Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የባራክ ኦባማና የወይዘሮ አዜብ መስፍን ታሪካዊ ግንኙነት

$
0
0

Azeb  Mesfin, wife of Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi

ይሄይስ አእምሮ

 

ጊዜው ትንሽ ራቅ ስለሚል ወሩንም ሆነ ዓመቱን አሁን በትክክል አላስታውስም፡፡ ያንን ጊዜ ዛሬ ጧት ያስታወሰኝ የዚያን ጊዜው አንዱ ልጄ የተናገረውን ነገር በጣም በተራራቀ ነገር ግን በጣም በሚመሳሰል አጋጣሚ ታናሽ ወንድሙ በሚያስደንቅና በሚያስገርም ሁኔታ በዚህች ዕለት ስለደገመው ነው፡፡ ታሪክ ለምን እንደማይሞት ዛሬ በሚገባ ተማርኩ – ከገዛ ልጄ፤ ታሪክ ራሱን እንደሚደግምም ጭምር፡፡ ለካንስ የሊቢያ እውነተኛ ባንዲራ ከ42 ዓመታት በኋላ የተነሣችው ለዚህ ኖሯል? እንግዲያውስ የኛም ብርቅዬና እየተገለባበጠች ለብዙ ሀገሮች ባንዲራነት የዋለች ሰንደቅ ዓላማችን እንደሞተች አትቀርም ማለት ነው፡፡

ሶሎሞን ተካልኝ ጎራ በቀየረና ወደ ወያኔ ገባ በተባለ ወቅት ዜናው በትኩስነት እየተስተጋባ ሳለ ያኔ ዕድሜው በአሥራዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የነበረው ልጄ “ቴዲ አፍሮም እንዳይደገም” በማለት በፍሬ ሃሳቡ ብቻ ሣይሆን በፖለቲካ ግንዛቤው መዳጎስ በጣም አስገርሞኝ ነበር፡፡ አያችሁ – ታሪክ የሚጽፈው ቢጠፋ እንኳን አይሞትም – ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል ሣይቀር ይተላለፋል፡፡ አባትና እናት እናት እንዲሁም ሌሎች የቤተሰብ አባላት ሲገናኙ የሆድ የሆዳቸውን የሚጫወቱት በአብዛኛው ታሪክ ቀመስ ነው፡፡ ስሆነም ትናንሾቹ የቤተሰብ አባላት ከብበው እኛን ሳይታወቀን የሚኮመኩሙት የኛን ጨዋታ ነው – ያልሰሙና ያልተከታተሉ እየመሰሉ ጭምር፡፡ በዚያም ምክንያት ያለ ውድ በግዳቸው እኛ የምንጠላውን ይጠላሉ፤ እኛ የምንወደውን ይወዳሉ፡፡ በልጆች አስተዳደግ ላይ የቤተሰብ ተፅዕኖ ቀላል አይደለም፡፡ የዚያኔው ሕጻን ልጄ የዛሬው … ጎረምሣ ከቤተሰቡ ሲቀስም ያደገውን ወያኔን የመጥላትና ተቃዋሚን ያለመጥላት ጠባይ የገለጠው “ቴዲ አፍሮም እንዳይደገም” በሚል ነበር – አሳስቦት፡፡ ከንግግሩ ጀርባ የሶሎሞንን ወያኔነት እንዳልወደደለት በተለይ እኔ አባቱ አሳምሮ ይገባኛል፡፡ በወያኔው ሸፍጠኝነት በተጨናገፈው የ1997ዓ.ም ብሔራዊ የቴሌቪዥን የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት አንድ ዓመት አካባቢ ዕድሜ የነበረው አንዱ ሌላው ልጄ ደግሞ የቅንጅት ተራ ሲደርስ ፊቱ ፋሲካ እየመሰለና ሁለት ጣቶቹን ለማሳየት እየፈለገ ግና የቀለበት ጣቱ እያስቸገረችው ጭናችን ላይ ፊጥ ብሎ እንዴት በደስታ ይፍነከነክ እንደነበር ቤተሰቤ በሙሉ አሁን ድረስ ያስታውሰዋል፡፡ መንገድ ላይ ባለመውጣቱ ግን ጣቱ ሳይቆረጥና እንደታዳጊ ወጣት ነቢዩ ደረቱና ግንባሩ በአግዓዚ ቅልብ የወያኔ ጦር ሳይበሳሱ እስካሁን በሕይወት አለ፡፡ አሁን የማይታወሰኝ  የመግቢያ ሙዚቃ ገና ከመጀመሩ ምልክቱን እያሳዬ እንዲያ ይቅበጠበጥና ይደሰት የነበረው ምኑን ዐውቆትና ምንስ ገብቶት እንደነበር  ሲያስቡት በርግጥም ይገርማል፡፡ ምናልባት በደም ተላልፎበት? አዎ፣ ቤተሰብ እስካልጠፋ ሀገርም አትጠፋም!! ሃሌ ሉያ! ኢትዮጵያም ትነሣለች፡፡ አልሃምዱሊላህ – የሃይማኖትና የዘር ልዩነት የማይደረግባት ኢትዮጵያ ከወያኔ ከርሠ መቃብር ላይ ታብባለች – ብዙ ተምረናልና!

በነገራችን ላይ በየብሔር ብሔረሰቡ ቤተሰቦች ውስጥ በምናብ እየገባን ብንቃኝ አንዱ ላንዱ ያለውን ጥላቻና ውዴታ ልጆች ተሰባስበው በሚጫወቱበት ወቅት በሚወራወሯቸው የቀልድና የምር ቃላት በደንብ ልንረዳ እንችላለን፡፡ በአንፃራዊ ሁኔታ ይህ ዓይነቱ ክስተት የሁሉ እናትና ማረፊያ በሆነችው በእምዬ አዲስ አበባ ቀለል የሚል ቢመስልም ለወያኔው የዘር ከፋፋይ አገዛዝ ምሥጋን ይንሳውና በሌሎች አካባቢዎችና አነስተኛ ከተሞች ግን የጎላ እንደሚሆን መገመት አይከብድም፡፡

አንድ ወቅት እዚሁ አዲስ አበባ የሆነውን አሣዛኝ ነገር ልንገራችሁ፡፡ አንድ ልጅ አባቱ ይታሰርበታል፡፡ የሁለት ተኩል ወይ ግፋ ቢል የሦስት ዓመት ልጅ ቢሆን ነው ያኔ፡፡ ከቤተሰብ ጋር አባቱን ሊጠይቅ አሁን የአፍሪካ ኅብረት ወደተገነባበት የዱሮው ከርቸሌ ይሄዳል፡፡ አባቱ እስኪመጣ ታዲያ ሕጻኑ ከአንድ የእሥር ቤቱ ጠባቂ የፌዴራል ፖሊስ ጋር ጨዋታ ይይዛል – እነሱ በወያኔያዊ ተፈጥሯቸው ዐውሬ ቢሆኑም ደፍሮ የተጠጋቸውን ሕጻን መቼም ጨክነው ማባረር መጥፎ ግምት ያሰጣቸዋልና ያ ፌዴራል ፊት አልነሳውም፡፡ የሕጻን ነገር ሆነና ነገሩ ወታደሩን “እሹን ሽጠኝ” ይለዋል – ያነገበውን ክላሽንኮቭ፡፡ “ዋይ፣ ምን ይገበረልካ ማሙሼ ?”ብሎ ቢጠይቀው ሚስቶው ቋንቋ በደንብ የገባው የሚመስለው ሕጻን “ኢሃዲግን ልገልበት!” ይለዋል፡፡ አይ ሕጻንነት! ይሉኝታ የለ፤ ምሥጢር የለ፤ ሀፍረትና ፍርሀት የለ – ግልጽነት ብቻ፡፡ ወታደሩ በምንተፍረታዊ ሣቅ ቢሸፍነውም መደንገጡ ግን ያስታውቅ ነበር፡፡ እሥረኛ ሊጠይቅ የመጣው የሕጻኑ ቤተሰብም ክፉኛ ደነገጠ – በርግጥም ለጠርጣራና ጥላውን እንኳን ለማያምን የከሃዲዎችና የወሮበሎች መንግሥት አንድን ቤተሰብ በሽብርተኝነት ወንጀል ለመክሰስ ከዚህ በላይ ማስረጃ የሚያስፈልገው አይመስለኝም፤ ደግነቱ ጊዜው ረዘም ስለሚል እንደምንም “የሕጻን ነገር” ተብሎ ታለፈ እንጂ “በኢቴጲያ ሁዝቮች ፈªድ ለፀደቀ ህገ መንግሥቱን በኃይሊ ለመናድ” ያ ሕጻን ያደረገው ሙከራ ቀላል አልነበረም፡፡ አለበለዚያ “ይህ ልጅ ከቤቱ እንደዚህ የመሰለ ታሪክ ባይሰማ ኖሮ እንዲህ ያለ የከረረና የመረረ ጥላቻ በዴሞክራሲያዊ መንግሥታችን ላይ ሊኖረው አይችልም ነበር” በሚል ቤተሰቡ ለእሥራትና ከዚያም ለባሰ የከፋ ችግር መዳረጋቸው አይቀርም ነበር – ወያኔን እያወቅነው! “አስበሃል” በሚል የትም የሌለ የወንጀል ዓይነት ይቅርና “ልታስብ ማሰብህን የደረስንብህ መሆናችንን ገልጸን ብናስጠነቅቅህም እምቢ ብለሃልና ፀረ ኢህወደግ ዕላማህን ከማሰብህ በፊት ለማሰብ ማሰብህን ልናስቆምህ ተገደናል” ብሎ በዓለም ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ “ወንጀል” አስሮ የሚያሰቃይና ደብዛ የሚያጠፋ የማፊያ ቡድን ያለን መሆናችንን መቼም አንዘነጋም፡፡ እናም ይህ ሕጻን ለቤተሰቡ ጠንቅ ሊሆን ሲችል ፈጣሪ ታደጋቸው፡፡ ከፍላት የሚያወጣው አምላከ ኢትዮጵያ እኛንም ከነዚህ ጉግማንጉጎች በቶሎ ነፃ ያውጣን፡፡

ልጅ አስተዳደግ በማኅበረሰብ ቀረፃ ላይ ወሳኝ ሚና የሚጫወት መሆኑ የሚነገረው እንግዲህ ለዚህ ነው፡፡ የፍልስጥኤምና የእስራኤል ልጆች ሒሳብ ሲማሩ “በአንድ ጥይት 50 እስራኤላውያንን/ፍልስጥኤማውንን ብትገድል በአሥር ጥይት ስንት እስራኤላውያንን/ፍልስጥኤማውያንን ትገድላለህ?” እየተባሉ እንደሚያድጉና ንጹሓንና አፍቃሪያን ሊሆኑ የሚጠበቅባቸውን ታዳጊ እምቦቀቅላዎች እየመረዙ እንደሚያሳድጉ እንሰማለን፤ ይህ ዓይነቱ ፀያፍና ኢ-ሰብኣዊ ነገር በአንድ ወይ በሁለት ሥፍራዎች የተወሰነ ሣይሆን በብዙ ቦታዎች እንደሚተገበር መገመት አይቸግርም፡፡ ተጠያቂዎቹ እንግዲህ ክፉና ደግን ለይተዋል የተባሉት ግን ወደ ክፋት ዓለም ገብተው በግል ቂም በቀልና ጥላቻ በመታወር መላ ኃይላቸውንና መላ ዕድሜያቸውን ለጠብና ለአምበጓሮ የተሠለፉ ዐዋቂ ተብየዎች መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡ ዐዋቂ ማለት አስተዋይና ብልኅ ማለት ሊሆን ሲገባው በተቃራኒው መሆኑ ከማስገረም አልፎ ያሳዝናል፡፡ ክርስቶስ “ሕጻናት ወደኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው”፣ “ወደ ሕጻንነት ካልተመለሳችሁ መንግሥተ ሰማይን አትወርሱም” ወዘተ. የሚለን ትልቅ ስንሆን የሚቆራኘን ሰይጣናዊ መንፈስ በሕጻንነት ወቅት ይኖረብናል ተብሎ ስለማይጠበቅ ያኔ እውነተኛ የሰው ልጆች መሆናችንን ለማሳየት ይመስለኛል፡፡ እርግጥ ነው – ትርጉሙ እውናዊ ሣይሆን ፍካሬያዊ ነው፡፡ እናም ሁላችንም ሕጻናት እንሁንና የጋራ ኢትዮጵያችንን እንደገና እንገንባት፡፡ ሕጻናት ቂም የላቸውም፤ ሕጻናት ስላለፈ ነገር እያነሱ እንደትልቆች አይጨቃጨቁም፤ አይወራከቡም፡፡ ለሕጻናት ትናንትናና ነገ ብዙም ዋጋ የላቸውም፡፡ ለሕጻናት ትልቅ ዋጋ ያላት ዛሬ ናት፡፡ ሕጻናት እጃቸው የገባችን ማንኛዋንም ዕድል በከንቱ አያባክኑም፡፡ ጠቀማቸውም ጎዳቸውም በጃቸው ያለ ጊዜ ወርቃቸው ነው፡፡

ከተነሣሁበት ጉዳይ በተገናኘ መልኩ ለማኮብኮብ ያህል ስለሕጻናት አስተዳደግ ከፍ ሲል በገደምዳሜ ትንሽ ሃሳብ ከሰጠሁ ዘንዳ የ15 ዓመት ዕድሜ ያለው ሌላኛው ልጄ ሰሞኑን የተናገረውን አስደናቂ ነገር ልጠቁምና ጅምሬን ልቋጭ፡፡

የርሱን የቴሌቪዥን ቻናል በኔው ፍላጎት ደፍጥጬበት አለውድ በግዱ የኔን ጣቢያ አብረን እየተመለከትን ነው፡፡ በዚያ ጣቢያ – ጥቂት ቀናትን ቆይቼ ቀደም ሲል ጀምሬው ወደነበረው መጣጥፍ በመምጣቴ ጣቢያውን በትክክል ማስታወስ አልቻልኩም ግን ኢሣት ይመስለኛል – ስለ አሜሪካውያን ፕሬዝደንታዊ የምርጫ ቅስቀሳ በዜና ቀርቦ ሂደቱ እየተዘገበ ነበር፡፡ በዜናው ላይ “በአሜሪካ ህገ መንግሥት ድንጋጌ መሠረት ፕሬዝደንት ኦባማ ለሦስተኛ ዙር መወዳደር ስለማይችሉ ለተመራጩ አዲስ ፕሬዝደንት ሥልጣናቸውን አስረክበው በቀጣዩ ዓመት የፈረንጆቹ ጥር ወር ላይ ቤተ መንግሥቱን  ለቀው ከነቤተሰባቸው ይወጣሉ፡፡” የሚለውን ወሬ እንደሰማን ይህ ልጄ “እሱም እንደ አዜብ እንዳይሆን” አለና እንደዋዛ ወሬ ጣል አደረገ፡፡ እኔም አትኩሮቴ በአብዛኛው ቲቪው ላይ ስለነበር የልጁን አነጋገር ከቁብ አልጣፍኩትም ነበር፡፡ ቢያንስ ለሞራሉ ስል ዝም ብዬ ላልፈው ደግሞ አልወደድኩም፡፡ ለምን እንደዚያ እንዳለ ታዲያ ፊቴን ወደሱ ሳላዞር እንደዋዛ ጠየቅሁት፡፡ “የመለስ ሚስት አዜብ ለኃይለ ማርያም ቤተ መንግሥቱን አላስረክብም ብላ በግድ አይደል እንዴ የወጣችው?” ሲለኝ ታሪኩ ትዝ አለኝና በራሴ አፈር አልኩ፡፡ ስንትና ስንት የነገር ብልት የማወጣ ሰውዬ “እዚያ ድረስ ሄዶስ አያስበውም” ከሚል በኔ ዘንድ እምብዝም ያልተለመደ አስተሳሰብ የልጄን የፖለቲካ ንቃት መናቄን ስገነዘብ ለራሴውና በውስጤ በገዛ ልጄ ፊት የመቅለል ስሜት ተሰማኝ፡፡ በርግጥም ይህ ልጅ በ13 ዓመት ዕድሜው የተከናወነን ሀገራዊ ጉዳይ በደንብ ያውቅ ነበር ማለት ነው – ይህም ብቻ አይደለም፡፡ በ12 እና በ15 ዓመት ዕድሜው የተከሰቱ ሁለት የተለያዩ ፖለቲካዊ ኹነቶችን በማገናዘብ ከዴሞክራሲያውያን ቅቡልነት ያለው ልማድ ተነስቶ ኢ-ዴሞክራሲያውንን በምፀት ዱላ መምታት ይችላል ማለትም ነው፡፡ ሲገባኝና “ስባንን” ብዙም እንዳይታዘበኝ ብዬ ምክንያት ቢጤ ሰጠሁትና ጥቂት አዋራሁት፤ እርሱ ለቀልድ ያህል ቢናገረውም የአሜሪካ ህግ እንደኢትዮጵያ በአምባገነኖች መዳፍ ሥር የወደቀ ሳይሆን በህገ መንግሥት አስፈጻሚ መንግሥታዊ መዋቅሮች በአግባቡ የተያዘ በመሆኑ ማንም ከህጉ ውልፊት እንደማይል በእግረ መንገድ ነግሬው – እንደሚውቀው እየነገረኝም ጭምር – ወደሌላ ርዕስ ገባን፡፡

ኦ! ረስቼው፡፡ “ዐይን እንዳይገባብኝ” እንጂ ስለዚሁ ልጅ አንድ ሌላ ሰሞነኛ አጋጣሚም አለ፡፡ የወያኔ ሰንደቅ ዓላማ የሚከበርበት ዕለት ተማሪዎች ሁሉ በየት/ቤታቸው እንዲገኙ ታዘው ነበር፡፡ ይህ የኔው ልጅ እንደወትሮው ቁርሱን በጧት በልቶ እንዲሄድ ስቀሰቅሰው “አልሄድም” ይላል፡፡ ያስገረመኝ አለመሄዱ አይደለም፡፡ “ሰንደቅ ዓላማ ያለን ይመስል…” በማለት የሰጠው ከርሱ ያልጠበቅሁት መልስ ነው በጣም ያስገረመኝ፡፡ ወያኔዎች ጮርቃ ሕጻናትን አለርህራሄ የሚጨፈጭፉት ለካንስ “እባብ የወጣበትን ጉድጓድ አይረሳም” ከሚለው ነባር ብሂል በመነሣት “እነሱም ሲያድጉ የወላጆቻውን የኢትዮጵያዊነት ስሜትና ወኔ ይቀሰቅሳሉ፤ ትልልቅ ሲሆኑ የጥንቷን ትምክህተኛ ኢትዮጵያ አፍርሰን በምትኳ በአዲስ መልክ የሠራናትን አዲሲቷን የብሔር/ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሀገር ኢትዮጵያን ገልብጠው የዱሮውን ሥርዓት ያመጡብናል”  ከሚል ፍራቻ መሆን አለበት፡፡ ሞኞች ናቸው፡፡ የኔ ልጅ እንዲህ ከሆነ – ስሙን ለጊዜው “አልፎአይቼው” ልበለውና –  ብዙ አልፎአይቼዎች በየቤቱ እንዳሉ እረዳለሁና የነገይቷ ኢትዮጵያ መፃዒ ሕይወት ለኔ እጅግ ብሩኅ ነው፡፡ አልደብቃችሁም – በፊት በፊት እፈራ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ተስፋየ እየለመለመ መጥቷል፡፡ የአንዳርጋቸው ጽጌና መሰል ቆራጥ ኢትዮጵያውያን ደም የውሻ ደም ሆኖ አይቀርም፡፡ አንዲ ለእምዬ ኢትዮጵያ የተሰዋ በበግ ያልተተካ ይሥሃቅ ነው፤ አንዲ አቤል በቀናተኛ ወንደሙ ቃየል መለስ የተገደለ ሰማዕት ነው፤ ግዴለም አልሞተም ቢባልም ስቃዩ ከሞት በላይ ነውና ሰማዕት ነው፡፡

ይገርማችኋል የዛሬ ልጆች በጣም የረቀቁ ናቸው፡፡ ጥቂቶቹም ቢሆኑ ለቴክኖሎጂው ቅርበት ስላላቸው ይመስላል ከኛ ከነባር ገትጋታ ኢትዮጵያውያን በተለዬ በአንዳንድ መልካም ባሕርያት እየታነጹ መምጣታቸው ይሰማኛል፡- ለምሳሌ እንደኛ ዘረኞች አይደሉም፤ ስለዘር ሐረግ ሲነሣ ብዙዎቹ አይገባቸውም፤ ሰውን በሰውነቱ ነው ማየት የሚፈልጉት፡፡ ስግብግብነት ብዙም አላይባቸውም – እየተሻሙና እየተካፈሉ ሲበሉ እታዘባለሁ፤ ሲጋቡ ወያኔ በቀየሰላቸው የዘር መሥፈርት አጥንትና ደም እያነፈነፉ አይደለም፤ … ብቻ አለ አይደል … ብዙ ደስ የሚሉ ነገሮች አሏቸው – ወያኔያዊ ተፅዕኖዎች የሉም ማለቴ ግን አይደለም፡- ይሁንና እነዚህ ከ25 ለሚበልጡ ዓመታት የተዘሩ የወያኔ ተፅዕኖዎች በጊዜ ሂደት ተሸናፊ መሆናቸውን መመስከር አይቸግረኝም፡፡

ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት በሕጻናት ተተኪዎቻችን ትልቅ ተስፋ አለን ማለት ነው – ከወያኔ የማያቋርጥ ጥቃት ግን እንታደጋቸው፤ የምንችል ከሆነና ራሳችንን መለወጥ የማይከብደን ከሆን በቤት ውስጥ በጥሩ ጠባይ እንቅረጻቸው፡፡ እንከታተላቸውና ከጥፋት እንታደጋቸው፡፡ ከወያኔ የትውልድ ማምከን ዕኩይ ተግባር የሚያመልጡ ልጆችን በወቅቱ እንድረስላቸውና ጭራሽ ጠፍተን እንዳንቀር ከዘንዶው አፍ እናድናቸው፡፡ በትምህርቱ ረገድም ቢሆን በቤት ውስጥ እናግዛቸው፡፡ ትምህርቱን ከቤት የማለፊያ ካርዱን ከትምህርት ቤት፡፡ “ኑሮ በዘዴ ጦም በኩዳዴ” ነው ወገኖቼ፡፡ አዎ፣ “ቀን እስኪያልፍ ያባትህ ባሪያ ይግዛህ”ስ እንል የለም? ምን እናርግ?

