላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ኤፌም ኦኔራ በተጋጣሚ ቡድኖች እንደዚያ ተቀጥቅጦና ተበልጦ ከሄደ በኋላ እነ አሉላ፤ ሽመልስ፤ኡመድን ብሄራዊ ቡድን ያመጣኋቸው እኔ ነኝ ብሎ በሰራው ቡድን ሳይሆን በልጆቹ ክሬዲት እንዲያዝለት ሲወተውት ነበር፡፡ባሪቶም ናትናኤልን አንዳርጋቸውን ብሄራዊ ቡድን ያመጣሁት እኔነኝ አሉን፡፡ አሁን ደግሞ ‹‹ራምኬሎን ብሄራዊ ቡድን ያመጣሁት እኔ ነኝ››በሚል እየተወተወትን ነው …አኛ እንትናን ማምጣታቸው ሳይሆን ባለጋራን መቋቋም የሚችል ተስፋ ያለውና የምንመካበት ቡድን ሲሰሩልን ነው፡፡ካለበለዚያ እገሌን ብሄራዊ ቡድን ያመጣሁት እኔ ነኝ በሚል የለጥው ቡድን ሳይሰሩልን ቢቆዩ ፋይዳ የለውም፡፡የእኔ ከእከሌ አሰልጣኝ ይለያል ለማለት ነው፡፡በአንድ ወቅት በሴኔጋል 3ለ0የተሸነፈው ቡድን አሰልጣኝ ‹‹የእኔ ቡድን ጥሩ ነው፡፡ያለፈው አሰልጣኝ 4ለ0 ነው የተሸነፈው፡፡ እኛ እንደነርሱ በዙ አልገባብንም›› በሚል የእሳቸው ቡድን በምን ከሌሎች እንደሚለይ ነግረውን ነበር ፡፡4ለ0 የተሸነፈው 3ለ0 የጠጣውም በተመሳሳይ እንቀሰስቃሴ ተበልጠው ምን የተሻሻለ ነገር ሳያስቀምጡልን ነው የሄዱት፡፡
– ያሁኑም አሰልጣኝ ደሞዝ ተቀብሎ ለመሄድ ሳይሆን ለለውጥ ቢሰራ አይረሳም፡፡

The post Sport: የአሮጊት ፉትቦል…..የሴት ጨዋታ – ከገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የበጎች መንጋ ግዙፉ የመጓጓዣ አውሮፕላንን በድንገት እንዲያርፍ አሰገደዱት

0
0

singapoor

ከታምሩ ገዳ
ንብረትነቱ የሲንጋፖር አየር መንገድ የሆነ አንድ የእቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን በውስጡ ጭኖ የነበረውን በረካታ በጎች ይዞ በረራውን አቁርጦ ለሰአታኣት እንዲያርፍ ተገዷል። አቪዮሽን ሀራልድ የተሰኘው ድህረ ገጽ እንደዘገበው ከሆነ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ ስደሰት (2186) በጎችን ጭኖ መነሻውን ከ ሲዲኔ( አውስትራሊያ )አደርጎ ወደ ኳላላምፑር (ማሊዢያ) ይበር የ ነበረው የማጓጓዣ አውሮፕላን በበረራ ላይ እንዳለ ከጭስ አነፈናፊው (ስሞክ ዲክተክቶር ) መሳሪያ ላይ ያለተለመደ የጭስ ምልክት የታያል ።

ፓይለቶቹም አውሮፕላኑን ወዲያውኑ በድንገተኛ እንዲያርፍ አድርገው መንሰኤው ሲጣራ በውስጡ ምንም አይነት እወነተኛ የእሳት ዘር (ጭስ) አለተገኝም። ለዘመናዊ ቴክኖሎጂ ምስጋና የገባውና በሁዋላ ሰለ ጭሱ መንሰኤ ሲጣራ እንዚያ ለመታረድ ይሁን ለመራባት ወደ ሲንጋፖር ሲጓጓዙ የነበርቱት በጎች “ከረጅም ጉዞ ሳቢያ ፣ ሲያመነዥጉት ከነበረው ግሳት ፣ ከተጸዳዱት (በጠጣቸው) አና በመጸዳጃቸው ካሰወገዱት ከተቃጠለው አየር (ፈስ) የወጣ ጋዝ ለካ ወደ ጭስ መመረመሪያዋ ማሽን ዘልቆ የእሳት አደጋ መመረመሪያውን አስጨንቆ እና አሰጠንቅቆ አውሮፕላኑም በአደጋ ጊዜ እንዲያርፍ ተገዷል “ ሲሉ የአየርመንገዱ ባለሰልጣናት ግምታቸወን የሰነዘሩ ሲሆን በተለይ ደግሞ የእንሰሳ ባለሙያዎች በጎች ሲደክማቸው የተቃጠለ አየር(ጋዝ) በብዛት ያሰወጣሉ ብለዋል። አሮፕላኑም ከሁለት ሰእት ተኩል የድንገተኛ ማረፍ በሁዋላ መንገዱን በማቅናት ከመዳረሻው(ኳላላምፑር) በሰላም ደርሷል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም ሌላ የሲንጋፖር አየርመንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ባለፈው ነሃሴ ወር ወስጥ ከግሪሳ ወፎች ጋር ተጋጭቶ በድንገት ለማረፍ ተገዷል። መቸም ጥንቃቄ ማድረግ ባይከፋም በሰንካላ ምክንያት አውሮፕላኖች እንዲያርፉ ሲገደዱ ማየት እየተለመደ የመጣ ጉዳይ ሲሆን በተለይ ከሽብር ጋር በተያያዘ ብዙ ሰዎች በምርመራ ሰም ይያዛሉ አሊያም ከመንገዳቸው ይደናቀፋሉ። ይሁን እና ሰሞኑን ግዙፉ አወሮፕላንን በማሰደንገጥ በደንገት እንዲያርፍ ያደረጉት የበጎቹ እጣፈንታ (በቀጥታ ወደቄራ ሰለመላካቸው ወይም ወደማጎሪያ ቤታቸው ሰለመላካቸው ) ለጊዜው አልታወቀም።

The post የበጎች መንጋ ግዙፉ የመጓጓዣ አውሮፕላንን በድንገት እንዲያርፍ አሰገደዱት appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ረሃቡና እድገታችን፡ ተጠያቂው ማን ነው? –በአብዱረዛቅ ሑሴን

0
0

.
ክፍል አንድ፡ እድገቱን የጎሪጥ!
.
ምስራቅ አፍሪካ ላይ በዚህ አመት 22 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በረሃብ እንደሚጠቁና ከዚያም ውስጥ 68% (15 ሚሊየኑ) ከኢትዮጵያ እንደሚሆን የተባበሩት መንግስታት እየተናገረ ይገኛል፡፡ መጀመሪያ ምንም አይነት ስጋት እንደሌለ፣ ከዚያም 4 ሚሊየን ቆየት ብሎ ደግሞ 8 ሚሊየን ህዝብ ተጠቂ እንደሆነ ዘግይተው ላመኑት ሹማምንቶቻችን ከፍተኛ ዱብ እዳ እንደሚሆንባቸው አያጠያይቅም፡፡ የሀገርም ውስጥ ይሆን አለም አቀፉ ህብረተሰብ አንድ ተመሳሳይ ጥያቄ እንደሚጠይቅ ይጠበቃል፡- #‎ላለፉት አስር አመታት በሁለት ዲጅት ያደገ ኢኮኖሚ እንዴት የህዝቡ 15% በረገብ ሊጠቃ ቻለ?;፡፡
.

rehab 7
ለዚህ ጥያቄ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትራችን ያላቸውን የኢኮኖሚክስ እውቀት ተጠቅመው ቢያንስ መልስ ሚመስል ነገር ይሰጡን እንደነበረ እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡ እሳቸው ከነጎዱ ወዲህ ግን #‎ወይ አያውቁ፣ ወይ የሚያውቁትን አያመጡ፣ ወይ አይወጡ; ሆኖብን እንጨት እንጨት የሚል የወረዱ ትንታኔዎቻችን የሚሰጡን ከጠቅላይ ሚንስተሩ እስከ ኮሚኒኬሽን ሚንስትሮቻቸው ድረስ ያሉ ባለስልጣናት ግራ አጋብተውናል፡፡ የዋጋ ግሽበት ፣የኑሮ ውድነቶችን እና የመሰረታዊ አገልግሎት አቅርቦት እጥረትን የመሳሰሉ ችግሮች ሲነሱ አቶ መለስ በተደጋጋሚ የእድገታችን ውጤት እንደሆነ ለኛም ለተተኪዎቻቸውም ሲነግሩን ነበር፡፡ ይህ ምላሽ መንግስትን ከተጠያቂነት ባያስመልጥም በከፊልም ቢሆን ኢኮኖሚክሲያዊ መሰረት ያለው ምሁራዊ ትንተና ሊባል የሚችል ነው፡፡ ከሳቸው መሞት በኋላ የመጡ መሪዎቻችን ለተመሳሳይ ጥያቄዎች ተመሳሳይ መልስን ሲሰጡን ቆይተዋል፡፡ ራእያቸውንም ብቻ ሳይሆን ለጥያቄዎች የሰጡትንም መልሶቻቸውን እያስቀጠሉም ይገኛሉ፡፡ ረሃብ ሀገራችንን ተለይቷት ባያውቅም በዚህ መጠን ግን የሁለት ዲጅት እድገት ትርክት ከተጀመረ ወዲህ ስላልተከሰተ የቀድሞውም ጠቅላይ ሚንስትር አልተጠየቁምም ለወራሾቻቸውም መልሱን አላስቀመጡም፡፡ በተወሰኑ አጋጣሚዎች ወደ ሚዲያ ብቅ ያሉትም ባለስልጣናት ችግሩን ከመካድ፣ መጠኑን ከማስተባበልም አልፎ የወረዱ ምክንያቶችን ሲደረድሩ ታዝበናቸዋል፡፡ መልሽ ያጣውን ጥያቄ ዛሬ በከፊልም ቢሆን ለመመለስ እንሞክር፡፡
.
ረሃብ! ድሮና ዘንድሮ
.
የሰባ ሰባቱ ድርቅና ረሃብ ሀገራችንን አለም ፊት አንገት ያስደፋ አሳዛኝ ክስተት ነበር፡፡ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተው ድርቅ ከፍተኛ የሆነን ረሃብና እልቂት አስከትሎ ነበር፡፡ ዶክተር እሌኒን የመሰሉ ምሁራን እንደሚሞግቱት በወቅቱ የሰሜኑ ክፍል በድርቅ ቢጠቃም በሌላው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ግን በቂ ምርት እንደነበረ ይገልፃሉ፡፡ ሀገሪቱ በዛ ወቅት ምርት ከተትረፈረፈበት ደቡብ እጥረት ወደተከሰተበት ሰሜን እንዲሄድ የሚያስችል በቂ የኢንፍራስትራክቸርና በተለይም የገበያ ተቅዋም አለመኖሩን ለችግሩ መባባስ እንደ ዋና ምክንያትም ያቀርባሉ፡፡ በሌላ አባባል በቂ የኢንፍራስትራክቸር ዝርጋታ ኖሮ በነበረና ምርትን ከፍላጎት ጋር ለማገናኘት የሚያስችል የገበያ መረብ ኖሮ በነበረ ድርቁ ያስከተለውን እልቂት መቀነስ ይቻል ነበር፡፡ ይህ ምልከታም በዶክተር እሌኒ መሪነት የተቋቋመውን የEthiopia Commodity Exchangeን ለመመስረት እንደ ዋነኛ መከራከሪያ ሆኖ በተለያዩ የጥናት ፅሁፎቻቸው ውስጥ ተካቶ እናየዋለን፡፡
.በኢትዮጵያ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ የተነሳ በቀን 2 ህፃናት ይሞታሉ * (ቢቢሲ በቆቦ አካባቢ ያለውን ድርቅ የዘገበበት አሳዛኝ ቪዲዮ ይዘናል)
አስከፊው የሰባ ሰባቱ እልቂት ከተከሰተ ከሰላሳ አመት በኋላም ይኸው ድርቅ አገሪቱን እያሳሰበ ይገኛል፡፡ እነ ዶክተር እሌኒ የሞገቱለት የኢንፍራስትራክቸርና የገበያ ተቋማት አለመኖር በፊት ከነበረው በእጅጉ የተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጥርጥር የለውም፡፡ የመንገዶችም ሆነ የኮሚኒኬሽን ኢንፍራስትራችቸሩ ከድሮው ጋር ሊወዳደር በማይችል መልኩ አድጓል፡፡ በሀገሪቱ በየትኛውም ቦታ የአቅርቦት እጥረት እናዳለና ተመጣጣኝ ትርፍ ሊገኝ እንደሚችል የሚያውቅ ነጋዴ ወሬውን ሰምቶ ተኝቶ ያድራል ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ ወሬውን ለመስማት የሚያስችለው የኮሚኒኬሽን ኢንፍራስትራችቸርም ይሁን ምርቱን እጥረት ወደ አለበት ቦታ ወስዶ ለማትረፍ የሚያስችለው የትራስፖርት አማራጮች በብዙ እጥፍ ተሻሽለውለታል፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ ረሃቡ በድጋሚ መከሰቱ እነ ዶክተር እሌኒ የዘነጉት ወይም ትኩረት ያልሰጡት ሌላ ተጨማሪ የረሃብ መንስኤ እንዳለ ያሳየናል፡፡ ይህም የህዝብ ወይም የመንግስት የመግዛት አቅምን ይመለከታል፡፡
.
ነጋዴው ያማሩ መንገዶችን ተጠቅሞ ትርፍ ምርት ካለበት ወደ እጥረት ወደተከሰተበት የሀገሪቱ ክፍል ምርቱን ቢያቀርብ ለረሃቡ መፍትሄ ሊሆን አይችልም፡፡ በችግሩ የተጠቃው የህብረተሰብ ክፍል የምርት አቅርቦት ብቻም ሳይሆን የመግዛት አቅሙም ሊኖረው ይገባል፡፡ ምርቱ በድርቅ የረገፈበት ገበሬ በደህናው ጊዜ ተቀማጭ ሀብት እስካላፈራ ድረስ የምርት አቅርቦትን ማሻሻልና ማቀላጠፍ ብቻ በራሱ ችግሩን አይፈታውም፡፡ ኑሮው ከእጅ ወደ አፍ ስለሆነና የመግዛት አቅሙም ስለማይኖረው ከመንግስት እርዳታን መከጀል ብቸኛ ምርጫው ይሆናል፡፡ መንግስት ፈርጣማ አቅሙን በመጠቀም ትርፍ ምርት ካለባቸው አካባቢዎችም ካልሆነም የውጭ ሀገራት ገዝቶ ተጠቂውን ህዝብ የመድረስ ግዴታ ይወድቅበታል፡፡ አሁን እንደሚታየው ከሆነ ግን ገበሬውም ለነገዬ ብሉ ያስቀመጠው ቅሪት ሳይኖረው በረሃብ አለንጋ እየተጠበሰ፤ መንግስትም ሲፎክርበት የነበረው ፈርጣማ አቅሙ በሞት አፋፍ ላይ ላሉት 15% ህዝቡ የቁርጥ ቀን ደራሽ መሆን ያዳገተው ይመስላል፡፡ ላለፉት አስርት አመታት ተኣምራዊ እድገትን ስታድግ የነበረችው ኢትዮጵያ፤#‎ግብርናን መሰረት ያደረገ; የእድገት ስትራቴጂ እየተከተለች እንዳለች የምትነግረን ኢትዮጵያ፤ ገበሬዋ እራሱን መመገብ ሲያቅተውና መንግስቷም የክፉ ቀን ደራሽ መሆን ሲሳነው እድገቱን የጎሪጥ ብናየው ይፈረድብን ይሆን?

The post ረሃቡና እድገታችን፡ ተጠያቂው ማን ነው? – በአብዱረዛቅ ሑሴን appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ቴዎድሮስ አድሃኖም መለስን ያጣነው በእጃችን ነው አሉ !!!!!! –ሳሙኤል አሊ ከ- ኖርዌይ

0
0

meles and adhanom

ጋዜጠኛ ትዝታ በላቸው በአሜሪካ  አማረኛ ድምጽ ሬድዮ በቀረበላቸው ጥያቄዎች ላይ መልሶችን እንዲሰጡ  የተጋበዙት  የወያኔ ቱባ ባለስልጣን የፌስ ቡክ ሚኒስቴሩ ይቅርታ ይደረግልኝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቴዌድሮስ አድሃኖም ነበሩ።  እኔ በተረቱ  የማውቀው  ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ  ይቀዳሉ የሚለውን ነበር።  እንደውም ይህ ተረት   ለኋለኛው  ትውልድ  እንጂ  አሁን ላለው ትውልድ  ግን ከባድ ይመስለኛል።  ምክንያቱም በአሁን ጊዜ እንደ ባልና  ባልና ሚስት  በአንድ ሃሳብ ተስማምተው የሚዘልቁት በጣም ጢቂቶቹ  ናቸውና።  ይሄንን አባባል ግን በሚገርም ሁኔታ  ወያኔዎች ላይ በጠበቀ  መልኩ አየዋለው ።የሁሉም ወያኔዎች ሃሳብ  ከአንድ

ሳሙኤል አሊ

ሳሙኤል አሊ

ወንዝ እንደተቀዳ   ተመሳሳይነት አላቸው። ሁሉም ውሸታሞች፤ ሁሉም ወያኔ ትምከተኞች፤ ሁሉም ወያኔ ዘራፊ ፤ሁሉም ወያኔ ዘረኛ፤ ሁሉም ወያኔ ነፍሰ ገዳይ ፤ ሁሉም ወያኔ  ኢትዮጵያን የሚጠሉ ፤ ሁሉም ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ  የሚጠሉ፤   ሁሉም ወያኔ  የአገር ክብርን አሳልፈው ለባእድ የሚሰጡ፤  ሁሉም ወያኔ  በሚገርም ሁኔታ የሰይጣን ደቀ መዝሙር በመሆን ከክፋት፤ ከመጠፋፋት ፤ከጥላቻ፤  ከውሸት፤  በስተቀር መልካምነትን መፋቀርን መዋደድን እውነትን መቼም የማይናገሩ ሆነው  ማየታችን የሚደንቅ ጉዳይ  ቢሆንም  የተገነዘብኩት ደግሞ  በሰላም በመነጋገር  በድርድር  ከወያኔ ጋር መግባባት ይቻላል የሚለውን ሃሳብ መቶ በ መቶ  ያጣሁበት  ውይይት ነበር።

ከሃያ አምስት አመት በሃላ  እንኳን የማይለወጡ የውሸት ትጥቃቸውን ያልፈቱ የጥፋት ዝናራቸውን ያላወለቁ መሆናቸውን ሳይ ኢትዮጵያ  ሕዝብ ላይ እስከመቼ እንዲህ  እየቀለዱብን  እንዲኖሩ እንደምንፈቅድላቸው አልገባኝም ። ባለጌ  ጫንቃችን ላይ ያለአግባባ  ወጥቶ  ጎንበስ ብለን እንድንሄድ እያደረገን  ስለሆነ  ከጫንቃችን ላይ  የወጣውን የውሸት ጥርቅም የሰይጣን መልክተኞችን አስወግደን ቀና ብለን የምንሄድበትን ዘመን ማምጣት ከኛ ኢትዮጵያን ይጠበቃል ።

እኚሁ ሚኒስትር የመለስ ዜናዊ በሂወት ሆኖ ያልተናገረውን ትልቅ የውሸት ሚስጢር ሹክ ብለውናል። እስከ ሞተበት ግዜ  ስልጣኑን እንዴት ማቆየት እንዳለበት ተንኮል በመሸረብ ሰው ከሰው ፤ ሕዝብ ከ ሕዝብ በማጋጨት የቆየውን መለስን።

በ97 የምርጫ ግዜ  ሁለት  ትልልቅ ሰልፎች ተጠርተው ነበር ቅዳሜ  እለት የወያኔ ጉጅሌ የጠራው ሰልፍ እንዲሁም እለተ እሁድ  ደሞ የቅንጅት ሰልፍ ተጠርቶ  ነበር ።በየቀበሌው የነበሩት  ካድሬዎች  እና ትልልቅ የሚባሉት የወያኔ ባለስልጣኖች በሰልፉ ለሚወጣው ሰው በነፍስ ወከፍ ለእያንዳንዱ የቀን አበል 50 ብር ከቲሸርት ጋር ታስቦላቸው መስቀል አደባባይ ይወጣሉ።  የዚህን ግዜ  በሰልፉ ላይ የወጣው ሰው ደግፋቸው የወጣ  መስሎአቸው ያለምንም ማጭበርበር  ምርጫውን እናሸንፋለን ብለው በአደባባይ አወጁ።  ወያኔዎች አጭበርባሪ  እንደሆኑ ነገር ግን ሰልፍ የወጣውን  ሰው ብዛት ሲያዩት በስሜት ያለማጭበርበር  ምርጫው እንደሚያሸንፉ ተናገሩ።

