Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

(አፈትልኮ የወጣ ምስጢራዊ ቪድዮ) መጅሊሶች በራሳቸው አንደበት መንግስት እንዳስቀመጣቸው ሲናገሩ ተጋለጡ

0
0

መጅሊሶች በራሳቸው አንደበት መንግስት እንዳስቀመጣቸው ሲናገሩ ተጋለጡ ቪዲዪዎን ይመልከቱ

(አፈትልኮ የወጣ ምስጢራዊ ቪድዮ) መጅሊሶች በራሳቸው አንደበት መንግስት እንዳስቀመጣቸው ሲናገሩ ተጋለጡ


አይፎን (Iphone) 6S ምን አዳዲስ ነገሮችን ይዟል?

0
0

iphone 6s

የአሜሪካ ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል አዲሱን የአይፎን 6S የሞባይል ስልክ ባለፈው ዓርብ ለአለም ገበያ ቀርቧል:: በሰሜን አሜሪካ በርካታ የሞባይል መሸጫ ሱቆችም ወረፋው ብዙ እንደነበር ማስተዋል ተችሏል:: አሁንም በርካታ የአፕል አድናቂዎችም እነዚህን ስልኮች ለመግዛት እየተጠባበቁ ነው።

ዲዛይኑ ከቀደሙት የአይፎን ስልኮች ጋር የሚመሳሰለው አይፎን 6S ምን አዳዲስ ነገሮችን ይዟል?

በተጫነው መጠን የተለያየ ስራን ያከናውናል (3ዲ ተች ነው)

የአይፎን 6S ስክሪኖችን በደንብ በመጫን እና በስሱ በመንካት የተለያየ ስራ መከወን እንችላለን።

ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ በተለይም ትልቅ ጣት ላላቸው ሰዎች መልካም ነገር ይዝ መምጣቱም ተነግሯለ።

የአይፎን 6S ስክሪኖችን በደንብ ስንጫን የመንዘር ምላሽ ስለሚሰጥም ሳናውቅ ስክሪኑን አጥብቀን ከመጫን ይታደጋል።

iphone-6s new

ካሜራ

የአይፎን 6S ካሜራ ከሶኒ ኤክስፕሪያ Z4 እና ጋላክሲ S6 የተሻለ ካሜራ ይዞ መምጣቱንም ነው ሜትሮ የዘገበው።

አዲሱ የአፕል ምርት ካሜራ 8 ሜጋፒክስል ሌንሶች ያሉት መሆኑም ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም የነበረው የፊት ለፊት ፎቶ (ሰልፊ) ማንሻ ካሜራውም ከ1 ነጥብ 2 ሜጋ ፒክስል ወደ 5 ሜጋ ፒክስል ማደጉም ነው የተነገረው።

ተከታታይ ምስሎች (Live Photos)

ሌላኛው የአይፎን S6 ገፀበረከት ነው የተባለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተከታታይ ምስሎችን ማንሳቱ ነው።

ይህ ላይቭ ፎቶ የተሰኘው አገልግሎት በምስል እና ቪዲዮ መካከል የሚገኙ በጣም አጭር ተንቀሳቃሽ ምስሎችን (gif) መቅረጽ የሚያስችል ነው።

ሽፋን

አፕል ባለፈው አመት ከሞባይሎቹ ሽፋን ጥንካሬ ጋር ተያይዞ ከደረሰበት ተቃውሞ በመነሳት በዚህኛው ምርቱ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል።

አዲሶቹ አይፎን ስልኮች ከብረት 60 እጥፍ ጠንካራ በሆነ አልሙኒየም የተሰሩ መሆናቸው ተነግሯል።

ቀለሞች

አዲሱ የአይፎን s6 በአዲስ ቀለም መጥቷል፤ ሮዝ ቀለም ይዞ።

ከ2006 ወዲህ ሮዝ ቀለም ስልኮችን ያልተመለከቱ የአፕል አድናቂዎችም አዲሱን አይፎን s6 ለመግዛት በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የአፕል መደብሮች ተሰልፈው እየተጠባበቁ ነው።

አንዳንድ ግለሰቦችም የሰልፍ ወረፋ በሮቦቶች ማስያዛቸው እየተዘገበ ነው።

ምንጭ፦ http://metro.co.uk/

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መምህር ግርማን ያተኮረ እና የሚያመሰጥር እይታው የተፃፈ መልስ

0
0

Memeher Girma
ክፍል አንድ

እርግጠኛ ነኝ ይህ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የፃፈው በይበልጥ ለመምህር ግርማ መፃፉን እገነዘባለሁ። ይህ የመልስ ጽሁፍ ብዙ ሐሳዊያን ስላሉ ፣ባህታዊያን ነን ብለው ብዙ ችግር የሚፈጥሩትን የሚያታልሉትን በድጋፍ መልክ አይወክልም ። ወንድማችን በሐሳብህ እነሱን ብለህ ከሆነ በጣም ጥሩ ነው ጥሩ ብለሐል በርታ … ነገር ግን እንደምረዳውም እሳቸውን መምህር ግርማ የሚያጠቁም መሆኑን ስለተረዳሁ ይህን ጽፌልሀለሁ :: ይህ ጽሁፍ ስለ መምህር ግርማ እና በንጹ መንፈስ ለሚያገለግሉ ሁሉ ነው
ለእይታዎችህ በየተራ ቁጥሩ መልስ ለመስጠት ያህል :-

ቁ1/ A/ መምህርን እንድታውቃቸው ያህልትንሽ ልንገርህ ብዙዎቻችን አንተም ሳትወለድ በፊት
A.1/ መምህር ግርማ ዲያቆን ሆነው ለረጅም አመታት በባሌ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በምግባር በታዛዝነት በጽናት እግዚአብሔርንና ቤተክርስቲያንን ምእመንን አገልግለዋል
A.2/ እንደማንኛውም ሰባኪ ለዘመናት ከዲቁና ጀምሮ እግዚአብሔር እንደገለጠላቸው ህዝበ ክርስቲያናችንን በመንፈሳዊ ስብከት በዚያን ግዜ ጅምሮ አገልግለው ። ፍሬው ያማረ ከብዙሺህ የሚቆጠር ምእመንን ለንስሐና ለቅዱስ ቁርባን አብቅተዋል፣ ክርስቶስን እንዲያውቁ አርገዋል ፣ሕዝቡ የቤተክርስቲያን ሀብት እንዲሆን አርገዋል።
A.3/ ሌላው ልነግርህ የምፈልገው ነገር አንተ አቡነ ጎርጎሪዩስን ሳታውቃቸው በፊት ከብዙ አመታት በፊት መምህር ግርማ የአቡነ ጎርጎሪዩስ በፍቅር ተወዳጅ ተማሪ እንደነበሩ እወቅ። በጣም የሚዋደዱ አባትና ልጅ እንደነበሩ ለእውቀት ያህል እንድትረዳ እፈልጋለሁ። ማለት ምኑንም ሳትጀምሩት መምህር ግርማ የመንፈሳዊ ትምህርትና የጸሎት ብርታ እንደነበራቸው ከአቡነ ጎርጎሪዩስ ጋር የጠነከረ የጠራ የአባትና ልጅ የፍቅር እንደነበራቸው ተረዳ።

ተቺና፣ነቃፊ ስላልሆኑ፣ተንኮል ስለሌላቸው፣በድብቅ ሌላውን ለመጉዳት የማይጠነስሱ ስለሆነ እሳቸው ፍቅር ስላላቸው በጎነታቸውን ስላየ መንፈሳዊ ጉዛቸውን ክርስቶስ ስለወደደው እሱ አብዝቶ ሰጣቸው
እርግጠኛ ነኝ ይህ ሁሉ አልታየህም ያየህው በምን አይን እንደሆነ አልገባኝም

B/ የጸሎት ሕይወት ላልከው መንፈስህ ከፈቀደልህ ጠጋ ብለህ ጠይቃቸው እያቸው ። እግዚአብሔር እረድቶአቸው ምን ያህል በጸሎቱ ህይወት እንደረዳቸው ግንዛቤ ታገኝ ይሆናል
C/ ሌላው ነገር ወገንህ ምን ያህል በእርኩስ መንፈስ እንደተወጠረ የገባህ አይመስለኝም። መሰበኩን ብዙ ትናገራለህ እንጂ የልቡን ጭንቀት ለማየት የተጠጋህ እንካን አልመሰለኝም። አንተ እንዳልከው ማጥመቅ ስራው የሆነ የለም ብለሃል ይህ ያንተ አባባል ነው ። እግዚአብሔር ከተያዘውና ካለቀው ትውልድ አንፃር እንዲያገለግሉ ከወደደላቸው አንተ ምን አስቀናህ አገባህ ።
ክርስቶስ ልጆቹ ይድኑ ዘንድ ፍላጎቱ ነው ። እውነት እልሃለሁ በኔ እይታ ደግሞ አንተ ያልከው የመዳንን በር የሚዘጋ አባባል ነው ፣ ትውልድ በሰይጣን ተጨንቆ ይኑር ብዙ ግልፅ የሆነ ጥምቀትና መናፍስትን ማስወጣት ጥሩ አይደለም ይበቃል የሚል አባባል ያዘለ ይመስላል::

D/ የመንፈስ ቅዱስን አሰራር ከመረጃ ፍለጋ ልታገኘው አትችልም በፍጹም ልትደርስበት አትችልም ካልተፈቀደልህ
E/ ላንተ ጥያቄ … ክርስቶስ ሲመርጣቸውና ሲያድርባቸው ላንተና አልገባ ላላቸው መንገር ነበረበት እንዴ??
አንተን መጠየቅ ነበረበት ወይ?? ይህን በእውነት ከመለስከው ግራ ሊያጋባ ለፃፍከው ነግር ብዙው መልስ ይሆንሃል

ቁ2/ A/ ሌላው ነገር ለምሳሌ አንተ ….. ከመምጣትህ በፊት ዳንኤል ክብረት ሊመጣ ነው ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተብሎ ከወር በላይ አይደል እንዴ ጥሪውና ዝግጅቱ … ምን አለበት ታዲያ መምህርም በተሰጣቸው ጸጋ የወንጌልና የፈውስ ግልጋሎት ማዘጋጀቱ ምኑጋር ነው ችግሩ? ባይሆን ጥላቻ ካልሆነ
B/አንድ ነገር ልንገርህ ክብሬ ይገለጣል ብለህ ከምትሸሽ ። ተገልጠህ ነፍሳትን ማዳን ወደ ክርስቶስ ማምጣት እንደሚበልጥ እርግጠኛ ሆኜ እነግርሃለሁ።
C/ ሌላው ስለሌሎች ክብር መገለጥ መጨነቅህና ስብከትህ በዚያ ዙሪያ ማጥፋትህ ጥሩ አይደለም ። ያአንድ ግለሰብ መምህር ራሳቸውን ጠንቅቀው ከክርስቶስ ጋር ስለሚያውቁ ብዙ አትድከም። በቅድስና ላይ ብታተኩር ይሻላል
D/ ስለመሸጥ ተናግረሃል .. ልጠይቅህ ጥንት አባቶቻችን መጸሐፍ መሸጥ የሚባል ነገር አልነበረም ። አንተ ወይም ሌሎች ለምን መጸሃፍ ትሸጣላቹሁ? ይህን ከመለስክ መምህር ለምን እንደሚሸጡ መለስክልን ማለት ነው።
E/ብዙ ነገሮችህ ቅዱሳኖችን እየጠራህ እነሱ እንዲ አያረጉም ነበር እነዚህ ግን እንዲህ ነው ትላለህ ። አሁንም ልጠይቅህ … የድሮዎቹ ሰባኪ ለአገልግሎታቸው ብር አይቀበሉም ነበር ። ልምንድነው አንተም ሌሎችም ግን የግልጋሎት ዋጋ በብር ይሰጣቹሃል ለምን ይመስልሃል? … ይህን ከመለስክ መምህር ለምን እንደሚሸጡ መለስክልን ማለት ነው። በተጨማሪ ላሳውቅህ የምፈልገው መምህር ሁሉ ጋር በነፃ በፍቅር ነው የሚያገለግሉት ሰዎች አስገድደው ዋጋ ካልተቀበሉ ብለው ያስገድዳሉ እንጂ

