Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Health: 30 አስደናቂ ጤና ነክ  ዕውነታዎች

$
0
0

 

heart burn

– አንድ አዲስ ሰው አንድ ቤት ውስጥ ሲገባ 37 ሚሊዮን ባክቴሪያዎች አብረው ይገባሉ፡፡

– አንጎል 10 ዋት አምፖል በሚሰራበት የኃይል መጠን ነው የሚሰራው፡፡

– ኒውሮኖች በዕድሜ ዘመናችን በሙሉ ማደጋቸውን አያቋርጡም፡፡

– የፊት ፀጉር ከየትኛውም አይነት የቆዳ ፀጉር የበለጠ በፍጥነት ያድጋል፡፡

– የሰው ልጅ ፀጉር አማካይ ዕድሜ ከ3-7 ዓመት ነው፡፡

– ልብ 9 ሜትር ርቀት ደም ወደፊት ለመርጨት የሚያስችል ግፊት ይፈጥራል፡፡

– ጥርሳችሁ ከመወለዳችሁ በኋላ የመስማት ኃይላችሁ ይቀንሳል፡፡

– ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ ሰኞ ድንገተኛ የልብ ህመም በብዛት የሚከሰትበት ቀን ነው፡፡

– ጠዋት ጠዋት ቁመታችን ከማታ ቁመታችን በአንድ ሴንቲ ሜትር ይረዝማል፡፡

– ራሱን የማይጠግን ብቸኛው የሰውነታችን ክፍል ጥርሳችን ነው፡፡

– በእያንዳንዱ ደቂቃ 300 ሚሊዮን ሴሎች ሰውነታችን ውስጥ ይሞታሉ፡፡

– በየቀኑ አንድ አዋቂ ሰው 300 ቢሊዮን ሴሎችን ያመርታል፡፡

– የእያንዳንዱ ሰው ምላስ አሻራ የተለያየ ነው፡፡

– ዓለማችን ላይ በብዛት የሚገኘው የደም አይነት ኦ ነው፡፡

– የምትተኙበት ክፍል ቅዝቃዜ በጨመረ መጠን የምትመለከቱት ህልም መጥፎ የሚሆንበት ዕድልም ይጨምራል፡፡

– ስሜታቸው ሲነካ ማልቀስ የሚችሉ እንስሳት ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡

– ሴቶች ከወንዶች ባነሰ መልኩ ካሎሪ ቀስ ብለው ያቃጥላሉ፡፡ በቀን በአማካይ 50 ካሎሪ ብቻ ሴቶች ያቃጥላሉ፡፡

– ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ጠረንን መለየት ይችላሉ፡፡

– ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ስቅ ይላቸዋል፡፡

– ምራቃችሁ ከምግብ ጋር ካልተቀላቀለ ወይም ምግብ በምራቅ ካልሟሟ የምግቡን ጣዕም መለየት አትችሉም (ምላሳችሁን ካደረቃችሁ በኋላ ሞክሩት)

– ከሰውነታችን ውስጥ እጅግ በጣም ጠንካራው ጡንቻ ምላስ ነው፡፡

– እጅግ በጣም ጠጣሩ የሰውነታችን አጥንት የመንጋጋ አጥንት ነው፡፡

– አንድ ሰው ሳይበላ 20 ቀን መቆየት ይችል ይሆናል፡፡ ሳይጠጣ ግን ከ2 ቀን በላይ ለመቆየት ይቸገራል፡፡

– ደም በቀጥታ የማያገኘው ብቸኛው የሰውነታችን ክፍል የዓይናችን ኮርኒያ ነው፡፡ ኮርኒያ የኦክስጂን አቅርቦት በቀጥታ ከአየር ያገኛል፡፡

– ሳንባችን በቀን ከሁለት ሚሊየን ሊትር በላይ አየር ይስባል፡፡

– አፍንጫችን የአየር ማሞቂያ እና ማቀዝቀዣ መሳሪያችን ነው፡፡ ቀዝቃዛውን አየር ያሞቃል፣ ሞቃቱን አየር ያቀዘቅዛል፡፡

– የደም ሴሎች በአማካይ 120 ቀናት ይኖራሉ፡፡

– በእያንዳንዱ ጊዜ ሰውነታችሁ ውስጥ 25 ትሪሊዮን ቀይ የደም ሴሎች ይኖራሉ፡፡

– ፈገግታ ቢያንስ ሰላሳ ጡንቻዎችን ያንቀሳቅሳል፡፡

ጤናዳም መጽሔት

መጣችልዎ

በቅርብ ቀን በመላው አሜሪካና ካናዳ

The post Health: 30 አስደናቂ ጤና ነክ  ዕውነታዎች appeared first on Zehabesha Amharic.


በድርቅ በተጠቁ የአማራ ክልል አካባቢዎች የውኃ ወለድ በሽታዎች ሥጋት ተፈጠረ

$
0
0

(ሪፖርተር ጋዜጣ) በአማራ ክልላዊ መንግሥት በድርቅ በተጠቁ በተለያዩ ዞኖች የተከለሉ ውኃ ምንጮች ውስንነት፣ ከንፅህና ጋር ለተያያዙ በሽታዎች መፈጠር ምክንያት መሆኑ ተገለጸ፡፡

UN: 9 million need aid in drought-hit East Africa

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በዚህ ሳምንት በወጣው ሪፖርት፣ ‹‹ስካቢስ›› የተሰኘ ወረርሽኝ በምሥራቅ ጎጃም፣ በሰሜን ጎንደር፣ በደቡብ ወሎና በዋግ ህምራ ዞኖች በሚገኙ 20 ወረዳዎች መከሰቱን አስታውቋል፡፡ በዋግ ህምራ ዞን ብቻ 88,905 ግለሰቦች በወረርሽኙ መያዛቸው ታውቋል፡፡ የጤና ጥበቃ  ሚኒስቴር በበሽታው ለተጠቁ ሥፍራዎች መድኃኒቶችን በመላክ ላይ መሆኑን የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ የችግሩ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ የተለያዩ ዘርፎችን ትብብር የሚጠይቅ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡

በሽታው ተዛማች በመሆኑ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተጀመረው ጥረት በአፋጣኝ ተስፋፍቶ መቀጠል እንደሚኖርበት የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ ወረርሽኙ የተከሰተው ከድርቁ ጋር ተያይዞ እንደሆነ በሪፖርቱ አስፍሯል፡፡

ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ በምግብ እጥረት የተጎዱ ሕፃናት ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ የምግብ ፕሮግራም የሚያስፈልጋቸው ሕፃናት ቁጥር ከሌላው ጊዜ በ20 በመቶ መጨመሩን፣ የተጎጂዎቹ ቁጥር በየወሩ እየጨመረ መሄዱን ጽሕፈት ቤቱ በሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

በመስከረም ወር የተመዘገቡ በምግብ ዕጦት የተጎዱ ሕፃናት ቁጥር 35,216 የነበረ ሲሆን፣ በነሐሴ ወር ከተመዘገቡት 43,391 ሕፃናት የ19 በመቶ ቅናሽ ያሳየ ቢሆንም፣ በአገር አቀፍ ደረጃ በመስከረም ወር የተመዘገበው በምግብ ዕጦት የተጎዱ ሕፃናት ቁጥር ከሌላው ማንኛውም ዓመት የ20 በመቶ ብልጫ አለው፡፡

ከፍተኛው ቁጥር የተመዘገበው በአማራ ክልል እንደሆነ የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ በየወሩ በክልሉ 6,489 በምግብ ዕጦት የተጎዱ ሕፃናት ወደ ምግብ ፕሮግራም እንደሚገቡ ጠቁሟል፡፡

በኤልኒኖ ምክንያት በተፈጠረው አየር መዛባት የተከሰተው ድርቅ እየተባባሰ መምጣቱን ጠቅሶ፣ እየጨመረ የመጣውን የምግብ ዕርዳታ ፍላጎት መጠን ለማሟላት የኢትዮጵያ መንግሥት ተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም አጥጋቢ ምላሽ አለመገኘቱን አስታውቋል፡፡ እ.ኤ.አ. የ2015 እና የ2016 የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ፍላጎት ማሟላት የሚያስችል የገንዘብ ምንጭ አለመኖሩ አሳሳቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ እ.ኤ.አ. ለ2016 የሚያስፈልገው ዕርዳታ በአስቸኳይ መገኘት እንዳለበት የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ ዕርዳታውን አጓጉዞ ከሚፈለገው ሥፍራ ለማድረስ ከሦስት እስከ አምስት ወራት ቀድሞ መዘጋጀት እንደሚኖርበት ጠቁሟል፡፡

መንግሥት ከለጋሾች የሚፈለገውን ያህል የገንዘብ ድጋፍ ባለማግኘቱ ሁኔታዎች በከፉበት አካባቢ በራሱ ወጪ ዕለታዊ ዕርዳታዎች በማድረግ ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ከመንግሥት የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት 50,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴና 300 ሜትሪክ ቶን የምግብ ዘይት በመከፋፈል ላይ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ የከብቶች መኖ በመታደል ላይ መሆኑን፣ የውኃ ጉድጓዶች ጥገና ሥራ እየተከናወነ እንደሆነና የውኃ ማጣሪያ ኬሚካሎች በመሠራጨት ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት በተፈጠረው ድርቅ ምክንያት 8.2 ሚሊዮን ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፣ የዕርዳታ አቅርቦቱ ካልተፋጠነና የአየር ፀባዩ ካልተለወጠ የተረጂዎች ቁጥር በሁለት ወራት ውስጥ 15 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል፡፡

The post በድርቅ በተጠቁ የአማራ ክልል አካባቢዎች የውኃ ወለድ በሽታዎች ሥጋት ተፈጠረ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢንጂነር ይልቃል ሞባይል ስልካቸው ባልታወቁ ሰዎች እጅ መግባቱን አስታወቁ 

$
0
0

Hiber Radio Interview with Eng Yilkal Getnet

(ዘ-ሐበሻ) የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የሞባይል ስልካቸው ባልታወቁ ሰዎች እጅ መግባቱን እና ከዛሬ ጀምሮ በኢሜይል; በፌስቡክ እና በቴክስት በርሳቸው ስም የሚላክ ሁሉ የርሳቸው እንዳልሆነ አስታወቁ::

ስልካቸውን “ባልታወቁ ሰዎች እጅ ከመግባቱ” ውጭ ስም ጠርተው ተጠያቂ ያላደረጉት ኢንጂነሩ ያስተላለፉት መል ዕክት ነው::

ማሳሰቢያ!

የእጅ ስልክ (ሞባይሌ) ባልታወቁ ሰዎች እጅ ስለገባ ከዛሬ ጥቅምት 24/2008 ዓ.ም ጠዋት 2 ሰዓት ጀምሮ በፌስቡክ፣ በኢሜልና በሌሎችም አድራሻዎቼ የሚተላለፉ መልዕክቶች የእኔ አለመሆናቸውን ወዳጆቼ እንድትገነዘቡልኝ እፈልጋለሁ፡፡

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

The post ኢንጂነር ይልቃል ሞባይል ስልካቸው ባልታወቁ ሰዎች እጅ መግባቱን አስታወቁ  appeared first on Zehabesha Amharic.

በስዊድን ለአርበኞች ግንቦት ሰባት መርጃ ገንዘብ ተሰበሰበ

$
0
0

ወለላዬ ከስዊድን

አቶ ዘለሌ ፀጋ ስላሴ ዝግጅቱን ሲከፍቱ

አቶ ዘለሌ ፀጋ ስላሴ ዝግጅቱን ሲከፍቱ

 

ቅዳሜ ኦክቶበር 31 -2015 (ጥቅምት 20 – 2008 ዓ.ም ) በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ መርጃ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተደረገ። በዝግጅቱ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተገኝተዋል።በቦታው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ አበበ ቦጋለ  የውጪ እንቢተኝነት ሊቀመንበር እና አቶ ቸኮል ጌታነህ የንቅናቄው ከፍተና አመራር ናቸው።

አቶ አበበ ቦጋለ ንግግር ሲያደርጉ

አቶ አበበ ቦጋለ ንግግር ሲያደርጉ

 

ዝግጅቱ ረፋዱን 14፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን አቶ ጌታሁን ማሬ የዝጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ  የስዊድን የአርበኞች ግንቦት ሰባት የስራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ ዘለሌ ፀጋ ሥላሴን ስለዝግጅቱ ገለጻ እንዲያደርጉና ዝግጅቱንም እንዲመሩ  ጋብዘዋል። አቶ ዘለሌ በበኩላቸው የከተማው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ያለበትን ሁኔታ ገልጸው እንግዶቹንም በማስተዋወቅ አቶ አበበ ቦጋለና አቶ ቸኮል ጌታሁን ንግግር እንዲያደሩ ጋብዘውል።

አቶ ቸኮል ጌታሁን ንግግር ሲያደርጉ

አቶ ቸኮል ጌታሁን ንግግር ሲያደርጉ

አቶ አበበ በአሁኑ ሰዓት አርበኞች ግንቦት ሰባት እየሰራ ስላለው የስራ ክንውን እቅድና አላማ እንዲሁም ደጋፊዎቹና አባላቶቹ እያደረጉ ስላሉት እንቅስቃሴ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ ቸኮል ጌታሁን በበኩላቸው በኤርትራ ቆይታቸው ወቅት ስለተመለከቱት የአርበኛው ቆራጥነትና የአላማ ጠንካራነት የገለጹ ሲሆን በአሁን ሰዓት የድሮ ጀግናችን ስም  በመጥራት የምንቀመጥበት ጊዜ ሳይሆን እኛው እነሱን ተክተን በጀግንነት ስማችን ማስጠራት የሚገባን ጊዜ ነው  በማለት ደጋፊውንና አባላትን የሚአበረታታና የሚነሳሳ መል ክት አስተላልፈዋል።

ከሁለቱ አመራሮች ንግግር በኋላ ተሰብሳቢው ሰው ጥያቄ እንዲያቀርብ ተጋብዞ ለቀረቡት ጥያቄዎች መልስ ተሰጥቷል። እንዲሁም ንቅናቄውን በተመለከተ ግልጽ ውይይት ተደርጓል። ከዚህ በመቀጠል « በደል ይረሳል ወይ?» የሚል ግጥም በማራኪና በወለላዬ ከቀረበ በኋላ  የገቢ ማሰባሰቢያ ጨረታ ተደርጓል። ለጨረታ የቀረበው የንቅናቄው ሊቀመንበር የሆኑት የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ቆራጡ አርበኛ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከሚመሯቸው አርበኞች ጋር ሆነው የሚታዩበት «ላንቺ ነው ኢትዮጵያ » የተባለ ምስል ሲሆን ይሄው ምስል በግልና በቡድን ተጫርቶ ከፍተኛ ፉክክር ከተደረገ በኋላ  በአንድ መቶ አራት ክሮነር( የስዊድን ገንዘብ ) የስዊድን የስደተኞች ማህበር አሸንፎ ምስሉን የግሉ አድርጎታል። ከዚህ ከጨረታ ከተገኘው ገንዘብ ሌላ ሁለት የቃል ኪዳን ቀለበቶች የመግቢያ ገንዘብ ሦስት መቶ ዶላርና ከእጣ የተሰበሰበ ገቢ ተገኝቷል።

የጨረታው አሸናፊዎች

የጨረታው አሸናፊዎች

በወቅቱ በስደተኛ ማህበሩ አባላት ይደረግ የነበረው ተሳትፎ ዝግጅቱን አድምቆት አርፍዷል በጨረታው ጊዜም በማሃል እረፍት በሚደረግበት ወቅት የ/ሪት ሙሉቀን አማረ «ኢትዮጵያዊት ነሽ አትበሉኝ » የሚል ግጥምና  የ/ሮ ውቤ ማሞ እንዲሁም የአቶ መብራቱ ፀሐዩ  ቀስቃሽ ግጥሞች  ቀርበዋል።

የጨረታው አሸናፊዎች በተቀበሉበት ወቅት

የጨረታው አሸናፊዎች በተቀበሉበት ወቅት

The post በስዊድን ለአርበኞች ግንቦት ሰባት መርጃ ገንዘብ ተሰበሰበ appeared first on Zehabesha Amharic.

በፕሮፌሰር መስፍን “አዳፍኔ“ መጽሐፍ ላይ አንዳንድ የሀሳብ ፍንጣቂዎች፡ ኢትዮጵያውያንን ከእራሳቸው መጠበቅ?

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

Prof. Mesfin
አሁን ከቅርብ ጊዜ በፊት “አዳፍኔ፡ ፍርሀት እና መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው እና ታትሞ የወጣው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የአማርኛ መጽሐፍ የኢትዮጵያ ህዝቦች በብልሹ አስተዳደር፣ በአምባገነናዊነት የጭቆና አገዛዝ እና በሞራል ስብዕና መብከት ምክንያት ተዘፍቀው ከሚገኙበት የኃጢአት ባህር ውስጥ እራሳቸውን በንስሀ በማደስ ከሀጢአት እንዲጸዱ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስዱ የሚያሳስብ ነው፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ቀደም ሲል ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ እየተባለ ይጠራ በነበረው አሁን ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመባል በሚታወቀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ የመልክዓ ምድር/Geogeraphy ትምህርት ያስተምሩ ነበር፡፡

አዳፍኔ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሐፋቸው ፕሮፌሰሩ እውነታን በተላበሰ መልኩ ወይም ደግሞ ምክንያታዊ አመክንዮን ባካተተ ድምጸት እና አንደበታቸው ሀገር ወዳዱ የምሁር ቁንጮ አርበኛ በጎሳ ፖለቲካ ተዋቅሮ ሀገራቸውን እያተራመሰ ባለው የደናቁርት ስብስብ ዕኩይ ድርጊት በከፍተኛ ደረጃ በመበሳጨት ይህንን ሀገር አውዳሚ የሆነ ድርጊት የሀገር ተረካቢ የሆነው ወጣቱ ትውልድ ፍቅር እና ሰላም የሰፈነባት፣ እድገት በባዶ ፕሮፓጋንዳ በደናቁርት ስብስብ የውሸት የቁጥር ድርደራ የሚነዛባት ሳይሆን በተጨባጭ እውን የሚሆን ዕድገት የሚመዘገብባት፣ እድገት እና ሹመት በፖለቲካ ታማኝነት እየተዘገነ የሚታደል ሳይሆን በትምህርት ብቃት እና ችሎታ የሚሰጥባት፣ በሀብት መክበር በማጭበርበር እና የሕዝብን ሀብት በማን አለብኝነት በመዝረፍ ሳይሆን ነጭ ላብን አፍስሶ፣ አዕምሮን እና አካላዊ ብቃትን ተጠቅሞ ሀብት የሚፈራባት፣ ሙስና፣ ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ የጥላቻ እና የበቀልተኝነት ሰይጣናዊ አስተሳሳብ፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የሚወገድባት ሀገር እንድትሆን ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ ለሀገር ተረካቢው ለወጣቱ ትውልድ ምሁራዊ እና አባታዊ ምክርን ለመስጠት የሞከሩበት መጽሐፍ ነው፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን በስልጣን ማማ ላይ ተንጠልጥለው እና ለዘመናት ሕዝቡን በመጨቆን ላይ ለሚገኙት ኃይል አምላኪ አምባገነኖች ሁሉ እኔ ላስታውሰው ከምችለው በላይ ለበርካታ ዓመታት ምንም ነገር ሳይፈሩ ፊት ለፊት እውነታውን እስከ አፍንጫቸው ድረስ ሲናገሩ የቆዩ እና ያሉ ብርቅዬ አንደበተ ርትኡ ምሁር ናቸው፡፡

“አዳፍኔ“ የተባለው መጽሐፋቸው አሁን በስልጣን ላይ ለሚገኙትም ሆነ ለሌሎቹ የመጨረሻውን እውነታ የገለጹበት አዋጃቸው ነው፡፡

በእኔ አመለካከት ፕሮፌሰር መስፍን ቢያንስ ላለፉት አራት አስርት ዓመታት ሲታገሉ የቆዩ የአደባባይ ምሁር ናቸው፡፡

በ21ኛው ክፍለ ዘመን ምሁራን የሰው ልጆችን ነጻነት እና እውቀት ለማበልጸግ እየወሰዱ ያለውን ተልዕኮ ከግንዛቤ በማስገባት ፕሮፌሰር ኤድዋርድ ሳይድ የተባሉ ምሁር እንዲህ ብለው ነበር፣ “በስልጣን ላይ ላሉት እውነታውን መናገር ለመሰቃየት፣ መከራን ለመቀበል ምስክርነት መሆን እና ለፍትህ እና ለርትዕ ሲባል የአመጽ ድምጽን ከፍ አድርጎ በማሰማት በስልጣን እርካብ ላይ ተቆናጥጠው ከሚገኙት ገዥዎች ጋር ከቅራኔ ውስጥ መግባት ማለት ነው“ ብለው ነበር፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን በተጠናቀቀው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ጀምረው በኢትዮጵያ እውነትን በስልጣን ላይ ላሉ ገዥዎች ሁሉ በይፋ የመናገር ተግባራቸውን ጀመሩ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተቀበለ ላለው ስቃይ እና መከራ ዋና ምስክር ናቸው፡፡

እኒህ ምሁር ባፈጀው እና ባረጀው ንጉሳዊ አገዛዝ እና ደም በጠማው እና እራሱን “ደርግ” እያለ ይጠራ የነበረው ወታደራዊ አምባገነን ስርዓት አስከትለውት በነበረው ጭቆና ስርዓቱን በመቃወም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በመጮህ ተቃውሟቸውን በአደባባይ አሰምተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በዓለም አቀፍ ምጽዋዕት እና ልመና በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጠው ሕዝቡን በማተራመስ ላይ ለሚገኙት ወሮበላ የዘራፊ ብድን ስብስቦች የጭቆና አገዛዝ ምስክር ናቸው፡፡

ምናልባትም እኒህ ምሁር ለዘመናት ተከታታይነት ባለው መልኩ በስልጣን እርካብ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው በሕዝብ ላይ ብልሹ አስተዳደር እንዲንሰራፋ እና በሰው ልጆች ላይ ሰብአዊ መብትን በመደፍጠጥ የሚኖሩ ጨቋኝ አገዛዞች ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምድር እንዲወገዱ እውቀታቸውን እና ምሁራዊ ክህሎታቸውን በመጠቀም የምክንያታዊነት እና አመክንዮአዊ አስተሳሰብ ዋና ድምጽ ናቸው ብሎ መናገር የበለጠ ገላጭ ይሆናል፡፡

ጥረታቸው ሁሉ ሲመክን ሲመለከቱ ገደቡን አልፎ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ጭቆና በማጋለጥ እና ገደብ እዲበጅለት ድምጽ ለሌለው ሕዝብ ድምጽ በመሆን በአደባባይ መጮህ ጀመሩ፡፡

እንደ ዕድል ሆኖ የእርሳቸው የጭቆና የእምቢተኝነት ትግል ለማህበራዊ እና ለፖለቲካዊ ለውጥ ምቹ መደላድል መፍጠሩ ቀርቶ በተቃራኒው እርሳቸውን የስቃይ ዒላማ አደረጋቸው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ እራሳቸውን መንግስት አስመስለው እርኩሰትን የተላበሰ የገዳይ ወሮበላ ዕኩይ ስብስብ በመፍጠር የጭቆና አገዛዝ አንሰራፍተው የሚገኙት እና በሙስና እስከ አፍንጫቸው ድረስ ሰምጠው ለሚገኙት ዘራፊ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ዘ-ህወሀት) በማለት ለሚጠሩት የደናቁርት ስብስብ ወሮበሎች ፕሮፌሰሩ ፍርሀት የለሽ ብቸኛው የሰብአዊ መብት ጥበቃ ድምጽ እምቢተኛ አመጸኛ ለመሆን በቅተዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ ለእምነታቸው እና በአመክንዮ ላይ ለተመሰረተው ጽኑ አስተሳሰባቸው ከፍተኛ መስዋዕትነትን ከፍለዋል፡፡

ላለፉት 24 ዓመታት ፕሮፌሰር መስፍን በ ዘ-ህወሀት በግፍ እንዲሰቃዩ ተደርገዋል፣ እንዲሁም ሸፍጥን በተላበሰ መልኩ ምንም ዓይነት ጥፋት ሳያጠፉ እውነትን ፊት ለፊት በመናገራቸው ብቻ በዝንጀሮው የይስሙላ ፍርድ ቤት በየጊዜው እየተመላለሱ እንዲቀርቡ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የማጉላላት ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ሰላማዊ በሆነ መልኩ የፖለቲካ እና የሰብአዊ መብት ጥበቃ እንቅስቃሴዎችን በማድረጋቸው ዘ-ህወሀት ለአስከፊ እስራት ዳርጓቸዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜም እንኳ ቢሆን ከፍተኛ ለሆነ የመሽማቀቅ እና የማስፈራራት ዕኩይ የወያኔ ድርጊቶች የጥቃት ዒላማ ሆነዋል፡፡

ዘ-ህወሀት ፕሮፌሰር መስፍን እትብታቸው የተቀበረበትን ሀገራቸውን ትተው እንዲሰደዱ ይፈልጋል፡፡

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2015 ፕሮፌሰር መስፍን እያሰቃዩአቸው ላሉት የዘ-ህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስቦች እንዲህ የሚል የመሞገቻ ጽሑፍ በድረ ገጽ በአማርኛ ቋንቋ ጽፈው አስነብበዋል፡

“…ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እየሰራሁ በነበርኩበት ጊዜ ወያኔዎቹ በቀጥታም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ ሀገር ለቀቅን እንድንሰደድ ወይም ደግሞ ወንጀል እድንሰራ የማስገደድ ድርጊት ይፈጽሙብን ነበር፡፡

