Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የትግራይ ምእራባዊ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ከ44 ሚልዮን ብር ለግል ጥቅሙ ማዋሉ ተጋለጠ

$
0
0

AMEHADAR ZOBA MERAB AYTEFISHA BERHE

የትግራይ ምእራባዊ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ከ44 ሚልዮን ብር በላይ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ የተነሳ የዞኑ ነዋሪዎች ምሬታቸውን በማሰማት ላይ መሆናቸው ተገለፀ።

ለደህሚት በደረሰው መረጃ መሰረት የምእራብ ትግራይ ዞን አስተዳዳሪ የሆነው ፍስሃ በርሀ ለሁመራ ከተማ መሰረተ ልማት ተብሎ በተለያየ መልኩ ከህዝብ የተዋጣው 44 ሚሊዮን ብር ስልጣኑን ተገን በማድረግ ለግል ጥቅሙ ማዋሉን ታውቆ እያለ እስከ አሁን ድረስ ሊጠየቅ አልቻለም በሚል የሁመራ ከተማ ከንቲባ አቶ አለሙ አየነው ይመራው በነበረው ስብሰባ ላይ ጉዳዩ ቢነሳም አጥጋቢ የሆነ ምላሽ እንዳልተሰጠበት ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው በማከል ይህ በትክክል የተመደበውን በጀት ያጠፋፋው ፍስሃ በርሀ እንደሆነ አስቀድሞ በማስረጃ አስደግፈው ቢያቀርቡም የተጠፋፋው ገንዘብም የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት እጅ ሰላለበት ገንዘቡን ያጠፋፋው ሃላፊ አንድ ጊዜ ወደ ሌላ ስራ ሄደዋል። ሌላ ጊዜ ደግሞ ታምመዋል በማለት እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ምክንያቶችን በመደርደር እስከ አሁን ድረስ ወደ ህግ ሊቀርብ ባለመቻሉ ምክንያት ነዋሪውን ህዝብ እንዳስቆጣው መረጃው አስረድቷል።


በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በየዓመቱ ከ1.5 ቢልዮን ብር በላይ ይመዘበራል

$
0
0

አዲሱ ዓመት ቤተ ክርስቲያን በፀረ ሙስና እንቅስቃሴዋ ልዕልናዋን የምታስመልስበት እንደሚኾን ፓትርያርኩ ተናገሩ
የለውጥ እንቅስቃሴውን ለማስቀረት “የተለያዩ ነፋሳት እየነፈሱ” መኾኑን ጠቁመዋል
የሰንበት ት/ቤቶች የፀረ ሙስና እንቅስቃሴውን በማጠናከር በጋራ እንዲሠሩ ጠይቀዋል

ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው:

መጪው 2008 ዓ.ም.፣ ቤተ ክርስቲያን የመልካም አስተዳደር ችግሮቿን አስተካክላ ልዕልናዋን የምታስመልስበት እንደሚኾን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናገሩ፡፡
abune-matyas
ከቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረታዊ ባሕርይ ጋር የማይስማሙ የሙስና እና የሥነ ምግባር ብልሹነትን ለማስወገድ የተጀመረው እንቅስቃሴ፣ “ጭላንጭል እየታየበት ነው” ያሉት ፓትርያርኩ፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ የቤተ ክርስቲያኒቷ ልዕልና እና ሕይወት እስኪመለስ በሰላማዊ መንገድ እና በአቋም መታገላቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል፡፡

አቡነ ማትያስ በፓትርያርክነት በተመረጡበት በዓለ ሢመት፣ በቆራጥ የለውጥ ርምጃዎች የፀረ ሙስና ሥርዐት ለመደንገግ የገቡትን ቃል መነሻ በማድረግ በተካሔዱ እንቅስቃሴዎች ላይ ከየሰንበት ት/ቤቶች ሥራ አመራር አባላት ጋር ከትላንት በስቲያ ከቀትር በኋላ በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡
በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ሀገር አቀፍ አንድነት እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሥራ አመራር ጉባኤ ተወካዮች በተገኙበት ውይይት፤ “ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ለማረም እና ለማስወገድ በሚደረገው ከፍተኛ ጥረት ከጎኔ እንድትቆሙ” በሚል ፓትርያርኩ የሰጡት አባታዊ መመሪያ ምእመኑን ያስደሰተ እና ወጣቱን ያነቃቃ መኾኑ በተወካዮቹ ተገልጧል፡፡
መመሪያውን ለማስፈጸም የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ እንዳሉ የተናገሩት የማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ፣ ችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንዳይገኝለት የሚጥሩ ኃይሎች ፓትርያርኩ ከወጣቶች እንዳይገናኙ የፈጠሩትን ዕንቅፋት አስረድተዋል፤ ዕንቅፋቶቹን በመቋቋም በተሠሩ ሥራዎች ወጣቶቹን እንዲያበረታቱም ጠይቀዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እና ሰፊ የመሬት ይዞታ ቢኖሯትም የሚገባውን ያኽል ተጠቃሚ እንዳልኾነች ሰሞኑን ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደር ጉባኤ የቀረበው የአዲስ አበባ አድባራት የመሬትና ሕንፃዎች ኪራይ ተመን ጥናታዊ ሪፖርት ማረጋገጡን የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ በውይይቱ ላይ ጠቅሰዋል፡፡ የንግድ ተቋማቱ የሚያመነጩት ገቢ የግለሰቦች መጠቀሚያ ከመኾኑ ባሻገር፣ በሀገረ ስብከቱ የቃለ ዐዋዲውን ሕግና መመሪያ ተደግፎ በታማኝነት ባለመሠራቱ በየወሩ ብር 100 ሚሊዮን፣ በዓመት ብር 1ነጥብ5 ቢልዮን ለራስ አገዝ ልማት መሰብሰብ ሲቻል እንደሚመዘበር ልዩ ጸሐፊው ገልጸዋል፡፡
በሙሰኛ ሓላፊዎች ላይ አስተማሪና ሕጋዊ ርምጃ በመውሰድ ብልሹ አሠራርን በወሳኝ መልኩ ለማረምና ለማስወገድ፤ በመሪ ዕቅድ የሚመራ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው፣ ለለውጥ የተዘጋጀ አስተዳደራዊ መዋቅር ለማደራጀት፤ ዘመኑን የዋጀና ወጥነት ያለው የፋይናንስ አያያዝና አጠቃቀም ሥርዐት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ለመዘርጋት በፓትርያርኩ የተጀመረው ጥረት በቅርቡ በተሳካ መልኩ ከዳር እንደሚደርስ ልዩ ፀሐፊው አብራርተዋል፡፡ “የጠቅላይ ቤተክህነቱ የአስተዳደር ጉባኤ ብዙ ከደከመበት ጥናታዊ ሪፖርት ጋር ተያያዞ በቅርቡ ኹላችንም በጉጉት የምንጠብቀውን ነገር እናያለን፤” ያሉት ልዩ ጸሐፊው፣ “በአዲስ ዘመን፣ በአዲስ መንፈስ ቤተ ክርስቲያናችን የተሳካ አስተዳደራዊ የለውጥ ኹኔታ ይኖራታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤ እናንተ ወጣቶች ስለኾናችኹ በሩ ክፍት ነው፤ አግዟቸው፤” ብለዋል፡፡
የተጀመረውን የፀረ ሙስና እንቅስቃሴ ለማዳከምና ተቋማዊ ለውጡን ለማስቀረት “ብዙ ነፋሳት እየነፈሱ” እንዳሉ ያመለከቱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች “ሕይወት የሚሰጠውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ነፋስ (መልእክት)” ብቻ ማድመጥ እና መከተል እንደሚገባቸው መክረዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያን የካህናትም የምእመናንም መኾኗንና ልዩነቱ የሓላፊነት ድርሻ ብቻ እንደኾነ ያስረዱት አቡነ ማትያስ፣ ‹‹ትውልዱ ዛሬ በሚሠራው ሥራ የታሪክ ተጠያቂም ተመስጋኝም በመኾኑ ወጣቶች አያገባችኹም አይባልም፤ የነገ የቤተ ክርስቲያን ተረካቢዎች ናችኹ፤ በሞያችኹ፣ በዕውቀታችኹ የበለጸጋችኹ ስለኾናችኁ ትልቅ ሚና አላችኹ፤ ይኼን ጸያፍ ነገር አስወግደን የቤተ ክርስቲያንን ሕይወቷን፣ ልዕልናዋን እስክናስመልስ አብረን በጋራ መቀጠል አለብን፤›› በማለት የሰንበት ት/ቤቶቹን አመራሮች አሳስበዋል፡፡
ፓትርያርኩ፣ ጭላንጭል ታይቶበታል ባሉት የፀረ ሙስና እንቅስቃሴ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን መብቶች እና ጥቅሞች አሳልፎ በመስጠት አላግባብ የበለጸጉ የአድባራት ሓላፊዎች በሕግ አግባብ እንዲጠየቁ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአስተዳደር ጉባኤ ውሳኔ እንዳሳለፈ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ወያኔ ያሰረው ህግን ነው! –ሳሙኤል አሊ

$
0
0

ሳሙኤል አሊ ከ- ኖርዌይ

habitamuህግ በታሰረበት አገር ሰለ ህግ ማውራት ቀልድ ሊሆን ይችላ ይሆናል። ነገር ግን  ትግልን የሚወልደው ወይም ታጋይን የሚያበዛው የህግ የበላይነት ሲጠፋ ነው። ህግ ባልተከበረባት አገር ዜጎች ሁል ግዜም ሰቆቃ ውስጥ እንደሆኑ ማሰብ አለብን። ህግ እራሱ ሰለታሰረ ፍርድ ቤቶች የቧልት ቤት ሆነዋል።

የፖለቲካ እስረኞች ጋዜጠኞች ጦማሪያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አሸባሪ በሚል ታርጋ ወደ እስር ቤት ተወርውረው የመከራና የሰቆቃ ግዜአቶችን ሲያሳልፉ ምን ባደረጉት ወንጀል ነው የሚል  በሁሉም ልብ ውስጥ ጥያቄ መጫሩ አይቀሬ ነው። ታዲያ የሚፈለገው እኮ እርሱ ነው  እነዚህ ሰወች እኮ  ለኛ ትልቅ የትምህርት ተቋም  መምህሮቻችን ናቸው። የወያኔን ስርአት ቁልጭ አድርገው ያሳዩን በነዚህ በእውነተኛ ብዕረኞችና ፖለቲከኞች ነውና ። ኢትዮጵያዊው ሁሉ ጎበዝ ተማሪ ሆኖ የታሰረውን ህግ ማስፈታት የሚችል እንደ መምህሮቻችን ቆራጥና  ጀግና  የሚሆን ትውልድ  እነደ ሰደድ እሳት ውስጥ ውስጡን ሊቀጣጠል ይገባል። ጊዜው በኢትዮጵያ የታሰረውን ህግ በማስፈታት ነጻና እውነተኛ ፍታዊ ስረአትን መዘርጋት  እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል እንጂ፡ ህግ አሳሪን አስወግደን በምትኩ ሌላ ህግ ጨፍላቂ ለመተካት አለመሆኑ ይታወቅ።

ምርጫ በቀረበ ቁጥር ጭንቅ ጥብብ የሚለው ወያኔ አሉ አሉ የተባሉትን ፖለቲከኞች እና ፀሐፍትን፤ ጋዜጠኞችን፤ ለቅሞ ማሰር የተለመደ ተግባሩ ነው። ምክንያቱም በክፍተኛ ሁኔታ ሕዝቡን ሊያነሳሱት ይችላሉ በማለት እና ሕዝቡንም መሪወቻቹህ እና ጋዜጠኞቻቹህ ታስረዋል እናተም አንዳች ነገር አደርጋለው ካልቹህ ካለችሁበት ተለቃቅማቹህ  እነሱ የገቡበት ትገባላቹህ የሚል መልእክት ማስተላለፊያ መንገድ ነው።  ሰለዚህ የኢትዮጵያ ህግ ቀድሞ ስለታሰረ የህግ ከለላ ማግኘት አይችሉም።

ታዲያ እኛ እንሱ ሲታሰሩ እሪ ብሎ ማልቀስና መጮህ ሲፈቱ ደግሞ እልል ብሎ መዘመር ነው እኔዴ ስራችን? ይሄ አይደለም የኛ ኢትዮጵያን ስራ ሊሆን የሚገባው ስታስሩ ለምን? ሲፈቱስ በምን የህግ አግባብ ተፈቱ? ብሎ የመጠየቅ ሃላፊነት አለብን። እዚህ ጋር ሊሰመርበት የሚገባው አሳሪውም ማን ነው? ፈቺውስ ማን ነው? አሳሪውም ፈቺውም በህግ ሊጠየቁ ይገባል ለምንስ አሰርካቸው ለምንስ ፈታሃቸው?

ዛሬ የፈታቸውን ነገ አለማሰሩ ምን ዋስትና አለ? ዛሬ ነጻ ናቸው የተባሉት ነገ ወንጀለኛ ናቹሁ ተብለው አለመያዛቸው ምንስ ማረጋገጫ አለ? ወያኔ ሲጨንቀው ማሰር ሲጠበው ሊፈታ የሚችልበትን ህግ ማን ሰጠው ይህ ሁሉ ዘግናኝ ስህተቶች እየተፈጸሙ ያሉት እራሱ ህግ እሰር ላይ ስለሆነ ነው።

እንጠይቃለን፦

1 ህግ (ፍርድ ቤቱ) ይፈታልን ነጻ ይሁንልን።

2 ያለወንጀላቸው አሸባሪ ተብለው ንጹሃን የኢትዮጵያ ልጆች በእስር መማቀቃቸው ይታወቃል ስለዚህ እነዚህ ንጹሐን ወደ እስር ያስገባቸው አካል በአስቸካይ ለፍርድ ይቅረብልን።

3 ያለ በቂ ማስረጃ ታስረው ቆይተው አሁን ላይ ነጻ ናቹህ ብሎ የለቀቃቸው አካል የደረሰባቸውን የሞራል፤ የጊዜ ፤ የስነ ልቦና ጉዳት፤ ሳይመለከት ነጻ ናቹህ ብሎ አሳሪወችን  ለፍርድ ሳያቀርብ የፈታው አካል  ለፍርድ ይቅረብልን።

4 በነዚህ ንጹሃን ኢትዮጵያን ላይ የተሰራው ግፍ በነሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ እየተፈጸመ ያለ ጉዳይ ስለሆነ  ያለምክንያት ከተያዙበት ጊዜና ሰዓት ጀምሮ  ሰለደረሰባቸው የሞራልና እና እንዲሁም ያለአግባብ በእስር ስላባከኑት ጊዜ ተገቢውን ካሳ እንዲከፈላቸው እንጠይቃለን።

5 ሌሎች ንጹሃን ኢትዮጵያን በወያኔ ጉጅሌ  የፈጠራ አኬል ዳማ ድርሰት የታሰሩት በአፋጣኝ ተፈተው ተገቢውን ካሳ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን።

ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነው። ወያኔ ከአሁን በሃላ በአንተ ስራ ማንም አይታለልም የካንጋሮ ፍርድ ቤትህንም ማንም ኢትዮጵያዊ አያምነውም የምንታገለው የታሰረው ህግ እስከሚፈታ ድረስ ነው እንጂ በፈጠራ ድርሰት ያሰርካቸው ብቻ  እስኪፈቱ አይደለም። የምንታገለው ህግን ያሰሩትን እና  ሕዝብን የሚያሰቃዩበትን ህግን አስፈትተን ህዝባችን ነጻ አደርገን ህግ አሳሪ እና ሕዝብ ጨቋኝ የነበሩትን ለፍርድ ለማቅረብ ነው። አገራችን ነጻ እስከምትሆን ድረስ ነጻ የሆነውን ህዝባችንን ልታሰቃዩ  ትችሉ ይሆናል፡ አሳሪ እና ገዳይ እንዲሁም አረመኔ የሆነው ወያኔን አስወግደን የሁላችን አገር እስከምናደርጋት ድረስ ልታስሩን ልትገድሉን ትችሉ ይሆናል፡ በደል ጭቆና እስራት እንግልት ግድያ የመብት ጥሰት  ሲበዛ  ሰው ፈሪ ይሆናል ብላቹሁ አስባቹ ከሆነ በወያኔ  አእምሮአችሁ ማለትም በጠባብ እና እውቀት በሌለው ማሰቢያቹህ የተጨቆነ ሕዝብ የሚባላ አብዮት እንደሆነ የምታዩበት ጊዜ  ቅርብ ነው። ህዝብ አብዮት ነው አብዮት የሚመጣው የተጨቆኑ ህብረተሰብ ለለውጥ የሚነሳበት አንባገነኖች የሚያለቅሱበት  የማይጠፋ እሳተ ገሞራ ነው ይሄም ሕዝባዊ አብዮት አንባገነኖችን የሚያጠፋ እሳት ነው።

ጋዜጠኞች እንዲሁም ፖለቲከኞች እንዲሁም ፀሃፊያኖች በመፈታታችሁ ደስተኛ ነኝ።  አሁን  ግን ትግሉ ኢትዮጵያን ለማስፈታት ነውና ትግሉን ሁሉም በአንድነት ተቀላቀሉ  ኢትዮጵያዊ ሁል ጊዜ አሸናፊ ነው።

 

ድል ለሰፊውየኢትዮጵያ ሕዝብ

ሞት ለዘረኛው ወያኔ ይሁን

 

ሳሙኤል አሊ ከ-ኖርዌይ

Email samilost89@yahoo.com

በሰላም አስከባሪ ስም የሕወሓት ባለስልጣናት የሚቀራመቱትን የሰራዊቱን ዶላር ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እንዲህ ይመሰክራል

$
0
0

መሳይ መኮንን

ዛሬ ለኢሳት የደረሰው ጥብቅ መረጃ 11ዓመታትን ወደ ኋላ በትዝታ ወሰደኝ:: ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዋናው ጸሀፊ ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያጋልጠው ለሰላም አስከባሪ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከፈለው ደምወዝ ከ90 በመቶ በላይ የህወሀት ካዝና ውስጥ የሚገባ ነው:: በወር 13 ሚሊዮን ዶላር(500 ሚሊዮን ብር ገደማ) የወታደሩ ገንዘብ ህወሀቶች ይቀራመቱታል:: ይህን ጉዳይ የመንግስታቱ ድርጅት የሚያውቀው ይመስለኛል:: ለዚህም እኔ የተሳተፍኩበትን የሰላም አስከባሪ ዘመቻ አጋጣሚ በአስረጂነት ማሳየት እችላለሁ::

Mesay mekonenn
እኤአ በ2003-2004 በመንግስታቱ ድርጅት የበላይነት: በአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚነት ከተላከው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት ጋር ወደ ቡሩንዲ ሄጄ ነበር:: ወደ 18 የምንሆን አስተርጓሚዎች ከ8 ወር እስከ 1 ዓመት ቆይተናል:: ዝርዝሩን ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለስበታለሁ:: ከገንዘብ ጋር በተያያዘ የተፈጸመውን የህወሀቶችን ለከት ያጣ ስግብግብነትን ላጫውታችሁ:: 


በዘመቻው በUN ደረጃ ወርሃዊ ደምወዝ ከ1000 ዶላር ያላነሰ: የመስክ ክፍያ በቀን 60 ዶላር: የበዓል ክፍያ በአንድ በዓል 1000 ዶላር: የላብ መተኪያ: …..በጣም ብዙ ዓይነት ክፍያዎች ነበሩት:: አብዛኛው የሰላም አስከባሪ ሰራዊት አባላት በተስፋ ነበር ወደ ቡሩንዲ የተጓዘው:: እዚያ እንደደረስን ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆኑ:: ቃል የተገባው: በውል የታሰረው( የሚገርመው የውሉን 3 ኮፒዎች አንሰጥም ብለው እዚያው መከላከያ ግቢ ቀርቷል:: መንግስትን አምነን ነው የተጓዝነው) ክፍያ የለም:: በወር 40 ዶላር ለኪስ እየተሰጠን: ምግብና መጠጥ በአላሙዲን እየቀረበልን: እየበላንና እየጠጣን መኖር ብቻ ሆነ:: ከኢትዮጵያ ሌላ የደቡብ አፍሪካና ሞዛምቢክ የሰላም አስከባሪ ሃይሎችም ለተመሳሳይ ዘመቻ ቡሩንዲ ገብተዋል:: ለእነሱ የሚገባቸው ክፍያና ጥቅማጥቅም ሀገራቸው በባንክ አካውንታቸው የሚገባላቸው ይህንንም የሚያረጋግጥ ደረሰኝ በየወሩ እንደሚደርሳቸው በነበረን ቅርበት ተረዳን:: እኛ ግን ምንም የለም:: ስንጠይቅ ኢትዮጵያ ይጠራቀምላችኋል የሚል መልስ ከማስፈራሪያ ጋር ይሰጠናል::

በእኛና በሌሎቹ ለተመሳሳይ ዘመቻ በመጡ ሀገራት የሰላም አስከባሪው ዘመቻ አባላት መሃል ያለው የኑሮ ሁኔታ የሰማይና የምድርን ያህል የሚራራቅ ነበር:: በህወሀት ስግብግብነት የተነሳ በጣም በሚያሳፍር የኑሮ ገጽታ መቀለጂያ ሆንን:: በሰራዊቱ ውስጥ ቅሬታው ስር ሰደደ:: ተስፋው ጨለመ:: በወር 40 ዶላር እየወረወሩ እዚያ ይጠራቀምላችኋል በምትል ከቃል ያለፈ በደረሰኝ ያልተረጋገጠች ተስፋ ብቻ ይዘን በብስጭት ገፋን:: በመሃል ሲብስብን አስተርጓሚዎች ተነጋግረን ቡጁምቡራ በሚገኝ የUN ጽ/ቤት አቤቱታ ልናቀርብ ሄድን:: የተሰጠን ምላሽ ተስፋችንን ይበልጥ ገደለው:: “ስለ እናንተ የተፈራረምነው ከመንግስታችሁ ጋር በመሆኑ አይመለከተንም:: መንግስታችሁን ጠይቁ::” የሚል ወሽመጥ የሚቆርጥ ምላች ተሰጠን::


በመሃሉ መለስ ዜናዊና ሳሞራ የኑስ ሊጎበኙን ቡጁምቡራ መጡ:: ሳሞራ ሰብስቦን ችግር ካለ ንገሩኝ አለ:: ሰራዊቱ የክፍያው ነገር ሲያንገበግበው ስለከረመ ሳሞራን ሲያገኝው በየተራ እየተነሳ ጠየቀው:: ሳሞራ ጀት ሆነ:: ባለጌ አፍ እንዳለው ያረጋገጥኩት የዚያን ዕለት ነው:: የኢትዮጵያን የችግር መዓት ሲዘረዝር: መዓት ሲያወራ ቆየና ” ሰው እንደ ቤቱ እንጂ እንደ ጎረቤቱ አይኖርም:: የሌሎችን እያያችሁ እንደነሱ እንሁን ማለት አደጋ አለው:: እዚህ ገንዘብ ምንም አያደርግላችሁም:: በብር ኢትዮጵያ እየተጠራቀመላችሁ ነው:: ለሸርሙጣ ፈልጋችሁ ከሆነ ኢትዮጵያ ስትመለሱ ትደርሱበታላችሁ…..” እያለ ወረደብን::

ሰራዊቱ ቅስሙ ተሰበረ:: ብዙ የምንሰራው ስራ አለ:: ትምህርት ቤት እንገነባለን:: ….እያለ ተንዘባዘበ:: የዚያን ዕለት ሌሊት ከአምቦ የመጣ የሰራዊቱ አባል በታጠቀው መሳሪያ ራሱን አጠፋ:: ባርቆበት ነው የሚል ሪፖርት እንድናዘጋጅ በህወሀት የጦር አዛዦች መመሪያ ተሰጥቶን የውሸት ሪፖርት አዘጋጅተን ለUN ተላከ:: ይህ የሆነበትም ራሱን ካጠፋ UN ካሳ አይከፍልም:: እርግጠኛ ነኝ በዚህ የተገኘውን በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ዶላር ህወሀቶች ኪስ ገብቷል::
ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ እየተጠራቀመላችሁ ነው እየተባለ ስንሸነገል የከረምንበትን ገንዘብ ሊሰጡን ተዘጋጁ:: ለአንድ የሰላም አስከባሪ ሰራዊቱ አባል በትንሹ ከ250ሺህ ብር በላይ ወይም በወቅቱ ምንዛሪ 10ሺህ ዶላር መከፈል ነበረበት:: በጣም የሚያሳፍር የሚያስደነግጥ ነገር ነበር የጠበቀን:: እንደ ቆይታ ጊዜ ከ15ሺህ እስከ 25ሺህ የኢትዮጵያ ብር ሰጥተው አሰናበቱን:: ከእያንዳንዳችን ከ200ሺህ ብር በላይ ህወሀቶች ተቀራመቱት:: …በሌላ ጊዜ በስፋት እመለስበታለሁ::

የኢትዮጵያ የስደት መንግስት፤ ከህሳቤ ወደ ተግባራዊነት –

$
0
0

entc-and-eynm-logo

የኢትዮጵያ የስደት መንግስት መመስረት አስፈላጊነት ላለፉት ሁለት አስርት አመታት፣ በተለይ ደግሞ የግንቦት 1997 ዓ.ም. ሃገራዊ ምርጫን የህወሃት/ኢህአዴግ ስርዓት በጠመንጃ አፈሙዝ ከህዝብ መንጠቁን ተከትሎ ውይይትና ክርክር ሲደረግበት ቆይቷል። የተሰረቀውን የህዝብ ድምፅ ለማስመለስ የተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የተለያየ የትግል ስልት መከተልን መርጠዋል። አንዳንዶች የትጥቅ ትግል ሲመርጡ፣ ሌሎች የምርጫ ፖለቲካን ገፍተውበታል። የአፖርታይዱ ወያኔን አምባገነን ስርዓት አስወግዶ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም እስካሁን ያልተሞከረ መንገድ ቢኖር የፓርቲ ፖለቲካን ወደ ጎን በመተው ባለድርሻ አካላትን ሁሉ ያሳተፈ የስደት መንግስት አለመመስረቱ ነው።

ይህን ሃሳብ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሸጋገር ሐምሌ 2012 እ.አ.አ. አያሌ ኢትዮጵያውያን በዳላስ ቴክሳስ በመሰባሰብ የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤት መስርተዋል። የሽግግር ምክር ቤቱም ላለፉት 3 ዓመታት ሃሳቡን ለማስረፅና ስምምነት ለመድረስ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በርካታ ስብሰባዎችና የምክክር ጉባዔዎች አካሂዷል።

ባሳለፍነው ወር ሐምሌ 2015 የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤቱና የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ ከተለያዩ የድርጅቶች ተወካዮችና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ለሁለት ቀናት በዋሽንግተን ዲሲ ውይይት ካደረጉ በኋላ የኢትዮጵያ የስደት መንግስት አደራጅ ኮሚቴ ለማቋቋም ተስማምተዋል። በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ የስደት መንግስት አደራጅ ኮሚቴ በመመስረት ላይ ይገኛል። የመጀመሪያ መዋቅሩ ተዘጋጅቷል። የኮሚቴው ተቀዳሚ ስራ የሚሆነው፤ 1) የኢትዮጵያ የስደት መንግስት መመስረት አስፈላጊነትን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ 2) አስፈላጊ የሆኑ ህዝባዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና የፋይናንስ ድጋፎችን ማሰባሰብ 3) የስደት መንግስቱን መሰረት መገንባት። የስደት መንግስት ምስረታው ብዙ ደረጃዎች ይኖሩታል። የኢትዮጵያን ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት በጣም በጥንቃቄ ታቅዶ ጠንካራ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ኮሚቴው ይረዳል። በተጨማሪም ዘርፈ-ብዙ ስራዎችም እንዳሉት ይገነዘባል። በሚቀጥሉት ቀናትና ሣምንታት አደራጅ ኮሚቴው የነደፋቸውን እቅዶች ለህዝብ ይፋ በማድረግ የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናል።

የኢትዮጵያ የስደት መንግስት የመጨረሻ ግብ የሚሆነው ኢትዮጵያ ውስጥ የተረጋጋ፣ ሰላማዊና ወደትክክለኛ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር መኖሩን ማረጋገጥ ነው። ከዚህ በፊት ያልታቀደ የስርዓት ለውጥ የሚያስከትለውን ቀውስ አይተናል። ለዚህ ደግሞ ሃገራችንን መመልከት በቂ ነው። በአሁን ወቅት በሶሪያና ሊቢያ እየሆነ ያለውን መመልከትም እንችላለን። ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጠነም ዘገየም ለውጥ መምጣቱ የማይቀር ነው — ምክንያቱም አምባገነን ስርዓትን ለመታገል ህዝብ በየትኛውም ሀገር ቢሆን ማመጹ ስለማይቀር። በተቻለ መጠን ሌላ ቀይ ሽብር፣ ሌላ አፖርታይድ ስርዓት፣ ሌላ የህዝብ እልቂት በሀገራችን እንዳይከሰት የሚመጣው ለውጥ በሰላማዊ ሂደት እንዲያልቅ እንፈልጋለን። የታቀደ፣ የተደራጀና ሠላማዊ ለውጥ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲመሰረት በሚደረገው ጥረት ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንድትሳተፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

ለግንኙነት በኢሜል፤ contact@etntc.org ወይም ethioyouthmov@gmail.com

የአዲሱ ህውሀት መንግስት መጥፎ አጋጣሚ!! –ከኤርሚያስ ለገሠ

$
0
0

ከኤርሚያስ ለገሠ

1• ደስታ እና ሀዘን

ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ ስትነቃ አቅፎ ሊያነሳት በመቻሉ ደስ ይለኛል። እንኳን ለዚህ አበቃህም ማለት እፈልጋለሁ።
ermias copy
በሌላ በኩል ገዥው ቡድን በምክንያት እያሰረ በምክንያት የሚፈታበት ሁኔታ ለራሱ ስልጣን መቆያ ትክክል ቢሆንም ለኢትዬጲያ የፍትህ ስርአት ምን ያህል ንቀት እንዳለው የሚያሳይ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው። ሰዎች በህውሀት ላይ አደጋ ሲጋርጡ በፓለቲካ ውሳኔ ይታሰራሉ…ህውሀታዊ ምክንያት !። ገዥው ቡድን ላይ የተጋረጠው አደጋ በሌላ ጐን ሲያጋድል ደግሞ በእጁ ይዞ የሚያሰቃያቸውን ይፈታል…ህውሀታዊ የመፍታት ምክንያት!!

