Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የግብጽ እና የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ሲኖዶሶች በዝግ ይመክራሉ ተባለ

$
0
0

ፖፕ አቡነ ቴዎድሮስ፣ የደመራ በዓልን በመስቀል ዐደባባይ ያከብራሉ
አክሱም ጽዮንን፣ ጎንደርን፣ ላሊበላንና የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ይጎበኛሉ

የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሃይማኖት አባቶች፣ በሃይማኖታዊ ጉዳዮችና በማኅበራዊ ግንኙነቶች ዙሪያ በአዲስ አበባ እንደሚመክሩ ተገለጸ፡፡
pat-abune-mathias-and-pope-abune-tawodros1
በእስክንድርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ ከሚመራው ልኡክ ጋር በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ የሚካሔደው ምክክር፤ የኹለቱን አገሮችና አብያተ ክርስቲያናት የቆየ ታሪካዊ፣ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ግንኙነት አጠናክሮ በማስቀጠል ወደ ከፍተኛ መተማመን እንዲያመራ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፤ ተብሏል፡፡

በክርስትናው አስተምህሮ ባላቸው የትምህርተ ሃይማኖት አንድነት፣ “እኅትማማች” የሚባሉት ኹለቱ አብያተ ክርስቲያናት፣ የጋራ ተልእኮዎቻቸውን በአንድነት በመፈጸም ጥንታዊውንና ታሪካዊውን ግንኙነታቸውን ለማዳበር የጋራ ኮሚቴ እንዲቋቋም የኢትዮጵያው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባለፈው ዓመት ጥር ባደረጉት የግብጽ ይፋዊ ጉብኝታቸው ወቅት ጠይቀዋል፡፡

የግብጹ አቻቸው ፖፕ አቡነ ቴዎድሮስም ጥያቄውን በመቀበል፤ በሃይማኖታዊ፣ በጤና እና በማኅበራዊ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር አብሮ የሚሠራና በሊቀ ጳጳስ የሚመራ ኮሚቴ ለመሰየም ዝግጁ መኾናቸውን አስታውቀው እንደነበር ተወስቷል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ፣ ፈለገ ግዮን ተብሎ የሚታወቀውና ኹለቱ አገሮች በጋራ የሚጠቀሙበት ተፈጥሯዊው የዓባይ ውኃ የማኅበራዊ ትስስሩ መሠረት ሲኾን በዝግ በሚካሔደው የኹለቱ ቅዱሳት ሲኖዶሳት ምክክርም ዐቢይ ትኩረት እንደሚያገኝ ተጠቁሟል፡፡

የዓባይ ውኃን በመተማመን ከተጠቀሙበት ከኹለቱ አገሮች አልፎ ለመላው አፍሪካ የሚበቃ የአምላክ በረከት እንደኾነ ለግብጽ ባለሥልጣናት የተናገሩት ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ “የግብጽ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አንድ የሚኾኑት የእግዚአብሔር ጸጋ በኾነው በዓባይ ነው፤ እግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ደግሞ ሰው ሊለያየው አይችልም፤” ያሉ ሲኾን ፖፕ አቡነ ቴዎድሮስም፤ “እኛ የግብጽ ሕዝቦች ከዓባይ ወንዝ አንድ ብርጭቆ ውኃ በጠጣን ቁጥር ኢትዮጵያን እናስታውሳታለን፤” ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡

በወቅቱ ፖፕ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ በ2008 ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ላይ እንዲገኙ ከፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በቀረበላቸው ግብዣ፣ ትላንት ሌሊቱን ዘጠኝ አባላት ያሉትን የሃይማኖት አባቶች ልኡክ በማስከተል ዐዲስ አበባ የገቡ ሲኾን ከዛሬ ጀምሮ የአምስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ ለጉብኝቱ የወጣው መርሐ ግብር እንደሚያመለክተው ፓትርያርኩ፣ ትላንትና መስከረም 14 ቀን ሌሊት 9፡00 ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና የፕሮቶኮል ባለድርሻ አካላት አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ፣ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 2፡30 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የመንበረ ፓትርያርኩና የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት፣ የእንኳን ደኅና መጡ ፕሮግራም ይደረግላቸዋል፤ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋርም ይወያያሉ ተብሏል፡፡

ጠዋት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ተገኝተው ጸሎተ ቅዳሴውን በመምራት፣ ሥርዐተ ቅዳሴውን የሚያከናውኑ ሲኾን ከቀትር በኋላም በመስቀል ዐደባባይ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጋር የመስቀል ደመራ በዓልን ያከብራሉ፡፡
ከመስከረም 17 – 19 ቀን የርእሰ አድባራት ወገዳማት አኵስም ጽዮን ማርያምን፣ የጎንደርን፣ የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትንና ታሪካዊ ስፍራዎችን፣ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን እንዲኹም በአዲስ አበባ የሰበታ ጌቴሰማኔ ቤተ ደናግል ወጠባባት ገዳምንና የጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በመጎብኘት ጸሎት እንደሚያደርጉና እንደሚባርኩ ታውቋል፡፡ በግብፅና በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ታሪክ የኹለቱ እኅትማማች አብያተ ክርስቲያናት ትብብር እንደ ድልድይ ይታያል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የራሷን ፓትርያርክ በ1951 ዓ.ም እስከሾመችበት ጊዜ ድረስ ለ1600 ዓመታት ከግብጽ ቅዱስ ሲኖዶስ በሚሾሙ ጳጳሳት ስትመራ ቆይታለች፡፡ በሀገራቱ መንግሥታት ምክክር ጭምር የመንበሩ ነጻነት ከተገኘም በኋላ የሚካሄዱ ፕትርክናዊ ጉብኝቶች ለውጭ ግንኙነታቸው መጠናከር አስተዋፀኦ እንዳለው ይታመናል፡፡

Source: Addis Admass News


(የሳዑዲ ጉዳይ) የሚና ጀማራት አደጋና ኢትዮጵያውያን! –ሪፖርታዥ በነብዩ ሲራክ

$
0
0

የማለዳ ወግ … የሚና ጀማራት አደጋና ኢትዮጵያውያን ! =================================
* አደጋው ከተከሰተ ወዲህ ሪፖርት ያላደረጉ ሀጃጆች ስም ይፋ ሆኗል!
* ልዩነትና አስዎግደን ዜጎቻችን በማፈላለግ እንትጋ
* የተወሰኑ ቁስለኞች ከሚናና መካ ወደ ጅዳ ሆስፒታሎች ገብተዋል
* በዝርዝሩ የሌሉ የጠፉባችሁ ቤተሰቦች ካሉም አሳውቁ
የተጎዱ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው እውነት ነው …
================================
በሚና ጀማራት አደጋ ኢትዮጵያውያን ስለመኖራቸው ስለ መጎዳታቸው ከመንግስት አካላትም ሆነ ከሀጅ ኮሚቴው የታወቀና የተሰጠ መረጃ የለም ። ያ ማለት ግን አደጋው አልጎዳንም ማለት አይደለም ። በዘንድሮው ኢድ አል አድሃ በጸሎት በተበሰረ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በአካል በቦታው በመገኘት የሞቱና የቆሰሉ ስለመኖራቸው ጭብጥ መረጃ ያቀበሉኝ አሉ ፣ እናም የሞቱና የቆሰሉ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው የሚያሳዝን አውነት ነው ። እዚህ በጅዳና በሪያድ ዙሪያ ከአንድም ሁለት ሶስት ኢትዮጵያውያን በአካል ሚና ተገኝተውና ቁርጣቸውን አውቀው ለቀሩት ዘመዶቻቸው መርዶ ነግረው ሀዘን የተቀመጡ በቅርብ የማውቃቸው አሉ ! በአደጋው ከተጎዱትና ካጣናቸው መካከል በአካል የማውቀው አንድ ወዳጀ ከወንድሙ ጋር በሀጅ የመጡ ቤተሰቦቹን ለመደገፍ ወደ መካ አቅንቶ በአደጋው ህይዎቱ ማለፉን አደጋው በተከሰተ ቀን ነበር የሰማሁት ፣ ከሁሉም የሚያመው የአደጋው ሰለባ እሱ ብቻ ሳይሆን ወንድሙም ጭምር መሆኑን ትናንት ማለዳ የፎቶ ማስረጃ ጭምር ሳገኝ በጣም አዘንኩ frown emoticon ነፍሳቸውን ይማር !
ዛሬም አደራሻቸው የጠፋ በአለም ዙሪያ ወደ ለሀጃጅ የመጡ የ18 ሀገር ሀጃጆች አሉ ፣ በርካታ ሀገራት የጠፉ ሀጃጆችን ስም ዝርዝር አውጥተው በፍለጋው ተግተዋል ። አንዳንዶች የሞቱ የቆሰሉና የጠፉት ዝርዝር ይፋ አድርገዋል ! በርካታ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶችና የሀጅ ኮሚቴ አባላት በመካና ሚና ዙሪያ ባደረጉት ማጣራት አደጋው ከተከሰተ ወዲህ ሪፖርት ያላደረጉ ኢትዮጵያውያን ሀጃጆች 179 ደርሰዋል ! የሚመለከታቸው አካላት በጅዳ ቆንስል የፊስ ቡክ ገጽ ሀጃጆች ያሉበትን አድራሻ አለመታወቁን ዝርዝርን ከአፋልጉን መልዕክት ጋር አሰራጭተዋል ። በዝርዝሩ የተጠቀሱት ሀጃጆች አደጋው ከተከሰተበት ካሳለፍናቸው ሁለት ቀናት ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያውያኑ ሀጃጆች መሰባሰቢያ ያልቀረቡት ሲሆን በተለያየ መንገድ ለአደጋ የተዳረጉ ፣ ቦታ የጠፋባቸው ወይም ጅዳ መካ፣ መዲናና ወደተለያዩ ቦታዎች በዘመዶቻቸው የተወሰዱ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል ።

neb 2

neb 3

neb 4

nebበማዕከላዊነት የማፈላለግ ስራው ይሰራ …
===========================
በጅዳ ቆንስል ፊስ ቡክ ከተጀመረው የአፋልጉኝ መረጃ ልውውጥ በተጓዳኝ የጅዳ ኮሚኒቲ ምክር ቤት አፋልጉኝ የሚል መልዕክትና መረጃ አስተላልፏል ። መተባበሩ ክፉም ባይሆን አሰራሩ ውጤት እንዲኖረው ማዕከላዊ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ቢኖር ይመረጥ ይመስለኛል ! በአንድ ማዕከላዊ የመረጃ ልውውጥ መጠቀም መረጃዎችን ከመደጋገም ያድናቸዋል ፣ ጊዜንም ይቆጥባልና በማዕከላዊነት የማፈላለግ ስራው ይሰራ !

ጅዳ ከመጡት ቁስለኞች ቤተሰብ፣ ዘመድና ወዳጀ ፍለጋ …
===================================
ከትናንት ማለዳ ጀምሮ በአደጋው የቆሰሉ ሰዎችን ወደ ጅዳ ሆስፒታሎች የማስተላለፉ ስራ መጀመሩን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው የመረጃ መንጮች ያገኘሁትን መረጃ ማቅረቤ አይዘነጋም ። ይህንኑ መረጃ ተከትለው ቤተሰባቸውን ሲፈልጉ የነበረ አንድ ወንድም በፍለጋው ያጋጠማቸውን የገለጹበትን መልዕክት እንዲህ ይላል ”
ሰላም ነብዩ ደህና አደርክ ማታ ከመካ የመጡ ቁስለኞች የት እንደሚገኙ ጠይቄህ ነበር ፣ ስፈልግ ነው ያደርኩት ፣ ሀበሻ ሊኖር የሚችለው ሙስተሽፈል ሀረስ ጠሪቅ መካ ያለው ይመስለኛል ። ከመቶ በላይ ቁሰለኛ አለ ብለዋል ፣ ግን አላስገቡንም ። ጀዋዛት ነገ አሻራ አንስቶ ስም ዝርዝር ይሰጠናል ነገ ጠዋት መጥታቹ ጠይቁ አሉን ! ሌላ ኡብሁር ያለው መሊክ አብደላ መርከዝ ጥብ 25 ሙስተሸፈል ጃምአ 15 ቁስለኞች አሉ ሀበሻ የለም ነበር ግን ሌላም እየመጡ ነው ብለዋል !” ይላል !

መረጃው ይህን ካለ የጅዳ ቆንስልና የሚመለከታቸው አካላት ወደ ጅዳ ያሉ የተለያዩ ሆስፒታሎችን በማንኳኳት በግለሰብ ደረጃ ውጣ ውረዱና ቢሮክሲው የሚቻል አይደለም ። ይልቁንም ህጋዊ የመንግስት ተወካዮች ተመድበው የጠፉ ዜጎችን ማፈላለግ ይጠበቅባቸዋል ።

መረጃ መስጠትና መቀበሉ …
===================

መረጃ መስጠትና መቀበል ፣ መቀባበሉ በዚህ ወሳኝ በሆነበት ወቅት ላይ መሆናችን ልብ እንበል ፣ ልዩነትን በዚህ አደጋ ጊዜ አናስፋ ፣ የተጎዱ የተጨነቁትን ማስቀደሙን እናስቀድም ! የመንግስት ተወካዮች ስልኮቻቸውን ያንሱ ፣ የሚያቀርቧቸው መረጃዎች የተሟሉ ይሁኑ ፣ ለምሳሌ ያህል የቀረበው ዝርዝር በጥሩ የእጅ የቁም ጽሁፍ ለመጻፉ ጊዜ ባይኖር የሀጃጆችን ስም ከነ አያታቸው ሙሉ ስም መጻፍ ነበረበት ። ይህ ወደ ፊት መታረም ይኖርበታል !
የተዘረዘሩትን 179 ሀጃጆች አድራሻቸውንና ያሉበትን ሁኔታ የምናውቅ ለሚመለከታቸው የኢንባሲ ፣ ቆንስላ ፣ የሀጅ ኮሚቴ ተወካዮች ወይም ለእኔ ማቀበል የቀለላችሁ ላኩልን ፣ ዋናው በማፈላለጉ ረገድ ትብብር ልናደርግ ይገባል ! ” የወገን ጉዳይ ያገባናል !” የምንል ጉዳዩ ለሚመለከታቸውን ኃላፊዎች ከዚህ ጋር በተሰጠው ስልክ በመደዎል አናሳውቅ ! ከዚህ ጋር በቀረበው ስም ዝርዝር ስማቸው ያልተመዘገበ ነገር ግን የጠፉ የምታውቋቸው ሀጃጆች ወይም ከሀጃጅ ቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ሚና ጀማራት መጥተው የጠፉ ኢትዮጵያውያንን ካሉ መረጃ በማቀበል የዜግነት ድርሻችን እንዎጣ እላለሁ !
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 15 ቀን 2008 ዓም

ተጠርጣሪው የኦሮሚያ ባለሥልጣን ከግለሰቦች ከ10.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ መቀበላቸው ተገለጸ

$
0
0

–በተጠረጠሩበት የነፍስ ግድያ መርማሪዎችና ዓቃቤ ሕግ መመሳጠራቸው ተጠቆመ

newsየኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ ወንድሙ ቢራቱን በተጠረጠሩበት ከባድ የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመራቸው የሚገኘው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን፣ ሰሞኑን ባካሄደው

ምርመራ ተጠርጣሪው ከግለሰቦች 10.5 ሚሊዮን ብር ጉቦ የተቀበሉበትን ሰነድ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡

መርማሪ ቡድኑ ከግለሰቦች ጉቦ ለመቀበላቸው የምስክሮችን ቃል መውሰዱን አክሏል፡፡ ተጠርጣሪው በሕገወጥ መንገድ ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪዎችን በሌሎች ግለሰቦች ስም ማስገባታቸውን የጠቆመው መርማሪ ቡድኑ፣ ተሽከርካሪዎቹን ማሳገዱን አስረድቷል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ በድን ባለፉት ሳምንታት ባካሄደው ምርመራ፣ ተጠርጣሪው በተጠረጠሩበት የነፍስ ግድያ ወንጀል በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖችና በአዲስ አበባ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መሰብሰቡን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ አቶ ወንድሙ በነፍስ ግድያ ተጠርጥረው እያለ፣ መርማሪዎችና ዓቃቤ ሕግ ተመሳጥረው ወደ ምስክርነት እንዲዛወሩ ማድረጋቸውንም የሚያስገነዝብ ማስረጃ መሰብሰቡን ገልጿል፡፡

ቀደም ብሎ እንደሚያከናውናቸው ከገለጻቸው የምርመራ ሥራዎች ውስጥ በተጠርጣሪው ላይ በጉምሩክ ተጀምሮ የነበረውንና በመመሳጠር ተቋርጦ የነበረውን ጅምር የምርመራ መዝገብ ከጉምሩክ መቀበሉንም ገልጿል፡፡ ሐሰተኛ ሰነድ እያሳተሙ በተለያዩ ከተሞች ሲፈጽሙ የነበረውን ግብር የመሰብሰብ ድርጊት የሚያስረዱ ምስክሮችን እያፈላለገ እንደሚገኝ መርማሪ ቡድኑ ገልጿል፡፡

የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ጨምሮ እንደገለጸው፣ ለተጠርጣሪው ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግሥት ግብርን እንዲሰበስቡ ደረሰኝ አትሞ ከሰጣቸው ግለሰብ የምስክርነት ቃል መቀበል ይቀረዋል፡፡ ሌሎች ለመንግሥት መግባት የነበረባቸውን የተጨማሪ እሴት ታክስና ግብር ለማስቀረት ጉቦ የተቀበሉበትን የባንክ ሰነድ መሰብሰብና ተጨማሪ የሰው ማስረጃ መሰብሰብ ይቀረዋል፡፡

ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሰው ማስረጃ ቃል መቀበሉን፣ ተጨማሪ የሰነድ ማስረጃ መሰብሰብ እንደሚቀረውና ሎሎች ተፈላጊ ተጠርጣሪዎችን አድኖ መያዝ እንዳለበት ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ጉቦ ሲቀበሉና ሲያቀብሉ የነበሩበት የባንክና ሌሎች ሰነዶችን ከመጠቀም በተጨማሪ፣ በሥልጣን ዘመናቸው ሲያጠራቅሙ የነበረውን ተጨማሪ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ሀብት ማፈላለግ እንደሚቀረው ለፍርድ ቤቱ ገልጾ፣ ይኼንን ለሚያከናውንበት ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲፈቀዱለት ጠይቋል፡፡

የተጠርጣሪው ጠበቃ መርማሪ ቡድኑ ያቀረበውን ተጨማሪ ጊዜ በመቃወም፣ እስካሁን ያደረገው ምርመራ በቂ መሆኑንና ተጨማሪ ምርመራ እንደማያስፈልግ በማስረዳት፣ የደንበኛቸው የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸውና ከእስር እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ግን ቀሪ ምርመራ እንደሚቀረው ማስረዳቱን በማስታወስ ዋስትናውን ተቃውሟል፡፡

ተረኛ ችሎቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ፣ የተጠርጣሪውን ጠበቃ አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ለመርማሪ ቡድኑ የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

ግርሻ – (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 26.09.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

(„እነሆ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ ነኝ። በውኑ ለእኔ የሚያቅተኝ ነገር አለን“ ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፪ ቁጥር ከ፳፯ እስከ ፳፰)

መቼም ይህን ዘመን – ዘመነ ግራሞት የዘምን ሚስጥር ልበለው ይሆን? እንዴት ናችሁ ቤቶች – ደህና ናችሁ ደህና ናችሁን?

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ቸገረን እኮ 6ቱ ህዋሳታችሁ የሉም እየተባል ነው። ስድስት ያልኩት የቀደመውን አምስቱን እንዳለ ተቀብዮ የሁሉ ዓይነታ የሆነውንም ጭንቅላትን በማከል እንጂ – የሳይንስን ሊቃውንት ለመጋፋት አይደለም። ሞልቶ ጭላጭ ባልሰራለት ዙሪያ ብክንክን ስንል ሰነባበትን። ቆስቁስ የሚል ቅጥል ሥም የነበራቸው የአባባ የአባቴ የሥጋ ዘመድ – ልጅ እያለሁ ቤት ይመጡ ነበር። ሰሞናቱን የቆሰቆሱ – የቀሰቀሱም ሁኔታዎች ቸል ተብለው ተዳምጠው ቢታለፉ፣ እነዛ በዘረኝነት ክርኒ የደቀቁ ሰማዕታት ሆኑ፤ በጉስቁል ህይወት ያልፋልን የሚጠብቁ ምንዱባን መንፈስ የት ናችሁ እያለ ያፋጥጣል። ሊታለፋ የማይገቡ ጉዳዮች ተክለ ሰውነት ነጥረው መፈተሽ – ይኖርባቸዋል። ቢያንስ በድምስሱ አለመሄዳችን ህዋሶቻችን ከእኛ ጋር ያሉ  ስለመሆናቸው ፊርማ ገጭ – ይደረግበታል።

ሰሞኑን በVOA እና በኢሳት ዶር አረጋይ በርኽ የህወሓት አንጋፋ መስራች፣ የትዴትም መሪ  የሸንጎውም አባል ሰሞናቱና የኢትዮጵያ ፖለቲካ በተመለከተ በሰጡት ቃለ-ምልስ ዙሪያ ትንሽ ልል ወደድኩ። ሁለት አዲስ ዕሳቤም አምጥተዋል። መነካካት የማይፈልጉትንም የህወሓት አንጡራ ሃብት የሆነውን ጄኒራል ዘረኝነትን ሆነ ልጆቹን – የልጅ ልጆችን ሸወድ አድርገው አልፈዋል። ዛሬ እኔ በነዛ ዙሪያ የምለውን እላለሁ።

እርግጥ ነው በአንዲት ብጣቂ የዕስቤ ክርክር ከሟቹ ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ ጋር የነበረውን – ጊዜ የበላ የረጅም ጊዜ እሰጣ ገባ ባውቅም፤ ቋጭቼ ነው ላልመለስበት በዛሬው ፁሑፌ እምከውነው። ያን ጊዜ የፓለቲካው እጭጌ ስለ ነበሩ፤ በዛ ሰብዕና ውስጥ የነበረውን ሙግት ስንታዘበው፤ እኒህ ሰው የኢትዮዽያ መሪ ቢሆኑ ከፕሬስ ነፃነት ጋር እንዴት ሊታረቁ ይችላሉ? በሚለው ዙሪያ ከጓደኞቻን ጋር እንነጋገር ነበር። ከሰሞናቱም በተለይ ከጋዜጠኛ ፋሲል ጋር የነበራቸው ቆይታ ብስጩ ድባብ ነበረው። የትግራይ ነገር ከተነሳች በስጨት ይላሉ። ግርሻ። የሆነ ሆኖ የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ ከእውነት የወጣ  አይደለም በማለት ክፋኛ የኮነኑትን፤ ቁም ተቀመጥ በማለት ያጣጣሉትን – ተንተርሼ ልጀምረው፤ ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ መጀመሪያ ካነሳው ጥያቄ ለጥቆ እንዲህ ነበር የጠዬቃቸው ዶር አረጋይን ……

„ዶር አረጋዊ ሌላ አንድ ተጨማሪ ጥያቄ ማንሳት እምፈልገው አርበኞች ግንቦት ባወጣው በዚህው በሰሞኑ መግለጫ አንድ ያነሳው ጥያቄ አለ በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ትግል ታሪክ ውስጥ ባጠቃላይና በተለይ ደግሞ ሕወሓት/ኢሕአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን በተቆጣጠረባቸው ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጥ ሕወሓት/ኢሕአዴግን እንቃወማለን በሚለው ወገን ገንነው የመጡ ሁለት አፍራሽና ኋላቀር የፖለቲካ አዝማሚያዎች (trends) አሉ። ከነኝህ ውስጥ አንደኛው ራስን በፖለቲካ አመለካከት ዙሪያ ከማሰባሰብ ይልቅ በጎጥና በዘውግ ደረጃ የመመልከትና ሀገራዊ ፖለቲካን በደም ቆጠራ የመመንዘር አባዜ ነው።  እርስወ አሁን የተፈጠረው ሁኔታ በዚህ የተቃውሞ ትግል ውስጥ የዘር መራራቅ መሻከር መጠራጠር እንዲፈጠርና እንዲህ አይነት ሁኔታ እንዲባባስ ያደርጋል ብለው ያስባሉ ወይስ ስጋት የለወትም?