ስለእራሴ ትንሽ ልናገር፡፡ እኔን ለምን እደሚያስፈራሩኝ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ በአሁኑ ጊዜ እያስፈራሩኝ ያሉት ምናልባትም እየኖርኩበት ያለውን አፓርትመንት በመፈለጋቸው ምክንያት እንደሁ በእርግጠኝነት አላውቅም፡፡ በእኔ ቤት ውስጥ ያሉ እና የወያኔ ሎሌዎች ትልቅ ዋጋ ያወጣሉ ብለው የሚያስቧቸው ነገሮች አሉ ከተባለ ምናልባትም በገብረ ክርስቶስ ደስታ የተሳሉ ሁለት ስዕሎች ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ ውጭ ግን በቤቴ ውስጥ ሊገኙ የሚችሉት ለወያኔ ምንም ዓይነት ዋጋ ሊያወጡ የማይችሉት መጽሐፍት ብቻ ናቸው፡፡ ስለሆነም እኔ በወያኔ እጅ እየተሰቃዬሁ ያለሁት ሀገሬን ትች እንድሰደድ ከመፈለግ ዓላማ የመነጨ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን ድርጊት እ.ኤ.አ በ1992 ሞክረውት ነበር፡፡ ሆኖም ግን አልሰራላቸውም፡፡ እኔን መጠነ ሰፊ በሆነ መልኩ እያሰቃዩኝ ያሉበትን ምክንያት በእርግጠኝነት ላውቀው የማልችል ቢሆንም በአንድ በደህና ቦታ ላይ በተቀመጠ የወያኔ ሰው ግልጽ እንደተደረገልኝ በእኔ ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ የማሰቃየት ዘመቻ ተከፍቶብኝ ይገኛል፡፡

ይህች ሀገር ለአንድ በጥባጭ ለሆነ ወሮበላ ስብስብ ብቸኛ ሀብት ናት የሚል እምነት የለኝም፡፡ ይህች ሀገር የተመሰረተችው በእኛ እናት እና አባት፣ በአያት እና ቅድመ አያቶቼ ነው፡፡ ማንም ቢሆን እኔን አስገድዶ ከሀገሬ በማባረር ስደተኛ ሊያደርገኝ ፍጹም አይችልም፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ ማንም ቢሆን እኔን በማስፈራራት መብቴን ነጥቆ ሊወስድ በፍጹም አይችልም፡፡ ይህ ድርጊት ይፈጸም ዘንድ በፍጹም አልፈቅድም፡፡ ለወያኔዎች በጠራ መልኩ ግልጽ እንዲሆንላቸው እንዲህ በማለት ያለኝን አቋም በአጽንኦ ልነግራቸው እፈልጋለሁ፡ በህይወት እየኖርኩባት ያለሁት እና ስሞትም የምቀበረው በዚህችው በኢትዮጵያ ምድር ነው፡፡
adafne
ለወያኔ እና ለሎሌዎቹ አንድ ሊካድ የማይችል እውነታን ልንገራቸው፡ እኔን የጥቃት ሰለባ ለማድረግ ሲሉ ሕገወጥ ድርጊት እና ወንጀሎችን ቢሰሩ ያለምንም ጥርጥር ነገ ከዚህ የበለጠ ታላቅ መሰቃየትን እና ቅጣቶችን ይቀበላሉ፡፡ እነዚህ ስልጣናቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ በሚጠቀም ነጹሀን ዜጎችን በመግደል ኃያል የሆኑ የሚመስላቸው እብሪተኞች አንድ ጊዜ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባቸዋል፡፡ ማንም ሰውን በመግደል ድልን ሊቀዳጅ ይችላል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ማንም ሰው በመሞት ድልን በገዳዮቹ ላይ ሊቀዳጅ ይችላል፡፡“

“አዳፍኔ” የእርሳቸው የግላቸው ሙያዊ ተሞክሮ እና የእራሳቸው የነገሮችን ታሪካዊ አመጣጥ ዳህራ በውል የመገንዘብ እና ትንታኔ በመስጠት ችሎታ ላይ መሰረት በማድረግ በእኩዮሽ የታሪክ መስመር ላይ የማይሄደውን የሀገሪቱን ታሪክ እና ኋላቀር የስልጣኔ ደረጃ ከግምት ውስጥ በማስገባት የተሰጠ የሀሳብ ፍንጣቂ ነው፡፡

ፕሮፌሰሩ ከወያኔ ማሰቃየት በፊት በሌሎች አገዛዞችም ስቃይ ሲደርስባቸው የቆዩ ናቸው፡፡

እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ ሁለተኛ አጋማሽ የመጨረሻዎቹ እና በ1980ዎቹ ዓመታት በሙሉ “ደርግ” እየተባለ ይጠራ በነበረ ወታደራዊ አምባገነን ወሮበላ አገዛዝ ስቃይ ደርሶባቸዋል፡፡

ደርግ በሰው ልጆች ላይ ሲፈጽም ከነበረው የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ጋር አመለካከታቸው ሊሄድ ስላልቻለ ስማቸውን ማጥፋት እና ማብጠልጠል ጀመሩ፡፡

እንደዚሁም ሁሉ የግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ ዓመታት በሙሉ የማሸማቀቅ እና የማስፈራራት ድርጊቶችን ሲፈጽማቸው ነበር፡፡ ስርዓቱ እርሳቸውን የማይበገሩ ቆጥቋጭ እና ካመኑበት በፍጹም ፍንክች የማይሉ ሞገደኛ አድርጎ ይቆጥራቸው ነበር፡፡

ሆኖም ግን በስልጣን ላይ የነበሩት ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ እና ሚኒስትሮቻቸው እንዲሁም ልዑላን መሳፍንት እና መኳንንት ፕሮፌሰሩ አንድም ነገር እንዳይናገሩ በፈለጉበት ጊዜ እንኳ ሳይቀር እርሳቸው መንፈሳቸው የመራቸውን እና የማኑበትን ነገር ፊት ለፊት ከመናገር የታቀበቡት ጊዜ ሳይኖር በእምነታቸው ቀጥለውበት ሄደዋል፡፡

በተለያዩ ስርዓቶች የተለያዩ ከበሮዎች ቢደለቁም ቅሉ እርሳቸው ግን ረዥሙን የነጻነት ጉዙ ተያይዘውት እስከ አሁን ድረስ በጉዞ ላይ ይገኛሉ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ከመሆናቸው በፊት የነጻነት ሙያዊ እምቢተኝነትን የሚያራምዱ ሰው እንደነበሩ በድፍረት መገመት እችላለሁ፡፡

እርሳቸው በጭንቅ ኑሮ እየተሰቃዩ የኖሩ ስለሆኑ፣ ለፍትህ እና ለርትዕ ሲሉ ሁልጊዜ የእምቢተኝነትን ዓላማ ሲያራምዱ ስለኖሩ እና ምንጊዜም በስልጣን ላይ ተጣብቀው ሊሚገኙት፣ ስልጣናቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ ለሚጠቀሙት ገዥዎች እና ከስልጣን ለተወገዱት ሁሉ እውነታውን ፊት ለፊት ከመናገር የማይቆጠቡ ምሁር ስለሆኑ ከስማቸው በስተመጨረሻ በአህጽሮተ ቃል ሙ.እ/P.D (ሙያዊ እምቢተኛ/Professional Dissenter) በመባል መጠራት አለባቸው ብየ አስባለሁ፡፡

በስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጠው የሚገኙት ገዥዎች አመልካች ጣታቸውን ወደ እርሳቸው በመቀሰር፣ ቡጢዎቻቸውን በመጨበጥ በሀይል መገፍተር እና ወደ እስር ቤት እየወሰዱ በማጎር ይበቀሏቸው ነበር፡፡

እርሳቸው ግን እንደማትበገርዋ ግመል ረዥሙን ጉዝ መጓዝ ቀጥለዋል፡፡ የመንግስት ውሾች እየተከተሉ ይጮሀሉ፣ እናም ውሾቹ ጥርሶቻቸውን ያፋጩባቸዋል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን በመስበክ፣ በማስተማር፣ ያልተደረሱ ሕዝቦችን በመድረስ እና በህዝቦች ላይ ወንጀል የሚሰሩትን ባለስልጣኖች በማጋለጥ እና በመክሰስ ላይ ቀጥለው ይኖራሉ፡፡

አዳፍኔ በሚለው መጽሐፋቸው ላይም ያንኑ ባህል ነው ቀጥለውበት የሚታዩት፡፡

እንደምሁር፣ እንደ አደባባይ ልሂቅ፣ እንደ ኢትዮጵያ ታሪካ ተቆርቋሪ እና እንደ መልካም እና እንደ እውነተኛ የሰው ተፈጥሮ ለፕሮፌሰር መስፍን ከፍተኛ የሆነ ከበሬታ አለኝ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን የአጭበርባሪነት የቁማር ካርታን አይጫወቱም፣ በሁለት ቢላዋ አይቆርጡም እናም ቆሻሻ የማታለል ዕኩይ ድርጊቶችን አይፈጽሙም፡፡

ማለት ያለባቸውን በግልጽ ይናገራሉ፣ የተናገሩትንም በተግባር ይፈጽማሉ፣ በመንታ ምላስ አይናገሩም፡፡ የምታየው ነገር በእርሳቸው ላይ ያለውን እውነታ ብቻ ነው፡፡

እርሳቸው የሚናገሩትን እውነታ የማትወድ ከሆነ ምንጊዜም ቢሆን ቀዝቅዞ ወደማያውቀው ወደ ገሀነም በቀጥታ መጓዝ ትችላለህ፡፡

እውነት መናገር እውነት ተናጋሪዎችን ለመኖር በሚዋሹት እና እየዋሹ በሚኖሩት ዘንድ አይወደዱም፡፡

በእኔ አመለካከት ፕሮፌሰር መስፍን በኢትዮጵያ የቦቅቧቃ ምሁራን፣ በፖለቲካ አድርባይነት እና በአስመሳይ ሎሌ ምሁራን የጨለማ ሰማይ ዘንድ ለዘመናት በማይደበዝዝ መልኩ የተቀጣጠሉ ብቸኛ የመቅረዝ ላይ ሻማ ናቸው፡፡

ፕሮፌሰር መስፍንን “የሚያስብ ሰው“ በማለት እንደጻፉት እንደ ራልፍ ዋልዶ ኢመርሶን አድርጌ እቆጥራቸዋለሁ፡፡

Adafneኢመርሰን እ.ኤ.አ. ነሐሴ 1837 በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ በመገኘት አንድ አሜሪካዊ ምሁር እጅግ በጣም ጠቃሚ እና አስፈላጊ ነው የሚባለው የሚከተለውን ማድረግ ሲችል ነው በማለት እንዲህ ተናግረው ነበር፡

“ምሁር ከሌሎች በተለየ መልኩ ተለይቶ የሚኖር፣ በጣም ከፍተኛ በሆነ መልኩ ስለጤንነት የሚያስብ- ጩቤ በመጥረቢያ ላይ እንደሚያደርገው ሁሉ በአንድ ሰው ወይም በህዝብ ጉልበት በተሰራው ስራ ላይ ስምምነት የማያደርግ ነው የሚል ዓለም አቀፋዊ አስተሳሰብ አለ… ለጠንቃቃ የህብረተሰብ ክፍሎች እውነት እንደሆነ ሁሉ…ድርጊት በምሁር ቁጥጥር ስር ነው፣ ሆኖም ግን በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ከድርጊት ውጭ ሰው እራሱ ገና ሰው አልሆነም ማለት ነው፡፡ ከድርጊት ውጭ ሀሳብ በምንም ዓይነት መልኩ ወደ እውነትነት ሊደርስ አይችልም፡፡ ዓለም የቆንጆዎች ሁሉ ቆንጆ ሆኖ በዓይናችን ላይ ቢደቀንም ቆንጆ መሆኑን እንኳ ልናየው አንችልም፡፡ የድርጊት ሰው ያለመሆን የቦቅቧቆች እና የፈሪዎች ወራዳ ተግባር ነው፡፡ ስለሆነም ከጀግና አዕምሮ ውጭ ምንም ዓይነት ምሁራዊነት የለም፡፡ የሀሳብ መግቢያ ካለማሰብነት ወደ ማሰብ ደረጃ የሚደረገው ሽግግር የሚገለጸው በድርጊት ነው፡፡ በህይወት እስከኖርኩ ድረስ እኔ የማውቀው ይህንን ያህል ብቻ ነው፡፡ ወዲያውኑም ቃሎቻቸው በህይወት የተሞሉትን እና ያልተሞሉትን እናውቃለን፡፡“

ፕሮፌሰር መስፍን ጀግና አዕምሮን የተጎናጸፉ የኢትዮጵያ “አሳቢ ሰው” ምሁር ናቸው፡፡

ከሌሎች ህዝቦች ተለይተው በፍጹም ኖረው የማያውቁ እና ለጤናማ የአኗኗር ህይወት ጠንቃቃ የሆኑ ሰው ናቸው፡፡

እርሳቸው ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል የተግባር ሰው ሆነው የቆዩ ሰው ናቸው፡፡

የእርሳቸው አመለካከቶች እና የሚያቀርቧቸው እና የሚጽፏቸው ሀሳቦች በርግጥ እውነተኛ ድርጊቶች ናቸው፡፡

እኔ እርሳቸውን ጀግና አሳቢ ሰው ከሆኑት ከኢመርሰን የበለጠ “የሚያስቡ ሰው” አድርጌ እቆጥራቸዋለሁ፡፡

እኔ ፕሮፌሰር መስፍንን ስለኢትዮጵያ “የሚጽፉ ሰው”፣ “የሚናገሩ ሰው”፣ “የሚያዳምጡ ሰው”፣ “የሚያነሳሱ ሰው”፣ “የሚቀሰቅሱ ሰው” ለፍትህ እና ለርትዕ ሲሉ በአመኑበት ጉዳይ ላይ በጽናት እና በአይበገሬነት የሚቆሙ “የእምቢተኝነት” ሰው አድርጌ እቆጥራቸዋለሁ፡፡

እርሳቸው የሚያምኑበትን ነገር ለስርዓቱ ተጠቃሚዎች እና ስልጣናቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ በስራ ላይ ለሚያውሉ ብቻ አይደለም ከፍርሀት ውጭ የሚናገሩት፡፡ ሆኖም ግን እርሳቸው አስረግጠው እና በጽናት በመቆም የሚናገሩት ኃይል ለሌላቸው፣ ለስልጣን ረሀብተኞች እና በስልጣን ለሰከሩ ህዝቦች እንዲሁም መስማት ለሚፈልጉ ሁሉ ለእውነት እና ለእውነት ብቻ ነው የሚናገሩት፡፡

ኢመርሰን “የዓለም ዓይን” በማለት እንደጻፉት ሁሉ ፕሮፌሰር መስፍንም ”አዳፍኔ” በሚለው መጽሐፋቸው ላይ የኢትዮጵያን ያለፈ ታሪክ ታላቅነት በመጠበቅ፣ ፍቅርን በተላበሰ መልኩ ይህንን ታላቅነት ለአቻ ምሁራን ጓደኞቻቸው (አብዛኞቹ ከእርሳቸው ጎን ቆመው ለሀገራቸው እና ለሕዝባቸው ሰላም እና ደህንነት በጋራ በአደባባይ ከመታገል ይልቅ በግል እያብጠለጠሉ የሚያሟቸው) ለመግለጽ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን እርሳቸው “የኢትዮጵያ ዓይን” በመሆን ከኢትዮጵያ ተነጥሎ ላለው እና ከአያቶቹ እና ከቅድመ አያቶቹ ታቅነት ጋር ተለያይቶ ለሚገኘው ለአዲሱ እና ለሀገር ተረካቢው ወጣት ትውልድ ለማመላከት ነው፡፡

“አዳፍኔ” በሚለው መጽሐፋቸው ውስጥ ፕሮፌሰር መስፍን በዳሳሹ ዓይናቸው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት የት ላይ እንደነበሩ እና አሁንስ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ወይም ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በሚሰሩት ስራ ምርጫ ላይ ተመስርቶ ወደፊትስ የት ላይ እንደሚሆኑ እና እንደማይሆኑ በግልጽ የተመለከቱበትን ዘገባቸውን አቅርበዋል፡፡

ይህ መጽሐፍ ጥንት ታላቅ የነበረችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ምስቅልቅ ሁኔታ ላይ የምትገኝ መሆኗን እና የኢትዮጵያ የተሻሉ ቀኖች እየመጡ እና ከአድማስ ጫፍ ላይ እየታዩ መሆናቸውን የግል ሀሳባቸውን በውል እያስቀመጡ ጥልቀት እና ስፋት ባለው ሁኔታ ትንታኔ የሰጡበት ነው፡፡

“አዳፍኔ” በሚገባ የተቀቀሉ ታሪካዊ እና የዘመኑ የፖለቲካ ትንታኔዎችን በማጣመር እንዲታዩ የተደረገበት እና በርካታ ኢትዮጵያውያን የሞራል ግዴታቸውን ባለመወጣት እና ከዳር ቆመው እየተመለከቱ ሀገሪቱ ወደከፋ አዘቅት ውስጥ እየተጋዘች ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያውያን ታላቅ ጥንቃቄን በተላበሰ መልኩ እንዴት አድርገው እራሳቸውን ከእራሳቸው መጠበቅ እና ማዳን እንደሚችሉ ለማሳየት ጥረት የተደረገበት ብሩህ መስተዋት ነው፡፡

የመጽሐፉ ርዕስ ተመሳስሎ በርካታ የተወሳሰቡ ስሜቶችን እና ትርጉሞችን አካትቶ ይዟል፡፡

“አዳፍኔ” የሚለው ቃል የመቅበር ሂደትን የሚያሳይ ወይም ደግሞ አንድን ነገር በአፈር መሬት ወይም ደግሞ በአመድ ውስጥ መደበቅን የሚያመላከት መሆኑን ግንዛቤ ሊሰጥ ይችላል፡፡

እንደዚሁም ደግሞ የእሳት መጥፋትን እና የቀረዉን ፍም በአፈር ወይም ደግሞ በውኃ ማጥፋት መሆኑን ሊገልጽ ይችላል፡፡

በሌላ መልኩ ይታይ ከተባለ ደግሞ ጥቂት ተግባራት ገና በመጀመሪያው የአፈጻጸም ደረጃቸው በድንገት የመክሰማቸውን ሁኔታ ሊያመላክት የሚችል ይሆናል፡፡

በኢትዮጵያ የወታደራዊ ስርዓት የቋንቋ አጠቃቀም “አዳፍኔ” በተለምዶ “ባዙቃ” እየተባለ የሚጠራው ጸረ ታንክ መሳሪያ ነው፡፡

በአጠቃላይ “አዳፍኔ” የሚለው ቃል አንድን ነገር ወይም ደግሞ ሂደትን የሚያፍን፣ የሚያንቅ፣ ትንፋሽ የሚያሳጣ፣ የሚያጠፋ፣ የሚከለክል እና የሚያደናቅፍ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ይህንን “አዳፍኔ” የሚለውን ተመሳስሎ በአሁኑ ጊዜ እና ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ስልጣናቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ የሚጠቀሙትን አምባገነን አገዛዞች፣ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ እና ፍልስፍና አዘል የሆኑ እውነታዎችን በመጠቀም ለመክሰስ እና ለፍትህ አካል ለማቅረብ ሲሉ የገለጹበት ቃል ነው፡፡

እንደዚሁም ደግሞ ኃይል የለሾችን፣ የስልጣን ጥመኞችን እና በስልጣን የሰከሩትን ለመሞገት እና ለመገዳደር በማሰብ ከስልጣን ጋር ተያይዘው የሚመጡትን በርካታ የሆኑ ኃላፊነቶችን ለመገንዘብ እና ህዝቡን በቅንነት ለማገልገል ሲባል የህንን ተመሳስሎ ይጠቀማሉ፡፡

“አዳፍኔ” የሚለው ቃል ድብቁ መልዕክት የበለጠ አሳማኝ ነው፡፡ (እርሳቸው አዳፍኔን በአሁኑ ጊዜ ላለው ለወጣቱ ትውልድ እና ለመጭው ትውልድ ማስታወሻ እንዲሆን በማሰብ የሰጡት ስያሜ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡)

በአዳፍኔ ውስጥ በአሁኑ ወቅት እና ቀደም ሲል የደረሰውን የትውልድ ውድቀት በሚገባ አጢኖ በርካታ የአፍሪካ ሀገሮች ከደረሰባቸው አስፈሪ እና አስደንጋጭ ሁኔታ ውግዘት ለማላቀቅ እና ኢትዮጵያን ከአስከፊ ውድቀት በማውጣት ንስሀ ለመግባት የማይቀረውን ታሪካዊ፣ በጋራ መስራት አለመቻልን ወይም ራዕይ ያለው አመራር ያለመኖርን ወጣቱ ትውልድ በውል ተገንዝቦ የእራሱን ኃላፊነት መወጣት እንዲችል የተሰጠ ማስጠንቀቂያ መሆኑን እገነዘባለሁ፡፡

የኢትዮጵያ ውጣቶች የ“አዳፍኔን“ አስፈሪ ሁኔታ በውል አጢነው ያለፉት አባቶች፣ አያቶች እና ቅድመ አያቶች የፈጸሟቸውን ስህተቶች በመድገም እራሳቸውን ከውሸት ተራራ ስር ቀብረው እንዳይገኙ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ለኢትዮጵያ ወጣቶች በሶስት ቀላል ሀሳቦች ሊገለጽ የሚችል ታላቅ መልዕክት አላቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) ከተወሰኑ ቡድኖች የእራስን በእራስ ከማጥፋት አስከፊ አደጋ ኢትዮጵያን ሊታደጓት የሚችሉት የኢትዮጵያ ወጣቶች ብቻ ናቸው፡፡

2ኛ) ኢትዮጵያን ከጎሰኝነት እሳት እና ከኃይማኖት ጽንፈኝነት ሊታደጓት የሚችሉት የኢትዮጵያ ወጣቶች ብቻ ናቸው፡፡

3ኛ) የማህበረሰቡን የግንኙነት ክር ከበጠሱት የድሮዎቹ እና የአሁኖቹ ትውልዶች፣ አውዳሚ ከሆነው የፖለቲካ መዋቅር፣ ግራ ከተጋባው የኢኮኖሚ ስርዓት እና የህዝቡን መንፈሳዊ ህይወት ሊመለስ በማይችል መልኩ ካጠፋው ትውልድ ኢትዮጵያን ሊመልሱ እና ሊያድኑ የሚችሉት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ብቻ ናቸው፡፡

“አዳፍኔ” በአንድ ወቅት ምናልባትም በቅኝ ግዛት ዘመን የተገኘ ስር የሰደደ የአፍሪካ በሽታ ነው፡፡

“አዳፍኔ” አህጉሪቱን ሙሉ በሙሉ በመበከል ታላላቅ መልካም ባህሪ፣ እውቀት፣ ታማኝነት እና ክብረ ሞገስ ያላቸውን ወንዶች እና ሴቶች እንዳታፈራ በማድረግ ምድረበዳ አድርጓታል፡፡

“አዳፍኔ” አህጉሪቱን የጊንጥ ማጠራቀሚያ ቅርጫት አድርጓታል፡፡ አንድ ጊንጥ ከቅርጫቱ ውስጥ ለመውጣት ሙከራ በሚያደርግበት ጊዜ ሌሎቹ ጊንጦች ወደ ቅርጫቱ ውስጥ ስበው ያስቀሩታል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ “አዳፍኔ” የአዕምሮ በሽታ ነው፡፡ የ”አዳፍኔ” በሽታ ሰለባዎች በዘላቂነት ጸረ ነጻነት፣ ጸረ እኩልነት፣ ጸረ ፍትህ እና ጸረ ዕድገት ናቸው፡፡

በሌላ አባባል ለማስቀመጥ ለ”አዳፍኔ” በሽታ ሰለባዎች ነጻነት ማለት የእነርሱ ነጻነት ብቻ ነው፣ እኩልነት ማለት የእነርሱ እኩልነት ማለት ብቻ ነው፣ ፍትህ ማለት ለራሳቸው ብቻ ነው ፣ ልማት ማለት በሚያስገርም ሁኔታ ብዙሀኑ ሕዝብ በረሃብ እየተሰቃዬ ባለበት ሁኔታ እነርሱ ግን ከመሬት እና ከሌላም ሀብት በርካታ የታሰረ ረብጣ ገንዘብ እያግበሰበሱ ወደ ኪስ ማጨቅ ማለት ነው፡፡

እንደዚሁም ሁሉ “አዳፍኔ” የአምባገነናዊ የጭቆና አገዛዝ መለያ የስብዕና ባህሪ መገለጫ ነው፡፡ “አዳፍኔ” መሬቱን፣ ማዕድናቱን እና ጌጣጌጡን ሁሉ በእራሱ ደብቆ ይይዛል፡፡ “አዳፍኔ” ሐይቆችን እና ወንዞችን ሁሉ በእራሱ ቁጥጥር ስር ያደርጋል፡፡ አዳፍኔ አምላክ መሰል ስልጣን አለው፡፡ የ”አዳፍኔ” ምኞት ለሌላው ህዝብ ትእዛዝ ነው፡፡

“አዳፍኔ” የኢትዮጵያውያን ነብሶች በሽታ ነው፡፡

“አዳፍኔ” በምን መልኩ ይታያል ፡

1ኛ) እውነትን በመጨቆን እና በማጥፋት፣

2ኛ) ትምህርትን እና እውቀትን በመጨቆን እና በማጥፋት፣

3ኛ) እውነት ሊሰራጭበት እና ሊስፋፋበት የሚችለውን ማናቸውንም ቀዳዳ ሁሉ በመዝጋት፣

4ኛ) መንታ ምላስ ያላቸውን ቅጥፈት እና ውሸት ሲገምዱ የሚውሉ እና የሚያድሩ ደናቁርት ካድሬዎችን እና አስመሳዮች ሆድ አደርን በመቅጠር፣ እና

5ኛ) ሀሳቦች እና እውቀቶች በሕዝብ መካከል እንዳይሰራጩ የህትመት ውጤቶችን በሁሉም መንገዶች በመዝጋት ኢትዮጵያን የባዶ ዲስኩር ማሰሚያ መሬት አደረጋት፡፡

የ”አዳፍኔ” የሶስትዮሽ ውልደት በኢትዮጵያ የእህት እና ወንድሞችን ፍርሀት እና ውድቀት ጨምሮ ሰይጣናዊ ስብዕና ያላቸው፣ ተቋማዊ ስርዓትን የተላበሱ፣ መንፋሳዊ እሳቤን እንዲላበሱ የተደረጉ፣ ሞራል የለሽ እና በሞራል ስብዕና የከሰሩ እንዲሁም ምሁራዊ አስመሳይነትን የተላበሱ ዕኩይ ምግባራት ናቸው፡፡

“አዳፍኔ” የሚለው ተመሳስሎ ሮበርት ጄ. ኦፔንሃይመር ፣ አለምን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የሚያጠፋ ስለ አቶሚክ ቦምብ ተናግረው ነበር ። ኦፐንሄይመር የሂንዱ አምላክ የሆነውን ቪሽኑን በመጥቀስ እንዲህ ብሎ ተናግሮ ነበር፣ “እኔ በአሁኑ ጊዜ ዓለምን ለማጥፋት የምችል ሞት ሆኛለሁ፡፡“

