Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ትህዴን በአስመራ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማስመረቁን አስታወቀ

0
0

TPDM

TMDM 2
የሕወሓት መንግስት ሞላ አስገዶምን አስኮብልሎ ወደ ኢትዮጵያ ካስገባ በኋላ ካሁን በኋላ ትህዴን የሚባል ድርጅት አስመራ ውስጥ የለም ሲል ፕሮፓጋንዳ ሲነዛ ቢቆይም አስመራ የሚገኘው ትህዴን አዳዲስ ምልምል ወታደሮችን ማስመረቁን አስታውቋል::

የትህዴን ድምጽ እንደዘገበው የትህዴን ማሰልጠኛ ክፍል ሰልጣኝ አሰር የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸው ለበርካታ ወራት በወታደራዊ በፓለቲካዊ በማሰልጠኛ የቆዩትን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኝ በጥቅምት 20 /02/2008 ዓ/ም የበላይ ሃላፊዎች፥ ወታደራዊ አዛዥ የትህዴን ደጋፊና ወንድማዊ ድርጅቶዎች እንዲሁም የትግል ደጋፊ በተገኙበት እንግዶዎች በደመቀ ሁኔታ አስመርቋዋል።
በዚህ ምረቃ ላይ የተገኙ የትህዴን የበላይ አመራር መኮንን ተስፋየ ባሰሙት ቃል አንዳንድ ወላዋይ የሆኑ ታጋዮች የትግል መሰመር እየለቀቁ ቢሂዱም የትህዲን ድርጅት ትግል ግን በተቃራኔው በወታደራዊ በፓለቲካዊ አቅም በመጠናከር ወደፊት በመገስገስ ላይ እንደሚገኝና እንዲዚሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ አሰር ተመራቂዎች በቂ እውነተኛ ምስክር መሆናቸውን በንግግራቸው ባሰሙበት ወቅት ገልፀዋል።

ይህን ብአል ለማድመቅ የሚያስፈልጉ ነገሮች አዘጋጅተው የተገኙ የትህዴን የባህል ቡድን በተለያዩ የአገራችን ቋንቛዎች በተዋሃዱ ዜማዎችና ድርማዎች ይዘው የቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም ሌሎችም ዝግጅቶዎች ጨምረው ለተመራቂ ሰልጣኞዎች በደመቀ ሁኔታ አቅረበዋል።

The post ትህዴን በአስመራ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማስመረቁን አስታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.


በደቡብ ክልል የሐመር ሕዝቦች 25% የሚሆነው ሕዝብ በድርቅ ምክኒያት በምግብ እጥረት እየተጎዳ ነው

0
0

በኢትዮጵያ በደቡብ ክልል የሚገኙ የሃመር ህዝቦቸ አጋጥሞት ባለው ድርቅ ምክንያት 25% የሚሆነው ህዝብ እርዳታ ጠባቂ ከመሆኑ ምክንያት ተሎ የሚደርስላቸዉ መንግስት ኣካል ባለመኖሩ በምግብ እጥረት እየተጎዱ መሆናቸው ተዘገበ::

hamer ethiopia
ዜናውን የዘገበው የደህሚት ድምጽ በደቡብ ክልል ሃመር አካባቢ በህዝቡ ላይ አጋጥሞት ያለው ድርቅ በሰውና በእንስሳት ከፍተኛ የምግብ ችግርና ከባድ አደጋ ላይ በመወደቁ ምክንያት በተለይ በአሁኑ ውቅት በጠቅላላው የዚህ ኗሪ ህዝብ 25% የሚሆነው። የእርዳታ ጠባቂ ሆኖ በሚገኘበት ሰአት ገዢው መንግሰት እርዳታ ሊያገኝ ባለመቻሉም የተነሳ ህዝቡ ድርቅ በፈጠረው ችግርና ስቃይ ውስጥ ገብቶ እንዳለ ዘገባው አመልክቷል።
መረጃው በማስከተል በስልጣን ላይ ያለው ስረአት በኢትዮጵያ ያለው ፈጣን እደገት ለሶስት አመት ለድገተኛ አደጋ ሊውል የሚችል ሃብት ሰብስበናል እያሉ ሲናገሩ ቢቆዩም አሁን ግን በአገር ደረጃ በድርቅ ተይዞ ያለው 8.5 ሚሊዮን ህዝብ ለመመገብ 500 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ሲታወቅ። ለአለም የእርዳታ ለጋሽ አገሮች ልመና መጠየቅ መልእክት እያስተላለፈ ይገኛል፣ ከዚህ በፊት ለሶሰት አመት ለድንገተኛ አደጋ የሚሆን ገንዘብና ሃብት አለን የሚባለው አነጋገር የነበረው ይቅርና ለሶሰት ወር የሚሆን መመገብ አቅቷቸው እጃቸውን ወደ ልመና መዘርጋትና መቅረብ እስከ አሁን ድረስ ሲናገረው የነበር ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ መሆኑን የአገሩና የአለም ህዝብ ለማደናገር የተጠቀመው ስልት እንደሆነ መረጃው ጨምሮ አስረደቷል።

The post በደቡብ ክልል የሐመር ሕዝቦች 25% የሚሆነው ሕዝብ በድርቅ ምክኒያት በምግብ እጥረት እየተጎዳ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቁስለኛ ወታደሮች ዳሽ-6 በተባለ አውሮፕላንና ኤም.አይ-17 ሄሊኮፕተር ከሶማሊያ አየተጫኑ ድሬ ደዋ ላይ በመራገፍ ላይ ናቸው

0
0
Photo File

Photo File

የህወሓት አገዛዝ የሚቆጣጠረው መከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑ እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቁስለኛ ወታደሮች ዳሽ-6 በተባለ አውሮፕላንና ኤም.አይ-17 ሄሊኮፕተር ከሶማሊያ አየተጫኑ ድሬ ደዋ ላይ በመራገፍ ላይ ናቸው

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) ራሱን በመንግስትነት ስም የሚጠራው የማፍያው ቡድን ህወሓት የምዕራባዊያንን ቁሳዊና ፖለቲካዊ ድጋፍ በማግኘት ስልጣኑን ለማደላደል ሲል ብቻ ከ10 ዓመታት በፊት ማለትም ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ የድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ የሆኑ ዕልፍ አዕላፍ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ያለማቋረጥ ወደ ሶማሊያ በረሃማ ምድር እያስገባ እጅግ በጣም አሰቃቂ ለሆነ እልቂት እየዳረጋቸው ይገኛል፡፡

የህወሓት አመራሮች የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረትን ከሁለት ሳምንታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በመደምሰስ አፈራርሰውት ለቀው እንደሚወጡ ለህዝቡ ገልፀው ወደ ምድራዊ ሲኦል ወደሆነችው ሶማሊያ ጦር ጭነው ያስገቡ ሲሆን ነገር ግን አልሸባብ የተባለ ሌላ ፅንፈኛ ቡድን ፈጥረው ምስኪን ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን ከማይወጡበት የጦርነት አዙሪት ውስጥ ከተዋቸው ለድፍን 10 ዓመታት ሰቅጣጭ የሞት ገፈትን ሲግቷቸው ቆይተዋል፡፡ ቀጠናውንም የባሰ አለመረጋጋት እንዲሰፍንበት አድርገውታል፡፡
በዶላር ፍቅር ዓይኑ የታወረው የህወሓት አገዛዝ ከ10 ዓመታት በፊት ጦሩን ወደ ሶማሊያ ሲያስገባ እሱ እንደሚነግረን መጀመሪያ ላይ ጦርነት የገጠመው ከእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት ሽምቅ ተዋጊዎች ጋር ብቻ ሳይሆን በዋነኝነት ከሶማሊያ ጎሳዎች መካከል በጠንካራነቱና በታላቅነቱ ከሚታወቀው የሃውዬ ጎሳ ጋር ነበር፡፡ በመሆኑም በገብረ ዲላ እና በሌሎች ህወሓታዊ ድኩማን የጦር አዛዦች የሚመሩት 43ኛ እና 44ኛ ክፍለ ጦር ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል፤ መሪዎቹ ጭነዋቸው የሄዱትን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮች ለሶማሊያ በረሃ ገብረው አምስትና ስድስት ወታደሮችን ብቻ አስከትለው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡ ሞቃዲሹ ውስጥ አንድ የሃውዬ ጎሳ አባል በአንድ ህንፃ ውስጥ መትረየስ ጠምዶ ቢያንስ አንድ ሻምበል ጦር ብቻውን ጨርሷል፡፡ የድሃ ልጆች ለኢትዮጵያ ምንም አይነት ጠቀሜታ በሌለው ጦርነት በክንቱ ደማቸው ፈሶ ረግፈው ያለቀባሪ ቀርተዋል፡፡ አሁንም በዘግናኝ ሁኔታ መገደላቸው ቀጥሏል፡፡ ሬሳቸውም እንዳያርፍ ተፈርዶበት በየጎዳናው በገመድ ታስሮ ሲጎተት ታይቷል፡፡
ምንም እንኳን አሮጌዎቹ የአየር ኃይል አውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች የወታደር ሬሳና ቁስለኛ ወደ ድሬ ደዋ ያለማቋረጥ ማመላለስ የጀመሩት ካለፈው 2007 ዓ.ም ጀምሮ ቢሆንም አሁን አሁን ደግሞ የባሰውኑ ስራ በዝቶባቸዋል፡፡ ዳሽ-6 አውሮፕላንና ኤም.አይ-17 ሄሊኮፕተር በቁስለኛ ወታደሮች ጥቅጥቅ ብለው ተሞልተው ከወደ ሶማሊያ እየመጡ ድሬ ደዋ ላይ በማራገፍ ላይ ናቸው፡፡
ከሶማሊያ በአውሮፕላንና በሄሊኮፕተር ተጭነው ድሬ ደዋ ላይ የተራገፉት ቁስለኛ የሰራዊቱ አባላት ወደ ሐረር ወታደራዊ ሆስፒታል እየተወሰዱ በመግባት ላይ ናቸው፡፡ በመሆኑም የሐረሩ የመከላከያ ሆስፒታል ከአቅሙ በላይ በቆስለኞች መሞላቱን የሆስፒታሉ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
ሆኖም ለቁስለኞች የሚደረገው ህክምና እና እንክብካቤ በራሱ ከአድሏዊነት የፀዳ እንዳልሆነ ተጎጅዎች ቅሬታቸውን እየተናገሩ ነው፡፡ የህወሓት ታጋዮች የነበሩ የሰራዊቱ አባላት ሆዳቸውን በቆረጣቸው ቁጥር ደቡብ አፍሪካና ሳዑዲ አረቢያ ድረስ እየሄዱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እየታከሙ ተገደው የሶማሊያው ጦርነት ውስጥ ተማግደው ስጋቸው በእሳት ተጠብሶ የተመለሱት ወታደሮች ግን ጦር ኃይሎች ሆስፒታልን እንኳን በዓይኖቻቸው የማየት እድላቸው የጠበበ እንደሆነ እና አካላቸውን ላጡትም ምንም አይነት የሞራልም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ እንደማይደረግላቸው ብሶታቸውን ዘርዝረዋል፡፡
በተጨማሪም ሶማሊያ ውስጥ የሚገኙ የአየር ኃይል አባላት በአውሮፕላኖችና ሄሊኮፕተሮች ብልሽትና እንዲሁም የመለዋወጫ እጥረት ምክንያት ስራ ፈትተው ለረጂም ጊዜ በመቀመጣቸው በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ያዘለ ጥያቄ በአንድነት አንስተዋል፡፡ የአየር ኃይሉ ምክትል አዛዥ ጀነራል ማዕሾ ሐጎስ ወደ ቦታው አምርቶ ጥያቄ ያነሱ አባላትን የማረጋጋት ሙከራ ያደረገ ቢሆንም ለተነሳው ጥያቄ ተገቢ መፍትሄ ባለመሰጠቱ አሁንም ቅሬታው ባለበት ቀጠለ እንጂ ሊቀረፍ አልቻለም፡፡
የእነዚህን ሶማሊያ ዘማቾች የአየር ኃይል አባላት ሚስቶች የምስራቅ አየር ምድብ አዛዥ የሆነው ኮሎኔል አበበ ተካ በየተራ እያማገጠ እንደሚገኝም ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡
በአጠቃላይ ሰሞኑን በኢትዮጵያና በሶማሊያ አዋሳኝ ድንበር ላይ በህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊትና በአልሸባብ ተዋጊዎች መካከል ከባድ ጦርነት እንደተካሄደ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

The post ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቁስለኛ ወታደሮች ዳሽ-6 በተባለ አውሮፕላንና ኤም.አይ-17 ሄሊኮፕተር ከሶማሊያ አየተጫኑ ድሬ ደዋ ላይ በመራገፍ ላይ ናቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

