Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ለሳሙኤል አወቀ መታሰቢያ ደም ተለገሰ

0
0

ነገረ ኢትዮጵያ

‹‹ስርዓቱ ገዳይ ቢሆንም እኛ በደማችን ነፍስ እናድናለን›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ

yonatሰኔ 8/2007 ዓ.ም ደብረማርቆስ ከተማ ላይ ለተገደለው ወጣት ሳሙኤል አወቀ መታሰቢያ ዛሬ ሀምሌ 26/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት ደም ተለገሰ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣ ደጋፊዎችና ሌሎችም ሳሙኤልን ለማስታወስ የተገኙ ግለሰቦች ደም ሰጥተዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በዛሬው ቀን ደም መስጠት ያስፈለገው ሳሙኤልን ለማስታወስ መሆኑን ገልጾ በቀጣይም ሳሙኤልን የሚዘክሩ ሌሎች ፕሮግራሞች እንደሚደረጉ ገልጾአል፡፡
አቶ ዮናታን አክሎም ‹‹እንደሚገድሉት እያወቀ ትግሌን አደራ ያለውን ወጣት ሳሙኤልን ደም በመለገስና በሌሎች ፕሮግራሞችም እንዘክረዋለን፡፡ የምንታገለው ስርዓት ገዳይ ቢሆንም እኛ ግን በደማችን ነፍስ እናድናለን›› ብሏል፡፡


መንግሥት በቤተ ክርስቲያኒቱ የሙስና ወንጀሎች ላይ ርምጃ እወስዳለሁ አለ

0
0

“አትስረቅ እያሉ በሌላቸው ገቢ የሚልዮን ብር መኪኖችን የሚነዱ አካላት፣ ለሀገር መልካም ዜጋ የምታወጣውን ተቋም በማማሰን በሕዝብ ላይ ተጽዕኖ እየፈጠሩ ናቸው”

“ሙሰኞቹ÷ በሙዳየ ምጽዋት፣ በስእለትና በስጦታ ምእመኑ የሚሰጠውን ገንዘብ ለራሳቸው ዓላማና ጥቅም እያዋሉ፤ የአድባራቱን መሬትና ሕንፃ ከዋጋ በታች እያከራዩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ጥቅሞችና መብቶች ከገቢያቸው በላይ ሕገ ወጥ ሀብት ያካብታሉ፤ በሦስትና በአራት ሺሕ ብር ደመወዝ ኤሮትራከር ይገዛሉ፤ ሕንፃ ይሠራሉ፡፡”

አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው:-

ከመልካም አስተዳደር ዕጦት እና ከተጠያቂነት ሥርዐት መጥፋት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ ሰፍኗል በተባለው ምዝበራ እና ሙስና  መንግሥት መዋቅሩን ጠብቆ ሕጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከትላንት በስቲያ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራሮች ጋር በተካሔደው ውይይት፣ መንግሥት ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በሰላም እና በልማት ጉዳዮች ላይ አብሮ እንደሚሠራ የጠቀሱት የሚኒስቴሩ ከፍተኛ ሓላፊዎች፣ ‹‹ የሕዝብ ሀብት ለህዝብ ጥቅም መዋል አለበት፤ በሕዝብ ገንዘብ እንዲቀለድ አንፈልግም፤ መንግሥት ሰላምንና የሕግን የበላይነት ከማረጋገጥ አኳያ ደረጃውን ጠብቆና የሙስና ወንጀል መፈጸሙን አጣርቶ ርምጃ ይወስዳል፤›› ብለዋል፡፡
‹‹ሙዳየ ምጽዋቱን ማን ነው የሚጠቀምበት፤ ሕዝብ ይጥላል፤ ጥቂት ሰዎች መኪና እና ቤት ይሠሩበታል፤›› በማለት የአለመግባባት መንሥኤዎችን የዘረዘሩት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሙሉጌታ ውለታው፣ የሚዘርፉት ሃይማኖት ሳይኖራቸው በሃይማኖት ስም የሚነግዱ ግለሰቦች እና አካላት እንደኾኑ ገልጸዋል፡፡ በሚፈጽሟቸው ወንጀል ነክ ጉዳዮችም ‹‹መንግሥት ለምን ጣልቃ ይገባል አይባልም፤ ከሀገረ ስብከቱ ጋር ኾኖ ይከታተላል፤ ወንጀለኛውን ይይዛል፤ ይቀጣል፤ ያጸዳል፤›› ብለዋል፡፡

Ethiopian_Orthodox_Church_Siege_Addis_Abeba_2
የግልጽነት እና የተጠያቂነት አሠራር ዘመኑ የሚጠይቀው እና መንግሥትም በአቋም ያስቀመጠው መኾኑን ያወሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ የሀገረ ስብከቱ ሰንበት ት/ቤቶች ሙስናና ብልሹ አሠራር እንዲወገድ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና ሃይማኖት እንዲጠበቅ የጀመሩትን እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡

‹‹እንቅስቃሴአችኹን ከሁከት በራቀ፣ ስልታዊ በኾነና በሰላማዊ መንገድ ቀጥሉ፤ መንግሥትም ድጋፍ ያደርግላችኋል፤›› ሲሉም አበረታተዋቸዋል፡፡
የሰንበት ት/ቤት አባላት ሰላም ፈላጊዎች እንደኾኑ የገለጹት የአንድነቱ አመራሮች በበኩላቸው፣ ለቤተ ክርስቲያን ሰላም መደፍረስ ዋነኛ ምንጩ የመልካም አስተዳደር ዕጦት እንደኾነ አስረድተዋል፡፡ እንደ አመራሮቹ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ እና ቅዱስ ፓትርያርኩ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ለማስወገድና ተቋማዊ ለውጥን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ውሳኔዎችን በየጊዜው ቢያሳልፉም ትግበራው አስተዳደራዊ መዋቅሩን ከላይ እስከ ታች በኔትወርኪንግ በተቆጣጠሩ ሙሰኞች ስለሚታገት ተፈጻሚ ለመኾን አልቻለም፡፡
ሙሰኞቹ÷ በሙዳየ ምጽዋት፣ በስእለትና በስጦታ ምእመኑ የሚሰጠውን ገንዘብ ለራሳቸው ዓላማና ጥቅም እያዋሉ፤ የአድባራቱን መሬትና ሕንፃ ከዋጋ በታች እያከራዩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ጥቅሞችና መብቶች ከገቢያቸው በላይ ሕገ ወጥ ሀብት ያካብታሉ፤ በሦስትና በአራት ሺሕ ብር ደመወዝ ኤሮትራከር ይገዛሉ፤ ሕንፃ ይሠራሉ፡፡
ይኹንና የተጠያቂነትና የግልጽነት አሠራር ባለመኖሩ ሲነቃባቸውና ተቃውሞ ሲበረታባቸው የበለጠ ወደሚዘርፉበት ቦታ በዕድገት እንደሚዘዋወሩ ጠቅሰው፣ ለዚኽም በጎጠኝነትና በጥቅም ትስስር ተሞልቷል ያሉት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፅ/ቤት ተጠያቂ ነው ብለዋል፡፡ “ሀገረ ስብከቱ ሌባን አሳልፎ አይሰጥም፤ በሹመት እና በዝውውር ጉቦ እየተከፈለ አብሮ ይበላል፤” በማለት የወቀሱት አመራሮቹ፣ “የሕዝብ ንብረት እየባከነ ስለኾነ መንግሥት ጣልቃ ይግባልን፤ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሀብታቸው ተሰፍሮ ተቆጥሮ ይታወቃል፤ አሠራሩ እዚኽም ይምጣልን፤” ሲሉ አመልክተዋል፡፡
ሙሰኞችን በመቃወማቸውና እውነቱን በመናገራቸው አሸባሪዎች ተብለው ለእስር እንደሚዳረጉ  አመራሮቹ ጠቁመው፣  የጸጥታ አካላት ርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት ኹኔታቸውን በሚገባ እንዲያጣሩና ፍትሐዊ አሠራር እንዲከተሉ ጠይቀዋል። ከአስተምህሮ ውጭ የኾኑ ግለሰቦችን የማጋለጥ ድርሻ የእነርሱ መኾኑን ገልጸው፣ በዚኽም በአክራሪነት መፈረጃቸው አግባብነት እንደሌለው ተናግረዋል፡፡
“አክራሪነትና ጽንፈኝነት በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ መኖሩ የሚያከራክር አይደለም፤” ያሉት ሚኒስትሩ ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም፣ ኾኖም ጥያቄው በሃይማኖት አጥባቂነት እስከተነሣ ድረስ ከአክራሪነት ስለሚያርቅና ከሙስና ስለሚጠብቅ የሚደገፍ መሆኑን ጠቁመው የፍረጃው አካሔድ ስሕተት መኾኑን አብራርተዋል። እንደ ሚኒስትሩ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ የማይፈቅደውን የአክራሪነት አስተሳሰብና ተግባር በሃይማኖት ሽፋን የሚያራምዱ ግለሰቦች ለተቋሙ ደኅንነት ሲባል መለየት አለባቸው፡፡
ሕዝብ ከተግባርም እንደሚማር ዶ/ር ሺፈራው ገልጸው፣ አትስረቅ እያሉ በሌላቸው ገቢ የሚልዮን ብር መኪኖችን የሚነዱ አካላት፣ ለሀገር መልካም ዜጋ የምታወጣውን ተቋም በማማሰን በሕዝብ ላይ ተጽዕኖ እየፈጠሩ ናቸው ብለዋል፡፡ ይህም ለሀገር የሚጎዳ በመኾኑ ድንጋይ በመወርወር ሳይኾን በምእምኑ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በቀጣይነት መጋለጥ እንደሚገባቸው መክረዋል፤ የሰንበት ት/ቤት አባላትም ከቤተ ክርስቲያኒቷ አልፎ ለሀገርና ለዓለም የሚበቁ ሊቃውንቷን በማስተባበር ለመልካም አስተዳደር መስፈን የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፤ መንግሥትም ‹‹መዋቅሩን ጠብቆ በወንጀሉ ላይ ይገባል፤ በሕግም ይጠይቃቸዋል፤ በሃይማኖቱ መሸፈን አይችሉ፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
በሚኒስቴሩ የስብሰባ አዳራሽ በተደረገው በዚኹ የግማሽ ቀን ምክክር ማጠናቀቂያ ላይ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የዋና ክፍል ሓላፊዎች የተገኙ ሲኾን ሚኒስትሩም “የወጣቶቹን ጥያቄ እንደ ቀላል አትዩት፤ በአስቸኳይ ፍቱ” ሲሏቸው ተደምጠዋል፡፡
ቀደም ሲል ሚኒስቴሩ፣ ከሀገረ ስብከቱ የአድባራት አለቆች፣ ካህናት እና ሰባክያነ ወንጌል ጋር ተመሳሳይ ምክክር ያደረገ ሲሆን፤ ይኸውም በቅርቡ በሃይማኖት ተቋማት በሰላም አብሮ መኖር እና ጤናማ ግንኙነቶች ማስፈንን በተመለከተ በጋራ እንደሚካሔድ ለሚጠበቀው ውይይት ቅድመ ዝግጅት እንደኾነ ተጠቁሟል፡፡

ከብር 6 ሚልዮን በላይ የተመዘበረበት የደ/ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ሒሳብ እንዲመረመር ተጠየቀ

0
0

st ourael church addis ababa

ከብር 6 ሚልዮን በላይ የተመዘበረበት የደ/ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ሒሳብ እንዲመረመር ተጠየቀ፤ ‹‹የበጀት ዓመቱን ሒሳብ ዘግቼ ለመመርመር ሰባት ቀን ሲቀረኝ ተዘዋውሬአለኹ››/ሒሳብ ሹሟ/

  • በኹለት ዓመት ውስጥ ለደብሩ ከብር 18 ሚልዮን በላይ ተቀማጭ አስመዝግቤአለኹ

  • የተነሣሁት ሕገ ወጥ ክፍያዎችን በመቃወሜ እና ምዝበራዎችን ለመሸፋፈን ሲባል ነው

  • ሕገ ወጥ አሠራር ቢረጋገጥም ውሳኔ አያገኝም፤ በአጥፊዎችም ላይ ርምጃ አይወሰድም

  • የሰነዶቹ ደኅንነት ታይቶ ቢሮዬ ይታሸግልኝ፤ መንግሥት ኦዲተሮችን መድቦ ያጣራልኝ

  • በቤተ ክርስቲያኒቱ ስለሚፈጸሙ አደገኛ አሠራሮች ቀርቤ በቃል እንዳስረዳ ይመቻችልኝ

*         *         *

  • የሀገር ሀብት በባለሥልጣናት በሚያስፈራሩት ዋ/ሥ/አስኪያጁ ሲዘረፍ ማየቱ አደጋ ያስከትላል

  • በመላዋ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርኩን እንዲያማክሩ በመንግሥት ትእዛዝ እንደተሾሙም ይናገራሉ

  • የሊ/ማዕ. የማነ ቢሮ የንግድ ማስታወቂያ አልተለጠፈበትም እንጂ የሰው ዘር መሸጫ መደብር ኾኗል

  • አላግባብ በማዘዋወር የሚንገላቷቸውን ሠራተኞች ‹‹ምንም አታመጡም›› በማለት ያንኳስሷቸዋል

  • ፓትርያርኩ ሙስና ይጥፋ ቢሉም ከሚዲያ አላለፈም፤ በሥራ እንጂ በሚዲያ አይጠፋም

/ሒሳብ ሹሟ ወ/ሮ መና የማነ ብርሃን ሥዩም/

(ኢትዮ-ምኅዳር፤ ቅጽ ፫ ቁጥር ፻፲፬፤ ቅዳሜ ሐምሌ ፲፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.)

 

ከብዙኃን ምእመናን የተሰበሰበ በብዙ ሚልዮን ብር የሚገመት የቤተ ክርስቲያን ሀብት እና ንብረት አላግባብ ተመዝብሮበታል የተባለው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ሒሳብ፣ በገለልተኛ እና ሕጋዊ አካል በይፋ እንዲመረመር ተጠየቀ፡፡

ሓላፊነትን አላግባብ በመጠቀም እና የሒሳብ አያያዝ እና የንብረት አጠባበቅ ድንጋጌዎችን በመጣስ በደብሩ አስተዳደር ተፈጽሟል በተባለው ምዝበራ እና ብክነት÷ ጥናት እና ጥራት ለጎደላቸው ሥራዎች ከፍተኛ ወጪዎች ይታዘዛሉ፤ ከተመደበው እና ከተወሰነው ውጭ በሕገ ወጥ ትእዛዝ የደብሩን ካፒታል የሚንዱ የተለያዩ ክፍያዎች ይፈጸማሉ፤ ለተከራይ በሚያደሉ እና የደብሩን ጥቅም በሚጎዱ የሕንፃ ኪራይ ውሎች ግለሰቦች መቶ ሺሕዎችንና ሚልዮን ብሮችን ያካብታሉ፤ በዐውደ ምሕረት በምንጣፍ አና በስእለት የተሰበሰበ ገንዘብ በአግባቡ ሳይቆጠር እና በሞዴል ገቢ ሳይኾን እየተወሰደ የገባበት አልታወቀም፡፡

ከኹለት ዓመታት በላይ የደብሩ ሒሳብ ሹም ኾነው ሲሠሩ የቆዩት ወ/ሮ መና የማነ ብርሃን ሥዩም÷ የተሰበሰበው ገንዘብ የት ገባ ብለው በመጠየቃቸው ያለምንም ማጣራት እና ቅድመ ኹኔታ፣ ንብረት እና መዛግብት አስረክበው ወደ ማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ተዛውረው እንዲሠሩ ባለፈው ሰኔ 22 ቀን ከሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ መታዘዛቸውን ይናገራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን አንዲት በመኾኗ በተዛወሩበት ደብር ለመሥራት ፈቃደኛ ቢኾኑም፣ የ2007 ዓ.ም የበጀት ዓመት ሊዘጋ ሰባት ቀናት ሲቀሩት ዝውውር የተደረገበትን አሠራር ግን እንደሚቃወሙት ገልጸዋል፡፡

የሒሳብ ሠራተኛ የተመረመረ ሰነድ ማስረከብ እንዳለበት ሒሳብ ሹሟ ጠቅሰው፣ ከመጋቢት/2005 ዓ.ም. ጀምሮ እስከተዘዋወሩበት ሰኔ 22/2007 ዓ.ም. ድረስ በደብሩ በቆዩባቸው 27 ወራት ከብር 54 ሚልዮን በላይ ገቢ እና ወጪ የሠሩባቸው፤ ከብር 18 ሚልዮን በላይ ተቀማጭ ያስመዘገቡባቸው የሒሳብ ሰነዶች እና መዛግብት በይፋ እንዲመረመሩ በአድራሻ÷ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ በሀገረ ስብከቱ ለፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ እና ለዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በጻፉትና በግልባጭ ደግሞ ለሰብአዊ መብቶች ተቋማት እና ለመንግሥት የደኅንነት አካላት ባደረሱት ሰፊ ጽሑፍ ጠይቀዋል፡፡

ወ/ሮ መና እንደሚሉት፣ ሰነዶቹ እና መዛግብቱ ያልተመረመሩ ብቻ አይደሉም፡፡ የቃለ ዐዋዲውን ድንጋጌ በመጣስ ተፈጽሟል የሚሉት የአስተዳደርና የፋይናንስ አሠራር ችግር እንዲጣራ ለፓትርያርኩ ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት ያለአግባብ የባከነውና የተመዘበረው የብዙኃን ምእመናን ገንዘብ በሀ/ስብከቱ በሚመደቡ ሠራተኞች ተጣርቶ ለሕግ እንዲቀርብ በቋሚ ሲኖዶስ መመሪያ የተሰጠበት ከፍተኛ ክሥ ያለባቸው ሰነዶች እና መዛግብትም ናቸው፡፡ ይህንንም ዋና ሥራ አስኪያጁ ከመሾማቸውም በፊት እንደሚያውቁት ያወሱት ሒሳብ ሹሟ፣ ሳይመረመሩ ከብር 54 ሚልዮን በላይ ገቢና ወጪ የሠራኹባቸውን ሰነዶች እና መዛግብት እንደ ቀላል ወረቀት አስረክበው ይውጡ ማለት ‹‹ከአንድ ተቋም ሓላፊ የሚጠበቅ አይመስለኝም፤ አጥፊዎቹ ወገኖቼ ናቸውና ተደብስብሶ እንዲቀርላቸው በማሰብ ነው፤›› ይላሉ፡፡

በቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት የሒሳብ ብክነቱን ለማጣራት፣ የሀገረ ስብከቱ የቁጥጥር ዋና ክፍል ሓላፊ ባሉበት ልኡክበመስከረም ወር 2007 ዓ.ም. ምርመራ ቢካሔድም ውጤቱ የት እንደደረሰ እንደማይታወቅ ሒሳብ ሹሟ ይገልጻሉ፡፡ ሓላፊው እንኳንስ በደብዳቤ ለምርመራ ተልከው ገንዘብ ጠፋ፤ ንብረት ባከነ ሲባል አጣርተው ለውሳኔ ማድረስ እንደሚጠበቅባቸው ያስገነዘቡት ሒሳብ ሹሟ፣ ‹‹ቁጥጥር ሳይኾን ቁጥርጥር ነው የያዙት›› ሲሉ ይወቅሷቸዋል፡፡

ውሳኔን በውሳኔ በመሻር ከደብሩ የሕንፃ ገቢ ላይ ከብር ስድስት ሚልዮን በላይ ወደ ግለሰቦች ኪስ መግባቱ፤ በውል ላይ ውል በመዋዋል ከአንድ የሕንፃ ኪራይ ብቻ ብር 487,869.32 መመዝበሩ ለቋሚ ሲኖዶሱ ካቀረቧቸው አቤቱታዎች እንደሚገኙበት ሒሳብ ሹሟ ይዘረዝራሉ፡፡ ይህንንም የሕንፃ አጣሪ በሚል ተሠይሞ በደብሩ ጽ/ቤት ለተገኘ ሌላ ኮሚቴ ከመዝገብ ቤት ፋይል እያስቀረቡ በጋራ በማየት መተማመን ላይ ቢደርሱም ‹‹እስከ አኹን ውጤቱ የት እንደደረሰ አይታወቅም›› ይላሉ፡፡

ሒሳብ ሹሟ በስፋት ከዘረዘሯቸውና በየጊዜው በሚካሔዱ ማጣራቶች ቢረጋገጡም ውጤት ላይ አልተደረሰባቸውም ካሏቸው ሕገ ወጥ አሠራሮች መካከል፡- የቀድሞው አስተዳዳሪ ባልተሾሙበት ዘመን ወደ ኋላ እየተመላለሱ አግባብነት የሌለው ወጭ አድርገዋል፤ በአንድ ወር ከአበልና ከነዳጅ ውጭ እስከ ብር 8,000 በሠንጠረዥ እየፈረሙ ወስደዋል፤ ለአንድ የሰበካ ጉባኤ አባል በወር እስከ ብር 30,000 ወጪ ተደርጓል፤ የበዓል መዋያ ድጎማ ተከፍሏል፤ በሰበካ ጉባኤው የሰንበት ት/ቤቱ ተወካይ ከቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ ውጭ ቅጥረኛ ተደርገዋል፡፡

ጥራት ለሌለው የሕንፃ ጠርዝ መሠረት ሥራ፣ ጄኔሬተር ለማዘዋወር፣ ለመኪና እድሳት፣ ለካህናት ጊዜያዊ ቤት ሥራ ጥናት የጎደላቸው ወጭዎች ተደርገዋል፤ በሰኔ 2006 ለኹለት የሰበካ ጉባኤ አባላት ብር 250,000 በአስቸኳይ ወጭ ኾኖ ያለደረሰኝ በሞዴል 6 እንዲከፈል ሕገ ወጥ ትእዛዝ በማዘዝ፤ በነሐሴ 2006 ለደመወዝ ከተወሰነው በላይ በልዩነት ከብር 236,000 በላይ ወጭ በማድረግ የደብሩ ካፒታል ተንዷል፤ የደብሩ ጠበቃ በፍርድ ቤት የተከሰሱ ተከራዮች ውዝፍ ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ለማድረግ ሲዳረስ ክሡን በይቅርታ በማንሣት በምትኩ የደብሩ ገቢ ለግል ጥቅም ውሏል፤ የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡

ወ/ሮ መና እንደሚገልጹት፣ የተጣሩት ሕገ ወጥ አሠራሮች ውሳኔ ሳያገኙ በመቅረታቸው እና ርምጃ ባለመወሰዱ ‹‹ያለፉት አጥፊዎች ምን ተደረጉ?›› በማለት በወቅቱ የደብሩ እና የሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ የወቅቱ የደብሩ አስተዳዳሪ የተለቀቀ ሱቅ በጨረታ ማከራየት ሲገባቸው ሽያጭ አካሒደዋል፤ ቤተሰቦቻቸውን አስቀጥረዋል፡፡ በሚያዝያ 22 እና ግንቦት 22 የቅዱስ ዑራኤል ክብረ በዓል በዐውደ ምሕረት አስተዳዳሪው በተቀመጡበት ምንጣፍ እና በስእለት ከምእመናን የተሰበሰበ ገንዘብ ሳይቆጠርና በደረሰኝ(በሞዴል 30) ገቢ ሳይደረግ በሻንጣዎች ተሞልቶ ተወስዷል፤ የት እንደገባም አይታወቅም፡፡

የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ቆጠራው በባንክ የመቁጠሪያ ማሽን እንዲከናወን የወቅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በየስብስባው መመሪያ እንደሚሰጡ የጠቀሱት ሒሳብ ሹሟ፣ በዐውደ ምሕረት በምንጣፍ እና በጥላ ስለተሰበሰበው ገንዘብ ቢጠየቅም ሀገረ ስብከቱ እንኳ እንዲያጣራ አለመፈለጉን ይገልጻሉ፡፡ ሒሳብ ሹሟ ለምን በማለት ይጠይቁና ምላሹን ራሳቸው ሲሰጡ ‹‹ፈቃጁ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በመኾናቸውና አያገባችኹም ስላሉ››ብለዋል፡፡

እንደ ወ/ሮ መና፣ በማጣራት የተረጋገጡ ጥፋቶች ተገቢው ርምጃ የማይወሰድባቸው፣ የደብሩ የአስተዳደር ሓላፊዎች ለበላይ አካል ያለትእዛዝ በሚያቀርቧቸው ማባበያዎች ስለሚሸፋፈኑ ነው፡፡ የደብሩ ሒሳብ ክፍል ሳያውቀው፣ ገንዘብ ከባንክ ሳይወጣ በዋና ተቆጣጣሪው አማካይነት ከዕለት ገንዘብ ተቀባዮች በብድር በተወሰደ ብር 430,000 ለፓትርያርኩ ቢሮ በስጦታ የተበረከተው ሶፋ፣ ሒሳብ ሹሟ በጽሑፉ ካሰፈሯቸው ኹለት ማባበያዎች የመጀመሪያው ሲኾን የቅዱስ ዑራኤል ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በማይመለከተው እና ባልታዘዘበት በቀድሞው አለቃ የሥራ ዘመን የተፈጸመ ነው፡፡

‹‹ለአባቶች ራት ግብዣ›› በሚል በሰበካ ጉባኤው የተወሰነውን ብር ስድሳ ሺሕ ወጪ ከማወራረድ ጋር በተያያዘ ከወቅቱ የደብሩ አለቃ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ወ/ሮ መና በጽሑፋቸው አስፍረዋል፡፡ እንደ እርሳቸው፣ መስከረም 8 ቀን 2007 ዓ.ም. በፓትርያርኩ ቢሮ ለተደረገው የመስተንግዶ ወጭ የሚያስፈልገው ብር 38,611.66 ሲኾን አስተዳዳሪው፣ ‹‹ለምግብ ማስገቢያ የኮቴ የከፈልኩትን አብረሽ አወራርጂ፤ ገንዘቡ ተወስኖና ተፈቅዶ ከባንክ ወጪ ኾኗል›› በማለት እንዳዘዟቸው ጠቅሰዋል፡፡

ሒሳብ ሹሟ አክለውም ‹‹ደረሰኝ የሌለው የኮቴ ወጪ አላወራርድም ብዬ ስላልተግባባን ሕጋዊው ሰነድ ሳይወራረድ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ለዘጠኝ ወራት ከቆየ በኋላ ተወራርዷል፤›› ካሉ በኋላ ‹‹የኮቴ ክፍያውም በቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ተፈጻሚ ይኾናል› ብለዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቷ በዚኽ መልክ ያለደረሰኝ ወይም ያለሞዴል 6 እየተመዘበረች እንደምትገኝ ያስታወቁት ወ/ሮ መና፣ ‹‹ሕገ ወጥ ኾኖ አላወራርድም ያልኩት የፓትርያርኩን መመሪያ ወደ ተግባር የለወጥኩ መስሎኝ የነበረ ቢኾንም በእንደራሴ ነን ባዮች የሚፈጸምብኝን ደባ አላሰብኩትም ነበር፤›› በማለት በደብሩ የፋይናንስ አሠራር ላይ ያቀረቧቸው አቤቱታዎች በዝውውር ሽፋን ተድበስብሰው እንዳይቀሩ ተማፅነዋል – ‹‹ምርመራው በቤተ ክህነቱ ሳይኾን መንግሥት በሚመድባቸው ኦዲተሮች ከመሠረቱ ከመጋቢት 2005 እስከ ሰኔ 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ እንዲደረግልኝ እፈልጋለኹ፤ ቢሮዬም ተሰብሮ ሰነድ እንዳይወጣ ሕጋዊ የመንግሥት አካል ባለበት እስከ አኹን ያለው ደኅንነት ታይቶ እስኪመረመር ድረስ እንዲታሸግልኝ፤ ለማሳያነት ካቀረብኋቸው ጉዳዮች ባሻገርም በቤተ ክርስቲያኒቱ ስለሚፈጸሙ አደገኛ አሠራሮች በአካል ቀርቤ በቃል ለማስረዳት እንድችል ይደረግልኝ ዘንድ እጠይቃለኹ፡፡››

በወ/ሮ መና የማነ ብርሃን ‹‹እንደራሴ ነን ባዮች›› የተባሉት፣ በቤተ ክህነቱንም ኾነ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥራ ከሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር ፓትርያርኩን በወሳኝነት ያማክራሉ የተባሉ ሦስት የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችን (መልአከ መንክራት ኃይሌ ኣብርሃ፣ መልአከ ብርሃናት ዘካርያስ ሓዲስ እና መልአከ ገነት ተስፋ ፍሥሓ) እንደኾነ በጽሑፋቸው ተመልክቷል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ሹመታቸው ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ቢኾንም ‹‹በምስጢር ለመላው ኢትዮጵያ ነው››እንዳሏቸው ወ/ሮ መና ጠቁመው፤ ዋና ሥራ አስኪያጁ እና እንደራሴ ነን ባዮቹ በሚሏቸው ብቻ እንዲሠሩ ለፓትርያርኩ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጥብቅ መመሪያ እንደተሰጣቸው በሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡

ሀገረ ስብከቱ ‹‹በዘመናዊ የሙስና አደረጃጀት›› እየተመራ እንዳለ ገልጸው፣ ከዝውውር አሠራር ጋር በተያያዘ በአንድ አካባቢ ተወላጅ ሠራተኞች ላይ እየደረሰ ባለው የአስተዳደር እና የሰብአዊ መብት ጥሰት የዋና ሥራ አስኪያጁ ቢሮ ‹‹የሰው ዘር መሸጫ መደብር ኾኗል›› ይላሉ፡፡ የፓትርያርኩ የፀረ – ሙስና ዐዋጅ ከሚዲያ ፍጆታነት እንዳላለፈ ተችተው፣ ሙስና በሥራ እንጂ በሚዲያ እንደማይጠፋ የሚገልጹት ሒሳብ ሹሟ፣ ችግሩ አስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጠው ወደፊት ቤተ ክርስቲያኒቷን ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍላት አሳስበዋል፡፡

ወ/ሮ መና የማነ ብርሃን ተዛውረው በተመደቡበት የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሒሳብ ሹም የነበሩት ሠራተኛ፣ በሰነድ ማጭበርበር በተፈጸመ ከፍተኛ የእምነት ማጉደል ወንጀል ተከሠው በሰኔ ወር መጨረሻ የተላለፈባቸውን የአንድ ዓመት ከስምንት ወራት የእስር ቅጣት በመፈጸም ላይ እንዳሉ ተገልጧል፡፡

ኢህአዴግን ለመጣል መጀመሪያ እኛ መውደቅ አለብን

0
0

(ኤርሚያስ አለማየሁ)

ኢህአዴግ በትረ ስልጣኑን ከተረከበበት 1983 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ህዝባዊ ጥያቄዎች ተፈጥረው ሳይመለሱ ጥያቄዎቹ በጥያቄ ምልክት ውስጥ ተከበው በወረቀት ላይ እንደሠፈሩ ቀሩ፡፡ እጅግ ስፍር ቁጥር የሌላቸው መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ያስቀመጡ ጥናታዊ ፅሁፎች በየምሁራኑ ተፅፈው በየትምህርት ተቋሙ ተነበቡ በየጋዜጣው እና በየመፅሔቱ ላይ ሠፈሩ በርካቶች አነበቧቸው አንባቢው ከንፈሩን መጠጠ ግና ለውጥ ሊመጣ አልቻለም፡፡ በርካታ የሠብዓዊ መብት ታጋዮች ህብረተሠቡን ሠብስበው በንግግራቸው በርካታ ህዝብን አስጨበጨቡ፤ ጭብጨባው ያልቃል የሠብዓዊ መብት ታጋዮቹ ግን ዛሬም ላይ ያወራሉ ሌላ አዳዲስ አጨብጫቢዎች ተፈጥረው ስለንግግር አጨበጨቡ፡፡ እዚህች ሐገር ላይ ከጭብጨባ በቀር ምንም አይነት ተስፋ ሠጪ ነገር ሊታይ አልቻለም፡፡
eprdf

