Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአባይን ግድብ እንዲያጠና የተሰየመው የሆላንዱ ኩባንያ ስራውን በገለልተንነትና በጥራት ለመስራት ባለመቻሉ ኮንትራቱን ማቋረጡን ገለጸ

0
0

grand-renaissance-dam-1የሆላንዱ ዴልታሬስ ኩባንያ ከፈረንሳዩ ቢአር ኤል አይ ኩባንያ ጋር በመሆን በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ጥናት እንዲያካሂድ በግብጽና በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተወክሎ ነበር። ይሁን እንጅ ጥናቱ ከመጀመሩ በፊት በምን መንገድ መካሄድ አለበት በሚለው ነጥብ ዙሪያ ከፈረንሳዩ ኩባንያ ጋር ሲነጋገሩ ቢቆዩም መስማማት አልቻሉም። ኩባንያው ከኢሳት ለቀረበለት የጽሁፍ ጥያቄ በሰጠው መልስ ” ጥናቱን በጥራትና ገለልተኛ በሆነ መንገድ ለማካሄድ እንደ ቅድመ ሁኔታ ብናሰቀምጥም፣ ሌላው ኩባንያ የሚቀበለው አልሆነም” ብሎአል። ዴልታሬስ ገለልተኛ ተቋም እንደመሆኑ ፣ ይህንን ውስብስብና ጠቃሚ ፕሮጀክት በጥራት ለማካሄድ ያሳየው ፍላጎት ተቀባይነት በማጣቱ ከስምምነቱ መውጣቱን ቢገልጽም፣ ውሳኔውን በተመለከተ እስካሁን ከሁለቱም መንግስታት መልስ እንደላገኘ ተናግሯል።
ዴልታሬስ የሰጠውን ውሳኔ በተመለከተ ሁለቱም አገራት እስካሁን በይፋ የተናገሩት ነገር የለም። ይሁን እንጅ በግብጽ የተመረጠው ዴልታሬስ ኩባንያ ያነሳው የገለልተኝነትና የጥራት ጥያቄ፣ ግብጾች በፈረንሳዩ ኩባንያ ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ የሚያደርጋቸው ነው። በኢትዮጵያ በኩል የተመረጠው የፈረንሳዩ ኩባንያ በሆላንዱ ኩባንያ ለቀረበው ጥያቄ በይፋ መልስ አልሰጠም፣ ጥናቱን እንደሚቀጥል ወይም እንደማይቀጥል አላስታወቀም።

Source:: Ethsat


ብሔራዊ ባንክ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አምስት ከፍተኛ አመራሮችን ከኃላፊነት አነሳ

0
0

5f4e0390b5b4234013a70cd55f8dda4a_XLየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከውጭ ምንዛሪ አያያዝ ጋር በተገናኘ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አመራሮችን ከኃላፊነት አነሳ፡፡ ዕርምጃ የተወሰደባቸው ኃላፊዎች የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታና የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር አበራ ደሬሳ፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ፣ ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶች አቶ ቶሎሳ በየነና አቶ አበበ ጥላሁን፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ባንኪንግ ዲፓርትመንት ዳይሬክተሩ አቶ ባንታየሁ ከበደ ናቸው፡፡
ምንጭ :-ሪፖርተር

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት (ክፍል 8) –በአየር ኃይል በህወሓታዊያን ብቻ የተያዙ ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎች

0
0
Photo File

Photo File

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት
ክፍል 8

በአየር ኃይልና በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ውስጥ ያሉት በህወሓታዊያን ብቻ የተያዙ ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎች
===================================================
• ብ/ጀነራል መዓሾ ሀጎስ የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ (ህወሓት)
• ኮ/ል ደሳለኝ አበበ የአየር ኃይል የዘመቻ ዕቅድ መምሪያ ኃላፊ (ህወሓት)
• ኮ/ል ሰለሞን ገ/ስላሴ የማዕከላዊ አየር ምድብ ዋና አዛዥ (ህወሓት)
• ኮ/ል ፀጋዬ አርፋይኔ የማዕከላዊ አየር ምድብ ዘመቻ (ህወሓት)
• ሻምበል ገ/እግዚአብሄር ኃ/ስላሴ የምዕራብ አየር ምድብ 3ኛ ሚሳይል ክንፍ አዛዥ (ህወሓት)
• ሻምበል ዝናቡ አብርሃ የምዕራብ አየር ምድብ የ301ኛ አየር መቃወሚያ አዛዥ( ህወሓት)
• ኮ/ል ኪዱ አሰፋ የምዕራብ አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ(ህወሓት)
• ሌ/ኮ ክብሮም መሃመድ የምዕራብ አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የሎጅስቲክ ኃላፊ (ህወሓት)
• ኮ/ል ኃይሌ ለምለም የሰሜን አየር ምድብ ዋና አዛዥ (ህወሓት)
• ኮ/ል ፀጋዬ ካህሳይ የሰሜን አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የአስተዳድርና ፋይናንስ ኃላፊ (ህወሓት)
• ኮ/ል አበበ ተካ የምስራቅ አየር ምድብ ዋና አዛዥ (ህወሓት)
• ኮ/ል ሙሉ ገብሬ የምስራቅ አየር ምድብ ዘመቻ ኃላፊ (ህወሓት)
• ሻላቃ ፀጋዘዓብ ካሳ የምስራቅ አየር ምድብ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ክንፍ አዛዥ(ህወሓት)
• ሻለቃ ሀብቶም ዘነበ የምስራቅ አየር ምድብ ዘመቻ ምክትል ኃላፊ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን አብዬ ሰላም ማስከበር የስምንተኛ ታንከኛ ሻምበል አዛዥ ሻላቃ ተክላይ ወ/ገሪማ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን አብዬ ሰላም ማስከበር ምክትል የኃይል አዛዥ ብ/ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር 9ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል ጥጋቡ ተወልደ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን አብዬ ሰላም ማስከበር 10ኛ ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል ገ/ህይወት አደራ (ህወሓት)
• በደቡብ ሱዳን አብዬ ሰላም ማስከበር የ17ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል መለስ ብርሃን (ህወሓት)
• በዳርፉር የኢትዮጵያ ሰላም ማስከበር ድጋፍ ሰጭ ቡድን አስተባባሪ ኮ/ል ዮሴፍ አሮን (ህወሓት)
• በዳርፉር የ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም ማስከበር ሻለቃ አዛዥ ኮ/ል ተክላይ ወ/ጊዮርጊስ (ህወሓት )
• በዳርፉር የ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም ማስከበር ሻለቃ የዘመቻ አዛዥ ሻለቃ ሀጎስ ነጋሽ (ህወሓት )

አብዮቱና ትዝታዬ (ኮ/ል ፍሥሓ ደስታ) –ቅኝት ክንፉ አሰፋ

0
0

አዲስ መጽሃፍ – አዲስ ምስጢር

 

 

የመጽሐፉ ርእስ፣            አብዮቱና ትዝታዬ

ደራሲ፣                      ፍሥሓ ደስታ (ኮ/ል)

አሳታሚ፣                   ፀሐይ አሳታሚ ድርጅት

የገጽ ብዛት፣                 598 ገጾች

ዋጋ፣                        $44.95

 

(ቅኝት ክንፉ አሰፋ)

5786 - Satenaw
ፀሐይ አሳታሚ ድርጅት ከዚህ ቀደም ሁለት የአብዮቱ መጽሃፍቶችን አበርክቶልናል። የኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም – “ትግላችን”  እና ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ወግደረስ – እኛና አብዮቱ”  የኮ/ል ፍሥሓ ደስታ “አብዮቱና ትዝታዬ” ከቀድሞዎቹ ትንሽ ለየት ይላል። ኮ/ል ፍሥሓ ደስታ ተድበስብሶ የቆየውን የወታደራዊ መንግስት ውስጣዊ ገመና ብቻ ፈልፍለው አላቀረቡም። በአብዮቱ ሂደት ለተከሰቱ ጥፋቶች ከራሳቸው ጀምረው ተጠያቂው የሆነው ወገንን ከማመልከትም አልታቀቡም። ደራሲው ብዙ ምስጢሮችንም ያስነብቡናል።

 

መጽሃፉ ዳጎስ ያሉ ምዕራፎች ይዟል። በአምስት ክፍሎች የተመደቡ አስራ አምስት ምእራፎች ተካትተውበታል።   ከቅድመ 1966 ዓ.ም. ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ፣ በደራሲው አገላለጽ – እስከ የ”መጨረሻዋ እራት” የነበሩትን ሂደቶች በስፋት ይቃኛል።  ባጭሩ በአፄው መንግሥት ላይ የተነሱ ዓመፆችን በቀላል አማርኛ እያስነበበ የአብዮቱን አፈጣጠር፣  “የየካቲት አብዮት ከነገሌ እስከ መሿለኪያ” በሚል ምዕራፉ ያስነብበናል።  ስለ አብዮቱ ውስብስብ ሂደት፤ ስለ ነጭና ቀይ ሽብር፣ የሶማሊያ ወረራ፣ የሕወሓት እንቅስቃሴ፣ የኤርትራ ችግር፣  የግንቦት 8 መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ … በስፋት ያወጋና በመጨረሻዎቹ ምዕራፍ ግዙፉ ሠራዊት ለምን እንወደቀ ይነግረናል።

 

ጸሐፊው ኮ/ል ፍሥሓ ደስታ ከ1967-1983 ኢትዮጵያን ባስተዳደረው ወታደራዊ መንግስት እስከ ምክትል ፕሬዚዳንትነት የዘለቀ ሥልጣን ነበራቸው።  ከ1983 በኋላ ለሃያ ዓመታት በእስር ቆይተዋል።  በመጽሐፋቸው ረጅሙ የህይወት እና የሥራ ተመክሯቸውን በመንተራስ፤ በቡድን ለስላጣን ባለቤትነት ከተደረጉ ሽኩቻዎች እስከ ሀገራዊ የመሪነት ግዴታዎችን መወጣት፣ ከግድያና የጥልፍልፎሽ ሴራዎች እስከ የሥር ነቀል አዋጆች ውጥንና አተገባበር፣ ከሙያ ጓዶቻቸው ድብቅ ስብዕና እስከ የውስጥና የውጭ ጣልቃ ገብነቶች፣ የአገርን ክብርና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የተደረጉ እልህ አስጨራሽ ትግሎችና የውድቀቶቻቸው መንስኤዎች ወዘተ በስፋት ዳስሰዋል።

 

አብዮት ራስዋን እየበላች በነበረበት ሰሞን የእነ ጀነራል ተፈሪ ባንቲ የአገዳደል ሁኔታ የሚገልጸው ክፍል የአንባቢን ቀልብ ከሚስቡት ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው። ኮ/ል ፍሥሓ ደስታ ሁኔታውን በዚህ መጽሃፋቸው እንዲህ  በማለት ይተርኩታል።

 

“…ኮ/ል መንግሥቱ ጠመንጃቸውን እንዳነገቱ ብቅ ብለው በደንብ ከተመለከቱን በኋላ “ትክክል ነው” ብለው ተመለሱ። የመጡትም ቀደም ብለው ማን መቅረት ማን መገደል እንዳለበት በወሰኑት መሠረት ስህተት እንዳይፈጠር ለማረጋገጥ እንደነበር ግልፅ ነው።

 

ከጥቂት ቆይታ በኋላ መጀመሪያ ወደነበርንበት የስብሰባ አዳራሽ ተጠራን። ወደዚያ ስናመራ ኮ/ል ተስፋዬ ገብረኪዳንን “ባለፈው ጄኔራል አማን ተገደሉ አሁን ደግሞ ሥራቸውን ከሚሰሩበት ቦታ አምጥተን፣ ራሳችን ሾመን እንዴት እኒህ ሽማግሌ [ጄነራል ተፈሪ] ይገደላሉ? ስለዚህ ለመንግሥቱ እንንገራቸው” አልኩትና ተያይዘን ወደቢሯቸው ገባን። እኛም የመጣንበትን ስንነግራቸው “እውነታችሁን ነው”  በማለት የውስጥ ስልክ አንስተው ከደወሉ በኋላ መነጋገሪያውን እያስቀመጡ “አዝናለሁ ጓዶች አልቋል” ብለው ነግረውን እያዘንን ወደ ስብሰባው አመራን።  እንደገባን ኮ/ል መንግሥቱ መጥተው “ስለሁኔታው ለጦሩ ማስረዳት ስላለብኝ ኮ/ል ተስፋዬ ገብረኪዳን ከኔ ጋር እንድትሄድ” በማለት ጠየቁ። ኮ/ል ተስፋዬም “በማዛቸው ወታደሮች ፊት እጄን ሰቅዬ ወጥቼ ጦሩን ለማነጋገር ፈጽሞ ሕሊናዬ ሊቀበለው ስለማይችል አልሄድም፤ እንደውም ወደክፍሌ እመለሳለሁ” አለ። እኔም “ከእንግዲህ በዚህ ዓይነት እዚህ ግቢ ለመሥራት ፍላጐት የለኝም እኔም እንደተስፋዬ ወደክፍሌ መመለስ እፈልጋለሁ” አልኩ። መንግሥቱም ሽጉጣቸውን በማውጣት “ይህን እርምጃ ባልወስድ ኑሮ ሁላችንም  አልቀን ነበር፤ በድያችሁ ከሆነ ግን ግደሉኝ” በማለት ሽጉጡን ጠረጴዛው ላይ ወረወሩት…”

 

በወቅቱ ከነበሩት ሁለቱ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች፤ በኢሕአፓ እና በመኢሶን ላይ ጸሃፊው የሰጡት አስተያየት ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም እና ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ወግደረስ ካስነበቡን ትንሽ ለየት ይላል። ኮ/ል ፍሰሃ፤  የሁሉንም ፓርቲዎች ብቃት ያወድሳሉ፣ የአመራሩን ችግሮች ደግሞ ይወቅሳሉ። እንዲህ በማለት፣

 

“…የኢሕአፓ ቆራጥነት፣ የመኢሶን የርዕዮተ-ዓለም ብስለትና የደርግ ሀገር ወዳድነት ተጣምሮ አገሪቱን ወደ ላቀ ደረጃ ሊያደርስ ይችል የነበረ ኃይል በአመራሮቹ ስህተት ያለአግባብ እርስ በርሱ ተጨራርሷል።”

 

ደራሲው በወታደራዊው መንግስት አመራሩ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወቱ የነበሩ በመሆናቸው በወቅቱ በነበሩ ስህተቶች ከሃላፊነት ነጻ ያለመሆናቸውንም እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል።

 

“… ኢትዮጵያ ትቅደም! ያለምንም ደም!’ ብለን በተነሣን ማግሥት… እነዚያ ለሀገራቸው የለፉትንና የደከሙትን አዛውንቶች መጦር ስንችል ገደልናቸው።”

 

ይህንን መጽሃፍ ከቀድሞዎቹ የአብዮቱ መጽሃፍት ለየት የሚያደርገው ደራሲው እንደ ጲላጦስ ከደሙ ነጻ ለመሆን የሌሎቹን ጥፋቶች ብቻ እየኮነኑ የጻፉት አለመሆኑ ነው። ራሳቸውን ከመውቀስ፣ ይቅርታ እስከመጠየቅ መድረሳቸው ደግሞ ከወገንተኝነት የራቁ መሆነቸውን ያሳየናል። ለዚህም ነው “… በማወቅ፣ በድፍረት፣ ባለማወቅና በስህተት ለተፈጸሙት ደግሞ ሙሉ ሃላፊነትን በመውሰድ በበኩሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።…” ያሉት።

 

ከመጽሐፉ ድንቅ ትረካዎች መካከል የተወሰኑት ማቅረቡ ሰለ መስጽሃፉ ለአንባብያን ፍንጭ ሊሰጡ ይችላሉ።  አንዳንዶቹ መረጃዎች ከዚህ ቀድመው አልተሰሙም። ፍጹም አዲስ ናቸው። ለምሳሌ የፓትሪያርኩን ማምለጥ በተመለከተ ከዚህ ቀደም የሰማነው ነገር አልነበረም። መጽሃፉ እንዲህ ይላል፣

 

… ፓትርያርኩ እንደሌሎቹ እስረኞች ሳይሆን ብሔራዊ ቤተመንግሥት በሚገኘው የአድሚራል እስክንድር መኖሪያ ቤት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደረገ። በታሰሩ በጥቂት ቀናት ግን ጠባቂዎቻቸው መነኩሴ ስለሆኑ የትም አይሄዱም ብለው ሲዝናኑ ቆባቸውን አውልቀው፣ ጺማቸውን ተላጭተውና ልብሳቸውን ለውጠው በግዮን ሆቴል በኩል ወጥተው ጠፉ። መጥፋታቸው እንደተነገረም በደርግ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጠረ። …

 

ደርግ በዓሉን በሚያከብርበት ወቅት የወቅቱ የደርጉ ሊቀመንበር ጀ/ል ተፈሪ ባንቴ በአብዮት አደባባይ ንግግር አድርገው ነበር። በንግግራቸውም ለኢሕአፓ ጥሪ አድርገዋል።  አብዮት አደባባይ የነበረው አከባበር እንዳለቀ የሕዝብ ድርጅት አባላት ኮ/ል መንግስቱን  እንዴ እንዳዋከቡዋቸው ሲጽፉ፣

 

…የሕዝብ ድርጅት አባላት መስፍን ካሡ፣ ነገደ ጐበዜ፣ እንዳርጋቸው አሰግድ፣ ሰናይ ልኬ እና ሌሎችም ወደተቀመጥንበት ቦታ እያለከለኩና እየሮጡ መጡ፤ ኃይሌ ፊዳም ተከተለ። ምነው ጓድ መንግሥቱ እርስዎን አምነን ተሰብስበን ኢሕአፓ አየገደለን አላስጣላችሁን፤ ይባስ ብላችሁ ደግሞ እኛን የበለጠ ለማስመታት ለኢሕአፓ ጥሪ እንዴት ታደርጋላችሁ ብለው ከግራ ከቀኝ ያዋክቧቸው ጀመር። መንግሥቱም አንዴ ይቅርታ አድርግልኝ ብለው  ኃይሌ ፊዳንና የተቀሩትን ይዘው ቡና ቤት ውስጥ ወደምትገኘው አነስተኛ ሣሎን ገቡ። በዚያች ቀንና ሰዓት መንግሥቱ የተነጠቁትን ስልጣን ለማስመለስ መኢሶን ደግሞ ኢሕአፓን በማስመታት ለሥልጣን መንገዱን ለመጥረግ ሴራ ሳይጠነሰስ አልቀረም።…

 

ቀይ ሽብርን መኢሶኖች እንደጀመሩት እና የጀመሩትም ከኢሕአፓ ነጭ ሽብርና ግድያ ራሳቸውን ለመከላከል እንደሆነ ጽፈዋል። ‘ብሳና ይነቅዛል ወይ ቢሉት ለዛፎች ሁሉ ማን አስተማረና’ እንደተባለው በአብዮቱ ሰፈር ደግሞ ቀይ ሽብር የሚለውን መፈክር በቲዎሪም በተግባርም ለደርግ ያስጨበጠው መኢሶን መሆኑ አገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ሀቅ በመሆኑ ቃላትን በማውገርገርና ነገሮችን በማድበስበስ ከዚህ የታሪክ እውነታ ለማምለጥ መሞከር ትርፋ ትዝብት ነው።…’ ይላል።

 

ይህንን በመኢሶኖች ተጀመረ ያሉትን ቀይ ሽብር ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም እንዳስቆሙት “አብዮቱና ትዝታዬ” ይነግረናል። እንዲህ ሲል፣

 

… መንግሥቱ ፊታቸው ተለዋወጠ። “ግድየለም እኔ መንግሥቱ ብቻዬን አስቆመዋለሁ፤ ከእንግዲህ እኔ ሳላውቅና ሳልፈቅድ አንድም ሰው አይገደልም” በማለት ከስብሰባው ወጥተው አንድ ሁለቴ ሲጋራቸውን አቦነኑና ወደ ቢሮአቸው ሄዱ። እውነትም እንዳሉት ከመጋቢት 30፣ 1970 ጀምሮ ቀይ ሽብርም ሆነ ነፃ እርምጃ ቆመ። ኮ/ል መንግሥቱ ይህንን ማድረግ የቻሉት በኢማሌዲህ ሥራ አስፈጻሚ  ሰብሳቢነታቸው እንዲሁም በርዕስ መንግሥትና የርዕሰ ብሔር ሥልጣናቸው ተጠቅመው እንደሆነ ግልፅ ነው። ዛሬ አንዳንዶች ሊመፃደቁ አንደሚሞክሩት ሳይሆን ቀይ ሽብርን ሊያስቆም የሚችል ከሳቸው ውጭ አንዳችም ኃይል አልነበረም።…