በንጋታው እሁድ  የቅንጅት ሰልፍ ግዜ  ሱናሚ በሚመስል ህዝቡ  ንቅል ብሎ  ቅዳሜ  እለት የወያኔን ቲሸርት  የለበሰው  በሙሉ  ቅንጅትን  እንደሚመርጥ  እና የቅንጅት ደጋፊ መሆናቸውን  በስሜት ድጋፉን ሲሰጥ  ሲመለከቱ  ወያኔዎች ዘንድ ትልቅ ውዥንብር ተፈጥሮ  ወዲያው  በነጻነት ያለማጭበርበር ያሉት ወዲያው አጥፈው  አዲስ  አበባን የወታደር ቀጠና በማስመሰል  ታንክ፤ መኪና ላይ የተጠመደ ከባድ መሳርያ፤  ከመተኮስ በስተቀር ምንም የማያውቁትን አጋዚ ጦር  አሰማርቶ የተናገረውን ቃል ሽሮ ኢትዮጵያኑን የጨፈጨፈው።

ከዛ በሃላ ያላማቃረጥ ኢትዮጵያ  ላይ ከበደል ሁሉ በደል  እየሰራ  ቆይቶ በመጨረሻም ከመሞቱ  በፊት እራሱ ስልጣን ላይ እንዴት  መቆየት እንዳለበት  ተንኮልና ውሸትን በመወጠን  1 ለ 5 የሚለውን የመጠርነፊያ ስትራቴጂ በማምጣት በ2007 የምርጫ ዘመን 5 ሚሊዮን ተመራጭ  እንዲኖር በማድረግ  ወያኔን የሚቃወሙትን የፖለቲካ  ፓርቲዎች  ለማዳከም  ተንኮል  ሲጎነጉኑ  ሞት ቀድሞት ወደማይመለስበት  እንደሄደ  እያወቅን፤  የመለስ ደቀ መዝሙር  ደሞ ሊዋሸን በአሜሪካ ድምጽ የአማረኛው ክፍለ ጊዜ ሬድዮ መምጣቱ መቼም የማያፍሩ እና ምንም ይሉንታ ያልፈጠረባቸው መሆኑን ያሳያል።   መለስ በሂወት  እያለ ማረፍ  እፈልጋለው  ተቀበሉኝ ብሎ እሺ ብለን ብንቀበለው ምን አልባትም ላይሞት ይችል ይሆናል ብለው በመናገር በስልጣኑ እንዲቆይም ድጋፍ ከሰጡት  ውስጥ አንዱ  እርሳቸው እንደሆኑ እና የመለስም ደም በእጃቸው ላይ እንዳለ በቀጣፊው  እና ውሸት  በለመደው  አንደበታቸው ነገረውናል።

በርግጥ  እዚህ ጋር አንድ እውነት አለ  የመለስ መሞት ለወያኔዎች  ቡድን ሞታቸው ነው። ምክንያቱም  የኢትዮጵያ ሕዝብን  እንዴት ከባርነት ባልተናነስ ሁኔታ  ሕዝቡ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየታየ  እየተረገጠ የሚገዛበትን ሰይጣናዊ ጥበቡን አጥማቂያቸው  እሱ  ስለነበር።  አሁን ያንን የክፋት መርዝ  ስራዎችን በተቀነባበር መልኩ  የሚሰራላቸው  በማጣታቸው የወያኔም ሞት ከመለስ ጋር አብሮ ሞቷል።  አሁንም እያስኬዳቸው ያለውም  የመለስ ሰይጣናዊ ራዕይ የሚቆየው  እስከ ጥቂት ግዜ ነው። የወያኔ ሞት በነጻነት ታጋዮች መሰዋትነት  እውን የሚሆንበት ጊዜው ቀርቧል ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም በልጆቿ  ተከብራ  ትኑር !!

ሳሙኤል አሊ ከ- ኖርዌይ

Email samilost89@yahoo.com

Date 11.11.2015

The post ቴዎድሮስ አድሃኖም መለስን ያጣነው በእጃችን ነው አሉ !!!!!! – ሳሙኤል አሊ ከ- ኖርዌይ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

አገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል፤ በአክሊሉ ወንበር ቴዎድሮስ ተቀምጧል

0
0

High-level Meeting on Disability and Development

  ይገረም ዓለሙ

በዕድሜአችን የደረስንባቸውንም ሆነ  በታሪክ የምናውቃቸውን በዚህች ሀገር በመሪነትም ሆነ በከፍተኛ ሥልጣን ላይ የነበሩ ሰዎች ስናስብ የዘመናችን ባለሥልጣናት በብዙ መንገድ አንሰውና ቀለው ነው የሚታዩት፡፡ በውሸታምነታቸው በዘረኛነታቸውና  ለሀገርና ለሕዝብ በአላቸው እኩይ አመለካከት ደግሞ አይደለም ትናንት ከነበሩት ወደ ፊትም ከሚመጡት የሚስተካከላቸው የሚገኝ አይመስልም፡፡ ነገረ ስራቸው ሲመዘን፣ የማይታመን የማይጨበጥ ንግግራቸው ሲሰማ እንዲህ የሚያደርጋቸው ከደደቢቱ እኩይ ዓላማቸው በላይ የተቀመጡበት እነዚያን ታላላቅ ኢትዮጵያውያንን  ያስተናገደ ወንበር እያቃዣቸው ሳይሆን አይቀርም ያስብላል፡፡

በቃል እየተነገረ በጽሁፍ እየሰፈረ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ ከእኛ ከደረሰውና ለልጆቻችንም ከሚተላለፈው የአባት አናቶቻችንን ብሂላዊ አነጋገር  መካከል “አንበሳው መኝታ ጅቡ ተኝቶበት ይባንን ጀመረ በህልሙ እየመጣበት” የሚለው የእነዚህን  ዘመንኞች አድራጎት የሚገልጽ ይመስለኛል፡፡ ይህን እንደ አዲስ ለማለት ያበቃኝ ሰሞኑን በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የሰማናቸው  የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ነገር ነው፡፡

ከወራት በፊት በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛው ክፍል ቀርበው  አንዳርጋቸው ልማታችንን ማየት አስጎምጅቶት ከተማ እያስጎበኘነው ነው፤ እስር ቤት ላፕ ቶፕ ገብቶለት መጽኃፍ እየጻፈ ነው ከሚለው ጀምሮ ሰሞኑን በሶስት ክፍል በቀረበው  ከቀረቡላቸው ጥየቄዎች ጋር የማይዛመድ ምላሻቸው  የእነ አክሊሉ ሀብተወልድ መንፈስ እያባነናቸው  በቅዠት ውስጥ ሆነው አንጂ በእውን ሆነው በደንብ ነቅተው እያሰቡ የተናገሩት ነው ብሎ ለማመን ይቸግራል፡፡

ዶ/ር ቴዎድሮስ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በድንገት ቀርበው ከተደመጡ በኋላ  የተናገሩትን ሲያስቡ አሳፍሮአቸው ይሁን  ወይንም በድንብርብር የተናገሩት የሚያስነሳው ጥያቄ አስፈርቶአቸው ባይታወቅም ለጥያቄዎ መልስ ፕሮግራም ላይ ለመቅረብ የገቡትን ቃል ሽረው  ቀጠሮ እየሰጡ የውኃ ሽታ ሆኑ፡፡ ሰሞኑን በራዲዮ ጣቢያው በድብቅ ያውም በጨለማ ተገኝተው  ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችን ማነጋገራቸው ይፋ ከሆነ በኋላ  ቀጠሮ ያሰረዛቸው  ፍርሀትም ይሁን ሀፍረት እንዴትና በምን አንደለቀቃቸው ባይታወቅም የሸሹት ፕሮግራም ላይ ተገኝተው በሶስት ክፍል ሰምተናቸዋል፡፡ የሚገርመው ማለት የሚያበዙት ዶ/ር ነገር የሚገርመው  ባለፈው ቃለ ምልልሳቸው   ከተናገሩትም ሆነ ከተነገራቸው የተማሩም የታረሙም ሆነው አለመገኘታቸው  ነው፡፡

በአንድ ነገር ግን ላመስግናቸው አምነውበት ይሁን ወይንም ሰሞኑን ወያኔ የተያያዘው የማስቀየሻ ስልት አካል ይሁን ባይታወቅም ኩራቴ እትዮጵያዊነቴ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ በፍርሀት ይሁን በጥላቻ ኢትዮጵያ የሚለውን የሀገራችንን ድንቅ ስም ላለመጥራት ሀያ አራት አመታት የሀገራችን ሕዝቦች ሲሉ ከምናውቃቸው ሰዎች መካከል  ኢትዮጵያዊነት ኩራቴ ሲሉ መስማት የኢትዮጵያዊነትን ኃያልነት የሚያሳይ ነው፡፡በወያኔ አንደበት ይህ አንዲነገር ያበቃ የኢትዮጵያ አምላክ ይክበር ይመስገን፡፡

በክፍል አንድ መጀመሪያ ላይ ኢህአዴግ ከሕዝብ የሚደብቀው ነገር የለም ይሄ ሊሰመርበት ይገባል በማለት በውሸት የጀመሩት ምላሽ በሶስት ክፍል በውሸት ነው ያለቀው፡፡  እኛ የምናውቀው ኢህአዴግ አይደለም ሌላ ሌላውን ሞትን እንኳን ለመደበቅ የሚታገል መሆኑን ነው ፡፡ የአቶ መለስን ሞት በወቅቱ መግለጽ ያልተፈለገው  ኢህአዴግ ከጫካ ጀምሮ ይዞት በመጣው የድብቅነት ባህርይው  መሆኑን በመግለጽ  አቶ በረከት ትክክለኛውን ኢህአዴግ  በወቅቱ ነግረውናል፡፡  ሥልጣን ላይ ያለነው ለመከብር ሳይሆን ሀገርና ሕዝብ ለማገልገል ነው አሉን፣ እልሰሜን ግባ በለው ነው የሚለው የሀገሬ ሰው፡፡  አቅለው ብለው ቆለለው እንዲሉ ከ96 ሚለዮን ሕዝብ 8. ምናምን ሚሊዮን ቢራብ ምንድን ነው ሲሉም ሰማናቸው፡፡ በክፍል ሶስት እንዲሁ የሚጠየቁትን መመለስ ትተው የቡና ላይ ወሬ የሚያወሩ ይስል አስር ግዜ ምን መሰለሽ ትዝታ እያሉ መለስን ቀጥል ባንለው አይሞትም ነበር፣ እኔ አሁን ከሁለተኛ ተርሜ በኋላ እለቃለሁ ሲሉ አነጋገራቸው ሁሉ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር አልመስል ያላት ጋዜጠኛ  በጤና ጥበቃ ምኒስትርነትዎ እንጠብቅዎት አለቻቸው፡፡ እውነት ብላለች ቢያንስ እዛ ቦታ ሳይሻሉ አይቀሩም፡፡ በአጠቃላይ ጋዜጠኛዋ ትዝታና ዶ/ር ቴዲ አልተገናኝቶም፡፡ ጥያቄና መልሱ  ሀራምባና ቆቦ ነበር ማለት ይቻላል፡፡  ዶ/ር ቴዲ  እነ አክሊሉ  ሀኃብተወልድን የመሰሉ ቀን ከሌት ለሀገራቸው ጥቅምና ክብር ይታትሩ የነበሩ ሰዎች  የተቀመጡበት ወንበር ላይ ተቀምጠው  እያባነናቸው ነው እንዲህ ከእውነት ጋር የሚጣሉት፣ እያቃዡ ለትዝብት የሚዳረጉት አንበል!

የጋጠኞቹ የሙዚቃ ምርጫም ለዶ/ር ቴዎድርስ መልእክት ያለው ነበር፡፡ በተደጋጋሚ የተያዘላቸውን ቀጠሮ ሰርዘው በመቅረታቸው ጋዜጠኞቹ  ይህንኑ ለአድማጮቻቸው ገልጽው በተለያየ መንገድ የደረሱዋቸውን ለዶ/ር ቴዎድሮስ የተጠየቁ ጥያቄዎችን ከአስደመጡ በኋላ ስለሆነ የቀረቡት ለክፍል ሁለቱ መንደርደሪያ ያጫወቱት የሙሀሙድ አህመድን “የዘገየሽበት ምን ይሆን ምክንያቱ” የሚለውን ዘፈን ነው፡፡ ጥሩ ምርጫ፡፡ ዶክተሩ ለተጠየቁት ጥቄ ለአንዱም ቀጥተኛ ምላሽ ባለመስጠታቸውም ይመስላል ጋዜጠኞቹ ወደ ክፍል ሶስቱ ዝግጅት ያንደረደሩን “ፍቅሬ በምን ቋንቋ በምን ቃል ላስረዳሽ” በሚለው የታምራት ሞላ ሙዚቃ ነው፡፡  አዎ ትዝት የራስዋንም የአድማጮችንም ጥያቄዎች ለማስረዳት ብዙ ደክማ አልተሳካላትምና ጥሩ ገላጭ ሙዚቃ ነው የተመረጠው፡፡

ዛሬ ዶ/ር ቴዎድሮስ በተቀመጡበት ወንበር ላይ የነበሩት ጸኃፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ኃብተወልድ ለዚህች ሀገር የደከሙትን በአካል ኖሮም ይሁን የተጻፈ አንብቦ የሚያውቅ  በሁለት ነገር የሚያፍርም የሚያዝንም ይመስለኛል፡፡አንደኛ አንደዛ ቀን ከሌት ማድረግ ከሚገባቸው በላይ ለሀገራቸው የደከሙና በርካታ ውጤታማ ተግባራትን ያከናወኑ ሰው ሊሾሙ ሊሸለሙ ብሎም በክብር ሊጦሩ ሲገባ  ይህችው ሀገር ባፈራቻቸው ጉዶች በግፍ  በመገደላቸው፤ሁለተኛም በርሳቸው ወንበር ላይ እነ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እነ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ሲፈራረቁበት በማየቱ፡፡

እነ አክሊሉ  በአርቆ አሳቢነት አንድ  ያደረጉትን ሀገር  የዶ/ር ቴዎድሮስ ቡድን  በዘረኛ አሰተሳሰቡ  ሁለት አደረገው፤ ከስንት ወሮበላ ነጭ ጋር ታግለው ከስንት ሀገር በቀል ከሀዲ ጋር ተፋልመው ያስከበሩትን የባህር በር ወያኔዎች  የግመል መጠጫ ብለው  እንደ እንደአልባሌ ነገር ጣሉት፡፡ በአለም መድረክ ያስከበሩትን ኢትዮጵያዊነት አዋረዱት፡፡( ዛሬ ኩራቴ ኢትዮጵያዊነቴ ሲሉ ቢደመጡም) በዚህ ዘመን መገኘት እንዴት አያሳፍር! ዶ/ር ቴዎድሮስን እያዩና እየሰሙ የቀደሙትን እዛ ወንበር ላይ የነበሩ ታላላቅ ሰዎች ሲያስቡ እንዴት አይነድ እንዴትስ ውርደት አይሰማ!

ሰለ ዶ/ር ቴዎድሮስ የመዋሸት ድፍረት ምክንያት እያሰብኩ ዛሬ ርሳቸው በተቀመጡበት ወንበር እነማን ነበሩ በማለት በማስታወስ ሳሰላስል የአክሊሉ ማስታወሻ በሚል ርዕስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በ2003 ያሳተመውን መጽኃፍ አገኘሁ፡፡ ጸሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ መስከረም 10ቀን 1967 ዓም ለመርማሪ ኮሚስዮኑ ያቀረቡት ጽሁፍ በሚለው  በዚህ መጽኃፍ ውስጥ  ከብዙ በጥቂቱ የተገለጸው የአክሊሉ ተግባር በርግጥም በወንበራቸው የሚቀመጡትን በተለይም ለቦታው የማይመጥኑትን የሚያባንን የሚያቃዥ ነው፡፡

ወያኔ በማን አለብኝትና በአፍቅሮተ ሻዕቢያ ሰክሮ ያስገነጠላትን ኤሪትሪያን በተመለከተ ያከናወኑትን ተግባር ኤርትራን ለማስመለስ ያደረግሁት ጥረት በማለት  ጸሀፊ ትዕዛዝ እንዲህ ገልጸውታል፡፡

…… ያራቱ መንግሥታት በሎንዶን ተሰብስበው የኢትዮጵያን ሀሳብ እኛ አንሰማለንና በዚህች ቀን አንድትገኝ የሚል መልዕክት አርብ /ሁለት ቀን ሲቀረው/አስታወቁ፡፡ያን ግዜ አውሮፕላን የለን፤ የእንግሊዝ  / B.o.c./  የሚመጣው በሳምንት አንድ ቀን ነው፡፡የትራንስፖርት ችግር ስላለብኝ ለአራትና ለአምስት ቀን አስተላፉልኝ ብዬ ጠየቅሁ፡፡ እነሱም ባልነው ቀን ታልሆነ ብለው ጥያቄየን አልቀበል አሉ፡፡ ችግር ላይ ሆንን፡፡አንድ ትንሽ አይሮፕላን ፤ለጃንሆይ የአንግሊዝ መንግሥት የሰጣቸው ፣አንሬጅስተርድ የሆነች፤ይዤ ለመሄድ ቆረጥሁ፡በሱዳን፤ግብጽ፤ግሪክ፤ፈረንሳይ አገር እያረፈች ቤንዚን በመውሰድ መጓዝ ስላለባት ተነኝህ አምባሰደሮች የተጻፈ ወረቀት ተቀብዬ ቅዳሚት ተነሳሁ፡፡ ሱዳን ደህና ተቀበሉን፡፡ ግብጽ ግን ሉክሶር ስንደርስ ወረቀቱን ባሳየውም “እኛ ተእስራኤል ጋር ጦርነት ላይ ነው ያለነው፡፡ ይህ ወረቀት እውነት መሆኑን አላውቅም፤ፓይለቱም ነጭ ስለሆነ  ታስር ሰዓት /4 afternoon/  በኋላ መብረር ክልክለል ነው፡፡ ስለዚህ በቀጥታ ወደ ካይሮ ሄዳችሁ እዚያ ትመረመራላችሁ ፤ በአውሮፕላን እናስከትላችኋለን አለኝ ” እሽ ብለን ተሳፈርን፡፡ ፓይለቱ ምን ላድርግ አለኝ፡፡ ካይሮ የሄድን  ጊዜ ተሰኞ ቀጠሮ ሊሰናከልብኝና የኢትዮጵያ ጉዳይ ሊበላሽ ነው፡፡ ለፓይለቱ ዝም ብለህ ቀይ ባህርን እየተከተልክ ሂድ፤ ሪስክ ማድረግ አለብን አልኩት፡፡ በዚሁ ዝም ብለን እየሰጋን ተጓዝን ፡፡ሜዲትራኒየን ባህር ስንደርስ እፎይ አልን፡፡ ማታ በጨለማ በ3 ሰዓት ሼፐር ደረስን፡፡ ቤንዚን አለቀብን፤እንድንወርድ ፈቃድ ጠየቅን፡፡ መብራት ስለሌላቸው የካሚዎን መብራት አብርተው ለመውረድ ቻልን፡፡ አዚያም አደርን፡፡በማግስቱ ዕሁድ ግሪክ ደረሰን፤ደህና ተቀበሉን፡፡ ወዲያው ተነስተን ፈረንሳይ አገር ማርሴይ አረፍን፡፡ ቤንዚንም ታልከፈላችሁ አንሰጥም ብለው ያልታወቀ አውሮፕላን ነው በማለትም አስቸገሩን ፡፡ በእንደዚህ አኳኋን እንደምንም ሎንዶን ደረስን፡፡ ይህ አንዱ ምሳሌ ብቻ አንዲሆን ነው፡፡ ( ገጽ 46)

አክሊሉ እንዲህ ያለ መስዋዕትነት ሊያስከፍል የሚችል ርምጃ እየወሰዱ፤በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መድረክ በእውቀትም በዲፕሎማሲያዊ ጥበብም በድፍረትም እየተከራከሩ ነበር የኢትዮጵያን አንድነት አስጠብቀውና  በአለም አቀፍ መድረክ አስከብረው ያቆዩዋት፡፡ በርሳቸው ወንበር የተቀመጡት ግን ተከራክሮ መርታት አይደለም ሲፈረድባቸውና ሲፈረደላቸው አንኳን ማወቅ ተስኖአቸው አለም አቀፉ ፍርድ ቤት ለኢትዮ ኤርትሪያ ግጭት ( የለም ለወያኔ ሻዕቢያ ግጭት ማለቱ ነው እውነት የሚሆነው) ምክንያት ተደርጎ የቀረበውን ባድመን  ለእኛ ተፈረደልን ብለው አደባባይ ወጥታችሁ ደስታችሁን ግለጹ አሉን፡፡ የተወሰነው ለኤርትራ መሆኑ ታውቆ ውሸታው ሲጋለጥም ሀፍረት አልተሰማቸውም፡፡በርግጥ ሀገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል፡፡