በኢትዮጵያ የሞት ስብዕናን የተላበሰው “አዳፍኔ” ሆኗል፡፡

“አዳፍኔ” ከኢትዮጵያ እና ከሕዝቦቿ ቀስ በቀስ የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና መንፋሳዊ ህይወትን በመጭመቅ ዕኩይ ምግባር ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡

አዳፍኔ በኢትዮጵያ የተስፋ፣ የእምነት፣ የልግስና፣ የፍላጎት መነሳሳት፣ የቃል ኪዳን፣ የክብር፣ የታማኝነት፣ የክብረ ሞገስ፣ የትክክለኛነት፣ የሞራል ስብዕና፣ የመልካም ፈቃድ ማውደሚያ ዕኩይ ምግባር መሳሪያ ሆኖ ይገኛል…

አዳፍኔ በእውቀት ብቻ ሊወገድ ይችላል፡፡ እውቀት እና ትምህርት የአዳፍኔ ጠላቶች ናቸው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አዳፍኔ የሚሞት የእውቀት እና የትምህርት ጠላት ነው፡፡

አዳፍኔ ተጽእኖው በወጣቶች ላይ የጠነከረ ነው፡፡ እነዚህ ወጣቶች አያት እና ቅድመ አያቶቻቸው በሰሯቸው ስኬታማ ስራዎች ላይ ኩራት እንዲኖራቸው ከማድረግ ይልቅ በአባቶቻቸው እና በእናቶቻቸው ላይ ስለደረሰው ስቃይ እንዲጸጸቱ ይገደዳሉ፡፡ በኢትዮጵያዊነታቸው እራሳቸውን እንዲያሳትፉ ከማድረቅ ይልቅ ወጣቶች በጠባብ የጎሰኝነት እና የኃይማኖት ጽንፈኝነት ላይ ኩራት እንዲሰማቸው ይገደዳሉ፡፡ ወጣቶች መብቶቻቸውን እንዳይጠቀሙ ኃይል እንዲያጡ እና አቅመቢስ እንዲሆኑ ይደረጋሉ፡፡ ወጣቶቹ ድምጾቻቸውን እንዲያጡ እና በእራስ የመተማመን ስሜት እንዲያጡ ይገደዳሉ፡፡

የአዳፍኔ የሶስትዮሽ ውልደት ግዙፍ የሆነ የስርዓት መውደቅን እና በማህበረሰቡ ደረጃ መዋቅራዊ የውድቀት ቀውስ መንስኤን ያስከትላል፡፡ እንግዲህ ያንን የህልውና ውድቀት (መክሸፍ) ነው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ኢትዮጵያውያንን እንደ ኢትዮጵያውያን በመጽሐፋቸው ለማሳየት ጥረት ያደረጉት፡፡

የፕሮፌሰር መስፍን የመክሸፍ ትንታኔ በርካታ መገለጫዎች አሉት፡፡ አንድ የማህበረሰብ ፕሮጀክት የአፈጻጸም ብቃት ሳይኖረው እና ከፍጻሜ ሳይደርስ ሲቀር ወይም ደግሞ ለማህበረሰቡ ፍሬ ሳያፈራ ሲቀር “መክሸፍ” ሊከተል ይችላል፡፡ አንድ ሰው ዓላማውን ሳያሳካ ሲቀር እና እድገትን ማስመዝገብ ሳይችል ሲቀር መክሸፍ ይመጣል፡፡ በጋራ ልማት እና ማህበራዊ ለውጥ ማምጣት ሳይቻል ሲቀር መክሸፍ ይከተላል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውን መክሸፍ ሶስት ዋና ዋና ምክንያቶችን እንደሚከተለው ግልጽ አድርገው አቅርበዋል፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) የአስተዳደር ስርዓቱ በሕግ የበላይነት ቁጥጥር ስር መዋል ሲሳነው፣

የዚህ መክሸፍ ውጤት አምባገነን ጨቋኝ መንግስትን ያለምንም ችግር መቀበል ወይም ደግሞ በእግር በመወሰን ወደ ስደት መንጎድ ይሆናል፡፡

2ኛ) የኢትዮጵያ ምሁራን መክሸፍ፣ ምሁራን እና የልሂቃኑ መደብ በማንኛውም ጊዜ ለሚመጡ እና ስልጣንን በሕዝብ ድምጽ ሳይሆን በመሳሪያ ኃይል ለሚቆጣጠሩ አምባገነኖች እራሳቸውን እና ስብዕናቸውን ይሸጣሉ፡፡ በእያንዳንዱ አገዛዝ ዘመን ምሁራን ምንም ዓይነት ሰይጣናዊ ድርጊት አልሰማሁም፣ ምንም ዓይነት ሰይጣናዊ ድርጊት አላዬሁም እና ምንም ዓይነት ሰይጣናዊ ነገር አልተናገርኩም በሚሉ እና እራሳቸውን እንደ ሶስት ጦጣዎች እንደተሰየሙ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡

ምሁራን እና የተማረው ህብረተሰብ መደቦች በስልጣን ላይ ያለው አካል ትክክለኛ የሆኑ ነገሮችን በመያዝ ሕዝቡን አስተባብረው በመምራቱ ረገድ ሳይሳካላቸው ቀርቶ ከሽፈዋል፣ እንደዚሁም ሁሉ በስልጣን ላይ ያለው አካል ወንጀሎችን ሲሰራ እና የተሳሳቱ ስራዎችን ሲሰሩ መዝግበው በመያዝ ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍ ምንም ነገር የማያደርጉ ስለሆነ ከሽፈዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የእራሰቸውን ስህተቶች እንደገና ለማባዛት በሚመስል መልኩ ከሁሉም በላይ አስከፊ የሆነው ነገር ያለፈውን ትውልድ ስህተት እንደ ትክክለኛ ነገር እና አግባብነት እንዳለው ሁሉ ለመጭው ትውልድ ሌት ቀን እንደበቀቀን እየደጋገሙ የመንዛታቸው ሁኔታ ነው፡፡

የኃይማኖት መሪዎች መንፈሳዊ አመራር መስጠት ባለመቻላቸው እና ምንም የተሻለ ነገር ባለመኖሩ ከሽፈዋል፡፡

ከሁሉም በላይ ልብን የሚሰብረው እውነታ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተንጠልጥለው የሚገኙት የደናቁርት ስብስብ የአካዳሚ የትምህርት ማስረጃዎችን ከዲፕሎማ መቀፍቀፊያ የኢንተርኔት ወፍጮዎች በሕዝብ ገንዘብ እየገዙ ልከበር እያሉ የማስቸገራቸው ጉዳይ ነው፡፡ ስልጣናቸውን ለማሳመር እና ማስዋቢያ ነገሮችን በመቀባባት በስልጣን ላይ ያሉት የደናቁርት ስብስቦች ባለስልጣን መሳይ አካል የፈረመበት ማህትሞችን በመጠቀም እና የሸፍጥ የምስክር ወረቀቶችን በመግዛት ዶክተር፣ ፕሮፌሰር፣ የመንግስት አማካሪ እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች በማለት እራሳቸውን በመጥራት የአስመሳይነት ስራቸውን በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡

በእኔ አመለካከት የደናቁርት ስብስቦቹ ያልተረዱት ነገር ቢኖር አንድ አህጽሮተ ቃል የተጻፈበት ብጣሽ የተጭበረበረ የዲፕሎማ ወረቀት አንድን ወንድ ወይም ሴት ታላቅ መሪ ሊያደርግ እንደማይችል በውል ያለመገንዘባቸው ጉዳይ ነው፡፡

አንድን ሰው ታላቅ የሚያደርገው ራዕዩ፣ አዕምሮው እና የወንዱ ወይም ደግሞ የሴቷ ልብ ነው እንጅ በስርቆት የተገዛ ዲፕሎማ አይደለም፡፡

ቢል ጌትስ እንደ ስቴቭ ጆብስ እና ማርክ ዙከርበርግ ሁሉ ከኮሌጅ ትምህርት ያቋረጡ ናቸው፡፡

ዋልት ዲስኔይ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያቋረጡ ናቸው፡፡

አብርሃም ሊንከን የአንደ ዓመት መደበኛ ትምህርት ብቻ ነበር ያላቸው፡፡ ቁም ነገሩ እዚህ ላይ ግልጥ ነው ፡፡

3ኛ) ለኢትዮጵያውያን አርዓያ ሊሆናቸው የሚችል አካል ያለመኖሩ ጉዳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ስኬታማ የሆኑ ሀገሮች ባለመኖራቸው ምክንያት ኢትዮጵያውያን ስለተሻለ አመራር እና ህብረተሰብ ለመማር እና ለማወቅ አልቻሉም፡፡

አዳፍኔ በኢትዮጵያ ሰፊ መሰረት ባለው ታሪካዊ እና ማህበረ ፖለቲካ ከባቢ አየር ላይ የተዋቀረ ነው፡፡ መጽሐፉ ኢትዮጵያን ለዘመናት ቀጣይ ሆና እንድትዘልቅ የሚያግዙ ዋና ዋና እሴቶችን ግልጽ አድርጓል፡፡

“አዳፍኔ” እና የእርሱ እህቶች እና ወንድሞች ፍርሀት እና መክሸፍ (የማይነገርለት የእነርሱ የአጎት ልጅ የሆነው የፍርሀት ፍርሀት) በኢትዮጵያ ባህል እየሆነ እና እያደገ በመምጣት የሕዝቡን ደስታ፣ ብልጽግና እና ፍቅር እንዲሁም ግለሰቦች በእራስ የመተማመን እና የእራስ ክብር አለመስጠት ነገሮች እንዲከስሙ አድርጓል፡፡

በኢትዮጵያ የአዳፍኔ እና የእህት እና ወንድሞቹ ዋና መነሻ ምክንያት ምንድን ነው?

“አዳፍኔ” አንድ ልዩ ዓይነት የሆነ “ፍርሀት” እንደሆነ አምናለሁ፡፡

የእውነትን መሰረታዊ ሀሳብ የመፍራት ጉዳይ ነው፡፡

እውነትን የማሰብ ፍርሀት ነው፡፡

እውነትን የመናገር ፍርሀት ነው፡፡

እውነትን የመስማት ፍርሀት ነው፡፡

እውነትን የማየት ፍርሀት ነው፡፡

በእውነት መኖር ፍርሀት ነው፡፡

ከእውነት ጋር የመኖር ፍርሀት ነው፡፡

እውነትን የመስበክ ፍርሀት ነው፡፡

እውነትን የማስከበር/የመጠበቅ ፍርሀት ነው

ከዚህም በተጨማሪ ፍርሀት እና እርስ በእርስ ያለመተማመን ጉዳይ ነው፡፡ ህሊናዎቻችንን መፍራት ማለት ነው፡፡ ትክክለኛውን ነገር ለመስራት መፍራት ነው፡፡ ከሁሉም ነገር የከፋው ደግሞ እራሳችንን መፍራት እና በግል እና በጋራ ለእራሳችን እና ለሀገራችን ምን ማድረግ እንዳለብን የመፍራት ጉዳይ ነው፡፡

በአዳፍኔ “እውነትን የመፍራት ነገር” በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስልጣን መክሸፍ፣ የትምህርት መክሸፍ፣ የባህል መክሸፍ፣ የኢኮኖሚ መክሸፍ፣ የምሁርነት መክሸፍ፣ የመንፈሳዊት መክሸፍ፣ እና የሞራል ስብዕና መክሸፍ ምክንያት ቀጥተኛ ተጠያቂ ነው፡፡

የፕሮፌሰር መስፍን ታሪካዊ የጽሑፍ ዘገባ በኢትዮጵያ የአዳፍኔ የሶስትዮሽ ውልደት ተጽእኖ ጥልቅ የሆነ ሀዘንን ያባብሳል፡፡

ኢትዮጵያውያኖች ጥሩ ዕድል ሲያገኙ ጥሩ ዕድል ያገኙትን ለማጣት አይከሽፉም፡፡

የኢትዮጵያ ምሁራን እና ልሂቃን ለቀጣዩ ትውልድ መዝግበው ለማስተላለፍ ትልቁ ትኩረት በመስጠት ስራዎችን እስካከናወኑ ድረስ የአዳፍኔ የሶስትዮሽ ትውልድ ታሪክ ብቻ ሊነገር ይችላል፡፡

አዳፍኔ በኢትዮጵያውያን እና በአውሮፓውያን በጣም የሚፈሩትን እና የአቢሲኒያ ጀግና እያሉ ና የሚርበተረቱላችው እንደ ራስ አሉላ እንግዳ (አባ ነጋ) የመሳሰሉትን ጀግኖች የሚያጠፋ ገደል የሚጥል ነገር ነው፡፡

ራስ አሉላ እ.ኤ.አ በ1887 የጣሊያን ወራሪ ብርጌዶችን በዶጋሊ ጦርነት ላይ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ድል አድርገዋቸዋል፡፡ የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን እንደ ዳቦ ቅርጫት ሲቀራመቷት እና ግዛቶቿን ቅኝ ግዛት ሲያደርጉ እና ዜጎቿን ባሮች ሲያደርጓቸው ራስ አሉላ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት እና ክብር አስጠብቀዋል፡፡

ከአውሮፓ ኃያላን ሀገራት ጋር ህብረት ፈጥረው የነበሩት አጼ ዮሐንስ 4ኛ ለራስ አሉላ ማግኘት ከነበራባቸው ማዕረግ በታች ዝቅ አድርገው በመስጠት ክህደት ፈጽመውባቸዋል፡፡ ያ ዓይነት ድርጊት ገና በመጀመሪያ መደረጉ ጣሊያን ወደ መሀል ሀገር ዘልቃ እንድትባ እና ወረራ እንድታደርገ አግዟታል፡፡ አዳፍኔ! ግዙፍ የሆነ የአመራር እና አስተዳደር ክሽፈት፡፡

እንደ አጋጣሚ ሆኖ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ እ.ኤ.አ በ1896 በአድዋ ላይ በተካሄደው ጦርነት ለጣሊያኖች ሊረሱት የማይችሉት ዓይነት ትምህርት ሰጥተዋቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የእራሷ ፊደል ያላት ብቸኛዋ የአፍሪካ ሀገር ናት፡፡ ሆኖም ግን የእውቀትን የመጨረሻውን ጠርዝ ለመመርመር ወይም ደግሞ በግብርና፣ በመስኖ፣ በስነ ሕንጻ እና በመጓጓዣ የነበረውን የጥንቱን እውቀት መዝግቦ እና ጠብቆ ለአዲሱ ትውልድ እንዲደርስ ለማድረግ አላስቻለም፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ትንሽ ጠንከር ባለ ሁኔታ እውቀት የለውጥ መሳሪያ ነው በማለት ይጽፋሉ፡፡ እውቀት ለፍትህ፣ ለእኩልነት እና ለመልካም አስተዳደር ቅድመ ሁኔታ ነው…በጥንት ጊዜ እውቀት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚወደድ ወይም ዋጋ የሚሰጠው ጉዳይ አልነበረም፡፡ ያ ሁኔታ እስከ አሁንም ድረስ አልተለወጠም… አዳፍኔ! ሌላው የህብረተሰብ ታላቅ መክሸፍ!

በግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ጊዜ ዘመናዊ የመንግስት ስርዓት ተመስርቶ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ብቸኛው የስልጣን ባለቤት ሆኑ፡፡ የወታደሩ ክፍል፣ የፖሊስ እና የደህንነት ኃይሉ በእርሳቸው ቀጥተኛ ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ከእርሳቸው የበለጠ አምባገነን እና ጨካኝ በነበረ ወታራዊ አምባገነን መንግስት በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣናቸው በኃይል እስከሚወገዱ ድረስ እራሳቸውን ጠቃሚ ሰው በማድረግ በአምባገነንነት በስልጣናቸው ተጣብቀው ቆይተዋል፡፡ አዳፍኔ! ግዙፍ የሆነ የአመራር እና አስተዳደር ክሽፈት፡፡

የኢትዮጵያ ልሂቃን ለበርካታ ዘመናት የውጭ ጠላቶችን በሚወጉ ጀግኖች (አርበኞች) እና ከውጭ ጠላቶች ጋር ተባባሪ በመሆን የእራሳቸውን ወገኖች በሚወጉ (ባንዳዎች) ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን እንዲህ በማለት ይጽፋሉ፡ “በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ላይ ያሉ የባንዳ ልጆች የከሀዲ ወላጆቻቸውን አሳፋሪ እና ዲቃላ ታሪክ ይደብቃሉ፡፡ አሳፋሪ የሆነ የወላጆቻቸውን ታሪክ ለመደበቅ ሲሉ ወዲያ እና ወዲህ ሲወራጩ ይታያሉ፡፡ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ስለመሆን እና አለመሆናቸው በእራስ የመተማመን ስሜት ይጎድላቸዋል፡፡ እራሳቸውን ከከፍታ ቦታ ላይ ለማውጣት በማሰብ የኢትዮጵያን ታሪክ ለእነርሱ በሚመቻቸው መልኩ እየነጣጠሉ እና እያዛቡ በመከለስ ያቀርቡታል፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ ታሪክ ከ100 ዓመታት አይበልጥም በማለት ያለምንም ሀፍረት በመናገር ላይ ገይኛሉ… በእራሳቸው የሚፈበርኩትን ታሪክ አጉልተው ለማሳየት ሲፈልጉ የኢትዮጵያን ታሪክ በጠማማው አዕምሯቸው አጥቁረው እና አዛብተው ያቀርባሉ፡፡” በአጭሩ የዘ-ህወሀት ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ታሪክ የለሽ የፍብረካ ታሪክ ይደሰኮራል፡፡ አዳፍኔ! ታላቅ የታሪክ እና የታሪክ ትንተና መከሸፍ፡፡

በጦር ሜዳዎች አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው የሀገራቸውን ነጻነት አስከብረው ስለቆዩት ስለኢትዮጵያ ጀግኖች የተጻፈው በጣም ትንሽ ነገር ነው፡፡ እውነተኛ አርበኛ ጀግኖች በሰላሙ ጊዜ እንደ ባንዳ እና ከሀዲ ዓይነት አያያዝ ሲደረግላቸው በተቃራኒው ደግሞ ባንዳ ለነበሩት እና ሀገራቸውን ከውጭ ጠላት ጋር በመተባበር ሲወጉ ለነበሩት እንደ ጀግና የሚቆጠሩበት እና የሚሸለሙበት እንዲሁም ስልጣን እና ሀብት የሚታደሉበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን እንዲህ በማለት ይጽፋሉ፣ “እስከ አሁን ድረስ የተጻፈው የእውነተኛ ጀግኖች ታሪክ ከቁጥር የሚገባ አይደለም፡፡ ስለ አርበኛ እና ጀግናው ስለ ደጃዝማች ገረሱ ዱኬ፣ ስለ ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ፣ ስለሻለቃ በቀለ ወያ ትንሽ ተጽፏል፡፡

[ከዚህ ዝርዝር ውስጥ እ.ኤ.አ በ1930ዎቹ ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በኩል በጥቂት ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ በጦር ሜዳ ዉጊያ ጣሊያንን መግቢያ ቀዳዳ እያሳጡ በመዋጋታቸው ብቻ ሳይሆን ከዚህም በተጨማሪ በእርጅና ዘመናቸው የደርግን አምባገነን መንግስት ለሶስት ተከታታይ ዓመታት በጀግንነት ሲዋጉ ለነበሩት እና በእግዚአብሔር እንጅ በሰው ዘንድ ሳይታወቁ የቀሩትን ያልተዘመረላቸውን የጦር ሜዳ ጀግና የኢትዮጵያ አርበኛ የነበሩትን አርበኛ ደጃዝማች ከበደ ብዙነሽ (አባ መርዞ) ግልጽ በሆነ መልኩ እጨምራለሁ፡፡ በእነዚህ ጀግኖች በጣም እኮራለሁ፣ ከፍ ያለ ምስጋናም አቀርባለሁ!]

የታላላቅ ጀግኖች ኢትዮጵያውያንን ታሪክ ስማቸውን በትክክል መዝግቦ እና ያልታወቁትን እና በጦር ሜዳ ለውድ ሀገራቸው ሲሉ የወደቁትን ጀግኖች ደግሞ ዩኒቨርስቲዎች እያጠኑ እና እየተመራመሩ ስማቸው ለመጨው ትውልድ እንዲተላለፍ በማድረግ የድርሻቸውን ሚና መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ለእንደነዚህ ዓይነት ጀግኖች ትኩረት በመስጠት ጥረት የሚያደርጉ ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡ እናም ታሪካቸውን መዝግቦ ማስቀመጥ ጠቀሜታው ለእነዚህ ጀግኖች ሳይሆን ለመጭው ትውልድ ነው፡፡ አዳፍኔ! ግዙፍ የሆነ የኢትዮጵያ ምሁራን እና ልሂቃን መክሸፍ፡፡

በአዳፍኔ ውስጥ ፕሮፌሰር መስፍን ቀደም ሲል በሰሯቸው ስራዎች ላይ ትችት ላቀረቡላቸው (ከገጽ 165 – 268) ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በርካታዎቹ ትችቶች በስብዕናቸው ላይ ያነጣጠሩ ቀጥታ ግለሰባዊ ናቸው፡፡ ጥቂቶች ግን የእራሳቸውን ሀሳቦች ወይም ትንታኔዎች የምር የሚገዳደሩ ናቸው፡፡

ያ ግንዛቤ ሊወሰድበት የሚችል ጉዳይ ነው ምክንያቱም በኢትዮጵያ ታሪክ፣ ፖለቲካ እና ማህበረሰብ ላይ ጥልቅ እውቀት እና የመከራከር ብቃቱ ያላቸው ምሁራን ናቸው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ፕሮፌሰሩ ግልጽ በሆነ መልኩ በአደባባይ ጠንካራ እና ጽናትን በተላበሰ መልኩ ለምንም ለማንም ሳይበገሩ ሀሳቦቻቸውን ማቅረብ የሚችሉ ምሁር በመሆናቸውም ትችት ቀርቦባቸዋል፡፡

ይኸ ጉዳይ እኔን የሚያሳስበኝ አይደለም ምክያቱም ፊቱን ሳያጥፍ፣ ምንም ዓይነት ድርድር ሳያቀርብ ጠንካራ እና በመርህ ላይ የተመሰረተ የነጻነት እና የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተማጓች ሰው ጠላት ተደርጎ መፈረጅ እንደሌለበት እምነት ያለኝ ስለሆነ ነው፡፡

ሆኖም ግን ፕሮፌሰር መስፍን ቀደም ሲል ባቀረቧቸው ስራዎች ላይ በቀረቡት ትችቶች እና እርሳቸውም አሳማኝ በሆነ መልኩ እና በቂ አመክንዮዎችን እየዘረዘሩ በሰጧቸው ምላሾች ብዙ ተምሬባቸዋለሁ፡፡

በሀሳቦች ግጭት እና ጠንካራ በሆኑ ክርክሮች እምነት አለኝ፡፡ በአዳፍኔ መጽሐፍ ላይ በርካታ ክርክሮች ይኖራሉ የሚል ተስፋ አለኝ፡፡

በዚህ ትችቴ ላይ ያሉኝን ሀሳቦች ፈነጠቅሁ እንጅ የመጽሐፍ ግምገማ ያካሄድኩ ያለመሆኔ እንዲታወቅልኝ እጠይቃለሁ፡፡

የመጽሐፍ ግምገማ በይዘቱ፣ በአቀራረቡ እና መጽሐፉ ባካተታቸው ፋይዳዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰጥ የስነጽሑፍ ትችት ነው፡፡

እኔ ሀሳቦቼን መፈንጠቅ ነው የመረጥኩት ምክንያቱም ፕሮፌሰር መስፍን በኢትዮጵያ ታሪክ፣ ህዝብ እና ፖለቲካ ላይ ስላላቸው ጥልቅ እውቀት፣ ግንዛቤ እና ትንታኔ ላይ ሀሳቤን እንድገልጽ እና ያለኝን ከፍተኛ አድናቆት እንድገልጽ ዕድሉን የሚሰጠኝ ሆኖ ስላገኘሁት ነው፡፡

በአዳፍኔ ፕሮፌሰር መስፍን የእራሳቸውን የልጅነት ዘመናቸውን አንጸባርቀዋል፡፡

ልጅ በነበሩበት ጊዜ ሲያድጉ ምን ለመስራት ይፈልጉ እንደነበር ሲጠየቁ “ትምህርቴን በሚገባ ተምሬ ሀገሬን አገለግላለሁ“ የሚል ምላሽ ነበር የሰጡት፡፡

እኔም በልጅነት ዘመን እንደዚህ ለማድረግ ነበር የማስበው፡፡

በእርግጠኝነት እንዲህ በማለት አውጃለሁ፣ “በአሜሪካ ትምህርቴን እማራለሁ፣ እናም ትምህርቴን ካጠናቀቅሁ በኋላ ተመልሸ ሀገሬን አገለግላለሁ፡፡“

በኢትዮጵያ የሚገኙ ወጣቶች ሁሉ በኔ ጊዜ በልጀነታቸው የሚከተሉት መርህ እንደዚህ ያለ እንደሆነ እምነት አለኝ፡፡

እ.ኤ.አ በ1975 ሀገሬን ለማገልገል ለአጭር ጊዜ ወደ ሀገር ቤት ተመልሸ ነበር፡፡ እዚያ ሄጀ ሁኔታውን ሁሉ በቃኘሁት ጊዜ ምንም ዓይነት እገዛ ከማንም እንደማይፈልጉ ግንዛቤ ወሰድኩ፡፡

እየተንፏቀቀ ለመጣው የመፈንቅለ መንግስቱ ዋና አድራጊ ፈጣሪ ማኔጀሮች እራሳቸውን ብቻ በደህና ሁኔታ ይረዱ ነበር፡፡

በዋና ዋና የከተማይቱ መንገዶች ላይ ታንኮች ሲርመሰመሱ አስተውያለሁ፡፡ የወታደር መለያ ዩኒፎርም የለበሱ ወታደሮች በጅፖች ላይ ሆነው ባለ 50 ካሊበር ጠብመንጃዎቻቸውን እየወደሩ ሲዞሩ ተመልክቻለሁ፡፡