ሀብታሙ አያሌውና ድርጅቱ ” አንድነት” ህውሀትን በሰላማዊ ትግል ፈተና ውስጥ ለመክተት ስትራቴጂ ነድፈው ሰፊ እንቅስቃሴ ጀመሩ። የለውጥ ንፋስም በስሱ መንፈስ ጀመረ። እነ ሀብታሙ በአደባባይ ” እመኑኝ ኢህአዴግም ይወድቃል! ኢትዬጲያም ነጳ ትወጣለች!” በሚል መሪ መፈክር ገዥዎችን አስጨነቁ። የስርአቱን ባህሪያት በቅርብ የምናውቅ ሰዎች የእነ ሀብታሙ እድሜ አጭር እንደሚሆን አሳወቅን። ርግጥም ” ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም!” በሚል መርህ የሚመራው ገዥ ቡድን እነ ሀብታሙን የውሸት ክስ በማዘጋጀት ወደ ማእከላዊ ወረወረ። ” አንድነት” ፓርቲንም አፈረሰ። ኩሸቱን በመደጋገም የራሱን እውነት ፈጠረ። እነ ሱዛን ራይዝን “በ100%” ጦሽ ብለው እንዲስቁ አደረገ።

በሌላ በኩል ለውጥ በሁሉን አቀፍ ትግል ብቻ መምጣት እንዳለበት የሚያምኑ ኢትዬጲያውያን የለውጥ እንቅስቃሴውን በግላጭ ማቀጣጠል ጀመሩ። ምሁራን ዱር ቤቴ በማለት ወደ በረሀ ተመሙ። አዲስ ህልምና አዲስ አቅጣጫ ይዘው የነጳነት ትግሉን ዙር አከረሩት። እናቶች ከጣታቸው ቀለበት፣ ከአንገታቸው ሀብላቸውን እያወለቁ ትግሉን ወደማገዝ ተሸጋገሩ። የመኪናቸውን ቁልፍ ለአርበኞች አስረከቡ። በየቦታው አዳራሽ ሞልቶ እስኪፈስ ድረስ ” እኔ አርበኞች ግንቦት ሰባት ነኝ!”፣… ” እኔ አንዳርጋቸው፣ ብርሀኑ፣ ኤፍሬም፣ ንአምን… ነኝ!” የሚል ቃልኪዳን ከመግባት ባሻገር እስከ መቶ ሺህ ዶላር መዋጣት ተጀመረ። ይህን የለውጥ ስሜት በስማ ስማ ሳይሆን በአይኔ በብረቱ ተመልክቻለሁ። ቆም ብዬም ለማሰላሰል ሞክሬያለሁ።

እንደ እውነቱ ከሆነ ህውሀት ቆም ብሎ ለትክክለኛው መፍትሔ የማሰቢያው ግዜ ነበር። ይሁን እንጂ አፈጣጠሩ፣ ባህሪውና የበታችነት ስሜቱ ይህን ስለማይፈቅድለት ሌላ መፍትሔ ማሰብ ነበረበት። ከእነዚህም ውስጥ በቁጥጥሩ ስር ባሉት አንዳርጋቸው ጵጌ ስም መጵሀፍ መጳፍና እንደ ሀብታሙ አያሌው ያሉትን የፓለቲካ እስረኞች መፍታት የሚጠቀሱ ናቸው። በበረከት ፀሀፊነት በአንዳርጋቸው ስም የሚወጣው መጵሀፍ ” የሶስት ምርጫዎች ወግ!” ( ስያሜው የእኔ ነው) ገና ባይወጣም በቅርብ ቀን እንደሚወጣ ይጠበቃል። ምርቃቱም ሸራተን አዲስ አንዳርጋቸው በሌለበት ይሆናል። …እነ ሀብታሙ አያሌውም ተፈተዋል።

( ” የሶስት ምርጫዎች ወግ” በተመለከተ ” የነጳነት ትግሉና ስድስት የህውሀት ማደናገሪያ ነጥቦች” በሚለው ሀሳብ ውስጥ አካትቼ በዳላስ ቴክሳስ በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ አቅርቤ ነበር። ብዙዎች እንዲለጠፍ ስለጠየቁኝ በሌላ ክፍል እንደምመለስበት ተስፋ አደርጋለሁ።)

2• ” መውጫ መንገድ ያሳጣ ሰላማዊ ትግል”

አዲሱ የህውሀት መንግስት ሁለተኛው መጥፎ አጋጣሚ በኢትዬጲያ ሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ነው። እነዚህ ለሀይማኖታቸው ነጳነት የሚታገሉ ታጋዬች የያዙት አቋም ገዥው ቡድንን ወደ ከፍተኛ ፈተና ጐትቶ ወስዶታል። ይህን ለማለት ያስደፈረኝ ያለምክንያት አይደለም። ከልምድ በመነሳት እንጂ!

የዛሬ ሰባት አመት በዚህ አካባቢ የአዲስ አመት መምጫ በድርቡም የኢትዬጲያ ሚሊኒየም መግቢያ ነበር። በመላው ኢትዬጲያ በተለይም በከተሞች የቅንጅት መሪዎች ካልተፈቱ ” በሚሊኒየም ምንም የለም!” የሚሉ መፈክሮች ተስተጋቡ። ሁኔታዎች አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር (” ታላቁ መሪ” ባለማለቴ እቴጌን ከወዲሁ ይቅርታ እየጠየኩ) መውጫ መንገድ ፈለገ። “የኢትዬጲያ ሚሊኒየም የፈጠረው መልካም አጋጣሚ መጠቀም” የሚል የውስጠ ድርጅት ሰነድ እንዲዘጋጅ አደረገ። ይህ ሰነድ የታሰሩ ተቃዋሚዎችን በይቅርታ የመፍታት ፋይዳውን የሚተነትን ነበር። በዚህ ጵሁፍ ህዝቡ የይቱልን ጥያቄ ያለማቋረጥ እያነሳ ያለው ከአርቆ አስተዋይነት የመነጨ እንደሆነ ዘረዘረ። ህዝቡ ይፈቱልን የሚል ጥያቄ እያነሳ ያለው ” እኔው መርጬ ለዚህ አደረስኳቸው” ከሚል የህሊና ፀፀት እንደሆነ ተገለፀ። በመሆኑም ታሳሪዎችን በይቅርታ መፍታት ህዝቡን ከፀፀት የማውጣት ሁኔታ ስለሚፈጥር መንግስት የሚፈታበት ሁኔታ ማማተር እንዳለበት በሰፊው ተነገረ።

ታሳሪዎች የይቅርታ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የፍርዱ ሂደት እንዲፋጠን ተደረገ። በአስቂኝና ባዶ ማስረጃ ታሳሪዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲወሰን አደረገ። ( በነገራችን ላይ በመስካሪነት የቀረቡት የቀበሌ ካድሬዎች የነበሩት እነ አበባ ሽመልስ ከማል ልምምድ የሚያደርግላቸው በኢህአዴግ ቢሮ ነበር) ። የፍርድ ውሳኔውን አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እስከ እድሜ ይፍታህ አምዘገዘገው። ይህ ውሳኔ ታሳሪዎችና ቤተሰባቸው ተደናግጠው ወደ ይቅርታ ሂደቱ በፍጥነት ይገባሉ የሚል ታሳቢን የወሰደ ነበር። በወቅቱ በታሳሪዎች መስመር ያለውን ተጵእኖ በቀጥታ ከራሳቸው መስማት የምችልበት እድል ባይኖርም በአንዳንድ የቅንጅት አመራሮች እና ቤተሰባቸው ዘንድ ተጵእኖ እንዳሳደረ ሰምቻለሁ። በሌላም በኩል እንደ አንዱአለም አራጌ ያሉ አመራሮች ውሳኔውን ከመቄብ ባለመቁጠር ይቅርታ ለመጠየቅ እንዳስቸገሩ በተባራሪ ሰምተናል።

ዞሮ ዞሮ ህውሀት የገባበት አጣብቂኝ የኢትዬጲያ ሚሊኒየም የፈጠረው መልካም አጋጣሚ መፍትሔ ሊያገኝ ቻለ። ይህን አስመልክቶ አቶ በረከት በጳፈውና የህውሀትን ገድል በሚያሳየው መጵሀፋ ገጵ 233 ላይ እንደሚከተለው አስፍሮ እንመለከታለን፣

” …የፍርድ ሂደቱ ነጳ መሆን በግልፅ መታየቱና መንግስት የቅንጅት መሪዎች የተከሰሱባቸውን ወንጀሎች ከበቂ በላይ በማስረጃ አቅርቦ በማረጋገጡ ህብረተሰቡ የሰዎቹን ጥፋተኝነት በጥያቄ ውስጥ የሚጥልበት አልነበረም። በመሆኑም መንግስት በህዝቡ የቀረበው የይፈቱ ጥያቄ ፣ ማንኛውም ህዝብ በአርቆ አስተዋይነቱ የሚያደርገው… እኔ መርጬ ለእስር አበቃኃቸው ከሚል የህሊና ፀፀት ነጳ ለመውጣት በመፈለግ ያቀረበው ጥያቄ እንደሆነ ተገንዝቧል። ለዚህ አይነቱ የህዝብ ጥያቄ በጐ ምላሽ መስጠት ምንግዜም ቢሆን ግዴታው እንደሆነ የሚገነዘበው መንግስት፣ ጥያቄው የህግ የበላይነት ለድርድር ሳያቀርብ ሊመለስ እንደሚችል አምኗል። እናም በአንድ በኩል የህግ የበላይነትን እያስከበረ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝብን የይፈቱ ጥያቄ ለማስተናገድ የሚችልበትን ሁኔታ ማማተር ነበረበት። በዚህ አኳኃን ነው የኢትዬጲያ ሚሌኒየም ራሱን እንደ መልካም አጋጣሚ የከሰተው” ይለናል።

እንግዲህ ከዚህ ልምድ በመነሳት የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጣቸው። ውሳኔውን መሰረት በማድረግ እስከ ሀያ አመት የሚደርስ እስራት ተፈረደባቸው። ይህ ለመጥራት የሚዘገንን ቁጥር የተበየነበት ምክንያት ታሳሪዎችን ለማስደንገጥ እና ወደ ይቅርታ ሂደቱ በፍጥነት እንዲገቡ ታስቦ እንደሆነ በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል። አንድ ግጥም አቅርበሀል የተባለ ወጣት የተፈረደበትን አመት ለተመለከተ ደግሞ በህውሀት የተጠነሰሰውን ሴራ ለመገንዘብ የእነሱን ያክል ማሰብ ከቻለ በቂው ይሆናል።

ይሁን እንጂ ይህ “የይቅርታ ይደረግልን” ሴራ ቅንጅት ላይ እንደሰራው በሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎቹ ላይ የሚሰራ አይደለም። ሲጀመር የመጀመሪያዉ ፓለቲካዊ፣ የአሁኑ ደግሞ ሀይማኖታዊ ነጳነትን በግንባር ቀደምትነት ያስቀመጠ በመሆኑ በባህሪ የተለያዩ ናቸው። ርግጥ ፓለቲካዊ መብቶች ባልተከበረበት ሀይማኖታዊ መብቶች ይከበራሉ ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ቢሆንም። ከዚህም በተጨማሪ የሀይማኖታዊ ነጳነታዊ ጥያቄዎች ለድርድር የመቅረብ እድላቸው እጅግ ጠባብ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው።

ከላይ የተቀመጠውን ከግምት በመውሰድ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴው አባላት አጥፍተናል እና ይቅርታ ይደረግልን የሚሉ ከሆነ እስከዛሬ ያነሷቸው ሶስት ጥያቄዎች ( ለጊዜው የማውቃቸው) ትክክል አልነበሩም፣ አሊያም ምላሽ አግኝተዋል የሚል እንድምታ ይኖረዋል። ይህም የህውሀትን ድል አድራጊነት ከማረጋገጥ ባሻገር የኢትዬጲያ ሙስሊሞችን የሶስት አመት ትግል ውሀ ይቸልስበታል። ወደ ኃላ የመመለስና በቀላሉ የመክሰም እድል ያጋጥመዋል። የኮሚቴዎቹ አባላት ይህን በመገንዘብ ይመስላል አስደንጋጩ ብይን ሲሠጣቸው ያለምንም መደናገጥ የትግል ጵናታቸውን ለማሳየት የቻሉት። ቤተሰቦቻቸውም ቢሆን የኮሚቴው አባላት እየከፈሉ ያሉት መስዋእትነት ለሀይማኖታቸው ነጳነት መሆኑን በመገንዘብ ከጐናቸው የቆሙት።

ስለዚህ እነዚህ የኮሚቴ አባላት እንደ ቡድን የይቅርታ ጥያቄ ያቀርባሉ ብሎ ማሰብ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደመውጣት ይሆናል። በግለሰብ ደረጃ በተለያዩ ምክንያቶች የይቅርታ ሂደት ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ቢሆንም። ይህ አማራጭ ዝግ ሆነ ማለት ህውሀት መራሹ አዲሱ መንግስት ዝም ብሎ ይቀመጣል ማለት አይደለም። በሁኔታዎች አስገዳጅነት ያለ ይቅርታ ጥያቄ ምህረት የማድረግ ግን ደግሞ በፍርድ ቤት እንዲወሰን ያደረገውን የህዝብ እንቅስቃሴ ገደብ ያለማንሳት ሊኖር ይችላል። ይህም ኮሚቴዎቹን በአይነ ቁራኛ በመከታተል የቁም እስረኛ ወደ ማድረግ መሸጋገር ይሆናል። ይህም ቢሆን ለገዥው ቡድን የሚያመጣለት አንዳችም ፓለቲካዊ ትርፍ አይኖረውም።

ግራም ነፈሰ ቀኝ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ የአላማ ጵናት ለአዲሱ የህውሀት መራሹ መንግስት የእግር እሳት እንደሆነ ይቀጥላል። የኢትዬጲያ ሙስሊሞች የነጳነት ትግልም በኢትዬጲያ ታሪክ ውስጥ የሚኖረውን የላቀ ደረጃ እንደጠበቀ ይኖራል!…”መውጫ መንገድ ያሳጣ ሰላማዊ ትግል” ይሉሀል ይህ ነው!!

የሰላም ትግሉ በኢትዮጵያ (መዝጊያ) –አንዱዓለም ተፈራ –የእስከመቼ አዘጋጅ

$
0
0

ረቡዕ፤ ሰኔ ፲ ቀን፤ ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህቱረት ( 6/17/2015 )

እንዴት ትግሉን በትክክል ወደ ፊት ማስኬድ ይቻላል?
eskemecheበመጀመሪያ ደረጃ ሁላችን መረዳት ያለብን፤ ይህ ትግል በአምባገነኑ ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ብቻ ነው። ይህ መነሻና መድረሻ ተደርጎ መወሰድ አለበት። አሁን ሁላችንንም ወጥሮ የያዘን፤ ትግሉን ለምን በአንድነት፤ የሀገራችን የነፃነት ትግል አናደርገውም? የሚለው ጥያቄ ነው። አንዳችን ከሌላችን የተለየ አመለካከት ስለያዝን ብቻ፤ በመካከላችን ጠላትነት ነግሦ፤ “አንተ ወያኔ ነህ!” የሚል ወፍ ዘራሽ ውንጀላ አስቀድሞ መወርወር ትክክል አይደለም። በመደማመጥ በውይይት ሊፈታ የሚችለውን የሃሳብ ልዩነት፤ እንደ የፖለቲካ ውጊያ አድርጎ መበጣጠሱ ጎድቶናል። የተለያየ ሃሳብ ይዞ፤ በሚስማሙበት አብሮ መስራት ይቻላል። የግድ በሁሉም ነገር ሁላችን መስማማት የለብንም። ይህ መሠረታዊ የዴሞክራሲን ሀ ሁ የተቀበሉ ሁሉ የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ታዲያ ለምንድን ነው በመካከላችን መግባባት ያልቻልነው? የዛሬው የማጠቃለያ ጽሑፍ የሚያተኩረው፤ በመካከላችን መግባባትን እንዴት መፍጠር እንችላለን? ምንስ ብናደርግ ትግሉን ወደፊት ማስኬድ እንችላለን? ካለንበት የምስቅልቅል ሀቅ ወጥተን ወደፊት ለመሄድ ከየት እንጀምር? ለሚሉት መልስ በመሥጠት፤ ትክክለኛ አስተባባሪና አስተማማኝ መፍትሔ አቅርቦ፤ ትግሉ በትክክል እንዲመራና ወደ ሕዝባዊ ድሉ ጉዟችን እንዲያቀና መጋበዝ ላይ ነው።

ትግል ወደው የሚገቡበት ክስተት አይደለም። ትግል የሙያ መስክ አይደለም። ትግል ግድ ብሎ የሚመጣ የኅብረተሰብ ክንውን ነው። የአንድ ሀገር ነዋሪዎች፤ በሀገራቸው ያለው ሥርዓት “ትክክለኛ አይደለም!” “ከመስመር ወጥቷል!” ብለው ሲነሱና የሥርዓቱ አራማጅ እንጃላችሁ ሲል፤ ሕዝቡ በእምቢታ ሲነሳ፤ ሕዝባዊ ትግል ነው። ይህ ደግሞ ሁሌ የሚደረግና ለአንዳንዶቹ የሙያ ዘርፍ ሆኖላቸው የሚከርሙበት መኖሪያ አይደለም። በአንድ የታሪክ አጋጣሚ የሚከሰት ነው። አሁን ሀገራችን ላለችበት ሁኔታና ታጋዮች ላለንበት ሀቅ፤ በቂ ምክንያት አለ። ምክንያቱን መርምረን ማግኘት አለብን። ሌሎችን ለዚህ ምክንያት ተጠያቂ ማድረጉ አግባብነት የለውም። ያንን ምክንያት የፈጠርነውና አስተካክለንም ወደፊት መሄድ የምንችለው፤ እኛው ነን። ለየብቻችን መፍትሔ ፈላጊዎች ብቻ ሳንሆን፤ ለየብቻችን ተግባሪዎቹም በመሆን በየበኩላችን ሩጫ ይዘናል። ለምን? ይህ የሀገራችን የሁላችን ጉዳይ አይደለም! ታዲያ ለምን በአንድነት የምንዘምትበትን መንገድ አንፈልግም። በመካከላችን ያለው፤ የትግሉን መንገድ በሚመለከት ያለ ልዩነት አይደለም። በኔ አመለካከት፤ ያሉትን ልዩነቶች በሶስት ከፍዬ አስቀምጭቸዋለሁ።

የመጀመሪያውና ዋናው ማጠንጠኛ፤ የትግሉን መሠረታዊ ምንነት በሚመለከት ያለው ልዩነት ነው። ይህ የትግሉን ሂደት ቅደም ተከተል በሚመለከት የተወሰነ አይደለም። ይህ መሠረታዊ የሆነውን ለምን እንደምንታገል የሚደነግገውን ጉዳይ የሚመለከት ነው። “በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሀቅ ምንድን ነው?” የሚለውን መመለሱ ላይ ነው። ለዚህ የሚሠጠው መልስ ወሳኝ ነው። ከዚህ ተነስቶ ነው የትግሉ እጅና እግር የሚታወቀው። በሀገራችን ምን ዓይነት ሥርዓት አለ? ምን ዓይነት የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ ያቀነቅናል። የዚህ ሥርዓት ጉዳቱ ምንድን ነው? የሥርዓቱስ ባለቤት ማነው? በዚህ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ይላል? የት ነው የምንቆመው? ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ወይንስ ከአምባገነኑ ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ጋር? እዚህ ላይ፤ ትግሉ የዴሞክራሲ ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚደረግ ሩጫ አይደለም። ትግሉ የነፃነት ጥያቄ ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎችን ምርጫ አይደለም የያዝነው። ሁለት ሰፈሮች ብቻ ነው ያሉት። አንደኛው የአምባገነኑ ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሲሆን ሌላው የሕዝቡ ሰፈር ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ሆኖ ነው፤ አምባገነኑን ወገንተኛ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር እምቢ ያለው። ስለዚህ አንድ ኢትዮጵያዊነት ብለን፣ አንድ ወገናችን ብለን፣ አንድ ሀገራችን ብለን፣ አንድ ትግል ብለን መነሳት አለብን።

ሁለተኛው ደግሞ፤ የሀገርን ጉዳይ ለድርጅቶች ኃላፊነቱን መሥጠቱ ላይ ነው። ትግሉን አሽከርካሪዎች ድርጅቶች ናቸው ብለን፤ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ኃላፊነቱን በነሱ ላይ ጥለናል። ሀገሪቱ እኮ ለተደራጁት ብቻ አይደለችም። ለሁላችንም እኩል ነች። ታዲያ ኃላፊነቱን ሁላችን እኩል መካፈል የለብንም? በርግጥ በድርጅት የተሰባሰቡ ሰዎች ጠርቀም ያለ ጉልበት አላቸው። እናም ቅድሚያ ይሰለፋሉ። ይህ ማለት ግን፤ ኃላፊነቱ የነሱና የነሱ ብቻ ነው ማለት አይደለም። ይልቁንም በሀገራችን ላይ ባለው ሀቅ፤ ቅድሚያ መስለፉን ዘንግተውታል። እናም በየድርጅቶቻቸው መርኀ-ግብር ተቆልፈው፤ ከመጠጋጋት ይልቅ መራራቁን መርጠው፤ ከመፍትሔ ይልቅ የችግሩ አካል ሆነዋል። ስለዚህ፤ ኃላፊነቱ በሌሎች፤ ማለትም በግለሰብ ባለነው ሀገር ወዳዶች ላይ ተጥሏል። ለሀገር መታገልና ለድርጅት መታገል አንድ አይደለም። በርግጥ ትግል ሳይደራጁ አይካሄድም። ያ ድርጅት ደግሞ ትግሉ ምን ዓይነት መስመር እየተከተልን መሆናችንን ይናገራል። ለድርጅት መታገል ማለት፤ ድርጅትን መነሻና መድረሻ አድርጎ፣ የኔ ድርጅት ትክክለኛ ስለሆነ፤ በኔ ድርጅት ብቻ ተመርታችሁ ትግሉን ቀጥሉ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ማስተላለፍ ነው። በርግጥ ይሄ በብዙ የተለያየ የሚመስል ነገር፤ ነገር ግን መሠረቱ አንድ በሆነ መልክ ይከሰታል። መሠረቱ ደግሞ፤ ለግል ማስብና ለሀገር ማሰብ በሚለው መካከል ያለው ልዩነት ነው። የያዝነው ትግል የግል ትግል አይደለም። የሀገር፣ የነፃነት ትግል ነው።

ሶስተኛውና ማጠቃለያው፤ መፍትሔውን በሚመለከት ያለው ልዩነት ነው። አንድ ሀገር፣ አንድ ኢትዮጵያዊነት፣ አንድ ትግል ብለን ከተነሳን፤ የአንድነቱ ትግል ዋናና አማራጭ የሌለው ነው። አንድነትን ከግል የተግባር እርምጃ ማስቀደም አለብን። አዎ! ትግሉ ተጀምሯል። ሰዎች በተለያየ የትግል መስክና ሁኔታ ከገዥው ቡድን ጋር እየተፋለሙ ናቸው። ነገር ግን ትግሉ ትክክለኛ ስኬት እንዲኖረው መቀጠል ያለበት፤ ከዓላማ ጋር ተቆራኝቶ እንዲቀርብ ሲደረግ ነው። ግቡ አንድነትን የሚመሠርት፣ አስተማማኝ የሆነና፤ ሁሉን ለአንድ ዓላማ አሰባስቦ የሚያታግል እንዲሆን፤ አንድነቱ አሁኑኑ፤ ባለንበት ደረጃ ቅድሚያ ሊሠጠው ይገባል። ይህ ማለት፤ አንድ ሳንሆን የተያዘው ትግል አደጋው ከፍተኛ ስለሆነ፤ ታጋዮች በየደረሱበት የትግላቸው ሂደት፤ ከሌሎች ጋር እንዲሆን ማድረግ ነው። ይህ ግድ የሚለው፤ የሚከተለውን አደጋ ተረድተው፤ የያዙትን ትግል ለአንድነቱ እንዲገዛ አድርው፤ ድሉንም ሆነ ጉዳቱን ለአንድነቱ እንዲያስረክቡ ነው። ይህ ማለት፤ በመሰባሰብ ለሚመሠረተው የአንድነት ድርጅት፤ ሙሉ ተገዥ ሆኖ፤ በሙሉ ልብ በኢትዮጵያዊነት መምጣት ነው። በተደጋጋሚ የተገለጹትን የትግሉ ራዕይና መታገያ ዕሴቶች በመቀበል ወይንም አስፈላጊ የሆኑ ማሻሻያዎችን በማድረግ፤ አንድ ድርጅት፣ አንድ ትግል፣ አንዲት ኢትዮጵያ፣ አንድ ኢትዮጵያዊነት ብሎ መነሳት ነው። መታገያ ዕሴቶቻችን የሚከተሉት ናቸው፤

፩ኛ.   በኢትዮጵያዊነታችን አንድ ነን። በሀገራችን፤ በኢትዮጵያዊነታችን  የፖለቲካ ተሳትፏችን እናደርጋለን።

፪ኛ.   ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ ዳር ድንበሯን አስጠብቀን ለኛው ለኢትዮጵያዊያን እናደርጋታለን።

፫ኛ.   በሀገራችን በኢትዮጵያ፤ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን እናደርጋለን።

፬ኛ.   በኢትዮጵያዊነታችን የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችንን እናስከብራለን።