የዶር አረጋይ በርኽ ምላሽ „በውነቱ ለመናገር ግንቦት ይህን መግለጫ ብሎ ከሆነ በጣም ተሳስቷል። የኢትዮጵያ ህዝብ በእርግጥ ህወሓት የፈጠረው ህወሓት ማለትም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም እነመለስ  የፈጠሩት የዞግ ወይንም የጎጥ ፖለቲካ በእርግጥም ገፍተው ህጋዊም አድርገውታል። በህገ መንግስትም  ጨምረውታል። እና ይሄ ነገር የጥቂቶች ጉዳይ እንጂ የመላው ህዝብ ጉዳይ አይደለም። ለማስፈጸም ሞክረዋል፤ ህዝቡን ለመከፋፈል ሞክረዋል። ግን ህዝቡ የደረሰበት ጭቆና አንድ እየሆነ ስለመጣ የደረሰበት ጭቆና አንድ አይነት መሆኑ እያዬው ስለመጣ ፤ገዢዎቹ ላይ ያለው ገዢው መደብ አንድ አይነት ጭቆና እየደረሰበት እንዳለ እየተገነዘበ ሲመጣ፣ የወለጋ ገበሬ የትግራይ ገበሬ የሚያሳልፈው ያለ ስቃይ፤ የይፋትና ጥሙጋ ገበሬ የብቸና ገበሬ የሚያሳልፈው ያለ ጭቆና እየተረዳ ስለመጣ፤ በዚህ በጎጥ ምክንያት የሚፈጠር ሁኔታ ያለ አይመስለኝም። በእርግጥ እነዚህ ሰወች በዛ ስለተከፉ፣ ሥልጣን ላይ ያሉ ሰወች በዚህ ስለተከፉ በዛ ሊቀጥሉበት ይጥራሉ። ህዝቡ ግን ተፍቶታል። ይሄ ነገር አይቀበለውም። እንዲያውም በጋራ ሆኖ ለመታገልና አንድነቱን ፈጥሮ በአገሪቱ ለሁሉም እኩል የሆነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመፍጠር ነው፤ የሚይ ያለው፤ የሚተምን ያለ፣ ፕላን የሚያደርግ ያለ፤ ስለዚህ ይሄ የጎጥ ትንተናው የግንቦት 7 ዝም ብሎ ለጊዚያዊ ጥቅም፣ ካልሆነ ለጊዜያዊ ማናፈሻ አንድን ወገን በጀርባ ለማሰለፍ ካልሆነ በስተቀር፣ ዋጋ ያለው ትንተና አድርጌ አልወስደውም።“  ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ በተመስጦና በአጽህኖት ያዳመጠውን እህ በማለት ውስጡን እንድንቃኝ ለአክባሪ አድማጮቹ የቤት ሥራ ሰጥቶን፤ ወደ ቀጣዩ ጥያቄ አምርቷል። ከቅኔው ልዑል ትንሽ የሥንኝ ዘለላ ….

„ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅሰው።“

„ከወዳጅ ዘመድ ርቆ

አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ

ተሸሽጎ ተገልሎ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ

ከቤተ – ሰው ተደብቆ

መሽቶ የማታ ማታ ሌት ነው የወንድ ልጅ እንባው

ብቻውን ነው የሚፈታው። …

ብቻውን ነው የሚረታው። …..

ብቻውን ነው፥  ብቻውን ነው …

የእንባ ጨለማ ለብሶ ነው

ወንድ ልጅ የሚነጥበው።“

የብላቴ ሎትሬት ጸጋየ ቅኝትን የዋጠ ነበር የጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ „እህ“ ። ዘመኑን መከታ ያደረጉ መስቃዎች ጡሯዊ ገለጣዎች ወይንም ዝንባሌዎች – የኢትዮዽያውያንን ውስጥ እንዲህ ሲያከስሉ – ይታያል። እንባቸውን በውስጥ ለሚያፈሱ – ደጎች። ታመው እንደሚያድሩም አስባለሁ።

ዕይታ።

  1. ዶክተሩ አዲሱን ዶክትሪያቸውን ሲጀምሩ እንዲህ ብለው ቀደሱት „ህወሓት ማለትም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም እነመለስ የፈጠሩት የዞግ ወይንም የጎጥ ፖለቲካ በእርግጥም ገፍተው ህጋዊም አድርገውታል። በህገ መንግስትም  ጨምረውታል።“ ግርሻ።

አዲስ የተወለደው የዶር አረጋይ ዶክተሪን ሟቹን ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ከህወሃት ማንፌስቱ ለይታችሁ ማየት ይገባል ነው የሚሉን። ይህም ማለት ደርሷል ለምትሉት ሰቆቃ የህወትን ማንፌስቶ ለቀቅ፤ መለስን ጠበቅ እያሉን ነው። አፈርን ጠይቁ ነው የሚሉን። ይህ መስቃ የት ሊያደርስ እንደሚችል፤ እግዜሩ ብቻ ነው የሚያውቀው። ዕጣ ፈንታችን ለህወሃት ማንፌስቶ ይስገድ እየተባልን ነው። ሎቱ ስብኃት። ለዚህ የተሃድሶ ዕሳቤ ነው ተጎዝጉዞ ተነጥፎ የምናቡ የሽግግር መንግሥት የሹመት ፍርርም። ሞፈር – ቀንበር፣ ገበሬ፣ የእርሻ ማሳ የለም። ጎታው ግን በረድፍ ተሰልፎ „ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ“ እያለ በባንድ – ይዘምራል።

  1. „ይሄ የጎጥ ትንተናው የግንቦት 7 ዝም ብሎ ለጊዚያዊ ጥቅም፣ ካልሆነ ለጊዜያዊ ማናፈሻ አንድን ወገን በጀርባ ለማሰለፍ ካልሆነ በስተቀር፣ ዋጋ ያለው ትንተና አድርጌ አልወስደውም።“

racism discrimination and genocide in the 21st century

ይሄንን ያዳምጡት በአክብሮት፤ ገለጣዎች ወይንም ዝንባሌዎች ግፉ ከእርከኑ በላይ አልፎ፤ የአውሮፓ ማህበረሰበ በዘመነ ጨለማ ለደረሰው የአንድ ዘር የበላይነት፤ በእውነት ላይ የተመሰረተ ወላዊ ውሳኔ በተደሞ – ሰጥቶበታል። የትግሬ መንግስት እያለ፤ ይህስ አርበኞች ግንቦት የሰራው አርቲፊሻል አንድምታ ነውን – ልትሉ ይሆን ?

http://ecadforum.com/ethiopianvideo/2015/02/03/u-s-policy-ethiopia-a-failed-state-documentary

  1. ኦሾቲዝም በኢትዮጵያ

(„የክፋት ምስክሮች ተነሱብኝ የማላውቀውን በእኔ ላይ ተናገሩ“ መዝ ምዕራፍ፴፬ ቁጥር ፲፩)

በዚህ በናንተው ወገኖች ዘመን ከተፈጸመው ኦሾቲዝም በኢትዮጵያ ለቅምሻ፣ ለእርሰወም ብቻ ሳይሆን የመከረኛው ቤተሰቦች የእርሰዎን መልስና የአርበኞች ግንቦት መግለጫ የእውነት አውደ ምህረት ይመዝኑት ዘንድ በትህትና አሳስባለሁ።

https://www.youtube.com/watch?v=9ylowukO6yQ

https://www.youtube.com/watch?v=RWVt6ZSmXR8

https://www.youtube.com/watch?v=-bw1CQxaVqg

https://www.youtube.com/watch?v=4f0kkHnB4H4

https://www.youtube.com/watch?v=jPDnEkQPUNk

https://www.youtube.com/watch?v=dDhbbXTU9zk

ከአራዊቶች፤ ከፋሽስቶች መካከል ግን አንድ ፃድቅ፣ አንድ መላክ፤ አንድ ቅዱስ አለ።

  1. ነገረ አርኞች ግንቦት ሰባት

የተከበሩ ዶር አረጋይ በርኽ  – ለኢህአድግ የሰጡት እውቅና በዛች አጭር የሦስትዮሽ ቃለ ልልስ ወደ 14 ጊዜ ነበር። ይገርም።  በሌላ በኩል ደግሞ ሁለት ጊዜ ግንቦት ሰባት እያሉ ነበር የተናገሩት። አንድ የፖለቲካ መሪ የብቃቱ አቅም ለሌሎች አቻ ፓርቲዎች ያለው አክብሮት ምጣኔ እሱ – እራሱ ይለካበታል። ይህ ሰሳ ብሎ የቀረበው ነገረ የጎሪጥ – የአርበኞችን እና የግንቦት ውህደት በህሊና ውስጥ ያለውን የዕውቅና አቅም ቁልጭ አድርጓል። ይሄ ታዝሎ ነው ስለ ትብብር ሆነ ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚሰበከው። ሚሊዎኖች ተስፋቸውን ያስጠለሉበት የታሪክን ምዕራፍ አላዬሁም ቢሉት ትርፋ ተደማጭነትን በላፒስ ማጥፋት ይሆናል።

በጠቅላላ ከአሜሪካው ድምጽ ራዲዮ ጋር በነበረወት ቃለ ምልልስ ስውሩን መንግስት የተጣፈበትን ቅርፊት ኢህድግ እያሉ እውቅና ሲሰጡ የሚሊዎኖችን ድምጽ የሆነውን ውህደት ሆን ብለው – ድጠውታል። ይሄ ነው የታላቋ ትግራይ ህልመኛ ማኒፌስቶ – ትሩፋት። የማከብራቸውን አቶ ገመድህን አርያን አይመለከትም። ክቡርነታቸው ትእቢትም – የለባቸውም። ሌላው በዚህ አመክንዮ ውህደቱን ለፈጠረው ድርጅት ለቀድሞው አርበኞች ግንባር ያለውን ዓይን ያወጣ ንቀት በጉልህ  – አይቸበታለሁ። ስለሆነም ለአቶ ወንድም ለአቤ በለው እንኳን ይህን ውርዴት መሸከም የሚችል ደንዳና ትክሻ ሰጠህ – እላለሁ። ለማንኛውም የት ቦታ ላይ የቁስል ጥዝጠዛ እንዳለ በተመስጦ – ተመልክቸበታለሁ።

  1. እጥረት የሚዛን።

„ግን ህዝቡ የደረሰበት ጭቆና አንድ እየሆነ ስለመጣ የደረሰበት ጭቆና አንድ አይነት መሆኑ እያዬው ስለመጣ ገዢዎቹ ላይ ያለው ገዢው መደብ አንድ አይነት ጭቆና እየደረሰበት እንዳለ እየተገነዘበ ሲመጣ፣ የወለጋ ገበሬ የትግራይ ገበሬ የሚያሳልፈው ያለ ስቃይ፤ የይፋትና ጥሙጋ ገበሬ የብቸና ገበሬ የሚያሳልፈው ያለ ጭቆና እየተረዳ ስለመጣ፤ በዚህ በጎጥ ምክንያት የሚፈጠር ሁኔታ ያለ አይመስለኝም።“ ዋው¡ – ግርሻ።

አንድን ነገር ለማወዳር የሚቻለው ሊወዳደር ከሚችለው ጋር ብቻ ነው። ጨርቅና ድንጋይ አይወዳደርም። ወይንም ውሃ እና አፈር፤ ወይንም ወርቅና ብረት ለዚህ ነው የጎጃም ገበሬ ሴቶች እንዲመከኑ፤ የጎንደር – የወሎ – የአፋር ገበሬዎች ከእርስታቸው መነቀል ብቻ ሳይሆን በእርስተ ጉልታቸው ዜግነታቸውን ተቀምተው ሃያ አምስት ሙሉ ምጥ ላይ ያሉት፤ ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ ለትግራይ ቁሞ እራት የሚያበላው የጎንደር ገበሬ። የጋምቤላ ገበሬ ከመሬቱ መነቀሉ ብቻ ሳይሆን እንደ ወልቃይት ጸገዴ ጀኖሳይድ የተካሄደበት፤ የመተከል፣ የጉራ ፈርዳ፤ የወተር፤ የአንቦ ወዘተ ገበሬዎች ምኑ ያልቃል፤ እነኝህ ወገኖች ሰው አይደሉንም?

አርበኞች ግንቦት የወገኖቹ ችግር በሚገባ በዝርዝር ስለሚያውቀው፤ ከመከራው ጠርን በመነሳቱም ነው ሌላው ሲያባንነው ውሎ የሚያድርበት የቤተ መንግሥቱ ጉዳይ ባእዱ የሆነው። የህዝብ የሥልጣን ምንጭነትን ለማረጋገጥ ነው ዱር ቤቴ ያለው። ስለሆነም በሥራም በኑሮም ለማያውቁት – የማየት አጋጣሚ ላለገኙት መግለጫውን ለማመሳጣር ዳታ ያበዙት። የተከበሩ ዶር አረጋይ በርኽ  ከአመት በፊት ነው ይህን ህዝብ ያዩት – ለሥራ በደረሱበት ዘመን የኢትዮዽያን ህዝብ ሥነ ልቦና ጋር በቅርበት ለመደማመጥ አጋጣሚውን ባለማግኘተወት ይመስለኛል፣ እንዲህ መቀራረብ የማይችል ዕይታ ሊኖር የቻለ፤ ይመስለኛል። እንጂ የአርበኞች ግንቦት መግለጫ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ሳይሆን ከመከራችን ልብ፤ ከእውነት ማህደር፤ ከእንባችን ብሄራዊ ጥሪ ነው የተነሳው። መታመን የሚቻለውም ከመራራው ሃቅ ሲነሱ ነው።

አድሎና ዘረኝነት እንዲሁም የኢትዮጵያዊ ዜግነት ዕጣ ፈንታ፤

(„እግዚአብሄር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው“ መዝ ምዕራፍ ፴፫ ቁጥር ፩፰)

የተከበሩ ዶር አረጋይ በርኽ  – በመቅድምነት ለቀረበለወት ጥያቄ ስለ ጉስቁሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ያለበትን ከመከራ፣ ስደቱን፣ እራህቡን፤ መከፋቱን ገልጸው፤ ምክንያቱን ዘለው በሳቢያው ላይ ነበር – ያተኮሩት። የዚህ ሁሉ ምንጭ የህወሓት ማኒፌስቶ ዘረኝነት ነው። ይህን ደግሞ ወደ ውስጥ ሳይገባ የደጀ ሰላሟን የዘረኝነትን ስልባቦት ያዳምጡት እስኪ – በአክብሮት። የጹሁፌ ታዳሚዎችም የአርበኞች ግንቦት መግለጫ የእውነት መሰረትነቱን ማገናዘብ – ትችላላችሁ። ኢትዮጵያ በሽምቅ ውጊያ ሚሊሺያዎች ትተዳደራለች፤ ሲቢል ሰርቢሱ ተልዕኮም ይሄው ነው። አሁንም በአማተር ወታደራዊ ሥርአት አሳሯን – ታያለች። እንዲህ …..

https://ethsat.com/video/2015/09/09/esat-yesamintu-engeda-capitain-kinde-damte-september-2015/

https://ethsat.com/video/2015/08/17/esat-bezhi-samint-colonel-derese-capitain-teshome-ermias-august-16-2015/

https://ethsat.com/video/2015/08/23/esat-bezhi-samint-colonel-derese-capitain-teshome-ermias-august-23-2015-part-2/

ይህ እንግዲህ ከገጠር እስከ ከተማ በተዘረጋው – መዋቅር፤ በየትኛውም ቀዳዳ የሥነ – ልቦና የበላይነቱ በህግ የጸደቀለት የበላይና የበታች፣ የባሬያ እና የጌታ፣  የክትና የዘወትር፣ ወርቅና ነሃስ የፈጠረው የቆሰለ፤ የመገለ ግፍ ባልታሰበ ቀን፤ ካልሆነ ቦታ ከፈነዳ እንደ ሰው ለምናስብ – ያስጨንቀናል። ይሉንታ በሌለው ጭካኔ – አድሎ የተጠቀጠቀው ወገን ኮቴው ቋያ ነው። ረመጥ ነው። ቢያንስ የዕዳው ባለ ዕዳ ባልበሉት ዕዳ ህፃናት ገና ለሚወለዱት – ትግራይ ላይ ለሚፈጠሩ ህፃናት ጉዳይ ገዶት ነው አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ በርሃ የወረደው። ስለዚህም ዘመናዮችን ተወት አድርገን – ነገን ለማሳደር በሰብዕዊነት ዙሪያ እንስራ፤

የኢትዮጵያዊነት ስብዕና ሰፊ የሆነ የምርምር ማሳ ነው። አልተሰራበትም ከምል – አልጀመርነውም። የኢትዮጵያዊነት ሰብዕና በፈረሃ እግዚአብሄር የተሟሸ ነው። ህዝባችን ትውፊቶቹን – የባህል ዕሴቶቹን – እንደ ሃይማኖቱ ነው የሚቀበላቸው። ለዚህም ነው እኔ ኢትዮጵያ ሀገራችን ባልተፃፈ ህግም ትተዳደራለች አዘውትሬ የምለው – ስለተፈቀደለትም በአፈፃጸሙ እጅግ ጉልበታምና ጉልህ ሆኖ የምናገኘው። ለፍትህ አዳሪነቱ እራሱ የፍትህ አካል መሆኑ ነው። ዛሬ ባደገው ዘመን መቻቻልን የሚያበረታቱ ቢሮዎች እልፍ ናቸው። ኢትዮጵያ ግን ስትፈጠር የተሰጣት ናት። እና ዶር አረጋይ በርኽ የዛሉት ከዚህ ላይ ነው። በሚታይ ግፍ ውስጥ የማይታይ – ግን ተመስጥሮ ከደም ጋር የተቀመመ መቻቻል። ሌላ ዓለም የሌለ ይሉኝታ፤

ከሁሉ በላይ የሰው ትክክለኛ ትርጓሜ ከፈጣሪ ስጦታ ጋር የማመሰጠር ብቃት። እነዚህ ነገሮች በአንድ ዘር የበላይነት የሚደርሰውን ሰቆቃ ለመሸከም ታጋሽነትና መጠን ያለፈ ትእግስቱ እንደምናያቸው የሌሎች ሀገሮች እልቂቶች የታዬ ነገር አለመኖሩ ግፉ ተዘለለ ማለት አይደለም። ስለዚህም የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ ከምንዱባኑ ዕለታዊ የዕንባ መሃጸን የተነሳ ተጨባጭና እውነት ነው። ነፍስም ትንፋሽም ያለው መግለጫ ነው። የዚህ ረቂቅ ጸጋ ባለቤቶችን መምህርና ጋዜጠኛ ውዴ አብረሃም ደስታ ሆኑ አቶ ገብረመድህን አርያ ክብር ናቸው ለታሪክም – ለዘመንም። የኢትዮዽያን ህዝብ ማስተዋል የሚሰብል። ጌታችን መዳህኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለሚሊዎን ተላላፊዎች የአንድ ጻድቅ ድንቅ ተግባር የምህረት፣ የይቅርታ፣ የሥርየት መልእክተኛ ይሆናል። ኢትዮጵያዊነት ማለት ይህ ነው።

ኢትዮዽያዊነት ሰው ሰራሽ ንጥረ ነገር አይደለም። ኢትዮዽያዊነት ሰማያዊ ነው እንጂ ዶር. አረጋይ እንደሚሉት “ጭቆናው አንድ አይነት ሆኖ አይደለም።“ የታላቋ ትግራይ ማኒፌስቶ ያልተሳካለት አምክንዮ ኢትዮዽያዊነትን ከደማችን ማውጣት አልተቻለም። የነፃነታችን አንባሳደር የሆነውን ብሄራዊ አርማችን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅዓላማችን የሰናፍጭ ያህል ከክብሩ ዝቅ ማድረግ አልቻለም እንዲያውም እንዲበረከክ እራሱን እያደረገ መሆኑን ዘመን ጥሩ ነውና እያዬን ነው። ከዚህ በተጨማሪ አማርኛ ቋንቋ የኢትዮዽያ ህዝብ አንጡራ ሃብት መሆኑን ሊያከስለው ያሰናዳለትን ደባ ሁሉ ድል ማድረጉን ማኒፌስቷችሁ እንዲቀበል ስለተገደደ ለመቀዬጥ እየተደረገ ያለው የስዋሰው ህግ ረገጣ እያዳመጥን ነው። የ25 አመት ሸር – ብንን።