ከወያኔ አዲሱ ማደናገሪያ ይጠንቀቁ –በረከት ስምዖን ጉዳይ…

0
0

በጠዋቱ ወደ ዘ-ሐበሻ ዝግጅት ክፍል የሚደርሱ መረጃዎች በጠቅላላ “ድሬ ቲዩብ የተባለ ድረ ገጽ በረከት ስምዖን ሞቱ ብሎ ዘግቧል:: መረጃው እውነት ነው ወይ?” የሚሉ ናቸው:: ራሱ ድሬ ቲዩብ ድረገጽ እንዳሰራጨው መረጃ “በስሜ ሌሎች ሰዎች ያስወሩብኝ ወሬ እንጂ እኔ ማንም ባለስልጣን ሞተ ብዬ አልዘገብኩም” ብሏል::

bereket

ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል እንደሚባለው ወያኔዎች በየጊዜው ሕዝቡን ለማደናገር የተለያዩ ዘዴዎችን እንደሚጠቀሙ ይታወቃል:: በኢትዮጵያ ውስጥ የነፃ ፕሬስ ጋዜጦችን ለማስጠላትና በሕዝብ ዘንድ ተአማኒነትን እንዳያገኙ ለማድረግ ራሱ ወያኔ ራሱ ባሰማራቸው ሰዎች የግል ጋዜጣ በማውጣትና ሐሰተኛ ወሬዎችን ለሕዝብ በማድረስ በኋላም ይህን ራሱ ያሰራጨውን ሃሰተኛ ዜና በሚቆጣጠራቸው ቲቭ እና ራድዮ “እዩ እነዚህ የግል ጋዜጦች የሚዘግቡትን ሃሰት እያለ” በአንዱ ስም ሌላውን ሲያጥላላ እና ተአማኒነት እንዲያጡ ሲያደርግ ቆይቷል::

አሁን ለሕወሓት መንግስት ራስ ምታት የሆነበት መረጃዎች በፍጥነት የሚደርሱት በሶሻል ሚዲያዎች እና በድረ ገጾች መሆኑ ነው:: በሃገሪቱ ያሉ ነፃ ጋዜጦች ተዘግተው ከ150 በላይ ጋዜጠኞቿ በተሰደዱባት ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት ከመንግስት ጫና ነፃ የሆነ ሚዲያ የላትም:: አብዛኞቹ መረጃዎች ከውጭ ሃገርም ሆነ ከሃገር ውስጥ የሚሰራጩት በድረገጾች እና በሶሻል ሚድያዎች በመሆኑ የሕወሓት መንግስት ሕዝቡ እነዚህን እንዳያምን ከዚህ ቀደም ያደርጋቸው የነበሩትን ዘዴዎችን በመጠቀም ላይ ነው::

ከነዚህም መካከል ራሱ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ራሱ የሚያስተባብልበት መንገድ አንደኛው ነው:: ሁለተኛው ደግሞ በርካታ ተሳዳቢዎችን በሶሻል ሚድያ በማሰማራት አንዱ አንዱን ብሄር እንዲሳደብና እንዲከፋፈል የሚያደርገው ጥረት ነው::

የሕወሓት መንግስት የኢትዮጵያን ሕዝብ ከናቀው ቆይቷል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቅ አይመስለውም:: ሕዝብ ግን ከመንግስት በላይ የነቃና ሁሉን የሚያውቅ መሆኑን በተደጋጋሚ አውቋል:: አሁንም ሕዝቡ እንደ በረከት ስምዖን ሞቱ አይነት የሕወሃት መንግስት ሆን ብሎ የሚያሰራጫቸውን ዜናዎች በብልጠት በማየት ጥሬውን ከገለባው መለየት ይኖርበታል::

በርግጥ አቶ በረከት በከፍተኛ ሕመም እንደሚሰቃዩና በተደጋጋሚ በሳዑዲ አረቢያ; በደቡብ አፍሪካና የተለያዩ ሃገሮች ህክምናቸውን እየተከታተሉ ወደ ሃገር ቤት እንደሚመላለሱ የታወቀ ነው:: ሼህ መሀመድ አላሙዲም በአንድ ወቅት ደቡብ አፍሪካ እጁን አንጠልጥዬ ወስጄ ያሳከምኩት እኔ ነኝ ሲሉ ስለ አቶ በረከት መናገራቸው አይዘነጋም::

The post ከወያኔ አዲሱ ማደናገሪያ ይጠንቀቁ – በረከት ስምዖን ጉዳይ… appeared first on Zehabesha Amharic.

ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ አሜሪካ ገባች

0
0
በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ አቀባበል አድርገዋል

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ አቀባበል አድርገዋል

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ አቀባበል አድርገዋል

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ አቀባበል አድርገዋል

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ አቀባበል አድርገዋል

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ አቀባበል አድርገዋል

(ዘ-ሐበሻ) በቅርቡ ከሕወሓት መንግስት እስር ቤት የተለቀቀችው ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ ዛሬ አሜሪካ ገባች::

ዛሬ ኖቬምበር 7, 2015 ዋሽንግተን ዲሲ ዱልስ ኤርፖርት የደረሰችው ርዕዮት በዲሲና አካባቢዋ በሚኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ደማቅ የሆነ የ እንኳን ደህና መጣሽ አቀባበል አድርገውላታል::

በሕወሓት መንግስት እስር ቤት ውስጥ ስቃይ ሲደርስባት የቆየችው ጠንካራ ሴት በበቀል ተነሳስተው ህክምና ሁሉ ሳይቀር ከልክለዋት ሲበቀሏት እንደነበር በተደጋጋሚ ሲዘገብ ቆይቷል:: ዓለም አቀፍ ተቋማት በታሰረችበት ጊዜ ሲሸልሟት የቆየችው ር ዕዮት ለበርካታ ሴቶች ተምሳሌት በመሆን ትጠቀሳለች::

ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ ምናልባትም በሰሜን አሜሪካ ቆይታዋ ትምህርቷን ልትቀጥል እንደምትችል ይገመታል::

The post ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ አሜሪካ ገባች appeared first on Zehabesha Amharic.

ፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ ዜናዎች:- ውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውን ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የገንዘብ ፈሰስ በአመት 1.5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ * የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትን ለመገምገምና የተወሰኑትን ለማባረር እቅድ መኖሩ ታወቀ * የሱማሊያ ፍርድ ቤት ህገ ወጥ የሆኑ ዜጎች ከአገር እንዲወጡ አዘዘ * የዘንድሮ የወያኔ ብሄረሰብ ቀን በጋምቤላ ይደረጋል የተባለ ሲሆን የግዳጅ መዋጮ ተጀምሯል እና ሌሎችም…

0
0

national bank of ethiopia
ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ በሳተላይት የሚሰራጭ የራዲዮ ፕሮግራም

# የዘንድሮ የወያኔ ብሄረሰብ ቀን በጋምቤላ ይደረጋል የተባለ ሲሆን የግዳጅ መዋጮ ተጀምሯል
# ውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውን ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የገንዘብ ፈሰስ በአመት 1.5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ
# የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትን ለመገምገምና የተወሰኑትን ለማባረር እቅድ መኖሩ ታወቀ
# ሳኡዲ አረቢያና የተባበሩት ኤምሬት ለሻዕቢያ የሰጡት ገንዘብ የጸጥታውን ምክር ቤት ውሳኔ የሚጻረር መሆኑን ተመድ ገለጸ
# በብሩንዲ ዜጎች ከግጭቶች ለማምለጥ ቤት ንብረታቸው ጥለው በመሸሽ ላይ ናቸው
# የሱማሊያ ፍርድ ቤት ህገ ወጥ የሆኑ ዜጎች ከአገር እንዲወጡ አዘዘ
# በረሃብ በተጠቁ የደቡብ ሱዳን ክፍሎች እርዳታ ማድረስ ያልተቻለ መሆኑን የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ገለጹ
# በርናርዲኖ ሊዮን ኃላፊነታቸውን ለግል ጥቅም ማራመጃ አውለዋል ተብለው ተከሰሱ
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to listen detail news click below)

The post ፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ ዜናዎች:- ውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውን ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የገንዘብ ፈሰስ በአመት 1.5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ * የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትን ለመገምገምና የተወሰኑትን ለማባረር እቅድ መኖሩ ታወቀ * የሱማሊያ ፍርድ ቤት ህገ ወጥ የሆኑ ዜጎች ከአገር እንዲወጡ አዘዘ * የዘንድሮ የወያኔ ብሄረሰብ ቀን በጋምቤላ ይደረጋል የተባለ ሲሆን የግዳጅ መዋጮ ተጀምሯል እና ሌሎችም… appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ስንፈተ-ወሲብ መንስኤዎቹን እንዴት መለየት ይቻላል?

0
0

ስንፈተ-ወሲብ ማለት የወንዱ ብልት ግንኙነት ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ መዘጋጀት (መቆም) አለመቻል ሲሆን ግንኙነት ከተጀመረ በኃላም ቶሎ ጥንካሬውን በማጣት ከግንኙነት በፊት ወደነበረው ሁኔታ መመለስ ማለት ነው፡፡
ስንፈተ-ወሲብ ማለት የወንዱ ብልት ግንኙነት ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ መዘጋጀት (መቆም) አለመቻል ሲሆን ግንኙነት ከተጀመረ በኃላም ቶሎ ጥንካሬውን በማጣት ከግንኙነት በፊት ወደነበረው ሁኔታ መመለስ ማለት ነው፡፡

sexual-problems
(ስንፈተ-ወሲብ) – ስንፈተ-ወሲብ ማለት የወንዱ ብልት ግንኙነት ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ መዘጋጀት (መቆም) አለመቻል ሲሆን ግንኙነት ከተጀመረ በኃላም ቶሎ ጥንካሬውን በማጣት ከግንኙነት በፊት ወደነበረው ሁኔታ መመለስ ማለት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ ምን ያህል ወንዶች የችግሩ ሰለባ ናቸው የሚለውን ለማወቅ የሚያስችሉ ጥናቶች ባይደረጉም በአሜሪካ ብቻ ከ15-30 ሚሊዮን የሚደርሱ ወንዶች ለስንፈተ ወሲብ ተዳርገዋል። በዚህም ምክንያት ብዙ ወንዶች ለስነልቦና ችግሮች ተጋልጠዋል ብዙ ትዳሮችም የመፍረስ ዕድል አጋጥሟቸዋል፡፡ የወንድ ልጅ ብልት ለግንኙነት ዝግጅ እንዲሆን የተለያዩ ወሲብ ቀስቃሽ ከሆኑ ነገሮች ጋር በተያያዘ ከአንጎላችን ወደ ነርቮቻችን መልዕክት ይተላለፋል በዚህም ምክንያት በብልት ውስጥ የሚገኙ የደም ስሮች ይለጠጡና ደም ወደ ብልት ይገባል ከገባም በኃላ እስፖንጅ መሳይ ክፍሎች ደሙን መጥጠው በመያዝ ለወሲብ ዝግጅ እንዲሆንና በግንኙነት ወቅትም ተገቢው እርካታ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ጥንካሬውን እንዲጠብቅ ያስችሉታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ቴስተስትሮን/ Testosterone የተባለው ሆርሞን በሰውነታችን ውስጥ በተገቢው መጠን መኖሩ ለሂደቱ ጠቃሚ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ከላይ ያየናቸው ጤናማ ተፈጥሮአዊ ስርዓቶች በተለያዩ ምክንያቶች ሊስተጓጎሉ ይችላሉ በዚህም ምክንያት ስንፈተ ወሲብ ሊከሰት ይችላል፡፡

ስንፈተ ወሲብና መንስኤዎቹ

– የልብና ከልብ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ህመሞችና የስኳር በሽታ ችግሩን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ከእነዚህ የጤና ችግሮች ጋር በተያያዘ በተለይም ከስኳር በሽታ ጋር በተያያዘ በሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ ደምን የሚያስተላልፉ የደም ስሮ ለከፍተኛ ጉዳት ይጋለጣሉ በዚህም ጤናማ የሆነ የደም ዝውውር ይስተጓጎልና ችግሩ ይከሰታል፡፡ አንዳንድ የምርምር ውጤቶችን እንደሚያሳዩት ከ35-50 ፐርሰንት የሚሆኑት የስኳር ህመምተኞች ለዚህ ችግር የመጋለጥ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡

Testosterone “ቴስተስትሮን” የተባለው ሆርሞን እጥረት በሰውነታችን ውስጥ ካለ ለወሲብ ያለን ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስና አንዳንድ ጊዜ ለስንፈተ ወሲብ ሊያጋልጠን ይችላል፡፡

ለተለያዩ ህመሞች ህክምና ተብለው የሚወሰዱ አንዳንድ መድኃኒቶች ከሚያስከትሉት የተለያዩ የጎንዮሽ ጉዳቶችም ውስጥ ስንፈተ ወሲብ ይገኝበታል በእነዚህ መድኃኒቶች እስከ 25 በመቶ ለሚሆነው ስንፈተ ወሲብ መከሰት ምክንያት ናቸው፡፡