እንግዲህ ከላይ ያሉትን ሶስት ነጥቦች ትኩረት ሠጥተናቸው፤ በቁጥር ፩, ፪, ፫ ትና ፬ የሰፈሩትን መታገያ ዕሴቶች አንግበን፤እና አሁን ያለንበትን የያንዳንዳችንን ሁኔታ ራሳችን መርምረን፤ በግለ ሰብ ደረጃ፤ እኔ በኢትዮጵያዊነቴ ምን ማድረግ እችላለሁ? የሚለውን እኔ በኢትዮጵያዊነቴ ምን ማድረግ አለብኝ? ከሚለው ጋር አቆራኝተን፤ መሰባሰብ አለብን። በድጋሜ፤ እያንዳንዱ ድርጅት የያዘው የራሱን ድርጅት ትግል አንጂ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ትግል አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነት ትግል የሚካሄደው በኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ነው። እናም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድነት የነፃነት ትግል ጥረት እናድርግ። የዚያ አካል እንሁን። ይሄን በሚመለከት ለመተባበር ዝግጁ የሆናችሁ ጥሩኝ፤ ወይንም ወደኔ መልዕከት በመላክ ቅረቡ። የዚህ ትግል ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ፤ አንድ ግለሰብ ወይንም አንድ ድርጅት አይደለም።

eske.meche@yahoo.com   http://nigatu.wordpress.com

“ሀገር የተቀማ ትውልድ” የተሰኘው የዳንኤል ተፈራ መጽሐፍ እየተነበበ ነው

$
0
0

ሀገር የተቀማ ትውልድ እየተነበበ ነው

……………

10982923_1628074940797036_6567925336806387860_nሰሞኑን በዳንኤል ተፈራ ተፅፎ ለገበያ የቀረበው ‹‹ሀገር የተቀማ ትውልድ›› የተሰኘው ወጥ የሆነ የፖለቲካ መፅሐፍ እየተነበበ መሆኑን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡

እንደምንጮቻችን ገለፃ ወጣቱ ደራሲ፣ አርታኢና ፖለቲከኛ ዳንኤል ተፈራ በአጠቃላይ ለአንባቢ ያደረሳቸው መፅሐፎች ሦስት ሲሆኑ ስድስት ለሚሆኑ የፖለቲካ መፅሐፎችም የአርትኦት ስራ ሰርቷል፡፡ ሰሞኑን ገበያ ላይ ውሎ እየተነበበ ካለው ‹‹ሀገር የተቀማ ትውልድ›› ከሚለው መፅሐፉ በፊት እጅግ ተነባቢ የሆኑ ሁለት መፅሐፎችን ለአንባቢያን እንዳደረሰም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የደራሲው ቀዳሚ ስራ በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት እና በኋላም የተቃውሞ ጎራው መሪ የነበሩትን ዕውቅ ሰው ዶ/ር ነጋሶ ጎዳዳ ሶለንን የህይወት ታሪክ የሚዳስስ ‹‹ዳንዲ- የነጋሶ መንገድ›› የተሰኘው ነው፡፡ ይሄ መፅሐፍ በ2003 ዓ.ም ለህትመት የበቃ ሲሆን በአንድ ሳምንት ብቻ ሃያ ሺ ኮፒ በመሸጥ ተወዳጅነትን ያተረፈ ነው፡፡ ከዚያ በኋላም ለአራት ጊዜ እንደታተመ ደራሲው አረጋግጧል፡፡ ደራሲው እንደሚገልጠው መጽሐፉ 384 ገፆችና አምስት ንዑስ ክፍሎች ያሉት ሲሆን የዶክተሩን ከልጅነት እስከ ዕውቀት እንዲሁም የፖለቲካ ታሪካቸውን ያካተተ ነው፡፡ መፅሐፉን ለማዘጋጀት አመት ከሶስት ወር እንደፈጀ ደራሲው ይናገራል፡፡

Daniel Tefera

ዳንኤል ተፈራ

ቀጣዩ የዳንኤል ስራ ከ1997 ዓ.ም በኋላ በፓርላማ አባልነታቸው በከፍተኛ ተከራካሪ በነበሩት የተከበሩ አቶ ተመስገን ዘውዴ የፖለቲካ ህይወትና እንዲሁም በፓርላማው ውስጥ ሕወሃት/ኢህአዴግ ሲፈፅም የነበረውን ሸፍጥ ያጋለጡበት ‹‹ከፓርላማው በስተጀርባ›› የተሰኘው መፅሀፉ መሆኑን ለዘጋቢያችን ተናግሯል፡፡

ሰሞኑን ገበያ ላይ የዋለው ‹‹ሀገር የተቀማ ትውልድ›› ደግሞ የፀሃፊው ወጥ የፖለቲካ ስራ ሲሆን 224 ገፅ ያለው ነው፡፡ መፅሐፉ በ27 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን በዋናነት በዘመነ ኢህአዴግ ወጣቱ ትውልድ እንዴት የሀገር ፍቅር እንዲያጣ እንደተገረገና ሀገር አልባ ለማድረግ የተከናወኑ የፖለቲካ ሸፍጦችን የሚተርክ መፅሐፍ ነው፡፡ ደራሲው እንደገለፀው፡- ‹‹ስርዓቱን በአሽከርነት ካላገለገልክ እጣ ፈንታህ ሃገር መቀማት ነው፡፡ ‹‹ሃገር ማለት ሰው ነው!›› ይሉሃል እንጂ ሃገር ኢህአዴግ ሆኗል፡፡ ኢህአዴግ ካልሆንክ ስራ አይኖርህም፣ ኮንዶሚንየም አይደርስህም፣ መነገድ አይፈቀድልህም፣ ደመወዝ አይጨመርልህም፣ ጡረታ አይከበርልህም፣ የትምህርት እድል አይሰጥህም፣ በነፃነት መወዳደርና ጨረታ ማሸነፍ አያስችልህም፡፡ ይህ ማለት ሃገር ተቀምተሃል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ለመፃፍና ትውልዱ ሀገር እንዲቀማ የሰሩ፣ የቀሙ፣ ያስቀሙ፣ ያቀማሙና የተቀሙትን ታሪክ በማንሳት ሀገር ይረከባል የሚባለው ትውልድ እንዲነቃቃና የሀገር ባለቤት እንዲሆን በማሰብ የተፃፈ ነው በማለት ሀሳቡን ገልጧል፡፡


ነጻነታችን በእጃችን፣ ህወሃትን ካልተገረሰሰ እስሩም ግድያውም ይቀጥላል!

$
0
0

ተስፋዬ ነጋ (ዋሽንግተን፣ ዲሲ)

habitamuዛሬ እነሆ እነ ሀምታሙ አያሌው፣ ዳኤል ሽበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋና፣ አብርሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ የወያኔ ፍርድ ቤት ወስኗል የሚል ዜና ሰማሁ። እንኳንም በውሸት ክስ የታሰሩት ወደየቤተሰቦቻቸው በሰላም ተቀላቀሉ። ከሚወዱት ቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ እጅግ ደስ የሚል ስሜት ይፈጥራል። የቤተሰቦቻቸውን ናፍቆታቸውን በአግባቡ እንዲያጣጥሙ ምኞቴ ነው። እውነት መጨረሻ ላይ እውነት ሆና መውጣቷ አይቀርም፣ ይኸው እውነት ነጻ አወጣቻቸው።

የሆኖው ሆኖ እነዚህ ወጣቶች ከመጀመሪያውም መታሰር አልነበረባቸውም። በወንጀል ደም ተጨማልቀው የሚዋዥቁ አረመኔዎች አልነበሩም። ለአገራቸውና ለህዝባቸው ከፍተኛ ራዕይ የሰነቁ ንጹህ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፣ አሁንም ንጹሃን ናቸው። ወያኔዎች ሰላማዊ ዜጎችን በማሰር የፖለቲካ ትርፍ እናገኛለን ብለው ቢያስቡም፣ የእነአብርሃ ደስታ መታሰር የህወሃትን ድንቁርና ከማጋለጥ ውጭ በተቃዋሚው ወገን ላይ ያመጣው አሉታዊ ተፅዕኖ የለም። እንዲያውም ተቃዋሚዎች የትግሉን ዳራ በጥልቅ እንዲመረምሩና የወደፊቱን የትግል አቅጣጫ በጥንቃቄ እንዲቀይሱ አደረጋቸው እንጂ! የታሳሪዎችን ንጹህነት ደግሞ ህወሃቶችም (እዉነትና ውሸት የማያገናዝቡ ሆዳም ካድሬዎችም ጭምር) በሚገባ የሚመሰክሩ ይመስለኛል፣ ያው የሞት ሽረት ነገር ሆኖባቸው  ቢያስሯቸውም! የህወሃት ሰዎች ለስልጣናቸው የሚያሰጋቸውን ሁሉ በሃሰት ክስ ከመወንጀል ተቆጥበው አያውቁም፣ እነዚሁ ፖለቲከኛ ወጣቶች በምሳሌነት ሊቀርቡ ይችላሉ፣ የእስሩ ገፈት ቀማሾች ዞን 9ኞችም ሌሎች ሰለባዎች ናቸው። ተመስገን ደሳለኝ፣ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙ፣ ውብሸት ታዬ የፈሪው ህወሃት የሃሰት ፍርድ በትር ተጎጂዎች ናቸው። የህወሃት መንግስት በውሸት የተካነ፣ የፈጠራ ክስ ጸሃፈ-ተውኔት እንደሆነ የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። ህወሃቶች ተቃዋሚ የመሰላቸውን ሁሉ በፈለጉ ጊዜ ሲያስሩ፣ በፈለጉ ጊዜ ሲፈቱ ኖረዋል፣ ጠንከር ያለ ተቃውሞ ሲመጣ ከመግደል ወደኋላ አይመለሱም። ህወሃት በ1996 ዓም ሰላማዊ ሰልፈኞችንና ህጻናትን ሳይቀር በጠራራ ጸሃይ በካሊበር ጥይት በሳስቶ ገሏቸዋል። ወደፊትም የፈጠራ ክስ ማቀናበር፣ ማሰር፣ መፍታት፣ መግደል፣ ስራቸው ሆኖ ይቀጥላል።

ሕወሃት ሁለት መገለጫዎች አሉት። የመጀመሪያው የጦር ሃይሉን በመተማመን፣ በጉልበት ስልጣን ላይ እንደተቆናጠጠ ዘላለም እገዛለሁ ብሎ ማሰቡ ነው። የመሳሪያ ባለቤት በመሆኑ፣ የተቃወመኝን እያሰርኩ፣ ጠላቴን እየገደልኩ፣ እንዲሁም ከተቃውሞ የማይታቀበውን እያስፈራራሁ ለረጅም ጊዜ እኖራለሁ ብሎ ያምናል። እዉነትም ህወሃት በከፊል ትክክል ነበር፣ በጉልበት እያስፈራራ፣ እያሰረ፣ እየገደለ ለ25 አመታት ያለምንም ችግር ዘልቋል። ከራሱ ከህወሃት የተፈጠሩ የጦር መኮንኖችን ብቻ ስልጣን ላይ አስቀምጦ፣ በሙስና እንዲዘፈቁ በማበረታታትና፣ የሚያማልል ስጦታ በመስጠት፣ እንዲሁም እነዚሁን የጦር መኮንኖች የወንጀል ተባባሪና መሪ በማድረግ የ”አብረን እንዝለቅ” ጨዋታ ተክኖበታል። ሁሉንም የጦር መኮንኖች ከአንድ ብሄር ብቻ በመሾም፣ ለተቃዋሚ እንዳያደሉ “ከካዳችሁን በጦር ወንጀለኝነት ትፈለጋላችሁ፣ የትግራይን ህዝብ ታስጨርሳላችሁ” በሚል ሰንካላ ማስፈራሪያ ከሌላው የኢትዮጵያዊ ጋር እንዳይነናኙና እንዳይተባበሩ አድርገዋቸዋል።

ሁለተኛው የህወሃት መገለጫ ደግሞ ከመንግስት ባለስልጣናት ያውም ከሚኒስትሮች የማይጠበቁ ዘረኝነት፣ ስግብግብነት፣ ውሸትና፣ የሞራል ዝቅጠት ነው። አብዛኞቹ ባለስልጣናት በዘረኝነት ዛር የሰከሩ ወፈፌዎች ናቸው። የራሳቸውን ብሄር “ወርቅ” በማለት የሚያሞካሹ፣ ሌላውን ብሄረሰብ ግን “ትምክህተኛ፣ አክራሪ፣ ብሄርተኛ” የሚል ታፔላ በመለጠፍ በጅምላ የሚሳደቡ [የራሳቸውን ቃል ልጠቀምና] “ወራዳ” ናቸው። በተለይም ለአማራና ለኦሮሞ ብሄረሰቦች ከፍተኛ ጥላቻ ያላቸውና በካድሬዎቻቸው አማካኝነት እስከዛሬ ድረስ አርሶ አደር ገበሬዎችን በማፈናቀል የተካኑ በክፋት ሃሴት የሚዝናኑ ናቸው።።

አቶ መለስና የህወሃት ባለስልጣናት ዋና ዋና መስሪያ ቤቶችን፣ ወታደራዊ ተቋማትን፣ የገንዘብ ተቋማትን፣ የፖለቲካ ተቋማትን፣ የማህበራዊ አገልግሎት ድርጅቶችን በብቸኝነት በመቆጣጠር ለግላቸው ስልጣን ማስረዘሚያና ኪስ ማድለቢያ ማድረጋቸው አሌ የማይባል ሃቅ ነው። ዛሬም የአየር መንገድን፣ የኮንስትራክሽንና የንግድ ድርጅቶችን፣ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን፣ የውጭ ንግድንና የአገር ውስጥ ገቢን፣ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን፣ ብሄራዊ ባንክን መብራት ሃይልንና ቴሌኮም የመሳሰሉትን ዋና ዋና ተቋማትን ምንም ሃፍረት ሳይሰማቸው ከአንድ ብሄር በተውጣጡ ቡድኖች ቁጥጥር ስር በማድረግ፣ ወይም ደግሞ “ታኮ” ከመጋረጃ ጀርባ በማስቀመጥ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል። ከላይ እንደተገለጸው የትግራይ ተወላጅ ሃላፊዎችን በሙስና እንዲዘፈቁ በማድረግ፣ ወይም ሙስና ውስጥ ሲዘፈቁ አይቶ እንዳላዩ ሆኖ በማለፍ፣ በመፍቀድና፣  በማበረታታት የመንግስት ለውጥ ቢታሰብ እንኳን ከተቃዋሚው ጋር ተባባሪ እንዳይሆኑ የማስፈራሪያ ሪሞት ኮንትሮል ገጥመውላቸዋል።  ይህ ስግብግብ ባህርያቸው እንቆረቆርለታለን ለሚሉት ለትግራይ ህዝብም እንቆቅልሽ እንደሆነ ነው የሚሰማው። በጦርነቱ ወቅት የትግራይ ህዝብ እነዚህን ግፈኞችን የደገፋቸው ታጋዮቹ እንዲህ አይነት የግለኝነት እና የአምባገነንነት ባህርይ ይኖራቸዋል ብሎ ሳይገነዘብ ነበር። የትግራይ ህዝብ የህወሃት ባለስልጣናት በጊዜው የደገፋቸው ዛሬ ለራሳቸው እልል ያለ ቪላ ቤት እንዲሰሩ፣ ለራሳቸው እጅግ ውብና ውድ መኪና እንዲገዙ፣ ከድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ጉሮሮ በመንጠቅና በውጭ አገር በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለግላቸው እንዲያስቀምጡ አልነበረም። ለስልጣናቸው ሲሉ የሃውዜንን ምስኪን ህዝብ በአውሮፕላን ያስጨፈጨፉ እጅግ እኩይ ሰዎች ናቸው። አቶ መለስ ሞት ባይገላግላቸው ኖሮ ከ22 አመት በኋላም ቢሆን ስልጣናቸውን ለመልቀቅ፣ ተተኪም ለማዘጋጀት ፈቃደኛ አልነበሩም።

የህወሃት ባለስልጣናት የራሳቸው ኪስ ስለደለበ ብቻ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የደላው ስለሚመስላቸው የውሸት የእድገት ቁጥር ጨዋታ ያቀርባሉ። እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ከ22 አመታት በኋላም ቢሆን ከችግር፣ ረሃብና፣ እርዛት ኣልተላቀቀም። የህወሃት ባለስልጣናት ግን ገንዘብ ተርፏቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወደ ውጭ አገር እያሸሹ እንደሆነ አለም የሚያውቀው ሃቅ ነው። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ይኸው ከ 24 አመት የስልጣን ጊዜ በኋላም ከ24 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን እርዳታ ይፈልጋሉ። የህወሃት ሰዎች ግን ሌላ መልስ አላቸው። ኢትዮጵያ፣ ከካሊፎርኒያ፣ ወይም ከአውስትራሊያ በተለየ መልኩ ድርቅ አልጎዳትም። እኔ ግን ለእነዚህ ሰዎች ጥያቄ አለኝ። በየትኛው ስሌት ነው የካሊፎርኒያና የአውስትራልያ ድርቅ ከኢትዮጵያ ድርቅ ጋር የሚወዳደረው? በካሊፎርኒያ በድርቅ ሳቢያ የተራበ ሰው የለም። አውስትራሊያም ቢሆን በድርቅ የተነሳ እርዳታ የሚቀበል ሰው የለም። እኛም ጋ በድርቅ ሳቢያ የተራበ ሰው የለም ሊሉን ይሆን? ካሊፎርኒያም ይሁን አውስትራሊያ በድርቅ ምክንያት የቤት እንስሳት አልሞቱም፥ አዝርዕት አልተበላሸም። ቢሆንም በቂ ክምችት አላቸው። የእኛስ?  በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ አርብቶ አደር ወይም ገበሬ ነው፥ ያውም ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ምርት የሚያመርት ወይም ከእንስሳት ተዋጽኦ ተጠቃሚ። አዝርዕቱ ከደረቀ፣ ከብቶቹ ከሞቱበት ምን ይሆናል? አቶ ሃይለማሪያም የህወሃት የትሮይ ፈረስ ሆነው እንጂ ይህንን ከመናገራቸው በፊት ሊያስቡበት ይገባ ነበር። ውድድሩን ከማድረጋቸው በፊት የካሊፎርኒያስ ድርቅ ምን ይመስላል? የአውስትራሊያስ? የውሃ አጠቃቀማችንስ እንዴት ነው? የቁም እንስሳት አያያዛችንስ ምን ይመስላል? የሚለውን ሃሳብ እንኳን የማያገናዝቡ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በጭብጨባ በታጀበ መግለጫ አፋቸውን ሞልተው ሶስቱን አገሮች (?) በአንድ ሚዛን ሲለኩ ሰማሁ።  የህወሃት የትሮይ ፈረስ ማለት እኚህ ናቸው። ህወሃቶች የሚፈልጉትን ሁሉ በእሳቸው ተመስለው የሚፈልጉትን መልዕክት ያስተላልፋሉ፣ እውነታው ግን ሌላ ነው። አቶ ሬድዋንም ቢሆኑ ያው “አርብቶአደሮቹ በጊዜው ውሃ ስላላጠጧቸው ነው ከብቶቹ ያለቁት” አሉ። አጃኢብ ነው! ከባለቤቱ በላይ ያወቀ ቡዳ ነው ይባል የለ! ጋዜጣዊ መግለጫውን የባዮሎጂ ክፍለጊዜ አስመሰሉት እኮ!

የህወሃት አሽከሮችና ጭፍሮቻቸው በምግብ ራሳችንን ችለናል የሚል ልፈፋ ሲያሰሙ ከርመው ነበር። የታል ታዲያ? እርግጥ ነው የህወሃት ባለስልጣናት ኪስ በ11 ሚሊዮን % አድጓል። የህዝቡ ኑሮ ግን 1% እንኳን ከፍ አላላም። እርግጥ ነው በህወሃት መንደር እና ሎሌዎቻቸው ቤት ምግብ ተትረፍርፏል፣ በሱማሌ፣ በአፋርና፣ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች፣ የገበሬዎች የቤት እንስሳትና የቀንድ ከብቶች ተረፍርፈዋል።

በጣም የሚገርመው የህወሃት ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አይነት የፖለቲካ ግንዛቤ የለውም ብለው ማሰባቸው ነው። ያኔ ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በኋላ አቶ ስዩም መስፍን ባድመ ለኢትዮጵያ ተሰጠች ብለው አስጨፈሩን፣ በኋላ ስንሰማ ግን የጨፈርነው በሞት ለገበርናቸው ወንድሞቻችን ደም ላይ ነበር!

ሌላው ህወሃት ኢትዮጵያ ውስጥ በማህበረሰባችን በነውርነት የሚታወቀው የውሸት ልማድ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው። ትውልድ ከእነዚህ መሃይማን ምን ይማራል? የህወሃት ቁልፍ የበላይ ሃላፊዎች ድርጀቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀመሮ በሸፍጥ፣ በመግደል፣ በማሳደድ፣ በማሰር፣ በማሸማቀቅ እዚህ ለመድረስ በቅተዋል። በህልማቸው እንኳን አስበውት የማያውቁትን ሃብት አካብተዋል፣ አቅማቸው የማይፈቅድላቸውን ስራ ሰርተዋል፣ በማይመጥናቸው ወንበር ተቀምጠዋል፣ ታዛዥ መሆን ሲኖርባቸው በተገላቢጦሽ አዛዥ ሆነዋል። ከሁሉም በላይ ይቅርታ የማያስደርግ ወንጀል ውስጥ ተዘፍቀዋል። 100% የፓርላማና የአካባቢ ምርጫ አሸነፍን ብለዋል። ከህወሃት በላይ ጀግና የለም፣ አገሪቷን ከፈለግን እንደዶሮ ብልት ገነጣጥለን እንሄዳለን ብለዋል፥ አፍርሰን እንሰራለንም ብለዋል… ሌላም ሌላም።

የህወሃት ሰዎች የተከበሩ ተቋማትን አዋርደዋል። በአገራችን ውስጥ ለረጅም ጊዜ የተከበረው ሽምግልና በነፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ አማካኝነት   ፈሩን ስቶ ገደል ገብቷል። ፍርድ ቤቶች የህወሃት የፖለቲካ መሳሪያ በመሆን በንጽሃን ላይ የውሸት ክስ በመመስረት ታሪክ ይቅር የማይለውን ፍርድ አስተላልፈዋል። በተለይም ወጣቶቹ የሚሰሩበትን የወጣትነት ጊዜያቸውን በግፍ በወህኒ ቤትና እንዲያሳልፉ በውሸት ክስ ከአሸባሪዎች ጋር በማያያዝ አስረዋቸው፣ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፈተዋቸዋል። ለምሳሌ የዞን 9 ጦማሪያን በአሸባሪነት ክስ ተከሰው በወህኒ ቤት ከአንድ አመት በላይ ሲማቅቁ ቆይተው ፕሬዚደንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ያለምንም የፍርድ ቤት ሂደት ፈተዋቸዋል። እንግዲህ ህወሃቶች ለስልጣናቸው ሊያሰጋቸው የሚችል ሰው ባይሆንም እንኳን ለሆድ የማይደለል ተቃዋሚ ወይም ጋዜጠኛ ባጋጠማቸው ቁጥር በመጀመሪያ ማስፈራራትና ማሰር፣ ካልሆነም መግደል ለአስርተ-አመታት የተካኑበት አሳዛኝ ድራማ ነው። እናም በኢትዮጵያ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ በውሸት ፖለቲካዊ ክስ ተፈርዶባቸው የሚማቅቁ ኢትዮጵያውያንን ማዕካላዊ፣ ቂሊንጦ፣ ዝዋይ፣ ሸዋሮቢት፣ እና ስማቸው የማይታወቁት የጨለማ እስርቤቶች ይቁጠሯቸው!

እንግዲህ ምርጫ በመጣ ቁጥር ተቃዋሚዎችን እያደኑ ማሰር ምርጫው ካለፈ በኋላ እንደገና መልሶ መፍታት የተነቃበት የህወሃት ታክቲክ ከሆነ ሰነባብቷል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ጋዜጠኞችን ሰሞኑን የተፈቱበት ሁኔታም ይኸው ነው። ወቅቱ ስለተቀየረ፣ ተፈተዋል። በሌላ ወቅት ደግሞ እነሱን ብቻም ሳይሆኑ ሌሎች ወጣቶች እንዲሁ ዘብጥያ መውረዳቸው አይቀርም። ሀብታሙ አያሌው፣ ዳኤል ሽበሽ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሸዋስ አሰፋ፣ አብሃም ሰለሞን ሲፈቱ ሌሎች ባለሳምንት ደግሞ በቅርቡ ይገባሉ። እነዚህ ፖለቲከኞች አሁን የተፈቱበት ምክንያት የጦዘውን ፖለቲካዊ ተቃውሞ ለማቀዝቀዝ ይሆናል። ሰሞኑን ህወሃት ከባድ ፈተና ገጥሞታል። በአንድ በኩል ከልዕለ-ሃያላን ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶታል። በሌላ መልኩ ደግሞ ህወሃት ለማድረግ የፈለገው አንድ ነገር ይኖራል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ድል ገንኖ መውጣት የመጀመሪያው ሲሆን፣ በኤርትራ በኩል የሚመጣውን ማንኛውንም ሃይል ለመምታት ያኮረፈውን የኢትዮጵያ ህዝብ “5 የፖለቲካ እስረኞችን” በመፍታት መካስ ይፈልጋል። በመሆኑም እነዚህን የተፈቱት የፖለቲካ እስረኞች ለኢትዮጵያ ህዝብ የቀረቡ የእርቅ ገጸበረከቶች መሆናቸው ነው።

በአሁኑ ሰአት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ይህ የህወሃት መንግስት በሰላማዊ መንገድ ስልጣን እንደማይለቅ በጥብቅ ያምናል። በሌላ በኩል በጉልበት ስልጣን ላይ የወጣ እና በሙስና በአንድ ዘር የበላይነት የነገሰ “መንግስት” በምንም መልኩ አሁን ያለውን ጥቅሙንና ክብሩን ለመልቀቅ አይፈልግም። የራሱን ህልውና ሊያጠፋ የሚችል ነገር  በምንም መልክ ይሆን ማዳፈን የመጀመሪያ ስራው ነው። በመሆኑም ትናንሽ መደለያዎችን በማቅረብ ህዝቡን ለማታለል መሞከር ከፍተኛ ጅልነት ነው።  አቶ ሃይለማሪያም እንዳሉት፣ “የኢትዮጵያ ህዝብን ፈቃድ ጠይቀን ከኤርትራ ጋር ጦርነት እንገጥማለን” የሚል ጨዋታ ከዚህ በኋላ ሰሚ ጆሮ የለውም። ኣንደከዚህ በፊቱ ህዝቡ ሆ ብሎ ሻዕቢያን (አሁን ደግሞ  አርበኞች ግንቦት ሰባትን) ለመደምሰስ በነቂስ ይወጣል ብለው ማሰባቸው ምን ያክል ህዝቡን እንደናቁት ያሳያል።

አሁን የጨዋታው ህግ ተቀይሯል። እንደከዚህ በፊቱ ሆ የሚወጣላቸው ተቃዋሚ ወይም ህዝብ አይኖርም። ህወሃሃት የራሷን አባላት ይዛ መዝመት ተችላለች። የአባላቱ ቁጥር ስንት ነበር? 7 ሚሊዮን? አዎ ሰባት ሚሊዮን አባል ለዘመቻ ብቻ ሳይሆን አገር ለመመስረትም በቂ ነው። 85 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብን ግን ይተውት! አይሆንም! ህዝቡ ጠላቶቹና አሸባሪዎቹ እነማን እንደሆኑ አብጠርጥሮ ስለሚያውቅ ከሁለት አስርተ አመታት በላይ ሲያሸብሩ የኖሩ ወያኔዎች ላይ አፈሙዙን ማዞሩ አይቀርም። አዎ! ህወሃት የአየር ሰአቷን አሟጥጣ ጨርሳለች። የተወሰኑ ሰዎችን በመፍታት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘትና ስልጣናቸውን በጦርነት ለማስረዘም መሞከር በፊት አዋጥቷቸው ይሆናል፣ ለሁለተኛ ጊዜ ግን አያዋጣም። ህዝቡ ነቄ ብሏል፥ ህወሃት እስረኞችን ስለፈታች ተለውጣለች ማለት እንዳይደለ በደንብ ተገንዝቧል። ነገ ደግሞ ሌሎችን ማሰሯ እንደማይቀር ከልምድ የተማረው ህዝብ የህወሃትን ልብና ኩላሊት በደንብ መርምሯል።

ስለዚህ መቀየር ያለበት የህወሃት ሶፍትዌር ነው። አርጅቷል። በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት የዘረኝነት፣ የአምባገነንነት፣ የማን አለብኝ ባይነት፣ አድሏዊና የቂመኝነት አስተሳሰብ ይዞ አገርን የሚያክል ግዙፍ ነገር መምራት አይቻልም። ስለሆነም በአዲስ አሰተሳሰብ መቀየር አለበት። ከአርባ አመት ከፊት በነበረ ሶፍትዌር አሁንም አገር እየመሩ ያሉ ቡድኖች መፍረስ አለባቸው። ያ የሚሆነ ደግሞ የህወሃት ዘረኞችን ከስልጣን በማባረር ነው። ትግል መደረግ ያለበት ከሻቢያ ወይም ከግንቦት ሰባት ጋር አይደለም ፣ ከወያኔ ጋር ነው። ወያኔ ከተለወጠ ዘላቂ ሰላም ያመጣል፣ የሚገደል፣ በውሸት ክስ የሚታሰር አይኖርም። ከሁሉም በላይ ውሸት የሚፈበርክ ተቋም አይኖርም!