ቁ3/ በኢየሱስ አልወጣም በማሪያም ነው ብለሃልይህ? እዚህ ጋር እንደመናፍቅነት እይታህ የጎላ ነው ። ይህ በስህተት እይታ ያየ ፣ የሰይጣንን ቃል ሰምተህ እንጂ መምህር ጋር እንዲህ አይደለም ። እይታህ ለመንቀፍ ችኩል እንደሆነ እረዳለሁ።
አጋንንት በሚካኤል ስም ቢወጣ ። የክርስቶስን ክብር ዝቅ ማረግ አይደለም ።በሚካኤል ስም ቢወጣ የጌታ ፈቃዱ ሆኖ መሆኑን ዘንግተሃል። በየትኛው አይን እና ህሊና እንዳየህው እራስህን ጠይቅ?
ቁ4/አንተ በመቁጠሪያ ይወጣል ይላሉ ብለሃል:: እይታህ በጣም መሳሳቱን እይ ። እሳቸው እንዲህ አላሉም ከሄዱበት መንፈሳዊ መንገድና ጉዞ አንፃር የተደበቀ መናፍስትን በክርስቶስ ስም ማድከሚያ የእኛ ጦር መሳሪያ ነው። አሁንም ላይገባህ ይችላል ግን ምን ማረግ ይቻላል ለብዙዎች ግን ጦር መሳሪያችን ነው እወቀው።
ቁ5/ያ ግዜና ይህ አንድ አይደለም ለምሳሌ በዚያ ግዜ ከ200 ሰው 1 ስው በመናፍስት የተጎዳ ነበር አሁን ግን ከ200 ሰው በትንሹ 190 ሰው የተጠቃ ነው።
ሌላው ደግሞ መተተኞቹና አስማተኞቹ በጣም በዝተው ። ትውልዱን ከዲያብሎስ ጋር አንድ ሆነው በስውር የጨረሱበት ዘመን ነው ።ሰይጣንን ለአላማቸው ጠርተው ሂድ ይህን አድርግልኝ የሚሉ ብዙ እንዳሉ እኔ ላንተ አልነግርህም ። አይ አላውቅም ውሸት ነው ካልክ የቆሎ ተማሪ የሆነን ሰው በተወለድክበት ቦታ ጠይቃቸው በጣም ብዙ ይነግሩሃል።
አንተ እንዳልከው ይህ የሰይጣንን ኃይል የሚያሳይ ነው ብለሃል ። እየውልህ እይታህ በተሳሳተ መንገድ መቆሙን አየን ።የእኛ እይታ ደግሞ ደግሞ የሰይጣን ደካማና አልቃሻ ነቱን በክርስቶስ እንዴት እንደሚባረር ተረዳን መምህር ግርማ አስተማሩን ።
ይህ ሁሉ ሰው በሰይጣን ሲያዝ ክርስቶስ የለምን ጥምቀቱና ቁርባኑ አይሰራምን ብለህ ጠይቀሃል
ጥያቄ ላንተና የተመሳሰለ ሃሳብ ላላቸው
በመፃህፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙዎች ተይዘው የተጎዱ አሉ ። ለምን ይመስልሃል ሲያዙ ዝም የተባለው? ይህን ከመለስክ አሁንም መልሱን አግኝተሃል።
ክርስቶስ ነፃነት ሰጥቶናል ግን በራሱ እጅ ሰው ይያዛል። ጥምቀቱና ቅዱስ ቁርባል ታላቅ የክርስቶስ ልጅነትና ኃይልን አሲዞን ነበር ነገር ግን በራስ እጅ የዲያብሎስ እጅ ውስጥ እየገባን እንጂ
ቁ6/ክፉ የሚሰሩ ሰዎች ይጋለጡ ዘንድ ለነሱና ለዲያብሎስ አጋዝ የሆነ አስተያየት መሆኑን እገነዘባለሁ። ሰይጣን ውሸታም ነው ። የክፉዎች መረብ የመታቾች ተንኮል የነቃና ይፈርስ ዘንድ የማይፈቅድ ጥንቃቄ ያለበት አባባል ይመስላል
ቁ7/መምህር ግርማ ይህ ቅድስና ነው አላሉም ። ለክርስቶስ መንጋ እንዲያገለግሉ ክርስቶስ ሾማቸው እንጂ። በክርስቶስ ሹመት አንተ ምንም አያገባህም ። ብትችል ከበረከታቸው ተካፈል እንጂ እንዲህ ነው እንዲህ ነው ልትል አቅሙም ስልጣኑም የለህም ። ገዳምም ይሁን ከተማ በክርስቶስ ምርጫና አሰራር የሚያገባህ አይመስለኝም።
ቁ8/አንተ የወደፊቱን አሳች እያሰብክ እየፈራህ ዛሬ ክርስቶስ የመረጣቸው የጠራቸውን መምህር ግርማን ወቃሽና አዋራጅ ለመሆን ምክንያት ትደረድራለህ ። ከሩቅ ሆነህ መረጃ ሰብስበህ ያወሩልህን እውነት ብለህ ከምትነዛ ቀረብ ብለህ ትምህርታቸውን ተማር በጣም ብዙ ትምህርት ታገኝበትና እይታህ ይቃናል የክርስቶስ ሐዋሪያ መሆናቸውን ትረዳለህ። ለዚህ እድል ክርስቶስ ይርዳህ።
ቁ10/ ከክርስቶስ ይልቅ መምህር ግርማ አልጎሉል አልከበሩም ይህ እይታህ እዚህ ጋር እንደመናፍቅነት እይታህ የጎላ ነው ። በመምህር ግርማ ስብከትና ፈውስ ክርስቶስ ከበረ ክርስቶስ ሰራ እንጂ እኔ ያሉበት ቦታ አላየሁም ።ሌሎች ሌላ ነገር ብለውክ ይሆናል በራስህ ቀርበህ ከማየት ይልቅ።
በአጠቃላይ በመምህር ግርማ ዙሪያ ላወጣህው ድብቅ ገላጭ ጽሁፍ ወንድማችን እይታህ እንደተሳሳተ እነግርሃለሁ ሕዝቡም አይቶት ይመሰክራል
ሁሉ ሰው እንደ እምነቱና እንደገባው መጠን መርከስም መቀደስም ተፈቅዳል ስለዚህ መቀበልም አለመቀበልም እንደዚሁ ። እኔ ለምን መምህር ግርማን አልተቀበላቹሁም አይደለም ነገር ግን
ልክ ለሌላው ሊድን ሲል ከሰይጣን ሰንሰለት ሊላቀቅ ሲል ግን ብዙዎች አወቅንልህ ብለው የሚከለክል የዲያብሎስን ያህል ምክር ይመክራሉ … ሰውየው ግን ተይዞ ለዘመናት ሲያነደው ማንም ትንፍሽ ያላለ …. የመዳኛው ሰአት ሲደርስ ግን … ሁሉ የሞት ሽረት ላንተ ጠበቃ ሆኖ ሲከለክልህ ግራ ሲያጋባህ ይታያል ። ይህም ያስጠይቅሀል….
“ሉቃ 11፥52
እናንተ ሕግ አዋቂዎች፥ የእውቀትን መክፈቻ ስለ ወሰዳችሁ፥ ወዮላችሁ ራሳችሁ አልገባችሁም የሚገቡትንም ከለከላችሁ”
የሌላውን ሰይጣን ያሰረበትን ሰንሰለት እንዳይበጠስ ወደ መዳን የሚገቡትን ከልካይ ሆነህ መቀመጥህን አስተውል
አስተውል ልኡል እግዚአብሔርን ዝም ብለህ ተቃዋሚ ሆነህ መቆምህን እንድትረዳ ልብህን መርምረው። አንተ ክፍ ትውልድ ልኡል እግዚአብሔር ያነሳውን ባለሞል ልታሰናክል እንደማትችል እነግርሀለሁ ።ባይሆን በምኞትህ እንደምትወድቅ የጌታ መለኮታዊ ቃሉ ይነግረናል:: ከመደፋፈርህ በፊት አስተውል ከቻልክ ቅዱስ መንፈስ ካለብህ በፀሎት ጌታን ለምን!!
እግዚአብሔር መምህር ግርማን ሀይሉን ፍቅሩን ለመንጋው የገለጠባቸው የሚገልጥባቸው ታማኝ ባለሟል ከሆኑት ውስጥ ስለሆኑ ።(ይህንንም ስል በሌሎች በጣም ብዙ አባቶቻችን ገልፃል ይገልፃልም ማለቴም ነው)እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሳቸው በኩል ስለሚገስፀን የጌታን ቃል እንማራለን እናድጋለን ። ግን ሌሎች በቅናት ልቦና ቆመው ሆይ ሆይ እንደሚሉት “አድናቂና ዝምብሎ ተከታይ ቲፎዞ ግን አይደለንም”

መንፈሳዊ ወገኖቼ አምላካችን ክርስቶስ በባለሞሉ በመምህር ግርማ በኩል ሊያሳስበን የፈለገውን መንፈሳዊ ንቃት ያስተዋላቹሁ ። አይዛቹሁ በርቱ አብዝቶ ይግለፅልን በሀይማኖት ምግባር ፍቅር እምነት በርቱ ”ፊሊጽሲዮስ 1፥ 28-29 በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ” ሳያውቁ ግራ ለተጋቡብን ወገኖቻችንም በፀሎታቹሁ አሳስቡላቸው ወደማስተዋል ህሊና እንዲኖሩ

በወደደን በክርስቶስ እንሻገራለን!!

በክፍል ሁለት እንገናኝ!

ከኢያሱ ሚካኤል

የትጥቅ ትግልና ግራ የሚያጋባ አስተያየት – ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

0
0

getachewበኢትዮጵያ ትከሻ ላይ የተቆለፈውን ቀምበር ለማላቀቅ ቍልፉ የትጥቅ ትግል መሆኑ በተነሣ ቍጥር ከአንዳንድ ሰዎች የሚሰጠው አስተያየት ግራ የሚያገባ ነው። ገዢዎቹና ደጋፊዎቻቸው ቢቃወሙ ይገባኛል። የሚሰጡት አስተያየት ግን ሕፃንን ሳይቀር የሚያሥቅ ነው። “ጦርነት በቃን” ይላሉ። “አትንኩን” ማለታቸውን የማናውቅ ይመስላቸዋል። ጦርነት ካላስፈለገ፥ ለምን ከንጉሣዊው አስተዳደር ጋር ተዋጉ? ለምን ከደርግ ጋር ተዋጉ? ጨቋኝ ገዢ የት አገር ነው በሌላ መንገድ ሥልጣን ለሕዝብ ሲለቅ የታየው? የምሥራቁ ዓለም ጨቋኞች የወደቁት በሕዝብ ዐመፅ ነው ማለት፥ የምዕራቡን ዓለም ከባድ እጅ ሚና መርሳት ይሆናል።

የኛዎቹ ጦርነት ከመረራቸው፥ ሕዝብን ወደጦርነት የሚመራ በደል አይሥሩበት። ምን ጊዜም ቢሆን የትጥቅ ትግል የመጨረሻው አማራጭ ነው። የትጥቅ ትግል የሚያደርሰው ጉዳት በአንዱ ወገን ላይ ብቻ አይደለም። መሣሪያ የሚያነሣ መሣሪያ ማንሣት የሚያመጣበትን ጉዳት ሳያውቅ አይነሣም። ሰው ሆኖ እንደከብት መገዛት ያልቻለ ሰው በቃኝ ሲል፥ ክብሩን በመጠበቁ ከተቀመጡበት ተነሥቶ “ነወር” የሚባል እንጂ፥ በባርነት ጥላ ሥር ተቀምጦ የሚተች አይደለም። “ጦርነት መርሮናል” የሚለውን ምክር መገዛት ለመረረው አይመክሩም።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ግራ አጋቢ አስተያየት “ጦርነትስ አስፈላጊ ነው፥ ግን . . .” የሚለው ነው። ይህ አስተያየት በቅን አሳብ፥ የተሰጠ ሊሆን ይችላል። ግን አዛኝ መስሎ፥ ቀምበረኛውን ለመደገፍ የተሰጠ አስተያየት አለመሆኑ በምን ይታወቃል? እውነተኛ አሳቢና ሠጊ ሰው አስተያየቱን የሚሰጠው ሲጠየቅ፥ ካልተጠየቀም በግሉ ትጥቅ ያነሡትን ፈልጎ በጨዋ ደምብ መንገር ነው። ሳይጠየቁ ተነሥቶ በይፋ ምክር መስጠት ግን ሰሚው ሕዝብ ትግሉን እንዳይደግፍ መገፋፋት ነው። የትጥቅ ትግል ከታመነበት እንዲፋፋም የማይፈለግበት ምክንያት ምንድን ነው?

ትጥቅ ትግል የራስን ሕይወት ለወገን ነፃነት መሠዋት ማድረግ ነው። ሌላ ዓለማ የሌለው ሰው መሣሪያ ሲያነሣ፥ እንዴት ይኸንን የሚሰነዘርበትንና የሚሰነዘርለትን ምክር ሳያስብበት ራሱን ለመሥዋዕትነት ያቀርባል? የሚካኼደው የትጥቅ ትግል የሚያዋጣ የመሰለው እርዳታውን ያቅርብ፤ የማያዋጣ የመሰለው ለምንድን ነው የሚቃወመው? ተቃውሞው ማንን ለመጥቀም ነው? ለታጋዮቹ አስቦ ከሆነ፥ ከባለቤት ያወቀ ቡዳ ነው። “የኔን ያህል የማሰብ ችሎታ የላችሁም” ማለት ነው። እንዴት ነው ለታጋዮቹ ያልተገለጠ ሥጋት ለምክር ሰጪዎቹ የተገለጠው?

አንዳንዱ ደግሞ፥ “ይኸው እንታገላለን ሲሉ ዓመታት አሳለፉ፥ ግን አንዳች ውጤት አላሳዩም” ይላል፤ ውጤት እንዲያሳዩ የቀጠራቸውና ካልሆነላቸው የሚያሰናብታቸው ሹም ይመስል። አርፎ መቀመጥ ስንት ውጤት አሳየ? ሌሎችን ሙከራዎችም “አንዳች ውጤት አላሳዩም” ብለን እንንቀፋቸዋ!ውይስ ውጤት አሳይተዋል?

“በመካሄድ ላይ ያለው የትጥቅ ትግል ኢትዮጵያን የሚጎዳ ነው” ከተባለ፥ እርግጥ ሊታሰብበት ይገባል። ግን አሳሳቢው ምክንያት ሊቀበሉት በሚገባ መልኩ አልተሰጠንም። ይህ ትግል የሚያመጣው ጉዳት ከተሸከምነው ቀምበር ይበልጥ ሊከብድ እንደሚችል አሳዩን።

የወያኔ ቀምበር መሰበር አለበት የምንል ሁሉ በመሰለንና በተቻለን መንገድ እንታገል። ካልተቻለን፥ ካልመሰለን፥ አርፈን እንቀመጥ፤ ታጋዮችን አለማደናቀፍ፥ እንደ ትግል እንዲቈጠርልን።

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/10537#sthash.Kvap5EbS.dpuf

የተቦርነ በየነ በቴዲ አፍሮ ላይ ያለው ጥላቻ መነሻ እና ከአፈርኩ አይመልሰኝ

0
0

teddy afro vs teborneh
ቤተልሄም ክፍሌ ከቨርጂኒያ

ተቦርነ በየነ በወያኔ ራድዮ ላይ ሲያገለግል የቆየና በአሁኑ ወቅት ደግሞ በኢሳት ራድዮ ላይ የሚሰራ ጋዜጠኛ ነው:: ይህ ሰው ስለሙዚቃ ያለው እውቀት የሚያስወድሰውን ያህል በቴዲ አፍሮ ላይ ያለው ጥላቻ ግን እጅጉን የሚስተዛዝብ ነው::

ቴዲ አፍሮ እምነቱን በሙዚቃዎቹ የሚያስተላልፍ ጀግና በመሆኑና ተቦርነ እንደሚያደንቃቸው ዘፋኞች ስለጥርስና ስለአይን የማይዘፍን አርቲስት ባለመሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ የተከበረ ሆኖ እንዲቆይ አድርጎታል:: ቴዲ አሁን ባለው ስርዓት በየጊዜው የሚደርስበት ጫና እና ስም ማጥፋት ሳይበግረው ዛሬ ድረስ በጥንካሬ አለ::

ከ9 ዓመት በፊት በስልጣን ላይ ያለው መግስት በቴዲ አፍሮ ላይ በየራዲዮው የስም ማጥፋት ሲጀምር ተቦርነ አንዱ አራጋቢ ነበር:: ቴዲ አፍሮ “እንደ ቢራቢሮ’ የሚለውን ዘፈን ከሰው ወስዶ እንደሰራ በማስመሰልና የፈጠራ ሰው እንዳልሆነ በማድረግ እያቀረበ በሕዝብ ዘንድ ያለውን ከበሬታ እንዲቀንስ ከወያኔ ጋር ተባብሮ ቢሰራም አልተሳካለትም::

ዛሬ ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ “እንደ ቢራቢሮ” የሚለውን ዘፈን በሸክላ ሰርቼው ነበር ሲል ሃብቴ አወሎም የተባለ ዘፋኝ በባላገሩ አይዶል የመዝጊያ ዝግጅት ላይ መናገሩን ተከትሎና ተቦርነ በየነም በፌስቡክ ገጹ ላይ የአወሎምን ንግግር ይዞ ፈንጠዝያውን ሲለቅ ታዝቤ ነው::

እንደቢራቢሮ የሚለውን የሃብቴ አወሎምን ዘፈን ደጋግሜ ሰማሁት:: የቴዲ አፍሮን በደንብ ሰማሁት:: “እንደቢራቢሮ ሁሉን አትቅሰሚ እኔ እበቃሻለሁ ተይ ፍቅሬ ስሚ” ከምትለው አዝማች በቀር የሁለቱም ዘፈኖች አይገናኙም:: በሃገራችን አማርኛ ላይ እንደቢራቢሮ እንዲህ አትሁኚ የሚለው አባባል የተለመደና በዘወትር አነጋገራችን ላይ የምንጠቀምበት አረፍተ ነገር በመሆኑ ይህ አዝማች የሃብቴ አወሎም ነው ብሎ መደምደም አይቻልም::

ቴዲ አፍሮም በቢሆን በመጀመሪያ አልበሙ ላይ የሰው ዘፈኖችን በሲዲው ላይ ማካከቱን አስመልክቱ በወቅቱ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ባሰጠው ቃለ ምልልስ ቃል በቃል ባይሆንም እንዲህ ብሎ ነበር:: “የመጀመሪያ አልበሜ እንደመሆኑ አሳታሚዎች ሲዲው ይሸጣል ብለው እምነት አይኖራቸውም… ስለዚህ አንድ ሁለት የሰው ዘፈኖችን እንድታካትት ያስገድዱሃል:: የራሴ ብዙ ሥራዎች ቢኖሩኝም የሰዎችን ዘፈኖች ያካተትኩት በአሳታሚዎች ግፊት ነው”

በወያኔ ራድዮ ላይ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር በመሆን የቴዲ አፍሮን ስም ሲያጠፋ የከረመው ተቦርነ ለሰይፉ ፋንታሁን ሰርግ ቭዲዮ ቀርጾ መልዕክት ለማስተላለፍ ጊዜውን ሲያጠፋ በቴዲ አፍሮ ላይ መንግስት ባደረገው ጫና የአዲስ ዓመትም ሆነ የመስቀል ኮንሰርት ሲሰረዝ ድምጹን ሲያሰማ አላየነውም:: የዘፋኞች ጉዳይ ሲነሳ እኔ አውቃለሁ ብሎ በቅድሚያ ፊት የሚቆመው ተቦርነ አንዳችም ቀን በቴዲ አፍሮ ላይ ይህ መንግስት የሚሰራበትን ግፍ “ግፉ ይብቃ” ብሎ ሲናገር አላየንም – አልሰማንም:: ያስተዛዝባል:: አሁን የሃብቴን ንግግር ተከትሎ ከ9 ዓመት በፊት እኔም ይህን ስል ነበር እያለ ራሱን እንደ እውነተኛ አድርጎ ለመቁጠርና ዛሬም ድረስ በቴዲ አፍሮ ላይ ያለውን ጥላቻ “ትክክል ነበርኩ” በሚል ለማሳረግ መሞከሩ እርግጥም ጥላቻው አብሮ ያደረ እንደሆነ ያሳብቅበታል:: ካፈርኩ አይመልሰኝም ነው::

ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የተወደደና የተከበረ ነው:: በተቦርነ እና በቤተሰቡ ተወደደ አልተወደደ የሚመጣበት ነገር የለም:: (ከ2 ዓመት በፊት “ቴዲም በዚህ ቁመቱ ‘ሰው በልኬ’ እያለ ዘፈነ” ሲል መድረክ ላይ ማን እንደተዋረደ ሁላችሁም ታስታውሳላችሁ)

ይልቁንም ከአዲስ አበባው የወያኔ ራድዮ ተንደርድሮ የምንወደው ኢሳት ጓዳ የተቀላቀለው ተቦርነ በቴዲ ላይ እጅህን አንሳ:: በሃገሩ ላይ በነፃነት እንዳይሰራ እየተዋከበ ያለው ቴዲ አፍሮን በቤተሰባዊ ጥላቻ ከማጥቃት ይልቅ ከጎኑ ቆመን ወከባውን የምንጋራበት ወቅት ላይ ነን:: ወያኔ የሚያሰቃየው ይበቃዋል እላለሁ::

በቀጣይ እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት – አለ ጋዜጠኛ::

ካፍ ኢትዮጵያን 5 ሺህ ዶላር ቀጣ

0
0

ethiopian national tea
(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሌስቶ ብሄራዊ ቡድን ጋር በባህር ዳር ከተማ ባደረገው ጨዋታ ላይ ስፖርታዊ ጨዋነት የጎደለው ተግባር ተፈጽሟል ያለው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ላይ የ5 ሺህ ዶላር ቅጣት አስተላለፈ::

ብሔራዊ ቡድናችን በባህር ዳር ስታዲየም ባደረጉትና የሌሴቶ አቻቸውን 2 ለ 1 በረቱበት ጨዋታ ላይ በታየ ስፖርታዊ ጨዋነት የጎደለው ድርጊት ምክንያት ነው ካፍ ውሳኔውን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ላይ ሊያስተላልፍ የቻለው። ካፍ ስፖርታዊ ጨዋነት የጎደለው ተግባር ያለው ጨዋታው እንዳለቀ ደጋፊው ግር ብሎ ሜዳ ውስጥ በመግባቱ ነው:: በዚህም የተነሳ 5 ሺህ ዶላር ፌዴሬሽኑ ተቀጥቷል::

አገር የምትኖረው በ3 ነገር ነው  በወታደር በገበሬ እና በመምህር!!! –ከአዲስ ብርሃኑ

0
0

Ethiopiaethiopiaአገር ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳው ወያኔ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንድትኖር በመሰሪ ሃሳቡ ሌት ተቀን የማይቆፍረው ግድጓድ የለም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ነገር ግን እንደ አሳቡ ሊሆንለት አልቻሉም  ዘር  ከዘር ሊያጋጭ ብዙ ጣረ አልተሳካለትም፤ ሐይማኖት ከሃይማኖት ሞከረ ይሄም አልሰራ አለው ሃሳቡ ሁሉ መና  ሲቀርበት  እራሱ ከሳሽ  እራሱ ፈራጅ  በሆነበት ፍርድ ቤት  የብዙሃን ነጽሃን  ሰው መሰቃያ  ወደ ሆነው ወህይኒ እየወረወረ ባልሰራበት ወንጀል ባላደረጉት  ድርጊት ንጽሐኑን ማሰቃየት ከጀመረ ድፍን 24 አመት አለፈ።

መምህር…..

አንድ አገር ከሚያስፈልጋት ዋናው መሰረታዊ ነገር መምህር ነው። መምህር ከሌለ የተማረን ህብረተሰብ ማግኝት አይቻልም።  መምህር በጠመኔው ለአገር የሚሆን ፍሬ ለህዝብ የሚጠቅም ዘር በሰው አእምሮ  ውስጥ የሚዘራ እና ብዙ ጥበቦች ባለ ብዙ እውቀት  ባለቤት አገርን በጥበብ የሚመራ ላገሩ በእውቀት የሚያገለግል ለአገር የሚጠቅመውን ካመነበት የሚሰራ ካላመነበት ደግሞ እንቢ የሚል  ማንኛውንም ነገር ሰለ ህዝብ ብሎ ስለ አገር  ብሎ ማድረግ የሚቻል ዜጋን የሚቀርጹት መምህራናን ናቸው።  ዛሬ  ወያኔ እያደረገ ያለው እኔ የምላቹሁን አድረጉ እኔ የምላቹሁን አስተምሩ እኔ የምላቹሁን  መመርያ ተቀበሉ  ብሎ አገርን የሚያጠፋ ሆኖ ሰላገኙት የወያኔ ደጋፊ ባለመሆናቸው ብቻ  አገርን የሚያቀኑን መምህራን ትውልድን የሚቀርጹ  መምህራን በካድሬ በመተካት የተማረ እንዳይበቅልባት ያወቀ  እንዳይወጣባት ትምህርት ቤቶችና ዪንቨርስቲዎች ያቃጣሪወች መናህርያ  አድርጓታል። እንግዲህ ወገኔ የመምህራን መነካት የኢትዮጵያ አንዱ መሰረቱ እየተናጋ ነውና  ልትነቃ እና  የወያኔ አገር አጥፊነቱን አውቀን በቃህ ልንለው ይገባል።

ገበሬ……

አገር የምትኖረው ገበሬው አምርቶ በሚያበቅለው ምርት ነው ገበሬው ጠንክሮ በማረስ አገርን በመመገቡ ሂደት የአገርን መሰረት ነው። ዛሬ  ገበሬው ከመሬቱ በማፈናቀል ለውጪ ባለሃብት  ለኢንቬስተር በመስጠት እንዲሁም በግድ  ማደበርያ  እንዲወስድ እያደረጉት  ባለ  እዳ በማድረግ እዳውን መክፈል ሳይችል ሲቀር መሬቱን ጥሎ እንዲሄድ በማድረግ ተሳዳጅ አድርገውታል። ገበሬ የለም ማለት አገር የለችም ማለት ነው ።ገበሬው በማሰቃየት እረፍት በመንሳት  እስመርረውት ያሉት ወያኔወች ሃሳባቸውም ራያቸውም ሰለ  ኢትዮጵያ  እና ሰለ ሕዝቧ ስላልሆነ ስለሚያደርጉት ነገር  መጸጸት እንኳን አያሳዩም ስለዚህ ገበሬው ሲነካ የአገር መሰረት  መነካት ነውና ወገኔ እንግዲህ ንቃ።

ወታደር…..

አገር የምትጠበቀው በወታደር ነው አንድ አገር ጠንካራ የወታደር ከሌላት  ጠላት በቀላሉ ይዳፈራታል። ስለዚህ ጠንካር የወታደር ተቋም  ለአገር አጥርም መሰረት ነው። ዛሬ ግን ወያኔ እየሰራ ያለው የወታደር ተቋም  በወታደራዊ ስልጠና  እንዲሁም ትምርት በብቃት  የሚበልጣቸው እያሉ  ትግሬ በመሆኑ ብቻ  አዛዥ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ይደረጋል  ይሄ አካሄድ ለወያኔወች የአገር ማፍረስ አላማቸው ስለሆነ  ምንም አይሰማቸው  ለትግሬወች ግን  ጊዚያዊ ሹመት ሲሰጣቸው ሁሉንም ቦታ ያለ እውቀታቸው ቦታውን እንዲይዙት ሲደረግ ለምን ብላቹ መጠየቅ  ሲገባቹሁ የተሰጣችሁን ስልጣን ተቀብላቹ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ላይ  በደልና ጫና የምትፈጥሩ እንግዲህ እዳው በእጃቹ ነው። የወያኔ ባለስልጣን ባንተ ስም የአገርን ንብረት እየዘረፉ  እያሸሹ ይገኛሉ አንተ ግን  ከህብረተሰቡ ጋር የትም አትሄድም  ያኔ  በሰፈሩት መስፈርያ  እንዳይሆንባቹሁ የትግሬ ተወላጆች  በወታደር  ላይ የምታደርጉትን በደል ታቆሙ ዘንድ ያስፈልጋል። እንተም ከጥቂት የአገር አጥፊ እና ዘረፊ ጋር ባለመወገን አንድነታቹሁን የምታሳዩበት ጊዜ በጣም አጭር ነውና ይታሰብበት። ካለበለዚያ ግን  ወደ የኢትዮጵያ  የመከላከያ ሰራዊት ደምና ጉልበት እንዲሁም በኢትዮጵያ ሕዝብና  ሃብት እንደፈለጋቹ እየሆናቹ የምትኖሩበት ጊዜ ማብቂያው ይመጣል።

ወታደሩም እራሱንና  አገሩን ሕዝቡን የመጠበቅ ነጻ የማውጣት ሃላፊነት እንዳለበት ወያኔ የሚያውቅበት ጊዜ  ቅርብ ነው።  ወያኔወች የመከላከያ  ሰራዊት የሃገር መሰረት ስለሆነ ይህንም ለማፍረስ  እና ለመበተን ሌት ተቀን እየሰሩ ነው።  እውነት ነው መምህሩም ወደቀድሞ ቦታቸው  ተመልሰው ባላቸው እውቀት ጠመኔን ይዘው ያለምንም ተጽእኖ ዜጋን የሚያፈሩበት ጊዜ ቅርብ ነው። እውነት ነው ገበሬው ሞፈሩን አንስቶ  እርሻውን አስፍቶ  በትራክተር አርሶ  ሕዝቡን የሚመግብበት ቅርብ ነው ። እውነት ነው ወታደሩ ወያኔን የተባለ ወንበዴን አጥፍቶ ለሕዝቡና ለአገሩ ዘብ የሚቆምበት ጊዜ ቅርብ ነው ።

 

ሞት ለወያኔ!!!

አዲስ ብርሃኑ

Email- berhanu.addis@yahoo.com

29.09.2015

 

 

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ውሸትና የእኛ እውነት  ! –ነቢዩ ሲራክ

0
0
Nebiyu Sirakየማለዳ ወግ … ሀጃጆችን ፍለጋ …
===================
*  መረጃ ግብአት የሚና ጀማራት አደጋ  ፣
* ፍለጋው ! ጅዳ ቁስለኛ መካ ሟቾችና የጠፉትን …
* በሚና የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ሟች ፎቶ ቁጥር 1100 ደርሷል
* ከሌላ ሀገር ዲፕሎማቶች ምን እንማራለን  ?ፍለጋው ጅዳ ቁስለኛ መካ ሟቾችና የጠፉትን …
==============================ሁለት ሞቱ ሶስት ቆሰሉ የሚለውን የተዛባ መልዕክት ለአለቆቻቸው አስተላለፉ የተባሉት የሪያዱ ሀጃጅ ዲፕሎማት ወደ መጡበት ሪያድ ተመልሰዋል አሉ! በጠፉት ሀጃጆች ዙሪያ ማምሻውን የመከሩት የጅዳ ቆንስል ዲፕሎማቶች ነገ ጅዳ ባሉ ሆስፒታሎች የቆሰሉ ካሉ በሶስት ግሩፕ ተከፍለው ሊፈልጉ ተስማምተዋል ፣ ነገ ፍለጋ ይጀምራሉ መባሉን መረጃ ደርሶኛል።

ሚና ላይ ካሉት ሟቾችን ለማጣራት እርባና ያለው ስራ ያልሰራው የሀጅ ኮሚቴን ጨምሮ አንድ የጅዳ ዲፕሎማት መሰማራታቸውንም ሰምቻለሁ!  ከአፈጋው በኋላ የጠፉት እንደ ቀድሞ ጸሎተኞች ለስራ ቀርተዋል የሚል ጥርጣሬን ያነገቡት የሀጃጅ ኮሚቴው አባላት እስካሁን ኃላፊነት ወስደው ስላመጧቸው ሀጃጆች የጠራ መረጃ እየሰጡ አይደመም ።

እኔ የደረሰኝ ተጨባጭ መረጃ …
====================

እኔ ባለኝ መረጃ ፎቷቸው ከተለጠፈ ሟቾች የአስር ያህሉ ሬሳ ተገኝቷል ። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ግን 2 ሞቱ 3 ቆሰሉ ይለናል!  አንድ በሚና ሆስፒታል ግፊት ተቀብሯል! እንዲያግባባን የተቀባሪውን ሬሳ መለያ ኮድ 36.1.832 መሆኑን የተጨበጠ መረጃ ይዘን ስለመነጋገራችን አስረጅ ከሆነ መልካም … ይሁን እንጅ ቆንስል መ/ቤቲ ያለ ቤተሰብ ፍላጎት የተቀበረውን ወንድም ጉዳይ ለማጣራት እስካሁን የተጋ የለም!

ከሌላ ሀገር ዲፕሎማቶች ምን እንማራለን  ?
===========================

በነገራችን ላይ አደጋውን ተከትሎ ሞቱ ተብሎ የተነገሩ ሀጃጆች ቁጥር 769 ደርሷል ቢባልም በሚና ፎቷቸው የተለጠፈ ሟች የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ቁጥር 1100 ደርሷል ። ጉዳዩ እንዴት ነው ? ቁጥሩ ማደጉ ለምን አልተነገረም ብሎ የጠየቀ የሳውዲ ጋዜጥ አዘጋጅ ወዳጀ ቁጥሩ ያፈገበት ምክንያት በሀጅ ወቅት አደጋውን ብቻ ሳይሆን በልብ ድካምና በተለያዩ ምክንያቶች የሞቱትን ሃጃጆች ስለሚጨምር መሆኑ እንደተገለጸለት አጫውቶኛል ። ሌላው የበርካታ ሀገር ዲፕሎማቶች መካ ፣ ሚናና ጀማራት የዜጎቻቸውን መዳረሻ ለማጣራት ነቅለው መከተማቸውን ዛሬ በሳውዲ ጋዜጥ ባቀረበው ዘገባ ገልጾታል። ዲፕሎማቶቹ የዜጎቻችን ናቸው ብለው የሚጠራጠሩትን የፎቶ ክምችት በመቀበልና በኮንፒተራቸው በመጫን ከሳውዲ አልፎ ሀገር ቤት በመላክ የሚያውቋቸውን እያፈላለጉ መሆኑ ተጠቁሟል ።

ጠፉ ፣ ሞቱና ቆሰሉ የሚባሉትንም ዝርዝር መረጃ በማህበራዊ ድህረ ገጾችና በቆንስልና በኢንባሲዎቻቸው ለእይታ ቅርብ ማድረጋቸው ይጠቃሳል  ! ከዚህ መሰሉ አሰራር የምንማረው ቢኖር ልምዳቸውን ማጋራት ወደድኩ  !
ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በሚና ጀማራት አደጋ ዙሪያ የሰራው ዘገባ ከዚህ ጋር ተያይዟል!

ነፍስ ይማር  !ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 18 ቀን 2008 ዓም

 


ኢትዮጵያዊ ማንነት እንዴት ያለ ነው? ኢትዮጵያዊ አንድነትስ ምን ይመስላል? (የግል እይታ –ዮናታን ረጋሳ

0
0

እውን ኢትዮጵያዊነት ወይም የኢትዮጵያ አንድነት ሲባል በሁላችንም አእምሮ ውስጥ አንድ አይነት ምስል ይከሰታል? አንድ አይነት ትርጓሜስ ይኖረዋል?

Yonatan Regas - Satenawአንዳንዴ ሳስበው በእያንዳንዳችን አእምሮ ውስጥ ያለውን የኢትዮጵያዊነት እይታ ወደ ውጪ አውጥተን ብናስተያየው አንዱ ከአንዱ እጅግ የተለየ እንደሚሆን አልጠራጠርም፡፡ አንድነት/ ኢትዮጵያዊነት የሚለው እሳቤ በመርህ ደረጃ ሁሉም የሚቀበለው ሸጋ ሀሳብ ቢሆንም በአረዳዳችን ላይ ግን እጅግ እንደምንለያይ ይሰማኛል፡፡ ይህን ፅሁፍ ማዘጋጀቴም በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ የተለያየ ስሜት እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን አውቆ መመርመር እና መረዳት ምናልባትም የተቀራረበ እይታ ለመፍጠር ይረዳል ብዬ ስለማስብ ነው፡፡ በቀናነት ታነቡልኝ ዘንድ እጠይቃለሁ!