ኢህአዴግን በጋራ ካልታገልነው ከስልጣኑ አይወርድም በሚል እሳቤ በርካታ በነጠላ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የሐገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች ከነጠላነት ወደጋቢነት ተቀየሩ ነገር ግን ነጠላ የሆነ ለውጥ ለሐገራችን ህዝብ ሊያስመዘግቡ አልቻሉም ይልቁንስ ጋቢያቸውን አውልቀው በነጠላ መጓዝ ጀመሩ፡፡

ኢህአዴግ በሠለማዊ መንገድ ከስልጣን እንደማይለቅ እሙን ስለሆነ ያሉ የትጥቅ ትግልን ለመጀመር ፎክረው ነፍጥ አነሱ ግና እላያቸው ላይ አሸባሪ የሚል ተቀፅላ ከማግኘት ውጪ ለሐገራችን ፖለቲካ ኢምንት የሆነ ለውጥ ሲያመዘግቡ ለማየት አልታደልንም፡፡ እነርሱም ጫካ ነን ይላሉ ኢህአዴግም ምንሊክ ቤተመንግስት ነኝ እንዳለ አመታት እየመጡ ሔዱ፡፡
በተለያዩ የአለማችን ክፍል በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሠላማዊ ሠልፍ በአሜሪካ እና በአውሮፓ መንግስታት ፅ/ቤቶች ፊት ለፊት አደረጉ በሠልፋቸውም ኃያላን ሐገራቱ በተለይም ዩ.ኤስ አሜሪካ ለኢትዮጵያው መንግስት የምታደርገውን ድጋፍ ታቆም ዘንድ ጠየቁ ከተቻለም ተፅእኖ እና ማዕቀብ መጣል እንዳለባት ተማፀኑ፡፡ በርካታ ሠልፎች ተደረጉ የውጭ መንግስታት ተወካዮች ሠልፈኞቹን ተስፋ ሠጥተው በተኑ ግና ምን ተፈጠረ? ምንም ጭራሽ ኦባማ ኢትዮጵያ ሄዶ አምባገነኖቹን የልብ ልብ ሰጥቷቸው ተመለሰ ኢህአዴግን ከውጭ ሆኖ ከመታገል ይልቅ የፓርቲው አባላት ከህዝብ ጎን ይቆሙ ዘንድ ስራ መሰራት እንዳለበት በማመን የፓርቲውን አባላት ለማሳመን ስራ ተጀመረ የተወሰኑት የኢህአዴግ አባላት ከድተው ወጡ ግና ኢህአዴግ አሁንም በስልጣን ላይ ነው፡፡ ስለነፃነት፣ ስለሐገር ፍቅር እና ስለኢትዮጵያዊነት በብዕራቸው የሠበኩ ጋዜጠኖች እና ጦማሪያን እነሲሳይ አጌና፣ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ፋሲል የኔዓለም፣ ሠርካለም ፋሲል፣ ውብሸት ታዬ፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ ዘላለም ክብረት፣ ደረጄ ሀብተወልድ እና የመሳሰሉ ስለዚህች ሐገር ሲሉ ታሠሩ ገሚሶቹ ተፈትተው ለስደት ተዳረጉ ገሚሶቹ በእስር ላይ ይገኛሉ ግና ህልማቸው አሁንም አልተፈታም ብእራቸው ቤቱን ሊመታ አልቻለም፡፡

በተለያዩ አጋጣሚዎች ከህፃኑ ነብዩ አለማየሁ ጀምሮ እስከ አዛውንቱ ፕ/ር አስራት ወልደየስ ድረስ በተነሡ ግጭቶች እና ህዝባዊ ጥያቄዎች ምክንያትነት ህይወታቸው ዓለፈ አልቅሰን ቀበርናቸው እነርሱም ላይመለሱ ሔዱ እኛም ሐዘን ታቅፈን ከመቀመጥ ውጪ ኢህአዴግ ወርዶ ለማየት አልታደልንም፡፡ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት የኢትዮጵያውያን ሙከራ ኢህአዴግን ለመጣል ተብለው የተደረጉ ቢሆኑም ውጤት ሲያመጡ ለማየት አልቻልንም ይህንን ያህል ከተለፋ ስለምን ኢህአዴግ ከስልጣኑ ሊወርድ አልቻለም ኢህአዴግ ባይወርድ እንኳን ለማየት የምንጓጓላት ኢትዮጵያ ልትፈጠር አልቻለችም ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት በአንድ የጋዜጣ ፅሁፍ ከባድ ቢሆንም እንደዚህ ፀሐፊ እምነት ትግሉ ሁሉ ፍሬ አልባ የሆነው መሰረቱን የለቀቀ ትግል ስለነበረ ነው፡፡ በኔ እምነት ኢህአዴግን ከስልጣን ላይ አውርደን የተሻለች ዴሞክራሲያዊ፣ የጎሳዎች እኩልነት እንዲሁም ፍትሐዊ የሀብት ከፍፍል ያላትን ኢትዮጵያን መፍጠር የምንችለው ቀጣይ በተዘረዘሩት ነጥቦች ዙሪያ መስራት ስንችል ይመስለኛል፡፡

1. የህዝብ ልብ ውስጥ ለመግባት መስራት

በአንድ ወቅት ለስራ ጉዳይ ወደሠሜኑ የሀገራችን ክፍል ባቀናሁበት ወቅት ያገኘኋቸው ወጣቶችን ስለተለያዩ የሀገራችን የጋራ ጉዳዮች የማዋራት እድሉን አግኝቼ ነበር፡፡ እነዚህ ወጣቶች ትምህርት ቀመስ ባይሆኑም በየመፅሔቱ እና ጋዜጣው ባይፅፉም በየማህበራዊ ድሕረ ገፁ ባይጦምሩም በሚኖሩበት አካባቢ በሚኖረው ህዝባቸው እና ወገናቸው ላይ የሚደርሱት ግፎች መነሻቸው የት እንደሆነ ግን ያውቁታል ስለእነርሱ መብት የሚታገል ስለመኖሩ ግን እርግጠኞች አይደሉም ማንስ ያሳውቃቸው? የትኛው ፓርቲስ ቀርቦ አይዟችሁ እኔ ስለእናንተ መብት የምታገል ነኝ አለ?

መርሳት የሌለብን ሐቅ እነዚህ ወጣቶች የብዙሐኑ ኢትዮጵያውያን ነፀብራቅ ናቸው አዎ እነዚህ ወጣቶች 80 ከመቶ ናቸው፡፡ እነዚህ 80 ከመቶ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ለመግባት አዲስ አበባ አልያም ዋሺንግተን ላይ ሆኖ መንቀሳቀስ ፋይዳ ቢስ ነው እዛው ገበሬው መሐል ሰተት ብሎ መግባት ያስፈልጋል፡፡ ገበሬውን በየአካባቢው አግኝቶ ችግሩ ምን እንደሆነ ማወያየት፣ ተስፋ እንዳለው መንገር ከተቻለም በስራ ማገዝ ስልጠናዎችን መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ያኔ እንዲህ ያደረገ የፖለቲካ መሪ እስር ቤት ቢገባ አንድም ቀን እስር ቤት ውስጥ እንደማያድር እርግጠኛ ነኝ፡፡ አልያማ ዋሺንግተን ተቀምጦ በፓልቶክ ቅስቀሳ ማድረግ ለአንድ ማንበብ እና መፃፍ ለማይችል ኢትዮጵያዊ ምኑ ነው?

2. የኢህአዴግን ጭራ እየተከተሉ ከመቃወም መውጣት

በሐገራችን የተቃውሞ ፖለቲካ እንደልማድ ከተያዙት አብይት ጉዳዮች መካከል አንዱ ይህ የኢህአዴግን ጭራ እየተከተሉ የመቃወም አባዜ ነው፡፡ ዘወትር ገዢው ፓርቲ አውቆም ይሁን በስህተት የሚፈፅማቸውን እኩይ ተግባራት እየተከታተሉ የተቃውሞ መግለጫ ከማውጣት ልንወጣ ይገባል፡፡ የኢ/ር ሳሙኤል ጉዳይ ሲከሠት የተቃውሞ መግለጫ፤ በደሌ ቢራ የቴዲ አፍሮን ኮንሠርት ሠረዘ ሲባል መግለጫ፤ ኃይለመድህን አበራ ጥገኝነት ሲጠይቅ መግለጫ የፓርቲዎቹ ስራ ከእነደዚህ አይነት ትርኪ ምርኪ መግለጫዎች በላይ ሊዘል ይገባል፡፡ ግለሠቦች በተሳሳተ የትምህርት ማስረጃ የሚንቀሳቀሱባት ሐገር እያሉ ያዙኝ ልቀቁኝ ከማለት ወደህዝብ ወርዶ ህዝብን ማማከር የተሻለ ነው አሁን ላይ ህዝብን ካላዳመጡ መቼ ሊያዳምጡ ነው፡፡

3. ቅድሚያ ለሚሠጠው ቅድሚያ መስጠት

ሌላው ለሐገራችን ፖለቲካ ትንሳኤ አለመምጣት እንደምክንያት ከሚጠቀሱት መካከል የአንዳንዶች በማያፀድቀውም ሆነ በማያስኮንነው የሚያርደርጉት መረጋገም እና መተቻቸት ነው፡፡ በተለይም ኢህአዴግን በመጣል ሊሻሻሉ የሚችሉ ጉዳዮችን ኢህአዴግን ከመጣል አስቀድሞ እንደመከራከሪያነት ከማቅረብ ልንወጣ ይገባል፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ሠንደቅ ዓላማ አደረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ መሆኑ እሙን ነው ነገር ግን እርስ በእረስ ሠንደቅ አላማው ላይ ያለው አርማ ትክክል ነው ትክክል አይደለም የሚል ኢህአዴግን ሊጥል የማይችል ክርክር በማንሳት መፋጨት ትርጉም አልባ ነው፡፡ የጎሳ ጥያቄ፣ የቋንቋ ጉዳይ እና የመሳሰሉት ልዩነት ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮች መፈታት ያለባቸው ከኢህአዴግ ህልፈት በኋላ እንጂ በዘመነ ኢህአዴግ እንፍታቸው ብንል ከመራራቅ በቀር ሊያቀራርቡ የሚችሉ ጉዳዮች አይደሉም ስለሆነም የመጀመሪያ እቅዳችን በኢትዮጵያ ህዝባዊ ተቀባይነት ያለው መንግስት ስለመመስረት መሆን አለበት፡፡

በእነደዚህ አይነት መልኩ መንቀሳቀስ ካልቻልን ግለሠቦችን ስናሳስር ስናስፈታ፣ ህዝብን ሠብስበን ንግግር ስናደርግ፣ ለፓርቲዎች የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ስንለምን እና ስንሠጥ ከመኖር ውጪ አማራጭ የለንም፡፡ ኢህአዴግን ለመጣል መጀመሪያ እኛ መውደቅ አለብን::

እኛ የዚህ ዘመን ልጆች ነን

በረከት ስምዖን ሞቶ አንዳርጋቸውን ሆኖ ተነሳ ( ሄኖክ የሺጥላ )

0
0

simon
አማሪካዊው ጠሐፊ ዊልያም ጀምስ ስለ ( pragmatism, radical empiricism, and pluralism) ብዙ የፍልስፍና አዲስ መሰረተ ሃሳቦችና እና የ ሃሳብ ፍሰቶችን ያመጣ ( ያመነጨ ) ፣ የጻፈ ፣ ያሳወቀ እና የሞገተ ፣ ግሩም የፍልስፍና ሊቅ ነው ። ይህ ሰው > በሚለው ሃሳቡ እና የሃሳብ ትርጉም ፣ ውስጠ ሚስጥራዊ ጥናት ይታወቃል ። ለነገሩ አብዛኛው ሰው ፣ የዚህንን አባባል ባለቤትነት ለዊልያም ጀምስ ቢሰጠውም ፣ ራሱ ጀምስ ይህንን አባባል ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማው ፣ እ ኤ አ በ 1904 ዳን ሀራልድ ሆፍዲንግ [ Dane Harald Høffding (1843-1941)] በጀምስ ተጋብዞ ፣ በጀምስ ፍልስፍናዊ አስተሳሰቦች ላይ ፣ በይበልጥም (pragmatism, radical empiricism, and pluralism) ላይ ፣ ለጀምስ ተማሪዎች ፣ በሃርፋርድ ዩኒቨርስቲ ተገኝቶ ፣ ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ፣ ከ ዴንሹ የፍልስፋና ሊቅ Kierkegaard ( ኪኢርክጋርድ ) እንደ ጥቅስ ወስዶ የተናገረው ነበር ። እኔም ዛሬ በዚህ ጥልቅ እና ትልቅ አባባል ዙሪያ ፣ ስለ ማህበረሰባዊ የአስተሳሰብ ክሸፍቶች ፣ ስለ ማንነት ብክነቶች ፣ ህዝቦች የሚመሩበት ንዑስ ስርዓት ሲዝግ ፣ ህገ-መንግስት በራሱ በመንግስት-ሲናድ ፣ እና ያ የምንግስት አካል ፣ በማናለብኝነት እና ምን አገባኝ ጉልበት ታጅሎ ፣ ሕዝብ አስገድዶ ለመምራት ሲያስብ ፣ ማህበረሰቡ በእውነት እና እውነት ባልሆነ ነገር መሃከል ያለውን ልዩነት ፍጹም መለየት እስከማይችልበት ደረጃ እንደሚደርስ ፣ ይህም በውሸት ላይ የተመሰረተ የለት-ተለት ኑሮ ፣ በሀገር ህልውና ላይ ስላለው ተግዳሮቶች እና የተግዳሮቶቹ መስተጋብር የሚያትት ይሆናል ። በመጨረሻም አንዳንድ የምሳሌ ዘውጎችን አነሳለሁ ።

በመጀመሪያ ጀምስ > የሚለውን አባባል ደጋግሞ የተጠቀመው በ > ትንተናው ላይ ሲሆን ፣ ይህም በ 1905 ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ ይመስለኛል ፣ በዚህም አተኩሮ የሚዘግበው > > ስላለው ዝምድና የሚያትት ሲሆን ፣ የሰው ልጅ በቀደመው ታሪኩ ያሳለፈው ማንነቱ ፣ ወደፊት ሊሄድ ሲል እየመዘዘ የሚያወጣው የማንነት መለኪያ መስፈርቱ እንደሚሆን ይናገራል ። ይህም ማለት ፣ ሰውየው ገበሬ ከነበረ እና ፣ በቀጣይ ህይወቱ ነጋዴ ቢሆን ፣ የነጋዴነቱ ስኬት ወይም ውድቀት የሚለካው ፣ ገበሬ በነበረ ጊዜ በነበረው ጥንካሬ ወይም ስንፍና ነው ወይም ይሆናል ፣ እንደማለት ነው ። ይህም > የሚለውን አባባል በደንብ እንደሚዘክረው ያብራራል ። ከዚህ አገላለጽ ተነስተን ደሞ ፣ ስለተለያዩ ጉዳዮች ሰፋ ያለ ማብራሪያ መስጠት እንችላለን ማለት ነው ። ለምሳሌ ህውሃት ( ወያኔ ) ፣ ወደፊት እየኖረ ወደ-ሗላው ብቻ የሚረዳ ስርዓት ለመሆኑ ከበቂ በላይ መረጃ አለን ። ለምሳሌ ፣ ዛሬም ደርግን ስለመጣሉ ያወራልሃል ፣ ዛሬም እኔ ጀግና ነኝ ፣ አንተ ግን አይደለህም ይልሃል ፣ ዛሬም ነገሮችን ሁሉ በጉልበት ለመወሰን ብቻ እንደሚችል የነገሮች ሁሉ አዛዥ እና ነዛዥ እሱ ብቻ እንደሆነ ይነግርሃል ፣ ዛሬም ተራራው ፣ ደኑ ፣ ሳሩ ፣ ቅጠሉ ለሱ እንደሚንቀጠቀጡ ፣ ለሱ እንደሚረግዱ ፣ እሱ ብቻ በደሙ የታደጋቸው ተራርሮች፣ ያለሱ ቢዘሩ እንደማያበቅሉ ፣ ቢታረሱ እንደማያፈሩ ፣ ቢጎለጎሉ እንደማይለሙ ይነግርሃል ። ከምንም በላይ ፣ ታሪካዊ ውሸታምነቱን አጠናክሮ መቀጠሉ ፣ የሃውዜን ማንነቱን ትናንት በነ- አኬል-ዳማ ሲደግመው ፣ ዛሬ ደሞ- > የቅጥፈት ዜና አጠናክሮት ሊያደልበው እንደተዘጋጀ ስንረዳ ፣ ጀምስ እንዳለው > የሚለውን አባባል ያለ አንዳች ግድፈት እየፈጸመ ያለ ስርዓት ስለመሆኑ እንረዳለን ።
እውነቶችን ወይም ኩነቶችን ከራሳችን ልምድ ብቻ ተነስተን ለማርቀቅ ስንተጋ ፣ የዛሬ ማንነታችን ሙሉ በሙሉ > ባልነው ሲገደብ ፣ ከኛ ወዲያም ወይም ከኛ ወዲህ ያሉትን እውነቶች ስንጥል ፣ ስለ-ራሳችንም የምናወራው ወይም እኛ ነን ብለን የምንናገረው ፣ የገሃዱ ዓለም እኛ ምን እንደሆንን በአደባባይ የሚመሰክረውን ግድፈታችንን ሳይሆንን ፣ ቀባብተን ያቀረብነውን ሰባራ ሸክላ መሳይ ስብእናችንን ሲሆን ፣ የጥንካሪያችን መለኪያ ፣ የለውጣችን ማሳያ አስረጅ ሲነጥፈው ፣ ያለፈ የጦርነት ታሪካችንን ከፊት እያስቀደምን > ፣ በሚል ማስፈራሪያ ለመኖር ስንተጋ ፣ እኛ እውነትም ወደፊት እየኖርን ፣ ወደ- ሗላ የምንረዳ ስለመሆናችን ምንም ነጋሪ እና ነዛዥ አያስፈልገውም ።

ኃያሉ ጎልያድን የገነደሰው ዳዊት ፣ በሐጸ- ዝሙት ተነድፎ ፣ ኃጢያት ነግሶበት ፣ የኦርዮንን ሚስት ሲቀማ ፣ ኦርዮንንም በደቂቀ አሞናውያን ሰይፍ ሲያስመታ ፣ የድሀውን ጠቦት ሲቀማ ፣ እሱንም ደግሞ ሲያስገድለው ፣ ዳዊትም ወደፊት እየኖረ ፣ ወደ- ሗላ ይረዳ ስለነበረ ነው ። ዛሬም አንዳርጋቸው በቅያፋ ፊት ሲቆም ፣ ሕግ በበደነበት ፣ እውነት በተረሳበት ፣ ታሪክ በተጨማለቀበት ፣ ይሉኝታ በፈገመበት ፣ ወደ- ፊት እየኖረ ወደ ሗላው በሚረዳ ስርዓት ፣ ሕግና ደንብ ውስጥ ፍትህ እና ፍርድ እንዲያገኝ ሲደረግ ፣ ከልብ ወለድ ፈጠራ ፣ ከሐሰት ክስ ፣ ከተምታታ መረጃ ፍርጃ ነጻ ይሆናል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው ። በይበልጥም ሐሰት ከተንዠረገገብት ፣ ቅጥፈት ኩልል ብሎ ከሚፈስበት ፣ ክህደት እንደ ሰብል በማዳበሪያ ከሚያድግበት ፣ ልቃሚነት ከሚወደስበት ፣ ተራነት ከሚወደስበት ፣ ልቅነት ከነገሰበት፣ ከህውሃት መንደር እንዲህ ያለው ዜና ሲሰማ ፣ ሰሚውንም ተሰሚውን ግራ የሚያጋባ አዲስ ነገር ይሆናል ብለን አናስብም ። የሁሉም ቅጥፈቶች በሽታ ወደፊት እየኖሩ ወደ ሗላ ከመረዳት የመነጨ ነውና ።

አልክሳንደር ዱማስ ( The Three Musketers ) በሚለው መጥሀፉ ላይ ፣ በሶስተኛው ክፍል ፣ ስለ አንድ እስረኛ ያወራል ። በምጽሐፉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ( The Prisoner ) በሚለው ክፍል ስር ፣ ፊቱን በብረት ከተሸፈነው እስረኛ ጋ ፣ አራሚስ የተባለው ገጸ ባህርይ ፣ ከ እስረኛው ጋ የሚያደርገውን ቃለ ምልልስ በጣም በጥቂቱ ይህንን ይመስላል

አራሚስ “Well, then, you ought, as a penitent, to tell me the truth.”
እስረኛው “My whole desire is to tell it you.”
አራሚስ “Every prisoner has committed some crime for which he has been imprisoned. What crime, then, have you committed?”
እስረኛው”You asked me the same question the first time you saw me,” returned the prisoner.
አራሚስ “And then, as now you evaded giving me an answer.”
እስረኛው”And what reason have you for thinking that I shall now reply to you?”
አራሚስ”Because this time I am your confessor.”
እስረኛው”Then if you wish me to tell what crime I have committed, explain to me in what a crime consists. For as my conscience does not accuse me, I aver that I am not a criminal.”
በነገራችን ላይ ዱማስ ይህህንን ታሪክ የጻፈው ከእውነተኛ ታሪክ ላይ ተነስቶ ነው ፣ የዱማስ የዚህን ታሪክ መጻፍ ተከትሎ ፣ ታታላላቅ ጸሐፍት ( እንደ ቮልቴር ያሉ ይህ የብረት ጭንብል ፊቱ ላይ አርጎ ( ተሸፍኖ ) ታስሮ ስለነበረው ሰው ሌሎች ታሪኮችን ጽፈዋል ። በአብዛኛው፣ የፈረንሳዩ ንጉስ የሊውስ 16ኛ ልጅ ነው ተብሎም እንደታመነ ካነበብኩት መረዳት ችያለሁ ።

ወደ ተነሳሁበት የእስረኛ እና የአናዛዥ የሃሳብ ምልልስ ስንገባ ፣ እጅግ አበክሬ፣ (በአሕጽኖት እንደሚሉት ማለት ነው ) መመልከት የምፈልገው አራሚስ ፣ > > የሚለው ላይ ነው ። አንዳርጋቸው ጽጌ ታፍኖ ከተወሰደበት ጊዜ ጀምሮ ፣ በያንዳንዷ ደቂቃ ፣ አናዛዦቹ > እያሉ ሲያሰቃዩት እንደከረሙ መገመት ሳይሆን እንዳደረጉት እናውቃለን ። አንተ ወንጀለኛ ነህ ሲሉት ፣ > ሲላቸው ፣ > ሲባል ፣ >ሲል ፣ ዛሬ የአንዳርጋቸው ሕይወት ፣ እንደ ሞንቴ ክርስቶው እንደራሲ ፣ እንደ ቄስ ፋሪያ ፣ እንደ ቄስ ቡሶኒ ፣ የልብ-ወለድ ምልዓት ተላብሶ ፣ በህውሃት ደሴቶች ላይ የተቀበረ የምኞት እንቆዎችን ፣ የሐሰት ክብሮችን ፣ የጭብርብር እድገቶችን፣ ጽፎ እንዲያመሰግን ፣ ሀሌ-ህውሃት እንዲል ፣ ዳጎስ ባለ መጥሃፋው የተረቺነት እና የተሸናፊነት ስነ ልቦና በሕዝቡ ልብ ውስጥ ለማስረጽ ፣ ስሙን ለማጥቆር የሚደረገው ነገር ሁሉ ፣ ህውሃት ዛሬም ወደፊት እያየ ወደ -ሗላው የሚረዳ ጨቋኝ አካል ከመሆን የዘለለ አንድም የሚያመጣው ወይም የሚነቀንቀው ስብእና እንደሌለን ይረዳ ዘንድ ፣ አራሚስ የሚጠይቀው እስረኛው መልስ ፣ የኛ አንዳርጋቸው ቃል እንደሆነም ለምናውቀው እኛ ፣ የአንዳርጋቸው መጽሐፍ ጻፈ ቅጥፈት ለ- ህውሀቶች ሌላ አኬልዳማዊ ድግስ ከመሆን አልፎ ፣ ሌላ ጅሃዳዊ ሐረካት ከመሆን አልፎ ፣ የተለየ ጭብጨባ እና መረዳት ያተርፍላቸዋል ብለን አናምንም ፣ አንጠብቅም ።

ዛሬ በረከት ስምዖን የሞተው ወይም የታመመው ፣ በአንዳርጋቸው ስም መጽሐፍ ሆኖ ሊነሳ ፣ የደደቢት ደሴቶች ግሁሣን ፣ የሞንቴክርሥቶ እንደራሲ ደራሲ ሆኖ ብቅ ልል ታስቦ እንደሆነም ሰምተናል ። በይበልጥም ፣ ለአድ ዓመት ከዘለቀው የአንዳርጋቸው ስቃይ ( ቶርቸር ) ውስጥ ምንም ያላገኙት ህውሀቶች ፣ ከሱ ጋ በርሃ ሳሉ ፣ ስለሱ በቅርብ ያውቁ ከነበሩ ሰዎች ( አንዱን እኔም በቅርብ አውቀዋለሁ ፣ በደቡብ አፍሪካ ይኖር የነበረ ልጅ አሁን ወያኔ ቪላ ቤት ሰጥቶ ፣ አቀማጥሎ የያዛቸው ሆድ አደሮችን ታሪክ በማሰናሰን ) ፣ ታሪኩ እውነት እንዲመስል ፣ በይበልጥም አንዳርጋቸው ሲያዝ ከ ላፕ-ቶፑ ውስጥ ያገኙትን መረጃዎች እንደ አንድ ትልቅ የመጽሐፉ ግብአት በመጠቀም ፣ ሕዝቡን ለማሳመን ፣ ሃያልነታቸውን ለማስያት ፣ የግንቦት ሰባት ደጋፊና አባሎችን ስም ዝርዝር በመጽሐፉ ውስጥ በማስቀመጥ ፣ ሰዎችን ይበልጥ ለማስፈራራት ፣ ከተቻለም ይቅርታ እንዲጠይቁ ለማግባባት የተጻፈ መጽሐፍ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለንም ።

ያም ሆኖ ፣ አሁንም ወያኔ ከመውደቅ አይድንም ። በወሬ የማንፈታ ፣ ስለምንም አይናችን የማይጨፈን ቆራጦች መሆናችንን ያውቁት ዘንድ ፣ ትግሉን በመቀላቀል ፣ እና በሙሉ ልብ በመደገፍ እንብታችንን እናሳያለን ። ደሞም እናሸንፋቸዋለን ። ምክንያቱም እኛ እነሱን ለማሸነፍ የተፈጠርን ልጆች ስለሆንን ። ወደፊት እየኖረ ወደ -ሗላ እያሰበ የሚኖር ስርዓት መጨረሻው ሽንፈት እና ውርደት ስለሆነ !