ከኛ ከድኩማኖቹ የተሻሉ ልጆችን ማፍራት አለመቻላችን ነበር የእስካሁኑ ችግራችን፡፡ እንደኛው አሲድና ቀናተኛ እየተካን ከድጥ ወደማጥ የመዘፈቅ ባህል ነበር ለብዙ ዘመናት ያዳከረን አባዜያችን፡፡ እንደኛው በሥልጣን አራራና ባልተገባ መንገድ ሀብት የማጋበስ ሱስ የተጠመዱ ልጆችን ማፍራት ነበር የዘመናት ዋና ተግባራችን፡፡ አባት ልጁን፣ ልጅ አባቱን በሥልጣን ሽሚያ ምክንያት የሚገድልና ቆንጥር ለቆንጥር የሚያሳድድ እርጉም ሽንት የመፈልፈል አባዜ ነበር ተጠናውቶን የቆየው፡፡ በመተትና በሟርት በመጠላለፍ አንዱ የሌላውን ውድቀት የሚያፋጥንበት ባህላዊ እሥር ቤት ውስጥ መዘፈቃችን ነበር ልንቀርፈው ያልተቻለን የዘላለም ራስ ምታታችን፡፡ ሀገርን የሚያቀጭጭና ከዕድገት ይልቅ ውድመትን የሚያስፋፋ የከንቱ ፉክክር እሥረኞች መሆናችን ነበር ትልቁ ወረርሽኛችን፡፡ አለመተሳሰብንና አለመተዛዘንን የተፈጥሮ ጠባያቸው ያደረጉ እርጉም ሽሎችን ወልዶ ማሳደግ ነበር ለከፋ ጉዳት እየዳረገን የመጣው የትውልድ መርገምታችን፡፡ … ከዚህ አዙሪት የወጡ በሀገራችንም ሆነ በሌላው ዓለም ከሚገኝ ነፃ አስተሳሰብና መልካም የሰው ልጅ አመለካከት በብዙው የሚማሩ ወጣቶችና ጎልማሦች፣ በዴሞክራሲያዊ መንግሥት ሥር ታንጸው የሚያድጉ ልጆችን ኢትዮጵያ ካገኘች እንደማንኛውም ሀገር በአጭር ጊዜ ውስጥ ያልፍላታል፡፡ ሁሉም በየቤቱ ከክፋትና ከምቀኝነት አባዜ የፀዱ ልጆችን ለማፍራት ቢጥር ቀስ በቀስ እኛ ስንሞትና ቦታ ስንለቅ ደህናው ትውልድ ሀገሪቱን ተረክቦ በጥፋትና በውድመት ወደኋላ ሣይሆን በዕድገትና በሥልጣኔ ወደፊት ያሽቀነጥራታል፡፡ (አንድ ሀብታም ሰው ቢቸግረው አሉ – የጨነቀው እርጉዝ ያገባል (ስትወልድበት ገደል ይገባል) እንደሚበላው መሆኑ ይመስለኛል – ምቀኝነት ከጤፍ እንደሚመጣ ጭንቅላቱ ውስጥ ማን እንደተከለበት አላውቅም አንድያ ልጁን እንጀራ ሳይበላ እንደጣሊያኖች በፓስታና በመኮረኒ፣ በላዛኛና በአኞሎ ዲቢቴሎ አቀማጥሎ ከሀበሻ ምግብ በማራቅ አሳደገው አሉ፡፡ ሰውዬው ያለፈለት ማይም ቢጤ ነውና ልጁን በገዛ ሀገሩ አዲስ አበባ ላይ ከእንግሊዝኛ በስተቀር ሌላ ቋንቋ እንዳይችል አድርጎም ነው ያሳደገው፡፡ አሃ! ለካንስ ኢትዮጵያን ለመምራት በፕሬዝዳንትነት ቦታ እወዳደራለሁ ያለው ኃይሌ ገ/ሥላሤም ልጁን ያስተማረው “አማርኛ መናገርና ድንጋይ መወርወር ያስቀጣል” ብለው ማስታወቂያ ከለጠፉ ዘመናዊ ት/ቤቶች በአንደኛው በመሆኑ ሞልቃቂት በ“ትውልድ ሀገሯ” እምብርት አዲስ አበባ ውስጥ ከቤተሰቧ ጋር እየኖረች አንድም ሀገርኛ ቋንቋ ጠፍቷት በእንግሊዝኛ ነበር ስትኮላተፍ አንዴ በቲቪ ያየኋት! አይ ኢትዮጵያ! ማለፉ አይቀርምና ሲያልፍ ስንቱን አውርተን እንጨርሰው ይሆን? ውጭ ያሉትስ በያሉበት ሀገር ቋንቋ ቢኮላተፉ አማራጭ አጥተው ነው፡፡ እዚህ ስንቱ ደንቆሮ ማይም መሰላችሁ ለልጆቹ አማራጭ እያሳጣ እንትን ላይ ተቀምጦ እንት ገማኝ የሚል! እንዲያው በውነት ከማይምነት የከፋ ለሰው ልጅ ጠላት ይኖር ይሆን? ከሰማችሁ አደራ እንዳትደብቁኝ፡፡  ለነገሩ ይህን ይህን አሁን እዚህ ማንሳት አይገባም፡፡) የኔው አውግቼውና አልፎአይቼው በስንት ጣማቸው! ይቺ ነገር የምቀኝነት ታስመስልብኝ ይሆን እንዴ? “ያጣ ወጉ ነው” ልባል፤ ግዴለኝም እችለዋለሁ፡፡ ለማንኛውም ደህና ሰንብቱልኝ እስኪ፡፡

 

yiheyisaemro@gmail.com

 

The post የባራክ ኦባማና የወይዘሮ አዜብ መስፍን ታሪካዊ ግንኙነት appeared first on Zehabesha Amharic.


(ሰበር ዜና) መምህር ግርማ ታሰሩ

$
0
0

Memeher Girma

(ዘ-ሐበሻ) በአውሮፓ የተለያዩ ሃገራት በማጥመቅ ላይ ቆይተው ወደ ሃገራቸው የተመለሱት መምህር ግርማ ወንድሙ በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመምህሩ ቅርብ ሰዎች የሆኑ ታማኝ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገባ ከሆነ መምህር ግርማ ወንድሙ ፈቃድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ተጠቅመው በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በማስተማር እና በማጥመቅ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል በሚል በቤተክህነት በቀረበባቸው ክስ ነው የታሰሩት::

በአገልግሎታቸው የተነሳ በወንጀል እንደሚጠየቁ በፖሊስ እንደተነገራቸው የተገለጸው መምህር ግርማ በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ላይ ውለው ምርመራቸው እንደቀጠለ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

ምንጮቻችን የሚያደርሱንን መረጃዎች ይዘን እንቀርባለን::

The post (ሰበር ዜና) መምህር ግርማ ታሰሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

እንደ ባቡር ፉርጎ የተቀጣጠለዉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት (ሳዲቅ አህመድ ከአንድ የህወሃት የጦር መኮንን ጋር ያደረገው ቆይታ)

10 የፌ. ፖሊስ አባላት ኮንሶና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ተደመሰሱ ሲል አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ዘገበ

$
0
0

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ራድዮ በሰበር ዜናው እንደዘገበው በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡

newsእንደ ራድዮው ዘገባ በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር “የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!” የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን “አልሄድም” ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና እንዲመጣላቸው በማድረግ ተሳፍረው ጉዟቸውን ቀጥለው ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ሲደርሱ ቅፅበታዊ ጥቃት ተከፍቶባቸው ከነተሳፈሩበት መኪና ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል ብሏል የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ::

ራድዮው ዘገባውን በመቀጠል የአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ ጦር ተወራ ጓዳ ጎድጓዳዋ ሳይቀር እየታሰሰ ነው ብሏል::
ራድዮው እንደሚልው እየተፋፋመ ያለው የፀረ-ወያኔ ትግል እየተካሄደባቸው ከሚገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ አርባ ምንጭ መሆኗ እና በህወሓት የደህንነት ተቋም ጥርስ ውስጥ ገብታ አገዛዙ በአዓይነ ቁራኛ እየተከታተላት የምትገኝ መሆኗ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከሰሞኑ ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 አንድ አይሱዙ ሙሉ የጦር መሳሪያ ወደ ከተማዋ አስገብቷል በሚል የህወሓት ልዩ ኃይሎች፣ ፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች በየመንደሩ ተሰራጭተው ከፍተኛ አሰሳ እያደረጉ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴና ሰላም በማወክ ላይ ናቸው፡፡
በተያያዘ ዜና ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ የተባሉ የህወሓት ጆሮ ጠቢዎችና የአካባቢው ቆራጭ ፈላጮች ፎቶግራፋቸው በማህበራዊ ሚዲያው መሰራጨቱን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ ተጥለቅልቃ እየታመሰች ትገኛለች ሲል ራድዮው ዘግቧል::

ይህን ዜና የሚያስተባብል መረጃ ከመንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ ነገር የለም:: ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ያደረገችው ሙከራም አልተሳካም::

The post 10 የፌ. ፖሊስ አባላት ኮንሶና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ተደመሰሱ ሲል አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ዘገበ appeared first on Zehabesha Amharic.

መምህር ግርማ ዋስትና ተከለከሉ * የማታለል ክስ የቀረበባቸው መምህሩ “ሴራ ነው –ከሳሹን አይቼው አላውቅም”አሉ

$
0
0

girma wendimu
ትናንት ዘ-ሐበሻ በሰበር ዜና መምህር ግርማ ወንድሙ መታሰራቸውን መዘገቧ አይዘነጋም:: ፖሊስ ዛሬ መምህር ግርማን ፍርድ ቤት አቁሞ ጠርጥሮ ያሰረበትን ምክንያት አስረድቷል:: የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የወንጀል ችሎት በመምህር ግርማ ላይ ፖሊስ የፈጸመውን ክስ ከሰማ በኋላ ፖሊስ አቶ ግርማ ቢፈቱብኝ መረጃና ሰነዶችን ሊያሸሹ ይችላሉና 14 ቀን ይፈቀድልኝ ሲል ጠይቋል:: የመምህር ግርማ ጠበቃ የተጠረጠሩበት ክስ ዋስትና የሚያስከለክል አይደለም ሲል ሲል በዋስ እንዲለቀቁ ጠይቆ ነበር:: ሆኖም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ አብዛኛውን ምርመራ በማጠናቀቁ የጠየቀውን 14 የምርመራ ቀን ሰርዞ በ7 ቀን ውስጥ አሉኝ የሚላቸውን ማስረጃዎች አሰባስቦ እንዲጨርስ ፈቅዶ ውጤቱን ለመስማትም ጥቅምት 25 2008 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። መምህር ግርማ ወደ ማረፊያ ቤት ሄደዋል::

በመምህር ግርማ ወንድሙ ላይ የቀረበው ክስ የሚከተለው ነው:- (ከመንግስት ሚዲያዎች እንደወረደ የተገኘ ነው)
የወንጀሉ ዝርዝር

ፖሊስ መምህር ግርማ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ምክንያት የሆነው ወንጀል የተፈፀመው መስከረም 2006 ዓ.ም ነው ብሏል።

በየካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ወሰን ግሮሰሪ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩት አቶ በላይነህ ከበደ በመምህር ግርማ የማታለል ወንጀል የተፈጸመባቸው ግለሰብ ናቸው።

እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እኚህ ግለሰብ ከትዳር አጋራቸው ጋር 400 ካሬ ሜትር ላይ ባረፈ መኖሪያ ቤታቸው ይኖሩ ነበር።

እንደ ምርመራ መዝገቡ መምህር ግርማ የግል ተበዳይን እምነት በመጠቀም የምትኖርበትን መኖሪያ ቤት እስከ ጥር 30 2006 ሽጠህ ካልወጣህ አስከሬንህ ይወጣል ይሏቸዋል።

የፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚለው ልጅ ያልወለዱት ባልና ሚስት ከመሞት መሰንበት በማለት ይህንን ቤት በጣም በዝቅተኛ ዋጋ በ800 ሺህ ብር ይሸጡታል።

ቤቱ በዚህ ዋጋ እንዲሸጥ መምህር ግርማ በራሳቸው ሰዎች አማካኝነት ብዙ ያልተገባ ስራ ሰርተዋል ነው የሚለው የምርመራ መዝገቡ።

ከዚያም መምህር ግርማ በዚህ ብቻ ሳይመለሱ የግል ተበዳዩን ቦሌ አካባቢ በራዕይ ያየሁት ቦታ አለ እዚያ ነው ገዝተህ የምትኖረው ይሏቸውና ሌላ የማታለያ ዘዴ ቀየሱ ይላል ምርመራው።

ቤቱ የተሸጠበትን 800 ሺህ ብር አምጣና እንዲበረክትልህ ልፀልይበት ብለው በመውሰድ በዚያው ውለው አደሩ፤ የግል ተበዳዩም በእርሳቸው ላይ ያላቸው እምነት ባለመጥፋቱ በትዕግስት ስልክ ቢደውሉላቸውም ስልካቸው ዝግ ሆነባቸው፤ ይባስ ብሎ ከሀገር ወጡ ተባለ የሚለውም ተጠቅሷል።

የግል ተበዳይ ሁኔታው ማታለል መሆኑን ስለተረዱ 2007 መጋቢት ወር ገደማ ለፖሊስ ያመለከቱ ሲሆን፥ እርሳቸው ከሄዱበት እስኪመለሱ ፖሊስ የግል ተበዳዩን እና የምስክሮችን ቃል ተቀብሎ ቆይቶ ተጠርጣሪው መምህር ግርማ ወንድሙን ትናንት በቁጥጥር ስር አውሏቸው ነው ዛሬ ፍርድ ቤት ያቀረባቸው።

ተጠርጣሪው መምህር ግርማ እኔ የተባለውን ሰው ቀይ ይሁን ጥቁር አይቼው አላውቅም፤ ሆን ተብሎ ከጀርባ የተጠነሰሰብኝ ሴራ አለ በማለት ለችሎቱ አስረድተዋል።

The post መምህር ግርማ ዋስትና ተከለከሉ * የማታለል ክስ የቀረበባቸው መምህሩ “ሴራ ነው – ከሳሹን አይቼው አላውቅም” አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

10 የፌ. ፖሊስ አባላት ኮንሶና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ተደመሰሱ ሲል አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ዘገበ

$
0
0

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ራድዮ በሰበር ዜናው እንደዘገበው በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡
ginbot 7እንደ ራድዮው ዘገባ በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር “የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!” የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን “አልሄድም” ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና እንዲመጣላቸው በማድረግ ተሳፍረው ጉዟቸውን ቀጥለው ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ሲደርሱ ቅፅበታዊ ጥቃት ተከፍቶባቸው ከነተሳፈሩበት መኪና ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል ብሏል የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ::

ራድዮው ዘገባውን በመቀጠል የአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ ጦር ተወራ ጓዳ ጎድጓዳዋ ሳይቀር እየታሰሰ ነው ብሏል::
ራድዮው እንደሚልው እየተፋፋመ ያለው የፀረ-ወያኔ ትግል እየተካሄደባቸው ከሚገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ አርባ ምንጭ መሆኗ እና በህወሓት የደህንነት ተቋም ጥርስ ውስጥ ገብታ አገዛዙ በአዓይነ ቁራኛ እየተከታተላት የምትገኝ መሆኗ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከሰሞኑ ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 አንድ አይሱዙ ሙሉ የጦር መሳሪያ ወደ ከተማዋ አስገብቷል በሚል የህወሓት ልዩ ኃይሎች፣ ፌደራል ፖሊሶችና ደህንነቶች በየመንደሩ ተሰራጭተው ከፍተኛ አሰሳ እያደረጉ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴና ሰላም በማወክ ላይ ናቸው፡፡
በተያያዘ ዜና ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ የተባሉ የህወሓት ጆሮ ጠቢዎችና የአካባቢው ቆራጭ ፈላጮች ፎቶግራፋቸው በማህበራዊ ሚዲያው መሰራጨቱን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ ተጥለቅልቃ እየታመሰች ትገኛለች ሲል ራድዮው ዘግቧል::

ይህን ዜና የሚያስተባብል መረጃ ከመንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ ነገር የለም:: ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ያደረገችው ሙከራም አልተሳካም::

The post 10 የፌ. ፖሊስ አባላት ኮንሶና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ተደመሰሱ ሲል አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ዘገበ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአማራው ስም የሕወሓት ተላላኪ የሆኑ ሆዳም የብአዴን አመራሮች በአማሮች ላይ የሠሯቸው 14 እርጉም ግፎች

$
0
0

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው


እርጉም ቀናት (ይገርማል)

በትናንትናው እለት የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቃለምልልስ ሲያደርጉ ተከታተልሁ:: ርእሰ መስተዳድሩ ባንድ ወቅት “አማራ የራሱን የጦር ጀኔራል መርጦ ህዝቡን እያስታጠቀ ነው” በሚል በትግራዩ ገዥ አቶ አባይ ወልዱ ለቀረበባቸው ክስ “አዎ ለክልሌ ጀኔራል ነኝ” ብለው መልስ ሰጡ የሚል ጽሁፍ አንብቤ ስለነበር ልቤ በኩራት እብጥ ብሎ ክብር ሰጥቻቸው ነበር:: በአማራው ላይ የሚደርሰው ዘርፈ ብዙ ጥቃት ያበቃ ዘንድ በብአዴን ውስጥ ያሉት አማሮች በቁጭት “በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ በቃ!”ብለው ተነስተዋል ማለት ነው ብየ ገምቸ ነበር:: ምንም ቢሆን ልጅ የወላጆቹን ባህሪ መውረሱ አይቀርም: ይኸው የብአዴን አማሮች ያባቶቻቸውን ወኔ ተላበሱ ብየ በደስታ የምሆነውን አጥቸ ነበር:: ይሁንና ሰውየው በሰሞኑ ያደረጉት ቃለመጠይቅ ላይ ብአዴን የአማራ ህዝብ የዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ከሌሎቹ ወገኖቹ ጋር በእኩልነት እንዲኖር ከትምክህተኞችና ከጠባቦች ጋር ብዙ ትግል እንዳደረገና ውጤት እንዳስገኘ ሲገልጹ ሰማሁና ከልብ አዘንሁ:: አቶ ገዱ እናንተ የምታወሩትን ወይስ ምድር ላይ የሚታየውን እንመን? እንደእኔ እምነት የአማራ ህዝብ መቸም ቢሆን ያላገጠመውን ፈተና በናንተ ጊዜ እየተፈተነ ነው:: አማራ ተኮር የሆነ ጭፍጨፋ የተፈጸመውና ህዝባችን አጎንብሶ እንዲኖር የተደረገው በናንተ ጊዜ ነው:: ይህ ሁሉ መከራ በአማራው ላይ ሲፈጸም “ለምን እንዲህ ይሆናል” ብላችሁ ለመሟገት የሚያስችል እንጥፍጣፊ ወኔ የላችሁም:: እንዲያውም ድርጅታችሁ በተላላኪነት ተግባር ተሰማርቶ ግፍ አንገፈገፈን ብለው ተቃውሞ ያሰሙትን ወገኖች አሳዶ በመምታት የወያኔ አፋኝ ስኳድ ሆኖ እየሰራ ያለ ድርጅት እንደሆነ ህዝባችን አሳምሮ ያውቃል:: “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ” ነውና እስቲ በኢህአዴግ ጊዜ በአማሮች ላይ የተፈጸመውን ግፍና የናንተን አቋም በጥቂቱ እናስታውሳችሁ:-

1. በደርግ የመጨረሻ ዘመን አሶሳ ላይ አማሮች ብቻ ተለይተው ሲታረዱና በእሳት ሲቃጠሉ ድርጅታችሁ አንድም ተቃውሞ አላሰማም::

2. የናንተን ድርጅት ያካተተው ኢህአዴግ መላ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ አማሮች እየተለቀሙ ከነነፍሳቸው በገደል ሲጣሉ:በገጀራ ሲታረዱ: በእሳት ሲቃጠሉ ድርጅታችሁ የወገንተኝነት ስሜት ተሰምቶት “ለምን ምንም ያላጠፉ ሰዎች አማራ በመሆናቸው ብቻ እንዲህ አይነት ግፍ ይፈጸምባቸዋል?” ብሎ በመቆርቆር እወክለዋለሁ የሚለውን ህዝብ መብት ለማስከበር ሲንቀሳቀስ አልታየም:: እንዲያውም ያሁኑ ፓስተር የያኔው የድርጅታችሁ ሊቀመንበር ታምራት ላይኔ በጅጅጋ ተገኝቶ በሶማሊያ ክልል በሚኖሩት አማሮች ላይ የሶማሌ መንግስትና ህዝብ እርምጃ እንዲወስዱባቸው በመቀስቀስ ድርጅታችሁ ጸረ አማራ መሆኑን እናንተም የጠላት ሀይል አንድ ክንፍ መሆናችሁን አስመስክሯል::

ፎቶ መፍቻ: ከሕወሓት ጋር በመተባበር አማራውን ካስፈጁት መካከል አቶ ታምራት ላይኔ እና በረከት ስምዖን በብአዴን 3ኛ ጉባኤ ላይ::

ፎቶ መፍቻ: ከሕወሓት ጋር በመተባበር አማራውን ካስፈጁት መካከል አቶ ታምራት ላይኔ እና በረከት ስምዖን በብአዴን 3ኛ ጉባኤ ላይ::


3. ከንጉስ ኃይለስላሴ ጊዜ ጀምሮ ለብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበር: ለሰው ልጅ እኩልነትና ነጻነት እልህ አስጨራሽ ትግል ሲያደርጉ ከነበሩትና መስዋእትነት ክከፈሉት ሰወች መሀል የአማሮች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም:: ይሁንና በነገስታቱና በደርግ ጊዜ በኤርትራ ላይ ተፈጽሟል ለተባለው ወንጀል አማሮችን ቀጥተኛ ተጠያቂ በማድረግ አስመራ ድረስ ሄደው “ማሩን” ብለው ከሻእቢያ እግር ላይ ወድቀው ይቅርታ እንዲለምኑ ሲደረግ “ለምን እንዲህ ይሆናል? ባለፉት ስርአቶች በገዥነት የተቀመጡ አማሮች ብቻ አልነበሩም: ታዲያ እንዴት አማራው ብቻ ይቅርታ ጠይቅ ይባላል?” ብላችሁ ለህዝባችሁ መብትና ክብር ያሰማችሁት ተቃውሞ አልነበረም::

4. አማራ ከየክልሉ ሀብት ንብረቱን ጥሎ የሞተው ሞቶ ማምለጥ የቻለው እግሩ ወዳመራው ሲሰደድ “አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ ሀገር ውስጥ የሚኖር አማራ ካላግባብ ሀብት ንብረቱን ሊነጠቅ: ህይወቱን ሊያጣ አይገባም” ብላችሁ ስትከራከሩ አልተሰማችሁም:: ይባስ ብሎ የድርጅታችሁ የወቅቱ ሊቀመንበር አቶ አዲሱ ለገሰ ከኦሮሚያ የተባረሩትን አማሮች በተመለከተ ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ የተባረሩት ሰዎች አጭበርባሪወችና ዘራፊወች ናቸው ነበር ያሉት:: የአማራ ሰዎች እንደዚያ በጅምላ ከየክልሎች አላግባብ እንዲፈናቀሉ ሲደረግ በአማራ ክልል ግን የሌሎች ክልሎች ተወላጆች በድርጅታችሁ ታቅፈውና ሹመኛ ሆነው በአማሮች ላይ እየፈረዱና ሀብቱን እየመዘበሩ በማናለብኝነት ቀጥለዋል:: ለዚህስ የምትሰጡት መልስ ምንድን ነው? የሚገርመው ደግሞ የአማራን ህዝብ ጥንብ እርኩሱን አውጥቶ ያዋረደው የክልሉ ተወላጅ አቶ አለምነው መኮንንን ህዝብን ያህል ነገር እንዴት እንዲህ ታረክሳለህ ተብሎ ሊጠየቅ ሲገባ እርስዎን ጨምሮ ሌሎች የድርጅቱ አባላት ባንድ ላይ ሰውየው የህዝብ ተቆርቋሪ እንደሆነና የተወራበት ሁሉ የጠላት ወሬ እንደሆነ ልታሳምኑን ስትደክሙ ሰምተን እጅግ አዝነናል:: በህዝብ ላይ ያን ያልተገረዘ የባለጌ መላሱን ያስረዘመውን ስድ አደግ ሰው ልትቀጡ ወይም ልትገስጹ ሲገባ ከህዝብ በላይ አድርጋችሁ በማየት የተገላቢጦሽ ለህዝብ የተቆረቆሩትን ሰዎች ወረፋችሁ::

5. በአማራ ክልል የሚኖሩ ብሄረሰቦች በዞን ተደራጅተው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ሲደረግ አማሮች በብዛት በሚገኙባቸው ሌሎች ክልሎች ግን ይህ እድል አልተሰጠም: ሌላው ቀርቶ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን እንኳ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ዕድሉን አላገኙም:: ታዲያ እናንተ የታዘዛችሁትን ከመፈጸም አልፋችሁ እንዲህ የተዛነፈ አሰራር ሲታይ ምን ያደረጋችሁት ነገር አለ?