ከ10-20 በመቶ የሚሆኑት መንስኤዎች ደግሞ ስነ ልቦናዊ ችግሮች ናቸው። ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛ ጭንቀት፣ ለራሳችን ያለን ዝቅተኛ አመለካከት ምክንያታዊ ያልሆነ የጥፋተኝነት ስሜት፣ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ያለን ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት፣ ወሲብን እንደአስፈሪ ነገር አድርጎ መቅረፅ የመሳሰሉት ይገኝለታል፡፡

በአንጎልና በህብለሰረሰር እንዲሁም በተለያዩ የደም አስተላላፊ ቧንቧዎችና የደምስሮች ላይ የሚከሰቱ አደጋዎች ለችግሩ መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የተለያዩ ጎጂ ሱሶች ችግሩን ያስከትላሉ ከእነዚህም ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጋራን ማጨስ የደም ስሮችን እንዲጠቡ በማድረግ ጤናማ የሆነውን የደም ፍሰት በማስተጓጎል ስንፈተ ወሲብን ሊያመጣ እንደሚችል እንዲሁም አልኮልን አብዝቶ መጠጣት በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ቴስተስትሮን/Testosterone/ የተባለውን ሆርሞን ምርት በመቀነስ ለወሲብ ያለን ፍላጎት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖችን ያስከትላል፡፡

የፕሮስቴትና የፊኛ ካንሰር ቀዶ ጥገናዎችና እንዲሁም በፈንጢጣና ብልት አካባቢ የሚደረጉ ቀዶጥገናዎች የተለያዩ ነርቮችን ሊጎዱ ስለሚችሉ አልፎ አልፎ ለችግሩ ሲያጋልጡ ይስተዋላሉ፡፡

የኩላሊት ህመም

ደካማ የሆነ የጤናና የአመጋገብ ሁኔታ

ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት

ከማንኛውም ጎጂ ሱሶች ራሳችንን መጠበቁ ችግሩ ሳይመጣ ለመከላከል ይረዳናል ሲጋራ፣ አልኮል፣ ጫት የመሳሰሉትን ጎጂ ነገሮች የምንጠቀም ከሆነ እነዚህን ነገሮች ማቆም ያኖርብናል። – አንዳንድ ጥናቶች ስንፈተ ወሲብ ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ ሊመጣ እንደሚችል ያሳያሉ፡፡ 5 በመቶ በሚሆኑት ዕድሜያቸው በ40ዎቹ ክልል ውስጥ በሚገኝና ከ15-25 ፐርሰንት በሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ በሆናቸው ሰዎች ላይ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ በተጨማሪም በ2002 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በየቀኑ ለረዥም ሰዓታት ብስክሌት መንዳት የተለያዩ ነርቮች ላይ ጉዳት በማድረስ የችግሩ መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።

መንስኤዎቹን እንዴት መለየት ይችላል?

– የስንፈተ ወሲብን መንስኤዎች ለማጠራት የሚደረጉ የተለያዩ አይነት ምርመራዎች አሉ ከእዚህም መካከል የሰውየውን ያለፈ የጤናና የወሲብ ታሪኩን ጠይቆ በመረዳት እንዲሁም ይህ ሰው ከዚህ በፊት ምን ዓይነት የጤና ችግር እንደነበረበትና ለእነዚህም ችግሮች ህክምና ምን አይነት መድኃኒቶችን እንደተጠቀመ ወይም እየተጠቀመ እንዳለ ለይቶ በማውጣት ችግሩ በመድኃኒት ወይም በሌላ ምክንያት እንደተከሰተ ለይቶ ማወቅ ይችላል፡፡ – አካላዊ ምርመራ በማድረግ ከእነዚህም ውስጥ የሰውየውን የደም ግፊትና የልብ ምት መጠንን በመለካት ትክክለኛ የሆነ የደም ስርጭትና ዝውውር መኖሩን ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡ እንዲሁም ሰውየው ብልቱ አካባቢ በሚነካበት ወቅት ምንም አይነት ስሜት የማይሰማው ከሆነ መንስኤው ከነርቭ ጋር የተያያዘ እንደሆነ በቀላሉ ለመረዳት ያስችላል፡፡ – በላቦራቶሪ በሚደረጉ ምርመራዎች “ቴስተስትሮን” የተባለውን ሆርሞን በሰውነት ውስጥ ያለውን መጠን በመለካት ለችግሩ መንስኤ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡ – ለችግሩ ሰላባዎች የተለያዩ ስነልቦናዊ ምርመራዎችን ማድረግ

ስንፈተ ወሲብና ህክምናዎቹ

ለስንፈተ ወሲብ የሚሰጡ ህክምናዎች እንደየመንስኤያቸው የተለያዩ ናቸው፡፡ የህክምና ባለሙያዎች እንደሚገልፁት የችግሩ መንስኤ የሆኑትን ነገሮች መለየትና እነዚህንም መንስኤዎች መቆጣጠር መቻል ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠቁማሉ፡፡ 1. ከማንኛውም ጎጂ ሱሶች ራሳችንን መጠበቁ ችግሩ ሳይመጣ ለመከላከል ይረዳናል ሲጋራ፣ አልኮል፣ ጫት የመሳሰሉትን ጎጂ ነገሮች የምንጠቀም ከሆነ እነዚህን ነገሮች ማቆም ያኖርብናል። 2. ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ማስወገድ ይኖርብናል፡፡ በጤና ባለሙያ በመታገዝ የአመጋገብ ስርዓትን መለወጥ አስፈላጊ ነው ለምሳሌ ከፍተኛ የሆነ ጨውና ጣፋጭ የበዛባቸውን ምግቦች መቀነስ እንዲሁም ፍራፍሬና አትክልቶችን አዘውትሮ በመመገብ ጤናማ የሰውነት ክብደት ክልል ውስጥ መግባት ይቻላል፡፡ የተለያዩ እስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍም ያስፈልጋል፡፡ 3. የችግሩ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉትን የስኳርንና የደም ግፊትን ህመም ከጤና ባለሙያ ጋር በመመካከር በሚገባ መቆጣጠርና የሚታዘዙልንን መድኃኒቶች በአግባቡ መውሰድ ይኖርብናል። 4. በተለያዩ በሽታዎች ህክምና የምንወስዳቸው መድኃኒቶች ካሉ እነዚህን መድኃኒቶች ለጤና ባለሙያ በማሳየት የችግሩ መንስኤ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ማጣራት ይገባናል 5. መንስኤው ስነ ልቦናዊ ችግሮች መሆናቸው ከተረጋገጠ የሥነ-ልቦና ባለሙያዎችን ማማከርና ምክሩንም ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ ይገባናል፡፡ ከፍቅር አጋራችን ጋር ግልፅ የሆኑ ውይይት ማድረግ፣ ለራሳችን ያለንን ዝቅተኛ አመለካከት ማስተካከል፣ ጭንቀትን ማስወገድ ይኖርብናል፡፡ እነዚህ ከላይ ያየናቸው ህክምናዎች ማንኛውም የችግሩ ሰለባ ተግባራዊ ሊያደርጋቸው የሚችሉና በቀላሉ ከፍተኛ ለውጥ ሊያስገኙ የሚችሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ የችግሩ መጠን ከፍ ሲል የተለያዩ መድኃኒቶችን መጠቀም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ችግሩ የተከሰተው ቴስተስትሮን በተባለው ሆርሞን ማነስ ምክንያት ከሆነ ይህ ሆርሞን መጠኑ እንዲስተካከል በጤና ባለሙያ የሚታዘዙ መድሐኒቶችን መጠቀሙ መፍትሔ ሊያመጣ ይችላል፡፡ ባሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ በገበያ ውስጥ ተሰራጭተው በጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት መድሐኒቶች sildenafil (viagra), Verdanafil & Taldanafil የተባሉት መድኃኒቶች ሲሆኑ እነዚህም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የጠበቡትን የደም ስሮች እንዲለጠጡ (እንዲሰፋ) በማድረግና የደም ዝውውርን በማስተካከል ለችግሩ ከፍተኛ መፍትሔ ይሰጣሉ፡፡ እነዚህ መድኃኒቶች ተገቢው የጤና ምርመራ ከተደረገ በኃላ በጤና ባለሙያ የሚታዘዙ ሲሆኑ ባአሁኑ ወቅት ግን የችግሩ ሰለባዎች ያለህክምና ባለሙያ ትዕዛዝ እነዚህን መድኃኒቶች ገዝተው ሲጠቀሙ ይስተዋላል ይህም ለከፋ የጤና ችግር ሊዳረግ ይችላል። ምክንያቱም እነዚህ መድኃኒቶች እንደማንኛውም መድኃኒት የራሳቸው የሆነ የጎንዬሽ ጉዳት አላቸው። ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት፣ የምግብ ያለመፈጨትና የሆድ ህመም፣ የእይታ ችግር በተለይም ብርሃንን ለመለየት መቸገርና ቀለሞችን ያለመለየት እና የመሳሰሉትን ጊዜያዊ ችግሮች ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም እነዚህ መድኃኒቶች ከተለያዩ መድኃኒቶች ጋር በተለያየ ለልብ ህመምና የደም ግፊትን ለማስከተል ከሚወሰዱ አንዳንድ መድኃኒቶች ጋር ስለሚጋጩ እነዚህን መድኃኒቶች ያለህክምና ባለሙያ ትዕዛዝ ገዝቶ መጠቀም ለጉዳት ሊያጋልጠን ይችላል፡፡ ከላይ ካየናቸው መድኃኒቶች በተጨማሪ በበለፀጉት ሀገራት በወንዱ ብልት ላይ በቀጥታ በመርፌ የሚወጉ እንዲሁም አልፕሮስታዲል (Alprostadil) የተባለ ንጥረ ነገር የያዙ በቅባት መልክ የተዘጋጁ መድኃኒቶች፤ የተለያዩ የሚነፉ እስፕሬዎች በጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ በቀዶ ጥገና አማካኝነት የሚቀበሩና የተስተካከለ የደም ፍሰት በመፍጠር ብልት ለወሲብ እንዲዘጋጅ የሚረዱ መሳሪያዎችንም በስፋት ወደገበያ እየገቡ ነው፡፡

 

Source: Farmanet Magazine

The post Health: ስንፈተ-ወሲብ መንስኤዎቹን እንዴት መለየት ይቻላል? appeared first on Zehabesha Amharic.

ከፖለቲካው በስተጀርባ ያሉት እውነታዎች –ከተማ ዋቅጅራ

0
0

ክፍል

በክፍል ሁለት በደርግ አገዛዝ ዘመን እና በወያኔ አገዛዝ ዘመን ያሉትን እውነታዎች ከብዙ በጥቂቱ ተመልክተናል ክፍል ሦስት እንሆ:-

ወያኔዎች በኃይል ስልጣን ከያዙበት ግዜ ጀምሮ በሁሉም ረገድ እነሱ ብቻ የበላይ የሚሆኑበትን ስራ በመስራት ሌላው  ኢትዮጵያዊ እውቀት ያለውን ችሎታ ያለውን ከሚሰራበት ከፍተኛ ቦታ እየተባረረ እውቀት እና ችሎታ በሌላቸው በወያኔ ሰዎች እየተተካ በመባረር የበዪ ተመልካች መሆን ከተጀመረ ሰናባብቷል። በተለይ ደግሞ ከዘጠና ሰባት ምርጫ በኋላ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ሃገር ዘረፋ በቀጥታ በመግባት የኢትዮጵያን ጠቅላላ ኢኮኖሚ በማን አለብኝነት በመቆጣጠር ዛሬ የድርጅት ባለቤት እነሱ፣ የትልልቅ ህንጻ ባለቤት እነሱ፣ አስመጪና ላኪዎች እነሱ፣ ባጠቃላይ ከህዝቡ በስተቀር የኢትዮጵያ ሃብትና ንብረት የነሱ ብቻ እንደሆነ አውጀው በህዝባችን ላይ መቀለድ ከጀመሩ ቆይተዋል። ወያኔዎች በዘረፉት ንብረት የፈለጉትን ገዝተው መብላት ስለቻሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ርሃብ የለም ብለው የሚያወሩ፣ እነርሱ ሃብት ስላካበቱ ደሃ ጠፍቷል ብለው የሚሳለቁ፣ እነርሱ ባለ ብዙ ህንጻ እና ባለሞዴል መኪና ባለቤት ስለሆኑ ኢትዮጵያ አድጋለች ተለውጣለች ብለው የሚደሰኩሩ ባአጠቃላይ  ኢትዮጵያ ማለት ወያኔ ወያኔ ማለት ኢትዮጵያ አድርገው በመሳል የዘጠና ሚሊዮን ህዝብ ስቃይና ችግር መታየት ያልቻላቸው የ21ኛው ክፍለ ዘመን አውሬ በመሆን የተቀመጡ መቼም ከስተታቸው የማይማሩ የክፍለ ዘመኑ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ያላቸው ፍጡሮች ናቸው። ኢትዮጵያዊ የሚመስሉ ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ለህዝቡም ሆነ ለአገሪቷ መጥፋት የማይጨነቁ ኢትዮጵያን በግዞት ይዘዋል።

