Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ሌሊሴ ተፈታች!

0
0

lelissie
ላለፉት 5 ዓመታት ያህል ከልጆቿና ባለቤቷ ተለይታ በእስር ስትማቅቅ የነበረችው ሌሊሴ ወዳጆ መፈታቷ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ማስደሰቱ ተጠቆመ፡፡
የጋዜጠኛ ሌሊሴን መፈታት አስመልክቶ Ayyaantuu News Online ለንባብ ባበቃው ዜና እንዳመለከተው በስደት አውስትራሊያ ከሚኖረው ከባለቤቷና ከልጆቿ ጋር ተቀላቅላለች፤ ድረገጹ ዜናውን በምስል በማስደገፍም አቅርቦታል፡፡
በጋዜጠኝነት ሲያገለግል የነበረው ባለቤቷ ዳቢሣ ዋቅጂራ አገር ጥሎ መሰደዱን ተከትሎ በማታውቀው ምክንያት የኦነግ አባል ነሽ በማለት ኢህአዴግ 10ዓመት ያለ አመክሮ ፈርዶ ወኽኒ እንዳወረዳት ይታወሳል፡፡ ይህንን ህዝብን ያበሳጨና ያስቆጣ ጉዳይ ሌሊሴ ከታሰረችበት ጊዜ ጀምሮ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ጥበቃ ድርጅት (CPJ) ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሲያወግዙትና እንድትፈታ ሲሟገቱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
“በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኛ የለም” በማለት ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ የተናገሩትን ተከትሎ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ታህሳስ 24፤2005ዓም (January 2, 2013) በዘገበበት ወቅት፤ ጋዜጠኛ ሌሊሴ ወዳጆን የሰው ልጆችን ኅሊና ከሚፈታተኑት የማኅበራዊ ጉዳዮች ጋር በማያያዝ የግምባር ዜና አድርጓት እንደነበር ይታወሳል፡፡
ከአብራኳ የወጡትን ልጆቿን የማሳደግ ወግ የተነፈገችው እናት ከ3 ልጆቿ ጋር ሆና የሚያሳየውን ምስሏ አስደግፎ ጎልጉል በወቅቱ ሲዘግብ ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ለተናገሩት ቅጥፈት ማጣፊያ በማድረግ ነበር፡፡
በእስር ቤት ታጉረው ከሚገኙት በርካታ የኢትዮጵያ ውድ ልጆች መካከል አንዷ ስለሆነችውና ስለአጠቃላይ የግፍ ቀንበር የተጫነባቸው ወገኖች በወቅቱ ለጎልጉል አስተያየት የሰጡት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ የአቶ ሃይለማርያምን ንግግር “በእውነቱ ይህ ፍጹም ቅጥፈት የተሞላበትና አጸያፊ ነው፤ እነዚህ እስረኞች እኮ በቁጥር የሚታወቁ ብቻ ሳይሆኑ ስም፣ ቤተሰብ፣ ልጅ፣ ዘመድ፣ ወዘተ አላቸው፡፡ እናውቃቸዋለን፤ ዓለም ያውቃቸዋል፤ እንግዲህ ጠ/ሚ/ሩ ለእነዚህ ልጆችና ቤተዘመዶች ነው አባታችሁ/እናታችሁ/ዘመዳችሁ ወንጀለኛ አሸባሪ ነው እንጂ የፖለቲካ እስረኛ አይደለም እያሉ ነው ያሉት፤ … ይህ ሥነምግባር የጎደለው ንግግር ነው” በማለት ዕርቃኑን አስቀርተውት ነበር፡፡
“ሌሊሴ ከዚህ ቀጥሎስ?” በሚል በህይወት የተፈተነችበትን የእስርቤት ቆይታዋና በተመሳሳይ ሁኔታ በእስር የሚማቅቁትን ኢትዮጵያዊ ወገኖቿን አስመልክቶ የሚደርስባቸውን ከአንደበቷ ለመስማት የሚጠብቁ ወገኖች እንደሚሉት ከሆነ “ሌሊሴ ጭንቀቷን ለተጨነቀላት የኢትዮጵያ ህዝብ የመፈታቷን ዜናና የእስር ቤት ቆይታዋን ከራሷ አንደበት እንሰማለን” ብለው እንደሚጠብቁ ይናገራሉ፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ለባለቤቷ፣ ለልጆቿ፣ ለቤተሰቦቿና ከእስር እንድትፈታ እንደየእምነታቸው ለጸለዩና ለተጨነቁ በሙሉ በጋዜጠኛ ሌሊሴ ወዳጆ መፈታት እንኳን ደስ አላችሁ ይላል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በየእስርቤቱ የሚማቅቁትን የቤተሰብ አውራና የአገር ተረካቢዎች፣ የፖለቲካ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የድምጻችን ይሰማ አስተባባሪዎች እና ሌሎች ንጹሃን ዜጎች መንግሥት እስርቤት አጉሮ ዕርምና ቂም ራሱ ላይ ከሚከምር ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ ችግሩን ቢያስተነፍስና ወደ ዕርቅ ቢመጣ የተሻለ እንደሆነ የአገር ጉዳይ የሚያሳስባቸው የመብት ተሟጋቾች ምክራቸው ይሰጣሉ፡፡ (ፎቶዎቹ የተወሰዱተ ከ Ayyaantuu News Online)

ምንጭ ጎልጉል ድረገጽ


ነሀሴ 26ን በደቦ ሸኝተን 2006 ዓ.ምን በተስፋ!

0
0

araya
የዘንደሮ ክረምት ከቀደምቶቹ በጥቂቱ ጠንከር ያለና ብዙዎችን በተለይም አዲስ አበቤዎችን እያማረረ ነው፡፡ ሌላው “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” የሚያስብለው ደግሞ የከተማዋ መንገዶች በአብዛኛው ጥገና ላይ መሆናቸውና በዚህም ሳቢያ የበርካቶች መኖርያና የንግድ ሱቆቻቸው መፍረሳቸው ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ በምናብ ለማየት ለምትፈልጉ ቅዳሜ ነሀሴ 4 ቀን 2005ዓ.ም በወጣቺው ፋክት መጽሄት ላይ ፕ/ር መስፍን እንዲህ ሲሉ ገልጸዋታል “አዲስ አበባ በመሬት መናወጥ ፈራርሳ በመጠገን ላይ ያለች ከተማ ትመስል የለም እንዴ”:: ብቻ ክረምቱም ወደማለፉ እየተቃረበ አዲሱንም ዘመን ለመቀበል ሽርጉዱ ሳይጀመር አይቀርም፡፡
ምን ክረምቱ ብቻ ፖለቲካውም ክረምቱን ተከትሎ ከ8 ዓመታት በኋላ እሱም ጠንከር ያለ ይመስላል፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሀገር ውስጥ ሲደረጉ የነበሩት የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴዎች በአመት ውስጥ እንኳ አንድ የሚረባ ለዜና የሚሆን ስራ ሳይሰሩ በውስጥ ጉዳያቸው ተጠምደው፤ የሀገሪቷን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከህብረተሰቡ እኩል ተመልካች መስለው ነበር፡፡ ምንም እንኳ የአሁኑ የፖለቲካ ጡዘት መነቃቃት የፈጠረው ግንቦት 25 በአዲስ አበባ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ነው ብንልም፤ ላለፉት 2 ዓመታት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሰላማዊ ትግሉን በጽናት ሲያካሄዱ የቆዩት የሙስሊሞቹን እንቅስቃሴ ለአፍታም ሳንዘነጋ መሆን ይኖርበታል፡፡
ወደዋናው የጽሁፌ አላማ ስመለስ የፊታችን ነሀሴ 26 ቀን 2005ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ከመድረሱ በፊት ከኛ ምን ይጠበቃል የሚለውን መነሻ ሀሳብ ለማቅረብ ነው፡፡ ከዚህ ቀን ቀደም ብሎ አንድነት ፓርቲ ከአዲስ አበባ ውጪ የሚያደርጋቸውን በርካት ሰላማዊ ሰልፎችን እና ስብሰባዎችን ሳልዘነጋ ነው፡፡ ይህ የነሀሴ 26 ግን በይዘቱም በጥያቄዎቹም እንዲሁም በቦታውም ለየት ያለ በመሆኑ የተለየ ትኩረት ይሻል፡፡ በመጀመሪያ በፓርቲው የተነሱት ጥያቄዎች በቀጥታ ከድርጅቱ የተገኛኙ ሳይሆኑ አጠቃላይ ድርጅቱ እታገልለታለሁ ያለውን ህብረተሰብ የሚወክሉ በመሆናቸውም ጭምር ነው፡፡
የተነሱት አራት መሰረታዊ ጥያቄዎች ለማስታወስ ያህል፡-
• የመጀመሪያው “ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባላትን በአሸባሪነት ስም ማሰርና ማሰቃየትን አጥብቀን የምንቃወም መሆኑንና እስረኞችንም እንዲፈታ”
• በሁለተኛ ደረጃ የተነሳው ደግሞ “የዜጎችን ሰብዓዊና ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ኢሰብዓዊ በሆነ ድርጊት በታጠቁ ኃይሎች እንዲፈናቀሉ ማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሆኑ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡና የተፈናቀሉት ዜጎችም በአስቸኳይ ወደየመኖሪያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ በመንግስትም ሆነ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው”
• ሶስተኛው ጥያቄ “መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ፣ የእምነት ስርዓታችንና የሃይማኖት መሪዎቻችንን እምነታችን በሚፈቅደው ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን በአሸባሪነት ወንጀል በመክሰስ በእስር እንዲማቅቁና ሰብዓዊ መብታቸው እንዲጣስ መደረጉ እንዲቆምና ያነሷቸውም የእምነት ነፃነት ጥያቄዎቻቸው እንዲከበር”
• በአራተኛነት የተነሳው “የኑሮ ዉድነትን፣ የሥራ አጥነትንና በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሌቦችን የሚቆጣጠርባቸውን መንገዶችና ፖሊሲዎች በማዉጣት ሐገራችንን ከቀውስና ዜጎችንም ከሰቆቃ እንዲያወጣ”
የሚል ነው ይህ ጥያቄ በአብዛኛው የስርአቱ ተቃዋሚዎችን የሚወክል በመሆኑ እንዲሁም ይህንን ጥያቄ ለመደገፍ እና ለዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ድጋፍ ለማድረግ የማንንም የፖለቲካ ፍልስፍና ወይም አቋም የማይጻረር እና ሰማያዊ ፓርቲም የራሱን የፖለቲካ ፍልስፍናም ሆነ አቋም ለመጫን ያልሞከረበት በአጠቃላይ የእያንዳንዱ ሀገር ወዳድ ዜጋ መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው ብዬ ስለማምን ነው፡፡
ምንም እንኳ ፓርቲው ለነዚህ ጥያቄዎች ከመንግስት መልስ እንዲሰጠው ለ3 ወር ጊዜ የሰጠው ቢሆንም፤ ስርዓቱ ግን ይባስ ብሎ አፈናውን በማጠናከር ከማሰርና ከማፈናቀል በዘለለ ንጹሀን ዜጎችን አንድ ተራ ሽፍታ እንኳ የማይፈጽማቸውን በህጻናት እና በእናቶች ላይ ተኩስ መክፈትና መግደል ጀምሯል፡፡
ይህ ምናልባት ለኢህአዴግ መራሹ መንግስት አዲስ ታሪኩ ባይሆንም ከ20 ዓመታት በላይ ድርጅቱን በፍጹም አምባገነናዊነት የመሩት አቶ መለስ ሞትን ተከትሎ ተስፋ ላደረጉ ጥቂቶች የስርዓቱን መበስበስና የማይቀየር መሆኑን አሳይቷቸዋል፡፡ ይህንን ስርዓት ከህብረተሰቡ ጫንቃ ላይ ለማንሳት የሚደረገው የሰላማዊ ትግልም ከዚህ የስርዓቱ ባህሪ አንጻር ፍጹም መራርና ከባድ መስዋዕቶችን ሊያስከፍን እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡
ከነዚህ የሰላማዊ ትግሎች ውስጥ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም የተጀመረው የሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴ አንዱ ነው፡፡ ፓርቲው ከሰልፉ በኋላ ሲያደርጋቸው የነበሩት እንቅስቃሴዎችም የሚቀጥለው እንቅስቃሴው ከሰልፍ በዘለለ የሰላማዊ ትግል መርሆችን እየተከተለ መሆኑን ያሳያል፡፡ ከዚሁ ጋርም ተያይዞ ነሀሴ 26 የሚደረገው ሰልፍ አዲስ አበባ ላይ መሆኑ የሰልፉ ስኬታማነት አንድነት ፓርቲ በክልሎች ከጀመረው የማንቃት ስራ ጋር ተዳምሮ ለመላዊ የሀገሪቱ ህዝብ ትልቅ መነቃቃትንና ቁርጠኝነት ሊፈጥር ይችላል “አዲስ አበባ ላይ ያካፋው ክልል ላይ ይዘንባል” እንዲሉ ፡፡
እንግዲህ ለዚህ ሰልፍ ወደ 15 ያህል ቀናት ይቀሩታል፡፡ በነዚህ በተቀሩት ቀናቶች የዚች ሀገር የቁልቁለት ጉዞ የሚያሳስባችሁ በተለይ ለኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች፤ ለድረ ገጽ ባለቤቶች እና ለማህበረ ድረ ገጽ አክቲቪስቶች ይህንን የነሀሴ 26 ሰልፍ ከቀደመው ግንቦት 25 ሰልፍ ላቅ ባለና የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ያካተተ ይሆን ዘንድ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በተለየ መልኩ ያለባችሁን ሀላፊነት ከቡድናዊ ስሜት ወጥታችሁ በሀገራችን በአሁኑ ሰዓት ያለውን የሚዲያ ክፍተት በመሙላት የተጀመረውን ትግል አንድ እርምጃ ወደፊት እንድትገፉ በኢትዮጵያዊ ዜግነቴ እጠይቃለሁ፡፡ እንደምታውቁት በአዲስ አበባ ከሌሎቹ ከተሞች በተለየ የተሻለ የኢንተርኔት ስርጭት ያለበት በመሆኑ በዚህ ከተማ የሚገኘውን ማህበረሰብ ለመቀስቀስና ለማስተማር ማህበራዊ ድረ ገጾች የፈረጠመ አቅም አላቸው፡፡
የዚህን ክረምት ድብታ ከፖለቲካ ድብታችን ጋር ነሀሴ 26 ሸኝተን የሚቀጥለውን 2006 ዓ.ም በተስፋ እና በመነቃቃት እንጀምረው ዘንድ የሁላችንንም ያላሰለሰ ጥረት ይጠይቃል፡፡ በድጋሚ የሚቀጥሉትን 15 ቀናት ሁላችንም በትጋት እንስራ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
አርአያ ጌታቸው
(majiesty02@gmail.com)
ነሀሴ 2005 ዓ.ም

ሞሄ አሳካህው! ዛሬም ዳግም ኮራን (ከነብዪ ሲራክ)

በሙስሊሞች ጉዳይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫና የሕግ ባለሙያው አስተያየት- አቶ ተማም አባቡልጉ የሕግ ባለሙያ

0
0

አቶ ተማም አባቡልጉ – የሕግ ባለሙያ

በሙስሊሞች ጉዳይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫና የሕግ ባለሙያውአስተያየት


Ato Kemal Ababulguየሙስሊሞችን ተቃውሞ በሚመለከት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ጋር ቃለመጠይቅ አድርገዋል፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ነፃነት አለ፤ እምነታቸውን በሰላም የሚያራምዱትን የሚነካ የለም፤ በሃይማኖት ሽፋን አክራሪነትንና ፅንፈኝነትን የሚያራምዱትን ግን ከሰላማዊ አማኞች መነጠል አለብን” ብለዋል፡፡
የሕግ ባለሙያው አቶ ተማም አባቡልጉ በበኩላቸው ደግሞ “ይህ የጅምላ ክስ እንጂ ማስረጃ የለውም ይላሉ፡፡ ለሙሉው መረጃ አዳነች ፍስሃዬ ከአቶ ተማም አባቡልጉ ጋር ያደረገችውን ቃለምምል የያዘውን ፋይል ያዳምጡ፡፡

ከቁጫ እስከ ኦሮሞ –ማንነትና የማንነት ፖሎቲካ እንደምታና መዘዞቹ

0
0

OLF rebels from the front-line hold their weapons as they return to their training camp in Southern Ethiopia near the border town of Moyaleዩሱፍ ያሲን

የአሜሪካ ድምፅና የዶቼቬሌ አማርኛ ራዲዮ ፕሮግራሞች ላይ የቁጫ ሕዝብ የራሱን ማንነት የመወሰን ጉዳይ አስመልክቶ ለመንግሥት ጥያቄ ያቀረቡ ሰዎች መታሰራቸው ዜና በቅርቡ ተዘግቦ ሰምተናል። 40 የሚሆኑ የአካባቢ ሽማገሌዎች እነዚህ የተሳሩ ሰዎችን ለማስፈታት አዲስ አባባ ድረሰ መምጣታቸውንም ተዘግቧል። የቮይስ ኦፍ አሜሪካ ባልደረባ ጋዘጤኛ ሰሎሞን ክፍሌ ባመዛኙ በማንነት ዙርያና ሳቢያ የተነሳውን ውዝግብ ርእሰ ጉዳይ ላይ የሽማገሌዎች ወኪል ከተባሉት ጋርም ቃለ ምልልስ አስደምጦናል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የሽንጎው ከፍተኛ የአመራር አካል ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

0
0

shengoሸንጎ ለዘ-ሐበሻ የላከው ጋዜጣዊ መግለጫ

ነሃሴ ፯ ቀን ፳፻፭
Aug 13, 2013
የኢትዮጰያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ ከፍተኛ የአመራር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ቅዳሜ ነሃሴ 4 ቀን፣ 2005 (August 10, 2013) በተሳካ ሁኔታ አካሄደ።
ይህ ስብሰባ የሽንጎው ሁለተኛ ጉባኤ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎችና የተለማቸውን የትግል አቅጣጫዎች በሀገር ውስጥና በውጭ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያሰችሉ የተግባር መመሪያዎችን የሰጠ ሲሆን ይህንንም እውን ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ ኮሚቴዎችን መስርቷል፣ የሰው ሀይልም መድቧል።
ምክር ቤቱ በሀገሪቱ ውስጥ እየተከሰቱ ያሉትን ወቅታዊ ሁኔታዎች በመመርመር ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ በተከታታይ ሲያደርግ እንደቆየው ሁሉ ህዝብን የማሸበር ተግባሩን በመቀጠል፣ በኢትዮጵያውያን ሙሰሊሞች ላይ በኢድ አል ፈጥር ያካሄደውን ድብደባና ማንገላታት በታላቅ ሀዘን ተገንዝቧል፣ ድርጊቱንም በጥብቅ አውግዟል።
በሰላማዊ መንገድ መሰረታዊ የእምነት ነጻነት እንዲከበርና መንግስትም በሃይማኖት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆም፣ የታሰሩ የሀይማኖት መሪዎችም እንዲፈቱ የቀረበን ሰላማዊ ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ሙስሊሙን ማህብረተሰብ በጀምላ በሽብርተኛና አክራሪነት የመወንጀል ዘመቻ መቀጠሉ እጅግ ሀላፊነት የጎደልውና አደገኛ እርምጃ እንደሆነ በመገንዘብ ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ ከዚህ አይነት እኩይ ተግባሩ ተቆጥቦ ለሙስሊሙ ማህብረተሰብ ጥያቄዎች ባስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ አሳሰቧል። ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር ያለውን የትግል አንድነት በድጋሜ ገልጿል።
ከዚህም ሌላ በቅርቡ በአንድነት ፓርቲ ፣ በመድረክ፣ በሰማያዊ ፓርቲና በመኢአድ አባላት ላይ ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ እያካሄደ ያለውን እስራት፣ ወከባና ድብደባ ባሰቸኳይ እንዲያቆም፤ የህዝብንም መሰረታዊ መብቶችንና የህግ የበላይነትን እንዲያከብር በጥብቅ አሳሰቧል።
ሽንጎው እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ፣ የህዝባችንን መብት ለማስከበር ቆራጥ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኙት ከነዚህ የተቃዋሚ ድርጅቶችና አባሎቻቸው ጋር ያለውን የትግል አንድነት በድጋሜ አረጋግጧል።
በመጨረሻም፣ ትግሉ ውጤታማ ለመሆን የተቃዋሚዎችን መተባበር የግድ የሚል መሆኑን በመገንዘብ በኢትዮጵያ አንድነትና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ምስረታ ላይ ጽኑ እምነት ያላቸው ሁሉ አሁንም ሽንጎውን እንዲቀላቀሉ ቀጣይ ጥሪ አቅርቧል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

ሶስት ፓርቲዎች በሙስሊም ማኀበረሰብ አካላት ላይ መንግሥት እየወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ አወገዙ