6. የአዊ ዞን ልጆቻቸው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአማረኛ እንዲማሩ ተስማምተው ያሳለፉትን ውሳኔ ከበላይ የመጣ ትእዛዝ ነው በሚል የብሄሩን መብት ገፍፋችሁ አዊወች በአዊኛ እንዲማሩ አደረጋችሁ: ይህን ውሳኔውን ያሳለፉትን ሰዎችም “የመንግስትን ፖሊሲ ተቃርነው የቆሙ” በማለት ፈርጃችሁ ከስራ እስከማባረር ድረስ የደረሰ ቅጣት ቀጣችኋቸው::

7. ለሱዳን ሊሰጥ በታሰበው መሬት ላይ የህዝብ ቁጣ ሲባባስ “የምንሰጠው መሬት የለም: ከሌላ የወሰድነውም የለም:: የራሳችን የሆነውን አንሰጥም የሌላውንም አንፈልግም” ብለው ነበር:: ይሁንና በተጨባጭ ከመተማና ካካባቢው በሱዳን ወታደሮች በሀይል እንደተፈናቀሉ ተፈናቃዮቹ አዲሳበባ ድረስ በአካል ተገኝተው ለፓርላማው አቤቱታ ማቅረባቸው በተጨማሪም ለአሜሪካው የአማረኛ ሬዲዮ ስርጭት (VOA) ቃለምልልስ መስጠታቸው አይዘነጋም:: አቶ መለስ ይህንን አስመልክቶ ከፓርላማው ለቀረባቸው ጥያቄ ሲመልሱ “አንድም ሰው አልተፈናቀለም” ብለው ሙልጭ አድርገው ዋሽተው ነበር:: እርስወም ድንበሩን በተመለከተ ለቀረበልወት ጥያቄ ከአቶ መለስ የተለየ መልስ አይደለም የሰጡት::

ተላላኪው ም/ል ሊቀመንበር ደመቀ መኮንን; ሕወሓት የሚሳደበው አንሶ የአማራውን ሕዝብ ከተሳደቡት አቶ አለምነህ መኮንንና ከተላላኪ የአማራ የጦር መኮንኖች ጋር::

ተላላኪው ም/ል ጠቅላይ ሚ/ር እና የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ም/ል ደመቀ መኮንን; ሕወሓት የሚሳደበው አንሶ የአማራውን ሕዝብ ከተሳደቡት አቶ አለምነህ መኮንንና ከተላላኪ የአማራ የጦር መኮንኖች ጋር::


8. ከ10 አመት በፊት በተደረገው የህዝብ ቆጠራ ከሌሎች ክልሎች በተለየ መልኩ በአዲስአበባና በአማራ ክልል ብቻ ፕሮጀክት ከተደረገው ቁጥር በእጅጉ ማነሱ ይታወቃል:: በአዲስ አበባ ከሚኖረው ህዝብ መሀል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አማራው መሆኑን ያጡታል ብየ አላስብም:: ታዲያ ይህ የአማሮች በ2.5 ሚሊዮን ቁጥር መቀነስ መላው ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን በንዴት ሲያርገፈገፋቸው ብአዴን ግን አንድም ሰው እንዳልጎደለበት ሆኖ ማስተባበያ በአቶ አዲሱ ለገሰ በኩል ሲሰጥ ነበር::

9. በአማራ ክልል ላይ ብቻ ያተኮረ በቤተሰብ ዕቅድ ስም እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል በወያኔ ተቀርጾ በናንተ የሚፈጸም አስነዋሪ ተግባር ነው:: የቤተሰብ ብዛትን መመጠን በሚል ምክንያት በአማራ ክልል ህዝብ ላይ ብቻ ያተኮረ የሴቶችን ማህጸን መቋጠር: የወንዶችን የዘር ፍሬ ማኮላሸት የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው:: አሁን ደግሞ ስልቱ ተቀይሮ የአማራ ሴቶችን የበሽታ መከላከያ ክትባት በማስመሰል መሀን የሚያደርግ መድሀኒት እንዲከተቡ ሲደረግ ብአዴን የወያኔን አላማ ለማስፈጸም ቀዳሚ ሆኖ የተሰለፈ ቡድን ነው::

10. አማሮችን ትጥቅ አስፈቱ የሚል መመሪያ በወረደላችሁ ጊዜ ምን ያህል ግፍ እንደፈጸማችሁ ትዝ ብሏችሁ ያውቃል? ወያኔ ይህን መመሪያ ሲያስተላልፍ ምክንያት እየፈጠረ አማሮችን ለመበቀል ካለው ፍላጎት በመነሳት ነበር:: ይህን ለማድረግ ደግሞ በራሱ ሰዎች ሳይሆን ህዝቡን እንወክለዋለን በምትሉት በናንተ ቢፈጸም ከተጠያቂነት ነጻ እንደሚሆን አሰበና “ህገወጥ መሳሪያ ታጣቂወችን መሳሪያቸውን እንዲያስገቡ አድርጉ” ሲል ትዕዛዝ ሰጣችሁ:: ይህን የበላይ ትእዛዝ ለማስፈጸም ነበር መሳሪያ ያልነበረውን ሳይቀር አስራችሁ የገረፋችሁት ብሎም የገደላችሁት:: የናንተ ህዝባዊነት መገለጫ የሰውን ክብር ገፋችሁ አባቶችን ሳይቀር ማሰቃየት ነው?

11. ለመሆኑ ቁልፍ በተባሉት የወታደራዊና የሲቭል ተቋማት ውስጥ የአማሮች ድርሻ ምን ያህል ነው? ይህስ አሳስቧችሁ ያውቃል? ወያኔ ገንዘብ የሚታፈስባቸውንና ስልጣንን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ተቋማትን ተቆጣጥሮ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ያገር ሀብት ዘርፎ ከሀገር ሲያስወጣ ምን ያደረጋችሁት ነገር አለ? የሀገር ሀብት ለሁሉም ክልሎች እንጅ ለአንድ ቡድን ብቻ አገልግሎት እንዳይሰጥ ለማድረግ የሰራችሁት ስራስ ምን አለ?

12. የብድርና የቁጠባ ወይም የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አገልግሎት ለሁሉም አማራ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ነው የምታከፋፍሉት? አገልግሎት ማግኘት የህዝብ መብት ነው:: እናንተ በአመራር ላይ የተቀመጣችሁ አገልግሎት ለማግኘት ሳይሆን ያለአድልዖ አገልግሎት ለመስጠት ነው:: ግን እናንተ በተግባር እያደረጋችሁ ያላችሁት ምንድን ነው? የአማራው ህዝብ በሙሉ እንደናንተ ፍጹም የወያኔ ሎሌ ሆኖ የታዘዘውን እንዲፈጽም: ሲገድሉት እንዲሞት ለማድረግ ስንት ግፍ ሰራችሁ? ጠላትና ወዳጅ በማለት ከፍላችሁ እንደናንተ ሊሆን ያልፈቀደውን ሰላማዊ ዜጋ በተለያየ መንገድ አላሰቃያችሁም?

13. ህዝቡ የፖለቲካ አማራጭ የማግኘት መብቱ በህገመንግስቱ የተጠበቀ ነው:: ይህንን የህዝብ መብት አክብራችሁ ህዝቡ በመረጠው እንዲተዳደር ምን አድርጋችኋል? በግድ ውጣ ተብሎ እንዲመርጥ የተደረገን ህዝብ ምርጫውን ነፍጋችሁ እጅ እጅ በሚል ውሸት እኛ ተመረጥን ስትሉ የብዙሀኑን መብት የነፈጋችሁና በህዝብ ላይ በጉልበት የነገሳችሁ አምባገነኖች እንደሆናችሁ አስተውላችሁት ታውቃላችሁ? መቸ ነው ወደህሊናችሁ የምትመለሱት?

14. ክልሎች ታሪክ እየጠቀሱ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ሲያነሱ የአማራ ክልል ግን በግላጭ በታሪክ የሚታወቀውን መሬቱን ማስከበር አልቻለም:: አንዳንድ የዋህ ሰዎች በአንድነት እስከኖርን ድረስ አንድ አካባቢ በዚህ ወይም በዚያ ክልል ቢካተት ችግር የለውም ሲሉ ይደመጣሉ:: እንደእኔ ከሆነ ይህ አባባል ፍጹም ስህተት ነው:: የመገንጠል መብት በተከበረበት ሀገር ትክክለኛ የራስን መሬት ሳይዙ ህገመንግስቱን ማጽደቅ አደጋው ቀላል አይደለም:: ዛሬ እየኖርን ያለነው አንድነቷ በተጠበቀ ሀገር ውስጥ አይደለም:: ህገመንግስቱም ቢሆን በአንድነት ለመቀጠላችን ዋስትና የሚሰጥ አይደለም:: የፈለገውን ማድረግ እየቻለ ያለው ወያኔ የተፈራረምንበትን ህገመንግስት መሰረት በማድረግ ነገ ብድግ ብሎ ለመገንጠል ወስኛለሁ ቢል በምን ነው ልንከላከል የምንችለው? የክልል መንግስታት ተፈራርመው ያጸደቁት ህገመንግስት በአለም አቀፍ መድረክ ተቀባይነት የማይኖረው ይመስላችኋል? በርግጥ በአሁኑ ጊዜ ከትግራይ ውጪ ያሉት ክልሎች መገንጠል እንፈልጋለን የማለት ድፍረቱ አይኖራቸውም: ድፍረቱ ቢኖራቸው እንኳ ወያኔ ጥያቄውን ለማዳፈንና ጥያቄ አቅራቢወችን ለመበቀል የሚሄድበት መንገድ አያጣም:: ነገር ግን የወያኔ ፈቃድ ሆኖ ክልሎች እንዲገነጣጠሉ ቢያደርግ ታሪካዊ መሬታችን ነው የምንለውን አካባቢ እንዴት ነው ማስመለስ የምንችለው? የአማራ ክልል ለመሆኑ ታሪካዊ መኖሪያ አካባቢው የቱ ነው? ይህ ጥያቄ ከተመለሰ በኋላ ነበር ህገመንግስቱ ቢፈረምም መፈረም የነበረበት:: ድርጅታችሁ አላግባብ የተወሰደበትን መሬት ለማስመለስ ያደረገው ምን ነገር አለ? “አማራ ነን:: ያላግባብ ወደትግራይ ክልል እንድንካተት ተደርገናል” እያሉ ለሚጮሁት የወልቃይት ወገኖቻችንስ ምን አደረጋችሁ? ታዲያ ለአማራው ህዝብ መብትና እኩልነት ያደረጋችሁት የሚያስፎክር ትግል የት አለ!

በርግጥ ማንም አሌ የማይለው ነገር ቢኖር አማራው ሀገሩ ኢትዮጵያ መሆኗን ነው: የኖረውም የሀገሪቱን ዳር ድንበር ለማስከበር: ሰላምና ጸጥታ ለማስፈን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢወች ነው:: ይህችን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አስከብሮ ለእኛ ያስረከበ ህዝብ እንደጠላት እየታደነ ሲገደል አባሪ ከመሆን ውጭ ለክልሉና ለህዝቡ ያበረከታችሁት አንድም አኩሪ ስራ የለም:: እናንተ የአማራውን ህዝብ የምታኮሩ ሳትሆኑ የምታሳፍሩ: የምታስከብሩ ሳትሆኑ የምታዋርዱ ሙሉ ትኩረታችሁን በሰፈር እየተደራጃችሁ ስልጣን ለመያዝ በርስ በርስ ሽኩቻ ጊዜአችሁን የምታባክኑ እንጥፍጣፊ ህዝባዊ ስሜት የሌላችሁ የምትገርሙ ሰዎች ናችሁ:: አይናችሁን ጨፍናችሁ በምትዋሹት ውሸት የአማራው ህዝብ አምኖ ይቀበለናል ብላችሁ አስባችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል:: ብታምኑም ባታምኑም ህዝቡ እናንተን ህሊና የሚባል ነገር የሌላችሁ የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ ሮቦቶች እንደሆናችሁ አድርጎ ነው የሚያያችሁ:: ወያኔም ቢሆን በፈለገው መንገድ ሊያሰልፋችሁ የሚችል ጅሎች አድርጎ እንደሚያያችሁና እንደሚታዘባችሁ አንጠራጠርም::

ሰሞኑን አቶ ኃይለማርያም ከፓርላማ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ የዶ/ር ደብረጽዮንን ስሜት ሳትገነዘቡ የቀራችሁ አይመስለኝም:: መቸም ኃይለማርያም ከራሳቸው የፈለቀች አንዲትም ቃል ሊናገሩ ድፍረት ይኖራቸዋል ተብሎ አይታሰብም:: ታዲያ ለሚቀርብላቸው ጥያቄ በወያኔ ተዘጋጅቶ የተሰጣቸውን መልስ ሸምድደው ገብተው “መንግሥታችን ርምጃ ይወስዳል…” ምናምን ሲሉ ዶክተሩ ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው የፌዝ ፈገግታ ሲያሳዩ ነበር:: ዶ/ር ደብረጽዮን “ነገ ቃላችንን አጥፈን ተቃራኒውን ለማድረግ ብንወስንና ይህንን ባደባባይ ተናገር ብንለው ያው እንደለመደው መንግስታችን እንዲህ ያደርጋል እያለ መናገሩ አይቀርም:: የነዚህ ሰዎች ሰውነት ከምኑ ላይ ነው?” የሚል አይነት የግርምት ፈገግታ ነበር ሲያሳዩ የነበሩት:: ወያኔ እንዲህ የሚያሾፈው በሁላችሁም ላይ ነው::

አማራን የሚያህል ትልቅና ታሪካዊ ህዝብ እንወክላለን ብላችሁ ግን ለውርደትና ለእልቂት ስትዳርጉት: ለዚህ ውለታችሁ የሚሰጣችሁ ክፍያ በአናሳው ቡድን እንዲህ መሳቂያ መሳለቂያ መሆን ከሆነ ምን አይነት ህሊና ቢኖራችሁ ነው አሜን ብላችሁ ተሸክማችኋቸው የምትኖሩት:: “አማራ ሆዳም ነው” እንደሚሉን እናውቃለን:: የህዝብ ክብርና ነጻነት ከምንም በላይ አይደለም እንዴ! ባትበሉት ባትጠጡት ባፍንጫችሁ ቢወጣ ምን ነበረበት::

አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከመሃል የሶራ ዘፈን ተጫዋቹ አርቲስት ካሳሁን ታዬን ይዘው- በነ አለምነህ መኮንን ታጅበው በአማራው ሕዝብ ላይ ሲቀልዱበት ይታያል::

አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከመሃል የሶራ ዘፈን ተጫዋቹ አርቲስት ካሳሁን ታዬን ይዘው- በነ አለምነህ መኮንን ታጅበው በአማራው ሕዝብ ላይ ሲቀልዱበት ይታያል::


እስከቀበሌ ድረስ በዘለቀው አደረጃጀታችሁ ተጠቅማችሁ “መላው የአማራ ህዝብ ሆይ ደምና አጥንት ከፍለህ ባስከበርሀት ሀገር ላይ መኖር ተከልክለህ ዘርፈ ብዙ ግፍ እየተፈጸምብህ ስለሆነ ይህንን ባንተ ላይ ያነጣጠረ ሰቆቃ ለማስወገድ ከጎናችን ተሰልፈህ መብትህን እንድታስከብር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::” የሚል አዋጅ ብታስነግሩ አማራው “ሆ” ብሎ ተነስቶ የተበላሸውን ለማስተካከል ጊዜ ይፈጅበት ነበር!
ለነገሩ ወያኔ ከራሱ ክልል ውጪ ላሉት ክልሎች ባለስልጣናትን ሲያስቀምጥ በተጠና መንገድ ሆድ እንጅ ህሊና የሌላቸውን ስለህዝብና ስለሀገር ደንታ ቢሶችን መርጦ ነው:: ለዚያም ነው አማራው ከያለበት እየተያዘ ግፍ ሲፈጸምበት አንድም ተቃውሞ ያላሰማችሁት! እናንተም ብትሆኑ አፋችሁ ያውራ እንጅ ለህዝብ ቀርቶ ለራሳችሁ እንደማትሆኑ ልባችሁ አሳምሮ ያውቃል:: ሙሉአለም ሲገደል ምን አደረጋችሁ? ታምራት ላይኔ በአደባባይ “በትግል ያልተሸነፈ ሰው በስኳር ተሸንፎ እጁን ሰጠ” ተብሎ ሲቀለድበት: ራሱን አዋርዶ “ቢመክሩኝ አልሰማ ብየ” ብሎ ቀበጣጥሮ ይቅርታ እንኳ ተነፍጎት ወህኒ ሲወርድ ከማጨብጨብ ውጪ ምን ሰራችሁ? ለነገሩ እንደፖለቲከኛ ሳይሆን እንደሆደ ቡቡ ህጻን በፍርሀት የቀባጠረ ሰው ሲመራው ከነበረ ድርጅት ምን ይጠበቃል?

የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ እናንተም ሆናችሁ ጌቶቻችሁ ከፍርድ አታመልጡም: የውሻን ደም ከንቱ የማያስቀር ግፍን የሚቆጥር አምላክ አለ:: እስከዚያው ድረስ እናንተ ስልጣን ላይ ተቀምጣችሁ ለምታገኙት ፍርፋሪ አማራውን ረግጣችሁ እንድትይዙ የእድል በር የከፈተላችሁን የልደት ቀናችሁን በፌስታ ስታከብሩ እኛ ደግሞ ያችን የተረገመች ቀን በሀዘን እናስታውሳታለን:: መቸም ከአንጎል ክፍላችሁ የሆነ የጎደለ ነገር አለ መሰለኝ ጸጸትና ቁጭት ይሰማችኋል ብየ አላምንም:: የህዝብን አስተያየት በግብአትነት ተጠቅማችሁ ራሳችሁን ወደውስጥ አይታችሁ ስህተታችሁን ለማረም ከመሞከር ይልቅ የሚተቿችሁን ለማጥፋት የምትተጉ እንደሆናችሁ ግን እናውቃለን:: እስካሁን በሰራችሁት ስራ ክብር ያገኛችሁ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል:: እና ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር ነውና በስራችሁ ከማፈርና ከማዘን አልፈን ምነው ሳትወለዱ በናታችሁ ማህጸን ውስጥ ውሀ ሆናችሁ በቀራችሁ ነበር ብለን ድርጅታችሁ የተወለደበትን ቀን ብቻ ሳይሆን እናንተ የብአዴን ሰዎች እራሳችሁ የየተወለዳችሁበትን ቀን ሳይቀር እረግመናል::

The post በአማራው ስም የሕወሓት ተላላኪ የሆኑ ሆዳም የብአዴን አመራሮች በአማሮች ላይ የሠሯቸው 14 እርጉም ግፎች appeared first on Zehabesha Amharic.

የስልጤ ዞን ወጣቶች የመንግስት ኃይሎችን እየተጋፈጡ ነው * የተጎዱ ተማሪዎች አሉ (አጭር ቪድዮም ይዘናል)

$
0
0
ፎቶ ከሳንኩራ ወረዳ በአልም ገበያ ከተማ የተደረገ ተቃዉሞ ነው

ፎቶ ከሳንኩራ ወረዳ በአልም ገበያ ከተማ የተደረገ ተቃዉሞ ነው

ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ

ህወሃት መራሹ መንግስት በስልጤ ዞን ተማሪዎችን ከትምርት ቤት፤ የመንግስት ሰራተኞችን ከስራ ገበታ ለማፈናቀል የጀመረዉ ግልጽ ዘመቻ ትኩረት የተሰጠዉ በሚዲያ ብቻ ነዉ። እነዚህ የነገን የብሩህ ተስፋ እሸት የጨበጡ ወጣቶች የራሳችንን አሳተሳሰብና አመለካከት በምንሻዉ መልኩ እንተገብራለን በማለት አንባገነናዊዉን ስርዓት ፊት ለፊት እየተጋፈጡት እየደሙ እየቆሰሉ ነዉ።

አቅጣጫ የሚያሳይ፣ አይዞአቹ የሚል ወገንንም ይሻሉ። አንዳንድ ወንድሞችን ለማናገር ሞክሬ ነበር። ጉዳዩ አገራዊ ስለሆነ እንደ ስልጤ ጉዳይ ብቻ መታየት የለበትም በተናጠል የምናደርገዉ ነገር የለም ሲሉ ገልጸዉልኛል። አፋር ሲበደል፥ አፋር ያገር ያለህ ጩኸቴን ስሙኝ ብሎ ኢትዮጵያዊዉን በሙሉ ቢያሰልፍ፤ ሱማሌ፣አማራ፣ኦሮሞ ወዘተ በደልና ጭቆና ሲደርስበት የራሱን የመጀመሪያ የድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ወደ አገራዊ ጉዳይ የመቀየሩ ሒደት ያለና የነበረ ነዉ።

ስለዚህ ባገርም ይሁን ባህር ማዶ ያለዉ የስልጤ ማህበረሰብ አቅሙ በሚፈቅደዉና ማድረግ በሚችለዉ መጠን አስቸኳይ ስብሰባዎችን በማድረግ፣መግለጫዎችን በማዉጣት፣ ሰላማዊ ሰልፎችን በማድረግ ከቅበት እስከ ሁልባረግ፤ ከሁልባረግ እስከ ዳሎቻና ጦራ ያለዉን ወገን የመታደግ ሐላፊነት አለበት። ዝምታዉ በቅቶ የተቀናጀ ስራ የሚሰራበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነን። ልብ ያለዉ ልብ ይበል። ጅግ ባሎቲ ይከታን!

ፎቶ ከሳንኩራ ወረዳ በአልም ገበያ ከተማ የተደረገ ተቃዉሞ ነው። ተማሪዎች እንደተጎዱ መረጃ ደርሶናል።

The post የስልጤ ዞን ወጣቶች የመንግስት ኃይሎችን እየተጋፈጡ ነው * የተጎዱ ተማሪዎች አሉ (አጭር ቪድዮም ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.


መምህር ግርማን ዘመነኞች ለምን ወንጀለኛ ብለዉ ወደ እስር ቤት ከተቷቸዉ?