በውስጣቸው የታጠቁ ወታደሮችን ያጨቁ ወታደራዊ ካሚዮኖች ከተማዋን እያቋረጡ ሲፈተለኩ እመለከት ነበር፡፡

ለውጥን እንኳን መጣህ ብዬ ደስ ብሎኝ ነበር፣ ዳሩ ምን ያደርጋል ንጉሳዊውን አገዛዝ የተኩት ወታደሮች ናቸው፡፡ በሌላ አገላለጽ ንጉሳዊ አምባገነንነት በወታደራዊ አምባገነንነት ተተካ ማለት ነው፡፡

ይህም ማለት ከመጥበሻው ወደ እሳቱ ወይም ከድጡ ወደ ማጡ እንደማለት ነው፡፡

ይህንን ጉዳይ ካስተዋልኩ በኋላ ቀኝ ኋካ ዙር አልኩ እና ወዲያውኑ ወደ ዩኤስ አሜሪካ ፈትለክ አልኩ እና የድህረ ምረቃ ትምህርቴን ቀጠልኩ፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ በ1975 በበጋው ወቅት ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር አዲስ አበባ ተገናኘን፡፡

ይህንን ጊዜ እና ከስተት የሚያስታውሱት አይመስለኝም፡፡

ከትምህርት ሚኒስቴር አጠገብ ካለች አንዲት የሻይ ቡና መሸጫ ክፍል ውስጥ አሁን በሕይወት ከሌለው እና በኢትዮጵያ ታሪክ ታዋቂ ከሆነው እና ከሰብአዊ መብት ተሟጋች ከነበረው አጎቴ ከፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ ጋር ለመገናኘት ሄድን፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን እኔ ምንድን እንዳጠናሁ እና በአሜሪካ ሀገር ውስጥ ምን ተሞክሮ እንዳለኝ ጠየቁኝ፡፡ ለብዙ ጊዜ ከኢትዮጵያ ርቄ በመቆየት ከተመለስኩ በኋላ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ስላለኝ ምልከታ እንድናገርም ጠየቁኝ፡፡

በዚያን ጊዜ በእርግጠኝነት ምን ምላሽ እንደሰጠኋቸው አላስታውስም፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን እና ፕሮፌሰር አለሜ እሸቴ ሁለቱም ዘ-ህወሀት ስልጣን ከያዘ በኋላ በነበሩት ዓመታት ውስጥ ስለሰብአዊ መብት ጥበቃ ጠንካራ በሆነ መልኩ ገቡበት፡፡

ዘ-ህወሀት ስልጣን ከያዘ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ፕሮፌሰር መስፍን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉበኤን እንዳቋቋሙት አምናለሁ፡፡

ምናልባትም በተመሳሳይ ጊዜ ፕሮፌሰር አለሜ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሊግን አቋቋሙ፡፡ በዚያን ጊዜ የነበሩኝ በርካታ ትውስታዎች አሁን ላይ ሆኝ ሳይ እረስቻቸዋለሁ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን እና ፕሮፌሰር አለሜ በፖለቲካ እና በሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ዙሪያ ባከናወኗቸው ምሁራዊ ክንውኖች ታላቅ ኩራት ይሰማኛል፡፡ ያልከሸፈው የወደፊቱ ትውልድ የእነዚህን ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ልሂቆች አስተዋጽኦ ለታሪክ መዝግቦ መያዝ እና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅበታል፡፡

እውነታውን ፍርጥርጥ አድርጎ ለመናገር በአዳፍኔ ላይ በሰጠሁት የሀሳብ ፍንጣቂ ፕሮፌሰር መስፍን በታላቅ ሀዘን ከተናገሯቸው ሰዎች መካከል እንደ አንዱ ሆኘ ተሰማኝ፡፡

እ.ኤ.አ በ1975 ኢትዮጵያን ተሰናብች በሄድኩ ጊዜ ዳግም ላልመለስ ምዬ ተገዝች ነበር፡፡ የእራሴ የሆኑ ግላዊ ምክንያቶች ነበሩኝ፡፡

እ.ኤ.አ በ1975 እንዲህ የሚሉ ግልጽ እና ቀላል ምርጫዎች ነበሩኝ፡ በስደት ነጻ ሆኖ መኖር ወይም ደግሞ በወሮበላ ወታደራዊ አምባገነን ስርዓት መዳፍ ስር ሆኖ ሲሰቃዩ መኖር፡፡

ያለምንም ማቅማማት ነጻ ሆኖ መኖርን መረጥኩ፡፡

ከደንቆሮ እና ያልሰለጠነ ወታደራዊ እና ወሮበላ አምባገነን መንግስት ነጻነትን መምረጥ የሞራል ስብዕና ዝቅጠት ወንጀል ነውን?

ሳልሞን ሩሽዲ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ሁሉንም ነገር ማለት ነው፣ አዲስ የሆነ ልዩ ክስተት፡፡ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ በእራሱ ህይወት ነው፡፡“

ከዚህም በተጨማሪ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ህይወት ያለውን ከሞተው እና እየሞተ ካለው የሚለይ ነው፡፡ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ በማይቻልበት ጊዜ እና ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ህይወት የለሽ በሆነበት ጊዜ በድን የሆኑ ሙት ነብሶች ብቻ አሉ ማለት ነው፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን መብቶቻቸውን በነጻነት ለመጠቀም እዚያው ሀገራቸው ውስጥ ቀጥለው በመታገል ላይ ይገኛሉ፡፡

ኢትዮጵያን ትቻት ሄድኩ፣ ሆኖም ኢትዮጵያ እኔን አልተወችኝም ለማለት እውዳለሁ፡፡

አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በ2005 የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ውዝግብ ድምጻቸው በጠራራ ጸሐይ መዘርፉን በመቃወም ለኢትዮጵያ እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሰላማዊ በሆነ መልክ ተቃውሟቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ባሰሙ ንጹሀን ዜጎች ላይ ወሮበላ ነፍሰ ገዳይ ሎሌዎቹን በአዲስ አበባ ከታማ በማሰማራት እልቂትን እንዲፈጽሙ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ በዚያ እልቂት የግድያ ጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን እና በዚያ እልቂት ቁስለኛ ለነበሩ ሌሎች ወገኖች በመቆም መናገር ጀመርኩ፡፡

ባለፉት 9 ዓመታት ውስጥ ሁልጊዜ ሰኞ ለእነዚህ ኢትዮጵያውያን ሰማዕቶች ጥብቅና በመቆም ጩኸቴን ማሰማት ቀጥዬ እገኛለሁ፡፡

ሆኖም ግን ሁልጊዜ በፕሮፌሰር መስፍን ጽሑፎች፣ በድረ ገጽ የሚለቀቁ ጽሑፎች እና በሚያሰሟቸወ ንግግሮች እመሰጣለሁ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ያንን የቅጥፍና ምሁር እና አስመሳይ ባህሪ ተላብሶ ይቀርብ የነበረውን መለስን ስለኢትዮጵያ የጠራ ታሪክ እና ፖለቲካ ሲያስተምሩ ስመለከት ደስ ይለኝ ነበር፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ለዘ-ህወሀት ታማኝ ሎሌዎች ጠንካራ ትችት ሲያቀርቡ እና ጥልቅ የሆነ ትንታኔ እና አመክንዮ እየሰጡ ሲያሳፍሯቸው እና አንገታቸውን ሲያስደፏቸው በቪዲዮ በምመለከትበት ጊዜ ታላቅ እርካታ ይሰማኛል፡፡

እውነታውን ፍርጥርጥ አድርጎ ለመናገር ፕሮፌሰር መስፍንን በሕዝብ ፊት አደባባይ ለመሞገት በማሰብ የሚቀርቡ የዘ-ህወሀት ታማኝ ሎሌዎችን ድፍረት ስመለከት አንዳንድ ጊዜ ይገርመኛል ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን አስደማሚ በሆነው የታሪክ እውነታዎችን በማስታወስ ልዩ እውቀታቸው እነዚያን የደናቁርት ስብስብ ድባቅ መተው እና በሕዝብ ፊት አሳፍረው በቅሌት ሲያሰናብቷቸው፣ በሰላው አንደበታቸው እና በማራኪ አመክንዮአዊ አቀራረባቸው ሲያሸማቅቋቸው ስሜትን የሚገዛ ትይንት መመልከት ማለት ነው፡፡

ምን ዓይነት አስገራሚ እይታ!

ባለፉት በርካታ አስርት ዓመታት ውስጥ ሲያቀርቧቸው ለነበሩት አስደማሚ የሆኑ ጽሁፎች እና ለሚሰጧቸው ትንታኔዎች በቂ እውቀት የለኝም ፡፡

ይኸ የእራሴ ስህተት ስለሆነ ወደፊት እንደማስተካክል ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ሆኖም ግን ከፕሮፌሰር መስፍን የመልክዓ ምድር/የጀኦግራፊ እና ወሰን ድንበሮች ምርምሮች እና ጥናቶች ጋር ተላምጃለሁ፡፡

ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያን አንጡራ ግዛት ለሱዳን እና ለሌሎች አሳልፎ የሰጠበትን ፕሮፌሰር መስፍን ለወደፊቱ ለዘ-ህወሀት መሞገቻ በቂ ማስረጃ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታዎችን ምርምሮች እና ጥናቶች የመስክ ስራዎች በኃላፊነት መርተዋል ወይም ደግሞ ተሳታፊ ሆነው አግለግለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት ለእራሳቸው የፖለቲካ ግብ እና የባንክ አካውንቶቻቸውን ለማድለብ በማሰብ የኢትዮጵያን ሕዝብ መሬት ለጎረቤቶቻቸው በመስጠት ተመችቶን ተቀምጠናል በማለት ተቀምጠዋል፡፡

ቀደም ሲል እንዳቀረብኩት ትችት ሁሉ የዘ-ህወሀት አመራሮች ሁሉንም የድንበር ስምምነቶች ሚስጥር አድርገው ይዘዋል፡፡

ሆኖም ግን በዚህ ትውልድ ወይም ደግሞ በቀጣዩ ትውልድ የኢትዮጵያ ልጆች ሕጋዊ በሆነ መልኩ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ የግዛት መሬት ለባለቤቷ ለኢትዮጵያ የሚያስመልሱበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ጊዜውን ጠብቆ ይመጣል፡፡

ወደፊት ምን ያህል መሬት እንደምናስመልስ ፕሮፌሰር መስፍን እና የስራ ጓዶቻቸው ለዘመናት በያዙት መጠነ ሰፊ የመረጃ መጠን የሚወሰን ይሆናል፡፡

ዘ-ህወሀት የፈለገውን ያህል መሬታችንን እየቆረጠ መሸጥ ይችላል፣ ሆኖም ግን የፍርድ ቀን በመጣ ዕለት እድሜ ለፕሮፌሰር መስፍን የምርምር እና ትንተና ተግባራት ይሁን እና እያንዳንዷን የተቀደሰችዋን ቅንጣት መሬት ሳትቀር አናስመለሳለን እየቆጠርን እንረከባለን፡፡

በሽያጭ፣ በዝውውር እና ሊዝ እየተባለ በሚጠራው ወይም ደግሞ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ዘ-ህወሀት ስለሚያድርገው ማንኛውም ዓይነት የመሬት ስምምነት ድርድር አንዳንድ ማስታዎሻዎችን ላቅርብ፡፡

ወያኔ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት ለባዕድ ሀገር አሳልፎ የሰጠበተ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ክሽፈቶች ሁሉ ከፍተኛው እና በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የማስቀምጠው ይሆናል፡፡

በእኔ አመለካከት ዘ-ህወሀትም እንደዚሁ እንዲህ የሚሉት የዊሊያም ኮውፐር የግጥም ስንኞች እንደሚያስገነዝቡን ሁሉ ጊዜውን ጠብቆ ወደ ማይቀረው ሞት ይሄዳል፡

“በረቀቀ መንገድ እግዚአብሔር ይሰራል፣

ታምራቱን ሁሉ በግልጽ ያሳየናል፣

ዕቅዱን በባህር ዘርግቶ ይነድፋል፣

ሞገድ ማዕበሉን ጸጥ አርጎ ይነዳል…”

የተጠናከረ የማዕበል ስብስብ ከፊታችን ተደቅኖ ይታያል፡፡ ሆኖም ግን በሙስና ተዘፍቆ ዓይኑ የታወረው እና በስልጣን ጥማት የሰከረው ዘ-ህወሀት ከፊት ለፊቱ እየመጣ ያለው ማዕበል ሊታየው አይችልም፡፡

ዘ-ህወሀት የአፍሪካ ባሮች ቀደም ሲል ወደ አሜሪካ በሚጋዙበት ወቀት የተዘመረውን እንዲህ የሚለውን የሙዚቃ የግጥም ስንኝ ምክር በአንክሮ መከታተል ይኖርበታል፡ “እግዚአብሔር ለኖህ የቀስተደመናን ምልክት ሰጠው፡፡ ከዚያ በኋላ ምንም ዓይነት ውኃ አልነበረም፡፡ በቀጣዩን እሳትን ጠብቅ!“

በዚህ የሀሳብ ፍንጠቃዬ ለትንታጉ ልሂቅ እና የሕዝብ ልጅ ለፕሮፌሰር መስፍን ክብር መስጠት እፈልጋለሁ፡፡

እርሳቸውን እንደ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ልሂቅ ጀግና አርበኝነታቸው ከፍተኛ የሆነ ክብር ልሰጣቸው እፈልጋለሁ፡፡

ኔልሰን ማንዴላ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “እንደ አፍሪካ አርበኝነቴ ሁልጊዜ እራሴን ከፊተኛው ረድፍ በማድረግ በጽናት እቆማለሁ፡፡“

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን ለሚወዷት ሀገራቸው በግንባር ቀደምትነት ከፊት የሚቆሙ ልሂቅ አርበኛ አድርጌ እቆጥራቸዋለሁ፡፡

ለምሁራዊ ስራቸው እና ለበርካታ አስርት ዓመታት ለሀገራቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ የሆነ አድናቆት እና ክብር አለኝ፡፡

ኢመርሰን በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “የምሁራን ቢሮ ዋናው ተግባሩ ዜጎችን ማበረታታት፣ ማነሳሳት እና ከሚታየው በርካታ ነገር ሁሉ መርጦ እውነታውን በማሳየት ለስኬታማ ውጤት አመራር መስጠት ነው፡፡ ልሂቅ ለነገሮች ጊዜ ወስዶ ጠንክሮ በመስራት የማይከበር እና ክፍያ የማይፈጸምበት ብርቱ ምልከታ አለው፡፡“

የምሁርነት የጊዜ ህይወት ቀላል አይደለም፡፡ ረዥም የዝግጅት ጊዜ እና ጥናትን ይጠይቃል፡፡ምሁር ሰይጣናዊነትን አስቀድሞ የሚገነዘበው በመሆኑ በአገዛዙ መከራ እና ስቃይ ይደርስበታል፡፡ እንደዚሁም ሰይጣናዊነትን እንዴት ማስወገድ እንዳለበት የእውቀት እጥረት ሊያጋጥመው ይችላል፡፡

እውነተኛ ምሁር የጥላቻ መንፈስ ከባቢ አየር በተንሰራፋበት ጊዜ ለነገሮች እልባት ለመስጠተ ከብዙሀኑ ሕዝብ ጎን በተለይም ከተማረው የህብረተሰብ ጋር በጽናት በመቆም ይታገላል፡፡

ምሁር ምንጊዜም የዘለፋ እና የውንጀላ ክስ ዒላማ ነው፡፡

ለዚህ ሁሉ ማዋረድ እና ዘለፋ የምሁሩ ማካካሻ ምንድን ነው?

ለሰው ልጅ ታላቅ የተባለውን ስራ በመስራት እርካታን እና ደስታን ማግኘት ነው፡፡ ከግል ጉዳይ እራሱን መዞ ያወጣው እራሱ ምሁሩ ነው እናም በሚያፈልቀው ሀሳብ እና በሚያከናውናቸው ህዝባዊ ስራዎች ኮርቶ እና ተደስቶ በህብረተሰቡ ዘንድ ይኖራል፡፡ ምሁር የዓለም ሕዝብ ዓይን ነው፡፡ ምሁር የዓለም ሕዝብ ልብ ነው፡፡ ወደ ኋላ የጀግንነት ስሜቶችን በመንከባከብ እና በህብረተሰቡ ውስጥ ግንኙነቱን በማጠናከር፣ የተከበሩ ሰዎችን የህይወት ታሪክ በመመዝገብ፣ የሙዚቃ ግጥሞችን በመድረስ የታሪክን መደምደሚያ በማዘጋጀት የታሪክ ጎማን ወደኋላ ለማሽከርከር ጥረት የሚያደርጉ ያልሰለጠኑ ኋላቀሮችን እና ጋጠወጥ ወሮበሎችን ያለምንም ማቅማማት በጽናት በመቆም ይታገላቸዋል፡፡

እንግዲህ የፕሮፌሰር መስፍን ምሁራዊ ተግባር እና የአደባባይ ህይወት ይህንን እንደሚመስል አምናለሁ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ስቃይ ደርሶባቸዋል፣ በፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶባቸው ያለምንም ጥፋታቸው በአምባገነኖች መጉላላት እና ውርደት እንዲደርስባቸው ተደርገዋል፡፡

እንግዲህ የእርሳቸው ሽልማት ምንድን ነው? ምናልባት ህዝባቸውና ባልደረቦቻቸው ፍቅር፣ አድናቆት እና ምስጋና?

የእርሳቸው እውነተኛው ሽልማታቸው የእርሳቸውን ሰው ሆኖ የመፈጠር ከፍተኛ የሆነ የነጻነት መብት መተግበር መቻላቸው ነው፡፡ አዕምሯቸው ያሰበውን የመናገር ነጻነታቸው ትክክለኛው ሽልማታቸው ነው፡፡

ለበርካታ አስርት ዓመታት ከእርሳቸው የግል ጉዳዮች ይልቅ ለኢትዮጵያውያን መብት፣ ዕድገት እና ልማት አበርትተው ሰርተዋል፣ በመስራት ላይም ይገኛሉ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን የኢትዮጵያ ዓይን እና ልብ ለመሆን በቅተዋል፡፡

ሀገሪቱን ወደ ኋላ በመጎተት ሰላሟን እና ልማቷን በማደናቀፍ ላይ ለሚገኙት ወሮበላ ያልሰለጠኑ የደናቁርት ስብስቦች ፊት ለፊት በመሞገት የህዝቡ የጀግንነት አስተሳሰቦች እንዲጠናከሩ፣ የተከበሩ ልማዶች እና ለህዝባቸው የሀገራቸው ታሪክ ትምህርት በህዝቡ ዘንድ እንዲታወቅ ለማድረግ የሰሩ እውነተኛ ቁንጮ ምሁር ናቸው፡፡

ያለምንም ፍርሀት የልባቸውን እና ያሰቡትን በአደባባይ አውጥተው መናገር እና የጨቋኞችን፣ የአምባገነኖችን፣ የወሮበሎችን፣ በስልጣን እርካብ ላይ ሆነው በህዝብ ላይ ወንጀል የሚፈጽሙትን ዕኩይ እና ድብቅ ሚስጥር በህዝብ ፊት በአደባባይ አውጥተው የሚያጋልጡ መንፈሰ ጠንካራ የአደባባይ ምሁር ናቸው፡፡

ፕሮፌሰሩ በግል ሀሳቦቻቸው እጅግ በጣም የመጠቁ እና መቸውንም ጊዜ ቢሆን በስልጣን ኮርቻ ላይ ላሉት ለጨቋኞች እና ለወሮበሎች እርሳቸው በሚያውቁት ቋንቋ ብቻ ማለትም እውነት በመናገር ብርክ ያስይዟቸዋል፣ በመጠቀው ሀሳቦቻቸውም ድባቅ ይመቷቸዋል፡፡

በአዳፍኔ ፕሮፌሰር መስፍን ከአምሳ ዓመት አካባቢ ጀምሮ ሲያቀርቡት የነበረውን ጥያቄ እኔ አሁን እንዲህ በማለት አቀርበዋለሁ፡

አንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፡

እ.ኤ.አ በ1950ዎቹ በዩኒቨርስቲው ውስጥ ውይይት ይካሄድ ነበር፡፡ ከውይይቱ በኋላ እንዲህ የሚል አንድ ጥያቄ አቀረብኩ፡ ኬንያ ጆሞ ኬንያታ አሏት፡፡ ታንዛኒያ ጁሊየስ ኔሬሬ አሏት…ኢትዮጵያ ለምንድን ነው ታላቅ ሰው የሌላት? አንድ ጮሌ አስደንጋጭ በሆነ መልኩ እኛም ጃንሆይ (ቀ.ኃ.ሥ) አሉን በማለት መለሰ፡፡ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁና ትክክል አለመሆኑን እንዲህ በማለት ተናገርሁ፡፡ ጃንሆይ በእድሜ ታላቅ ናቸው፡፡ እኔ እየጠየቅሁ ያለሁት በስራው ታላቅ የሆነ እና ከፍተኛ ስኬቶችን የተጎናጸፈ ኢትዮጵያዊ ለምን የለም ነው ያልኩት በማለት ጥያቄውን የበለጠ ግልጽ አደረግሁት፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያለኝ ጥያቄም ያው ጥያቄ ነው፡፡ እስከ አሁንም ድረስ ታላቅ ሰው የለንም፡፡

እኔ ደግሞ ይህንን አባባል ሙሉ በሙሉ እቃወማለሁ!

ሐቁ አይካድም አንድ ታላቅ ሰውማ አሉን፡፡

ስማቸውም መስፍን ወልደማርያም ይባላል፡፡ መምህር ናቸው፡፡ የሙያ እምቢተኛ ናቸው፡፡ እውነት ተናጋሪ ናቸው፡፡ ተቃዋሚ ናቸው፡፡ ላመኑበት ነገር ምንም ዓይነት ነገር የጥገና ለውጥ የማያደርጉ መንፈሰ ጠንካራ ሰው ናቸው፡፡ በተጫባጭ እውናዊ ነገሮች ላይ ብቻ የሚያምኑ ሰው ናቸው፡፡ የሕዝብ ቀስቃሽ ናቸው፡፡ አመጸኛ ልሂቅ ናቸው፡፡ የሀሳብ ሰው ናቸው፡፡ የሚጽፉ ሰው ናቸው፡፡ የሚያነሳሱ ሰው ናቸው፡፡ ህዝብን ለመልካም ነገር የሚቀሰቅሱ ሰው ናቸው፡፡

ጆርጅ ኦርዌል እንዲህ ብለው ነበር፣ “ዓለም አቀፋዊ ማጭበርበር በተንሰራፋበት ዓለም ውስጥ እውነትን መናገር አብዮታዊ ድርጊት ነው፡፡“

ደህና፣ ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እንዲህ የሚል አንድ ሌላ ማዕረግ እሰጣቸዋለሁ፡ “እውነት ተናጋሪ አብዮተኛ”!

በአዳፍኔ ጨለምተኛ መልዕክት ላይ ሀሳቤን እንደፈነጠቅሁ በርካታ ክሽፈቶችን ድል ያደረገው እና እንዲህ በሚሉት የአቤ ሊንኮልን ቃላት ምቾትን ተጎናጽፊያለሁ፡ “የእኔ ትልቁ ስጋት የአንተ መክሸፍ ያለመክሸፍ አይደለም፣ ሆኖም ግን ውድቀትህን ተቀብለሀል ወይ ከሚለው ላይ ነው፡፡“

እንደ ኢትዮጵያውያን ሁላችንም አስከፊ በሆነ መልኩ ወድቀናል፡፡ ከሽፈናል። መጥፎ አስተዳደር ተጭኖብናል፡፡ ለሀገር መሪነት ወሮበሎችን ተሸክመናል፡፡ ሕዝቦቻችንን መመገብ አልቻልንም፡፡ ሀገራችን ዓለም አቀፍ የረኃብ ማስታወቂያ የስዕል ሰሌዳ ሆና ቀጥላለች፡፡ እውነትን እንፈራለን፡፡ እርስ በእርሳችን እንፈራራለን፡፡ እራሳችንን እንፈራለን፡፡ ጥቂቶቻችን እራሳችንን በፈቃደኝነት ስደተኛ አድርገናል፡፡ እጅግ በርካቶቻችን ደግሞ እንድንሰደድ ተገድደናል፡፡

በቀላሉ ለማስቀመጥ ምስቅልቅል ባለ ሁኔታ ላይ እንገኛለን!

“አዳፍኔ” ሆነናል፡፡

በእኔ ትውልድ እና ከእኔ በፊት በነበረው ትውልድ ላይ እምነት የለኝም ብዬ ስናገር ሀፍረት ይሰማኛል፡፡ ስለሆነም አሁን መናገር አልችልም፣ ሆኖም ግን ሰላሜን ለብዙ ጊዜ ይዠ ማቆየት አልችልም፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን በአሁኑ ጊዜ ላለው ኢትዮጵያዊ ወጣት እና ለመጭው ትውልድ ሶስት ቀላል ጥያቄዎችን መዝግበው አቅርበዋል፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) የወላጆቻችሁን ትውልድ መክሸፍ በጸጋ ተቀብላችኋልን?

2ኛ) የአያቶቻችሁን እና የቅድመ አያቶቻችሁን ትውልድ መክሸፍ በጸጋ ተቀብላችኋልን?

3ኛ) የእራሳችሁን ትውልድ መክሸፍ በጸጋ ተቀብላችኋን?