0
0
ሰንደቅበሰንደቅ ጋዜጣ ሪፖርተር  
የመብት ጥያቄ ያነሱ የሙስሊሙ ማኀበረሰብ አካላት ላይ መንግሥት እየወሰደ ያለው የኃይል እርምጃ አጥብቀው እንደሚቃወሙት ሶስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰሞኑን ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ እና የመላ ኦሮሞ ሕዝብ ድርጅት ነሐሴ 5 እና 6 ቀን 2005 በተናጠል ባወጡት መግለጫዎች መንግሥት አለመግባባቱን ለመፍታት እየተከተለ ያለውን የኃይል እርምጃ ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል።
ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቃለምልልስ ‘‘ጽንፈኞች’’ ያሏቸውን የመብት ጥያቄ ያነሱ የሙስሊም ማኀበረሰብ አካላት እያደረጉ ያሉት እንቅስቃሴ ፀረ-ሕገመንግስታዊ መሆኑን አመልክተዋል። ‘‘የሃይማኖት መንግስት እንመሰርታለን፣ የሸሪዓ ሥርዓት እናሰፍናለን’’ የሚል አቋም እንደሚያራምዱ የጠቀሱት ጠ/ሚኒስትሩ መንግስት ሃይማኖታዊ ተልዕኮ ያላቸው መስሏቸው ከፅንፈኞች ጋር የሚተባበሩ ተከታዮችን በጅምላ ላለመጉዳት በትግስት ሁኔታውን ሲከታተልና የማሳመን ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። ጽንፈኞችን ከሌሎች የእምነቱ ተከታዮች ለመለየት የተደረገው ጥረት የተሳካ እንደነበርና መንግስት ሰሞኑን የወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። ከጽንፈኞች ጋር ተቀናጅተው የአገሪቷን ሠላም ለማወክ ይንቀሳቀሳሉ ያሏቸውን የተቃዋሚ ፓርቲዎችንም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል። (የሦስቱ ፓርቲዎች ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ተስተናግዷል)
ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ የተሰጠ መግለጫ
‘‘በሙስሊሙ ወገኖቻችን ላይ መንግስት እያካሄደ ያለው እስር፣ ድብደባና ግድያ መንግስታዊ የሽብር ተግባር ስለሆነ አጥብቀን እናወግዛለን፣ በአስቸኳይ እንዲገታም እንጠይቃለን’’
ኢትዮጵያ የምትመራበት ሕገ መንግስት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ኮንቬንሽንን የሕጉ አካል አድርጎ የተቀበለው ሲሆን ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 14 እስከ 29 ያሉት ሕጎችም የዜጎችን የሕይወትና የአካል ደህንነት፣ የሃይማኖት ነፃነትና የሰብአዊ መብት እኩልነት ክብርና እንዲሁም የመልካም ስምን የሕግ ጥበቃ በዝርዝር ይደነግጋል። እነዚህ በአገሪቱ የበላይ ሕግ ውስጥ የተካተቱ መብቶችን መንግስት የማክበርና የማስከበር ግዴታም እንዳለበት ጨምሮ ተደንግጓል።
የኢሕአዴግ መንግስት ግን ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እነዚህን ሕገ መንግስታዊ መብቶች ሲጥስ ይታያል። የአብዛኛው ሕዝብ ጥያቄ ኢሕአዴግ ራሱ የማያከብረውን ሕገ መንግስት ለምን አወጣው? የሚል ነው። ምክንያቱም ሕገ መንግስቱን መጣስ የዕለት ተዕለት ተግባራቱ እየሆነ መጥቷል፤ እንዲያውም ሕገ መንግስቱን የፃፈውና ያፀደቀው ለይስሙላ በዓለም አቀፍ ማኀበረሰብ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ያሰፈነ መንግስት ለመምሰል እንጂ ከምስረታው ጀምሮ ዲሞክራሲያዊና ተዓማኒ ሊያሰኘው የሚችል ገፅታ እንደሌለው ግልፅ ሆኗል። የሕዝብን የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች መጣስ የጀመረው ገና ከጅምሩ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ነበር። ለአብነት ለመጥቀስም በንፁሃን የአኙአክ ዜጎች ላይ፣ ቅሬታቸውን በሠላማዊ መንገድ ለመግለፅ በወጡ የአዲስ አበባ እና የሐዋሳ ነዋሪዎች ላይ በአሳሳ፣ በዶዶላና በገርባ ሙስሊም አማኞች ላይ የፈፀማቸው የግድያ ወንጀሎች ጉልህ ማሳያዎች ናቸው። በነዚህ የግድያ ወንጀሎች እስከ ዛሬ የተጠየቀ የመንግስት አካል ወይም ባለሥልጣን የለም፤ ዛሬ ዜጎች በግፍ እየተገደሉ ደማቸው ደመ-ከልብ ሆኖ ሲቀር መንግስት የሕግ ጥበቃ ያደርግልናል የሚለው ተስፋ እየተሟጠጠ ሄዷል።
የዓለም የሰብዓዊ መብት ኮንቬንሽን በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የፀደቁ የዜጎች መብትን በመደፍጠጥ በፀረ ሽብር ሕግ ሽፋን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን ማሰር፣ ማጉላላት፣ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ጣልቃ በመግባት፣ የሃይማኖት መሪዎችን በማሰር፣ የዜጎችን በነፃ አስተያየታቸውን የመግለፅ ሕገ መንግስታዊ መብት ከመጣሱም በላይ በቅርቡ በሃይማኖት ጉዳዮች መንግስት ጣልቃ እንደማይገባ የተደነገገውን በመጣስ መንግስት በሚያስተዳድረው ቀበሌ የሃይማኖት መሪዎችን ማስመረጡ፣ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ለመግባቱ ጉልህ ማስረጃ ነው። ይህን የተቃወሙትንና ድምፃችን ይሰማ ያሉ ሰላማዊ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በሽብርተኛነት ፈርጆ ማሰሩና አሁን በሐምሌ ወር መጨረሻ አካባቢ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን በኮፌሌና በዶዶላ በአሳሳ እንዲሁም በሌሎችም የኦሮሚያ ዞኖችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ያለማስረጃ በማሰርና በመደብደብ የግድያ ወንጀልም ፈጽሟል። የታጠቀ የመንግስት ኃይል ባልታጠቀ ሕዝብ ላይ እስራት፣ ግድያና ድብደባ መፈፀም መንግስታዊ የሽብር ተግባር በመሆኑ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ከዚህ ኃላፊነት ከጎደለው ሕገ ወጥ ድርጊቱ ሊቆጠብና ሕገ መንግስቱን ሊያከብር ይገባል።
የእስራቱ፣ የብርበራውና የግድያው ዓላማ ሽብርተኛነትን ወይም አክራሪነትን ለማስወገድ መፍትሔ ነው ብለን አናምንም። ይልቁንም መንግስት በሕገ መንግስቱ በተደነገገው መንገድ ብቻ የዜጎችን የእምነት ነፃነት በማክበር ለሙስሊሙ ሕብረተሰብ ሰላማዊና ሕጋዊ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ ቢሰጥ ኖሮ ይኸ ሁሉ የዜጎች ሕይወት አይጠፋም ነበር እንላለን። አክራሪነትንና ሽብርተኛነትን ምክንያት በማድረግ የዜጎችን ሕጋዊና ሰላማዊ ተቃውሞ ለመደፍጠጥ የተወሰደውን የጭካኔና ሰብአዊነት የጎደለው ተግባር በመሆኑ አጥብቀን እናወግዛለን። መንግስት በታጣቂዎቹ እየታገዘ የሚጽመው እስራትና ግድያ ለአገር ሠላምና ለሕዝብ ደህንነት እጅግ አስጊ እየሆነ ስለመጣ መንግስት ከዚህ ድርጊቱ እንዲገታ እንጠይቃለን። በዚህ አጋጣሚ ሙስሊሙ ሆነ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢሕአዴግን ኢ-ሕገመንግስታዊ ድርጊት በመገንዘብ ትግሉን በሕጋዊና ሠላማዊ መንገድ አጠናክሮ በመቀጠል አንድነቱንና ሠላማዊ የትግል ትብብሩን እንዲያሳይ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
መንግስታዊ የሽብር ተግባር በተባበረ ሕጋዊና ሠላማዊ የሕዝብ ትግል ይገታል!
ከኢዴፓ የተሰጠ መግለጫ
‘‘ውይይትና ድርድር ደከመኝ፣ ሰለቸኝ የማይባልበት ብቸኛው የሰላምና የዴሞክራሲ አማራጭ ነው።’’
የመብት ጥያቄ ያነሱ የሙስሊሙ ማኀበረሰብ አካላትና መንግስት በተለያየ መድረክ መፋጠጥ ከጀመሩ ከአስራ ስምንት ወር በላይ ሆኖታል። በአብዛኛው ከአዲስ አበባና አካባቢዋ የሶላት ስግደት ቀን የማያልፈው የመብት ጥያቄ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንቅስቃሴው እየሰፋና እያደገ በመሄድ በርካታ ሙስሊሞችን ማካተት ችሏል። እንቅስቃሴውን ለመግታት መንግስት በተከታታይ በወሰደው እርምጃ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ የተለያዩ ጉዳቶች ደርሰዋል። በተለይ ደግሞ ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ግጭቱ በስፋትና በቅርጽ እየጎለበተ በመሄድ ወደ ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች በመዛመት በበርካታ ዜጎች ዘንድ አነጋጋሪና አሳሳቢ ጉዳይ ለመሆን በቅቷል።
በኢዴፓ እምነት ዜጎች በሃይማኖታዊም ሆነ በፖለቲካዊ አሊያም በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ የማንሳትና ከመንግስትና ከመንግስታዊ ተቋማት ጋር ወይም በተናጠል የመብት ጥያቄዎችን የማቅረብ፣ የመደራደርና መፍትሄ የመሻት መብታቸው ያለአንዳች ገደብ ሊከበር እንደሚገባ አጠንክሮ ያምናል። ኢዴፓ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የመቃወም፣ ያለማንም ጣልቃ ገብነት የማምለክና የመሳሰሉ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች እንዳይሸረሸሩ ዘብ የሚቆምላቸው አጀንዳዎቹ መሆናቸውም ይታወቃል።
በሌላ በኩል ኢዴፓ እነዚህ የመብት ጥያቄዎች በስምምነት ካልሆነ በስተቀር የሌሎችን ጥቅምና መብት በማይነኩበትና በሕገ-መንግስቱ ላይ በሰፈረው መሰረት መቅረብ፣ መደመጥና አግባብነት ያለውን ፍትሐዊ መልስ ማግኘት እንዳለባቸው ያምናል። ከዚህም በላይ ዜጎች ጥያቄዎቻችን በበቂ ሁኔታ አልተመለሱም ብለው ሲያምኑ ጥያቄዎቻቸው እንዲመለሱ በሕጋዊ መንገድ ሰላማዊ ሰልፍ፣ የአዳራሽና ሕዝባዊ ስብሰባ በማድረግ በመንግስት ላይ ገንቢ ተጽእኖ በመፍጠር ለጥያቄዎቻቸው መፍትሄ የመሻትና የማግኘት መብታቸው ሊሸረሸርና ሊገሰስ እንደማይገባ ኢዴፓ በጽኑ ያምናል።
መንግስትና ተቋማቱ ዜጎች በሕገ-መንግስቱ ላይ የሰፈሩ መብቶቻቸው ወደ ተግባር እንዲለወጡ ሁኔታዎችን የማመቻቸትና ጥያቄዎቻቸው በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበትን አቅጣጫ የማሳየት፣ የማገዝና ቅራኔዎችን በሰለጠነ መንገድ በትዕግስት የመፍታት ኃላፊነት አለበት። መንግስት በአጣብቂኝ ውስጥም ሆኖ ቢሆን ከዜጎች የሚቀርቡ የመብት ጥያቄዎች እንዳይጨፈለቁ ጥበቃ ማድረግ ይገባዋል። በተለይ ደግሞ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም የሚቀርቡ የመብት ጥያቄዎችን ለማስከበር የሚሄድበት ርቀት የዜጎችን የመብት ጥያቄ ለማስተናገድ የሚኖረውን ቁርጠኝነት የምንለካበት ነው። መንግስት በማንኛውም መለኪያ ዜጎች ጥያቄዎቻቸውን በነፃነት የማቅረብ መብታቸው እንዳይታፈን በማድረግ ቁርጠኝነቱን ማሳየት ይጠበቅበታል። አጀንዳዎቹ ተጠልፈዋል ብሎ ሲያምን የችግሩ ምንጮችን ብቻ ለይቶ በማውጣት ቀሪው ዜጋ ጥያቄውን የማስተጋባት መብቱ እንዲቀጥልና መፍትሄ እንዲያገኝ በማድረግ ሕገ-መንግስታዊ ግዴታውን መወጣት አለበት። መንግስት በዚህ የመብት ጥያቄ ሂደት ውስጥ መብታቸውን በአግባቡ መጠቀም ያልቻሉ ዜጎች ቢገኙ እንኳን በዜግነታቸው ተገቢውን ሕጋዊ ጥበቃና እንክብካቤ ሳያጓድልባቸው ሕግ ፊት በማቅረብ ሳይፈረድባቸው የመወንጀል ሕገ-መንግስታዊ መብታቸውን በማስከበር ዋስትና መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።
ኢዴፓ ‘‘መብቶች ሁሉ ግዴታ ያዘሉ መሆናቸው’’ የምናምነውን ያህል የመብት ጥያቄዎች በቅድመ ሁኔታዎች መጨናገፍና መጨፍለቅ እንደሌለባቸው ደግሞ በጥብቅ የምንታገልለት ፍልስፍናችን ከመሆኑም በላይ ስህተት ሊሰራበት የማይገባ ጉዳይ መሆኑን ግልጽ ማድረግ ይፈልጋል።
ከላይ በዝርዝር ያነሳናቸው የሰብአዊና የዴሞክራሲያዊ መብቶች በመርህ ደረጃ እንደተጠበቁ ሆነው። ካለፉት አስራ ስምንት ወራት ወዲህ በሙስሊሙ ማኀበረሰብ ውስጥ የተነሳውንና እስከ አሁንም የዘለቀውን የመብት ጥያቄ መፍትሄ ሳያገኝ በእንጥልጥል መቆየቱና ከነአካቴውም ስፋት እያገኘ መምጣታቸው መንግስት በተናጠል በሚወስደው የእመቃ እርምጃዎች ጥያቄዎቹ ሊፈቱ እንደማይችሉ ጠቋሚ ምልክቶች ናቸው። አሁን ለመገንዘብ እንደተቻለውም የመብት ጥያቄዎቹ መልስ ሳያገኙ ለበርካታ ወራት መዝለቃቸው ቅራኔው እየሰፋና መልኩን እየለወጠ ወደ አልተጠበቀ አቅጣጫ እየተገፋ ዜጎቻችንን ለሞት፣ ለአካልና ለንብረት ጉዳት እየዳረገ መሆኑን ኢዴፓ በሃዘኔታ ለመታዘብ ችሏል።
በተለይ ደግሞ በሙስሊሙ ማኀበረሰብ የኢድ አልፈጥር በዓል ላይ የታየው ፍጥጫ፣ ድብደባ፣ መጠነ ሰፊ እስርና እንግልት በማንኛውም መስፈርት ሃይል የተቀላቀለበት ፈጽሞ ያልተገባ እንደነበረ ኢዴፓ ያምናል። በዚህ አጋጣሚም በእለቱ ጉዳት ለደረሰባቸውና ለታሰሩ የሙስሊሙ ማኀበረሰብ አባላትና ቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን መግለጽ ይወዳል። መንግስት የመብት ጥያቄ ያነሱ የሙስሊሙ ማኀበረሰብ አባላትን በየበዓላቱ ቀኑ የመብት ጥያቄዎቻቸውን በመያዝ ማብቂያ በሌለው አዙሪትና ፍጥጫ ውስጥ ገብተው ለሃይል እርምጃ እንዳይጋለጡ ማድረግ እንዳለበት እናምናለን። መንግስት አሁን በእስር ላይ የሚገኙት ሙስሊሞች ያሉበትን ሁኔታ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ኢዴፓ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ጥያቄዎቹ ከዚህ በላይ እየተገፉ ከሄዱ የጉዳዩን ጥልቀት በመረዳትም ሆነ ባለመረዳት ወይም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ላልተፈለገ ግጭትና አለመረጋጋት በር መክፈቱ አይቀሬ ነው። በዚህም ምክንያት በጉዳዩ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በሚመለከታቸው ፖለቲካዊ፣ ማኀበራዊና የሃይማኖት ተቋማት አማካኝነት አጀንዳውን ወደ ውይይት መድረክ መመለስ ጉዳዩ መፍትሄ እንዲያገኝና በቅራኔ የተወጠሩ አካሄዶች እንዲረግቡ መንገድ እንደሚከፍት ኢዴፓ ያምናል። በፍጥጫና በውጥረት ውስጥ ያለን የሕዝብ ጥያቄ ማፈን ጊዜ ከመግዛት ያለፈ ፋይዳ የማይኖረው ከመሆኑም በላይ ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ የአጠቃላይ ማህበረሰቡ ጣልቃ ገብነትን መጋበዙ አጠራጣሪ አይደለም።
ከዚህም በላይ እጅግ አደገኛ የሆነው መንገድ ይህንን ክፍተት በመጠቀም በክርስትያንና በሙስሊሙ ማኀበረሰቡ መካከል ልዩነትን የሚፈጥሩና ለቁርሾ የሚዳርጉ አደገኛ ዝንባሌዎች ከየአቅጣጫው እየተደመጡ መምጣታቸው የጉዳዩን አሳሳቢነትና አደገኛነት እንድንገነዘብ የሚረዳ ሆኖ አግኝተነዋል። በኢዴፓ እምነት እንደዚህ ዓይነቶቹ አደገኛ ዝንባሌዎች ምንጫቸውና ባለቤታቸው ማንም ይሁን ማን በሁላችንም የተባበረ ድምጽ ሊወገዙ እንደሚገባ ያምናል።
በመንግስት በኩል በተደጋጋሚ የሚነሳው ስጋት የመብት ጥያቄው የአክራሪ ሃይሎች ሰለባ ሆኗል የሚል ነው። ኢዴፓ ይህ ጥያቄ አሳሳቢ መሆኑን ቢያምንም፤ በተጋነነ ሁኔታ የቀረበ መሆኑን ለመረዳት አዳጋች አይደለም። ኢዴፓ፣ ኢትዮጵያዊያን የዓለም ማኀበረሰብ አካል እንደመሆናችን መጠን የጐረቤት ሃገሮችን ጨምሮ አንዳንድ ሃይሎች የውስጥ ጉዳዮቻችንንና ተፈጥሮ ልዩነቶቻንን አላግባብ በመለጠጥና በማራገብ የስግብግብ አጀንዳቸው ማራመጃ አድርጎ ለመጠቀምና ሃገራችንን ከአደገኛ ሁኔታ ጋር ለማላተም የሚተጉ ሃይሎች የሉም የሚል የዋህ እምነት ያለው ድርጅት አይደለም። ይህም ሆኖ እያለ ለእንደዚህ ዓይነቱ አደጋ አጋልጦ ወይም አመቻችቶ የሚሰጥን ምዕራፍ የሚከፈተው ውስጣዊ ችግሮቻችንን በመደማመጥና በመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለን አቅም ሲዳከም ብቻ እንደሆነ ኢዴፓ ለማሳሰብ ይወዳል።
ከዚህ መሰረታዊ ሃሳብ በመነሳት የመብት ጥያቄ ያነሱ የሙስሊሙ ማኀበረሰብ አባላትን ጉዳይ መንግስት እንደገና ወደ ውይይትና ድርድር መድረክ በማምጣት መልስ እንዲገኝ ጥረት እንዲያደርግና የተጀመረውን ፍጥጫን ቅራኔ የሚያረግቡ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጥሪያችንን እናቀርባለን። የመብት ጥያቄ ያነሱ የሙስሊሙ ማኀበረሰብ አካላትም ጥያቄዎቻቸው መልስ እንዲያገኙ ወደ ውይይትና ድርድር መድረክ መመለሱ ወደ ውጤት የሚወስደው ብቸኛ መንገድ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፍጥጫዎቹንና ግጭቶቹ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ያልተገባ ዋጋ እንዳይከፍሉ የድርድርና የውይይቱን መንገድ በቁርጠኝነት እንዲገፉበት ኢዴፓ ጥሪውን ያስተላልፋል። የሃይማኖት ተቋማት፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሙያ ማኀበራትና ማኀበራዊ ተቋማት ይህ ጉዳይ የራሳቸው ጉዳይ መሆኑን ከወዲሁ ተረድተው ቅራኔውን ተቀራርቦ በመወያየት መፍትሄ እንዲያገኝ ገንቢ ግፊትና ጥረት እንዲያደርጉ ኢዴፓ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ሰላምና ሕብረ ብሔራዊነት ዓላማችን ነው
የኢዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ   
ከመላ ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
‘‘ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ሕዝበ ሙስሊም ጥያቄ በኃይል፣ በጠመንጃ መፍታትን ያቁም’’
ኢህአዴግ የሕዝበ ሙስሊም ጥያቄን በኃይል፣ በጠመንጃ ለመፍታት መሞከር ችግሩን አባባሰው እንጂ ሊፈታው ስላልቻለ ኢህአዴግ ያሰራቸውን ሕዝበ ሙስሊም በአስቸኳይ ፈቶ የኢትዮጵያ ሕዝበ ሙስሊም ጥያቄ በዲሞክራሲያዊ ውይይት እንዲፈታ ጥሪአችንን እናቀርባለን።
በአዲስ አበባ ከተማ በአወሊያ ት/ቤት የተቀሰቀሰው ጥያቄ ዛሬ ተስፋፍቶ በአገሪቷ ላይ ሊፈታ ወደማይችልበት እድገት ሊደርስ የቻለው የገዥው ፓርቲ ‘‘ኢህአዴግ’’ የኃይል የጠመንጃ አፈሙዝ እርምጃ በመሆኑ በአስቸኳይ በቶሎ እርምት ተወስዶ ወደ ዲሞክራሲያዊ ውይይት እንዲመለሱ ጥሪአችንን እናቀርባለን።
ኢህአዴግ በሺ የሚቆጠር ሕዝብ ኢድአልፈጥር የበዓል አከባበር ተንተርሶ ያሰራቸውን ሁሉ እንዲፈታም ጥሪአችንን እናቀርባለን። ዛሬ ‘‘የኢህአዴግን’’ የኃይል እርምጃ ምክንያት በማድረግ ብዙ ሕዝብ አገሩን ለቆ ወደ ሌላ አገር በመኮብለል ላይ ስለሚገኝ ገዢው ፓርቲ ስህተቱን በአስቸኳይ በማረም ወደ ዲሞክራሲያዊ ውይይት እንዲመለስ እንጠይቃለን።
ኢህአዴግ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄም ሆነ የጐረቤት አገር ጥያቄን በዲሞክራሲያዊ ውይይት የማይፈታ ከሆነና ወደ ኃይል እርምጃ የሚዞር ከሆነ በአሁኑ ጊዜ እየተሰሩ ያሉት ትላልቅ የልማት ስራዎች ስለሚደናቀፉ ‘‘ኢህአዴግ የአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መንገድን ይዞ አገሪቷን እንዲመራ ጥሪአችንን እናቀርባለን።’’n
ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ

የ6 አመቷን ህፃን የደፈሩት የ60 አመት አዛውንት በ14 አመት እስራት ተቀጡ

0
0
ሰንደቅ*ዐቃቤ ህግ ቅጣቱ አንሷል ሲል በውሳኔው ላይ ቅሬታ አለኝ ብሏል
በአሸናፊ ደምሴ
የ6 አመቷን ህፃን አታለው ደፍረዋታል ሲል የፌዴራሉ ዐቃቤ ህግ ክስ የመሰረተባቸው የ60 አመቱ አዛውንት አቶ አምደላ ነአምሳ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው ፍርድ ቤት በ14 አመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ሲል የቅጣት ውሳኔውን አስተላለፈ። የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽሕፈት ቤት ዐቃቤ ህግ ግን በቅጣት ውሳኔው ላይ ቅሬታ እንዳለው በመግለፅ ለፍርድ ቤቱ ደብዳቤ ፅፏል።
በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 7ኛ ወንጀል ችሎት ግለሰቡን ጥፋተኛ ያላቸው የዐቃቤ ህግን የክስ መዝገብ መርምሮና የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ ነው። ዐቃቤ ህግ በክሱ እንዳመለከተው፤ ተከሳሽ ለአቅመ ሔዋን ካልደረሰች ልጅ ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ለመፈፀም አስበው በሐምሌ 8 ቀን 2004 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 7 ሰዓት ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 14/15 ክልል ልዩ ቦታው ገብስ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ስሟን የማንገልጽላችሁን የ6 አመቷን ህፃን አታለውና አግባብተው ወደመኖሪያ ቤታቸው በማስገባት፤ አልጋ ላይ እንድትተኛ አድርገው የመድፈር ወንጀል ፈፅመውበታል ሲል ይከሳል።
የጉዳዩን ግራና ቀኝ ሲመረምር የቆየው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 7ኛ ወንጀል ችሎትም ተከሳሹ ዐቃቤ ህግ ያቀረባቸውን የሰውና የሠነድ ማስረጃዎች በአግባቡ ማስተባበል አልቻሉም ሲል ጥፋተኛ ብሏቸዋል።
ፍ/ቤቱ ሐሙስ ሐምሌ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት፤ ተከሳሹ ጥፋተኛ በሆኑበት ወንጀል ላይ ቅጣት ያስተላለፈ ሲሆን፤ የወንጀሉን ደረጃ ከባድ በማለት የህፃኗን ዕድሜ እንደምክንያት ያቀረበው ፍርድ ቤቱ ከ20 አመት እስከ 22 አመት ሊያስቀጣ እንደሚችል ይጠቅሳል። ዐቃቤ ህግ ምንም አይነት የወንጀል ማክበጃ ያላቀረበ ሲሆን፤ ተከሳሹ በበኩላቸው የቤተሰብ አስተዳዳሪና ምንም አይነት የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው መሆናቸውን መጥቀሳቸው የቅጣት እርከኑን ዝቅ እንዳደረገላቸው ለመረዳት ተችሏል። በዚህም የቅጣት መነሻው 22 አመት ላይ እንዲያርፍ ሆኗል።
የግራቀኙን አስተያየት ያደመጠው ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ የ60 አመት አዛውንቱን ጥፋተኛ በተባሉበት ወንጀል በ14 አመት ከ5 ወር ፅኑ እስራትና ለአምስት አመታት በሚዘልቅ ከመምረጥ መመረጥ ህዝባዊ መብታቸው እንዲታገዱ ሲል ውሳኔ አሳልፏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ደስተኛ ያልሆነው የክፍለ ከተማው ፍትህ ጽ/ቤት ዐቃቤ ህግ ቅሬታውን ጠቅሶ ደብዳቤ መፃፉንና ቅጣቱ መሻሻል እንደሚገባው ማመልከቱን ለማወቅ ተችሏል።n

ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ


ከአንድ ሥጋ ቤት ሥጋ ገዝተው የተመገቡ 60 ሰዎች በህመም እየተሰቃዩ ነው

0
0
 ሰንደቅፀጋው መላኩ
ከአንድ ሥጋ ቤት በተመሳሳይ ወቅት ሥጋ ገዝተው የተመገቡ የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በህመም እየተሰቃዩ ነው። ነዋሪዎቹ ከቆየ ደንበኛቸው ሥጋ ገዝተው ለልደት፣ ለሽምግልና፣ ለሰርግ የተጠቀሙበት ሁኔታ ቢኖርም ታዳሚዎቹም ሆነ ባለቤቶቹ በሙሉ ለህመም መዳረጋቸውን ገልፀውልናል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ወጣት ፀሐይ ሙላቱ ቤተሰቧ ለነበረበት የሽምግልና ፕሮግራም ከሥጋ ቤቱ 25 ኪሎ ሥጋ የገዙ መሆናቸውን ገልፃ ተጠርተው የነበሩት ወደ 60 የሚጠጉት ታዳሚዎች በዕለቱ ከምሽትና ከሌሊት ጀምሮ ለከባድ ህመም የተጋለጡ መሆናቸውን ገልፃልናለች። በአመጋገብ በኩልም የተገዛውን የከብት ሥጋ ሳይሆን ዶሮ ብቻ የተመገቡ ሰዎች ግን ያልታመሙ መሆናቸው ወጣት ፀሐይ ገልፃለች።
በተመሳሳይ መልኩ አቶ ተሾመ ሙላቱ የተባሉ በልደታ ክፍለከተማ የቀድሞው ወረዳ 5 የቤት ቁጥር 048 ነዋሪ ከሥጋ ቤቱ የተገዛውን ምግብ ተመግበው ለህመም መዳረጋቸውን ገልፀውልናል። ጌጃ ሰፈር የሚባል ነዋሪዎችም ከዚያው ተመሳሳይ ሥጋ ቤት ገዝተው ለልደት ዝግጅት የተጠቀሙ ነዋሪዎችም ለከፍተኛ ህመም የተዳረጉ መሆናቸውን ገልጸውልናል። የህመሙን ሥሜት በተመለከተ የገለፁልን ታማሚዎቹ በዋነኝነት ማንቀጥቀጥ፣ ማስመለስ፣ ተቅማጥ፣ የአቅም ማነስ፣ ቁርጠት የራስ ምታትና ለመግለፅ የሚያስቸግር የህመም ስሜት የፈጠረባቸው መሆኑን ገልፀውልናል።
በልደታ ተክለ ሃይማኖት ክሊኒክ በተደረገላቸው ምርመራም ውጤቱ የምግብ መበከል የሚያሳይ መሆኑን የተገለፀ መሆኑን ነዋሪዎቹ ገልፀውልናል። ነዋሪዎቹ ምግቡን ከተመገቡ ቀናት ቢቆጠሩም የህመሙ ስሜት ባለመጥፋቱ የምርመራቸውን ውጤት ይዘው ወደ ክስ የሚያመሩ መሆኑን ጨምረው አመልክተዋል።n
(ምንጭ፡-ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 414 ረቡዕ ነሐሴ 8/2005)

‘‘የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ገዥ እንጂ መሪ አግኝቶ አያውቅም’’ ፕሮፌሰር በፍቃዱ ደግፌ