$
0
0

Memhir girma
ሸንቁጥ አየለ
ልክ እንደ መምህር ግርማ ሁሉ ባህታዊ ገብረመስቀልን የዛሬ 20 አመት ህዝቡ ከኋላቸዉ እንደተከተላቸዉ ያስተዋለችዉ ወያኔ ባህታዊ ገብረመስቀልን በሀሰት ወንጅላ እስር ቤት ወርዉራ በርካታ ዉንጀላ አድርጋባቸዉ ነበር:: ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች መሃከል በእዉቀት መሰረት ላይ የቆመ ጽኑ እና ሀሰት የሌለበት እምነት የሚያራምድ እንደሆነ ሲያዉቁ አሸባሪ ብለዉ ድርጅቱን ለማፍረስ እየሰሩ ነበር:: አሁንም አጀንዳዉ የተንጠለጠለ ይመስላል::

እንግዲህ በርካታ ንጹሃንን ሀሰተኛ እና ወንጀለኛ ናቸዉ ለማለት በርካታ የሀሰት ፊልሞችን መስራት የለመደችዉ ወያኔ በመምህር ግርማ ላይ የተቀነባበረ የሀሰት ፊልማና ድራማ አዘጋጅታ ለህዝብ ታቀርባለች:: በህዝብ ለማስጠላት: ከህዝብ ለመነጠል::

ህዝቡ የሚያድነዉና የሚፈዉሰዉ እንዳይኖር ለማድረግ እንዲሁም ህዝቡ ተስፋ የሚያደርገዉ እንዳይኖር ለማድረግ ሁሉንም ደባዎችና ተንኮሎች
በመምሀር ግርማ ላይ ትሰራለች::ሀሰተኛ የሆኑ: የመፈወስ ጸጋ የሌላቸዉ: ጉበኞች: በክርስቶስ የማያምኑ: በቅናት የሚቃጠሉ : በርኩስ መንፈስ ሀይል የሚመሩ: ጉሰኞች የሆኑ ሰዎች ግን በእምነት ስም የሚነግዱ ሰዎችንም መልምላ በምስክርነት ታቀርባለች:: በቃ ይሄዉ ነዉ:: እዉነትን እፍን አድርጎ በገመድ መስቀል:: ከዚያም መምህር ግርማን ወንጀለኛ ናቸዉ እያሉ በሚዲያቸዉ ያናፋሉ::

እዉነተኞችን የሚፈራ : የሚያሳድድ: የሚወነጅል እና ከምድረ ገጽ እዉነትን የሚሰብኩ ወገኖች እንዲጠፋ የሚሰራ የማን ሀይል እንደሆነ የተገለጸ ነዉ:: እርኩሱ መንፈስ ነዉ:: ቢሆንም የኢየሱስ ክርስቶስን የጥበበ ስራ ማንም አያሸንፈዉም::

መምህር ግርማ ሁል ጊዜ ትምህርት ሲጀምሩ መዝሙር 68 ማለትም
1 እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።
2 ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ ኅጥኣን ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።
3 ጻድቃንም ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ፥ በደስታም ደስ ይበላቸው።
4 ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ በፊቱም ይደነግጣሉ።
የሚለዉን ሙሉዉን የመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አንብበዉ : አስከትለዉም የዮሐንስ ወንጌልን ቁጥር አንድን ሙሉዉን ማለትም 1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።
2 ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።
3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።
4 በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።
5 ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።

የሚለዉን የወንጌል ቃል ሙሉዉንም ዕራፍ አስተምረዉ እንዲሁም ልዩ ልዩ የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ስራዎች ካስተማሩ ብኋላ የማዳን ስራቸዉን ይጀምራሉ:: በተጨማሪም እግዚአብሄር ለቅዱሳን እና ለመላዕክት እንዲሁም ለጻድቃን የሰጣቸዉን በርካታ ጸጋዎች እያጣቀሱ ካስተማሩ ብኋላ የሰዉን ልጅ እያጠቁ ያሉ ልዩ ልዩ አጋንንትና እርኩስ መንፈሶችን ከክቡሩ የሰዉ ልጅ ላይ ያባርራሉ::
በመላዉ አለም እዬሄዱ የአዳምን ልጆችም ጥቁር ነጭ ሳይሉ ይፈዉሳሉ:: ከአለም እስከ አለም ያለ እርኩስ መንፈስ ያለበት ሀይል እኝህ ሰዉ በሚሄዱበት ሁል ይርዳል:: ይርበተበታል:: በኢየሱስ ክርስቶስ ሀይልና ጥበብ ሁሉ ይከናወንላቸዋልና መምህር ግርማ ሲመጡ እርኩሳን መናፍስት ሁሉ ከክቡሩ የአዳም ልጅ ላይ ይወገዳል:: ልክ እንደ ቀደሙ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊ አባቶች እንደ እነ አቡነ ዜናማርቆስ ያለ የማስተማርና የመፈወስ ጸጋ የተሰጣቸዉን መምህር ግርማን ግን ሰይጣን ማጥቃትና ማስጠቃት ከጀመረ ቆዬ:: የሰይጣን ሰራዊቱ ብዙ ነዉ:: ድምጹን ከፍ አድርጎ የሚጮህዉም በዛ:: በስማ በለዉ እኝህን ክርስቲያን አብረዉ የሚሳደቡ አንዳንድ የዋሃን በደራሽ ዉሃ ተወሳጅ የዋህ ሰዎችም ሞልተዋል::

ትምህርታቸዉን አንድ ቀን ሳይሰሙ: አስተምህሮታቸዉን ሳይመረምሩ: የማዳን ስራቸዉን ሳያስተዉሉ በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን እና የመፈወስ ሚስጢር የሚሰሩትን የማዳን ስራ ሳይመረምሩ ዝም ብለዉ ከዲያቢሎስ ሀይል ጋር የሚጨፍሩ አንዳንድ የዋሃንም ያሳዝናሉ:: ሳይገባቸዉ እና በማያዉቁት ፈራጅ ሆነዉ የእርኩስ መንፈስ መጠቀሚያ ሆነዋልና እዉነትም ጸሎት ይገባቸዋል::

የቀደሙ ኢትዮጵያዉያንን ቅዱሳን አባቶችን ታሪክ እና ገድል በሙሉ ተረት ተረት እና ሀሰት ነዉ በማለት ወገቡን ገትሮ ስልጣን እና ጊዜ መከታ አድርጎ በሰዉ ስጋ ተመስሎ የመጣዉ እርኩስ መንፈስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዉስጥ የሚደረጉ የክርስቶስን የማዳን ስራዎች ወንጀል ናቸዉ: አሸባሪነት ናቸዉ: ጽንፈኝነት ናቸዉ እንዲሁም ትምክህት ናቸዉ እያለ በመፈረጅ የክርስቶስን ቤት ለማፍረስ ከተጋ ይሄዉ እሩብ ምዕተ አመት ሆነዉ::የክርስቶስ ቤት ግን አስካሁን የኮሰመነ ቢመስልም አልፈረሰም:: ደግሞም አይፈርስም:: ሀይል እና ዘመን የክርስቶስ ኢየሱስ እንጅ የማንም አይደሉምና::

ኢየሱስ ክርስቶስን ወንጀለኛ ነዉ : ሀሰተኛ ነዉ ህዝቡን አታሏል ብለዉ እርኩስ መንፈስ ያለባቸዉ እና እግዚአብሄርን የማያዉቁ ሰዎች ስልጣንንና ዘመንን ተገን አድርገዉ እንደሰቀሉት ሁሉ በርካታ ንጽሁን የእግዚአብሄር ሰዎች አሁንም እየተሳደዱ ነዉ::
ጉልበትን እግዚአብሄር የሰጣቸዉ ዘመነኞች ሀሰት በመፈብረክ ነጹሃንን ያስወግዳሉ::

ሀሰት መሰረት ላይ የቆመ ዘመነኛ ባለ ጉልበት እዉነተኛ ክርስቲያኖችን : ሰዉን የሚፈዉሱትን የማንነት መሰረት ያላቸዉን : ኢትዮጵያዉያንን በእምነት አንድ የሚያደርጉትን መንፈሳዊ አባቶችን ፈጽሞ አይወዱም:: መምህር ግርማ ከአረብ እስከ ነጭ : ከነጭ እስከ ጥቁር እንዲሁም መላዉ ኢትዮጵያዊን ሁሉ እምነት ሳይለዩ በኢየሱስ ክርስቶስ ሀይል እየፈወሱ ሳለ በወንጀል ጠረጠርኳቸዉ ሲል ዘመነኛዉ ሀይል አስሯቸዋል::
የሆነ ሆኖ ግን በሀሰት የወንጀል ሰበብ ቢታሰሩም መምህር ግርማ ምንም የሚጎዱት ነገር የለም:: እሳቸዉ ቅዱስ ጳዉሎስ በሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 8 እንዳለዉ እንዲህ የሚል ጽኑ እምነት አላቸዉና:-
35 ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? 36 ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
37 በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
38 ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
39 ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።

እናም በመምህር ግርማ መታሰር ማን ይጎዳል? እየተፈወሰ ያለዉ ህዝብ: በቀን በቀን የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ስራ እያዬ የእምነት መሰረቱን እያጠበቀ ያለዉ ህዝብ ይጎዳል:: ማንስ ይጠቀማል? የሚጠቀመዉማ ያዉ እርኩስ መንፈስ ነዉ:: እንግዲህ ቢያንስ አንድ የማዳን እና የመፈወስ ጸጋ ያለዉን ሰዉ በሀሰት ወንጅሎ አሳስሯል እና ለጊዜዉ ደስታዉ ወደርም አይኖረዉም::

ቢሆንም ይሄ ሁሉ የሆነዉ እግዚአብሄር ቢፈቅድ እንጅ እርኩስ መንፈሥ በክርስቶስ አማኞች ላይ አንድም ስልጣን የለዉምና ሰይጣን ደስ እናዳይለዉ ጠላትም እንዳይኩራራ ቅዱስ ዳዊት እንዳለ እንዲህ እያል እንዘምራለን (መዝሙር 68):-
1 እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።
2 ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ ኅጥኣን ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።
3 ጻድቃንም ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ፥ በደስታም ደስ ይበላቸው።
4 ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ በፊቱም ይደነግጣሉ።

The post መምህር ግርማን ዘመነኞች ለምን ወንጀለኛ ብለዉ ወደ እስር ቤት ከተቷቸዉ? appeared first on Zehabesha Amharic.

የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ድምፃቸውን አጥፍተው የሚገቡበት አግባብ ስውሩ የህወሓት አመራር በጀርባ በር በኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ የመደራደሩ ማሳያ ነው።

$
0
0

የጉዳያችን ማስታወሻ

የስርዓቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ድንግዝግዝ፣ሙስና-ገዝ እና ጥቂቶች በውስጥ ስብሰባ እንደፈለጉ የሚገለባብጡት ነው።በአደባባይ ባለስልጣናቱ የሚናገሩት እና በውስጥ መስመር የሚሰሩት ፈፅሞ አይገናኝም።ይህ ደግሞ በድንግዝግዝ፣ወጥነት እና አቅጣጫ የሌለው አሰራር እና ለአገር ጥቅም ሳይሆን ለጥቂቶች ብልፅግና የሚዋትት ስርዓት መለያ ነጥቦች ናቸው።በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው አምባገነን ስርዓት ምን እንደሚያቅድ፣የት ለመድረስ እንደሚያስብ እና ወጥ የሆነ ፖሊሲው ምንድነው? ብሎ ለማወቅ በጎሳ ላይ የተመሰረተ የምጣኔ ሀብት፣ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መሰረቱን ከመናገር ውጭ ወጥ የሆነ ስዕሉን ለማግኘት ለባዕዳንም አስቸጋሪ ሆኗል።በመሆኑም በሚናገራቸው ነገሮች ከማመን ይልቅ ሊያደርግ የሚያስበው ይህንን ነው ብሎ መተንበዩ አዋጪ ነው።
CBE

ለእዚህም አመላካቾቹ ሁለት ነጥቦች ናቸው። እነርሱም

1/ የአገሪቱን ፖለቲካዊ፣ማጣኔ ሃብታዊ እና ወታደራዊ መዘውር የሚያሽከረክረው ህወሃት ዋናው አመራር እራሱን ከቤተ መንግስት ጀርባ ሆኖ አቶ ኃይለማርያም እና መሰሎቻቸውን ከማዘዝ በቀር ወደ አደባባይ ወጥቶ ጋዜጣዊም ሆነ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ አለመታየቱ እና

2/ ከፊት እንዲሰለፉ የተደረጉት እና የእራሳቸው ሃሳብ የማይናገሩቱ እነ አቶ ኃይለማርያም ነገር አሳመርን እያሉ ”ከመምህሩ ደቀመዝሙሩ” እንዲሉ የበለጠ ታማኝነታቸውን ለማፅናት የሚሉት ከሚፈፀመው ጋር አለመገናኘቱ የሚሉት ናቸው።

ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የሚሄድ አንድ የውጭ አገር ባለስልጣን ሁለት አይነት ባለስልጣናት እንዳሉ ጠንቅቆ ያውቃል።እነርሱም የይስሙላ እና ዋናው ባለስልጣን የሚባሉ ናቸው።በምጣኔ ሀብት ጥናት እውነተኛ (real) የሚሉት እና ”እውነተኛ” ያልሆነው (nominal) የተሰኙ ሁለት አፈራረጆች እንዳሉ ሁሉ ባዕዳኑም ከባለስልጣናት ጋር የሚኖራቸውን ቀጠሮ ኤምባሲዎቻቸውን ”እውነተኛው ነው ወይንስ የይምሰሉ ባለስልጣን ነው?” ( Is he nominal or real?) እያሉ መጠየቅ ይዘዋል።አቶ ኃይለማርያም ከይምሰል ውስጥ የሚመደቡ ሲሆኑ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ደግሞ ከዋናው ፖሊሲ ዘዋሪው ውስጥ ይመደባሉ።

የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ድምፃቸውን አጥፍተው እየገቡ ነው
በኢትዮጵያ የአደባባይ መግለጫዎች እና ከበሩ ጀርባ የሚሰሩ ስራዎች የመለያየት አይነተኛ ማሳያዎች ውስጥ አንዱ የግል ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያለበት አግባብ ነው።የይምሰሉ የባለስልጣናት ቡድን በአደባባይ የውጭ ባንኮችን ወደ አገር ቤት ለማስገባት በቅድምያ የአገር ውስጥ ባንኮች መጠንከር አለባቸው ይላል።የውስጥ አመራሩ ደግሞ የግል ባንኮች ከገቢያቸው እስከ 27% ድረስ ለአባይ ቦንድ መግዛት አለባቸው እያለ የባንኮቹን አቅም ያዳክማል። የአደባባዩ አመራር ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች መብራት እና ስልክ ሽጡ ሲሉን አልተቀበልናቸውም ይላል።የውስጥ አመራሩ ግን በመብራት ሥራ ላይ የግል ባለሀብት መግባት ይችላል ይል እና እራሱ ያደራጀውን የግል ባለ ሀብት ቦታውን እንዲይዝ በጎን ይፈቅዳል።

የእዚህ አይነቱ አሰራር ኢትዮጵያ በምን ያህል ደረጃ ለባእዳን እንደተሸጠች ለመለካት በማያዳግት ደረጃ አደጋ ላይ መሆናችንን አመላካች ነው።ከእዚህ ጋር ተያይዞ የግል አለማቀፍ የገንዘብ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ መግባት በእራሱ ጉዳት ወይንም ጥቅም አለው ብሎ ለመናገር የእራሱ የሆነ የተለያየ አቅጣጫዎችን እና የሌሎች አፍሪካ አገራትን ተሞክሮ አንስቶ መተንተን ስለሚጠይቅ በእርሱ ላይ ሃሳብ ለመስጠት ሌላ ጊዜ መመለሱ ይሻላል።ሆኖም ግን ኢትዮጵያ በአደባባይ ለሕዝቧ፣በአገር ውስጥ ላሉ የግል የገንዘብ ተቋማት እና ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ከፊት በተሰለፉ ፖሊስ አውጭ ባልሆኑት ባለስልጣናት እንዲናገሩ የሚደረገው እና በውስጥ መስመር ህወሃት የሚሰራው ሥራ መለያየቱን በትክክል መመልከት ጠቃሚ ነው።

በኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ በውጭ ባንኮች ላይ ያለው ፖሊሲ መቀየሩ በአደባባይ ሳይታወጅ እና በውጭ ያሉ ባንኮችም ፖሊሲው ግራ እንዳጋባቸው በውስጥ መስመር እየገቡ ከህወሃት ጋር በልዩ መስመር እየተደራደሩ አዲስ አበባ ላይ ቢሮ የከፈቱ የውጭ ባንኮች ቁጥር በርክቷል።ቢሮ ሲከፈት ደግሞ ሁለት ስራዎችን ለመስራት ይረዳል።አንዱየተከማቸ ገንዘባቸውን ለማበደር የሚደረጉ የውስጥ ድርድሮችን እና ባለስልጣናትን የማግባባት ሥራ ያቀላጥፉበታል።ሌላው ደግሞ ወደፊት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ሲገቡ እንዴት የአገር ውስጥ ባንኮችን አሸንፈው ገበያውን እንደሚቆጣጠሩ ያጠኑበታል።ከእዚህ በተረፈ በተለያየ መንገድ ከአገር የሚወጣ የውጭ ምንዛሪ ‘እኛጋር አስቀምጡ’ ብለው ከባለስልጣናት ጋር ምንም አይነት ድርድር እንደማያደርጉ ተስፋ እናድርጋለን።

በነገራችን ላይ አሁን አዲስ አበባ ላይ ቢሮ እየከፈቱ የሚገኙት ባንኮች ብለን የምናነሳቸው አህጉር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ የልማት ባንኮች ማለትም የአፍሪካ ልማት ባንክ፣የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እና የመሳሰሉትን አይጠቀልልም።እነኝህ በየትኛውም የዓለም ክፍል ቢሮ የሚኖራቸው እና በንግድ ባንክ ደረጃ የሚሰሩ ስራዎች ውስጥ የማይገቡ የልማት ባንኮች ናቸው።አሁን የምንነጋገረው በኢትዮጵያ ያሉትን የግል ባንኮች ሥራ ጋር ተመሳሳይ ሥራ ያላቸው ባንኮች ግልፅ ባልሆነ መንገድ የመግባታቸው አግባብ ላይ ነው።እዚህ ላይ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት የፖሊሲ ለውጥ ኖሮ የኢትዮጵያ ህዝብም ጥቅምና ጉዳቱ ተነግሮት፣የአገር ውስጥ ባንኮችም በግልፅ ተነግሯቸው እና ብሔራዊ ባንክ ግልፅ የሆነ መመሪያ እና ፖሊሲ አውጥቶ የሚገቡ ቢሆን ለአገር ጉዳት ያለው አይመስለኝም።በእርግጥ ከኢትዮጵያ አንፃር የእራሱ የሆነ ጥናት የሚያስፈልገው ቢሆንም።እስካሁን በሌሎች አፍሪካ አገራት የታየው ተሞክሮ ብዙ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ክስተቶች ተስተውለውበታል።ባጭሩ ግን አሁንም ሊሰመርበት እና አደገኛ አገባብ ያለው ያለ አንዳች መመርያ እና ፖሊሲ ወይንም ድብቅ ስምምነት እየተስማሙ ቢሮ ስለሚከፍቱት ባንኮች ጉዳይ ነው።

በመጨረሻም እስከ ያዝነው ዓመት ድረስ ብቻ ድምፃቸውን አጥፍተው አዲስ አበባ ላይ ቢሮ የከፈቱ እና የብሔራዊ ባንክ በየትኛው ፖሊሲ ቢሮ እንዲከፍቱ እንደፈቀደ ግልፅ ያልሆኑት የውጭ ዓለም አቀፍ ባንኮች ዝርዝር አይተን ፅሁፌን ልደምድም። እዚህ ላይ ከተዘረዘሩት በላይ ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገመታል።እዚህ ላይ ባንኮቹ በአገር ውስጥ ቢሮ መክፈታቸውን የምንሰማው በውጭ አገር ከሚወጡ ዜናዎች እና አልፎ አልፎ የአገር ውስጥ ጋዜጦች የሚያወጡት ዜና ላይ እንጂ የመንግስት የዜና አውታሮች ለጉዳዩ እንግዳ መሆናቸው በእራሱ አነጋጋሪ ነው።

1/ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ ቢሮ የሚከፍተው የቱርክ መንግስት ባንክ ”ዚራት ባንክ”፣

2/ የእንግሊዙ እና ደቡብ አፍሪካ መሰረቱን ያደረገው ”ስታንዳርድ ባንክ”፣

3/ የጀርመኑ ግዙፉ ”ኮሜርዝ ባንክ” እና

4/ ግዙፉ የአሜሪካ ባንክ ”ሲቲ ባንክ” ይጠቀሳሉ።

ባጠቃላይ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ጉዳት ወይንም ጥቅም አለው ብሎ ለመደምደም ማጥናት የሚጠይቅ ቢሆንም በአገር ውስጥ ያሉ የግል ባንኮች አድገው ድንበር ተሻጋሪ ቢያንስ አፍሪካ ከተሞች ላይ የመድረስ አቅማቸው እንዲጎለብት መንግስት ምን አደረገ? ብሎ መጠየቅ ግን ተገቢ ነው።ባንኮች የአንድ ምጣኔ ሀብት ዋና አነሳቃሽ ሞተሮች ናቸው።የመንግስት ጥበቃ እና እንክብካቤ ይሻሉ።በተቃራኒው በኢትዮጵያ ግን ከባእዳን የተሰጠ ተልኮ እስኪመስል ድረስ በተለያዩ መመሪያዎች እንዲታነቁ ተደርገዋል።እዚህ ላይ በግድ የተጫነባቸው እና በግል ባንኮች ማኅበር ጭምር ክፉኛ የተተቸው የአባይ ቦንድ ግዥ ግዳጅን መጥቀስ ይቻላል።ባንኮቹ እንዲገዙ በግድ የተነገራቸው የአባይ ቦንድ ግዥ ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ እና ተወዳዳርነታቸውን በእጅጉ እንደሚጎዳው ቢገልፁም ሰሚ አላገኙም።

ጉዳያችን GUDAYACHN
ጥቅምት 20/2008 ዓም (Oct.31,2015)
www.gudayachn.com

The post የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ድምፃቸውን አጥፍተው የሚገቡበት አግባብ ስውሩ የህወሓት አመራር በጀርባ በር በኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ የመደራደሩ ማሳያ ነው። appeared first on Zehabesha Amharic.

