Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ከህዝብ ጆሮ እና አይን የተደበቁ የዲያስፖራ ቀን ትችቶች –ልዩ ፕሮግራም በሳዲቅ አህመድ (ቢቢኤን ሬዲዮ)

0
0

ከህዝብ ጆሮ እና አይን የተደበቁ የዲያስፖራ ቀን ትችቶች
“መላኒየም አዳራሽ በሰላ ትችት ስትናወጥ፣ በመዋሸት የሚታወቁት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከማፍጠጥና ከመንቆራጠጥ በስተቀር አማራጭ አልነበራቸዉም”
እንደ ታዳሚዎች አገላለጽ
ልዩ ፕሮግራም በሳዲቅ አህመድ
(ቢቢኤን ሬዲዮ)


Sadik Ahemed Journalist

ግሪን ኮፊ ቴፒ ቡናን ጠቀለለ

0
0

መንግሥት ከቡና እርሻ ባለቤትነት ውጪ ሆነ መንግሥት በቴፒ እርሻ ልማት ድርጅት ላይ ያለውን 49 በመቶ ድርሻ ሙሉ ለሙሉ ለግሪን ኮፊ አግሮ ኢንዱስትሪ ኩባንያ አስተላለፈ፡፡ግሮን ኮፊ ኅዳር 2003 ዓ.ም. ከፕራይቬታይዜሽንና ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ፣ የቴፒ እርሻ ልማት ድርጅትን 51 በመቶ አክሲዮን በመግዛት ከፍተኛ ባለድርሻ መሆኑ ይታወሳል፡፡

coffee1.5 ቢሊዮን ብር የሚያወጣው የቴፒ እርሻ ልማት 51 በመቶ በግሪን ኮፊ ቀሪው 49 በመቶ (750 ሚሊዮን ብር) በመንግሥት የተያዘ ነበር፡፡ ግሪን ኮፊ ከፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ጋር በመደራደር 256.6 ሚሊዮን ብር በመክፈል፣ ቀሪውን 476.6 ሚሊዮን ብር በአምስት ዓመት ለመክፈል በመስማማቱ ሙሉ ለሙሉ የእርሻ ድርጅቱ ባለይዞታ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረ መስቀልና የግሪን ኮፊ አግሮ ኢንዱስትሪ ኩባንያ ባለቤትና ዋና ዳይሬክተር አቶ ታደለ አብርሃ፣ የቴፒ እርሻ አክሲዮን ማኅበር ዝውውርን በፊርማቸው አረጋግጠዋል፡፡

ነሐሴ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በተካሄደው የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ አቶ በየነ እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል በቡና ተክል ድርጅት ሥር የነበሩት ሦስቱ የቡና እርሻዎች ለግል ኩባንያ ተላልፈዋል፡፡

የበበቃና የሊሙ እርሻዎችን የገዛው የሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ኩባንያ የሆነው ሆራይዘን ፕላንቴሽን ነው፡፡ ሆራይዘን ፕላንቴሽን 10 ሺሕ ሔክታር ስፋት ያለውን የሊሙ እርሻ በ1.3 ቢሊዮን ብር፣ አሥር ሺሕ ሔክታር ስፋት ያለውንና ከቡና በተጨማሪ ቅመማ ቅመም ምርት ላይ ያተኮረውን የበበቃ እርሻ ደግሞ በ700 ሚሊዮን ብር ግዥ ፈጽሟል፡፡ ሦስቱም የቡና እርሻዎች ወደ ግል በመዛወራቸው መንግሥት ከቡና እርሻ ባለቤትነት ውጪ ሆኗል፡፡

አቶ በየነ ጨምረው እንደገለጹት፣ ግሪን ኮፊ በቀጣይነት አሮጌ የቡና ማሳዎች በአዲስ መተካት፣ ነበር ማሳዎች የተሻለ ምርት እንዲሰጡ ማድረግና በባዶ መሬት ላይ ችግኝ መትከል ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እሴት በመጨመር ቡና ቆልቶ መላክ፣ ከዝናብ ጥገኝነት ለመላቀቅ መስኖ መጠቀም እንደሚኖርበት አቶ በየነ ገልጸው፣ እነዚህ ተጨማሪ ሥራዎች ኩባንያውን 450 ሚሊዮን ብር ያስወጣዋል ብለዋል፡፡

የቴፒ እርሻ በደቡብና በጋምቤላ ክልሎች ውስጥ ይገኛል፡፡ እርሻው በጠቅላላ 10 ሺሕ ሔክታር ላይ ያረፈ ሲሆን፣ 72 በመቶ በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን፣ 28 በመቶ ደግሞ በደቡብ ክልል ሸካ ዞን ውስጥ ይገኛል፡፡ የቴፒ እርሻ ከመነሻው ጀምሮ የምርት ሒደቱ የሚታወቅ በመሆኑ፣ ለዘመናዊው የቡና ግብይት ምሳሌ ነው በማለት የቡና ዘርፍ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ግሪን ኮፊ ከዚህ እርሻ በተጨማሪ በደቡብ ክልል ከፋ ዞን ውስጥ አራት ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ ቡና በማልማት ላይ ይገኛል፡፡ አቶ ታደለ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ ከጋምቤላ ክልል ባገኙት ሦስት ሺሕ ሔክታር ተጨማሪ መሬት ላይ የቡና ልማት ለማካሄድ ፕሮጀክት ነድፈዋል፡፡ የግሪን ኮፊ ትልቁ ገዥ ዓለም አቀፉ ግዙፍ የቡና ኩባንያ ስታርባክስ ነው፡፡

በ25 የእርሻ ጣቢያዎች የተከፋፈለው ግሪን ኮፊ በቴፒ እርሻ ብቻ አሥር ሺሕ ሠራተኞች አሉት፡፡ የእርሻ ጣቢያው የተለያዩ ፍራፍሬዎች፣ የፓልም ዛፍ፣ ቅመማ ቅመሞችና ማር ያመርታል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

የኔ አባት ገበሬው (ሄኖክ የሺጥላ)

0
0

Henok

የኔ አባት ገበሬው ( ሄኖክ የሺጥላ )
የኔ አባት እሱ ነው
አባይ ስር የነቃ
ሃገሩን ያነቃ
አንቅቶ ያለፈ
አልፎ የገዘፈ ።

የኔ አባት ገበሬው
ቃላት እና ዘየው
ዘየና ዝማሬው
ዝማሬና ስራው
የሲና ላይ በትር
ጦሩን ሲነቀንቅ
ቀስቱን ሲያነጣጥር
አነጣጥሮ ሲጥል
የጣለው ሲያጣጥር
እዩት ሲንጎማለል
ዝናር በወገቡ
ጋሻና ጥሩሩ
ኢትዮጵያ ናት ክብሩ !

የኔ አባት ገበሬው
አፈሩን ሲገፋ
ሲገፋ ሲለፋ
ዋሽንቱን ሲነፋ
ነዶውን ሲቀምር
በሮቹን ሲጠምር
ሲወቃ ሲያ-በራይ
አገዳን ከግቻ
ሲነጥል ሲለያይ ።

የኔ አባት ገበሬው
አልቤኑ ነው አልቦው
ሰኔ-ጎሎጎታው ፣ ማረሻና ወገሉ
ግማሽ ጎን አካሉ
ፍቅር ነው እምነቱ
እምነቱ ነው-ቃሉ !

የኔ አባት ገበሬው
አሂዶ ያስሄደ
ጤፍን ያስዘመመ
አደይ ያነጠፈ
ለሀገር እዮሃ ዘርዶ የዘነጠፈ
ግልገል እና ደቦል አጣምሮ ያቀፈ ።

የኔ አባት ገበሬው
እምነቱ ነው ሃብቱ
ፍቅሩ ነው ንብረቱ
ተዋዶ መኖሩ
ተካፍሎ መብላቱ !
የኔ አባት ገበሬው
የኦፊር ስጦታ
የራማ ነጭ እጣን
ሚኒሊክ ሚኒሊክ ፣ የሶሎሞን እጣን
የሰብ’አ ጥር
ውልደትን አብሳሪ
ተጏዥ በጨረቃ
በኮከብ ምልክት ፣ በአምላክ ፍቅር ሲቃ
የኩሽ ምድር ንጉስ የግብጦች አለቃ !

የኔ አባት ገበሬው ነጻነት አይነቱ
የደሙ ቀለም ነው እምቢ ወንድነቱ !