The post አገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል፤ በአክሊሉ ወንበር ቴዎድሮስ ተቀምጧል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

መምህር ግርማ ባሳለፍነው ሳምንት – (የጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ ትንታኔ)

0
0

በመምህር ግርማ ወንድሙ ጉዳይ ዛሬም መነጋገሩ መወያየቱ አልቆመም። የፖሊስ የመጀመሪያ ለክስ መነሻ የሆነው መምህሩ ተጠረጠሩበት የተባለው የማጭበርበር ወንጀል ላይ ተጨማሪ ሌሎች ወንጀሎች እየተፈለፈሉ መሆኑን የሰሞኑ የፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ያሳያል። የዕምነቱ ተከታዮች የአገዛዙን በመምህሩ ላይ የሚያቀርበውን ክስ ብዙዎቹ የተቀበሉት አይመስልም። ዛሬም ጎራ ለይተው የሚነታረኩ አሉ። የግራ ቀኙን የአገዛዙን ተጨማሪ ወንጀል ለመፈለግ የሚደረግን ሩቻ ጨምሮ ስለ መምህሩ የተሰጡ ምስክርነቶችን አብረን ቃኝተኛል። ይህ ዘገባ የተዘጋጀው መምህር ግርማ ከ እስር በዋስ ከመለቀቃቸው አስቀድሞ መሆኑን በቅድሚያ ማሳወቅ እንሻለን::

መምህር ግርማ ባሳለፍነው ሳምንት

The post መምህር ግርማ ባሳለፍነው ሳምንት – (የጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ ትንታኔ) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የአቶ ኃይለማሪያም ንግግር የስርዓቱ ኑዛዜ ወይስ ተከትሎ ለሚመጣ ፖለቲካ ሾኬ መንገድ ለመጥረግ? (ቃለ-መጠይቅ ከጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ጋር)

0
0

አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ <<…እዚህ እናወራለን ስንወጣ የራሳችን ኔትወርክ እንዳይነካ እንከላከላለን …>> ሲሉ በምሬት፣ተስፋ በመቁረጥ የተናገሩት ንግግር ዕውነት ለውጥ ለማምጣት ወይስ አቶ ሀይለማሪያም <<እመራዋለሁ>> የሚሉት ገዢ ፓርቲ ወይም አቶ ሀይለማሪያምን ከሁዋላ ሆነው የሚመሩት ለተለመደ የፖለቲካ አክሮባት የተነገሩት ነው? ድምጹን መቶ በመቶ የዘረፉት ሕዝብ ንግግራቸውን ከቁብ ቆጥሮት ሰምቷቸዋል? ንግግሩን ስርዓቱ ወደ መቃብር ከመሄዱ በፊት እንደ ኑዛዜ መቁጠር ይቻላል? ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ የአቶ ሀይለማሪያም ንግግርን መሰረት አድርጎ ከህብር ሬዲዮ ጋር ቆይታ አድርጓል።የአቶ ሀይለማሪያምን ንግግር በቃለመጠይቁ መግቢያ አካተነዋል።

የአቶ ኃይለማሪያም ንግግር የስርዓቱ ኑዛዜ ወይስ ተከትሎ ለሚመጣ ፖለቲካ ሾኬ መንገድ ለመጥረግ? (ቃለ-መጠይቅ ከጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ጋር)

The post የአቶ ኃይለማሪያም ንግግር የስርዓቱ ኑዛዜ ወይስ ተከትሎ ለሚመጣ ፖለቲካ ሾኬ መንገድ ለመጥረግ? (ቃለ-መጠይቅ ከጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ጋር) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

(ሰበር ዜና) መምህር ግርማ ወንድሙ እንደገና ታሰሩ

0
0

Memhir girma
(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው አጥማቂና መምህር ግርማ ወንድሙ ትናንት በ50 ሺህ ብር ዋስ ከተፈቱ በኋላ እንደገና ወደ እስር ቤት መመለሳቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

መምህር ግርማ ትናንት በዋስ የተለቀቁበት ክስ የማጭበበር ወንጀል ሲሆን ሁለተኛ ክስ ደግሞ ቤተክህነት እንደመሰረተችባቸው ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: መምህር ግርማ በቤተክህነት በቀረበባቸው ክስ ህዳር 3 ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሏል::

ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን::

The post (ሰበር ዜና) መምህር ግርማ ወንድሙ እንደገና ታሰሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

Health: ትዳርና እና 3ቱ ገንዘብ ነክ ውሣኔዎች

0
0

 

ለትዳራችሁ ስኬትም ሆነ ውድቀት ጉልህ ድርሻ ካላቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የገንዘብ አያያዝና አስተዳደር ነው፡፡ ትዳር ከመመስረታችሁ በፊት የግላችሁን የገንዘብ አወጣጥ ሥርዓት ስትከተሉ ቆይታችሁ ይሆናል፡፡ ከትዳር በኋላ የሚኖረው የገንዘብም ሆነ የሃብት አስተዳደር ግን የሁለታችሁንም ፍላጎትና ውሣኔ መሠረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡ በጋራ ተቀምጣችሁ በገቢና ወጪያችሁ ላይ እንዲሁም እያንዳንዱ የገንዘብ አቅማችሁ በትዳራችሁ ስኬት ላይ ስለሚኖረው አዎንታዊ ተፅእኖ በግልፅ መወያየት ይኖርባችኋል፡፡ ውሳኔ ከሚያስፈልጋቸው ገንዘብ-ነክ ጉዳዮች መካከል ተከታዮቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

Expensive alliance

የወቅቱ ገንዘብ ነክ ጉዳይ

ጥንዶች ለሠርጋቸው ወጪም ሆነ ለሌሎች ጉዳዮች የተበደሩት ገንዘብ ካለ አጠቃላይ የገንዘቡን መጠን አስልተው የሚከፍሉበትን የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ ይኖባቸዋል፡፡ የሁለታችሁን የጋራ የገቢ መጠን በማስላት ዕዳችሁን በተያዘው ጊዜ ውስጥ ከፍላችሁ በማጠናቀቅ ተጨማሪ ገቢ የምታገኙበትን መንገድ ማመቻቸት ተገቢ ነው፡፡

ኃላፊነቱ የማን ነው?

ገንዘባችሁንበየግላችሁየምታስቀምጡከሆነየሚያስፈልጋችሁን ወጪ ከየትኞቻችሁ ባንክ ማውጣት እንዳለባችሁ በቅድሚያ ተነጋገሩ፡ ፡ ገንዘባችሁ የሚቀመጠው በጋራ አካውንታችሁ ከሆነ ደግሞ ከሁለት አንዳችሁ ገቢና ወጪን የመቆጣጠር ኃላፊነት ብትወስዱ ይመረጣል፡፡ ኃላፊነቱን የወሰደው አካል አስፈላጊውን ገቢና ወጪ በተገቢ መንገድ ካስተዳደረ በኋላ ከሌላኛው አካል ለሚነሱት ገንዘብ ነክ ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡

ቀውሶችን መቋቋም

በትዳራችን ውስጥ ቅድሚያ ለምንሠጣቸው ነገሮች የምንመድበው የገንዘብ መጠንም ከፍተኛ መሆን አለበት፡፡ የወጪያቸውን ያህል ጥቅም ለሌላቸውና ኪሣራቸው ለሚያመዝን ነገሮች ትኩረት መስጠት ውድቀትን ማፋጠን ነው፡፡ ባል ወይም ሚስት አባካኝ ከሆኑ ተቀራርቦ በመነጋገር ችግሩን መፍታት ያስፈልጋል፡፡ ሁለታችሁም ሰራተኛ ከሆናችሁና የገቢ ምንጭ ያላችሁ ከሆነ ምናልባት የአንዳችሁ መታመም ሊያጎድል የሚችለውን ገቢ ከግምት በማስገባት ሌሎቻችሁ ወጪውን መሸፈን አለባችሁ፡፡ በትዳር ውስጥ ልጆች በሚወለዱበት ወቅት በተለይ የልጆች እናት እንክብካቤ የምታደርግበት በቂ ጊዜ ያስፈልጋታል፡፡ ለዚህም ቢያንስ ለሁለት ዓመታት ያህል ሥራዋን ለማቋረጥ የምትገደድበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ በእንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች ሊፈጠር የሚችለውን የገንዘብ ከፍተት ለማሟላት አስቀድሞ መነጋገርና በቂ ገንዘብ በማስቀመጥ ራስን ማዘጋጀት ተገቢ ነው፡፡

ምንጭ፡- about.com (2015)  ቁምነገር መጽሔት ተርጉሞ እንዳቀረበው

The post Health: ትዳርና እና 3ቱ ገንዘብ ነክ ውሣኔዎች appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ሰማያዊ ፓርቲ ህዳር 18 ህዝባዊ ስብሰባ ጠራ • መስተዳደሩ ለ5ኛ ጊዜ ማሳወቂያ ደብዳቤውን አልቀበልም ብሏል • ‹‹መልካም አስተዳደር የሚባለው ከወሬ ያለፈ እንዳልሆነ ያሳያል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

0
0

 

semayawi party

ሰማያዊ ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከአባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር ውይይት ለማድረግ ህዳር 18/2008 ዓ.ም በመብራት ኃይል አዳራሽ ህዝባዊ ሰብሰባ እንደሚያደርግ ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ይሁንና የማሳወቂያ ደብዳቤውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት በአካል ለማድረስ ጥረት ቢደረግም በሰራተኞቹ ዘንድ ለአምስተኛ ጊዜ ‹‹ኃላፊዎቹ የሉም፡፡ እኛ አንቀበልም›› መባላቸውን ም/ሊቀመንበሩ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ‹‹ጠዋት ስንሄድ፣ ከሰዓት ኑ፣ ከሰዓት ስንሄድ፣ ስብሰባ ላይ ናቸው ጠዋት ኑ እያሉ 5 ጊዜ አንቀበልም ብለውናል፡፡›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

‹‹ለአንድ መስሪያ ቤት ደብዳቤ ለማድረስ በመዝገብ ቤት አሊያም በፀኃፊ በኩል መቀበል በቂ ነው፡፡ ኃላፊውን የግድ መጠበቅ አያስፈልግም ነበር፡፡›› ያሉት ኢ/ር ይልቃል ‹‹ይህ አስተዳደራዊ በሆነ መንገድ ህገ መንግስታዊ መብትን የሚያግዱበት ስልት ነው›› ብለዋል፡፡ ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ስለመልካም አስተዳደር በሚያወሩበት በአሁኑ ወቅት አስተዳደራዊ በሆነ መንገድ መብትን እያገዱ መቀጠላቸው መልካም አስተዳደር የሚባለው ከወሬ ያለፈ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው›› ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ለ5ኛ ጊዜ የሰማያዊ ፓርቲን የስብሰባ ማሳወቂያ ደብዳቤ በአካል መቀበል ባለመፈለጉ ፓርቲው ደብዳቤውን በሪኮመንዴ ለመላክ መገደዱን ፓርቲው ለፅ/ቤቱ በላከው ደብዳቤ ላይ አመላክቷል፡፡ በዚህም መሰረት ዛሬ ህዳር 1/2008 ዓ.ም ፓርቲው ማሳወቂያውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት በሪኮመንዴ መላኩን ሊቀመንበሩ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

The post ሰማያዊ ፓርቲ ህዳር 18 ህዝባዊ ስብሰባ ጠራ • መስተዳደሩ ለ5ኛ ጊዜ ማሳወቂያ ደብዳቤውን አልቀበልም ብሏል • ‹‹መልካም አስተዳደር የሚባለው ከወሬ ያለፈ እንዳልሆነ ያሳያል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ርሃብና የነጻነት እጦት በአንድነት –|የሳዲቅ አህመድ ፕሮግራም

0
0
የኢትዮጵያ መንግስት በምግብ እራሳችንን ችለናል ከማለቱ የኢትዮጵያዉያን መራብና ለ አደጋ መጋለጽ እየተዘገበ ነዉ። ቀደም ሲል የተከሰቱትን ድርቆችና የርሃብ አደጋዎች በመርመር ብሎም ወቅታዊ የርሃብ ችግሮችን በማከተት ተዘጋጀ የሳዲቅ አህመድ ፕሮግራም።

Sadik Ahemed Journalist

The post ርሃብና የነጻነት እጦት በአንድነት – | የሳዲቅ አህመድ ፕሮግራም appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ፕሮፓጋንዳው ስብዓዊነት ይኑረው!!! ሰው እየሞተ ነው!! ቁጥሩን ቤቱ ይቁጠረው!!! – ከግርማ ሰይፉ ማሩ

0
0

በሀገራችን ያለው ድርቅ ክብደት ከ1977ጋር የሚመሳሰል እንደሆነ የመንግሰት ሹም ከሸገር ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ምልልስ አረጋግጠዋል፡፡ ልዩነቱ ግን አሁን መንግሰት ይህን ለመቋቋም የሚያስችል አቅም አለን የሚልው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ አቅም ግን መሬት ላይ ወርዶ ስናየ ወኔ ብቻ ይመስላል፡፡ ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ የፈረንጆቹን ደጅ እንዳይጠኑ የሚያደርጋቸው አይደለም፡፡

(ግርማ ሰይፉ)

(ግርማ ሰይፉ)


“ደርግ” በ1977 የነበረፈውን ድርቅ ለዓለም ይፋ አድርጎ የነበረ ሲሆን የዚያን ጊዜ በነበረው ቀዝቃዛ ጦርነት መነሻ በሁለቱ ጎራ በሚደረገው ፍልሚያ ግዳይ የሚጣልብት ወቅት ነበር፡፡ ደርግ ለዓለም ህብረተሰብ ጥሪ ባቀረበበት ወቅት የሶሻሊስቱ ተከታይ በመሆኑ ይህ ጎራ ይህን ድጋፍ የሚያደርግበት አቅም የሌለው ሲሆን ይህን ለማድረግ አቅም ያላቸው ምዕራባዊያን ግን ውጤቱን በደንብ ሳናየው ድጋፍ ላለመስጠት መቁረጣቸው ለችግሩ ክብደት አንዱ እንደ ነበር ለመረዳት ሊቅ መሆን አያስፈልግም፡፡ በተጨማሪ ለ1997 ድርቅ ተገቢው ምላሽ በምዕራባዊያን እንዳይሰጥ በወቅቱ በትጥቅ ትግል ላይ የነበሩት በተለይ ህወሃት እና ሻቢያ የተጫወቱት ሚና ቀላል የማይባል ብቻ ሳይሆን አሁን ላይ ሆነን ስናየው ሰብዓዊነትን ለፖለቲካ ጥቅም እንዳዋሉት ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ የኢህአዴግ መንግሰት ከምዕራባዊያኑ ጋር ያለው ቅርበት ከደርግ እንደሚሻል ስለሚታመን በተጨማሪ ህውሃትና ሻቢያ በዛን ጊዜ የሰሩትን ዓይነት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ለመስራት የሚችል ታጣቂ ሀይል ባለመኖሩ ችግሩን ለመቋቋም በተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ መንግሰት አቅሙ የከብቶቹን ህይወት ለመታደግ ለምን አልተጠቀመበትም? ካልቻለ ደግሞ ምዕራባዊያኑ ድጋፍ ለማድረግ ከፈለጉ አሁንስ ቢሆን ከብቶቹ ሳይሞቱ እንዲደርሱልን ለምን አልተደረገም? የሚለው ጥያቄ ለማንሳት አርብቶ አድር መሆን አይጠበቅብንም፡፡

(Photo File)

(Photo File)


ሁሉም የሚረዳው አንድ ሀገር በድርቅ መቼም ቢሆን ሊጋለጥ ይችላል፡፡ ይህ በዓለም ላይ ተደጋጋሚ ክስተት እንደሆነ ማንም ያውቃል፡፡ ድርቅ ሲኖር ግን ይህን ድርቅ የሌላ ሶሰተኛ ሀገር ድጋፍ ሳይጠየቅ ለመፍታት አቅም መፍጠር መቻል ነው፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ባላት ስነ ምህዳር ከዚህ የተሻለ ማድረግ እና ለሌሎች መትረፍ ይገባት ነበር፡፡ ይህ ደግሞ አሰማት ሳይሆን ሊተገበር የሚችል የሀገር ሉዓላዊነት መገለጫ ነው ብሎ የሚያምን መንግሰት ያስፈልጋል፡፡ ኤክስፖርት የሚደረግ ታንክ ሰራን በፍፁም በዚህ ወቅት ሊያኮራን የሚችል ስ አይደለም፡፡ አሁን የምንረዳው መንግሰት ችግሩን ሪፖርት አድርጊያለሁ ማለትን እንደመውጫ ቀዳዳ እየተጠቀመበት መሆኑን ነው፡፡
አሁን በመሬት ላይ ያለው ሀቅ በምግብ እና ውሃ እጥረት ከብቶች በብዛት እየሞቱ ሲሆን፤ መቼም እንደ እንሰሳቱ በብዛት ሰው እየሞተ እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን አሁን በተፈጠረው ሁኔታ ከምግብ እጥረት ጋር ተያይዞ ቀደም ሲል የነበረባቸው የጤና ችግር አግርሽቶም ይሁን አዲስ ጤና መቃወስ ተፈጥሮ ህፃናት ብቻ ሳይሆን አረጋዊያንም ሆኑ ባለጡንቻው ጎልማሳ የሚሞቱበት ሁኔታ እንዳለ ግን መካድ አይቻልም፡፡ ከዚህ ስንነሳ በምግብ እጥረት ምክንያት ሞት የለም ብሎ ፈሊጥ፤ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ሁለት ህፃናት በቀን ይሞታሉ ያለው ለሌላ ዓላማ እና የሀገር ገፅታ ለማበላሸት ነው የተባለውን የመንግሰት ሹም መግለጫ ስንሰማ ከማፈር ውጭ ምን ልንል እንችላለን፡፡ የመንግሰት ሹሞቸ ፕሮፓጋንዳውን ጋብ አድርገው ሰብዓዊነት በመላበስ እየሞተ ያለውን ሰው መታደግ የግድ ነው፡፡ ስንት ሰው ሞተ ቤቱ ይቁጠረው፡፡

አንድም ሰው በድርቅ አልሞተም የሚል መግለጫ የሰጡትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ቢሆኑ አሁን የተፈጠረው ሁኔታ ከላይ እንደገለፅኩት ቀደም ሲል በአካባቢዎቹ የኖረው ችግር ላይ ሲታከል ሰዎች እንደሚሞቱ መገንዘብ አቅቷቸው ሳይሆን ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የተደረገ መሆኑን ማውቅ ግድ ይለናል፡፡ በዚህ ፕሮፓጋንዳ ማፈራችን እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡ የምናፍረው ደግሞ ከ30 ዓመት በኋላ ድርቅን ለመቋቋም የሚችል ህብረተሰብ ሊገነባ የሚችል ስርዓት መመስረት ያለመቻላችን ነው፡፡ ይህን መንግሰት ዛሬም ስህተቱን “በኤሊኖ” ክስተት አሳቦ በስልጣን እንዲቆይ የፈቀድነው እኛው ነን፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራችን በምንም መመዘኛ አምስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በፈለገ የተራዘመ የተፈጥሮ ችግር ጊዜ ቢሆን እንኳን ምግብ ለመለመን የማትችል ሀገር ለማድረግ የሚያስችል ፖሊሲና ሰትራቴጂ የሌለው መንግሰት እንዳይኖር ማድረግ ካልቻልን ምርጫው የራሳቸን ነው፡፡ ምን ማለት ነው? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ እኛ ከላፈቀድን መሬትን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ፤ ሴፍቲኔት በሚባል የመንግሰት ድጎማ ስር ህዝቡን በተራዘመ ሰንፍና እንዲኖር በማድረግ በአምስት ዓመት በሚመጣ የይስሙላ ምርጫ ካርድ አግኝቶ አገዛዙን ለማራዘም የሚፈልግ መንግሰት ይህን ዓይነት ሰርዓት ሊዘረጋ አይችልም፡፡ እንዲህ ሲያደርገን እንቢ ብለን መከላከል ምርጫው የእራሳችን ይሆናል ማለት ነው፡፡
በተለጠጠ ዕቅድ ተሰፋ ውስጥ (የመጀመሪያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ልብ ይሏል) የከተማ ነዋሪውን ሸምቶ ለማብላት የውጭ ሀገር የሰንዴ ገበያን አማራጭ ያደረገ መንግሰት፤ በሀገር ውስጥ በእርሻ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ዘመናዊ ገበሬዎች እርሻ መሰሪያና ሌሎች ግብዓቶች ድጎማ አድርግ ሲባል ነፃ ኢኮኖሚ ነው ይለናል፡፡ አንድ በዘመናዊ እርሻ ለመሰማራት የሚፈልጉ ዘመናዊ ገበሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰበሰቡት ስብሰባ ላይ ከጎኔ ቁጭ ብለው የነገሩኝ አስደማሚ ነገር “መንግሰት ሰንዴ ለመግዛት በጨረታ የሚያባክነው ጊዜ እና ገንዘብ ለእኛ ድጋፍ ቢያደርግ ለጨረታ ከሚባክነው ጊዜ ባነሰ በሀገር ውስጥ ሰንዴ ለማምረት እንችላለን” የሚል ነው፡፡ ይህን ሀቅ ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ለግብርና ሚኒሰትሩ የኪራይ ስብሰቢዎች ወሬ ነው የሚሆነው፡፡ ግብርና መር ስትራቴጂና ፖሊሲ ብለው ምግብ በሀገር ውስጥ ማሟላት ሳይችሉ ለዘላለም ሊገዙን ሲፈልጉ እሺ ብለን አለን፡፡

ለማነኛው ኢትዮጵያ ሀገራችንን ምድሯ “በኤሊኖ” ክስተት ይሁን በሌላ “ድርቅ” ጎብኝቷታል፡፡ ይህ ድርቅ አድጎ ደግሞ ዜጎችን ህይወት ቀሰ በቀስ እየወሰደ ነው፡፡ ይህን “ችጋር” ለመቋቋም ዜጎች በጋራ መነሳት ይኖርብናል፡፡ ፈረንጆቹ ይህ ውጤት እንዲቀለበስ ከልብ ከፈለጉ አንድም ሰው ሳይሞት ሊደርሱ የሚያስችል ሰርዓት አላቸው ነገር ግን የሰጡት ድጋፍ ህይወት አድን መሆኑ እንዲታወቅ ችግሩ እስኪሰማን ብዙ ሀይወት መጥፋቱ በሚዲያ ታይቶ ቅሰቀሳ እስኪደረግ ሊዘገዩ ይችላሉ፡፡ በዚህ መሃል ምትክ የሌለው የሰው ልጅ ህይወት ያልፋል፡፡ ይህ እንዳይሆን መንግሰት አሁን ከጀመረው ተራ ፕሮፓጋንዳ ወጥቶ ወደ ቀጥተኛ ህዝቡን ያሳተፈ ምላሽ እንዲሰጥ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

The post ፕሮፓጋንዳው ስብዓዊነት ይኑረው!!! ሰው እየሞተ ነው!! ቁጥሩን ቤቱ ይቁጠረው!!! – ከግርማ ሰይፉ ማሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

“የድርቁ ጉዳይ እንቅልፍ ነስቶኛል!…የህዝብ መሆናችን የሚረጋገጥበት ሰዓት አሁን ነው”– (ቴዲ አፍሮ)

0
0

teddy afro
እንዳንቀደም !
(ቴዲ አፍሮ)

የድርቁ ጉዳይ እንቅልፍ ነስቶኛል!