 

መጽሃፉ እንዲህ እያለ የአስራ ስባት አመቱን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሂደት በአዳዲስና አስገራሚ መረጃቆች እያዋዛ እስከመጨረሻዋ ሰዓት ያዘልቀናል። የመጨረሻዋ እራት በምትለው ምእራፍ ኮሎኔል መንግስቱ በሚስጥር የያዙትን ስንብትና ከሃገር ጥለው የመሄድ ምስጢር፣

34757 - Satenaw

… ግንቦት 10፣ 1983  ቅዳሜ ማታ በጡረታ የተገለልነውን፣ በአዲሱ ካቢኔ ያልተካተቱት፣ እንደዚሁም አዲስ የተሾሙት በተገኙበት በፕሬዚደንቱ መኖሪያ ቤት ለኛ መሸኛ ለአዲሶቹ መቀበያ የእራት ግብዣ ተደረገ። … በዚህ ግብዣ ላይ ከወትሮው በተለየ የታዘብኩት ቢኖር ፕሬዚደንቱ አምቦ ውሃ ብቻ ሲጠጡ ስላየኋቸው ለምን እንደማይጠጡ ስጠይቃቸው ጤንነት ያልተሰማቸው መሆኑን ገለፁልኝ። ወደኋላ ተመልሸ ሳስበው ግን ሆድ ያባውን ብቅል ስለሚያወጣው አገር ጥለው ስለመሄዳቸው ሚስጢር እንዳያመልጥ ለጥንቃቄ ያደረጉት ነበር። ግብዣው እንዳለቀ ቤታቸው በራፍ ላይ ቆመው አንድ በአንድ እየጨበጡ አሰናበቱን። ዳግም ላንገናኝ የመጨረሻዋን እራት በልተን ተለያየን።…

 

ሲሉ ገልጸዋል።

 

የኢትዮጵያ አብዮት ሰፊና ውስብስብ የነበረ ቢሆንም በግላቸው ተካፋይ የነበሩበትን፣ በዓይናቸው ያዩትንና በማስረጃ ያረጋገጧቸውን እውነታዎች በተቻለ መጠን ከወገናዊነት በፀዳ መልኩ በዚህ መጽሐፍ ለማቅረብ ሞክረዋለሁ።

 

ጸሃፊው የታሪክ ባለሞያ አይደሉም። ታሪክን፤ በተለይ ባለሙያ ያልሆኑ ሰዎች ሲጽፉ ወገንተኝነት ጉዳይ መነሳቱ አይቀርም።   ከሰው ስህተት አይጠፋምና መጽሐፉን በሚገባ አንብበው በጭፍን ሳይሆን በገምቢ መልኩ የሚሰጡትን ማንኛውን ምአስተያየትና ሂስ ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውንም ኮ/ል ፍሰሃ በመግቢያው ላይ ገልጸዋል።

 

ጸሃይ አሳታሚ ድርጅት በኢትዮጵያ ጥንታዊ እና ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ጉዳዮች ላይ በርከት ያሉ መጽሃፍት እያሳተመ ለአንባብያን እያቀረበ ይገኛል። ይህም የታሪክ ቅርስን እየጣለልን የሚያልፍ ስራ ነው።   ሊበረታታም ይገባዋል። እነሆ ዛሬም “አብዮቱና ትዝታዬ”  ጀባ ብሎናል። ግንዛቤ ለመግኘት ያንብቡ – መጽሃፉ መተቸት ካለበትም ይተቹ። …  በመጀመርያ ግን ያንብቡ!  መልካም ንባብ!

 

ቋንቋ መግባቢያ ነው ፤ ከዚያ ዉጭ ማየት ዘረኝነት ነው –ግርማ ካሳ

0
0

Language - Satenawአንድ የማደንቃቸው የአማርኛ አስተማሪ ነበሩኝ። ከሰባት ቤት ጉራጌ ስለነበሩ ጉራጌኛ ይናገራሉ። ብዙ አመት ሰሜን ስለኖሩም ትግሪኛ ለምደዋል። እንግሊዘኛን ስትጨምሩበት አራት ቋንቋዎች መሆናቸው ነው። አንድ የማውቃት ነርስ አለች። ከወላይታ ብሄረሰብ ናት። ይርጋለም አድጋ ሲዳምኛ ትናገራለች። ባል አግብታ ወደ አርሲ አካባቢ ለብዙ አመት ኖራለች፡ ከዚያም የተነሳ አካም ቡልቴም ትላለች። (እንግዳ የሆነውን ቁቤ ማንበብ አትችልም እንጂ) ለአንድ ስምንት አመት አስመራ መካነ ሕይወት ሆስፒታል ሰርታለች። ትግሪኛን እዚያ ለመደች። እንግሊዘኛን ስትጨምር ስድስት ቋንቋዎች መሆናቸው ነው።

ቋንቋ መግባቢያ ነው። ቋንቋ ማወቅ መቼም ቢሆን የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ አይደለም። ታዲያ በአገራችን ቋንቋንን የጠብና የመከፋፈያ መጠቀሚይ ብዙዎች ሲያደርጉት እየታዘብን ነው። በተለይም በአክራሪ ኦሮሞ ብሄረተኞች ዘንድ። አንዳንዶች ሌሎች አፋን ኦሮም እንዲማሩ ከማበረታታት ይልቅ፣ ለምን አማርኛ ይነገራል ይላሉ። ለኦሮምኛ አለማደግ አማርኛን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ከዚህም የተነሳ አማርኛን ይጸየፋሉ። አማርኛን ማየት አይፈልጉም። ትግላቸው ኦሮሞ የሚሉትን ማኅበረሰብ ለመጥቀም ሳይሆን፣ ጸረ-አማርኛ ትግል ነው።

በኦሮሚያ ለምሳሌ በብዙ ቦታዎች( ከአዳማ አካባቢ በስተቀር ፣ (እርሱም ሕዝቡ ተቃዉሞ ስላሰማ) የአማርኛ ትምህርት አይሰጥም። ለምን አማርኛ እንደ ጠላት ቋንቋ ስለሚታይ። ከዚህም የተነሳ ብዙ የኦሮሞ ልጆች በተቀረው የኢትዮጵያ ክልሎች ሥራ የማግኘት እድል የላቸውም። ይሄ ትልቅ በደልና የኢኮኖሚክ ግፍ ነው። ኦሮሞው ከሌላው ማህበረሰብ ሥራ የምግኘት፣ በኢኮኖሚ የመሽሻል እንድል በጣም ያነሰ ነው የሆነበት።

በጣም የሚያሳዝነውና የሚያሳፍረው ደግሞ ኦሮሞው አማርኛ መማር እንደሌለበትና በኦሮሚያ አማርኛ የሥራ ቋውንቋ መሆን እንዳለበት የሚነገሩን፣ የኦሮሞ ልሂቃን፣ እነርሱ ግን ልጆቻቸውን በአዲስ አበባ፣ በአዳማ ምርጥ ትምህርት ቤቶች ነው አማርኛ በደንብ አውቀው እንዲማሩ የሚያደርጉት። አንድ የኦሮሚያ ዳኛ የነበረ ሰው አሉ፣ የኦሮሞ ድህረ ገፆች ላይ የሚጽፉ። አዳማ ነበር የሚኖሩት። “ልጆችዎት አማርኛ መጻፍና ማንበብ ይችላሉ ወይ ?” ብዬ ጠየቅኳቸው። “”አማርኛ ብቻ ሳይሆን አፋን ኦሮሞ በደንብ መጻፍና ማንበበ ይችላሉ” አሉኝ። “ታዲያ የርስዎ ልጆች ያገኙትን እድል ለምን ሌላው ከአዳማ ውጭ ያለው ኦሮሞ ይነፈጋል ? ምን ችገ አለው አማርኛም ኦሮሞኛ ሁለቱም ትምህርት ቢሰጥ ? ” ብዬ ጠየኩ። እኝህ ዳኛ መልስ አልመለሱልኝም። ለብዙ አመታት የኦህደድ መሪ የነበሩት አባ ዱላ፣ ልጆቻቸዉን ያስተማሩት በዝነኛው የቅድሱ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ነው እንደሆን ነው የሚነገረው። ሌሎች የኦህዴድና ተቃዋሚ ነን የሚሉ የኦፌኮ አመራሮች ልጆችን ብትመለከቱ አብዛኞቹ የሚማሩት በቅዱስ ዩሴፍ፣ በሳንፈርድ፣ በባይብል አካዳሚ፣ በሊሴ ገበረማሪይም በመሳሰሉት ት/ቤቶች ነው። ይሄን ምን ትሉታላላችሁ?

በኦሮሚያ የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ብቻ ነው። ለምሳሌ በአዳማ ሰማኒያ በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ኦሮሞ ያልሆነ ቢሆንም፣ የናዝሬት ማዘጋጃ ቤት ግን የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ነው። ይሄ ኢፍትሃዊና ጸረ-ዲሞክራሲያዊነት አይደለምምን ? ያው አዳማ፣ ከመንግስት መስሪያ ቤት ዉጭ ሌሎች መስሪያ ቤቶች በሙሉ የሚሰሩት በአማርኛ ስለሆነ ፣ አዳምም ከአዲስ አበባ ጋር ከመቼዉም ጊዜ በላይ እየተገጣጠመች በመገጣጠሟ ችግሩ ከፍቶ በጣም አልታየም። በሌሎች የኦሮሞያ ቦታዎች ግን ያለው ሁኔታ በጣም ይሳዝናል። ኦሮሞኛ የማይነገረው ማህበረሰብ ፣ ንብረቱን፣ ገንዘቡን ይዞ ከአብዛኛዎ ኦሮሚያ እየሸሸ ፣ አዲስ አበባ አካባቢ እንደ አዋሳ ባሉ ቦታዎች እየተከማቸ ነው። ግድ የለም ብሎ የቆየውምም በሃይል መሬትህ አይደለም ተብሎ ይፈናቀላል። (እስቲ እግዜር ያሳያችሁ ፣ ለመኖር ወይንም ለመዝናናት አይደለም ፣ እየነዱ እንኳን ለማለፍ የተቆረጠ ጡት የሚመስለው የጥላቻ ሐዉልት የቆመበት፣ የአርሲ አካባቢ ማን ነው የሚሄደው?) በኦሮሚይአ ኢንቨስት ለማድረግ፣ ለመኖር፣ ለመዝናናት ፣ ለመጎብኘት የሚፈልግ ሰው የለም። ያ ደግሞ ሕዝቡን የበለጠ አይዞሌት ከማድረጉ የተነሳ፣ የበለጠ ወደ ኋላ እንዲቀር ነው ያደረገው። ከሌሎች ጋር ንግድ፣ ትስስር ከሌለ፣ የኦሮሞው ማህበረሰብ ራሱን አግሎ ከተቀመጠ, ከምንም በላይ የሚጎዳው ራሱን ነው። ለዚህ ደግሞ ተጠያቂዎችቹ የኦሮሞ ልሂቃን ናቸው። ይሄ መስረታዊ የሕዝብን የኢኮኖሚ ችግር አለማየታቸው በአፍ እንጂ በተግባር ለኦሮሞው እንዳልቆሙ የሚያሳይ ነው።

እስቲ አዋስን እና መቱን ወይንም ነቅምቴን አወዳድሮ። በደርግ ጊዜ ነቀምቴ የወርቅ አገር የወለጋ ዋና ከተማ፣ እንደመቀሌ ካሉ የትናየት የምትበልጥ ነበረች። አሁን ነቀምቴ አቧራ ብቻ ናት። ወድቃለች። ሞታለች። በኢሊባቡር ብዙ ለቱሩስት የሚሆኑ፣ ፏፏቴዎች፣ ወንዞች አሉ። በዚያ ሆቴል ቤቶችን ሪዞርቶች ቢገነቡ ብዙ ሰው ሊስቡ ይችሉ ነበር። ግን ማንም ወደዚያ አይሄድም። ፖለቲካው፣ ዘረኝነቱ፣ አፋን ኦሮሞ ብቻ ወይም ሞት የሚለው አመለካከት፣ ብዙዎችን አፋን ኦሮሞ የማይናገሩት እያራቀ ነው።

ታዲያ የኦሮሞ ልሂቃን ለምን የኦሮሞ ማህበሰብ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን፣ ኑሮዉን እንዲቀይር የሚረዱትን ፖሊሲዎች አያስቀምጡም? ለምንድን ነው ሁልጊዜ የነርሱ አጀንዳ ቋንቋ ብቻ የሚሆንው ? ለምንድን ነው አሁንም አይምሯቸው በጥላቻ የሚበረዘውው ? ምን ችግር ነበረው፣ ኦሮሞ፣ አማራ፣ አፋን ኦሮሞ፣ አማርኛ ከምንባባል፣ አማርኛም የኔ ነው፣ አፋን ኦሮሞም የኔ ነው። ብለን ሁለቱንም ቋንቋ ብንማር፣ በሁለቱም ቋንቋ ብንሰራ ? እንዴት ቋንቋን በመካከላችን ልዩነት እንዲኖር ምክንያት አድርገን እንጠቀምበታለን ?

አፋን ኦሮሞ የኢትዮጵያ ቅርስ ነው። ዜጎች፣ ከኦሮሚያም ዉጭ ያሉም ሳይቀር፣ ሊማሩትና ሊናገሩት ይገባል። ያንን የሚያበረታታ ሐሳቦችና ፖሊሲዎች መቀመጥ አለባቸው። እንዴት አፋን ኦሮሞን እናስፋፋለን ብለን ከጥላቻ በጸዳ መልኩ መነጋገር እንችላለን። ግን አፋን ኦሮሞ እንዲያድግ አማርኛ ይጥፋ፣ አማርኛ አይነገር፣ የሚለው ግን ዘረኝነት ነው። ጠባብነት ነው። በሽታ ነው። ይህ አይነቱ አስትተሳሰብን መታገሥ ሳይሆን እንዲሸነፍ ማድረግ ነው ያለብን።

(በሚቀጥለው ጽሁፍ አክራሪ የኦሮሞ ልሂቃን፣ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ለምን እንደሚቃወሙ አንዳንድ ሐሳብ እሰጣለሁ ለኦሮሞው ጥቅም ብለው ሳይሆን ፣ አሁን ያለው ኦነግ የቀረጸውና ሕወሃት ኦነጎችን ለማስደሰትት ያስቀመጠው ኦሮሚያ የሚለው ክልል ሊከፈል ነው፣ ወደፊት ደግሞ ኦሮሚያ ሪፑብሊክ የማየት እድል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊጠፋ ነው ብለው ነው። ነገር ግን በሜዳ ያለው ዴሞግራፊክ እዉነታ የሚያሳየው ኦሮሚያ የሚባለው ሊቀጥል እንደማይችል ነው። ዘጠኝ ሚሊዮን የሚሆነው የአዲስ አበባ ህዝብን ጬምሮ፣እስከ አምቦ፣ ወሊሦ፣ ቡታጅራ፣ አዳማ፣ ፍቼና ደብረ ብርሃን ድረስ ያለው ግዛት ፣ ከአዲስ አበባ ጋር ባለው ትስስር፣ ሕብረ ብሄራዊ (ኮስሞፖሊታን) ይዘት ያለው እየሆነ ነው። በመንግስት ባይታወጅም በተግባር ግን የራሱ ክልል እየሆን ነው። ያንን ደግሞ ጊምቢናና ደምቢደሎ ውይንም ሜኔሶታ ያሉ አክራሪ ኦሮሞዎች ሊለዉጡት አይችሉም። ጥያቄዎች ቀርበው ሕዝቡ እንዲመርጥ ከተደረገ፣ ህዝቡ በኦሮሚያ ሥር ሳይሆን የራሱ ክልል እንዲኖር እንደሚፈልግ፣ ራሳቸውው የኦሮሞ ልሂቃን የሚያውቁት ነገር ነው)

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት በቦታው ይመለስ –አፈንዲ ሙተኪይ

0
0
12036507_901350993264225_2577506944876999080_nአዎን! በሌሎች ጉዳዮች ላይ ልዩነት ሊኖረን ይችላል፡፡ በሰማእቱ አቡነ ጴጥሮስ ታሪክ ላይ ግን ተመሳሳይ ወይንም ተቀራራቢ አመለካከት ነው ያለን፡፡ ለሳቸው የተገነባው ሐውልትም ለክብራቸው ተገቢ ነው ብለን እናምናለን፡፡

አቡነ ጴጥሮስ ህዝብ ያስመረሩ ሀገረ-ገዥ አልነበሩም፡፡ “ዓለም ለምኔ” ብለው ከአዱኛ ኑሮ ተገልለው በምንኩስና ህይወታቸውን ሲገፉ የነበሩ ሰው ናቸው፡፡ በዚሁ በምንኩስና ኑሮአቸው እያሉ ነው በብቃታቸውና በምግባራቸው ተመርጠው ለመጀመሪያ ጊዜ ጳጳስ ተብለው ከተሾሙት ስድስት ኢትዮጵያዊ መነኮሳት መካከል አንዱ የመሆንን ክብር ያገኙት፡፡ ወራሪው የኢጣሊያ ጦር ደግሞ ህዝቡ ለጌታ ሙሶሊኒ እንዲያድር ጥሪ እንዲያቀርቡ ቢነግራቸው “በጭራሽ አላደርገውም! እንዲያውም ላንተ ለወራሪው የተገዛውን ሁሉ ገዝቼዋለሁ” በማለት ጀግንነት የተመላበት መልስ ሰጡት፡፡ በዚህም የተነሳ በመትረየስ ጥይት ተደብድበው ተገደሉ፡፡ ሆኖም የሳቸው መስዋዕትነት በዱር ለነበሩት ጀግኖች የሞራል ስንቅ ሆኖላቸው ትግላቸውን ይበልጥ አጠናከሩ፡፡ ጣሊያን ተባሮ ከወጣ በኋላ ደግሞ ገድላቸው ገዝፎ በመገኘቱ ሃውልቱ ተሰራላቸው፡፡ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህንም “ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት” የተሰኘውን ምርጥ ቴአትር ጻፈላቸው፡፡ ይገባቸዋል!!

በነገራችን ላይ የኤርትራው ኢሳያስ አፈወርቂ የአቡነ ጴጥሮስን ጀግንነት አድንቆላቸው እንደነበረ ታውቃላችሁን! አዎን! የደርግ ማስታወቂያ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ገሥጥ ተጫኔ “ነበር” በተሰኘው ተወዳጅ መጽሐፋቸው ውስጥ እንዳወጉን የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ (ሻዕቢያ) ተዋጊዎች ከመንግሥት ጋር እንዲደራደሩ ለማግባባት የኤርትራ ተወላጅ በነበሩት አቡነ ፊሊጶስ መሪነት መቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ እና ፊታውራሪ አመዴ ለማ የታቀፉበት የሽማግሌዎች ቡድን ወደ ኤርትራ በረሃ ተልኮ ነበር፡፡ የሰላም ቡድኑ ብጻይ ኢሳይያስ አፍወርቂን ከቀይ ባህር ብዙም በማትርቀው “ሸዒብ” ከተማ አቅራቢያ አግኝቶ ሊያናግራቸው ሲሞክር ግን ብጻይ ኢሳያስ አቡነ ፊሊጶስን እንዲህ አላቸው፡፡

“አንተ ሆዳም መነኩሴ!! የሸዋው አቡነ ጴጥሮስ ለጣሊያን አትገዙ ብሎ ወራሪዎቹን አውግዞ በጀግንነት ሞተ፡፡ አንተ ግን እኛን ከድተህ የሰላም ድርድር የሚል ማታለያ ይዘህ እጃችሁን ስጡ ልትለን መጣህ!! አሁን በመጣህበት እግርህ ተመለስ”

የብጻይ ኢሳያስ አነጋገር ለሽማግሌ (ለዚያውም ለመነኩሴ) የማይገባ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ኢሳያስ አቡነ ጴጥሮስን ምሳሌ ማድረጉ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት መሪዎቻችን ለአቡነ ጴጥሮስ ገድል ያላቸው አድናቆት ከኢሳያስ አድናቆት ያንሳያል ተብሎ አይጠበቅም፡፡
—-
ለእኚህ ብዙ ለተነገረላቸውና ብዙ ለተጻፈላቸው ሰማእት አቡን የተሰራው ሃውልት በባቡሩ መስመር ግንባታ ምክንያት ተነስቶ ነበር፡፡ ባቡሩ ተሰርቶ አገልግሎት የጀመረ በመሆኑ የአቡኑ ሐውልት በነበረበት ቦታ መመለስ ይገባዋል፡፡ የደጎል፤ የማርክስ፣ የፑሽኪን፣ የቦብ ማርሊ ወዘተ… ሃውልት በአደባባይ ላይ እንዲቆም እየተፈቀደ የጴጥሮስ ሃውልት የሚነቀልበት ምክንያት ሊኖር አይችልም፡፡ አራት ነጥብ!!

