Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአቶ ግርማ ካሳ ነገር –ይገረም አለሙ

$
0
0

ማስታወሻ፤ ለዚህች አስተያየት መጻፍ ምክንያት የሆነውን የአቶ ግርማ ካሳን ጽሁፍ ያነበብኩት በዚህ መድረክ በመሆኑ አስተያየቱ የተላከው ለዘሀበሻ ብቻ ነው፡፡

ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም የነገሩን ምንነት የአድራጊውን ማንነት የአፈጻጸሙን እንዴትነት ወዘተ ማወቅ ይጠይቃል፤ እውነትን መሰረት አድርጎ መቆም ያስፈልጋል፡፡ አቶ ግርማ ካሳ ግን ከሀገር ርቀው እየኖሩ በስማ በለው ወይንም ስሜታቸው በሚነግራቸው ብቻ እየተመሩ በማይጨበጥና በየግዜው በሚዋዥቅ አቋማቸው እየተቃወሙና እየደገፉ ሲጽፉ አመታት አስቆጥረዋል፡፡ እንደ ግዜው ርዝመት አንደሚሰጣቸው አስተያየት ምንም ለውጥ ሳያሳዩና የአቋም ማስተካከል ሳያደረጉ እስካሁን አሉ፡፡ አንድነት ከተመሰረተበት ገዜ ጀምሮ ከመሪዎቹ በላይ መሪ ለመሆን በሚቃጣ ስሜት የአቃፊ መሳይ ገፍታሪ ተግባር ሲጫወቱ የነበሩትና አንድነትን ለሞት ካበቁት ሰዎች አንዱ የሆኑት አቶ ግርማ አሁን ደግሞ መንጠላጠያ ፍለጋ ኢዴፓ መኢአድ መድረክ እያሉ ነው፡፡
2053fountain_pen
ኢሕአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር ስብሰባ ጠርቷል- መልካም ጅማሬ በሚል ርዕስ በቅርቡ ያስነበቡን ጽሁፍ አቶ ግርማ ምን አንደሚደግፉም ሆነ ምን እንደሚቃወሙ ለራሳቸውም የማያውቁ ወይንም ሆነ ብለው የማደናገርና አቅጣጫ የማስለወጥ ስራ የሚሰሩ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ ጽሁፉን እንዳነበብኩ አስተያየት በመስጠትና ባለመስጠት መሀል ሀሳቤ ሲዋልል የመድረካችን እንቁ ብቸኛዋ ሴት ጸኃፊ (ሌሎች ካሉ ባለማወቄ ይቅርታ) እህት ስርጉተ ተገቢ መልስ ሰጠች፡፡ እኔም ትንሽ አንድል መነሳሳት ፈጠረችብኝ፡፡

አቶ ግርማ እውነትና አንድነት፤ ለእውነት የቆመ ሰው ነገሮችን የሚመዝነው ከነገሩ ምንነትና እንዴትነት እንጂ ከአድራጊው ጋር ባለው ፍቅር ወይም ጥላቻ አይደለም፡፡ ወይንም ጉዳዩ ለግል ከሚያስገኘው ጥቅም አንጻርም መሆን የለበትም፡፡ አንዱ ሲሰራው ህገ ወጥ ብለው ያወገዙትን ድርጊት ሌላው ሲፈጽመው ማድነቅ አልያም በዝምታ ማለፍ ካለ ከእውነት ጋር ሆድና ጀርባ ተኩኗል ማለት ነው፡፡ ህግ ከሚጥሱ፤ ሥርዓት ከሚያፋልሱ፤ ስራን ሳይሆን ሴራን ምርጫቸው ካደረጉ ወዘተ ጋር የግል ጥቅምን እያሰቡ መተባበር ካለ በእውነት ላይ መሸፈት ብቻ ሳይሆን ከሰዋዊ ባህርይም መወጣት ነው፡፡

አቶ ግርማ በተለይ አንድነትን አስመልክቶ ከርቀት ሆነው በብዕራቸው ሲፈጽሙት የነበረው ተግባር ከእውነት ጋር ሆድና ጀርባ መሆናቸውን ብቻ የሚያሳዩ አልነበሩም፡፡ በአንዱ ጽሁፋቸው ያነሱት ሀሳብ ከቀጣዩ ጽሁፋቸው ሀሳብ ጋር የሚቃረን፤ በአንዱ ጽሁፋቸው ያሞገሱትን ሰው በሌላኛው ጽሁፋቸው የሚኮንኑት በመሆናቸው ከራሳቸውም ጋር የተጣሉ መሆናቸውንም ያሳብቃሉ፡፡

ራሳቸውን አንደ መሪ የቆጥሩበት አንድነት (በተወሰነ ተሳክቶላቸው በርቀት ሆነው የጎንዮሽ አመራር ለመስጠት እስከመቻል የደረሱበት ወቅት ነበር) ሲመሰረት መሪ ሆና የተመረጠችው ወጣቷ የህግ ባለሙያና የጠላለፉ ፖለቲካ ያልነካካት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ነበረች፡፡ የብቱካን የመጀመሪያዋ ሴት የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ሆና ወደ መድረክ መምጣት ስጋት የሆነው ለወያኔ ብቻ ሳይሆን በተቃውሞው ጎራ ላሉ ያለእኛ ፖለቲካ ለሚሉትም ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ ዳግም ለእስር በተዳረገችበት ዋዜማና ማግስት የተፈጸመባት ክህደትና ድጋፍ መንሳት በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡ ይህንም መለስ ብሎ በወቅቱ የተጻፉትን በማየት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ይሄው አድራጎት አመራሩ ለፓርቲው ሊቀመንበር በህገ ወጥ ሁኔታ መታሰር ትኩረት አልሰጠም የሚል ጥያቄ አስነስቶ በፓርቲው አባላት ዘንድ ቅራኔ ሲፈጠር አቶ ግርማና መሰሎቻቸው ጥያቄ አንሺዎቹን ሲዘልፉ ሲያወግዙ ከዛም አልፈው በወያኔነት ሲፈርጁ ነው የሰማን ያነበብነው፡፡ ቅራኔው ሰፍቶ ነገሩ ተስፋፍቶ በርካታ አባላት ሲባረሩና አንዳንዶችም አመራሩን በመጥላት ራሳቸውም ሲለቁ ( ሰማያዊ ፓርቲን የመሰረቱ) እነ አቶ ግርማ ችግራችሁን በውይይት ፍቱ ከማለት ይልቅ አመራሩን በማበረታታት የርምጃው ደግፊ ነው የሆኑት፡፡

አቶ ግርማ አንድነትና መድረክ፤ አንድነት ከመድረክ ጋር የሚኖረው ግንኙነት የተጠና የተመከረበት ሊሆን ይገባል በማለት አባላት የጥድፊያውን መቀላቀል ሲቃወሙ አቶ ግርማና መሰሎቻቸው ለፓርቲው ከአባላቱ በላይ ሀሳቢ ሆነው ተቀዋሚዎቹን ሲያወግዙ ነበር፡፡አንድነት ለአምስት ዓመታት ያህል የመድረክ አባል ሆኖ ራሱም ሳይጠቀም መድረክንም ሳይጠቅም አንካሰላንትያ ውስጥ ሲገባና በመድረክ የእገዳ ርምጃ ሲወሰድበት መድረክ ወይንም ሞት ያሉት አቶ ግርማ መድረክን ኮንነው አንድነት ከመድረክ እንዲፋታ መካሪና አመራር ሰጪ ሲሆኑም ታዝበናል፡፡
አቶ ግርማ አንድነትና ምርጫ 2002፤ አንድነት በምርጫ 2002 የሚሳተፍ ከሆነ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ሊቀመንበሩ አንድትፈታ ይጠይቅ፤እሱ ብቻም አይደል አባል የሆነበት መድረክም በምርጫው የምንወዳደረው ብርቱካን ከተፈታች ብቻ ነው በማለት እንዲጠይቅ ያድርግ በማለት አባላቱ ጠየቁ፡፡ የአንድነት አመራሮች ግን በመድረክ ተወዳድረን ስየና ነጋሶን ይዘን የሚያቆመን የለም በማለት በምርጫው እንደሚያሸንፉና ራሳቸውን ፓርላማ አንደሚገኙት ርጠኛ በመሆን “የብርቱካንን እስር የምርጫ 2002 ቅድመ ሁኔታ እርጎ ማቅረብ ፖለቲካውን ያስነሰዋል አንኳን አንድነት አንድነት አባል የሆነበት መድረክም ይህን አያደርግም በማለት በድፍረት በአደባባይ ተናገሩ፡፡ አነ አቶ ግርማም ሰልፋቸውን ከእነዚህ ሰዎች ጎን አድርገው ቀጠሉ፡፡ ከምርጫው የተገኘው ግን አንድ ወንበር ብቻ ሆነ፡፡

አቶ ግርማ አንድነትና ኢ/ር ግዛቸው፤ በብርቱካን መታሰር ምክንያት የፓርቲው ሊቀመንበር የሆኑት ኢ/ር ግዛቸው ዶ/ር ነጋሶ በተመረጡበት ጉባኤ ፊት “ወኔየ ሞቷል ሞራሌ ወድቋል በአመራርነት አይደለም በፓርቲ አባልነትም አልቀጥልም ብለው” ተሰናበቱ፡፡ እነ አቶ ግርማም አድንቀው ደገፉ ለፈፉ፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ፓርቲው ጉባኤ እያዘጋጀ ከመሆኑ ዜና ጋር ኢ/ር ግዛቸው ለሊቀመንበርነት እንደሚወዳደሩ ሲገለጽ እነ አቶ ግርማ አንዴት ሆኖ ለምንስ ተብሎ የሚል ጥያቄ አላነሱም፡፡ ኢ/ር ግዛቸውም በከፍተኛ ድምጽ ተመረጡ ተብሎ ሊቀመንበር ሆኑ፡፡ የእነ አቶ ግርማ ድጋፍም ተቸራቸው፡፡አስገራሚውና ለአንድነት ሞት ምክንያት የሆነውን የመጨረሻውን በር ለወያኔ ብርግድ አድርጎ የከፈተው ከዚህ በኋላ የሆነው ነው፡፡

ከላይ በገለጽኩት መልኩ ተመረጡ የተባሉት ኢ/ር ግዛቸው ስድስት ወር ሳይሞላቸው የሚደርስባቸውን ጫና መቋቋም እንዳልቻሉና በተለይ ከዲያስፖራው የገጠማቸው ተግዳት ሊያሰራቸው አንዳልቻለ ለምክር ቤቱ ገልጸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ፡፡ (ዲያስፖራ ማለት እነ አቶ ግርማ መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡) የዲያስፖራው ግፊት ኢ/ር ግዛቸውን በመቃወም ከሥልጣን ማስነሳት ብቻ ሳይሆን ሌሎቹን በመደገፍም አስቷል፤አሳስቷል፡፡ሊቀመንበር የመምረጥ ሥልጣን የጠቅላላ ጉባኤ ብቻ መሆኑ ተዘንግቶ በእነ አቶ ግርማ ሆይ ሆይታ ምክር ቤቱ አቶ በላይን ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ፡፡ የእነ ግርማም የብእርም የብርም ድጋፍ ተቸረ፡፡ የሚያሳዝነው ከኋላ ሆኜ መስራት ነው የምፈልገው በማለት በተደጋጋሚ የቀረበለትን የሊቀመንበርነት ጥያቄ ሲገፋ የኖረው አቶ በላይ በውጪም በውስጥም ግፊት በመጨረሻ ሰአት ሊቀመንበር ሆኖ ለመከራ መዳረጉ ነው፡፡ ምነው አንድነት መሞቱ ካቀረ በኢ/ር ግዛቸው እጅ ላይ ቢሞት ኖሮ፤

ዛሬ የኢህዴግ መልካምነት የታያቸው አቶ ግርማ፤ ዛሬ ተቀዋሚዎችን ወደ ኢህአዴግ ግብዣ ሂዱ በማለት የሚመክሩት አቶ ግርማ በእነርሱ ግፊት የተፈጠረን ስህተት አንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ወያኔ አንድነትን ለማፍረስ ቢሮው ደጃፍ ላይ ጉድጓድ በሚቆፍርበት ሰአት ረጋና ሰከን ተብሎ ለወያኔ መግቢያ ሊሆኑ የሚችሉ ቀዳዳዎችን የመድፈን ስራ እንዲሰራ ለምን አይመክሩም ነበር፡ በቅርብ እንደታዘብነውና ከጽሁፎቻውም አንደተረዳነው እነ አቶ ግርማ በዛን ሰአት ይገፉና ያደፋፍሩ የነበረው የውግዘት መግለጫ እንዲወጣና እንኳን በዛን ሰአት ከዛ በፊት ያልሆነ ያልተቻለው ሰላማዊ ሰለፍ እንዲጠራ ነበር፡፡ አንድነት እንዲህ መሆኑ ላይቀር ሰልፍ ተብሎ ቢሮአቸው በር ላይ የተደበደቡት አባላት ያሳዝናሉ፡፡ እነ አቶ ግርማ ይህን ያደረጉት አንድነትን በመግለጫና በሰላማዊ ሰልፍ ማዳን ይቻላል ብለው አምነው ነው ወይንስ አንድነት እንዲሞት ከመፈለግ?
አቶ ግርማና የተባበሩ ጥያቄአቸው፤ አበው ከአንድ ብር ሁለት መድሀኒቱ፤ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ወዘተ በማለት የመተባበርን አስፈላጊነትና ጠቃሚነት ይገልጻሉ፡፡ አልሆን እያለ ተቸገርን አንጂ ፓርቲዎች መተባበር አይደለም ተጨፍልቀው ከሶስትና ከአራት ባይበልጡ የብዙው እምነት ነው፡፡ ተለያይቶ በመቆም ከሚያተርፈው ውጪ፡፡ አቶ ግርማ ስለ ፓርቲዎች ትብብር የሚጽፉትን ከምር የሚያምኑበት አይመስለኝም፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ርሳቸውም አንደ ፖለቲከኞቹ ትብብርን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ነው የሚያውሉት ብሎ መጠርጠር ይቻላል፡፡ ከዚህ ሲያልፍም ለወቅታዊ ትኩረት ማስቀየሻ ይሆናል ማለትም ይቻላል፡፡

የፓርቲዎችን መተባበር ከምር የሚፈልግ ሰው የተወጠነው ሲጨነግፍ፤ የተመሰረተው ሲፈርስ እያየ ዝም ብሎ ተባበሩ አይልም፡፡ መተባበር ያልተቻለበትን ምክንየት መርምሮ መፍትሄ ይጠቁማል፤ ፖለቲከኞቹን ሆድና ጀርባ የሚያደርጋቸውን በሽታ አጥንቶ መድሀኒት ያዛል፤ ከዚህ ሲያልፍም የመተባበር እንቅፋት የአብሮ መስራት ጋሬጣ የሆኑ ፓርቲዎችንም ሆነ መሪዎችን በተጨባጭ ማስረጃ ይኮንናል ያጋልጣል፡፡አቶ ግርማ ግን ለተቃውሞአቸውም ሆነ ለድጋፋቸው ስሜት አለያም የማናውቀው ምክንያት እንጂ የእውነት መሰረት ስለሌላቸው ሾላ በድፍን ተባበሩ ይላሉ እንጂ ማን ከማን ጋር እንዴትና በምን ሁኔታ በምንስ ደረጃ መተባበር እንደሚችሉና አንዳለባቸው አያመላክቱም፡፡

ወያኔን የሚገዳደር ጠንካራ ትግል ለማድረግ የሚበቃ መተባበር ለመፍጠር መጀመሪያ የፖለቲካውን መድረክ የሙጢኝ ባሉት ሰዎች ዘንድ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋል፤ከዛ በየፓርቲው ተሀድሶ ማድረግና ፓርቲዎቹን ከግለሰብ ድርጅትነት ወደ ትክክለኛ ፓርቲነት ማሳደግ፤ከዛ በኋላ መተባበሩም ሆነ ቅንጅት ግንባርም ይሁን ውህደት የመፈጸሙ ንግግር በፓርቲዎች መካከል ይሆናል፡፡ አቶ ግርማ የተባበሩ ጩኸተዎ ከምር ከሆነ በዚህ መንገድ ተግተው ይጻፉ፡፡ ሾላ በድፍን ተባበሩ ግን የጤና አይደለም፡፡

ስለ ሰላማዊ ትግሉም ቢሆን መጀመሪያ ትግሉን ሊመራ የሚችል ጠንካራ ፓርቲ መኖር ያስፈልጋል፡፡ አቶ ግርማ ደግሞ ከላይ ለማሳየት የሞከርኩት ተግባራቸው እንደሚያረጋግጠው እንደ መሪ ይቃጣቸው በነበረው ፓርቲ ውስጥ ውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲ ጎልብቶ ውይይት ባህል ሆኖ፤ የሀሳብ ልዩነት ተከብሮ ድርጅታዊ አንድነት ጎልብቶ ፓርቲው አንዲጠናከር ሳይሆን የጥቂት ግለሰቦች ቤት አንዲሆን ሲሰሩ የነበሩ ናቸው፡፡ ይህን ደግሞ ያኔ መርህ ይከበር ይባሉ ከነበሩት ወጣች ጋር ይመላለሱዋቸው የነበሩት ጽሁፎችዎ ያሳያሉ፡፡እባክዎን አቶ ግርማ መጀመሪያ ከእውነት ጋር ታረቁ፤ ከዛም የተቃውሞዎንም ሆነ የድጋፍዎን ምክንያት ይወቁ፤ ከቻሉም መለስ ብለው የጻፉዋቸውን ጽሁፎች በማየት ራስዎን ይጠይቁ፡፡

The post የአቶ ግርማ ካሳ ነገር – ይገረም አለሙ appeared first on Zehabesha Amharic.


የወያኔ ስራ  በቤተክርስትያናት ላይ!! በዘመናችን ያለ የቤተክርስቲያን ትልቁ ፈተና –ጉዞ ወደ እናት ቤተክርስቲያን (እንቀላቀል) ለምን ትልቅ ፈተና ሆነ ስንል?

$
0
0

 

ከጌታቸው ካሳሁን

          የእስከዛሬዎቹ  ጥቃቶች የሚፈፀሙት ከቤተክርስቲያን ውጪ በሆኑ ሰዎችና ተመሳስለው በገቡ ማንነታችውን በደበቁ ሰዎች ሲሆን ይህኛው ግን ለየት የሚያደርገው የሃይማኖት ሽፋን ያለው እንዲሁም እውቅና በሰጠናችውና በፈቀድንላቸው ጥፋታቸውን እራሳቸውን ሳይደብቁ በግልፅ እያሳዩን እንኳን ዝም ብለን የተቀበልናቸው የቤተክርስቲያን አማሳኞች  አባቶችና ምዕመናን የሚከናወን በመሆኑ ነው።እንግዲህ ወደ ጉዳዩ ስንገባ በመጀመሪያ ቤተክርስቲያን አንዲት ናት ርትዕት ናት በዶግማ ምንም ችግር የለባትም ነገር ግን በአስተዳደር ችግር ምክንያት ለሶስት ቦታ ተከፍላለች ። ልብ በሉ በዶግማ አላልኩም በአስተዳደር ምክንያት ነው ያልኩት።

በአስተዳደር  ለ3 ( ሶስት) ቦታ የተከፈሉትን እንደዚህ እናያቸዋለን

  1. በኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሚተዳደሩ
  2. በአሜሪካን ሀገር ባለው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሚተዳደሩ ሲሆኑ፡
  3. ገለልተኛ ቤተክርስቲያን፡-የሚባሉት ደግሞ በአሁን ግዜ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ሁለት ፓትርያርክ ስለሆነ ያላት ለየትኛውም ፓትርያርክ አንወግንም  የሚሉና ገለልተኝነታቸው ከሁለቱ አባቶች እንጂ ከቤተክርስትያኒቱ ያልሆነ እንዲሁም  እርቀ ሰላም ወርዶ አንድ ሲኖዶስ በቦታው እስኪመለስ ድረስ ለየትኛውም አንወግንም የሚሉ ናቸው።

ነገር ግን በሶስቱም  አስተዳደር  ስር ያሉት ቤተክርስቲያኖች መተዳደሪያ ደንባቸው በቅዱስ ሲኖዶስ የተዘጋጀው ቃለ ዓዋዲ ሳይሆን ከቤተክርስትያኑ አባላት በተውጣጡ ጥቂት ሰዎች በሚቀርጹት መተዳደሪያ ደንብ ነው። ቤተክርስቲያንነታቸው የአንዲት (እናት) ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲሆን፤  አንዱ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ሌላው ደግሞ እንጀራ ልጅ ሊባሉም አይችሉም።  እንዲሁም ምእመኖቻቸው የአንዲት እናት የኢ/ ኦ/ተ ቤተክርስቲያን ልጆች ናቸው። ጊዜ ያመጣው ፖለቲካ አስተዳደሩን ለሶስት ከፈለው እንጂ  ሁሉም አሃዱ አብ ቅዱስ ብለው የሚቀድሱ እና የሚያመሰግኑ ልዩነት የሌላቸው በአንድ አምላክ የሚያምኑ ናቸው።

በዚህ ጊዜ በአንድነት ስም ቤተክርስቲያንን መክፈል ያስፈለገበት ምክንያት

ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው መንግስት ከጫካ ጀምሮ አንግቦ በመጣው የኢ/ኦ/ተ ቤተክርስቲያንን የማፍረስ ዓላማ በተለያዩ ጊዜያት ቤተክርስቲያንን ሲያቃጥል፣ ሲያስፈርስ፣ ሲያርስ፣ ታሪኳን በጠራራ ፀሀይ ሲያጠፋ የሀይማኖት ቦታዋን እየነጠቀ ለሌላ ሲሰጥ ስለ ቤተክርስቲያን ብሎ አንድም የተናገረላት አባትም ሆነ  የበላይ አካል ዝም ብሎ ከማየት ወጭ ያደርጉት አስተዋፆ የለም። በትንሹ ቢሆን በየአካባቢው ያሉ ምእመናን አትንኩ ቤተክርስቲያኔን ሲሉ በአፀፋው እስር፣ እንግልት፣ መገደል  ደርሶባቸዋል።  በእኛ ዝምታ መንግስት ተግባራዊ አድርጎታል ነገር ግን በተቻለው ፍጥነት የማፍረስ ሂደቱ እንዳይከናወን ሁለት ነገሮችን ይፈራል።

  1. ማህበረ ቅዱሳንን፡- ማህበሩን ለምን ይፈራዋል ስንል የቤተክርስቲያን የጀርባ አጥንት ነው በሎ ስለሚያስብ  ስለዚህ ማህበሩን ለማፍረስ በተለያየ ጊዜ ብዙ ሙከራ ቢያደርግም አልሳካ  በማለቱና ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ የሚደረገውን እሩጫ ማህበሩ ባያቆመውም ወደ ኋላ ስለጎተተበት እንዲሁም ውጤቱ እንዲያዘግም ስላደረገና መዋቅሩም በጣም ጥልቅና እስከ ታች ድረስ ዘልቆ ስለገባ ማፍረስ ባለመቻሉ በዚህ ጉዞ ወደ እናት ቤተክርስቲያን በሚል ከተቻለ ለማፍረስ አለበልዚያም ለማዳከም ነው።

ይህ አቅጣጫ እንዴት ማህበሩን ያፈርሳል   ?