0
0

ፕሮፌሰር በፍቃዱ ደግፌ

prof, Bekadu Degife

ፕሮፌሰር በፍቃዱ ደግፌ

ባለፈው እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ ባዘጋጀው የመወያያ መድረክ ላይ ቀርበው ታዳሚዎችን የመሰጠና ያወያየ ኃሳብ አንሸራሽረዋል። በፓርቲው ጽ/ቤት የተገኙ ወጣት ምሁራንም የፕሮፌሰሩን ኀሳብ በሌላ ኀሳብ በመሞገት ምሁራዊ አስተሳሰቦችና ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ጥልቅና ማራኪ ውይይት ተደርጓል።

ፕሮፌሰር በፍቃዱ በመወያያ መድረኩ ላይ ቀርበው የመነጋገሪያ ኀሳቦችን ያቀረቡት ፓርቲው በወጣቶች የሚመራ በመሆኑ አቅጣጫ የሚጠቁሙ ኀሳቦችን ለማሳየት ነበር። ጎን ለጐንም ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል። ፕሮፌሰሩ በዋናነት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ማነቆዎች ላይ የመንግስትና የሕዝቡ ሚና ምን መሆን እንዳለበት የራሳቸውን የመፍትሄ ኀሳቦች ሰጥተዋል። ከሁሉም በፊት ግን ፕሮፌሰሩ የሰሞኑ ወቅታዊና አነጋጋሪ ጉዳይ ስለሆነው የኃይማኖት ጉዳይ የተናገሩትን እናስቀድም። ፕሮፌሰሩ በኢትዮጵያ ክርስትናና እስልምና ምን ያህል መስተጋብር ፈጥረው እየኖሩ መሆኑን ከራሳቸው የቤተሰብ አወቃቀር በመነሳት የተናገሩት የታዳሚውን ቀልብ ያሳበ ነበር።

‘‘የእኔ ቅድመ አያት ሙስሊም ናቸው። እናቴ ጌጤ ትባላለች። አያቴ ደግሞ ብሩ ይባላሉ። ቅድመ አያቴ መንሱር የሚባሉ ሲሆን፤ የመንሱር አባት ደግሞ በፈቃዱ ይባላሉ። እኔ በቅድመ አያቴ ስም ነው የምጠራው። ስሜን ያወጡልኝ አያቴ ናቸው። ቀኝ አዝማች ብሩ ይባላሉ። በፍቃዱ ሙስሊም ነው ያገቡት፤ ሰባት ልጆች ወልደው ነበር። ሦስቱ ሙስሊም ሲሆኑ አራቱ ክርስቲያን ሆነዋል። ከነዚህ ውስጥ ሴቷ ሙስሊም አግብታ አብራ ኖራለች። አብረን ነው የምንበላው አብረን ነው የምንኖረው’’ በማለት ለሀይማኖቶች መቀራረብ ከዚህ የተሻለ ማነፃፀሪያ የለም ብለዋል።

ፕሮፌሰሩ ወደ ዋናው ነጥባቸው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሲመለሱ መነሻ ያደረጉት የሀገሪቱን የድህነት ደረጃ በመጥቀስ ነበር። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በአለም ላይ ማሊ ከምትባል ምዕራብ አፍሪካዊት ሀገር ብቻ ነው የምትሻለው ብለዋል።

‘‘ሀገሪቷ የገበሬና የገጠሬ ሀገር ናት። ስለዚህ ግብርና ትልቁ ስራ ነው። የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ምንጭ ግብርና ነው። ግብርናው ወደ ኢንዱስትሪ አድጎ ብዙ ሰራተኛ መቀጠር አለበት። ሰራተኛው ከግብርናው ወደ ኢንዱስትሪ መምጣት አለበት’’ ያሉት ፕሮፌሰሩ አሁን ግን ገበሬው ከራሱ አልፎ ከተማን መመገብ ብቻ ሳይሆን የእራሱም ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ነው የጠቀሱት።

‘‘ኢትዮጵያ ባት የሌለው ገበሬ ነው ያላት። ባት የሌለውም ማለት እግሩ አጥንት ነው። የዚህ ሀገር የግብርና ስራ ጉልበት በጣም የሚፈልግ ቢሆንም ገበሬው አቅሙን ያጣ ነው። ይሄ ሀገር እራሱን መመገብ ስላልቻለ በፈረንጅ ቸርነት ያለ ሀገር ነው’’ ሲሉ የጠቀሱት ፕሮፌሰር በፍቃዱ ‘‘ከተሞችም የድህነት መሸሸጊያና መጠለያ ሆነዋል’’ ብለዋል።

ገበሬው የተጎዳ በመሆኑና በቂ ምርት የማያመርት ስለሆነ የኑሮ ውድነት መከሰቱን የጠቀሱት ምሁሩ የኑሮ ውድነቱ ምስጢር አይደለም ብለዋል። የሰራ አጥነት በከተሞች የተስፋፋው ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሰውና ድህነትን የሚሸሸው ሰው ስለበዛ ነው። ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት የተመረቁ ተማሪዎችንም እንደሚያካትት በመግለፅ ከተሞች የሰራ አጥነት ማዕከል ለመሆን በመገደዳቸው የችግር ቋት ሆነዋል።

በአሁኑ ወቅት ያለውን የሀገሪቱን ችግር ለመፍታት አንድ ትውልድ መስዋዕት መሆን እንዳለበትም ጠቅሰዋል። በተለይ አሁን ያለው ትውልድ የድሎት ኑሮ ለመኖር ያለው ዕድል የጠበበ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

የሀገሪቱ ሁኔታ ለመቀየር ግብርና ብቸኛው አማራጭ መሆኑንም የጠቀሱት ፕሮፌሰር በፍቃዱ፤ አሁን ሀገሪቱ የምትመካበት ምንም ሀብት ወይም ጥሪት የላትም ብለዋል። ‘‘ሀገሪቱ ቤንዚን የላትም። በእርግጥ ቤኒዚን ሌሎች ሀገሮችን ሲያባልግ አይተናል። ኢትዮጵያ ቤንዚን ከማግኘቷ በፊት ሕዝቡ በጥረቱ መልማት እንደሚችል ማመን አለበት። ከቤኒዚን በፊት የስራ ዲሲፕሊን መቅደም አለበት። ጥረቱ ካለ ቤንዚን ብቻ ሳይሆን ዩራኒየምንም ሆነ ወርቁንና ፕላቲኒየምን አውጥቶ መጠቀም ይቻላል። ጥረቱ መጀመር ያለበት ደግሞ ከግብርናው ነው’’ ብለዋል።

የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ከግብርናው መጀመር አለበት ከተባለ የሀገሪቱ የመሬት ስሪትና ይዞታ መታየት እንዳለበት ነው የገለፁት። ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ገጠሩ በአንድ አካባቢ ታፍኖ እንዲቀመጥ በመደረጉ ገበሬዎች የሚያርሱት የመሬት ስፋት በከፍተኛ ደረጃ እያነሰ ነው። በመንግስት ስታስቲክስ መሰረት በኢትዮጵያ ከአንድ ሄክታር በታች የሚያርሱ ገበሬዎች ወደ 11 ሚሊዮን ገበሬዎች ናቸው። ከሁለት ሄክታር በታች የሚያርሱ ወደ 14 ሚሊዮን ናቸው። ይሄ ደግሞ ገበሬው ምን ያህል ውልቅልቁ እንደወጣ ያሳያል’’ ብለዋል። በመፍትሄነትም የመሬት ጥበትን የሚቀንሱ አማራጭ የገቢ ምንጮች በመፍጠር መሬቱ ላይ በውርስም ሆነ በሌላ መንገድ የሚደረገው እየቆራረጡ መከፋፈል መቆም አለበት ብለዋል። በመሆኑም አንድ ገበሬ ቢያንስ ሦስት፣ አራት ወይም አምስት ሄክታር በመያዝ ትርፍ ሊያመርት ይገባል። ለዚህ ደግሞ በሀገሪቱ እንደገና የመሬት ክፍፍል ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። ገበሬውም ለሚወልዳቸው ልጆቹ መሬት እየቆረጠ የሚሰጥበት አካሄድ አንድ ቦታ መቆም አለበት። ልጆቹ ወደ ሌሎች አማራጭ የስራ ዕድሎች መሰማራት አለባቸው ብለዋል። ገበሬው ትርፍ ባመረተ ቁጥር አነስተኛ ኢንዱስትሪ በማስፋፋት ግብርናን ከኢንዱስትሪው ጋር ማመጋገብ ተገቢ እንደሆነም አስረድተዋል።

ግብርናውና ኢንዱስትሪው ከተመጋገበ በኋላ ገበያ መፍጠር ወሳኝ መሆኑንም ፕሮፌሰሩ በገለፃቸው ላይ አፅንኦት ሰጥተውታል። ‘‘የሀገር እድገት መሰረቱ ብዙ ማምረት ነው። በብዛት ያላመረተ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት አለ ለማለት አይቻልም። እድገት ያለ ገበያ ደግሞ አይሳካም። በአሁኑ ወቅት የገበያ አማራጭ ሁለት አይነት ሲሆን የውጪና የሀገር ውስጥ ገበያ ነው። የውጪውን ገበያ ለመወዳደር የምርት ጥራት በቂ ነው’’ ያሉት ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያ ካለችበት ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ አንፃር ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ገበያ ጥሩ ዕድል ያላት መሆኑን ጠቅሰው፤ ‘‘የሰው ኃይላችንን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ከምንልክ የግብርና ውጤቶችን ብንልክ የተሻለ አማራጭ ነበር’’ ብለዋል።

መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ስለሚኖረው ሚና

‘‘በፕሮፌሰር በፍቃዱ እምነት በአሁኑ ወቅት ትልቁ ቀጣሪ መንግስት ነው። መንግስት የሀገሪቱ ግዙፍ ተቋም ነው። በዚህ ሁኔታ መንግስትን ከኢኮኖሚው ማስወጣቱ ተገቢ አይደለም። ተወደደም ተጠላ መንግስት መንገድ፣ ግድብ፣ ትልልቅ ፋብሪካዎችን ካልገነባ ማን ሊገነባው ነው?’’ ሲሉ የሚጠይቁት ፕሮፌሰሩ ከመንግስት ውጪ ያለው ኢኮኖሚ የጉሊት ኢኮኖሚ ነው። የኢትዮጵያን እድገት በኃላፊነት ለመያዝ የሚችል የግል ክፍለ ኢኮኖሚ የለም። ስለዚህ መንግስት የግሉን ሴክተር መፍጠር አለበት። በ1959 ዓ.ም ኮሪያ ከእኛ እርዳታ የምትቀበል ሀገር ነበረች። ሲንጋፖር ብትሄዱ ‘‘የኢትዮጵያ አደባባይ’’ የሚባል ቦታ አለ። በችግራቸው ጊዜ እርዳታ ስለላክንላቸው ነው። ኮሪያም ዘምተናል እና ይሄ ሀገር ትልቅ ሀገር ነበር። ‘‘ትልቅም ነበር ትልቅ እንሆናለን’’ የሚለው አባባል እውነት ነው። ነገር ግን ትልቅ ነበርና ትልቅም እንሆናለን ማለት አሁን ግን ትልቅ አይደለንም ማለት ነው። የምስራቅ ኢሲያ ሀገሮች የኢኮኖሚ ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ጠቃሚ መሆኑንም በ1959 ዓ.ም ጀኔራል ቹንኪ ፓርክ የኮሪያን መንግስት ገልብጦ ስልጣን ከያዘ በኋላ የሀገሪቱን የፊውዳል ሐብታሞች ሰብስቦ የግሉን ሴክተር መፍጠር ችሏል። እነ ሳምሰንግ ዘዩናድይ ወዘተን ሊፈጠሩ ችለዋል። በእኛም ሀገር መንግስት ጠንካራ የግል ሴክተር መፍጠር አለበት። መንግስት የግል ሴክተር ይፍጠር ሲባል አሁን እንዳለው መንግስት የግሉን ሴክተር ተክቶ ይስራ ማለት አይደለም ብለዋል።

ጃፓኖች ከድህነት አዘቅት የተነሱት አፄ ቴዎድሮስ በሞቱበት እ.ኤ.አ 1868 ዓ.ም ወደስልጣኔ ማምራት የጀመሩበት ዘመን እንደነበር ያወሱት ፕሮፌሰሩ በዚያን ጊዜ አፄ ቴዎድሮስም ሀገሪቱን ወደ ኢንዱስትሪ የመቀየር ራዕይ የነበረው ንጉስ ነበር ብለዋል። በመሆኑም መንግስት የሀገሪቱን ኢንዱስትሪ ለመቀየር የቅድሚያ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበትም አስገንዝበዋል። ኢንዱስትሪ ሲባል ግዙፍ ፋብሪካ ማቋቋም ብቻ ሳይሆን የመንደር ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የምርት ሰንሰለትን መመጋገብ መፈጠር አለበት ብለዋል። ለምሳሌ ጥሬውን ጤፍ ከገበሬው ይዞ ወደ ከተማ ከማምጣት እዛው ወፍጮ ቤት በመትከል ኢንዱስትሪ መጀመር ይቻላል። ከወፍጮ ቤቱ ጎን ለጎን ለጤፍ መያዣ ጆንያ ፋብሪካ ማቋቋም ይቻላል፤ ጆንያውን ለማምረት ደግሞ የቃጫ ፋብሪካ እያሉ ምርት የማመጋገብ የምርታማነት ሰንሰለት በመፍጠር ኢንዱስትሪን በመንደር ደረጃ መጀመር እንጂ ግዙፍ ፋብሪካን በማሰብ ሊሳካ አይችልም ብሎ ተስፋ መቁረጥ አይገባም ብለዋል።

ሀገሪቱን ለመለወጥ የትምህርት ስርዓቱም መለወጥ አለበት ያሉት ፕሮፌሰር በፍቃዱ በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ ትምህርት የምንማረው፤ ለልማት ሳይሆን ቋንቋ ለመተርጎም ነበር። በዚያን ጊዜ ወደ ሀገሪቱ የገባው ትምህርት የአርስቶክራት ትምህርት ነበር። የመደብ (class) ትምህርት ነው። ለስነ-ፅሁፍና ከፈረንጆች ጋር ለመግባባት ነበር። አሁን ግን የትምህርት ስርዓቱ ወደ ዳቦ የሚቀየር መሆን አለበት። ነገር ግን እየተሰጠ ያለው ትምህርት እውቀት እንጂ ስኪል የለውም። በአሁኑ ወቅት 27 ከመቶ የዲግሪ ተመራቂዎች ስራ የላቸውም። ዩኒቨርሲቲዎች የስራ አጥ ማምረቻ ሆነዋል። ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡት የተለዩ የነጠሩና የሳይኒስትነት ደረጃ ያላቸውን እንጂ ሁሉንም በጅምላ እንዲገቡ ማድረጉ ኪሳራ ነው። ጥራት ያላቸውን ወደ ዩኒቨርሲቲ እያስገቡ የቀረውን ደግሞ ስኪል እናስተምረው ብለዋል። የትምህርት ስርዓቱ ሰው ሰርቶ ለመብላት የሚያስችል እውቀት እንዲኖረው በሚያስችል መልኩ መከለስ አለበት ሲሉም ገልፀዋል።

በዕለቱ ከነበሩ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የፓርቲው አባላት ለፕሮፌሰር በፍቃዱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች አቅርበውላቸው ነበር። ከነዚህም ጥያቄዎች መካከል ሀገሪቱ የፖሊሲ ሳይሆን የብሔራዊ ስሜት ማጣት ዋነኛ ችግሯ መሆኑ ተጠቅሶ ነበር። ፕሮፌሰሩ ግን የሀገሪቱ ብሔራዊ ስሜት ሙሉ በሙሉ አለመሞቱንም ይልቁኑ በዚህኛው ትውልድ እየተነሳ መሆኑን ከገለፁ በኋላ ‘‘ሐገሪቷ ያጣችው ብሔራዊ ስሜት ሳይሆን ብሔራዊ መሪ ነወ። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ገዥ እንጂ መሪ አግኝቶ አያውቅም። ልማት በሕዝብ ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ ስሜት ባለው መሪ ሊረጋገጥ ይችላል’’ ሲሉ መልሰዋል።

‘‘በተጨማሪም የሀገሪቱ ብሔራዊ ስሜት በአሁኑ ጊዜ በወጣቱ እያንሰራራ ነው።’’ ያሉት ፕሮፌሰሩ ለብሔራዊ ስሜት መጎዳትም ኦነግን ተጠያቂ አድርገዋል። ‘‘በዚህ ሀገር ከመንግስቱ ኃይለማርያም ቀጥሎ ወንጀል የፈፀመው ኦነግ ነው። ኦነግ በሁለቱ ትላልቅ ሕዝቦች መካከል በአማራና በኦሮሞ መካከል ክፍተት እንዲፈጠር ጥረት አድርጓል። በክፍተቱም ወያኔ እንዲገባ አድርጎ ተገዥ አድርጎናል። ወያኔ ደግሞ ያጠፋው ነገር የለም። እኛ ዝም ብለን እየተገዛንለት ነው’’ ብለዋል።

ሰፈራ በተመለከተ የሕዝብ እንቅስቃሴ አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ የሰፈራ ፕሮግራም ደጋፊ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ነገር ግን ሰፈራው በዋናነት የሚሰፍረውን ሕዝብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ማረጋገጥ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ‘‘ኮንዶሚኒየም የከተማ ሰፈራ ነው’’ ያሉት ምሁሩ፤ ሰፈራ የሕዝብን ቅድሚያ ጥቅም በሚያረጋግጥና ልማትን በተለይም ግብርናን በሚያፋጥን መልኩ ቢፈፀም ችግር እንደሌለው ነው የገለፁት። ለሁሉም ግን ይቻላል፤ እንችላለን ብለን ልንንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።

የወላድ መካን በጐንቻው!

