Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Sport: ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ ስለኢትዮጵያ እና ሲሸልሽ ብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ትንታኔውን ይሰጣል

0
0

ethiopian national teaወዳጄ ማርቆስ ኤልያስ የሲሼልስ እና የኢትዮጵያን ጨዋታ በራዲዮ እያሰማ ነው፡፡ ጋዜጠኛው ስሜቱን መደበቅ ስለማይችል እና ሳይቸገር በርካታ ነገሮችን ስለሚያስታውስ በቀጥታ ጨዋታን ሲያስተላልፉ ከምመርጣቸው ጋዜጠኞች አንዱ ነው፡፡ እናም ይኽን ጨዋታ ሲያስተላልፍ የብሔራዊ ቡድኑ እንቅስቃሴ ስላላማረው ይቆጣ፣ ይበሳጭ እና “ይሄ ተጨዋች ምን እያደረገ ነው?” ብሎ በግርምት ይጠይቅ ነበር፡፡ እንድ ቦታም እጅግ ሲበሳጭ “90000 (ዘጠና ሺህ) ህዝብ ያላት ሲሼልስ 90000000 (ዘጠና ሚሊዮን) ህዝብ ካላት ኢትዮጵያ ጋር የምታደርገው ጨዋታ ላይ ምንም ልዩነት አላየሁም፡፡ ሜዳው ላይ የሚደረገው ጨዋታ ተመጣጣኝ ነው፡፡ እዚህ ጋር ስለ እግርኳሳችን ቆም ብለን ማሰብ አለብን” በማለት በንዴት ተናገረ፡፡ ለእኔ ግን ሜዳው ላይ እየታየ የሚገኘው ነገር ብዙም አልገረመኝም፡፡ የፊፋ የደረጃ ሰንጠረዥን ከተመለከትን አዎ ……የሲሼልስ ብሔራዊ ቡድን በጣም ደካማ ነው፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ከግዜ ወደ ግዜ እየወረደ እንጂ መሻሻልን እያሳየ አይደለም፡፡ የህዝብ ቁጥር በጥራት ከተሰራበት የምርጫ አድማስን ሰፋ ያደርጋል እንጂ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመስራት ማረጋጋጫ መሆንም አይችልም፡፡ የፈለገ በርካታ ህዝብ ቢኖርም ሜዳ ላይ የሚሰለፉት 11 ተጨዋቾች ብቻ በመሆናቸው ጥራት ያለው ቡድንን ይዞ የቀረበ አሳምኖ ያሸንፋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ ለጥራት አልታደለም፡፡ እንደ ሲሼልስ አይነት እጅግ የወረደ ቡድን ማሸነፍ እንኳን የሚከብደን ለዛ ነው፡፡ የምልመላ ዘዴያችን እጅግ የወረደ ነው፡፡ ተጨዋቾች እግርኳስን እችላለሁ ብለው ወደ ክለቦች ይመጣሉ እንጂ ክለቦች ሰፊ የምልመላ መረብ የላቸውም፡፡ አሁን….አሁን በርካታ እግርኳስ ተጨዋቾችን እያፈራን የምንገኝበትን ጋምቤላን እንኳን ረጅም ግዜ ረስተነው ነበር፡፡ ይኽ ቦታ መፈተሽ እንኳን የጀመረው በአንዳንድ ግለሰቦች ጥረት እንጂ በተደራጀ መንገድ አልነበረም፤ አሁንም አይደለም፡፡ ህፃናትን የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ስሜቱ እንጂ ክህሎቱ የላቸውም፡፡ ወይም ክህሎቱን እንዲያዳብሩ ምንም የተመቻቸላቸው ነገር የለም፡፡

ethiopian National Team Manager

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደግሞ ልክ በሁሉም ነገር የሞላለት ይመስል ከሀይቲ ሳይቀር በሚመጡ ብቃታቸው እጅግ በወረደ ተጨዋቾች ሲሞላ እግርኳስ ፌዴሬሽኑ ዝምታን መርጦ ነበር፡፡ ይባስ ብሎም ከፈለጋችሁ አምስት….አምስት….ተጨዋቾችን አምጡ ብሎ ኢትዮጵያዊያን በመከራ የሚያገኙትን ዕድል አጥቦባቸዋል፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆነው የዛሬው ጨዋታ ነው፡፡ ከመጀመሪያ ተሳላፊዎቹ 11 ተጨዋቾች (ታሪኬ ጌትነት፣ ስዩም ተስፋዬ፣ ዋሊድ አታ፣ ተካልኝ ደጀኔ፣ አስቻለው ታመነ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ሽመልስ በቀለ፣ ኤፍሬም አሻሞ፣ ዑመድ ዑክሪ፣ ጌታነህ ከበደ እና ሳላኹዲን ሰዒድ) መካከል አንዱም ተጨዋች በዚህ ዓመት ሻምፒዮን በነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫወቱ አይደሉም፡፡ ይኼ በራሱ በብዙ መንገድ ሊመነዘር ይችላል፡፡

Seychelles
የኢትዮጵያ እግርኳስ በተለይ ጥራት ላይ ለውጥን ብቻ አይፈልግም፤ አብዮት እንጂ፡፡ የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ ሰዎች አማተር እና ፖለቲከኛ በመሆናቸው አመራራቸው የተጨማለቀ ነው፡፡ ለሙስና እና ከእግርኳስ ጋር ብዙ ዓመታት በኖሩት የክለብ አመራሮች ለመታለል ቅርብ ናቸው፡፡ ፌዴሬሽኑ በጥቃቅን የሊግ ውድድር ንትርኮች ግዜውን ያሳልፋል እንጂ እግርኳስ ልማት ላይ ለመስራት ሀሳቡም የለውም፡፡ በቅርቡ የተከወኑ የደንብ ለውጦች እና የተፈጠረው ንትርክ ብቻ ለእኛ ብዙ ነገርን ይነግረናል፡፡ በስሜትም ቢሆን ወጣቶችን ከየሰፈሩ እየለቃቀሙ የሚያሰለጥኑ ወጣት አሰልጣኞች በትልልቅ ክለቦች መዘረፍ የለባቸውም፡፡ እነዚህ ወጣቶች ምርጦቹን ታዳጊዎች ላገኙበት ብቻ ሊከፈላቸው ይገባል፡፡ ስለዚህም ታዳጊ ተጨዋቾቻቸውን ከሚፈልገው ክለብ ጋር እንዲደራደሩ የሚያስችላቸው ህግ ቶሎ መውጣት አለበት፡፡ በርካታ የታዳጊ ማዕከላትን እና አሰልጣኞች ለማግኝት አቋራጩ መንገድ ይሔው ነው፡፡ ብዙ መፃፍ ይቻል ነበር….ንዴት ላይ ስለሆንኩ ላቁመው፡፡

እንደኔው ለተናደደው ወዳጄ ማርቆስ ግን ስዊድን፣ ሰርቢያ፣ ቦስኒያ-ሄርዞጎቪና፣ ዴንማርክ፣ ኦስትሪያ፣ ክሮሺያ፣ ኮስታሪካ፣ ስዊዘርላንድ፣ ፖርቱጋል እና ዑሯጓይ ከ10000000 (አስር ሚሊዮን) ህዝብ በታች እያላቸው ቆንጆ ብሔራዊ ቡድን የሚያሳዩን እንደሆኑ ላስታውስህ እወዳለሁ፡፡ በሉ…..ጨዋታውም ሲሼልስ 1-1 ኢትዮጵያ ሆኖ አለቀ……..በዚህ ንዴት ከዚህ በላይ ከፃፍኩ ሁሉም ነገር ይበላሻል……ላቁም!!!


“የዘመርኩት ‘ጠንቋይ’ [ታምራት ገለታን] ለማሳፈር ነው”–ሽመልስ አበራ ጆሮ

0
0


ሽመልስ አበራ ጆሮ በቅርቡ ከቶም ሾ ጋር ባደረገው ቆይታ ለአንድ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ ሊዘምር የቻለው አንዳንድ ሰዎች ጠንቋዩ ታምራት ገለታ (እያንጓለለ) ጋር እየሄዱ የእግሩን እጣቢ ሳይቀር በመጠጣታቸው እርሱን ለማሳፈር እንደሆነ ገልጿል:: ቃለምልልሱ ብዙ ቁምነገር ይዟል ይመልከቱት::
“የዘመርኩት ‘ጠንቋይ’ [ታምራት ገለታን] ለማሳፈር ነው” – ሽመልስ አበራ ጆሮ

በሕወሃት፣ በ5ለ1 ስብሰባ ምክንያት የቲያትር መድረክ በኢትዮጵያ ጠፍቷል ይለናል ሽመልስ አበራ (ያድምጡት)

0
0

በሕወሃት፣ በ5ለ1 ስብሰባ ምክንያት የቲያትር መድረክ በኢትዮጵያ ጠፍቷል ይለናል ሽመልስ አበራ (ያድምጡት)

shimelis abera

አርብን በቂሊንጦ እስር ቤት –‹‹ኢህአዴግ ልጅነታችንን ቀምቶናል››

0
0

————————————————-
‹‹ኢህአዴግ ልጅነታችንን ቀምቶናል››
‹‹በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ በእጅ የሚዳሰስ ኢ-ፍትሃዊነት ተፈጽሟል››
ጦማሪ አቤል ዋበላ
——
‹‹የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ በደንብ መመርመር አለበት››
‹‹ማክሰኞ ሻይ እንጠጣለን (ፈገግታ ያጀበው ሳቅ)›› ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ
——
‹‹ለውጥ እንዲመጣ ፖለቲካችን መዘመን አለበት››
‹‹በመከራ እስር ቤት ውስጥ ተገኝተንም የፍረጃ ፖለቲካ ሥራውን ሲሰራ ስትመለከት በጣም ያሳዝናል››
ብርሃኑ ተ/ያሬድ

———————-

ከኤሊያስ ገብሩ ጎዳና (ጋዜጠኛ)

natnaiel Felekeየአዕምሮ እረፍት ከሚሰጡ ነገሮች መካከል አንዱ የታሰረን ሰው መጠየቅ ነው፡፡ ከትናንት በስትያ አርብ ነሐሴ 29 ቀን 2007 ዓ.ም፣ ጠዋት ላይ ከወዳጆቼ አቤል ዓለማየሁ እና ኢዩኤል ፍስሐ ጋር ወደቂሊንጦ እስር ቤት አምርተን ነበር፡፡ እኔ እና አቤል ወደዞን ሶስት አመራን፣ ኢዩኤል ደግሞ ወደዞን ሶስት፡፡ መደበኛውን ምዝገባውን እና ፍተሻውን ቀድሜ እኔ ጨረስኩና ወደመጠየቂው ቦታ አመራሁ፡፡ አራት የሚሆኑ ፖሊሶች በጥበቃ ማማ ሥር ሆነው እየሳቁ እንጨት ላይ ስፖርት ይሰራሉ፡፡ እንደወታደር ስፖርታቸው አይማርክም፡፡ …ላስጠጣራቸው የነበሩት ልጆች በቤተሰቦቻቸው እየተጠየቁ ነበር፡፡ የዞን 9ኙ ጦማሪ አቤል ዋበላን ከጓደኛው ናትናኤል ፈለቀ ታናሽ እህት ጋር አገኘኋሁ፡፡ ሰላምታ ተለዋወጥን፡፡ ከናትናኤል እህት ጋር ‹‹ተዋዋቁ›› ሲለን፣ ‹‹ኧረ እንተዋወቃለን›› ብለን ፈገግ አልን፡፡ ናትናኤል ከርቀት ሰዎች እያናገረ ስላየሁት በዚሁ ዞን የሚገኘውን ብርሃኑ ተ/ያሬድን ጥራልኝ አልኩት አቤልን፤ እሱም ሊጠራልኝ ሄደ፡፡ ናቲ በቦታው ተተካ፡፡ ሞቅ ካለው ሰላምታ በኋላ ‹‹ሰኞ ከመውጣታችሁ በፊት እንያችሁ ብለን ነው፡፡›› ብዬ አሳኩት፡፡ ‹‹ብዙዎች እንዲህ እያሉ መጥተው እየጠየቁን ነው›› አለኝ – ፈገግ እያለ፡፡ ሳቁን ገታ አድርገን፣ ስለክሳቸው የፍርድ ሂደት ቁምነገሮችን ማውራት ቀጠልን፡፡ ‹‹አንዴ ሁላችንም ተሰብስበን፣ ‹የክሳችን ጉዳይ ምን ሊሆን ይችላል?› ብለን ተመካክረን ነበር፡፡ ግምታችን ትክክል ሆኖ አግኝተናዋል፡፡ የሚገርምህ ፣አምስት ሰው ይፈታሉ ብለን ጠብቀን ነበር፡፡ እንደጠበቅነውም ሆነ … ኢህአዴግ አስቦ ነው አንድን ድርጊት የሚያደርገው፡፡›› አለ ናትናኤል፡፡ እኔም ‹‹አንድን ነገር ትርፍ እና ኪሳራውን አስልቶ ነው የሚያደርገው›› ብዬ ጨመርኩለት፡፡ ብዙ ኢትዮጵያኖች ዋጋ እያስከፈለ ስለሚገኘው የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅን በተመለከተ ትንሽ ሰፋ ያለ ሀሳብ በተመስጦ ለተዋወጥን፡፡ ናትናኤልም ‹‹የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ በደንብ መመርመር አለበት›› አለበት ሲል አጽንኦቱን ሰጠ፡፡

ሁለቱ ጦማሪያንና ሶስቱ ጋዜጠኞች ከመፈታታቸው 26 ቀናት ቀደም ብሎ፣ በዚህ እስር ቤት ዞን 2 ሄጄ ተስፋለምን፣ በፍቃዱንና አጥናፍን ጠይቄያቸው ነበር፡፡ በወቅቱ በፍቃዱ ‹‹የተወሰናችንን ፈትቶ የተወሰናችንን ደግሞ ያስቀራል፡፡›› ሲል አጥናፍ በበኩሉ፣ ‹‹በእኛ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ የእነሀብታሙን የፍርድ ጉዳይ ይወስናል፡፡ ከእኛ መካከል የሚፈታ ካላ ከእነሀብታሙም መካካል የሚፈታ ይኖራል›› ብሎኝ ነበር፡፡ እንዳለውም ሆነ፣ በእነሀብታሙ አያሌው ላይ ያልተተገበረ ነገር ቢኖርም! በአጠቃላይ የእነዚህ ወጣቶች ግምት ትክክል ነበር፡፡ የአገዛዙን አካሄድ እና ድርጊት በአንክሮ አስተውሎ ማሰላሰል ለዚህ ይጠቅማል፡፡ አስበውና አሰላስለው ለእውነተኛ ነገር የቀረበ ግምት ለሚሰጡ ሰዎች ትልቅ አክብሮት እሰጣለሁ፡፡ የቀድሞ የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ደኤታ የነበሩት አቶ ኤርሚያስ ለገሰ በዚህ ረገድ ያስደስቱኛል፡፡ ‹‹ከስርዓቱ ጋር 10 ዓመት ያህል አብረው ዘልቀው እንዴት አይገምቱ?›› የሚል ጥያቄ ከተነሳም ‹‹ሥንቱ አለ አይደለም ከሥርዓቱ ጋር አርጅቶ ምን እንደሚሰራበት የማያውቅ፣ ሥንቱ አለ አይደል የድል አጥቢያ አርበኛ ሆኖ ምን እንደሚከወን የማይረዳ …›› የሚል መልስ ሰጥቻለሁ፡፡

Birhanu-Tekele-Yaredአቤል ዓለማየሁ ፍተሻውን ጨርሶ መጣና በሰላምታ ተቀላለቀን፡፡ ከጎናችን ዞር ስንል ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ አለ፡፡ ‹‹ተጠያቂው ጠያቂ ሆነ!›› ብዬ ስቄ ሰላም አልኩት፡፡ ወዲው ብርሃኑ ተ/ያሬድ መጣ፡፡ ብርሃኑን ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ከጓደኞቹ ጋር ታስረው አራዳ ፍርድ ቤት ለተጨማሪ ምርመራ ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ በጠየቀባቸው ወቅት በአካል ከተያየን ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ያገኘሁት፡፡ ‹‹ኤሊ እንዴት ነህ? የግንቦት ሰባት ወታደር እስከአራት ሰዓት ድረስ ነው የሚተኛው›› ብሎ በመሳቅ አልጋው ላይ ጋደም ካለበት ተነስቶ መምጣቱን ተናገረ፡፡ …እሱ፣ እየሩሳሌም ተስፋውና ፍቅረማሪም አስማማው ወደኤርትራ ሄደው ግንቦት ሰባት አርበኞች ግንባርን ለመቀላቀል ካቀዱበት ጊዜ ጀምሮ፣ ባለፈው ሳምንት ስለተሰማባቸው የምስክርነት ቃልና በቀጣይ ስለሚኖራቸው የፍርድ ሂደት ጭምር ዝርዝር አድርጎ ለእኔ እና ለአቤል አጫወተን፡፡ ስለፓርቲ ፖለቲካም የራሱን አተያይ ሰነዘረ፡፡ ‹‹ለውጥ እንዲመጣ ፖለቲካችን መዘመን አለበት፡፡ ደካማ ቤተሰቦቻችንን ትተን፣ በመከራ እስር ቤት ውስጥ ተገኝተንም የፍረጃ ፖለቲካ ሥራውን ሲሰራ ስትመለከት በጣም ያሳዝናል፡፡ …ለሁላችንም አንድ ሀገር ነው ያለችን›› አለኝ፡፡ ‹‹ለውጥ እንዲመጣ ፖለቲካችን መዘመን አለበት፡፡›› የምትለዋ በውስጤ በደንብ የመዘገብኳት የብርሃኑ ቃል ነበረች – እኔም ስለማምንባት፡፡ ያለንበትን ጊዜ ባልዋጀ ፖለቲካ ውስጥ ለዘመናት መሽከርከራችን አይደለ የመከራ ዘመናችንን ያረዘመው? ፖለቲካችንን በቸከ የመጠፋፋት ባህል ስለታነጸም አይደል እርስ በእርስ በጠላትነት ተቧድነን ያለርህራሄ የምንመታታው? ኧረ ብዙ ማለት ይቻላል ….
ያው ሶስት ተጠያቂዎችና ከሶስት በላይ ጠያቂዎች በቆሙበት ቦታ እየተቀያየሩ ማውራት ተገቢ ነውና ወደ አቤል ዋበላ ዞርኩ፡፡ የክስ ሂደታቸውን እና ብይን ለመስጠት ተደጋጋሚ ቀጠሮ በተሰጣቸው ጉዳይ ላይ ሀሳቦችን ተለዋወጥን፡፡ ሕዳር ወር ላይ በዚህ ዞን ታስሬ ስለነበርኩ፤ ስለምናውቃቸው ሰዎች አንስተን አወጋን፡፡ ‹‹የቀድሞ የመኢአድ አመራር የነበረው አቶ ማሙሸት አማረ፣ ከሰሞኑ እስኪፈታ ድረስ አንተ ለአንድ ሳምንት ትተኛበት በነበረበት ቦታ ላይ ነበር መኝታው፡፡›› አለኝ፡፡ [በቂሊንጦ አልጋ ያላገኘ እስረኛ የሚተኛበት ቦታ ‹‹ደቦቃ›› የሚል መጠሪያ አለው፡፡ የቤቱ በር ሲዘጋ፣ አልጋ ያላገኙ እስረኞች ፍራሽ ደርድረው በር ሥር ያድራሉ፡፡ አቤል እና ዘላለም ክብረት ከማዕከላዊ ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት ሲዘዋወሩ ከ15 ቀናት በላይ በዚህ ሁኔታ ለመተኛት ተገድደው እንደነበረ ነግረውኛል፡፡ እኔም እተኛ የነበረው አቤል ከሚተኛበት ተደራራቢ አልጋ ጎን ባለ ሌላ ተደራራቢ አልጋ መካከል፤ መሬት ላይ ነበር፡፡ እንግዲህ ማሙሸትም እዚሁ ነበር ይተኛ የነበረው]

ጦማሪ አቤል ዋበላ

ጦማሪ አቤል ዋበላ

‹‹ከማሙሸት ጋር ብዙ ሀገራዊ ቁምነገሮችን ተካፍለናል›› የሚለው አቤል፤ በቼዝ ጨዋታ ጎበዝ መሆኑንም ይመሰክርለታል፡፡ ባለፈው ወር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ከአቤል ጋር ዝዋይ እስር ቤት ስንጠይቀው መጽሐፎች ስለማይገቡለት ቼዝ በመጫወት ቀኑን እንደሚያሳልፍ አውግቶኛል፡፡

ጦማሪ አቤል ቀልድ ይችላል፤ ቁምነገር ሲናገርም የምሩን ነው፡፡ ወደቁምነገሩ ገባና እንዲህ አለኝ፡-
‹‹ኢህአዴግ ልጅነታችንን ቀምቶናል፡፡ ከአሁን በኋላ ልጅነት የለም፡፡ ከእስር ስንወጣም በጣም ከፍ ያለነገር ለሀገራችን በተግባር ማድረግ ይገባናል፤ ይጠበቅብናል፡፡ በእስር ቆይታችንም ብዙ የሀገራችንን ችግሮች ለማወቅ ችለናል፡፡››