በአሜሪካዋ ጆርጂያ ጠፍተው የነበሩት ሶስት ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ተገኝተዋል

$
0
0

admas

ከባለፈው ሐሙስ ኦክቶበር 29/2015 ዓ.ም ጠፍተው የነበሩት 3 ኢትዮጵያውያን ህፃናት መገኘታቸውን ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ:: በዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ስለ ልጆቹ መጥፋትና ሕዝቡም በማፈላለግ እንዲተባበር መጠየቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል::

የ5 አመቷ በጸሎት ታገሰ – የ5 ዓመቱ በቃሉ ታደሰና የ4 ዓመት ከ6 ወሯ የውብዳር ዳንኤል ከጠፉበት በሰላም በመገኘታቸው ቤተሰቦቻቸው ለተደረገው ትብብር አመስግነዋል::

The post በአሜሪካዋ ጆርጂያ ጠፍተው የነበሩት ሶስት ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ተገኝተዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

የኮሚኒኬሽን ሚ/ሩ እቶ ጌታቸው ረዳ “ጨረቃ ላይ” ጥለውን ነጎዱ

$
0
0

ከታምሩ ገዳ

በርካታ ኢትዮጵያኖችን ለ ወከባ፣ ለ አሰራት እና በመጨረሻም ለሰደት የዳረጉት አወዛጋቢዎቹ የጸረ ሽብር እና የፕሬስ ህጎች በገዢው መንግስት በኩል እንከን የለሽ መሆናቸውን ቢነገረንም ዛሬም ድረስ ብዙዎችን ከአገዛዙ ጋር ሆድ እና ጀርባ አንዳደርጋቸው ይገኛል።ችግሩም በቅርቡም የፈታል ተብሎ አይጠበቅም።

Reda Getachew

ታዲያ ባለፈው እሁድ የጀርመን ራዲዮ የአማሪኛው ክፈለ ጊዜ (ዶቼ ቬሌ ) “ በአትዮጵያ ሃሳብን በነጻ የመግልጽ መብት፣የ ፕሬስ ህጉ እና በጸረ ሽብር ሕጉ ዙሪያ” አራት የተለያዩ እንግዶችን ለንትርክ (Cross Talk )ፕሮግራም ጋብዞ ነበር ። እንርሱም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት እቶ ጌታችው ረዳ ከሃሳይ፣ እውቁ የህግ መምህር እና የአለማቀፍ የህግ ባለሙያው ዶ/ር ያቆብ ሃይለማሪያም፣ ታዋቂው የህግ ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጉ እና ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ ነበሩ። የእንግዶቹ ሰብጥርን ገና ከጅማሪው ሰሰማ ፕሮግራሙ አሰተማሪ እና ዘና የሚያደርግ ፕሮግራም አንደሚሆን ገምቼ ነበር ። በተለይ ደግሞ አንዳንድ ምእራባዊን የመንግስት ባለሰለጣናት ከሕዝብ ሰለሚሰነዘሩ ቅሬታዎች እና ትችቶች ከሚዲያ ፊት ቀርበው ምላሻቸው ምንም ይሁን ምን ሲሟገቱ ወይም ሰህተታቸውንም ሲያምኑ ሰሰማ “ይህ አይነቱ እድል እና መደረክን ኢትዮጵያ ውስጥ መቼ ይሆን በነጻ የምናየው?” የሚል ጥያቄ ውሰጤን ሁሌም ስለ ሚኮረኩረኝ እና በእነርሱ የሰለጠነ የሚዲያ ባሕል ሰለ ምቀናም ጭምር ነበር።
ከ ንትርክ ፕሮግራሙ አዘጋጅ እና ጋዜጠኛዋ ከተወረወሩት በርካታ ጥያቄዋች መካከል “ከ አንድ አመት ተኩል እሰራት በሁዋላ ሰሞኑን በነጻ ሰለተለቀቁት(አንዱ በ20 ሺህ ብር ዋስ ነው የወጣው) የዞን 9 ጦማሪያኖች እና ጋዜጠኞች ከእስራት መፈታት ምን ትላላችሁ?፣,ምንስ ተሰማችሁ? ፣እነዚህ ለተለያዩ ችግሮች የተዳረጉት ወጣት ጦማሪዎች በፍርድ ቤት ነጻ ናችሁ ከተባሉ የሞራል ካሳ ሊከፈላቸው አይገባም ወይ?፣ገዢው መንግስትስ ወደፊት ከነጻው ፕሬስ ጋር አብሮ መሰራት ይችላል? …ወዘተ።” የሚሉ ይገኙበታል ። ከ ሚ/ር ጌታቸው በቀር ሶስቱም እንግዶች “የዞን 9 ጸሃፊዎቹ በእስር ቆይታቸው የተለያዩ ስቃዮች እንደ ደረሱባቸ ው፣ከጅማሪው ሊታሰሩ አንደማይገባ በፍትሕ እጦት መሰቃየት እና መጉላላት እንዳልነበረባቸው፣የሞራል ካሳ ጥያቄ የሚባለው ጉዳይ ደግሞ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንደማያዋጣ እና ፌዝ መሆኑን ፣ ኢሕአዲግ በተፈጥሮው ዲሞክራሲያዊ መንግስት መሆን እንደማይችል ፣ጦማሪዎቹ የፖለቲካዊ ውሳኔ ሰለባዎች መሆናቸውን ፣ ወጣቶቹ በመለቀቃቸው ገዢው መንግስትን ማመሰገን አንደማይጠበቅባቸው “እና መሰል መልሶችን እንግዶቹ በተናጥል እና በዝርዝር አስረድተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የአቶ ጌታቸው ረዳ አቋም የነበረው ደግሞ በከፊል “አቃቢ ህግ እና ፖሊስ በቂ ማስረጃ ባለማቅርባቸው/ የቤት ስራቸውን ባለመሰራታቸው ፍ/ቤቱ ታሳሪዎቹን በነጻ አሰናብቷቸዋል፣ዶ/ር ያቆብ እና አቶ ተማም ወጣቶቹ በመፈታታቸው የተበሳጩ ይመሰላሉ፣ጉዳዮን ለፖለቲካ ሟሟቂያ ካለተጠቀምንበት በቀር ፣አንዳንዴ ፍ/ቤት ጥፋተኛ ያላቸው ሰዎች ከ20 አመት እሰራት በሁዋላ ነጻነታቸው የሚረጋገጥበት ሁኔታ ስለ ሚከሰት ታሳሪዎቹን እንኳን ደሰ ያላችሁ ነው ማለት ያለብን ።” በማለት በጦማሪያኖቹ እና በጋዜጠኞቹ ያላግባብ ከ አንድ አመት በላይ መታሰር በደረሰባቸው የአካላዊ እና የስነልቦናዊ ጉዳት ከ መቆጨት ለፍትህ ስርአቱ(ለዳኞቹ) ያላቸውን አክብሮት ለመግለጽ ሞክረዋል። በነገርራችን ላይ እነዚህ ወጣቶች ከወራት በፊት “በሽብር ስራዎች ሰለመዘፈቃቸ በቂ መረጃ አለን”ተበሎ በጠ/ሚ/ሩ ሳይቀር ለአለም መገናኛ በዙሃናት ሳይቀር የታወጀባቸው ልጆች መሆናቸውን ማሰታወስ ግድ ይላል።
እየተሟሟቀ እና አጓጊ እየሆነ የሄደው ንትርኩ በተለይ ጠበቃ ተማም ከዚህ ቀደም ደንበኞቻቸው ማቆሚያ በሌለው የክስ ምክንያቶች እንዴት እንደተጉላሉባቸው በመግለጽ ላይ እያሉ ተራቸው እስኪ ደረስ ዝም ብለው ለመሰማት ፍቃደኛ ያለሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ከ አስምት ጊዜያት በላይ “ተማም…!ተማም…! ተማም….!”በማለት ተናጋሪው አቶ ተማምን ለማቋረጥ እና የረሳቸውን አቋም ለመግለጽ ሲሞከሩ ተሰተውለዋል።ይህ አይነቱ የመደርክ አና ይማይክ ሺሚያ ደግሞ ብዙውን ጊዜ በእኛ አገር ባለሰልጣናት እና እንግዶች ዘንድ የተለመደ አይደለም ። በንትርርኮች ወይም ቃለ መልልሶች ላይ ያለመደማመጥ ችግር እንደ አረብ አገራት ግን በሰፋት የዘወተራል ። ክቡር ሚ/ሩ ከሰነዘሯቸው ግለሰባዊ ውንጀላዎች ለምሳሌ ያህል ባነሳ “ ለአንሰተኛ ጥብቅናቸው ካለሆነ በቀር አቶ ተማም ጥብቅና ለቆሙላቸው ከፍተኛ ፕሮፋይል ያላቸው ደንበኞቻቸው ጉዳይን አላሸነፉም ፣ዶ/ር ያቆብ ከዚህ በፊት መንግስትን በሃይል ለመጣል ሞክረው ያለተሳካለቸው ግለሰብ ናቸው ።”የሚሉ ይገኙበታል።

በንትርኩ ላይ “ከጥያቄው ጋር የማይዛመዱ ጉዳዮች ለማቅረብ እየተሞከረ ነው” የሚል ወቀሳ ያሰሙት አቶ ጌታቸው “ወደፊት ከተማም ጋር እንገናኝ ይሆናል ፣አሁን ሌላ ፕሮግራም አለኝ።” በማለት አገሪቱ በህይወት እስትንፋስ መሰጫ መሳሪያ (ላይፍ ሰፖርት ማሺን ) ወስጥ እንዳለች እና ቁልፉም በእርሳቸው እጅ ብቻ እንዳለ እስኪመሰል ድረስ ፣ምንም እንኳን በፕሮግራሙ እዘጋጅዋ “አቶ ጌታቸ ተሰናብተውን ሄደዋል “ብንባለም በእኔ እምነት ግን ሞቅ ብሎ የነበረው ንትርኩን “በበቃኝ”በማቋረጥ ፣ከማይክሮፎኑ ባሻገር ጆሯቸውን እና ልቦናቸውን ሰጥተው ሁሉንም እንግዶች እና ሃሳባቸውን አክብረው ፕሮግራሙን በጥሞና ይከታተሉ የነበሩ(እኔንም ጨምሮ) በርካታ አደማጮችን እና የነጻፕሬስ ወዳጆችን ጨረቃ ላይ ጥለውን እነደ ነጎዱ ሆኖ ነው የተሰማኝ።
እኔ የምለው “የህዝቡን ሙሉ ልብን በማግኘት ፣ ተቋዋሚዎችን በዝረራ በመጣል ምርጫውን 100%ያሸነፈ ፣ኢኮነሚውን በ ሁለት ዲጅት ያሳደገ፣ ተራራዎችን እሰከ ማንቀጥቀጥ ድረስ የቻለ ፓርቲ ሹም ” የሆኑት እኚህ አቶ ጌታቸው ረዳ የተሰጣቸው ትልቅ እድልን/መድረክን በመጠቀም ከ ፕሬስ እና ከጸረ አሸባሪው ሕጉ አኳያ ሊሟገቷቸው የቀረቡት ሶሰቱ እንግዶችን በመሞገት ለተሾሙበት የ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊነት ትልቅ ቦታ በብቃት መወጣት ሲገባቸው፣ድርጅታቸውን ሆነ መንግስታቸውን ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ለማሸጋገር መጣጣሩን ትተው ንትርኩን በነገር ጀምረው ዶ/ር ያቆብንም “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ”በማለት እርሳቸውም (አቶ ጌታቸው) በቅጡ ሳይሰናበቱን መነጎዳቸው ሚኒስትሩ በመጀመሪያ አስተያየታቸው ላይ “ፖሊስ እና አቃቢ ሕግ በቂ ማስረጃ ባለማቅረባቸው ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዋችን በነጻ አሰናብቷል።” እንዳሉት ሁሉ በእለቱ የንትርክ ፕሮግራም ላይ ኢሕአዲግ ማሰረጃ ማቀረብ የተሳናቸው /ደካማ ፖሊሶች እና አቃቢ ህጎች የተነሰራፉበት ድርጅት ብቻ ሳይሆን በክፉ ቀን በሃሳብ አተካሮ ሸንጣቸውን ገትረው መሟገት የተሳናቸው ሚኒስተሮች የተበራከቱበት መንግስት መሆኑን ያሳያል ። ለማንኛውም አንዳንዴ ለመሪዎቻችን ቅን ልቦና ፣ብሩህ አይምሮ እና አንደበተ ርእቱነተን ብንመኝላቸው አይከፋም።

The post የኮሚኒኬሽን ሚ/ሩ እቶ ጌታቸው ረዳ “ጨረቃ ላይ” ጥለውን ነጎዱ appeared first on Zehabesha Amharic.

የህወሓት አገዛዝ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩትን እየለቀመ እያባረረ ነው

$
0
0

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ እንደዘገበው) ህወሓት በ1983 ዓ.ም መላ አገሪቱን በነፍጥ እንደተቆጣጠረ በሁለት ያለፉ የኢትዮጵያ መንግስታት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት፣ ዕውቀትና ጉልበት ፈሶበት ለዘመናት በስንት ልፋትና ጥረት የተገነባውን የአገር መከላከያ ሰራዊት ባደረበት ጭፍን ጥላቻና ቂም ብቻ ተመስርቶ “የደርግ ነው” በሚል ሰበብ ባንድ ጀምበር ንዶ ማፈራረሱን አገር ያወቀው ፀሃይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡

(ፎቶ ፋይል መፍቻ) የሕወሓት መንግስት በስማቸ እየነገደ ገንዘቡን የሚበላባቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ወታደሮች በሱማሊያ ሬሳቸው ሲጎተት::

(ፎቶ ፋይል መፍቻ) የሕወሓት መንግስት በስማቸ እየነገደ ገንዘቡን የሚበላባቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ወታደሮች በሱማሊያ ሬሳቸው ሲጎተት::


ከበረሃ የመጡ ድኩማን ታጋዮቹን ለሙያው የሚመጥን ምንም አይነት ዘመናዊ ዕውቀት ሳይኖራቸው የጀነራልነት ማዕረግ በማሸከም በአየር ኃይሉና በምድር ኃይሉ ውስጥ በሚገኙ የአዛዥነት ቦታዎች ላይ እነሱን ብቻ አስቀምጦ ስልጣኑን ለመጠበቅ ብቻ እንዲተጉለት በማድረግ የአገራችንን ብሄራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ጥሎት ይገኛል፡፡


ህወሓት የተባለው ዘረኛ ቡድን ውስጡ በቂምና በጥላቻ ብቻ ተሞልቶ ያፈራረሰውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አደጋ ባንዣበበበት ጊዜ ጥሪ በማድረግ መልሶ ለመሰብሰብ የሞከረ ሲሆን ከጦርነቱ በኋላ ደግሞ አብዛኞቹን ከተጠቀመባቸው በኋላ እንደገና አባሯቸዋል፡፡


አሁን ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ እያፋፋመው ከሚገኘው የአርበኝነት ትግል ጋር በተያያዘ ከትግራይ ተወላጅ የህወሓት ተጋዮች ውጭ በሆኑ ወታደራዊ አዛዦች ላይ ዕምነት በማጣቱ የመከላከያ ኃይሉን የማጥራት የወቅቱ አንገብጋቢ ውሳኔውን የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን በማባረር ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል፡፡


ቂምና በቀሉ መቸም የማይበርድለት ህወሓት በተደጋጋሚ የደም ቁማር ሲቆምርባቸው ከኖሩት የተባረሩ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት አብዛኞቹ የአርበኝነት ትግሉን በመቀላቀል ላይ ናቸው፡፡

The post የህወሓት አገዛዝ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩትን እየለቀመ እያባረረ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

አይኔ አያየ እዚህ ዉስጥ አልገባም – መሠረት ሙሌ (ኤፍሬም ማዴቦ ከአርበኞች መንደር)

$
0
0

Ephrem Madebo

መብራቱን አጥፍቼዉ አልጋዬ ላይ የወጣሁት በግዜ ነዉ። አለወትሮዬ እንቅልፍ የሚባል ነገር በአይኔ አልዞር ብሎኝ ከጨለማዉ ጋር ፊት ለፊት ተፋጥጠናል። የነፋስ ሸዉታ እንኳን የማይሰማበት ደረቅ ሌሊት ነዉ። ጨላማዉ አይን ይበሳል። እቤቱ ዉስጥ ያለዉ ሰዉ ሁሉ ተኝቷል። ቀኑን በሠላም ላዋለኝ አምላክ ምስጋና ሰጥቼ ሌሊቱንም አደራ ብዬዉ ፀሎቴን ጨረስኩ። ያ ምቀኛ እንቅልፍ ግን አሁንም እንደከዳኝ ነዉ። ትንሿ አልጋዬ ላይ ግራ ቀኝ እያልኩ ተገለባበጥኩ። እንቅልፍ ተጎትቶ የሚመጣ ይመስል አሁንም አሁንም ላይ ታች እያልኩ አልጋዉ ላይ እራሴን ጎተትኩት . . . እንኳን እንቅልፍ ሊወስደኝ ጭራሽ አይኖቼ መርገብገባቸዉን ያቆሙ ይመስል ቀጥ ብለዉ ቀሩ። ከተጋደምኩበት ብድግ ብዬ መብራቱን አበራሁና ለመንገድ ከያዝኳቸዉ ሁለት መጻህፍት አንዱን አዉጥቼ ማንበብ ጀመርኩ። እኔ ላንብበዉ ወይ መጽሀፉ ያንብበኝ አላዉቅም። ጧት ስነሳ ግን “The Architecture of Democracy” የሚል መጽሐፍ ደረቴ ላይ ተለጥፎ ነበር። ሰዐቴን ሳየዉ ከሌሊቱ ስምንት ሰዐት ተኩል ይላል። ከአልጋዬ ላይ ዘልዬ ወረድኩና ሰዉነቴን ታጥቤ ልብሴን ከለበስኩ በኋላ መኪናዉ ዉስጥ ገብቼ “I’m ready” አልኩ። የመኪናችን መብራት ጨለማዉን እየገላለጠዉ የአስመራ ከረንን መንገድ ተያያዝነዉ። መኪናዉ ዉስጥ ከገባሁ በኋላ እንደገና አፌን የከፈትኩት ባሬንቱ ደርሰን ቁርስ ሳዝ ነዉ። ባሬንቱ በግዜ መድረሳችን ደስ ቢለኝም የቀረን መንገድ ርዝመት ታየኝና ቁርስ መብላቴን ትቼ . . . በሰዐት ይህን ያክል ብንጓዝ እያልኩ ዋናዉ ጉዳያችን ቦታ የምንደርስበትን ሰዐት ማስላት ጀመርኩ። የስሌቱ ዉጤት ከሦስት ሰዐት ሲበልጥብኝ ተናደድኩ። ቀሪዉ መንገድ ገና ሳልጀምረዉ ሰለቸኝ። በተፈጥሮዬ መንገድና መኃላ ሲረዝም አልወድም።

ተሰነይ ስንደርስ መኪናዉ ዉስጥ የነበረዉ ሰዉ ሁሉ ቡና ካልጠጣሁ አለ። መኪናችንን አቁመን በቁማችን ቡናችንን ፉት አድርገን መንገዳችንን ተያያዝነዉ። እሁድ ጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓም አርበኞች ግንቦት ሰባትን የፈጠሩት ሁለት ድርጅቶች ከተዋሃዱ በኋላ ለሁለተኛ ግዜ የሰለጠኑ ታጋይ አርበኞች የሚመረቁበት ቀን ነበር። ከዚህ ቀደም እንደዚህ አይነቱን የምርቃት ዜና የምሰማዉ በኢሳት ሬዲዮና ቴሌቭዥን ብቻ ስለነበር እቦታዉ ደርሼ የምረቃዉን ስነስርዐት ለማየት የነበረኝ ጉጉት እጅግ በጣም ከፍተኛ ነበር። የምሳ ሰዐት ከመድረሱ በፊት በቀኝ በኩል ዋናዉን መንገድ ለቅቀን ዉስጥ ዉስጡን ወደ ምርቃቱ ቦታ የሚወስደዉን ኮረኮንች መንገድ ተያያዝነዉ።

ግቢዉ ዉስጥ ያለዉ ጥድፊያና ግርግር አንድ ትልቅ ዝግጅት መኖሩን በግልጽ ይናገራል። የተለያየ ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱና መሳሪያ የተሸከሙ አርበኞች ግቢዉን ሞልተዉታል። ያነገቱትን ጠመንጃ ስመለከት ቆራጥነታቸዉ ታየኝ። በቀጭኑ ተጎንጉኖ ማጅራታቸዉ ላይ የወደቀዉን ፀጉራቸዉን ሳይ ቴዎድሮስና ዮሐንስ ትዝ አሉኝ። ፈገግታ በፈገግታ የሆነዉን ፊታቸዉን ስመለከት ደግሞ የእናት አገሬ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ደጃፍ ላይ መሆኑ ታየኝና የኔም ፊት እንደነሱ በፈገግታ ተሞላ። ተራ በተራ እየመጡ “ጋሼ አፍሬም” እንደኳን ደህና መጣህ ብለዉ ሲጠመጠሙብኝ በአንዱ ትከሻዬ ፍቅራቸዉ በሌላዉ ጀግንነታቸዉ ዘልቆ ሰዉነቴ ዉስጥ ገባ። ጥንካሬያቸዉ በጅማቴ ፍቅራቸዉ በደም ስሬ ዘለቀ። እኔነቴ ሲታደስና በአገሬ ላይ ያለኝ ተስፋ ሲለመልም ተሰማኝና ደስ አለኝ። አዎ ደስ አለኝ . . . እየመጣ የሚሄድ ግዜያዊ ደስታ ሳይሆን የዉስጥ አካላቴን የዳሰሰ ዘላቂ የመንፈስ ደስታ ተሰማኝ። በጣም ደስ የሚልና በአሁኖቹ ቋንቋ “የሚመች” ቀን ነበር። የዕለቱን ዝግጅት ለማየት መቸኮሌን ያወቁት እግሮቼ የምረቃዉ በዐል ወደሚከበርበት ዳስ- ፍትህ፤ ነጻነትና እኩልነት የናፈቀዉ ልቤ ደግሞ ወደ ወደፊቷ ኢትዮጵያ ይዘዉኝ ጭልጥ አሉ፡ . . . ለካስ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ሩቅ አይደለችም።

“ማነዉ ሚለየዉ . . .ሚለየዉ፤ ይህም ትዉልድ ፍም እሳት ነዉ” የሚለዉን የናቲ ማን እና ጃኪ ጎሲ ዘፈን በርቀት ሲሰማ በቀኑና በዘፈኑ መግጠም ተገረምኩ። “እዉነትም ይህ ትዉልድ ፍም እሳት ነዉ” እያልኩ በለሆሳስ ለራሴ እየነገርኩት ዳሱ ዉስጥ ገብቼ ቁጭ አልኩ። እርግጠኛ ነኝ ይህንን ጽሁፍ የሚያነብ ሰዉ ዳሱ ዉስጥ የነበረዉን ፍጹም ኢትዮጵያዊ የሆነ የጀግንነት፤ የቆራጥነት፤ የእልህና የመተማመን ልዩ ስሜት መረዳት የሚችለዉ እኔ በዚህ ባልተባ ብዕሬ ስገልጸዉ ሳይሆን እንዳዉ በደፈናዉ ዳሱ እራሱ ኢትዮጵያዊ ነበር ብዬ ባልፈዉ ነዉ።

አገራችን ኢትዮጵያ ከራሱ ምቾትና የተደላደለ ኑሮ ይልቅ የወገኖቹ መብትና ነጻነት የሚያንገበግበዉና እራሱን ለፍትህ፤ ለአንድነትና ለነጻነት ለመሰዋት ዝግጁ የሆነ የየዘመኑ ምርጥ ትዉልድ አላት። ይህንን የኛን ዘመን ምርጥ ትዉልድ ነዉ አርቲስት ጃሉድ “ይህም ትዉልድ ፍም እሳት ነዉ” ብሎ በጣፋጭ ዜማዉ ያወደሰዉ። እኔ ጥርጥርም የለኝ ይህ ትዉልድ አንድና ሁለት ብቻ ሳይሆን ለቁጥር የሚታክቱ ብዙ ፍም እሳቶች አሉት። ችግሩ የእሳት ነገር አዚህ ቤት ነደዳ እዚያም ቤት ነደደ ስራዉ ማቃጠል ነዉና አንዱን እሳት ከሌላዉ እሳት መለየት አስቸጋሪ ነዉ። እኔም ችግሬ እዚህ ላይ ነዉ። ፊት ለፊቴ ላይ ቁጭ ብለዉ ስለማያቸዉ ፍም እሳቶች (ጀግኖች) ላወራችሁ እየፈለኩ ምርጫዉ አዋጅ ሆነብኝ. . . የራሱ ጉዳይ ብዬ አንዱን ጀግና መረጥኩ። ይህንን ዛሬ የምተርክላችሁን ጀግና ስመርጥ ግን እንዳዉ በደፈና አልነበረም። ጉዳይ አለኝ . . . . ጉዳዩ አንዲህ ነዉ።