ሰላም ምንድነው? ታደሰ ብሩ

Sport: መሠረት ደፋር የ5ሺህ ማጣሪያ ያሸነፈችበት ቪድዮ

Art: አማኑኤል ይልማ –ከታዋቂ ድምፃዊያን ጀርባ ያለ ታላቅ የሙዚቃ ሰው

0
0

amanuel & Aster
ዘርፈ ብዙ የኪነ ጥበብ ባለሙያ ነው፡፡ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ፣ የሙዚቃ ፕሮዲውሰር፣ የቪዲዮ ክሊፕ ፕሮዲውሰርና የፊልም ተዋናይ! አማኑኤል ይልማ፡፡
ለጌዲዮን ዳንኤል፣ ኃይልዬ ታደሰ፣ ሸዋንዳኝ ኃይሉ፣ አለማየሁ ሂርጶ፣ አረጋኸኝ ወራሽ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ፣ ማዲንጎ አፈወርቅ፣ ብርሃኑ ተዘራ፣ ጸሐይ ዮሐንስ፣ ኤፍሬም ታምሩ፣ ማቲያስ ተፈራ፣ ጥበቡ ወርቅዬ፣ ግርማ ተፈራ፣ አቦነሽ አድነው፣ ፋሲል ደመወዜና ሌሎችም በርካታ ድምፃዊያን በአልበማቸው ውስጥ በግጥም፣ በዜማና በቅንብር ተሳትፎ አለው፡፡ እንዲሁም የተለያዩ ድምፃዊያንን ሙሉ አልበም አቀናብሮ ፕሮዲውስ አድርጓል፡፡ በቅርቡ ‹‹ዜማ አማን›› በሚል ኃይለየሱስን፣ ትዕግስትን፣ ህብስትን፣ ብዙአየሁን፣ ግርማ ተፈራን፣ ገረመውንና ፀጋዘአብን ያካተተ ኮሌክሽን አልበምም በፕሮዲውሰርነት አቅርቧል፡፡ በሚዲያዎች ራሱን ለማስተዋወቅ እንብዛም ግድ የሌለውን አማኑኤል ይልማን አነጋግረነዋል፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- በኢትዮጵያ ሚሊኒየም ጊዜ የነበረውን በአል ለማክበር ከ50 በላይ ድምፃዊያን የተለያዩ ሙዚቃዎችን አውጥተው ነበር፡፡ ነገር ግን ከሁሉም ጎልተው የወጡት አንተ ያቀናበርካቸው የቴዲ አፍሮ ‹‹ጊዜ ለኩሉ›› እና የብርሃኑና ማዲንጎ ‹‹አንበሳው አገሳ›› ነበሩ፡፡ ያ እንዴት ሊሆን ቻለ?
አማኑኤል፡- እንዳልከው የ2000 በአልን ለማክበር ህዝቡን ለማንቀሳቀስ ብዙዎች ዘፈኖችን ሰርተዋል፡፡ በዚያ አጋጣሚ አንዱ ሆኜ እንደዜማ ደራሲና እንደ አቀናባሪ ተሳትፌ ነበር፡፡ ዕድለኛ ያደረገኝ እኔ የሰራሁት ዘፈን ህዝቡ የተቀበለው ሆነ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የቴዲ አፍሮ ‹‹ጊዜ ለኩሉ›› ወይም ‹‹አበባ አየህ ወይ›› የሚለው ዘፈን ሲሆን፣ ከዛ በመቀጠል ‹‹አንበሳው አገሳ›› የሚለው በብርሃኑ ተዘራና ማዲንጎ አፈወርቅ የተዜመው ነው፡፡ በጊዜው በታዋቂ ድምፃዊያን ጭምር የተሰሩ ብዙ ዘፈኖች ውድድሩ ውስጥ ነበሩ፡፡ ከእነዛ ውስጥ ግን በተለይ ‹‹አበባአየህ ወይ›› በአንድ ጊዜ ሒት ሆኖ ወጥቷል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የምነግርህ ያኔ ከቴዲ ጋር ብዙ አብረን ስንጓጓዝ ‹‹ቴዲ አትዘፍንም ወይ?›› እያሉ ይጠይቁት ነበርና በጣም የተጨነቀበት ወቅት ነበር፡፡ ምን ይዤ ልምጣ? ብሎ በተጨናነቀበት ወቅት ሌሎች ስራዎችን ስንሰራ ቆይተን አበባአየህ ወይን ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ነበር የጀመርነው፡፡ ወደ 11፡00 ሰዓት ላይ ጨረስነው፡፡ ከዚያ በኋላ ምንም ግጥም አልጨመረም፡፡ ድጋሚም አልዘፈነውም፡፡ አንዴ ስቱዲዮ ውስጥ የተሰራ ስራ ነው፡፡ ዜማና ግጥሙ የቴዲ አፍሮ ነው፡፡ ቅንብሩ ከእነሚክሲንጉና ማስተሪንጉ የእኔ ነው፡፡ ከዛ በኋላ የብርሃኑና የማዲንጎ ‹‹አንበሳው አገሳ›› ወጣ፡፡ (ዜማው የህዝብ፣ ግጥሙ የመሰለ ጌታሁን ሲሆን ቅንብሩ ሙሉ በሙሉ የእኔ ነው) ሁለቱም ላይ የሰቀሉ ዘፈኖች ነበሩ፡፡ እኔን የሚሊኒየሙ ዕድለኛ ያደረገኝ ሁለቱም ዘፈኖች ዓመት በዓል በመጣ ቁጥር የምንሰማቸው ማለትም ድሮ ከነበሩት ከእነጥላሁን ገሠሠ፣ ከእነ ብዙነሽ በቀለ የአመት በአል ዘፈኖች ጋር በማይተናነስ መልኩ እየተሰሙ ዘመን ተሻጋሪነታቸውን በማስመስከራቸው ነው፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- በተለይ የቴዲ አፍሮን ‹‹ጊዜ ለኩሉ›› ቢዮንሴ አዲስ አበባ መጥታ በሰራችው ኮንሰርት መድረክ ላይ ተጫውተው ደንሳበታለች፡፡ ያ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ብታጫውተኝ?
አማኑኤል፡- በወቅቱ እኔም እዚያው ሚሌኒየም አዳራሽ ነበርኩ፡፡ እና ሰርፕራይዝ ያደረገች ጊዜ እንደማንኛውም አድማጭ ደንግጫለሁ፡፡ በጣም አሪፍ ነበር፡፡ ሙዚቃውን የመረጠችው ሳውንድ ማኗ ናት የሚል ነገር በኋላ ሰምቻለሁ፡፡ እርግጥም በዚያን ጊዜ የሳውንዱ ግሩቭ (Groove) በጣም ሒት ነበረ፡፡ ብዙ ጊዜ እንደ አጋጣሚ ሆኖ እንደዚያ አይነት ሚክሲንግ አልተሰራም ነበር፡፡ በመሆኑም ሳውንድ ማኗ ወደደችው፡፡ በሳውንድ በኩል በጣም ብዙ የሚጠበቅብን ነገር ያለ ቢሆንም በወቅቱ ግን ያ ሳውንድ በቂ እንደነበረ አምናለሁ፡፡ በተጨማሪም ያን ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ ይለቀቅ የነበረው ይህ ዘፈን ነበር፡፡ ህዝቡ ያብድበት የነበረ በመሆኑ የቴዲ አዘፋፈንም ምርጥ ስለነበረ መርጠውታል፡፡ በአጠቃላይ በዚያ የሚሌኒየም ወቅት ለቢዮንሴ ይመጥን የነበረ ሙዚቃ ስለሆነ ነው ብለን ብንወስደው ደስ ይለኛል፡፡
amanuel & ephrem Tamru
ዘ-ሃበሻ፡- ብዙ ጊዜ በግጥምና ዜማ ስራዎችህ ላይ እውነተኛ ታሪኮችን ወደ ሙዚቃ እየቀየርክ እንደምታቀርብ ይሰማል፡፡ ይህን ስታይል የመረጥከው ለምንድን ነው?
አማኑኤል፡- ይሄን ጥያቄ ለመመለስ ትንሽ ወደኋላ መለስ ብዬ ልጀምርልህ፡፡ ከያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት የተመረቅኩበት መሳሪያ ደብል ቤዝ ይባላል፡፡ ፒያኖ ማይነሬ ሲሆን፣ በባህል መሳሪያ ማሲንቆን ተጫውቻለሁ፡፡ ማሲንቆ በጣም ዜመኛ ያደርጋል፡፡ ከዚያ ውጭ ደግሞ የአዝማሪ ግጥሞችን መስማት በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ረጅም ጊዜ እየሄድኩኝ የእነሱን ስራዎች እከታተላለሁ፡፡ አንድ የአዝማሪ ስራንም ፕሮዲውስ አድርጌያለሁ፡፡ እንደነዚህ አይነት በድሮ ጊዜ የሚሰሩ ነገሮች ሪያሊቲ አላቸው፡፡ ለምሳሌ ከድሮ ድምፃዊያን የማደንቀው የጋሽ ባህሩ ቀኜ ግጥሞችን ነው፡፡ በዚህ ዘመን ‹‹አንጣላ›› ብሎ የሚዘፍን የለም፡፡
ልቤን ጅብ በበላው ባወጣው አጥንቱ፣
ተጣልቶ መታረቅ አይሆን እንደ ጥንቱ፡፡
የመሳሰሉ ግጥሞች ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ቀድመው የሚነግሩህ ናቸው፡፡ እንደዚህ አይነት ፍልስፍና ውስጥ ስትገባና ይህን እያዳበርከው ስትሄድ፣ ላይፍን ወደ ሙዚቃ አምጥተህ የሰውን ታሪክ ስትፅፍ ከዛ የበለጠ ቀድመህ ሁሉ መድሃኒት ታዘጋጃለህ፡፡ እኔ ደግሞ ፊት ለፊት ያሉኝን ችግሮች ወደ እውነተኛ ታሪክ ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ ለምሳሌ በአንድ ዘመን እሰራቸው የነበሩት ስራዎች በአብዛኛው አፍቅሮ የተጎዳ ሰው ላይ ያመዝን ነበር፡፡ የተወሰኑትን ብጠቅስልህ ‹‹እንዳረከኝ አድርገኝ፣ ሳታመሀኝ ብላ፣ ኋላ እንዳይቆጭሽ፣ በአይኔ ላይ ዋልሽሳ በአይኔ፣ የማታ ማታ…›› ሌሎችም አሉ፡፡ በሴት ደግሞ የነፃነት አየለ ‹‹ላያገባኝ›› አለ፡፡ ማለትም እንዴት ይሄ ሁሉ ጊዜ አልፎና ዛሬ ከእኛ አልፎ ለሰው ተርፎ፣
ለካ ይሄን ሁሉ ጊዜ እያለፋኝ ነበረ ለካ
ሳያገባኝ እያለች የምትጫወተው ማለት ነው፡፡
ይህም አንዲት ሴት ረጅም ዓመት አንድ ወንድ ይዟት ሄዶ ጊዜዋን ሁሉ ገድሎ በመጨረሻ ሳያገባት ሲተዋት ያመላክታል፡፡ የብዙ ሴቶችን፣ ችግር ያሳየሁበት ነው፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- በጎሳዬ ተስፋዬ የተዘፈነውን ‹‹ሳታመሀኝ ብላ›› ግጥም የፃፍከው ከእውነተኛ በምታውቀው ሰው ላይ ከደረሰ አጋጣሚ ተነስተህ መሆኑም ይነገራል፡፡
አማኑኤል፡- ልክ ነህ፡፡ ‹‹ሳታመሀኝ ብላ›› ትልቅ ታሪክ ነው፡፡ በአንድ የቅርብ ጓደኛዬ የደረሰ ታሪክ ነው፡፡ አንድ ሰው የሚወደውን ጓደኛውን በምን መንገድ እንደሚያጣው፣ ሚስቱን ደግሞ በጓደኛው እንዴት እንደሚያጣ የሚገልፅ ነው፡፡ የክሊፑ አለመሰራት ዘፈኑን በውስጥ ደረጃ አስቀረው እንጂ ትልቅ ታሪክ ያለው ነው፡፡
የሚገርምህ ከዚህ ዘፈን ጋር በተያያዘ ብዙ ገጠመኝ አለኝ፡፡ ለምሳሌ ‹‹እንዴት ሰውን ጅብ ትላለህ?›› ያሉኝ ሰዎች ነበሩ፡፡ እኔ ግን ‹‹ጅብ›› ስል በልመናና በጨዋነት ነበረ የገለፅኩት፡፡
አንቺም ትዳሬ ነሽ እሱም ጓደኛዬ፣
ጥፋቱ የማን ይሆን ስሄድ አንችን ጥዬ፣
አወይ ክፉ ዘመን ልቤ አዘነብሽ
እሱም ተሳሳተ የእኔ እናት አንቺም አልታመንሽ
ታማኝ ያንቺ ገላ ያለኔም አያውቅም
ምነው ደከመሳ አነሰው ወይ አቅም
ስደተኛ ታርገኝ ደሞ ብላ ብላ
ጅብ ረሃብ አይችልም ብለህ ወንድሜ ሳታመሀኝ ብላ
አየህ ‹‹ወንድሜ›› ነው ያልኩት፡፡ ጭካኔ የለውም፣ ግን መልዕክቱ ሃያል ነው፡፡ በጓደኛዬ ላይ የደረሰው ህመም ነው ያንን እንድፅፈው ያደረገኝ፡፡ ብዙዎች ይህ የእኔ ስራ መሆኑን ሲያውቁ የኔ ታሪክ መስሏቸው ደውለው ሀዘናቸውን የገለፁልኝ አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ‹‹የእኔን ታሪክ ነው የሰራህልኝ›› ያሉኝም አሉ፡፡
amanuelዘ-ሃበሻ፡- አንተ በጥሞና ዜማውን የሰራኸውና ኤፍሬም ታምሩ የተጫወተው ‹‹ኋላ እንዳይቆጭሽ›› ሙዚቃም እውነተኛ ታሪክ ነው አይደል?
አማኑኤል፡- ኋላ እንዳይቆጭሽ እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ በአንድ ጊዜ የሰራሁት ስራ ነው፡፡ ታሪኩን በዝርዝር ባልነግርህም የዚያን ጊዜ የተፈጠሩት ‹‹ኋላ እንዳይቆጭሽ››፣ የጌዲዮን ዳንኤል ‹‹እንዳደረግከኝ አድርገኝ››፣ የፀሐዬ ዮሐንስ ‹‹ፍቅርሽ እንደ ጥላ፣ አንድ በይኝ…›› ወዘተ እውነተኛ ታሪክን መሰረት ያደረጉ ናቸው፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- አማን አንተ ሌላ የምትታወቅበት ‹‹ለታናሿ ልስጋ›› በሚለው የሙዚቃ ቪዲዮ ነው፡፡ ይህንን ቪዲዮ ግጥምና ዜማ ሰርተህ ከማቀናበርህም በላይ ራስህ ፕሮዲውስና ዳይሬክት አድርገህ ያቀረብከው መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ለመሆኑ ይህን ስራ ለማቅረብ እንዴት ተነሳሳህ? ከአድማጭ ያገኘኸው ምላሽስ?
አማኑኤል፡- የምር ለመናገር ደራሲ ስትሆን፣ በሰው ችግር ውስጥ ማለፍ ስትጀምር፣ ዘፈኖችን ወደ ሪያሊቲ ስታመጣና ወደ እውነተኛው በሄድክ ቁጥር አርቱም ይሳካልሃል፡፡ የምትፅፈው ነገር ይሳካል፡፡ ዳይሬክት የምታደርገው ነገር ሁሉም ወደ እውነት ይቀርብልሃል፡፡ ከቅንነት ከተነሳህ ማለት ነው፡፡ እና የሚገርምህ ነገር በቡና ቤት ሴቶች ላይ፣ በጎዳና ተዳዳሪዎች ላይ፣ በአላቻ ጋብቻ ላይ እንደዚህ አይነት ነገሮችን ለመስራት እያሰብኩ ባለሁበት ሰዓት ወደ ገጠር ውስጥ እየሄድኩ፣ በቀንም በማታም ያለውን ሁሉ እያየሁ እየቀረብኩ እፅፍ ነበር፡፡ እና በዚህን ወቅት አንዲት ልጅ በጣም አዝና አየሁኝ፡፡ ያቺ ልጅ በሀዘን አገጯን የያዘች፣ ከንፈሯ የሚንቀጠቀጥ፣ እንባ ያቀረረችና ደንግጣ የተቀመጠች ነበረች፡፡ እኔም የፃፍኩት ያንኑ ነው፡፡ ግጥሙንም ስፅፈው፤-
እንባ አዝሎብኝ አይኖቿ፣
መዳፏ አልፎ ከጉንጮቿ
እንባዋ ይፈሳል ሳያባራ
ብቻውን ያወራል ከንፈሯ
እያልኩ ጀመርኩት፡፡ ከዚያ ይህችን ህፃን ሊድሯት፣ ቤተሰቦቿም ፈረዱባት፣ እያልኩ ዘፈኑን እየሰራሁት ይህን ዘፈን በደንብ ሊጫወተው የሚችለው ማነው? የሚለው ውሳኔ የኔ ነበር፡፡ ጎሳዬን መረጥኩት፡፡ እንደውም ለጎሳዬ ክፍያ ስከፍለው ‹‹እንዴት እንደዚህ አይነት አይዲያ?›› ሲለኝ ግድየለህም ብዬ አስጀመርኩት፡፡ ከዚያ ቡሬ አንድ ጥጃ አጠገቧ ስለነበረች ‹‹ቡሬ ቡሬ ቀናችን አይደለም እኔና አንቺ ዛሬ፣ አለጊዜው ታርደሽ አለጊዜው ተድሬ›› የሚለው በመስታወት አራጋው ተቀረፀ፡፡ ታገል ሰይፉም ገባበት፡፡ በእንደዚህ አይነት ተቀረፀ፡፡ ዘፈኑን ከቀረፅን በኋላ የዚህን እውነተኛ ታሪክ ሰው ጭፈራ ይመስለዋል፡፡ ምክንያቱም ሲሰማው እንደዘፈን የሚያደምጠው ነው፡፡ ስለዚህ ክሊፑን በመስራት መልዕክቱን ህዝቡ እንዲረዳው ማድረግ ያስፈልግ ነበር፡፡ የዚህንም ሪስክ ወስጄ ወደ 50 ሺ ብር በማውጣት ክሊፑን አሰርቼዋለሁ፡፡ እዛ ውስጥ ያለ ሁሉ ድምፃዊ፣ አንባቢ ተከፍሎታል፡፡ ይሄ ሁሉ አልፎ እስካሁን ከሰራኋቸው በርካታ ስራዎችና ሙዚቃዎች በላይ በየሄድኩበት ዓለም ሁሉ ‹‹ለታናሿ ልስጋ›› ነው የሚሉኝ፡፡ ምክንያቱም በህዝብ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት ያገኘሁበት በዚህ ስራ ነው፡፡ እንደምታውቀው የአላቻ ጋብቻን በተመለከተ ብዙ ወረቀቶች፣ ብዙ ወርክሾፖች፣ ብዙ ስብሰባዎች ተደርገዋል፡፡ ግን በሰባት ደቂቃ አንድ የሙዚቃ ክሊፕ ብዙ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል መሆኑን ብዙዎች መስክረውለታል፡፡ ሰውን እያዝናና ለቀጣዩዋ ለታናሿ ደግሞ ይታሰብበት በሚል መንገድ የቀረበ በመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓም፣ በአሜሪካም፣ በካናዳም አውስትራሊያም፣ አረብ አገር ጭምር ያሉት የወደዱትና እንዲዘፈን ደጋግመው ያዩት ክሊፕ ሊሆን ችሏል፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- በቅርቡም ሌላ ይህን መሰል ክሊፕም ሰርተሃል? ይህኛውስ?
አማኑኤል፡- አዎ፣ በቅርብ ጊዜ ድጋሚ ከጎሳዬ ጋር ሰርቻለሁ፡፡ ያቀናበረው አበጋዝ ነው፡፡ ግን ዜማውም ግጥሙም የእኔ ነው፡፡ ‹‹ፍጥረትን እንደቀላል›› የሚል ነው፡፡ ይህኛው ደግሞ ህፃናቶችን ብዙ ጊዜ ከገጠር እያመጡ ዘመድ ጋ ይቀመጡ በሚልና በተለያየ መንገድ በማምጣት ትልልቅ ስራ ከአቅማቸው በላይ ያሰሯቸዋል፡፡ እኔም የሰራሁት ያንን በመቃወም ነው፡፡ ይህም ስራ አስተማሪ፣ ትልቅ ተቀባይነት ያገኘና ማህበረሰቡን የሚነካ፣ ለውጥና ዕድገትን የሚያመጣ የህፃናትን ኃላፊነት እኛ መውሰድ እንዳለብን የሚያስገንዘብ ሆኗል፡፡ እንደ አጋጣሚ ይህን ያሰራኝ አንድ ድርጅት ነው፡፡ ለታናሿ ልስጋን አይተው በዚያ መንገድ እንዲሰራላቸው ፈልገው ጠይቀውኝ ቦታው ድረስ ሄጄ፣ እንዴት ሽመና እንደሚያሸምኗቸው እህል እንዴት እንደሚያስፈጯቸው ከባባድ ስራ ሲያሰሯቸው አይቼ በጣምም እንዳይከፉ አድርጌ ቀለል አድርጌ የሰራሁት ነው፡፡ ግን ያለው ሁኔታ በዚህ መንገድ ብቻ የሚገለፅ ሳይሆን ሁለትና ሶስት እጥፍ የበለጠ መገለፅ የሚችል ነው፡፡ እኔ ግን የማምነው ማንኛውንም አይነት ችግር ነገሮችን በማቅለል ማህበረሰቡ በሚረዳበት መንገድ ማስተማርና ማዝናናት እንዳለብን ነው፡፡ በመሆኑም ያቀረብኩት በዚህ ሁኔታ ነው፡፡ ከሁለቱ ስራዎቼ በተጨማሪ በቀጣይነት እንደዚህ አይነት ስራዎችን ማለትም ማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን ችግር እየፈለፈልኩ የማውጣት አቋም አለኝ፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- እስቲ ስለዜማ ላሰታስ ባንድስ እናውራ፡፡ እንዴት ተቋቋመ? እንዴትስ ሊፈርስ ቻለ?
አማኑኤል፡- እኔ ዜማ ላስታስ ባንድ ለሙዚቃ ዕድገት አንድ መሰረት ነው ብዬ የማምንበት ነው፡፡ ከያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት የተመረቅን ልጆች ማለትም ኤልያስ መልካ፣ ሁንአንተ ሙሉ፣ ሚካኤል መላኩ፣ ምስጋናውና እኔ ሆነን ያቋቋምነው ሲሆን፣ ስንጀምር ድምፃዊዎች ትዕግስት በቀለ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ እዮብ መኮንን፣ ኃይሌ ሩትስ ባንዱ ውስጥ ነበሩ፡፡ ባንዱ ትልቅ የሳውንድ ለውጥ ይዞ የመጣና አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነበር፡፡ ባንዱ ሊፈርስበት የቻለው ዋንኛ ምክንያት ሁላችንም ወደየስራችን ስቱዲዮ መበታተናችን ነው፡፡ መጀመሪያ ኤልያስ መልካ፣ ቀድሞን የራሱን ስቱዲዮ ሲከፍት ሁንአንተ ተከተለው፡፡ ከዚያ እኔም ወደ ስቱዲዮ ገባሁ፡፡ ከዚያ የየራሳችንን የስቱዲዮ ስራ ስንሰራ ወደ ባንዱ ለመስራት ስላልቻልን ሊፈርስ ችሏል፡፡ ይሁንና ባንዱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዓለማየሁ እሸቴ፣ የባህት ገ/ህይወት፣ የፍቅር አዲስና የመሳሰሉትን የድሮ ሙዚቃዎች አምጥተን በጥሩ ሁኔታ ቀርፀን ሰው በሚገርም ሁኔታ ተቀብሎታል፡፡ በዚያ ሳውንድም ባንዱ በጣም አሪፍ ከሚባሉት ባንዶች ስሙን አስቀምጦ ለማለፍ ችሏል፡፡
amanuel teddy afro and maritu legesse ዘ-ሃበሻ፡- አንተ በሙዚቃ ስራ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ለመዞር የቻልክ ነህ፡፡ የአቡጊዳ ባንድ ውስጥ ተካተህም ከቴዲ አፍሮ ጋር ብዙ መድረኮች ላይ መስራትህን አውቃለሁ፡፡ የሙዚቃ ጉዞህን በተመለከተ እናውራ?
አማኑኤል፡- የሚገርምህ ከታዋቂ ድምፃዊያን ጋር ወደ ውጭ አገራት ከመሄዴ በፊት ከያሬድ ት/ቤት እንደተመርቅኩኝ አንድ ‹‹ፎርኤቨር ያንግ›› የሚል የባህል ቡድን አቋቁሜ ነበር፡፡ ከዚያ ቡድን ጋር ሀኖቨር የባህል ኤክስፖ በተዘጋጀበት ወቅት ከዛሬ 13 ዓመት በፊት በመሄድ ጀምረን በተከታታይ ለአንድ 6 ዓመታት የተለያዩ ቦታዎች ሰርተናል፡፡ ከዚያ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ከእነፍቅር አዲስ፣ ኃይልዬ፣ ይርዳው፣ ህብስት ቴዲ አፍሮን ጨምሮ ራሴ ፕሮሞተር እየሆንኩኝ ከአገር ውስጥ እስከ አረብ አገሮች እሰራ ነበር፡፡ የመጨረሻ ጉዞዬን ያደረግኩት ደግሞ ከቴዲ አፍሮ አቡጊዳ ባንድ ጋር በመቀላቀል ነው፡፡ ከአቡጊዳ ጋር ከ24 ሾው በላይ ሰርቻለሁ፡፡ ይህም በመላ አውሮፓ፣ አረብ አገራት፣ እንዲሁም አሜሪካና ካናዳ ዞሬያለሁ፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- ምንም አልበም ሳይኖረው በመላው ዓለም ታዋቂ ለመሆን የበቃው ጃኪ ጎሲ (ጎሳዬ ቀለሙ) ከዚህ ቀደም በዚሁ ዘ-ሃበሻ ጋዜጣ ቃለ ምልልስ ሲያደርግ አንተን አመስግኗል፡፡ ከስኬቱ በስተጀርባ ያለህ ቁልፍ ሰው መሆንህንም ተናግሯል፡፡ ለመሆኑ ከጃኪ ጋር የነበራችሁ የስራ ግንኙነት ምን ይመስላል?
አማኑኤል፡- ጃክ ከጥቂት ዓመታት በፊት እኔ ጋር ሊሰራ በአጋጣሚ ወደ ስቱዲዮ መጥቶ ነበር፡፡ ይዞት የመጣው ስታይልም ትንሽ ወጣ የሚል ነው፡፡ ማለት ከአማርኛ ሙዚቃዎች ወጣ ያለና እንደ ሒፕ ሆፕ አይነት ነገር ነበር፡፡ እና የሒፕ ሆፕ ስታይሉን በሚያሰማኝ ጊዜ ልጁ አንድ ቃናና በጣም የሚገርም ድምፅ እንዳለው ተረዳሁ፡፡ ይሄን ድምፁን ደግሞ በእርግጠኝነት የሌላ ዜማ ስታይል ቢሰራበት ጥሩ ይሆናል በሚል ትንሽ ደቂቃ ተነጋገርን፡፡ ልጁም ጥሩና ቅን ስለሆነ ወዲያው ተመለሰ፡፡ ምክንያቱም የዜማ ደራሲ ስትሆን የመጀመሪያው ነገርህ ሰው መፍጠር ነው፡፡ አንድን ድምፃዊ አምጥቶ መስራት እንደማለት ነው፡፡ እንደፊልም ለዚህ ተዋናይ ይህን ካራክተር ብሰጠው ይዋጣለታል ብሎ መቅረፅ ነው፡፡ ስለዚህ በዚያ መንገድ የመጀመሪያውን ‹‹ጭራሽ›› የሚለውን ሰራሁለትና ይዞት ወደ አገሩ ሄደ፡፡ እዛ ከለቀቀ በኋላ አቀባበሉ የሚገርም ሆነ፡፡ እኔ መልዕክቱንም ስፅፈው ውጭ አገር ስላሉ ሰዎች በመለያየትና በመነፋፈቅ ውስጥ እንዴት እንደሚተሳሰቡ በሚያደርግ ስሜት ነበር፡፡ በመሆኑም ውጭ አገር ያሉ ሰዎች በጠቅላላ ወደዱት፡፡ ከዚያ ከስድስት ወር በኋላ ደወለልኝና ‹‹ዘፈኑ በጣም ቡም ብሏል›› አለኝ፡፡ አላመንኩም፡፡ ‹‹እውነትህን ነው?›› አልኩና ዩቲዩብ ላይ ሳየው ደነገጥኩኝ፡፡ የሚገርምህ ወደ 2 ሚሊዮን 800 ሺ ህዝብ አይቶለታል፡፡ በደወለልኝ ጊዜ ሌላ ዘፈን እንዳዘጋጅለት በጠየቀኝ መሰረት ‹‹ደሞ አፌን›› ሰራሁለት፡፡ የመጀመሪያው የባህል ዘመናዊ ሲሆን ይህ ግን ችክችካ አይነት ለመድረክ የሚሆን ነው፡፡ ከዚያ፣ በየኮንሰርቶች ተመራጭ ለመሆንና ለመስቀል ቻለ፡፡ ቀጥሎ ‹‹ሰላ በይ›› የሚለውን በሌላ ስቱዲዮ መጥቶ ሰራው፡፡ እሱም ውጤታማ ሆነለት፡፡ ይሄ ልጅ የተሾመ አሰግድን ‹‹የእኔ አካል›› የሚለውን ድጋሚ በመዝፈን አንድ ዘፈን ጨምሮ በአራት ዘፈን በዓለም ላይ እየተዘዋወረ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
እኔ ለጃክ የመጀመሪያውን ሙዚቃ ግጥምም ዜማም ቅንብርም ስለሰራሁለት ሊያመሰግነኝ ቢችልም፣ እኔ ደግሞ በጣም ብልህ ልጅ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ለምን ብትል በደራሲ ያምናል፡፡ የድሮዎቹን ትልቅ ደረጃ የደረሱት እነ ኤፍሬም ታምሩን ብትመለከት ለረጅም ጊዜ የሰሩት ደራሲዎችን ይዘው በመምጣታቸው ነው፡፡ ልጁ በዚሁ ከቀጠለ ታዋቂዎቹ የደረሱበት ቦታ የማይደርስበት መንገድ የለም፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- ብዙውን ጊዜ የድሮ ድምፃዊያንን በተለያዩ መንገዶች ታነሳለህ፡፡ ለምንድን ነው?
አማኑኤል፡- ያለጥርጥር እኔ የድሮዎቹ ድምፃዊያን አድናቂ ነኝ፡፡ ከ50ዎቹ ጀምሮ የነበሩት በተለይ ባህሩ ቀኜ፣ አሰፋ አባተ፣ ወደዚህ ስትመጣ ጋሽ ይርጋ ዱባለ በጣም ድምፃዊ ናቸው፡፡ በዚያን ጊዜ የሚያገኙት ግጥምም ሆነ ዜማ ያስገርመኝ ነበር፡፡ በተለይ ጋሽ ባህሩ የሚፈጥረው ዜማና ግጥም በጣም ለኢትዮጵያ ሙዚቃ መሰረት የነበረና ለረጅም ዓመት የተደመጠ ነው፡፡ ወደዚህ ስንመጣ ደግሞ የእነ ጥላሁን፣ የእነ ብዙነሽ፣ የእነ ሒሩት ዘመን አለ፡፡ ሲቀጥል ሮሀ ባንድ፣ በ70ዎቹ እነ ኤፍሬም ታምሩ፣ ሙሉቀን መለሰ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ፣ አስቴር አወቀ እያልን መዘርዘር እንችላለን፡፡ እነዚህ ሰዎች ሙዚቃን ለ40 እና 30 ዓመታት ያሻገሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ እንደቀላል አይታዩም፡፡ አሁን የእኛ አገር ሙዚቃዎች ለሶስትና ለአራት ወር ተሰምተው ሲቆዩ እንደትልቅ ነገር የምናይበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ስለዚህ እኔ የዚያን ጊዜ ሰዎች በምን መንገድ ቢሰሩት ነው ቴክኖሎጂ በሌለበት ሰዓት፣ በአናሎግ ሲስተም እየቀዱ፣ ኮምፒውተር ሳያግዛቸው፣ ላይቭ እየቀዱ፣ ወጣቱ በእነሱ ዘፈን እየተማረከ እኛ እንዴት እንደነሱ መስራት አቃተን? የሚሉ ጥያቄዎች ስላሉኝ ያኛው ትውልድ ይበልጥብኛል፡፡ ይሄ የእኔ ብቻ ሳይሆን፣ የአድማጭ፣ የህዝብና የአርቲስቱ ጥያቄ ይመስለኛል፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- የዚህ መፍትሄው ምንድን ነው ትላለህ?
አማኑኤል፡- አንደኛው ነገር ራሳችንን እየሆንን አይደለንም፡፡ ራሳችንን መሆን መቻል አለብን፡፡ ሁሉም በየፊናው የተለያየውን ዓለም ሙዚቃ ይሰራል፡፡ አይስራ አልምም፡፡ በስታይሉ ውስጥ ደግሞ ስራውን በማቅለል ደረጃ በአንድ ሞኖ ስቱዲዮ (ሆም ስቱዲዮ) ውስጥ በመሰራቱ አንድ ሰው ሙዚቃውን እንደፈለገው ማድረግ ጀመረ፡፡ ድምፃዊያኑም ስለቀለለው ገባ፡፡ መአት ድምፃዊያን ተፈጠሩ፡፡ ግን ከዚያ ውስጥ ምን ያህሉ ድምፃዊ ነው? ብለህ ብታስብ ሁሉም አይደሉም፡፡ ስለዚህ ህዝቡንም አሰለቸነው፡፡
እኛ የእኛነት የምትለው ነገር የለም፡፡ ሬጌው ምን ያህል በኢትዮጵያ ሄዷል? ብትል የለም ገና መጀመሩ ነው፡፡ ሒፕ ሆፕ አለ ወይ? ብትል ሒፕ ሆፕ የሚባል ሙዚቃ የት አለ? ሌላው ዓለም መጥቶ ሲሰማን በጣም ያዝንብናል፡፡ በየስቱዲዮው ነጮቹ ጥቁሮቹ መጥተው አይተው የተሰማቸውን ስሜት አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በዚህ ትውልድም እንደድሮው የራሳቸውን ቀለም ይዘው መስራት እንዳለባቸው ይሰማኛል፡፡ ኢንዱስትሪው እንዲያድግና አድማጭ እንዲሰማን ከፈለግን ጥሩ ዜማ፣ ለግጥሙም መጨነቅ፣ ለአሬንጅመንቱም መጨነቅና ጥሩ ድምፃዊም መስራት ያስፈልገናል፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ፣ የሙዚቃ ቪዲዮ ክሊፕ ዳይሬክተር ፕሮዲውሰር ስለመሆንህ እስካሁን በነበረን ቆይታችን ስናወራ ቆይተናል፡፡ አሁን ደግሞ በፊልሙ ዓለም ስላለህ ተሳትፎ እናውራ፡፡ እንችላለን?
አማኑኤል፡- ይቻላል፡፡ ስለፊልም ካነሳን የመጀመሪያው ‹‹የማያልቀው መንገድ›› ነው፡፡ እንኳን እኔ ኢትዮጵያ ውስጥም ፊልም ገና እየገባ በነበረበት ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ነበረ፡፡ የያኔው ከነበረው ሁኔታ አንፃር ጥሩ ነው፡፡ ወደ አሁኑ ዘመን ስንመጣ ‹‹ፔንዱለም›› እና ‹‹ከመጠን በላይ›› የሚሉ ፊልሞች ላይ ሰርቻለሁ፡፡
የፔንዱለም ፕሮዲውሰር ቶማስ ጠርቶ ሲፈትነኝ ሌሎች ዳይሬክተሮችም ይዞ ነበር፡፡ ከተፈተንኩ በኋላ የተቀረፅኩትን በቪዲዮ ስመለከተው እውነቴን ነው የምልህ ጠላሁት፡፡ እናም ‹‹እኔ መግባት የለብኝም፡፡ እኔ አልሆናችሁም›› አልኳቸው፡፡ ግን ዳይሬክተሩ ለዚህ ቦታ አማን ይሆናል ብሎ ከወሰነ ሪስኩን ይወስዳል፡፡ ስለዚህም ‹‹ይህን ልጅ እለውጠዋለሁ፣ በዚህ አይነት ፎርም አመጣዋለሁ›› ብሎ ስላሰበ ዳይሬክተሩንም አምኜ ገባሁበት፡፡ እውር አሞራ እንደማለት ነው የማታውቀው ነገር ውስጥ መግባት፡፡ በዚህ መንገድ ሰራሁ፡፡ ፊልሙ እስኪያልቅ ድረስ ስቱዲዮ ዘግቼ ነው የሰራሁት፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- የፔንዱለም ፊልም ምርቃት ከተማውን ሁሉ በነቀነቀ ሁኔታ ነበር የተከናወነው፡፡ በዚህ ረገድ የአንተም ወሳኝ ድርሻ እንደነበረበት ሰምቻለሁ፡፡ እውነት ነው?
አማኑኤል፡- ፊልሙ ከተጠናቀቀ በኋላ በአንዳንድ ቦታዎች ማስታወቂያውን ሰማሁ፡፡ ያኔ ለፕሮዲውሰሩ ቶም ደወልኩለትና መተዋወቅ ያለበት በዚህ አይነት መንገድ አይደለም አልኩት፡፡ ምክንያቱም እንደ አበባዮሽ አይነት እን ደጃኪ አይነት ስዎች ጎልተው ሲወጡ ደስ ይለኛል፡፡ ዘፈን ከተሰራ ጎልቶ መውጣት አለበት፡፡ ፊልምም ቢሆን እንደዚያው ነው፡፡ ስለዚህ የሚዲያውን ስራ ሁሉ ጠቅልዬ ያዝኩት፡፡ እንደውም የማልረሳው ለሳውንድ ትራኩ ብዙአየሁ ብዙ ብር ጠየቀ፡፡ እኔ ‹‹በቃ ራሴ እገዘዋለሁ›› ብዬ አሰራሁትና ጨርሼ ቶምን ሰራሁት፡፡ ቶምም ሲሰማው ዘፈኑን ሳላጋንን ከ30 ጊዜ በላይ ቆሞ ሰማው፡፡ ፊልሙን ግልፅ አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ ዘፈን ይሄን ያህል ፓወር አለው ወይ? ብሎ ደነገጠ፡፡ ከዚያ ተጀመረ፡፡ ቶም ሁሉንም ወጪ አወጣለሁ በማለቱ ወደ ሚዲያ መጥተን ሬዲዮኑን ተቆጣጠርነው፣ ጋዜጦችን ተቆጣጠርን፡፡ ቀጥሎ የሚሊኒየም አዳራሽ ሀሳብ መጣ፡፡ ቀይ ምንጣፍ ታሰበ፡፡ እኔ ወደ ባንድ መጣሁኝ፡፡ ሔለን በርሄ ገባች፡፡ በዚህ ጊዜ ሰዎችን ሳማክር ‹‹እናንተ እብድ ናችሁ ወይ፤ እንዴት ዘፈንና ፊልም አንድ ላይ ይታያል? በዚያ ላይ ሚሊኒየም አዳራሽ›› ብለው አልተቀበሉኝም ነበር፡፡ ግን ነገሮችን ትልቅም ትንሽም የምታደርገው አንተ ነህና በውጥናችን ገፍተንበት በስተመጨረሻ 14 ሺ ሰው መጥቶ ፊልሙን ሊያየው ችሏል፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- ለዚሁ ፊልም ማጀቢያነት ሔለን በርሔ የተጫወተችውን ሙዚቃ በግጥምም በዜማም በማቀናበርም ሰርተሀል፡፡ ይሄ ሙዚቃዋ ደግሞ ከፊልሙም በኋላ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲደመጥ ይታያል፡፡ ሙዚቃውን ስታዘጋጅላት ከፊልሙም ውጭ ይደመጣል ብለህ አስበህ ነበር?
አማኑኤል፡- ይኸውልህ አንድ ምሳሌ ልንገርህ፡፡ ‹‹ለካ ለካ ያንተ ዓለም፣ ወዲህ ወዲያ ፔንዱለም›› የምትለዋ የዘፈኑ ግጥም ኤዲት ሲደረግ ነበርኩኝ፡፡ እና ያኔ ‹‹በናታችሁ ልብስ ስለካ እዚህች ቦታ አስገቡኝ›› አልኩ፡፡ ፊልሙ ላይ የምሰራው ልብስ ሰፊ ሆኜ ነው፡፡ እና ለካ፣ ለካ ማለት ልብሱን ለካ እንደማለት ነው፡፡ በፊልሙ ላይ ግን ዝም ብለህ ፊልሙን ባታየውም ደግሞ ‹‹ለካ ከእኔ ጋር አልነበርክም›› የሚል ትርጉም ይሰጥሃል፡፡ የውጪዎቹን ስራዎች እያደነቅንና የእነሱን ተሞክሮ እየቀሰምን መሄድ ያለብን ይመስለኛል፡፡ ታይታኒክ ፊልም ለእኔ ምርጥ ፊልም ነው፡፡ የፊልሙን ማጀቢያ ሙዚቃ የሰራችው ሴሊንዲዮን ናት፡፡ ይህ ማጀቢያ ሲሰራ ስሎው ነው፡፡ ከፊልሙ ጋር ልክክ ብሎ ገብቶ እንዳትወጣ አድርጎ ዘፈኑን በሰማህ ቁጥር ብዙ የፍቅር ትውስታ እንዲኖርህ ያስችላል፡፡ ይሄ ዘፈን ቴክኖና ሐውስ ሆኖ ወጥቷል፡፡ ወደ ጭፈራ ዘይቤ ሆኖ ቀርቧል፡፡ እኔ የሄለን በርሔንም ሙዚቃ እኔ አንዳንዴ ሲጨፍሩበት አያለሁ፡፡ ጥሩ ነው፡፡ ይሄ ከፊልም ማጀቢያ ሙዚቃ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው መነሳሳትን የሚፈጥር ይመስለኛል፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- ከሰሞኑ ‹‹ዜማ አማን›› በሚል ርዕስ አዲስ አልበም በፕሮዲውሰርነት አቅርበሃል፡፡ በዚህ አልበምህ ካመጣኸው ድምፃዊያን ኃይለየሱስ አንዱ ነው፡፡ ኃይለየሱስ ከሙዚቃው አካባቢ ጠፍቶ ነበርና የት አገኘኸው?
አማኑኤል፡- የኃይለየሱስ ነገር እንደማንኛውም አድማጭ እኔንም ይቆጨኝ ነበር፡፡ ተማሪ ሆኜ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት እያለሁ እሱን ለማየት ለመስማት ስል ኤግዚቢሽን ማዕከል ድረስ እሄድ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ያንን የመሰለ ድምፅ ይዞ ጠፋ፡፡
‹‹ይለፍ ዕድሜ፣ አንችን ስል ቆሜ›› የሚለው ወረድ ብሎ ጀምሮ በኋላ ላይ በጣም ከፍ የሚል ነው፡፡ ሀይለየሱስን ውስጤ ሁሌም ስለሚያስበው በቀጥታ እሱ ነው ይህን የሚዘፍነው ብዬ ወስኜ ደወልኩለት፡፡ እሱም ለረጅም ጊዜ ይፈልገኝ ነበርና ተነጋገርን፡፡ ዘፈኑን ሰጠሁት፡፡ በአጭር ጊዜ ይዞት ሰራው፡፡ አድማጭም በጣም የእሱን ዘፈን ወዶታል፡፡ ኃይለየሱስ የሚገርም ድምፃዊ ሲሆን፣ አብሬው በመስራቴ ደስተኛ ነኝ፡፡
ዘ-ሃበሻ፡- በአልበምህ የተካተቱት ድምፃዊያን በአሜሪካና በኢትዮጵያ የሚኖሩ ናቸውና እነሱን ማሰባሰቡና መጠበቁ አላስቸገረህም?
አማኑኤል፡- በጣም ተስፋ የሚያስቆርጥ ደረጃ ያደርሳል፡፡ አንዳንዴ ምን ውስጥ ነው የገባሁት? እስከማለት ደርሼ ነበር፡፡ ሙዚቃ ግን ከገባህበት አይለቅህም፡፡ አንዳንዴ ፈተና ቢበዛብ ህም በእልህ ተስፋን ሰንቄ ለአድማጭ ላበቃው ችያለሁ፡፡ ወደ አምስት ዓመት ያህል የፈጀብኝም ለዚህ ነበር፡፡S