አንድ በጣም ሚገርመኝ ነገር አለ ፣ እኛ አርቲስቶች ትንሽ እውቅና ስናገኝ መንግስትን መተቸት ይቀነናል ። መንግስትን መተቸት ካለብን መተቸቱ ትክክል ቢሆንም ፣ መንግስትን መተቸት ብቻ ለኢ/ያ ህዝብ ጉርሻ ዳቦ የሚሆነው አይመስለኝም። ሁሌ ከመንግስት ጋር አተካራ ከመግጠም ይልቅ መጀመርያ የራሳችን ድራሻ ተወጥተን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን አንድ ነገር እንስራ !

በእውነቱ በየሚድያው ህዝቤ ወገኔ እያልን ስንነግድለት የነበረው ህዝባችን ነው ረሀብ እያንካካው ያለው።

የህዝብ መሆናችን የሚረጋገጥበት ሰዓት አሁን ነው! አዎ አሁን በክፉው ቀን ህዝባችን ባጣበት እጁን ባጠረበት ያውም ብዙ የለመደ!!

እንደ ከዚህ ቀደሙ በአውሮፓም በአሜሪካም ያሉትን የጥበብ ሰዎች እንዳይቀድሙን ፣ የአለም መሳቅያ እንዳንሆን ሰጋሁኝ !

“እኛ ነን አለም” ይህ መፈክር ብዙዎቻችን የምናውቀው ይመስለኛል። ሀገራችን በ1977 በድርቅ ስትጎዳ የሀገራችንን ህዝብ ለመታደግ የአለም አርቲስቶች በታዋቂው እንግሊዛዊው ዘፋኝ ቦብ ጊልዶፍ አስተባባሪነት የተዘጋጀ የኮንሰርት ስያሜ ነው።

በዚህ ዘመን ያንን አይነት ድምበር ዘለል ድጋፍ የምንጠብቅበት አይደለም እንደውም ያልተከፍፈለ እዳ ያለብን ሆኖ ይሰማኛል።

በተከሰተው የድርቅ አደጋ የተጎዳ ወገናችን መርዳቱ የመግስት ሰራ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮያዊ ትብብርና ድጋፍ ይጠይቃል። የማይቻል የለም ራሳቸን በራሳቸን ከተባበርን ህዝባችን ከረሀቡ ልንታደገው እንችላለን !

ስለሆነም እኛ አርቲስቶች የተለያዩ ኮንሰርቶችን በማዘጋጀት የበኩላችን አስተዋፆ እንድናደርግ ጥሬዬን አቀርባሎህ።

ቸሩ እግዚአብሔር አምላክ ቅድስቲትዋ አገራችን ኢትዮጵያ ሰላምዋን ጠብቆ ለዘላለም ያኑርልን።
ፍቅር ያሸንፋል

The post “የድርቁ ጉዳይ እንቅልፍ ነስቶኛል!… የህዝብ መሆናችን የሚረጋገጥበት ሰዓት አሁን ነው” – (ቴዲ አፍሮ) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በኢትዮጵያ ውስጥ መታተም ያልቻለውን አዲሱን “ድርጅታዊ ምዝበራ ”መጽሐፋቸውን በአገር ቤት እንዲነበብ በኢንተርኔት በነጻ ለቀቁት 

0
0

Dr_Akelog_book_cover_front_001

የቀድሞ የኣለም ባንክ የኢኮኖሚ አማካሪና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኢኮኖሚያዊ  ጉዳዮች ላይ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማቅረብ የሚታወቁት ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በአሜሪካን አገር ታትሞ በአማዞን ላይ ዛሬም ድረስ በ22.44 ዶላር ሚሸጠውን <<ድርጅታዊ ምዝበራ የኢትዮጵያ<<እድገታዊ መንግስትና>> የስልጣን ባለጸጋዎች ኢኮኖሚ የተሰኘውን  መጽሐፍ በአገር ቤት እንዲነበብ ለማድረግ ለማሳተት ያደረጉት ጥረት መቶ ሺህ ብር ጭምር አሳጥቷቸው ያልተሳካ ቢሆንም በኢንተርኔት አማካይነት በነጻ እንዲነበብ በዛሬው ዕለት መፍቀዳቸውን የመጽሐፉን ቅጂ በመላክ ለህብር ሬዲዮ ገለጹ።

ዶ/ር አክሎግ አስቀድሞም በኢትዮጵያ ለማሳተት የታሰበው በአነስተባ ዋጋ ተሽጦ ያሳተሙት ወገኖች ተጠቃሚ ሆነው ነገር ግን ወጣቱ ትውልድ በአገሩና በሕዝቡ ላይ የሚፈጸመውን ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ፣የተደራጀው የአገሪቱ ሀብት ዘረፋና በሙስና የማይጠየቀው ሀይል በስልጣን መዳድሉ ላይ መኖር፣ አገሪቱ እየገባችበት ያለው አጣብቂኝ፣ስር የሰደደ ድህነትና ከዚህ አስከፊ ሁኔታ ለመውጣት ሚቻልባቸው ዝርዝር በጥናት ላይ የተመሰረተና በመረጃዎች የበለጸገው ይሄ መጽሐፍ በአገር ቤት ተነባቢ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚአደርጉ ከዚህ ቀደም ለህብር ሬዲዮ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ መግለጻቸው ይታወሳል።

የዶ/ር አክሎግ ቢራራን ሙሉውን መጽሐፍ ለማንበብ የፒዲኢፍ ፋይሉን ይክፈቱ ወደ አገር ቤት በወዳጆችዎ አማካይነት ያሰራጩ። 

 

The post ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በኢትዮጵያ ውስጥ መታተም ያልቻለውን አዲሱን “ድርጅታዊ ምዝበራ ” መጽሐፋቸውን በአገር ቤት እንዲነበብ በኢንተርኔት በነጻ ለቀቁት  appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

“መልካም አስተዳደርን እውን ለማድረግ ድክመትንና ስህተትን ከመቀበል ያለፈ እርምጃን ይጠይቃል”–ሸንጎ

0
0

shengo
በአለፉት ቀናቶች በልዩ ልዩ የሚዲያ ዘርፎች ሲስተናገድና ትችት ሲሰነዘርበት የከረመው ጉዳይ በቅርቡ የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ስለመልካም አስተዳደርና ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ለመቀራረብ ፍላጎት እንዳላቸው በሰጡት መግለጫ ዙሪያ ነበር። ትልቁ የአንድነት ሀይሎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ጉዳዩን ተከታትሎና ሊያስከትል የሚችለውን ጥቅምና ጉዳት በመመርመር የሚከተለውን አቋም ወስዷል።

በአገሪቱና በሕዝቡ ላይ የደረሰው በደል ተጠራቅሞ ወሳኝ ደረጃ ላይ በመድረሱ የተነሳ መንግስት እራሱ በአስተዳደሩ ውስጥ የሚታዩ ጉድለቶችን የሚያጠና የባለሙያዎች ቡድን ለማቋቋም ተገዷል።ሸንጎ በመንግስት የተቋቋመው ቡድን ሰፊ ጥናት አድርጎ ያቀረበውን ዘገባ ይፋ በማውጣቱ ነቀፋና ተቃውሞ ባይኖረውም የተደረሰበት ጥናትና የቀረበው ሃሳብ በተግባር መገለጽ እንዳለበት ፣ያ ካልሆነ ግን ለይስሙላና ለማደናገሪያ ብሎም ጊዜ መግዣና ተቃውሞን ለማለሳለስ የተደረገ እርምጃ ሆኖ እንደሚቀር ከወዲሁ ለማሳሰብ ይወዳል።
አሁን አገዛዙ በይፋ ያወጣው ውስጣዊ ድክመት ሸንጎና የተቃዋሚው ጎራ ላለፉት ዓመታት እያነሱና እያጋለጡ ሲታገሉበት የነበረ ፣ ሕዝቡም በአንክሮ የሚያሰማው ብሶት በመሆኑ በስልጣን ላይ ያለው አካል ጥፋቱንና ድክመቱን ከማመን ሌላ አማራጭ ስላላገኘ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ ያለበትን ውስጣዊ ድክመት ለመቀበል ተገዷል።እዚህ ላይ መቀበል ማለት መፍትሔ መሻትና በተግባር መግለጽ እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል።

ፎቶ ምንጭ: ሪፖርተር ጋዜጣ

ፎቶ ምንጭ: ሪፖርተር ጋዜጣ

ሆኖም ግን አይኔን ግንባር ያድርገው ወይም የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ከሚለው የተለመደ የክህደት አቋም የተለዬ በመሆኑ አንድ እርምጃ ወደፊት የመሄድ ያህል ይቆጠራል።ጥናቱ ሁሉንም ከመልካም አስተዳደር ጋር የተዛመደ ጉዳይ በተለይም በፖለቲካው ዙሪያ ያለውን መጠነ ሰፊና ዘግናኝ በደል የሚያነሳ ባይሆንም በአገልግሎት ዘርፍ፣በኢንቨስትመንት በመሬት ይዞታና ስርጭት፣በቀረጥና ግብር አሰባሰብ ዙሪያ ስርአቱ የሚስተናገደውንና ከላይ እስከታች የተንሰራፋውን የሙስና ሰንሰለትና ንቅዘት የሚያጋልጥ ነው።
በፍትህና አስተዳደር ዙሪያም ላይ ያሉትን ድክመቶች እጅግ በተወሰነ መልኩ ነካ ነካ አድርጓል።ጥናቱ ተጠናቆ የመንግስት ተጠሪዎች ጋር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባካሄዱት ውይይት ላይ እንደታየው የጥናቱ ደጋፊዎች የቀረበው ጥናት ሁሉንም ያካተተ አለመሆኑንና እንደውቅያኖስ ጥልቀትና ስፋት ካለው ችግርና የመንግስት አሰራር ጉድለት ውስጥ በማንኪያ የተጨለፈ ነው በማለት ይበልጥ በቀሩት ጉዳዮች ላይ ጥናቱ እንዲቀጥል ሲናገሩ አንዳንዶቹ ደግሞ የጥናቱ ሰለባ የመሆን እድል የሸተታቸው ይመስላሉ የቀረበው ጥናት በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በማለት ለማጣጣልና ደግሞ እንደተለመደው ሁሉ ለመሸፋፈን ሲሞክሩ ተሰምተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመደምደሚያ ሃሳባቸው እያንዳንዳቸው የመንግስት ባለስልጣኖች የችግሩ ምንጭና ባለቤቶች መሆናቸውን ”ችግሩን የፈጠርነው እኛው ነን፤እራሳችን ልዩ ልዩ የጥቅም ሰንሰለቶች ስላሉን እነሱ እንዳይፈርሱብን ወይም እንዳይነኩ አሁን በስብሰባ ላይ የተነጋገርነውንና የተስማማንበትን ጉዳይ ከስብሰባው ስንወጣ በተግባር እንዳይገለጽ አናደርጋለን” በማለት ስርዓቱና የስርዓቱ ተጠሪዎች ለደረሰው ጥፋትና ውድቀት ተጠያቂ መሆናቸውን አምነዋል።አቶ ሃይለማርያም እንዳሉት ባለስልጣኖቹ በተለመደው አሰራራቸውና የግል ጥቅማቸው ውድድር ከቀጠሉበት አንድ ቀርቶ አስር ጥናት ቢካሄድ ለውጥ አይመጣም። ይህ ደግሞ የሀገራችንን ሀብት የጥቂቶች መደለቢያ ከማድረግም አልፎ ሀገራችን፤ ህዝባችንና መጭውም ትውልድ ለዘመናት ወደማይወጡት አዘቅት እንዲያመሩ ያደርጋል።

ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራትም ያለው ፍላጎት ከቃላት አልፎ እውነት የሚሆነው በስበብ ባስባቡ ካለምንም ማስረጃ በእስርቤት የታጎሩት ጋዜጠኞች፣የፖለቲካ ድርጅት ተጠሪዎችና ደጋፊዎች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ተለቀው በፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው፣እምነታቸውና በሙያቸው ላይ ካለምንም ተጽእኖ ለመስራት የሚችሉበት ሁኔታ ሲፈጠር ነው።ያ በተግባር ሳይታይ፣ሕዝብ የሚያምናቸውና የሚከተላቸው እውነተኛ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ጠፍንጎና አሸብሮ፣በሰርጎ ገብ አዳክሞ፣ በቃላት ብቻ ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ሰላም እፈጥራለሁ፣ለለውጥ ተዘጋጅቻለሁ ብሎ መናገርና ጥናት ማዥጎድጎድ፣ በተቃዋሚ ድርጅቶች ስም ለስርዓቱ ቅርበትና አድናቆት ያላቸውን ቡድኖች ሰብስቦ መወያየትም የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት አይደለም። አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት እርምጃ ወደዃላ ይሆንና በጥፋት ላይ ጥፋት እየተቆለለ አገር አፍራሽ ሱናሚ ይሆናል።

ሸንጎ አሁን በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው መጠነ ሰፊ ስብራት፣በመንግስት ባለስልጣኖች ዙሪያ የሚታየው አይን ያወጣ ዘረፋ፣ የጥቅም ሽኩቻና የእርስ በርስ አለመተማመን የአጠቃላዩ የስርዓቱ ብልሽት ውጤት እንደሆነ ያምናል።ይህም በአገሪቱና በሕዝቡ ላይ የደረሰው ችግርና ስብራት ለዘለቄታው ሊወገድ የሚችለው የጥፋቱ ተጠያቂ የሆነው መንግስት አንዳንድ ለውጥ አድርጎ በስልጣን ላይ በመቆየቱ ሳይሆን፤ የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍቶ በልዩልዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ተሳትፎና ነጻ የሕዝብ ምርጫ የመንግስት ለውጥ ሲመጣ ብቻ ነው። ወደዚህ የሚወስደውን ጎዳና ለማመቻቸት ደግሞ እስካሁን እንቅፋት የሆኑትን ጉዳዮች ነቅሶ በማውጣት እንዳይደገሙ ለማድረግ የሚያስችል ግልጽና ሰፊ አገራዊ መግባባትንና ብሄራዊ እርቅን ተጋባራዊ ማድረግን ይጠይቃል። ለዚያም ሸንጎ ይታገላል።

በአገሪቱ የሚታየው የመልካም አስተዳደር እጦት በአገልግሎትና በመሬት ባለቤትነትና በሀብት ዝርፊያ ዙሪያ ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በሰባዊ ና ዴሞክራሲ መብቶች ፣ በአገሪቱ አንድነትና በሕግ የበላይነት፣በተቃዋሚ ሃይሎች ድርሻ፣ የተሳትፎና የመንቀሳቀስ መብት ዙሪያ ጭምር ነው። መልካም አስተዳደርን እውን ለማድረግ ከቃላት አልፎ የሚታየው የመንግስት እረገጣ ተወግዶ በተግባር መታየት ይኖርበታል።

መልካም አስተዳደርን እውን ለማድረግ የፍትህ አካሉ ከመንግስት ጫና ነፃ መሆን ይኖርበታል። ለህዝብ መብት ተሟጋች የሆኑ የሲቪክ ድርጅቶችን ለማፈንና ለማገድ የወጣው ህግና የአሸባሪነት ህግ ህዝቡ እንዳይናገርና እንዳይደራጅ የሚያግዱ በመሆናቸው መሰረዝ አለባቸው። ያለ ህዝብና ሲቪክ ድርጅቶች ነፃ ተሳትፎ የኢህአዴግን ያህል በሙስና የነቀዘና በጎሳ የተዋቀረ ስርዓት ማስተካከልና ድክመቶቹን ማስወገድ በፍፁም አይቻልም። ይህን ሁሉ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ሙሉ ለሙሉ ይፈጽመዋል ባይባልም በውስጡ ያሉና የያዙት መንገድ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ የተረዱ ባለስልጣኖችና ደጋፊዎች ሰልፋቸውን ከሕዝቡ ጋር እንዲያስተካክሉ ሸንጎ ጥሪና ምክር ያቀርብላቸዋል።

የተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅቶችም መንግስት አምኖ የተቀበለውን ጥፋትና ድክመት ተሸክሞ እንዳይቀጥልበት ሃይላቸውን አስተባብረው በሀገራችን አንድነት ስር ለስርዓት ለውጥ ሕዝቡን ለማደራጀት ቆርጠው መነሳት ይኖርባቸዋል። የለውጥ መስኮት ከተከፈተ ያንን ቀዳዳ በር ለማድረግ አንድ ላይ ተባብረው ሊታገሉ ይገባል። በመንግስት አካሄድና ስልት ላይ በጋራ መወያየትና መልስ ሊሰጡበት ይገባል።እንዳለፈው ጊዜ በራሳቸው ጠባብ ድንኳን ወይም የፖለቲካ ገዳም ውስጥ መሽጎ መቀመጥን ከመረጡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የችግሩ ተጠያቂዎች ይሆናሉ። ላለውም ስርዓት ቀጣይነት አስተዋጽኦ ማድረግ ይሆናል። ስለሆነም በተከሰተው ሁኔታና በአገሪቱ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ከሁሉም ያገባኛል ባይ ድርጅት ግለሰብና ስብስብ ጋር በየትኛውም ቦታና ወቅት ለመወያየት ሸንጎ ዝግጁና ፈቃደኛ መሆኑን ይገልጻል።

ለሰላማዊ ሕዝባዊ የትግል እንቅስቃሴና ለውጥ እንነሳ!
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ

The post “መልካም አስተዳደርን እውን ለማድረግ ድክመትንና ስህተትን ከመቀበል ያለፈ እርምጃን ይጠይቃል” – ሸንጎ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

እንግዲህ ህዝቡን ለማዳን ከፈለጋችሁ እርዳታዉን ከፖለቲካዊ ዉሳኔ አላቁ : አጋራችሁ የሆነዉንም የአለም አቀፍ እርዳታ ሰጭ ሀይልም ይቅርታ ጠይቁ

0
0

ሸንቁጥ አየለ

-መንግስት በምግብ እራሳችንን ችለናል እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች: አለም አቀፍ ድርጅቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አፋችሁን ያዙ : ከፈለጋችሁም ጨርቃችሁን ጠቅልላችሁ ዉጡ እያለ በየመድረኩ ዘለፋና ስድብ ከጀመረ አመታት አለፉ::

-በሴፍቲኔት እና በልዩ ልዩ የእርዳታ መልክ ባላቸዉ ፕሮግራሞች በየአመቱ ከ17 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዉያን በእርዳታ ጥገኝነት በየአመቱ እንደኖሩ መንግስት እያወቀ አጉል እብሪት ዉስጥ ገብቶ ለጋሾቹን ሁሉ ያንጓጥጥ ገባ::

