Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አርበኞች ግንቦት 7 በሙስሊም እንቅስቃሴ መሪዎች ላይ የተሰጠውን ፍርደገምድል ፍርድን እንደሚያወግዝ አስታወቀ

$
0
0
photo file

photo file

ጋዜጣዊ መግለጫ:

የህወሓት አገዛዝ የሚዘውረው የይስሙላ ፍርድ ቤት ዛሬ ሀምሌ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በሙስሊም ወገኖቻችን መሪዎች ላይ ፍርደገምድል ውሳኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሳኔ መሠረትም የእምነት መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው በሰላማዊ በሆነ መንገድ የጠየቁ ወገኖቻችን መሪዎች እስከ 22 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

ሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄዎቻቸው ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ሥርዓቱ ያደረገውን ተደጋጋሚ ትንኮሳዎችን ተቋቁመው “ድምፃችን ይሰማ!” የሚል አቤቱታ ከማቅረብ የዘለለ አንዳችም የኃይል እርምጃ ወስደው አያውቁም። ሆኖም “በደል ደርሶብኛልና ልሰማ” ብሎ አቤቱታ ያቀረበ ሕዝብ መሪዎችን እስከ ሃያ ሁለት ዓመታት በእስር መቅጣት የአገዛዙ እብሪትና ማናለብኝነት አጉልቶ የሚያሳይ ተግባር ነው።

አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህን ፍርደገምድል ውሳኔ አጥብቆ ያወግዛል።ይህ ፍርደገምድል ውሳኔ የተሰጠው ፕሬዚዳንት ኦባማ በአገራችን መዲና ተገኝተው “ለሰላም ሲባል ነፃነትን ማፈን ሁለቱንም ያሳጣል” ባሉ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መሆኑ አገዛዙ የሚሰማ ጆሮ የሌለው መሆኑ የሚያረጋግጥ ሆኗል።

የሙስሊም መሪዎች በእስር ላይ በነበሩት ጊዜ በምርመራ ስም ተደብድበዋል፤ ክብራቸው ተደፍሯል፤ የተለያዩ ዘግናኝ ሰቆቃዎች ተፈጽሞባቸዋል፤ የሀሰት ዶክመንታሪ ፊልሞች እንዲሰራጩ ተደርገው ስማቸውን ለማጥፋት ሙከራ ተደርጓል።

በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የደረሰው በደል ሃይማኖት ሳይለይ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰ በደል ነው፤ መፍትሄ የምናገኘውም በጋራ በምናደርገው ትግል ህወሓትን አስወግደን በምትኩ ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና የአገር አንድነት የሚጠብቅ የመንግሥት ሥርዓት ስናቆም ነው። ከዚህ በመለስ የሚገኝ መፍትሄ የለም። የእምነት መብቶች የሚከበሩት ሰብዓዊ መብቶች ሁሉ ሲከበሩ እንደሆኑ “በድምፃችን ይሰማ” ሥር የተሰባሰቡ ወገኖቻችን ይረዳሉ ብለን እናምናለን።

ginbot 7አርበኞች ግንቦት 7 ሙስሊም ወገኖቻችን ለዓመታት ያለመታከት ያካሄዱትን ትግል ያደንቃል። ከእንግዲህ ደግሞ እጅ ለእጅ ተያይዘን፤ ተደጋግፈን በመታገል ህወሓትን አስወግደን በምትኩ ለሁላችንም የምትመች አገር እንድንገነባ ጥሪ ያደርጋል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ


አርቲስት ይሁኔ በላይ በምረቃው ዕለት አዲሱን “መማር”ነጠላ ዜማ አቀነቀነ (ቭዲዮን ይመልከቱት)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኮምፒውተር ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ ባችለሩን የተቀበለው አርቲስት ይሁኔ በላይ በምረቃው ዕለት በርከት ያሉ ተመራቂዎች በተገኙበት አዲሱን መማር የተሰኝውን ነጠላ ዜማ አቀንቅኗል:: ለአርቲስት ይሁኔ በላይ እንኳን ደስ ያለህ እያልን ይህን ታሪካዊ ቭዲዮ ጋብዘናችኋል::

ሁለቱ ትግሎች፤ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ የዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም የማስቀየስ ስልት

$
0
0

andargachew
ርቀ ሰላም (ከደቡብ አፍሪቃ )

ብርሁኑ ነጋ ዱር ገባ!
አንዳርጋቸው ጽጌ መፅሀፈ ጽፎ ጨረሰ!
ኦባማ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መመረጣችንን አውቅና ሰጠ!

እነዚህ እንግዲህ የሰሞኑ ፖለቲካዎች ናቸው።

ያለወትሮዋቸው በአሜሪካ ድምፅ ላይ ለቃለመጠይቀ የቀረቡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኅኖም ያልበላቸውን ሲያኩ ተደምጠዋል። አድማጭ ልብ ሊሊው የሚገባ ጉዳይ አለ። ዶፍተሩ ስለ ብርሀኑ ነጋም ሆነ ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ የተናገሩት ሳይጠየቁ ነበር ይኼ እንግዲህ “ማርያምን … ምን የበላ ..” እንዲሚባለው ነው።Tedros Adhanom interview

ሲጀመር ዶፍተሩ ቪኦኤ ላይ የቀረቡት ስለ ኦባማ መምጣትና መሄድ ላይ አስተያየት ይሰጡ ዘንድ ነበር። ማርሻቸውን ቀየሩት!

የተጠየቁት “ከአንበሳና ነብር ማን ያሸንፋል?” ተብለው ሲሆን፣ የእርሳቸው መልስ ግን

“ዝሆንን ማን አህሎት!” እንደሚባለው ፈሩን የለቀቀ ምላሽ ሰጥተዋል። የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ወያኔ ሸገር ሰተት ብሎ ሲገባ ግፋ ቢል የአምስት አመት ልጅ ነበርኩ፤ ሀያአራት አመት ግን የወያኔ ባህሪ ለመረዳት እጅግ በጣም ብዙ ነውና ይህንን መሳት አይኖርብንም የሚል ሀሳብ አለኝ።

አገራችንን አንቆ እየሳማት ያለው ገዢያችን ስልታዊም ዘላቂያዊም እቅዶችን በመጠንሰስ ከችግር እንዴት መወጣት እንዳለበት ሲተልም፥ ሲያስፈፅም ይኸው ዛሬ ላይ ደርሰናል። የገዢዎቻችንን ስስ ብልት ብቻ ሳይሆን ጠንካራ ጎናቸውንም ልናውቅ ግድ ይላል።

የወያኔ አመራር አንድ እንዳልሆነ እርስ በርስ እንደሚናናቁ ብዙ የተባለለት ነው። ሆኖም ግን ችግር ሲመጣ አንድ መሆንንም ያውቁበታል፤ ከዚህ ባለፈም አቅጣጫ በማስቀየር በኩል የተጨበጨበለት እንደሆነ ባለፉት ጊዜያት ያየነው ነው። ይህንን ስልትም ከበረሀው ጀምሮ ያዳበሩት ስለሆነ ኢትዮጵያን ለመግዛት (የዋህ የሆነውን ህዝብ) በእጅጉ ጠቅሟቸውል።

ይህች የማሳለጫ ስልታቸውም በተደጋጋሚ ሲጠቀሙባት ተስተውሏል።

የምርጫ ዘጠና ሰባት ትኩሳት አልበረድ ብሎ ራስ ምታት በሆነባቸው ጊዜ ሚሊኒየም የሚሉትን ጅራፍ ማጮህ ጀመሩ ሁሉም ተቀብሎ ማስተጋባት ሆነ፤ ዲያስጶራው፥ ሚዲያው፥ ተቃዋሚዎ፥ የቤተ እምነት ሰዎች፥ ተማሪ ቤቶች፥ መስሪያቤቶች፥ ስፖርታዊ ክንውኖች ሁላ ስለ ሚሊኒየም ሆነ ወሬያቸው። ወያኔም እፎይ አለ ለሶስት አመታት ከማእበሉ ወደ ደሴቱ ሲያላጋው የነበረው ችግር ተቀረፈለት። የህዝቡ አቅጣጫም ተቀየረ! ያ ስንት ዋጋ የተከፈለበት ትግል ወሀ ተቸለሰበት፤ ዳግመኛም እንዳይመጣ ተድርጎ ተሰናከለ (በነገራችን ላይ አንዳንድ የዋሆች የማይመጣውን ሲጠብቁ ይስተዋላሉ። አፋቸውንም ሞልተው ያኔ ወደነበራቸው ተክለ ቁመና ተመልሰናል ሲሉ ይደመጣል።)

ሁለተኛ ማስቀየሻ – የአባይ ግድብ!

የ2002 አ.ም. ምርጫ ተደርጎ ካበቃ በሁዋላ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ (ጂቲፒ) የሚባለውን ልማታዊ ቅዥት ይፋ አደረጉ። ይህንን ማድረጋቸው ኢህአዴግ የፓርላማውን ወንበር በሙሉ በማሸነፉ ተደስቶ ህዝብን ሊያገለግል ፥ ልማትን ሊያፋጥን ቆርጦ የተነሳ ተደርጎ እንዲሳል ሆኗል። ከምርጫው ትኩሳት ብዙም ሳይቆይ የአረብ ፀደይ አብዮት ተጀመረ።

ለቀጣዩ አምስት አመት እንሰራዋለን ብለው ካቀዱት ውስጥ ያልተካተተውን የአባይ ግድብ ግንባታ ዋነኛ የልማት አጀንዳ በማድረግ አጎኑት። ሁሉም ነገር አባይ ሆነ። ስለ አባይ የሚያወሱ ዘፈኖች አቧራቸው እየተጠረገ ተደመጡ፤ ስለ አባይ የተገጠሙ ፥ የተጻፉ ጽሁፎች ተጎልጉለው ወጡ። (ስለ አባይ በብዛት የተገጠሙ ግጥሞች “አባይ ስም ነው እንጂ ምን ጠቅሟል ለአገሩ” ፥ “አንተን ብሎ አባይ”፥ “አባይ ቀላባይ”፥ “እውነትም አባይ” የሚሉ አሉታዊ መሆኗችን ያጤኗል። ነገር ግን እድሜ ለወያኔ ሳንሱር እነዚህን አዎንታዊ ማድረግ አይሳናቸውም።)

እዚህ ስለ አባይ ሲዘፈን የአባይ ስጦታ ወደሆነችው ግብጽ አብዮት ይካሄድ ነበር። የሆነው ሆኖ ግን ያቺን የጭንቅ ቀን እንደምንም ብሎ ወያኔ ተላለፋት።

ዘንድሮ 2007 አ .ም. ነው!

ወያኔም ምርጫውን ያለማንም ተቀናቃኝ አሸንፌያለሁ ሲል ተንግሯል። እውቅና የሰጡት ባይጠፉም ከት ብለው የሳቁበትም አሉ። (ነገሩን በደንብ ካጤነው ፈረንጇ የሳቀችው በወያኔ ድራማ ቢሆንም እንደ ሀገር ግን ያላዋቂ ሳሚ በሚገዛት ጦቢያ ላይ መንከትከቷ ያሳፍራል።)

ወያኔ አሸነፈ … ድሉንም አወጀ … ኦባማንም ተቀበለ። በቬኦኤም ተጠየቀ። ምላሽም ሰጠ። የሚፈልገውን መልእክትም ለስለስ ባለ ቆዳው አስተላለፈ።

የወያኔ ሚንስተር ለቬኦኤ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አንጉአ ማግኘት ከትግሉ ተግዳሮቶች አንዱን ጠጠር እንደማስወገድ ይቆጠራል።

አንጉአ አንድ – ስለ አርበኞች ግንቦት ሰባት

ዶፍተሩ ወያኔ ባሁኑ ወቅት እያቃዠው ስለሚገኘው ጉዳይ ሳይጠየቁ መመለስ ጀምረው ስለ ዶከተር ብርሀኑና አንዳርጋቸው ተናግረዋል። የያዙትን ትግልም “አበጀህ! >ብለውታል። በፊት በፊት እንደዚህ አይነት ጥያቄዎችን ሲመልሱ የደሀውን ህዝብ ለማስጨረስ”፥ “ቢያንስ ቢያንስ መሬት ላይ ተገኝቶ ቢያደርገው አላማውን ባልደግፈውም አከብረዋለሁ” “<የላፕ ቶፕ ጦርነት” “ሁልት ሺህ ማይል ተርቆ ስለ ኢትዮጵያ የመናገር ሞራል የላቸውም።” ወዘተ… ነበር መልሳቸው።

ለነገሩ አሁን በቅርቡ አዲስ አለም ባሌማ የተባለው የህወኀት ቀንደኛ አመራር “አሸናፊ የሚሆነው ጠንካራው አይደለም ብልሁም አይደለም፤ የሚያሸንፈው ራሱን ከጊዜው ጋር ፈጥኖ የሚቀያይረው ነው።” ብለውን የለ።

እናም ዶፍተሩ ስለ አንዳርጋቸው እንደ እንቁላል በክብካቤ መያዝ፥ የቻይና ላፕቶፕ ሰጠነው፥ መፅሀፈ አፈና ፅፎ ጨረሰ (ሜጋ ያሳትመዋል?)፥ ናዝሬት ሄዶ ጉብኝት አደረገ።

(እርሳቸው ሆነው ነው እንጂ ስብሃት ነጋ ኖሮ <እገረ መንገዱንም አዳማ (ናዝሬት) በሚገኘው ጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት ተገኝቶ የታዘበውን መፅሀፉ ላይ አካቷል ይሉን ነበር።) ሲሉን አመሹ። እንዲህ የተደናባበረ መልስ መስጠታቸው ኦባማ አንድ ናገር ሳይላቸው ቀርቶ ይሆንን? ብለን እንድንጠራጠርም አድርጎናለ።

ዶፍተር ቴዎድሮስ! ሳይበሉ ያከኩበት ምክንያት አርበኞች ግንቦት ሰባት የቀን ራስ ምታት የሌሌት ቅዠት ስለሆነባቸው እንደሆነ ቆሪጥን መቀለብ አያሻም።

አንጉአ ሁለት – ስለ ሰላማዊ ፓርቲዎች

ሰማያዊ ፓርቲ ፥ አንድነት እንዲሁም መኢአድ (በህይወት የሌሉ ቢሆንም) አሁንም ድረስ ህዝባዊ አመፅ በማስነሳት ፥ ማህበራዊ መሰረታቸውን በመጠቀም የስልጣን ዘመናችንን ያሳጥራሉ የሚል ስጋት አላቸውና፤ በቃለ መጠይቃቸው በገደምዳሜ ከኛ ጋር አይሰሩም በሚል ስጋትቸውን ወይንም ማስፈራራታቸውን ተናግረዋል።

ወያኔ በቀጣይ አምስት አመት እሰራዋለሁ ላለው (ጂቲፒ ድራማ ክፍል ሁለት) እቅድም ተቃዋሚዎችን አሳትፋለሁ ማለቱ ምን ታይቶት ይሆን ? ብለን እንደንጠይቅም አድርጎናል። መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ዶፍተር ቴዎድሮስ በቃለ መጠይቃቸው የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ከኢህ አዴግ ጋር ጥምረት ቢፈጥሩ የተሻለ እንደሆን መናገራቸውም ሌላ አንድምታ ሳይኖረው እንዳልቀረ መገመት አያዳግትም። ስልጣን ለማን እንደሚያስረክቡም ግራ ገብቷቸው ሊሆን ይችላል ። (መንግስቱ ኃይለ ማርያም “…በወቅቱ ስልጣን እናስረክብ ብንል ኖሮ ለማን ነበር የምናስረክበው? ለወያኔ? ለሻቢያ? ስለሆነም የአፍሪቃ መሪዎች ስልጣናቸውን የሙጥኝ እንዳሉ ይኖራሉ።ማለታቸውንም ልብ ይሏል አስረጅ – የመንግስቱ ኃይለ ማርያም ትዝታዎች ክፍል ሁለት – 2004 አ.ም.)

አንጉአ ሶስት – ስለ ደጋፊ (ደጀን) ሀይሉ

ዶፍተሩ! በቃለ መጠይቃቸው በራሳቸው ተነሳሽነት ካነሷቸው ነጥቦች ስለ ዲሲ ኢትዮጵያውያን የተናገሩት አንዱ። የወያኔ ካምፕ ለነጻነት በሚደረገው ትግል ዋና ደጋፊ ብሎ የፈረጃቸው በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያንን እንደሆነ ለማንም ነጋሪ አያሻውም። ይህንን ራስ ምታታቸውንም ዶፍተሩ ዲሲ ላይ ያለውን አጋዥ ሃይል ለማኮሰስ ያልተሳካ ሙከራ አድረገዋል።

አንጉአ አራት – አቅጣጫ ማስቀየሪያ

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ወደ ትግል ሜዳው መግባት ያስደነገጠው ወያኔ ነገሩን አሳንሶ ለማሳየት ያደረገው ጥረት አልሳካ ሲለው አቅጣጫ ወደማስለወጥ ያመራ ይመስላል። (እንደነርሱ ፍላጎት ቢሆንማ ከቁጥጥራቸው ውጪ ያልሆነ የምርጫ ድራማ በየአምስት አመቱ እየሰሩ ለመቀጠል ነበር።)

ይህንንም የማስቀየሻ ሽጉጥ ይዘው ወደ አሜሪካን ድምፅ መስመር የመጡት ዶፍተር ቴዎድሮስ ቃታኣውን በመሳብ የመጀመሪያውን ጥይት ተኩሰዋለ። በርግጥ በዚህ የተሳሳቱ (እልህ የገባቸው ሀገር ወዳዶች) በወጥመዱ ሰተት ብለው ሊገቡ ችለዋል። በዚህም ምክንያት ዶፍተሩ ቃለ መጠይቁን በሰጡ ማግስት የጀመረው ምላሽና አስተያየት የሳይበር ማህበረሰባችን መወያያ ሆኗል።

ነገር ግን ይህንን ፋይዳ ቢስ የሆነ እሰጥ አገባ ትተን ትኩረታችን የተጀመረውን ትግል እንዴት እናግዝ ? እንዴትስ ዘላቂና አስተማማኝ እንድርገው ወደሚለው መሆን ይኖርበታል። አስተያየት መስጠት ቀላል ነው፤ ተግባር ግን ቆራጥነትን ፥ ፅናትንና ዋጋን ይጠይቃል። ፈረንጆቹ “who dares win – ደፋር ያሸንፋል” ብለው ይጀምሩና “to dare is to do – ድፈረት ማለት መተግበር ነው።” ሲሉ ያፀኑታል።

“ተዋህደናል”–የሰማያዊ እና የአንድነት ፓርቲ የድጋፍ ኮሚቴዎች በሰሜን አሜሪካ

$
0
0

ሰማያዊ አንድነት ድጋፍ በሰሜን አሜሪካ
ጋዜጣዊ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ በአገራችን ካሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በዲሞክራሲ ወገንኝነቱ የሚታወቅና በጠመንጃ አፈሙዝ ሀገሪቱን ላለፉት 25 አመታት በመግዛት ላይ ያለውን አምባገነን ስርአት በሰላማዊ ትግል በማስወገድ በዲሞክራሲያዊ ስርአት የሚመራ መንግስት ለመመስረት የሚታገል ፓርቲ ነው። የፓርቲው ዋና መመሪያ የሆነውና በሰላማዊ ትግል በመታገዝ የዲሞክራሲያዊ ስርአትን መመስረት የሚለው ይህው አላማው በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ኧንዲያገኝ አስችሎታል። መንግስት በአንድ ወቅት ጠንካራ የነበረውን አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በህገወጥ መንገድ ኧንዲፈርስ ሲያደርግ አባላቱ የጀመሩትን ትግል ለመቀጠል ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸው ለዚህ አባባላችን በቂ ማስረጃና የምናስታውሰው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።
udj-Blue
ይህንኑ ፈለግ በመከተልም በውጪ የሚገኙ የሰማያዊና የአንድነት ፓርቲዎች ድጋፍ ሰጪዎች ለሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የሚውል ፋይናንስ በጋራ የማሰባሰቡን ተግባር በአግባቡ ተወጥተዋል። ከዚህ ባለፈም ተዋህደው ኧንደ አንድ አካል የሚሰሩበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል። በዚሁ መሰረት ባሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ኧና የአንድነት ዲሲ ሜትሮ ቻፕተር ተዋህደው የሰማያዊ አንድነት ድጋፍ በሰሜን አሜሪካ በሚል ሰያሜ ስር መሆናቸውን ስናበስር ታላቅ ደስታ ይሰማናል።

የሰማያዊ አንድነት ድጋፍ በሰሜን አሜሪካ ዋና አላማዎችም ሰማያዊ ፓርቲን በሁለንተናዊ መልኩ መደገፍ፤ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የትግሉ አካል በመሆን የበኩላቸውን ድርሻ ሊያበረክቱ የሚችሉበትን ፎረም ማመቻቸት፤ የተለያዩ አርቲክሎችን ማዘጋጀት ኧንዲሁም በኢትዮጲያ ጉዳይ ዙሪያ ያሉ ወቅታዊ መረጃዎችን በማሰባሰብ በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ማሰራጨት የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው።

የህወሃት ኢህአዴግ አፈናና ጭቆና ኧየጨመር በሄደ መጠን ለነጻነት የሚደረገው ትግል በላቀ ሁናቴ ሊፋፋም ይገባዋል። ለዚህ ኧውን መሆን ደግሞ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊው ዲያስፖራ ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል። በመሆኑም የሰማያዊ አንድነት ድጋፍ በሰሜን አሜሪካ በሰላማዊ ትግል ዲሞክራሲን ኧውን ለማድረግ፤ የሰብአዊ መብቶች ኧንዲከበሩ፤ የነጻ ፕሬሱ ኧንዲያብብና መልካም አስተዳደር ኧንዲሰፍን ኧንዲሁም የነጻ ገበያ ስር አት ኧንዲያብብና ብሄራዊ አንድነታችን ኧንዲጸና ለሚታገሉ ተቃዋሚዎች ሁሉ መሳሪያ ሆኖ ኧንደሚያጋለግል ኧምነታችን የጸና ነው።
ሐምሌ ፳፯ ቀን ፳፻፯ ዓ/ም

Semayawi Andnet (Semayawi) Support North America (SASNA)
Press Release
Semayawi (Blue) Party is one of the foremost pro-democracy political parties in Ethiopia that is conducting a non-violent struggle to establish a democratic system of government in a country that has been ruled with an iron fist by a totalitarian regime for the past 25 years. The party’s main principle of non-violent struggle to democratize Ethiopia enjoys broad public support. It is to be remembered that after the regime illegally banned the once strong Andenet Party, most of its members joined Semayawi Party in order to continue their struggle.