 

ሥህነ-ቤዛ! ቅኝተ-ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 21.08.2015 /ሲወዘርላንድ –  ዙሪክ/

„ … በሀገሬ ውስጥ በነፃነት መኖር የሰው ልጅነቴ መለኪያ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህን የሚከለክለኝን ማንኛውም ኃይል ከመቃወምና የምችለውን ከማድረግ ወደኋላ አልልም። ይህን ሳደርግ የሚመጣውን ዕዳ ተቀብዬ ነው።“ የሞት ፍርድ በወያኔ  ሃርነት ትግራይ ዘራዊ አስተዳደር የተፈረደበት ዬአርበኛ ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ – ቃል።

ምዕራፍ – ሦስት፤

Birhanu nega asmera erእንዴት ናችሁ የሐገሬ ልጆች?! ደህና ናችሁ ወይ? በጨለመ የጥላቻ ዋሻ ውስጥ ተሁኖ ተጫባጭ እውነትን ማዬት አይቻልም። ባለገርዶሹን የጥላቻ ጥቁር ዋሻ በመደርመስ ብቻ ፀሐይ ትወጣለች። ጸሐይዋ ስትወጣ ይነጋል – የጥነት ሆነ የቅናት ቅጥም – ይራገፋል።

የማከብራችሁ – ባለፈው ጊዜ ክፍል ሁለትን በዚህ ነበር የቋጨሁት፤

„ለእኛ ቁርባናችን – ታቦታችን – ጸሎታችንስግደታችንሳላታችንየወልዮሽ የባህል ዝክረ ነገራችንየሃይማኖት ማዕዳችን – ቤተ አምልኳችን ንግሥት ኢትዮጵያ ናት። ለነፃነት ፍላጎታችን ማደሪያ የተመረጠው ደግሞ ሥህነ – ቤዛ ነው። እሱ የእርቅ ጉባኤን ከአድማስ ወዲህና ባሻገር መሳላል – የሥርዬት መክሊት መገናኛ መርከባችን አንባችን – ነው።“

ከብሄራዊ ፍላጎት ጋር መፈጠር – አነባቢ (Vowel።)

ኢትዮጵያዊነትን አሳምሮ ይተርጉመዋል – አናባቢ (Vowel) ስለሆነ፤ ሥህነ – ቤዛ ኢትዮጵያዊነትን አደላድሎ – የማመሳጠር አቅሙ በውስጥነት ውስጡ አድርጎ ነው።

አናባቢ ከሌላ ተነባቢ ቃል አይኖርም። (BCDFGHJK) (ሀለመሰሸቀበተ) አናባቢ ባይኖር ዬዓለም የማድመጫ ዓይኖች እውር በሆኑ ነበር። የኑሮም የማሰቢያ ጭንቅላቱ ትንፋሽ አልቦሽ ግዑዝ በሆነ ነበር። ወንጌላዊው ዮኋንስ „በመጀመሪያ ቃል ነበረ። ቃልም በእግዚአብሄር ዘንድ ነበረ፣ ቃልም እግዚአብሄር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሄር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፣ ከሆነውም አንዳችስ ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። በእርሱ ሕይወት ነበረች፣ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። ብርሃንም በጨለማ ይበራል፣ ጨላማም አላሸነፈውም። ዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 1 ከቁጥር 1 እስከ 5“ ሲል ያስተማረው የቃልን ህይወት የመፈጠር ሆነ የመነበብን ሚስጢር በመኖር ሲያመሳጥልርን ነው። ያ ቃል ነው ዓለምን፣ ሰማይና ምድርን፣ ህይወት ያላቸውንና የሌላቸውን የፈጠረ። ስለዚህ ለእኔ የኢትዮጵያዊነት ዜግነትን ታማኝ ህዋስ ጥልቅ ሚስጢሩን ተነባቢም – አናባቢም ሆኖ በመገኘት እረገድ ሥህነ – ቤዛ ቤተኛነቱ በመሆን ያከበረ ህብራዊ ቃል – ኢትዮጵያዊ ቋንቋ መሆኑን በጥልቀት – አስተውዬበታለሁ። እንዲህ በተዋርድንበትና በተናቅንበት ዘመን በ እውቀት ላይ የተመሠረተ ንጥር ሁለገብ ብቃቱ – መካሻ! ይህም ብቻ ሳይሆን የሀገሩ የኢትዮጵያ ሁለመና ባለትርጉም መምህር መሆኑንም በሚገባ በጥልቀት – ተርድቻለሁ። መነሻው ኢትዮጵያ መድረሻው ኢትዮጵያ፤ እንዲያውም አለፍ ብሎ አፍሪካንም! ኢትዮጵያ ተኮር ዝንባሌውን እና የአፍሪካዊ ፓለቲካዊ ችግሮች በሚመለከት „ዬአፍሪካ ቀንድ የውይይት ፕሮግራምን“ በአሜሪካን ሀገር በኒዎርክ ከተማ በመስራችነትና በንቁ ተሳትፎ ለአምስት ተካተታይ ዓመት ያደረጋቸው፤ የአዲስ ዓለም ራዕይ የቀደምቶች መንገድ የተከተለ፣ የፓን አፍሪካንዚም ንድፍ ተግባራዊነት – የተመነ መሆኑን ያመሳክራል። በአሜሪካን ሀገር ፊላደልፊያ ላይም „ኢንቢልታ“ መጽሄት  የእናቱን ሐገሩን ሁለንትና ችግር ለመጋራት ውስጥነቱን ያሳዬበት መድረክ ነበር። ስለዚህም ጎጥ ላይ ያልተቀረቀረው ውድ ሰብዕናው ፈተናውን በአጥጋቢ ውጤት አልፏል!

በፅሞና በቂ ጊዜ ወስጄ ያለፈባቸውን ሂደቶች፣ ውስጡን የገለጸበት መንገዶችን – በተደሞ፣ ከመሬት ሰቅ ላይ በትክክሉ ሆኜ በአራቱም ማዕዘን በአንክሮ ሁሉን ተመክሮዎቹን  – መረመርኳቸው፤ ከኢትዮጵያ ህዝብ ወላዊ ብሄራዊ ጸጋ ሆነ ማዕከላዊ አጀንዳ ማዕቀፍ የወጣበት አንዲት ዬነቁጥ ግድፈት – አላገኘሁበትም። ስለዚህም በተለይ ዬአዲስ አዕምሮ ብቁ ሰለዴ ባለቤቶች የሆናችሁ የእኔ ወጣቶቼ /ጌቶቼና ልዕልቶቼ/ መምህራቸውን ይከተሉ ዘንድ ተግቼ በዚህ ዙሪያ መሥራት እንዳለብኝ – ወስኛለሁ። ግዴታዬም ነው። ለእኔ ነገ ነግቶ – ታይቶኛልና። በአርበኝነት ግንባር ላይ ሆነ በማናቸውም ሁኔታ ያሉት ወገኖቼ ቢሆኑ ሥጦታቸውን ያከብሩት ዘንድ አብክሬ በአፅህኖት ላስገነዝባቸው – እወዳለሁ። ሥህነ – ቤዛ ወላፈኑ በግራ በቀኝ  የበዛበት ምክንያቱን እኔ ሳዳምጠው የመዳኛችን ፈውስ መንገድን በመምረጡ ነው። በመልካም ነገሮች ዙሪያ ፈተናው – መጠራቅቁ ያዬለ፣ መንገዱም እጅግ ጠባብ ነው፤ ሲያልፉት ግን ገነት! ሁልጊዜም በግል ህይወት ሆነ በማህበራዊ ህይወት፤ እንዲሁም በፖለቲካ ይሆን በሃይማኖታዊ አቋም፤ በተጨማሪም በሙያዊ መብትና ግዴታም ዙሪያ ቢሆን በተዕቅቦ የሰከኑ ሥነ – ምግባሮች ተፈታታኝ ወይንም ተቀናቃኝ መንፈሶች አዘውትረው ወጆቦችን – ያበራክቱባቸዋል። ስለምን? እራሳቸውን መሆን ዬቻሉ ብስል ወገኖች ያልተገቡትን ሥነ -ምግባሮች – ስለማያስጠጉ፣ ፊትም ስለማይሰጡ። ጥንቃቄያቸው ብልሃት – ዘለቅ፣ ዓላማቸው ስልት – ቀደም፤ ሥልጣኔያቸው መርህ – ገብ ስለሚሆን አውሎው ያዬለ ነው። ቀናዎች ወይንም የአዎንታ አርበኛ መንፈሶች ሥነ – ድንግልና በመንደርተኝነት ዕሳቤ ወይንም በአስተሳሰብ ድህነት ለማስገሰስ ስለማይፈቅዱ። የሰብዕናቸው ሁለንትናው ፀ ———-አዳ፤

ዬመንትዮሹ መስተጋብራዊ ውህድ መንፈስ ከእኛ የሚጠብቀው ብሄራዊ ግዴታ።

የአናባቢነት ውህድ መንፈስ የመንገድ ጠራጊው ዬድርጁው የጀግና አንዳርጋቸው ጽጌ መንፈስ የማያንቃላፋ የማይሞት ስለመሆኑ በፍቅር በመስተጋብር ያዋድዱት ዘንድም በትህትና  – ለቅኖቹ ዝቅ ብዬ አሳስባለሁ። ወጣቶችና ቅንነት ያልነጠፈባቸው ወገኖቼ በራሱ የተማመነ ማስተዋልን እንዲፈቅዱለት – አሳስባቸዋለሁ። ከዚህ ላይ ብልህነትን የሚጠይቅ ብሄራዊና ወቅታዊ ግዴታ አለብን። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ዬጀግናው አንዳርጋቸው ፅጌ የህዝብ ፍቅር መንፈስ ገናናነት „እራቁት¡“ ለማድረግ በቅናት ድብን ብሎ ስለ አበደ፤ የለመደበትን ዬስውር ደባ ሥራ ማስኬጃ የሆነውን የአቶ መብራቱ ገ/ህይወት ወይንም በበርሃ ሥማቸው የአቶ በረከት ስዕሞንን እውር ራዕይ፤ ቹቻን ተንትርሶ የተዘጋጀውን የኑዛዜ በድን ድምጽ አመድ ማድረግ የቅድሚያ ተግባራችን ሊሆን ይገባል። ይህም ማለት በፈላስማው አንዳርጋቸው ፅጌ ሥም ይወጣል የተባለውን መጸሐፍ ዬኢትዮጵውያንን ክብራችን ገፎ ለውርዴት የዳረገን፤ በእስር ቤት እንኳን ብትን አፈር የነፈገን ሥርዓትን „በቃኝ“ ከምንልባቸው ጉልበታም እርምጃዎች ቀዳሚው በመሆኑ፤ ይህ ደባ የታሪካችን ውርዴም ስለሆነ – አዲሱን የለበጣ ሴራ የበቀል ማዋራረጃ መጸሐፉ ነውና፤ ከገብያ ውጪ በማድረግ የመጋዝን እራት እንዲሆን ቁጣችን – ፀፀታችን – እልሃችን – ቁጭታችን አቅማችነን በማጥገብ „አንገዛውም“ በማለት ተግባር ላይ እንገኝ ዘንድ እንደ አንድ ኢትዮጵያው ዜጋ ጥሪዬን – በአክብሮት አቀርባለሁ። እስኪ ልዬው፣ እስኪ ልፈትሸው ብለን ውርዴታችን በገንዘብ በመሸመት የንጹህ መንፈሳችን ቤተኛ እንዳናድርገው! በነፃ ህወሓት ቢያድለው እንኳን – እንዳናስጠጋው። ያን የጀግና መንፈስ ስቃይ እንዴትስ – አንገዛዋለን? ያ የድብደባ የወገኞቻችን የስቃይ ዬጩኽት መንፈስን በራችን ከፍተን ቤት ለእንግዳ እንዴትስ እንለዋለን?፤! የዛ ዬኢትዮጵያዊነት የማንነታችን ሰቆቃ ረስተን መጸሐፉን ብንገዛው ለብሄራዊ ዕንባችን ድፍረትም ንቀትም ነው። ቢያንስ በገንዘባችን ሀገራዊ ወኔን ሁነኛችን እናድርገው! ይህ ለይደር የሚቀጠር አይደለም። „ቁርጥ ያጠግባል“ ቁርጣቸውን ማሳወቅ – በተባ እርምጃ። ከእነሱ ጋር ሆነ ከጄሌዎቻችው ጋር እራሱን ላልቻለ ጥገኛ መንፈስ ህብረትም ትብብርም ሊኖረን አይገባም። እራሱን ችሎ የቆመ ብቁ ርቁቅ ሥልጡን – ቅዱስ – መሪ መንፈስ አለን- እኛ! የምን ብድር የምን ውሰት – ለባንዳነት ————-?~!

ክብረቶቼ – ኢትዮጵያዊነታችን እምናበለጽገው ቢያንስ በእጃችን በሚገኘው ሙሉ አቅም፣ በተጻራሪ የቆመውን መንፈስ ቅስሙን ለመስበር አሁኑን ተግባርን ስንውጥ ብቻ ይሆናል። „በቃን!“ ቃሉ እራሱ ሁለገብ ነው። የህወሓት ጠረን ሁሉ ድብዛውን ለማጥፋት መዶሻችን ነው „በቃን!“ እርግጥ ነው አካ – ደጅጠኝ – ፍርፋሪ ለቃሚ – እፎዎ መንፈሶች ዝቅ ብለው ለአራጃቸው – ያረግሩ ዝል መንፈሳቸውን – ይገበሩ፣ ድብድባ የወጣውን የበታችነታቸውንም –  ያቆላምጡ። እኛ ግን ደማችን ውርደትን – ባርነትን – የበታችነትን፤ ሥነ – ልቦናዊ ቅኝ ተገዢነትን ይጸዬፈዋልና ልዩ ቃናችን ኢትዮጵዊነታችነን ድርጊት እናስታጥቀው። ዛሬ እስር ቤት ውስጥ የዱካ ማስቀመጫ ብትን አፈር ቦታ ተነፍጎል፤ አንድ ጆሮውም አይሰማም የጀግናችን ዬጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ አካል የሌለው አገልጋይ ቃለ ወንጌል ሳይቀር ፈቃድ ተነስቶ አባ ትርጉም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መንፈሱን ጉስቁል ለማድረግ፤ በሥነ ልቦናው እዬትዘናኑ እዬተሳለቁ ይገኛሉ – አራዊቶች፤ ዛሬ የአርበኛ አበበ ካሴ ጥፍር በግፍ ተነቅሎ የመክራ ዝክረ ሙዚዬም እየሆነ ነው፤ የእመቤቴ የጀግኒት ዬወይንዬ ሞላ ማህጸንስ ነገ ፍሬ ያበቅል ይሆን? በካቴና ቃለ ምልስስ ላይ ያዬነው የአርበኛ አቡበክርስ – ዛሬ የወንጀል ቅጥረኞችን በእስር ቤት በማሰማራት ማገዶውን አንዱአለም አራጌን ያስደበድባሉ – ለነፃነት የቁም ሰማዕትነት። ሌሎችንም፤  ምን ዬማያደርጉት አለና …. ምን የማይሰማ መራራ ዜና አለና፤  ይህን መጸሐፍ ከገዛን እኛ ስቃዩን እንደ ፈጸምን አንደ ፋሽስንትም እንደ ተባበርን ያስቆጥራል።

ስለ እስር ቤት ካነሳሁ ትንሽ ምራቂ ነገር ልበል። ወላጅ እናቴ ምህርት ጠይቃ በተሰጠኝ ምህረት የጫካ ኑሮዬን ትቼ አንድገባ አደረገችኝ። እውነት ለመናገርም የግንኙነቴ መስመሩ ስለተቋረጥ ሎጅስቲኩ ሆነ ሁሉ ነገር ከባድ ስለሆነ ግድም ነበር። በምህረት ከገባሁ በኋላ ግን ጎንደር ባታ እስር ቤት ታሰርኩኝ። ሰው በምህረት ገብቶ እንዴት ይታሠራል?! በቬርሙዳ ትርያንግል ሥርአት እኮ ነው ህወሓት የሚመራው። ስፈታ ደግሞ ያን ጊዜ ብዙ ነው በ50000 የኢትዮጵያ ብር ዋስ በቁም እስር ነበር። መንፈሴም አካሌም ሥነ – ልቦናዬም ታስሮ። ዋሴንም የተከበሩ ሸሕ ሲራጅን ሊያስቀምጧቸው ስላልቻሉ ሀገራቸውን – ለቀቁላቸው። ቅብም ቢሆን ፍርድ ቤት፣ ክስ፣ ምስክር የሚበላው በመዲናችን አዲስ አባባ ላይ ብቻ ነው የሚሠራው። የዛሬን ባላውቅም ያን ጊዜ ከክ/ ሀገር ጀምሮ እስከ ነጥብ ጣቢያ አንድ የህወሓት ባለዘር ሜዳሊያ ባለጊዜ ካድሬ ያሰረውን፤ አስተውሉ ወገኖቼ አሳሪው ሀገር ቢለቅ ወይንም ቢሞት ወይንም ከድርጅቱ ቢባረር ሌላው – አይፈታውም። እዛው ተረጅቶ ሞት ብቻ ይጠብቀዋል – ወገናችን። ሌላው ማጣሪያ የሚባለው ነገር ደግሞ የላሜ ወለደች ዓይነት ነው። የእስረኞች ሥም ዝርዝር በከተማ የህዝብ አደባባዮች – ይለጠፋል። በፈለገው ዓይነት በቂም፤ በቅናት፤ በክፋት አንድ ሰው ከጠቆመ ያ እስረኛ መፈቻ የለውም። ምርመራው ደግሞ ታሥራችሁ ልማዳችሁን አንድታቀኑ መገደድ ነው። ግራ እኮ ናቸው። የቬርሙዳ ትርያንግሉ ሥርዓተ አራዊት እንዲህ ነው። በፍጹም ሁኔታ በክ/ሀገርና ከዛ በታች ያሉ የእስረኛ አያያዝ ሁኔታ ከአዲስ አባባ ጋር መወዳደር ቀርቶ – አይቀራረብም። ዓይነቱም ይዘቱም የተለዬ ጭፍን ሸጎሬ ነው። ድፍን ታውቃላችሁን?!

ሚስጢር ዘለቁ – ነገረ ኢትዮጵያዊነት፤

ያደለው ከሚስጢሩ ጋር መፈጠሩ ብቻ ሳይሆን በቁምነገር አብሮ ይኖራል። ነገረ ኢትዮጵያ የሚስጢራት ሁሉ የሥነ – ፍጥረት ሁሉ ነፍስ ነው። ኢትዮጵያዊነት የገድላት – ሩኽ ነው። ኢትዮጵያዊነት የፍጥረት – ህሊና ሥነ – ምግባር ነው። ኢትዮጵያዊነት የጸሎት መንፈስ ነው። ይመራል – ያስተዳድራል፤ ስናጠፋ – ይመክራል ብቁ መካር ነውና። ስናኮርፈው ያቆላምጣል – ሩህሩህ ነው፤ ህጉን አብዝተን ስንተላለፍ ደግሞ ቆንጠጥ አድርጎ – ይገስጻል፤ ስንዳፈረውም ይፈራዳል – ይቀጣል። ዳኝነቱ ሚዛናዊ ከመሆኑ በላይ ራሱን የቻለ ተቋም ነው – ህሊና ላለው፤ ዜግነቱ ውስጡ ለሆነ ሁሉ መዕዋለ ህይወቱ ት/ቤት ነውና – ያስተምራል።

የአትዮጵያዊነት ሥነ – ህግጋቱ የመሆን መቻል ሰማይና ምድር ናቸው። ገሃዱ ዓለም እና መንፈሳዊውን ዓለም ያስማማ በትረ – ዓምድ፤ በፍቅር እያዋዛ ያዋደደ የዘመናት የተደሞ አናት ነው – ኢትዮጵያዊነት። ኢትዮጵያዊነት የቀለሞች ሁሉ አዲስ ቀለም ነው። ኢትዮጵያዊነት የነገዎች ሁሉ አዲስ ቀን ነው። ኢትዮጵያዊነት ሲፈጠር ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ የሚስጢር ሊቀ – ሊቃውንት ነው። ኢትዮጵያዊነት እንደ ወንዝ ዳር ዕጽዋት በጋ ከክረምት፤ መኸር ከጸደይ እዬለመለመ እያሸተ የሚሄድ፤ እርጅና ከቶውንም ዝር የማይልበት ሁልጊዜ ለሁለመና በነፋሻማ ጤናማ አዬር የሚጎበኝ የጤና ፍውሰት ነው። ሙቅ የሆነው ወጣት ፍቅሩ ከቶም አይጠገብም። ቋሚ መንፈሱ ትጉኽ ገበሬ ነው፤ ማራኪ አቀራረቡ በቁሙ የጸደቀ የሁሉዬ በመሆን እኩላዊ፣ ራስነትን የፈቀደ ነው።

ኢትዮጵያዊነት ከኩራት በላይ መኩሪያ፤ ከጋሻ በላይ መከታ፤ ከጥላ በላይ መጠለያ፤ ከመቻል በላይ መቻቻል፤ ከማክበር በላይ መክበር፤ ከማድመጥ በላይ መደመጥ፤ ከሚስጢር በላይ መመሳጠር፤ ከታማኝነት በላይ ታማኝ፤ ከትህትና በላይ ትሁት፤ ከፍቅር በላይ ፍቅራዊነት (Loveism)፤ ከትእግስት በላይ ታጋሽነት፤ ከአብሮነት በላይ ዬአብሮዊነት ልዕልና ነው። ኢትዮጵያዊነት በራስ የመተማመን የደም ማህተም ነው። የነጠረው መንፈሱ ቅኝ ተገዝቶ በፍጹም – አያውቅምና። እራሱን ሆኖ የኖረ ብቻም ሳይሆን ሌላውንም በውስጡ ያኖረ የአደራ ትውፊት ነው። የእኔ የሚለው – ሁሉ ያለው፤ ሁሉንም – የሆነ፤ ለሁሉም ለመሆን የሚችል – ኩን የመኖር ሥነ – ደንብ ነው – ኢትዮጵያዊነት። ተዝቆ የማያልቀው መክሊቱ የፈለቀው ከእውነት ማህደር ብቻ ነውና። ተመርቆ የተፈጠረ በመሆኑ አስተዳደራዊ ሆነ ጣልቃ ገቢያዊ ፈተና አያጣውም፤ ግን ተቀናቃኙን ድል የመንሳት ተስጥዖው ደግሞ ገድላማ ነው። ዬኢትዮጵያዊነት ድፍረቱ የሚቀደው ከምንጩ ከአለው ረቂቅ ጸጋው – ከራሱ ነው። አለው! ትውስት ክፍሉ አይደለም፤

በሌላ በኩል ኢትዮጵያዊነት ለመንፈስ የርትህ ብሩኽ የችሎት አደባባይ ነው። ኢትዮጵያዊነት በተፈጥሮው የዳኝነት ውሎ ነው። ኢትዮጵያ ሀገራችን ህግ ናት። የተፃፈውም ሆነ ያልተጻፈው ህጓ እሷን ለዬት ብላ፤ እኛ ልጆቿም ኢትዮጵያውያንን ለዬት ብለን ኑሯችን እንድናስተዳድር ይመራል። በኢትዮጵያ ማህጸን ውስጥ የተፈጠረው ኢትዮጵያዊነት አማናዊው ሲሆን በክርስትና እምነት ከዘመነ ብሉያት በፊት በህገ ልቦና አምላኩን የተቀበለ፤ ሃዲስ ኪዳንንም የወደደ ዬፈርኃ እግዚአብሄር ማማ ሲሆን፤ ዬእስልምናም ሃይማኖትን በሚመለከትም፣ ታሪክን የቀደመ፣ የሐዋርያነት ተግባር የፈጸመ የተግባር አንቱ ጉልላት ነው። ለኢትዮጵያዊነት ሃይማኖት አለኝ፤ እማመልከው አምላክ አለኝ ብሎ ማመን ርስተ – ጉልቱ ነው። ተፈጥሮው ነው ማለት ይቻላል። እርግጥ ነው በተፈጥሮ የሚያምኑትንም የራሱን አካላትንም – አይጋፋም። ሳሃ የሌለበት ሥልጡኑ ማንነት – ኢትዮጵያዊነት!

ኢትዮጵያዊነት በግጭቶች ማህል እንኳን ዬስምምነትን ስበት የመወለድ አቅሙ ከጸሐይ ጉልበት በላይ ነው። ኢትዮጵያዊነት ሥርዬት ፈላጊነቱ  የመልካም ነገሮች ዓውደ ምህረት እንዲሆን – አድርጎታል። ኢትዮጵያዊነት ነብያትን ቀድሞ ያናገረ፤ ሳይንቲስትን የመራ፤ ቅዱሳንና የፈጠረና ከተለያዩ የዓለም ክፍላት ሰማዕታትን ደናግላንን ሐዋርያትን ሳይቀር በብቃቱ ዬጠራ፤ በብልህነት ያስተናገደ – የገሃዱ ዓለምና የመንፈሳውው ዓለም  ፍጹማዊ ዬመርኽ  የአብርኃሙ ማዕዶት ነው።

ኢትዮጵያዊነት ጠላቱን የሚያስተምረው ምክንያት ፈልጎ ነው። በዬአጋጣሚዎች እሱን ለማጥቃት የሚነሱትን የዶግ አመድ የሚያደርግበት አቅሙ የሚቀዳው ከሰማዩ ዳኛ ነው። እንሆ የወያኔ ሃርነት ትግራይን በ40 ዓመት ህይወቱ ሉሲ ድንቅነሽን አስቀድሞ  ዕውቅና አሰጥቶ፤ ህወሓት በተኛ በ40 ዓመቱ ከእንቅልፉ የቀሰቀሰ፤ የማያልቅ ወይንም የማይቋረጥ ትኩስ ዬአቮል ቡና ፏፏቴ ነው። የማንቃት መዳህኒት በመዳፉ ያለው፤ ቅንኛ – ቀና – ቅኔኛም። ወንዳታ! ዛሬ በጠላቱ በህወሓት መንፈስ አስለፍልፍን አስርፆ ነጋ ጠባ „ኢትዮጵያዊነት፤ ሐገራችን፤ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን“ እያሰኜ ጠላቶቹ በፖሊሲ ያሰሩትን፤ ገድለን ቀብረነዋል ያሉትን ቅዱስ መንፈስ በልሳናቸው ሲቃጁ ውለው እንዲያድሩ ያደረገ የጀግኖች ቁንጮ፤ አንበሳ ነው ኢትዮጵያዊነት!  የመሆን የትጋት – የንጋት ገበሬ!