ሞትን የደፈረ
በመድፈር የኖረ
በሕይወት ምልአት
በዜማ ቅኔ ቤት
የተገመደ እውነት ።

ላገሩ ነጻነት
ጥይት ለነብሱ ሕይወት
አ! ብሎ የጠጣ
ጠጥቶ ያለፈ
አልፎ የገዘፈ !

እምቢ ዝባዝንኬ
ዝባዝንኬ ዘኬ
ላገሬ ነጻነት
አባቴ ነው ልኬ
አባቴ ነው መልኬ
እንቢ ! እንቢ ! እንቢ ! እንቢ ! እንቢ !

Henoke Yeshetlla's photo.

Henoke Yeshetlla's photo.

በኢህአዴግ አድናቂ ማብዛት ያስገመግማል!

0
0

ሚኒስትሩ ዳያስፖራውን ሲያዝናኑና ሲፈርሙ አመሹ

hailemariamየቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (መሬት ይቅለላቸውና!) ፓርቲያቸው ኢህአዴግ ሥልጣን በያዘ ማግስት፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ለውይይት መቀመጣቸው ይታወሳል፡፡ (ውይይት ሳይሆን ሽንቆጣ ነው የሚሉም አሉ!)
በእርግጥ ማንም ቢሆን ጠ/ሚኒስትሩ ከምሁራኑ ጋር ይወዳደሳሉ ብሎ ሊገምት አይችልም (የመተኳኮስ እንጂ የመወዳደስ ታሪክ የለንም!) ለነገሩ ምሁራኑም ቢሆኑ ጠ/ሚኒስትሩን በዝምታ አላለፏቸውም፡፡ የቻሉትን ያህል በነገር ወጋ ወጋ አድርገዋቸል ይባላል፡፡ (40ዎቹ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የተባረሩት ከውይይቱ በፊት ነው በኋላ?)
የሆነ ሆኖ ውይይቱ በሉት ሽንቆጣው ከተጠናቀቀ በኋላ ጠ/ሚኒስትሩ የተማሪነት ዘመን ዶርማቸውን የጐበኙ መሰለኝ (ሩብ ክ/ዘመን ስለሞላው ብሳሳት ወይም ብስት አትፍረዱብኝ!) እናላችሁ … ያን ጊዜ ነው ምድረ ምሁር በሰልፍ ጠ/ሚኒስትሩን ሲያስፈርም በኢቲቪ መስኮት የተመለከትነው፡፡ (የታዘብነው ለማለት ፈልጌ ነው!) ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣን … ያውም አድራጊ ፈጣሪ የአገሪቱ መሪ … ድግሪ ለጫኑ አድናቂዎቹ ሲፈርም ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁትና የተገረምኩት ያኔ ነው፡፡
ለነገሩ ሁኔታው ለጠ/ሚኒስትሩም ዱብዕዳ ሊሆንባቸው እንደሚችል አያጠራጥርም፡፡ (ድንገተኛ መስሎኝ?!) አልነገሩንም እንጂ ጠ/ሚኒስትሩ በፓርቲያቸው ክፉኛ ተገምግመውም ይሆናል፡፡ (በኢህአዴግ አድናቂ ማብዛት ያስገመግማላ!)
ግን እኮ ኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን ደርግም ሆነ ጃንሆይ በአድናቂ ጉዳይ የተለዩ አይመስለኝም (አርፎ የሚገዛ እንጂ አድናቂ ምን ይረባል?) በእነ ምኒልክና አፄ ቴዎድሮስ ዘመን ግን የነበረውን አላውቅም፡፡
እኔ የምለው … እንዲያ ተሰልፈው ጠ/ሚኒስትሩን ሲያስፈርሙ ያየናቸው ምሁራን ከአንገታቸው ነው ከአንጀታቸው? (ሃቀኛና አስመሳይ አድናቂ ሊኖር ይችላል ብዬ እኮ ነው!) ከአንገትም ይሁን ከአንጀት ግን ጠ/ሚኒስትሩ በርካታ ምሁራንን አሰልፈው ፊርማቸውን በማኖር የመጀመሪያው የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹም ይመስሉኛል፡፡
በነገራችን ላይ በዚያን ሰሞን በዚሁ ጋዜጣ “መልዕክቶቻችሁ” ዓምድ ላይ ስለጉዳዩ የወጣ አንድ ፅሁፍ፤ “አድናቆት ነው ማመልከቻ?” በሚል ምሁራኑን በነገር ሸንቆጥ ማድረጉን አስታውሳለሁ። ጠ/ሚኒስትሩ ግን በጋዜጣ ሳይሆን በፓርቲያቸው ተሸንቁጠው ሊሆን ይችላል፡፡ (ኢህአዴግ “ቀናተኛ” ነው አሉ!) የዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ድባቅ ለመምታት ሄደው ድንገተኛ አድናቂዎች ማፍራታቸው እንዴት ላያስገመግም ይችላል? (“ከምሁራን ጋር መሞዳሞድ” ተብሎ ይሆናል?)
ኢህአዴግ ግን ለምንድነው ለግለሰቦች ዕውቀትና ብቃት፣ ምጥቀትና ጥልቀት ዋጋ የማይሰጠው? (ለራሱ ሹማምንት ማለቴ እኮ ነው!) ራሳቸው ጠ/ሚኒስትሩ መወደስ የጀመሩት ካረፉ በኋላ እኮ ነው!! (ማድነቅ በህይወት እያሉ ይሻላል!)
በቅርቡ የኢህአዴግ ሹማምንት እርስ በርስ በተገማገሙ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከፌስ ቡክ አጠቃቀማቸው ጋር በተያያዘ መገምገማቸወን በወሬ ወሬ ስሰማ (ግልፅ መረጃማ ከየት ይምጣ?!) በግርምት ተሞላሁ። (ሚኒስትሩ በማህ….

http://goo.gl/qnKxck

Source – Addis Admas

 

በሐብታሟ ምድር …የርሃብ ችግር (ከተማ ዋቅጅራ)

0
0

b3ce60ceየአለማችን ጠበብቶች የሰው መገኛ ኢትዮጵያ እንደሆነች ብዙ ብዙ ብለዋል። እየሄድኩበት ያለሁት እንደ ሳይንስ ገለጻ እንጂ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እንዳልሆነ ይረዱልኝ ። ሳይንስ የምድርን እድሜ በሚሊዮን ሲቆጥር መጽሐፍ ቅድስ ደግሞ  መሺዎች ይቆጥራል። እናም ስለ ድንቅነሽ (ሉሲ)ሳይንሱን ተከትዬ መግለጼን ልብ ይበሉልኝ።

ድንቅነሽ (ሉሲ) በኢትዮጵያ መኖር ከጀመረች ከሶስት ሚሊዮን አመት በፊት እድሜ እንዳላት ተመራማሪዎች ነግረውናል። በዚህም የተነሳ  ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ አገር እንደሆነች እና የሰው ዘር ከኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ ተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በመሄድ አሁን ያለውን የሰው ዘር ስብጥር እንደተፈጠረ  ተመራማሪዎቹ ማስነበብ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ድንቅነሽ (ሉሲ) ከአዲስ አበባ ሙዚዬም ተነስታ ወደ አሜሪካ በመውሰድ ትላልቅ የአለማችን ሰዎች እንዳዩአት እና ሳይንስቶችም ከፍተኛ ጥናት እንዳደረጉበት ይታወቃል። ድንቅነሽ (ሉሲ) ለምን መሄድ አስፈለጋት? ያስገኘችውስ ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳስ ምንድን  ነው? ለሚለው ጥያቄ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲገለጽልን ሰምተን አናውቅም። የሆነው ሆኖ በጉብኝቷ ወቅት ያስገኘችው ገቢ ቀላል የሚባል እንዳይደለ ይታወቃል። በትንሹ ለክልሉ ተወላጆች ሃምሳ የውሃ ጉድጓድ በስሟ አስቆፈረው ህብረተሰቡ እንዲጠቀም ቢደረግ በተወሰነ መልኩ የሚታየውን የውሃ እጥረት መቅረፍ በቻለ ነበረ።

