Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ለዜጎች የሚቆረቆሩ የመንግስት ተወካዮችን አፋልጉኝ ! ኮንትራቱስ ይቁም፣ የቀሩትነኘን ዜገኮች መብት ማን ያስከብር ?

$
0
0

YeMaleda Weg

ሳውዲዎች ከኢትዮጵያ ከኬንያና ከኢንዶኖዥያ የቤት ሰራተኛ ቅጥር ካቆሙ     ሰነባበተ ! ይህነኑ ተከትሎ የቤት ሰራተኛ እጥረት የሳውዲዎች መነጋገሪያ ሆኗል። ባለጸጎቹ የሳውዲ ዜጎች በያዝነው የረመዳን ወር ብቻ 32 ቢሊዮን ሪያል የሚገመት ገንዘብ በሃገር ውስጥ ገበያ ልውውጥ ላይ እንደዋሉ በሰማን መባቻ የሳውዲዎች ችግር ሆኖ በመነገር ላይ ያለው የቤት የሰራተኛ አቅርቦቱን ጉዳይ ነው። ይህንንም የሃገሪቱ ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ሰጥተው በመዘገብ ላይ ናቸው ። በሰራተኛ አያያዝ በኩል አለም አቀፍ ውግዘት ተለይቷቸው የማያውቁት ሳውዲዎች እንደ ኢትዮጵያ መንግስት    ተወካዮች ለዜጎቹ መብት ተከራካሪ የሌላቸውን ዜጎችን ጩኽት መስማት ተስኗቸዋል። “ስብአዊ መብት ገፈፋ ደረስብን!” ሲሉ የዝሆን ጀሮ ይስጠኝ ብለው ይስተዋላሉ ፣ ይህም የሚጠፋው ጥፋት እንደዳይታረም አድርጎታል።   የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ክብር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እያሉ ከሳውዲዎች ጋር በህግ ማዕቀፍ ሳይስማሙ መንገዱን ከከፈቱት ወዲህ ባለፉት ሶስት አመታት ከግማሽ ሚሊዮን ያላነሱ ኢትዮጵያውያን በኮንትራት ስራ ስም ወደ     ሳውዲ ገብተዋል። ሳውዲዎች ከዛሬ ከሶስት አመት በኋላ በአያያዝ ጉድለት ጥፋትና   ወንጀል ሲከተል ጤናቸው ተሟልቶ የተቀበሏቸውን ዜጎች በሽተኛ ላካችሁብን

እስከሚል ቧልት ተሻግረዋል። ዜጎች ባለፉት አመታት ህጋዊ ተብለው እየመጡ ህገ   ወጥ የመብት ገፈፋ ይፈጸምባቸዋል ።

      ለዚህ ሁሉ በደል ግን ሳውዲዎችን ብቻ መውቀስ ሚዛናዊ አያደርግም ባይ ነኝ! ይህን የምልበት ዋንኛ ምክንያት ከኢትዮጵያ በኩል የሚላኩት ሰራተኞች ያለ በቂ ቅድመ ዝግጅትና ህጋዊ የሁለቱ ሃገራት የኮንትራት ውል ካለመላካቸው ባሻገር ስለመጡበት ስራ ፣ ስለመጡበት ሃገር፣ አረብኛ ቀርቶ የሃገራችን ብሔራዊ ቋንቋ አማርኛ መናገር የማይችሉ ከገጠሩቱ የሃገራችን ክፍል ተግዘው የመጡ መገኘታቸውን አውቃለሁና ነው! ለ ስራ ያልደረሱ ታዳጊዎች እንደሚላኩ አይቻለሁና ነው ! በዚህ መሰል መንገድ       የመጡት ዜጎች የት እንደሚገቡ ? የት እንደሚድርሱና ምን እንደሚፈጸምባቸው አለመታወቁ ሳውዲ ሲገቡ ክትትል ተደርጎ አይመዘገቡምና ነው ! በተባራሪ የምናየው የመብት ገፈፋ በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እንደጨው በየ ሳውዲው ገጠር ከተማ ተበትነው ሊደርስባቸው የሚችለውን አደጋና ተደራሽ አለመሆናቸውን በግልጽ ያሳይ ይመስለኛል ። ይህን ስል ሰብአዊ መብታቸው ተጠብቆ በሰላም መስራት የቻሉ በሽዎች የሚቆጠሩ መኖራቸውን ጭምር በመጠቆም ነው ። ስለሚደርሰው በደል ስናወራ ግን ከላይ    እንዳስቀመጥኩት ለዚህ የመብት ጥሰት ዋና ተጠያቂ አሰሪዎች ቢሆኑም የኢትዮጵያ መግስት ተወካዮች ለተሰየሙበት የዜጎች መብት ጥበቃ ዋና አላማ ትግበራ ዳተኛ መሆናቸው በተጠያቂነቱ ረድፍ ያሰልፋቸዋል ። ይህ ዳተኝነትም ችግሩ ከመቀነስ እንዲስፋፋ ምክንያት ሆኗል !

(በሳዑዲ አረቢያ ራሷን በኤክይሪክ ገመድ አንቃ የገደለችው ኢትዮጵያዊት)

(በሳዑዲ አረቢያ ራሷን በኤክይሪክ ገመድ አንቃ የገደለችው ኢትዮጵያዊት)

ለስራ በመጡ ሰራተኞች ላይ የሚደርሰው መብት ረገጣ ውሎ ባደረ ቁጥር ዜጎች ራሳቸውን ከማጥፋት ጀመሮ ለሚደርስባቸው በደል የአሰሪዎችን ቤተሰቦች በበቀል እስከማጥቃት ያደረሰ የአእምሮ መታወክ ገጥሟቸው አይተናል፣ ይህ እርምጃም ባይተዋሮች ግራ እንደተጋቡ “የአተርፍ ባይ አጉዳይ!” ሆነው ዘብጥያ ወርደዋል ! ለምን ይህን ጥፋት ፈጸሙ ? ምን ገጥሟቸው       ለዚህ ወሳኔ ደረሱ ? ብሎ የሚያማክር፣ ለመብታቸው መከበር የሚቆም ተወካይ አጥተናል ! እህቶች ወንጀል ፈጸሙ ተብሎ    ህግ ፊት ቀረቡ ሲባል የሚያስተረጉምላቸው ተወካይ አጥተው በአረቡ መገናኛ ብዙሃን ስማችን ሲጎድፍ ያየንባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው! እንደ ዜጋ ዜጎች ግፍና ወንጀል ሲሰራብን ፣ ስንሰደብ ፣ስንደበደብ ፣ ስንደፈር እና ስንገደል ጠያቂ የለንምና      የእኛ ጉዳይ ለአረብ መገናኛ ብዙሃን ጉዳያቸው አይደለምና አይገንም ! በአንጻሩ ጥቂት ዜጎቻችን በሚፈጥርባቸው ጫና ተነሳስተው ፈጸሙት ብለን በምንገምተው ተቀባይነት የሌለው አስቃቂ ወንጀል እየተደጋገመ ከተነገረንና ስማችን ካጎደፈው በኋላ       ሳውዲ  ከኢትዮጵያ የቤት ሰራተኛ የመቅጠር ውል ማቋረጧን በይፋ አስታውቃለች! ከኢትዮጵያ የቤት ሰራተኛ የማምጣት ውል መቋረጥ ተከትሎ ከፍተኛ የሰው ሃይል እጥረት ተከስቷል። ይህንኑ ክፍተት ለመሸፈንም የሳውዲ ቀጣሪዎች ፊታቸውን    ወደ ቀድሞዋ የሶብየት ግዛቶች አዙረዋል !

ኢትየጵያን ጨምሮ ከኬንያና ከኢንዶኖዥያ ጋር የቆመውን ውል ለመሸፈን       የድሃ አረብ ሃገራትን ዜጎች ለማስመጣት ያደረጉት ሙከራ ” በአወቅኩሸ ናቅኩሽ! ” ይሁን ሳውዲዎች በሚሰጡት ከዚህ የተለየ ምክንያት የሚሳካ አልሆነም ! ሳውዲዎች ችግሩ ለመፍታት የሚሄዱበት መንገድ ለውጥ ያመጣል በሎ መገመት አይቻልም፣ ትናንት ፊሊፒኖች ተረኛ ነበሩ ፣ ትናት ሲሪላንካ እና ኢንዶኔዥያ ተረኞች ነበሩ ፣ ውሉ ሲሰረዝ ደግሞ እንደተለመደው  ”በአሰሪዎቻቸው ቤተሰቦች ወንጀል ፈጽመዋል!” የሚለውን ሙግት አስነስቶ ተከላካይ ተወካዮቻቸው የስራ ውላቸውን አገዱት!

 ሳውዲዎች ወደ ኢትዮጵያና ኬንያ አቀኑ! የኬንያ መንግስት ተወካዮች በዜጎች የሚደርሰውን እንግልት ተመልክተው ወራት ሳይቆይ የስራ ውሉን ካች አምና ሰረዙት ! እኛ ብቻ ያለ መብት ተከራካሪ ቀርተን ለአሁኑ ውርደት ተዳረግን ! ያም መጣ ይሄ ሄድ     የሳውዲ መንግስት ዜጎቻቸው መሰረታዊ የሰው ልጆችን መሰረታዊ መብት እንዲያከብሩና የአያያዝ ይዞታው እንዲያስተካክሉ ካላደረገ ነገም አዲሶቹን ተቀጣሪ የሩስያ      ድሆች ከእኛው የጎደፈ ስም ረድፍ እንደሚያሰልፋቸው አያጠራጥርም !

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ በኢትዮጵያ ላይ የተጣለውን እገዳ ተከትሎ      ስራተኛ ማስመጣቱ ለበርካታ ወራት እንደሚቋረጥ ሲጠቆም በስራ ላይ ያሉትን       ኢትዮጵያውያንን ከሃገር የማባረር እርምጃ እንደማይወሰድ አንድ የሰራተኛ ሚኒስትር ሃላፊ ገልጸዋል! በስራ ላይ ያሉትን ዜጎች የመብት ጥበቃ ጉዳይ በሚመለከት ግን    አሁንም ጉዳዩ አሳሳቢ እንደሆነ ቀጥሏል! በቅርቡ በማህበራዊ ገጾች የተሰራጨውን አንዲት ራሷን የሳተች እህት በሳውዲ አንቡላንስ የጤና ረዳት ሰራተኞች ጋር አይኗን አፍጥጣ ስትታገል የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል እና ራሷን በማቀዝቀዣ መስኮት ስር በኮረንቲ ራሷን አንቃ የገደለችውን ዜጋ ምስል ተመልክቶ ልቡ ያልተሰበረ አለ        አልልም !       በቅርቡ ያገኘሁት መረጃ ደግሞ ሊሰሙት እንኳ አሰቃቂ ነው ። ከወራት በፊት     እዚህ ጅዳ ከተማ ውስጥ በጩቤ መላ አካሏ ተወግታ በአሰሪዎችዋ ቤት ሞታ የተገኘችው እህት ጉዳይ አሳዛኝ ሆኖ እናገኘዋለን። ገዳይዋ ለፍርድ መቅረብ ሳይችል በድኗ እየተቆራረሰ ለሳውዲ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መማሪያ ሲሆን መባጀቱን በቂ የምስል መረጃ የያዘው ወንድም የተሰፋፋውን የዚያች ምስኪን አካል አስከፍኖ እንደቀበረ    ሲናገረው ሰው መሆን ያስጠላል! ይህ ሁሉ ሲሆን የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች አያውቁም አይባልም ! ይህ ወንድም እንገለጸልኝ  መረጃውን ከማቀበል አልፎ ሬሳውን       ለማስቀበር ውክልና ይዞ ከቆንሰሉ ፍቃድ ለማውጣት ቢሔድም ፈተና ተጋርጦበት    እንደነበር የሚያመውን መረጃ አቀብሎኛል ! . . .

ከዚህ መሰሉ መረጃ ጋር ተዳምሮ ራሳቸውን ያልሳቱት ፣ ትንሽ ቀለም ቢጤ የቀሰሙት ፣ ስልጡን የሆኑት እህቶች  ቀዳዳ   እየፈለጉ ችግራቸውን ከመናገር አልቦዘኑም ! አድራሻየን ፈላልገው በተንቀሳቃሽ ስልኬ እየደወሉ የችግር ጭንቅ በደል ድምጻቸውን እንዳሰማላቸው የሚጠይቁኝ እህቶች እንባ ሰላም ነስቶኛል! በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ ለማቀበል ወደ ሪያድ ኢንባሲና ጅዳ        ቆንስል ተደጋጋሚ ስልክ ብደውልም ሃላፊዎችን ስልካቸውን አይመልሱም ! ያን ሰሞን በምስራቅ የሳውዲ ክፍል በደማም በአሰሪዎቿ ቤተሰቦች በደል እየደረሰባት አደሆነ ያጫዎትኳችሁ እህት ውሎ አዳርም ከቀን ቀን እየከፋ መምጣቱን ገልጻልኛለች          ” አንዱ ልጅ ሊደፍረኝ ከኋላየ መጥቶ ተናነቀኝ ፣ አምርሬ ሳለቅስና ታግየ ስመነጨቀው ተወኝ፣ እናት ለምን ታለቅሻለሽ ብላ በስድብ አመናጭቃ ተቀበለችኝ ፣ ምን ላድርግ  ብቻየን ሰቅሰቅ ብየ አለቀስኩ !” ስትል ትናንት ምሽት ስልክ ደውላ አጫውታኛለች !   የዚህችን እህት ጉዳይ ያሳዘናቸው ወገኖች ከደማም ኮሚኒቲ ሃላፊዎች ጋር አገናኝተውኝ ሙሉ መረጃውን ሰጥቻቸዋለሁ!

       ለትብብራቸው ምስጋናየ ይድረስ ! የሪያድ ኢንባሲ ሃላፊዎችም ተመሳሳይ ትብብር ታደርጉ ዘንድ ከአደራ ጋር እማጸናችኋለሁ  !             ልድገመው ! ሳውዲው ሃላፊ እንዲህ አሉ . .” ቅጥሩ ቢያቆምም በስራ ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አይባረሩም! ” እኔም ይህንን አከልኩበት . .ለዜጎች የሚቆረቆሩ የመንግስት ተወካዮችን አፋልጉኝ ! በማለት. . . ኮንትራቱስ ይቁም፣ የቀሩትን ዜጎች መብት ማን ያስከብር ? ስል ቢጨንቀኝ የዛሬ የማለዳ ወጌ መነሻ መድረሻ ወግ አድረግኩት!
የሚሰማኝ ባገኝ . . . !
ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ   / ነሓሴ 2005

↧

↧

ሰላማዊ የመብት ጥያቄ በሠለጠነ ውይይት እንጂ በአፈናና ግድያ መቼም ቢሆን አይፈታም!

$
0
0

ኅምሌ 27 ቀን 2005 ዓ/ም

shengo22 ዓመት ሙሉ ነፍጡን ከፊት አስቀድሞ የተፈጥሮ፣ ዴሞከራሲያዊና ሕጋዊ የሆኑ መብቶቹን ለማሰከበር በግምባር ሲታገል የቆየውን ምስኪን ህዝብ በገፍ እያሠረ፤ ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ እያሠቃየውና ግፍ በተሞላበት ግድያም እየቀጣው የቆየው የህወሓት/ኢሕአዴግ ግፈኛ አገዛዝ፣ ይኸው ዛሬም በሰላማዊው ሕዝብ ላይ ባፈናና ግድያው ቀጥሎበት ይገኛል።

ሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓ/ም በምዕራብ አሩሲና በሻሸመኔ አካባቢ ኢማሞቻችን/መሪዎቻችን ይፈቱ እያሉ በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ባሰሙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የግፍ ግድያ መፈጸሙን ሽንጎው የተገነዘበው በከፍተኛ ሃዘን ነው። ልጆቻችሁ፣ አባቶቻችሁ፤ እናቶቻችሁ፣ እህቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ለህወሓት/ኢሕአዴግ ጥይት ሰለባ ለሆኑባችሁ ወገኖች ሁሉ ጽናቱንና ቁርጠኝነቱን ይስጣችሁ እያልን፤ ዛሬም እንደትናንቱ የታፈነ ድምጻችሁን በማስተጋባትና ጥያቄያችሁም ፍትሃዊ ምላሸ እንዲያገኝ ከጎናችሁ በመቆም ለመታገል ቃል እንገባላችሁዋለን።

የህወሓት/ኢሕአዴግን ማንቁርት ይዞና ሥልጣኑን ጠቅልሎ በመያዝ ከፋፋይ የፖለቲካ መርዙን ሲረጭ የኖረው አምባገነን መሪያቸው የዛሬ ዓመት ገደማ ሲሞት ምናልባት የፖለቲካ ምህዳሩ በመጠኑም ቢሆን ተከፍቶና ተለሳልሶ ቢያንስ አፈናና ጭፍጭፋ ይቆምና የፖለቲካ እሥረኞችም ይፈቱ ይሆናል የሚል እጅግ አናሳም ቢሆን ግምት ተንጸባርቆ ነበር። ባመቱ የመሠከርነው ዕውነታ ግን ያው የተለመደው አፈናና ግድያ በማናለብኝነት መቀጠሉን ነው። ከዚህ ካሁኑ ግድያ አንድ ቀን አስቀድሞ ባዲሱ የፖሊስ ኮሚሸነር ትዕዛዝ ባገር ውስጥ የዜና ማሠራጫ ተነገረ እንደተባለው ማስጠንቀቂያ ከሆነ፤ ደም አፍስሰው ያልጠገቡትና ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ ያሉ መሪዎች የግፍ ዱላቸውን በሌሎችም አካባቢዎች ሊቀጥሉበት የወሰኑ ይመስላል።

ከዘመን ብዛትና ከኢትዮጰያ ህዝብ ቁርጠኝነት እነዚህ የዘመናችን ገዢዎቹ የተማሩትና ሊማሩም ያሰቡት ነገር ምን ይሆን እያልንና ሥልጣኔ በጎደለው ድርጊታቸው እየተደመምን፤ ሕዝባችን ግን በገዥዎች ትንኮሳ ሳይረበሽ ባጠመዱለትም ወጥመድ ሳይጠለፍ የጀመረውንም እልህ አሰጨራሽ እና የሰለጠነ ትግል አጠናክሮ እንዲገፋ አደራ እያልን፤ እኛም ከጎኑ ቆመን ከመታገል ወደሁዋላ እንደማንል ቃል እንገባለን።

ሁሉም ኢትዮጵያውያንም ይህን የህወሓትን/ኢሕአዴግን ኋላቀር አረመኔአዊ ጭፍጨፋ አጥበቀው እንዲያወግዙና የመብት ጥያቄን ከሚያነሱ ሁሉ ጎን በመሰለፍ ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የዕምነት ነጻነት እንዲከበር፣ እንዲሁም የታሰሩት እንዲፈቱ ትግሉን እንዲያጠናሩ ጥሪአችንን እናቀርባልን።

 

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

↧

የኢትዮጵያ መንግስት ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ኢላማ ሊሆኑ ከሚችሉ አገራት መካከል ባለመመደቧ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ገባ!

$
0
0

ድምጻችን ይሰማ
muslim1

 

መንግስት በመጪው አርብ በኢትዮጵያ የሽብርተኞች ጥቃት ሊፈጸም ስለሚችል ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉ ሲል ለበርካታ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች የቅድመ ማስጠንቀቂያ መልክት (ኬብል) ላከ!
የዩናይትድ ሰቴትስ መንግስት በመላው ዓለም የሚገኙ 22 ኤምባሲዎቹና የቆንስላ ጽ/ቤቶቹ የድንገተኛ ሽብር ጥቃት ሊፈጸምባቸው ይችላል በሚል ባወጣው የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ኢትዮጵያ ባለመካከተቷ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ መግባቱ ታወቀ፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በስለላ መረጃዎች ተመርኩዛ በተለያዩ አገራት በሚገኙ ጥቅሞቿ ላይ በአሸባሪዎች ሊፈጸም ይችላል በሚል ባወጣችው መረጃ 22 አገራት የሚገኙ የአሜሪካ ጥቅሞች ቦታ የተጠቀሰ ሲሆን፤ በእነዚህ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ መሰል የሽብር ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል የሚያሳይ መረጃ ባለመገኘቱ ኢትዮጵያ ሳትካተት ቀርታለች፤ በዚህም መንግስት ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ መግባቱ ተረጋግጧል፡፡
ይህ ያልተሰበ ጥቃት ሊፈጸምባቸው ነው ተብሎ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ አገራት ውስጥ ያሉ የዩናይትድ ስቴትስ ጥቅሞች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ለማድረግ ሲባል እስከ መጪው ቅዳሜ ነሀሴ 4 ድረስ ዝግ እንደሚሆኑ ተነግሯል፡፡ በዚህም መሰረት የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት በአራት አፍሪካ አገራት ማለትም በማዳጋስካር፣ በብሩንዲ፣ በርዋንዳና በሞሪሺየስ የሚገኙ ኤምባሲዎች እንደሚዘጉ ገልጿል፡፡ የአንዳንዶቹ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች መዘጋት እስከ ፈረንጆቹ ኦገስት ወር መጨረሻ ድረስ ሊዘልቅ እንደሚችልም መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡ ሆኖም ይህ የሽብር ስጋት አለባቸው በተባሉ አገራት ውስጥ ኢትዮጵያ መካተት አለመቻሏ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል በበጎ ካለመታየት አልፎ ከፍተኛ ቅራኔ እና ብስጭት እንደፈጠረ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ለዚህም ምላሽ ይሆን ዘንድ የኢትዮጵያ መንግስት ትናንት በውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በኩል ያልታሰበ የሽብር የጥቃት አደጋ ሊከሰት ይችላል በሚል በአዲስ አበባ ለሚገኙና ከ30 በላይ ለሚሆኑ አገራት ማስጠንቀቂያ (ኬብል) መስጠቱ ታውቋል፡፡ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በመጪው አርብ ሊፈጸም ይችላል ባለው የሽብር አደጋ አገራት የራሳቸውን የቅድመ ማስጠንቀቂያ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል፡፡ በዚህም መረጃ መሰረት መንግስት የራሱን የተቀነባበረ የሽብር ተግባር በመፈጸም ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ለጥቃቱ ተጠያቂ ለማድረግ እቅዳ እንዳለው ታውቋል፡፡ መንግስት ለሁለት አመታት የዘለቀውና ምንም አይነት የኋይል እንቅስቃሰሴ ያልታየበትን፤ ለዚህም አለም አቀፍ ተቋማት ምስክርነት የሰጡትን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ማስከበር እንቅስቃሴ ለመቀልበስ የተለያዩ የሽብር ውንጀላዎችን ሲሰነዝር የቆየ ቢሆንም ምንም አይነት ተቀባይነት ከአገር ውስጥም ሆነ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሳያገኝ ቆይቷል፡፡
መንግስት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የምናደርገውን የመብት ማስከበር እንቅስቃሴ ከሽበርተኝነት ጋር የተቆራኘ ነው የሚለውን ውንጀላውን ለተለያዩ አገራት ለማሳመን ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የሎቢ (ጉትጎታ) ስራ ሲሰራ የቆየ ቢሆንም ምንም አይነት ተአማኒነት ለማግኘት ካለመቻሉም በላይ የአሜሪካ መንግስት የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽንን የመሳሰሉ ተቋማት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ፍጹም ሰላማዊ መሆኑን በተደጋጋሚ በሪፓርታቸው መስክረዋል፡፡ በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ግላዊ ሹመት በሚመረጡ ግለሰቦች የሚመራው የአሜሪካ መንግስት የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ከወር በፊት ባወጣው ሪፖርቱ ይህን እውነታ ከማስታወሱም በላይ የኢትዮጵያ መንግስት የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የሃይማኖት ነጻነት እየነፈገ መሆኑን መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡
መንግስት ይህ ተአማኒነት ያጣውን ውንጀላውን በተግባር ፈጽሞ ስጋትን ለማሳየት በታቀደው የሽብር ጥቃት የትኛው ተቋም ወይም ድርጅት ኢላማ ሊሆን እንደሚችል በውል አልታወቀም፡፡ አንደመላምቶች ገለጻ ኤምባሲዎች፣ የትራንስፖርት ሰጪ አገልግሎቶች፣ የመንግስት ተቋማት ኢላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ የተገመተ ሲሆን በቤተክርስቲያኖችና በመስጂዶች ላይም መንግስት ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችልም ታምኗል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ የመብት ጥያቄዎችን የጠየቁ ሙስሊም ዜጎችን በሽብር ስራ በመወንጀል እስከ አሁን በተለያዩ ወቅቶች የሰሞኑን የአርሲ ኮፈሌ ጨምሮ 30 ንጹሀን ዜጎች በመንግስት ታጣቂዎች ጥይት ተገድለዋል፡፡ በተቃራኒው ሙስሊሞች ጁምአን ቀን በመጠበቅ መንግስት ሕገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄውን እንዲመለስ በሰላማዊ መንገድ ከመጠየቅ በዘለለ ምንም አይንት የኃይል ዝንባሌ ታይቶብን አይታወቅም፡፡
መንግስት አሁን ባሰበው ሴራ መሰረት ንጹህንን በተቀነባበረ የሽበር ድርጊት በመግደልና ደማቸውን በማፍሰስ የራሱን ፖለቲካ ጥቅም እና ሽብርን ለመከላከል በሚል ከውጪ አገራት የገንዘብ ድጋፍ ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡ መንግስት ከዚህ ቀድም መሰል የሽብር ድርጊቶችን ራሱ በመፈጸም አሻባሪ ያላቸው ድርጅቶች ላይ ሲያሳብና ውንጀላ ሲሰነዝር እንደነበር ከአሜሪካ መንግስት ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት አፈትልከው ወጥተው የነበሩ የዊኪሊክስ መረጃዎች ለአለም ማጋለጣቸው ይታወቃል፡፡ መንግስት ከዚህ ቀደም በመጓጓዣ መኪናዎች ላይ ሆቴሎች እና መሰል ተቋማት ላይ ነበር ጥቃቶችን የሰነዘረው፡፡ መንግስት የምናደርገው ሰላማዊ ትግል በሰላማዊ መርህ ብቻ የሚመራ መሆኑን አሁንም ለመቀበል ባይፈቅድም ሰላማዊ ትግላችን በአገራችን እንደዜጋ መታየት እስክንጀምርና ሕገ መንግስታዊ መብታችን እስከሚከበር ድረስ ይቀጥላል፡፡

አላሁ አክበር!

↧

Health: ጉንፋን አሰቃየኝ፣ እባካችሁ መላ በሉኝ!

