Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በተፋፈነ ሁኔታ በአንድ ትልቅ መኪና ተደብቀው ሲሄዱ የተያዙ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን ታሰሩ

$
0
0

ዳዊት ሰለሞን እንደዘገበው

በኬንያ መሩ ካውንቲ በቁጥጥር ስር የዋሉት 100 ኢትዮጵያዊያን ዛሬ አመሻሽ ነው፡፡በወጣትነት የእድሜ ክልል የሚገኙት ታሳሪዎቹ በተፋፈነ ሁኔታ በአንድ ትልቅ መኪና ተሳፍረው ወደ ናይሮቢ በመገስገስ ላይ እንዳሉ በፖሊሶች በተደረገ ፍተሻ መያዛቸው ታውቋል፡፡ታሳሪዎቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት አቅደው የነበሩ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡
እንደ ዴይሊ ኔሽን ዘገባ ከሆነም ስደተኞቹ በሞያሌ በኩል በድብቅ በማለፍ ወደ መሩ ካውንቲ ማምራታቸውን መረጃ የነበራቸው የኬንያ ፖሊሶች በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው ችለዋል፡፡
ethiopia
ኢትዮጵያዊያኑ የሚገኙበት የካንጌታ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች ምርመራ በማከናወን ላይ እንደሚገኙ መናገራቸው ተወስቷል፡፡

በሚያዘያ ወር ከሁለት የተለያዩ ቤቶች ከኢስሊና ኪማኢኮ 40 ኢትዮጵያዊያን በፖሊሶች በተደረገ አሰሳ መታሰራቸው ይታወቃል፡፡

እስረኞቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማምራት ወደ ኬንያ መግባታቸውን ከመናገር ውጪ ምንም አይነት የጉዞ ዶክመንት አለመያዛቸው ተስተውሏል፡፡

ስደተኞቹ በሁለት ቡድን ተከፋፍለው ወደ ሁለት ቤቶች እንዲያመሩ ከመደረጋቸው አስቀድሞ ወደ ኬንያ በአንድነት መግባባቸውን የተናገሩት ፖሊስ ኦፊሰሩ በርናርድ ኒያክዋካ ‹‹ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዲኖሩ ተደርገው ነበር፡፡በዚህ ውስጥ ተሳትፎ ሲያደርጉ የነበሩ ሰዎች ላይ ክስ ለመመስረት ወኪሎቻቸውን በማፈላለግ ላይ እንገኛለን››ብለዋል፡፡


በኢትዮጵያ ቆይታዬ ያነሳኋቸው ፎቶዎች – (ይናገራል ፎቶ)

$
0
0

የዘ-ሐበሻ አንባቢ የሆኑት ግለሰብ ኢትዮጵያ ሄጄ መመለሴ ነው ካሉ በኋላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የተመለከትኳቸው አሳዛኝ ሁኔታዎችን በፎቶ ግራፍ አንስቼያቸዋለሁ በማለት ፎቶዎቹን ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች አድርሱልን ብለዋል:: በዚህም መሰረት ፎቶዎቹን “ይናገራል ፎቶ” በሚል አቅርበነዋል::
ethiopia 1

ethiopia 2

ethiopia 3

ethiopia 4

ethiopia 5

ethiopia 7

ethiopia 8

ethiopia 10

ethiopia 11

ethiopia 14

ethiopia 16

ethiopia 17

ethiopia 18

ethiopia 19

ethiopia 22

ethiopia 23

በአፋር ክልል በባለስልጣናቱ የስልጣን ሽኩቻ 4 ወጣቶች ታሰሩ

$
0
0

የኣፋር ክልል ፕረዝደንት የነበሩት ኣቶ ኢስማዒል ዓሊ ሲሮ ስልጣን መልቀቃቸዉን ተከትሎ በክልል ካቢኔ ዉስጥ በተፈጠረው የስልጣን ይገባኛል ውዝግብ፣ የአንዱ ቡድን ድጋፊዎች ናቸው የተባሉ አራት ወጣቶች ትናንት ታስረዋል።

1ኛ. አቶ ማሃመድ ኣመድ
2ኛ. አቶ ብልዓ ማሄ
3ኛ. አቶ ማሃመድ ኡመር
4ኛ. ፖሊስ ዳዋ ማሃመድ
የተባሉ ወጣቶች ትናንት ድንገት ባልታወቀ ሁኔታ ታስረው እስካሁን ፊርድ ቤት የት እንዳሉ አይታወቅም።

በአፋር ክልል ምን ጊዜም ቢሆን የበላይንት የሚሰማው አቶ ስዩም ኣወል የኣፋር ወጣቶችን ስያስሩ ዛሬ የመጀምሪያቸው ባይሆንም ዛሬ ግን ብሶበታል ይላሉ የኣፋር ወጣቶች።
ካሁን በፊት ኣቶ ኣዳን ሃባና የተባለ ግልሰብ ያለ ምንም ክስ በኣቶ ሱዩም ሴራ ታስሮ ሶስት ኣመት ያለ ምንም ፊርድና ፊትህ ታስሮ ይገኛል።

ኣቶ ሱዩም ኣወል

ኣቶ ሱዩም ኣወል


ለመሆኑ ኣቶ ሱዩም ኣወል ማን ናቸው ?

ኣቶ ሱዩም ኣወል የኣፋር ክልል የጸጥታ ዘርፍ ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ የክልሉ ፖሊሶች እንዳሻቸው ማዘዝ የሚችሉ፣ በክልሉ ሙሉ በሙሉ በ1ርብ ቤተሰቦቻቸው የሚመራ ልዩ ፖሊስ ያላቸው፣ ኣሁን ከስልጣን የተንሱት ኣቶ ኢስማዒልን እንደ ልጃቸው ያስፈራሩ የነበሩ፣ከኣፋር ሽማግለዎች ጋር ፍጹም የዋህ መስለው የሚቀርቡ፣ ግን የመጨረሻ ያልታወቁ እባብ የሆኑ የእነ ገብረጽዮን ገብረሚካኤል ቀኝ እጅ የሆኑ፣ ትንሽ ራስ ምታት ሲሰማቸው በቀላሉ ታይላንድ ባንኮክ ታክመው የሚመለሱ፣በየኣመቱ ለይስሙላ ሳኡዲ ኣራቢያ ለሀጅ ደርሰው የሚመለሱ፣ በክልል ፖሊስ እና ልዩ ፖሊስ ከመቶ ኣለቃ እስክ ኩማንደር የራሳቸው ቅርብ በተሰቦች የሾሙ፣ ኣዲስ ኣበባን ጨምሮ በኢትዮጲያ ብትላልቅ ከትሞች ኣሉ የሚባሉ ህንጻዎች የገነቡ፣ የወያኔ ቁጥር ኣንድ ካድረ ናቸው።

ኣሁንም ቢሆን በክልሉ እንደ ኢስማዒል ሲሮ እንደፈልግኩት ማዘዝ የሚችለው መሪ ካልሾምክ በማለት የተቃወመዉን ሁሉ ማሰር ማሳቃየት ቀጥለዋል።

በአማራ ክልል አንዳንድ ዞኖች አርበኞች ግንቦት 7ንና ትህዴንን ትደግፋላችሁ በሚል እስራትና ድብደባ እየደረሰባቸው ነው

$
0
0

Arebegnoch Ginbot 7
በአማራ ክልል የሚገኙ አንዳንድ ዞኖች ላይ የሚኖሩ ንፁሃን ዜጎችን የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ትደግፋላችሁ በሚል እስራትና ከፍተኛ ድብደባ እየደርሰባቸው መሆኑ ታወቀ።

የደህሚት ድምጽ ደረሰኝ ባለው መረጃ እንዳመለከተው በክልሉ አንዳንድ ዞኖች ላይ የሚኖሩ ዜጎችን ከፌድራል የደህንነት መስሪያ ቤት የተላኩ ደህንነቶች ንፁሃን ዜጎችን የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ድርጅቶችን እየደገፋችሁ ወጣቶችንም ወደ አርበኞች ግንቦት 7ና ትህዴን እየላካችሁ ነው በሚል የሃሰት ውንጀላ እየደበደቡና እያስፈራሩ መሆኑን የገለፀው መረጃው እንደዋና መነሻነትም የኢሳትን ቴሌቪዥንና የተቃዋሚዎችን ሬዲዮ ስታዳምጡ ተገንታችኋል የሚል መሆኑን አስረድቷል።

በክልሉ የአምባገነኑ መንግስት ተላላኪነት የሃሰት ውንጀላ ከደርሰባቸው መካከል በአዊ ዞን አንከሻ ጓጉሳና ጃዊ ወረዳዎች በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ሰከላና ወምበርማ ወረዳዎች በሰሜን ወሎ ዞን መቄትና ዋድላ ወረዳዎች የሚገኙ ንፁሃን ዜጎችን እያሰቃዩ ናቸው::

አርሰናል ጌድዮን ዘላለምን ለሬንጀርስ አዋሰው

$
0
0
Photo Credit ESPN

Photo Credit ESPN

(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያዊ የዘር ሐረግ ያለውና ለአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን እንዲጫወት በጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሊንስማን የታጨው የአርሰናሉ ወጣት የመሃል ሜዳ ጨዋታ አቀጣጣይ ጌድዮን ዘላለም በተያያዝነው የዘንድሮው የፕሪምየር ሊግ ሲዝን 2015 ዓ.ም እስከሚያልቅ በስኮትላንዱ ክለብ ሬንጀርስ እንዲጫወት ክለቡ በውሰት እንደሰጠው ተዘገበ::

ዘ-ሐበሻ ከአርሰናል ድረገጽ ካገኘችው መረጃ መረዳት እንደተቻለው የአርሰናሉ የመሃል ሜዳ ጨዋታ አቀጣጣይ ለስኮትላንዱ ክለብ በውሰት የተሰጠው ይህ ዓመት እስከሚያልቅ ቢሆንም በሁለቱ ክለቦች መካከል ባለው ስምምነት መሰረት ሬንጀርስ ውስጥ ሲዝኑ እስከሚያልቅ ሊቆይም ይችል ይሆናል::

አርሰናልን በወጣትነት እድሜው የተቀላቀለው ጌድዮን በ16 ዓመቱ አርሰናል ከኮቨንትሪ ሲቲ ጋር ባደረገው የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ ጨዋታ ላይ መሳተፉ ይታወሳል:: እንዲሁም አርሰናል ከቱርኩ ጋላታሰራይ ክለብ ጋር ለቻምፕዮንስ ሊግ ባደረገው ጨዋታ ላይ በመሳተፍ ታሪክ አስመዝግቧል::

Health: ጂም መሥራት ያቆሙ ሰዎች ውፍረትን የሚከላከሉባቸው 10 ብልሃቶች!!

$
0
0

በአንድ ወቅት ጥሩ አድርገን የገነባነውን የሰውነት ቅርፅና ወደምንፈልገው ደረጃ ያመጣነውን ክብደት እንዲሁም ጤናችንን በቶሎ እንዳናጣ የተለያዩ አማራጮችን መከተል ያስፈልጋል፡፡

ባለሙያዎች በዚህ ረገድ እንቅስቃሴ በማቆም ላይ ለሚገኙት መፍትሄ ያሉትን በየጊዜው ይፋ ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ ምክሮች እንቅስቃሴን በስንፍና ለማቆም ለወሰኑ ብዙ አይፈይዱም ብለዋል የምክሩ ባለቤቶች፡፡
gym
ወደ አካላዊ እንቅስቃሴ እንዲገቡ ከሚጠየቁ ሰዎች የሚሰማ የተለመደ ምላሽ ነው፡፡ ‹‹የእንቅስቃሴ ጥቅሙ ምንድነው? በሆነ አጋጣሚ ያቆምኩ ዕለት መወፈሬ እንደሁ አይቀር?›› የሚል፡፡ እነዚህ ሰዎች የህይወታቸው አንዱ አካል አድርገው እስካልተረዱት ድረስ ወደ እንቅስቃሴ እንዲገቡ ቀድሞም አይመከርም፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ሰዎች ስፖርት መሥራት ባቆሙ ከ8ኛው ሳምንት ጀምሮ እንደገና መወፈር የሚጀምሩ ሲሆን ለዚህ መሰሉ ማቆምም የሚገደዱባቸው ሁለት ምክንያቶች ጊዜ ማጣትና የአካል ጉዳት ናቸው ተብሏል፡፡ እንቅስቃሴ ስናቆም ለግርሻ ክብደት እንዳንጋለጥም ልንከተላቸው የሚገቡ ስልቶች ምንድን ናቸው? 10 ጠቃሚ አማራጮችን ይዘናል፡፡

1. በዚህ ረገድ እጅግ መሰረታዊ የተባለው፣ እንቅስቃሴ ሲቆም በምንወስደው የካሎሪ መጠን ላይ ከፍተኛ ቅናሽ ማድረግ ነው፡፡ መደበኛውና የወትሮ እንቅስቃሴ ሲቆም ከፍተኛ ክብደት መከተሉ እርግጥ ነው፡፡ ለሚሊዮኖች ዝቅተኛ የአመጋገብ አማራጭ ሲቀርብላቸው ደስተኞች ባለመሆናቸው እንቅስቃሴን ካቆሙ በኋላ በቀላሉ ለማይገላገሉት ክብደት የሚጋለጡትም ለዚሁ ነው፡፡ ነገር ግን አመጋገብን (በተለይ ከፍተኛ የካሎሪ መጠን ያላቸው) በመቀነስ ብቻ ይሄንን ልናሳካ እንችላለን፡፡ ስፖርቱ ውስጥ ባለን ጊዜ ወደ ሰውነታችን ስናስገባ የቆየነው የካሎሪ መጠን፣ በእንቅስቃሴ አማካኝነት የመቃጠል እድል ስላለው ጉዳቱ ዝቅተኛ ይሆን ነበር፡፡ በአንፃሩ እንቅስቃሴው ሲቆምና የምግብ ፍጆታችን የማይቀንስ ከሆነ፣ የማይቃጠል ከፍተኛ የካሎሪን መጠን በሰውነታችን ውስጥ በማከማቸት (የቅባት ኢንቬንተሪ) ለውፍረትና ውፍረት አመጣሽ ችግሮች ያጋልጠናል፡፡

2. በተቻለ መጠንና ባገኘነው አጋጣሚ (እንደ መደበኛው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እርካታ ባይሰጥም) እዛም እዚህም መራመዱና ዕቃዎችን ማንሳትና ማውረዱ፣ ሰውነታችን እንዲሰራና ድብርትም በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሊቀንስልን ይችላል፡፡ ድብርት እንቅስቃሴን በሚያቆሙ ሰዎች መካከል የተለመደ ችግር ነው፡፡ እናም መራመዱና አነስተኛ የቤት እንቅስቃሴዎች ማድረጉ ረዥም ጊዜ ተቀምጦ ከማሳለፍ እንድንቆጠብ ያደርገናል፡፡

3. በስራ እና በሌሎች ፕሮግራሞች ጊዜአችን የተጣበበ ከሆነ፣ በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ የክብደት እንቅስቃሴዎችን በማከናወን፣ ለረዥም ጊዜ የገነባነውን የቱንቻ ጥንካሬ እና ቅርፅ በነበረበት ማቆየት እንችላለን፡፡ ይሄንን ሳያቋርጡ በመቀጠል ጊዜው ሲፈቅድ ደግሞ ወደ መደበኛው ልምምድ መግባት ይቻላል፡፡ በየሁለት ሳምንቱ የሚደረገው ይህ ስፖርታዊ ልምምድ ለረጅም ጊዜ መቆየት እንደሌለበት መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በቶሎ ወደ መደበኛ ልምምዶች ለመግባት ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይኖርብናል፡፡

4. እንቅስቃሴ ለማቋረጥ ያስገደደን የጊዜ እጥረት ከሆነ ቀደም ሲል ይደረግ የነበረውን ልምምድ ጊዜ በግማሽ ለማሳጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸት ሌላው አማራጭ ነው፡፡ የኤሮቢክስ ስፖርት ተመራማሪዎች፣ ልምምዱን በግማሽ ወደ ማሳጠር ስንገባ የቀድሞውን የእንቅስቃሴ መጠን እና ጥንካሬ በዚህ ጊዜ እንድንሸፍን ይመክሩናል፡፡

5. የቤት ውስጥ ሥራ መሸፈን፡- ቤትና ግቢ ማፅዳት፣ ልጆችን መንከባከብ፣ ማብሰል እና ሌሎች የቤት ውስጥ የሥራ ድርሻዎች እንቅስቃሴን ካቆምን በኋላ የእኛ የሥራ ድርሻ እንዲሆኑ ማድረግ ጥቅሙ ለራስ ነው፡፡ የሚገዙ ዕቃዎች ሲኖሩም ነቃ ብሎ መሳተፍ ነው፡፡

6. በሥራም ሆነ ያለ ሥራ ወደ ትላልቅ ህንፃዎች በመሄድ፣ ደረጃዎችን ወደ ላይ እና ታች ማለት ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ በተለይ በዚህ አጋጣሚ መደበኛ እንቅስቃሴ ማድረግ ላልቻሉት ይሄ ተመራጭ መፍትሄ ይመስላል፡፡

7. ሰውነታችን ክብደታችንን ለመቀነስ እንደ መሳሪያ መጠቀም እንችላለን፡፡ በተለይ የቤት እንቅስቃሴዎች የሚባሉትን ፑሽ አፕ ፑል አፕ፣ ቁጭ ብድግ፣ እግርን እና አንገትን የሚያፍታቱትን ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነቃና ማታም ልንተኛ ስንዘጋጅ መስራት ይኖርብናል ይላሉ ባለሙያዎቹ፡፡ እነዚህ በቀላሉ ባለንበት ቦታ ሆነን ልንተገብራቸው የሚችሉ ነገር ግን ውጤት የሚያመጡ ናቸው፡፡

8. ቴሌቪዥንና ኮምፒውተር ላይ የምናሳልፈውን ጊዜ መቀነስ ይኖርብናል፡፡ ይሄ ከመደበኛው እንቅስቃሴ በተለያዩ ምክንያቶች ስንገለል ልንከተላቸው ከሚገቡ አማራጮች መካከል ነው፡፡ ለረዥም ጊዜ መቀመጥን የሚያስገድዱ ተግባሮችም በዚህ ውስጥ ይካተታሉ፡፡ እናም በጥንቃቄ እንቅስቃሴዎች ይተኳቸው፡፡

9. ልምምድ በምናደርግበት ወቅት ከእንቅልፋችን ከምንነሳበት 20 እና 30 ደቂቃዎች ቀድመን መንቃት ይኖርብናል፡፡ ይሄ ተግባራችን ሰውነታችን የሚንቀሳቀስበትን የጊዜ ርዝመት በማስፋት፣ ያቆምነውን የስፖርት ልምምድ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እንድናካክስ ይረዳናል፡፡

10. በጊዜ እጥረት ምክንያት ከልምምድ ልንርቅ ከሆነ የተሻለ የሚባለው፣ አጭር እና ውጤታማ በሚባል የሰውነት እንቅስቃሴዎች መሸፈን ላይ ትኩረት ማድረግን አለመዘንጋት ነው፡፡ ይሄም ቢያንስ የ10 ደቂቃ እንቅስቃሴን በቀን ከሁለት እስከ ሶስት ጊዜ ማከናወን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ጊዜአችንን በሚገባ ማስተዳደር የሚጠይቅ መመሪያ ነው፡፡ ሆኖም ካላስፈላጊ የግርሻ ክብደት ይገላግላል ይጠቀሙበት መልካም ጤንነት!