በኔእምነት በኢትዮጵያ ግዛት ስር ያለው ሁሉ ኢትዮጵያዊ ነው ቢባልም ቅሉ ከቦታ ቦታ ያለው የኢትዮጵያዊነት ስሜት ግን የተለያየ ነው፡፡ ግለኝነት እና አለማቀፋዊነት ተፅዕኖ ስር ያለ ማንነት፤ ከተለያየ የህብረተሰብ ክፍል በመወለድ(ቅይጥ በመሆን) የሚፈጠር ማንነት፤ በፖለቲካ የተቃኘ ታሪክን (politicized narrative of history) መሰረት ያደረገ ማንነት፤ ያለፉ ነገስታት እና ገዢዎች የእርስ በእርስ ጦርነት ባስከተለው ‘የእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ’ ስነልቦና የተፈጠረ ማንነት፤ በነገስታቱ እና በፈላጭ ቆራጮች አምሳል ተገንብቶ ተከታይ ያፈራ ማንነት . . . እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች የሚፈጥሯቸው ማንነቶች ተደባልቀው በውጥረት ውስጥ የተገነባ አንድነት መገለጫችን ይመስለኛል፡፡

በመሰረቱም ኢትዮጵያዊነትም ሆነ የኢትዮጵያ አንድነት ወጥነት ያለው አይደለም፡፡ በዘመነ መሳፍንት ተበታትኖ የነበረው ሀገሪቱ ክፍል በነ አፄ ሱስኒዮስ ከነበረው ሰፊ የግዛት ክልል በፍፁም የተለየ ነው፡፡ አፄ ቴዎድቶስ ያቀኑት ሀገር አፄ ምኒልክ ካቀኑት ሀገር የተለየ ነው፡፡ አፄ ምኒልክ ይገዙት የነበረው ሀገር በቀኃሥ እና በኮምኒስት ኢትዮጵያ መልኩን እየቀያየር አልፎ አሁን ላይ አድርሶናል፡፡ የማንነት ትርክቱም ሆነ የአንድነት ይዘቱ በነዚሁ ዘመናቶች እንደገዢዎቹ የተለያየ ነው፡፡

ይህ ልዩነት በየዘመኑ ከተነሱ ነገስታት እና ፈላጭ ቆራጮች ፍላጎትና ህልም ጋር ተሳስሮ አሁን ካለንበት ዘመን ያደረሰን ሲሆን፤ ህዝቡ ግን ከገዢዎቹ ፍላጎት ውጪ የራሱን እድል በራሱ የወሰነበት አንድነቱንም ሆነ ማነቱን በራሱ የማህበረሰብ ስብጥር አምሳል የፈጠረበት ጊዜ የለም፡፡ (ይህ ሲባል ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ በርካታ ማህበረሰቦች የእርስ በእርስ ትስስር እና ዝምድና አልመሰረቱም ለማለት ሳይሆን – በዘመናት ውስጥ በነበረው የአንዱ አካባቢ ገዢ ሌላኛውን በጉልበት አስገብሮ ለመግዛት በተደረጉ ጦርነቶች ከቦታ ቦታ የተለያየ ስነልቦና የተላበሱ ማህበረሰቦች እንደሚኖሩ ማድረጉ የሚካድ አለመሆኑን ለማመላከት ነው፡፡)

ለዚህም ነው የኢትዮጵያ አንድነት ተጀምሮ ያልተጠናቀቀ፤ ኢትዮጵያዊነት ሲባልም ወጥነት የሌለው ነው የሚል የመከራከሪያ ሃሳብ ለማንሳት የምወደው፡፡ በታሪክ አንዱ አንደኛውን ማህበረሰብ በጉልበት እያስገበረ አሁን ላይ ደረስን እንጂ – በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ በህዝቦች መተማመን እና መፈቃቀድ የተገነባ አንድነትም ይሁን ወጥ ኢትዮጵያዊ ማንነት ዛሬም ቢሆን የለንም፡፡ ኢህአዴግም ሆነ ፋሺስት ኢጣልያ የልዩነታችን ፈጣሪዎች ሳይሆኑ በዘመናት ውስጥ በተለያየ ትርክት የነበረ ልዩነታችንን ተጠቅመው ‘የከፋፍለህ ግዛ’ አገዛዝን ለማስፈን መሞከራቸውን መገንዘብ – በነሱ እያሳበቡ ልዩነትን በመሸፋፈን ለበለጠ ችግር ከመጋለጥ ያድናል፡፡

ከላይ ያሰፈርኩትን ሀቲት መሰረት አድርገን የከተሜውን (በተለይም የትልልቅ ከተሞች) የማህበረሰብ ክፍል የሚኖረውን ስነልቦና እንፈትሽ እና ወደ ቅድመ ነገራችን እንመለሳለን፡፡ (ይህን የመፈተሸ አስፈላጊነት ከተሜው በፖለቲካው ላይ የሚኖረውን ጉልህ ተፅዕኖ ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡)

{{ከተሞች የነገስታት እና የፈላጭ ቆራጮች መቀመጫ የነበሩ ከመሆናቸው አንፃር (በአንዳንድ ስፍራ መስራቾቹም እነሱው ናቸው) የከተማው የማንነት እና ሀገራዊ አንድነት መንፈስ የነዚህኑ የገዢዎች እምነት የሚያንፀባርቅ ይሆናል፡፡ አንድነት የሚለውንም ሆነ ኢትዮጵያዊነት የሚለውን እሳቤ እንደ ገዢዎች እምነት፣ ፍላጎት እና ህልም የሚገነባ ነው፡፡ ወደነዚህ ከተሞች ከተለያየ ማህበረሰብ ክፍል ፈልሰው የሚመጡ ሰዎችም ከተሞቹ ውጠው የሚያጠምቋቸው ማንነት በነገስታቱ መልካም ፈቃድ የተገነባውን ማንነት ይሆናል፡፡ ወደ ከተማው የሚዋሃዱ ሰዎችም ይህንኑ የከተሜ ስነልቡና መላበስ እና እንደኖርም የተዘረጋውን ማንነት ተቀብለው መኖር ይጠበቅባቸዋል (ይመቻቸውም አይመቻቸውም)፡፡ እዚህ ላይ ልብ እንዲባል የሚያስፈልገው ነጥብ ታዲያ ነገስታቱም ሆነ ፈላጭ ቆራጮቹ ፍላጎታቸውም፣ እምነታቸውም ሆነ ማንነታቸው ከተፈጠሩበት ማህበረሰብ የሚመነጭ መሆኑና በሚገዙት ሀገር የሚያሰፍኑት ስርዓትም በዚሁ መልክ የሚቃኝ መሆኑ ነው፡፡}}

እንግዲህ ይህን ይዘን ስለ ታሪካዊ ዳራው እና የት እንዳደረሰን ጠቅለል ያለ ዳሰሳ እናድርግ –

ከላይ እንዳነሳሁት ‘ስዩመ እግዚአብሔር’ ገዢዎች በታሪክ አጋጣሚ የጀመሩት ‘ኢትዮጵያ’ የሚለውን ግዛት የማስፋፋት፤ በውስጡ ያቀፈውንም ማህበረሰብ የማዋሃድ (with their mighty)፤ በዚሁ ግዛትም ኢትዮጵያዊ የተሰኘ ማንነት የመገንባት ውጥናቸው ሳይቋጭ የዓለም ሁኔታ በፍጥነት መቀያየር ጀመረ፡፡ የዲሞክራሲ ጥያቄ በዓለም ጭቁን ህዝቦች ዘንድ እንደ ሰደድ እሳት ተዛመተ፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያም የዘመኑ የፖለቲካ አካሄድ በመቀየሩ ያስገበሩትም ሆነ የገበሩት ማህበረሰቦች ጨርሰው ሳይዋሃዱ የተነሳው የዲሞክራሲ ጥያቄ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ስለህልውናውም ጭምር እንዲታገል የሚገፋፋ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ተከፈተ፡፡ የኢትዮጵያዊ ማንነትም ሆነ አንድነት አንዱ አንደኛውን እያስገበረ የመሆኑ ትርክት አክትሞ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በእኩልነት እና በመተማመን ላይ ተመስርቶ በግዛቲቱ ውስጥ ውህደቱን የማካሄድ ጉዳይ 19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ክስተት ሆነ፡፡ (ሜጫና ቱለማ፤ ቀዳማይ ወያኔ እንዲሁ ሌሎች ንቅናቄዎችም በዚሁ ማእቀፍ መታየት የሚችሉ እንደሆኑ ይሰማኛል)

በዚህ ታሪካዊ ኩነት የተፈጠሩ መልካም አጋጣሚዎች እና ንቅናቄዎች ግን በኣዳዲስ ጉልበተኞች እና ኋላቀር የስልጣን ጥመኞች ተጠለፉ፡፡ ግልፅ የነበረውን የሀገሪቷን የጦርነት ታሪክ አንዱ አንዱን በማስገበር ግዛት የማስፋፋት እና ማንነት የመገንባት የታሪክ ኩነቶችን የሚያዛቡ አዳዲስ የታሪክ ድርሳናት በብዛት ተከተቡ፡፡ የእነዚህ ድርሳናት ትርክትም በአመዛኙ የጉልበተኞቹን የስልጣን ፍላጎትና የፖለቲካ ዓላማ ለማሳካት የተፃፉ በመሆናቸው ብዙኃኑን ሰው የጠራ ምልከታ እንዳይኖረው አድርገዋል፡፡ አንዳንዶቹ የታሪክ ኩነቶችን የበቀል መሳሪያ ሊያደርጓቸው አዛብተው መርዝ እየረጩ ሲፅፏቸው፤ አንዳንዶች ደግሞ የተለያየ የታሪክ ኩነቶችን የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል ገድሎች ብቻ አድርገው ማቅረባቸው – በእኩልነት እና በመተማመን ሀገር ለመገንባት የተነሳሳውን ቀና መንፈስ እንዲጠለፍና ልዩነታችን የጠላትነት ስሜት መንሰራፊያ እንዲሆን በር ከፈተ፡፡

ሁሉም የየራሱን ፖለቲካዊ ትርክት እያበጃጀ ከሌላው ጋር ሊያግባቡት የሚችሉትን ድልድዮች በማፍረስ ተጠመደ፡፡ ስለማንነት በሚደረጉ ክርክሮችም ላይ አንዱ ትግሬ ነኝ ቢል ‘ዘረኛ’፤ ሌላው ኦሮሞ ነኝ ሲል ‘ጠባብ’፤ አማራ ነኝ የሚለውንም ደግሞ ‘አማራ በዚህ ደረጃ አይወርድም’ በሚሉ ሽምቀቃዎች እና ፍረጃዎች ቀናው መንፈስ በክፉ መንፈስ ተበከለ፡፡ ኢትዮጵያዊነቴን ብቻ ነው የማውቀው የሚልም ነፍጠኛ የሚል ማእረግ ተለጠፈለት፡፡ ኢትዮጵያዊነትም ለአንደኛው ወገን የመጨቆኛ መሳሪያ ሲሆን ለአንደኛው ወገን ደግሞ ሰው የመሆንና የሀገር ወዳድነት ደረጃን አጎናፀፈ፡፡ መጨቆኛ አይደለም የሚለው የጨቋኝ ጠበቃ ተደርጎ ሲሳል፤ በኢትዮጵያዊነት ላይ ነቀፋና ሂስ የሚሰነዝር ደግሞ ‘ውግዝ ከመ አርዮስ’ እየተባለ ተወገዘ፡፡ አፎች ተከፈቱ – አንደበቶች ተለጎሙ – ችግራችን ስር ሰደደ፡፡ እንግዲህ በሁለት ስለት መወጋት ለማንም አልበጀምና ሁሉም ወደመረጠው እና ወደወደደው ጎራ ገብቶ በጥርጣሬ መተያየት የወቅቱ እጣ ፈንታችን ሆነ፡፡

እኔ በፍቅር የነደድኩላት፤ ጠንካራ አንድነቷን የማልምላት ኢትዮጵያ እንግዲህ ይህን ትመስላለች፡፡ አንገቷን ተቀንጥሳም ትምህርት መውሰድ አቅቷት፤ ልሂቃኖቿም ጎራ ለይተው እንደተፋጠጡ፤ ከተሜውም በግላዊነት ግዴለሽ ስሜት ሲሰምርለት ወደ ሌላው የዓለም ክፍል እየሄደ ራሱን የአዲስ ማንነት ባለቤት ሲያደርግ – የተቀረው ደግሞ ከላይ በጠቀስኩት መልኩ በገዢዎች አምሳል የተፈጠረ ማንነት ላይ በፍቅር ተጣብቆ ሌላውን ለመስማት ጆሮ ዳባ ልበስ ያለ ይመስላል፡፡ ጥቂቶች ደግሞ ከታሪክ ተምረን አካሄዳችንን እንድናስተካክል፤ ከስሜት ወጥተን በምክንያታዊነት እንድንነጋገር ዛሬም በብዙ ፍረጃ እና ማሸማቀቅ መሃል ይመክራሉ – አድርባይ፣ አሽቃባጭ፣ ዘረኛ፣ መሃል ሰፋሪ… መባል ሳይገታቸው/ፋቸው አቅጣጫ ይጠቁማሉ፣ መላ ይላሉ፡፡ ሰሚ ግን የለም! ጉልበተኛውም ተመችቶታል፤ የለውጥ ሀይሎችም እነሱ ከያዙት ውጪ ሌላ መንገድ አይታያቸውም ወይም ሌላኛውን መንገድ በመፈረጅ ያርቁታል – ሁሉም ለየራሱ ልክ መሆንን መርጧል፡፡ እውን ይሄ አካሄድ የት ድረስ ይወስደናል??? ነፃነት፣ እኩልነት እና ፍትህ የተነፈገው ህዝባችን የፖለቲካ ድራማችንን ሳይሆን የነፃነት ትግላችን ችግሮቹን ይፈታለት ዘንድ ያስተማራቸው ልሂቃኖቹን ሆደ ሰፊ እና አስተዋይነት የተመላ መሪነት በተስፋ ይጠብቃል፡፡

ከዚህ በኋላም ቢሆን ከፖለቲካ መሪዎች፣ ከአክቲቪስቶችም ሆነ የኔ ብጤ የመብት ታጋዮች የሚጠበቀው ነገር በተመስጦ ማሰላሰል፣ መደማመጥ እና አብሮ ለመስራት እውቅና መሰጣጣት ወሳኝ ነገር ይመስለኛል፡፡ በየትኛውም የፖለቲካ አሰላለፍ ውስጥ እንሁን ከመናናቅ ወጥተን የሁላችን የሆነች ኢትዮጵያን በሁላችን መልካም ፈቃድ እና መተማመን ለመገንባት መከባበር የመጀመሪያው እርምጃችን መሆን አለበት፡፡ የደጋፊ ብዛትና የስሜት መስመር ተከትለን ስም ከመሰጣጣት ተላቀን፤ እኔ ብቻ ልክ ነኝ ከሚል አስተሳሰብ ወጥተን – ሁሉንም ማስተናገድ የሚችል የፖለቲካ ምህዳር የመፍጠር ፍላጎት እና አቅም እንዳለን ከአሁኑ ማሳየት – ለዚህም መነጋገር ይጠበቅብናል፡፡ “የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል” እንደሚባለው ሊያጠፉን የሚሹ ሃይሎች መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኙ ከተራ ብሽሽቅ እና እልኸኝነት ተላቀን፤ ዶግማቲክ የሆነውን ነባር የፖለቲካ ባህል ትተን – እውቅና በመሰጣጣትና በመቀራረብ ቀዳዳዎቹ የሚደፈኑበትን መንገድ መምረጥ ወቅቱ የሚጠይቀን ወሳኝ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡

ኢትዮጵያ ለሁሉም፣ ሁሉም ለኢትዮጵያ!

/በአገላለፄ ያስቀየምኩት ሰው ካለ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ! ለውይይት፣ ለሙግት እንዲሁም ከተሳሳትኩ ለመታረም ክፍት ነኝ፡፡/

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ! ዮናታን ረጋሳ

ማስተዋል። (ሥርጉተ ሥላሴ)

0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 30.09.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

አትቀመሽ – ኃይለኛ ነሽ። …..

አትጠጪ – መራራ ነሽ። …….

አትዋጭም – ጎምዛዛ ነሽ፤

አፈ ታሪክ እልም – አይደለሽ። …..

ቁልጭ ብለሽ  – ትታያለሽ፤

እውነት ደፋር ካላገኘሽ፣

ቃና የለሽ ትሆኛለሽ። ሽሽሽ-ሽሽሽ-ሽሽሽ-ሽሽሽ-ሽሽሽ ……

ሰላም ነው – እንዴት አላችሁልኝ – ክብረቶቼ? ደህና ናችሁ ወይ?