$
0
0

ክረምት መግባቱን ተከትሎ ሀይለኛ ጉንፋን ይዞኛል፣ ሌሎች የቤተሰብ አባላቶቼን ወዲያው ሲተዋቸው እኔን ግን አሁንም ድረስ አፍንጫዬን እንደዘጋኝ አልፎ አልፎም ከባድ የአፍንጫና የጉሮሮ ፈሳሽ ያከታትልብኛል፡፡ ምን ባደረገው ሊተወኝ ይችላል? እባካችሁን መላ በሉኝ፡፡
ዓለም ተስፋ

ውድ ዓለም፡- ጉንፋን ሲያጓድዱት በሽታ ይሆናል- ባያጓድዱትስ? ለነገሩ የት ሊደርስ! ይሁን እንጂ ተጠቂ ለሆነ ግለሰብ የበሽታ ትንሽ የለውም፡፡ ያልተነካ ግልግል ያውቃል እንደሚባለው ላልተነካ ሰው ጉንፋን እንደበሽታ ላይቆጠር ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ የህመም ቀላል የለምና ጉንፋንም በቀላሉ ሊታይ አይገባም፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት በመዲናችን አዲስ አበባ እየታየ ያለው ጉንፋን ከተላላፊነቱና ክብደቱ አንፃር ሲታይ ይሄ ነገር ‹‹ጉንፋን ነው ወይስ በርድ ፍሉ?›› የሚል ጥያቄ እንድናነሳ ዳድቶናል፡፡ ለማንኛውም መንስኤውንና መፍትሄ ያልነውን እንዲህ አቅርበነዋል፡፡
ጉንፋን ተብሎ የሚጠራው በጥቅሉ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ የላይኛው የመተንፈሻ አካላችን ኢንፌክሽን ሲሆን፣ በዓለማችን በአጠቃላይ በተላላፊ ኢንፌክሽንነትና የዕለት ተዕለት ተግባራችን በብቃት እንዳንወጣ በሚፈጥረው ሳንካ፣ ቁጥር አንድ ተጠቃሽ በሽታ ሆኗል፡፡
እነዚህ ቁጥራቸው ከ200 ያላነሰ የቫይረስ አይነቶች ከብዛታቸው የተነሳ ሰውነታችን ለነዚህ የሚሆን የመከላከያ አይነት አምርቶና አዘጋጅቶ ሙሉ በሙሉ ሊቋቋም አይችልም፡፡ ይሁን እንጂ የሰው ልጅ በዕድሜው በገፋ ቁጥር ከሞላ ጎደል በጉንፋን የመያዝ ዕድሉ እየቀነሰና በጉንፋን ሳቢያ የሚመጡትንም ስሜቶች የመቆጣጠር ሁኔታው እየጨመረ ይሄዳል፡፡

Photo Credit:  health.thefuntimesguide.com

Photo Credit:
health.thefuntimesguide.com

በአጠቃላይ በጉንፋን ቫይረስ ከሚያዙ ሰዎች ውስጥ 75 በመቶ የሚሆኑት ስሜቱን የሚቋቋሙ ሲሆኑ 25 በመቶ ደግሞ የጉንፋን ስሜቶችና ህመሞች የሚጎሉባቸው ናቸው፡፡ በአማካኝ ቤት የሚውሉ ህፃናት ከ6-10 ጊዜ፣ በመዋዕለ ህፃናት የሚውሉ ልጆች ከ10-12 ጊዜ እንዲሁም ወጣቶችና ጎልማሶች ከ2-5 ጊዜ በዓመት የጉንፋን ተጠቂዎች ይሆናሉ፡፡
ይህ የጉንፋን ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን በዋነኛ የሚተላለፍባቸው መንገዶች፣ በጉንፋን የተያዘ ሰው ሲያወራ፣ ሲያስል፣ ወይንም ሲያስነጥስ፣ በአማካኝ ሁለት ሜትር ርቀት አካባቢ ሆነን ቫይረሱ የያዘውን አየር ወደ ውስጥ ስንስብ፣ ጉንፋን የተያዘን ሰው በእጃችን ጨብጠን ወይንም የተጠቀመበትን (በእጁ የያዘውን) ማንኛውም ዕቃ ነክተን አይናችንን አፍንጫችንን ወይንም አፋችንን የያዝን እንደሆነ ነው፡፡
ይህ ቫይረስ በአብዛኛው ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው ጉንፋን በተያዘ በመጀመሪያው ከሁለት እስከ ሶስት ባሉት ቀናት ውስጥ ሲሆን በጥቅሉ ግን እስከ ሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥም ሊተላለፍ የሚችልበት አጋጣሚ አለ፡፡
ጉንፋን በአብዛኛው በክረምት (በብርድና ዝናባማ ወቅት) በዝቶ ሚታይበት ምክንያት በተለምዶ እንደሚባለው፣ ብርድ መትቶን፣ በቅዝቃዜ ወቅት ልብስ ሳንደርብ ወጥተን፣ ድራፍት መትቶን ወይንም በቅዝቃዜ በእርጥብ ፀጉር ከቤት ወጥተን ሳይሆን፣ የጉንፋ ቫይረሶች ቀዝቃዛ አየር ለመራባት አመቺ ስለሚሆንላቸውና እንዲሁም በክረምት ወቅት ከቤት ያለመውጣትና ቤት ውስጥ አብሮ የመቀመጥ ሁኔታ የጉንፋንን የመተላለፍ እድል ስለሚጨምረው ነው፡፡
በጉንፋን የመያዝ ምልክቶችስ ምን ምን ናቸው?
የጉንፋን ቫይረስ እንደ ብዛቱ ሁሉ ሰዎች ላይ የሚያስከትለው ስሜትም የተለያየ ቢሆንም፣ በላንቃችንና በጉሮሮአችን አካባቢ የመከርከር ስሜት ብሎም በሚወጡበት ጊዜ የህመም ስሜት መሰማት፣ የአፍንጫችን መደፈንና ከአፍንጫ የሚወጣው ቀጭንም ሆነ ወፍራም ፈሳሽ መብዛት፣ ማስነጠስ፣ ማሳል፣ የራስ ህመም መሰማት፣ በትንሹ የትኩሳት ስሜት መሰማት፣ ድካም ድካም ማለት፣ ቁርጥማት መሰማት፣ እንዲሁም የምግብ ፍላጎት መቀነስ ከሞላ ጎደል ይጠቀሳሉ፡፡ አንድ ሰው በጉንፋን ቫይረስ ከተያዘ በኋላ ከሁለት እስከ ሶስት ቀናቶች ባሉት ጊዜ ውስጥ የጉንፋን ስሜት ሊጀምረው ይችላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ በአብዛኛው የጉንፋን ስሜት ያለው ሰው በአማካኝ በአንድ ሳምንት ውስጥ ሊሻለው ቢችልም እስከ ሶስት ሳምንታት ያክል የሚቆይበት አጋጣሚ አለ፡፡
በጉንፋን ላለመያዝ የመከላከል እርምጃ
በጉንፋን ከተያዘ ሰው በተቻለ መጠን መራቅ፣ እጅ አለመጨበጥ፣ ምክንያቱም ጉንፋን የተያዙ ሰዎችን መጨበጥ በጉንፋን የመያዝ ዕድልን በ70 በመቶ ስለሚጨምር ነው፡፡
ነገር ግን ጉንፋን የተያዘን ሰው ከጨበጡ ወይንም የነካውን ዕቃ ከያዙ በቶሎ ከ15 ሰከንድ ባላነሰ ጊዜ ውስጥ እጅዎን በውሃና በሳሙና መታጠብ ይኖርበታል፡፡ በህዝብ አገልግሎት መስጫዎች ወይንም ጉንፋን የያዘው ሰው ባለበት አካባቢ ለዕጅ ማድረቂያ ከፎጣ ይልቅ ሶፍት መጠቀም ጥሩ ነው፡፡
ጉንፋን የያዘው ሰው የተጠቀመበትን ብርጭቆ ወይንም የመመገቢያ ማንኪያና ሹካ አለመጠቀምና ጤነኛ አመጋገብና የሰውነት እንቅስቃሴ በማድረግ የሰውነትን ህመም መከላከያ አቅም መገንባት ትልቅ የመከላከያ ዘዴ ነው፡፡
በተጨማሪም እርስዎ ጉንፋን በሚይዝዎት ጊዜ
በተቻለ መጠን ቤት መቀመጥና ወደ ሰው ላለማስተላለፍ መጠንቀቅ፣ የሚጠቀሙበትን ሶፍት ቶሎ ቶሎ (ወዲያው ወዲያው) ማስወገድና በተገቢው ቦታ መጣል፣ እንዲሁም በመሀረብ ከመጠቀም ይልቅ በተቀያሪ ሶፍት መጠቀም፡፡
በሚስሉበት ወይንም በሚያስነጥሱበት ወቅት እጅዎን በአፍዎና በአፍንጫዎ ላይ መሸፈንና እጅን ተጠንቅቆ መታጠብ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡
ከዚህ ሁሉ በፊት ጉንፋን ቢይዝዎትስ?
ጉንፋን በእርግጥ መድሃኒት የሌለውና በሂደትም በራሱ የሚጠፋ ወይም የሚድን ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ሰው በጉንፋን ከተያዘ በኋላ ስሜቶቹን ለማቅለል የህመሙን የቆይታ ጊዜ ለማሳጠርና እንግልቱን ለመቀነስ የሚከተሉትን ተግባራት ማከናወን ይችላል፡፡
- ውሃና ሌሎች ፈሳሾችን በብዛት መውሰድ ከሰውነታችን በአፍንጫ ፈሳሽና በላብ መልክ የሚወጣውን ፈሳሽ በመተካት የሰውነታችንን የውሃ ድርቀት ከመከላከሉም በላይ፣ ለአፍንጫችን መደፈንና ለሚከተለው የራስ ህመም ምክንያት የሆነውን ወፍራም ፈሳሽ በማቅጠን ስሜቶቹን ይገታል፡፡ ጉሮሮን ለብ ባለ ውሃና ጨው በመጉመጥመጥ የጉሮሮ መከርከርንና ተጓዳኝ ስሜቶች መቀነስ፣ ውሃ አፍልተን እንፋሎቱን በመታጠን የመተንፈሻ አካላችን እንዳይደርቅ መከላከል፡፡ ውሃ መታጠን ወይም እንደ ‹‹ስቲም ባዝ›› መጠቀምም በድርቀት ሳቢያ ለሚመጡ ስሜቶች መፍትሄ ከመሆንም አልፎ ለቫይረሱ መራቢያ ምቹ የሆነውን የደረቅ አየር ሁኔታ ይቀይራል፡፡
ሰውነታችንን በማሳረፍ የሰውነታችንን የመከላከያ ብቃት መገንባትና ማር በመብላት ለሰውነታችን ኃይል መስጠት፣ እንደ ብርቱካንና ሎሚ የመሳሰሉትን የቫይታሚን ሲ ምንጮችን በመውሰድ ሰውነታችን ትግሉን እንዲያበረታ ማገዝ፣ ከዶሮ የተሰራ ሾርባ መጠጣት የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል ብቃት ሊያጎለብት በተጨማሪም ትኩስ፣ ኃይል ሰጪና፣ ፈሳሽ እንደመሆኑ መጠን ከላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት ያከናውናል፡፡ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶችን በአማራጭነት መጠቀምዎም እንደ ራስ ምታትና መሰል የሰውነት ህመሞችን ይገታሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ግን ስሜቱ የበረታ እንደሆነና ጊዜው የረዘመ ከሆነ፣ የትንፋሽ ማጠርና የደረት ውጋት ከጀመረ፣ የአክታ መብዛት፣ ሀይለኛ ትኩሳት፣ ማስመለስ፣ እንዲሁም የጉሮሮ ህመም በርትቶ አላስውጥ ያለ እንደሆነ ወደ ሐኪምዎ በመሄድ መፍትሄ ማግኘት እንደልብዎ አይዘንጉ፡፡
ውድ አንባብያን ዓለም ላይ የተጠቀሱትን መፍትሄ ያልናቸውን መንገዶች በመጠቀም ችግር ለመቅረፍ መሞከር መልካም ነው፡፡ እናም በሂደት ያለውን ለውጥ ማየት ነው፡፡ ሁኔታው በዛው ከቀጠለ ግን ሌላም ተያያዥ ችግር ሊኖር ስለሚችል ወደ ሐኪም መሄድ ያዋጣል ነው የእኛ ምክር፡፡ ሰላምና ጤና ለሁላችን ይሁን፡፡

↧

Sport: ሂጓይን አርሰናል ይመጣል?

$
0
0

በመጨረሻ…፣ በመጨረሻ አርሰናል ከፍተኛ ገንዘብ ሊያወጣ ነው? በመጨረሻም ትልቅ ተጨዋች ሊገዛ ነው? ይህ ያለፉት ሳምንታት ወሬ ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት አብዝቶ ፋይናንሳዊ የጥንቃቄ ጉዞ እያደረገ የዋንጫ መደርደሪያውን ባዶ ላስቀረው የክለብ ደጋፊዎች ይህ ትልቅ ዜና ነው፡፡ አርሰን ቬንገር በስልጣናቸው እያሉ ትልልቅ ተጨዋቾች ሲገዙ መመልከት ለክለቡ አፍቃሪዎች ያጓጓል፡፡ የከዋክብት መምጣት በስኬት ማጣት ፊታቸው የጠቆረባቸውን የኢምሬትስ ታዳሚዎች በደስታ ይሞላል፡፡ ሆኖም የትኞቹ ትልልቅ ተጨዋቾች? የሚለው ጥየቄ ብዙ ያነጋግራል፡፡
በእርግጥ ይህ ክረምት በኢምሬትስ ትልቅ ተጨዋች እንዲያመጣ ይጠበቃል፡፡ ይህ ጥያቄ ባለፉት ዓመታት ተመሳሳይ ወቅቶች ሲነሳ ቢቆይም አሁን ወሳኝ ጊዜ ላይ ደርሷል፡፡ የውድድር ዘመኑ ከተጠናቀቀ ወዲህ አርሰናል የዝውውር ገበያው ዜናዎች ማጣፈጫ ሆኗል፡፡ እስካሁን ጠብ ያለ ነገር ባይኖርም የክለቡ ስም ከዌይን ሩኒ፣ ስቴፋን ዩቬቲች፣ ጎንዛሎ ሂጓይን እና ባለፉት ቀናት ደግሞ ከሉዊስ ሱአሬዝ ጋር ተነስቷል፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ተጨዋቾች ዝውውሩ እውን ሊሆን የተቃረበ የሚመስለው የሂጓይን ነው፡፡ ክለቡ አርጀንቲናዊውን አጥቂ በማስፈረም የደጋፊዎችን እምነት መልሶ ለማግኘት የቆረጠ ይመስላል፡፡

Photo Credit: Skysports

Photo Credit: Skysports


የሪያል ማድሪዱ ተጨዋች ትልቅ ግዢ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ሆኖም ለዚህ ልጅ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ማውጣት ይገባል? የሚለው ጥያቄ ከብዙዎች አዎንታዊ መልስ ቢያገኝም ጥቂቶች ደግሞ ተጨዋቹ ቡድኑን ከሚጠቅመው ይልቅ ክለቡ የደጋፊዎችን ልብ ለመደለል ሊጠቀምበት ሊሆን ይችላል ሲሉ ይጠራጠራሉ፡፡
ሂጓይን ጎል ጨራሽ ነው፡፡ በየውድድሩ ዘመኑ ከ20 በላይ ጎሎች ለማስቆጠርም አይቸገርም፡፡ ሆኖም ይህ ለአርሰናል ዋንጫ ያመጣል? ይህንን የሚጠራጠሩ ብዙ ናቸው፡፡ ምክንያቱም አርሰናል ሻምፒዮን ለመሆን ከጎል አግቢም በላይ ያስፈልገዋል፡፡
የሂጓይን መምጣት በኦሊቪዬ ዢሩ ቀጣይ ሚና ላይ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ፈረንሳዊው ጎል ከማስቆጠር መሰረታዊ ችግሩ በስተቀር የተሟላ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ሂጓይን ሊፈፅማቸው የማይችሉ እና የእንግሊዝ እግርኳስ አጥብቆ የሚጠይቃቸውን ብቃቶችን ይዟል፡፡ ቬንገር ሁለቱን አጥቂዎች በአንድነት ለመጠቀም ፍላጎቱም ሆነ ዕድሉ የሚኖራቸው አይመስልም፡፡ ስሊዘህ ዢሩ ወደ ተጠባባቂ ወንበር ወርዶ ሂጓይን በቋሚነት የፊት መስመሩን ይመራል ማለት ነው፡፡ ይህ ግን ብዙ ጥያቄዎች ያስከትላል፡፡ ዘመናዊው እግርኳስ በተለይም በፕሪሚየር ሊጉ የሚተገበረው አጨዋወት ቴክኒካዊ እና ጎል ጨራሽ ተጨዋቾችን ብቻ የፊት አጥቂነት መጠቀም አያስመርጥም፡፡ በዚህ ረገድ ሲታይ ለአርሰናል ከሂጓይን ይልቅ ሌሎቹ ስማቸው ከክለቡ ጋር የተያያዙ አጥቂዎች ይሻሉታል፡፡
ለሂጓይን ይከፈላል ተብሎ የሚጠበቀው የዝውውር ሂሳብ 25 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ነው፡፡ ሆኖም ከአርጀንቲናዊው በተለይ በፕሪሚየር ሊጉ ምርጥነታቸውን ያስመሰከሩት ሩኒ ወይም ሱአሬዝ ከ30-35 ሚሊዮን ፓውንድ ቢበዛ ያስወጣሉ፡፡ እነዚህ ተጨዋቾች ጎል አግቢዎች ብቻ አይደሉም፡፡ ወደ ኋላ እየተመለሱ ኳስን ከመሀል ይዞ መውጣት እና እንደ ፕሌይ ሜከር ሌሎቹን የቡድን ተጨዋቾችን መርዳት እንዲሁም ከማጥቃት በተጨማሪ የመከላከል አጨዋወቱን ማገዝ ያውቁበታል፡፡
ቬንገር ብዙ ጊዜ የወደፊቱ ጊዜ በመመለከት ችሎታቸው ቢታወቁም ለሂጓይን ዝውውር ሊከፍሉ ያሰቡት ዋጋ የወቅቱን የአውሮፓ እግርኳስ ዝንባሌ ችላ ያሉ አስመስሏቸዋል፡፡ ከርናቢዩው ልጅ ይልቅ በአነስተኛ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ለገበያ የቀረበውን ካርሎስ ቴቬዝ ዝም ብለው ከማሳለፋቸውም ሌላ ለዝውውሩ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ይበቃዋል እየተባለ ያለውን ሮቤርት ሌቫንዶቭስኪ ለመግዛትም ገፍተው አልሄዱም፡፡ ሌላው ቀርቶ የሂጓይን ዝውውር በተለያየ ምክንያት ቢደናቀፍ በሚል በዋጋ ረከስ የሚሉትን ዴቪድ ቪያ ወይም ሚቹን ለማስፈረም ሙከራ አላደረጉም፡፡
እነዚህ ሁሉ ተጨዋቾች ዘመናዊው እግርኳስ የሚፈልጋቸው አይነት አጥቂዎች ናቸው፡፡ ጎሎች ያገባሉ፣ የጎል እድሎች ይፈጥራሉ እና ቀዳዳዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ሂጓይን እና ዢሩ የዘመናዊውን እግርኳስ
ቬንገር ሂጓይንን አስፈርመው የፊት መስመሩ ዋነኛ መሪ ካደረጉት ቡድኑ ትንንሽ ቡድኖችን ሲያገኝ በርከት ያሉ ጎሎች ሊያስቆጥር ይችላል፡፡ ሆኖም ከትልልቆቹ ጋር ሲፋጠጥ በአማራጭ ማጣት ይቸገራል ሲሉ ስጋታቸውን የሚያብራሩ ጥቂት አይደሉም፡፡ ቡድኑ ጎሎች እንዳያገባ ሲከለክል ተስፋ መቁረጥ እና መርበድበድ ይጀምራል፡፡ ይህ በራሱ የአርሰናል ትልቅ ችግር ጎል ያለማስቆጠር ሳይሆን የመከላከል ድክመት እና የአዕምሮ የበላይነት ማነስ መሆኑን ያሳያል፡፡ ባለፉት በርካታ ዓመታት የመድፈኞቹን ክፍተት በሚገባ ላስተዋለ ቬንገር ሁለት ምርጥ አጥቂዎች በ60 ሚሊዮን ፓውንድ ገዝተው ችግሮችን ሁሉ እንደማይፈቱ ግልፅ ነው፡፡
አርሰናል ከ2004ቱ ጠንካራ ቡድን መፈራረስ በኋላ የአሸናፊነት ስነልቦናቸው ከፍ ያለ፣ መሪዎች እና ታጋዮች ይጎድሉታል፡፡ የቶኒ አዳምስ እና ፓትሪክ ቪዬራ አይነት ተጨዋቾች አሁንም የሉትም፡፡ በቴክኒኩ ረገድም ክለቡ አንድ በአንድ ያጣቸውን ሴስክ ፋብሪጋዝ እና ሮቢን ቫን ፔርሲን የመሳሰሉ ከዋክብት አልተሳካም፡፡
ሂጓይን ዋንጫ ያመጣል?
የአጥቂው ዝውውር ብዙ ከመጓተቱ የተነሳ ለአድማጭ አሰልቺ ሆኗል፡፡ በስፔን እግርኳስ እውቀቱ እና በውስጥ አዋቂ ምንጮቹ የሚታወቀው ጋዜጠኛው ሲድ ሎው ሳይቀር ተጨዋቹ ከአርሰናል ጋር የሶስት ዓመት ውል እንደሚፈርም እና በሳምንት 100 ሺ ፓውንድ ደመወዝ እንደሚከፈለው እንዲሁም ባለፈው ሐሙስ አመሻሹ ላይ የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ቢናገርም በተግባር አልታየም፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ የመጡ መረጃዎች ደግሞ ዝውውሩ የተጓተተው ሪያል ማድሪድ በመጨረሻ ሰዓት የሽያጩን ገንዘብ ከፍ በማድረጉ መሆኑን ያትታል፡፡ የተጫዋቹ ዝውውር አሁንም ከመልሶቹ ይልቅ ጥያቄዎች እንደበረከቱበት አለ፡፡
ሂጓይን ወደ ኢምሬትስ ያመጣዋል የተባለው ከ22-25 ሚሊዮን ፓውንድ ለአርሰናሎች ትልቅ ገንዘብ ነው፡፡ ለማንቸስተር ሲቲ፣ ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ግን ብዙ አይደለም፡፡ የአጥቂው ሪከርድ በወረቀት ላይ ሲታይ ግሩም ነው፡፡ ታዲያ ሌሎች ክለቦች እንዲህ በተጓተተው የሂጓይን ዝውውር እጃቸውን ከማስገባት የተቆጠቡት ለምንድነው? ቢያንስ ባለፉት የውድድር ዘመናት አብረውት የሰሩት ጆዜ ሞውሪንሆ ከፈርናንዶ ቶሬስ እርሱ ይሻለኛል ለምን አላሉም?
ሞውሪንሆ ብቻ ሳይሆኑ አሁን የማንቸስተር ሲቲ አሰልጣኝ የሆኑት ማኑዌል ፔሌግሪኒም አርጀንቲናዊውን አሰልጥነውታል፡፡ ታዲያ ለምን ወደ ኢቲሀድ ሊያዘዋውሩት ሳይፈልጉ ቀሩ? በተጫዋቹ ላይ የአርሰናል ብቸኛ ተፎካካሪ የነበረው ጁቬንቱስም ቴቬዝን በአስነተኛ ዋጋ ሲያገኝ ፍላጉቱን አንስቷል፡፡
ሂጓይን ሪያል ማድሪድን ሲለቅ መሆኑን የተነገረው ቀደም ብሎ ቢሆንም ከአርሰናል እና ጁቬንቱስ የበለጠ በትኩረት ወደ ዝውውሩ የገባ ሌላ ክለብ የለም፡፡ በአንፃሩ ሱአሬዝ በአንፊልድ እንደሚቆይ እየተነገረ እያለም ፒኤስጂ፣ ሪያል ማድሪድ እና ማነቸስተር ሲቲ በኋላም አርሰናል እየተረባበረበበት መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ለሂጓይን ይህ ሁሉ የለም፡፡
ምናልባት ሌሎቹ ክለቦች ጣልቃ ላለመግባት የተደረጉት አርሰናል ቀደም ብሎ በመርህ ደረጃ ተጫዋቹን ለማስፈረም ስለተስማማ ነው የሚሉ አሉ፡፡ አርሰናል አጥቂውን ድንገት አስፈርመውት ቢሆን ኖሮ በደጋፊዎቹ ዘንድ ሊፈጠር ይችል የነበረው ደስታ ከዚህ በኋላ የሚኖር አይመስልም፡፡ክለቡ በይፋ ዝውውሩ መጠናቀቁን ቢገልፅ እንኳን ከእፎይታ የዘለለ ምላሽ ከደጋፊዎች መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡
የክለቡ ደጋፊዎች ለሂጓይን ዝውውር ብቻ ሳይሆን ለስምንት ዓመታት ያለዋንጫ ጉዞም በትዕግስት ሲጠብቁ ኖረዋል፡፡ ሆኖም የክለቡ አስተዳደር የደጋፊዎቹን የትዕግስት ዋጋ በተገቢው መንገድ አልከፈለም፡፡ ይባስ ብሎ እንዲያውም የስታዲየም ቲኬት ዋጋቸው እየጨመረ መጥቶ አሁን በእንግሊዝ የማይደረስበት እጅግ ውዱ ሆኗል፡፡ በደጋፊዎቹ ልብ እየገዘፈ የመጣውን ለመቀነስ ምናልባት ክለቡ የቀረው ብቸኛ አማራጭ ምርጥ ተጨዋቾን በአስፈላጊው ቦታ ሁሉ ገዝቶ በውድ ዋጋም ቢሆን ወደ ስታዲየም መግባታቸውን እንዲወዱት ማድረግ ነው፡፡
በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አጋማሽ የተነሳው እና እየተሟሟቀ ሄዶ የነበረው ፀረ ቬንገር ጩኸት ይጀመራል፡፡ ሰውየው የደጋፊውን ልብ ለመመለስ እና የራሳቸውን እየደበዘዘ የመጣ ታሪክ መቀየር ከፈለጉ ዋንጫ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ዋንጫ ለማምጣት ደግሞ ከዋክብት ያስፈልጋሉ፡፡ አሁን ደጋፊዎቹ የሂጓይንን ዝውውር ከጥርጣሬ የሚመለከቱትም ለዚህ ነው፡፡

↧
↧

ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ………. ጦቢያን ገረመው

$
0
0

ጦቢያን ገረመው

 

Penይህች አነስተኛ መጣጥፍ ለታዋቂው ጋዜጠኛና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ መታሰቢያነት ትዋልልኝ፡፡ ምክንያት አለኝ፡፡ ርዕሱ በመጠኑ ተሻሽሎ የተወሰደው በእርሱ ባለቤትነትና አዘጋጅነት ይመራ ከነበረው ከምኒልክ ጋዜጣ ነው፡፡ ባጭሩ ለማስታወስ – የዛሬ 12 ዓመት ገደማ በ93 ዓ.ም ወያኔ ለሁለት ተሰንጥቃ ነበር፤ ከዚያ በፊትም በ90 አካባቢ ንፋስ ይገባባቸው እማይመስሉት ወያኔና ሻዕቢያ ባላሰቡትና ባልጠበቁት መንገድ መቃቃራቸው የሚታወስ ነው፡፡ ያኔ ወያኔ በተቸካይነትና በተሃድሶነት ተከፋፈለች በተባለበት የዘመነ ህንፍሽፍሽ ወቅት ታዲያ አንድ ጸሐፊ በምኒልክ ጋዜጣ ‹እልልልልልልልል…› በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ ልኮ ‹አስነብቦን› ነበር፡፡ የሚገርማችሁ መጣጥፉ በእልልታ ጀምሮ ያለቀውም አንድም ሌላ ቃል ሳይጨምር በእልልታ ነበር፡፡ በምናባዊነቱ እየተገረምኩ በደስታ ‹ያነበብኩት መጣጥፍ› ስለነበር መቼም አይረሳኝም፡፡ ያቺን በማስታወስ ነው እንግዲህ ለኔ የዛሬዋ መጣጥፍ ተቀራራቢ ርዕስ የሰጠሁት፡፡