Following their footsteps and recognizing the need for unified support, Andenet and Semayawi Support Groups have been fundraising in support of Semayawi Party during its campaign for election. In addition to this collaboration, the groups have been working towards merger. Today, we gladly announce that Semayawi Support North America and Andenet DC Metro Support Chapter have finalized the process and completed the merger. The new unified support group will operate under the name Semayawi Andnet (Semayawi) Support North America (SASNA).

Semayawi Andnet (Semayawi) Support North America (SASNA) mission is to provide all rounded support to Semayawi Party; to provide a forum for Semayawi supporters and other like-minded individuals in North America to get involved in the struggle; to disseminate research articles and/or materials and information which have relevant bearings on Ethiopia, Semayawi supporters, and the Ethiopian Diaspora in North America.

As the repression level of the TPLF/EPRDF regime continues, the need for more intensified struggle for freedom becomes necessary; and for these efforts to succeed, the support of Ethiopians in the diaspora will continue to play a vital role. It is our belief that SASNA will serve as an instrument in supporting the effort of non-violent opposition political parties in promoting democracy, human rights, free press, good governance, free market, and national unity.
August 3rd, 2015

በፈረንሳይ በስቃይ ላይ የምትገኘው የኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ ማሰብ ገሰሰ አሳዛኝ ታሪክ (Video)

$
0
0

sad
(ዘ-ሐበሻ) ዘ ቴሌግራፍ ድረገጽ የኢትዮጵያዊቷን ማሰብ ገሰሰ አጭር ታሪክ በቭዲዮ አስደግፎ አቅርቧል:: ማሰብ በሃገር ቤት አክቲቭስት የነበረች ሲሆን ስለሰዎች መብት በመታገሏ በደረሰባት ስቃይና በሱዳን በኩል ሃገሯን ጥላ ሰሃራ በረሃን አቋርጣ ወደ ሊቢያ ገባች:: በሰሃራ በረሃና በሊቢያም በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ እያየች የሜዲትራያንን ባህር አቋርጣ በብዙ ስቃይ ጣሊያን ደረሰች:: ከጣሊያንም አምልጣ በአሁኑ ወቅት የብዙ አፍሪካውያን ስደተኞች መሰቃያ የሆነችው የፈረንሳይዋ ካላይስ ከተማ ገብታለች:: ይህች ኢትዮጵያዊት በአሁኑ ወቅት በጉዳና ተዳዳሪነት ላይ ያለች ሲሆን ቴሌቭራፍ ድረገጽም ያገኛት እዚያው ጎዳና ላይ ነው::

በፈረንሳይ የሚደርስባት ስቃይ ስታስረዳ እንባዋ በአይኗ እየፈሰሰ “ሰው ነን እንስሳ አይደለንም” ትላለች:: ቀሪውን ከቭድዮው::

የአረንጓዴ ሻይ የጤና ጥቅሞች

$
0
0

Green Tea
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)
*ለስኳር ህመም
አረንጓዴ ሻይ የስኳር መጠንን መቆጣጠር እና ከምግብ በኋላ በደም ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን እንዳይጨምር በማድረግ ያግዛል።
*ለልብ ህመም
አረንጓዴ ሻይ የደም ስር ግድግዳዎችን ጤናማና የግፊት መጠን የመቆጣጠር አቅማቸውን ያዳብራል ይህም የደም መርጋት እንዳይከሰትና ለድንገተኛ የልብ ህመም እንዳንጋለጥ ይረዳል።
*ለኮለስቴሮል
መጥፎ ኮሌስቴሮል በመባል የሚታወቀውን በመቀነስ የጥሩ ኮሌስቴሮል መጠን እንዲጨምር ያግዛል።
*ለደም ግፊት
በመደበኛ ሁኔታ አረንጓዴ ሻይን መውሰድ ለደም ግፊት ህመም የመጋለጥ እድልዎን ይቀንሳል።
*ለመደበት
አረንጓዴ ሻይ በውስጡ አእምሮን የሚያፍታቱ እና የሚያረጋጉ ንጥረነገሮችን እንደሚይዝ ጥናቶች ያሳያሉ።
*ለቆዳ
የቆዳ መሸብሸብ እንዳይኖረን የማድረግ አቅም አለው።
*ፀረ ባክቴሪያነት ባህርይ ስላለው ኢንፌክሽኖች እንዳይስፋፉ የማድረግ አቅም እናዳለው ጥናቶች ያሳያሉ።
ጤና ይስጥልኝ

ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል በተለያዩ ንብረቶች ላይ ውድመት አደረሰ

$
0
0

–ንብረት የወደመባቸው በ24 ሰዓታት ውስጥ ማስመዝገብ አለባቸው

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍላተ ከተሞችና በተለያዩ ወረዳዎች ያሉ ነዋሪዎች፣ በመኖሪያ ቤታቸውና በሚሠሩበት አነስተኛ ድርጅቶች ላይ ድንገት የተለቀቀ የኤሌክትሪክ ኃይል ንብረታቸው እንዳቃጠለባቸው ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

Ethiopian Electric Power Corporationነዋሪዎቹ እንደገለጹት፣ በተለይ በኮልፌ ቀራኒዮ አካባቢ በድንገት የተለቀቀው የኤሌክትሪክ ኃይል ከ24 ሰዓታት በላይ በመቆየቱ ያለመብራት ለመቆየት ተገደዋል፡፡ በሥራ ላይ እያሉ በድንገት ይቋረጥና ወዲያው የሚመጣው ኃይል እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ በሥራ ላይ ያሉ ኮምፒዩተሮች፣ ቴሌቪዥኖች፣ የሞባይል ቻርጀሮች፣ አምፖሎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና አነስተኛ ማሽኖች መቃጠላቸውን የሚናገሩት ተጎጂዎቹ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም ሆነ የአገልግሎት ድርጅት ኃላፊነቱን ሊወስዱ ይገባል ብለዋል፡፡

የደረሰባቸውን ችግር አስረድተው አፋጣኝ መፍትሔ ለማግኘት ወደ ዲስትሪክት መሥሪያ ቤቶች ሲሄዱ፣ ተገቢ መስተንግዶ ካለማግኘታቸውም በተጨማሪ፣ ሊያናግራቸው የሚፈልግ እንደሌለም ገልጸዋል፡፡ መሥሪያ ቤቱ በውጭ ድርጅቶች ታግዞ የተሻለ የኃይል አቅርቦትና አገልግሎት ይሰጣል የሚል እምነት እንደነበራቸው የሚናገሩት ተጎጂዎቹ የኃይል መቆራረጥ፣ ድንገተኛ የኃይል መለቀቅና ሲያስፈልግም ከሳምንት በላይ ኃይል አጥቶ መቆየት የዘወትር ተግባር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የኤሌክትሪክ መሥሪያ ቤቶቹ የሆነውን ሁሉ እንደሚያውቁና የደረሰውን ችግር ተመልክተው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጧቸው የጠየቁት ጉዳት የደረሰባቸው ነዋሪዎች፣ አሁንም ችግሩ በቀላሉ ስለማይፈታ የሚመለከታቸው አካላት ዘላቂ መፍትሔ መስጠት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

ድንገት በተለቀቀ የኤሌክትሪክ ኃይል ንብረታቸው እንደወደመ የገለጹትን ነዋሪዎች አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የኤሌክትሪክ ኃይል ኃላፊዎችን ለማነጋገር ሪፖርተር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ነገር ግን አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አገልግሎት የሥራ ባልደረባ እንደገለጹት፣ በአጠቃላይ በብሔራዊ የኃይል ማሠራጫ ሥርዓቱ የቮልቴጅ መጨመርና መቀነስ ሊኖር ይችላል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ቮልቴጁ ከፍ ሲል በንብረቶች ላይ ጉዳት ያስከትላል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኃይል ማመንጨት በኩል በቂ አቅም ቢኖርም፣ በሁለቱም መሥሪያ ቤቶች ማለትም በህንዱ ፓወር ግሪድ ኮርፖሬሽን ኦፍ ኢንዲያ የሚመራው የአገልግሎቱ ዘርፍም ሆነ፣ በኢንጂነር አዜብ አስናቀ የሚመራው ኤሌክትሪክ ኃይል ሁለቱም በጥራት ላይ ችግር እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡

መሥሪያ ቤቶቹ ኃይል አቅራቢውም ሆነ ኃይሉን ተቀብሎ የሚያሠራጨው፣ ከብሔራዊ የኃይል ማሠራጫ ቋት (National Grid) ተመጣጣኝ ኃይል እንዲሠራጭ የሚያደርግ ሥርዓት ማበጀት እንደሚገባቸውም የመሥሪያ ቤቱ ባልደረባ ገልጸዋል፡፡ ብዙ ዋጋ ስለሚጠይቅ በጥራት ማሻሻል ላይ ብዙ መሥራት እንደሚቀር የገለጹት ሠራተኛው፣ ሁለቱም መሥሪያ ቤቶች ለሚደርሱ ችግሮች ኃላፊነት በመውሰድ አፋጣኝ ምላሽ መስጠትና ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡

ሌላው ደንበኞች በሚፈጥሩት የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ችግር በርካታ ጥፋቶች እንደሚከሰቱ ሠራተኛው ጠቁመው፣ በአንድ ቤት ውስጥ የተደራረበ የኤሌክትሪክ ገመድ በመዘርጋትና ከሙያው ውጪ ያለ ሰው በማሠራት ችግሩን እያባባሱት መሆኑን በመጠቆም፣ ለኤሌክትሪክ አደጋ መድረስ ተጠያቂ መሆን ያለባቸው ደንበኞችም ጭምር መሆናቸውን አክለዋል፡፡ የመሥሪያ ቤቱ ባለሙያዎችም በተለይ ቆጣሪ ሲያስገቡ የመስመር ዝርጋታውን በመመርመርና የመቆጣጠሪያ ማሽን ቆጣሪያቸው ላይ እንዲያስገጥሙ ማስጠንቀቅና ማስገደድ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ሰሞኑን በተወሰኑ የአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ችግሩ መከሰቱን ያመኑት የመሥሪያ ቤቱ ባልደረባ፣ ችግሩ ያጋጠማቸው ደንበኞች ወዲያው በ905 እና ለሕዝብ በሚነገሩ ስልኮች በመደወል ማስመዝገብ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ በ24 ሰዓታት ውስጥ በመሥሪያ ቤቱ ባለሙያዎች እንዲታይላቸው ማድረግ እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡ ጉዳቱ በባለሙያ ተለክቶና ተመርምሮ እውነት ሆኖ ከተገኘ የጥገናና የካሳ ክፍያ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡ ጉዳቱ ከባድ ከሆነ ጉዳቱ የደረሰበት አካል ከሦስት ታዋቂ ድርጅቶች የዋጋ ማነፃፀሪያ ፕሮፎርማ በማቅረብ በመሥሪያ ቤቱ የግዢ ዲፓርትመንት ተረጋግጦ የተተኪ ዕቃ ግዢ እንደሚፈጸም ባልደረባው ገልጸዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

የፌዝ ችሎት—ይገረም አለሙ

$
0
0

Islamበኢትዮጵያ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የታሰሩበትን  ፖለቲካዊ ጉዳይ ህጋዊ ለማስመሰል የተሰየመው የፊዝ ችሎት ለአመታት የከረመበትን ተውኔት ከ 7 አመት እስከ 22 አመት እስር በመፍረድ አጠናቋል፡፡  የፍርዱን ዜና ተከትሎ የሚሰማው የሚነበበው ስሜት ከዚህ በተቃራኒ ፍትሀዊ የሆነ ፍርድ የጠበቁ ሰዎች እንደነበሩ የሚያመለክት ነው፡፡ ከወያኔ የፌዝ ችሎት ይህን ማሰብ ወያኔን አለማወቅ ወይንም ትናንትን መርሳት ይመስለኛል፡፡ ይህ ደግሞ ትግሉ  በሚጠይቀው ጽናትና ቁርጠኝት እንዳይካሄድ የሚያደርግ ነው፡፡

ወያኔ በፍትህ ሲያላግጥ በህግ ሽፋን ወንጀል ሲፈጽም እውነትን በጠመንጃው ሲረግጥ ወዘተ  ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በሀሰት ወንጅሎ፣ በትእዛዝ የሚፈርዱ ዳኞች ሰይሞ፣ የፌዝ ችሎት አቋቁሞ፣ ኣቃቤ ህግ ሳይሆን አቃቤ ወያኔ አቁሞ ፣ በፍትህ ላይ ትያትር ሲሰራ እኛ በተለያየ ምክንያት  በተዋናይነት ወይ በተመልካችነት እናስተፍና ተውኔቱን እናደምቅለታለን፡፡ አለም አቀፉ ማህበረሰብም የወያኔን ማንነትና ምንነት የማያውቅ ይመስል የታሰሩ ሰዎች በአፋጣኝ ፍትሀዊ ፍርድ አንዲያገኙ እንጠይቃለን በማለት ለወያኔው  ትያትር እውቅና ይሰጣል፤፡

የሙስሊሙ ማህረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ወንድሞቻችን ፍትህ የተዛባባቸውና ሕገ ወጥ ተግባር የተፈጸመባቸው የታሰሩ ግዜ ነው፡፡ የሙስሊሙ ተወካይነታቸውን ተቀብሎ መፍትሄ አፈላላጊነታቸውን አምኖ ከእነርሱ ጋር ለወራት የተወያየውና የተደራደረው መንግሥት መከራከሪያ ምክንያት አጥሮት፤ ማሰመኛ ሀቅ ቸግሮት በውይይት ያልቻለውን በጉልበት ለመፈጸም የተነሳ እለት ነው የእነርሱ ጉዳይ በህግ ሳይሆን በፖለቲካ፤ በዳኞች ሳይሆን በጠመንጃ እንደሚወሰን የታወቀው ፡፡ ለነገሩ ፍትህ  በጠመንጃ መዳፍ  ስር ወድቃ አቅመ ቢስ ከሆነች አመታት ተቆጥረዋል፡፡ ፖለቲከኞቹ ሥልጣን እያቃዣቸው አንባገነንት እያወራቸው ነው ፍትህን የሚረማመዱባት፡፡ ለአመታት ተምረው ጥቁሩን ካባ ለብሰው ቀኝ እጃቸውን ሰቅለው በእውነት ለማገልገል ቃል የገቡት ዳኞች በስልክ እየታዘዙ የሚወስኑበት ከባለስልጣኖች ተጽፎ የተሰጣቸው ፍርድ ግርጌ ፊርማቸውን አኑረው የራሳቸው አስመስለው በችሎት የሚያሰሙበት ህሊና አንዲኖራቸው ያደረጋቸው ምክንያት ምን ይሆን፡፡ ጥቅም፣ የፓርቲ አባልነት፣ ፍርሀት ምንቸገረኝ  ባይነት ሕዝብን መናቅ  ህሊና ቢስነት፤ ወዘተ የቱ ይሆን!