ሰንበትን ተንተርሶ የትንቢቴን ፍጻሜ – እያያችሁ፤ ልዑቅ በሉኝ ሲል ሌላም፤ በሰው ልጆች በመኖር ሂደት ውስጥ ስለሚፈጠሩ ገጠመኞችም ሟርትን በመመኘት፤ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ – አስነብቦናል። መርመጥመጥ። የሆነ ሆኖ ባላገኛቸው ህልሞቹ – የቁራኛ እስረኛ ዕሳቢዎቹ ዙሪያ ትንሽዬ ነገር ማለት – እሻለሁ።

Neamen zeleke zehabeshaየተከበሩ አቶ ነአምን ዘለቀ የአርበኞች ግንቦት 7 የዓለም አቀፍ አመራር፤ የውጪ ግንኙነት ኃላፊና የንቅናቄው የምክር ቤት አባል፤ የዘመቻ እንቅስቃሴያቸውን አስመልክቶ ብዬም ነበር ዓይነት ነው። እንዲህም ይለናል እኛንም አክሎ … ይወርፈናል፤ „ተመላሹ  ታጋይ የኢሳት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የአርበኞች ግንቦት ሰባት የውጪ ጉዳይ ሃላፊ፤ ጓዜን ጠቅልዬ ለትግል ገባሁ ብለውን በሰበር ዜና ሰምተን ነበር። ሰው፤ ምነው ለድል ሳያበቁን ተመለሱ ብሎ ህዝቡ መጠየቁ አይቀርምና፤ አስቀድመው በየሜዲያው ላይ፤ ወከባ መፍጠር ተገቢ መስሎ ታይቷቸዋል። “ጉሮ ወሸባዬ ባልዘፈንሽ፤ ዘንድሮ ባላፈርሽ” ይላል የአገሬ ሰው። ምናልባት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች፤ በራሳቸው ፈቃድ፤ ይሸወዱ እንደሆን ነው እንጂ፤ የሚዲያ ወከባው፤ በነቃው ሕ/ሰብ ዘንድ ውኃ አልቋጠረም ። ዛሬ ሰው ፤ እንደ ድሮው ዝም ብሎ “ይሁን እስቲ” እያለ ማለፉን ትቶታል ። መጠየቅ ጀምሯል ። እኔም እንዲሁ አንዳንድ ጥያቄዎችን ላነሳ ነው ። በአሜሪካ ድምፅ ከተላለፈውም ሆነ ፤በኢሳት ተደረገ፤ ከተባሉት ቃለ-መጠይቆች፤ ባዶ የሆኑትን ስሜት የማይሰጡ፤ አባባሎች ትቼ፤ የተወሰኑ ነጥቦችን ቀጥዬ አነሳለሁ።“

„ምናልባት ደጋፊ የሆኑ ሰዎች፤ በራሳቸው ፈቃድ፤ ይሸወዱ እንደሆን ነው እንጂ፤“ ይሄ ነው መነሻዬ። ስለምን እንሸወዳለን? የራሳችን ጌቶች እራሳችን መሆናችን ብቻ ሳይሆን፤ መነሻችንም፤ መድረሻችንም በበቀልና በጥላቻ ያልበከተ፤ ለመርህ የሚገዛ ህሊና ስላለን ጊዚያዊ ወጀብ ወይንም አውሎ ከዓላማችን ንቅንቅ – አያደርገንም። ወይንም በፋሻ ተጠቅልለን የግል ኢጓ ገመናችን እንደ ቄጤማ -አንነሰንስም። ቋሚ ፍላጎት አለን። ጽላታችን ከፋሽቱ ህወሓት የምትላቀቅበት ማናቸውም መንገድ ውስጣችን ነው። ለበጎ ነገሮች – ለአዎንታዊ ጠረን ብቻ መፈጠራችነን አስምረን – እናውቃለን። „አቤቱ ንፁህ ልብን ፍጠርልኝ፤ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ  አድስ።“ (መዝ ምዕራፍ ፶ ቁ. ፲ ) የህይወት ዘመናችን ሰማያዊ መርህ ይህ ነው፤

የማከብራችሁ  – ናፍቆቶቼ የእናት ኢትዮጵያ ልጆች። „ባዶ“ የተባለውን የጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ስላቅን – እንዲህ ከመሰረት ብነሳ የተሻለ ነው። በጥልቀት ሳይሆን በጫፍ እጅግ በስሱ ንድፈ ሃሳብ ትንተና ነገር ….

ድርጅት ማለት ምን ማለት ነው? ድርጅት ማለት – ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ወይንም ስብስቦች፤ በፍላጎታቸው ወይንም በዓላማቸው ወይንም በእምነታቸው ዙሪያ የሚሰባሰቡበት የሰዎች ማህበር – የወልዮሽ ማእከል ሲሆን፤ ጊዜያዊ ወይንም ቋሚ ሊሆንም ይችላል። ድርጅት አጭርና ረጅም ራዕዮችን ለማሳካት የሚያስችል ተቋም፤ አሰባሳቢ ማእድ ነው። ሰብሳቢም ነው።

በተለይ የፖለቲካ ድርጅት ከሆነ ሰፊ ህዝባዊ ኃላፊነትን ወስዶ – ይደራጃል። ስለሆነም የፖለቲካ ድርጅቶች መሰረታዊ ሰነዶቻቸውን መሰረት ያደረገ መርኃ ግብር አላቸው። አካሎቻቸው የሚፈጠሩትም በአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ነው። በየደረጃው የሚካሄዱት ጉባኤዎች ምክር ቤታቸውን ይመርጣሉ። ምክር ቤቱ ደግሞሥራ አስፈጻሚውን ይመርጣል።

ተግባራቸው — ጉባኤው እስኪሰበሰብ ድረስ ምክር ቤቱ የጉባኤውን ኃላፊነት ወስዶ – ይሰራል።፤ ምክር ቤቱ እስኪ ሰበሰብ ድረስ ደግሞ የድርጅቱን ዕለታዊ ተግባሩን የሚከወነው ሥራ አስፈጻሚው ይሆናል።

የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቲው የበቃ ውክልና ስላለው፤ የድርጅቱ አካላትን ሆኑ አባላትን እንደ የኃላፊነታቸው – ይደለድላል፤ ያሰማራል፤ ተግባራቸውን – ይገመግማል፤ ተጨማሪ ኃላፊነቶችን – ይሰጣል። በፈለገው የግዳጅ መስመር – ይልካል። የፓርቲ አባላትም በየደረጃው ያሉ አካላትን በመብታቸው ተጠቅመው በፈቃዳቸው እንደ መረጡ ሁሉ፤ ለመረጡት አካላት የስምሪት ድርሻን በውዴታ ተቀብሎ ኃላፊነትን የመወጣት ግዴታ – ይኖርባቸዋል። መብትና ግዴታ ተግባር ላይ በዚህ መልክ ኪዳን – ያስራሉ።

እና ለእኔ የአቶ ወንድም የትንተና አግባብ – የፓርቲ የአደረጃጀት መሰረታዊ መርህን ካለማገናዘብ የመጣ ነው። በተጨማሪም ዘመኑ 21 ኛው ምዕተ ዓመት ላይ ነን። የሰለጠኑ ሂደቶች እንዲስተናገድባቸው ግድ ይላል። ሰው አልባ አውሮፕላን የግዳጅ ስምሪትን እያዬን እኮ ነው። ሥልጣኔው በራሱ ከዴሞክራሴያዊ ፍላጎት አፈጻጸም ጋርም በመስተጋብር የተቃኜ ነው። ይህም ብቻ አይደለም፤ ስለ አርበኞች ግንቦት 7 መሪዎች የተግባር ስምሪት ቀዳሚ መረጃ ለማግኘት አቅሙ – አይፈቅድም። በፓርቲው ውስጥ እሱ እራሱ ጋዜጠኛው የለም። በይሆናል እና በነሲብ ደግሞ የፓርቲ መርህ እንዲህ ለቡና ተርቲም – አይደፈርም። ስለዚህም እንደ ማንኛውም ዜጋ እኩል ሁሉ የሚሰማውን ብቻ መስማት ግድ ይላል። በሌላ በኩል የነፃነት ትግል የሠርግ ርችት የሚተኮስበት – አይደለም። እንደ ቄጤማ የአካላቱ ስምሪትም አይነሰነስም። መራር ትግል – ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ዲስፕሊንን – ይጠይቃል።

ከሁሉ በላይ እንደ ቀደመው ጊዜ የፍንጪ ቧንቧው አይገኝም – ተከርችሟል። እስከ አሁን የተከፈለው መስዋእትነት – ይበቃል። የኢትዮዽያ ህዝብ አርበኞችና የግንቦት ውህደቱ ይህን ሁሉ እምስ ፍላጎቶችን – አምክኗል። ለዚህም ነው ነጋ ጠባ ሥጋ እንደ ተቀማ ሥጋ በይ እንሰሳ ጉምጅቱ በብራና እና በብዕር ላይ ሲደፋ የምናዬው፤ የእንብርክክ – የሚያስኬደውም፤ ለዚህም ነው በመደዴና በድንብስ ታቱ – የሚባላው። የባላደራው ራዕይ እንደ ቀደመው ጊዜ – እንደ ረጋ ኩሬ ባለህበት እርገጥ ዛሬ የለም። እያንዳንዷ ማዕልት በቅኔ ጥልፍ የተቃኘች ስለሆነች፤ ከፍጥነቱ ጋር ለመጓዝ ነሲብ የሙጥኝ ማለት ግድ – የሆነውም ለዚህ ይመስላል። ሰረገላው ባለቤት አለው። ገና ምን ታይቶ። የአፍሪካ ቀንድ የፍቅር ናሙና ቀንዲል – ትሆናለች። ምእራቡ ዓለም ይሁን የኤርትራ መንግስት ፋሽስቱን ህወሃትን ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን፤ የነገውን የተረጋጋ ሥርዓት ለመዘርጋት በሰፊ ትእግስት የጠበቁትን፣ የተመኙትን አግኝተዋል –  ብየ አስባለሁ – እኔው። ህልሙ ያልተሳካለትም አቅሙን – ይጠይቅ። የአቅሙ ምጣኔ – ኮከብ ቆጣሪ ሳይጠይቅ  – ደረጃውን ይነግረዋል። ምን ያህል ተጉዞ  – ምን እንዳተረፈ?

አርበኞች ግንቦት 7 ተገብቶ የተፈለገው መረጃ ተዝቆ የሚወጣበት – አይደለም። አመሰራረቱ፥ የአትኩሮት መሰረቶቹ መርኽ  ከወትሮው እኛ ከምናውቀው ሆነ ከተለመደው የተለየ ነው። ስለሚጠጥርም ነው ወደ ትችቱ የሚዘነበለው። ፍልስፍናው እረቂቅ፤ በእውቀትና በብቃት የተገነባ ነው። ልምዱም ተመክሮውም በአዲስ የአስተሳሰብ ዲዛይን እንደ ራሳችን ሆኖ፣ ለነባር ድክመቶች በር ዘግቶ ከአዲሶችም ለመማር ፈቅዶ ነው  – የተፈጠረው። ማስተዋል። ለአዲሱ ሥልጡን ዘመን በተወሳሰበ ችግር ለማለፍ ብልህና ጥንቁቅነትን – ያስቀደመ። ማስተዋል። በእጁና በመንፈሱ ያለውን ስለሚያውቅም ነው ለተረት ተረቶች መልስ ሰጥቶ ደረጃውን ዝቅ የማያደርገው። ማስተዋል። ለዚህም ነው ለንቅናቄው አክብሮትን መንፈሳችን አብዝቶ የሚለግሰው። ጥቂቶች ደግሞ አዳዲስ ጠቃሚ ግኝቶችን እንደ መፍትሄ አመንጪ ሳይሆን፤ እንደ አንጡራ ጠላት በማዬት፤ አቅም ማጠሩ የብጭት እስረኛ ሲያደርጋቸው የሚታዩትም በዚህ ምክንያት ነው።

የተከበራችሁ የጹሁፌ ታዳሚዎች – ታስታውሱ እንደሆን ኤርትራ የገባው የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ መሪ አካል፤ በአርበኞች ካንፕ ተገኝቶ ባደረገው ንግግር የአቶ ነአምን ዘለቀ ቃል ጭብጥ እንዲህ ይል ነበር „ውጪ የሚገኘው ወገናችሁ ድጋፉ እንደማይለያችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።“ ይህ ማለት አቶ ነአምን ዘለቀ ይህን ሀገራዊ ኃላፊነት መውሰድ የሚችሉ ስለመሆኑ ይገልፃል። ለዚህ ቃል ጠንቋይም መጸሐፍ ገላጭም – አያስፈልግም። በኪዳኑ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ክቡርነታቸው እንዳሉበት፤ በኤርትራ ቋሚ ቆይታ እንደለላቸው – ይገልጣል። አንድን ሃሳብ ለዛውም የፖለቲካ ንግግር እንደ ወረደ – አይተረጎምም። ፈልፈል አድርጎ እያገላበጡ በቅንነት መመርመር – ያስፈልጋል። ይሄን ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ አላዳመጠውም። ወይንም ንግግራቸውን ለመረዳት አልቻለም ማለት ነው።

ለማንኛውም ይህ ገለጻ በቀጥታ ውጭ ባለው ተግባር ላይ እንደሚያተኩሩ፤ እድምታው ካለ አስተርጓሚ – ያብራራል። እንዲያውም ከሀገረ አሜሪካ ነቅለው እንዲወጡ አስደረግናቸው የተባለው ዜና ነው  „በሬ ወለደ“ የሚያሰኘው። ከዚህም በተጨማሪ ሌላም አመክንዮ ልከል፤ ፓርቲያቸው የመደባቸው ቦታና ድርሻቸው „የውጪ ግንኙነት ኃላፊ“ ይሄ ነው።

ይህ ዓለምአቀፋዊ ኃላፊነት ኤርትራ መሬት ላይ ተሁኖም  – አይሰራም። አቶ ነአምን ዘለቀ ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት የግድ ነው ወደ አሜሪካ መመለስ፤ ነገም ቢሆን ወቅቱ እንደሚጠይቀው ኃላፊነት ፓርቲው አካሎቹን ሊያንቀሳቅስ – ይችላል። በፈለገው ቦታና ጊዜ፤ በሚገጥመው አወንታዊ ሆነ አሉታዊ ተጨባጭ ሁኔታ የፈለገውን እርምጃ – ይወስዳል። ኮከብ ቆጣሪ – አያሻውም።

ወገኖቼ ጠቃሚው ነገር በልካችን „ልክ“ ሙያችን ለማስከበር መጣር ብልህነት – ይመስለኛል። ጎንደሬም ሲተርት „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላል። ቅን ወገኖቼ – የሀገሬ የኢትዮጵያ ልጆች እውነቱ ያለው ከፖለቲካ ድርጅቱ ከንቅናቄው ከመርኹ እንጂ ከቂምና ከጥላቻ ማሳ አይደለም። ቀረብ ብላችሁ የቆዩትን የምስረታ ንጥር ሂደቶች መልሳችሁ፣ መላልሳችሁ ስታዳምጡት ብልሃቱ  – ያስተምራችኋል። ከሽሽትም – ይታደጋችኋል።  እድሜ ያላስተማረው አልቃሻ ፍላጎት ጸጸትን አዝሎ – ይኖራል። ጊዜን ያላዳመጠ ስብዕና ማለቁን የሚያውቀው ከሹልከቱ በኋላ ነው።

አንዲት የመጨረሻ ብልህ ነገር፣ ልባም ግን የተመሰጠረች ነገር ላንሳ፤ ታስታውሳላችሁ አይደል? በውጭ ሀገር የሀገር ውስጥ ሰላማዊ ትግሎችን ለማገዝ ሆነ ለርዳት ስለሚደራጁት፤ በሀገር ቤት ላሉት ሁለገብ እንቅስቃሴው የውጭ ሀገሩ የሥነ – ልቦና እስረኛ ወይንም ጥገኛ ያደርገዋል። ፍላጎቶቹ በጫና የተወጠረ ነው። የሉዓላዊ ልዕልናው ነፃነቱ በስውር የታፈነ ነው። የኢኮኖሚ አቅም ጥገኝነቱ መብቱን – ይጫነዋል። እንደልቡ አያንቀሳቅሰውም ዋ፥ ሱ ስለሚባል ለብዙ ነገር የተጋለጠ ነው። የጥቅሙን ያህል ጉዳቱም ያን ያህል ነው። እርግጥ እነ ቅንዬ ሊኖሩ ይችላሉ፤ ቅኖች ግን ጥቂት ናቸው። በአርበኞች ግንቦት 7 ግን የጥፋቱ በሽታ ሁሉ አይደገምም። ስለምን? ማርከሻው በመዳፉ ውስጥ ነውና። አርበኞች ግንቦት 7 ሌላ ቅጥልጥል ቻፕተር – አላስፈልገውም። የእራሱ አካል ይህንን የውጭ ሀገሩን ተግባር በኃላፊነት – ይከውናል። መደበኛ ሥራው ነው። ሽክፍ ያለ – ትጥቁ ያማረ – ስንዱ። ማለፊያ። ልባም የተመክሮ – ተቋም።