ዛሬ ጧት የግዛው ለገሰንና የብርሃኑ ዳምጤን ‹የእሁድ ወግ› በኢሳት እኮመኩም ነበርና አንድ በሣቅ የሚያፈነዳ ነገር ከውይይቱ አገኘሁ፡፡ በቅድሚያ ግን መተቸት ከሁሉ የቀለለ ነውና በኢሳት አቀራረብ ላይ እኔም ትንሽ ልበል – ኢሳቶች እንዳትቆጡኝ አደራ፡፡ ግዛው ለወደፊቱ እንግሊዝኛ ላለመጨመር ሞክር፤ የቋንቋ ‹ጥራት› ምናምን በሚሉት ሥነ ልሣናዊ አርበኝነት ተመርኩዤ አይደለም እንዲህ የምል፡፡ የወፍ ‹ቋንቋ› ከሰው ቋንቋ እየተዛነቀ ቢነገር እኔን እስከገባኝ ድረስ በበኩሌ ግዴለኝም፡፡ ግን ግን ኢሳትን የሚከታተለው ሕዝብ በአብዛኛው ጆሮውን ቢቆርጡት እንግሊዝኛ የማይሰማና የማይገባውም ከመሆኑ አንጻር በተለይ በጋዜጠኝነት ሙያ የተሰማራ ሰው ወደደም ጠላም ሚዲያው በኦፊሴል ሊጠቀምበት በወሰነበት ቋንቋ ነው የግዱን መጠቀም ያለበት፡፡ ከዚህ ነጥብ አኳያ ብዙዎች የኢሳት ጋዜጠኞች ጥንቃቄ ቢጨምሩ በሀገር ቤቱ ተከታታይ ዘንድ ተደማጭነትን ላለማጓደል ተገቢ ነው እላለሁ – እነሲሴንና አፈወርቅን ጨምሮ ብዙዎቹ የሚያደርጉትን ጥንቃቄ ግን ሳላደንቅ መቅረት ባልፍ ኅሊናየ ይቀየመኛል፡፡ እርግጥ ነው በዚህ የግሎባላይዜሽን ዘመን የቋንቋን ‹ጥራ› መጠበቅ እጅግ አስቸጋሪ መሆኑ ይገባኛል – ራሴም የችግሩ ሰለባ ስለሆንኩ ቋንቋን በጉራማይሌነት እያዛነቁ መናገር በተለይ በዚህ ዘመን በጣም እየተለመደ መጥቷልና አንዳንዴ በተለይም በሚዲያው አካባቢና የሚዲያው ሰዎች care መውሰድ ይገባናል በማለት ጉራማይሌያውያንን advise ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ otherwise የምንለው ነገር የማይገባቸው እንደኛ ጥቂትም ቢሆን ቋንቋ learn ያላደረጉ ዜጎች ስላሉ ይቸገራሉ የሚል ግምትና estimashin አለኝ because ብዙውን ጊዜ ሲቸገሩ ስለማይ፡፡ መቼም understand እንደምታደርጉኝ guess አደርጋለሁ፡፡ እሺ ok አሁን ወደሌላ አቃቂር ልለፍና ስለኢሳት toke ማድረጌን ላብቃ – by the way የእንግሊዝኛና የአማርኛ መምህሮቼ በspeilling puor ነህ ይሉኝ ነበርና አሁንም ድረስ እንደዚያው ሳልሆን እንደማልቀር እገምታለሁ፡፡ ብዙ ነገር ይቸግረኛል፡፡ አሁንም በሽምግልና ዘመኔ እንደዛው ሳልሆን የምቀር አይመስለኝምና በቀጣይ አንቀጾች ይህ ችግር ቢገጥመኝ አደራችሁን እንዳትዘከሩብኝ፡፡ ይህን የምለው አባመላ ስለ አንጋፋው ወያኔ ስለብስናት አማረ ሲናገር የሰማሁትን ማስከተሌ አይቀርምና ምናልባት እዚያ ገደማ ከተሳተኝ ብዬ ነው፡፡

ኢሳት ይህችን ፕሮግራምን በጣም የመደጋገም ነገር እንዴት እንደሚያሻሽላት እኔንም እየጨነቀኝ መጥቻለሁ – በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እያሳየ ያለውን መሻሻል ግን በዚህ አጋጣሚ ላደንቅ እፈልጋለሁ፤ ብዙ የመፈለግ ጣጣ ባለህ አለመርካትን እንደሚያስከትል እየተረዳሁበት የመጣሁበት ሁኔታ ተፎጥሯል ይመስለኛል፡፡ ከቤተሰቡ ጋር ጦርነት ውስጥ በመግባት እነ‹ሰው ለሰው›ንና የ‹ቤቶች› ድራማን ዘሩ ቀለጠንና እከደከ ማንችሎት … አበጀን ማየት እንዲችሉ መላ ቤተሰቡን ወደጎረቤት ለስደት በመዳረግ ሁሉንም ቲቪዎች ጠርቅሞ ዘግቶ ኢሳትን ብቻ ለሚከታተል ለእንደኔ ዓይነቱ ተስፈኛ ይቺ ነገር ቅር ታሰኛለችና እባካችሁን በብርቱው አስቡበት፡፡ የዐርብና የሐሙስን ዜናም ሰኞና ማክሰኞ በሰበር ዜናነት ከማቅረብ ተቆጠቡ፡፡ ምነው ሸዋ! እነሱው ምንም ባይሉን እኛው በኛው እንተቻችና እንተራረም፡፡ መተራረምን ደግሞ የባሕርይ ስጦታችን ካላደረግነው የአሁኑና የእስካሁኑ አስጠሊታ የመፈራራትና ባላስፈላጊ ሁኔታ በጎራዎች የመፈራረጅ ጅል ይትበሃል ምርኮኛ እንዳደረግን ይቆያል፡፡ ትችትን መፍራት ለባሰ ትችት ይዳርጋልና በግልጽነት መነጋገርን ባንቃወም መልካም ነው፡፡ በገምቢ ሁኔታ ብንተቻች እንጠቀምበታለን፤ በአእምሮም እናድግበታለን እንጂ አንጎዳም፡፡ መፈራራትና ‹ለጠላት በር ላለመክፈት ሲባል እንቻቻል› የሚሉት ፈሊጥም የትም አያደርሰንም ብቻ ሳይሆን ፍጹም ጎጂ ነው፡፡ ለመሆኑ ከፀሐይ በታች ምን አዲስ ነገር አለና ነው ትችትን እንደጦር የምንፈራው? ምናችንን ማንና እነማን ሳያውቅ/ቁ ሊቀር/ሩ? ሞኝነት ነው፡፡ እንደእውነቱና እንደኣካሄድ እንዲህ የምለው ለኢሳቶች አይደለም – በጭራሽ፡፡ ምክንያቱም ይህን የኔን መሰል ትችት በዚያው በኢሳት በኩል ዜጎች በተደጋጋሚ ሲናገሩ እሰማለሁና፡፡ እንዲህ የምለው ለማላውቃቸው ጥቂት ወገኖቼ ነው – ልክ እንደኔው ለኢሳት ለሚሳሱ ወገኖች፡፡ ግዴለም፤ ይህ ዓይነቱ እንስፍስፍነት አይጠቅምምና እንተወው፡፡ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ይልቁናስ በአወንታዊና ገምቢ አስተያየቶች በቅድሚያ ራሳችንን በየሙያ ዘርፋችን አሳድገን በራሱ የሚተማመንና በፍርሀት ምክንያት ለሂስና ግለሂስ በሩን የማይጠረቅም ጀግና ትውልድ እንፍጠር፡፡ …

በሣቅ የገደለኝ ነገር – አባ መላ ሲናገር ከፍ ሲል የጠቀስኩት ብስናት አማረ የሚባል ወያኔ መለስ ከሞተ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል በአንድ ግለሰብ ቀጭን ትዕዛዝ – በ‹ጄኔራል› መሀመድ የሎስ ጥብቅ መመሪያ ምክንያት ከቦሌ እንዲመለስ የተደረገበት ምክንያት ነው፡፡ የየሎስ እውነተኛ ቁርሾኣዊ ብስናትን ወዳገር እንዳይገባ የመከልከል ምክንያት የፈለገው ይሁን ግን ብስራት መጣ ሲባል “መለስ ሲሞት አለማልቀሱን የደኅንነት ሰዎቻችን ባደረጉት ሥውር ክትትል አረጋግጠዋልና ወደ ሀገር እንዳይገባ ታግዷል” በሚል ሰበብ ሰውዬው ማለትም ብስናት አማረ ወደ ሀገሩ እንዳይገባ መከልከሉን ስሰማ የሳቅሁት ሣቅ መቼም የሚደገም አይመስለኝም፡፡ ኢትዮጵያ የደረሰችበት የአስተዳደር ፈሊጥና የዘመናዊ መንግሥትነት ባሕርይ ቁልጭ ብሎ ታየኝና በምን ዓይነት ‹ሰዎች› እየተገዛን እንዳለን በማሰብ ለተወሰነ ጊዜ ወደማይታወቅ ሰማይ ጠፋሁ – በስላቃዊ ሣቄ ታጅቤ፡፡ እንዴት ያለ ጉደኛ መንግሥትና የመንግሥት ሹማምት ናቸው ያሉን ጃል? እስከዚህም ደርሰናል ለካንስ? ልቅሶና ዕንባም በሀገር ካጅነት ያስፈርጁ ጀመር? እንዴ፣ ስዬ አብርሃ በመለስ ሞት ጊዜ ለሰባት ቀናት ሀዘን ተቀምጦ ነበር ሲባል የሰማሁት ይህን በመፍራ ይሆን? የኔን ቢሰሙ አንቀው ይገድሉኝ ወይም ተቃርጠው ያነክቱኝ ነበር በሉኛ! (አንድ ወያኔን እምብዝም የማይወድ ትግሬ ወዳጄ ቤት ለሆነ ጉዳይ አንድ ጊዜ ሄጄ ምን ታዘብኩ መሰላችሁ – የሣሎኑ ግድግዳዎች ላይ የመለስ ሦስት የተለያዩ ትላልቅ የማስተዛዘኛ ፎቶዎች ገጭ ብለው ተሰቅለው የቤቱን አባላትና ወጪ ገቢን ይታዘባሉ – በተጉረጠረጡ ዐይኖቻቸውና የሚሞት በማይመስል ወያኔያዊ የተጋዳላይነት ስሜት፡፡ ይህም ከማዘን አለማዘን ግምገማና ያም ከሚያስከትለው በሀገር ከሃዲነት የማስፈረጅ አሰቃቂ ዕጣ ለመዳን ሳይሆን አይቀርም፡፡ ምንድነው በሀገራችን የመጣብን ጉድ ውድ ጤናማ ነን የምትሉ ዜጎች? እንዴት ዓይነት ትንሽነትስ ነው ተፈጥሯዊ ስሜትን በሰውኛ መክሊት የመስፈርና ማዘን አለማዘንን በኣሃዛዊ ስሌት እያስቀመጡ ዜጎችን የማሳቀቅ አዲስና በሀገራችን ባህል ያልተለመደ ጠያፍ ነገር? ከሰሜን ኮሪያ ሌላ ይህ ዓይነት በሽታ ያለባቸው ‹መንግሥታት› ይኖሩ ይሆን? ኧረ ምን ዓይነት ውርደት ውስጥ ነው የምንገኘው? አንድ ሰው እኮ ለልጁም፣ ለሚስቱም፣ ለአባትና እናቱም፣ ለሌላ ለሚወደውም ሰው ላያለቅስና ፊቱን በባና ላይነጭ ይችላል፡፡ እንዴ – ይህ እኮ ፍጹም የግል ጉዳይ ነው፡፡ ከሀዘን ብዛት እንዲያውም ማንባቱንና ማልቀሱን ትቶ የሚስቅም እኮ እኮ አለ – ወደጤናማ ኅሊናው እስኪመለስ ድረስ፡፡ በዚያ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሰው በወያያዊ ፍርድ ሣቀ ተብሎ በጭፍን ብያ ይሰቀል ይሆን? ) ለማንኛውም ውስጥ ዐዋቂውን አባ መላን እግዜር ይስጠው – ቢያንስ በዚህች አስደስቶኛልና ልጅ ይውጣለት፡፡ በሌላስ ቅሬታ አለኝ – ወረድ ብዬ በትህትና ለመጠቆም እሞክራለሁ – ካልተቀየመኝና ‹መቃብርህ ላይ አያቁመኝ› ብሎ ካልረገመኝ፡፡(አንዳንዴ መንጌ ሲናገር – ‹እኛ እኮ እኮ ለውዲቷ አብዮታዊት እናት ሀገራችን …› ይል ነበር – በስሜት ማዕበል እየተናጠ፡፡)

በደርግ ዘመን አንዲት ጥንቸል ልቧ እስኪፈርጥ እየሮጠች በሁለቱም ሞያሌዎች በኩል የኢትዮጵያንና የኬንያን ድንበር አቋርጣ ማርሳቤት የሚባለው የስደተኞች መንደር ትደርሳለች አሉ፡፡ ማምለጧን አላመነችም – ዝም ብላ ማለትም እያለከለከች ሩጫዋን ታስነካው ይዛ ሳለ “ ምን ሆነሽ ነው እንዲህ የምትሮጪ አንቺ ጥንቸል? ያንቺ ስም እኮ ከሚፈለጉት እንስሳት የስም ዝርዝር ውስጥ የለም፡፡ የሚፈለገው ዝኆን ነው፡፡ ምን ሆንኩ ብለሽ ነው አንቺ ደግሞ እንዲህ በማይመለከትሽ ነገር እምትኳትኚ?” ብለው ይጠይቋታል፡፡ እሷም “አይ እናንተ፣ የኢትዮጵያን ነገር እያወቃችሁት? ዝኆን አለመሆኔ እስኪረጋገጥ ድረስ ታስሬ ከሚደርስብኝ ስቃይና እንግልት የሚበልጥ ስለሌለ ራሴን ለማዳን ነው እንዲህ እምሆነው!” ትላለች፡፡ አዎ፣ እውነቷን ነው፡፡ ዱሮ ‹ዝኆን› አለመሆንህ እስኪረጋገጥ ነበር የምትሰቃይ፡፡ ዛሬ ደግሞ ከዚያ በባሰ አስገዳጅና ቀፍዳጅ ሁኔታ ውስጥ ስለገባን በወያኔ የማሳደድ ቀለበት ውስጥ የምትገባው የወያኔ ደጋፊ ትግሬነትህ እስኪጣራና የሆዳም አማራነትህ ሊቼንሳ እስኪወጣልህ ድረስ እንጂ ከዚያ በኋላ ላለው ሕይወትህ ምርጫው በእጅህ ነው፡፡ ወያኔ ካልሆንክ በኢትዮጵያዊነትህ ኢትዮጵያ ውስጥ የመኖር ዕድልህ በዜሮና በእንድ የመቶኛ ምናልባታዊነት ግምት የሚሰላ በመሆኑ የሚደርስብህ ስቃይ ከኢዮብ የማይተናነስ ነው፤ በሕይወት ለመትረፍም ያለህ ብቸኛ አማራጭ እግርህ ባወጣህ ከሀገርህ ወጥተህ መሰደድ ነው፡፡ በምትሰደድበትም ቦታ ሁሉ እስስቱ ወያኔ ከአካባቢው ጋር እየተመሳሰለ ስለሚጠብቅህ ኅልውናህ ሁልጊዜ አደጋ ላይ ነው – ኬንያ ላይ በወያኔ ሠርጎ ገብ የተገደለውን መባጽዮን ጃተኒን አስብ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በሕይወት ላለመኖር ከፈለግህ ኅሊናውን የሚጠቀም አማራና ትግሬ ወይም ኦሮሞና አማራ ሁን – በቃ፡፡ ወያኔ መሆንህ ካልተረጋገጠ አትላንቲክና ፓሲፊክም ግባ እንጂ የሚለቅህ የለም፡፡ እንኳንስ ተወልደህና ወደዚህች እርጉም መሬት መጥተህላቸው ገና በማሕጸን ውስጥ ሳለህም አሳድደው ያጠፉሃል – ኢትዮጵያዊ ለመሆን ካሰብህ፡፡

አንዳንዴ ደግሞ በሃሳብ ካልተጣጣምህ ፣ ትዕዛዝን እንደወረደ ካልፈጸምህ ወይ ካላስፈጸምህ፣ በሥልጣን ተቀናቃኝ ሆነህ ከተገኘህ በመሰል የወያኔ አለቆችም ልትንገዋለል ትችላለህ – ልክ እንደነብስናት አማረ፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ከኋላችን ወያኔ ሲያሳድደን፣ በኢኮኖሚ ደረጃ ኑሯችን ክፉኛ ሲያንገላታንና በገዛ ሀገራችን መኖር ሲያቅተን ባገኘነው መንገድ ሁሉ እየወጣን ለስደተኝነት የተዋራጅ ሕይወት፣ ለቤት አሽከርነትና ገረድነት፣ ለሀብታም ሰውነት የሰውነት ስፔርፓትነትም እንዳረጋለን – ይህን ዘመን አልፎ አይተነው መቼም – ያልሆንነው እኮ የለም፡፡ ዱሮ መጠጊያቸው በነበርንባቸው የዐረብ ሀገራት ዜጎች ቤት ውስጥ እየተቀጠርን ከመስኮትና ከፎቅ ላይ እየተወረወርን እናልቃለን – በዚህም ሺዎች የመኖር ተስፋቸው ጨልሞ ያለ ጧሪና ቀባሪ ይቀራሉ፡፡ በየቀኑ በገፍ እየተሰደድን ዓለምን እናጥለቀልቃለን – በዚህም ሌሎች እየሰለቹን መጥተዋል፤ መውደቂያ አጣን – ምን ይዋጠን? እንዲህ ስንል ደግሞ እነገዛኢ ‹ከሀገር ቤት የምትወጡት ልማታዊ መንግሥታችን ያረጋገጠላችሁ ድሎትና ምቾት እንዲሁም አይታችሁት የማታውቁት ዴሞክራሲ መጠኑ በዝቶባችሁ (an overdose of democracy) አንጎላችሁ ውስጥ ገብቶ ጥጋብ ስለሚያናፍላችሁ ነው!› እያሉ ያላግጡብናል – ራሳቸው የፖለቲካ ሳይሆን የኢኮኖሚ ስደተኞች ሆነው ሲያበቁ ለዚያውም፡፡ አንድ መሆን አቅቶንና ለወያኔ የከፋፍለህ ግዛ ወጥመዶች ተንበርክከን ለተሸናፊነት ስሜትም አጎብድደን የዓለም መዘባበቻ ሆነን ቀረን፡፡ ይህ የማይቆጨው ገልቱ ዜጋ ሁሉ በየዘርና በየሃማኖት ጎራ እየተቧደነ እርስ በርስ ሲቆራቆስ የወያኔን ዕድሜ ያራዝማል፤ ለተሸራጭ ሠርጎ ገቦች የጥቃት ዒላማ ምቹ በመሆንም የነጻነት ትግሉ መቅኖ አጥቶ እንዲቀር ያደርጋል፡፡ በዚህም ሳቢያ ስደቱና መከራው እንደተባባሰ ይቀጥላል – አሁን አዲስ አበባን ለሚያይ ታዛቢ ስደት የወያኔ ቁጥር አንድ የዕድገት ትልም ይመስል በየኤምባሲው – ፊጂና ጂቡቲ ሳይቀር – ዜጎች ተኮልኩለው ሲታዩ በሀገር ውስጥ ከቱባዎቹ ወያኔዎች በስተቀር ሌላ ሰው ባገር የሚቀር አይመስልም – ቢሳካለት ሁሉም ለመሄድ አቆብቁቧል – ወያኔና ጌቶቹ በዚህ ሊኮሩ ይገባል፤ አጸፋውን ከቻሉት ያለሙት የጥፋት ድግስ ሁሉ ለጊዜው መስመሩን ይዞላቸዋል፡፡ በዚህም አለ በዚያ የወያኔ ሸፍጠኛ አገዛዝ በቁስላችን እየገባ ዕድሜውን ማራዘሙን ቀጥሏል፡፡ የሞኞች ጠብ ለብልጦች ሠርግና ምላሽ ነውና እኛ ስንከናታ/ስንጃጃል እነሱ በብልጥነታቸው ግመልነታቸውን አስከብረዋል – እኛም ውሻነታችንን፡፡ አይክፋህ ወንድሜ – አይክፋሽ እህቴ፡፡ እምናገረው እውነትንና እውነትን ብቻ ነው፡፡ ሰው በወደደው ይቆርባልና እኛም የወደድነውን ወያኔዎችም የወደዱትን አግኝተናል፡፡ የአንዱ ሀዘን ለሌላው ሠርግ ነው፡፡ ‹ላሊበላ በሰው ተዝካር ይዳዳራል› እንዲሉ ወያኔዎች ይበልጡን እኛው ለኛው  ባፋጠንነው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ መምነሽነሻቸው ተዓምር ሳይሆን አስቀድሞ የተገመተና የሚጠበቅም ነበር፡፡ መጥኖ መደቆስ ጥንት ነበር ወዳጄ!

ልደቱን ያዬ በአባ መላ የአነጋገር ላህይ ልቡ አይሸፍትም ብል ምን እሆን ይሆን? አባ መላ ወይም ብርሃኑ ዳምጤ በተቃውሞው ጉራ ማለትም ጎራ ሰሞነኛ ቀሲስ የሆነ ይመስለኛል – ባለወርተራ፡፡ ከአንገት ሣይሆን ከአንጀት ያድርግልን እንጂ በዚህ ኹነት ደስታየ ወሰን የለውም፡፡ ራሱም ተናግሮታል – የተቃውሞው ጎራ የወያኔን ያህል ጎራ ለዋጭን አያንገላታም፡፡ አባ መላ በአዲሱ ሕይወቱ የተደሰተ ይመስላል፡፡ ከልደቱ አያሌው የማይጋራቸው የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ባሕርያት እንደማይኖሩት የማረጋገጥ ኃላፊነት የማን እንደሆነ ግን እስካሁንም ሆነ ወደፊት አላውቅም፡፡ ፖለቲካ በጣም መጥፎ ነው፡፡ ጨምላቃ ጨዋታ ነው – ማን እንደሆነ ዘነጋሁት እንጂ politics is a nasty/dirty game. ብሎ አያ ፖለቲካን ልክ ልኩን ነግሮታል አሉ፡፡ አዎ፣ እጅግ ከሚያስፈሩኝ የዓለም ዜጎች መካከል ፖለቲከኞች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ጨውና ስኳር ወይም እሬትና ማር አይደሉ አትቀምሷቸውና አትለዩዋቸው፡፡ በመልክ በቁመት አትፈርዷቸው፡፡ በአነጋገር እንደሆነ ያነሆልላሉ፡፡ የማያነሆልል ንግግር የማያውቅ እንዲያውም ከናካቴው ወደፖለቲካ አይገባም፡፡ እንደሌባውና አጭበርባሪው ልደቱ አያሌው ያለ ሣተናና ሞጭላፋ ዱርዬ ማር በተቀባ ምላሱ የሕዝብን ሥነ ልቦና ተመርኩዞና ቦጥቡጦ፣ የወያኔን ገንዘብ ተንጠላጥሎና ድብቅ አጀንዳውን አሸምቆ ይዞ በተቃውሞው ጎራ ትልቅ ደረጃ ከደረሰ በኋላ የልቡን አድርሶ በ‹ሚሽን አኮምፕሊሽድ› ፖለቲካዊ ዕቃ ዕቃ ጨዋታ ሕዝብን ጨረቃ ላይ አስቀምጦ ወደተዘጋጀለት ቦታ የሚሄድ ወራዳ – እደግመዋለሁ – ወራዳ ዜጋ – አለ፡፡ ካለበት የተጋባበት ነው፡፡ መሌ ገሞራው ይህችን ቃል ይወዳት ነበር – ‹ወራዳ›ን፡፡ እኔን! – በየሄደበት እንዳሞሌ ጨው ራሱ እንደተዋረደና እንደቀለለ ጥርኝ አፈር ሆነ፡፡ በዚያች ያማሪካ ስብሰባ ላይ ያ ልጅ በመብረቃዊ ድምጽ ሲያምባርቅበት የሆነው መሆን አሁን ድረስ ይታየኛል፡፡ አየ የመጥፎ ሰው መጨረሻ!

ጥሎብኝ አባ መላን እወደዋለሁ – የምወደው ሁሉ እንደሚወደኝ የማረጋግጥበት ዘዴ በማጣቴ ግና ዘወትር እንደተጨነቅሁ አለሁ፡፡ ማን ናት ያቺ – ባል ያልነበራት አንዲት ሴት – ‹ገንዘብ ያለው ያግባሽ ወይንስ አፍ ያለው?› ተብላ ብትጠየቅ አሉ – ‹አፍ ያለው ያግባኝ!› ብላ መለሰች ይባላል፡፡ ግራ እየገባኝ ነው ወገኖቼ፡፡ ማመን አይገደኝም – እንዲያውም ካለማመን ማመን ሳይሻል አይቀርም – ሥነ ቃላችን “ያልጠረጠረ ተመነጠረ” እያለ ሆድ ያስብሳል እንጂ፡፡ ግን ማንን መቼና እንዴት ማመን እንደሚገባኝ አለማወቄ አንጎሌን እያሳመመኝ ነው፡፡ ሰዎችን እንዴት ነው የምናምናቸው? በአነጋገር ችሎታቸው? በተግባራቸው? በዘራቸው? በቀለማቸው? በሃይማኖታቸው? በትምህርት ደረጃቸው? በሥልጣናቸው? በተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው? በአለባበሳቸው? በዝናቸው? በጨዋታና ቀልድ ዐዋቂነታቸው? በገንዘብና በሀብታቸው? በደም ምርመራ ውጤታቸው? በጎጣቸው? በእውኑ በምን እንመናቸው? ኣኣኣ… ትልቅ ችግር!!

አባ መላ ሲናገር ደስ ይለኛል – ወያኔን ከከዳ ወዲህ ነው ታዲያ፤ ከዚያ በፊት አላውቀውም – ማወቅ ከነበረብኝ ይቅርታ፡፡ ብዙ የንግግር ዐዋቂ ሰዎችን ዐውቃለሁ፡፡ ኢንጂኔር ኃይሉ ሻውል በኢትኦጵ መጽሔት ላይ በጣም ማራኪ ቃለ ምልልስ አድርገው ማንበቤ ትዝ ይለኛል – እንደተናገሩት ሆነው ስለመገኘታቸው ግን ጊዜው ስለራቀም ሊሆን ይችላል ትዝ አልልህ አለኝ፤ አብርሃም ያዬህንም በንግግር ለዛውና ጤፍ በሚቆላ ምላሱ በጣም እወደው ነበር፡፡ አሁን የት እንዳለም አላውቅም፤ ነገር ግን ለገዛ የታዋቂነት ዝናው አምላኪ ሆኖ ከቅድስት ቢዮንሴና ከ‹ብፁዕ አባታችን› ቀጥሎ በዐርባ ሰባተኛነት ታቦት ይቀረጽልኝ እያለ ባስቸገረን የዝነኝነት ልክፍት ተጠምዶ የደረጃ መዋዠቅ እንዳሳየና ከአንደኛ ዲቪዚዮን ይልቅ የወራጅ ቀጣናን መርጦ መቀላቀሉን ቀደም ሲል ሰምቻለሁ፡፡ የሆነው ሆኖ ማንም ምን ይናገር የኔ ግላዊ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ግን ከዚያን ጊዜው በመቶዎች ዕጥፍ አድጎ ይሄውና ዛሬ ካሉት በታች ከሌሉትም በታች ሆኛለሁ፡፡ የቅርቡን ልደቱዬንም በሚገባ አስታውሳለሁ፡፡ ‹እንደበርናባስ ታስሮልኛል፤ እንደክርስቶስም ተገርፎልኛል፤ ተጠምቶልኛል፤ በሚጠሉት ተጠልቶልኛል…› በመጨረሻም ብዙ ሚሊዮን ብር ከቱጃሩ ሰውዬ ‹ተቦጭቆለት› – እንዳነበብኩትና እንደገመትኩት – ሊማርልኝና በዶክትሬቱ ደግሞ ተመልሶ “ዶክተር ልደቱ አያሌው፣ የፌዴራላዊት ብጥስጣሽ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ራስ-ገዝና ራሰ-አገዝ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትርና የዕድሜ ልክ ፕሬዝደንት እንዲሁም የጦር ኃይሎች ኤታ ማዦር የይስሙላ ሹምና የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረትና አንድነት ድርጅት ሊቀ መንበር፣ የሕወሓት የክብር አባልና የብኣዴን ነባር ሥውር ስፍ፣ የጽላትና የንዋየ ቅድሳት ሽያጭ አስተባባሪ ኮሚቴ ሊቀ መንበር … “ (ያኔ ሳላምን አሁን ገና አመንኩ!) እየተባለ  በወያኔያዊ ሠርጎ ገብነት በወጣትነቱ ያመሳትን ሀገር በወመሽነቱ ደግሞ ሊያምሳት እየተዘጋጀልኝ ነው ( ወመሽ – ወጣት መሳይ ሽማግሌ – ማለት ነው ወንድሜ)፡፡ ይህ ሸለምጥማጥ በጣፋጭ አንደበቱ ከሲሳይ አጌናና ጥቂት እሱን መሰል ጥንቁቅ ዜጎች በስተቀር 80 ሚሊዮኑን ሕዝብ እንዲያ ያነሆለለ እግዜር ካልጠበቀን በስተቀር አባ መላን የመሰለማ እንዴቱን ያህል አያነሆልለን? ይህን የምለው ለአባ መላ ትልቅ የቤት ሥራ ለመስጠት አስቤ እንጂ እንደልደቱ ወይም እንደሌሎች ልደቱን መሰል ብሽቅ ዜጎች ሊያታልለን ከጠላት መንደር ተልኮብናል ለማለት ፈልጌ አይደለም – ቤዛይቴን፡፡ ሥጋቴንና ጥርጣሬየን በጨዋ ደንብ የማቅረብ መብት ግን አለኝ፡፡ ለነገሩ አሁን ሰዓቱ ለአሥራ ሁለት ምናምን ጉዳይ በሆነበት ሁኔታ ማንም ማንንም ሊያታልል የሚችልበት ዕድል ያለ አይመስለኝም – ሁሉም ‹ባኗል› እህቴ፡፡ ትንሽ ነው እምትይው ሊስትሮው ወይም ድንጋይ ፈላጩ ሁሉን ያውቃል፡፡ ለነገሩ ባለዲግሪ ኮብልስቶን አንጣፊ ሞልቶም አይደል? አይ መንጌ – ‹የት እንደምታመሹ፣ ምን እንደምትበሉና እንደምትጠጡ… ብታምኑም ባታምኑም ሕዝቡ ያውቃል› ነበር አይደል ያላቸው ሚኒስትሮቹን ሰብስቦ? አዎ፣ ወያኔም ሁሉም ነገር ተባኖበታል – በአራዳ ቋንቋ ተነቅቶበታል ለማለት ነው፡፡ ቀሪው ሌላ ጉዳይ ነው – ሌላ፡፡