Health: በትዳር መካከል ጸብ ሲነሳ እንዴት መፍታት ይቻላል?

0
0

ከሊሊ ሞገስ

ትዳር በባህር ወይም ውቅያኖስ ውስጥ ያለችን ትልቅ መርከብ ይመስላል፡፡ መርከቧ ረጅም ርቀት እንደመጓዟ ለተለያዩ አየር ፀባይ ለውጦች መጋለጧ አይቀሬ ነው፡፡ ፀጥታና ሰላም የሰፈነበት ጉዞ እንደምታደርግ ሁሉ አንዳንዴ ማዕበልና ሞገድ ለበዛበት ነፋስ፣ ለተተናኳሽ ሻርኮች፣ ከበረዶ ክምር ጋር ለግጭት፣ ቀደም ብለው ሳይፈተሹ ላለፉት የቴክኒክ ብልሽቶችና በቅርብ ጊዜ ደግሞ ለባህር ላይ ወንበዴዎች ስትጋለጥ እየሰማን ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ከሆነው አደጋ ለመውጣት ወይንም ቀድሞውኑ ላለመጋለጥ ካፒቴኑ፣ ረዳቶቹና ቴክኒሺያኖቹ የበኩላቸውን ጥረት ያደርጋሉ፡፡ የሚጠበቅባቸውን ጥንቃቄ ካላደረጉ ደግሞ ለመዘረፍ፤ እንደ ታይታኒክም ለመስመጥ፣ ከዚያም ባለፈ ለሞት ይዳረጋሉ፡፡
ትዳርም እንዲሁ ነው፡፡ የዕድሜ ልክ ኃላፊነት የምንወስድበት፣ ከተለመደው የግንኙነት አካሄድ በዘለለ ራሳችንን ለገባንበት ትስስር መስዋዕት የምናደርግበት፣ መልካምና አሳዛኝ የሆኑ ክስተቶችን የምናስተናግድበት ረጅም የህይወት ጎዳና ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ ገጠመኞች ለምን ተፈጠሩ? ብለን ብቻ አንቆዝምም፤ ጠዋትና ማታም እያብሰለሰልን ዕድሜያችንን አንገፋም፡፡ ለችግራችን መሰረታዊ የሆነውን መንስኤውን ማወቅ፣ ለገጠመን ጉዳይ እንዴት መመለስ እንደሚገባን ማተኮር ያስፈልገናል፡፡ ይህን ዕውን ለማድረግ ደግሞ ሁለቱ ባለትዳሮች የሚወስዷቸው እርምጃዎች ወሳኞች ናቸው፡፡ ስለዚህ ጥንዶች ትዳራቸውን ሊያወፍሩት፣ ሊያቀጭጩት፣ መልካምና አስደሳች አሊያም በሰቆቃ የተሞላ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
Marrage and facebook
የዛሬው እንግዳችን ጌታቸው የሰላሳ ስድስት ዓመት ጎልማሳ ነው፡፡ ቆንጅዬ ሚስትና የአምስት ዓመት ሴት ህፃን ልጅ አለው፡፡ በሃያዎቹ አጋማሽ ዕድሜው አካባቢ በነበረው የቅድመ ጋብቻ የወሲብ ልምምድ ከቀድሞዋ ጓደኛው የአስር ዓመት ወንድ ልጅ አድርሷል፡፡ ልጁ የሚኖረው ከአያቶቹ ማለትም ከእናቱ ወገኖች ጋር ነው፡፡ ‹‹ባለቤቴ ይህን ከመጋባታችን በፊት ታውቃለች፣ እኔም በተወሰነ ጊዜ እየሄኩ እጠይቀዋለሁ›› ይለናል፡፡
‹‹ይሁንና ባለቤቴ ለሴት ልጃችን በቂ ክብካቤ ሳላደርግ ለወንድ ልጄ ብዙ ትኩረት እንደምሰጥና የተለያዩ ነገሮችን እንድምገዛለት ነገረችኝ፡፡ በትንሽ ነገር ከኔ ጋር መጠላት ጀምራለች፤ አለመግባባት ሲፈጠርም የወንድ ልጄን ጉዳይ ሁሌ ታነሳለች፡፡ የርሱን ጉዳይ ትታው የራሳችንን ህይወት እንድንመራ ብነግራትም ትዳራችን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እየገባ ነው ያለው፡፡ በጣም ተጨንቄያለሁ፡፡ ከርሷ ምንድነው ማድረግ ያለብኝ?›› በማለት ጌታቸው ጠይቆናል፡፡
ወጣትነት ብርታትና ጥንካሬ የሞላበት፣ ብዙ ሰዎች ሊመለሱ ቢናፍቁት የማያገኙት፣ ራሳቸውን ለመለወጥ ቢሞክሩ መሆን የማይችሉበት ብዙ ውጣ ውረዶች ያሉበት በህይወት ዘመናችን የምናሳልፈው ጊዜ ነው፡፡ ወጣትነት ከነችግሮቹ በዕውነት ደስ የሚል የህይወታችን አንዱ ክፍል ነው፡፡ አንዳንዶች በእርግጥም ይህን ዘመን በትኩስ ሃይላቸው ይጠቀሙበታል፤ ሌሎችንም ያገለግሉበታል፤ ራዕያቸውንም እውን ለማድረግ የወደፊቱን መሰረት በማስያዝ የተቻላቸውን ያደርጉበታል፡፡ ሌላው ደግሞ በተባለው እየተመራ፤ መኖር የተፈቀደው ለዛሬ ብቻ ይመስላል፡፡ ነገን ሳይመለከት እንዲሁ በዋል ፈሰስ ወርቃማ ጊዜውን ያባክነዋል፡፡
እንግዲህ ከወንድማችን ጥያቄ መረዳት እንደምንችለው በአንድ ወቅት በነበረው የቅድመ ጋብቻ የወሲብ ልምምድ ልጅ ወለደ፡፡ መልካም አደረገ ባንለውም በወቅቱ ለፈፀመው ወይም ለገጠመው ነገር ምንም ሊያደርግና ሊመልሰው የማይችለው ነገር እንደሆነ ሁላችንም እንረዳለን፡፡ ያ ያለፈው ታሪኩ ነው፤ አንፍቀውም፡፡ ልንፍቀው እንሞክር ብንልም መላጥ፣ ማድማትና ማቁሰል ነው የሚሆንብን፡፡ ስለዚህ… ከሄድን ሁል ጊዜም ቢሆን ሊፈጠር ወይም ሊከሰት የሚችል ነገር እንዳለ ቀድሞውኑ ማሰብ ነው፡፡ አያችሁ በድርጊታችን ልጅ ሳይፈለግ ወደዚህ ምድር ይመጣል፤ ለኤች.አይ.ቪና ሌሎች የአባላዘር በሽታዎች መዳረግ አለ፤ ባልና ሚስት… ከገጽ 8 የዞረ
ከቤተሰብና ጓደኛ መገለል፤ እግዚአብሔርን ማሳዘን ይመጣል፣ ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ ልቦና ችግሮች መጋለጥ ይኖራል፡፡ አያችሁ በወጣትነት ዘመን ሁሌ ቸበርቻቻ የለም፤ አንዳንዴ የሚጎረብጡ ሁኔታዎችንም ማሳለፍ አለ፡፡ አካሄዳችንን ካላስተካከልን፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድም ካላደረግን ደግሞ ዘወትር ልንረሳው የማንችለውን ጠባሳ ነው የምንሸከመው፡፡ ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ የምንመክረው ከጋብቻ በፊት ያለ ማንኛውም ግንኙነት ለቀጣይ ህይወታችን መሰረት የምንገነባበት ጊዜና ወሳኝ ቢሆንም የወሲብ ልምምድ ማድረግ ግን አይጠበቅብንም፤ አይጠቅምም፡፡ ብዙዎቻችን አድርገን አልፈን ይሆናል፤ ግን ገንቢ አልነበሩም፡፡ ለጊዜው ተደስተንባቸው ይሆናል፤ መጨረሻቸው ግን አያምርም፡፡ ሐጢያት ከመሆኑም ባሻገር ዘርፈ ብዙ ለሆኑ ችግሮችና ጭንቀቶች ይዳርጉናል፡፡ ልምምዱን ከጋብቻ በኋላ ለጋብቻና ለትዳር ብቻ ማድረግ ነው፡፡
በጣም የሚገርመው ነገር ያልተፈለገ እርግዝና በሁለቱ ሰዎች ላይ ከሚደርሰው የስሜት ችግርና ማህበራዊ ጫና ባሻገር በተወለደው ልጅ ላይ የሚገጥመው ሚዛናዊ ያልሆነ አስተዳደግ በወደፊት ስብዕናው ላይ ከፍተኛ ችግር ማስከተሉ ነው፡፡ ሰዎች ብዙውን ጊዜ የሚያስቡት የራሳቸውን ጊዜያዊ ችግር ከመቅረፍ እንጂ ሳይፈልግ ወደዚች ምድር በሚያመጡት ልጅ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ችግር አያስተውሉትም፡፡ ይህን በምን መንገድ እንደፈቱት ሊፈቱት እንደሞከሩ ባናውቅም አንድ እውነታ አለ፡፡ ተለያይተው ነው የሚኖሩት፡፡ አባት ሌላ ትዳር መስርቶ በሌላ ዓለም ውስጥ ሲመላለስ ልጅ ደግሞ ከእናቱና ቤተሰቧ ጋር ሌላ ህይወት ይገፋሉ፡፡ ከዚህ የሚከፋው ደግሞ አሁን ባለ ው አዲስ ህይወት ላይ በፊት የተፈጠረው ችግር ከአሁኑ ላይ ሌ ላ ችግርን እየወለደ ትዳርን መበጥበጡ ነው፡፡ እየተረዳችሁን ነው?
ከላይ ያነሳናቸውን መነሻዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት በወንድማችን ትዳር እያንዣበበ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ይበጃሉ የምንላቸው ምክሮች ካነበብናቸውና በህይወታችን ተሞክሮ ካየናቸው ነገሮች በመነሳት የሚከተሉትን አቅርበናል፡፡ (ይሁንና እነዚህ እውነታዎች በሌሎች የባልና ሚስት ጭቅጭቅ ችግሮች ውስጥ መፍትሄ ሊሆኑ እንደሚችሉ መረዳት ያስፈልጋል)
- የችግሩን መንስኤ ማወቅ
በእርግጥ ላለመግባባታችሁ ምክንያት የሆነው የወንድ ልጅህ ጉዳይ ነው ብለህ ታስባለህን? መሸፈኛ ላለመሆኑ ምን ያህል እርግጠኛ ነህ? ተፈጠረ ለምትለውስ ችግርና አለመግባባት ባለቤትህ ሳትሆን አንተ ለችግሩ ያበረከትከውን ነገር እንዳለስ አስበህ ታውቃለህ? አየህ መጀመሪያ እነዚህን መለየትና መሰል ጥያቄዎችን መመለስ የመጀመሪያ ጉዳይህ ሊሆን ነው የሚገባ ህ፡፡ ለዚህ ደግሞ መፍትሄ ሊመጣ የሚችለው መጀመሪያ ከራስህ በኩል ያለውን ስታስተካክልና ስታፀዳ ነው፡፡ ሁሉም ቤቱን ቢያፀዳ አካባቢም ንፁህ ይሆናል እንደሚባለው ነው፡፡
የኛ ችግር ምን መሰለህ? ብዙውን ጊዜ ለችግሮቻችን ሌላው ላይ መቀሰርና ሁኔታዎች ላይ ማላከክ እንጂ የለመድነው ወደራሳችን መልሰን መመልከቱን አናስብም፡፡ እንዲህ አደረጉብ ኝ፤ ይህን ሰጡኝ እንጂ ጉዳዩ ለመከሰቱ የኛ እጅ አለበት፤ የስራ ዬን አገኘሁ አንልም፡፡ በእጃችን ያለውን መፍትሄ ሳንጠቀም ሌላ አዲስ ነገር እንፈልጋለን፡፡ ባለን ሳናመሰግን የሌለንን እንናፍ ቃለን፡፡ ስለዚህ የመጀመሪያው ምክራችን የሚሆነው ከርሷ ጋር ምን ላድርግ ሳይሆን ከኔ በኩል ምን ላድርግ ብለህ ራስህን እንድትጠይቅና ለችግሩ ትክክለኛውን መንስኤ እንድታውቅ ነው፡፡ መቼም ወደህና ፈቅደህ ያለህበትንና ያሳለፍከውን ሁኔታ ተረድታ ነው ያገባችህ የሚል እምነት አለን፡፡
ቃል ኪዳናችሁን አክብሩ
በየትኛውም ስርዓት ተጋቡ ብቻ በሰርጋችሁ ዕለት አንዳችሁ ለሌላኛው ቃል መግባታችሁ አይቀርም፡፡ በተለይ ደግሞ መንፈሳዊ ጋብቻ ሲሆን በእግዚአብር በጉባኤ መካከል የገባችሁትን ቃል ማስታወስ ነው፡፡ ጋብቻ ውስጥ መጎርበጥ ቢኖርም፣ መውደቅ መነሳት ቢፈጠርም ቃል ኪዳናችሁን ማሰብ ተገቢ ይመስለናል፡፡ ስለዚህ ከመጋባታችሁ በፊት ስለልጁ ጉዳይ ከተነጋገራችሁ እንዴት ልታሳድጉት ነበር ያሰባችሁት? ልትረዱትስ ተነጋግራችኋል? የተባባላችሁትን እናንተው ስለምታውቁ ያንን ኃላፊነት በተሰማው መንገድ መጠበቅ ነው፡፡
ልጅህን በፊት አልረዳውም፤ ምንም አላደርግለትም ብለህ ነግረኻት ከሆነና አያቶቹና እናቱ ይበቁታል ብለህ ወደ ትዳር ከገባህ ያንን ማክበር ነው፡፡ እርሷም ምንም ችግር የለም፤ ዋናው ፍቅሩ ነው በውጪ ሆኖ ልትረዳው ትችላለህ ብላህ ከነበረ ቃሏን መጠበቅ ይኖርባታል፡፡ ጠቅልለህ ቤትህ ካስገባሃት ወይም ጠቅላላ ቤት ከገባች በኋላ ባህሪያችሁንና የገባችሁትን ቃል አጥፋችሁ ከሆነ አግባብ ይመሰለንም፡፡
ደግማችሁ በግልፅ ተነጋገሩ
ከላይ የጠቀስነው ነገር ሊሰራ መስሎ ካልታያችሁና፣ ቃላችሁን ማጠፍ ከጀመራችሁ ማድረግ የሚገባችሁ ነገር በጉዳዩ ላይ መነጋገር ነው፡፡ በስሜት ተገፋፍታችሁና የነበራችሁበት ወቅታዊ ፍቅር አርቃችሁ እንዳትመለከቱ ካደረጋችሁ ደግማችሁ በጉዳዩ ላይ በግልፅ መወያየት ነው፡፡ መቼም እንደ ባለአዕምሮ ሰው አትርዳው አትልህም፤ አንተም እርሷ እንዳለችው ከሴት ልጅህ በማስበለጥ እየረዳኸው ካለ አግባብ ነው ለማለት አንደፍርም፡፡ ሁለቱም ልጆችህ ቢሆኑም በአንድ አይነት ማየት አለብኝ ብለህ መሰብ ግን የዋህነት ነው የሚመስለን፡፡ ለዚህም የአብርሃምን ታሪክ ማስታወሱ የምንልህ የበለጠ ይገባሃል የሚል እምነት አለን፡፡
አብርሃም ሚስቱ ሳራ መውለድ ባልቻለችበት ወቅት አገልጋይ ከሆነቻት አጋር ጋር እንዲተኛ ፈቀደችለት፡፡ ኢስማኤል የተባለ ልጅም አገኘ፡፡ ሳራም በእግዚአብሔር ዘንድ መጎብኘትዋ በደረሰ ጊዜ ፀነሰች፣ ይስሃቅንም ወለደች፡፡ ይሁንና ኢስማኤል ከይስሃቅ ጋር እኩል በአባቱ ቤት ያድግ ዘንድና ያለውንም ይካፈል ዘንድ ሳራ ደስተኛ አለነበረችም፡፡ አጋርን ከነልጁ ያሰናብታቸው ዘንድ ጠየቀችው፡፡ አብርሃምም የተባለውን አደረገ፡፡ አብርሃም ልጁን ኢስማኤልን ጠልቶት ይመስልሃል ከአጋር ጋር እንዲሄድ ያደረገው? ከቃልኪዳን ሚስቱ ከሳራ ሀሳብ ጋር በመተባበር አይመስልህምን? የተስፋውን ልጅ ይስሃቅን የመረጠው ዝም ብሎ ይመስልሃልን? አየህ በቃል ኪዳን የተገኘ ለጅና በመወስለት የመጣ አንድ አይደለም፡፡ ከዚህ የምንማረው ነገር ያለ ይመስለናል፡፡
ባለቤትህን አማክር
ሌላው ስለትዳር ሲታሰብ ሁሌ መዘንጋት የሌለብህ ነገር ከጋብቻ በኋላ የኔ የሚባል ነገር የለም፡፡ የእኛ የሚባል አጀንዳ ነው የሚመጣው፡፡ ያንተ ጉዳይ የርሷ ነው፤ የርሷም ደግሞ የአንተ ነው፡፡ ለልጅህ የምታወጣውን ጊዜና ገንዘብ ከባለቤትህ ጋር በመመካከር ሊሆን ይገባል፡፡ አንድ ነገር ማሰብ ያለብህ ልጅህን መርዳትህ ወንጀል ባይሆንም፤ ሄደህ መጎብኘትህንም ማንም ባይጠላውም መርሳት የሌለብህ ነገር ልህንን ልታይ ስትሄድ የቀድሞ ጓደኛህንም የማግኘቱ አጋጣሚ የሰፋ መሆኑ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከባለቤትህ ፈቃድና እውቅና ውጪ ሲዘወተር ሌላ ነገር እንድትጠረጥር ያደርጋታል፡፡ ሰው ነችና ደግሞ ቢሰማት ሊገርምህ አይገባም፡፡ በትዳራችሁ ላይ የወንድ ልጃችሁ ጉዳይ እስከገባ ድረስ የርሱን ነገር ተይው ልትላት አይገባም፡፡ ልጁ እኮ እያነጋገራችሁ ነው? ልጁ እኮ ላለመግባባታችሁ መንስኤ እየሆነ ነው፡፡ የራሳችሁን ኑሮ ለመኖር ከፈለጋችሁ በጋራ ጉዳያችሁ ብቻ ነው ልታተኩሩ የሚገባው፡፡ ግን እውነታውን እንይ ካልን አይደለም ከአብራካችን ስለወጡት ልጆች ከሌላውም ጋር ቢሆን መገናኘታችን፣ መነካካታችን የግድ ይላል፡፡ ደሴት ሆነን ልንኖር አልተጠራንም፡፡ ስለዚህ የርሱን ነገር ትተሽ የራሳችንን ኑሮ ብቻ እንኑር አትበላት፡፡ አማክራት፡፡ ነገሩን በመሸሽ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ልናመጣ አንችልም፡፡ ነገሩን አዳፍነነው በአፈር ሸፋፍነነው ላሁኑ በዚሁ ብናልፍ ዝናብ ሲዘንብበትና ነፋስ ሲመጣበት አግጦ መውጣቱ አይቀርም፡፡
- የእግዚአብሔርን ቃል አጥኑ
ከላይ ያነሳናቸው ጠቃሚ ምክሮች ቢረዷችሁም በትዳራችሁ ዘላቂ የሆነ ውጤት እንድታመጡ ግን ከናፈቃችሁ ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ማሰብ ነው፡፡ ክርስቲያን እንደመሆናችሁ ለማሰብ ከዛም ባለፈ የሚታየ ለውጥ በህይወታችሁ ለማምጣት ቃሉን ማጥናት መልካም ነው እንላለን፡፡ ቃሉ ህይወት አለው፤ መዳን በርሱ በኩል ብቻ እንደሆነ ነው የሚናገረው፡፡ አየህ ቃሉ ውስጥህ ሲገባ ተመሳሳይ ስሜት አይኖርህም፡፡ ስታጠፋ ይወቅስሃል፤ ስታዝን ያፅናናሃል፤ ስትደክም ያበረታሃል፤ ከመንገድ ወጣ ትስትልም ወደ ቀናው ጎዳና ይመልስሃል፡፡
ስለዚህ ይህን ማድረግ በህይወታችሁ ስትለማመዱ እናንተ ስላላችሁ ወይም ልጆቻችሁን ስለተንከባከባችሁ ብቻ በስርዓት ያድጋሉ ማለት እንዳልሆነ ትረዳላችሁ፡፡ አብርሃም ልጁን ከአጋር ጋር ሲሰድ እግዚአብሔር ዝም አላላቸውም፡፡ በሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ይረዳቸው ነበር፡፡ ስለዚህ ቃሉ ሲገባችሁ ልጅህ የመከራከሪያ አጀንዳ፤ ላለመግባባታችሁ መንስኤ አይሆንም፡፡ ያላችሁን ነገር ለአምላካችሁ አሳልፋችሁ መስጠት ትጀምራላችሁ፡፡ የሰጣችሁትንም ይጠብቅና ያሳድግ ዘንድ እርሱ ታማኝ ስለሆነ ቃሉን ዕለት ዕለት ለማጥናት ሞክሩ፡፡
እንግዲህ ይበጃችኋል ብለን ያሰብነውን በተለያየ አቅጣጫ ለመጠቆም ሞከርን፡፡ ለውጥና ፍተሻ ከራስ ነውና የሚጀምረው ስራህን በራስህ እንድትጀምር፤ እንድትመካከሩ፤ በግልፅ እንድትወያዩ ቃል ኪዳናችሁንም በማክበር የአምላካችሁን ቃል ተግባራዊ እንድታደርጉ አውግተናል፡፡ እኛ እንግዲህ መጠቆምና አቅጣጫ ማሳየት እንጂ ተሳታፊዎቹ እናንተው የችግሩ ባለቤቶች ስለሆናችሁ ከዚህ በላይ ልንሄድ አንችልም፡፡ ሁሉን የሚችለው አንድዬ እርሱው ይርዳችሁ፡፡ ለዛሬ አበቃን፡፡ ቸር እንሰንብት!