እነዚህ ከላይ በዝርዝር የቀረቡት ጥያቄዎች በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በአዳፍኔ መጽሐፍ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የሚንቀሳቀሱ አንገብጋቢ ጉዳዮች ናቸው፡፡

በአዳፍኔ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሊማሩት ይገባል የምንለው አንድ ታላቅ ጉዳይ አለ ብለን የምናስብ ከሆነ ከብዙ ዓመታት በፊት ሸክስፒር የተናገሩት እንዲህ የሚለው አባባል ነው፡ “የወደፊት ዕጣ ፈንታችን በእኛው በእራሳችን እንጅ በሌላ በማንም የሚወሰን አይደለም፡፡“

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እንደ ቀደምቶቻቸው ሁሉ የጀግና ህይወትን የሚኖሩ ምሁር በመሆናቸው ለእንደዚህ ያሉ ጥያቄዎች ምንም የሚየስጭንቃቸው ጉዳይ አይደለም፡፡ እርሳቸው በስልጣን ላይ ያሉትን ወሮበላ የደናቁርት ስብስብ ብቻ ሳይሆን የእነርሱን በውጭ የሚገኙትንም አጭበርባሪ እና በጥቅም ስሌት ብቻ የሚጓዙትን ንጉሳዊ አለቆቻቸውን ጭምር የሚተገሏቸው ብዕሮቻቸውን፣ እርሳሶቻቸውን፣ ወረቀቶቻቸውን እና አስደማሚ የሆነ ከታቢ አዕምሯቸውን በመጠቀም ነው፡፡

ስለሆነም ለአይበገሬው ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እንዲህ የሚሉትን እና በዊሊያም ኤርነስት ሄንሌይን የተቋጠሩትን ግጥም ስንኞች ላቀርብላቸው ወደድኩ፡

ከምንጊዜም በላይ በሩ ቢጣመም
የተንሸዋረረው ፍትህ ቢጓደልም፣
በኔ ላይ ደጋግሞ ቅጣት ቢቆልልም፣
ከዓላማዬ ፍንክች በፍጹም አልልም፡፡

የእራሴ እጣፈንታ ወሳኙ እራሴ ነኝ፣
ማንም አምባገነን የማይጨፍርብኝ፣
በዲያብሎስ መንገድ የማያስገድደኝ
የነብሴ መርከቡ ካፕቴኑ እራሴ ነኝ፡፡

ካፒቴን መስፍን ለእርስዎ የህይወት እና የፍቅር ምንጭ ለሆነችው ለአንዷ ኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ ለሰሩት ስራ፣ አሁን በመስራት ላይ ላሉት እና ለወደፊቱ ለመስራት ላቀዱት ስራ ሁሉ እግዚአብሔር የተመኙትን እንዲያሳካልዎት እና ስኬታማ እንዲሆኑ ምኞቴን እየገለጽኩ እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ፡፡

በሀገርዎ እውነተኛ ዴሞክደራሲ እና ሰላም ሰፍኖ፣ እንዲሁም በሸፍጠኞች የቁጥር የቁማር ጨዋታ ሳይሆን እውነተኛ የምጣኔ ሀብት ዕድገት እና ልማት ተመዝግቦ፣ የሚታገሉለት ሕዝብዎ ከችጋር እና በየጊዜው በረሃብ ከመሰቃዬት ተላቆ ለማየት እንዲያበቃዎት እመኛለሁ፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ጥቅምት 23 ቀን 2008 ዓ.ም

The post በፕሮፌሰር መስፍን “አዳፍኔ“ መጽሐፍ ላይ አንዳንድ የሀሳብ ፍንጣቂዎች፡ ኢትዮጵያውያንን ከእራሳቸው መጠበቅ? appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰሞኑ የሕወሓት/ኢሕአዴግ ‘ከብስባሴዬ ልሻሻል ነው’ዲስኩር “የድመት ፈገግታ አይጥን አሳስቃ ለመብላት ነው”

$
0
0

hailemariam Desalegn
ከአሰገደ ገብረሥላሴ

ሰሞኑን የህወሐት/ኢሕአዴግ ስራ አሥፈጻሚ ኮሚቴ የሞት ዋዜማ ኑዛዜ ሢያሠማን ሰንብቷል ::
ከኑዛዜዎቹ ጥቂቶቹ በሙስና ተበላሽተናል; እቺ ሀገራ ችን የምትመራው በደላዮች ነው:: የደላሎዮችና የመንግስት መዋቅሮች ከቤተመንግሥት እስከቀበሌ ተዘርግተዋል:: ህዝባችን ጠልቶናል አማርሮዋል; ባለሀብቶች ልናሠራቸው ኣልቻልንም; ከተሞች የብልሹው አስተዳደር ማእከላት ሆነዋል; ለመንግት የፕሮጀክት ማሥፈጸምያ የተመደበ ባጀት በደላሎችና የመንግሥት ባለስልጣኖች ተወረዋል… ወ ዘ ተ ብለው ሲነግሩን ሠንብተዋል ::

የሚገርመው ነገር ግን የህዝብ መሬትና ቤት መውረስና ማፍረሥ ማውደም በሚመለከት በአድዋ የአንድ ኢንቨስተር መሬትና ብር መዘረፉ ብቻ ሥህተት እንደፈጸሙ ሲያምኑ በትግራይ ክልል ከ200 ሽህ ቤቶች አፍርሰውና ዘርፈው በጎንደር በጎጃም በወሎ በኦሮሞ በአዲስ አበባና አካባቢዋ የፈረሱ ቤቶች የህዝብ መሬት ቀምተው የቸበቸቡ በተጨማሪ በባለሥልጣኖችና በኣጃቢዎቻቸው የተዘረፉ ምርጥ መሬት ዘርፈው ምንጩ ባልታወቀ ገንዘብ ኣድርገው ከኣቅማቸው በላይ ህንጻዎች ላሠሩ ፎጹም ደፍረው ሊያነሱ ኣልደፈሩም ::

በሌላ በኩል ስለ ዲሞክራሢና ሠብኣዊ መብቶች ጥሠትና አፈና ሥለ የፕሬሥ ነጻነት ሥለ የብዙሀን ፓርቲ ነጻነት ስለ ፖለቲካ መሪዎችና ኣባሎቻቸው የጋዜጠኞች በግፍ መታሠር መገረፍ መሠቃየት; በግፍ መገደል; ሥለ በነጻና በህጋዊ መንገድ የተደራጁ ፖለቲከኞች የሥራ እድልና ሁሉም ኣቀፍ መብቶች ማፈን በሚመለከት ለማንሣት ኣልቻሉም ::

ለሁም ህዝብ አግራሞት የፈጠረው ግን የህወሐት/ኢሕአዴግ ሀቀኛ ኣማራጭ ይዘው በፓርቲ ተደራጅተው ለፓርላማ ሊቀርቡ ዋዜማ ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሥለማፍረሳቸው በውድድር ለቀረቡም ድምጻቸው በመቀማት 100 % ለራሣቸው በማድረግ ፓርላማው እንቅልፋምና ሕይወት የሌለው የማድረጋቸውን ጉዳቸውን ለማጋለጥ ኣልደፈሩም ::

በእኔ እምነት እነዚህ ጨካኝ ፍጡራን የነገሩን ኣሥመሣይ ንግራቸው የድመት ፈገግታ ኣይጥን አሳስታ ለመብላት ዓይነት አጭበርባሪ አባባል አድርጌ ነው የምረዳው ::
ለመሆኑ እነዚህ መሪዎች ያሁሉ የጭንቀት ዲስኩራ ቸው በዚህቺ ሀገር ከላይ የተጠቀሱ ዝባዝኬ ችግሮች ለመጠራረግ ቆርጠው ተነሥተው ከሆነ በአንገታቸው ገመድ ኣስግብተው እንደመስቀል ይቆጠራል :: እዚህ ላይ ግን አያደርጉትም እንደዚህ አይነት የማታለያ መንገድ ከረጅም ጊዜ ጀምረው ይዘውት የመጡ ከህዝብ ሲነጠሉ ሲከተሉት የነበረ የማረጋጋት ሥልት ነው ::

“የደላላዎች ኔት ወርክ ከታች መዋቅር እስከ ቤተመንግስት ገብቷል” – ሃይለማርያም ደሣለኝ

ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማርያም “የሃገራችን መሪዎችና መዋቅራችን እያንዳንዳቸው የየራሣቸው የድለላና የምዝበራ ኔትወርክ አላቸው; የድለላና የሙስና ኔትወርክ እስከ ቤተመንግሥት ሰርገው ገብተዋል” ብለዋል ::
በተለይ በአቶ ደብረጽዮንና በኣባይ ጸሀየ ለተሠነዘረው አሣፋሪ አስተያየት ባልተለመደ ድፍረት በማሣየት; የበላይነትን በማሣየት የበላይነትን ማረጋገጣቸው ለብዙ ዜጎች አግራሞትን ፈጥሯል ::
በሌላ በኩል ሁሉም የህወሐት/ኢሕአዴግ ሥራ ኣሥፈጻሚ ኮሚቴ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላትና ጋዜጦኞች በኢህአዴግ ባለሥልጣናትና ደላሎቻቸው ዘር ማንዘራቸው የፈጸሙት ወንጀልና ግፍ ሕዝብ እንዲያውቃቸው በማጋለጣቸው አሸባሪዎች; ነውጠኞች; ጠባቦች; ትምክህቶኞች; ዘረኞች እየተባሉ በግልጽና ህቡእ እስር ቤት; ወህኒ ቤት በስቃይ የተወረወሩበት; ቤተሰቦቻቸው የተሠቃዩበት በሙሉ በነዚህ የዘመናችን ግራዝያኒ መሰል ፉጡራን እንደወንጀል ሳይሆን እንደ ተራ ንግግር ሲደሠኩሩበት ታዩ::

እኔ የሚገርመኝ እነዚህ ፍጡራን የ24 ኣመት የግፍ ዘመን አገዛዛቸውና ምዝበራቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎችና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባለሀብቶች; ጦማርያን; ጋዜጦኞች እንደዚሁም ዲሞክራት አገሮች የዓለም ባንክና አይኤምኤፍ የሚለጉሱሏቸው ምክርና አሥተያየትን እያሥፈነጠሩ ቆይተው ኣሁን በ 11 ኛው ሰዓት ጉዳቸውን ማጋለጣቸው በእውነት ችግራቸው ጨክነው ለመፍታት ወይ ለመቅረፍ ነው? ወይስ ድራማ እየሠሩ ናቸው?

በእኔ እምነት ይሀ ጉዳይ ድራማ እየተሠራ ነው ያለው ነው የምለው :: ምክንያቱም እነዚህ ሰውች ከከፍተኛው የኢህአዴግ አመራር እስከ የጎጥ መዋቅራቸውና በስተጀርባቸው ያሉ ደላሎች ተጠቃሚ ሙሰኞች የበሰበሱና የላሸቁ በመሆናቸው ለዚህ ሁሉ የበሠበሠውን ጋንግሪን እንቆርጣለን ብለው ለማጥራት ከሞከሩ ህወሓት ኢህአዴግ ከነንግዱ ይጠራረጋል :: በመሆኑም አይጨኩኑም – ይህም የሚነግሩን ያሉ ሁሉ ድራማ መሆኑን ያረጋግጣል :: ምክንያቱም በኣሁኑ ጊዜ ሁሉም የህብረተ ሰብ ክፍል ሥለጠላቸወና ሥለናቃቸው የህዝቡን ሥሜት ለማብረድ የሚሠሩት ያሉት ድራማ ነው እንጅ አንዳች ለውጥ አያመጡም:: ከላይ እንደገለጽኩት እንደገለጥኩት የድመቷን ፈገግታ አይጧን አለሣልሶ ወይ አታሎ ለመብላት ይሠራ ያለው ድራማ ነው::

ሥለዚህ የኢትዮጱያ ህዝብ በሙሉ! እነዚህ ፍጡራን እያሉን ያለው ሁሉ ውሸት ነው:: ቅንጣትም ታህል በተግባር አትታይም :: የምናልባት ለጠላቸው ህዝብ ለማሥመሠል ጥቂት ወንድሞቻቸው ይገነድሱ ይሆናሉ::

የሀይለማርያም ደሣለኝ መድፈርም ፋይዳ የለውም:: ራሣቸው የሙስናና የደላሎቸ መዋቅር ኔት ወርክ ከቀበ ሌ እስከ ቤተመንግሥ ገብተዋል እያሉን ታድያ ማን መቺ? ማን ተመቺ ሊሆን ነው? ይሉቅንስ የኢትየጱያ ህዝብ ከሠላማዊ ትግልህ አትቦዝን : :ኢህአደግ እንደሆነ እንደዚህ ድራማ መሥራት ከረጅም ጊዜ ይዞት የመጣ የተካነ የሥራ ልምድ ነው ::

The post የሰሞኑ የሕወሓት/ኢሕአዴግ ‘ከብስባሴዬ ልሻሻል ነው’ ዲስኩር “የድመት ፈገግታ አይጥን አሳስቃ ለመብላት ነው” appeared first on Zehabesha Amharic.

መንግስት በመምህር ግርማ ላይ ከግድያ ወንጀል ጋር በተያየዘ ተጨማሪ ክስ ሊመሠርት መሆኑ ተሰማ

$
0
0

girma wendimu
(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው አጥማዊ መምህር ግርማ ወንድሙ በማታለል ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ወህኒ ከወረዱ በኋላ አቃቤ ሕግ የጠየቀባቸው 7 ቀን ዛሬ በማለቁ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ በዘ-ሐበሻ መዘገቡ አይዘነጋም::

ከአዲስ አበባ የመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ፖሊስ በማታለል ወንጀል ያቀረበባቸው ክስ ዋስትና ሊያስፈቅድ የሚችል በመሆኑ ከግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ክስ ለመመስረት አሁንም የጊዜ ቀጥሮ ሊጠይቅባቸው እንደሚችል ነው::

ፖሊስ የመምህር ግርማ ቤትን ከታሰሩ በኋላ እርሳቸው በሌሉበት መበርበሩ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ብርበራ አሁን ሊመሰረትባቸው ከታቀደው የነብስ ግድያ ጋር ከተያያዘ ክስ ጋር ተያያዥነት ይኑረው አይኑረው የታወቀ ነገር የለም ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል::

በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ በታዋቂው አጥማቂ መምህር ግርማ ወንድሙ ላይ የመታሰራቸው ዜና ሲነበብ በርካታ ተከታዮቻቸው መታሰራቸው ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሴራ ነው በሚል ሲቃወሙ ሰንብተዋል::

ከፍርድ ቤት ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን እናቀርባለን::

The post መንግስት በመምህር ግርማ ላይ ከግድያ ወንጀል ጋር በተያየዘ ተጨማሪ ክስ ሊመሠርት መሆኑ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ በቡራዩ ከተማ የፊታችን እሁድ ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ

$
0
0

 

(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የኢሕ አዴግ መንግስት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተግባራዊ አደርጋለሁ በሚል እንቅስቃሴውን መቀጠሉን ተከትሎ ከሕዝብ ጋር ለመወያየት ሕዝባዊ ሰብሰባ የፊታችን እሁድ ጠራ::

ኦፌኮን ለዘ-ሐበሻ በላከው በራሪ ወረቀት (ፍላየር) ላይ እንዳስታወቀው ይህ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እና በሌሎች ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ለመወያየት የተጠራው ስብሰባ በቡራዩ ከተማ ስታዲየም የፊታችን እሁድ የሚደረገው ከጠዋቱ ከ9 ሰዓት (በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከጠዋቱ 3 ሰዓት) ጀምሮ ይሆናል:: በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይም የድርጅቱ አመራሮች ዶ/ር መረራ ጉዲና; አቶ በቀለ ገርባና አቶ በቀለ ነጊያ እንደሚገኙ ኦፌኮን አስታውቋል::

በራሪው የጥሪ ወረቀት የሚከተለው ነው::

OFC

The post ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ በቡራዩ ከተማ የፊታችን እሁድ ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ appeared first on Zehabesha Amharic.


ሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ አወጣ –“ከነካባው የተቀበረውን የፍትህ ሥርዓት ነፃ ለማውጣት ትግላችን አጠናክረን እንቀጥላለን!”

$
0
0

(ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)

ኢትዮጵያ ውስጥ ከህገ መንግስቱ ጀምሮ አዋጅና በሌሎችም የዜጎችን መብት የሚደነግጉ በርካታ መሰረቶች ቢኖሩም ለይስሙላ ህጋዊ ሥርዓት እንዳለ ከማስመሰልም አልፎ ለአገዛዙ ማጥቂያና መግዢያ ከመሆን ባለፈ የዜጎችን መብት እያስከበሩ አይደለም፡፡ ባለፉት 6 ወራት እንኳን ህግ እንደተቀበረች፣ በዚሁ አገዛዙ ውስጥ ተፅዕኖ ያለው የፍርድ ቤት አልፎ አልፎ የሚወስነው ውሳኔ በፖሊስ ቀጭን ትዕዛዝ ሲታጠፍ ታዝበናል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱትን ህገወጥ ተግባሮች በአንክሮ በመከታተል በየጊዜው ጩኸቱን ከማሰማቱም ባሻገር አባላቱም ጭምር የዚህ ህገ ወጥ ተግባር ተጠቂዎች በመሆናቸው በፍርድ ቤት በአጠቃላይ በህግ ላይ እየተደረገ ያለውን ጉዳይ ቀዳሚ ምስክር ነው፡፡

semayawi Party

የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ የሺዋስ አሰፋና ከእሱ ጋር በአንድ መዝገብ የተከሰሱ ፖለቲከኞችና ሌሎች ዜጎች ያለ ምንም መረጃ ቤታቸው ተበርብሮ ታስረው በማዕከላዊ፣ በቂሊንጦና በኋላም በቃሊቲ እስር ቤቶች ከፍተኛ ሰብአዊ መብት ጥሰት ደርሶባቸዋል፡፡ እነ የሺዋስ በእየ እስር ቤት የሚደርስባቸውን በደል ለፍርድ ቤቱ ቢያመለክቱም ሰሚ ከማጣትም ባሻገር ‹‹ችሎት ደፈራችሁ›› ተብለው ለተጨማሪ ቅጣት ተዳርገዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ያለ ምንም መረጃ የታሰሩትን ነፃ ናቸው ቢልም በካድሬ ትዕዛዝ የማረሚያ ቤቱ ፖሊስ ከእስር ቤት እንዳይወጡ በማገዱ፣ ይግባኝ ቢጠየቅ እንኳ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው መከታተል እየቻሉ በአስከፊው እስር ቤት እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡

 

በተጨማሪም መንግስት ራሱ በጠራው ሰልፍ ሰበብ ባልተገኙበት፣ የተገኙትንም በፈጠራ ክስ እየለቀመ ያሰራቸው የፓርቲያችን አባላትና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ከ6 ወር በታች በማያሳስር ክስ እስከ አራት አመት ተወስኖባቸው፣ አብዛኛዎቹም አሁንም ድረስ ምንም አይነት ፍትህ ሳያገኙ በእስር ቤት እየተንገላቱ ይገኛሉ፡፡ በሰልፉ ሰበብ ከታሰሩት መካከል አባላችን ናትናኤል ያለምዘውድ 3 አመት ከ3 ወር ሲፈረድበት፣ ብሌን መስፍን፣ ማቲያስ መኩሪያ፣ ተዋቸው ዳምጤ ከ6 ወር በታች በሚያሳስር የፈጠራ ክስ ተከሰው አሁንም ድረስ ፍትህ ሳያገኙ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ እነ ብሌን በተደጋጋሚ በመከላከያ መረጃነት የሚያገለግላቸውንና አቃቤ ህግም አለኝ ያለውን የቪዲዮ ማስረጃ እንዲቀርብላቸው ቢጠይቁም ሊቀርብላቸው አልቻለም፡፡ ይባስ ብሎ ማረሚያ ቤቱ ‹‹መጓጓዧ መኪና ስለሌለን ነው›› በሚል ለምክንያትነት እንኳ መቅረብ በማይገባው ሰበብ በቀጠሯቸው እንዳይቀርቡ በማድረግ ለተጨማሪ ጊዜያት በእስር ላይ እንዲቆዩ እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ አቶ አለነ ማህፀንቱ አንዱ ፍርድ ቤት በዋስ ሲለቀው በደህንነቶች እየተያዘ አሁንም ድረስ በእስር ላይ ይገኛል፡፡ ሌሎችም የመኢአድና የአንድነት አባላት የነበሩ በተመሳሳይ የፍርድ ሂደታቸው ሆን ተብሎ እንዲጓተት እየተደረገ ይገኛል፡፡

 

አገዛዙ ሰማያዊን ለማዳከም በተለያዩ አካባቢዎች እየታደኑ የሚታሰሩት የፓርቲ አመራሮቻችንም በተመሳሳይ ሁኔታ ህግ ተነፍጓቸው በእስር ቤት ይገኛሉ፡፡ ባህርዳር ላይ ታስረው የሚገኙ የፓርቲያችን 7 አመራሮች የ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ቢወስንም እንደተለመደው ካድሬዎች የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሽረው በእስር ቤት እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡ ሽዋሮቢትና ጎንደር ላይም በርካታ የፓርቲያችን አባላትና አመራሮች ለወራት የታሰሩበት ሳይታወቅ ከቆዩ በኋላ ወደ ማዕከላዊ ተዛውረው ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው ተደርገዋል፡፡

 

ይህ ፓርቲውን የማዳከም የአገዛዙ ህገ ወጥ እርምጃ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ከሳምንት በፊት በአርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አደራጆችን፣ አባላትንና ቤተሰቦቻቸውን በሀሰተኛ ክስ እስከማሰር ደርሰዋል፡፡ ከታሳሪዎች መካከል የጋሞ ጎፋ ዞን አስተባባሪ የሆነው አቶ ሉሉ መሰለና ቤተሰቦቹ ከሌሊቱ 8 ሰዓት ቤታቸው ተበርብሮ ሲታሰሩ፣ በእስር ላይ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ አስተባባሪ አቶ በፍቃዱ አበበ የ65 አመት አዛውንት እናቱ እና እህቱም ታስረው፡፡ አብዛኛዎቹ የዜጎች ሰብአዊ መብት ወደሚገፈፍበትና ጭካኔ ወደሚፈፀምበት ማዕከላዊ እስር ቤት ተዛውረዋል፡፡

 

የፍትህ ስርዓቱ ለአገዛዙ መግዢያ፣ ፍርድ ቤትም በተራ ካድሬ የሚታዘዝ በመሆኑም ከመቼውም ጊዜ በላይ ህግ ከእነ ካባዋ ተቀብራለች፡፡ ለይስሙላ የተቀመጠው ህግ እስረኞች በቤተሰቦቻቸው፣ በህግ አማካሪዎቻቸው፣ በእምነት አባቶቻቸውና በሌሎችም መጠየቅ እንዳለባቸው ዓለም አቀፍ የሆኑትን የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ጠቃቅሶ ቢያስቀምጥም በእውኑ ግን እነ እስክንድር ነጋ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ ተመስገን ደሳለኝ እና አሁንም በእስር ላይ የሚገኙት በርካታ አባላቶቻችንና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዳይጠየቁ ተከልክለዋል፡፡ ምግብ እንዳይገባላቸው ይደረጋል፡፡ እስር ቤቱ የሚያደርስባቸውን በደል ለፍርድ ቤት በሚያመለክቱበት ጊዜው ጨለማ ቤት ውስጥ እየታሰሩና እየተደበደቡ ነው፡፡

 

የፓርቲያችን አባላትና ሌሎች ዜጎች በተለያዩ ጊዜያት ያለ መረጃ ታስረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንደተያዘ አገዛዙና በስሩ የሚገኙት ሚዲያዎች ከፍርድ ቤቱ በፊት አጥፊዎች ተብለው ተፈርዶባቸዋል፡፡ ያለ መረጃ በመታሰራቸውና በመከሰሳቸው ይኼው ካድሬ የሚያዘው ፍርድ ቤት ነፃ ሲላቸውም ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ እስር ቤት ውስጥ እያከረማቸው ይገኛል፡፡ አገዛዙ የሚደርስበትን ጫና በህግ ሥም ለማቃለልና ህግን ለመግዢያነት እንደሚጠቀምም ያለ ምንም መረጃ ታስረው መረጃ ስላልተገኘባቸው ከበርካታ ስቃይ በኋላ የተለቀቁትን ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ለአብነት ከአንድ አመት ስድስት ወር በኋላ በስቃይ እስር ቤት የቆዩት የዞን ዘጠኝ አባላት እና አሁንም በፖሊስ ትዕዛዝ እስር ቤት እንዲቆዩ የተደረጉትን እነ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ በታፈነው ፍርድ ቤት እንኳ ነፃ መባላቸው ለፀረ ሽብር ህጉና ሌሎች የመግዢያ ህጎችን ያጋለጠና ፍትህ እንደተቀበረች በግልፅ አሳይቷል፡፡

 

በአጠቃላይ ዜጎችን ያለ መረጃ አፍኖ ማሰር፣ በቀጠሯቸው አለማቅረብ፣ እንዳይጠየቁ እና ምግብና ሌሎች ቁሳቁሶች እንዳይገቡላቸው መከልከል፣ በፍርድ ቤት ነፃ የተባሉ ይግባኝ ቢጠየቅባቸው እንኳ ከእስር ቤት ውጭ ሆነው መከራከር እየተገባቸው ከእስር እንዳይለቀቁ ማድረግና ሌሎችም በህገ መንግስቱና በአዋጆች አገዛዙ የደነገጋቸውን ሳይቀር መጣሱ በኢትዮጵያ ህግ ለፖለቲካው መሳሪያ እንጅ የበላይነት እንደሌለ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው፡፡ አንድ ሀገር እንደ ሀገር ለመቀጠል፣ ዜጎችም ሀገር አለን ብለው ለመኖር ህግ ትልቅ ነገር እንደመሆኑ አገዛዙ ፍትህ ሥርዓቱን ለራሱ በሚመቸውና በሚጠቅመው መንገድ እየዘወረ ኢትዮጵያንና ዜጎቿን ለባሰ አደጋና ስቃይ እየዳረገ እንደሆነ ተገንዝበናል፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ ህጋዊ ሥርዓት እንዲመሰረትና የህግ የበላይነት እንዲከበር ሰማያዊ ፓርቲ ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ይህን ትግላችንን ከዳር ለማድረስ የሚመለከታቸው የፖለቲካ ኃይሎች፣ የኢትዮጵያ ህዝብና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ጥቅምት 24/2008 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

The post ሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ አወጣ – “ከነካባው የተቀበረውን የፍትህ ሥርዓት ነፃ ለማውጣት ትግላችን አጠናክረን እንቀጥላለን!” appeared first on Zehabesha Amharic.