በትግርኛ አንዲት ቆንጆ አባባል አለች፡፡ “ዝአኽለን ጥኽነን በዓል ማርያም ትብላ” ትሰኛለች፡፡ እንዴት እንደምወዳት አትጠይቁኝ፡፡ በውርስ ትርጉም “የሚበቃትን ያህል ከፈጨች በኋላ ‹ውይ! ረስቼው፤ ለካንስ ዛሬ ማርያም ናት!› ትላለች” እንደማለት ነው፡፡ ሰዎች ነን፡፡ ሰዎች ከባድ ፍጡራን ነን፡፤ ውሻ ከሰው ይበልጣል፡፡ ትንኝ ከሰው በእጅጉ የተሻለ ፍጡር ነው፡፡ ውሻና ትንኝ ተፈጥሯቸውን ስተው በሣቅና በቃላት እያታለሉ የልባቸው እስኪደርስ አይሸምቁም፡፡ ፍቅራቸውም ጥላቻቸውም፣ ርቀታቸውም ቅርበታቸውም ግልጥ ነው፡፡ ድብቅ ባሕርይ የላቸውም፡፡ ሰው ግን አሳቻ ሥፍራና ምቹ ሁኔታ እንዲሁም ምቹ ጊዜ እስኪያገኝ አንተን ተመሳስሎ በመቆየት አደባይቶ የሚጥልህ አካይስት ፍጡር ነው፡፡ ‹ሰውን ከመምራት ወይም ከማስተዳደር  በአውላላ ሜዳና በዳገት ላይ የተበተኑ አንድ ሺህ ፍየሎችን መጠበቅ ይቀላል› እያልኩ ጓደኞቼ ፊት ዘወትርና እንዳስፈላጊነቱ የምናገረው ወድጄ አይደለም፡፡ እባብን ያዬ በልጥ ቢበረይ፣ ያበራሽን ጠባሳ ያዬ በእሳት ባይቀልድ ማንም ሊፈርድበት አይገባም፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በመታለልና በመሸወድ ከዓለም እንዲያውም ከዚያ ባለፈ እንደኛ ሳንሆን አንቀርም – ወዳማርኛ የተመለሰው “የመጀመሪያው ቂጣ ቢያርር ሁለተኛው አያርም” የምንለው የሃድይኛው ተረታችን በኛ ዘንድ በጭራሽ አይሠራም – ሁሉም እንዳረረብን እንገኛለንና፡፡ ብዙ ጊዜ ብዙ ሰዎች አሞኝተውናል፤ ልባችንን በልተው በሞራና በአኞ እየተኩ ባዶ አስቀርተውናል፤ እምነታችንን ሸርሽረውታል፡፡ ከአሁን በኋላ ማንንም እንዳናምን እየተደረግን ያለነው አለማመን ጠባያችን ሆኖ ተደንግጎ ሳይሆን ማመናችን ገደል እየከተተን ለበርካታ ዓመታት ስለተጎዳንበት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር አባ መላ ብዙ የሚጠብቀው አለና ቀን ከሌት የሚለፋበት፣ ባለፉት ሰባት ዓመታት ያስከፋውን ወገን የሚክስበት አስቸጋሪ ጊዜ ከፊቱ ተደቅኗል ላለማለት አልፈልግም፡፡ እሱን መሰሎችን ግዴለም እንመናቸው – ግን ማመናችን ጉድ እንዳይሠራን መቀየጃ እናብጅለት፡፡ (እርግጥ ነው – ጎራ ለዋጮች ከልባቸው ከመጡልን የጨዋታን ሕግ በመቀየር ለድል እስከማብቃት የሚደርስ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ እረዳለሁ – I mean, we may be fortunate to get gamechangers from among those Abbamelas who can shorten the time of our victory, if they honestly dedicate their entierity to the freedom fighting.)፡፡ በሌላ አቅጣጫ አዲስ ተጠማቂዎችም ወደተቃውሞው ጎራ ሲመጡ ‹የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ› እንደሚባለው እንዳይሆን ከፓትርያርኩ የበለጡ አጥባቂ ክርስቲያን  ላለመሆንና ሰው ዐይን ውስጥ እንዳይገቡ ጠንቀቅ ቢሉ ለነሱም ጥሩ ነው – ‹የሰው ዐይን ድንጋይ ይሰብራል› ይባላል፡፡ ትንሽ ዕውቀት መቼም መጥፎ ናት ‘more catholic than the Pope’ ሲባል እኮ ተሰምቶ ነው ፓትርያርክ ቅብጥርስ የምል፡፡ ይህ ነገር በዝርዝር ቢወራ አያልቅም ወገኖቼ፡፡ መታመን አስቸጋሪ ነው – ይሁንና ከማመን የበለጠ አስቸጋሪ እንደማይሆን እገምታለሁ፡፡ ምክንያቱም በማመንና ባለመታመን መካከል የሚወለደው ነገር ይበልጥ የሚጎዳው ታማኙን ሳይሆን አማኙን ነውና፡፡ እኔ ምን ዐውቃለሁ – ስሜት ነው፡፡

መድረኮችም ከዚህ አንጻር ብዙ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ‹ፊት የበቀለ ጆሮ እያለ ኋላ የመጣ ቀንድ በለጠ› እንዲሉ እንዳይሆን ወዶገቦችን ጥንቃቄ በተሞላት ሁኔታ ሊያስተናግዱ እንደሚገባቸው ማሳሰብ ምቀኝነት አይመስለኝም፤ እንደዚያ ሊታሰብም አይገባውም፡፡ ሹመትና መታመን አቀያያሚ ናቸውና በነዚህ ሁለት ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ኑባሬዎች ረገድ መጠንቀቅ መጥፎ አይደለም፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ላይ ብዙ ተቃውሞ በርክቶ የነበረው ማንን ከማን ለይተው መሾምና መሸለም እንደነበረባቸው እመለየቱ ላይ መጠነኛ ችግር ስለነበረባቸው ነበር ይባላል – በዘመኑ የአማካሪነትን ዕድል ባላገኝም እኔም ይህ ስሜት ነበረኝ፡፡ እውነት ነው – ለነጻነት የተዋጉና ደማቸውን ያፈሰሱ ችላ ተብለው ጣሊያንን በባንዳነትና በሹምባሽነት ያገለገሉ አሰለጥ ዜጎች በአፍ ጂዶኣቸው ንጉሡን ጠርበው በመጣላቸው ምክንያት ተሹመው ነበር መባሉ እውነት ከሆነ ችግር አልነበረም ማለት አይቻልም፤ እንዲህ የምለው ለጥንቃቄ ያህል እንጂ አሁንም ልድገመው በአባ መላ ወይም በመሰል ወዶገቦች ላይ ምቀኝነት ይዞኝ አይደለም፡፡ እውነቴን ነው – ‹አገባሻለሁ ያለ ላያገባሽ ከ(ሁነኛ) ባልሽ ሆድ አትባባሽ› ይባላልና ወዶገብም ወዶ አልገብም ሁሉም በየፊናው ራሱን ቢመረምር ከተደጋጋሚ ጸጸትና ጥቃት እንጠበቃለን፡፡ የሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ትዝብት ያስከትላልና ፍቅርንም ሆነ ጥላቻን በገደብና በመለኪያ ብናደርገው ከኋለኛ ነዳማ ወይም ቁጭት ነጻ እንሆናለን፡፡ ካጠፋሁ እታረማለሁ – ኧረ የምን መታረም ብቻ – ዝም ልልም እችላለሁ፡፡ እንዴ፣ በዚህ ነገር እኮ ብዙ ተሰቃየን!

ወደተቃውሞው ጎራ የሚመጡልን ወገኖቻችን ደግሞ ከልብ እንዲመጡልን መጸለይ ይገባናል፡፡ አመጣጣቸው ምክንያታዊ እንጂ ግብታዊ እንዳይሆንም እነሱም እኛም ሁላችንም መጸለይ አለብን፡፡ ሲመጡ መሠረታዊ የአስተሳሰብና የአመለካከት ልዩነት ካልኖራቸውና በተራ ቂምና በተራ ጠብ ከሆነ ወይንም የአሁንና የወደፊት የኃይል ሚዛን አሰላለፍን በታሳቢነት በያዘ መልኩ ለሥልታዊ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ከሆነ ተጎጂዎቹ ይበልጡን እኛው ጭቁኖቹ ነን – እነሱ አይጎዱም የሚል እሳቤ የለኝም፤ እንክትክት ብለው ይጎዳሉ፡፡ የጉዳታቸው መጠን እንዲያውም ከመጀመሪያው በባሰ ይሆንና የቀዳሚ ስህተታቸውን ዕዳ ሁሉ ደርበው የሚከፍሉበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል – ስለዚህ የበለጠ ተጠንቃቂዎች እነሱ ሊሆኑ እንደሚገባ እረዳለሁ – እንደ አካሄድ፡፡

የማንወሻሽበት አንድ ነገር አባ መላን እንድጠይቅ ቢፈቀድልኝ ደስ ይለኛል – መለስ ከሞተ በኋላ ወደኅሊናህ ለመመለስ ምን አነሳሳህ?(የተመለስከው ከመለስ ሞት በፊት ከሆነ ግን ትልቅ ይቅርታ!) ሳይሞት ብትመለስ አይቻልም ነበር ወይ? ባክህ እንግሊዝኛ አማረኝ – well, መቼም ቢሆን መመለሱ ምንም ማለት አይደለም ይሆናል፡፡ ግን እስከምትመለስበት ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስቃይና የወያኔ ጀብደኝነት እንዴት ሳይታይህ ቀረ? ምን አሳወረህ – ጥቅም? ዝና? ተሰሚነት አጣለሁ የሚል ሥነ ልቦናዊ ችግር? የሕዝቡ ከቦታ ቦታ ፍልሰትና ወደውጪ ስደት፣ ሞት፣ እሥራት፣ የአንድ ዘር ፍጹማዊ የበላይነት፣ የሀገሪቱ በጎጥና በቋንቋ መሸንሸን፣ በአማራው ላይ የታወጀው የዘር ፍጅት፣ የጥቂቶች አለቅጥ መክበር፣ የብዙኃን አስከፊ ድህነት ውስጥ መግባት፣ የድንበር እየተቆረሰ ለባዕዳን መሸጥ፣ የገበሬው መፈናቀልና መሬቱ ለውጭ ባለሀብቶች መሰጠት፣ … በጥቅሉ የወያኔ በኢትዮጵያ ላይ ጢባጢቤ መጫወትና እንደልብ መፈንጠዝ ሳይከሰትልህ እስከመለስ ሞት ድረስ የመቆየትህ ምሥጢር በእውነቱ ምን ይሆን? እማምላክን – አባ መላን መጠራጠሬ አይደለም፤ ግን አንዳች ነገር ጠይቀው ጠይቀው አለኝ፡፡ አንድ ክፉ ነገር እስኪገባን ስንት ጊዜ መፍጀት ይኖርበት ይሆን? – ‹ረሀብ ስንት ቀን ይፈጃል – ነበር ያለው ጋሼ ፀጋዬ ገ/መ ዋቀዮ? አሁንስ የተመለስከው በእውነት ነውን? የብዙ ሰው ጥያቄ ስለሆነ ሳትንቀንና በምንምነትህ ሳትታበይ ብትመልስ(ልን/ኝ) መልካምና ወቅታዊም ነው – ሰውን አክባሪነትህንም ያመለክታል፡፡ አለበለዚያ ኅሊናችን የማያርፍልን ድንጉጥ ዜጎች እንጎዳብሃለን፡፡ እንደምታስታውሰው ክርስቶስ በምሳሌው ሲናገር መቶ በጎች ያሉት ሰው አንዷ ብትጠፋበትና … ራስህ ጨርሰው ወንድማለም፡፡ አዎ፣ አንዱ ለጠቅላላው ብቻ ሣይሆን ለግለሰብም መጨነቅ አለበት፡፡ ለተጨባጩ ግለሰብ ካልተጨነቅን ለረቂቁ ጥቅል ማኅበረሰባዊ ሕይወት እንጨነቃለን ማለት ውሸትና ታይታዊ ነው፡፡ ‹አጠገብህ ያለውን ወንድምህን የማትወድ ሆነህ ሳለ በመልክ በቁመት የማታየውንና የሩቁን እግዚአብሔርን እወደዋለሁ ብትል ከትዝብት በስተቀር ምን ታተርፋለህ?› የተባለውን ቁም ነገር እናስብ፡፡ እኔን በእኔነቴ የማይወደኝ ማንም ቢሆን ሀገሬንና ሕዝቧን አይወድም – አራት ነትብ፡፡ እኔን ሳይወድ ሀገርና ሕዝብ እወዳለሁ የሚል ሀሰተኛ ነው፡፡

የፈሰሰ አይታፈስም፡፡ አንዳንድ መያዣ መጨበጫ የሌላቸው ‹ቁም ነገሮችን› የወረወርኩ ይመስለኛል፡፡ ሁሉም ነገር ደግሞ በአንድ ቀን አያልቅም፡፡ ያስከፋሁት ወገን ካለ ይቅርታ የምጠይቀው ከልብ ነው – ባለፉ ደብዳቤዎቼ ከኃይሌ ገ/ሥላሤና ከዚያች መልቲ ጀማነሽ ሶሎሞን ጋር ‹ተጣልቻለሁ›፤ ዛሬ ደግሞ ከማን ጋር እንደተጣላሁ አላውቅም – የልደቱ ከጠብ አይቆጠርም – እስስትና ዓሣማ እንጂ ሰው አይደለምና፡፡ በመሰለህ ጊዜ አስተሳሰብህን ትለውጣለህ፤ በመሰለህ ጊዜ የመሰለህን ትናገራለህ ወይ ትጽፋለህ፤ ሲርብህ ካገኘህ ትበላለህ፤ እንቅልፍህ ሲመጣ ቦታ ካለህ ትተኛለህ፡፡ በቃ፡፡ ለምን አስተሳሰብህን ለወጥህ፤ ለምን ተናገርህ ወይ ጻፍህ፤ ለምን በላህ፤ ለምን ተኛህ … አይባልም፡፡ ብዙ ነገሮች የተፈጥሮ ሂደቶች ናቸው፡፡ መልስ መስጠት የሚያስፈልግህ ነገር ከገጠመህ እንዳመጣጡ ልትመልስ ትሞክራለህ፤ ሌሎች ያላቸው የቋንቋ ችሎታ አንተም ጋ በብዛት ስላለ በንዴት ከመንተክተክና በምናብ የሸሚዝ እጅጌህን ከመሰብሰብ ይልቅ ቋንቋህን በመጠቀም ጠላትህን በቃላት ‹ማደባየት› ትችላለህ፡፡ ግን እውነት ትኑርህ – ትንሽም ብትሆን የእውነትን ዘገር ካልያዝክ በመጨረሻው ወዳቂ ትሆናለህ – ምናልባት ውዳቂም፡፡ ‹ለምን ተነካሁ፤ ምን ሲባል ተደፈርኩ›ም አትበል፡፡ ይህን ለማለት አንተ ማን ነህ? በምድር ጠቅላላ የጊዜ ሥሌት መሠረት የአንተ ምድራዊ ዕድሜ ቢታይ ከአንዲት ቅማል የማትሻል መሬታዊ ገጸ ባሕርይ መሆንህን አትርሳ – የዕድሜህ አንጻራዊ መጠን ከተወርዋሪ ኮከብ የሰብኣዊ ዐይን ዕይታ የሚዘል አለመሆኑን ተገንዘብ፤ ይህችን ቅጽበታዊ ዕድሜያችንን ደግሞ ለመጥላትና ለመቀያየም ሣይሆን ለመዋደድና ለመፈቃቀር ብናውላት የማይሞት ስምና ዝናን ከመገንባት አንጻር ብዙ እንጠቀማለን፡፡ ዛሬ አለህ ወይም ያለህ ይመስልሃል – ከአፍታ በኋላ ግን እዚህ አጠገብህ አይተኸው በቅጽበት እንደሚጠፋ ጉም ነህና ራስህን ብዙም አክብደህ አትየው፡፡ ሁሉም ያልፋል – አንተም፡፡ ዘና በልና ዓለምን ቃኛት፡፡ የልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ልጅ ንጉሥ ሶሎሞን እንዳለው ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለምና በሚሆነው ሁሉ አለልክ አትደነቅ፡፡

 

AAAAAAAAAA

 

መብራት ጠፍቶ ከመጣ ከ8 ሰዓት በኋላ የታከለ ሃሳብ፡፡ ሰበር ዜና፡- ወያኔ አደጋ ለማድረስ እንዳሰበ ፍንጭ ሰጠ፡፡

የደሴዋ ዕብድ ‹የተነበየችው› ትዝ አለኝ፡፡ ‹ነገ ቤት ይቃጠላል!› አለች – ያቺው የደሴዋ ዕብድ፡፡ በማግሥቱ ብዙ ቤቶች ተቃጠሉ፡፡ ሁኔታው ሲመረመር ቤቶቹን ያቃጠለችው ለካንስ ያቺ እንደትናንትና ከተማውን እየዞረች ‹ነገ ቤት ይቃጠላል!› ያለችዋ ዕብድ ነበረች፡፡ ሴትዮዋ እንደወያኔ ዐውቆ አበድ ስለነበረች ያልተጠበቀ ኪሣራ አስከተለች – ሰውንም አስገረመች፡፡ የቆዬ እውነተኛ ታሪክ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ወያኔ ዛሬ እንዳስታወቀው በመጪው ዐርብ ‹አሸባሪዎች› አደጋ ለማድረስ ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል – ‹ወፍ ነግራዋለች› ማለት ነው፡፡ ‹የሽብር ጥቃቱን መታቀድ› ወያኔ በሚገባ ዐውቋል – ‹አሸባሪዎቹ› ለልብ ዐውቃው ወያኔ አማክረውትም ሊሆን ይችላል፡፡ ስላወቀም ከ30 ለሚበልጡ ኤምባሲዎች አስታውቋል – ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በማሳሰብ ጭምር፡፡ ወያኔን ‹ሂድና ሌላህን ብላ› በሉት እባካችሁን፡፡ እንደወያኔ ጀዝባና ደንቆሮ በዓለም ላይ የለም፡፡ ስንትና ስንት የከሸፉ ድራማዎችን የፈበረከው ወያኔ ሰሞኑን ለሚፈጥረው የሽብር ተግባር – ሊያውም ‹ዕድል ገጥሞት› ሁኔታዎች የሚመቻቹለት ሆኖ አደጋው የሚፈጠር ከሆነ – ሙስሊሞችን ተጠያቂ ለማድረግ የተዘጋጀ ይመስላል፤ ምሥኪን ሙስሊሞች – መንግሥትም ስማቸውን የሚጠቀም ሌላ ጅራቱን ውጭ ያሳደረ አክራሪ አካልም በመሀል አጣብቀው ሊያንገላቷቸው አቅደው ከሆነ ፈጣሪ ለንጹሓን ዜጎች ሲል ተራዳኢነቱን ቀድሞ ያሳየን፤ ዓለም የደረሰችበት የጭካኔ ትርዒት ትዕይንት አስከፊ በመሆኑ ብዙ ነገሮችን መገመትና መጠርጠር ይቻላል፡፡ እግዜር ባይጠብቀንና እንደወያኔ ተንኳሽነት ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያችን እስካሁን ከኢራቅ፣ አፍጋኒስታንና… ጎን ስሟ በየቀኑ የሚዲያዎች አፍ ማሟሻ በሆነ ነበር፡፡

የወያኔው ሞግዚት ታላቋ ሀገር አለኝ በምትለው መረጃ መሠረት የኤምባሲ ሠራተኞቿን ከ19 እስላማዊ ሀገሮች በማስወጣት ላይ እንደሆነች በዚሁ ሣምንት ተገልጧል፡፡ ጅሉ ወያኔም የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ወደዚሁ ዓለማቀፍ ሁኔታ በመጎተት ራሱ የሚፈጥረውን የሽብር ተግባር ከዓለማቀፉ ‹የሽብር ጥንስስ› ጋር ለማመሳሰል እየሞከረ ነው፡፡ ይቀናው ይሆን? የሁለት ቀን ዕድሜ ከሰጠን የምናየው ይሆናል፡፡ የገበያ ግርግር ለቀጣፊ ያመቻልና የታላቋን ሀገር የልብ ትርታ ለመግዛት ወያኔ በዕቅዱ ከገፋበት አደጋ አለው፡፡ እሱ ይሁነን፡፡

ለማንኛውም ወያኔ እንደለመደው ራሱ አሸብሮ ንጹሓን ዜጎችን በሽብርተኝነት በመክሰስ የጫካ ፍርዱን ሊያስተላልፍባቸው እንዳቆበቆበ ተረድተን የሚሆነውን በንቃት መከታተላችንን እንቀጥላለን፡፡ ሴትዮዋ ‹ወንዶቹ እንዳሳደሩን› እንዳለችው እኛም ወያኔዎቹ እንዳሳደሩን የመጪውን ዐርብ ሁኔታ ልናይ በጉጉት እየተጠባበቅን አለን፡፡ መልካም ዐርብ፡፡

ግን ግን እስላምና አማራ እየተባባልን የወያኔን ዕድሜ የማቱሣላን ያህል ማስረዘማችን እኔን መሰሉን ሞኝ ፍጡር ሳያስገርም እንዳልቀረ ሳልጠቁም መቅረት አልፈልግም፡፡ በዚህ አንገብጋቢ ወቅታዊ ጉዳይ ጥቂት ምክሮችን ብሰነዝር አልጠላም፡፡ እናም የወቅቱ ፋሽን በሆነው ሙስሊሞች ዐርብ፣ ዐርብ  ወያኔን በ‹ጩኸት›ና በ‹መፈክር› ‹ተዋጉት‹፤ ካቶሊክና ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ደግሞ ዕሑድ፣ ዕሑድ በ‹አንተ ያመጣኸውን አንተው መልሰው› የኪሪያላይሶን ጸሎት ‹ተፋለሙት›፤ ፕሮቴስታንቶች ቅዳሜ፣ ቅዳሜ በመንታ በመንታ እያነባችሁ ወያኔን ተግትጉት፣ ባለዛሮችና ባለአውሊያዎች በከሚስና በከድር ሁሴን የሐሙስና የቅዳሜ፣ የረቡዕ አብዶዬ ጅላሌና የማክሰኞ ኑራሁሴን መጀን በናንተ የአዶከርቤ ወዳጃ ፈጣሪ የምትሉትን ጠዝጥዙት፣ ኢአማኒያንና ጥዩር ምሁራን በብሔረ ብርጭቆ የክርክርና የፍልስፍና ቱማታ ውስጥ በትጋት በመሣተፍ በሞኝ አንግሥ የውጭና የሀገር ውስጥ ቁንድፍቶች(ኪል ሚ ኲክ) ተጀቡናችሁ የ‹ቢሆን ኖሮ› ሎጂካችሁን አሞስኩ፣… ኦሮሞዎች በመሪ የመታገያ ድርጅቶቻችሁ በነኦነግ፣ ኦብነግ፣ኦብኮ፣ኦፌዴን፣ኦህዴድ፣ ኦልማ፣ ኦስሌድ፣ኦቅሌድ… አማካይነት ወያኔን ሸጥሽጡት፣ ወዲታት ተጋሩ በአረና፣ በቲፒዲኤም፣ በትልማ፣ በኤፈርት…ሥር ተደራጅታችሁ ወያኔን ፈስፍሱት፣ አማሮችና ከኢትዮጵያ በስተቀር ጎጣዊ መጠሪያ አድራሻ  የሌላችሁ ምሥኪኖች ደግሞ በአርበኞች ግምባር፣ በኢሕአሠ፣ በአብግን፣ በኢሕዲን፣ በአድብን፣ በብአዴን፣ በበረከት ስምዖን፣ በኅላዌ ዮሴፍ፣ በአያሌው ጎበዜ፣ በአበጀ በለው፣ በአልማ፣ በወልማ፣ በጎልማ፣ በሸልማ፣ በደልማ፣… ሥር እየተደራጃችሁ ወያኔን መቆሚያ መቀመጫ አሳጡት፤ ጉራጌዎችና ሥልጢዎች በጉሕዲግ፣ በጉልዲግ፣ በጉምዲክ፣… ሥር እየተዋቀራችሁ ይህን ከፋፋይ ዘረኛ የወያኔ ‹መንግሥት› መተንፈሻ አሳጡት… ያኔ ምን አለ በሉኝ ወያኔ ድራሹ ይጠፋል፤ የኢትዮጵያ ትንሣኤም ይበሠራል፡፡

በቃ – ቢገባንም ባይገባንም አንድ ነገር እናስታውስ፡፡ በአንድ ጊዜ አንድም መቶም እየሆን ወያኔን አናሸንፍም ብቻ ሣይሆን ዝምቡን እሽ ማለት አንችልም፤ ይህችን ስለሚያውቁ በልዩነታችን የአፍዝ አደንግዛዊ ኃይል በመሳለቅ አውዳሚ አገዛዛቸውን እስከዓለም ፍጻሜ ለማቆየት ሁለ ገብ ጥረታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ዋና ንድፍ አውጪው ሰውዬኣቸው እንኳን ሞቶ አስደናቂው የኛ ቂልነት በመቀጠሉ ምክንያት ብቻ ይሄውና ካለግልጽ አመራር ሀገሪቱን እያበሻቀጧት በውር ድንብር እስካሁን ይዘዋታል – የሚገርም ልዩ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው፡፡ ዋናው መሃንዲስ ከሞተ በኋላ በነርሱ ግዛት ለአንዲትም ቀን ልታድር የማይገባት ሥልጣን በተቃውሞው ጎራ መልፈስፈስና አለመተማመን እንዲሁም በአስተማማኝ ሁኔታ በተለይ በሀገር ውስጥ አለመደራጀት ምክንያት በዚህን ዓመት ሐምሌ ሰባት አንድ ዓመቷን ደፍና ሁለተኛዋን ያዘች – ከነርሱው ጋር እንደተንገላታች፡፡ ለአገዛዛቸው ምቹ ሆነን እስከተገኘን ድረስ ደግሞ በቅጡ ተደራጅተው ሌላ መለስ እስኪፈጥሩ ድረስና ከዚያም ባለፈ ለመቶዎች ዓመታት ይቺው በሸርሙጣነት የምትመሰል ሥልጣን ከነርሱው ጋር እንዳለች እስመለዓለም ትኖራለች፡፡ አንድና አንድ ብቻ ስንሆን ወያኔን እናሸንፋለን – አንድና አንድነት ደግሞ በግድ የሃሳብ ተመሳሳይነትን፣ የአመለካከት ፍጹማዊ መሳነትን አይጠይቅም – አንድነት የነጻነት ትግልን አስፈላጊነት ያጠይቃል እንጂ የሃሳብ ግዳዊ ቁርኝትን መሠረት አያደርግም፡፡ በነጻነት አስፈላጊነትና በሀገር ሉዓላዊነት አንድና አንድ ለመሆን ግን እንደገና መፈጠር የሚኖርብን ይመስለኛል – እርግጥ ነው በ‹ይመስለኛል› ተስፋ አንቆርጥም፤ አስተሳሰብን መቃኘትና አመለካከትን ማስተካከል ይቻላልና፡፡ በአካል ሳይሆን በአስተሳሰብ እንደገና ለመፈጠር ፈቃደኛ የሚሆን ማን ነው? ይህን እግዜር ይወቅ፡፡ ሰላም ለኢትዮጵያና ሕዝቧ! ስደት ወደ ኢትዮጵያ የሚሆንበት ዘመን …

 