TPLF leaders

በወያኔ ዘመን መምህር ማለት የማስተማር እውቀት ኖሮት የመምህርነትን ድርሻ ይዞ  የሚያስተምር ማለት አይደለም። አንድ መምህር ለመምህርነት ሊያበቃው የሚችለው ያለው እውቀት እና የማስተማር ብቃት መሆን ነበረበት። መምህሩም ተማሪዎቹን ልክ እንደ ልጆቹ በማየት ነገ የአገር ተረካቢ እንደሆኑ ስለሚታወቅ ተቆጣጥሮ  እና ተንከባክቦ እውቀት አስጨብጦ በማስተማር ለፍሬ ማብቃት ነው። እድሜ ለወያኔ ዛሬ…. ዛሬ የሚበዙት መምህራኖች የወሬ ጥርቅም የያዙ ሆኖ ሳለ በከፍተኛ ስልጣን የመማር ማስተማሩን ስራ እንዲቆጣጠሩት በማርደግ የእውቀት ባለቤት እና የማስተማር ችሎታ ያላቸውን ኢትዮጵያዊ መምህራንን በሙሉ አባሯል። ሌላው ደግሞ  ተማሪ መምህርን እንዲገመግሙ ተደርጓል በዚህም እውነተኛ መምህራኖቹ ተማሪውን እንዲፈሩት አድርገዋቸዋል። በነገራችን ላይ ግምገማው በአግባቡ ቢሆን ችግር ላይኖረው ይችል ይሆናል ነገር ግን ይሄ አሰራር የመጣው ለአገር ፍቅር ኖሯቸው ዜጋን በማፍራት በትክክል የማስተማር ሙያ ላይ ያሉትን መምህራኖች ለመምታት ታቅዶ የተደረገ ሴራ ነው። ይሄ ደግሞ  በአገር የመጣ ጥፋት ነው። ወያኔ መቼ ነው እውነት የሚናገረ? መቼስ ይሆን ክፋትን የሚተወው?

ሙህራኖች  ኽረ ወዴት ናችሁ?።

የኢትዮጵያ ሙህራኖች ለአገር መስራት ከሁሉም በላይ ክብር አለው። ሳይንቲስት ቅጣው እጅጉ ገና 43  አመት ጎልማሳ ሆኖ  ነው ለአገሬ መስራት አለብኝ ብሎ የተነሳው። ሌሎችም ሙህራኖች የኢትዮጵያ ጉዳይ አሳስቧቸው ወደ እውነተኛ ትግል ውስጥ የገቡት። ነገር ግን ኢትዮጵያ በአለም ዙሪያ ካሏት የተማረ ኃይል በመቶኛ ብናስቀምጠው 5% እንኳን አይሞላም። ሙህራኑ በአገር ቀልድ እንደሌለ ከናንተ በላይ ሊረዳው የሚችል አለ ብዬ ማሰብ ይከብደኛል። ወያኔ ኢትዮጵያን የምትባለውን አገር አጥፍቶ ህዝቦቿን እርስ በራስ አጣልቶ የደም መሬት ለማድረግ ባለ በሌለ ኃይሉ እየሰራ ባለበት ሰዓት የሙህራኑ ዝምታ አስገርሞኛል። አሁን አጭር መልእክት ማስተላለፍ እፈልጋለው ሙህራኑ ሁሉ አገር ወደማዳኑ ስራ በመግባት ህብረት ፈጥራችሁ ኢትዮጵያን ከጥፋት በመታደግ ስራ ውስጥ ትሳተፉ ዘንድ ኢትዮጵያ ጥሪ አድርጋላችኋለች። የኢትዮጵያ ባላደራዎች ናችሁና  ኢትዮጵያንም የምትጠብቁም ናችሁና ስለ አገራችሁ  ብላችሁ ስራችሁን በተቀናጀ እና በተጠናከረ መልኩ ታሳዩን ዘንድ የኢትዮጵያ ህዝብ ይጠይቃችኋል።

ሌላው ወያኔ በፈጠረው የዘር ፖለቲካ ተጠላልፈን ነገሮችን ወደ ኋላ ተጉዘን ለማየት ግድ ሆኖብናል። በዚህ የተነሳ ብዙ ያልተገቡ ነገሮችን ባልሰራው ህዝብ ላይ የሰላ ትችት በመሰጣጠት አንዱ ጎጂ ሌላው ደግሞ ተጎጂ አድርጎ በማቅረብ የታሪክ መልካምነትን ሆነ መጥፎ ክንውኖችን ወደ አንድ ጎን በማዘንበል የሚሰጠው ትችት ከእውነት የራቀ ጉዳይ ነው። ምንም የጽሁፍም ሆነ የአርኬሎጂ ማስረጃ ሳይኖር የሚደረገው የታሪክ ዝርጠጣ ተቀባይነት የለውም። ይሄ አካሄድ ወያኔን እና የአረብ አብዬት ናፋቂዎችን ሊያስደስት ይችል ይሆን ይሆናል እንጂ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅመው አንዳች ነገር የለውም። የኢትዮጵያ ታሪክ መልካሙም መጥፎውም በሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች የተሰራው እንጂ የእገሌ ጎሳ ነው ተብሎ የሚመዘዝ ታሪክ የለንም። ይሄንን አብዮት የሚያካሂዱ አካሎች  በኢትዮጵያ ህዝብ ሌላ አጀንዳ ያላቸው መሆናቸውን ልናውቅባቸው ይገባል። ወያኔ ባመጣው የዘር ፖለቲካ ሁሉም ብሄሮች የራሳቸውን ግዛት ለማስመር ችለዋል። ያሰመሩትንም የግዛቴ አካል ነው ያሉትንም ይዘው ብቅ ብለዋል። ትግሬው፡- ትግሬ ትግሪኛን ለመመስረት፣ አማራው፡- በታሪክ የነበረው የአማራ መሬት በማለት፣ ኦሮሞው፡- ኦሮሚያ መሬት በሚል፣ ኦጋዴኖች፡- ታላቋን ሱማሌ ለመመስረት ኦጋዴን ነጻ መሬት ብለው መጥተዋል። ካርታውም እንደሚከተለው ነው።

እንኳን አገርን ወረረ ለተባለው ጠላት ይቅርና አብሮ ላደገው ጎረቤቱ እንዲሁም ለገዛ ቤተሰቡ ድንበሬን ገፋህ ተባብለው የሚፈሰውን ደም እናውቀው የለ ታዲያ አገርን የሚያክል ተወስዶበት ያውም ጠላት በተባለ አካል ዝም የሚል አለ እንዴ? እየሄድንበት ያለው አካሄድ በጣም አደገኛ ነውና የኔ ግዛት ይሄ ነው የሚለውን አካሄዳችንን በአፋጣኝ ልናቆመው ይገባል። <<ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮን በቆቅ ለውጥ>> ይባላል። አንዱ አንዱም በማጥፋት በይገባኛል ጥያቄ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እንዳንገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ያስፈልጋል። ካለበለዛ ዶሮን በአግባቡ ማርባት ሲጠበቅበት የበለጠ ያገኘ መስሎት ቆቅን ይዞ እንዳመጣ እና ሁለቱንም እንዳጣው ሰነፍ ገበሬ እንዳንሆን ልናስብበት የሚያስፈልገን ጉዳይ እንደሆነ ይሰማኛል።

olf ONLF

ጥቂት ስለ ኦነግ እና ኦብነግ ጠቀስ አድርጌ ልለፍ፡-

ኦነግ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ በኦርቶዶክስ እምነት ላይ እና በአማርኛ ቋንቋ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ አለው። ይህንን የምልበት ያለምክንያት አይደለም ብዙ ማስረጃ እና መረጃዎችም አሉ ይሄ ጉዳይ ደግሞ በዝምታ አልያም በቸለተኝነት የሚታለፍም ጉዳይ አይደለም። እና በትንሹ ጠቀስ አድርጎ ማለፉ አውቀው ለሚሰሩት የማስጠንቀቂያ ደውል ለማያውቁት ደግሞ የማንቂያ ደውል ነውና አንባቢው ልብ ይሉት ዘንድ አስፈላጊ ነው። ኦርቶዶዶክስ እምነት ማለት የአማራ እምነት ነው ብለው እስከማስተማር የደረሱበት አካሄድ አለ። የፓርቲው አባል የሚሆነው ሰው በሁለቱም ማለትም በናቱም በአባቱም ኦሮሞ  የሆነ ሰው አልያም ወይ በአባቱ አልያም በእናቱ ኦሮሞ የሆነ ሰው አባል መሆን ቢችልም ቅሉ አማርኛ ተናጋሪ ማለትም ኦሮምኛ የማይችል ከሆነ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ከሆነ የፓርቲው አባል መሆን አይችልም። ከኦነግ ፖለቲካ በስተጀርባ ያለው እውነት ይሄ ነው።

ፖለቲከኞች ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ብቻ ይዞ መሄድ እና መጓዝ ሲገባቸው የግል ህይወት ውስጥ በመግባት በፖለቲካ ሽፋን ሃይማኖትን ማስለወጥ የሚወገዝ ጉዳይ ነው። 40% ኦርቶዶክስ የሆነውን የኦሮሞ ህዝብ የምታምኑትን እምነት የአማራ ነውና ተዉትና ወደተለያየ እምነት መግባት አለባችሁ ማለት የኦሮሞ ህዝብን  መናቅ፣ መድፈር እና ማዋረድ ነው። ኦርቶዶክስ የአማራ ነው ማለት መንግስተ ሰማያት የአማራ ነው ብለው መናገራቸው እንደሆነ አልተረዱት ይሆንን? ስለዚህ በሚሊዮን የሚቆጠር አማርኛ ተናጋሪ ኦሮሞ እና በሚሊዮን የሚቆጠር የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ኦሮሞ እንዳለን እየታወቀ በድብቅ ፖለቲካ አጀንዳነት መንቀሳቀስ የፖለቲካ ሂደታችሁ በከፍተኛ ሁኔታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንደገባ ልነግራችሁ እወዳለው። ለአንድ ሰው መገኘት ምክንያት  እናቱ እና አባቱ ቢሆኑም እግዚአብሔር ግን የሁሉም አስገኒ እንዲሁም ፈጣሪ ነው። ከቤተሰቡ በላይ የኦርቶዶክስ አማኝ ለሃይማኖቱ ትልቅ መሰዋትነት እንደሚከፍል አታውቁ ይሆንን? ሃይማኖት ማለት የህይወት መሰረት ነውና ኦነግ በኦርቶዶክስ እምነት ያለውን የጥላቻ አመለካከት ከፖለቲካው ጋር አያይዞ መሄድ ተገቢ አይደለም። ኦርቶዶክስን የመጥላት ፖለቲካዊ አመለካከት እና አካሄድ በፍጥነት መቀየር ያለበት ጉዳይ ነው። የኦርቶዶክስን እምነት አጣጥሎ እና ንቆ የሌሎች እምነቶችን በፓርቲው ውስጥ ማቀፍ የሚደረገው ፖለቲካዊ ጉዞ የሃይማኖት ትግል እንዳያስመስልባቹ መጠንቀቅ ተገቢ ነው። ከፖለቲካው በስተጀርባ ሆኖ ግልጽ ያልሆነ እና የተደበቁ አጀንዳዎችን መስራት ከህብረተሰቡ የሚሰወር ስላልሆነ በጥልቀት ይታሰብበት ህብረተሰቡም ይሄንን ጉዳይ በጥልቀት ይከታተለው። በዚህ ጉዳይ እና በሌሎች ተያያዝነት ባላቸው አስፈላጊ ሆኖ ካገኘሁት ሰፋ ባለ መልኩ እመለስበታለው።

ሌላው ኦጋዴኖች የራሳቸውን መንግስት ለማቋቋም እየታገሉ ነው። ሊሰመርበት የሚያስፈልገው ጉዳይ ከላይ ከላይ የሚካሄደውን ትግል ሳይሆን ከዛ በኋላ የሚያስከትለውን አደጋ ነው። ለግዜው እስኪሳካላቸው ኦጋዴን ነጻ አውጪ በመባል ይጠሩ ይሆናል። በኋላ ላይ ግን ማለቂያ የሌለው መከራ ውስጥ እና ጦርነት ውስጥ እንደምንገባ ከፖለቲካው በስተጀርባ ያለው እውነታዎች ይነግሩናል። በካርታው ላይ እንደተመለከትነው ከኦሮሚያ ብዙ መሬቶችን በመውሰድ የቦረናንን፣ የሸዋን መሬቶችን በመከለል የሱማሌ መሬት እንደሆነ አስቀምጠውታል። እንግዲህ ልብ ያለው ልብ ይበል የሚባለው እዚህ ጋር ነው በተናጠል የሚደረገው ጉዞ ወይንም የዘር ፖለቲካ ወዴት ሊያመራን እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው። መጀመሪያ ነው እንጂ መጥኖ መደቆስ ኋላ ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ የሚለው ተረት ሊሰማ የሚገባው ዘመን አሁን ነው።