ቤተክህነት በታሰሩት መምህር ግርማ ላይ ተጨማሪ ክስ ደረበች * ፖሊስ ቤታቸው የተገኘውን 8 ሲምካርዶች እያጣራሁ ነው አለ

$
0
0

Memeher Girma

(ዘ-ሐበሻ) ፖሊስ በማታለል ወንጀል ጠጥርሬ አስሬያቸዋለሁ ያላቸው መምህር ግርማ ላይ ተጨማሪ ክሶች እየተደራረቡ ይገኛሉ:: ፖሊስ ከሰው ሕይወት መጥፋት ጋር በተያያዘ ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ክስ ለመመሥረት እየተዘጋጀ እንደሆነ በተነገረበት በዚህ ወቅት ቤተክህነት ዛሬ ተጨማሪ ክስ ደርባባቸዋለች::

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት መምህር ግርማ ከዚህ ቀደም ዘ-ሐበሻ እንደዘገበችው ተጨማሪ 14 ቀናት የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግን 5 ቀን ብቻ ፈቅዷል:: ፖሊስ 14 ቀን የጠየቀበትን ምክንያት ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎች አሉ፤ ከቤት ሽያጭ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪው ከሚኖሩበት ወረዳ የሰነድ ማስረጃ አልቀረበልኝም፤ ቤታቸው ላይ በተደረገው ብርበራ ስምንት ሲም ካርዶች የተገኙ በመሆኑ ሲም ካርዶቹ በማን ስም የወጡ ናቸው? እና በስልኩ ውስጥ የሚገኙ መረጃዎችን ኢትዮ ቴሌኮም አጥርቶ እንዲልክልን ደብዳቤ ጽፈን ውጤቱን እየተጠባበቅን ነው የሚሉት ይገኙበታል።

ሌላው እና ዛሬ በፍርድ ቤት የተሰማው ክስ ቤተክህነት ያቀረበችው ክስ ነው:: በዚህም መሠረት መምህር ግርማ ወንድሙ በሐሰተኛ ሰነድ ቤተክህነት እንደፈቀደችላቸው በማስመሰል ቤተክርስቲያኒቱ ስም በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር ሲያስተምሩና ሲያጠምቁ ቆይተዋል የሚል ክስ ነው:: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለመምህር ግርማ ወንድሙ የተፃፉ ያላቸውን ባለ ሰባት ቅፅ ደብዳቤዎችን ጠቅላይ ቤተክህነት ለፖሊስ እንደማስረጃ ልኳል:: ፖሊስ ይህንን ምርመራ ለማከናወን 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ቢጠይቅም በዚህኛው ክስ 7 ቀን ብቻ ተፈቅዶለታል::

በ እስር ላይ የሚገኙት ተጠርጣሪው መምህር ግርማ ወንድሙ በበኩላቸው ደቡብ ወሎን ጨምሮ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ቤተክህነት ደብዳቤ እየፃፈልኝ ነው ሳገለግል የሰነበትኩት የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል:: ጠበቆቻቸውም እሳቸው በቋሚነት በሚያገለግሉባቸው የረር ስላሴ እና ጀሞ ሚካኤል እንኳን ህገ ወጥ ናቸው የሚል በቤተክህነት የተላከ አንዳችም ደብዳቤ ያለመኖሩን እንዲሁም መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት ወንጀል ስላልሆነ ፍርድ ቤቱ የተጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ አቤቱታ ውድቅ አድርጎ ደንበኛችን የዋስትና መብታቸው ይከበርላቸው ሲል ጠይቋል። ፖሊስም መምህር ግርማ የተከሰሱት በሃሰተኛ ሰነድ መገልገል ከፍተኛ ወንጀል በመሆኑ ዋስትና እንዳይፈቅድ ተከራክሯል::

ፍርድ ቤቱ ፖሊስ አቶ ግርማ ቤት ስበረብር አገኘኋቸው ያላቸውን 8ሲምካርዶች ለመመርመርና ከኢትዮ ቴሌኮም መረጃ ለማግኘት 14 ቀን ይሰጠኝ ላለው ጥያቄ የ5 ቀን ብቻ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል::

በዚህም መሠረት መምህር ግርማ በመጀመሪያውና አሁን የተጨመረው ክስ ጉዳይ ጥቅምት 30 እና ህዳር 3 ቀን 2008 እንዲታይ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዘ-ሐበሻ ምንጮች መረዳት እንደተቻለው መምህር ግርማን አስሮ ለረጅም ጊዜ ለማቆየት ተጠርጥረው የታሰሩበትን ጉዳይ ከሰው ሕይወት መጥፋት ጋር ለማያያዝ ፖሊስ ምስክሮችን እያፈላለገ ይገኛል::

The post ቤተክህነት በታሰሩት መምህር ግርማ ላይ ተጨማሪ ክስ ደረበች * ፖሊስ ቤታቸው የተገኘውን 8 ሲምካርዶች እያጣራሁ ነው አለ appeared first on Zehabesha Amharic.

በርሃብ የተጠቁት ዜጎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው • መንግስት በርሃብ ለተጠቁት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ አይደለም

$
0
0

rehab 7

መንግስት በርሃብ ለተጠቁት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ታወቀ

 

• ‹‹ሰው በርሃብ እያለቀ ነው››

• ‹‹የሚላስ የሚቀመስ የለም፡፡ ቤተሰባችን ፈርሷል››

• ‹‹እርዳታ ቢሰጥማ ከዚህ ድረስ አንመጣም ነበር፡፡››

መንግስት በርሃብ ለተጎዱት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ቀያቸውን ለቀው አዲስ አበባ የገቡት የርሃቡ ሰለባዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ከወሎ የተለያዩ አካባቢዎች በርሃብ የተጠቁ ዜጎች ህይወታቸውን ለማትረፍ ወሎ ውስጥ ከሚገኙት ከተሞች አልፈው ወደ ጎጃም፣ ጎንደርን እንዲሁም አዲስ አበባ እየተሰደዱ ሲሆን አዲስ አበባ በርካታ ተጎጅዎች ህፃናትን አዝለው እየለመኑ ይገኛሉ፡፡ የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ካነጋገራቸው መካከል ሁሉም መንግስት ለርሃቡ ተጎጅዎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸውና ጎረቤቶቻቸውም እንደነሱ ቀያቸውን ጥለው ወደ መተማ፣ ሁመራ፣ ባህርዳር፣ ደሴ፣ እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ መሰደዳቸውን በሀዘን ገልፀዋል፡፡

rehab3

ወሎ ውስጥ ጮሬ ሶዶማ ከተባለ ቦታ ተነስታ እንደመጣች፣ አዲስ አበባ ከገባች ሶስት ሳምንት እንደሆናት የገለፀችውና ሁለት ህፃናትን ይዛ ስትለምን ያገኘናት፤ በግምት በ30ዎቹ መጨረሻ ዕድሜ የምትገኝ እናት ‹‹የመጣነው የሚላስ የሚቀመስ ስለሌለ ነው፡፡ ከብቶቻችን አልቀዋል፡፡ አዝመራ የሚባል የለም፡፡ ሰው በርሃብ እያለቀ ነው፡፡ እኛ ሴቶቹ ወደ ከተማው ስንመጣ ወንዶቹ ደግሞ ወደ ሁመራና መተማ ሄደዋል፡፡ እኛም ከዚህ የመጣነው ጉልበት ስላለን ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ደካሞች በዛው አካባቢ ቀርተዋል፡፡›› ስትል በሀዘን ገልፃልናለች፡፡ መንግስት እርዳታ አይሰጥም ወይ ብለን ላነሳንላት ጥያቄም ‹‹ምንም እርዳታ አልተሰጠንም፡፡ እርዳታ ቢሰጥ ኖሮ ቤታችን ጥለን አንመጣም ነበር፡፡ ባያበቅልም መሬት አለን፡፡ የከተማው ሰው ይሻላል ብለን ነው ወደዚህ የመጣነው›› ስትል ስለ ርሃቡ አስከፊነትና መንግስትም እርዳታ እየተሰጠ እንዳልሆነ ገልፃልናለች፡፡

rehab 4

ባለቤቷ ወደ መታማ ሲሄድ እሷም ቤቷን ጥላ ወደማታውቀው አዲስ አበባ እየጠየቀች እንደመጣች የገለፀችልን ወጣት በበኩሏ ‹‹ቤቴ ተፈትቷል፡፡ ባለፈው አመት ከብቶችም እህልም ነበረን፡፡ ዘንድሮ ግን ምንም ነገር የለም፡፡ ጊዜው ከፍቷል፡፡ ባሌ ወደ መተማ ሄዷል፡፡ እኔም ልጄን አዝዬ እስከ ደሴ በእግሬ መጣሁ፡፡ ከዛ በኋላ እየለምንኩ ከዚህ ደርሻለሁ፡፡ ማንም እርዳታ አልሰጠንም፡፡›› ስትል ስለሁኔታው ገለፃልናለች፡፡

ከመርሳ ወረዳ እንደመጡ የገለፁልንና ከልጃቸው ልጅ ጋር እየለመኑ ያገኘናቸው የ65 አመት አዛውንት በበኩላቸው ‹‹ዝናቡ ሲቀር ከብቶቻችንም ሞቱ፡፡ አዝመራ የሚባልም ነገር የለም፡፡ ከመርሳ ደሴ እየለመንኩ መጣሁ፡፡ ደሴም እንደኛ ብዙ ሰው አለ፡፡ አገኝ ብሎ በየከተማው ተሰራጭቷል፡፡ ወደዚህ ይሻላል ብዬ በለመንኳት ተሳፍሬ መጣሁ፡፡ ርሃቡ ሲብስብን ወደማናውቀው አገር መጣን፡፡›› ሲሉ የርሃቡን አስከፉነት ገልፀውልናል፡፡

‹‹እርዱኝ!›› እያሉ እየለመኑ ያገኘናቸው ከኬሚሴ አካባቢ እንደመጡና ከ8 ቀን በፊት አዲስ አበባ እንደደረሱ የገለፁልን ሌላኛዋ እናትም ቤታቸውን ጥለው እንደመጡና፣ ሌሎች ቤተሰቦቻቸው ወደ የት እንደሄዱ እንኳን እንደማያውቁ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ መንግስት እርዳታ እየሰጠሁ ነው እንደሚል ስንገልፅላቸው ‹‹ለእኔ አልደረሰኝም፡፡ እርዳታ ተሰጠኝ ያለም አልሰማሁም፡፡ እርዳታ ቢሰጥማ ከዚህ ድረስ አልመጣም ነበር፡፡ አሁን ነው ከከተማው ሰው ትንሽ ትንሽ እያገኘን ያለነው፡፡ በየ ከተማው ስንደርስ ሰው አይነፍገንም›› ሲሉ ከህዝብ እንጅ ከመንግስት እርዳታ እንዳላገኙ ገልፀዋል፡፡

rehab 5

ካሳንቺስ አካባቢ ልጅ አዝለው ታክሲ ተሳፋሪዎችን ምንም አይነት ቃል ሳያሰሙ ልጃቸውን በመዘርጋት ብቻ እንዲረዷቸው እየጠየቁ ያገኘናቸው እናትም የራሳቸውንና የታዘለውን ልጅ ነፍስ ለማዳን ቀያቸውን ጥለው ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

የርሃቡ ተጎጅዎች አዲስ አበባ ውስጥም ነፍሳቸውን ለማቆየት በጠራራ ፀሀይ ሲለምኑ እንደሚውሉና ምቹ ያልሆነ ቦታ አንድ ላይ የሚያድሩ በመሆኑ ልጆቻቸው ለበሽታ እየተጋለጡ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ተማሪ የነበሩና በርሃቡ ምክንያት ለማቋረጥ የተገደዱት ልጆቻቸው ከእነሱ ጋር ወይንም ወደ ሌላ አካባቢ ነፍሳቸውን ለመዳን መሰደዳቸውን፣ በያለፉበት ከተማም በርካታ ስደተኛ እንዳለም ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

The post በርሃብ የተጠቁት ዜጎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው • መንግስት በርሃብ ለተጠቁት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ አይደለም appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: ፍቅረኛዬ ቤተሰቦቼ አግቢ ስላሉኝ አግባኝ ወይም እንለያይ የሚል ምርጫ ሰጠችኝ፤ ምን ይሻለኛል?

$
0
0

ፍቅረኛዬ ቤተሰቦቼ አግቢ ስላሉኝ አግባኝ ወይም እንለያይ የሚል ምርጫ ሰጠችኝ፤ ምን ይሻለኛል?

ቢ ነኝ

የኢሳያስ ከበደ ምላሽ፦ ውድ ጠያቂያችን ቢ የሁኔታህን አሳሳቢነት ግምት ውስጥ በማስገባት ከሌሎች ደብዳቤዎች ያንተን በማስቀደም ይኸው ፈጣን ምላሻችንን ሰጠንህ፡፡ ከጽሑፍህ እንደተረዳነው በማግባትና በመለየት መካከል አንዱን ለመምረጥ ተቸግረሃል፡፡ ለዚህ ደግሞ መፍትሄው ውሳኔ የመስጠት ክህሎትን (Decision Making Skill) ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ክህሎት ስር ያሉ የተለያዩ ስልቶችን/techniques/ በማንሳት ላንተ ሁኔታ አቅጣጫ በሚጠቁም መልኩ እናሳይሃለን፡፡

marraige

እንደዚህ አይነት ውሳኔ ለመስጠት የሚያስቸግሩ ነገሮች በሚያጋጥሙ ጊዜ መጨነቁና መወጣጠሩ የግድ ነው፡፡ ነገር ግን ቁምነገሩ መጨናነቁ ሳይሆን፣ ጊዜ ወስዶ ስለጉዳዩ በጥሞና በማሰብ የመፍትሄ እርምጃ መውሰዱ ነው፡፡ ይህንንም ለማድረግ የመጀመሪያው ተግባር ችግሩን በሚገባ መለየት (Identify the problem) ነው፡፡ ፍቅረኛህ ለምንስ ሁለት አማራጮችን ብቻ ሰጠችህ? በጽሁፍህ እንደገለፅከው ቤተሰቦቿ እንድታገባ ስለፈለጉ ፍቅረኛህን ወጥረው ያዟት እሷም ላንተ ይህንን ምርጫ ሰጠችህ፡፡ ስለሆነም አሁን ያንተ ዋነኛ ችግር እሷን ከማግባትና ከእርሷ ጋር ተለያይቶ በመኖር መካከል መወጠርህ ነው፡፡ ያ ማለት የመጀመሪያው ተግባርህ ችግሩን መለየት ሲሆን ይህንንም ከውነሃል፡፡

ቀጣዩ ተግባርህ፣ ያሉህን አማራጮች በሙሉ ማየት (brain strom all possible option) ነው፡፡ በዚህም መሰረት ያሉህ አማራጮች አንደኛ ቤተሰቧ በሚሰጧችሁ ገንዘብ መሰረግና ከፍቅረኛህ ጋር አብሮ መኖር፣ ሁለተኛ ፍቅረኛህን አለማግባትና ከእሷ ተለይቶ መኖር ሲሆን ሶስተኛ አማራጭም አለህ፡፡ ይህም ፍቅረኛህን በማሳመን የተወሰነ ጊዜ ቆይቶ ራስን አጠንክሮ መጋባት ነው፡፡

ዋናው ጉዳይ ደግሞ ያለው፣ ከእነዚህ አማራጮች ውስጥ አንዱን መምረጡ ላይ ነው፡፡ ይህንንም ለማድረግ ቀጣዩን ተግባር መወሰኑ ወሳኝ ነው፡፡ ይህም እያንዳንዱ አማራጭ በአጭር ጊዜና በረጅም ጊዜ የሚያስከትለውን ጥሩና መጥፎ ነገሮችን መለየት ነው፡፡ ውድ ቢ ሶስቱንም አማራጮች በወረቀት አስፍራቸውና በእያንዳንዱ ስር ያን አማራጭ ብትመርጥ ምን ጥሩ፣ ምንስ መጥፎ ነገሮችን ሊያስከትል ይችላል ብለህ በሚገባ በማሰብ በዝርዝር ጻፋቸው፡፡

ምሳሌ ልስጥህ፤ የመጀመሪያው አማራጭ ፍቅረኛህን ማግባት ነው፡፡ ይህንን አማራጭ ብትተገብረው ተከትሎ ከሚመጡ ጥሩ ነገሮች አንዱ፣ የምትወዳት ፍቅረኛህ ጋር አብሮ መኖር ትችላለህ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ተከትለው ከሚመጡ መጥፎ ነገሮች ውስጥ አንዱ በሌሎች ገንዘብ ሠርግህን ታከናውናለህ፡፡ እንዲህ እያደረክ ይህንን አማራጭ ብትመርጥ የሚከተሉትን ጥሩና መጥፎ ነገሮችን በዝርዝር ፃፋቸው፡፡ ለሌሎች አማራጮችም በተመሳሳይ ምርጫውን ተከትለው የሚመጡ ጥሩና መጥፎ ነገሮችን ዘርዝረህ ፃፍ፡፡

እዚህ ላይ ሁለት ነገሮችን መናገር ይኖርብኛል፡፡ አንደኛው ይህ ጥሩ ወይም መጥፎ ነገር ይከሰታል ብለህ ብታሰፍር በቂ መረጃዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ ይገባሃል፡፡ በሌላ ቋንቋ ለእያንዳንዱ ይከሰታል የምትለው ጉዳይ አላማና የሆነና ምክንያታዊ መረጃ ሊኖርህ ይገባል፡፡ ለምሳሌ ሶስተኛውን አማራጭ ብትመርጥ ፍቅረኛዬን ማሳመን አልችልም የሚል ነገር ብታስቀምጥ፣ ይህ እምነትህ ትክክል ለመሆኑ በቂ የሆነ ማስረጃ ሊኖርህ ይገባል፡፡

ሌላው ጉዳይ ደግሞ ዲካታስትፎፊንግ /Decatastrophing/ የሚባል ስልት አለና ይከሰታሉ የምትላቸውን መጥፎ ነገሮን ስታስቀምጥ ይህን ስልት ተጠቀምበት፡፡ ይህ ስልት ማለት ደግሞ አንድ መጥፎ ነገር ይከሰታል ስትል፣ ነገሩ የመከሰት ዕድሉ ምን ያህል ነው የሚለውን ማጤን፣ የችግሩ መጠን ምን ያህል ክብደት /Magnitude/ ይኖረዋል የሚለውን መገመት ብሎም ችግሩን ከመከሰቱ በፊት ለመከላከል የምትችልባቸውን መንገዶችን ወይም ችግሩ ሊከሰት መቋቋም የምትችልበትን መንገዶች ቀደም ብሎ ማሰብ ማለት ነው፡፡ በምሳሌዎች ላስረዳህ፡፡ አንደኛውን አማራጭ ብትመርጥ ከሚከተሉት መጥፎ ነገሮች አንዱ ራሳችሁን ሳትችሉ ልጅ መውለድ ይመጣል የሚል ነገር አሰፈርክ እንበል፡፡ በዚህ ጊዜም ልጅ የመውለድ እድላችሁ ምን ያህል ነው፡፡ ልጅ ቢወለድ የሚከሰትባችሁ ችግር ምን ያህል ነው እና ልጅ እንዳትወልዱ ማድረግ የምትችሉባቸው መንገዶች ወይም ልጅ ቢወለድና ችግር ውስጥ ብትገቡ እንዴት አድርጋችሁ ችግሩን መቋቋም እንደምትችሉ ማሰብ ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው አማራጭ ሁለትን ብትመርጥ ከፍቅረኛህ ጋር መለያየት ተከትሎ የሚመጣ መጥፎ ነገር ነው ብለህ አሰብክ እንበል፡፡ ስልቱንም በተግባር ለማዋል አንጋባም ብትላት፣ ፍቅረኛህ ጥላህ የመሄድ ዕድሏን ማጤን፣ ጥላህ ብትሄድ ምን ያህል እንደምትጎዳ መገመትና ጥላህ እንዳትሄድ ማድረግ የምትችልበትን መንገዶች ወይም ጥላህ ስትሄድ የሚደርስብህን ጉዳት ለመቋቋም የምትችልበትን መንገዶች ማሰብ ይኖርብሃል፡፡

በአጠቃላይም፣ እያንዳንዱ አማራጭ ብትመርጠው ተከትለው የሚመጡ ጥሩና መጥፎ ነገሮን በዝርዝር ማብሰልሰልና በጽሑፍ ማስቀመጥ ዋናው ጉዳይ ነው፡፡ በመቀጠል ደግሞ ከሶስቱ አማራጮች ብዙ ጥሩ ነገሮችን የሚያስከትለውን ወይም ብዙ መጥፎ ነገሮች የማያስከትለውን አንዱን አማራጭ መምረጥ፣ ብሎም በዛ ምርጫህ ምክንያት ሊመጡ የሚችሉ ጉዳቶችን አምኖ ለመቀበል ራስን ማዘጋጀት ነው፡፡

እዚህ ላይ አንድ ነገር ልጠቁምህ፡፡ አሁን አንተ እየመረጥክ ያለኸው ምርጫ እንደ ሌሎች አይነት ምርጫዎች /ለምሳሌ ሁለት ቦታ ስራ አልፈህ አንዱን መምረጥ/ ቀላል አይደለም፡፡ ለዚህ ደግሞ አይነተኛ ምክንያቱ አንተ እየመረጥካቸው ያሉ አማራጮች ስሜታዊ የሆኑ ጉዳዮች (emotional component) አሉት፡፡ የብዙ ዘመን ፍቅረኛን ማጣት የሐዘን ስሜት፣ እሷን ከቤተሰቦቿ በሚገኝ ገንዘብ ማግባት የተረጅነት ስሜት፣ እሷን አሳምኖ ሰርጉን ማዘግየት በእሷ በኩል የመናደድ ስሜት፣ ባንተ በኩል እሷን ለማሳመን የትዕግስት መፈተን ስሜት፣ ወዘተ በውሳኔህ ውስጥ አብሮ ይኖራል፡፡ እንደነዚህ አይነት ስሜታዊ ጉዳዮችን ለመወሰን የስነ ልቦና ባለሙያዎች ጥሩ ስልት የሚሉት፣ ከእያንዳንዱ ምርጫ ጋር የሚመጡ ሁኔታዎችን ማጤን ብሎም ራስን ውሳኔው በሚነካው ሰው ቦታ የማስቀመጥ ስልትን (reattribution) መጠቀም ወሳኝ ነው፡፡ በመሆኑም ፍቅረኛህን አላገባሽም የሚለውን ውሳኔ ለማሳወቅ ከመነሳትህ በፊት፣ ራስህን በፍቅረኛህ ቦታ አድርገህ፣ ላገባ ነው የሚለውን ውሳኔ ለቤተሰቦችህ ከማሳወቅህ በፊት፣ ራስህን በቤተሰቦች ቦታ አድርገህ፣ የተወሰነ ጊዜ ጠብቂኝ ብለህ ለፍቅረኛህ ከመናገርህ በፊት እራስህን በፍቅረኛህ ቦታ አስቀምጠህ ወዘተ ማሰቡ ጠቃሚ ነው፡፡

አንዱን አማራጭ ከመረጥክና በምርጫህ የተነሳ የሚመጣውን ነገር ለመቀበል ከተዘጋጀህ በኋላ፣ የመጨረሻ ተግባርህ የወሰንከውን ለፍቅረኛህ ማሳወቅ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ ሁለት ዘዴዎችን መጠቀሙ ጠቃሚ እንደሆነ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ አንደኛው ፍቅረኛህ ራሷን በአንተ ቦታ እንድታስቀምጥና ውሳኔ እንድትሰጥ መጠየቅ (Reattribution) ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ካንተ ሁኔታ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ታሪኮችን በመንገር (story telling) ወደ ራስህ ውሳኔ የማሳወቅ ተግባር መሄድ ነው፡፡ ብሌን ኪኖር የተባለ ምሁር በ2005 እ.ኤ.አ በሰራው ጥናት ለሰዎች የሌሎችን ታሪክ መናገር፣ ሰዎቹ ሀሳባቸውን እንዲቀይሩ ወይም ቢያንስ የእኛን ሁኔታ እንዲረዱና እንደሚያደርጋቸው አሳይቷል፡፡ ስለሆነም አንተ ተመሳሳይ ታሪኮችን በመንገርና ፍቅረኛህ ባንተ ቦታ ሆና እንድትወስን በማድረግና ውሳኔህን በማሳወቅ በውሳኔህ መሰረት በመንቀሳቀስ ውጥረትህን ማርገብ ትችላለህ፡፡ በስተመጨረሻም እላይ የጠቀስኳቸውን ተግባራት በቅደም ተከተል በመተግበር፣ ከችግርህ እንድትወጣ እያሳሰብኩ መልካሙን በመመኘት የዛሬ ምላሼን በዚሁ አጠናቀቅሁ፡፡

The post Health: ፍቅረኛዬ ቤተሰቦቼ አግቢ ስላሉኝ አግባኝ ወይም እንለያይ የሚል ምርጫ ሰጠችኝ፤ ምን ይሻለኛል? appeared first on Zehabesha Amharic.