እስከማዕዜኑ እግዚኦ ትረስዐኒ ለግሙራ፤

እስከማዕዜኑ ትመይጥ ገጸከ እምኔየ፡፡

እስከማዕዜኑ አነብር ኀዘነ ውስተ ነፍስየ፡፡

ወትጼዕረኒ ልብየ ኵሎ አሚረ፡፡

እስከማዕዜኑ ይትዔበዩ ጸላእትየ ላዕሌየ፡፡

ነጽረኒ ወስምዐኒ እግዚኦ አምላኪየ፡፡

አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢይኑማ ለመዊት፡፡

ወከመ ኢይበሉኒ ጸላእትየ ሞዕናሁ፡፡

ወእለሰ ይሣቅዩኒ ይትፌስሑ ለእመ ተሀውኩ፡፡

ወአንሰ በምሕረትከ ተወከልኩ፡፡

ይትፌሥሐኒ ልብየ በአድኅኖትከ፡፡

እሴብሖ ለእግዚአብሔር ዘረድአኒ፡፡

ወእዜምር ለስመ እግዚአብሔር ልዑል፡፡

የዳዊት መዝሙር 12

↧

በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ወያኔ ያካሄደውን ጭፍጨፋ ኢሕአፓ ያወግዛል

$
0
0

Download (PDF, 148KB)

<script type=”text/javascript”><!–
google_ad_client = “ca-pub-8555893555560582″;
/* Add 468 x 60 – Banner */
google_ad_slot = “5735223818″;
google_ad_width = 468;
google_ad_height = 60;
//–>
</script>
<script type=”text/javascript”
src=”http://pagead2.googlesyndication.com/pagead/show_ads.js”>
</script>

↧

የመላው ኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦህዴድ የኦሮሞን ህዝብ ችግር አይፈታም አለ

$
0
0
diriba-kuma-
መስከረም አያሌው
የኦሮሚያ ክልልን የሚያስተዳድረው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት በኃይል ላይ የተመረኮዘ መንገድ መጠቀሙ የኦሮሞን ህዝብ ችግር መፍታት እንደማይችል ያሳያል ሲል የመላው ኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ገለፀ።
ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ኦህዴድ የኦሮሞን ሕዝበ – ሙስሊም ጥያቄም ሆነ የአጠቃላይ የኦሮሞን ህዝብ መብት ማስከበር እና ፍላጎቱን የማሟላት የማይችል፤ እንዲሁም የህዝቡን ችግር መፍታት የማይችል ድርጅት ነው ብሏል። ድርጅቱ ጊዜ ካለፈበት በኃይል ችግርን መፍታት አሰራር ታርሞ ዘመናዊ ወደሆነው ዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲመጣም ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።
ድርጅቱ በአርሲ ዞን አሳሳ ከተማ የኦሮሞ ሙስሊምን ጥያቄ በጠመንጃ ለመፍታት ባደረገው ሙከራ የሶስት ሰዎች ህይወት መጥፋቱን፣ በበርካቶች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን እና ንብረትም መውደሙን የገለፀው ፓርቲው፤ ድርጅቱ ካለፈው ስህተቱ ሳይማር በአሁኑ ወቅትም ተመሳሳይ ድርጊቶችን እየፈፀመ መሆኑን ገልጿል። በዚህም ሳቢያ ችግሩ ተስፋፍቶ በሐምሌ 27 ቀን 2005 ዓ.ም በአሳሳ ከተማ፣ ከዚያ በፊትም በዶዶላ፣ በኮፈሌ እና በሻሸመኔ የህዝብ ሙስሊሙ ጥያቄ ሊቀሰቀስ ችሏል ብሏል።
“ኦህዴድ ከዚህ በፊት የፈፀመው ስህተት ሳያንሰው በአሁኑ ሰዓትም ለችግሩ መፍትሔ የጠመንጃ አፈሙዝ በመጠቀም በአስር ሰዎች ላይ ሞት እና በብዙ ሰዎች ላይም የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል” ያለው ፓርቲው፤ ኦህዴድ እየተጠቀመ ያለው የችግር አፈታት ዘዴ በኃይል ላይ የተመረኮዘ በመሆኑ ዛሬ ያለውንም ሆነ የወደፊቱን የኦሮሞ ህዝብ ችግር መፍታት የማይችል ድርጅት ነው ብሎታል። እየፈፀመ ያለው ድርጊት ከፍተኛ ስህተት ከመሆኑም ውጪ መፍትሄ የማያመጣ ስለሆነ ድርጅቱ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ እና ለችግሩ በውይይት መፍትሔ እንዲፈልግ ፓርቲው ጨምሮ አሳስቧል።¾
(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 413 ነሐሴ 01/2005)

↧

የመድረክ መስቀለኛ መንገድ

$
0
0

ተጻፈ በ  የማነ ናግሽ
Medrek Meeting in Addis
መድረክ በዘገምተኛ ሒደትም ቢሆን በጥናት ላይ የተመሠረተ የአደረጃጀት ሥልቱን ጀምሮ የጋራ አስተሳሰብ የያዘ ማኒፌስቶ በማውጣት ምናልባት በአገሪቱ ግንባር ቀደም ተቃዋሚ ድርጅት እየሆነ ይመስላል፡፡

ቀደም ሲል ይፋ ያደረገውን የፖለቲካ ፕሮግራሙን  አሻሽሎና ከጊዜ ጋር አጣጥሞ አሁን በድጋሚ ለሕዝብ ይፋ ባደረገው ማኒፌስቶው፣ በአብዛኛው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በስፋት የሚተቹበትንና በኢሕአዴግ ላይ ብዙ ጊዜ የሚያጠፉትን ጣት ቅሰራ ለጊዜውም ቢሆን በመተው ካለፈው የተማረ ይመስላል፡፡ ግንባሩ የመፍትሔ ሐሳብ የሚላቸውን አማራጭ የፖለቲካ እሳቤዎች ይዞ መጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ‹‹ተረኛ›› ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻው፣ የግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና የግንባሩ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር መረራ ጉዲና በጋራ ሰሞኑን በሜክሲኮ የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን አዳራሽ ባለፈው እሑድ ያቀረቡት ማኒፌስቶ፣ ወቅቱን ያገናዘበ የፖለቲካ ዳሰሳ ከመሆኑም በላይ በተለይ መንግሥትን የሚያሳስብ ነው፡፡ በዚሁ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ በርካታ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ በውይይቱ ላይ የነቃ ተሳትፎም ነበራቸው፡፡

<em><strong>‹‹በሌሎች አገሮች የሆነው በእኛ የማይሆንበት ሁኔታ የለም››</strong></em>
‹‹የኢትዮጵያ ወቅታዊና መሠረታዊ ችግሮች የመፍቻ አቅጣጫዎች ማኒፌስቶ›› በሚል የቀረበው ይኼው ማኒፌስቶ አገሪቱ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ጉዳዮች ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ አገሪቱ ፍፁም አምባገነናዊ የአገዛዝ ባህሪያት ይታዩባታል ይላል፡፡ በተለይ በ2002 ዓ.ም. ምርጫ ማግስት መድረክን፣ ኢዴፓንና መኢአድን ጨምሮ በሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሲቀርቡ የነበሩትን አቤቱታዎች አንድ በአንድ ይዟል፡፡ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ዘርፎችም ከፋፍሎ አቅርቧቸዋል፡፡ በፖለቲካ ዘርፍ አብዮታዊ ዲሞክራሲ የተባለው የኢሕአዴግ የፖለቲካ ፕሮግራም የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት እንዲጠፋ ማድረጉን፣ የሕግ የበላይነትንና ገለልተኝነትን መጣሱን፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ጨርሶ እያጠፋ መሆኑን፣ ‹‹ሀቀኛ›› ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚደግፉ የሚደርስባቸው ሁሉን አቀፍ ማግለልና ጭቆና፣ እንዲሁም መንግሥት በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ለመደራደር ፈቃደኛ አለመሆን በስፋት ተንትኗል፡፡

ግንባሩ በመፍትሔነት ካስቀመጣቸው መካከል፣ አዘቅት ውስጥ ገባ ያለውን የመድበለ ፓርቲ ሥርዓትን ለመታደግ ይቻል ዘንድ፣ ‹‹ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ የምክክርና የውይይት መድረክ›› መፍጠር አስፈላጊነት በማስቀደም፣ የሚመለከታቸው የአገሪቱ ኃይሎች በሙሉ የመድረኩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይጠይቃል፡፡ ቀጥሎም ነፃ ዳኝነት እንዲኖር፣ ገለልተኛ ተቋማት እንዲፈጠሩና በነፃ ሚዲያ ላይ እየደረሰ ያለው አፈና እንዲቆም ይጠይቃል፡፡ በአገሪቱ እየተከሰቱ ያሉት የብሔርና የሃይማኖት ግጭቶች በሕገ መንግሥቱ አግባብ ገለልተኛ መፍትሔ ይሻሻሉ ይላል፡፡ የአገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር እንዳያላውስ አድርገውታል ያላቸው ሕጎችም እንዲከለሱ ማኒፌስቶው ይጠይቃል፡፡

ይህንን በተመለከተ ለተሰበሰቡት የመድረክ ደጋፊዎች ያቀረቡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ ሕገ መንግሥቱን በመጣስ ታች ያሉ ካድሬዎችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት በጋራ ተጠያቂ እንዲሆኑና ነፃ የሕገ መንግሥት አጣሪ ኮሚቴ እንዲቁቋም ጠይቀዋል፡፡ ነፃ ሚዲያን በተመለከተ ጫና የሌለባቸው ነፃ የግል ሚዲያዎች እንዲፈጠሩ ጠይቀው፣ ‹‹ስለምርጫ ብዙ የምናወራው ዓለማችን ሕዝቡን የሥልጣን ባለቤት ለማድረግ ስለሆነ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ሐሳባቸውን ሲያጠቃልሉም፣ ‹‹ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሌሎች አገሮች አይቻልም ሲባል የነበረው ተችሏል፡፡ በእኛ የማይቻልበት ሁኔታ የለም፤›› ሲሉ በከፍተኛ ጭብጨባ ታጅበዋል፡፡

<em><strong>‹‹ኢሕአዴግ መሪም ነጋዴም ነው››</strong></em>
የማኒፌስቶው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ክፍል ኢሕአዴግ የአገሪቱ ኢኮኖሚ አድጓል የሚል የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ መሆኑን፣ አብዛኛው ሕዝብ በከፍተኛ ኑሮ ውድነትና በሰቆቃ እንደሚገኝ ከፍተኛ የፖለቲካ አድልኦ የሰፈነበት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መኖሩን ያትታል፡፡ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ጥራት እንደሚጎድልባቸው፣ የፋይናንስ ሴክተሩን ወጥሮ በመያዝ የባንኮችና የኢንሹራንስ ድርጅቶች ሚና ገድቦ የያዘው የፋይናንስ ሥርዓት እንዲከለስ፣ ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ በመጣስ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ መዛባትን ይፈጥራሉ ያሉዋቸውን የገዥው ፓርቲ የኢንቨስትመንት ድርጅቶች ወደ ገበያ ኢኮኖሚ አካልነት የሚዘዋወሩበት ሁኔታ ላይ መነጋገር ይገኝባቸዋል፡፡

በማኅበራዊ ጉዳዮችም የሥራ ዕድል አጥተው ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ ያሉት ወጣቶች መታደግ፣ የሥራ ዕድል ከፖለቲካ ወገንተኝነት ለሁሉም ዜጎች ነፃ እንዲሆን፣ የትምህርት ፖሊሲው ብቃት ያላቸው ዜጎች እንዲያፈራ መከለስ፣ እንዲሁም የትምህርትና የሥልጠና ዕድሎች ከፖለቲካ ወገንተኝነት ለሁሉም ዜጎች በብቃትና ተወዳድረው የሚገቡበት እንደሆን በመፍትሔነት ያስቀምጣል፡፡

ይህንን ክፍል ለደጋፊዎቻቸው እያዋዙ ያቀረቡት ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ‹‹ዶ/ር ነጋሶ የኢሕአዴግን ሥራ ከእኔ በተሻለ ሁኔታ ስለሚያውቅ›› በማለት ተሰብሳቢዎቹን ፈገግ ያሰኙ ሲሆን፣ ‹‹የተቃዋሚዎች አንዱ ድላችን አቶ ስዬ አብርሃ፣ አቶ ገብሩ አስራትና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ወደተቃውሞ መድረክ ማምጣት መቻላችን ነው፤›› ይላሉ፡፡ ‹‹የኢሕአዴግ ሃይማኖት›› ያሉት አብዮታዊ ዲሞክራሲ መሪነት የአገሪቱ የኢኮኖሚ መድረክ ከካድሬዎች ቁጥጥር ውጪ የሚሆንበት ሥርዓተ እንፈጥራለን ይላሉ፡፡ አገሪቱ እጅግ አሳሳቢ ሙስና መዘፈቋን ገልጸው፣ ‹‹ኢሕአዴግ መሪም፣ ነጋዴም ነው፤›› በማለት የድርጅቱ የቢዝነስ ኢምፓየር መሰበር አለበት ብለዋል፡፡

‹‹ኪራይ ሰብሳቢ ይለናል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢ ራሱ ኢሕአዴግ ነው፤›› ሲሉ በደጋፊዎቻቸው ከፍተኛ ጭብጨባ ታጅበው ነበር፡፡ እንደ መጨረሻ የመፍትሔ ሐሳብ ‹‹ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት በጥምረት ማቋቋም›› የግንባሩ እምነት ሲሆን፣ ይኼም ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ተደርጎ የፓርላማ ወንበር ካገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ነው፡፡ ሁሉም ‹‹ሀቀኛ›› የሚላቸው ተቃዋሚዎች እንዲተባበሩ የሚጠይቀው የመድረክ ማኒፌስቶ፣ የታሰበው የጥምረቱ መንግሥት ዋነኛ ሥራም አገሪቱ ገባችበት ከሚለው ሁለንተናዊ አዘቅት ለማውጣት በጋራ መረባረብ ነው፡፡ ዶ/ር መረራ መድረክና ሌሎች ‹‹ሀቀኛ›› እያሉ የሚጠሩዋቸው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ እንዲሰጣቸው የጠየቁ ሲሆን፣ ሕዝቡም ከየትኛውም ጊዜ በላይ በላዩ ላይ የተጫነው አምባገነናዊ አገዛዝ ሥርዓት ለመላቀቅ ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

<em><strong>‹‹የመድረክ የትከሻ ስፋት ምን ያህል ነው?››</strong></em>
በርካታ የስብሰባው ታዳሚዎች አስተያየቶች ሲሰጡ አንዳንድ ጥያቄዎችም አንስተዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል፣ ‹‹ከዘረዘራችሁት ሁሉ ችግር የምንወጣበት የነፃነት መንገድ ምንድን ነው? ወደዚህ ነፃነት ለመምራት የመድረክ ትከሻ ስፋት ምን ያህል ነው?›› በሚል ለቀረቡት ጥያቄዎች ዶ/ር ነጋሶ ሲመልሱ፣ ‹‹ሕዝቡ ነፃ መውጣት የሚችለው በራሱ ነው፡፡ እኛ የማታገያ ስልትና ስትራቴጂ ብቻ ነው መቅረፅ የምንችለው፤›› ሲሉ፣ ዶ/ር መረራ በበኩላቸው፣ ‹‹የመድረክ ትከሻ ስፋት የኢትዮጵያ ሕዝብን ትከሻ ያህል ነው፤›› በማለት አገር አቀፍ ውክልና ያለው ስብስብ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ መድረክ የተለያዩ አደረጃጀቶች ያላቸውና ከአራቱ የአገሪቱ ክፍሎች የሚወከሉ ፓርቲዎች የመጀመርያ ስብስብ ነው ብለዋል፡፡

ሰላማዊ ሠልፍን በተመለከተም ጥያቄ የቀረበ ሲሆን፣ ‹‹ቁፋሮ እስኪያልቅ በሚል የቀረበውን ሰበብ ለምን ትታገሳላችሁ? ቁርጠኛ ከሆናችሁ እስረኞቻችንን ለማስፈታት እስከ ቃሊቲ እስር ቤት ወስዳችሁ አሠልፉን፡፡ ሕዝቡን ከሚያሰቃየው ኢሕአዴግ ጋርም ጥምረት ትፈጥራላችሁ ወይ?›› የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ዶ/ር መረራ ‹‹ብሔራዊ እርቅን›› አስመልክተው ለጥያቄውን ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ ‹‹እርግጠኛ ነኝ የኢሕአዴግ ጆሮ አንድ ቀን መስማት ይጀምራል፡፡ የአፄ ኃይለ ሥላሴም የደርግም ጆሮዎች በመጨረሻ ሰዓታት መስማት ጀምረው ነበር አልተሳካላቸውም እንጂ፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ያለትብብር የሚሠራ ሥራ የትም አያደርስም፡፡ አንድ ቡድን የትም አገር ብቻውን መግዛት አይችልም፡፡ ማሸነፍ ይቻል ይሆናል መግዛት ግን አስቸጋሪ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻው ነፃነትን በተመለከተ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱ ጭቆና በቃኝ ማለት ሲችል ነው፤›› ብለው በጎሳ የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ ውስጥ አሉ ለተባለው በስሜት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ብሔሮች ‹‹በጎሳ›› መፈረጃቸው ያልጣማቸው አቶ ጥላሁን፣ ‹‹በብሔርና በኅብረ ብሔር እንጂ በጎሳ የተደራጀ ድርጅት የለም፡፡ አልነበረምም፡፡ ዋናው ጥያቄ የጋራ ራዕይ አለን ወይ ነው? በኢትዮጵያ ብሔርተኝነትም አንዳችን ከሌላችን የምንበላለጥ አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

አንድነት ሰላማዊ ሠልፍ እያካሄደ ነው የመድረክ ሚናስ ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ አመራሮቹ ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጡም፡፡ በባንዲራው ላይ ያለውን ‹‹ዓርማ›› አስመልክቶ ለቀረበው ጥያቄ ግን መድረክ ተቃውሞ እንደሌለው አስታውቋል፡፡ ‹‹ምልክቱ የሃይማኖትና የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነትና አብሮነት አመላካች ከሆነ ምን ችግር አለው? ሕዝቡን ግን ማወያየት ይቻላል፤›› የሚል ምላሽ የሰጡት አቶ ጥላሁን፣ ‹‹የብሔራዊ አንድነትን ጥምረት›› በተመለከተ ጠንከር ያለ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹ምርጫ በነፃነት ይካሄድ እንጂ ኢሕአዴግን ለሚመርጥ ትልቅ አክብሮት ይኖረናል፣ ጥምረትም እንፈጥራለን፤›› ካሉ በኋላ፣ ‹‹ከዚህ ውጪ ዛሬም አንድ ብሔር አንድ ቋንቋ አንድ ሃይማኖት የሚል እምነት ያለው ፓርቲ ካለ ይሞክራት!›› በማለት ከዚህ በፊት ከተለመደው ከተቃዋሚዎች ወጣ ያለ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹ይኼ አገር የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና ሃይማኖቶች አገር ነው፡፡ ይህንን የማይቀበል አስተሳሰብ የትም አይደርስም፤›› በማለት ስም ሳይጠቅሱ ሸንቆጥ አድርገዋል፡፡

<em><strong>የመድረክ ረዥሙ መንገድ</strong></em>
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተቃውሞ ታሪክ እንደ አገሪቱ ዲሞክራሲ ሁሉ ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረ አይደለም፡፡ ኢሕአዴግ በትረ ሥልጣኑን ከተቆጣጠረ ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 22 ዓመታት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለማቆም ሙከራ አድርጓል፡፡ ሕገ መንግሥቱ ውስጥ ከተካተቱ መብቶች ሁሉ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት የሚቋቋምበት መንገድ የሚመለከት ሲሆን፣ እሱም በዲሞክራሲያዊ ምርጫ አግባብ ብቻ መሆኑን ይደነግጋል፡፡

ይህ የበለፀጉ አገሮች (በአብዛኛው ምዕራባዊያን) የሚያቀነቅኑት ሥርዓት አተገባበሩ ከአገር ወደ አገር በመጠኑ ቢለያይም ዋነኛ ማጠንጠኛው ግን አንድና አንድ ነው፡፡ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ቅድመ ሁኔታም፣ ግብም ነው፡፡ በሊብራል ሥርዓት ኢኮኖሚው በነፃ ገበያ መመራት እንዳለበት ሁሉ ፖለቲካው በነፃ መደራጀት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽና የተደላደለ የፖለቲካ ሜዳ መፍጠር የሚጠይቅ ሲሆን፣ ለዚህም ገለልተኛ የዲሞክራሲ ተቋማት መኖር፣ ነፃ ፕሬስ መበልፀግና የተለያዩ የፖለቲካ አስተሳሰብና ፕሮግራም ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች መኖርን ይጠይቃል፡፡ መድረክ ያነሳቸው ጥያቄዎችም እዚህ ላይ የሚያጠነጥኑ ናቸው፡፡

በ1987 ዓ.ም. በኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት የፀደቀው ሕገ መንግሥት ለእነዚህ ሁሉ መብቶች ከለላ የሚሰጥ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያትም እስካሁን አራት አገራዊ ምርጫዎች የተካሄዱ ሲሆን፣ ኢሕአዴግ አሸናፊ እየሆነ ሥርዓተ መንግሥቱን ቀላል ለማይባል ጊዜ በቁጥጥሩ አድርጎ ቆይቷል፡፡ ድርጅቱ በተደጋጋሚ ምርጫ ያሸነፈበት መንገድ ግን አወዛጋቢ ነው፡፡ ቀደም ሲል የጠቃቀስናቸው ፖለቲካዊና ሕጋዊ ማዕቀፎች በተግባር እንደሌሉ የሚያምኑ የመድረክ ሰዎች ሜዳው ለሁሉም ተወዳዳሪዎች እኩል አለመሆኑንና የፖለቲካ ጨዋታው ሕጉ ለኢሕአዴግ ያደላ ነው በሚል መከራከርያ ያቀርባሉ፡፡ ኢሕአዴግ በበኩሉ፣ ‹‹ተቃዋሚዎች ከጥላቻና ከቂም በቀል ስላልወጡ፣ አገር የመምራት አቅምም የላቸውም፡፡ ኢሕአዴግን ከመጣል ባሻገር አገር ለመምራት የሚያስችል የፖለቲካ አስተሳሰብና ፕሮግራም የላቸውም፤›› በማለት ይከራከራል፡፡ በተደጋጋሚ የሚሸነፉበት ምክንያትም የሕዝቡን አመኔታ ማግኘት ባለመቻላቸው መሆኑን ያስረዳል፡፡

በአገሪቱ የ20 ዓመታት የፖለቲካ ጉዞ ላይ ዳሰሳ ለማድረግ የሚሞክር ገለልተኛ አካል ግን እውነታውን በሁለቱም ጫፎች አያገኘውም፡፡ ሀቁ ያለው በሁለቱም ጫፎች መካከል ነው፡፡ ኢሕአዴግ የሚመራው የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ ለሁሉም የፖለቲካ ተዋናዮች የሚያሠራ የተስተካከለ ሜዳ አለመሆኑን ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡ እስካሁን በአገሪቱ የተከሰቱ ተቃዋሚዎችም፣ ከጥላቻና ከቂም በቀል ወጥተው የሕዝቡን አመኔታ የሚያስገኝ አማራጭ የፖለቲካ አስተሳሰብ እንዳልነበራቸውም ይገነዘባሉ፡፡ ‹‹በመተባበር ወይም በመሰባበር›› አንድ ላይ የተሰበሰቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢሕአዴግን የፈተኑ ቅንጅትና ኅብረት ‹‹ኢሕአዴግን ከመጣል›› ባሻገር ይኼ ነው የሚባል ግልጽ አማራጭ ፕሮግራም እንዳልነበራቸው ይወሳል፡፡ ለመተባበር የቸኮሉትን ያህልም ለውድቀት ሲፈጥኑ ለኢሕአዴግ ጣልቃ ገብነትም የተመቹ እንደነበሩ ብዙ ተብሏል፡፡

ቅንጅት ካረቀቀው እዚህ ግባ የማይባል ማኒፌስቶ ይልቅ ዶ/ር ነገደ ጎበዜ ለምርጫ 97 ያበረከቱት ‹‹ሕገ መንግሥት፣ ምርጫና ዲሞክራሲ›› የሚለው መጽሐፍ በተቃዋሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት የነበረውና እንደ መመርያ የተከተሉት ሥራም ነበር፡፡ መደምደሚያው ባያምርም፡፡ ‹‹ኢሕአዴግን በ97 ዓ.ም. ምርጫ መጣል ምንም አማራጭ የለውም፡፡ ከተቻለ በምርጫ በእሱ ካልተቻለ በአመፅ ፈረንጆች (Election or Otherwise) የሚሉት ‹‹ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ›› ዓይነት መንገድ የተከተለ ነበርና መጨረሻም አገሪቱ ወዳልተፈለገ የፖለቲካ አዘቅት ውስጥ የሚከት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ሁለቱም ተቃራኒ ወገኖች በዚሁ የተሳሳተ መንገድ ያበረከቱትን ድርሻ ከፍና ዝቅ ቢያደርጉም፣ በየፈርጃቸው የፈጸሙትን ስህተት ሙሉ ለሙሉ አይክዱም፡፡ በሕዝቦች መካከል ሊከሰት የነበረው የእርስ በርስ ግጭት ባይሳካም፣ አሁንም ያልበረደ ጠባሳ ትቶ አልፏል፡፡ መድረክ ካለፉት ከእነዚህ ስህተቶች በአግባቡ ተምሮ ይሆን?

<em><strong>‹‹መቼም እንዳይደገም››</strong></em>
በ1997 ዓ.ም. ምርጫ ሥልጣን ለመያዝ በተደረገው ትንቅንቅ አላስፈላጊ ድርጊቶች መፈጸማቸው አይረሳም፡፡ ከምርጫው በኋላ የወጡ ሕጎች የፖለቲካ ምኅዳሩን የማያፈናፍን በማድረግ አሉታዊ ሚና መጫወታቸው ብዙ ተብሎለታል፡፡

ከአዲሱ የዲሞክራሲ ጭላንጭል አላግባብ የተጠቀሙትን ጨርሰው ከአገሪቱ የፖለቲካ ተሳትፎ የራቁ አሉ፡፡ የአንዱ ስህተት በሌላ የአፀፋ ስህተት እየተደገመ፣ የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ በ20 ዓመት ወደኋላ ተጎትቷል፡፡ ይህ የሚባልበት ምክንያት ሕዝቡ በተቃዋሚዎች ላይ ተስፋ ቆርጦም ይሁን፣ የአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር በመታፈኑ፣ ኢሕአዴግ የአገሪቱን የፖለቲካ አስተሳሰብ በሞኖፖል መቆጣጠር የሚያስችል 99 በመቶ የፓርላማ ወንበር ለብቻው መቆጣጠር ችሏል፡፡ ተፃራሪ ሐሳቦች ሲስተናገዱበት የነበረው ፓርላማ የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ሰዎች መሰብሰቢያ ሆኗል፡፡

<em><strong>‹‹አማካይ ስፍራ….››?</strong> </em>
ከ2002 ምርጫ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ መድረክ የተባለ ስብስብ ለመፍጠር የቀረቡት የእነ አቶ ስዬ አብርሃ፣ የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና የዶ/ር መረራ ጉዲና ጥናታዊ ዳሰሳዎችም እነዚህን እውነታዎች ያገናዘቡ ነበሩ፡፡ ከዚህም ትምህርት የተወሰደ ይመስላል፡፡ ተቃዋሚዎቹን በሐሳብ ለማሰባሰብ ያስቻለና በብዙዎች ተቀባይነት ያገኘ የሚመስል ‹‹አማካይ ስፍራ›› የመፍጠር ሐሳብ ቀርቦ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ በብሔር ላይ የተመሠረቱትን ድርጅቶች የማይቀበሉ ሳይቀሩ ለመጀመርያ ጊዜ በብሔር ላይ ከተመሠረቱት የእነ ዶ/ር መረራ የኦሮሞ ድርጅቶችና የአቶ ገብሩ አሥራት የትግራይ ተቃዋሚ ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት ተስማምተው አንድ አማካይ ስፍራ መድረክን ፈጥረዋል፡፡

በኅብረ ብሔር ላይ የተመሠረቱ የመድረክ ግንባር አባል ድርጅቶች አሁንም በአገሪቱ ፖለቲካ አወዛጋቢ በሆኑ፣ በተለይም በመሬት ባለቤትነትና በፌዴራሊዝም ሥርዓት አወሳሰን ላይ ስምምነት ላይ ደርሰው መድረክ ምን ማለት እንደሆነ የሚያሳዩበት ግልጽ የፖለቲካ አሃዳዊነት ግን አልፈጠሩም፡፡ በተቀሩት ጉዳዮች ላይ ግን ባልተለመደ ሁኔታ ሰፊና ፈርጀ ብዙ ፕሮግራም (ማኒፌስቶ) ይፋ አድርገዋል፡፡

አንድነት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ሰላማዊ ሠልፍ እያካሄደ ሲሆን፣ መድረክ በሌላ በኩል ማኒፌስቶውን እያስተዋወቀ ነው፡፡ መለያየታቸው በግልጽ ይፋ ባይወጣም፣ ግንኙነታቸው ግን ለብዙዎች ግልጽ አይደለም፡፡ አንዱ በሌላው እንቅስቃሴ ጣልቃ ባይገባም፣ አንዱ ከሌላው ጋር በትብብር እየሠራ ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለም፡፡ በጉዳዩ ላይ ለሚቀርቡ ጥያቄዎችም በሁለቱም ወገኖች በኩል መሸፋፈን ይስተዋላል፡፡ የመድረክንና የአንድነትን የወደፊት ግንኙነት የአገሪቱ የፖለቲካ ዕጣ ፈንታ የሚወስነው ይሆናል፡፡ ምናልባትም ኅብረ ብሔር ድርጅቶች ከብሔር ድርጅቶች ጋር አብረው መሥራት እንደማይችሉ ትልቁ የማሳያ ፈተና ይሆናል፡፡ የመድረክ መንገድ ወዴት ይሆን?