እነዚህ ወንድሞች ከታሰሩበት ግዜ ጀምሮ ድምጻችን ይሰማ በሚል ትግል የጀመሩ ወገኖች መሪዎቻችን ናቸው ፣ ጥፋት የለባቸውም የታሰሩት በህገ ወጥ መንገድ ነው ወዘተ ይፈቱ በማለት ያካሄዱት ትግል ትክክልና ተገቢ ነበር፡፡ በአንጻሩ ፍርድ ቤቱ ሀቅ እንዲፈርድ ይቀርቡ የነበሩ ጥያቄዎች የወያኔን ማንነት የዘነጉ በየግዜው በፍትህ ስም የተሰሩ ትያትሮችን ያላስታወሱ እንደውም ለፌዙ ችሎት እውቅና የሰጡ ናቸው፡፡

ወያኔ እያንዳንዷን መሰሪ ተግባር  በማን አለብኝነትና በስልት የሚያካሂድ ሲሆን ለዚህ እኩይ ተግባሩ ስኬት ደግሞ የእኛ ትናንትን እየረሱ ከአዲስ ነገር ጋር አዲስ መሆን በእጅጉ ጠቅሞታል፡፡ ወያኔ መሰሪ  ተግባሩን ለመፈጸም ሲወጥን መጀመሪያ  አሸባሪ ተላላኪ ጽንፈኛ ወዘተ በማለት ይፈርጃል፡፡ቀጥሎ የሀሰት የወንጀል ትያትር ያዘጋጅና መንገዴን ያደናቅፋሉ ለስልጣኔም ያሰጋሉ የሚላቸውን ስም አየሰጠ ባልዋሉበት እየፈረጀ በጅምላ ያስርና ፖለቲካዊውን ስራውን የህግ ጉዳይ ለማስመሰል የማይዛመዱ የህግ አንቀጾችን ሁሉ ጠቅሶ የወንጀል መአት ቆልሎ ክስ ይመሰርታል፡፡ በክስ መዝገቡ ላይ ካሰፈረው የውሸት ክስ ጋር ሳይቀር የማይዛመዱ ወረቀቶችን ይሰበስብና ይህን ያህል ገጽ ማስረጃ አቅርበናል ይህን ያህል የሰው ምስክር አለን አንደም ሰው ያለ ማስረጃ አላሰርን በማለት ይደነፋል፡፡ (ቅንጅቶች በዘር ማጥፋትና በሀገር ክህደት ተከሰው እንደነበር መዘንጋት ወያኔን በቅጡ አለማወቅን ያስከትላል)

ወያኔዎች  ቂመኛና በቀለኛ  ናቸውና ለስልጣኔ ያሰጋሉ ያሏቸውን ሰዎች በመንፈስም ሆነ በአካል ሽባ ካላደረጉ አንቅልፍ ስለማይወስዳቸው በመጀመሪያ ፖሊስ የግዜ ቀጠሮ እየጠየቀ ኋላም ፍርድ ቤቱ በሆነ ባልሆነው ቀጠሮ እየሰጠ መደበኛው ክስ መታየት ሳይጀምር ሰዎችን ለአመታት በማሰር ይቀጣሉ፡፤ በዚህ ወቅት በምርመራ ስም የሚፈጸመውን ከደረሰባቸው ሰዎች ምስክርነት የሰማነው ነው፡፡ በመቀጠል ሂደቱን እውነተኛ የፍርድ ቤት አሰራር ለማስመሰል የተወሰኑ ሰዎች እንዲለቀቁ ይደረግና ክርክሩ ይቀጥላል፡፡ በዚህ ወቅት ሰዎቹ የተፈቱት ለማስመሰያነት በፖለቲካ ውሳኔ መሆኑን በመዘንጋት ታሳሪዎቹ ተከራክረው ነጻ ሊባሉ ይችሉ ይሆናል የሚል ስሜት በብዙዎች ዘንድ ያድርና ችሎቱን በጉጉት መከታተልና ነጻ ናቸው የሚል ፍርድ መሰማት ይቀጥላል፡፡ ይህም ለፌዙ ችሎት እውቅና ያስገኝለታል፡፡ክርክሩ ቀጥሎ የአቃቤ ወያኔ የሀሰት ምስክሮች ከተሰሙ በኋላ ደግሞ አሁንም ማስመሰያውን ይበልጥ ለማጠናከር ጥቂቶቹን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በማለት ፍርድ ቤቱ በነጻ ያሰናብታል፡፡ ይህም ተከላከሉ የተባሉት በቂ መከላከያ አቅርበው የአቃቤ ወያኔን ምስክሮች ምስክርነት ማፍረስ ከቻሉ ነጻ ይባላሉ የሚለውን ስሜት ይበልጥ ያንረውና የወያኔ ተውኔት አድማቂም አጃቢም ተመልካችም እንዲያገኝ ያደርገዋል፡፡ በዋናነት ለሚፈሩት ሰዎች  የሚሰጠው ፍርድ ግን ሰሙኑን ያየነው አይነት ይሆንና አዲስ ጩኸት አዲስ ውግዘት እናሰማለን፡፡ ወያኔ ከጨዋታ ውጪ ሊያደርጋቸው የፈለጋቸው ሰዎች ተመሰከረባቸው አልተመሰከረባቸው፤በበቂ ተከላከሉ አልተከላከሉ፤ተከራከሩ አልተከራከሩ ለውጥ የለውም፡፡ለዚህም ወደ ኋላ ሄዶ ሌሎች ፍርዶችን ማስታወስ ሳያስፈልግ ተከላካይ ጠበቃ የነበሩት አቶ ተማም ቡልጉ ስለዚህኛው ፍርድ የተናገሩትን መስማት ብቻ በቂ ነው፡፡

የወያኔ ትያትር ግን በዚህም አይበቃ ይግባኝ ተብሎ ጉዳዩ ለቀጣዩ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ከአንዳንዶቹ የእስር ቅጣት አመት ላይ የተወሰነ በመቀነስ ጉዳዩ በህግና በህግ ብቻ እየተስተናገደ እንደሆነ ለማሳየት ይሞከራል፡፡ ይህን ያዩ  የሰሙ በራሳቸው በታሳሪዎቹም ይሁን ወይንም በቤተሰብ አለያም በጠበቃቸው ፍላጎትና ግፊት  ጉዳያቸው  በይግባኝ ለሚመለከተው ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እዛም ፍትህ ሳይሆን ፖለቲካ ነውና የሚዳኘው የሚታየውም ማስመሳያ አንጂ በህግ የበላይነት የተሰራ አይደለምና ውሳኔው ጸንቶ ይመለሳሉ፡፡

ይህ ሁሉ ሂደት አንደም ለፖለቲካው የፌዝ ችሎት እውቅና ያስገኝለታል ሁለትም በፍርድ ቤት ውሳኔ ለሚለው የወያኔ ስብከት አጋዥ ይሆናል ሶስተኛ የፍድ ቤት ውሳኔ በመጠበቅ ሊደረግ የሚገባው ትግል በወቅቱ እንዳይካሄድ ቢኖርም የተጠናከረ እንዳይሆን ያደርጋል፡ወያኔ የፈራቸውንና ቅስማቸውን ለመስበር  ያሰራቸው ሰዎች ላይ  በእስር ቤት የተለያዩ አረመኔያዊ ድርጊቶች እንደሚፈጽም  በተጨባጭ ማስረጃ የቀረበ አይተናል ሰምተናል፡፡ ይህም በመሆኑ በተለያየ ግዜ በወያኔ እስር ቤት ቆይተው ከወጡ በኋላ  በቀደመ ተግባራቸው  (ፖለቲከኛም ሆነ ጋዜጠኛ ብሎም የመብት ተከራካሪ) የቀጠሉ በጣም ጥቂቶች ናቸው፡

ለወያኔ የፌዝ ችሎት እውቅና ባለመስጠት ረገድ የተሻለ ነገር የሰሩት የቅንጅት አመራሮች ናቸው ፤ጉዳዩ ፖለቲካዊ  ስለሆነ ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው የሚያስፈልገው፤ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመገናኛ ብዙሀን ወንጀለኞች ብለውናል፤ርሳቸው ወንጀለኛ ያሉትን ይህ ፍርድ ቤት ነጻ ለማለት አቅሙም ነጻነቱም የለውም፤ ስለሆነም አንከራከርም ፤ፍርድ ቤት መመላለስ ሳያስፈልገን የጠቅላይ ምኒስትሩን ውሳኔ በፍርድ ቤቱ ስም አድርጋችሁ አለንበት ድረስ ላኩልን በማለት አልተከራከሩም፡፡ ቢከራከሩም የሚለውጡት ነገር እንዳልነበረ ከመጨረሻው አፈጻጸም ተረጋግጧል፡፡ ለማስመሰል የተወሰኑ ሰዎችን ነጻ ብሎ አሰናብቶ  የተወሰኑ ሰዎችን በተለያየ አመት የቀጣው በፍርድ ቤት ስም የቀረበው የፖለቲካ ፍርድ ይህን አደረጉ ማለት ቀርቶ አንዲህ ብለው ተናገሩ ተብሎ አንኳን በክሱ ውስጥ ያልተጠቀሱ ሰዎችን የቅንጅት ምክር ቤት  አባል ስለሆናችሁ በሚል ነው በጅምላ የእድሜ ልክ እስራት የፈረደባቸው፡፡

ስለሆነም ነጻ ፍርድ ቤት በሌለበት ፍትህ እንደማይገኝ በተግባር የታየ በመሆኑ፤ወያኔ ሥልጣን ላይ እያለ ደግሞ ነጻ ፍርድ ቤት የማይታሰብ ስለሆነ ሰዎች ሲታሰሩ የማይገኝ ፍትህ ከመጠየቅና መጨረሻ ላይ እንዲህ አንደ ሰሞኑ ከማዘን ከመናደድና ከመጮኸ በህግ አምኖና በህግ ተከብሮ  ለመኖር የሚያስችል ሥርአት ለመፍጠር በአንድነትና በጽናት መታገል ይበጃል፡፡ ተለያይቶ ቆሞ ተራ በተራ ሲጠቁና በደል ከቤት ሲገባ ብቻ መጮህ የሚያመጣው ፋይዳ አንደሌለ ታይቷልና በጎሳ በኃይማኖት በቋንቋም ሆነ በሌላ ምክንያት  ሳንለያይ በሀሰት የማንወነጀልበት፤እውነት በጠመንጃ ስር የማትውልበት፤ማንም ሰው (ጠቅላይ ምኒስትሩም ቢሆን) ከህግ በላይ የማይሆንበት ሰው በሰውነቱ የሚከበርባት ዴሞክራሲዊት ሀገር አንድትኖረን በአንድነትና በጽናት መታገል ነው መፍትሄው፡፡

ያለበለዚያ ትናንት የሆነውን እየረሳን ከአዲሱ የወያኔ ድርጊት ጋር አዲስ እየሆንን፤በፍትህ ለሚቀልደው የፌዝ ችሎት በአንድ ወይንም በሌላ መልክ እውቅና እየሰጠን በእኔ ካልደረሰ እያልን አንዱ የሌላውን ጩኸት መስማትና ማገዝ እያቀተው የደረሰበት ብቻ ተራ በተራ ለየብቻው መጮኹን ከቀጠለ፡ወያኔም በህግ መቀለዱን በፍህ ትያትር መስራትን ዜጎችን በሀሰት  እየወነጀለ ማሰሩን ይቀጥላል፡፡


አቶ በቀለ ገርባ አሁን አሳት ጭረዋል !

$
0
0

11817131_136434770028205_2307074121292844835_nከኢሳት ጋር የሰጡትን ቃለ መጠይቅ አዳመጥኩ። ከዚህ ሁሉ ዓመት አስራት በኋላ አንዲህ አይነት ብሄርተኝነት የተሞላበት አቋም ይዘው ብቅ አንደማይሉ ትንሽም ብትሆን ተስፋ ነበርረኝ። አስር ቤት ሆነው አብረዋቸው የነበሩት ከተለያዩ ብሄር የተውጣጡ አስረኞች ጋር ከርመው አንዴት ሰው ይህን ያክል ግፍ ቀምሶ ሲወጣ ከዘር ባልወረደ ሃሳብ ተመልሶ ብቅ ይላል??? አስር ቤት አንደ ሰው አንዲያስቡ የሚያረግ ተስፈ ነበረኝ። ይች ሃገር የማናት በለው ራሳቸውን ጠይቀው ለየት ያለ መልስና አቋም ይዘው ቢወጡ ምን በኮራንባቸው ነበር። መልሰው አዛው ነክረውናል።
አማራውን ሕዝብ ሳይሆን የምንወነጅለውን ከዛ ክፍለ ብሄር ወተው በኦሮሞ ህዝብ ላይ ግፍ ያወረዱበት ብለው አስምረውበታል። በተጨማሪም የኦሮሞ ህዝብ በአንድብሄር ስር ተጽኖ ተደርጎብን፤ ተገደን ነበር አማራው ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል አሉ። በሌላው በኩል ውበታችን ልዩነታችን ስለሆነ ግን አንድነት አየተባለ አንድ ቋንቁ ብቻ አናውራ የሚለው አንደማይመቻቸው አስረድተዋል።
አኝህ ሰው ለፖለቲካ ፍጆት ካልሆነ አንዲህ ዓይነት ውንጅልና በጣም ደካማነታቸውንና ከማሳየቱም በላይ የፖለቲካል ፍጆታውን ለመቀጠል ቆርጠው የተነሱ የመስላል ። ለምን?? አንድ ሃገር ከነታሪኩ ከነጉድፉ ይዘን መኖር ካልቻልን አንዴት ልንኖር ነው?? አማራውን ወክሎ የሚቀርበው ማነው ? ማነው ይቅርታስ የሚጠይቀው?? ሰጪውስ ማን ነው?? አማራ ማለት አራሱ ውስጡ ህብረ ብሄር ነው በሃይማኖትም የተለያዩ አምነቶች አሉት። አንዴት ሆኖ ነው አንድ የአማራ መሪ መቶ [ማንን ወክሎ??ይህንን አንኳን አንዴት አቶ በቀለ መረዳት አልቻሉትምን ወይስ አንደው ድብቅብቆሽ ፓለቲካ ? ] አማራ ለማንስ ነው ይቅርታ ሚለው አንደው ጥፈት ተሰራ ተብሎ አንኳን ቢታመንበት?? ሌላው ደግሞ አማራውስ ተሰራብኝ ያለውን ወንጀል ለኦሮሞ የተባለው ክፍለ ብሄር መቅረብስ የለበትም ? ያ በማስረጃ ከመጣ ኦሮሞን አንወክላለን የምትሉት ለአማራው ሕዝብስ ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ናችሁ ወይ??
የሚገርም ነገር ነው በአውነት ! በጣም አዘንኩኝ ። አያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አኩል ከሁሉ ብሄር አሉን አቶ በቀለ ዞር ይሉና ወደ መጨረሻው ! አንዴት? በወቀሳና በማስፈራራት?? ማ ሸሽቶ ማ ልፈራ?? ይህ የሚያመጣው አዙሪት የጥላቻ አካሄድ ነው ። አንዱን ወንጆሎ፤ በኦሮሞ ክፍለ ብሄር የተሰራውን ወንጀል[አማራውም የራሱ ናሬሽን አለውና ] ሳያነሱ መዝለሉ ያሳዝናል።
ታሪክ የሰራውን ጥፈት ከይተም ይምጣ በሳይንቲፊክ መልኩ ታይቶ ይታረማል አንጂ አርሶ ስላሉት አውነት አያረገውም!! አማራውም ወንጀል ተሰርቶብኛል ካላ ማስረጃውን ካላቀረብ የሱም ውድቅ ይሆናል። ለዛም ትክክለኛ ፍትሃዊ የሆነ ፓድየም ይስፈልጋል። አንዱን ብሄር መቶ ወንጅሎ ከዛ ቀስ ብሎ ደሞ ሰው ሳይሆን ከነሱ የወጣው ብሄር ስርዓት ነው ማለት ምን ማለት ነው?? ማንን ነው ?? የትኛውን መንግስት.ስርዓት ነው ተጥያቂ ለአርሶ ?? ያ ስርዓት አማራን ወክያለው ብሎ ሃገርን በድሏል ወይ? መውንጀል ተገቢ ነው ግን ከማስረጃ ጋር ሲሆን ነው ።፡ ይቅርታ ይገባናል ብሎ ማስፈራራት የትም አያደርስም። ሁሉም የራሱ የሆነ የታሪክ ዓይን የሚያነብበት አለው አና ማነው ፈራጁ አስፈራጁ!!
በተጨማሪም ኢሳቶች ለነ አኦሮሞ ኮንፌዴርሽን በር ከፍተው ኢንተርቪው ካደረርጉ ፤ ይህ አድል አኩል ለአማራውም መሰጠት አለበትና አማራውን አውክላለው የሚለው ድርጅት ተጋብዞ ይሄንን ያቀረቡትን የወቀሳ ጥያቄ የመከላከል መብት መስጠት አለበት !!!!
አውነት ይነገር ከተባለ አንግዲህ ሁሉም የራሱን የታሪክ አይታ ያቅርብ ማለት ነው ።

አሳዛኝ ዘመን ! አኔ ተምራችሁ ጭቃ ብያለው!! ትውልድ በታትናችሁ ከማለፍ ምን ልታመጡ አንደሆነ አይገባኝም!! ለዚህ ለዚህ ሁላችንም አንገነጣለና ተለያይተን አንኑር!!! ይች ደሞ ሁልሽም አንደማታዋጣ ታውቅያለሽ! አና ማንን ገለህ ማንን ልታኖር ነው??? አቶ በቀለ ገርባ ከይቅርታ ጋር በጣም ወርደዋል!!! ኤፍ!!

Hewan Mandefro

የሀይማኖት መብታችን የሚከበረው በነፃነት ትግል ነው! –ሰማያዊ ፓርቲ

$
0
0

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ethiopia-blue-party-300x164ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ለስልጣን ለሚያሰጋው ድርጅትና ተቋም ለራሱ ስልጣን የሚበጀውን ሌላ ድርጅትና ተቋም በመፍጠር እንዲሁም ኢትዮጵያውያንን በቋንቋ ልዩነት ከፋፍሎ ሲገዛ ቆይቷል፡፡ ለመምህራን ማህበር ለመምህራን ሳይሆን ለእሱ የሚመች ማህበር፣ ለፖለቲካ ድርጅቶች ለህዝብ የሚቆም ሳይሆን ለአገዛዙ መሳሪያ የሚሆን ድርጅት፣ ለሰብአዊ መብት ድርጅቶችም እንዲሁ ለኢትዮጵያውያን የሚቆሙ ሳይሆን ከእሱ ጋር የሚወግኑ ድርጅቶችን በማቋቋም እውነትና ከእውነተኞችን ሲታገል ኖሯል፡፡ ከዚህም አልፎ አሁን በሀይማኖት ውስጥ ለእሱ የሚመች ሌላ ሀይማኖት በመቋቋም ላይ ነው፡፡

የቆየው የአገዛዙ እኩይ ባህሪ ስልጣን ላይ ለመቆየት በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ በሀይማኖት ተቋማትም ጭምር ጣልቃ በመግባት እሱ የሚፈልገውን እምነት በመደገፍ፣ ሌላው ላይ ቅጣት በመጣል ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህም አገዛዙ ባለፉት ሶስት አመታት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ እያደረሰ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት መመልከት በቂ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ኢህአዴግ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠብ ንቅናቄ ማድረግ በጀመሩበት ወቅት ስርዓቱ ለመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው እውቅና ሰጥቶ ሲደራደር እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይሁንና በሚፈልገው መንገድ አልሄድለት ሲል የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሜቴ አባላትን አስሯል፡፡ ‹‹አሸባሪ›› ብሎ ከሷል፡፡ ሀምሌ 27/2007 ዓ.ም እውቅና ሰጥቶ ሲደራደራቸው የነበሩትን የሙስሊሙ ማህበረሰብ አመራሮች ከ7 እስከ 22 አመት እስራት ፈርዶባቸዋል፡፡ ይህ የሚያሳየው ‹‹ሽብር›› የሚባለው ክስ ስርዓቱ ያልፈለገውን የሚያስርበት መሆኑን ነው፡፡ በዚህ ክስ ሰላማዊ ታጋዮችን ጥፋተኛ የሚለው ፍርድ ቤትና ህግም የአገዛዙ ዋነኛ መሳሪያ ሆነው ቀጥለዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄ የፖለቲካ ሰነድ ከሆነው ህገ መንግስት ላይ በቅዳሚነት ከሚሰፍሩት መብቶች መካከል አንዱ የሆነው የሀይማኖት (የሰብአዊ መብት) ጥያቄ እንደሆነ ያምናል፡፡ ይህም በመሆኑ ስርዓቱ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ይህን እመን፣ ይህን አትመን በሚል እምነት ወደመወሰን ጣልቃ ገብነት ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ትክክል እንዳልሆነ ለማስገንዘብ ጥሯል፡፡ ሆኖም ለሀገርና ለህዝብ ከሚጠቅመው ሀሳብ ይልቅ የስልጣኑ ጉዳይ ብቻ የሚያሳስበው ኢህአዴግ የሚሰማ ሆኖ አልተገኘም፡፡ ኢህአዴግ ሰላማዊ ታጋዮችን በፈጠራ ሽብር ወንጀል ከሶ ሲያስር፣ ለፖለቲካ ድርጅቶችና ለተቋማት ለእሱ የሚመቹትን በመፍጠር አባዜው ሀገራችንን አደጋ ውስጥ እየጣላት ይገኛል፡፡ ይህ አልበቃ ብሎት በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሌላ አደጋ ውስጥ እንድንገባ እያደረገም ነው፡፡

ከአሁን ቀደም ካሉት በርካታ ተሞክሮዎች ለመረዳት እንደሚቻለው አገዛዙ ምክርና ትችት አዳምጦ ማስተካከያ ከማድረግ ይልቅ በእልህና በማን አለብኝነት እያባባሰ መቀጠሉ የማይቀር ነው፡፡ አሁንም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የፈፀመው በደል ተተችቶ የሚያስተካክለው ነው ብሎ ለመገመት ይከብዳል፡፡ ይልቁንም ሀገራችንን አደጋ ላይ ለመጣል በየ ጊዜው የፈፀማቸውና ወደፊትም ለመፈፀም ወደኋላ የማይላቸውን ችግሮች ለመቅረፍ ብቸኛው አማራጭ በጋራ መታገል ነው፡፡ የችግሮች ሁሉ ምንጭ ስርዓቱ እንደመሆኑ ለየብቻችን የምናስመልሳቸው መብቶች አይኖሩም፡፡ የሰብአዊም ሆነ ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችን ልናስከብር የምንችለው ዋነኛው የችግሮቹ ምንጭ የሆነውን ስርዓት ታግለን ለኢትዮጵያችን የሚበጅ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ስንገነባ መሆኑን ተገንዝበን ሰላማዊ የነፃነት ትግሉን መቀላቀል ይኖርብናል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አገዛዙ እየፈፀመበት ያለውን በደል በመቃወም ሲያደርግ የቆየውን ሰላማዊ ትግል ያደንቃል፡፡ በኮሚቴው ላይ የተወሰደው እርምጃ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ይበልጡን ትግሉን አጠናክሮ፣ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ተባብሮ አምባገነንነትን ከምንጩ ከማድረቅ ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለው ትልቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው፡፡ በመሆኑን ሰላማዊ ትግሉን በመቀላቀል በሰብአዊነታችን፣ በዜግነታችን ከዚህም አለፍ ሲል በሀገራችን ላይ እየፀመው ያለውን አደጋ በመገናዘብ፣ የፖለቲካ ትግሉን እንዲቀላቀል ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ኑ! ራሳችን ነፃ በማውጣት የሀገራችንን እጣ ፋንታ እንወስን!