እኔስ እላለው ኢትዮጵያ ውስጥ ተገንጥዬ በሰላም እኖራለው የሚል አካል ካለ ማስተዋል ያልቻለ ሰው ብቻ ነው። ከእህል መሃል ረዝማ የወጣች የእህል ዛላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ነው እንደሚባል ሁሉ ከኢትዮጵያ ተለይቼ እወጣለው የሚል አካል ካለ እራሱን ለወንጭፍ እንዳዘጋጀ መቁጠር አለበት። በኢትዮጵያ ካለው ነባራዊ እውነታ መገንጠል መቼም የማይሆን ሊሆንም የማይችል ጉዳይ ነው። ትክክለኛው መንገድ የፖለቲካ የበላይነት ፈጥሮ ኢትዮጵያን እንደ ኢትዮጵያ መምራት ብቻ ነው። አንባ ገነን የሆነውን ወያኔን ጥሎ ዲሞክራሲ አገር ሁሉም በእኩል እና በሰላም የሚኖሩባት ስርዓትን ማምጣት ነው እንጂ ሌላ አጀንዳዎችን ከሃሳባችን ማስወጣት ያስፈልገናል።

ከተማ ዋቅጅራ

06.11.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

The post ከፖለቲካው በስተጀርባ ያሉት እውነታዎች – ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.


ኢህዴን/ብአዴን  የአማራን ሕዝብ አይወክልም ሞራሉም ብቃቱም የለውም !!

0
0

መብርሓቱ ገብረእግዚአብሔር ወይም በረከት ስምኦን በበርሃ ስሙ (አንበርብር) እየተባለ የሚታወቀው ጎንደር የተወለደው ኤርትራዊ የአማራ ሕዝብ ጠላት ከኢህአፓ እስከ ብአዴን የፈፀማቸው ፀረ-ሕዝብ ተግባሮቹ ።

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ይህን ሰው በሚመለከት ከዚህ ቀደም ትውልዱና የዘር ሀረጉን የቤተሰቡን ሁኔታ መጻፌና ጹሁፉ ለአንባቢያን መቅረቡን አስታውሳለሁ። ሌሎች ለሕዝብ ይፋ ያልተደረጉ ኅልቆ መስፈርያ የሌላቸውን ጉዳዮች ጊዜ ወስዶ ለማጋለጥ ይህ ባካናም ዘመን እድል ሊሰጠኝ አልቻለም እንጅ በውስጥ ከመቃጠል አላረፍኩም። ያም ሆነ ይህ በዚህ በያዝነው ወር 35ኛውን ዓመት የአማራውን ሕዝብ የገደሉበትን፤እስር ቤት ያጎሩበትን፤አካሉን ያጎደሉበትን፤ንብረቱን የዘረፉበትን፤አገር ጥሎ እንዲሰደድ ያደረጉበትን፤የዘር ፍሬውን ያመከኑበትን፤ጦርነት ውስጥ ማግደው ያስፈጁበትን፤እንደከብት ቆዳውን ገፈው በሕይወቱ ገደል የጨመሩበትን፤እቤት ውስጥ አስገብተው በሳት ያቃጠሉበትን፤ደሙን የመጠጡበትን፤የሰውነት ክፍሉን አውጥተው የሸጡበትን፤ተወልዶ ካደገበት ቀየው አፈናቅለው መሬቱን የሸጡበትን ልደት ለማክበር የቀረህን አራግፈህ ወዲህ በል እያሉ አማራውን እያመሱ ያሉበት ወቅት ላይ ስለምንገኝ እንደ አንድ የአማራ ነገድ ተወላጅ በአለሁበት ሆኜም አንደበቱ የታፈነውን አማራ ሕዝብ ድምጽ ማሰማት ኃላፊነትና ግዴታየ በመሆኑ ለዛሬ ይህን መጣጥፌን አቀርባለሁ።

በረከት ከላይ እንደተገለጸው ትውልዱ በእናት በአባቱ ኤርትራዊ መሆኑ ግልጽ ነው ተወልዶ ያደገው ጎንደር ሲሆን በረከት ያችን የጎንደሬነት ካርድ እየመዘዘ የጎንደርን ተወላጆች ከሌላው ነጥሎ ለማስመታት የሄደባቸው መንገዶች በጣም አደገኛ እንደነበሩና አሁንም ስልታቸውን እየቀያየረ እየተጠቀመባቸው እንደሆነ በግልጽ ሊታወቅበት ይገባል።ይህን ጉዳይ ነባር የኢህዴን ታጋዮችም ሆነ የአሁኖቹ የብአዴን ታጋዮች ያውቁታል።አዲሱ ለገሰ የአማራ ክልል ገዥ በነበረበት ወቅት በረከት በቀጥታ ወደ ጎንደር እየሄደ ጎንደርን አትንኩ አይነት ቃላትን እየተጠቀመ ጎንደሬ የሆኑ ካድሬዎችን ይቀጣ ነበር።ካድሬዎችን ለምን ቀጣ ሳይሆን ወደ ጎንደር መመላለስ ሲያበዛ አንድ የፈለገው ነገር እንዳለ አውቅ ነበር።

1ኛው ጉዳይ አንዳንድ አስተሳሰበ ደካማ የሆኑ ቅማንቶችን አስተባብሮ በአማራው ላይ አመጽ እንዲያነሱ ለማድረግ መሆኑ ግልጽ ነበር ይህም አሁን እየተደረገ ያለ ጉዳይ ነው።

2ኛው ጉዳይ የህወሃትን ወደ ጎንደር መስፋፋት ለማጠናከር እንደሆነም ይታወቃል። ጎንደሬ ነኝ እያለ ግን የጎንደር ሕዝብ ሥራ የማይወድና ሰነፍ ሕዝብ ስለሆነ መሬቱ ጦሙን ከሚያድር ቢለማ ምን አለበት? የምትለዋን ቃላት በስፋት ይጠቀማል።

ስለጎንደር ሲነሳ ትግሬዎችም ሆኑ ትግርኛ ተናጋሪዎች አስቀድመው የሚወረውሯት ቃል ይህችው ናት።በረከት እንደ የብአዴን አመራር ከብአዴን ማ/ኮ ጋር ሳይሆን የሚማከረውና ትእዛዝ የሚቀበለው መለስ በነበረበት ወቅት ከመለስ ሲሆን አሁን ደግሞ የመለስ ራእይ አራማጅ ከሆኑ የህወሃት መሪዎች ጋር ነው። ይህን የብአዴን ማ/ኮ ሳያውቀው በስሎ የሚቀርብን ሃሳብ በተግባር ለማዋል በተናጠል እያሳመኑ እጅ እንዲሰጡ በማድረግ መሄድ የተለመደ ነበር።ዋናው ግብ በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ጎሳዎችን ውስጥ ለውስጥ በማደራጀት በአማራው ላይ አምጸው እንዲቆሙ ማድረግና በተለመደው የአማራ ጥላቻ ከአናሳዎቹ ጎን በመሆን አማራውን ለመምታት የሚጠቀሙበት መሣርያ ነበር አሁንም በዚሁ መንገድ እንደሚሄዱ ሥራዎቹ ወይም የሚፈጽሟቸው ተግባሮች በግልጽ ያሳያሉ።

sion bereketየዚህን መሰሪ ሰው ተንኮል ለመመልከት ወደ ኋላ ሄጀ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፦በደርግ አገዛዝ ወቅት ህወሃት ጎንደርን በተለይም የሰሜኑን ክፍል ይዞ ነበር በ1977 ዓ/ም የተወሰነውን ቦታ ለኢህዴን አስረክቦ ሲንቀሳቀስ በመጀመርያዎቹ አካባቢ ህዝቡ ከደርግ ጋር በነበረው ጥላቻ ብቻ ተቀብሎ ማስተናገዱ አልቀረም ይህ በዚህ እንዳለ በ1978 እና በ1979 ዓ/ም ኢህዴን በሁለት ተከፍሎ የመበተን አደጋ ላይ ወድቆ ነበር።ምክንያቱ ያሬድ ጥበቡ ወይም ጌታቸው ጀቤሳ እየተባለ የሚጠራው የኢህዴን ሊቀመንበር የነበረ በኋላ ታምራትና መለስ በፈጠሩት ሴራ ጌታቸው በውጭ ሄዶ የማደራጀትና ኢህዴንን የማጠናከር ሥራ እንዲሰራ ተብሎ ወደ ውጭ ወጣ የሱን ቦታ ታምራት ተካ።በዚህ ወቅት አብዛኛው ታጋይ በታምራት ላይ ቅሬታ ያሳደረና በጌታቸው መነሳት ቅሬታ የተሰማው ነበር። ጌታቸው ሳያኮርፍና ተስፋ ሳይቆርጥ ኢህዴንን የማጠናከር ተግባሩን ቀጥሎ ተጓዘ በየጊዜው የሚፈጽመውን ተግባርም አገር ቤት ላለው የኢህዴን ማ/ኮ ሪፖርት ያደርግ ነበር።መልእክቱ ከአሜሪካ ወደ ሱዳን በህወሃት መስመር ይላካል የራዲዮ መልእክት የጹሑፍ ይላካሉ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የህወሃትን በጎ ፈቃድ ማግኘት ነበረበት።ከእለታት አንድ ቀን ህወሃት የኢህዴንን የጹሑፍ መልእክት ይጠልፍና ፖስታው ተከፍቶ ይነበባል የሰው ስም ዝርዝር ያለበት ነበር ጌታቸው የላከው ለኢህዴን አባልነት፤ደጋፊና ተባባሪ ይሆናሉ የተባሉትን ስም የያዘ ደብዳቤ።

ኋላስ ምን ሆነ?አጅሬ ህወሃት ይህን ደብዳቤ አፍኖ ከቆየ በኋላ በውጭ ያለውና በአገር ቤት ያለውን የኢህዴን አመራር በጥርጣሬ ላይ አክርመው ደብዳቤው እጃቸው መግባቱንና ጌታቸው የመለመላቸው ሰዎች ለኢህዴን አደገኛ ስለሚሆኑ ኢህዴንን ከአደጋ ለመከላከል ስንል ያደረግነው ነው ተብሎ በበጎነት እንዲታይና የኢህዴን አመራር እምነት እንዲጥሉበት ተደረገ።አደጋው ግን ለኢህዴን ሳይሆን ለህወሃት እንደነበር ግልጽ ነበር ይህ ይፋ ሲሆን የኢህዴን አባላትና አመራር በጌታቸውና ታምራት ቲፎዞነት ሲጦዝ ከረመ ህወሃትና ኢህዴን በጹሑፍ መባጠስ የጀመሩበት ወቅትም ነበር ዋናው ነጥብ አረጋዊ በርሄና ግደይ ዘርዓ ጽዮንን በገዳሪፍና ካርቱም የኢህዴን ጽ/ቤት በማስተናገዱ ህወሃትን ደፍሯል የሚል ሲሆን ኢህዴን ደግሞ ምሥጢሬን አይታችኋል በሚለው ዙርያ ነበር።በዚህ ወቅት አያ በረከት ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ሲሸመገል የነበረው ከጌታቸው ወገን በመሆን ሲሆን እስከ መቼ የህወሃት ሸሚዝ ሆነን ልንኖር ነው በማለት አኩራፊ ነበር ይህች ግን በነመለስ ቅንብር ከጌታቸው ጎን ገፍተው የሚወጡትን የአማራ ተወላጆች ለማጥመድና ጊዜ ገዝቶ(ጠብቆ)ፀጥ ለማድረግ ያለመ ነበር ተሳካ። የበረከት ወንድም ካሣሁን የተገደለው በህወሃትና በኢህአፓ በተደረገ ጦርነት ከህወሃት በተተኮሰ ጥይት ነው ይህ ግን ለበረከት ምኑም አልነበረም በሬ ካራጁ ብንልም የበረከት ዓላማ ሌላ ነበርና ዛሬ ላይ ሆነን በረከት የመጣበትን መንገድ ስንመለከት ዘለቀ፤ሙሉዓለም፤ጌጡ(ኡስማን)፤አውጃኖ፤አገኘሁ፤ንጉሤ…ወዘተ የተገደሉበትን ሁኔታ በገሃድ ያስያል።