የአሁኑ የኢትዮጵያ ወጣቶች ትግል

0
0

ከአቻምየለህ ታምሩ

የኛ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ሕልም የሆነ ታላቅ ግብ አለ። ይህም ግብ ምድራዊ ገነትን ፈጥሮ የሰው ልጆች ከችግር፣ ከበሽታና ከድንቁርና ነጻ ወጥተው፤ ወንጀል፣ እስራት፣ ጭቆና፣ ግፍና የኑሮ ጭንቀት ተረስተው የሰው ልጆች በፍቅርና በደስታ እንዲኖሩ ለማድረግ መጣጣር ነው። ብዙ ሀገሮችም ከዚያ ገነት በመጠኑ ቀረብ ብለው አሁንም እርምጃቸውን እያፋጠኑ ወደዚያው ጨርሶ ለመግባት በመገስገስ ላይ ናቸው። በወያኔዋ ኢትዮጵያ የምንኖር እኛ ገባሮች ግን ከሁሉ በተለየ ሁናቴ ተፈርዶብን ከትግራይ በበቀለው አጥፊያችን የወያኔ ዘረኛ ቡድን ምክንያት ከገነቱ ቀርቶ ከመካነ-ንስሐው ሳንደርስ ገና በሲኦል ውስጥ ሁነን ስንሠቃይ እንገኛለን።

Tensaye

በሥልጣኔ ወደፊት ከገፉት አገሮች ጥቂቶችንም ሆነ ብዙዎችን የምዕራቦችንም ሆነ የምስራቆችን ያየ አንድ ያገሬ ልጅ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ሰው ነው የሚኖረው ብሎ ማመን እጅግ ያስቸግረዋል። እኛ ኢትዮጵያን የምንኖረው ወያኔ ባበጀልን በቁም መቃብራችን ውስጥ ነው። ይህም የሆነው አባቶቻችን የሰሯትን አገር ልጆቻቸው ተረክበው እንዳባቶቻችን ወደፊት በማየት ለመጪው ትውልድ የሚሆን አገር መፍጠር ባለመቻላቸው ነው። ወደድንም ጠላንም ዛሬ ያለችው ልዩነትና ጥላቻን መሰረት ያደረገ የክልልና የፖለቲካ አገዛዝ የተንሰራፋባት፤ የጎሳ ድንበሮችን በማጠናከር የተወናከረ መንግስታዊ ስርዓት ላይ የተፈጠረችዋ «አዲሲቷ» ኢትዮጵያ በዚህ መልኩ እንዳለች ከቀጠለች ከመቶ አመት በኋላ ዛሬ የተፈጠሩት ተፎካካሪ ብሔረሰቦች [Rival Ethnic Nationalities] ርስ በራስ እየተከሳከሱ ሞትን ያነግሱና እያንዳንዳችን ከምድረ ገጽ ጠፍተን፤ «በኢትዮጵያ» ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ መቃብር ብቻ ይሆናል። ስለሆነም ዛሬ የኛ የኢትዮጵያ ወጣቶች የመጀመሪያው ተግባራችን መሆን ያለበት ከምንኖርበት የቁም መቃብራችን መግነዛችንን ቀዳደንና በጣጥሰን የተጫነብንን የመቃብር ድንጋይና አፈር ፈነቃቅለን ወደ ብርሀን ዓለም የምንወጣበትን ከጥላቻ የጸዳችን የራሳችንን አገር መፍጠር ይሆናል። ይህንን ከግብ ለማድረስ በቅድሚያ የምንፈጥረው ዋናው ኃይላችን «በመወያት የተሠወረው ይገለጣል፤ የጠመመው ይቀናል እንዲሉ አበው» እኛ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በቅዱስ መንፈስ ተነሳስተን፤ ፍርሀትና አለመተማመንን አስወግደን በጋራ ችግሮቻቸው ዙሪያ እንደ አዲስ በፌስቡክና በትዊተር ዛሬዉኑ የምንቀሰቅሰው ውይይት ነው። ይሄ የምንጀምረው ውይይት የተባበረ ክንድና የጋራ ኃይል ለመፍጠር መሰረት የምንጥልበት የተባበረ ኃይላችን ነው።

ከዚያም በተባበረ ኃይላችን የራሳችንን አገር ገነት ለማድረግ ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን። በቆራጥነትም እንራመዳለን። በምንፈጥረው ገነት እኛ አሁን ያለነው ሰዎች ገብተን ልንንቧች መጓጓት የለብንም። ለዚህ ብንታደል ኖሮ አባቶቻችን እኛ እያጋጠመን ያለውን ችግርና መከራ በሙሉ ጨርሰው አስወግደውት አሁን የምንኖባት «አገራችን» ዕድልና ድል ሞልቶ የተረፈባት ምድር ትሆን ነበር። እኛ ለዚህ አልተመደብንም፤ አምላክ እኛን የመደበን «እኔ ከሞትሁ ሰርዶ አይብቀል» ያለችውን የአህዮች ፈላስፋ ትምህርትና «ከራስ በላይ ንፋስ» የሚለውን የበሰበሰ የምሳሌ አነጋገር ከወደቀው የኑሮ ስርዓታችን ጋር ደምስሰን «እያንዳንዱ ትውልድ አለምን እሱ በተረከበባት ጊዜ ከነበረችበት ሁኔታ እጅግ የተሻለ አድርጎ ለተተኪው ትውልድ የማስረከብ ኃላፊነት አለበት።» የሚለውንና ብዙ ፈላስፎች የተስማሙበትን ቁም ነገር ፈጽመን አንድ የተሻለችና በእውነት የታደሰች የኢትዮጵያ ልጆች አገር ለትውልዳችን ለማስረከብ ነው። ወያኔ እዚህ ላቀረብሁት አይነት የኢትዮጵያ መፍትሔ ሊሆን አይችልም። ወያኔ አገርን በመዝረፍና ድሀን በመቀማት በጥቅም ጆሮው ስለተዳፈነ ስለኢትዮጵያ መጻኢ እድል የሚበጅን ቅን ሀሳብ መስማት አይችልም።

ከዚህ ላይ በታላቅ ምሳሌነቱ የማንኛውም አገር ሰው የሚጠቅሰውን የአንድ የዓረብ ሽማግሌ ታሪክ ልጠቅሰው እፈልጋለሁ። ታሪኩም የሚከተለው ነው። ዘጠና አመት እድሜ የነበረው አንድ ዓረባዊ ሽማግሌ በጓሮው የተምር ዛፍ ችግኞች በትጋት ይተክላል። አንድ መንገደኛ ይህን ስራ ሲያይ በነገሩ ይደነቅና መንገዱን አቋርጦ ወደ ሠራተኛው ሽማግሌ ሔዶ «በዚህ የርጅና ዘመንህ በማረፍ ፈንታ እነዚህን የተምር ችግኞች በመትከል የምትደክመው መቼ ደርሰውልህ ልትጠቀምባቸው ነው?» ይለዋል። ሽማግሌውም በመንገደኛው ሰውዬ ሞኝነት ስቆ «እኔ ስበላ የኖርሁት ተምር እኔ ሳልሆን አያት ቅድመ አያቶቼ የተከሉት ነው። ከነሱ የወሰድኩትን ዕዳም ለልጅ ልጆቼ መክፈል ስላለብኝ ለነርሱ እተክልላቸዋለሁ» ሲል መለሰ ይባላል።

ሽማግሌው እንዳለው ሁሉ የሰው ጠቅላላ ህይዎት በማያቋርጥ ረጅም ገመድ የተቀጣጠለ በመሆኑ አንድ ትውልድ ላለፉት ትውልዶች ባለ ዕዳ እንደመሆኑ መጠን ለሚተካው ትውልድ አሳሳቢ የሆነ የውለታ ዕዳ ትቶ ማለፍ አለበት። በተለይም እንደኛው ቅድመ አያቶች በሀገሩ ያገኘው ጥቅም ለሀገሩ ካፈሰሰው ላብና ደም በምንም የማይመጣጠን የሆነ ብዙ ስለሌለ ያባቶቻችን ባለዕዳዎች ነን። በዚህ ካላመንና ልክ እንደ ወያኔዎች «የኔ ዕለተ-ምጽዓት እኔ የምሞትበት ዕለት ነው» እያልን ራሳችንን ብቻ የምንወድ ከሆነ በሕይዎት ያለው ምስኪን ኢትዮጵያዊ ወያኔ ህጋዊ ባደረገው የጥላቻ ማንነቶች አጥር ሰርቶ የጋራ ትውስታውን በማጥፋት ርስ በርስ እየተከሳከሰ ጨርሶ ከምድረ ገጽ እስኪጠፋ ድረስ የኢትዮጵያ ምድር የድኩማን፣ የለማኞች፣ የረኃብተኞችና የደንቆሮዎች ሲሆን፤ በሌላም በኩል ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ያቀኗትና አረመኔው ወያኔ የኢትዮጵያውያን የመቃብር ዋሻ ያደረጋት ምድረ ደግሞ የጨቋኞች፣ የዘራፊዎች፣ የቀማኞች፣ የወንጀለኞች አገር እንደሆነች ትቆያለች።

እኛ የዛሬዎቹ የኢትዮጵያ ልጆች ይህንን ጠንቅቀን ተረድተን ለኢትዮጵያ አገራችን ካልደረስንና የህዝባችንን የወደፊት አገር ካላቀናን፤ በተቀነባበረ እቅድ ድኩማን፣ ለማኞች፣ ረኃብተኞችና ደንቆሮዎች ሆነው በወያኔ ጨቋኞች፣ ዘራፊዎች፣ ቀማኞችና ወንጀለኞች ፍዳቸውን እያዩ ኖረው እንዲጠፉ የምንፈርድባቸው ዛሬ የምንወልዳቸውና ከራሳችን በላይ እንወዳቸዋለን የምንላቸው የያንዳንዳችን ልጆች ይሆናሉ። ለየራሳችን ልጆች ደኅንነት ብቻ እንጥራለን ብለን ራሳችንን ብናሞኝ ደግሞ አንድ አይነት ትውፊትና ወግ ያለው ህዝብ አንድ ላይ እንዲሻሻል ካልተደረገ የሐያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ብዙዎቹን በአዘቅት ውስጥ ጥለው ራሳቸው ብቻ በምቾት መፈንጨት ለሚፈልጉ ጥቂት ጮሌዎች ምንም ቦታ የሌላቸው መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ለዚህም ምሳሌ ወደሩቅ ቦታ፡ ወደሩቅ ዘመን ሳንሄድ በዓይናችን ያየናቸው ለሀያ አራት አመታት «ሀገራቸውን» በጉድ አዘቅት ውስጥ ጥለው ኑረው በመጨረሻው በራሳቸው ስራ በጉድ አዘቅት ውስጥ የወደቁትንና እየወደቁ ያሉትን ወያኔዎችን ማስታወስ ይበቃል።

እንግዲህ ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽመው ደባ ሁሉ ውጤት እንዲህ መሆኑ ከታወቀ ዘንድ፤ የየግል ምኞታችንንና ፍላጎታችንን ከታላቁ ህዝባችን ጠቅላላና ዘላቂ ጥቅም ሳናስቀድም እኛ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድርና ማግ ሆነን መስራት ከቻልን እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ከወያኔ ጥፋት ታድገን የጨለመ ተስፋውን በማለምለም፤ ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ተከብረው የሚኖርበት አገር ባለቤት እንዲሆንና የሚኮራበት ርስተ ምድር የመፍጠር ችሎታውም ሆነ አቅሙ አለን። የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት መቆምና በጋራ ለመታገል ቁርጥ ማድረግ፡ ከጅምሩ ጀምሮ «ዘራችን ከዘራቸው፤ ደማችን ከደማቸው ይበልጣል» ብለው ተከታዮቻቸውን ሲጠምቁ የኖሩት ወያኔዎች ለግል ጥቅማቸው ያቋቋሙትንና ህዝባችንን እየፈጁበትና ሀብቱንም እየበዘብዙበት እንዲኖሩ በወንጀል ያቋቋሙትን የሌብነትና የቅሚያ ማህበራቸው የሆነውን «ስመ መንግስት» ገርስሶ፤ ኢትዮጵያውያንን ከጥፋት በመታደግ፤ የሰላም፣ ብልጽግና፣ ፍቅርና የኑሮ ዋስትና የሚገኝበት ኃይል ነው።

በመጨረሻም ሁላችንም ኢትዮጵያውያን መንፈሳዊ መኔውን አግኝተን ይህንን የጋራ የሀሳብ ኃይል መፍጠር ከቻልን ህዝባችንን ከአደጋ ማውጣት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ምድር የምንመካበት አገር ልናደገው ችሎታው አለን። እኔ ዛሬ የሰነቅሁትን እምነት በየቦታው ተበታትኖ ያለው የኢትዮጵያ ምሁር ለኢትዮጵያዊ ወገኑ ለመድረስ በአንድነት ቢገምደው ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት ኢትዮጵያ በአንድ ትውልድ የአፍሪካ ጃፓን ለመሆን ትችላለች። ግን ጊዜ የለንም፤ በአንድነት ተነቃንቀን የጋራ ኃይላችንን መፍጠር ዛሬ መጀመር አለብን።

ጤና ይስጥልኝ!

የዲላ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞች ኣመፅ ኣስነሱ

0
0

Zehabesha News
ከአምዶም ገብረሥላሴ

የዲላ ዩኒቨርስቲ ሰራተኞች በፕሬዝዳንታቸው “ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ኮሬ” ላይ ዓመፅ በማስነሳት ወደ ትምህርት ምኒስቴር ጥያቄያቸው ልከዋል።
ፕሬዝዳንቱ “ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ኮሬ” ላይ 16 ክሶች ቀርቦላቸዋል።

ከክሰቹ መሃል
፩) ከ229 በላይ ሰራተኞች ከህግና ድንብ ውጪ በራሳቸው ስልጣን እንዲቀጠሩ ኣድርገዋል፣
፪)ሰራተኞች ዩኒቨርስቲው ለቀው እንዲሰደዱ እያደረጉ ነው።
፫) ለኢስትራክተሮችና ሰራተኞች የሚደበድብ ሃይል ኣደራጅተው ኣስደብድበዋል
፬ )በ ስልጣን ያለ ኣግባብ መጠቀም
፭) በኪራይ ሰብሳቢነት
፮) በሃብት ኣባካኝነት
፯) በጠባብነት
፰) “እኔ በሂወት እያለው የኣማርኛና ታሪክ ትምህርት ክፍል በዩኒቨርስቲው ኣላስከፍትም” የማለት ወዘት ያካተቱ 16 ጥያቄዎች ለትምህርት ምኒስቴር ምኒስትር ለሆኑት ኣቶ ሺፈረኣው ሽጉጤ ኣቅርበዋል።
ይህ የሰራተኞች ዓመፅ በታማኝ የዩኒቨርስቲ ሹሞኞች ላይ ኣዲስ ጅምር ነው።
በኣክሱም ዩኒቨርስቲም ፕሬዝዳንቱና ምክትሉ በተመሳሳይ ምክንያት ከቦታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል።
መቐለ ዩኒቨርስቲም የሆነ የለውጥ ድባብ እያንዣበበ ይመስላል።
እየተጀመሩ ያሉት የለውጥ ጅምር ዩኒቨርስቲዎቻችን የምር ዩኒቨርስቲ ለመሆን የጀመሩት እንቅስቃሴ ይሆን…?
ነፃነታችን በእጃችን ነው።


የስብሰባ ጥሪ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባላት በሙሉ !!

0
0

ጉዳዩ፦ አመታዊ ጠቅላላ የአባላት መደበኛ ስብሰባ !

ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባላት በሙሉ መተዳደሪያ ደንቡ በሚያዘው መሰረት የአባላት ጠቅላላ አመታዊ መደበኛ ስብሰባ ጥቅምት 25.10. 2015 ከቀኑ 14፡00 ሰአት ጀምሮ ስለሚያደርግ አባላት ሁሉ በስብሰባው ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን በስብሰባው ላይ

1. አመታዊ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ስድስትወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት

2. እንዲሁም ለቀጣይ ስድስት ወራት የምንደግፋቸው ድርጅቶችን መገምገምና ማጽደቅ

3. ድርጅቱን ለቀጣይ የስራ ዘመናት የሚመሩ የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ

በመሆኑም በዚህ ስብሰባ ላይ አባላት በሙሉ በመገኘት የድርጅት ግዴታቸውን ይወጡ ዘንድ ድርጅቱ በታላቅ አክብሮት ያስገነዝባል በማያያዝም የተለያዩ ምግቦች እና መጠጦች በቦታው ተዘጋጅቶል
የስብሰባ ቦታውን በቅርብ ጌዜ እናሳውቅ አለን

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ !!

Norway - Satenaw

ትግሉ ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ወይንስ ለምንይልክ ቤተ መንግሥት?

0
0

ይገረም አለሙ

ፈጣሪ ዕድሜ ከጥንካሬ ጋር ያደላቸው በሀገር ጉዳይ የማይታክቱት ፕ/ር መስፍን ወልደ ማሪያም ሰሞኑን በምድረ አሜሪካ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ጋር ያደረጉትን ውይይት ዘመነ ቴክኖሎጂ ምስጋን ይግባውና በያለንበት ሆነነን ተከታትለናል፡፡ ከውይይቱ ታዳሚዎቸች ከቀረቡ በርካታ ጥያቄዎች አንዱ በያ ትውልድ ላይ ጨከኑበት የሚል ነበር፡፡ ፕ/ር መስፍን ሲመልሱም አልጨከንኩበትም እውነቱን ነው የተናገርኩት አንዳንዶቹ እንደውም ተማሪዎቼ ነበሩና አነጋሬአቸዋለሁ፣ ፍላጎታቸው ለሀገርና ለሕዝብ ሳይሆን ሥልጣን ነበር ብለዋል፡፡

በዚሁ ሰሞን እጄ የገባው ባለ 96 ገጽ ሰነድ ውስጥ ፕ/ር የተናገሩትን የሚያረጋገጥ ከጉዳዩ ባለቤቶች አንዱ በሆነው የተነገረ አገኘሁ፡፡ ሰነዱ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ“ በሀገርና ሕዝብ ደህንነት ጥበቃ ምኒስቴር የማዕከላዊ ምርመራ ድርጅት የወንጀል መዝገብ ቤት” የሚል ማኅተምና “ጥብቅ ምሥጢር” የሚል ማሳሰቢያ ያረፈበት ሲሆን ከኢህአፓ መሪዎች አንዱ የነበረው ብርሀነ መስቀል ረዳ በእስር ቤት የሰጠውን የምርመራ ቃል የያዘ ነው፡፡ ከአጀማመራቸው አንስቶ እስከ መንዝና መርሀ ቤት ቆይታው ይዘረዝራል፡፡