አዬ! ዓፄ  ዘመን እንዴትና እንዴት አድርገህ ነው ኢትዮጵያዊነት – የምትከሰው! ብርሃኑ ሲነጋ  በሃቅ – ታታመ። በእንቁላል ውሃ ተገናባ። ዬማግስትነት ክብሩ – ታወጀ። ዘመን ተናገረ – ያደመጠውን በሐዋርያነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ልቅና ዓለም መሰከረ ….. ሲፈጠር ከብሄራዊ ፍላጎት ጋር የሆነው ሥህነ – ቤዛችንም እንኳን ደስ አለህ። ትጋትህ ከጥዋቱ ለዚህ ልቅና ነበር፤ … ለጋ ዕድሜህን ለበርሃ የሸለምከው። ዝንፍ ሳትልም በዞግ ንክኪ ከቶውንም ሳትጠመድ በማተብህ የጸናኽው፤ በተማሪዎች ንቅናቄ ውስጥ ብሄራዊ ፍላጎትን ዕውን ለማድረግ አፍላነትህን – የሰጠኽው። ጉልምስናህንም ለሀገርህ ለኢትዮጵያ እንደ ዘመኑ እድገትና ብልጽግና በነፃነትና በዴሞክራሲ አሰራር ያለህን እምነት ውስጥህ በማድረግ፤ የናፈቀህን ዴሞክራሲ ርትህ ዕውን አንዲሆን፤ የምትፈልገውን የእኩልነት ምድር እናትህን ለማድረግ ወደ ኋላ የማትል የኢትዮጵያ ዘላቂ ልጅ። ለአንዲት ሰከንድ በእምስ ዬመንደርተኛነት አጀንዳ ጊዜህን ያለባከንክ የልዕልት ኢትዮጵያ የተቋማት – ምርጥ ተስፋ። …. ኢትዮጵያዊነት ህግህ ያደረክ፤ ለኢትዮጵያዊነት ፍጹም ታማኝ የሆንክ የአዮ ትሩፋት …

ውድ ታዳሚዎቼ – በምዕራፍ ሁለት ጹሑፌ ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ ሚስጢር ነው ብያለሁ። ስለምን?  ሚስጢር መሆኑ ስለተገለጠለት። ስደት ሽርሽርሽር አይደለም፤ ፈተናው ያላችሁበት ነውና – ታውቁታላችሁ። ሁለተኛ ዜግነት መውሰድ – የስደቱን ውሃ ያዘለ ተራራ ለመሸከም፤ ጊዜያዊ ሆነ ዘላቂ ችግር መፍቻ የሚሆኑ ቁልፎችን ለማግኘት፤ ወይንም ቤተሰብ ከተመሰረተ በኋላ በስደቱ መንደር ዬልጆችን የተስፋ ትልም ለማሳካት፤ ቤተሰባዊ ኑሮን በአንድ ለማድረግ፤ ረቂቅና ወስብስብ ፈተናን ለማሸነፍ፤ ባይታዋርነትን ከግንባር ገፋ ለማድረግ ግድ የሚሉ ነገሮች – ይገጥማሉ። ባትወዱትም – ባትፈልጉትም። በማናቸውም ሁኔታ ይህን እርምጃ መወስድን አስፈላጊ የሚያደርጉ የተጽዕኖ ምሽጎች በዬአቅጣጫው ጦርነት – ይከፍታሉ። ታዲያ ትውልደ ኢትዮጵያዊነትን እንደያዙ በተደራቢነት ችግርን ለማስተጋስ ወይንም ለማሸነፍ ወይንም መንፈስን ለመረጋጋት እርምጃው ይወሰዳል – ዬተጨማሪ ዜግነት። ይህ ወንጀል አይደለም። የታህሳስ 10. 1948 ዓለምአቀፍ የሰብዕዊ መብት አስከባሪ ህግ „አንቀጽ 15 እንዲህ ሲል መብት ስለመሆኑ በአጽህኖት – ደንግጎታል።

  1. እያንዳንዱ ሰው የዜግነት መብት አለው።
  2. ማንም ሰው ያለፍርድ ዜግነቱ አይወሰድበትም፤ ወይንም ዜግነቱን የመለወጥ መብት አይነፈገውም“። ስደትና መከራውን – በስደት ያለፈ ሁሉ ስለምን ሁለተኛ ዜግነት መውሰድ እንዳለበት፤ ወሳኝና አስፈላጊ እንደሆነ – ይገነዘበዋል።

ወገኖቼ – ይህን ነጥብ ነጥዬ ማንሳት የፈለግኩት መሰረታዊ ምክንያት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን  „ኢትዮጵያዊነትን አግላይ“ የሚል ተቀናቃኝ ተቀጥላ ሃሳብ ጎልቶ ስለወጣ ነው፤ ያን ከሥሩ የፈለሰ ሃሳብን በተጨበጠ ዕውነትን fact አቅርቤ እርባና ቢሱን፣ የፋደሰ ከንቱ የላመ አጀንዳ መቅበርም – ስላልብኝ ነው። በሌላ በኩልም ሚስጢር ከሚስጢሩ ጋር ስለመኖሩ የጭብጥ አቅም ያነሳቸው ትችቶች በተያያዥነት ስለ ነበሩ ብኩን ስለመሆናቸውም አስረግጬ ለመግለጽ ነው። እገረ መንገዴን ጠረግ ለማድረግም ጭምር ነው። አንቱው አመክንዮ „ታላቋን አሜሪካን የፈጠረ የኔ ማንነት ነውና እኔ ያለኝ ነገር ሌላው የሌላው ብቻም ሳይሆን፤ ዓለምን ፈጣሪ ስለሆነ ስለምን ብድር እሄዳለሁ? ማንነቴ ኢትዮጵያዊነቴ ይበቃኛል – መቅድም ነውና“ ማለት፤ ለዛውም ሁሉ ነገር እያለው፤ እዬቻለ፤ እራሴን ሆኜ መኖሬ የክብር ክብር፤ የግርማ ግርማ፤ የሐሤት ሐሤት፤ መርሄ  ነው ብሎ ኢትዮጵያዊነቱን የፈቀደ፤ ኢትዮጵያዊነቱን የመረጠ፤ ኢትዮጵያዊነቱን የወደደ ከዚህ ጋር የተያያዙ ማናቸውም የስደት ውጣ ውረዶች ለዛውም በወጣትነት ዘመን ብዙ ወጣ ገብ ችግሮች ሳይበግሩት – መልካም ዕድሎችም ሳያታልሉት፤ እንዲህ በውሳኔው መዝለቅ የቀደመ – ሐዋርያነት ነው ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ። ሥህነ – ቤዛ የትኛውም የስደት ፈተና አላሸነፈውም። ችግሮችን ተጋፈጦ ገዢ መሬቱን – ተቆጣጥሯል።

በዚህ ውስጥ ድፍረቱን፣ ቁርጠኝነቱን፣ ውሳኔ የመስጠት ጉልበታም አቅሙን፤ እራሱን ለመምራት ያለውን አቅም ወቄትም ማዬት ይቻላል። እራስን ማሸነፍ የወርቅ አንክብል ነው። እንዲህ ያለውን በውስጡ ለውስጥነት መርኽ የተገዛ መንፈስ ለሁላችንንም ዬአብነቱ ተመስጦ – ትውፊትን ቀልቦናል። ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ውህደትም በአካል ሥህነ ቤዛ ያልተገኘበት መሠረታዊ ምክንያት የመጓጓዣ ሰነዱ ጊዜ ያስፈልገው እንደ ነበር – ከኢሳት አምስተርዳም – አዳምጠናል። ሳያበራ ብዕር የጨበጠ፣ ዬማይክ ራህብተኛ፤ የአትራኖስ ጉጉተኛ መንፈስ ሁሉ ዱላ /ቆመጥ/ ባለማቋረጥ ይቆረጣል፤ ዱላው ወይንም ቆመጡን አስተካክሎ ዓይንህ ጥርስህ ብሎ ከርክሞ ይዘጋጃል፤ ያው መሰናዶው ተዘውትሮ ለፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋና ለመንትያው ይሆናል። አቤት! – ትእግስቱ! እንዲህ ዓይነት ሆደ ሰፊነት ብቻ ነው ኢትዮጵያን ከእነህልቆ መከራዋና ችግሮቿ መሸከም – የሚችለው። ሰለጠነበት – በመከራው። ኖረበትም። ፍጹም ያልተገባ፤ ከፖለቲካዊ መንገዶች የወጡ ከኢትዮጵያዊነት ሥነ ተፈጥሮም ያፈነገጡ ዬተቸዎችን – ከሰብዕ ዝቅ የሚያደርግ ዘለፋ ሁሉንም አስመችቶ – ቻለ። ይህ ከብረት ቁርጥራጭ የተሠራው ጥንካሬውና ብርታቱ ደግሞ እልፎች አጥር ቅጥር እንዲሆኑለት ግድ አላቸው። የመንደር ሆነ የጎጥ ሪጋ ቤት ባልደረባ ያልሆነው – ጥልቅነቱን ለማዳመጥ እንፈቅዳለን! ተግባሩ ብቻ ነው የስምሪታችን መሃንዲስ! ሩቅ አሳቢነቱ ቅዱስ መንፈሳችን ነው! …. የመሪነት ጥራቱ ርትህ ሰጪ ትርጉማችን ነው! ዓይናችን የህሊናችን ሚዛን ነው! እሱ ራሱ ነፃነት ነው።

ጽናትን ለዋጠ ኢትዮጵያዊነት – እኔ ምን እላላሁ? ምንስ አቅም አለኝ? እግዚአብሄር ይስጥልን ከማለት በስተቀር። ይህ ሰው በጣም እጅግ ሩቅ ነው። ይህን በእውነቱ በመከራ ብዛት ከሃገሩ ለሚፈልሰው ወጣት የዜግነት ብቃት ት/ቤት ተቋም ነው። በህልሜም በውኔም የሚነስተኝ በሀገሬ በኢትዮጵያ ብሄራዊነትን አጀንዳው ያደረገ ትምህርተ – ዜግነት፤ ፍትህን ማዕከሉ የሆነ ትምህርተ ሥነ – እኩልነት፤ ሰማያዊ የተፈጥሮ ሥጦታዎችን በአስኳልነት የተንተራሰ ትምህርተ ሥነ – ፍቅራዊነት በመደበኛ ትምህርትነት ሥርዓት ተቀርፆላቸው በመደበኛ ት/ቤት የሚሰጥበት፤ ሙያም ሆነ ዬሥራ መስክም አንዲሆኑ ምንአልባትም ወደ ኮሌጆች ወይንም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያም መስፈርት እንዲሆኑ መስከረምን እጠብቅ ነበር። እንሆ የአሁኑ መንገዱ ድባባዊ ውበት አለው። ዬዋዜማው ጣፋጭ ጠረን እያወደን ነው። እኔስ እላለሁ እንዲህ ዓይነት ስንዱነት፤ ቀዳዳውን ሁሉ ቀድሞ የደፈነ አንበሳነት፤ ልዑቅ ብልህነት ለወለደችህ እናትህ፤ ለምትማራቸው የፖለቲካ ድርጅት አካላትና አባላት ብቻም ሳይሆን እርምጃህ – ውሳኔህ – በፈተና የመጽናት በርነትህ የትውልድ አዲስ የሰንደቅዓላማ ትምህርት ቤት ስለሆነ – ታኮራለህ!  እኛ የስደቱን መከራ መቋቋም ተስኖን የሌላ ሀገር ዜግነት ለማግኘት እንጠቁራለን – እንከስላለን፤ አንተ ግን የአብነቶች ቀንዲል ብርኃነ – ሞገስ ሆንክለት – ለኢትዮጵያዊ ዜግነትህ። ….. እንዲህ ነው ተምሳሌነት፤ እንዲህ ነው የመሆን መቻል አርበኝነት። እኔስ ኮራሁብህ። እኔስ አምነቴን ጣልኩብህ። እልፎችም ይህን መሠረታዊ በኽረ ጉዳይ ልብ ይሉት ዘንድም በትህትና – አመለክታለሁ፤ አብሶ ለነገ ዕንቡጥ ወጣቶቻችን። ነገ ማደሪያው በውል – የመንፈስ ማረፊያ አግኝቷል። ልጆች ከሚስሙት ነገር ይልቅ ከሚያዩት ነገር ብዙ ይማራሉ። ከሚጨበጥ ሃቅ ዕውቀትን – ይገበያሉ። „ልብ ያለው ሸብ“ ይላል ጎንደሬ ሲተርት ….

ሰሞኑን ኢትዮ ሚዲያ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና የግንቦት 7 ለፍትህ ለነፃነትና ለዴሞክራሲ ሲዋህዱ „ዬኢትዮጵያ ህዝብ“ የቀረበትን ተያያዥ ጉዳዮችን ያብራራ – ክፍል ሦስት ከክፍል ሁለት ቀድሞ ከወንድሜ ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ አንድ ጹሑፍ አንብቤያለሁ። በጹሑፉ ጭብጥ ዙሪያ እምለው – አይኖረኝም። ቀደም ባሉት ጹሑፎቼ በአግባቡ ከውኘዋለሁና። ለአለቀበት ለተሸናፊ አጀንዳም ጊዜ ማዋስም አስፈላጊ – አይደለም። ነገር ግን የህሊና ዓይን የሚሆን ቁምነገር ባለው ዕውነት ላይ የተቃጣውን ዘላላ ስንኝ ከእርእሴ ጋር የሚሄደውን ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት እሱን ልሂድበት ወደድኩኝ። ወሳኝ ጉዳይ ነውና። ማስተዋልን –  „ታላቋ አሜሪካን ሆነ ዓለምን የፈጠረው ማንነቴ ኢትዮጵያዊነት ዜግነቴን ለሚዛን ሊያቀርብ አይችልም፤ ምርጫዬም ህይወቴም“ ያለው አንበሳ እኮ ነው የግንቦት 7 ሊቀመንበር በቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ ሃሳቡን አፍላቂ፤ በኋላም መሥራችነቱ ደግሞ ከመንፈስ መንትያ ወንድሙ ጋር በሀገረ – አሜሪካ። ይህ ድንግልናው ያልተገሰሰ መንፈስ ነው ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር መንፈስ ጋር የተዋህደው። የሥህነ – ቤዛን ተቀናቃኞቹን መፈናፈኛ የሚያሳጣ አሸናፊው የቀደመ ዝግጁነት፤ ተመስጥሮ የከተመበት ረቂቅ እጅግ ጥልቅ መንፈስን አለማወቁ ነበር ፆምን – ያስገደፈው።

„አያውቁንም እኛን አያውቁንም“ ይላሉ በህብረ ዜማ – ሁለመናው። በምንም ብሄራዊ አምክንዮ ግድፈት የሚታማባት ነገር የለም። ስንዱ ነው። …. እርግጥ ነው ያላወቅነው፣ ውስጡን ዘልቀን ለመመርምር ያልፈቀድን ወይንም የተሰወረብን ግን ተከድኖ የኖረ የራሳችን የእኛ ሲሳያችነን  ዕውቅና ለመስጠት ድፍረት ስለሚያንሰን ብቻ ነው። ስለምን? ኢጎና የበታችነት ስሜት ቤተ ዘመዶቻችን –  ስላደረግናቸው። እኔ እንደማዬው ፓለቲካ ሳይንስ መሆኑ ቀርቶ ግላዊ ጥላችን ጥግ ነው ብለን ስለምናምን። ፓለቲካ በተጨባጭ እውነት ላይ ስምምነት፤ ትብብር፤ መወያዬት፤ መግባባት፤ ለብዙሃኑ ፍላጎት ራስን ለማስገዛት መፍቀድ፤ ሰጥቶ መቀበል ወዘተ … መሆንም ረሳነው። በእውነቱ በብሄራዊ ሐገራዊ ጉዳይ ሙሉ ተሳታፊ ለመሆን እኔን ጨምሮ የውስጥ ለውጥ – ያስፈልገናል። ቀናዎች አይደለንም። ኃይል ፈጣሪነታችን ለአሉታዊ ነገሮች ብቻ ነው። ህወሓትማ – ተራሳ። በጎዊ ለሆኑ ለውጦች ጥቂቶች አልተዘጋጀነም – አንፈቅድም። ጎጥን መሻገር ነው የሰውነት መለኪያው። ኢጎን መደርመስ ነው ጀግንነት፤ መንደርተኝነትን ማሸነፍ ነው ለቀጣዩ ብሄራዊ ቀልም – ስምረት። አቅምን መለካት ነው ሥልጡንነት። በ እጅ በአለ ሃብት ብቻ መተንበይ ነው ብልህነት።

ወገኖቼ ኢትዮጵያዊነት የሚንጠለጠል፤ የሚለጠፍ፤ በጎን የሚታደርበት፤ ወይንም የሚለበጥ አይደለም፤ በውስጡ የሚኖርበት ሚስጢር እንጂ። አፈፃጸሙ፤ አተረጓጎሙ፤ አካሄዱ እንደ ተፈጠረበት መክሊት ይሆናል። ውድ የሐገሬ ልጆች ሥህነ – ቤዛ  ዬአሜሪካ ዜግነት ባለመውሰዱ ወይንም አሜሪካዊ ባለመሆኑ እንደ አሻው መንቀሳቀስ – አይችልም። ሌላም በፖለቲካ አቋሙ የሚደርስበትን ማናቸውም ቅጣቱን መቋቋም የሚችልበት መጠለያ ተደራቢ ዜግነት – የለውም። ከኢትዮጵያዊነቱ ውጩ ጥበቃ የሚያደርግለት ምንም ምድራዊ ነገር የለም። በጣም የሚገርም የራስ መተማመን ጣዝማ ባለሃብት ነው። ብልህ ሆናችሁ ውስጡን አዳምጡት – በትህትና። ለዛውም እንዲህ  በዬአቅጣጫው ጦር በተመዘዘበት ሁኔታ። … ህሊና የሚባለው ነገር እኮ ሚዛን ሊኖረው ይገባል። ለትችቱም – ለወቀሳውም። አሁን አሁን ሳስበው የበታችንት ስሜት አብዝቶ የሚንጣቸው የራሳችን ናቸው የሚባሉት ሳይቀሩ ፊት ለፊት ቢያገኙት ምን ያደርጉት ይሆን እንዲህ በደም ፍላት ሲወራጩ – እላለሁ። አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ሲታሠር ድምጽ ያላሰሙትም ዛሬ በተቆርቋሪነት ስለ አስተሳሰሩ ሂደት በፖለቲካ ተንታኝነት ይሁን በልብ ወለድ ጸሐፊነት ተስልፈው እያዬሁ ነው። ይህ ለእኔ ቆዳ መልስ ንሰኃ እንደ መግባት ነው። ያን ሰቅጣጭ ጥቃት – ጥቃቴ ነው ብሎ ለመቀበል ጊዜ ሊቀለበው ባልተጋባ ነበር። እስኪ ልሰብበት የሚያሰኝ አልነበረም። ዬብሄራዊ ውርዴት ብስጩነት አደብ ወይንም ታዛቢነት ሊሸለመው ባልተጋበ ነበር። የጥቃት ትኩስ እሬሳን አስቀምጦ ሠርግና መልስን – አዳምጠናል – ዛሬም እንዲሁ ተዛነፍ ነገር እናዳምጣለን ዘመኑን የምንታዘብ ሰዎች። ቢያንስ ፈጣሪ አምላክ „ሰው“ ብሎ ሲፈጥር የሠራለትን ሰማያዊ ህግ የእኛ – እንበለው።

መከራን መጋራት ኢትዮጵያዊ መለያችን ነበር። ችግርን መካፈል ፍጹማዊ ዓርማችን ነበር። ጥቃትን አለማስመችት የአደራ ሥጦታችን ነበር። እራቅነው ልበል ወይንስ አራቆትነው?! የሆነ ሆኖ የኔዎቹ – የኢትዮጵያዊነት ንባቡን ትርጓሜውና ሚስጥሩን እናመሳጥር፤ በተደሞና በአርምሞ ቢባል „ከአሜሪካው ዜግነት ኢትዮጵያዊነት ይበልጥብኛል። እንዲያውም አይመጣጠኑም“ ላለ የቀደመ መንፈስ ከዚህ በላይ ስለ ኢትዮጵያዊነቱ ከቶ ምን ሊገልጸው ይችላል? ምን አምክንዮ አለ ይህን ዕውንት (fact) ታግሎ ሞግቶ የሚረታ? የአውነት ጭብጥ ብቻ ነው የሰውን ልብ ቀልብ – የሚገዛው እንጂ የተገለበ ስሜት አይደለም። በስሜት ፌስታ አንጂ ውስጥን ማንበብ ሆነ መተርጎም  – አይቻልም። በጥላቻም አምላክን ማስከፋት፤ የሆኖ ሆኖ ከተወረወረ ቀስት የሚጠብቀው አምላክ ጠበቀው እንጂ …. እንደሚቃጣው ጦርማ ….

የብልጹጉ ቅብዕ በብሄራዊ ፍቅር  – ህትምተ።

አውነት ለመናገር እንዛ ቀኑን በሐሩር ጨለማውን ደግሞ በግርማ ሌሊት የሚተጉት ቅዱሳን ደናግል ዬአቨው እና ዬእናቶቻችን ጸሎት የሰጠን ሙሴ ነው ፕሮፌስር ዶር. ብርሃኑ ነጋ። ባለቤት ያልነበረው ዬብሄራዊ አመክንዮ መንፈሱ ጥግ አገኘ። ስለዚህም ሥጦታውን አናቅለው! ይህን የእውነት ውቅያኖስ እንቀበለው ዘንድም አቅም እንዲኖረን ፈጣሪያችን በፀሎት – እንጠይቅ። በፍቅር አሸናፊነቱ በእሱ ክህሎት ብቻ የተከወነ – አይደለም። የቀደመ ቅብዕ“ አለበት። እደግመዋለሁ ይህን ቃል ህቅ የሚላቸው ደሞቼ ስላላችሁ የቀደመ „ቅብዕ“ አለበት። „ቅብዕው“ የጸሎት አጥር ከምንም ነገር በላይ ያስፈልገዋልና ሱባኤ በግል አቅም ያላችሁ፤ ህይወቱ ያላችሁ ትተጉበት ዘንድ እኔ ሎሌያችሁ ሥርጉተ ሥላሴ በአጋጣሚው በትህትና አሳስባለሁ። ትውልዱ ትውልድ እንዲሆን የምትሹ ቅን ወገኖቼ – መሆን ብቻ አንዲመራችሁ እባካችሁን – ፍቀዱ። የህልም ስኬት የሚገኘው በመሆን አውራ መንገድ ብቻ ነው እንጂ ገብያው በተፈታ በትነት ንድፈ ሃሳብ አይደለም።

ይህ ፎቶው ላይ ያለው  ዬሥህነ – ቤዛ ህይወቱን ለመስጠት ቃል ያሰረባት የተግባሩ ቀለበት ነው፤ ለእርቃንነት አባት ለነበሩት ለሟቹ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ የህቅታ ቋት፤ የኮሶ ተክል – ነበር። ሲዮት ያንገፈግፋቸው ነበር። በሽታቸውም ይነሳ ነበር።  ሰንደቅአላማችን አይደለም በእጃቸው ለአንድም ደቂቃ በጎናቸው ተቀምጦ – አያውቅም። በመጤ እንደራሴ የተናጡ ስለነበሩ። „ሐገሬ“ ማለት „ኢትዮጵያ“ „ሰንደቅአለማዬ“ ማለት ዛራቸውን ያስነሳ ነበር። የሌለህን ነገር ከአንተ ሥር ያሉ ወይንም በቅርብህ የሚገኙ ሰዎች ሲያደርጉት ወይንም ሲኖራቸው የህሊና ስውር ቅጣቱ ስለሚነስትህ ያን የማዬት አቅም ምሶ መቅበር ቀዳሚ ተግባርህ ይሆናል። ለዚህም ነበር ለሰንደቅዓላማችን የማሰሪያ ህግ ተረቆ – የጸደቀበት። አርበኛ ያልሆነ የሐገር መሪ ባንዳን ይሾማል – ይሸልማል። ስለምን? አርበኛው ደረቱን ነፍቶ ቀና ብሎ የመሄድ አቅም ስለሚኖረው አርበኝነት አልቦሹ መሪ መንፈሱ እያዬ እንዳይቀጣ መሰሎቹን – ይመርጣል። ጀግኖችንና አቅም ያላቸውን ያባራቸዋል ወይንም ያገላቸዋል። ጎባጣው የሚፈልገው እንደ እሱ የጎበጠውን ወይንም ተጎንብሶ የሚሄደውን ነው። ቀና ብሎ የሚሄደውን የመቋቋም አቅሙ ሙት መሬትን የሙጥኝ ስለሚል። በነፃነት ትግሉም በዬነጥብ ጣቢያው አቅምን የሚበላው የዚህ በሽታ ውርስነት ነው። በአጋጣሚው አቅም ያላችሁም – አንድ በሉት። ለነገም ነቀርሳ ስለሆነ። የነፃነት ትግሉ ሰብል ትርጉሙ ከትንሹ ዛሬ መጀመርም አለበት።

ለዚህም ነበር ሄሮድስ መለስ ዜናው ከአርበኝነት ጋር የነበሩ የቦታ ሥሞች ሳይቀር እያደኑ፤ ኢትዮጵዊ ተቋሞቿን – እያሳደዱ፤  ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ክብር እዬረገጡና እዬገፈፉም፤  ማናቸውንም የክብር መግለጫዎቻችን በሙሉ በጥርሳቸው እንዳያዟቸው ማለፍ አይቀርምና – ያለፉት፤ ለእርሳቸው ባንዳዊ መንፈስ ፍሰኃ ሲሉ፤ ያ የክብር – የሞገስ ተክሊል ባላውለታችን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅዓላማችን በሽታቸው ነበር። ለነገሩ – አይመጣጠኑም፤ ከወላጃቸው የወረሱት ባንዳነትን ነበርና። ለመሰሎቻቸውም ቢሆን ዛሬም – ይበጠብጣቸዋል። እንደ ጎደለ እንስራ ውሃ – ያንቦጫቡጫቸዋል። ለአርበኛው ደም ግን ዘውዱ ነው! ነገም ከኢትዮጵያ ህዝብና ከመሬቷ ከደረሰው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማኒፌስቶ በደል ባላነሰ ብሄራዊ ቋሚ ሰንድቅዓላማችን ያሳለፈውን የ24 ዓመት የአፓርታይድ ዬተገላይነት ዘመን አሳር ሊክስለት የሚችለው ፍሬ ነገር ዬአንድ ዬአምክንዮ ዕሴት ብቻ ነው። ይህ ትውልድ ያሸነፈ ፓርቲ ቢያሸንፍ፤ ከንጹህ ተፈጥሮ ላይ ምንም ዓይነት የፍላጎት ነቁጥ እንዲኖርበት መፍቀድ – የለበትም። ከነተፈጥሮው እንዲዘልቅ እሱን ማስቀደም የመንፈሳችን ዓይን ሊሆን ይገባል። ይህ እንደ አንድ ተራ ዜጋ የአደራ ቃሌ ነው። ሰንደቅዓላማችን ይበቃዋል – ተቃጥሏል – ተቃሏል – ታስሯል – ተቀዷል፤ ከረጢት ሆኗል፤ በፍዳ ተቀቅሏል፤  „ቀብረነዋልም“ ብለውናል። የቻሉትን ያህል የቂምና የቋሳ መገበሪያ – አድርገውታል። „በቃን!“ የሰንደቅአላማችን መከራ የነፃነት ትግላችን መሪ መርህም ሊሆን ይገባል። የብሄራዊ ዜግነታችን መለያ የጋራ ጋሻ አሻራ ዓርማችን፤ የሁለንትናችን ቀላማም ውበት – ማራኪነት – ተወዳጅነት – አድማቂነት፤ ሳቢነት፤ ተፈቃሪነት ብቁ ገላጫችን ነውና። ሰንደቅዓላማችን ምራቁን የዋጣ የተረጋጋ ምሩቅ የድል ዋዜማችን – ዝልቅ ቅርሳችን ነው።

እርግጥ ነው። ሥህነ – ቤዛ ከድንኳኑ ሲደርስ ዓርማውን  ፎቶው ላይ እንደምታዩት በእጁ ይዞ ትልሙንም አደራ ሰጥቶ ነው። አሁን ተመስገን ነው። ጊዜና ዘመን የማይሽረው ሰንደቅዓላማችን በእጁ ብቻ ሳይሆን በመንፈሱ የታታመ ሥህነ – ሙሴ ፈጣሪ በሥነ ጥበቡ – ፈጠረ። በቅጡ 17 ዓመት ሳይሞላው ነበር ገና በታዳጊ ወጣትነቱ ሐገሬ ውስጤ፤ ፍላጎትሽ – ፍላጎቴ፤ መንፈስሽ – መንፈሴ፤ ራዕይሽ – ራዕዬ፤ ችግርሽ – ችግሬ በማለት ልዕልቱን በልቡ አስቀምጦ አጋጣሚዎችን ሳያሾልክ ወይንም በአጋጣሚዎች ሳይሾልክ፤ ሁሉንም እንደፈቀደለት በተድሞና በበዛ ታጋሽነት – የታደመበት። መቻልን – በመቻቻል አስጊጦ ኖረበት። በርሃም ቤቱ ነበር። ዱር ገደሉም በአርበኝነት ቤቱ ነበር። ስደትም ጊዜያዊ መጠለያው ነበር። ወደ ሀገሩ ተመልሶ በስብዕዊነት ዙሪያ፤ በነፃነት አኩልነት የዲሞክራሲያዊ ፈለግ ዙሪያ የበኩልን ሙሉ ድርሻ በቅንነት አበርክቷል፤ ችግርን በዬአይነቱ አስተናግዷል። እግር ብረቱንም ቢሆን በስደት በኢህአፓ ሱዳን መሬት ላይ፤ በሀገሩም በህወሓት በማዕከላዊና በቃሊቲ አዲስ አባባ ሁለም እንዳይቀርበት አይቶታል። አብሶ እስር ቤት ሌላ የህይወት ምዕራፍ ነው። ጣፍጭነቱ የህዝብን ፍላጎት ፈቅደህ ለመስዋዕትነት ቤተኝነት ስለሆነ በቁም የመጽደቅ ያህል ነው – ለእኔ።  ሥህነ ቤዛ ሁሉንም የመኖር ዓይነቶች ረሃብን ሳይቀር ኑሮ እንሆ የፋፋ ተግባር አኖረ። ዛሬም ቀን በጠፋን፣  ኢትዮጵያዊው ቀን በዘረኝነትና በጭቆና በተጠፈረበት ጭንቅ ወቅት፣ ለእስርኛው ኢትዮጵያዊነት ለአዲስ ቀን ተስፋ ጥብቅና ቆሞ ዱር ቤቴ አለ። ዋቢ!