 

ጉዞ ወደ እናት ቤተክርስቲያን በሚል እውነትነት ያለው በሚመስል የሃይማኖት ሽፋን ነገር ግን ህዝብን ከህዝብ፤ ባልን ከሚስት፤ በአጠቃላይ የምእመናንን ልብ ለሁለት ከፍሎ እስከመለያየት የሚያደርሰውን አጀንዳ የማህበረ ቅዱሳን አጀንዳ አድርጎ  በምእመን ዘንድ ሰርጾ እንዲገባ በማድረግ ማህበሩ በምእመናን እንዲጠላ ማድረግና ከተቻለ በዚህ አጋጣሚ ማህበሩን አፍራሽ አድርጎ በይፋ በማውጣት ማፍረስ ወይም ከምእመናን ልብ ውስጥ ማውጣትና ማዳከም ነው።  እዚህ ጋር ግን የሚያሳዝነው የማህበሩ አባል በሆኑ ነገር ግን የማህበሩ ዓላማ ባልሆነው ነገር እነርሱን ከፊት በማሳየት መጠቀምና ተአማኒነትን ለማግኘት በመሞከር የማህበሩን ተልእኮ እያስፈፀሙ አስመስሎ በማሳየት በእነርሱ መጠቀም ነው።

  1. ብዙ ህዝብ የተሰበሰበበት በዘር በጎሳ ያልትከፋፈለና ስርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቀ አገልግሎት የሚሰጥበትን ቤተክርስቲያንን  ፦   እነዚህን ለምን ይፈራል ስንል አንድነትን አጥብቆ ስለሚፈራ ለስልጣኔ ያሰጋኛል ስለሚል። እንደዚህ ዓይነት ቤተክርስቲያኖች የሚገኙት ደግሞ በገለልተኛ ቤተክርስቲያን ስር ያሉት ጋር ነው። እነዚህ ቤተክርስቲያኖች አንድነታቸውን ጠብቀው ፍፁም ኢትዮጵያዊነት ስለሚታይባቸውና በቂ ባይሆንም ቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን አደጋ በመግለጫም ቢሆን በጥቂቱ ይቃወማሉ። እንዲሁም በሰው ኃይል፣ በፋይናንስ እና ከእዳ ነፃ የሆነ ቤተክርስቲያን ባለቤትና በአገልግሎትም ጠንካራ ስለሆኑ መንግስት በስጋት ያያቸዋል።                                                                      ይህን ቤተክርስቲያንን የመክፈል (የማዳከም) ስራ ማን ይስራው

እንግዲህ በአሁን ግዜ በቤተክርስትያኒቱ ውስጥ ሁለት አይነት ሰዎች ዲያቆናት፣ካህናትና እንዲሁም ጳጳሳት ከታች እስከ ላይ በተዋረድ ከስር አጥቢያ ቤተክርስትያን አንስቶ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ድረስ አሉ። እነርሱም፦

1.  የመጀመሪያዎቹ ፡- በመንግስት ተመልምለው ለዚህ ለቤተክርስቲያን የማፍረስና የማዳካም ስራ ስልጠና ወስደው ከድቁና እስከ ጵጵስና ደረጃ ተምረው ወይም የነበሩትን በዘር፣ በስልጣን፣ በጥቅማ ጥቅም ተደልለው ቤተ ክርስቲያኒቱን ከአጥቢያ ቤተክርስትያን እስከ ቤተክህነት እንዲሁም ጵጵስና ደረጃ የያዙት ሲሆኑ

2.ሁለተኞቹ፡- ደግሞ በታማኝነት፣ በፍፁም ፍቅር ፣በፍጹም እምነት በቤተክርስቲያኒቱ ያደጉና ለቤተክርስቲያኒቱ ዘብ የሚቆሙ ህመሟ ህመማቸው የሆነ ችግሯ ችግራቸው የሆኑ ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን እስከ ጵጵስና ያሉ ሲሆኑ እነዚህኞቹ ግን በአጥፊዎቹ ተውጠው በፍፁም እንዳይንቀስቀሱና ድምፃቸው ወደ ውጭ እንዳይወጣ ታፍነው የተያዙ ናቸው። እንግዲህ ይህን ያህል ካልን ይህን የማፍረስ ስራ በበላይነት እንዲመሩ የተመረጡት ደግሞ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ናቸው።
abune-matyas
ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ፦ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን እንደዚህ ሳትከፋፈል በአንድ አስተዳደር ስር በነበችበት ግዜ ማለትም ሲኖዶስ አንድ መንጋውም እረኛውም አንድ በነበረበት ወቅት አቡነ ማትያስና አቡነ ጳውሎስ በገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን ሆነው አሁን ለአለው መንግስት ገንዘብ እየሰበስቡ ይረዱ የነበሩ፤ እንዲሁም በአሁን ጊዜ በስርዓት ቤተክርስቲያን ያልተሾሙና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የፕትርክና አሿሿም ስርዓትና ደንብ ያልተሾሙ በመንግስት ፊት አውራሪነት ስራዬን ይሰሩልኛል ብሎ በመንግስት ፈቃደኝነት የተሾሙ ፓትሪያርክ ሲሆኑ ይህን ደግሞ የቤተክርስትያኒቱ ፍትሃነገስት እንደሚቃወም ኤጲስቆጶሳት አንቀጽ 5 ቁጥር 175 ረስጠብ 21<< በዚህ አለም መኳንንት ቢረዳ ከእነርሱም ዘንድ ለቤተክርስትያን ቢሾም ይሻር እርሱና ግብረአበሮቹ ሁሉ ይለዩ ብሎ ይነግረናል>> ቤተክርስቲያንን የማፍረሻ (የመክፈያ) ዋና አጀንዳቸው ደግሞ ስርዓት ቤተ ክርስቲያን ፈርሷል የሚል ነው

ስለ ስርዓት ከመነሳቱ በፊት የቤተክርስቲያንን ስርዓቶችና እና አገልግሎቶች በጥቂቱ እንመልከት

  1. ሠዓታት መቆም
  2. ማህሌት መቆም
  3. ቅዳሴ መቀደስ
  4. ስብከት ወንጌል ካሉት ግልጋሎቶች በጥቂቱ እነዚህን ስናይ

እንግዲህ እነዚህ አማሳኞች የሚጠቀሙት አንዱን ቅዳሴን በማጉላት (በማዉጣት) ሌላው አገልግሎት ላይ ሥርዓት እንደሌለ በማድረግ ያውም የፓትርያርክ ስም አለመጥራትን እንድ ትልቅ ክህደት (ዶግማ) የተጣሰ ያህል በማራገብ ቤተክርስቲያን መክፈልን ተያይዘውታል። እነርሱን የሚያስጨንቃቸው የፓትርያርክ ስም መጠራት አለመጠራቱን እንጂ የቤተክርስቲያኒቱ አገልግሎቶች ሰዓታቱ፣ ማህሌቱ፣ ስብከተ ወንጌሉ ፣ ቀኖናው፤ዶግማው ስርዓት የጠበቁ አገልግሎቶች መሆናቸው ላይ ግድ የላቸውም። ይህ ማለት በቅዳሴ ጊዜ ስም አለመጥራት ችግር አይደለም ሥርዓት አልፈረሰም ማለት አይደለም። ነገር ግን በቅዳሴ ጊዜ ስም  መጥራት የቤተክርስትያኒቱን ስርአት ሙሉ ያደርገዋል ማለት አይደለም የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም የማይጠራበት ምክንያት እልባት ቢያገኝ የቤተክርስትያኒቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮችና  የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓትና አገልግሎቶች ሙሉና አንድ ወጥ ይሆናሉ። የቤተክርስቲያኒቱ ሰላም አንድነት እንዲሁም አስተዳደር አንድ ይሆናል። አባቶች በቅዳሴ ጊዜ የፓትርያርክ ስም እንዲጠራ ሲደነግጉ በስርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተሾመ ስርአቷንና ዶግማዋን ቀኖናዋን ጠብቀው የተሾሙ የፓትርያርክ ስም እንዲጠራ እንጂ ከቤተክርስትያን የፓትርያርክ አሿሿም ስርዓት ውጭ ማለትም በመንግስት የተሾሙትን እንዲጠራ የሚል አይደለም ስርዓት ከተባለ ደግሞ አንድ ፓትርያርክ ፓትርያርክ ሊባል የሚችለው የቤተክርስቲያን ስርዓትዋንና ደንቧን የጠበቀ የእግዚአብሔርን ህዝብ በስርዓት የሚጠብቁ ኃይማኖቷን ቀኖናዋን ዶግማዋን ተከትሎ በእኩል የእግዚአብሔርን ህዝብ የሚመሩ አባትን እንጂ ከእግዚአብሔር ህዝብ ጡንቻ ያለውን መንግስት የሚያስቀድምን አባት አይደለም።ለዚህ ፍትሃ ነገስቱ ኤጲስቆጶስ  አንቀጽ 5 ቁጥር 175 ረስጠብ 21 <<በዚህ አለም መኳንንት ቢረዳ ከነርሱም ዘንድ ለቤተክርስትያን ቢሾም ይሻር እርሱና ግብራበሮቹ ሁሉ ይለዩ >>ነው የሚለው።

ለአብነት ያህል የኤርትራውን ፓትርያርክ እንመልከት። የኤርትራው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ አንቶኒዮስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጥር 13/ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ከመንበራቸው አንስቶ የቁም እስረኛ ያደረጋቸው የኤርትራው መንግስት ነው። ምክንያቱም ደግሞ መንግስት ገዝቱ ያላቸውን 3000 ምእመናን አልገዝትም በማለታቸውና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በመጠየቃቸው ሲሆን እርሳቸውም ከመንግስት ጡንቻ የእግዚአብሔር ይበልጣል በማለት አስካሁን በቁም እስር ላይ ይገኛሉ። መንግስትም አሳቸውን አስሮ በምትካቸው የመንደፈራውን አቡነ ዲዩስቆሮስን መሾሙ ይታወቃል።ይህን መረጃ በድሬቲዩብ January 22 2015 ላይ ተገልጾ እናገኛለን ልብ በሉ እውነት አሁን አባቶች ሥርዓቱን ሲሰሩ በቅዳሴ ሰዓት በመንግስት የተሾሙትን የአቡነ ዲዮስቆሮስ  ስም እንዲጠራ ነውን? አይደለም። ትክክለኛው ስርዓት በእስር ላይ ያሉት የአቡነ አንቶኒዮስ ስም እንዲጠራ እንጂ በመንግስት የተሾሙትን አለመጥራት እንደውም ስርዓትን መጠበቅ ነው።በመንግስት እንደተሾሙ እየታወቀ መጥራት ስርአት ማፍረስ ነው። እንደ ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ቀኖና መሰረት በአሁን ሰአት ቤተክርስትያን ፓትርያርክ የላትም ምክንያቱም ፓትርያርክ ይሰደዳል መንበር ግን አይሰደድም በስደት ላይ ያለው ሲኖዶስ ግን መንበር አቋቁሟል እንዲሁም የሃገር ውስጥ ሲኖዶስም በመንግስት በተሾመ ፓትርያርክ ተሰይሟል ቀኖና ቤተክርስትያን ደግሞ በመንግስት የተሾመ ይሻር ይላል እኔ ሳልሆን ቀኖናው ይሽራል ስለዚህ የትኛው ስም ይጠራ ?

እነዚህ አማሳኞች እውነት አንድነት ከሆነ ዓላማቸው ለምን ቃለ አዋዲውን አይቀበሉም? ለዚህ የሚመልሱት ደግሞ ከአሜሪካን ሀገር ጋር የማይስማማ ስላለው ነው ባይሎ የምንቀርፀው ይላሉ። ምክንያቱም የተነሱበት ዓላማ ያ ስላልሆነ ነው፤ እንጂ ከአሜሪካን ሃገር ጋር የማይስማማ ቢሆን እንኳን ጥያቄ ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርበው ቅዱስ ሲኖዶስ ከአሜሪካ ሃገር ህግ ጋር የሚስማማ ሊያወጣላቸው ይገባል እንጂ ማንም ሰው ተነስቶ ቃለ አዋዲውን ሊያሻሽል አይችልም። ምክንያቱም የማሻሻልም ሆነ የማስተካከል ስልጣን ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ስለሆነ ። እንዲሁም እነዚህ በኢትዮጵያ ስር ነን ብለው ቃለ አዋዲውን የማይቀበሉት አንድ ባይሎ(መተዳደሪያ) እንኳን የላቸውም። ለምሳሌ በአንድ እስቴት ውስጥ 10 ቤተክርስቲያን ቢኖር እንኳን 10 የተለያየ ባይሎ(መተዳደሪያ) ነው ያላቸው እንጂ ለአስሩ እንኳን አንድ ባይሎ(መተዳደሪያ)  የላቸውም ምክንያቱም ዓላማው  መለያየት ስለሆነ ባይሎው አንድ ከሆነ አንድነትን ስለሚያመጣ አያስፈልግም። ይህን ደግሞ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ፓትርያርኩን ጨምሮ በማፍረስ ስራ ላይ የተሰማሩት አንድም ምእመናንን በመከፋፈል በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት እድሜ ማራዘም ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የራሳቸውን  የወደፊት መውደቂያ እያመቻቹ ነው። መንግስት ተቀይሮ ወይም በሆነ ምክንያት የቤተክርስቲያን አንድነት ቢመለስ እነዚህን ቤተክርስቲያኖች ገለልተኛ ለማድረግና ሸሽተው መጥተው በቁጥጥራቸው ስር አድርገው የቤተክርስቲያናችን ትንሳኤ እንደገና ወደ ኋላ ለመጎተት የታለመ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምእመን ሆይ  ይህ ሁሉ ደባ በቤተክርስቲያን ላይ ሲሰራ ከዚህ ነገር ላይ ጥቂት ተጠቃሚዎች ካህናትና ግለሰቦች ስላሉ ጉዳዩን በደንብ አጢነን ዝም ብለን ከምንከተል ተው ልንላቸው ይገባል።

ይህ የአስተዳደር ችግር በምእመን የሚፈታ ችግር አይደለም የጀመሩትም አባቶች ናቸው የሚፈቱትም አባቶች ናቸው። ሁለቱ አባቶች ከፈለጉ አንድ ያደርጉታል ከፈለጉ እንደበተኗት ያስቀሯታል። ሁለቱ ከታረቁ  ሁሉም መንጋውም ግን እረኛውም አንድ ይሆናል። ምእመን ቤተክርስትያንን አንድ እናድርግ ቢል ግን ሁከትና እረብሻ  ነው የሚፈጠረው ምክንያቱም አባቶች አይፈልጉማ። አንድነት እንዳይመጣ እጃቸውን ያስገባሉ። ስለዚህ እኛ ምእመናን ግን ስደተኛ ገለልተኛ በኢትዮጵያ ሳንል አንድነታችንን ጠብቀን በያለንበት ቤ/ተክርስትያን እየተገለገልን በፍጹም ወንድማማችነት መፍትሔ እስኪመጣ ድረስ እግዚአብሔርን እየጠየቁ መኖር ያስፈልጋል።

እነዚህ አማሳኞች በተለያዩ ቦታዎች ከሰሯቸው የማፍረስ ስራዎች ውስጥ ለኣብነት ያህል በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን ያደረጉትን እንመልከት

በመጀመሪያ የሜኒሶታ ደ/ሰ/መ/ቤተክርስትያን ማን ናት?በሜንሶታ ካሉ አብያተክርስቲያናት አንዱ                     ላይ ያዉም ደብረሰላም መድኃንያለም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ለምንተመረጠ?

ደብረሰላም መድኃኒዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ከተመሰረች ከ1993 እ. ኤ. አ.በገለልተኝነት የምትታወቅ ሲሆን በተለያዩ ጳጳሳት የተባረከችና በአሁን ጊዜም የተለያዩ ጳጳሳትና የቤተክርስትያን ታላላቅ አባቶች ከኢትዮጵያ ድረስ በመምጣት ምክር ትምህርትና ቡራኬ ያልተለያት እንዲሁም በአሜሪካን ሀገር አሉ ከሚባሉት ታላላቅ አድባራት በአሁን ሰዓት ግንባር ቀደም ናት ቢባል ማጋነን አይሆንም በአሁን ግዜ አገልግሎቷን በማስፋት በአመት 365 ቀናት ማለትም አመቱን በሙሉ ለተገልጋዮች ክፍት በመሆን የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት ብቸኛዋ ቤተክርሰትያን ናት ቢባል ማጋነን አይደለም።

በደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • (1)ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 6am – 10am ለጸሎት ክፍት ሆኖ የእጣን ጸሎት እና የኪዳን ጸሎት ይደረጋል።
  • (2)ዘወትር እሁድ የሰንበት ቅዳሴ ከነግህ ጸሎት ጋር  ከንጋቱ 5am ጀምሮ ይሰጣል።
  • (3)ዘወትር የአዘቦት ቅዳሴ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ባሉት ቀናት ወር በገባ የሚካኤል ፣ ፣ የኪዳነምህረት፣ የገብርኤል

የማርያም እና  የመድኃኒዓለም ቀን ይቀደሳል።

  • (4) በአመት 8 ግዜ አመታዊ በአለ ንግስ ይደረጋል።በሁሉም በዓላት የዋዜማ አገልግሎት ከ3pm ጀምሮ ይሰጣል።

እንዲሁም በበዓሉ ቀን በማህሌት ከ2am ጀምሮ እስከ በዓሉ ፍጻሜ በድምቀት ይከበራል። እንዲሁም ከዓመታዊ

በዓላት በተጨማሪ የጽጌ ፤ የደብረታቦር ፤የስብከት፤የኖላዊ፤የልደት፤ የጥምቀት፤የሆሳእና፤የትንሳኤ፤ የዳግማ ትንሳኤ እና የጰራቅሊጦስ ማህሌት ይቆማል።

  • (5)በዓብይ ጾም 5 ቀን ሙሉ ስርአተ ሰሙነህማማት ከጠዋቱ 6am ጀምሮ ይከናወናል።
  • (6)14 ቀን የፍስለታ ሱባኤ በለሊት ሰዓታት፤በውዳሴ ማርያም ትርጓሜ እና በቅዳሴ አገልግሎት ይሰጣል።
  • (7)የመስቀል በዓል በየዓመቱ ኢትዮጵያዊ በሆነ መልኩ በድምቀት ይከበርል።
  • (8)ዘወትር ሐሙሰ ከምሽቱ 5pm ጀምሮ የስብከተ ወንጌል ትምህርት ይሰጣል ።
  • (9)ዘወትር እሁድ ከቅዳሴ በሁዋላ ማህበረ ካህናቱ እና የሰንበት ት/ቤት መዘምራን በህበረት የየእለቱን እና የየባእላን ያሬዳዊ ዜማ (ወረብ) ይዘመራል።እንዲሁም ከአገልግሎት በሁዋላ የባእላቱ ቀለም ይጠናል።
  • (10)ዘወትር እሁድ ከቁርባን በሁዋላ ለህጻናትና ወጣቶች መንፈሳዊ እና የቋንቋ ትምህርት ይሰጣል።
  • (11)ለቤተክርስትያን ዓባላት መረዳጃ እድር ይሰጣል።
  • (12) በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተለያዩ አድባራትና ገዳማት በተለያዩ ጊዜያት ከፍተኛ የገንዘብ እርዳታ ያደርጋል።

በተጨማሪም ቤተክርስትያኒቱ ከእዳ ነጻ ፤የዘር፤የጎሳ፤ልዩነት ሳይኖራት ከሁሉም አይነት የብሄር ተዋጽኦ በእኩል ፍጹም ኢትዮጵያዊነትን በተሞላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ህጉዋን፣ ስርአቷን፣ ቀኖናዋንና ዶግማዋን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት እስከ አሁን ድረስ በመድኃኒዓለም ሃይል ያለች እና ወደፊትም የምትኖር በተጓዳኝም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የህንጻ ዲዛይን አሰራር መሰረት በእዚህ በሜንሶታ ለቤተክርስቲያኒቱና ለሃገራችን እንዲሁም ለተተኪ ትውልድ አሻራ ጥሎ ለማለፍ ባለ 3 ጉልላት ያለው የተለያዩ የአገልግሎት ዘርፍ መስጠት የሚችል ካቴድራል ለመገንባት እንዲሁም ቤተክርስትያኒቱን በውጭው ዓለም ከፍ አድርጎ ሊያሳይ የሚችል እና  ዶግማዋና ቀኖናዋ ተጠበቆ ሳይበረዝ ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚደረገው ርብርብ ለቤተክርስትያኒቱ እጅግ ጠቃሚና ለመንግስት ደግሞ እራስ ምታት ስለሆነበት የመንግስት አይን አረፈበት ።

እስቲ ልብ በሉ ይህን ሁሉ አገልግሎት እና ስርአት ጠብቃ የያዘች ቤተክርስትያን ልትደገፍና ልትበረታታ ይገባታል እንጂ  ይህንን ሁሉ ስርአተ ቤተክርስትያንን እና አገልገሎትን ወደጎን ትቶ የአቡነ ማትያስን ስም አልተጠራም ተብሎ በአንድ ቀን ቤተክርስትያንን አፍርሶ መሔድ ባልተገባ ነበር። ይሁን ስህተት እንኳ ተገኝቶም ከሆነ በምክር በትምህርት መስተካከል ሲችል  በክፉ መተያየትን እና መለያየትን ባላመጣን ነበር። እዚህ ጋ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የተናገሩትን ጠቅሼ ልለፍ [በዘልማድ ሆኖ ገለልተኞች ብለው ፈረጇቸው እንጂ በሀገረ ስብከትም እንተዳደራለን የሚሉ የራሳቸውን ባይሎ ቀርጸው የሚተዳደሩ እንጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቃለ አዋዲን አንድም የሚተገብር ቤተክርስቲያን በመላው አሜሪካ አለ ብዬ አልጠብቅም………እንዲሁ ገለልተኛ ብሎ ማራቅ ለቤተ ክርስቲያን ጉዳት እንጂ ጥቅም የለውም በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ያልተወገዙና ያልተለዩ አካላት መሆናቸው እየታወቀ ገለልተኛ ብሎ ማራቅ አይገባም። ልዩነት ሊኖር ይችላል ይህን አምነን መቀበል አለብን። የአስተዳደር እንጂ የሀይማኖት ልዩነት የለንም ሁሉም በስርዓት የሚቀድሱ ማህሌት የሚቆሙ ክርስትና እየተነሳባቸው ሰው እየተዳረባቸው ፍታት እየተፈታባቸው አስፈላጊው መንፍሳዊ ነገር ሁሉ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን እየተፈጸመባቸው እየታወቀ ገለልተኛ ብሎ መጥራት ምን ማለት ነው? ሊታረም የሚገባው ነው……..ወግድ ብሎ ማራቁ ክርስቲያናዊ ተግባር አይደለም በቅዳሴ ላይ የፓትርያርክ ስም አለመጠራቱ ችግር አይደለም አልልም ችግር ነው። ነገር ግን በዚህ ምክንያት ሊለያየን አይገባም ብዬ አምናለሁ] እኚህ አባት ይህንን ያሉት ጁን 12,2012 ላይ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ ነው።

በተጨማሪም በፋይናነስ በአካውንት ውስጥ ሚሊየን ዶላር አለ የሚባል ነገር ሲመጣማ በጣም ትኩረት ተሰጠው ስለዚህ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድበት ከመንግስት ትእዛዝ ተላለፈበት ።

መንግስትም ይሰሩልኛል ብሎ ባስቀመጣቸው አባት መሪነትና በተላላኪዎቻቸው አንድ ተብሎ ተጀመረ  ይህንንም የማፍርስ ስራም እንዲሰሩ ሰዎች ተመለመሉ።

የተመለመሉት እነማን ናቸው?

  1.   ብጹዕ አቡነ ዘካርያስ የኒወርክና አካባቢው ሀገረስብከት ጳጳስ፦ የጎጃም ሃገረስበከት  ጳጳስ የነበሩና የፓትርያርክ የበላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ሆኖ ሳለ ነገርግን አቡነ ጳውሎስ ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይ  በመሆን  ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝና ፍቃድ በአቡነ ጳውሎስ ትእዛዝ ለኒዎርክና አካባቢው ሃገረ ሰብከት የተዘዋወሩና በፍትሃነገስት ላይ ኤጲስቆጶሳት አንቀጽ 5 ቁጥር 158  ኒቅያ 77<<ኤጲስቆጶስ በአገሩ መስፋትና መጥበብ በህዝቡ ማነስና መብዛት ምክንያት ኤጲስቆጶስነት ከተሾመበት አገር ወጥቶ ወደ ሌላ አገር አይሂድ ስለዚህም ከእርሷ የሚሻለውን ሊፈልግ አይገባውም ይህ ለእርሱ አይገባውምና።ለሰው ሁሉ ድርሻው ከእግዚአብሄር ተሰጥቶታል እንጂ ይህ ከህዝባውያን ወገን ሚስት ያገቡ ሰዎችን ይመስላል ያለዝሙት ምክንያት ሰው ከሚስቱ ቢሰነካከል ከእርሷ በምትበልጥ ሊለውጣት ቢፈልግ እርሱ በጣም በደለኛ ነው።ከአገራቸው የተሻለ አገርን የሚፈልጉ ኤጲስቆጶሳትም ካህናትም እንደዚሁ ናቸው ስለዚህም አውግዘን ለየናቸው ።ይህ ልማድ መጥፎ ነውና ።>>የሚለውን በመተላለፍ የተሾሙበትን ሃገረ ስብከት ትተው የመጡ ፤  ኤጲስቆጶሳት አንቀጽ 5 ቁጥር 167 ድስቅ 30<<ከነውር ወገን አንዲቱ ነውር በኤጲስቆጶስ ላይ ብትታወቅ ከመዓርጉ የሚዋረድበትን ከሹመቱ  የሚሻርበትን ምክንያት ይናገራል።>>ይህንን በመተላለፍ እምነት ያጎደሉ እንዲሁም በኤጲስቆጶስ አንቀጽ 5 ቁጥር 172<<አንድ ሊቀጳጳስ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አልመጣም አይበል የታወቀ ምክንያት ካላገኘው በቀር ወደኋላ አይበል የቀረበትንም ምክንያት ይጻፍ ፈቃድም ይቀበል>> የሚለውን በመተላለፍ እዚህ ሀገር ከገቡ ጀምሮ ከ10 ግዜ በላይ አንድም ስብሰባ ያልተካፈሉ እንዲሁም   እንደ ቤተክርስትያን ቀኖና ህግና ስርአት  ቅዱስ ሲኖዶሱ የማያውቃቸውና ጵጵስናቸው የተሻረ አባት ናቸው።እንዲሁም በፓትርያርክ ቀብርም ሆነ ሹመት ላይ ያልተገኙ  አባት ናቸው።ለዚህ ስራ ሲመረጡ ስልጣናቸውን ተገን በማድረግና በመጠቀም በማውገዝና በማስፈራራት ከቀኖና ውጭ በሆነ መንገድ እንዲያስፈጽሙ ማድረግ ነው።
  2.   በእዚህ በሚንሶታ እስቴት ውስጥ የሚገኙ በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ስር ነን የሚሉ ነገር ግን ያይደሉ ከመንግስት ጋር በቅርበት የሚሰሩ ካህናትና ግለሰቦች ናቸው።
  3.   በዛው በደብረሰላም መድሃንያለም ለብዙ ግዜ አገልጋይ የነበሩ እንዲሁም ተገልጋይ የነበሩ ካህናትና ዲያቆናት ቤተክርስትያኒቱ የነበረባቸውን ስጋዊ ችግር በገንዘብም ሆነ በተለያየ ነገር የቀረፈችላቸው በችግራቸው ግዜ የቀረቧት ዛሬ ደግሞ ሲሞላላቸውና ጊዜ ፊቷን ዞር ስታደርግላቸው የተነሱባት የእናት ጡት ነካሾችና እንዲሁም ለዚህ ስራ የተመረጡ ጥቂት የቤተክርስትያን ተቆርቁዋሪ መስለው ቤተክርስትያን የማፍረስን ስራ የሚሰሩ ግለሰቦችና እግዚአብሄርን የማያውቁ ነገር ግን የእግዚአብሄር አገልጋዮች የነበሩ የሰንበት ት/ቤት አገልጋዮች ናቸው።

እነዚህ ከላይያየናቸው አማሳኞች ለስራቸው መጀመሪያ የተቀበሉዋቸው                                          ሁለት መመሪያዎች