ኖርዌይ ያራ የሚባለው ካንፓኒ ከአፋር ምድር ፖታሽ (potash) ለማውጣት ከገዚው ፓርቲ ተፈራርመዋል። የማጓጓዛዋ አገር በጅቡቲ ወደብ እንደሆነ ታውቋል። ከፖታሹ ብዛት የተነሳ የኖርዌይ የማዕድን አውጪ ካንፓኒ አጋር አገር እያፈላለገ እንደሆነ ተዘግቧል። ስራውን ሲጀምር በየአመቱ ከፍተኛ ፖታሽ (potash) እንደሚያወጣ አሳውቆናል። ለአገር ገቢ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረገች አፋር ከሚገኘው ገቢ መትንሹ መቶ የውሃ ጉድጓድ ተቆፍሮ ለህብረተሰቡ ቢሰጣቸው ኖሮ እንስሳታቸውም አይሞቱም አገሪቷም በድርቅ ምክንያት ከሚመጣው ችግር ባልተጋለጠች ነበረ። በሚገኘው ገቢ የግለሰብ ኪስ ሲሞላ እንጂ የህብረተሰቡ ኑሮ ሲሞላ አላየንም። የግለሰቦች ሃብት ሲጨምር እንጂ የአገር ሃብት ሲጨምር አላየንም። አፋር ላይ ያየነውም የዚህ ነጸብራቅ ነው።

በድስ ውስት ሆና እንደምትተንተከተክ ሽሮ በኤርታሌ የሚታየው የሳተ ጎሞራ ሁኔታ የሚያሳየን ይሄንኑ ነው። ተመራማሪዎችን ትኩረት የሳበ ስለ እሳተ ጎሞራ ባህሪ ለማጥና ከአለማት የሚመጡባት አገር ናት። ቱሪዝምን በመሳብ በድንቅ ተፈጥሮዋ በብዙ ጎብኚዎች የምትጎበኘው ምድር ከቱሪዝም ከሚገኘው ፍሰት ለአካባቢው ነዋሪዎች የሚያስፈልጋቸው ቀዳሚ ነገር የውሃ ፍላጎታቸው ተሟልቶ ቢሆን ኖሮ ዛሬ የተከሰተው ድርቅን ባላየን ነበረ።

የአሞሌ ጨው ክምር ሜሬት ላይ ተነጥፎ በቀላሉ ተቆፍሮ የሚወጣባት አገር ሁሉ ነገር ኖሯት ሃብታም ሆና ሳለ ምንም እንደሌላት በውሃ እጦት እንሰሳዎቿ በውሃ እጦት ሲረግፉባት ማየት ለኢትዮጵያን ሞት ነው።

ጅቡቲን ውሃ ለማጠጣት የውሃ ጉድጓድ በመቆፈር ያውም በነጻ ሲለግስ የሱማሌ ክልል ምድሪቷ ሃብት ኖሯት ውሃ ተጠማን እያሉ መስማት ለኢትዮጵያን የሚያም ጉዳይ ነው። የአልሙኒዬም መአድን እንዲሁም የጋዝ ክምችት ያላት አገር ለወገን አሳቢ መንግስት ስሌለ ብቻ የኢትዮጵያ ልጆች ማደግ ስንችል መበልጸግ ሲኖርብን ከራሳችን አልፈን ሌሌላው የሚተርፍ ስራ መስራት እየቻልን የአገሩን ዜጋ ሳያጠጣ ለጎረቤት አገር በነጻ የሚሰጥ መንግስት በመኖሩ …በውሃ እጦት እንስሳታቸው እየሞቱባቸው ነው? ዜጎች ከፍተኛ አደጋ ላይ ናቸው? የሚለው ጥያቄ ህዝብን እንጂ መንግስትን የሚያሳስበው ጉዳይ እንዳልሆነ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው።

የወያኔ መንግስት ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ህይወት የሚጨነቅ ወይም የሚያስብ ሳይሆን ከውጪ መንግስታት ስለሚያገኘው ጥቅማ ጥቅም ወደ ግል ካዝናቸው የሚገባበትን ጉዳይ አብዝተው የሚጨነቅ ስለሆኑ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ ምንም ሃላፊነት የሚሰማው ስላልሆኑ ህዝባችን በተለያየ አካባቢ ከፍተኛ ችግር እየተጋለጠ ይገኛል። አንድ ቢሊዮን ዶላር በማውጣት የነጻ ሚድያዎችን እና ዌብ ሳይቶችን ለማፈን ወጪ ከምታደርጉ ይልቅ በዚህ ብር የዝናብ እጥረት የሚታዩበትን የኢትዮጵያ አካባቢዎች የውሃ ጉድጓድ ለህዝቡ ቢዳረስ ኖሮ ከእንደዚህ አስከፊ የድርቅ ችግር ሆነ የእንስሳት እልቂት ባልተከሰተ ቀድሞ መቆጣጠር በተቻለም ነበረ። ከሁሉ በፊት ስለ ህዝብ አስቡ! ከሁሉ በፊት ስለ ሰው ክብር እወቁ! ከሁሉ በፊት ስለ ግለሰብ መብት እንዲከበር ስሩ! ከሁሉ በፊት ስለ አገር ክብር ስለ ህዝብ ችግር ቀደሞ ለመገኘት ጣሩ እላለው። ለነገሩ ህዝብና መንግስት በሃሳብም ሆነ በማንኛውም ነገር አልተገናኝቶም።

ከተማ ዋቅጅራ

16.08.2015

Email- waqjirak@yahoo.com

“በኦሮሚያ ክልል ከ70 በላይ አርሶ አደሮች የብሔር ጥቃት ደርሶባቸዋል” –የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ)

0
0

(አዲስ አድማስ) ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ከ70 በላይ አማርኛ ተናጋሪ ገበሬዎች፣ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ከመኖሪያ ቀዬአቸው መፈናቀላቸውን የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) በሪፖርቱ አመለከተ፡፡ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱንም አረጋግጫለሁ፤ ብሏል፡፡
Zehabesha News
ሰመጉ ጉዳዩን ሲመረምር መክረሙን ጠቁሞ፣ “ብሔር ተኮር ማፈናቀልና እንግልት በአስቸኳይ ይቁም” በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው 136ኛ ሪፖርቱ የወረዳው የጸጥታ ሓላፊዎችና ባለሥልጣናት የብሔር ግጭቱን መቀስቀሳቸውን አስታውቋል፡፡

እንደ ሪፖርቱ፣ የወረዳው ባለስልጣናትና የፀጥታ ኃላፊዎች አርሶ አደሮቹን፣ “እናንተ የዚህ የአካባቢው ተወላጅ ሳትሆኑ ሀብት እያፈራችሁ የአካባቢው ተወላጆች ግን ከእናንተ ያነሰ ገቢ ነው ያላቸው፤ … ይህን ገቢ ያገኛችሁት በኛ መሬት ነው፤ የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችሁ ክልሉን ለቃችሁ ውጡ፤” በማለት በተለያዩ ጊዜያት ንብረታቸውን በመንጠቅና ለእስራት በመዳረግ እንግልት ሲፈፅሙባቸው ቆይተዋል፡፡ በተለይ መጋቢት 27 ቀን 2007 ዓ.ም አንድ የአካባቢው ተወላጅ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ የወረዳው የፀጥታ ኃላፊ “ግድያው የተፈፀመው በአማራ ብሄር ተወላጆች ነው” በማለታቸው ግጭት ተቀስቅሶ፤ ሚያዚያ 9 ቀን 2007 ዓ.ም 85 አርሶ አደሮች ለእስራት መዳረጋቸውን፣ የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች መኖሪያ ቤቶች እንዲቃጠሉ መደረጉን እንዲሁም የታሠሩትን የነዳጅ በሚል 300 ብር ከእያንዳንዳቸው በመቀበል እንደተለቀቁ ሰመጉ አጣርቻለሁ፤ ብሏል፡፡ በግጭቱ የአንድ ሰው ሕይወት ሲጠፋ 10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ 99 የሳር ክዳን ቤቶችና 25 የቆርቆሮ ቤቶች በእሳት ተቃጥለው መውደማቸውን የዘረዘረው ሰመጉ፤ መኖሪያ ቤታቸው ለተቃጠለበቸውና በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው ለሚገኙ ዜጐች አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ እንዲያገኙ ጠይቋል፡፡ መንግሥትም ለተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የተጠናና የማያዳግም የመፍትሔ ርምጃ ከሕዝብ ጋር በመመካከር እንዲወሰድ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አመልክቷል፡፡

ቃልኪዳን አለማየሁ የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራን “እውነት ማለት”ግጥም እንዲህ ያነበዋል (Video)

0
0

የዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚኒሶታ ተማሪ የሆነው ወጣት ቃልኪዳን ዓለማየሁ የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራን ተወዳጅ ግጥም እንደሚከተለው አንብቦታል:: ይመልከቱት::