በአማራና በትግራይ ክልል መካከል ያለው መሬትን መነሻ ያደረገ ግጭት የሰውን ሕይወት እየቀጠፈ ነው ተባለ

0
0

(ሁመራ ከተማ)

(ሁመራ ከተማ)


የደህሚት ድምጽ እንደዘገበው በአማራና በትግራይ ክልል መካከል ያለው መሬትን መነሻ ያደረገ ግጭት እስካሁን መፍትሄ ባለማግኘቱ የሰው ህይወት እየጠፋ መሆኑን ተገለፀ።

የአማራና የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ከዚህ በፊት በቆየ የመሬት አለመግባባት በተነሳ ግጭት ምክንያት ብዙ ወገኖቻችን እየሞቱ የሁለቱ ክልል የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ጉዳዩን በትኩረት አይተው እልባት ከመስጠት ይልቅ በቸልተኝነት እያዩት መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በዚህ ምክንያትም በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ ግጨው በተባለ ቦታ ሃምሌ 13 ቀን 2007 ዓ/ም ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች አንድ ዜጋ ተገድሎ መገኘቱን ለማወቅ ተችሏል።

ይህ ተገድሎ የተገኘው ወገን የትግራይ ክልል ተወላጅ ሲሆን ሁኔታውን ተከታትሎ የሚያጣራ አካል እንደሌለ የገለፀው መረጃው ይህም ገዢው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ባለስልጣናት ሁለትም ብሄሮች በግጭት እንዲኖሩና አንድነት እንዳይፈጥሩ ለማድረግና የስልጣን እድሜያቸውን ለማራዘም የሚጠቀሙበት መላ መሆኑን ታውቋል።

«ከመጥረቢያ ብረት የተሰራ ጦር ወደ አቡጀዲ ቢወረውሩት ወደ ጉቶ ይሄዳል»

0
0

tplf-rotten-apple-245x300
ይገረም አለሙ

ይህ በርዕስነት የተጠቀምኩበት አባባል በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፋል ሸካ ዞን በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የሚነገር ነው፡፡አባባሉ በአካባቢው ቋንቋ ሲነገር ለጆሮ ይጥማል፣ ቀልብ ይስባል፣ እንዲህ ወደ አማርኛ ተመልሶም ቢሆን መልእክቱ ግልጽና በቀላሉ ለመረዳት የማያስቸግር ነው።

ተፈጥሮው ሆኖበት እንጂ የሚቀለው አቡጀዲው ነበር፣ ጉቶው ግን ከባድ ነው፣ እንደውም የጦሩን ጫፍ ሊያጥፈው ሲብስም ሊሰብረው ይችላል፡ነገር ግን ጦሩ የተሰራው ከመጥረቢያ ብረት ሆነና መጥረቢያው ደግሞ ተፈጥሮውም ለጉቶ መፍለጥ፣ የኖረውም ከጉቶ ጋር ሲታገል በመሆኑ አቡጀዲውን አያውቀውምና ወደ ለመደው ግን ጠንካራና አስቸገሪ ወደ ሆነው ጉቶ መሄዱን ነው የሚመርጠው፡፡

የህውኃት መስራቾች ለሥልጣን ሲሉ ጫካ መግባታቸውን ብሶት የወለደን በሚል ማስመሰያ ጋርደው ዱር ገደሉን መኖሪያቸው አድርገው፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻቸውን ገድለው፣ በዛው መጠን የትግል ጓዶቻቸውን ካጠገባቸው አጥተው ለሥልጣን የበቁ በመሆኑ ሰላማዊ ትግል ብሎ ነገር አያውቁም፤ በልዩነት ተከባብሮ መኖርንም ሆነ የዓላማም ሆነ የአደረጃጅት ልዩነት ካላቸው ጋር ውይይት ብሎ ነገር አያስቡትም፤ከፖለቲካ አመለካከት ልዩነት በላይ የአንድ ሀገር ልጅነት ሚዛን የሚደፋ መሆኑ አይገባቸውም፡፡ ከመጥረቢያ ብረት የተሰራው ጦር ወደ ቀላሉ አቡጀዲ ሲወረወር ወደ ጠንካራው ጉቶ እንደሚሄደው ሁሉ ወያኔዎችም የህይወት ጥፋት፣ የሀገር ሀብት ውድመት፣ የትውልድ ተወቃሽነት፣ የህግና የታሪክ ተጠያቂነት በማያስከትለው የሰላማዊ ትግል መንገድ የሰለጠነ ፖለቲካ እናራምድ ሲባሉ እነርሱ የሚታያቸው ትናንት ለቤተ መንግሥት ዛሬ ለከበርቴነት ያበቃቸውና 24 ዓመት በሥልጣን የቆዩበት የሀይሉ/የጡንቻው መንገድ ነው፡፡

ተፈጥሮአቸው ይህ በመሆኑም ነው ስለ ሰላም የሚያዜሙትን፣ ሰላማዊ ትግል መርሀችን ብቻ ሳይሆን እምነታችን ነው ብለው ሁሉን ችለው የሚንፈራገጡትን፤ህገ መንግሥቱን መሰረት አድርገውና በቃል የሚነገረውን ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ተማምነው ብዕራቸውን ለዴሞክራሲ ምስረታ ዘብ ያቆሙትን ወዘተ ጸረ ሰላም፣ አሸባሪ፤ወዘተ በማለት መወንጀልና ማሰርን ስራቸው ያደርጉት፡፡

ዝናር ታጥቀው፣ ጠብ-መንጅ አንግበው ከደደቢት በረሀ እስከ ምኒልክ ቤተ መንግሥት የደረሱት ነባር ታጋዮች መተካካት እያሉ እንዳንድ ጠብ-መንጃ ያልጨበጡ አዳዲሶችን ቢያሳዩንም የሚተኩት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ዶክትሪን ታንጸውና በህውኃት ጸበል ተጠምቀው በመሆኑ ራሳቸው ይለወጣሉ አንጂ ወያኔን አይለውጡትም፡፡ ስለሆነም የመጥረቢያው ብረት ወደ ጦር በመቀየሩ ተፈጥሮውን ሊተው እንዳልቻለው ሁሉ ከጫካ ሳይሆን ከከተማ የተገኙ አንዳንድ ሰዎች በወያኔ ውስጥ መታየት ወያኔ የተወለደበትንና ያደገበትን ማንነቱን ሊለውጠው አልቻልም፡፡

ተፈጥሮ በተመክሮም በተሞክሮም የሚለወጥ ባለመሆኑ ስለ ምርጫ እያወሩ ደም ገብረን ያገኘነውን ሥልጣን በስመ ዴሞክራሲ በምርጫ መንጠቅ ያምራችኋል ወይ ይላሉ፡፡ ስለ ዴሞክራሲ ሲነገር ስለአንባገነንት ያስባሉ፡፡ስለ መድብለ ፓርቲ እየደሰኮሩ ስለ አውራ ፓርቲ ይዘምራሉ፡፡ ስለ ሰላም እያወሩ ወንድ ከሆናችሁ እንደኛ ታግላችሁ ኑ በማለት ይሳለቃሉ፡፡ ይህም በመሆኑ ነው አምስት ሀገራዊ ምርጫዎች ተካሂደው ለውጥ ሊታይ ቀርቶ አንዳቸውም ምርጫዎች በተወዳዳሪ ፓርቲዎች ስምምነት፤ በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት በአለም አቀፉ ማህበረሰብም ተቀባይነት ሊያገኙ ያልቻሉት፡፡

ስብሰባ፣ ግምገማ፣ ወርክ ሾፕ፣ ሥልጠና፣ የአቅም ግንባታ ወዘተ የወያኔ የእለት ተእለት ሥራ ቢሆንም ተፈጥሮ በስር ነቀል ለውጥ እንጂ በእነዚህ የሚሻሻል ባለመሆኑ ነው ወያኔ የደደቢቱና ወያኔ የቤተ መንግሥቱ ምንም ልዩነት የሌላቸው ሆነው የሰላሙን መንገድ ሲያሳዩዋቸው የጦርነቱ መንገድ የሚታያቸው፡፡

ወደ አቡጀዲ ሲወረውሩት ወደ ጉቶ የሚምዘገዘገው ጦር ተምሳሌት የሚመለከተው ወያኔን ብቻ አይደለም፡፡ በተቃውሞው ጎራ ተሰልፈው፤ ተባበርን ባሉ ማግስት መለያታቸውን የሚያውጁ፣ ፍቅር ሲሉዋቸው ጸብ የሚያነፈንፉ፤ ከመከባበር መናቆር የሚቀናቸው፤ በተግባሩ ሳይሆን በመፎከሩ ቀዳሚ የሌላቸው ወዘተ እነርሱም ተፈጥሮአቸው ሆኖ ነው ጥሩውን ሲሉዋቸው መጥፎውን መምረጣቸው፡፡

ደግሞ አንዳንዶች አሉ ተፈጥሮአቸውም ሆነ እድገታቸው መቃወም ብቻ ሆኖ ለድጋፍ ሲያስቡዋቸው ለትብብር ሲጠሩዋቸው ምክር ሲጠይቋቸው ምላሻቸው ተቃውሞ፣ ማጥላላት ማንኳሰስ የሆነ፡፡ ጸባያቸው ታውቆ ሲተዉ ደግሞ እኛ የለለንበት በማለት ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉ፡፡ እንዲህም ሆነና ለውጥ እንደናፈቀን፣ ዴሞክራሲ እንዳማረን ኖረን እኛ ወደማንወደው ለወያኔ ግን ተፈጥሮው ወደ ሆነው ጦርነት ማምራት ግድ ሆነ፡፡ ብእር ሊጨብጡ የሚገባቸው እጆች ጠመንጃ ለመያዝ ተገደዱ፡፡ ስንት የሰሩና ወደ ፊትም ብዙ ሊሰሩ የሚችሉ ሰዎች ያለ ተፈጥሮአቸው፤ ያለ ልምድና ፍላጎታቸው ዱር ቤቴ ለማለት ተገደዱ፡፡

ፍላጎት ዓላማችን ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ማንሳት ብቻ ሳይሆን እየተረገዘ የሚጨነግፈው ዴሞክራሲ ለውልደትና ለእድገት እንዲበቃና ደራሲ አያልነህ ሙላቱ በአንድ ተውኔቱ እንደገለጸው በጋሜ የቀረችው ኢትዮጵያ ሹርባ ተሰርታ ማየት ከሆነ በሁሉም ዘንድ መሰረታዊ የሆነ ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ እስካሁን የመጣንበት መንገድ ወደ ድል ጎዳና አላመራንም፡፡ በተፈጥሮም ይሁን በተሞክሮ ያዳበርነው አስተሳሰብ ለለውጥ አላበቃንም እናም ¾ አሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት አብርሀም ሊንከን የተናገሩት ተብሎ የሚጠቀሰው ይህ ዘመን የማያደበዝዘው አባባል ምክር የሚሆን ይመስለኛል፡፡

«አንድ ትውልድ ያልፍና ሌላ ትወልድ ይተካል፣ ዓለም/መሬት ግን ለዘለአለም ትኖራለች፡፡ ጸጥ ረጭ ያለው ያለፈው ግዜ ፍልሰፍናዎች (ዶግማስ) አውሎ ነፋሳዊ ለሆነው ለዛሬው ችግር ለመፍትሄነት አይመጥኑም፡፡ ጊዜያችን ችግር ያዘለ ስለሆነ በአዲስ ሁኔታ ማሰብና በአዲስ ሁኔታም መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ራሳችንን ከሰቀልንበት ከፍታ ማውረድ ይገባል፡፡ ያን ግዜ አገራችንን ለማዳን እንችላለን፡፡ ታሪክን ልናመልጥ አንችልም፣ ልንሸሸው አይሆንልንም፣ ክፉም ሰራን ደግ እንዘከራለን፣ (እንታወሳለን) ግለሰባዊ መታወቅ ወይም አለመታወቅ አንዳችንንም ሆነ ሁላችንን አያተርፈንም፣ የምናልፍበት እሳታዊ ፈተና (ፍርድ) በክብር ወይንም በውርደት ማለፋችንን ይመሰክራል»

የናትናኤል ማስታወሻ –ጥቂት ስለ ማዕከላዊ

0
0

ይህንን ጽሁፍ ስጽፍ ዓላማዬ ማዕከላዊ ያሉ ሥራቸውን አክብረው የኢትዮጵያውያንን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የሚሰሩ ጥቂት ፖሊሶችን (ምናልባትም በአንድ እጅ ጣቶች ተቆጥረው የሚያልቁ መርማሪዎችን) ለማበረታታት አይደለም፡፡ይህን ዓላማ በሌላ ጽሁፍ እመለስበት ይሆናል፡፡ ለነገሩ ሥራቸውን አክብረው የሚሰሩ ባለሙያ ፖሊሶች የኔ ማበረታታትን የሚፈልጉ አይደሉም፡፡ያሉበት ደረጃ ላይ ለመድረስ በኃላፊነት ማሰብ የቻሉ ስለሆኑ፡፡
natnaiel Feleke
ስለዚህ የዚህ ጽሁፍ ዓላማ በተቋሙ ውስጥ ኢትዮጵያ የምትተዳደርባቸውን ሕጎች ለማክበር(የተላለፉትን ለይቶ ለማስቀመጥና በስህተት የተጠረጠሩትን ነጻ ለማውጣት) ሳይሆን የአገዛዙን ዕድሜ ለማርዘም የሚሰሩትን አብዛኞቹን ሙያቸውን የማያከብሩ ፖሊሶች ‹‹ምርመራ›› ሴራቸውን እንዴት እንደሚፈትሉ ለማሳየት፣ ቢያንስ ሌላ ስልት እስኪፈጥሩ ድረስ በሀገሪቷጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያውያን አንዴ በተቋሙ ውስጥ ከገቡ በኋላ ሊገጥማቸው የሚችለውን የተንኮል መረብ ለማስረዳት እና ቀድሞለማዘጋጀት ያሰበ ነው፡፡
እውነት ለመናገር እነዚህ የስርዓቱ ጠባቂ ሎሌዎች የህዝብን ደህንነት ለአደጋ የሚያጋልጥ ወንጀልን እና ወንጀለኞችን ለይተው አውቀው ፍትህ እንዲያገኙ አድርገው ጭራሹንም አያውቁም ማለት አልችልም፡፡ ስለዚህ አሁን የማብራራው ጉዳይ ለወንጀለኞችም መዘጋጃ ሊሆን እንደሚችል አምናለሁ፡፡ ነገር ግን ወንጀለኞች ከፍትህ እንዲያመልጡ ጠብታ ውሃ ማቀበል አልፈልግም፡፡አንድ ነጻ ሰው ባልሰራው ወንጀል ከሚቀጣ መቶ ወንጀለኞች ቢያመልጡ ይሻላል የሚለው የህግ መርህ የበለጠ አቋሜን ያስረዳል፡፡

ሁለት ማሳሰቢያዎች አሉኝ፤ አንደኛ፡-እኔ ተይዤ ማዕከላዊ እስክገባ ድረስ ልታሰር እንደምችልአስቀድሜ ባውቅም ሊጠብቀኝ የሚችለውን የ‹‹ምርመራ›› ሂደት (የሴራ መረብ የበለጠ ይገልጸዋል) አጽንዖት ሰጥቼ አላሰብኩበትም፡፡የምርመራው ሂደትን ተንተርሼ የማነሳቸውን ሀሳቦች የተረዳሁት በምርመራ ውስጥ ካለፍኩ በኋላ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ይህንን ጽሁፍየሚያነቡ ሰዎች እኔ በፍርሃት ያላደረኳቸውን ነገሮች እንዲያደርጉ (በምርመራ ሂደት) የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ሁለተኛ ይህንን ጽሁፍ በሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል እና ሀሳቡን ሕገ-መንግስታዊ ድንጋጌዎች በሚፈቅዱት መሰረት በነጻነት የሚገልጽ ሁሉ ጊዜ ሳይሰጥ ቢያነበው እመክራለሁ፡፡

ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሀሳብ የአቃቤ ህግ ምስክር ከተሰማ በኋላ በብይን የተለቀቁ ሙስሊምወንድሞች መጻፋቸውን አስታውሳለሁ፡፡ ያ ጽሁፍ የተሻለ የተደራጀ ነው ብየ ስለማስብ እንዲነበብ እጋብዛለሁ፡፡ በተጨማሪም ስርዓቱንየሚደግፉ ሰዎች ይህንን ጽሁፍ በማንበብ ወንጀለኞች ከሚጠቀሙበት ለተሻለ አላማ ያውሉታል ብዬ ስለማስብ ሁለቱም ባያነቡት ይሻላቸዋል፡፡

ወደ ዋናው ሀሳብ ልግባ፤ ከተያዝኩ በኋላ በነበሩ የመጀመሪዎቹ ቀናት ውስጥ የነበሩት‹‹ምርመራዎች›› እውነቱን እና የማውቀውን ብቻ በመናገር እራሴን ነጻ ማውጣት እንደምችል መተማመኛ መስጠትን ያለሙ ነበሩ፡፡ ለምሳሌሚያዝያ 18/2006 (በተያዝኩኝ በማግስቱ ቅዳሜ) የነበረውን ምርመራ ም/ሳጅን መኮንን በተረጋጋ ሁኔታ የምርመራው ሂደት በመከባበርእንደሚቀጥል፣ ልክ እኔ የዕለት ስራየን ለማከናወን ሙያ እንደሚጠይቀው ያክል የፖሊስ ምርመራም ተመሳሳይ እንደሆነ፣ በቁጥጥር ስርየዋልኩት ተጠርጥሬ ብቻ እንደሆነ እና በምርመራው ሂደት ወንጀል አለመፈጸሜ ከተረጋገጠ በነጻ ወደቤቴ እንደምሄድ ነበር ያስረዳኝ፡፡ይንቁናል የሚል ስሜት አስቀድሞ ስለሚያድርባቸው ተቋሙን እና እራሳቸውንም ከፍ የሚያደርግ ነገር በነዚህ የመጀመሪያ ‹‹የምርመራ››ቀናት ይናገራሉ፡፡

‹‹ይህ የወረዳ ጣቢያ አይደለም፡፡ የክልልም አይደለም፡፡ ይህ የፌደራል ወንጀል ምርመራነው፡፡ ሚኒስትር ደረጃ የደረሱ የመንግስት ባለስልጣናት ሳይቀር እዚህ ተመርምረዋል›› ነበር ያለኝ ም/ሳጅን መኮንን በአጽንኦት፡፡ከዚህ ገለጻ በኋላ ነበር ስለህይወት ታሪኬ በመጠየቅ ቃል የመስጠት ሂደቱን የጀመርኩት፡፡

ማስታወሻ- 1. ቃል ያለመስጠት መብት

ቃሌን ያለመስጠት መብት ስላለኝ ቃሌን አልሰጥም ለማለት መጀመሪያ መብቱ እንዳለ ማወቅይጠይቃል፡፡ በወቅቱ ይህ መብት እንዳለኝ ማወቄን እጠራጠራለሁ፡፡ አውቅ ከነበረም ግን በፍጹም ትዝ አላለኝም፡፡ ቃል አለመስጠትአንድ ለምርመራ ሂደቱ ተባባሪ አለመሆንን ማሳያ ነው፡፡ ለተቋሙ የጭቆና መሳሪያ ስለመሆኑ በቂ ማስረጃ እንዳለ አምነን ተጨማሪ ማረጋገጫዕድል (benefit of the doubt) መስጠት የማንፈልግ ከሆነ ይህ ትክክለኛው አማራጭ ይመስለኛል፡፡ ከግምት መግባት ያለበትቃል በመስጠቱ ሂደት ውስጥ ፖሊስ በእርግጠኝነት ስህተት መስራቱ አይቀርም፡፡ ይህም የማይቀረው ክስ ሲመጣ ተቋሙን ማጋለጥ እንደስልት የሚወሰድ ከሆነ እንደማስረጃ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በኛ ጉዳይ የቀረበብን ክስ የሽብር ቡድን በኅቡዕ አደራጅተዋል በሚልሲሆን ሁላችንም ቃል ስንሰጥ የተጠየቅነው እና ስናብራራ የነበረው ግን በይፋ ስንጽፍበት እና ዘመቻዎቻችንን ስናካሂድበት ስለነበረውዞን 9 ነው፡፡
አቃቤ ህግ በክሱ እያለ ያለው የከሰስኳችሁ በመጻፋችሁ እና መብትን የሚጠይቁ ዘመቻዎችንበማድረጋችሁ (በአጠቃላይ ከዞን-9 ጋር በተያያዘ) ሳይሆን ሌላ የህቡዕ ቡድን መስርታችሁ ለሽብር ዓላማ ስትንቀሳቀሱ ስለነበር ነው፡፡የሰጠነው ቃል እና ክሱን ለመደገፍ የቀረቡት ማስረጃዎች ግን ስለ ዞን-9 አውርተው አይጠግቡም፡፡ በመጀመሪያዎቹ ቀናት የሚነግረውን‹‹ተቋሙ ገለልተኛ ነው፣ ሰዎችን ወንጀለኛ ለማድረግ ሳይሆን እውነትን ፈልፍሎ አግኝቶ ነጻ ሰውን ወደቤቱ ይሸኛል›› የሚለውን ዕምነትበቀላሉ ማስረጽ ከቻሉ የሚቀጥሉት ጥርጣሬ ወደመዝራት ይመስለኛል፡፡ በቀላሉ ያሉትን የማያምኑ ከሆነ ግን የተጠርጣሪውን በራስ መተማመንለመሸርሸር ህገ-ወጥ ተግባራቸውን ይቀጥላሉ፡፡
‹‹ምርመራ›› በጀመርኩ በአራተኛው ቀን የተከሰተው ይሄው ነው፡፡ ሚያዝያ 21/2006ዓ.ም ምሽት ድረስ ‹‹በምርመራው›› ሂደት ውስጥ ስሳተፍ የነበረው በሙሉ የራስ መተማመን ነበር፡፡ ለምሳሌ ም/ሳጅን መኮንን፣ ም/ሳጅንእቴነሽ፣ እና ሳጅን ፈይሳ በነበሩበት ታስሬ ‹‹እየተመረመርኩ›› ያለሁት ሀሳቤን በነጻነት ለመግለጽ ባለመፍራት ነው፡፡ ያኔ ‹‹ፖሊስለህዝብ የሚሰራ ተቋም ነው የምትሉትንም አላምንም፡፡ በአሁኑ ሰዓት ፖሊስ እንደ ተቋም እየሰራ ያለው አገዛዙን ስልጣን ላይ ለማቆየትነው›› ብያቸዋለሁ፡፡
ከላይ በጠቀስኩት ቀን ማታ ግን ሌላ ሊከሰት እንደሚችል የማውቀው፣ ግን ከምር ያልተዘጋጀሁበትነገር ተከሰተ፡፡ ምሽት 1፡00 አካባቢ የተጀመረው ‹‹ምርመራ›› ቶሎ ኃይለ ቃል ወደመሰንዘር እና ዛቻ ተለወጠ፡፡ በወቅቱ ም/ሳጅንመኮንን፣ የመጀመሪያ ቀን ፍርድ ቤት የወሰደን እና በየመተላለፊያው ሳገኘው ጭምር ቤተሰብ እንዲያገኘን መብት አለን፣ ፍርድ ቤትአዝዞልን ሳለ ለምንድነው የማታገናኙን እያልኩ ስጠይቀው የቆየሁት ሳጅን ምንላርግልህ እና ማዕረጉን የማላስታውሰው ፀጋየ (በቅጽልስሙ ጥጋቡ) የሚባል መርማሪ ነበሩ፡፡ የ‹‹ምርመራ››ውም ዋነኛ አጀንዳ የዞን 9 ድብቅ ግብ እና የውስጥ የስራ ክፍፍል (መዋቅር)በተመለከተ ነበር፡፡ በሁለቱ ጉዳይ ላይ እውነተኛው የማውቀው መልስ ‹‹መዋቅር የለውም›› የሚለው ነበር፡፡ ዞን 9 ድብቅ ግብምመዋቅርም ኖሮት አያውቅም፡፡ ሳጅን ምንላርግልህ መልሴ አላጠገበውም፡፡ ‹‹እኔ እንደሱ እንዳልመስልህ (የእኔን ጉዳይ በዋነኛነትወደያዘው ም/ሳጅን መኮንን እየጠቆመ) አለቅህም! ሽባ ነው ማደርግህ! ልብስህን አስወልቄ ሳልለጠልጥህ እውነቱን ብትነግረኝ ይሻልሃል!››የሚሉ ዛቻዎች ደረደረ፡፡ እኔ ግን መዋቅሩን በተመለከተ ስራ ለማቅናት ሲባል ምክረ ሀሳብ ቀርቦ እንደተወያየንበት፣ ነገር ግን ሀሳቡውድቅ እንደተደረገ ከማስረዳት በቀር የምጨምረው የማውቀው እውነት አልነበረም፡፡ ም/ሳጅን መኮንን እና ፀጋየ (ጥጋቡ) በየተራ ክፍሉንለቀው ከወጡ በኋላ ሳጅን ምንላርግልህ ከወንበሩ በመነሳት ምቾት በሚነሳ ሁኔታ ከተቀመጥኩበት ፊት ተጠግቶኝ ቆሞ ጥያቄዎችን ይደረድርጀመር፡፡
ጥያቄ፡- ‹‹ለምንድነው እነ ርዕዮትን ብቻ የምትጠይቁት?››
መልስ፡- ‹‹ኢትዮጵያውያን ስለሆኑ እና የታሰሩት በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ነው ብለንስለምናምን፡፡››
ጥያቄ፡- ‹‹(በቁጣ) ባንክ የዘረፈውስ ኢትዮጵያዊ አይደለም? ለምንድነው ሌላውን ወንጀለኛየማትጠይቁት?››
በእውነት እዚህ ጋ ሳቄ መጥቶ ነበር፡፡ በርግጥ የታሰረን ሁሉ ከተቻለ መጠየቅ ለህሊናየሚያስደስት ስራ ነው፡፡ እግዜርም ይወደዋል፡፡ ግን ርዕዮትን ስጠይቅ እንዲሰማት የምፈልገው፣ ትግሏ ዋጋ እንዳላጣ እና እንዳልተረሳችነው፡፡ ይህም ትንሽም ቢሆን ብርታት ይጨምርላታል ከሚል ተስፋም ጭምር ነው፡፡ ተመሳሳይ ነገር የባንክ ዘራፊ እንዲሰማው በፍጹምአልፈልግም፡፡ ጥያቄው ቀጠለ፣
‹‹ዝዋይ ለምን ሄዳችሁ?››
‹‹እነ ውብሸትን ለመጠየቅ››
‹‹አትዋሽ! በቀለ ገርባን ለመጠየቅ ነበር?››
‹‹አዎ በቀለንም ለመጠየቅ ነበር፡፡››
‹‹በቀለ ምን እንደሚል ታውቃለህ? ለምን እንደታሰረ ታውቃለህ? ኦሮምኛ ትችላለህ?››
‹‹አልችልም››
‹‹በቀለ እኮ የሚለው ኦሮምኛ የማይችሉ ሰዎች በሙሉ ይታረዱ ነው፡፡››
ስለ በቀለ ገርባ የማውቀው ጥቂት ነገር ከሚለኝ ጋር ፍጹም የሚጣጣም ስላልነበር የፊቴንመለዋወጥ መቆጣጠር አልቻልኩም፡፡ ፊት ለፊቴ ተደንቅሮ የጥያቄ ዝናብ ሲያወርድ የነበረው ሳጅን ምንላርግልህ አሁን ማድረግ የሚፈልገውንለማድረግ በቂ ምክንያት አገኘ፡፡ የመጀመሪያዋን ጥፊ ሰነዘራት፡፡ መብቴን እየነካ እንደሆነ ስነግረው ‹‹ይህንን ነው አይደል ፈረንጆቹወስደው የሚያሰለጥኗችሁ?›› በማለት ስራውን ቀጠለ፡፡ ድብደባው እዚያ ቤት ከሚፈጽሙት ሰቆቃዎች (torture) አንጻር ትንሽ ቢሆንምአሸነፈኝ፡፡ አሁን የሚጸጽቱኝንም ቃላት ተናገረኝ፡፡ ከውጭ የነበሩት ሁለቱ መርማሪዎች ድብደባ ሲፈጸምብኝ በነበረበት ወቅት በመሐልመጥተው ገላጋይ ሆነው ነበር፡፡ ምንላርግልህ ግን ለያዥ ለገናዥ አስቸገረ፡፡

ማስታወሻ፡-2. መርማሪዎች አንድ አላማ ነው ያላቸው

ሁለትና ከዚያ በላይ ሆነው ሲመረምሩ የትኛውንም ማመን አያስፈልግም፡፡ በኋላ ላይ ከሌሎችተጠርጣሪዎች ጋር ሳወራ የተረዳሁት ይህ የተለመደ አሰራር መሆኑን ነው፡፡
ሌላ ተጠርጣሪ ሲመረመር ሳጅን ምንላርግልህ ገላጋይ ሌላኛው ደግሞ እምቡር እምቡር ይላል፡፡ከዚያም ፀጋየ (ጥጋቡ) እኔ ላይ ሲያደርግ እንደነበረው ገላጋይ የሚሆነው መርማሪ ‹‹እኔ ችግር ውስጥ እንድትገባ አልፈልግም፤ ለምንእውነቱን አትነግረንምና ራስህን አትጠብቅም? ደግሞ ዘጠኝ ሆናችሁ ለሰራችሁት ስራ አንተ ብቻህን ለምን ትጎዳለህ? ሌሎቹ እኮ እየተናገሩነው፤ አይደለም ዘጠኝ ሰው የሚያውቀው ነገር ይቅርና ለሌላ አንድ ሰው የነገርከው ነገር እኮ ሚስጥር መሆኑ ያበቃል›› የሚሉ ማግባቢያዎችበመደርደር ምስኪን ምስኪን ሊጫወት ይሞክራል፡፡

የዛን ምሽት ምርመራ ሲጠናቀቅ የሁለት ሰዓት ማሰቢያ ጊዜ ተሰጥቶኝ የዞን 9 ግብ ምንእንደሆነ እና የመዋቅራችንን እያንዳንዱን የስራ ዘርፍ እንዳስታውስ የቤት ስራ ተሰጥቶኝ ከሌሊቱ አምስት ሰዓት ተመልሼ እንደምጠራተነግሮኝ ነበር ወደ ማረፊያ ቤት ውስጥ የተመለስኩት፡፡

በተለምዶ ሳይቤሪያ የሚባለው ማረፊያ ቤት ባለአንድ ፎቅ ህንጻ ሲሆን የታችኛው ወለል በኮሪደርተከፍሎ በግራና በቀኝ አምስት አምስት ክፍሎች አሉት፡፡ ኮሪደሩ መሀል ላይ አንዱ የግድግዳ ሰዓት ተሰቅሏል፡፡ የመጀመሪያ ሰሞንልብ ስላልኩት ሰዓት የማውቀው ምርመራ ክፍል ካሉት ሰዓቶች በመነሳት በግምት ነበር፡፡ ከሳጅን ምንላርግልህ በተሰጠኝ የቤት ስራመሰረት ከምሽቱ አምስት ሰዓት ሲል ተመልሼ ወደምርመራ እጠራለሁ፡፡ ከምርመራ ከተመለስኩ ጀምሮ በአዕምሮዬ ሲመላለስ የነበረው ነገርተጨማሪ መልስ ልሰጣቸው እንደማልችል እና በዚህ ምክንያት ተመልሼ ከሄድኩ በኋላ የሚደርስብኝ ሰቆቃ ማብቂያ ምን እንደሚሆን ማሰብነበር፡፡ ቀኑን ሙሉ በምርመራ በማሳለፌ ድካም የነበረብኝ ቢሆንም እንቅልፍ ሊወስደኝ ግን አልቻለም፡፡ ራሴን አረጋግቼ በተሰጠኝሁለት ሰዓት እረፍት መውሰድ ብፈልግም ምንም ዓይነት ድምጽ በሰማሁ ቁጥር አምስት ሰዓት የሆነ እየመሰለኝ እባንን ነበር፡፡ እነምንላርግልህ ግን አልፈለጉኝም፡፡ አይነጋ የለም ሌሊቱም ነጋ፡፡ ጠርተው ቢደበድቡኝ ይሻል ይሆን እንደነበር እንጃ!

ማስታወሻ፡- 3. እራስን አረጋግቶ በቂ እረፍት መውሰድ

መርማሪዎቹ መቼም ቢሆን ምርመራ ጨርሰናል ደህና እደሩ ብለው አይሸኙም፡፡ ሁል ጊዜ‹‹በኋላ እንገናኛለን፤ አስብበት›› ብለው ነው የሚጨርሱት፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቀጠሮ መሰረት ምርመራው ይቀጥላል፡፡ አንዳንድ ጊዜደግሞ የውሃ ሽታ ይሆናሉ፡፡ በቀጠሮ መሰረት ብጠራም ባልጠራም ያለችውን ጊዜ በቂ እረፍት ለማድረግ መጠቀሚያ ማድረግ የሚያዋጣውአማራጭ ነው፡፡ ከድብደባው በባሰ የሚጎዳው የማያቋርጥ ጭንቀት እና የእረፍት እጦት ነው፡፡ ከአሁን አሁን ወደምርመራ ተጠራሁ ብሎመጨነቅ ጥሪውን የማዘግየትም የማስቀረትም አቅም የለውም፡፡ ‹በኋላ እንገናኝ› የምትለዋ ቀጠሮ እረፍት መንሻ ዘዴ ናት፡፡
በመቀጠል የምርመራው ዓላማ የነበረው ከጓደኞቼ ያገኟቸውን መረጃዎች በመጠቀም ብዙ እንደሚያውቁጥያቄ የሚጠይቁትም ከኔ ይምጣ ብለው እንጂ ሁሉ ነገር ላይ መረጃ እነዳላቸው ለማሳመን መጣር ነበር፡፡ በወቅቱ የእኔ ምላሽ የነበረውሁሉንም የሚያውቁ ከሆነ ለኔ ጥሩ እንደሆነ እና ምንም ጥፋት እንደሌለብኝ ከዛ በላይ ማስረጃ እንደሌለ የሚያስረዳ ነበር፡፡

ማስታወሻ፡-4. አብረው የሚሰሩ ጓደኛሞች ወጥ መልስ ለመስጠት አስቀድመው ስምምነት ላይ መድረስ

ስለ አንድ ጉዳይ ሁለት ጓደኛሞች የተለያየ መልስ ከሰጡ ሰቆቃው ሁለቱም ላይ የጠና ነው፡፡አንደኛው ወደሌላኛው መልስ የሚጠጋ ነገር እስካልተናገረ ድረስ ሁለቱም ይሰቃያሉ፡፡ በኛ ምርመራ ወቅት አስቀድመን ምንም የምንደብቀውወይንም የምንዋሸው ነገር እንዳይኖር ስንነጋገር ስለከረምን በተነጋገርነው መሰረት የአንዳችን ቃል ከሌላችን የጎላ ልዩነት አልነበረውም፡፡

በጓደኞች መሀከል ክፍተት ለመፍጠር ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ ለምሳሌ ለበፍቄ ‹‹ናትናኤል እኮእውነቱን ነግሮናል፡፡ በፍቃዱ ነው አብዮት እና አመጽ እንድንጠራ የሚገፋፋን ብሏል፡፡ አንተ ለምንድነው እንዲህ የምትደብቅላቸውእነሱ እውነቱን እየተናገሩ›› ብለውታል፡፡ ቀዳዳ ካገኙ ቅያሜ በመፍጠር ከጓደኛሞች መሀል አንዱን መስካሪ ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ ማስፈራሪያዎችበታጨቁበት ምርመራ መሀል እራሴን ነጻ ማውጣት ቀላሉ አማራጭ እንደሆነ ደጋግመው ይነግሩኝ ነበር፡፡ ፀጋዬ (ጥጋቡ)፣ ም/ሳጅን መኮንንእና ኢንስፔክተር አሰፋ እየመረመሩኝ በነበሩበት ወቅት ፀጋዬ ተራ ስድቦችን እና ዛቻዎችን ከሰነዘረ በኋላ በዛው አፉ እኔን ማቆየትእንደማይፈልጉ እና የሚፈልጉትን ካልኩላቸው ወዲያውኑ ወደቤቴ እንደሚሸኙኝ አባቴንም መንከባከብ እንደሚሻለኝ ሲነግረኝ ነበር፡፡ የአባቴጤንነት እንዳሳሰበኝ ስለገባቸው ባገኙት አጋጣሚ ለምርመራው ግብአትነት ይጠቀሙበት ነበር፡፡
አብዛኛው የምርመራ ጊዜ በተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና ተደጋጋሚ መልሶች የሚያልፍ ነው፡፡ ይህምምርመራዎችን እጅግ አድካሚ እና አሰልቺ ያደርጋቸዋል፡፡ ዝርዝር ጉዳዮችን በተደጋጋሚ በመጠየቅ ከምሰጠው መልስ ላይ ልዩነት ለማግኘትይህንንም ተጠቅሞ ሌላ አዲስ ነገር ለማውጣጣት ይጥሩ ነበር፡፡ የተሳካላቸው ግን አይመስለኝም፡፡ በተቻለኝ አቅም ቀዳዳ ሳገኝ የማምንበትንአቋም ከመናገር ወደኋላ አላልኩም፡፡ የማውቀውን ለማካፈልም እንደዚያው፡፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 39ን የሚቃወም መርማሪአግኝቼ ለምን ልክ ነው ብዬ እንደማምን አስረዳኋቸው፡፡ በተለያየ ጊዜ የወሰድኳቸው የበይነ መረብ ደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎችንምበተመለከተ ያብራራሁለትም መርማሪ ነበር፡፡

ማስታወሻ፡-5. በተገኘው አጋጣሚ አቋምን ማስረዳት

መርማሪዎቹ በተደጋጋሚ ስለተነገራቸው ብቻ የሚያምኑት ብዙ ነገር አለ፡፡ ኢህአዴግ ትግልላይ በነበረበት ወቅት ጭራቅ ተደርጎ ይሳል እንደነበረው አሁንም የነጻነት ትግል እያደረጉ ያሉትን ሰዎች እንደ ሰው በላዎች የሚቆጥሯቸውመርማሪዎች ብዙ ናቸው፡፡ በነዚህ መርማሪዎች ይህን ከተማ (አ.አ) ተወልዶ ያደገ ሰው ፖለቲካ ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ ተደጋግሞ ሲነሱልኝከነበሩት ጥያቄዎች መሀል ይህ መንግስት ምን በድሎሃል (በግል) እንዴት እንደዚህ አይነት አቋም ልትይዝ ቻልክ? የሚለው እንደነበርአስታውሳለሁ፡፡ መልሴ ግን አጭር ነበር፡፡ ነጻነቴን ዋጋ እሰጠዋለሁ!!