  1. አንደኛው በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ ቤተክርስትያኒቱን ከነሙሉ ንብረቷ በመንግስት ቁጥጥር ስር ማዋል ይሄኛው  በጣም  አዋጭ ሲሆን ብዙ ጊዜ ፤ገንዘብና ጉልበት ቆጣቢ እንዲሁም በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ነው።
  2. ሁለተኛው ደግሞ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ያችን ትልቅ የኢ/ ኦ/ተ/ቤተክርስትያንን ዶግማዋንና ቀኖናዋን እንዲሁም ስርዓተ ቤተክርስትያን ጠብቃ የምትሄደውን ለሁለት ከፍሎ ከተቻለ ማጥፋት ካልሆነም ማዳከም የሚል ነው ይህ ደግሞ ግዜ ይወስዳል። እንግዲህ እነዚህ አማሳኞች በመመሪያቸው መሰረት ኔትወርካቸውን ዘርግተው ከኢትዮጵያ ድረስ መመሪያ ሲያስፈልግ በይፋ በቡራኬ መልክ አይዟችሁ በርቱ ከጎናችሁ ነን በማለት እንደየ አስፈላጊነቱ ደግሞ ከሃገረስብከቱና ከቅዱስ ፓትርያርኩ በሚመጡ ፍጹም መንፈሳዊነት በሌላቸው ቤተክርስትያንን የሚከፍሉና የሚበትኑ መልእክቶችን በመጻጻፍ የክርስቲያኑንና  የቤተክርስትያኑን ክብር ያላገናዘበና የኢትዮጵያን ኦ/ተ/ቤ አማኙን አንገት ያስደፋ እንዲሁም የሚያሸማቅቅ ደብዳቤዎችን በመላላክና  ግልጽ በሆነና በድብቅ የስልክ ግንኙነቶች በማድረግ ቤተክርስቲያኒቱ ላይ ጥቃታቸውን ቀጠሉ።

 

የአጀንዳቸው መሠረት ስርአተ ቤተክርስቲያን ፈርሷል

እንግዲህ እነዚህ ለማፍረስ በተመለመሉ ኅይሎች አማካኝነት ከ20 ዓመት በላይ ቤተክርስትያኒቱ ሰላሙዋንና አንድነቷን ጠብቃ የኖረችበትን አቋሟን ወደጎን በመተው የቤተክርስትያን አገልግሎት ቅዳሴ ብቻ በማስመሰል ስርአተ ቤተክርስትያን ተጥሷል በማለት በቅዳሴ ግዜ የፓትርያርክ ስም አልተጠራም መጠራት አለበት በሚል በሰፊው ማራገብ ጀመሩ ።ጥያቄአቸውንም አቀረቡ ጥያቄአቸውም አግባብ፤ተገቢና መብታቸውም ስለሆነ መልስ መሰጠት አለበት በሚል በቤተክርስትያኒቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት ተደረገ በአብዛኛው አባላት ከጠቅላላ አባላቱ ከ50+1 በላይ የሆነው አባል አንድነቷ ተጠብቆ በአለችበት አቋሟ እንድትቀጥል የሚል ውሳኔ ተሰጠ። እነርሱ ግን አላማቸው ሌላ ነበርና ተስማምተው ድምጽ የሰጡበትን በማጠፍ ጠቅላላ ጉባኤ አልተሟላም አሉ እሺ ካልተስማማች እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራ ሲባሉ በፍጹም እኛ በመረጥነው መንገድ ብቻ ነው መሆን ያለበት አሉ።

እነዚህ አማሳኞች በመጀመሪያ ደረጃ ያስቀመጡት አልሳካ ሲላቸው ሁለተኛ አማራጫቸውን በመጠምዘዝ በሁከትና በረብሻ ቤተክርስትያኒቱን ማወክ ተያያዙት ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራና አባላቱ ይወስንበት ሲባሉ በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ እንደማይሆንላቸው ስላወቁት በፍጹም ጠቅላላ ጉባኤ ሳይጠራ እኛ የፈለግነውን ነገር ብቻ ካልተደረገ አሉ ። ይህን ግዜ ነበር ህግ ያለበት ሀገር ስለሆነ በህግ እንዲዳኝ ወደ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ያመራው ።  ጉዳዩም በፍርድ ቤት እያለ በዘረጉት ኔትዎርክ በመታገዝ እንዲያስታርቁ ሳይሆን ከተቻለ አስፈራርተውም ሆነ አውግዘው ወደ እራሳቸው አላማ ማለትም መንግስት ወደ ሚቆጣጠራት ቤተክርስትያን የማስገባት ስራ እንዲሰሩላቸው ካልሆነም የተፈለገውን የመክፈል ሰራ እንዲሰሩላቸው ሁለት ጳጳሳትን አመጡ

  1. አቡነ ማርቆስን ከኢትዮጵያ
  2. አቡነ ዘካርያስን ከአሜሪካን

በማስመጣት በአዳራሽ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ያውም በአርምሞ ሱባኤ በሚያዝበት በታላቁ አብይ ጾም ህዝብን ከሚመራ ጳጳስ የማይጠበቅ የስድብ አፍ በቤተክርስትያኒቱ፤በንዋያተ ቅዱሳቱ፤አላማቸውን በማይደግፉት ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም ምእመናን ላይ ሲሳደቡ፤ሲሳለቁና ሲስቁ ውለው እና አድረው እንዲሁም በማግስቱ የመጋቢት መድኃኒዓለም በዓለ ንግስ ላይ በአቡነ ማትያስ እየተመሩ የመጡት ልዑካን ከነግብራበሮቻቸው በጣም ከአቅም በላይ የሆነ ትእግስት እና እልህ አስጨራሽ ትእይንት በቤተክርስትያኑ ዓውደ ምህርት ላይ በማሳየታቸው ምእመኑ ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት አግባብ ያልሆነ ስድብ በጳጳሳቶቹ ላይ እንዲሳደብ አድርገውታል የእነርሱም አላማ በአውደምህረቱ ላይ ያልተገባ ትእይንት በማድረግ ምእመኑን ንዴት ውስጥ በመክተት ያልሆነ ቃል እንዲናገር ማድረገ ነበረና እነዚህ አፍራሽ ሃይሎች ይህችን አጋጣሚ በመጠቀም ጳጳሳቶች ተሰደቡ እያሉ ምእመኑ ላይ ተጽእኖ ለመፍጠር ሞክረዋል ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ማንነታቸው ተጋለጠ። እዚህ ጋር አንድ ልብ ልንለው የሚገባ ነገር አለ ጳጳስ ይሰደባል ግን አይሳደብም ፣ይመታል ግን አይማታም፣ይገደላል ግን አይገድልም፣ያስታርቃል ግን አያጣላም፣ ምእመንን ይሰበስባል ግን አይበትንም ፣ፍቅርን ይዘራል ግን ጥላቻን አያበቅልም እንዲሁም አንድ ጳጳስ ገና ሲመነኩስ እንደሞተ (የሞተ)ስለሆነ በቁሙ ተስካሩን  ያወጣል የጵጵስናውን አስኬማ ሲደፋ ደግሞ ለሃይማኖቱ፣ለህዝቡ፣ለተበደለ፣ለተገፋ፣ፍትህ ላጣ ፣ለተጨቆነ ፣ለቤተክርስትያን ለመሳሰሉት ሊሰደብ፣ሊገረፍ፣ሊታረዝ፣ሊታሰር፣ ብሎም ሞትም ከአስፈለገ ሊሞት ነው እንጂ ሹመቱ እንደ አለማዊ ሹመት አይደለም። እነዚህ ጳጳሳት ግን እንደነርሱ ፍላጎት ከፍለውት ነው የሄዱት ሆኖም ግን በመድኃኒዓለም ቸርነት ምእመኑ ለቤተክርስትያኑ ጠንክሮ እንዲቆም ነው ያደረጉት ቆሞም ተገኘ ።ከዛም ጳጳሳቶቹ ለአፍራሽ ካህኖቻቸው መመሪያ ሰጥተው የአቡነ ማትያስን ስም ሳትጠሩ ከእንግዲህ እንዳትቀድሱ ብለዋቸው ለሰሩት ሁከትና ብጥብጥ ተመራርቀው እና ተመሰጋግነው ጳጳሳቶቹም ወደ መጡበት ተመለሱ።

እለተ ሆሳዕና፦

እነዚህ አማሳኞች የሆሳዕና በዓል ከመደረሱ ከቀናት በፊት አንድ ቤተክርስትያኒቱን በእጃቸው የሚያስገቡበት የመሰላቸውን ተንኮል(ዘዴ) ቀይሰው ያች ቀን እስክትደርስ መጠባበቅ ጀመሩ። ድንጋዮች ያመሰገኑበት ሻጮችና ለዋጮች በጅራፍ እየተገረፉ ከቤተመቅደስ የወጡበት ክርስቶስ ቤቱን ያጸዳበት ቀን እለተ ሆሳህና በታላቋ የምስጋና ቀን ሆሳህና በ2006  በሚንሶታ በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስትያን አሳዛኝ ነገር ተከሰተ።

የሚገርመው ደግሞ እርስ በእርሳቸው ስለማይተማመኑ እንዳይካካዱ ተፈራርመው በሌሊት ወደ ተከበረችው የእግዚአብሄር ቅዱስ ስጋው እና ክቡር ደሙ ወደ ሚፈተትበት ቅድስት መቅደስ ገቡ። ህዝበ ክርስትያኑ ለአገልግሎት መጡ ነው ያለው እነርሱ ግን ለአሰቡት አላማ ነው የመጡት እቅዳቸውም ከቅዳሴ በፊት የሚከናወኑ ስርአቶች ከተከናወኑ በሁዋላ በቅዳሴ ጊዜ የአቡነ ማትያስ ስም ከተጠራ እንቀድሳለን ካልተጠራ አንቀድስም ብለው አቋማቸውን በፊርማቸው በይፋ አሳወቁ በዚህን ግዜ በሆሳዕና እለት ድንጋዮች በአመሰገኑበት ዕለት  እኛ ካልቀደስን እንዲሁም የሰንበት ተማሪዎች ካልዘመሩ ቤተክርስትያኑ ይዘጋል ሳይወዱ በግዳቸው የእኛን ፍላጎት ያሟላሉ ብለው የእግዚአብሄር ቤት መሆኑን እረስተው የትዕቢት ስራን ሰሩ። በዚህን ጊዜ ነበር መድኃኒዓለም ጅራፉን ያነሳው መድኃኒዓለም ከተነሳ ያውም በሆሳዕና ዕለት እስከ መጨረሻው ካላጸዳ አይመለስም እናም የማጽዳቱን ስራም ጀመረ።

እነሆ ከወደ ቤተመቅደስ አንድ ድምጽ ተሰማ “ እባካችሁ በዚህ በታላቅ ቀን በሆሳዕና ድንጋዮች ባመሰገኑበት ቀን የጳጳስ ስም ካልተጠራ ብለን የእግዚአብሔርን ስም አንጠራም አይባልም እውነት ከእግዚአብሔር ምስጋና የሰው ምስጋና ይበልጣልን ? በረከት ያስወስድብናል በጅራፍም ያስገርፈናል ከቤቱም ያስባርረነናል አሁን ምእመኑን ከምንበትን ቤተክርስትያኑንም ከምንዘጋ እስከዛሬ ድረስ ለብዙ ዘመን የጳጳስ ስም ሳንጠራ የቀደስንበትን ቤተክርስትያን አንቀድስም ከምንል እንቀድስና ጥፋትም ሆኖ ቢገኝ እንኳን ይቅርታ እንጠይቅበት’’ የሚል ቃል መጣ እነርሱ ግን ከበላይ ነው የታዘዝነው ብንቀድስ ክህነታችን ይያዛል መቀደስ አንችልም ብለው አቋማቸውን ገለጹ በዚህን ግዜ ነበር መድኃኒዓለም ያዘጋጃቸው ካህናትና ዲያቆናት ቅዳሴ  መቀደስ ሲጀምሩ የአማሳኞቹ ካህናትና ዲያቆናት ተከታይ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች እንዲሁም ጥቂት የእነርሱ አጀንዳ የእውነት የቤተክርስትያን አንድነት የመሰላቸው ወደ 50 የሚጠጉ ንጹሃን የቤተክርስትያን ምእመን አንድ በአንድ በየተራ ቤተመቅደሱን ለቀው ወደ ፓርክ በማመራት የሆሳእና እለት እግዚአብሔር መድኃኒዓለም በእየሩሳሌም ለቤቱ አልታዘዝ ያሉትን ጠራርጎ እንዳስወጣ ሁሉ በዳግማዊቷ እየሩሳሌም በሚንሶታ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ ተደገመ።  እግዚአብሔር በቤተመቅደሱ ተመሰገነ ከበረ ተወደሰ አቡነ ማትያስ በፓርክ ተመሰገኑ ከበሩ ተወደሱ ።

ከሁሉም በጣም ለየትና ግርም የሚለው ደግሞ እሁድ እሁድ ሁልጊዜ  ከቅዳሴ በሁዋላ የዕለቱ ያሬዳዊ ዜማ (ወረብ) ይወረባል (ይዘመራል) ያን ግዜ ግን ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በሙሉ ወጥተው ፓርክ ሄደው ስለነበር ማን ሊዘምር ነው ሲባል  ለካ እግዚአበሔር እኛ ስናምጽ ለራሱ የሆነ ሰው ለቤቱ ያዘጋጃል፤ ከምእመን እርሱ መረጠ አንድ አንድ እያሉ አውደ ምህረቱን ሞሉት እግዚአብሔር እንዲያመሰግኑት ከመረጣቸው መካከል አንዲት ልትወልድ የደረሰች እህት የመድኃኒዓለምን ድምጽ በሰማች ግዜ ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ ልታገለግል ልትዘምርለት መጣች የአምላካችን ስራው ድንቅ ነው ።አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ትዝ አለኝ በሉቃስ ወንጌል ላይ ምዕ 1 ቁጥ 41 እንዲህ የሚል ቃል አለ  “ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ግዜ ጽነሱ በማህጸኗ ውስጥ ዘለለ በኤልሳቤጥም መንፈስቅዱሰ ሞላባት   ………… ኤልሳቤጥም እነሆ የሰላምታሽ  ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ግዜ ጽንሱ በመሃጸኔ በደስታ ዘሏልና’’ ብላ እንዳመሰገነች አንዲት ልትወልድ የደረሰች ነብሰጡር የመድኃንያለምን ድምጽ በሰማች ግዜ ከተቀመጠችበት በድግ ብላ መቁዋሚያውንና ጽናጽሉን አነሳች በዚህን ግዜ በማህጸኗ የነበረው ጽንስ ዘለለ ፤ሰገደ፤አመሰገነ እግዚአብሄር በሆሳዕና እለት በድንጋዮችና በህጻናት ተመሰገነ ማለት ይህ አይደል።

እንግዲህ ምእመናን እሺ ብንል ለእግዚአብሔር ብንታዘዝ የምንከብረው የምንባረከው እኛው ነን እምቢ ብንል ደግሞ የምንጎዳው እኛው ነን እግዚአብሔር እንደው ምንም የሚጎልበት አንዳች ነገር የለውም ቢፈልግ በመሃጸን ያሉትን ያስነሳል ቢፈልግ ህጻናትን ያስነሳል ቢፈልግ ድንጋዮችን ያስነሳል ይህንንም ደግሞ በሚንሶታ ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አይተነዋል ።

የአውጋዡንና የተከታዮቹን ማንነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ውግዘት አውጋዡም ሆነ ተከታዮቹ በእውነት የኢ/ኦ/ተ ቤተክርስትያን አማኞች ናቸውን?

እዚህ ጋር ተከታዮቹ ብዬ የገለጽኩት ይህንን ተግባር ተቀብለው የሚያስፈጽሙትን እንጂ ምዕመኑን አይወክልም ምክንያቱም ምዕመኑ በንጹህ ልቡ የእውነት አንድነት መስሎት ስለሚከተል በበመጀመሪያ በኢትዮጵያ  ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ቀኖና መሰረት ስልጣኑ የተሻረ አባት ሊያወግዝም ሆነ ሊለይ አይችልም የተወገዘ እንዴት ያወግዛል ሲቀጥል በሰሞነ ሕማማት ማለትም ከሆሳእና እስከ ትንሳኤ ባሉት ቀናት ውስጥ እንኳን ማውገዝ ፤ማሰርና መለየት ቀርቶ መፍታት እንኳን በማይቻልበት ቀን አቡነ ዘካርያስ የደብረሰላም መድኃንያለም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ካህናት ፤ዲያቆናት እንዲሁም ምእመንን በፍትሐነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 600 <<በሰሞነ ሕማማት ክርስትና ማንሳት፤ ክህነት መስጠት፤ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም በእነዚህም ቀኖች ውስጥ ፈጽሞ ማገልገል ይገባል እንጂ በሰሞነ ሕማማት ስለሚሞቱት ሰዎች የሙታን ግንዘትና የሃዋርያት ስራ ወንጌላት የሙታን ፍታት በሆሳዕና በዓል ይነበብ እንጂ በጸሎተ ሐሙስ ጸሎተ ተአምኆ እግዚአ ሕያዋን የቡራኬ ጸሎት  አይባልም(አይጸለይም)ቅዳሜ ግን እግዚአ ሕያዋን ይባላል ፍትሃት ይፈታል ከመሳለም በቀር ጸሎተ እጣንም ይጸለያል በእለተ እሁድ ግንዘት ማድረግ በፋሲካ ቀንም ማልቀስ አይገባም >> የሚለውን በመተላለፍ በሰሞነ ሕማማት ቀኖናውን ጥሰው አናገለግልም ብለው የወጡትን ምንም ሳይሉ ቀኖናውን ጠብቀው ምንም ሳያጉዋድሉ ያገለገሉትን በሙሉ  በጸሎተ ኅሙስ ካህናቱና ዲያቆናቱ ቅዳሴ ቀድሰው ሲወጡ እነዚህ አማሳኞች ከአቡነ ዘካርያስ የመጣ የውግዘት ደብዳቤ ነው ተቀበሉ ብለው ፎቶና ቪዲዮ ደግነው ደብዳቤውን ለመስጠት ሞከሩ የተቀበለውም ተቀበለ ያልተቀበለም አልቀበልም ብሎ ወደ ቤቱ ሄደ።የተላለፈውንም ውግዘት እንደሚከተለው እናያለን፦

  1. ቤተክርስትያኒቱ ፦ከተመሰረተች ከ20 ዓመት በላይ የሆናት በጳጳሳት ተባርካ ብዙ ክርስትያን የተጠመቀባት ፤የቆረበባት ፣የተዳረባት ፣ሰው ሲሞት ፍትሃት የተደረገባት፣ብዙ መንፈሳዊና ሚስጥራዊ ግልጋሎት የተሰጠባት ቤተክርስትያን እግዚአብሔር አምላክ የምእመኑን ጸሎት የተቀበለባትና የፈጸመባት ቤተክርስትያንን ከዛሬ ጀምሮ አሮጌ ህንጻና የአሳማ(የከብቶች) ማርቢያ ትሁን ብለው በህንጻ ቤተክርስትያኒቱ ላይ እንዲሁም በንዋያተ ቅድሳቱ ላይ የውግዘት ቃል ተላለፈ።
  2. ካህናቱና ዲያቆናቱ ፦ከሆሳዕና ቀን ጀምሮ በደብረ ሰላም ቤተክርስትያን ብቻ የአቡነ ማትያሰን ስም ሳይጠሩ የቀደሱ ካህናትና ዲያቆናት ተወገዙ ልብ በሉ በሌላ ቤተክርስትያን ስም ሳይጠሩ መቀደስ ግን አያስወግዝም ቤተክርስትያን ሁሉንም በእኩል የሚዳኝ አንድ አይነት ህግ ያላት እንጂ አንዱን የሚኮንን አንዱን የሚያጸድቅ ህግ የላትም አለመጥራት የሚያስወግዝ ቢሆን እንኳን አይደለም እንጂ በዓለም ላይ ያሉት ገለልተኞች በሙሉ በተወገዙ ነበር ። ነገር ግን አላማው ጠንካራና ስርአተ ቤተክርስትያንን የጠበቁ ቤተክርስትያንን እየተከታተሉ የማጥፋት ዘመቻ ስለሆነ በደብረሰላም ብቻ ያሉት ተወገዙ ።
  3. ምእመኑ(ህዝበ ክርስትያኑ)፦በዚህች ቤተክርስትያን ውስጥ ቅዳሴ ያስቀደሰ ፣የቆረበ ፣ክርስትና ያስነሳ፣የተዳረ፣ቤተክርስትያን ውስጥ አገልግሎት የሰጠውን ካህን መስቀል የተሳለመ እንዲሁም ማንኛውንም አገልግሎት የተገለገለ በሙሉ ተወገዘ ።

እንግዲህ በኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርዓትና ደንብ ውግዘት እንዲሁ በቀላሉ የሚመጣ ነገር አይደለም በጣም ከባድ ነገር ነው እንደው በአሁን ግዜ ግን በጣም ያሳዝናል ። እንደ አንድ ኢ/ኦ/ተ/ቤ ምእመን ሆኜ ስመለከተው  አንገቴን እንድደፋ አድርጎኛል። ስለውግዘት በፍትሃነገስት ላይ አንድ ካህን ስለ ሁለት ነገር ይወገዛል እርሱም ቢሆን ተመክሮ አልመለስ ሲል ነው።

  1. በነውር ምክንያት        2. በምንፍቅና (በሃይማኖት ክህደት) ናቸው

እዚህ ግን የሆነው የሊቀጳጳሱን ፍላጎት ስላላሟሉ ለምን ቀደሳችሁ ተብለው ነው የተወገዙት መወገዝ ከነበረባቸውም አንቀድስም ብለው  የሄዱት ነበር መወገዝ የነበረባቸው እንዲሁም በፍትሃነገስት ላይ ኤጲስቆጶስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 184 ረስጠብ 24<< አንድ ሊቀጳጳስ በቂም በበቀል ቢያወግዝ ከሹመቱ ይሻር በተጓዳኝ የተወገዘው ካህንም ይቋቋመው ነው የሚለው >>።ደግሞ ካህናቱ አጥፍተው ተወገዙ ቢባል እንኩዋን ቤተክርስትያኒቱንና መዕመኑ በምን ጥፋታቸው ነው የሚወገዙት ቤተ ክርስትያን በሄደ ፣ በቆረበ ፣ በአመሰገነ መቼም ይህንን ለቤተክርስትያኒቱ ትልቅ ውርደት ስለሆነ አንድ ሊባል ይገባዋል።

 

ስቅለት(ዕለተ አርብ)

እነዚህ አማሳኞች ቤተክርስትያኒቱ ተወግዛለች አንሄድም እንዳትሄዱ ብለው ለምእመኑ ቤት ለቤት በመሄድና በስልክ እየደወሉ ይናገሩ ጀመር እዚህ ጋር ልብ ልንለው የሚገባው ነገር በእለተ ሃሙስ ከቅዳሴ በሁዋላ ለካህናቱና ለዲያቆናቱ በደበዳቤ ነው ውግዘቱ የደረሳቸው ታድያ ምነው በዕለተ ዓርብ መጥተው አገለገሉ ። ዕለተ ዓርብ ውግዘቱ ተነስቶ ነበር ወይስ ለእነርሱ የማፍረስ ስራ ሲሆን እንዳይሰራ ቤተክርስትያንን የሚያንጽ ሲሆን ውግዘቱን እንዲሰራ ተደረጎ ነው የተወገዘው ነገሩ እንዲህ ነው ጸሎተ ሃሙስ ዕለት ወደ 300 የሚሆኑ የቤተክርስትያኒቱ አባላቶች እነዚህ አፍራሽ ካህናትና ዲያቆናት በራሳቸው ግዜ በዕለተ ሆሳዕና ስራቸውን እረግጠው ስለወጡ ከዛሬ ጀምሮ የቤተክርስትያናችን አገልጋዮች አይደሉም የሚል በፊረማ የተደገፈ ወረቀት ለዳኛው ስለተሰጠው የአሜሪካን ህግ ደግሞ ተፈጻሚ እንደሚሆን  ስለሚያውቁት ሌላ ነገር መፈለግ ነበረባቸው እርሱም፦

  • ሌላ ቤተክርስትያን
  • ለቤተክርስትያኑ መገለገያ የሚሆን ነዋያተ ቅድሳት

ስለዚህ አዳራሽ ተከራይተው የትንሳኤን በዓል በአዳራሽ ብለው አወጁ  በቤተክርስትያኒቱም ምንም አይነት አገልግሎት አይሰጥም ብለው ምእመኑን ለማወናበድ ሞከሩ እንዲሁም ለእኛ ወፈ ግዝት ለእነርሱ ደግሞ ግዝት የሆነውን ተላልፈው ቤተክርስትያን መጥተው ንዋያተ ቅድሳቱን ዘርፈው ከእንደገና ውግዘቱን አውጀው ላይመለሱ ወጥተው ሄዱ።ከዚህም ቀን ጀምሮ በድምጽም በሁከትም እንደማይሆንላቸው  እንዲሁም በመድኃኒዓለም ቸርነትና በምእመኑ ያላሰለሰ ጥረትና ብርታት እንዳልተሳካላቸው ስላወቁት ቤተክርስትያን ለመክፈት አንድ ብለው ጀመሩ።

ሜይ 11  ወሳኙና አሳዛኙ ቀን

ለቤተክርስትያኒቱ በጣም አሳዛኝ ነበር ፤ የፍርድ ቤቱ ዳኛ በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ድምጽ ተሰጥቶ  የቤተክርስትያኒቱ አቋም የተገለጸበት ቀን ነበር። እዚህ ጋ ሳልጠቅሰው የማላልፈው ነገር ትላንት አባቶች ጳጳሳት ተሰደቡ ብለው ሲናገሩ የነበሩ በዚህ ቀን ከ8 አመት በላይ የማይጠገበውን የቤተ ክርስቲያንን ያሬዳዊ ዜማ ያስተማሯቸውን፣ንስቸውን የተቀበሏቸውን ፣ በእጃቸው የተባረኩት እና የቆረቡትን አባት በአደባባይ መሳደብ የማይረሳና አሳዛኝ ትእይንት ነበር። ይህች ቀን ለአማሳኞቹ የደስታ ቀን ነበር ምክንያቱም ከሆነላቸው ቤተክርስትያኒቱን ከነ ሙሉ ንብረቷ መረከብ ካልሆነላቸው ደግሞ ለሁለት መክፈል  ሁለቱም ውጤት ለእነርሱ የአሸናፊነት ነው ። ለቤተክርስትያኒቱ ምዕመን ግን የሃዘን ቀን ነበር ምክንያቱም ሁለቱም ውጤት የሃዘን ነበር ውጤቱ አፍራሾች ቢወስዱት በመንግስት ቁጥጥር ስር አውለው ቤተክርስትያኒቱን ባለቤት አልባ አድርገው የመንግስት ፍላጎት ማስፈጸሚያ ሊያደርጉአት  ስለሆነ ውጤቱ በ ተቃራኒውም ቢሆን ከእህት ከወንድሞቻቸው በመለየታቸው ምክንያት የሃዘን ቀን ነበር ያም ሆነ ይህ ውጤቱ የመድኃንያለምና የምዕመኑ ሆነ ቤተክርትያኒቱ  በነበረችበት አቋሟ እንድትቀጥል ሆነ ።ቤተክርስቲያኔ ብለው ደፋ ቀና እንዳላሉባት በአፋቸው ሞልተው ለመጥራት እንኳን የሚሳሱላትን ቤተክርስቲያንን ከዚህች ቀን ጀምሮ እንደ ቤተክርስትያን ሳይሆን 4401 ሕንጻ እያሉ የእግዚአብሔርን ቤት ማዋረዳቸውን ቀጠሉ።