ሀምሌ 29/2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በኢትዮጵያውያን እስላሞች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ –ድምጻችን ይሰማ !

$
0
0

 

ክቢላል አበጋዝ

ዋሽንተን ዲ ሲ  / ኦገስት 5 ቀን 2015

Dimtsachin Yisemaዛሬ በዓለማችን ለፍትህ ለነጻነት ለኩልነት የሚደረገው ትግል እየጎመራ ውጤትም እያሳየ ነው።በሌላው አንጻር ደግሞ ብዙ እልቂት፡ ስደት እስራትና እንግልት በንጹሀን ላይ ሲደርስ እናያለን።ኢትዮጵያ የትግል ውጤት እያየች መከራም በጎኑ እየቀመሰች ነው።ከሚፈጸሙት የወያኔ ህወሀት ግፎች በኢትዮጵያውያን እስላሞች ላይ እየተፈጸመ ያለው ነው።

እያንዳንዱ የምስራቅ አፍሪካ አምባገነንና ሞሽላቃ “ሽብርተኛን ተዋጊ ነው”:: ወያኔ፤የኬንያው፤የኡጋንዳው ሁሉም የተሰለፈ መሆኑን ለምእራቡ ሀያላን ይገልጣል።በዚህም ይደጎማል።ይሞገሳል።የገዛ ህዝቡን ቢያሸብር፡በሃሰት የሽብርተኛ ስም ለጥፎ ቢያስር፡ሰቆቃ ቢፈጽም የሚነካው የለም።ሽብርተኛን እየተዋጋሁ ነው የማይል ዱለቻው አምባገነን ሮበርት ሙጋቤ ነው።እሱም ምዕራቡ አፈር ብላ የሚለው ነው።የኛ ሙስሊሞች ትኩረት አገራችንና ነጻነታችን ላይ ብቻ ነው።አምባገነንን የሚሸከም ትክሻ የለንም።

ኢትዮጵያውያን እስላሞች ሽብርተኞች አይደለንም።በአገራችን ኢትዮጵያ መብታችን ይከበር! የሀይማኖት ነጻነታችን አይደፈር ነው የምንለው።በቆራጥነታቸው፤ኢትዮጵያዊ እምቢተኝነታቸው መሪዋቻችን ግፍ እየተፈጸመባቸው ይገኛል።ህወሃት መሩ መንግስት እስላሙን ከስላሙ ክርስቲያኑን ተክርስቲያኑ ሆን ብሎ የሚያጋጭ ነው።የሃያ አራት ዓመታት ሬኮድ አለው ።ኢትዮጵያን አምላክ እየጠበቃት ከህወሃት ሌላ ሽብርተኛ አልመጣባትም።እስላም ክርስቲያኑ አገሩን ይጠብቃል።በአንድ ወገን ሁኖ ለመብቱ፤ለነጻነቱ ይፋለማል።

ፋሽስት ኢጣሊያ ሲወረን አርበኛው ከመሃል ሲዋጋ የዳር አጥሮቹ አፋር ወንድሞቻችን ነበሩ።እምቢተኛነታቸው ያበገነው ጠላት የጦርነት ወንጀል ፈጽሞባቸዋል።ላአብነት እንጅ በሌሎች አካባቢም የእስልምና ተከታዮች ላገራቸው ተዋድቀዋል።ፋሽስት ኢጣሊያ ሃይማኖትን ካይማኖት ሊያጋጭ ቢጥርም አልሆነለትም። ጠላት ከተነቀለም በኋላ ሰላምን ያደፈረሰ ነገር አልተፈጠረም።የውጭ ጣልቃ ሲገባ እንጂ ፍቅርና ሰላም ነው ወጋችን።

የየካቲት 66 ህዝባዊ አብዮት ከመጀመሩ በፊት እስላም ክርስቲያኑ ምሁር፡ከተሜና ሰራተኛው ታሪክ መዝግቦ የያዘው ታላቅ ሰልፍ አካሂዷል።ክርስትናም እስልምና ወደ ኢትዮጵያ በሰይፍ አልገቡም።በሰላም ተሰብከው እንጂ።ቅኝ አገዛዝም ቦታ ስላልነበረው ከምንጩ ያገኘነውን የጥንቱን ሃይማኖቶቻችንን የበረዘብን የለም። የዛሬውን ብረዛ ያመጣ ጸረ አገር፤ጸረ ሃይማኖት አፍቃሪ ባእድ የሆነው ወያኔ ነው።

ዛሬ እስላም በእስላም ላይ የተነሳበት ጊዜ ነው።ይህን በአረብ አገራት እያየን እናዝናለን። በኢራቅ፤በሶሪያ፤በየመን እየሆነ ያለው ዘግናኝና እጅጉን አሳዛኝ ነው።ህወሃት መሩ መንግስት ይህን ቢመኝልንም የኢትዮጵያ አምላክ ወዴት ሄዶ? አላህ ወዴት ሄዶ? ኢትዮጵያ ወያኔን ያለ አረም አፈራች።ዛሬ በህብረት ይህን አረም ከስሩ ለመንቀል እስላም ክርስቲያ ልጆችዋ ባንድነት ቁመዋል።ጸረ ሃይማኖት፤ጸረ አንድነት፤ጸረ ፍቅርና ሰላም የሆነው የህወሃት ቱጃር ወንበዴን የሚያስወግዱበት ጊዜ ከመቸውም በበለጠ ተቃርቧል።የሚከፋፍለን ኢትዮጵያዊነት ጥላሸት መቀባት የሚችል ምድራዊ ኅይል የለም።

ወያኔ ህወያት ባሻንጉሊት ፍርድ ቤቱ የግፍ ፍርድ ማስፈረዱ ሳይሆን በግፍ የተፈረደባቸው ሁሉ ለነጻነት የከፈሉት ነው ጎልቶ የሚታየው።ፍርድማ ቢኖር የዲራማው ዝግጅት ይህን ያህል ጊዜ አይፈጅም ነበር።ቀድሞ ጥንቱን በስልምና ሃይማኖት ቡራኬ ያገኘችው ኢትዮጵያ ወያኔ ተወግዶ እንደ ጥንቱ እንደወጋችን በሰላም አንድ አምላክን የምናወድስባት ሰላማዊ አገር ትሆናለች።በስላም በክርስቲያኑ ህብረት የጠና የአገር ፍቅር ኢትዮጵያ ታጥራለችና የውጭ ሽብርተኛ መግቢያ ቀዳዳ የለውም።ወያኔ ህወያት መሃላችን ያለ ሸብርተኛ መሆኑን ለሃራት ዓመታት አይተናል።በቃን ብለናል።እጅ ለጅ ተያይዘናል።

ወያኔ ህወያት ክያቅጣጫው በመወጠሩ ይህን ውጥረት የሚወጣ እየመሰለው ማሰር መግደል መሰወሩን ቀጥሎበታል።”የሽብርተኝነት አጋርነቱ” ውሸት የት ሊያደርሰው እንደሚችል ግልጥ ነው።የአረብ ከበርቴ ሆነ ወያኔ ኢትዮጵያውያን የምናመልክበትን ወግና ስርዓት ከላይ አይጭኑብንም። ለሃይማኖታችን ስንከራከር የምንወዳትን ኢትዮጵያን ከልባችን ጠብቀን ነው።ይህን ቅንነት፤የአገር ፍቅር፤ አምላክ ይመሰክራል።ብርታታችንም እሱ ታላቁ ፈጣሪያችን ነው።አላሁ አክበር!

ትግሉ መሯል አላህ ይርዳን።የኢትዮጵያን ጸሎት ይሰማል።

ድምጻችን ይሰማ የኢትዮጵያን ሁሉ ጥሪ ነው!

ኢትዮጵያን አምላክዋ ይጠብቃታል:: እብሪተኞችን ያንበረክካል::

በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች፡የሀይማኖት መሪዎችን፡ የፖለቲካ መሪዎችን ለማስፈታት እንጩህ! የፍርድ ያለህ ! የነጻነት ያለህ!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

አቤላ! –በዘላለም ክብረት

$
0
0

11822504_851775224910971_4792977184625325100_n (1)

የእስረኛ ፊት ብዙ ነው፡፡ ታሪኩም ብዙ ነው፡፡ ብሶቱም ብዙ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ‹ዎክ› የሚያደርግበትመንገድ እንኳን ብዙ ነው፡፡ የሆነ በፅሁፍ ለመግለፅ የሚያስቸግር ከአራት እስከ ስድስት የሚሆኑ ርምጃዎችን ተጉዞ መመለስ ከዛ እንደገናመመለስ … ከዛ እንደገና መመለስ …በጣም በተደጋጋሚ … የሚደረገው ‹ደረስ – መለስ› የዎክ አይነት ግን የእስር ቤት መገለጫ ነው፡፡አብዛኛው እስረኛ ወደ ሰፊው ‹ማረፊያ ቤት› ከመምጣቱ በፊት በፖሊስ ጣቢያዎች ስለሚቆይና ጣቢያዎች ደግሞ ጠባብ በመሆናቸው ምክንያትወይም በራቸው ተዘግቶ ስለሚውል እዛው እዛው ‹ደረስ – መለስ› ዎክማድረግ እዛ ጣቢያ የተለመደ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ የዎክ አይነት በተለየ ደግሞ ማታ ቆጠራ ከመካሔዱና ‹በየበዓታችን› ከመስፈራችንበፊት ባሉት ደቂቃዎች በዛ ያለ ሰው አንድ ላይ ሁኖ ክብ ሰርቶ የሚርመሰመስበት ‹አዙሪት› የዎክ አይነት አለ – በኢትዮጵያ እስርቤት፡፡ በአብዛኛው እኔና አቤላ የዚህ አዙሪት አካሎች ነበርን፡፡

 

አንድ ቀን አዙሪቱ መሃል እየተጓዝን እያለ አቤላ ‹ፖሊስ ጣቢያ› በነበርንበት ወቅት መጀመሪያ የተደበደበበትንምክንያት ሲነግረኝ፤ ‹የሱማሌ ተራ ልጅ ነኝ› በማለቴ ምክንያት ‹አንተ ማነህ ብሔር የለኝም የምትል?› ተብየ ነበር መጀመሪያ የተደበደብኩት፡፡ዞላ ከ40 እና 50 ዓመታት በፊት ሰዎች ‹ብሔሬ እንትን ነው› በማለታቸው ይሰቃዩ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ‹ዜግነት እንጅ ብሔር የለኝም›ማለት የሚያስገርፍ ሀጢያት ሁኗል›› አለኝ፡፡ ተከዝን፡፡ አቅማችን ‹ሕምምም› ማለት ብቻ ነበርና ‹ሕምምም› ከማለት ውጭ አማራጭአልነበረንም፡፡ መሬት በፀሃይ ዙሪያ ትሽከረከራለች ማለትም ያስገርፋል፡፡ ፀሃይ በመሬት ዙሪያ ትሽከረከራለች ማለትም ያስገርፋል፡፡‹ሕምምም›፡፡ ከአቤላ ጋር ብዙ ትካዜዎችን አሳልፈናል፡፡

ሌላ አንድ ቀን ደግሞ እስር ቤት ካገናኝናቸው በጣም ብዙ ሰዎች አንዱ ወዳጃችን ‹ገ› እኔና አቤላወዳለንበት መጣና ‹ክሳችሁ ምንድን ነው› ብሎ ጠየቀን፡፡እኛም ‹ሽብርተኝነት› አልነው፡፡ እሱም ትንሽ ደንገጥ በማለት ‹እንዴ ኢትዮጵያዊያንአይደላችሁም እንዴ› አለን፡፡ ‹ኧረ ኢትዮጵያዊያን  ነን› አልነውእየሳቅን፡፡ ‹አይዋ! ብረት (መሳሪያ ማለቱ ነው) እና ፌፍ – ዎን (የቦምብ አይነት ነው) ተይዞባችኋል ማለት ነው?› አለን፡፡በፍፁም! እኛ (አቤላም እኔም) የታሰርነው ከቢሯችን ከስራ ላይ ተይዘን እንደሆነ ነገርነው – ለየዋኹ ‹ገ›፡፡ እሱም በጣም ተገርሞታዲያ ‹በሽብርተኝነት› እንዴት ተከሰሳችሁ› ሲለን ሳቃችን መቆጣጠር አልቻልንም ነበር፡፡ ሳቅን፡፡ ከአቤላ ጋር በእውነት ብዙ ሳቆችንተካፍለናል፡፡ በሳቅ ሆዳችን ታሟል፡፡

 

Frank MacCourtን አንብበን በሳቅ ጠሽ ብለናል፣ Robert Fiskን አንብበን ስለ ዓለምብዙ አውርተናል፣ Tariq Ramadanን አንበብን በለውጥ ሰባክዎች ቀንተናል…፡፡ ብቻ አብረን ያሳለፍናት እጅግ በጣም አጭር አንድዓመት የምታስቀና ነበረች፡፡

 

ብዙ ጠያቂዎቻችን ሊጠይቁን ይመጡና ጓደኝነት ማለት ‹ታቦት አብሮ ማንገስን› አልያም ‹ሶላት አብሮመስገድ› ይመስል ሃይማኖት እያነሱ ‹እንዴት ተመቻችታችሁ ትኖራላችሁ› አይነት ነገር ሲሉን ብዙ እንገረም ነበር፡፡ ጓደኝነት እኮበጣም ትልቅ ነገር ነው፡፡ ከአንድ የመሰሎች ጎራ ወደ ሌላው የሚያሸጋግር ድልድይ!

 

ሰዎች ያለፍንበት ከአንድ ዓመት የሚበልጥ አስቸጋሪ ጊዜ (እነ አቤል አሁን ያሉበት) ብዙ የሚያበሳጨንይመስላቸው ይሆናል፣ በፍጹም፡፡ አቤላ ፍ/ቤቱን ተዳፍረሃል ተብሎ ቅጣት በተወሰነበት ጊዜ እየሳቀ መጥቶ ‹3 ዳገት ተለመጥኩ›(በእስር ቤት ቋንቋ ‹3 ዓመት ተፈረደብኝ› እንደማለት ነው) ነበር ያለን፡፡ እኛም ቀልድ መሆኑን ተረድተን ወደ ብስጭትና ቁጭትአልገባንም፣ ይልቁን ስለ Freedom of speech in the court of law እያነሳን ተወያየን እንጂ፡፡ ምንም እንኳንታላቁ ዳኛ Justice Holmes “The court is not a market of ideas” ቢሉም ከእርሳቸው ተከትለው የመጡትዳኞች ደግሞ “A judge should show a higher moral character which refuse to be offendedin every statements”  እያልን ነበር የምንሳሳቀው፡፡ በጣምየሚገርም ዓመት እኮ ነው አብረን ያሳለፍነው፡፡

 

አቤላ ወዳንተ ስመጣ፣

ይህችን አጭር ሜሞ ባልተመቻቸ ሁኔታ መንገድ ላይ ሁኜ ነው የምፅፍልህና በማጠሯ አትዘንብኝ እሺ፡፡

 

እንዲህ ነው፣

Zone9

እኔም አንተም በማናዉቀው ምክንያት እኔ ተፈትቼ አንተና ወንድሞቻችን አሁንም አበሳችሁን እያያችሁነው፡፡ ለዚህ ልቤ ይደማል፡፡ ምን ላድርግ? ብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ ወ/መስቀል የተባሉ ሊቅ ስለ ወዳጅነት ምን አሉ?

 

“ወዳጅ ‘ማ ማለት አብሮ ባካኝእንጂ፤

እንደ አይን፣ እንደ ዦሮ፣ እንደ’ግርእንደ’ጅ፡፡

 

አቤላ እኔ አሁን አይንም፣ ዦሮም፣ እጅም፣ እግርም ላልሆንህ ካንተ ርቄያለሁ፡፡ ያማል፡፡ ግን ቢያንስሃሳቤ ውስጥ ትመላለሳለህ፡፡

በመጨረሻ ልደትህን ከአምናው ለየት የሚያደርገው አምና መሬት ላይ “እየተደቦቅን” (እየተኛን) ነበርያከበርነው ዘንድሮ ግን አልጋ ላይ ሁነህ ማክበርህ ነው፡፡ GTP -2ን ያስታውሷል፡፡

 

መልካም ልደት አቤላ!

 

ወንድምህ ዘላለም

 

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በሰበር ሰሚ ችሎት ለ3ኛ ጊዜ ተቀጠረ

$
0
0

Temesgen Desalegn behindbar
(ዘ-ሐበሻ) የፌደራሉ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ሰበር ውሳኔ ለማስተላለፍ ለዛሬ ሐምሌ 29, 200 ዓ.ም ቀጠሮ ይዞ የነበረ ሲሆን አሁንም በተልካሻ ምክንያት ለ3ኛ ጊዜ ቀጠሮው ተላልፎ ለነሐሴ 12 ተቀጥሯል::

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ሰበር አቤቱታ የሰማው ችሎቱ ውሳኔ ለመስጠት ከዚህ በፊት ሁለት ቀጠሮዎችን ሰጥቶ በተልካሻ ምክንያት ጋዜጠኛውን በማጉላላት የሚገኘው ሰበር ሰሚ ችሎቱ ለ3ኛ ጊዜ ተመሳሳይ የቀጠሮ ማራዘም ተግባሩን ቀጥሎበታል::

እንዲህ ያለው በተልካሻ ምክኒያት ፍርድን የማጓተት ተግባር የጋዜጠኛውን ስነልቡና ሆን ተብሎ በሕወሓት መንግስት የሚደረግ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ያምናሉ::

ኦቦ ሌንጮ ለታ ተመላሽ ዲያስፖራ የመሆን መብቱ ለምን ተከለከለ?