የቡሄ በዓል አከባበር በዱባይ (Video)

$
0
0

የቡሄ በዓል አከባበር በዱባይ (Video)

የቡሄ በዓል አከባበር በዱባይ (Video)

ስለ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቅዐገኘሁ…

$
0
0

በተድላ ደ. ተክሌ
ነሃሴ 12, 2007

ከስራና ትምህርት መስተጋጎል፣ ቤተሰብን እና አዛወንት ወላጆችን ከእስር ቤት ፍርድ ቤት ማንገላታት፣ ያለተጠበቁ የገንዘብ ወጪዎችን ማውጣት፥ ለጠበቃ፣ ለትራንስፖርት፣ ለምግብ፣ ቤተሰብ: ያለጧሪ ወይም ረዳት መቅረት፣ በተለይ ደሞ በአሸባሪነት መከሰስ፣ ከዛም መታሰር ፣ታስሮም በሰቆቃዎች መቀጣት፣ በእስር ወቅትም በሽታን መሸመት እነዚህ ሁሉ ማናችንም ላይ እንዲከሰቱ የማንፈልጋቸው ግን የተከሰቱ ናቸው።

Drawing of  De Birhan’s co-blogger Zelalem Workagegnehu by Melody Sundberg

Drawing of De Birhan’s co-blogger Zelalem Workagegnehu by Melody Sundberg

ዘላለም ወርቃገኘሁ ጋሻው የረጅም ግዜ ጒደኛዬና ደ ብርሃን ብሎግ ላይ ሲጦምር የቆየ ፅኑ ሰው ነው። በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ ሲባል መቼም ሰምታችዃል። ዘላለም ከታሰረና ከላይ የገለፅኳቸውን መከራዎች መቀበል ከጀመረ ኣሁን አንድ አመት ከአንድ ወር ሆነው። ህዳር ፪፻፯ አገር ቤት በሚታተም ጋዜጣ ታትሞ የወጣው ክስ እንዲህ ይላል “የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የወንጀል ሕግና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር ፮፭፪፨፪፻፩ን በመጥቀስ፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፩፱ኛ ወንጀል ችሎት፣ ጥቅምት ፪፩ ቀን ፪፻፯ ዓ።ም። ከቀኑ ፲፡፴ ሰዓት በኋላ ክስ የመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች፣ ዘላለም ወርቅነህ (የታይፕ ስሕተት ነው ወርቅዐገኘሁ ለማለት ነው )፣ ዮናታን ወልዴ፣ አብርሃም ሰለሞን፣ ሰለሞን ግርማ፣ ባህሩ ደጉ፣ ተስፋዬ ተፈራ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሽና የሸዋስ አሰፋ ናቸው፡፡”

የተጠርጣሪዎቹ የክስ መዝገብ መጠሪያና አንደኛ ተከሳሽ የሆነው ዘላለም (ወርቅዐገኘሁ) የተባለው ተጠርጣሪ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪና የግል ሠራተኛ መሆኑ በክሱ ተጠቅሷል፡፡ ተጠርጣሪው የግንቦት ፯ አመራር ነው ከተባለው ተድላ ደስታ (እኔን ነው) ከሚባለው ግለሰብ ጋር ከ፪፲፻ ዓ።ም። ጀምሮ በስልክና በፌስቡክ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዴት እንደሚመጣ ሲመካከሩ ከርመው፣ በ፪፻፫ ዓ።ም። ግንቦት ወር ላይ የግንቦት ፯ አባል መሆኑንም ተጠቁሟል፡፡ የሁለቱ ግንኙነት እንዳይታወቅ deresetariku@gmail.com የሚል አድራሻ በመክፈት፣ ግንኙነታቸውን ማጠናከራቸውን የሚገልጸው የዓቃቤ ሕግ ክስ፣ በ፪፻፬ ዓ።ም። ደግሞ ለግንቦት ፯ አባል የሚሆኑ እየመለመለ እንዲልክና በዓረቡ አገር የተከሰተው ሽብር በኢትዮጵያም ተከስቶ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመጽ ለመጣል በሴል እንዲያደራጅ፣ ከተድላ ደስታ ጋር መወያየታቸውን ክሱ ያብራራል፤ ዘላለም ወርቅነህ (ወርቅዐገኘሁ) የሚጠቀምበት አሥር ሺሕ ብር ከግንቦት ፯ አመራረ ተልኮለት መቀበሉንም ክሱ ይጠቁማል፡፡ ዘላለም ወርቅነህ deresetariku@gmail.com የሚለው አድራሻና የፌስቡክ አድራሻቸው እንዳይታወቅ Debirhanblogandargachewtsige@facebook.com የሚል ሌላ ማኅበራዊ ድረ ገጽ በመክፈት፣ በአንድ አገር በአመጽና በግጭት ማኅበራዊ ለውጥ የሚመጣበትን ማብራሪያ የሚጠይቅ መልዕክት መላላካቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያን በአመጽ እንዲዘጋ ቢደረግ ውጤት ሊመጣ እንደሚችልም መምከሩን ክሱ ያመለክታል፡፡” ይሄ ብቻ አደለም። የዘላለም ክሶች ሌሎችም ናቸው። ስለጎንደር ዩንቨርሲቲ ረብሻ በፈረንጆች አቆጣጠር ፳፩፩ መፃፉና ይህም በውጭ አገር ባሉ ድህረ ገፆች ላይ መውጣቱ፣ ሃገር ቤት ውስጥ ካሉ ጓደኞቹ ጋራ ስለፖለቲካ መወያየቱ መምከሩ ሁሉ በክሱ ወስጥ ተጠቅሰዋል።

የተከበሩ ከሳሾች ከፍተኛ የሆነ ስልጣን ለኔም ለዘላለም ወርቃገኘሁም አሽረውናል። ለዛውም አመራር!

ከዘላለም ጋራ ሌሎች ሶስት ጓደኞቹ ታስረዋል: ዮናታን ወልዴ፣ አብርሃም ሰለሞንና ባህሩ ደጉ፣ ጥፋታቸው ደሞ አንድ አሜሪካን አገር ያለ ኢትዮጲያውዊ ጋዜጠኛ አለ ባለው የኢንተርኔት ስልጠና ላይ ለመካፈል በማመልከታቸው። ክሱ ግን የሽብር ስልጠና ነው ይለዋል። ስለዚህ ጉዳይ ወደፊት በሰፊው እናገራለው። ለዐሁኑ ግን ዘላለም ላይ ላተኩር።
የክሱን ትንተና ለናንተ ልተወው ነገር ግን እኔም እሱም የማንኛውም የፖላቲካ ፓርቲ አባል አደለንም። ነገር ግን ለተጎዱ አዝነናል። ላዘኑና ለተከዙ፤ ለተበደሉ ሁሉ ከከንፈር መምጠጥ በላይ እንጥራለን። ስለገዢዎች ሳይሆን ስለተጠቂዎች ብለን ፅፈናል የቻልነውንም ሞክረናል። ይሄ እንግዲህ በዘመነ ሽብር ሐጢያት ነው። በነገራችን ላይ ገዢና ተጠቂ እንደተመልካቹ ነው። እኛ ራሳችንን እንደተበዳዮች ስናይ አሳሪዎቻችን ደግሞ ራሳቸውን እንደ ተባዳይ ያዩ ይሆናል።

አንድ እማልክደው አቋም ግን ኢትዮጲያ ውስጥ መልካም አስተዳደር መስፈን እንዳለበት በተለይ ደሞ የብሄሮች የበታችነትና የበላይነት (ethnic hegemony) አብቅቶ የብሄር እኩልነት (ethnic equality) መስፈን ለዐሁኗ ኢትዮጲያ ችግሮች መፍትሄ ነው ብዬ አምናለሁ ለዚህም እስከመጨረሻው የምችለውን ሁሉ አደርጋለው። ይሄም ሽብር ይሆን?

ዘላለም በሰላሳዎቹ የመጀመሪያ እድሜ ክልል የሚገኘ ወጣት ነው። በትምህርቱ በጣም ጎበዝ ከሚባሉት ወስጥ ሊምደብ ይችላል። የመጀመሪያ ዲግሪውን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት ጨርሶ ወደ ቤተሰቦቹ ቤት አዲስ አበባ ከተመለሰ በሁዋላ የተላያዩ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የግሉን ንግድ ሲሰራ ነበር። ለምሳሌ መቂ አካባቢ እርሻ ጀምሮ ነበር። የተወሰኑት ቢዝነሶቹ ሲቀጥሉ ሌሎቹ ደግሞ ቆመዋል። ከብዙ አመታት እረፍት በሁዋላ ደግሞ ወደ ትምህርት በመመለስ የማስትርስ ዲግሪ ትምህርቱን በ፪፻፮ አም ጀምሮ ነበር። በታሰረበትም ወቅት የመመረቂያ ርእሱን መርጦ ጨርሶ መፃፍ ብቻ ነበር የቀረው። አሁን ቂሊንጦ ወስጥ ምርጥ የመመረቂያ ፅሁፍ ርእሶች እንዳገኘ አምናለሁ። ትምህርቱን ሲጀምር ብዙ ግዜውን ከፌስቡክ ርቆ ላይብረሪ ያሳልፍ ስለነበር እኔም በግል ህይወቴ በተፈጠሩ ለውጦች ምክንያት ግንኙነታችን ቀንሶ ነበር። አልፎ አልፎ ግን እንነጋገር ነበር።

ስለዘላለም በሃሪ አብረውት ታስረው በቅርብ የተፈቱ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች እንዲሁም እስርቤት ለጉብኝት ሲሄዱ የተዋወቁት ሰዎች ሁሉም “በጣም ትሁትና ጨዋ” ብለው ይገልፁታል። ዘላለም በጣም ጥሩ በሆነ ቤተሰብና ሰፈር ውስጥ ታንፆ ያደገ ልጅ ነው። ሀገሩን የሚወድ ፤ በተለያዩ የምእራብ ሃገሮች ወንድምና እህቶች ቢኖሩትም ፈረንጅ ሃገር ሄዶ ለመኖር የማይጓጓ፤ በሃገሩ ሰርቶ መለወጥን የሚሻ; ብልጭልጭ የማይደንቀው ሰው ነው።

እንደ ዘላላም ያሉ ምሁሮች የትኛውም መንግስት ቢሆን ለሃገሪቱ እድገት ሲል እስር ቤት ውስጥ ሳይሆን የሃሳብ ማፍለቂያና ማንሸራሸሪያ መዐከል ከፍቶ ሊጠቀምባቸው የሚጋባ ዜጎች ናቸው። ይህን የምለው ዘላለምን እንደግላሰብና እንደ አንድ ብዙ ግዜ አብሮት እንደተወያየ ሰው ሆኜ ነው። በደ ብርሃን ብሎግ ላይ እምፅፋቸው ትንታኔዎች ብዙዎቹ ከዘላላም የፈለቁ የሃሳብ ውልዶች ናቸው። ከግጭት አፈታት ዘዴዎች መሃል አንዱ አንዱን የሚረታበት ዊንሉዝ (win-lose) ሲስተም ሲባል ሁለቱም ወገኖች የሚያሸንፉበት ዊንዊን(win-win) ይባለል ሶስትተኛው ደሞ ክሪኤቲቪቲ (creativity) ወይም ደሞ አዲስ ያልታሰበ አማራጭ ማመንጨት ነው። ይሄ ቀላል አደለም። የዘላለምን የክሪኤቲቪቲ ችሎታ ለማሳየት የሚከተለውን ምሳሌ ልጥቀስ። ከጥቂት አመታት በፊት የአባይ ግድብ ጉዳይ በግብፅና በኢትዮጲያ የከረረ አለመግባባት በፈጠረበት ወቅት ፤ እኛም ስለዚህ ጉዳይ ለምን አንፅፍም ብለን ሃሳብ በፌስቡክ መላዋወጥ ጀመርን። ዘላለም እንዲህ አለኝ። ግብፅ ዛፍ መትከል አለባት። ለዛፍ ተከላውም ማገዝ አለብን። ሃሳቡ እንዲህ ነው ኢትዮጲያ በዐባይ የመጠቀም ሙሉ መብት አላት፤ ግብፃውያንም በውሃ ጥም እንዳያልቁ የሰብዐዊ ግዴታ አለብን ስለዚህ ሁሉንም የማይጎዳ መፍትሄ ያስፈልጋል። ግብፅ አብዝታ ዛፍ ብትተክል ለዚህም ብትረዳ በቂ ዝናብና ውሃ ይኖራታል። ይሄ ታድያ ሰፋ ብሎ ቢጠና ምርጥ የፖሊሲ አማራጭ አደለም? እንዲህ አይነት ኢትዮጲያውያንን መንከባከብ አይስፈልግም?

ዘላለምን ለማስፈታት
ዘላለምን ለማስፈታት አንድ አመት ሙሉ ዲፕሎማቶች፤ ሸምጋዮችንና እነሱን ሊቀርቡ ይችላሉ የተባሉ አካላትን ሁሉ ተማፀንን: ጠየቅን። የሁሉንም ወገኖች ሃሳቦች የምናስተናግድ መሆናችንን ለማሳየት ሞከርን። ይሄን ሁሉ የዝምታ ዲፕሎማሲ (quiet diplomacy) ስናካሂድ ልንከላከለው የሞከርነው ነገር ሁሉ ለካ ተከስቷል (the damage was done) መከሰትም ብቻ አደለም ኖረነዋል። ሊያደርሱብን የሚችሉትን ሁሉ አድርሰዋል: የክሶችም ክስ የሆነው የሽብርተኘነት ክሱም (slander) ቀጥሏል ።
የሽብርተኘነት ክስ ሲነሳ ሁልጊዜ የሚገርመኘ ነገር አለ። ክፉው የደርግ ስርዐት ፖለቲካንና ጋዜጠኘነትን ሞት የሚል ትርጉም እንዲኖራቸው: አይነኬ አይጠጌ አድርጎ አልፏል። አሁን ደሞ ፖለቲካና ጋዜጠኘነት ሽብር ማለት ሆነዋል። የኢትዮጲያ ጸረ ሽብር ህግ ከአሜሪካንና ከእንግሊዝ የጸረ ሽብር ህጎች ሙሉ በሙሉ የተወሰደ ነው ብለው የዐገሪቱ መሪዎች በብዛት ይከራከራሉ። መቶ ፐርሰንት ኩረጃ! ምንም እንኳን አሽባሪነት በግልፅ የሚያሰጋን ችግርና ሕግም አሥፈላጊ ቢሆንም አሁን ባለው መልኩ ግን መሆን የለበትም እላለሁ። በመጀመሪያ ችግሩ የሚመነጨው በቀልን ያማከለ ህግ አወጣጥ መኖሩ ነው። እሱ ብቻ አደለም አይምሮውን ተጠቅሞ ነባራዊ ሁኔታዎችንና ችግሮቹን አጥንቶ ተገቢ የሆነ ህግ እሚያወጣ ታላቅ መሪ እና ሲስተም አለመኖሩ ነው። ታላቅ መሪ የራሱን ወገን በፖለቲካዊ ልዩነቶች ብቻ አሽባሪ ብሎ አይፈርጅም፣ አይከስም። ታላቅ መሪ በጥናት እና ምርምር ላይ የተመሰረተ ሽብርን የሚከላከል (ግዴታ ጸረ ሽብር ህግ መባል የለበትም) ህግ ይቀርፃል። ይኸው በዚህ መቶ ፐርሰንት ኩረጃ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ታስረዋል ቀሪው ህዝብ ደሞ ፈርቷል።

ከዐመት በፊት ዘላለም ሲታሰር ሊያስሩት የመጡት ፖሊሶች በጥቆማ ነው የመጣነው ማለታቸውን ሰምቻለው። ከዐንድ አመት በላይም በጠቋሚዎቹ መረጃ መሰረት ዘላለምና ጓደኞቹ ታስረው አካላዊና አእሮአዊ ጥቃቶችን አስተናግደው ተከሰው ፍርድ እየተጠባበቁ ነው። እዚህጋ ነው እንግዲህ የዐሳሪዎቹም የከሳሾቹም የስሌት ስሕተት እሚታየው። አጥፍተውም ቢሆን እንኳን በምክርና ማስጠንቂያ ሊታለፉ የሚችሉ ልጆችን ወደ ቂሊንጦ ሲልኩ የጠቆሙትን ደሞ ወደ ቪላ ቤት ልከዋል። ህሊናው የታሰረው ግን የቱ ነው? የቪላው ወይስ የቂሊንጦው? እነዚህን ልጆች ቂሊንጦ በመላክና እዛው በማክረም ህጋዊም ፖለቲካዊም ትርፍ ይገኛልን? ይህን እንግዲህ በጊዜ እናየዋለን። ለኔ ግን የተሳሳተ ስሌት ነው።

የነዚህ ግለሰቦች ብዙ መከራከሪያዎቻቸው በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርገው፤ ከአንድ አመት በላይ ከሆነ እስር በሁዋላ ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ በነፃ ይሰናበቱ ወይንም ይከራከሩ የሚለውን ለመወሰን ለብይን ለሃሙስ ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ማን እንደሆነ ባላስታውስም ይህን የዐንድ አውሮፓዊ አባባልን ልጥቀስ “ክፋትን፤ ውሽትን፤ ጭቆናን ከመጥላትና እነሱንም ለመቀየር የቆሙ ጣእማቸው፤ ኩራታቸውና ጥንካሬያቸው በመከራ ውስጥም አይክዳቸውም፤ አካላቸው ቢሞት እንኳን ይኖራል። ህይወት ከሞት ወስጥ ይመነጫል። ከመስዋእትነት። ከጀግኖች መቃብር ደግሞ ነፍስ ያላቸው ሃገራት ይወለዳሉ::” የኢትዮጲያና የኢትዮጲያውያን ችግር እንዲህ ተቆጥሮ እሚያልቅ አደላም፤ ከሃገር ቤት እስከውጭ አገሮች። ብዙዎቹ ችግሮች ሃገሪቱን በእርቅና በፍቅር ዳግም በማዋለድ ሊፈቱ ይችላሉ፤ ሌሎቹ ደሞ በሌሎች መንገዶች።

እነዘላለም ከዐመት በላይ ያለፍርድ እስር ቤት ናቸው። በፍርሃትም በግል ህይወት ምክንያት የሚጠይቋቸውም አብረዋቸው የሚቆሙት ሰዎች ቁጥር ሊቀንስ ይችላል። እኔ ግን ዛሬም እንደ ትላንቱ እስከመጨረሻው ከዘላለም ጎን እቆማለሁ!