በዕለቱ በተመራቂ አርበኞች ተዘጋጅተዉ ከቀሩቡት የተለያዩ የኪነት ስራዎች ዉስጥ አንዱ የድራማ ዝግጅት ነበር። ሦስት የተለያዩ ድራማዎች መታየታቸዉ ትዝ ይለኛል። ዳሱ ዉስጥ የተሰበሰበዉን በብዙ መቶዎች የሚቆጠር ሰዉ ስሜት የኮረኮረዉና የእያንዳንዱን ሰዉ የልብ ትርታ ሰቅዞ የያዘዉ ግን በእዉነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተከወነዉ የመጨረሻዉ ድራማ ነበር። ድራማዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለይ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ናችሁ እየተባለ በየቀኑ በህወሃት የደህንነት ሠራተኞች እጃቸዉ እየታሰረ በየወንዙና በየፈፋዉ በግፍ እየተገደሉ ስለሚጣሉ ኢትዮጵያዉያን የሚተርክ ድራማ ነበር።

ድራማዉ “ኮሜዲ” የሚባል ክፍል የለዉም። ተጀምሮ እስኪያልቅ “ትራጄዲ” ብቻ ነዉ። ያሳዝናል፤ ያስቆጣል፤ ያስቆጫል፤ያንገበግባል፤ አንጀት ያቆስላል፤ ልብ ያነድዳል . . . ወይ ነዶ ያሰኛል ። እኔማ እንኳን ትራጄዲ አይቼ በተፈጥሮዬ ሆደ ቡቡ ነኝና በደል ስመለከት ማዘን ልማዴ ሆኖ አምባዬ መፍሰስ የጀመረዉ ገና ድራማዉ ሲጀምር ነበር። በተለይ አናታቸዉ እየተደበደበ የሚቀበሩበትን ጉድጓድ በግድ እንዲቆፍሩ የተደረጉትን ሁለት ወጣት ወገኖቼን ሳይ ሆዴ ባባ፤ አንጀቴም ቆሰለ። ልቤ ዉሰጥ የነደደዉ እሳት ትንታጉ እየተንቦገቦገ ወጥቶ የዉጭ ሰዉነቴን ጭምር ለበለበዉ። ለወትሮዉ ነገር ማመዛዘን የሚቀድመዉ አዕምሮዬ በቀል በቀል አሰኘዉ። የነደደዉ ልቤም ለበቀል አደባ። ጉድጓዱ ተቆፍሮ ካለቀ በኋላ የደህንነት ሠራተኛዉ AK ጠመንጃዉን አንደኛዉ ወጣት አገጭ ላይ ቀስሮ በአፈሙዙ አንገቱን ቀና እንዲያደርግ እያስገደደዉ . . . “አየኸዉ የምትገባበትን ጉድጓድ” እያለ ወጣቱ ወገኔ ላይ ሲሳልቅበት ሰማሁና በሀይወቴ ለመጀመሪያ ግዜ ኢትዮጵያዊነቴን ጠላሁት። አጠገቡ የቆመዉና በቁሙ ሞቱን የሚጠባበቀዉ ሌላዉ ወጣት ወገኔ ደግሞ . . . ግደለኝ . . . ግደለኝ. . . ግደለኝ እንጂ! . . . ምን ትጠብቃለህ እያለ የጓደኛዉን ሞት በአይኑ ከሚያይ የራሱን ሞት የሚለምነዉን ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ድምጽ ስሰማ ደግሞ 360 ዲግሪ ተገለበጥኩና ከደቂቃዎች በፊት የጠላሁትን ኢትዮጵያዊነት መልሼ ወድድ አደረኩት። የወያኔዉ ጨካኝ ነብሰ ገዳይ ፉከራና ቆራጡ ኢትዮጵያዊ ያደረጉት የቃላት ምልልስ እምባዬን ጎትቶ አመጣዉና ፊቴ እምባ በእምባ ሆነ። ያ ከግማሽ ሰዐት በፊት ሲጨፈርበትና ሲደነስበት የነበረዉ ዳስ ሰዉ የሌለበት ባዶ ቤት ይመስል ጭጭ አለ። እኔ ኤፍሬም ሰዉ አልገድልም፤ በእኔ እጅ የሰዉ ህይወት ይጠፋል ብዬ አስቤም አልሜም አላዉቅም። ያንን የህወሃት ቅጥረኛ በዚያች ሰዐት ባገኘዉ ኖሮ ግን ለመበቀል ሳይሆን ለሰዉ ልጅ ህይወት ክብር ስል እገድለዉ ነበር።

ድራማዉ እንዳለቀ ወደ ዉጭ ወጣሁና ድቅድቅ ጨለማ ዉስጥ ብቻዬን ቁጭ አልኩ። ሀሳብ. . . የትናንት ሀሳብ፤ የዛሬ ሃሳብ፤ የነገ ሀሳብ፤ የከረመ ሀሳብና ሁሉም ሀሳብ አንድ ላይ ተሰባስበዉ ወረሩኝ። ግራ ሲገባኝና መላቅጡ ሲጠፋኝ ግዜ ትንፋሼን ዋጥ አደረኩና አንቺ እማማ ብዬ አገሬን ተጣራሁ . . . አሁንም አሁንም ደግሜ ተጣራሁ። ህመሟ ብርቱ ነበርና አልሰማችኝም። አይዞሽ ይህ ቀን ያልፍና አንቺም ከህመምሽ እኔም ከማያባራዉ የሀሳብ በሽታ ድነን አዲስ ታሪክ እንጽፋለን ብዬ ከአገሬ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ዳሱ ዉስጥ ከነበሩት አርበኞች ጋር ተቀላቀልኩ። እለቱን ሲያስጨፍረን የዋለዉ አደራ ባንድ “ነይ ደኑን ጥሰሺ” የሚለዉን ቆየት ያለ የመሀሙድ አህመድ ዘፈን ሲጫወት ልጅነቴ ትዝ አለኝና ከፍም እሳቶች ጋር መደነስ ጀመርኩ።

ጭልጋን ይዞ፤ጋይንትን ይዞ፤ የጎበዞቹን ጎራ ጃናሞራን ይዞ፤ ደምቢያን ይዞ፤ ወልቃይት ጠገዴን ይዞ፤ ላይ አርማጭሆንና ታች አርማጭሆን ይዞ ወዘተ . . .ድፍን ጎንደር የጀግኖች አገር ነዉ። አዎ! ወልቃይት ጠገዴ ከጀግናም የጀግና አገር ነዉ።ወልቃይት ጠገዴ ጎንደሬ አይደለህም ተብሎ ከተነገረዉ ከሃያ አራት አመታት በኋላ ዛሬም ህልዉናዉን ለወያኔ ፋሺስቶች አላስረክብም ብሎ ጎንደሬነቱን ለማረጋገጥ ሽንጡን ገትሮ የሚዋጋ የጀግኖች አገር ነዉ። ጎንደር የአፄ ቴዎድሮስ፤ የእቴጌ ምንትዋብ፤ የፊትአዉራሪ ገብርዬ፤ የአየለ አባ ጓዴና የጄኔራል ነጋ ተገኝ አገር ናት። ጎንደር ኢትዮጵያ ከሌለች እኛ የለንም ብለዉ ሙሉ ህይወታቸዉን ለትግል የሰጡ እነ ታማኝ በየነንና እነ አርቲስት ሻምበል በላይነህን ያበቀለች አገር ናት። ወላድ በድባብ ትሂድ. . . የጎንደር ማህፀን ዛሬም አልነጠፈም።

ዛሬ ይዤላችሁ የመጣሁት ጀግና ተወልዶ ያደገዉ አማራ ክልል ጭልጋ ወረዳ ልዩ ስሟ ጫኮ በምትባል ቦታ ነዉ። የገበሬ ልጅ ነዉ፤ እሱም ምኞቱ ገበሬ መሆን ነዉ። የሚኖረዉ መተማ ከተማ ዉስጥ ነዉ። ስሙ መሠረት ሙሌ ይባላል። ፈገግታ የማይለየዉ ፊቱ የዋህነቱንና ገራገርነቱን አፍ አዉጥቶ ይናገራል። ሲናገር ረጋ ብሎ ነዉ። አተኩሮ ላየዉ ሰዉ አይነ አፋር ይመስላል፤ የቁርጥ ቀን ሲመጣ ግን እንደ መሠረት ሙሌ ደፋር ሰዉ የለም። አይኑ እፊቱ ላይ ቆሞ ከሚያናግረዉ ሰዉ አይን ጋር ሲጋጭ አንገቱን ይሰብራል። እቺ የሰዉ አይን የመሸሽ በሽታ ደግሞ አበሾች ስንባል የሁላችንም በሽታ ናት። ጠይም ፊቱ ላይ እንደ ችቦ የተተከሉት የመሠረት ሙሌ አይኖች የሰዉን ዉስጥ ዘልቀዉ የሚያዩ ይመስላሉ። ሰዉነቱ ደንዳና ቁመቱ መካከለኛ ነዉ። ልቡ ግን ትልቅ ነዉ። አዎ መሠረት ሙሌ ልቡ ትልቅ ነዉ።

ዕለቱ ሰኞ ነዉ – ሰኞ ሚያዝያ 26 ቀን 2007 ዓም። የህወሃት የደህንነት ሰዎች አንድ ኮሎኔልና ሌሎች አራት ሰዎች ተገድለዋል በሚል ድፍን መተማን እያመሷት ነዉ። እያንዳንዱ የመተማ ነዋሪ በግድያዉ የተሳተፈ ይመስል በአጠገባቸዉ ያለፈዉን ሁሉ ወንድ፤ ሴት፤ ወጣትና ሽማግሌ ሳይለዩ ሁሉንም እያስቆሙ አጥንት ዉስጥ ዘልቆ የሚገባ ስድብ ይሰድባሉ፤ ይደበድባሉ ያስራሉ። በሠላም አዉለኝ ብሎ በጧት የተነሳዉ መሠረት ሙሌ የእህል ወፍጮዉን አስነስቶ የዕለት ስራዉን ለመጀመር ጉድ ጉድ ማለት ጀምሯል። ሴቶች እህላቸዉን ያስመዝናሉ። ሸክም የተራገፈለት አህያ ያናፋል። ነጋዴዉ፤ ደላላዉ፤ ገበሬዉና ሸማቹ ዋጋ ቀንስ ዋጋ ጨምር እያሉ ይንጫጫሉ። መተማ መደበኛ ስራዋ ላይ ናት።

“ቁም . . . እጅ ወደ ላይ . . . እንዳትነቃነቅ” የሚል ድምጽ የደራዉን የመተማ ገበያ በአንድ ግዜ ጭጭ አሰኘዉ። መሳሪያ ያነገቡ ፖሊሶችና ሲቪል የለበሱ የደህንነት ሰራተኞች ከመኪና እየዘለሉ ወርደዉ መሠረትን የፊጥኝ አስረዉ መኪናዉ ላይ ወረወሩት። ምነዉ? ምን አጠፋሁ . . . ዬት ነዉ የምትወስዱኝ? አለ መሠረት በሁኔታዉ እጅግ በጣም ተደናግጦ። አንድ አጠገቡ የነበረዉ የህወሃት ነብሰ ገዳይ . . . ዝም በል ብሎ በጥፊ አጮለዉና ለአርበኞች ግንቦት 7 የመለመልካቸዉን ሰዎች አድራሻና ስም ዝርዝር ካላመጣህ ዕድሜህ ከአንድ ጀምበር አያልፍም አለዉ።

መኪናዉ ዉስጥ ከተቀመጡት ሁለት ሰዎች አንደኛዉ አንሂድ ብሎ በእጁ ምልክት ሲያሳይ መሬት ላይ የነበሩት ፖሊሶች እየዘለሉ መኪናዉ ላይ ወጡና መሠረትንና ሌሎች ሦስት እስረኞችን የያዘችዉ ቶዮታ ሂሉክስ መኪና ፍጥነት እየጨመረች የመተማ ሁመራን መንገድ ተያያዘቸዉ። በሚቀጥለዉ ቀን ጧት ሲነጋጋ ሁመራ ደረሱና አራቱ እስረኞች እጃቸዉ እንደታሰረ ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ተደረገ። ከምሽቱ ሦስት ሰዐት ሲሆን መሠረትና ጓደኞቹ እጅ ለእጅ እንደተሳሰሩ ጉዞ ወደ ተከዜ ወንዝ ሆነ። የዚህች ከንቱ አለም የመጨረሻ ጉዟቸዉ ነበር።

ዶማና አካፋ ያዙ እንጂ . . . ደግሞም ፈጠን በሉ ግዜ የለንም. . . አለ የነብሰ ገዳዮቹ አለቃ። ከሁመራ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ተከዜ ወንዝ የሚያደርገዉ ጉዞ በህይወቱ የመጨረሻዉ ጉዞ እንደሆነ የተረዳዉ መሠረት . . . አንተዬ ልትገድሉን ነዉ እንዴ ብሎ ጠየቀ። ፊት ለፊቱ የነበረዉ ፖሊስ ከተቀመጠበት ዘልሎ ተነሳና . . .ዝም በል . . . አንተ የሴት ልጅ . . . ምን አስቸኮለህ ይልቅ የተጠየከዉን ጥያቄ መልስ አለዉና የያዘዉን የእጅ መከርቸሚያ ካቴና ፊቱ ላይ ወረወረበት። ካቴናዉ ሳይሆን ከዚያ ባለጌ አፍ የወጡት ቃላት ጅማቶቹ ድረስ ዘልቀዉ ገብተዉ መንፈሱን ጎዱትና መሠረት ለመጀመሪያ ግዜ ተስፋ ቆረጦ . . . ምንም የምሰጥህ መልስ የለኝም አለና አንገቱን ደፋ። . . . አንቺ ወላዲት አምላክ ምነዉ . . . ምን አደረኩሽ ብሎ ቀና ሲል እሱንና ሦስት ጓደኞቹን ለመዋጥ አፋቸዉን ከፍተዉ የሚጠባበቁትን አራት ጉድጓዶች ተመለከተ። አይኔ እያየ እዚህ ወስጥ አልገባም ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ተከታታይ የጥይት ድምጽ ሰማ። ዞር ሲል ፖሊሶች አብረዉት ከታሰሩት ሦስት እስረኞች ዉስጥ አንዱን በእግራቸዉ እየገፉ የተቆፈረዉ ጉድጓድ ዉስጥ ሲጨምሩት አየ። ደቂቃዎች የቀሩት የሱ የራሱ ህይወት ሳይሆን በህወሃት ነብሰ ገዳዮች በግፍ የተገደለዉ የጓደኛዉ ህይወት አንገበገበዉ። አዘነ – በአይኑም በሆደም አነባ። “አይኔ እያየ እዚህ ወስጥ አልገባም” ብሎ የተናገረዉ የራሱ ድምጽ ጆሮዉ ላይ አቃጨለበት። መሠረት ሞት ፈርቶ አያዉቅም፤ ግን ህይወቱ የህይወትን ክቡርነት በማይረዱ ባለጌዎች እጅ እንድታልፍ አልፈለገም። ያ የንጹሃን ኢትዮጵያዉያንን ሰዉነት ማፍረስ የለመደዉ የህወሃት ጠመንጃ ወደሱ ከመዞሩ በፊት አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ ብሎ ወሰነ። እጁ ከጓደኛዉ ጋር የታሰረበትን ገመድ በጥርሱ በጣጠሰዉና ከቀለሁ እንደተላቀቀ ጥይት ተወርዉሮ እግሬ አዉጭኝ ብሎ ጫካ ዉስጥ ዘልሎ ገባ። የህወሃት ነብሰ ገዳዮች የጥይት ናዳ ለቀቁበት፤ እሱ ግን ጫካ ጫካዉን ይዞ ወደማያዉቀዉ ቦታ ሩጫዉን ተያያዘዉ።

መሠረት- ቆራጥነቱና የልቡ ትልቅነት ጉልበት እየሆኑት ነዉ እንጂ ያ የሚጠላዉ የህወሃት ጥይት አካሉን በሳስቶ ወንፊት አድርጎታል። ሰዉነቱ ቁስል በቁስል ሆኗል። ከራሱ ሰዉነት እንደ ጎርፍ የሚፈስሰዉ ደም ጠልፎ የሚጥለዉ እስኪመስለዉ ድረስ አካሉ ደምቷል። ሩጫዉን ግን አላቆመም። ደም እንዳይፈሰዉ ጥይት የበሳዉን ቦታ ሁሉ በሁለት እጆቹ ሸፈነ። እንደኛዉ ቁስል ጋብ ሲልለት እጁን ከሱ ላይ እያነሳ ሌላዉን ቁስል ሸፈነ። ደሙ መፍሰሱን ግን አላቆመም። መሠረትም ሩጫዉን አላቆመም። መሠረት ሙሌ ህይወቱን ለማዳን ወደ ፊት የህወሃት ነብሰ ገዳዮች ደግሞ ወንጀላቸዉን ለመደበቅ ወደኋላ በተለያየ አቅጣጫ ሩጫቸዉን ተያያዙት። ሁለቱም አግሬ አዉጭኝ አሉ።

መሠረት ሞትን እየሸሸ መሆኑን ነዉ እንጂ ከሞት ለመራቁ ምንም ዋስትና አልነበረዉም። ደግሞም መሮጡን ብቻ ነዉ እንጂ ወዴት እንደሚሮጥ አያዉቅም ነበር። ከኋላዉ የሚከተለዉ ማንም ሰዉ እንደሌለ ቢረዳም ከፊት ለፊቱ ህይወቱን የሚታደግለት ሰዉ እስኪያገኝ ድረስ ሩጫዉን ቀጠለ። ጧት ጎህ ከመቅደዱ በፊት “ጠጠዉ በል” የሚል ድምጽ ሲሰማ ያ ሁሉ ሩጫዉ መልሶ ሞት ዉስጥ የከተተዉ መሰለዉና ደነገጠ። ሩጫዉን እንዳይቀጥል ቁም ያሉት ሰዎች ከበዉታል። እሺ ብሎ እንዳይቆም ሞትን አልቀበልም ያለዉ ልቡ አሁንም እንደደነደነ ነዉ። ትንፋሹን ሰበሰበና. . . ማናችሁ እናንተ ብሎ ያቆሙትን ሰዎች ጥያቄ ጠይቆ መልሱን ሳይሰማ ተዝልፍለፎ መሬቱ ላይ በግንባሩ ተደፋ።

የኤርትራ ድንበር ጠባቂ ወታደሮች መሠረትን አንድ ወር ሙሉ በህክምና ሲንከባከቡት ቆዩና እሱ እራሱ በጠየቃቸዉ መሠረት ሃሬና ወስደዉ ለአርበኞች ግንቦት 7 አስረከቡት። መሠረት ሙሌ ጥቅምት 7 ቀን ከተመረቁት አርበኞች ዉስጥ አንዱ ነዉ። ለዚህ ጀግና ያቀረብኩለት የመጨረሻ ጥያቄ . . . ሊገድሉህ የነበሩትን የህወሃት ሰዎች አሁን ብታገኛቸዉ ምን ታደርጋቸዋለህ የሚል ጥያቄ ነበር። ነጻ አወጣቸዋለኋ! አለኝና ጭፈራዉ ዉስጥ ዘልሎ ገባ። አርግጠኛ ነኝ መሠረት ሙሌ አንድ ቀን ሁላችንንም ሸገር ላይ ያስጨፍረናል። ቸር ይግጠመን።

ኤፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር

The post አይኔ አያየ እዚህ ዉስጥ አልገባም – መሠረት ሙሌ (ኤፍሬም ማዴቦ ከአርበኞች መንደር) appeared first on Zehabesha Amharic.

ፎረም 65፦ በብሔራዊ መግባባት ለመሳተፍ መሰረታዊ መስፈቶች ምን ይሁኑ?