$
0
0

lencho leta
ከአብሼ ገርባ

የዛሬ ስድስት ወር ገደማ ኦቦ ሌንጮ ያለኝ የፖለቲካ ሀሳብ ኢንቨስት ማድረግ እፈልጋለሁ ብሎ ጏዙን ጠቅልሎ ሀገር ቤት መግባቱ ይታወቃል:: ሆኖም በፍጥነት በመጣበት እግር ሀገሩን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ::

የሌንጮ ለታን መባረርና አሁን ያለውን የዲያስፖራ ጥሪ ስንመለከት የተለየ የፖለቲካ ሀሳብ ኢንቨስት ማድረግ እንደማይፈቀድና ዶላርና ቦዶ ሀሳብ ብቻ ይዞ መምጣት እንደሚቻል ነው::

አንድ የኦሮሞ ዲያስፖራ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ በዚህ ሀገር ውስጥ አንድም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የለም ብሎ በአንድ ቀን አዳር የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለመኖሩን ገምግሞ ምስክርነት መስጠት የሚችል ጭንቅላት ያለው ዲያስፖራንም ለማየት ችለናል::

ኢህአዴግ ፖለቲካውን መቶ በመቶ ዝግ በማድረግ ዶላሩን ብቻ አምጡ እያላቸው ነው::

ዋናው ቁልፉ ግን ሀገሪቱን አንቆ የያዘው የዶላር ችግር ሳይሆን ፖለቲካው ስለተቆለፈበት ነው::

በኔ ግምት የዲያስፖራ ዶላር አይደለም የአሜሪካ ዶላር ጠቅላላ ተሰብስቦ ቢመጣ የሀገራችን የፖለቲካ ችግር እስካልተፈታ መፍትሄ ሊሆን አይችልም:

ፍቃዱ በቀለ ዛሬ ከእስር ተፈታ * አበበ ቁምላቸውም በዋስ እንዲወጣ ታዟል

$
0
0

elias 1

elias

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እንደዘገበው:- የቀድሞ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች ም/ሰብሳቢ የነበረው እና የዛሬ 20 ቀን በሽብር ወንጀል ተርጥሮ፣ ‹‹ሰዎችን ለግንቦት ሰባት በመመልመል ወደኤርትራ ትልክ ነበር›› የተባለው ፍቃዱ በቀለ ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ገደማ በዋስ ከታሰረበት ካሳንችስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተፈታ፡፡ በተጨማሪም በተመሳሳይ ክስ ተጠርጥሮ ከ25 ቀናት በላይ በዚሁ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው የቀድሞ አንድነት እና በአሁን ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አበበ ቁምልቸውም በዋስ እንዲወጣ መታዘዙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ ዜናም፣ ‹‹የአልሸባብ ህዋስ ነህ፤ ባራክ ኦማባ በሚገኙበት ስብሰባ ወቅት የሽብር ወንጀል ልትፈጽም አሲረሃል›› ተብሎ ለ28 ቀናት፣ መገናኛ አሚቼ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው የ‹‹ቀዳሚ ገጽ›› ጋዜጣ ሥራ አስኪያጅና የቀድሞ የ‹‹ሚሊየኖች ድምጽ›› ጋዜጣ ሪፖርተር ሀብታሙ ምናለ ከትናንት በስትያ ምሽት 2፡30 ገደማ ከእስር መውጣቱ ይታወሳል፡፡


ከሳሽ ሲከሰስ –ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ቢኖር ነበር እኛ ኢትዮጵያን ሙስሊሞች እንዲህ ብለን እንከስ ነበር

$
0
0

muslim addis
ተዘጋጀ በመአኮ

የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001

የተመለከተውን በመተላለፍ የተከፈተ ክስ

የቀ/ቁ/      001/2006

የወ/መ/ቁ.    01/0001/06

ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ

በመላው ዓለም

ከሳሽ ….. ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች (የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ)

ተከሳሾች… 1/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት

የሽብር ቡድኑ አጠቃላይ አስፈጻሚ

2/ የህውኃት/ኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ

የሽብር ቡድኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

3/ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (በሌሉበት)

የሽብር ቡድኑ የቀድሞ አመራር

4/ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ

የሽብር ቡድኑ አመራር

5/ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን

የሽብር ቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ

6/ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ

የሽብር ቡድኑ መረጃ ክፍል

7/ የኢ.ፌዲ.ሪ የፌዴራል ጉዳዮች ሚነስቴር

የሽብር ቡድኑ የስልጠናና ምልመላ ክንፍ

8/የኢ.ፌዲሪ. የፍትህ ሚኒስቴር

የሽብር ቡድኑ የህግ ሽፋን ሰጭ ክፍል

9/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር

የሽብር ቡድኑ ተባባሪ

10/ የኢ/እ/ጉ/ጉባኤ (መጅሊስ

የሽብር ቡድኑ ተቀዳሚ ተባባሪና ኃይማኖታዊ ሽፋን ሰጭ ተቋም

11/የፌዴራል ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ)

የሽብር ቡድኑ ቶርቸርና ማወጣጫ (inquisition) ክፍል

12/ አቶ ጌታቸው አሰፋ

የሽብር ቡድኑ መረጃ ክፍል ሃላፊና አመራር

13/ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም

የሽብር ቡድኑ የስልጠናና ምልመላ ክፍል ሃላፊና አመራር

14/ አቶ ጸጋዬ በርሄ

የሽብር ቡድኑ የፀጥታ ክፍል ሃላፊና አመራር

15/ አቶ ሬድዋን ሁሴን

የሽብር ቡድኑ ቃል-አቀባይ

16/ አቶ አህመዲን አብዱላሂ ጨሎ

የሽብር ቡድኑ ተቀዳሚ ተባባሪና የኃይማኖታዊ ሽፋን ሰጭ ተቋሙ አመራር

17/ ፕሮፌሰር ሃጋይ ኤርሊኽ (በሌሉበት)

የሽብር ቡድኑ ዋና አማካሪ

18/ ዶ/ር ሰሚር አል-ሪፋዒ (በሌሉበት)

የሽብር ቡድኑ አማካሪና የአይዲዮሎጂ ክፍል ተጠሪ

19/ ፔትራም ኃ/የተወ/የግል ማህበር

የሽብር ቡድኑ የፋይናንስ ድጋፍ ሰጭ ክንፍ

20/ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (አዲስ ዘመን ጋዜጣ)

21/ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት (ኢ.ቲ.ቪ)

የሽብር ቡድኑ የድምጽ-ከምስል ስርጭት ክፍል

1ኛ ክስ

(ከ1ኛ እስከ 21ኛ ተከሳሾችን ይመለከታል

ወንጀሉ

በ1996 የወጣውን የኢ/ፊ/ዲ/ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/(1)(ሀ)(ለ)፣ 38(1) እነ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3፣4፣5፣6፣7፣8፣10፣እና 11 የተመለከተውን በመተላለፍ ወንጀል ተከሰዋል፡፡

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋ በመሆን እና የወንጀል አድማ ስምምነት በማድረግ በመላ ሃሳባቸው እና አድራጎታቸው የወንጀል ድርጊቱን እና ወንጀሉ የሚሰጠውን ውጤት ሙሉ በሙሉ በመቀበል እነ የራሳቸው በማድረግ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ——— ከተረጋገጠው የእመነት ነጻነት በመቃረን ከራሳቸው “አህባሽ” የተሰኘ አክራሪ አስተሳሰብና አስተምህሮት ውጭ በኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ የእስልምና አስተሳሰብና አስተምህሮት መኖር የለበትም የሚል ፖለቲካዊ ዓላማ በማንገብ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጉባዔን (መጅሊስን ) ፖለቲካዊ ዓላማን ለማስፈፀም የተቋቋመ ኃይማኖታዊ ተቋም እንዲሆን እቅድና ግብ በማስቀመጥ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለውን የህገ-መንግስቱን አንቀጽ 11ን በመቃረን ቀኑና ወሩ በውል ባልታወቀ 1987 ጀምሮ ህውኃት /ኢህአዴግ በተሰኘው የሽብር ቡድን በመሠባሰብ የረጅም፣ የመካከለኛ እና የአጭር ጊዜ እቅድ በማውጣት እና ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ተንቀሳቅሰዋል፡፡

ተከሳሾች “አህባሽ” የተሰኘው አንጃ በእርስ በርስ ጦርነት በምትታመሰዋ ሊባኖስ ውስ የሚንቀሳቀስ ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው የኃይማኖት ሴክት መሆኑን እያወቁ፣ እንዲሁም የቀድሞውን የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ረፊቀስ ሀሪሪን ግድያ የሚያጣራው የተባበሩት መንግስት የወንጀል አጣሪ ቡድን “አህባሽ” የተሰኘው አንጃ ግድያውን እንደፈፀመ ሪፖርት ያወጣ መሆኑን እያወቁ፤ የአህባሽ አንጃ መስራች የሆኑት ሽህ ዐብደላህ አልሃረሪ ሀረር የሶማሊ አካል ነች የሚል ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም ያላቸው መሆኑን እያወቁና ይህንን አቋም የሚገልፀውን መጽሀፍ በመጅሊስ በኩል እያሰራጩ፤ ይህንን በሀገር ሰላም ላ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችልን አንጃ ህዝብ የሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ አስመጥተዋል፣ በዚህም ከህዝብና ከሀገር ደህንነት ይልቅ ጊዜያዊ ፖለቲካዊ ጥቅምን በመምረጥ ስልጣናቸውን ለሽብር ዕቅዳቸው ማስፈፃሚያነት ተጠቅመዋል፡፡

(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)

ይህን አክራሪ አስተሳሰብ የተጠናወተው “አህባሽ” የተሰኘውን አንጃ ከ1996 ጀምሮ በጦር-ኃይሎች ሦስት ቁጥር ማዞሪያ በሚገኘው ተቋሙ አክራሪ አስተሳሰቡን እንዲያስፋፋ በህቡዕ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ከዚህም አልፎ ዕለቱና ወሩ ባልታወቀ 2003 ላይ በቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፊርማ በቦሌ ክ/ከተማ የሚገኝ አንድ መቶ ሺህ (100000) ካሬ ሜትር ቦታ እንዲሰጣቸውና ለአንጃው ማሰልጠኛ ተቋ ግንባታ ይሆን ዘንድ የፔትራም ኩባንያ ስራ አስኪያጅ አቶ ዐብዱልከሪም በድሪ እንዲከታተለው ትዕዛዝ ሰጥተዋልል፡ በዚህም ተግባራቸው ህዝብ የሰጣቸው ስልጣን ለሽብር ዕቅዳቸው ማስፈፀሚያ ተጠቅመዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ ከሐምሌ ወር 2003 ጀምሮ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ይህንኑ “አህባሽ” የተሰኘ አክራሪ አስተሳሰብ እንዲቀበሉ በማስገደድ፣ ማንኛውም ሙስሊም እነርሱ ከሊባኖስ ካስመጡት የአስተሳሰብ መስመር ውጭ መከተል የማይቻል መሆኑን በአደባባይ በመግለፅ እና የእምነት ነፃነታቸውን ለማስከበር የተንቀሳቀሱ የኃይማኖት መምህራን፣ ዑለማዎችና ምሁራንን ለሥነ-ልቦና እነ ለአካል ጉዳት በመዳረግ እስር ውስጥ በማዋል፣ የህገ-መንግስት ጥሰታቸውን በተቃወመው ህዝበ-ሙስሊም ላይ የህይወት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት አድርሰዋል፡፡

ቀደም ሲል ባቀዱት መሰረትም መጅሊስ (የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጉባኤ) ውስጥ ከእነርሱ አክራሪ አስተሳሰብ ውጭ የሆነ ወይም የሽብር ቡድኑ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ ግለሰብ በየትኛውም የመጅሊሱ አስተዳደራዊ እርከን እንዳይሳተፍ አግደዋል፡፡ ህዝብ የማያውቃቸውና የኃይማኖትም ይሁን የአካዳ ዕውቀት የሌላቸው ግለሰቦችን የመጅሊሱ አመራር አድርጎ በመሾም ተቋሙ ህዝበ-ሙስሊሙ ላይ ለሚፈፀመው የሽብር ድርጊት ኃይማኖታዊ ሽፋን እንዲሆን ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ይህንንም ለማሳካት የመንግስት መዋቅርን በመጠቀም በትጋት ሰርተዋል፡፡ በተለይም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮው ሙሉ ኃይሉን ለዚህ እኩይ ጉዳይ በማዋል በንፁሃን ዜጎች ላይ የእስር፣ የእገታ፣ የድብደባና የግድ ወንጀል ፈፅሟል፡፡ መጅሊሱን ለሽብር ዓላማቸው ማስፈፀሚያነት ለማመቻቸት ይችሉ ዘንድ ህዝበ-ሙስሊሙ ባልተሳተፈበትና የህዝበ-ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በፌ/ወ/ምርመራ (ማዕከላዊ) ኢ-ሰብዓዊ ግፍ እየተፈፀመባቸው (እፈፀሙባቸው) ባሉበት ሁኔት ህገ-ወጥ ምርጫ- የመንግስት ተቋም በሆነው ቀበሌ ውስጥ-አካሂደዋል፡፡ በሂደቱም ህገ-ወጥ የመጅሊስ አመራሮችን በሌላ ህገ-ወጥ አመራሮች ተክተዋል፡፡ በዚህም የሽብር ቡድኑ ተሳታፊዎች በኃይማኖት ጉዳይ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነታቸውን አሳይተዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ የሀገሪቱን መንግስታዊ ተቋማት በመጠቀምና የሀገሪቱን የፀጥታ ኃይል ሙሉ በሙሉ ለህገ- ወጥ ዓላማቸው በማዋል በ “ህገ-መንግስት ማስተማር” ስም አዲሱን አክራሪ አስተሳሰብ በኃይል ጭነዋልል፡ የግዳጅ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ስልጠናቸውን ለመሳተፍ ፈቃደኛ ያልሆኑና የፀጥታ ኃይላት ማስፈራሪያና ዛቻ ያልበገራቸው የመስጅድ ኢማሞች ከኢማምነታቸው (ከስግደት መሪነታቸው አባርረዋል፡፡ በኃይማኖት ጉዳይ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት የመስጅድ ኢማሞችን ሾመዋል፤ እነርሱ የሾመዋቸውን ኢማሞች “ተከትለን አንሰግድም” ያሉ በርካታ ሙስሊሞችን ዘብጥያ ወርውረዋል፣ ለህገ-ወጥ ድርጊታቸው ማስፈፀሚያ ያቋቋሟቸውን ፍ/ቤቶች በመጠቀም በ “ዋስትና” ስም በርካታ ሚሊዬን ብር ከህዝበ-ሙስሊሙ መዝብረዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በሀገራቸው ሙስሊም ሆነው የመኖር ነፃነታቸውን ነፍገዋል፡፡

የሽብር ቡድኑን ህገ-ወጥ ድርጊት በመቃወም ህገ-መንግስት ይከበር! የሚል ድምፃቸውን ለማሰማት አደባባይ የወጡ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን “ጥቂቶች” ሲሉ አሸማቀዋል፤ የነፃነት ጩኸታቸውን ለሚመለከተው የመንግስት አካል ያደረሱላቸውና ለመብት ጥያቄያቸው መፍትሄ ያፈላልጉላቸው ዘንድ በፊርማቸው አረጋግጠው ውክልናቸውን የቸሯቸውን የህዝብ ልጆች የሽብር ቡድኑ ራሱ በሚፈፅመውና ግዙፍ የወንጀል ድርጊት በሆነው በሽብር በመወንጀል አሰቃቂ ግፍ ፈፅመዋል፡፡ ይህንኑ የሽብር ዕቅዳቸው አካል የሆነውን ህገ-ወጥ ተግባር የህግ ሽፋን ለመስጠት የኢ/ፌ/ዲ/ሪ ፍትህ ሚኒስቴር የተሰኘ ክፍላቸውን በመጠቀም የህዝብ ወኪሎችን ከሃያ ወራት ያላነሰ በእስር ቤት አጉረዋል፡፡ በተጨማሪም በሺህዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን “በሁከትና በብጥበጥ” በመወንጀል ተመሳሳይ ወንጀል ፈፅመዋል፡፡ መረጃ ለህዝብ እንዳይደርስ ለማገድ በማሰብ በሙስሊሙ ህ/ሰብ ጉዳይ ላይ በማጠንጠን የሚዘግቡ ሃይማኖታዊና ማህበራዊ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን አግደዋል፤ አዝዘግተዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ አባስት ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን በተለያ ስያሚዎች በመከፋፈል፣ አክራሪ አስተሳሰባቸውን በኃይል በመጫን፣ ይህንን ህገ-ወጥ ተግባራቸውን በተቃውሙ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፤ በርካታ የኃይማኖት መምህራንና ምሁራን ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርገዋል፡፡ ህዝብ የሰጣቸውን ስልጣን ህዝብን ለማሸበር ተጠቅመዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ በኮፈሌ፣ በአሳሳ፣ በሀረር፣ በሀርጉ፣ በደጋን፣ በአዲስ አበባ አወሊያ መስጂድ፣ በአንዋር መስጅድና በአዲስ አበባ ስቴድዮም በህዝበ-ሙስሊሙ ላይ የህይወት፣ የአካልና የንብረት ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡ጰ፡

ተከሳሾች የሽብር ቡድኑን ዓላማ ለማስፈፀም በማሰብ አክራሪ አስተሳሰባቸውን የማቃባሉ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን በኢኮኖሚ ለማዳከም የተለያዩ እቅዶችን ነድፈው ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት ብልጽግና የሚጨበጥ ተሳትፎ ማድረግ የሚያስችላቸውን ከወለድ ነፃ ባንክ ማቋቋም እንዳይችሉ ከልክለዋል፡፡ ከወለድ ነፃ ባንክ ማቋቋም የሚፈቅድ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀ ቢሆንም የሽብር ቡድኑ አመራሮች በሰጡት ቀጭን ትዕዛዝ ከ6800 (ስድስት ሺህ ስምንት መቶ) አባላት በላይ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ያቀፈውን ዘምዘም ባንክ በብሔራዊ ባንክ ፕሬዝዳንት ፊርማ አዋጁን በመጣስ በኃይል በትነዋል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያላቸውን የትምህርት ተሳትፎ ለማቀጨጭ በማቀድ ሆን ብለው ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚቃረንና የእምነት ነፃነትን የሚጋፋ አግላይ ደንብ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በማውጣት ከፍተኛ ጫና አሳድረዋል፡፡ ይህንኑ ህገ-ወጥ ደንብ የተቃወሙ ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አንድም ለእስራት አሊያም ከትምህርት ገበታ ለመገለል እንዲደረጉ አድርገዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ ዓላማውን ለማስፈፀም ባቋቋማቸው የመገና ብዙሃን የሽብር ቅስቀሳ አድርጓል፡፡ አባላቱ መረጃን አዛብቶ በማቅረብ የጠወሰነን የህበረተሰብ ክፍል በተወሰነው ላይ የማነሳሳት ወንጀል ፈፅመዋል፡፡ ህዝበ-ሙስሊሙ ያነሳቸውን የእምነት ነፃነት ጥያቄዎች በመቀልበስ ሙስም ላልሆኑ ወገኖቹ ስጋት እንደሆነ አድርገው በመሳል ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በዚህም ድርጊታቸው ለዘመናት ተከባብሮ የኖረውን የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ለማስገባት በማስብ ያልተሳካ ሙከራ አድርገዋል፡፡ ቀስቃሽ የመገናኛ ብዙሃናቸውን በመጠቀም በእስር ላይ ያሉ ንፁሃን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን እና የኃይማኖት መምህራንን በ “ሽብር” በመፈረጅ “ጅሃዳዊ ሀረካት” የተሰኘ ከእውነት የራቀና የተቀነባበረ ዘጋቢ ፊልም በማሰራቸት ህዝብን በህዝብ ላይ አነሳስተዋል፡፡ የሽብር ቡድኑ አባላት በደሴ ከተማ በሸህ ኑሩ ኢማም ላይ ግድያ በመፈፀም የመገናኛ ብዙሃናቸውን በመጠቀም የህዝበ-ሙስሊሙን የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴ ለማጠልሸት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ የተዛባ መረጃ በመስጠትና በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ያደራጇቸውን ዜጎች በጥቅም በመደለል አሊያም በማስፈራራት በመላ ሀገሪቱ የሀሰት የድጋፍ ሰልፍ እንዲወጣ በማድረግ ህዝብን ለማታለል ሞክረዋል፡፡ በግድያው ማግስትም በርካታ ንፁሃን ሙስሊሞችን ለእስር በመዳረግ በሽብር ወንጅለዋል፡፡

በአጠቃላይ ተከሳሾች የሽብር ቡድኑን ዓላማ ለማስፈፀም በማቀድ በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት እነርሱ ከመረጡት አክራሪ አስተሳሰብና አይዲዮሎጂ ውች ያለን ለማጥፋት በመንቀሳቀሳቸው፣ የተወሰነን የህብረተሰብ ክፍል በማስፈራራታቸው በህይወት፣ በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት በማድረሳቸው፣ እገታ በመፈጸማቸው፣ የሽብር ድርጊት ለመፈፀም በማቀዳቸው፣ በመዘጋጀታቸው፣ በማሴራቸው፣ በማነሳሳታቸው እና በመፈፀማቸው በግዙፍ የወንጀል ድርጊት ተከሰዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ አባላት የወንጀል ተሳትፎ እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡-