ቃልኪዳን አለማየሁ የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራን “እውነት ማለት” ግጥም እንዲህ ያነበዋል (Video)

ለአርበኞች ግንቦት 7 በሰሜን አሜሪካ የተሳካ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ተደረጉ * ሕዝቡ ተነቃቅቷል

0
0
ሲያትል

ሲያትል

washinton DC

dallas
(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ከዘመቱ በኋላ እንዲሁም ከጁላይ 2015 መጀመሪያ ጀምሮ ድርጅቱ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በሕወሓት መንግስት ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰንዝሬያለሁ ማለቱን ተከትሎ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር ነፃነትን በሚናፍቀው ሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትን መፍጠሩን ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ ስትዘግብ ነበር:: ይህን ተከትሎ መሪዎቹን ያዘመተውን አረበኞች ግንቦት 7ን በገንዘብና በቁሳቁስ ለማጠናከር በሰሜን አሜሪካ እና በተለያዩ ሃገራት የተለያዩ ዝግጅቶች መድረግ ጀምረዋል::

ትናንት በቴክሳስ በተጠራ ሕዝባዊ ስብሰባ ለድርጅቱ ማጠናከሪያ ከ50 ሺህ ዶላር በላይ ተዋጥቷል:: ትናንት ቅዳሜ በቴክሳስ በተካሄደው ሀገርን የማዳን ህዝባዊ የአርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ላይ በርካታ በቴክሳስ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች መገኘታቸው ሲታወቅ በክብር እንግድነትም አበበ ገላው እና ኤርሚያስ ለገሰ ተገኝተዋል:: አበበ ገላው “አሁን የተጀመረው የነጻነት ትግል ተጠናክሮ ማህበረሰቡ የሚገባውን ማድረግ ይገባዋል” ሲል የቀድሞው ኮሚኒኬሽን ሚኒስተር ኤርምያስ ለገሰ በበኩሉ “ዛሬ የህወሃት ሰራዊት ይህን ሃይል የሚቋቋምበት ሞራል ያለ አይመስለኝም; ምክንያቱም በሰራዊቱ የተፈጠረው አለመግባባትና የማንነት ጥያቄ የጭዋታውን ሜዳ ይቀይረዋል” ብለዋል::

ይህ ሕዝባዊ ስብሰባ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ቀጥሎይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ (ከጨረታ እና ከአዳራሽ መግቢያ) ከ$100 ሺህ ዶላር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን ማሰባሰቡም እየቀጠለ ነው:: :: ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በስካይፕ ንግግር ማድረጋቸው ሲታወቅ በሌላ በኩልም አቡነ ፊሊጶስና የድርጅቱ አመራር አቶ ሙሉነህ እዩኤልም በ እንግድነት ቀርበዋል::

በሌላ በኩል አርቲስት ሻምበል በላይነህ; ብዙነህ ጽጌ እንዲሁም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በስካፕ ከአስመራ የተሳተፉበት የገቢ ማሰባሰብ በሲያትል እየተደረገ ሲሆን ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን::


በዋሽንግተን ዲሲ ብቻ 100 ሺህ ዶላር (ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ) ለአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጣ

0
0

በዋሽንግተን ዲሲ ብቻ 100 ሺህ ዶላር (ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ) ለአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጣ

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን በስካይፒ ይዞ አቡነ ፊሊጶስ; ሙሉነህ እዩኤል እና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት ለአርበኞች ግንቦት 7 በተካሄደ የገንዘብ ማሰባሰብ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፎቶ ግራፍ በጨረታ $70 ሺህ ዶላር ተሸጠ:: በአጠቃላይ ገቢም ከ$100 ሺህ ዶላር በላይ ተዋጥቷል:: ይህም በኢትዮጵያ ምንዛሪ ሲሰላ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል:: ለአርበኞች ግንቦት 7 ማጠናከሪያ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ በዳላስ እና በሲያትልም የተደረጉ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ይኸው ማሰባሰብ ይቀጥላል:: በዲሲ በተደረገው ገንዘብ ማሰባሰብ ሕዝቡ ወርቁን ሁሉ እያወለቀ ሲሰጥ ነበር ተብሏል::

የዲሲውን ዝግጅት በከፊል የሚያሳይ ቭዲዮ ይመልከቱ

DC A

ኤርትራ ሊገቡ ሲሉ ተያዙ ተበለው የተከሰሱት እነ ብርሃኑ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ ‹‹ድርጊቱን ፈጽመናል፣ ጥፋተኞች ግን አይደለንም››

0
0

birhanu tekle
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን በማቋረጥ ኤርትራ ከሚገኘው ግንቦት ሰባት የተባለ በተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀ የሽብር ቡድን ጋር ለመቀላቀል ሲጓዙ ድንበር አካባቢ ማይካድራ ላይ እንደተያዙ በመግለጽ በመንግስት የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡

ዛሬ ነሐሴ 11/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 14ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ ‹‹በክሱ ላይ የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል ወይስ አልፈጸሙም›› የሚል ጥያቄ ከፍርድ ቤቱ እየተነሳላቸው፣ በየተራ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህም አራቱም ተከሳሾች ድርጊቱን እንደፈጸሙ በመግለጽ፣ ነገር ግን ጥፋተኛ አለመሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ‹‹ሀገሬ በፋሽስት አምባገነኖች ተይዛ ዜጎች በጨቋኝ ስርዓት ውስጥ ስላሉ ሀገሬንና ህዝቤን ነጻ ለማውጣት ወጣትነቴን ሰውቼ ለመታገል ግንቦት ሰባት ከሚባል ነጻ አውጭ ድርጅት ጋር ለመቀላቀል ወስኜ ወደዚያው አቅንቻለሁ፡፡ ስለዚህ ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ፣ የግንቦት ሰባት አባል ነኝ፡፡ ወንጀለኛ ግን አይደለሁም›› ሲል ቃሉን ለፍርድ ቤቱ ሰጥቷል፡፡ ሁለተኛ ተከሳሽ እየሩሳሌም ተስፋው በበኩሏ፣ ‹‹ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ፤ ነገር ግን ጥፋተኛ አይደለሁም›› ብላለች፡፡
ሦስተኛ ተከሳሽ ፍቅረማርያም አስማማው ደግሞ፣ ‹‹ህገ-መንግስቱን አምኜ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ስሳተፍ የደረሰብኝን አውቃለሁ፡፡ ሰላማዊ ትግል እንደማያዋጣም ተረድቻለሁ፡፡ በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲን ለመገንባት የሚያስፈልገው የነጻነት ትግል ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ግንቦት ሰባት ነጻ አውጭን ለመቀላቀል ስጓዝ ማይካድራ ላይ ተይዣለሁ፡፡ ስለዚህ ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ፤ ጥፋተኛ ግን አይደለሁም›› ብሏል ለችሎቱ፡፡

አራተኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ በበኩሉ፣ ‹‹አርሶ አደር ነኝ፣ ሰሊጥ አመርታለሁ፡፡ ነገር ግን ያመረትሁትን ሰሊጥ የኢህአዴግ ወታደሮች ይዘርፉኛል፤ መስራት አልቻልኩም፡፡ በዚህ ምክንያት ሌላ ስራ መስራት ስላልቻልኩ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርን ተቀላቅያለሁ፡፡ ለዚህ ግን ጥፋተኛ አይደለሁም›› ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን ቃል ካዳመጠ በኋላ የአቃቤ ህግን አስተያየት የጠየቀ ሲሆን፣ አቃቤ ህግ ተከሳሾች ጥፋተኝነታቸውን ስላላመኑ ማስረጃ እንዲያቀርብና እንዲያሰማ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ የአቃቤ ህግ ማስረጃን ለመስማት ለነሐሴ 22/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

አቶ መለስ ምን አዲስ ነገር አበረከቱ? –ጌታቸው ሺፈራው

0
0

(የግል አስተያየት)