Ethiopia12

-ብዙ ሚሊዮን ብሮች እየባከኑ በየአመቱ በርካታ መንግስታዊ: መንግስታዊ ያልሆኑን እና አለም አቀፍ ድርጅቶች የሚሳተፉበት አመታዊ የምግብ ዋስትና ጥናት እየተካሄደ የሚራበዉ ህዝብ 6 ሚሊዮን ነዉ ወይም ሰባት ሚሊዮን ይሆናል እያለ ጥናታዊ ሰነድ ሲቀርብላቸዉ የመንግስት ባለስልጣናት ግን ባለሞያዎችን እያንጓጠጡ እና እየተሳደቡ ጥናቱን ዉድቅ በማድረግ የጥናቱ ዉጤት ከሚያሳዬዉ በግማሽ እና በሶስት እጅ እየቀነሱ የተራበዉ ህዝብ 4 ሚሊዮን ነዉ አንዳንዴም ሁለት ሚሊዮን ነዉ ሲሉ እረዥም አመታት አሳለፉ::

-አለም አቀፍ የእርዳታ ህግ እንደሚያዘዉ የምግ ዋስትና ሲደረግ ሊረዳ የሚገባዉ ሰዉ መቆጠር ያለበት እንደግለሰብ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ መንግስት ግን አስርም : አምስትም የቤተሰብ አባላት ያለዉን አንድ ቤተሰብ እንደ አንድ ሰዉ ይቆጥራና ለአስር የቤተሰብ አባላት እርዳታ ማድረግ ሲኖርበት የአንድ ሰዉ እርዳታ ይመድባል:: ይሄን አሰራር በመቃወም የምግብ ዋስታና ባለሞያዎች በየመድረኩ ይጮሃሉ:: ባለስልጣናቱን ለማስረዳት ይደክማሉ:: በተለይም አመታዊ ጥናት ሲደረግ በርካታ ደፋር የሆኑ እንዲሁም የብዙ አመታት ልምድ ያላቸዉ የምግብ ዋስትና ባለሞያዎች ከተባበሩት መንግስታት ድርጅቶችም: መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችም እንዲሁም ከመንግስት መስሪያ ቤትም ተሰባስበዉ ስለሚገናኙ ጉልበታቸዉን አሰባስበዉ እንደ ባለሞያ ብዙ ለመምከርና ለማስረዳት ይሞክራሉ:: ግን የሚሰማቸዉ የለም:: ብዙ ጌዜ በእርዳታ ጠባቂነትና ፈላጊነት ይተቻሉ::

-ከፌደራል እና ከክልል ባለስልጣናት በየወረዳዉ ላሉ ትንንሽ ባለስልጣናት የሚሰጠዉ መመሪያ ደግሞ ሰዉ እየተሰደደ እየተፈናቀለ እና እየሞተ እንኳን እርሃብተኛ የለም ብላችሁ መልሱ የሚል ነዉ:: በጣም ብዙ ድርጅቶች እርዳታ ይዘዉ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ:: ብዙዎቹም ያመጡትን እርዳታ ተረጅ የለም በሚል መጨረሻ ወደ ሌላ ሀገር ያስተላልፋሉ:: ለዚህ ጥሩ ማስረጃ የሚሆነዉ እኔ የምሰራበት ፕሮግራም ነዉ:: የዛሬ አራት አመት 1.5 ሚሊዮን ህዝብ መርዳት ያስፈልጋል የሚል ጥናት አጥንተን በቂ እህል ከዉጭ በፕሮግራሙ ታዘዘ:: ብኋላ ግን ፕሮግራሙ ሊረዳ የሚችለዉ አምስት መቶ ሽህ ህዝብ ብቻ ነዉ ብሎ መንግስት ስለወሰነ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ የታዘዘዉ እህል በዚያዉ ቀረ:: ልብ በሉ ተጨማሪ አንድ ሚሊዮን ህዝብ በአንድ ፕሮግራም ብቻ ሊረዳ ሲችል : በቂ እርዳታ እህልም ከአሜሪካ መንግስት ተገኝቶ ሳለ : እኛም ያጠናነዉ ጥናት ተጨባጭ ሆኖ ሳለ ነዉ መንግስት ተረጅ እያለ ተረጅ የለም በማለት አምስት መቶ ሽህ ህዝብ ብቻ እርዱ ያለዉ:: በየወረዳዉ በርካታ እርዳታ ፈላጊ ህዝብ የእርዳታ ያለህ እያለ ይጮህ እንደነበረ እኛም መንግስትም እናቃለን::

-አንዳንዴ ፈረንጆቹ የሚጠይቁት ጥያቄ ፈገግ ያደርጋል:: “መንግስት ግን እንዲህ የሚያደርገዉ ለምንድን ነዉ ?” ይላሉ:: መልሱን እኔም ሆንኩ በርካታ ኢትዮጵያዊ አያዉቀዉም:: የመንግስትን ልብ በመብላት ተቋዳሽ ነን የሚሉ ወይም እራሱ የመንግስት ልብ ነን የሚሉ ሰዎች እራሳቸዉ ያዉቁትም እንደሆነ አላቅም:: ግን ፖለቲካ ነዉ ይሉታል:: ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሳይንስ ሳይሆን ስሜት: ሆድ : ጥላቻ መሰረት ላይ የቆመ እይታ: ጠላትን በመደባዊ ትግል ለመደምሰስ ሁሉንም ጠጠር ህዝብ ላይ የመወርወር አመለካከትና የፍርሃትን ጎዳናን መከተል እንደሆነ ግን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወደ ጎርጁ ገብቶ የተነተነ ሰዉ ያዉቀዋል::

-በተለይ አዳዲስ የዉጭ ሀገር ሀላፊዎች ተሾመዉ ሲመጡ የኢትዮጵያ መንግስት ባህሪ እስኪገባቸዉ ብዙ ጥያቄ ይጠይቃሉ:: የመንግስት ባለስልጣናት ሲፈልጋቸዉ ተረጅ የለም ይላሉ:: አንዳንድ መድረክ ላይ ደግሞ ለርዳታ የሚሆን እህል ስለሌለን የተረጅ ቁጥር ቀንሱ እያሉ ወረዳዎች ላይ ይጮሁባቸዋል:: እንዲያዉም የተረጅ ቁጥር ከፍ

ካደረግን ለእርዳታ የሚሆን እህል ስለማናገኝ ነዉ ተረጅ የምንቀንሰዉ ሲሉ ለአንዳንድ ትልልቅ የአለም አቀፍና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሀላፊዎች ይናገራሉ::እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በርከት ያለ እርዳታ ለመስጠት በቂ ጥናት አድርገዉ ሲመጡ ደግሞ ያመጡትን እህልና ቁሳቁስ እንዲመልሱ መንግስት ያዛል:: ከዚህ የባሰ ምን ዉስብስብ ነገረ አለ?

-ከዛሬ አራት አመት በፊት የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት ሀላፊዎች በተለያዩ ክልልሎች ዉስጥ ባሉ ልዩ ልዩ ወረዳዎች እንቅስቃሴ በማድረግ ያለዉን ችግር ማሰስ ጀመሩ:: የወረዳ ሀላፊዎች በስብሰባ ላይ ተረጅ የለም ሲሉ ይናገራሉ:: እሻይ ላይ ወይም የአሜሪካ እርዳታ ድርጅት ሃላፊዎቹን ለብቻቸዉ ሲያገኟቸዉ ግን ህዝቡ እየሞተ ነዉ እርሃብ ሰዉን ጎዳዉ ሲሉ ይናገራሉ:: በአንድ አፍ ሁለት ምላስ ይሆናሉ::

-እንዴዉም አንድ ቆፍጣ የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት ሀላፊ የኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሞያዎችን ይተች ነበር:: እንዲህ ሲል:: “እናንተ ምን ያስፈራችኋል :የምታመጡት ጥናት እዉነታዉን አያረጋግጥም:: መሬት ላይ ያለዉ ችግር ብዙ ነዉ:: የእናንተ ጥናት ግን የሚናገረዉ ሌላ ነዉ:: ” ሰዉዬዉ በሙሉ የሀገሪቱን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራ ሲተች ደፋር ነበር:: አንዳንድ ባለሞያዎች ታዲያ የችግሩን ምንጭ ሊያስይስረዱት ቢሞክሩም አይሰማቸዉም ነበር::

-በተግባር እመሬት ላይ ወርዶ ችግሩን ካዬዉ ብኋላ ግን የኢትዮጵያ መንግስት እንዴት ዉስብስብ ባህሪ እንዳለዉ ገባዉ መሰለኝ ዝም አለ:: ነገሩ እንዲህ ነዉ:: ሰቆጣ ወረዳ አማራ ክልል ላይ ሰዎች እየሞቱና በብዛት ወደ ልዩ ልዩ ቦታም እየተሰደዱ ባለበት ወቅት ይሄዉ ቆፍጣና ሰዉ ወደ ወረዳዉ ጉብኝት አደረገ:: መሬት ላይ ያለዉን የወረዳዉን ችግር በደንብ መዝግቦ ለስብሰባ ከወረዳ ባለስልጣናት ጋር ቁጭ አለ:: ሆኖም ከወረዳ ባለስልጣናት ጋር ሲቀመጥ ሽምጥጥ አድርገዉ ካዱት:: “አንድም ችግረኛ የለም : የተራበም የለም : የተሰደደም የለም” ሲሉ ካድ አደረጉት:: ቆፍጣናዉ ሰዉዬ ተናደደ:: መረጃዎቹን አቀረበ:: እናም የወረዳዉ ባለስልጣናት እንዲህ አሉ:: “በርግጥ ጥቂት ወደት ትግራይና ወደ ጎዳም እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ የተሰደዱ ጥቂት የወረዳዉ ሰዎች አሉ:: ከዚያ ዉጭ ግን በወረዳችን የተራበ የለም::” ይሄ ቆፍጣና ሰዉ ጥሏቸውዉ ብድግ ብሎ እቃዉን ሰብስቦ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ:: በተመሳሳይ ወደ ወላይታ ሶዶም ደቡብ ክልል ሄዶ ተመሳሳይ ገጠመኝ ገጠመዉ:: ብዙ ወረዳዎች ዉስጥ በተመላለሰና እዉነታዉን እና የወረዳ ባለስልጣናት : የክክልል ባለስልጣናት እንዲሁም የፌደራል ባለስልጣናት የሚናገሩትን እያነጻጸረ ካስተዋለ ብኋላ ነገሩ ሲገባዉ ዝም አለ:: እዉነቱን ነዉ:: ምን ያድርግ? እርሱ ኢትዮጵያ ያለዉ መንግስት እርዳታ ሲፈልግ ለማገዝ እንጅ አስገድዶ ለመርዳት አይደለም:: ከዚያ ጊዜ ብኋላ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ላይ መበሳጨቱን አቆመ::

-እንዴዉም የወረዳ ባለስልጣናት ከላይ ከፌደራል መንግስት እና ከክልል ባለስልጣናት በሚደርስባቸዉ ጫና ግራ እስከመጋባት እና የሚናገሩትን እስካለማወቅ ይደርሳሉ:: አንዳንዴ እነዚህን ትንንሽ ባለስልጣናት መተቸት ነዉር ሆኖ የሚሰማኝ ጊዜ አለ:: ግን እዳዉና መከራዉ ሁል ጊዜም የሚያርፈዉ እነሱ ላይ ነዉ::በተለይ የደቡብ እና የአማራ ክልል ወረዳ ባለስልጣናት ከህሊናቸዉ ጋር ሁሌ እንደተሟገቱ ነዉ:: ያለፉት ሁለትና ሶስት አመታታን ደቡብ ክልል በየወረዳዉ ስንት ችግረኛ እያለ አንድም ተረጅ የለኝም ወደማለት ሄዶ ነበር:: አማራ ክልል 100 የሚረዱ ሰዎችን አስቀምጦ አንድ ተረጅ ብቻ ነዉ ያለኝ ወደ ማለት ተራምዶ ነበር::

-አንዳንዴም የወረዳና የክክልል ባለስልጣናትን አንዳንድ ደፋር የምግብ ዋስትና ባለሞያ አንቆ ሲይዛቸዉ ሰዉ እስካልሞተ ድረስ እርዳታ አንፈልግም: ቢራብም ያለዉን ከብት ሸጦ ይብላ ሲሉ ይቆጣሉ:: በተወሰነ ደረጃ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ጥቂት ምክናያታዊ ለመሆን ይሞክራሉ:: የኦሮምያ ባለስልጣናት እኔ እንዳዬሁት ደፍረዉ ለመወሰን ቢፈሩም ቢያንስ እንዲህ ይሁን ብሎ ደፍሮ የሚወስንላቸዉና ድምጹን ከፍ አድርጎ የሚጮህ ባለሞያ ሲያገኙ ከመሳደብ ይቆጠባሉ:: የአማራ ክልል ባለስልጣናት ባለሞያዎችን ማንጓጠጥ ይቀናቸዋል:: በተለይም መንግስታዊ ያልሆኑና አለም አቀፍ ድርጅቶች የሚያቀርቡትን ሀሳብ ለማጣጣል ወሳኝ ናቸዉ:: ህዝባቸዉ እያለቀ ጠላት የሞተ ሳይመስላቸዉ አይቀርም:: ሌሎቹ ክልሎችም እንዲሁ የተለያዬ ባህሪ አላቸዉ:: አጠቃላይ የኢትዮጵያ ክልልሎች ባለስልጣናት የጋራ መገለጫ ግን ሁል ጊዜ ዉሳኔን በፖለቲካ መነጽር መቃኘት እና እዉሳኔአቸዉ ላይ ሀስት እና ማስመሰል መጨመራቸዉ ነዉ:: ለባለሞያ ንቀት እሁሉም ክልልሎች ጋ አለ:: ፌደራል ላይ ባለሞያን በለበጣ እና በሾርኔ የማዬት ካንሰር የሆነ እይታ አለ:: የምግብ ዋስትና ባለሞያዎች ፈጽሞ የሞያ ነጻነት የላቸዉም::

-ከሁሉም የሚያሳዝነዉ ነገር አንዳንድ ባለሞያዎች አሉ መንግስት የሚወስነዉ ዉሳኔ ሀሰትና ዉሸት እንደሆነ ሲያዉቁ ሁል ጊዜ በምግብ ዋስትና ላይ እዉነት የሚናገሩ ባለሞያዎችን እየሰለሉና እያጣጣሉ ለመንግስት ባለስልጣናት

የሚያቀርቡት አካሄድ ነዉ:: በተለይ በአመታዊ የምግብ ዋስትና ጥናት ወቅት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ከመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚመጡ ቁርጠኛ ባለሞያዎች ይሄን ተናገሩ ; ይሄን አሉ : መንግስት በምግብ ዋስትና እና በእርዳታ ላይ ያለዉን ፖሊሲ ተቹ እየተባሉ የሚደርስባቸዉ ስለላ : ጉንተላ: ማሽሟጠጥና ስድብ ለጉድ ነዉ::

-የምግብ ዋስትና ባለሞያዎች ደጋግመዉ ደጋግምዉ ያስረዳሉ:: የሚሰማ የለም:: አንድ አመት የሚከስት የምግብ ዋስትና ጉዳት በተለይም የአንድ ቤተሰብ እሴት መሟጠጥ ለሃያ አምስት አመታታ አያገግምም ሲሉ መረጃ አጣቅሰዉ ተያያዥ ጥናቶችን ድርድረዉ ያስረዳሉ:: ስለዚህ ማህበረሰቡ እሴቱን እና ጥሪቱን ከመብላቱ በፊት ድጋፍ እና እርዳታ ያስፈልገዋል ይላሉ:: ማህበረሰቡ እሴቱን እና ጥሪቱን (ከብቱን : የቤት እቃዉን እና ሌሎች ቁሳቁሶቹን ) አንዴ መሸጥና መብላት ከጀመረ የሚደርሰዉ ጉዳት ለሃያ አምስት አመታት አያገግምም:: በተለይም በሚቀጥለዉ አመት ጥቂት የምግብ ዋስትና ችግር ከገጠመው ላንዴና ለመጨራሻ ግዜ ተሰባብሮ ይወድቃል እያሉ ያስረዳሉ:: ምክንያቱም የሚቋቋምበትን ጥሪትና እሴት ሸጦ በልቷልና::

-እናም የሆነዉ ይሄዉ ነዉ::ለባለፉት ብዙ አመታት ማህበረሰቡ ያለዉን እሴትና ጥሪት እየሸጠ ሲበላ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አዲስ አበባ ላይ ቤት ስለገነቡ ; በርካታ ኢንቨስትመንትን እየተሞዳሞዱ በማከናወን ሼር ካምፓኒዎች ዉስጥ እጃቸዉን ስላስገቡ ህዝቡ በሙሉ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ማዕቀፉ ዉስጥ የገባ የመሰላቸዉ ባለስልጣናት ተረጅ የለም እርዳታ አንፈልግም እያሉ ሲያዉጁ ነበር:: ይባስ ብሎም ህዝቡ ያለዉን እየሸጠ ይብላ እንጅ እርዳታ ከንግዲህ ኢትዮጵያ አያስፈልጋትም ሲሉ ነበር:: ምክንያታቸዉም ሀገሪቱ በምግብ እራሷን ችላለች ሲሉ ነበር::

-በተታያያዥም የሚያስከፋዉ ደግሞ በርካታ የምርምር: የግብርና : የምግብ ዋስታና ባለሞያዎች መሬት ላይ ያለዉን ደረቅ እዉነት እያወቁት በስራቸዉ ዉስጥ ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ቻለች የሚል ሀረግና ሀሳብ እንዲለጥፉ ሲገደዱ የሚያሳዩት የንዴት ስሜት ብሎም የማዘን ስሜት ልብ ይሰብራል::

-በየአመቱ በሴፍቲ ኔት የሚረዳዉ 17 ሚሊዮን ህዝብ እራሱ የምግብ ዋስትና ተረጅ መሆኑን ባለስልጣናቱ ሆዳቸዉ እያወቀ ቢክዱትም በርካታ ባለሞያዎች ችግርና ድርቅ ሲመጣ ይሄ የሴፍቲ ኔት ተረጅ ዋነኛዉ የምግብ ዋስትና ተጠቂ እንደሚሆን ሲያስረዱ ነበር:: መንግስት ግን ሆን ብሎ ሴፍቲ ኔት በምግብ እራስን የመቻል ማሳያ ነዉ የሚል አይነት ግዴለሽ አይሉት የተንኮል አቋም በመያዝ ነገሩ አሁን እደረሰበት ላይ እንዲደርስ ሆኗል::

-ለብዙ አመታታ በቂ ድጋፍ ሳይደረለት ጥሪቱን እና እሴቱን እየባለ የኖረ ማህበረሰብ ቅስሙ የተሰበረ ማህበረሰብ እንደመሆኑ መጠን ጥቂት ችግር ሲመጣ ይንገዳገዳል ብቻ ሳይሆን ይሰባበራል:: ህዝቡ እንዲህ በአንዴ ወደ ከፋ የረሃብ አዘቅት ዉስጥ ተወርዉሮ አልገባም:: በሂደት እንጂ:: መንግስት ግን ልክ ርሃቡ ዛሬ እንደተከሰት ተነስቶ ያዉጃል:: ለዚያዉም ፖለቲካዊ አዋጅ::ርሃቡ ትናንትም ነበር:: መንግስት ግን የርሃብ እና የምግብ ዋስትና ችግር መኖርን ሽምጥጥ አድርጎ ክዶ ነበር:: ህዝቡን በመርዳት አጋዥ የሆኑትንም ሀይላት አታስፈልጉም እያለ በመድረክ ላይ እየወረፈ ነበር::

-በዚህ ሂደት ዉስጥ የአለም የምግብ ፕሮግራም እንዲሁም በርካታ መንግስታዊ ያልሆኑ ፕሮግራሞች የእርዳታ ፕሮግራማቸዉን ማጠፍ : ወደሌላ ሀገር ማስተላለፍ ሲያከናዉኑ ነበር:: ይሄ እንዲከናወን ደግሞ መንግስት ያዉቅ ነበር::