ከምክትል ሳጅን መኮንን ጋር በነበረን ጊዜ የተረዳሁት ስለ አቋሞቼ በጥልቀት ማወቅ ቢፈልግምእንደ ጦር እንደሚፈራቸው ነው፡፡ ገና ማስረዳት ስጀምር ቶሎ ብሎ ‹ወደጉዳያችን እንመለስ፣ ዳግም ወደ አንተ ልትስበኝ ነው?› ይለኝነበር፡፡ ሌሎችም መርማሪዎች ተመሳሳይ ፍላጎት አይቸባቸዋለሁ፡፡ አንድ የማይረሳኝ ምሳሌ ከኢሜሌ ላይ የተገኘውን የዜና መጽሔት በተመስጦሲያነብ የነበር አንድ መርማሪ አለቃቸው ድንገት ቢሮውን ከፍቶ ሲገባ ወረቀቱን በድንጋጤ ወርውሮታል፡፡ ከዚህ መገንዘብ የቻልኩት እነዚህን በአንድ በኩል መረጃ የተደፈኑ ሰዎች ሌላኛውን ጎን ማሳየት በሌላ አማራጭ የማያገኙት መረጃ ምንጭ መሆን ስለሆነ በምርመራወቅት እንደ አንድ ዓላማ ሊወሰድ እንደሚገባ ነው፡፡
አልፎ አልፎ ከሌላ ቦታ የሚመጡ (ከደህንነት መስሪያ ቤት) መርማሪዎች ለመመለስ አደጋችየሆኑ ውስብስብ ጥያቄዎችን ከመጠየቃቸው ውጭ የሚጠየቁት ጥያቄዎች እዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ መርማሪዎች የሚጠይቋቸውጥያቄዎች ለራሳቸውም ግልጽ አይደሉም፡፡ ጥያቄዎችን የሚያበጁት ከጀርባ ሆነው ምርመራውን የሚመሩት አለቆቻቸው ናቸው፡፡ አልፎ አልፎለመመለስ አደጋች የሚመስሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ ለምሳሌ ሚያዝያ 27 ቀን (የአርበኞች ድል ቀን) ኢንስፔክተር አሰፋ እና አንድየደህንነት ባልደረባ ሆነው ባካሄዱብኝ ምርመራ ወቅት አንድ አስቸጋሪ ጥያቄ ተነስቶ ነበር፡-
የደህንነት ባልደረባው፡- ‹‹ዞን 9 ምን ማለት ነው?››

መልስ ፡- ‹‹ዞን 9 ማለት ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱንየተነጠቀ ታሳሪ ነው ለማለት የተጠቀምንበት ስም ነው፡፡››
‹‹እኔም የዞን 9 አባል (ነዋሪ) ነኝ ማለት ነው?››
‹‹አዎ!››
‹‹ጥሩ! ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነቱን የተነጠቀ ከሆነ መቼ እና እንዴት ነው ዞን9 ነጻ የሚወጣው?››
ይህ ጥያቄ ትንሽ ለመመለስ አስቸጋሪ ነበር፡፡ በርግጥ እንደማነኛውም ግለሰብ የኢትዮጵያህዝብ ነጻነቱን መቼ ያገኛል ለሚለው ጥያቄ የራሴ አስተያየት ቢኖረኝም በዚህ ምርመራ ወቅት ሀሳቤን በነጻነት ብናገር የሚያመዝነውአደጋው ነበር፡፡ ስለዚህ ማለት የቻልኩት ዞን 9 የሚለውን ተምሳሌታዊ ስያሜ አምነንበት ብንጠቀምም የዞን 9 ነዋሪዎችን ነጻ ማውጣትግን እንደ ግብ ያስቀመጥነው እና እንዲሳካም ኃላፊነት ወስደን የሰራንበት ጉዳይ እንዳልነበር ነው፡፡
አጠቃላይ የእስር ቤቱ የአያያዝ ሁኔታና የምርመራው አሰልቺነት በየዕለቱ መርማሪዎቹ ከሚነግሩኝየራሳቸው እውነት ጋር ተደማምሮ ሊያሸንፈኝ ዳር ዳር ብሎ ነበር፡፡ ነገር ግን በተባራሪየምንሰማቸው ጓደኞቻችን እና መታሰራችን የሚቆረቁራቸው ሰዎች የሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ እና የበይነ መረብ ዘመቻ ተጨማሪ የጥንካሬምንጭ ሆነውኛል፡፡ የማታዎቹ ምርመራዎች ለዚህ ምቹ ናቸው፡፡ ካስተዋልኩት የተረዳሁት የማታውን (የሌሊቱን) የምርመራ ጊዜ መርማሪዎቹለሚከፈላቸው ተጨማሪ ገንዘብ እና ስላመሹ መ/ቤቱ ለሚያቀርብላቸው ቆሎ እና ውሃ ካልሆነ በስተቀር አይፈልጉትም፡፡
በማታው ምርመራ ወቅት ቶሎ የመሰላቸት እና የኃይል እርምጃ ወደመውሰድ ይሄዳሉ፡፡ ብዙ ማውራት አይፈልጉም፡፡ ስለዚህአለቆቻቸው የሰጧቸው ጥያቄዎች ሲያልቁባቸው የተለያዩ ስፖርታዊ ቅጣቶች በማዘዝ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው አማካኝነት ጨዋታ(game) ይይዛሉ፡፡ ወይንም ሌላ ክፍል ምርመራ ላይ ካለ ጓደኛቸው ጋር በኢንተር ኮም ወግ ይይዛሉ፡፡ በተመርማሪዎች ላይ ያላግጣሉ፡፡በማታዎቹ ምርመራዎች ወቅት ለሚነሱ ጥያቄዎች ረዘም ያሉ መልሶችን መምረጥ ተገቢ ይመስለኛል፡፡ መልሶችንም በህገ-መንግስቱ ስለተፈቀዱመብቶች፣ ስለ ተቋማት ነጻነት አስፈላጊነት፣ እና መሰል ፖለቲካዊ ጉዳዮች ወደማብራራት ማጠጋጋት፣ ከተቻለ የመርማሪዎቹን ቀልብ ለመሳብእና ከሚወስዷቸው አላስፈላጊ የኃይል እርምጃዎች መከላከል ይቻላል፡፡

ማስታወሻ፡-6. አቤቱታ ማሰማት

የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ፍርድ ቤት በሚወሰዱበት ጊዜ ያለውን አጋጣሚ በሚገባ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በተለምዶ ፍርድቤት በፖሊስ የአያያዝ በደል ተፈጽሞብኛል ብሎ የሚያመለክት ሰው ከፍርድ ቤቱ መልስ ተመልሶ ማዕከላዊ እንደሚገባ ስለሚያውቅ የባሰአደጋ ለመቀነስ በሚል አቤቱታ ከማቅረብ ሊቆጠብ ይችላል፡፡ ነገር ግን አቤቱታውን አቀረበም አላቀረበም ሰብዓዊ መብቱን ከመረገጥአይድንም፡፡ ልዩነቱ የሚሆነው የፍርድ ቤቱ መዝገብ ላይ የመብት ጥሰቱ ተመዝግቧል ወይስ አልተመዘገበም የሚለው ነው፡፡
እዚህ ላይ የምመክራቸውን ነገሮች ያለማድረግ ቁጭት በእኔ ብቻ ሳይሆን ብዙ ታሳሪዎች ላይ ያስተዋልኩት ነው፡፡ ያላደረግሁትንአድርጉ ብሎ የመጠየቅ ይሉኝታም ጽሁፉን ልጻፍ ወይስ ይቅርብኝ ብዬ እንዳንገራግር አድርጎኝ ነበር፡፡ ውስጤ ከሚብላላ ግን ጽፌውአንብቦ ቢያንስ አንድ ሰው የተለየ መንገድ ተከትሎ ጉዳት ቢቀንስ የተሻለ ነው የሚለው ሀሳብ የተሻለ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ሌሎቹምጓደኞቼ ተመሳሳይ መንገድ አልፈዋል፡፡ የነሱንም የምርመራ ሂደት ይጽፉታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እስከዛው ድረስ መታገስ ያልቻለየሀገር ውስጥ ነዋሪ ግን ወደ ቂሊንጦ ጎራ ብሎ ከራሳቸው አፍ ጠይቆ መረዳት ይችላል፡፡ እኔ ቀረኝ የምለው ነገር ካለኝ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ፡፡

ማስታወሻ፡-7. የማዕከላዊ ቤቶችን (ክፍሎች) ይተዋወቁ

በግቢው ውስጥ ሶስት የእስረኛ ማቆያ ቦታዎች አሉ፡፡ በተለምዶ ጣውላ ቤት፣ ሳይቤሪያ እና ሸራተን በመባል ይታወቃሉ፡፡ጣውላ ቤት አምስት ክፍሎችን በተርታ የያዘ ሲሆን የምርመራ ቢሮዎች ያሉበት ህንጻ ጀርባ ምድር ላይ ያሉ ክፍሎች ናቸው፡፡ እኛ ማዕከላዊታስረን በነበርንበት ወቅት ሶስቱ ክፍሎች ለሴት ተጠርጣሪዎች ማቆያ ሲሆኑ ቆርቆሮ መከለያ ተደርጎለት፣ ደግሞ የተቀሩት ሁለቱ ምስክርለመሆን የተስማሙ ወንድ ተመርማሪዎች ማቆያ ነው፡፡ ማሂ እና ኤዶም ከሶስቱ ክፍሎች በአንደኛው ከሌላ ሴት ታሳሪዎች ጋር እንዳይገናኙሁለቱ ብቻ ተለይተው ነበር፡፡ ጣውላ ቤት ፊት ለፊት የክፍሎቹ ወለል ጣውላ መሆኑ ነው ጣውላ ቤት የሚል ስያሜ ያሰጠው፡፡ ይህንንማቆያ ቤት አልፎ አልፎ ሂልተን በማለት የሚጠሩት ሰዎች ገጥመውኛል፡፡

ሳይቤሪያ የሚባለው የእስረኛ ማቆያ በቅዝቃዜው ምክንያት ነው ስሙን ያገኘው፡፡ ይህ ባለአንድ ፎቅ ህንጻ ምድር ላይየሚገኘው ማቆያ ቦታ በረጅም ኮሪደር የተከፈለ ሲሆን በግራና በቀኝ ከ2 ቁጥር እስከ 10 ቁጥር የተለጠፈባቸው አምስት አምስት ክፍሎችአሉት፡፡ 8 ቁጥር ከተለጠፈበት ውጭ ሌሎቹ ወጥ ክፍሎች ሲሆኑ 8 ቁጥር የተለጠፈበትን በር ተከፍቶ ሲገባ ግን ሌሎች ራሳቸውን የቻሉአራት ክፍሎች አሉት፡፡ የበለጠ ቅጣት እንዲቀጣ የሚፈልጉት ተመርማሪ እነዚህ ሁለት ሜትር በሁለት ሜትር የሆነ ጨለማ ክፍል ውስጥያስሯቸዋል፡፡ ሳይቤሪያ የምርመራ ግለቱ እስኪሰክን ድረስ ተመርማሪዎች የሚቆዩበት ቦታ ሲሆን ሁሉም ክፍሎች ከኤሌክትሪክ መብራትውጭ ምንም አይነት ብርሃን አይደርሳቸውም፡፡ የክፍሎቹ ግድግዳዎች ወለሉና ጣራው ከኮንክሪት የተሰራ ነው፡፡ ቀኑን ሙሉ ከውጭ ተዘግቶየሚውለው ክፍል በቀን ለሶስት ጊዜ ያክል ይከፈታል፡፡
ሳይቤሪያ ውስጥ ያሉ ክፍሎች ጠዋትና ማታ በተራ በተራ እየተከፈቱ ተመርማሪዎች በጋራ ወደሚጠቀሙት ባለስድስት ክፍል ሽንት ቤት እና መታጠቢያ ቤት እንዲሄዱና ተጠቅመው እንዲመለሱ ለደቂቃዎች ፈቃድ ያገኛሉ፡፡ ለሌሎች ጥቂት ደቂቃዎች ደግሞ የፀሐይብርሃን ለማግኘት ይፈቀድልን ነበር፡፡ ፀሐይ የምናገኘው በጣውላ ቤት እና በህክምና ክሊኒኩ መሐከል ባለ ክፍት ቦታ ላይ ነበር፡፡ጣውላ ቤት ያሉት ክፍሎች በር ክፍት ስለሚሆን ከማሂ እና ኤዶም ጋር በዓይን እና በምልክት ብቻ እናወራ ነበር፡፡ የሳይቤሪያ ክፍሎች በየተራ በሳምንት አንድ ቀን የሚጸዱ ሲሆን ባለችን መታጠቢያ ጊዜም የምናገኘው በነዚህ ቀናት ብቻ በሳምንት አንዴ ነው፡፡

ሸራተን ለ12 ሰዓት ፀሐይ የሚገኝበት፣ ቲቪ የሚታይበት እና የሽንት ቤት እና የመታጠብ ፍላጎት ያለው ሰው የፈለገውን ማድረግ የሚችልበት ቦታ ነው፡፡ የምርመራው ሂደት ሲጠናቀቅ ቀለል ባለ ጉዳይ የሚመረመር ሰው ወይንም ደህና ባለስልጣን ዘመድ ያለውሰው ሸራተን ሆኖ የማዕከላዊ ቆይታውን ያጠናቅቃል፡፡

በመጨረሻም አንድ እብሪተኛ መርማሪ በተናገረኝ ንግግር ማስታወሻየን ላጠናቅቅ፡፡ እንዲህ ነበር ያለኝ፣ ‹‹መንግስትብዙ ዓይኖች እና ጆሮዎች አሉት፡፡ እናንተ ደግሞ ስታወሩ የነበረው በእኛው ስልክ፣ ከሀገር ስትወጡ የነበረው በእኛው በሀገራችንአየር መንገድ እና በቦሌ በኩል ነበር፡፡ እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችሁን መረጃ አለን፡፡ አንተ አሁን እየደበቅህን ነው፡፡ ይህ ደግሞለአንተ አይጠቅምም፡፡ እኛ ምርጫ እንሰጥሃለን፡፡ ሕይወትህን ወደብርሃን መውሰድ የምትፈልግ ከሆነ ወደዚያው እንመራሃለን፡፡ አይአልፈልግም የምትል ከሆነ ደግሞ መውጣት ወደማትችለው ድቅድቅ ጨለማ እንከትሃለን፡፡ ምርጫው የአንተ ነው፡፡››


የኢሕአፓ ድምጽ ራድዮ ወቅታዊ ዜናዎች

0
0

eprpወያኔ‬ የዴያስፖራ ቀን ዝግጅትን አጠናቀቅኩ ይላል
የወያኔ‬ የጦር አለቆች ስብሰባ ሊቀመጡ ነው
‪‎የመኢአድ‬ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ቤተሰባቸው እንዳያያቸው ተደረገ
‪ደቡብ‬ ሱዳ የኢጋድን የሰላም ሀሳብ ውድቅ አደረገው
‪‎የአፍጋን‬ ታሊባን አዲስ መሪ መምረጡን አሳወቀ
‪ካሜሩን‬ ህገ ወጥ ናቸው ያልቻቸውን ናይጄሪያውያን ከአገሯ አባረረች
‪‎በሊቢያ‬ ታግተው ከነበሩ አራት የህንድ አስተማሪዎች መካከል ሁለቱ ተለቀቁ
‪ሻእቢያ‬ ዜጎቼ ከአገር የሚወጡት በተሸረበ ተንኮል ነው በማለት የተባብሩት መንግስታት ድርጅት የሰዎች አስተላላፊዎችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠየቀ
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to listen detail news click below)

Part 1

Part 2

(ሰበር ዜና) ካንጋሮው ፍርድ ቤት በነአቡበከር ላይ እስከ 22 ዓመት እስራት ፈረደ

0
0

Mandela+Obama+The Ethio-Muslims cause
(ሰበር ዜና) ፍርድ ቤቱ በነአቡበከር ላይ እስከ 22 ዓመት እስራት ፈረደ

(ዘ-ሐበሻ) ካንጋሮው ፍርድ ቤት በሚል በብዙሃን የሚተቸው የሕወሓት መንግስት ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት ሰሚት ምድብ በእነ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተጠቀሱ 18 ተከሳሾችን ዛሬ ከ7 አመት እስከ 22 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ፈረደባቸው::

በዛሬው ዕለት በካንጋሮው ፍርድ ቤት የቀረቡት የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት
1.አቡበከር አህመድ
2.አህመዲን ጀበል
3.ያሲን ኑሩ
4.ካሚል ሸምሱ
5.በድሩ ሁሴን
6.ሼህ መከተ ሙሄ
7.ሳቢር ይርጉ
8.መሃመድ አባተ
9.አህመድ ሙስጠፋ
10.አቡበከር አለሙ
11.ሙኒር ሁሴን
12.ሼህ ሰኢድ አሊ ጁሃር
13.ሙባረክ አደም
14.ካሊድ ኢብራሂም
15.ሙራድ ሽኩር
16.ኑሩ ቱርኪ
17.ሼህ ባህሩ ኡመር
18.የሱፍ ጌታቸው የነበሩ ሲሆን ፍርድ በሽብር ወንጀል ጥፋተኛ ብሏቸዋል::

22 ዓመት የተፈረደባቸው

1ኛ. አቡበክር አህመድ
2ኛ.አህመዲን ጀበል
3ኛ. ያሲን ኑሩ
4ኛ. ከሚል ሸምሱ ሲሆኑ በሽብር ወንጀሉ ከፍተኛ ተሳታፊ ነበሩ ሲል ፈርዶባቸዋል::

በሌላ በኩል 18 ዓመት የተፈረደባቸው
1ኛ. ድሩ ሁሴን
2ኛ. ሳቢር ይርጉ
3ኛ. መሃመድ አባተ
4ኛ. አቡበክር አለሙ
5ኛ ሙኒር ሁሴን ናቸው::

15 ዓመት የተፈረደባቸው
1ኛ. ሼህ መከተ ሙሄ
2ኛ. አህመድ ሙስጠፋ
3ኛ. ሼህ ሰኢድ አሊ
4ኛ. ሙባረክ አደም
5ኛ. ካሊድ ኢብራሂም ናቸው::

7 ዓመት የተፈረደባቸው

1ኛ. ሙራድ ሽኩር
2ኛ. ኑሩ ቱርኪ
3ኛ. ሼህ ባህሩ ዑመር
4ኛ የሱፍ ጌታቸውን ናቸው::

በዛሬው ችሎት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ሙስሊም ወደ ሲኤም ሲ ወደሚገኘው የቦሌ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት በችሎቱ ለመታደም የተጓዘ ቢሆንም ፌደራል ፖሊሶች ማባረራቸው ተዘግቧል፡፡ ለዘ-ሐበሻ በደረሰው መረጃ ፍርድ ቤቱ በከፍተኛ ፖሊስ ጥበቃ ስር የነበረ ሲሆን ከቤተሰብ በስተቀር ማንኛውም ሰው ችሎቱ ውስጥ እንዳይገባ በኃይል ሰዎች ሲባረሩ እንደነበር ተጠቅሷል::

በነዚሁ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የካንጋሮው ፍርድ ቤት ከእስራት ቅጣት በተጨማሪ ተከሳሾች ይህ ውሳኔ ከፀናበት እለት ጀምሮ ለአምስት አመታት እንዳይመርጡ ፣ እናዳይመረጡ ፣ በየትኛውም ቦታ ዋስም ምስክርም እንዳይሆኑ በአጠቃላይ ከማህበራዊ መብታቸው መታገዳቸው ተዘግቧል::

ተከሳሾቹ የቅጣት ማቅለያ አለማቅረባቸው በፍርድ ቤቱ ተገልጿል::

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱላቸው በሰላማዊ መንገድ ላለፉት ዓመታት ሲጠይቁ ቆይተዋል:: ፍርዱን ተከትሎ ሕዝበ ሙስሊሙ በተለያዩ ቦታዎች ሆኖ ቁጣውን በመግለጽ ላይ ይገኛል::

የፍርድ ሂደቱ ከ3 አመታት በላይ ሲንጓተት ቆይቷል::

 

 

ዕውን አቶ መልኬ መንግስቴ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር መንፈስ መሥራች አባል ነበሩን?! ሃቅና ታሪክ እስኪ –ተፋጠጡ።

Next: Hiber Radio፡ በኢትዮጵያ መንግስት በሚዲያ የጦርነት ቅስቀሳ ጀመረ፣የጋሞ ብሄረሰብ አገዛዙ በቃን ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድራለን አሉ፣ኤርትራ በማንኛውም ሰዓት ኢትዮጵያ ልትወረኝ ትችላለች አለች፣በአርባ ምንጭ ወንድሙ የነጻነት ትግሉን በመቀላቀሉ አንድ ወጣት በደህነቶች ተይዞ ከፍተኛ ማሰቃየት ተፈጸመበት ብገደል ሀላፊነቱ የመንግስት ነው ብሏል፣የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች ለእንግሊዝ መንግስት በምሬት ተማጽኖ አቀረቡ፣የጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ እና የኤድዋርዶ ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 04.08.2015 /ሲዊዘርላንድ — ዙሪክ /

                             እናፍቅሻለሁ ስለእናት ወለላ – የሚስጢር ወላባ!

smenጤና ይስጥልኝ የማከብራችሁ ወገኖቼ – እንዴት ሰነበታችሁልኝ ደህና ናችሁ ወይ? የሃሳብ ልዩነት ተፈልጎ አይገኘም። ማደግ የሚቻለውም በዚህ መስመር ነው። ነገር ግን ሆነን ያለፍነበትን ሌላው ሲሆን ወንጀል መሆኑ አይመችም። ዛሬ አርበኛው የሚያደርገው ተጋድሎ „የአማራውን ህዝብ ለማስጨረስ ሆን ብሎ የታሰበ ትልም ነውን?“ ሌላው የማሌ ርዕዮት ጽንሰ ሀሳቡና መሬት ላይ በህዝብ ውስጥ ያተረጓጎም ክህሎቱ ደግሞ በፍጹም ሁኔታ የተለዬ ነው። ርዕዮት ዓለሙን ተኖረበት፤ ነገርግን የጽንሰ ሃሳቡን ተግባራዊ ለማድረግ ዕድሉ በህጋዊነት  – አጋጣሚ አላገኘም፤ ዘመኑም … የሆነ ሆኖ —-“የዛሬ 40 ዓመት ኢህአፓ ጎንደር ላይ ነበር – እነኝህን የምታዮዋቸው የተፈጥሮ ምሽጎች ነበሩ ደጀኖቹ፤ ኢዲዩም ጎንደር ላይ በዚኸው ነበር ዱር ቤቴ ያለው፤ ዬአርበኞች ግንባር ጥንስስም ጎንደር ላይ ነበር አህዱ ያለው፤ ከፋኝም ቢሆን /አንዱ የአርበኛ ክንፍ/ ነውና የጎንደርን ጫካዎች ነበር ልዩ ባዕቱ ያደረገው፤ ወያኔም የማጥቃት ዘመቻው ለስኬት ያበቃለት፤

በዛሬው ጹሑፌ የተንጠለጠሉ ዕሳቤዎችም እግረ መንገዴን ይኬድባቸውል – „ባዶዎች ናችሁ፤ በምንም ትኮፈሳላችሁ፤ ሥልጣን ቀረብን ብላችሁ ታሳድማላችሁ“ ይሉናል፤ ድሮ ድሮ በሀሜት በአሽሙር – ጎሸም ነበር። ዛሬ ግን አደባባይ እዬወጣ ነው። ምን ያለው ገመና ተገኝቶብናል? ለረጅም ጊዜ በመንግሥት ምሥረታ ታሪክ ውስጥ ለነበረ ማህበረሰብ ዬ/heredity/ ጉዳይ መሆኑን በአዎንታዊነት በጽሞና ቢታይ ለትውልዱ ጠቃሚ ነው። ሌላው ግን ባዶን ማን ፈልጎት ያውቅና? ምን – አጥተን? ምን እንዳለን – ምን እንደምንችል – ምን እንደምንፈልግ አቅማችን አሳምርን ስለምናውቅ የበታችነት ለሚያናውዛቸው፤ የመንደርተኝነት ስሜት ላለባቸው የሚፈልጉትን ሸልመን እኛ የ /cosmopolitan city/ መናህሪያ ልጆች ወደ – ሥራችን። በተለይ ዛሬ ብልህ አደራ አለብን! አደራ ማውጣት የበቃ ትውፊታችን ነውና ለዚያ መትጋት ግሎባላዊ ጥሪያችን ነው። በሌላ በኩልም ይህን ተግባራችን ብላችሁ የያዛችሁት አበክሬ ልገልጸው እምሻው ቁምነገር የነፃነት ናፍቆትን እዬጠቀመችሁትም አለመሆኑን ነው። አሉታዊ የፍላጎት ኃይልን እያባባላችሁም ነው። የዘመቻውን ተክለ ቁመና ስገመግመው – የተወላጆችን ልብ ለማሸፈትም – ይመስላል። ትግሉን የጠቀምን እዬመሰለን መንፈስ እዬበተን ነው። ለማንኛውም ትንሽ እሰቡ – ማይካችሁ – የነፃነት ራህባችን በእጅጉ መቅኖ ይውጣልና – እስታግሱት! አደብ ግዙ እንላለን፤ የነፃነት ትግላችን ዬሁሉንም ተሳትፎ በእኩልነት – በጥራት ይፈልጋል። ሁሉም እንደ ችሎታው ያደርግ ዘንድ መጋኛ አትሁኑ። ፓርቲዎች፤ ንቅናቄዎች ደንብና ህግ አላቸው። መንፈሱን ማዋህድ ያስፈልጋል። ማንበብ!