አቶ መለስ እንደ አንድ ‹‹ኢትዮጵያዊ መሪ›› የሚገባቸው ክብር ካለ ቢሰጣቸው ክፋት አልነበረውም፡፡ ሆኖም እየተደረገ የሚገኘው ከሚገባቸው በላይ ማግነን ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ አቶ መለስ የሞቱበትን ጊዜ ያመነበትን ሶስተኛ አመትን አስመክክቶም ይህ ለአቶ መለስ የማይገባ ክብር ገዥው ፓርቲ በያዛቸው ሚዲያዎች በኩል ቀጥሏል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ አቶ መለስን ለህዝብ ‹‹የተፈጠሩ፣ ለህዝብ የኖሩና ለህዝብ የተሰዉ›› ሲል ከአምላክ የተላኩ ያህል እያስመሰላቸው ነው፡፡ ከዚህ አለፍ ሲል ደግሞ ‹‹የተላኩ›› ከማስመሰል አልፈው የፈጣሪነት ሚና ሰጥተዋቸዋል፡፡ አቶ መለስ ለሁሉም እቅዶች፣ ፖሊሲዎች፣ መፍትሄዎች አመንጭ፣ የሁሉም መጽሐፍት ጸሃፊና ሁሉንም ተቋማት የመሩ ተደርገው እየተወራላቸው ነው፡፡ አቶ መለስ ምን ያህል ጊዜ ቢኖራቸው ነው ይህን ሁሉ መጽሐፍ የጻፉት? ተቋማት፣ ባለሙያዎች፣ አማካሪዎቻቸውና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ምን እየሰሩ ነበር? ይህን ያህል ተዓምር ሰሩ በሚል ሳይሆን ታማኞቻቸውን በመጠቀም ተቋማትንና አጠቃላይ አገሪቱን በራሳቸው አስተሳሰብ እንደሚያጠምቁ በመግለጽ ተቃዋሚዎች መለስ አገሪቱን በብቸኝነት እያስተዳደሩ መሆናቸውን ሲወተውቱ በተቃራኒው ኢህአዴግ ‹‹ፓርቲው የሚከተለው የጋርዮሽ አመራር ነው!›› ሲል የነበረውን ከመቼው ረስቶት ይሆን? ነው ይህ ኢህአዴግ የፈጣሪነት ሚና የሰጣቸው አቶ መለስ እነዚህ ተግባራት በመለኮታዊ ኃይል አከናውነዋቸው ይሆን?
meles zenawi
በ1993 ዓ/ም ህወሓት ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል ተከትሎ አቶ መለስ በበላይነት የመሯቸው የተለያዩ ስብሰባዎች ተካሂደዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል አንዱ ስለ ቦናፓርቲዝም መበስበስ የተወራበት ስብሰባ ነው፡፡ በዚህ ስብሰባ አቶ መለስ ስለጉዳዩ የሚያትት አንድ መጽሐፍን በማንበብ ለውይይት ሶስት ጽሁፎችን አቅርበዋል፡፡ በተለይ ሁለቱ የመጀመሪያ ጽሁፎች ከተሰብሳቢዎች በርካታ ጥያቄዎች ተነስቶባቸዋል፡፡ አድበስብሰው ሊያልፉ ቢሞክሩም ታጋይነታቸውን እንደዛሬው ጣል እርግፍ አድርገው በፍጹም ታማኝነት ያልቀየሩት የያኔዎቹ ፖለቲከኞች የዋዛ አልነበሩምና መለስን እስከመጨረሻው ሞግተዋቸዋል፡፡ በመሆኑም ሶስተኛና ማጠቃለያ ጽሁፋቸውን ሲያቀርቡ ስህተታቻቸውን ለአፋጠጧቸው ታጋዮች በግልጽ ከመናገር ውጭ አማራጭ አልነበራቸውም፡፡

‹‹ባለፉት ሁለት ጥናቶች EIGHTEENTH BRUMAIRE የሚባለውን መጽሐፍ ገረፍ ገረፍ አድርጌው የነበረ ቢሆንም ባመዛኙ ቀደም ሲል ካነበብኳቸው ተነስቼ ነበር የጻፍኩት፡፡ ….ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን ጽሁፍ እንደማንኛውም ሰው በተደጋጋሚ ያነበብኩት ቢሆንም በትክክል አልተረዳሁትም ነበር፡፡ ቦናፓርቲዝምን፣ ቢዝማርኪዝምንና አብሶሊውቲዝም (ፍጹም ዘውዳዊ አገዛዝን) አንጻራዊ ነጻነት እንዳላቸው ሶስት የተለያዩ አይነት መንግስታት ነበር የወሰድኳቸው፡፡ አሁን ግን እንዳልሆኑ ተረድቻለሁ፡፡›› ብለው ሂሳቸውን ውጠዋል አቶ መለስ፡፡

እንግዲህ አቶ መለስ ፓርቲው አደጋ በተደቀነበት ወቅትና ከፖለቲከኞች ከባድ ፈተና ሲገጥማቸው በነበረው ጊዜ በአንድ ወቅት ገረፍ ገረፍ አድርገው ያነበቡትን አንድ መጽሐፍ ወደ ኢትዮጵያ በመገልበጥ ለማሳመን መሞከራቸውን ራሳቸው በአንደበታቸው ገልጸውታል፡፡ ይህ ከምንም በላይ ትኩረት እንደሚሰጡት የሚታወቀው የራሳቸው ስልጣን ጉዳይ እንጂ የፓርቲ ስልጣን አሊያም በተደጋጋሚ ቸልተኝነታቸውን ያስመሰከሩበት አገራዊ ጉዳይ አልነበረም፡፡ ከምንም በላይ ስልጣናቸውን ለሚወዱት አቶ መለስ ተቀናቃኞቻቸውን ለመርታት በጊዜው ሞጋች ታጋዮች ፊት ሊያቀርቡት ይችል የነበረው ጽሁፍ ከዚህ የተሻለ መሆን ነበረበት፡፡ በእርግጥ አቶ መለስ ያቅርቡት እንጂ ለጸሁፉ በቅርበት ይገኙ የነበሩ ጓዶቻቸውና አማካሪዎቻቸውም ሚና ሊኖር እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡ ያም ሆኖ አቶ መለስ ኢትዮጵያንም ሆነ ፓርቲያቸውን ይመሩ የነበሩት ገረፍ ገረፍ አድርገው ያነበቡትን መጽሃፍት በመገልበጥ መሆኑን ከራሳቸው አንደበት መረዳት ይቻላል፡፡ ተቃውሞ ሲገጥማቸው ደግሞ ይኸውን መጽሐፍ እንደገና አንብበውም ሆነ አስነብበው ከማቅረብ ውጭ የራሳቸው የሚባል አዲስ አመለካከትም ያበረከቱበት ጊዜ አልነበረም፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ የኖሩት ገረፍ ገረፍ በተደረጉ ጥናቶች ተደጋጋሚ ሙከራ (trial and error) ስልት ነበር ማለት ነው፡፡ በዚህ ረገድ ከማርክሲዝም፣ ሌኒኒዝም፣ ስታሊኒዝም፣ ማኦይዝም፣ ኒዮሊብራሊዘም፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲ…..የመሳሰሉት አስተሳሰቦች እንደወረዱም ሆነ ተዳቅለው የተወሰዱ ፖሊሲዎች ኢትዮጵያን ቤተ ሙከራ አድርገዋታል፡፡

ከ1993 በፊት በህወሓት ውስጥ ችግር ሳይከሰት በተለይም በትግል ስልቱ ወቅትም መለስ፣ ህወሓትና ኢህአዴግ ይጠቀሙት የነበረው ተመሳሳይ ስልትን ነው፡፡ የሌኒን የፖለቲካ ስልቶችን በመገልበጥ ‹‹የትግራይ ማርክሲስት ሊኒኒስት ሊግ›› የመሳሰሉትን ጨምሮ ስሞች፣ይወጡ የነበሩ ፖሊሲዎችና ስልቶች በሩሲያና በኢትዮጵያ ምንም ልዩነት ሳይደረግባቸው በቀጥታ የሚተገበሩ ነበሩ፡፡ ምንም እንኳ አቶ መለስን እንደ ወታደራዊ መሃንዲስ ተደርገው የሚቀርቡበት ሁኔታ ከሚገባው በላይ የተጋነነ ቢሆንም አቶ መለስም ሆነ ህወሓት አዲስ ሳይሆን የማኦንን ወታደራዊ ስልት ገልብጠው እንደተጠቀሙበት ይታወቃል፡፡ ሞስኮ፣ ቤጂንግ ወይንም ምስራቅ ጀርመን የታተመ አንድ ግራዘመም መጽሄት ውስጥ የተቀመጠን ወታደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስልት ሳይቀር ህወሓት/ኢህአዴግ እየገለበጠ ኢትዮጵያ ላይ ሲተገብር እንደነበር የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