ከአቤል ጋር፣ በዚህ በዚህ ዞን ታስረው ስለነበሩት ኡስታዝ አብበከር አሕመድ፣ አቡበከር ዓለሙ፣ ካሚል ሸምሱ ከሰዓት አኳያ ጥቂት ማወጋታችን አልቀረም፡፡ ‹‹ከአቡበከር ዓለሙ ጋር በአንድ ወቅት ስናወጋ፣ ስለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አጫውቶኝ ነበር፡፡›› የሚለው አቤል ፍርዳቸውን አስመለክቶ ቀጣዩን ተናገረ፡- ‹‹አቡበከር ዓለሙ በአንድ ወቅት ከእስክንድር ጋር በአንድ ዞን ታስረው በነበረበት ወቅት ጋዜጠኛው ጊዜ ምን ያህል ጨዋ፣ ሥነ-ምግባር ያለው፣ አስተዋይ፣ ለሀገር አርቆ አሳቢ እንደሆነ ጠቅሶልኝ ‹እስክንድር ላይ እንዴት 18 ዓመት ይፈረድበታል?› በማለት ሀዘኔታውን ነግሮኛል፡፡ ይኸው እሱም (አቡበከር) 18 ዓመት ተፈረደበት፡፡ ያሳዝናል፡፡ በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ በእጅ የሚዳሰስ ኢ-ፍትሃዊነት ተፈጽሟል፡፡››

ያው የመለያያ ጊዜ ደረሰና ቻው ልንባባል ምዕራፉ ሆነ፡፡ ናትናኤልን ‹‹እንግዲህ ሰኞ በቀጠሯቸው መሰረት ፍርድ ቤት እንገናኝ›› አልኩት፡፡ ‹‹እሺ፣ ማክሰኞ ሻይ እንጠጣለን›› አለ እየሳቀ፡፡ ከእስር ተፈትተን ለማለት ነው፡፡ ብርሃኑም፣ የናቲን መልስ ሰማና በፈገግታ እየሳቀ ‹‹አንድ ቀን ማክሰኞ ድራፍት እንጠጣለን›› ካለኝ በኋላ ሰላም ሁኑ በመባባል ከእስር ቤቱ ግቢ ወጣን፡፡

ከእስር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውጪም ኢዩኤል ቀድሞን ወጥቶ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ ፀሐዩ በጣም ከበድ ያለ ነበር፡፡ የዛሬ ሁለት ወራት ገደማ ‹‹ክሳችሁ ተቋርጧል›› ተብለው ከእስር ከተፈቱት መካከል የሚገኙበት፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ ጓደኞቻቸውን (በፍቃዱ ሃይሉንና አጥናፍ ብርሃኔን) ጠይቀው ሲወጡ አገኘናቸውና ሰላም ተባባልን፡፡ እነተስፋለምን መጠበቅ ስለነበረባቸው ፀሐዩን ለመከላከል አንድ ጃኬት ነጥለው በጋራ ራሳቸው ላይ በማድረግ በቀስታ ጥላ ለመፈለግ ተንቀሳቀሱ፡፡ እኛም ወደመጣንበት ተመለስን፡፡

በእስር ላይ የሚገኙት አራት የዞን 9 ጦማሪያንና ከሀገር ውጪ የምትገኘዋ ሶሊያና ሽመልስ፣ በሌለችበት በነገው ዕለት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ብይን ይሰጣቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ‹‹መከላከል ሳስፈልጋችሁ በነጻ እንድትሰናበቱ›› የሚል ውሳኔ ተሰጥቷቸው ሁላችንም ደስ ይለን ዘንድ ከልቤ እሻለሁ!
ለዛሬ አበቃሁ፣ ሰናይ እሁድ ይሁንልን!!!

Sport: የአትሌት ማሬ ዲባባ የዚህ ዓመት ገቢ ብቻ ከ1 ሚሊዮን ዶላር አልፏል

0
0

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ የተሳትፎ ታሪክ በማራቶን የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ የወሰደችው ማሬ ዲባባ፤ ማራቶንን በየዘርፉ በመሪነት ተቆጣጥራለች፡፡ በኦል አትሌቲክስ ድረገፅ በሰፈረው አሃዛዊ መረጃ መሠረት በሴቶች ማራቶን ማሬ ዲባባ በ1351 ነጥብ አንደኛ ናት፡፡ ባለፈው ሰሞን በማራቶን የዓለም ሻምፒዮን ከሆነች በኋላ ደግሞ በ2015 የዓለም ታላላቅ ማራቶኖች (World Marathon Major Series) ሊግ በነጥብ 1ኛ ሆና እየመራች ሲሆን፤ የውድድር ዘመኑን በአሸናፊነት ልትጨርስ ትችላለች፡፡

mare dibaba zehabeshaበሌላ በኩል በቤጂንጉ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የማራቶን ሻምፒዮን ስትሆን በሽልማት ካገኘችው 60ሺ ዶላር በተጨማሪ ከቡድን ሽልማትና ከስፖንሰር ጥቅሟ ጋር ገቢዋ በዕጥፍ የጨመረላት ማሬ ዲባባ ከማራቶን ሊግ አሸናፊነቷ ጋር የዘንድሮ ገቢዋ ብቻ ከ1 ሚሊዮን ዶላር ሊያልፍ ችሏል፡፡ በዓለም አቀፉ የጐዳና ላይ ሩጫዎች ማህበር (ARRS) ማሬ ዲባባ ከ2008 እ.ኤ.አ በጐዳና ላይ ሩጫዎች ከ15 በላይ ድሎች በማስመዝገብ 534,465 ዶላር በሽልማት ገንዘብ መሰብሰቧ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በውድድር ዘመኑ በዓለም ዙሪያ የሚካሄዱ 6 ታላላቅ የማራቶን ውድድሮችን ተንተርሶ በሚሰጥ ነጥብ የማራቶን ሊግ አሸናፊ የሚወሰን ሲሆን፤ በየፆታ መደቡ በነጥብ መርተው የሚጨርሱ አትሌቶች እያንዳንዳቸው 500ሺ ዶላር ይሸለማሉ፡፡

ማሬ ዲባባ ቤጂንግ ላይ የዓለም ሻምፒዮና ከሆነች በኋላ የማራቶን ሊጉን በ42 ነጥብ አንደኛ ሆና እየመራች ሲሆን፤ በቅርብ ርቀት የምትፎካከራት የኬንያዋ ሄለን ኬፕሮን በ32 ነጥብ ነው፡፡

ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ብርሃኔ ዲባባ እና ትዕግስት ቱፋ እንዲሁም ሌላዋ ኬንያዊት ካሮሊን ሮቲች በ25 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ተጋርተው ይከታተላሉ፡፡ በተያያዘ በወንዶች ምድብ በ25 ነጥብ የማራቶን ሊጉን መሪነት የተቆጣጠረው ቤጂንግ ላይ የብር ሜዳሊያ ያገኘው የማነ ፀጋዬ ነው፡፡ ኤሊውድ ኪፕቾጌ ከኬንያ፣ ግርማይ ገ/ስላሴ ከኤርትራ እንደሻው ንጉሤ እና ሌሊሣ ዴሲሳ ከኢትዮጵያ በእኩል 25 ነጥብ ይከተላሉ፡፡

የማራቶን ሊግ አሸናፊዎች የሚወሰኑት በ6 የዓለማችን ታላላቅ ማራቶኖች ባስመዘገቡት ውጤት በሚሰጠው ነጥብ ይሆናል፡፡ ማሬ ዲባባ በ2014 የቦስተን ማራቶን 3ኛ እንዲሁም በቺካጐ ማራቶን 1ኛ ደረጃ ከማግኘቷም በላይ፤ በ2015 በቦስተን ማራቶን 2ኛ እንዲሁም በዓለም ሻምፒዮና 1ኛ ከሆነች በኋላ ያስመዘገበችው ነጥብ 42 አድርሳለች፡፡ በወርልድ ማራቶን ሜጀር ሲሪዬስ ታሪክ ኢትዮጵያ ለ3 ጊዜያት የማራቶን ሊጉን አሸናፊዎች አስመዝግባለች፡፡

በ2007 እና በ2008 እ.ኤ.አ አከታትላ ያሸነፈችው ጌጤ ዋሚ ስትሆን በ2003 እ.ኤ.አ ደግሞ ፀጋዬ ከበደ ሊጉን በነጥብ መሪ ሆነው በማጠናቀቅ በነፍስ ወከፍ 500ሺ ዶላር አግኝተዋል፡፡

ምንጭ: አዲስ አድማስ ጋዜጣ

Health: የጥቁር አዝሙድ የጤና ጥቅሞች

0
0

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
*ለካንሰር ህመም
የክሮሽያ ተመራማሪዮች ጥቁር አዝሙድ በውስጡ የያዛቸው ንጥረ ነገሮች የካንሰር ሴሎችን የመቀነስ ሀይል እንዳለው ይናገራሉ።
*ለጤናማ ጉበት
ጥቁር እዝሙድ ለጉበት ጤና እጅግ ጠቃሚ ሲሆን መድሀኒት በብዛት በመውሰድ፣ በአልኮል መጠጥ ወይንም በሌሎች ህመሞች ምክንያት የተጎዳን ጉበት የመዳን ሂደትን ያፋጥናል።
*ለቆዳ ጤናማነት
ቆዳችንን ከጉዳት የመከላከል ጥቅምን ይሰጣል
*ለጤናማ ፀጉር
ጥቁር አዝሙድ ለፀጉር ተስማሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ስለያዘ የፀጉር መነቃቀል እንዳይኖር ይረዳል። ከዚህም በተጨማሪ ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል።
tikur azmud

Black Seed Oil Benefits

Of the many ways that black seed oil benefits the body, the 6 that stick out in the scientific literature its ability to help prevent cancer, diabetes, obesity, hair loss, skin disorders and infections like MRSA.

Cancer

Croatian scientists evaluated the antitumor activity of thymoquinone and thymohydroquinone in mice and discovered that the two phytochemicals in black seed oil can resulted in 52% decrease in tumor cells!

Being rich in both chemicals, black seed is unique in that it can help prevent and treat cancer through a variety of mechanisms:

Anti-proliferation
Apoptosis induction
Cell cycle arrest
Reactive oxygen species generation
Anti-metastasis
Anti-angiogenesis
According to one study,

“The anti-tumor effects of thymoquinone have also been investigated in tumor xenograft mice models for colon, prostate, pancreatic and lung cancer. The combination of thymoquinone and conventional chemotherapeutic drugs could produce greater therapeutic effect as well as reduce the toxicity of the latter.”

Liver Health

The liver is one of the most important organs in the body. Nearly every toxin gets processed through the liver, and the bile from the liver is the key to digesting fats and keeping your mind and body happy and healthy. For those that have struggled with poor liver function due to medication side effects, alcohol consumption, or disease, black seed oil could greatly speed the healing process. In a recent study scientists discovered that black seed oil benefits the function of the liver and helps prevent both damage and disease.

Diabetes

Explained in a recent article published by the Journal of Endocrinology and Metabolism, researchers from the Indian Council of Medical Research highlight that black seed oil “causes gradual partial regeneration of pancreatic beta-cells, increases the lowered serum insulin concentrations and decreases the elevated serum glucose.” This is actually quite profound because Nigella sativa is one of the few substances on the planet that is suggested to help prevent both type 1 and type 2 diabetes.

In fact, according to the study, black seed “improves glucose tolerance as efficiently as metformin; yet it has not shown significant adverse effects and has very low toxicity!” This is HUGE because metformin, one of the most commonly prescribed type 2 diabetes drugs, can cause a wide slew of side effects including:

Bloating
Constipation/Diarrhea
Flushing of the skin
Gas/Indigestion
Heartburn
Headache
Nail changes
Metallic taste in mouth
Muscle pain
Stomach pain
Weight Loss

The Journal of Diabetes and Metabolic Disorders published a study last June systemically reviewing the literature for plants that have anti-obesity properties and discovered that black seed oil was amongst the most effective natural remedies on the planet.

Not traditionally believed to treat obesity, Nigella sativa is a marvelous anti-inflammatory agent that is known to help people lose weight in the same way that it helps diabetics. Specifically, by decreasing these weight gain triggers, black seed oil has helped millions shed excess weight:

Appetite
Glucose absorption in the intestine
Liver gluconeogenesis
Blood glucose levels
Cholesterol
Triglycerides
Healthy Hair

Probably one of the most unique black seed oil benefits is its uncanny ability to help restore hair loss. No one quite understands why it happens, but it’s not too hard to guess that it has something to do with its powerful antioxidant and antimicrobial properties. By strengthening hair follicles, there is very good reason to see how black seed oil can help promote strengthened hair roots.

Healthy Skin

Produced in the retina, choroid and epidermis, melanin are pigments that protect the skin from damage. You probably are most family with it being the main chemical responsible for giving our eyes and skin their individual color. Known to promote and inhibit melanogenesis (melanin production), black seed oil benefits on the skin and other cells are profoundly healing.

For example, in a recent study conducted by Iranian researchers, Nigella saliva was found as effective as the skin cream Betamethasone in improving quality of life and decreasing severity of hand eczema. When you consider that black seed oil has virtually no side effects, the benefits of Nigella, in fact, far exceed medical intervention!

Infections (MRSA)

Of all the superbugs that black seed oil can kill, Methicillin resistant Staphylococcus aureus (MRSA) is one of the most important. MRSA is plaguing hospitals and nursing homes across the globe because ordinary staph infections are becoming resistant to generic antibiotics. The elderly population is especially at risk because it is generally associated with invasive procedures such as surgeries, intravenous tubing, and artificial joints. Primarily due to weakened immunity, the growing population of senior citizens has made MRSA a global public health risk.

Thankfully, one of the strongest black seed oil benefits comes to the rescue. Pakistan scientists took several strains of MRSA and discovered that each one was sensitive to N. Sativa, proving that black seed oil can help slow down or stop MRSA from spreading out of control.

ሰይፉ ፋንታሁን እና ቬሮኒካ ኑረዲን ተሞሸሩ

0
0

saifu

siefu Fantahun

seifu Fantahun
ከጌጡ ተመስገን

ቬሮኒካ – አባቷ ሙስሊም እናቷ ክርሲቲያን ሆነው በአንድ ጎጆ – በሚያስቀና የቤተሰብ ፍቅር ያደገች የዛሬ ወብ ሙሽሪት ናት፡፡ በሥራዋ ሆስተስም ነበረች፡፡
የሙሽሪት ሚዜዎች ስድስት ናቸው፡፡ እፀገነት ይልማ ፣ ቤተልሄም ተክሉ እንዲሁም አራቱ ሆስተሶች ናቸው፡፡ እነርሱም አዜብ ደስታ፣ ረድኤት አጥናፉ፣ ሰብለ ኃይለማርያም እና የዲት ካሳ (ጁዲ) ናቸው፡፡
የሰይፉ ፋንታሁን ሚዜዎች – ታደለ አሰፋ፣ ታደለ ሮባ ፣ ሚኪያስ መሐመድ፣ ጀርማይ አበበ፣ ዮናታን አለማየሁ (ሚጣ)፣ አብዱ ናቸው፡፡

ሰይፉ ፋንታሁን አላሙዲንን $100 ሸለመ (Video)

0
0


ላለው ይጨምራሉ እንጂ ደሃ አይረዱም እየተባሉ የሚወቀሱት ሼህ መሀመድ አላሙዲ የሰይፉ ፋንታሁንን ሰርግ ሙሉ በሙሉ ወጪ መሸፈናቸው ይታወቃል:: ሼኩ በተለይ በቅርቡ በአይሲኤል ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ቤሳቤስቲን ሳይረዱ መቅረታቸው ብዙ ትችት አስከትሎባቸው ነበር::

ዛሬ በሸራተን ሆቴል በተደረገው የሰይፉ ፋንታሁን ሰርግ ላይ የተገኙት አላሙዲ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር እየጨፈሩ ቆይተው በኋላም ከኪሱ $100 አውጥቶ ሸልሟቸዋል:: ቭዲዮውን ይመልከቱ::
alamudi


አዳፍኔንም መክሸፍንም ነው ያየሁበት –ዳዊት ዳባ

0
0

ዳዊት ዳባ:: Tuesday, September 01, 2015

መማር ካለብኝ እየጠየኩ; እየተከራከርኩ; እየተወቀጥኩም እማራለው እንጂ ዝም ብዬ አልማርም። ዝም ብዬም አልስማም። ዝም ብለህ ተገዛ፤ዝም ብለህ እመን;ዝም ብለህ ተከታይሁን…. ብቻ ዝምብለህን አስከትለው የሚመጡ ነገሮች ሁሉ አልቀበልም፡፡ ከመፀሀፉ ልዋስና ያዳፍኔ ባህሪዎች አድርጌ ነው የምወስዳቸው። ናቸውም። ለማዳፈን መሳርያ እንጂ ቃላትና ከመሳርያ ውጪ ያሉ ተጽኖ ማሳደርያ መንገዶች ጉልበት አይሆኑም ትክክል አይመስለኝም። እንደውም የገዘፈ ጉልበት እላቸው። ይህው አሁን ማን ይድፈር። ፀጥ እረጭ። እኔም መክሸፍን ለመተቸት በሞከሩት ላይ የመልስ ምቱን ስላየው ሳልፈራ ግን አይደለም። ግን የግድ ማድረግ ነበረብኝ። የመጀመርያው ምክንያቴ መፀሀፉ ውስጥ ዋና የሆነውን ቁምነገር እኔ በተለየ አቅጣጫ የተረዳሁት ወይ አየው የነበረ ስለሆነ ነው።  በዋናነት ግን ማጥቃት ስላለበት ነው። የተለመደ እየሆነ የመጣው ጦር ውርወራ ስላለው ነው።

 

“እንዴት” የሚለውን መንደርደርያ ገና አብዘተን በማንጠይቅበት ሁኔታ ሌሎች በሁሉ ነገሮች ላይ ጠይቀው መልሶች አሏቸው። ዛሬም መልስ መፈለጉን በርትተውበታል። እንዳንቀደም  ካደረጉን ምክንያቶች ውስጥ አንዱና ዋንኛው “እንዴት” ሲሉ አብዝተው የሚጠይቁ በመሆናቸው ነው። ጠቃሚ ነው ጎጂ የሚለው እንዳለ ከዶሮ ጋር እንዴት ፍትዎት እንደሚፈፀም ሁሉ መልስ አለ። እንዴት ያሳ መረቅ እንደሚሰራ ፤ የተሰበረ ቦርጭማ እንደሚጠገን፤ የእግር ጠረን መከላከል እንደሚቻል። አገዛዝን መገርሰስ እንደሚቻል። ብቻ ለሁሉም ነገሮች አጥጋቢ ካነሰም መነሻ የሚሆን መልስ ሰርተዋል። ይህ የሚስረዳን አብዝተው ‘እንዴት” ሲሉ መጠየቃቸው ብቻ ሳይሆን፤ መፍትሄ ፍለጋ ላይ፤ ለአዲስ ሆነ ለተሻሻለ ፈጠራ ባጠቃላይ ለሁለንተናዊ የሰው ልጅ እድገት  መነሻም ሚስጥር አድርገው እንደወሰዱትም ነው።

ወደኛ ሲመጣ በዋናነት  “ማወቅ”፤ “እውቀት” አድርገን የወሰድነው፤ ጌዜ ወስደን ልንመረምረው፤ ልንወያይበት፤ ልናነብበት፤ አልፈንም ቡጢ መሰናዘር ድረስ የሚመስጠን ታሪክ ነው። “መቼ?”፤ “ማን?”፤ “እንዴት”፤ “ምን”  ከሚሉ መጠየቂያዎች ከተነሳን ሁሌም በሚሰኝ ደረጃ ስለዛሬ ወይ ስለነገ ሳይሆን  ስለትናንትና ነው።  ለዛሬና ነገ መፍትሄ ከትናንት መነሻ ማድረጉ አንዳንዴም ሙሉ በሙሉ ካልተቀዳ ማለታችን  መፍትሄ ፍለጋ ላይ ከባድ ችግር ሆኗል። ይህ በራሱ ክፉም ከባድም ችግር ሆኖ እያለ የባሰ የከፋ የሚያደርገው አብዝተን ከትናንት ጋር ፍቅር ላይ በመውደቃችንና  ዛሬን ወይ ነገን አናውቀውም። በቂ በሚሰኝ አኳሐን ጠይቀንበት ችግሩም መፍትሄውንም ልንረዳው ሆነ ሊታየን አልቻለም። ከሞከርንም መፍትሄ ብለን የምንሰራው ወደፊት ሊያስኬደንና የማያዳግም መሆን አይደለም አንድ ክረምት ሊያሻግረን አልቻለም። እዚህ ላይ ከትናንት ስላልተነሳን ነው የሆነ ጊዜ ላይ እንግዳ በሆነው ሶሻሊዝም የተጠመቅነው የሚል መከራከርያ ዋና ሆኖ መምጣቱ አይቀርም። እሱም ቢሆን ሲጀምር የኛ አይደለም። ይባስ ብሎም ከትናንትና የተቀዳ ነው። ለዛሬና ለነገ በተገቢው ከታሰበበት አይደለም ከሌላ አገር የተቀዳ ከኛም ከትናንት ልንቀዳው ወይ ፍፁም ተመሳሳይ ሆኖ ልንጠቀምበት የሚቻለን መፍትሄ  የለም። “ ሶሻሊዝም የተንኮታኮተበት አንዱ ምክንያት አንዴ የሆነ ጊዜ ላይ የተቀመጠ መፍትሄ ሁሌም ሁሉም ቦታና ችግሮች ላይ  ይስራል የሚል ይዘት ስላለው ነው።