መንግስት በአዲስ አበባ ኤርፖርት ሁለት ተቀጣጣይ ሲሊንደሮች አገኘሁ አለ

0
0

addis ababa airport
(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ መንግስት የደህነነት መስሪያ ቤት ባለፈው እሁድ ኦገስት 11 ቀን 2013 በአዲስ አበባ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሁለት ተቀጣጣይ ባዕድ እቃ የያዙ ሁለት ሲሊንደሮች መገኘታቸውን አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግስት የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል በመንግስት ሚዲያዎች ላይ ባሰራጩት ዜና እንደገለጹት ሲሊንደሮቹ በአውሮፕላን ማረፊያው የመንገደኞች መነሻ አከባቢ እንደሚገኙ ጥቆማ ያደረሱት የፅዳት ሰራተኞች ናቸው ብሏል።
የመንግስት ሚድያዎች እንደዘገቡት የፈንጂ አምካኝ ባለሙያዎች ሲሊንደሮቹ ተቀጣጣይና በቀላሉ በእሳት በመያያዝ ጉዳት ማድረስ የሚችሉ መሆናቸውን መረጋገጡን እና ሲሊንደሮቹ የያዙት ተቀጣጣይ ንጥረ ነገር ባህሪም እየተጣራ ነው።

መንግስት ይህን ተቀጣጣይ ሲሊንደር በአዲስ አበባ ኤርፖርት ማን እንዳስቀመጠው ባይገልጽም አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ግን መንግስት ከዚህ ቀደም ካለው ባህሪ አኳያ ራሱ ሲሊንደሩን አስቀመጦ በአንድ ድርጅት ላይ ለማላከክ ነው ይላሉ። አስተያየት ሰጪዎቹ ጨምረውም ከዚህ ቀደም መንግስት ኦነግን ለማስጠላት የትግራይ ሆቴልን ጨምሮ የተለያዩ ቦታዎችን በማፈንዳት ኦነግን በአሸባሪነት መፈረጁን፣ ይህን ሆቴል አፈነዱ ተብለው በቴሌቭዥን የቀረቡት ሰዎች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በሌላ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መገነታቸውን፤ በግንቦት 7 ላይም አኬልዳማ ድራማን ለመሥራት የጠቀመውን በማስታወስ አሁን በአዲስ አበባ ኤርፖርት ተቀመጠ የተባለውን ተቀጣጣይ ሲሊንደር ከመንግስት ውጭ ሌላ ሰው ያደርገዋል የሚል እምነት እንደሌላቸው አስታወቀዋል።

“ኢሕአዴግ ፖለቲካውን የሚመራው በዕዝ ነው እንጂ በሃሳብ የበላይነት አይደለም”–አቶ ሃብታሙ አያሌው

0
0

አቶ ሃብታሙ አያሌው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባልና ምክትል የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ ነው፡፡ወደ ፖለቲካው ዓለም የገባው በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት በማስተማር አገልግሎት ተጠምዶ ሳለ አንድ ችግር ይነሳና ቤተክርስቲያኑ በሚገኝበት ቀበሌ በአስተዳደሩ ይጠራል፡፡በቀበሌው የተገኘው ሃብታሙ የተፈጠረውን ችግር ያብራራበት መንገድ በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን የሆኑ ግለሰብን ይማርካል፡፡ግለሰቡ ከስብሰባው በኋላ ሃብታሙን በመቅረብ በቅርቡ የሚመሰረት አንድ ነጻ የወጣት ማህበር ስላለ በዚያ የምስረታ በዓል ላይ እንዲገኝ ያግባባዋል፡፡መንፈሳዊው ሃብታሙም በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ አጀንዳውን መንፈሳዊ ህይወት ባላደረገ ማህበር ምስረታ ላይ ይታደማል፣በዚያው ዕለትም ስሙ ተጠቁሞ ይመረጣል፡፡ ዳዊት ሰለሞን ከገዢው ፓርቲ ጋር በቅርበት በመስራት በአሁኑ ሰዓት ገዢውን ፓርቲ እየታገለ የሚገኘውን ሃብታሙን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዩች አነጋግሮታል፡፡
habtamu
ላይፍ — አምላክን ከማገልገል ህይወት ወደ ፖለቲካ የመምጣት ውሳኔን ማሳለፍ ምን ያህል አስቸጋሪ ነበር ?
ሃብታሙ—ፖለቲካ እውቀት ብቻ ሳይሆን ስብዕናን ይፈልጋል፡፡ፖለቲካን ከሃይማኖት የሚለየው ምድራዊ መሆኑ ነው፡፡ሃይማኖት ለመንፈሳዊ በረከት የምትሰራበት ከሞት በኋላ ስላለ ህይወት በአብዛኛው የምትኖረው ነው፡፡ሃይማኖት የሚፈልገው ስብዕና ይህ ስብዕና ውሸትን መጠየፍ፣እውነትን መከተልና ለተበደለው መጮህን የሚይዝ ነው፡፡ፖለቲካውም ይህንን ይፈልጋል፡፡እርግጥ ነው ፖለቲካው ከስብዕና በተጨማሪ እውቀትን ይፈልጋል፡፡ነገር ግን ይህንን ክፍተት መሙላት ይቻላል፡፡በሃይማኖት ቤቶች ፖለቲካውን የአለማዊ ሰው መገለጫ በማድረግ የመመልከት አዝማሚያ አለ ይህ ግን መለወጥ መቻል አለበት፡፡ፈሪሃ እግዚአብሄር ያላቸው ሰዎች ወደ ፖለቲካው መምጣት እንደሚገባቸው አምናለሁ፡፡
ላይፍ — ወደ ማህበሩ ከመጣህና በአመራርነት ከተመረጥክ በኋላ ምን ተፈጠረ ?
ሃብታሙ — የአዲስ አበባ ፎረም ሲመሰረት የሄድኩት ከአንድ ጓደኞዬ ጋር ነበር፡፡አንድ የማላውቀው ሰው ስሜን ጠርቶ በአመራርነት እንድመረጥ ጠቆመኝ፡፡እኔ ግን ምንም ልምድ እንደሌለኝ በመግለጽ ጥቆማውን ለመቃውም ሞከርኩ፡፡መጀመሪያ የጠቆመኝን ሰው ከአመታት በኋላ አግኝቼው ካድሬዎች እኔን እንዲጠቁም ስላዘዙት እንደጠቆመኝ ነግሮኛል፡፡ጥቆማውን እንድቀበል በዚያ የነበሩ ሰዎች ግፊት ስላሳደሩብኝም ተመረጥኩ፡፡ከዚያም የማህበሩ የክፍለ ከተማው ምክትል ሰብሳቢ ሆኚ ተመረጥኩ ብዙም ሳይቆይ የአዲስ አበባ የፎረም ሰብሳቢ ተደረግኩ፡፡በመለጠቅም ዘጠኝ አደረጃጀቶች ማለትም የአዲስ አበባ ወጣት ፎረም፣የኢህአዴግ ሊግና ሌሎች ማህበራት የመሰረቱት ፌደሬሽን ፕሬዘዳንት ሆኜ ተመረጥኩ፡፡ከመንግስት በደረሰኝ ደብዳቤም የሕዝብ ግኑኝነት ሆኜ እንድሰራ ተደረግኩ፡፡ነገር ግን በዚህ መንገድ ከሁለት አመት በላይ መቀጠል አልቻልኩም፡፡
ላይፍ — ምንድን ነው በዚህ መንገድ እንዳትቀጥል ያደረገህ?
ሃብታሙ — ፌደሬሽኑም ሆነ የወጣቶች ፎረም ሲመሰረት ኢህአዴግ በነጻነታቸው ዙሪያ ምንም ጥያቄ አላነሳም፡፡ነገር ግን ቀስ በቀስ ማህበራቱን በካድሬ ትዕዛዝ ለመምራት መንቀሳቀስ ተጀመረ፡፡በዚህ ላይ ማህበራቱ መቶ በመቶ በጀታቸውን የሚያኙት በመንግሰት መሆኑም በነጻነታቸው ዙሪያ ጥያቄ ያስነሳል፡፡የሲቪክ ማህበራት በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርጋቸው የህግ ድንጋጌ ቢኖርም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ከዚህ ወጣ ያለ ነው፡፡እኔም ሆንኩ ሌሎች ወጣቶች አንዲህ መሆኑን በግልጽ ስንቃወም ቆይተናል፡፡በመጨረሻ ግን የነበረውን ነገር በውስጥ ትግል መለወጥ እንደማይቻል ስገነዘብ ለቅቄ ወጥቻለሁ፡፡
ላይፍ — በፎረምና በፌደሬሽኑ ውስጥ የነበረህን ከፍተኛ ሃላፊነት ከለቀቅክ በኋላ ባለ ራዕይ ወጣቶች ማህበርን መስርተሃል፡፡ማህበሩን ለመመስረት መነሻ የሆነ ምክንያት ምንድን ነው?
ሃብታሙ — አንድ ነገር ማስታወስ እፈልጋለሁ በሃላፊነት በነበርኩባቸው ወቅቶች ዘወትር ይነሱ የነበሩ ክርክሮች ‹‹አንተ ከኢህአዴግ ጋር እየሰራህ እንዴት ማህበራት ነጻ መሆን አለባቸው ትላለህ? ይህንን የምትለው በኢህአዴግ ስለማታምን ነው ይሉኝ ነበር፡፡ሃሳቤን ለማስለወጥም ብዙዎች ሽምግልና እስከመቀመጥ ደርሰው ነበር፡፡ባለ ራዕይ ማህበርን ለመመስረት ያበቃን በኢትዩጵያ ውስጥ ለማንም ወገንተኛ ያልሆነ ሲቪክ ማህበር መኖር አለበት የሚል አቋም ያለን ወጣቶች በተለያዩ አጋጣሚዎች መገናኘት በመቻላችን ነው፡፡
ላይፍ — ከገዢው ፓርቲ በመለየትና ታገኘው የነበረን ጥቅማ ጥቅም በመተው ‹‹በቃኝ ››የሚል ውሳኔን መሳለፍ ከባድ ምርጫ አልነበረም ?
ሃብታሙ — ኢህአዴግ ቤት እያለሁ ወፍራም ደሞዝ ነበረኝ ፣መኪና ተመድቦልኝ የተለያዩ አበሎች ይከፈሉኝ ነበር፡፡ስልጣን በራሱ የሚፈጥረው ወዳጅም አለ፡፡በሆድ ለሚያስብ ሰው እኔ ከነበርኩበት ሁኔታ መውጣት አስቸጋሪ ነው፡፡እኔ ግን ህሊናዬ ላልፈቀደው ነገር በሆዴ እየተደለልኩ መኖር የምችል ሰው ባለመሆኔ የምመራውን ህይወት በህሊና ለመለወጥ አልተቸገርኩም፡፡ በርካታ ዜጎች በችግር እየተቆራመዱ ለስደት ሲጋለጡ እያየሁ እኔን ተመችቶኛልና ስለ ሌላው ምንም አያገባኝም ለማለት አልደፈርኩም፡፡ኢህአዴግ ለተቃዋሚዎች ምን እንደሚያስብም አውቃለሁ ነገር ግን ያንን ኢህአዴግ ለተቃዋሚዎቹ ያዘጋጀውን ጽዋ መጠጣት ለእኔ ክብር እንደሆነ በማሰቤም በቃኝ ለማለት እንዳልቸገር አድርጎኛል፡፡
ላይፍ — ወደ ተቃዋሚው ጎራ ስትመጣ በዚያ ያሉ ሰዎች ከኢህአዴግ ጋር የነበረኝን ቆይታ ስለሚያውቁ ሊያምኑኝ አይችሉም የሚል ስጋት አላደረብህም ?
ሃብታሙ — በእርግጥ የአገራችን የፖለቲካ አስተሳሰብ የሚገኝበት ደረጃ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ነገሮች አስቸጋሪ ይሆናሉ፡፡ከገዢው ፓርቲም ሆነ ከተቃዋሚነት ወደ ኢህአዴግነት ለሚሄዱ ሰዎች ሁኔታዎች ቀላል አይሆኑም፡፡በሁሉም ወገን በጥርጣሬ የመታየት ዕድል ሰፊ ነው፡፡በእኛ አገር የአንድ ፓርቲ አባል ከሆንክ እስከ ዕለተ ሞትህ የዛ ፓርቲ ወይም አስተሳሰብ አካል እንደሆንክ እንደምትቀጥል ይጠበቃል፡፡ለምሳሌ ኢህአዴግ ቤት ሃሳብ በመሸጥ መቀጠል አይቻልም፡፡በኢህአዴግ ውስጥ ኢህአዴግን በሃሳብ መታገል አይቻልም፡፡ፖለቲካውን የሚመራው በዕዝ ነው እንጂ በሃሳብ የበላይነት አይደለም፡፡በእንዲህ አይነት በዕዝ ሰንሰለት በሚመራ ድርጅት ውስጥ መቆየት ደግሞ የማይታሰብ በመሆኑ የተቃውሞውን ጎራ ለመቀላቀል አብቅቶኛል፡፡
ላይፍ — ኢህአዴግ ቤት በነበርክባቸው ወቅቶች ያፈራሃቸው ጓደኞች አሁን የቀድሞውን መስመር ስትቃወም ሲመለከቱ ምን ይሉሃል?
ሃብታሙ — እኔ ወደ ህዝብ የምሄደው እኔን ብቻ አድምጠኝ ለማለት አይደለም፡፡በግሌ በፊትም ይሁን በቀጣይ የሚኖሩኝ ወይም የነበሩኝ ጓደኞች አቋም እንዳለው ሰው እንዲያስቡኝ እፈልጋለሁ፡፡እስካሁንም ያለው ነገር ይህ ነው፡፡ኢህአዴግን የተውኩትና አንድነትን የተቀላቀልኩትም የአቋም ልዩነት ነው፡፡በአንድነት ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎችን በማግኘቴ ለውጥ እናመጣለን የሚል እምነት በመሰነቄ እየታገል እገኛለሁ፡፡
ላይፍ — ተቃዋሚዎችን በመቀላቀልህና ኢህአዴግን በመታገልህ የደረሰብህ ችግር የለም?
ሃብታሙ — እውነቱን ለመናገር ችግር የለም ማለት አይቻልም፡፡ችግር ብቻ ሳይሆን የተከተልኩት መስመር የህይወት መስዋዕትነትን ጭምር የሚጠይቅ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ገዢው ፓርቲ የምበላውን አጥቼ እንድንበረከክ በመፈለግ ያሸነፍኳቸውን ጨረታዎች እንኳን እንዳላገኝና በዜግነቴ ሰርቼ እንዳልኖር እያደረገ ይገኛል፡፡ይህንን የሚያደርገው ግን ኢትዩጵያዊያንን ካለማወቅ በመሆኑ አልገረምም፡፡ኢትዩጵያዊ ክብሩን የሚጠብቅና ለፍርፋሬ ሲል ማተቡን የማይበጥስ ነው፡፡
ላይፍ — ወደ ፓርቲው ህዝባዊ ንቅናቄ እንምጣ ፣አንድነት እያደረገው የሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባ ሌላ ፓርቲ በቅርቡ ማድረጉን ተከትሎ በኩረጃ መልክ እየተደረገ የሚገኝ ነው ወይስ በጥናት ነው?
ሃብታሙ — ማንንም አልኮረጅንም ፣እያደረግነው የምንገኘው እንቅስቃሴ በስትራቴጂክ መጽሀፋችን ቀደም ብሎ የሰፈረ ነው፡፡ስለዚህ እየሰራን የምንገኘው በእቅዳችን መሰረት ነው፡፡ዞሮ ዞሮ ማንም አደረገው ማን የተደረገው ነገር የአገሪቱን ፖለቲካ አንድ እርምጃ ከገፋው ጥቅሙ የሁላችን በመሆኑ ጀማሪው እከሌ ነው አይደለም የሚለው ነገር አስጨናቂ አይሆንም፡፡አንድነት በዚህች አገር ለውጥ እንዲመጣ ያቅማቸውን ላበረከቱና እያበረከቱ ለሚገኙ ሁሉ እውቅና ይሰጣል፡፡በደፈናው ባለፉት አርባ አመታት ምንም አስተዋእጾ አልተበረከተም የሚል ድምዳሜ ላይ ፓርቲያችን አይደርስም፡፡እነ ፕሮፌሰር አስራትን ጨምሮ በዙ ሺህዎች ለዚህች አገር የህይወት መስዋዕትነትን ከፍለዋል፡፡ለዚህ እውቅና መቸር ይገባናል፡፡እውንት ለመናገር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የህዝብን አይን የገፈፉት በታዲዩስ ታንቱ የሚመራው የአገር ወዳድ ኢትዩጵያዊያን ማህበር ነው፡፡ለግራዚያኒ ሃውልት እንዲቆምለት መወሰኑን በመቃወም ሰልፍ እንዲጠራ ያነሳሱት እን ታዲዩስ ናቸው፡፡ለዚህ ተገቢውን አክብሮት ሊቸራቸው የሚገባ ቢሆንም ሌሎች መድረኩን በመቆጣጠር የማይገባቸውን ውዳሴ ለመሸመት ተንቀሳቅሰውበታል፡፡በሃይል በተቀለበሰው ሰላማዊ ሰልፍ ከአርባ በላይ አባላቶቹ የታሰሩበት ባለ ራዕይ ማህበርም ከሰላማዊ ሰልፉ አዘጋጆች አንዱ ነበር፡፡
ላይፍ — መስከረም አምስት አንድነት በአዲስ አበባ ለማድረግ ያቀደውን ሰልፍ የአንድ ፓርቲ ሊቀመንበር‹‹አንድነት ይህንን ሰልፍ የጠራው እነ አንዷለም የታሰሩበትን ቀን ለማክበር ነው፣እኛ ግን ሰልፍ የምንወጣው እነ አንዷለም እንዲፈቱ ነው ››ብለዋል፡፡እስኪ የሰልፉን አላማ ንገረኝ?
ሃብታሙ — (ረዥም ሳቅ)ፖለቲካ እንግዲህ እንደተርጓሚው ነው፡፡ይህ አስተሳሰብ ተገቢ ባይሆንም አስተሳሰቡ ግን የመደመጥ ዕድል ማግኘት እንደሚገባው ይሰማኛል፡፡ግለሰቡ እንዲህ የሚያስቡ ከሆነ ማድረግ የሚጠበቅብን አስተሳሰባቸውን እንዲያሳድጉ መርዳት ነው፡፡ለኢትዩጵያ ፖለቲካ የሚጠቅም አስተሳሰብ ባለመሆኑም የራስን ገጽታ ለመገንባት የሌሎችን መልክ ማቆሸሽ ቅንነት የጎደለው ድርጊት ነው፡፡በግሌ ይህንን የተናገሩት አቶይልቃል አንድ ሰልፍ በመጥራት ስማቸው በየቦታው መነሳት በመጀመሩ ስካር ውስጥ የገቡ ይመስለኛል፡፡ኢትዩጵያ ውስጥ ፓርቲ አለ ብዬ አላምንም ማለትና በመድረክና በአንድነት ውስጥ ለጊዜው ተፈጠረ የተባለውን ልዮነት በማራገብ እየተባሉ ነው ማለት እንዴት አይነት ፖለቲካ እንደሆነ አይገባኝም፡፡እዚህ አገር ፓርቲ የለም ብሎ የሚያምን ፓርቲ በምን ስሌት ከሰላሳ ሶስት ፓርቲዎች ጋር በትብብር ለመስራት መፈራረሙ አስገራሚ ነው፡፡የሉም ካሉ እንዴት አብረው ሊሰሩ ፈረሙ፡፡ኢህአዴግም እኮ የሚለው ይህንኑ ነው አኔ ከሌለው ይህች አገር ትጠፋለች የሚለው ፓርቲዎች አሉ በማለት ስለማያምን ነው፡፡ይህንን ጥያቄ ስላነሳህው ልመልሰው እንጂ ዝሆን የሚያባርር ለወፍ ድንጋይ አይወረውርም፡፡እኛን እንቅልፍ የሚነሳን የአገራችን ጉዳይ ነው፡፡እንዴት ይህንን አምባገነን ስርዓት እንለውጣለን የሚለው ያስጨንቀናል እንጂ የቃላት እሰጥ ገባ ውስጥ በመግባት ጊዜ ማባከን አንፈልግም፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ፍርዱን እንደሚሰጥ በግሌ አምናለሁ፡፡
ላይፍ –ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየተሯሯጡ ነው፡፡እነዚህ የፖለቲካ ሃይሎች ከዚህ ድርጊታቸው ካልተቆጠቡ እርምጃ እንወስዳለን በማለት ዝተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስም ባይጠሩም ይህ ማስጠንቀቂያ በዋናነት አንድነትን የሚመለከት አይመስልህም?
ሃብታሙ –ኢህአዴግ ሲጨነቅ የሚናገራቸው ነገሮች ፍጹም የማይገናኙ ናቸው፡፡አቶ ሃይለማርያም በምንና እንዴት መታገል እንደሚገባን ሊያዙን ወይም የምንታገልባቸውን ነገሮች እየቆነጠሩ ሊሰጡን አይችሉም፡፡እኛንና እሳቸውን የሚዳኘን የአገሪቱ ህግ ነው፡፡ስልጣን ስለያዙ ለህገ መንግስቱ ቅርብ ናቸው አያስብልም፡፡እኛም የህገ መንግስት ጥሰት እየተፈጸመ ነው በማለት እየከሰስን ነው፡፡ነጻ የፍትህ ስርዓት ቢኖር ማን ህጉን እንደጣሰም በግልጽ ይታይ ነበር፡፡ለማንኛውም ግን ሙስሊም ወገኖቻችን ያነሱት ጥያቄ የሃይል ሳይሆን ስልጡን ምላሽ እንዲሰጠው ከመጠየቅ ወደ ኋላ አንልም፡፡በማስፈራሪያው በመሸማቀቅ ለወገኖቻችን አጋርነታችንን ከማሳየት እንደማንቦዝንም መታወቅ አለበት፡፡