ሌላው በረከት በአማራ ህዝብ ደም ምን ያህል እንደቀለደ የሚያሳየው በ1984 ዓ/ም ደቡብ አካባቢ ምክንያቱ ኦነግን ያደረገ ነገር ግን ኢህአዴግ በዋናነት የመራው በሐረር፤በአርባ ጉጉ፤ወተርና እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች የአማራ ነገድ ባላቸው ምስኪን ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመው እልቂትን አስመልክቶ እኔ ከደሙ ንጹሕ ነኝ በማለት ማስረጃዎች ተቀብረው የሚቀሩ ይመስል ነገርን ከራስ አውርዶ ለመጣል በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አማራዎችን ሆድ ለማባበል ሲባል የጎንደር 21 ቀበሌዎች ያዘጋጁት እንዲባልና ኢህዴን ወደ ብአዴንነት ሽግግርን በሚያደርግበት ወቅት ለደቡብ አማራዎች ትርንስፖርት ተዘጋጅቶ ጎንደር ከተማ ድረስ እንዲሄዱ ተደርጎ ሰፊ ድግስ ተደርጎ የደቡብ አማራ ወገኖቼ አይዟችሁን ተችረው እንዲመለሱ የተደረገው ትራጀዲ ወደ ኋላ ተመልሸ ሳስበው ያመኛል።በድርጅት ገንዘብ ወጭ ተመድቦ ነገር ግን ገንዘቡ ደብዛው ጠፍቶ ዝግጅቱ በ21ዱ ቀበሌዎች በጀት ተሸፈነ። ያ ዝግጅት በጎንደር አማራዎችና  ከደቡብ ወገኖቹ በመጡ አማራዎች መካከል ልብ ለልብ ያገናኘ ከበረት የጠነከረ አንድነትን  ፈጥሮ ነበር የሚያሳዝነው ነገር ያኔ የተወረወረች የውሸት አይዟችሁ ለምን ከክልሌ መጣችሁብኝ በማለት በሽፈራው ሽጉጤ ፊታውራሪነት በጉራ ፈርዳና በቬንሻንጉል በጋምቤላ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች አማራን አያሳየኝ በማለት ምስኪን ወገኖቻችን ሲያልቁ የደረሰላቸው አልተገኘም በራሳቸው የአማራ ክልል በሚባለው  እንኳን የሚተባበራቸው ጠፍቶ የአማራው ገዥዎች ጀርባቸውን ሲሰጡ ተመልክተናል።

ዛሬ የ35ኛ ዓመታችን ልደት ልናከብር ስለሆነ ገንዘብህን አምጣ የሚሉት ደሙን መጥምጠው የጠቡትን አጥንቱን የጋጡትን አማራ ምን አለውና ነው ገንዘብ የሚጠየቀው? ለነ ህላዊ ታደሰና ዓለምነው መኮንን ፈንጠዝያ ወይስ የአማራው ህዝብ እንባ አባሽና ድምጽ ለሆነ ድርጅት?መንደር ለመንደር የእያንዳንዱን አርሶ አደርና አባወራ ቤት በማሰስ አስገድዶ ገንዘብ መሰብሰብ ሊቆም ይገባዋል።ማን አለብኝነት ለደርግ አልበጀም ይህ ሕዝብ ሆ!! ብሎ ሲነሳ የሚከፈለው ዋጋ እጥፍ ድርብ እንደሚሆን መዘንጋት አይገባም ዛሬ ሆድህን ወደህ አንድነትን ከሚንዱ የውጭ ጌቶቻቸውን ለማስደሰት ታሪክ ከሚያጠፉ፤አገር ከሚሸጡ የሀገር ሀብት ከሚዘርፉና ትውልድን እየበሉ ከሚገኙ ፀረ-ሕዝቦች ወግነህ ዜጐችህን እያጫረስክ ያለህ ካድሬ፤የደህንነትና የፖሊስ ኃይል፤የመከላከያ ሰራዊት የአማራውን ሕዝብ ክንድ ጠምዝዘህ እያሳረድክ ያለህን እያንዳንድህን ታሪክ ስለሚፋረድህ ነገ ይህ የአማራ ነገድ ሕዝብ አንገቱን ቀና አድርጎ መሄድ ሲጀምር መሬት ከምትጠብህ አሁን ታሪክ ለመስራትና ከወገንህ ጐን ቆመህ አይዞሽ እማየ!! አይዞህ አባየ!! አይዞህ ወንድም ዓለም!! ይዞሽ እህት ዓለም!!ማለት ብትሞክር ትናንት ለግል ጥቅም ስትል የፈጸምክበትን በደል ሁሉ ይቅር ሊልህ እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ።

 

(አንተነህ ገብርየ)

የአማራ ህዝብ አማራ ባልሆኑ መሪዎች አይገዛም!

The post ኢህዴን/ብአዴን  የአማራን ሕዝብ አይወክልም ሞራሉም ብቃቱም የለውም !! appeared first on Zehabesha Amharic.

በጎንደር ጭልጋና ትክል ድንጋይ መካከል በሚገኝ ማውራ የተባለ ቦታ በገበሬዎችና በህወሓት ልዩ ኃይል ጦር መካከል ውጊያ ተካሄደ

0
0

news

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) 

በጎንደር ጭልጋና ትክል ድንጋይ መካከል በሚገኝ ማውራ የተባለ ቦታ ላይ በአካባቢው ገበሬዎችና በህወሓት ልዩ ኃይል ጦር መካከል ከፍተኛ ግጭት ተቀስቅሶ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ፍልሚያው የተጀመረው ትናንት ረፋድ ላይ ሲሆን አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው፡፡ አካባቢው ትንሽ እንኳን ፋታ በሌለው ተከታታይ የጦር መሳሪያ ፍንዳታ ድምፅ እየተናጠ ይገኛል፡፡

እስካሁን ድረስ በደረሰን መረጃ መሰረት በትንሹ 5 የልዩ ኃይሉ ጦር አባላት ተገድለዋል ከ9 በላይ ደግሞ ቆስለዋል፡፡ ነገር ግን በማውራ ገበሬዎች በኩል የደረሰ ጉዳት ይኑር አይኑር ምንም የታወቀ ነገር የለም፡፡

የጎንደር-ጭልጋ ማውራ ገበሬዎችንና የህወሓትን ልዩ ኃይል ለመዋጋት ያበቃቸው ምክንያት ምን እንደሆነ በውል ተለይቶ አልታወቀም፤ ነገር ግን በጭልጋና አካባቢው ቀደም ሲል የተነሳው የብሄር ጥያቄ ሳይሆን እንዳልቀረ ምንጮቻችን ያላቸውን ግምት አስቀምጠዋል፡፡

በተጨማሪም በጭልጋና አካባቢው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከግጭቱ አንድ ሳምንት ቀደም ብለው መዘጋታቸውና ሙሉ በሙሉ ማስተማር ማቆማቸው ተገልጿል፡፡

The post በጎንደር ጭልጋና ትክል ድንጋይ መካከል በሚገኝ ማውራ የተባለ ቦታ በገበሬዎችና በህወሓት ልዩ ኃይል ጦር መካከል ውጊያ ተካሄደ appeared first on Zehabesha Amharic.

(ሰበር ዜና) በስደት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ተጨማሪ ጳጳሳትን ሊሾም ነው * ለአቡነ መልከጼዲቅ ረዳት የሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ተሾመ

0
0

holy sinod ethiopia

(ዘ-ሐበሻ) በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስና የአጠቃላይ መንፈሳዊ የሰበካ ጠቅላላ ጉባኤ በደብረ መድሃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል በኮለምበስ ኦሀዮ ከጥቅምት 24 እስከ ጥቅምት 26, 2008 ዓ.ም ተካሄደ:: በዚህ ጉባኤ ላይ ተጨማሪ ጳጳሳትን ለመሾም ውሳኔ ላይ የተደረሰ ሲሆን አስመራጭ ኮሚቴዎችም መመረጣቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል:: በተጨማሪም ለሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ መልከጼዲቅ ረዳት የሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ተሾሞላቸዋል:: እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለፃ ለአቡነ መልኬጼዲቅ የተሾሙት ረዳት የሲኖዶሱ ዋናጸሀፊ; ዋና ጸሐፊው በ እድሜ መግፋት ምክንያት መስራት የማይችሏቸውን ሥራዎቹ በሙሉ ተክተው ይሰራሉ::

ረዳት ሲኖዶስ ሆነው የተሾሙትን ሊቀጳስ ስም ዝርዝር ዘ-ሐበሻ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ይፋ ታደርጋለች::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ቅዱስ ሲኖዶሱ ባለ 9 ነጥብ መግለጫ አውጥቷል:: መግለጫውን ለማንበብ ፎቶ ግራፎቹን ይጫኑ::

Holy Sinod 1 Holy Sinod 2 Holy Sinod 3

The post (ሰበር ዜና) በስደት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ተጨማሪ ጳጳሳትን ሊሾም ነው * ለአቡነ መልከጼዲቅ ረዳት የሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ተሾመ appeared first on Zehabesha Amharic.

በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናት በቤ/ክርስቲያናቱ እንዳያገለግሉ አገደ* አቡነ ሚካኤል የሲኖዶሱ ረዳት ጸሐፊ ሆነው ተሾሙ

0
0

* በፖለቲካው አሸባሪ ብሎ እንደሚፈርጀው ሁሉ በተሐድሶ ስም በስደተኛው ሲኖዶስ ውስጥ ያሉ መምህራንን መንግስት ባሰማራቸው ካድሬ ሰባኪያን ለማጥቃት እየሞከረ ነው
* የጳጳሳት አስመራጭ ኮሚቴዎችን ስም ዝርዝር ይዘናል
* ከ9 በላይ አዳዲስ ጳጳሳት ይሾማሉ
* አቡነ ሚካኤል የሲኖዶሱ ረዳት ጸሐፊ ሆነው ተሾሙ

የቅዱስ ሲኖዶሱ ረዳት ዋና ጸሐፊ ሆነው የተሾሙት አቡነ ሚካኤል

የቅዱስ ሲኖዶሱ ረዳት ዋና ጸሐፊ ሆነው የተሾሙት አቡነ ሚካኤል

(ተጨማሪ የዘ-ሐበሻ ሰበር ዜና) በኮለምበስ ኦሀዮ; ከጥቅምት 24 እስከ ጥቅምት 26, 2008 ዓ.ም በደብረ መድሃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል በተደረገው የስደተኛው ሲኖዶስ ዓመታዊ ጉባኤ አዳዲስ መመሪያዎችን ማውጣቱን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::

ከዚህ በፊት በነበረው የዘ-ሐበሻ ሰበር ዜና ቅዱስ ሲኖዶሱ በ እድሜ መግፋት ምክንያት ብዙ ለመስራት በማይችሉት አቡነ መልኬጼዲቅ ረዳት ዋና ጸሐፊ የሾመ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል:: በዚህም መሠረት በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ረዳት ሊቀጳጳስ አድርጎ የሾማቸው ብጹዕ አቡነ ሚካኤል መሆናቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል:: ብጹዕ አቡነ ሚካኤል የምዕራብ ካናዳ ሃገረ ስብከት (የካልጋሪ) ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ናቸው:: አዲሱ የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አብዛኛውን የአቡነ መልከጼዲቅን ሥራ ተክተው እንደሚሰሩ በጉባኤው ጸድቆላቸዋል::

በዚህ ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው ሲኖዶሱ በቅርቡ ከ9 በላይ ጳጳሳትን ይሾማል:: አዲስ የሚሾሙትን ኤጲስ ቆጶሳትን ለማስመረጥም ከቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና ከምዕመናኑ አስመራጭ ኮሚቴዎች መመረጣቸውን ያስታወቁት ምንጮቻችን ስምዝርዝራቸውን አድርሰውናል::

በዚህም መሠረት አዳዲስ የሚሾሙትን ጳጳሳት የሚያስመርጡት ሰዎች
1ኛ. አቡነ ሚካኤል
2ኛ. ሊቀ ካህናት ምሳሌ
3ኛ. መምህር ልዑለ ቃል (የፓትርያርኩ ጸሐፊ)
4ኛ. መምህር ፍሬሰው
5ኛ. ቀሲስ ልሳነወርቅ (ከአውሮፓ)
6ኛ ቀሲስ መንግስቱ
7ኛ ዶ/ር አምባቸው (ከምእመናን) ናቸው:: በአማካሪነት ደግሞ ብጹዕ አቡነ ኤሊያስ ተመርጠዋል::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ አዳዲስ የሚሾማቸውን ጳጳሳት (ኤጲስ ቆጶሳት) በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ባሉ ሃገረ ስብከቶች ያስቀምጣል:: በዚህም መሠረት:

ለአውሮፓ 2
ለአፍሪካ 1
ለካናዳ 2
ለአውስትራሊያ 1 አዳዲስ ጳጳሳት የሚሾሙ ሲሆን ቀሪዎቹ በአሜሪካ ይሾማሉ ተብሏል::

በኦሃዮ በተደረገው የሲኖዶሱ ጉባኤ አዲስ የወጣው መመሪያ ደግሞ በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ውስጥ እያገለገሉ በስደተኛው ሲኖዶስ ውስጥም የሚያገለግሉ ካህናትን ይመለከታል:: ሲኖዶሱ ባወጣው መመሪያ መሠረት በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ውስጥ እያገለገሎ በተጨማሪም በስደተኛው ሲኖዶስ ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናት ከዚህ በኋላ አንዱን መምረጥ ይኖርባቸዋል:: ይህ ካልሆነ ግን በሁለቱም ሲኖዶሶች ውስጥ በአንድ ጊዜ ማገልገል እንደማቻል ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል::

በሌላ በኩል ቅዱስ ሲኖዶሱ ባወጣው መግለጫ መንግስት ተቃዋሚዎችን አሸባሪ ብሎ እንደሚከሰው ሁሉ አሁን ደግሞ በስደተኛው ሲኖዶስ ውስጥ እያገለገሉ ያሉትን ካህናት እና መምህራንን ተሐድሶ በሚል ከሕዝብ ጋር ለመነጠል የሚደረገውን ሴራ አውግዟል:: ሕዝቡ እንዲህ ያለውን ማደናገሪያ እንዳይቀበል የጠየቀው ሲኖዶሱ ሆን ብሎ በተሐድሶ ስም ስደተኛው ሲኖዶስን ለማጥቃት የሚደረገውን ሴራ እንዲያወግዝ አሳስቧል:: ሲኖዶሱ እንዳሳሰሰበው መንግስት ያሰማራቸው ካድሬ ሰባኪያን የስደተኛው ሲኖዶስን ስም ለማጥፋትና ሰባኪያኑን ከሕዝቡ ለማግለል የሚያደርጉትን ሴራ ሕዝብ ሊቃወመው ይገባል::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች አዳዲስ ጳጳሳት ሆነው የሚሾሙትን እጮዎች ስም ዝርዝር አድርሰውናል – ከሰሞኑ ዝርዝራቸውን እናሳውቃችኋለን::

The post በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናት በቤ/ክርስቲያናቱ እንዳያገለግሉ አገደ* አቡነ ሚካኤል የሲኖዶሱ ረዳት ጸሐፊ ሆነው ተሾሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ሂውማን ሄር (የሰው ጸጉር) የሚሰኩ ሴቶች ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄ

0
0

Human Hair

ለሴት ልጅ ፀጉር ውበቷ ነው ይባላል ፡፡ ለዚህም ይመስላል ብዙ ዘፋኞች በፀጉር ላይ የዘፈኑት፡ ፡ የጸጉር ውበቱ ማጠሩና መርዘሙ እንዳልሆነ የውበት ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ሁሉም ጸጉር በአግባቡ ከተያዘና ለኛ የፊት ቅርጽ ስታይል እንዲስማማ ሆኖ ከተሰራ ውበት ያጎናጽፋል፡፡

አሁን አሁን የአብዛኛዎች ሴቶች ምርጫ የሆነው ረዘም ብሎ የበዛ የፀጉር ስታይል ነው፡፡ ሁሉም ሴት ግን የዚህ አይነት ፀጉር ሊኖረው አይችልም ፡፡ ለዚህም ነው አብዛኞቹ የከተማችን ሴቶች ሂውማን ሄርን የሚጠቀሙት፡፡

ሂውማን ሄር መጠቀም እንዴት እንደተጀመረ በትክክል የሚያሳዩ መረጃዎች ባይኖሩም አንዳንድ ምንጮች ግን አመጣጡ ከወደ ህንድ ነው ይሉናል፡ ፡ በህንድ አንዲት ሴት 18 ዓመት እስኪሞላትድረስ ፀጉራን የማሳደግ ባህል ሲኖራቸው፤ ሴቷ ልክ 18 ዓመት ሲሞላት ፀጉሯ ይቆረጥና ለፈጣሪ እንደ መባ ይሰጣል፡፡ ይህን ባህል ምክንያት አድርጎ የሚቆረጥን ፀጉር በፋብሪካ ለጥቅም እንዲውል ተደርጎ መመረት ለሂውማን ሄር መፈጠር ምክንያት ሆነ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ሂውማን ሄር በብዛት የሚመረትባቸውና ታዋቂ የሆኑ ሀገራት ህንድ፣ ብራዚል እና ጣሊያን ሲሆኑ የነዚህ ሀገራት ሴቶች ፀጉር በጣም ታዳጊና ብዛት ያለው ነው፡፡

ሴቶች ሂውማን ሄር ለምን

ይጠቀማሉ?

አብዛኞቹ ሴቶች የተለያዩ ምክንያት ሲኖራቸው በብዛት ግን የሚሰጡት ምክንያት ተፈጥሯዊው ፀጉራቸው ብዛት ወይም ርዝመት ስለሌለው ሂውማን ሄርን በመጠቀም ውበት ለመጎናጸፍ እንደሆነ ይገልጻሉ፡ ፡

የሂውማን ሄር ዓይነት፡-

እንደሚመጣበት ሀገር የተለያየ ዓይነት ሲኖረው ለፍሪዝ የሚመቹ እንዲሁም ለፔስትራ ስራ የሚመች የሂውማን ሄር አይነቶች አሉ፡፡ ከነዚህ ውጭም በሀገራችን ብዙም ያልተለመደው ለሹሩባ ተብሎ የሚዘጋጅ ሂውማን ሄር አለ፡፡

አጠቃቀም፡- የሂውማን ሄር በሦስት ዓይነት መንገድ ለመጠቀም እንዲያመች ተደርጎ የሚዘጋጅ ሲሆን አንደኛው የራሳችንን የተፈጥሮ ፀጉር መጀመሪያ ሹሩባ በመስራት የሂውማን ሄሩን መስፋት ሲሆን ሌላው መንገድ ደግሞ ለራሱ ተብሎ በተዘጋጀ ግሉ ማጣበቅ ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ በክሊፕ መልክ የተዘጋጀ የሂውማን  ሄርን የተፈጥሮ ፀጉራችንን በደንብ ከተሰራን በኋላ በሚያመቸን መልኩ ማህል ማህሉ ላይ  የክሊፑን የሂውማን ሄር መሻጥ ነው፡፡

የሂውማን ሄር የጎንዮሽ ጉዳት፡

እንደባለሙያዎች ገለጻ ከሆነ የሂውማን ሄር የመጀመሪያውና ትልቁ ጉዳት የሥነልቦና ጫና ነው፡፡ አንዲት ሴት የሂውማን ሄር አዘውትራ የምትጠቀም ከሆነ ከጊዜ በኋላ ያለሱ ራሷን መቀበል ወይም ማየት ያቅታታል፡፡ ይህም የራሷን የተፈጥሮ ፀጉርና የየፊት ገፅታ ባለመቀበል ትልቅ የሥነልቦና ችግር ውስጥ ይከታታል፡ ፡ ከዚህ ውጭ ደግሞ የሂውማን ሄር በስፌት በምንጠቀምበት ወቅት ስፌቱ ጨምድዶ ከያዘን ለራስ ምታትና ለፀጉር መነቃቀል ሊዳርገን ይችላል፡፡ በግሉም በምንጠቀምበት ጊዜ የራስ ቅል ቆዳን እንዳይነካ ጥንቃቄ ካልተደረገ ኬሚካሉ ቆዳችን ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፡፡

ሂውማን ሄር ስንጠቀም መደረግ ያለበት ጥንቃቄ

-ሂውማን ሄር በምንጠቀምበት ጊዜ ቢቻል የተፈጥሮ ፀጉራችንም ሆነ የሂውማን ሄሩ እንዳይጎዳ ቢበዛ 15 ቀን በላይ አለማቆየት፡፡

– ሂውማን ሄርን አላሥፈላጊ የሥነልቦና ጫና ውሥጥ ላለመግባት

በፕሮግራም ብቻ መጠቀም፡፡
-ሄውማን ሄርን በምንገዛበት ወቅት

ከሰውሰራሽ ዊጎች ጋር ተቀላቅለው የሚዘጋጁ የሂውማን ሄሮች ስላሉ ባለሙያ ማማከር፡፡

– የሂውማን ሄር በምንጠቀምበት ጊዜ የሂውማን ሄርሩን የምንቀባውን ማንኛውም ስፕሬም ሆነ ቅባት የፊታችንን ፀጉር እንዳይነካ

መጠንቀቅ፡፡

The post Health: ሂውማን ሄር (የሰው ጸጉር) የሚሰኩ ሴቶች ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄ appeared first on Zehabesha Amharic.

እስቲ ቸር ወሬ ነገ ያሰማን –የሚሊዮኖች ድምጽ

0
0

Habtamu abrhayeshiwas daniel

እነ ሃብታሙ አያለው የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ፣ ነሐሴ 2007 ፣ ከተበየነላቸው በኋላ፣ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው፣ ሕገ ወጥ በሆነ መልኩ የዋስትና መብት ተነፍገው በወህኒ እንዲቆዩ መደረጉ ይታወሳል።

የከፍተኛው ፍርድ ቤት ለመስከረም 22 ቀጠሮ ሰጠ። ሆኖም በቀጠሮው ቀን ዳኞች ስልጠና ላይ ናቸው በሚል ፣ እነ ሃብታሙ ፍትህ ተነፈጉ።፡ የመጀመርያው ፍርድ ቤት ነጻ ብሏቸውም፣ ከአንድ ወር በላይ በወህኑ ማቀቀ። ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 17 ቀን ቀጠሮ ሰጠ።

ጥቅምት 17 ቀን ፣ ፖሊስ እነ ሃብታሙን ፍርድ ቤት ሳይዝ ቀረበ። በዚህ ምክንያት እንደገና ለጥቅምት 22 ቀጠሮ ተሰጠ። እንደገና ያለምንም ወንጀል፣ ፖሊስ ስላለ ብቻ እስረኞች መሰቃየታቸው ቀጠለ።

እስረኞች በሌሉበት እንደገና ለጥቅምት 29/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ፣ አቃቢ ሕግ ማቅረብ የነበረበት ሰነድ አላቀረበም በሚል ፣ ሰጠ።

አቃቢ ሕግ በዉሸት ምስክር፣ ምስክሮችን እያሰለጠ በቂ ባልሆነ መልኩ ዜጎችን ይከሳል፤ ዳኞች ደግሞ ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት ፍርድ መስጠት ይፈራሉ። ተከሳሾችን ከፖሊሲ የመጠበቅ ሃላፊነታቸው ትተው፣ ከፖሊስ ጋር የ ተከሳሾችን ስቃይ የሚያራዝሙ ሆነዋል። የአገራችን የፍትህ ስርዓት እንግዲህ ይሄን ይመስላል።

ነገ ጥቅምት 29 ቀን የነ ሃብታሙ ጉዳይ በቀጠሮው መሰረት ይታያል ተብሎ ቢጠበቅም, ነገም ደግሞ ሌላ ምክንያት ተሰጥቶ ሌል ቀጠሮ ሊሰጣቸው የሚችልበትም ሁኔታ አለ። ታዲያ ፍርድ ቤቶች እንደዚህ ከሆኑ፣ “ይሄ ለምን ይሆናል ?” ተብሎ የሚኬድበት፣ የሚክሰስበትና አቤት የሚባለበት ሌላ ቦታ በመድረ ኢትዮጵያ ከወዴት ይገኛል ?

ለማናንው እስት ቸር ወሬ ነገ ያሰማን ።፡

The post እስቲ ቸር ወሬ ነገ ያሰማን – የሚሊዮኖች ድምጽ appeared first on Zehabesha Amharic.

አርቲስት ደበበ እሸቱ በካናዳ ተሸለመ

0
0

debebe eshetu wins

ከአረአያ አለዩ

አርቲስት ደበበ እሸቱ ትናንት በካናዳ ቫንኮቨር በተካሄደው “the Golden Leopard award” በሚል የሚጠራው እና በሰሜን አሜሪካ መልቲ ካልቸራል አለምአቀፍ የፊልም ሰሪዎች ማህበር የሚያዘጋጀው ስነስርዓት ላይ “ቀያይ ቀምቦጦች” “עלים אדומים Red Leaves” በሚለው ፊልም መሪ ተዋናይ ሆኖ ባሳየው ብቃት የምርጥ ተዋናይ “Best Lead Actor” የሚለውን ዘርፍ አሸናፊ በመሆን በተወካዩ አማካኝነት ሽልማቱን ተቀበለ::

debebe eshetuበ እስራኤል ሃገር የተሰራው Red Leaves ፊልም በአሁኑ ሰዓት በበርካታ ሀገሮች ታላላቅ የፊልም ፌስቲቫል ላይ እየታየ እና ከፍተኛ አድናቆት እየተቸረው ሲሆን በተለይም የመሪ ተዋናዩ ደበበ እሸቱ ብቃት በአለም አቀፍ የፊልም መድረክ ላይ ተመልሶ ያንጸባረቀበት እንደሆነ እየተገለጸ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም “ቀያይ ቀምቦጦች” ፊልም በአውስትራሊያ፣ በጀርመን፣ ሳንፍራነሲስኮ፣ በማንሀታን ኒውዮርክ፣ በለንደን እና በርካታ ከተሞች ላይ እየታየ ይገኛል፡፡

The post አርቲስት ደበበ እሸቱ በካናዳ ተሸለመ appeared first on Zehabesha Amharic.