1ኛ. ተከሳሽ – የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት

የሽብር ቡድኑን እቅድና ዓላማ ለማስፈፀም በመዋቅሩ ተዋረድ ያሉ መስሪያ ቤቶች እንዲንቀሳቀሱ መመሪያ ሰጥቷል፡፡ የሚፈፅማቸውን የሽብር ድርጊቶች ህጋዊና ትክክለኛ ለማስመሰል የሀገሪቱን የፍትህ ስርዓት እንደ ሽፋን ተጠቅሟል፡፡ ለዚህም ከ8ኛ ተከሳሽ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ንፁሃንን ለእስርና ለኢ-ሰብዓዊ ግፍ ከመዳረጉም በተጨማሪ በሺዎች ከሚቆጠሩ ሙስሊሞች በዋስትና ማስጠበቂያ ስም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር መዝብሯል፡፡ ለሽብር ዓላማው መደለያ ይሆን ዘንድ በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ በማደራጀት ለ2005 የበጀት ዓት ብቻ 350,000,000.00 (ሦስት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ብር) በመመደብ ተንቀሳቅሷል፡፡ ለሽብር ዓላማው የሚገለገልባቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት (ኢቲቪ) እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን (አዲስ ዘመን ጋዜጣን) በመጠቀም የሀሰት መረጃ ለህብረተሰቡ በማሰራጨት ህዝበ-ሙስሊሙን ሙስሊም ካልሆነው ወገኑ ጋር ለማጋጨት ተንቀሳቅሷል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመውን የሽብር ድርጊት በፊታውራሪነት የመራና ያስፈፀመ በመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት በፈፀመው የሽብር ድርጊትን ማቀድ፣ ማሴርና መፈፀም ወንጀል በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3 እና 4 የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡

2ኛ. ተከሳሽ የህውኃት/ ኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ

የሽብር ቡድኑ ስራ-አስፈፃሚ በመሆን ሰርቷል፡፡ የሽብር ድርጊቱን በማቀድ፣ በማሴር እና አመራር በመስጠት ተሳትፏል፡፡ ቀኑና ወሩ በውል ባልታወቀ 1996 ዓ.ል ጀምሮ በሽብር ድርጊቱ ዙሪያ በህቡዕ በመወያትና የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም  ጊዜ እቅድ በማውጣት የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን መሪ ድርጅት የኢ/እ/ጉ/ጉባኤ (መጅሊስን) የፖለቲካዊ ግባቸው ማስፈፀሚያ ኃይማኖታዊ ተቋም እንዲሆን ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በህገ-መንግስት አንቀጽ 11 እና አንቀጽ 27 የተደነገገውን የእምነት ነፃነት በመቃረን በእምነት ተቋና በኃይማኖት ጉዳይ በቀጥታ ጣልቃ ገብተዋል፡፡ ይህን ህገ-ወጥ ድርጊት በተቃወሙ ንፁሃን ላይ የኃይል እርምጃ በመውሰድ የሽብር ድርጊት እንዲፈፀም ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ ስለሆነም ለሽብር ድርጊት በማሴር፣ በማቀድና አመራር በመስጠት ወንጀል በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 4 እና አንቀጽ 7(2) የተመለከተውን በመተላለፋቸው ተከሰዋል፡፡

3ኛ. ተከሳሽ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (በሌሉበት)

የሽብር ቡድኑ የቀድሞ አመራር በመሆን ሰርተዋል፡፡ የሽብር ድርጊቱን በማሴር፣ በማቀድና አመራር በመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ ከ17ኛ ተከሳሽ ሃጋይ ኤርሊኽ የተሰጣቸውን ምክር ከልብ በመቀበል ያላቸውን የግል ክህሎት በማከል የሽብር ቡድኑን ዓላማ በመቅረፅ የቡድኑን ጥንስስ ጥለዋል፡፡ በሚያዚያ 9/2004 ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባደረጉት ንግግር በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ለመከፋፈል ሞክረዋል፡፡ የሽብር ዘመቻው ለመጀመር የነበራቸውን እቅድ የመብት ጥያቄ ያነሳውን ህዝበ-ሙስሊም “ጥቂቶች” በማለት ከማሸማቀቅ አልፈው “በእንጩጩ ማስቀረት” ሲሉ ዝተዋል፤ አስፈራርተዋል፡፡ ይህንኑ የፓርላማ ንግግራቸውን ተከትሎ 5ኛ ተከሳሽ የፌ/ፖሊስ ኮሚሽን በሚያዚያ 2004 በአሳሳ ከተማ በንፁሃን ሙስሊሞች ላይ የህይወትና የአካል ጉዳት አድርሷል፡፡ ምንም እንኳን የሽብር ድርጊቱን ከመፈፀማቸው በፊት እርሳቸው ራሳቸው በእንጩጩ የቀሩ ቢሆንም የሽብር ቡድኑ በእርሳቸው የተዘረጋለትን የአፈፃፀም እቅድ በመከተል ከፍተኛ የህይወት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት አድርሷል፡፡ ግለሰቡ በአዋጅ የፀደቀውን የወለድ ነፃ ባንክ የመመስረት መብትን በመንጠቅ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችና በክርስቲያን ወንድሞቻቸውም ተሳትፎ የተቋቋመውን “ዘምዘም ባንክ” እንዲበተን ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመስጠት በትነዋል፡፡ በዚህም የሽብር ቡድኑ ዓላማ አንዱ የሆነውን የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን የኢኮኖሚ ተሳትፎ ማኮሰስን ለማሳካት በማሰብ አዋጅን በመመሪያ ጥሰዋል፡፡ ግለሰቡ በ2004 ለአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በተፃፈ ደብዳቤ ለአህባሽ ማሰልጠኛ ተቋም ግንባታ የሚውል በቦሌ ክ/ከተማ የሚገኝ 100ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ እንዲሰጥ በፊርማቸው አዘዋል፡፡ በዚህም የህዝብ ስልጣንን ለራሳቸው የሽብር ዓላማ ማሳኪያ ተጠቅመዋል፡፡ ስለሆነም ግለሰቡ የሽብር ድርጊትን በማቀድ፣ በማሴር፣ በማነሳሳትና በመፈፀም ወንጀል በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 4 እና 7(2) የተመለከተውን በመተላለፍ ወንጀል በሌሉበት ተከሰዋል፡፡

4ኛ ተከሳሽ -ጠ/ሚኒስቴር ኃ/ማርያም ደሳለኝ

ተከሳሽ የቀድሞውን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን (3ኛ ተከሳሽን) የእግር ኮቴ ያለምንም መጨመርና መቀነስ በመከተል የሽብር ቡድኑን መርተዋል፡፡ የሽብር ድርጊቱን የተቃውሙ ሙስሊሞች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ በሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ- 21ኛ ተከሳሽ እና በአልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ህዝበ-ሙስሊሙን “ጥቂቶች” ሲሉ አሸማቀዋል፡፡ ለሚፈፀሙ የሽብር ድርጊቶች ሁሉ አመራር ሰጥተዋል ባባልም የሀገሪቱ የበላይ አመራር ከመሆናቸው አንፃር በይሁንታ በማለፍ በቀጥታ አመራር የመስጠት ያህል ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ ስለሆነም ሀገሪቱ ውስጥ የተፈፀሙ የሽብር ድርጊቶችን በሙሉ በማቀድ፣ በመፈፀምና አመራር በመስጠት ወንጀል የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 2 እና 7(2)ን በመተላለፍ ወንጀል ተከሰዋል፡፡

5ኛ. ተከሳሽ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን

የሽብር ቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ በመሆን በዜጎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሷል፡፡ በሚያዚያ 2004 በአሳሳ፣ በሀምሌ 2005 በኮፈሌ፣ ቀኑና ወሩ ባልታወቀ በ2005 በሀርቡ፣ በ2004 በሀረር፣ በሀምሌ 06/2004 በአወሊያ መስጅድ፣ በሐምሌ 14/2004 በአንዋር መስጅድ እና በሐምሌ 2005 በአዲስ አበባ ስቴዲዮም ዙሪያ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ የህይወት፣ የአካልና የንብረት አሰቃቂ ጉዳት አድርሷል፡፡ በሐምሌ 06/2004 በሌሊት አወሊያ መስጅድ ውስጥ ለምፅዋት የሚሆን ምግብ ሲያዘጋጁ የነበሩ ሙስሊሞች ላ እገታ በማድረግ፣ በተዘጋ መስጅድ ውስጥ ባሉ ሙስሊሞች ላይ አስለቃሽ ጥይት ወደ ውስጥ በመተኮስ በህዝብ ጤና ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ በሐምሌ 2005 የዒድ አልፊጥር ባዕልን ለማክበር በአዲስ አበባ ስቴዲዮም በመገኘት የ1ኛ ተከሳሽን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስትን በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገብነት በመቃወማቸው በሺህዎች በሚቆጠሩ ሙስሊሞች ላይ አሰቃቂ ድብደባ እና እስር ፈፅሟል፡፡ በዕለቱ ከአስር ሺህ በላይ ሙስሊሞችን ለእስርና እንግልት ዳርጓል፡፡ በመሆኑም ከ2ኛ ተከሳሽ ህውኃት/ኢህአዴግ በተሰጠው አመራር የሽብር ድርጊቱን በቀጥታ የፈፀመ በመሆኑ በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(1)(2)(4) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡

6ኛ. ተከሳሽ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ

የሽብር ቡድኑ መረጃ ክፍል በመሆን ለቡድኑ አመራሮች ሀሰተኛ መረጃን በመስጠት የሽብር ድርጊቱን አቀጣጥሏል፡፡ የሽብር ቡድኑ አመራሮችን ከጀርባ ሆኖ በመምራት ሆን ብሎ በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ ሽብር እንዲፈፀም አበረታቷል፡፡ የተለያዩ በህቡዕ የተፈፀሙ ግድያዎችን አሲሯል፣ አቀነባብሯል፣ ፈፅሟ፡፡ በ2005 በደሴው ሸህ ኑሩ ኢማም ላይ የተቀነባበረ ግድያ ፈፅሟል፡፡ ይህን በማድረግም የህዝበ-ሙስሊሙን የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴ ለማኮላሸት ንፁሃንን አስሯል፤ በሀሰት የከሰሳቸውን ዜጎች ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች “ህገ-መንግስት ይከበር” እንቅስቃሴ ጋር ለማዛመድ ጥረት አድርጓል፡፡ ቢሮው ከ5ኛ ተከሳሽ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ዜጎችን የማገት፣ የማሰር፣ ቶርች የማድረግና የመግደል ወንጀል ቀጥተኛ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በተጨማሪም ቢሮው በሐምሌ 08/2004 በተወሰኑ የህዝበ-ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የመኪና እገታና ጠለፋ ሙከራ አድርገዋል፡፡ በሀሰት በተወነጀሉት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴና በተለያዩ ምድብ ችሎት በቀረቡ ንፁሃን ሙስሊሞች ላይ ከ11ኛ ተከሳሽ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ጋር በመሆን ለሽብር ድርጊታቸው የሚሆኑ የሀሰት ምስክሮችን በማባበል አሊያም በማስፈራራት አዘጋጅተዋል፡፡ ስለሆነም የሽብር ድርጊት ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን እና ምስክር በማባባል ወይም በማስፈራራት ወይም ማስረጃ በማጥፋት ወንጀል በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(1)(2)(3)(4) እና 10(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡

7ኛ. ተከሳሽ የኢ.ፌዲ.ሪ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር

የሽብር ቡድኑ የስልጠናና የምልመላ ክፍል በመሆን ሰርቷል፡፡ የህዝብን ሃብትና ጊዜ ለእኩይ ዓላማው በመጠቀም የሽብር ቡድኑን ዓላማ ለማስፈፀም በሙሉ ልቡ ተንቀሳቅሷል፡፡ 10ኛ ተከሳሽን (መጅሊስን) እንደ ኃይማኖታዊ ሽፋን በመጠቀም አክራሪ ስልጠናዎችን አዘጋጅቷል፤ አካሂዷል፡፡ “ህገ-መንግስት ማስተማር” በሚል ስም በኃይማኖታዊ ጉዳዮች በቀጥታ ጣልቃ በመግባት ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት የሚያምኑባቸውን ጉዳዮች በአዲሱ አክራሪ አስተሳሰብ መተካት እንዳለባቸው በ2003 ሐምሌ ወር በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ከ10ኛ ተከሳሽ የኢ/እ/ጉ/ጉባኤ (መጅሊስ) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የአህባሽ ስልጠና ላይ የ1ኛ ተከሳሽን (የመንግስትን) አቋም አንፀባርቋል የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአክራሪ አስተሳሰቡን ማስፋፋትና በሙስሊሙ ኃይማኖታዊ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እየገባ ቀጥተኛ ትዕዛዝና መመሪያ መስጠት የዕለት ከዕለት ተግባሩ በማድረግ ህገ-መንግስታዊ ጥሰት ፈፅሟል፡፡ የሽብር ቡድኑ ለመፈፀም ላቀደውና ለፈፀመው የሽብር ድርጊት የአስተሳሰብ መደላድል በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ስለሆነም የሽብርተኝነት ድርጊት እንዲፈፀም ስልጠና በመስጠት ወንጀል በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 5(1)(2) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡

8ኛ. ተከሳሽ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር

የሽብር ቡድኑ ለሚፈፅማቸው ህገ-ወጥ ድርጊቶች የህግ ሽፋን በመስጠት ተንቀሳቅሷል፡፡ በስሩ በሚገኘው የፌዴራል ዓቃቢ ህግ በኩል ከ11ኛ ተከሳስ የፌዴራል ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ) ጋር በመተባበር የሽብር ቡድኑ የሚፈፅማቸውን የህገ-መንግስት ጥሰቶችና የሽብርተኝነት ተግባራት የሚቃወሙና ለህዝብ የሚያጋልጡ የነፃነት ታጋዮችን፣ ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ ሰዎችን በሀሰት ውንጀላ በመክሰስ እና የሀሰት የምስክርና ሰነድ በማዘጋጀት ወንጀል ፈፅመዋል፡፡ በተለይም የህዝበ-ሙስሊሙን ህጋዊ ወኮሎች የሽብር ቡድኑ በፈፀመው በሽብር ወንጀል በመክሰስ ለሽብርተኝነት ከለላና ጥበቃ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም የህዝበ-ሙስሊሙን የመብት ጥያቄ የዓለም ማህበረሰብን ባስደመመ ሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የመሩና ያስተባበሩ የህዝብ ልጆችን ያለምንም ሀፍረት ወይም ርህራሄ ለእስርና እንግልት ዳርገዋል፤ የንፁሃንን ቤተሰብ አባወራ አልባ አድርገዋል፡፡ ህፃናቶቻቸውን ያለ አባት እንክብካቤ እንዲያድኑ አድርገዋል፡፡ በአጠቃላይ ሚኒስቴር መ/ቤቱ የሽብር ቡድኑ የዜጎች ዋስትና የሆነውን የፍትህ ስርዓት ለጊዜያዊና ለርካሽ የፖለቲካ ጥቅም እንዲያውል ተባብሯል፡፡ በዚህም የሚ/መ/ቤቱ የህዝብን ደህንት አደጋ ላይ በመጣል የፍትህ ስርዓቱን ለጥቂት የሽብር ቡድኑ አባላት ፖለቲካዊ ጥቅም በማዋሉ እና ለሽብር ድርጊት ከለላና ሽፋን በመስጠቱ በሽብር ድርጊት ተባባሪነት የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 5(2) እና 7(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡

9ኛ. ተከሳሽ የኢ.ፌዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር

የሽብር ቡድ በረጅም ጊዜ እቅዱ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን የከፍተኛ ትምህርት ተሳትፎ ለማኮሰስ በሚያደርገው ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴርን ሲጠቀም የሚስቴር መስሪያ ቤቱ ለሽብር እቅዱ ስኬት በፈቃደኝነት ተባብሯል፡፡ ተከሳሹ የእምነት ነፃነትን የሚቃረን የተማሪዎች ደንብ በማርቀቅ ተማሪዎች የመማር ማስተማር ሂደቱን በማያደናቅፍ ሁኔታ የሚተገብሯቸውን ኃይማኖታዊ ስርዓቶች ለማገድ ተንቀሳቅሷል፡፡ በዚህም የእስልምናም ይሁን የክርስትና እምነት ተከታዮችን ከኃይማኖተኝነት በማራቅ ለሽብር ቡድኑ አጎብዳጅ ትውልድ የመፍጠር የረጅም ጊዜ የጎድንዮሽ ዓላማ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው ሆን ብሎ የሽብር ቡድኑ ተባባሪ ሆኗል፡፡ ስለሆነም ሽብርተኝነትን በመርዳት ወንጀል የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 7(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡

10ኛ. ተከሳሽ የኢ/እ/ጉ/ጉባኤ (መጅሊስ)

የሽብር ቡድኑ ኃይማኖታዊ ሽፋን ሰጭ ተቋም በመሆን ከ1992 ጀምሮ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግና የሽብርተኝነት ድርጊትን ሲረዱና ሲተባበር ቆይቷል፡፡ በህገ-ወጥ መንገድ ስልጣን የተቆናጠጡ አባላቶቹ ህገ-ወጥ ምርቻ በማድረግ ህዝበ-ሙስሊሙ ባስሰጣቸው ውክልና ያለፈቃዱ ሲመሩት ቆይተዋል፡፡ ተቋሙ የ1ኛ ተከሳሽ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት አንድ ቢሮ በመሆን የመንግስት ባለስልጣናት በተለይም 13ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም በቀጥታ የሚያዙት በኃይማኖት ሽፋን የፖለቲካ ዓላማ የሚራመድበት ተቋም እንዲሆን ፈቅዷል፡፡ የህዝብን አደራ ወደ ጎን በመተው የመጅሊሱ አመራሮች በከፍተኛ ምዝበራ በመዘፈቅ ከሐጅና ዑምራ ጉዞ የሚገኘውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ለግል ጥቅማቸውና አክራሪ አስተሳሰባቸውን ለማስፋፋት ተጠቅመዋል፡፡ በተጨማሪም በምዝበራ የተገኘውን ገንዘብም ለ6ኛ ተከሳሽ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በማካፈል የህዝብን ንብረት ህገ-ወጥ ዓላማን ለማስፈፀም አውለዋል፡፡ ያስመጣውን አህባሽ የተሰኘ አስተሳሰብ በኃይል በመጫን የእምነት ነፃነትን ተቃርነዋል፡፡ ተቋሙ ከ7ኛ ተከሳሽ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጋር በመሆን የግዳጅ ስልጠናዎችን አዘጋጅቷል፡፡ በ8ኛ ተከሳሽ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ስር ከሚገኙ የፍትህ ቢሮዎች ጋር በመተባበር በግዳጅ ስልጠናዎች ለመሳተፍ ፈቃደኛ ያልሆኑና ከአክራሪ አስተሳሰባቸው ውጭ የሆኑ የመስጅድ ኢማሞችን አባርረዋል፤ በምትካቸውም ምዕመናኑ የማፈልጓቸውን ኢማሞች ሾመዋል፤ በህዝብ በተመረጡ የመስጅድ ኮሚቴዎች የሚተዳደሩ መስጅዶችን ከ6ኛ ተከሳሽ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ ጋር በመተባበር ከህዝብ በኃይል ነጥቀዋል፡፡ “መንግስት የሾማቸውን ኢማሞች ተከትለን አንሰግድም” በማለት ስግደታቸውን ለብቻቸው የከወኑ ምዕመናን ለእስርና እንግልት እንዲዳረጉ ምክንያት ሆነዋልል፡ በአጠቃላይ ተቋሙ የሽብር ቡድኑ (ህውኃት/ኢህአዴግ) በህዝበ-ሙስሊሙ ላይ የፈፀማቸውን የሽብር እንቅስቃሲዎች ኃይማኖታዊ ቡራኬ የሰቱ በመሆኑ በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 7(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡

11ኛ. ተከሳሽ የፌ/ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ)