ድል ለመቀዳጀት በአንድ ማሊያ መጫወት –ይገረም ዓለሙ

$
0
0

የላቀ የኳሽ ችሎታ ያላቸው ተጨዋቾች በሀገራቸውም ሆነ ከሀገራቸው ውጪ በከፍተኛ  ገንዘብ እየተሸጡ  ይጫወታሉ፡፡ እነዚህ ዘር፣ቀለም ፤ኃይማኖትም ሆነ ቋንቋ ሳይገድባቸው በችሎታቸው ተመርጠው በየትኛውም የአለም ክፍል  የሚጫወቱ ተጨዋቾች  ገንዘብ የሚከፍላቸውን ቡድን የዋንጫ ባለድል ለማድረግ ለራሳቸውም ተዋቂነት ለማትረፍ በቁርጠኝነት ይጫወታሉ፡፡ የአንድ ሀገር ልጆች የተለያየ ማሊያ ለብሰው   ለተለያዩ ቡድኖች ተሰልፈው ሲጫወቱ የተሰለፉለትን ቡድን ለአሸናፊነት ለማብቃት ይሻኮታሉ  ይጎሻሸማሉ፡

unity

አህጉራዊ ወይንም ዓለም አቀፋዊ ጨዋታ ሲኖር ግን ከየሄዱበት ተመልሰው ከተበታተኑበት ተሰባስበው በአንድ ማሊያ ለሀገራቸው ይሰለፋሉ፡፡ ለሀገራቸው ቡድን የመሰለፍ ምክንያታቸው በአሰልጣኙ መመረጣቸውና ሀገራቸው ችሎታቸውን መፈለጉ ብቻ ሳይሆን የእነርሱም ሀገራቸው አሸንፎ ባለ ድል አንዲሆን ከምር መፈለጋቸው ጭምር ነው፡፡ ባለፈው የዓለም ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር ላይ ከአሸናፊነት ክብር ብር በልጦባቸው ከሀገራቸው አልፎ አፍሪቃን መሳቂያ ያደረጉትን  ተጨዋቾች ሳንጨምር ነው ታዲያ፡፡

በዚህ ተምሳሌት የሀገራችንን ፖለቲካ ብንመለከተው ወያኔ በዚህ መንገድ በሚገባ እየተጠቀመበት መሆኑን እናያለን፡፡ ተቀዋሚው ግን….. ፡፡ ወያኔ አባል አጋር ሌላም በውል ስም ያልወጣላቸው ቡድኖችን አቋቁሞ በተለያየ ማሊያ የክልል ጨዋታውን ያካሄዳል፤ አምስት ዓመት ጠብቆ ሀገራዊው ጨዋታ ሲካሄድ ደግሞ ሁሉንም በአንድ ማሊያ በኢህአዴግ ስም ያሰልፋል፡፡

ወያኔ  ማሊያ እየቀያየረ መጫወት የጀመረው በህውኃት ማሊያ  ወደ ጎነደርና ወሎ መሸጋገር እንደማይቻል  በተረዳበት ግዜ ነው፡፡እናም የአማራ ክልል የሚል ስያሜ በሰጠው የኢትዮጵያ ክፍል ለመረማመድ እንዲቻለው ኢህዴን ይባል የነበረውን ሕብረ- ብሔራዊ ድርጅት ስሙንም ዓላማውን አስለውጦ ብአዴን በሚል መጠሪያ  የአማራነት ማሊያ አለበሰው፡፡ወያኔ ይህን ሲያደርግ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ነው የመታው፡፡ አንዱ በአማራ ክልል ለመረማመድ የሚያስችለው  ቡድን መፍጠር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የማይፈልገውንና ለእቅዱ አንቅፋት አድርጎ የሚያየውን ሕብረ ብሄር ፓርቲ ማክሰም፤ ሀገራዊ አስተሳሰብን ማጥፋትና ዘረኝነትን ማስፋፋት ነው፡፡  ወደ ሸዋ ሲጠጋ ደግሞ እሱም ጋር ሻዕቢያም ዘንድ የነበሩ ኦሮምኛ ተናጋሪ ምርኮኞችን ሰብስቦ በኦሮምያ ውስጥ ለመረማመድ የሚያስችለውን የኦሮሚያ ማሊያ ለብሶ የሚጫወት ቡድን ( ኦህዴድን) ፈጠረ፡፡አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ደግሞ የሱን ሥልጣን የሚያረጋጉና የሚያስጠብቁ  ደኢህዴንና እና አጋር የሚባሉትን ቡድኖችን መፍጠሩን ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡

Unity of Eth

እነዚህ የተለያያ ማሊያ ለብሰው የተለያየ ቡድን ተመስለው የሚጫወቱ ቡድኖች የቡድን መሪያቸው አሰልጣኛቸው አስተዳዳሪያቸው ህወኃውት መሆኑን አሌ የሚል አይኖርም፡፡እናም ለዘወትሩ ጨዋታ  በክልል ማሊያ እያሰለፈ በየአምስት ዓመት ለሚካሄደው ጨዋታ ደግሞ የኢህአዴግን ማሊያ እያሰለፈ ሀያ አራት አመት ሙሉ የዋንጫው ባለቤት እንደሆነ አለ፡፡

ይህን ጨዋታ ቅንጅትም ሞክሮት ውጤታማነቱን አሳይቷል፤ምርጫ 97 በአጃቢነት የምንገባበት፣ ለአድማቂነት የምንሰለፍበት ሳይሆን ከምር ተወዳድረን የምናሸንፍበት መሆን አለበት ያሉ ወገኖች ለማሸነፍ ደግሞ  በተለያየ ስም ሆኖ የተለያያ ማሊያ ለብሶ ሳይሆን  በአንድ ቡድን መደራጀት በአንድ ማሊያ መሰለፍ እንደሚስፈልግ ተናገሩ-ሰሩ፡፡ በዚህ ጥረትም  አደረጃጀታው ሀገራዊ  መገኛቸው ሀገር ቤት የሆኑ አራት ድርጅቶች ስማቸውን ቅንጅት ብለው ምልክታቸውን ሁለት ጣት አድርገው በአንድ ማሊያ ተሰልፈው መጫወት በመቻላቸው መቼም የማይረሳውንና መቼ ሊደገም እንደሚችል መተንበይ የማይቻለውን ውጤት አስገኙ፡፡

ይህ ከሆነ በኋላ ሁለት ምርጫዎች ተደርገው ተቀዋሚው እንደለመደው ጨዋታውን በተለያየ ማሊያ ማድረጉን በመቀጠሉ በአንዱ አንድ ወንበር ሲያገኝ በሁለተኛው ፓርላማውን ጨርሶ አስረክቧል፡፡ ሀገራዊ ውድድርን በአሸናፊነት ለመወጣት ካልሆነም ትንሽ ወንር ከፓርላማ ለማግኘት  አንድ ቡድን መስርቶ በአንድ ማሊያ መጫወት  ያለውን ጠቀሜታ ከወያኔ መማር ባይቻል ወይንም ባይፈለግ እንደምን ከቅንጅት መማር ይቸግራል፡፡

ለውጤታማነት በአንድ ማሊያ መጫወት የሚያስፈልገውና የሚጠቅመው በሀገር ቤት ለሚደረገው ትግል ብቻ አይደለም፡፡የትግሉ መነሻ ቦታ ኢትዮጵያም ይሁን አሜሪካ፣ ኤርትራም ይሁን በርበራ፣አሰብም ይሁን ሱዳን  በሁሉም የሚፈለገው ውጤት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ማየት ከሆነ በአንድ ቡድን ተሰባስቦ  አንድ ማሊያ ለብሶ አንድ ሀገራዊ ገዢ መርህ አንግቦ መጫወት  የግድ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ውጪ እስካሁን በተመጣበት ሁኔታ የሚካሄድ ውድድር(ትግል) ይህን ያህል ቡድን እዛና እዚህ አለ ከመባል ባለፈ ብሎም አንድ ቡድን ብቻውን ለጨዋታ ሜዳ አይገባምና የወያኔ አጨዋች ከመሆን የዘለለ የሚፈይደው ነገር የለም፣ አለ ከተባለ እገሌ የዚህ ቡድን መሪ እገሌ የዛኛው ቡድን ሊቀመንበር እየተባሉ መኖርን ትግልም ድልም ላደረጉ ሰዎች የሥልጣን ጥም ርካታ ማስገኘቱ ብቻ ነው፡፡ የፓርቲ መሪነት ሥልጣን ሆኖ፡፡

ሀያ አራት አመት እጅግ ብዙ ነው፡፡ስለሆነም ከዚህ በኋላ ሊመረን ይገባል፡፡በርግጥ ለውጥን ዓላማቸው አድርገው ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሥረታ ከልብ አምነው ለዚህም ከምር ቆርጠው ለመታገል የወሰኑትና የፓርቲ ሊቀመንበር እየተባሉ መኖርን መነሻ ዓላማቸው መድረሻ ግባቸውም አድርገው የሚኖሩት ይለዩ፡፡ አንድ ቡድን መስርቶ በአንድ ማሊያ ተወዳደሮ የዋንጫ ባለቤት ላለመሆን ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው  ቡድኖች ያላቸው የአደረጃጀት ፣ የጨዋት ስልት ፣የሚገኙበት ቦታ ወዘተ ልዩነት አሳማኝ አይደለም፡፡ ዋናው ምክንያት ሀገራዊ ለውጥ እንዲመጣ ያለመፈለግ ወይንም ቁርጠኝት ማጣት ነው፡፡ ለለውጥ በቁርጠኝነት የተሰለፈ ለለውጥ እንቅፋት ለሆኑ ችግሮች መፍትሄ ይፈልጋል እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ሰበቦችን  ያስወግዳል እንጂ  ልዩነትን ለማስፋት ሲማስን አያድርም፣በእያንዳንዱ ርምጃ ሰበብ እየፈለገ እንቅፋት አይፈጥርም፣ስለ ሀገራዊው ድል እንጂ ስለ እርሱ ቦታ አይጨነቅም፡፡

አንድ  በግልጽ የሚታይ ነገር ላንሳ  ጀነራል ከማል ገልቹና ጀነራል ሀይሉ ጎንፋ  ሁለቱም ከወያኔ ከድተው አስመራ የገቡ የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው፡፡እዛ ደርሰው ግን በአንድ ቡድን ተሰልፈው አንድ ማሊያ (ኢትዮጵያዊ ቢቀር ኦሮሚያዊ)ለብሰው መጫወት ተስኖአቸው ተለያይተው በኦሮሞ ስም የተለያየ ቡድን መስርተው እንደሚገኙ ነው የሚሰማው፡፡ ለያዙት ማእረግ የበቁት ውትድርናውን መቼ ጀምረውት እንደሆነ ማስረጃ ባይኖረኝም እዚህ ማዕረግ እስኪደርሱ በቃልም በተግባርም፤ በክፍልም በመስክም  ወዘተ ሰፊ ወታደራዊ እውቀት እንደቀሰሙና ልምድ እንዳካበቱ እሙን ነው፡፡ ታዲያ  በዚህ ወቅት  ከሀገር ቤት ብቻ አይደለም  ከአውሮፓና አሜሪካ ጭምር ከፕሮፌሰር እስከ ጳጳስ ከምር ቆርጠው  ትግሉ ቦታ ሲወርዱ ጀነራሎቹ አሥመራ ተቀምጠው እንኳን ከሌላው መተባበር ርስ በርሳቸውም መነጋገር አቁመው አመታት መቁጠራቸውን መስማት እንቆቅልሽ አይሆንም!

ከምር ራሳቸውን ለትግሉ የሰጡና ለሥልጣን ሳይሆን  ለነጻነት የሚታገሉ ስራቸው ምስክር ነውና በተግባራቸው እንለያቸው በምንችለውም አንደግፋቸው ይጠናከሩ፡ከውጤት አልባው የአመታት ጉዞአቸው ተምረው ለመለወጥ ያልፈቀዱትና ትግሉን ለስማቸው መጠሪያ ብቻ አድርገውት የሚኖሩት እንደዚሁ በተግባራቸው ይለዩ ፡፡ የእነዚህ  መኖር ለሀገራዊው ትግል ከሚጠቅም ይልቅ ጉዳት ናቸውና ድጋፍ እንነሳቸው፤ከመኖራችሁ አለመኖራችሁ ይሻላል ብለን በግልጽ እንንገራቸው፡፡

ለነገሩ ሀገር ውስጥ ያሉት ብዙዎቹ ፓርቲዎች  በወያኔ ዘንድ ነው እንጂ አሉ የሚባሉት ቆሞ ያልጠቀመ ሞቶ ምን ሊጎዳ ብሎ ሕዝቡ ከሸኛቸው አመታት ተቆጥረዋል፡፡ በውጪም በሚገኙት ላይ ይሄው መደገም አለበት፡፡ ሀገራዊውን ጨዋታ በአሸናፊነት ለመወጣት በአንድ ማሊያ መጫወት በምንልበት በዚህ ሰዐት እንወክለዋለን በሚሉት የአንድ አካባቢ ሕዝብ ስም የተደራጁ ሁለትም ስድስትም ድርጅቶች ስም እንሰማለን፡፡ የድርጅቶቹ መስራቾች ሁሉም ሊቀመንበር መባል በመፈለጋቸው ነው፡፡ ብዙም አባል አንደሌላቸው ይታወቃል፤ደጋፊው ግን ምን ይባላል፡፡ ትግሉን ከምር ያዙት አለያም ተዉት ማለት አያስፈልግም ትላላችሁ፡፡

በመጨረሻም ሎሬትን እንጋራ

pastedGraphic.png

The post ድል ለመቀዳጀት በአንድ ማሊያ መጫወት – ይገረም ዓለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.

እነ መሳይ ትኩ ለህዳር 14 ተቀጠሩ * እስማኤል ዳውድ መከላከያ ምስክሮቹን አሰማ

$
0
0

 

udj udj1

ኢዩኤል ፍሰሀ ዳምጤ እንደዘገበው

በ2001 ዓ.ም የወጣውን የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 7/1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ፤ የሚል ክስ በፌደራል አቃቤ ሕግ በኩል የቀረበባቸው፣ 1ኛ ተከሳሽ መሳይትኩና 2ኛ ተከሳሽ ሰጠኝ ሙሉ ተለዋጭ ቀጠሮተሰጣቸው፡፡

ልደታ በሚገኘው ከፍተኛ ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለማድመጥ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው የነበሩት መሳይ ትኩና ሰጠኝ ሙሉ ምስክሮቻቸውን ሳያሰሙ ለ5ኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይህን በማስመልከት 1ኛ ተከሳሽ መሳይ ትኩ፣ ለፍ/ቤቱ አቤቱታውን አሰምቷል፡፡ ‹‹የተከበረው ፍ/ቤት እኛም ሃሳብ አለን››በሚል በስሜት ተውጦ የተናገረው መሳይ፣ ከጥቅምት 16 ቀን ጀምሮ ምስክሮችን ለማድመጥ ተደጋጋሚ ቀጠሮ እየተሰጣቸው እንደሚገኝ፣እስካሁን ድረስም ምስክሮች ባለመደመጣቸው የተነሳ ከክፍለ ሀገር የሚመጡት ቤተሰቦቻቸው ላይ እንግልት እየደረሰ እንደሚገኝ አስረድቷል፡፡ በዕለቱ በችሎቱ የተሰየሙት ዳኛ ምስክሮች ተሟልተው እስኪቀርቡ ድረስ መታገስ እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡ ‹‹በእኔ ላይ አቃቤ ሕግ ሊያሰማው ያዘጋጀው ምስክር በፍ/ቤት ውስጥ አይቼዋለሁ›› በማለት ለችሎቱ ያስረዳው መሳይ፣ ምስክሩ እንዲደመጥልኝ ሲል ፍ/ቤቱን ጠይቋል፡፡ አቃቤ ሕግ በበኩሉ ‹‹ምስክሩ አልቀረበም›› በማለት ለፍ/ቤቱ ሲናገር ተደምጧል፡፡ ፍ/ቤቱ አቃቤ ሕግ ምስክሮቹን አሟልቶ እንዲያቀርብና ምስክሮቹን ለማድመጥም ተለዋጭቀጠሮ ለህዳር 14 ቀን 2008 ዓ.ም ሰጥቷል፡፡

አቃቤ ሕግ በመሳይ ትኩ ላይ አንድ ምስክር ያዘጋጀ ሲሆን፤ በሁለተኛ ተከሳሽ ሰጠኝ ሙሉ ላይ ደግሞ ሁለት የደረጃ ምስክሮችን እንዳዘጋጀ ለመረዳት ተችሏል፡፡ አቶ መሳይም ሆነ አቶሰጠኝ ከየካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

በሌላ ዜና፣‹‹ስብሰባንበማወክ›› ወንጀል ተከሶ ላለፉት 6 ወራት ክሱን በማረሚያ ቤት ሆኖ እየተከታተለ የሚገኘው፤የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አባል ወጣት እስማኤል ዳውድ፣ በትላንትናው እለት መከላከያ ምስክሮቹን አሰምቷል፡፡ እስማኤል፣ የቀረበበትን ክስ በሚመለከት ለመከላከል ይረዱኛል ብሎ ያሰባቸውን ሁለት ምስክሮች ያስደመጠ ሲሆን፤ ፍ/ቤቱ ብይን ለመስጠት ለህዳር 7 ቀን 2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ መንግስት አይኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ በመገኘት ‹‹ስብሰባንአውከሃል›› የሚል ክስየቀረበበት እስማኤል፣ ከሚያዚያ 20 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

The post እነ መሳይ ትኩ ለህዳር 14 ተቀጠሩ * እስማኤል ዳውድ መከላከያ ምስክሮቹን አሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሕወሓት መንግስት በመደለያዎች እና በግዳጅ ጭምር የመከላከያ ሠራዊት አባላትን በየሥፍራው እየመለመለ መሆኑ ተሰማ

$
0
0
የሕወሓት መንግስት ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን ወደ ሶማሊያ ልኮ ሬሳቸውን በአደባባይ ሲያስጎትት

የሕወሓት መንግስት ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን ወደ ሶማሊያ ልኮ ሬሳቸውን በአደባባይ ሲያስጎትት

የህወሓት አገዛዝ ልዩ ልዩ ማማለያዎችንና መደለያዎችን በመጠቀም በግዳጅም ጭምር ወጣቶችን ለእግረኛ ተዋጊ ጦር ሰራዊትነት ለመመልመል በመላ አገሪቱ በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ እንደዘገበው በኢትዮጵያ ውስጥ ለተንሰራፋው የህዝቡ የከፋ ድህነትና ስራ አጥነት መንስኤ የሆነው የህወሓት አምባገነናዊ አገዛዝ ድህነታቸውን ተጠቅሞ ዕልፍ አዕላፍ ወጣቶችን በአገር መከላከያ ስም በመመልመል በየጠረፉ በሚደረጉ የሽምቅ ውጊያዎች ውስጥ በመጨመር ያለቀባሪ በየበረሃው ወዳድቀው እንዲቀሩ በማድረግ በደምና አጥንታቸው የስልጣን ዘመኑን ለመቀጠል ሲፍጨረጨር መቆየቱ በግልፅ የሚታወቅ እውነታ ነው፡፡


በስልጣንና የንዋይ ፍቅር የነሆለለው ዘረኛው የህወሓት ቡድን ምስኪን ኢትዮጵያዊ እናቶች ኩበትና እንጨት ለቅመው ሽጠው፣ ለባለፀጋ ተገርደው በችጋር አለንጋ እየተገረፉ ያሳደጓቸውን ልጆቻቸውን ወደ ሶማሊያ ምድር በማስገባት በጥይት እያስጨፈጨፈ ሬሳቸው ሳይቀር በሞቃዲሹና በሌሎች ከተሞች ጎዳናዎች ላይ ልክ እንደውሻ በድን በገመድ ታስሮ እንዲጎተት እያደረገ በምስኪኖች ሞት እሱ ረብጣ ዶላር እያፈሰ ይገኛል፡፡


አሁንም ቢሆን ህወሓት ያንን የደም ቁማሩን በድሃ ልጅ ላይ መቆመሩን ቀጥሏል፡፡ እሱ ራሱ በሚፈፅመው ማባሪያ የሌለው ግፍና በደል ምክንያት በመላ አገሪቱ ተቃውሞ ተነስቶበት ህዝቡ ልቡ በረሃ ገብቶ በመሸፈቱና የአርበኝነት ትግል እያፋፋሙ የሚገኙ የነፃነት ድርጅቶች እንድ እየሆኑ ወታደራዊ ተክለ ቁመናቸው እየገዘፈ በመምጣቱ እንዲሁም በተጨማሪ በየጊዜው እያሰለጠነ ሲያከማቸው ለዓመታት በኖረው መከላያ ሰራዊቱ ላይም አንዳች እምነት በማጣቱ ምክንያት ስራ አጥ የሆኑ የድሃው ህዝብ ልጆችን በአገር መከላከያ ስም መልምሎ ለስልጣኑና ለጥቅሙ ሲል ብቻ እሳት ውስጥ ለመክተት በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡
የህወሓት አገዛዝ ወጣቱን በዲስኩራቸው የሚያሳምኑ ካድሬዎችን አሰልጥኖ በየመንደሩ አሰራጭቶ በሶስት የማታለያ መንገዶች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተዋጊ ጦር መልምሎ የማሰልጠን ስውር ዕቅዱን ለማስፈፀም ደፋ ቀና በማለት ላይ ይገኛል፡፡ 

በሶማሊያ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች

በሶማሊያ የተገደሉ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች


የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተዋጊ ጦር መልምሎ የማሰልጠን ህልሙን ዕውን ለማድረግ ወጣቱን ያማልላሉ ብሎ ያወጣቸው ሦስቱ የማስመሰያ ቅጥር የሙያ መስኮች ለመከላከያ ኢንጅነርኢንግ ኮሌጅ ትምህርት፣ ለአየር ኃይል አብራሪነት እና ለልዩ ኮማንዶና አየር ወለድ የሚሉ ናቸው፡፡
በመሆኑም ለመከላከያ ኢንጅነርኢንግ ኮሌጅ ከፍተኛ ትምህርት በሚል ሰበብ ቴክኒክና ሞያ ት/ቤት ተመርቀው ስራ ማግኘት ያልቻሉትን በእግረኛ ተዋጊ ሰራዊትነት ለመመልመል ከፍተኛ ጉትጎታ ላይ ነው፡፡ 


ለአየር ኃይል አብራሪነት ደግሞ ከከዚህ ቀደሙ የመመልመያ መስፈርት በተለየ ሁኔታ በፊዚክስ፣ ሂሳብ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ “C” በቂ ነው የሚል አዲስ የቅጥር መስፈርት አውጥቷል፡፡ 


በየመንደሩ የተሰገሰጉት መልማይ ዲስኩራም ካድሬዎችም “ዳርፉር ሄዳችሁ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠር ብር ዝቃችሁ ትመለሳላችሁ…” በማለት ወጣቱን የእርጎ ባህር እያሳዩ ወላጆችን ደግሞ “ልጆቻችሁ በመንግስት ተምረው ኢንጅነርና ፓይለት እንዲሆኑላችሁ እና ከችጋር እንዲያወጧችሁ መምከርና በገሰፅ አለባችሁ…” እያሉ የድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ደም በከንቱ እንደ ጅረት መፍሰሱን እንዲቀጥልና በአገራችን ላይ የተጫነው የባርነት አገዛዝ ዘመን እንዲራዘም ቀን ከሌሊት እየተጉ ነው፡፡


ህወሓት ከዚህ ቀደምም በ1980ዎቹ ዓ.ም መጨረሻ በመላ አገሪቱ የሚገኙ 12ኛ ክፍልን አጠናቀው ዩኒቨርሲቲ መግባት ያልቻሉ ወጣቶችን ለኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርት ስልጠና በሚል አታሎ በገፍ መልምሎ በሙያ ዘርፉ ከተመረቁ በኋላ የሚያገለግሉት “በአገር መከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች ውስጥ እንደሆነና በመጀመሪያ ወታደራዊ ስልጠና መውሰድ ግዴታቸው እንደሆነ አሳምኖ ወደየ የእግረኛ ተዋጊ ማሰልጠኛ ማዕከሎች ካስገባና አሰልጥኖ ካወጣቸው በኋላ ቆይቶ በፈነዳው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ውስጥ ማግዶ ሁሉንም አስጨርሷቸዋል፡፡ 


የሀወሓት አገዛዝ ከማማለያው ጎን ለጎን የድሃው ህዝብ ልጅ የሆኑ ወጣቶችን አስገድዶ የመመልመል ሙከራም እያደረገ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ “በደቡብ ክልል” በጎፋ ሳውላና በቁጫ የሚኖር እያንዳንዱ ወላጅ ቢያንስ አንድ አንድ ልጅ እንዲያዋጣ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ 


ሆኖም የህወሓት አገዛዝ የቱንም ያክል ማማለያና መደለያ ቢያቀርብ እንዲሁም በጉልበት ቢያስገድድ እስካሁን ድረስ ተታሎ አንድም የተመዘገበ ወጣት እንደሌለ እንዴውም በተቃራኒው ወጣቱ የሚደርስበት ጭቆና አንገሽግሾት እየተደራጀ ጫካ በመግባት ላይ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)

The post የሕወሓት መንግስት በመደለያዎች እና በግዳጅ ጭምር የመከላከያ ሠራዊት አባላትን በየሥፍራው እየመለመለ መሆኑ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.


መንግስት ”ለውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያቱ እድገቱ ነው”በሚል አዲስ የማምለጫ ምክንያት እየደረደረ ነው; እውን እድገት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ያመጣል?