እዚህ ጋር ነበርኩ። ስጨምር ስቀንስ እያለው ነው መስኮቴን አንኳክቶ ባልንጀራዬ መፀሀፉን ያዋሰኝ።  ከዛም ማንበብ ነው የቀጠልኩት። ከላይ ያለው ሀሳብ በወረቀት ለማስቀመጥ እንዳሰብኩት ቀላል ባይሆንልኝም የዛሬ አይደለም። ውስጤ ብዙ ቆይቷል። በተለያየ መንገድ ስገለፀው የነበረ ነው። ታዲያ አዳፍኔን ይህን ሀሳቤን ይመታዋል። ይገለባብጠዋል።

“በዋናነት የመክሸፍ ምንጭ ሁለት ይመስለኛል። አንደኛው ትናንትን አለማስታወስ ሁለተኛው ነገን አለማሰብ።” ገጽ 61 ሁለተኛ ምእራፍ ላይ።

እዚህ ላይ ነገን አለማሰብ የሚለው ምክንያት ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል መፀሀፍ ትኩረት ያደረገውና አጉልቶ የሚያሳየን ትናንትን አለማወቅ የሚለውን ነው።  እኔ ዋና መሆን አለበት ብዬ የታሰበኝ የነበረው ደግሞ  ዛሬን

አናውቀውም ነው። ነገንም እንዲሁ። መፀሀፉ ደግሞ ዛሬን ብቻ ነው የምናውቀው ነው የሚለው። ለዚህ ነው ገለባብጦብኛል ያልኩት። የተራራቁ በቀላሉ ሊስማሙ የማይችሉ ልዩነቶች ሆኑብኝ። እንዳናምታታ ትናንት መታወቅ የለበትም አይደለም ክርክሬ። አንድ ህዝብ ትናንትናን ማወቅ ያለበት ምን ያህል ነው? ስንል እኛ የሚያስፈልገንን ያህል አይደለም  ከበቂ በላይ ትናንትን እናውቀዋለን ነው መልሴ። ትናንት ለመኖር ግድ እንደሚሉት አየርና ምግብ አይነት አድርገንዋል ነው። ትናንት ሙሉ ጉልበታችን፤ እውቀታችን፤ ጊዜያችን የሚጠፋበት ሆኗል ነው። ዛሬን በትንሹ ላዛውም በዜናና በመተረክ ደረጃ ነው

የምናውቀው። ያሉ ችግሮች ላይ መፍትሄን ከመስራት አኳያ ገና አናውቀውም ነው። ነገንም እንዲሁ።  ይህ የሆነበት ምክንያት ሁለንተናዊ በሆነ ሁናቴ በትናንት በመያዛችን ነው የሚል ነው መደምደሚያዬ።

በዛ ላይ ትናንትን ከዛሬም ከነገም በተሻለ የምናውቀው ቢሆንም አልፈየደም። ከባህሪው ላዛሬና ለነገ ልንጠቀምበት የምንችለው  መፍትሄ አናገኝበትም። ካለም እጅግ በጣም ትንሽ ነው። ዛሬ መፍትሄያችንን የሚሻው ችግር ከትናንትን መሰረት ያደረገ ሲዋረድ የመጣም ቢሆንም እንኳ። ሂደት ነውና ችግሩ  ዛሬ የተለየ ባህሪና ቅርጽ ይይዛል። ስለዚህም ዛሬ ችግሩ ያለውን ይዘት ባህሪና ቅርጽ ዋና ትኩረት በማድረግ መስራት ነው ትክክል የሚሆነው ነበር እሳቦቴ። ዘላቂነት እንዲኖረውና የማያዳግም እንዲሆን ደግሞ ነገን ግምት ውስጥ በማስገባት መፍትሄ መስራቱ   ነው ትክክለኛ አካሄድ አድርጌ የወሰድኩት። በነገራችን ላይ ዋና የሆነውን የፖለቲካ ልዩነት በተመለከተ በዛም በዚህም በኩል ያሉት ችግሩ ትናንትን አለማወቃችን ነው በሚለው ይስማማሉ። አለመግባባቱም መፍትሄውንም ያከበደው ትናንት ስለማናውቅ፤ ስለምንክድ፤ማመን ስለማንፈልግ፤ ስለምንዋሽ ነው በሁሉም ጎን ያሉ የሚያቀርቡት መከራከርያ። ትናንትን በራሳቸው አረዳድ ማየቱ እነዳለ ማለት ነው። ስለዚህ በታሪክ ላይ አንድ አይነት የጋራ ግንዛቤ ላይ መድረስ ካልተቻለ ወይ ንቅንቅ። መቼም ደግሞ የምንደርስ አይመስለኝም።

አለመሳሳቴን እርግጠኛ ለመሆን በመጀመርያ ያደረኩት በመፀሀፉ ትናንት አለማወቅ ምክንያቶች ሆኖው የቀረቡ ጉዳዬች መመርመር ነበር። መፀሀፉ በተናጠል በግለሰብ ደረጃ ማየት አለው። በግለሰብ ደረጃ ዛሬን አይደለም ነገም ላይ ችግር የለብንም። ሆዳችንን በመቀነት ቋጥረን ለነገ ቅሪት የምንሰበስብ ብዙ ነን። ችግሩ የጋራ ለሆኑ ጉዳዬች አገር፤መብት፤ መልካም አስተዳደር፤ መልካም አገልግሎት፤ ፍትህ፤ እኩልነት……የመሳሰሉ በጋራ ካልሆነ በቀላሉ የማንነቀንቃቸው ችግሮችና መፍትሄዋቻቸው ላይ ነው። ዘሬ መሀይም የሆነው። እንዴት?፤ ምን? መቼ?፤ከየት፤ ማን?፤ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ? ለሚሉት መልስ የለንም። መፈለጉም ጠቃሚ ሆኖ የታየ አይመስልም።

ትናንትናን ማወቁ “እውቀት ነውና የማሰብ ችሎታችንን በማሳደግና በማስፋት፤ በማነቃቂት፤ የችግሩን የሗላ ታሪክ አጥንቶ በተገቢው ለመረዳትና ዛሬ ላለብን ችግርና ተሻግረንም ለነገ ሁሉ መፍትሄ ለመስራት የሚኖረው ጠቀሜታ አሌ የማይባል ነው። በዚህ መንፈስ የቀረበውን ሙሉ በሙሉ እስማማበታለው። ዛሬና ነገን እንደሌሉ አድርገን ከሰጠነው ቦታ አኳያ ግን ጥቅሙ አይመጥንም። ትናነት መኖሩ በራሱ የዛሬ ቸግር ላይ መፍትሄ ለመስራት ሳንካ የሚሆንባቸውን ሁኔታዎች ስንደምር ደግሞ ጥቅሙን የበለጠ ያሳንሰዋል።

በመፀሀፉ ትናንተናን ባለማስተወሳችን በሚል ምሳሌ ተደርገው ከቀረቡት ምክንያቶች አንዱን ላንሳና ለሌሎቹም መልስ የሰጠሁበትን መንገድ ላስቀምጥ።

እናት ኢትዬጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፤

የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ፤

ባንዳ ነግሶ አርበኛ እንዲሳደድና እንዲያዝን የሆነው ትናንትን ካለማወቅ አይመስለኝም። በጊዜው ትናንት ዛሬ በነበረ ጊዜ ትክክለኛ ምርጫ ማድረግ አለመቻል ነው ችግሩ። ይህ ድርጊት ነገ ላይ የሚያስከትለውን ጦስ ባለማጤን የተሰራ ስህተት ነው።  እንደውም ንጉሱ በግል ከገቡበት ችግር አኳያ መውጫ መፍትሄ ወደሗላ ሄደው ከትናንትና  ያሰቡና ምን አልባትም የተመከሩ መሆኑ ለስህተቱ ምክንያት የሆነ  ይመስላል። አርበኞቹም ያኔ ዛሬን ቆም ብለው አስበው ቢሆን ኖሮ ጥቃቱን በተሻለ መከላከል ወይ ማስቀረት ይችሉ ነበር። ትናንት መንግስትና ንጉሱ ላይ በነበረ እሳቦት መዘነጋተቸው ነው ያስጠቃቸው። ባጠቃላይ ትናንት ችግር ከነበረ መፍትሄ ካልተሰራለትም መፍትሄው ስህተት ከሆነም፤ በቂም ካልሆነ ትናንት

ዛሬ በነበረበት ጊዜ የመስራት ችግር እንዳለን እንጂ የሚያሳየው ክትናንትና ወዲያን አለማወቅን አይደለም። ችግሮች ትናንት የጀመሩ የትናንት መሰረት ይኑራቸው ዛሬ ነገን ሁሉ ግምት ውስጥ አስገብቶ በጊዜው መፍትሄ ሊሰራላቸው ይገባል። ለዛሬ ከተላለፈ የትናንት መሆኑ ቀርቶ የዛሬ የኛ ያሁኖቹ ችግር ነው። ዛሬም ነግን እያሰብን ካልሰራነው የልጆቻችን ችግር ይሆናል። ለልጆችን ካወረስነው ደግሞ መፍትሄ  ለመስራት ቁርጠኝነቱና መስራት የሚያስችለን እውቀቱ አለን የለንም ከሚለው ጋር ነው ቀጥተኛ ቁርኝቱ።

ትናንትናን እንጂ ዛሬን ላለማወቃችን አሳማኝ ምሳሌዎች።

እስከዛሬ በስነ ፅሁፍ፤ በኪነ ጥበብ፤በኪነ ስእል ስራዎቻችንን በሙሉ አይቶ ምን ያህሉ ስለዛሬ፤ ምን ያህሉ ስለነገ፤ ምን ያህሎቹ ደግሞ ስለትናንት ያወራሉ የሚለውን ማየት ይቻላል። ማወቅ ያለብን ዛሬን እንደትናንት መተረክ ዛሬን ማወቅ በጭራሽ አይደልም። የዛሬን ችግር ባግባቡ ተረድቶ ሙሉ የሆነ መፍትሄ ምን አልባታም ካንድ በላይ  ማስቀመጥና የተሻለውን መርጦ ተግባራዊ ማድረግ ካልተቻለም ስራውን ዛሬ መጀመር ነው ዛሬን ማወቅ።

ሌላው ጥናት ነው ሊባል ባይችልም  ለስምንት አመታት ሻይና ቢራ እያስተናገድኩ የብዙ ደንበኞች የሚወያዩበትን፤ የሚከራከሩበትን፤ የሚጣሉበትን፤ የበዛ ጊዜ የሚሰጡትን ጉዳይ ለማየት ሞክሬያለው። ስለአገርና ህዝብ ከሆነ   እጅግ የበዛውን ጊዜ የቀደመ ታሪክ ላይ መሆኑን ተገንዝቤያለው። በተመሳሳይ ዛሬ ላይ የየለትና በቅርብ መነጋገርያ በሆኑ አንኳር ጉዳዬች ላይ እንደምንወያይም እንዲሁ። ጠቅለል ሲደረግ ዛሬ ላይ በትንሹ መፍትሄ ድረስ በማይሄድ  ነገን ላይ እስከጭራሹ እንደማንነጋገር ነው የተረዳሁት። ስለትናንት መወያየቱ ከድህንነት አኳያ ችግር ስለሌው ብቻ ግን አይደለም። ውይይቱ ላይ ተሳትፎ ለማድረግ የሚያስችለው እውቀት ሁሉም አለኝ ብሎ ስለሚያስብ በእርግጥም ስላለው ነው። የግድ የታሪክ ምሁር ያህል ሁላችንም ማወቅን አያሻም። አይፈልግምም።

ለነዚህ ረጅም አመታት እኔም ድርሻ ያደረኩበት ውይይት ሁሌ ትናንት ላይ ብቻ መሆኑ ስለመረረኝ የሆነ ጊዜ ላይ ስለትናንት ማውራቱ ብቻ ፋይዳ የለውም። ከዛሬ ጀምሮ መፍትሄ ድረስ በሚሄድ ስለዛሬና ስለነገ እንወያይ የሚል ሀሳብ አቅርቤ ተቀባይነት አግኝቶ ነበር። መነሻ የሚሆን ሀሳብ ለማቅረብ ቢሞከርም ውይይቱ ብዙ አልሄድ አለ። ጊዜ አልበቃው ይል የነበረ ውይይት ዝምታና መፋጠጥ ስለበዛበት ቀስ ብሎ ወደድሮው ልምድ ተመለሰ። ይህ የሆነው በትንሹ ካስር አመት በፊት  ነው።

መንገድ በመንገድና ህንፃ በህንፃ ሆነች ተብላ ብዙ የተወራለትን አዲስ አበባ ላይ ለዚህች ትንሽ ስራ የብዙ ዜጎችን ሂወት በእጅጉ ተመሳቅሏል። ብዙ እውቀት፤ገንዘብና ጉልበት ፈሶበታል። መነሻ ፍላጎቱማ ሀሳቡም ዛሬ ነበር የተባለ ችግርን ለመቅረፍ ነው።  ባጠቃላይ ለነገ አይደለም ላዛሬ ችግር በማይሆንበት መንገድ ግን አልተሰራም። ለምን ማፍረስም መስራትም እንደጀመሩ በቅጡ እንኳን አያውቁም ነበር። አለማወቃቸውን እነሱም እያመኑ ነው። ትራፊክ ተጨናነቀ፤ የሚኪና አደጋ በዛ፤ ማቆሚያ የለም። ታክሲዎች ለመጫንና ለማውረድ ማቆም እንዳለባቸው እንኳ አልታሰበም። አረንጓዴ ቦታ አልተተውም። የሚባለው እውነት ከሆነና በሐይለስላሴ ጊዜ የተሰራ እቅድ ተጠቅመው ከሆነ ለምን ይህ እንደተፈጠረ ችግሩን ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል። ያው ተሰሩ የተባሉ ህንፃዎች መንገዶቹ ጫፍ ላይ ተደርድረዋል። ለማስተካከል እንደጋና ማፍረስ፤ እነደገና ማመሳቀልን ይፈልግብናል ማለት ነው።

አሜሪካኖች እኛ ዜግነት ለማግኘት አጥንተን የምንፈተነውን ፈተና ለሙከራ ተፈትነው ብዙዎቹ እንደማያልፉ ሲነገር ሰምቻለው። ለተላላቅ ሰዎቻቸው መዘክር፤ መታሰቢያ፤ ላይብረሪ ቢሰሩ የተሰራለትን ግለሰብ ጋር ተያያዥነት ያለቸውን ታሪክ መሰብሰብ ትንሿ ሀላፊነት ነው። እነዚህ ማእከላት ወና ትኩረት አድርገው የሚሰሩት ስለዛሬና ነገ ነው።  ሌላ ብዙ አመት ደግሞ ታክሲ እየሰራው ብዙ አሜሪካኖችን አመላልሻለው። ብቻቸውን ሆነው በስልክ ወይ ካንድ በላይ ሆነው ሲሳፈሩ የሚወዩበትን አርስትና ይዘት ምን እንደሆነ ለማወቅ ሆን ብዬ አድምጫለው።  አርእስቱ ቢለያይም ስለ ትናንትና ታሪክ ሲያወሩ የሰማሁበት ጊዜ እጅግ በጣም ውስን ነው። አብዛኞቹ ሰረተኞች ስለሆኑም ይሆናል በስራ ደረጃም ሆነ ከስራ ውጪ ባለ ጉዳይ ላይ መፍትሄ ድረስ በሚሄድ እንደውም ብዙውን ጊዜ መፍትሄ ላይ እንደሆነ ግን በእርግጠኛነት መናገር እችላለው።

መጻፌ ካልቀረ ብዬ ነው እንጂ እንደሁሌው ከዚህ በላይ የፃፍኩትን ሁሉ እራሴን ችዬ ብጽፍበት እችል ነበር።  ይሻል የነበረውም እሱ ነው። በዋናነት አዳፍኔ ላይ ለመፃፍ ምክንያት የሆነኝ ከዚህ በታች የማስቀምጠው አንድ ገፅ ላይ ያለች ሀሳብ ብቻ ነች። ቁንፅል ብትሆንም  ትልቅ ጉዳይ አድርጌ ወስጃታለው።

‘እራሱን እንደነጻ ስው፤ እንደግለሰብ ማየትና በዚያው መሰረት መወሰን የማይችል ፍጡር ከአየራልንድም ይምጣ ከስኮትላንድ ፤ ከኢትዮጵያ ይምጣ ከኬንያ ወይም ከሱማልያ ገና ዝቅተኛ የሰውነት ደረጃ ላይ ያለ ነው።ገና የራሱ ባለቤት አልሆነም ማለት ነው። ወደግለሰብነት ደረጃ ላይ ያልደረሰና የግለሰብነት የሀላፊነት ባለቤትነትን ያልተረዳ በሰውነት ደረጃው ዝቅተኛ ነው። አስከትለው ስልጣን መቼ ትለቃለህ ተብሎ ደንግጦ የሞተው መሪ ሲጠየቅ ድርጅቴ ነው የሚወስነው ሲል የመለሰው ላይ ያብራራሉ። በማስከተል “ይህንን ያልተማረ ወይም ያልተገነዘበ ግለስብ ከእንሰሳት ደረጃ አልወጣም። ነግረ ግን በዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩና የሚማሩ ሰዎች በጎሰኛነት ሕመም ተይዘው ማደግና መሻሻል የሚባሉት ነገሮች በየት በኩል ግብቶ ቦታ ያገኛል።” እያሉ ይቀጥላሉ።

በጥንቃቄ እንዳያስጠይቅና አሻሚ ለማድረግ አስበው እሳቸው በደብተራ አፃፃፍ በሚሉት ነው ያስቀመጡት። ለነገር ከሆነ የዝንብ ጠንጋራን ለሚያውቅ አይደለም ለማንም ቀና አሳቢ ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት ግን ግልፅ ነው። ለነገሩ መለስ ዜናዊም ቢሆን ያን በማለቱ ተሳስቷል ሊባል ይችላል እንጂ ከሳቸው እኩል ሰው ነው። ዝቅ ብለው እሳቸውም አባባሉን

ብልጠትና ውሸቱን እንደሆነ ገልፀዋል። ታዲያ ብልጥ ስለሆነ ነው ከሰው ያነሰው።  ወይስ ስለዋሸ?። እዚህ ላይ መለስ ማደነጋርያ ሆኖ ነው የገባው። ጎሰኛ አስተማሪና ተማሪዎቹም እንዲሁ።

ለማንኛውም ጎሰኛ የተባሉት መምህራንና ተማሪዎች ለዚህ ደረጃ የደረሱት ሆነ ሂወታቸውን እየኖሩና እየመሩ ያሉት እራሳቸውን ችለው እያሰቡና እየወሰኑ ነው። እኔ ነበርኩ የማስብና የምወስንላቸው መቼም አይሉም። በጎሳ ያስባሉ ሲባልም ጭንቅላታቸውን የሸረሪት ድር በመሰለ ነገር አገናኝተው አንድ ትልቅና ውስብስብ አይምሮ ፈጥረዋል ለማለትም አይደለም። ይህ ቢሆንም ምንኛ ድንቅ ነበር። ኢትዬጵያ አይደለችም አለም በታደለች። ስላሴዎችን መሰሉ። ለማለት የተፈለገው በኢትዬጵያ ስም ብቻ ካልሆነ ትናንሽ ማንነቶችን ለምን ይፈጥራሉ ነው። የሚጋሩት የተለዩ ችግሮች ቢኖርም እንኳ በኦሮሞነት ወይ በትግሬነት ችግርም ቢኖርባቸው መናገር ወይ ለመሰማት መተባበር የለባቸውም ነው።

ዛሬ በወያኔ ኢሕአዲግ ስርአት ነፃነቴን አጥቻለው የምንል ግለሰብ ወይስ እኛ?። እኛ ነን። የጋራ ችግረችንን አውቀን፤ መፍትሄው ስንሰራ ተባብረንና መክረን አስማምተን ነው። ታዲያ ዝቅተኛ የሰውነት ደረጃ ላይ ነን ማለት ነው?።ትግሉ ውስጥ ድርሻ ያለው ሁሉ በግሉ ችግር አለ መፍቴሄም ይሻል፤ ለዚህም ትግሉ ላይ የድርሻዬን ማበርከት አለብኝ ብሎ በደንብ አስቦበት ውሳኔ አድርጎ ይሳተፋል። ከሌሎች ጋር አስተዋፆውን ያስተባብራል። ታዲያ በሰውነትህ ያንስክ ነህ የሚያስብለው የትኛው ተግባሩ ነው። እኩል የተሻለስ የሚያደርገውስ?። ሰው መህበራዊ ፍጡር የሆነውስ በምንድን ነው?።

ጎሳም እንደቤተሰብ፤መንደር፤ብሔር፤ ብሔረሰብ፤ ያንድ አገር ህዝብ፤ ጥቁር ህዘብ፤ ጋናዊ፤ አረብ፤ክርሲቲያን…ማህበረሰብ ነው። ልዩነቱ በብዛቱ፤  በቆዳ ቀለሙ፤ በእምነቱና በሚኖርበት ቦታ ነው። ሁሉም ከግለሰብ በላይ የሆኑ የሰዎች ስብስብ ነው። እንደተለያየ ማህበረሰብነቱ ልዩ ባህሪ ያላቸው የጋራ ችግር ይኖረዋል። መጨፍጨፍ አድሎ መንቋሸሽ ….ሊኖርበት ይችላል። ወይ አለ ብሎ ካመነ  በጋራ ሆኖ  ቢታገል፤ ድምፁን ቢያሰማ፤ ቢቃወም፤ ቢዋጋ ጭምር በእንሰሳት ደረጃ ያለ የሚያደርገው ምኑ ነው። ግለሰብ ሆኖ የዚህ የዛ ስብስብና ማህበረሰብ ሳይሆን የሚኖርስ ማነው። በቤተሰቡ ላይ የተቃጣን አደጋ በተለየ የማያይ አለ። በቤተሰብ ደረጃ የተለየ ፍላጎትስ የሌለው። ታዲያ  ፀሀፊው ከኔ  ከሰው ጋር እኩል አይደሉም ሲሉ ምን ለማለት ፈልገው ነው?።