የሆነ ሆኖ ከምታብጠለጥሉት ማህጸን የበቀሉ ቤተኛ ማገዶዎችም ከእኛ ወዲያ ላሳር በምትሉት የትግል መሥመር የፊት ረድፈኞች ናቸው – አሉበት። ማተበ ቢስም መሆን አይገባም። እንዚህ ጡቶች ናቸው ቀደም ባለው ጊዜም ቢሆን ልጆቻችሁን፤ ወንድሞቻችሁን፤ እህቶቻችሁን፤ ትዳራችሁን ጠብቀው – ለአደራ ያበቁት። ለዛሬው የሚሊዮን አለኝታ – ያበቁት። የዛሬው ትሩፋት የትናንት የጎንደር ንጡርና ቅዱስ ውለታ ነው። ለተባው ቅርሳዊ ኢትዮጵያዊ ተሳትፏችን ሆነ ተስፋነታችን – አናፍርበትም። ወርቅ ለሰጠ ብርት ግን እንደ ማተበ ቢሱ ወያኔው – አይገባም። እግዚዬሩም ያያል – ቢያንስ እሱን ፍሩ። አንደበታችሁን ሰብስቡ – ተከወኑ እንላለን! ተውንም እንላለን! ቀደም ባለው ጊዜም ቢሆን እዛው ኤርትራ ድረስ ተሂዶ ተስፋውን ለማምከን – ተሴረ፤ በግልባጭ ካርቦን  ከአዲሱ ጋር ደግሞ ለተሰወረ ደባ ቦታው በእሽቅድም – ተያዘ። በባለጊዜነት ሽፋንነት ብዙ ቡቃዬዎች – ደረቁ። ዛሬ ደግሞ ፈጣሪ ደግ ነውና ያ የተናቀ ቁምጣ ለበሽ ባለገር የተባለው ለብቁ አመራር – ታደል። በክፉ ቀን ጥቃትን ሳይቀበል አብሮነትን ከማንም በማስተዋል ቀድሞ ፈቀደ። ይታደሉታል እንጂ አይታገሉት የሚባለውም ለዚህ ነው። እነ የውስጥ አርበኞች ከእሳት እንደገባ ፕላስቲክ ኩፍፍትርትር – አላችሁ። ለዚህም ነው እንደተለመደው ሌላ ሴራ – የጠነሰሳችሁት። እንተዋወቃለን። የሆነ ሆኖ ከጥንትእስከ ዛሬ ሚስጢር ይቀዳል በዚህ – ባዕት። ጸጉራችሁ ቢቆምም ዕውነቱ ይኼው ነው። የትግራይ ትግርኝ እሿኽማ ህልም ቀድሞ የተረዳ ብልህነትም ነው። ስለሆነም ዛሬ በዚህ ዙሪያ የመጨረሻዬ ስለሆነ ተጋባቢ ዕይታዎችን ሁሉ ነው መልክ ማስያዝ እሻለሁ።

ክብሮቼ – የሀገሬ ልጆች አሁን ወደ ተነሳሁበት – ታዲያ ከላይ ያነሳኋቸው በተለያዬ ጊዜ የተፈጠሩ የነፃነት ፍለጋ መንፈሶች ዕውን የአማራውን ህዝብ ለመጨረስ ነበርን?! ነው ቁምነገሩ። አሁን የሰሙኑ ዳንኪራ ቅርንጫፉም ሆነ ቅጠሎቹም ረግፈው መለመላውን ቁሞ እንደምታዩት ልብ ልክ ነው። ኢህአፓ የመሸገው ጎንደር ላይ ለዛ ነበርን – ከቶ የአማርን ህዝብ ለማስደምሰስ ነበርን?! እንደገናስ የሱማሌ ወረራን ያጸደቀውና የወደደው „አትዋጉ¡“ እያለ የለፈፈው ዘመቻስ ፈቃድ አግኝቶ ቢሆን ዛሬ የአልሸባብ መጨፈሪያ ኢትዮጵያ አትሆንም ነበርን?! ሌላም የወርቅ እንክብል አለ – ብቸኛዋ በቅኝ ያልተገዛች አፍሪካዊት ሀገር ኢትዮጵያ ቀለማሙ የሺህ ዘመናት ታሪክ እንዲህ አንገቱን ቀና አድርጎ ይቀጥል ነበርን?! የቀስተዳመና ቅኔ በዓለሙ መሪ በልበ ሙሉነት ይዘረፍበት ነበርን?! በተጨማሪነት – „የብሄረሰቦች መብት እስከ መገንጠል“ መርኽ ግንባር ቀደሙ ተልዕኮስ የኢትዮጵያን አንድነትና ልዑላዊነት ክብር አስጠባቂ ነበርን?! ከዚህ የነጠረ ሃቅ ጋር ትውልዱ ማን ለዬትኛው ጎራ ተሰላፊ እንደሆነ – ይፍረደው። የ20ኛው ምዕተ ዓመት ጀግኖቻችን ሱማሌን አመድ ያደረገው ክብርንስ ማን ተቀብሮ እንዲቀር – አደረገው?! ወያኔ ሃርነት ትግሬ ብቻ – እእ፤ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ሠራዊት፣ የአዬር ኃይላችን፤ የባህር ኃይላችን፤ የምድር ጦርችን ያን ሳይንስን ጥበብ የዋጠ ብቁ ታሪክ ቁጭ ብለው ከመስማት ሞታቸውን ይመርጣሉ እነ እንቶኔ። የአድዋው የጥቁሮች ገድል ዳግሚያ ትንሳኤን ትውፊት ማደመጥ – ያንገሸግሻቸዋል። ይመራቸዋል። ይኮሰኮሳቸዋል። በዚያ ጦርነት ገድላማ ጀግንነትን ያሳዩትን የአደራ አርበኞች ማዬት አይሹም። ኢትዮጵያ የገድል ሐገርነቷ ዛሬም – አይዋጥላቸውም። ዘመንን – ይዘላሉ። ታሪክን – ይጸዬፋሉ። ነገር ግን ዛሬም ከእኛ ወዲያ ላሳር ይላሉ። ኢትዮጵያ ስተወደድ ከነመከራዋ መሸከምን ይጠይቃል። በስተቀረ የተቃጠለ – ካርቦንነት ነው!

አሁንም ይህን የተቃጠለ አውሎ በዚህው መከወን ስላለብኝ ተያያዥ ነገሮችን ማንሳትን – ወደድኩኝ። አለ ሌላም – የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ከግንቦት ሰባት ጋር ሲዋህድ „የኢትዮጵያ ህዝብ“ የሚለው ቀርቷል ነው አንዱ። 40 ዓመት ሙሉ ትግል ላይ ያለው ዬኢህአፓ ሥያሜ „ኢትዮጵያ“ በዚህ ነው የሚጀምረው። ሥሙ ብቻውን የተነሳበትን ዓላማ አሳክቷል ወይ?! ከሆነስ ስለምን በጎጥ አስተዳደር 24 ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያ ፍዳውን – ከፈለች?! የታገለው የቀድሞው የኢትዮጵያ መንግሥት ስለነበር ሲወድቅስ እሱ ለመሆኑ የት ነበረ?! ሥያሜው ብቻውን ድል ከሆነ። እንደገናም አሜሪካን ሀገር /Republican – Democratic – Independent/ ጀርመን ከ(SPD በስተቀር ሌሎቹ (CDU – ‘90 GREEN – FDP)፤ ሲዊዝም ከ(SVP/UDC በስተቀር ሌሎቹ SPS /PSS/ – FDP/ PLR/ – CVP/  PDC/ PPD/) እያለ ይቀጥላል። ዬዬሐገሮች ፖለቲካል ፓርቲዎች ሰፊው እጁ ከሀገራቸው ሥያሜ አልተነሱም። ከፓርቲያቸው ፕሮግራም ዓላማ – ራዕይና ፕሮግራም – እንጂ። ስለሆነም ክርስትያን – ሶሻል – ሊብራል – ዩኒቲ – ዲሞክራት፤ ሪፓብሊክ፣ አረንጓዴ እዬተባሉ ነው የሚጠሩት። የፓርቲዎች የማሸነፍን አቅም ውጤታመነታቸው ስኬቱ የሚለካው ደግሞ ሥልጣኔያቸው፣ ያሰገኙት ትሩፋት፣ ተርፈው አዳሪነታቸውን በተግባር ደረጃ ያለንበት ህይወት ነው።

ሌላም ተጨማሪም አለኝ። የወቅቱ ፓለቲካ መጠለያ በቦሌ ጫካ እንደሆነ ነው – የሚደመጠው። ጉልሆቹ የሰላማዊ ትግል ፓርቲዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትም ቢሆኑ መድረክም ሆነ ሰማያዊም „ኢትዮጵያ“ ብሎ ሥያሜያቸው አይጀምርም። ስለለሆነም የህውከቱ አንጎል አሳማኝነት ከተጨበጠ ነገር (fact) ውጪ ነው። ለነገሩ ሰማያዊም ፓርቲም እኮ ግጥማቸው አይደለም /ውቃቤዬ አልወደደውም ሲሉ ነበር – ሲያንገሸግሻቸውም አስተውለናል/ የሆነ ሆኖ እያደቡ የሚነሱ አጀንዳዎቻቸው ለእውነት አምክንዮዊ ክስተትም ዕጣ ፈንታው – እስረኛ ነው፤ ተተኪ ሆነ ተከታይ የማፍራት ቁመናው መሃን – ይሆናል። ምክንያቱም የመከራከሪያው ክስተታዊ አምክንዮ /phenomenological/ ወይንም ዬማዕከላዊ መዋቅሩ ቁልፍ የሆነውን የመከራከሪያ ሥርዓት ወይንም ህገ ደንብ ስለሚተላለፈው። ስለሆነም የሂደቱ ግብዕት በፍልስፍና ሥያሜው /Phenomenology/ በእውነቱ ምድረ በዳ ነው። ተሸነፊም ነው። ሽንፈትን መቀበል ደግሞ ደካመነት – አይደለም። ከተጨበጠ ነገር /fact/ ለተፈጠረ ሰብዕና። የአዕምሮ ብቃትም መለኪያው መሸነፍና – ማሸነፍን እኩል የማስተናገድ አቅም ይመሰለኛል። ሃሳብ ለማቅናት ሸማች – ያስፈልጋል። የሸማቹ ፍላጎት የሚገዛው በሥነ – ህሊናው ካለው ጥሪት ጋር አቅርቦቱ የሚመጥን ሆኖ ሲያገኘው ብቻ ነው። በስተቀር ከገብያ ውጪ ይሆናል /inflation/ ማለት የመሸመት አቅሙ expired – ያደርጋል።

በዬጊዜው የሚነሱት ገራራ ነጥቦች ቁጭ ብሎ ለመከራከር ወይንም አንፃራዊው አመክንዮ በተደራጀ ሁኔታ ለማስተዳደር አቅም የላቸውም። ስለሆነም በዚህ ዙሪያ የሚነሱት አውሎዎች ለመሸነፍ በጣም የተጋለጡ የሚያደርጋቸው ዓብዩ ጉዳይ እንደ ዕድሜ ጠገብ ልምዱ፣ የታለፈበት የመስዋዕትነት ሂደት፣ የሙያ ብቃቱ ሆነ የቀለም ዕውቀቱ ደረጃ ከፍተኛነት ብቻውን ለሚቀርቡ የተቃውሞ ጭብጦች ወይንም ምክንያቶች /objection/ የሚመጥን አቅም ያላቸው ብልህ ቁምነገሮችን መሆን አለመቻላቸው ነው። በሁሉም አቅጣጫ ጦርነት ያስነሳሉ፤ ግን ፍልሚያውን ሊቋቋሙ የሚችል የሚመጥን አቻዊ አቅም ያጥራቸዋል – ስለሆነም የጦር አቀጣጣይ ሃሳቦች ትንፋሻቸው የተቆራረጠ ሆኖ የሚታዬውም ለዚህ ነው። የማጥቂያ ትልሞቹ አዘውትረው አቋራጭ መንገድ ስለሚሹ በዬጊዜው ተዋጊ ሃሳቦችን አዝለው እንደተንጠለጠሉ ጠውልገው መንገድ ላይ – ይቀራሉ። ለተቀናቃኝነት የሚቀርቡት አጀንዳዎች የፍላጎትን መሠረተ ሃሳብ ወይንም ፍሬ ነገር /substance/ እናጠቃዋለን ብለው የሚነሱበትን ሃሳብ አቅምና ተጨባጭ ህይወት በአግባቡ የመተርጎም መቅኖም በእጅጉ ያጠራቸውም – ናቸው። በአቻነት መሳ – ለመሳ የመቆም ጉልበት እንኳን የላቸውም እንኳንስ ማሸነፍ። ስለምን? ተዘውትሮ የሚታዬው በበቀሉ ወይንም በአቆጠቆጡ ሰብሎች የሚሰነዝሩት የማጥቂያ ዘመቻዎች ተጨባጭ ሁኔታን ሆነ የህዝብን ቅርባዊ ሙቅ ስሜት ያላደመጡ በመሆናቸው ቶሎ – ይበጠሳሉ። ለጦርነት የሚሰማሩት ሃሳቦች እንደ ተመክሮ ማሳው ሆነ እንደ ዕድሜ ጠገብነት ድርጁ መሆን ሲገባቸው ሽብርክና ተሰባሪ ሆነው – ይታያሉ።

እንዲህ ከውስጥነት ያልበቀሉ ተናካሽ ጀውጃዋ አጀንዳዎች አቅመ ቢሱች በመሆናቸው፤ ዬዕድሚያቸው ቁጥር ለሂሳብ እንጂ የተግባርን መዳፍ በማሰብል ልቅና በቀላሉ መረታት አለመቻላቸው የተሸናፊ ዕጣ እንዲቀበሉ – ያስገድዳቸዋል፤ አሸናፊው ተመክሮን ልምድን የዕውቀት ደረጃን ከአደገ ደረጃ የሚያደርስለት ዬተጨባጩ ሙቀታዊ ስሜትን በብልህነት ከማድመጥ ጋር ስለሚጋባ ብልጫ ያለው ባለሙሉ አቅም ሆኖ ያሸንፋል። ለዚህ ነው በዬወቅቱ ጅጉድጉድ ብለው ከአንዱ መረብ ወደ ሌላው በፍጥነት እንደ ፌንጣ የሚዘሉ ሃሳቦቹ እርጋታ ያነሳቸው፤ ክልፍልፍና ሸውሻዋና ተናዳፊ – የሚሆኑት። የመንፈስ አቅም ብልጫ ሆነ – የሥነ ልቦና የበላይነት ገብያ ተሂዶ – አይሸመትም። መሪና አሸናፊ ኃሳቡ ፈተናን የመታደግ ሂደቱ ችሎታን፣ ሙሉዑ ሥነ ምግባርን /አለመተላለፍን ደንበር አለመጣስን/ የብስለት ደረጃ ልቅና ዘላቂነትን፣ የምራቅ መዋጥ – መደርጀትን፣ ወቅትን በጥሞና የማድመጥና የመተርጎም ሥልጡንነትን እንዲሁም ችግርን ለመፍታት በአጅ ያለን አቅም በአግባቡም በመሳትዳደር እረግድ ሥልታዊ የሆነ ብልህ መብቃትን ይጠይቃል። /god handling problems/ እንግዲህ አቶ መልኬ መንግሥቴ መደባቸው የት ላይ እንደሆነ ዳኝነቱን – ለክብረቶቼ።  ስለሆነም ዛሬ በምልሰት ጥቂት ተወራራሽ ታሪክ ቀመስ ነገሮችን ስለማነሳሳ ትእግስታችሁንም አብዝቼ – እሻለሁ። አመሰግናችኋለሁም።በቅድሚያ ግን እንዴት ሰነበቱ አቶ መልኬ መንግሥቴ ደህና ነዎት ወይ? ለክብርት ባለቤተዎት የከበረ ሰላምታ አቀርባለሁ። ልዩዬ ናቸውና እጅም – እነሳለሁ።

እኔ እንደ ሥርጉተ – ለአቶ መልኬ የተሰጠውን ተቀጥላ ክብር ሳዳምጥ በእውነት – አዘንኩኝ። „ክቡር“ ለማለትም ያልደፈርኩት እኒያ አዛውንት – አባት፤ ባለ ግራጫማ ፀጉር፤ ብዙ ነገር ያዩ – እንደ አባት አዳሩ የእሳቸው ያለሆነው „ክብር“ እንደ ቶፋ /እንስራ/ ሲደለዝላቸው፤ እንደ ቁሮ ከሰል ሲንጠለጠልላቸው የእኔ አይደለም ብለው ሊጸዬፉት ሲገባ አጋጠመኝ በማለት ደልደልና ኮራ ብለው በአዎንታዊነት በደስታ ስለተቀበሉት ነበር። ከዚህ ባሻገር ገዳዳ የሆነውን የሰብዕና ምስክርነትም ሲሰጡ ታዛቢውን ሰፊ አድማጭ ዘንግተውታል። ያልተገባ „ክብርን“ መቀበለዎት ብቻ ሳይሆን ያልተገባ „የሃቅ ጥነትም“ አዳምጨበታለሁ ቃለምልልሱን። ያልበቀለ ክብርን ተቀብሎ ያልተገባ ክብርን መስጠት ጂዋጂዊት ነው። ቢያንስ ሁላችንም በመንታዘበው ዕውነት ላይ ቀጥ ያለ አቋም ሊኖረወት አለመቻሉና የሄዱበት እጅግ የወረደ ከንቱ ውዳሴ ባለቤቱ እራሱ በውስጡ ደረጃዎትን እንዲይበት – ያደርገዋል። ያው ህሊና የሚባለው ከኖረ – ካልተነነ። በተረፈ በአርበኞች ግንባር ላይ የነበረዎት የተሳትፎ ደረጃ አርበኛ ባያሰኘዎትም አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ዬሚችለውን፤ የድርሻውን ለማድረግ ለወቅቱ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት መትጋት መልካም ነው። እኔ አርበኞችን በተገባ ሁኔታ ያግዙና ለአርበኛው ተግባር ቅርብም የነበሩ ከኮሎንቦስ – ኦሃዩ ወንድሞቼ መረጃውን ከማደምጠው በስተቀር፤ ቦቦታው ስላልነበርኩኝ፤ ይህን ዘልዬ እርእሴ ወደ ሆነው አብረን እላለሁ – በትህትና። ዕውን አቶ መልኬ መንግሥቴ የአርበኞች ግንባር መንፈስ መሥራች አባል ነበሩን? መልሱ ህዝብ ይዳኘው ዘንድ ትቼ ለመነሻ የሚሆኑ ነጥቦችን – አነሳሳለሁ።

መነሻ – የአርበኞች ግንባር መንፈስ አህጉራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለምአቀፋዊም – ነው። መነሻውም ዬአብዛኞቹ ብሄራዊ – ነበር ማለት ይቻላል። ለዛሬው ዬአርበኞች ግንባር ጥንስስ ጎንደር ለታላቋ ትግራይ ትግርኝ ቅዠት ስትከለል አሻም ዬህወሓትን ማንፌስቶ ያሉት የጎንደር ልጆች ሃቁን ካወቁበት ዕለት ጀምሮ አፈንግጠው በመውጣት እራሳቸውን እንደ አባት አደሩ በሽምቅ ውጊያ አደራጅተው ትግል የጀመሩት በዘመነ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሳይሆን፤ አስተውሉት ወገኖቼ – በወደቀው ብሄራዊ መንግሥት ወቅት በዘመን ደርግ ነበር። ከዚህም ባሻገር በወቅቱ ያላፈነግጡት –  ዬአካባቢው ተወላጆችም ቢሆኑ፤ በነበረው የውይይት ክፍለ ጊዜ ሲታገሉት የነበረ – ሲሆን፤ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ለድል ሲበቃ ለእስር ተዳርገው ዛሬ ውጭ ሀገር የሚገኙ ወንድሞች አሉ። ስለሆነም – የፍሬ ነገሩን ልብ ለማግኘት ከቃሉ ፍቺ መነሳት አስፈላጊ – ይሆናል።

መሠረት …. ማለት ምን ማለት ነው? መሠረት ማለት መነሻ – መጀመሪያ – መጠንሰሻ – መወጠኛ፤ የጅምሩን ንድፍ ብቻ ሳይሆን የግቡንም አናት መንፈሱን ዬመሸከም ሙሉ አቅም ያለው የግንባታው አስኳል ማለት ይሆናል፤ ቃሉ በአውራነት በቤተ ሥምነት ሲራባ መሠረትነት – መነሻነት – መጀመሪያነት – መቅድምነት ማለት ሲሆን፤ የሐረጋማ እርባታው በጊዜ ሲታይ ደግሞ ሊመሠረት፤ እዬተመሠረተ – ሲመሠረት – ተመሠረተ – ተመስርቶ – ይሆናል። ዬሂደቱ እርባታ ቅኝት ደግሞ አመሠራረት – ምሥረታ – ተመሥራች — መሥራችነት – እያለ ይተማል። ስለዚህ „ምሥረታ“ እንደ አለ በቁሙ ሲተረጎም አዲስ በህሊና የተወጠነ ግኝተ – ዬሃሳብ ፍልስፍና መሬት ላይ ዕውን ሆኖ ሲታይ ይሆናል። ጸሐይ ያለዬው ወይንም ያልሞቀው፤ ቀድሞ በሌላ ሰው ያልታዬ የአመክንዮ ይዘታዊ ቀንበጥ ፍሬ – ነገር እንደ ማለት፤ ወይንም በሌላ ወገን ያልተጀመረ የመንፈስ አዲስ ውልደ፣ – ዕንቡጥ በኽር፣ የብቻ ጥሪት ሲሆን፤ ውጥኑ በአጭር ታጥቆ ለተወሰነ ዒላማ ወይንም ረጅምና ቋሚ ዓላማን ይዞ መርህ ነድፎ፤ አህዱነትን /ጀማሪነትን/ በአካልነት ሲሆኑበት ወይንም ሲገኙበት ማለት ነው። ከዚህም አለፍ ተደርጎ ሊታይ የሚችልበትም ሁኔታዎችም – ይኖራሉ። በይዘትና በቅርጽ ልዩነት እና አንድነትንም በዘርፉ ማዬት – ይቻላል። የሆነ ሆኖ በምንም መሥፈርት „መሥራችነት“ በውክልና ወይንም በትውስት ወይንም በአጃቢ ወይንም በደጋፊነት – ወይንም በተለጣፊነት ወይንም በተጨማሪነት – አይለካም። በአህዱነት ውስጥም ቢሆን በአምልኮ እንደ ድንጋይ ሐውልትነት ሳይሆን እራሱ ሰብዕናው፤ የአዲስ ሃሳብ ፈጣሪ አፍላቂ – ፈላስፋው ወይንም አስገኝው ኃይል በቀዳሚ ተዋናይነት ሆኖ ሲገኝበት ብቻ ነው። ከዚህ አንፃር ስለምን አቶ መልኬ መንግሥቴ ከአርበኞች መንፈስ ጋር ተያያዥነት ባላቸው እውነቶች፤ በቅርብም ሆነ በሩቅም ዝምድናቸው፤ እንዲሁም በእትብታዊ ሃዲድነት ከሰመሩት ብሄራዊ ተደሞዎች ጋር በመሥራችንት አባል ሊያደርጋቸው እንደማይችል፤ የተሰጣቸው ያልሆኑት ሥያሜ መሻገሪያው ሰባራ መሆኑን ጹሑፌ ያመለክትና፤ ፍርድና ዳኝነቱን ከወቅቱ ትኩስ የሚሊዮኖች ፍላጎትና ተስፋ ጋር ብዙኃኑ ይዳኘው ዘንድ በክፍትነት እተወዋለሁ …. ሸበላ – የመደማመጥ ጊዜ  – በአክብሮት።

የዘመናች ዬአርበኝነት ብሄራዊነት፤ ዕትብታዊ ሃዲድ ምሥረታ፤ ይዘታዊ ውህድነት፤ በአኃቲ መሥመር – አካልነት።  

  1. በታችና ላይ አርማጭሆ ቆላማ ቦታዎች በዛ ጀግና አርበኛ አበጀ በለው የጎበዝ አለቃነት ሌሎችንም አክሎ ትግሉ ሁሉንም መከራ ተቀብሎ – ሲቀጥል፤ አርበኛው በነበረው የኢትዮጵያ መንግሥትም ደስተኛ ስላልነበረ ግራ – ቀኙን ነበር የሚታገለው። ማለትም በወቅቱ የነበረውን የኢትዮጵያ መንግሥትና የጫካውን የወያኔ ሃርነት ትግራይን። አርበኛው ዱር ቤቴ በማለት በደፈጣ ውጊያ በጥምር ሁለቱንም ይፋለም ነበር። ይህ መረጃ የደረሳቸው የወቅቱ የስሜን ጎንደር ክ/ሀገር አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ሽፈራው እንቁባህሬ እና የተከበሩ ጓድ ገዛህኝ ወርቄ የፓርቲው አንደኛ ጸሐፊ ከትግራይ መለቀቅ ጋር የወያኔ ሃርነት ትግራይ ይዞታውን እያሰፋ ሲመጣ በሀገር ሽማግሌ ተደራድረው አርበኛው የማጥቃትና የመከላከል ትግሉን እንዲቀላቀል ጥሪ – አቀረቡለት። ከዛ በኋላ ጥሪውን ተቀብሎ ሙሉ የትጥቅና የስንቅ ድጋፍ ተደርጎለት ዱር ቤቴነቱን – ቀጠለበት። እኔ በተፈጥሮዬ ከሥራ ሰዓቴ ቀድሜ ነበር ቢሮ እምገባው። ሀገሬ ሥራ ነውና። አንድ ቀን ጥዋት ወደ ቢሮዬ ስገባ ያዬኋቸው ጸጉረ ልውጦች መልካቸው – ቁመናቸው  – የትጥቃቸውና የመንፈሳቸው ብቃትና ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን ጽዳታቸው፤ ዬቆፋጣናነታቸው ቅልጥፍና ወዙና – ጠረኑ እስከ ዛሬ ድረስ ከዓይኔ – አይጠፋም። የበረኃ ሰው ሆነው ግን የጀግንነት ዘመናት አገናኙ ተብለው የተፈጠሩ የአደራ ልዩ ውሎች – ድልድዮች ነበሩና። በተመስጦ ቀጥ ብዬ ቆሜ ሰላምታ ሰጥቻቸው በማስተዋል – ቃኘኋቸው። እኔ ጀግና እወዳለሁ። እነኛ ጸጉረ ልውጦች – እንግዳ ማረፊያው ወንበሮች ላይ ቆርጠጥ – ቆርጠጥ ብለው በመደዳ ተቀምጠው – ነበር። የሥራ ሰዓት ሲደርስ መረጃ ክፍሉን ጠይቄ – ዝርዝር ታሪኩን – ተራዳሁ። የእኔ የተግባር መስክ ሲቦክስ ማህበራትን ማደራጀት ስለነበረ ከጉዳዩ ጋር የተያያዘ አቅም ወይንም ኃላፊነት – አልነበረኝም። ደረጃዬም –  አይፈቅድም።

እንዲህም ሆነ – … ትግሉ እዬከረረ ሲሄድ ትግራይ የነበረው 604ኛ ኮር ወደ ጎንደር ተዛውሮ – ነበር። እንደገናም 7ኛ ክ/ጦር አዘዞ ላይ 603ኛ ክ/ጦሮች ጨዋሰፈር ጎንደር ከተማ ላይ ነበሩ። በማዕከላዊ ወታደራዊ ትእዛዝ ጎንደር የነበረው ሠራዊት ጥርግርግ ብሎ ወደ ጎጃም እንዲሄዱ ተደረገና ጎንደር ብቻዋን – ቀረች። እንደሚመስለኝ ተለዋጭ ሠራዊት ይመጣል በሚል ነበር እንጂ፤ አመራሩ እሺ ብሎ የሚቀበለው ውሳኔ አልነበረም እንዲሁ ሳስበው። ምክንያቱም እኛም በከፋ ቀውጢ ሁኔታ ላይ ነበርን እና። ደባው ሳይታወቅበት ሹልክ ብሎ ገብቶ ሰላማዊ ሽግግሩን ሸውዶ ከወነ። ብቻ በወሳኝ ወቅት የድል ግልበት – ስለነበር የታሪክ ትውከት – ልበለው። ደንቀዝ ላይ በከባድ መሳሪያ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሠራዊት እንደ ጉድ ይለቀው የነበረው ድብዳባ ባለማቋረጥ አካባቢውን ሰላም – አሳጣው። በዛን ጊዜ አንዲት ቀን ነፃ ነበረች። ጎንደር ጭስ – ለበሰች። ስታሳዝን።

ከዬት የመጣ አቧራ እንደሆንም አላውቅም፤ በአውሎ ታጅቦ ሰሞናቱን በጭስ አባልነት እርሰ ከተማዋ ጉም ለበሰች፤ ከጢሱ ጋር ቀናቱ ድብዛቸው የጠፋ ጭስ ለበስ ድንብስ ነበሩ። ሰው ለሰው መንገድ ላይ ይተላለፍ ነበር። ቀኑ አስቀድሞ – ጨለመ። እንደ ጨለመም ይኼው የጎንደር ሱዳን አዋሳኝነት፤ ዬጎንደር ከከተማነት ከሜተሮፖሊታን ከተሞች ዝርዝር ህዉሓት መሰረዙን“ ተያያዥ የውጭ ኢንቬስተሮች እድገት መሰላሎች ሁሉ መምከናቸውንም እያዳመጥ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ዓይኑ የከፈተለት ሁሉ መዶሻውን ያው ጎንደር ላይ። አዬ! ነገረ –  ጎንደር! ብቻ በዛ ወቅት ለዳኮታ ሰፊ ቦታ ያስፈልጋል ተብሎ እዛው አቧራ ተለብሶ እዬተዋለ እዬታደረ የአዬር ማረፊያ ነዋሪዎች ስንት ደሃ ከኑሮው የተፈናቀለበት አውሮፕላን ማረፊያ መሰናዶም ሳይሰረባት ባክኖ ውሃ በልቶት – ቀረ። ለነዋሪዎቹ ካሳም – አልተሰጣቸውም። አንዲት ቀን ሠራዊት በዳኮታ ማሳረፍ የሚቻልበት አጋጣሚም ውሃ ብልቷት – ቀረ። የራዲዮ መልዕክቱ  „ለአጋሰሱ ስንቅ ልከናል የሚል“ እንደ ነበር ሹክ አሉኝ። ብቻ ተስፋው ካለ ይግባኝ – ሞተ። ለአገሰሱ ተላከ የተባለውም ስንቁም ቢሆን አቀባበል ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ሠራዊት እንዳይቸገር ተግባሩን ቀለል ለማድረግ ታስቦ ነበር። የመንግሥት ሠራዊቱ ቀድሞ – መሸኘቱን ቀደም ብዬ አጫውቻችኋለሁ። ነገር ግን  ጎንደርን አናስደፍርም ያሉ እነዛ ቀደምት የሽምቅ አርበኞች ከቦታቸው ተነስተው ወደ ጎንደር ገሰገሱ፤ በሶስት እጥፍ ተዘጋጅቶ በነበረው የውጊያ መስመር ጉድብ ውስጥ ሆነው 18 ቀን ሙሉ ከሀገሬው ጋር አቧራ ለብሰው ውጊያውን አስከ መጨረሻው ድረስ – ተጋፈጡት።

ሌላው ቀርቶ እኔ በአለፋ ጣቁሳ በር ከነበረው ቡድን ጋር ስለነበርኩ፤ ክፍትም ነፃ ቦታ ደንቢያ ላይ ይሁን በአዋሳኙ ተንከል ላይ አዬር ወለድ የማሰረፍ ሰፊ ዕድል – ነበር። ቦታው ምቹ ለጥ ያለ ሜዳማ – ነበር። በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ከእግረኛው ባላነሰ ጀርመንን ከናዚ ያወጣው ታላቅ ኃይል አዬር ወለድ ነበር ከታሪክ – እንዳነበብኩት። እኛ ላይ ግን ያ የነፍስ ደራሹ ኃይል ዕቀባ – ተደረገበት። የሆነ ሆኖ ከተማ ላይ ጦርነቱን ማካሄድ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን፤ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንዳሉትም ጎንደር በውጭ ከሚታዩት ሃብታት ይልቅ ዬማይታዩት የቅርስ ዲታነቷን ያሰተዋሉት መሪ ቅኑ ጓድ ገዛህኝ ወርቄ ስልታዊ ማፈግፈግ አድርገው ወደ ላይ አርማጭሆ ኮማንድ ፓስቱን – አዛወሩት። እንደ ጓድነታቸው ዕሳቤ ሴራው ማዕከላዊ ድጋፍ መኖሩ የተረዱት – አልመሰለኝም፤ እንመለሳለን በሚል ተስፋ ነበር ወደ አርማጭሆ  – የሄዱት። እርግጥ ከዛ በፊት ኤሊኮፍተር ተልኮላቸው ከጎንደር ህዝብ ጋር ነው እምሞተው ብለው ስለቀሩ እንዳሉት ሆነው – ተገኙ። ለመጨረሻ ሳላያቸው ሰንብቼ ኮሪደር ላይ – አገኘኋቸው። እንደ ተለመደው በዛ ትሁት መምህር ፊታቸው ከመንገዳቸው ገታ ብለው ቆም ብለው – ጠበቁኝ። በጥልቀትም – አዩኝ። ያ የሚያበራ ግንባራቸው ተለውጧል፤ አንድም ቀን ሱሪ ለብሼ ለዛውም በሙሉ ትጥቅ አይተውኝ ስለማያውቁ በተመስጦ – ቃኙኝ፤ እኔ ብቻ ነበርኩኝ – ሴት። „ጥሩ ነው አይዞሽ!“ አሉኝ – በራዲዮን ጩኽት ብዛት ጉሮሯቸው ዝግት ብሎ – ነበር። የሆነ ሆኖ ከእሳቸው ዕልፈት በኋላ አርበኛው እራሱን እንደገና አደራጅቶ ትግሉን በባዕቱ – ቀጠለ።