የሽብር ቡድኑ ቶርቸር እና ማውጣጫ (Inquisition) ክፍል ሆኖ አገልግሏል፡፡ ዜጎች ያልፈፀሙትን ወንጀል እንዲናዘዙ የአዕምሮ፣ የስነ-ልቦና የአካል ቶርቸር በማካሄድ የሀሰት ሰነድና ማስረጃ በማቀነባበር ከ8ኛ ተከሳሽ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሀሰት ክስ በመመስረት ንፁሃንን ወንጅሏል፡፡ ያልተፈፀመ ወንጀልን በማውጣጣት ሂደትም እጅግ ኢ-ሰብአዊ የምርመራ መንገዶችን በመጠቀም በከሳሾች ላይ ከፍተኛ የአካልና የስነ-ልቦና ጉዳት አድርሰዋል፡፡ የክፍሉ አባላት የሽብር ቡድኑ የሚፈፅማቸውን የሽብር ድርጊቶች ለመደበቅና ከለላ ለመስጠት ሆን ብለው ንፁሃን ላይ አሰቃቂ ድብደባና የማሰቃያ መንገዶችን በመጠቀም ሽብር የተፈፀመው በእነኝህ ንፁሃን መሆኑን ለማስመሠል ከሞራል ህግጋትም ሆነ ከህገ-መንግስት የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ የተቃረኑ ዘግናኝ ወንጀሎችን ፈፅመዋል፡፡ ተቋሙ በሀሰት በሚወንጅላቸው ንፁሃን ላይም የሀሰት ምስክሮችን በማዘጋጀት፣ በማባባል፣ አሊያም በማስፈራራት የሽብር ድርጊቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረጉ በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 5(1)(ሀ)፣5(2) እና 10(1)(2) የተመለከተውን በመተላለፍ ወንጀል ተከሷል፡፡

12ኛ. ተከሳሽ አቶ ጌታቸው አሰፋ

የሽብር ቡድኑ የመረጃ ክንፍ የሆነውን 6ኛ ተከሳሽ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮን በበላይነት መርተዋል፡፡ ፍፁም በሆነ አምባገነናዊ አመራራቸው ንፁሃን ዜጎች እንዲታሰሩ፣ እንዲሰቃዩ እንዲታገቱና እንዲገደሉ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ህጋዊና ሰላማዊ እነቅስቃሴ ለማኮላሸት አቅደዋል፣ አሲረዋል፣ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ የሽብር ቡድኑ ለሚፈፅማቸው የሽብር ድርጊቶች የሚውሉ ግለሰቦችን መልምለዋል ወይም እንዲመለመሉ አድርገዋል፡፡ ስልጣናችውን በመጠቀም በእጅ አዙር እና በቀጥታ የሽብርተኝነት ድርጊት እንዲፈፀም አመራር በመስጠት በወንጀሉ ተሳትፈዋል፡፡ ለሽብር ቡድኑ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት የሽብር ድርጊቱን አፋፍመዋል፡፡ ስለሆነም በሽብር ድርጊቱ ቀጥተኛ ተሳታፊና አመራር ሰጭነት በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(1)(3) እና 7(2) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሰዋል፡፡

13ኛ. ተከሳሽ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም

የሽብር ቡድኑን የስልጠናና የምልመላ ክፍል የሆነውን 7ኛ ተከሳሽ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴርን በበላይነት መርተዋል፡፡ የሽብር ቡድኑ ከሊባኖስ ያስመጣውን አህባሽ የተሰኘ አክራሪ አስተሳሰብን በግዳጅ ለማሰልጠን 10ኛ ተከሳሽን (መጅሊስን) እንደሽፋን በመጠቀም ተንቀሳቅሰዋል፡፡ አክራሪ አስተሳሰቡን የማስፋፋት ጥረታቸውን ዋነኛ የቢሮ ስራቸው በማድረግ የህዝብን ስልጣን ያለ አግባብ ተጠቅመዋል፡፡ በግዳጅ ስልጠናውም በተለያዩ ዙር እና በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች 80000 (ሰማንያ ሺህ) ሙስሊሞችን ለማሰልጠን ሞክረዋል፡፡ በተለያዩ የስልጠና መድረኮች በተለይም በሐምሌ ወር 2003 በሐሮሚያ ዩኒቨርስቲ በተካሄደው የግዳጅ ስልጠና በመገኘት ህገ-መንግስቱን በተቃረነ መልኩ በኃይማኖታዊ ጉዳይ በቀጥታ ጣልቃ ገብተዋል፡፡ ህዝብ የሰጣቸውን ስልጣን በመጠቀም የእርሳቸውን አስተሳሰብ ያልተቀበሉ ወገኖችን አስፈራርተዋል፣ ዝተዋል፣ ሙስሊሙን ህ/ሰብ የተለያዩ ስያሜ በመስጠት ለመከፋፈል ጥረዋል፤ 20ኛ ተከሳሽን (አዲስ ዘመን ጋዜጣን) እና 20ኛ ተከሳሽን (ኢ.ሬ.ቴ.ድ፣ ቲቲቪን) በመጠቀም ንፁሃን የመብት ጠያቂ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን በሽብር ፈርጀዋል፡፡ በአጠቃላይ የሽብር ቡድኑ ስራ-አስፈፃሚ አባል እንደመሆናቸው የሽብር ድርጊት እንዲፈፀም አመራር ሰጥተዋል፡፡ ስለሆነም በፈፀሙት ግዙፍ የወንጀል ድርጊት በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 5(1)(ረ) እና 7(2) የተመለከተውን በመተላለፋቸው ተከሰዋል፡፡

14ኛ. ተከሳሽ አቶ ፀጋዬ ኃ/ማርያም

የሽብር ቡድኑ የፀጥታ ክንፍ በመሆን አገልግለዋል፡፡ የቡድኑን ፀጥታ ለማስከበር በማቀድ የህዝብን ፀጥታ አደፍረሰዋል፡፡ በተለያ የአክራሪነት ስልጠናዎች በአካል በመገኘት ንግግር በማድረግ ለሽብር ቀስቅሰዋል፣ የአክራሪ አህባሽ አስተሳሰብን አበረታተዋል፣ የህዝብን ስልጣን በመጠቀም ዜጎችን አስፈራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የግዳጅ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ አስገድደዋል፡፡ ሙስሊሙን ህ/ሰብ ለመከፋፈል በማሰብና አክራሪ አስተሳሰባቸውን ለማስፋፋት ከ7ኛ ተከሳሽ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጋር በመሆን በርካታ የግዳጅ ስልጠናዎችን አዘጋጅተዋል፡፡ በተለይም በኢትዮ ቻይና ካምፓስ በመስከረም 2004 የተለያ ስያሜ በመስጠት ሙስሊሙን ለመከፋፈል ሞክረዋል፡፡ በተለይም ከ5ኛ ተከሳሽ የፌ/ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላ የሽብር ድርጊት እንዲፈፀም አቅደዋል፤ ለአፈፃፀሙም ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በዚህም በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(1)(2)(4) እና 5(1)(ረ) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሰዋል፡፡

15ኛ. ተከሳሽ አቶ ሪድዋን ሁሴን

የሽብር ቡድኑ ቃል አቀባይ በመሆን ለህዝብ የተዛባ መረጃ አስተላልፈዋል፡፡ በተለይም በሰንደቅ ጋዜጣ 2004 እትም ላይ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ህዝበ-ሙስሊሙን በሽብርተኝነት ፈርጀዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን አደጋ አድርጎ በመሳል ህዝብን በህዝብ ላይ አነሳስተዋል፡፡ ቀደም ሲል የህውኃት /ኢህአዴግ የሽብር ቡድን ፀሀፊ በመሆን ለቡድኑ የሙያ፣ የልምድ እና የሞራል ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡ ስለሆነም በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 5(1)(ለ) እና 7(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሰዋል፡፡

16ኛ. ተከሳሽ አቶ አህመዲን አብዱላሂ ጨሎ

የሽብር ቡድኑ ኃይማኖታዊ ሽፋን በመሆን በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ዓለማዊና መንፈሳዊ ክህደት ፈፅመዋል፡፡ ከግብረ አበሮቻቸው ህገ-ወጥ የመጅሊስ አመራሮች ጋር በመሆን የህዝበ-ሙስሊሙ መሪ ድርጅት የሆነውን የኢ/እ/ጉ/ጉባኤ (መጅሊስ ለ2ኛ ተከሳሽ ህውኃት/ኢህአዴግ ፖለቲካዊ ግብ ማስፈፀሚያ ኃይማኖታዊ ሽፋን ይሆን ዘንድ ተንቀሳቅሰዋል፡፤ የህዝበ-ሙስሊሙ ብቸኛ ሚሲዮናዊ ተቋ የሆነውን የአወሊያን ተቋም “ለማፈራረስ” ተንቀሳቅሰዋል፡፡ የሽብር ቡድኑ ለሚያደርጋቸው ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች መሣሪያ በመሆን ህዝበ-ሙስሊሙን ለሽብር ጥቃት ዳርገዋል፡፡ ስሆነም ለሽብር ቡድ በሰጡት ከለላና ለሽብር ድርጊቱ ተቀዳሚ ረዳት በመሆናቸው በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 5(2) እና 7(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሰዋል፡፡

17ኛ. ተከሳሽ ፕሮፌሰር ሃገሮ ኤርሊኽ (በሌሉበት)

የእስራኤል ቴልአቢብ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ይሁዳዊው ሃጋይ ኤርሊኽ የሽብር ቡድን አስተሳሰብ በመቅረፅና የአፍሪካ ቀንድ ከባቢያዊ ፖለቲካ ለሀገራቸው እስራኤል ጥቅም አንፃር እንዲቃኝ በማድረግ ከአይሁዶች ጋር ጥብቅ የስራና የዓላማ ትስስር እንዳለው የሚነገርለትን የ “አህባሽ” አስተሳሰብ ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ለሽብር ቡድኑ እኩይ ምክር ሰጥተዋ፡፡ በተለይም ከ3ኛ ተከሳሽ የቀድው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በነበራቸው የግል ቀረቤታ የሽብር ቡድኑ እኩይ ዓላማቸውን እንዲያራምዱ አድርገዋል፡፡ በመስከረም ወር 2004 በ20ኛ ተከሳሽ (ኢቲቪ)  “Meet ETV” የእንግዝ ፕሮግራም ላይ በመቅረብ የአህባሽ አስተሳሰብ ለኢትዮጵያ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ስለሆነም ለሽብር ቡድኑ ለፈጠሩት የአስተሳሰብ መደላደልና ባደረጉት የልምድ፣ የሞራል ድጋፍና ምክር በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 5(1)(ለ) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሰዋል፡፡

18ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ሰሚር አልሪፋዒ

በሽብር ቡድኑ አመራሮች ጋባዥነትና በ21ኛ ተከሳሽ ፔትራም ኃ/የተወ./የግል ኩባንያ ተባባሪነትና አስተባባሪነት ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የተደራጀ የአክራሪዎች ቡድን በማዘጋጀት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ያደራጃቸው ሊባኖሳዊያን የአህባሽ ግዳጅ ስልጣና ላይ በአሰልጣኝነት እንዲሰሩ አድርገዋል፡፡ ቀኑና ወሩ ባልታወቀ በ2004 በጊዮን ሆቴል ከ13ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ጋር በመሆን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እርሳቸው ከሚያራምዱት አክራሪ አስተሳሰብ ውጭ ያውን ኢስላማዊ አስተሳሰብ በሽብር ፈርጀዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም ሊታገለው እንደሚገባ በመግለፅ ለህገ-ወጥ እርምጃ አነሳስተዋል፤ ቀስቅሰዋል፡፡ ስለሆነም ለሽብር ቡድኑ የሙያ፣ የልምድና የሞራል ምክርና ድጋፍ በመስጠታቸውና ለሽብር ድርጊት በመስጠታቸው በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 4 እና 5(1)(ለ) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሰዋል፡፡

19ኛ. ተከሳሽ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (አዲስ ዘመን ጋዜጣ)

የሽብር ቡድኑን ዓላማ ለማሳካት የሚያገለግል የህትመትና ስርጭት ክፍል ነው፡፡ የክፍሉ ጋዜጣ የሆነው አዲስ ዘመን ጋዜጣ መረጃን አዛብቶ በማቅረብ የሽብር ድርጊት እንዲፈፀም አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ በርዕስ አንቀፁና በገጽ 3 የፖለቲካ አምዱ ተከታታይ እትሙ ህዝበ-ሙስሊሙ አዲሱን የአህባሽ አክራሪ አስተሳሰብ መቀበል እንዳለበት ዛቻ አዞል ሀተታዎችን አሰራጭቷል፤ የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴውን በሽብር ፈርጇል፤ በሀሰት የሽብርተኝነት ድርጊት አስፈራርቷል፡፡ የሽብር ቡድኑን አመራሮች በተለያዩ ጊዜ ቃለ-መጠይቅ በማድረግ  ለሽብር ቡድኑ የሚዲያ ድጋፍ ሰጥቷል፡፡ ስለሆነም በፀረ-ሽብረተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 6 እና 11 የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡

20ኛ. ተከሳሽ  የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት (ኢ.ሬ.ድ- ኢቲቪ)

ከህዝብ መገናኛ ብዙሃን አንዱ የሆነው ኢ.ቲ.ቪ. የተቋቋመበትን ዓላማ ወደ ጎን በመተው የሽብር ቡድኑን ዓላማ ለማሳካት የታሰቡና የታቀዱ የተዛቡ መረጃዎችን ለህዝብ በማድረስ ህዝብን በህዝብ ላይ አነሳስቷል፤ የህዝበ-ወኪሎችን በሽብር የፈረጀና በሀሰት ቅንብር ተሞላ “ጅሃዳዊ ሀረካት” የተሰኘ ገዛቢ ፊልም በተደጋጋሚ አሰራጭቷል፡፡ የሽብር ቡድኑ የሚፈፅማቸውን ህገ-ወጥ ድርጊቶች በማስመሰል ህዝብን ለማሳሳት ሙከራ አድርጓል፡፡ የሽብር ቡድኑ አመራሮችና ረዳቶች በተለያዩ ጊዜ ያደረጓቸውን የሽብር ቅስቀሳዎች አሰራችቷል፡፡ በዚህም የሽብርተኝነት ድርጊቱ ተባባሪ ሆኗል፡፡ ንፁሃንንና የሽብር ሰለባዎችን ሽብርተኛ በማስመሰል በሀሰት የሽብርተኝነት ድርጊት ህዝብን አስፈራርቷል፡፡ በተለይም የክርስትና እምነት ተከታዮች በእስልምና ተከታይ ወንድቻቸው ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው በማድረግ የእርስ በርስ ጦርነት ለማስነሳት ያልተሣካ ሙከራ አድርጓል፡፡ ስለሆነም በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 6 እና 11 የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡

21ኛ. ተከሳሽ ፔትራም ኃ/የተወ/የግል ማህበር

የሽብር ቡድኑ የፋይናንስ ድጋፍ ሰጭ በመሆን በህግ ከተቋቋመበት የንግድ ተቋም ውጭ የአህባሽን አክራሪ አስተሳሰብ ወደ ኢትዮጵያ በማስመጣት ሂደት ላይ የሎጀስቲክ ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም 18ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ሰሚር አልሪፋዒይ የተባሉ ሊባኖስዊያንና እርሳቸው ያደራጁዋቸው ሊባኖሳዊያን አሰልጣኞች ወደ ኢትዮጵያ በማስመጣት ሂደት ላይ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ ተከሳሹ በ3ኛ ተከሳስ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፊማ የታዘዘውን በቦሌ ክ/ከተማ የሚገኝ 100000 ካሬ ሜትር (አንድ መቶ ሽህ ካሬ ሜትር) ቦታ ለአህባሽ ማሰልጠኛ ተቋም ግንባታ ይውል ዘንድ ኃላፊነት ወስዶ ተንቀሳቅሷ፡፡ በአጠቃላይ ከፍተኛ የገንዘብ ወጭ በማድረግ ለአህባስ አስተሳሰብ መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ የሽብር ቡድኑን ረድተዋል፡፡ ስለሆነም በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 5(1) (ሐ)(መ) እና 7(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡

2ኛ ክስ

(16 እና 21ኛ ተከሳሾችን በተመለከተ)

ወንጀሉ

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብን እና ሽብርተኝነት በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀፅ 31(1)(ሀ)(1) የተመለከተውን በመተላለፍ፡-

የወንጀሉ ዝርዝር

16ኛ ተከሳሽ አቶ አህመዲን አብዱላሂ ጨሎ

ተከሳሽ አህባሽ የተሰኘውን አክራሪ አስተሳሰብ ለማስፋፋት በማቀድ መጠኑ 203000000.00 (ሁለት መቶ ሦስት ሚለዮን ብር) የሆነ ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ በርሳቸው ፊርማ ብቻ እንዲንቀሳቀስ በማድረግ በሽብር ቡድኑ የሚያዘጋጃቸውን የግዳጅ ሥልጠናዎች ወጭ ሸፍነዋል፤ ለ5ኛ ተከሳሽ ለፌ/ፖሊስ ኮሚሽን አባላት የሽብር እንቅስቃሴ የውሎ አበል ክፍያ በመስተት፣ የህዝበ-ሙስሙን እንቅስቃሴ ለማኮላሸት ለተመደቡ ግለሰቦችና የደህንነት አባላት የው አበል በመክፈል፤ በግፍ ለሚወነጀሉ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የሀሰት ምስክር ለሚሆኑ የአህባሽ አስተሳሰብ አራማጆች አበል በመክፈል የሽብር ድርጊቱ ቀጥተኛ ረዳት በመሆንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ በመርዳታቸው በአዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀፅ 31(1)(ሀ)(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሰዋል፡፡

21ኛ. ተከሳስ ፔትራም ኃ/የተወ/የግል/ማህበር

የሽብር ቡድኑ የፋይናንስ ድጋፍ ሰጭ ክንፍ በመሆን በህግ ከተቋቋመበት የንግድ ተቋነት ውጭ አክራሪ አስተሳሰብን ከፍተኛ በጀት በመመደብ ረድቷል፡፡ ተከሳሹ ምንቹ ያስታወቀ ግምቱ $30,000,000.00 (ሰላሳ ሚሊዮን) ዶላር ገንዘብ ህጋዊ በማስመሰል ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት የንግድ ተቋሙ ራሱን ከማጠናከር ጎን ለጎን አህባሽን ለማስፋፋት ተጠቅሞበታል፡፡ ከ1996 ጀምሮ በህቡዕ ሲንቀሳቅስ የነበረውንና በጦር ሃይሎች 3 ቁጥር ማዞሪያ የሚገኘውን የአህባሽ ማሰልጠኛ ተቋም ሙሉ በሙሉ ዓመታዊ በጀቱን በመሸፈን ሲረጁ ቆይቷል፡፡ የተከሳሹ ስራ አስኪያጅና ባለቤት አቶ አብዱልከሪም በድሪ ያላቸውን የገንዘብ አቅም በመጠቀም ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ትስስር በመፍጠር አህባሽን ከሊባስ ወደ ኢትዮጵያ በማስመጣት ሂደት ላ የአምባሳደርነት ሚና ተጫውተዋል፡፡ በዚህም ፔትራም ሃ/የተወ/የግል ማህበር በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ ለደረሰው የህገ-መንግስት ጥሰትና የሽብር ድርጊት የገንዘብ እርዳታ ያደረገ በመሆኑ ተከሳሽ በአዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀፅ 31(1)(ሀ)(1) የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሷል፡፡

 

የማስረጃ ዝርዝር

ሀ/ የሰው ምስክር

  1. መላው የኢትዮጵያ ህዝብ

ለ/ የሰነድ ማስረጃ

  1. 10000 ገጽ የተለያ አስረጂ ሰነዶች

ሐ/ የድምፅ ከምስል ማስረጃ

  1. 15 ቴራ ባይት ማስረጃ

መ/ የፎቶ ግራፍ ገላጭ ማስረጃዎች

  1. 2000 ፎቶዎች (በቁጥር)