ጎሳ ምንድን ነው፤ ጎሳስ ማነው የሚለው እንዳለ ጠቅለለል ባለ ሌኔ ይህ እነሱ ማለት! አራት አይን ያላቸው።እጃቸው ወገባቸው ላይ ያለ።ጅርባቸው ላይ አምስት ቀንድ ። አረንጓዴ ግራጫና ሀምራዊ ቀለም ያላቸው። ጭራቅ አይነት አስፈሪ አውሬዎች ናቸው የሚለው ገለፃ ተሻሽሎ መጣ ነው ።ከዚህ ደረጃ ተነስቶ ተሻሽሏል ማለት ለፈለገ ይችላል። ለኔ ግኔ ከኛ በላይ ጥሩ አሳቢና የተማረ ኢትዬጵያዊ የለም ከሚሉ።  አሉልን ከምንላቸው አንዱ አይደለም ሁለቱም ፕሮፌሰሮች መስፍን ወልደማርያምና፤ ጌታቸው ሀይሌ ይህን ተራኪዎች መሆናቸው አሳፍሮኛል። በቃ አሁን ሴጣን የሚለውን አውሬ ነው። ነገር ግን ሰው የሚመስል በሚል ነው ያሻሻሉት። ይህ ክሽፈት የተባለው ምን ያህል የከፋና ለምን እንደከሸፍን ምንጩንም ያየሁበት ነው።

ለነገሩ ይህ ልዩ ፍጡር ቆንጆ ገፀ ባህሪ ለልጆች ይወጣዋል። የልጆች ስለሆነና የኦሮሞ ህዝብ የተሳለበት ስለሆነ ጥሩ ገፀ ባህሪና  ብናላብሰው ጀግና ብናደርገው በልጆች በፍቅር የሚወደድ ካርቱን ይወጣዋል። ለነገ የተሻለ ዜጋ በመፈጠሩም አስተዋፆ አለው። ፍልሙ ሲጀምር አስገራሚ በሆነ ሁናቴ ባህሩ ይናጥና ከውሀ ውስጥ አውሬው ሲወጣ እናደርጋለን።

ግጥም አድርጌ እንደ ኦሮሞ አስባለው። እወስናለው። ነግር ግን እንደ ኦሮሞ ብቻ አላስብም። እንደ ዳዊት አስባለው። እንደ ዳባ ቤተሰብ፤ እንደኮንጎ ሰፈር ልጅ፤እንደጥቁር፤ እንደአፍሪካዊ አስባለው። እንደጁም አስብ ነበር። አሁን እንደ ፍልስጤምና እንደአፋር አስባለው እወስናለው…..። ፍትህ የተጓደለበት የተጨቆነ፤ የሚገደል.. ባለበት ሁሉ ሳልፈልግ በመንፈስ እዛ አለው። ስለዚህም ያ አውሬ እኔ ነኝ። ከርሶ በሰውነቴ አንሳለው ማለቴ ነው። እንደ ኢትዬጵያው የሚለውን አውቄ ነው የተውኩት። ሰው ለመሆን የግድ እንደ ኢትዬጵያዊ ማሰብ የለብኝም። ኢትዬጵያዊ ስለሆንኩ ግን ማሰብን ፈልጌ የምተወው ፈልጌ የማደርገውም አይደለም።

ሐይለስላሴ የናታቸውን ማንነት አልደበቁም። የደበቁት ታሪከኞች ናቸው። በይበልጥም የንጉሱ ታሪክ ላይ የፃፉ። ያም ሆኖ ይህ ተደበቀ ታወቀ ይህን ያህል ፋይዳ የለውም። አሳሳቢው ሌላስ ስንት ነገር አውቀው ደብቀውናል የሚለው ነው። የየጁ

አሮሞዎች ኢትዬጵያን አስተዳድረው ነበር የሚል አዲስ ታሪክ ብቅ እያለ ነው። እዚህ ታሪክ ላይ ትልቁ ጉዳይ ኦሮሞዎች መግዛት አለመግዛታቸው ሳይሆን ወይ ጎንደር ማእከል መሆኑ አለመሆኑ ወይ ስፋቱ አይደለም። ያስተዳደሩት ለምን ቀበሌ አትሆንም ዋናው ቁምነገር። እውነት ከሆነ ለመቶ ሀያ አመት በስምንት ገዳ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተደርጓል። ይሄ ለኢትዬጵያዊያን እጃችንን ጭንቅላታችን ላይ አድርገን የሚያስጨበጭብ ብቻ ሳይሆን የሚያስጮህን ነው። ሀውልት ሊቆምለት የሚገባስ ይህ ነበር።

ከዚህ በታች ያሉትን ቁም ነገሮች በኦሮመነት አይደለም በጊዜው የወሰድኳቸው። በኢትዬጵያዊነትም አይደለም።   በጣም ልጅ እያለው ለክረምት አያቶቼ ጋር ሄጄ የተለዩ ስለሆኑ ወድጃቸዋለው። እያደኩ ስሄድ ደግሞ እጅግ ጥሩ፤ ትክክለኝ ነገሮች አድርጌ አስቤያቸዋለው። ስለዚህም ውስጤ ትልቅ ቦታ ይዘዋል። አሁን ግን በኦሮሞነት አስቤና ወስኜ እፅፋቸዋለው።

ፈታና ደስታ ያለበትን ጊዜ መርጠው በሰከነና ስርአት ባለው መልክ አንድን ችግረ ከስሩ መርምረው መፍተሄ መስራት እንደሚችሉ አይቻለው። ችግሮችን ለሌላ ጊዜ መቆየት ድረስ በግዚያዊ መፍትሄ ሰርተውለት ጊዜ ወስደው አክርመው ማየት እንደሚችሉና በመጨራሻ መፍትሄ እንደሚሰሩለትም እንዲሁ። ዛና የሚያደርገው ጊዜ ከሶስት ወር በሗላ የታህሳስ ቅዱስ ገብርኤል ንግስ ሊሆን ይችላል። ከያዙት ቁምነገር ጋር የሚያያዙና የሚመሳሰሉ ድንቅ ታሪኮች፤ አባባሎች፤ ቀልዶች ሁሌም በገፍ አላቸው። ጉዳዬ የግለሰብ ከሆነ ባለጉዳዬች እኩል መናገር ያለባቸውን ሁሉ እንዲናገሩ፤ እንዲከራከሩ ይደረጋል። እኔም፤ ሴቶች ልጆችም ውጡና ውጪ ተጫወቱ አልተባልንም።

ለተፈጥሮ መቆርቀርና መውደድ በገዘፈ መንገድ አይቻለው። ፀሎታቸው ሁሉ ስለተፈጥሮ ደህንነት ነው። ለደስታና ለዝና ሲሉ ለገደሉት እንሰሳ አምላክን ለመለማመን የፀሎትና የልመና ዝግጅቱ አንድ ዲል ያለ የሀብታም ሰርግ አድርጋችሁ ውሰዱት። ስለዚህ ዝም ብሎ መግደል ክልክል ነው። ውሻ ባጮጮሁ ወይ እራት ላይ መረሳቱን ካስታወሱ ለሊት ላይ ተነስተው ምጣድ ይጣዳሉ።ለውሻ ምግብ ማዘጋጀት የሰው እኩል የሁል ጊዜ ስራ ነው።  እንክብካቤው ስላላቸው ዶሮዎች በየቀኑ እንቁላል ይጥላሉ። በቀን ሁለቴ የሚጥሉ ሁሉ ያየው ይመስለኛል። በስራ ላይ የዋለ እንሰሳ የተለየ እንክብካቤ አለው። ፈረስ በፍቅር ይወዳሉ። ይንከባከባሉ። ያስውባሉ። እንሰሳትን ለስራ ስትጠቀምም ሆነ ስታግድ ለመመለስና ለመግራት ያህል እንጂ መደብደብ ሁሉንም ጨርቃቸውን ነው የሚያስጥላቸው። እንዲህ አድርግህ እንደመታህው በሽታ ወይ አምላክ ይምታህ ብሎ ሊያስረግምህ ይችላል። ሲያውሱ እንዳትመታብኝ፤  በተለየ ለብቻው እንድትመግበው ሲሉ ማሳሰብ ሁሌም የማይረሱት አደራ ነው። እረኛ ሆነህ ከብቶቹ ታከው የማይበላም ቢሆን እያደገ ያለ እፀዋትን ካጠፉ ያስገስፃል። ሲያደርጉ አይቼ ግራር ከስሩ ስቆርጥ አላፍ ገበሬ ዠልጦኛል። ከቆረጡ በምትኩ ወይ መልሶ ማደግ አለበት ይላሉ…..።

ለህፃናት ለሴቶችና ለአቅመ ደካሞች ከለመድኩትና ከማውቅ በተለየ እንክብካቤ ያደርጋሉ። ህፃናት በፍቅር ይወዳሉ። ዱላ እጅግ ያልተለመደ ነው። ህፃናቱ ከፍ ሲሉ ሴቶችም ነፃነታቸው በተሻለ ከኢኮኖሚ ነፃነት ጋር ነው። ይህ ምን ማለት እንደሆነ መቼም ይገባናል። ከቁም ነገር ቆጥረውን በየቀኑ ቁጭ አድርገው ህፃናትን ያወሩናል። ያጫውቱናል። በመጠየቅና በተረት፤ ታሪክ በመንገር ያስተምራሉ። የሚለብሷቸው ልብሶች  አብዛኛው ከተሜ ከሚለብሳቸው በላይ ወጋቸው ውድ ነው። በነሱ የፍትህ ሰስርአት ሽምግልና ልጆችም ሴቶችም እኩል ይዳኛሉ። ቤተሰብ ሲያወራ እንደሰማሁት ትንሽ መሬትና ጥቂት ከብቶች የነበራት አርበኛዋ አያቴ ያልወለደቻቸውን ሀያ ስድስት ህፃናትን አሳድጋለች።

ባህላዊም ቢሆን የሚጠቀሙባቸው ቁሳቁስ ድንቅ የጅ ስራ ውጤቶች ናቸው። ዱላ መያዝ እንወዳለን። ዱላው ዝም ብሎ ከዛፍ ላይ ተቆርጦ የሚያዝ እንዳይመስለን። በፍለጋ ለማዘገጃት የሚወስደውን ጊዜ  የሚደረግለትን እንክብካአቤ ብታዩት ሁልሽም በኖረኝ የምትይው ነው። ከልብስ ከለር ጋር አስማምቶ ለመያዝ በአይነት ነው ያላቸው። የተለየ አይነት የበዓላት አከባበር አላቸው። በተለይ መስቀል። አዲስ አመታቸው ነው መሰለኝ። በአሉን ሰዎች ብቻ አይደሉም እንሰሳቱም ናቸው የሚያከብሩት። አንዱ ችቦ አዲስ አበባ ደመራ ብለን በየቤታችን የምንሰራውን ያክላል። መሸከም ስለማልችል እሱ በትከሻ ይዞ እኔ የጎረምሳውን ልብስ ይዥ ነው በመከተል ችቦው የኔ የሚሆነው። ጅራፉ አራት መአዘን ነው።  የሚተኩሱት ወደፊት ወደላይና ወደታች ነው። ከፈለጉ ወደላይ ወደታች ወደጎን አከታትለው ሶስቴ ይተኩሳሉ። ይህቺ በሁለት ክረምት በልጅነቴ ካየሗት በትንሹ ነው። የኖረበት ብዙ ሊል ይችላል።

የኦሮሞ ህዝቡ ድሮም ዛሬም ቅሬታ ይዞ ነው የሚኖረው። በኔ ግንዛቤ አናኗሩ የዚህ አይነት የስልጡን ህዝብ ነው።  ቅሬታው  ኑሩ የተባልነው ወደሗላ የሚመልስንና ሗላ ቀር ነው የሚል ነው። የተሻል ካላችሁ አምጡ። አለበለዛ ተውን የራሳችን ይሻለናል ነው። እውነታቸውን ነው ብግድ ካልኖራችሁ ስንለው የነበረው አሁን እኛም የከሸፈ ነው እያልን ነው። ያኔ እኔ የማውቃቸው በሙሉ እራሳቸውን ኢትዬጵያዊም አድርገው ነው የሚያዩት። አርበኛ፤ወዶ ዘማቾች፤ ሚሊሻ፤ ወታደሮች ብብዛት አሉበት። ለዝች አገር ነብስና አካላቸው የገበሩም ብዙ ናቸው።

ለፈለገ መፃፍን መተቸትን አልከለክልም። ዳዊት ይህን ሰለፃፍክ ወይ ይህን ወይ ያንኛውን ስላልክ ወይ ስላደረክ ከኔ ወይ ከኛ ታንሳለህ ሊለኝ ለሚፈልግ  ሁሉ መልሴ አንድ ነው። ይህንን ለናትህ ንገራት። ለምን እራሱ አምላክ አይመጣም። በተመሳሳይ አንተ ዘረኛ ነህ ለሚለኝ ሲጀመር እኔ ካንተ በሰውነት እበልጣለው ብሎ ማሰብ ነው ዘረኝነት ነው መልሴ። በዛ ላይ መብራት ይዘህ በገበያ መሀል ስትፈልግ ብትኖር የኦሮሞ ዘረኛ የለም። ምን አልባት ብሶተኛ ያስኬዳል።” ጠባብ ነህ”። እኔ ጠብቤ ሳይሆን አንተ ጠብህ ነው ሊሆን የሚችለው። የምናወራው በሁሉም መልክ ስለሰፊ ጉዳይ ነው።  ጤፍን በሲኒ መስፈር ልምድ አድርገህ እንዳይሆን። ቆም ብለህ እራስህን ጠይቅ ነው መልሴ። የበታችነት ይሰማሀል። አልክ? ይጥላኝ ብልህ መፍጠርህም አይደንቀኝ።  ያው ከዚህ የተለየ አይኖርም ብዬ ነው።

 

ዘርኝነት ድንቁርና ነው። ደንቁራችሁ አታዳናቁሩን።

Comment

 

 

 

ትግሉንና ድሉን የጋራ በማድረግ መርህ ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ለሃገራችን የወደፊት እጣ ፋንታ ወሳኝ ነው!

0
0

የኢትዮጵያ የስደት መንግስት አደራጅ ኮሚቴ ለህዝብ ክፍት የሆነ አለም አቀፍ ጋዜጣዊ መግለጫ ቀን፥

9/5/2015 እ.አ.አ.

entc-and-eynm-logoየኢትዮጵያ የስደት መንግስት አደራጅ ኮሚቴ በኢትዮጵያ የስደት መንግስት የምስረታ ሂደትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ለመስጠት፤ ቅዳሜ፣ሴፕቴምበር 12፣ 2015 ከቀኑ 3pm ጀምሮ (በዋሽንግተን ዲሲ ሰአት አቆጣጠር) ለህዝብ ክፍት የሆነ አለም አቀፍ ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጅቷል። በእለቱ የኢትዮጵያ የስደት መንግስት አደራጅ ኮሚቴ ተወካዮች፤ የስደት መንግስት ምስረታው ሂደቶችንና የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝርና በጥልቀት ከማቅረባቸውም ባሻገር፤ በሚዲያ ተወካዮችና የተለያዩ በርካታ ተካፋይ ጋዜጠኞች ለሚነሱ ማንኛውም ጥያቄዎች ግልፅ በሆነ መንገድ ማብራሪያዎችን ይሰጣሉ።  —-

[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

 

 

የሰራዊቱ መልእክት: “ዝምታችን አጋጣሚን በመጠበቃችን!”ሳዲቅ አህመድ ያዘጋጀዉ ፕሮግራም (ክፍል 2)

0
0

የሰራዊቱ መልእክት:
“ዝምታችን አጋጣሚን በመጠበቃችን!”
ሳዲቅ አህመድ ያዘጋጀዉ ፕሮግራም (ክፍል ሁለት)


Sadik Ahemed Journalist

Hiber Radio: አሜሪካ ሶማሊያ ለሚገኘው የኢሕአዴግ እና የጅቡቲ ጦር የመረጃና የስለላ ስልጠና እየሰጠች መሆኗ ታወቀ –ሕንድ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ማንን እንደምመርጥ ተቸግሬያለሁ አለች (ሌሎችም ዜናዎች አሉ)

0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ጳጉሜ 1 ቀን 2007 ፕሮግራም

<...> ዶ/ር መረራ ጉዲና የመድረክ ም/ሊቀመንበር በወቅቱ የስርዓቱ የ ሰብሳቢነት ፕሮፖጋንዳና ለአዲሱ ኣመት የተቃዋሚዎችን ሚና በተመለከተ አነጋግረናቸው ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<... ...> አቶ ማሙሸት አማረ ሕጋዊው የመኢአድ ፕሬዝዳንት ከእስር ቤት መልስ ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

በምንሸኘው 2007 ዓመት የተከናወኑና 21 ዋና ዋና ክንውኖች (የህብር አዘጋጆች ምልከታ)

በቬጋስ ባህታዊው የተገኙበት መንፈሳዊ የአደባባይ የጸሎትና የፈውስ ስርዓት አዘጋጆች አንዱ ጋር ቆይታ ( ሙሉውን ያዳምጡ )

በቬጋስ የሚከበረው የኢትዮጵያ ቀን ዝግጅትን በተመለከተ ቆይታ ከአዘጋጆቹ ጋር(ቃለ መጠይቅ)

በደቡብ ኦሞ ወንዝ ዙሪአ ለተገነባው የሀይል ማመንጫ ፣ የግዳጅ የሰፈራ ፕሮግራም እኛ ስለታቀደው መጠነ ሰፊ የሸንኮራ እርሻ በተመለከተ የእንግሊዝን መንግስት መሰሪነት ያጋለጠው እና የአውሮፓ ህብረት ያወጣው የመስክ ዳሰሳ ሪፖርት(ልዩ ጥንቅር)

ኢትዮጵያ (ግጥም)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

– አሜሪካ ሶማሊያ ለሚገኘው የኢሕአዴግ እና የጅቡቲ ጦር የመረጃና የስለላ ስልጠና እየሰጠች መሆኗ ታወቀ

– ሕንድ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ማንን እንደምመርጥ ተቸግሬያለሁ አለች

– አልበሽር ከእስር ወዳመለጡባት ደቡብ አፍሪካ ተመልሰው ሊሄዱ ነው

– ጦማሪያኑ ከእስር ይፈታሉ ብለው ብዙዎች እየጠበቁ ነው

– ኢትዮጵያ ለውጭ ዜጎች የተመቸችና ለራሷ ዜጎች አስቸጋሪ ስርዓት ያለባት መሆኗ ተገለጸ

– አቶ ማሙሸት አማረ በደህነቶች ክትትል ውስጥ መሆናቸውን ገለጹ

– የሕወሃት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሙስና ፋይላቸው እንዳይገለጥ ተፈራርተው አሳለፉ

– በኢትዮጵያ ከሞቱ ሰዎች ለታማሚዎች ተለዋጭ ዐይን ማግኘት ከባድ መሆኑን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ገለጹ

– ሊፍት በኔቫዳ ከሁበር ያነሰ ተሽከርካሪዎችን ለማሰማራት መወሰኑን ገለጸ

– በአዲስ አበባ የውጭ ዜጋው የሒልተን ሆቴል ስራ አስኪያጅ ታስረው ተፈቱ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ድምፃዊ ብዙአየሁ ደምሴ በካናዳ ከአንድ ወጣት በተወረወረ ጠርሙስ ጉዳት እንደደረሰበት ተሰማ

0
0

bizuayehu demise

‘ሳላይሽ’ የተሰኘ ተወዳጅ አልበሙን ለሕዝብ ካቀረበ በኋላ ከፍተኛ ተቀባይነትን በማግኘቱ በየሃገራቱ እየተዘዋወረ የሙዚቃ ኮንሰርቶቹን በማቅረብ ላይ ያለው ድምፃዊ ብዙአየሁ ደምሴ በካናዳ ዊኒፔግ ግዛት ትናንት ሴፕቴበር 6 አምርቶ ነበር:: ኮንሰርቱን ለመሥራት ወደዚያው ያመራው ይኸው ተወዳጅ ድምፃዊ በአንድ ወጣት በተወረወረ ጠርሙስ ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር ከስፍራው ማለዳ ታይምስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል::

በጠርሙስ ፍንከታ የደረሰበት አካሉ መሰፋቱን የገለጹልን ምንጮቻችንን ጠርሙሱን የወረወረበትን ሰው ለመያዝ ፖሊስ እየጣረ መሆኑም ተሰምቷል::

ብዙአየሁ በዌኒፒግ ኮንሰርት ሊያቀርብ ሲሄድ የም ዕራብ ካናዳ የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ውድድር ይካሄድ እንደነበር ታውቋል::

ዘ-ሐበሻ ወደ ብዙአየሁ ደምሴ ደውላ ጉዳዩን ከ እርሱ አፍ ለመስማት ያደረገችው ሙከራ ባይሳካም ከርሱ እንደሰማን የምናቀርብ መሆናችንን እንገልጻለን::

ኢትዮጵያውያን በውጭ ሃገር ኮንሰርት ለማየት ሄደው በኮንሰርት ላይ መደባደብን እንደ ትልቅ ጀብዱ ማየታቸው የሚያሳዝን ጉዳይ ሲሆን; ይህን ዓይነቱን ድብድብ የሚፈጥሩት ደግሞ የራሳቸው ወገን ባዘጋጀው ኮንሰርት ላይ እንጂ በውጭ ሃገር ኮንሰርቶች ላይ አለመሆኑ ብዙዎችን ያሳዘነ ጉዳይ ነው::

የአፋር ሕዝብ ንቅናቄ፣ ትህዴን፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄና አርበኞች ግንቦት 7 የጋራ ንቅናቄ መሰረቱ

0
0

(photo File)

(photo File)


ዘ-ሐበሻ ከአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ ብረት አንስተው በበረሃ የመሸጉ አራት ታላላቅ የነፃነት ድርጅቶች አምባገነኑን የህወሓት አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በጋራ ደምስሰው ግብአተ መሬቱን ለመፈፀም ተጣምረው “የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ” የሚል አዲስ ድርጅት መሰረቱ፡፡

ተጣምረው የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄን የመሰረቱት አራቱ ታላላቅ የነፃነት ድርጅቶች የአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ፣ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ እና አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ናቸው፡፡
Arbegoch Ginbot 7
የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ /በአጭሩ የአገር አድን ንቅናቄ/ የተቋቋመው ጳጉሜ 3 ቀን 2007 ዓ.ም ሲሆን የንቅናቄው ምክር ቤት፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና የተለያዩ መምሪያዎች ተቋቁመው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበር እና ታጋይ ሞላ አስገዶም ም/ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ ከአራቱ አባል ድርጅቶች የተውጣጣ እጅግ በጣም ግዙፍ አገር አድን ሰራዊት አቋቁሟል፡፡

ቴዲ “የፍቅር ነብዩ”ን ተውት ስለ ፍቅር ደግሞ ደጋግሞ ይዘምር…

0
0

teddy afro
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

እረ ተዉኝ ባትነኩኝ ምናለበት
አባካችሁ ሰዎች ስራዬን ልስራበት።
ታላቁ ጥላሁን ገሠሠ

ፍቅር ሁሉንም ድል ያደርጋል !