አንዲት መሸብያ አመክንዮ ልከል – አቶ ነአምን ዘለቀ የአባቱ ታሪክ አስከባሪ ልጅ ፤ የጀግኖች ቁንጮ – ልዕልት ኢትዮዽያ በ100 ዓመት ከማታገኛቸው በኢትዮዽያ የባህር ኃይል ታሪክ ጉልላተ – ጀግና የሆኑት የኮማንደር ዘለቀ ቦጋለ ልጅ እኮ ነው። ኧረ ቀልድ – ይቁም። ወጣቶች – የእኔ ውዶች የለጠፍኩላችሁን – የውስጣችን ታሪክ ነበብ አድርጉና፥ ትናንትና ዛሬን የጀግናውን የአብራክ – መንፈስ ቃኘት – አድርጉት፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ አለ ከእኛ ጋር የጀግና – ጠረን። ታሪክ የጨዋታ ማሟያ አይደለም፣ ለባለ – ህሊናዎች። http://www.abugidainfo.com/index.php/9920/

ክወና – የማከብራችሁ የጹሁፌ ታዳሚዎች፥ ለኢትዮዽያ ህዝብ መልካም ዜና፣ የተስፋው ማህደር ነውና፤ በተስፋው ላይ የጉሮሮ አጥንት የሆኑ ዕሳቤዎችን መዋጋት የተግባራችን ሁሉ አህዱ ሊሆን  -ይገባል። ዛሬ አንድ በረሃብ የተጎዳ ወገናችን መልካም ሰምቶ ደስ ብሎት ሲተኛ፥ ላይመለስ ሊያሸልብ – በዛው እንደ ተኛ ሊቀር ይችላል። የዛች ቅጽበት ደስታውን እንደ ሰነቀ እንዳያልፍ፥ ይህ እንኳን ረመጥ የሆነባቸውን፤ አንደበቶች ሆኑ ብዕሮችን ልንታገላቸው – ይገባል። ለተስፋ ቀማኛ ርህርህና ወንጀል ነው። ተስፋ ለተስፈኛው ኑሮው፣ ህይወቱ፣ እስትንፋሱ፤ ቀልቡ፤ አደቡ፤ ነገው ነው። ነው። ነው። ይህ ሲያስቀና፤ ይህም ሲቀናበት የተገፋው ህዝብ ከፋሽስቱ ህወሓት የተላቀቀ ቀን ገመድ እራት ሳይሆን – አይቀርም። እንበርታ። ያ …. እንዳለፈው ….. ይህም ያልፋል። ይነጋል – በያነጋል።

የመስከረም 24.09.2015 የራዲዮ ሎራ Tsegaye Radio or www.tsegaye.ethio.info Aktuell Sendung ዝግጅት የመስከረም 5.2015 የአርበኞች ግንቦት 7 የድጋፍ ስብሰባ ሁለተኛ ክፍልና ሌሎችንም ለምትፈቅዱ ቅኖች አርኬብ ላይ ማዳመጥ – ትችላላችሁ። የጥራቱ ግድፈት የእኔ – አይደለም፤ የራዲዮ ዝግጅቱ ነው።

ሀገር የማዳን የደጀንነት ብሄራዊ በሳል የዕንባ ጥሪ  ….  የእመቤት ኢትዮጵያ ልባዊ ጥሪ ….

የማሸነፋችን መልእክቱ – የነፃነት ቀበኛ መረቦችን በተግባር ስንረታ ብቻ ነው። የእምዬዋ የመሃጸን ፍሬ ዘሮች – የጥቁር አንበሳ ጥሪ በረከት ተሳታፊ ለመሆን፤ የእናት ሀገር ብሄራዊ ለዕንባዋ ዋቢነት፤ ቀጠሮ አልባ፤ በቦታው መገኘትን በማስተዋል ይጠይቃል። ለሃዘኗ ቀን ጋባዥና ተጋባዥ – የለም። በህወሓት ለተጠቀጠቀው ዜግነት ሁሉም ደምመላሽ መሆን – ይገባዋል። የተቀደሰ ተሳትፎ የአደራ ኪዳናዊነት ነው። ሊንኮቹን ተከትለው ዝርዝር መረጃ – ያገኛሉ። በተሳትፈወት መጠን የነፃነት ናፍቆትን – ያቅፋሉ። በፍጥነተወት ልክም ህሊናዎት የእርስዎ፤ ስለእርስዎ የተፈጠረ መሆኑን – ይለኩታል። ሁሉም  – በመዳፈዎ። ፍቅር – ተስፋ  – ሐሤት – ማሸነፍ የነጋ ነገ። ቅድስት ነፃነት በብርክት አንባ።

http://ecadforum.com/category/events/

A call to the Salvation of Ethiopia in Chicago, IL, USA

A call to the Salvation of Ethiopia in Atlanta, Georgia, USA

A call to the Salvation of Ethiopia in San Jose, CA, USA

A Call to the Salvation of Ethiopia in Boston, USA

መሸቢያ ሰሞናት – ዘሃበሻ ትእግስታችሁ ዕለታዊ ትምህርት ቤቴ ነው። ኑሩልኝ።

አርበኞቻችን መንገዶቻችን ናቸው።

እልፍ ነን፤ እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

ይድነቃቸው ነፍስ ይማር !

0
0

[ቴዲ ድንቅ – አትላንታ]

ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ፣ የተወለዱት መስከረም አንድ ቀን ነበረ። በዚህ ወር መጀመሪያም ልደታቸው ታስቧል። አቶ ይድነቃቸውን የሚያውቅ ኢትዮጵያዊ ፣ ስለ ሥራቸው ጥቀስ ቢባል፣ ጋዜጠኞችም አውሩ ቢባሉ፣ ዘፋኙም ዝፈን ቢባል፣ በርግጠኝነት፣ የአፍሪካን ስፖርት ከአልኮል የጸዳ ለማድረግ ያደረጉት ጥረት መጠቀሱ አይቀርም። ከኢትዮጵያም አልፈው በአፍሪካ ደረጃ፣ በኳስ ሜዳዎች ውስጥ የአልኮልና ሲጋራ ማስታወቂያዎች እንዳይኖሩ ጥረዋል።
yid
በዚህ ነገር ሁሉም ያደንቃቸዋል – ዛሬም ድረስ። የሚገርመው ግን ይድነቃቸው ይደነቁበት እንጂ፣ ዛሬ ነገር ሲገለበጥ ማንም ምንም አላለም። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፣ ከእንግዲህ በኋላ” ካስትል [ቢራ] ፕሪሚየር ሊግ” መባሉ ዛሬ ይፋ ሆኗል።

ምክንያቱም ፣ የቢራ ፋብሪካው የፌዴሬሽኑ ትልቅ ስፖንሰር ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው። ድርጅቶች የተለያዩ ዝግጅቶችን፣ ግለሰብን፣ የግለሰብን ሥራ ስፖንስር ሊያደርጉ ይችላሉ። ቢራ ፋብሪካም ይሁን ወተት ፋብሪካ ፣ ያለ ገንዝብ መንቀሳቀስ በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ዝግጅቶችን፣ ግለሰቦችን ስፖንሰር ቢያደርጉ፣ ያንን ተጠቅመውም ራሳቸውን ቢያስተዋውቁ በግሌ አልከራከርም።

ነገር ግን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ የኢትዮጵያ፣ ለዚያውም በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያለ ተቋምን “ስፖንሰር” አደረጉ ተብሎ ስሙን እስከማስቀየር መድረስ፣ ለዚያም አንድ ወቅት ይድነቃቸው ተሰማ ሲመሩት ለነበረውና ብዙ የደከሙበት ፣ እንኳን ስሙን አሳልፈው ሊሰጡ፣ ከሜዳው ሁሉ ሊያርቁት የሞከሩትን ቢራ ስም ይዞ ሲመጣ ያስደነግጣል።

ይህን ያህል ፌዴሬሽኑ ገንዘብ አስፈልጎታል ማለት ነው? አንዳንዴ እኮ ባለው መንቀሳቀስ እንጂ፣ ያልታሰበና ከሰማይ ገንዘብ ዱብ ስላለ ብቻ ወስዶ ፣ ራስን ማስረከብ ተገቢ አይመስልም። ዛሬ ዛሬ የአንድ የአገር ቤት ክለብ ተጫዋቾች እንኳን የወር ደሞዛቸው ከ80ሺ ብር በላይ በደረሰበት ጊዜ፣ ያን ያህል ስምን በቢራ ፋብሪካ እስከማስቀየር ድረስ ለመድረስ ምን መዓት መጣ?

እንደተሰማውም፣ ለዚህ ስም መቀየር ፌዴሬሽኑ በዓመት 6 ሚሊዮን ብር ይከፈለዋል። ግን 6 ሚሊዮኑን ብር ምን እንደሚያደርገው ገና አላወቀም። ቀድመን ዕቅድና ፕላን አውጥተን፣ ይህን ይህን ልንሰራ ነው.፣ ግን ይህን ያህል ብር ያስፈልገናል ብለን ያላሰብንበት ነገር ከሆነ ፣ ገንዘቡ ያን ያህል አንገብጋቢ አይደለም ማለት ነው። ብር ስለተገኘ ብቻ አይወሰድም እኮ!

ነገ ደግሞ “ሲጋራ አጭሱ” የሚል ስም ያለው ፋብሪካ ስፖንስር ላድርግና 10 ሚሊዮን ልክፈል ቢልስ? “ሲጋራ አጭሱ ፕሪሚየር ሊግ” ሊባል ነው? በ እንደዚህ ዓይነት ጉዳይ ላይ ስፖርቱ የት ድረስ ነው ራሱን የሚጠብቀው?

ከ እንግዲህ በኋላ “ይድነቃቸው ተሳስተዋል” ልንል ነው ማለት ነው? እሳቸውን ነፍስ ይማር ማለት አሁን ነው።

(የሳዑዲ ጉዳይ) ኢትዮጵያቷ ሀጃጅ እስከዛሬ አልታወቀችም ነበር –ኢትዮጵያ 13 በላይ ሞተውባታል ፣ 26 ቆስለውባታል ከ204 በላይ ጠፍተውባታል ፣ ፍለጋው ቀጥሏል

0
0

nebyu sirak
የማለዳ ወግ…አድካሚው ስራ ፣የጠፉትን ሀጃጆች ፍለጋ !
ኢትዮጵያ …
* ኢትዮጵያ 13 በላይ ሞተውባታል ፣ 26 ቆስለውባታል
ከ204 በላይ ጠፍተውባታል ፣ ፍለጋው ቀጥሏል
* ጅጃ ከተላለፉት ቁስለኞች ኢትዮጵያዊ የለም
* ጅዳ ማህጀር የተላፈው ሬሳ ማንነት ገና አልተጣራም
* ከማህጀሩ ሬሳ የአፍሪካውያን አለበት ተብሏል
* ኢትዮጵያውያን መካ ላይ ለፍለጋው በግል ተደራጅተዋል
* ማፈላለጉን በሁሉም ሆስፒታሎች መከዎን ገዷቸዋል
* ቤተሰብ ወይም የኢንባሲ ውክልና አምጡ ተብለዋል
* በመካው ክሬን የተጎዳች ኢትዮጵያዊት ሀጃጅ ተገኘች
* ኢትዮጵያቷ ሀጃጅ እስከዛሬ አልታወቀችም ነበር
* ልክ የዛሬ ሳምንት መሞቷ ተጠቁሟል
ህንድና ፖኪስታን …
* በማፈላልጉ የሳውዲ መንግስት አፋጣኝ እርዳታ ተጠየቀ
* የህንድን ፖኪስታን ቆንስሎች መግለጫ ሰጥተዋል
* ህንድ 46 ሞቶባታል 62 ቆስለዋል 82 ጠፍተውባታል
* ፖኪስታን 46 ሞተውባታል ፣ 8 ቆስለዋል 42 ጠፍተውባታል
የጠፉትን ፍለጋና ጭንቅ ድካሙ …
======================
ተቀማጭነታቸውን ሳውዲ ያደረጉ ፣ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ፣ በሀጅ ጸሎት ከአደጋው የተረፉ ሀጃጆችና ቤተሰቦቻቸው በሚና ጀማራት አደጋ የጠፉና የሞቱትን ሰዎች ለማፈላለግ ሌት ከቀን ወደ ሚና ፣ ጀማራትና መካ በመመላለስ አድካሚ የጭንቅ ሳምንት መግፋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። የጠፉ ሃጅ ቤተሰቦች በግሩኘና በተናጠል ቢያፈላልጉም በርካታዎች እንዳልተሳካላቸው ይናገራሉ ። በአደጋው የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጠር ገና ከአደጋ ቀን አንስቶ ከአምስት በላይ መሆኑ ግልጽ እያለ በኢትዮጵያ ኢንባሲ ፣ ቆንስልና የሀጅ ኮሚቴ የሚደረገው ፍለጋ የተቀናጀ ባለመሆኑ ዝርዝር መረጃው ቀርቶ የሞቱና የቆሰሉትን ዙሪያ ትክክለኛ መረጃ አልቀረበም ነበር ። ከብዙ ጉትጎታ በኋላም ትክክለኛውን መረጃ ለህዝብ ለማድረስ በርካታ ቀናት ወስዷል ።
አሁንም በኢትዮጵያ ተወካዮች በኩል ቀናት የወሰደው የሞቱና የቆሰሉትን የማሳወቅ መረጃ ቅበላ ከቀናት በፊት ይፋ ቢደረግም አሁንም ቁጥሩ እየጨመረ ከመጣው የሟቾቸ ብዛት አንጻር የመረጃ ክምችቱን የማሻሻል ስራ እየተሰራ አይደለም ! ጉዳዩ ያሳሰባቸው በመካ ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካ ላይ በሚገኙ በ13 ሆስፒታሎች ፍለጋ ተደራጅተዋል ጀምረዋል ። ያም ሆኖ መሊክ ፈይሰል ፣ ሄራ ፣ ጀበለር ኑርና መሊክ አብደላ በተባሉ ሆስፒታሎች ቢከለከሉም በቀሩት አንዳን ሆስፒታሎች ማፈላለግ ችለዋል። ማፈላለጉን በተወሰነ መልኩ ማሳለጥ ችለው 15 ያህል ቁስለኞችን አግኝተዋል። ነገር ግን የተጠቀሱት ሆስፒታል ሃላፊዎች የቤተሰብ ወይም የኢንባሲ ውክልና አምጡ በማለት የተከለከሉት ወጣቶች ከሀጅ ኮሚቴ ጋር ተቀራርበው ለመስራት የሚየሰደርጉት ሙከራ አለመሳካቱን ገልጸውልኛል! ውክልናውን ወይም መታወቂያ ይሰጣቹሃል ቢባሉም እስካሁን ከኮሚቴው መልስ ባለመሰጠቱ ጥረታቸው መሰናክል እንደገጠመው አንድ የገላጊው ቡድን አባል ገልጸውልኛል !
በአንጻሩ የመሳሳይ ችግር ያለባቸው የአንዳንድ ሀገራት የመንግስት ተወካዮችና ዲፕሎማቶች ነዋሪዉን ለበጎ ስራና በማቀናጀትና በማቀዳጀት በሽዎች የሚቆጠሩ ልዩ የፈላጊ ግብረ ሃይል አቋቁመው በመካ ፣ ሚናና ጀናራት አሰማርተዋል ። የነዋሪውንና የሀጃጆችን ጭንቀት በመረዳትም የቆሰሉትንና የሞቱትን ፎቶ መረጃዎች ከሳውዲ መንግስት በመውሰድ ለዜጎቻቸው አቅርበዋል።
በሳምንት የአደጋው አድሜ በዋናነት አሳሳቢ የሆነው ቁርጡ የታወቀው የሞቱትና የቆሰሉት ዜጎች አልሆነም። ሞተው ፎቷቸውና ቆሰለውም ከሆነ ዝርዝራቸው ያልተገኙት ጉዳይ ብዙ ዜጎችን በመንፈስ እያስጨነቀና እያንገላታ ይገኛል። መዳረሻቸው ” ጠፋ” ከሚባሉት መካከል በደረሰው አደጋ ፊታቸው መለየት ያስቸገረ ይገኙበታል የሚል ጥርጣሬ ቢኖርም የሟቾችን ሬሳ ለመለየት የተለያዩ እርንጃዎች ቀርበዋል። ሀጃጆች በገቡበት አሻራ ለመለየት እየተወሰደ ያለው ማጣራት ረዠም ጊዜ መውሰዱ ተቃውሞ እየቀረበበት መሆኑ ይጠቀሳል ። የሳውዲ መንግስት የየጤና ጥበቃና የፖስፖርት ክፍል ኃላፊዎች ስለመለየቱ ስራ ሲናገሩ በሶስት መንገድ እንደሚከወን ያስረዳሉ ። እስካሁን መለየት ያልተቻለውን ሬሳ ለመለየት የቀረቡት ዘዴዎችም 1ኛ / በገቡበት አሻራ 2ኛ / በገቡበት ፎቶ መለየት እና 3 ኛው / የስጋ ዘመድ ቤተሰቦቻቸው እየቀረቡ DNA በመስጠት መለየቱ እንደሚከወን ይናገራሉ ! አሻራቸው የተነሱ ሬሳዎች ውጤት በከነገ ጀምሮ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ቢጠበቅም የተረጋገጠ መረጃ እስካሁን አላገኘሁም !
የሳውዲ መንግስት የጠፉትን በማፈላለግ ሂደቱን እብዲያፋጥንና የዜጎቻቸው እጣ ፈንታ እንዲያሳውቅ ህንድና ፖኪስታን የሳውዲ መንግስት አስቸኳይ እገዛ እንዲያደርግ በተለያዩ መንገዶች ተማጽኗቸውን በማቅረብ ላይ ናቸው !