የአምስተርዳሙ ኢሳትና ዶር አረጋይ በርኽ የዕይታ አንድምታ ጭማቂ።

ዶር አረጋይ በርኽ ከኢስት ጋር በነበራቸው ቆይታ ከጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ጋር ባደረጉት ቃለ – ምልልስ አዲስ ዶክተሪን አዳምጠናል፤ ቀደም ባለው ጊዜ „ትግራይ የተሰዋንላትን ያህል አልተጠቀመችም“ ይሉን ነበር። አሁን ደግሞ „ተበድላለች“ ያሉን ከውቅያኖስ በሾርባ ማንኪያ ውሃ እንደ መቅዳት ቢያስቆጥርም – ሊንኮችን የጹሁፌ ታዳሚዎች እንድታዩ እጋብዛለሁ። ግብዣ ያልኩት ያልተመጣጠነ የሃብት ስርጭት መኖሩ የተገባ ነው ለማለት ሳይሆን፤ የትግራይ ልጆችም ወገኖቻችን የእኛው ስለሆኑ ነው። ምነው የግለሰብ መደለቢያ የሆኑ የተዘረፉ አንጡራ ሃብቶች ለህዝብ ጥቅም በዋሉ – እዛው ትግራይ ላይ። ቱቦ የህወሓት ባለስልጣናት ከሚዘምኑበት – ትግራይ ላይ እንጀራ በሆነ። ሰው በውሃ እየተጠማ ከሚፈስ ትልቅ ወንዝ አፍ ያረጠበ ምንጭ የተባረከ ነውና።

“የእኔ ዓላማ የግሌ ማለት ነው” ይሉና “ብቻም አይደለም፤ የስብስብ ይሄ ደግሞ ዝም ብሎ ተራ ዓላማ አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሙሉ በእኩልነት የሚይ ሥርዓት ህግ የሚገዛው አስተዳደር፣ እንዲፈጠር የቆምኩለት ዓላማ ነው። ይሄ ዓላማ ገና ተማሪ ሆኜ አዲስ አበባ የጀመርኩት ስለሆነ በቀላሉ የሚፍረከረክ አይደለም።”

ዶር አረጋይ በርኽ እውን ለዚህ ነበር ወጣትነታቸውን የሸለሙት አሁንም እኮ ከህወሃት ማንፌስቶ ዞር በሉ መለስን ጠይቁ እያሉን ነው። ይሄም ብቻ አይደለም ውጪ ከወጡ በኋላ እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ ትግራይ ዴሞክራሲ ትብብር (ትዴት) አለ። የአሁኑን አላውቅም ቀደም ባለው ጊዜ የኢተፖድህ የድጋፍ ድርጅት ጥቆማ ላይ አብረዋቸው መድረክ ላይ የተቀመጡት የማያደርጉትን እሳቸው ሲያደርጉ – ተመልክቻለሁ። እራሳቸው ሀጎስ፣ ተክላይ እያሉ ቦታ ሲሻሙ አይቻለሁ። እና “በጎሳ አስተሳሰብ ኋላቀሮች፤  የዘቀጡ – የተጋረዱ” እያሉ የሚዘልፏቸው ወገኖች ወይንስ ከልጅነት እስከ እውቀት የጎጥ ችግኝ አብቃይ ወይንም መሥራቹ ማነው ለጎጡ ጥብቅና ደፋ ቀና የሚለው? “የራስን ዕድል በራስ መወሰን የብሄረሰቦች መብት እስከመገንጠል” ትክክል እንዳልነበር ገልጸዋል፤ በሁለቱም በኩል ላለፈው ህይወት ተጠያቂነቱ የማን ነው? ካሳውስ?

ወይ መዳህኒተ አምላኬ – አዲስ መደብ ያሉት የሁሉምብሄረሰብ አባላት በማድረግ የስልጣን ክፍፍሉን ወዛማ አድርገውታል፤ ምድር ጦሩ፤ አየር ኃይሉ፤ ደህንነቱ፤ የፖሊስ ሠራዊቱ፤ የፍትህ ተቋማት፤ የወይን ቤቶች አስተዳደር፤ ቁልፍ የኢኮኖሚ ተቋማት በትግራይ ተወላጆች ተይዞ ነው፥ ሙሁሩ የእንቅልፍ ክኒን የሚጋብዙን። ፍርፋሪ የሚወረወርላቸው ግን በካማ ጎብጠው የሚሄዱትን ነው፤ ሌላው የሥነ ልቦና የበላይነት የራስ ጌታ ያደርጋል። ይሄ ዜግነቱን የተነጠቀው ሰቆቆኛው የኢትዮዽያ ህዝብ አሳምሮ፣ አበጥሮ፣ አንተርትሮ ያውቀዋል። በራስ የመተማመን ተፈጥሮዊ ጸጋውን ነው በግፍ ያጣው።

ሌላው የህወሓትን ዘረኛና ሚሊሻዊ አስተዳር ለመጣል የተደረጉ ጥረቶችን አቃለውታል ዶር አረጋይ በርኽ፤ በድርጅትም በህብረትም ተጽዕኖ ፈጣሪ አልነበረም ብለውናል፤ ጉልበታም ተሳትፎና ታሪካችን እኮ ነው የብዕር አርበኞቻችን በአለም አደባባይ የህወሓትን ረገጣ በማጋለጥ የድርብርብ ሽልማት ባለሟል የሆኑት፤ ሌላም ልከል -ህወሓትን ለፈተና የጣለ ፤ እንደ ድርጅት ቅንጅት፤ አንድነት፤ ግንቦት 7 ማንሳት ይቻላል፤ እንደ ሰብአዊ መብት ተሟጋች የሰማእቱ የኔሰው ህልፈት፤ ጋዜጠኛ አበበ ገላው፤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ ጋዜጠኛና መምህር ርዕዮት ዓለሙ፤ ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ጋዜጠኛና መምህር አብረሃም ደስታ፤ የዞን ዘጠኝ አንበሶች፤ አቶ ኦባንግ ሜቶ፤ አቶ ኦኬሎ አኳይና አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ገናናው የድምፃችን ይሰማ እንቅስቃሴ እና የተከበረው የህወሃትን መፍረክረክ ብቻ ሳይሆን፤ ህወሃትን ምጥ ላይ አስቀምጦታል።

በዱር ቤቴ መስመርም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ውህደት  ህወሓት የእንብርክክ እያስኬደው ነው። ሰፊ አድማጭም አለው። ይህ እውነት ነው። በተለይም የመሪዎቹ ሁሉን ሆነው አርበኛውን መቀላቀላቸው – የአርበኞች ግንቦት ጅምር የዘሩን ዛር ቁንጮ ህወሃትን ትቅማጥ እንደያዘው – እያራወጠው ነው። ይህን የሚሊዎኖችን የተስፋ ሃዲድ ማቃለል አይቻልም። ጠንካራ መሪ ጠንካራ ድርጅት አለን። የመሪነት ብቃት ተጽዕኖ ፈጣሪነት እያዬን ነው። ተመስገን።

የኢትዮጵያ አገር አን ጥምረትም ብሄራዊውን ጥሬ በሩን ከርችሞ ሳይሆን ቧ አድርጎ ከፍቶ ፏ ብሎ እየጠበቃችሁ ነው። መወሰን የነፍስ ወከፍ፤ እንዲሁም የወል ጉዳይ ነው። አሁን ማመሃኛ የለም። ያደገ፣ የቀደመ በሳል መግለጫ ነው፤ ለራሱ ለህወሓት ሳይቀር፤ እንኳንስ ለአጋር ድርጅቶች። በመጨረሻ ንግግረዎት አበክረው ለሚዲያ ሰዎች ያስገነዘቡትም ቢሆን በሀገር ጉዳይ ፉታ አጥተው ካላነበቡት በስተቀር የአገር አድኑ ሚዲያዎች እንዲተጉበት ላሳሰቡት ጉዳይ — የአገር አድኑ ጥምረቱ የሚዲያን የቤት ሥራ አስቀድሞ ሠርቶታል። የነገ ኢትዮጵያን ቀና መንፈስ ንድፍ አሃዱ ብሎታል። ይህነን ዘሃ ግራው – ትብትብ ሁኔታ የመሻገሪያ አስኳሉን በጥንቁቅ ህሊና ተልሞታል።

የማከብረወት ዶር አረጋይ በርኽ ——ያስታውሳሉ የኢተፓድህ ሁለተኛ ጉባኤ ተውሎ – ታድሮ፤ ታድሮ – ተውሎ፤ እንደገናም ታድሮ አጀንዳ እንኳን ማጽደቅ እንዳልተቻለ፤ ያ … ከሀገር ቤት ሳይቀር የጉባኤ አባላት የተሳተፋበት ታላቁን ጉባኤ እድምታ ህዝብ ተሰብስቦ ሲጠብቅ ምን እንደነበር እኔው እራሴ – አይቸዋለሁ። ለዚህም ነው ዛሬ ፈተናን እየደፈሩ የሚገሰግሱ ተግባራት የመንፈሴ ዘውድ የሆኑት፤ ለተባ ተግባር ዕውቅና ለመስጠት ቆጥቋጣ ባይሆኑ መልካም ይመስለኛል – በትህትና። ቅንነቱ ካለ የጎደለውን እየሟሉ፤ ያነሰውን እያከሉ የወል ፍላጎትን ማሳካት ይቻላል።

የሁለቱ ቃለ ምልልሳ ሚዛናዊነት ከመሪነት ሰብእና አንፃር

ዶር አረጋይ በርኽ ስለ አቶ ሞላ በአሜሪካው ራዲዮ አማርኛው ዝግጅት ላይ አቶ ሞላ አስገዶምን እንደማያውቁት ከእርሳቸው በርቀት አስቀምጠው ኢሳት አምስተርዳም ላይ ሻሩት፤

1           ሌላው ስለ አቶ ሞላ አስገዶም ከህወሓት ጋር መስራት ዕድሜ ጠገብ እንደሚሆን ግምታቸውን አስምረውበታል፤ ይህ ባንድ በኩል የሚያውቁት ነገር እንዳለ ቢጠቁምም፤ በሌላ በኩል ለደማለት ድል ባይተዋር ነህ ተብሎ ሲባረር የዛችን ወቅት እልህ – ቁጭት ላይ ሆኖ ለዚህ ተግባር ይሰለፋል ማለት ይቸግራል። የቀደመው ዋጋው ደጅ አዳሪ ሆኖ በተቀራረበ ጊዜ አብሶ ከሄሮድስ መለስ ዜናዊ ሞት በፊት ይህን ኃላፊነት ሊያስወስድ የሚያስችል አመክንዮ አላየሁበትም፤ ሰብዕናውም ለዚህ ረጅም ጊዜ ስውር ድርሻ ብቃት – ያንሰዋል። በዚህ  የዶር አረጋይ በርኽ  የግምት ጉዞ ሌላ ሁለት ነገሮችን ባነሳ አንደኛው የስለላ ተግባር ለመሐበረሰባችን ነውር ሳለሆነ ወንዱን ጆሮ ጠቢ፤ ሴቷን ደግሞ ቀልበጡሊ በማለት እንዲገለሉ ያደርጋል። ስለዚህ በዚህ አምክንዮ ዙሪያ ከዶር አረጋይ በርኽ ይልቅ ታጋይ መኮነን ተስፋዬ ለትግራይ ህዝብ የታሪክ ህልውና ዘብ መቆማቸው – ነገን የሚያበረክት ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ታጋይ መኮነን አላሟሟቁትም፤ ለቅኖች አብዝተው ጥንቃቄ ማድረጋቸው፤ ለእኔ ተመችቶኛል። ሌላው የስለላው መረብ ረጅም ዕድሜ ነበረው ለማለት ማሰቡ የአገር አድን ጥምረቱ በጥርጣሬ ስጋት እንዲወጠር ነቅንቅ አይነት ይመስላል፤ ነገም ቢሆን ይህ ሊፈጠር ይችላል በማለት ያለውን ዘመን ጠገብ የትስስር ሥነ ልቦናዊ ጋብቻ ትርትር የሚፈጥር ዓይነት ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ስለዚህም መድህናችነን ኢትዮጵያዊነትን እንዋጥ።

2          በአሉታ በጥላቻ መጀመር ለአንድ የጎሳ ፓለቲካ መሪ ሳቢነትን፣ ተእማኒነትን፣ ተቀባነትን፣ ተስፋነትን፣ ወላዊነት መፍቀድን፣ ከዘመን ጋር ለመጓዝ መፍቀድን በጥቅሉ የአመራር ደረጃ ብቃትን ጥራት ላይ ተጽእኖ ያሳድራል፤ ወደ ስድብ ከወረደ የመሪነቱ ደረጃ ይቀዘቅል „የተጋረዱ“ „በአንድ ጀሮ ተሰምቶ በሌላው ይፈሳል“ በእኛ በተራዎች አያምርም እንኳንስ በእርሰዎ። ዋጥ ተደርገው መሪ ሆደ ሰፊ መሆን አለበት፤ የሚንቁትም ሆነ የሚጠሉት የህዝብ አስተያዬት ከሚደፋት ቢያደምጡት ነው የሚበጀው፤ አሁንም እቀጥላለሁ እንደምፈልገው ከሆነ በሀገሬ ውስጥም እስካሉ ድረስ፥ ለህዝብ ቅሬታዊ ትችት አቅል። ከሚወርፉት ሰው ተሽሎ መገኘት ብልህነት ነበር።

3          „በውነቱ ለመናገር ግንቦት ይህን መግለጫ ብሎ ከሆነ በጣም ተሳስቷል። ብሎ ከሆነወይ ጉድ፣ በአንድ በኩል በአቶ ሞላ አስገዶም ዙሪያ ሚዲያ ላይ የወጡትን እንዳዩ፣ እንዲሁም እንዳታደሙበት ይነግሩናል፣ በሌላ በኩል የጉዳዩን የኣናት ምንጭ መግለጫ እንዳላነበቡ – ይነግሩናል። ንቀት ነው? ማጣጣል ነው? ጉዳዬ አይደለም ነው ወይንስ ከፖለቲካው ውጭ ነኝ ነው? እኔ እንደ ሥርጉተ በኢተፓድህ ታሪክ ቤተኛ የነበሩት የዛሬው የሸንጎ ቤተኛ የሚተናነቃቸው የሃቅ የወርቅ ጓል እንዳለ ተመልክቻለሁ፣ ለውጥ ፈላጊው መንፈሱን የገበረለት ተወዳጅ አዲሱ ምእራፍ ለማድመጥ እንዳቃታቸው – እውነት እንዲህ ናት ትመራለች። ለአርበኞቿ ግን ትጣፍጣለች። የእውነት ሽሽት እራስን – ይገልጣል።

ልከውን – የማከብራችሁ ብልሁን ሚዛን ለማየት የተለጠፉ ሊንኮችን ጊዜ ሰጥታችሁ ብትመረምሩ መልካም ነው። በተረፈ ውዴ ዘሃበሻን በማመስገን መሸቢያ ሰንበት። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ሊንኮች …..

ዶር አረጋይ በርኽ ስለ ጥዴን ሁኔታ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46742

http://ethsat.com/video/2015/09/18/esat-eneweyay-with-dr-aregawi-berhe-sep-18-2015-ethiopia/

„የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃን ሥራው እየተካሄደ መሆኑን ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ ሥራው ባለመጠናቀቁ መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46868#sthash.bSgpTko2.dpuf

የኢፈርት የገዢው ፓርቲ ንግድና ኢንዱስትሪ ዝርዝርና የካፒታል መጠን

http://ethioentertainment.tumblr.com/post/69174617650

ሞሃ 8ኛ ፋብሪካ በመቀሌ ተመረቀ

http://ajebnew.net/news/story-in-amharic

የምጥን ማዳበርያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ

http://www.google.ch/

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስትክፍል 8
http://www.ethioaddislink.com/aggregator/categories/16

የትግራይ ክልል በብዙ መልኩ ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የተሻለ ተጠቃሚ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ! ለምን የሌሎች ክልሎች ለውጥ እንዲህ አይታይም?

http://ethiopiaobservatory.com/2015/04/10

http://ethiopiaobservatory.com/2015/09/15/update

 

 

 

ኮለኔል ባጫ ሁንዴ አረፉ

$
0
0

የኮለኔል ባጫ ሁንዴ የህይወት ታሪክ

colonel bacha

ኮለኔል ባጫ ሁንዴ በአንቦ አካባቢ በጊንጪ ከተማ ተወለዱ ።በአምቦ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ በ1965 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በኢትዮጵያ አየር ሃይል በአውሮፕላን ጥገና አገራቸውን ለማገልገል ተቀጥረው ስልጠናቸውን እንደጨረሱ ከክፍላቸው ያመጡት ውጤት የላቀ በመሆኑ እና የተዋጊ አውሮፕላን በራሪ ለመሆን ባሳዩት ከፍተኛ ፍላጎት ሙያው የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስፈርት በማሟላት ወደ በረራ ትምህርት ቤት ገቡ ።

የሚፈለግባቸውን የበረራ ትምህርት እንደጨረሱ ወደ ተዋጊ ስኳድሮን በመመደብ የኤፍ 86 አውሮፕላን ሲበሩ ቆይተው የኢትዮጵያ አየር ሃይል F-5E የሚባል አዲስ አውሮፕላን ሲገዛ ወደ አሜሪካን አገር ተልከው በዚሁ አውሮፕላን ስልጠና በመውሰድ እና በማጠናቀቅ ወደ አገራቸው ተመልሰው በወቅቱ አገራችንን የወረሩትን የሱማሌ ወራሪዎች ጋር ፍልሚያ ውስጥ በመግባት በአየር ላይ ውጊያ ሁለት የሱማሌ ሚግ አውሮፕላኖችን መትተው የጣሉ ሲሆን በዚህም ላሳዩት ከፍተኛ ጀግንነት ከኢትዮጵያ መንግስት የጦር ሜዳ የላቀ ጀግንነት ሜዳይ ተሸላሚ ሆነዋል።

ኮለኔል ባጫ ሁንዴ በአየር ሃይል ሰራዊት ዘንድ እንዲሁም በጓደኞቻቸው በጣም ተወዳጅ ከነበሩት መካከል እና በስራቸውም አሉ ከሚባሉት የተዋጊ አውሮፕላን አብራሪዎች አንዱ እንደነበሩ ይታወቃል።

ኮለኔል ባጫ በወቅቱ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት አስተዳደር ባለመደሰት በ1986 ሲሲና የምትባል አውሮፕላን በማብረር ወደ ሱዳን ተሰደው በመጨረሻም ወደ አሜሪካ በመምጣት በሳንፍራንሲስኮ ከተማ ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ ኖረዋል።

ኮለኔል ባጫ የአንድ ሴት እና የሁለት ወንዶች አባት ሲሆኑ ሶስት የልጅ ልጅ ለማየትም በቅተዋል።

የኮለኔል ባጫ የቀብር ስነ ሥርዓት የፊታችን ቅዳሜ ኦክቶበር 3 (Oct 3, 2015) በሚኖሩበት ካሊፎርንያ ግዛት ልጆቻቸውና የቅርብ ጓደኞቻቸው በሚገኙበት ይፈፀማል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ሃይል ማህበር በዋሽንግተን ዲሲ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እየተመኘ በመኮንኑ እረፍት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልፃል።

ኢሳት ዋዛ እና ቁምነገር አዘጋጅ እና አቅራቢ – አቤ ቶኪቻው

$
0
0

September 26, 2015

ኢሳት ዋዛ እና ቁምነገር አዘጋጅ እና አቅራቢ – አቤ ቶኪቻው
Yeawaza - satenaw

ነገ ሽሮሜዳን ያድርገኝ…አለች ቦሌ –አቤ ተኮቻው

$
0
0

Demera - satenawእንግዲህ ዛሬ ደመራው በድምቀት ተለኮሰ አይደለ… (ለመሆኑ ወዴት ወደቀ… አወዳደቁስ ምን ተናገረ…. እስቲ ቅርብ የነበራችሁ አጣሩና ንገሩን….) ታድያ ደመራው በተለኮሰ በነጋታው አዲሳባ ላይ ከሆኑ፤ ማይትስ ሽሮሜዳን ነው… መኖርስ ሽሮሜዳ ላይ ነው… የምንል እኛ፤ መስቀል እና ሰኞ ሲገጥሙ ደግሞ በቃ ሽሮሜዳ አለሟ ነው፤ እና እነ ቦሌ ሳይቀሩ ምነው እርሷን ባደረገኝ እያሉ በጉምዥት ነው የሚያዩዋት… ስንል ምስክረነታችንን እንሰጣለን።

ድሮም ሽሮሜዳ ሰኞ ቀን እጣ ፈንታዋ ነው… ፈታ የሚባልበት ላንቺም ጠጪ ለኔም አምጪ ተግባራዊ የሚሆንባት…. ቸበር ቻቻ የሚነግስበት እቁብ የሚጣልበት እቁብ የሚበላበት ጠጅ እንደ ጮማ የሚቆረጥበት…. ዘገየ ዘለግ ባለ ድምጹ ”የዝናዬ…. አንቺ የዝናዬ….የዝናዬ ማሬ ወለላዬ….” ብሎ እየዘፈነ የሰፈሩን ሰው የሚያስደምምበት… እነ አቡሌ በግሩፕ ”ዴንዳ ዴንዲኪ”ን የሚያቀልጡበት… ሰኞ ለሽሮሜዳ በቃ ምን ልበላችሁ ሰኞ ነው!!!

መስቀል እና ሰኞ ሲገጥሙ ደግሞ…. ”ዮ…..ኦ……ካ መስቀሌ… ዮ….ኦ…ኦ…ኦ..ኦ” እየተባባሉ ቤት ያፈራውን ተቃምሰው ጠጅ ቤት ያፈራውንም ድጋሚ ተቃምሰው ፌሽቲያው ይደራል፤ እለቱ መስቀል ነውና… ጠጅ ቤቶቻችን ጠጅ ቤት ብቻ ሳይሆኑ የሰርግ አዳራሽም ይሆናሉ… እግር የጣለው ሁሉ የሰርጉ ታዳሚ ነው… ሞቅ ያለው ሁሉ ሙዚቃ አውጪ ነው… ጉራግኛ ዶርዝኛ ኦሮምኛ እና ሽሮሜድኛ ይዘፈናል…

ይሄኔ እነ ሰንጋ ተራ አይቀሩ እነ ስጋ ሜዳ አይቀሩ ምነው ሸሮሜዳን በሆንኩ ባይሉ ታዘቡኝ….

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!

ምችት ይበላችሁ!