-አሁን መንግስት በትክክል ለተጎዳዉ ህዝብ መፍተሄ መፈለግ ካለበት እስከዛሬ የሄደባቸዉን አካሄዶች መተዉ አለበት:: በዋናነት እስከዛሬ የሰራቸዉን ስህተቶች ማመንና እዉነታዉን ቁልጭ አድርጎ መቀበል ይገባል:: ከአለም አቀፉን የእርዳታ ሰጭ ሀይል ጀርባ የቆመዉን የአለም አቀፍ ማህበረሰብም ይቅርታ መጠዬቅ ወሳኝ ነዉ:: ምክንያቱም ብዙ ወሳኝ የሆኑ የአለም አቀፍ እርዳታ ዉስጥ የሚሰሩ ሀይሎች የኢትዮጵያ መንግስት ትናንት እየተሳደብ ሲያንጓጥጣቸዉ የነበሩ ወገኖችን ዛሬ እርዱኝ የሚለዉን ጥሪ ሲያቀርብ እንደ ቀልድ ሊወስዱት ይችላሉና:: እንዲሁም ይሄዉ የአለም አቀፉ እርዳታ አድራጊ ሀይል በቂ ዉሳኔ ማሳለፍ የሚችልበትን እድል መስጠት ተገቢ ነዉ:: በወረዳ ደረጃ ያሉ ባለስልጣናት እና የመንግስት ባለሞያዎች ያለመሸማቀቅ የሞያ ግዴታቸዉን እንዲወጡ በክልል እና በፌደራል ደረጃ ያሉ ቱባ ባለስልጣናት ጣልቃ እየገቡ ከመፈትፈት መታቀብ: እንዲሁም እርዳታዉን ከፖለቲካዉ ነጥሎ ማዬት ተገቢ ነዉ::

-አሁንም ቢሆን ሀያ ሚሊዮን ተራበ : አስራ አምስት ሚሊዮን ተራበ የሚለዉን ዉሳኔ የመንግስት ባለስልታናት እጓዳቸዉ ተደብቀዉ መወሰን የለባቸዉም:: ይሄን ጥያቄ ባደባባይ ሲጠየቁ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የሚመልሱት መልስ አስቂኝ ነዉ:: እኔ ባንድ ስብሰባ ላይ እንዲህ ስል ጠይቄ ነበር:: “ጥናት ስናጠና የተባበሩት መንግስታ ቢሮዎችም: እኛ መንግስታዊ ያልሆንን ድርጅቶችም እንዲሁም መንግስትም አብረን እናጠናለን:: በጥናቱ መሰረት የሚወሰነዉን የተረጅ ቁጥር ስትወስኑ ግን በመንግስት ባለስልጣናት ቢሮ ለብዙ ወራት መረጃዉን አስቀምጣችሁ ስታበቁ በተቆለፈ ቢሮ ዉስጥ ብቻችሁን ቁጭ ብላችሁ ትወስናላችሁ:: ይሄ ለምን ይሆናል:: ጥናቱ እንዳለቀ ወዲያዉኑ የጥናት ቡድኑ እንደተሰበሰብ የተረጅዉ ቁጥር መወሰን አለበት እንጅ የምን ዙሪያ ጥምጥም ነዉ? እተረጅዉ ቁጥር ላይ እስካልተሳተፍን ድረስ ለምንድ ጥናቱ ላይ መሳተፋችን ምን ትቅም አለዉ?”:: ባለስልጣኑ ነገሩ ገብቶታል :: እናም ሳቅ ብሎ እንዲህ መለሰልኝ:: “የተረጅ ቁጥር የመወሰን ጉዳይ የሀገር ልኡዋላዊነት ጉዳይ ነዉ::” ብሎኝ ቁጭ::

በተለያዬ ሰዓት ይሄን ጥያቄ በርካታ ባለሞያዎች የመንግስት ባለስልጣናትን ፊት ለፊት እያፋጠጡ እንደጠዬቁ ያደባባይ ሚስጥር ነዉ:: ግን የመንግስት አቋም ሁሉም የሚሆነዉ “የተረጅ ቁጥር የመወሰን ጉዳይ የሀገር ልኡዋላዊነት ጉዳይ ነዉ::” የሚል ነዉ::

-እኛም ሆንን መንግስት ግን እዉነታዉን ያዉቀዋል:: የተረጅ ቁጥር የመወሰን ጉዳይ የሀገር ልኡዋላዊነት ጉዳይ ሆኖባችሁ ሳይሆን የፖለቲካ ጉዳይ ሆኖባችሁ ነዉ:: የተረጅን ቁጥር የመወሰን ጉዳይ ፖለቲካዊ ነዉ ማለት ደግሞ የሚሞተዉን ህዝብ ቁጥር በፖለቲካዊ ዉሳኔ እንደ መወሰን ማለት ነዉ:: ስለሆነም እርዳታዉ ከፖለቲካዊ ዉሳኔ ሳይላቀቅ ምንም ዉጤታማ ስራ መስራት አይቻልም:: እንግዲህ ህዝቡን ለማዳን ከፈለጋችሁ እርዳታዉን ከፖለቲካዊ ዉሳኔ አላቁ : አጋራችሁ የሆነዉንም የአለም አቀፍ እርዳታ ሰጭ ሀይልም ይቅርታ ጠይቁ:: እነዚህን ስህተቶቻችሁን አርማችሁ በእዉነት ስለ እዉነት ህቡን ለማዳን ትችሉ ዘንድ ወደ ስራ መግባት ይጠበቅባችኋል:: እስኪ ፖለቲካዊ መነጽራችሁን ለጥቂት ጊዜ እንኳን ህዝቡን ለማዳን አዉልቃችሁ አስቀምጡት::

ከሰማችሁኝ ብዬ ያወቅሁትን በጥቂቱ አካፈልኳችሁ:: ከኔ የበለጠ እጅግ ብዙ የሚያዉቁ ባለሞያዎች አጠገባችሁ አሉላችሁ:: ሳታሸማቅቁ እህ ብላችሁ አድምጧቸዉ:: ባለሞያዎቹን ካደመጣችሁ ህዝቡን ማዳን ትችላላችሁ:: አለዚያ ግን ያዉ ዉሃ ወቀጣ ነዉ::

The post እንግዲህ ህዝቡን ለማዳን ከፈለጋችሁ እርዳታዉን ከፖለቲካዊ ዉሳኔ አላቁ : አጋራችሁ የሆነዉንም የአለም አቀፍ እርዳታ ሰጭ ሀይልም ይቅርታ ጠይቁ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

Health: የድድ እንፌክሽን | Gingivitis

0
0

gij

በማስረሻ መሀመድ

ጄንጅቫይትስ (የድድ እንፌክሽን) ብዙ ጊዜ የሚከሰት የድድ/የጥርስ ዙሪያ ላይ ህመም ሲሆን መቆጥቆጥ፣ ቅላትና እብጠት በድድዎ ላይ እንዲከሰት ያደርጋል:: ብዙዉን ጊዜ ህመሙ መጠነኛ የሆነ ምልክት ስለሆነ ያለዉ ታማሚዉ ሳያስተዉለዉ ሊያልፍ ይችላል::

የህመሙ ምልክቶች፡ ጤናማ ድድ ጠንካራና ቀላ ያለ ሮዝ ቀለም ያለዉ ሲሆን የድድ ላይ ህመም ሲከሰት የሚከተሉትን ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል:: እነርሱም • የድድ እብጠት

• ልልና የተነፋ ድድ

• አንዳንዴ ሲነካ ህመም መኖር

• ጥርስዎን በሚፍቁበት/በሚቦርሹበት ወቅት በቀላሉ መድማት

• የድድዎ መልክ መቀየር(ከጤናማ ቀይ ወደ ደበዘዘ ቀይ)

• መጥፎ የአፍ ጠረን መከሰት ናቸዉ

የህመሙ ምክንያቶች

ጄንጅቫይትስ በብዛት የሚከሰተዉ የአፍ ዉስጥ ንፅህናን በደንብ በማይጠብቁና በዚህ የተነሳ በድድና ጥርስ ላይ የሚጋገር ነገር/ plaque/ እንዲፈጠር እድል የሚፈጥሩት ሰዎች ላይ ነዉ:: ይህ የተጋገረዉ ነገር በዐይን የማይታዩ ባክቴሪያዎችን የያዘ ነዉ::

ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች

የድድ ችግር በማንኛዉም ሰዉ ላይ ሊከሰት የሚችል ነዉ:: ነገር ግን ተጋላጭነትዎን ከሚጨምሩ ነገሮች ዉስጥ

• የአፍ ጤንነታቸዉን/ ንፅህናቸዉን በደንብ በማይጠብቁ

• ሲጋራ በሚያጨሱ ሰዎች ላይ • የስኳር ህመም

• በእርጅና እድሜ ወቅት

• መድሃኒቶች

• የአፍ ድርቀት

• የሆርሞን ለዉጥ( በተለይ በሴቶች ላይ እርግዝና፣ በወር አበባና የእርግዝና መከላከያ እንክብል በሚወስዱበት ወቅት)

• ጥሩ አመጋገብ ከሌለዎ እና
• አደንዛዥ ዕፅ የሚጠቀሙ ከሆነ ነዉ::

ሊደረግ የሚችል ህክምና

ለህመሙ የሚደረግ ህክምና የህመም ምልክቶቹን ከመቀነስ ባሻገር ህመሙ ወደከፋ ደረጃ እንዳይሄድና የጥርስ መዉለቅን ሊከላከል ይችላል:: ዉጤታማ ህክምና ለማግኘት የባለሙያ ክትትልና ከህመሙ በኃላ የአፍ ዉስጥ ንፅህናን መጠበቅ ያስፈልጋል::

የቤት ዉስጥ ህክምናና የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ • የጥርስ ህክምና ባለሙያዉ በሚያዘዉ

መሰረት መደበኛ የሆነ የጥርስ እጥበት ማካሄድ • ለስለስ ያለ የጥርስ ቡርሽ መጠቀምና ቢያንስ በየሦስትና አራት ወራት መቀየር • በቀን ሁለቴ አሊያም ከእያንዳንዱ ምግብ መርሃግብር በኃላ አፍዎን ማፅዳት • የጥርስ ህክምና ባለሙያዎ ካዘዘልዎ የጥርስ ማጠቢያ አንቲሴፕቲክ መጠቀም • በጥርስ መካከል ለማፅዳት ተብለዉ የተዘጋጁ የጥርስ መጎርጎሩያ/ዴንታል ፒክ መጠቀም::

The post Health: የድድ እንፌክሽን | Gingivitis appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የቅዱስ ሲኖዶስን ስምና ሥልጣን የተጠቀመው የመናፍቃኑ መግለጫ!

0
0

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ቅዱስ ሲኖዶስ ያደረገውን ዓመታዊ ስብሰባው በቀደም ጥቅምት 26 2008ዓ.ም. ሲቋጭ ጠንከር ያለ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የሦስት ገጽ መግለጫ አውጥቶ ነበር፡፡ መግለጫው በሀገራችንና በሕዝቧ ላይ ወያኔ እያደረሰው ያለውን ጥፋት በማውገዝ ሀገራችን ለገጠማት ችግር ትኩረት ሰጥቷል፡፡ ሲኖዶሱ ይሄንን ማድረጉ ከማንም በላይ የሚመለከተው ጉዳይ በመሆኑ የሚያስመሰግነውና ማድረግም ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

Holy sinod addis ababa

በነገራችን ላይ ሲኖዶስ ብየ ስል በስደት አሜሪካ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤን ወይም አሥተዳደርን ማለቴ ነው፡፡ እርግጥ ነው እዚህ ሀገር ቤት አራት ኪሎ የሚገኙት እግዚአብሔርን ሳይፈሩና ሳያፍሩ እረኝነታቸው ሳይቆጫቸው ወያኔ በልጦባቸው ያላቸውን አቅም አሟጠው ወያኔን በትጋት እያገለገሉ ያሉ “ጳጳሳት” እና ወያኔን ማገልገል ባይፈልጉም ወያኔን ከሚያገለግሉት ጋር ከማጫፈር ያለፈ ሌላ ሚና መጫወት ያልቻሉት የወያኔ መጫወቻ መቀለጃ የሆኑት የተቀሩት ጳጳሳትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ እኛ ነን ይላሉ፡፡ ይሁንና የቤተክርስቲያን ሕግና ቀኖና የሚቀበለውና የሚያውቀው የቤተክርስቲያኗ ሲኖዶስ ግን በስደት ያለው ሲኖዶስ እንጅ በወያኔ ወሳኝነት እራሳቸውን ፓትርያርክ አድርገው የሾሙትና ሲኖዶስ ነን የሚሉትን የጳጳሳት ቡድን አይደለም፡፡

ሲኖዶስ ይሰደዳል ወይ? ምንትስ ለሚሉ ጥያቄዎች ከዚህ ቀደም መጽሔቶች ላይ በጻፍኳቸው ጽሑፎች መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ ከሌሎች የቤተክርስቲያኗ የሕግ የሥርዓትና የቀኖና መጻሕፍት ድንጋጌዎችና አስተምህሮዎች አንጻር በስፋት የዳሰስኩት ጉዳይ ስለሆነ አሁን እዚህ ላይ አልመለስበትም፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ ሌላው ትኩረት የሰጠውና በመግለጫው ላይ በቅድሚያ ያነሣው ጉዳይ ደግሞ ቅድስት ቤተክርስቲያን የመንጋዋን በአስደንጋጭ ሁኔታ መቀነስ በተመለከተ አባ ማትያስ የተናገሩትን በመጥቀስ ለዚህ የቤተክርስቲያን ጉዳትና ኪሳራ ተጠያቂው ወያኔ ነው በማለት ወያኔ እንዴት አድርጎ ምእመናን እንዲቀንሱ እንዳደረገ አምስት ነጥቦችን ጠቅሷል፡፡

እዚህ ላይ ነው እንግዲህ በሲኖዶስ ውስጥ እንዳሉ የሚታወቁት መናፍቃን ጳጳሳትና ካህናት የጥፋት ሥራቸውና ሸረኛ ተግባራቸው እጅግ አሳፋሪ በሆነና “ምን ይሉናል!” የሚል ቅንጣት ሥጋት ባልታየባቸው መልኩ ድፍረትና ንቀት የተሞላበት ነውረኛ ተግባራቸው ቁልጭ ብሎ የታየው፡፡

እነኝህ የሲኖዶስ አባላት መናፍቃን ጳጳሳት ቤተክርስቲያን የመንጋዋ በአስደንጋጭ ሁኔታ የቀነሰበትን ትክክለኛ ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶሱ እንዳያውቀውና መሥራት ያለበትን ሥራ እንዳይሠራ፣ መፍትሔ እንዳይጠቁም፣ ምእመናንንም እንዳያስጠነቅቅ ሆን ብለው ትኩረቱን ወዳልሆነ አቅጣጫ በማስቀየስ አስቂኝ አስቂኝና ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግኑኝነት የሌላቸውን ምክንያቶች እንዲጠቅስ በማድረግ የችግሩን ትክክለኛ መንስኤ እንዳይደርስበት አድርገዋል፡፡ እነኝህ ሰዎች በዚህ መግለጫ ከየአቅጣጫው በመናፍቅነታቸው የሚሰነዘርባቸውን ውግዘት ተቃውሞና መገለል ለመከላከል ከቻሉም እንዲቆም ለማድረግ በማሰብ ውንጀላው ሐሰተኛ እንደሆነና የተወነጀሉት ጳጳሳት፣ ካህናት፣ የወንጌል አገልጋዮች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ዘማርያንና ትጉ አገልጋዮች መሆናቸውን በማድነቅ ጭምር በመግለጫው አመስግኖ የሚሰነዘርባቸውን ክስ አስተባብሎ እንዲገልጽ አድርገዋል፡፡

ይህ “የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ነው” የተባለው የመናፍቃኑ መግለጫ በአሁኑ ሰዓት በቤተክርስቲያን ውስጥ መናፍቃን ሃይማኖታቸውን ባስካዷቸው ተሐድሷዊያን ከሀዲያን እየታወከች እየታመሰች መሆኗን ፈጽሞ እንደማያውቅ እንዳላየ እንዳልሰማ ለመምሰል ከመሞከሩም በላይ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲህ ዓይነት የክህደት የመናፍቅነት ችግር ያለበትና በጎችን የሚያውክ ተኩላ አንድም ሰው እንኳን ቢሆን እንደሌለ አድርጎ ነው መግለጫቸው እንዲገልጽ ያደረጉት፡፡

እንዲያውም እነዚህ መናፍቃን ጳጳሳት በመግለጫቸው ይድነቃቹህ ብለውም ቤተክርስቲያንን እያመሱ ምእመናንን እያስካዱ በኑፋቄ እየመረዙ ያሉትን ተሐድሶ መናፍቃን ከሀዲያንን “የወንጌል አገልጋዮች፣ ዓይናማ ካህናት!” ሲሉ ጠርተዋቸዋል፡፡

መግለጫው ለማስመሰል ብቻ በአራተኛው ነጥብ ላይ “እውነተኛውን የቤተክርስቲያናችንን እምነት ሥርዓትና ትምህርት ከመጠበቅና ከማስጠበቅ ጋር ይሄንን የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት የማይቀበሉትና የስሕተት ትምህርት ያለባቸውን ሁሉ ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ያወግዛል!” ቢልም መናፍቅነታቸው እየታወቀ ተወግዘው የተለዩትንና እንዲለዩ እየተጠየቀባቸው ያሉትን መናፍቃንን “ዓይናማ ካህናት፣ የወንጌል አገልጋዮች” ብለው አወድሰዋቸዋልና “እውነተኛውን የቤተክርስቲያናችንን እምነት ሥርዓትና ትምህርት” ብለው የገለጹት ቃል ለማደናገር የተጠቀሙት ቃል መሆኑን ልብ ማለት ይቻላል፡፡ እነሱ “እውነተኛው የቤተክርስቲያናችን እምነት ሥርዓትና ትምህርት” የሚሉት ከሀዲያኑ እየነዙት ያለው ኑፋቄ እንደሆነ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡

እዚህ ላይ ሲኖዶስ ውስጥ ካሉትና መናፍቅ እንደሆኑ ስለሚታወቁት ሁለት ጳጳሳት የማውቀውን መናገር የሚኖርብኝ ይመስለኛል፡፡ የጉዳዩ መቸት 1988ዓ.ም. ጎንደር ከተማ መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ይህ ደብር ከጥንት ጀምሮ አራቱ ጉባኤያት የመጽሐፍ ትምህርት የሚሰጥበትና ማስመስከሪያ ታላቅ ደብር ነው፡፡ በወቅቱ የእነዚህ ጉባኤያት መምህር የነበሩት ታላቁ አራት ዓይና ሊቅ ሊቀሊቃውንት መንክር መኮንን ነበሩ፡፡ በጠቀስኩት ዘመን እነዚህ ዛሬ የሲኖዶስ አባል የሆኑት ሁለቱ ጳጳሳት የዚህ ጉባኤ ቤት ተማሪዎች ነበሩ፡፡

በወቅቱ ከሁለቱ አንደኛው አባ ጽጌ የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ኃላፊ ነበሩና “በወንጌል የበሰላቹህና ለአገልግሎት ብቁ ትሆኑ ዘንድ” በሚል ሰበብ ሌላኛው አጋራቸው ትምህርቱን ይሰጠን ዘንድ ዓሥር የምንሆነውን ዲያቆናትና የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮችን ቅዳሜና እሑድ ሌሊት ሌሊት የወንጌል ጥናት ትምህርት እንዲሰጠን አግባብተውን ትምህርቱ ይሰጠን ነበር፡፡ በኋላ ሲገባኝ ትምህርቱን ሌሊት ያደረጉበት ምክንያት ሊያደርጉት ከፈለጉት ጉዳይ አኳያ ምሥጢራዊነቱን ከሌሎች የተጠበቀ እንዲሆን በማሰብና ከእኛ በኩል ግን ልጆች ናቸው ምንም አያመጡም ብለው በማሰብ ሥጋት እንደማይኖር በመተማመን ኖሯል፡፡

ይሄው ብርሃነሕይዎት የተባለ ሰው ሁለት ሦስት የሚሆን የተለያዩ ሰንበታትን ካስተማረን በኋላ በአንደኛው ቀን ያልተጠበቀ ጉዳይ ተከሰተ፡፡ ለካ የዚህ ትምህርት ዓላማ ሌላ ኖሯል መርዙን መርጨት ጀመረና የክህደት ወይም የኑፋቄ ትምህርቱን መጫን አስቦ በትምህርቱ መሀል “ታቦት ወይም ጽላት በሐዲስ ኪዳን አገልግሎት የለውም ተሽሯል! አገልግሎቱ በኦሪቱ ሥርዓት አብቅቶለታል!” አለ፡፡ እኔ ይሄንን ዓይነት የክህደት ትምህርት በፍጹም አልጠበኩም ነበር፡፡ ከዚህ እንዲቀጥል አልፈለኩም ነበርና “እንዴ! ብርሃነ ሕይዎት! ይሄ ትምህርት የቤተክርስቲያናችን ትምህርት ነው?” ስል ጠየኩት፡፡ ከምንማረው ውስጥ ሁለቱ ዲያቆናትም ከእኔ ጋር አጋር በመሆን አስከትለው “እንዴት! ምን ማለት ነው?” ብለው ጠየቁ፡፡