Source: <a href=”http://www.ethiopianreporter.com/index.php/politics/

</div>

↧
↧

የመድረክ ጥሪ ለኢሕአዴግና ለተቃዋሚዎች

$
0
0


የመድረክ ጥሪ ለኢሕአዴግና ለተቃዋሚዎች
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሔ ሳያገኙ ከቀጠሉ የሃገሪቱ ኅልውና ለአደጋ የተጋለጠ እንደሚሆን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረቱ መድረክ ገለፀ።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ችግሮች መፍትሔ ሳያገኙ ከቀጠሉ የሃገሪቱ ኅልውና ለአደጋ የተጋለጠ እንደሚሆን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረቱ መድረክ ገለፀ።

መድረክ ይህን የገለፀው የትናንት በስተያው ዕሁድ (ሐምሌ 28/2005 ዓ.ም) አዲስ አበባ ላይ ባካሄደው ሕዝባዊ ስብስባ ላይ ሲሆን ገዥውን ፓርቲ ኢህአዴግን ለተቃዋሚዎች የፖለቲካ መድረክ በመንፈግ፣ በንግዱ ውስጥ ገብቶ የአገሪቱን ምጣኔ ኃብት በማዛባት፣ ሕዝብን በማፈናቀል፣ በሃይማኖት ጉዳይ በመግባትና በፀረ-ሽብር ሕጉ አሳብቦ በማሰር ኮንኗል።

ከሰላማዊ ትግል የተለየ አማራጭ የያዙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሰላማዊ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አድርጓል።

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ መድረክ የሚያነሳቸውን ክሦች አይቀበልም፡፡

ይልቁንስ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በማስፈን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዳስገኘ ነው የሚናገረው።

ዝርዝሩን መለስካቸው አምኃ ከላከው ዘገባ ያድምጡ፡፡

↧

ፖፕ ፓየስ 11ኛ አጼ ኃይለ ሥላሴን ለማስከዳት ስላደረጉት ሙከራ ኪዳኔ ዓለማየሁ

$
0
0
↧

የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ደብዳቤ ከቃሊቲ:- ‹‹የስልጣን ጥመኝነት የወለደዉ የፀረሽብር አዋጅ››

$
0
0

 ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ

የፀረሽብር አዋጁንና እየተተገበረ ያለበትን መንገድ ባሰብኩ ቁጥር  ወደአይምሮዬ የሚመላለሱ በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ከነዚህ መሀከል አዋጁ ለምን ሰብአዊ መብትን የሚጥሱ አንቀጾች ኖሩት/  ከሽብር ጋር ምንም አይነት ንክኪ የሌለን ንጹሀን ሰዎችስ በአዋጁ መሰረት እየተባለ ለምን ይፈረድብናል የሚሉት ይገኙበታል፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ አዋጁ የወጣበትን ምክንያት መመርመር ግድ ይላልና ይህንኑ አደረስኩ፡፡

 

የፀረሽብር አዋጁ ለምን ወጣ

 

ኢህአዴግ የፀረሽብር አዋጅ እንዲወጣ ያደረገዉ እዉተኛ የሽብር አደጋ ተደቅኖበት አለመሆኑን ለመረዳት ብዙ መጓዝ አያስፈልግም፡፡ በአሽባሪነት የተጠረጠርንና የተፈረደብንን ሰዎች ማንነት ማወቁ ብቻ ይበቃል፡፡ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዉያን ላይ እየተፈጸመ ያለዉ ግፍ ይብቃ ብለዉ ስርዓቱ በሌላ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ይለወጥ ዘንድ በሰላማዊ መንገድ ሲታገሉ የነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ በመስርያ ቤታቸዉ ወይም ደግሞ በመኖርያ ቤታቸዉ አካባቢዎች የመንግስት ሀላፊዎች በሚጠሯቸዉ ስብሰባዎች ላይ ደፋር ጥያቄዎችን በማቅረባቸዉ ብቻ ጥርስ የተነከሰባቸዉ የነፃ አስተሳሰብ  ባለቤቶች፣ መንግስት ለአገዛዙ  አመቺ በመሰለዉ መልኩ ሀይማኖታቸዉን ለመበረዝና ለመከለስ ያደርግ የነበረዉን እንቅስቃሴ በሚያስገርም ጀግንነት የመከቱ የእስልምና ሀይማኖት መሪዎችና ተከታዮች እንዲሁም የህዝብ ድምፅ መሆናችንን አምነን ሀላፊነታችንን በአግባቡ ስንወጣ የነበርን  የነፃዉ ፕሬስ አባላት የፀረሽብር አዋጁ ሰለባ ሆነናል፡፡

 

ይህ የመንግስት ድርጊት አዋጁን ያወጣበት እዉነተኛ ምክንያት በስልጣን ወንበር ላይ ያለምንም ተቺ፣ ተቃዋሚና ተቀናቃኝ ተደላድሎ ለመቀመጥ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ይህ አይነቱ አካሄድ ደግሞ ኢህአዴግ የጀመረዉ ሳይሆን እሱን ከመሰሉ አምባገነኖች የኮረጀዉ ያረጀና ያፈጀ አሰራር ነዉ፡፡ የአፍሪካዉያን የቀድሞ ቅኝ ገዢዎች አልንበረከክ ብለዉ ያስቸገሩዋቸዉን የነፃነት ታጋዮች የአሸባሪነት ታፔላ ይለጥፉባቸዉ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ዛሬ ደግሞ ኢህአዴግ ሰብአዊና የዜግነት ክብራችንን ለመጣል እምቢ ያልነዉን የገዛ ሀገሩን ልጆች እስር ቤት ለማጎርና ለማሰቃየት አመቺ ነዉ ብሎ ባመነበት በዚህ የቅኝ ገዢዎች አስቀያሚ መንገድ ላይ እየተጓዘ ነዉ፡፡

 

ምን ይሻላል?

 

የፀረሽብር አዋጁን በመታከክ ኢህአዴግ እየፈፀማቸዉ ያሉትን የመብት ረገጣዎች ለማስቆም ከባድ ትግል ይጠይቃል፡፡ አሁን ያለዉ  የፀረሽብር አዋጅ ተገቢ በሆነ በሌላ የፀረ ሽብር አዋጅ መተካት ይኖርበታል፡፡ ይህ ባይሆን እንኳን አሁን ያለዉ አይነት ለኢህአዴግ የገበረ የፍትህ ስርዓት እስካለ ድረስ ግን ንፁሀን ዜጎች በአሸባሪነት መታሰራቸዉ አይቀርም፡፡ አሁን ባለዉ የፀረሽብር አዋጅ መሠረት በትክክል ብንዳኝ ኖሮ እንኳን ጥፋተኛ ልንባል የማይገባን ምንም አይነት ወንጀል ያልፈፀምን ግለሰቦች አሸባሪ ተብለን በእስር ላይ መገኘታችን ይህንን መራራ እዉነት የሚያሳይ ነዉ፡፡ በመሆኑም አዋጁንና በይበልጥ ደግሞ አዋጁን ለስልጣኑ ማራዘሚያነት ኢፍትሀዊ በሆነ መንገድ እየተጠቀመበት ያለዉን ኢህአዴግን በማዉገዝ እየተደረጉ ያሉትን የተቃዉሞ ሰልፎችና ሌሎች ሰላማዊ የተቃዉሞ እንቅስቃሴዎች ጠንክረዉ መቀጠል ይኖርባቸዋል፡፡

 

የተቃዉሞ እንቅስቃሴዎች በዋናነት ኢህአዴግ ላይ ማተኮር እንዳለባቸዉ የማምነዉ በፀረሽብር አዋጁና በአተገባበሩ ብቻ ሳይሆን የሌሎች ለቁጥር የሚያዳግቱ የኢትዮጵያዉያን ችግሮች ምንጭ ራሱ ኢህአዴግ በመሆኑ ነዉ፡፡ ኢህአዴግ ስልጣኑን ለማራዘም የሚረዳዉ እስከመሰለዉ ድረስ ማንኛዉንም አይነት ተግባር ከመፈፀም ወደኃላ የማይል መሆኑን እስኪያንገሸግሸን ታዝበናል፡፡ በሌላ አነጋገር የኢህአዴግ ድርጊቶች ሁሉ ምክንያቶች ( motives ) ከዘረኝነት፣ ከስልጣን ጥመኝነት፣ ካለአግባብ ከመበልፀግና ከመሳሰሉት እኩይ ፍላጎቶች ጋር የተያያዙ ናቸዉ፡፡ “If one”s motives are wrong, nothing can be right” ከሚለዉ የአርተር ጎርደን አባባል እንደምንረዳዉ አንድ ነገር የሚደረግበት ምክንያት ስህተት ከሆነ ትክክል የሚሆን ነገር አይኖርም፡፡ በዚህም ምክንያት ከኢህአዴግ መልካም ነገር መጠበቅ አይቻልም፡፡ በመሆኑም የሚኖረን ብቸኛ አማራጭ የሰለጠነና ሰላማዊ ትግል የሚጠይቀንን መስዋዕትነት ከፍለን ስርዓቱን መለወጥ ነዉ፡፡

 

ስርዓቱን ስለመለወጥ ስናስብ አብረን ልናስባቸዉ የሚገቡ በርካታ ተያያዥ ጉዳዮች አሉ፡፡ ስርዓቱን ለመለወጥ በምንሄድበት መንገድ ላይ ገዢዉ ፓርቲ ያስቀምጣቸዉን በዘር፣ በሀይማኖት፣በፖለቲካ ርዕዮተ ዓለምና በጥቅም የመከፋፈል እንቅፋቶች እንዴት ማለፍ እንደምንችል በጥልቀት አስቦ መንቀሳቀስ ግድ ይላል፡፡  በየአቅጣጫዉ የተበታተኑ እንቅስቃሴዎችን ከማካሄድ ይልቅ በህብረት ሆነን መታገል መቻል ይኖርብናል፡፡ ከኢህአዴግ በኋላ ስለሚመሰረተዉ ስርዓትም በደንብ ማሰብና መመካከር የሀገሬ ጉዳይ ይመለከተኛል ከሚል ማንኛዉም ሀላፊነት ከሚሰማዉ ዜጋ በተለይም ደግሞ የተቃዉሞ እንቅስቃሴዎችን ከሚመሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሌሎች አካላት ይጠበቃል፡፡ የሚጠበቅብንን ሁሉ እስካደረግንና በፅናት እስከቆምን ድረስ ደግሞ ብሩህ ቀን የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡

 

ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ከቃሊቲ

 

↧

ፌደራል ፖሊስ በረመዳን ጾም ፍቺ በሙስሊሞች ላይ ድብደባ ፈጸመ

$
0
0

ከመሐመድ
ፖሊስ የኛ አይደለም ሊሆንም አይገባውም፡፡ “ፖሊስ” ለዚህ ጽሁፍ ሲባል “ኢህአዴግ” የተባለ የማፊያዎች ስብስብን ለመጠበቅ ህዝብን በአደባባይ ሊያሸብር ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው የደደቦች ስብስብ ነው፡፡ ፖሊስ ደደብ ነው፡፡ ማገናዘቢያውን በኢህአዴግ የሽብር ቡድን የተቀማ ህጻናት ፣ ሃረጋውያን ፣ ነብሰ ጡር ፣ ሴት ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ፣ መንገደኛ መለየት የተሳነው እንሰሳ ነው፡፡ ፖሊስ ክብሪት ነው፡፡ አምጣ የወለደችውን እናቱን ለመደብደብ የማያቅማማ ቅል ራስ፡፡
ጉዞ በጦር ቀጠና….
ከብሔራዊ …በአዋሽ ወደ ኮሜርስ….. ቱርርር ድጋሚ ወደ አዋሽ ባንክ ፣ በአርቲስቲክ ወደ ብሔራዊ ባንክ ሆም መዘክር ፣ ታጥሯል መንገዱ ቱርርር ወደ ተገኘው ቅያስ ሰዎች ተደብድበዋል ፣ መስገጃ ፣ ጫማዎች ፣ አማይማ ፣ ኮፊያ ፣ የተፈነከቱ ሰዎች ፣ የተያዙ ወጣቶች ፣ ረጃጅም አጠና የያዙ የባንዳው ውሾች ፣ በፋራረሱት መንደሮች አቆራርጠን እዚያችው ትንሽ ፈቀቅ ብለን…
b_400_300_16777215_00_images_mejlisqebr

Addis_august8_2013_21

Addis_august8_2013_20

Addis_august8_2013_17

Addis_august8_2013_16
…አትሩጡ …አትሩጡ… ጥግህን ያዝ!! ጥግጥጉን ወደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር … የተለያዩ የመንግስት መስሪያቤቶች የሙስሊሙ እስር ቤት ሆነዋል፡፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በብዙ ውሾች መሃል የተያዙ ወንድሞቼን ተመለከትኩኝ….አንዱ ውሻ ጋረደኝ ሁሉንም ለመቁጠር አልቻልኩም ……..አንድ ..እእ….ሁለት ተነጥለው ሌላ …ሁለት…. ወዲ…ያ ….ሌሎች የታሰሩ ግን በስንቱ መስሪያ ቤቶች ስንቱ ሙስሊም ታስሯል…! መስሪያ ቤቶች ባጠቃላይ (ያሲን ኑሩ በሆነው ሲዲው ላይ አጀልህ ከደረሰ ሁሉም ነገር አንተን ለመግደል ሰበቢያ መሆን ይችላል ብሎን ነበር) ሙስሊሙን ለማሰር አፋቸውን ከፍተው ሲጠብቁን አስተዋልኩ…ናሽናል ጂዎግራፊ ቲቪ ላይ በብዙ ነብሮች የተከበበችውን ሚዳቋ ትዝ አለችኝ… ከመንጋዋ የተነጠለችውን አንዷን ሚዳቋ ጥቂት የነብር መንጋ ከበው ሲበሏት ለመን መንጋው አይታደጋትም ስል ጠየኩ…..ዛሬም ከጀምአው እየነጠሉ የሚደበደቡትን ወንድሞቼን ለመርዳት ሳይሞክሩ ነብስን ለማዳን የሚራወጡት ወንድሞቻቸውን ለመርዳት ከሚናዝኑት ከብዙው የህዝን መንጋ ጥቂቱን ብቻ አስተዋልኩ…ጥቂት ናቸውና የባንዳው ሰራዊት በቀላሉ አጠቃቸው….
አንድም ባስ አልተሰበረም ፣ አንድም ድንጋይ ሲወረውር የተመለከትኩት ሰው አልነበረም፡፡ በእርግጥ …..መብትን መጠየቅ ሽብር አይደለም ፣ እራሱ ገዳይ እራሱ ከሳሽ ፣ በሃገራችን ሰላም አጣን ፣ መንግስት የለም ወይ ፣ እንትን የህዝብ ነው (ይሄን እኔ አላልኩም) ፣ ኢቴቪ ፣ዛሚ ፣ ፋና ፣ መንግስት ፣ ወዘተረፈዎች ሌባ ናቸው ብለናል፡፡ የህዝብን አደራ የበሉ ፣ ከህዝብ አብራክ ወጥተው ህዝብ ላይ ቁልቁል የሚተፋ ወሽካታ አድርባይነታቸውን ነግረናቸዋል፡፡ ጥፋታችን በግፍ የታሰሩብንን መሪዎቻችንን እንዲፈቱልን መጠየቃችን ነበር፡፡ በሃይማኖት ጣልቃ አትግቡብን ፣ ህገ መንግስቱ ካልተተገበረ የወረቀት ነብር ነው ብለን ብሶታችንን ማሰማታችን …….
በአጠና ተነረትን ፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፊት ለፊት ግንቡ ጥግ ስር እራሱን ስቶ የወደቀው በግምት እድሜው ወደ ስልሳዎቹ የሚጠጋው አዛውንት መሃል አናቱ ተበርቅሶ ደሙ እየፈሰሰ ማንም እንዳይረዳው የባንዳው ሰራዊት ከበው ሞቱን ይጠብቃሉ ፣ ጉዞ ወደ ጥቁር አንበሳ!! ብሔራዊ ሜትሪዮሎጂ ፊት ለፊት ያለው የባንዳው ሰራዊት ጣቢያ ፊት ለፊት ባለው ሚዲያን/የአስባልት አካፋይ ተዘርግፈው የወደቁ ሰዎች ይታዩኛል ፣ አንድ አባት ከሁለት (በግምት የአስራ አራት እና ከአስራ ስምንት የማይበልጡ) ልጆቹ ጋር አፈር መስለው ሶስቱም በባዶ እግራቸው የሰውዬው ኮት በጭቃ ጨቅይቶ የሴቶቹ ልብሶች አፈር መስሎና ጸጉራቸው ተንጨባሮ በቢታንያ ክሊኒክ ቅያስ ብቅ አሉ፡፡ የሰራዊቱ ጣብያ በር ላይ ደም ረግጠን በቅያስ ወደ ሞሃ እድገት በስራ ት/ት ቤት ደረስን፡፡ ከጦር አውድማው ወጥተን መስሎን ጫማችንን ሱሪያችንን ልናነጻ ቀልባችንን ልናረጋጋ ሊስትሮ ፍለጋ ስንኳትን ከእናቱ ጋር የተለያየ አንድ ከአስራሁለት አመት የማይበልጥ ልጅ አይኖቹ ወዲያ ወዲህ ሲሉ አይን ለአይን ተገጣጠምን፡፡
እየተቅለሰለሰና እየተርበተበተ “ከእናቴን ጋር ተጠፋፋን ወደ መሳለሚያ 01 መንገዱን አሳዩኝ..” ሲል ልመናውን አቀረበ፡፡
እናቱ ታየችኝ!! ልክ ብሔራዊ ባንክ ጋር ጥጉን ካሰለፏቸው ሰዎች መካከል አንዲት ነብሰ ጡር ሁለት ልጆቿን ይዛ ርህራሄ የማያውቁትን እነዚህን የባንዳውን ሰራዊት ያዝኑላት ዘንድ ስትለምናቸው…ሚጣ በሚሯሯጡት ሰዎች ተረግጣ እሪሪሪ ስትል ከልጇ እኩል የምታነባዋ ብሔራዊ ቲያትር ጋር የየኋት እናት በአይኔ ይዞሩ ጀመር፡፡

“እናትህ ስልክ ይኖራታል..!” የኔ ጥያቄ ነበር ከልጁ ይልቅ የእናቱ ጭንቀት በአይኔ እየዞረ…

“የላትም!”

“ና” በል! ጉዞ በሞሃ ወደ በርበሬ በረንዳ…ከአብነት ፣ ከምራብ ፣ ከተክለሃይማኖትና ከሜክሲኮ ያሚመጡ መንገዶችን የሚያገናኘው መስቀለኛው መንገድ ላይ ሊስትሮ ስንፈልግ ከተክለሃይማኖት ቱርርር እያሉ አናታችን ላይ ሊወጡ … ወደ ጭድ ተራ ቱርር…ሃደሬ ሰፈር ውስጥ ውስጡን ሰዎች ይሯሯጣሉ ዞር ስል ልጁ ከአጠገቤ የለም!! የት ገባ!! በቃ አንድ ሰው ያሳየዋል ብዬ ጥሩውን ጠረጠርኩ!! ከጭድ ተራ ወደ ምናለሽ ተራ ምናለሽ ተራ ጋር የሰላም ቀጠና ነው ብለን እርግት ፣ ቅዝቅዝ ፣ ትክዝ ፣ ፍዝዝ እንዳልን…ከወደ ሰላም ባልትና አካባቢ ቱርርር ወይ ዛሬ!! ምናለሽ ተራ ያላትን ቁሶች ኁላ ቆሽ…ኮሽ…ስብር …ብረታብረቶችን ድስጣድስጦችን ፣ ማንኪያዎችን ምናምኖችን ሽክም ይዞ ቱርርር ….የጭንቅ ቀን አይመሽም!! በሃያሁለት ቀበሌ ወደ ድሬ ህንጻ ሰባተኛ፡፡ አሁን ሰላም ነው፡፡

ስለምን ይሄ ሁላ ውርጅብኝ….አንድም ጠጠር እንኳ ባላነሳ ህዝብ ላይ ግን ለምን!!

የመንግስትን መግለጫ ለማዳመጥ ሞባይሌን አውጥቼ ዛሚን ከፈትኩ …ኤንሶ ኤንሶ…ይላል…ወደ መስተዳድሩ ኤፍ ኤም….አይኬ ..ጫምባላላ ይላል…ወደ 97.1 የእስፖርት ዝውውር ይዘግባል አንዱን ሃገር በቀል ተጫዋች ጋብዘው….98.1 የአምስት ሰዓት ዜና ጀመረ…ጆሮዬን ሰክቼ ቀልቤን ሰብስቤ በትካዜ ማድመጥ ጀመርኩ፡፡
“የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት አቶ እከሌ በአዲስ አበባ እስታዲየም በመገኘት መንግስት ድህነትን ለመቀነስ በሚያደርገው እርብርብ ህዝበ ሙስሊሙ እያደረገ ያለውን አስተዋጽዎ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገነዘቡ፡፡ የኢድ ሶላትም ህዝበ ሙስሊሙ በተገኘበት በአዲስ አበባ እስታዲየም በሰላም ተካሂዶ እንደተጠናቀቀ ከኢዜአ ባገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል” ብሎ ኩም አደረገኝ፡፡ አሁን አመመኝ፡፡ አሁን ጆሮዬን ጠዘጠዘኝ፡፡ /…./

↧
↧

አንድነት በአርባምንጭ ከተማ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 1, 2, 3, 4 and 5

$
0
0

አንድነት በአርባምንጭ ከተማ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 1

አንድነት በአርባምንጭ ከተማ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 2

አንድነት በአርባምንጭ ከተማ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 3

አንድነት በአርባምንጭ ከተማ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 4

አንድነት በአርባምንጭ ከተማ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ክፍል 5

↧

በአዲስ አበባ፣ በወልቂጤ፣ በአፋር፣ በደሴና በአዳማ ሙስሊሞች ላይ መንግስት እርምጃ ወሰደ

$
0
0

ሙስሊም 1
ሙስሊም 3
ሙስሊም(ዘ-ሐበሻ) ለኢድ ሶላት በወጡ ሙስሊሞች ላይ መንግስት ድብደባ መፈጸሙ ታወቀ። በአዲስ አበባ፣ በወልቂጤ፣ በአፋር፣ በደሴ፣ በአዳማና በሌሎችም ከተሞች ለኢድ ሶላት በወጡ ሙስሊሞች ላይ መንግስት ከአንድ ሳምንት በፊት በሰጠው ማስጠንቀቂያ መሠረት ዛሬ ድብደባውን ሲፈጽም በተለይም አዲስ አበባ የጥይት ድምጽ መሰማቱን እና አድማ በታኝ ፖሊሶችም አስለቃሽ ጭስ መጠቀማቸውን ከድምጻችን ይሰማ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የ1434ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል በዛሬው ዕለት በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች እያከበሩት ሲሆን በኢትዮጵያ የተከበረው በተቃውሞ፣ በእስር፣ በድብደባና በ እንግልት መሆኑ በርካታ ሙስሊሞችን እንዳስቆጣ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ከምናገኛቸው የሕዝብ አስተያየቶች መረዳት ችለናል። በአዲስ አበባ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ድብደባ የደረሰባችው ሲሆን የተደብዳቢ ሰዎችም ፎቶ ግራፍ ከነደማቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተለቋል።
“የመንግስት ታጣቂዎች የዒድ ክብረ በዓልን ለመፈጸም የወጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ኃይል የተቀላቀለበት ድብደባ ፈጽመዋል፡፡ መንግስት ለኢትዮጵያውያን ሙስሊም ዜጎቹ ያለውን ከልክ ያለፈ ጥላቻ በዛሬውም በኢድ በዓል ቀን አሳይቷል፡፡” ሲል ሁኔታውን የገለጸው ድምፃችን ይሰማ ፌዴራል ፖሊስ ሙስሊሞችን እስከቤታቸው ደጃፍ ድረስ እየተከተለ ጥቃት ሲዘነዝሩባቸው ውለዋል ብሏል።
በሙስሊሞቹ በዓል ላይ እንዲህ ያለው ተግባር ቢፈጸምም መንግስታዊ ሚዲያዎች ግን በዓሉ በሰላም መጠናቀቁን እየዘገቡ ነው። በተለይ የሕወሓት ራድዮ የሆነው ራድዮ ፋና የዛሬውን በዓል በማስመልከት የዘገበው የሚከተለውን ነው። “ሙስሊሙ ማህበረሰብም ከማለዳው ጀምሮ ወደ ስቴዲየም በማምራት በአሉን በሰላት ፣ በስግደት ተክቢራና ሌሎችንም ሀይማኖታዊ ስነ ስርአቶች በማካሄድ አክብሮታል። በበአሉ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ ኪያር ሙሀመድ አማን እንዳሉት ፥ በረመዳን ሙስሊሙ ፈጣሪው ያዘዘውን መልካም ነገሮች ሁሉ ሲከውን መቆየቱን አንስተዋል። መልካም ነገሮች የሚደረጉት በረመዳን ብቻ ባለመሆኑ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከረመዳን በኋላም መልካም ነገሮችን ማድረጉን እንዲቀጥል አሳስበዋል። በሀይማኖት ስም አንዳንድ አክራሪዎች ሰላምን የሚነሳ ድርጊት እየፈጸሙ መሆኑን ጠቁመው ፥ ይህም መላው ሙስሊሙ በየመስጊዱ ጸሎቱን በአግባቡ እንዳይከውን እያደረገ ይገኛል ብለዋል። ይህን ተቀባይነት የሌለውን ድርጊትም ሙስሊሙ መታገል አለበት የሚሉት ፕሬዝዳንቱ ፥ በአሉን ካጡና ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በጋራ ማክበር ይገባል ነው ያሉት።
የመንግስት ሚድያዎች በዓሉ በሰላም መጠናቀቁን ቢዘግቡም ድምፃችን ይሰማ ደግሞ ተቃውሞውን በቪድዮ ለአደባባይ በማብቃት የመንግስትን ውሸት እርቃኑን እንዳስቀረው ታዛቢዎች የሚናገሩት።

↧

“ኃይሌ ፕሬዘዳንት ከሚሆን የሪዞርቱ አስዳደር ቢሆን ይሻለዋል”–አቶ ግርማ ሰይፉ

$
0
0

በኢትዮጵያ ፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ የኃይሌ ገብረስላሴን ወደ ፖለቲካው ዓለም መግባትና ለፕሬዚዳንትነት እወዳደራለሁ ማለቱን ተከትሎ ለላይፍ መጽሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ “‹‹ሃይሌ ፕሬዘዳንት ከሚሆን የሪዞርቱ አስዳደር ቢሆን ይሻለዋል›› አሉ። በመጽሔቱ የቀረበው ቃለምልልስ እንደወረደ ይኸው፦