በዱባይ አውቶቡስ ውስጥ ስለታረደችው ኢትዮጵያዊት አዳዲስ መረጃዎች ከአለምነህ ዋሴ (ያድምጡ)

$
0
0

በዱባይ አውቶቡስ ውስጥ ስለታረደችው ኢትዮጵያዊት አዳዲስ መረጃዎች ከአለምነህ ዋሴ (ያድምጡ)

በዱባይ አውቶቡስ ውስጥ ስለታረደችው ኢትዮጵያዊት አዳዲስ መረጃዎች ከአለምነህ ዋሴ (ያድምጡ)


Hiber Radio: ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ ፈጥኖ ደራሽ ጦር እንዳይቋቋም እንቅፋት ሆነዋል ተባሉ * ኢትዮጵያ የሶማሊያ ወጣቶችን ለጦርነት እያሰለጠነች መሆኑ ታወቀ * በሳውዲ ለሐጂ ሀይማኖታዊ ስርዓት ሔደው በአደጋ የሞቱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር ዛሬም ተለይቶ አልታወቀም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ መስከረም 16 ቀን 2008 ፕሮግራም

<... ...> ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ አረቢያ በሐሙሱ አደጋ ሳቢያ የሞቱና የቆሰሉ ኢትዮጵያውያን አለመታወቁን በተመለከተ ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ

በቬጋስ የመስቀል በዓል አከባበር (ልዩ ቃለ መጠይቅ)

<...> አቶ ተመስገን ዘውዴ ቀድሞው የፓርላማ አባልና በጉልበት የፈረሰው አንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ም/ቤት ሰብሳቢ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለህብር ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ ክፍል አንድና ሁለት (ሙሉውን ያዳምጡ)

በአገር ቤት ባለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ሳቢያ ዓለማቀፋዊ እውቅና ያላቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሜሪካ ውስጥ ለጉሰቁለና ኑሮ መዳረጋቸው ተገለጸ(ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ ፈጥኖ ደራሽ ጦር እንዳይቋቋም እንቅፋት ሆነዋል ተባሉ

ኢትዮጵያ የሶማሊያ ወጣቶችን ለጦርነት እያሰለጠነች መሆኑ ታወቀ

በሳውዲ ለሐጂ ሀይማኖታዊ ስርዓት ሔደው በአደጋ የሞቱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር ዛሬም ተለይቶ አልታወቀም

የሟቾች ቁጥር መጨመሩን የአገሪቱ ባለስልጣናት ገለጹ

በዲሲ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በፖለቲካ ሳቢያ ተሰደው ብርቱ ፈተና ገጥሟቸዋል ተባለ

ከኢትዮጵያ በሕገወጥ መንገድ ወደ አየርላንድ እና ወደ ስሎቫኪያ የገባ በርካታ ደረቅ ጫት በቁጥጥር ሰር ዋለ

አንድ ኢትዮጵያዊ ተጠረጣሪም ከፖሊስ እጅ ወደቋል ተባለ

አገዛዙ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር የአገሪቱ ችግሮች እየተባባሱ ስለሚሄዱ ለውጥ በአገሪቱ መምጣት አለበት ሲሉ የቀድሞ የፓርላማ አባልና የተቃዋሚ መሪ ገለጹ

የሙዚቃው ንጉስ ጥላሁን ገሰሰ በማህበራዊ ሚዲያው ልደቱ እንዲዘከር ጥሪ ቀረበ

ኦብነግ በአልሸባብ ለተቀሉ ሁለት አመራሮቹ ሞት የኢህአዴግ ደህነቶች እጅ ከጀርባ ሊኖርበት እንደሚችል ገለጸ

ኢትዮጵያ ለከፋ የረሀብ አደጋ መጋለጧን የኢሕአዲግ ባለሰለጣናት አመኑ

ዓለማቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች ፊታቸውን ወደ ጎረቤት ኬኒያ አዙረዋል

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ሑመራ የገበያ ማእከሏ በእሳት ጋየ

$
0
0

humera
አምዶም ገብረሥላሴ እንደዘገበው

ሑመራ ከተማ የ150 ነጋዴዎች ንብረት የሆነው የገበያ ማእከል በእሳት ቃጠሎ ሙሉ ወድሟል።

ቃጠለው ሓሙስ 13/ 01 / 2008 ዓ/ም ሌሊት ያጋጠመ ሲሆን የ150 ነጋዴዎች ንብረት የሆነ ከ50 ሚልዮን ብር በላይ ንብረት በቃጠለው መውደሙ ታውቋል።
ህብረተሰቡ ቃጠለው ለማጥፋት የተቻለው ቢጥርም ሊሳካ እንዳልቻለ ኑዋሪዋሪዎች ገልፀዋል።

ከሁሉም በላይ ሒመራን የምታክል ትልቅ ከተማ የእሳት ማጥፍያ መኪና መንግስት ባለማዘጋጀቱ ቅሬታቸው ኣሰምተዋል።
የቃጠለው መነሻ እስካሁን ከመንግስት የተሰጠ መግለጫ የለም።

መንግስት ለተለያዩ ምክንያት መሬቱ ሲፈልገው እሳት የማስገባት ልምድ እንዳለው ይታወቃል። ለምሳሌ በመቐለ ኢንዳስትሪ ቀበሌ በተነሳው ቃጠሎ ሱቃቸው የወደመባቸው ሰዎች መልሰው ለመገንባት ሲሞክሩ መንግስት ቦታው ለሌላ ስራ ስለፈለገው መስራት ኣትችሉም ተብለው ተከልክለዋል።

ሑመራ እነሞላ ኣስገዶም የገቡበት መንገድ ስለሆነ የጣሉት ወይም የተንጠባጠበ ቢሆንስ ማን ያውቃል።

ንብረታቸው ቃጠሎ ያወደመባቸው ዜጎቻችን ፅናት እንመኝላቸዋለን።
ህዝባችን በስንት ይቃጠል ባካቹ…?
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

Sport: ጁቬንቱስ ዘንድሮ ለ5ተኛ ጊዜ ሻምፒዮን ይሆናል? ‹‹አዎ ይሆናል!!›› የስፖርት ተንታኞች

$
0
0

Foto LaPresse - Daniele Badolato25/07/2015 San Gallo ( SWZ )Sport CalcioPartita amichevole Juventus - Borussia DortmundNella foto: formazionePhoto LaPresse - Daniele Badolato25 July 2015 Sankt Gallen ( SWZ )Sport SoccerFriendly match between Juventus and Borussia DortmundIn the pic: team photo

Foto LaPresse – Daniele Badolato25/07/2015 San Gallo ( SWZ )Sport CalcioPartita amichevole Juventus – Borussia DortmundNella foto: formazionePhoto LaPresse – Daniele Badolato25 July 2015 Sankt Gallen ( SWZ )Sport SoccerFriendly match between Juventus and Borussia DortmundIn the pic: team photo


የትልልቅ ተጨዋቾች ስም ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጋር ተያይዞ ሊነሳ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከጣሊያን ‹‹ሴሪ አ›› ጋር ማነፃፀር ያስቸግራል፡፡ ዘንድሮም በሴሪ አ ማራኪ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ይጠበቃሉ፤

ሴሪ አው እንደተፈራው ወርዷል?
የጣልያን ሴሪ አ የዓለምን እግር ኳስ የተቆጣጠረበት ጊዜ ታሪክ ሆኖ ከቀረ ከ10 ዓመት በላይ ተቆጥሯል፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በሴሪአው የነበሩ ተጨዋቾች በሙሉ ዕድሜያቸው የገፋ ነበር፡፡ አንድሪያ ፒርሎ(36)፣ ጂጂ ቡፎን(37)፣ ፍራንቼስኮ ቶቲ(38) እንዲሁም ከ2005/06-2012/13 የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ ተጫውቶ ያሳለፈው ካርሎስ ቴቬዝ የስኩዴቶው ኮከብ ነበሩ፡፡
አሁን ደግሞ ፒርሎ እና ቴቬዝ ሴሪአውን ለቅቀዋል፤ ካለው እና ከሚታየው አንፃር ሴሪአው ከላ ሊጋ ወይም ፕሪሚየር ሊጉ ጋር ይፎካከራል ማለት ያስቸግራል፡፡ ያም ቢሆን ግን ጁቬንቱስ ባለፈው ዓመት የቻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ተፋላሚ ነበር፤ ፊዮረንቲና እና ናፓሊ በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ደርሰዋል፡፡ ይሄ ደግሞ ሴሪአውን እንዳንንቅ የሚያደርገን እውነታ ነው፡፡ ነገር ግን ዓለም ላይ አሉ የሚባሉ ከዋክብት የሚገኙት በሴሪአው አይደለም፤ ሁሉም ክለቦች ያላቸው የታክቲክ አቀራረብ እና ቴክኒክ ደረጃ የሚናቅ አይደለም፡፡

ለሻምፒዮንነት የሚፎካከረው ማነው?
ለጊዜው ጁቬንቱስ ቀዳሚውን ቦታ ይወስዳል፡፡ የቢያንኮኔሪው ክለብ ቴቬዝ፣ ፒርሎ እና ቺሊያዊው አርቁሮ ቪዳልን ቢለቅቅም አሁንም ቡድኑ ለሻምፒዮንነት እንደሚፎካከር በመጀመሪያ ጨዋታቸው ጎል አስቆጥረዋል፡፡ ‹‹አሮጊቷ›› ለአምስተኛ ተከታታይ ዓመት የሴሪአው ሻምፒዮን መሆን አስገራሚ ሊሆን አይገባም፡፡

ሌሎች ተፎካካሪዎችስ?
ከጁቬንቱስ በስተቀር ሌሎች ክለቦች በአውሮፓ መድረክ የሚያሳትፋቸውን ውጤት ለማግኘት የሚያደርጉት ጥረት አዝናኝ ነው፡፡ የሮም ከተማ ክለቦች ሮማ እና ላሲዮ ባለፈው ዓመት በሴሪአው 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው ፈፅመዋል፡፡ ሁለቱ የሚላን ክለቦች ግን በአውሮፓ መድረክ የሚያሳትፋቸውን ውጤት ማግኘት አልቻሉም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በቡድን ግንባታ ሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኤሲሚላን በ63 ሚሊዮን ፓውንድ አዳዲስ ተጨዋቾች አስፈርሞ ሲነሳ ሚሃይሎቪዕን በአሰልጣንነት ሾሟል፣ ኢንተር ሚላንም ቢሀን ተጨዋቾችን አሰናብቶ አዳዲስ ተጨዋቾችን አስፈርሟል፡፡
ፊዮረንቲና እና ናፖሊ አዳዲስ ተጨዋቾችን አስፈርመዋል፤ የ44 ዓመቱ የቀድሞው የፖርቹጋል ኮከብ ፓውሎ ሶሳ ከቪዮላዎቹ ጋር ስኬታማ ጊዜያትን እንደሚያሳልፍ እምነት ተጥሎበታል፡፡ ናፖሊም ቢሆን ካረፉ ቤኒቴዝ መልቀቅ በኋላ ማውሪዚዮ ሳሪን ሾሟል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ ከዋክብት ጥምረት?
ናይጅል ዴ ዮንግ በኤሲ ሚላን፣ ፓትሪስ ኤቭራ በጁቬንቱስ እንዲሁም ኔማንያ ቪዲች በኢንተር ሚላን ቁልፍ ተጨዋቾች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ቪዲች እስከ 2016 ድረስ በጉዳት ምክንያት ከሜዳ ርቋል፣ በአርሰናል እና ቼልሲ ቆይታው የፕሪሚየር ሊግ፣ ቻምፒዮንስ ሊግ እና ዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ያነሳው አሽሊኮል ከሮማ ጋር ተለያይቷል፡፡
ስቴቫን ዩቬቲች በእንግሊዝ በነበረው ቆይታ ስኬታማ ባይሆንም በፊዮረንቲና የምናውቀውን ምርጥ ብቃት መልሶ ለማግኘት ወደ ኢንተር ሚላን አምርቷል፤ ኤዲን ዤኮ እና መሐመድ ሳላህ የሮማን የአጥቂ መስመር ያመራል፤ በማንቸስተር ዩናይትድ ተጫውተው ያሳለፉት ፖል ፓግባ እና ራቬል ሞሪሰን በአሁኑ ሰዓት በቅደም ተከተል የጁቬንቱስ እና ላሲዮ አድማቂ ይሆናሉ ተብለው ይጠበቃል፡፡

ትኩረት የሚደረግባቸው ተጨዋቾች
የጁቬንቱሱ አጥቂ ፓውሎ ዲባላ እንደ ዚነዳን ዚዳን እና አንድሪያ ፔርሎ 21 ቁጥር ማልያ ይለብሳል፤ 23 ሚሊዮን ፓውንድ ወጥቶበት ከፓሌርሞ ‹‹አሮጊቷን›› የተቀላቀለው ኮከብ በአጥቂ አልያም ተደራቢ አጥቂነት መጫወት ይችላል፡፡ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና የማይበት ተጨዋች ነው፡፡

መሳጭ እውነታዎች
ጁቬንቱስ ለአምስተኛ ጊዜ የሴሪአው ሻምፒዮን ለመሆን የተዘጋጀ ይመስላል፡፡ የቢያንኮኔሪው ክለብ ለመጨረሻ ጊዜ በተከታታይ የሴሪ አ ሻምፒዮን የሆነው ከ1930-1935 ድረስ ያሳካው ድል ነው፡፡
በሴሪአው አዲስ ሕግ ወጥቷል፤ ቡድኖች 25 ተጨዋቾችን ይይዛሉ፤ ከእነኚህ ተጨዋቾች መሀከል አራት ያህሉ ከአካዳሚው የተገኙ መሆን አለባቸው፤ እንዲሁም አራት የሚደርሱ ተጨዋቾች በጣልያን ያደጉ መሆናቸው ግድ ይላቸዋል፡፡
ፖል ኢንስ ኢንተር ሚላንን ከ20 ዓመት በፊት ሲቀላቀል ትኩረትን ስቦ ነበር፤ እንደ ፖል ጋስኮኝ ሁሉ ከእንግሊዝ መጥተው በሴሪአው ከተሳካላቸው ተጨዋቾች መሀከል አንዱ ነው፡፡ ቶሪኖ ከ40 ዓመት በፊት የሴሪአው ሻምፒዮን ከሆነ በኋላ የጁቬንቱስ አጃቢ ከመሆን ያለፈ ስኬት ማስመዝገብ አልቻለም፤ ዘንድሮም የጁቬንቱስ ሻምፒዮንነት የሚጠበቅ ነው፡፡

Health: ወንዶች በፍፁም ችላ ሊሏቸው የማይገቡ 4 አደገኛ የጤና ችግር ምልክቶች

$
0
0

Health ethiopia
ጤናና ገንዘብ አያያዝን ጨምሮ በብዙ ነገሮች ጥንቃቄ በማድረግ ከወንዶች በተሻለ ሴቶች ፈጣን ናቸው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሚበዙት ወንዶች ግን በተለይ የጤና ችግሩ የሆስፒታል አልጋ ላይ የሚጥል ካልሆነ በቀር በምልክቶች መነሻነት ወደ ሆስፒታል መሄድን ልምድ አላደረጉም፡፡ ነገር ግን ይህ የቸልተኝነት ልምድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወንዶችን ከክፉ የጤና ችግር እስከሞት በሚያደርስ አደጋ ላይ እየዋለ መሆኑን ጥናቶች እያመለከቱ ነው፡፡

ችላ የማይገባቸው የጤና ችግሮች
የ52 ዓመቱ ሰው አቶ ግርማ ደጋግሞ ያስቸግራቸው የነበረውን ተደጋጋሚ የትንፋሽ ማጠር በምንም ምክንያት ከክፉ የጤና ችግር ጋር የተያያዘ ነው ብለው አስበው አያውቁም፡፡ አንድ ቀን ግን ነገሮች ተጣደፉና ሐኪም ቤትን በድንገተኛ ታካሚነት መጎብኘት ግዴታቸው ሆነ፡፡ ምርመራ ያደረገላቸው ሐኪም ችግሩ ከልባቸው ጋር የተያያዘ መሆኑንና ሳምባቸውም ውሃ ሳይቋጥር እንዳልቀረ ሲነግራቸው ከፍተኛ ድንጋጤም ውስጥ ገቡ፡፡ የልብ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከፍተኛ ኦፕሬሽን ማድረግ ግዴታ ሆኖባቸው ነበር፡፡ በተደጋጋሚ ችላ ይሉት የነበረውን የትንፋሽ ማጠር ተጠራጥረው ቀድመው ወደ ሐኪም ቢሄዱ ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ህክምና ውስጥ ከመግባት ይድኑ እንደነበርም አቶ ግርማ ይገልጣሉ፡፡ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖ የቅርብ ሰዎችና ባለቤታቸው እቤት ባሉበት ወቅት ችግሩ መከሰቱ ፈጣን ህክምና ለማግኘት አስቻላቸው እንጂ የትንፋሽ ማጠሩ የትም ሊከሰት እና ህይወታቸውንም ሊያሳጣቸው ይችል እንደነበር ሐኪሙ እንደገለጠላቸው እና እድለኛ እንደነበሩም ያስታውሳሉ፡፡

ሁሉም ሰው ግን እን አቶ ግርማ ዕድለኛ ሊሆን አይችልም፡፡ የህመም ምልክቶችን ችላ በማለት ቆይተው በቂ ህክምናን አግኝተው ከከባድ በሽታዎች የሚያገግሙ ሰዎችም ብዙ አይደሉም፡፡ አንዳንዴ እጅግ ከዘገዩ የሚታወቁ ምልክቶችም በቀጥታ ለዘላቂ የአካል ጉዳት አለዚያም ሞት የሚያደርሱበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡ ከሴቶች በበለጠ ወንዶች የበሽታ ምልክቶችን ችላ የማለት እና የህክምናን እርዳታ ለመጠየቅም እጅግ እንደሚዘገዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ እንዲያውም በቅርቡ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው በብዙ አገራት ከ38 በመቶ በላይ ወንዶች ሆስፒታሎችን የሚጎበኙት ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥል ችግር ሲገጥማቸው ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ተደጋጋሚ ጥናትን ያካሄዱ ባለሙያዎች እባካችሁ ወንዶች የከፋ የጤና ችግርን ጠቋሚ ለሚሆኑት ምልክቶች ትኩረት አድርጉ ሲሉ የሚያሳስቡት፡፡

4. ሽንት መሽናት መቸገር፣ ደም የቀለመ ሽንት
ሽንት ሰውነት ቆሻሻን አጣርቶ የሚያስወጣበት ፈሳሽ እንደመሆኑ ጤነኛ መጠን፣ ቀለም እና ድግግሞሽ የሰውነትን የማጣራት አቅም እንዲሁም ኩላሊትና መላውን የማጣሪያ ስርዓት ጤንነት ደረጃ ይገልጣል፡፡ በወንዶች ዘንድ ከሚታዩ የችግር ምልክቶች አንዱ ሽንት ለመሽናት መቸገር ነው፡፡ በተለይ ሲሸኑ ህመም የሚሰማዎት ከሆነ እና መሽናት እየፈለጉ ከመፀዳጃ ቤት ሲደርሱ ግን የሚታገሉ ከሆነ ጉዳዩ የፕሮስቴት እጢ ችግርን ይጠቁማልና ቶሎ የሐኪም እርዳታን ይጠይቁ ሲሉ ይመክራሉ፡፡ የፕሮስቴት እጢ የወንድ ዘርን እንደልብ ለመቀስቀስ የሚያስችለውን ፈሳሽ የሚያመርት ከሽንት ከረጢት በታች የሚገኝ በጣም አነስተኛ ዕጢ ነው፡፡ የዚህ እጢ ችግር በጊዜ ካልተቀረፈ ከፕሮስቴት ካንሰር እስከ ልጅ የመውለድ ብቃትን ማሳጣት የሚያደርስ ጥፋት ሊያደርስ ይችላል፡፡
ሽንት በተፈጥሮ ጤናማ ቀለሙ ቢጫ ነው፡፡ ከዚህ በመጠኑ የተለየ ሽንት ማየት ከተመገቡት ምግብ ጋር የሚያያዝ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ ባለፈ ሁኔታ ግን በተደጋጋሚ ደም ማየት ከበድ ያለ ችግርን ጠቋሚ ምልክት ነው፡፡ ይህ መሰሉ ችግር የፕሮስቴት እጢ ካንሰርን ከመጠቆም ባለፈ የሽንት ቧንቧ መስመር መቆጣት፣ ኢንፌክሽን፣ የኩላሊት ጠተር እንዲሁም ሌሎች የኩላሊት በሽታ አይነቶች እየተከሰቱ መሆናቸውን አመላካች በመሆኑ በፍፁም ችላ ሊሉት አይገባም ሲሉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

4. የደረት ላይ ህመም
ድንገትደረትን ስቅዝ አድርጎ የሚይዝ ህመም በአንድ ወይም በሌላ ጊዜ ገጥምዎት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ መሰሉ ምልክት ደገምገም የሚያደርግ ከሆነ ግን ብዙ የሚናገረው የጤና ችግር ስላለ ፈጣን እርምጃ ሊወስዱና ሐኪም ጋር ሊቀርቡም ይገባል ባይ ናቸው ባለሙያዎቹ፡፡ የደረት ላይ ህመም የልብ ድካምን ጠቋሚ ከመሆኑ በተጨማሪ እንደ ኒሞኒያ፣ አስም እንዲሁም ሌሎች ከምግብ መፍጫ ስርዓት ችግሮች ጋር የተያያዘ እክል እየተፈጠረ መሆኑን አመላካች ነው እና ችግሩ ገፍቶ እስኪመጣ መጠበቅና እራሱ በራሱ እንደሚሄድ መገመት ችግርን መጥራት ነው፡፡

3. ተደጋጋሚ ድብርት
ሁላችንም የየራሳችን መጥፎ ቀናት አሉን፡፡ ሰው ማናገር የምንጠላበት፣ የምንወደው ነገር ሁሉ ትርጉም የሚያጣበት እና በአጠቃላይ ሁሉ ነገር የሚያስጠላን ጊዜ አለ፡፡ ነገር ግን ይህ አልፎ አልፎ የሚከሰት እና በዕለት ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴያችን ከሚከሰቱ ደስታችንን ከሚያደምኑ ጉዳዮች ጋር የሚያያዝ እና ችግሮቹ መፍትሄ ሲያገኙ አብሮ የሚፈታ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ አልፎ መደበኛ የህይወት አካል መሆን ሲጀምር ግን ከጀርባው ሌላ ያልተፈታ ስነ ልቦናዊ ወይም ማህበራዊ ችግርን ጠቋሚ ሊሆን ይችላል፡፡
ሴቶች ከወንዶች በተሻለ ድብርትን ለይቶ የማወቅና ምክንያቱን የመፈለግ እንዲሁም ከጓደኛና ቤተሰብ ጋር በመወያየት የመፍታት ተፈጥሯዊ ልምዶች አሏቸው፡፡ ወንዶች በተቃራኒው መጠጥን ትርጉም የሌለው ወሲብን እና እንደ ጫት መቃም የመሰሉ አጉል ልምዶችን በመተግበር ወይም መጠልን በመምረጥ ድብርታቸውን ለማስታገስ ቀዳሚው የባለሙያዎች ምክር ሲሆን ተደጋጋሚ ድብርት ደግሞ ህይወትን እስከማጣት የሚያደርስ ጥፋት ውስጥ ሊከት ስለሚችል በቅድሚያ በቅርብ ላለ የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ ችግሩን ማዋራት፣ በዚያ የሚቀል ካልሆነ በአፋጣኝ ወደ ባለሞያ መቅረብና ዘላቂ መፍትሄ ማበጀት ይገባል፡፡ ድብርት ችላ አይበሉ!