ምንም ዘመናዊ የግንኙነት ዘዴ ባልነበረበት ዘመን አፍሪካ አውሮፓና አሜሪካ ሆነው በደብዳቤ ግንኙነት ሰነድ ማዘጋጀት ድርጅት መመስረት አመራር መምረጥ መቻላቸው ብሎም ከተለያዩ ሀገራትና ድረጅቶች ጋር ግግንኙነት በመፍጠር ወታደራዊ ሥልጠና መውሰዳቸውና በኤርትራ እስከ አሲምባ መዝለቃቸው አዲስ አበባም ላይ በህቡዕ ያደረጉት አንቅስቃሴ በእውነቱ የሚያስደንቅ ነው፡፡ ግና ምን ዋጋ አለው ያንን ችሎታ፤ ያንን እውቀት፤ ያንን ድፍረትና ቁርጠኝነት የሥልጣን ጥም በላው፡፡ እንታገልለታለን ብለው የተነሱለትን ዓላማ የሥልጣን ፍላጎት በለጠውና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ቀርቶ ርስ በርሳቸውም መስማማት አንዳይችሉ አደረጋቸው፡፡ሁሉንም ሊደፈጥጥ የተዘጋጀው ደርግ አፍንጫቸው ስር እያለ የሥልጣን ጉጉት የሀሳብ ልዩነቶቻቸውን በውይይት ከማስታረቅ ይልቅ አጥፊና ጠፊ ሆነው አንዲሰለፉ አበቃቸውና፤ የአንድ ድርጅት አባላት ርስ በርሳቸው አንዲሁም አንዱ ድርጅት ከሌላው ያለምንም በቂ ምክንያት እየተጠፋፉ ለአጥፊያቸው ራሳቸውን አመቻቹ፡፡ ሊድን ያልቻለ በሽታም አስፋፉ፡፡
Pro Mesfin
ብርሀነ መስቀል ከማዕከላዊ ኮሚቴ ከተባረረ በኋላ ክሊክ ብሎ ከሚጠራቸው የትግል አጋሮቹ ግድያ ሽሽት ድርጅቱ ካስቀመጠው ሰባ ደረጃ አካባቢ ለቆ እንደተሰወረና የእርማት ንቅናቄ የሚል ስራ እንደጀመረ ብዙም ሳይቆይ ደግሞ የደርግን አሰሳ በመሸሽ ከሌሎቹ አጋሮቹ ጋር ከአዲስ አበባ ወጥተው መንዝና መርሀቤት ጫካ ለመግባት እንደበቁ ይናገራል፡፡ በትግል አጋሮቻቸው የተገደሉ የአመራር አባላትን ስምም ይዘረዝራል፡፡ ግን ለምን መጠፋፋት መገዳደል! ይገኝ አይገኝ ላልታወቀ ገና ላም አለኝ በሰማይ ለሆነ ስልጣን በአንድ አላማ ስር ተሰልፈው በአንድ ድርጀት ታቅፈው ለትግል የተማማሉ የአንድ ሀገር ልጆች እስከመገዳደል መድረሳቸው ያሳዝናል፤ ይበልጥ የሚያሳዝነው ደግሞ የዛ ድርጊት መሪ ተዋናዮች ሲያዝኑም ሲያፍሩም ሲጸጸቱም አለመሰማቱ ነው፡፡
እንደ ብርሀነ መስቀል ገለጻ ከሆነ ኢህፓ ከውስጥ አመራሩ ርስ በርስ ይቆራቆሳል፣ ይህን መልክ ሳያሲዝ ከላይ ከደርግ ከጎን ደግሞ በተለይ ከመኢሶን ጋር ይታገላል፡፡ በወቅቱ የችግሮች ሁሉ ቁንጮ የነበረው የመኢሶንና የኢህአፓ ቅራኔያቸው አንቶ ፈንቶ ልዩነታቸው መሰረት የለሽ ጠባቸው የግለሰቦች የሥልጣን ጥም(ድርጅታዊ ያልሆነ) አንደነበረ በተለያየ ሁኔታ ተገልጹዋል፡፡ ይህንኑ የሚያሳይ ትንሽ ግን የትልቅ ነገር ምልክት ከብርሀነ መስቀልም ቃል ውስጥ እናገኛለን፡፡
“ሚያዚያ 13/68 የታወጀው የብሔራዊ ዴሞክራሲዊ አብዮት ፕሮግራምና በተቀዳሚ ም/ል ሊቀመንበሩ ለተራማጆች ሁሉ የተደረገውን አስቸኳይ የግንባር መቋቋም ጥሪ… በሳምንት ውስጥ ማ/ኮ ተሰብስቦ የግንባሩን ጥሪ አንቀበል የምንል ወገን የብዙሀኑን አባላት ደምጽ አግኝተን ክሊኩ በግልጽ ተሸነፈ”፣ ይልና ተሸናፊው ወገን የተለያየ ሰበብ እየፈጠረ አዘግይቶ ባወጣው መግለጫ “በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ለግንባሩ ብቁ ተብለው ሲዘረዘሩ ያኔ ፕሮግራሙን በይፋ አውጆ የነበረው መኢሶን ሳይጠቀስ ቀረ” ካለ በኋላ “ለግንባር ጥሪው ምላሽ የሚለው የፓርቲው መግለጫ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተለይ የሰፊው ሕዝብ ድምጽ ጋዜጣ “ኢህአፓን ለግንባር ማን ጠራትና ተኳኩላ ቀረበች” ወዘተ የሚል የኩርፊያ ጽሁፍ አወጣ” ይላል፡፡ እስቲ ይታያችሁ ጋባዡ ተቀምጦ ተጋባዦቸ ሲጣሉ፡፡ ይህ ታዲያ የጤና ነው፡፡ በሽታው ተዛምቶ በቅርብ ግዜም እገሌ የሚባል ድርጅት ከተገኘ አንገኝም አገሌ የሚባል ሰው ከተጋበዘ አንካፈልም ሲባል ሰምተናል፡፡ መድሀኒት ያልተገኘለት መጥፎ በሽታ፡፡

የሀሳብ ልዩነትን በውይይት ማስታረቅ ሳይሆን በጉልበት መደፍለቅ፣ የተለየ ሀሳብ የሚያራምዱትን በማዳመጥ ሳይሆን በመርገጥ/በማስወገድ እኔ ብቻ ትክክል ማለትና አሻቅቦ ቤተ መንግሥትን እያዩ አባሉንና ተከታዩን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እየጋቱ ለመስዋዕትት መዳረግ፤ተደጋጋፎ ሊታገሉ የሚገባን ድርጅት ስም እየሰጡ ወንጀል እየፈበረኩ ከቻሉ ለማጥፋት ካልሆነም ሽባ ለማድረግ እቅልፍ የሚነሳ በሽታ መቼ አንደጀመረ ባላውቅም ጎልቶ የታየውና ነጥሮ የወጣው በአብዮቱ ዘመን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይሄው በሽታ መድሀኒት የሚፈልግለት ጠፍቶ፣ ሊያረጅም ሊዘምንም አልችል ብሎ እስካሁን የፖለቲካችንና የፖለቲከኞቻችን መታወቄያ እንደሆነ ይገኛል፡፡ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም ሆኖብን አንደሁም አንጃ ዛሬም ከኢትየጰጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ መነሳት አለበት ከምንለው ሀይል ጋር ከሚደርገው ትግል ይልቅ የጎንዮሽ ርስ በርስ የሚደረገው ትግል የከፋ ሆኖ ነው ወያኔ ከሀያ አራት አመታት አገዛዙ በኋላ መቶ በመቶ በምርጫ አሸነፍኩ ብሎ ሊቀልድብን የበቃው፡፡

ሰሞኑን አሜሪካ ለንባብ የበቃው የሌ/ኮ ፍሰሀ ደስታ መጽሀፍ ሲተዋወቅ ጸኃፈው የኢህአፓ ቆራጥነት የመኢሶን ርዕዮተዓላመዊ ብቃት የደርግ ሀገር ወዳድነት ቢቀናጅ ተአምር ሊሰራ ይቻል እንደነበረ በቁጭት መግለጻቸውን ሰምተናል፡፡ኮረኔሉ ከዚህም አልፈው እስካሁን ማንም ያልደፈረውን ደፍረው አውቀው በድፍረት ሳያውቁ በስህተት ለፈጸሙት የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ በሁሉም ዘንድ ያለው የሥልጣን ጥም በምን ልጓም ተገቶ እንደምንስ ሰክኖ ለዚህ መብቃት ይቻላል፡፡ ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ እንዲሉ ይቅርታው ቀርቶ ባለፈ ስራ መጸጸትና ለአለቀው ወጣት ማዘንም አይታይም፡፡ ካለፈ መማር ቢኖር የቤተ መንግሥቱ ወንበር ለሁሉም ሊሆን አንደማይችል ነገር ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ሥርዓት መፍጠር ሁሉንም ንጎሶች እንደሚደርጋቸው አምነው እውቀት ልምዳቸውን ተሰጥኦ ተሞክሮአቸውን በማቀናጀት ትግሉ አንዴት፤ የት፤ በምን ሁኔታና በማን መካሄድ እንደሚችልና አንደሚገባው ሊመክሩ ሊያቅዱና ስትራቴጂ ነድፈው አንደ አቅም ችሎታው ተደጋግፈው በመታገል የግዞቱን ዘመን ባሳጠሩት ነበር፡፡ ግና አልታደልንምና ዛሬም ብዙዎቹ ራሳቸው ለሥልጣን ስለሚበቁበት ብቻ እያሰቡ የሚያውቁትን ያደጉበትንና አላረጅ ያለውን የጎንዮሽ ትግል የሙጢኝ አንዳሉ ናቸው፡፡ላያገኙት ሥልጣን ትግሉንና ታጋዩን በትንሹም ቢሆን ይጎዳሉ፤ለገዢው እድሜ መርዘም ይሰራሉ፡፡
34757 - Satenaw
በአብዮቱ ወቅት ከነበሩት ፓርቲዎች የአንዱ የወዝ ሊግ መሪ የነበሩት አቶ ተስፋየ መኮንን ይድረስ ለባለታሪኩ በተሰኘው መጽሐፋቸው “በሕዝባችን ፊት ተሰባስበን ችግሮቻችንን ለመፈታት ችሎታው ያልነበረን የኢትዮጵያ ልጆች የኮ/ል መንግሥቱ የግድያ ጉሮኖ ውስጥ ለመጨረሻ ግዜ ተገናኘን፡፡

ሁላችንም በተዘዋዋሪ መንገድና ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ሲበዛ ለድርጅት ሲያንስ ለግል የሥልጣን ሽኩቻ ስንባላ ለዚያው ተመሳሳይ ዓላማ የቆሙት ኮ/ል መንግሥቱ በአሸናፊነት ሊበሉን በአንድ ቦታ አሰባሰቡን ፡፡ ክቡር በሆኑ የሕዝብ ጥያቄዎች ላይ ካደረስነው በደል አንጻር ከዚህ የበለጠ ምን የታሪክ ፍርድ ይኖራል፡፡” በማለት ነበር የወቅቱ አብይ ችግር የሥልጣን ጥም አንደነበረ ያሳዩት፡፡ ይሄው ድርጊት ነው እስከዛሬ የቀጠለው፣ ዛሬም ያለውና ወደፊትም የማይቆም የሚመስለው፡፡ ተባብሮ መስራት ቀርቶ ተከባብሮ መኖር የተሳናቸው ፓርቲዎች አባላት በወያኔ እስር ቤት በአንድ ላይ ይታሰራሉ፡፡ በመሪዎች የሥልጣን ጥም ምክንያት ትግሉ አንድ ርምጃ መራመድ ተስኖት አባላትና ደጋፊዎች ግን ሞት እስር ስደት ስቃይ እየደረሰባቸው ነው፡፡ይህንንም የዜጎች መስዋዕትነት ለእነርሱ ፍላጎት ማሳኪያ ሊጠቀሙበት የሚዳዳቸው ፖለቲከኞች እናያለን፡፡

በኢትጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ይዘጋጅ በነበረው ርዕይ 2020 መድረክ ላይ ዶ/ር ታደሰ ብሩ ኬርሴሞ ሰላም ዴሞክራሲና ልማት የልሂቃን ሚና ዛሬና ነገ በኢትዮጵያ በሚል ርእስ ባቀረቡት ጽሁፍ «የኢትዮጵያ ልሂቃን በጣም መበታተናቸው ሳያንስ እርስ በርሳቸው በእጅጉ የሚጻረሩ አንዱ ሌላኛውን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ከመረረ ጥላቻ ጋር የተነሱ መሆናቸው አገራችን ዛሬ ለምትገኝበት አሳዛኝ ሁኔታ የዳረገን ይመስለኛል፡፡ የመጠፋፋቱ ትግል በደርግ ግዜ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም አሁንም መልኩን እየቀያየረ ቀጥሏል ፡፡ ኢትዮጵያዉያን ልሂቃን በአገራዊ ጉዳዮች የጋራ መግባባት ላይ ካልደረሱ በስተቀር ይህ የጥላቻና የመጠፋፋት ፖለቲካ በቀላሉ የሚቆም አይመስለኝም፡፡ ብለው ነበር ፡፡ ዶ/ር ታደሰ እንዲህ ብለው ብቻ አላበቁም፣የልሂቃኑ ለድርድር መዘጋጀት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ሲገልጹ « እዚህ ላይ አጽንኦት ልሰጥበት የምፈልገው ጉዳይ ግን ጥሩ ሕገ መንግሥት፣ ጥሩ የምርጫ ሕግ እና ግልጽና ፍትሀዊ ምርጫ ወዘተ..ቢኖሩም እንኳን ልሂቃኑ ለድርድር የተዘጋጁ ካልሆኑ ዲሞክራሲ መኖር የማይችል መሆኑ ነው» ነበር ያሉት፡፡ ጽሁፉ ከቀረበ 10 አመታት ያለፉት ቢሆንም የተለወጠ ነገር የለም፤ እንደውም መሻል ቀርቶ ብሶበታል፡፡ዛሬስ ወደፊትስ…፤

ለውጥ ያለመታየቱ ምክንያትም ፕ/ር መስፍን በአሜሪካው የውይይት መድረክ ላይ የተናገሩትና በተለያዩ ጽሆፎቻቸው የገለጹት በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለው የሥልጣን ጥም ነው፡፡ ከዚህ እንዴት መገላገል ይቻል ይሆን! ፕ/ር መስፍን ሥልጣን ባህልና አገዛዝ፣ፖለቲካና ምርጫ በሚለው መጽሀፋቸው አንዲህ ይላሉ ፡፡ « እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወደ ፖለቲካ ሲገባ ከልጅነት እስከ እውቀት በውስጡ የተመረገውን የጌትነትና የሎሌነት ባህል ፍቆ ፈቅፍቆ ማርገፍ አለበት፡፡በግድ የአሰተሳሰብ የጽዳት ዘመቻ ያስፈልገናል፡፡ ዓላማን የማጥራት ዘመቻ ያስፈልግናል፡፡በግድ የነጻነትና የእኩልነት አራማጆች በቁርጠኝነት መነሳትና ማሳየት ያስፈልገናል፡፡ ብዙዎቹ የተቀናቃኝ መሪዎች ላይ የሚታየው የድሮው መኳንንትና መሳፍንት ለመምሰል የመሞከር ጠባይና ከዚህም ጋር ተያይዞ ሎሌዎችን በገንዘብ ሆነ በወደፊት ተስፋ እየገዙ የአገዛዝን ባህል ለማራማድ የሚደረገው ሙከራ የፖለቲካውን ሥርዓት አያራምድም ፡፡ ጥረቱ ሁሉ በሥልጣን ላይ ያሉትን ሰዎች ለመለወጥ እንጂ ሥርዓትን ለመለወጥ አይመስልም(ገጽ 32)

ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን በአንድ ወቅት ከጦቢያ መጽሄት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ በገለጸው ስጋት ልሰናበት “ኔልሰን ማንዴላ እንደ ስምጥ ሸለቆ ቁልቁል የጠለቀውን ‹የልዩነት›› መቀመቅ በዴሞክራሲ ድልድይ ገደሉን አስተካሎ የመቻቻልን ጥበብ ለወገኑ ሲታደግ የኛ ተቀዋሚዎች ፖለቲከኞች ግን. በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል አዳስ ሰምጥ ሸለቆዎች አንዳይቆፍሩ እሰጋለሁ፡፡ ”

በሕዝብ ጫና የሕወሓት መንግስት የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ወደ ቦታው ሊመልስ ነው

0
0

abune_petros
የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ከስፍራው በልማት ስር አንስቶ ታሪክን ሊያጠፋ ነበር ተብሎ ሲተች የነበረው የሕወሓት አስተዳደር ሕዝቡ በአደባባይ ይህን ታሪክ ሐውልት እንዲመልስ ባደረገው ጫና መሰረት ወደ ቦታው ሊመልስ መሆኑ ተሰማ:: መንግስታዊው ራድዮ ፋና “የአደባባይ ዲዛይን ስራ እየተገባደደ በመሆኑ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት በቅርቡ ወደ ቀድሞ ስፍራው እንደሚመለስ ተገለፀ” በሚል ዜናውን ቢያስነብብም ሕዝቡ አሁንም ሐውልቱ እስኪመለስ ድረስ ተቃውሞውን እንደሚቀጥል ታውቋል::

በተለያዩ ሶሻል ሚድያዎችም ሐውልቱ ቦታው እስኪመለስ እንጮሓለን የሚሉ መል ዕክቶች እየተሰራጩ ነው::

መንግስታዊው ራድዮ ፋና ስለሐውልቱ ወደ ቦታው ሊመለስ መሆኑን እንደሚከተለው ዘግቦታል:: እንደወረደ እነሆ:-

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት የሚያርፍበት አደባባይ ዲዛይን ዝግጅት የመጨረሻ ምእራፍ ላይ የደረሰ በመሆኑ ግንባታ ተካሂዶ ሀውልቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀድሞ ስፍራው እንደሚመለስ የፌደራል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ ገለፁ።

አቶ ዮናስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ሀውልቱ የሚያርፍበት አደባባይ ገፅታ እና ይዘት ምን መምሰል አለበት ለሚለው የመጨረሻ መልስ ለመስጠት የቀላል ባቡሩ ስራ የሚጀምርበት ጊዜ ሲጠበቅ ቆይቷል።

ይህም ያስፈለገው ባቡሩ በሚንቀሳቀስበት ወቅት የሚፈጠረውን ንዝረት አጥንቶ የአደባባዩን ዲዛይን ማጠናቀቅ ስላስፈለገ ነው ብለዋል።

አደባባዩ ሊኖር የሚችለውን ንዝረት በተግባር ተፈትሾ መገንባቱ ወደፊት ሀውልቱ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳይደርስበት ያደርጋልም ነው ያሉት።

ታሪካዊው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሲነሳ

ታሪካዊው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሲነሳ


ባለፈው እሁድ ቀደም ሲል ሀውልቱ የነበረበትን ስፍራ የሚያካልለው የሰሜን-ደቡብ የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር መስመር አገልግሎት በመጀመሩ የንዝረት መጠኑን በተመለከተ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን አቶ ዮናስ አስረድተዋል።

መረጃ የመሰብሰቡ ስራ እንዳበቃም የአደባባይ ዲዛይኑ ተጠናቆ ወደ ግንባታ ይገባል፤ ከዚያም ሀውልቱ በቀድሞ ስፍራው ይተከላል ብለዋል።

ለአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ግንባታ ሲባል 2005 ዓመተ ምህረት ሚያዚያ ወር ላይ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ከቆመበት ተነቅሎ በብሔራዊ ሙዚየም በክብር እንደሚገኝ ይታወቃል።

የደህነቱ ሀላፊ ጌታቸው አሰፋ ወንድም የመቀሌ ከንቲባ ሆኑ ፣የህወሓት የስልጣን ሽኩቻ የመቀሌው ቡድን መሪ አባይ ወልዱ በአዲሱ ካቢኔ ተመልሰው ፕሬዝዳንት ሆኑ

0
0

የህወሓት ባለስልጣናት የስልጣን ሽኩቻ የመቀሌውን ቡድን በመምራት የበላይነታቸውን አስጠብቀው ወጥተዋል የተባሉት አቶ አባይ ወልዱ በአዲሱ ካቢኔ ተመልሰው ክልሉ ፕሬዝዳንት ሆኑ ሲሆን የመቀሌን ከተማ በከንቲባነት ለመምራት ሙሉ በሙሉ በህወሓት ቁጥጥር ስር ያላውን የአገሪቱን ደህነት መ/ቤት የሚመሩትና ስርዓቱ የሚፈጽማቸውን ግድያና ማሰቃየት ተጠያቂው አቶ ጌታቸው አሰፋ ወንድም ዳንኤል አሰፋ በአዲሱ ካቢኔ የመቀሌ ከንቲባ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
abay weldu 2

abay weldu
የክልሉ ም/አስተዳዳሪ ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማ፣የትዕምት ሀላፊ አቶ በየነ መክሩ ፣በቀድሞው የህወሃት ፕሮፖጋንዳ ሀላፊ ቴዎድሮስ ሀጎስ አቶ አለም ገብረዋህድ በቦታው በአዲሱ ካቢኔ የተመረጡ ሲሆን በአቶ ኤርሚያስ ለገሰ ቱርፋቶች ባለቤት አልባ በካሳንቺሱ መንግስት ውስጥ የተጠቀሰችው ሞንጆሪኖ (ፈትለወርቅ) የህወሃት ህዝብ አደረጃጀት መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ይገልጻል።

ህወሓት የአገሪቱን ዋና ዋና ስልጣን በአንድ ብሄር የበላይነት፣ወታደራዊ፣ዋና ዋና ኢኮኖሚ ተቃማቱንና ደህነቱን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ በቤተሰብና በቡድን የተከፋፈሉትን ስልጣን ከፌዴራል እስከ ክልል መቆጣጠራቸውን አንዳንዶች ከህወሃትም በስልጣንና በሀብት የናጠጠው ቡድን ጥቂት ግለሰቦች የሚያሽከረክሩት ነው ይባላል። ቀድሞ የመለስ አዜብ ቡድን፣የስብሃት ቡድን፣የነአርከበ ቡድን ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው።