ሸክስፒር “አስራሁለተኛው ሌሊት“ በሚለው የትያትር ፁሁፋቸው ላይ የኦርሲኖ መስፍን በአዳራሹ ተሰባስበው ለነበሩት ድምጻውያንና ሙዚቀኞች እንዲህ በማለት ተናግረው ነበር፣ “ሙዚቃ የፍቅር ምግብ እስከሆነ ድረስ አሁንም ዘምሩ፣ በርካታ ሙዚቃዎችን ደግማችሁ ደጋግማችሁ ዘምሩልኝ…“

እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በቅጽል ስሙ ቴዲ አፍሮ እየተባለ የሚጠራውን ቴዎድሮስ ካሳሁንን በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከብዙ ጊዜ በፊት ጀምሮ ለመንፈሳቸው እርካታ ምግብ የሆነውን የህዝቦች የፍቅር ሙዚቃ እንዳይጫወት እገዳ ሲጥልበት ቆይቷል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የቴዲን ህይወት እንደ እነርሱ በመከራ የታጀበ እንዲሆን አጥብቀው ይሰራሉ፡፡ እንደ እነርሱ “የመከራ ፍቅር ኩባንያ“ እንዲሆን ይፈለጋል፡፡

ቴዲ ግን ስለሰው ልጆች ፍቅር ደስታ እንጅ በምንም ዓይነት መልኩ ስለመከራ አይዘምርም፡፡

ቴዲ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን ለማገልገል የተፈጠረ ድምጻዊ ከያኒ አይደለም፡፡ ስለመከራ እና ስቃይም አይዘምርም፡ መዘመርም አይችልም።

ቴዲ መቸውንም ጊዜ ቢሆን ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ባዶ ፕሮፓጋንዳ ማድመቂያ የሆኑትን የጥላቻ፣ የበቀል፣ ኢፍትሀዊ እና ጥልቅ ጥላቻዎችን የሚያነግሱ ሙዚቃዎችን በምንም ዓይነት መልኩ አያቀነቅንም፡፡

እርሱ የሚያቀነቅናቸው ስለደስታ፣ ስለሰላም፣ ስለአንድነት፣ ስለሀገር እና አህጉራዊ ፍቅር፣ ስለኢትዮጵያዊነት፣ ስለአፍሪካዊነት እና በአጠቃላይ ስለሰው ልጆች ፍቅር ነው፡፡ እንደ ሙዚቀኛ ሊዘምር የሚፈልገው እና በተግባር እያሳየ ያለው ስለዚያ ብቻ ነው፡፡ ስለፍቅር ብቻ ነው፡፡

ጥቂት ሰዎች ጥላቻን ለማራገብ የተፈጠሩ ናቸው፣ ሌሎቹ ደግሞ የዕድል ዕጣ ፈንታቸው ስለፍቅር መኖር ነው የሚል አባባል አለ፡፡

ቴዲ የተፈጠረው እና የዕድሉ ዕጣ ፈንታም የፍቅርን ድል አድራጊነት ወንጌል በዓለም ላይ ለሚገኙ ህዝቦች ሁሉ ለመስበክ ነው፡፡ ይኸው ነው ሌላ ተክዕኮ የለውም፡፡

ቴዲን ከሚወዳት ኢትዮጵያ ለማለያየት እና ጥሏት እንዲሰደድ ሌት ከቀን ጥረት የሚያደርጉት ለምንድን ነው?

አሁን በቅርቡ በአማርኛ ቋንቋ ተዘጋጅቶ በድረ ገጽ የግንኙነት መስመር በተለቀቀ ዘገባ መሰረት ይፋ እንደተደረገው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቴዲን ከሀገር ለማስወጣት እና በግዞት ወይም ደግሞ ከዚያ በከፋ መልኩ እንዲኖር ለማድረግ የወሰነ መሆኑን በግልጽ አመላክቷል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚወዳትን ሀገሩን ጥሎ እንዲሰደድ ለበርካታ ዓመታት በቴዲ አፍሮ ላይ የስነ ልቦና፣ የሕግ እና የኢኮኖሚ ጦርነቶችን እና ጫናዎችን ሲያካሂድበት እና ሲፈጽምበት ቆይቷል፡፡

እነዚህ የጥላቻ እና የበቀል ጎተራዎች ታዋቂውን ድምጻዊ ከያኒ አሳንሶ የማየት፣ ስብዕናውን በማንኳሰስ ዝቅ አድርጎ እንዲያስብ እና የማዋረድ ዕኩይ ድርጊቶችን ሲፈጽሙበት ቆይተዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2008 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በቴዲ አፍሮ ላይ ሰውን በመኪና ገጭቶ በማምለጥ የሚል የፈጠራ ክስ በመክሰስ በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርገዋል፡፡

ይህንን የፍብረካ ወንጀል በመጎንጎን ለይስሙላው የዝንጀሮ/የጦጣ ፍርድ ፍቤት እንዲቀርብ በማድረግ ለ6 ዓመታት ያህል በእስር ቤት እንዲማቅቅ ውሳኔ ተላልፎበት ነበር፡፡

ሆኖም ግን ድምጻዊው በእስር ቤት ቆይታው ወቅት ባሳየው ጥሩ ስነምግባር በሚል በአመክሮ 6 ዓመታት የነበረው የእስራት ጊዜ ወደ 2 ዓመታት ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡
teddy afro
በድምጻዊው ላይ የሀሰት ውንጀለቀ ተፈብርኮ የተቀነባበረውን የፈጠራ ክስ በማስመልከት “ጀግናው ከያኒ፡ የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ግጥም ስንኞች“ በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ የነበረ ሲሆን በዚያ ትችት ላይ ሰውን ገጭቶ በመግደል እና በማምለጥ በሚል የፈጠራ የውንጀላ ክስ ላይ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አቀረብኳቸው ያላቸውን ማስረጃዎች በመመርመር ከሕግ አንጻር ምንም ዓይነት ውኃ የማይቋጥር እና በተራ በቀልተኝነት ላይ የተመሰረተ እና በደፈናው ከያኒውን ለማጥቃት በማሰብ የእስራት ቅጣት የተወሰነበት መሆኑን አጋልጨ ነበር፡፡

ቴዲ እ.ኤ.አ በ2012 “ጥቁር ሰው“ የሚለውን አልበሙን በለቀቀበት ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በቴዲ አፍሮ ላይ በማህበራዊ የግንኙነት ዘዴዎች አማካይነት ከፍተኛ በሆነ የማዋረድ እና ስም የማጥፋት ዕኩይ ዘመቻ ከፈተ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ማንነታቸውን በደበቁ አጥቂ ተዋጊ ሰው አልባ ስም አጥፊ ተዋጊዎች በማህበራዊ ድረ ገጾች እና ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ቴዲን ጥላሸት የመቀባት ዘመቻ ላይ ተጠመደ፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስቦች በ19ኛው ክፍለ ዘመን ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የአፍሪካዊ ክብር መገለጫ እና የነጻነት ታጋይ በማለት በሀሰት በመኮፈስ ይልቁንም ጨካኝ እና ጨፍጫፊ የነበረ ንጉስ ነው በማለት የሀሰት የውንጀላ ክስ በማሰማት ቴዲ በሙዚቃው ንጉሱን የገነነ እና ታዋቂ ለማድረግ ጥረት አድርጓል በማለት የባጥ የቆጡን ቀባጥረዋል፡፡

ይህንን የወያኔውን ክህደት እና ቅጥፈት፣ እንዲሁም ተራ ውሸት እና የደንቆሮ የበታችነት ስሜት የበቀል ቅጥፈት በቴዲ አፍሮ የሙዚቃ የግጥም ስንኞች እና ቃና ባለው ዜማው የተዜመ ብቻ ሳይሆን መላው የአፍሪካ ህዝብ እና ዓለም ያደነቀው እና የመሰከረለት ታላቅ ገድል ነው፡፡ ምኒልክን አክብሯቸው፣ አድንቋቸው ታላቁ እና እውነተኛው ሀገር እና ህዝብ አፍቃሪ ንጉሳችሁ የነበሩ እንጅ አሁን እናንተ ሌት ቀን እንደበቀቀን እንደምትለፈልፉለት ከሀዲ እና የባንዳ ዝርያ፣ ሀገር ሻጭ እና በጎሳ ከፋፋይ የሀገር እና የህዝብ ጠላት አልነበሩም፡፡

በእርግጥ ቴዲ በሙዚቃ አልበሙ ለሀገራቸው ሉዓላዊነት እና ክብር ሲሉ ሁሉም ጎሳዎች እና ቡድኖች ሲዋደቁ እና የህይወት መስዋዕትነትን ከፍለው ይህችን ሀገር ያስረከቡንን ጀግኖች እና ታዋቂ ሰዎችን አንበሳ አድርጎ በመሳሉ እና በመዘከሩ ምክንያት ይህ ለወያኔው ታላቅ ሸክም እና ጥላቻ ነው፡፡

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2013 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በቴዲ ላይ የማጠልሸት፣ ጥለሸት የመቀባት፣ የማዋረድ እና ዝቅ አድርጎ የማየት ሌላ ዘመቻ ከፈተ፡፡

ቴዲ “ለእኔ የምኒልክ የአንድነት ዘመቻ ቅዱስ ጦርነት ነበር“ ብሎ ቃለ መጠይቅ ላይ ተነግሯል ብለው የሐሰት ወሬ በመንዛት የውንጀላ ውርጅብኝ ክስ በመመስረት አደንቋሪ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻቸውን ቀጠሉ፡፡

ለመሆኑ ህዝብን ሰውን ሁሉ አንድ ማድረግን እና በፍቅር እንዲተሳሰሩ ከማድረግ በላይ ምን ቅዱስነት ነገር አለ!?

በጎሳ መለያየት፣ እርስ በእርስ ማባላት፣ በህዝብ መካከል የጥላቻ መርዝ መዝራት፣ ጎጠኝነትን ማስፋፋት፣ የኃይማኖት ጽንፈኝነትን በማራገብ ልዩነትን መፍጠር፣ ህዝብን በረሀብ እና በችጋር እየለበለቡ ኢኮኖሚው በሁለት አሀዝ አድጓል፣ ተመንድጓል እያሉ መቀባጠር፣ ትውልድ ገዳይ የትምህርት ፖሊሲ ነድፎ ለምንም ለማንም የማይጠቅም ትውልድን እየፈጠሩ የጫት እና የሌሎች አደንዛዥ ዕጽ ሰለባ እያደረጉ ብሎኬቶች በመቆለል ብቻ እድገት እና ልማት ይመጣ ይመስል ህዝብ ግብር እየከፈለ በሚያስተዳድራቸው በብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች ሌት ቀን ፕሮፓጋንዳ መስራት????

ለእናንተ ዕድገት ማለት ይኸ ነው፡፡

በህዝባቸው ዘንድ እምዬ ምኒልክ የሚል ተቀጽላ ስም የተሰጣቸው እናንተ በፈጠራ ውሸት ተክናችሁ ሁሌ እውነትን ሀሰት፣ ሀሰትን እውነት፣ ቀዩን ጥቁር፣ ጥቁሩን ነጭ እያላችሁ እንደምታቀርቡት የበሬ ወለደ ዓይነት አስተሳሰብ ላይ ተመስርቶ የተሰጠ ስያሜ ሳይሆን በእርግጥም ምኒልክ ለአንድ ጎሳ፣ ቡድን፣ ብሄረሰብ፣ ዘር፣ ኃይማኖት፣ ማንነት ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ወገኖቻቸው ሁሉ የእናትነትን ባህሪ የተላበሱ፣ እንደ እናት ፍቅርን የሚለግሱ እውነተኛ አፍሪካዊ መሪ በመሆናቸው ብቻ ነው፡፡

ይህ ታሪካው እውነት የማይካድ ነው።

ከዚህ አንጻር በቴዲ አፍሮ “ቅዱስ ጦርነት” ብሏል የተባልዌ ሐሰት ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ የተደረገውን ተጋድሎ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጠምዝዞ እና በሚያውቅበት ሸፍጥ የመስራት ተንኮሉ በማጣመም “ዘር ማጥፋት” ብሎ ፈረጀው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በቴዲ አፍሮ ላይ የከፈተው ዋና ስም የማጠልሸት ተልዕኮ ማጠንጠኛው የዳግማዊ ምኒልክን ስም የማጠልሸት ዘመቻ ነው፡፡

በእርግጥ ያ ሁሉ ድንፋታ በመንግስትነት ደረጃ ስልጣንን ተቆጣጥሪያለሁ ከሚል ድርጅት የማይጠበቅ የወረደ እና ተራ ወሮበልነት ነው፡፡ የሀገሩ መሪ በህዝቡ፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፋዊ መድረኮች ሁሉ ስለደግነቱ እና ስለጀግንነቱ ሲወደስ ደስ ሊለው እና ሊኮራ ይገባዋል እንጂ መሰሪ ቀናተኛ ጠላት ሆኖ መቅረብ ከአስተሳሰብ ዝቅጠት የመነጨ ነው ከማለት ሌላ ምን ሊባል ይችላል!

ይልቁንም የወያኔው ድብቁ እና እውነተኛው አጀንዳ አሁን በህይወት የሌለውን እና በጨፍጫፊነቱ እና በአምባገነንነቱ እውቅና ያለውን እ.ኤ.አ በ2005 የተካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ውዝግብ በእራሱ ትዕዛዝ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ሰላማዊ ዜጎች ምርጫው መጭበርበሩን በማስመልከት ተቃውሟቸውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ የገለጹትን ወገኖቻችንን በአደባባይ እንዲጨፈጨፉ ያደረገውን የመለስ ዜናዊን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመሸፋፈን እና ለመደበቅ ሲባል የሚደረግ ሸፍጥ ነው፡፡
TeddyAfro_NYC-12
ይህ ብቻ አይደለም ከዚያ ቀደም ሲልም ሆነ ከዚያ ወዲህ በበደኖ፣ በአሰበ ተፈሪ፣ በጎንደር በእየሱስ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ፣ በአርሲ፣ በጋምቤላ፣ በኦጋዴን እና በሌሎች በተለያዩ ቦታዎች እና አካባቢዎች ዘርን መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ፍጅት መፈጸሙን ልብ ይሏል! የአቦን ቅጠል የቀመሰች ፍየል ያስለፈልፋታል ይባል የለ! ነገሩ እንደዚያ ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በፈጠረው ውዝግብ ምክንያት ቴዲ አፍሮ በአሁኑ ጊዜ የደች/ሆላንድ ንብረት በሆነው በሄይከን ኩባንያ እየተዳደረ ከሚገኘው ከበደሌ ቢራ ፋብሪካ ጋር ስምምነት በማድረግ ሊያቀርብ የነበረውን ኮንሰርት እንዲሰረዝ ተደርጓል፡፡

እ.ኤ.አ በ2014 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ”ግብር ማጭበርበር” የሚል ሌላ የፍብረካ ውንጀላ በማቀነባበር ቴዲ አፍሮን እንደገና በእስር ቤት ለማማቀቅ ሙከራ አደረገ፡፡ የውንጀላ ክሱ የቀረበው ከ7 ወይም ደግሞ ከ8 ዓመታት በፊት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ላስገባው ተሽከርካሪ ግብር አልከፈለም የሚል ነበር፡፡

ሊገመት ከሚችለው በላይ ድፍረትን በተላበሰ መልኩ ፍርድ ቤቱ የግብር ማጭበርበሩን ጉዳይ ለማጣራት ተጨማሪ ቀናትን ለፖሊስ ለመስጠት እና ቴዲ አፍሮም በእስር ቤት ይቆያል የሚለው አስፈላጊ አይደለም ይህንንም አልቀበልም አለ፡፡ (ደፋር ዳኛው ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ፊት ለፊት በመቆም! አይታመንም!!)

እ.ኤ.አ በ2015 የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጆሮ ጠቢዎች ቴዲ በሚሄድበት ቦታ ሁሉ እንደጥላ ይከታተሉት ጀመር፡፡

ቴዲ እናቱን ለመጎብኘት በሚሄድበት ጊዜ አነፍናፊ አዳኝ ውሾችን ያስከተሉ ጆሮ ጠቢ ወሮበሎች ተከትለውት ሄዱ፡፡

ወደ ከተማ በሚሄድበት ጊዜ ሞተር ብስክሌት በሚይዙ ወሮበሎች አማካይነት መሰናክል እንዲፈጠርበት ይደረጋል፡፡

የሲቪል ልብስ የለበሱ ወሮበሎች አንገቱን እንቅ አድርገው ይይዙታል፡፡ በመንገድ ላይ በመጓዝ ላይ እያለ ድንገት ያስቆሙት እና ያስፈራሩታል፡፡

የስልክ መስመሮቹ ይጠለፋሉ፡፡

ቤቱ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በፖሊስ ምርመራ ስር ነው፡፡

በየጊዜው በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶቸ እየቀረበ የማስፈራሪያ ድርጊት ይፈጸምበታል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በኤፍ ኤም የሬዲዮ ጣቢያው በመጠቀም ቴዲን በገንዘብ ኪሳራ ውስጥ እንዲወድቅ እና የገነባውን ታላቅ ስሙን ለማጥፋት ሌት ቀን የፕሮፓጋንዳ ስራውን ይቀጥላል፡፡ ስሙን በማብጠልጠል ላይ ይገኛሉ፡፡ ያለምንም የሕግ ተጠያቂነት እያወገዙት እና ስም የማጥፋት ዘመቻቸውን ቀጥለውበት ይገኛሉ፡፡

በሀገር ውስጥም ሆነ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ህይወቱን መምራት እንደማይችል ከፍተኛ የሆነ ችግር እየፈጠሩ ከህዝብ ለመለየት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

አሁን በቅርቡ የቴዲ አፍሮ ባለቤት ለህክምና ጉዳይ ወደ ኬንያ ሄዳ በነበረችበት ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አውሮፕላኑን በማስቆም ቴዲን ምንም ዓይነት ክፍያ ሳይከፍል ተደብቆ ለመሄድ ሲሞክር እንደተያዘ ሕገ ወጥ ሰው እየገፉ እና እየጎተቱ በአደባባይ ሲያንገላቱት በህዝብ ተስተውሏል፡፡

እንደዚሁም በሌላ ጊዜ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቴዲን በማዋረድ እና የሞራል ስብዕናውን ዝቅ በማድረግ እነርሱ የእርሱ ጌቶች እንደሆኑ የማሳየት ስራ ሰርተዋል፡፡

ቴዲ ያለው ትልቁ ጌታው ወያኔ ሳይሆን ታላቁ የፍቅር ኃይል ነው!

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ተከታታይነት ባለው ሁኔታ ቴዲ አፍሮን ያስፈራሩታል ምክንያቱም ቴዲ የእነርሱን ሙዚቃ አይዘምርም፣ የእነርሱን ዳንስ አይደንስም፣ እንደዚሁም የእነርሱን የጥላቻ ከበሮ አይደልቅም፡፡

ለዚህም ነው እትብቱ ከተቀበረችባት እና ከሚወዳት ሀገሩ እንዲሰደድ ጥረት በማድረግ ላይ ያሉት፡፡

ሆኖም ግን ቴዲ እስከ አሁን ድረስ በሚወዳት ሀገሩ ቆይቷል፡፡ የእራሱን ሀገር ትቶ በማንም ወሮበላ አስገዳጅነት የትም ቦታ ቢሆን አይሄድም፡፡

በውጭ ሀገር ተሰድዶ ነጻ ሆኖ ከመኖር ይልቅ በሀገሩ ውስጥ ሆኖ እጆቹ በካቴና ታስረው በግፈኛ አምባገነኖች እየተሰቃዬ እና ሰብአዊ መብቱ እየተደፈጠጠ መኖርን ይመርጣል፡፡

የእውነተኛ አርበኝነት ባህሪ እንደዚህ ነው!