‹‹ለሚሚ ስብሃቱ የምሰጠው ምላሽ እንኳን ብቻ ነው››
‹‹መለስ በመሞታቸው ፓርላማው ተነቃቅቷል››

የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በታሪክ አጋጣሚ በፓርላማው ብቸኛ የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚ በመሆናቸው የሁሉን ትኩረት እንዲያገኙ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡እጅግ የተጣበበ ጊዜ ያላቸው ግርማ በቅርቡ የነጻነት ዋጋው ስንት ነው? የሚል መጽሀፍ ለንባብ አብቅተዋል፡፡ዳዊት ሰለሞን መጽሀፉን እንደመነሻ በመውሰድ ነገሮችን በተለየና በሰለጠነ መንገድ መመልከት የሚወዱትን ግርማን አነጋግሯቸዋል፡፡የፓርላማ አባሉ ጊዜያቸውን በማጣበብ ለቃለ ምልልሱ ፈቃደኝነት በማሳየታቸውም ምስጋናችን ይድረሳቸው ፡፡
ላይፍ– በቅርቡ የነጻነት ዋጋው ስንት ነው የሚል መጠይቅ ያለው መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል፡፡በፓርላማ ንግግር በማድረግ፣በየሳምንቱ በጋዜጦች ላይ አርቲክሎችን ከመጻፍና አንድ ጥራዝ መጽሐፍ በማውጣት መካከል ያለው ልዮነት ምንድን ነው
ግርማ — ምንም ልዮነት የላቸውም፡፡በቀን ውስጥ ያለውን ጊዜ እንደየድርሻቸው ይከፋፈላሉ እንጂ ልዮነት የላቸውም ብዬ አምናለሁ፡፡እንደውም አንዱ ሌላኛውን ይደግፋል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ላይፍ — የነጻነት ዋጋው ስንት ነው የሚለው መጽሐፍዎ በዋናነት ሊያስተላልፍ የፈለገው መልእክት ምንድን ነው
Girma-Seifu2ግርማ –ያው ሰዎች ለነጻነታቸው ምን ያህል ዋጋ እየከፈሉ እንደሆነ ለማሳየት ነው፡፡በመጽሀፉ ውስጥ በተለያየ ገጸ ባህሪ የተወከሉ ሰዎች አሉበት፡፡ነጋዴዎች፣የተማሩ የሚባሉ፣ሐይማኖተኞችና ባተሌዎች አሉበት፡፡ሁሉም በእጁ ላይ ያለውን ነጻነቱን ተደራድሮበት እየሸጠው ሳይሆን እንዲሁ እያጣው መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ልቦለድ ሳይሆን እውነተኛ ገጠመኝ ነው፡፡ሁሉም ሰው በእጁ ያለውን ነጻነት አሳልፎ እየሰጠ እንደሆነ መጽሐፉ ያሳያል፡፡በእርግጠኝነት መጽሐፉን የሚያነብ ሰው ራሱን አንድ ቦታ ያገኘዋል፡፡
ላይፍ— ‹‹እዚህ አገር ያለውን ፍርሃት 95 ከመቶ የፈጠርነው እኛው ራሳችን ነን›› የሚል መደምደሚያ ላይ በመጽሐፉ ደርሰዋል፡፡የሌለ ነገር ነው የምትፈሩት እያሉን ነው
ግርማ — የሚያስፈራራን ነገር የለም አላልኩም፡፡እኔ ሁልጊዜም 80 ከመቶ የሚሆነውን ፍርሃት የፈጠርነው እኛ ነን እል ነበር ፡፡ነገር ግን አንድ ቀን ጃዋር መሐመድ በሰላማዊ ትግል ዙሪያ ንግግር ሲያደርግ ነው ይህንን ቁጥር ያገኘሁት፡፡ማተኮር ያለብን ፐርሰንቱ ላይ አይደለም፡፡ለምሳሌ መቶ ሰዎች ቢኖሩ ሊያስፈራራው የሚችለው አንዱን ብቻ ነው፡፡ቀሪዎቹ አንዱ ሰው ላይ የደረሰውን በመመልከት የሚፈሩ ናቸው፡፡በተለያየ መንገድ ማስፈራራቱ ሊኖር ይችላል ነገር ግን ብዙዎቻችን የምንፈራው ሌሎቹን እየተመለከትን ነው፡፡በየቀበሌው የሚገኙ ሰዎች የሚበዙት ኢህአዴግ የሆነ ነገር ይጥልልኛል በማለት የተጠጉ ናቸው፡፡እነዚህ ሰዎች ናቸው ወደ የቤቱ እያመሩ ሊያስፈራሩ የሚሞክሩ፡፡ነጻነታችንን ነጻነት በሌላቸው ሰዎች እያስነጠቅን መሆኑን መመልከት አለብን፡፡እስኪ ተመልከት ከፍርሃት የወጡ አንድ ሚልዮን ሰዎች ቢኖሩን ኢህአዴግ እንዴት ነው አንድ ሚልዮኑን ሊያስፈራራ የሚችለው?
ላይፍ — በ2002 በተሳተፉበት ምርጫ ከጎንዎ ሊያገኟቸው ይፈልጓቸው የነበሩ የቅርብ ሰዎችዎን በመፍራታቸው የተነሳ ሊያገኟቸው አለመቻልዎን በመጽሐፍዎ ጠቅሰዋል፡፡እነዚህ ሰዎች መጽሐፉ ከወጣ በኋላ በአንድም በሌላ መንገድ የተናገሩት ነገር ይኖራል?
ግርማ –አይተውት ራሳቸውን ያገኙበት ይሆናል እንጂ እኔን እንዲህ አልነበረም ያለኝ የለም፡፡ደግሞም አይኖርም ምክንያቱም እውነት ነው፡፡እውነት ሲሆን እኮ ብዙም ክርክር አያስነሳም፡፡እነዚህ ሰዎች ብዙ ሚልዮኖችን የሚወክሉ መሆናቸውም መዘንጋት የለበትም፡፡
ላይፍ -ሰዎች የእኛን አገር ፖለቲካ ሲያስቡ ወደ አእምሯቸው የሚመጣው ሴረኝነት ነው፡፡በሴራ ፖለቲካ የተነሳ ብዙ ርቀት መጓዝ አልተቻለም፡፡እርስዎ ደግሞ ሐይማኖተኛ ለመሆንዎ በመጽሐፍዎ ደጋግመው የጠቀሷቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃላት በመመለከት መገመት አያስቸግርም፡፡ፖለቲከኛና ሐይማኖተኛ መሆን በእኛ አገር የሴራ ፖለቲካ ውስጥ ፈታኝ አይሆንም?
ግርማ — በጣም ለብዙ ሰው መናገር የምፈልገው ፖለቲከኛ ለመሆን ውሸታም ሴረኛ መሆን አለማስፈለጉን ነው፡፡ፖለቲከኛ መሆን የሚጠይቀው በመጀመሪያ ሐቀኝነትንና ሴረኛ አለመሆንን ነው፡፡እንደምታስታውሰው በፓርቲው ውስጥ ነጻ ውድድር መኖር አለበት የምለው በድርጅታዊ አሰራር ባለማመኔ ነው፡፡ድርጅታዊ አሰራር ማለት የሆነን ሰው በማንሳት የምታስቀምጥበት ነው፡፡ነገር ግን እችላለሁ የሚል ሰው ተወዳድሮ ማሸነፍ ይኖርበታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ያን ያህል ሐይማኖተኛ አይደለሁም፡፡ክርስቲያን ነኝ፡፡ለእምነት ክብር እሰጣለሁ፡፡ሰው ሁሉ የእኔን እምነት መከተል አለበት አልልም፡፡ነገር ግን ከማያምን የሚያምን የተሻለ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ለምን ጠንቋይን አይሆንም እምነት ያለው ሰው የሆነ የሚፈራው ነግር እንዳለው አስባለሁ፡፡እግዚአብሄርን ወይም አላህን የሚያምን ሰው በጨለማ የምሰራውን ገልጦ የሚያይ አምላክ አለ ብሎ ስለሚያምን ክፉ ነገር የማድረግ ድፍረት አይኖረውም፡፡
ላይፍ– የፖለቲካ ህይወትዎን በጀመሩበት የኤዴሊ ፓርቲ ውስጥ በነበረ ሴራ ወደ ቅንጅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳይመጡ መደረግዎን በመጽሀፍዎ በማስታወስ ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴው ብመጣ ኖሮ ግን እታሰር ነበር ብለዋል፡፡ይህ በእኔ ያልተፈጸመው አምላክ ስለጠበቀኝ ነው ይላሉ፡፡ነገር በዚያ የ1997 ምርጫ ወቅት ለእስር የተዳረጉ የትግል ጓደኞችዎ እንደመሆናቸው መጠን እኔን አምላክ አስመለጠኝ ማለት ምን ያህል ተገቢ ነው?
ግርማ — እግዚአብሄር የሰው ልጆችን በንፍር ውሃ ባጠፋ ጊዜ በኖህ አማካኝነት በሰራው መርከብ እርሾ ማስቀረቱ አይዘነጋም፡፡መርከቡ ላይ የተሳፈሩ ሰዎች ግን በጠፉ ሰዎች ደስተኛ ነበሩ ማለት አይቻልም፡፡የእኔም እንደዚሁ ነው፡፡በመጽሀፉ ለማሳየት የሞከርኩት ይህንን ነው፡፡ሴራ የሚሰሩ ሰዎች ነበሩ፡፡እነዚህ ሰዎች ባላሰቡት መንገድ እንዲህ አይነት ነገር በመፈጠሩ ለእስር ተዳርገዋል፡፡እኔ አልታሰርኩም፡፡መቼም ብታሰር ጥሩ ነበር ይለኛል ብለህ እንደማትጠብቀኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ላይፍ –የአገሪቱ ህገመንግስት ፌደራላዊ ስርዓት መገንባቱን በማወጅ ሁለት የፌደራል ክልሎችንና ዘጠኝ ክልሎች እንዲቋቋሙ አድርጓል፡፡ስርዓቱ በብሄር ብሄረሰቦች የሚያምን በመሆኑም በዛ ያሉ ብሄር ተኮር ፓርቲዎች ተፈጥረዋል፡፡እርስዎ ደግሞ ብሄር ተኮር ፓርቲዎች ከፓርቲነት ወደ መንግስታዊ ወደልሆኑ ተቋማት እንዲወርዱ መፈለግዎን በመጻህፉ ጠቅሰዋል፡፡አባባልዎ ከነባራዊው የአገሪቱ ሁኔታ ጋር አይጋጭም?
ግርማ – እረ በፍጹም አይጋጭም፡፡በግልጽ መጽሀፉ ላይ እንዳስቀመጥኩት እነዚህ ድርጅቶች የሲቪክ ማህበራት መሆን ይችላሉ፡፡ለምሳሌ በኦሮሞ ላይ ህገ ወጥ ነገር ሲፈጸም እነዚህ ድርጅቶች ተጎዳ የሚሉትን የህብረተሰብ ክፍል በመያዝ ችግሩን ማሳየት ይችላሁ፡፡ፓርቲዎች መመስረት ያለባቸው በአስተሳሰብ እንጂ በብሄር መሆን የለበትም ምክንያቱም የኦሮሞ የአማራ የሚባል አስተሳሰብ የለም፡፡እንደዚህ ከሆነ እኮ አይሁዶች አንድ ፓርቲ ብቻ ይኖራቸው ነበር፡፡አረቦች ጋርም የምናገኘው አንድ ፓርቲ ብቻ ይሆን ነበር፡፡ኦሮሞ ላይ የሚደርስ ችግር እንዲሰማን የግዴታ ኦሮሞ መሆን አይጠበቅብንም፡፡ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው፡፡በብሄር ላይ ተመስሮቶ ፓርቲ መፍጠር የሰውን ልዮ አፈጣጠር አለመገንዘብ ነው፡፡
ላይፍ — ህብረ ብሄራዊነትን በመስበክ አንድነትን ለማጎልበት የሚጥሩት የፊውዳል ልጆችና የቀድሞ ስርዓት ናፋቂዎች ናቸው ይባላል፡፡እርስዎ የፊውዳል ልጅ ይሆኑ እንዴ ?
ግርማ — የፊውዳል ልጅ አይደለሁም፡፡ነገር ግን በባዮሎጂ መደራጀት የለብንም ብዬ አምናለሁ፡፡አይ መደራጀት አለብን የሚሉ ካሉም መብታቸው ነው፡፡ይህንን አከብራለሁ፡፡ሰው ከተሰጠው ነጻነት አንጻር መሳሳት መብቱ ነው የማይችለው ማሳሳት ነው፡፡እስኪ አስበው አንድ የኦሮሞ ልጅ ኦሮሞ ስለሆንኩ ምረጡኝ ቢል አያሳፍርም?፡፡አንድ አማራ እኔ አማራ በመሆኔ ልትመርጡኝ ይገባል በማለት ቢንጎማለል አያሳፍርም?፡፡ ኢትዮጵያ በጣም የተለየች ናት፡፡ኦሮሞ ወይም አማራ ስለሆንኩ ምረጡኝ ብለህ በክልልህ ብትመረጥ አገሪቱን መምራት አትችልም፡፡ኢትዮጵያን ለመምራት ኢትዮጵያዊ መሆን ያስፈልጋል፡፡እነዚህ ድርጅቶች ምንም አይነት ነገር መፍጠር አይችሉም እያልኩኝ አይደለም፡፡ነገር ግን አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ከክልሉ ውጪ ያለውን ህዝብ ድጋፍ ለማግኘት ሁሉንም የሚወክል ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡ይህን ለማድረግ ደግሞ ከብሄሩ ይልቅ የሁሉንም ልብ ሊያስገኝለት የሚችልን ሃሳብ መያዝ
ላይፍ — አሁን እርስዎ ከሚነግሩን በተቃራኒው ኢትዮጵያ ውስጥ መንደርተኝነት፣ብሄርተኝነትና ክልላዊነት እየተስፋፋ ይገኛል፡፡በዚህ ክበብ ውጪ በኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ነገሮች አስቸጋሪ አይሆኑም?
ግርማ — የህብረ ብሄራዊፓርቲዎች ፈተናም ይህ ነው፡፡ሰዎች ስሜታቸው ተነክቶ የሚነሱት ሐይማኖታቸው ብሄራቸውን የተመለከቱ ነገሮች ሲነካባቸው ነው ይህ በጣም መጥፎ ነገር ነው፡፡ለምሳሌ አንተ የቡርጂ ህዝብ ተወካይ ነኝ ብለህ ብትነሳ በፓርላማው የምታገኘው አንድ ወንበር ነው፡፡ታዲያ እንዴት ነው በአንድ ወንበር በዚህች አገር ተጽእኖ ለመፍጠር የምታስበው? እኔም የወረዳ 6 ህዝባዊ ንቅናቄን በማቋቋም እንዴት ነው አገር መምራት የምችለው?፡፡ በትልቁ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ ምንም ለውጥ እንደማያመጡ አልተረዱም፡፡
ላይፍ — በምክትል ፕሬዘዳንትነት የሚመሩት የፓርቲዎ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የፖለቲካ ፍልስፋና ወይም የሚከተለው ርዕዮት ምንድን ነው?
ግርማ — ይህ በግልጽ በፕሮግራማችን ላይ ተቀምጧል፡፡ጋዜጠኞች ስለማትመለከቱ ወይም ከእኔ ለመስማት ካልፈለግክ በስተቀር ማ ለት ነው፡፡አንድነት በግልጽ የሊበራል ዲሞክራሲ አራማጅ ነው፡፡ነገር ግን ይህንን የምንከተለው በኢትዮጵያ ነባራዊ እውነታ ነው፡፡ለምሳሌ ተማሪዎች በሙሉ እየከፈሉ መማር አለባቸው አንልም፡፡ይህ ቢሆን ብዙ ልጆች ትምህርት ቤት መሄድ አይችሉም፡፡ከስምምነት ዲሞክራሲም በተወሰነ ደረጃ የምንወስደው ነገር አለን፡፡እንደ አስተሳሰብ መውሰድ ያለብን ጠቃሚ የሆነውን ነገር ነው፡፡አንድነት ውስጥ በጣም ብሄርተኛ የሆነ ሰው በመግባት ፓርቲው የሆነን ብሄር ሆን ብሎ የመጨቆን አላማ እንደሌለው መመልከት ይችላል፡፡
ላይፍ — ይህንን ጥያቄ ያነሳሁት በቅርቡ የፓርቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ‹‹አንድነት ሊበራል ነኝ ካለ ችግር ይፈጠራል››በማለት በመናገራቸው ነው
ግርማ — እሱ እንግዲህ በቅርቡ ጠቅላላ ጉባዔ ስለምንጠራ ምላሽ ያገኛል፡፡በሌላ መንገድ ካልሆነ ጭልጥ ብለን ነጭ ሊበራል የምንሆንበት ምክንያት ስለሌለ እርሳቸውም የሚወጡበት ነገር የለም፡፡
ላይፍ — ወደ ፓርላማው እንመለስ፣በቅርቡ ባስነበቡን አንድ አርቲክል ፓርላማው በቀኝ ክንፍ ሲያጠቃ ዋለ ብለዋል፡፡ሌሎችም በፓርላማው ውስጥ መጠነኛ የሆነ መነቃቃት ስለመፈጠሩ ይናገራሉ፡፡ይህ መነቃቃት እውነት አቶ መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ የተፈጠረ ነው?
ግርማ — ምንም ጥርጥር የለውም እርሱ ስለመሆኑ፡፡ነገር ግን በፓርላማውም ይሁን ከመንገስት ባለስልጣናት ይህ የሆነው የእርሳቸውን ሞት ተከትሎ ነው ይላሉ ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡እነርሱ ሊሉት የሚችሉት ባለፉት ሶስት አመታት የአቅም ግንባት ተካሂዶ በመጨረሻዎቹ ሁለት አመታት ሰራንበት ነው፡፡ይህ ግን ትክክል አይደለም፡፡አቶ መለስ በነበሩበት ግዜ ፓርላማው ምንም አለ ምን እርሳቸው የሚሉት ነገር ብቻ ስለሚፈጸም ለምን እናገራለሁ የሚል ስሜት ነበር፡፡እርሳቸው ከሄዱ በኋላ ግን አቶ ሃይለማርያም ፓርላማውን እንደተቋም መጠቀም ግድ ይላቸዋል፡፡ምክንያቱም እርሳቸው እንደ ቀድሞው ሁሉን ሉጠቀልሉ አይችሉም፡፡እዚህ ላይ ካነሳህው አይቀር ፓርላማው በቀኝ በኩል ሲያጠቃ ውሎ በግራ በኩል ጎል አገባ ብዬ ነበር ነገር ግን አሁን ፓርላማው ያገባው ጎል ተሰርዟል፡፡በእግር ኳስ ጎል ካገባህ በኋላ ጎሉ የሚሰረዘው አመከልክተህ ነው አይደል?እዚህ ግን ጎሉ የተሰረዘው እንዲህ አይደለም፡፡የተሰረዘው ጎል የሚያመጣው ነገር አለው፡፡ፓርላማው በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ቢወስን በግምገማ ውሳኔው የሚታጠፍ ከሆነ ፓርላማው ወደ ቀድሞ ቦታው ሊመለስ ይችላል የሚል ስጋት አለኝ፡፡የአንድ የምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት የሚነሳ ጥያቄው በፍትህ ሚኒስትር በኩል ነው፡፡ከዚህ በፊት የአቶ ያረጋል አይሸሹም አለመከሰስ ሲነሳ በህጉ መሰረት አልነበረም አሁንም እንዲህ ይደረግ ተብሎ ነበር ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነበር ፓርላማው የወሰነው ግን አሁን ውሳኔው እንዲታጠፍ ተደርጓል፡፡ሰውዬውም ከአገር ወጥተዋል፡፡በእውነት የ500 ካሬ ጉዳይ አይደለም፡፡አባሉም መሬቱን ከአንዱ ወስደው ለሌላ ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡ለማን ነው የሰጡት ከማን ነው የወሰዱት የሚለውን ነገር እንደ ጋዜጠኛ ማጣራትና ለህዝብ ማሳወቅ የእናንተ ድርሻ ነው፡፡
ላይፍ — በፓርላማው የሚያደርጓቸው ንግግሮችና የሚያቀርቧቸው ሞሽኖች ተቀባይነት አጥተው ወይም የተለየ ትርጉም ተሰጥቷቸው ሲቀርቡ ሲመለከቱ ምን አለበት ፓርላማ ባልገባሁ ብለው አያውቁም?
ግርማ – አላውቅም፡፡ምክንያቱም ከመግባቴም በፊት የማቀርበው ሃሳብ ተቀባይነትን ያገኛል ብዬ አልጠበቅኩም፡፡ነገር ግን ተናድጄ አውቃለሁ ስትናደድ ንግግር ማቋረጥ ትችላለህ እኔ ግን ለመበጥበጥ አልገባሁምና ይህንን ማድረግ አልፈለግኩም፡፡እኔ እዛ ስገባ አማራጭ እንዳለ አውቀው እንዲወስኑ የታሪክ ጨዋታ ለመጫወት ነው የገባሁት፡፡ሁሉም ነገር በታሪክ የሚመዘገብ በመሆኑ በታሪክ ተጠያቂ እንሆናለን፡፡
ላይፍ — በተለያየ አጋጣሚ ከአገር ሲወጡ በውጪ የሚያገኟቸው የሌሎች አገራት የፓርላማ አባላት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በፓርላማ መሆንዎን ሲሰሙ ምን ይልዎታል?
ግርማ — ያው መገረማቸው አይቀርም፡፡አብረውኝ የሚሄዱት የፓርላማ አባላትም እንዲህ አይነት ነገር ሲነሳ ይሸማቀቃሉ እኔ ግን አልሸማቀቅም የሚሸማቀቁት እነርሱ ናቸው፡፡በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ኢህአዴግ ሜዳውን ክፍት በማድረግ ለመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ የሚጠቅም ነገር ያደርጋል የሚል እምነት ነበረኝ ነገር ግን ምንም ቀዳዳ ሳይፈጥር ሁሉንም አሸንፊያለሁ አለ፡፡ዝግጁነት አለመኖሩን በዚህ አሳይቶናል፡፡ስለዚህ ለ2007 ምርጫ ነጥቀን ለመውሰድ ጠንክረን መስራት ይኖርብናል፡፡እንደ አንድነትም ይህንን ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምረናል፡፡
ላይፍ — አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ በቅርቡ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት መሆን እንደሚፈልግ ይፋ አድርጓል፡፡የአትሌቱን የፕሬዘዳንትነት ፍላጎት እንዴት አገኙት?
ግርማ –ከራሱ ከሃይሌ ጋር ተነጋግሪያለሁ፡፡በመጀመሪያ ሃይሌ ፕሬዘዳንት ለመሆን የፈለገው እንደ አሜሪካ መስሎት ነው፡፡ምንም ስልጣን የሌለው ፕሬዘዳንት ሃይሌ መሆን ይፈልጋል የሚል እምነት የለኝም፡፡አሁን ግን የፓርላማ አባል ሆኖ የሆነ ነገር ማበርከት ፈልጓል፡፡ነገር ግን በግሉ ተወዳድሮ ፓርላማ ቢገባ ምንም የሚጨምረው ነገር እንደሌለው ነግሬዋለሁ፡፡ሃይሌ ኢህአዴግ መሆን አይችልም ምክንያቱም አስተሳሰቡ የካፒታሊስት ነው፡፡ሃይሌ የአንድነት አባል መሆን ግን ይችላል፡፡የምችለውን በግሌ ማድረግ እችላለሁ ካለ መብቱ ነው፡፡አንዳንድ ሰዎች ሃይሌ ወደ ተቃዋሚዎች ቢመጣ በገንዘብ ይደግፋቸዋል ይላሉ ነገር ግን ይዞ መምጣት ያለበት ሊበራል የሆነ አስተሳሰቡን ነው፡፡ከዚህ ውጪ ግን ሃይሌን በኢህአዴግ መስመር ውስጥ አገኘዋለሁ ብዬ አልጠረጥረውም፡፡ ስልጣን የሌለው ፕሬዘዳንት ከሚሆንም የሪዞርቱ አስተዳዳሪ ቢሆን ይሻለዋል፡፡
ላይፍ — የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል መሪ ቃል ፓርቲዎ ህዝባዊ ንቅናቄ እያደረገ ይገኛል፡፡በአጠቃላይ ተቃዋሚዎች የሚገኙበትን መነቃቃት እንዴት ተመለከቱት?
ግርማ — ብዙዎች አንድነት ንቅናቄውን የጀመረው ከሌሎች ኮርጆ ነው ይላሉ ፡፡ነገር ግን ኮርጀንም ከሆነ ችግር የለብንም፡፡አውነታው ግን ይህ አይደለም እያደረግነው ያለው በስትራቴጂክ ፕላናችን መሰረት ነው፡፡ጎንደርና ደሴ ላይ ያደረግናቸው ሰላማዊ ሰልፎች በመዋቅራችን አማካኝነት የሰራነው ነው፡፡በቀጣይም ይህንን በተለያዮ ክልሎች እናደርጋለን፡፡ሚልዮኖች ከእኛ ጋር ሆነው የሚጠይቁት የተለያዩ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ነው፡፡
ላይፍ — የፓርቲውን ንቅናቄ መጀመር ተከትሎ በዛሚ ሬዲዩ በጋዜጠኞች የክብ ጠረጴዛ ፕሮግራም ሚሚ ስብሃቱ አንድነት ይህንን ንቅናቄ የጀመረው ከውጪ በተለይም ከግንቦት 7 ከግብጽ ካገኘው ገንዘብ ፍርፋሪ እንዲደርሰው አስቦ ነው ብላለች ይህ አለመሆኑን እርስዎ በምን ሊያስረዱ ይችላሉ?
ግርማ — እንኳን ነው የምንላት፡፡በስተርጅና ሚሚ መሆኗን ከማሳየቷ ውጪ እርሷ እንዲህ ብላናለችና አይ እኛ እንዲህ ነን ማለት አንፈልግም፡፡አንድ ወቅት ላይ ሚዲያውን በተመለከተ የሆነ ካውንስል ለማቋቋም መንቀሳቀሷን በተመለከተ ለንባብ የበቃ ጽሁፍ አንብቤ ነበር፡፡ጽሁፉ ካውንስሉ መቋቋሙን ቢደግፍም የሚሚን መኖር ግን ክትፎ በፖፖ ብሎት ነበር፡፡እኔም ከዚህ ውጪ የምለው ነገር የለኝም፡፡
ላይፍ — ገዢው ፓርቲ ንቅናቄውን ከአክራሪነት እያቆራኘው ከመሆኑም በላይ ፖሊስ ወረቀት የሚበትኑ አባሎቻችሁን እያሰረ ነውና ንቅናቄው የሚሳካ ይመስልዎታል?
ግርማ — ንቅናቄው እኮ ይህንንም ለመታገል ታስቦ የተጀመረ ነው፡፡እያንዳንዱ ሰው አምባገነንነትን እምቢ ማለት አለበት፡፡ዋነኛው የንቅናቄው ግብ ከፍርሃት መውጣታችንን ማሳየት ነው፡፡ይህንንም እያደረግን እንደሆነ እናምናለን፡፡
ላይፍ –ህዝባዊ ንቅናቄው የሶስት ወር ዕድሜ እንዳለው ተነግሯል፡፡ከሶስት ወር በኋላ ምን ልታደርጉ ነው?
ግርማ — የሶስት ወሩ ንቅናቄ እንደ መነሻ ነው፡፡መስከረም ላይ ጠቅላላ ጉባዔ ይደረግና የሁለት አመት እንቅስቃሴያችን ይገመገማል፡፡ከዚያም 2007 ምርጫ የምናደርገውን ዝግጅት ህዝብን በሚያሳትፍ መልኩ እንገፋበታለን፡፡እናም ይህ የመጀመሪያ እንጂ በየትኛውም መንገድ የመጨረሻችን አይሆንም፡፡መጽሐፍስ የፈራ ይመለስ ይል የለምን?