ይቀጥላል …
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 20 ቀን 2008 ዓም

ኢትዮጵያ ቦስትዋናን 3ለ2 የረታችበት ጨዋታ ጎሎችን ይመልከቱ

ጸብ ለማብረድ በማለት ሽጉጣቸውን የመዘዙት ዳኛ እራሳቸውን ለችግር ዳረጉ

0
0

ከታምሩ ገዳ

ብራዚላዊው ገብሬል ሞርቶ የታችኛው ሊግ የእግር ኳስ ዳኛ ሲሆኑ ባሳለፍነው ሳምንት ማብቂያ ቤርኑዲያኖ እና አሚኒቲስ ዳ ቦ(በአገሬው ቋንቋ የኳስ አፍቃሪዎች ቡድን ማለት ነው ) የተባሉ ሁለት ክለቦችን የብራዚል 6ኛ ትልቋ ከተማ በሆነችው ሆሪንዘንቴ ውስጥ በመዳኘት ላይ ሳሉ አንድ ቀይ ካርድ በተሰጠው ተጨዋች ምክንያት በደል ደረሰብን ያሉ የአሚኒቲስ ደ ቦላ ክለብ ተጨዋጮች ዳኛ ገብሬልን የከቡዋቸዋል፣ የክልቡም አሰልጣኝ ከ መሃል ሜዳ ዘልቀው በመግባት “ቀይ ካርድ ሊሰጠን አይገባም ” በማለት ዳኛውን ይሞግታሉ። በ አሰልጣኙ እና ከተጨዋቾች የተወሰኑት በንዴት ዳኛውን በካልቾ እና በጥፊ ይነርቷቸዋል። ሁኔታው ያላማራቸው ዳኛ ገብሬልም ወደ ልብስ መቀየሪያ ክፈል በፍጥነት በመሮጥ ብዙም ሳይቆዩ የመለሳሉ።
tamriu geda

Tamru geda
ታዲያ እኛ በተጨዋቾቹ የተዋከቡት እና የተጎሸሙት ዳኛ ጫዋታውን ለበጠበጡት ተጨዋቾች ከቀይ ካርድ ወይም ከቢጫ ካርድ አንዱን በመምዘዝ ተግስጽ ከመሰጥት ፋንታ ከመልበሻ ክፍል ቁም ሳጥን ውስጥ አስቀምጠውት የነበረውን ሽጉጥ መዘዝ በማደረግ “እስቲ ልብ ያለው ካለ አሁን ይጠጋኝ!?” በማለት ይፎክራሉ ። ቀይ ካርድ ሲሰጠው “ከሜዳ አልወጣም “ብሎ የነበረው ተጨዋች ዳኛው ሽጉጥ መያዛቸውን ሲረዳ እግሬ አወጪኝ ብሎ ሮጧል ተብሏል።ሁኔታውን የተከታተሉት ረዳት ዳኞች እና አንድ ደፋር ግብ ጠባቂ ተጨዋች ግን በንዴት እየተንጨረጨሩ እና ሽጉጣቸውን በማወናጨፍ ላይ ወደ ነበሩት የመሃል ዳኛው ገብሬል በመጠጋት እና በማግባባት ሁሌም ከውሰጡ ጥሩ ነገር የማይወጣው ያ ሸጉጡን ከአካባቢው ዞር አንዲያደርጉ(ወደ ልብስ መቀየሪያ ሰፈራ እንዲወስዱት) አስችለዋል።ዳኛው በበኩላቸው እርምጃውን የወስዱት ሁኔታውን “ለማቀዝቀዝ “እንደሆነ ተናግረዋል።

ከመደበኛው የፖሊስ ሰራቸው በተጓዳኝነት (off –duty cop) በኳስ ሜዳ በዳኝነት የሚያገለግሉት ፖሊስ(ዳኛ) ገብሬል ሕዝብን እንዲያገለግሉበት የታጠቁት ሽጉጥን ከኳስ ሜዳ ዘልቀው በመግባት ተጨዋቾችን እና አሰልጣኙን ማሰፈራራታቸው የተገነዘበው የ ብራዚል የእግር ኳስ ዳኞች ፊዴሪሽን በበኩሉ “ዳኛው ለህይወታቸው ሰገተው ነበር፣እራሳቸውን ለመከላከል የወ ሰዱት እርምጃ ነው።” ቢልም በደርጊቱ ማዘኑን፣ ዳኛውን ማነጋገሩን እና በዳኛው ላይም የአይምሮ አቋም በሕክምና ባለሙያዎች እንዲፈተሽ እና ከ ዳኝነት ሰራቸው ለጊዜው ወይም እሰከ መጨረሻው እንዲታገዱ ለመወስን በሂደት ላይ ናቸው ። ሁኔታው እንግዳ የሆነባቸው በረካታ የእግር ኳስ አፈቃሪዎች በበኩላቸው “ቀይ ካርድ ፣ ቢጫ ካርድ እና ፊሽካ በ ሸጉጥ ሊተኩ ይሆን ወይ?” ብለው መጠየቃቸው አልቀረም።

አብዱ ኪያር “ጥቁር አንበሳ”የተሰኘ ሃገራዊ ነጠላ ዘፈን ለቀቀ

0
0

መርካቶ ሰፈሬ በተሰኘው ተወዳጅ አልበሙ ወደ ሙዚቃው ዓለም ገብቶ ከሕዝብ ጋር የተዋወቀው አብዱ ኪያር ሰሞኑን “ጥቁር አንበሳ” የተሰኘ ሃገራዊ ዘፈን ለቋል:: ዘፈኑን ያድምጡት::

አብዱ ኪያር “ጥቁር አንበሳ” የተሰኘ ሃገራዊ ነጠላ ዘፈን ለቀቀ


Health: የልብዎን ጤንነት ለመጠበቅ 4 ቀላል ዘዴዎች

0
0

heart
ብዙ ጊዜ በተለያዩ ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎች ጤናን አስመልክተው የሚወጡ መረጃዎችና ማብራሪያዎችን ከማንበብ ባለፈ የመጠቀም ልማድዎ ምን ያክል ነው ?

በእርግጥ ሁሉንም እንደ ወረዱ ተቀብሎ ለመተግበር ከሁኔታዎች አንጻር ከባድ ቢሆንም አንዳንዶቹ ግን ቀላል እና ለመተግበርም ምቹዎች ናቸው።

የአለም የልብ ቀንን በማስመልከትም ዶክተር ፒክሲ ማኬና እና ዶክተር ሞንትጎመሪ ፥ የልብ ጤንነትን ለመጠበቅ መደረግ ስላለባቸው ነገሮች ያስቀመጧቸውን ነጥቦች ያንብቡት።

1. አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣

በጣም በቀላሉ ጤናን መጠበቂያ ከሆኑ መንገዶች መካከል አካላዊ እንቅስቃሴን ማድረግ ነው።

ከዚህ ውስጥ ደግሞ ለደቂቃዎች የሚደረግ የእግር ጉዞ የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖር በማድረግ ጤናን በቀላሉ መጠበቅ ያስችላል።

በቀን እስከ 30 ደቂቃ ያክል የእግር ጉዞ ማድረግም የልብ በሽታ ተጋላጭነትን በመቀነስ ጤናማ ኑሮን መምራት ያስችላልና ይህን ማድረግ ይመረጣል ይላሉ።

የጤናዎን ሁኔታ መከታተል፣ የልብ ህመም ተጋላጭነትን የሚጨምሩ የሲጋራ ሱስ፣ ያልተስተካከለ አመጋገብ፣ ከልክ በላይ የሰውነት ውፍረት እንዲሁም የስኳር ህመምተኛ ከሆኑ ወደ ሃኪም ቤት ጎራ ማለቱ ይመረጣል።

ይህም ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ሳይታሰብ የሚከሰትና ለህልፈት ለሚዳርግ የልብ ህመም እንዳይጋለጡ ይረዳወታልና ነው።

ከዚህ ባሻገርም፤ ደረት ላይ የሚሰማ የህመም ስሜት፣ ያልተስተካከለ እና የተቆራረጠ የአተነፋፈስ ስርአት፣ ጡት እና አጥንት አካባቢ ምቾት የማይሰጥ ስሜት፣ የሰውነት መድከም እና መዛል መጨመር እንዲሁም

ተደጋጋሚ እና ረጅም ጊዜ የሚቆይ ሳል የዚሁ ምልክት ሊሆን ይችላልና ሃኪም ማማከሩ መልካም መሆኑን ይናገራሉ።

ቅባት የበዛባቸው ምግቦች ተመጋቢ እና የስብ ክምችት ካለብዎትም ይህን ማድረግዎን አይዘንጉ፤ በተጨማሪም የደም ግፊትዎን በየጊዜው በመለካት ጤንነትዎን ይጠብቁ።

2. አመጋገብን ማስተካከል፥

ጤናማ የልብ ስርአት እንዲኖርዎት የአመጋገብ ስርአትን ማስተካከል ሌላው አማራጭ ነው።

ለዚህም አትክትልትና ፍራፍሬዎችን፣ ጥራጥሬ፣ አሳ እንዲሁም በኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ በእጅጉ ይረዳል።

ከዚህ በተጨማሪም ሂደት የበዛባቸው የተቀነባበሩ የፋብሪካ ምግቦችን መመገብ መቀነሱም ዋነኛው አማራጭ ነው።

ይህን ሲያደርጉም ሰውነት ላይ የሚፈጠርን አላስፈላጊ የስብ ክምችትን ማስወገድና ጤናማ የደም ዝውውርና የልብ ስርአትን ማግኘት ይችላሉ።

3. ራስን አለማስጨነቅ፥

መጨነቅ አዕምሮን ከመበጥበጥ እና አላስፈላጊ ስሜት ውስጥ ከመግባት ያለፈ ትርጉም የለውም።

ከዚህ በተጨማሪ ግን አብዝቶ መጨነቅ ልብን ከመጠን ባለፈ መልኩ እንዲሰራ በማድረግ የልብ ስራን ማስተጓጎልና ባስ ሲልም ለከፋ ጉዳት ይዳርጋል።

ስለዚህም መጨነቅን ማስወገድ ወይም እንደዛ አይነት ስሜት ሲከሰት ለቅርብ ወዳጅዎ ማማከር አልያም ከባለሙያ ጋር ተነጋገሮ መፍትሄ በማበጀት ጤንነትን መጠበቁ መልካም ነው ይላሉ እነዶክተር ማኬና።

4. በቂ እረፍት መውሰድ፥

አካላዊ እንቅስቃሴን ከማድረግ ባለፈም ሰውነት ተመጣጣኝ እና በቂ እረፍት እንዲያገኝ ማስቻል የልብ ጤንነትን ለመጠበቅ ሌላው አማራጭ ሲሉም ይጠቁማሉ።

ምክንያቱ ደግሞ በስራ እና በእንቅስቃሴ የደከመው ሰውነት ሲያርፍ ልብም ስራው ቀሎለት የማረፊያ ጊዜን ያገኛልና።

በዚህም ራሱን ማደስና መደበኛ ስራውን በአግባቡ መስራት የሚችልበት እድል ይፈጠርለታል።

በእንቅልፍ ሰአት የልብ ስራ አነስተኛ ሲሆን የሰውነት የደም ዝውውር እና እንቅስቃሴም በዛው መጠን ይቀንሳል።

ስለዚህም በጤና ለመሰንበት እና ለመቆየት ከላይ የተጠቀሱት ማብራሪያዎች ያግዙዎታልና ይጠቀሙባቸው ይላሉ ባለሙያዎቹ።

ምንጭ፥ ሚረር እና ዌብ ሜድ ዶት ኮም

በምናለ ብርሃኑ

ከመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የስንብት ጥያቄ የሚያቀርቡ መኮንኖች ቁጥር እያሻቀበ ነው

0
0

መቶ በመቶ ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ከአንድ አካባቢ በወጡ የህወሓት አባላት ድኩማን ወታደራዊ አዛዦች ብቻ ቁጥጥር ስር ሆኖ በከፋ አስተዳደራዊ በደል እየማቀቀ በዘር ሸለቆ ውስጥ የሚገኘው ብዙኃኑ የመከላከያ ሰራዊት የሰባት ዓመታት አገልግሎት የኮንትራት ጊዜውን የጨረሰው የስንብት ጥያቄ ያዘሉ ደብዳቤዎችን ያለማቋረጥ እያስገባ በየእርከኑ የሚገኙ የመከላከያ የአስተዳደር ቢሮዎች በማመልከቻ ማዕበል ክፉኛ እየተመቱ የሚገኙ ሲሆን የአገልግሎት ጊዜው አልሞላ ብሎት የስንብት ደብዳቤ ማስገባት ያልቻለው የሰራዊቱ አባል ደግሞ የሰቀቀን ኑሮውን ለማሳጠር በራሱ እርምጃ እየወሰደ ያለምንም ፋታ እየከዳ ነው ሲል የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ዘግቧል::

(Photo File)

(Photo File)

ድኩማኖቹ ህወሓታዊያን የመከላከያ ሰራዊቱ አዛዦች የአገልግሎት ጊዜ ኮንትራታቸውን ጨርሰው የስንብት ደብዳቤ ለሚያስገቡት በስርዓቱ የተንገሸገሹ እና በእጅጉ ተማረው ተስፋ የቆረጡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የሰራዊቱ አባላት “ከመከላከያ ሰራዊቱ ፈፅሞ መልቀቅ አይቻልም…” የሚል አሉታዊና ድፍን ያለ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም ድኩማኖቹ ወታደራዊ አዛዦች የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ ማንኛውም የመከላከያ ሰራዊት አባል በአሁኑ ሰዓት የስንብት ጥያቄ የማቅረብ መብት እንደሌለውና አሰናብቱኝ ብሎ በሚያመለክት ላይ እርምጃ የሚወስዱ መሆናቸውን ጠንከር ያለ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡

ከየማሰልጠኛው ተመርቀው በየጊዜው ሰራዊቱን የሚቀላቀሉ አዳዲስ አባላት ብዙም ሳይቆዩ ስለሚከዱ “ነባሩ ሰራዊት” ከተሰናበተ በእነሱ ላይ ቅንጣት ታክል እምነት ስለሌላቸው በአገዛዙ ላይ የከፋ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል በማብራራት በማሳመን ለማባበል እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡

የህወሓት አገዛዝ በየጊዜው ከመከላከያ ሰራዊቱ የሚከዱትን አባላት ከየተሸሸጉበት አድኖ የመያዝ ሰፊ እንቅስቃሴ አድርጎ ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡
በየጊዜው ያለምንም ፋታ የሚከዱ የሰራዊቱ አባላት ወደየ ትውልድ ቀያቸው አይደለም የሚመለሱት፤ ገሚሶቹ ከነትጥቃቸው በረሃ ወርደው ይሸፍታሉ፤ አብዛኞቹ የነፃነት ትግሉን ይቀላቀላሉ፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ድምበር ተሻግረው እግራቸው ወደመራቸው ይሰደዳሉ፡፡

በአጠቃላይ አሁን እጅግ በጣም በርካታ አባላት ላነሱት የስንብት ጥያቄ የተሰጠውን “አይቻልም” የሚል ድኩማን ህወሓታዊ ወታደራዊ አዛዦች ምላሽ ተከትሎ በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ከዳር እስከ ዳር ሰፍኖ የቆየውን ውጥረትና አለመተማመን ከጫፍ አድርሶት አገዛዙ ሊቆጣጠረው ከሚችለው በላይ የሆነ ከባድ አደጋ እያንዣበበ ይገኛል፡፡

በጎንደር ከተማ የመስቀል በዓል ዕለት “የፈራ ይመለስ”የሚል ቀይ ጽሁፍ የታተመባቸው ቀያይ ቲሸርቶች የለበሱ ወጣቶች ተቃውሞ ሲያሰሙ ዋሉ

0
0

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) በክርስትና እምነት ተከታዮች የመስቀል በዓል ዕለት የጎንደር ከተማ “የፈራ ይመለስ” የሚል ፅሁፍ የታተመባቸው ቀያይ ቲሸርቶች በለበሱ ወጣቶች ተጥለቅልቃ ከፍተኛ የሆነ አመፅን አስተናገደች፡፡

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

የጎንደር ከተማ (ፎቶ ፋይል)

የጎንደር ከተማ ለውጥ የሻቱ ወጣቶች ከ500 በላይ የፈራ ይመለስ የሚል ፅሁፍ የታተመባቸው ቀያይ ቲሸርቶች አሳትመው በማሰራጨት በጎንደር በከፍተኛ ድምቀት በየአመቱ መስከረም 17 ቀን የሚከበረውን የመስቀል በዓል ለመታደም ደመራው ወደ ሚለኮስበት መስቀል አደባባይ ይተማሉ፡፡
ቀጥሎም ደመራው የሚለኮስበት መስቀል አደባባይ ከምዕመኑ ቁጥር ባልተናነሰ ሁኔታ በፌደራልና በልዩ ኃይል የህወሓት ፖሊሶች ተወሮ በማግኘታቸው የደመራውን በተለመደው ሰዓት አለመለኮስ በምክንያትነት በመጠቀም በአምባገነኑ የህወሓት ዘረኛ አገዛዝ ላይ ተቃውሟቸውንና በጉልበት አንገዛም ባይነታቸውን በተለያዩ መንገዶች ገልፀዋል፡፡
የህወሓት ፌደራልና ልዩ ኃይል ፖሊሶች ለአገዛዙ ያላቸውን ጥላቻና ተቃውሞ የገለፁትን “የፈራ ይመለስ” ያሉ ባለቀያይ ቲሸርት የጎንደር ወጣቶችን በቆመጥና በአፈሙዝ በብርቱ በመደብደብ ተቃውሞውን ለማርገብ ሞክረዋል፡፡ በመሆኑም በወጣቶቹ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች በርካታ ምዕመናን ላይም ጉዳት ደርሷል፡፡
ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የከተማዋ ወጣቶች እና ነዋሪዎች ጭምር በህወሓት ፖሊሶች እየታፈሱ ወደ ዘብጥያ ተወስደዋል፡፡ በተለይም ደግሞ “የፈራ ይመለስ” የሚል ቀያይ ቲሸርቶች የለበሱ ወጣቶች በልዩ ሁኔታ እየታደኑ ታፍነው እየተወሰዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ከ100 በላይ የሚሆኑ የጎንደር ወጣቶች በልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ ብቻ ታጉረው ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ ተረጋግጧል፡፡

በወልቃይት በርካታ አካባቢዎች የሚገኙ ገበሬዎች አዝመራቸውን እንዳይሰበስቡ በፌ. ፖሊስ በመታገዳቸው ጥይት ያታኮሰ ከፍተኛ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ

0
0

clash
በተኸለ አምባ እና በሌሎች የወልቃይት በርካታ አካባቢዎች የሚገኙ ገበሬዎች አዝመራቸውን እንዳይሰበስቡ በፌደራል ፖሊስ በመታገዳቸው ጥይት ያታኮሰ ከፍተኛ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ ውጥረቱ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው፡፡

በወልቃይት የሚገኙ ገበሬዎች ማንኛውም ሰው ተነስቶ የሚያርሰውን በተለምዶ “ሞፈር ዘመት” እየተባለ የሚጠራውን መንገድ ተጠቅመው በግንቦትና በሰኔ ወራት ጫካ መንጥረው ምድረ በዳውን በማረስ የተለያዩ አዝዕርቶችን በተለይም ሰሊጥ ዘርተው ያበቀሉ ሲሆን አሁን በመኸር ክወና ላይ ተሰማርተው ባሉበት የህወሓት አገዛዝ ደን ጨፍጭፋችሁ አርሳችኋል በሚል ተልኮሻ ምክንያት ፌደራል ፖሊስ በየማሳቸው በማሰማራት ለማገድ በመሞከሩ ነው “ግንቦት እና ሰኔ ገና መሬቱን ማልማት ስንጀምር ከተቆረቆራችሁ ለምን አልከለከላችሁንም?” በሚል ህዝቡ በአንድነት ተነስቶ ግጭት የተቀሰቀሰው የህወሓት ፌደራል ፖሊሶች ተክላይ የተባለውን ገበሬ ከማሳው አስረው ወስደው አደባይ ላይ በመረሸናቸው የዘርባቢትና እድሪስ ቀበሌዎች ነዋሪዎች በአንድነት “ሆ” ብለው ተነስተው ፖሊሶችን ትንቅንቅ ገጥመዋቸዋል፡፡

በተለይም የአካባቢው ሚሊሻዎች ከህዝቡ ጎን በመቆም በፌደራል ፖሊሶች ላይ ተኩስ ከፍተው ውጊያ በመግጠም ሁለት ፖሊሶችን አቁስለዋል፡፡

በአካባቢው የታጠቁ ሚሊሻዎችና ገበሬዎች የደረሰ አዝመራቸውን እንዳይሰበስቡ ለማገድ በየማሳው በተሰማሩ ፌደራል ፖሊሶች መካከል የተከፈተው ጦርነት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ኃይል በአካባቢው ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ግጭቱ የባሰውን ተቀጣጥሎ የሰፈነውን ውጥረት እንዲያይል አደረገው እንጂ ሊያረግበው እንዳልቻለ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡

ወያኔዎች ሂሳብ የምታወራርዱበት ግዜ መጣ!!!

0
0

ሳሙኤል አሊ ከ- ኖርዌይ

WoyaneEFFORTCompaniesአንድ ድርጅት በአመት 2 ጊዜ ወይም አንድ ጊዜ የድርጅቱን ጠቅላላ ሂሳብ ይፈትሻል ። ወጪው ምን ያህል ነው? ገቢውስ ምን ያህል ነው? ከወጪ ቀሪ  ምን ያህል አስገባ? እያለ ድርጅቱ ማትረፉን እና  ማክሰሩን ያውቅበታል። እንዲሁም ሃላፊ ቦታ ያሉትም ሰወች የሚገመገሙበት ነው። የታማኝነት ስራ፤የታማኝነት እድገት፤ የታማኝነት አገልግሎት፤ ለአገራችንም ይገባል።

ወያኔወች አገሪቱን ከተቆጣጠራቹሁበት  ግዜ ጀምሮ እንደፈለጋቹ ስትዘርፉ እንዳሻቹሁ ስታዙ ከርማቹሃል። ባንኮችን የሃገሪቷ ህግ ከሚያዘው ውጪ ቢሮአቹሁ ቁጭ ብላቹሁ በቀጭን ትእዛዝ ብቻ ወደ ውጪ አገር በምትሄዱበት ግዜ የፈለጋቹሁን  ያህል ዶላር በማን አለብኝነት  እየዘረፋቹ እንደሆነ  እናውቃለን። የህዝብ ንብረት የሆነውን ሁሉ  በመዝረፍ ለራሳቹሁ በጣም ብዙ ድርጅቶች እንደከፈታቹ  እናውቃለን። የህዝብ  ሃብት በመንጠቅ ትልልቅ ፎቆችንም እንደገነባቹ እናውቃለን።  በህዝብ ስም ከውጪ እርዳት በመለመን  እንዲሁም ለጋስ አገሮች ለህዝብ እንዲደርስ የሚሰጡትን የእርዳታ ገንዘብ   በልጆቻቹህ ስምና በተለያዩ  ስሞች በተለያዪ አለም አቀፍ ባንኮች እንደምታከማቹ እናውቃለን። አሁን ግን ግዜው ሂሳብ የምታወራርዱበት ግዜ ነውና ተዘጋጁ።

በዘረፋቹሁት የህዝብ ንብረት የተለያዩ  ድርጅቶችን  በስማቹሁ ከፍታቹሁ   የወያኔ  መንግስት ስልጣን ከያዘ በሃላ እንዚህን ሁሉ ድርጅቶች ተከፍቷል ብላቹ  ለኢትዮጵያ ለህዝብ እንደምትሰሩ ለማስመሰል የምትሞክሩትን እና የምትቀልዱትን ቀልድ መለወጥ አልተቻላቹሁም። ብዙ ህንጻወች ተሰርተው ከተሞች አድገዋል ብላቹ በናንተ ስምና በልጆቻቹ ስም እንዲሁም  ለሆዳቸው ሲሉ በሰገዱ ጥቅመኞች የተገነባ እንደሆነ  ስለምናውቅ ከተማዋ  ፎቅ በፎቅ ሆነች የምትሉትን ቀልድ  ሰሚ ጆሮ የለም። አሁን ግን እንዲዚህ አይነት የድናቁርት ወሬ የምንሰማበት ግዜው አልቋል እና ሂሳባቹሁን ልናወራርድላቹ ከዳር እስከዳር ተነስተን እየመጣንላቹሁ ነው ።

ልማት ላይ ነን እድገት ላይ ነን እያላቹሁ  በሕዝብ ስም የምታሾፉ ልማት ማለት እህል እንደማያውቅ አንበጣ በሁሉም የኢትዮጵያ ወሳኝ ቦታወች ላይ ሰፍራቹሁ መብላታቹሁን ነው ልማት የምትሉን ? ልማት ላይ ነን የምትሉን ብቃት ያላቸውን ሰራተኞች በማባረር የራሳቹሁን ደናቁርት  ካድሬን መሰግሰግ ነው ?  ልማት የምትሉን  አየር መንገዱን 90%፤ መከላከያ 95%  ፤ሚኒስትሮች 85%፤ ጉምሩክ 90% ፤ኢምግሬሽን 90% ፤አየር ሃይል 90% ፤የአገር ውስጥ ተቆጣጣሪ 90% ፤የውጪ  ንግድን ተቆጣጣሪ 90%፤ የስልጣኑን  ቦታ ይዛችሁት  አውቃቹሁ ወይም ቦታው መጥናቹህ ቢሆን መልካም ነበር  ነገር ግን ደናቁርቶች እራሳቹሁ ተደናቁረው ሌላውን የሚደናቁሩትን  ሰብስባቹ በበላይ መቀመጣቹሁን ነው ልማት የምትሉን ?  የትምህርት ውጤታቹህም  እንደዚሁ በ 90% ቢሆን ኖር ምነኛ ባማረ ነበረ ። እኛም የቀልድ ጊዜው  ማብቃቱን የወያኔ ደናቁርቶች የሚናገሩትን የምንሰማበት ሰዓት ማብቃቱን ነግረናቸሁ ሂሳባቹሁን ለማወራረድ ሰለመጣን ለዛ ተዘጋጁ።

ጊዜው ለወያኔዎች የምጥ ግዜ እንደሆነ እናውቃለን። ውስጣቸው በከፍተኛ  ሁኔታ መባላት ውስጥ እንዳሉም እናውቃለን። የዘረፉትን  የሕዝብ ሃብት ኪሳቸውን ሞልቶ  አስጨንቆአቸዋል። እንደዚህ እየዘረፉ እና ህዝቡን እየገደሉ ለሁል ግዜ ስልጣናቸው ላይ ተቀምጠው መኖርን ቢመኙም ይህንን ምኞታቸውን አጨልሞ ለኢትዮጵያን የብርሃን ጊዜ ሊያመጣ የሚችል እራይ ይዘው በአርበኞች ግንቦት ሰባት በሌሎችም የኢትዮጵያ  ታጋዮች በመዋህድ ከኤርትራ ምድር አልፎ  ከጫፍ እስከጫፍ  ባለችው ኢትዮጵያ  የትግሉ አላማ እና ትግሉን የማቀጣጠሉ ስራ  በሚገባ ተሰርቶ  ህዝባችን በሚገርም  ፍጥነት ወደ ትግሉ በመቀላቀል የተዘረፈውን ንብረት ለማስመለስ የተነጠቀውንም ሰላም ለመመለስ  ወያኔ ላይ የሰላ ብረት ደግኖ ሂሳቡን ሊያወራርድ መጥቷል።

ይሄኔ ነው ወያኔ በሻንጣ ብር ይዘው መሰወር የጀመሩት። ያላቸውን ንብረት ወደተለያዩ የውጪ ባንኮች ማስገባት ልጆቻቸውንና የቅርብ ዘመዶቻቸውን በማሸሽ  እውን እነሱ እንዳሰቡት የኢትዮጵያንን  ሃብትና ንብረት ማሸሽ ይችላሉን ?

ትግሉ የተቀጣጠለው በአገር ቤትም በውጪም ነው ለውያኔዎች ውስጡም  እሳት ውጪውም እሳት ሆኖ ነው የሚጠብቃቸው።  የኢትዮጵያንን ሃብት ዘርፈው  የኢትዮጵያን ህዝብ ገድለው ወዴት ሊሰወሩ ወድዬትም መሰወር አይችሉም። በውጪ ያለው ኢትዮጵያዊ  ዘርፌ እና ገድዬ አመልጣለው  ብሎ ያሰበውን የወያኔ ሰወችን ነቅቶ  በመጠበቅ ላይ ነው። አሁን ሂሳብ የምታወራርዱበት  ስለሆነ በአለም ላይ ያሉት ባንኮች በሙሉ ከኢትዮጵያን  ህዝብ የተዘረፉ ንብረት መሆኑን በማሳወቅ አገርን ለማጥፋት ህዝብን ከህዝብ ለማጫረስ የሰራቹሁት ስራ ለአለም በማሳወቅ በይፋ የሚነገርበት  ግዜ ከፊታቹ በቆረጦቹ የኢትዮጵያ ልጆች ስለመጣ ሂሳባቹሁን  እናወራርዳለን።

1 የዘር ማጥፋት ወንጀል የሰራቹሁ ወንጀለኞች

2 አገሪቷን ለባእዳን ቆርሳቹሁ የሸጣቹሁ ወንጀለኞች

3 ዘርን ከዘር ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጠፋፋት የተነሳቹ ወንጀለኞች

4 ንጹሃንን በማሰር በማሰቃየት እስርና መከራ በማብዛት ወንጀል

5 የአገሪቷን ሃብት ያለአግባብ ለግል ጥቅማቹሁ በማዋል ወንጀል

6 ስልጣንን ለአፈና  ስራ በመጠቀም ወንጀል.

7 ስልጣንን አለአግባብ በማን አለብኝነት በቦታው ለማይመጥን ሰው በመስጠት ወንጀል

ኢትዮጵያኑን በማግለል  በመስሪያቤቱ የአንድ ብሄር ተናጋሪ ሰዎችን  ብቻ  በመቅጠር ወንጀል…… እያሉ የሰራቹሁትን ወንጀሎቻቹሁን የምናወራርድበት  ሰዓት አሁን ነው። የትም ማምለጥ የለም። የትም መደበቅም የለም። በሁላቹሁም በራፍ አንኳኩተን እንመጣለን። ያኔ ሂሳባቹሁን ታወራርዳላቹሁ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

ሳሙኤል አሊ ከ-ኖርዌይ

Email samilost89@yahoo.com

01.10.2015

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live