 

ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ለሁለት ተከፈለች ፦   አብዛኛው ምእመን ደብረሰላም መድኃኒዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያንን ይዘው እንደበፊታቸው ሲቀጥሉ በሌላው ወገን ያሉት ደግሞ ጽርሃርያም ቅድስት ስላሴ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ብለው ሌላ ቤተክርስትያን መክፈታቸውን በይፋ አወጁ ሁለቱም በየአሉበት አገልግሎታቸውን ማከናወን ጀመሩ።

ከተከፈሉ በሁዋላ ደብረሰላምን የማዳከሙ ሂደት

ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ከተከፈለችበት ጊዜ ጀምሮ የመድኃኒዓለም ጥበቃ ያልተለያት ቤተ ክርስቲያን በመሆኗ እግዚአብሔር ለራሴ የሚለውን እራሱ በፍቃዱ እያመጣ አገልግሎቱ ከዱሮ በበለጠ እየሰፋ በመሄዱ   መንግስት በፖለቲካው ይጠቀምበት የነበረውን አሰራር ማለትም ለመንግስቴ ያሰጉኛል የሚላቸውን ጠንካራ ተቃዋሚዎችን የሚያዳክምበትን አሰራር በቤተክርስትያን ውስጥ በእነዚህ አፍራሽ ሃይሎች አማካኝነት እየተጠቀመበት እንዳለ እናያለን።  እስቲ የሚንሶታ ደብረሰላም መድኃኒዓለምን ለሁለት ከተከፈለ በኋላ ለማዳከም የተጠቀሙበትንና እየተጠቀሙበት ያለውን ነገር በዝርዝር እንመልከት

  1. የሚንሶታው ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ቤተክርስትያኒቱ ከተመሰረተች ጀምሮ ላለፉት 19 ዓመት  የነበረውና ያለው የሰንበት ትምህርት ቤት  መጠሪያ ስም ቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት ነው። አሁን ደግሞ ጽርአርያም ቅድስት ስላሴ ስደተኛው  ቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት በማለት ሰይመውታል በጣም የሚገርመው ጽርአርያም ስላሴ ከተመሰረተ ገና አንደኛ አመቱ ሆኖ ሳለ እነርሱ ግን  ጽርአርያም ስላሴ ስደተኛው ቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት አስራ ዘጠነኛ አመት ብለው ለሰሚው ግራ የሆነ  ዓመታዊ በዓል አክብረዋል እዚህ ጋር ስሙ ላይ ችግር የለበኝም እውነት ለሃይማኖት ከሆነ ቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት አንደኛ አመት ነበር መባል የነበረበት። ለዚህ ደግሞ የሚሰጡት ምክንያት አብላጫዎቹ ዘማሪዎች ከቤተክርስትያን ስለወጣን ነው ይላሉ ልብ በሉ አብላጫዎቹ ምእመናን አይደለም ያሉት ምእመንም ቢባል እንኳን ስህተት ነው  ሰንበት ት/ቤት ከመቼ ወዲህ ነው የግለሰቦች ሆና የምታውቀው ቤተክርስትያን ከ2000 ዘመን በላይ በኖረችበት በታሪኳ የዚህ አይነት ውርደት የቤተክርስትያን ልጆች  ነን በሚሉት ልጆቿ ሰንበት ት/ቤት የኛ የተወሰንን ሰዎች ነው የሚል የተነሳባት የመጀመሪያዎቹ ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም ። የሰንበት ት/ቤቱ ባለቤቶች ነን የሚሉት ደግሞ ሰንበት ት/ቤቱ በደብረሰላም መድኃንያለም ቤተክርስትያን ሲመሰረት እንኩዋን ያልንበሩ ናቸው።ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም ይባል የለ አባቶች ካላችሁ ስደተኛ ሰንበት ት/ቤት በሚንሶታ የተጀመረው በሌላውም እንዳይስፋፋ አንድ ልትሉ ይገባል ጅብ በቀደደው እንዳይሆን ስል የእኔን ሃሳብ እናገራለሁ።የሲኖዶስ መቀመጫ ኢትዮጵያ እንደሆነ ሁሉ የሰንበት ት/ቤቶችም መቀመጫቸው የተመሰረቱበት ቤተክርስትያን ነው የቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤትም መቀመጫ በተመሰረተበት ደብረሰላም ቤተክርስትያን ነው እንጂ በሌላ ሊሆን አይችልም።ሰው ይመጣል ይሄዳል እንጂ ሰንበት ት/ቤት ሰው ተከትሎ አይሄድም እንዲሁም ታሪክ ታሪክ የሚባለው ጊዜን እና ቦታን ሲገልጽ እንጂ የሰውን የሙቀት መጠን እየተለካ አይደለም የሚመለከተው አካል ካለ ኅይማኖታዊ ማስተካከያ ሊሰጠው ይገባል።
  2. ደብረሰላም ቤተክርስትያን ውስጥ ያሉት ታቦታት (ሀ)የመድኃኒዓለም (ለ)የኪዳነምህረት (ሓ)የሚካኤል (መ)የገብርኤል  ሲሆኑ እነዚህ አማሳኞች የመድኃኒዓለምን ታቦት በማስመጣት ሁለቱ ቤተክርስትያኖች ተለያይተው እንዲቀሩ ምዕመን   ከምዕመን እንዳይገናኝ የማድረግ ስራ ሰርተዋል ለቤተክርስትያኒቱና ለህዝበ ክርስትያኑ ቢያስቡ ኖሮ በአንድ  ከተማ ውስጥ ያለን ታቦት ባላስመጡ ነበር ። የሌለውን ነበር ማምጣት የነበረባቸው እግዚአብሔርም  በአንድነትና በፍቅር እንዲከብር በተደረገ ነበር ። እነዚህ ሰዎች ለስርዓት የሚጨነቁ በማስመሰል በሃይማኖት ሽፋን ነበር ቤተክርስቲያኗን ለሁለት የከፈሏት እነርሱ ግን ዶግማውን እስከማፍረስ ሲደርሱ ተው ያላቸውም የለም ምክንያቱም ደግሞ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን  አስተምሮ ስላሴ ማለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው መድኃኒዓለም ማለት ወልድ ነው። ሁለቱም አንድ ናቸው ብላ ነው የምታስተምረው እንደ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በስላሴ ታቦት ላይ የመድኃኒዓለም ታቦት አይገባም ምክንያቱም ሁለቱም አንድ ናቸውና በስላሴ ላይ እመቤታችን ፤ጻድቃን፤ ቅዱሳንሰ ናቸው የሚገቡት እንጂ በየትኛውም አስተምሮ መድኃኒዓለም አይገባም እነዚህ አማሳኞች አላማቸው ስለስርአት ጥሰት ሳይሆን የመንግስትን አላማ ማስፈጸም ስለሆነ አስገብተውታል።አራት መለኮት ሊባል ይሆን እግዚአብሔር ይሰውረን አንድ ሊቀ ጳጳስ እንደተናገሩት “እንደዚህ አይነት ድርጊት አራት አምላክ አለ ብለን እንደ ማመን ነው የሚቆጠረው ይህ አይነት ድርጊት በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ ቢቀርብ እና ቢታይ ጵጵስናን እስከ ማሻር እንደሚደርስ” ገልጸዋል ። በመቀጠልም ለምእመኑ ለገብርኤል ንግስ መድኃኒዓለም ሄደው እንዳያነግሱ ከዚህ በፊት ዞር ብለው አይተውት የማያውቁትን የኤርትራ ገብርኤል ቤተክርስትያን ሄዳችሁ አንግሱ ብለው ለህዝቡ አስታወቁ ሔደውም አንግሰው ጥሩ ቀን እንዳሳለፉ ገለጹ እውነት ንግሱን ፈልገው ቢሆን ችግር አልነበረውም ነገር ግን ደብረሰላም መድኃኒዓለምን ለማዳከም የተደረገ ነው። እንጂ  የሚደረገው ስራ አሁንም አላቆመም የቤተክርስቲያኗ አባት ከኢትዮጵያ የሚካኤልንም ታቦት ይዘው መጥተዋል። የሚቀራቸው የገብረኤል እና የኪዳነምህረትን ታቦት ነው ወደፊት ምን እንደሚሆን እናያለን፤   ስለዚህ ምእመናን ሆይ ይህ አስተምሮ የኢ/ኦ/ተ/ቤ አስተምሮ እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባል ዝም ብለን ተከታዮች ከምነሆን ቆም ብለን ልናስብ ይገባናል በተለይ ደግሞ ጉዞ ወደ እናት ቤተ ክርስትያን(እንቀላቀል) የሚለው ስሙ እና ከእላዩ ሲታይ  መልካም የሚመስለልና የሃይማኖት ሽፋን ያለው ውስጡ ግን ዶግማውን የሚንድ የዘመናችን የቤተክርስትያን ፈተና አስተምሮው የቤተክርስትያን ያልሆነ የመንግስትና የእነርሱን ተልኮ ለማስፈጸም የሚሮሯሯጡ ሰዎች ያስገቡብን ስለሆነ በእውነተኞቹ የቤተክርስትያን አባቶች እርምት ሊወሰድበት ይገባል። ምዕመናንም ማንም ተነስቶ ቤተክርስትያንን አንድ ላደርግ ነው ተከተሉኝ ቢል ልንከተለው አይገባም የበላይ አካል የሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠውን መመሪያ ብቻ ነው መከተል ያለበን። የቤተክርስቲያንም ክብር ሊጠበቅ ይገባል።

3 ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ለምዕመኖቿ ወንጌልን ለማስፋፋት በምታደርገው መምህራንንና ዘማርያን    ከተለያዩ ደብራት የምትጋብዛቸውን እየተከታተሉ ደብረሰላም መድኃኒዓለም ብትሄዱና ወንጌልን ብታስተምሩም ሆነ ብትዘምሩ ትወገዛላችሁ በማለት በማስፈራራት እንዲሁም አቡነ ዘካርያስ እዚያ ቤተክርስትያን አወግዝሃለሁ በሚል ማስፈራርያ ለመምጣት የአየር ትኬት ከተቆረጠላቸው በሁዋላ በዛቻው ምክንያት የሰረዙ መምህራን  እንዳሉ በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ ለዚህ ደግሞ ኤጲስቆጶስ አንቀጽ 5 ቁጥር 182 እንዲህ ይለናል <<ፈጽሞ ቂመኛ የሆነ ወይም በየጊዜው ሁሉን እስከማሰርና እስከ ማውገዝ ድረስ ፈጥኖ ለማውገዝ ቂሙን የማይረሳ ቢሆን ይሻር >> ይለናል እንዲሁም ምንም እንኳን ቤትክርስትያን የሰጠቻችሁ ሃላፊነት ቢሆንም ይህንን ሁሉ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ተቋቁማችሁ ሃይማኖታዊ ግዴታችሁን ለተወጣችሁ ሰባክያንና ዘማርያን በሃያሉ በመድኃኒዓለም ስም  ምስጋናዬን  አቀርባለሁ።

ሽልማት

እንግዲህ እንደሚታወቀው ከዋልድባና ከመሳሰሉት ታላላቅ ገዳማትና አድባራት የመጡ አባቶች ተገፍተው፤ ተበድለው፤ፍትህ አጥተው፤ ቤተክርስትያን ሲቃጠልባቸው፣ ሲፈርስባቸው አቤት ለማለትና ለማሳወቅ በአሁን ግዜ ወደ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቢሮ ለመግባት በፍጹም ዝግ በሆነበትና በማይቻልበት ሁኔታ እንዲሁም ደግሞ በሌላ በኩል የመንግስት ጉዳይ አስፈጻሚዎች የቤተክርስትያን አፍራሽ ሃይሎች ለእነርሱ ደግሞ ክፍት ሆኖ እንደፈለጉ የሚወጡበትና የሚገቡበት በሆነበት በአሁን ጊዜ የሚንሶታው ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አፍራሽ ሃይሎች እንደ ፈለጉ ሲወጡና ሲገቡ እንዲሁም ላደረጉት(ላበረከቱት) ቤተክርስትያንን የመክፈል ስራ ሽልማታቸውን ከአቡነ ማትያስ ጋር ፎቶ በመነሳት አሳይተውናል።

ማጠቃለያ

እንግዲህ ይህ ሁሉ ሲፈጸም እነዚህ ቤተክርስትያንን በማፍረስ(በመክፈል) ላይ የሚገኙ አማሳኞች እራሳቸውን ንጹህ፣ ቅዱስ ፣ጻድቃን ፣ሃይማኖተኞች በማድረግ ሌላውን ለማዳከምና ለማፍረስ የሚፈልጉትን ቤተክርስትያንና ምእመናንን  ፖለቲከኛ ፣ሃጥያተኛ ፣ በማድረግ በድፍረት የናገራሉ እንዲሁም ከእነርሱ ጋር የሚሰሩትን ጳጳሳት ትክክለኛ ናቸው ሲሉ የእነርሱን ሃሳብ የማይደግፉትን ፣የሚያስታርቁትን፤የሚመክሩትን ያውም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑትን እውነተኛ አባቶችን ይሳደባሉ፤ያንቋሽሻሉ ትክክለኛ አባት እንዳልሆኑ ለደጋፊዎቻቸውና ለምእመን ይናገራሉ ደግሞ ልዩ መለያቸው ዓይን ያወጣ ውሸት ነው ።ይህን ደግሞ በሚንሶታ ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አይተነዋል።

እንግዲህ ውድ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ምዕመን ሆይ አንድ ልናጤነው የሚገባ በአሜሪካን አገር በሲኖዶስ ስር ነን የሚሉት በሙሉ በስም ብቻ በሲኖዶስ ስር ነን ይላሉ እንጂ  አንድም ቅዱስ ሲኖዶስ የአዘጋጀውን መመሪያ ማለትም ቃለ ዓዋዲ ተግባራዊ የሚያደርግ የለም የሲኖዶሱን መመሪያ ተግባራዊ ሳያደርጉ (በሲኖዶስ ማዕቀፍ) ውስጥ ሳይገቡ ሌላውን መወንጀል ከፈረሱ ጋሪውን ማስቀደም ነው እንዲሁም  ለግለሰቦች መጠቀሚያ መሆን እንጂ ለቤተክርስትያኒቱ የሚያስገኘው ነገር ስለሌለ እርምት ሊወሰድበት ይገባል።  ደግሞም ቅዱስ ሲኖዶሱ ከስርአት ውጭ ነው ብሎ ምንም አይነት ተግሳጽም ሆነ ውግዘት ያላደረገበትን ቤተክርስትያን እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን የሚጠይቅ ጉዳይ አንድ ጳጳስ በግሉ ተነስቶ ሊለየው (ሊያወግዘው) አይችልም ተቀባይነትም አይኖረውም እንደውም  ቅዱስ ሲኖዶሱ ስርአትን በመጠበቃቸው የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያንን ቀኖናና ዶግማ  በመከተላቸው ህዝበ ክርስትያኑን በደንብ በስርአትና በኃይማኖት መምራት ይችላሉ ብሎ፦

  1. አቡነ ዳንኤልን ከሚንሶታው ደብረሰላም መድኃኒዓለም ገለልተኛ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶሱ ለጵጵስና ሲሾማቸው እንዲሁም
  2. አቡነ ፋኑኤልን ከዲሲ ሚካኤል ገለልተኛ ቤተክርስትያን ያን ቅዱስ ሲኖዶሱ ለጵጵስና ሲሾማቸው እነዚህ ስርአት አስከባሪዎቹ የት ነበሩ ?

ቅዱስ ሲኖዶስ ከገለልተኛ ቤተክርስትያን እየጠራ ሹመትን ሰጣቸው እንጂ አልለያቸውም ቅዱስ ሲኖዶስ ሲሾም ሌላው የቅዱስ ሲኖዶስ የበላይ ሆኖ ሊያወግዝም ሆነ ሊለይ እንደማይችል ለመግለጽ እወዳለሁኝ ስለዚህ በአሁን ግዜ እንደወረርሽኝ እየተስፋፋ የመጣውን  ጉዞወደ እናት ቤተክርስትያን(እንቀላቀል)የሚለው የተሞከረባቸውን የተለያዩ አብያተ ክርስትያናትና ምእመናን ላይ ያስከተላቸውን ችገሮች ስንመለከት እንኩዋን አንድነትን ሊያመጣያ ቀርቶ በአንድነት የነበሩትን ምእመናን የበተነ፣ዘመዳማቾችን የለያየ ፣ባልና ሚስትን ያለያየ ፣በኢኮኖሚና በማህበራዊ ምዕመኑን ያቃወሰ እነዲሁም ስለቤተክርስትያን በጋራ ሆኖ ይሰራና ይነጋገር የነበረውን እንዳይሰራና እንዳይነጋገር ያደረገ ነው። ስለዚህ ማንኛውም የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስትያን አማኝ ሊያደርገው የሚገባው ጥንቃቄ ማንም ተነስቶ እንቀላቀል ቢል ቤተክርስትያንን የሚያፈርሱና የሚያዳክሙ አማሳኞች መሆናቸውን ማወቅ አለብን ይህ ጉዳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሚጠይቅ ስለሆነና ማንም ጳጳስም ሆነ ፓትርያርክ በግል የሚጽፉት ደብዳቤም ሆነ መልእክት የቤተክርስትያን ድምጽ አለመሆኑን በማወቅ ልንቃወመው ይገባል የቤተክርስትያን የበላይ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚመጡት መልእክቶች ብቻ የቤተክርስትያን ድምጽ መሆናቸውን መረዳት ይኖርብናል ።

በመጨረሻም በመንግስት የምትመኩ ፤በዘርና በጎሳ የተመካችሁ፤ በስልጣን ጥማት የሰከራችሁ፤በፍቅረ ነዋይ የታወራችሁ፤ክርስቶስን የማታውቁ ግን የክርስቶስ አገልጋዮች ነን የምትሉ በሙሉ ቤተክርስትያንን በማወክና ሰላሟን በማደፍረስ በመክፈል እንዲሁም በማዳከም ላይ የተሰማራችሁ  ጳጳሳት ፤ካህናት፤ዲያቆናት ፤ግለሰቦች እስቲ ለአንድ ሰከንድ ቆም ብላችሁ የተሰቀለውን ክርስቶስን አስቡት ያን ግዜ እውነትን ታይዋታላችሁ እውነት ደግሞ የተሰቀለው ክርስቶስ እንጂ መንግስት አይደለም መንግስትም ይቀየራል፤ስልጣንም ይቀራል፤ገንዘብም ይጠፋል  ሁሉም ያልፋል የማያልፈው እውነት ብቻ ስለሆነ ስለ እውነትን መስክራችሁ ሰማእት ለመሆን ሞክሩ።ከቻላችሁ እውነትን ተናገሩ ካልቻላችሁ ሃሰትን አትናገሩ ይህንንም ካልቻላችሁ ዝም በሉ።

ስለ እውነት ምንነት ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ከጻፉት ላይ በማቅረብ ጽሁፌን ልደምድም

እውነት ማለት የኔ ልጅ

እውነት ጽድቅ እንዳይመስልሽ ኩነኔ ነው እውነት ያማል

አይታከሙት ደዌ ያከሳል ያጎሳቁላል

ሁሌ አያስከብርሽም አንድ አንዴ ህይወት ያስከፍላል

ልጄ እውነት ከህይወት ይከብዳል

በመኖር ከህይወት ተገኝቶ መልሶ ህይወት ይበላል ።

__

<< እግዚአብሄር አምላክ ፍቅርን ይስጠን >>

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

The post የወያኔ ስራ  በቤተክርስትያናት ላይ!! በዘመናችን ያለ የቤተክርስቲያን ትልቁ ፈተና – ጉዞ ወደ እናት ቤተክርስቲያን (እንቀላቀል) ለምን ትልቅ ፈተና ሆነ ስንል? appeared first on Zehabesha Amharic.

በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ ተረኛ ችሎት የወሰነውን ይግባኝ ሰሚ ሻረው

$
0
0

᎐የአቃቤ ህግ ይግባኝ ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም የሚለው ጥቅምት 17/2008 ይወሰናል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ የተበየነላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆ በተረኛ ችሎት ይግባኙ ያስቀርባል ቢባልም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ይህንን ውሳኔ በመሻር ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም የሚለውን ለመበየን ለጥቅምት 17/2008 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Habtamu abrhayeshiwas daniel

ዛሬ ጥቅምት 3/2008 ዓ.ም የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት የፓርቲ አመራሮቹ ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሽ እና አብሯቸው ይግባኝ የተጠየቀበት አብርሃም ሰለሞን ዛሬ የቃል ክርክር እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ የነበር ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ግን በነሀሴ 15/2007 ዓ.ም ተረኛ ችሎት ይግባኙ ያስቀርባል ያለውን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው አቃቤ ህግ የይግባኝ አቤቱታውን እንደገና እንዲያሰማ አድርጓል፡፡

በመሆኑም አቃቤ ህግ የስር ፍርድ ቤት በአቃቤ ህግ የቀረቡትን የቴክኒክና የሰነድ ማስረጃዎች ይዘት በአግባቡ ሳይመረምር ውሳኔ ስለሰጠብን ውሳኔው አግባብ ስላልሆነ ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ እንዲመረምርለት ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ይህንኑ የይግባኝ አቤቱታ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 17/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል በነጻ እንዲሰናበቱ የተበየነላቸው ተከሳሾች እስካሁን በእስር ላይ የቆዩበት ምክንያት አግባብ ስላልሆነ አቤቱታ እንደሚያቀርቡ ተከሳሾች ገልጸዋል፡፡ እስካሁን በእስር ላይ ሊቆዩ የቻሉት ተረኛ ችሎቱ በሰጠው እግድ መሆኑ ቢገለጽም፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ግን አቤቱታው እንዲቀርብ ፈቅዷል፡፡ ተረኛ ችሎቱ ነሀሴ 15/2007 ዓ.ም ብይኑን ሲሰጥ ተከሳሾች ችሎት ሳይቀርቡ እንደነበር ይታወሳል፡፡

The post በእነ ሀብታሙ አያሌው ላይ ተረኛ ችሎት የወሰነውን ይግባኝ ሰሚ ሻረው appeared first on Zehabesha Amharic.

ወገን እማማ ኢትዮጵያ ተርባለች … የድረሱልኝ ጥሪዋንም እያሰማች ነው?!

$
0
0

1966 እና 77ዓይነት የረሃብ እልቂት ከመድረሱ በፊት ለወገኖቻችን እንድረስላቸው!