የህወሓት ባለስልጣናት የመቀሌና የአዲስ አበባ በሚል ከህወሃት ጉባዔ በፊት የጀመሩት የስልጣን ሽኩቻ አንዱ የአንዱን ደጋፊ ወደ ማሳደድ እንደዘለቀ አስቀድመን መዘገባችን አይዘነጋም።የመቀሌው ቡድን በአቶ አባይ ወልዱ የሚመራ ሲሆን የአዲስ አበባው በዶ/ር ደብረጽዮን ይመራ እንደነበርና የአቶ አባይ ቡድን በጉባዔው በአነስተኛ ድምጽ ተመርጦ በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ለትልቁ የፓርቲ ስልጣን በርካታ ደጋፊዎቹን ማስመረጡን አምዶም ገ/ስላሴን ጠቅሰን በስፋት መዘገባችን ይታወሳል።

የኢሕአዴግ አይቀሬ ዕጣ – አስጊው የኢትዮጵያ ጣጣ (አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ) – See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/10462#sthash.zjRZKMSV.dpuf

0
0

ሰኞ፤ መስከረም ፲ ቀን ፳፻፰ ዓመተ ምህረት ( 9/21/2015 )

መከወኛ ሃሳብ፤

eskemecheዛሬ ካለንበት የፖለቲካ ሀቅ ላይ ቆመን የነገዋን ኢትዮጵያ በሃሳብ ብንመለከት፤ ሶስት እውነታዎች ገጠው ይታያሉ። የመጀመሪያው፤ አሁን በሥልጣን ላይ ባለው የገዥ ቡድን አስተዳደር፤ ምንም ቢሆን ምንም፤ ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ሊኖራት አለመቻሉ ነው። ሁለተኛው ደግሞ፤ ኢሕአዴግ፤ ውስጡ እየነቀዘ፤ ወደ አንድ ፓርቲነት ከማደግ ይልቅ፤ በየድርጅቶቹ መጎነታተል እየተወጣጠረ፤ ከውስጥ መርቅዞ ወደ መበታተኑ በመሄድ ላይ ያለ መሆኑ ነው። ሶስተኛው ደግሞ፤ አሁን በያዝነው ሂደት፤ ሀገራችን እጅግ ወደ ከፋና ልትወጣበት ወደማትችለው መቀመቅ ውስጥ እየዘቀጠች መሆኗ ነው። እኒህ ፈጠው ያደገደጉ የፖለቲካ ሀቆች፤ በዚህ ጽሑፍ ተተንትነው ቀርበዋል።

ዛሬ ካለንበት የፖለቲካ ሀቅ ላይ ቆመን የነገዋን ኢትዮጵያ በሃሳብ ብንመለከት፤ ሶስት እውነታዎች ገጠው ይታያሉ። የመጀመሪያው፤ አሁን በሥልጣን ላይ ባለው የገዥ ቡድን አስተዳደር፤ ምንም ቢሆን ምንም፤ ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ሊኖራት አለመቻሉ ነው። ሁለተኛው ደግሞ፤ ኢሕአዴግ፤ ውስጡ እየነቀዘ፤ ወደ አንድ ፓርቲነት ከማደግ ይልቅ፤ በየድርጅቶቹ መጎነታተል እየተወጣጠረ፤ ከውስጥ መርቅዞ ወደ መበታተኑ በመሄድ ላይ ያለ መሆኑ ነው። ሶስተኛው ደግሞ፤ አሁን በያዝነው ሂደት፤ ሀገራችን እጅግ ወደ ከፋና ልትወጣበት ወደማትችለው መቀመቅ ውስጥ እየዘቀጠች መሆኗ ነው። እኒህ ፈጠው ያደገደጉ የፖለቲካ ሀቆች፤ በዚህ ጽሑፍ ተተንትነው ቀርበዋል።

መግቢያ፤

በ፳፩ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ፤ ዓለም በሥልጣኔ እየገሰገሰ፤ የሳይንስ ስነ-ምርምር የእደ ጥበብ ግኝቶችን በብዛት እያዥጎደጎደና ተዓምር የሚባሉ እምርታዎችን እያስከተለ ባለበት ወቅት፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በወገንተኛ አምባገነን አስተዳደር ሥር፤ የኋልዮሽ ስትጓዝ ትገኛለች። የዚህ ገዥ ቡድን ፍላጎትና ተግባር፤ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት በተቃራኒ የቆመ በመሆኑ፤ ሰላም፣ ብልፅግናና ዕድገት ከሀገራችን ፍጹም ርቀው ሸሽተዋል። አድልዖና ሙስና አስተዳደሩን አግምተውት፤ አፍንጫ ካስያዘ ውሎ አድሯል። በጣም ጥቂት ምርጥ ዜጎች በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ሲያካብቱ፤ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠረው ደሃ ወገናችን፤ በውጪ መንግሥታትና በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ምጽዋት፤ ቀኑን ይገፋል። የፖለቲካ ምኅዳሩ ትርጉም በማይሠጥ መንገድ፤ በገዥው ቡድን ተጠራቆ የተያዘ በመሆኑ፤ የተለዬ አቋም ያላቸው ግለሰቦችና የአስተዳደሩን ተግባር የማይደግፉ ሁሉ፤ ለእስር የተዳረጉበት፣ የሚዳረጉበት፣ የተገደሉበትና የሚገደሉበት ሁኔታ፤ የዕለት ተዕለት የኑሮ ሀቅ ሆኗል። በሕዝቡ ዘንድ፤ በተለይም በወጣቱ ውስጥ ተስፋ መቁረጥ ነግሷል። ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት ቀርቷል። ተማሩም አልተማሩም፤ የሥራ አጡ ቁጥር ሀገሪቱን ለውጥረት ዳርጓታል። አሁንም ሀገሪቱን እየጣሉ፣ ከገዥው ክፍል እየሸሹ፣ ሞትን በከበበ አስፈሪና አስጊ መንገድ፤ ወደ ውጪ የሚነጉዱት ወጣቶች ቁጥር ልክ አጥቷል። ይህን ሁሉ ምን አመጣው? ይሄስ ምን ያህል የሚሰነብት እውነታ ነው? ይህ ጉዟችን ወደየት ያመራል? ምን መደረግ አለበት? የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ይሄን ሀቅ በመመርመር፤ በግልጽ ተንትኖ ማቅረብ ነው።

ላለንበት ሀቅ የዳረገን ሂደት፤

በወርሃ የካቲት ፲፱፻፷፮ ዓመተ ምህረት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዳር እስከዳር፤ ከነበረበት የጉልተኛ ሥርዓት ማነቆ ለመላቀቅ፤ ሆ ብሎ ተነሳ። በነበረው ኋላ ቀርና አፋኝ የፖለቲካ ሥርዓት ምክንያት፤ በዚያ ወቅት ብቁ የሆነና የተዘጋጀ የሕዝቡ የፖለቲካ ድርጅት ባለመኖሩ፤ የፖለቲካ ሥልጣን ክፍተት ተፈጠረ። በወቅቱ ጉልበቱን ያሳየውና የተደራጀው ክፍል የሀገሪቱ የጦር ሠራዊት ነበርና፤ አጋጣሚውን በመጠቀም፤ የወጣት መኮንኖች ስብስብ ቦታውን በጦር ሠራዊቱ ስም ወሰዱት። ይህ የወጣት መኮንኖች ስብስብ፤ ወታደራዊ ደርግን አቋቁሞ፤ በሂደቱ የአንድ ግለሰብ የበላይነትን ፈጠረ። ይህ ሰው በላው አረመኔ መንግሥቱ ኃይለማርያም፤ የግለሰብ አምባገነንነቱን ጨብጦ፤ በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ እልቂትን አስከተለ። እንዲያ ያለ አስተዳደር ዘለቄታ የለውምና፤ በሚዘገንን መንገድ አገሪቱን አፋልሶ፤ ወገን ጨርሶ፣ ብሩህና ለወገን ተቆርቋሪ፣ ሀገራቸውን ወዳድና አስተዋይ የሆኑ የአንድ ትውልድ ልጆቿን መትሮ፣ ሀገራችንን አመሰቃቅሎ፤ ለወገንተኛ አምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በሩን ከፍቶ ለቀቀለት። ሰው በላው መንግሥቱ ኃይለማርያምም ጅራቱን ቆልፎ እንደሚሸሽ ውሻ፤ እግሬ አውጭኝ ብሎ ሾልኮ ጠፋ።

በዚያ በተፈጠረው ሁለተኛ ክፍተት፤ በ ፲፱፻፹፫ ዓመተ ምህረት፤ ሰተት ብሎ አዲስ አበባ የገባው ወገንተኛው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ የሀገሪቱን ሥልጣን ከመጨበጡ በፊትና ከጨበጠ በኋላ፤ ሁለት የተለያዩ መሠረታዊ የሆኑ ግልጽ የፖለቲካ እምነቶች ነበሩት። ይህ ድርጅት ሲመሠረት፤ የትግራይን ክፍል ሀገር ነፃ አውጥቶ፤ የራሱን አንድ ሀገር ለመመሥረት ነበር። የሥልጣን ክፍተቱ ተፈጥሮ አመቺ ሁኔታ ሲያጋጥመው፤ ይህን ዓላማውን እንደያዘ፤ “ሌሎች”ን አስተባብሬ ገዥ እሆናለሁ የሚል የፖለቲካ እምነት ገዛ። ለዚህ ዓላማው፤ ከ”ሌሎች” ጋር መተባበሩ ሊያስከትል የሚችለው የባለቤትነትና የበላይነት ጥያቄ ስላላማረው፤ ራሱ ጠፍጥፎ የሚያቋቁማቸውን ድርጅቶች አጋሮቹ በማስመሰል አንኳለለ። እኒህ ድርጅቶች፤ ከ”ሌሎች” ድርጅቶች ከድተው የወጡ፣ ከደርግ በፍርሃት የሸሹ፣ ምርኮኛ እስረኞችና እነዚህን ባንድ ላይ ሰብስበው ከሚቆጣጠሩ የራሱ ድርጅት አባሎች የተዋሀዱ ነበሩ። በዚህ ስሌት የተመሰረቱት ድርጅቶችን ከራሱ ጋር በመቁጠር፤ ኢሕአዴግን አቋቋመ። አሁን ኢትዮጵያዊ ጋቢ ለበሰ። እዚህ ላይ ግን፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ “ሌሎች” እያለ የመደባቸውን ድርጅቶችና “እኔ” በማለት ያጠነጠነውን፤ ራሱን በበላይና “ሌሎች”ን በበታች አድርጎ ነው።

የተነሳበት የፖለቲካ እምነቱ እንደተጠበቀ ነበር። በተለይም ከእምነቱ ውስጥ ሁለት እንደ አንገት ማተብ ያነገታቸው አሉት። የመጀመሪያው፤ “ትግራይ እስከዛሬ የበታች ሆና ተበድላለች። አሁን በኛ አማካኝነት የበላይ ሆና፤ ‘ሌሎችን’ በዳይ መሆን አለባት!” የሚለው ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር ጎን ለጎን የሚሄደው ሁለተኛው ደግሞ፤ “አማራ እስከዛሬ የበላይ ሆኖ ሁሉን ሲበድል ነበር። አሁን የበታች ሆኖ፤ በትግሬዎችና በ’ሌሎች’ ተበዳይ መሆን አለበት፤” የሚለው ነው። እንግዲህ እኒህ ከገዥና ተገዥ መደቦች ውጪ ሆነው፤ የአንድን ግለሰብ ነፃነት ለትውልድ ሐረጉ በማስረከብ፤ “የበደለህ አማራ ነው!” “የተበደልከው አማራ ስላልሆንክ ነው!” በሚል እምነቱ፤ የበዳይና ተበዳይ ወገን የሽክርክር አዙሪት አስተዳደሩን መሠረተ። ትናንት አማራ ሁሉን በዳይ፤ ትግሬ ተበዳይ ነበር። ዛሬ ትግሬ በዳይ፤ አማራ በሁሉም ተበዳይ ነው። ነገ ደግሞ . . . እያለ የሚቀጥል የትውልድ ሐረግ ቆጥሮ፤ በደልንና መበደልን የመረካከብ አባዜ ዘፈዘፈበት። ሌላው የፖለቲካ እርምጃ ሁሉ ከዚሁ ምንጭ ተቀዳ።

በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል፤ በጥቂት የገዥው ቡድን አባላት ላይ፤ የአብዛኛው ተገዢ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነቱ መነሳት ቦታ አጥቶ፤ በኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች፣ ላብ አደሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ነጋዴዎች መካከል ያለው የሙያና የመደብ አንድነት ተሰርዞ፤ የትውልድ ትስስሩ መነሻና መድረሻ ሆነ። ይህ ደግሞ፤ በአንድ በኩል ሰው ሁሉ በየትውልድ መንደሩ ብቻ እንዲሰፍር አስገደደ። በሌላ በኩል ደግሞ፤ አድልዖ፣ ሙስና፣ ምዝበራ፣ ለከት የለሽ ብልግና፤ የሥርዓቱና የሰዎች የርስ በርስ ግንኙነት ወሳኙና መታወቂያዎች እንዲሆኑ አደረገ። በገዥነት አሁን ቢቆናጠጥም፤ እንዳለፈው አረመኔ ገዥ ሁሉ፤ ይሄም ገዥ ቡድን ያልፋል። በርግጥ እስኪያልፍ እያለፋ ነው። አይቀሬ ዕጣው እያንዣበበበት ነው። የነገዋ ኢትዮጵያ ምን ትሆን ይሆን?

ፍሬ ሃሳብ፤

የነገዋን ኢትዮጵያ በሃሳብ ስንመለከት፤ የመጀመሪያው እውነታ፤ አሁን በሥልጣን ላይ ባለው ገዥ ቡድን አስተዳደር፤ ምንም ቢሆን ምንም፤ ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ሊኖራት አለመቻሉ ነው። እንግዲህ ይህ ነጥብ፤ ለምን? የሚል ጥያቄ ማስከተሉ አይቀርም። ለዚህ መልሱ የሚገኘው ከኢሕአዴግ ማንነት ነው። አሁን ያለውን አስተዳደር፤ ማለትም የኢሕአዴግን አስተዳደር ብንመለከት፤ በመንግሥትና በኢሕአዴግ መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም። መንግሥት ማለት ኢሕአዴግ ማለት ነው። ኢሕአዴግ ማለት መንግሥት ማለት ነው። መንግሥት የተለዬ አካል፤ ገዥ የፖለቲካ ፓርቲ የተለዬ ሌላ አካል፤ መሆኑ ተወርውሮ ተጥሏል። መንግሥታዊ መዋቅሩና የኢሕአዴግ መዋቅር አንድ ሆነዋል። ሕግ አውጪው ክፍል፣ ወሳኙ ክፍል፣ እና ፈጻሚው ክፍል፤ አንድ ሆኗል። አብዮታዊ ዴሞክራሲ፤ ኢሕአዴግን የበላይና ዘለዓለማዊ ያደርገዋል። በኢሕአዴግ እምነት፤ “ተዋግቶና ደሙን አፍስሶ ያገኘው ሥልጣን!” ስለሆነ፤ በምንም መንገድ በሰላም ሥልጣኑን መልቀቅ አይታሰበውም። ደሙን የከፈለው፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አይደለም። ደሙን ያፈሰሰው ለራሱ ሥልጣን ለመያዝና ዓላማውን በማራመድ ነው። ስለዚህ ከሀገሪቱ መሪ ጀምሮ እስከ ቀበሌ ዘበኛው ድረስ፤ የኢሕአዴግ አባል መሆን ግዴታ ነው። ከኢሕአዴግ ውጪ መንግሥታዊ መዋቅር የለም፤ ከመንግሥታዊ መዋቅሩ ውጪም የኢሕአዴግ አካል የለም፤ ኢሕአዴግ መንግሥት ነውና!

ከዚህ ተነስቶ፤ እንዴት ያለ መንግሥታዊ አካል፤ ከኢሕአዴግ ውጪ ያለ፣ ሕግ ሊያወጣ፣ ፍርድ ሊመለከት፣ ፖሊስ ሆኖ ሥርዓት ሊጠብቅ፣ የሕዝብን አቤቱታ ሊሰማ ይችላል? እንዴትስ ያለ ነፃ የምርጫ ዝግጅት ሊያደርግ ይችላል? እንዴትስ ያለ ሕግ አውጪና ሕግ አስከባሪ ሊኖር ይችላል? ይህ የኢሕአዴግ አወቃቀር፤ ግድ የሚለው፤ ሀገር አቀፍ ድርጅት እንዳይኖር ነው። በየክልሉ ያሉ የኢሕአዴግ አባልና ተቀጥላ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ሌላ የነሱ ተቃዋሚ ድርጅት እንዳይኖር የዕለት ጉዳያቸው ነው። መገንዘብ ያለብን፤ በየክልላቸው የፖለቲካ ድርጅት ለምፍጠር የሚያመለክቱ ሰዎች፤ ፈቃድ ሠጪዎቹና ነሺዎቹ እኒሁ ድርጅቶች ናቸው። በመጀመሪያ ደረጃ፤ እነኚህን በየክልሉ ያሉ ድርጅቶች መቃወም ማለት፤ መንግሥትን መቃወም ማለት ነው። ቀጥሎ ደግሞ፤ መንግሥትን መቃወም፤ ያስከስሳል፣ ያሳስራል፣ ያስደበድባል፣ ንብረት ያስቀማል፣ ካገር ያስባርራል፣ ያስገድላል። በጠቅላላው ኢሕአዴግን ከሥልጣን ለማውረድ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ፤ መንግሥትን ለመገልበጥ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። ስለዚህ ይህንን ለመቆጣጠርና ለመቅጣት፤ አስፈላጊ ሕጎችን ማርቀቅ፣ ካስፈለገም ያሉትን መሰረዝ፣ በተግባር ላይ ማዋል አለዚያም የማይስማማውን ሕግ አውጥቶ መጣል፤ የኢሕአዴግ ዋና ተግባር ነው።

ታዲያ አሁን ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በኢትዮጵያ አሉ አይደል? ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? የሚሉ ጥያቄዎች ሊከተሉ ይችላሉ። አሁን ያሉትን በተቃውሞ የተሰለፉ ድርጅቶች ሕልውና፤ በደንብ መመርመር ያስፈልጋል። አዎ! ተቃዋሚ ድርጅቶች አሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ፤ በኢሕአዴግ እይታ፤ እኒህ አሸባሪ ድርጅቶች እንጂ፤ ተቃዋሚ ድርጅቶች ተብለው አይታመኑም፤ አይታወቁም። ማንኛውም ኢሕአዴግን የሚቃወም ወይንም ኢሕአዴግ ያላቋቋመው ድርጅት በሙሉ፤ ፀረ- ኢሕአዴግ ነው። ፀረ-ኢሕአዴግ ደግሞ፤ ፀረ-ሀገር ማለት ነው። እናም ፀረ-ሕዝብ ነው። እናም፤ አድኀሪ፤ ኋላቀር፣ ትምክህተኛ፣ ጠባብ ብሔርተኛ፣ ሀገር ከፋፋይ ጠላት ነው። ይህ የፖለቲካ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን፤ የሙያ ማህበራትንና የሃይማኖት ተቋማትን ሁሉ ያጠቃልላል። የኢሕአዴግን ሰበካና ወቀሳ ደጋግሞ ላዳመጠ የፖለቲካ ሂደቱን ተከታታይ፤ እኒህ የተጠቀሱ ውንጀላዎች፤ በተደጋጋሚ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በጋዜጣ፣ በድረገጾችና በየስብሰባ አዳራሾች የሚዥጎደጎዱ ዘለፋዎች ናቸው። ስለዚህ ሌሎች ከኢሕአዴግ ነፃ የሆኑ ድርጅቶች እንዳያድጉ ተብታቢ ማሰሪያዎች ናቸው። ለምን ሲባል፤ ያልተፈለጉ ደንቃራዎች ስለሆኑ ነው። የተፈለገው፤ አጃቢ ሆኖ እሺ ጌታዬ የሚል ድርጅት ብቻ ነው። አጃቢ ያስፈለገውም፤ ለውጭ ሀገሮች መታያና የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት አለ ማስባያ የጀሮ ጉትቻዎች፣ ያንገት ማስጌጫዎች እንዲሆኑ ብቻ ነው። ያ ከሌለ ብድርም ሆነ እርጥባን አይገኝማ! ከሌሎች ጋር እኩል መሰለፍና መታየት አይገኝማ!