የጓድ ገዛህኝ ወርቄ ዕልፈት ተመሳሳይ ግድፈት እንዳይፈጸም ትንሽ ልበል። መዘግዬት ጸጸት ተከል ነውና። እጅግ ወቅታዊና በጣም ተፈላጊም ስለሆነ። እኔ በቁስቋም በር ነበር ብቻዬን – የወጣሁት። እኔ የወጣሁበት መሥመር በሰማይም በምድርም ዬተቃጠለ የጦርነት ቀጠና ነበር። እነሱ ደግሞ አንፃራዊ ሰላም በነበረው በወገራ በር ሆኖ ተገንጥሎ ወደ አርምጭሆ በሚወስደው መንገድ ነበር፤ ቀን ግዳጅ ላይ አብረን እንሰማራለን በዬቡድን መሪዎቻን – ሌሊት ግን ከፍተኛ የመንግሥት፣ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አካላት እንዲሁም የህዝብ ድርጅት መሪዎች ብቻ የሚያድሩት ቦታ በተጠናከረ ጥበቃ በተለዬ ሁኔታ ነበር። ቦታውን እኔ እራሴ አላውቀውም። አውሮፕላን ማረፊያው አዘዞ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ቆጥጥር ሥር ሲውል እንዳሉ በጋራ ነበር የተጓዙት። ስለዚህ እኔ በተመቸኝ ቦታ ወጥቼ መሬት ከያዝኩ በኋላ ወደ እነሱ መቀላቀል ነበር – ዓላማዬ። የእኔ ትልቁ ጸጋዬ መዋጋት ሳይሆን ከዬት እንደመጣ አላውቅም አስቸጋሪ በሆነ ጉዳይ ወይንም አጀንዳ ተልኬ ግን ገበሬዎችን በፍቅር አሳምኜ የመምጣት የተለዬ አቅምና ሥጦታ ነበረኝ ማህተም ነው ማለት እችላሁ። ለዚህም ነበር ጫካ የወጣሁት፤ እናም መልዕክተኞችን – ላኩኙ። ዘርፉን በባለቤትነት ለመያዝ የበዛ ፍላጎት – ነበረኝ። አለቆቼም ይህነን ጸጋዬን ስለሚያውቁ፤ ስለሚያከበሩትም አይነፍጉኝም – ነበር። መልዕክተኞች ሲመለሱ መርዶ ይዘውልኝ – መጡ። ጓድ ገዛህኝ ወርቄ እስከ ልጃቸው ማለፈቸውን። ድርብ ሃዘን ነበር ለእኔ። የተግባር ሰው ነበሩ። የሌሎች ልጆች በቦሌ ለከፍተኛ ትምህህርት የጓድነታቸው ግን በብሄራዊ ውትድርና በኋላም ከአባቱ ጋር ተሳዋ። በምንም ተልካሻ ግለኝነት ሆነ ትዕቢትም የማይጠረጠሩ ነበሩ። የሆነ ሆኖ ምክንያቱ ምን እንደሆን ገበሬዎቼን ስጠይቃቸው የነገሩኝ ጀግና አበጀ በለው ትግሉን ከተቀላቀለ በኋላ በተሳሳተ መረጃ በጀርባ ሊያስወጋ ነው በሚል እርምጃ እንዲወሰድበት በመደረጉ ምክንያት መሆኑን ነገሩኝ። ይህም እጅግ በጣም አሳዘነኝ። መልዕክተኞች እንደነገሩኝ ጎንደር ላይ በጀግንነት አብሮ ሲዋጋ የነበረው አርበኛ ከእሳቸው ጎን የነበረ ሲሆን፤ የሀገሬው ህዝብ ጉዳዩን ቀድሞ መረጃው ደርሶት – ቀን ይጠብቅ ስለነበር፤ መተላለፊያ በሩን ዘግቶ በተደራጀ ሁኔታ ገዢ መሬቱን ይዞ አናሳልፍም ብሎ ተዋግቶ እንደገደላቸው ነበር የሰማሁት።

ለዚህ ነው ብዙ ሰዎች በጎንደር ላይ ያነጣጠረ የማያውቁትን ሥነ ልቦና ውስጥ ሲዳፈሩት ሳይ አልፎ አልፎ አንዳንድ ነገሮችን – እምጠቋቁመው። በተከታታይም የጻፍኳቸው ጹሑፎች ነበሩ „ጎንደር ከክፍል አንድ እስከ አራት“ ይህ ታላቅ ተቋም ነው ለዬትኛውም ዘመን። የአካባቢው ህዝብ አንቴናው ከዘመን አመጣሹ ኔት በላይ ሆኖ የኖረ ነው። አሁንም በአርበኛው አያያዝ ስምሪት ድልድል ላይ አርበኛውን የማይመቹ ነገሮችን ላይ የተደረጃ የህሊና መሰናዶ – ያስፈልገዋል። ሞትን የፈቀደው አርበኛው ቢቀበለው እንኳን የአካባቢውን ሥነ – ልቦና የሚገዙ የሃቅ መንገዶች አትኩሮትና ክብር ሊሰጣቸው ይጋበል – እላለሁ። በተለይ የአካባቢው ሰው በሥም በሚያውቃቸው መሪዎቹ አርበኞቹ ላይ ነቁጥ ናት የምትባለው ጉድፍ ግድፈት ግዙፍ ችግር – ትወልዳለች። ምክንያቱን አሁንም በዚህ ዙሪያ ጥንቃቄ ዬሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ። በወቅቱ የነበሩ ያን ጊዜ ዘመቻውን የተጋሩ እንዳሉ – አውቃለሁ። ነገር ግን ለደህንነታቸው ስል ሥማቸውን መስጠት ግን – አልችልም።

  1. እኔ አብርሃም ነው የምለው በክርስትና ሥሙ አሁን ያለውን አቋሙን ስለማላውቅ፤ እኔ በምጠራው ሥም ይሆናል መረጃውን – እምሰጣችሁ። አብርሃም እና እኔ ለዬካቲት 66 ፓለቲካ ኢንስቲቲዩት የመግቢያ ፈታና ለመውሰድ ከታጩት ውስጥ ነበርን። ጎጃም ባህርዳር ላይ የመግብያ ፈተናው ይሰጥ ስለነበር አብረን – ተጓዝን። ፈተናው ቅይጥ aptitude test ዓይነት – ነበር። ብዙም ከባድ ባይባልም ቀላል – አልነበረም። በውጤቱ አብርሃም አልፎ እኔ እንደወደቅኩኝ – ተነገረኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ ህልሜ በሀገር ውስጥ መማር እና እዬሩሳሌምን ማዬት ነበር። የሆነ ሆኖ እኔ ከፍቶኝ አሱ በወቅቱ ደስ ብሎት አብረን – ተመለስን። አብርሃምን ብዙም እምቀርበው – አልነበረም። እርግጥ ለተለያዬ ሁኔታ ወደ ማህል ሀገር ሲሄድ ከተለያዩ ክ/ሀገራት የሚያገኙት ጓዶቻችን ሲተዋወቃቸው መጀመሪያ የሚጠይቁት እኔን በመሆኑ፤ ይህ ነገርም ሁልጊዜ ስለሚገጥመው እኔ የማልሰጠውን እሱ አብዝቶ ያከብረኛና –  የታደልሽም ይለኝ ነበር። የሆነ ሆኖ ስለማልቀርበው ፈተናውን አልፎ መሄዱ እንደ ሌሎቹ ውስጤን ባዶ አላደረገውም – ነበር። እኔ ከግብርና ሚ/ር ሠራተኝነቴ ነው በጥዋቱ ኢሠፓ ቀለብ – ያደረገኝ። የመስክ ሠራተኛ በመሆኔ ጓደኞቼ በሙሉ ወንዶች – ነበሩ። ፓርቲው ውስጥም funktionary ስሆንም ያው ወደ ቀልቦቼ ነበር የታደምከት። ነገር ግን አብርሃም – አልነበረም። የሆነ ሆኖ አብርሃም የካቲት 66 ኢንስቲቱዩት ሲመረቅ ጎጃም ውስጥ – ተመደበ። ጭንቅ ሰዓት ነበር። ለትምህርት መላኩም ሆነ የተመደበበት ኃላፊነት – አላረካውም። ኩርፊያ – ነገር። እንዲያውም ሁላችንም ከተሰደድን በኋላ ሲነግረኝ አንቺ ወሳኝና ተፈላጊ ብርቅም ስለሆንሽ እኔ ደግሞ ስለማልፈለግ ለወቅቱ ተገፋሁ – ብሎኛል። ይህ ይመስለኛል የወያኔ ሃርነት ትግራይ መጣሁ መጣሁ ይል በነበረበት ወቅት መደበኛ ሠራተኛ ሆኖ በውስጥ የአርበኛ አንጃ ነገር  – ያስፈጠረው።

አጋጣሚው ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሠራዊት ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር የኢትዮጵያን ሰንድቅ ዓላማ የእግሩ ገንባሌና ስንቅ መቋጠሪያ ከረጢት አድርጎ /በዓይኔ ያዬሁት/ ይንቀሳቀስ የነበረበት ጊዜ ነበር። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተሳካለትና መላ ኢትዮጵያን – ተቆጣጠረ። በዚህን ጊዜ አብርሃም አዲስ አባባ ውስጥ ሆኖ በጎጃምና በሽዋ ጫካዎች የአርበኝነት ትግል – ጀመረ፤ በኋላም ወደ አሳደገው ጫካ ወደ ጎንደር አመራ። አዲስ አበባ ውስጥ እያለ የትውልዱ ዓራት ዓይናማ የቤተ ክርስትያን ሊቃውንት አባትን በህወሓት የተገለሉ /አሁን በህይወት የሉም – ነፍስ ይማር/ የትግሉ አካል እንዲሆኑ መጠዬቁን፤ ግን አዎንታዊ ምላሽ እንዳለገኘ፤ ከአዲስ አባባ ከተማ ሳይቀር መሳሪያዎችን በድፈረት በመኪና ወደ ትጥቅ ትግሉ ያጓጉዝ እንደነበር እራሱ በአንደበቱ – ነግሮኛል። ከዛ የወያኔ ሃርነት ትግራይ መረጋጋት ሲጀመር ተነቃበትና በጋዜጣ በራዲዮን መፈለግ – ተጀመረ። እኔ ሥራ ዓለም እያለን „ላንቁሶ – ሞልፋጣው“  የምለው አብርሃም የሽዋና የጎጃምን ጀግኖችን ይዞ ጫካ ለጫካ በአርበኝነት ትግሉን – ቀጠለ። በመጨረሻም ሱዳን ውስጥ እግሩ ችግር – ገጠመው። የተባበሩት መንግሥታት የሰደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን በቂ ዕውቅና ሰጥቶት በጥሩ ሁኔታ ሱዳን ላይ ካቆዬው በኋላ፤ ለህክምና ውጪ ሀገር ተለከ። ከዛ በኋለ ሲድን ኮማንድ ፓስቱን ኡጋንዳ አድርጎ የአርበኝነት ትግሉን – ቀጠለ። ጀርመን እንዲሁም ይመስለኛል ኖርወይ ተጨማሪ አስኳላት – ነበሩት። እደገናም ከጋንቤላ የነፃነት ትግሉ አርበኞች ጋርም የሰመረ ግንኙነት እንደበረው አውቃለሁ – ፍቅሩ አክብሮቱ ልዩም ነበር። በስሜንና የደቡብ ሱዳን ማህል ላይ በነበረው የነፃነት ትግልም ልዩ ተመስጦ ነበረው። ምልከታው መንደር ላይ የቆመ አልነበረም፤ ኢትዮ-  አፍሪካዊነትን / pan africanism/ አብዝቼ አይቸበታለሁ። ዓይነታ ሥነ ምግባሩ እንደ አርበኛ ድርጅት መሪነቱ ሌሎችን ድርጅቶች ሆነ መሪዎችን ሲዘልፍ ሰምቼው – አላውቅም። ሲያደንቅ ሲያከብር እንጂ። እሱ ዬትጥቅ ትግል እያለ ሰላማዊ ትግልን በሚገርም ሁኔታ ያከብር ነበር። ለጠንካራ ሴቶች ያለው ከበረቴም ዝቀሽ ነው። ለሴቶች የእኩልነት መንፈስ ያለው አመለካከት ቃላት – አይገልጸውም። ግን ዕይታዬን አልነግረውም – ነበር። አድንቄውም – አላውቅም። ይልቁንም ተረብ እያበዛሁ ነበር – እማጫውተው – ውስጡኑም እምጎረጎረው። ውጪ ሁለታችንም ከወጣን በኋላ ከልቤ የገቡ እነዚህን እመሳሳላቸውን ወርቅ ብቃቶችን እነሆ ከድኜ ያቆዬኋቸውን ዛሬ ለነፃነት ትግላችን መምህር ይሆኑ ዘንድ አደባባይ እንዲውሉ – ፈቀድኩኝ። ስለዚህ የእሱም በአርበኞች መንፈስ ምሥረታ ታሪካዊ ዘርፍ የሚካተት – ነው። ጀምሮት የነበረውን ትግሉን የት ደረጃ እንዳደረሰው አላውቅም። … አሁን መረጃ የለኝምና።

….. አልፎ አልፎ ጹሑፎችን ኢትዮ ሚዲያ ላይ – አነባለሁ። ትንሽ ሊብራል የመሆን መንፈስ – አይቸባቸዋለሁ። ምክንያቱም ጹሑፎቹ ድፍረት የበዛባቸው – ከረረ ያለ ጸረ ወኔያዊ ጠረናቸው ሆነ ትችቱ እጅግ ጉልበታም እንደነበሩ – ስለማውቅ። ይህም ምክንያታዊ መሆኑ – ይገባኛል። ታሞ ውጪ ሐገር እንዲታከም ሲላክ፤ ወያኔ የዋዛ፤  በስቃዩ ውስጥ መከራውን በመጋራት በቅርብ እረዳትና ተንከባካቢው የወያኔ ሃርነት ትግራይ እጅ ከእሱ ቀድሞ ነበረበት። እነሱ – ያውቁበታል፤ ጠንከራ መንፈስን የረገበ አልጋ ማድረግ። እርግጥ በልጅነት ያው በተሰጠው ቁመና መዝናናት እጅግ አብዝቶ ይወድ ስለነበር ከእኔ እጅግ የባዛ ዬቁጥብነት ባህሪ አንፃር ዬእሱ መንፈስ ቅርቤም ግጥሜም በፍጹም – አልነበረም። … እኔ ብቻ ሳልሆን የእኛ ጉርፕም – ጭምር ። ያን ጊዜ ቲማችን ተደማጭ – በቂ ተቀባይነት የነበረው፤ ሥልጡንና ትኩስ ነበር። ወጣትነት የማትገኝ የአቅም  – ሸጋነት፤ ታዲያንላችሁ ከኮበሌዎቹ ጋር በአባልነት የተመዘገብኩት ሴት ግን እኔ ብቻ ነበርኩኝ – ስለዚህም ብርቅ ነበርኩኝ። ሳቄ የሚናፈቅ – ቀልዴም የሚወደድ – …. ትጋቴ የሚደነቅ … ደከመኝ አልነበረም በእኔ ቤት። በበላዮቼ አመራሮች፣ ባቻዎቼ፣ በምመራቸው የሲቢክስ ማህበራት፤ በተለያዩ አጋጣሚዎች ያገኘኋቸው ታላላቅ ጓዶቼና መሪዎቼ እኔን በሚመለከት ተመሳሳይ ዕድምታ ነበራቸው። ሥርጉተ ማለት በልብ ውስጥ የምትቆዬ ጭራሽም የማትረሳ መሆኗን በህይወት ያሉት – ዛሬም ይመስክራሉ። የተሰጠኝን ምስክርነት ጥበቃዬ ከውስጥ ነበርና። በተዘርክረክ ቦታ ሥርጉተ ዝር ብላ – አታውቀም። ወጣትነቷንም ጭራሽ  አስተውሳው አታውቅም፤ በሴትነት /በፆታ/ አቅሜም በቂ አቅም የነበረው ሙሉ እገዛ – ተደርጎልኛል። ያለኝን ጸጋ ሁሉ አበረክት ዘንድ በሮቹ ቧ ብለው የተከፈቱ ነበሩ። የደረጃ እድገቴም እጅግ ፈጣን ነበር። … እንጃ ከዚህ በኋላ ማግኘት አይደለም በህልሜም ያን መሰል የወል ፍቅር፤ ፈጽሞ የማይጠገብ ትስስር የትም ቦታ ማግኘት – አልቻልኩም። ጥንቁቅ የሆነ ግን የበዛ ማህበራዊነት ከግጥሞቼ ጋር – ነበረኝ። አሁን ግን ቁልፍ ነው። ሰላዩ – በዛ።

የሆነ ሆኖ አብርሃም ሌላም ልዩ ድንቅ ጥናካሬ እንዳለው – ታዝቢያለሁ። ከስደትና ከአርበኝነት ውሎ በኋላ — በውጪ ሀገር

  • እነዛ አዲስ አበባ ላይ እሱን ሆነ ቤተሰቦቹን እንደ እናት እቅፍ አድርገው ሸሽገው የያዙለትን ባለ ኪዳን ቤተሰቦች ልጃቸውን ውጭ ሀገር በማምጣት እንደ ልጁ አድርጎ እጅግ በሚገርም ፍቅር አቆላምጦ – አሳድጓታል።
  • ሌላም ቤተስብ እንዲሁ በዛ ጭንቅ ቀን የተገኙለትን እረዳት ያልነበራቸውን፤ ለቤተሰቡ አጋዥ ይሆኑ ዘንድ ከተለያዩ ቤተሰቦች ሁለት ወንድ ልጆችን፤ ልጆቼ ብሎ ውጭ ሀገር እንዲኖሩ በማደረግ ከቁም ነገር – አድርሷል።
  • በተንቀሳቀሰባቸው የገጠር የሽዋ ትናንሽ ከተሞች የረዱትን በፍጹም – አረሳም፤ የፈረሰና ጥገና የሚያስፈልጋቸውን ቤታቸውን – ሠርቷል፤ የታመሙትን – አስታሟል፤ አራሶችን ሽልንጓን እዬለከ – አርሷል፤ እረዳት ያጡትን በተከታታይነት – ረድቷል፤
  • እሱ ካለበት ከተማ በጋራ ሰብሰብ ብለው ለጉብኝት የሚሄዱ ኢትዮጵያዊ ወገኖችን በኃላፊነት ስሜት – ያስተናግዳል። ልዩ መስተንግዶም – ያዘጋጃል። ባህልና ትውፊትን በባለቤትነት መፍቀድ ለዛውም ስደት ላይ ተሁኖ ቤት ለእንግዳ ማለት ድንቅ ተግባር ነውና ከምጠብቀው በላይ መልካም ነገር – ፈጽሟል። አድናቆቴ በአክብሮት ይድረስህ – አብርሃም፤
  • ኢትዮጵያዊ ወጣት ሴቶች በሞዴልነት ተሳትፎ ሲያደርጉ ግልጥልጥ ብለው ካዬ እጅግ ነው የሚበሳጨው፤ ባህሌ – ትውፊቴ – ታሪኬ፤ ተዛባ የሚል ህመማዊ ስሜት – አይቸበታለሁ። እንኳንስ ሰውነት መጋለጥ አርቲፈሻል ጸጉር በምታደርግ ሴት ይናደዳል። ተፈጥሮን የጣሰ ውበት – ይለዋል። በዚህም እኛነትን በኃላፊነት የመወሰድ ተቆርቋሪነት መሆኑን አስተውዬበታለሁ፤
  • እጅግ እማከብርለት እማደንቅለትም ሸበላ ተግባር ደግሞ እሱ በሚኖርበት ከተማ፤ ወጣት ኢትዮጵውያን በት/ቤት በክብር ማዕረግ ሲመረቁ የተለዬ ዝግጅት በማደረግ አድናቆቱን የሚገልጽበት ሥርዓቱ ልቤን እና መንፈሴን አብዝቶ – ይማርከዋል። ለዚህም ነው ግድፈት ግድፈት የሚያሰኛቸውን የአቅም ድሃ ያልሆኑ ወንድሞቼን ብዙ ክፍት ቦታዎች አሉ፤ ቀዳዳችን ብዙ ነው፤ ያልታዩና ያልደረስንባቸውን ቦታዎች ስላሉን ህሊናችሁን ወደዛ ብታሰማሩ በማለት ጠቋሚ ሃሳብ – የማቀርበው።
  • ሌላው ሰው የመርዳት አቅሙና ፍላጎቱ ላቅ ያለ ነው። ኬኒያ ላይ ለሞተ ጓዳችን የትዳር አጋሩም ማለፏን ሲሰማ ልጆቹን ወደ ውጪ ለማውጣት ሲያሰተባብር እንደነበረ – አውቃለሁ። ከዚህም ባለፈ አንድ የተዋህዶ አባት እዚህ ሲዊዘርላንድ ውስጥ ከማህበረ ምዕመናን ጋር የበዛ መግባባት የነበራቸው፤ የተግባርም ት/ቤት የነበሩ ነበሩ። እና እሳቸው የሲዊዝ የስደተኛ ቢሮ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ሲወስንባቸው – አማከርኩት፤ የመጡበትን አካባቢ ሳይጠይቀኝ በሚኖርበት ሀገር ካህን የሚፈልጉ ወገኖችን ፈልጎ ካገኘ በኋላ፤ እስፓንሰር ለመሆን ፈቅዶ አግኝቶ በስልክ ሲያነጋግራቸው „ስደት በቃኝ። ከእኔ ይልቅ ግብጽ ውስጥ በእንግልት ያሉ አባት አሉና እርሳቸውን እርዳልኝ አሉት።“ ከዚህ ላይ አንድ ነገር መስታወስ – እሻለሁ። እሳቸው ወደ አገኘላቸው ቦታ ቢፈቅዱ ኖሮ፤ እሱም አብሮ ሽፍት ማደረግ እንደሚችል ነበር – የነገረኝ። ብቸኝነት አባታቸን ሊሰማቸው አይገባም ባይ ነበረ። ከዛም በኋላ ግብጽ ላይ ከነበሩት አባት ጋር ተገናኝቷል – በምን ሁኔታ ጉዳዩ እንዳለቀ – አላውቅም። ሌላው ግን የእሱን አቅም ቀጣይነት ምን በላው ለሚለው፤ ሁለት ነገር ይመስለኛል። አንደኛው – ለአርበኝነት ውሎ የኮማንድ ፖስቱ ማዕከል ከመሬቱ መራቅ ጋና አክራ መሆኑ ተጽዕኖው ቀላል – አልነበረም። በራሱ መንገድና ገቢም ነበር የሚንቀሳቀሰው፤ ለዚህም ነው ብዙ ሰው የማያውቀው፤ ሁለተኛው ደግሞ ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት ውጪ ሀገር ለህክምና ሲሄድ የጠበቀው የታቅደ ወጥመድ – ነበር። እርዳታ ማግኘቱ መልካም ሆኖ ሳለ ያልተጠነቀቀበት ፍሬ ነገር – ያለ ይመስለኛል፤ ብቻ ለመቁረጥ አቅም – አነሰው። ውለታን አላውቅህም ለማለት ለዛውም በባዕድ ሀገር በታማሚነት ዓይን የከበደው – ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊ ይሉኝታ „ፈርሃ እግዚአብሄር“ ያጠቃዋል። የሚበልጥበትን መወሰን የሚችል እሱ ብቻ ነው። እርግጥነው አሜሪካ የሚኖሩ ብልህና ጠንካራ ቤተሶቹ ችግሩን ከሥሩ ለመንቀል መላ መተው – ነበር። ታግለዋል – ግን የቻሉ – አይመስለኝም። ይህ ማለት ግን በወያኔ ሃርነት ትግራይ ሀገር አጥፊነት ላይ ይደራደራል የሚል ዕድምታ እኔ በግሌ – የለኝም። የሰንደቅ ዓላማው ሆነ የነገረ ኢትዮጵያ ሚስጢራዊ ክህሎት ጉዳይ ፍቺው ሆነ ትርጉሙም በአብርኃም ህይወት ውስጥ ልዩ መሆናቸውን አሳምሬ አውቃለሁ እና። አብሶ ከተማረ በኋላ በብዙ ነገሮች ተለወጦ እጅግም በስሎ ነበር – ያገኘሁት።
  • የሌሎች ነፃነት ፈላጊ ድርጅቶችን አይነቅፍም። አሁን ቅንጅትን እንዴት ይወደው ነበር መሰላችሁ። ተግባራቸውንም ያደንቃል። „ትንሳኤ“ ራዲዮንን ደስ ብሎት ነበር – የሚከታተለው። ይህን ቅንነት በብዙዎቹ የድርጀት መሪዎች – አላይም። አዝናለሁ።
  • ብሄራዊ ክብርና የነፃነት ፍላጎት ቀጨጨ በሚልበት ቦታ ላይ ደግሞ የራሳችነን ገመናን ሚዲያ ላይ ሳይዘረግፍ፤ በቀጥታ ለሚመለከታቸው አካላት ደፋር ደብዳቤዎችን፤ ማሳሳቢያዎችን – ይጽፋል። ይህ ደግሞ ድርብ ጥቅም አለው።
  1. መቸም ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰፊ የሆነ የውጊያ ቀጣና ከገጠመው ቦታ ውስጥ አብዩ ደቡብ ጎንደር ላይ ነበር። ረጅም ጊዜ ነበር የውጊያው ቆይታ። የኢትዮጵያ ሠራዊትና የሀገሬው አርበኞች ቦታቸውን ሳያስደፍሩ ሞጥረው በጀግንነት በሚያኮራ አኳኋን ነበር – የተዋጉት። የፋርጣ አውራጃ አስተዳዳሪ የነበረው ሻ/ አጥናፉ ገላው ያ እናት ሆዱ – ወዳጄም፤ የተግባር አባቴም በውጊያው – ተሰዋ። እና ሌሎችም። የወያኔ ሃርነት ትግራይ የደቡብ ጎንደርን እርእሰ ከተማ ደብረታቦርን ሙሉ ለሙሉ ሲቆጣጠር፤ በወቅቱ የደቡብ ጎንደር ክ/ሀገር ኢሠፓ አንደኛ ጸሐፊ የነበሩት አርበኛ ጄ/ ኃይሌ መለስ ለወያኔ ኃርነት ትግራይ ለሰከንድ ሳይገዙ „አሻምን በተባ ተግባር ታጥቀው – ከፋኝ በማለት“ ትግሉን በጎንደር ጫካዎች – ጀመሩ፤ በወቅቱ ሰፊ የሆነ የማጥቃት እርምጃ መውሰድ ብቻ ሳይሆን የወያኔ ኃርነት ትግራይ እንቅልፍ ያጣበት፤ የተቁነጠነጠበት፤ ስጋት ላይ የወደቀበት ወቅት – ነበር። እኔም በርቀት እዛው ዱር ወስጥ ነበርኩኝና በገብያ ለመረጃ የምልካቸው ገበሬዎች ዜናውን ያመጡልኝ ነበር። ከእሳቸው ጋር ለመገናኘት ግን የሚያመች ሁኔታ ላይ – አልነበርኩም። ከዛም ወደ ሱዳን አርበኞቻቸውን ይዘው መጓዛቸውን – ሰማሁኝ። አሁን በህይወት ኖይዝላንድ ስላሉ ሂደቱንና ዕውነተኛ ታሪኩን አቅርቦ መጠዬቅ የሚቻል – ይመስለኛል። ኢሳትን „እሳት“ ያሉትም እሳቸው ናቸው። አርበኛ ጄ/ ኃይሌ መለስ ጠላትና ወዳጃቸውን የሚለዩ ስለሆነ በአቋማቸው እንደሚጸኑ – አምናለሁ። እኔም ልጃቸው እና የበታቻቸው ያለኝን ዘመን የማይሽረው አክብሮትና አድናቆት በአጋጣሚው – እግልጽላቸዋለሁ። መኩሪያ ናቸውና! በሥራም እሳቸው ግር ሊላቸው ቢችልም እኔ ግን በአካል – አውቃቸዋለሁ … ብዙ ስብሰባዎችን አብረን – ታድመናልና።
  2. ሌላው የአርበኝነት መንፈስ ኮማንድ ፓስቱ ኬኒያ ላይ የነበረ ከኢትዮጵያ መንግሥት ፍረሰት በኋላ ትውልድ ከቶውንም ሊተካቸው በማይችለው፤ ለወጣት ወገናቸው ችግር እናት ሆዱ በነበሩት፤ በፈላስፋውና በሳይንቲስት ኢንጂነር ቅጣው መሥራችነት ባለ ተስፋ ዬአርበኝነት ውሎም – ነበር። „የኢትዮጵያ አንድነት ብሄራዊ ግንባር“ ‚በሁልአቀፍ‘ መርህ ወቅቱን በተግባር በአርበኝነት መንፈስ – አስጊጦት ነበር። መንፈስን ለወቅቱ – ሰብስቧል። በአጋጣሚ ዕድሌ ውብ ነውና አብሮ ከተጓዛቸው ውስጥ ከሙሉ ሥነ ምግባር ጋር፤ ቀድም ብሎ በአቻነት በክፍል ኃላፊነት ከእኔው ጋር የሠራ፤ በኋላ ከእነ አብርኃም በፊት በነበረው ኮርስ ላይ ታዳሚ የነበረው፤ በየካቲት 66 የፖለቲካል ሳይስንስ ኢንስቲቲዩት የ2 ዓመት ትምህርቱን ሲያጠናቅቅ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀው፤ የክ/ሀገር ኢሠፓ ኮሜቴ የድርጅት ጉዳይ ኃላፈ ሆኖ የተመደበው ጓደኛዬ እና እብሮ አደጌም ከሳይንቲስ እንጂነር ቅጣው ጋር ወደ ኤርትራ ከተጓዙት የመጀመሪያዎቹ ውስጥ አንዱ ነበር። ጓድ ገ/መድህን በርጋ እንደ እኔ አብዝቶ ይሳሳለት ነበር። ሙሉውን አቅም ከእርሱ ነበር የወረሰ፤ በዛ ከእሳት ከውሃ ይባልበት በነበረበት የወጣትነት አፍላ ዕድሜ ላይ ቁጥብ – የተረጋጋ – እጅግ የሰነከነ – መቀመጥ የማይሰለቸው – ማድመጥ አድባሩ የሆነ፤ ብሩኽና ሁልአቀፍ የህሊና አቅም የነበረው ጸባይማም ነበር፤ አንድ ቀን ሲበሳጭ ሲቆጣ አይቼው – አላውቅም። ከመናገር የተቆጠበ የተግባር ዓፄ ነበር። የሚገርመው ምክትሉም በኋላ እሱን የተካው እንደ እሱ – ነበር። ዛሬ ሁለቱም ውጪ ሀገር ይኖራሉ። ትግሉን የተውት ይመስለኛል። እንዲያውም በእኔ ደረጃ ከነበሩት እኔ ብቻ ነኝ ያለሁት። ሴትማ ፈጽሞም – አይታሰብም። ለማንኛውም እኔ በሁለገብ ብቃቱ ልምዱና ተመክሮው አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን መንፈስ የመተካት አቅም ያለው ብቁ አርበኛ ነው የምለው ነው። ያን ጊዜ ወላጅ እናቱ የቅዱስ ገብርኤል የስለት ልጅ ስለነበር ከወሎ ክ/ሀገር ቤታቸውን ትተው፤ ኑሯቸውን አፍረሰው መጥተው ከእሱ ጋር ጎንደር ለመኖር – ወሰኑ። እማ መጀመሪያ ያዩኝ ዕለት ነበር „ጸጋ“ ብለው የጠሩኝ። ዛሬ እኔ እንዲህ በብላቴ ጸጋዬ ገ/መድህን ፍቅር ዙሪያ ስታቀፍ በቅርብ ቀን ነው ትንቢታቸው – የገባኝ። የኢትዮጵያ ሴቶች ብልህነታቸው – ይቀድማል – ጥልቆች! እማ ይህም ብቻ አልነበረም ተልዕኳቸው „ከእኔ ቤተሰቦች ጋር ወሎ አብሮ አድጓል፤ ይህ ግንጥል ጌጥ ነው“ በማለት የአባቱን ቤተሰቦች በጎንደር ገጠሮች አፈላልገው እሱ ሳያውቅ – አገናኙት። የአባቱን የወንድም ልጅም ኃላፊነቱን ወስደው ያስተምሩ – ነበር።