ጥላቻ የበለጠ እየከረረ እና እየመረረ በሄደ መጠን ጥቂቶች ሀገር ለቀው ይሰደዳሉ፣ ሌሎች ጥቂቶች ደግሞ መከራውን እና ስቃዩንም አሳቱንም ችለው በሀገራቸው ይቆያሉ ይባላሉ፡፡

ቴዲ ግን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን እሳት ፊት ለፊት ተቋቁሞ በሀገሩ በመኖር ላይ ይገኛል፡፡

ቴዲ የኢትዮጵያ ነገስታት የነበሩትን ዳግማዊ ምኒልክን እና ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴን በማወደሱ እና ጀግንነታቸውን በመመስከሩ ብቻ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከልቡ ምርር አድርጎ ጠልቶታል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራሮች እና አባላት “የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት መቀባት“ በሚል ርዕስ አዘጋጅቸው በነበረው ትችቴ ላይ ከዳግማዊ አጼ ምኒልክ እና ከቀዳማዊ አጼ ኃይለስላሴ ይልቅ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የፈጸማቸው ትግባራት የበለጡ ናቸው የሚለውን ቅጥፈታቸውን ለማጋለጥ ሞክሪያለሁ፡፡

ቴዲ አሁን በህይወት ለሌለው ለአምባገነኑ መለስ ዜናዊ እና ለእርሱ ታዛዥ ሎሌዎቹ የሚዘምር ቢሆን ኖሮ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በዚህ ከያኒ ላይ እንደዚህ ያለ ማቋረጫ የሌለው ጦርነት እና የማሰቃዬት እኩይ ድርጊት ሊፈጽሙበት ይችሉ ነበርን?

ቴዲ በእውነታው ዓለም ላይ ያሉትን ጅቦች አንበሳ አድርጎ ቢያቀርባቸው ኖሮ ጆቦቹ ለምን እንደ አንበሳ ተደርገን ተፈረጅን ብለው ቅሬታዎቻቸውን ያቀርቡ ነበርን?

አሁን በህይወት ስሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የሌለውን ስብዕና እንዳለው በማስመሰል “የአፍሪካ አባት” የሚል የሙገሳ መዝሙር ቢያሰማ ኖሮ በቴዲ ላይ እንደዚያ ያለ ጥላሸት የመቀባት እና የማዋረድ ድርጊት ይፈጸምበት ነበርን?

ቴዲን መዘለፍ አልፈልግም ሆኖም ግን የመለስ ዜናዊ ምስል ያለበትን ቲ ሸርት (ካናቴራ) በመልበስ በኮንሰርቱ ላይ ቢታደም ኖሮ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የማስፈራራት ድርጊት ይፈጸምበት ነበርን?

በቴዲ ላይ ማቋረጫ የሌለው ስቅይት እና ማስፈራራት ቢፈጸምበትም ቅሉ ምንም ዓይነት ቅሬታ አላሰማም፡፡ ሌላ ምንም ነገር ትንፍሽ አላለም፣ እንዲህ ነበር ያለው፣ “ፍቅር ሁሉንም ነገር ያሸንፋል፡፡“

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለ25 ዓመታት ያህል በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጦ “ጥላቻ ሁሉንም ነገር ያሸንፋል“ በማለት የእራሱን ደስታ በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡

ጥላቻ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን አሸናፊ ሆኖ ሊታይ ይችላል፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሚወዱት ብቸኛው ነገር ቢኖር ጥላቻን እራሱን ነው፡፡

ሆኖም ግን ቴዲ የማይበገር ጀግና ነው፡፡ እንዲህ እንደሚሉትን የዶ/ር ማርቲን ሉተር መርሆዎች እያስተጋባ የሚኖር ይመስላል፣ “ጥላቻን ጥላቻ አያስወግደውም፣ ይህንን ማድረግ የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡“ በሌላ አባባል “ፍቅር ሁሉን ነገር ያሸንፋል፡፡”

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቴዲ አፍሮን የሚፈራው ለምንድን ነው? ቴዲን እንደዚህ ጥቁር ጥምድ አድርገው የሚጠሉት ለምንድን ነው!?

እስቲ ስለቴዲ የማያወዛግቡ ጥሬ ሀቆችን ይፋ እናድርግ፡

እንደ ድምጻዊ አቀንቃኝ ቴዲ አፍሮ አቻ የማይገኝለት ድምጻዊ ነው! ምንም ዓይነት ተወዳዳሪ የለውም!

ቴዲ እንዲህ የሚሉትን ባህሪት የተላበሰ ምጡቅ ድምጻዊ ነው፡ በስብዕናው አንድ ዓይነት ወጥ ነው፣ የግጥም ስንኞቹ ምትሀታዊ ኃይልን የተላበሱ ናቸው፣ የዜማ ቅላጼዎቹ ማራኪ፣ መንፈስን በደስታ ስሜት ውስጥ የማስጋለብ እና የሰውን ቀልብ የመቆጣጠር ኃይል ያላቸው ናቸው፣

ቴዲ አፍሮ ልዩ ተሰጥኦ ያለው የሙዚቃ ሰው ነው! ምንም ዓይነት ጥያቄዎች ሊነሱበት የሚገባ ጉዳይ አይደለም! ምንም ዓይነት!

እንደዚሁም ሁሉ ቴዲ አፍሮ ነገሮችን በጥልቀት የማየት ችሎታ ያለው የጥልቅ ሀሳብ ባለቤት ሰው ነው፣ ለሁሉም ነገር ጥንቃቄን የሚያደርግ፣ በፍቅር የተሞላ እና ብሩህ አዕምሮ ያለው ሰብአዊ ፍጡር ነው፡፡

በሚያቀርባቸው በሁሉም ሙዚቃዎቹ ስለህይወት ፍልስፍናው ያስተምረናል፡፡ ይህ ፍልስፍናው በሶስት ቃላት እንደሚከተለው ተጠቃሎ ሊቀርብ ይችላል፡ “ፍቅር ሁሉንም ያሸንፋል”፣ ይኸው ነው! ሌላ ምንም ነገር የለም!

ቴዲ ስለይቅርታ ማድረግ እና ዕርቀ ሰላም ስለማውረድ ይዘምራል፡፡

ስለሀገሩ እና አህጉሩ ፍቅር ይዘምራል፡፡

ስለብሄሮች እና ስለኃይማኖቶች ተቻችሎ መኖር ይዘምራል፡፡

ስለኢትዮጵያ ዝና አጥብቆ ይዘምራል፡፡

ኢትዮጵያ ነጻነቷን እንድትቀዳጅ፣ ከቅኝ ገዥነት ነጻ እንድትወጣ፣ ከውጭ የበላይነት ነጻ እንድትሆን ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ እንድትኖር መተኪያ የሌላት ህይወታቸውን ገብረው ላቁዩአት ጀገኖች ልጆቿ ይዘምራል፣ ያቀነቅናል፡፡

የነጻነት መዝሙሮችን ይዘምራል፡፡

ቴዲ እንደ ቦብ ማርሌይ ሁሉ እንዲህ የሚሉ የሙገሳ ሙዚቃዎችን ይዘምራል፡

እነዚህን የትንሣኤ ሙዚቃዎች ለመዘመር እገዛ አታደርጉምን/እነዚህን የነጻነት ሙዚቃዎች?/እስከ አሁን ያሉኝን ሁሉ ዘምሩ፡/የትንሣኤ ሙዚቃዎች/እስከ አሁን ያሉኝን በሙሉ፡/የትንሣኤ ሙዚቃዎች፡/እነዚህን የነጻነት ሙዚቃዎች፡፡/የነጻነት ሙዚቃዎች አብራችሁኝ አትዘምሩም።

ሁሉም የትንሣኤሙገሳ ሙዚቃዎች የቴዲ አፍሮም ናቸው፡፡

ቴዲ እንዲህ በማለት ይጠራዋል፣ “የኢትዮጵያ ትንሳኤ” (የኢትዮጵያ የሙገሳ/ትነሳኤ)፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአሁኑ ጊዜ ቴዲ አፍሮን ማቋረጫ በሌለው መንገድ ለምን እያሰቃዬው እንዳለ ምንም ሀሳብ የሌኝም ፈፅሞ አይገባኝም፡፡

ቴዲ እውነታውን በመዘመሩ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?

እውነትን በሚጠሏት መካከል ጠላቶችን እንዴት እንደሚያፈራ ልገንዘብ እችላለሁ፡፡

ቴዲ ስለፍቅር በመዘመሩ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?

ጥላቻ በደም ስሮቻቸው በተዋሀዱት መካከል የማይሞቱ ጠላቶች እንደሚያፈራ እገነዘባለሁ፡፡

ቴዲ ስለይቅርታ አድራጊነት በመዘመሩ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?

በበቀል እና በጥላቻ በተዘፈቁት መካከል ጠላቶችን እንዴት እንደሚያፈራ ልገነዘብ እችላለሁ፡፡

ቴዲ ስለዕርቀ ሰላም በመዘመሩ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?

የህይወት ተልዕኳቸው ከፋፍሎ መግዛት በሚሉት መካከል ጠላቶች እንዴት እንደሚያፈራ ልገነዘብ እችላለሁ፡፡

ቴዲ ስለ ኢትዮጵያ ትንሳኤ በመዘመሩ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?

በኢትዮጵያ ገዳዮች መካከል ጠላቶች እንዴት እንደሚያፈራ ልገነዘብ እችላለሁ፡፡

ቴዲ ስለኢትዮጵያ አንድነት በመዘመሩ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?

ኢትዮጵያን በመክተፊያ ቢላዋ በመተሯት እና እንዴት የጎሳ፣ የብሄረሰብ ቡድኖች፣ የኃይማኖት እና የክልል ጎጠኛ ደሴት ባደረጓት መካከል ጠላቶች እንዴት እንደሚያፈራ ልገነዘብ እችላለሁ፡፡

ቴዲ ስለለሁሉም ኢትዮጵያውያን የወደፊት የተሻለ ህይወት በመዘመሩ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?

በዕኩይ ምግባራቸው ምክንያት ዕጣ ፈንታቸው ወደ ታሪክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ መጣል ባለባቸው መካከል ጠላቶች እንዴት እንደሚያፈራ ልገነዘብ እችላለሁ፡፡

ቴዲ ስለኢትዮጵያ ጥንታዊ ዝና በመዘመሩ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?

በጥላቻ በተሞሉ ሰይጣኖች፣ በቀልተኞች፣ እምነተቢስ መርህ አልባ ፍጡሮች እና በጫካ ወሮበሎች መካከል ጠላቶች እንዴት እንደሚያፈራ ልገነዘብ እችላለሁ፡፡

ቴዲ ስለኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ ውበት እና ስለህዝቧ በመዘመሩ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?

በሀሳብ የለሽ ጋጠወጦች እና በጭካኔ በተሞሉት ድድብና በተጠናወታቸው ወሮበሎች መካከል ጠላት እንዴት እንደሚያፈራ ልገነዘብ እችላለሁ፡፡

ሆኖም ግን ቴዲን ለመጥላት ወይም ደግሞ ለመፍራት ጥሩ ምክንያቶች አይደሉም፡፡

ሙሉ ህይወቱ ስለፍቅር፣ መልካም ጉርብትና፣ ስለሀገር ፍቅር እና ክብር፣ ስለአህጉር ፍቅር፣ ስለታሪክ ፍቅር እና ክብር፣ ስለሀገሩ ብዝሀነት እና ስለህዝብ ፍቅር እና ክብር መርሁ እና ተሞክሮው አድርጎ የሚንቀሳቀስን ሰው እንዴት መጥላት ይቻላል?

የሰው ልጆች ፍቅር የሆነ ሐዋርያትን እንዴት መጥላት ይቻላል?
TeddyAfro_NYC-7
ፍቅርን እራሱን የሚጠሉትን ምንነት የሚገልጽ እራሱን የቻለ ቃል/ሀረግ አለ፡፡ ይህም ቃል/ሀረግ “በሰዎች መጥፎ ዕድል ላይ የሚረካ“ እየተባለ የሚጠራ ሲሆን ቃሉም የተገኘው ከጀርመን ሆኖ አንድ ሰው በተፈጥሮው በሰዎች መጥፎ ዕድል፣ ስቃይ እና መከራ እጅግ የበዛን ደስታ የሚያደርግ እኩይ ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ያለው የሚል የእንግሊዝኛ ትርጉም ያለው ሆኖ ይገኛል፡፡ በጥላቻ የተሞሉ ሰው መሳይ ሰይጣኖች ብቻ በሌሎች መከራ፣ ስቃይ እና ውርደት ሀሴትን ይጎናጸፋሉ፡፡

በሰዎች መጥፎ ዕድል ላይ የሚረካ ግብዝ ሸፍጠኛ/sadist በሌሎች ሰዎች ላይ በሚደርሰው ስቃይ፣ መከራ እና መጥፎ ዕድል እጅግ በጣም ደስተኛ እና ሀሴትን የሚያደርጉ፣ ለዚህ እኩይ ምግባርም ለእራሳቸው አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጡ ሰው መሳይ በሸንጎዎች የሆኑ ሰይጣኖች ናቸው፡፡

በእንደዚህ ያለ በሰዎች ስቃይ እና መከራ ከፍተኛ የሆነ ሀሴት ባህሪያትን በተጎናጸፉ ሰዎች ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ውስጥ ስቃይ፣ ሀዘን፣ እና የሌሎች ሰዎች መጥፎ ዕድል ማግኘት ማለት ለእነርሱ ደስታ፣ የሌሎች ስቃይ የእነርሱ ሀሴት፣ የሌሎች መከራን መቀበል ለእነርሱ ፍጹም የሆነ እርካታ ማለት ነው፡፡

በሌላ አባባል ከጥላቻ የመጨረሻ የሆነውን ደስታ ያገኛሉ፡፡ ይኸ ልዩ የሆነ ሰይጣናዊ ድርጊት ዋነኛ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አመራር እና አባላት መገለጫ ባህሪ ነው!

ለፍቅር ፍቅር ያላቸውን እና ፍቅርን እራሱን የሚጠሉ የፍቅር ጠላቶች ናቸው፡፡

ከተቃዋሚዎች ጋር ህብረት ፈጥሯል በሚል እሳቤ ነውን?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቴዲ አፍሮ ተቃዋሚዎችን ይደግፋል የሚል ውንጀላ ያሰማል፡፡ ይህ እራሱ ምን ማለት ነው?

በእርግጥ እነዚህ የጥላቻ ዕኩይ ምግባር አራጋቢዎች ቴዲ አፍሮን ፖለቲከኛ እንጅ ሙዘቀኛ አይደለም የሚል ሀሳብ ለማራመድ ይሞክራሉ፡፡

ቴዲ ፖለቲከኛ የሚሆንባት ዕለት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ከሸፍጥ ነጻ የሆነ (ለዝንጀሮው/ጦጣ ፓርላማው ከ547 መቀመጫዎች ውስጥ 547ቱንም አሸንፊያለሁ ብሎ የሚያውጅ ሳይሆን) እውነተኛ ዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት ጥበቃን እውን በሚያደርግባት ዕለት ነው፡፡

ያም የማይሆን ነገር ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ተቃዋሚ ቡድኖችን ማገዝ ወንጀል ነው በማለት በዝንጀሮው/ጦጣው የይስሙላ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ ንጹሀን ዜጎችን ያሰቃያል!

አንድ ሰው የፈለገውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመደገፍ ሕገ መንግስታዊ እና የሰብአዊ መብት ምርጫው አይደለምን?

ሆኖም ግን ቴዲ የፖለቲካ ሰው አይደለም፡፡ እርሱ የሙዚቃ ሰው ነው፡፡

በተጻራሪ መልክ አስገራሚው ነገር ደግሞ የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቴዲ ገንዘብ በመስጠት፣ በሙዚቃ ኮንሰርት በማዘጋጀት እንዲያቀነቅንላቸው፣ እነርሱ እንዲዘምርላቸው የሚፈልጉትን ሙዚቃ በመስጠት በአደባባይ እንዲዘምርላቸው እና በፖለቲካ እንዲደግፋቸው ይፈልጋሉ፡፡

የቴዲ አጭር መልስ ግን አመሰግናለሁ ሆኖም ግን ይቅርታ አላደርግም የሚል ነው፡፡

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ቴዲ እንዲያደርግለት የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ ለሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችም በተመሳሳይ መልኩ አንድም ነገር አላደረገም፡፡ ለምንድነው ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት የሚጀምረው?

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አለቆች ከተራ ሀሳብ ይልቅ የበለጠ ገንዘብ አላቸው፡፡

እንዲህ የሚለውን አባባል መዳመጥ እና መተግበር ይኖርባቸዋል፣ “ገንዘብ ፍቅር ሊገዛልኝ አይችልም፡፡“

“ገንዘብ ፍቅር ሊገዛልኝ አይችልም/ፍቅርን ሊገዛልኝ አይችልም፣ እያንዳንዱ ሰው ይህንን ነገር ይነግረኛል/ፍቅርን ሊገዛልኝ አይችልም፣ በፍጹም፣ በፍጹም፣ በፍጹም፣ በፍጹም…“

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በማንኛውም መንገድ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍቅር ወይም ደግሞ የፈለገውን ያህል ገንዘብ እንደጎርፍ ቢያወርድ የኢትዮጵያን ህዝብ ድምጽ ፍቅር ቴድን በምንም ዓይነት መልኩ አያገኝም! ሊገዛ አይችልም።

እኔ የቴዲ አፍሮ ቁጥረ 1 አድናቂ ነኝ!

ለበርካታ ዓመታት የቴዲ አፍሮ ቁጥር 1 አድናቂ ነኝ፡፡

በእርሱ ሙዚቃ ስዘምር እና ስደንስ ቆይቻለሁ፡፡ የሮጌን የሙዚቃ ምቶች እንዴት አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ ባህላዊ የሙዚቃ ቅላጼ እንደሚቀይራቸው አደንቃለሁ፡፡

በአንድ በተወሰነ ቦታ ወይም አካባቢ የሙዚቃ ኮንሰርት በሚያዘጋጅበት ጊዜ ከሁሉም ወጣቶች ህዝቦች ጋር በመቀላቀል መልካም ጊዜን አሳልፋለሁ፡፡

በተለያዩ አጋጣሚዎች ስለቴዲ አፍሮ ጽፊያለሁ፡፡

እ.ኤ.አ በ2010 በሁሚንግ ፖስት ትችት ቴዲ በአካል በሚተላለፍ ትዕይንት ባቀረበው ስራው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በመገኘት ከተመለከትኩ በኋላ እንዲህ የሚል ጽሁፍ አቅርቤ ነበር፡

ቴዲን በአካል በሚተላለፍ ስራው ላይ በመገኘት ያቀረበውን ኮንሰርት ከዚያ በፊት ያልተመለከትን እና በአዳራሹ ከአፍ እስከ ገደቡ ጢም ብሎ ሞልቶ የነበረውን የተመልካች ብዛት በማየት ምስክርነቱን ለምንሰጥ ሰዎች ሁሉ በሀሳብ አውሮፕላን ወደ ኋላ ጭው ብሎ በመብረር በትዝታ ማዕበል ውስጥ እንድንዋኝ ያደርገናል፡፡ እንደዚህ ያለ በህዝቡ እና በከያኒው መካከል ጥልቅ የሆነ ትስስር በህይወቴ የተመለከትኩት ከብዙ አስርት ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ ግንቦት 30/1978 በሜኖሶታ ዩኒቨርስቲ እየተማርኩ በነበርኩበት ቦታ ቦብ ማርሌይ በመምጣት አቅርቦት በነበረው (ካያ ቱር/Kaya Tour) እና እ.ኤ.አ ህዳር 15/1979 (ሰርቫይቫል ቱር/Survival Tour) የተሰኙትን ኮንሰርቶች ያቀረበባቸው ጊዚያት ትዝ አሉኝ፡፡ በእነዚያ ቦብ ማርሌይ ባቀረባቸው ኮንሰርቶች ላይ የመገኘት አጋጣሚ ዕድሉን ያገኛችሁ በእርግጠኝነት ምን ለማለት እንደፈለግሁ በትክክል ትገነዘባላችሁ የሚል እምነት አለኝ፡፡

እ.ኤ.አ ሰኔ 2014 ኮካኮላ የተባለው ድርጅት ቴዲ አፍሮን የማግለል ድርጊት ፈጽሞ ስለነበር ማንም ቢሆን ይህን ለውፍረት የሚዳርገውን እና በስኳር የተሞላውን ኮካኮላ የሚባለውን እርባናየለሽ መጠጥ ባለበት ድርሽ እንዳትሉ የሚል ትችት አቅርቤ ነበር፡፡

ኮካኮላ የተባለው ድርጅት ለ2014 በብራዚል ተደርጎ በነበረው የዓለም እግር ኳስ ጨዋታ ሻምፒዮን 32 የአካባቢ ድምጻውያን ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ እና እንዲወዳደሩ ጋብዞ ነበር፡፡

ኮካኮላ ይፋ በሆነ መልኩ ከቴዲ አፍሮ በስተቀር የሁሉንም ተወዳዳሪዎች ስራዎች ለቅቆ ነበር፡፡ በእርግጥ ኮካኮላ በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አለቆች ትዕዛዝ መሰረት የቴዲ አፍሮን ስራ ውድቅ እንዲያደርግ ትዕዛዝ ተሰጥቶት ነበር፡፡