 


በቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በሚኖሩ ዐማሮች ላይ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ወንጀል

$
0
0

በዐማሮች ላይ የተፈፀመ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ልዩ ዘገባ
ቅፅ ፫፣ ቁጥር ፩

ማክሰኞ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም.
ለመስማትም ሆነ ለማውራት ይዘገንናል!!
በምን ቋንቋ እንግለጸው! ሰውን ሰው በላው!
ጉምዞች ዐማሮችን አርደው በሏቸው!

ሀ) መግቢያ
ሞረሽ-ወገኔ ይህ አስደንጋጭ ዜና እንደደረሰው የድርጊቱን ዘግናኝነት እና ፍፁም ኢሰብዓዊነት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ ከዚያም አልፎ ያለአግባብ ግለሰቦችንም ሆነ ድርጅቶችን ላለመወንጀል፣ ስለሁኔታው ከሥር መሠረቱ መረጃዎችን ለማጣራት ሙከራ አድርጓል። ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን እና ሰብዓዊነት የሚሰማችሁ ግለሰቦች ሁሉ እንድትገነዘቡልን የምንፈልገው፣ በእንዲህ ዓይነት እጅግ የሚሠቀጥጥ ድርጊት ላይ ዘገባ ለማዘጋጀት ምን ያህል ከባድ የኅሊና ፈተና እንደሚደቅን ንፁሕ ኅሊና እና አስተዋይ አዕምሮ ያለው ሰው ይስተዋል አልባልም።
Benishangul

አንዳንድ ጊዜ «ቋንቋ ኃሣብን በትክክል ለመግለጽ ያስቸግራል» ይባላል። ዕውነት ነው፣ እንደዚህ ያለ ለመስማትም ሆነ ለመናገርም የሚቀፍ እና የሚከብድን ድርጊት፣ ድርጊቱን ባየው ሰው፣ በተረዳው እና በገባው መልክ ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ወገን ለመግለጽ ይቸገራል። የቋንቋ ሊቃውንቱም «ቋንቋ አንዳንድ ጊዜ ኃሣብን በትክክል አይገልጽም» የሚሉት እንደዚህ ያሉ ድርጊቶችን በአዕምሯቸው በተቀረጸው መንገድ በቃላት አሳክቶ ለመግለጽ ሲፈልጉ ተስማሚ ቃል ስለሚያጡ ነው። በዚህ በምንኖርበት በ፳፩ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፣ ያውም የክርስትና ኃይማኖትን ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ተቀብሎ በኖረ እንደ ኢትዮጵያ ባለ የረጅም ዘመን ታሪክ ባለቤት በሆነ ሕዝብ መሃል፣ «ሰውን ሰው በላው፣» «ጉምዝ የተባለው ጎሣ አባሎች የዐማራውን ነገድ አባሎች በጠላትነት ስሜት ተነሳስተው ከወያኔ በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት አርደው በሏቸው» የሚለውን ክፉ ዜና ላልሰሙና ላላወቁ ሰዎች ማስረዳት እጅግ ይከብዳል፣ ይቀፋል፣ በምን ቃላትም ለመግለጽ እንደሚቻል ያስቸግራል። ድርጊቱ ግን በአሳዛኝ መልኩ ተፈጽሟል። በዕውነትም አንበሣ፣ ጅብ ወይም ሌሎች ሥጋ-በል አራዊት በመሰሎቻቸው ላይ የማይፈጽሙትን ድርጊት፣ ሰው ፣ሰውን አርዶ በሚጥሚጣ አጣጥሞ ሲበላው ላየ ሰው፣ ለሌላ ወገኑ ለመግለጽ ቃላት ያጥረዋል። የአገላለጽ መንገዱም ይጠፋዋል፤ ይከብደዋል። «ሰው ሰውን በላው» ማለት ተራ አባባል ይሆናል፤ የተለመደ ተራ አጠቃቀም ይሆናል። በምን ቃል ቢገለጽ ነው ድርጊቱ «ትንግርት፣ ጉድ፣ እግዚኦ የፈጣሪ ያለህ» የሚያሰኘው! ይህ ነው እንግዲህ «አንዳንድ ጊዜ ቋንቋ ኃሣብን በትክክል ለመግለጽ አያስችልም» የሚባለው። የሰው ልጅ ከጅብ እና ከአንበሣ፤ በአጠቃላይ ሥጋ- በል ከሆኑ እንስሶች የከፋ አውሬ መሆኑ እንዴት ይገለጻል?

Read Full Story in PDF/ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ዛሬ ማምሻውን በላስቬጋስ ለአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰብ ይደረጋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በዳላስ የተጀመረው የአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በዋሽንተን ዲሲ እና በሲያትል ከቀጠለ በኋላ ዛሬ በላስቬጋስ ከተማ እንደሚደረግ ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል::

በትልቁ ጎልድ ኮስት ካዚኖ ውስጥ በሚደረገው በዚሁ የአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰብ ላይ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ሙሉነህ እዩኤል እንዲሁም አቶ ጋሻው ገብሬ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል::

እስካሁን በ3 ከተሞች ብቻ በተደረገ የአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ($200 ሺህ) ዶላር መገኘቱን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል::
Las Vegas Arebegnoch G 7

Sport: ጆ ጎሜዝ አዲሱ ቀይ አንፊልድ ‹‹የሊቨርፑል ትልቅ ስኬት እንደምሆን እርግጠኛ ነኝ››

$
0
0

የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ የዝውውር ገበያ በማድረግ ላይ ባሉት እንቅስቃሴያቸው ከአንድ ስኬት ወደ ሌላው ስኬት እየተሸጋገረላቸው ይገኛል፡፡ ሰሜን አየርላንዳዊው አሰልጣኝ ሊቨርፑል የ2014-15 ሲዝንን የፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ በ6ኛ ስፍራ ላይ በመቀመጥ ለማጠናቀቅ የተገደደበት ውጤቱን የፊታችን ኦገስት 8 በሚጀምረው የ2015-16 ሲዝን ዘመን ለማረም የዝውውር መስኮት እንቅስቃሴያቸውን የጀመሩት እንግሊዛዊው ሁለገብ የአማካይ ክፍል ተጨዋች ጀምስ ሚልነርን በነፃ ዝውውር በማስፈረም መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሚልነርን ተከትሎ ሌላው እንግሊዛዊ የአጥቂ መስመር ተጨዋች ዳኒ ኢንጊስ ወደ ዝቅተኛ ዲቪዚዮን የወረደው በርንሌይን በመልቀቅ ወደ አንፊልድ ተጉዟል፡፡ አሁን ደግሞ ሊቨርፑል የዘንድሮው የፕሪ ሲዝን ዝውውር መስኮት አዲሱ ፈራሚ ጆ ጎሜዝን በእጁ አስገብቶታል፡፡
Joe Gomez

FILE PHOTO: Charlton Athletic's Joe Gomez set for Liverpool medical tomorrow Joe Gomez, Charlton Athletic.  ... Soccer - SkyBet Championship - Middlesbrough v Charlton Athletic - Riverside Stadium ... 07-02-2015 ... Middlesbrough ... United Kingdom ... Photo credit should read: Richard Sellers/Unique Reference No. 22193898 ...

 Joe Gomez  Photo credit Richard Sellers/

በተጠናቀቀው ሲዝን ለቻርልተን አትሌቲኮ በመሰለፍ ባበረከተው ታላቅ ፐርፎርማንስ የብዙዎችን ቀልብ የሳበው እንግሊዛዊው የተከላካይ መስመር ተጨዋችን ሊቨርፑል በእጁ ያስገባው ለግዢው ያቀረበው 3.5 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ ተቀባይነት አግኝቶ ነው፡፡ የ18 ዓመቱ የእንግሊዝ ወጣት ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ቻርልተንን በመልቀቅ ለሊቨርፑል በይፋ የፈረመው በሳምንቱ መጨረሻ በሜልውድ የትሬኒንግ ካምፕ በመገኘት የጤንነት ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ነው፡፡ ለቀዮቹ ለአምስት ዓመታት የሚዘልቅ የኮንትራት ውልን መፈረሙም ታውቋል፡፡

የ18 ዓመቱ እንግሊዛዊ አንፊልድ መድረሱን ተከትሎ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ በሰጡት መግለጫ ከዋናው ቡድናቸው ጋር የፕሪ ሲዝን ዝግጅት ፕሮራምን እንደሚሰራ ቢጠቁምም የእቅዳቸው ቁልፍ አካል እንደሚያደርጉት ግን ከማረጋገጥ ተቆጥበዋል፡፡ የብዙዎች ግምትም በቂ ልምድን እንዲያገኝ በመመኘት በውሰት ውል ለዝቅተኛ ዲቪዚዮኑ ደርቢ ካውንቲ ይለቁታል የሚል ነው፡፡ ጆ ጎሜዝ ቻርልተንን በመልቀቅ ለሊቨርፑል ከፈረመ በኋላ መግለጫውን የሰጠው ‹‹ከዓለማችን እጅግ ዝነኛ ክለቦች አንዱ ወደሆነው ክለብ የመምጣት እድልን በማግኘቱ ከፍተኛ የሆነ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ ገና በ18 ዓመት ዕድሜዬ ሊቨርፑልን ለመሰለ ክለብ የመፈረም ዕድል ይኖረኛል የሚል እምነትም ስለሌለኝ የተሰማኝ ደስታ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡ ሊቨርፑል በዓለም ፉትቦል ትልቅ ታሪክ ያለው ክለብ ነው፡፡ ከልጅነቴ አንስቶም በከፍተኛ ትኩረት ስከታተለውና ስደግፈው የዘለቅኩት ክለብ መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡ ተስፋ የማደርገውም ሊቨርፑል ፉትቦሌን ወደ ትልቅ ደረጃ ለማሸጋገር ከፍተኛ እገዛን ያደርግልኛል ብዬ ነው፡፡ የሊቨርፑል ኃላፊዎችና አባላት በእኔ ችሎታ ሙሉ እምነትን በማሳደር ወደዚህ ዝነኛ ክለብ እንድመጣ የፈፀሙልኝ ትልቅ ውለታን በአግባቡ እንደምከፍላቸው እርግጠኛ ነኝ፡፡ በአሁኑ ወቅት ያለኝ ዋነኛ ትኩረትም ከሊቨርፑል ጋር ሙሉውን የፕሪ ሲዝን ዝግጅት ፕሮግራምን በከፍተኛ ትኩረት በመሥራት ለዋናው ቡድኑ በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት ለመጫወት የሚያስችለኝን ብቃትን መላበስ መቻሌን ማስመስከር ነው፡፡ ሊቨርፑል እኔን ለማስፈረም እንደሚፈልግ ስሰማ የማይታመን እንደሆነልኝም አልደብቅም፡፡ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ ያቀረቡልኝ ጥሪን የተቀበልኩት ካለምንም የማመንታት መንፈስ ነው፡፡ ምክንያቱም ለእኔ የፉትቦል ህይወት ወደ ትልቅ ደረጃ መሸጋገር ከአንፊልድ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ ቦታ እንደሚኖረኝ አስቀድሜ የማውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ጎሜዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በእንግሊዝ ፉትቦል እውቅናን ማግኘት የጀመረው በማልታ አዘጋጅነት በ2014 በተደረገው የአውሮፓ የታዳጊ ብሔራዊ ቡድኖች ውድድር ላይ ከእንግሊዝ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር የዋንጫውን ድልን ከተቀዳጀ በኋላ ነው፡፡ ልክ የዛሬ ዓመት በተደረገው ከዛ አህጉራዊ ውድድር ላይ ያበረከተውን ታላቅ ፐርፎርማንስን ከግንዛቤ በማስገባትም ቻርልተን አትሌቲክ በዋናው ቡድኑ ስኳድ አካትቶታል፡፡ የ2014-15 ሲዝንን ያሳለፈውም ለቻርልተን በ24 ግጥሚያዎች የመሰለፍ እድልን አግኝቶ ነው፡፡ ለቻርልተን በተሰለፈባቸው ግጥሚያዎች ላይ ያሳየው ጥሩ አቋም ወደፊት የሊቨርፑል የተከላካይ መስመርን ቀጥ አድርጎ ለመያዝ የሚስችለው የተሟላ ብቃትን መላበሱን ያስገነዘባቸው መሆኑን ባለመደበቅ ብሬንዳን ሮጀርስ ጆ ጎሜዝን በማስመልከት አስተያየታቸውን የሰነዘሩት ‹‹ገና 18 ዓመት ወጣት ቢሆንም ከወዲሁ ግን ሁሉንም አይነት የተከላካይ መስመር ብቃቶችን በተፈጥሮው አሟልቶ የያዘ ተጨዋች ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በማንኛውም የተከላካይ መስመር የጨዋታ ሚና ላይ ለመሰለፍ የሚችልበት ሁለገብ ብቃቱ ልዩ ትኩረትን የሳበ ሆኗል፡፡ ተስፋ የማደርገውም በቀጣዮቹ ዓመታት ውስጥ ከሊቨርፑልም ባሻገር የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ትልቅ ስኬት ይሆናል ብዬ ነው፡፡ እርግጠኛ ሆኜ ለመናገር ክለባችን ከቀጣዮቹ 10 ዓመታት በላይ በተከላካይ መስመሩ ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታን የሚያገኝበት አስገራሚ ብቃቶችን የተላበሰ ወጣትን ለማግኘት መቻሉን ነው፡፡ ይህንን ያልኩት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የእንግሊዝ ፉትቦል ካፈራቸው ወጣት የተከላካይ መስመር ተጨዋቾች ውስጥ በተደናቂ ብቃቱ አቻ የማይገኝለት መሆኑን ስለማምንበት ጭምር ነው›› በማለት ነው፡፡

Health: ወጣት ልጆችዎን በክትባት ይጠብቁ!

$
0
0

Zehebasha 7-15

Minnesota Department of Health (MDH)

ወጣት ልጆችም ክትባት እንደሚያስፈልጋቸው ያውቃሉን? ልጆች እያደጉ በሄዱ ቁጥር፣ በልጅነታቸው የወሰዱዋቸው ክትባቶች በሽታ የመከላከል ብቃት መዳከም ይጀምራል። በተጨማሪ ወጣት ልጆች በዚህ የህይወት ዘመናቸው ሊያጣቋቸው የሚችሉ ኣዳዲስ በሽታዎች ኣሉ። የልጆችዎን ጤንነት በቲዳፕ (Tdap)፣ መኒንጎኮካል (meningococcal)፣ ኤች.ፒ.ቪ. (HPV)፣ እና ኢንፍሉዌንዛ ክትባቶች ኣማካኝነት ይጠብቁ።

የወጣት ልጆች ክትባቶች

Tdap ክትባት

ይህ ክትባት ከሶስት ከባድ በሽታዎች ይከላከላል፦ መንጋጋ ቆልፍ (tetanus)፣ ዲፍተሪኣ (diphtheria)፣እና ፐርቱሲስ (እንዲሁም ትክትክ በመባል ይታወቃል)። ወጣት ልጅዎ ቲዳፕ ክትባት 11 ወይም 12 ዓመት ሲሞላው መውሰድ አለበት።

መኒጎኮካል ክትባት (MCV4)

መኒንጎኮካል ኮንጁጌት ክትባት፣ እንደዚሁም የMCV4 ክትባት በመባል የሚታወቅ፣ ማጅራት ገትር በሽታ ጠንቅ ሊሆኑ ከሚችሉ የተወሰኑ ጀርሞች ይከላከል። ማጅራት ገትር በጭንቅላት ሽፋን እና የጀርባ ኣጥንት ላይ እብጠት ሊያስከትል የሚችል ከባድ በሽታ ነው። እንዲሁም ለሂወት ኣዳጋች የሆነ የደም ኢንፌክሽን ሊያስከትል ይችላል። ልጅዎ ይህንን ክትባት መውሰድ የሚያስፈልገው 11 ወይ 12 ዓመት ሲሞላው ነው። 16 ዓመት ሲሞላቸው ኣንድ የመኒንጎኮካል ክትባት ያስፈልጋቸዋል።

HPV ቫክሲን

ይህ ክትባት የካንሰር መከላከያ ነው። በአብዛኛው ሁሉም ሰው በሂወት ዘመኑ የተወሰነ ወቅት ላይ ለ HPV ኢንፌክሽን ይጋለጣል እንዲሁም የተወሰኑ የ HPV ዓይነቶች የካንሰር ጠንቅ ሊሆኑ ይችላሉ። HPV ክትባት ከHPV ኢንፌክሽን እና ከሚያስከትሉት ካንሰር ለመከላከል ይጠቅማሉ። ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የ HPV ክትባት መውሰድ ይጠበቅባቸዋል። ወጣት ልጆች 11 ወይም 12 ዓመት ሲሞላቸው ሶስት ተከታታይ የ HPV ክትባት መውሰድ አለባቸው።

የኢንፍሉዌንዛ ክትባት

ይህ ክትባት ከኢንፍሉዌንዛ (ጉንፋን) የሚከላከል ሲሆን ሁሌ በፎል/መፀው ወቅት መሰጠት አለበት። ኢንፍሉዌንዛ የውስጥ ሰውነት ፈሳሽ ማጠር ወይም የሳምባ ኢንፌክሽን የመሳሰሉ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።

ክትባት አስፈሪ መሆን የለበትም!

ወጣት ልጅዎ ክትባቶቹን በሚወስዱበት ጊዜ በተቻለ መጠን አንዲረጋጉና ዘና እንዲሉ በማድረግ ይርዱዋቸው። የሚወዷቸውን ሙዚቃዎቻቸውና ሄድፎኖቻቸው ይዘው እንዲመጡ ያድርጉ፤ ወይም አይናቸውን ጨፍነው ስለሚወዱት ቦታ ወይም ጨዋታ እንዲያስቡ ያድርጉ። ክትባት መውሰድ በትንሹ ሊያሳምም እንደሚችል ሆኖም ግን ከመታመም በጣም እንደሚሻል ያስታውሷቸው።

ልጄ መከተብ ያለበት መቼ ነው?