ከፍል- ፪

 

በዲ/ን ኒቆዲሞስ

በአገራችን በኢትዮጵያ የተከሰተውን የረሃብ አደጋ አስመልክቶ ከሰሞኑን በመጀመሪያ ክፍል ያስነበብበኳችሁን ጽሑፍ ባወጣሁ ማግሥት አንዲት በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነች ወዳጄ የRFI ድረ-ገጽ ‹‹Sever Drought Threatens Millions of Ethiopia›› በሚል ርዕስ በአገራችን ስለተከሰተው ረሃብ የሚያትት ጽሑፍ በሾሻል ሚዲያ ላከችልኝ፡፡ ይህ የrfi ድረ ገጽ ያስነበበው ጽሑፍ እንደሚያትተው የኤሊኒኖ ክስተት በምሥራቅ አፍሪካና በኤዥያ በሚገኙ አገራት ባስከተለው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት አገራችን በድርቁ በከፍተኛ ኹኔታ ተጠቂ መሆኗን ዘግቦአል፡፡

hanger

ይህ ዘገባም አገራችን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ1984-85 በርካታዎች ከቀዬአቸው በተፈናቀሉበትና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ካለቁበት የረሃብ ክስተት ጀምሮ አገሪቱ በምግብ እህል ራስን የመቻል ጥያቄ ውስጥ የወደቀች አገር መሆኗን በመግለጽ፤ የዘንድሮ በዝናም እጥረት ምክንያት የተከሰተው የድርቅም ከምሥራቅ አፋር ክልል እስከ ደቡብ ሶማሊያ ያለውን ሰፊ ቦታ እንደሚሸፍንና ረሃቡ በእነዚህ ቦታዎች ላይም ከፍተኛ የሆነ ማኅበራዊና ሰብአዊ ቀውስ እያደረሰ እንዳለ ይገልጻል፡፡

ይኸው rfi.fr ድረ ገጽ የተባበሩት መንግሥታት ባስነበበው ጽሑፉ ከጥቂት ወራት በፊት ያወጣውን ፬.፭ ሚሊዮን ተረጂዎች ቁጥር በአሁን ሰዓት ድርቁ ወደ ሌሎች የአገሪቱ ክልሎች በመስፋፋቱ የተነሣ ወደ ሚሊዮን እንዳሻቀበና ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ጠቁሟል፡፡

ይህን በአገራችን የተከሰተውን የረሃብ አደጋ በተመለከተ በአፋርና በሶማሌ ክልሎች ባደረጓቸው ሰፊ ምርምሮችና ጥናቶች የሚታወቁት የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ክርስቶፈር ክላፕሃም ለRFI በሰጡት ጠቅለል ያለ አስተያየት፡- ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ላለፉት ዐሥር ዓመታት ድርቅን ይህን ተከትሎም ሊከሰት የሚችለውን ረሃብን ለመከላከልና ዜጎቼ በምግብ እህል ራሳቸውን የሚችሉበትን የተሳካ ውጤታማ የሆነ ሥራን ሠርቼያለሁ በሚልበት በዚህ ወቅት እንዲህ ዓይነቱ የረሃብ አደጋ መከሰቱ ነገሩን እንቆቅልሽ ያደርገዋል ሲሉ ነው፡፡ አስተያየታቸውን የሰጡት፡፡

The Ethiopian government having established what is generally considered to be quite an efficient system for controlling the effects of drought and malnutrition is probably embarrassed and surprised that such a serious issue has risen, Christopher Clapham, a Professor specialized in the region at Cambridge University, told to rfi. አሳዛኙ እውነታ ደግሞ ይህ የረሃብ አደጋ በቀጣይ ዓመታትም ተባብሶ የሚቀጥል መሆኑን ነው ጥናቶች የሚጠቁሙት፡፡

ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የኢትዮጵያ መንግሥት 33 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ መድቦ ድርቁ የከፋ አደጋ ባደረሰባቸው የአገሪቱ ክልሎች አፋጣኝ የሆነ የምግብ እህል እርዳታ እያደረገ መሆኑን ቢናገርም የተባበሩት መንግሥታት ከሰሞኑን ባወጣው ዘገባ ግን ለረሃብ የተጋለጡ ወገኖቻችንን ቁጥር መሻቀቡንና እነዚህን ወገኖቻችንንም ለመታደግ ከ237 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ጠቅሶአል፡፡

መንግሥት ዘግይቶም ቢሆን በአገሪቱ የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ ለጋሽ አገራትና ዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅቶች እጁን እንዲዘረጉለት የተማጸነ ቢሆንም ድርቁ በአገሪቱ የጋረጠውን የከፋ የረሃብ አደጋና እልቂት በተመለከተ ግን ሰፋ ያለና የተብራራ መረጃ በመስጠት በኩል ጉልህ ችግር እንዳለበት የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና መገናኛ ብዙኃን በሰፊው እየተናገሩና እየወቀሱ ነው፡፡

rehabበአገራችን በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱትን የረሃብ አደጋዎች ከወዲሁ አስቀድሞ በመግለጽ፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ረገድና በረሃብ የሚያልቁ ወገኖቻችንን ለመታደግና አደጋውን ለመቀነስ መወሰድ ስላለበት አፋጣኝ ዕርምጃዎችን በተመለከተ ትልቅ ችግር እንዳለ ግልጽ ነው፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት ፈጣን ልማትና ዕድገት እያስመዘገብን ነው፣ ሚሊዬነር የሆኑ አርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን እያፈራን ነው፣ ረሃብ ካሁን ወዲያ ታሪክ ይሆናል እያለ ባለበት ወቅት እንዲህ ዓይነቱ አንገትን የሚያስደፋ የረሃብ አደጋ መከሰቱ ራሱን በደንብ መፈተሽ እንዳለበት ትልቅ መሳያ ይመስለኛል፡፡

ይኸው የረሃብ አደጋ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ብቻ ሣይሆን በከተሞችም እየተስፋፋ ያለ መሆኑን መስማት፣ ማወቅ ደግሞ እጅጉን የሚያሰቅቅ ነው፡፡ የፌዴራሉ መንግሥት መቀመጫና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በሚገኙባትና የአፍሪካ ርእሰ መዲና በምትባለው በአዲስ አበባ ሣይቀር ባሉ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ሕፃናት በረሃብ የተነሣ በትምህርት ገበታቸው ላይ እያሉ ተዘልልፍለፈው እወደቁ መሆናቸውንና እንዲሁም በኑሮ ውድነት ምክንያት በርካታ ቤተሰቦች በፈረቃ ለመብላት መገደዳቸውን በአገሪቱ የሚገኙ እንደ ሪፖርተር ጋዜጣና ሸገር ራዲዮ በተለያዩ ጊዜያት ዘግበዋል፡፡

በተለይ በብዙዎች ዘንድ አፍቃሪ ኢሕአዴግ፣ እንደው ያሰበውንና የተመኘውን ያህል ሰሚ ጆሮ፣ አስተዋይ ልቦና አላገኘም እንጂ የመንግሥት መልካም መካሪና ዘካሪ እንደሆነ አብዝቶ የሚታማው የሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው እሑድ ዕትሙ ርዕሰ አንቀጹ ላይ፡- ‹‹በድርቅ ለተጎዱትም ሆነ ለከተማ ድኅነት ፈጣን ምላሽ ያስፈልጋል›› በማለት ያስነበበው፣ በአደጋ ማስጠንቀቂያ የታጀበው ርዕሰ አንቀጹ አገሪቱ ያለችበትን እውነታና የተጋረጠባትን የረሃብ አደጋ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው ለማለት ያስደፍራል፡፡

ዘንድሮ በአገራችን የተከሰተውን ድርቅና ይህንም ተከትሎ በአገራችን የተከሰተውን የረሃብ አደጋ በተመለከተ መንግሥትም ሆነ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተው እየዘገቡት ነው ብሎ ለመናገር አያስደፍርም፡፡ ያው በታሪካችን እንደምናውቀው ሺዎች ከቀዬአቸው ካልተፈናቀሉና ካልሞቱ በስተቀር ‹‹ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም›› እንደሚባለው እየሆነ ያለ ነው የሚመስለው፡፡

ታሪካችን እንደሚነግረን በ፲፱፻፷ዎቹ በአገራችን ሰሜናዊ ክፍል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው ሲፈናቀሉና ለአሰቃቂ ሞት ሲዳረጉ የዘውዱ መንግሥት በክብረ በዓልና በሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ነበር ተጠመዶ የነበረው፡፡ እናም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቹን ከቀዬአቸውና ላፈናቀለውና ለአሰቃቂ ሞት ለዳረጋቸው ለነበረው የረሃብ አደጋ ምላሽ የሰጠው ዘግይቶ ነበር፡፡

በወቅቱ ይህ የረሃብ እልቂት እንዴት ወደ አደባባይ ሊወጣ እንደቻለ በሰማኒያዎቹ በሰሜን አሜሪካ ይታተም በነበረው ‹‹ሰምና ወርቅ›› በተባለው ጥናታዊ መጽሔት ‹‹ድርቅና ጠኔ በኢትዮጵያ›› በሚል ጥናታዊ ጽሑፋቸው ውስጥ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ እንዲህ ገልጸውት ነበር፡፡ በወቅቱ የረሃቡን መከሰት የሰሙት ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፣ ዶ/ር አሉላና ለሌሎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ባልደረቦቻቸው በግላቸው ሴስና አውሮፕላን ተከራይተው ረሃቡ የከፋ አደጋ ወዳደረሰበት ወደ አገራችን ሰሜናዊ ክፍል መረጃ ለመሰብሰብ ተጓዙ፡፡

ከወሬ ባለፈ በዓይናቸው ያዩትና ምስክር የሆኑበት የረሃብ አደጋና የወገኖቻቸው አሰቃቂ የሆነ እልቂት እጅጉን ልባቸውን የነካቸው እነዚህ ምሁራን በድርቅ የተጋለጡትን የአገሪቱን ግዛቶች፣ በረሃቡ የተነሣ እጅጉን የተጎዱትን ወገኖቻቸውን በማነጋገር በምስልና በቪዲዮ ያሰባበሰቧቸውን መረጃዎች በፕ/ር መስፍን አማካኝነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ እንዲታይ ተደረገ፡፡

ይህን አሰቃቂ የሆነ የወገኖቻቸውን እልቂት፣ የሞት ጥላ ያንዣበባቸውን፣ ቆዳቸው ገርጥቶና አንጀታቸው ተጣብቆ፣ ከሰው መልክና ወዘና የወጡትን ወገኖቻቸውን፣ በእናቶቻቸው ደረት ላይ ተጣብቀው የሟች እናቶቻቸውን ጡት ሲመገምጉ የሚታዩ ሕፃናትን ምሰልና ቪዲዮ የተመለከቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ማኅበረሰብ ወገኖቻችን በረሃብ እያለቁ አንማርም፣ መንግሥት የረሃቡን እልቂት ለለጋሽ አገራትና ለዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ያጋልጥ በሚል ያስነሱት ዓመፅ ቀስ በቀስ ተባብሶ ለዘውዱ ሥርዓት መገርሰስ ምክንያት ሊሆን እንደበቃ እናውቃለን፡፡

ፕ/ሮ ጌታቸው ኃይሌ በዚሁ ጥናታዊ ጽሑፋቸው ላይ እንደሚያትቱት በወቅቱ ረሃቡ በአገሪቱ ላይ ያደረሰውን የከፋ እልቂት ያሰባበሱትን መረጃዎች ለኤምባሲዎችና ለውጭ አገራት በመስጠታቸው ረሃቡ ሊጋለጥ መቻሉንና ከዚሁ የ፷፮ቱ የከፋ የረሃብ እልቂት ጋራ በተያያዘ ስሙ በእጅጉ የሚነሳው ጆንታን ዲምቢልቢም ረሃቡ የከፋ አደጋ ባደረሰበት በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ተገኝቶ መረጃውን በዓለም ሁሉ እንዲናኝ ያደረገው ከነፕሮፌሰር ባገኘው መረጃ በመነሣት እንደሆነ ጠቅሰውታል፡፡

ፕ/ር ጌታቸው በዚሁ ጥናታዊ ጽሑፋቸው መደምደሚያ ላይም፡- ‹‹ኢትዮጵያ ትገብር ፋሲካ ታኅፂባ በደም ውሉዳ፣ ወንዞቿንም በከንቱ ወደ ግብጽ ምድር ሰዳ›› በማለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ን በፋሲካ በዓል ሌሊት፣ ካህናቱና ሊቃውንቱ ‹‹ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ታኅፂባ በደም ክርስቶስ››፣ ‹‹ምድር በክርስቶስ ኢየሱስ ደም ታጥባና ነጽታ በሐሤትና በደስታ የፋሲካን በዓል ታድርግ!›› የሚለውን ማኅሌት ‹‹ኢትዮጵያ በአብራኳ ክፋይ በገዛ ልጆቿ ደም ተነክራና ታጥባ፣ ከፈጣሪ የተሰጣትንም የተፈጥሮ ጸጋ ወንዞቿን ሳትጠቀምባቸው እንዲሁ በከንቱ ወደ ምድር ግብጽ ሰዳ በዓለ ፋሲካዋን ታድርግ!›› በማለት አገሪቱ በረሃብ አለንጋ የምትገረፍ፣ ልጆቿ በረሃብ የሚያልቁባት፣ ትውልድ በእርስ በርስ ጦርነት የሚጫረስባት፣ የእልቂት ምድር፣ አኬል-ዳማ መሆኗን እንዲህ አመስጥረውታል፤ ገልጸውታል፡፡

የ፷፮ቱን ረሃብ ተከትሎ ከዐሥር ዓመት በኋላ በ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የተከሰተው ድርቅ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ሲያፈናቅልና ብዙዎችንም ለሞት ሲዳርግ የደርግ መንግሥት ግን የአብዮቱን ፲ኛ ዓመት ለማክበር ሽር ጉድ እያደረገ፣ ሰማይ ምድሩ ጠቦት ፌሸታ ላይ ነበር፡፡ በተመሳሳይም በዘመነ ኢሕአዴግም በዘንድሮው ዓመት ስለተከሰተው የረሃብ አደጋ ለሕዝቡም ሆነ ለለጋሽ አገራት በቂ የሆነ መረጃ በመስጠት አፋጣኝ የሆነ ዕርምጃ ተወስዷል ብሎ ለመናገር አያስደፍርም፡፡

ለአብነትም መንግሥት በወርኻ ክረምቱ ማብቂያ ላይ ‹‹የዲያስፖራ ቀን›› ብሎ በሰየመው ሳምንት በሺዎች ሚቆጠሩ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሰብስቦ በግብዣ ሲያንበሸብሻቸውና የልማታችን ውጤት ነው በሚል ፌሽታና ፈንጠዝያ ሲያደርግ በአገሪቱ ስለተከሰተው ድርቅና ስለተጋረጠብን ክፉ የረሃብ አደጋ በቅጡ አለመናገሩንና በቂ የሆነ የተብራራ መረጃ አለመስጠቱን ነው ያስተዋልነው፡፡ ወይስ መንግሥት ሆይ የድርቁ፣ የረሃቡ አደጋ ዜና ለመሆን የሚበቃው ሺዎችን ከቀዬአቸው ሲያፈናቅልና ለአሰቃቂ ሞት ሲዳርጋቸው ብቻ ነው ማለት ነው እንዴ …!?

በሌላም በኩል ከጠቅላይ ሚ/ሩ እስከ ታች ባሉ የወረዳ ካድሬና ሹመኛ ድረስ እስኪሰለቸን በነጋ ጠባ የሚነገረን፣ የሚደሰኮረው አገሪቱ አስመዝግበዋለች ስለሚሉት ባለ ኹለት ዲጂት ዕድገትና ፈጣን ልማት ጉዳይ ነው፡፡ እንደ ዜጋ እንደ ኢትዮጵያዊ የአገራችን ፈጣን ዕድገትና ልማት ሁላችንንም ያስደስተናል፡፡ የሁላችንም ምኞት አገራችን በልጽጋና አድጋ፣ ሕዝባችንም ከስደትና ከጉስቁልና ወጥቶ ማየት ነው፡፡ ግና መንግሥት አገሪቱ አስመዝግበዋለች በማለት ከሚያስተጋባው ፈጣን የሆነ የልማትና የዕድገት ድምፅ ይልቅ የሚሊዮኖች ወጎኖቻችን የዋይታና የሰቆቃ፣ የእልቂትና የመከራ ድምፅ፣ እንባና ጩኸት በምድሪቱ ኹሉ ጎልቶና ደምቆ እያስተጋባ መሆኑን ልብ ሊለው ይገባል፡፡

ኢሕአዴግ ከአጋር ድርጅቶች ጋራ በመሆን ባለፈው ባደረገው ዓመታዊው ስብሰባውና ግምገማው የመልካም አስተዳደር እጦት ድርቅ መመታቱን፣ ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስና ለሥርዓቱ የከፋ አደጋ መሆናቸውን መማመኑንና ይህ አደጋም በአፍጢሙ ሊደፋው ያለ መሆኑን  የገለጸበት እውነታ፣ የሙሰኛ ባለሥልጣናቱ ማን አለብኝነትና አምባ ገነንነት፣ ግፍና ዓመፃ፣ የፍትሕ ረሃብና የመልካም አሥተዳደር መታጣቱ ከተጋረጠብን የረሃብ አደጋ ባልተናነሰ ሕዝባችንን ክፉኛ አስጎብጦትና እንደ መርግ ተጭኖት፣ ምድሪቱን በእንባ አጨቅይቶ፣ የዋይታና የሰቆቃ ምድር እያደረጋት ነውና መንግሥት ቆም ብሎ አብዝቶ ሊያስብ፣ ሊጨነቅ ይገባዋል፡፡ አለዚያ አደጋው እጅጉን ሊከፋ እንደሚችል አያጠያይቅም!!

ይቀጥላል፡፡

ሰላም!

 

The post ወገን እማማ ኢትዮጵያ ተርባለች … የድረሱልኝ ጥሪዋንም እያሰማች ነው?! appeared first on Zehabesha Amharic.

በሚኒሶታ ሕይወቱ ያለፈውን ኢትዮጵያዊ አስከሬኑን ወደ ሃገር ቤት ለመላክ ገንዘብ እየተሰባሰበ ነው

$
0
0

solomon akalu

(ዘ-ሐበሻ) ወደ አሜሪካ ከመጣ ከአንድ ዓመት በላይ የሆነውና ነዋሪነቱም በሴንት. ፖል ሚኒሶታ የሆነው ወጣት አካሉ ኪዳኔ በካንሰር ሕመም ሕይወቱ እንደሚያልፍ ከተነገረው ወዲህ ወደ ሃገሩ ለመመለስ እየተዘጋጀና ጥቂት ወዳጅ ዘመዶቹም ወደ ኢትዮጵያ የሚሄድበትን ገንዘብ ለማመቻቸት እየሰሩ በነበረበት ወቅት ድንገት ሕይወቱ አልፏል::

ወላጅ እናቱ እያስታመሙት የቆየው የ35 ዓመቱ ኪዳኔ ሕይወቱ ኦክቶበር 11 ቀን 2015 ከዚህ አለም ከተለየች በኋላ እናቱ አስከሬኑን ወደ ሃገር ቤት ይዘው እንዲሄዱ ገንዘብ እየተሰባሰበ ይገኛል:: በኢንተርኔት በhttps://www.gofundme.com/akalu አማካኝነት እየተካሄደ ባለው የገንዘብ ማሰባሰብ እስካሁን ድረስ ሊሰበሰብ የቻለው $4000 ሲሆን እስከ አርብ ድረስ ባለው ጊዜ $15000 መሰብሰብ እንዳለበት አስተባበሪዎቹ ጠቁመዋል::

በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ለዚህው ወጣት አስከሬን መላኪያ የሚሆነውን ወጪ ለመሸፈን የሚደረገውን ርብርቦሽ በማገዝ የገንዘብ እርዳታችሁን በhttps://www.gofundme.com/akalu በኩል እንድትልኩ አስተባባሪዎቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::

በሚኒሶታና አካባቢው የምትገኙና ለቅሶ ለመድረስ ለምትፈልጉ አድራሻው የሚከተለው ነው:-
ከሰኞ እስከ አርብ በመኖሪያ ቤታቸው አድራሻ
2500 Edgecumbe Rd. Apt. 104
Saint Paul, MN 55116
ወይም
ቅዳሜ እና እሁድ በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ
አድራሻ 265 Oneida Street,
Saint Paul, MN 55102
መድረስ ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ቁጥር ይደውሉ (952)807 1385
ከምስጋና ጋር ::

The post በሚኒሶታ ሕይወቱ ያለፈውን ኢትዮጵያዊ አስከሬኑን ወደ ሃገር ቤት ለመላክ ገንዘብ እየተሰባሰበ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

በትግራይ ሽሬ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን በሰላም ተገላገለች

$
0
0

mother
mother 1 (ዘ-ሐበሻ) በትግራይ ክልል በሽሬ እንደስላሴ ቀበሌ 05 ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ኢልሃም ብርሃኑ በሽር በአንድ ጊዜ የአራት ልጆች እናት ሆነች::

የአራት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ ኢልሃም በሽር ከባለቤቷ ከማል አብዱልዋስ ጋር የጋብቻ ስነስርዓቷን የፈጸመችው ሰኔ 3 ቀን 2005ዓ.ም ነበር፡፡ ይህች ወጣት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን የተገላገለችው እዚያው ሽሬ እንደስላሴ ውስጥ በሚገኘው ሱኁል ሆስፒታል መሆኑንም ታውቋል::

ለዘ-ሐበሻ እንደደረሰው መረጃ እናት ወ/ሮ ኢልሃም አራት ልጆችን በአንድ ጊዜ ከተገላገለች በኋላ “በ እርግዝና ወቅት ምንም የተለየ የሚሰማኝ ስሜት አልነበረም; በጥሩ ሁኔታ በሰላም ተገላግያለሁ” ብላለች:: አራቱን ልጆች ያዋለዱት ዶ/ር እዮብ ገላን “ወ/ሮ ኢልሃምም ሆነ ልጆቿ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ” ብለዋል::

mother 2

The post በትግራይ ሽሬ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን በሰላም ተገላገለች appeared first on Zehabesha Amharic.

ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ወደ ቦስትዋና ከተጓዘው የኤርትራ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ 10ሩ ተጫዋቾች በዚያው ጥገኝነት ጠየቁ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ለዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ማጣሪያ ጨዋታዎች ወደ ቦስትዋና ተጉዞ ከነበረው የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ 10 ተጫዋቾች እዚያው ቦስትዋና የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቃቸው ተዘገበ::
ERITRIA
ሰንደይ ስታንዳርድ የተሰኘ የቦስትዋና ጋዜጣ እንደዘገበው የኤርትራ ብሄራዊ ቡድን ከቦስትዋና አቻው ጋር ባደረገው ጨዋታ 3ለ1 የተሸነፈ ሲሆን 10ሩ ተጭዋቾች እዚያው ቀርተዋል:: የኤርትራ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እስካሁን ድረስ በተለያዩ ጊዜያት የብሄራዊ ቡድኑን ተጫዋቾች ወደ ሌላ ሃገር እየሄዱ በመቅረታቸው የተነሳ አሁን ወደ ቦስትዋና በሄደው ብሄራዊ ቡድን ውስጥ በውጭ ሃገር የሚጫወቱ ተጫዋቾች እንዲካተቱ ማድረጉን ከአስመራ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ጠቁመዋል::

አስመራ የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ወደ ቦስትዋና ከተጓዘው የኤርትራ ቡድን ውስጥ እዚያው ያልቀሩት በሌላ ሃገር የሚጫወቱት ብቻ ናቸው::

ሰንደይ ስታንዳርድ ጋዜጣ እንደዘገበው፣ የ ኤርትራ ቡድን ከቦትስዋና ጋር ተጫውቶ 3-1 ከተሸነፈ በኋላ በማግስቱ፣ ከ ከ 24 የቡድኑ ጠቅላላ አባላት፣ አስሩ እዚያው ቦትስዋና ቀርተው ጥገኝነት ጠይቀዋል። የ ኤርትራ ቡድን፣ ለጨዋታ ከአገር በወጣ ቁጥር በርካታ ተጫዋቾቹ እየጠፉበት የሚቸገር መሆኑ ይታወቃል፣ ከዚህ በፊትም በኡጋንዳ፣ በአንጎላ፣ በኬንያና በታንዛኒያ፣ አብዛኞቹ ተጫዋቾች መጥፋታቸው ይታወሳል።

The post ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ወደ ቦስትዋና ከተጓዘው የኤርትራ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ 10ሩ ተጫዋቾች በዚያው ጥገኝነት ጠየቁ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአገዛዙ የቀድሞው የአየር ሀይል አዛዥ የይስሙላው ፓርላማ የአገሪቱን ሀብት ከሚያባክን ይፍረስ ሲሉ ጠየቁ

$
0
0

* የመቶ በመቶ ምርጫ ውጤት አያስጨፍርም የችግር ማሳያ ነው
* ሙስናና የመልካም አስተዳደር ዕጦት አገሪቱን አደገኛ ሁኔታ ላይ ሊጥል ይችላል አሉ

ጥንቅር በሃብታሙ አሰፋ

abebeየአገሪቱ ከፍተኛ ስልጣን የተሰጠው ፓርላማ ህገ-መንግስታዊ ስልጣኑን ተጠቅሞ የዜጎችን ጥቅም ማስጠበቅ ካልቻለ አሁን እንዳለበት የገዥው ፓርቲ የሚሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም ብቻ ለይስሙላ ከተቀመጠ የህዝቡን አደራ መሸከም ካልቻሉ የአገሪቱዋን ሀብት ያለ አግባብ ከሚባክን ህዝበ ውሳኔ አዘጋጅቶ የማይረባ መሆኑ ህጋዊ ድጋፍ አግኝቶ ተቋሙን ማፍረስ ነው ሲሉ የአገዛዙ የቀድሞ የአየር ሀይል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አበበ ተክለሀይማኖት በቅፅል ስማቸው ጆቤ ሰሞኑን ይፋ ባደረጉት ጥናት ላይ ገለፁ።
በ1993 ህውሐት ለሁለት ሲከፈል አንጃ ተብለው ከተባረሩት መካከል አንዱ የሆኑት ጆቤ (ሜጄር ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት) ከእነ አቶ ስየ ገብሩ አስራት በተለየ የስርዓቱ ደጋፊ ሆነው የቆዩ ሲሆን ሰሞኑን በኢንተርኔት በተሰራጨው ብልሹ አስተዳደርና የዴሞክራሲ ምህዳር በማስፋትና በተቋማት ግንባታ በሚለው ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ባቀረቡት ጥናት ስርዓቱ እየተባለሸ የሔዱ የፍትህ መጓደልና ሙስናና በሀብታምና በደሃ መካከል ያለው የተጋነነ ልዩነት ድህነት አደገኛ ሁኔታ ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ዘርዝረዋል።
አገዛዙ የሚፎክርበትን የመቶ በመቶ የምርጫ ውጤት ማሸነፉን በተመለከተ ሜ/ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት (ጆቤ) በዚሁ ጥናት እንደገለፁት “ብዙ ማንነቶች፣ በርካታ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች መልስ እንሻለን የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ባሉበት አገር አንድ ግንባር (ኢህአዴግ) እና አገሮቹ መቶ በመቶ መቀመጫውን መቆጣጠር እሚያሳየን ነገር አንድም ፖለቲካዊ ስርዓቱ ላይ ችግር መኖሩን አልያም የምርጫ ስርዓቱ ችግር እንደነበረበት ነው። መቶ በመቶ እሚባል ውጤት አስቁኝ ግን ደግሞ አደገኛ ነው ይሔ ውጤት አስቂኝ ግን ደግሞ አደገኛ ነው ይሔ ውጤት አርቆ ለሚያስብ ሰው አደጋ እንጅ የድል ምልክት ተደርጎ መቆጣጠር አይቻልም ሲሉ አጣጥለውታል የዴሞክራሲ ምህዳሩ እየጠበበ መሔድ አገሪቱዋን ወደ አላስፈላጊ መንገድ ይመራል የሚለው ይሄው ጥናት አያይዘውም ተራ ፍርድ የማግኘት ጉዳይ አይደለም ሙስናና የመልካም ያልሆነ አስተዳደር አገርን ሊበትን የሚችል ነው ይላል::
wey enqilf
የቀድሞው የአገዛዙ ጄኔራል በጥናታቸው ለስርዓቱ አደገኛ ያሉዋቸውን ዋና ዋና ችግሮች ያመላከቱ ሲሆን አንድ ገዥ ፓርቲ በእኔ አውቅልሃለሁ ብቻ መራመድ አደገኛ ሁኔታን ይጋብዛል የመንግስትና የፓርቲም ሆነ ጥቂት በግል ስም የሚንቀሳቀሱ መገናኛ ብዙሃን ተራ አድርባይነት መስተካከል አለበት በዚሁ ከቀጠሉ አደገኛ ነው ካሉ በኋላ ህግ ከሚፈቅደው ውጭ ገለልተኛ ሊሆን የሚገባው መከላከያ ሳይቀር ለህውሓት ልሳን የሆነውን ወይን ጋዜጣን በገንዘብ በተዘዋዋሪ መደጎሙ አስገራሚ ዕብሪት ነው ካሉ በኋላ በምርጫ ሰሞን በአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በሙሉ የህውሓት 40ኛ ዓመት ልደት ከፍተኛ ሽፋን መስጠቱ በተቃራኒው ለተቀዋሚዎች የሚተነፍሱበት ሁኔታ መጥበቡን አመላክተዋል።
በሕውሓት ጉባኤ ሰሞን የተወሱ ጄኔራሎች መቀሌ ላይ መታየታቸውን ሰው ነገረኝ ነገር ግን የሔዱት ልግል ጉዳይ ሊሆን ይችላል እንጂ በህግ የሚያስቆጣ ተግባር ስለሆነ የፖለቲካ ተፅዕኖ ለመፍጠር መቀሌ ገብተዋል ለማለት ማስረጃ የለም እያሉ የደረሳቸውን መረጃ በዚሁ ጥናት ያጣጣሉት የቀድሞው የአገዛዙ የአየር ሀይል አዛዥ በጥናቱ እንዳስቀመጡት “በተለይ የመከላከያ ጉዳይ አሳሳቢ ነው በታዳጊ አገር ስለምንገኝ እና ዴሚክራቲክ ተቋሞቻችን ደካማ በሆኑበት ግዜ የታጠቀው ሃይል ወይ ራሳዩ ንጉስ ወይም አንጋሽና አፍራሽ ለመሆን ይዳዳዋል አሁን የታየው ምልክት እንዳይሰፋ ከወዲሁ መጠናት አለበት የሲቪሉ ቁጥጥር መጠናከር አለበት ሲሉ ስጋታቸውን ጠቅሰዋል ። የመከላከያን ከፍተኛ ስልጣን ሙሉ በሚያሰኝ ደረጃ የተቆጣጠሩት ከአንድ የትግራይ ብሔር የተውጣጡ መሆናቸውን ተከትሎ የሚቀርበውን ቅሬታ በዚህ ጥናት ሳያነሱ አልዋል።