$
0
0

hailemariam desalegn

65Percent.org

October 29, 2015
ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሩዋንዳ፡ ኪጋሊ በተደረገው የአቶ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ስብሰባ ላይ በህገመንግስት ላይ የመግባባትንና የብዝሃነትን አስፈላጊነት አመልክተዋል። *

በተጨማሪም መንግስት ለሁለተኛ ዙር የእድገትና ለውጥ/ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (GTP II) ለመንደፍ ካደራጃቸው ኮሚቴዎች የአንዱ ኮሚቴ አላማ “ዴሞክራሲን ማስፈን፣ ብሔራዊ መግባባት መፍጠርና የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሥራን የተመለከተ ነው፡፡ ይህ ኮሚቴ ስምንት አባላት አሉት፡፡ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ የአምስት ዓመት ዕቅድ የሚነድፈውን ኮሚቴ አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ይመሩታል፡፡ ” **

የብሔራዊ መግባባትን አስፈላጊነት በሚመለከት ከገዢው ፓርቲ አስቀድሞ ልዩ ትኩረት ሰጥተው በድርጅት መርሃ ግብራቸው ላይ ጭምር አቋም የወሰዱ ህጋዊ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና እንዲሁም ከአገር ውጪ የተደራጁ በሰላማዊ ትግል መታገል የመረጡ ድርጅቶች ናቸው። የትጥቅ ትግል ከመረጡትም ውስጥ የሂደታዊና ጥገናዊ ለውጥ (reform) ደጋፊዎች በመኖራቸውና፥ ብሔራዊ መግባባት የሂደታዊና ጥገናዊ  ለውጥ ዋና አካል በመሆኑ፥ በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ በሚታገሉ አካላት ጋር ብሔራዊ መግባባት  አስፈላጊነቱ የታመነበት ነው ማለት ይቻላል።

ብሔራዊ መግባባት በጥልቀት ሳይሆን ላይ ላዩን፥ አልፎ አልፎ ሲዳሰስ ቆይቷል። በተጨማሪም ከብሔራዊ መግባባት ጋር በሚያያዘው በብሔራዊ እርቅ፥ ወቅታዊና ታሪካዊ ቁስሎችን ለፓለቲካ ፍጆታ ከማዋል ባለፈና ዘለቄታዊ በሆነ መልኩ፥ ቅራኔዎችን ለመፍታት እውቅናና ትኩረት አልተሰጠም። አለመግባባት የአገራችን ፖለቲካ ቅራኔ ምልክትና መገለጫ ነው። አለመግባባት መኖሩን የሚክድ ድምፅ ከገዢው ፖርቲም ሆነ ከተቃዋሚዎች ጎልቶ ባይሰማም፥ ወደ መግባባት እንዴት እንደምንደርስ ግን በዝርዝር የቀረቡ መሰረታዊ ነጥቦች የሉም።

በ65Percent.org ሳምንታዊ የውይይት መድረክ (ፎረም 65) ላይ ካነሳናቸው ጉዳዮች አንዱ በብሔራዊ መግባባት ላይ ለመሳተፍ መሰረታዊ መስፈርቶችን መለየት ነው። ሶስት መሰረታዊ ብለን ያነሳናቸው ነጥቦች በዚህ ፅሁፍ ቀርበዋል። ***

በብሔራዊ መግባባት ላይ ሊሳተፉ ሚችሉ ምን አይነት መስፈርት ሚያሟሉ እንደሆኑ ለይቶ ማወቁ የመግባባት ሂደት ለመጀመር ቀዳሚ ጉዳይ ነው። ለብሔራዊ መግባባት ስለኢሕአዴግ፥ ስለብሔረሰቦችና ስለታሪክ የጋራና ተመሳሳይ አቋም የያዙ ግለሰቦች፥ ስብስቦች፥ ቡድኖች፥ ድርጅቶችና ፓርቲዎች “በምን ላይ እንግባባ?” ሚለው ጥያቄ ላይ አብረው ለመወያየት የሚያስችል መሰረት ሊኖራቸው ይችላል።

ሶስቱ ነጥቦች፦

1. ስለኢሕአዴግ
************

ገዢው ፓርቲ አገሪቱን እስከገዛ ድረስ የብሔራዊ መግባባት ሂደት አካል ነው።  ኢሕአዴግን እንደ ጠላት ሚፈርጁ አካላት በብሔራዊ መግባባት ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ አቋማቸው ለገዢው ፓርቲ ህልውና ዋስትና ስለማይሰጥ፥ ኢህአዴግን እንደ ጠላት መፈረጃቸውን ትተው ኢሕአዴግን እንደ ተፎካካሪ ቢመድቡት በብሔራዊ መግባባት ሂደት ውስጥ ጠቃሚ ተሳትፎ ማድረግ ይችላሉ ብለን እናምናለን ።

የአገሪቱ የሃይል ሚዛን እስካልተለወጠና ኢሕአዴግ የበላይነቱን ጨብጦ እስከቀጠለ ድረስ ለኢሕአዴግ ህልውና ዋስትና የሚሰጡ፥ ህገመንግስቱን ሚቀበሉና በሂደት ማሻሻል እንደሚቻል የሚያምኑ አካላት በብሔራዊ መግባባት ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ መሰረታዊ መስፈርት እንደሚያሟሉ እንረዳለን።

2. ስለብሔረሰቦች
*************

ኢትዮጵያ የብሔሮች አገር ናት። ይሄንን ጭብጥ ሚክዱ፥ ሚያጣጥሉና የብሔሮችን ህልውና “ጎሳ”፥ “ጎጥ” በማለት እውቅና ሚነሱ አካላት በአገር ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ተቀብለው ብሔራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ ገንቢ ሚና መጫወት ይችላሉ።

‘የግለሰብ መብት ከተከበረ የብሔረሰቦች መብትም ይከበራል’ የሚለውን አቋም ሚያስተናግዱ አካላት የብሔረሰቦችን መብት እንደ አበይት (primary) ሳይሆን እንደ ንዑስ (secondary) ጉዳይ ያስቀምጡታል።

የግለሰብና የቡድን መብቶች ሊነጣጠሉ አይችሉም፥ ተመጋጋቢ ናቸው። የዜጎች ግላዊ መብት እንዲከበር የቡድን መብታቸውም መከበር ይኖርበታል፥ የቡድን መብታቸው እንዲከበር ግላዊ መብታቸውም መከበር ይኖርበታል።

በብሔረሰቦች ጉዳይ ላይ የሚወሰዱ አቋሞች በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ዓመታት የሰረፀውንና የማይቀለበሰውን የብሔር ተኮር ማንነት ግንባታ (empowerment)  ከግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ፥ የግለሰብንና የብሔሮችን መብቶች እኩል ዋጋ ሰጥቶ በብሔራዊ መግባባት ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ አቋሞችን ማሻሻል ይቻላል።

3. ስለታሪክ
*********

የዘመናዊ ኢትዮጵያ ታሪክ ዛሬ ባለንበት የፓለቲካ አለመግባባት ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ መኖሩ አያከራክርም። የመዘናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ሁሉም መጥፎ እንዳልሆነ ሁሉ፥ ሁሉም መልካም ሊሆንም አይችልም።

ታሪካዊ ጥቁር ነጥቦችን እንደ አገር በአንድነት እውቅና ሰጥተን ወደፊት መራመድ ለብሔራዊ መግባባት ገንቢ እርምጃ ነው። ስለሆነም ታሪክን በሚመለከት ቢያንስ በመርህ ደረጃ በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ በደሎች እንደነበሩ መቀበል በብሔራዊ መግባባት ለመሳተፍ ወሳኝ መስፈርት መሆኑን እንረዳለን።

በአገራችን ብሔራዊ መግባባት ላይ እንድንደርስ ገንቢ ውይይት ማድረግ ዋንኛው መንገድ ነው። ከላይ በተጠቀሱት ነጥቦች ላይ ገንቢ ሃሳቦችን እናስተናግዳለን።

መግባባትን እናውርስ!

65Percent.org

info@65Percent.org

www.Facebook.com/65PercentOrg

———

* “We need to have a plural society [where] both parties, media and organized groups all have their say in the decision making bringing the country forward. Have a broad consensus on basic issues, specially on constitution.” https://youtu.be/JnGWCm208og Accessed on Oct 25, 2015; Go to video time 1:12:00

** http://www.ethiopianreporter.com/index.php/news/item/8580, Accessed on Oct 25, 2015

*** “ፎረም 65” በብሔራዊ እርቅና መግባባት ላይ ሳምንታዊ ዝግ ውይይት የሚያደርግ የ65Percent.org መድረክ ነው።

The post ፎረም 65፦ በብሔራዊ መግባባት ለመሳተፍ መሰረታዊ መስፈቶች ምን ይሁኑ? appeared first on Zehabesha Amharic.


በሚችጋን የ14 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት በመኪና ተገጭታ ሕይወቷ ከ2 ቀን በኋላ አለፈ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ረቡዕ ኦክቶበር 28, 2015 ዓ.ም በቤተሰቧ ሰላም ያውልሽ ተብላ ተመርቃ ወደ ትምህርት ቤት ለማምራት ከቤት ወጣች:: ሕሊና ደሪባ:: ነዋሪነቷ በኤተን ካውንቲ ሚቺጋን አሜሪካ ውስጥ ነው::

Helina Dirba

የ14 ዓመቷ የዋቨርሊ ከፍተኛ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው ይህችው ልጅ ድንገት የሚበር መኪና መትቷት ሹፌሩም እንደወደቀች መኪናውን ሳያቆም ጥሏት ጠፋ:: ሰዓቱ ገና ከጠዋቱ 7:30 ነበር::

ሕሊና ወዲያውኑ የህክምና እርዳታ ብታገኝም ከሁለት ቀናት በኋላ ሕይወቷ ሊያልፍ ችሏል::

የዓይን እማኞች ጠቆር ያለ ሲዳን መኪና ያሽከረክር የነበረ ሹፌር ገጭቷት እንደሄደ ለፖሊስ ምስክርነታቸውን በሰጡት መሰረት ተከሳሹ ትናንት እዚያው ሚችጋን ተይዞ በኤተን ካውንቲ በሚገኘው ፍርድ ቤት ቀርቦ ክስ እንደተመሰረተ ከወደ ሚችጋን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል::

የ14 ዓመቷን ሕሊና በመኪና ገጭቶ በማምለጥ ወንጀል ተጠርጥሮ የታሰረው የ68 ዓመቱ ሄክተር አሮዮ እስከ 15 ዓመት የሚደርስ ቅጣት እንደሚጠብቀው ተገልጿል:: ተጠርጣሪው 3 ክስ እንደተከፈተበት ያስረዱት የዘ-ሐበሻ የመረጃ ምንጮች 1ኛው ክስ የታገደ መንጃ ፈቃድ ይዞ በመንዳት 2ኛው ያለ ውዴታ በስህተት ሰው በመኪና በመግጨትና 3ኛው ሰው ከገጨ በኋላ ሳይረዳ በግዴለሽነት መኪናውን አስነስቶ በመሄድና በዚህም የተነሳ ለሞት በመዳረጓ የሚሉ ክሶች ተከሷል::

ተከሳቹ ኖቬምበር 22 ፍርድ ቤት ለቀጣይ ቀጠሮ እንዲቀርብ ታዟል::

የሟች እናት የልጇን አስከሬን ኢትዮጵያ ወስዳ መቅበር እንደምትፈልግ ያስታወቁት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በኢንተርኔት የወላጆቿን ወጪ ለመጋራት የገቢ ማሰባሰብ እየተደረገ ነው:: መርዳት ለምትፈልጉ ሊንኩ የሚከተለው ነው:: https://www.gofundme.com/ev7qcnxq

 

The post በሚችጋን የ14 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት በመኪና ተገጭታ ሕይወቷ ከ2 ቀን በኋላ አለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የለሊቱ የቪኦኤ ሚስጥራዊ ጉባኤ –በአበበ ገላው (ትርጉም በታኬ)

$
0
0

The post የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የለሊቱ የቪኦኤ ሚስጥራዊ ጉባኤ – በአበበ ገላው (ትርጉም በታኬ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ለአማራ በብአዴንና በዲያብሎስ መካከል ምን ልዩነት አለ?

$
0
0

bereket

 (መለክ ሐራ ከቤተ አማራ)
(ይህንን ጽሁፍ ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል አያንብበው)

ጥላየ ጌጤ የማርቆስ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት የነበሩ በቅርብ ጊዜ ደግሞ ሚኒስተር ዴታ እና የኢሃዲግ የማእከላዊ ኮምቴ ትናንት በ10/02/08 ቀን የመቀሌ ዩንቨርሲቲ አስተማሪዎችን ሰብስበው የብአዴን አመጣጥ እና ልማቶች ሲያሰለጥኑ ከቆዩ በሆላ አስተማሪዎች በአነሱአቸው ጥያቄዎች ላይ የሰጡትን መልስ በትንሹ ከዚህ በታች ለማስፈር እሞክራለሁ። በመጀመሪያ ስለ ብአዴን አመጣጥ ከኢሀፓ ጀምሮ በራሳቸው ታሪክ ሲተርኩልን ቆዩ። ለምሳሌ ኢሀፓ ከህወሀት ጋር የተጣላው ኢሀፓ በብሄር ጭቆና አያምንም ነበር፡፡ ለውጥ ለማምጣት ብቻ ነበር የሚታገለው፡፡ ህወሀት ግን የብሄሮችን ጭቆና በኢትዮጵያ ነጻ ለማውጣት ነበር የሚታገለው። ከዚያ በህውሀት አሸናፊነት ተጠናቀቀ እና የቀሩትም ኢህዴን በመሆን እና የህዉሀትን ማኒፌስቶ በመስማማት ህወሀትን ተቀላቀሉ እያለ ለብዙ ስአት ሲቀድብን ቆየ።

ጠያቂ 1፡:
የድሮ መሪወች ከአማራ ኅዝብ የወጡ ገዥወች ለማለት የከብዳል ከአክሱም ስልጣኔ ጀምሮ ብናስብ ከተለያዩ ጎሳዎች የወጡ መሪዎች ኢትዮፕያን መርተዋታል። በቅርብ ጊዜ ብናይ እንካ አጼ ዮሀነስ አሉ። በሚኒሊክ ጊዜ ብናይ እንካ ከአማረው ህዝብ የወጡ አያስብልም ምክንያቱም ከብዙ ጎሳዎች የወጡ ሰዎች ነበር ኢትዮጵያን የመሩአት። ስለዚህ የአማራ ህዝብ ገዝቶ የሚለው ብቻ ሳይሆን ከአማራው ህዝብ የወጡ ገዥወች ማለት እራሱ አያስደፍርም ወይ የቃላት ለውጥ ያስፈልገዋል።

መልስ፡ ይህ አያስኬድም ዝም ብላችሁ ጭቃ ሹሙን ሁላ ገዥ ልትሉት ነው? ( ከሌላ ጎሳ የነበሩት ጭቃ ሹም ነበሩ ገዥ አልነበሩም) ውሸት አያስፈልግም ከአማራ ህዝብ የወጡት ነበሩ ገዥ ነበሩት። የቃላት ለውጥም አይደረግለትም ገላጭ ይህ ነው።

ጥያቄ 2፡
ድሮ የብኄር ጭቆና አልነበረም የአማራ ገዥም ከተባለ ሌላውን ጎሳ በጎሳነቱ አልጨቆኑትም (ከሰፊ ትንታኔ ጋር)፡ ስለዚህ የአማራ ገዥ ጨቁኖአል የሚባለው ውሸት ነው።

መልስ፡ አውሮፓ ስማር አውሮፓ የተማራ ካለ ያውቀዋል ሁሌ በሚባል ደረጃ የጀርመኖች ጭፍጨፋ ይዘገባል። በጣም ‘horor’ የሆነ እኔም ይገርመኝ ነበር እንዴት ይህን ያሳያሉ እያልኩ ግን በመጠየቄ ተረዳሁት። ያን ጭፍጨፋ በመደበቅ ሳይሆን እውነቱን አውጦ ግልጥ በመነጋገር እነዳይደገም ማድረግ እና ወደፊት ሰላም ማስከበር እንደሆነ ነገሩኝ እኔም ገባኝ። እና አማራ መጠነ ሰፊ የሆነ በሌሎች ላይ ጭፍጨፋ አድርሱአል እዚህ መናገር የሚከብደኝ ግፍ አድርሱአል ዘር እስከማጥፋት ደርሱአል ማንበብ አለባችሁ ወዲያውም እናንተ የተማራችሁበትን proffesion ብቻ አይደለም ማንበብ ያለባችሁ የአማራ ገዥ አስፈሪ የሆኑ ግፎችን በሌላ ጎሳወች ላይ ፈጽሞአል እንዲህ በወሬ ሳይሆን የተፃፉ መጽሀፎች ስላሉ ማንበብ አለባችሁ። ስለዚህ እኛም እነደ አውሮፓ ግልጥ ሊሆንልን ይገባል። አማራ ያን ሁሉ ግፍ መፈጸሙን አምነን እና ተግባብተን ለወደፊት ህብረ ብሄራዊ ዲሞክራሴ መፍጠር አለብን።(የአማረ ጭፍጨፋ እኩል ይሆናል ከናዚ ጭፍጨፋ ማለቱ ነው)……………(ይህ ሰው የአምሮ በሽተኛ መሆን አለበት መጻፍ አንብቡ የሚለውስ የተስፋየን ገብረአብን ልብወለድ ነው ይሆን?)

simon bereket

ጥያቄ 3፡

ድሮ የብሄር ጭቆና አልነበረም ግን አሁን ላይ አለ ለምሳሌ አማ የሚል የሚኪና ታርጋ ከታየ ገብያ ጺወን እንደደረሰ የትራፊክ ሰወች በረባ ባረባው በሹፌሮች ላይ ብዝበዛ ያካሂዳሉ። አንድ አስር ሹፌሮችን ሰብስበን መጠየቅ እንችላለን.። (ከሌሎች ማብራሪያዎች ጋር)

መልስ፡ አማራ በቃንቃህ አትናገር እና አትማር አልተባለም፣ ባህልህን እና ወግህን እርሳ እና የሌላ ባህል ተቀበል አልተባለም ስለዚህ ይህ ውሸት ነው።(ይገርማል አማራ በመሆኑ የሚገደሉት እና የሚፈናቀሉት ምን ሊለው ነው ይሆን)

ጥያቄ4፡

የአማራ ህዝብ በየጊዜው በሽወች የሚፈናቀሉት እና የሚገደሉት ከ 1983 ጀምሮ በተላያዩ የአገሪቱ ክልሎች እስከቅርቡ ቤንሻንጉል ድረስ እንዲሰበሰቡ ተደርገው በጥይት የተረሸኑት እና የተገደሉት ማብቂያው መች ነው፡ የናንተስ ስራ ምንድን ነበር? ወደፊትስ ምን ልትሰሩ ነው? አይነት ጥያቄዎች ያዘለ (ከ 83 ጀምሮ ይህ ነገር የታየበትን በመዘርዘር ከወልቃይት ጠገዴ በስተቀር)

መልስ፡ አሁን እናንተ እዚህ ትግራይ በሰላም እየኖራቸሁ አይደል፣ በቤንሻንጉል ብዙ አማራ እና አገው በሰላም እየኖሩ ነው፣ በኦሮሞም፣በደቡብም ብዙ አማሮች በሰላም እየኖሩ ነው። ከክልላችን ውጭ በተለያዩ ክልሎች ከ 3 ሚሊዮን በላይ አማሮች ይኖራሉ ሁሉም በሰላም እየኖሩ ነው። የተባረሩት አማሮችም በሚኖሩበት ክልል በጎሮቤቶቻቸው ላይ የድሮ ስድቦችን ይሰድቦአቸዋል፣ የንቃቸዋል፣ ትምክታቸውን ያሳያሉ፣ ጫካቸውን ያቃጥሉባቸዋል ለዚያ ነው የሚያባርሩኣቸው። እኛ ግን ከክልላችን ውጭ ስለእነሱ ሀላፊነት የለብንም በሚተዳደሩት የክልል አስተዳዳሪዎች ነው የሚተዳደሩት ግን በትንሽ ጠባቦች ይሀ ነገር ይታያል፡ አንዴ የጎጃም ሰወች ከወለጋ ተሰደው ሂደው በመንግስት ሲመለሱ የወለጋ የጎረቤት ኦሮሞወች እንዴት ከአንዳንድ ሰወች ጋር ተጣላን ብላችሁ አብረን የኖርንበትን አገር ትታችሁ አገሬ ጎጃም ነው ብላችሁ ትሄዳላችሁ ነው ያሉአቸው። ግን የአስተዳደሩ ወይም የህዝቡ ችግር አይደለም። ቤንሻንጉልም እንደዚያ ያደረጉ ሰወች ተከሰዋል። (ወይ ጉድ በመቶወች የሚቆጠር አማራ ሙቶ እና ታርዶ ሁለት ሰዎች ላልተወሰነ ጊዜ ቢታሰሩ ፍትህ ነው፣ ምን አይነት በሽተኛ ፣ካሀዲ፣ ውሸታም፣ የዘመዶችህ ነፍስ እና ልቅሶ ትንሽ እንኮ የማይሰቀጥጠው ነው።))

ጥያቄ 5፡

ባህርዳር ስፖርት ላይ ተጣሉ ተብሎ ETV ነበር ሆን ብሎ ነገር ለማባባስ ሲያራግበው የነበረው ይህ ነገር እንዴት ነው? መልስ፡ አኔ ባህር ዳር ጭዋታውን ቁጭ ብየ እያየሁ ነበር በጣም የተናደድኩበት ነገር ነው፡ ጭዋታው በትግራይ እና በአማራ ቡድን ነበር አማሮች ጭወታ ላይ ደክመው ነበር ግን ትግሬዎች በጣም እየተጫወቱ ነበር ከዚያ ሶስት ወይም ከዚያ በላይ ትግሬወች በትምክተኛ ግሩፖች ጭንቅላታቸውን ተመቱ እና ፊታቸው በደም ተጥለቀለቀ (3 ጊዜ ደገመው በንዴት) ዶክተር ክንድያ (መቀሌ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት፣ አሱም እስብሰባው ውስጥ ስላለ በመጣራት) ይህን ነገር አንተም አጣራው (3 ጊዜ ተናገረው) ትምክተኞችም ወደ ከተማ እሩጠው ጠፉ በኃላ ግን አላመለጡም ተያዙ። ከአካባቢው የሚሰነዘረው ስድብ በጣም የሚዘገንን ነበር። (እረ ይገርማል ሊያስደበድበን ነው? ደግሞ ዶ/ር ክንድያ ይህን ነገር አንተም አረጋግጠው የሚለው እሱ ምን እንዲሰራ ነው። ነገሩ ክንድያ ሁሉም ነገር የህወሀት ስራ ስለሆነ ጠንቅቆ ያውቀዋል እንዲያስመታለት፣ እንዲያስገድልለትም ወይም እንዲባርርለትም ከሆነ ማነን ምን ማድረግ እንዳለበት እሱ ክንድያ እራሱ ያውቀዋል።)

ጥያቄ 6፡የአማራ ህዝብ ምን ያህል ለመሬቱ ክብር እንዳለው ይታወቃል። ለአንድ ኢንች መሬት እራሱ ከዘመዱ ጋር ሊገዳደል አንደሚችል ይታወቃል ግን በእናንተ ምክንያት የአማራ መሬት በኢሀዲጎች እስከዚህ ድረስ ነው ተብሎ ህዝቡ ሳይስማማ ተከለለበት። አሁን ደግሞ በመተማ ያለውን እና በዚያው ዙሪያ ያለውን እየሰማን ነው።

መልስ፡ ይህ ነገር ተደጋግሞ የሚጠየቅ ጥያቄ እና እንተን ፈርሞ ሰጠ ምናምን የሚባል ወሬ አለ። እኔ መተማ ተሰጠ የተባለው 1600 square kilometer ተብሎ ሲናፈስ ገርሞኛል እኔ እረሴ አውቀዋለሁ ከዚያ የሚያንስ ተንሾአጦ መጦ ኮረም የሚደርስ መሬት ነው ይህ ደግሞ በሀይለስላሴ ጀምሮ የነበረ ነው። ይህ 1600 የሚባል ውሸት ነው። ቢሆንም እራሱ የፌደራል ስራ ነው እንጂ የክልሉ ስራ አይደለም። የክልሉ ስራ የሚባለው ከሌሎች ክልሎች ጋር ያለውን ግንኙነት ነው ይህ ደግሞ በጎንደር በኩል የትግራይ ወልቃይት ጸገዴ ወረዳ አለ በትግረኛ የሚያወሩ በትግረኛ የሚዘፍኑ አሉ የአማራ ደግሞ ወልቃይት ጠገዴ ወረዳ አለ በአማረኛ የሚዘፍኑ በአማርኛ የሚያወሩ አሉ ተቻችለው እና ተስማምተው ተዋደው የሚኖሩ ናቸው። የቀረውን ደግሞ ወልቃት አካባቢ በሰላም እንዲፈታ የአገር ሽማግሌዎች ተመርጠዋል። በሰቆጣ እና በትግራይ አካባቢ ደግሞ በሰላም ነው የሚኖሩት ትንሽ በኦሮሚያ ልዩ ዞን አካባቢ ያሉት ከአፋር ጋር በግጦሽ መሬት ይጣላሉ እንጂ (ምን አይነት ካሀዲ፣ የዘመዶችህ ነፍስ እና ልቅሶ ትንሽ እንኮ የማይሰቀጥጠው ሰው ነው።)

ጥያቄ 7፡

አማራ ላይ ልማት የለም፣ ዩንቨርስቲዎችም እየሰሩ አይደለም፣ ቅርሶቻችን እየተጠበቁ አይደለም፣የጠና ችግር በጣም አለ፣ ፋብሪካዎች የሉም፣ የጭስ አባይ ፉፉቴ እንደምንም አልታየም፣ መቀሌን በጥቃቅን ሰራተኝነት ያጥለቀለቁት የጎንደር ከ 18 አመት በታች በሆኑ ልጆች ነው። የትግራይ ህዝብ ሰራተኛን የሚጠብቀው ከጎንደር ነው፣ ልጅ ከማሳዘል እስከ ሆቴል ምግብ አብሳዮች የተጥለቀለቀው የጎንደር ወጣት ሴቶች ናቸው፣ የሰቆጣ አካባቢ ከፍተኛ ችግር እና እራብ ነው ያለው እና ትምህርት ቤቶች ችግር አለ ወዘተ የመሳሰሉት ትያቄዎች ተጠይቀው ነበር።