እነዚህ ክትባቶች ለመውሰድ ኣመቺው ጊዜ ዓመታዊ ምርመራ በሚደረግበት ወቅት ነው። በተጨማሪ ለስፖርት፣ ለትምህርት ቤት፣ ወይም ለካምፕ አስፈላጊ የሆነውን የሰውነት ምርመራ በሚደረግበት ወቅት ልጅዎ እነዚህ ክትባቶችን መውሰድ ይችላል። ምንም እንኳን ወጣት ልጅዎ 11 ወይም 12 ዓመት በሞላው ወቅት እነዚህን ክትባቶች ሳይወስዳቸው ቢቀርም፣ አሁንም ቢሆን ከፍ ባለ ዕድሜ ላይ ሆኖም መውሰድ ይችላል። ከሀኪምዎ ጋር በሚገናኙበት እያንዳንዱ ወቅት ላይ ልጅዎ መውሰድ ስላለበት ክትባቶች መጠየቅ የሚደገፍ ሀሳብ ነው።

ስለነዚህ ክትባቶች ሌላ ማወቅ ያለብኝ ነገር ምንድን ነው?

እነዚህ ክትባቶች በሙሉ በጥንቃቄ የተጠኑ እና ደህንነታቸው የተጠበቀና ውጤታማ ናቸው። ክትባት በተሰጠበት የሰውነት ክፍል ቀለል ያለ የህመም ስሜትና መቅላትን የመሳሰሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊያስከትሉ ይችላሉ። አልፎ አልፎ ደግሞ ወጣት ልጆች ክትባት ከወሰዱ በኋላ ነፍሳቸው ሊስቱ ይችላሉ። ክትባት ከወሰዱ በኋላ ለ 15 ደቂቃ ማረፍ የሚደገፍ ሃሳብ ነው። ወጣት ልጅዎ ከባድ አለርጂ ያለው ከሆነ ማንኛውም ዓይነት ክትባቶት ከመውሰዱ በፊት ለኪምዎ ይጠቁሙ።

የእነዚህን ክትባቶች ወጪ የሚሸፍን እርዳታ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

ክትባት ለልጆች (Vaccines for Children) (VFC) ፕሮግራም ለአንዳንድ ህጻናት እና ወጣት ልጆች ነጻ ወይም ዋጋቸው ርካሽ የሆኑ ክትባቶችን ያቀርባል። ይህን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እና ብቁ መሆንዎት ወይም አለመሆንዎት ለማወቅ ሀኪምዎን ያነጋግሩ።

ተጨማሪ መረጃ ከየት ማግኘት እችላለሁ?

የልጅዎን ጤንነት እና ደስተኛነት ለማስጠበቅ የሚረዳ የበለጠ መረጃ ለማግኘት www.vax4teens.com የሚለውን ድረ-ገጽ ይጎብኙ።

ኦ አዳም አንተ!! (አስፋ ጫቦ)

$
0
0

 

አስፋ ጫቦ Dallas Texas USA

No Man is an Island

John Donne

…………
Any man’s death diminishes me,
Because I am involved in mankind,

አምባሳደር ፍስሐ ገዳ

Fisha Gedaወንድሜና ጓደኛዬ የነበረው አምባሳደር ፍስሐ ገዳ  አሜሪካን አገርሐምሌ 8፣2007  አርፎ  Fairfax County, Virginia USA የቀብሩ ስነስረአት ተፈጽሟል።እኔ ግን አልተገኘሁም።ይኸ መታደለ ፤መረገም ፤ወይም አጋጣሚ   መሆን አለመሆኑን ገና በቅጡ ያላበራየሁት ነው።እስከዛሬ የሚቀርቡኝ ስዎችና ዘመድ አዝማድ ቀበር ላይ ተገኝቼ አላውቅም።ሁለት ትንንሽ እህቶቼ ባህር ዳር እያለሁ ነበር ያረፉት።እናቴና የባለቤቴ እናት ያረፉት ማእከላዊ እያለሁ ነበር።አባቴና ልጅ የራፉት ደግሞ እዚሁ አሜሪካ እያለሁ ነበር።

የህ ራሱ ራሱን የቻለ የሞትና የቀብር ምስል ይፈጥራል።ልኔ የፈጥርበኛል።መታደለ ያሰኜኝ እነዚህን ዘምድ ወዳጆቼን ያማስታውሳቸው፣ትዝ የሚሉኝ ልክ የመጨረሻ ቀን እንደየኋቸሁ ነው። ስለዚህም ያ ምስል ስለአለ እነሱም አሉ። መረገሙ ያሰኜኝ የሉም። የሌሉትን አሉ ብሎ የተወሰን የሒሊና ክፍሌ ማማለሉ ነው።አፈር ሲመለስ ካልታዬ ቀዳዳው  አይዘጋም። ወይም ቁስል ሁኖ ሊኖር ይሻል።

ፍስሐን ሞሞት ያነበብኩት አንድ ገጽ ላይ ነበር።ሌላው ወንድሜ፤ግርማ ይልማ፤ያባህልም የማስታወቂያም ሚንስቴር የነበረው፤በኋላም መስኮብ አምባሳደር  የነበረው ከSeattle, Washington  ስልክ ደውሎልኝ ኖሮ ጥሪውን አለስማሁትምና  መልክት ተወልኝ።ወደ ፍስሐ ቀብር ሊጓዝ ከነበርበት አየር ማረፊያ ነበር የደውለልኝ።በሁለተኛው ቀን መልእክቱን ሰማሁት። ያኔ ነገረ-አለሙ የትላትንት ዜና ሆኗል።

ግርማ ይልማ በቀብሩ ስነ ስርአት ንግግር ካደርጉት አንዱ ነበር።እኔ ባልገኝም ግርማ እኔ ልል ከምችለው የበለጠና የተሻለ ስለፍስሐ ገዳ ሊል እንደሚችል እርግጠኛ ነበርኩ። ምክንያቱም ፍስሐን ከኔ የተሻለና የበለጠ እንደሚያውቀው አውቃለሁ::የሁለተኛ ደርጃ ትምህርት ቤት ትውውቁ እንደተጠበቀ ሁኖ ከአመታት በኋላ ደርግ ሲመሰረት የተገናኙ ለረዝም አመታት አብረው ደርግ ማስታወቂያ ኮሚቴ ውስጥ አብረው ሰረተዋል።

ፍስሐ፤ግርማና እኔ የተገኛነው በ1953 አዲስ አበባ፤ቀበና፤ኮከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት ነበር::በዚያን አመት ኮከበ ጽባሕ የመምህራን ማስልጠኛ ዘርፍ ከፍቶ ስለነበር ስምንተኛ ክፍል ከነበረባቸው 12ቱም ጠቅላይ ግዛቶች በከፍተኛ ውጤት የ8ኛ ክፍል ፈተናን ያለፉ ሁለት ሁለት ተማሪዎች መጥተው ነበር።

ለአዲስ አበባ ልጆች ከጠቅላይ ግዛት የመጡትን ማየት በውቅቱ ያዩት የነበረውን የነታራዛንን ፊልም የስታወሳቸው ይመስለኛል።አማርኛችን፤እንግሊዚኛችን፤ከመምህራን ጋር የነበረን ግንኙነት፤በክፍል ውስጥ ለጥያቄ አመላለሳችን፤በአጭሩ ሁለንተናችን ቲያትር መስሎ ታይቷቸዉ በታመቀ ሳቅ  ይሞቱ ነበር።ኮከበ ጽባህ ደግሞ የአዲስ አበባ ልጆች ትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን  የመኳንንት፤የመሳፍንትና የሚኒስተር ልጆችም የሚማረበት ነበርና ይህ እንግዳ ደራሹ ቢገርማቸዉኘው አይገርምም።በኋላ እንዳስብኩት ለማለት ነው!

ፍስሐ ገዳንም የአዲስ አበባ ልጅ አድርጌ ነበር የወስድኩት። ለየት ያለ የአዲስ አበባ ልጅ! አለመሆኑን ያውኩት ቅይቶ፤ኖሮ ኖሮ ነበር። አላነሳሁበትም።ለየት ያለ የአዲስ አበባ ልጅ የሰኜኝ ሁለመናው ነበር።የያጋሞ ስብእና (personality)ያለው አይነት ነበር። ወይም የጋሞ ሰው አሻም የሚለው አይነት ስብእና።አሻም በነጠላው ቢተርጎም እንኳን ደህና መጣህ(ሽ) ማለት ይሆናል።አንድምታው ግን ቅባትና ወዝ ያለው ይመስለኛል። ከደርቁ እንኳን መጣህ(ሽ) ላቅ የሚልበት መንገድ ያለው ይመስለኛል። የሲዳዎችን ዳኤ የሚያውቅ የተሻለ የሚረዳኝ ይመስለናኛል። ሞቅ፤ደማቅ የማለት ቃና አላው።ሁለት እጆችን ከፍቶ እቅፍ የማድረግ ቃና። እዚህ አሜሪካኖቹ  ሀግ (Hugging) የሚሉት  አይነት።ማስመስሉ ሲቀነስ!ፍስሐ ገዳ ላይ መጀመሪያ ያስተውልኩት ይህንን አሻም ባህርይ ነበር።ይህ የጋራ ባሕርይ  ካቀራረበን ውስጥ መግቢያ በሩ ይመስለኛል። ማየት ማመን(Pereception is Reality) ነው እንዲሉ

ጓደኞቼም፤ያልሆኑትም ቅዳሜና እሁድ ለጥናት ቀበና ጫካ ውስጥ ይሔዳሉ።እኔ ደግሞ ፒያሳ ሻይ ቤት እሔዳለሁ።በኪንግ ጆርጅ ባርና በጆኖፖሎስ መጽሐፍት መሸጫ መካከል አንድ አፈ ሰፊ ሻይ ቤት ነበረ።፣ፒያሳ በሔድኩ ቁጥር ፈስሀ ገዳን አገኘዋለሁ።በቀኝ ክንዱ የሚሸጡ መጽሐፍት አቅፎ ይዞራል።ሲሸጥም ለመሸጥ ሲያግባባም አየዋለሁ።ያለጥርጥር የአዲስ አበባ ልጅ፤በተለይም ነጋዴው የሚፈልቅበት የመርካቶ ልጅ ነው የሚለውን ግምቴን ያጠናከረልኝ ይመስለኛል።የመጽሐፍቱ አይነት ባብዛኛው ያጠሩና (abridged) አጫጭር ልበወልዶችና የስለላ ታሪክ  ናቸው።ዋጋቸው በአብዛኛው በሱሙኒና በብር መካከል የነበር ይመስለኛል። አንዴ ይሁን ሁልቴ በ 50 ሳንቲም ማግዛቴ ትዝ ይለኛል።በሳምንቱ ይሁን እንዲያ ሻይ ቤቱ ገብቶ ሻዬንም ፓስቲውንም ከፈለልኝ። “እንዴት ለወንድም ይሸጣል!” የሚል ውስጠ ታዋቂነት የነበረው አድርጌ የወሰድኩት ይመስለኛል። በዚህ ሁሉ ውስጥ ያስተዋልኩት ፈስሀ ገዳ መጽሀሐፍ ሻጭ አለመምስሉ ነበረ።ተቸግሮ  የእለት ኑሮ ለማሸነፍ የሚሯሯጥ ሳይሆን አንድ የሚያስደስት ስራ (Hobby) እያሰራ ያለ የሚመስል ነገር ነበረው።

ከፍስሐ ገዳ ጋር፤ኮከበ ጽባህ ለመጨረሻ የተገናኛነው ስኔ 1954  ትምህርት ቤት ለክርምቱ ሲዘጋ ይመስለኛል።ቆይቶ እንዳውኩት ፍስሐም ለመኮንንነት ኮርስ ሆለታ እኔም ሲብል አቪየሽን ገባሁና የሁለተኛ ድረጃ ትምህርታችን እዚሁ ላይ አበቃ።ሁለታችንም ብንሆን በሌላው መልኩ ትምህርትና ስራ አጋብተን የቀጠልን ይመስለኛል።

ከአመታት በኋላ አንድ ምሽት ባልቻ ሆስፒታል ጎን የሚገኘው የጦር ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ተገናኘን።ቦርሳዬ ከሳ ስትል የጦር ወሠራዊት ጓደኞቼን ማፈላለጌ የተለመደ የታወቀ ነበር። ከፍስሀ ጋር ተገናኘን። ትንሽ ተጯጯህንና ጓደኞቼቸን ጣጥዬ ከፍስሀ ጋር አመሸሁ። የመኮንን ልብሱን ገጭ አድርጎ ነበርና የመጣው ጦር ሠራዊትነቱ እንዳማረበት የነገርኩት ይመስለኛል። ሐረር እንዳለ የነገረኝ ያን ለት ነበር። ውስኪዬንም ብራውንም ከፋፈለው። ለመግደርደር ብሞክርም “እዚህ ለመክፈል መብት የለህም!!” ያለኝ ይመስለኛል።

ቀጥሎ የተገናኘነው አራተኛና ክፍለ ጦር የደርግ ማስታውቂያ ኮሚቴ ቢሮ ነበር። በራዲዮና ተለቨዝን በተናገርኩት እንቅስቃሴሰውን  ቅራሪ ብሏል ተበዬ ተከስሽ ነበር። ወዳጄ ተክሉ ታቦር ነበር ይዞኝ የሔደው።”አስፋን ውልደው!” ብለው አፋጠውት ኖሯል። ፍስሐገዳንና ግርማ ይልማና እዚያ አገኜኋቸው።በወቅቱ የኮምቴው ሰበሳቢ የነበረ ሻለቃ አስራት ደስታ  ቆራጭ ፈላጫ እንደሆነ ሊያስረዳኝ በፊቱም(Body Language) በቃላትም ከበቂ በላይ መልእክት ላከልኝ።”ከአንተ አይጠበቅም!” የሚለው ነገር ነበረው።ተክሉ ቴፑን ይዞ ስለመጣ እስቲ የሚጠበቅብኝን ለማውቅና ላለማውቅ መጀመሪያ ቴፑን እናዳምጥ አልኩት። ተደመጠ።አስራት ያለውም ሌላም ተፈልጎ ታጣ። ”ካፈርኩ አይመልሰኝ!” ሆኖበት መስል” ካንተ አ ..” አቋርረጨ ተነሳሁ። ሁለተኛ እኔንም ሆነ ሌላ  ሰው ባልታጣራ ነገር አትጥራ” ብዬ  ተነስቼ ወጣሁ። ፍስሀ ተክተሎኝን ወጥቶ ኖሮ” አሁንም ያው ነህ !!” ብሎ ስቆ ተመለሰ። ተክሉ ታቦር ፊቱ ላይ ምን ያክል እፎይታ ያነበብኩ መስለኝ።ለነገሩ እኔ ቅራሪ አለማለቴ ተረጋገጠ። የአብዮቱ እንግዴ ልጆች ተሰባስበው ቅራሪ ማድረጋቸው ግን እርግጥ ነው። ይኸ አሁን ሳሰበው ማለት ነው።

ፍስሐ ገዳ በኢትዮጵያ አብዮት ከልደት እስከሞቱ ተካፋይ ነበር።የሚያውቀውን፤የሚያምነውን የሚችለውን በቅን መንፈስ የሰጠ በአይነቱ ከጥቅቶቹ ውስጥ የሚደመር ነበር።አሁንም ያው ነህ!” ያለኝ አንድምታ ያለው 1954  በኮከበ ጽባህ ትምህርት ቤት የተካሔደዉን፣ተመሳሳይም ተቀራራቢም የማይገኝለትን የተማሪ የተሳካ አብዮት ለማስታወስ ይመስለኛል። ፍስሐገዳና ግርማ ይልማ የዚያ አብዩት አካል አምሳል ብቻ ሳይሆኑ ንቁ ቀማሪዎችና ተከፋዮች ነበሩ።

ታሪኩ እንዲህ ነበር። በውቅቱ የኮከበ ጽባህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ሚስተር ዉድ ትንሹ (Mr.Wood Junior)ይባላል። ሚስት አለችው። አባቱና እናቱንቱም ዉድ ትልቁ (Wood Senior) የሚባሉም ነበሩ።በዜግነታቸው ካናዳዊን ነበሩ።የክፍለ ጓደኛችን፤በደርግ ዘመን መንዝ ሸፍቶ ለብዙ ገበሬ እልቂት ሰበብ የነበረው የመሳፍንቱ ወገን መርዕድ ብሩም ኗሪነቱ ሚስተር ዉድ ቤት ነበር።የሚስተር ዉድ ቅጣት 2,3,4,5 በያንዳንዱ እጅ (2,3,4,5 On Each Hand) የሚል ነበር።ያ ማለት በጉማሬ አለንጋ የውስጥ እጅን መተለተል ማለት ነው። ገራፊው ድንገት ስቶ መሀል ለመሀል ካላሳረፈ ያ አይቆጠርም። ቆሞ ነበር የሚያስገርፈው።ሁለት ገራፊዎች ነበሩ።ብቻ ምን ጥፋት ለዚያ እንደሚያበቃ አላውቅም። የሚያውቅም ያለ አይመስለኝም። አንዱ የሚያስቀጣው  ትዝ የሚለኝ  ዉድ ትልልቆቹ(Wood Seniors) በተማሪ አጠገብ ሲያልፉ የተቀመጠው ተነስቶ እንዴናችህ ብሎ እጅ ካልነሳ ለግርፊያ ይላካል።

በኔ ግምት እነዚህ ካናዳዊያን ስለአፍሪቃ፣ስለጥቁር ፤የቅኝ ገዝዎቹ እንግሊዛዊያንና ፈርንሳይ ደራሲዎች የጻፉትን አጓጉል መጽፈሐፍት ሳያነቡ የቀሩ አይመስለኝም።ለጥቁር ፊት አለምስጠት ነው!” የሚል። ያላነበቡበት መጽሐፍ ቢኖር ከኢትዮጵያ በስተቀር የሚል መኖር ያለመኖሩን ልብ አለማለታቸው ይመስለኛል።  የዚህ የዘመኑ አውሩድልኝ ልብስ አይነት ለሁሉም የሚመን (Fits All Sizes) አይነት መሆኑ ነው።