ሰላም ምንድነው? (ታደሰ ብሩ)

0
0

Ethiopian Flag
ከታደሰ ብሩ

1. መንደርደሪያ

የወያኔ ሰዎች ጋር የፓለቲካ ሙግት መሰል ነገር ከገጠማቸው ውይይቱን ያለ ጥርጥር የሚረቱበት ወደሚመስላቸው ወደ “ሰላም” ጉዳይ ይስቡታል። ከዚያም አገራችን ለዘመናት ሰላም የራቃት የነበረ መሆኑን ያስቷውሷችሁና “እድሜ ለኢሕአዴግ ይኸው የሰላም አየር እየተነፈስን ነው” ይሏችኋል። ንግግራቸውን የመቀጠል እድል ካገኙ መረር ብለው “ነገር ግን ፀረ-ሰላም ኃይሎች አልተኙልንም። በሰሜን፣ በምሥራቅ፣ በአገር ውስጥ፣ በዲያስፓራ ….” እያሉ የፀረ-ሰላም ኃይሎች ረዥም ዝርዝር ያቀርቡላችኋል።

የእርስዎ ጭንቅላት “ድልድይ እያፈረሰ አዲስ አበባ የገባ ድርጅት ስለ ሰላም ለመስበክና ሌሎቹን በአሸባሪነት ለመክሰስ እንዴት ልብ አገኘ?” በሚል ጥያቄ ተጠምዶ ሊሆን ይችላል።

ወያኔ ወዳጅዎ ግን እርቆ ሄዷል “አንተም የፀረ-ሰላም ኃይሎች መጠቀሚያ ሆነሃል፤ ከዚህ ተግባርህ ብትታቀብ ይሻልሃል። ዓለም ዓቀፍ መስፈርት ያሟላ የማያፈናፍን የፀረ-ሽብር ሕግ አለን” …. እያለ ይቀጥላል። በሰላም ስም ሰላምዎን አድፍርሶት ይውላል።

በወያኔ ቴሌቪዥንና ራድዮ የሚተላለፉ ቃላት ብዛት ስታትስቲክስ ቢኖር ኖሮ “ሰላማችን” አንደኛ ይወጣ ነበር ይሆናል። ምናልባት አንደኝነት ካጣ ደግሞ “በልማታችን” ተበልጦ ሁለተኛ ይወጣ ነበር።

በሰላም ስም ማጭበርበር የተጀመረው ዛሬ አይደለም። አዶልፍ ሂትለር የቼክ ሪፑብሊክን ከመውረሩ በፊት አስገራሚ የሰላም ጥሪ አድርጎ ነበር፤ ሩሲያን ከመወረሩ በፊት ደግሞ የሰላም ውል ተፈራርሞ ነበር። በአንድ ወቅት የሶማሊያው ዚያድ ባሬ መቋድሾ ውስጥ ታላቅ የሰላም ሰልፍ መርቷል። ከዩጋንዳው ማርሻል ኢዲአሚን ዳዳ በርካታ ኒሻኖች አንዱ “የእንግሊዝ የሰላም ኒሻን” የሚባለው ነው። ሆኖም ግን ከላይ የተጠቀሱ ሰዎች የሚታወቁት በሰላምተኝነታቸው አይደለም። ልክ እንደእነሱ ሁሉ የኛዎቹም ወያኔዎች ለሰላም ከእኔ ወዲያ ላሳር ቢሉ አይግረመን።

ለመሆኑ “ሰላም” ምንድነው?

እኔ ይህን ይህንን ጥያቄ ለራሴ ካነሳሁ ከሀያ ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል። የዛሬ 23 ዓመታት ገደማ ከፃፍኩት የተማሪነት ጊዜዬ ረዥም ግጥም ውስጥ ሶስት አንጓዎችን ብቻ ልጋብዝዎት።

ሰላም

ሰላም !!!!!

አንዱ ለፀሎተ ውዳሴው

ሌላው ለፍሬከርስኪ ጉባዬው

ደሞ ሌላው … ለነገር ማጣፈጫ

ለፈራጅ አዕምሮ ማቀጨጫ

ለአምባ-ገነን ሥልጣን መጨበጫ

ስንቱ ለከንቱ በከንቱ ያነሳሻል

አንስቶ …. ክቦ … ክቦ … ይጥልሻል

ከልጅነቴ ጀምሮ የምሰማት

ልጅ፣ ሽማግሌው የሚወዳት

የማትለወጥ ጣፋጭ ቃል

“ሰላም” የምትባል

ትርጉሟ ጠፍቶብኛል

እባካችሁ የገባችሁ አስረዱኝ

ሰላም ምንድን ናት ንገሩኝ።

በኢራን፣ በኢራቅ፣ በጋዛ ሠርጥ፣ ካምፑቺያ

ኒኳራጓ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ናምቢያ

በሰሜን ሕንድ ፣ በአፍጋኒስታን፣ በኢትዮጵያ

ያለሽ እናት፣ ያለህ ወገን

ያለህ ሕፃን

ሰላም ምን ማለት ነው ንገረኝ

ዋጋዋ ምን ያህል ነው አስረዳኝ

አንተም የአውሮፓው ሰው ንገረኝ

ስንት ነብስ፤ ስንት ሀብት፤ ስንት ጥይት ነው

ሰላምን ገዝቶ ለማቆየት ‘ሚከፈለው?

ሕዳር 1982

2. ሰላም ምን ማለት ነው?

ከላይ ቅንጫቢውን ብቻ ያቀረብኩት ረዥም መራር ግጥም ከፃፍኩ 23 ዓመታት ተቆጥረዋል። ከዚያ ወዲህ የፓለቲካ ሥርዓት ተቀይሯልጥያቄው ግን ከያኔው ይበልጥ ዛሬ አንገብጋቢ ሆኗል።

እውን ሰላም ምን ማለት ነው?

በጣም አጭርና ግልጽ የሆነ ትርጓሜ በመስጠት ልጀምር፤

ሰላም ማለት የሁከት (violence) አለመኖር ማለት ነው።

ይህ ትርጓሜ ትክክል ቢሆንም እዚህ ላይ መቆም ግን ነገር ማድበስበስ ነው።

የሚከተሉትን ሁለት ምሳሌዎችን ያጢኗቸው።

1. ማጅራት መቺዎች የበዙበት መንደር ውስጥ ሁከት እንጂ ሰላም የለም። ቶሎሳ ማጅራት መቺዎች የበዙበት መንደር ነዋሪ ነው፤ እናም በሰላም እጦት ኑሮውን በስጋትና በሰቀቀን እንዲያሳልፍ ተገዷል። ቶሎሳ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የመንደሩ ነዋሪዎች ሰላማቸው ተናግቷል።

2. “ረዥሞ” የተባለው ሰፈር አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች ረዣዥሞች ሲሆኑ አጭር ሰው አይወዱም። ሆኖም ግን ተፈጥሮ “ጠማባቸው” አጭር አድርጋ የፈጠረቻቸው ጥቂት ሰዎች ረዥሞ ሰፈር ውስጥ ይኖራሉ። እነዚህ ሰዎች በሚደርስባቸው መድልዖ፣ ማንጓጠጥና ማግለል ምክንያት ሰላማቸው ተናግቶ ኑሮዓቸውን በምሬት፣ በስጋትና በሰቀቀን እንዲያሳልፉ ተገደዋል። ጠንክር ይህንን የስጋትና የሰቀቀን ኑሮ በረዥሞ መንደር የሚገፋ ቁመተ አጭር ሰው ነው።

ቶሎሳና ጠንክር ሰላም የራቃቸው ሰዎች ናቸው። የሁለቱ የሰላም እጦት ምክንያት ግን ለየቅል ነው። የቶሎሳው ቀጥታና ግልጽ ጥቃት ሲሆን የጠንክር ግን ውስብስና መዋቅራዊ ነው። መፍትሔዎቻቸውም ለየቅል ናቸው። የቶሎሳን ችግር ዘበኛ ወይም ጠባቂ በመቅጠር መወጣት ይቻላል። የጠንክርን ችግር ለመፍታት ግን የሥርዓትና የአስተሳሰብ ለውጥ ይፈልጋል።

ሰዎች በማጅራት መቺዎች በሚዘረፉበት ከተማ ውስጥ ሰላም የሌለ መሆኑን ማሳመን ቀላል ነው። ሰዎች በመንግሥት በሚዘረፉበት ከተማ ውስጥ ሰላም የሌለ መሆኑ ማሳመን ግን የዚያን ያህል ቀላል ላይሆን ይችላል። የመንግሥት ዘረፋ እንደ ግለሰብ ዘረፋ ቀጥተኛና ግልጽ አይደለም። መንግሥት ሲዘርፍ ማጅራት መቺዎችን ማሠማራት ላያስፈልገው ይችላል። መንግሥት ኢፍትሃዊ ታክስ በመጫን ዘረፋውን ሕጋዊ ሊያደርገው ይችላል። የመንግሥት ዘረፋ በግልጽ ላይታይ ይችላል፤ ቀስ እያለ እየተብላላ ቆይቶ ሲፈነዳ ግን ውጤቱ አንድ ወይም ሁለት ማጅራት መቺዎችን ለፍርድ ከማቅረብ ጋር የሚመሳሰል አይደለም።

ከላይ ከቀረቡት ምሳሌዎች ሁለት ዓይነት ሰላሞች መኖራቸውን መገንዘብ እንችላለን። እነዚህ ሁለት ዓይነት ሰላሞች አሉታዊ ሰላም እና አዎንታዊ ሰላም ተብለው ይጠራሉ።

1. አሉታዊ ሰላም (Negative Peace) – አሉታዊ ሰላም በግለሰብ ወይም በቤተሰብ ላይ ግልጽ ሁከት (Direct Violence) ያለመኖር ውጤት ነው።

በሰዎች ሕይወት ወይም ንብረት ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ሲፈፀም ግልጽ ሁከት ተፈፀመ ይባላል። ለምሳሌ፣ ጦርነት በሰውም በንብረትም ላይ ቀጥተኛ ጥቃት የሚያደርስ በመሆኑ ግልጽ ሁከት ነው። ዝርፊያና ቅሚያም ግልጽ ሁከቶች ናቸው። ግልጽ ሁከት ከሌለ ዘራፊዎች፣ ኪስ አውላቂዎች፣ ወመኔዎች፣ ልጃገረዶችን የሚደፍሩ ምግባረ ብልሹዎች የሉም ማለት ነውና ሰዎች በሰላም ወጥተው በሰላም ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።

በግልጽ ሁከት መወገድ ሳቢያ የሚገኘው ሰላም “አሉታዊ ሰላም” ይባላል። አሉታዊ ሰላም ሲኖር “ሁሉ አማን” የሆነ ሊመስል ይችላል ሆኖም ሁከቱን እንጂ የሁከቱን ሥረ ምክንያት ስለማያስቀረው ወደፊት ሁከት የመነሳት እድሉ ከፍተኛ ነው።

2. አዎንታዊ ሰላም (Positive Peace) – አዎንታዊ ሰላም የመዋቅራዊ ሁከት[1] (structural vilolence) ያለመኖር ውጤት ነው።

መዋቅራዊ ሁከት በአድሎዓዊ ሥርዓት ሳቢያ የሚደረግ ተቋማዊ ጥቃትን ይመለከታል። ዘረኛ ፓሊሲ ለምሳሌ አንዱ ዘር ሌሎቹን እንዲያጠቃ መንገድ የሚያመቻች በመሆኑ ተቋማዊ ሁከትን ይፈጥራል። ወንዶች በሴቶች ላይ የበላይነት እንዲኖራቸው ሥርዓቱ የሚፈቅድ ከሆነ ውጤቱ በሴቶች ላይ የሚደርስ ተቋማዊ ጥቃት ነው። በተዛባ የሀብት ክፍፍል ሳቢያ የሚመጣ ድህነት የመዋቅራዊ ሁከት ውጤት ነው። የፍትህ መዛባት፣ ግዙፍ ሙስናዎች (Grand Corruption)፣ በሥልጣን መባለጎች የመዋቅራዊ ሁከት ውጤቶች ናቸው። ማይምነትም ቢሆን በአብዛኛው የመዋቅራዊ ሁከት ውጤት ነው።

በመዋቅራዊ ሁከት መወገድ ምክንያት የሚገኝ ሰላም “አዎንታዊ ሰላም” ይባላል። በሌላ አነጋገር አዎንታዊ ሰላም የሚሰፍነው ማኅበራዊ ፍትህ ሲሰፍን ነው። አዎንታዊ ሰላም ሲኖር ሰዎች ችግሮቻቸውን በድርድር ይፈታሉ። አዎንታዊ ሰላም በማኅበራዊ ቡድኖች መካከል ቀና የሆነ መስተጋብር መኖሩ አመልካች ነው።

3. አሉታዊ ሰላም እና አምባ-ገነን አገዛዞች

በአንድ አገር ውስጥ አዎንታዊ ሰላም አለ ማለት በዜጎች መካከል መዋቅራዊ መድልዎ አይደረግም ማለት ነው። አዎንታዊ ሰላም የሰፈነበት አገር ሕዝብ ከራሱ ጋር የታረቀ ነው። በዚህ አገር ውስጥ ለዘላቂ ሰላም አስተማማኝ መሠረት ተጥሏል ብለን አፋችንን ሞልተን መናገር እንችላለን። ይህ ማለት ግን አንድ ሰካራም ሌላውን የሚፈነክትበት አጋጣሚ የለም ማለት አይደለም። ፈጽሞ ግጭቶች አይነሱም ማለትም አይደለም። እንዲያውም በየጊዜው ሰልፎችና ተቃዉሞዎች በአደባባይ የሚሰሙበት ግርግር የበዛበት አገር ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን አለመግባባቶች ቢነሱ መፍትሔ የሚያገኙበት አሠራር አለ። አዎንታዊ ሰላም ችግሮች ሲፈጠሩ መፍትሔ እየፈለገላቸው ራሱን ጠብቆ የሚያቆይ ሰላም ነው። የአዎንታዊ ሰላም መኖር ለዘላቂ ሰላም ዋስትና ነው።

በአንፃሩ አዎንታዊ ሰላም ሳይኖር አሉታዊ ሰላም ሊኖር ይችላል። ማኅበራዊ ችግሮች ሳይነኩ ግልጽ ሁከቶችን ብቻ በማስወገድ ወይን በማፈን አሉታዊ ሰላምን ማስፈን ይቻላል።

አምባገነን መንግሥታት የአሉታዊ ሰላም አፍቃሪዎች ናቸው። የመንደር ሌቦችን፣ ማጅራት መቺዎችን፣ ወመኔዎችን እያደኑ አይቀጡ ጥቃት ይቀጣሉ። በዚህም ዓይነቱ ሥራቸው “የሰላም አባት” የተባሉ አምባገነኖች ብዙ ናቸው። ታድያ ግን ተቃዋሚዎቻቸውንም ከሌቦችና ዘራፊዎች ጋር ደብልቀው ይቀጣሉ። በውጤቱም ብዙዎች አምባገነን መንግሥታት የሚኩራሩበትን “ሰላም” ያሰፍናሉ። ይህ ዓይነቱ አሉታዊ ሰላም “አደገኛ ሰላም” ብለን መጥራት እንችላለን።

ታሪክን ገረፍ እናድርግ። በጆሴፍ ስታሊን “ቆራጥ አመራር” ሳቢያ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ እስከ ሚካኤል ጎርባቾች አመራር ድረስ ለአርባ ዓመታት ያህል የዘለቀ አደገኛ አሉታዊ ሰላም በመላው የሶቭየት ኅብረት ግዛት ውስጥ ሰፍኖ ነበር። ምሥራቅ ጀርመንን 1949 እስከ 1990 እአአ ለ 41 ዓመታት ሉዓላዊት አገር አድርጎ ያቆያት ሕዝብን በክርን በመደቆስ በተገኘ አሉታዊ ሰላም ነው። አልባኒያም ከ30 ዓመታት በላይ በጡንቻ “የሰላም ደሴት” ሆና ኖራለች። ሊቢያ በኮሎኔል ሞአመር ጋዳፊ ብርቱ “ሕዝባዊ ክንድ” እና በአረንጓዴው መጽሐፍ አረንጓዴ መመሪያ ለ30 ዓመታት ኮሽታ የማይሰማባት ሁለመናዋ አረንጓዴ የሆነች አገር ሆና ነበር። ሙባረክ እስራኤልን የመሰለ የጎረቤት ባላንጣ እያለበት እንኳም ግብጽን ለ30 ዓመታት “በሰላም” ገዝቷል። አውሮፓ ውስጥ አሉታዊ ሰላም ለተራዘመ ጊዜ ከቆየባቸው አገሮች ግንባር ቀደሟ ዩጎዝላቢያ ናት። እአአ 1929 እስከ 1991 ለ68 ዓመታት ጉልበት ያፈረጠው አሉታዊ ሰላም ዩጎዝላቪያን ሰብስቦ አቆያት።

ከላይ ከተዘረዘሩት ምሳሌዎች በቀላሉ መረዳት እንደሚቻለው አደገኛ የሆነው አሉታዊ ሰላም ለተወሰነ ጊዜ መልካም ቢመስልም ከረዥም ጊዜ ውጤቶቹ አንዱ ውድመት መሆኑ ነው። ሶብየት ኅብረት ተበታትና ከካርታ ጠፋች። ምሥራቅ ጀርመን በምዕራብ ጀርመን ተውጣ ከካርታ ጠፋች። ዮጎዝላቢያ እጅግ አሳዛኝ በሆነ መንገድ ተበታትና ከካርታ ጠፋች። አልባኒና አዲስ አገር እንደና ተዋቀረች። ሊቢያ አረንጓዴ ሰንደቅ ዓላማዋን ጥላ ከአርባ ዓመታት በፊት ወደነበረው ማንነቷ ለመመለስ እየጣረች ነው። ግብጽ ገና ራሷን ፈልጋ ማግኘት አልቻለችም። አብዛኛውም ጊዜ አሉታዊ ሰላሞች ሲደፈርሱ የቆሙበትን ሥርዓት ይዘው ነው የሚጠፉት።

ወደ ራሳችን ጉዳይ እንመለስ። ወያኔ ነጋ ጠባ “ሰላማችን፤ ሰላማችን” የሚለው የትኛውን ዓይነት ሰላም ፈጥሮ ነው?

ዘረኝነት የፓለቲካ ሥርዓቱ መታወቂያ ሆኖ እያለ፤
ኢፍትሃዊ የሀብትና የሥልጣን ክፍፍል እና ሙስና የሥርዓቱ መለያ ሆነው እያለ፤
ፍትህ ተዋርዳ ፍርድ ቤቶች ገዢዎች የሰጡት ቅጣት ማሳወቂያ በሆኑበት፤
በዘርና በፓለቲካ ወገንተኝነት የተዋቀሩት የጦር ሠራዊት፣ የፓሊስና የስለላ ተቋማት ኢትዮጵያዊያንን ማጥቂያ ሆነው እያለ፤
በፓለቲካ እምነታቸውና በሀይማኖቻቸው ምክንያት ታስረው ሰቆቃ እየተፈፀማቸው ያሉ ወገኖቻችን ብዛት በአስደጋጭ ፍጥነት እየጨመረ ባለበት ሁኔታ፤
ሚሊዮኖች ድሀ ገበሬዎች ከይዞታቸው እየተፈናቀሉ በገዛ አገራቸው ስደተኛ የሆኑበት ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን እያየን፤
ኢትዮጵያዊያን ገበሬዎች ቤተሰቦቻቸውን የሚመግቡት ቁራጭ መሬት አጥተው እያለ ሰፋፊ ለም መሬቶች ለውጭ ባለሀብቶች በገፍ እየተሸጠ ባለበት ሁኔታ፤
የወያኔ ሹማምንት በሀብት ላይ ሀብት እየጨመሩ ከተሞችን በሕንፃዎች ሲያሽቆጠቆጡ ዛንጋባ እንኳን አጥተው በረንዳ ላይ የሚያድሩ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መሆኑን በገዛ ዓይኖቻችን እያየን፤
ከፍተኛ ትምህርታቸው ያጠናቀቁ ወጣቶች ለሚጠብቃቸው የሥራ እድል ባይማሩ ኖሮ ይበልጥ ተመራጭ ይሆኑ የነበረ የመሆኑ አሳዛኝ ሐቅ እያየን፤
ወጣቶች በተስፋ እጦት ከአገር ሲሰደዱ በባህር ሰጥመው አሊያም በበረሃ ንዳድ ተቃጥለው እያለቁ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት፤
አብዛኛው ሰው ቁርስ፣ ምሳና ራቱን ደርቦ “ቁምራ” እየበላ ስለ ተከታታይ ዓመታት 11.6 % ዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገት መስማት ግዴታ የሆነበት የጉድ አገር ሆኖ እያለ፤
የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃና የአረብ አገራት እስር ቤቶች በኢትዮጵያዊያን ወንዶችና ሴቶች ተሞልተው እያለ፤ እና
ወያኔ የሚያደርሰው ግፍ ሞልቶ በፈሰሰበት በአሁኑ ወቅት “ሰላማችን፣ ሰላማችን” እያለ ሲነዘንዘን መስማት ልብን ያቆስላል።
ይኸ ሁሉ ኢፍትሃዊነት ባለበት ሊኖር የሚችለው ሰላም አሉታዊ ሰላም ያውም ተቃውሞን በጉልበት በመደፍጠጥ የሚገኘው አደገኛ አሉታዊ ሰላም ብቻ ነው። ለዚህም ነው ወያኔ ሕገወጥነትን ሕጋዊ የሚደርጉ አዋጆችን የሚያወጣው።

በጉልበት የሚመጣ አሉታዊ ሰላም ለአገራችን አይበጃትምና የወያኔን ሰላም መቃወም ተገቢ ነው። ከብዙ አገሮች ልምድ እንዳየነው አደገኛው አሉታዊ ሰላም ከመኖሩ አለመኖሩ ይሻላል። የወያኔ ሰላምም ለኢትዮጵያችን የሚበጅ አይደለም።

4. ሰላምተኛነት ሁሌ ትክክል ነውን?