ይሄኔ አባ ጽጌ የተባሉት መነኩሴ እንደጠነከርንና መልስ ሳናገኝ እንደማንተው ሲገባቸው “አይ! ቤተክርስቲያን እንዲህ ብላ አታስተምርም!” አሉና “ለዛሬ ትምህርቱ እዚህ ላይ ይበቃናል” ብለው ወደ መኝታችን አሰናበቱን፡፡ ብርሃነሕይዎት ይሄንን የክህደት ትምህርት ሲሰጠን ከምንማረው ልጆች ውስጥ ከሦስታችን በስተቀር ተቃውሞውን ያነሣ አልነበረም፡፡ ለካ የተቀሩቱን ውስጥ ውስጡን መርዟቸው ኖሯል፡፡ እኛ ሦስታችንም ከዚያ ቀን በኋላ መሳተፍ አቆምን፡፡ እነሱ ግን ቀጠሉበትና ጭራሽም ፓስተር ዳንኤል የተባለ መናፍቅ ከናዝሬት አስመጥተው ይሄንን የክህደት ትምህርት ይጠጡት ያዙ፡፡ ይሄ ነገር እየከበደ መምጣቱ አሳሰበኝና ያለውን ነገር ለደቀመዛሙርት ነገርኳቸው፡፡

ይሄንን ችግርና አደጋ ለመግታት ለእነሱ ብቻ መንገሩ በቂ ሆኖ ስላልታየኝ ለየንታ (ለሊቀ ሊቃውንት መንክር መኮንን) ለመንገር ቀጥ ብየ ወደ በአታቸው ሔድኩና ለረዳቸው እንደምፈልጋቸው እንዲነግርልኝ ተናግሬ መልስ ስጠባበቅ እንድገባ ተፈቀደልኝና ገባሁ፡፡ የሰርክ ጸሎታቸውን አድርሰው ገና መቀመጣቸው ነበር፡፡ ደኅንነቴን ጠየቁኝና ዝም አሉ፡፡ እኔም የመጣሁበትን ጉዳይ ሁሉንም ነገርኳቸው አቀርቅረው ነበር በጥሞና ያዳምጡኝ የነበሩት፡፡ ነግሬያቸው እንደጨረስኩ በድንገት ካቀረቀሩበት እንባቸው ዱብ ዱብ እያለ ሲወርድ ዓየሁ፡፡ እጅግ በጣም ደነገጥኩ፡፡ የማደርገውን አጣሁ መሬት ተከፍታ ብትውጠኝ ወደድኩ፡፡ እራሴን ያገኘሁት ሌላ ቦታ ነው፡፡ የንታን እንዴት ብየ እንደተሰናበትኳቸውና እንዴት ብየ እንደወጣሁ ምንም ትዝ የሚለኝ ነገር የለም፡፡

“ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይቀርም” ሆነና ነገሩ ሰዎቹ ከዚህ ዕኩይ ተግባራቸው ሳይመለሱ ቀሩ እንጅ ከዚያ በኋላ የንታ ለዚህ ፈተና ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው ተንቀሳቅሰው ነበር፡፡ የንታ አባጽጌንና ብርሃነ ሕይዎትን ጠርተው አናግረዋቸው ነበር፡፡ እነሱ ግን እንደ አይጥ እየተሽሎከለኩ በየመኖሪያቤታቸው እየተሰባሰቡ ይሄንን የጥፋት ተግባራቸውን ቀጠሉበት፡፡ ልዑለ ቃል የተባለውንና ዛሬም አብሯቸው ያለውን መናፍቅ ከአዲስ አበባ በማስመጣት ሰንበት ትምህርት ቤት እንዲሰብክ በማድረግ ደጋፊ ለማሰባሰብ ጥረት አደረጉ ጭራሽም ፓስተር ዳንኤልን ሰንበት ትምህርት ቤት ላይ እንዲሰብክ ሊያደርጉ እንደሆነ መስማታችን ከእኛ ጋራ ያላቸው ግንኙነት ይበልጥ ለመሻከሩ ምክንያት ሆነና አለመግባባቱ ወደ ጠብ ስላመራ የንታ ሰብስበውን እርቅ እንድንፈጥር ለማድረግ ጣሩ፡፡ እነሱ ግን የግብር አባታቸው ስላገበራቸው ትልቅ ሰውንና ቅዱሳንን አስጠልቷቸዋልና እዚያው ላይ የንታን የሚያህል አባት ሳይፈሩና ሳያፍሩ ለጸብ ተጋበዙ፡፡

የንታ በእነዚህ ልጆች ተግባር እጅግ በማዘንና በመደናገጥ አውጥተዋት የማያውቋትን የእጅ መስቀላቸውን አውጥተው “እኔ አወግዛለሁ! እረፉ ብያለሁ!” እያሉ ተናገሩ እርቁም ሳይሰምር ቀረ፡፡

ሰንበት ላይ ሰንበት ተማሪው እንዲሰበሰብ አደረግንና የንታ በሆነው ሁሉ እጅግ ማዘናቸውን አባ ጽጌና ብርሃነ ሕይዎት ከዚህ ተግባራቸው የማይመለሱ ከሆነ አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር እንደሚያመለክቱባቸው አስጠነቀቁ፡፡ ሰዎቹ ግን ይሄም አላስደነገጣቸውም ነበር፡፡ ሁኔታው በእንዲህ እንዳለ በመሀሉ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ አሳትማ ስለማታውቅና በምእመናን እጅ የሚገኙት የተለያዩ እትሞች በሌሎች የታተሙና አስተምህሮዋን ያልጠበቁ የተቆነጻጸሉ በመሆናቸው ይህ ጉዳይ በቤተክርስቲያናችን ዘወትር የሚነሣ አንግብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ አባ ጳውሎስ “ቤተክርስቲያን ያልተቆነጻጸለ የራሷን መጽሐፍ ቅዱስ ልታሳትም ነውና መጥተው እንዲያርሙ!” በሚል ምክንያት የንታን አዲስ አበባ ስለጠሯቸው የንታ አዲስ አባባ ሔዱ ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያንም በተዘጋጀላቸው ቦታ እንዲያርፉ ተደረገ፡፡ ሳምንት እንኳን ሳይቆዩ በጠና ታመሙ ተብሎ ህክምና ሲደረግላቸው ቢቆዩም ሊድኑ ግን አልቻሉም፡፡ እንደዘበት ደረስ ብለው እንደሚመለሱ ከወጡባት ሀገራቸውና ደብራቸው ሳይመለሱ አረፉ፡፡ እነ አባ ጳውሎስ ከያዙት ሰይጣናዊ ተልእኮ አኳያ መርዘው እንደገደሏቸው ታወቀ፡፡

ይህ ከባድና መራራ ኃዘን የቤተክርስቲያንና የሀገር ቢሆንም ጎንደር ግን አምርራ አለቀሰች፡፡ ከትንሽ እስከ ትልቅ ሕዝቡ በእንባ ተራጨ፡፡ እግዚአብሔር ፍርዱን እንዲሰጥ ተማጸነ፡፡ ብዙ ሳይቆዩ አባ ጽጌና ብርሃነ ሕይዎት መነኩሴ ያልነበረው ብርሃነ ሕይዎትም መነኮሰና ወዲያውኑ ወደ አሜሪካ ተጓዙ፡፡ እነዚህ ሁለቱ ግለሰቦች ዛሬ አባ ጽጌ አቡነ ሰላማ ተብለው ብርሃነ ሕይዎት ደግሞ አቡነ ዮሐንስ ተብለው የሲኖዶስ አባላት በመሆን ይሄንን ሲኖዶስ ከሌሎቹ ቢጤዎቻቸው ጋር በመሆን ሥራውን እንዳይሠራና የቤተክርስቲያንን አደራ እንዳይወጣ መስመርም እንዲስት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ መናፍቃን የሲኖዶስ አባላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባላት በአስደንጋጭ ሁኔታ የቀነሰበት ምክንያት መናፍቃን ከወያኔና ወያኔ ካስቀመጣቸው ከሀዲያን ጳጳሳትና ካህናት ጋር በመቀናጀት በሚሠሩት የጥፋት ሥራና እነሱም ራሳቸው ከቤተክርስቲያን ጉያ ውስጥ ተቀምጠው የቤተክርስቲያንን እንጀራ እየበሉ ምእመናንን በማስካድ የሚሠሩት ሥራ እንደሆነ እንዳይታወቅ “የሲኖዶስ መግለጫ” ተብሎ በወጣው መግለጫ ላይ ምክንያቶች ናቸው ብለው የጠቀሷቸው አምስት ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

ሀ. ገዥው መንግሥት በያዘው የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ኦርቶዶክሳዊያን ምእመናንን በልማት ስም ከመኖሪያ ቀያቸው ስላፈናቀላቸው ቤታቸው ፈርሶ የገቡበት የማይታወቅና ቤት ስለሌላቸው ሳይቆጠሩ የቀሩ ስለሚኖሩ፡፡

ለ. የመንግሥቱ የፖለቲካ መርሕ ኦርቶዶክሱን አማኝ ማኅበረሰብ ከመጥላቱና ካለው ረጅም ክፉ ዓላማ የተነሣ የቤተክርስቲያን ንብረት የነበሩ የታቦት ማደሪያዎች ሳይቀሩ ከቤተክርስቲያን ላይ እየተነጠቁ ለልዩልዩ ድርጅቶች ተላልፈው ስለሚሰጡና መንግሥት ካስቀመጣቸው የቤተክርስቲያን መሪዎችም ድጋፍ ሲያጣ ምእመናኑ እየተማረሩ ከአባልነት የሚወጣው ቁጥሩ ቀላል ባለመሆኑ፡፡

ሐ. ካለው የኢኮኖሚ ችግር የተነሣ በየጊዜው ወደ ዓረብ ሀገር የሚገቡ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዓረብ ሀገር ሲገቡ የእምነት መቀየር ግዳጅ ስላለ የሚደርስባቸውና በዚሁ ስደት የተነሣ በአፍሪካና በሌላው ሀገር የተበተነውን ክርስቲያኑን ማኅበረሰብ የሚቆጥረው ስለሌለና መንግሥትም የኦርቶዶክሱ ቁጥር ዝቅ ብሎ መታየቱ ደስ ስለሚለው፡፡

መ. በቤተክርስቲያኒቱ የሚካሔደው ገደብ የሌለው ዓይን ያወጣ የሙስና ሥራ እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸውን ኦርቶዶክሳዊያን ልብ እየሰበረና እያደማ ከአባልነት እንዲወጡ ስለሚያደርግ፡፡

ሠ. በቤተክርስቲያኒቱ የሚከናወነው የወንጌል አገልጋዮችና የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ዘማርያንና ዓይናማ ካህናት በልዩ ልዩ ምክንያት በሐሰት በመወንጀል እያስመረሩ የሚያባርሩት ሕዝበ ክርስቲያኑንም ስለሚሰደድና ስለሚጠፋ ከዚህም ጋር በረሀብ መፈናቀል ከሚገጥማቸው ጋር ተጨምሮ የዚህ ሁሉ የመከራ ውጤት የቤተክርስቲያኒቱ አማኞች የመቀነሱ ምሥጢር ይህ መሆኑን ያምናል፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እድገትና አንድነት እንዲጠናከር ከዚህ በላይ ለዘረዘርናቸው ችግሮች መነሻው የአሁኑ መንግሥትና እርሱ ያስቀመጠው ቤተክህነት ነው፡፡ በመሆኑም ሕዝበ ክርስቲያኑ ይህን አውቆ በልዩ ልዩ ምክንያት በሚደርስበት መከራ ተመርሮ ከቤት ከመዋልና ወደሌላ ሃይማኖት ከመግባት ይልቅ ባለበት ቤተክርስቲያን ጸንቶ ይሄንን ቀን እግዚአብሔር እንዲያሳልፈው ሁሉም ሕዝበ ክርስቲያን ተግቶ እንዲጸልይ ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ የሚሉት ናቸው፡፡

እነዚህ ነጥቦች ሆን ተብለው ምእመናንን ለማዘናጋት የተጠቀሱ ናቸው፡፡ መግለጫቸው በአንድ ቦታም እንኳን ቢሆን ቤተክርስቲያን አላግባብ አባል የሆነችበት ማኅበርም ቢሆን “የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት በመባል በሚታወቀው ማኅበር መተዳደሪያ ደንብ መሠረት አባል የሆነው ሁሉ አንዱ የሌላውን አማኝ ሰብኮም ይሁን አታሎ መውሰድ አይኖርበትን አይችልም!” የሚለውን ደንብ በመተላለፍና በምዕራባዊያን መንግሥታት ወያኔን እያስገደዱና እየደለሉ የገዛ ሕገ መንግሥቱን በሚቃረን አካሔድ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ልዩ ልዩ ሁኔታዎችንና ጉዳዮችን እንዲያመቻችላቸው በማድረግ ወደ ሕዝቡና ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሰርገው እየገቡ የቅድስት ቤተክርስቲያንን እምነት ሥርዓት እሴት ዶግማና ቀኖና አጋንንታዊ በሆነ መንገድ እያጠቁ እየተቃወሙ እየሻሩ እያስተኃቀሩ ምእመናንን በማስካድ በገፍ አግዘው የወሰዱትንና እየወሰዱ ያሉትን ለዚህች ሀገር ክፉ በሚመኙትና እንድትጠፋ በሚያሴሩት በምዕራባዊያኑ ተመሥርተው እንዲንቀሳቀሱ ተደርገው በሀገራችን እንደ አሸን የፈሉትን የመናፍቃን ድርጅቶችን ለዚህ ወንጀላቸው አንዲትም ቦታ ላይ ተጠያቂ ሊያደርጓቸው አልቻሉም አልፈለጉም፡፡ እንዲጋለጡ አይፈልጉምና፡፡

በመግለጫቸው የምእመናን ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ የቀነሰበት ምክንያት ብለው የጠቃቀሷቸው ምክንያቶች ተጨባጭነታቸው ምን ያህል እንደሆነ እንመርምር፡-

(ሀ) ላይ እንደገለጹት “በልማት ስም ከመኖሪያ ቀያቸው ስላፈናቀላቸው ቤታቸው ፈርሶ የገቡበት የማይታወቅና ቤት ስለሌላቸው ሳይቆጠሩ የቀሩ ስላሉ ነው” ያሉት፡፡ መናፍቃን በሚሠሩት ሥራ መንጋውን አግዘው እንደወሰዱት እንዳይታወቅና የቀረውንም አግዘው መውሰድ እስኪችሉ ድረስ እንዳይታወቅ ለማድረግ ሽፋን ለመስጠት ነው ይሄንን ያሉት፡፡ በልማት ስም የሚፈናቀለውና በመፈናቀሉም የማይቆጠር ዜጋ ካለ ወያኔ በልማት ስም እያፈናቀለው ያለው የእኛን ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ዜጋ በመሆኑ ይህ ምክንያት ብለው የጠቀሱት ነጥብ ምእመናን ለመቀነሳቸው ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ የቀነሰው የእኛ እንጅ የሌሎቹ አይደለምና፡፡

(ለ) ላይ የገለጹት “ምእመናን ወያኔ ካስቀመጣቸው መሪዎች ድጋፍ ስለሚያጡ በዚህ በመማረር” የሚለው ነጥብም በፍጹም ምክንያት ሊሆን አይችልም ባይባልም ለዚህ ኪሳራ ዋነኛውን ሚና ከተጫወቱ ነጥቦች አንዱ ግን ሊሆን የሚችል አይደለም፡፡

(ሐ) ላይ የገለጹት ምክንያት “ተሰዶ የወጣው ስላልተቆጠረ” የሚለለውና “በግድ እንዲሰልሙ ስለሚደረግ” የሚለውም በግድ ማስለሙ ከቀረ የቆየ በመሆኑና እንዲህ ይደረግ በነበረበት ጊዜም ቢሆን ለሥራ ብለው እስላም ሳይሆኑ እስላም ነን እያሉ የሚሔዱ ዜጎች ሲመለሱ እስላም ሆነው የማይቀሩ ቄዴር እየተጠመቁ የሚቀደሱ የነበሩ በመሆኑ፣ የሕዝብና ቤት ቆጠራ በስደት ያሉ ዜጎች እዚህ ባሉ ቤተሰቦቻቸው የሚቆጠሩበት አሠራር ያለ በመሆኑ ኢትዮጵያ ክርስቲያኑም እስላሙም ምኑም ተደምሮ ባጠቃላይ ያላት ስደተኛና ከሀገር ወጥቶ የሚኖረው ሕዝብ ሦስት ሚሊዮን (አእላፋት) ብቻ በመሆኑና ከዚህ ቁጥር ግማሹ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተከታይ ነው ብንልና ሆን ተብሎ እንዳይቆጠር ተደርጓል ብንል እንኳ ቤተክርስቲያን ከተነጠቀችው መንጋ አንጻር ይሄ ቁጥር ሲታይ ኢምንቱን እንኳን የሚያህል ባለመሆኑ ይሄም ምክንያት እንደዋነኛ ነጥብ ሊጠቀስ የሚችል አይደለም፡፡

(መ) ላይ የጠቀሱት “ምእመናን በሙስና ልባቸው እየደማ ከአባልነት እንዲወጡ ስለሚያደርጋቸው” ያሉትም እንደሌሎቹ ነጥቦች ሁሉ በፍጹም ምክንያት ሊሆን አይችልም ባይባልም ከዋነኛ ምክንያቶች አንዱ እንዳልሆነ ግን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

በመጨረሻው ነጥባቸው (ሠ) ላይ የገለጡት ግን ይሄንን መግለጫ በቅዱስ ሲኖዶስ ስም ያወጡ ሰዎችን ማንነት በትክክል ያጋለጠ ነጥብ ነው “በቤተክርስቲያኒቱ የሚከናወነው የወንጌል አገልጋዮችና የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ዘማርያንና ዓይናማ ካህናት በልዩ ልዩ ምክንያት በሐሰት በመወንጀል እያስመረሩ የሚያባርሩት ሕዝበ ክርስቲያኑንም ስለሚሰደድና ስለሚጠፋ” ያሉት፡፡ ይታያቹህ ምእመናንን እያስኮበለሉ ወደ መናፍቃኑ እንዲጋዙ እያደረጉ ያሉትን ከሀዲያን ተኩሎችን “የወንጌል አገልጋዮችና ዓይናማ ካህናት” ብለው ከማድነቃቸውም በላይ ተኩላዊ ተግባራቸው ተነቅቶባቸው ምእመታንና ታማኝ ካህናት ተባብረው እንዲገለሉ በማድረጋቸው “እነሱ ስለተባረሩ ነው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አማኞች ቁጥር የቀነሰው” ብለው አረፉት፡፡ መገለል እንደሌለባቸውም አበክረው ይናገራሉ ያስጠነቅቃሉ፡፡

ሲጀመር እዚህ ያሉት የወያኔ ጳጳሳት እነ አባ ማትያስም ኑፋቄ ያለባቸው ጳጳሳት ያሉበት በመሆኑና እነ አባ ማትያስ የሙሉ ጊዜ ሥራቸው የወያኔን ደኅንነትና ህልውና ተግቶና ነቅቶ መጠበቅ እንጅ ሐዋርያዊ ተልእኮን መወጣት ቤተክርስቲያንን መጠበቅ ባለመሆኑ ለወያኔ አደጋ እስካልሆኑና እስካልተቃወሙ ጊዜ ድረስ የመናፍቃኑ በቤተክርስቲያን ውስጥ መፈንጨትና በጎችን ማስኮብለል የሚያስደስታቸው እንጅ የሚያሳስባቸው ጉዳይ አይደለምና ማንንም ሰው መናፍቅ ወይም ተሐድሶ በመሆኑ አባረው አያውቁም፡፡

ሰሞኑን ግን ተፈጻሚነቱ ባይታወቅም የምእመናን ጫናና ጥያቄ እጅግ እያየለ በመምጣቱ ተሐድሶ መሆናቸው የሚታወቁ ቡድኖችን በቤተክርስቲያን ስም የራሳቸውን አገልግሎት እንዳይሰጡ እንዳይሰብኩ ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡ ከዚህ ቀደምም እርምጃ የተወሰደባቸው መናፍቃን እርምጃው የተወሰደባቸው እነ አባ ጳውሎስ የቤተክርስቲያን ጠባቂነቱ ተሰምቷቸው እርምጃውን የወሰዱ ሆነው ሳይሆን እንደዚሁ የምእመናንና የምሁራን ጫናና ጥያቄ እጅግ አይሎ ለራሳቸውም የሚያሠጋበት ደረጃ በመድረሱ ነው እርምጃው የተወሰደው እንጂ እነ አባ ጳውሎስ ለቤተክርስቲያን ባላቸው ቀናኢነት ይሄንን እርምጃ እንዳልወሰዱና እነ አባ ጳውሎስም ሆኑ እነ አባ ማትያስ ኑፋቄ ያለባቸውን ካህናትን ዘማርያንን ሰባክያንን አማሳኞቹን እንደሚያተጉ እነደሚያበረታቱ እንደሚደግፉ ወደ ኋላ በምገልጸው መረጃ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ባጠቃላይ የጠቀሷቸው አምስት ምክንያቶች ሕዝበ ክርስቲያኑ ትክክለኛውን ምክንያት አውቆ አስፈላጊውን እርምጃ እንዳይወስድ የሚጋርዱ የሚከልሉ የሚያዘናጉ ናቸው፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሰዎች የሄንን ያህል ናቸው፡፡ ማንነት አስተሳሰባቸውም ይሄ ነው፡፡ አሁን ታዲያ እነዚህ ናቸው የመንጋው እረኞች? እነዚህ ናቸው የቤተክርስቲያን ጠባቂዎች? ይሄ መግለጫስ መናፍቃኑ ሲኖዶስን ሳይቀር በመውረር ምን ያህል ቤተክርስቲያንን እስከመቆጣጠር እንደደረሱ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አይደለም?

ቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ከበዋቸው ያሉትን መናፍቃን ጉድ የማያውቁ እንዳይመስላቹህ ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ ይሄ ችግር ፈጥጦ የሚታይ ግልጽ ጉዳይ ቢሆንምና ቅዱስ አባታችን እየተቀበሉት ያለው መከራ እየፈጸሙት ያለው ተጋድሎ ለብቃት ደረጃ ያበቃቸው ቢሆንም ቅሉ የመነፈቁ ጳጳሳትንና ካህናትን ለይተው እንዲያውቁ ብቃት ደረጃ ላይ መድረስ አያስፈልጋቸውም ባይጠበቅባቸውም ነበር፡፡ “ካወቁ ታዲያ ለምን በዝምታ ይመለከቱታል?” የሚል ጥያቄ ይነሣ ይሆናል፡፡ መልሱ ግን እንዲህ እንደጥያቄው ቀላል አይደለም ብዙ የቸገረ ነገር አለ፡፡

ቅዱስ አባታችን ከበዋቸው ያሉት መናፍቃን ጳጳሳት ከአቅማቸው በላይ ሆነውባቸው እርምጃ ለመውሰድ በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ ስላልሆኑ፣ አብረዋቸው ያሉት ደኅናዎቹ ጳጳሳትም እንደሳቸው ሁሉ በመናፍቃኑ ጳጳሳት ስለሚዋከቡና አቅመ ቢስ ስላደረጓቸው፣ እንደ ቅዱሳን አባቶቻቸው ሁሉ እንዲህ ዓይነት የቸገረ ነገር ሲገጥም “ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር” ብለው እግዚአብሔር ሥራውን እንዲሠራ ለእግዚአብሔር ፋንታን ስለሰጡ ነው ምንም እንደማያውቅ ሰው በዝምታ የሚመለከቱ መስለው የሚታዩት፡፡

ይህ የገጠማቸው ፈተና ከአቅማቸው በላይ በመሆኑና ለቤተክርስቲያንም ለሀገርም ለታሪክም ለማንነትም የከፋ አደጋ ያለው መሆኑን ጠንቅቀው ስላወቁም ነው እግዚአብሔር መፍትሔ እንዲሰጥ ከስደት ዘመናቸው የሚበዛውን ያለ እረፍት በሱባኤያት በማሳለፍ በእርጅናቸው ላይ እራሳቸውን እንደዚህ ዓይነት የሱባኤ መከራ በመቀበል በመጥመዳቸው ጤናቸው በየጊዜው ለአደጋ እየተዳረገ ለህክምና የሚወሰዱ የሆኑት፡፡ ሱባኤ እንዲያቆሙ ምግብ በአግባቡ እንዲመገቡ ሀኪሞች አበክረው ቢያሳስቡም እሳቸው ግን በፍጹም ሱባኤ ሊተው አልቻሉም፡፡

ሱባኤ በጣም ከባድ ነው እንኳንና ይሄንን ያህል ዘመን ያንድ ጊዜና የሁለት ጊዜው እንኳን ሰውነትን እንዴት አድርጎ እንደሚጎዳ የመናንያንን ሕይዎትና ተጋድሎ በቅርበት የሚያይ ያውቀዋል፡፡ እንግዲህ ምን እላለሁ? እንዲህ ሆነው የሚማጸኑትና የተማመኑበት አምላካቸው መድኃኔዓለም ክርስቶስ ጩኸታቸውን ተማጽኗቸውን ልመናቸውን ሰምቶ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከአጋንንት አፍ ይታደጋታ!!!

ቅዱስ አባታችን ከመጀመሪያው የእነኝህ የወረሯቸውን መናፍቃን አደገኛነትና በቤተክርስቲያን በሀገር ላይ የጋረጡትን አደጋ እጅግ ከመፍራታቸው የተነሣ ከአዲስ አበባዎቹ የወያኔ ጳጳሳት ቡድን ጋር የእርቅ ድርድር ይደረግ በነበረበት ጊዜ ሕገ ቤተክርስቲያን ባይፈቅድላቸውም እነ አባ ጳውሎስ ለቤተክርስቲያን ታማኝ መሆናቸውን በመሐላ ሊያረጋግጡላቸው ከቻሉና ቃል የሚገቡላቸው ከሆነ ፕትርክናቸውን አሳልፈው በመስጠት በበአት ለመወሰን እስከመሻት ድረስ እንዲያስቡ አድርጓቸው ነበር፡፡ ከበዋቸው ያሉት መናፍቃኑ ይሄንን የቅዱስ አባታችንን ሐሳብ ስለሚያውቁ ከማንም ጋር እንዳይገናኙ አድርገዋቸዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ በዘመዶቻቸው እንኳን እንዲጎበኙ እንዲጠየቁ በፍጹም አይፈቅዱላቸውም፡፡

በዚህ አጋጣሚ እዚያው ሀገር ላላቹህት ካህናትና ምእመናን የተዋሕዶ ልጆች በሙሉ አጥብቄ ማሳሰብ የምፈልገው ጉዳይ ቢኖር ቤተክርስቲያን በዘመኗ ዓይታው በማታውቀው ከባድና እጅግ አሳሳቢ ፈተና ላይ ነው ያለችው፡፡ እዚህ ሀገር ቤት ያለነው ካህናትና ምእመናን የወያኔ ጳጳሳትና ካህናት ቤተክርስቲያንን መጫዎቻ መቀለጃ ሲያደርጓት በቆመችበት ደርቃ እንድትከስም ደም ስሮቿን ሲቆርጡና በርካታ አጋንንታዊ ተልእኳቸውን ሲፈጽሙባት ዓይተን መታገስ ባለመቻላችን ስንቃወም በጠባቂያቸውና አሠሪያቸው ወያኔ አፈሙዝ እየተቀጠቀጥን የመከራ ዓይነት እየዘነበብን እንድናርፍ ስለተደረግን ይሄው እንደምታዩን በዝምታ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡

እናንተ እዚያ በነጻነት ሀገር ያላቹህትና ለመብታቹህ ተጋደላቹህ፣ ቤተክርስቲያናቹህን ጠበቃቹህ፣ ለቤተክርስቲያናቹህ ተቆረቆራቹህ፣ ተሟገታቹህ ብሎ አፈሙዝ የሚያዞርባቹህና በእኛ ላይ እንደሆነው የመከራ ዓይነቶችን የሚያዘንብባቹህ ኃይል ሳይኖር በቤተክርስቲያን ላይ ይሄንን ያህል ጉዳት ያደረሱብንን የመጥፋት አደጋን በቤተክርስቲያናችን ላይ የጋረጡትን መናፍቃን ጳጳሳትና ካህናትን መቃወም ማስወገድ ማባረር እየቻላቹህ ቤተክርስቲያንን ያስበላቹሀት ምን ነክቷቹህ ነው? ምእመናኑን አጠቃለው እስኪበክሉና እስኪረከቡ ነው ወይ የምትጠብቁት? መናፍቃኑ በቤተክርስቲያን ላይ እንዲህ ሲበረቱባት ሲያጠቋት ሲያጠፏት በዝምታ በማየታቹህ በጌታ ዘንድ ከእነሱ እኩል ተጠያቂ የማትሆኑ ይመስላቹሀል? ጳጳሳት ለሃይማኖት የመቆርቆር ቤተክርስቲያንን የመጠበቅ ላቅ ያለ አደራና ኃላፊነት ቢኖራቸውም ቤተክርስቲያንን ከጥፋት የመጠበቅ ግዴታ ግን የአንድ ጳጳስና የአንድ ተራ ምእመን ግዴታ አንድ እንደሆነ አታውቁምን?

እናም እባካቹህ በእነዚህ መናፍቃን ላይ ቆርጣቹህ ተጠናክራቹህ በመዝመት ቅዱስ አባታችንንና ሌሎቹንም ደኅና የሆኑትን ጳጳሳት ማለትም ሲኖዶሱን ነጻ አውጥታቹህ የመናፍቃኑን እጅ በመቁረጥ ቤተክርስቲያንን ከጥፋት ታደጓት??? አሁኑኑ ፈጥነን ያልተነሣን እንደሆነ ይሄንን አደጋ መቀልበስ በፍጹም እንደማንችል ሁሉም ሰው ሊያውቀው ይገባል፡፡

ትክክለኛውና እውነተኛው ምእመናንን በአስደንጋጭ ሁኔታ እንዲቀንሱ ያደረገውና በአጭር ጊዜ ውስጥም ቤተክርስቲያን አንድም እንኳ ምእመን እንዳይኖራት አድርጎ እርቃኗን ሊያስቀር የሚችለው ዋነኛውና ብቸኛው ምክንያት የሚከተለው ነው፡-

ደርግ ወድቆ የወያኔን መተካት ተከትሎ ወያኔ “ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብዛኛውን ቁጥር የያዘችውንና ጠንካራ መዋቅር ያላትን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በቁጥጥሬ ስር ሳላደርግ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ተቆጣጠርኩ ማለት ከቶውንም አልችልም! አሥተዳደሬም የተረጋጋ ሊሆን አይችልም!” የሚል እምነት በመያዙ ቤተክርስቲያን የምትተዳደርባቸውን ቀኖናዎቿንና ሥርዓቷን በማፈራረስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያን አሳዶ ከሀገር በማስወጣት የራሱን ሰው አባ ጳውሎስንንና ወያኔ በትግል ላይ እያለ አስቀድሞ ለዚሁ አገልግሎቱ ሲል መጠነኛ የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዲያገኙ አድርጎ ያዘጋጃቸውን ታጋዮቹን በካህን ስም አስገብቶ (ብዙዎቹ ዛሬ ላይ ጳጳሳት ሆነዋል) ቤተክርስቲያኗን መቶ በመቶ በቁጥጥሩ ስር በማድረግ ዶግማ ቀኖናዋን ከመቆነጻጸል ጀምሮ እስከ ቅርስ ንብረት ገንዘቧ ድረስ ያሻውን የፈለገውን በማድረግ ዝርፊያና ውድመት ሲፈጽምባት ቆይቷል እየፈጸመባትም ይገኛል፡፡

ይህች ቤተክርስቲያን በወያኔ ከደረሰባት ኪሳራና ጉዳት ከሁሉም በላይ የሚቆጨውና የሚያገበግበው ደግሞ ወያኔ እሱን ለዚህ ካበቁት ምዕራባዊያን በተሰጠው ተልእኮ ምክንያት ከመናፍቃን ድርጅቶች ጋር ተቀናጅቶ በመሥራትና የገዛ ሕገመንግሥቱን በመጻረር ለመናፍቃኑ በሚያደርገው ሁለንተናዊ ድጋፍ የቤተክርስቲያኗ ምእመናን እንዳለ ተወስዶ የምእመናኖቿ ቁጥር ከኢትዮጵያ ሕዝብ 55 በመቶ ከነበረበት የቅርብ ጊዜው አኃዝ በዘመነ ወያኔ በተደረጉ ሁለት ቆጠራዎች እየቀነሰ መናፍቃኑ ደግሞ በወያኔና አባ ጳውሎስን ጨምሮ እሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ባስቀመጣቸው ከሀዲያን በሚደረግላቸው ድጋፍ በሚፈጥርላቸው ሕገ ወጥ የሆነ ምቹ ሁኔታዎች በመታገዝ በእጥፍ በእጥፉ እየጨመሩ መጥተው ምእመናኖቿን አግዘው በመውሰዳቸው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አባላት አሽቆልቁሎ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ዘንድሮ ይደረጋል በተባለው የኢትዮጵያ ሕዝብና ቤት ቆጠራ ከ15 እስከ 20 በመቶ ባለው ቁጥር መሀከል እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

እጅግ የሚያስደነግጠውና የሚያሳዝነው ጉዳይ ይሄ ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ቆጠራ በየ ዓሥር ዓመቱ እንደመደረጉ ሁሉ ወደ ፊት ከ10 ዓመታት በኋላ ማለትም 2018ዓ.ም. በሚደረግበት ጊዜ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አንድም አባል እንኳን ሳይኖራት ነበረች ተብሎ የሚነገር መሆኑ ነው፡፡

ይህ የመናፍቃንና የወያኔ የተቀናጀ ጥረት ስኬት እንዴት ሊገኝ ቻለ? ብለን የጠየቅን እንደሆነ  ወያኔ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ በገዛ ሕገ መንግሥቱ ላይ “ለአምልኮ ከተፈቀደ ቦታ በስተቀረ በመንገድ፣ በመጓጓዣ መጠበቂያ (ፌርማታ)፣ በሥራ ቦታዎች፣ በመዝናኛ ቦታዎች ወዘተረፈ. መስበክ የተከለከለ ነው!” ብሎ ቢደነግግም መናፍቃኑ በእነዚህ ቦታዎች ብቻ ሳይሆን ቤት ለቤት ሁሉ ሳይቀር እያንኳኩ የክህደት ስብከታቸውን እየሰበኩ በጎቻችንን ሲነጥቁ ይህ አድራጎት የተከለከለ በመሆኑ ከዚህ አድራጎታቸው እንዲታቀቡ ማድረግ ሲገባው ያለ አንዳች ሥጋትና እቀባ የክህደት ስብከታቸውን በምእመናን ላይ እንዲዘሩና እንዲያሰናክሉ በማድረጉ፣ በመላ የሀገሪቱ ቦታዎች የቀበሌ አዳራሾችንና “የእርሻ ሰብል” ይባል የነበረውን ድርጅት የእህል መጋዘኖችን ሌሎች የመንግሥት ንብረቶች የሆኑ አዳራሾችን ሁሉ ሕገ ወጥ በሆነና አግባብነት በሌለው አሠራር ለመናፍቃኑ መስበኪያ መደንከሪያ ማበጃ እየሰጠ ለዚህ የጥፋት ተልእኳቸው የማያሰልስ ድጋፉን በማድረጉ፣ አሁንም በሕገ መንግሥቱ የተከለከለውን ማለትም ማንኛውም ድርጅት “ትምህርት ቤቶችን፣ ጤና ጣቢያዎችን፣ ወፍጮ ቤቶችን ወዘተረፈ. በመክፈት፤ እርዳታ በመለገስ ሃይማኖትን ማስቀየር የተከለከለ ነው!” ቢልም ወያኔ ግን በዚህ ረገድም ለመናፍቃኑ የማያሰልስ ድጋፉን እየሰጠና ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረላቸው ተጠያቂ ሳያደርጋቸው ትምህርት ቤቶችን፣ ጤና ጣቢያዎችን፣ ወፍጮ ቤቶችን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ እየከፈቱ ለተቸገሩ ዜጎች ወርኃዊ እርዳታ በመለገስና ወደ እነሱ እንዲገቡ ሃይማትን እንዲክዱ እያደረጉ እንዲስፋፉ በማድረጉ፣ በአንጻሩ ደግሞ ቤተክርስቲያንን ግን በሾማቸው ከሀዲያን አሳስሮ በማስቀመጥ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን እያሳደደ በማጥፋት፣ ትክክለኛና የቤተክርስቲያን የመንጋው ጉዳይ የሚገዳቸውን አባቶችን መምህራንን ካህናትን በየትኛውም ቤተክርስቲያን ላይ ማገልገል እንዳይችሉ በማድረግና በማባረር በማሳደድ በማጥፋት፣ እራሳቸው መናፍቃን የእኛን ቤተክርስቲያን መድረኮችና የቤተክርስቲያንን ንብረቶች ሁሉ እየተጠቀሙ እንዲስፋፉ በመደረጉ (አባ ጳውሎስ ለመናፍቃኑ የተለያየ ዓይነት ድጋፍ ማድረጋቸው በመረጋገጡ ለመጨረሻ ጊዜ በተሳተፉበት የጳጳሳት ስብሰባ ላይ እነሱ ሲኖዶስ ይሉታል “ሃይማትዎ ምንድን ነው?” ተብለው ተጠይቀው በማግስቱ ለሚቀጥለው ስብሰባ መልስ እንዲያቀርቡ ተቀጥሮ ጳጳሳቱ ቢጠብቁም አባ ጳውሎስ ግን ሳይገኙ መቅረታቸው ያታወሳል) እነዚህ እነዚህን በመሳሰሉ መሰናክልና ፈተናዎች ቤተክርስቲያን እንድትሽመደመድ በመደረጉና እየተደረገም ስላለ ነው መንጋዋ ተጠርጎ የተወሰደው፡፡ ለዚህም ነው አቦይ ስብሐት ነጋ “የኦርቶዶክስን አከርካሪ ሰብረናል እንዳያንሰራራ አድርገን አዳክመነዋል!” ሲሉ የተናገሩት፡፡

መድኃኔዓለም ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ከአጋንንት አፍ ታድጎ ሰላሟን ይመልስ ህልውናዋን ያረጋግጥ ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን አሜን!!!

amsalugkidan@gmail.com

 

The post የቅዱስ ሲኖዶስን ስምና ሥልጣን የተጠቀመው የመናፍቃኑ መግለጫ! appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

Health: ለሚሰነጣጠቅና ለሚደርቅ ከንፈር ቀላል የአጠባበቅ ዘዴ

0
0

dry lips

በሊሊ ሞገስ | Zehabesha

ፊት (Aloe)

ፊት ለቆዳ በጣም አስፈላጊ ጥቅም ይሰጣል፡፡ የፊት ጄልን ሁልጊዜ ከንፈር ላይ በማድረግ የከንፈርን ጤንነት መጠበቅ ይቻላል፡፡

የኮከናት ዘይት (Coconut Oil)

የኮኮናት ዘይት የተሰነጣጠቀ እና የደረቀ ከንፈር እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ትንሽ የኮከናት ዘይት በተደጋጋሚ በተለይ በቅዝቃዜና በደረቅ ወቅት መጠቀም የከንፈርን ጤንነት፣ ውበት እና ልስላሴን ለመጠበቅ ይረዳል፡፡

የፈረንጅ ዱባ (Cucumber)

የተቆረጠ የፈረንጅ ዱባ መውሰድ እና ከንፈርን በዚያ ማሸት (ማሳጅ ማድረግ) የከንፈርን ጤንነት እና ልስላሴን ይጠብቃል፡፡

ማርና ቫዝሊን (Honey and Petroleum Jelly)

ከፍተኛ የምግብነት ኃይል ያለው ማር ባክቴሪያ እንዳይኖርም ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ቆዳን ከድርቀት ይከላከላል፡፡ ማርና ቫዝሊን በመቀላቀል ምርጥ የሆነ ቅባት አዘጋጅቶ መጠቀምም ይቻላል፡፡

አዘገጃጀት እና አጠቃቀም

ትንሽ ማር በመውሰድ መቀባትና እንዲደርቅ ለትንሽ ደቂቃ መጠበቅ፡፡ በመቀጠልም ከንፈር ምንም ሳይንቀሳቀስ ከላይ ትንሽ ቫዝሊን በመቀባት ከ10-15 ደቂቃ እንዲቆይ ማድረግ፡፡ በመጨረሻም ለብ ባለ ውሃ መታጠብ፡፡ ይህንንም በቀን አንድ ጊዜ ቢያንስ ለ5 ደቂቃ ያህል ማድረግ ደረቅ ከንፈር እንዳይኖር ያደርጋል፡፡

ፓፓያ (Papaya)

ፓፓያን በመጠቀም የተሰነጣጠቀ ከንፈርን መከላከል ይቻላል፡፡ የውስጡን ፓፓያ መውሰድና ከ10-15 ደቂቃ ከንፈር ላይ መቀባትና በመጨረሻም መታጠብ፡፡ ከንፈር ለስላሳ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ውሃ

በቂ ውሃን በደንብ አለመጠጣት ደረቅ እና የተሰነጣጠቀ ከንፈር እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ በቀን ከ2-3 ሊትር ውሃ መጠጣት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የከንፈርን መሰነጣጠቅ የሚከላከል ሲሆን ሰውነት ውስጥ የሚገኝንም ቆሻሻ ለማስወገድ ይረዳል፡፡

ቫይታሚን ኤ

የቫይታሚን ኤ እጥረት ለከንፈር መሰነጣጠቅ እና መድረቅ ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡ በቫይታሚን ኤ የበለፀጉ ምግቦችን እንደ ካሮት እና መሰል አትክልቶችን እንዲሁም ቲማቲም የመሳሰሉትን መመገብ ከንፈርን ጤናማ እና ለስላሳ ያደርጋል፡:

The post Health: ለሚሰነጣጠቅና ለሚደርቅ ከንፈር ቀላል የአጠባበቅ ዘዴ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live