የናፍቆት እፍታ።

ሥህነ – ቤዛ እናት ሐገሩን ከምንምና ከማንም በላይ – ይወዳል። ጠረኗ አዘውትሮ – ይናፍቀዋል። ገፆዋ በፍቅር – ይጠራዋል። ውስጧ አሳምሮ – ይመራዋል። መንፈሷ በትህትና  – ይገዛዋል። ወዟ – ይስበዋል። እናቱን — ይናፍቃታል ሽው — ትዝ  ትለዋለች። አልሆንለት ብሎ እንጂ ከእሷ ተለይቶ መኖሩ ባዕዱ ነው። ለዚህም ነው በነበረው ቀዳዳ ወደ እናት ሀገሩ ሁለመናውን ይዞ በቅንነት ለማገልገል – የተመለሰው። ከፍቅሩ ጥልቅነት የተነሳ የተወሰደ፤ ከናፍቆቱ ርህርና የተቀዳ ውሳኔ ነበር። በሙያው ሀገሩን ለመጥቀም አስልቶ ነበር። በዛን ጊዜም  ዬእናቱን ውለታ ለመወጣት ናፍቆቱን ያወራረደው በመሃያ አልነበረም። ፍቅሩን የገለጠበት መንገዱ ከማንኛችም እጅግ በረቀቀ መልኩ በነፃ እልፍኝ ነበር። በሂሳባዊ ስሌት ከእናቴ ጋር እንዴት ተብሎ ብሎ ነበር ትጋቱን – ያስመሰከረው። ይህም ሌላ ወግ ያለው ዘለግ አድርገን ለማዬት ያልፈቀድንለት ንጡር አንጡራ ሚስጢር ነው፤ ለነገ መገኘት፤ ለነገ መዋል፤ ለነገ – ማደር ብቻ ሳይሆን – ለነገ መሰንበት፤ አልፎ ተርፎ ለነገ – ተወዲያም ደልደል ያለ ድልድል ለመሆን – በመፍቀድ፤ የሚገርመው እስከ ዛሬ በአበረከተው መልካም ነገር ሳይዝናና፤ ሳይኩራራ፤ ሳይዝልም አለ እንደአለ። አንዲት ብጣቂ ሽልማት ሳናዘጋጅለት፤ የምስጋና ቀን ሳናዘጋጅለት። እናት ሐገሩን ኢትዮጵያን ጽላቱ እንደ አደረገ – ኖረበት። መታደል ነው። ዘመን የማይሽረው፤ ድንበር ያለወሰነው የእናትና የልጅ ንጡሕ ጡታዊ ሃዲድ፤ እትብታዊ ትስስር በፍቅራዊነት ክህሎት ሲመነዘር እናት ሆዱ ያሰኘዋል። የእትብት ጥሪኝ አንዲህ ረቂቅ ግን ብቁና ብልህ አስተዳዳሪነት ነው። እራሱን በዜግነት ፕሮግራም ወይንም ማኒፌስቶ ለመምራት የቻለ ዘላቂ ተስፋችን መምራት ስለመቻሉ ምስክሩ ተግባሩ ብቻ ነው። ያዬነው ከመሆን ተነስቶ ነው ወደ መሆን ሲሄድ ነው።

ክወና።

አዎን! ሥህነ ቤዛ ከግብዝነት ጋርም የተፋታ ነው፤ በተለያዬ ጊዜ ከሰጣቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች፤ ቃለ ምልልሶች እንዲሁም የስብሰባ ሂደቶች፣ የተረዳሁት ቁም ነገር …  እጅግም አሳንሶ የነፃነት ጎህ ሲቀድ መጸሐፉን “ ይህቺው የኔው ጹሑፍ መውጣቷ … ልክ እንደ ተራ መጣጥፍ ፤ ክቡር አትበሉኝ – በቁጣ፤ ዶር. የሚለው ይበቃኛል – በትህትና ፤ የተለዬ ጸጋ እኔ የለኝም – ዝቅ ባለ ሙሁራዊ ሥነ ምግባር። እኔ በግሌ ይህን አደርኩት የምለው የለም – ከግል ኢጎ ጋር ፍቺ በመፈጸም፤ ከእኔም የተሻሉ ወገኖቼ አሉ – በልዩ ውስጣዊ አክብሮት“  ይለናል። ስለሆነም እንደ ዘመኑ ታዳሚነታችን ያዬነው ወይንም የሰማነውን ወይንም ካነበብነው ያገናዘብነው፤ እሱን የተረጎምንበትን ሆነ ወደ ውስጡ ዘልቀን መክሊቱን ያደመጥነው ነገር ምን ሌላስ ይኖረው ይሆን? ወጣቱ መማር ያለበትን፤ መከተል ያለበትን ትክክለኛ መንገድ ማሳያት ድርሻዬ ነውና በምዕራፍ አራት እንገናኝ ዘንድ – በቀጠሮ። ከስንብት በፊት ግን ትንሽ ቋጠሮ …

በቃኝ! ቤቱን ሠርቶ፤ ጉልቻ – ጎልቶ

ኪዳን – አሰማርቶ፤ መሆንን – አስልቶ፤

ከሥሩ – ተብራርቶ፤ ይሁን – አጎልብቶ

እሺታን – ጠጥቶ፤ አለልኝ – መጥቶ

ድምጽ ለቃል ሰጥቶ፤ መቻልን ገንብቶ

ሰንደቁን አስልቶ፤ ኢትዮጵያዊነትን ከሁሉ – አጉልቶ

ጀግና መንገድ ያዘ አደራን አንግቶ!

ሥጦታ – ለአርበኞቼ። እርእሱ በጉልህ የተጻፈው መጨረሻ ላይ ያለው ነው። ይህ የእኔ መንገድ ነው። 18.08.2015

ዛሬን ባርኮ እንዲህ በማዕዳችን በሃበሻ ቤት ያገናኘን አምላክ ልዑል እግዚአብሄርን አመስግኜ ልሰናበት – ወደድኩኝ። መሸቢያ ሰንበት – የኔዎቹ። ጌጤን ዘሃበሻን – ከውስጤ አመሰገንኩኝ – ኑሩልኝ።

ማሳሰቢያ – አባቱ የእኔ ጀግና ናትናኤልሻ እሺ –  እኔ ሎሌህ ነኝ። በጹሑፎቼ መልእክትህን – እለጥፋለሁ። በራዲዮ ፕሮግራሜም ከበጋ እረፍት በኋላ በድምጽ መልእክትህን ሙሉውን – አስተላልፋለሁ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45527

የብሄራዊ ነፃነት ትግላችን ለህወሓት ብጣቄ መላሾ አያጎበድድም!

ዬነፃነት ትግላችን የብሄራዊ ማንታችን ክብር ጉልህ መግለጫ ቁልፋችን ነው!

የነፃነት ትግሉ መሠረታዊ ዓላማ 90 ሚሊዮን ህዝብ ከህወሓት የባርነት እስር ቤት ማስለቀቅ ነው!

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 

ለ24ኛው ክፍለጦር ውሃ የምታመላልሰው ቦቴ ተገልብጣ 6 ወታደሮች መሞታቸው ተዘገበ

$
0
0
Photo File

Photo File

ለ24ኛ ክፍለጦር ሰራዊት ስታገለግል የነበረችው ወታደራዊ የውሃ ማመላለሻ ቦቴ በመገልበጧ ምክንያት በውስጧ የነበሩት የስርዓቱ ወታደሮች ሙትና ቁስለኞች መሆናቸውን የደህሚት ድምጽ አስታወቀ:: ደህሚት ከምንጮቼ አገኝሁት ባለው መረጃ መሰረት- በአውደ ራፊዕና አካባቢው ለሚገኙት ለ24ኛ ክፍለጦር ሰራዊት ስታገለግል የቆየች አንድ የውሃ ቦቴ በመገልበጧ ተሳፍረው ከነበሩት ውስጥ 6 ወታደሮች ሲሞቱ የመኪናዋ ሾፌር ጨምሮ በርካታ ወታደሮች ደግሞ በከባድ መቁሰላቸውን ታወቀ።

ከሞቱት ወታደሮች የተወሰኑት ለመጥቀስ ያህል- ወታደር ግርማቸው አለበልና ከድር በድሩ የተባሉ እንደሚገኙባቸውና የቆሰሉትም ወደ ህክምና እንደተወሰዱ መረጃው አክሎ አስረድቷል ሲል ዘገባው መረጃውን ቋጭቷል::

የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አቶ ሙሉነህ እዩኤል ስለ አሰብ ወደብ ተናገሩ

$
0
0

“[ሕወሓቱ] ሰውዬ ስቃወም አይቶ እናንተ ከምባታዎችን ሰው ያረግናችሁ እኛ ነን እንዴት ትቃወመናለህ አለኝ”

“ተወልደ ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ ወ/ሮ እማዋይሽን ጡታቸውን በምላጭ እየተለተለ ሽንታም አማራ እያለ ነው የሰደባት”

“ገመቺስን ብልቱ ላይ በላስቲክ ውሃ አንጠልጥለው እየገረፉት በኦሮሞነቱ ሲሰደብ ነበር”

“ወያኔ አሜሪካ በጣም ታስፈልገዋለች:: [አሜሪካን ለማስደሰት] በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ ቅጥረኛነቱን በደንምብ ማሳየት ይኖርበታል”

– የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አቶ ሙሉነህ እዩኤል


የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አቶ ሙሉነህ እዩኤል ስለ አሰብ ወደብ ተናገሩ

በአዲስ ዓመት ፍቅር ብንመሰርት –ይገረም አለሙ

$
0
0

 ፍቅር ያስታግሳል፣ፍቅር ያስተዛዝናል ፣ፍቅር አያቀናናም፣ፍቅር አያስመካም፣ፍቅር አያስታብይም፤ብቻየን ይድላኝ አየሰኝም፤አያበሳጭም፤ክፉ ነገርን አያሳስብም፤ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል አንጂ ስለ አመጻ ደስ አይለውም ሁሉን ይታገሳል፣ሁሉን ያምናል፣ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣በሁሉ ይጸናል፡፡

                                                               ( ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 ም13 ቁ.1-7)
ከቁጥር መለወጥ ውጪ አዲስ ዓመት የመባሉ አዲስነት ምንነት የማይታወቅበት የአዲስ አመት መባቻ ላይ አንገኛለን፡፡ በሀገራችን የተለመደ በሆነው ይህን…ልዩ የሚያደርገው በሚለው አነጋገር ካየነው  ይህን የአዲስ አመት ጅማሮ ልዩ የሚያደርጉ ሁለት ጉዳዮች አሉ፡፡ አንደኛው ሀያ አራት አመታት ኢትዮጵያን የገዛው ወያኔ በመቶ ከመቶ አሸናፊነት ለቀጣይ አምስት አመታት አገዛዝ መንግስት የሚመስርትበት ዋዜማ መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው የነጻነት ታጋዮች ወደ ተግባር የተሸጋገሩበት ማግስት መሆኑ ነው፡፡

እንዳንችል የሚያደርጉ ግለሰባዊ ባህሪያቶቻችን አላስችል እያሉን እንጂ ይህን አዲስ ዐመት ልዩ የሚያደርገው የሚያስብል ከላይ ከተጠቀሱት ከሁለቱም የሚልቅና የሚበጅ ነገር ማከናወን እንችል ነበር፡አለመታደላች ይሆን ወይንም እንደሚባለው ርግማ ኖሮብን ማድረግ እየቻልን ባለመቻላችን ብዙዎች በጥቂቶች ለመገዛታችን እኛው ምክንያት ሆነን እንገኛለን፡፡

አነርሱ የአገዛዝ ዘመናቸውን በመቶ ከመቶ ውጤት አድርሰው ለአምስት አመታት እየተዘጋጁ ለሀያና ሰላሳ አመትም ሊገዙን እያሰቡ ናቸው፡፡ እኛ ደግሞ አገዛዙን ለማውገዝ ለመርገም አንድ ሆነን ከምናወግዘው አገዛዝ ለመላቀቅ ለሚያስችለው ትግል ግን አንድ ሆነን መቆም ተስኖናል፡፡ ይህ ደግሞ ዛሬ የጀመረ ሳይሆን በየዘመናቱ የነበረ የማያረጅ የማይለወጥ የራሳችን ጠላት ራሳችን እንድንሆን ያደረገን መጥፎ በሽታ ነው፡፡

ታዲያ ከዚህ በሽታ የመዳኛችንን መድሀኒት ብናገኘው ይህን የአዲስ አመት መባቻ ከልዩም ልዩ አያደርገውም ነበር ትላላችሁ!  ከራስ በላይ ለሀገር ማሰብ በመጥፋቱ፣ በቃል የሚናሩትን በተግባር ሆኖ መገኘት አለመቻሉ፣ ከህዝብ ነጻነት ይልቅ የራስን ጥቅም ማስቀደሙ ወዘተ ግድግዳ ሆኖ አላገናኝ ማለቱ እንጂ ጉዳዩ የማይቻል ከባድ ነገር ሆኖ አይደለም፡፡ የበርሊንም ግንብ ፈርሷል፡፡

እስቲ ይታያችሁ፣ደግሞም ይቆጭ ያንገብግባችሁ፣በኢትጵያዊነታችን አንድ ነን፣ ወያኔ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ መወገድ ያለበት ዘረኛና አንባገነን አገዛዝ በመሆኑ ላይ ልዩነት የለንም፡፡ ኢትዮጵያ የቀደምት ሥልጣኔ ባለቤት ነገር ግን የዴሞክራሲ ባይተዋር መሆኗ አብቅቶ  የህግ ልዕልና የተረጋገጠባት፣ ሰብአዊ መብት የተከበረባት ልጆቿ በሰላም፣ በፍቅር፣ በእኩልነትና በነጻነት የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊት ሀገር እንድትሆን በመመኘትም ልዩነት ያለን አይመስለኝም፡፡ታዲያ እነርሱ ጥቂቶቹ ህውሀቶች ለጥፋት ሲተባበሩ፣ የአገዛዝ ዘመናቸውን ለማራዘም አንድ ሆነው በአንድ ተሰልፈው የበደል ናዳ ሲያወርዱብን እኛ ኢትዮጵያውያን ናዳውን ለመመከትና የአገዛዝ ዘመናችንን ለማሳጠር አንድ ሆነን የማንቆምበት፣ በአንድ ተሰልፈን የማንታገልበት ምክንያት ምን ይሆን፡፡ እንዳይቻል ያደረግነው እኛው ራሳችን ነን እንጂ ይቻላል፡፡ጥቂቶች በአንድነትና በጽናት ቆመው ሲገዙን እኛ ብዙ ሆነን በጽናት ጉድለትና አንድነት በማጣት ሀያ አራት አመታት መገዛታችን አያስቆጭም፡ውጤት አልባ የእድሜ ልክ ተቀዋሚነትስ አያሳፍርም፣አረ በቃ እንበል፡፡ ካልን ደግሞ ወንድም እህቶቻችን እየከፈሉት ካለው መስዋዕትነት አንጻር ይህ ብዙም የሚባል አይሆንምና አሁኑኑ በአዲስ አመት ዋዜማ ተግባራዊ እናድርገው፡፡

በሀገራችን ባህል/ልማድ በተለይ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በከተማም ከጥንቱ ባህል ጨርሶ ባልተለያዩት ዘንድ በአዲስ አመት መግቢያ የቅዱስ ዮሐንስ እለት ችቦ ተለኩሶ ከቤት ሲወጣ ከቤቱ በር ግራና ቀኝ እየተተረኮሰ የጎመን ምንቸት ውጣ የገንፎ ምንቸት ግባ ይባላል፡፡ ይህ መልእክቱ ግልጽ ነውና ዝርዝር ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡

እኛስ አገዛዝ በቃ የምንል ኢትዮጵያውያን በያለንበት ችቦ ለኩሰን አንደ ባህል ወጉ እየተረኮስን ባይሆንም በዚህ የዘመን መለወጫ እለት የድምጻዊት አስቴር አወቀን አንድ አድርገን ጌታ የሚለውን ዘፈን እያንጎራጎርን የጥል ምንቸት ውጣ የፍቅር ምንቸት ግባ፣ የበቀል ምንቸት ውጣ የይቅርታ ምንቸት ግባ፣ የጥርጣሬ የሸፍጥና የሴራ ምንቸት ውጣ፣ የመተማመን የቀናነትና የግልጽነት ምንቸት ግባ የማቃር ምንቸት ውጣ የመግባባት ምንቸት ግባ ወዘተ ማለት ብንችል ምንኛ መታደል ነበር፡፡

ለሀገር ይበጃሉ የተባሉ ያልተነገሩ ያልተጻፉ ነሮች የሉም ተግባራዊነት የለም እንጂ፡፡ ሌላው ቀርቶ በተቃውሞው ጎራ የነበሩና ያሉ ከተናገሩትና ከጻፉት ከፊሉን እንኳን ተግባራዊ ማድረግ ችለው ቢሆን  ሀገራችን ዛሬ ካለችበት በብዙ መልኩ የተለወጠች ለመሆን በቻለች ነበር፡፡ እናም ከላይ የገለጽኩትን ለማለት መድፈሩ የመጀመሪያ ርምጃ ሆኖ ያሉትን ለመፈጸም መቻል ደግሞ ዋናውና ወሳኙ ጉዳይ ይሆናል፡፡ የምንለውን ተፈጻሚ ለማድረግ ለቃል የመታምን፣ ለህሊና የመገዛትና ከራስ በላይ የማሰብ ቁርጠኝነቱ ካለ 2008ን ለአስተማማኝ ለውጥ የሚያበቃንን ጠንካራ መሰረት የምንጥልበት አመት ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህን ማድረግ ቻልን ማለት ደግሞ ለለውጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠርና ትውልድ ተሻጋሪ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት የሚያበቃንን ጥርጊያ ጎዳና ተያያዝነው ማለት ነበር፡፡  ለሀገርና ለትውልድ ማሰብ ካለ ይህ የማይቻልም የሚገድም አይደለም፡፡ ይቻላል!

ዛሬም እንደ ትናንቱ ወያኔን በማውገዝ አንድ ሆነን  ከወያኔ አገዛዝ ለመላቀቅ ግን በየሰበብ ምክንያቱ አንድ ሆነን መቆም ካልቻልን የነጻነቱን ቀን እናራዝመዋልን፡፡ ነገር ግን ዘላለማዊ ምድራዊ ሥልጣን የለምና አንድ ቀን ወያኔና የምንይልክ ቤተ መንግሥት መለያየታቸው አይቀርም፡፡ የሚቻለው እንዳይቻል እንቅፋት ሆነን መስዋእትነቱ እንዲከብድና የወያኔ አገዛዝ ዘመን እንዲራዘም ያደረግን ወገኖች ያኔ ታሪክ ይመሰክርብናል ትውልድም ይፈርድብናል፡፡

በአንድ ሀገር ልጅነት መንፈስ ለጋራ ሀገራችን እንዳንቆም የሚያደርጉንን ሳንካዎች ከውስጣችን አስወጥተን የሀሳብ ልዩነት ያለ፣የሚኖር፣ሊጠፋም የማይችል መሆኑን ተገንዝበን አንድነታችንን አጠንክረን በልዩነቶቻችን ተከባብረን መተማመን፣ ፍቅርና አንድነት በመፍጠር ከወያኔ አገዛዝ ለመላቀቅ የሚያስችለንን መንገድ ለመያዝ ዋናው ቁልፍ መነጋገር መቻል ነው፡፡መቀራረብ መደማመጥ፤

የቱንም ያህል ስንቆፍር ውለን ስንቆፍር ብናድር የሚያለያዩን ጉዳዮች አንድ ከሚያደርጉን በዝተውም ልቀውም ሊገኙ አይችሉም፡፡ እንደውም በሀቅና በንጹህ ህሊና በንጽጽር ከተፈተሸ የሚያለያዩን ሚዛን የማይደፉ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ገነውና ጎልተው ማዶና ማዶ እንድንቆም ለማድረግ የሚያስችል አቅም ያገኙት ከእኔ በላይ የሚል አጋንንት ሰፍሮብን  የመነጋገር ፈቃደኝነት፣ የመወያየት ባህል፤ የመደማመጥ ትእግሰት ያሳጣን በመሆናችን ነው፡፡ እናም በዚህ አዲስ አመት ዋዜማ ይህን አጋንንት እናስወጣና የፍቅርን አምላክ ወደ ውስጣችን እናስገባ፡፡

Comment

በአዲስ ዓመት ፍቅር ብንመሰርት –ይገረም አለሙ

$
0
0

ፍቅር ያስታግሳል፣ፍቅር ያስተዛዝናል ፣ፍቅር አያቀናናም፣ፍቅር አያስመካም፣ፍቅር አያስታብይም፤ብቻየን ይድላኝ አየሰኝም፤አያበሳጭም፤ክፉ ነገርን አያሳስብም፤ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል አንጂ ስለ አመጻ ደስ አይለውም ሁሉን ይታገሳል፣ሁሉን ያምናል፣ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣በሁሉ ይጸናል፡፡
( ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 ም13 ቁ.1-7)

ethiopian newyear 2008
ከቁጥር መለወጥ ውጪ አዲስ ዓመት የመባሉ አዲስነት ምንነት የማይታወቅበት የአዲስ አመት መባቻ ላይ አንገኛለን፡፡ በሀገራችን የተለመደ በሆነው ይህን…ልዩ የሚያደርገው በሚለው አነጋገር ካየነው ይህን የአዲስ አመት ጅማሮ ልዩ የሚያደርጉ ሁለት ጉዳዮች አሉ፡፡ አንደኛው ሀያ አራት አመታት ኢትዮጵያን የገዛው ወያኔ በመቶ ከመቶ አሸናፊነት ለቀጣይ አምስት አመታት አገዛዝ መንግስት የሚመስርትበት ዋዜማ መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው የነጻነት ታጋዮች ወደ ተግባር የተሸጋገሩበት ማግስት መሆኑ ነው፡፡
እንዳንችል የሚያደርጉ ግለሰባዊ ባህሪያቶቻችን አላስችል እያሉን እንጂ ይህን አዲስ ዐመት ልዩ የሚያደርገው የሚያስብል ከላይ ከተጠቀሱት ከሁለቱም የሚልቅና የሚበጅ ነገር ማከናወን እንችል ነበር፡አለመታደላች ይሆን ወይንም እንደሚባለው ርግማ ኖሮብን ማድረግ እየቻልን ባለመቻላችን ብዙዎች በጥቂቶች ለመገዛታችን እኛው ምክንያት ሆነን እንገኛለን፡፡

አነርሱ የአገዛዝ ዘመናቸውን በመቶ ከመቶ ውጤት አድርሰው ለአምስት አመታት እየተዘጋጁ ለሀያና ሰላሳ አመትም ሊገዙን እያሰቡ ናቸው፡፡ እኛ ደግሞ አገዛዙን ለማውገዝ ለመርገም አንድ ሆነን ከምናወግዘው አገዛዝ ለመላቀቅ ለሚያስችለው ትግል ግን አንድ ሆነን መቆም ተስኖናል፡፡ ይህ ደግሞ ዛሬ የጀመረ ሳይሆን በየዘመናቱ የነበረ የማያረጅ የማይለወጥ የራሳችን ጠላት ራሳችን እንድንሆን ያደረገን መጥፎ በሽታ ነው፡፡
ታዲያ ከዚህ በሽታ የመዳኛችንን መድሀኒት ብናገኘው ይህን የአዲስ አመት መባቻ ከልዩም ልዩ አያደርገውም ነበር ትላላችሁ! ከራስ በላይ ለሀገር ማሰብ በመጥፋቱ፣ በቃል የሚናሩትን በተግባር ሆኖ መገኘት አለመቻሉ፣ ከህዝብ ነጻነት ይልቅ የራስን ጥቅም ማስቀደሙ ወዘተ ግድግዳ ሆኖ አላገናኝ ማለቱ እንጂ ጉዳዩ የማይቻል ከባድ ነገር ሆኖ አይደለም፡፡ የበርሊንም ግንብ ፈርሷል፡፡

እስቲ ይታያችሁ፣ደግሞም ይቆጭ ያንገብግባችሁ፣በኢትጵያዊነታችን አንድ ነን፣ ወያኔ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ መወገድ ያለበት ዘረኛና አንባገነን አገዛዝ በመሆኑ ላይ ልዩነት የለንም፡፡ ኢትዮጵያ የቀደምት ሥልጣኔ ባለቤት ነገር ግን የዴሞክራሲ ባይተዋር መሆኗ አብቅቶ የህግ ልዕልና የተረጋገጠባት፣ ሰብአዊ መብት የተከበረባት ልጆቿ በሰላም፣ በፍቅር፣ በእኩልነትና በነጻነት የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊት ሀገር እንድትሆን በመመኘትም ልዩነት ያለን አይመስለኝም፡፡ታዲያ እነርሱ ጥቂቶቹ ህውሀቶች ለጥፋት ሲተባበሩ፣ የአገዛዝ ዘመናቸውን ለማራዘም አንድ ሆነው በአንድ ተሰልፈው የበደል ናዳ ሲያወርዱብን እኛ ኢትዮጵያውያን ናዳውን ለመመከትና የአገዛዝ ዘመናችንን ለማሳጠር አንድ ሆነን የማንቆምበት፣ በአንድ ተሰልፈን የማንታገልበት ምክንያት ምን ይሆን፡፡ እንዳይቻል ያደረግነው እኛው ራሳችን ነን እንጂ ይቻላል፡፡ጥቂቶች በአንድነትና በጽናት ቆመው ሲገዙን እኛ ብዙ ሆነን በጽናት ጉድለትና አንድነት በማጣት ሀያ አራት አመታት መገዛታችን አያስቆጭም፡ውጤት አልባ የእድሜ ልክ ተቀዋሚነትስ አያሳፍርም፣አረ በቃ እንበል፡፡ ካልን ደግሞ ወንድም እህቶቻችን እየከፈሉት ካለው መስዋዕትነት አንጻር ይህ ብዙም የሚባል አይሆንምና አሁኑኑ በአዲስ አመት ዋዜማ ተግባራዊ እናድርገው፡፡

በሀገራችን ባህል/ልማድ በተለይ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በከተማም ከጥንቱ ባህል ጨርሶ ባልተለያዩት ዘንድ በአዲስ አመት መግቢያ የቅዱስ ዮሐንስ እለት ችቦ ተለኩሶ ከቤት ሲወጣ ከቤቱ በር ግራና ቀኝ እየተተረኮሰ የጎመን ምንቸት ውጣ የገንፎ ምንቸት ግባ ይባላል፡፡ ይህ መልእክቱ ግልጽ ነውና ዝርዝር ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡

እኛስ አገዛዝ በቃ የምንል ኢትዮጵያውያን በያለንበት ችቦ ለኩሰን አንደ ባህል ወጉ እየተረኮስን ባይሆንም በዚህ የዘመን መለወጫ እለት የድምጻዊት አስቴር አወቀን አንድ አድርገን ጌታ የሚለውን ዘፈን እያንጎራጎርን የጥል ምንቸት ውጣ የፍቅር ምንቸት ግባ፣ የበቀል ምንቸት ውጣ የይቅርታ ምንቸት ግባ፣ የጥርጣሬ የሸፍጥና የሴራ ምንቸት ውጣ፣ የመተማመን የቀናነትና የግልጽነት ምንቸት ግባ የማቃር ምንቸት ውጣ የመግባባት ምንቸት ግባ ወዘተ ማለት ብንችል ምንኛ መታደል ነበር፡፡