ይህ ድርጊት ሁይትነይ እንደዘመረው ሁሉ ትክክል አይደለም ሆኖም ግን እሽ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ እንደምታ አለው፡፡

(በዚያ እኩይ ድርጊቱ እስከ አሁንም ድረስ የኮካኮላ ምርት ውጤት የሆኑት ባሉበት ቦታ ድርሽ አልልም! ከዚህ አንጻር የኮካኮላ ምርትን ከምጠቀም ይልቅ የምጠጣው አጥቼ በውኃ ጥም ድርቅ ማለትን እመርጣለሁ፡፡ ይህ ለእኔ ሌላ ለምንም ነገር ሳይሆን ቀላል የመርህ ጉዳይ ነው፡፡ እንደዚህ ያለ ምርመራን እና አድልኦን የሚፈጽም ዓለም አቀፋዊ የንግድ ድርጅትን ልደግፍ የምችልበት ሞራሉ የለኝም፡፡ በዚያን ጊዜ ባቀረብኩት ትችቴ ላይ “ኮካኮላ ገሀነም ይግባ” በማለት ተናግሬ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኮካ ኮላ ገሀነም እንደደረሰ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡)

ቴዲ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ብዙም የሙዚቃ ኮንሰርት አያቀርብም፣ ሆኖም ግን በዓለም እንደ የአፍሪካ የሬጌው ንጉስ እየተባለ ሲወደስ እንደነበረው እንደ ቦምብ ማርሌይ በፍቅር መንፈስ የህዝብን ልብ ያስተሳሰረ ከያኒ መሆኑ ይነገርለታል፡፡ እንግዲህ ቴዲ አፍሮ በሙዚቃ ጥበቡ፣ በፍቅር ዘማሪነቱ እና በአጠቃላይ የዘርፉ ልቅናው የዚህን ያህል ክብር እና ሞገስ ያለው ከያኒ ነው፡፡

(“ሬጌ” የሚለው ቃል ከላቲን “ሬጊ” ከሚለው እና ንጉስ የሚል ትርጉም ካለው ቃል የመጣ ስለመሆኑ ስንቶቻችን እንደምናውቅ ብገነዘብ የሚገርመኝ ይሆናል፡፡ የሬጌ ሙዚቃ “የንጉስ ሙዚቃ” ነው፡፡)

እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ እያለ የሚጠራው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደናቁርት ቴዲ የንጉሱን ሙዚቃ በማቀንቀኑ እና በሙዚቃ ሰራ ቅላጼዎቹ የዳግማዊ አጼ ምኒልክን እና የቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴን ስም እያነሳ በማወደሱ ምክንያት ወንጀል ተደርጎ በይስሙላው የዝንጀሮ/ጦጣው ፍርድ ቤት አንዳያንገላታው ተስፋ አረጋለሁ፡፡ (ሬጌ ሙዚቃ “የንጉስ ሙዚቃ” ነው ለጃማይካ ራስ ተፈሪያውያን፡፡)

እኔ ቴዲ አፍሮን የማውቀው በሰራቸው ቪዲዮ፣ በሚያዘጋጃቸው የሙዚቃ ኮንሰርቶች፣ በድረ ገጽ የግንኙነት መስመር በሚሰጣቸው ቃለ መጠይቆች እና ከሁሉም በላይ ደግሞ በሚያስተላልፋቸው የፍቅር፣ የመግባባት፣ የይቅርታ አድራጊነት እና ዕርቀ ሰላም ናፋቂነት ነው፡፡

ለዚህም ነው አንግዲህ የእርሱ ቁጥር 1 አድናቂው ለመሆን የበቃሁት፡፡

በእኔ የግል የግምገማ መስፈርት መሰረት ቴዲ አፍሮ እንደሙዚቃ ባለሞያነቱ ከፖፕ ሰታር (pop star) በላይ የመጠቀ እና የላቀ ድምጻዊ ከያኒ ነው፡፡ በእኔ አመለካከት ለዶ/ር ኪንግ፣ ለማንዴላ እና ለማህተመ ጋንዲ እሴቶች እና መርሆዎች ተግባራዊነት የቆመ የሙዚቃ ሐዋርያ ነው፡፡

ቴዲ ከፍተኛ የሆነ ክብር፣ ምስጋና እና አድናቆት ያለው ከያኒ ነው፡፡ በእርግጠኝነት ቴዲ ከእርሱ ትውልድ የተስፋ፣ የእምነት፣ የብሩህ አመለካከት እና የጽናት ተምሳሌት ቀንዲል ነው፡፡

(ለእኔ እውን ሆኖ የሚታይ ጉዳይ ነው!!! ቴዲ አፍሮ ከእርሱ የተስፋ፣ እምነት፣ የብሩህ አመለካከት እና የጽናት ተምሳሌት ቀንዲል ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት በወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ መሰቃየት ሊኖርበት ይችላልን?)

በቅርቡ ኢትዮጵያዊው ገጣሚ ሄኖክ የሽጥላ ስለቴዲ ክብር በአማርኛ ጥቂት የግጥም ስንኞችን ቋጥሮ ነበር፡፡

እርሱ የቋጠራቸው ሶስት የስንኝ ግጥሞች ወደ እንግሊዝኛ እንዲመለሱ በማድረግ ያቀረብኩ ሲሆን እንደገና የአማርኛ ትርጉማቸው በግጥም ስንኝ መልክ እንዲመለሱ በማድረግ ሁሉንም መተርጎም እችል ነበር፣ ሆኖም ግን የግጥሙ አንኳር የሆኑት ሶስቱ ስንኞች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡

ቴዲ እንደ ዳዊትዘይት በቀንድ ዋንጫ
ቀብቶታል አምላክ ፣ ለብርሃን መውጫ !

ነፃነት ለሀገሬ ደግሞ አንዲህ ይለዋል:

ቴዲ እንደ ንጉስ ዳዊት ለብሶ ካባ፤
ከቀንዱ ቅዱሱን ቅባት የተቀባ፣
ጨለማን ሊያስወግድ የመጣ ያምላክ መባ፡፡

ለቴዲ አፍሮ ሰላማዊት አበባየሁ የፃፈችዉን ተደናቂ ግጥም ለመስማት እዚህ ይጫኑ።

አሜን!

ሰይጣኖች እባካችሁን ቴዲን ለቀቅ አድርጉት! አባካችሁ ተዉት ስራዉን ይስራበት !!!

ታላቁ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉስ ጥላሁን ገሠሠ አንደዚህ ብል ዘፍኖ ነበር “እረ ተዉኝ ባትነኩኝ ምናለበት” ሙዚቃዉን ለመስማት እዝህ ይጫኑ

(ይህን የጥላሁንን ሙዚቃ ለቴዲ በክብርና በወንድምነት አቀርብለታለሁ።)

እረ ተዉኝ ባትነኩኝ ምናለበት
አባካችሁ ሰዎች ስራዬን ልስራበት።

የሰው ሃሳብ አመረረ በተንኮል እየከረረ
ሰው ካልኖረ ስራ ሰርቶ
ባለው አቅሙ ዘር አምረቶ
በችሎታው በያለበት
ሰርቶ ቢኖር ምናለበት
ነገር ሲጭር ስራ አይሰራም
ሌላዉንም አያሰራም።

እረ ተዉኝ ባትነኩኝ ምናለበት
አባካችሁ ሰዎች ስራዬን ልስራበት ።

አምሮ በነገር ሰግዶ
በወሬ ከሆነ ኑሮ
ምን ሊሆን ነው ምን ሊጠቅም
በስራ ካልሆነ ጥቅም
ባቅሜ ሰርቼ ስራ
ለሀገር ጥቅም ላፈራ
ነው አንጂ የባከንኩኝ
ምን አለበት ባትነኩኝ።

እረ ተዉኝ ባትነኩኝ ምናለበት
አባካችሁ ሰዎች ስራዬን ልስራበት።

የተንኮል ምንጩ ይደፈን
ስራ ሰርተን መኖር አርፈን
ይሻለናል ስራ ስሩ
ምን ይገኛል ካፈሩ
ፍቅር ሰላም ከኛ ጋራ
አስወጥተው ባላጋራ
አንደየአቅማችን ሰርተን
መኖሩ ነው የሚበጀን።

እረ ተዉኝ ባትነኩኝ ምናለበት
አባካችሁ ሰዎች ስራዬን ልስራበት።

የሕግ የበላይነትን ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ማስተማር እና መስበክ ማለት ለአሕዛብ መጽሐፍ ቅዱስን ማሰትማር መሞከር አንደማለት ነው። አለዝያም በጥቁሩ ባልጩት ድንጋይ ላይ ውኃ እንደማፍሰስ ነው፡፡

አሁን ደግሞ ስለፍቅር፣ ስለይቅርታ አድራጊነት እና ስለዕርቀ ሰላም ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ማስተማር እና መስበክ ማለት ለጀርመን ብሄራዊ የሰራተኞች ሶሻሊስት ፓርቲ (ናዚዎች) አባላት ስለፍቅር፣ ስለይቅርታ አድራጊነት እና ስለዕርቀ ሰላም ማስተማር እና መስበክ እንደማለት ነው፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እንዲያዳምጠኝ ጥያቄ ማቅረቤ አይደለም፡፡ ለዚህማ የሚያዳምጡበት ልቦና የላቸውም እንጅ ሁልጊዜ በየሳምንቱ ትምህርት እያቀረብሁ አይደለምን?

teddyለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጥያቄ የማቀርብላቸው ግን የቴዲ አፍሮን ሙዚቃ በጥሞና እንዲያዳምጡ ነው፡፡ በእውነት የእርሱን እውነተኛ ሙዚቃ፣ መሳጭ የሆኑ የግጥም ስንኞቹን እና መንፈስን የሚያድሰውን የድምጹን ቅላጼ ብያዳምጡ የመቀራረብን እና የፍቅር ስሜትን በተላበሱ ነበር፡፡

ከቴዲ ሙዚቃ በሚወጣው ፍቅር፣ እያንዳንዱ ቃሉ በክፋት የተሞላውን የግፈኞች አዕምሮ ወደ ስምምነት እና ፍቅር በመለወጥ፣ የእርሱ የሙዚቃ ምት የእነርሱን የልብ ምት በመምታት በፍቅር እንዲሸነፉ እና እጃቸውን እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡

የእንግሊዝ የተውኔት ጸሐፊ እና ገጣሚ የነበሩት ዊሊያም ኮንግሬቭ እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “ሙዚቃ ጨካኙን አውሬ ሩህሩህ የማድረግ፣ ጠንካራ አለቶችን የማለስለስ ወይም ደግሞ የተቋጠረ ጠንካራ የዋርካ ዛፍ ግንድን እንዲለነበጥ የማድረግ ኃይል አለው፡፡“

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የቴዲ አፍሮን ሙዚቃ የሚያዳምጡ ከሆነ ሩህሩህ መንፈስን እንደሚላበሱ፣ የተዘጉ ልቦቻቸው ለስላሳ እንደሚሆኑ፣ አውሬያዊው ኋላቀር መንፈሳቸው የተረጋጋ እንደሚሆን እና የተቋጠሩት ልቦቻቸው ሊፈቱ እንደሚችሉ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የቴዲን ጣፋጭ የሙዚቃ ምግቦች በመመገብ እና በመሳተፍ ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ፣ መንፈስ ይቀርባችኋል ከእኛ ጋር ሁኑ፡፡

በፖለቲካ፣ በሕግ ወይም ደግሞ በሰብአዊ መብት ጥበቃ ቋንቋ ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጋር ለመነጋገር የሚታሰብ ነገር አይደለም፡፡

ሆኖም ግን ሙዚቃ የዓለም ህዝብ የመግባቢያ ቋንቋ ነው የሚለው እውነት ከሆነ በመጨረሻው ሰዓት በቴዲ አፍሮ ሙዚቃ አማካይነት ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጋር መነጋገር እንችላለን ማለት ነው፡፡

በቴዴ ያስተሰርያል በሚለው ፈዋሽ ድምጹ መሰረት ከወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ጋር መነጋገር እችላለሁ ብዬ አስባለሁ!

የወያኔ ወንድሞች! የቴዲን የፍቅር ሙዚቃዎች ለማዳመጥ ሞክሩ፣ በእርግጠኝነት አዳምጡ!

ከጥላቻችሁ በስተቀር የምታጡት ምንም ነገር የለም!

ሙዚቃ የፍቅር ምግብ ከሆነ ቴዲ እባክህን ዘምር፡፡ ደግመህ ደጋግመህ ተጫወት፣ ዘምር፡፡

“ፍቅር ሁሉንም ያሸንፋል፡፡“ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

አሜን!

ቴዲ፣ እንወድሀለን፡፡ እናከብርሀለን፡፡ እናደንቅሀለን!!!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ጳጉሜ 2 ቀን 2007 ዓ.ም


የአርበኛው ኑዛዜ፣ ከፍል 1 ለቅምሻ –መልኬ መንግስቴ

0
0

ይህን ለሚመለከተው ሁሉ የአክብሮት ሰላመታየን አቀርባለሁ|

ለረጅም ጊዜ ማስታወሻ ስይዝ ቆይቸ የደረስኩት መጽሀፍ ወደማጠናቀቅ ስለደረሰኩ አምላክ ፈቃዱ ከሆነ በቅርብ ጊዜ ለሕዝብ ለማበርከት በዝግጅት ላይ ነኝ፣ይህን ለቅምሻ የአቀረብኩት እንደመንደርደሪያ ሁኖ ዝርዝር ሁኔታውን በመጽሐፋ ውስጥ ሰለተጠቃለለ መጽሀፋን እንዲመለከቱልን በአክብሮት እጋብዛለሁ፣ ስደት.ወደ ሱዳን፤
በደርግ ዘመነ መንግሰት በነበረው ስርዓት ተጠቃሚ አልነበርኩም እንደሌላው ኢትዮጵያዊ በደሉ እኔንም ደቁሶኝ አልፎአል፣በዚያ ዘመን በፀረ መንግስት ተከስሼ ታስሬ ነበር  በእስር ሁነው የመሞቻቸውን ጊዜ ከሚጠባበቁት ሙታን አንዱ ነበርኩ፣በራሴ ላይ ወስኝ በዓምላክ ፈቃድ ከእስር አምልጨ ወደበርሀ ገባሁ‹ ከወህኔ ለማምለጥ የነበረው ፈተና ከሞት ጋር የሚደረግ ትንቅንቅ ስለነበር ከስር ከአመለጥኩ በኋላ በዘመኑ የነበሩት የአካባቢ ምልሻወች አመለጠ ያዙት ወይም ግደሉት ሹመት ይጠብቃችሁአል የሚለው ትእዛዝ በሹመት ፈላጊና ከሞት ለማምለጥ የነበረው ፍጥጫና ግብ ግብ በመላ ከባድ ፈተና ነበር/ከእስር አምልጨ በርሀ ከሚታገሉ አማጽያን ጋር ተቀላቀልኩ ከተወሰነ ውጣ ውረድ በኋላ ሱዳን በስደት ቆየሁ በምህረት ወደአገሬ ተመለሼ ዛሬ በስልጣን ያለው መንግሰት እስከመጣ ድረስ ከአገሬ በሰላም እኖር ነበር፤

የደብረታቦር መያዝ ድጋሜ ከአሰርቤት ማምለጥ ስደት ወደኬንያ፣

የህዋት አማጽያን የትግራይን ምድር በመላ ከተቆጣተሩ በኋላ ቀጥለው የተቆጣጠሩት ደቡብ ጎንደር ደብረታቦር ነው እኔ ደብረታቦር ከተማን ሲቆጣጠሩ ከቤቴ ነበርኩ  ለውጥ እንዲመጣ የደርግን መንግስት ከተቃወሙት አንዱ ዜጋ ነበርኩ ማለት እችላለሁ.የደርግ መንግስት ወድቆ እታሰራለሁ እሰደዳለሁ የሚል ግምት አልነበረኝም ያሰብኩት ሣይሆን ቀርቶ ያልጠበኩት ተከሰተ፣የስደትን መከራንና ውጣ ውረድ ስለማውቀው ድጋሜ ከስደት ላይ ላለመውደቅ ቤተሰቦቸንም ከችግር ላይ ላለመጣል ሁሉንም ነገር ዓሜን ብየ ተቀብየው ነበር በሰላም ለመኖር ያላደረኩት ጥረትና ሙከራ አልነበረም፣የሀገርንና የወገንን በደል ማየትና መሼክም አልቀበልም በማለት ሲያስቸግረኝ የኖረው ህሊናየ ክብደቱና ጫናው ስለበዛብኝ ወደኬንያ ለስደት በቃሁ፣ቤቴና ንበረቴ በመላ ተወረሰ ወንድሞቸ አለቁ/ኬንያ አዲስ ትግል ለመጀመር ከደቡብ ኢትዮጵያ የተሰደደው ወታደር ከብላቴን ማሰልጠኛ የተሰደደው የዮንበርስቲ ተማሪዎች ጭምር እጅግ በርካታ ሠራዊት ነበር የደርግ ባለስልጣኖች ነበሩ ለትግል ማሰባሰብ ቀርቶ እነሱም ሼሸጉኝ ብለዋል፣አንድ የሲብል ባለስልጣን ስማቸውን ከመጥቀስ ተቆጥቤ ወደዝንባቦይ ህደው ፐሬዘዳንቱን አነጋግሬ መጣሁ ከኢትዮጵያ ምድር ገብታችሁ ከአንድ ቦታ ሁናችሁ ጥሩኝ መጥቸ ከናተ ጋር እዋጋሁ ብለዋል የሚለው የትግል ጥሪ ብቅ ስላለ ብዙ ሰወችን ማሰባሰብ ተሞክሮ  ነበር በዚህ ሄደት ላይ እንዳለ ድምጥ በለለው መሳሪያ ብዙ ሰወች መገደላቸው ነገሩን ውስብስብ እያደረገው መጣ፤ለመደራጀት የተመረጠው ቦታ ካኩማ የስደተኛ ካነፐ ነበር ይህ ስፍራ ለኢትዮጵያ ደንበር ቅርብ ነበር፣ጋንቤላጉዞ፣በቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ 75 ወታደሮች ተዘጋጅተው በጎምጎፋ አቋርጠው ጋንቤላ ገቡ ኮሎኔል ጋራንግ በፊት ፈቅደው ነበር በኋላ ግን በ24 ስዓት ካልወጣችሁ እርምጃ ውሰዱባቸው በማለት ትእዛዛ አስተላለፋ ተባለ አንድ የኑየር ተወላጅ ጀኔናር በአደረገው እርዳታ በሰላም ተመለሱ/በዚህ እንቅስቃሴ ላይ እንዳለን እኔም ተመታሁ ገደለነ ብለው ጥለውኝ ህደዋል ቤተሰቦቸና ፓሊስ አንስቶ ኮፐቲክ ወደተባለው ሆስፐታል ወስደው አስተኝተውኛል በሁለተኛው ቀን ስነቃ ከእጀ ላይ ግሊኮዝ አለ ልጆቸና ባለቤቴ ያለቅሣሉ ሰውነቴን ማንቀሣቀስ ስሞክር እንቢ ሲለኝ መመታቴን አወኩ ወደከፍተኛ ሆስፔታል ተላኩ ኩኩዮ ሆስፐታል ይባላል የተሰበረው እግሬ በጀሶ ታሰሮ ከ3ወር በኋላ ተመለስ  ተብየ የምራመድበት2 ክራንች ተቀብየ ተመለስኩ;ኬንያ ገንዘብ ነው ህግ ለአንተ ከለላ አይሆንም 3ወር ቆይቸ ቁስሉን ለማስፈታት ስህድ አሁንም ለ3ወር መታሼግ አለበት ተብሎ ድጋሜ ታሸጎ ተመለስኩ አቤቱታ ለማቅረብ ወደ u.n.h.c.R፣ቢሮ ህድነ ቀደም ሲል የኔን ጉዳይ ያውቁት ስለነበር አድራሻኅ ጠፍቶነ ነበር ቦታ ተዘጋጅቶልህል ተባልኩ ከከተማ ወጣ ያለ ስፍራ  ከነቤተሰቦቸ ከአንድ ሆቴል ቤት አስቀመጡን ከዚህ ግቢ እንዳትወጣ ተባልኩ፣ትንሸ ወራት እንደቆየን3ኛ አገር ተገኝቶልሀልዴንማርክ ፈቃደኛ ከሆንክ ተዘጋጅ ተባልኩ  በክራንች ተደግፊ ከአይሮፓላን ተሣፈርኩ፣ወዲያው እንደደረስኩ ወደሀኪም ቤት ተወሰድኩ መዳህኔት ተሰቶኝ ተመለስኩ ከትንሸ ወራት ቆይቸ በራጅ አይተው ስብራቱ መዳኑን ሀኪሙ አረጋገጠልኝ፣በእጀ የነበረውን ምርኩዝ ትቸ መራምድ ቻልኩ የሚቀጥለው እርምጃ ምን ይሆን,