ከ1993 በኋላ ያለው ደግሞ ከዚህም የባሰ ሆነ፡፡ አቶ መለስ ገረፍ ገረፍ አድርገው ጽሁፍ ሲያቀርቡባቸው በነበሩት ስብሰባዎች ተቀናቃኞቻቸውን አሸንፈው ብቸኛው የስልጣን ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ ታጋዮች አቶ መለስን በጥያቄ ሲያጣድፉት የነበሩትና ‹‹የተራገፉት›› ጓዶቻቸው እጣ ፈንታ እንዳይገጥማቸው አቶ መለስ መጽሐፍ ጠቀሱ አልጠቀሱ ያሉትን በሙሉ ተቀብለው የሚያስተገብሩ ታማኞች ለመሆን ተገደዋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ አቶ መለስ ገረፍ ገረፍ አድርገውም ሆነ ‹‹አስታውሸዋለሁ!›› ብለው ያቀረቡት ጽሁፍ ሁሉ በጥልቅ ምርምራዊ ጥናትነት መቅረብ የጀመረበት ወቅት ነው፡፡
MelesCisor3
በእርግጥ ኢህአዴግ አሁን እያለ ከሚገኘው በተቃራኒ አቶ መለስ ስብሰባ ላይ የሚያቀርቡት ‹‹ጥናታዊ ጽሁፍ›› ሁሉ የእርሳቸው ስራ አልነበረም፡፡ በተለይ ከ1993 በኋላ ለፓርቲውም ሆነ ለአገሪቱ የቀረቡት ስልትና ስትራቴጅዎች እንዲሁም ፖሊሲዎች በተቋማት የተሰሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ጥናቶች የፓርቲና አገራዊ ጉዳዮች ስም እንጂ በክፍፍሉ ወቅት ስልጣንን ለማዳን እንደተደረገው በሚስጥራዊነት ሳይሆን ተቋማት፣ አማካሪዎችና ሌሎችም ግለሰቦች ሊሰሯቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ ለአብነት ያህል ከ1993 ዓ.ም ክፍፍል አንድ አመት በኋላ የወጡት የውጭ ጉዳይ፣ የአቅም ግንባታ፣ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ፖሊሲና ስትራቴጂ የሚያብራሩትን ጥራዞች በማስታወቂያ ሚኒስተር የፕሬስና ኦዶቪዥዋል መምሪያ የተዘጋጁ መሆናቸውን በመጽሐፍቱ መግቢያ ላይ ተቀምጧል፡፡ አቶ መለስ በወቅቱ በማስታወቂያ ሚኒስተር የፕሬስና ኦዶቪዥዋል መምሪያ ውስጥ ተመራማሪ ሆነው ሰርተውም ይሁን የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን ጉዳዮች አያነባቸውም ተብሎ እነዚህ መጽሐፍቶች ለአቶ መለስ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡

አንድ የግብርና ፖሊሲና ስትራቴጅን የሚተነትን ጥራዝ ለማዘጋጀት ከአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ጋር የሚውሉት የግብርና ሰራተኞች የሚሰበስቡት መረጃ በየአካባቢው በሚገኘው መስሪያ ቤታቸው ጥናት ይደረግበታል፡፡ በመሆኑም በወረዳ፣ ዞንና ክልል ባሉት ተቋማት በየደረጃው ጥናቱ ተሰርቶና ውይይት ተደርጎበት ለግብርና ሚኒስቴር እና ሌሎች አጋር አካላት ጨምሮ መሪው ቢሮ (ጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ) ድረስ ያሉ አካላት ለፖሊሲው ትልቅ ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡ ለመሆኑ አቶ መለስ የግብርና ፖሊሲን የሚጽፉት የግብርና ሚኒስትር ሰራተኞች፣ አመራሮቻቸው፣ አማካሪዎቻቸው፣ የአቶ መለስ የግብርና አማካሪና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የት ሄደው ነው?

በውጭ ጉዳይ ላይም ያለው እውነት ተመሳሳይ ነው፡፡ በአንድ አገር ኤምባሲ የሚላኩ የየመስኩ አታሼዎች የራሳቸውን ጥናት ሰርተው ኤምባሲው በየወቅቱ ጥናት ይሰራል፡፡ በየአገራቱ የሚገኙ ኤምባሲዎች፣ ስለአገራቱ እውቀት ያላቸው ምሁራን፣ ተቋማት ያደረጉት ጥልቅና ዝርዝር ጥናት አጠር ባለ መልኩ አንዲት አገር አጠቃላይ የውጭ ፖሊሲ እስትራቴጅን የሚመራበት ጭምቅ ፖሊሲ ይወጣዋል፡፡ አቶ መለስ የዓለምን አገራት ተጽዕኖ፣ መልካም ተሞክሮ፣ ለኢትዮጵያ የሚኖራቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና የደህንነት ጥቅምና ጉዳት በዝርዝር ተረድተው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን የመጻፍ ጊዜውም ሙያዊ ብቃቱም አልነበራቸውም፡፡ በአንጻሩ ከ50 በላይ በውጭ አገር የሚገኙ ኤምባሲዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር መስሪያ ቤት፣ የጠቅላይ ሚኒስተሩ አማካሪዎችና ቢሮ ከአቶ መለስ በተሻለ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ጥራዙ ላይ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል፡፡

ከዚህም አለፍ ሲል ኢህአዴግ በተለያዩ መስኮች እውቀት አላቸው ብሎ ያመነባቸውን የውጭ አማካሪዎች ሁሉ በከፍተኛ ደሞዝ ምኒልክ ቤተ-መንግስት ድረስ አስመጥቶ ሀሳብ እንዲያካፍሉት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም አቶ መለስ በበላይነት የመምራት እንጂ በየመስኩ ጥናት ለማድረግም ጊዜም ሆነ እውቀት አልነበራቸውም፡፡ እንደ እነ ሌኒን ያሉት መሪዎች አዲስ ሀሳብ ያመነጩ (ቢያንስ ማርክሲዝምን አሻሽሎታልና) የአገሪቱ ፖሊሲዎች በራሳቸው ርዕዮት መነጸር እንዲዘጋጁ ከማድረግና ከመቆጣጠር ውጭ ዝርዝር ፖሊሲዎችን የሚሰሩ አልነበሩም፡፡ ሌኒን ስለ ኢትዮጵያና ሶቬት ህብረት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊና ማህበራዊ ግንኙነት የሚሰራበት ጊዜም ዝርዝር እውቀት (መረጃ) አልነበረውም፡፡ አቶ መለስን በመለኮታዊ መነጸር ለማሳየት የፈለገው ህወሓት/ኢህአዴግ ግን የኢትዮጵያ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞችን፣ አማካሪዎች፣ የጠቅላይ ሚኒስተሩ ቢሮ፣ ሌሎች የኢህአዴግ ፖለቲከኞች፣ የአገር ውስጥና የውጭ ምሁራን የነበራቸውን ሚና ያለ ሀፍረት ለአቶ መለስ ብቻ አስረክቧል፡፡

ሌላው ይቅርና አቶ መለስ ለመመረቂያ ጻፉት የሚባለውን ጽሁፍ ጭምርም የአማካሪዎቻቸውና የሌሎች ተሳትፎ እንደሚኖርበት አያጠራጥርም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚቀርብን ጽሁፍ አቶ መለስ ገረፍ ገረፍ አድርገው አንብበው ከማቅረብ ይልቅ አማካሪዎቻቸውንም ተጠቅመው ጥልቅ ጽሁፍ ለማድረግ ስለሚጥሩ ነው፡፡ ይህ ጽሁፍ የራሳቸው ነው ቢባል እንኳ አቶ መለስን ልዩ አያደርጋቸውም፡፡ ከአቶ መለስ በተጨማሪ በርካታ አምባገነኖች መጽሐፎችን ‹‹ጽፈዋል››፡፡ ለምሳሌ ያህል ሞሶቬኒ እና ጋዳፌ መጽሐፍ ከጻፉት የአፍሪካ አምባገነኖች መካከል በቀዳሚነት የሚወሱት ናቸው፡፡ የሞሶቬኒ መጽሃፍ ከአቶ መለስ በርዕዮት፣ ፓርቲውን በማጋነንና በመሳሰሉት የሚመሳሰል ነው፡፡ የሞሶቬኒ መጽሐፍትና የአቶ መለስ መመረቂያ የሌሎች ጽሃፍትን ሀሳብ በማጣቀሻነት በመውሰድ የተሰሩ እንጂ አዲስ የፍልስፍና ውጤቶች አይደሉም፡፡