ለሀገር ይበጃሉ የተባሉ ያልተነገሩ ያልተጻፉ ነሮች የሉም ተግባራዊነት የለም እንጂ፡፡ ሌላው ቀርቶ በተቃውሞው ጎራ የነበሩና ያሉ ከተናገሩትና ከጻፉት ከፊሉን እንኳን ተግባራዊ ማድረግ ችለው ቢሆን ሀገራችን ዛሬ ካለችበት በብዙ መልኩ የተለወጠች ለመሆን በቻለች ነበር፡፡ እናም ከላይ የገለጽኩትን ለማለት መድፈሩ የመጀመሪያ ርምጃ ሆኖ ያሉትን ለመፈጸም መቻል ደግሞ ዋናውና ወሳኙ ጉዳይ ይሆናል፡፡ የምንለውን ተፈጻሚ ለማድረግ ለቃል የመታምን፣ ለህሊና የመገዛትና ከራስ በላይ የማሰብ ቁርጠኝነቱ ካለ 2008ን ለአስተማማኝ ለውጥ የሚያበቃንን ጠንካራ መሰረት የምንጥልበት አመት ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህን ማድረግ ቻልን ማለት ደግሞ ለለውጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠርና ትውልድ ተሻጋሪ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት የሚያበቃንን ጥርጊያ ጎዳና ተያያዝነው ማለት ነበር፡፡ ለሀገርና ለትውልድ ማሰብ ካለ ይህ የማይቻልም የሚገድም አይደለም፡፡ ይቻላል!
ዛሬም እንደ ትናንቱ ወያኔን በማውገዝ አንድ ሆነን ከወያኔ አገዛዝ ለመላቀቅ ግን በየሰበብ ምክንያቱ አንድ ሆነን መቆም ካልቻልን የነጻነቱን ቀን እናራዝመዋልን፡፡ ነገር ግን ዘላለማዊ ምድራዊ ሥልጣን የለምና አንድ ቀን ወያኔና የምንይልክ ቤተ መንግሥት መለያየታቸው አይቀርም፡፡ የሚቻለው እንዳይቻል እንቅፋት ሆነን መስዋእትነቱ እንዲከብድና የወያኔ አገዛዝ ዘመን እንዲራዘም ያደረግን ወገኖች ያኔ ታሪክ ይመሰክርብናል ትውልድም ይፈርድብናል፡፡

በአንድ ሀገር ልጅነት መንፈስ ለጋራ ሀገራችን እንዳንቆም የሚያደርጉንን ሳንካዎች ከውስጣችን አስወጥተን የሀሳብ ልዩነት ያለ፣የሚኖር፣ሊጠፋም የማይችል መሆኑን ተገንዝበን አንድነታችንን አጠንክረን በልዩነቶቻችን ተከባብረን መተማመን፣ ፍቅርና አንድነት በመፍጠር ከወያኔ አገዛዝ ለመላቀቅ የሚያስችለንን መንገድ ለመያዝ ዋናው ቁልፍ መነጋገር መቻል ነው፡፡መቀራረብ መደማመጥ፤

የቱንም ያህል ስንቆፍር ውለን ስንቆፍር ብናድር የሚያለያዩን ጉዳዮች አንድ ከሚያደርጉን በዝተውም ልቀውም ሊገኙ አይችሉም፡፡ እንደውም በሀቅና በንጹህ ህሊና በንጽጽር ከተፈተሸ የሚያለያዩን ሚዛን የማይደፉ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ገነውና ጎልተው ማዶና ማዶ እንድንቆም ለማድረግ የሚያስችል አቅም ያገኙት ከእኔ በላይ የሚል አጋንንት ሰፍሮብን የመነጋገር ፈቃደኝነት፣ የመወያየት ባህል፤ የመደማመጥ ትእግሰት ያሳጣን በመሆናችን ነው፡፡ እናም በዚህ አዲስ አመት ዋዜማ ይህን አጋንንት እናስወጣና የፍቅርን አምላክ ወደ ውስጣችን እናስገባ፡፡

የማለዳ ወግ …ያለ ደጋፊ ፍትህን ፍለጋ ድፍን 9 ዓመት ! (ነቢዩ ሲራክ)

$
0
0
* ብርቱዋ እናት ሀሊማ  !
* የብላቴናው መሀመድና የቤተሰቡ መከራ ጠልቆ አያም ይሆን  ????unnamed (2)
በእርጉም ሀኪሞች ስህተት ፣ በጨካኝ የግል ሆስፒታል አስተዳደርና ባለቤቶች የተገፋች ፣ መገፋት መብቷን ከመጠየቅ ያለንበረከካት ፣ ከምንም በላይ ፍትህን ከፈጣሪ የምትሻ እናት አውቃለሁ ፣ የብላቴናው መሀመድ እናት ሀሊማ  …

እህት ሀሊማ በገንዘብ የእናት ጥልቅ ሰብዕናዋን ያልሸጠች ፣ በብልጭልጭ ስጦታ ያልተደለለች ፣ ለዘጠኝ አመት ከመካ ጅዳ እየተንከራተተች ከዚህ ቀደም ከነነሩት የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት እስከ ሳውዲ ሰበአዊ መብት አስከባሪ ድርጅትና ልዑላን ቤተሰቡች አቤት ብላ ሰሚ ያጣች ብርቱ መንፈሰ ጠንካራ እናት ናት  ! ሀሊማ ደከመኝ ሰለቸኝ የማትል ዛሬም ” በደሌ ይሰማ ፣ ፍርዱን ከፈጣሪ አገኛለሁ! ” በማለት በበደሏት ላይ ፍትህ ታገኝ ዘንድ የሳውዲ ፍትህ አካላትን ደፍራ የምትጠይቅ ድንቅ የዘመናችን እናት ናት  !

ውድ ወገኖቸ ፣ ልብ ሰባሪውን ታሪክ ደግሜ ደጋግሜ አቅርቤዋለሁና ነገር አልደጋግምም ። ለሳውዲ መገናኛ ብዙሃን በተደጋጋሚ ዳሩ ግና መረጃዎች ቀርበው ሲሰናከል የባጀው የድምጼን ስሙልኝ የእናት አቤቱታ እነሆ ሰሚ አግኝቶ በሳውዲ ጋዜጥ የፊት ገጽ ዛሬ ተስተናግዷል  ! የኢትዮጵያዊ እናት የሀሊማ ፍትህ ፍለጋ ታሪክ ከታዋቀው የሳውዲ እለታዊ ጋዜጣ ያንብቡ ፣ ላለወሰሙት ያሰሙ ፣ መረጃውን በማሰራጨት ስለጎደለው ፍትህ ድምጽዎን ያሰሙ  !

ነቢዩ ሲራክ
ነሀሴ 17 ቀን 2007 ዓም
unnamed (1)
A mother fights for justice for her paralyzed child !

Fatima Muhammad
Saudi Gazette

JEDDAH — A mother has been reportedly forced out of a hospital dormitory where she had been living with her paralyzed child after she filed a complaint against the hospital to the Ministry of Health following medical malpractice.

Some four months back, a medical committee at the Ministry of Health found the hospital guilty and asked it to pay  compensation of SR2.4 million, according to documents seen by Saudi Gazette. …

Heart breaking story of Ethiopian mother anose son,  victim of Saudi private hospital confirmed error  !
Must read …


በዝናብ እጥረት የምግብ ዋስትና ችግር ለገጠማቸው በውስን ጨረታ ስንዴ እንዲገዛ ተፈቀደ

$
0
0

unnamedበዝናብ እጥረት ምክንያት የምግብ ዋስትና ችግር ለገጠማቸው ወገኖች በውስን ጨረታ የስንዴ ግዥ እንዲፈጸም ተፈቀደ፡፡ በውስን ጨረታ ግዥ መፈጸም በመንግሥት የሚደገፍ ባይሆንም፣ የስንዴው አስፈላጊነት አጣዳፊ በመሆኑ ምክንያት የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በውስን ጨረታ ግዥ እንዲፈጸም ፈቃድ ሰጥቷል፡፡

በዚህ መሠረት የመንግሥትን ግዥዎች በማዕከላዊ ደረጃ እንዲፈጸም የተቋቋመው የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት፣ ግልጽ ጨረታ የማውጣት ሐሳቡን በመሰረዝ በውስን ጨረታ የስንዴ ግዥ ለመፈጸም የመጨረሻ ዝግጅት ማድረጉ ተገልጿል፡፡

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መልካሙ ደሳሊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል ስንዴ በማቅረብ ከሚታወቁ 40 ኩባንያዎች መካከል ሰባት ኩባንያዎች በደብዳቤ ይጠየቃሉ፡፡ ነገር ግን እነማን እንደሆኑ በውል አልተለዩም፡፡

“ኩባንያዎች ማቅረብ እንደሚችሉ ካሳወቁና በዋጋ ላይ ስምምነት ከተደረሰ ሥራው ይሰጣቸዋል፤” በማለት አቶ መልካሙ ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች መንግሥት በ2007 ዓ.ም. ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ግዥ የፈጸመው 300 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ያቀረቡ ናቸው ተብሏል፡፡

አብዛኛዎቹ የውጭ አገር ኩባንያዎች ሲሆኑ በአገር ውስጥ ካላቸው ወኪል ጋር የሚሠሩ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ስንዴ ግዥ ጨረታ ውስጥ ከ40 በላይ ኩባንያዎች ሲሳተፉ ቆይተዋል፡፡

አብዛኛዎቹ የምሥራቅ አውሮፓ፣ የመካከለኛው ምሥራቅ፣ የእንግሊዝና የሱዳን ኩባንያዎች ናቸው፡፡ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አብረውት ከሚሠሩት ውስጥ ለመረጣቸው ሰባት ኩባንያዎች ብቻ ነው ደብዳቤ በማዘጋጀት ላይ የሚገኘው፡፡

አቶ መልካሙ እንዳሉት፣ ከሰኞ ነሐሴ 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ኩባንያዎቹ ደብዳቤ ይደርሳቸዋል፡፡ በኤልኒኖ ምክንያት ክስተት በኢትዮጵያ የክረምት ወራት የዝናብ መዛባት ማጋጠሙ ይታወቃል፡፡ በዚህ ምክንያትም አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የምርት መስተጓጎል እንዳጋጠማቸው መንግሥት በይፋ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚቴ 222 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ እንዲገዛ መወሰኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይህ ስንዴ ከመጠባበቂያ እህል ክምችት ውጭ ተደርጎ እየተከፋፈለ ያለውን ስንዴ የሚተካ መሆኑ ታውቋል፡፡

ከስንዴ ግዥ በተጨማሪ መንግሥት 700 ሚሊዮን ብር በጀት በመመደብ፣ የተለያዩ አስቸኳይ ዕርምጃዎችን መውሰድ መጀመሩን የግብርና ሚኒስቴር አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምትኩ ካሳ ባለፈው ሳምንት ለሪፖርተር ገልጸው ነበር፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

ከመድፍ ድምጽ አይሎ የተሰማ የጽናት ቃል (ዳኛቸው ቢያድግልኝ)

$
0
0

birhanu tekleከመድፍ ድምጽ ያየለ፣ ጽናትን፣ እምነትንና ጥንካሬን የሚያሳይ ታላቅ ድምጽ በመዲናችን ተሰማ። ማንም ቀስቃሽ ከሚያደርገው ጥሪ በላይ የክተት አዋጅ የመሰለ የእምነት ቃል ፈጽሞ ሊሆን ይችላል ተብሎ ከማይጠበቅበት አቅጣጫ ተሰማ! አዎ ለፍልሚያው ቆርጫለሁ እናንተን ከመንበረ ሥልጣኑ ለማንሳት በኔ አቅም ያለውን ሁሉ ለማድረግ ጉዞ ጀምሬአለሁ። በአካል ከስፍራው አልደረስኩም እንጂ በመንፈስ ሸፍቻለሁ ይህንን አምናለሁ ግን ግን ፈጽሞ ጥፋተኛ አይደለሁም! አሁንም ባለሁበት ሁኔታና ካለሁበት ለመታገል ከቶውንም ወደሗላ አልልም!

በእርግጥም ከነጎድጓድ ያየለ ከመድፍ ድምጽ አስርሺህ ጊዜ የበለጠ ሃያል ድምጽ በ‘አንበርካኪዎቹ’ ማማ ላይ በ‘አስጎንባሾቹ’ መድረክ ላይ ተሰማ። ኢትዮጵያ ያልታደለ ሕዝብ የሚኖርባት ግን የታደለች ሀገር ናት። አፈርና ውሀዋ የሰራው ዜጋዋ ከአየሩ ጋር አብሮ ከሚተነፍሰው የነፃነት መንፈስ ጋር ተዳምሮ ከዘመን ዘመን በኩራት እንዲረማመድ ሆኖ የተሰራ ነው። ለዚህም ነበር የጥቁር አፍሪካ ፈርጥ ለነፃነት ፈላጊዎች የመንፈስ ምርኩዝ ተብሎ የሚጠራው። ግና የእናት ሆድ ዥጉርጉር እንዲሉ ባርነትን የተከተቡ፣ ጥላቻ የተጠናወታቸው በአእምሮ ድህነት የሚሰቃዩ ከዚችው ኢትዮጵያ የተፈጠሩ የሰው አረሞች ቁልቁል ደፍቀው እምነትና ነፃነቱን ክፉኛ ፈትነውታል። አወቅን ባይ የትምክህት ባሮች እንቅፋት እየሆኑት በጠላት ወጥመድ ውስጥም እየጣሉት ከችግር ወደመከራ ከበረዶ ወደ እሳት የሚገላበጥበትን ገሃነማዊ ህይወት እንዲመራ አድርገውታል። የትግራይ ጎጠኞች ተስፋውን ያሟጠጠ እንዳሻን የምናደርገው ፈሪ ሕዝብ ፈጥረናል በሚሉበት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ አለንልሽ የሚሏት ለክብሯ ለነፃነቷ ሊሞቱላት የቆርጡ ጀግኖች ወደ ትግል ሜዳ ሲተሙ፣ በያሉበት ስንደቅዓላማዋን ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ ለተመለከተ ግን እውነትም የታደለች አገር! እንዲል ያስገድደዋል።

ይህ ያበቃለት የመሰለው የራሱ ወገኖች ደካማና ፈሪ አድርገው የሚስሉት ሕዝብ ጀግንነትና ቆራጥነት በደሙ ውስጥ መመላለሱን የሚያረጋግጥና ያለነፃነት ከመኖር ማናቸውንም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ግን ዕለት በዕለት እያስመሰከረ ነው። በየአደባባዩ፣ በየጉድባውና ሰርጣ ሰርጡ ጣዕረሞት ከመሰሉት የሀገርና የሕዝብ ጠላቶች ጋር ለመፋለም መቁረጣቸውን የሰማ ሁሉ ተስፋ በውስጡ እያበበች ነው። በርገር በሊታዎቹ ቂጣ ለመብላት የተዘጋጀ ስነልቦና እንዳላቸው አስመስክረዋል። ስሜታቸው ብቻ ሳይሆን አጥንታቸው የሟሟ የሚመስል በወያኔ እስር ውስጥ ተጠፍረው ያሉ ከአሳሪዎቻቸው ገዝፈውና ታላቅ ሆነው ደካሞቹን ቁልቁል ሲመለከቱ ማየትም ያለውን እምቅ ሃይል አመላካች ነው። የርዕዮት ብዕር ወረቀት ማድማቱን ማየት ስሜት የሚያሞቅ ነው። እነ አብርሃ ደስታ ቁም ነገር ሊከትቡ ወደ ትልቁ እስር ቤት መመለሳቸው እነ ሃብታሙ ‘እመነኝ!’ ሲሉ እንደገና ልንሰማ መሆኑን ማሰብ ደስ ያሰኛል።

በሌላ ወገን ወያኔ የተማመነበት ሰራዊት ኢትዮጵያዊነቱ በልጦበት እየከዳ ነው። መሳርያውንም ወደ አገር አፍራሽ ጎጠኞች እንደሚያዞር ምልክቶቹ ሁሉ እየታዩ ነው። ስማቸውን ያልሰማን ማንነታቸውን ያላወቅን ለጊዜው ማወቅም የማይገባን በርካታ ጀግኖች በዚህ የትግል መስመር ገብተው ለፍልሚያ ስለመዘጋጀታቸው ከቶወንም ጥርጣሬ የለንም። የሰላም በር ሲዘጋ የፍልሚያ መስኮቶች ይበረገዳሉና በየአቅጣጫው መነሳሳትን ማየታችንም ለዚሁ ነው። ከተሞች ሁሉ የትግል አምባ ወደመሆንና ጎጠኞችንና የሀገር ጠላቶችን በህግም በትጥቅም ቢሆን ለመፋለም ዝግጁነታቸውን እያረጋገጡ ነው። ፍርሃት ያራዳቸው የወያኔ ጉልተኞች ብር በሻንጣ ይዞ መሮጥ መጀመራቸውም የዚሁ አይነተኛ የውድቀት ምልክት ነው።

ወደ ጀመርኩት ርዕስ ልመለስና የነብርሃኑ ተክለያሬድን ዜና እንደሰማሁ ኢካድፍ የለጠፈውን ምስል ተመለከትኩ ሰውነት የሚወር ስሜት ተሰማኝ በወጣቶች ያለኝ ጽኑ እምነት ታደሰ። ኢየሩሳሌምን በስስት ዐይን ተመለከትኩ፣ የጀግና ክብር የሚገባት የጣይቱ ልጅ በሰላሙም ጎዳና ሁሉን ችላ በፅናት የሄደችበት ጀግናዬ ናት። ሽንታም እያሉ ለሚሳደቡት እንደኛ ለመሆን የጫካውን መንገድ ሞክሩ ለሚሉና ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ሆነው ኢትዮጵያን ወግተው በፈረንጅና በተጃጃሉ ኢትዮጵያውያን ትከሻ ስልጣን ላይ የወጡትን እብሪተኞች ለመፋለም ጉዞውን የጀመሩትን ጀግኖች አንኳን እኔ ጠላትም እንዲያደንቃቸውና እንዲያከብራቸው ግድ ይለዋል። መድረኩን አገኙ ቃላቸውን ሰጡ። ቃላቸው ግን ድፍን የኢትዮጵያ ወጣቶችን የሚያስሸፍት እንዲሆን ቅንጣት ታክል አልጠራጠርም።

ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ኢየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው፣ ዳሴ ካሳሁን ክብር ለናንተ ይሁን። ካሰባችሁበት ያልደረሳችሁ መስሏችህ ከሆነ አትሳሳቱ ማናችንም ከምናሰበው በላይ ግዳጃችሁን ተወጥታችሗል። መድረስ ብቻ አይደለም አልፋችሁ ሄዳችሗል። ከጠላት ምሽግ ገብቶ የጨበጣ ውጊያ ከመግጠም በላይ የእምነት ቃላችሁ ስራውን ሰርቷል። በዚህ በርካቶች አንገት በደፉበት ሰዐት፣ በርካቶች በሌሎች ትከሻ መሸጋገርን በሚሹበት ጊዜ እናንተ ድልድይም መስዋዕትም ሆናችሁ ለታሪክ የሚተርፍ ገድል ፈጽማችሗል። አዎ ጥፋተኛ ሳትሆኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግኖቹ ናችሁና ደስ ይበላችሁ። ፈለጋችሁን የሚከተሉ በረሃ የሚዘልቁም ሆነ ባሉበት ሆነው በተጠንቀቅ የሚጠብቁ በርካቶችን በማነሳሳታችሁ ክብር ለእናንተ ይሁን።

ኢትዮጵያ በነፃነትና በክብር ለዘለዐለም ትኑር!

‹‹በሕገ መንግሥቱ ውስጥ የአውራ ፓርቲ ሥርዓት ቦታ የለውም›› ዶ/ር አበራ ደገፋ፣ የሕገ መንግሥት ኤክስፐርት

$
0
0
ዶ/ር አበራ ደገፋ፣ የሕገ መንግሥት ኤክስፐርት

ዶ/ር አበራ ደገፋ፣ የሕገ መንግሥት ኤክስፐርት

ዶ/ር አበራ ደገፋ የሕገ መንግሥት ኤክስፐርት ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ዶ/ር አበራ በሕገ መንግሥት ጉዳዮች ላይ በርካታ ሥራዎችን አሳትመዋል፡፡

ከቀናት በፊት ነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. በሥራ ላይ ከዋለ 20ኛ ዓመቱን በደፈነው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት፣ በተለይም ሕገ መንግሥቱን የመተርጎም ሥልጣን በተሰጠው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣንና ከአተገባበሩ ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ላይ ሰለሞን ጎሹ ከዶ/ር አበራ ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

ሪፖርተር፡- ሕገ መንግሥቱ በሥራ ላይ ከዋለ በኋላ በአስተዳደር ጉዳይ ላይና በዜጎች አስተሳሰብ ላይ ምን ዓይነት መሠረታዊ ለውጥ አምጥቷል?

ዶ/ር አበራ፡- ሕገ መንግሥቱ ሲወጣ ብዙ ነገሮች ይለወጣሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ ቃል የገባቸውን ነገሮች ወደ ተግባር ይለውጣል ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ነበር፡፡ ከ20 ዓመት በኋላ ግን የተጠበቀውን ያህል ሕገ መንግሥቱ ለውጥ አላመጣም፡፡

ሪፖርተር፡- የሕገ መንግሥቱ ተግባራዊነት የተገደበበትን ምክንያት አንዳንዶች ከዲዛይን ጋር ሲያገናኙት ሌሎች ግን ከፖለቲካ ልሂቃኑ በጎ ፈቃድ ጋር ያዛምዱታል፡፡ ለእርስዎ ቁልፍ የችግሩ ምንጭ ምንድነው?

ዶ/ር አበራ፡- ዲዛይን በተደረገው የተቋማት ሚናና የግለሰቦች ተፅዕኖ መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት አለ፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ የግለሰቦች ሚና ቀላል አይደለም፡፡ ነገር ግን ከዲዛይንም አንፃር ሕገ መንግሥቱ ክፍተቶች አሉበት፡፡ ለምሳሌ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ብንወስድ ይሠራቸዋል ተብሎ የተሰጡትን ተግባራት በስኬት ለመፈጸም በሚያስችል መልኩ ነው ወይ የተዋቀረው የሚለውን ብንመለከት፣ ያ ዓይነት ሥልጣን እንዳልተሰጠው ማየት ይቻላል፡፡ ምክር ቤቱ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሚታቀፉበት ነው፡፡ ነገር ግን የእነዚህን ቡድኖች መብት ለማስጠበቅ የሚያስችል አወቃቀር የለውም፡፡ የመጀመሪያው ችግር ሕግ የማውጣት ሥልጣን የሌለው መሆኑ ነው፡፡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር ሲነፃፀር ሥልጣን የለውም ማለት ይቻላል፡፡ በፌዴራል መንግሥት አወቃቀር የላይኛው ምክር ቤት የፌዴሬሽኑን መሥራች አባላት መብት ያስጠብቃሉ፡፡ በኢትዮጵያ ሁኔታ ክልሎችና ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አንድ አይደሉም፡፡

በእርግጥ እንደ ኦሮሚያ ባሉ ክልሎች ሁለቱ ተደራርበው ይገኛሉ፡፡ አንቀጽ 39(3) ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ ራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለው ይላል፡፡ ይሁንና የክልልነት ደረጃ የሌላቸው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ይህን መብት ለመጠቀም ይቸገራሉ፡፡ ሌላው የዲዛይን ችግር ሕገ መንግሥቱ ራሱ ለፌዴራል መንግሥቱ አብዛኛውን ሥልጣን የሰጠና ለክልሎች ደግሞ የተወሰኑትን የሰጠ መሆኑ ነው፡፡ የፋይናንስና የተፈጥሮ ሀብትን የመጠቀም ሥልጣን ለክልሎች የተሰጠው በተወሰነ መልኩ ነው፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የተሰጠውን ሥልጣን ነው ሊያስከብር የሚችለው፡፡ ባልተሰጣቸው ሥልጣን ላይ ሊሠራ አይችልም፡፡

ሪፖርተር፡- የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከማንነት ጥያቄ፣ ከግጭት አወጋገድ፣ ከጋራ ገቢና ከክልሎች ድጎማ፣ ከፌዴራል መንግሥቱ በክልል ጣልቃ ከመግባት ጋር በተያያዙና በመሰል ጉዳዮች ላይ በርካታ ሥልጣኖች ተሰጥቶታል፡፡ የተቋሙ አፈጻጸም ደካማ የሆነው በሥልጣን እጦት ሳይሆን በፖለቲካ ቁርጠኝነት ማነስ ነው በማለት የሚቀርበውን ክርክር እንዴት ያዩታል?

ዶ/ር አበራ፡– እነዚህም ሥልጣኖች ቢሆኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ብቻውን የሚጠቀማቸው አይደሉም፡፡ ለምሳሌ ያህል በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62(9) ላይ ‘ማንኛውም ክልል ይህን ሕገ መንግሥት በመጣስ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ የፌዴራሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ያዛል’ በማለት ለምክር ቤቱ ሥልጣን ይሰጠዋል፡፡ በነገራችን ላይ እንዲገባ ያዛል እንጂ በሚወጣበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ ስለመስጠት ሕገ መንግሥቱ ምንም የሚለው ነገር የለም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የፌዴራሉ መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣው አዋጅና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴርን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ምክር ቤቱ ብቸኛው ወሳኝ እንዳልሆነ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ምክር ቤቱ ሳይጠየቅ የፌዴራል መንግሥቱ ጣልቃ የሚገባበት ዕድል ሁሉ አለ፡፡ የፌዴራል ሥርዓቱን ጠንካራና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥልጣንና ተግባራት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አልተሰጡም፡፡ የፌዴራል መንግሥቱ በተለይም የአስፈጻሚው አካል ሥልጣን ላይ ገደብና ቁጥጥር በማድረግ ለክልሎች ወይም ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት ጥብቅና በሚቆምበት መልኩ አልተደራጀም፡፡

ሪፖርተር፡- በሕገ መንግሥቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን የክልል ምክር ቤቶች በራሳቸው ወይም በቀጥታ በሕዝብ እንዲመረጡ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተደንግጓል፡፡ በተግባር ግን ሕዝቡ በምርጫው ተሳትፎ እንዲያደርግ ተደርጎ አያውቅም፡፡ የክልል ምክር ቤቶች ደግሞ ሕገ መንግሥቱ ወደ ሥራ ከገባ ጀምሮ ተለውጦ በማያውቀው ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ተፅዕኖ ሥር ናቸው ተብለው ይታማሉ፡፡ ከዚህ አንፃር የፖለቲካ አካሄዱ ተፅዕኖ ከዲዛይን ችግር እጅግ የላቀ ነው በማለት የሚከራከሩትን እንዴት ያዩዋቸዋል?

ዶ/ር አበራ፡– የፖለቲካው ምኅዳርና የፓርቲው ሥርዓት የባሰ ችግር ፈጥሯል፡፡ የክልል ምክር ቤቶች በገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ሥር ናቸው፡፡ ይኼ ቢለወጥ የተወሰነ ለውጥ ሊመጣ ይችላል፡፡ ነገር ግን ዋናው ነገር የፌዴሬሽን ምክር ቤት ድምፅን በድምፅ የመሻር (ቬቶ) መብት የሌለው መሆኑ ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱንም የሚተረጉመው ጉዳዩ ሲቀርብለት እንጂ በራሱ ተነሳሽነት የክልሎች ወይም የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መብት ተነካ ብሎ አይደለም፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን ሕግ ያዘጋጀለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው፡፡ ስለዚህ የራሱንም መብት ማስጠበቅ ያልቻለ ምክር ቤት ነው፡፡ በአጠቃላይ ነፃና ገለልተኛ ተቋም አልሆነም፡፡ አሁን ያለው የአንድ ፓርቲ ሥርዓት ብዙ ነገር አበላሽቷል፡፡ ይሁንና ወደ መድበለ ፓርቲ ሥርዓት ብንሸጋገርም የፌዴራል ሥርዓቱ ውጤታማ እንዲሆን የክልሎች ሥልጣን ሊጨምር ይገባል፡፡

ሪፖርተር፡- ዋነኛው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣን ሕገ መንግሥቱን መተርጎሙ ነው፡፡ ባልተለመደ መልኩ ይህ ሥልጣን የተሰጠበት ምክንያት ለእርስዎ አሳማኝ ነው?