ሲብላላ ቆየና ፈነዳ።ይበልጥ የሚገርመው ለፍንዳታው ጫሪ የሆኑት ከጠቅላይ ግዛት ትላንት የመጡት መሆናቸው ነበር። አሁን መለስ ብዬ ሳየው!! አንድ ለሊት ግርማ ይልማና እኔዉርደቱ ይብቃ!! ተነስ!! አመጽ!! ዛሬ ክፍል አትግባ!! ኳስ ሜዳ ተሰብሰብ!!” የሚል  በደብተራችን ቅዳጅ ወረቅት ጽፈን  ገና ተማሪ ዝር ሳይል በየክፍሉ  ክ1-12 ለጠፍን።ጥሪውን ተቀብሎ ኳስ ሜዳውን አጥጠለቀለቀው !ነግረነው!!አባቶቻችንን ጣሊያን ዶቅሰው እንዳላስወጡ ሁሉ…..!!”    አንዴ ከተሎኮሰ እሳቱን የሚያራግብ እጥረት  አልለነበረም።ተቀጣጠለና እሳቱን አጥፊም ሆነ እንዴትስ መጥፋት እንደሚገባው ነጋሪ አዋቂ ታጣ።ሚስተር ዉድሊማጸንም ሊያስፈራርም ቢሞክር ሜዳ ሙሉ  ተማሪ አንዴ ሲያንቧርቅበትነፍሴ አውጭኝ !”ብሎ ሸሸ። ከዚያ ከትምህርት ሚኒስቴር ተራ በተራ ባለስልጣናት ለማስፈራት፤ለማባበል ከዚያ ለመለማመጥም ተቀያየሩ።”ፍንክች ያባ ቢለዋ ልጅ !!”ሆነ።በመጨረሻም ሚስተር ውድ ከነጓዝንጉዙ ተነቅሎ ወደሚሔድበት ሔደ። ጋሼ አማረ ጉልላት አዲሱ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዳይረክተር ሆኖ መጣ። ይህ የመጀመሪያዉ፣ብቸኛውየተሳካ የተማሪ ንቅናቄ ይመስለኛል። አምባሳደር ፍስሐ ገዳ የዚህ ንቅናቄ አካልና አምሳል ነበር። ግርማ ይልማ ቆይቶ የተማሪዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ፕረዚዳንትም ሆኖ ነበር።

አንድ አራት አመት ያክል ደርግ ጽሕፈት ቤት ቢሮ ነበርኝና ፍስሐ ገዳን በየቀኑም ባይሆን ብዙ ጊዜ የማግኘት እድል ነበረኝ። ብዙም የምንነጋገረው አልነበረም። አስፈላጊ በሆኑ ነጥቦች ብቻ ካልሆነ በስተቀረ። የቀረውን ሳንነጋር የምንግባባ (Given) ይመስለኛል። የታውቀ ነው በሚሉት መልክ። ከማስታውቂያ ኮምቲ በኋላ የፕሬዚዳንቱ፤የመንግስቱ ኃይለ ማርያም፣ የፕሮቶኮል ሹም ሆነ። ይህ የሚሰማማው ስራ መሆኑን የነገርኩት ይመስለኛል። የፕሮቶኮል ሹም ስራ አሻማ ነው ብዬ ስለማምን።ከዚያ እኔ ማእከላዊ ከወርድኩ በኋላ የሆቴሊና ቱሪዝም ኮሚሽነር ሆኖ መሾሙን ሰማሁ። ዋናውን የአሻም ስራ አገኘ አልኩኝ በልቤ። በሆቴሊና ቱሪዝም ዘርፍ ከመስራቹ አቶ ኃብተ ስላሴ ታፈሰ ጋር የሚነጻጸር ምናልባትም ሊበልጥ የሚችል ለውጥ ያመጣ ፍስሽ ገዳ መሆኑን ዛሬ ወዳጅም ጠላትም አምኖ ተቀብሎ በዚያ ላይ ተንተርሶ  ወደሚቀጡለት ደርጃ ያደረሱት ይመስለኛል። ወዳጅም ጠላትም ከማለት ሁሉም ተቀብሎ ብል የሚሻል ይመስለናኛል። ፍስሀ ጠላት ያለው ሊኖረውም የሚችል ስለማይመስለኝ ነው።ስሜን ኮሪያ  አምባሳደር መሆኑን እኔ፤በግሌ፤ ግዞት እንደተላከ ነበር የቆጠርኩት። ዝግ አገር ነውና አሻም የሚላቸውም አሻም የሚሉትም ያሉ አይመስለኝም። ከስሜን ኮሪያ ጋር መንግስቱ ግኑኝነት ሊያጠናክር የፈለገው የሶቭየቱ ጋርባቾቭ “እስቲ ጦርነቱ ይብቃና ስላም መንገድ ፈልግ !” ብሎ መሳሪያም ፊትም ስለነሳው አማራጭ መፈለጉ ነበር።

የሆተልና ቱሪዝም ኮሚሽነር ሆኖ እንደተሾመ ፍስሐ ገዳ የሰራውን ፤ከምንጩ የሰማውን አያሌው ነገረኝ።እንደተሾመ  “እኔ ስለሆቴልና ቱሪዝም ምንም የማውቀው ነገር የለም!” ብሎ ለመንግስቱ ነገረው  “ታዲያ ምን ይሻላል!?” ተብሎ ሲጠየቅ “ስራውን የማያውቁ እስር ቤት ናቸውና ይፈቱልኝና ያስተምሩኝ!” አለ። በዚሁ መስረት የቱሪዝም እናት አባት የሆነው አቶ ኃብተ ስላሴ ተፈስና አቶ ዮንስ ክፍሌ ከእስር ቤት ተፈተው ወደስራቸው ወይም ፍስሐ ገዳ ወደሚመድባቸው ስራ ተመለሱ።

በማስፈታት ብቻ አልተገታም። ስራውን በተረጋጋና በተዝናና ሙሉ መንፈስ ሊያካዱ ይችሉ ዘንድ እርፍት ቦታና ጊዜ ስጣቸው። ለሚመደቡበት ስራ እውቀት ብቻ ሳይሆን ከስራው ባህርይ ጋር ተመጣጣኝ የሚሆን እይታ ይኖራቸው ዘንድ ልብስ ከጣሊያን አገር አስመጣላቸው።

ከቀበሩ ስነስርአት እንደተመለሰ ይህንኑ ለግርማ ይልማ ነገርኩት። “አሴ ልክ ነው! የአቶ ኃብተ ስላሴ ታፈሰ ልጅ የቀብሩ ስነ ስርአት ላይ ንግግር ካደርጉት አንዱ ነበር.. ይህንኑ  ተናገር” አለኝ። ለዚህም ነው ይህንን  አያሌው  በግል የነገርኝና  አደባባይ ያወጣሁት።

Fisha Geda 1
ከፍ ብሎ “ሁለታችንም ብንሆን በሌላው መልኩ ትምህርትና ስራ አጋብተን የቀጠልን ይመስለኛል” ወዳልኩት ለአፍታ መመለስ ፈለኩ። ሁለታችንም ከ10ኛ ክፍል አቋርጠን ወደየምንሔድበት ሔድን። እኔም የምሆነውን ሆንኩኝ። አሁን ዞር ብዬ ሳየው ግን ፍስሀ ገዳ እድሜ ልኩን ትምህርት ቤት ነበር ለማለት የሚያስችሉ ምልክቶች አያለሁ። የመጽሐፍት አዟሪነቱ የሕዝብ ግንኙነት ትምህርት መማሪያ  መድረክ ሆነው። ተፈጥሮ የስጠውንና የእለት-ተለት ኑሮ አስገድዶት መጽሐፍት ሲሸጥ አለበለዚያ ሊያገኛቸው የማይችላውን ግለስቦችን ድርጅቶችንም  ማገኘትና መገናኘት ቻለ። ታዋቂውን ደራሲና የረዥም ጊዜ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረውን ብርሐኑ ዘሪሁንን የተዋወቀው በዚህ አጋጣሚ ነበር። የልዑል ራስ እሙሩን ልጅ፤ወይዘሮ የምሥራች እምሩን፤ ተዋውቆ ቤተሰብ የመሆን ደርጃ የደረሰውም በዚሁ መጽሐፍ አዟሪነቱ  ምክንያት ነበር። ሁለት ስም ለዐይነት ጠቀስኩኝ እንጅ ያ ስራው የብዙ ሰዎች መተዋወቂያ፤የብዙ ቢሮዎች መክፈቻ ቁልፍ ሆኖት/ሆኖለት ነበር ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ፍስሐ ገዳ በአዟርነቱ ያገኘውን ትምህርት ወደሚቀጠለው ሕይወቱና ሙያው ከፍ ያደረገው ይመስለኛል። በመኮንንቱ ሐረር ሶስተኛ ክፍለ ጦር ሲመደብ  የክፍለ ጦሩ የሕዝብ ግንኙነት መኮንን ሆነ :: ለ11 አመታት የሠራዊቱ መጽሔት አዘጋጅ ነበር። የደረግ የመስታወቂያ ክፍል ሰራተኛ ነበር። የፕሬዚዳንቱ የፕሮቶኮል ሹም ከዚያም የሆቴልና ቱሪዝም ስራ አስኪያጅ ፤ከዚያም አምባሳደር ሆነ።በስደት አሜሪካ ከመጣም በኋላVienna,VerginiaATI Career Institute,School of International Hotel and Resautarant Mangment  ገብቶ በሙያው መስልጠን ብቻ ሳይሆን አስልጣኝም ሆነ። በዚህ ስራውም አለምን ዞረ። ይህ ሁሉ የጋዘጤኛና የህዝብ ግኑኝነት ስራ ሙያ ነው። ዩኒበርስቲ ገብተዉ የሚማሩት! ፍስሐ ለዚህ ሙያ የሰለጠነው በአዲስ አበባ የመንገድ ላይ ዩኒቨርስቲ ነበር።

አንድ ሌላ ስለፍስሐ ገዳ መነገር ያለበት አለ። ፍስሐ ከደሀ ቤተሰብ መውለድ ብቻ ሳይሆን ህይወትን በጸጋ ፊት ለፊት ተጋፍጦ ከደረሰበት የደረስ ነበር። አንድ እውቂ ባሕርዩ ማን እነደነበር፣ከየት እንደተነሳ፣ አንዴትስ እዚህ እነደደረስ መስማት ለሚፈልግ ሁሉ ሳይጠቀየም ይናገራል። ከራሱ አይሸሽም ነበር። ከራሱ ጋር ጸብ አልነበረውም። የሚናገረው በኩራት መልክ አለነበረም።በጸጸትም መልክ አልነበረም። በማፈረም አልነበረም። እኔ የኸው ነኝ፤እንዲህ ነበርኩ በሚል እውነቱን በመናገር (A matter of fact) መልኩ ብቻ ነበር።

 ለኔ ፍስሐ ገዳ ሰዉዬው የሚባል ሰው ነበር ።የKipling “IF”  የሚለውን ግጥም ያስታውሰኛል ።ይህን ግጥም አቶ ከበደ ሚካኤል ወደ አመርኛ መልሰውት ነበር።

If you can talk with crowds and keep your virtue,

Or walk with kings –not lose the common touch,

Yours is the Erath and everything that is in it

And –what is more, you will be a Man, my son

አንዳንዴ በጸጸት መልክ ወደኋላ የማያቸው አሉ። ከነዚህ አንዱ፤በደርግ አካባቢ ብዙ እቡያን መሰባሰባችን እውነት ነው።ጥቂት ብጹአንም መኖራቸው እርግጥ ነው። ፍስሐ ገዳ ከነዚህ አንዱ ነበር። በዛ ያሉ ፍስሐዎች ቢኖሩ ኖሮ  የወደአዘቅት ጉዟችንን ሊያስቀሩት ከዚያም ሊለዉጡት ይችሉ ነበር?  እላለሁ። ይህ  እንግዲህ ጸጋዬ ገብረ መድኅን:-

ትዝታ ነው የሚርበን

ላናገኘው ላያጠግበን  ወዳለው የሚደመር ይመስለኛል።

የማይሞት ሰው ሞተ!!በፍስሐ የሕይወት ታሪክ ውስጥ ደግሞ:-

ባለቤታቸው፣ ከወ/ሮ እቴነሽ ሸዋዬ ጋር፣ በ፩፱፭፱ ጋብቻ በመመስረት፣ ከ፬፰ ዓመት በላይ፣ በትዳርና ባማረ ፍቅር ኖረዋል። ከአብራካቸውም ሰርካለም ፍሰሐን፣ ብሩክታዊት ፍሰሐን፣ ደረጀ ፍሰሐን፣ በላይ ፍሰሐንና ንጋት ፍሰሐን አፍርተው አምስት የሚሆኑ የልጅ ልጆችን ለማየት በቅተዋል”  የሚል ተጽፏል።

ሰው ዘለዓለማዊ ነው!! የሚለው አንድምታም ያለው ይመስለኛል። አንድምታው ፍስሐ ማዉን የሚያነሱ ተክቷል። በዚህ ደግሞ እንጽናናለን!!

 

 

 

 

የፕሬዝደንት ኦባማ “ታሪካዊ ጉብኝት” አምባገነን አወዳሽ ወይንስ ዲሞክራሲ አጎልማሽ? –አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

$
0
0
ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር

የዚህ ሃተታ ዓላማ የፕሬዝደንት ኦባማን ጉብኝት አግባብና ሚዛናዊ ባለው መንገድ ተንትኖ አሉታዊና አወንታዊ ገጽታወቹን ለአማርኛ ተናጋሪዎች ለማቅረብ፤ የወደፊቱ የኢትዮጱያ ህልውና አስተማማኝ ሆኖ፤ የሰብአዊ መብቶችና የሕግ የበላይነት መከበር አለባቸውና የዲሞክራሳዊ አገዛዝ ምስረታ ሂደቶች ሕዝብን ማእከል ማድረግ አለባቸው የሚለው ብሂል ያገባናል የሚሉ ክፍሎች፤ ፈቃደኛነት ካላቸው፤ በጋራና በተናጠል ሊሰሯቸው የሚችሉትን የተወሰኑ መንደርደሪያ ሃሳቦች ለማቅረብ ነው። ባለፈው ሳምንት በድህረ ገጾች ላይ የተሰራጨው ተመሳሳይ ትችት ሆነ ተብሎ ለእንግሊዘኛ ተናጋሪዎች፤ በተለይ ለአሜሪካ ሕዝብ ቀርቧል፤ ብዙ ጠቃሚና የተለመደው “ለምን ይኼ ተባለ፤ ለምን ይኼ አልተባለም” የሚሉ ትችቶች ተሰራጭተዋል። ሁለቱንም አስተናግዳለሁ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

አክራሪና አሸባሪዉ ኢህአዴግ ወይስ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት? (ርዕዮት አለሙ)

$
0
0

ርዕዮት አለሙ

(ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ)

(ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ)

ልጆች ሆነን “እከሌ (እከሊት) አክራሪ ነዉ (ናት) ” ሲባል ይሰጠን የነበረዉ ትርጉም እና አሁን አክራሪነት እየሰጠ ያለዉ ትርጉም ለየቅል ይመስለኛል፡፡ ያኔ አንድ ሰዉ በአክራሪነት ሲጠራ ከብዙሃኑ በተለይ ሁኔታ ሃይማኖቱን ወይም የሚያምንበትን አንዳች ነገር አጥብቆ መያዙን እና በሚያምንበት ነገር ላይ የማይደራደር መሆኑን ከማሳየት አልፎ የአሁኑን አይነት አሉታዊ ትርጉም አይሰጥም ነበር፡፡ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል የተዘጋጀዉ የአማርኛ መዝገበ ቃላትም ያኔ ቃሉን እረዳበት ከነበረዉ ትርጉም ብዙም የራቀ ፍቺ አያቀርብም፡፡ በ1993 ዓ.ም የካቲት ወር የተዘጋጀዉ ይኸዉ መዝገበ ቃላት አክራሪ ለሚለዉ ቃል የሚሰጠዉ ፍቺ “በሚከተለዉ እምነትና አስተሳሰብ ዉስጥ ፍፁምነት ሊኖር ይገባል ብሎ የሚያምንና የቆየዉን እምነትና አስተሳሰብ ከዘመናዊዉ ሁኔታ ጋር ማስተካከል እና ማጣጣም የማይፈልግ አጥባዊ (ሰዉ)” የሚል ነዉ፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የቃሉ ፍቺ እየተቀየረ መጥቶ አሁን ያለዉን እጅግ አሉታዊ የሆነ ገፅታ ይዟል፡፡

የህግ ባለሙያዉ ተማም አባቡልጉ የካቲት3 2007ዓ. ም በወጣዉ ኢትዮምህዳር ጋዜጣ ላይ “አክራሪ ሰዎች እነማን ናቸው?” በሚል ርዕስ ባስነበቡት ፅሁፋቸዉ “የራሱን ዘር፣ ሃይማኖትና ቡድን ጥቅም ሌሎችን በመጉዳት ጭምር ለማስጠበቅ የሚንቀሳቀስ ወይም ከማስጠበቅ የማይመለስ” ሰዉ እንደሆነ አክራሪ የሚባለዉ ገልፀዋል፡፡

የዚህ ፅሑፍ አላማ አሁን እየተግባባንበት ካለዉ ፍቺ አንፃር ” የአክራሪነትና የአሸባሪነት ባህሪ የሚንፀባረቀዉ በቅርቡ በተፈረደባቸዉ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ወይስ በከሳሹ መንግስት?” የሚላዉን ጉዳይ መፈተሽ ይሆናል፡፡

የኢህአዴግ የምናብ ቀበሮዎች

ኢህአዴግ እኔን ጨምሮ በርካታ ከሽብር ጋር ሊገናኝ የማይችል ማንነት ያለንን ዜጎች የአሸባሪነት ስም ሰጥቶናል፡፡ ይሄን በአሰብኩ ቁጥር ሁሌም ወደ አእምሮዬ የሚመጣዉ ብዙዎቻችሁ የምታዉቁት የዉሸታሙ እረኛ ታሪክ ነዉ፡፡ እንደምታስታዉሱት ሌሎችን በማታለል የሚዝናናዉ ዉሸታም እረኛ ቀበሮ መጥቶ በጎቹን እየበላበት እንደሆነ አድርጎ የድረሱልኝ ጥሪ በጩኸት በማቅረብ አላፊ መንገደኞችን ይሰበስባል፡፡ መንገደኞቹ ለእርዳታ ሲመጡ ታዲያ ቀበሮዉ በገሀዱ አለም ያለ ሳይሆን የእረኛዉ የምናብ ዉጤት መሆኑን ይረዱና እየተበሳጩ ወደየመንገዳቸዉ ይመለሳሉ፡፡ ኢህአዴግም “አክራሪ ደረሰብን ፤ አሸባሪ መጣብን” እያለ አደንቋሪ ጩኸቱን ለቁጥር በሚያዳግት መልኩ በተደጋጋሚ አሰምቷል፡፡ ጩኸቱን ሰምተዉ ስለሁኔታዉ ለማወቅ የሞከሩትን ሁሉ ግን የጠበቃቸዉ እንደዉሸታሙ እረኛ የምናብ ቀበሮ ሁሉ የዉሸት አክራሪና አሸባሪ ነዉ፡፡የምናብ ቀበሮ የሚበላዉ በግ እንደሌለ ሁሉ የምናብ አክራሪና አሸባሪም የሚያወድመዉ ንብረትም ሆነ የሚያጠፋዉ የሰዉ ህይወት የለም፡፡ እስክንድር ነጋና ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን አሸባሪ ሊያሰኝ የሚችል ምን አደረጉ? አንዷለም አራጌ እና ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ምን አጠፉ? ምንም!

የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትም እንደከዚህ ቀደሞቹ ሁሉ የኢህአዴግ የምናብ ቀበሮዎች ናቸዉ፡፡ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ይሁን ሌሎቹ የኮሚቴ አባላት አክራሪም ሆነ አሸባሪ ለመባል የሚያበቃ ያደረጉት ነገር የለም፡፡ ይልቁንም መንግስት በሃይማኖታቸዉ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ እምነቱን ለመበረዝና ለመከለስ የሚያደርገዉን ጥረት እንዲያቆም እጅግ በሰለጠነና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሲጠይቁ የነበሩ በህዝበ ሙስሊሙ የተመረጡ የአላማ ሰዎች ናቸዉ፡፡ ለመረጣቸዉ ህዝብና ለሃይማኖታቸዉ ታማኝ ሆነዉ መገኘታቸዉ ግን ለኢህአዴግ ስላልተስማማዉ እንዲያስራቸዉ ብሎም ለመስማት የሚከብድ አሰቃቂ በደሎችን እንዲፈፅምባቸዉ ምክንያት ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በስህተት ያሳየዉ የአንደኛ ተከሳሽ የአቡበከር አህመድ እጆች በካቴና ታስረዉ ሲመረመር የሚያሳየዉ አሳዛኝ ምስል የተመለከተዉን ሁሉ ልብ የሚያደማ ነበር፡፡ በሁኔታዉ ልባቸዉ የተነካ ሙስሊም ወገኖቻችንን

አቡኪ ወንድሜ የእስልምና ብርሃን
ሁኔታህን አይተን ሁላችን አነባን
ብለዉ እንዲያዜሙ ያስገደደ ነበር፡፡

ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ኮሚቴዎቹ ከታሰሩበት አሰቃቂ ቦታም ሆነዉ ሰላማዊ የሆነዉ ጥያቄ መንግስት በሚወስዳቸዉ ያልተገቡ የአፈና ምላሾች ሳቢያ ሌላ መልክ እንዳይዝ በጎ መልዕክት ከማስተላለፍ ወደኋላ አላሉም፡፡ ኮሚቴዎቹ በዚህ መጠን ከህዝበ ሙስሊሙ አልፈዉ ለሀገር ሰላም ቢጨነቁም ዉሸታሙ እረኛ ግን የተለመዱ የሀሰት ዶክመንተሪዎችን በማቅረብ ስማቸዉን ለማጥፋት ሲታትር ነበር፡፡ ይብስ ብሎ ደግሞ በቅርቡ ከሰባት እስከ ሃያሁለት አመታት የሚደርስ ፍርድ ቀኝ እጁ በሆነዉ ፍርድቤት በኩል አስተላለፈባቸዉ፡፡ ይህ አስገራሚ ፍርድ በሚተላለፍበት ወቅት ግን ኮሚቴዎቹ በጀግንነት ቆመዉ እንባ የሚራጩ ዘመድ ወዳጆቻቸዉን ሲያፅናኑ እንደነበር ችሎቱን የተከታተሉ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ አስቀድመዉ በነበሩ ችሎቶች ላይ “እዚህ የቆምነዉ ፍትህ እናገኛለን በሚል እምነት አይደለም፡፡ ለታሪክ ምስክር ለመሆን እንጂ” በማለት እንደገለፁት ከካንጋሮ ፍርድቤት የሚጠብቁት ፍትህ ባለመኖሩ የተሰጣቸዉ ፍርድ እንደማያስደነግጣቸዉ ግልፅ ነዉ፡፡ የኮሚቴዎቹ አባባል ኔልሰን ማንዴላ ያልተገባ ስም ተሰጥቷቸዉ ለፍርድ በቀረቡበት ወቅት የተናገሩትንና የግል የህይወት ታሪካቸዉን ባሳተሙበት መፅሐፍ ዉስጥ የሚገኘዉን የሚከተለዉን ሃሳብ ያስታዉሰኛል፡፡

ይህ የፍትህ ስርዐት ጥፋተኛዉ ንፁሑን በህግ ፊት እንዲያቀርበዉ ጉልበት የሚሰጠዉ በመሆኑ ትልቅ ስጋት ዉስጥ ይከተኛል፡፡ የፍትህ ስርዐቱ ልክ ያልሆነዉ ልክ የሆነዉን እንዲከስና ማስቀጣት እንዲችል የሚያደርግ ነዉ……. በመሆኑም ፍትሃዊና ተገቢ ፍርድ አላገኘም፡፡

ያኔ ኔልሰን ማንዴላ አስቀድመዉ እንደተናገሩት የአፓርታይድ መሪዎቹ የሚያሽከረክሩት ፍርድቤት ያልተገባ ፍርድና የወንጀለኛነት ስም ሰጥቷቸዋል፡፡ ዛሬም ኮሚቴዎቹ ኢህአዴግ በሚያሽከረክረዉ ፍርድቤት አማካኝነት ከማንዴላ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ፍርድና ተመሳሳይ የሆነ ስያሜ አግኝተዋል፡፡ “አሸባሪነት” ዛሬም እንደትላንቱ ሁሉ አምባገነኖች የሚቃወሟቸዉን ንፁሃን የሚመቱበት ዱላ መሆኑን ቀጥሏል፡፡

አክራሪዉ ኢህአዴግ ነዉ!

የኢህአዴግ ባላስልጣናት አክራሪነት ከሱ ሌላ የሆነ ቡድን ወይም ማንነት እንዲኖር የማይፈቅድ እንደሆነና “ለልማታችን እና ለዲሞክራሲ ግንባታችን” ዋነኛ ጠር መሆኑን ሁሌም እንደነገሩን ነው፡፡ ከአባባሉ ተነስተን አክራሪ ስንፈልግ ዉለን ብናድር የምናገኘዉ ትልቁ አክራሪ ግን እራሱ ኢህአዴግ ሆኖ ይገኛል፡፡

ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሌላ ርዕዮተ አለም በሀገራችን እንዳይኖር አይደለም እንዴ የተለየ መስመር የሚከተሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚያፈርሰው? በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጦችና መፅሔቶች የመዘጋታቸዉና ጋዜጠኞቹ የመታሰርና የመሰዳደቸዉ ምክንያትስ እርሱ ከሚቆጣጠራቸዉ ዉጪ የሆኑ ሚዲያዎች እንዳይኖሩ ከመፈለግ የመጣ አይደለምን? የደሃ ሀገራችንን አንጡራ ሃብት እንደ ሃኪንግ ቲም ላሉ የጣልያን ተቋማትን የሚከሰክሰዉ ሁሉን ለመቆጣጠር ባለዉ ክፉ አባዜ ምክንያት መሆኑን መች አጣነዉ? የትምህርትም ሆነ የስራ እድል የኢህአዲግ አባል ካልተሆነ ለማግኘት የጠበበዉ ከኢህአዲግ አክራሪ ባህሪይ የመነጨ መሆኑ ግልፅ ነዉ፡፡ ሌሎች ብዙ የኢህአዲግ አክራሪነት መገለጫዎችን መዘርዘር ይቻላል፡፡ ለማጠቃለል ያህል አንዱን ልጥቀስ

በሜታ ሮቢ ወረዳ አስተዳደር የወራቦ ቀበሌ አስተዳደር ነዋሪ የሆኑ አስራ አራት ግለሰቦች “በ2007ዓ.ም በተካሄደዉ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ሲደግፉ ነበር” በሚል አስገራሚ ምክንያት የተነሳ ማናኛዉንም የህግና የአስተዳደር አገልግሎቾችን ማግኘት እንዳይችሉ በቀበሌ አስተዳደሩ ለሚመለከተዉ ሁሉ ስማቸዉ ተዘርዝሮ ተፅፏል፡፡ ባለፈዉ ረቡዕ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻዉ እንዚህን ግለሰቦች ጨምሮ በርካታ የፓርቲዉ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየደረሱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የችግሩን ምክንያት ሲያስረዱም “እነዚህ ታጋዮቻችን ህዝቡ መድረክን እንዲመርጥ ምን ሲሰሩ እንደነበር ስለሚያዉቅ አሁን እየወሰደ ያላዉ የበቀል እርምጃ ነዉ” ብላዋል፡፡ በዚህ መጠን ከእርሱ ሌላ እንዳይኖር የሚፈልገዉና ኖሮ ሲገኝ ደግሞ ተሸብሮ ህዝቡን የሚያሸብረዉ ኢህአዲግ የማይገባቸዉን ሰዎች አሸባሪ እና አክራሪ ሲል አፉን ያዝ እንኳን አያደርገዉም፡፡ ገዢዉ ፓርቲ ያልተገባ ስም የሰጣቸዉ ሙስሊም እህቶቻችን ቢቸግራቸዉ እንዲህ በማለት ሊያርሙት ሞክረዉ ነበር

የሂጃቡ ነገር ከላይ ከፈጣሪ
የኒቃቡስ ነገር ከላይ ከፈጣሪ
ልባል አይገባም አክራሪ አሸባሪ

የኮሚቴዎቹ እስርና ፍርድ ምን ሊያስከትል ያችላል?

ገዢዉ ፓርቲ ጥያቄዎችም ሆነ ተቃዉሞዎች ሲነሱበት ራሱን ከመመርመር ይልቅ በድፍረት ድምፃቸዉን ያሰሙ አካላትን ማሰርን ይመርጣል፡፡ በዚህም እፎይታን የሚያገኝ ይመስለዋል፡፡የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትም ላይ ያደረገዉ ይህንን ነዉ፡፡ ነገር ግን ይሄ አካሄዱ የተመኘዉን እፎይታ ሊያስገኝለት ይቅርና ለሀገር የሚተርፍ ችግር ሊያመጣ እንደሚችል ጉዳዩን በጥልቀት የተከታተሉ ወገኖች ይገልፃሉ፡፡

ከነዚህ ወገኖችአንዱ የሆነው ጋዜጠኛ ሀይለመስቀል በሸዋምየለህ በቅርቡ ገበያ ላይ በዋለዉና “የሀይለማርያም እዳ እና የሙስሊሙ ትግል” በሚል ርዕስ ባዘጋጀዉ መፅሐፉ ዉስጥ በርካታ በጉዳዩ ላይ የተሰሩ ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ እንደገለፀዉ ኢህአዲግ የሙስሊሙን ጥያቄ ለማፈን እየተጓዘበት ያለዉ መንገድ እጅግ አፍራሽ ዉጤት ይኖረዋል፡፡ ከአፍራሽ ዉጤቶቹ አንዱ ደግሞ “ኢህአዴግ እየተከላከልኩት ነዉ የሚለዉ ፅንፈኝነት መፈጠር” ሊሆን እንደሚችል መፅሐፉ ያስረዳል፡፡ ዶ/ር አባድር ኢብራሂም ADDIS STANDARD በተሰኘ ወርሃዊ መፅሔት የዚህ ወር እትም The unfair trial of Muslim Leaders ; why it undermines counter terrorism in Ethiopia በሚል ርዕስ ባቀረቡት ፅሁፋቸዉ ዉስጥም ተመሳሳይ ስጋት እናገኛለን፡፡ ዶ/ር አባድር ኮሚቴዎቹ ላይ የተሰጠዉን የጥፋተኝነት ዉሳኔ መነሻ በማድረግ ባዘጋጁት በዚህ ፅሁፋቸዉ የተላለፈዉ ውሳኔ የፍትህን መክሸፍ ከማሳየቱ በላይ እነዚህ የሲቪል ማህበረሰብ መሪዎች ወደፊት ከሚመጣ የሽብር አደጋ የመስዕዋት ጠቦት ሆነዉ ሊያድኑን አለመቻላቸዉ እንዳሳዘናቸዉ ገልፀዋል፡፡ ዶክተሩ ኮሚቴዎቹ ላይ የተላላፈዉ ውሳኔ እንደዉም የሽብር ስጋቱን እንደሚጨምር አምስት መከራከሪያዎችን በማቅረብ ይሞግታሉ፡፡ እኚሁ የህግ ምሁር ከመከራከሪያዎቹ በአንዱ እንዳብራሩትኮሚቴዎቹ በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ እጅግ ተሰሚነት ያላቸዉ መሪዎች እንደመሆናቸዉና በፀረ ሽብር ትግሉ አገላለፅ “ለዘብተኛ” የሚባሉ ስለሆኑ አክራሪነትን ለመከላከል ግንባር ቀደም አጋር ሊሆኑ የሚችሉ ነበሩ፡፡ ኢህአዲግ እነዚህን ትልቅ አጋር ሊሆኑ የሚችሉ መሪዎችን በመክሰስና በማሰር እዋጋቸዋለሁ የሚለዉን አክራሪ ድርጅቶች የቤት ስራ እንደሰራላቸዉ ዶክተሩ በፅሁፋቸዉ ይገልፃሉ፡፡ ምክንያቱን የሚያብራሩትም እንደነ አቡበከር አይነቶቹ ቅሬታዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍረታት የሚታትሩ ሙስሊም መሪዎች ባላቸዉ ተቀባይነት ፅንፈኛ ድርጅቶች ቅቡልነት እንዲያጡ በማድረግና የድርጅቶቹን ትምህርቶች ሊገዳደር በሚችል የሃይማኖቱ ትምህርት በመምታት እስልምናን ሽፋን አድርጎ የሚመጣን የሽበር አደጋ ለመከላከል የነበራቸዉን አቅም በመጥቀስ ነዉ፡፡ ዶክተሩ በሌላኛዉ መከራከሪያቸዉ ደግሞ በሰላማዊ መንገድ ለመወያየት ጥያቄያቸዉን ለማቅረብ በሞከሩ ሙስሊሞች ላይ መንግስት እየፈፀማቸዉ ባሉ በደሎች ሳቢያ አመፅአልባ ትግሉጥያቄ ዉስጥ መግባቱና ሰዎች ወደሌላ አማራጭ ለማየት መገደዳቸዉ እንደማይቀር ያስገነዝባሉ፡፡

ጋዜጠኛ ሀይለመስቀልም ሆነ ዶ/ር አባድር ይሄ ትልቅ ሀገራዊ ችግር የሚያመጣዉ ኪሳራ አሳስቧቸዉ መፍትሄ ፍለጋ ላይ ታች ቢሉም ኢህአዲግ ግን አሁንም ከመጥፎ ድርጊቱ አልታቀበም፡፡ በትላንትናዉ ዕለት እራሱ ኮሚቴዎቹን ለማስፈታት ተንቀሳቅሳችኋል ያላቸዉ ሃያ የዕምነቱ ተከታዮች ላይ ክስ እንደመሰረተ በማህበራዊ ድረገፆች እያነበብን ነዉ፡፡ እስርቤት በነበርኩበት ወቅትም የአዳማ ሙስሊምተማሪዎችን ጨምሮ በተመሳሳይ ክስ በርካታ ሙስሊሞች ይታሰሩ እንደነበር አዉቃለሁ፡፡

ገዢዉ ፓርቲ ስህተቱን በስህተት ለማረም የሚያደርገዉ እንዲህ አይነቱ አሳፋሪ እንቅስቃሴ መገታት ይኖርበታል፡፡ አለበለዚያ በሀሰት ቀበሮ እየተባሉ ፍዳቸዉን የሚያዩ ንፁሃን ወገኖቻችን ጉዳይ አሳስቦን በአንድነት መቆምና ገዢዉን ፓርቲ መታገል ካቃተን ነገ እዉነተኛ ቀበሮዎች ቢመጡ የምንመክትብት ጉልበት አይኖረንም፡፡ ለአሁኑ ግን ለእኔ የታየኝ አደገኛ ቀበሮ ኢህአዴግ ራሱ ነዉ፡፡


ሃብታሙ አያሌው; ዳንኤል ሺበሺ; አብርሃ ደስታ; የሽዋስ አሰፋ እና አብርሃም ሰለሞን በነፃ እንዲሰናበቱ ተወሰነ

$
0
0

Habtamu abrhayeshiwas danielዛሬ ነሃሴ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱትን 2ኛ ተከሳሽ ሀምታሙ አያሌው፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 5ኛ ተከሳሽ የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ አብሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡ በአንፃሩ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ከአሁን ቀደም ተከሶበት በነበረውና ከ15 አመት በላይ እንደሚያሳስር የሚታወቀው የፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ‹‹ማሴር፣ ማቀድ ተግባረት›› ላይ መረጃ ስላልተገኘበት አንቀፁ ወደ 7/1 ላይ በተመለከተው ላይ ተቀይሮ እንዲከላከል ተበይኖበታል፡፡

በዚህ አንቀፅ ለግንቦት ሰባት በመመልመል ተግባር ተሰማርቷል በሚል እንደተከሰሰም ተገልጾአል፡፡ በተመሳሳይ 6ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ ፣10ኛ ተከሳሾች ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር እንዲከላከሉ ተብለዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ አራቱ ፖለቲከኞች ሲታሰሩ በኢግዚቢት የተያዘባቸው ተለቆላቸው እንዲፈቱ ሲወንስ እንዲከላከሉ ያላቸው የመከላከያ ምስክር እንያስመዘግቡ በይኗል፡፡

የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች በነፃ የተሰናበቱት፣ የቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክስ ከጥርጣሬ ባለፈ ተሳትፎአቸውን ማረጋገጥ ባለመቻሉ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አስታውቋል፡፡

በውሳኔው መሠረት አቶ ሀብታሙ የሚጠየቁበት ወይም ሌላ የሚፈለጉበት ጉዳይ ከሌለ በዛሬው ዕለት እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺና አቶ የሺዋስ አሰፋ ከዚህ ቀደም ችሎት በመድፈር የተፈረደባቸውን ቅጣት እንዳጠናቀቁ እንዲፈቱ ወስኗል፡፡

 

በአንደኛ ዙር 14 ሚልዮን ርሃብተኛ አምራቹ የኢህአዴግ/ወያኔ የትራንስፎርሜሽን እቅድ በሁለተኛው ዙር ስንት ሊያመርት አቀደ? – (ጉዳያችን)

$
0
0

እና አቶ ኃይለ ማርያም፣እውነት ለርሃብ መንስኤ የአየር ንብረት ለውጥ ብቻ ነው?

unnamedሰሞኑን የአራት ኪሎ ቅምጥሎች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለሌላ ዙር የጥፋት ተግባር ለመሰማራት ደፋ ቀና እያሉ ናቸው።ርሃቡን በአየር ንብረት ሰበብ የጥፋት ተግባራቸውን ማጠብያ ሰበብ አድርገው በማቅረብ እና 14 ሚልዮን ርሃብተኛ ያፈራውን የመጀመርያ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተብዬ በሌላ ማደናገርያ ሁለተኛ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በሚል ማደናገርያ ለመተካት።

በአንደኛው የትራንስፎርሜሽን እቅድ ውጤት መሰረት 14 ሚልዮን ርሀብተኛ አመረታችሁ። በሁለተኛውስ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስንት ርሀብተኛ ልታፈሩ አቀዳችሁ?