መናሻና መድረሻው ሲገናኙ – የዕድምታዬ።

ሽበት በሆድ የበቀለ ዕለት ክብርን – ይሸልማል። የአቶ መልኬ መንግሥቴ የአርበኞች ግንባር መሥራችነት ሳዳምጥ ከልቤ ነበር ያዘንኩት። አቶ መልኬ መንግሥቴ የአርበኞች ግንባር መሥራች አባልነት ከታሪክም ከእውነትም ጋር ሲታይ በዕብለት የተጀቦነ ለባዶነት – የተመረጠ ስለሆነ። አይደለም በምሥራታው፤ በመንፈሱ በእውነት – አለነበሩበትም። ከሚያድር ነገር ላይ ማረፍ ምንኛ – መታደል ነው። የነገ ሰውስ መሆን ምንኛ – ረድኤት ነው። ውዶቼ የሀገሬ ልጆች – የሚገባነን ክብር ብቻ – እንቀበል፤ የማይገባን ግን የተውሶ ነውና – ልንጸዬፈው ይገባል። አይሰነብትምና። እንትን ታውቃላችሁ? … በረዶ …  ስለዚህ ባልዋሉበት ባልነበሩበት የተሰጠው ልብድ ክብር – ቀላጭ ነው ዬጭቃ እራት። የአደራ ተቀባይነት መንፈሱም –  ፍልስ ነው፤ ተከታይም አይኖረውም። አብዛኛውን የጎረቤት ሀገሮች በአገኙት አጋጣሚ ያዩት አዛውንት ዕድሜቸው የፈቀደውን፤ መሆን የቻሉትን፤ የዕውቀት ደረጃቸው የመጠነውን ያህል እንደ ዜጋ በሚያምኑበት መስመር ማድረጋቸውን – ግን አከብራለሁ። ትልልፉ ግን – አይመችም። እንደገናም በዚህ ምስቅልቅል ሁኔታ መዳከሩም የውስጥን የራስን ሰላም – ይቀማል። ለምን እንደ መረጡት – በፍጹም አላውቅም። ሌላው ግን  በአዲሱ አውሎ የተለጋ መንፈስ በተቃራኒውም ወገንም አድምጫለሁ። ግንቦት 7 ዓላማውን ሲያስተዋውቅ አቅሙን በመመልከት በፍርሃት ተውጠው „ሊሻማ“ ደግሞ መጣ በማለት በቅናት ድብን ብለው ድንኳን ጥለው ሐዘን ላይ የተቀመጡ፤ በመንደርተኝነት ስሜት እያደኑ ሰዎችን ያግባቡ፣ ያስተባብሩ የነበሩ፤ ምስክሮች ተቀምጠን ዛሬ ደግሞ ስለታችን ሰምሮ ግንቦት 7 ቁልፉን ኃላፊነት ወሰደ ብለው ሲፈነጥዙ፤ እነሱ ዘመንተኛ ሌላው ተግባር ላይ ያለው አጥር አልባ የሚማስነው መከረኛ ደግሞ ዕትብቱ ተፈልጎ ተወቃሽ ሲሆን፤ ህሊና ከአካል ቀድሞ ቀብር የተበዬነበት ስለመሆኑ ግራ ቀኙን የምንታዘብ ሰዎች ጉድና ጅራት – ብለናል። አጥቂ ሃሳብን ማድነቅ – መከተል – ተባባሪነትን ማሳዬት፤ አብሮ ለመሆን ከልብ መፍቀድ መልካም ሆኖ ሳለ ከእኔ ወዲያ ላሳር ማለት ግን …. ትናንትን መዝላል – ሽበትንም -ማቃጣል ይሆናል። ስለዚህ ግድፈቱ የእርስዎ ብቻ አይደለም። ማተበኛ ቦታ ተፈጥራችሁ ማተባችሁን ብትጠብቁ መልካም ነው። ከሁሉ የሚከፋው እራስን መዝረፍ ነው።

ምራቂ – መረጃ።

እኔ አቶ መልኬ በአካል – እጅግ በደርበቡ – አውቃቸዋለሁ። በ2008 መጨረሻ ከታህሳስ 18 ጀምሮ እስከ 24 ድረስ የG7 ስበሰባ ኃያላን ሐገሮች ስብሰባ የሄሮድስ መለስ ዜናዊን አስተዳደር የተቃውሞ ሰልፍ ለመሳተፍ ኮፕን ሀገን ዴንማርክ ሄጄ – ነበር። ያን ጊዜ በሙሉ ትጥቅ ነበር – የተገኙት። ዝግጅቱ የሁሉም  አውሮፓ አቀፍ ተሳታፊ የአጋርነት መሰናዶና እርዳታ ያስፈልገው – ስለነበር። ለዚህም ክብርት ባለቤታቸው ለነባራቸው የተሟላ ቅናዊ ተሳትፎና ሸግዬ ትህትና የበቃ መሰናዶ ምስጋናዬ የላቀ ነው። የዛሬን አያድርገውና የአቶ መልኬ መንግሥቴ መገኘት ተልዕኳችን ግርማ እንዲኖረው አድርጎት ነበር። ትናንት ለዛሬ እንጀራ እንዳይሆን እርሾውን እንዳለ መድፋት – የተገባ አይደለምና። ሌላው ቀርቶ ድክመቶች ከጥንካሬ በላይ ት/ቤቶችም ናቸው – ከምንጥላቸው ሆነ አያስፈልጉነም ከምንላቸውም ቢሆን እምንማርባቸው ዕንቁ ብልሃቶች – ይኖራሉና።

የዛን ጊዜ ዬገጠሙኝ ደመ ግቡ  እና ጠያይም ሁኔታዎች።

ደመ ግቡ – በሐሤት የፈነጠዝኩበት የቤቴን የከረንት አፊርስ ተናፋቂ – ፍቅራቸው የማይጠገበውን እህትና ወንድሞቼን በአካል – ማግኘቴ ነበር። አዬ ከረንት ትንሿ ኢትዮጵያ – የናፍቆት ማዕዶት፤ ፍቅሩ ሁልጊዜ – ያታል። ሌሎችንም አውሮፓ አቀፍ የነፃነቱ ትግሉ አባ እና እም ወራ ቤተኞች ጋር በመገናኘቴ – ውስጣቸውን በጥልቀት በማዬትም፤ ለዚህ በመታደሌም፤ ደስታዬ ወደር የለውም። ከሄድኩባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች ውስጥ አብዛኞቹ በአዘጋጆች ሙሉ ፈቃድ ተሰጥቶኝ ተልዕኮዬን – አሳክቻለሁ። ድካሜንም በፍሰኃ አወራርጃለሁ – ልበል። ወደ ቤቴ ስመለስ ፍጹም – ሰላም ነበረኝ።

ጠያይሞቹ – የታገሉኝ ሁኔታዎች፤ አንደኛው ይዤያቸው ከነበሩት በርካታ ፓስተሮችና ፍላዬሮች ውስጥ በወያኔ ሃርነት ትግራይ መፈንቅለ መንግሥት ተጠርጥረው የታሰሩት የእነ ጄኒራል አሳምነው ጽጌ እና በተለይም የአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ አባት  ዬአዛውንቱ እስር ሁኔታ ደሜን ነበር – የመረመረው። እንዲሁም የሌሎችንም ወገኖቼም። ስለሆነም ተዘጋጅቸበት ስለነበር – ይህ አልተፈቀደልኝም – ነበር። እስካሁንም ለምን? የሚለው መልስ አላገኘሁም። በእነሱ ዙሪያ ሚዲያ ላይም የማዬው ነገር እንብዛም – የለም፤ ምን አልባት የችግራችን መጫጫን ወይንም በችግራችን በብዛት መዋጣችን ሊሆን –  ይችላል። አዳዲስ ችግሮች ፋታ ስለነሱን …. ይሆን? ለነገሩ ሴት ጀግና እህቶቼና ጀግና ጦማርያን ከእሥር ተፈተው እኔ እራሴ እንኳን ደስ አለን ለማለት – አልቻልኩም። በሌሎች ነገሮች – ስለጠመድኩኝ።

– ሌላው ጠይም ገጠመኝ – አቶ መልኬ መንግሥቴ ጊዜ ወስደው በከረንቱ ዬፓልቶክ ተሳትፎዬ ላይ አበክረው በተደጋጋሚ አባታዊ፣ ታላቃዊ፣ አዛውንታዊ ተጽዕኖ ለማሳደር ያደረጉት ሙከራ ነበር። ታስታውሱ ከሆነ በወቅቱ የተከበሩ ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል የቅድሚያ ድርድር ፊርማ መሰናዶ ከሟቹ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ጋር ያደረጉትን ዬሂደቱን ጅምር አብዝቼ እታገልም እከራከር – ስለነበር። ይህ አልተመቻቸውም – ነበር። እሳቸው በአካላቸው ማታ ማታ በአርበኞች ግንባር ጉዳይ ላይ ሲከራከሩ ያመሹ ነበር። አንዲያውም ዛሬ በቃለ ምልሱ በኰ/ ታደሰ ሙሉነህ ጉዳይ ተቆርቋሪ ሆነው – አዳምጫለሁ። ያን ጊዜ ደግሞ ድርጊቱን በተከላካይነት በባዕድነት ከአንዲት እህታችን ጋር ሲከራከሩ ያመሹ ነበር።  መቼም ግራ ነው – ይህ ሰው የሚባለው ፍጡር። ቀን ላይ ደግሞ በመንፈሳቸው ሌላ ቦታ ላይ ነበሩ። ሁለቱም መብታቸው ቢሆንም የራሳቸው መንፈስ በቂ ሆኖ ሳለ ሌላ ለመዝረፍ ማሰባቸው ተጨማሪ ልብ ዬመፈለግ ስስታምነታቸው ገርሞኝ ነበር። ስለሆነም ልባቸውን ሊያሰገቡልኝ ያደረጉት ጥረት ባክኖ – የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል። በነፃነት የማሰብ፣ የመናገር ነፃነቴን የተጋፋ ዕይታ – ነበራቸው። እንደ ዕድል ሆኖ እኔ በአንድ አጋጣሚ በሆነ መሥመር ሰው ከገኘሁ በኋላ፤  … መንፈሴን መቆጣጠር – ይፈለጋል። ይህ ደግሞ የህልም መንገድ ነው። በታምር ዬማይሆን ነው። እኔነቴን ሳያውቁ ስለሆነ የሚጀመሩት ሙከራው ተኖ – ይቀራል። ለዚህም ነው ዛሬ በእኔ ጉዳይ ላይ ትንሽ ያነሳሳሁት፤ የሆነ ሆኖ አጋጣሚውን ታከው የሚጀመሩ ግንኙነቶች ልደታቸውን ሳያከበሩ በነው ይቀራሉ። የሚቻል ነገር ለማድረግ ተፈላጊውን መንፈስ በጥልቀት የማወቅን አቅም – ይጠይቃል። ይሄ ድንቡልቡል የሥነ -ልቦና ቅኝ ተገዢነት ግጥሜ አይደለም።

በነፃነት ፍለጋ መንገዴ ሆነ በኑሮ መርሆቼ እናቴም አትችልም። … እማምንበትን ብቻ ነው የምሆነው። ነፃነቴ ከእኔ ሰብዕና በላይ ክብር አለው። እርግጥ ነው ሳይሳካ ሲቀር ያው ቻሉኝ የሚል ጦር ይታዘዝብኛል ይህም ሠርጌ ነው – የምፍነሸነሽበት። ለእኔ ዬሚቀር – የለም። እንዲያውም ለጤናዬ ተፈላጊ ነው በቂ እረፍት አገኛለሁ። … ዘመን የሰጠኝ እጅግ ያሰበሉ – የበሰሉ አጋጣሚዎችም …. ወፍ ያወጣቸው ልዩ – ልዩ ተመክሮዎቼ … የተማርኩባቸው ሐዋርያ ብቁ ወገኖቼ፤ ጽሞናዊ አስተዳደጌ፤ የተፈጥረኩበት ዕለትም ለዚህ ሽምቅቅ የትውስት ሰብዕና ቦታ በፍጹም – የላቸውም። የሆነ ሆኖ በአንድ ቤት – በአንድ ማዕድ – እጅግ ከተባረኩ የትዳር አጋር ቤተሰቦች ሰንበትን ዴንማርክ ኮፕን ሀገን …. ግን እኔና አቶ መልኬ – አልቀጠልነም። የተገባም ስንብትም – አላደረግንም — ዬልባቸውን አላደረስኩምና። … እኔን የሚያዘኝ ህሊናዬና የማዬው የእውነት ማህለቅ ብቻ ነው። …. ለእኔ ጉዞ ሹፌሯ እኔው ብቻ ነኝ። ይህ በገጸ በረከትነት ለማንም – አይሸለመም።  የፈጣሪዬ የሰውነት ሥጦታ ሥርጉተን ብቻ እንዲተረጎም ሆኖ ነው – የተፈጠረው። ከዚህ ጸጋ ከወጣች ሥርጉተ – መሆኗ  … ቀርቶ ቀፎ ብቻ ትሆናለች ወይንም ግፋፎ። እንደ እራስ ለመኖር የፈቀደ ሰብዕና ቀጥ ባለ ግልጽነት፤ በቋሚ ፅናት፤ እራሱን ሆኖ – ይኖራል። ሲያልፍም ሥሙም እሱን እንደ ገለጸ – ይበለጽጋል።

የኔዎቹ ከመሰናበቴ በፊት አንድ የቤት ሥራ ልስጣችሁ – ትፈቅዳላችሁን? አንዲት የዶሮ ላባ ጸጉርን ነቅላችሁ ሚዛን ላይ አስቀምጡና ቁጥሩን የሚዛኑን feedback ለማንበብ – ሞክሩ። ድምስ ነው የሚሆነው። እና አቶ መልኬ በጎንደር ህዝብ ላይ ሊያሳድሩት የሚችሉት ተጽዕኖ ለእኔ ምንም ነው። በልበ ሙሉነት ነው ወገኖቼ – የምነግራችሁ። የሚታወቁ ሰውም – አይደሉም። ወያኔ ኃርነት ትግራይ ከሱዳን አስመጥቶ በእስር የገደላቸው አርበኛ ሻ/ አጣናው ዋሴ ቢሆን ኖሮ አዎን – እርግጥ ነው ይቻላሉ። … ኮከብና ዕውቅ ያላቸው ጀግና ናቸውና – ለማህበረሰቡ። ሞዴልም ናቸው። ሥማቸውም ተፈሪነቱ ዘመን ዘለቅ ነው። ወይንም ጀግና ራስ አሞራው ውብነህ ቢሆኑ ጉልቱ ናቸው – ለአርበኛውም ሆነ ለጎንደር ህዝብ። አቶ መልኬ መንግሥቴ ግን በምን አቅማቸው?! ጫና ያለው ተጽዕኖ ለማሳደር አይችሉም። መጠሪያ ሥማቸው ከቤተሰባቸው ወይንም አብረዋቸው በሥራ ገበታ ከሚያውቋቸው በስተቀር የተቀባይነት ሆነ የዕውቅና አቅም – የለውም። … አሁንም በጣም በእርግጠኝነት። ኤርትራ ላይ በአርበኞች ዙሪያ የነበረውን የተግባር ተሳትፎ ሆነ የቅሬታ ጽንስ – መሬቱን ረግጬው ስለማላውቅ ማን ምን ሠራ? ምንስ ሁኔታ – ተፈጠረ? ለሚለው ዕውቀት – የለኝም። እርግጥ የቀድሞው ዬአርበኞች ዬትግል ሂደት ትርምስን በተደሞ በተለያዬ ሁኔታ ሳዳምጥ ቆይቻለሁ፤ ሊያገኙኝ ለፈለጉትም መልስ በወቅቱ – ሰጥቻለሁ። ጹሑፍ ሲወጣ – አነባለሁ፤ ከዚህ ባለፈ ግን ብዕሬም ሆነ አንደበቴ ቁጥብ ሆኖ ነው – የኖረው። ህውከት፤ የኮፒ ራይት፤ የብቁ መሪ ዕጦት ጉዳይ አብዝቶ ይንጠው በነበረው የቀደመው ዬአርበኞች አቅም ብቅ ጥልቅ … ማለትን በጭራሽ – አልሞከርኩትም። እግዚአብሄር – ይመስገን።

የኔዎቹ – ለነበርን ወግ ያለው ቆይታ ከልብ – አመሰገንኩኝ – ክብረቶቼን። ተሸብልሎ የቀረበውን የነፃነት ፈላጊነት ሸንኮፍ ገለጥለጥ ማድርግ – እንዲህ ይገባል። አቶ መልኬ መንግሥቴ ይህ ዓይነቱን መገለብ አስኝቷቸው ነውና አደባባይ የወጡት፤ ልረዳቸው – አልቻልኩም። ዳኝቱን ለህዝብ – ህሊና። የልቤን አድራሹን ዘሃበሻን እጅግ አመሰግናለሁ። ኑሩልኝ – ውድድድድድ ….

አርበኛነት የዘመን ሥጦታ – የፈጣሪ ምርቃትነቱ ምስክሩ አድሮ የሚገኝ የተግባር ማህደር ብቻ ነው!

አርበኛነት በሙሉ ሥነ – ምግባር የበለጸገ – አብነትነት፤ በሂደቱ የማይታፈርበት፤ የመሆን መቻል – ሰማዕትነት ነው!

ትጥቁን የፈታ አርበኝነት ኑሮ አያውቅም፤ ምክንያቱም ነፍሱ ከሥጋው የተለዬችው ከመፈጠሩ በፊት ሙትቻ ሆኖ ነውና!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

Hiber Radio፡ በኢትዮጵያ መንግስት በሚዲያ የጦርነት ቅስቀሳ ጀመረ፣የጋሞ ብሄረሰብ አገዛዙ በቃን ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድራለን አሉ፣ኤርትራ በማንኛውም ሰዓት ኢትዮጵያ ልትወረኝ ትችላለች አለች፣በአርባ ምንጭ ወንድሙ የነጻነት ትግሉን በመቀላቀሉ አንድ ወጣት በደህነቶች ተይዞ ከፍተኛ ማሰቃየት ተፈጸመበት ብገደል ሀላፊነቱ የመንግስት ነው ብሏል፣የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች ለእንግሊዝ መንግስት በምሬት ተማጽኖ አቀረቡ፣የጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ እና የኤድዋርዶ ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም

0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 26 ቀን 2007 ፕሮግራም

ሀዴ አንበሴ የጋሞ ብሄረሰብ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው ቁጣቸውን ስለገለጹበት ተቃውሞ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ የፕ/ት ኦባማ ጉዞ እና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን የፍርድ ቤት ሂደት በተመለከተ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የታሪክ ተራኪው ኤድዋርዶ ባይኖሮ የአቡነ ጴጥሮስን 79ነኛ የሰማዕትነት መታሰቢያ አስመልክጦ ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የፕ/ት ኦባማ የኢትዮጵያው የይስሙላ ምርጫ ውጤት ላይ የሰጡት አወዛጋቢ አስተያየትና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ( ልዩ ጥንቅር)

አሜሪካና ዙምባብዌን እያወዛገበ ያለው ሰሞነኛ የአንበሳ ጉዳይ ( ልዩ ዘገባ)

በቬጋስ የታክሲ እንቅስቃሴ ላይ የተጋረጡት ፈተናዎች እና በቅርቡ የተጨመሩ ታክሲዎች በአሽከርካሪው ሕይወት ላይ የፈጠሩት ጫና (ቃለ መጠይቅ)

የኢትዮጵያን ቀን በቬጋስ ለማክበር እየተደረገ ያለው ዝግጅት(ውይይት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

መንግስት የጦርነት ቅስቀሳ በመገናኛ ብዙሃን ጀመረ

አርበኞች ግንቦት ሰባትን የሚያጥላላ ዶክመንተሪ እየተዘጋጀ ነው

ኤርትራ በማንኛውም ሰዓት በኢትዮጵያ ልወረር እንደምትችል የፕ/ት ኢሳያስ አማካሪ ገለጹ

የጋሞ ብሄረሰብ አባላት በመንግስት በጀት ታትሞ ባንቋሸሻቸው መጽሐፍ ሳቢያ በቃን ራሳችንን እናስተዳድራለን ሲሉ በሰልፍ ተቃውሟቸውን ገለጹ

በአርባ ምንጭ አንድ ወጣት ወንድሞ ወደ ኤርትራ በመሄዱ በደህነቶች ተደብድቦ ጉዳት ደረሰበት

ብገደል ተጠያቂው መንግስት መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይወቅልኝ ብሏል

የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች እንግሊዝ ተገቢውን ጫና እንድታደርግ ጠየቁ

የኦሳማ ቢን ላድን እናትና እህቱ እንግሊዝ ውስጥ የግል አውሮፕላናቸው ተከስክሶ ሞቱ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ግምገማ አባላቱን ከሁለት ከፈለ

Previous: Hiber Radio፡ በኢትዮጵያ መንግስት በሚዲያ የጦርነት ቅስቀሳ ጀመረ፣የጋሞ ብሄረሰብ አገዛዙ በቃን ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድራለን አሉ፣ኤርትራ በማንኛውም ሰዓት ኢትዮጵያ ልትወረኝ ትችላለች አለች፣በአርባ ምንጭ ወንድሙ የነጻነት ትግሉን በመቀላቀሉ አንድ ወጣት በደህነቶች ተይዞ ከፍተኛ ማሰቃየት ተፈጸመበት ብገደል ሀላፊነቱ የመንግስት ነው ብሏል፣የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች ለእንግሊዝ መንግስት በምሬት ተማጽኖ አቀረቡ፣የጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ እና የኤድዋርዶ ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም
0
0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃው በሚገኙ በኢህአዴግ ድርጅት ኃላፊዎች የተመራውና በተያዘው በጀት ዓመት ከተማዋን ይመራሉ ተብለው የሚሾሙ የድርጅት ካድሬዎችን የሚለይበት የከተማና የክ/ከተማ ከፍተኛ የግምገማ መድረክ አጋማሹን ካድሬ አስደስቶ አጋማሹን ደግሞ አሳዝኖና አበሳጭቶ ተጠናቋል፡፡
addis-ababa-realethiopia-141
በሃምሌ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ የተጀመረው ይህ ግምገማ በልዩ ትኩረት አጀንዳ ተቀርፆለት በተቀመጠለት መርሃ ግብር መሰረት በአጠቃላይ 20 ቀን የፈጀ ሲሆን ፣ ባለፈው ዓርብ ሃምሌ 24 ቀን 2007 ዓ.ም በከተማ ደረጃ የሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮችን መድረኩ ከገመገመ በኋላ ለከፊሎቹ አዛዛኝ ጊዜ ሆኖ ተጠናቋል፡፡
ይህ ተከታታይ ግምገማ በከተማና በክ/ከተማ የሚገኙ የኢህአዴግ አመራሮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ በየደረጃው የስራ ባህሪያቸው የሚመሳሰሉትን አመራሮች አካቶ በዞን ተካፋፍሎ ተገምግሟል።

በተለያዩ መድረኮች ማለትም የአዲስ አበባ ም/ቤትን ጨምሮ የከተማው ቁልፍ ካድሬዎች የመሩት ግምገማ ሲሆን፣ በግምገማው በከተማው ቀጣይ አመራር ሆኖ የሚቀጥልና የማይቀጥል በሚል የሚለዩበት ሆኖ ተጠናቋል፡፡

ግምገማው ከፍተኛ ጭቅጭቅ የተነሳበት፤በአመራሮች መካከል ስድብ ቀረሽ ዘለፋ የተካሄደበት፤ አንዱ ሌላውን ለመጣል ጓደኛ እና ጓደኛ የተጣላበት፤ በስራ እና በአመራር ቆይታ ወቅት በነበሩ የስራ አፈፃፀም ወቅት የነበራቸውን ጥንካሬና ድክመት ሳይገለጹ የቀሩበትና ዕርስ በዕርስ የተካካዱበት ግምገማ ሆኖ ተጠናቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የግምገማው ውጤት በአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት ደረጃ በቅርቡ ባሉበት ሹመት ደረጃ የሚቀጥሉና የማይቀጥሉ እንዲሁም ከአመራር የሚባረሩ በሚል የመጨረሻ የውጤት ደረጃ እስከሚገለጽ ድረስ እየተጠበቀ ነው።

ከወዲሁ የሚቀጥሉና የማይቀጥሉ ካድሬዎችን ለመለየት በሚያስችል ደረጃ በግምገማው ላይ የተለየ ሲሆን፣ ከማይቀጥሉ ወገን ያሉት አመራሮች ብስጭታቸውን ለማስታገስ የህመም ፈቃድና ማህበራዊ ጉዳዮችን ሰበብ በማድረግ ፈቃድ እየጠየቁ ነው።

በወረዳ ደረጃ ያለው ግምገማ ደግሞ ሃምሌ 17 ቀን 2007 ዓ.ም ተጀምሯል።

– ኢሳት ዜና

መኢአድ ፕሬዝደንት አቶ ማሙሸት አማረ የፍርድ ቤት ውሎ

0
0

ለገሰ ወ / ሃና

መኢአድ ፕሬዝደንት አቶ ማሙሸት አማረ ዛሬ ሰኔ 27 /2007 ዓም ፍርድ ቤት ቀጠሮ እንዳለው ገልጬ ነበር በቀጠሮው መሠረት ዛሬ አቅርበውታል

Mamushetሰኔ 15 / 2007 ዓም በቀረበበት ወቅት ምስክሮቹ አልቀረቡም ተብሎ ለዛሬ ምስክሮቹ ታስረው እንዲቀርቡ ነበር ታዞ የነበረው
ዛሬ ሰኔ 27/2007 ዓም 4 :00 አካባቢ የተሠየመው ችሎት ምስክሮቹ ዛሬም እንዳልቀረቡ በመግለጽ ሰኔ 15/2007 ዓም ቀርበው እንደነበረ ምስክርነቱን ያልሰጡት ተደራራቢ መዝገብ ስለነበረ እንደሆነ ተገልጿል በእለቱ ማለትም ሰኔ 15/2007 ተሰጥቶ የነበረው ምክንያት ምስክሮች አልቀረቡም በሚል ነበር ለዛሬ ታስረው ይቅረቡም የተባለው በዚህ ምክንያት ነበር ዛሬየተገለፀው ሀምሌ 15/2007 ዓም ቀርበው እንደነበረ ከዳኛ ተገልጿል
በዛሬው እለትም ምስክሮቹ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ምስክሮቹን የሚያውቃቸው አረጋግጦልኛል ችሎት ከመሠየሙ በፊት አቃቤ ህግ አነጋግሯቸው እንደነበረ ከዛ እውጭ ቆይተው የማሙሸት ጉዳይ ቀጠሮ ከተሰጠበት በኇላ አለን ማለታቸው አይተናል
አቃቤ ህግ በማሙሸት ላይ ያዘጋጃቸውን የሀሰት ምስክሮች ቀርበው እያለ እንዳልቀረቡ አድርገው ምስክሮቹ ታሰረው ይቅረቡ የሚል መልስ ከችሎት ተሰጥቷል በእውነቱ የኢትዮጵያን ውስጥ ያለውን እውነት ያልተገለጠለት ወይም ያልተገነዘበ ሰው ይህንን አላምንም ማለቱ አቀርም እንዲያምን አይገደድም እውነቱ ግን ይህ ነው ማመን ይገባዋል
ምንም እፍረት ያልፈጠረባቸው የዘመናችን ክፉ እና አረመኔዎች ውንብድና ያስገርማል አቃቤ ህግ በማሙሸት ላይ ያዘጋጃቸውን የሀሰት ምስክሮች ቀርበው እያለ እንዳልቀረቡ አድርገው ምስክሮቹ ታሰረው ይቅረቡ የሚል መልስ ከችሎት ተሰጥቷል አቃቤ ህግ በማሙሸት ላይ ለምስክርት የመለመላቸውን ሰዎች ለምን ሊያስመሠክር እንዳልቻለ በይታወቅም ማሙሸትን በእስር ለማቆየት ይመስላል
የተከሰሰበት አንቀጽ እስከ 6 ወር የሚደርስ ቀላል እስራት እና በብር አስከ 500 ብር የሚያስቀጣ ነው ማሙሸት ከታሰረ በህግ ያስቀጣል የተባለውን ጊዜ ከግማሽ ላይ ታስሮል
ይህም ሆኖ የቦሌ ምድብ ችሎት በነጻ አሁን የሚቀርብበት አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 5000 አስይዞ ይዉጣ ቢባልም ገንዘቡ ተይዟል እሱም ተስሮ እዚሁ ፍርድ ቤት ካላይ የተገለፀውን ምክንያት እየደረደሩ ያሰቃዩታል የፍርድ ቤቱን እና የፓሊስን አካሄድ ስንመለከት ማሙሸትን አስሮ ለማሰቃየት እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል
ዛሬም እንቀደሙት ጊዜያት ቀጠሮ ሰጥቷል ምስክሮቹ ታስረው ነሐሴ 5/2007 ዓም 5:00 ሰአት እንዲቀርቡ ታዟል ያኔ ደግሞ ምን እንደሚባል ጊዜው ሲደርስ የምናው ይሆናል የሀገራችን የፍርድ ሂደት ይህንን ይመስላል ::
በሌላ በኩል
አብርሃም ጌጡ ያለበት ሁኔታ እጅግ አሳስቦናል
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ ) የውጭ ግንኙነት ሀላፌ አቶ አብርሃም ጌጡ ታስሮ ከነበረበት አዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን (3ኛ ) ከሀምሌ 15/2007 ዓም ጀምሮ ወደ ማዕከላዊ ተወስዷል
ቀደም ሲል ቀርቦበት የነበረው ሚያዝያ 13/2007 በሊቢያ የታረዱ ወገኖቻችንን በተመለከተ መንግስት የጠራውን ሰልፍ የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችን አደራጅተህ ሚያዝያ 14/2007ዓም የተጠራውን ሰልፍ እንዲበጠበጥ አድርገሃል የሚል ነበር
ይህንን ክስ በተመለከተ በልደታ ፍርድ ቤት እና በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፓሊስ እያቀረበ የጊዜ ቀጠሮ እየጠየቀበት ቆይቷል ይቀርባል ባልተባለበት በበአል ቀን (የኢድ በአል እለት )ሀምሌ 10 2007 ዓም አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቅርበው ዳኛ ለመጨረሻ ጊዜ በማለት ለፓሊስ 7 ቀን ሰጥቶት ነበር ፓሊስ በተሰጠው ቀን ሀምሌ 17 /2007 ዓም መቅረብ ሲገባው አላቀረቡትም ፍርድ ቤት ይቅረብ ከተባለበት 2 ቀን ቀደም ብሎ ወደ ማዕከላዊ አዛውረውታል በቀጠሮው መሠረት ፍርድ ቤት ሄደን ስንጠይቅ አልቀረበም በምን ምክንያት እንዳልቀረበ ስንጠይቅ ክሱ መቋረጡን ነግረውናል ጠበቃው በተደጋጋሚ አብርሃምን ለማነጋገር ወደ ማዕከላዊ ቢሄድም አብርሃምን ማናገር እንደማይችል ተነግሮታል
በአሁኑ ሰአት አብርሃም በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አልታወቀም በዚህ ምክንያት ቤተሰቡና የትግል አጋሮቹን ስጋት ላይ ጥሏል ይህንን ስጋታችንን
በሰብአዊ መብት ዙሪያ የምትሰሩ ድርጅቶችና የሚዲያ ተቋማት የወንድማችን የአብርሃም ጌጡን ሁኔታ እጽንኦት በመስጠት የሚቻላችሁን እንድታደርጉ እናሳስባለን ።