ካንሰር በሁለቱም ጾታዎች ተደጋግሞ የሚታይ ችግር ቢሆንም በወንዶች ዘንድ ካንሰር በምርመራ ሲታወቅ ብዙ ጊዜ ዘግይቶ እና ለህክምናም አስቸጋሪ በሚሆንበት ደረጃ ላይ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በምክንያትነት ከሚነሱ ጉዳዮች ቀዳሚው ወንዶች ዘንድ የአካላቶቻቸውን የተለያዩ ለውጦች አለመከታተላቸውና ችግር ሲኖርም የህክምና እርዳታን አለመሻታቸው ነው ሲሉ ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ፡፡

ሴቶች የጡት ካንሰርን ቀድመው እንዲያውቁ ጡቶቻቸውን በየጊዜው እራሳቸው በእጃቸው እንዲፈትሹ እና የተለየ እብጠት ከተሰማቸው ለባለሞያ እንዲያሳዩ ይመከራል፡፡ በዚህም ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሴቶች ካንሰርን በጊዜ መፍትሄ አብጅተውለታል፡፡ በወንዶች ዘንድ ከሚታዩ የካንሰር አይነቶች አንዱ የወንድ ዘር ፍሬ ማምረቻ (ቆለጥ) ውስጥ የሚከሰት ካንሰር ነው፡፡ ይህን የካንሰር አይነት እንደ ሴቶች ጡት ሁሉ ቀላል ፍተሻን ራሳቸው ወንዶች በቆለጦቻቸው ላይ በማድረግ ቀድመው ሊደርሱበትና በባለሞያም እርዳታ ሊያገኙበት ይችላሉ፡፡ ወንዶች ሰውነታቸውን በሚታጠቡበት ወቅት አጠቃላይ ሰውነታቸውን ማስተዋል፣ አልፎ አልፎም በቆለጥ አካባቢ የተፈጠሩ በደንብ የማያስታውቁ አነስተኛ እብጠት መሰል ነገሮች ካሉምመፈተሽ፣ ካንሰሩን ቀድሞ ለመለየት ይጠቅማልና ይህንን ችላ አይበሉ ሲሉ ባለሞያዎቹ ያስረዳሉ፡፡

2.የሆድ ድርቀት
ከምንመገባቸው ጋር በተያያዘ የሚፈጠር የሆድ ድርቀት ጊዜያዊ ችግር በመሆኑ ለወንዶች ብቻ ሳይሆን ሴቶችንም ይህን ያህል ስጋት ላይ የሚጥል ችግር አይደለም፡፡ ነገር ግን በተደጋጋሚ የሆድ ድርቀት ሲከሰት በተለይ ወንዶች ትኩረት መስጠት እና ዋናውን ምክንያት ለይቶ መፍትሄ ማበጀት የግድ ይሆንባቸዋል፡፡ የሆድ ድርቀት መሰረታዊ ምክንያቶች በርካታ ሊሆኑ ቢችሉም የአንጀት ካንሰርን መጠርጠር የብዙ ባለሞያዎች ቀዳሚ ግምት ነው፡፡ የሆድ ድርቀት ከጀርባው ካለው ምክንያት በተጨማሪም በራሱ ሌላ ጣጣንም ይዞ ይመጣል፡፡

የሆ ድርቀት በቀላል መወሰድ የሌለበት ዋና ምክንያት ሄሞሮይድ የተሰኘውና በተለምዶ የፊንጢጣ ኪንታሮት ብለን የምንጠራው በአብዛኛው ወንዶችን የሚያሰቃየውን ህመም ለመከላከል ነው፡፡ ሄሞሮይድ ይህ ነው የተባለ መነሻ ምክንያት ባይቀመጥለትም በሆድ ድርቀት ወቅት አይነምድርን ለማስወጣት በከባድ ማማጥ የግድ ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜም የፊንጢጣ አካባቢ ስለ ህዋሳት የመጎዳትና የመድማት አደጋ ይገጥማቸዋል፡፡ ይህ የህዋሳቱ ነርቮቹ መቆጣተ የፊንጢጣ ጫፍ እንዲገለበጥና መቀመጥና መቆም እንዲሁም አይነምድር መውጣት ትልቅ ፈተና እንዲሆን ያስገድዳል፡፡ ለህክምና አስቸጋሪ ከመሆኑ አንፃር አንዳንድ ሰዎች እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ በባህል ህክምና ችግሩን ሳያዳግሙ ለመንቀል ሲጥሩ ለተወሳሰበ ቀውስ የተዳረጉበትን ጊዜ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ በቅርብ ያውቃል፡፡ የሄሞሮይድ ህመም እጅግ ከባድና ለማንም አይስጥ የሚባል አይነት ነው፡፡ ለዚህ ነው ረጅም ጊዜ የሚቆይ የሆድ ድርቀትን በባለሞያ እርዳታ በፍጥነት ማስወገድ የሚመከረው፡፡

1. የወሲብ ችግር
ሁሉም በሚቻል ደረጃ ወንዶች በአንድ ወይም በሌላ ጊዜ ብልታቸውን ለወሲብ ማቆም እና ከዚያም እስከወሲቡ ፍፃሜ የመዝለቅ ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ 70 በመቶው የሚደርስ ለወሲብ ዝግጁ አለመሆን ችግር ከስነ ልቦናዊ ጉዳዮች ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ጠለቅ ያለ ዳሰሳን ይጠይቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ግን የወሲብ ብልት አለመቆም ከበድ ካሉት የልብ ህመም፣ የስኳር ህመም እንዲሁም የደም ቧንቧ ችግሮች ጋር የሚያያዝ በመሆኑ በቀላል መውሰድ እንደማይገባ ባለሞያዎች ያሳስባሉ፡፡
በተፈጥሮ የወንድ ብልት ለወሲብ የሚቆመው ከአዕምሮ በሚሰጥ ትዕዛዝ ይሁን እንጂ ከልብ ተነስተው ወደ ብልት የሚነሳ የደም ቧንቧዎች ከልብ በሚወስዱት ደም ሲሞላ ነው ብልት የሚቆመው፡፡ በመሆኑም ማናቸውም በልብ እና ደም ቧንቧ ህመሞች ላይ የሚከሰት እክል በወሲብ ላይ እክል ያመጣል፡፡ የወሲብ ችግር ከአንድ ሰሞን አልፎ ተደጋጋሚ የሚሆንባቸው እና ብልታቸውን ማስነሳት የሚቸገሩ ሰዎች ችግራቸው ወሲብ ላይ ብቻ ሳይሆን ሰፋ ካሉት ሌሎች አካላትም ጋር ስለሆነ ይህንን ማስጠንቀቂያ የምር ወስደው አስቸኳይ የባለሙያ እርዳታ ማግኘት አለባቸው፡፡

በመነሻችን ታሪካቸውን ያካፈልናችሁ አቶ ግርማ ህይወታቸውን አደጋ ላይ የጣለውን ምልክት ሰዎች ችላ እንዳይሉ ደጋግመው ለወዳጆቻቸው ይነግራሉ፡፡ የትንፋሽ ማጠር ብቻ ሳይሆን ቀደም ብለን ያነሳሳናቸውም ምልክቶች ከበስተጀርባቸው ብዙ የጤና ችግሮቹን ይዘዋልና ትኩረትን ይሻሉ፡፡

ድምፃዊ ሃቻሉ ሁንዴሳ፤ ስለ ሙዚቃ ህይወቱ ይናገራል (Audio)

$
0
0

ድምፃዊ ሃቻሉ ሁንዴሳ፤ ስለ ሙዚቃ ህይወቱ ይናገራል (Audio)

ድምፃዊ  ሃቻሉ ሁንዴሳ፤ ስለ ሙዚቃ ህይወቱ ይናገራል (Audio)

የዘመናችን አጥማቂ ነን ባዮች፡- የሐሳዊው መሲሕ መንገድ ጠራጊዎች

$
0
0

ከዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ክፍል አንድ

በዚህ ዘመን በተደጋጋሚ ከሚነሡ መንፈሳውያን ጥቄዎች መካከል አንዱ የጥምቀትና አጥማቂዎች ጉዳይ ነው፡፡ ጥምቀት(የክርስትና ጥምቀትን አይመለከትም) በብሉይና በሐዲስ ኪዳን ምእመናን ፈውሰ ሥጋ ፈውሰ ነፍስ እንዲያገኙባቸው ከእግዚአብሔር ከተሰጡ ጸጋዎች አንዱ ነው፡፡(2ኛ ነገሥት 5፤ ዮሐ. 5፣ዮሐ. 9)፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክም ውስጥ በልዩ ልዩ ገድላተ ቅዱሳን ላይ እንደምናነበው በጠበል ሕዝቡን ሲፈውስ ኖሯል፡፡ ሕዝብ ፈውስ የሚያገኝባቸው እንደ ሰሊሆምና እንደ ቤተ ሳይዳ የታወቁ የቃል ኪዳን ቦታዎችም ነበሩ፡፡
daniel
አሁን በያዝነው ዘመን አያሌ ‹አጥማቂ> የሚባሉ ሰዎች ተነሥተዋል፡፡ ክብራቸውን የሚገልጥ ማስታወቂያ ያስነግራሉ፣ መቁጠሪያ ይሸጣሉ፣ ቅባት ይቀባሉ፣ አዳራሽ ከፍተው ወይም ሕዝብ በሜዳ ሰብስበው እንፈውሳለን ይላሉ፤ ሰይጣን ተናገረ የሚባለውን በካሴት ቀድተው ይሸጣሉ፡፡ ከዚህ ቀጥዬ በማቀርባቸው አሥር ምክንያቶች እነዚህን ሐሳውያን መቀበል የለብንም ብዬ አምናለሁ፡፡

1. በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ገዳማዊ ሕይወት፣ ክህነታዊ ሕይወት፣ የጸሎት ሕይወት ወይም ሌላ አንዳች ተጋድሎ ሳይኖረው ማጥመቅ ብቻ ሥራው የነበረ ክርስቲያን የለም፡፡ ሀብተ ፈውስ የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች የሌላው መንፈሳዊ ሕይወታቸው ውጤት ወይም ነጸብራቅ ነበር እንጂ ሥራቸው እየዞሩ ማጥመቅ አልነበረም፡፡ የሐዋርያት ሥራን ብናነብ ሐዋርያት ለወንጌል አገልግሎት ሲሠማሩ በአንድ በኩል አሕዛብን ወደ ክርስቶስ ለመጥራት በሌላ በኩል የአንደበት ትምህርታቸውን በእጃቸው ተአምር ለማጽናት ተአምራትን ያደርጉ ነበር እንጂ በአንድ ከተማ ውስጥ ሲያጠመቁ ውለው ያደሩበት፣ ወይም ከወንጌል አገልግሎት ተለይተው አጥማቂ ብቻ የሆኑበት፣ ወይም ደግሞ በዚህ ቦታ ፈውስ እንሰጣለንና ተሰብሰቡ ብለው ያስነገሩበት አንድም ማስረጃ የለም፡፡ በገድለ ቅዱሳንም ቅዱሳን ጸጋ እግዚአብሔር ሲያድርባቸው፣ ሥጋቸውንና ሰይጣንን ድል ሲነሡ፣ በክርስትናቸው ሲበስሉ ተአምራት ይከተሏቸዋል እንጂ እንዲሁ ማጥመቅና መፈወስ ብቻ ሕይወቱ የነበረ ቅዱስ የለም፡፡ ሰው ያለ ተጋድሎ እንዴት ጸጋ ያገኛል፡፡ በአሁኑ ዘመን ግን ከተራ ሰዎች የተለየ መንፈሳዊ ሕይወት የሌላቸው ሁሉ እየተነሡ አጥማቂ ሊሆኑ የቻሉበት አሳማኝ ምክንያት የለም፡፡

2. በገድለ ቅዱሳን ውስጥ ቅዱሳን በገዳማዊ ሕይወት፣ በሰማዕትነት፣ በክህነታዊ አገልግሎት ሲሠማሩ እግዚአብሔር ምእመናንን ለመጥቀም ወይም ክብረ ቅዱሳንን ለመግለጥ በእነርሱ ላይ ተአምራትን ያደርጋል፡፡ እነርሱ ግን ይህ ክብር እንዳይገለጥባቸው ሲሸሹ፣ እኔ አላደረግኩም ሲሉ ወይም ስለራሳቸው ደካማነት ሲነገሩ እናያለን እንጂ ‹ኑ እንፈውሳችኋላን› ብለው ዐዋጅ ሲናገሩ አይተንም፣ አንብበንም አናውቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ወጥተው ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም የሄዱበት ዋናው ምክንያት በገዳሙ እያሉ በፈወሱት አንድ በሽተኛ ምክንያት ስማቸው ከፍ በማለቱ፣ ብዙ ሰዎችም በመሰብሰባቸው የተነሣ ነው፡፡ ታላቁ አባት መቃርዮስ ገዳሙን ትቶ ወደ አንዲት መንደር መጥቶ የኖረው በገዳሙ ክብሩ በመገለጡና ተአምራቱ በመታየታቸው ከከንቱ ውዳሴ ለማምለጥ ነበር፡፡ ስምዖን ጫማ ሰፊው አካባቢውን ትቶ የጠፋው ተአምር አድራጊነቱ በመታወቁ ምክንያት ነበር፡፡ አሁን ግን ከዚህ በተቃራኒው ሰዎች እናጠምቃለን፣እንፈውሳለን ብለው ማስታወቂያ የሚያስነግሩበት፣ ካሴት የሚሸጡበት፣ ፖስተር የሚሰቅሉበት ዘመን ነው፡፡

3. ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ማን እንደሆነ፣ ድንግል ማርያም ማን እንደሆነች፣ ቅዱሳን መላእክት ማን እንደሆኑ ሌሎቹም ቅዱሳን ማን እንደሆኑ ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ የእግዚአብሔርን ክብር ለሰዎች ሰጥታ አታውቅም፡፡ ቅዱሳንን ከፈጣሪ አስበልጣ አታወቅም፡፡ የቅዱሳን መገኛና መሠረት በባሕርዩ ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር መሆኑን ታምናለች፣ታስተምርማለች፡፡ ለእግዚአብሔር የማይቻል ለቅዱሳን ይቻላል፣ በእግዚአብሔር የማይሠራ በቅዱሳን ይሠራል ብላ አታምንም፣ አታስተምርም፡፡ በዘመኑ አጥማቂዎች ዘንድ የምናየው ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው፡፡ በክርስቶስ ስም የማይወጣው ሰይጣን የቅዱስ ሚካኤልን ስም ሲጠሩበት ይወጣል፡፡ በክርስቶስ ስም የሚያሾፍ ሰይጣን የድንግል ማርያምን ስም ሲጠሩበት ተቃጠልኩ ይላል፡፡ ይኼ ፈጽሞ ክህደት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንም ትምህርት አይደለም፡፡ ‹‹በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ›› ብላ ያስተማረች ቤተ ክርስቲያን ላይ ‹‹በክርስቶስ ስም አንወጣም፣ በማርያም ስም ግን እንወጣለን›› እያለ አጋንንት ወጣ የሚል ትምህርት ማስፋፋት ክህደት ነው፡፡

4. መቁጠሪያ በቤተ ክርስቲያናችን ለጸሎት መቀስቀሻና ማስታኮቻ የሚውል ነው፡፡ ምእመናን እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ፣ በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ፣ ኪርኤ አላይሶን የተባሉትን የምሕላ ጸሎቶች በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተመደበላቸውን ቁጥር ሳይስቱ እንዲጸልዩ የተሠራ ሥርዓት ነው፡፡ በጸሎት ጊዜ ዝንጋኤ እንዳይገጥማቸው ኅሊናቸውን ለመሰብሰብም ይረዳል፡፡ አንድ ቅዱስ ለብዙ ዘመን የጸለየበት መቁጠሪያ፣ የተደገፈበት መቋሚያ፣ የቆመበት ምድር፣ የለበሰው ልብስ፣ የተጠቀመበት መጽሐፍ ተአምራት ቢያደርግ አይገርምም፡፡ ቅዱሳን የነፍሳቸው ቅድስና ለሥጋቸው፣ የሥጋቸውም ለልብሳቸው፣ የልብሳቸው ለጥላቸው ተርፎ አይተን እናውቃለንና(የሐዋ. 5፣12-17፤ 19፣ 11-12)ከዚህ ውጭ ግን የሚሸጥ መቁጠሪያ ሰይጣን የሚያስወጣበት፣ ሰው ራሱን በመቁጠሪያ ስለደበደበ ከዲያብሎስ እሥራት የሚፈታበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ሰይጣን በጾምና በጸሎት እንጂ በመቁጠሪያ ድብደባ አይለቅም(ማቴ.17፣21)፡፡ ያ መቁጠሪያ ተአምር የሚሠራ ቢሆን እንኳን አንድ ቅዱስ የተጋደለበት፣ ከዚያ ቅዱስም በረከት ያተረፈ መሆን አለበት፡፡ ልክ የቅዱስ ጳውሎስ የጨርቁ እራፊ ይፈውስ እንደነበረው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክም የትኛውም አባት መቁጠሪያ ሲያድልና በመቁጠሪያ ሰይጣን ታወጣላችሁ ብሎ ሲያስተምር አልታየም፡፡

5. ጌታችን በሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ አስተምሯል፡፡ በጌንሳሬጥ ምድር አምስት ሺ(ማቴ 1413-21)፣ በገሊላ ባሕር አጠገብ አራት ሺ(ማቴ 15፣32-39)፣ ይህ ሁሉ ሕዝብ የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይቶ ይኼድ ነበር እንጂ ሰይጣን አድሮበት በአንድ ጊዜ የጅምላ ጩኸት ሲጮህ ታይቶ አይታወቅም፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ግን እየቀረቡ ፈውሰ ሥጋ ፈውሰ ነፍስ አግኝተዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ቢሆን መድኃኒት ያደረገብሽ፣ ድግምት ያስደገመብህ፣ መተት ያስመተተብህ እገሌ ነው የሚል ሰይጣን አልተሰማም፡፡ ዛሬ ግን በአንድ ቦታ ለጥምቀት የሚሰበሰቡ ሰዎች አብዛኞቹ ይጮኻሉ፡፡ ሁሉም በሰይጣን ተይዘዋል ይባላሉ፣ ሁሉም ድግምት፣ መተት፣ መድኃኒት፣ ጥንቆላ እንደተደረገባቸው ይነገራቸዋል፡፡ ሰይጣንን አምነው ከባሎቻቸው፣ ከሚስቶቻቸው፣ ከእኅት ወንድሞቻቸው፣ ከጎረቤቶቻች፣ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ይጣላሉ፡፡ ከባቴ አበሳነትን ፈጽሞ የረሳ፣ ከፍቅር ይልቅ ጠላትነትን ለማስፈን የመጣ፣ ሰዎች እግዚአብሔርን አምነው ከመፋቀር ይልቅ ሰይጣንን አምነው እንዲጣሉ የሚያደርግ የሰይጣን አሠራር ነው፡፡ ለመሆኑ ይህንን ሁሉ ሕዝብ ሰይጣን ሲቆጣጠረው ክርስቶስ የለምን? የተጠመቅነው የልጅነት ጥምቀት፣ የቆረብነውስ ቁርባን አይሠራምን? ገና ወደ ክርስትና ያልመጡ የገሊላ ክርስቲያኖች እንኳን በጩኸት አልተደበላለቁም እንኳን እኛ በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉድ የተባልነው፡፡ ይህ አሠራር የክርስቶስን ነገረ ድኅነት የሚፃረርና ከማዳን ሥራውም የወጣ ነው፡፡ ከክርስቶስ ክብርና ኃይል ይልቅ የሰይጣንን ኃይል ለማሳየት የሚሠራም ነው፡፡