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጧት ማታ ኢትዮጵያ አደገች እያለ እንደሚለቀው ተራ ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የ2015 ዓም እ አ አቆጣጠር የሰው ልማት ሪፖርት የሚያሳየው ከ186 የዓለም ሃገራት ውስጥ ኢትዮጵያ 173ኛ መሆኗን እና ከአብዛኛዎቹ የሳሃራ በታች ካሉ ሃገራት አንፃርም መጨረሻ ላይ መሆኗን ነው። ”Even though Ethiopia is one of the 10 countries globally that has attained the largest absolute gains in its HDI over the last several years, it still ranks 173rd out of 186 countries in the latest UNDP Human Development Report.” UNDP National Human Development Report 2015 Ethiopia.

ይህንን ውርደታችንን ለእሩብ ክ/ዘመን ማሻሻል ያልቻለው ወያኔ በምርጫው 100% አሸነፍኩ እያለ አይን ያወጣ ፕሮፓጋንዳውን በሚነዛባት ሀገር ለሌላ ድህነት ሕዝቡን ለመዳረግ ”ሁለተኛ የትራንስፎርሜሽን እቅድ” እያለ ማደናገር ይዟል።እውነታው ግን ከቅኝ ግዛት ከተላቀቁ ሃገራት አንፃር ሲታይም በካድሬ ምሁር ነን ባይ እቅድ የሚነደፍልን እኛ በብዙ ደረጃ ወደኃላ የቀረን መሆናችንን ነው።ለምሳሌ በ 2014 እአውሮፓውያን አቆጣጠርም በወጣው ዘገባ መሰረት አንዳችም ለውጥ አለማሳየታችን የዘንድሮው የተባበሩት መንግሥታት ዘገባም ያሳያል።በእዚህም መሰረት-
ሱዳን በሰባት ደረጃ ቀድማን 166ኛ፣
ጋና በሰላሳ ሰባት ደረጃ ቀድማን 138ኛ፣
ኬንያ በሃያ ስድስት ደረጃ ቀድማ 147ኛ፣
ዑጋንዳ በዘጠኝ ደረጃ ቀድማ 164ኛ፣
ናሚብያ በአርባ ስድስት ደረጃ ቀድማን 127ኛ፣ይቀጥላል። ዝርዝሩን ይህንን በመጫን ይመልከቱ።

እውነታው ይህ ሆኖ ነው እንግዲህ የመጀመርያው ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተብዬ ጥቂት የስርዓቱን ሰዎች በሀብት ማዕበል ውስጥ መክተቱ እና ነውራቸው ለዓለም አደባባይ ተርፎ በለንደን አየር መንገድ ሳይቀር በእዚህ ሳምንት መጀመርያ በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እንደተዘገበው ከ5 ሚልዮን የእንግሊዝ ፓውንድ በላይ በግለሰቦች ቦርሳ ተይዞ ሲወጣ እየታየ አቶ ሃይለማርያም ”አይናቸውን በጨው አጥበው” ስለ ”ሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን” እያሉ መስበክ ጀምረዋል።ስለሀገር አስተዳደርም ሆነ ስለልማት አንዳች በማያውቁ የካድሬ ስብስብ የተዘጋጀው ሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ኢትዮጵያን ለበለጠ መቀመቅ ለመክተት ካልሆነ በቀር ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንዳች የማይፈይድ ለመሆኑ ብዙ እማኝ ምክንያቶችን ማቅረብ ይቻላል።

ኢትዮጵያን የሚያህል በርካታ የተማረ የሰው ኃይል ያላትን ሀገር ምሁራኑን በእስር ቤት አጉራችሁ የቀረውን ከሀገር አሰድዳችሁ ከመሰል ካድሬዎቻችሁ ጋር የአምስት ዓመት እቅድ እያላችሁ ስትዘባበቱ መስማት በእራሱ የሀገሪቱን የውርደት ደረጃ አመላካች ነው።የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት፣ፖለቲካ፣እና ማህበራዊ ሕይወት ዘረኛ ለሆነ ርኩስ መንገዳችሁ እንዲመች እያደረጋችሁ መቀየሳችሁን እናንተ ብቻ የምታውቁት ከመሰላችሁ መሳሳታችሁን እወቁት።በወረደ አስተሳሰብ ውስጥ ተዘፍቃችሁ በኢትዮጵያ ስም በአደባባይ ላይ ስትናገሩ ከመስማት በላይ ምን ውርደት አለ? ሰሞኑን አቶ ኃይለ ማርያም የከሸፈውን ያለፈውን እቅድ እያድበሰበሱ ስለመጪው ማውራት ሰሞኑን የተያዘ አዲሱ ፋሽናቸው ሆኗል።ለመሆኑ የሚቀጥለውን የአምስት ዓመት እቅድ የሚቀይሱት ምሁራን ሳይሆኑ ካድሬዎች መሆናቸውን ”ሪፖርተር ጋዜጣ” በአንድ ወቅት የዘገበውን መመልከት በእራሱ ነገሩ ሁሉ ”ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ” መሆኑን ለመረዳት አያዳግትም።ለሌላ 5 አመታት የ90 ሚልዮን ህዝብን ዕጣ እንወስናለን ብለው ሁለተኛ ትራንስፎርሜሽን እቅድ እናቅድላችሁ ያሉንን ባለ ጊዜዎች ይህንን በመጫን ተመልከቱ።
በልማት ጥናት ዘርፍ እቅድ አዘገጃጀት ልምድ ያላቸው ምሁራን እና የሀገሪቱን ሕዝብ ማወያየት 100% አሸነፍኩ ላለን እፍረተ ቢስ ምኑ ነች? ከሁለት ሳምንት በኃላ ኢህአዴግ አዲስ እቅድ አወጣ ብለው እየተዘጋጁ እና መስከረም ላይ ምክርቤቱ አፀደቀው ሊሉን አፋቸውን እያሟሹ ባለበት ወቅት ሕዝብ አወያየን ለማለት አቶ ሃይለማርያም ዛሬ ነሐሴ 13/2007 ዓም ኢቲቪ ላይ ቀርበው ግራና ቀኛቸውን ያልለዩ ምልምል ካድሬዎች ሰብስበው በሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ ተወያዩ የሚል ፌዝ አይሉት ቀልድ ማስደመጣቸው ነው።”ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ያፅናሽ” ማለት የእዚህ ጊዜ ነው።የሀገር ሀብት በጥቂት ካድሬዎች ያውም በዘር እና በጎሳ በተጠራሩ እጅ መውደቁ ይዘገንናል።

አቶ ኃይለ ማርያም እውነት ለርሃብ መንስኤ የአየር ንብረት ለውጥ ብቻ ነው?

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (FAO) በድረ-ገፁ ላይ ”ለረሃብ ምክንያት የሚሆኑት ምክንያቶች ምንድናቸው? ” በሚል ርዕስ ስር ባሰፈረው ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ የአየር ንብረት መዛባት አንዱ ምክንያት እንጂ ዋናው አለመሆኑን ያብራራል።በዓለም አቀፍ የልማት ጥናት ባለሙያዎች ገለፃ መሰረት ርሃብ ሰው ሰራሽ ክስተት እንደሆነ ያስረዳሉ።ይህ ማለት ግን የአየር ንብረት መዛባትን የሰው ልጅ ያስተካክለዋል ማለት ሳይሆን ከአየር ንብረቱ መዛባት በላይ የመንግስት ቸልተኝነት እና ከሁሉም በላይ የተዝረከረከ አሰራር ውጤት መሆኑን የዓለም ምግብ ድርጅት ይገልፃል።

በእዚህም መሰረት በዓለም ምግብ ድርጅት ማብራርያ መሰረት የርሃብ ምክንያቶች በርካታ መሆናቸውን እና በዋናነት ግን ስድስት መሆናቸውን ይገልፃል። በቅድምያ ፅሁፉ በመግቢያነት የሚይስቀምጠው ነጥብ ”ዓለም ለ7 ቢልዮን የዓለማችን ሕዝብ በቂ ምርት ያመርታል” በማለት ይጀምርና ስድስቱን በአንድ ሀገር ላይ ርሃብ የሚከሰትባቸውን ምክንያቶች ይዘረዝራል።

1/ ድህነት (Poverty trap)

2/ በእርሻ ላይ በቂ መዋለ ንዋይ አለመመደብ ( Lack of investment in agriculture)

3/ የአየር ንብረት ለውጥ ( Climate and Weather)

4/ ጦርነት እና የህዝብ ከስፍራው መፈናቀል (War and displacement)

5/ ያልተረጋጋ የምግብ ገበያ ( Unstable Market)

6/ የተረፈ ምግብ ብክነት ( Food Wastage)
ዝርዝሩን ለማየት ይህንን ይጫኑ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የርሃብ አደጋ እንዳንዣበበባቸው በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች መዘገቡ ይታወሳል።አቶ ኃይለ ማርያምን ለናሙናነት ያስቀመጠው የወያኔ መንግስት ግን ለሕዝቡ ትክከለኛውን የአደጋውን ጥልቀት ከማስረዳት ይልቅ ”ድርቅ በአሜሪካም፣አውስትራልያም አለ” እያለ ከመግለፅ ያለፈ ተግባር ሲፈፅም አይታይም።የሰው ሕይወትን የማዳን ሥራ ከመስራት ይልቅ የማደናገርያ ቃላትን መደርደር ከተጠያቂነት አይድንም።አቶ ሃይለማርያም የድርቅ መንስኤ የአየር ንብረት መዛባት ብቻ እንደሆነ አድርገው የገለፁበት ንግግር ባለፈው ሳምንት ስሰማ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚናገረው ንግግር አይመስልም።በሃያ አንደኛው ክ/ዘመን ላይ ተቀምጠው ህዝብን ለማታለል ለሚታትር ያውም በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ የተቀመጠ ሰው ከማየት የበለጠ ምን ያሳፍራል?

ከላይ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከዘረዘራቸው ምክንያቶች ውስጥ አምስቱ የማን ተግባራት ናቸው? ለአቶ ሃይለማርያም እና ለአራት ኪሎ ቅምጥል ባለስልጣናት የሚቀርብ ጥያቄ ነው።የተረጋጋ የምግብ ገበያ መፍጠር የማን ሥራ ነው? የህዝብ መፈናቀልን መከላከል የማን ሥራ ነው? (አፈናቃዩ በመንግሥትነት የተሰየመ መሆኑ ደግሞ ሌላው አስደንጋጭ ጉዳይ መሆኑን ሳንረሳ)፣ጦርነት እና የጦርነት ስጋት እንዳይኖር ማድረግ የማን ሥራ ነው? በእርሻው ዘርፍ ላይ በቂ መዋለ ንዋይ እንዲኖር ማድረግ የማን ሥራ ነው? ድህነትን መቀነስ የማን ሥራ ነው?

ባጠቃላይ ኢህአዴግ/ህወሓት የሩብ ክ/ዘመን ተግባሩ ከበቂ በላይ ማንነቱን እና ሀገር የመምራት ደካማ አቅሙን ብቻ ሳይሆን በመጪው ዓመታት ኢትዮጵያን ሊከታት ያሰበበት ትልቅ አዘቅት መጠን በትክክል እየታየ ነው።የመጀመርያ፣ሁለተኛ ትራንስፎርሜሽን እያሉ ማደናገር ጊዜ ያለፈበት የፈዘዘ እቅድ ነው።ለርሃቡ የአየር ንብረትን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ ደግሞ የበለጠ ምን ያህል ከሳይንስ የራቁ ቅምጥሎች እየመሩን እንዳሉ አመላካች ነው።በእርግጥ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ይህንን ስርዓት የምትገላገልበት ጊዜ መፋጠን እንዳለበት አእምሮ ላለው ሰው ሁሉ ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች በእራሳቸው በቂ ናቸው።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ነሐሴ 14/2007 ዓም (ኦገስት 20/2015)

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የተላለፈውን ኢ-ፍትሐዊ ውሳኔ በመቃወም የወጣ የአቋም መግለጫ

$
0
0

ዛሬ በአገራችን ውስጥ በፖለቲካ አቋም ልዩነት ሣቢያ እንዲሁም የሃይማኖት ነጻነት እንዲከበር በጠየቁ ወገኖቻችን ላይ የወያኔ አምባገነን መንግሥት እያደረሰ ያለው ኢሰብአዊ ድርጊት በእጅጉ ተባብሦ ይገኛል::

muslim addis
የወያኔ አገዛዝ ሠለባ የሆኑ የፖለቲካ መሪዎች፣ የሙስሊም ሃይማኖት መሪዎች፣ ከየቀዬያቸው እየተፈናቀሉ የሚገኙ ወገኖቻችንን በተመለከተ በተደጋጋሚ እና በማያቋርጥ መልኩ በዚህ ሰው በላ ሥርዐት እየተደረገ ያለው ጭቆና ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደደረሰ እንረዳለን::

አዎ ዛሬ በአገራችን በዴሞክራሲ እጦት ምክንያት በየእስር ቤቱ የሚማቅቁ ውድ ዜጎች ያሉባት፣ በእምነትና በዲሞክራሲ ነጻነት እጦት ሣቢያ ህብረተሰባችን አፉ ተሸብቦ የሚገኝባት፣ ህፃን አዋቂ ሳይባል በልማት ስም የሚፈናቀልባት፣ ለዘመናት በጽናት የቆዩ የእምነት ቦታዎች የሚደፈርባትና በህዝብ መካከል ጸንቶ የቆየውን አብሮነት ለመናድ ከፍተኛ ውንብር የሚፈጸምባት፣ የዘር ማጥራት የሚካድባትና በዝርዝር ቢገለፁ ቦታና ጊዜ የማይበቃቸው የአፈናና የጭቆና ተግባራት የሚከናወንባት ሀገር ሆናለች::

በህግ የተደነገጉ የሃይማኖት ነጻነታቸውን ለማስከበር ሠላማዊ ትግል ሲያደርጉ በነበሩ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ በርካታ የሃይማኖትና የህብረተሰብ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ አርቲስቶች እና አክቲቪስቶች ላይ ሲካሄድ የነበረው ለ3 አመታት የቆየ የችሎት ድራማ ሐምሌ 27 ቀን 2007 መንግስት ራሱ አሳሪ፣ ከሳሽ፣ መስካሪ፣ ፈራጅ ግልጽ በሆነበት ክስ የቅጣት ፍርድ ያስተላለፈ ሲሆን ንጹህ ወንድሞቻችን ላይ ከ 7 እስከ 22 አመታት የሚደርስ እስራት መበየኑ ይታወቃል:: በወንድሞቻችን ላይ የተሰጠው ኢፍትሐዊ ውሳኔ አገራችን ምን ያህል ከፍትህ የራቀች መሆኗን በድጋሚ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው::

የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ላለፉት አራት አመታት የመንግስትን አሰቃቂ ግፎች ሲያስተናግድ ቆይቷል:: “እኔ ለክቼ የሰራሁልህን እንጂ በነጻነት የመረጥከውን እምነት ማራመድ አትችልም” በሚል አምባገነናዊ ስርአቱ የከፈተበትን ዘመቻ እጅግ በሰለጠነና ሰላማዊ መልኩ ሲያስተናግድ ቆይቷል::

ሙስሊሙ ማህበረሰብ እነዚህን ግፎች በሰላምና በትእግስት ሲያስተናግድ የቆየው ድል ያለመስዋትነት እንደማይገኝ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነው:: ዛሬም በማንአለብኝነት በሙስሊሙ ውድ ኮሚቴዎችና ረዳቶቻቸው ላይ የፈጸመው የግፍ ውሳኔ የስርአቱን የተባ የፍርድ ስርአትና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ በአጠቃላይ ደግሞ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያለውን ንቀት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው::

እኛም በኦክላንድ ኒውዚላንድ የምንገኝ ኢትዮጵያን ከዚህ በፊት የተላለፈውን ጥፋተኝነት ብይን እንደተቃወምነው ሁሉ ዛሬም ይህንን ፍርድ በጽኑ እናወግዛለን:: ምንም እንኳን የሙስሊም መሪዎች ላይ የተሰጠው የፍርድ ውሳኔ አሳዛኝ ቢሆንም የተጀመረውን ትግል ይበልጥ እንዲቀጣጠል እንደሚያደርገው ቅንጣት ያህል አንጠራጠርም::

በተለያየ ጊዜያት እየተፈጸመ እንደሚገኘው በፖለቲካ እምነታቸው ለአገራቸው ቀናኢ ሆነው በግንባር ቀደምነት ትግሉን ሲመሩ የነበሩትን የፓርቲ መሪዎችና አባሎች እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ በሽብርተኝነት ስም የረዥም ጊዜ እስራት በመወሰን ከህዝብ እይታ በመሰወር በመግደል እንዲሁም በሞትና በህይወት እንዲኖሩ የተወሰነባቸውን ሁል ግዜም እናስባቸዋለን::

በአገራችን እየደረሰ ያለውን የግፍ አገዛዝ በማስመልከት በተባ ብእራቸው ሃሳባቸውን በጽሁፍ በማቅረባቸው እንደ ሽብርተኛ ተቆጥረው ለረዥም አመታት የእስር ሰለባ የሆኑትን ነጻ ጋዜጠኞችን አብረን እናስባችዋለን::

በመሆኑም እኛ በኦክላንድ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ያሉንን ልዩነቶች በማቻቻል መብታችንን ለማስከበርና ነጻነታችንን ለማግኘት ከማንኛውም ጊዜ በተለየ መልኩ በሃገራዊ ስሜት ተነሳስተው በሁሉም አይነት የትግል ዘርፍ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ወገኖቻችንን ለማገዝ የበኩላችንን ለመወጣት በጋራ የቆምን መሆናችንን እንገልጻለን::

የዜጎች ነጻነት ማጣት መሰቃየት መታሰር መሞት መሰደድ ግድ ብሎን አላማችንን ከእውነተኛ የነጻነት ትግል በመነሳት የወያኔን አረመኔያዊ ስርአት አስወግዶ ነጻነታችንን ለመቀዳጀት በኢትዮጵያዊነት ስሜትና ተነሳሽነት እስከሆነ ድልን የምንቀዳጅበት ቀን ሩቅ መስሎ አይሰማንም:: ለዚህም ፈጣሪያችንን ከልብ እንማጸነዋለን::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!!!