በነገራችን ላይ፤ የዚህ የኢሕአዴግ፤ ዋናው ፈጣሪና መስራቹ አንድ ድርጅት ሆኖ፤ የበላይነቱን በሌሎቹ በፈጠራቸው ላይ ያነገሰና፤ እኒህን ተፈጣሪ ድርጅቶች በአጃቢነት የሚጠቀም መኖሩ ከታች በዝርዝር ቀርቧል። አሁን ያሉትን ተቃዋሚ ደርጅቶች ስንመለከት፤ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፤ የአንድነት ለፍትኅና ለዴሞክራሲ ፓርቲና የሰማያዊ ፓርቲ፤ ቀጥሎም መድረክ ናቸው። እኒህ ደግሞ የራሳቸውን ፈለግ እየተከተሉ ስላስቸገሩ፤ ለምርጫ ሲወዳደሩ ሙሉ እንቅፋት በመፍጠር ሕልውናቸውን ለማሳጣት ከመጣር አልፎ፤ መሪዎቻቸውን መወንጀል፣ ማሰር፣ ማስቃየት፣ ማባረር፣ ከሀገር ማስወጣትና መግደል ተፈጽሞባቸዋል። የጎንዮሽ የስም ተመሳሳይ ተለጣፊ ድርጅቶችን እያቋቋመ እንዲዳከሙና እንዲጠፉ ያላባራ ጥረቱን ቀጥሎበታል።

በተጨማሪ ደግሞ ሌላው ሊከተል የሚችለው፤ ታዲያ እንዲህ ከሆነ፤ ይሄን አምባገነን መንግሥት ምን በሰላም ለመለወጥ ጥረት ይደረጋል? አጉል ድካም አይሆንም ወይ? ከንቱ ከመድከም፤ ገዥው ጠመንጃ አንግቦ ሥልጣኑን እንደነጠቀና ያለጠመንጃ ሌላ የማያውቅና የማይሰማ ስለሆነ፤ ሌሎቹስ ለምን ጠመንጃ አንግበው መታገል ብቻ አማራጫቸው አይሆንም? የሚሉ ጥያቄዎች ናቸው። ይህ ራሱን የቻለ ርዕስ ነው። ጠቆም አድርጎ ለማለፍ ያህል፤ ጠመንጃ አንግቦ ለትግል በመነሳት ሕዝባዊ ድልን ለመቀዳጀት፤ ወሳኝና መኖር ያለባቸው ግዴታዎች አሉ። መፈለግ ለብቻው ወሳኝ አይደለም። በጦርነት ማቸነፍ ይቻላል! የሚለው ብቻውን ወሳኝ አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ፤ በሰላም መንገድ እየተደረገ ያለው ትግል፤ በእውነት የሰላም ትግልን መንገድ የተከተለና፤ በትክክል ተተግብሮ ያለቀለት ነው ወይ? የሚለውን መመለስ ያስፈልጋል። ስለዚህ፤ በሰላም ወይንስ በትጥቅ ትግል የሚለውን፤ በሌላ ጊዜ እንመለከተዋለን። ከዚህ በፊት ይሄው ጸሐፊ ያቀረባቸው ጦማሮች አሉ። እነዚህን (http://nigatu.wordpress.com) ሄዶ መመልከት ይቻላል። እንግዲህ እዚህ ላይ፤ መድበለ ፓርቲና ኢሕአዴግ ሊቀራረቡና አብረው ሊሄዱ የማይችሉ መሆናቸው በግልጽ ሰፍሯል።

ሁለተኛው እውነታ ደግሞ፤ ምንም እንኳን ለረጅም ጊዜ በተደጋጋሚ በኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ ድርጅቶች ወደ አንድ ፓርቲ ለመዋሐድ እየተዘጋጁ ነው ተብሎ ከበሮው ቢደለቅም፤ ይህ ስብስብ፤ በአባል ድርጅቶች መካከል ያለው ትብብር ውስጡ ነቅዞ፤ ወደ አንድ ከመሄድ ይልቅ፤ በየድርጅቶቹ የየግል ፍላጎት መጎነታተሉ የስብስብ ውህደቱን እየወጣጠረው፤ ወደ ውድቀቱ በመሄድ ላይ ያለ መሆኑ ነው።

ከላይ እንደተጠቆመው፤ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባርን (ኢሕአዴግን) የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ሲመሰርት፤ የአራት “ትልልቅ” የፖለቲካ ድርጅቶች ጥምር አድርጎ ነው። እዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን፤ በጽሑፍ ያልሰፈረ ሁለት ክፍል አለ። ይሄም፤ “እኔ” የሚለው ራሱ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርና፤ “ሌሎች” የሚላቸው ቀሪውን የኢትዮጵያ ክፍል ይወክላሉ ብሎ የመደባቸው ድርጅቶች ናቸው። በነዚህ ሁለት ክፍሎች መካከል፤ የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አለ። ይህን በአእምሯችን እናስቀምጥና ወደ አራቱ “ትልልቅ” ድርጅቶች እንመለስ። እነሱም፤ ፩ኛ. የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ፪ኛ. የአማራዎች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ANDM) ፫ኛ. የኦሮሞዎች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (OPDO) ፬ኛ. የደቡብ ኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (SPDM) ናቸው። ሀገሪቱን ማስተዳደር ሲጀምር፤ ለመግዛት እንዲያመቸው፤ ተጨማሪ አምስት አናሳ የፖለቲካ ድርጅቶች አክሎበታል። እነሱም፤ ፩ኛ. የአፋሮች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ANDP) ፪ኛ. የኢትዮጵያ ሶማሊዎች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ESPDP) ፫ኛ. የሐረሬዎች ሊግ (HNL) ፬ኛ. የጋምቤላዎች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (GPDM) እና ፭ኛ. የቤንሻንጉልና ጉምዞች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (BGPDUF) ናቸው። እንግዲህ እኒህ እንዴት ተዋቀሩ? በምን ተገናኙ? እና የመሳሰለውን ለመመለስ፤ ወደ ጀማሪው ድርጅት ፊታችን ማዞር ይኖርብናል።

ከኢትዮጵያ ተገንጥዬ የራሴን መንግሥት እመሰርታለሁ ብሎ የተነሳው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ከተቋቋመ በኋላ፤ በትግራይ ውስጥ ያለኔ ሌላ ድርጅት መኖር የለበትም የሚል ስሌት ይዞ፤ መጀመሪያ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባርን (TLF) ደመሰሰ። ቀጥሎ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊትን (EPRP) ከትግራይ ወግቶ አስወጣ። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረትን (EDU) በታተነ። በተጨማሪም የሁለት ነፃ አውጪ ግንባሮች መፋለሚያ ታዛ በነበረችው ኤርትራ ውስጥ በመግባት፤ የኤርትራዊያን ነጫ አውጪ ግንባርን (ሸዓብያ – EPLF) በማገዝ፤ የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባርን (ጀብሃ – ELF) አብሮ ወግቶ ደመሰሰ።

ይህ ነው አሁን ኢሕአዴግ በመባል የሚታወቀው ድርጅት። ኢሕአዴግ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የመግዣ ስሙ ነው። ይህ ድርጅት በፈጠራቸው ድርጅቶችና በራሱ ስም ሀገሪቱን ይገዛል። እያንዳንዱ የተፈጠረ የስብስቡ አባል ድርጅት፤ የራሱ የሆነ ክልል አለው። የራሱ “የተወሰነ” ነፃነት አለው። የራሱ የሆነ “ሕዝብ” አለው። እናም ሊያሳድገው ወይንም ሊያጠፋው የሚችለው፤ ተገዥ ወገን አለው። ታዲያ ይህ ሁሉ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ሥርና ፈቃድ ነው። እዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን፤ የኅብረተሰብ ሕልውናና የፖለቲካ ድርጅቶች ክስተት፤ በዕለት ተዕለት ግንኙነትና በፖለቲካ ገበያ ሥምሪት ልውውጥ፤ የራሱ የሆነ የእምርታ ዕድገት ሂደት ያገባና፤ ባልተጠበቀ መንገድ፤ ጉልበት ያበጃል። ትናንት የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አዛዥ ናዛዥ የነበረበት እውነታ፤ ሀገሪቱን በማስተዳደር ሂደቱ ላይ፤ ያዝዛቸው የነበሩት የፈጠራቸው ድርጅቶች፤ አንጻራዊ ነፃነት ማበጀታቸውና፤ ጡንቻቸውን ማፈርጠማቸው፤ አይቀሬ የኅብረተሰብ ክንውን ግዴታ ነው። እናም ዛሬ ብቅ ብቅ እያለ የምናየው የዚህን ሂደት ገጽታ ነው።

እኒህ በኢሕአዴግ ስም የተካተቱ ድርጅቶች፤ በመካከላቸው፤ ከሚመሳሰሉብት የሚለያዩበት ጉዳይ ይበልጣል። በመጀመሪያ፤ ሁሉም የሚወክሉት የየራሳቸው የተለያየ ክፍል አላቸው። እናም እያንዳንዳቸው ተጠሪነታቸውም ሆነ ተቆርቋሪነታቸው ለየብቻ ለየራሳቸው ክልል ነው። እያንዳንዳቸው በውስጣቸው የሚያስተዳድሩት፤ ከፌዴራሉ ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ የራሳቸውን ክልል ነው። እናም የፌዴራል መንግሥቱ፤ በፈቃደኝነት ያሉበት የስብስብ መዋቅር ነው። ይሄ ምን ያህል ሊቆይ እንደሚችል መገመቱ ከባድ አይደለም። አንድ ሆነው ለመቆየት ምክንያቱ የለም። እስካሁን ያቆያቸው ደርግ፤ ማስፈራሪያነቱ አደፈ። አማራን ማጥቃቱ ማሰባሰቢያነቱ ሻገተ። “እኔ የበላይ ልሁን!” “የለም እኔ የበላይ ልሁን!” የሚለውና፤ “እኔ ይሄ አለኝ!” “አንተ ይሄ ይጎድልሃል!” የሚል ፉክክር በቦታው ተተካ። እስካሁን የነበረው የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር መፍራትና የታዘዙትን ማድረግ ብቻ የነበረው እውነታ፤ እያደር በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ላይ ጥላቻና ቁጭት ተተክቷል። አንድ ሊሆኑ አይችሉም። በፍርሃት የተወጠረው ረገበ። በቦታው የጥላቻ ጥርስ ተነከሰ። እስካሁን የሚደረገው ማንኛውም የፌዴራል ጉዳይ፤ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የጉልበት የበላይነት ነበር። አሁን ተለወጠ።

የክልሎችን ቦታ ወስኖ ያስቀመጠው ይሄው ፈጣሪና ፈላጭ ቆራጭ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነበር። በክልል አወቃቀር ላይ፤ ማንኛቸውም ቢሆኑ ደስተኛ አይደሉም። ትናንት የትግራይን ክልል ለማበልጸግ ብሎ በጉልበቱ ከአማራው ክልል ቆርሶ የወሰደውን፤ የወልቃይት፣ የሁመራ፣ የጠለምት፣ የጠገዴ፣ የወሎ መሬት፤ ነገ የአማራው ክልል ገዥ የኔ ነው ቢል፤ ሊገርመን አይገባም። በፍርሃት ፈንታ ድፍረት፣ በመታዘዝ ቦታ ጥላቻ ነግሷልና! ለአዲስ አበባ አስተዳደር ከኦሮሞ ክልል ቆርሶ የወሰደውን መሬት የኦሮሞ ክልል ገዥዎች እንወስዳለን ቢሉ፤ ሊገርመን አይገባም። በደቡቡ ክልል ውስጥ ያሉት የተለያዩ ወገኖች፤ በውስጣዊ የደንበር መካለል ምክንያት ግጭት ማድረጋቸው አይቀሬ ነው። ለምን ቢባል ሁሉን ያደረገው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ በላያቸው ላይ የጫነው የይስሙላ ጥብቆ እንጂ፤ ሕዝባዊ መሠረትና ድጋፍ እንዲኖረው የአካባቢውን ሕዝብ ተሳትፎና ድጋፍ ያልጠየቀ ነበርና! ደግሞም በየክልሉ ያለ አስተዳደር፤ በጉልበት ያፈተተውን በማድረግ በደል ቢፈጽም፤ ለፌዴራሉ ገዥ ክፍል፤ በውስጥ አስተዳደሬ ጣልቃ አትግባብኝ ብሎ አንገቱን ቢያቀና፤ አያስደንቅም። አክሱም ለወላይታው ምኑ ነው ተብሏልና፤ ሞያሌ ላይ የደቡቡ ክልል አስተዳደር ከኬንያ በኩል ችግር ቢገጥመው፤ ሞያሌ ለፌዴራል መንግሥቱ ምኑ ነው? ይባል ይሆን? በባጀት ቢጣሉ፣ በሕዝብ ቁጥር ቢነታረኩ፣ በክልል ደንበር ቢጋጩ፣ በፌዴራሉ ውክልናቸው፤ “እኔ የበላይ!” “እኔ የበላይ!” ተባብለው መኳረፉ፤ አይቀሬ ነው።

በርግጥ በፌዴራሉ ደረጃ፤ የኔን አባል አትሰሩ፣ የኔን አባል አትክሰሱ መባባሉ ታይቷል። እስከዛሬ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አባላት ብቻ የፈለጋቸውን ሲያደርጉ፤ የሌሎቹ አባላት አንገታቸውን ደፍተው መቀበላቸው ያለ ነበር። ይህ ግን ጧፉ በርቶ፤ ሰፈፉን አቅልጦ ጨርቁን አቃጥሎ ጨርሶ፤ በርሃኑ እየጠፋ ነው። ስለዚህ፤ በፌዴራሉ ለሚደረግ ማንኛውም ውሳኔና ተግባር፤ ተፎካካሪዎች እንጂ ተደጋጋፊዎች አይደሉም። ለፌዴራል ጉዳይ ሲሰለፉም፤ “እኔ ምን አገኛለሁ?” ከሚል እንጂ፤ “እስኪ ‘ሌሎች’ ምን ቸግሯቸዋልና ልርዳቸው!” ከሚል አይደለም። ስለዚህ ተፎካካሪዎች ናቸው። እስካሁን በአንድነት ያሰለፋቸው፤ የደርግ ማስፈራሪያነት ነበር፤ አበቃለት። ቀጥሎ የተተካው ከደርግ ወጥቶ የፀረ-አማራ አቋምቸውና የዚሁ ወገን ፍራቻቸው ነበር፤ ይህን ወገን እስኪቻላቸው ድረስ አጠቁት። አሁን ምን አለ ሊያዋህድ ቀርቶ እንዲተባበሩ የሚያደርጋቸው? ምንም! ስለዚህ እኒህ ተፎካካሪ ድርጅቶች የጥቅም ግጭት ነው በመካከላቸው የተረፈው። እናም አንደኛው ሌላኛውን መወንጀል ይከተላል። ከውስጡ መፈረካከስ ይቀጥላል። በዚህ ላይ፤ ወጣት አባሎቻቸው፤ ፍጹም የየግል ክልላቸውን የበላይነት ለመጠበቅ የሚቆሙ ይሆናሉ። የተማሩት ይሄንኑ ነውና! እናም ጠባብነት ንጉስ ይሆናል። ግጭቱ አይቀሬ ነው። ይሄንን ለማርገብና ጊዜ ለመግዛት፤ አጭር እርምጃ መውሰድ ይቻላል። ነገር ግን፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነባር አባላት፤ ይህ እንዳይሆን፤ የነሱን የበላይነት ለወጣት አባሎቻቸው እያስተማሩ ያሳደጉበት ሀቅ ስላለ፤ ራሳቸው ራሳቸውን አስረውታል። ወደኋላ ቢሉ በራሳቸው ወጣት አባላት የሚመቱት እነሱ ናቸው። እናም ወደፊት መግፋት ብቻ ነው ያላቸው ምርጫ።

ከዚህ ተነስተው፤ “ሌሎች” ክፍሎች ወታደራዊና የፖሊስ ኃይሎቻቸውን ማቋቁምና የውጭ ግንኙነታቸውን መመሥረት ተከታዩ እድገታቸው ነው። እስከዛሬ ይህ ሁሉ በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ፍላጎትና እምነት የሚካሄድ ነበር። የአማራዎች፣ የኦሮሞዎች፣ የደቡብ ኢትዮጵያዊያን ሆነ የሌሎች አናሳ የተባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች መስራች፤ ይሄው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነው። እናም ምን ጊዜም ቢሆን፤ ማንኛውም መዋቅር ሆነ የሂደት ውሳኔ፤ ለዚህ ወገነተኛ ቡድን ፍላጎት ተገዥ ካልሆነ፤ የመጀመሪያው አኩራፊ፤ ይሄው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ይሆናል። በመጀመሪያ ግጭቱን ፈጣሪ፤ ጥቅሜ ቀረብኝ በማለት፤ ይሄው ድርጅት ይሆናል። የመጀመሪያው ተገንጥሎ ለብቻው የሚሮጠውም ይሄው ድርጅት ነው። ለዚህም ከወዲሁ፤ ፌዴራላዊ የሆኑ ውሳኔዎችን፤ ክልሉን እንዲጠቅሙ አዘጋጅቷል። የዓለም አቀፍ አየር ማረፊያውን በትግራይ አዘጋጅቷል። ወታደራዊ ማዕከሎችን በትግራይ አቋቁሟል። በትምህርት የትግራይ ወገኖቹን በበላይነት አሰልፏል። አሁን ደግሞ የባቡር ሐዲድ ለትግራይ እንዲገባ፤ ፌዴራላዊ ወጪውን አስሸፍኗል። የሱዳን በር እንዲኖረው ከአማራው መሬት ጠቅልሎ ወስዷል። የሀገሪቱን ንብረት፤ በኤፈርት በኩል እጠቃሎ ትግራይ አግብቷል። ወሳኝ የፌዴራል መንግሥቱ ቦታዎች በሙሉ በአባላቱ ቁጥጥር ሥር ናቸው። ለስም እንኳ ከ”ሌሎች” ድርጅቶች የተወከሉ ሰዎች በኃላፊነት ላይ ቢቀመጡም፤ የወሳኝነቱን ሚና የሚጫወቱት፤ የዚሁ ድርጅት አባላት ናቸው። ስለዚህም የተስተካከለ የእኩልነት አሰራር በሌለበት ቦታ፤ አይቀሬው ግጭት ብቅ እያለ ነው። ይህ ከውጪ በሚደረግ ግፊት ሳይሆን፤ በራሱ በአደረጃጀቱና ( ማለትም፤ በዋናው በ”እኔ” ባዩ ድርጅትና በ”ሌሎች” ድርጅቶች መካከል ባለ አደረጃጀት ) በሂደቱ ምክንያት አይቀሬ ሆኖ የሚታይ ሀቅ ነው።

እንግዲህ በክልሎቹ መካከል የሚነሳው ግጭት ለሀገሪቱ ከፍተኛ አደጋ አለው። ይህ ወደ ሶስተኛው ነጥብ ይወስደናል። ሶስተኛው ገጦ የሚታየው እውነታ፤ አሁን በያዝነው ሂደት፤ ሀገራችን እጅግ ወደ ከፋና ልትወጣበት ወደማትችለው መቀመቅ ውስጥ እየዘቀጠች መሆኗ ነው። የክልሎች መጋጨት፤ የማይሰራ የፌዴራል መዋቅር ከላይ ተቀምጦ፤ ጉልበተኛ የክልል ገዥዎች የፈለጉትን የሚያደርጉበትን ሀቅ ያሳየናል። የኢትዮጵያ መንግሥት የሚባለው በኖ ይጠፋል። እኒህ የየክልል ገዥዎች ደግሞ፤ በምንም መንገድ በስምምነት ጎረቤት እንኳን ሆነው የሚኖሩበት ሁኔታ እንዳይኖር፤ በጠላትነት የሚፋረጁ ስለሚሆን፤ በመካከላቸው የማይበርድ ጦርነት አይቀሬ ነው። የሕዝብ ቁጥር መጨመር፣ የአካባቢ ንብረት መመንመን ወይንም አዲስ ሀብት በአንዱ አካባቢ መገኘት፣ ከውጪ በሚደረግ የጥቅም ድጋፍ አንዱ ከሌላው በልጦ መገኘት፣ በሃይማኖት ምክንያት በጎረቤት ክልሎች መካከል የሚፈጠረው ልዩነት መስፋት፣ ክልሎችን የበለጠ እንዲራራቁና አክርረው እንዲጋጩ ያደርጋል። ይህ ነው የነገዋ የሀገራችን የኢትዮጵያ ጣጣ። “እኔ የበለጠ ላግኝ፤ የለም እኔ የበለጠ ላግኝ!” በሚል የተጣሉ ክልሎች፤ ከተለያዩ በኋላ ፍርሻው የሚያስከትለው መዘዝ፤ የማይጨበጥ እሳት ነው። ይህ ሁሉ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የፖለቲካ ቀመር ውጤት ነው። ውጤቱ ደግሞ አይቀሬ ነው።