6. ለመሆኑ ስመ እግዚአብሔርን የሚጠራ ሁሉ ትክክለኛ ነውን? አንዳንድ ምእመናን እንዲህ ይላሉ ‹እግዚአብሔርን ይጠራሉ፣ እመቤታችንንም ያከብራሉ››፡፡ ልክ ነው ሰይጣን ለአመሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል ይባላል፡፡ ሰይጣን ምንም እንኳ የሐሰት አባቷ ቢሆንም (ዮሐ. 8፣44) ሙሉ ውሸት ግን አይናገርም፡፡ በከፊል እንጂ፡፡ ሔዋንን ‹ንግሥተ ሰማይ ወምድር› ሲላት ከፍሎ ነው የዋሻት፡፡ ንግሥተ ምድር ናት፤ ንግሥተ ሰማይ ግን አልነበረቺም፡፡ በወንጌል ውስጥ አጋንንት ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው ያውቃሉ፡፡ ሰይጣን ጌታን ሲፈትነው ከቅዱሳት መጻሕፍት ጠቅሶ ነው(ማቴ 4)፤ ጌታችን በጌርጌሴኖን ያገኛቸው አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎች ‹የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ› ብለው ነበር የተናገሩት፡፡ ንግግራቸው ልክ ነው፡፡ እነርሱ ግን አጋንንት ናቸው፡፡ ጌታም አስወጣቸው እንጂ ማን ድግምት እንዳደረገባቸው አላናዘዛቸውም፡፡ በሌላ ቦታም በምኩራብ ሲያስተምር አንድ ሰይጣን ያደረበትን ሰው አመጡለት፡፡ ሰይጣኑም ‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ‹ ብሎ ነበር የጠራው፡፡ ጌታ ግን ‹ዝም ብለህ ወጣ› አለው እንጂ መድኃኒት ማን እንዳደረገ ተናገር አላለውም(ማር. 1፣21-28)፡፡ የናዝሬቱ ኢየሱስ ስላለውም ሰይጣንነቱን አልቀየረውም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሲያስተምር ፊልጵስዩስ የተባለ ከተማ ደረሰ፡፡ በዚያም አንዲት በርኩስ መንፈስ የተያዘች ሴት እየተከተለቺው ‹‹የመዳንን መንገድ የሚነግሯችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው›› አለች፡፡ ሴትዮዋ የተናገረቺው ምንም ስሕተት የለውም፡፡ እነ ቅዱስ ጳውሎስ የመዳንን መንገድ ያስተምራሉ፡፡ የልዑል አምላክ ባሪያዎችም ናቸው፡፡ ይህ ትክክል ስለሆነ ግን ቅዱስ ጳውሎስ ዝም አላለም፡፡ መንፈሱን አስወጣው እንጂ(የሐዋ.16፣16-18)፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚነግሩን አንድ ሰው ስመ እግዚአብሔርን ወይም ስመ ቅዱሳንን ስለጠራ ብቻ ትክክል መሆኑን እንደማያሳይ ነው፡፡ እርስ በርሱ የማይጣረስ ርቱዕ የሆነ እምነትም ያስፈልገዋል፡፡ ርቱዕ የሆነ ሕይወትም ያሻዋል፡፡ በክርስትና አንድ ሰው መንገዱ ትክክል ሳይሆን ውጤቱ ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡ ያለ ትክክለኛ እምነት፣ ያለ ትክክለኛም መንፈሳዊ ሕይወት ትክክለኛ ተአምራት ሊኖረው አይችልም፡፡ በሲኦል በኩል ወደ ገነት ሊገባ አይችልምና፡፡

7. ተአምራት ማድረግ ብቻውን የቅድስና ማሳያ አይደለም፡፡ ተአምራት ከመንፈሳዊ ሕይወት ብቃት ሲመነጩ እንጂ፡፡ ተአምር ከመንፈሳዊ ሕይወት ብቃት የመጣ ሲሆን ‹ስም በመንግሥተ ሰማያት በመጻፉ እንጂ በድንቅ ነገር ማንም ደስ አይለውም››(ሉቃ. 10፣ 17-20)፡፡ ተአምራትን ሲከተሉ መኖርም የአሕዛብነት ምልክት እንጂ የክርስትና ምልክት አይደለም(ማቴ. 12፣ 39)፡፡ የክርስትና ዋና መሠረቱ ክርስቲያናዊ ትምህርት፣ ክርስቲያናዊ እምነትና ክርስቲያናዊ ሕይወት ናቸው፡፡ አንዳንዶች በማርቆስ ወንጌል መጨረሻ ላይ(ማር 16) ‹‹ያመኑት እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል›› የሚለውን ይጠቅሳሉ፡፡ እዚህ ላይ ያመኑት የተባሉት ‹የበቁት› ማለት ነው፡፡ ያማ ባይሆን ኖሮ ሁላችንም ተአምር ስናደርግ መኖራችን ነበር፡፡ አምነናልና፡፡ ደግሞም ያመኑት የሚለው ለሁላችንም ይሠራል ካልን እስኪ መርዝ ጠጥተን ምንም ሳንሆን ፣እባብም ጨብጠን ስንተርፍ እንየው፡፡ ይህ ሁሉ ግን በእመነት ለበሰሉ የሚቻል ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራም በሐዋርያት እጅ ያመኑት ሁሉ ተአምር ሲሠሩ አናይም፡፡ በሐዋርያት ሥራ ድንቅ ሲሠሩ የምናያቸው ክርስቲያኖችም በጸሎት የተጉ፣ በሐዋርያነት አገልግሎት ሰማዕትነት የከፈሉ፣ በገድል የተቀጠቀጡ ናቸው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ራሱ ሕይወቱ በተአምራት ከመገለጡ በፊት በሱባኤ የተወሰነ ነበረ(የሐዋ. 13፣ 1-3) የዛሬ አጥማቂዎች ግን ማጥመቅ ፕሮፌሽናቸው እንጂ የመንፈሳዊ ሕይወታቸው መገለጫ አይደለም፡፡ እንዲህ ባለው ገዳም በገድል የኖሩ፣ እንዲህ ያለ መሥዋዕትነት ለክርስትና የከፈሉ ወይም ለምእመናን አርአያ የሚሆን እንዲህ ያለ መንፈሳዊ ሕይወት የነበራቸው ናቸው ተብሎ የማይመሰከርላቸው ራሳቸውን በራሳቸው የሾሙ ናቸው፡፡

8. የሰይጣን ምትሐትም አለ፡፡ የሙሴ ጸጋና ሕይወት ድል እንዲሆኑ ባያደርጋቸው ኖሮ የፈርዖን ጠንቋዮች ብዙ አስደናቂ ነገር ሠርተው ነበር(ዘጸ. 7፣8- 13)፡፡ በዘመነ ሳዖል የነበረቺው ሟርተኛም የሙታንን መንፈሶች ትጠራ ነበር(1ኛ ነገሥት. 28፣ 8-24)፡፡ አይሁድም አጋንንትን ያወጡ ነበር(የሐዋ. 19፣13)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም የሐሳዊ መሲሕን አመጣጥ ሲያስተምረን ‹‹የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች፣ በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመጽም ማታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው›› ይላል (1ኛ ተሰ. 2፣9)፡፡ ይህም ከመንፈሳዊ ብቃት የማይመጣ ተአምር፣ ድንቅና ምልክት ምንጩ ከሰይጣን እንደሆነ ይጠቁመናል፡፡ ዛሬ በእነዚህ ይህንን ያህል የምንታለል ከሆነ ነገ ሐሳዊ መሲሕ ከዚህ የሚበልጡ አስደናቂ ተአምራትን ሲያደርግ ጨልጠን ገርኝተን መከተላችን የማይቀር ነው፡፡ ‹‹የተመረጡትን እንኳን እስኪያስት ድረስ›› ተብሏልና፡፡

9. ምሥጢረ ቀንዲል መሠረቱን መጽሐፍ ቅዱስ ያደረገ(ያዕቆብ. 5፣13) ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ነው፡፡ የሚፈጸመው በካህናት ሲሆን የራሱ የሆነ የጸሎትና የመቀባት ሥርዓት አለው፡፡ ለዚህም መጽሐፈ ምሥጢረ ቀንዲልን ማንበብ ይጠቅማል፡፡ አሁን የምናየው ግን በጀሪካል ቅባት ይዞ ማከፋፈል፣ ምእመናን ከአጥማቂዎች ‹ቅብዐ ቅዱስ› ወስደው እንዲጠጡና እንዲቀቡ ማድረግ፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያልነበረ፣ በምሥጢረ ቀንዲል ያልተፈቀደና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ውስጥ የሌለ ነው፡፡ አንዳንድ አጥማቂዎችም ‹‹ከኢየሩሳሌም የመጣ ነው›› ይላሉ፡፡ ከኢየሩሳሌም የሚመጣ የተለየ ቅባት የለም፡፡ አንድን ቅባት ቅዱስ የሚያደርገው ጸሎቱና ሥርዓቱ አንጂ የተሠራበት ከተማ አይደለም፡፡ ኢየሩሳሌም ውስጥ ግሪክ ኦርቶዶክሶች፣ ካቶሊኮች፣ የይሖዋ ምስክሮች፣ ፕሮቴስታንቶች፣ ሌሎችም አሉ፡፡ ከኢየሩሳሌም የመጣ ማለት ከየት የመጣ ነው? ምእመናን ለኢየሩሳሌም በጎ ኅሊና ስላላቸው ‹‹ከኢየሩሳሌም ተባርኮ የመጣ ›› ይባላል፡፡ ማን ባረከው? ብሎ የሚጠይቅ የለም፡፡

10. ከአክባሪው ይልቅ ከባሪው፣ከሰጭው ይልቅ ተቀባዩ፣ከጌታው ይልቅ አገልጋዩ የሚከብርበት ሥራ የእግዚአብሔር አይደለም፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት ዓላማው እግዚአብሔርን ማክበር፣ አሕዛብም እግዚአብሔርን እንዲያውቁ ማድረግ፣ ከመንገድ ጠራጊውም ይልቅ መንገዱን እንዲያገኙት ማስቻል ነው፡፡ አሁን የምናያቸው ‹አጥማቂዎች› እና ‹ተአምራት› አድራጊዎች ግን ራሳቸውን የሚያከብሩ፣ እግዚአብሔርን የሚሸፍኑ፣ ሕዝቡ ቅዳሴና ትምህርት እየተወ እነርሱን በየሜዳው እንዲከተል የሚደርጉ፣ ሕዝቡ ንስሐ መግባት፣ ሥጋወ ደሙ ከመቀበል ይልቅ የእነርሱ አድናቂና ካዳሚ እንዲሆን የሚስቡ ናቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ስለ ራሱ ሲናገር ‹እኔ ዝቅ ዝቅ ልል፣ እርሱም ከፍ ከፍ ሊል ይገባል›. ነበር ያለው (ዮሐ. 3፣29)፡፡ ለእነ ቅዱስ ጳውሎስም በልስጥራ እግሩ የሰለለውን ሰው በፈወሰው ጊዜ ሕዝቡ ተደንቆ እንደ አምላክ ሊሠዉላቸው ወድደው ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ግን ‹እንደ እናንተ ሰዎች ነን›. እያለ ለምኖ አስተዋቸው፡፡ ሕዝቡንም ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መለሳቸው፤ የእግዚአብሔርም ስም እንዲከብር አደረገ(የሐዋ 14፣8-18)፡፡

በእነዚህና ቤሎችም ምክንያቶች በዘመናችን የተነሡትን ‹አጥማቂ ነን ብለው ማስታወቂያ የሚያስነግሩትን፣ መቁጠሪያና ቅብዐ ቅዱስ የሚያከፋፍሉትን፣ በየሜዳው ሕዝብ ሰብስበው ምትሐት የሚሠሩትን ሰዎች መቀበል አለብን ብዬ አላምንም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የጸጋው ግምጃ ቤት ናት፡፡ በጸሎት የሚተጉ፣በእምነት ሕይወት ያሉ ክርስቲያኖች በየምሕረት አደባባዮች ምሕረትን ያገኛሉ፡፡ በቤተ ሳይዳ መልአኩ ውኃውን ይባርከው እንደነበር ሁሉ የጠበል ቦታዎችን ራሱ እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑ ባርኳቸዋል፡፡ የተለየ አጥማቂ አያስፈልገቸውም፡፡ የክህነት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው እንጂ፡፡ ደግሞም ሁሉም ሕመም መዳን የለበትም፡፡ ደዌ ዘእሴት(ለበጎ የሚሰጥ ሕመም) አለ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የብዙዎችን ሰይጣን እያስወጣ እርሱን ግን የሚጎስመው ሰይጣን ነበረው፡፡ ጌታን ሲለምንም ‹‹ተወው›› ነው የተባለው(2ኛቆሮ. 12፣ 7)፡፡ የዛሬ አጥማቂ ነን ባዮች ግን ሁሉም ሕመም ይድናል ይላሉ፡፡ ለቅዱስ ጳውሎስ ያልተቻለ ተቻላቸውን? ከሐዋርያት አንዱ የነገረው ያዕቆብ እግረ በሽተኛ ነበር(ዜና ሐዋርያት፣ በእንተ ያዕቆብ ሐዋርያ)፤ እርሱ ግን ብዙዎችን ይፈውስ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር ምሕረት አገኘን የምንለውም ስንፈወስ ብቻ መሆን የለበትም፤ የምንታገሥበት ዐቅም ስናገኝም ጭምር እንጂ፡፡ ልመናችንም ለፈውስ ብቻ ሳይሆን ለመታገሥ ዐቅም እንዲሰጠን መሆንም አለበት፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ለመፈውስ የሚችል ቢሆንም ሁሉንም ግን አይፈውስም፡፡ ለበረከት፣ ለተግሣጽ፣ ከከንቱ ውዳሴና ከትዕቢት ለመከላከል የሚፈቅደው ደዌም አለ፡፡ ያዕቆብ ወልደ ይስሐቅ ይህ ተሰጥቶት ነበር(ዘፍ. 32፣31)፡፡ ክርስትና በመንፈሳዊ ሕይወት በመኖር፣ በንስሐ መንገድ በመመላለስ፣ በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በመሳተፍ እንጂ በድንቅና በተአምራት የሚኖር አይደለም፡፡

አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ‹‹ገንዘብ ይሰበስባሉ፣ ገቢ ያስገኛሉ›› ብለው እነዚህን ሐሳውያን እንደሚደግፉ ይታወቃል፡፡ ምእመናንም ‹‹ታድያ አቡነ እገሌ ለምን ፈቀዱ›› ይላሉ፡፡ እኛ ግን መሠረት ማድረግ ያለብን የቅዱሳት መጻሕፍትን ትምህርት፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣ታሪከ ቤተ ክርስቲያንን፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ነው፡፡ ማንም ከዚህ የወጣ ቢኖር ትምህርቱን ለመቀበል አንገደድም፡፡ ታላቅነት በእምነት እንጂ በሥልጣን አይገኝምና፡፡ ታላቁ አባት ዲዮስቆሮስ በ451 ዓም የኬልቄዶን ጉባኤ የልዮንን የሁለት ባሕርይ ትምህርት አልቀበል ሲል የሮም ባለ ሥልጣናት ‹‹እርሱኮ በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የተቀመጠ የሮም ፖፕ ነውና አለቃህ ነው›› ባሉት ጊዜ ‹‹ሰይጣንም ለቅዱስ ሚካኤል አለቃው ነበረ›› ብሎ ነው የመለሰላቸው፡፡

ሳንድያጎ፣ ካሊፎርንያ

ዛሬ ስለተጠናቀቀው ባላገሩ አይዶል የግሌ ዕይታ

$
0
0

[ቴዲ ድንቅ – አትላንታ]
ባላገሩ አይድልን በጥቂቱ ካልሆነ በሚገባ አይቼው አላውቅም። ለነገሩ ከአገር ቤት ከሚተላለፈው የድራማ ብዛት ፣ የበዓል ልዩ ዝግጅት ብዛት፣ ከወሬ አቀባዮች ድረገጾች ብዛት፣ ከሶሻል ሚዲያው ብዛት፣ ሁሉንም ባላየው አይፈረድብኝም ።
dawit tsige
የመጨረሻውን ማየት ስለፈለኩ ግን አየሁት። ወይ ቀድሞ ብዙ ተወርቶለት ፣ በጣም ተክቧል፣ ወይም ደግሞ እኔ ችግር አለብኝ። ምክንያቱም ፣ ከዚህ በፊት አየነው የሚሉ ጓደኞቼ አድንቀው ስለሚያወሩ በጣም ብዙ ጠብቄም ይሁን አላውቅም የዛሬው የመጨረሻ ዝግጅት አልጣመኝም። የተወራላቸውና ከስንት ሺ ተወዳዳሪዎች መካከል፣ ከሶስት ዓመት አድካሚ ጉዞ በኋላ፣ ምርጥ አስር ሆኑ ተብለው የቀረቡትም (1 እና 2 ከወጡት በቀር) ገና ልምምድ ላይ ያሉ ነው የሚመስሉት።

የ እስከዛሬውን በሚገባ ስላላየሁት ልተወውና ዛሬ ሊስተካከሉ ይችሉ የነበሩትን ልጥቀስ፦
– እንደኔ ግምት አስተዋዋቂዋ ልጅ ድምጽ እንጂ የአቀራረብ ወዝ (ሂዩመር የሚለውን ተርጉሙና አስገቡት) አላየሁባትም። በየመካከሉ ለማዋዛትና ለማጣፈጥ የምትጨምረው ነገር፣ እዚያው ፈጥራ ዘና የምታደርግበት ነገር አላየሁም። የተጻፈውን ብቻ የምታነብ ነው የመሰለኝ።
– ዳኞቹ በበኩላቸው ፣ በየመካከሉ ፣ “ይቅርታ አንድ ጊዜ .. ፣ እዚህ ጋር … ” እያሉ ከአሰተዋዋቂዋ ጋር እየተጋፉ ለመናገር መሞከራቸው ትልቁን ዝግጅት ያኮስሰዋል። አዘጋጆች፣ ዳኞችና የዝግጅቱ ሞተሮች (ከጀርባ ያሉ ፕሮዲውሰሮች [ካሉ] ] በተለየ መነጋገሪያ ሊነጋገሩ ይችሉ ነበር። ወይም ቀድመው ምን ምን መደረግ እንዳለበት በሚገባ መግባባት ነበረባቸው።
– መብራት የሚጠይቅ ዝግጅት ያቀረቡት የቡድን ዳንሰኞች፣ የመብራት ቅንብርና ሃይል፣ እንዲሁም ቴክኖሎጂው ጭምር እንደሚፈልጉት መሆኑን ያረጋገጡ አልመሰለኝም። በመብራት መለዋወጥና መፍካት ሊደምቅ የሚችል ዝግጅታቸው እንደ ደበዘዘ ቀርቷል።
– ዳዊት ጽጌ አንደኛ መውጣቱ ድሮም የተጠበቀ ይመስላል፣ እንዲያውም ከውድድሩ በፊት ጀምሮ ፣ እሱ ራሱ ጭምር ፣ አንደኛ መውጣቱን ያመነበት ይመስላል። ጥሩ ድምጽ እንዳለው ተማምኗል። በርግጥም አለው። እናም የመጨረሻ የሙዚቃ ዝግጅቱን ሊያሸንፍበት ርግጠኛ እንዲሆን የተለየ ዝግጅት፣ አዕምሮ ውስጥ እንዲቀር ጥረት ያደረገ አይመስልም። ተመልካቹም ምንም አዲስ ነገር ያየ አልመሰለኝም፣ እንዲያውም፣ ከመጨረሻው ወሳኝ የዳዊት ጽጌ ሙዚቃ ዝግጅት ይልቅ፣ የጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ዝግጅት ነው ያስመሰለው።
– ውድድሩ ሶስት ዓመት ሙሉ ሲታይ እንደመቆየቱ መጠን የመጨረሻው ዕለት ዝግጅት ከስከዛሬው ለየት የሚልበት መንገድ የታሰበ አይመስልም። ለምሳሌ በየውድድሩ ጣልቃ፣ እንደ “ሰርፕራይዝ” ቴዲ አፍሮ፣ ወይ አስቴር አወቀ .. ወይ መሃሙድ አህመድ፣ ወይም ሌላ ሙዚቃ እንዲጫወቱ ቢደረግ ጥሩ ነበር የሚል ግምት አለኝ። አለበለዚያ “የመጨረሻ” ከመባሉ በቀር የሁልጊዜ አይነት ውድድር መስሎ ይቀራል።
በአዳራሽ ከቅርብም ይሁን፣ እንደኔ ከሩቅ አገር በቲቪ ያየው ተመልካች “አዲስ ነገር” ያየው “እገሌ አሸነፈ፣ አገሌ ሁለተኛ ወጣ!” የሚባለውን የመጨረሻ ድምጽ እንጂ፣ ከቀረበው ዝግጅት ውስጥ ከሌለው የተለየ ነገር ያየ አይመስለኝም። ምናልባት፣ ሁለት ሁለት ሆነው፣ ወይም ሁሉም ተወዳዳሪዎች በጋራ ለየት ያለ ነገር ይዘው ቢቀርቡ፣ ቢያንስ የሚወራ ነገር ይኖራል። አሁን ግን “ዳዊት ጽጌ” ከማሸነፉ ውጭ፣ እህ ተብሎ የሚወራለት ሌላ ነገር አልከተሰተም።
ዳር ሆኖ መተቸት መቼም ቀላል ነው (እኔ እንዳረኩት) ፣ ግን መቼም ከዚህ የተሻለ አጨራረስ እንዲኖር ከመመኘት ነው። አሸናፊ ሆኖ የጨረሰውን ዳዊት ጽጌ እንኳን ደስ አለህ እላለሁ። እንኳን ሶስት ዓመት አይደለም፣ እኛ የሶስት ሰአት የአዳራሽ ዝግጅት ለማዘጋጀት የምንደክመውን ስለማውቅ፣ ጽናት፣ ቁርጠኝነት፣ ራዕይ፣ ግብ፣ ጠንካራ መንፈስ፣ ትዕግስት፣ ትህትና፣ ብዙ ጨጓራና (በብስጭት እንዳይቃጠል)፣ ተራራ የሚያክል ትከሻ (ሁሉን እንዲችል) የተሰጠውን ጓደኛችን አብርሃም ወልዴ እንኳን ለዚህ ቀን አበቃህ፣ ከወገብ ህመምህን ፈጣን ፈውስን ታገኝ ዘንድ ምኞቴ ነው።


ዛሬ መስከረም 17፣ 2008 የጥላሁን ገሠሠ 75ኛ ዓመት የልደት ቀን ነው

$
0
0

ከዘከሪያ መሐመድ

 

ይህ ታሪካዊ ቀን፣ ለእኔም ታሪካዊ ሆኖ ያልፍ ዘንድ የአንድዬ ፈቃድ ሆነና፣ ዛሬ ሁለት እንግዶች በመኖሪያ ቤቴ አስተናገድሁ፡፡ አንደኛው የጥላሁን ገሠሠ የበኩር ልጅ፣ ምንያህል ጥላሁን ገሠሠ ሲሆን፣ ሌላው የጥላሁንን የሕይወት ታሪክ እጽፍ ዘንድ ያነሳሳኝን የቤተሰብ ታሪክ ማስታወሻ ከ1934 ጀምሮ የጻፉት የአቶ ፈይሣ ኃይሌ 8ኛ ልጅ ሳምሶን ፈይሣ ነበር፡፡ ጀምበር እስክትጠልቅ ድረስ እየተጨዋወትን ቀኑን በግሩም ሁኔታ አሳለፍን፡፡

ZEKERIA“ጥላሁን ገሠሠ፡ የሕይወቱ ታሪክና ምሥጢር” የተሰኘውን መጽሐፌን ለምንያህል ከታላቅ አክብሮት ጋር አበረከትሁለት፡፡ እርሱም በደስታ ተቀበለኝ፡፡ የጋሽ ጥላሁንን ባዮግራፊ ለበኩር ልጁ ባበረከትሁበት ቅጽበት፣ ከፊርማዬ በታች መስከረም 17፣ 2008 ብዬ ስጽፍ ልዩ ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡ ከምንያህል እና ከሳምሶን ጋር ከዚህ በፊት የያዝናቸው ሁለት ቀጠሮዎች በተለያዩ ምክንያቶች ተስተጓጉለውብናል፡፡ ዛሬ የመጡት ተቀጣጥረን አልነበረም፡፡ የሆነው ሆነና በዕለተ መስቀል፣ በጥላሁን የልደት ቀን ምንያህል እና ሳምሶን ከች አሉ፡፡ በታላቁ ከያኒ የልደት ቀን፣ የበኩር ልጁ ምንያህል ጥላሁን ገሠሠን በመኖሪያ ቤቴ በማስተናገዴ እና በዚሁ ዕለት መጽሐፌን ላበረክትለት በመቻሌ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡

‹‹የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም
በፍቅር አንቺን ነው ሌላ አላውቅም›› እያለ የዘፈነው ያ የ1970ዎቹ ወጣት ምንያህል ጥላሁን ገሠሠ፣ ምን ያህል እንደተቀየረ አያችሁን?