እረፍት ያጣው ህሊናየ ግን መዳህኔት አልተገኜለትም/

ተከፍሎ.ያላለቀ.እዳ፤ጉዞ.ወደ.ኤርትራ

በምንም.ተአምር ኤርትራ ምድር ህጀ እታገላለሁ ብየ አስቤም አላውቅ በወያኔና በሻቢያ መካከል ስድብና የጀግንነት ፍክክር ከመጨረሻ ጠርዝ ደርሶ ነበር እኔ ከምኖርበት አገር ዴንማርክ ድሮ በደርግ ዘመን ሻቢያንና ወያኔን ሲቃወም በራዲዎ አዳምጠው የነበረ ሰው እኔ ካለሁበት አገር መኖሩን ሰማሁ በአካል አላውቀውም  በአካል ተገናኜን ምን እናድርግ በሚለው ላይ ተስማምተን ተለያየን;በዚህ ዘመን ሻቢያም ተቃዋሚዋችን ሲፈላልጉ ንሮ ሱይድን የምትኖር የሻቢያ አንባሳደር ጋር በአካል ተገናኝተን ተነጋገርን በእለቱ ወስነን ትኬት ተገዝቶልን ጉዞ ወደአስመራ በረርን፤አስመራ ደረሰነ በክብር ተቀበሉን vip ማለት ነው፣አስመራ ከተማ3 ቀን ከቆየሁ በኋላ አብረን ከህድንው ጓደኛየ ጋር በጋራ ትግል መቀጠል አልቻልነም፣

ተለያየን ማለት ነው ከኮሎኔል ታደሰ ጋር ከዚያ በፊት አንተዋወቅም እንድንገናኝ ያደረጉት እነሱ ናቸው መኪና ተመደበልን ወደተከዜ ተጉዘን ተሰኔ ገብተን አደርን/ከምዕራብ ስሜን የጦር አዛዥ ከጀኔናር ተክሌ ጋር ተገናኜን በበነጋው ኩሎኔል ፍጹም ወዳለበት አሪና ተጉዘን በምሼት ገባን ኮሎኔል ፍጹም ተቀበለን ትንሸ እንደቆየን በመኪና  እያዞረ ገለጣ አደረገልን እነማን እንዳሉ ሁሉንም ማግኜት እንደምችል ተነግሮኝ ወደሱ ማደሪያ ቤት ተመለስነ በጣም ከመሼ በኁላ ተስፋየ ጌታቸው መጣ እኔ ከተኞሁበት ነበር የመጣው ሰላም አለኝ ተሰፋየ ነኝ ከምኝታየ ተንስቸ ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋወጥን ከተስፋየ ጋር ናይሮቢ ኬንያ እንተዋወቃለን ሱዳን መህዱን አውቃለሁ አስመራ መምጣቱን አላውቅም የድሮ ትውውቃችን በኔና በሱ ብቻ እንዲጠበቅ አድርገን ተለያየን በ92 ዓ.ም አስመራ ስንገባ ከአሜሪካና ከአውሮፓ የመጀመሪያወች ነበርን ማለት እችላለሁ ከኛ በፊት ከሱዳን አስመራ ገብተው መደራጅት የጀመሩ ነበሩ;ሁሉንም ማግኜት እንደምፈልግ ተነጋግረን እራት አብረን እንድንበላ ኮሎኔል ፍጹም ፈቀደ.ሁለት ፍየል አስገዝቸ እራት አብረን በላን ሁሉም በአሉበት የራሴን ድርጅት ልመስርት ወይስ አብረን እንታገል የሚለውን ሀሣብ አነሣሁ፣በሁሉም ማለት ይቻላል አብረን በውህደት እንታገል የሚለው ሀሣብ ዳብሮ ለኮሎኔል ፍጹም ቀርበ እናንተ ብቻ ሣትሆኑ ሌሎችም የጎሣ ድርጅቶች ይጠሩና ተመካከሩ ይህ እንዲሆን የኤርትራ መንግስት ይፈልጋል ይህንን ለማቀራረብ እየሰራን ነው በሚል የሀሣብ ስምምነት አደረግን የወረሞ ግንባር የሲዳማ ግንባር የሱማሌ ግንባር በያሉበት ተጠርተው መጡ ሚያአዝያ 10-11-12-92 ዓ.ም ለ3ቀን ጉባየ ተከሀዳ ይህ ጉባኤ ለኔ የሚጎፈንን ነበር ኢትዮጵያዊነቴን የገለጽኩበት የሀገሬን ውርደትና ስድብ ፊት ለፊት የሰማሁበት ነበር ስብሰባውን አቋርጨ ወጣሁ በምሣ ስአት አቶ የማነ መቶ ከኔ በጣገብ ተቀመጠ ምሣ አብረን በላን የሀሣብ ልውውጥ አደረግነ ተስማምተዋል በትግስት ከስብሰባው ግባ ተባልኩ ገባሁ ቀደም የነበረው ሀሳብ ተለውጦ ሁላችንም ቀዝቀዝ ብለን ጀመርነው እየጎመዘዘኝም ቢሆን ከ3ቀን በኁላ ከስምምነት ደርሰን ተፈራረምን.1ኛ በአማርኛ 2ኛ በትግርኛ 3ኛ በወሮሞ ኛ 4ኛ በአረብኛ 5ኛ በእንግሊዝኛ ተጽፎ ተፈራርምን ደብዳቤው እንዲበተን በየድርጅቱ ተወካዮች ደብዳቤ ይዘው እንዲህዱ ሲወሰን እኔ በተስፋየ ጌታቸው የተፈረመ የውክልና ደብዳቤ ተሰቶኝ ወደአውሮፓ ተመለሰኩ፤በአውሮፓና ወደ አሜሪካ አድራሻ እየጠየኩ የተሰጠኝን ደብዳቤ በተንኩ እኔ የተሰጠኝ ግዳጅ ነበር ወደአፍረካ ተጓዝኩ  ውጋንዳ ነበር የህድኩት ውጋንዳ በዘመኑ ቁልፍ ሰው ተብለው ከተመረጡት አንድ ሰው የዛሬው ዶክተር በዚያንጊዜ አቶ ካሣ ከበደ ነበሩ፣ውጋንዳ መኖራቸውን አስመራ ስለተነገረኝ በአካል ተገናኜኋቸው ከዚያ በፊት አላውቃቸውም ለመጀመሪያ ስንገናኝ አብሮኝ የነበረው የድሮ ኮሎኔል ከአስመራ መምጣቴን ነገራቸው ስሜን ጠየቁኝ አንተነህ በአስመራ እራዲዎ ቃለ ምልልሰ የሠጠህው አዳምጨሀለሁ በኛ መንግስት ጊዜ በምንስልጣን ነበርክ አላውቅህም አሉኝ እኔማ አባራችሁኝ በስደት ሱዳን ነበርኩ ይገርማል አነተ ነህ በርታ የሚል ሞራል ለገሱኝ ነገሩን ለሰስ ባለ አቀራረብ አነሣሁላቸው እኔ አሰመራማ አልህድም ከተቻለ ሀሣቡን አልቃዎምም የሚል መልካም ሀሣብ አገኜሁ ከአስመራ ይዤው የመጣሁት ስጋት እንደሰጋነው አይደለም፤ከ5ቀን ቆይታ በኃላ ወደ አውሮፓ ስመለስ ካናዳ የሚታተም ሀዋርያ የሚባል ጋዜጣና INDAN 0CEAN NEWS LETTER) የተባለ ጋዜጣ ዘግበውት አነበብኩ ማን እንዳስተላለፈው አላውቅም በዚሁ ዘመን ለፕሮፊሰር ጥላሁን ይልማ ስልክ አፈላልጌ አነጋገርኳቸው እኔ ለምትጠራኝ ጉባኤ የምመጣው የዓሉላ አባነጋን ሀውልት ለመስራት መቶ ሸኅ ብር እዤ እመጣለሁ ፐሬዘዳታችሁን አስፈቅደህ ጠይቀኝ የሚል ነበር ሀሣቡን ለተስፋየ ጌታቸው አወያየሁት ለሚመለከተው አቀረበው አንድ የኤርትራ ደህንነት ኮሎኔል ተመድቦ ጉዳዮን ይከታተል ነበር ደብዳቤ ይጻፋ ተባለ 3ገጽ ወረቀት በእንግሊዝኛ የተጻፈ ስጣቸው ብለው ላኩልኝ በፓስታ አሸጌ አደረሰኩ የተወከለው ኮሎኔል ወረቀቱ አልተመቸውም ቅሬታውን ገለፀልኝ፣ደብዳቤ ከላኩላቸው ሰወች አንድ ከሆላንድ አንድ ከእንግሊዝ ፈቃደኛ ሁነው ተነሱ አንዱ ቪዛ ሲከለከል አንዱ በቦታው ተገኙቶ Eppf የሚለውንም ስም  ያወጣው ይህዉ ኢትዮጵያዊ ዶክተር ነው፣ዛሬም እንግሊዝ አገር በህይወት አለ፣

አርበኞች ግንባር ከተመሰረተ በላ በውጭ አገር የማስተዋወቁ ፈተና፣

ለኢትዮጵያ ነፃነት ሻቢያ ይበጀናል ብሎ ወደሕዝብ እዞ ለመቅረብ የሚያስፈራበት ወቅት ነበር curent affirs) የተባለው.የሕዝብ መወያየ መድረክ ብዙ ሕዝብ አልነበረም በመጀመሪያ ጊዜ ከሁለት ወጣቶች ጋር ተነጋግረን፣ወደመድረክ እንዲወጣ አስተዋጽዎ አድርገናል፣

1ኛ ኖቫ የተባለ ወጣት ፣

2ኛ እንደልቡ የተባለ ወጣት፣

እነዚህ 2 ወጣቶች ለምን ለሕዝብ በግለጽ ወተው አይናገሩም አሉኝ በአሁኑ ስአት አስመራ ጦር አለኝ ለማት ቀርቶ ከእነሱ ጋር መነጋገር ወንጀል ነው በተባለበት ስአት አይቻልም ነበር የሚል የኔ ሀሣብ፣ሁለቱ ወጣቶች ግን አደፋፍረው በቅዳሜ ቀን ለሕዝብ ማስታወቂያ ጠርተው ቤቱን እነሱ እየመሩ ጃናሞራ የተባለውን ዘፈን እያጫወቱ በክብር አስተናገዱኝ ትልቁ ችግር ምንድነው ለሚለው ጥያቄ የመኪና ችግር አለባቸው ነበር የኔ መልስ ተመካክረን ችግሩን እንፈታለን በሚል ተለያየን፣በሌላ ጊዜ በገቡት ቃል መሰረት ሰው መርጠው ገንዘብ አዋተው ሰው ልከዋል፣ለዚህም ግንባር curent affairs) ባለውለታ ነበር ማለት ያስደፍራል፣ያ ሁሉ ድካም ተዘንግቶ በተፈጠረው የሀሣብ ልዮነት ጥሩ ተሣዳቢና ጥሩ አሰዳቤ አዘጋጅቶ በቦታው ያልነበሩትን ሰወች ሰማን በሚል ቱማታ ከሀቅ ውጭ የሚደረገው ዘመቻ አስተማሪነት የለውም፣ለሀገርም ለትውልድም አይጠቅምም ስድብ በሀሣብ የመቸነፍ ምንገድ ነው፣እኔ የተቃወምኩት የመታገያውን ሜዳ ነው፣ሀሣቤም እውነት ነው ለሀገሬ የማይበጀውን ሁሉ አቅሜ  እስከፈቀደ ድረስ እገፋበታለሁ፣ለትውልድና ለሀገር በሚጠቅም ደረጃ ጊዜን ገንዘብን እውቀትን ጀግንነትን እናበርክት፣የሚለውን ምክሬን ከአክብሮት ጋር እለግሣለሁ  የተከበራችሁ አንባብያን እነዚህን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ምሁራን ለጉባየ የጋበዝነው በስብሰባው ይገኛሉ በሚል ታሣቢ አይደለም ትግሉን ወደሕዝብ ለማውረድ በሚደረግበት ወቅት የሚሰጡት አስተዋጽዎ አዲስ እንዳይሆንባቸው የሚለውን በማገናዘብ ነው፣በሁለት ወር ተገናኝተን በመለስተኛ ፐሮግራም በጋራ ለመታግል የተያዘው ቀጠሮ ሣይደርስ ትልቁ የባድሜ ጦርነት ፈነዳ የተለያየ ምክንያት ከመስጠት የዘለለ የጎሣ ድርጅቶችን ማሰባስብ አልተቻለም፣ከ6ወር ቆይታ በኁላ ጥቅምት 7ቀን 93 ዓ.ም ቀደም ሲል በተነጋገርነው መሰረት አራቱ ድርጅቶቸ አርበኞች ግንባርን መሠረቱ፣ለትግሉ መሰናክል ማነው የሚለው እንዳለ ሁኖ ለአርበኞች ግንባር መመስረት ትልቁን ሚና የተጫወተው ከሎኔል ፍፁም ነው፤እሱ ባያግዘኝ ንሮ የኔም ተልኮ በቀላሉ ባልተሣካም ነበር፣ይህን ቭዲዎ ይመልከቱ፣

በምዕራፍ 2 እንገናኝ ቸር እንሰንብት ይቀጥላል

መልኬ መንግስቴ ነኝ

 

 

 

የሕወሓት መንግስት የታጠቁ ኃይሎቹን እና ካድሬዎቹን በማሰማራት በአርማጭሆ ሕዝብ ላይ ሰቆቃ እየፈጸመበት እንደሚገኝ ተዘገበ

0
0

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው የህወሓት አገዛዝ የታጠቁ ኃይሎቹን፣ ደህንነቶቹንና ካድሬዎቹን በማሰማራት በላይ አርማጭሆ ህዝብ ላይ እንደዘመተበትና ሰቆቃ እየፈፀመበት እንደሚገኝ ታወቀ፡፡

news
የህወሓት አገዛዝ በታጠቁ ቡድኖቹ፣ በደህንነቶቹና በካድሬዎቹ ቁም ስቅሉን እያሳየው የሚገኘው በላይ አርማጭሆ ማሂን አቦ፣ ዳዚሆን፣ ገንበራ-አንገረባ፣ ሌዳሆ ማርያም፣ ኩርቢና በሌሎችም በርካታ መንደሮች የሚኖረውን በድህነት የሚማቅቀውን የገበሬ ህዝብ ነው፡፡
የህወሓት አገዛዝ የታጠቁ ኃይሎች፣ ደህንነቶችና ካድሬዎች በጉልበት አልገዛ ያላችውን የአርማጭሆ ህዝብ ‘የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮችን ትቀልባላችሁ’ እና ‘መረጃ ትሰጣላችሁ’ በማለት እየወቀሷቸውና እየከሰሷቸው ሲሆን በተጨማሪም አርበኞች ግንቦት ሰባትን በአካል የተቀላቀሉ ልጆቻቸውን ከበርሃ ካላስመለሱ በእነሱ ላይ ከመቸውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ እርምጃ እንደሚወስድባቸው የአርማጭሆን ነዋሪዎች እያስፈራሯቸው ይገኛሉ፡፡
የህወሓት አገዛዝ የታጠቁ ኃይሎች የአርማጭሆን ገበሬ የሚያረባቸውን ከብቶች፣ በጎችና ፍየሎች በጥይት እየጨፈጨፉ የበቀል እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡
ህዝቡ ደግሞ በበኩሉ በተቃራኒው ምሬቱ አንገቱ ድረስ ደርሶ የበለጠ ዘረኛውን የህወሓት ቡድን ተፋልሞ ነፃነቱን ለመጎናፀፍ ቆርጦ መነሳቱንና እየተዘጋጀ መሆኑን የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች በላኩልት መረጃ አስታውቀዋል፡፡

የሪሳላ ኢንተርናሽናል የሰሜን አሜሪካ ጉዞ በሚኒሶታ፣ አትላንታ፣ ሲያትል እና ዋሽንግተን ዲሲ (ሁላችሁም ተጋብዛችኋል)

0
0

የሪሳላ ኢንተርናሽናል የሰሜን አሜሪካ ጉዞ በሚኒሶታ፣ አትላንታ፣ ሲያትል እና ዋሽንግተን ዲሲ (ሁላችሁም ተጋብዛችኋል)

11995627_412883195574008_1746198809_n

Health: የጨጓራ ሕመም

0
0

Gastric Ulcer
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

► የጨጓራ ሕመም የሚከሰተው በጨጓራችን ግድግዳ ላይ ቁስለት በሚያስከትሉ ምክንያቶችነው፡፡

እነዚህም፡-
✔ ለጨጓራ ተስማሚ ያልሆኑ መድሃኒቶችን በመውሰድ
✔ የባክቴሪያ ኢንፌክሽን
✔ ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ መውሰድ
✔ ቅመም የበዛባቸው ምግቦች መመገብ
✔ ጭንቀት
✔ ሲጋራ ማጤስ
✔ መርዛማ ኬሚካሎች ወደ ሆድ ማስገባት

► የጨጓራ ሕመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የጨጓራ ሕመም ምልክቶች ከሰውስው የሚለያዩ ቢሆንም በአብዛኛው ግን እነዚህን ያካትታሉ፡፡

✔ የማቅለሽለሽ ስሜት
✔ የሆድ መንፋት ስሜት
✔ ማስመለስ
✔ የምግብ አለመፈጨት
✔ የማቃጠል ስሜት በተለይ ከምግብ በኋላ
✔ የምግብ ፍላጎት መቀነስ
✔ የሠገራ ቀለም መለወጥ ወይም መጥቆር ናቸው

ከባድ የሆነ የጨጓራ ሕመም ያላቸው ሰዎች የጨጓራ ቁስለት እና መድማት ሊከሰትባቸው ስለሚችል በተጨማሪ እነዚህ ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላሉ፡፡

✔ የማላብ ስሜት
✔ የልብ ምት መጨመር
✔ የትንፋሽ ማጠር
✔ ከፍተኛ የሆነ የማቃጠል ስሜት
✔ ደም ማስመለስ
✔ ደም የቀላቀለና ከወትሮው የተለየ መጥፎ ሽታ ያለው ሠገራ መኖር ናቸው፡፡

እነዚህ ዓይነት ምልክቶች ያሉበት ሰው ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ ተገቢ የሆነውን ምርመራና ሕክምና ማግኘት ይኖርበታል፡፡

የሕክምናው ሁኔታ የጨጓራ ሕመሙ እንደተከሰተበት ምክንያት ሊለያይ ቢችልም ያሉትን ምልክቶች በማስወገድ ለሕመምተኛው ፋታ መስጠትና ሕምሙን ያስከተላውን ሁኔታ በምርመራዎች አረጋግጦ መፍትሔ መስጠት ተገቢ ነው፡፡

የጨጓራ ሕመምን ሊያስነሱብን የሚችሉ ማናቸውንም ነገሮች በማስወገድ ሕምሙ እንዳይቀሰቀስብን ማድረግ ይቻላል፡፡

ጤና ይስጥልኝ

ኤርትራ ‹‹የኢትዮጲያ አይነ ውሃ አላማረኝም ›› ማለቷ ተሰማ

0
0

isayas afewerki
(አሌክስ አብርሃም)

የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ትናንት መግለጫ አውጥቶ ነበር ….እናም በመግለጫው ኤርትራ ‹‹በኢትዮጲያ እየተደረገባት ያለው ዛቻና ወታደራዊ ትንኮሳ እየጨመረ ነው …ማስፈራሪያውም በርክቷል ›› መባሉን ዘ ገልፍ ቱዴይ ዘግቦታል ፡፡ የኤርትራው መግለጫ ጨምሮ እንደገለፀው ‹‹ኢትዮጲያ አይነውሃዋ አላማረንም ወረራ ማሰቧንና ለዚሁ መዘጋጀቷን የሚያመላክቱ መረጃዎች አሉ ….ለዚህም የልብ ልብ የሚሰጧት እንደአሜሪካ አይነት የኢትዮጲያ አጋሮች ናቸው›› ሲል ክሱን አስፍቶታል !

በኢትዮጲያ በኩል እስካሁን ለዚህ ክስ የተሰጠ ምላሽ ባይኖርም ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለኢትዮጲያ ፓርላማ ኤርትራ እጇን ካልሰበሰበች እና እያሰረገች የምታስገባቸውን ‹ሽብርተኞች› ሃይ ካላለች ‹‹ህዝባችንን አስፈቅደን›› እርምጃ ልንወስድባት እንጅላለን ›› ማለታቸው የሚታወስ ነው …አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በወቅቱ ‹‹ህዝብ ለግድቡ ሳንቲም ከማዋጣት ጎን ለጎን እንዲህ ለጦርነት ሃሳብ እና ፈቃድ ማዋጣት መጀመሩ የአገራችንን ባለሁለት አሃዝ እድገት የሚያመላክት ነው ›› ማለታቸው ይታወሳል፡) ….በነገራችንላይ ሁለቱም አገራት አንዱ አንዱን ‹‹ውስጥ ችግራቸውን መፍታት ሲያቅታቸው የህዝቡን ትኩረት ወደውጭ ለመመለስ ነው ጦርነት ሽብር የሚያስቡት›› እየተባባሉ ይወነጃጀላሉ እነፕሬዝደንት ኦባማም ዝምታን መርጠዋል ምናልባት ዘና ብለው ተቀምጠው ‹‹አስተናጋጅ ቡጥቡጡ ከመጀመሩ በፊት አንድ ቢራ›› እያሉ ይሆናል !….

ለማንኛውም አገራችን በዚህ ወቅት እንደገና ወደጦርነት ባትገባብን ምርጫችን ነው !! ‹‹አይ ሳንዋጋ አስር አመት አለፈንኮ እጃችንን እናፍታታ …ወንድነታችንም ትንሽ ይፈተሸ እንጅ ›› ከተባለ . . .፡)ማነሽ አልጣሽ ምንሽሬን አቀብይኝ…ወደሰማይም ቢሆን እተኩሳለሁ …እግዜርን በምንሽር ካልቀሰቀስነው ፆለታችንን አልሰማ ብሏል፡)፡) እናተ ልጆች ዝሆኖች እንደገና ሊጣሉ ነው ሳሩን ወደጥግ ወደጥግ አድርጉት እስቲ !

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live