↧

የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ቃለ ምልልስ ከጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋር

$
0
0

የጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋዜጠኛ ሸዋዬ ለገሰ የዘ-ሐበሻ እና የጤና አዳም ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁን አነጋግራዋለች። ቃለምልልሱ በጀርመን ድምጽ ራድዮ ላይ ተላልፏል። የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች እንድተከታተሉት እዚህ በማምጣት አካፍለናችኋል።

ስለጤና ጉዳይ የሚቀርቡ መረጃዎችን ምን ያህል ህዝብ እንደሚያገኛቸዉ፤ ወይም ለምን ያህል ህዝብ እንደሚደርሱ መገመት ይቸግራል። ነገር ግን አንድ ነገር ግልጽ ነዉ ሰዎች ለጤና ይዞታቸዉ ትኩረት መስጠትን ችላ ሊሉ አይገባም።
ጤና-ነክ ጉዳዮችን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ለማቅረብ መጣር የእኛን ኅብረተሰብ ሊነቃ ይችላል የሚል እምነት ያላቸዉ ወገኖች ራሱን የቻለ የጤና ድረገጽ ከፍተዉ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ወራት ተቆጥረዋል።
ዘመኑ የቴክኒዎሎጂ ነዉ የመረጃ፤ በአንዱ ጓዳ የተከሰተዉን ሌላዉ ባለበት ሆኖ ሊሰማዉ መንገዱ ተመቻችቷል፤ ለብዙሃኑ። በዘመነ ኢንቴርኔት ምስጢር የለም፤ ራዲዮና ቴሌቪዥን ዜናዎችን አልተከታተልኩም፤ የጤና ጉዳይ መረጃዎችን እንደልቤ አላገኝም ከሚባልበት ጊዜ ልንሻገርም ዳርዳር እያልን ይመስላል። አፍሪቃ ዉስጥም ቢሆን ይህ ዛሬ ብዙም የሚወራለት የራቀና ያልተደረሰበት ጉዳይ አይደለም።

ዛሬ ይላል የጤና አዳም ድረገጽ አንቀሳቃሽ፣ ዛሬ ሰዎች ለራዲዮና ቴሌቪዥኑ ጊዜ ቢያጡ እንኳ ከያሉበት በእጅ ስልካቸዉ በየመንገዱም ቢሆን የሚሹትን መረጃ ማንበብ ይችላሉ። የተለያዩ ወቅታዊ ዜናዎችን ከመዘገብ በተጓዳኝ ሄኖክ ዓለማየሁ ለጤና ጉዳይም ትልቅ ትኩረት መስጠቱን የሚያንቀሳቅሰዉ ድረ ገጽ ዘሃበሻ ይናገራል። ለጤና መረጃዎችን የምታጋራዉን ድረገጽም እዚያዉ ላይ ታዝላ ነዉ ያስተዋልኳት። አዘጋጅዋ ለጤና ጉዳዮችን ትኩረት መስጠት ይገባል በሚል ለኢትዮጵያዉያን አንባቢዎቹ መረጃ በመስጠት ለማበረታታት ታስቦበት የተጀመረ መሆኑን ነዉ የሚናገዉ፤
ጋዜጠኛ ሄኖክ እንደሚለዉ ባላቸዉ መረጃ መሠረት በርካታ የድረገጹ ጎብኚዎች የሚገኙት እዚያዉ ሰሜን አሜሪካ ነዉ። ከኢትዮጵያስ ጎብኚዎች ይኖሩት ይሆን? ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ

(ምንጭ፡ የጀርመን ድምጽ ራድዮ)

↧
↧

40 የዓድዋ ተወላጆች ታሰሩ

$
0
0

Abrham Destaከዓመታት በፊት በእርሻ መሬት ማነስ ምክንያት ወደ 400 የሚሆኑ የዓድዋ ተወላጆች (ልዩ ስሙ ‘ወርዒለኸ’ ከሚባል ቦታ) በመንግስት አካላት ከቀያቸው ተነስተው በቃፍታ ሑመራ ወረዳ (ጣብያ ማይወይኒ፣ ቁሸት መንሼን) እንዲሰፍሩ ተደረገ። ቤት ሰሩ፤ ኑሯቸው እዛው መሰረቱ።

አሁን ግን አዲስ ነገር ተከሰተ። የሰፈሩበት፣ ኑሯቸው የመሰረቱበት መንደር ለከብቶች እርባታ ‘ተስማሚ ሁኖ ስለተገኘ’ በኢንቨስትመንት ስም ከብቶች ለሚያረባ ድርጅት እንዲሰጥ ተወሰነ። አርሶአደሮቹ ያለ ምንም ካሳ ቀያቸው ለቀው እንዲነሱ ታዘዙ። ካሳ ጠየቁ፤ እንደማይሰጣቸው ተነገራቸው። ለመኖርያ የሚሆን ቅያሪ ቦታ ጠየቁ። መልስ አልተሰጣቸውም። ቀያቸው ባጭር ግዜ ዉስጥ ለቀው እንዲወጡ ሲነገራቸው አርሶአደሮቹ ጠንከር ያለ ተቃውሞ አሰሙ።

ከነዚህ 400 የሚሆኑ የተፈናቀሉ አርሶአደሮች ‘የተቃውሞው አስተባባሪዎች ናቸው’ ተብለው የተጠረጠሩ 40 አባወራዎች ታሰሩ። ክስ መመስረት እንኳን አይችሉም። ምክንያቱም መሬት የመንግስት ነው።

መሬት የሌለው ዜጋ ሀገር የለውም። መሬት የመንግስት ከሆነ የመንግስት አካላት (የገዢው ፓርቲ አባላት) በፈለጉበት ግዜ ዜጎችን ማፈናቀል ይችላሉ።

 

ለትግራይ ተወላጆች በሙሉ ……. 
Abraha Desta
—————————————-
‘ዜጎች ነንና ፍትሓዊ ልማት ያስፈልገናል’ ሲንል አሰሩን። ‘ደማችን ገብረናልና ሰለማዊ ሰልፍ የመውጣት መብታችን ይከበርልን’ ስንል ደበደቡን። ‘ብዙ መስዋእት ከፍለናልና ነፃነታችንን አትንፈጉን’ ስንል ትጥቃችንን አስፈቱን። መብታችንን ለማስከበር ስንሞክር ገደሉን።

ግን ይህን ሁሉ ወላጆቻችን፣ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የከፈሉት መስዋእት ዓላማው ምን ነበር? ደርግን ደምስሶ ሌላ ደርግ መመስረት? ይሄማ ሊሆን አይችልም። ደርግ’ኮ ደርግ ያሰኘው ተግባሩ ነው።

ደርግን የምንጠላው ደርግ ስለሆነ አይደለም። መጥፎ ምግባር ስለነበረው ነው። ጨቋኝ ስለነበረ ነው። ገዳይ ስለነበረ ነው። ገዳዮቹ ቢቀያየሩ እንኳን ተግባራቸው ያው ግድያ መሆኑ አይቀርም። ገዳይ ማን ይሁን ምን ያው ገዳይ ነው። ደርግ እንዲጠላ ያደረገው ገዳይነቱ ነው። ለኛ የገደለ ሁሉ ደርግ ነው። መግደል፣ በሰው ልጅ ላይ ግፍ መፈፀም፣ መጨፍጨፍ ምን ያህል መጥፎ መሆኑ ከልምድ እናውቀዋለን። ስቃዩ ምን ያህል መራራ እንደሆነ ከራሳችን በላይ ማንም ሊያስረዳን አይችልም።

የኢህአዴግ ወታደሮች (ይቅርታ የመንግስት ወታደር ስለሌለ ነው) ኮፈሌ አከባቢ በህዝቡ ላይ ችግር መፍጠራቸው እየሰማን ነው። ወታደሮቹ ለሚወስዱት እርምጃ ምክንያት ያቀርቡ ይሆናል። የፈለገ ምክንያት ቢኖር እንኳን በሰለማዊ ዜጎች ላይ ግፍ መፈፀም ሊደገፍ አይችልም። መፍትሔም ሊሆን አይችልም። የኃይል እርምጃ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንደማይሆን ለመገንዘብ የደርግ ስርዓት ትግራይን ሲደበድብ የተከሰተውን ማስታወስ በቂ ይመስለኛል።

የኢህአዴግ ወታደሮቹ በኮፈሌ ሰለማዊ ህዝብ ላይ ችግር ሲፈጥሩ በተጎጂዎች ስነልቦና የሚፈጠር ስሜት ልክ የደርግ ወታደሮች እኛ ላይ ግፍ ሲፈፅሙ በኛ አእምሮ ዉስጥ የተከሰተው ሓዘንና የእልህ መንፈስ ነው። ደርግ የፈፀመው ግፍ በኛ ከባድ ጠባሳ ጥሎ አልፈዋል። በኮፈሌዎችም ተመሳሳይ ነው። ለኮፈሌዎች (በኛ ስሜት) ኢህአዴግ ደርግ ሁነዋል። ደርግ እኛን ገደለ፤ ኢህአዴግ እነሱን ገደለ። ያው የሁለቱም ግድያ ነው። ሁለቱም ስርዓቶች በየ አቅጣጫቸው ተመሳሳይ ናቸው። ገዳዮች ናቸው።

በሰዎች ላይ ግፍ ሲፈፀም መቃወም ይኖርብናል። ደርግ ሲገድለን ግድያው ለደገፉ፣ የደርግ ተግባር ደጋፊዎች ለነበሩ፣ ወይ ተቃውሟቸውን በግልፅ ላላሰሙ ወገኖች የሚኖረንን ስሜት በራሳችን እንገምግመው። ቤተሰቦቻችን ላይ በደል ወይ ግድያ ሲፈፀም ከጎናችን ለቆሙ ወገኖች ትልቅ ውለታ እንደዋሉልን የሚሰማንን ያህል በሌሎችም ተመሳሳይ ግብረመልስ ይኖራል። ጉዳት ከደረሰባቸው ዜጎች ጎን መሰለፍ የብሄር ወይ የሃይማኖት ጉዳይ አይደለም፤ የሰብአዊነት ጥያቄ እንጂ።

ስለዚህ ይህን የኢህአዴግ ዜጎች የመበደል ተግባር መቃወም ይኖርብናል። ፖለቲከኞች ስልጣናቸው ለማደላደል ሰለማዊ ሰዎች ላይ ግፍ ይፈፅማሉ። ሰለማዊ ሰው ሲበደል ሌላ የሚጠቀም ሰለማዊ ሰው ሊኖር አይችልም (ከፖለቲከኞች በቀር)። በስልጣን ላይ ያለው አካል ሰው የሚበድለው በስልጣኑ ለመቆየት ሲል ነው፤ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችም ሰው መንግስት ሲበደል ድጋፍ የሚያገኙበት ዕድል ይኖሯቸዋል። ስለዚህ ከህዝብ በደል ሊጠቀሙ የሚችሉ ፖለቲከኞች ብቻ ናቸው። ለሰለማዊ ሰው ግን (የሰለማዊ ሰዎች በደል) ጉዳት ብቻ ነው ያለው። ስለዚህ መቃወማችን ግድ ይላል።

ህወሓት ኢህአዴግ ከኛ ወጣ። እኛን ተመልሶ በደለ። ይባስ ብሎ ደግሞ በኛ ስም ሌሎችን ይበድላል። ይህ ህዝቦችን የመበደል ተግባሩ ሁላችን እንቃወመው።

ይህ የሰብአዊነት ድምፅ ነው።

It is so!!!

 

 

↧

የችግሮች መንስኤ እኛ እራሳችን ነን –በይበልጣል ጋሹ

$
0
0

በይበልጣል ጋሹ

commnetዛሬ ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግር እየጨመረ መምጣቱ ዓለምን ስጋትና ጭንቀት ውስጥ ከቷታል። ለአንዱ ችግር መፍትሔ ይሆናል ተብሎ የቀረበው ሃሳብ በሌላ በኩል ሊፈታ የማይችል ችግር ፈጣሪ ሲሆን መመልከት የተለመደ ነገር ነው። ምንም እንኳ /ከተለዩ ሰዎች በስተቀር/ ሰው በራሱ ችግር ለመፍጠር ተነሳሽ ባይሆንም ለመፍትሔም የዘገኘና ቆራጥነት የማይታይበት በመሆኑ ለችግሩ መበባስ መንስኤም ምክንያትም ነው። በዚህች አጭር ጽሁፍም የእኛ የችግር መንስኤነትን በአጭሩ ለማሳየት እሞክራለሁ። ሙህራን በዚህ ዙርያ ሰፊ ጥናት በማድረግ እንዲያቀርቡልን ግብዣየ በደስታ ነው።

 

  • እንደሚታወቀው እንደ አህጉራችን አፍሪካና አገራችን ኢትዮጵያ ሁላችንንም የሚያሳስበንና ጎልቶ የሚታየው የአስተዳደር/ፖለቲካዊ ችግር ነው። እንደሚታወቀው ሁሉም የፖለቲካ ድርጅት/ገዢው ፓርቲ/ ለነጻነት፣ ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለሰባዊ መብትና ለዲሞክራሲ እቆማለሁ ብሎ መነሳቱንና የህዝብ ድጋፍ ማግኘቱን ረስቶ የበፊቱንና የአለፈውን የአስተዳደር ዘመን በእጅጉ የሚያስመሰግን ሁኖ እናገኘዋለን። ዘረኝነትንና አድሎአዊነትን ለመዋጋት የተነሳ ድርጅት ከበፊቱ በበለጠ ችግር ፈጣሪ ሲሆን ጎልቶ ይታያል። ሙስናን ለመዋጋት የተነሳ ድርጅት ለሙስና መስፋፋት ዋነኛ ተዋናይ መሆኑ በእጅጉ ያሳስባል። ድህነትን ለማጥፋት የተነሳ ድርጅት ራሱን ከማበልጸግ ባለፈ የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ከቲዮሪ/theory/ ባለፈ መቀየር አልቻለም። ዲሞክራሲን አሰፍናለሁ ብሎ የተነሳ ድርጅት ሚድያ ላይ ከመናገር ባሻገር ህብረተሰቡን የዲሞክራሲ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ግን አልቻለም። ምን አልባት ኢትዮጵያ በዲሞክራሲዊ አስተዳድር ስርዓት ትመራለች፣ ድህነት ቀንሷል ልንል እንችል ይሆናል፤ እውነት ነው የእኛም ትልቁ ችግራችን ይህ ነው። በመካከላችን 100% ልዩነት መኖሩ የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል በምቾት፣ በሰላም፣ በደስታ፣ በነጻነትና ዲሞክራሲ ሲኖር አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ደግሞ በእጅጉ በሚያሳዝን ሁኔታ በርሀብ፣ በችግር፣ በስቃይ፣ በአድሎአዊነትና በነጻነት እጦት ውስጥ መኖሩ ችግሩ ጎልቶ እንዲታይ አድርጎታል።

ለችግር መንስኤዎች እኛው ነን ያልኩበት ምክንያትም የፓርቲውን/የድርጅቱን ዓላም በሚገባ ሳንረዳና ሳንገነዘብ ከመጀመሪያው ጀምረን ይሁን ብለን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረጋችን ነው። ግማሾቻችን ደግሞ ሳይመቸን እንደ ተመቸን፣ ሳንጠግብ እንደ ጠገብን፣ ነጻነትና ዲሞክራሲ ሳይኖር በነጻነት እንደምንኖር ሁሉ እንደ ሄሮዶሳውያን ሺ ዓመት ንገስ፣ ከአለአንተ አገር ትገለበጣለች፣ ለህዝቡ ተቆርቋሪ የለም እያልን ችግሩን እንዲያስተካክል በግልጽ ከመናገር ይልቅ የማይገባውን የምስጋና ቅኔ ስለምናቀርብ፤ ከፊሎች ደግሞ በጊዜያዊ ጥቅም ተይዘው ችግሩን እንዳንመለከት ከለላ ስለሆነብንና መሰል ችግሮች ስላሉብን ለችግሩ መባባስ ዋነኛ ተጠያቂዎችም መንስኤዎችም እኛው እራሳችን ነን።

  • ለተለያዩ ችግሮች የመፍትሔ ሃሳብ ከምንጠብቅባቸው የእምነት ተቋማት ሳይቀር በመሪዎቻችን መካከል ዘርፈ ብዙ ችግሮችን እናገኛለን። ጥቂት የእምነት መሪዎች/አባቶች ነን ባዮች ከአለም ባለስልጣናት ባልተለየ መልኩ አስተዳደራዊ በደል በእምነት ተቋማቸው ላይ ሲያደርሱ መመልከት የተለመደ ነገር ሁኗል። ዘረኝነትንና ሙስናን ይዋጉልናል ያልናቸው ሰዎች ለችግሩ መፋጠን ዋነኛ አካል ሁነዋል። ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር በተሰጠችው መመርያ ተጠቅማ ለአለም ሰላም የማደል ፀጋ ቢኖራትም ዳሩ ግን እነዚያ ጥቅመኞች ፀጋዋን ለዓለም እንዳታድል አዚም ሁነውባታል።

ለዚህም ችግር መንስኤ  እኛው የእምነቱ ተከታዮች ነን። ለምን ቢባል በተለያየ ዘርፍ ላይ ለሚገኙ የእምነት ተቋም አስተዳዳሪዎች ፊት በሙስና፣ በስርቆትና በብልሹ አስተዳደር ስለበለጸጉ ሰዎች እናወራለን፣ እንተርክላቸዋለን። በእነዚህ ነውረኛ  ሰዎች ላይም ምንም አይነት የእምነት ሃላፊነታችንንና ግዴታችንን መወጣት ባለመቻላችን ሌሎች እንደማበረታቻ ቆጥረውታል። በእነዚህ እና መሰል ምክንያቶች ችግሮች እንዲበባሱ የእኛ አስተዋጾ ቀላል እንዳልሆነ መገንዘብ ይቻላል።

  • ወደ ባዕድ ሀገር በስደት የሚጎርፈው ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ሀገር ቤት ሰው የማይኖር እስኪመስል ድረስ ፍላጎቱና ፍልሰቱ ከፍተኛ ሁኗል። ለዚህ ችግር በዋናነት የመንግሥት አስተዳደራዊ ድክመት ቢሆንም እኛም የበኩላችንን ድርሻ ባለመወጣታችን የመጣ ትልቅ ችግር ነው። በስደት የሚኖሩ ወገኖች የስደትን አስከፊነት እያወቁ ነገር ግን በሀገር ቤት ለሚኖሩ ወገኖቻቸው ችግሩን በሚገባ አለማስረዳት፣ ወደ ሀገር ቤት በሚሄዱበት ጊዜም የተለየ ለብሰውና መስለው መታየታቸው እና የሚሰሩትን የሥራ አይነት እንኳ በትክክል አድካሚነቱንና አሰልችነቱን አለመናገር ለሌሎች ከሀገር መውጣት ምክንያት ሁኗቸዋል። ስለዚህ የሆነውንና የሚሆነውን በትክክል መረጃ መስጠት ብንችል ወገኖቻችን በይሆናልና በማይሆን ተስፋ ከሀገር ወጥተው የስደትን አስከፊ ህይወት ተጠቂ ባልሆኑ ነበር።

ስደት ምንልባት በኢኮኖሚ የተሻለ ነገር ሊኖረን ይችል ይሆናል እንጂ የሰላም ኑሮ  ግን መኖር የሚቻለው ተወልደው በአደጉበት ሀገር ነው። በስደት ህይወት የባህል፣ የእምነት፣ የአለማዊነትና የቋንቋ ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ የተረጋጋና ሰላማዊ ህይወት መምራት በጣም አስቸጋሪና ከባድ ነው። በዚህም የተነሳ በጭንቀትና በውጥረት የሚኖሩ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። ስለዚህ ሰውን ወደ ስደት ህይወት መጋበዝ በጭንቀትና በሃሳብ እንዲኖር መፍረድ የሚል ድምዳሜ ቢሰጥ ያንሳል እንጂ ማጋነን አይሆንም።

በአጠቃላይ እኛ ሁላችንም ብንችል የችግር መፍትሔዎች እንድንሆን ባንችል ደግሞ የችግር መንስኤዎች እንዳንሆን የራሳችንን በጎ አስትዋጾ ማድረግ ይኖርብናል። ለችግር መፍትሔ ይሆናሉ ያልካቸውን 2 ላንሳና ሌላውን እናንተ ቀጥሉበት።

  1.  ችግሮችን በትክክል መረዳት፦ ችግሩን ከስር መሰረቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ በአጠቃላይ ሀገራዊ ጉዳቱን መረዳትና ችግሩ እንዳይበባስ የራሳችንን አስተዋጾ ለማድረግ ችግሩን በትክክል መረዳት ይጠበቅብናል። ሙህራን “ችግሩን ማዎቅ የመፍትሔ 50% ነው” እንዲሉ  ችግሩን በትክክልና በጥልቀት መረዳት ካልቻልን መፍትሔ በቀላሉ ለማግኘት አስቸጋሪ ስለሚሆን የችግሩን የት፣ መቼ፣ እንዴትና ወዴት የሚሉትን ጥያቄዎች በማንሳት ችግሩን ከመሰረቱ ማዎቅ ከሁላችን የሚጠበቅ ተግባር ነው።
  2. ችግሩን ለማሶገድ በቆራጥነት መነሳት፦ ችግሩን በትክክል ከተረዳን መፍትሔ ለማምጣት ደግሞ  በቆራጠነት መነሳት ይኖርብናል። ፍራትን፣ ቸልተኝነትን፣ አይሆንም ባይነትን፣ አድርባይነትን፣ ጥቅመኝነትንና ዘረኝነትን ከውስጣችን አሶጥተን ለሀገርና ለተተኪ ትውልድ በሁሉም በኩል የበለጸገች ሀገር ለማስረከብ ቆራጥነትና ሰማትዕነት ያስፈልጋል። የማንም ርዳታ ሳያሻን በራሳችን ተነሳሽነት ሀገራዊ ሃላፊነታችንን ለመወጣት እና ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ሁላችንም ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል።…………………….+++

 

↧

Sport: ቲኪ ገላና የኦሊምፒክ ድሏን በሩሲያ ለመድገም ተቃርባለች

$
0
0

ከቦጋለ አበበ

በሁለት ዓመት አንዴ የሚካሄደው የዓለማችን ትልቁ የአትሌቲክስ የውድድር መድረክ (የአትሌቲክስ የዓለም ዋንጫ ) በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ ሊጀመር የሃያ አራት ሰዓታት እድሜ ይቀሩታል፡፡ ይህን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርካታ የስፖርት አፍቃሪዎች በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ፡፡
ውድድሩ ነገ ሲጀመር ማለዳ ላይ በጉጉት የሚጠበቀው የሴቶች ማራቶን ውድድር ይካሄዳል፡፡ በዚህ ውድድር ውጤት ያስመዘግባሉ ተብለው ከሚጠበቁ አትሌቶች መካከል የኦሊምፒክና የኢትዮጵያ የርቀቱ ባለ ክብረወሰን የሆነችው ቲኪ ገላና ግንባር ቀደሟ ነች፡፡
ባለፈው ለንደን ኦሊምፒክ ከወደቀችበት ተነስታ አስቸጋሪውን የማራቶን ውድድር በድንቅ የአጨራረስ ብቃት ማሸነፍ የቻለችው ቲኪ በዘንድሮው የዓለም ሻምፒዮናም የአሸናፊነት ግምት ያገኘች አትሌት መሆን ችላለች፡፡
tiki gelana
ቲኪ ባለፈው ዓመት በርቀቱ 2፡18፡50 የሆነ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ የስፖርቱን አፍቃሪዎች ያስደነቀች አትሌት መሆኗ በነገው የዓለም ሻምፒዮና ትኩረት የሚሰጣት አትሌት እንድትሆን አስችሏታል፡፡ ቲኪ በዘንድሮው ዓመትም በርቀቱ 2፡36፡55 የሆነ ሰዓት ያስመዘገበች ጠንካራ አትሌት መሆኗ በውድድሩ የአሸናፊነት ግምት እንዲሰጣት አድርጓል፡፡
ቲኪ ገና በርቀቱ ብዙ ያልተጓዘች ወጣት አትሌት እንደመሆኗ መጠን በነገው የዓለም ሻምፒዮና ውድድሯ ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት ብዙ ታሪኮችን ልትፅፍ እንደምትችል የስፖርቱ ተንታኞች እየተናገሩ ይገኛል፡፡ የነገው ውድድር ጠንካራ ፉክክር የሚደረግበት እንደሚሆን ቢገመትም ቲኪ በአይበገሬነቷ በድል ትወጣዋለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በውድድሩ የቲኪ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ኬንያውያንና የሌሎች አገሮች አትሌቶች አይደሉም፡፡ በዚህ ውድድር ዓመት በተለያዩ ታዋቂና ጠንካራ የማራቶን ውድድሮችን አሸንፈው ከቲኪ ጎን ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችም ነገ በውድድሩ ይጠበቃሉ፡፡
አበሩ ከበደ በነገው ውድድር ከቲኪ ያላነሰ የአሸናፊነት ግምት የሚሰጣት አትሌት ነች፡፡ አበሩ ባለፈው ዓመት በርቀቱ ባስመዘገበችው 2፡20፡30 ሰዓት በዓለም ሻምፒዮና አገሯን ለመወከል ሁለተኛዋ ተመራጭ አትሌት ለመሆን በቅታለች፡፡
አበሩ በዓለም አቀፍ መድረኮች የቲኪን ያህል የገዘፈ ስም ባይኖራትም በዛሬው ውድድር የአገሯንና የራሷን ስም የምታስጠራበት እድል አግኝታለች፡፡ አበሩ ይህን እድል ተጠቅማ ባለታሪክ ከሆኑ የአገሮቿ አትሌቶች ተርታ ለመሰለፍ ከቲኪ ጋር ተፋጥጣለች፡፡
በሌላ በኩል በዚህ የውድድር ዓመት በማራቶን ድንቅ ብቃት በማሳየት የተለያዩ ታዋቂ ውድድሮችን ማሸነፍ የቻለችው ፈይሴ ታደሰ የኦሊምፒክ ባለ ድሏን ቲኪን ልትፈትን የምትችል አትሌት ነች፡፡ ፈይሴ በርቀቱ ባለፈው ዓመት 2፡23፡07 የሆነ ሰዓት በማስመዝገብ በርቀቱ አሉ ከሚባሉ አትሌቶች ተርታ መሰለፍ ችላለች፡፡
ፈይሴ በዘንድሮው ዓመት በርቀቱ ቀድሞ የነበራትን ሰዓት ከሁለት ደቂቃ በላይ ያሻሻለች አትሌት መሆኗም በነገው ውድድር እንድትጠበቅ አድርጓታል፡፡ ፈይሴ ሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ የመግባት አቅም እንዳላት በዓመት ውስጥ ያሳየችው ድንቅ አቋም ምስክር ነው፡፡
መሰረት ኃይሉ ኢትዮጵያን ወክላ ከአገሮቿና ከሌሎች አትሌቶች ጋር ጠንካራ ፉክክር ታደርጋለች ተብላ ግምት የተሰጣት አትሌት ነች፡፡ መሠረት በውድድሩ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ለቡድን ጓደኞቿ የምታደርገው አስተዋፅኦ ቀላል እንደማይሆን ይጠበቃል፡፡
በለንደን ኦሊምፒክ የአስር ሺ ሜትር ውጤታማ የቡድን ሥራ በመሥራት ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ እንድታሸንፍ ያደረገችው መሰለች መልካሙ በነገው ውድድርም ከጠንካራ ተፎካካሪነቷ ባሻገር የተለመደውን ውጤታማ የቡድን ሥራ ትሰራለች ተብላ ትጠበቃለች፡፡
መሰለች ከቡድን ሥራው ባሻገር ውጤት የማስመዝገብ አቅም ያላት አትሌትም ነች፡፡ ለዚህም ባለፈው ዓመት በማራቶን ያስመዘገበችው 2፡21፡01 የሆነ ፈጣን ሰዓት እንዲሁም በዘንድሮው ዓመት ያስመዘገበችው 2፡25፡46 ሰዓት ምስክር ነው፡፡
ኢትዮጵያ በዘንድሮው ሻምፒዮና በተለይም በማራቶን ባሰባሰበችው ቡድን ከምንጊዜውም በላይ ውጤታማ እንደምትሆን የተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙኃኖች እየዘገቡ ይገኛል፡፡ በማራቶን ስብስብ ውስጥ የተካተቱት አትሌቶች የኦሊምፒክና ሌሎች ታዋቂ የማራቶን ውድድሮች ማሸነፍ የቻሉ መሆናቸው በነገው ውድድር ምንም መፍጠር አይችሉም ብሎ ለመገመት ከባድ እንዲሆን አድርጓል፡፡

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live