ለየት ባለመንገድ ደፈር ብሎ ስለማሰብ።ጉርብትናና በሰላም መኖር በየኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል።

$
0
0

ከቢላል አበጋዝ / ዋሽግቶን ዲ ሲ

እሑድ ፣ ሴፕቴምበር 27 ቀን 2015

south-africa-ethiopia-eritreaዛሬ ካለንበት ተነስተን ስናስብ ወያኔ ህወሃት ጋር ያለን ጠብ ሳይሆን ከወያኔ በኋላ በምን ሁኔታ የምትኖር አገርን እንሻለን የሚለው ጥያቄ ግዝፈት አለው።በኢትዮጵያም በኤርትራም ያለው ህዝብ ከወያኔም፤ከሻቢያም በላይ ነው።ያአንድ አገር እድል ከፖለቲካ ድርጅቶች ፤ከመሪዎችም በላይ ነው።የአካባቢውን ህዝቦች እጣ ፈንታ ስናስብ በወሰን ተገድበን እንዳይሆን ጥንታዊና በዙ መእዘን ያለው ትስስራችን አስበን ከስሜተኝነት ርቀን እንደ ችግር ፈችዎች እንድናስብ የግድ ይለናል። የኢትዮጵያና ኤርትራ ጉዳይ እንድንወያይበት በሚል ይህ ጽሁፍ ቀርቧል።

ችግርን ለመረዳትና ለመፍታት በተለያዩ አቅጣጫዎች ማውጣት ማውረድ አለ።ከውሳኔ በፊት ሁሉንም ማእዘናት ማየት ተገቢ ነው። ይህም በጣም የሚበጅ መንገድ ነው።ባለንበት ሁኔታ ደግሞ እጅግ ወሳኝ ነው።እንዲህ ያለው አቀራረብ ለግትርነት ቦታ አይሰጥም።ውሳኔ ጋ ሲደረስ ደግሞ የሚወሰነው ጉዳይ ምክንያትን የተመረኮዘ እንዲሆን ማረጋገጫ ይሰጣል።እዲህ መምከር ደግሞ ጥንቱንም ያገራችን ብልህ ሰዎች ዘዴ ነው።ከራሳቸው ለየት አድርጎ የሚያስበውን ይሰሙታል። አያጥላሉትም።”እሱ የመከረውን ጨምረን ሳንሰማ” ይላሉ፤ ሁሉን ከየመዓዘኑ ለመስማት ማለት ነው።ለየት ባለመንገድ ማሰብ ክፉ አይደለም።በእግሊዝኛ “ከሳጥኑ ውጭ ማሰብ” ይሉታል።(Thinking outside the box) ከግርግሙ ወጣ ብሎ ማየት።ከተለመደው መንገድ በድፍረት ወጣ ብሎ ለመተንተን፤ለማሰብ መሞከር ለማለት ነው።ይህንን እንሞክረው ካልን ብዙ ጉዳዮችን ማንሳት እንችላለን።አንዱ የአገሮች ጉርብትና ይሁን:ሌላው ደግሞ ብሄር ብሄረሰብ መገንጠል።ክልል እያልን አርባ ዓመታት የተወዛገብንበት አቢይ ናቸው።የአገሮች ጉርብትና ላይ ብቻ አተኩረን እንቀጥል።

ማንም አገር ከጎረቤቱ በሰላም ቢኖር ለራሱም ለጎረቤቱም መልካም ነው።ጎረቤት አገራት በሰላም በጉርብትና የሚኖሩ ከሆነ የምጣኔ ሃብትን እድገት ጎዳና ይያያዛሉ።ጠብ ተነስቶ የጥይት ውርጅብኝ መለዋወጣቸው የማንኛውንም ወገን ህዝብ የኑሮ ሁኔታ አያሻሽልም።ሁሉም የወሰኑን ጉዳይ፤ ሌላም ብሄራዊ ጥቅሙን ይርሳ ሳይሆን ተከባብሮ፤በሰላም መኖር ላይ ማተኮር የሚበጅ ነው ለማለት ነው።ኢትዮጵያ ብዙ ጎረቤቶች አሏት።ሶማሊያ አንድዋ ናት።ሶማሊያ ሰላም ያጣች አገር ናት።ጦሷ ለኢትዮጵያ የተረፈ ነው።ቀደም ብሎ በሁለቱ አገራት የሆነውን እናስታውሳለን።መጨረሻው የሶማሊያ መፍረስ ሆነ።ለኢትዮጵያ ደግሞ ችግር እንደሆነች መቅረትዋን ይሄው ዛሬ እናያለን።የሶማልያ ሰላም ማግኘት ለኢትዮጵያ ይጠቅማል።ከጦርነቱ የንግድ ልውውጡ ለሁለቱም አልሚ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ጥረት ሶማልያ ወደ ሰላምና መረጋጋት እንድታመራ መሆን አለበት።ወያኔ ህወሃት በዚህ ጉዳይ ከውድቀት ወደ ሌላ ውድቀት ሲሄድ እናየዋለን።ህወሃት ለሶማሊያ ሰላም አወንታዊ ሀይል አይደለም።ሶማልያ ካሉ ሀይሎች የአየለው ከዚው መውጣት አለበት።በውጭ ሀይላት የሚዘወር ከሆነ ለሰላም የተዘጋጀ አይሆንም።ባጭሩ የሶማሊያን ችግር ለሱማሌዎች መተው።ኢትዮጵያ ድንበር ጠረፏን ማስከበር።ወያኔ ህወሃት ይህን አድርጎ አያውቅም። በኢትዮጵያውያን ወታደሮች ላይ የደረሰው ከፍ ያለ በደል ሊሰማ ጊዜው እየጠበቀ ነው።

ሱዳንም የኢትዮጵያ አጎራባች ናት።ቀድሞ አንድ አገር ነበረች። ዛሬ ሁለት ያልተረጋጉ አገራት በመሆን ተከፋፍላለች።ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ሁለት ሰሜንና በደቡብ ያሉ የራስ ምታቶች አሏት ማለት ነው።ከመከፋፈሉ ይልቅ የሰላም መደፍረሱ ለኢትዮጵያ አስከፊ ነው።ቢያስ ስደተኛ ማስተናገድ አለ።የንግድ ልውውጥም ቀረ ማለት ነው።ዛሬ ኢትዮጵያ በጥቅሟ የሚደራደር መንግስት ሰንጎ ይዟት ከአረቧ ሱዳን ጋር ወያኔ ከተሸኘ በኋላ ጠብ የሚያስነሳ ስራ በወያኔ ተሰርቷል። ይህ አይበጅም።ጠብ ለኋላ ማሳደር ነው።ስለዚህ ሱዳንና የኢትዮጵያ መካከል ወያኔ ፈንጂ ቀበረ ማለት ነው።

ኬንያ ሌላዋ የኢትዮጵያ ወሰንተኛ ናት።የረጅም ጊዜ የሰላም ግነኙነት በመኖሩ በጦርነት ኢትዮጵያና ኬንያ አልተጠመዱም።የሶማልያ ሰላም ማጣት የጋራ ችግራቸው ነው።ኬንያ የንግድ መነሃረያ ናት።እየለማች ነው።ሶማልያ ውስጥ ግን ያለው አለመረጋጋት፤መንግስት አልባነት ኬንያን አልበደለም ማን ይላል?ምዕራባውያን በአፍሪካ ቀንድ የሚተኩሩት ሽብርተኛ ሀይሎችን መዋጋት ላይ ነው።ሽብርተኛነት የዓለማችን ችግር ነው።ለማንም አገር ቢሆን አውዳሚ ሀይል ነው።ሽብርተኛነት እንዲያውም አንዱ አፍሪካን ቀስፎ የያዘ ችግር ነው።ይህንም ችግር ተቋቁመው፤ተረጋግተውም ብቻ ነው አገራት ስለዕድገት ማሰብ የሚችሉት።ይህ ደግሞ ምዕራባውያን የሚፈቱት ችግር ወይም እነሱ አዝማች የሚሆኑበት ሳይሆን አፍሪካውያን እራሳቸው ጥረው ግረው መፍታት ያለባቸው መሆን አለበት።ኬንያ እንደምን አድርጋ ራስዋን ለሽብርተኞች መመልመያ እንዳደረገች ማስተዋል አያቅትም።እስላም የሆኑትን ዜጎችዋን በጅምላ በመኮነን፤በማሰቃየት፤በመግደል ለአልሸባብ ሰራዊት መመልመያ ሆነች።ሁኔታው ከበረታ የልማትዋ ደንቃራ ይሆናል ማለት ነው።ወያኔ ህወሃት ኬንያ ደፍሯል።የችግር ጅማሮንም ታዝበናል።

ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል የነበረች ዛሬ ደሞ ጎረቤት ናት።ከተበጠበጠች ኤርትራ ሰላም ያሰፈነባቱ ትመረጣለች።ጎን ለጎን ያሉ ቤቶች ለሳት አደጋ የሚጋለጡት በጋራ ነው።ለኤርትራም ሰላም ያላት የተረጋጋች ኢትዮጵያ ትሻላታለች። ሰላም ካለ ሁለቱም ጦር ከመስበቅ ይልቅ ወደልማት ያተኩራሉ። ይበለጽጋሉ።በመጨረሻ ኤርትራም ኢትዮጵያም ከጦርነት የሚያተርፉት የለም።መሳሪያው የገዙበትን ብድር ይዘው ይቀራሉ እንጂ።የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያን መበታተን አላማው መሆኑን በምክንያት ሳይደግፉ የሚያቀርቡ አሉ።ዛሬ ያለችው ኢትዮጵያ በሙስና ተቦርቡራ፤ተርባ፤ደካማ ሆና ትገኛለች።እነዚህ የህወሃት አፈቀላጤ ከትግራይ ብሄር ያልሆኑ ወያኔዎች ከወያኔ የበለጠ የጦርነት ከበሮ ደላቂዎች ናቸው።ለሁለቱም ለኤርትራም ለኢትዮጵያም ሰላም ላይ የተመረኮዘ ጉርብትና እንጂ ሌላ ምን ይበጃቸዋል? የህወሃት አፈቀላጤዎች የሚሉት “የባህር በር” ጥያቄ ላይ የመለሱ ህወሃት ምን ድርሻ ነበረው ?እዚህ ውዝግብ ውስጥ መግባት ሳይሆን ለመቶ ሚሊዮን ህዝብ ሰላም ማግኘት፤መብት መከበር፤በልቶ ማደር፤የዜግነት ክብር አሁን ምን ይደረግ ?ሀያ አራት ዓመታት የበደለው፤የቀማው፤የከፋፈለው ህዝብን ያዋረደው ህወሃት ይቀጥል አይቀጥል ነው ጥያቄው።ቅድሚያው ጥያቄ ይህ ነው።ድሮ ኢትዮጵያ ጠብ ቢኖራት ያው ከሶማሊያ ጋር ነበር በብዛት።ዛሬ ወያኔ አሁን ከተሰራችው ደቡብ ሱዳን ጉዳይ ጣልቃ ይገባል።ኬንያን ይደፍራል።ሶማሊያ ተቀርቅሯል።ኤርትራን ሳንቆጥር ዙሪያው በችግር አጥሯል ማለት ነው።

ለማንም አገር ቢሆን ሰላም ለዕድገት መራመድ ፋታ ይሰጣል።ቻይና ላለፉት አምሳ ዓመታት ሰላም ብታገኝ ይሄው ዛሬ ከዓለም ሁለተኛው የምጣኔ ሃብት አንቀሳቃሽ ሆናለች።ሰላም ፋታ ቢሰጣት ዕድገት ላይ አተኩራ ቆየች።በኢትዮጵያ ከኢጣልያ ወረራ በኌላ ቢያንስ ሰላሳ አምስት ዓመታት ትንሽ መተናፈሻ ተገኝቶ ትምርት፤እድገት፤የብልጽግናም መንገዱ ተይዞ ነበር።ከወያኔ በአንጻር ሲታይ የወታደራዊ ደርግ ብልጽግናን ያልተጻረረ ነበር ቢባል ስተት አይሆንም።ጭብጡን በአሃዞች ደግፈው የምጣኔ ሃብት ጠበብቶች አንድ ቀን ያወጡታል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ።ወያኔ እዚህ ትንታኔ ውስት አይገባም።ምክንያቱም ትንታኔው የተመሰረተው ልማት እድገት ብሄራዊ ብልጽግና መመሪያ የደረጉ መንግስታትን ስለሚመለከት ነው።በሃያ ዓመታት ለወያኔ ኩራቱ በሙስና መክበር ነው።ብሄራዊ ልማትን አልነካውም።ስልክ፤ኤሌትሪክ ሀይል፤ውሃ፤የራብ መወገድ፤ስደት፤የረባ ትምህርት ነው።የሃያ ዓመታቱ ውጤት አሳፋሪና አስከፊ ነው።

እስቲ ዛሬ እንድፈርና ኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሊሆን ስለሚችለው ሰላም እንነጋገር።ዛሬ ወያኔ ኢትዮጵያን ትልቅ እስር ቤት አድርጎ የሚገኝ መንግስት ነው።እንዲህም ለመቀጠል የጦርነት ከበሮ መምታትን ይመርጣል ወደ ሰላም ከማሰብ ይልቅ።ወያኔ በኢትዮጵያም በኤርትራም የበላይነትን ይመኛል።የሰላም ሀይል መግባባት ፈጣሪ ለሰላም ጥረት አድራጊ ቢሆን ኖሮ በሶማልያ፤በደቡብ ሱዳን ውጤት ባሳየ ነበር።ወያኔ ለኢትዮጵያም ለአፍሪካ ቀንድም ባዕድ ሀይል ነው።የዚህን አካባቢ ሰለም መረጋጋት መምጣት ጋር አይያያዝም።የራሱን ህልውና ከባዕዳን ፍላጎት ጋር ዘንቆ ህዝቡን ጠርጥሮ ለህልውናው ሁሌ ሰግቶ የሚኖር፤ በቋፍ ያለ፤ ገደል አፋፍ ላይ የቆመ መንግስት ነው።ላንዴም ቢሆን ላፍታው ከወያኔ የጦር ከበሮ ርቀን የኤርትራና የኢትዮጵያን በሰላም ተጎራብቶ መኖር፤ችግርን በጠረጴዛ ዙሪ መፍታትን እናስበው።ይህ ነው ከኤንቬሎፑ ውጭ ማሰብ።ደፈር ብሎ ወጣ ብሎ ማሰብ።እንቅፋት ሆኖ የሚገኝው ወያኔ ነው።ለህዝብ ተጠሪነት ሞቱ ነው።ከኤርትራ ጋር ግንኙነት ሲባል የሚታየው ተቃዋሚው ሀይል ነው።ተቃዋሚው ሀይል ደግሞ እራሱ ወያኔ ምርጫዎችን ሁሉ ወስዶ፤ ገፍቶ ያስወጣው ነው።ወያኔ ተቃዋሚውን ላጥፋ እንጂ ልደራደር የሚል ብልህ ሀይል አይደለም።ሁሉ በተንኮል ሁሉን በጉልበት እወጣዋለሁ የሚል ህልውናውን እንጂ ብሄራዊ ጥቅም የሚያስብ አይደለም።ባጭሩ ወያኔ ለጉርብትና ፈጽሞ የሚመች አይደለም።መልካም ግንኙነት አለኝ ቢል ዛሬ ከሰሜን ሱዳን ጋር ነው።አሳልፎ የሰጠው ሰጥቶ በዚያ ወሰን ተቃዋሚ እንዳይንቀሳቀስበት ድርድሩን አድርጎ ነው።

ኢትዮጵያና ኤርትራ ሁለቱም ኋላ ቀር ደሃ አገሮች ናቸው።ይህ አያከራክርም።ከዚህ ካሉበት ሁኔታ መውጫው ደግሞ ጦርነት ነው ማለት ከእብደት ብቻ የሚመነጭ አባባል ነው።ድህነትን ለማስወገድ ሰላም አግኝቶ ማምረትን ይጠይቃል ከላይ አንስተነዋል።በትላልቆቹ አገሮች እንየው።አማሪካና ኢራን ስምምነት ባይደርሱና ጦርነት ቢጀምሩ የሁለቱ አገራት የልማት እቅዶች ታጥፈው ጥረት ሁሉ ወደ ጦርነት ይሆናል።ሁለቱም ያጣሉ። አካባቢውም ዛሬ ካለው ሁኔታ ይብስበታል።የዓለምም ሰላም ከፍ ካለ ስጋት ይወድቃል።ሞት ስደት ይከተላል።ጦርነት መዘዙ አያሌ ነው።

ያለፉት ጥቂት ዓመታ የጦርነት አጥፊ ጎን ለማሳየት፤የአገር በሰላም መቆየት መበጀት አሳይተውናል።የአንድ ሊቢያ ሰላም ማጣት ራስዋን ሊቢያንና በታችዋ ያሉት አገራት እንዳናጋ አይተናል።የኢራቅን መፈራረስ ለዓመታት አይተናል።ሶርያ አሁን ከፊታችን እየነደደች፤እየፈረሰች ነው።እሷ ስትወድም ዜጎችዋ ወደ ስደት።የመን ደግሞ ባህር ይለየን እንጂ ታሪክ፤ባህልም፤ንግድም ያስተሳሰረን ነን።ሰላም ማጣት፤ጣልቃ የገባ ጠላት የመንን ምን እያደረጋት እንደሆን እያየን ነው።እንዲህ ወዳለች በጦርነት የደቀቀችን አገር ምርጫ አድርገው ወገኖቻችን ወደ የመን ይሄዳሉ።የኢትዮጵያ ሁኔታ ለመክፋቱ ማመሳከሪያ እንደተፈለገ ሁሉ።

ስለዚህ ወያኔና አፈቀላጤዎችን ትተን ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን የምንመኝ ሁሉ ደፈር ብለን ኢትዮጵያና ኤርትራ በሰላም ተጎራብተው ቢኖሩስ ብለን እፋስብ።ልብ እንበል ሁለት የነበሩ አገራት ያውም ሰው የሰራው ግንብ በመሃላቸው የነበረ ሁለት ጀርመኖች ዛሬ አንድ አገር ናቸው።አምሳ ዓመታት የተገለለችው ኩባ በምዕራቡ መታቀፍዋ ከኤንቬሎፑ ውጭ ለማሰብ የደፈሩ ሰዎች የስራ ውጤት ነው።ኩባና ምዕራቡም አቸናፊ የሚሆኑበት የድርድር ውጤት ማለት ነው። እኛም ደፈር ብለን እናስብ የወያኔ አሽቃባጮችን ንቀን።

ለክርስቲያን ወገኖቸ መልካም በዓል !

አነድነት ሀይል ነው!

ድል ለመብቱ ለነጻነቱ እየታገለ ላለው የኢትዮጵያ ህዝብ!

ኢትዮጵያ  በህዝቦችዋ አንድነትና ፍቅር ለዘለዓለም በነጻነት ትኑር!

የኛ ሃብታሞች ምን ነካቸው? –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

እኔ የምለው ጥቁር ጣልያን ነው እንዴ የሚገዛን?

Ketemaመቼም በዚህች ምርድ ላይ ሃብታም ሆኖ መኖር የማይፈልግ የለም። በሃብት ቁንጮ ላይ ለመቀመጥ የማይጥር የለም። ታዲያ የሮጠ ሁሉ አንደኛ እንደማይወጣ ሁሉ ቢሊዮነር ሆነው የሚታዩት ጥቂቶች ናቸው። እነዚህ የአለማችን ቢሊዮነሮች በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ላይ ቅድሚያ እንዲጠቀም ወይም መጥቀም የሚፈልጉት የራሳቸውን ዜጋ ነው። የአገራቸው ዜጋ ፍላጎቱ ከተሟላ ወይም ከበቂ በላይ የሚሆን ምርት ካመረቱ ወደ ሌላ አገር መሸጥም ሆነ መርዳት ይጀምራሉ። ይህ በአብዛኛው  አገራት የሚሰራበት አሰራር ነው። አንድ ባለሃብት  የሚያመርተው ምርቱን ቅድሚያ ለአገሩ ማዋል ግዴታ አለበት ለህዝቡም በቂ ምርት ማቅረብ ከተቻለ እና ትርፍ ሆኖ ከተገኘ ወደ ውጪ መላክ አንድ አገሩን እና ህዝቡን ከሚወድ ዜጋ የሚጠበቅ ነው። ታዲያ የኛ ሃብታሞች ምን ነካቸው?