“ኢሕአፓ –በሶማሊያ ጦርነት ወቅት የአገር ክህደት አልፈጸመም፤ የኤርትራን ጥያቄም የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው ብሎም አልተቀበለም።” –ስሎሞን ገብረሥላሴ

0
0

ሰለሞን ገብረሥላሴ፤  የኢሕ አፓ-አንድነት ቃል አቀባይ፤ የቀድሞው የኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዚደንት ከSBS የአማርኛው ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ የድርጅታቸውን አተያይ ይገልጣሉ።

ኢሕአፓ – በሶማሊያ ጦርነት ወቅት የአገር ክህደት አልፈጸመም፤ የኤርትራን ጥያቄም የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው ብሎም አልተቀበለም።

–      ስሎሞን ገብረሥላሴ


“ኢሕአፓ – በሶማሊያ ጦርነት ወቅት የአገር ክህደት አልፈጸመም፤ የኤርትራን ጥያቄም የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው ብሎም አልተቀበለም።”  –  ስሎሞን ገብረሥላሴ

The post “ኢሕአፓ – በሶማሊያ ጦርነት ወቅት የአገር ክህደት አልፈጸመም፤ የኤርትራን ጥያቄም የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው ብሎም አልተቀበለም።” – ስሎሞን ገብረሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዳና ድራማዋ ተዋናይት ቤዛዊት መስፍን ተፈታች

0
0

bezawit mesfin
(ዘ-ሐበሻ) በተለያዩ ድራማዎች እና ፊልሞች ላይ በመተወን የምትታወቀው ተዋናይት ቤዛዊት መስፍን ከእስር ተፈታች::

ከጓደኛዋ ጋር በመሆን ለ እስር ተዳርጋ የነበረው ከታዘዘላት ውጭ ተጨማሪ ገንዘብ ከባንክ ቤት በማውጣት ለግል ጥቅሟ አውላለች በሚል ነበር:: አርቲስት ቤዛዊት መስፍንች ከግብረ አበሯ ጋር በመሆን በተሰጣቸው የ4 ሺህ ብር ቼክ ላይ ከፊት ለፊቱ ሁለት ቁጥርን በመጨመር ያልተፈቀደላቸውን 24 ሺህ ብር ከወጋገን ባንክ ሰባራ ባቡር ቅርንጫፍ አውጥተዋል።ችበዚህም መሰረት የፌደራሉ አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ የማይገባቸውን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ በፈፀሙት ወንጀል ክስ በመመስረት የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ አርቲስቷ ድርጊቱን ማስተባበል ባለመቻሏ ከነጓደኛዋ ጥፋተኛ መባሏ ይታወሳል::

አርቲስት ቤዛዊት ከተፈረደባት 6 ወራት እስራት ውስጥ አብዛኛውን በማጠናቀቋና በአመክሮ ከተፈታች በኋላ በሰጠችው ቃል “ከምወደው ሕዝብ ጋር ለመገናኘት ጓጉቻለሁ:: በቶሎ ወደ ትወናዬ መመለስ እፈልጋለሁ” ብላለች::

The post የዳና ድራማዋ ተዋናይት ቤዛዊት መስፍን ተፈታች appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: አርበኞች ግንቦት ሰባት በፊኒክስ ያደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ እና የሕዝቡ ምላሽ (ልዩ ጥንቅር) * “የኦህዴድ አመራር ሆነው ኦሮምኛ የማይናገሩ አሉ –ኤርሚያስ ለገሰ * * በደቡብ ክልል በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ ለአባይ ቦንድ አንከፍልም ሲሉ ተቃውሞ ካሰሙ መምህራን መካከል አስራ አምስቱ ታሰሩ…ሌሎችም

0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 28 ቀን 2008 ፕሮግራም

<...>

ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ የሰሞኑን የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ከእውነታው ጋር አገናዝቦ ተመልክቶታል (ሙሉውን ቃለ መጠይቅ አዳምጡት)

መምህር ግርማ ላይ ተጨማሪ የተጠረጠሩበት ክስ አስቀድሞ የነበረውን የዕምነቱን ተከታዮች ጥርጣሬ ያባብሳል? በእርግጥ መምህሩ የስርዓቱ ሰለባ ናቸው? የዕምነቱ ተከታዮች አወዛጋቢ የሁለት ጎራ አስተያየትና ወቅታዊውን ሁኔታ ቃኝተነዋል(ልዩ ዘገባ)

አርበኞች ግንቦት ሰባት በፊኒክስ ያደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ እና የሕዝቡ ምላሽ (ልዩ ጥንቅር)

<...> አቶ ኤርሚያስ ለገሰ በፊኒክስ -አሪዞና በአርበኞች ግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከተናገሩት (ቀሪውን ያዳምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

* በደቡብ ክልል በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ ለአባይ ቦንድ አንከፍልም ሲሉ ተቃውሞ ካሰሙ መምህራን መካከል አስራ አምስቱ ታሰሩ

– በተቃውሞው ሳቢያ ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል

* አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የኤርትራዊያን ስደት እንዲገታ ከተፈለገ የአስመራ መንግስት መወገድ አለበት ማለታቸው ቁጣ ቀሰቀሰ

“የአቶ ሃይለማሪያም ንግግር የራሷ አሮባት የሰው ታማሰላለች ነው የሆነብኝ ”ሲሉ በተመድ የኤርትራ አመባሳደር ግርማ አሰመሮም ተናገሩ

* ሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ታጣቂ ተቃዋሚዎችን እየረዳች መሆኗ ተዘገበ

* ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ አመሪቂ የጥናት ውጤት አለተገኘም ስትል አቁሟን ይፋ አደረገች

* በጎንደር ልዩ ልዩ አካባቢዎች መብታችንን አናስነካም ያሉ የቅማንት ተወላጆች ከአገዛዙ ጦር ጋር ውጊአ ገጥመው ሙትና ቁስለና ማድረጋቸውን ገለጹ

* በኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት የአለም ባንክ አሰተርጓሚ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ተጠየቀ

“ግለሰቡ ባስቸኳይ ካለተፈቱ የሕይወታቸው መጨረሻ የኢትዮጵያ ወህኒ ቤት ይሆናል”ስጋት የገባው የሰባዊ መብት ተሟጋች ድርጅት

* ስደተኛው ሲኖዶስ በአገር ቤት አለው አገዛዝ ተቃዋሚዎችን > የሀይማኖት አባቶችንና ሰባኪያንን > የሚል ስም እየለጠፈ የሚያደርገውን ውንጀላ አወገዘ

– ዘጠኝ ተጨማሪ ጳጳሳት ሊሾም ነው

The post Hiber Radio: አርበኞች ግንቦት ሰባት በፊኒክስ ያደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ እና የሕዝቡ ምላሽ (ልዩ ጥንቅር) * “የኦህዴድ አመራር ሆነው ኦሮምኛ የማይናገሩ አሉ – ኤርሚያስ ለገሰ * * በደቡብ ክልል በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ ለአባይ ቦንድ አንከፍልም ሲሉ ተቃውሞ ካሰሙ መምህራን መካከል አስራ አምስቱ ታሰሩ… ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰው ስለታሰረ ብቻ ከድርጊቱ ይታረማል?

0
0

ከዳዊት ሰለሞን

ጥያቄው የአርቲስቷን እስር ከመደገፍና ከመቃወም ጋር ምንም ግኑኝነት የለውም፡፡መልስ ግን ከአርቲስቷ አለፍ ብለን ብንፈልግለት አጃኢብ ይመስለኛል፡፡የአርቲስቷ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች በስድብና በድጋፍ አቀባበል እያደረጉላት ነው፡፡አንዳንድ የፌስ ቡክ ሐይማኖተኞችም ‹‹የእርማት ግዜዋን ጨርሳ በመውጣቷ ልናበረታታት ይገባናል››እያሉልን ነው፡፡ጥያቄው የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው፡፡
bezawit mesfin

አንድ ሰው በፍርድ ቤት የተጣለበትን የእስር ግዜ ጨርሶ ስለወጣ ‹‹ታርሟል››ማለት ይቻላል?ወዲህም አራሚ የተሰኘው የኢትዮጵያ ወህኒ ቤት እስረኛውን ለእስር ከዳረገው ድርጊት ታርሙ እንዲወጣ የሚያደርግለት አንዳች ድጋፍ ስለመኖሩም መጠየቅ የአባት ነው?

ከእስር ቤት የሚወጡ ብዙዎች ተመልሰው በሌላ ወንጀል ለእስራት የሚዳረጉበት ሁኔታ በዛ ያለ መሆኑን የምታውቁ ሰዎችም ስለሁኔታው ማብራሪያ መስጠት ትችላላችሁ፡፡

ወህኒ ቤቶች በየት በኩል ነው ለማረሚያነት እንዲዘጋጁ የተደረጉት? ስንት የስነ ልቦና መምህራን አሏቸው? እነማን ናቸው ስለ ወንጀል አስከፊነት ለእስረኞች ስልጠና የሚሰጡት? ወንበር፣ኮፊያ፣ዳንቴል ማሰራት እርማት ይሆን?
ቆይ እስኪ እኛ ቀድመን ‹‹ታርመዋል››ከማለታችን በፊት የተፈቱትን በቆይታችሁ ከድርጊታችሁ እንድትታረሙና ጥሩ ዜጋ እንዲወጣችሁ ምን አይነት እገዛ ተደረገላችሁ ብለን እንጠይቃቸው፡፡ ስለ እርማት ትንፍሽ ያላለችን ልጅ ‹‹ታርማለች››የሚል ታፔላ ባንለጥፍላት አንጎዳትም፡፡

ሌላው አስቂኝ ነገር እስረኞቻቸውን ጠዋትና ማታ ከመቁጠር ውጪ አንዳች እርባና ያለው ነገር ለማያደርጉ ወህኒ ቤቶች ‹‹የአራሚነት››አክሊል እየደፋንላቸው ነውና ነገሩ እንዴት ነው ማለት ይጠቅማል፡፡

The post ሰው ስለታሰረ ብቻ ከድርጊቱ ይታረማል? appeared first on Zehabesha Amharic.

በኢትዮጵያ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ የተነሳ በቀን 2 ህፃናት ይሞታሉ * (ቢቢሲ በቆቦ አካባቢ ያለውን ድርቅ የዘገበበት አሳዛኝ ቪዲዮ ይዘናል)

0
0

(ዘ-ሐበሻ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ በተከሰተው ከባድ ድርቅ የተነሳ 15 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው አስታወቀ:: ድርጅቱ ባወጣው መግለጫውም በሃገሪቱ ሰሜናማው ክፍል ለዘገባ በተመረጠ ቦታ ብቻ በረሃብ የተነሳ (በቆቦ አካባቢ) በቀን 2 ህፃናት ሕይወታቸው እንደሚያልፍ አስታውቋል::

ዝናብ ባለመዝነቡ የተነሳ ሰብል ማምረት እንዳልተቻለ ያስታወቀው የተባበሩት መንግስታት የሚጠበቀውን ያህል ማምረት እንዳልተቻለ ጠቅሷል:: በዚህም መሠረት የተባበሩት መንግስታት በድርቁ የተነሳ የተጎዱትን ለመርዳት ከ330 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል::

በ2016 መግቢያ ላይ ይህን ያህል ገንዘብ ኢትዮጵያውያኑን ለመመገብ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ሲያስቀምጥ ቢቢሲ በሰሜን ኢትዮጵያ በቆቦ አካባቢ ተዘዋውሮ ድርቁን እንደሚከተለው ዘግቦታል::

በኢትዮጵያ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ የተነሳ በቀን 2 ህፃናት ይሞታሉ * (ቢቢሲ በቆቦ አካባቢ ያለውን ድርቅ የዘገበበት አሳዛኝ ቪዲዮ ይዘናል)

The post በኢትዮጵያ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ የተነሳ በቀን 2 ህፃናት ይሞታሉ * (ቢቢሲ በቆቦ አካባቢ ያለውን ድርቅ የዘገበበት አሳዛኝ ቪዲዮ ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live