የቀድሞው የአገዛዙ የአየር ሀይል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አበበ (ጆቤ) አቶ ገብሩ አስራት የህውሓትን ገበና ያጋለጡበትን> የተሰኘውን መፅሐፍ ተችተው አቶ መለስና ሜጄር ጄኔራል ሳሞራ የነሱትን ለመደገፍ መሞከራቸውን በዚህ ጥናት ግርጌ የግል መልእክት በሚል ለማስተካከል የሞከረቱ ሲሆን አንዳንዶች ለስልጣን እጅ መንሻ አድርገው እንደቆጠሩባቸው ያም ስህተት ነው ሲሉ ለማስተባበል ሞክረዋል። የጆቤ ዋናው የጥናት ትኩረት ዛሬም እደግፈዋለሁ ያሉትን ስርዓት ወደፊት ለማስቀጠል ይረዳል ያሉትን ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን ስርዓቱ አይታደስም ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል የሚለውን የብዙሃኑን ድምጽ ሳያካትቱ አልፈዋል።

በምርጫ 97 ቅንጅት በከፍተኛ ድምፅ አሸንፎ ህዝባዊ ድጋፍ ሲያገኝ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተሰጠው የህዝብ ድምጽ ሲሰረቅ እና ህዝቡ በየአቅጣጫቀው ተቃቀውሞ ሲያቀርብ ከህውሓት የተባረሩ ጥቂት ጓደኞቻቸውንና በድርጅቱ የተቀየሙትን ለማስተባበርና ህውሃትን እናድን የሚል እንቅስቃሴ የጀመሩ ቢሆንም በህወሃት የበላይነት የሚመራው አገዛዝ ከ193 በላይ ንፁሃን ገድሎ ሁኔታውን በመቆጣጠሩ ዕቅዳቸውን ተግባራዊ ሳያደርጉ መቅረታቸውን ነገር ግን በምርጫ የተሸነውን የሕወሃት-ኢህአዴግ አገዛዝ ለማዳን ከጓደኞቻቸው ጋር መምከራቸውን ያለ አንዳች ሀፍረት ለአንድ መጽሔት በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ መግለጻቸው አይዘነጋም።

በተቃውሞ ጎራው በኩል የስርዓቱ አደገኛ አዝማሚያ አገሪቱን ወደ አልተፈለገ ያለመረጋጋት ሊመራት ይችላል የሚለውን ስጋት የስርዓቱ ደጋፊዎች ጭምር እያሳሰባቸው መምጣቱን የቀድሞው የአገዛዙ አየር ሀይል አዛዥ ሰሞኑን ይፋ ያደረጉት ጥናት የተቃውሞው ጎራ ስጋት አግባብ እንደነበር ተጨማሪ ማስረጃ ሆኖ ይጠቀሳል::

The post የአገዛዙ የቀድሞው የአየር ሀይል አዛዥ የይስሙላው ፓርላማ የአገሪቱን ሀብት ከሚያባክን ይፍረስ ሲሉ ጠየቁ appeared first on Zehabesha Amharic.


የኢትዮ-ስታር ክለብ በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ የ2016 የስፖርት ክብረ በዓል ዓስተናጋጅ እንድትሆን በመመረጡ ደስታውን ገለጸ

$
0
0

Toronto ESFNA
ቶሮንቶ ኢትዮ-ስታር
=========================
የደስታ መግለጫ ዜና፥
የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ፥ ESFNA በካናዳ የቶሮንቶን ከተማ የ2016 የስፖርት ክብረ በዓል ዓስተናጋጅ እንድትሆን መረጠ፥
ቶሮንቶ ኢትዮ-ስታር የስፖርት ቡድን በ2016 ለሚከናወነው የ33ኛው የስፖርት ክብረ በዓል በሰሜን ዓሜሪካ ዓስተናጋጅ ሆኖ በመመረጡ የተሰማውን ደስታ ለስፖርት ዓፍቃሪ
ወገኖችና ለመላው ኢትዮጵያውያን ይገልጣል፥ የዘንድሮው የESFNA ዓመታዊ ጉባኤ በቶሮንቶ ከተማና ዓካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵዩውያን በጉጉት ሲጠበቅ የቆየውን መልካም ዜና እውን ያደረገ በመሆኑ፥ ለቶሮንቶ ኢትዮ-ስታር እና ጨዋታው ወደ ከተማችን እንዲመጣ ጥረት ሲያደርጉ ለቆዩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ደስታ ፈጥሮ ሰንብቷል::

ውሳኔው የተላለፈው፥ በኢትዮ-ስታር ቶሮንቶ የእግር ኳስ ክለብ ዓስተባባሪነት በቶሮንቶ ካናዳ በተዘጋጀው፥ የESFNA ዓመታዊ ጉባኤ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ የክለብ ተዎካዮችና የቦርዱ ዓመራር ዓባላት በተገናኙበት፥ ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ October 10 እና 11, 2015 የፌዴሬሽኑ ዓመታዊ የስራ ጉብኝት ላይ ነበር፥

የጉባኤው ዋና ዓላማ የፌዴሬሽኑን ድርጅታዊ ስራዎች እና ተጓዳኝ ተግባሮችን ከማካሄድ ባሻገር፥ በእያመቱ እንደሚያደርገው፥ ለዝግጅድቱ እጩ ከሆኑት ውስጥ በመረጡት ከተማ
የኢትዮጵያውያኑን ስነልቦናዊ ዝግጅትና የከተማውን ጠቅላላ ሁኔታ ገምግሞ ፌዴሬሽኑ ለሚያደርገው ዝግጅት ከዓለም ዙሪያ የሚሰበሰቡ ኢትዮጵያውያንን ለማስተናገድ ብቃት መኖሩን መዝኖና፥ ቅድመ ሁኔታዎችን ዓጣርቶ፥የሚቀጥለው ዓመታዊ የስፖርት ክብረ በዓል የት እንደሚደረግ ለመወሰን ነበር፥ ይህ የስፖርት ክብረ በዓል በከተማችን እንዲደረግ በመወሰኑ፥ በማንኛውም ጊዜ ድጋፋቸው ላልተለየን የቶሮንቶ ከተማ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና በንግድ ዘርፍ ለተሰማሩ ድርጅቶች ሁሉ ታላቅ ድል ነውና፥ እንኳን ደስ ያለን በማለት ደስታችን እንገልጻለን፥

ኢትዮ-ስታር ቶሮንቶ
ስልክ ቁጥር፥ 647-707-5638 / 416 878 4273

The post የኢትዮ-ስታር ክለብ በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ የ2016 የስፖርት ክብረ በዓል ዓስተናጋጅ እንድትሆን በመመረጡ ደስታውን ገለጸ appeared first on Zehabesha Amharic.

አንድ የአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ ተማሪ የህወሓትን አገዛዝ ግፍና በደል በመቃወም ራሱን አንቆ ገደለ

$
0
0

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ራድዮ እንደዘገበው ራሱን በመንግስትነት ስም የሰየመው የህወሓት አገዛዝ ምንም እንኳን ትምህርትን አስፋፍቻለሁ ብቻ ለማለት ያክል በየአካባቢው ከ30 በላይ የይስሙላህ ዩኒቨርሲቲዎችን ቢከፍትም የትምህርት ጥራት በእጅጉ እያሽቆለቆለ መጥቶ የኢትዮጵያ አንድ ትውልድ በድንቁርና ማዕበል ተመትቶ ባላዋቂነት ባህር ሰጥሞ የመጥፋት አደጋ ተደቅኖበት ይገኛል፡፡
news
በአሁኑ ጊዜ አንጋፋውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ማለት በሚቻል ሁኔታ ወጣቶች በእውቀት እና በግብረገብነት የሚቀረፁባቸው ሳይሆኑ የካድሬ መፈልፈያዎች ሆነው ይገኛሉ፡፡ዩኒቨርሲቲዎች በየዓመቱ ዕውቀት ሳይሆን ክርታስ ብቻ እየቸሩ የሚያስመርቁት በርካታ ቁጥር ያለው ወጣት ስራ ስለማያገኝ በሱስ ተጠምዶ ማንነቱን ከማጣት አለያም ተሰዶ በየበረሃው ረግፎ ከመቅረት በዘለለ ለአገራችን እያበረከተ የሚገኘው እዚህ ግባ የሚባል ጉልህ አስተዋፅኦ የለም፡፡
በመሆኑም በአገሪቱ ላይ የሰፈነውን ፍፁም የሆነና የለየለት የባርነት አገዛዝ እና ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቀት አድባር መሆናቸው ቀርቶ ወደ ካድሬ ትምህርት ቤትነት መቀየራቸውን በመቃውም እንዲሁም በተጨማሪ ከምረቃ በኋላ በአገሪቱ ምንም አይነት የተስፋ ጭላንጭል ባለማየቱ ነው ወጣቱ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ራሱን አንቆ ለመግደል የበቃው፡፡

ዘረኛውን የህወሓት አገዛዝ በመቃውም ራሱን ያጠፋው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደምም በተለያዩ አካባቢዎች ግፍ ያንገሸገሻቸው ወገኖቻችን ስርዓቱ ራሳቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ ጨክነው እንዲገድሉ ጋብዟቸዋል፡፡
ራሱን በእሳት አቃጥሎ የገደለው መምህር የኔሰው ገብሬ ሁሌም ሲታወስ የሚኖር ጀግና የፖለቲካ አክቲቪስት ነበር፡፡
በአሁኑ ስዓት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

The post አንድ የአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ ተማሪ የህወሓትን አገዛዝ ግፍና በደል በመቃወም ራሱን አንቆ ገደለ appeared first on Zehabesha Amharic.

በደቡብ ኦሞ በና እና ሐመር ውስጥ የሚሰሩ የግብረና እና ሌሎች መስሪያቤት የአገዛዙ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ መቱ

$
0
0

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ራድዮ እንደዘገበው የህወሓት አገዛዝ የታጠቁ ኃይሎችን በሐመርና አካባቢው አሰማርቶ ተደጋጋሚ ጭፍጨፋዎችን በህዝብ ላይ ሲያደርስ ቆይቷል፡፡ አገዛዙ ከፍተኛ የሆነ ግጭትና ፍጥጫ ውስጥ ገብቶባቸው ከሚገኙት በርካታ አካባቢዎች ሐመር አንዱና ዋናው ሆኗል፡፡
news
ህወሓት በፌደራል ፖሊሶቹ በሐመር ጎሳ ላይ እየፈፀመው የሚገኘውን ሰቆቃ በመቃወም የግብርና እና ሌሎች ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል፡፡ እሾህን በእሾህ እንዲሉ ሰብአዊነቱን በነፍጥ ተነጥቆ ከፍተኛ ግፍና በደል እየተፈፀመበት የሚገኘው የሐመር ጎሳ መብቱን ለማስከበር ነፍጥ አንስቶ መፋለም ጀምሮ አለመረጋጋት በመስፈኑ ጭምር በአካባቢው የሚገኙ የአገዛዙ ሰራተኞች ስራቸውን ለቀው ወደ ሌላ አካባቢ በመሰደድ ላይ ናቸው፡፡

The post በደቡብ ኦሞ በና እና ሐመር ውስጥ የሚሰሩ የግብረና እና ሌሎች መስሪያቤት የአገዛዙ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ መቱ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ሰቆቃ ዛሬም ከወደ ደ/አፍሪካ ይጣራል –“ይህ አስር ቤት ለእኔ በምድር ላይ ያለ ሴኦል ሆኖ ነው የሚታየኝ” የ 15 አመቱ ኢትዮጵያዊ እስረኛ

$
0
0

ከታምሩ ገዳ

በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸውን ለመለወጥ/ለማሻሻል በማለት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት ሲሉ በጎረቤት ማላዊ በኩል ለማቋረጥ የሞከሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በፖሊስ ተይዘው የተፈረደባቸወን የገንዘብ እና የእስራት ቅጣት ቢጨርሱም በአሳቃቂው የማላዊ እሰር ቤት ወስጥ ፈዳቸውን እያዩ እንደሚገኙ የፈረንሳዩ የዜና ወኪል (አጃንስ ፈራንስ ፕሬስ ) እሮብ ጥቅምት 14 2015 አኤአ አ ዘግቧል።
ethiopia 2

Ethiopia
“ለተሻለ ኑሮ ወደ ደ/አፍሪካ ለመሻገር የቋመጡት ኢትዮጵዊያን ሰደተኞች ምኞታቸው ቅዠት ሆነ። “ ያለው ዜና ዘገባው ከመዲናይቱ ሎላንግዊ 85 ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኘው እና ለ 800 እስረኞች ተብሎ በተገነባው የዲደዛ እስር ቤት ውስጥ ወደ 2,650 የሚጠጉ እስረኞች ከእነዚህ መካከል 317 በላይ ኢትዮጵያዊያኖች ያለ በቂ ምግብ እና ውሃ አቅርቦት እየተሰቃዩ ይገኛሉ ብሏል።የ15 አመቱ ኢያሱ ታዲዮስ ባለፈው ሃምሌ ወር ከ 29 ጓደኞቹ ጋር ማላዊ ውስጥ ታሰረው በፍርድ ቤት የተጣለባቸውን የገንዘብ አና የእሰራት ቅጣት ቢፈጽሙም “ወደ አገራቸው የሚያጓጉዛቸ ተቋም በመታጣቱ ለተጨማሪ ሰቆቃ ተጋልጠዋል ተብሏል።እያሱ ሰለደረሰበት ሰቆቃ ሲናገር “ይህ እሰር ቤት ለእኔ በምድር ላይ ያለ ሲኦል ሆኖ ነው የሚታየኝ። ቀድሞ የነበረኝ ሕልም እና ተሰፋ ሁሉ እዚህ ላይ ተገቷል ። ከ 5 ጓደኞቼ ጋር የተጣለብን 62 ዶላር ቅጣትን ብንከፍልም እና እስራቱን ብንጨርስም እስከ አሁን ድረስ አልተፈታንም ። አሁን የምፈልገው ነገር ቢኖር ወደ አገሬ መመለስ ብቻ ነው ።” በማለት ሰውነቱ በደካም እና በረሃብ የጠወለገው ታዳጊው ወጣት ኢያሱ በማላዊው እስርቤት ውስጥ የደረሰበትን ሰቆቃ እና መጥፎ ገጠመኝ በመግለጽ “የድረሱልን” ጥሪውን አቅርቧል።

ባለፈው መሰከረም ወር በአሜሪካው የሰደተ ተመላሾች ደረጅት አማካኝነት 70 ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች ነፍሳችውን ብቻ አትርፈው ወደ አገራቸው በበጎ ፍቃደተኝነት የተመለሱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በእሰራት ላይ ያሉተን 317 ወገኖቻችንን ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ በትንሹ የ አሜሪካ 200,000 ዶላር እንደሚያሰፈልግ ተገምቷል።የአለም አቀፉ ከሰደት ተመላሾች ድርጀት ተሰፋ የጠፋባቸው ኢትዮጵያዊያኑ ሰደተኞችን ወደ አገራቸው ለማጓጓዝ የበኩሉን ጥረት ቢያደረግም የአለማቀፉ ማህበረሰብ ወቅታዊ ትኩረቱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ (የሶሪያ ሰደተኞች) ላይ በመሆኑ አትዮጵያዊያኑ ሰደተኞች አሰተዋሽ አጥተዋል ተብሏል ። የደርጅቱ ዋና ሹም የሆኑት ሚስስ ካትሪን ሳኒ በበኩላቸው “እነዚህ ማስኪን ነፍሳት ከአገራቸው /ከኢትዮጵያ / እርቀው እንደዚህ አይነቱ አሰከፊ ሁኔታ ውስጥ መውደቃቸው በእጅጉ ያሳዝናል” በማለት በኢትዮጵያዊያኑ ሰደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ችግርን በሃዘኔታ ለማስረዳት ሞክረዋል።
በዚህ አጋጣሚ አገሪቱ በኢኮኖሚዋ “አድጋለች፣ ተመንደጋለች፣ ሰላም እና መረጋጋት ዙሪያ ገባዋን ሰፈኖባታል” ከተባለ ለምን ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ፖለቲከኞች ያልሆኑ ነገር ግን የወደፊቱ አገር ተረካቢ የሆኑ ሕጻናት እና ወጣቶች አስከፊውን የባህር እና የየብስ ጉዞ በማድረግ ለእንደዚህ አይነቱ እጅግ ዘግናኝ እና አሳቃቂ ችግር ይጋለጣሉ? ብለው የሚጠይቁ ወገኖች ተበራክተዋል።

The post የኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ሰቆቃ ዛሬም ከወደ ደ/አፍሪካ ይጣራል – “ይህ አስር ቤት ለእኔ በምድር ላይ ያለ ሴኦል ሆኖ ነው የሚታየኝ” የ 15 አመቱ ኢትዮጵያዊ እስረኛ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዞን 9 ጦማሪዎች ሶሊያና ሽመልስ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ እና አቤል ዋበላ ነፃ ተባሉ * ጦማሪ በፈቃዱ ኃይሉ ክሱ ተቀይሮ ይከላከል ተባለ

$
0
0

Soliana Shimeles zehabesha
(ዘ-ሐበሻ) የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዞን 9 ጦማሪዎች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ዛሬ በተሰየመው ችሎት በሌለችበት በሽብር ወንጀል ተከሳ የነበረችውን ጦማሪት ሶልያና ሽመልስ የቀረበባትን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋት በነፃ እንድትሰናበት ወሰነ::

አሁን በደረሰን ዜና ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ እና አቤል ዋብላ መከላከል ሳይጠበቅባቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ተወስኗል:: እንዲሁም ጦማሪ በፈቃዱ ሃይሉ አንቀጹ ተቀይሮ እንዲከላከልና የዋስ መብቱ ተጠብቆ እንዲከላከል ተወስኖበታል::

የዞን ዘጠኝ አባል የሆኑትና በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ላይ ከነበሩት 10 ጦማሪዎች መካከል አምስቱ ከዚህ ቀደም በነፃ መለቀቃቸው ይታወሳል::

ከሶሊያና ሽመልስ በስተቀር ዛሬ በነፃ የተሰናበቱት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች 541 ቀናት እስር ቤት ቆይተዋል::

The post የዞን 9 ጦማሪዎች ሶሊያና ሽመልስ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ እና አቤል ዋበላ ነፃ ተባሉ * ጦማሪ በፈቃዱ ኃይሉ ክሱ ተቀይሮ ይከላከል ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዞን 9 ጦማሪዎች ሶሊያና ሽመልስ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ እና አቤል ዋበላ ነፃ ተባሉ * ጦማሪ በፈቃዱ ኃይሉ ክሱ ተቀይሮ ይከላከል ተባለ (Updated)

$
0
0

Soliana Shimeles zehabesha
ZONE 9
(ዘ-ሐበሻ) የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዞን 9 ጦማሪዎች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ዛሬ በተሰየመው ችሎት በሌለችበት በሽብር ወንጀል ተከሳ የነበረችውን ጦማሪት ሶልያና ሽመልስ የቀረበባትን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋት በነፃ እንድትሰናበት ወሰነ::

አሁን በደረሰን ዜና ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ እና አቤል ዋብላ መከላከል ሳይጠበቅባቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ተወስኗል:: እንዲሁም ጦማሪ በፈቃዱ ሃይሉ አንቀጹ ተቀይሮ እንዲከላከል ተወስኖበታል::በፍቃዱ ሀይሉ በዋስ እንዲወጣ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን የዋስትናውን ጉዳይ ለማየት ለጥቅምት 10/2008 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡

የዞን ዘጠኝ አባል የሆኑትና በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ላይ ከነበሩት 10 ጦማሪዎች መካከል አምስቱ ከዚህ ቀደም በነፃ መለቀቃቸው ይታወሳል::

ከሶሊያና ሽመልስ በስተቀር ዛሬ በነፃ የተሰናበቱት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች 541 ቀናት እስር ቤት ቆይተዋል::

የዛሬውን ችሎት አስመልክቶ ከዞን9 ጦማር የተሰጠ ማስታወሻ

ዛሬ ጥቅምት 5 2007 በዋለው ችሎት አንድ አመት ከ5 ወር እስር ቤት የቆዪት አራት የዞን9 ጦማርያን ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።

በውሳኔው መሰረት አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ መከላከል ሳያስፈልጋት ከክሱ ነፃ
ሶስተኛ ተከሳሽ ናትናኤል ፈለቀ መከላከል ሳያስፈልገው ከክሱ ነፃ
አምስተኛ ተከሳሽ አጥናፍ ብርሃኔ መከላከል ሳያስፈልገው ከክሱ ነፃ
ስድስተኛ ተከሳሽ አቤል ዋበላ መከላከል ሳያስፈልገው ከክስ ነፃ የተባሉ ሲሆን
ሁለተኛ ተከሳሽ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ከሽብር ክስ ነፃ የተባለ ሲሆን መአከላዊ ምርመራ በሃይል እና በማሰቃየት የሰጠው ቃል ላይ አመፅ እንዳነሳሳ አምኗል በሚል በወንጀል ህጉ 257 መሰረት እንዲከላከል ግን ዋስትና መጠየቅ እንደሚችል ተገልፇል።

የጦማርያኑ ጠበቃ በፍቃዱ ይግባይ እንዲሰጠው የጠየቁ ሲሆን አቃቤ ህግ ተቃውሞ አሰምቶ ይግባኙ ላይ ለጥቅምት 10 ለማየት ቀጠሮ ሰጥቷል።

ባለፉት 1 አመት ከ5 ወራት በማንኛውም በቻላችሁት አቅም ሁሉ ከጎናችን ለቆማችሁ ከፍተኛ ምስጋና እያቀረብን በፍቃዱ ይፈታ የሚለው ጥያቄያችን እንደሚቀጥል ለማሳወቅ እንወዳለን።

የዞን 9 ጦማርያን ከማረሚያ ቤት ሲወጡም የምናሳውቅ ይሆናል።

እልፍ ምስጋና ለዞን9 ነዋርያንና ወዳጆች
ስለሚያገባን እንጦምራለን
ዞን9

The post የዞን 9 ጦማሪዎች ሶሊያና ሽመልስ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ እና አቤል ዋበላ ነፃ ተባሉ * ጦማሪ በፈቃዱ ኃይሉ ክሱ ተቀይሮ ይከላከል ተባለ (Updated) appeared first on Zehabesha Amharic.