ኢትዮጵያ ውስጥ የኑሮ ውድነትን የፈጠሩት መንግስት ያደራጃቸው የምንግስት ባለስልጣናት አብሮአቸው ከሚሰራው ልማታዊ ባለሃብቶች ለህዝባችን ማሰብ ባለመቻላቸው ከፍተኛ የሆነ እራስ ወዳድነት እና እራስን ለጥቅም አሳልፈው የሰጡ በመሆናቸው ነው።

የኢትዮጵያ ባላሃብቶች ከጥቂቱ በስተቀር ወደ ቢዝነስ ውስጥ ሲገቡ ህዝብን ለመጥቀም የህዝብን ኑሮ ለማሻሻል ሳይሆን በቀላሉ ትርፋማ ሆኖ ሚሊዮነር መሆን የሚችሉበትን መንገድ በቀላሉ ገንዘብ ማግኘት ወደሚችሉበት ያቶኩራሉ።

ባላሃብቶቹ ወደ ቢዝነሱ ከመግባታቸው በፊት እያንዳንዱ ባለሃብት  ከአንድ ባለስልጣን ጋር መጣበቅ ግድ ይላቸዋል ካለበለዛ ግን ማነቆዎቹ ብዙ ስለሚሆኑ አገር ጥሎ መውጣት ካልሆነ በቀር በአገሩ ውስጥ በነጻነት የመስራት መብት አያገኝም። የዱባዬ አገር ህግ አንድ የውጪ ዜግነት ያለው ባለሃብት የቢዝነስ ተቋም በዱባዬ ለመስራት ቢፈልግ ከአንድ ዱባዬ ዘግነት ካለው ሰው ጋር መሆን አለበት ካለበለዛ ግን ምንም አይነት ስራን ማከናወን አይቻልም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ዜጋችን እንደ ውጪ ዜጋ ተቆጥሮ ስልጣን ላይ ካሉት አካል ጋር ተጣብቀህ አብሮ ካልሆነ በስተቀር ልማታዊ ባለሃብት መሆን አይቻልም። ታዲያ ኢትዮጵያ ማለት የነእንትና ቡድን ናት ማለት ነው እንዴ? በአንድ ወቅት የጣልያን ማፍያ ቡድን በጣም ተጠናክረው ጣልያን ውስጥ ያለውን ትላልቅ ቢዝነሶችን በሙሉ በነሱ ስር ካልሆነ በስተቀር መንቀሳቀስ ወደማይቻልበት ደረጃ አድርሰውት ነበረ በኋላ ግን የጣልያን መንግስት ጠንካራ እርምጃ በመውሰድ ነገሮችን ሊያስተካክል አድርጓል። ዛሬም ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለው ይሄ ነው። የኛዎቹ ከጣልያን ማፊያ የሚለዩት በመንግስት ደረጃ የተደራ ዘራፊዎች መሆናቸው ነው።

ህዝብን የሚጎዳ ባለሃብትም ይሁን ህዝብን የሚጨቁን መንግስት በኢትዮጵያ ይኖር ዘንድ አይገባም። ባለሃብቱም መንግስትም ዘላለማዊ  በሚመስልቸው ጥቅም ውስጥ የተቀመጡ ቢመስላቸውም ቅሉ ሃብትም ይጠፋል ስልጣንም ይሻራል ህዝብ ግን ሁል ግዜ ኗሪ ነው። ህዝብን እያስራቡ ሃብታም ለመሆን ከመጣር ህዝብን እየረገጡ ስልጣን ላይ  ለመቆየት ከማሰብ ትቆጠቡ ዘንድ ግድ ይላችኋል። ነገሮች እንዳሉበት ይቀጥላል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ሁኔታዎች ሲቀየሩ የናንተም እጣ ፈንታ አደጋ ውስጥ ነውና ከወዲሁ ስለ አገር ክብር  እና ስለ ህዝብ ፍቅር አርቆ ማሰብ ብልህነት ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝባችንን በማስራብ በቀላሉ መመገብ የሚችላቸውን ምግቦች በማስወደድ የውጪ ዜጋን በመመገብ ስራ ላይ የተሰማራቹ ልማታዊ ባለሃብቶች ለህዝባችን በማንኪያ ህዝባችን ላልሆኑት ደግሞ በጭልፋ በማቀበል ዶላር ቆጠራ ይቁም።

የእንስሳት ስጋን ወደ ውጪ በመላክ የተሰማራችሁ ፣ በጥራ ጥሬ እህሎች ላይ፣ የቅባት እህሎች ላይ፣ ፍራፍሬ ምርቶች ላይ፣ የቅባት እህሎች ላይ የተሰማራችሁ ባለሃብቶች ህዝባችን ላይ በእለት ከእለት በሚመገባቸው ምግቦች ላይ የዋጋ ውድነትን በማምጣት ኑሮውን ያከበዳችሁት  እናተው ስለሆናችሁ በእንደነዚ አይነት ስራ ለይ የተሰማራችሁ ሰዎች መጀመሪያ ህዝባችንን መመገብ ከዛም ለህብረተሰባችን በቂ ምርቶችን ማቅረብ ቀጥሎም የሚያስፈልጉትን ነገሮች ቅድሚያ ለአገርሬ ሰው ማቅረብ ይገባችኋል እንጂ በበቂ ሁኔታ ህዝባችን ሳይዳረሰው ወገባችሁን ታጥቃችሁ  ውጪአዊያኖችን ለመመገብ ስራ ላይ የተሰማራችሁ ባለሃብቶች ከዚህ ድርጊታችሁ ተቆጥባችሁ ቅድሚያ ወገንን ወደመመገቡ ስራ በመግባት የስራ ዘርፋችሁን ትቀይሩ ዘንድ ግድ ይላችኋል።

የስጋ ተዋጽኦ ወደ ውጪ ከመላኩ በፊት የአንድ ኪሎ ስጋ በኔ ከስምንት አመት በፊት 20 ብር ነበረ አሁን ግን የሙክት በግ ዋጋ ደርሷል። አንድ በግ ከፍተኛው ዋጋ 500 ብር ሲሆን አሁን ግን 5000 ደርሷል። አንድ በሬ በፊት ከፍተኛው 5000 ሲሆን አሁን ግን  40.000  ደርሷል። ይህም የሆነበት ምክንያት የስጋ ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ውጪ በመላክ በህዝባችን ላይ ለፈጠረውን የዋጋ ውድነት እና የኑሮ  ቀውስ ተጠያቂ ያደርጋችኋል።ስጋ ላኪ ድርጅቶች የሚገበያዩት በዶላር ስለሆነ የዋጋ መናርን ቢያመጡም መንግስት ምንም አይጠይቃቸውም ምክንያቱም መንግስት ዶላሩ ይምጣለት እንጂ ህዝባችን ስጋ ቢበላም ባይበላም ቢወደድበትም ባይወደድበትም ግድ የለውም። ከመንግስት አካሎች ጋር በመጣበቅ እራሳችሁን ሚሊዮነር በማድረግ ስራ ላይ የተሰማራችሁ ልማታዊ ባለሃብቶች ህዝባችን ከሚጎዳ ስራ ትታቀቡ ዘንድ ግድ ይላችኋል።

በጥራጥሬም ዘርፍ የተሰማሩ እንደዚሁ ነው። የጥራጥሬን እህሎች በቀላሉ ከገበሬው በመግዛት በሰሩት ትላልቅ መጋዘን ውስጥ በማጠራቀም ለውጪ ሽያጭ ያውሉታል። በፊት አንድ ኪሎ ምስር 2 ብር ገዝቶ ይመገብ የነበረው ህዝባችን ዛሬ 60 ብር ሆኗል።  ከውድነቱ የተነሳ ምስርን እንደ ስጋ ጣል ጣል አድርጎ የሚመገቡ የህብረተሰባችን ክፍሎች በጣም ብዙ ናቸው። በመንግስት ድጋፍ ጥቂት ሚሊዮነሮችን ለመፍጠር አገርን ማስራብ ገዚው መንግስት ለህዝብ ያለውን ጥላቻ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነውና ህዝቤ ሆይ በህዝብ ሃብት እና ንብረት የሚቀልዱትን አንባ ገነኖችን ሁሉ ለፍርድ ለማቅረብ በህብረት በመሆን ለነጻነትህ፣ ለክብርህ፣ ለህልውናህ፣ የምትታገልበት ግዜ ነውና ቆርጦ መነሻው ሰዓቱ አሁን ነው። ካለበለዛ 60 ብር የነበረው ምስር አይናችን እያየ በቅርቡ 100 ከዛም 200 ብር ይገባል። የህዝባችን ሃዘን ለገዚዎቻችን የደስታ ዜማ መሆኑን አትርሱ።

ከየአንዳንዱ ባለ ሃብት በስተጀርባ የባለስልጣናቱ ጥምረት እንዲኖር የተፈለገበት ዋናው አላማ በስልጣን ላይ ያሉት አካላት የኢትዮጵያን ሃብትና ንብረት በነሱ ስር ካልሆነ በስተቀር በየትኛውም የቢዝነስ ስራ ውስጥ መሳተፍም ሆነ መስራት አይችልም የሚል የጥቂቶች የማፍያ ድርጅት መመሪያ ስላለ ነው። በነጻነት ስም አገርን ለመዝረፍ ተደራጅቶ ጫካ መግባት ቢያሳፍርም ቅሉ የኋላ ኋላ የዘረፉትን የሃገር ሃብት ሳይበሏት ዋጋ የሚከፍሉበት እንደሆነ ብናውቅም ከነዚህ ጥቂት የአገር  ንብረት ዘራፊ ጋር ተጣብቀው የህዝብን ኑሮ የሚያውኩ ባላሃብቶች የሚንቀሳቀሱት በህግ መሰረት ሳይሆን አብሮት ከተጣበቀው ባለስልጣን ህግ መሰረት ነው። በኢትዮጵያ በስራ ላይ የተሰማሩትን ባለ ሃብት የመቆጣጠሩ ስራ አብሮ ያለው ባለስልጣን ድርሻ ነው። የኢትዮጵያ ህግ እነሱን አይመለከታቸውም። ባለሃብቱ ከተሰመረላቸው መስመር ፈቀቅ ካሉ ሙስና የሚል ህግ ይመዘዝባቸውና ወደ እስር ይወረወራሉ ከመስመሩ ካልወጡ ግን የኢትዮጵያ ህግ በነሱ ላይ አይሰራም።

አንድ ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው ባለሃብት ያመረታቸውን ምርቶች መኪናዎቹ  ከሚችሉት አቅም በላይ ጭኖባቸው ሲሄድ ኬላ ላይ ይያዛል የኬላ ሰራተኞችም እንደዚህ ጭነህ ማለፍ አትችልም መኪናዎቹ ከሚችሉት አቅም በላይ ተጭኖባቸዋል ስለዚህ አደጋ ሊታደርስ ትችላለህና ህግም ተላልፈሃልና ትቀጣለህ በተጨማሪም ትርፍ የጫንካቸውን አውርደህ ነው ማለፍ የምትችለው ይሉታል። የዚህን  ግዜ ባለሃብቱ በጣም በመናደድ እንዴት ደፈራችሁኝ አታውቁኝም እንዴ እያለ ከህግ በላይ መሆኑን ሊያሳያቸው ህግ እሱጋር እንደማይሰራ ሊነግራቸው ስልክ አውጥቶ ይደውልና ትንሽ ካወራ በኋላ ለኬላ ሰራተኛ አላፊ ስልኩን ይሰጠዋል የኬላ ሰራተኛውም ስልኩን ካናገረ በኋላ ስልኩን ለባለሃብቱ ይመልስለትና ሰላምታ በመስጠት ይቅርታ ጠይቆት ማለፍ እንደሚችል ይነግረዋል። ባለሃብት የደወለው አብሮት ከሚሰራው ባለስልጣን ጋር ነው። ለኬላው ሰራተኛ የተናገረው የማይመለከትህ ጉዳይ ላይ አትግባ ካለበለዛ ትወገዳለህ የሚል ነበረ። ከጥቂትም ሰዓት በኋላ መኪናውን የሚያጅቡ የታጠቁ ሲብል ለባሽ በላንድክሩዘር መኪና መጥተው አጅበውት ዬዱ። እየተሰራ ያለው እንደዚህ ነው ህግ አይሰራም በየመስራቤቱ ትክክለኛ ስራን የሚሰሩ ሰራጠኞችን ከበላይ ቀጭን ትዛዝ በመስጠት በአገሩ ለአገሩ በትክክለኛ መንገድ እንዳይሰራ እያሸማቀቁ ሌባና ቀማኛ የበዛባት አገር እንድትሆን እየሰሩ ያሉት ጥቂቶች ናቸው። ጥቂቶችን ለማኖር አገርም ሆነ ህዝብ ቢጠፋ ግዴ  በሌላቸው ሰዎች ኢትዮጵያ እየመሯት እንዳለ የምናይበት ነው።

የውጭ መንግስታት ሆኑ ባለሃብቶች ከማንኛውም በፊት ቅድሚያ ለህዝባቸው ነው የሚሰጡት። የህዝባቸውን ፍላጎት ለማሟላት የአገራቸው ምርት አናሳ ሆኖ ካገኙት ከውጪ በመግዛት የህዝባቸውን ፍላጎት ሊያሟሉ ይጥራሉ። የኛዎቹ መንግስትና ባለሃብት ደግሞ የውጪ አገር ፍላጎትን ለማሟላት ህዝባችንን ያስርባሉ። ተገላቢጦሽ ማለት ይሄ ነው። እኔ የምለው ጥቁር ጣልያን ነው እንዴ የሚገዛን?።

የኛ ባለሃብቶች መጀመሪያ አእምሮአችሁን ቀይሩት ለወገንና ለአገር ማሰብ የሚችል አድርጉት ለጥቅማችሁ እና ጥቂቶችን በመታዘዝ መኖራችሁን አቁሙ ወደ  ውጪ ከመላካችሁ በፊት ቅድሚያ  ለህዝባችን በበቂ ሁኔታ  የምግብ ፍላጎቶች ተሟልቷል ወይ ብላችሁ ፍላጎቶችን ለሟማሟላት ጣሩ የህዝብን መሰረታዊ የምግብ ፍላጎት ከተሟላ በኋላ ከህዝብ የተረፈው ወደ ውጪ በመላክ ስራ  ውስጥ እንድትሰማሩ የንጹሃን አእምሮ ባለቤት፣ አገር የመውደድ ሃሳብ፣ ህዝብን የማፍቀር ልቦና፤ ሊኖራችሁ ግድ ይላል። የህዝብ መሰረታዊ የምግብ ፍላጎት ሳይሟላ ከህዝብ ጉሮሮ ላይ እየነጠቃችሁ ጥቂቶችን የማኖር ስራ እና የውጪ አገር ዜጋ የመመገቡ ሁኔታ በአፋጣኝ መቆም አለበት። በኢትዮጵያ ውስጥ በምግብ ውጤቶች ላይ ዋጋው እንዲንር በማድረግ  እናንተ እና የናንተ አዛዦች  ተጠቃሾችም ተጠያቂዎችም ናችሁ።

ከተማ ዋቅጅራ

29.09.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

 

 

 

 

 

 

 

 

 

አርባ‬ ምንጭ የነበረው የአሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን አካባቢውን ለቆ እየወጣ ነው

$
0
0

Zehabesha News

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
‪አርባ‬ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡
‪‎ህወሓት‬ በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡

አርባ ምንጭ የነበረው የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት የመከላከያ ኃይል ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ አካባቢውን ለቆ እየወጣ እንደሆነ ታወቀ፡፡
በአርባ ምንጭ እና አካባቢው ሲንቀሳቀስ እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ከዚያ እያስነሳ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ ለጥቃት ሲያሰማራ ለረጅም ጊዜ የቆየው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን ከአገሪቱ መንግስት በተሰጠው መመሪያ የቆይታ ጊዜ ኮንትራቱን አቋርጦ ሀሙስ ዕለት አካባቢውን ለቆ መውጣት መጀመሩን በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልፅዋል፡፡

ድሮን የታጠቀው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ቡድን የአርባ ምንጭን መሬት ለቆ መንቀሳቀስ የጀመረበት ምክንያት ለጊዜው በውል ተለይቶ ባይታወቅም መንግስት ነኝ በሚለው በህወሓት አገዛዝ እና በአሜሪካ መንግስት መካከል አለመግባባት ተከስቶ ቅራኔ ሳይፈጠር እንዳልቀረ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡

ቡድኑ ከአሁን በፊት ከአርባ ምንጭ በተጨማሪ በድሬ ደዋ ላይ ተቀምጦ በሰው አልባ አውሮፕላኖች በሶማሊያ በሚንቀሳቀሱ የአልሸባብ ተዋጊዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት መክፈቱ ይታወቃል፡፡

ህወሓት በሁመራ የሚገኙ 40 የንግድ ቤቶችን ራሱ በስውር በእሳት አቃጥሎ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለማላከክ እየሞከረ እንደሚገኝ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን የተገኘው መረጃ አጋለጠ፡፡

የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ገና ከሽፍትነቱ ጀምሮ በህዝብ ላይ ሴራ በማቀነባበር የሚታወቀው ህወሓት ራሱ ግንብቶ ለግለሰቦች ያከራየውን የንግድ ማዕከል ነው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ድርጊቱን እንደፈፀሙት በማስመሰል ከህዝብ ለመነጠል ሲል ነው በተቀነባበረ ሂደት በእሳት የለቀቀው ፡፡
በህወሓት የተቀነባበረ ሴራ የተከሰተው ከባድ የእሳት አደጋ የደረሰው መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም ሲሆን ከ40 በላይ ሱቆች ተበልተው ወደ አመድነት ተቀይረዋል፤ በሚሊዮኖች ገንዘብ የሚገመት ንብረትም ወድሟል፡፡

ህወሓት በአዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱት የቦንብ ፍንዳታዎች ትግራይ ሆቴልን ጨምሮ እጁ እንዳለበት የአሜሪካ ኤምባሲ ለስቴት ዲፓርትመንት የላከውን ደብዳቤ በዋቢነት ጠቅሶ ዊክሊክስ የተባለው ድረ-ገፅ ማጋለጡ የሚታውስ ነው፡፡

ባለ ኮከቡን ሰንደቅ አላማ አለመቀበል ምክንያታዊ ነው – (ጌታቸው ሺፈራው)

$
0
0

በዚህ የህዝብ ምርጫ በሚከበርበት ዓለም ሰንደቅ አላማ ያህል ነገር አንድ ገዥ ቡድን ‹‹ከአሁን በኋላ ሰንደቅ አላማው ይኼ ነው›› ብሎ አንዳች ምልክት ሊለጥፍበት አይገባም ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ያለው ሰንደቅ አላማ የመጣው ግን በዚህ መንገድ ነው፡፡

flag

ለዚህ ሰንደቅ አላማ በቅርቡ አዋጅ ወጥቶለታል፡፡ ስርዓቱም ግን አያከብረውም፡፡ ይህን አዋጅ እንዲያከብረው የሚፈለው ሌላው በተለይ ከስርዓቱ በተቃራኒ ያለው ህዝብ ነው፡፡ ይህን ስርዓቱ የሚጥሰው፣ ህዝብ ግን አክብረው ተብሎ የመጣበትን አዋጅ ያፀደቀው የ99.6 በመቶው ፓርላማ ነው፡፡ ህዝብ ለዚህ ፓርላማ ምን አይነት አመለካከት እንዳለው ደግሞ ግልፅ ነው፡፡ ህዝብ ይወክለኛል ብሎ የማያምነው ፓርላማ ነው፡፡ ለህዝብ ጥያቄ ሳይሆን የገዥውን ፓርቲ ትዕዛዝ በተዋረድ የሚያስፈፅም፣ እጅ እንኳን ሲያወጣ፣ ሲደግፍና ድምፀ ታዕቅቦ ነኝ ሲል በትዕዛዝ ነው፡፡ ይህን ፓርላማ የህዝብ ወኪል ነው ማለት ቀልድ ነው፡፡

ፓርላማው ይወክለኛል የሚል አካል እንኳን ቢኖር ፓርላማ አወጣው፣ ገዥው ፓርቲ አፀደቀው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገረው የሰላማዊ ትግል አንዱ መርህ ተገቢነት የለውም ብሎ ላመነው የአምባገነን ህግ አለመገዛት ነው፡፡ መቃወም የሚቻለው ደግሞ ተግባሩን በመቃወም ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ሰንደቁ ላይ የተለጠፈውን ኮከብ ምልክት ባለመቀበል፣ ወይንም ንፁሁን ሰንደቅ አላማ መጠቀም!

በሌላ በኩል በቅርብ አመታት ሰንደቅ አላማው ላይ የተለጠፈውን ምልክት ከሰይጣን አምላኪዎች ጋር አገናኝተው አይወክለንም የሚሉት ኢትዮጵያውያን እየተበራከቱ ነው፡፡ የእነዚህ ግለሰቦች ትንታኔ ለእውነታ የቀረበም ነው፡፡ ይህ የአብዛኛዎቹም ኢትዮጵያውያን እምነት የሚቃረን እና የተጠላ (የ666 ምልክት የሚባለው) ሰንደቁ ላይ ተቀምጦ ኢትዮጵያውያን ለሰንደቁ ክብር ይሰጣሉ ማለት ዘበት ነው፡፡ በመሆኑም ኮከቡ የባዕድ አምልኮ ምልክት ነውና ይነሳልን ብለው የሚቃወሙት ምክንያታዊ ናቸው፡፡ እንደ ትንታኔያቸው መቃወም ግዴታቸውም ነው፡፡

በተለይ በቅርቡ ስርዓቱ የሰንደቅ አላማ በዓልን ያከብራል፡፡ ሰንደቁ ላይ የተለጠፈውን ምልክት አንቀበልም የሚሉ አካላትም በየራሳቸው መንገድ ምልክቱን አንቀበልም ብለው ለመዝመት ጊዜ አሁን ይመስለኛል፡፡ በየራሳቸው መንገድ!

የአምባገንንን ህግ መቃወም አፀፋ እንደሚያስከትል እሙን ነው፡፡ ይህን አፀፋ ለመቀነስ ትልቁ አማራጭ በጋራ፣ በዘመቻ፣ በአንድነት የአምባገነንን ህግ መቃወም ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የመስቀል በዓል እለት አንድ ወጣት ኮከቡ የተለጠፈበትን ሰንደቅ አላማ በራሱ መንገድ ተቃውሟል፡፡ ይህ ወጣት ያመነበትንና ምክንያታዊ ነው ያለውን ግን አድርጓል፡፡ ወጣቱ ከስርዓቱ ቅጣት ሊገጥመው ይችላል፡፡ በተግባር የተቃወመው ብቻውን በመሆኑ ቅጣቱም ሊበረታበትም ይችላል፡፡ በጋራና በተጠናከረ መንገድ ከሆነ ግን ስርዓቱ እርምጃም ለመውሰድ ይቸገራል፡፡ እርምጃ እንኳን ቢወስድ ሌላ ብሶት ይፈጥራል፣ ለተጠናከረ ትግልም መንገድ ይከፍታል፡፡ በተቀናጀ መንገድ የሚደረገው ተቃውሞም ህዝብ በስፋት የእንቅስቃሴው አካል እንዲሆንና መረጃውም እንዲደርሰው ማድረግ ይቻላል!

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live