በዚህ ንዑስ አርዕስት ሥር ለማለት የፈለግሁትን ሁሉ ሁለት ትላልቅ ስም ያላቸው ሰዎች ስላሉልኝ ለእነሱ ቦታ እለቃለሁ።

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ታህሳስ 4 ቀን 2002 ዓ. ም. (December 10, 2009) የኖቤል የሰላም ሽልማት ሲቀበሉ ያደረጉት ንግግር ሙሉው መሰማት (ወይም መነበብ) ያለበት ቢሆንም አንባቢዎቼን ላለማሰልቸት አለፍ አለፍ ብዬ ልጥቀስ[2]።

እውነቱን በመቀበል እንጀምር − ብጥብጥ ያለበት ቅራኔን በእኛ እድሜ ማስቀረት አንችልም። ለወደፊቱም ሕዝቦች − በግልም ሆነ በጋራ − ኃይልን መጠቀም አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ከሞራል አንፃርም ተገቢ የሚሆንበት ሁኔታ ይኖራል።

አንሳሳት! ክፋት በዓለም ላይ አለ። በሰላማዊ ትግል ሂትለርን መግታት አይቻልም ነበር። ድርድር የአልቃይዳን መሪዎች መሣሪያዎቻቸውን እንዲጥሉ አያደርግም። አንዳንዴ ጉልበት መጠቀም ያስፈልጋል ማለት ከሃቅ የራቀ ምፀት አይደለም፤ ይልቁንስ ታሪክን በቅጡ መረዳት፤ የሰውን ልጅ ድክመቶችን ማወቅ እና የምክንያታዊነት ውስንነትን መገንዘብ ነው።

ሲቪል ዜጎች በገዛ መንግሥታቸው የሚታረዱበት ሁኔታ፤ የእርስ በርስ ጦርነቶች ወይም አንድን የዓለም አካባቢ ሊያምሱ የሚችሉ ብጥብጦችና ሰቆቃዎችን ለመከላከል ኃይልን የመጠቀም አማራጭ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።

ሰላም ተመራጭ መሆኑ መታመኑ ብቻውን ሰላምን ለማስገኘት አይበቃም። ሰላም ኃላፊነት መቀበል ይጠይቃል። ሰላም መስዋዕትነትን ይጠይቃል።

ሰላም የሚታይ ብጥብጥ አለመኖር ማለት አይደለም። ፍትሃዊ ሰላም ዘላቂነት የሚኖረው በእያንዳንዱ ግለሰብ ተፈጥሮዓዊ መብቶችና ክብር ላይ የተገነባ ሲሆን ነው።

ዜጎች የመናገር፣ የማምለክ፣ መሪዎቻቸውን የመምረጥ ወይም ያለፍርሃት የመሰብሰብ ነፃነታቸው በተገፈፉ ጊዜ ዘላቂ ሰላም አይኖርም። …. እንደምናውቀው አውሮፓም ሰላም ያገኘችው ነፃ ስትሆን ነው።

ፕሬዚዳንት ኦባማ ኢትዮጵያዊ ሁነው ይህንን ንግግር አዲስ አበባ ውስጥ ተናግረውት ቢሆን ኖሮ ሕገወጥነትን ሕጋዊ ያደረጉ አንቀጾች ተጠቅሰውባቸው ንግግራቸው ለአሸባሪነታቸው የማያሻማ ማስረጃ ሆኖ እድሜ ልክ ያስፈርድባቸው ነበር። እሳቸው ግን ኦስሎ ውስጥ በበርካታ ካሜራዎች ፊት ለፊት የሰላም የኖቤል ሽልማት ለመቀበል ይህንን ተናገሩ።

የሰላም የኖቤል ሽልማት ተሸላሚው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ “አንሳሳት! ክፋት በዓለም ላይ አለ። በሰላማዊ ትግል ሂትለርን መግታት አይቻልም ነበር” አሉ። ቀጥለውም “ሲቪል ዜጎች በገዛ መንግሥታቸው የሚታረዱበት ሁኔታ፤ የእርስ በርስ ጦርነቶች ወይም አንድን የዓለም አካባቢ ሊያምሱ የሚችሉ ብጥብጦችና ሰቆቃዎችን ለመከላከል ኃይልን የመጠቀም አማራጭ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል” አሉ።

ማርቲን ሉተርን ኪንግ

የማርቲን ሉተርን ኪንግን “ፍቅር፣ ሕግ እና ሕዝባዊ እምቢተኝነት[3]” ሙሉውን ማንበብ ይጠቅማል። ለአሁኑ ግን አንዲት ትንሽ ጥቅስ ብቻ ልውሰድ፡

ሰላም ማለት ፍትህ፣ ቀና ፍላጎትና ወንድማማችነትን የመሳሰሉ አዎንታዊ ነገሮች መገኘት ጭምር እንጂ ጭንቀት፣ ውዥንብር ወይም ጦርነት የመሳሰሉ አሉታዊ ነገሮች አለመኖር ማለት ብቻ አይደለም። ኢየሱስ “ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም” ሲል …… እኔ እንደሚመስለኝ ለማለት የፈለገው የሚከተለውን ነው። …. ውጥረትም ሆነ ቅራኔ የሌለበት የድሮዉን አሉታዊ ሰላም አይደለም ይዤላችሁ የመጣሁት። እኔ ይዤላችሁ የመጣሁት በብርሀንናና በጨለማ፣ በፍትህና ኢፍትሃዊነት መካከል ባለ ፍትጊያ የሚንቀለቀለውን አዎንታዊውን ሰላምን ነው።

….

5. ማጠቃለያ

የወያኔ ካድሬዎች፣ ራድዮና ቴሌቪዥናቸው ስለ ሰላም አውርተው አይጠግቡም። “ሰላማችንን አደጋ ላይ ሊጥሉብን ሞከሩ” በሚል ሰበብ በርካታ ወገኖቻችን በእስር ቤቶች እየማቀቁ ነው።

ሰላም አንድ አይነት ስታንዳርድ የወጣለት የፋብሪካ ሸቀጥ አይደለም። ጥሩ ሰላም አለ፤ መጥፎ ሰላምም አለ። እናም ወያኔዎች የሚዘፍኑለት የሚያቅራሩለት ሰላም ምን ዓይነት ሰላም እንደሆነ መርምረን ማወቅ የራሳችን ኃላፊነት ነው።

ሕዝብ በማፈንና በመርገጥ የሚመጣ ሰላም በረዥም ጊዜ አገርን የከፋ አደጋ ላይ ይጥላልና አንፈልገውም። አደገኛውን አሉታዊ ሰላምን መቃወም ሕዝብን፣ ነፃነቱንና አገሩን ከሚወድ ዜጋ ሁሉ የሚጠበቅ ተግባር ነው። በሰላም ስም ሲያታልሉን ልንታለልላቸው አይገባም።

ሰዎች በሰላም ውለው መግባታቸው ብቻውን የዘላቂ ሰላም ምልክት አይደለም። የዘላቂ ሰላም ዋስትና ማኅበራዊ ፍትህን ማስፈን ነው፤ ይህ ደግሞ ወያኔ ሥልጣን ላይ ሆኖ የሚሆን ነገር አይደለም።

አስተያየት መስጠት ከፈለጉ: tkersmo@gmail.com

[1]. በማኅበራዊ ሣይንስ በስፋት የሚታወቁ የሁከት (Violence) ዓይነቶች ሦስት ናቸው። ሦስተኛውና በዚህ ጽሁፍ ያልተጠቀሰው “የባህል ሁከት (Cultural Violence)” በመባል የሚታወሰው በባህል ላይ የሚደረግን ጥቃት የሚመለከተውን ነው።

[2] http://www.youtube.com/watch?v=AORo-YEXxNQ

[3] Martin Luther King Jr “Love, Law, and Civil Disobedience,” in “A Testament of Hope: The Essential Writings and Speeches of Martin Luther King Jr.,” pp. 6, 50-51. .

Sport: የተጨዋቾች ዝውውር ዋጋ ንረት ምክንያቱ ምን ይሆን?

0
0

arsenalየተጨዋቾች የዝውውር ሂሳብ እየናረ ከመጣ ከራርሟል፡፡ በእርግጥ ጭማሬ ማሳየቱ የማይቀር ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ለዝውውር እየወጣ ያለው ሂሳብ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ግን እንቆቅልሽ ነው፡፡ በክረምቱ የዝውውር ገበያ እስካሁን ለራዳሜል ፋልካኦ፤ ኤዲንሰን ካቫኒ፣ ኔይማር፣ ፈርናንዲንሆ፣ ማሪዮ ጎትዘ፣ ጀምስ ሮድሪጌዝ፣ አሲደር ኢላራሜንዲና ጎንዛሎ ሂጓይን ግዢዎች በአጠቃላይ 325 ሚሊዮን ፓውንድ ወጥቷል፡፡ በአማካይ ለአንድ ተጨዋች 40 ሚሊዮን ፓውንድ ማለት ነው፡፡ እነዚህ ግዢዎች የተፈፀሙት የክረምቱ የዝውውር መስኮት ከተከፈተ ገና አጋማሽ ላይ እንኳ ሳይደርስ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ሁሉም ተጨዋቾች አስደናቂዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ምርጡ ተጨዋች ከ30 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ እንዲሁም ኮከብ የሆነ ተጨዋች 50 ሚሊዮን ፓውንድና ከዚያ በላይ ሊከፈልለት ይገባል የሚል የተፃፈ ህግ የለም፡፡ ይህ ሂሳብ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህ ላይ የተጨዋቾቹ የደመወዝ መጠንም አልተካተተበትም፡፡
የታሪክ መዛግብትን መለስ ብሎ ለቃኘ የዝውውር ሂሳብ በምን ያህል ፍጥነት መጨመሩን ይመለከታል፡፡ ጂያንሎዊጂ ቤንቲኒ በ1992 በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ሲዘዋወር የወቅቱን የሽያጭ ሪከርድ በመስበር የራሱ አድርጎት ነበር፡፡ የሌንቲኒ ዝውውር ከተፈፀመ ከ14 ዓመታት በኋላ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ሪከርዱን 80 ሚሊዮን ፓውንድ አድርሶታል፡፡ በአጠቃላይ የዝውውር ሂሳብ ከፍተኛ ንረት ታይቷል፡፡ የዓለም አቀፉ ኢኮኖሚ በተንኮታኮተበት ወቅት ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ ግን የበለጠ ያስገርማል፡፡

የዦን ማርክ ቦስማን ወይም በአጭሩ የቦስማን ህግ መጽደቁ የዝውውር ገጽታውን በአጠቃላይ ቀይሮታል፡፡ የቦስማን ህግ በዝውውር ጉዳይ የበለጠውን ኃይል ለተጨዋቾችና ወኪሎቻቸው አጎናፅፏል፡፡ የተሻለ ኮንትራትና ክፍያ ለማግኘት በሚያደርጉት ድርድር የአንበሳውን ድርሻ እንዲይዙ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህ አካሄድ የተጨዋች የዝውውር ሂሳብና ደመወዝ በከፍተኛ ፍጥነት እንዲያድግ የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ የዩሮ መገበያያ ገንዘብ በ1999 ስራ ላይ ከዋለ ወዲህ 54 ተጨዋቾች በ35 ሚሊዮን ዩሮ ወይም በላይ በሆነ ሂሳብ ተዘዋውረዋል፡፡ ይህ ቁጥር የክረምቱ የዝውውር መስኮት ከመዘጋቱ በፊት ሊያሻቅብ ይችላል፡፡ ቤል፣ ዌይን ሩኒ እና ሉዊስ ሱአሬዝ የመሳሰሉት ተጨዋቾች በከፍተኛ ሂሳብ ሊዘዋወሩ እንደሚችሉ መዘገብ ከተጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡

ለተጨዋቾች ግዢ የሚወጣው ገንዘብ ለማሻቀቡ ምክንያት የቦስማን ህግ ብቻ አይደለም፡፡ እግርኳሱ እያገኘ ያለው ያልተቋረጠ የሚዲያ ሽፋን ሌላው ምክንያት ነው፡፡ ከቴሌቪዥን ስርጭት የሚገኘው ዳጎስ ያለ የገንዘብ ስምምነት ለስፖርቱ የበለጠ አቅም ሰጥቶታል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታዎች ለማስተላለፍ ስካይና ሲቲ የተሰኙት ድርጅቶች ለሶስት ዓመታት ኮንትራት 5.5 ቢሊዮን ፓውንድ ይከፍላሉ፡፡ ይህን መሰሉ ስምምነት ሌሎች ስፖንሰሮችም ይስባሉ፡፡ ክለቦች ከማሊያና ቁሳቁሶች ንግድ እንዲሁም ከስፖንሰሮች በሚሊዮን የሚገመት ገቢ ያገኛሉ፡፡ ይህ ግዙፍ የሆነ ገቢ ለዝውውር የበለጠ ገንዘብ እንዲያወጡ መንገድ ይከፍትላቸዋል፡፡
በዘመናዊው እግር በስፋት የሚሳተፉትን የራሺያ ቢሊየነሮችም ይጠቀሳሉ፡፡ በእርግጥ በርካታ ክለቦች ቱጃር ባለሀብቶች የተያዙ ናቸው፡፡ በሮማን አብራሞቪች፣ ሼህ መንሱር አልናህያን እና የካታር ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሚሊዮኖችን በክለቦች ላይ ማፍሰሳቸው ሌሎችም ወደ እግርኳሱ ተግተልትለው እንዲመጡ አድርጓል፡፡ የእነዚህ ባለሀብቶች ለዝውውር የሚጠየቀውን ሂሳብ መክፈላቸው ወይም ትንንሽ ክለቦች ከሽያጩ ጥሩ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ክለቦች ከሽያጩ ጥሩ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ውሳኔያቸውን ግትር በማድረግ ብዙ ተጨዋቾች በማይገባቸው ሂሳብ እንዲዘዋወሩ ያደርጋሉ፡፡

የክለቦች ዓለማ ዋንጫዎችን ማሸነፍ ነው፡፡ እነዚህ ድሎች ደግሞ ጠቀም ያለ ሽልማት ያስገኛሉ፡፡ ደጋፊዎችና ተጨዋቾች ዋንጫዎችን ማንሳት ቢወዱም የክለብ ባለቤቶች ግን ብዙ ገንዘብ ያስገኝላቸዋል፡፡ ከዋንጫ አሸናፊነት የሚገነው ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የክለቡ እውቅናም ይናኛል፡፡ አምና ባርን ሙኒክ የቻምፒየንስ ሊጉ አሸናፊ በመሆኑ 36 ሚሊዮን ዩሮ አግኝቷል፡፡ እነዚህ የተለያዩ ምክንያቶችን ስንመለከት በእግርኳሱ ላይ ገንዘብ ወሳኝነቱ መላቁን እንረዳለን፡፡ ባየርን ከቻምፒየንስ ሊጉ ድል ያገኘውን ሂሳብ ብቻ ለጎትዘ ዝውውር አውሏል፡፡ ባቫሪያኑ ወጣቱን በስኳዱ ውስጥ ማካተታቸው በመጪው የውድድር ዘመን ለስኬት ያላቸውን እድል የበለጠ ያሰፋዋል፡፡ ዋንጫ በድጋሚ ካነሱ ደግሞ የበለጠ ገቢ ያገኛሉ፡፡ በአንድ ዓመት ውስጥ 100 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያገኝ ክለብ ለተጨዋች ዝውውር 10 ሚሊዮን ፓውንድ ፓውንድ ከሚያወጣው ጋር ልዩነት የለውም፡፡

ከስፖርቱ ውጪ ያለውን ዓለም በአንፃራዊነት ስንመለከት ለአንድ ተጨዋች ዝውውር 40 ሚሊዮን ፓውንድና 250 ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ ደመወዝ መክፈል ተገቢ አለመሆኑ ይታያል፡፡ ይህ ከፍተኛ ገንዘብ ድህነትን ማስወገድና አደጋዎችን መከላከልን በመሳሰሉት መስኮች ላይ ፈሰስ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ የበርካቶች ፍላጎት ነበር፡፡ ሆኖም በእግርኳሱ መጠኑ ከልክ ያለፈ ገንዘብ ይንሸራሸራል፡፡ ገደብ እስከሚበጅለት ድረስ ወጪው እየናረ መሄዱን አያቋርጥም፡፡ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የፋይናንስ ጨዋነት ደንብ ወጪው ገደብ እንዲኖረው ተብሎ የተቀረፀ ነበር፡፡

ክለቦች ስኬታማ ለመሆን የገዘፈ ወጪ ማውጣት አለባቸው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ አዎ የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም በአብዛኞቹ ሀገራት ሊግ የበላይነት ያላቸው ጥቂት ቡድኖች ብቻ አልያም በቢሊዮኖች ታግዘው የሚመጡት መሆናቸው በቂ ማረጋገጫ ነው፡፡ ሆኖም በአነስተኛ ሂሳብ ውጤታማ የሆኑ ውስን ቡድኖችም ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ለመመልከት የሚያስደስተው የዶርትሙንድ ቡድን አጠቃላይ ወጪ ግን ያነሰ ነው፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ላይ የተሰለፉት የዶርትሙንድ ቋሚ 11 ተጨዋቾች የተገዙበት ድምር ዋጋ ከ38 ሚሊዮን ፓውንድ ያነሰ ነበር፡፡ ከእነርሱም ውስጥ 15 ሚሊዮን ፓውንዱ የማርኮ ሩስ ግዢ መሆኑ ሲታሰብ ቁጥሩ የበለጠ ያንሳል፡፡ ይህ ወጪ ጎትዘን አለመካተቱ ልብ ይሏል፡፡ በጀርመን ሱፐር ካፕ ዶርትሙንድ የፔፕ ጋርዲዮላን ባየርን 4-2 ሲረታም የተጫዋቾቹ የተገዙበት ዋጋ ተመሳሳይ ነው፡፡

fabrigasአርሰናልና ባርሴሎና በአነስተኛ ወጪ ስኬታማ በመሆን ሌሎቹ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ የሰሜን ለንደኑ ቡድን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዋንጫ ማንሳት ባይችልም በመደበኛነት በሊጉ እስከ አራተኛ በመውጣትና በቻምፒየንስ ሊጉ ጥሎ ማለፉ ደረጃ መድረስ ችሏል፡፡ አርሰን ቬንገር ለዝውውር ከፍተኛ ሂሳብ አለማውጣታቸው የመድፈኞቹን ደጋፊዎች ባያስደስትም ያመጡት ስኬት ግን የሚደነቅ ነው፡፡ ባርሳ በቀደመው ጊዜ ለዝውውር ከፍተኛ ገንዘብ ቢያፈስም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ላስመዘገበው ስኬት መሰረቶች የላ ማሲያ ውጤቶች ናቸው፡፡ ቪክቶር ቫልዴዝ፣ ካርሎስ ፑዩል፣ ዤራርድ ፒኬ፣ ዣቪ ሄርናንዴዝ፣ አንድሬስ ኢኒዬሽታ፣ ሰርጂዮ ቡስኬትስ፣ ፔድሮ ሮድሪጌዝና ሊዮኔል ሜሲ የቡድኑ ምሰሶዎች ሲሆኑ ሁሉም የተመረቁት ከላ ማሲያ ነበር፡፡ ከዚሁ አካዳሚ ተገኝተው ለሌሎች ክለቦች በመጫወት ላይ የነበሩትን ሴስክ ፋብሪጋዝና ዮርዲ አልባን ወደ ቀድሞ ቤታቸው ለመመለስ ግን ከፍ ያለ ሂሳብ ተከፍሎባቸዋል፡፡
እነዚህ የተጠቀሱት ምሳሌዎች በወጣቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ጠቃሚነቱ ያሳየናል፡፡ የጀርመን እግርኳስ በወጣቶች እንዴት ስኬታማ እንደሚሆን አሳይቷል፡፡ ሀገሪቱ ለወጣት አካዳሚዎች ስርነቀል ለውጥ በማድረጓ አሁን ፍሬውን እያጨደች ትገኛለች፡፡ ስፔንም ብትሆን በየዓመቱ ወጣት ከዋክብት ማውጣቷን እንደቀጠለች ነው፡፡ ይህን ማሳካት ግን እንደሚታሰበው ቀላል አይደለም፡፡

በክለብ ውስጥ ያለው አለመረጋጋት ግን በሂደቱ እንደ መሰናክል ይታያል፡፡ ገንዘብ ለእግርኳሱ ኃይል በመጨመሩ አሰልጣኞች በወጣቶች ስብስብ ቡድን ለመገንባት በቂ ጊዜ አይሰጣቸውም፡፡ ደጋፊዎችና ባለቤቶችም ፈጣን ስኬት መመኘታቸው ሌላው የአሰልጣኞች ፈተና ነው፡፡ አሰልጣኞች ስራቸውን በፍጥነት ማጣታቸው ተለመደ ሆኗል፡፡ አዲስ የሚሾመው አሰልጣኝ ደግሞ የተለየ ፍልስፍና ይዞ ስለሚመጣ ቡድኑ ቀጣይነት እንዳይኖረው ይደረጋል፡፡ በዝውውርና ደመወዝ ላይ ብዙ ገንዘብ የሚፈስ በመሆኑ በርካቶች ቅሬታቸውን ያሰማሉ፡፡ ሌሎች በአንፃሩ ለዝውውር የተመደበው ሂሳብ ወጪ ባለመደረጉ ያማርራሉ፡፡

ጁነዲን ሳዶ ተገደሉ የሚለው ዜና ሃሰት ነው ተባለ

0
0

junedin(ዘ-ሐበሻ) ፌስቡክን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች ላይ በሰፊው እየተወራ የሚገኘው የአቶ ጁነዲን ሳዶ በወያኔ ተገደሉ የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች እየገለጹ ነው። እነዚህ ለአቶ ጁነዲን ቅርብ ነን ያሉ ወገኖች “የወሬው ምንጭ ሁሌም ሕዝብን በወሬ ማራበሽ የሚወደው የወያኔ መንግስት ነው” ይላሉ።
ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ ጃዋር መሀመድ በፌስቡክ ገጹ “ጁነዲን ተገደሉ የሚለው ዜና ሃሰት ነው” ሲል በተለይ በአያንቱ ድረገጽ ላይ የወጣውን ዜና አስተባብሏል። አያንቱ ድረ ገጽ Gurmessaa Beekamaa የተባሉ ሰው በፌስቡክ የለጠፉትን ዜና “ይህ ዜና ከነፃ ምንጮች አልተረጋገጠም” በሚል በማቅረብ ዜናው እንዲቀጣጠል ያደረገ ቢሆንም፤ ድረገጹ ከሰዓታት በኋላ ደግሞ ጁነዲን በሕይወት ስለመኖራቸውና ስላለመኖራቸው የተምታታ መረጃዎች እየደረሰን ነው በሚል ጉዳዩን እያጣራ እንደሚገኝና የዜናው ምንጭ ናቸው የተባሉት ግለሰብም ስለጁነዲን ተጨባጭ ማስረጃቸውን እንዲያቀርቡ ጠይቋል።
የወያኔ ሚዲያ እንደሆነ የሚነገርለት ኢትዮቻናል የተባለውና በሃገር ቤት የሚታተመው ጋዜጣ ከዚህ ቀደም ጁነዲን ሳዶ ወደ ኬንያ ጠፍተዋል በሚል ሃሰተኛ ዜና ማሰራጨቱ የሚዘነጋ አይደለም ያሉት እነዚሁ የጁነዲንን ሞት የሚያስተባብሉ ወገኖች አሁንም ተገደሉ ብሎ የሚያወራው ራሱ ወያኔ፤ የሕዝቡን የአስተሳሰብ አቅጣጫ ለመቀየር ነው ይላሉ። በተለይ በነፃው ፕሬስ ላይ ለረዥም ዓመታት የሰሩ አንድ አንጋፋ ጋዜጠኛ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት “የወያኔ መንግስት ሃሰተኛ ዜናዎችን በመፈብረክ ሚዲያዎች ተአማኒነት እንዲያጡ ለማድረግ ሲጥር ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በነፃ ጋዜጦች ስም የራሱን ጋዜጦች በማሳተም ሃሰተኛ ዜናዎችን እያቀረበ በራሱ ቴሌቭዥን ደግሞ ‘ነፃ ጋዜጠኛ የሚባሉት እንዲህ እያሉ የውሸት ዜና እየጻፉ ነው’ የሚል ፕሮፓጋንዳ በመሥራት ራሱ በከፈተው ነፃ ጋዜጣ ሌላውን ነፃ ጋዜጣ ሲያሰደብና ተአማኒነት እንዲያጡ በማድረግ ቆይቷል። አሁን ደግሞ እንዲህ ያለው ዜና፣ ባለፈው ዓመት መንግስቱ ኃይለማርያም በዙምባብዌ ሞቱ የሚሉት ዜናዎች በራሱ በወያኔ ተዘጋጅቶ በፌስቡክ የሚለጠፈው ፌስቡክ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥ እንደሚያመጡ ስለሚያውቅ መንግስት ሕዝቡ ፌስቡክ ላይ የሚጻፉ መረጃዎችን እንዳያምን ለማድረግ ነው የተዘጋጀ ድራማ ነው” ይላሉ።
የጁነዲን ሳዶ ባለቤት በወያኔ መንግስት ሽብርተኛ ተብለው የታሰሩ ሲሆን ይህን ተከትሎም ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል። ጁነዲን የሕወሓት ተለጣፊ ከሆነው ኦሕዴድ ጋር በሚሰሩበት ወቅት በአውስትራሊያ እና በሚኒሶታ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሟቸው እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live