በኦክላንድ የኢትዮጵያውያን ነፃ የውይይት መድረክ
ነሐሴ 3 ቀን 2007 (ኦገስት 9 ቀን 2015

ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ማጠናከሪያ በቬጋስ ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ተዋጣ

$
0
0

የግንባሩ አመራር የወያኔን ሻዕቢያ ወረረን የማደናገሪያ ካርድ ቀደን መጣል አለብን ሲሉ ገለጹ

ቬጋሱ ሕብር ራድዮ ዋና አዘጋጅ
ሐብታሙ አሰፋ ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው

የአርበኞች ግንቦት 7 ትላንት ማምሻውን ረቡዕ ኦገስት 19 /2015 በላስ ቬጋስ ከተማ ባካሄደው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ጨረታን ጨምሮ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ብር ዌኢም ከ65 ሺህ ዶላር በማይ ገቢ ተሰበሰበ።ሕዝቡ ግንባሩ የጀመረውን ትግል በመደገፍ በስልጣን ላይ ያለውን የግፍ አገዛዝ ለመጣል እስከመጨረሻ ድጋፉ እንደማይለይ የተሌአዩ ተሰብሳቢዎች ገለጹ።
habtamu
በስብሰባው ላይ ለጨረታ የቀረበው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፎቶና በኤርትራ በረሃ የሚገኙ ሴት ወጣት ታጋዮች ምስል በአንድነት ያለበትን ከ35 ሺህ ዶአለር በላይ በስፍራው የተገኙት ኢትዮጵያውአን ተጫርተው አቶ መላኩ አምባቸው የተባሉ አገር ወዳድ የጨረታው አሸናፊ ሆነዋል።

በዚህ ስብሰባ ላይ በአካል የተገኙት የድርጅቱ አመራሮች አቶ ሙሉነህ እዩኤልና አቶ ጋሳው ገብሬ በየበኩላቸው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ከኤርትራ በረሃም የግንባሩ ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፣ ድርጅቱ ከፍተኛ አመራር አቶ ነአምን ዘለቀና የግንባሩ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ በተለያዩ ስፍራዎች ከሰራዊቱ ጋር ያደረጉት ውይይት ከሰራዊቱ አባላት ለመሪዎቹ የቀረቡ ጥያቄዎች በፊል ቀርቦ ታይቷል።

አቶ ሙሉነህ እዩኤል በስፍራው ባደረጉት ንግግር አርበኞች ግንቦት 7 በኢትዮጵያ ያለውን አገርና ሕዝብ አዋራጅ፣ዘረና ስርኣት ለመገርሰስ ሳይወድ ተገዶ በገባበት ጦርነት ከወያኔ በሚተኮሰው ጥይት ለሚሞተው ብቻ ሳይሆን አገሩን ነጻ ለማውጣት መስዋት የሚከፍለው በተኮሰውም ጥይት ለሚሞቱ እንደሚያዝን ገልጸዋል።

ግንባሩ ኤርትራን ለትግል የመረጠባቸውን እና በኢትዮጵያውያንም ሆነ በኤርትራውአን በኩል የሚነሱ ለምን መተባበር ያስፈልጋል የሚሉ ጥአቄዎችን አንስተው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጃፓንና አሜሪካ በአንድ ወቅት የገቡበትን የጦርነት ሁኔታ በማንሳት ዛሬ አገራቱ ያላቸውን ግንኙነት በማስታወስ ጠላትነት ብቻ ቢያስቡና መተባበር የለብንም ቢሉ ኖሮ ዛሬ የጃፓን መኪና የአሜሪካን ገበያ ባላጥለቀለቀ በሌላ ዙር ጦርነት ውስጥ በነበሩ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።

በቅርቡ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ሻዕቢያ ወረረን የምትለዋን ካርድ መጠቀም ይጀምራል ያሉት አቶ ሙሉነህ እዩኤል ይህ ሆን ብሎ የሚደረግ የቅስቀሳ ካርድን የወቅቱን ተጨባጭ ሁኔታ በመረዳት፣ወያኔ በአገርና በሕዝብ ላይ ያለውን ግፍና የማያቋርጥ በደል በመመልከት ከዚህ አዳራሽ ስንወታ ቀደን መታል አለብን በማለት ለምን ከኤርትራ ጋር መስራት እንደሚያስፈልግ ሰፊ ትንታኔ ሰጥተዋል። በስፍራው የተገኘው ሕዝብ አርበኞች ግንቦት 7 ለነጻነት ትግል በኤርትራ በኩል ለሚያደርገውን ትግል ያላቸውን ድጋፍ በከፍተና ሞራል ጭምር ሲገልጹ ተስተውላል።

አቶ ጋሻው ገብሬ ሌላው የግንባሩ አመራር በበኩላቸው በኢትኦጵአበስላለው አስከፊ አገዛዝ የፈተራው ስደት፣በዜጎች ላኢ የሚፈጸሙ ግልጽ የግፍ እርምጃዎች ወደ ትግሉ እንዲገቡ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል:፡ በውጭ ያለውም ኢትዮጵያዊ የቻለ ትግሉን በአካል ሌላውም ባለበት በመደገፍ የነጻነት ትግሉን በጋራ መደገፍ ይገባል ብለዋል። በስብሰባው ላኢ አንድ አባት ትግሉን ለመደገፍ የጣት ቀለበታቸውን አውጥተው ለትግሉ ሰልመዋል። አቶ ሙሉነህ እዩኤል በቬጋስ ያደረጉትን ሙሉ ንግግር ዘግይተን ለማቅረብ እንሞክራለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአርበኞች ግንቦት 7 ባለፈው ዕሁድ በዋሽንግተንና በሲያትል ቅዳሜ በዳላስ ከፍተኛ ሕዝብ በየስብሰባው አዳራሽ ተገኝቶ ለትግሉ አለውን ድጋፍ ላቅ ባለ ደረጃ አሳየ ሲሆን በዚህም ከሶስቱ ከተሞች ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ($200 ሺህ ዶላር) መገኘቱን ለማወቅ ተችሏል። በዳላስ በአንድ የውጭ አገር ዜጋ የተሰራው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ምስል በ38 ሺህ ዶላር ጨረታ ሲሸጥ በዲሲ በከፍተና ፉክክር ለሌላ የአቶ አንዳርጋቸው ምስል ከሰባ ሺህ ዶላር በላይ በጨረታ አውጥቶ ተሸጧል።

ከግንባሩ መሪዎች መካከል ሊቀመንበሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ኤፍሬም ማዴቦ እና ሌላው ከፍተና አመራር አቶ ነአምን ዘለቀ ለወሳኝ ትግል ኤርትራ መግባታቸው በአገር ውስጥና በውጭ በነጻነት ወዳዱ ወገን ከፍተና መነቃቃት የፈጠረ ሲሆን በተቃራኒው በአገዛዙ መሪዎች ዘንድ መደናገጥ መፍጠሩን አስቀድመን በህብር ሬዲዮ መዘገባችን ይታወሳል።

በፍትህ እንዲህ የተቀለደበት ዘመን ይኖር ይሆን?

$
0
0

ከፋሲል የኔዓለም
(የኢሳት ጋዜጠኛ)

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

ወንድሞቼ ዳንኤል፣ አብርሃም፣ የሽዋስና ሃብታሙ ይፈታሉ በመባሉ በጣም ደስ ብሎኛል። በመፈታታቸው ደስ እየተሰኝን የአገዛዙን ፖለቲካዊ ጨዋታ ማየቱም አይከፋም። ከዚህ ቀድም እንዳልኩት ነው፤ አገዛዙ እድሜውን የሚያራዝመው በሰላማዊ ትግል እና በትጥቅ ትግል መካከል ያለውን የሃሳብ ልዩነት በማራገብ ነው። ሰላማዊ ትግልን የሚያቀነቅኑ ሃይሎች እየጠነከሩ ሲመጡ፣ የትግሉን መሪዎች ያስርና ህዝቡ “ሰላማዊ ትግል አያዋጣንም” ብሎ ወደ ትጥቅ ትግል ፊቱን እንዲያዞር አድርጎ አደጋውን ይቀንሰዋል። የህዝቡ ትኩረት ወደ ትጥቅ ትግል ሲዞር ደግሞ፣ የታሰሩ ሰላማዊ ታጋዮችን ይፈታና የፖለቲካ ምህዳሩንም ትንሽ ከፈት አድርጎ ” አዲስ የተስፋ ዳቦ” ይሰቅላል ። ህዝቡም እንደገና በሰላማዊ ትግል ተስፋ ያደርግና ትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ልቡ ያመነታል- የታጋዩን ልብ እየከፋፈሉ የመግዛት ፖለቲካ ። የእነ አብርሃን መፈታት “ሃሳብን ከፋፍሎ በመግዛት የፖለቲካ ስልት ” ካየነው ስሜት ይሰጣል።

የተፈቱትም ሆነ ለወደፊቱ የሚፈቱት ታጋዮች ቆራጥ የሰላማዊ ትግል አቀንቃኞች ናቸው፤ ከመጀመሪያውም የታሰሩት ሰላማዊ ትግሉ በምርጫው ላይ ተጽኖ እንደሚፈጥር ስለታወቀ ነው። ከምርጫው በሁዋላ፣ በተለይም ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጓዙን ጠቅልሎ የትጥቅ ትግል ወደሚደረግበት በረሃ ሲወርድ፣ ህዝባዊ ንቅናቄው በከፍተኛ ደረጃ አድጓል። ይህን ህዝባዊ ንቅናቄ ለመቀልበስ አገዛዙ ፣ ሰላማዊ ታጋዮችን በመፍታትና የፖለቲካ ምህዳሩን ትንሽ ገርበብ በማድረግ የህዝቡን ልብ ለመከፋፈል የተለመደ ስልቱን ተግባራዊ ለማድረግ አቅዷል። ይህ ስትራቴጂ የተበላ እቁብ በመሆኑ ከእንግዲህ ውጤት ያመጣል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው። አንደኛው የትግል አማራጭ ( የትጥቅ ትግሉ) ጉልምስና እድሜ ላይ ደርሷል፤ አገራችን በውጭ ስትወረር ካልሆነ በስተቀር ህዝቡ በዚህ ደረጃ ተነቃንቆ ትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ፍላጎት ሲያሳይ ስመለከት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ” ትግሉን መቀላቀል እንፈልጋለን” እየተባለ ከአገር ቤት በየቀኑ የሚደወለው ስልክ አስገራሚ ነው፤ እንዲያውም ስልክ የምታነሳው ባልደረባዬ ” የኢትዮጵያ ህዝብ በመሉ ጫካ ከገባ ነጻ አውጪዎች ነጻ የሚያወጡት ማንን ነው? በማለት በጣም ተገርማ ጠይቃኛለች ። ከአገር ቤት ስለሚደወሉ ስልኮች ደግሞ አገዛዙ በቂ መረጃ አለው፤ የህዝቡንም ስሜት ያውቀዋል። ይህን የተባለበትን ቁማር እንደገና ለመቆመር የተነሳውም ለዚህ ነው። እኔ ሁለቱም የትግል ስልቶች በስልት ከተካሄዱ ተደጋጋፊ ናቸው ብዬ አምናለሁ። ስርዓቱን በውስጥም በውጭም በመወጠር፣ ልክ እሱ የታጋዮችን የትኩረት አቅጣጫ በመከፋፈል የነጻነት ትግሉን ለማዳከም እንደሚሞክረው ሁሉ፣ ታጋዮችም በተመሳሳይ ስልት የእሱን የትኩረት አቅጠጫ በማሳት ሊያዳክሙት ይችላሉ። የእነ ዳንኤል መፈታት ትግሉን ወደፊት ይገፋዋል እንጅ አያዳክመውም።
habitamu
እግረ-መንገዴን ስለሚያብከነክነኝ አንድ ነገር ትንሽ ልበል። ሃሳቡን ዮና ብር የተባለ ጎበዝ ጸሃፊ አንስቶት አይቻለሁ ። እንደሚታወቀው በዘፈቀደ እየታፈሱ የሚታሰሩና የሚፈቱ የአገሬ ብርቅዬ ልጆች ይቅርታም ካሳም ተከፍሏቸው አያውቅም። ዘመዶቻቸው እነሱን ለመጠየቅ ሲመላለሱ የገንዘብ ፣ የጊዜና የጉልበት ኪሳራ አጋጥሟቸዋል። ልጆቻቸው የወላጆቻቸውን ፍቅር እንዳያገኙ በመከልከላቸው በአእምሮ እድገታቸው እና በወደፊቱ ህይወታቸውም ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽኖ ይፈጠርባቸዋል። ስራ መስራት ባለመቻላቸው የኑሮ ቀውስ ያጋጥማቸዋል። ሽብርተኛ በመባላቸውም የሞራል ኪሳራ ይደርስባቸዋል። የግል ህይወቴን የተመለከቱ ጉዳዮችን ማንሳት ባልፈልግም፣ ለዚህ ውይይት ስለሚጠቅም ለዛሬ አንድ ነገር አነሳለሁ። ከ5 ዓመታት በፊት፣ ወደ ሆላንድ ከመጣሁ በሁለተኛው አመት፣ የገጠመኝ አንድ ትልቅ ችግር ነበር። ኢሳት እንደተቋቋመ፣ እንደዛሬው በቂ የሰው ሃይል ሳይኖርና በየአገሩ ስቱዲዮዎች ሳይመሰረቱ፣ የሆኑ ሃይሎች “ኢሳትን ማስቆም አለብን” ብለው ተነሱና በእኔ ላይ ክስ መሰረቱ። እነዚህ እኩይ ሰዎች፣ ” ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ይሰራል፤ ህገወጥ ገንዘብ ያገኛል፣ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ያስገባል ወዘተ” የሚል ደብዳቤ ጽፈው ለፖሊስ አስገቡ። የተጠቀሱት ወንጀሎች በጣም አደገኛና ከአገር የሚያስባርሩ ወይም የሚያሳስሩ ናቸው። ያው ጥቆማ ቀርቧልና ፖሊስም ምርመራ ጀመረ። ሁለት ጊዜ ተጠርቼ ተጠየኩ፤ መርማሪዎች ቤታችን ድረስ መጥተው አኗኗራችንን አዩት። የባንክ አካውንቴ ተመረመረ፣ ስለኢሳት አጀማመርና የገንዘብ ምንጭ ሳይቀር ተጠየቀኩ፣ የሁዋላ ታሪኬ ሁሉ ተመረመረ። የመንግስት ክፍያም ለሁለት ወራት በግማሽ ቀነሰ። ሰዎች መከሩኝና በነጻ ጠበቃ ወደሚያቆም ድርጅት ሄድኩ። በሳምንቱ፣ ከጠበቃዬ ጋር ፍርድ ቤት ቀረብኩ። ፍርድ ቤቱ ፋይሉን አገላብጦ እንደቆምኩ ውሳኔ ሰጠ። “በአጉል ጥርጣሬ ለተደረገው ምርምራ የይቅርታ ደብዳቤ ይጻፍ፣ ለቃለምልልስ በሚል ሁለት ቀናት ስራ በመፍታቴ ክፍያ ይከፈለው፣ የታገደው የሁለት ወር ክፍያ ይለቀቅለት እንዲሁም በእሱና በቤተሰቡ ላይ ለደረሰው የሞራል ካሳ መዘጋጃው በመስፈርቱ መሰረት ይክፈለው” አለ። አጠቃላይ የገንዘብ መጠኑ ተስልቶ እንደሚነገረኝ፤ በክፍያው ላይ ቅሬታ ካለኝመ ይግባኝ እንድል፣ ስራዬን እንደሚያደንቁ አበረታተው አሰናበቱኝ። በፍጹም ማመን አልቻልኩም። ከቀናት በሁዋላ የይቅርታ እና የገንዘብ ዝርዝር የያዘ ወፍራም ደብዳቤ ደረሰኝ። ጠበቃው ” ገንዘብ አንሶኛል የምትል ከሆነ ይግባኝ እጠይቃለሁ” አለኝ። (እሱም ራሱ ለአንድ ቀን ፍርድ ቤት ስለቀረበ ብቻ ጠቀም ያለ ክፍያ አግኝቷል። ) አይሆንም አልኩት።

የ97ቱን ምርጫ ተከትሎ ከሌሎች ጋደኞቼ ጋር ለአንድ አመት ከ ስምንት ወር ያክል ጊዜ ታስሬ በነጻ ተለቅቄያለሁ። በታሰርኩባቸው ወራት ስራ ብሰራ ኖሮ ላገኝ የምችለውን ገንዘብ እንርሳውና በተለያዩ ምክንያቶች ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ኪሳራ ደርሶብኛል። ባለንብረት የነበርኩ ሰው ንብረት አልባ ሆኜ ተፈትቻለሁ፤ ለዚህ ሁሉ ግን ካሳ ሊከፈለኝ ቀርቶ የተወሰደብኝ ኮምፒዩተር እንኳ አልተመለሰልኝም፤ ስጠይቃቸው ” ገና መቼ ተነካህና ነው” ብለው አሰናብተውኛል። በሰው አገር ለሁለት ቀናት ተጠርቼ በመጠየቄ ብቻ ጠቀም ያለ የሞራል ካሳ ክፍያ ሲከፈለኝ፣ በአገሬ ለረጅም ጊዜ ታስሬ ስፈታ፣ የሞራል ካሳ ሊከፈለኝ ቀርቶ የተወሰደብኝ ንብረት እንኳ በወጉ አልተመለሰልኝም። ልብ በሉ! ለአንድ ቀን ታስሬ ብፈታ ኖሮ የሚሰጠኝ የሞራል ካሳ በዚያው ልክ ይጨምር ነበር። እነርዕዮት፣ የሽዋስ፣ ሃብታሙና ሌሎችም በግፍ የታሰሩት ወገኖቻችን ሁሉ ፍትህ የሚያገኙበት ቀን እሩቅ ባለመሆኑ እንጽናናለን እንጅ፣ የደረሰው ጉዳትስ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live