$
0
0
ዶ/ር አብርሃም ተከስተ

ዶ/ር አብርሃም ተከስተ

  • ”ወደ አስር አመት ለሚጠጋ አመታት በውጭ ምንዛሪ እጥረት ስንሰቃይ ነበር” የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ ዶ/ር  አብርሃም ተከስተ የተናገሩትን ዛሬ የኬንያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደዘገበው።
  • ”በዕድገታችን ሳቢያ የውጭ ምንዛሪ ክምችታችን አስተማማኝ ነው” ቀድሞ አቶ መለስ በመቀጠል አቶ ሃይለማርያም ለምክር ቤት አባላት ባለፉት 10 አመታት ሲነግሩን የነበረው።
መንግስት ”ለውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያቱ እድገቱ  ነው” በሚል አዲስ የማምለጫ ምክንያት እየደረደረ ነው።የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ”የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ምክንያት እድገታችን ነው” ብለዋል።ቀጥለው ”ችግሩ (የውጭ ምንዛሪ ችግር) በርካታ የመንግስት እና የግል ፕሮጀክቶች ከመኖራቸው ጋር ይያያዛል” አሉ ይለናል  የኬንያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዛሬ የለቀቀው ዜና።
ጉዳዩ ከእውነታው ጋር ይቃረናል።የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ለውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያቱ የመንግሥታችን የተሳሳተ ፖሊሲ እና አሳታፊ አለመሆኑ ነው ከማለት ይልቅ በድፍኑ ”እድገቱ”ነው ካሉ በኃላ በማስከተል የፕሮጀክቶች መብዛት ነው ብለዋል።እዚህ ላይ ሁለት ነገሮችን ቀላቅለዋል።እድገትን እንደ አንድ ተጠያቂ ማድረግ እና የፕሮጀክቶች መለጠጥን ምክንያት ማድረግ የተለያየ ነው።ፕሮጀክቶች ስለተደረደሩ እና ሥራ ስለጀመሩ ብቻ እድገት አለ ማለት አይደለም።ፕሮጀክቶቹ አዋጪነት፣ለአገር የሚያመጡት ስልታዊ ጥቅም እና የእርሻውንም ሆነ የኢንዱስትሪውን ክፍል የማንቀሳቀስ አቅማቸው ሁሉ መፈተሽ አለበት።አቶ አብርሃም ግን በድፍኑ እድገቱ ነው በሚል ሊያልፉት ሞከሩ።
ለውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ምክንያት የፕሮጀክቶች መብዛት ብቻ ሊሆን አይችልም።እርግጥ ነው የፕሮጀክቶች መብዛት የውጭ ምንዛሪ ጥያቄን ያንረዋል።ሆኖም ግን  የፕሮጀክት መብዛት ነው ብለን ብንነሳ ይህ በእራሱ የስርዓቱን ስህተት የሚያሳይ ነው።ምክንያቱም የአለም ባንክን ጨምሮ ፕሮጀክቶች በአገሪቱ አቅም እና ቅድምያ የሚሰጣቸው አንገብጋቢ ፕሮጀክቶች ላይ ብቻ መሆን አለበት እንጂ ለምርጫ ፕሮፓጋንዳ ተብሎ ”አስር ወጥ አትጣዱ አንዱንም ሳታማስሉት እንዳያር” የሚል መሰል ምክር ሲሰጥ ነበር።ይህንኑ የተሳሳተ ተግባር በውጭ የሚኖሩ ምሁራንም በተለያየ ጊዜ ደግመውታል።በመሆኑም የፕሮጀክት መብዛት ነው ቢባልም አሁንም ስህተቱ ወደ እራሱ የስርዓቱ የተሳሳተ ፖሊሲን አመላካች መሆኑ  አይቀርም።
ለውጭ ምንዛሪ እጥረቱ የዓለም አቀፉ ኦርቢት ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ሲሳይ አሁንም ለኬንያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሰጡት መልስ ግን እውነቱም አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል።”የአገሪቱ ወደ ውጭ ሸቀጦችን የመላክ አቅም (ኤክስፖርት ሴክተር) ደካማ መሆን ነው ለውጭ ምንዛሪ እጥረት ዋናው ምክንያት” ነበር ያሉት አቶ አለማየሁ።
የአቶ አለማየሁ ምክንያት እንዳለ ሆኖ ሌሎች የተረሱ ግን ዋነኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያቶች አሉ። ከአገሪቱ በሕገ ወጥ መንገድ በሙስና በተዘፈቁ ባለስልጣናት እና አቀባባይ ነጋዴዎችየሚሸሸው ገንዘብ ጉዳይ ምነው ተረሳ? ከአራት አመታት በፊት ከኢትዮጵያ ‘ግሎባል ፋይናንስ ኢንተግሪቲ” የተሰኘው ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም ባወጣው ዘገባ ከኢትዮጵያ በአስር ዓመታት ውስጥ ብቻ በሕገ ወጥ መንገድ 16.5 ቢልዮን ዶላር ከአገር መውጣቱን መገለፁ ይታወቃል።
ከእዚህ በተጨማሪ ስርዓቱ ስልጣኑን ለመጠበቅ የሚያወጣው ወጪ ለምሳሌ የተቃዋሚዎችን የመረጃ መረብ ለመስበር በሚልዮን የሚቆጠር ዶላር ለአንድ የጣልያን ኩባንያ መከፈሉን ከሰማን ገና ወራት ማስቆጠራችን ይታወሳል።ከእዚህ በተጨማሪ ለጎጥ ድርጅቶች አመታዊ በዓል እየተባለ የሚደገሰው ድግስ በሚልዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ የሚያወጣ ውስኪ እና ሌሎች የቅንጦት እቃዎች ግዥዎች መፈፀማቸውን አንርሳ።ከእዚህ በፊት ለህወሃት፣ለኦሕደድ ሰሞኑን ደግሞ ለብአዴን ተብሎ የወጣው ገንዘብ በእራሱ ስንት ሆስፒታሎችን፣ለስንት ዜጎቻችንን የስራ ዕድል በፈጠረ እና ይልቁንስ በአሁኑ ጊዜ በረሃብ የሚሰቃዩትን ስንት ወገኖቻችንን በታደገ ነበር።
ስለሆነም ለውጭ ምንዛሪው እጥረት ዋነኛ ምክንያቱ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እንደሚሉት አይደለም።የዶ/ር አብርሀምን ንግግር ነገ አቶ ሃይለማርያም ሲደግሙት ለመስማት ተዘጋጅተናል።እውነታውን ግን ከመናገር እና ለኢትዮጵያ ህዝብም ከመግለፅ ወደኃላ ማለት የለብንም።ምክንያት ያለፈ ስህተትን አይሸፍንምና።

የአቶ አብርሃም ተከስተን ገለጣ ኬንያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ድረ-ገፅ ላይ ለማንበብ ይህንንበመጫን ይመልከቱ።

ጉዳያችን GUDAYACHN
ጥቅምት 25/2008 ዓም (November 5/2015)
www.gudayachn.com

The post መንግስት ”ለውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያቱ እድገቱ ነው” በሚል አዲስ የማምለጫ ምክንያት እየደረደረ ነው; እውን እድገት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ያመጣል? appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ለመንፈስ ጭንቀት

$
0
0

woman-exercise-back-photo-475x357-jsub-5287321_476x357
‹‹ለመንፈስ ጭንቀት መድኃኒት ከመጠቀም ይልቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ለአንዳንድ ህመምተኞች የተሻለ ውጤት ሊያስገኝ እንደሚችል›› ዘ ሃርቫርድ ሜንታል ሄልዝ ሌተር ተናግሯል፡፡ በሶስት ቡድን ለተከፈሉ በከባድ የመንፈስ ጭንቀት ለተያዙ 50 ሰዎች ለ4 ወር የሚቆይ የተለያየ ህክምና ተሰጣቸው፡፡ በመጀመሪያው ቡድን ውስጥ ለሚገኙት ጭንቀት የሚያስታግስ መድኃኒት ተሰጣቸው፡፡ በሁለተኛው ቡድን ውስጥ የሚገኙት የአካል በቃት እንቅስቃሴ ብቻ እንዲሰሩ ተደረገ፡፡ በሶስተኛው ቡድን ውስጥ የሚገኙት ደግሞ ሁለቱንም የህክምና ዘዴ እንዲጠቀሙ ተደረገ፡፡ ከአራት ወር በኋላ ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑት በሶስቱም ቡድን ውስጥ የሚገኙ ህመምተኞች ‹‹የነበረባቸው ከባድ የመንፈስ ጭንቀት ለቅቋቸዋል፡፡›› በማለት ሂልዝ ሌተር ተናግሯል፡፡ ይሁን እንጂ ለስድስት ወራት በተደረገው ክትትል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲሰሩ የተደረጉት ህመምተኞች ‹‹በስሜትም ሆነ በአካል በተሻለ ሁኔታ ላይ የተገኙ ሲሆን በበሽታው እንደገና የመጠቃት እድላቸው ስምንት በመቶ ብቻ ሆኖ ተገኝቷል፡፡›› ከዚህ ጋር ሲነፃፀር መድኃኒት እንዲወስዱ የተደረጉትና መድኃኒት እየወሰዱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲሰሩ የተደረጉት ህመምተኞች በበሽታው እንደገና የመጠቃት እድላቸው 38 እና 31 በመቶ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ከልክ ያለፈ ውፍረትና ካንሰር

የለንደኑ ዘ ታይምስ መጽሔት እንደዘገበው፤ ‹‹በምዕራቡ ዓለም ለማያጨሱ ሰዎች ዋነኛው ሲወገድ የሚችል የካንሰር ምክንያት ውፍረት ነው፡፡›› ለሃምሳ ዓመታት የተደረጉ ጥናቶች ወፍራም ከሆኑ ክብደት መቀነስን ጨምሮ የአኗኗር ለውጥ ማድረግ አጫሽ ላልሆኑ ሰዎች በካንሰር የመያዝን ዕድል በግማሽ እንደሚቀንስ አመልክቷል፡፡ ‹‹አጫሽ ካልሆንክ የሚያሳስቡህ ሁለት ነገሮች ውፍረትና የሆድ ዕቃና የማህፀን ካንሰር መንስኤ የሆኑት ቫይረሶች ናቸው›› ይላሉ የብሪታኒያ ካንሰር ምርምር ተቋም ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ጁልያን ፔቶ፡፡ ‹‹የአመጋገብ ቁጥጥር በተደረገባቸው እንስሳት ላይ የተደረጉ ሙከራዎች ለካንሰር የመጋለጥ ዕድል በእጅጉ ቀንሶ መገኘቱን አመልክተዋል፡፡›› በህክምና መመዘኛዎች መሰረት አንድ ሰው ወፍራም ነው የሚባለው ለዕድሜው፣ ለይታው፣ ለቁመቱና ለቁመናው ትክክል ነው ተብሎ ከሚታሰበው ሰውነት ክብደት 20 በመቶ በልጦ ሲገኝ ነው፡፡

The post Health: የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ለመንፈስ ጭንቀት appeared first on Zehabesha Amharic.

Health: የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን በዶሮ ሾርባ

$
0
0

Asthma
‹‹የዶሮ ሥጋ፣ እንደ ብዙዎቹ የፕሮቲን ምግቦች ሲሶቴይን የተባለ ተፈጥሯዊ አሚኖ አሲድ አለው፡፡ ሥጋው በሚቀቀልበት ጊዜ ይህ አሚኖ አሲድ ይወጣል፡፡ ሲሶቴይን ዶክተሮች በብሮንካይትስና በሌሎች የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ለተያዙት ሰዎች ከሚያዙት አሴትልሲስቴይን ከተባለው መድኃኒት ጋር በጣም ይመሳሰላል፡፡ በመሆኑም የዶሮ ሾርባ እንደ ጉንፋን ላሉት የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች ይጠቅማል›› ሲል ፉድ፣ ዩር ሚሩክል ሜዲሲን የተባለው መጽሐፍ አስታወቀ፡፡

ቀደም ባሉት ዓመታት ከዶሮ ላባና ቆዳ ይዘጋጅ የነበረው ይህ መድኃኒት በአፍንጫ፣ በጉሮሮና በሣንባ ውስጥ የተጠራቀመውን ንፍጥ የማቅጠንና ወደ ውጭ እንዲፈርስ የማድረግ ችሎታ አለው፡፡ ሾርባው የተዘጉ የመተንፈሻ አካላትን የመክፈት ኃይሉ እንዲጨምር ነጭ ሽንኩርት፣ ቀይ ሽንኩርትና እንደ ሚጥሚጣ የመሳሰሉትን ተኮስ የሚያደርጉ ቅመሞች መጨመሩ ጥሩ እንደሚሆን ዶ/ር ዚመንት ይመክራሉ፡፡

The post Health: የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን በዶሮ ሾርባ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፕሮፌሰር አየለ በክሪ፤ ስለንግሥተ ሳባ አፈ ታሪኮችና ታሪክ ይናገራሉ – Audio

‹‹የፌዴሬሽኑ አመራሮች ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል የገዢው ፓርቲ አባል ናቸው›› አትሌት ከላሊ ንጉሴ አብርሃ

$
0
0

ከላይ ንጉሴ ይባላል፡፡ የረዥም ርቀት እና ማራቶን ሯጭ ሲሆን አሁን የሚገኘው በስደት ቶሮንቶ፣ ካናዳ ውስጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በነበረበት ወቅት ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ያሳለፈውን የህይወት ተሞክሮ በማስመልከት ከኢትዮጵ ዛሬ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፤ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
Niguse
ኢ.ዛ.፡- በቅድሚያ ይህን ቃለመጠይቅ እንድናደርግ ፈቃደኛ በመሆንክ በትዝታ ጋዜጣ ስም እያመሰገንኩ፤ እሰቲ እራስክን በማስተዋወቅ እንጀምር፡፡ የት እንደተወለድክ ፣ ሙያህን እና የአስተዳደር ሁኔታክን ግለፅልኝ
አትሌት ከላሊ፡- ከላይ ንጉሴ እባላለሁ፡፡ የተወለድኩት ራያ ከሚባል አካባቢ ሲሆን ትንሽዬ ገጠር ውስጥ ነው፡፡ እድገቴም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሲሆን እዛው ራያ አካባቢ ነው፡፡ ትምህርቴንም ቢሆን እስከ ሁለተኛ ደረጃ እዛው ነው የጨረስኩት፤ በሙያ ደግሞ የረዥም ርቀት እና የማራቶን ሯጭ ነኝ፡፡

ኢ.ዛ.፡-ትንሽ ስለ ራያ ህዝብ እና አካባቢው ብትነግረኝ?
አትሌት ከላሊ፡- ራያ የሚገኘው በትግራይ ክልል ሲሆን፤ በህዝብ ቁጥር እንዲሁም በመሬት ይዞታው በክልሉ ደረጃ ሰፊ ነው ሊባል ይችላል፡፡ የራያ ህዝብ ዋነኛ መተዳደያው በእርሻ ነው፡፡ ምንም እንኳን ሰፋ ያለ ይዞታ ቢኖረውም ህዝቡ ግን ከፍተኛ የሚባል በደል የደረሰበት ነው፡፡ ራያ በትግራይ ክልል የተካለለ ቢሆንም የተገለለ አካባቢ ይመስላል፡፡ እንደሌሎቹ የትግራይ ግዛቶች የልማት እንቅስቃሴ ተጠቃሚ ሊሆን አልቻለም፡፡

ኢ.ዛ.፡- አካባቢው የልማት ተጠቃሚ አይደለም ስትል ምሳሌ ልትጠቅስልኝ ትችላለክ?

አትሌት ከላሊ፡- ለምሳሌ በከተማ እድገት ብንመለከት ማይጨው የራያ ዋና ከተማ ነው፡፡ እንደዋና ከተማነቱ ይኼ ነው የሚባል መሻሻል ወይም እድገት እንዲሁም ለእድገቱ የሚያስፈልጉ ከመንግስት የሚደረጉ አቅርቦቶች የሉም፡፡ ሌሎች በትግራይ ክልል የሚገኙ አካባቢዎችን ብንመለከት ልዩነቱን መገንዘብ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ለመጥቀስ ያክል አዲግራት ወይም ኡቅሮ የሚባሉ አካባቢዎች በአማካይ አንድ አይነት የህዝብ ቁጥር እና የመሬት ስፋት ይዘው ግን በመሀከላቸው ያለው የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ሰፊ ነው፡፡ አንድ መሰረተ ልማት ብናነሳ እንኳን፣ ህክምናን ብንመለከት በራያ አካባቢ ማይጨው የሚባል ቦታ ላይ አንድ መካከለኛ የሚባል ሆስፒታል ነው የሚገኘው፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ከጀመረ ይኸው አሁን ከ20 አመት በላይ አሳልፏል፤ ራያን በሚያክል አካባቢ አንድ ክሊኒክ ብቻ፣ አስበው ከተለያዩ የራያ ክፍሎች ሰው ታሞ የሚመጣው እዚችው ሀኪም ቤት፣ እዛ ድረስ እስኪደርስ ያለውን እርቀት፣ መንገድ ላይ የሚሞትም አለ፣ እንደዛም ሆኖ ብትደርስ ብዙ ጊዜ ወደሌላ የትግራይ አካባቢዎች ለሚገኝ ሆስፒታል ሪፈር ትደረጋለክ፡፡ የሌሎች አካባቢ እንቅስቃሴዎችን የማየት እድሉን ስላገኘው ከራያ ጋር ሳመዛዝነው ውስጤ ያዝናል፡፡ ይኼም ሳያንስ መንግስት እንዲህ እና እንዲያ እያደረኩ ነው ብሎ በሚዲያ ሲናገር ጉዳዩን ለምናውቀው የሚያሳዝን ነው፡፡

ኢ.ዛ.፡-በቋንቋ ስንመለከት ራያ በሦስት የተከፈለ ነው ብለው የሚናገሩ አሉ ይኸውም የአማርኛ ተናጋሪ፣ የኦሮምኛ እንዲሁም የትግርኛ ተናጋሪ፤ ሦስቱም አንድ ላይ ተጠቃለው ነው ወይስ እንደቋንቋቸው አካባቢያቸውም ይለያያል?

አትሌት ከላሊ፡- ራያን በአጠቃላይ ስንመለከተው በሁለት ልንከፍለው እንችላለን፤ ይኸውም ራያ ቆቦ የሚባለው ወደ አማራ አካባቢ የሚገኘው ሲሆን በአብዛኛው የአማርኛ ተናጋሪ ያለበት ክፍል ሲሆን፤ እኔ ወደምኖርበት አካባቢ ያለው ደግሞ ራያ አዘቦ የሚባለው አካባቢ ሲሆን ትግርኛ፣ አማርኛ እንዲሁም ኦሮምኛም ተናጋሪዎች ያሉበት ነው፡፡ እንዲህ ቢከፋፈሉም ያው እንደ አንድ ክልል ነው የሚታወቁት፡፡

ኢ.ዛ.፡-ወደ አትሌቲክሱ ህይወትክ እንመለስ እና እንዴት ወደ ሩጫው ገባህ?

አትሌት ከላሊ፡- ፕሮፌሽናል የአትሌቲክስ ህይወት የጀመርኩት እዛው ራያ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡ በጊዜው የከፍተኛ ሁለተኛ ተማሪ ነበርኩኝ ጊዜውም ወደ 1999 ዓ.ም. አካባቢ መሆኑ ነው፡፡ በጊዜው ከተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡ ሯጮች በክልሉ በተካሄደው ውድድር ይሳተፉ ነበር፡፡ እኔም የምኖርበትን ወረዳ በመወከል ለመሳተፍ በቃሁ፡፡በጊዜው ጥሩ የሚባል ሰዓት በማስመዝገቤ ከዛን ጊዜ በኋላ በሌሎች ውድድሮችም እንድሳተፍ ተደረኩኝ ማለት ነው፡፡

ኢ.ዛ.፡-እንደሚታወቀው እትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በብዙ የሚቆጠሩ ወጣት አትሌቶችን ታፈራለች፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ ችሎታ ኖሯቸው እንኳን እድሉን አግኝተው ወደ ከፍተኛ መድረኮች ወጥቶ ለመወዳደር በራሱ ትልቅ ፈተና እንደሚሆንባቸው በየጊዘው የሚሰማ ጉዳይ ነው፡፡ ታዲያ አንተም ከእነሱ አንዱ እንደመሆንክ እንዴት እድሉን አገኝተክ ልትወጣ ቻልክ?

አትሌት ከላሊ፡- እርግጥ ነው ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ተግዳሮቶች አሉበት፤ የኔም ጉዳይ ቢሆን እድል ተጨምሮበት እንጂ ሚናልባትም እዛው እቀር ነበር፡፡ ወረዳ ላይ ከተሳተፍኩ በኋላ ሌሎች ውድድሮችም ላይ አመርቂ ውጤት በማስመዝገቤ የትግራይ ክልልን ወክዬ እንድሳተፍ ተደረኩኝ፡፡ ከዛም ወደ አዲስ አዲስ አበባ በመምጣት ትግራይን ወክዬ ተወዳድሬያለሁ፡፡ በይበልጥ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2002/2003 ዓ.ም. ጥሩ ፐርፎርማንስ አሳይቼ ነበር በዚህም የተነሳ ማረሚያ ለሚባል የስፖርት ክለብ ውስጥ ለመሮጥ በቃሁ፡፡ እዛ በነበርኩበትም ወቅት በተለያዩ ውድድሮች ላይ የተሳተፍኩ ሲሆን ይኸውም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ በበርካታ መድረኮች ላይ ለመወዳደር ችያለሁ፡፡

ኢ.ዛ.፡-በተለያዩ ሀገራት የመወዳደር እድል እንዳገኘክ ነግረኸኛል፤ እንዴት ነበር በግልክ ነው ወይስ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመቻችቶልክ ነው?

አትሌት ከላሊ፡- በእርግጥ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው በውድድሩ ላይ እንድንሳተፍ የሚያደርገው፡፡ ይሁን እንጂ የምትወዳደርለትን ክለብ ወይም ሀገርህን አልያም ደግሞ በግልቅ መሳተፍ ትችላለክ፡፡ ዋናው ነገር በቅርብ ጊዜያት የምታስመዘግበው ውጤት ይወስነዋል፡፡ ለምሳሌ በረዢም ርቀቶች ላይ ስትሳተፍ ቢያንስ ጥሩ ሰዓት እና ከ1-7 ወይም እስከ 8ኛ ደረጃ ላይ የሚወጡት ሯጮች ቅድሚያ ያገኛሉ፡፡ ሀገር እንዲወክሉ ይደረጋል ማለት ነው፡፡

ኢ.ዛ.፡-ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በተያያዘ በርካታ መረጃዎችን እንሰማለን፤ ይኸውም እኩል የሆነ እድል ለሯጮች አይሰጥም፣ በሙስና የተጨማለቀ ነው፣ በብሔር የተከፋፈለ ነው፣ ሯጮች በሀገር ውስጥ እድል ሳይሰጣቸው ለሌላ ሀግር እየሮጡ ውጤት እያመጡ ነው እና የመሳሰሉ ቅሬታዎችን፤ ከዚህ አንፃር አንተስ የታዘብከው ወይም የደረሰብክ ነገር አለ?

አትሌት ከላሊ፡- በቅድሚያ የሰማኸው መረጃ ትክክል መሆኑን እኔው እራሴ ላረጋግጥልክ እወዳለው፡፡ ያው በየጊዜው የምንመለከተው ጉዳይ ነው፡፡ እንደው በቅርቡ እዛ በነበርኩበት ጊዜ የተከሰተውን አንድ ጉዳይ ብነግርክ፤ የሴቶች የረጅም ሩጫ ተካሂዶ ነበር፡፡ ታዲያ ውጤት ያመጡትን ይመርጣሉ ብለን እየጠበቅን 2ኛ ነው 3ኛ የወጣችውን ጥለው ውድድሩ ላይ አቋርጣ የወጣችውን ተወዳዳሪ መርጠዋል፡፡ እሷም ሄዳ ውጤት አላመጣችም በውድድሩ 24ኛ ነበር የወጣችው፡፡ ይህ እንግዲህ እኔ በቅርቡ የታዘብኩትን ነው የነገርኩህ፡፡ ይህ የሚያሳየው ፌዴሬሽኑ ምን ያክል በዝምድና፣ በሙስና፣ በብሔር እና በፖለቲካ አቋምህ እንደሚወሰን ነው፡፡ በዚህ ምክንያት አትሌቲክሱ አያድግም፣ ለታዳጊዎች እድል አይሰጡም ከዚህ የተነሳ ይኸው የድሮ ዝናውን እያጣ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ ብዙ ችግር አለበት፤ እውነተኛ ነገር እየተሰራ አይደለም፡፡ የመወዳደር አቅም እና ችሎታ እያለክ፣ ውድድር አግኝተክ፣ ኢንቪቴሽን ወረቀት መጥቶልክ እንኳን በውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ ብር ጉቦ መስጠት አለብክ፡፡ ይህን ደግሞ ማድረግ የሚችሉት ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡

ኢ.ዛ.፡-እንደገለፅክልኝ ይህ የሚያሳየው በፌዴሬሽኑ ውስጥ ከፍተኛ የሚባል ችግር እንዳለ ነው፡፡ ታዲያ አትሌቶቹስ ይኼን እያዩ እንደው ዝም ብለው ያልፋሉ፤ ተሰባስበው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አለ ከዚህ አንፃር?

አትሌት ከላሊ፡- የአትሌቶች ማህበር የተቋቋመ አለ፡፡ ሁሉንም አትሌቶች ያቀፈ ማለት ነው፡፡ ሰብሳቢዎቹም ትላልቅ የሚባሉ አትሌቶች ናቸው፡፡ በየጊዜው ስብሰባ ይደረጋል፣ ችግሮች ይነሳሉ፣ መፍትሄ ተብሎ ይወራል ነገር ግን እስካሁን ምንም ሊፈጥሩ አልቻሉም፡፡ አሁንም ችግሮቹ እንዳሉ ናቸው፡፡

ኢ.ዛ.፡-ፌዴሬሽኑ ከገዢው ፓርቲ ጋር በተያያዘ ባለው የፖለቲካ ትስስር ሲታማ ይሰማል፡፡ ለምሳሌ የቴክኒካል ዳይሬክተሩ አቶ ዱቤ ጁሎ የኢህአዴግ አባል መሆናቸው በራሱ ትልቅ ጥያቄ ያስነሳ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንተ ምን አስተያየት አለህ?

አትሌት ከላሊ፡- እውነቱን ለመናገር ዳይሬክተሩ ብቻ ሳይሆኑ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል የገዢው ፓርቲ አባል ናቸው፡፡ ምንመ እንኳን ፌዴሬሽኑ ከፖለቲካ ገለልተኛ አካል በመሆን መስራት ሲገባው አሁን ባለው ሁኔታ ግን ይህ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ከዚህም የተነሳ ማናቸውንም ጥያቄዎችን ማንሳትም ሆነ ወደ በላይ አካል ማቅረብ በራሱ ከባድ ነው፡፡ አንደኛ ሁሉም የተሳሰሩ ስለሆኑ ምላሽ አታገኝም፤ ድምፄን አሰማለሁ ያልክም እንደሆነ የፖለቲካ ታፔላ ተለጥፎብክ ሌላ ችግር ይደርስብካል፡፡

ኢ.ዛ.፡-አንተ እንደ አንድ አትሌት ለዚህ መፍትሄው ምንድነው ትላለክ?
አትሌት ከላሊ፡- በርግጥ እኔ ፖለቲካኛ ስላልሆንኩና ብዙ ፖለቲካ ስላማላውቅ እንዲህ ነው ብዬ ስፊ ትንተና ልሰጥህ አልችልም፡፡ ግን እርግጠኛ ሆኜ የምነግርክ መንግስት ከአትሌቲክሱ ውስጥ ጣልቃገብነት ማቆም አለበት፡፡ አጠቃላይ የስርዓት ለውጥ ካልመጣ በፌዴሬሽኑ አካባቢ ብቻውን ለውጥ ይመጣል ወይ የሚለው ነግር ለመመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡ ግን በአትሌቲክስም ይሁን በሌላው የህይወት መስክ ወጣቱም፤ የሚቀጥለው ትውልድም ይኼን ስርዓት በርትቶ መታገል አለበት ነው የምለው፡፡ ሌላ ምንም አማራጭ የለኝም፡፡

ኢ.ዛ.፡-በመጨረሻ እንደው ሌላ የምትጨምረው ወይም የምታስተላልፈው መልዕክት ካለህ?
አትሌት ከላሊ፡- በይበልጥ ወጣቱ የተወሰደበትን የእኩልነት እና የነፃነት መብቱን፣ ለእውነት እና ለማንነቱ መታገል አለበት፡፡ ሰው በድህነቱ በብሔሩ ወይም በፖለቲካ አስተሳሰቡ ሲጨፈጨፍ ዝም ብሎ መመልከት ሳይሆን አንድ ሆኖ መታገል አለበት፡፡ ሁሉም በሚችለው አቅሙ ማለት ነው፡፡

ኢ.ዛ.፡-ስለሰጠሀን ቃለምልልስ እናመሰግናለን፡፡

አትሌት ከላሊ፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡

The post ‹‹የፌዴሬሽኑ አመራሮች ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል የገዢው ፓርቲ አባል ናቸው›› አትሌት ከላሊ ንጉሴ አብርሃ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live