በተቃራኒው ‹‹አረንጓዴው መጽሐፍ›› የሚባለው እና ሶስት ጥራዝ ያሉትን መጽሃፍ የጻፈው ጋዳፌ ሀሳብ አዲስ ፍልስፍናዎች ያካተተ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የአቶ መለስና ሞሴቬኒ ‹‹የምስራቁን ዓለም›› ተሞክሮ በማድነቅና የምዕራባዊያን ስርዓት በመውቀስ ላይ የሚያተኩሩ ሲሆን መንግስት ከፓርላሜንታዊ ዴሞክራሲ የተለየ በአገር ሽማግሌዎችና በሌሎች በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ባላቸው አካላት ሊመሰረት ይገባዋል ያለውን ባህላዊ ስርዓት የሚያስቀምጠው የጋዳፌ መጽሃፍ በአንጻራዊነት አዲስ ሀሳብን የያዘ ነው፡፡ የአቶ መለስ አስተሳሰብና ጻፉት የሚባለው የጋዳፌን ያህል አዲስ ሀሳብ ሳያነሳ ከእነ ሌኒን፣ ማርክስና ሌሎች የራሳቸውን ርዕዮት ያፈለቁ ሰዎች በላይ እየጋነነ ይገኛል፡፡
MDG : Ethiopia : Meles Zenawi
የፖሊሲ ጥራዞችና መጽሐፍት ይቅርና የአቶ መለስ ንግግሮች ላይ የሌሎች አካላት ሚና ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ በዓለም ደረጃ የመሪዎችን ንግግር የሚጽፉ ሰዎች (speech writers) ለአብዛኛው የአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እውቀት ያካበቱ ናቸው፡፡ የመሪዎቹን ቃላት የሚፈጥሩ፣ የሚገሩ፣ የሚያሳምሩ ወይንም የሚያስተካክሉ በመሆናቸውም ‹‹word smiths›› ይሏቸዋል፡፡ ባራክ ኦባማ ከምርጫ ዘመቻው ጀምሮ አብዛኛዎቹን ጥቁሮች ያስለቀሰበት፣ ሌሎችን የአሜሪካና የዓለም ህዝቦች አፍ ያስከፈተበት ንግግር ጆን ፋቭሬአው የተባለ ወጣት የንግግር ጸሃፊ ድርሰቶች ናቸው፡፡ ጸሃፊዎች አንድ መሪ ፖሊሲውን፣ አቋሙን ለህዝብ በሚገባ መልኩ፣ ድምጸት፣ ምክንያትና ቋንቋ እንዲገልጽ ያድርጉታል፡፡ በአጭሩ እነዚህ ጸሃፊዎች የአዕምሮ ንብረት የሌላቸው ደራሲዎች ናቸው፡፡ የመሪዎች ወርቃማ አባባሎች እየተባሉ የሚነገሩት ሁሉም የንግግር ጸሃፊዎች አባባሎች ናቸው፡፡ የአንዲት አገር መሪ ብቻ ሳይሆን በየደረጃው የሚገኙ የተቋማት መሪዎችም የንግግር ጸሃፊዎች (speech writers) አላቸው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥም የሚደረገው ተመሳሳይ ነውና ለአቶ መለስ ንግግሮች ስሙ ያልተጠቀሰልን ደራሲ መኖሩ የግድ ነው፡፡ አቶ መለስ አገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያደርጉት እያንዳንዱ ንግግር በስተጀርባ የንግግር ጸሃፊዎች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ አቶ መለስ የሚነቀፉባቸውን ለጊዜው ትተን ኢህአዴግ አሁን እንዲወደሱ የሚጥርባቸው የአፍሪካ ህብረት ላይ ያደረጉት ቀስቃሽ ንግግር እና ሌሎችም ንግግሮች የራሳቸው አይደሉም፡፡ የንግግር ጸሃፊዎች የአእምሮ ንብረት ባለቤትነት የላቸውምና የአቶ መለስ ወርቃማ ንግግሮች ተብለው በኢቲቪና ኢህአዴግ የሚቀርቡትን የእነዚህ ሰዎች ድርሰቶች መሆናቸው ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ሆኖም አቶ መለስ እነዚህን ድርሰቶች በመተወን የተዋጣላቸው መሆናቸው የማይካድ ነው፡፡

ኢህአዴግ እንደሚያጋንነው ግን አቶ መለስ አዲስ የሌኒን፣ ስታሊንን፣ ማኦን፣ ማርክስንና ሌሎችን አስተሳሰቦች በተቋማት፣ ታማኞቻቸው፣ አማካሪዎችና ሌሎችንም ተጠቅመው ለስልጣን በሚጠቅማቸው መልኩ ከማዳቀልና ከማስመሰል ውጭ አዲስ አስተሳሰብ አላሳዩንም፡፡ ልማታዊ መንግስትን በስም ደረጃ ከምስራቅ ኤሲያ፣ የመገንጠል መብትን ከስታሊኗ ሶቬት፣ የሲቪክ ማህበረሰቦች አዋጅን ከሩሲያ፣ ግብጽና ዚምባብዌ፤ አብዮታዊ ዴሞክራሲን ከአልባኒያና ቻይና፣ ጠባብ ብሄርተኝነትን ከሶማሊያና ይጎዝላቪያ ‹‹በመልካም ተሞክሮነት›› ከመገልበጥ ውጭ የማሻሻልም ሆነ አዲስ ነገር ሲፈጠር አላየንም፡፡ ይባስ ብሎም ሌኒኒዝም፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ ልማታዊ መንግስትና የመሳሰሉት በስም ደረጃ አሊያም አሉታዊ ጎናቸው እንጂ አወንታዊ ጎናቸው ሲተገበሩ የማይታዩ ገረፍ ገረፍ ተደርገው ለአቶ መለስና ለህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን ብቻ በሚጠቅም መልኩ የተቃኙ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ ስለ ኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ ታሪካዊ ግንኙነቶች ይናገራሉ

0
0

ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ፤ የ “Ethiopia and the United States: History, Diplomacy, and Analysis” መጽሐፍ ደራሲ ስለ ኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ ታሪካዊ ግንኙነቶችና የፕሬዚደንት ባራክ ኦባማን የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክተው ይናገራሉ።

ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ ስለ ኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ ታሪካዊ ግንኙነቶች ይናገራሉ

ዛሬ የአጼ ምኒልክ ልደት ነው

0
0

Minilik
ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ከአባታቸው ከሸዋው ንጉስ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሤና ከእናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያም ቅዳሜ ነሐሴ 12ቀን 1836ዓ.ም ደብረ ብርሃን አካባቢ አንጎለላ ከሚባል ሥፍራ ተወልደዉ በአንጎለላ መቅደላ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ክርስትና ተነሱ::

አያታቸዉ ንጉስ ሣህለ ሥላሴ የልጁን መወለድ ሲሰሙ “ምን ይልህ ሸዋ” በሉት ብለዉ ስም አወጡ::

እሳቸዉ “…… ምኒልክ በሚል ስም የሚነግስ ንጉሥ ኢትዮጵያን ታላቅ ያደርጋታል” የሚል ትንቢት ስለ ነበር ‘ምኒልክ’ የኔ ስም ነው ብለዉ ነበር::
ሆኖም በህልማቸዉ ከልጁ አብረው ቆመዉ ከሳቸዉ ጥላ የልጁ ጥላ በልጦ በእግር የረገጡትን መሬት ሲያለካኩ እሳቸዉ ከረገጡት ልጁ የረገጠዉ ረዝሞ አዩ::
ከዚህ በኃላ “ምኒልክ የኔ ስም አይደለም የሱ ነው ስሙን ምኒልክ በሉት” ብለዉ አዘዙ::
ጳዉሎስ ኞኞ
ከአጤ ምኒልክ መፅሐፍ

የሕወሓት አባሉ ጥሬ ገንዘብ እና ወርቅ በሻንጣ ይዞ ሲገባ ለንደን ኤርፖርት ላይ ተያዘ

0
0

Zehabesha News
አንድ የህወሃት አባል 5 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ወርቅ በሻንጣው ይዞ ወደ ለንደን ሲገባ ጋትዊክ አየር ማረፊያ ላይ በፖሊሶች መያዙ ተሰማ::

ፍርድ ቤት ጋር በተያያዘ ለጊዜው ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ፣ ግለሰቡ ፍርድ ቤት ቀርቦአል። ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ እንዴት በሻንጣ ልትይዝ ቻልክ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ፣ ግለሰቡ ” ገንዘቡ የመንግስት መሆኑንና ለመንግስት ስራ ለማዋል መያዙን” ገልጻል።