መዝጊያ፤

ውጤቱ ቢያስፈራንም፤ በሀገራችን ላይ ከላይ የተጠቀሰው አደጋ የመከሰት እድሉ ያየለ ነው። በሂደት የዚህ ድርጅት የፖለቲካ ስሌት ሊስተካከል ሲገባው፤ አክራሪ የሆነው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ በጀመረው ጠባብ ዓላማ አሁንም መግዛት ስለያዘ፤ መገራት አቃተው። እናም ለዚህ አይቀሬ እውነታ ዳርጎናል። በርግጥ ስለማንፈልገው፤ ሊሆን አይችልም ብለን ልንሸመጥጥና ልንክደው እንችላለን። ይሄን ጸሐፊም ማብጣልጣል እንችላለን። ያ ግን፤ ሊሆን አደግድጎ የመጣውን ሀቅ፤ አይለውጠውም። ይልቅስ አሁን በቁጥጥራችን ሥር ያለውንና ማድረግ የምንችለውን መጀመር አለብን። በቁጥጥራችን ሥር ያለውና ማድረግ የምንችለው፤ በመጀመሪያ፣ የትግሉን ምንነት በአንድነት መቀበል ነው። ይህ ትግል የነፃነት ትግል ነው። ይህ ትግል የኢትዮጵያዊያን በሙሉ ትግል ነው። ይህ ትግል የዛሬ ነው። ይህ ትግል ከያንዳንዳችን የሚጠብቀው አስተዋፅዖ አለ። በመሳተፍ እናበርክት።

ይህን ትግል በአንድነት የምናደርገው እንጂ፤ እያንዳንዱ ድርጅት ለየራሱ ባፈተተው የሚጋልብበት ሜዳ አይደለም። እናም የትግሉ የመጀመሪያ አጭር ግብ፤ ታጋዮችን በሙሉ ወደ አንድ አሰባስቦ አንድ የትግል ማዕከል መፍጠር ነው። እናም በሀገራዊ ራዕይና ተልዕኮ፣ በጥቂት የመታገያ ዕሴቶች ዙሪያ መደራጀቱ፤ ግዴታ ነው። ይህን ግድ የሚለው፤ ተጨባጩ የሀገራችን የፖለቲካ እውነታ ነው። ዋናዎቹ ታጋዮች ያሉት በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ከፍተኛውን መስዋዕትነት በመክፈል፤ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ጋር ሌት ተቀን በኑሯቸው እየተገደዱ፣ እየተሰቃዩ፣ በእስር ቤት እየተንገላቱ፣ መታገያ ሰላማዊ ድርጅቶቻቸውን እየተቀሙ፣ ያሉት ሕዝቡና የሕዝቡ ታጋይ ልጆች ናቸው። ትግላቸው መስተካከል አለበት። ሰላማዊውን ትግል አንድ ድርጅት ብቻ ነው ሊመራው የሚገባ። በአንድ ሀገር ሁለትና ሶስት ሰላማዊ ትግል የለም። ግቡ ውስንና የጊዜው ገደብ ያለው የትግል አንድነትና መታገያ ድርጅት ነው ሊኖረን የሚገባ። አንድ ትግልና አንድ መታገያ ድርጅት ብቻ ነው የሚኖረው። አንድ የትግል ማዕከል እስካልተፈጠረ ድረስ ደግሞ፤ በተናጠል የምናደርገው ትግል፤ በተናጠል መመታትን ነው የሚጋብዘው። ትግሉ አንድ ነው። መታገያ ድርጅቱም አንድ መሆን አለበት። ይሄን እስካልተቀበልን ድረስ፤ የገዥውን እድሜ እያራዘምን ነው።

Read- PDF 

ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት በእምነት ሽፋን የወሲብ ቅሌት

0
0

ለክህደቱም በሰሜን አሜርካ የሚኖሩ ግብረ አባሮቹ ፓስተሮች እና የቤተክርስትያን ሽማግሌዎች በድርጊቱ ዋና ተዋናዮች ናቸው::

“ውሸተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አሰጸያፊ ነው፤ እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።” ምሳ 12: 22

ቢንያም መንገሻ September 25,2015

ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ከዚህ ቀደም የሰው ህጋዊ ሚስት በዝሙት እርኩሰት በማስነወር ለቀረበበት አቤቱታ ከረጅም ማንገራገር ቡኋላ በሚያደራድሩት የቤተክርስትያን ሽማግሌዎች እና እርሱን ለፓስተርነት በቀቡት የቤተክርስትያን መሪዎች ፓስተር ወዳጆቹ አማካኝነት አስነዋሪ ድርጊቱን ማድረጉን በግልጽ አምኖ ተቀብሎ ይቅርታ መጠየቁ በሁላችንም ዘንድ የሚታወስ የቅርብ ግዜ ታሪክ ነው:: እንደ ኢትዮጵያን አቆጣጠር በመስከረም ወር በወሩ መጀመሪያ ቀን 2008 ዓም አካባቢ ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት መቀመጫነቱ በሰሜን አሜርካ ላደረገው ዘ-አበሻ በሚባል የሚታወቀው የዜና አውታር ላይ የክህደት መልስ የመለሰው ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ለሶስተኛ ግዜ የአምላኩን ስም ተጠቅሞ ሰው ያደረገውን ኋያሉ እግዚያብሔርን ሽምጥጥ አድርጎ ክዶታል:: ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ዘ-አበሻ በሚባል የሚታወቀው የዜና አውታር እንዲህ ነበር ያለው:: “ሆቴል ክፍል ውስጥ ገብታ በጣም ስትፈታተነኝ ሌላ ጊዜ ፍላጎትሽን አሟላልሻለሁ አልኳት እጂ አልነካኋትም” “ቤተክርስቲያን መጥተው ያሰቡትን ያህል እኔን የጎዱኝ እና ያዋረዱኝ ስላልመሰላችው ቪ ኦ ኤ ሄደው ፓስተር ተከስተ አስገድዶ ደፍሮኛል ጉዳዩም በህግ ተይዞአል የሚል በሽምግልናው ወቅት በጭራሽ ያልተነሳ ሌላ ተጨማሪ የውሸት ታሪክ ፈጠሩ። ይህን አላማ እንዲያስፈጽም ጋዜጠኛ አዲሱ አበበን ይዘው መጡ። አቶ አዲሱ ጋር ስንነጋገር ሆን ብሎ እኔን ለማጥቃት እንዳሰበና እውነቱን ማወቅ እንደማይፈልግ ስለገመትኩ በጉዳዪ ለይ ምንም አይነት ኢንተርቪው ላንተ አልሰጥም፣ ጉዳዪም በቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ተይዟል አልኩት። የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ጉዳዩን የያዙትም ሽማግሌዎችም አቶ አዲሱን ይሄ የቤተክርሰቲያን ነገር ነው በዚህ ነገር ላይ ምንም አይነት ፕሮግራም በሬዲዩ ላይ መሥራት የለብህም ብለው እየነገሩትና እየተለመነ በማን አለብኝነት ጉዳዩን አጣሞ ሁላችሁም እንደሰማችሁት እኔን በሚያዋርድ ፣ስሜን በሚያጠፋ፣ ሕይወቴንና አገልግሎቴን በሚያበላሽ መልኩ ፕሮግራሙን ሰርቶ በሬድዮ አቀረበው።”

የእግዚያብሔር ቃል ስለሚክዱ ውሸታም ሰዎች ዋና አፈጣጠራቸውን ምንጩ ማን እንደሆነ እንዲህ ይናገራል:: “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።” ዮሐ 8:44

ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት የአምላኩን ስም ተጠቅሞ ሰው ያደረገውን ኋያሉ እግዚያብሔርን ለሶስተኛ ግዜ ሽምጥጥ አድርጎ ለምን ካደ?

ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ግልጽ ክህደትን ሁላችንም የሚያስታውሰን እና የምናውቀው አንድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ የሚገኝ ትልቅ ታሪክ አለ:: ይህም ታሪክ የእግዚያብሔር ሐዋርያው የቅዱስ (ስምኦን) ጴጥሮስ የክህደት ታሪክን እናገኛለን:: ሐዋርያው (ስምኦን) ቅዱስ ጴጥሮስ በአስጨናቂው ሰአት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ሶስት ግዜ የካደው በዘመኑ አይሁድ ለአምላካቸው ካላቸው ታላቅ ቅናት የተነሳ ለመበቀል በድንጋይ ወግሮ የመግደል የሀይማኖታዊ ልማድ ነበራቸው:: ስለዚህ ሐዋርያው ቅዱስ (ስምኦን) ጴጥሮስም በድንጋይ ተወግሮ ሞትን ፍራቻ ብቻ ጌታውን ኢየሱስ ክርስቶስን ሶስት ግዜ መካዱ የሚታወቅ ሲሆን ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጌታ ኢየሱስ ላይ የተናገረው የክህደት ቃል እራሱን ክፉኛ የተጸጸተበት እንዲሁም እራሱን የወቀሰበት ምርር ብሎ ያለቀሰበት ድርጊት እንደነበር በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ በግልጽ ተጽፎ እናገኘዋለን:: ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ግን የጠራው እራሱ እግዚያብሔር ስለነበር እስከመጨረሻ የህይወት ዘመኑ ህይወቱን ለእግዚያብሔር ወንጌል አሳልፎ እንደሰጠ እና እንደተሰዋ መጽሐፍ ቅዱሳችን በግልጽ ያስተምረናል::

ወደ ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ክህደት ስንመለስ ዘንዳ ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት እግዚያብሔርን ሶስት ግዜ የካደው በድንጋይ ተወግሮ እንዳይገደል:: ወይንም በሴፍ እራሱን ተቀልቶ እንዳይገደል ሳይሆን የአምላኩ የእግዚያብሔርን ስም ጠርቶ ዘፍኖ የሚኖርበትን መተዳደሪያ ስሙ እንዳይጠፋበት በማሰብ ብቻ ነው:: “ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል። ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።” 2ጴጥ2:1-3

ከእራሱ ከእግዚያብሔር ዘንድ ተመርጠው በዝሙት ወጥመድ ተይዘው የወደቁ ታላላቅ የእግዚያብሔር ሰዎች ስማቸው እና ምግባራቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ተጽፎ እናነባለን:: ከእነዚህም መካከል የእሰይ ልጅ ንጉስ ዳዊት፣ የንጉስ ዳዊት ልጅ ጠቢቡ ሰለሞን እና ጸጉራሙ እና ሀያላኑ ሳምሶንን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል:: እነዚህ የእግዚያብሔር ሰዎች በእግዚያብሔር ላይ እጅግ ክፉ የሆነውን ሀጥያት በሰሩ ግዜ አልሰራንም አላደረግንም ብለው አይኔን ግንባር ያድርገው ብለው ሽምጥጥ አድርገው አልካዱም:: እንዲያውም ማቅ ለብሰው ባደባባይ ወዮ! አምላካችን እግዚያብሔርን በድለናል ብለው የንስሀ ጬኀት በመጮህ እግዚያብሔርን ይቅርታ ጠየቁ እንጂ በየትኛውም ቦታ ሲያስተባብሉ እና ሲክዱ አልታዩም:: ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ግን ከእግዚያብሔር ስላልተጠራ ሀጢያት በሰራ ግዜ በዙሪያው ምስክሮቹን አስቀምጦ ለሶስተኛ ግዜ ካደ እንጂ በድርጊቱ ተጸጽቶ ንስሀ አልገባም:: ይህ የሚያሳየን ነገር ደግሞ ሀጢያት እርኩሰት ሲያደርጉ ሳይዋሹ እና ሳይክዱ መጸጸት እና ንስሀ መግባት የሚችሉት አገልጋዮች ከእግዚያብሔር ዘንድ የተጠሩ ብቻ መሆናቸውን ዘማሪ እና ፓስተር ተከስተ ጌትነት ህይወት አስረግጦ ያስተምረናል:: “ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።” 1 ዮሐ 1:8_10 “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤ ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።” ምሳ 6:16_19

አለምነህ ዋሴ ስለ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የሆነችው ነገር አለ ይላል –ከርሷ ወይም ከቤተሰቦቿ እንስማው ሲልም ይጠይቃል (ያድምጡ)

0
0

አለምነህ ዋሴ ስለ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የሆነችው ነገር አለ ይላል – ከርሷ ወይም ከቤተሰቦቿ እንስማው ሲልም ይጠይቃል (ያድምጡ)

New Music: Tedy Afro & GG – Ft Garrison Hawk – Jegena Ayeferam (survive)


የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል አቶ ናአምን ዘለቀ በ “ለጥያቄዎ መልስ” ዝግጅት ላይ – (VOA: ትዝታ በላቸው)

0
0

ዋሽንግተን ዲሲ

ትዝታ በላቸው/VOA

Neamin Zeleke -- Satenaw

የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል አቶ ናአምን ዘለቀ

የአርበኞች ግንቦት ሰባት የዓለም አቀፍ አመራር የዉጭ ግንኙነት ሃላፊና የንቅናቄዉ ምክር ቤት አባል አቶ ነአምን ዘለቀ፣ በኢትዮጵያ ስልጣን ለመያዝ ሳይሆን በስልጣን ላይ ያለዉን መንግስት አስወግዶ አገሪቱን ለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማመቻቸት ነዉ ብለዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት የዓለም አቀፍ አመራር የዉጭ ግንኙነት ሃላፊና የንቅናቄዉ ምክር ቤት አባል አቶ ነአምን ዘለቀን በዝግጅቱ ላይ ለአድማጮች በሰጡት መልስ የአገር አድን ጥምረት ንቅናቄ የተፈጠዉ በኢትዮጵያ ስልጣን ለመያዝ ሳይሆን በስልጣን ላይ ያለዉን መንግስት አስወግዶ አገሪቱን ለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማመቻቸት ነዉ ብለዋል። በእርሳቸዉ አገላለጽ የድርጅታቸዉ ዋና የትግራይን ሕዝብ በማይወክሉ ባሉዋቸዉ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች የተመሰረተ ኢዴሞክራሲያዊና አድሎኛ መንግስት ገርስሶ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለፍትሃዊ ስርዓት ማብቃት ነዉ። አብዛኛዉ የትግራይ ሕዝብ እንደተቀረዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ የስርዓቱ ሰለባ ነዉ ብለዋል የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል አቶ ነዓምን ዘለቀ።

በቀደሙት ዓመታት በጦርነት ተጎድታለች፥ ሕዝብ አልቋል ደህይቷል በሰላም ለምን አትታገሉም ሲሉ አድማጮች ላቀረቡት ጥያቄ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎች በተደጋጋሚ ለቀረቡ የብሔራዊ እርቅ ጥሪዎች ፈቃደኞች ሆነዉ አልተገኙም ብለዋል አቶ ነዓምን።

ኤርትራ ካሁን ቀደም በድንበርዋ ዉስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን አስራለች ግድላለች፥ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን አትተባበርም ይልቁንም አንድነትዋ እንዲበትን ትፈልጋለች እንዴት አስመራ ጋር ትተባበራላችሁ የሚሉ ጥያቄዎችም ቀርበዋል ከአድማጮች።

አቶ ነዓምን በሰጡት መልስ ኤርትራ ዉስጥ የታሰሩ ወይም የተገደሉ ኢትዮጵያዉያን የአገሪቱ ጸጥታ ላይ አደጋ የጋረጡ ናቸዉ የኤርትራ መንግስት ግን ሰላምና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ኢትዮጵያ ዉስጥ እንዲሰፍን ይፈልጋል ብለዋል የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል አቶ ነዓምን ዘለቀ።

ሙሉዉን ዝግጅት የተያያዘዉን የሁለት ክፍል ድምጽ ፋይሎቻትችንን በመጫን ያድምጡ።

 

የእስክንድርያ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ የኢትዮጵያ ጉብኝት መርሐ ግብር

0
0

pat-abune-mathias-and-pope-abune-tawodros1
፻፲፰ኛው የእስክንድርያ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባደረጉላቸው ወዳጃዊ ጥሪ መሠረት ባለፈው ፳፻፯ ዓ.ም.፣ ከጥር ፩ – ፯ ቀን ድረስ በግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የስድስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በጉብኝታቸው ማጠናቀቂያ ላይ በቀጥታ ስርጭት ለብዙኃን መገናኛ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ በ፳፻፰ ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ላይ እንዲገኙ ጋብዘዋቸዋል፡፡ ግብዣውን የተቀበሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ፣ መስከረም ፲፬ ሌሊት አዲስ አበባ የገቡ ሲኾን ከዛሬ መስከረም ፲፭ እስከ ፲፱ ቀን ድረስ የአምስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡

ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እና ከኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት እንደተገኘው፣ የቅዱስነታቸው የጉብኝት መርሐ ግብር የሚከተለው ነው፡፡


  • ቅዱስነታቸው መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሌሊቱ 9:00 ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሚደርሱበት ጊዜ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና የፕሮቶኮል ባለድርሻ አካላት አቀባበል ይደርግላቸዋል፡፡
  • Ethiopia-Mathias-I-Egypt-Pope-Tawadros-II-meet-in-Cairo-2ቅዳሜ መስከረም 15 ቀን፣ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሓላፊዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ መዘምራንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት፣ ‹‹የእንኳን ደኅና መጣችኹ›› ፕሮግራም ይከናወናል፤ በዚኹም ዕለት ከሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ፡፡
  • እሑድ መስከረም 16 ቀን፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ በቦሌ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ተገኝተው ሥርዐተ ቅዳሴውን በመምራት ጸሎተ ቅዳሴው ይፈጸማል፡፡ ከቁርስ እና ከምሳ ዕረፍት በኋላ በመስቀል ደመራ ክብረ በዓል ላይ ለመገኘት በክብር ታጅበው ወደ ዐደባባዩ ያመራሉ፤ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጋር በመኾን ያከብራሉ፡፡
  • ሰኞ መስከረም 17 ቀን፣ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አኵስም ጽዮንና በታሪካዊ ቦታዎች ኹሉ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ ከሰዓት በኋላ ደግሞ የጎንደርን ታላላቅ አድባራት እና ታሪካዊ ቦታዎች ይጎበኛሉ፡፡
  • ማክሰኞ መስከረም 18 ቀን፣ በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጉብኘት ይደረግና ወደ አዲስ አበባ መልስ ኾኖ ከተወሰነ ዕረፍት በኋላ በሒልተን ሆቴል የራት ግብዣ ይደረጋል፤ የስጦታ መርሐ ግብር ይካሔዳል፡፡
  • ረቡዕ መስከረም 19 ቀን፣ ወደ ታላቁ ደብረ ሊባኖስ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አምርተው ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ ከዚኹ መልስ በጌቴሰማኔ ቤተ ደናግል ወጠባባት ገዳም ከመነኰሳዪያት ጋር አጭር ውይይት ይካሔዳል፤ ከቤተ ደናግሉ የሥራ ውጤቶች ስጦታ በገዳሙ ከተበረከተ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ይደረጋል፡፡
  • በዚኹ ዕለት በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል፣ የሰማዕቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ኹለተኛ ፓትርያርክ መካነ መቃብር ጸሎት ይደረጋል፡፡ በመጨረሻም ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ የኹለቱም ቅዱሳት ሲኖዶሳት አባላት ዝግ የኾነ ትውውቅ እና አጭር ውይይት ያደርጋሉ፡፡
  • ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የተወሰኑ የመንበረ ፓትርያርክ ሓላፊዎች በተገኙበት ቅዱስነታቸው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር በቅዱስ ሲኖዶስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከ10፡00 – 12፡00 ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ፡፡
  • ከጋዜጣዊ መግለጫው በኋላ የጋራ የፎቶ መርሐ ግብር ይደረጋል፡፡ በዚኹ ዕለት ምሽት 3፡00 ይፋዊ የአሸኛኘት ሥነ ሥርዐት በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ይኾናል፡፡

የቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ዘመቻ ለምን?