“ገብጋባ ውሻ ነክሶ ለጅብ ይሰጣል”–ለሀራጥቃ ተሃድሶአዊያን – (ከመኳንንት ታዬ [ጸሃፊ])

$
0
0

orthodox-church Tehadiso

`
ቁጥር ባላት ተፈጠሮ ውስጥ ስንኖር መቁጠር የሚገባንን እንጂ ወደፊት ከእኛ በኋላ ይቆጠራል ብልን የተወሰነ ደረጃ ደርሰን አንቆምም። ከዚህ በፊት ተቆጥሮአል ብለንም ከምሃል አንጀምርም ። ለዚህ የቀደሙቱ የተውልንን እያሰደግን ለመጪው ትውልድ መስመር ሳይለቅ አባቶቻችን እንዲሉ አድርጎ ማስረከብ ተፈጥሮ የሸለመችን ሆኖ ይኼው ሲወራረድ እዚህ ደርሶ ሁሉም በየ አቅሙ ፍሰቱን ጠብቆ ለማስቀጠል ህሊናዊ ባህሪያቱ የፈቀዱለትን ያደርጋል።በዚህን ግዜ እንክርዳድ አልባ ዘር ወራቱን ያልሳተ አፈሩን የመረጠ(አዳም እንደተገኘበት ሆኖ) ሁሉን የሚወድ ባይሆንም ሁሉን ለማሸነፍ ጠንካራ ዘር ነኝ የሚል ሞራል ያለው ትውልድ ለሃገር እምብረት ለመልካምነቱ መጋቢ ሆኖ ለቤተክርስቲያአን ደግሞ ስሟንና ቅጥሯን በእሳት ዘንግ የሚጠብቅ ሲሆን ዘሩ ያለ እብቅ ተመርቶ በመንግስተ ሰማያት ጎተራ ሊከተት እውነት ይጠብቃል። ያደርጋልም።ከመስቀሉ ባለቤት እነኋት ተብሎአልና።

ለመንደርደሪያ ያህል ይህን ካልኩ ከላይ ካለው ቀለም ጋር የሚሰናሰለውን ከዚህ ጀምሮ ወረድ እያልን አብረን እናዝግም። ነገሩ እንዲህ ነው ። ሰሞኑን የተሸጡ ሰይጣኖች ዋጋ ሳንቀበል ከገበያ ወጣን ብለው በቁጭት ሲንገበገቡ ላስተዋለ የቤተክርስቲያን አምላክ ለአፍታ እንኳን እንደማይተዋት እና ለቃሉ የታመነ መሆኑን ልብ ያለው ልብ ይል ዘንድ ለአስተዋዮችና ዘመኑን ለሚዋጁ እተዋለሁ። እርግጥ ነው ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ከነሱ የቀደሙትና ብርቱ ጦር ሰብቀው የመጡት አነ ግራኝና እነ ዮዲት ጉዲት እና ሌሎቹም ከሃገር ውጭና ሐገር በቀል ጠላቶች አሁን ተገለጥልን ከምትሉ ከእናንተ ከዛሬዎቹ ጉዶች በጣም ያዳግቱ ነበር። ግን ለእነሱም ቢሆን ምላሽ ነበረውና በመጡበት ወደመጡበት ተመልሰዋል።እርግጥ ነው። በዘመናዊ ዘዴ ለማጥቃት ምዕራባዊያን ብዙ ዶልተው ስበሰባቸው ፈርሷል ።አዳራሻቸው ተዘግቶአል ።በስተመጨረሻም ያወጁትን አውጀው ተለያይተዋል። ግን በዚህ አላበቁም ።የአውሬው መንፈስ በመሰልቸት አይን የሚያያት የእኛዋ ቅድስት ቤ/ክ የቤት ስራው እንደሆነችና ለዚህ ብቸኛው አማራጭ ሰይጣኖችን መግዛትና ስልጠና መስጠት እንደነበር ያለነጋሪ በቁጭት ዲስኩራቸው ሰማን አየንም። በዚህም ስለታመነበት ለዚህ ደግሞ የዛሬዎቹ ተሃድሶ(ተዋስያን) እንደ ብቸና አገልጋይ መመልመል ሆኖ ስለተገኘ ሰይጣንን ሰይጣን ገዛና ከዚህ ደረጃ ተደረሰ። ታዲያ ” የእንቅቡ እያለ የምጣዱ ተንጣጣ ነውና “ለዚህ የጥፋት እዝ ካባ ለባሽ ያደረጋቸውን ሲናገሩ ፤ 1ኛ. የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን እየሱስዬ የማትል መሆኗ 2ኛ. እግዚአብሔርን የማትሰብክ 3ኛ….100ኛ ድረስ ምክንያት እየሰጡ መወንጀል እና ብሎም መክስስ አእምሮ ካለው ጤነኛ ሰው የሚጠበቅ አደለም። ከሐዋርያት በተቀበለችው ትምህርት ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ብላ አምላክነቱን ተቅብላ ተምራ ታስተምራለች።ታዲያ ስህተቱ እየሱስዬ አለማለቷ ነውን ? ለባኢድ አዳሯሽ ልጆቿን ወስዳችሁ ገበራችሁ። ንፁሃንን አታላችሁ ከድህንት ቤታችው ያወጣችኋቸው? እርግጥ እሱ በሆነና ባልንላችሁ።ችግሩ ግን እሱ አደለም ።የዘንዶው ልጆች ስለሆናችሁ ውጊያችሁና ጠላትነታችሁ የግብር አባታችሁን ከተዋጉት ቅዱሳን ጋር ስለመሆኑ ምንም ጥርጥረ የለውም ።ግብራችሁ ይመሰክራልና። የተሸጣችሁ ሴይጣኖች አስቲ ልጠይቃችሁ፤ አላማችሁ ክርስትና ከሆነ ለመሆኑ ከ እናንተና ከቅድስት ቤተክርስቲያን አስቀድሞ የመጣ ማነው ?እንዴትስ ቤተክርስቲያን ትላንት በተፈለፈላችሁ አንካሳ የዳቢሎስ ጫቹቶች መታደስ አለባት ብላችሁ አመናችሁ?።እርግጥ ነው የራሳችሁ አላማ እንደ ሌላችሁ እና እየጠረጋችሁ ወስዳችሁ የምትገብሩአቸው የአዳራሽ ወገኖች ብቸኛው ክፍያ የንፁአን ነብሳትን ነው።መቼም ቢሆን በራሳችሁም አትቆሙም አልቆማችሁምም። እንደው” ገብጋባ ውሻ ነክሶ ለጅብ ይሰጣል” ሆኖ ልፋታችሁ ከምንግዜውም በላይ ጨምሮ መጣ ለማለት ነው ።

በጣም የሚያሳዝነው በዘመናት መሃል አንዳንድ ክስተቶች በተለየ ልምምድ ባልተጠበቀ ሁኔታ በዘገምተኝነት አስተውሎት ሳይሰጠው የሚያነክሰውም የሚራመደውም የሚሮጥ በሚመሰስልበት ሁኔታ ጉዞ ይጀመርና በኋላ በተራራው ቆመው ሩጫውን ያስጀመረው አምላክ ማን እንደቀረና ማን እየሮጠ እነማንስ እንደሚያነክሱ ፀጋው ለበዛላቸው እየገለጠ አስኪ መጣ ድረስ ከመንገድ የማስቀረቱ ተግባር ተከናውኖ ይሆናል።ነገር ግን ይህ ለቤተክርስቲያን አዲስ አደለም።

ዛሬ ላይ ፈሰሰስን ብለው የሚፎኩሩት የከተማ ወንዞች ትላንት ከነበሩት አርዮስ፤ሰባልዮስ ፤ንስጥሮስ በእውቀትም አላዊያን ነገስታትን አሳምኖ ክርስቲያኖችን እንዲሰደዱ በማድረግም አይበልጡም። አይደርሱም።ትላንት እነዚህን መናፍቃንን ድል እንዲያደርጉ የረዳ የአባቶቻችን አምላክ የቅዱሳን በረከትና አማልጅነት ዛሬም ከመእመናኑ እና ከቤተክርስቲያን ጋር ነው ።እምነቱም ሄደቱም ከአባቶቻችን ሐዋርያት እንደተቀበልናት ሆኖ ሊቀጥል ግድ ነው :፡አውነት ነው ሁሉን የጨረሰ ትውልድ ሁሉን አውቃለሁ የሚል ከሚጠብቀው መስመር ይልቅ የሚያቋርጠው የበዛ የታናናሽ ሰዎች ክምችት ስራውም ባላቤቱም ትንሳኤ የለውም። የቤተክርስቲያን እናትነት እና እኛን ለማዳን ለሚሆነው መንገድ ብቸኛዋ ቦታ መሆኗን ለላልታሰበው በልቡ የሚበቅለው ይሁዳ ከአምላኩን ለመሸጥ የተቀበለው ሽልንግና ኋላም የበተነው የደም መሬት የተገዛበት ብር ነው ።አውነት ነው ። ቤተክርስቲያን እራሷን የቻለች ስንዱ እመቤት ናት። የማንም ያልተለመደ ጩኸትና ጋጋታ አያስፈልጋትም ።

ኢትዮጲያን አትዮጲያ አድረጋ ለመያዝ ትልቁንና የአንበሳውን ድርሻ ትወስዳለች ።ይህ ያልተመቻቸው የኢትዮጰያ ጠላቶች እናንተን ቢመለምሉአችሁና ቁልቁል የሚንደረደር ሀሳብ ይዛችሁ ዝለሉ ስትባሉ ለምን ከማለት አስከየት ለማለት እናንተ ተመራጮች ነን ካላችሁ ተሐድሶ እኮ አልነበረም መባል ያለባችሁ።ሐገርንም የማጥፋት ተልኮአችሁንም ይገልፅላችሁ ዘንዳ ከመልማዮቻችሁ ሌላ ስም ጠይቁ። ዛሬ ቤተክርስቲያናችንን ለቃችሁ እንድትወጡ እጣ ፋንታችሁም ከግብር አለቃችሁና እራሳችሁን ከሸጣችሁለት እንጂ ከበጎቹ ወገን አደለም። ዋል አደር ይበል እንጂ በእናት ሐገር ኢትዮጲያ ላይ ያላችሁንም አመለካከት እንድታብራሩ መጠየቃችን ቀጣዩ እርምጃችን ነው።አላማችሁ ምራብዊያንን ለራሳችው ክርስትና ሳይነሱ እኛን ሊያቋቁሙ የሚፈልጉትን ጫማ መጥረግና የነሱ ጫማ ጠራጊ ትውልድ ማፍራት ነው። እንጂማ ስንቱን ቅዱሳን ያፈራች ቤክርስቲያን፤ በራሱ በባለቤቱ በጌታችን በመድሃኒታችን በ ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰረተች ፤ በደሙ የዋጃት ፤አባቶች ሐዋርያት ያስተማሩባት ብሎም በአላዊያን ነገስታት ሰማትነትን የተቀበሉባት አንዲት ሐይማኖት እንዴትና በምን ሁኔታ ትላንት ኪሳችሁ ሲነጥፍ እና ግራ ሲገባችሁ በተገዘችሁ በእናንተ ትታደሳለች።

በጥቅሉ በግለኝነት ሞራል የተፈጠረ ግለኛ ባህሪ ከሚያፈልቀው ሙት እውቀት ነብስያ ያለው ትውልድ አይፈጠርም።አገራዊ ጥቅምም አይጠበቅም። ሀገርን የመክዳት ያህል የሐገርን ታሪክ እንዳልነበር አድርጎ ለመፃፍ የሚታገል እኩይ ማህበረስብ ውስጥ መልካም ነገር መጠበቅ የገማ እንቁላል የታቀፈች ዶሮ ከመሃሉ አንድ እንኳን ቢፈጠር አንካሳ ወይም ሸውራራ ነው የሚሆነው።ኢትዮጲያ ወንጌል አልተሰበከችም ወይም ቅድስት ቤተክርስቲያን የወንጌል ጠላት እንደሆነች አድርጎ ማውራት በቤተክርስቲያን ውስጥ መካን ሆነው ይመላለሱ ከነበሩ አስቀድመው ካረጡ ቃየል ልጆች የሚጠበቅም ብቻ ሳይሆን በቆራጣ እጁ ባለእጅ የተከለውን ችካል ለመንቀል እንደሚታገል የጎደለውን ከማያቅ ትውልድ የሚጠበቅ ነው። ስናጠቃልለው ወደ ቀደመ ስፍራችሁ ንስሃ ገብታችሁ ትመለሱ ዘንድ እናስባለን።ተስፋም አለን።ለመጠፋት ተዘጋጅታችሁበት ካለው ስፍራ የአዳራሽ ጉርብትና ቀድሞ በጠላትነት ከተነሱባት ጋር በቤተ ክርስቲያን መዝመታችሁን አቁሙ። በስጦታ ክዳችኋት ይሆናል ።ገንዘቡን ግን የደም መሬት እንዳገዙበት ተጠንቀቁ።በየዋህነታቸው ከቤተክርስቲያን ያስወጣችኋቸው እና አሳልፋችሁ የገበራችኋቸው ብዙዎች ናቸውና ዘመኑ ከማለቁ አስቀድማችሁ ትተልሙ ዘንድ ሰዐቱ በእጃችሁ ነው።
ይቆየን

The post “ገብጋባ ውሻ ነክሶ ለጅብ ይሰጣል” – ለሀራጥቃ ተሃድሶአዊያን – (ከመኳንንት ታዬ [ጸሃፊ]) appeared first on Zehabesha Amharic.


አቡነ መቃሪዮስ –የዘመናችን አቡነ ጴጥሮስ

$
0
0

Abune Mekariwos
ይሄይስ አእምሮ

እኛ ኢትዮጵያውያን በቁም መመሰጋገን ወይንም መወዳደስ ብዙውን ጊዜ ያቅተናል – ምክንያቱን በውል አላውቅም፡፡ ምናልባት ውዳሤ ከንቱ እንዳይመስልብን ከመፍራት አኳያ ይመስለኛል ሰውን በሕይወት ዘመኑ – እንደፈረንጆቹ – የማወደስ ባህላችን እስከዚህም የሆነው – ይህን የይሉኝታ እሥረኛ የሆነ ልማዳችንን ቅድስና ለመስጠት ታዲያ “ሆድ ያመስግን”፤ “ሙያ በልብ” የመሳሰሉ አባባሎች አሉን፡፡ ምናልባት “አመስጋኝ አማሳኝ” እንደሚባለው ተመስጋኙ የልብ ልብ እንዳይሰማውና እንዳይታበይ ታብዮም እንዳይበላሽብን ከመሥጋት አንጻርም ሊሆን ከቻለ የማናመሰግነው ይህንንም አላውቅም፡፡ ግን አንድ ሰው ከሞተ በኋላ የምሥጋናና የሙገሣ ዶፍ ከማዝነብ – ላያየው – በቁም እያለም አክብሮትንና ፍቅርን መግለጽ መልካም አጋጣሚ ይመስለኛል፡፡ ይህን በጎ ምግባር ብንለምደው አንድ ሰው ከዚህች ምድር ሲሰናበት ወይም ከተሰናበተ በኋላ በውዳሤ ለማንበሽበሽም ሆነ በዕንባ ጎርፍ ለመዘከር ከመጣደፍ የተሻለ አግባብነትና ጠቀሜታ አለው፡፡

አባ መቃሪዮስን በሚዲያ በሚገባ አውቃቸዋለሁ፡፡ ትናንት ማታ በኢሣት ቴሌቪዥን ከሎንዶኑ ጀግናችን ከወንድማገኝ ጋሹ ጋ ያደረጉትን መሳጭ ቃለ መጠይቅ አፌን ከፍቼ ስከታተል በአነጋገራቸው ዕንባየ ተንቆረዘዘ፡፡ በነገረ ሁኔታቸው ደግሞ ቁርጥ አቡነ ጴጥሮስን ሆኑብኝ፤ “ለካንስ ኢትዮጵያ የወላድ መካን አይደለችም” ብዬም ተጽናናሁ፡፡ ከሁሉም ግን የአንደበታቸው ቅላጼ እኚህ አባቴ ከወደ ሰሜኑ የሀገራችን ክፍል እንደሆኑ ምልክቶችን ሲሰጠኝ በሕይወት የመቆየትና የሀገሬን መጨረሻ የማየት ተስፋየ ይበልጥ ለመለመ፡፡ ስለሳቸው እርግጡን ለማወቅ ደግሞ ጓጓሁ፡፡ ወያኔ በየዘር ከረጪታችን ገብተን እንድንዳክር ያልቆፈረው ጉድጓድ እንደሌለ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጉድጓድ መውጣት እንደብርቅ በሚታይበት የፈተና ወቅት (ዘመነ መንሱት) እኚህ አባቴ የወያኔን ቀመር በጣጥሰው ራቁቱን ማውጣታቸውን ስታዘብ ኢትዮጵያ ተስፋ ያላት ሀገር፣ ኢትዮጳያ ያልተፈጸሙ የብዙ ድንቅ ትንቢቶች ሀገር፣ ኢትዮጵያ ወደፊት የዓለምን ስደተኞች ተቀባይ ሀገር መሆኗን ካለመጠራጠር አመንኩ፡፡ ሳይደግስ የማይጣላው ቸሩ እግዚኣብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ በነገራችን ላይ በርግጥም ሰሜነኛ መሆናቸውን ለማወቅ ለኢሣት ወዲያውኑ ኢሜል በማድረግ – ጥያቄየ መናኛ መሆኑን እየተረዳሁት ቢሆንም – እውነቱን ለመረዳት ሞከርኩ – እነሱም ቅጽበታዊ መልስ ሰጡኝና እውነቱን ዐወቅሁ – ሰሜነኛነታቸውን፤ ምን ዙሪያ ጥምትም አስኬደኝ – ትግሬ ናቸው፡፡ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት አካባቢ ስለነበር መልእክቱን ያነበብኩት ወዲያው ተነስቼ ይህችን አጭር ማስታወሻ ጻፍኩ – ወያኔዎች እንቅልፍንም ህልምንም ኑሮንም ከነሱን 25 ዓመታትን ሊደፍኑ ጥቂት ወራት ብቻ ቀርቷቸዋል፡፡ ለማንኛውም ስንከፋ ብቻ ሣይሆን ስንደሰትም መጻፍ ይኖርብናል ብዬ አስባለሁና ስለ አባቴ ስለ አባ መቃሪዮስ ይህን ጽሑፍ አሰናዳሁ – ላመሰግን፡፡(ስሜታዊ ደስታየን ለመግለጽ ያህል እንጂ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላንዱ የግዴታ ለሌላው የውዴታ እንደሆነ ቆጥሬ አለመሆኔን ወቀሳ ለሚሰነዝሩብኝ አንዳንድ ወገኖቼ በትህትና መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡)

አንድ ሰው የዘር፣ የሃማይኖት፣ የቀለም፣ የነገድና የጎሣ ድንበሮችን ጥሶ ሲሄድና ለሁሉም የሰው ዘር ጥብቅና ሲቆም ይህ ሰው በፈረንጅኛው አጠራር enlightened ሆነ እንላለን፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰው በማስሎው ቲየሪ ሲለካ የመጨረሻውን የ self-actualization ደረጃ እንደተጎናጸፈ ይነገርለታል፡፡ ከቡድሂዝም፣ ሂንዱይዝምና ጃይኒዝም እምነቶች አንጻር ካየነው ደግሞ ይህ ዓይነቱ ሰው የዳግም ልደቱን የመማሪያ ዑደት ጨርሶ ወደ ኒርቫና ደረጃ የደረሰና የነፍስ ብፅዓቱን የጨረሰ ማለት ነው – ሰውም ሆኖ ይሁን ዐይጥ ሁለተኛ ወደዚህች ምድር ተመልሶ አይመጣም – የእምነት ጉዳይ ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎችን ዓለማችን የምታፈራው በጣም በጥቂቱ ነው፤ በዚህ ረገድ ቀብቃባ/ስስታም ናት፡፡ አብዛኛው ዜጋ ሰውነት ደረጃ ለመድረስ ብዙ የሚቀረው ገና የሀሁ ተማሪ ነው፡፡ በመሠረቱ ዘረኝነትን፣ አድሎኣዊነትን፣ ፍርደ ገምድልነትን፣ ጎሠኝነትን፣ የሀገር ልጅነትን፣ ወንዘኝነትን/ጎጠኝነትን፣ የዝምድና ትስስርን፣ ወዘተ. በጣጥሶ የትክክለኛ ፍትህና የነፃ ኅሊና ባለቤት ለመሆን ብዙ ትግልን ይጠይቃል፡፡ ትግሉም እልህ አስጨራሽና ራስን እስመካድ የሚያደርስ ነው፡፡ ለአብነት አንተ ሥራ አሥኪያጅ በሆንክበት የግልም ይሁን የመንግሥት ድርጅት እኩል የትምህርት ደረጃ ያላቸው ልጅህና ጓደኛው ሥራ ለመቀጠር ቢያመለክቱ ለየትኛው ታዘነብላለህ? በተቀመጠው መሥፈርት በሃቅ አወዳድረህ ትቀጥራለህ ወይንስ እምዬ ማርያም ለበላዔሰብ አደረገች እንደተባለው አንተም ጥላህን ወዳንተው ልጅ ትጥላለህ? ቀልብህ የማይወደውን ተማሪህን ወይም አያድርግብህና ባለጌ ሆነህ ለሆነ ጉዳይ የፈለግሃትን ሴት ተማሪ አለምክንያት ወይም በቀጭን ሰበብ ትጥላለህ/ታሣልፋለህ? … ራሳችንን የምንለካባቸው ብዙና ብዙ የሕይወት ፈተናዎች(temptations)አሉ – እኔ ስላንተ የማውቃቸው አንተም ስለኔ የምታውቃቸው፡፡ አንድ የዐማርኛ ብሂል ላስታውስ፡- “ያንቺ ልጅ የኔን ልጅ መትቶት ከሆነ ምች ይምታው፤ የኔ ልጅ ያንቺን ልጅ መትቶት ከሆነ ግን መቼም፡፡” አለች ይባላል አንዷ ፍርደ ገምድል፡፡ አዎ፣ ፍርድ አስቸጋሪ ነው፡፡ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ የምንለውም ይህን ሁኔታ በሚገባ ይገልጸዋል፡፡

እንደዚያማ ባይሆን ኖሮ አቡነ ጳውሎስ(አባ ገብረ መድኅን) እነዚህን የሰይጣን ደቀ መዛሙርት ገስጸውና መክረው በመመለስ ኢትዮጵያን ከማጥፋት እንዲመለሱ ማድረግ ሲችሉ እሳቸው ራሳቸው ከክርስቶስ ቃል ወጥተው የጥፋት መንገድን ይከተሉ ነበርን? “ግም ልግም አብረህ አዝግም” እንዲሉ ምትካቸው አቡነ ናትናኤልስ (ስማቸውን ልክ እሆን? ማትያስ ነው ናትናኤል?) አባ ጳውሎስ በጀመሩት መንገድ ይጓዙ ነበርን? በነገራችን ላይ ስለሀገርህ ግድ ሳይኖርህ ሲቀር የባለሥልጣኖቹን ስም ሳይቀር አታውቅም፤ ለማወቅም አትጓጓም፡፡ የሚገርም ነገር ነው፡፡ ከምህዋር ትወጣና በገዛ ሀገርህ ባዕድ ትሆናለህ፤ የባዕድነት ስሜት ይጠናወትህና የትነትህ ጠፍቶህ እንደመፃተኛ ትሆናለህ – ከሰማይ እንደወረድህ ወይም ከመሬት እንደፈለቅህ ግዑዝ ነገር፡፡ ሲሰቀልና ሲወርድ የምትንቆራጠጥለት ባንዴራ የለህ፤ ብሔራዊ መዝሙር የለህ፤ ብሔራዊ ስሜት የለህ፤ የኔም ብለህ የምትቀበለውና በስስት የምትወደው ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ኃይል የለህ፤ በስሜት የምትናበበውና እንዳስፈላጊነቱም የምትተባበረው የደኅንነትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም የፍትህ አካል የለህ … በገዛ ሀገርህ የማንምነት ስሜት ሳይኖርህ ለመኖር ያህል ብቻ ምድራዊ ኮንትራትህ አልቆ ወደማይቀረው የወዲያኛው ዓለም እስክትጠራ ትንጠራወዛለህ፤ ጠግበህ ይርብሃል፤ ለብሰህ ይበርድሃል፤ በወገንህ መካከል እያለህ ሰው ይናፍቅሃል … ርሁቅ ብዕሲ፡፡ የኛስ ከሁሉም ባሰ!! አመክሮም የለንም እንዴ?