ይሁን እንጅ ዳኛው ” ይህን ያክል ገንዘብ በሻንጣህ የያዝከው በአገራችሁ ባንክ ስለሌለ ነው እንዴ? ” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል። ግለሰቡ በዋስ የተፈታ ሲሆን፣ መስከረም ላይ በድጋሜ ይቀርባል።

ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግርቲ በ8 አመታት ውስጥ ከኢትዮጵያ 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ከአገር መውጣቱን ከሁለት አመታት በፊት ይፋ አድርጎ ነበር።

የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ጠንከር ያሉ መልዕክቶችን በያዙ የግራቪቲ እና የወረቀት ፅሁፎች አሸብርቀው አደሩ

0
0

dectator 1

dictators

dictators 1
ገዢው ስርዓት የህዝበ ሙስሊሙን የሀይማኖት መብት ጥያቄን በደህንነት፣ የስርዓቱ ማፈኛ በሆነው ፍርድ ቤት እና በፖሊስ ሀይል አፍኜዋለሁ ቢልም ትላንት ማታ ግን መብታቸውን ማስከበር ቀዳሚ አጀንዳቸው ያደረጉ የከተማዋ ወጣቶች ከደህንነታቸው የሀይማኖታቸውን ክብር በማስቀደም ከተማዋን ፀጥ ባሉ ጩኸቶች አዳርሰዋታል።

ከዚህ ቀደም ይፃፉ የነበሩ ለዘብተኛ ፅሁፎችን በአንድ ደረጃ ከፍ በማድረግ ጠንከር ያሉ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ችለዋል። እንዲሁም ከሀይማኖታዊ የመብት ጥያቄዎች በተጨማሪ ሀገራዊ ጥያቄዎችንም አክለዋል።

የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዋን ትቀብራለች፣ we need freedom፣ Ethiopians stand against dictatorship ፣ ፍትህ ለታሰሩ፣ፍትህ ለሙስሊሞች ፍትህ ለኢትዩጵያዊያን፣ ዋ!፣ የግፍ አገዛዝ በቃን!፣ትግላችን እስከ ድላችን እና የመሳሰሉ ፅሁፎችን በግድግዳና በየፖሉ ተፅህፈው አድረዋል።


Sport: የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የ1970ዎችሁ ፈተና (ሊደመጥ የሚገባ)

0
0

Sport: የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የ1970ዎችሁ ፈተና (ሊደመጥ የሚገባ)

Sport: የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የ1970ዎችሁ ፈተና (ሊደመጥ የሚገባ)

አንዳርጋቸው ጽጌ በአባታቸው መጎብኘታቸው ተሰማ

0
0

andargacew Tsige
(ዘ-ሐበሻ) የት እንዳሉ ሳይታወቁ ቀርተው የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአባታቸው መጎበኘታቸው ተሰማ:: የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ላይ ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው ከተሰጡ በኋላ አፍቃሪ የመንግስት ድረገጾች በፎቶ ሾፕ አንዳርጋቸው የአዳማን መንገድ ሲጎበኝ በሶሻል ሚድያዎች ለጥፈው ሲዋሹ ነበር::

ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አቶ አንዳርጋቸውን ልማቱን እያስጎበኘነው ነው ሲሉ በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ላይ መናገራቸው ይታወሳል::

የአንዳርጋቸው ጽጌ እህት ብዙአየሁ ጽጌ እንደገለጹት አቶ አንዳርጋቸው በአባታቸው ቢጎበኙም ኢትዮጵያውያን ወደ ለንደን እስኪመለሱና ነፃነታቸውን እስኪያገኙ ድረስ ኢትዮጵያውያን አብረዋቸው እንዲቆሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::

አቶ አንዳርጋቸው በአባታቸው ሲጎበኙ ጤነነታቸው በደህና ሁኔታ ይገኛል ከመባሉ ውጭ ምን እንደተነጋገሩ የታወቀ ነገር አለመኖሩ ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል::

እነ ዶ/ር ብርሃኑ ከኤርትራ በረሃ መልዕክት አስተላለፉ –“ይህ ጠመንጃ ከሚያመጣው ትዕቢት ራሳችንን መጠበቅ አለብን”

0
0

“ይህ ትግል አንዱን አምባገነን አፍርሶ ሌላ ለመተካት አይደለም”

“ኢትዮጵያን በእኩልነት ለማስተዳደር የሚችል መንግስት ለመመስረት ነው የምንታገለው”

“ይህ ጠመንጃ ከሚያመጣው ትዕቢት ራሳችንን መጠበቅ አለብን”

የነዶ/ር ብርሃኑ ነጋ; ነአምን ዘለቀ; ኤፍሬም ማዴቦና የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደሮችን መል ዕክት ለማድመጥ ከታች ይመልከቱ

Dr sirak

የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ እድር ላይ ጥያቄ አነሳህ ተብለው ታሰሩ

0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) በባሌ ዞን ሰልጣ ቀበሌ፣ ሲናና ወረዳ የሰማያዊ ፓርቲ የፓርላማ ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት አቶ ወርቅነህ ጋድይ አያና የእድር ስብሰባ ላይ ጥያቄ ጠይቀሃል ተብለው መታሰራቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ አስተባባ አቶ ደመላሽ በቀለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ በተለይ ከምርጫው በኋላ ካድሬዎች አቶ ወርቅነህ እድርን ጨምሮ ከማህበራዊ ጉዳዮች እንዳይሳተፉ ጫና ሲያደርጉባቸው እንደነበረም ተጠቅሷል፡፡
semayawi party
ሆኖም የአካባቢው ህዝብ ‹‹በፖለቲካ መሳተፍ ህገ መንግስታዊ መብቱ ነው፡፡ እድር ደግሞ ማህበራዊ መብቱ በመሆኑ መሳተፍ አለበት›› በማለቱ እስካሁንም የእድር አባል ሆነው ቢቀጥሉም በእድሩ አካሄድ ጥያቄ አለኝ በማለታቸው ‹‹ለምን ጥያቄ ትጠይቃለህ?›› ተብለው እንደታሰሩ አስባባሪው ገልፀዋል፡፡ አቶ ወርቅነህ ጋድይ በአሁኑ ወቅት በሲናና ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የአስተዳደር አካላት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ላይ በሚፈፅሙት በደል ምክንያት ከትግል ውጭ ፍትህ እናገኛለን ብለው እንደማያምኑ አቶ ደመላሽ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በቤንሻንጉል ጉሙዝ የተገደሉት 11 ሰዎች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ነዋሪዎች ተናገሩ

0
0

-Benishangul-Gumuz_
ኢሳት ዜና :-ከአለፈው ምርጫ ጋር ተያይዞ ፣ የአካባቢው ህዝብ የስርዓቱ ደጋፊ አይደለም፣ በምርጫውም ለመሳተፍም ሆነ ከመንግስት ጎን ለመቆም ፍላጎት አላሳየም በሚል የበቀል እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአካባቢው ተወላጆች፣ የልዩ ሃይል አባላት በወሰዱት የጭካኔ እርምጃ እስካሁን በመንጌ ወረዳ 11 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው፣ ግጭቱ ወደ ዳቡስ አካባቢም የተዛመተ በመሆኑ የሟቾቹ ቁጥር ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።

በመንጌ ከተማ አካባቢ በነበረ የአርብ ቀን ገበያ ላይ በተወሰደው አሰቃቂ እርምጃ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በተለይም ወደ ሜዳ ኦዶ ከተማና ዳቡስ አካባቢ ወደ ሚገኙ መልስተናኛ ከተሞች በሸሹት ግለሰቦች ላይ እርምጃ ተወስዷል።

በአካባቢው አሁንም ውጥረት ሰፍኖ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአካባቢው የተቃዋሚ ፓርቲዎች በአለፈው ምርጫ እንዳይሰተፉ የተከለከሉ ሲሆን፣ ህዝቡም ይህን ተከትሎ በምርጫው ላለመሳተፍ አቋም ወስዶ ነበር።

ኢሳት ታጠቂዎች በወሰዱት እርምጃ 12 ሰዎች መገደላቸውን፣ ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ ህይወታቸው ያለፈው እስር ቤት ከተወሰዱ በኋላ በምግብ ተመርዘው መሆኑንና 56 ሰዎች በመንጌ ወረዳ በአሶሳ ሆስፒታል በህክምና ላይ መሆናቸውን እንዲሁም 54ቱ ሰዎች መታሰራቸውን፣ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄን በመጥቀስ ዘግቧል።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live