ዶ/ር አበራ፡- አገሮች ሕገ መንግሥት ሲያረቁ ከሌሎች አገሮች መማር ቢኖርባቸውም፣ ለራሳቸው ልዩና ተጨባጭ ሁኔታ ትኩረት መስጠትም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይሁንና የፌዴራል የመንግሥት አወቃቀርን የሚከተል ሕገ መንግሥት ሲረቀቅ ሊሟሉ የሚገቡ መሠረታዊ ሁኔታዎች አሉ፡፡ አንደኛው ሁኔታ የክልሎችን ውክልና የያዘው ምክር ቤት ወይ በሕግ ማውጣት ሒደቱ ሊሳተፍ ካልሆነም ውሳኔን በውሳኔ የመሻር መብት ሊያገኝ ይገባል፡፡ ሁለተኛው ሁኔታ በፌዴራል መንግሥቱና በክልሎች መካከል ግጭት ወይም አለመግባባት በሚኖርበት ጊዜ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ የሚያስታርቅ አካል መኖር አለበት፡፡ ይኼ አካል የፍርድ ቤቶች ባህርያት ሊኖሩት ይገባል፡፡ እኔ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፖለቲካ ተቋም ስለሆነ ሕገ መንግሥቱን ሊተረጉም አይገባም የሚለውን ክርክር አልደግፍም፡፡ ሕገ መንግሥት የሕግ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ሰነድም ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚወክለው ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ቢሆንም፣ በተግባር የሚያንሸራሽረው የክልሎችን አቋም ነው የሚለውን ክርክር እንዴት ያዩታል? በድምፅ ደረጃስ ብዙ ሕዝብና ብሔሮች ያሏቸው ክልሎች በርካታ አባላት እንዲኖራቸው መደረጉን እንዴት ያዩታል?

ዶ/ር አበራ፡– ብዙ ብሔሮች ያላቸው ክልሎች በምክር ቤቱ የተሻለ ድምፅ አላቸው፡፡ እነዚህ በአንድ ክልል የሚገኙ ብሔሮች ተመሳሳይ አቋም ሊያንፀባርቁ ይችላሉ፡፡ ደቡብ ክልል በርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ስላሉት በርካታ ተወካዮች በምክር ቤቱ አሉት፡፡ የኦሮሚያና የአማራ ክልል ተወካዮች ተደምረው ከደቡብ ያንሳሉ፡፡ ይኼ ውሳኔ አሰጣጡን ዴሞክራሲያዊ አያደርገውም፡፡ ይኼ ክልሎችን መወከል ለምን ብሔሮችን በመወከል ተቀየረ የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡

ሪፖርተር፡- በተግባር ደረጃ የፌደራልና የክልል አስፈጻሚ አካል አባላት የሆኑ ሰዎች የክልል ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል ሲሆኑ ይታያል፡፡ ይኼ በራስ ጉዳይ ላይ ዳኛ መሆን አይቻልም ከሚለው መርህ ጋር አይጋጭም?

ዶ/ር አበራ፡– የፖለቲካ ትኩሳት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ምክር ቤቱ የመሸሽ አዝማሚያ ያሳያል፡፡ እስካሁን ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጋጭ ነው ብሎ ውሳኔ የሰጠው በአቶ መላኩ ፈንታ የይግባኝ መብት ላይ ብቻ ነው፡፡ የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔውም በተመሳሳይ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ጠልቆ አይገባም፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትንና የአስፈጻሚውን አካል ውሳኔ ተገዳድሮ አያውቅም፡፡ ይኼ ዞሮ ዞሮ ከፖለቲካ ምኅዳሩ ጋር ይገናኛል፡፡

ሪፖርተር፡- የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር ለመደበኛ ፍርድ ቤቶች ከተሰጠው የዳኝነት ሥልጣን አንፃር ልዩነቱ በውል የተለየ አይደለም ተብሎ የሚቀርበውን ክርክር እንዴት ያዩታል?

ዶ/ር አበራ፡– ፍርድ ቤቶች ወይም የዳኝነት አካላት ራሳቸው ሥልጣናቸውን የሚያስከብሩ አይደሉም፡፡ እንኳን ተፈጥሯዊ ሥልጠናቸውን በመጠቀም ሊሟገቱ በግልጽ የተሰጠ ሥልጠናቸውንም የሚጠቀሙ አይመስሉም፡፡ በተለይ ጉዳዩ የፖለቲካ ትኩሳት ያለው በሚሆንበት ጊዜ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት መምራትን ይመርጣሉ፡፡ ምክር ቤቱም ጉዳዮችን በአግባቡ የመመርመርና ውሳኔን በተቀላጠፈ ሁኔታ የመስጠት ሪኮርዱ ደካማ ነው፡፡ ሁለቱም ፍርኃት አለባቸው፡፡ በመሀል እየተጎዳ ያለው ጉዳዩ ውሳኔ እንዲያገኝ የሚጠይቀው ዜጋ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በኢትዮጵያ የሚነሱ በርካታ ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎች ቢኖሩም፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ወይም ለአማካሪው የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔ እስካሁን የቀረቡት በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ ይህ አንዳንዶች ሕገ መንግሥቱ ገና ያልተፈተነ ነው እንዲሉ አድርጓቸዋል፡፡ እርስዎ በዚህ ይስማማሉ?

ዶ/ር አበራ፡- በቡድኖችም ሆነ በግለሰቦች ከሕገ መንግሥቱ ጋር የተገናኙ ቅሬታዎች ይኖራሉ፡፡ ለአንዳንዶች የማንነት ጥያቄ ይሆናል፡፡ ለሌሎች ደግሞ አዲስ የወጣው አዋጅ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን መብት ነክቶ ሊሆን ይችላል፡፡ በምታነሳው ጥያቄ ሌላ ተጨማሪ ጉዳት ይደርስብኛል ብለህ ከሰጋህ ጥያቄ ለማቅረብና ሥርዓቱን ለመፈተን አትበረታታም፡፡ አንዳንድ ጉዳዮችም ከሕጋዊ መንገድ ይልቅ በፖለቲካ ሲፈቱ ነው የሚታየው፡፡ ነገር ግን መፍትሔው ሁሉንም የሚያስማማ ከሆነ ሁሉም ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ወይም ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት መሄድ አለበት ብዬ አላምንም፡፡ አስቀድሞ በሥራ ላይ የነበረው ሥርዓት ውጤታማ ሆኖ አዲሱ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት እንግዳ የሆነበት ሕዝብ ይኼኛውን መንገድ ውድቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ሪፖርተር፡- በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይ ምርምር የሚሠሩ ምሁራን በርካታ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ይጠይቃሉ፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ደግሞ ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያን የመፍራት አዝማሚያ አለው ተብሎ ይተቻል፡፡ ይህን ተቃርኖ እንዴት ያዩታል?

ዶ/ር አበራ፡- ሕገ መንግሥት በመርህ ደረጃ የሕዝብ ነው፡፡ ሕዝቡ የባለቤትነት ስሜት ሊኖረው ይገባል፡፡ ስለዚህ ከሕገ መንግሥታዊ ቅቡልነት ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ካየነው ማንኛውም አካል ይኼ ሕገ መንግሥት ሊሻሻል አይገባም ሊል አይችልም፡፡ ማሻሻያ ጥያቄው ሕዝባዊ ድጋፍ ካለው ማንም በር ሊዘጋ አይችልም፡፡ ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ የሚጠየቅባቸው ጉዳዮች በአብዛኛው በማርቀቅ ሒደቱ ጊዜም አወዛጋቢ የነበሩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ የመሬት ባለቤትነትና የመገንጠል መብትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ያኔ በድምፅ ብልጫ የተሸነፉ አካላት በጊዜ ሒደት አብላጫ ድምፅ ሊኖራቸው ይችላል፡፡

ሪፖርተር፡- ቡድኖችም ሆኑ ግለሰቦች በእኩልነትና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ከዚች አገር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሕገ መንግሥቱ ምን ዓይነት ሚና ተጫውቷል?

ዶ/ር አበራ፡- ተጠቃሚነትን የምንለካው በምንድን ነው? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ ተሳትፎና ተደራሽነት ይኼን ለመለካት ወሳኝ ነገሮች ናቸው፡፡ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለሁሉም ተደራሽ መሆን አለበት፡፡ አሁን ሁሉም እኩል ተጠቃሚ ነኝ ብሎ ይገምታል ወይ ብለህ መጠየቅ አለብህ፡፡ መሬት ከደሃው ይልቅ ሀብት ላለው ዜጋ ነው ተደራሽ እየሆነ ያለው፡፡ በኢትዮጵያ እየመጣ ያለው ልማት ማንን ነው ተጠቃሚ እያደረገ ያለው የሚለውም ጥያቄ መልስ የሚያሻው ነው፡፡ በቅርቡ ከተደረገው ምርጫ አንፃር የፖለቲካ ምኅዳሩ ጠቧል ሳይሆን ተዘግቷል የሚሉ እየተበራከቱ ነው፡፡ የፖለቲካ ሥልጣን ለሁሉም ተደራሽ መሆኑ ላይ የምርጫው ውጤት ጥርጣሬ ያስነሳል፡፡ ሕገ መንግሥቱ ግን ቃል የገባው ይህን ዓይነት ሥርዓት ለመፍጠር አይደለም፡፡ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት፣ የመደራጀት መብት፣ ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት መብት፣ ፍትሐዊ ውክልናን የሚያረጋግጥ ሕገ መንግሥት በተግባር ላይ ውሏል ወይ ብለን መጠየቅ አለብን፡፡ ጥርጣሬ ቢኖረኝም ሕዝቡ እንዲህ ነው የሚያስበው ብዬ ልናገር አልችልም፡፡

ሪፖርተር፡- አሁን ገዥው ፓርቲ የሚከተለው የልማታዊ መንግሥት ርዕዮተ ዓለም ከኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ጋር የሚስማማ አይደለም በሚል የሚተቹ አሉ፡፡ የእርስዎ አቋም ምንድን ነው?

ዶ/ር አበራ፡- ሕገ መንግሥቱ በመሠረቱ የሊበራል አስተሳሰብ የሚያራምድ ነው፡፡ የሚያበረታታው የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት ከታች ወደ ላይ የሚሄድ ነው፡፡ የሕዝብን ፍላጎት መሠረት አድርጎ የሚሄድ የውሳኔ አሰጣጥ ነው የዘረጋው፡፡ ልማታዊ መንግሥት ይኼን አሠራር የሚገለብጥና ከላይ ወደ ታች የሚወርድ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ውስጥ የአውራ ፓርቲ ሥርዓት ቦታ የለውም፡፡ ይኼ ሕገ መንግሥቱ ላይ የተቀመጡ በርካታ መርሆዎችን አላስፈላጊ የሚያደርግ ሥርዓት ነው፡፡ በኢሕዲሪ ሕገ መንግሥት ላይ የተቀመጠ ሥርዓት ነው፡፡ ልማታዊ መንግሥት በኢትዮጵያ ያሉትን እንደ ብሔር፣ ሃይማኖት፣ የፖለቲከ አመለካከትና መሰል ብዝኃዊነትን ለማስተናገድ የሚያስችል አይደለም፡፡ አንድ ወጥ አመለካከት በዚህች አገር ተረጋግጧል ማለት የሚያሳምን አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡- በኢትዮጵያ ካለው የድህነት ሥር መስደድ አኳያ ያሉትን የተለያዩ ልዩነቶች በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለማስተናገድ መሞከር ከድህነት በፍጥነት ለመውጣት አያስችልም በሚል የሚቀርበውን ክርክር እንዴት ያዩታል?

ዶ/ር አበራ፡– ዴሞክራሲ የጋራ ራዕይ ላይ ያተኮረ አስተዳደር ይዘረጋል፡፡ የተለያዩ አመለካከቶችን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ካስተናገድን ልማትን በፍጥነት አናመጣም ለሚሉ አካላት የማቀርብላቸው ጥያቄ ስለማን ልማት ነው የምታወሩት ነው፡፡ ስለ ሕዝቡ ልማት የሚያወሩ ከሆነ ይኼ አመለካከት ስህተት እንደሆነ ይረዳሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብን ያልተመለከተ ልማትን እኔ ልማት ልለው አልችልም፡፡ አንድ ፓርቲ ሕዝቡ ላይ የሚጭነውና ሌላው አብዛኛው ዜጋ የማይጋራው፣ የተለዩ አመለካከቶችን የማያስተናግድ ልማትን ልማት ልለው አልችልም፡፡ አንድ ቡድን ስለልማት ያለውን አረዳድ ሌላው ላይ መጫን አለበት ብዬ አላምንም፡፡ ልማት መብት ተኮር መሆን አለበት፡፡ ሰው ሰው የሚሸትና ሰብዓዊነት ገጽታ የተላበሰ ልማት ነው ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት፡፡

ሪፖርተር፡- ሕገ መንግሥቱ ባለፉት 20 ዓመታት ከሄደበት ጉዞ የተሻለ በመጪዎቹ 20 ዓመታት እንዲጓዝ ምን መደረግ አለበት ይላሉ?

ዶ/ር አበራ፡– ለሁሉም ክፍት የሆነ የፖለቲካ ከባቢ ሁኔታን መፍጠር ዋናው ተግባር መሆን አለበት፡፡ ሕገ መንግሥቱ ያስቀመጠው የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ተግባራዊ መሆን አለበት፡፡ እያንዳንዱ ቡድንና ዜጋ የአገሪቱን ዕጣ ፈንታ የመወስን ዕድል እንዳለው ሊያምን ይገባል፡፡ ይህ ካልተፈጠረ የሕገ መንግሥቱ ቀጣይነትም ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ ካልሆነ ይህም ሕገ መንግሥት ዕጣ ፈንታው ከዚህ በፊት እንደነበሩት ይሆናል፡፡ ይኼ አካል ዕድል ካገኘ ይኼኛውን አንቀጽ ይቀይራል የሚለው ነገር አያዋጣም፡፡ የሕዝቡ ፈቃድ ከሆነ ሊከለከል አይገባም፡፡ አግላይ የሆነ ሥርዓት ይዞ መቀጠል አደጋ አለው፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

ኢሕአዴግ ራሱን ይመልከት! ጋዜጣው ሪፖርተር ርዕሰ አንቀጽ

$
0
0

በጋዜጣው ሪፖርተር

85e2b2dbb35ca49ffb94675c848f9135_Lኢሕአዴግ አሥረኛውን ድርጅታዊ ጉባዔ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ በመጪው መስከረም ወር አራተኛ ሳምንት ላይ ደግሞ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አገሪቱን ለመምራት የሚያስችለውን ፓርላማ ሥራ ያስጀምራል፡፡

ላለፉት 24 ዓመታት አገሪቱን በማስተዳደር ላይ ያለው ኢሕአዴግ አሁን ቆም ብሎ በአንክሮ ራሱን መገምገም አለበት፡፡ ውስጡን አብጠርጥሮ መፈተሽ አለበት፡፡ የተሸከማቸውን ጉድፎች አራግፎ በሥርዓት አገር ማስተዳደር አለበት፡፡ በስኬቶቹ የሚመፃደቀው ኢሕአዴግ በጣም በርካታ ጉድለቶች ስላሉት መፍትሔ ያስፈልገዋል፡፡ ኢሕአዴግ ራሱን ያጥራ! ራሱን ይመልከት!

ኢሕአዴግ በአሥረኛው ድርጅታዊ ጉባዔው የመጀመሪያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም፣ ሁለተኛውን ዕቅድ አጠናክሮ ለመቀጠል ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ባለፉት 12 ዓመታት በኢሕአዴግ አመራር የተመዘገበውን ዕድገት ለማስቀጠል፣ ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ለውጥና ትራንስፎርሜሽን ቀጣዩ ትኩረት እንደሚሆንም እንዲሁ ትልቅ ግምት የተሰጠው አጀንዳ ነው፡፡ ይህ ለአገር ጠቃሚ በመሆኑ ድጋፍ ይሰጠዋል፡፡ ነገር ግን ዕድገቱም ሆነ ትራንስፎርሜሽኑ ሰው ሰው ካልሸተተ፣ የዜጎችን መሠረታዊ መብቶች ካላከተተ፣ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ካልተመቸ፣ የሕዝቡን የነቃና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ተሳትፎ ካላረጋገጠ፣ ሙስናን ከሥሩ መንግሎ ካልጣለ፣ ፀረ ዴሞክራሲ ተግባራትን ካላስወገደ፣ ሕገወጥ ተግባራትን ካላጠፋ፣ ወዘተ ልፋቱ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡

አንድ አገር ሰላሟና ብልፅግናዋ ዘላቂና አስተማማኝ የሚሆነው የሕግ የበላይነት በተግባር ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ዜጎች በሕግ ፊት እኩል መሆናቸውን ሲያምኑ፣ ሕግም ለሁሉም ዜጎች እኩል ጥበቃ ሲያደርግ፣ ፍትሕ ለሁሉም ተደራሽ ሲሆንና የፍትሕ ሥርዓቱ በነፃነት ሲንቀሳቀስ የሕግ የበላይነት መኖሩ ይረጋገጣል፡፡ ‹‹አንድን ንፁኅ ዜጋ ከማሰር ይልቅ አንድ ሺሕ ዜጎችን መፍታት የተሻለ ነው›› የማለው የሕግ ጽንሰ ሐሳብ በአንድ አገር ውስጥ ተግባራዊ ሲደረግ፣ ዜጎች በነፃነት በአገራቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ውስጥ በንቃት ይሳተፋሉ፡፡ ነገር ግን በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ሰበብ እየተፈለገላቸው በሚከሰሱና በሚታሰሩ ዜጎች ምክንያት አገራችን ውስጥ በፍትሕ ላይ መተማመን ጠፍቷል፡፡ ኢሕአዴግ ይኼ ካላሳሰበው ሌላ ምን ያሳስበዋል? ሰዎች ያለጥፋታቸው ታስረው የቀረበባቸው ክስ የማያወላዳ በመሆኑ በነፃ ሲሰናበቱ አሁን መታየት ጀምሯል፡፡ የአንዳንዶችም ክስ ሲቋረጥም ተስተውሏል፡፡ ከመነሻው እንዲህ ዓይነት አሳዛኝ ተግባር ለምን ይፈጠራል? የፍትሕ ሥርዓቱስ ለምን ይሳጣል? ለሕግ የበላይነት ለምን ቅድሚያ አይሰጥም? ብዙ ማለት ይቻላል፡፡

ዜጎች በገዛ አገራቸው ሰብዓዊ መብታቸው ሲጣስ ዝም ይባላል፡፡ በአመለካከታቸው ምክንያት መደብደብ፣ መታሰር፣ መንገላታት፣ ከሥራ መባረር፣ የቤተሰብ መበተን፣ ወዘተ ሲደርስባቸውና ጩኸቱ ሲበረክት በተደጋጋሚ ተሰምቷል፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላቶቻቸው እንደተገደሉባቸው በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡ በታዳጊ ዴሞክራሲ ውስጥ የሚያጋጥም ነው እየተባለ ዜጎች በገዛ አገራቸው ሲሰቃዩ እስከ መቼ ይቀጥላል? የመልካም አስተዳደር እጦት ምሬት ከዳር እስከ ዳር ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ሥራ መሥራት ያቃታቸው ሹማምንት የተመደቡበት ኃላፊነታቸውን መወጣት ሳይችሉ በመቅረታቸውና ለአገር ደንታ የሌላቸው ሹማምንት የግል ጥቅማቸውን እያሳደዱ ሕዝብ ሲያስለቅሱ ዝምታው ምንድነው? ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ እነዚህን ችግሮች መፍታት ያቃተው ለምንድነው? ችግሮቹስ ለምን ይድበሰበሳሉ? በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡

የዴሞክራቲክ ተቋማት አለመጠናከርና በፍርኃት ቆፈን መያዝ፣ የሲቪል ማኅበረሰቡ ደብዛው መጥፋት፣ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓቱ ደብዝዞ የአውራ ፓርቲ ሥርዓት መንገሥ፣ የሕዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች ሕግ የማውጣትና አስፈጻሚውን የመቆጣጠር አቅም አለመጠንከር፣ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያሉ መገናኛ ብዙኃን የገዥው ፓርቲ ብቻ አገልጋዮች መሆን፣ የግሉ ሚዲያ መፍረክረክ፣ ወዘተ ግልጽነትና ተጠያቂነትን እያጠፋ ነው፡፡ በየቦታው ትንንሽ አምባገነኖች እየተፈለፈሉ ነው፡፡ ለአገር አደጋ ነው፡፡

ሙሰኞች የአገር ሀብት እየዘረፉ ሲከብሩ ዞር ብሎ የሚያያቸው የለም፡፡ ጭራሽ በድርጅት አባልነት ከለላ፣ በሹማምንት ትውውቅና ኔትወርክ ዕውቅና የተሰጠው ሙስና ግለሰቦችን በቀናት ውስጥ ሚሊየነር ሲያደርግ ዝም ይባላል፡፡ የፀረ ሙስና ትግሉ የለም እንዳይባል ያህል እዚህም እዚያም በአለፍ ገደም አንዳንድ የሚጠየቁ ግለሰቦች ቢኖሩም፣ ሙስና የሥርዓቱ መግለጫ እስኪመስል ከተራ ዜጋ እስከ ውጭ ኢንቨስተር ድረስ የምሬት ምክንያት እየሆነ ነው፡፡ በሕገወጥ የመሬት ወረራ፣ በሕንፃ ግንባታና ዕድሳት ፈቃድ፣ በወጪና ገቢ ንግድ የጉምሩክ ኬላዎች፣ በአገር ውስጥ ገቢ፣ በአነስተኛና በትልልቅ ግዢዎችና ጨረታ፣ በንግድ ፈቃድ ምዝገባና በብቃት ማረጋገጫ፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጀት ምዝበራ፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርፊያ፣ በኤሌክትሪክ፣ በውኃና በስልክ መሠረተ ልማት ዝርጋታዎች፣ በመንገድ ግንባታዎችና በመሳሰሉት አገሪቱንም ሕዝቡንም ራቁታቸውን የሚያስቀሩ የሙስና ተግባራት እየተፈጸሙ ነው፡፡ ኢሕአዴግ ሆይ የት ይሆን ያለኸው? አባላትህና ደጋፊዎችህ ምን እያደረጉ ነው? የምዝበራው ተሳታፊ ወይስ የዳር ተመልካች? ይኼም በደንብ ይፈተሽ፡፡ ራስህን ተመልከት፡

አገሪቱ ከነበረችበት የድህነት አረንቋ ውስጥ ለማውጣት የሚደረገውን ጥረት ሕዝቡ መስዋዕትነት እየከፈለበት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሕዝብ አሁንም በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እየተመታ ነው፡፡ መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች በየቀኑ ዋጋቸው እየጨመረ ኑሮን መቋቋም ተስኖታል፡፡ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ ከአቅም በላይ እየሆነበት ነው፡፡ የቤት ኪራይ ክፍያ ከሚቋቋመው በላይ ነው፡፡ በትራንስፖርት እጦት በፀሐይና በዝናብ ይንገላታል፡፡ ፈረቃ በይፋ ያልታወጀላቸው ኤሌክትሪክና ውኃ ለቀናት እየጠፉበት ይሰቃያል፡፡ ይህንን ሁሉ ጫና ተቋቁሞ አገሩን የሚገነባ ሕዝብ እንዴት ነው ድጋፍ ማግኘት ያለበት? በስሙ በድጎማ የሚመጡትን ዘይትና ስንዴ በጥቅም የተሳሰሩ ሌቦችና ደላሎች አየር በአየር ይሸጡበታል፡፡ የግብይት ሥርዓቱ እጅግ በጣም ኋላቀርና ተቆጣጣሪ የሌለው ከመሆኑ የተነሳ ሕዝቡን በቁሙ እየገደለው ነው፡፡ ኢሕአዴግ እስከ መቼ ጆሮ ዳባ ልበስ ይላል? አስቸኳይ መፍትሔ ያስፈልጋል፡፡ ኢሕአዴግ ራሱን ይመልከት፡፡

ዜጎች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችም ሆነ በተለያዩ መንገዶች የሚያቀርቡዋቸው አቤቱታዎችና ብሶቶች አይደመጡም፡፡ ቅሬታዎች በአግባቡ አይስተናገዱም፡፡ ችግሮች ሲፈጠሩ ጥድፊያው ለማድበስበስ እንጂ መፍትሔ ለመፈለግ አይደለም፡፡ ኢሕአዴግ ስኬቱን እያወደሱ የሚያሞካሹትን ጆሮውን ሰጥቶ የሚያዳምጠውን ያህል ለምን ተቃውሞዎችን፣ ምክሮችንና ቅሬታዎችን ለማዳመጥ አይተጋም? በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ከነአጋሮቹ ያገኘው መቶ በመቶ የፓርላማ መቀመጫዎችን እንጂ፣ መቶ በመቶ የሕዝቡን ይሁንታ አይደለም፡፡ ካገኘው የሕዝብ ድጋፍ ጋር ባይወዳደርም የማይናቅ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ይቃወሙታል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ኢሕአዴግ በውስጡ ከሕግ በላይ የሆኑ ግለሰቦችን በመያዙ፣ አድርባዮችና ሌቦችን በማቀፉ፣ ፀረ ዴሞክራሲና አምባገነን በህሪያት ይንፀባረቁበታል በሚል ነው፡፡ ይኼም በተደጋጋሚ ተተችቶበታል፡፡ አገራቸውንና ሕዝባቸውን በቅንነት የሚያገለግሉ እየተገፉና ዕድገት እየተከለከሉ ወረበሎች አገር እየበደሉ ነው፡፡ ኢሕአዴግንም እያስተቹት ነው፡፡ ይኼም መፍትሔ ይፈልጋል፡፡

ኢሕአዴግ አሥረኛውን ድርጅታዊ ጉባዔ ሲያካሂድ ወሳኝ የሆነ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጨክኖ መወሰን አለበት፡፡ ፀረ ዴሞክራቲክ ተግባራት ይወገዱ፡፡ የተዘጋጋው የፖለቲካ ምኅዳር ይከፈት፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃነት ይንቀሳቀሱ፡፡ ጦር አንስተው የሚፎክሩ ኃይሎች ሳይቀሩ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግሉ እንዲመለሱ ሁኔታዎች ይመቻቹ፡፡ ሰብዓዊ መብቶች ይከበሩ፡፡ ኢትዮጵያ ማንም እየተነሳ የሚፈነጭባት አገር እንዳትሆን የሕግ የበላይነት በተግባር ይረጋገጥ፡፡ ሙሰኞችና ሌቦች ለሕግ ይቅረቡ፡፡ ብቃት የሌላቸው ይሰናበቱ፡፡ አቅም ያላቸው ለሹመት ይታጩ፡፡ ሕዝቡን ደስ የሚያሰኙ ተግባራት ይከናወኑ፡፡ አስመሳዮችና አድርባዮች ይወገዱ፡፡ ኢትዮጵያ የሰላም፣ የነፃነትና የብልፅግና አገር ትሁን፡፡ ኢሕአዴግም ራሱን ይመልከት!

Source:: Ethiopian Reporter

 

በ800 ሜትር የመሀመድ ውጤት ተሰረዘ!

$
0
0

ሙሃመድ ድል አድርጎ ሲገባ!

በቤልጂንግ 2015 የአለም ሻምፒዮና በ800 ሜትር የፍፃሜ ማጣሪያ ውድድር አትሌት መሃመድ አማን ከውድድር ውጭ ሆናል።
IAAF መሀመድ አማን ውድድሩ ሊጠናቀቅ አካባቢ ሌላ ተወዳዳሪን ገፍትሯል በሚል ነው ይህ ውሳኔ ያስተላለፈው። የበርካታ ጀግኖች አትሌቶች ባለቤት ኢትዮጵያ በIAAF ውስጥ አንድም ተወካይ ስለሌላት በአትሌቶች በኩል የተለያዮ የቅሬታ ጥያቄ ወይም አጋጣሚዎች ሲፈጠሩ ቢያንስ ተናግሮ ተፅኖ የሚፈጥር ሲለሌለ ጉዳዮ የትም አይደርስም።

ምንጭ:-Ethio-Kickoff

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live