እኚህ አባታችን እንዲህ በሀገራቸው ወቅታዊ ሁኔታ እየተብከነከኑ ሕዝብን ለነፃነቱ እንዲነሣ ሲቀሰቅሱ ሳይ የታወሱኝ አቡነ ጴጥሮስ ናቸው ብያችኋለሁ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ እፊታቸው መትረየስ ተደግኖ እንኳን፣ ለሥጋቸው ሳይሳሱ የሀገራቸውን ነፃነት ነው የሰበኩት፡፡ ሕዝቡ ለጣሊያን እንዲገዛ ስበኩ ሲባሉ በተቃራኒው ለጣሊያን እንዳይገዛ በድፍረት ሰበኩ፤ ለጣሊያን የሚያድር ውጉዝ ከመአሪዮስ ይሁን አሉ፡፡ በዚያም ጽናታቸው ከሕይወት ይልቅ ሞትን መረጡ፡፡ ከውሸት ይልቅ እውነትን አከበሯት፡፡ ከማስመሰል ይልቅ ሃቅን ወደዱ፡፡ ከብልጭልጯ ዓለም ይልቅ የነፍሳቸውን መንገድ አስቀደሙ፡፡ ለኩነኔ ከሚዳርግ ምድራዊ ድሎትና ምቾት ይልቅ ለሰማያዊ ጽድቅ የሚያበቃቸውን መከራና ስቃይ መረጡ፡፡ አባት ማለት እንዲህ ነው፡፡ ሰው ማለት እንዲህ ነው፡፡ እነ ማህተመ ጋንዲና እነፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ያሳዩን ፈለግ ይህንን ነው፡፡ ሺህ ዓመት ቀርቶ መቶ ዓመት እንኳን በቅጡ ለማይኖርባት ምድር ብለን በውሸት ተጀቡነን እውነትን እንዳንረጋግጣት ይህ የነማህተመ ጋንዲ ፍኖት በግልጽ ያስተምረናል፡፡ ለዚህ መብቃት መታደል ነው፡፡ ለዚህ አለመብቃት ደግሞ እንስሳነት ነው፡፡

እንስሳት ስለማያስቡ፣ ስለማይጠበቡ ኑሯቸው የፊት የፊቱን ነው፡፡ ብዙዎቹ እንስሳት ስለነገ ማሰብ መቻላቸውን አናውቅም፤ ያስባሉ ብንል እንኳን ደመ ነፍሳዊ እንጂ እንደኛ ምጡቅነት የላቸውም፡፡ የነሱ ማሰብ ብዙውን ጊዜ ከሆድ ጋር – ከምግብ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ከሆድ ጋር በተያያዘ ማሰብ እንግዲህ የእንስሳነት እንጂ የሰውነት መለኪያ ሊሆን እንደማይችል መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ሰውን ሊያስጨንቀው የሚገባው ምን ታሪክ ጥሎ ማለፍ እንደሚኖርበት እንጂ ምን በልቶና ምን ለብሶ ምን ዓይነት ቤትስ ውስጥ ኖሮ ስንት ሀብትና ንብረት አፍርቶ ማለፉ ሊሆን አይገባም – ከዕዳሪነት ለማያልፍ ምግብና መጠጥና በብል ከመበላት ለማይድን ንዋይ እንዲሁም በጎርፍና በወጀብ ድራሹ ለሚጠፋ ቤትና ሕንፃ ሲባል እውነትን በሀሰት መለወጥ መጨረሻው ደይን ነው – መከራ፡፡ እነዚህን የምድር ፈተናዎች ያለፈ ሰው በርግጥም ሰው ነው፡፡በነዚህ ምድራዊ ፈተናዎች የተሰናከለ ሰው ግን ሰውነቱን አበላሽቷል – ሰውነቱን አማሰነው፡፡ ብዙዎቻችን የወደቅንበት ፈተና እንግዲህ ይህ የሆድና የዓለም የሥጋ ፈተና ነው፡፡ አዘውትረን እንደምንለው ለመኖር ይበላል እንጂ ለመብላት አይኖርም፡፡ እጅግ ብዙው የዓለም ዜጋ ግን ነፍሱን ስቶ ሲራወጥ የምናየው ለመብላት ሲኖር ነው፡፡ ይህ ሞኝነት ነው፡፡ ለነፍስ ሣይሆን ምሥጥን ለማወፈር ዘመቻ ይዘናል፡፡

የክርስትና እምነት የማዕዘን ራስ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣው ለዚህ ወይ ለዚያ ዘር አይደለም፡፡ ለነጭ ወይ ለጥቁርም አይደለም፤ ለሴት ወይ ለወንድ አይደለም፤ ለአውሮፓ ወይ ለአፍሪካ አይደለም፡፡ ያስተማረውም “ወንድምህን እንደራስህ ውደድ” እንጂ በዘርና በጎሣ የምትመሳሰለውን አፍቅረህ ሌላውን ገደል ክተት ወይም ባገኘኸው መሣሪያ እንደዐይጥ ጨፍጭፍ የሚል አይደለም፡፡ ነገር ግን ክርስቶስን በቅንዋተ መስቀል የቸነከረው የጨለማው ንጉሥ ሊቀ ሣጥናኤል ይህችን ምድር ከረጂም ዘመናት ጀምሮ በወኪሎቹ አማካይነት ይገዛት ስለነበርና አሁንም አንቀጥቅጦ እየገዛት ስለሆነ – ጊዜው መቃረቡንም በዚህ አጋጣሚ መጠቆም ይገባል – ሰዎች ከዋናው የሃይማኖት ጫፍ እስከ ዝቅተኛው ተራ ምዕመን ድረስ በግልጽ ከህገ-ልቦናና ከህገ-እግዚአብሔር ሲወጡ እናስተውላለን፡፡

ከታሪክ መዛግብት እንዳነበብነው ስሙን የማላስታውሰው የሮማው ሊቀ ጳጳስ የጣሊያን ወራሪ ኃይል የምሥኪን ሕዝብ ሀገር ኢትዮጵያን ቅኝ እንዲገዛ ባርኮና ቀድሶ ልኮታል – የጣሊያን ዘመናዊ ጦር በኢትዮጵያውያን ላይ የእሳት ድኝ እንደሚያዘንብና የእግዚአብሔር ፍጡርና የጽላቱ ማደሪያ የሆነው ቅዱስ ገላ አላበሳው እንደሚረግፍ ጳጳሱ እያወቀ፡፡ ያ ድርጊት ከአንድ ሊቀ ጳጳስ አይደለም ከተራ ዲያቆን እንኳን አይጠበቅም፡፡ ኃጥዕ ወአባሲ አባ ገብረ መድኅንም በዘረኝነት ደዌ የተለበጠ የተኩላ ለምድ ለብሰው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ የሠሩትን ደባና ተንኮል እንዲሁም ሃይማኖታዊ ህፀፅ አንረሳውም፡፡ ስለሆነም ሃይማቱኖና ሊቃነ ጳጳሣቱ በፍጹም አልተዋሃዱም ማለት እንችላለን – የሰይጣን ሠርጎ ገቦች እንጂ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንዳልነበሩ ተግባራቸው አፍ አውጥቶ ይመሰክራልና፡፡ እነሱ የሚመሯቸው ሃይማኖታዊ ተቋማት ደግሞ ቁልቁል እየወረዱ ለመንፈሣዊ ግሽበት መስፋፋት በርትተው ይሠራሉ እንጂ የመለኮትን ፀጋና ቸርነት የሚያበዛ አንድም የቅድስና በረከት አያስገኙም፡፡

ፍቅርን ለዓለም የሰበከው ክርስቶስ፣ “እጀ ጠባብህን ለሚፈልግ መጎናጸፊያህን ድገምለት” ብሎ ያስተማረው ክርስቶስ፣ “ቀኝ ጉንጭህን ቢጠፋህ ግራህን አዙርለት”” ብሎ በመስበኩ በድንጋይ የተወገረው ክርስቶስ፣ “ውኃ አጠጪኝ ያለሽን ሰው ብታውቂው አንቺ ነበርሽ ዳግም የማያስጠማውን ውኃ ከርሱ የምትጠይቂው” ብሎ ለሣምራዊቷ ውኃ ቀጂ በመንገር የተጻራሪ ጎሣዎችን ቅራኔ ለማስታረቅ የሞከረው ክርስቶስ፣ በዚህ የሮማ ጳጳስና በአቡነ ጳውሎስ ዘረኛ “ክርስቲያኖች” ምድር ላይ ሲወከል ማየት በእጅጉ ያምማል፤ የኅሊና ዕረፍትም ይነሣል፡፡ በዚህ የሃይማኖት አባት ድርቀት በሚያሰቃየን አሳሳቢና አስደንጋጭ ወቅት አቡነ መቃሪዮስን የመሰለ የክርስቶስና የፍጡራኑ እውነተኛ አገልጋይ ሲገኝ ውኃ እንዳገኘች ጽጌረዳ ሕይወትን ያለመልማል፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ በቁሙ ካልተዘመረና ካልተወደሰ መዝሙርና ውዳሤ ከናካቴው ባይኖሩ ይሻላል እላለሁ፡፡ እናም አባቴን አባ መቃሪዮስን ከልቤ አወድሳለሁ፤ ብችል በግዕዝ ቅኔ በተቀኘሁላቸው፡፡ ሰው በወደደው ይቆርባል ወገኖቼ፡፡
ብፁዕ አባታችን አቡነ መቃሪዮስ ሆይ!

እግዚአብሔር የዕድሜ ፀጋ ሰጥቶዎት ይህችን የሚወዷትን ሀገር በነፃነት ዘመኗ ለማየት ያብቃዎ፡፡ ኢትዮጵያ ያጣችው እንደርስዎ ያለ እውነትን ምርኩዝ ያደረገ አባት ነውና እርስዎን መሰሉን ያብዛልን፡፡ እኔ ኃጢያተኛ ልጅዎ በሀገር ውስጥ አዲስ አበባ ላይ የምኖር የምሥኪኗ ኢትዮጵያ ልጅ ነኝ፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ጀምሮ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ አቁሜያለሁ፡፡ ቤተ ክርስቲያን እጇ ተጠምዞ ለወያኔው መንግሥት ካደረችና እነ አለቃ አያሌውን የመሰሉ አባቶች ሲያርፉ እንኳን እንደውሻ ሞት አልባሌ ቦታ ከጣለች ወዲህ፣ አባ ፈቃደ ሥላሤን የመሰሉ አባት በዐውደ ምሕረት በጥይት ከገደለች/ካስገደለች ወዲህ ፈጣሪ እስኪያድሳት ድረስ ደጇን ላለመርገጥ ተጸይፌያለሁ – ስህተተኛ ልሆን እችላለሁ፡፡ ግን ሰው ነኝና ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመሄድ ሳስብ በዚያ የሚደረገው መልካም ያልሆነ ነገር ሁሉ ከፊቴ እየተደቀነ ይፈታተነኛልና አልሄድም – መናገር ብጀምር የማልጨርሰው ጉድ በየቤተክርስቲያኑ ይፈጸማል – ሕዝቡ ግን አማራጭ ስለሚያጣ ይሄዳል – አንዳንዱም መፍትሔ የሚያመጣ እየመሰለው ሃይማኖቱን ይቀይራል፤ ግን አላወቀውም እንጂ አለቃ ገ/ሃና “እዚያም ቤት እሳት አለ” እንዳሉት ነው፡፡ እግዚአብሔር ፈጥኖ ካልደረሰልን ልንጠፋ ነው ብቻ ሣይሆን ከጠፋን ቆየን – በአካል መንከላወስ በመጥፋት ሂደት እንደዋና ምልክት ካልተቆጠረ፡፡

ይሁንና አምላኬን ባለሁበት ቦታ ሁሉ አመልከዋለሁ – ስተኛም ስነሣም፣ ስበላም ስጠጣም ዘወትር ስሙን እየጠራሁ አመሰግነዋለሁ፤ መሓሪ መሆኑንም አምናለሁ፡፡ እንደኔ የሆነ ደግሞ ብዙ ሰው አለ፡፡ የእርስዎን ጸሎት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰምቶ ከነዚህ የጠፉ ገዢዎች በቅርቡ ነፃ እንዲያወጣንና ትክክለኛ አባቶች ቤተ ክርስቲያንን ተረክበው ምዕመናንን በእውነተኛው የእግዚአብሔር መንገድ እንዲመሩት እመኛለሁ – ያኔ የጠፉ በጎች ይሰበሰባሉ፡፡ ያኔ ደስታና ሃሤት በመላዋ ሀገራችን ይናኛል፡፡ ያኔ ኢትዮጵያዊነት ብቻውን ይበቃናል፡፡ ያኔ “ ብሔርህ/ነገድህ ምንድነው?” ተብሎ የማይጠየቅበት ለሁሉም ዜጎች እኩል የሚሠራ ህግና ሥርዓት ይተከላል፡፡ ያም ቀን የቀረበ ይመስለኛል፤ ምልክቶቹ ሁሉ ተፈጽመዋልና፡፡

ከአናት የተበላሸ ነገር ከሥር ይጠራል ማለት ዘበት ነው፡፡ ዕውርን ዕውር ቢመራው ተያይዞ ገደል እንጂ ድኅነት የለም፡፡ እኛም የሆንነው እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን መጽሐፉ “ከእናንተ አንዱስ እንኳ ያለ ኃጢኣት የለም፡፡” ቢልም ኃጢኣት እንደብርቅ የሚታይበት ዘመን አልፎ በአሁኑ ወቅት ኃጢኣት የጽድቅ ያህል እየተቆጠረች ስለምትገኝ ለይቶለት ያልጠፋ ሰው ለማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ የፖለቲካውን ክንፍ ትተን የሥጋን ፈተና መወጣት ባቃታቸው አባቶች እየተመራን ጽድቅን እናገኛለን ማለት ደግሞ በጣም በተለመደው አገላለጽ ከእባብ ዕንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ እንደመጠበቅ የሚቆጠር የዋህነት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ክርስቶስ ቀርቶ ገንዘብ የቤተ ክርስቲያናችን የማዕዘን ራስ ሆናለች፡፡ መልካም ሥራ ሣይሆን ኃጢኣት የጽድቅ መንገድ ከሆነች ሰነበተች፡፡ የሚጸየፋት ሰው አጥታ ከሞላ ጎደል የሁሉም ሰው ሞልቃቃ ልጅ ሆነች፡፡

ለማጠቃለል ያህል ውድ ኣባቴ አቡነ መቃሪዎስ! እግዚአብሔር የመረጠዎት መሆንዎን ከተግባርዎ መረዳት አያቅትምና በረከቱን ያብዛልዎ፡፡ በዚህ አብዛኛው ሰው በጎጥና በወንዝ ተከፋፍሎ ለወያኔ ዕድሜ መርዘም የድርሻውን አስተዋፅዖ እያበረከተ በሚገኝበት ክፉ ዘመን እርስዎን ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ማግኘት ለኢትዮጵያ ታላቅ መለኮታዊ ቡራኬ ነው፡፡ ይህን የምለው እዚህ ያለውን ሁኔታ በግልጽ ስለምረዳ ነው፡፡ ፖለቲካውና ሃይማኖቱ ተቀላቅለው አንድም ሁለትም እየሆኑ የዘረኝነቱ ጠረን አገር ምድሩን አግምቶታል፡፡ ይህን አደገኛ የታሪክ አንጓ በጤናማ አሠራርና በፍትሃዊ አስተዳደር ለመተካት በሚደረገው ሁለገብ ጥረት የእርስዎ ድርሻ ምትክ እንደሌለው ሁሉም ሀገር ወዳድ ይገነዘባል ብዬ አምናለሁ፡፡ በዚህ የተቀደሰ ሥራዎ ገና የሰማዕትነትን ግዳጅ ባይወጡም ጅምር ሰማዕትነትዎ ለኢትዮጵያ ሀገራችን የምሕረት ዝናብን እንዲያዘንብላት የዘወትር ጸሎቴ መሆኑን በታላቅ ትህትና መግለጽ እፈልጋለሁ – ደግሞም ሰማዕትነት በግድ የአንገት በሠይፍ መቀላትን ወይም የደረት በጦር መወጋትን የሚጠይቅ አይመስለኝም፤ የሞቀ የአውሮፓና አሜሪካ ኑሮውን ትቶ ለትግል በረሃ መውረድም አንዱ የሰማዕትነት መገለጫ እንደሆነ በበኩሌ ይገባኛል፡፡ ቸሩ ፈጣሪያችን እርስዎን ስለሰጠን ለዘላለሙ የተመሰገነ ይሁን፡፡ በጅምርዎ ሁሉ ኃያሉ አምላክ አጠገብዎ ሆኖ ይራዳዎት፡፡ ሌሎችም የእርስዎን ፈለግ እንዲከተሉና የጠፋውን ትውልድ እንዲታደጉ ፈጣሪ ያነሳሳልን፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

ይሄይስ አእምሮ
yiheyisaemro@gmail.com

The post አቡነ መቃሪዮስ – የዘመናችን አቡነ ጴጥሮስ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከአዲስ አበባ አስተዳደር የተባረሩት ከ800 በላይ ሠራኞች ከባድ ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል ተባለ

$
0
0

Photo File

Photo File


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተመድበው ሲሰሩ ከቆዩት ከ800 በላይ ሰራተኞች በመቀነሳቸው ምክንያት ለከባድ ማህበራዊ ችግር እንደተጋለጡ ተዘገበ::
የደህሚት ራድዮ እንደዘገበው የኢህአዴግ ካድሬዎች ስልጣናቸውን ለማደላደል ሲሉ ላይና ታች በሚሉበት በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ መስተዳድር ስር ባሉት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ሲሰሩ የቆዩትን ሲቪል ሰራተኞች 800 የሚሆኑትን በተለያዩ ምክንያቶችን በመፈጠር በዚህ ሳምንት ውስጥ ተቀንሰው እንዲወጡ በመደረጉ ምክንያት ያለ ስራ ተጥለው በመቅረታቸው የተነሳ ቤተሰቦቻቸው ለከባድ ማህበራዊ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ተገለፀ።
መረጃው በመጨመር ከሲቪል ሰራተኞች ጋር የትምህርት ደረጃቸው ዝቅተኛ ነው ተብለው ከሃላፊነታቸው የተቀነሱት የገዢው ቡዱን ካድሬዎች ግን በመንግስት ልዩ ትኩረትና ድጋፍ ተደርጎላቸው በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅተው እንዲሰሩና ከሌላው ዜጋ የበለጠ ሃብት አፍረተው እንዲኖሩ ሁኔታዎችን እንደተመቻቸላቸው ምንጮቻችን በላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

አስተዳደሩ በሙስና የተጨማለቁ ከፍተኛ አመራሮችና ሲቪል ሰራተኞችን ህግ ፊት በማቅረብ እንዲ ጠየቁ እንደሚያደርግ በተደጋጋሚ ቢገልፅም በተግባር ግን የበታች ሲቪል ሰራተኞች ለመክሰስ መረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ ሲሆን ይህ ግን ወደ በላይ አመራሮች እንዳይሸጋገር ታስቦ እየተከተለው ያለው የስርአቱ አስመሳይ አካሄድ እንደሆነና ከዚህም አልፎ እርምጃ እንዲወስድ የፖለቲካ ቁርጠኝነቱን እንደሚያንሰው የህግ ባለሞያዎች ዋቢ በማድረግ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

The post ከአዲስ አበባ አስተዳደር የተባረሩት ከ800 በላይ ሠራኞች ከባድ ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኤፍሬም ታምሩ እንደገና አልበም በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመጠለት ነው ተባለ

$
0
0

የኤፍሬም ታምሩ እንደገና አልበም በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመጠለት ነው ተባለ
(ዘ-ሐበሻ) ከሮሃ ባንድ ጋር ‘እንደገና’ የተሰኘውን የሙዚቃ አልበሙን በቅርቡ የተለቀቀለት ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ በሃገር ቤትም ሆነ በውጭ ሃገር ዘፈኖቹ በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመጡለት ይገኛሉ ተባለ::

ላለፉት 30 ዓመታት ከሠራቸው ተወዳጅ ሙዚቃዎች ውስጥ የተወሰኑትን መርጦ በኮሌሽን መልክ በሲዲ ያቀረበው ኤፍሬም ለአልበሙ መጠሪያ “እንደገና” የሚል ስያሜ ሰጥቶታል:: በዚህ የሙዚቃ አልበም የቀድሞው ሮሃ ባንድ እንደና ተሳትፎበታል::

ኤፍሬም ታምሩ ይህንን አልበም በኮሌክሽን መልክ ለማውጣት ረዥም ጊዜ የፈጀበት ሲሆን ከዚህ ቀደም አልበሙን ሰርቶ ሊለቀው ሲል የ እርሱን ድምጽ አስመስሎ የሚዘፍን ሌላ ድምፃዊ ራሱን ዘፈኖች በሲዲ በመልቀቁ ሲዲው ሊዘገይ ችሏል:: በተጨማሪም ባለፈው ዓመት ይኸው ሥራ ይለቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ በድንገት እናቱ በማረፋቸው እንደገና የሲዲው ሥራ ዘግይቷል:: ለዚህም ነው ኤፍሬም “ይህ የሙዚቃ አልበም የትዕግስትን ምንነት አስተምሮኛል” ያለው::

እንደልፋቱም ይህ የሙዚቃ አልበም በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመጠ መሆኑ ድምፃዊውን ሊያስደስተው እንደሚችል ይታመናል:: ኤፍሬም ሰሞኑን በአዲስ አበባ ታትሞ ለወጣው ቁምነገር መጽሔት በሰጠው ቃለምልልስ እስካሁን ለኢትዮጵያ ጀግና አትሌቶች መወደሻ የሚሆን ዘፈን አለመሥራቱን እና ወደፊት ግን እግዚአብሄር እንደሚያውቅ ተናግሯል:: ሙሉ ቃለምልልሱ ከቁምነገር መጽሔት እንደደረሰን እናስነብባችኋለን::

The post የኤፍሬም ታምሩ እንደገና አልበም በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመጠለት ነው ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.

ይደረጋል ሁሉም –ከበዕውቀቱ ሥዩም

$
0
0

Bewketu Seyoum – Hagere Mariam (Maryland) USA [Must Listen)
ምሽቴን ማን ወሸማት፤ ኣይሉም ኣይሉም
በሬየን ማን ነዳው፤ ኣይሉም ኣይሉም
ቤቴን ማን ወረሰው፤ ኣይሉም ኣይሉም
ቀን የጎደለ ቀን፤ ይደረጋል ሁሉም

ብሎ ኣንጎራጎረ ደጃዝማች ብሩ የተባለ መስፍን ፡፡ ይህ ሰው ባንድ ወቅት ራሱ ባለስልጣን ስለነበረ የስልጣን ባህርይ በደንብ ገብቶታል፡፡ በዘመናችን ይደረጋሉ ተብለው የማይታሰቡ ግፎች ሲፈጸሙ በተመለከትኩ ቁጥር ወደ ኣእምሮየ ቀድሞ የሚመጣው ይህ ስንኝ ነው፡፡ ኣዎ፤ ቀን የጎደለ ቀን ይደረጋል ሁሉም!
ኣባቶቻችን በጣም ኣቅመቢስ የሆነውን ሰው፤ ”ቀን የጎደለበት“ ብለው የሚጠሩትን ያህል፤ ገደብ የለሽ ስልጣን የጨበጠውን ሰውየ ደግሞ “ባለጊዜ” ብለው ሰይመውታል ፡፡

”ኣደባባይ ቆሞ፤ ኣበጀሁ ቢላችሁ
ይህን ባለጊዜ፤ ምን ትሉታላችሁ “

እንዲል የየጁው ተሸናፊ መስፍን ራስ ኣሊ፡፡ ለኔ ባለጊዜ ማለት ባለስልጣን ከሚለው የላቀ ትርጉም ይሰጠኛል ፡፡ ባለ ፈረስ፤ የፈረስ ባለቤት እንደ ሆነ ሁሉ ባለ ጊዜ የጊዜ ባለቤት ነው፡፡ ጊዜን መቆጣጠር ይችላል፡፡ ለምሳሌ በዘመናችን ኣንድ ጉልበተኛ ድንገት ኣፍሶ ይወስድህና ወህኒ ቤት ይወረውርሃል፡፡ ከእድሜህ ኣንድ ኣመት ወይም ሁለት ኣመት ይቀማሃል፡፡ ወህኒ ቤት ውስጥ ጸሀይ የምትሞቅበትን ግዜ ለክቶ ይሰጥሃል፡፡ ከተሰፈረልህ ጊዜ በላይ ከሞቅህ ይደበድብሃል፡፡ ከጠያቂዎች ጋር የምታውራበትን ሰኣት ቆንጥሮ ይሰጥሃል፡፡ በተንዛዛ ቀጠሮ እያሸ ቅስምህን ይሰብረዋል፡፡ ወደድንም ጠላንም ፤እድሜያችን ያለው በባለጊዜዎች ኪስ ውስጥ ነው፡፡

”ገደብየለሽ ስልጣን ያለገደብ ያባልጋል“ ይላል ሎርድ ኣክተን፡፡ ኣንድ ባለጊዜ ባቅመቢሱ ላይ ማድረግ የሚፈልገውን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡ ፈሪሃ እግዚኣብሄር፤ የህሊና ወቀሳ፤ የህብረተሰብ ወግና ደንብ የሚባሉት በገደብ የለሽ ስልጣን ፊት የገለባ ምርኩዝ ናቸው፡፡ ቱሱዲድየስ የተባለ የግሪክ ጸሀፊ እንዳለው“ኣንድ ጉልበተኛ ማድረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጋል፤ኣንድ ኣቅመቢስ ደግሞ መሸከም የሚችለውን ያክል ይቀበላል”፡፡ ይሄው ነው!!

ኣገር ኣማን ብሎ ጨምቶ የተቀመጠን ዜጋ ፤ እያዳፉ ወስደው በጨለማ ክፍል ውስጥ ለብዙ ወራት ዘግተው ካሰቃዩ በኋላ ነጻ ነህ ብለው ማሰናበት ምን ይሉታል? ይህን ሁኔታ “ቀን የጎደለ ቀን ይደረጋል ሁሉም “ ከሚለው ስንኝ የተሻለ ምን ኣይነት ርእዮተ ኣለም ያብራራዋል?

ሰውን የጸሀይን ብርሃን በመከልከል መቅጣትን ሳስብ ኣንድ ነገር ትዝ ኣለኝ፡፡ ስለስብሐት ገብረእግዚኣብሄር ከተነገሩ ያልተረጋገጡ ታሪኮች ኣንዱ እንዲህ ይላል፡፡ ኣንድ ቀን ስብሐት ከጓደኛው ቤት ሲጫወት ኣምሽቶ እዛው ይተኛል፡፡ በመንፈቀ ሌሊት ሌቦች ቤቱን ሰብረው ገብተው የሱንና የወዳጁን ልብስና ጫማ ዘርፈው ገለል ይላሉ፡፡ ቀድሞ የተነሣው ጓደኛው ቀስቅሶ ይሄንን ሲያረዳው ስብሐት ተጋግቶ “ ኣይዞህ !እንኳን ጸሀይንና ጨረቃን ኣልዘረፉን እንጅ ችግር የለም ” ኣለው ይባላል፡፡ እንደ ስብሐት እድለኛ ሳይሆኑ ቀርተው ጸሀይንና ጨረቃን የተዘረፉትን ዜጎችን ታሪክ ይዘክራቸው፡፡

ኣለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ የተረኩት ኣንድ ሌላ ታሪክ ላንሳ፡፡ ንጉስ በካፋ ካንድ መነኩሴ ጋር ተጣልቶ መነኩሴውን ጨለማ ቤት ውስጥ ኣስገብቶ ዘጋበት ፡፡ ከሦስት ኣመታት የጨለማ ቆይታ በኋላ መነኩሴው ከእስር ቤት ሲወጣ“ የበካፋ ጸሀይ እንዴት ነሽ!የበካፋ ጸሀይ እንዴት ነሽ!“ በማለት ኣለቀሰ ኣሉ ፡፡ በካፋ ሲሞት እነ መንግስቱ ሃይለማርያም እነ መለስ ዜናዊ ጸሀይን በፈረቃ ወርሰው የግል ንብረት ኣደረጓት፡፡ ኣሁን ይችን ስጽፍ እንኳ “የመለስ ጸሃይ እንዴት ነሽ?” የሚሉትን ቤት ይቁጠራቸው፡፡

The post ይደረጋል ሁሉም – ከበዕውቀቱ ሥዩም appeared first on Zehabesha Amharic.

ስሞት አታልቅሱ!!

$
0
0

simot
ጎርፍ በላየ ሲሄድ ዝም ካላችሁኝ፤
ምጠጣው አጥቸ ከንፍሬ እንዲህ ደርቆ ካላጠጣችሁኝ፤
ስትበሉ እያየሁ ወስፍቴ እየጮከ ካላበላችሁኝ፤
ምለብሰው አጥቸ እንዲህ ስንቀጠቀጥ፤
ልብስክን በሳጥን ቆልፈህ ካስቀመጥህ፤
ለምን ትጮሀለህ?፤
ለምን ታነባለህ?፤
ለምንስ ደረትክን ትደቁሰዋለህ?፤
“ማን ገደለው?” ቢሉህ እስኪ ማን ትላለህ?፤
***
እንባ ምን ሊጠቅመኝ እንባ ምን ሊፈይድ?፤
ያለቀሰ ሳይሆን በቁም ሚረዳ ነው ባምላክ የሚወደድ፤
***
እናልህ ወገኔ…
ደረትክን አትድቃ ሙሾው ገደል ይግባ፤
ገለከኝ አታልቅስ ይቅርብኝ ያዞ እንባ።
ከልብ ካዘናችሁ በነፍሴ ድረሱ፤
እናተ ገላችሁ ስሞት አታልቅሱ።
…….. ///…….
Tenager Ashenef
Columbus, OHIO, USA
12/2007 E.C

The post ስሞት አታልቅሱ!! appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live