ሠ/ በፍ/ቤት ትዕዛዝ የሚቀርቡ

1. በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ የሚገኙ ሚስጥራዊ ሰነዶች ከብሔራዊ መ/ደህንነት

2. የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በማዕከላዊ የደረሰባቸውን ስቃይና የግዳጅ ቃል እንዲሰጡ የደረሰባቸውን ጫና የሚያሳይ የድምፅ ከምስል ማስረጃ፣ ከፌዴራል ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ)

3. ኢቲቪ በጅሃዳዊ ሀረካት የተሰኘ የሀሰት ዘጋቢ ፊልም ባስተላለፈበት ፊልም ላይ የተጠቀማቸው ፊልሞች ሙሉ ይዘት ከኢቲቪ

4. የህውኃት/ኢህአዴግ የሽብር ቡድን በተለያዩ ጊዜ ያደረጋቸው ህቡዕ ውይይቶች፣ እቅዶች፣ ሴራዎችና ቃለ-ጉባዔዎች፣ ከድርጅቱ ጽ/ቤት

5. የጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪዎች የሚያቀርቧቸው ጥናታዊ ጽሑፎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ

6. የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የግል ማስታወሻ ደብተር ከባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን

7. የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን የመብት ጥያቄ ለመቀልበስ፣ ለማኮላሸትና ለማምከን የተደረጉ ሚስጥራዊ ውይይቶች ቃለ-ጉባዔዎች ከሁሉም የሚኒስቴር መ/ቤቶችና ከመጅሊስ፡፡

 

©መአኮ

የዋሺንግተን ዲሲ የጋራ ግብረሃይል “በሙስሊም ወንድሞቻችን ላይ የተፈረደው ፍርድ በ90 ሚሊዮን ሕዝብ ላይ የተፈረደ ፍርድ ነው”ሲል አወገዘ

$
0
0

abubeker

ጋዜጣዊ መግለጫ

የፍትሕ ያለህ

ፍትሕ የትንሽ የትልቁ የስላሙም የክርስቲያኑም የንግግር አልፋና ኦሜጋ ከሆነ ሰነበተ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎታቸውን ፣መስኪዶች ሶላታቸውን የሚያሳርጉት ስለ ፍትሕ እየጮሁ ነው።የጥንቱን ታሪክ እንዳለ ብናቆየው እንኳ ባሳለፍነው ከሬት የመረረ ወያነያዊ ስርዓት ፍትሕ በውን ተከስታ ልትትታይ ቀርቶ በዳሰሳና በሽታ እንኳ ደብዛዋ ጥፍቶ የ፺ ሚሊዮን ህዝብ የምኞት መዝሙር ሆና ፪፭ አመታትን አስቆጠረች። ዛሬም የፍትሕ ያለህ የህዝብ መዝሙር ሆኖ ቀጥሏል።

የፍትሕ ያለህ በሚል ርዕስ መግለጫ ስናውጣ ባለፈው ፪፭ አመታት የተደሰኮረልን ፍትሃዊ ስርዓት፣ሰፈነ የተባለው ሰላማዊና ልማታዊ አገዛዝ፣ጮቤ የተረገጠለት ዲሞክራሲ ቢከፍቱት ተልባ ስለሆነብን ነው።

በርካቶች በእንበለ ፍርድ በወያኔ ተከሰው በወያኔ ተመስክሮባቸው በወያኔ ዳኛ በወያኔ አቃቤ ህግ በወያኔ የግፍ ሰንሰለት አሳራቸውን የበሉ በዚያውም ያሸለቡ ደብዛቸው የጠፋ ለዛሬ ቤቱ ይቁጠራቸው ለማለት ተገደናል። ላሁኑ ግን በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ሰሞኑን የተጠበቀ ግና አስደንጋጭ ስለሆነው በንጹሃን የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊዎች ላይ የተበየነው ብይን ለተበየነባቸው ጀግኖች ሳይሆን ሃዘናችንን የምንገልጸው በራሱ ላይ ስለፈረደው የፍትሕን ገመድ ገምዶ አንገቱ ላይ ስላጠለቀው የወያኔ ስርዓት ነው።
ከ፱፯ ዓመተ ምህረት ምርጫ ህዝባዊ እንቅስቃሴ በሗላ በሃይል ተጨፍልቆ ብልጭብልጭ ሲል የከረመው ህዝባዊና ኢትዮጵያዊ ወኔ ድንገት ሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ ከዓወሊያ ተቋም ገንፍሎ ምድሪቷን ያጥለቀለቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል ስንቃኘው እንደዜጋ አድናቆት ስንቸረው በመብት ትግሉ ሂወት ያስከፈላቸውን አሳሳ፣ገርባ፣ኮፈሌዎችን፣እንዲሁም በፈሪ በትር የተቀጠቀጡትን አካል የጎደለባቸውን፣ ባኑዋር መስኪድ የጥቁር ሽብር ሰለባ የሆኑትን፣ለፍትሐዊ ትግሉ ቀንዲል ሆነው ዛሬ ለጠየቁት ጥያቄ ከ፯ እስከ ፪፪ አመት በሚል የቀልድ ቲያትር መጋረጃ የተዘጋባቸውን ወንድም እህቶች ታላቅ ወገናዊ አክብሮት እንሰጣለን።

ትግሉ የጋራ ነው ድሉም እንደዚሁ>>> እኛ በዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ የምንገኝ የጋራ ግብረሃይል በዚህ ሳምንት የሰማነው እምበለ ፍርድ የጠበቅነው ነውና ባንደነቅም ሆኖም ግን እንዲህ አይነት በ፺ ሚሊዮን ህዝብ ላይ የተቀለደ ቀልድን አንስቅለትም። እንዲያውም ትንታጎቹን ፈጣሪ ያበርታቸው፣ቤተሰቦቻቸውን አምላክ ያጽናናቸው ስንል ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ባጠቃላይ አብሽሩ የሚል መልዕክት እናስተላልፋለን።

ፍትሕ የተዘነበለችው ባጠቃላይ በኢትዮጵያውያኖች ላይ ነውና ለዚህ ሁሉ አብነቱ የፍትሕ ያለህ የሚል ጩኸታችን የሚቆመው ይህ ጸረ እስላም፣ጸረ ክርስቲያን ጸረ ሃገር የሆነው ሰይጣናዊ ስርዓት በጸሎትም በሁለገብ ትግልም በተባበረ ህዝባዊ እምቢታም ተመንግሎ ነጻነታችንን ስንጎናጸፍ ብቻ ነው ብለን እናምናለን።ለዚህም በኛ በኩል ሰላም ላጠጠበት ህዝባችን፣ፍትሕ ለጠፋበት ወገናችን፣በኩልነት ለምታኖረን ኢትዮጵያችን ባስገባን ቀዳዳ ሁሉ ገብተን የመጨረሻዋ እስትንፋሳችን እስክትቆም ድረስ አብረን ተባብረን ለመታገል ስለፍትሕ በሚጮህ ህዝባችን ስም ቃል እንገባለን።

እግዚዓብሄር ትልቅ ነው
አላህ ወኩበር

አዱሊስ ጋዜጣ –በPDF ያንብቡ

Health: መጾም ከመንፈሳዊው ጥቅም ውጭ ለጤና ያለው 7 በረከቶች

$
0
0

Fiftit

በሙለታ መንገሻ

ለተወሰነ ስዓት ከምግብና ከመጠጥ ዘሮች መራቅ ወይም መጾም ከሀይማኖታዊ ጥቅሙ በዘለለ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ጥናቶች ያመለክታሉ።

በሳምንት ውስጥ ቢያንስ ለሁለት ቀናት መጾም ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ይላል ጥናቱ።

መጾም የሚያስገኛቸውን የጤና ጠቀሜታዎች 

 1.የምግብ መፈጨት ስርዓታችን እንዲስተካከል ይረዳል

ጾመ የምግብ መፈጨት ስርዓታችን እረፍት እንዲኖረው በማደረግ የተረጋጋ እና ጤነኛ የምግብ ዝውውር እንዲኖር ያደርጋል። የምግብ መፈጨት ስርዓታችን መስተካከልም በሰውነታችን ውስጥ ያለን የስብ መጠን ለማቃጠል ይረዳናል።

  2.ትክክለኛው የረሃብ ስሜት እንድንለይ ያግዛል

መጾም የሰውነታችን ሆርሞኖች የተስተካከሉ እንዲሆኑ በማድረግ ትክክለኛውን የረሃብ ስሜት እንድንለይ ያደርገናል።

  3.የጠራ የሰውነት ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል

ጾም ሰውነታችንን ከምግብ መፍጨት ስራው ነጻ ስለሚያደረግ ሆርሞኖቻችን ወደ ሌሎች ስራዎች ይገባሉ።

ለአንድ ቀን ምግብ አለመመገብ ሰውነታችን በውስጡ ያሉትን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን እንዲያጸዳ እድል የሚሰጥ ሲሆን፥ በዚህ ጊዜም ኩላሊታችን፣ ጉበታችን፣ ቆዳችን እንዲሁም ሌሎች የሰውነታችን ክፍሎች ተግባራቸውን በአግባቡ እንዲከውኑ ያግዛል።

   4.የአዕምሯችን የማሰብ አቅም ይጨምራል

ጾም አእምሯችን ብሬይን ድራይቭድ ኔውሮትሮፊክ ፋክተር የሚባል ፕሮቲን እንዲያመርት ይረዳዋል። ይህም አእምሯችን ጤነኛ እንዲሆን ያደርጋል።

በተጨማሪም ፕሮቲኑ ከአእምሮ ጋር ተያያዥነት ያላቸው እንደ አልዛይመር እና ፓረኪሰንሰ በሽታዎችን ይከላከላል።

    5. የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል
አልፎ አልፎ መጾም የሰውነታችንን ክብደት ለመቀነስ እንደሚረዳ ጥናቶች ያመለክታሉ።

ለተወሰነ ስአት ከምግብ መራቅ ሰውነታችን ውስጥ ያለው የስብ መጠን እንዲቃጠል በማድረግ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል።

  6. ጥንካሬ እንዲኖረን ያደርጋል

መጾም የሰውነታችንን ጥንካሬ እንደሚቀንስ ነው በዙዎቻችን የምናስበው። ይሁን እንጂ ጥናቶች የሚያሳዩት የዚህን ተቃራኒ ነው።

ትንሽ መብላት የመኖር እድሜያችንን ለመጨመር ፋይዳው ትልቅ መሆኑም ነው የሚነገረው።
 7. በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል

መጾም ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲጨምር ይረዳል። ይህም በሽታ አምጪ ነገሮችን እንዲሁም ካንሰር አምጬ ሴሎች በውስጣችን እንዳያድጉ ያደርጋል።

ጥናቱ ላይ እንደተገለጸው እንስሳት በተፈጥሮ በሚያማቸው ጊዜ ምግብ ከመፈለግ ይልቅ ራሳቸውን ከምግብ በማራቅ እረፍት ይወስዳሉ።

ይህም ሰውነታቸው በቀላሉ በሽታን ለመከላከል ይረዳቸዋል።

በተቃራኒው በህመም ወቀት ምግብ ለማግኘት የምንሯሯጠው ብቸኞቹ ፍጡሮች የሰው ልጆች ነን ይላል ጥናቱ።

ምንጭ፦ ideadigezt.com

 

አራቱ የበረከት ስምዖን እንግዶች (ጥብቅ ምስጢር –ያንብቡ)

$
0
0

simon
ከሐና ሙሉጌታ

ጥር 6 ቀን 2002 ዓም በተለምዶ ጉበት ከለር እየተባለ የሚጠራውን ቀለም የተቀባች ኮድ ሁለት የታርጋ ቁጥሯ 63795 የሆነች ‹‹ ወያኔ›› ዲኤክስ የቤት አውቶሞቢል ሾፌሩን ጨምሮ አራት ሰዎችን ይዛ ወደ ኢህአዴግ ፅ/ቤት እየከነፈች ነው ሾፌሯ የመኪናዋ ባለቤት ነው ፡፡ሶስት እንግዶችን ባስቸኳይ አቶ በረከት ቢሮ እንዲያደርስ ነው የታዘዘው ሁለት ወጣቶችንና አንድ ሰውነቷ ሞላ ያለች ሴትይዟል ፤የካቴድራል ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን በር ሊደርሱ ጥቂት ሲቀር የግንብ አጥሩ ከቤተክርስቲያኑ ግምብ ጋር የተያያዘው ግዙፉ የኢህአዴግ ፅ/ቤት በር ላይ ቆሙ እጆቻቸውን ከመሳሪያቸው ምላጭ ላይ ከማይነቅሉት ላብ አደር የመከላከያ ሠራዊት መካከል አንዱ ጠጋ አለና ‹‹አቤት ›› አለ ከሾፌሩ አጠገብ የተቀመጠችው ሴት ወ/ሮ ‹‹ አቶ በረከት ጋር ቀጠሮ አለን ›› አለችው ወታደሩም ‹‹ሁላችሁም›› አለ ‹‹ አዎ ›› አለች ራመድ አለና ከአንድ ሌላ የእሱ ቢጤ ጋር ተነጋግሮ በሩ ስር ካለች አነስተኛ ቤት ወረቀት ይዞ ወጣና አነበበ ወደ መኪናዋም ተጠጋና የአራቱንም መታወቂያ ጠየቀ ተሰጠው በስማቸው ትክክል ከመታወቂያቸው ላይ ካመሳከረ በኋላ በባለ ዘንግ ክብ መስተዋት የመኪናዋ ሆድ እቃ ሳይቀር ተፈትሽው ወደ ውስጥ እንዲገቡ ተፈቀደላቸው ወታደሩ ይዟት መጥቶ የነበረው ወረቀት ‹‹ ወ/ሮ ሙሉ ከነመኪናቸው ይግቡ›› የሚል ከበረከት ስምዖን ቢሮ የተላከች የመግቢያ ፈቃድ ነበረች ፡፡

አራቱም ሰዎች ከበረከት ፀሐፊ ከዓለም ጠረቤዛ ደረሱ በሃይላንድ ውሃ ጉዳይ ከህላዌ ዮሴፍ ጋር እየተጨቃጨቀች ነበር ቀልደኛውና ሲፈጥረው ባለስልጣን መሆን ያልነበረበት ህላዌ አይቷቸው የማያውቀውን አንግዶች ሲያይ ደንገጥ አለና ወደ ኋላው ሁለት ርምጃ ተሳበ አንግዶቹ አለምን እየጨበጡ መግባት ይችሉ እንደሆነ ጠየቁ በወቅቱ የስምዖን ልጅ በረከት ከአዲሱ ለገሰ ጋር ውይይት ላይ ስለነበር ‹‹ ቁጭ በሉ ከሰዓታችሁ 20 ደቂቃ ቀድማችኋል አለቻቸው›› ተቀመጡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ አዲሱ እየሳቀ ከበረከት ቢሮ ሲወጣ እሱም አንግዶቹን አየና አልፏቸው ሊሄድ ብሎ መለስ አለና እጁን ለሰላምታ ዘረጋላቸው በአክብሮት ጨበጡት ወ/ሮዋን ሲጨብጥ ጠበቅ አድርጎ ያዛትና ‹‹የት ነው የማውቅሽ ሦስተኛ ጉባኤ ላይ ነው አራተኛ ነው … እዚህ ቦታ እዚያ ቦታ ››እያለ ሲያስጨንቃት ወ/ሮዋ ፈገግ በማለት ብቻ ዝም አለችው አዲሱ ግን ተሸውዷል በወቅት ወ/ሮ ሙሉን የትም ቦታ አያውቃትም ነበር፡፡

በረከት ከመቀመጫው ተነስቶ ተቀበላቸው ትንሽ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ሾፌሩ ወደ ውጪ ወጣና ፀሐፊዋ ዓለም ጋር የመጣለትን ወፍራም ቡና እየጠጣ ከፊት ለፊቱ ‹‹ልማታዊውን ባለሀብት አትንኩት›› የሚል ትዕዛዝ ይሁን ልመና ፁሁፍ ያለበትን የሼክ አላሙዲንን ፎቶ እያየ በሀሳብ ሄዷል ሶስቱ ሰዎች ረዘም ላለ ሰዓት ቆዩ ድንገት ያልታሰበ ነገር ተከሰተ የታላቁ ባለስልጣን የአቶ በረከት ቢሮ በኃይል ተበረገደና ወ/ሮዋ ስትቀር ሁለቱ ወጣቶች በቁጣ መንፈስ ወጡ በዚህ ጊዜ ጸሀፊዋ ዓለም በፍጥነት ተነስታ የበረከትን ቢሮ እንደመዝጋት ደህንቱን እንደማረጋገጥም ወደ ውስጥ አየት አድረጋ መልሳ ዘጋችው ሁለቱ በፍጥነት ደረጃውን እየወረዱ ነበር ከጥቂት ቆይታ በኋላም ወ/ሮዋ ወጣች በር ላይ ቆሟ ግን አንዲት ቃል ወረወረች ‹‹በረከት ግን ጊዜ ወስደህ አስብበት ይህ ለሁላችንም (ለማንም) አይበጅም አለችው ተጨማሪ ንግግር ልታደረግ ያሰበች ትመስል ነበር ግን ከአፍንጫው ከፍ ብሎ ባለው ቦታ ላይ ንቅሳት ያለው የበረከት ስምዖን የግል ጠባቂ ከዚህ መጣ ሳይባል ድንገት ከተፍ ብሎ ወ/ሮዋን እንደ ማባበልም እንደ መግፋትም አድርጎ ቢሮውን ከጀርባው እየዘጋ ደጋግፎ ሸኛት ፡፡

በወቅቱ በረከት ቢሮ የመጡት እነዛ ሰዎች እነማን ናቸው ? የተነጋገሩትስ ሰለምንድን ነው? ያልተግባቡትስ በምንድን ነው ? ይህን ጉዳይ ከእኔ ከፀሐፊዋ ይልቅ የአንድነት ፓርቲ የአመራር አባል የነበረው ኢ/ር ዘለቀ ረዲ አሳምሮ ያውቀዋል:: ፁሁፌን ከማጠቃለሌ በፊት እነዛ አራት ሰዎች አሁን የት ናቸው? ለሚለው ጥያቄ መልስ ልስጥ የመኪናዋ ባለቤትና ሾፌር የነበረው በአሁን ወቅት ከኢ/ር ዘለቀ ረዲ ጋር በገጠር መንገድ ሥራና በታላላቅ የውሃ ቁፋሮ ሥራ ተሰማርቶ ሚሊየነር ሆኗል:: አንደኛው ገጣሚ ሙሉ ሰሎሞን ራት ጋብዛው ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ከካዛንቺስ ወደ መገናኛ መኪናውን እያሽከረከረ ሲሄድ በተሳሳተ መንገድ ከሌላ አቅጣጫ በሚመጣ መኪና ይገጭና ይቆማል:: ድንጋጤው አልፎለት ከመኪናው ሊወርድ ሲል በገጪው መኪና ውስጥ ከነበሩ ሰዎች በተተኮስ ሽጉጥ ተገደለ:: ሶስተኛው ሰው በአሁን ወቅት ወሊሶ ወህኒ ቤት የማያውቀው ወንጀል ተለጥፎለት የሰባት ዓመት ፍርደኛ ሆኖ ተኝቷል:: አራተኛዋና ወ/ሮ ሙሉ ኃይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ በሚሊየን የሚቆጥር ገንዘብ አጭበርብራለች ተብላ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆነችና ነነዊት አፈወርቅ ከተባለች ልጇ ጋር 28 (ሃያ ስምንት) ዓመታት ተፈርዶባት ቃሊቲ ተጥላለች፡

እስኪ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ወ/ሮ ሙሉ ኃይለማርያም በምን እንደተሳረች የዘገቡትን አድምጡና ፍርድ ስጡ ምን ያህሉ ተዓማኒ ነበር ?እኚህ ስማቸውን መግለፅ አንፈልግም የተባሉና የተጠየቁትን ሚሊዮኖች እያወጡ የሚሰጡ ሰው ማናቸው? ሊንኩን ተጭነው ዜናውን ያድምጡ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live