መልስ፡ ሁሉንም በመካድ፣ ኮተት እና የሚያስቁ መልሶችን ተፉት፡ ከሌሎች ክልሎች በአንዳንዶችም እንደምንበልጥ በአንዳንዶች ደግሞ እኩል እንደምንሆን ተናገሩ። ዩንቨርስቲዎች ደግሞ እየሰሩ ነው ለምሳሌ ማርቆስ ዩንቨርስቲ የጎጃም ህዝብ ሀብታም ሁኖ እና ገንዘብ እያለው ለምን በባዶ እግሩ እንደሚሄድ ጥናት እየተጠና ነው ( ስድብ ከዚህ ሌላ ምን አለ ጎበዝ)፣ የጭስ አባይ ገንብተነው ከፍተኛ የቱሪስት ገብያ አምጦልናል፣ በሰቆጣ እየሰራን ነው፣ በጎንደርም በጣም እየሰራን ነው ትንሽ ተከዜ አካባቢ ትቀረናለች እንጂ፣ በትምህርተ አንደኛ ነን፣ እና ሌሎችንም ከብዙ ኮተቶች ጋር ቀላቅለው አዳፍነው ከእንግዲህ በኃላ ጥያቄ የለም በማለት ዘጉት።

Bahir dar Demo. 5

ዘመዶቸ ከላይ የተጻፈው የሚያስጠሉ ስድቦችን ለምሳሌ የዘቀጠ አስተሳሰብ ነው፣ ትምክተኞች እዚህም አሉ፣ትምክተኞች አስቸግረዋል እና ሌሎች ቀፋፊ ስድቦችን፡ ብዙ የሚያስጠሉ የቃላት ጋጋታወችን፣ በትምክተኞች ላይ ያለውን ብስጭት እና ንዴቱን እና ሌሎች ውይይቶችን አልጨመርኩም። በተረፈ ከላይ በተጠየቁ ሀሳቦች ላይ ሰውየው የሰጠውን መልስ ቃል በቃል ለመጻፍ ሞክሬአለሁ። እንግዲህ ይህ ሰውየ አንዴ ማርቆስ ላይ የህይወት ታሪኩን ሲያወራ እንደሰማሁት የቄስ ልጅ እንደሆነ፣ የቆሎ ትምህርት ጀምሮ እንደነበር፣ የደና ቤተሰብ ልጅ እንደሆነ፣ በጥሩ ሁኔታ እንዳደገ፣ እና አውሮፓ ሂዶ ያየ ቢያንስ የአውሮፓን ኑሮ እና የአማራን ኑሮ ማነጻጸር በሚችልበት ሁኔታ የተመለከተ፣ በ proffesion ኑ ብቻ ሀብታም ሁኖ መኖር የሚችል ነበር ምን ታደርገዋለህ በህወሀት ሰወች ውስጥ ያደጉ እና በብአዴን ውስጥ እያደጉ የመጡ ሰወች አምሮአቸው እንዳያስብ የሚወጉት ነገር አለ መሰለኝ፣ ወይም የአምሮ በሽተኞች ይሆናሉ መሰለኝ……..ግራ ገብቶኛል። ደግሞ እንደነሱ እዚሁ ከጎናችን ብዙ እውሮችን እንዳፈሩ አረጋገጥን።

ባጠቃላይ ታሪካችንን እኛው እንድንጠላው የአባቶቻችንን ደም እንድንረሳው በአባቶቻችን አጥንት ላይ አንደነሱ እንድንረማመድበት ። አባቶቻችን በሌሎች ጎሳዎች ላይ ለአይን የሚዘገንን ለማሰብ የሚከብድ ግፍ እንደሰሩ ፣ ጭካኔአቸውን እኛም እንደሆረር አይተን እንድንፈራው እና አያቶቻችን አውሬ አስመስለን እንድናያቸው እየተዶለተና እየተሰራ ነው። በአጠቃላይ በአያቶቻችን እንድናፍር እና መጨረሻው በኛ ላይ እንድናፍር እየተሰራ ነው። በመጨረሻም እኔ እና አንዳንድ ሰወች ለአንዴ እና ለመጨረሻ በብአዴን አመራሮች ተስፋ የቆረጥንበት ቀን ነው። ብአዴን is the same with ህወሀት። ብአዴን የአማራን ህዝብ እና መሬት አሳልፎ ለመስጠት ዝግጁ ነው። በህይወት ባሉት የአማራ ህዝቦች; በእግዛብሄር ቸርነት እና በህወሀት ርህራሄ እንደሚኖሩ አወኩኝ። በባለፈው የደመቀ መኮነን ንግግር እንደኔ ተስፋ አድርጎ የነበረ ካለ ተስፋ ይቁረጥ። ከእንግዲህ ሚኒሊክን በበጎ ያነሳ ሰው ሁሉ ትምክተኛ እና ነፍጠኛ ተብሎ በብአዴኖች እንደሚታሰር ሆነ እንደሚገደል ጥርጥር የለኝም። ትል-ያ ወይም ያ-ትል አወረደን አሳፈረን ሸጠን በዚያውም ግን የብአዴን አላማ ምን እንደሆነ ነገረን። ቤተ አማራን ተቀላቅለን መትረፍ እና መዳን ካልቻልን ብአዴኖች ለአማራ ህዝብ ፋሲካ እንደሚታረደው በግ እየታረድን ብናልቅ ግድ የላቸውም።

ቤተ አማራ ወደፊት

The post ለአማራ በብአዴንና በዲያብሎስ መካከል ምን ልዩነት አለ? appeared first on Zehabesha Amharic.

የአዲስ አበባና አካባቢዋ ወተት ከፍተኛ መርዛማ ህፃናትን የሚያቀጭጭ እና የሚያሳጥር ኬሚካል አለው ተባለ

$
0
0

milk
<strong>መንግሥቱ አበበ</strong>

ነገሩ፣ ለዘመናት ከምናውቀው እውቀት የተለየ በመሆኑ ግራ ማጋባቱ አይቀርም፡፡ እስካሁን ለሕፃናት ዕድገትና ጥንካሬ ጥሩ ነው በማለት ሕፃናትን ስንመግብ የኖርነው ወተት፤ በተቃራኒው ለሕፃናት ዕድገት ጥሩ አይደለም፤ ያቀጭጫቸዋል ቢባሉ ምን ይላሉ? የሚገርም ነው!ሰሞኑን በሂልተን ሆቴል ሲካሄድ በቆየው 4ኛ የአፍሪካ የምግብና የኑትሪሽን ፎረም ላይ አንድ ተመራማሪ፤ በመርዛማ ኬሚካሎች (አልፋ ቶክሲን) ላይ ያደረጉትን የምርምር ውጤት ሲያቀርቡ፤ እግረ መንገዳቸውን የአዲስ አበባና አካባቢዋ ወተት ከመጠን በላይ መርዛማ ኬሚካል (አልፋ ቶክሲን) እንዳለው ገልፀዋል፡፡ ተመራማሪው ዶ/ር አሻግረ ዘውዱ፤ ዓለም አቀፉ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት (ILRI) ባወጣው ሪፖርት፤ በ2016 በአዲስ አበባና አካባቢዋ ባደረገው ጥናት፣ ከተሰበሰቡት 140 ናሙና ከ90 በመቶ በላይ ዓለምአቀፍ ሕግ ከሚፈቅደው በላይ መርዛማ ኬሚካል (አፍላቶክሲን M1) እንዳለው ማስታወቁን ተናግረዋል፡፡

አልፋ ቶክሲን በሻጋታ ምክንያት የሚፈጠር መርዛማ ኬሚካል ነው ያሉት ተመራማሪው፤ መርዛማ ኬሚካሉ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ቢጐዳም በሕፃናት ላይ የበለጠ ጉዳት ያደርሳል፣ መቀጨጭና መጫጫት ያስከትላል፡፡ በዕድሜያቸው ልክ ቁመታቸው አያድግም፡፡ በኢትዮጵያ 40 በመቶ ሕፃናት ቀጫጫ ናቸው፡፡ መርዛማ ኬሚካሉ ከማጫጨት በተጨማሪ ረዥም ዕድሜ ሲቆይ የጉበት ካንሰር ያስከትላል ብለዋል፡፡

አልፋ ቶክሲኖች የተለያዩ ናቸው፡፡ እህል ላይ የሚገኙትና በይበልጥ የሚታወቁት 4 ናቸው፡፡ እነሱም B1 B2 G1 G2 ይባላሉ ያሉት ዶ/ር አሻግሬ፤ እህሉ ላይ የሚገኘውን B1 አልፋ ቶክሲን የበላ ከብት በሰውነቱ ውስጥ በሚካሄደው ሜታቦሊዝም፣ B1 መርዛማ ኬሚካል ወደ M1 ይቀየራል፡፡ ኤች አይ ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንደምታስተላልፍ እናት ለልጇ ጡት ስታጠባ መርዛማውን ኬሚካል ወደ ሕፃኑ ታስተላልፋለች፡፡ ከብትም እንደዚሁ፡፡ ሕፃኑ በአልፋ ቶክሲን የሚጠቃው፣ ጡት መጥባት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ነው በማለት አስረድተዋል፡፡ ወተት ለሕፃናት ዕድገት ጥንካሬና ውፍረት ጥሩ ነው ስለሚባል ወተት እየጠጡ ያድጋሉ፤ ለአልፋ ቶክሲን እየተጋለጡ ናቸው ያሉት ተመራማሪው፤ “በወሎ ድርቅ ጊዜ የእርጐ ፈንገስ የሚባል ነገር ተፈጥሮ ነበር፡፡ የሚበላ ነገር ሲጠፋ ፈንገስ የተቀላቀለበት ምግብ በልተው፤ ጋንግሪን ተፈጥሮባቸው እግራቸው የተቆረጠ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡” ብለዋል፡፡ ዓለምአቀፉ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ያወጣውን መረጃ በተመለከተ፤ መንግስት ከኢትዮጵያ ፐብሊክ ኢንስቲትዩት፣ የደረጃዎች ምዘናና ተስማሚነት፣ የምግብ ሳይንስና ኑትሪሽን ማዕከል እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ ባለሙያዎች ጥናት እንዲያደርጉበት ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡ ውጤቱ ልክ እንደተባለው ከሆነ ምን እናድርግ? በማለት ምክክር ይደረጋል ያሉት ዶ/ር አሻግሬ፤ ልክ ካልሆነ ደግሞ ኅብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል::

 

ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ (ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣ)

The post የአዲስ አበባና አካባቢዋ ወተት ከፍተኛ መርዛማ ህፃናትን የሚያቀጭጭ እና የሚያሳጥር ኬሚካል አለው ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የፓርላማው ድራማ –  ይገረም ዓለሙ 

$
0
0

ሙሉ በሙሉ በአብዮታዊ ዴሞክራቶች በመያዙ የተለየ ሀሳብ የማይሰማበት ሙት የሆነውን ፓርላማ ህይወት ያለው ለማስመሰል የተዘጋጀው ድራማ ማክሰኞ ጥቅምት 16/2008 መታየት ጀምሯል፡፡ ይህ የፓርላማ ድራማ  ቤቴሌቭዥን እንደምናያቸው ድራማዎች ሰሞነኛውን ትኩሳት እየተከተለ በየሳምንቱ የሚጻፍና የሚዘጋጅ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በዚህ የመጀመሪያ ቀን ትዕይንት መሪ ተዋናይ ሆነው የቀረቡት ጠቅላይ ምኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ  ከፓርላማው አባላት መካከል  በተመረጡት ተዋንያን እየተጠየቁ በመመለስ ሲተውኑ ታይተዋል፡፡

hailemariam

ከቀደሙት ጠቅላይ ምኒስትር ጀምሮ ሲነገር እንጂ ሲተገበር የማይታየው ከተቀዋሚዎች ጋር አብሮ የመስራት ጉዳይ ለመጀመሪያው ቀን ድራማ ማድመቂያነት ከተመረጡት ጉዳዮች አንዱ ነበር፡፡ ተባብሮ መስራት ማለት እንደ ተቀዋሚዎች  በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር ሀገራዊ መግባባት ከመፍጠር የሚጀምር  እንደ ወያኔ ደግሞ እሱ በሚፈልገው ጉዳይ ሲፈልጋቸው ብቻ በመጥራት የሚገለጽ ነው፡፡ እንዲ ሆነናም  በአምስት ዓመቱ ዕቅድ ላይ ለማወያየት  ምርጫ ቦርድ መዝግቦ ለሚያውቃቸው ፓርቲዎች በሙሉ መንግጨሥታቸው ሰነድና ደብዳቤ መላኩን የገለጹት አቶ ኃይለማሪያም ብዙዎቹ በስብሰባው ላይ ሲገኙ ጥቂቶች ውኃ የማይቋጥር ምክንያት በመስጠት አልተገኙም አሉ፡፡ ያልተገኙት ፓርቲዎች ያቀረቡት ምክንያት ውኃ የማይቋጥር ነው ያሉበትን ምክንያትም ሲያረዱ በሕጋዊ መንግድ የተመረጠ መንግሥት ስላልሆነ ከእርሱ ጋር አንነጋርም ማለታቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ለመሆኑ ጥሪያችንን ተቀብለው ብዙዎቹ ተገኝተዋል የተባሉት  ፓርቲዎች የትኞቹና እነማን ናቸው፡፡ዝቅ ብለን እናያቸዋለን፡፡

የመሳሪያ ትግል የሚያካሂዱትን ድርጅቶች አስመልክቶም ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ  ለራሱም መሆን ካልቻለው ሻዕቢያ ጋር ሆነው የሚያመጡት ውጤት ስለማይኖር ጊዜያቸውን በከንቱ ባያባክኑ በማለት ምክር ለመስጠት የዳዳቸው አቶ ኃይለማሪያም አንዳንዶቹ እኮ ጭራሽ የሌሉ ናቸው በማለት ኦነግን ኦብነግንና የጋምቤላ ህዝቦች ንቅናቄን ጠቀሱ፡፡ ይቺ ገለጻ የቀረበችው በደራሲውና  አዘጋጁ ስህተት ይሁን ወይንም በርሳቸው የጥናት ጉደለት ባይታወቅም ሁለት መልእክት ታስተላልፋለች፡፡ አንደኛ እነዚህ የተጠቀሱት ድርጅቶች ሰሞኑን ተባብረው ለመስራት የደረሱበት ስምምነት እነ አቶ ኃይለማያም ሰፈር የፈጠረው ነገር መኖሩን እንድንጠረጥር ያሚያደርግ ፣ ሁለተኛ ደግሞ በሰሜን በኩል ድምጻቸው የሚሰማው ድርጅቶች እነዚህ ብቻ አይደሉምና ለሌሎቹ መኖሮና ጠንካራ መሆን በዘወርዋራ እውቅና የሰጠ ነው፡፡

አቶ ኃይለማሪያም የአቶ መለስ ሌጋስ አስቀጣይ እንደመሆናቸው ስለ ድርጅቶቹ የተናገሩት ከርሳቸው የወሰዱትን ነው፡፡ አቶ መለስ ብረት አንስተው መንግሥታቸውን የሚታገሉ ድርጅቶችን አስመልክቶ ሲላቸው አጥፍተናቸዋል የሉም ሲሉ ሌላ ግዜ ደግሞ በግላቸው ብዙ ርቀት ሄደው ከድርጅቶቹ መሪዎች ጋር ለመገናኘትና ለመደራደር እንደጣሩ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ ሌላ ግዜ ደግሞ ወድመዋል ተደምስሰዋል የተባሉት ደርጅቶች በዚህ ቦታ እንዲህ አደረጉ ጥፋት አደረሱ የሚል ዜና ስንሰማ ኖረናል፡፡ የሉም በተባሉ ድርጅቶች ስምም ዜጎች እየተወነጀሉ ታስረዋል እየታሰሩም ነው፡፡ አቶ መለስ አይደለም የሀገር ውስጥ ተፋላሚዎችን ሶማሌ ተሻግረው አልሻባብን ድምጥማጡን አጥፍተነዋል ብለውንም ነበር፡፡

አቶ ኃይለማሪያም ባያስታውሱም እኛ አንረሳውም፡፡ አቶ መለስ ከርሳቸው ፍላጎት ውጪ ስንዝር መሄድ የማይችለውን ፓርላማ አስፍቅደው(ነግረው)  እንዲህ አስታዋሽ አጥቶ የቀረውን ሰራዊት  ሶማሊያ በላኩበት ወቅት  የገጠማቸውን ተቃውሞ ዝም ለማሰኘት  ሰራዊታችን አልሻባብን ደምስሶ አሁን የቀረው ቃርሚያ ብቻ ነው፣ ያንን አጠናቆ በቅርብ ቀን ይመለሳል ብለውን ነበር፡፡ ነገር ግን ይኸው እስካሁን አልሻባብም አልጠፋ ሰራዊቱም አልተመለሰ፡፡ እንደውም በተቃራኒው ወንድሞቻችን የአልሻባብ ጥቃት ሰለባ እየሆኑ ነው፡፡  አቶ ኃለማሪያም እኔም አንደ መለስ ብለው በንቀት ስሜት የሉም ጠፍተዋል ስላሉዋቸው ድርጅቶች መረጃ ስለሌለኝ የምለው አይኖርም፤ የላችሁም የተባላችሁ መኖራችሁን አሳይዋቸውና አቶ ኃይለማሪም በዚህ አፋቸው ምን እንደሚሉ ለመስማት አብቁን የሚለው ግን መልእክቴ ነው፡፡

አቶ መለስ የሻዕቢያና ወያኔ ጸብና ፍቅር ለወላይታው ምኑ ነው ብለው ለአቶ ኃይለማሪያም አለነገሯቸው እንደሁ እንጂ ወያኔን አዲስ አበባ ያደረሰው ለራሱም የማይሆን ያሉት ሻዕቢያ ነው፡፡ ይህም  ብቻ  አይደለም ሌላው ኢትዮጵያዊ (የወያኔ ታጋይ ጭምር ) የማይታመን ሆኖ እስከ ተጣሉበት ግዜ ድረስ ቤተ መንግሥቱ ይጠበቅ የነበረው በሻዕቢያ ሰራዊት እንደነበረ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ስለሆነም አቶ ኃይለማሪያም ወያኔዎች ስለ ሻዕቢያ ዛሬ የሚሉትን ብቻ እየተቀበሉ መናገር ሳይሆን ትናንት ምን ይሉ ምንስ ያደርጉ እንደነበር የተጻፈ አንብበው የነበረ ጠይቀው ቢናገሩ ቢያንስ ጠቅላይ ምኒስትር ለሚለው ማዕረጋቸው( ይስሙላም ቢሆን) የሚመጥን ይሆናል፡፡

ከላይ እንደተገለጸው አቶ ኃይለማሪያም ስለ አብሮ መስራት ሲናገሩ ምርጫ ቦርድ የመዘገባቸውን ፓርቲዎች በሙሉ ጠርተን አብዛኛዎቹ ተገኝተዋል ነው ያሉት፡፡ አብዛኛው የሚለው የጥቅል መጠሪያ  ለወያኔም ለፓርቲዎቹም ለምርጫ ቦርድም እያገለገለ ነው፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች በቁጥር ሲገለጹ እንጂ በስም ሲጠሩ አይሰማም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ምርጫ ቦርድ መዝገብ ላይ ሰፍረው የሚገኙት አንዳንዶቹ የሌሉ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ  ምርጫ ሲመጣ ብቻ ብቅ የሚሉና ለምርጫ የሚሰጣቸውን ገንዘብ ተቀብለው የአጃቢነት ሚናቸውን ተወጥተው ለአራት ዓመት የሚጠፉ ናቸው፡፡ ጥቂቶቹም ፓርቲ ለመባል የሚያበቃ ቁመና የሌላቸው አቶ በረከት የፓርቲዎቹ ጥቅማቸው አልታይ ብሉአቸው ይሁን ስሜት ገፋፍቶአቸው ወይንም እውነት ተናንቆአቸው ባይታወቅም በመጽሀፋቸው የቤተሰብ ፓርቲ ሲሉ  የገለጹዋቸው ናቸው ፡፡  በርግጥ ለመናገር አንዳንዶቹ ሊቀመንበር ተብሎ ከሚጠራው ሰው ቀጥሎ የሚጠራ ሶስትና አራት ሰው የሌላቸው በመሆኑ የቤተሰብ ፓርቲ የሚለውንም አያሟሉም፡፡ ብዙዎቹ ከተባሉት ከእነዚህ ስመ ፓርቲዎች ውስጥ  ብዙዎቹን እንኳን ህብረተሰቡ ምርጫ ቦርድም አያውቃቸው፡፡ ድረ ገጹን ብትጎበኙ ቦርዱ ስለማያውቃቸው የተመዘገቡበትን ቀን መሙላት አቅቶት  ቦታው ክፍት ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ ፤ብቻ ብዙዎች እየተባሉ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ይውላሉ፡፡እነዚህን በስም እየጠቀሱ መሪ የሚባሉትን ሰዎች ምንነትና ማንነት እያሳዩ መግለጽ የሚቻል ቢሆንም የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ የምርጫ ቦርድን ድረ ገጽ ከጎበኙ  ሌላም ነገር ይታዘባሉ፣ ምርጫ የማስፈጸም ብቃት አለው ተብሎ ምስጋና የተዥጎደጎደለት ይህ ተቋም ድረ- ገጹን ወቅታዊ ማድረግ ተስኖት ከአስር ዓመት በፊት የነበረ መረጃ ነው የሚያገኙት፡፡

ፓርቲ ማለት በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የህጋዊነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰጠው ነው ካልተባለ በስተቀር  ብዙዎች የሚባሉት ከወያኔ ዳረጎት እየተቀበሉ፤ በምርጫ ቦርድ መልካም ፈቃድ ፓርቲ እየተባሉ፤ በአዳማቂነትና በአጃቢነት  የሚያገለግሉ፣ እንኳን አባል የተሟላ አመራር የሌላቸው ናቸውና ፓርቲ ሊባሉ የሚበቁ አይደሉም፡፡ መሪ ለሚባሉት ሰዎች ግን የእለት እንጀራም የሕይወት መንገድም ሆኖ እየጠቀማቸው ነው፡፡ በአንጻሩ ብዙም ባይሆን ለወያኔ ዕድሜ መርዘምም እየረዱ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ኖሩም አልኖሩ “ተለበሰ ቀረ የደበሎ ቅዳጅ ”እንደሚባለው ናቸውና ምንም ፋይዳ የላቸውም፡፡ እንደውም የማይቻል ሆኖ እንጂ አለመኖራቸው ይሻል ነበር፡፡

ሙቱን ፓርላማ ህይወት ያለው ለማስመሰል የተጀመረው ድራማ  ደራሲና አዘጋጁ ሰልችቶአቸው እስካላቆሙት ድረስ በጀመረው መልኩ ወቅታዊ የትኩረት አቅጣጫዎችን እየተከተለ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ የእኛም ማየትና መስማት ብሎም ከምናይ ከምንሰማው ተነስተን ብዕር ከወረቀት ማገናኘት እንዲሁ ይቀጥላል፡፡እስካላቆሙት ድረስ ያልኩት አቅጣጫ ለማስቀየሻ እየተባሉ በዚህ መልኩ የሚጀመሩ ጉዳዮች ሲዘልቁ ስለማይታይ ነው፡፡ደግሞስ የማስመሰል ስራ መች ብዙ መንገድ ያስኬዳል፡፡ይህ የፓርላማ ድራማ ቀልቡን የሚስበው ሰው ኖር ይሆን!!

The post የፓርላማው ድራማ –  ይገረም ዓለሙ  appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live