0
0

(አፈንዲ ሙተቂ)
—-
ዘመቻው የተጀመረው የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ ይመስለኛል፡፡ ለመጀመሩ ምክንያት የሆነው ደግሞ “ቢቢሲ ትኩረቱን በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ላይ ያደረገ የስርጭት ፕሮግራም ይጀምራል” የሚል ዜና መነገሩ ነው፡፡ ታዲያ ይህንን ዜና ተከትሎ “የስርጭት ቋንቋዎቹ አማርኛ እና ትግርኛ ናቸው” የሚል ወሬ ተደመጠ፡፡ ነገሩ እስከ አሁን ገፍቶ ባይመጣም በትክክል ተብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም የውጪ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱን ነገር ለመወሰን ሲነሱ በቅድሚያ የሚያዩት በየሀገራቱ ውስጥ በኦፊሴል የሚሰራባቸውን ቋንቋዎች ነው፡፡ ትግርኛ በኤርትራ፣ አማርኛም በኢትዮጵያ የኦፊሴል ቋንቋ የመባል ደረጃ ያላቸው በመሆናቸው ቢቢሲ በዚሁ ምክንያት ፕሮግራሙን በሁለቱ ቋንቋዎች ለማስተላለፍ ወስኖ ሊሆን ይችላል፡፡ በየሀገራቱ ውስጥ ያሉት ቋንቋዎች ተናጋሪ ብዛት ሲታይ ግን አፋን ኦሮሞ ከሁሉም ይቀድማል፡፡
እንደሚታወቀው በሬድዮ የሚተላለፍ ፕሮግራም የሚሻው አድማጭ እንጂ አንባቢ አይደለም ፡፡ ስለዚህ በኤርትራና በኢትዮጵያ ላይ የሚያተኩረው አዲሱ የቢቢሲ የስርጭት ፕሮግራም አድማጮችን ታሳቢ ያደረገ መሆን ይገባዋል ተብሎ ነው የሚታመነው፡፡ ለቢቢሲም ሆነ ስርጭቱ በሚያተኩርባቸው ሀገራት በጣም የሚጠቅመው አካሄድ ይኸው ነው፡፡ እናም ይህንን ያዩ ተመልካቾች “ቢቢሲ የቪኦኤን ሞዴል ቢከተል የተሻለ ነው፤ አፋን ብዙ ተናጋሪ ያለው አፋን ኦሮሞ ከሁለቱ ቋንቋዎች ጋር መደመር አለበት” በማለት በኢንተርኔት የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ ጀመሩ፡፡ እኛም ዘመቻው ተገቢ ሆኖ ስላገኘነው ፊርማችንን ሰጠነው፡፡ ሌሎችም እንዲፈርሙ መቀስቀሱንም ተያያዝነው፡፡
bbc affaan oromo
በእስካሁኑ ሂደት የፈረመው ሰው ብዛት ወደ ሳላሣ ሺህ እየተጠጋ ነው፡፡ በኢንተርኔት ላይ ሆነን እንደታዘብነው ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው፡፡ ሁሉም ወገኖች ዘመቻውን በበጎ መልኩ እያዩት ነው፡፡ እነ አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ዓሊ ቢራን የመሳሰሉ ታላላቅ ሰዎችም የድጋፍ ፊርማቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሌሎችም ድጋፋቸውን እንዲሰጡ እየቀሰቀሱም ነው፡፡ ይህ በጣም ጥሩ ነው፡፡ በተለይም የኢንተርኔቱ ዓለም ከሚታወቅበት “ጽንፋዊ” (polarized) አካሄድ ወጥተን ሁላችንም ፊርማችንን ማኖራችን በእጅጉ የሚያስደስት ነገር ነው፡፡

የድጋፍ ፊርማችንን ያኖርነው በሙሉ በጎን የማሰብ ዓላማ እንጂ ሌላ ተቀጥላ መነሻ የለንም፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ምክንያቶች በደንብ የተብራሩ አይመስለኝም፡፡ በመሆኑም በጉዳዩ ዙሪያ ይህንን ጽሑፍ አሰናድቼአለሁ፡፡

እንደሚታወቀው “አፋን ኦሮሞ” (ኦሮምኛ) በአፍሪቃ ምድር እጅግ ብዙ ተናጋሪዎች ካሉት ቋንቋዎች አንዱ ነው፡፡ 40 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ቋንቋውን በአፍ መፍቻነት ይናገረዋል፡፡ ከስድስት ሚሊዮን የማያንሱ ህዝቦችም ኦሮምኛን በሁለተኛ ደረጃ ይናገራሉ፡፡ ይሁንና ኦሮምኛን ከሚናገረው ህዝብ መካከል ከ3/4 የሚልቀውና በገጠር የሚኖረው ህዝብ ከኦሮምኛ ውጪ ሌላ ቋንቋን አይናገርም፤ አይሰማም (ነገሩን በተነጻጻሪነት ለማወቅ ካሻችሁ የኦሮሚያ ክልል የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤትን ተመልከቱት)፡፡ ስለዚህ የቢቢሲ ስርጭት ኦሮምኛን ከዘነጋ ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ አይሆንም ማለት ነው፡፡

ታዲያ የሚገርመው ደግሞ በሬድዮ የሚሰማውን ፕሮግራም ከማንም በላይ የሚከታተለው የገጠሩ ህዝብ ነው፡፡ የከተማው ህዝብ በዝንባሌው ለቴሊቪዥን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ለኤፍ ኤም ሬድዮ ነው የሚያደላው፡፡ ቢቢሲ በሬድዮ ፕሮግራሙን ሲጀምር ተጨማሪ አማራጭ የሚፈጠርለት በአብዛኛው ለገጠሬው ህዝብ ነው፡፡ ነገር ግን ኦሮምኛ ከአዲሱ ፕሮግራም ውስጥ ከተዘነጋ የገጠሩ የኦሮሞ ህዝብ ሌሎች ቋንቋዎችን ባለመቻሉ እድሉ ሊያመልጠው ነው፡፡ እንግዲህ ቢቢሲ አፋን ኦሮሞን በስርጭት ሽፋኑ ውስጥ እንዲያካትት በድጋፍ ፊርማ መጠየቁ የተፈለገበት አንደኛው ምክንያት ይህ ነው፡፡

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ለህዝቡ አማራጭ የመፍጠር ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ከላይ የተገለጹትን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የኦሮምኛ ተናጋሪዎች የሚመለከት ነው፡፡ እንደሚታወቀው በሶስተኛው ዓለም ሀገራት በአጭር ሞገድ የሚተላለፉ ሬድዮዎች በመንግሥታት የተያዙ በመሆናቸው ህዝቦች መረጃን ከነጻ ምንጭ የማግኘቱ ጉዳይ በጣም ይቸግራቸዋል፡፡ በግል፤ በፖለቲካ ፓርቲ እና በኮሚኒቲ እየተቋቋሙ ወደ አፍሪቃ ምድር ስርጭታቸውን የሚያስተላልፉ ሚዲያዎች በበኩላቸው መንግሥታቱን ለማጋለጥ በሚል ነገሮችን ከልክ በላይ እየለጠጡና እያጋነኑ ለአድማጩ ስለሚተርኩ ግራ መጋባትንና መደናገርን ይፈጥራሉ፡፡ ቢቢሲ፣ ቪኦኤ፣ ዶቼ ቬሌ ወዘተ.. የመሳሰሉት ግን ከሁሉም የተሻሉ ነጻ ሚዲያዎች በመሆናቸው በነርሱ የሚተላለፉት ዘገባዎች ለእውነታ የቀረቡ መሆናቸው ይታመናል፡፡ እናም ቢቢሲ በአፋን ኦሮሞ ፕሮግራም ጀመረ ማለት ኦሮምኛን የሚሰማውና የሚናገረው ህዝብ ነጻ መረጃ የሚያገኝበት እድል ጨመረ ማለት ነው፡፡

ሶስተኛው ምክንያት ደግሞ የቢቢሲ በኦሮምኛ ፕሮግራም መጀመር ለአፋን ኦሮሞ እድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወት መሆኑ ነው፡፡ ቢቢሲ ሁሉንም አቀፍ እና በቢሊዮን የሚቆጠሩ አድማጮች ያሉት ተቋም ነው፡፡ የጣቢያው ስርጭት በተመራጭነቱ ቀዳሚ እንዲሆን ያስቻለው በየፕሮግራሙ የሚያስተላልፈው ጭብጥና ይዘት ብቻ ሳይሆን ቀዳሚነቱን ለማስቀጠል የሚያከናውናቸው ተያያዥ መርሐ ግብሮች ጭምር ነው፡፡ ከነዚህ መርሐ ግብሮች አንዱ ስርጭቱን የሚያስተላልፍባቸው ቋንቋዎችን ለማዘመን፣ ለማሳደግ እና ለማስተዋወቅ የሚያደርገው ጥረት ነው፡፡ ተቋሙ ፕሮግራሙን ሲያስተላልፍ የዘፈቀደ የቋንቋ አጠቃቀምን አይከተልም፡፡ ቢቢሲ እያንዳንዱን ቋንቋ በማጥናት የቋንቋው አድማጮች ሁሉ ሊረዱት የሚችሉትን አቀራረብ ይወጥንና በዚያ መሰረት ስርጭቱን ያስተላልፋል፡፡ ራሱ የሚገለገልበት BBC-Standard የተባለ የቋንቋ አጠቃቀም ዘይቤም አለው፡፡

በሌላ በኩል ቢቢሲ ስርጭቱን በሚያስተላልፍባቸው ቋንቋዎች ዙሪያ በሚደረጉት ምርምሮችም ተሳትፎ ያደርጋል፡፡ ቋንቋውንም ለማስተማር ልዩ ልዩ ጥረቶችን ያደርጋል (ለምሳሌ የቢቢሲ የዐረብኛው ፕሮግራም Learn BBC Arabic የተባለ ፕሮግራም አለው)፡፡ በቋንቋው የሚሰለጥኑ ተማሪዎችንም ይደግፋል፡፡ በቋንቋው የሚጻፉ የስነ-ጽሑፍ ውጤቶችን ያበረታታል፡፡ በሬድዮ ጣቢያውም ድርሰቶቹን ያስተዋውቃል፡፡ እነዚህ ተያያዥ ተግባራት ለኦሮምኛ ቋንቋ እድገት እጅግ በጣም ይጠቅማሉ፡፡
እንግዲህ “ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ” የተሰኘውን ዘመቻ ለመደገፍና ሌሎችም ድጋፋቸውን እንዲሰጡት ለመቀስቀስ የወሰንኩት እነዚህን ሁሉ መነሻዎች ካጤንኩ በኋላ ነው፡፡ በመሆኑም ለቋንቋው እድገት የሚቆረቆር እና በተለይም በገጠሩ የሚኖረው ህዝባችን አማራጭ ሚዲያ እንዲፈጠርለት የሚሻ ሰው በሙሉ ሊሳተፍበት የሚገባ ታሪካዊ ዘመቻ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ከዚህ ቀደም “ኦሮምኛን መማር እፈልጋለሁ” ፣ “ኦሮምኛ ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር ያለው ተዛምዶ ለማጥናት ወስኛለሁ”፣ “የዓሊ ቢራን ዘፈን ግጥሞች ትርጉም ማወቅና በርሱ ዙሪያ መጻፍ እሻለሁ” ወዘተ… ስትሉኝ ለነበራችሁት ወዳጆቼ ደግሞ ዘመቻው የናንተንም ሆነ ተመሳሳይ ፍላጎትና ዝንባሌ ያላቸው ሌሎችም ሰዎች ምኞታቸውን እውነት ሊያደርጉ የሚችሉበትን ውጤት ለማምጣት የሚረዳ በመሆኑ ተሳትፎአችሁ በእጅጉ ይጠበቃል፡፡

ይህ ዘመቻ ማንንም የመጉዳት ዓላማ የለውም፡፡ ዘመቻውን የጀመሩት ሰዎችም ሆኑ በሂደት የተቀላቀሉት ሁሉ ይህንን ጉዳይ በይፋ አስታውቀዋል፡፡ እያሳወቁም ነው፡፡ እኔም ደግሜ አስታውቃለሁ፡፡ ለምሳሌ ቢቢሲ የአማርኛውንም ሆነ የትግርኛውን ፕሮግራም እንዲያስቀር በጭራሽ አልተጠየቀም፡፡ ሊጠየቅም አይችልም፡፡ እንዲህ ብሎ መጠየቁ ከመጥፎ ምሳሌነቱ ሌላ ጥያቄው ተቀባይነት እንዳይኖረው ማድረግ ነው፡፡ ጥያቄው የቀረበው ቢቢሲ የቪኦኤን አርአያ በመከተል ስርጭቱን በሶስቱ ቋንቋዎች እንዲጀምር ነው (ስርጭቱን የሚያስተላልፍበትን የጊዜ መጠን የመወሰኑ ስልጣን የጣቢያው ነው፤ ያንን እኛ አንወስንለትም)፡፡ በመሆኑም ይህ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል፡፡
—-
ስለዚህ ወዳጆቻችን ሆይ!
ይህ ዘመቻ የተቀደሰ ሃሳብ ያለው ነው፡፡ የድጋፍ ፊርማችሁን በማኖር የዘመቻው ደጋፊ እንድትሆኑ በአክብሮት ትጠየቃላችሁ፡፡ ለዚህ ደግሞ ብዙ መሰዋት አያስፈልጋችሁም፡፡ ሶስት ደቂቃ ብቻ ወስዳችሁ ለዚሁ የተዘጋጀውን petition መፈረምንና ወደሚፈለግበት ቦታ send ማድረግን ብቻ ነው የሚጠይቀው፡፡ እናም ቀጥሎ የተመለከተውን ሊንክ ከፍታችሁ ፔቲሽኑን ፈርሙልን!! ዳይ
https://www.gopetition.com/…/bbc-consider-afan-oromo-for-ne… —-
ማስታወሻ
• ፔቲሽኑን መፈረም ማለት ሊንኩን ከፍቶ ፎርሙን መሙላት ነው:: ስለዚህ ሊንኩን ከፍታችሁ ወደ መፈረሚያው ሂዱልን!! ፎርሙ የሚመጣላችሁ sign the petition የሚለውን ቦታ ስትነኩት ነው፡፡
• ፔቲሽኑን ለመፈረም የግዴታ የኢ-ሜይል አድራሻችሁን ማስገባት አለባችሁ፡፡ ከዚያም የቀረቡትን ጥያቄዎች በመከተል ፎርሙን መሙላት ይገባችኋል፡፡ መጨረሻ ላይ የተሞላውን ፎርም send አድርጋችሁ ስታበቁ ፊርማውን ስለመስጠታችሁ ማረጋገጫው በኢ-ሜይል ይላክላችኋል፡፡

ግብጾቹ ግድቡ በእነርሱ ቁጥጥር ስር መሆኑን ተናግረዋል

0
0

grand-renaissance-dam-1
ከዳዊት ሰለሞን

በግብጽ በተፈጠረ የውሃ እጥረት ምክንያት የአገሪቱ ሚዲያ እጥረቱን ከአባይ ግድብ አያይዞት ነበር።የአገሪቱ የውሃ ሃብት ሚንስትር በበኩላቸው እጥረቱና ግድቡ አይገናኙም በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።ሚንስትሩ ለዚህ ሁለት ምክንያቶችን አስቀምጠዋል።
ምክንያት1
ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ ግድቡ በታችኛዎቹ የተፋሰስ አገራት ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ ሳይታወቅ ግድቡን በውሃ መሙላት እንደማይጀመር መስማማታቸው::
ምክንያት 2
ግድቡ ላይ የሳታላይት ቅኝት እያደረግን እንገኛለን ።በዚሁ መሰረትም ውሃ ወደ ግድቡ መግባት አለመጀመሩን እናውቃለን ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከሁለቱ አገራት ጋ የገባችውን ስምምነት ምስጢር ብታደርግም ግብጾቹ አንዱን ተንፍሰውታል።እንግዲህ ከሶስቱ አገራት አንዷ (ግብጽ) ሳትስማማ ብትቀር ግድቡ ምን ሊረባ እንደሆነ አስቡት?
ግብጽ የሳታላይት ቅኝት በማድረግም ግድቡን እየተቆጣጠረች እንደምትገኝ ነግራናለች።ይህ ምንድን ነው የሚያሳየን ወይስ ስምምነቱ ይህንን እንድታደርግ ይፈቅድላታል?
ለነገሩ ኢሳትና ቪኦኤን የመሳሰሉ ድምጾችን ለማፈን እንጂ ለግብጽ የሳታላይት ብርበራ ግድ የማይሰጣቸው ኃይሎች በመኖራቸው ግብጾቹ በነካ እጃቸው የጦሩን ሁኔታም ካልሰለሉ እነርሱ ሆነው ነው።

 

Water shortage in Egypt unrelated to Ethiopia’s dam reservoir

 

By THE CAIRO POST
CAIRO: Egypt denied Thursday media reports claiming that the reservoir of Ethiopia’s controversial Renaissance Dam is being filled with Nile water and has caused water shortages in Egypt’s major cities.

Egyptian Minister of Irrigation Hossam Moghazy said Wednesday in a statement that the ministry is following up construction works of the Ethiopian Dam and confirmed that the dam’s reservoir has not been filled with water, citing to satellite images taken in mid-September.

Ethiopia and the two downstream countries (Egypt and Sudan) agreed in March that operating the reservoir will only start after studying the environmental and economic impacts of the dam on the two countries.

The construction of the dam has been a high-priority issue for Egypt’s government, which has raised concerns it would negatively affect its water supply. Ethiopia has claimed the dam is necessary for its development; both states agreed to tripartite talks that started in August 2014 and have been hosted by Sudan.

During the August talks, the Tripartite National Committee (TNC) agreed to choose an international consultancy firm to evaluate the dam’s effects. The committee of the three countries assigned French and Dutch offices, BRL and Deltares, to conduct the studies; however, Deltares withdrew citing TNC and BRL’s failure to provide sufficient guarantees to transparent studies.

Last week, certain areas in Cairo and Giza suffered water shortages due to low Nile water level available for water plants, according to the Ministry of Irrigation.

Moghazy said that the ministry increased the water level by 35 centimeters to reach 16.45 meters; this increase is estimated at 20 million cubic meters of water, he noted in a statement Thursday.

Egypt’s Holding Company for Drinking Water and Sanitation spokesperson Mohey al-Serafi said Wednesday that the water level has decreased by 90 centimeters five days ago due to the company’s “annual measures of reducing water levels in the winter.”

Moghazy added Egypt’s water consumption in the summer records 250 million cubic meters mostly for irrigation purposes, compared to 90 million cubic meters in the winter.

“ሞላ በስርዓቱ ተገዶ 700 ሰራዊት ይዤ መጣሁ ይበል እንጂ በትክክል የሄዱት 115 ናቸው ከነርሱም ውስጥ 48ቱ ተመልሰዋል”–ታጋይ መኮንን ተስፋዬ

0
0

የትህዴን ድርጅት በወያኔ ሃይሎች ሊሰለል የማይችል ጠንካራ የስለያና የፀረ ስልያ ማዕከል የገነባ ታላቅ ድርጂት ነው ሲል የድርጂቱ ምክትል ሊቀመንበር ታጋይ መኮነን ተስፋይ በየካቲት ውለታ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ባደረገው ቃለ መጠየቅ ገለፀ::

mekonen
የደህሚት ድምጽ እንደዘገበው ታጋይ መኮነን ተስፋይ ሞላ ከወያኔ የደህንነት ሃይሎች ጋር ለአንድ አመት ያህል ስሰራ ቆይቻለሁ ይላል የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ሲመልስ ሞላ ይህን የማድረግ አቅም እንደሌለውና የትህዴንም ትልቅ ድርጂት እንደመሆኑ መጠን ጠላቱንና ወዳጁን ለይቶ የሚያውቅ ጠንካራ ድርጂታዊ የስልያና የፀረ ስለያ ማዕከል የገነባ ስለሆነ የወያኔ የደህንነት ሃይሎች ይህን የማድረግ አቅም የላቸውም ሲል አረጋግጧል::

ታጋይ መኮነን ተስፋይ ጨምሮም ሞላ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ድርጂታዊ ጉባኤ እንደሚካሄድ ፈርቶ አመለጠ እንጂ ከወያኔ ጋር አልነበረምየመሆን ሃቅምም የለውም ካለ በኋላ ይህ ለአንድ አመት ግንኙነት ነበረኝ ያለው መግለጫም ሃይለኛ መስሎ ለመታየትና የወያኔ የስለላ ማዕከል ጠንካራ እንደሆነ ለማስመሰል ህዝቡን ለማደናገር የተጠቀመበት የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ነው ሲል ገልጿል::

ሞላ 700 የሚሆኑ ታጋዮችን ይዠ የሚለውም ቢሆን በስርኣቱ በል ተብሎ ስለተገደደ እንጂ ከዚያ ባለፈም የነበረውን ድክመት ለመሸፈን ሃይለኛ መስሎ ለመታየት ካልሆነ በስተቀር ሞላ የወሰደው ታጋይ መጠኑ ከ115 የማይበልጡ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም 48ቱ ታጋዮች ተደናገረው ስለነበር ወደ ድርጂታቸው መመለሳቸውን አስታውቋል::

በተጨማሪም በሱዳን መሬት አካባቢ በርከት ያሉ ታጋዮች ሞላን በመቃወም ተበታትነው የሚገኙ ሲሆን ትህዴንም ወደ ድርጂታቸው ለመመለስ ሁኔታዎችን እያመቻቸ እንደሚገኝ ጨምሮ አስረድቷል::

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live