ከፕሬዝዳንት ኦባማ ጉብኝት ማግስት ….. ግርማ ሠይፉ ማሩ

0
0

 

girmaseifu32@yahoo.com , girmaseifu.blogspot.com

Girma  Seifuኦባማ ኢትዮጵያን መጎብኘት አለበት? የለበትም? የሚለው አጀንዳ ማከራከሩ መቆም ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ መጥተዋል በቃ!! በእኔ እምነት ኦባማ ኢትዮጵያ የመጡት ኢትዮጵያ ባሳየችው ፈጣን ዕድገት ተመስጠው፣ ይህ ዕድገት ካፈራው ፍሬ የአሜሪካን ህዝብ እንዲቃመስ (ብዙዎቹ እንደሚሉት ቦይንግን እየገዛንም ቢሆን) ብለው አይደለም፡፡ በእኔ እምነት ኦባማ ከስልጣን ከመልቀቃቸው በፊት የአባታቸውን ሀገር ኬኒያን መጎብኘታቸው በብዙ መመዛኛ የግድ አስፈላጊ ነገር ነበር፡፡ ለዚህ አንድ መናጆ በቅርብ ያለች ኢትዮጵያ እንድትሆን የግድ የሚሉ ነጥቦች ተገኝተዋል፡፡ በዋነኝነት ደግሞ ሁሉቱ ሀገሮች በግንባር ቀደምትነት እየተፋለሙት የሚገኘው አልሸባብ የሚባለው የሽብር ቡድን ነው፡፡ በአሜሪካ መንግሰት ዘንድ ይህ ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት የኦባማ ጉብኝት ፈቃድ እንዲያገኝ ይሁንታ ሊያስገኝ የሚችል ነጥብ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በተጨማሪ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆኗ ኦባማ በፀረ ሽብር ህጉ ህብረት አፍሪካዊያን በጋራ እንዲቆሙ በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት በኩል ማስተላለፍ አንዱ መንገድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚቻለው የሁሉም አፍሪካ ተወካዮች የሚገኙባት ሀገር ኢትዮጵያ እንደሆነች የሚስት የለም፣ ይህ ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም ቁንጮ በሆነች ሀገር መሪ እንድትጎበኝ ዕድል ሰጥቷታል፡፡ እንዲህም ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም በጎ ነገር የለም የሚለው ነገር በፍፁም የለኝም፡፡

በእኔ እምነት ኦባማ አፍሪካን መጎብኘት ካለባቸው እና አምስት ሀገር መመርጥ ካለባቸው ኢትዮጵያ አንድ መሆን እንዳለባት አምናለሁ፡፡ ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ካለኝ ግምት እንጂ ሀገሪቱን የሚመራው መንግሰት ኢህአዲግ ስለሆነ አይደለም፡፡ ለማንኛውም ፕሬዝዳንት ኦባማ ኢትዮጵያ የምትባል የሰው ዘር መገኛ የሆነች ድንቅ ሀገር ጎብኝተው ተመልሰዋል፡፡ ከዚህ ጉብኝት ምን ጠበቀን? ምን አገኘን? የሚለው ነገር በቅጡ መታወቅ አለበት፡፡ ይህ ጉዳይ ወደፊት በደንብ የሚፈተሸ ሲሆን አሁን ግን ካለብኝ ስጋት አንፃር አሳቤን ላጋራችሁ፡፡

እጅግ ብዙ የሚባሉ ምን አልባትም በፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ አለን የሚሉ ሰዎች ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ መጥተው ይህን አንባገነን መንግሰት በአደባባይ እንዲያውግዙ እና ይህን የመሰለ ድርጊታቸውን የማያቆሙ ከሆነ ዲፕሎማሲያዊም ሆነ ከዚያ የዘለለ እርምጃ ሊወስዱ እንዲሚችሉ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጡላቸው ነበር፡፡ ከዚያ በመነሳት ኦባማ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት “በዲሞክራሲያዊ አግባብ የተመረጠን መንግሰት በሀይል ማውረድ ተገቢ አይደለም” የሚለውን ቁንፅል ሃሳብ ይዘው ለምን አሉ በሚል ቡራ ከረዩ ሲባል ታዝቢያለሁ፡፡ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እንኳን ሰው ሀገር ለጉብኝት ሄደው አይደለም በሀገራቸው ቤተ መንግሰት (ኋይት ሀውስ) ተቀምጠው እንዲህ ዓይነት ከዲፕሎማሲ መስመር የወጣ የአንድን ሀገር መንግሰት ለማዘዝም ሆነ ለማስጠንቀቅ አይችሉም፡፡ በተለይ ኦባማ ከሚከተሉት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አንፃር ይህ በፍፁም የሚያስኬድ አይደለም፡፡ ለምሳሌ በሪፐብሊካን ዘመን ወዮልሽ ስትባል ከነበረችው ኢራን ጋር የተሻለ የሚሉትን መቀራረብ እና መነጋገር እንጂ ማስፈራራት ተገቢ አይደለም ብለው ይስራሉ፡፡ ኦባማ አሁንም ኢትየጵያ መጥተው ያስተላለፉት መልዕክት የኢትየጵያ መንግሰት አንባገነን ነው ብሎ በመራቅ ሳይሆን ቀርቦ በማነጋገር ማለዘብ ይቻላል ነው፡፡ ከቻይና ጋርም እንስራለን ሲሉን መልዕክቱ ግልፅ ነው፡፡ ኦባማ “በርማ” የሄዱት መንግሰቱ ዲሞክራሲያዊ ስለሆነ አይደለም፡፡ ኢትየጵያም የመጡት እንደዚሁ፡፡

የኦባማ ጉብኝት የአባታቸውን ትውልድ ሀገር ለመጎብኘት ካላቸው ቁርጥ አቋም ጋር መናጆ ተደርገን ነው የምንል ሰዎችም ብንሆን የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት ምንም የሚያመጣው ፋይዳ የለም የሚል እምነት የለንም፡፡ ይህን ፋይዳ ግን ገዢው ፓርቲ እና መንግሰት እንዴት ይጠቀሙበታል የሚለው ነው፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ገዢው ፓርቲ በዋነኝነት ይህን ጉብኝት መጠቀም የጀመረው ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ እና ይህን ጉብኝት የተቃወሙትን በተለይ ግልፅ ተቃዎሞ ሲያሰሙ የነበሩትን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ለማውገዝ እና ለማሸማቀቅ ነው፡፡ ይህ ትርፍ ከአስገኘም የአጭር ጊዜ እንጂ ዘላቂ ትርፍ ሊያመጣ የሚችል ሳይሆን መቃቃርን የሚያፋፋ አካሄድ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የኦባማ ጉብኝት ትርፍ በአፍንጫችን ቢወጣ ይሻለን ነበር፡፡ ከዚህ መንግሰት ባህሪ አንፃር ከኦባማ ጋር በሚስጥር በተደረገ ውይይት መነሻ የሚደረጉ ፈጣን የፖሊሲም ሆነ የአስራር ለውጥ በግሌ አልጠብቅም፡፡ ምክንያቱም “ኦባማ እንዲህ አድርጉ ብሎ አደረጉ” መባል አይፈልጉም፡፡ በሌላ ፅንፍ ያሉትም ቢሆኑ “ኦባማ አዟቸው አደረጉ” ማለታቸው አይቀርም፡፡ ይህ በኢትዮጵያዊ ስነ ልቦና ሲታይ ፊት ለፊት ያለው ሲሆን ይህ ደግሞ ለለውጥ እጅግ ደንቃራ የሆነ አስተሳሰብ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ይህን ሊሰብር የሚችል መሪ ያለን አልመሰለኝም፡፡ አግኝተን ግምቴ ልክ ባይሆን ደስ ይለኛል፡፡

ሌላው ከፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጉብኝት ከፍተኛ ጥቅም ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው በገፅታ ግንባታ እና እርሱን ተከትሎ የሚመጣው የግል ባለ ንዋዮች የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት ነው፡፡ ከፕሬዝዳንቱ ጋር እጅግ ብዙ ጋዜጠኞች ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ገፅታ በሚችሉት መስመር ሁሉ ለማግኘት እንደሞክሩ ይታመናል፡፡ እነርሱን መሰረት አድረገው መረጃ የሚተነትኑ እና የሚያወጡ አካላት የሚሰጡት ግመገማ ውጤት ለኢንቨስተሮች ውሳኔ መሰረት ሆኖ ያገለግላል፡፡ የአሜሪካና የቻይና መሪዎች በሀገሮች ጉብኝት ሲያደርጉ ጉልዕ ልዩነት አለ፡፡ የቻይና ፕሬዝዳንት መጥተው ጉብኝት አድርገው ቢሄዱ አንድ ቃል ሊገቡ የሚችሉት ነገር ይኖራል፡፡ መንግሰታቸው ከሚመሯቸው ተቋማት የተወሰኑትን በኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት አድርጉ ብለው ትዕዛዝ ሊስጡ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ፕሬዝዳን ባራክ ኦባማ ይህን ለማድረግ እድልም መብትም የላቸውም፡፡ የአሜሪካ ባለሀብቶች ከመንግሰታቸው ጥበቃን እንጂ የት ኢንቨሰት እንደሚያደርጉ መመሪያ አይሰጣቸውም፤ አይቀበሉም፡፡ የሚገርመው በራሳቸው ውሳኔ ባደረጉት የኢንቨስትምንት ውሳኔ ግን መንግስታቸውን በቂ ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ያስገድዱታል፡፡ ይህ ነው የአሜሪካ ስርዓት፡፡

የኢትዮጵያ መንግሰት ከኦባማ ጉብኝት ውጤት ይጠብቅ ከሆነ ያለ ምንም ይሉኝታ በሀገራችን የግል ኢንቨስትመን (በተለይ የውጭ) እንዳይመጣ ማነቆ የሆነውን የውስጥ ሰላምን (ፀጥታ አላልኩም) ማምጣት አለበት፡፡ ይህ ማለት በጠምንጃ ታፍኖ ዝም ያለ ህዝብን መፍጠር ሳይሆን በዲሞክራሲያዊ ሰርዓት ውስጥ የሚገኝ ስላምን መፍጠር ይጠበቅበታል፡፡ ለዚህም ዋነኛ ግብዓት ሆነው የሚያገለግሉትን ነፃ ሚዲያ፣ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታን፣ በህገ መንግሰት ላይ የተደነገጉትን የስብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፍታት፣ ልዩነቶች በህጋዊ አግባብ መፍታት የሚቻልበት የፍትሕ ሰርዓት መዘርጋት፣ ወዘተ እጅግ በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ እነዚህ ሲሟሉ የአውሮፓና አሜሪካ ባለሀብቶች ይመጣሉ፣ ኦባማም ኢትዮጵያን ባይጎበኙም፡፡

ኦባማ በአፍሪካ የስልጣን ገደብ ማጣት፣ ሙስና፣ የነፃው ፕሬስ እመቃ ወዘተ ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ካንሰር መሁኑን አበክረው ገልፀዋል፡፡ የሚገርመው መሪዎቻችን ያጨበጭቡ ነበር፡፡ ታመሃል ሲባል የሚያጨበጭብ ታማሚ አንባቢ ልብ ሊለው ይገባል፡፡ በአኔ እምነት በካንሰር የተያዘ የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ በሚገኝ ኢኮኖሚ ውስጥ መዋለ ንዋይ ለማፍሰስ የሚመጣ ይኖራል ማለት የሚታሰብ አይደለም፡፡ ከኦባማ ጋር የመጡት የልዑካን ቡድኖች ውስጥ የሚገኙት የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች በኢትዮጵያ ውስጥ የአንድ ፓርቲ አንባገነን ስርዓት እንዳለ አይሰሙም፣ በሲቪክ ማህበረስብ ውስጥ እየተደረገ ስለ አለው እመቃ አይረዱም፣ ከሲቪል ማህበራት ጋር የተደረገው ውይይት በሚዲያ ሳይገለፅ በሚስጥር ውይይት ይደረግበት ማለቱ ምን ማለት እንደሆነ አይገባቸውም ማለት እነዚህ ባለ ሀብቶች በሚወስዱት ውሳኔ ሳይሆን በድንገት ባለሀብት የሆኑ ያስመስላል፡፡ ኢቲቪ ማታለል የሚችለው በኢቲቪ መረጃ መሰረት አድርገው ውሳኔ ለሚያሳልፉ ብቻ ነው፡፡

በኦባማ ጉብኝት ምክንያት አንድ የተገኘ ውጤት አለ፡፡ ይህ ውጤት ለአሜሪካም ለኢትዮጵያም እኩል ነው ብለን አናምንም፡፡ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ መንግስታት ባስማማቸው ጉዳይ ላይ ቃል ኪዳናቸውን አድሰዋል፡፡ ከዚህ በፊት በሚስጥር ተይዞ የነበረው የኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የፀረ ሽብር (በተለይ አልሻባባም በሚመለከት) ኃይል ግንባር መሪ መሆን አሁን በይፋ ታውጇል፡፡ ለዚህም የሚያስፈልገውን ሁለቱም መንግሰታት ለማዋጣት አቅሙ አላቸው፡፡ እኛ ደምና ነብሳችንን እነርሱ ደግሞ ዶላር ሊሰጡን ተሰማምተናል፡፡ በዚህ አጀንዳ ዙሪያ በሁለቱ መንግሰታት ዘንድ ልዮነት የለም፡፡ ይልቁንም ሁለቱ ሀገራት በዚህ አጀንዳ ዙሪያ ባላቸው የጫጉላ ጊዜ ሌሎች አጀንዳዎች እንዲገፉ እና በተለይ የኢትዮጵያን የግፍ ቀን እንዲረዝም በር ከፍተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሰት አልሻባብና መሰሎችን ብቻ ሳይሆን ለዲሞክራሲ የምጮሁ ኢትዮጵያዊያንንም ከእነዚህ ጋር ቀላቅሎ ለመውቀጥ አስፍስፎ ይገኛል፡፡ እሰከ ዛሬ የበላቸውን እነ አንዱዓም አራጌን፣ ናትናኤል መኮንን፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሽን፣ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች ወዘተ ጨምሮ ማለት ነው፡፡

የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንበታን በሚመለከት አሜሪካኖች ምክር የሚሰጡ ሲሆን የወዳጅ ምክርን መስማት ያለመስማት ደግሞ በኢትዮጵያ መንግሰት እጅ የሚገኝ ነው፡፡ በኢትዮጵያ መንግሰት አተያየ በተለይ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም አገላለፅ “እንቁላል በአንድ ቅርጫት” አይቀመጥም፡፡ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ወዳጅ አንድ አይበቃም፡፡ ከቻይናም ከአሜሪካም ያስፈልጋል፡፡ አንዱ ቢያኮርፍ በአንዱ የሚል ዘይቤ ተጀምሮዋል፡፡ ኦባማ ማኩረፍና መራቅ አይጠቅምም- መነጋገር ነው የሚያዋጣው ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሰት ምንም ግልፅ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ቢፈፅም፣ ከዓለም ሁለተኛ ሚዲያ አፋኝ መንግሰት ቢሆኑም ኢትዮጵያን ከሚመስል ትልቅ ሀገር ጋር ጠብ አያስፈልግም፡፡ የኢትዮጵያ መንግሰትም ቢሆን አሜሪካ ምንም እንኳን ኒዎሊብራል የሆነች ሀገር ብትሆን እና በሀገሯ ኢኮኖሚያዊ ፍትህ የሚያሰፍን መንግሰት ሳይሆን ገበያ የሚመራት ቢሆንም፣ አይንሽን ላፈር ብሎ መሳደብ ጥቅም የለውም፡፡ ሰለዚህ ሁለቱ መንግሰታት የጫጉላ ጊዚያቸውን በሚያስማማቸው ጉዳይ ላይ ያደርጋሉ፡፡ የእኛ ደምና ነብስ እንዲሁም ዲሞክራሲያዊና ስብዓዊ መብታችን አሳልፎ መስጠት፣ የአሜሪካኖች የታክስ ከፋይ ገንዘብ ለጊዜውም ቢሆን ጋብቻ ፈፅመዋል፡፡

ቸር ይግጠመን

 

 

 

 


“ገንዘብ አላችሁ” ምንጩን ለሌላ ልቀቁ –ከ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

0
0
Getachew Haile

ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

“ገንዘብ አላችሁ” ምንጩን ለሌላ ልቀቁ ከጌታቸው ኃይሌ ፕሬዚዴንት ኦባማ አዲስ አበባ ላይ ለተሰበሰቡት የአፍሪካ መሪዎች ሰኞ ዕለት ሐምሌ 20 ቀን 2007 ዓመተ ምሕረት ንግግር እንዳደረገላቸው እናስታውሳለን። በንግግሩ ውስጥ ሥልጣን ለባለተራ የሚተው እንጅ እስከ ዕለተ ሞት የሚስገበገቡለት እንዳይደለ ለመሪዎቹ ሲያስታውሳቸው ገንዘብ እንደሆን አከማችታችኋል አላቸው። አፍሪካውያንን በሥልጣን ኮርቻ ላይ ለመንጠላጠል፥ ከተንጠላጠሉ በኋላም እዚያው ተጣብቆ ለመኖር የሚያጓጓቸው ገንዘብ ለመግፈፍ ብቻ ሊሆን አይችልም። ይህ አንዱ ነው እንጂ፥ ሁሉም አይደለም። ለምሳሌ፥ የደርግ ባለሥልጣኖች ለሥልጣኑ የተስገበገቡት ገንዘብ ለማካበት አይመስለኝም። ባለሥልጣን መሆን ስም ያስጠራል። አልባሌ ሆኖ ከመቅረት ያድናል። ሥልጣን ለኀይለ ማርያም ደሳለኝ የጠቀመው ይኸ ብቻ ይመስለኛል። በችሎታቸውና በሕዝብ ምርጫ የታላላቅ አገሮች መሪዎች ከሆኑ ጋር እኩል ይቆማል፤ አብሮ ይበላል። ከሰው ዓይንና ከሰው አፍ ላለመጥፋት ብዙ ሰዎች የቱን ያህል እንደሚጓጉለት በርሊን ከተማ ሄዶ ለሰፊ ሕዝብ በመታየት ራሱ መስክሯል። —-[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]–

 

በአርበኞች ግንቦት 7 ሕዝባዊ ትግል ላይ ከየአቅጣጫው እየተሰነዘሩ ያሉ ፈተናዎችና ማርከሻ መድኃኒታቸው!

0
0

Birhanu nega photo

እግዚአብሔር ይመስገንና አሁን የነገዋን ነጻይቱን ኢትዮጵያ ለማየት መንገዱ ላይ ቆመን መራመድ የቻልንበት ሰዓት ላይ ደርሰናል፡፡ ይሄ ትልቅ ትልቅ እመርታ ነው፡፡ አሁን ባለንበት ሁኔታ ራሱ ወያኔ ተሸንፎ እንደወደቀ መቁጠር ይቻላል፡፡ የቀረው የባለሥልጣኑ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ነገ የሚሆነው ነገ እንጅ ዛሬ ስለማይሆን ብቻ ነው፡፡ ነገ ግን ዛሬ መሆኑ አይቀርምና ነገ የምንጨብጠውን ዛሬ እንደጨበጥነው መቁጠር ይቻላል፡፡

ይህ ታላቅ እመርታ እንዳይመዘገብ ወያኔ የሀገር ክህደት በመፈጸም ለጎረቤት ሀገራት ሉዓላዊ የሀገሪቱን መሬት እየቆራረሰ ከመስጠት ጀምሮ በተለያየ ጥቅም በመያዝ መሸሻ መሸፈቻ መደራጃ መንቀሳቀሻ መንደርደሪያ እሱ ሱዳንን ይጠቀምባት እንደነበረውና ከሱዳን ያገኝ የነበረውን ድጋፍና ምቹ ሁኔታዎች የሚሰጠን ጎረቤት ሀገር እንዳይኖርና እንዳናገኝ ለማድረግ ያላደረገው ነገር ያላስቀመጠው መሰናክል ያልቆፈረው ጉድጓድ አልነበረም፡፡ ይሄንን ዕድል ልናገኝ የምንችልበት አንድ ቦታ ከተገኘ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሶተኛ ከመሆኑና ይሄንን አጋጣሚ የሚጠባበቅ ከመሆኑ የተነሣ አርፎ ተቀምጦ የነበረውም አማራጭ ስላጣ ብቻ እንደሆነ ይሄንን ዕድሉን ባገኘ ጊዜ ግን ወያኔ ዕድሜ እንደማይኖረው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚያልቅለት ጠንቅቆ ያውቀዋልና፡፡ መሸሻ መሸፈቻ ለማሳጣት ይሄንን ያህል ርቀት የተጓዘው ወያኔ ይህ አሁን ከባሕረ ምድር (ኤርትራ) ላይ ያገኘነውንም ለማሳጣት ለማበላሸት ይሄም አልሆን ሲለው ሐሰተኛ የፈጠራ ወሬና ሴራ በመጠንሰስ እንድንሸሽና እንዳንጠቀምበት ለማድረግ በከፍተኛ ደረጃ ሲጥር ነበር እየጣረም ይገኛል፡፡ እውነቱን መለየት ማወቅ መረዳት እስኪያቅተን ድረስ ባሕረ ምድር የመሸጉትን የነጻነት ታጋዮችን ትግል ሊያደናቅፍ ሊያሰናክል ሊያጨናግፍ የሚችሉ የሆኑና ያልሆኑ ነገሮችን መሠረት ያደረጉ ስሞታዎችን ስም ማጥፋቶችን ድምዳሜዎችን የያዙ መጣጥፎች አሁን ማንነታቸው ይበልጥ ግልጽ እየሆኑ እየታወቁ በመጡ ግለሰቦች ቀደም ሲል ግን በጣም ተአማኒነት በነበራቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ድረ ገጾች ላይ እየተለቀቁ እየቀረቡ ትግሉን እንድንጠራጠር እንዳናምን እንድንሸሽ ከዚያም አልፎ በጠላትነት እንድንፈርጅ ለማድረግ ከባድ ከባድ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

ከዚህ በኋላም ወያኔ እስካለ ድረስና የዕጣ ፈንታው የመጨረሻ መጨረሻ ሰዓት የደረሰ መስሎ እስከታየው ድረስ አያደርገውም የሚባል ነገር ሳይኖረው ሊያደርገው የማይችለው ምንም ዓይነት ነገር ሳይኖር እስከ የመጨረሻ ህቅታው ድረስ የጣረሞቱን በመንፈራገጥ አቅሙን አሟጦ በመጠቀም የተቻለውን ሁሉንም ዓይነት ጥረቶች በማድረግ ይቀጥላል እንጅ ይቆማል ብላቹህ አታስቡ፡፡ አሁን አሁን ከእነዚያ ስም ማጥፋቶች የተጋነኑ ስሞታዎችና የፈጠራ ውንጀላዎች ትክክለኛ የተፈጸሙ ከሆኑትም ጀርባ የወያኔ እጅ እንዳለ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ እኔ በእርግጥ ጥርጣሬው የነበረኝ ቢሆንም አብዛኞቻችን ይሄንን አለመገመታችን አለመጠርጠራችን ምን ያህል የዋሆች ብንሆን ነው እያሰኘኝም ነው፡፡

እነኝህን ጽሑፎች ይጽፉና በድረ ገጻቸው ይለጥፉ የነበሩ ግለሰቦችና ድረ ገጾች አንዳንዶቹ አስቀድሞ በነበረው ማንነታቸው በወያኔነት የምንጠረጥራቸው አልነበሩም፡፡ አንዳንዶቹ ግን ወያኔ በስውር ለዚሁ ዓላማው አስቀድመው ተአማኒነትን አግኝተው እንዲቆዩ አድርጎ ያዘጋጃቸው ናቸው፡፡ ቀደም ሲል በወያኔነት የማንጠረጥራቸው ወይም ወያኔ ያልነበሩትም ቢሆኑ ትናንት አልነበሩም ማለት ዛሬ አይሆኑም ማለት አይደለም፡፡ ወያኔ የመጨረሻው መጨረሻ የደረሰ መስሎ ከታየው እራሱን ለማዳን የሚቆጥበውና የሚሰስተው ምንም ነገር የለም፡፡ እንዳልኳቹህ የሀገርን ካዝና አራቁቶም ቢሆን ገንዘብ ይረጫል፣ ፍላጎታቸው ገንዘብ ሳይሆን ጉዳዮች እንዲፈጸምላቸው ለፈለጉት ጉዳዮቻቸውን ይፈጽምላቸዋል፣ ፍላጎታቸው እነዚህ ሁቱም ያልሆነና ሥልጣን ለሚፈልጉትም ከሚንስትርነት እስከ ዲፕሎማትነት (አቅናኤ ግንኙነት) ድረስ ሥልጣን እየሰጠ ይደልላል፡፡ ሌላው ቀርቶ አያገኝም እንጅ እንዲህ አድርገሀል እንዲህ ብሎ ለፍርድ ላቅርብህ ሳይለው ከሀገር ክህደት እስከ የዘር ማጥፋት ለፈጸመው ወንጀል ላይጠይቀው አስተማማኝ ዋስትና የሚሰጠው አካል ቢያገኝ የመንግሥት ሥልጣንን ሁሉ አሳልፎ በመስጠት እራሱን ለማዳን ዝግጁ ነው፡፡

photo file

photo file

አሁን በዚህ ዘመን በእነዚህ ወያኔ ያንዣበበበትን አደጋ ለማስቀረት ሳይሰስት በሚያቀርባቸው መደለያወች የማይለወጥ የማይደለል ሰው ማግኘት በጣም ከባድ እየሆነ ከመምጣቱ የተነሣ ብዙዎች ያውም በቀላል በቀላል ነገር እየተደለሉ ሕዝብን እንደካዱ ስናይ ቆይተናል፡፡ አብሶ ደግሞ ሀገርና ሕዝብ ነጻ ሆነው ማየት ቁርጠኛ ዓላማ ይዞ ሳይሆን ከግል ጥቅሙ ከዝናና እውቅና ፍለጋ አኳያ እንዲሁም ወያኔ ተወግዶ እሱም ሥልጣን ይዞ በተራው ባለ ሥልጣን ለመባል፣ ለመኮፈስ፣ ሕዝብን ከጫማው ስር ለመርገጥ፣ በግል ጉዳዩ ለገጠመው ችግር የተጣላውን ለመበቀል፣ ለማዘዝ ለመናዘዝ ወይም ደግሞ ለመብላት ምኞትና ፍላጎት ይዞ በተለያዩ የሕዝባዊ ትግል ዘርፎች ተሰማርቶ ወያኔን እየተገዳደረ እየተሯሯጠ ያለ ሰው ከሆነ እንዲህ ዓይነቱን ሰው የያዘውን ሕዝባዊ ትግል በማስካድ ወያኔ የሚፈልገውን ነገር አቅርቦለት አድርጎለት ደልሎ መጠቀሚያው አገልጋዩ እንዲሆን ለማድረግ አይቸግረውም፡፡ አሁን እያስቸገሩ ያሉ ግለሰቦች የተደለሉበት ገንዘብ ወይም ሌላ የመደለያ ነገር መጠንና ዓይነት ይለያይ እንደሆነ ነው እንጅ ከላይ የጠቀስኩትን ዓይነት ፍላጎቶች ይዘው በተለያየ መስክ ሕዝባዊ ትግል ያደርጉ የነበሩ ግለሰቦች እንደነበሩ አሁን ላይ እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡

በዚህ ጽሑፍ ላይ እኛ ሳናውቃቸው ቀርተን እራሳቸውን ሰውረው ወያኔ ደልሎ ለራሱ ጥቅም እንዲያድሩ ያደረጋቸው ግለሰቦች አሳቢ መስለው የተለያየ ነገር በማውራት የትጥቅ ትግሉ እንዳይታመን እንዳይጠነክር ከግብ እንዳይደርስ ለማድረግ ይጠቀሙባቸው በነበሩ ሐሳቦች ላይ አተኩረን ዕናያለን፡፡ ወደ መሀሉም ወያኔ ገዝቷቸው ካልሆነ በስተቀር ሌላ አሳማኝ ምክንያት ስላላቸው እየተደረገ ያለውን ሕዝባዊ ትግል የሸሹ እንዳልሆኑና ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክንያት አቅርበው ሊሸሹ ሊቃወሙ የማይችሉበትን አመክንዮም ዕናያለን፡፡

የትጥቅ ትግሉን የሚቃወሙ ወገኖች የትጥቅ ትግሉን ተአማኒነት ለማሳጣት የሚያነሡዋቸው ነጥቦች ምን ምን ናቸው? የሚለውን ቀድመን ዕንይ በአምስት ዋና ዋና ሐሳቦች ይጠቀለላሉ፡-

  1. ሸአቢያ ራሱ ስላልቻለ አቅም ስለሌለው በእኛ ተጠቅሞ ወያኔን ለመበቀል ለማስወገድ ነው እንጅ በፍጹም በፍጹም ሸአቢያ ለኢትዮጵያ በማሰብ ይሄንን ድጋፍ ሊያደርግ አይችልም፡፡ ሸአቢያ በዚህ ዓላማው ምክንያት በሚያደርግልን ድጋፍ ውጤት ቢመጣ እሱ እንጅ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ አትሆንም፡፡
  2. የወያኔና የሸአቢያ ፀብ የውሸት እንጅ እውነተኛ አይደለም እዛ ብንሔድ መልሶ ነው አሳልፎ ለወያኔ የሚሰጠን ወይም የሚፈጀን፣ ፀባቸው የእውነት ቢሆንም ወያኔና ሸአቢያ ቀደም ሲል ከነበራቸው ጥምረት ቁርኝትና ዝምድና አንጻር ለሸአቢያ ከወያኔ ይልቅ እኛ ቀርበነው ይሄንን ያህል ውለታ ሊውልልን አይችልም፣ ሊታመንልን አይችልም፣ ሸአቢያ ለኢትዮጵያ ከወያኔ የባሰ ሸረኛ ጠንቀኛ ጠላት ነው ብሎ ከመጠራጠር፡፡
  3. የታጠቀ ኃይል የምንፈልገውን ዓይነት ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፣ በአፈሙዝ የሚገኝ ዲሞክራሲ (መስፍነ ሕዝብ) የለም፣ የታጠቀ ኃይል የራሱን እንጅ የሕዝብን ፍላጎት አያሟላም፡፡ ከሚል ዓለም አቀፋዊውን ነባራዊ ሁኔታ ካልተገነዘበ አስተሳሰብ፡፡
  4. በዘመነ ደርግ ወያኔና ሸአቢያ ደርግን ሲታገሉ በነበረበት ወቅት የስንቅና ትጥቅ (logistics) ሌላም ድጋፍ ያደርጉላቸው እንደነበሩ ሀገራትና አንዳንድ አካላት በዚህ ዘመን ለእኛ ሊያደርግልን የሚችል ባለመኖሩ በቂ ስንቅና ትጥቅ ሊገኝ ስለማይችል ከንቱ ድካምና ከንቱ መሥዋዕትነት ነው ከሚል፡፡
  5. ሸአቢያ እኛን ይዞ ወያኔን ለማስፈራራትና ከወያኔ የሚፈልገውን ለማግኘት እንጅ የምናደርገው ትግል ፍሬ እንዲያፈራ ለስኬት እንዲበቃም በፍጹም አይፈልግም፡፡ የሚሉ ምክንያቶችን ያቀርባሉ፡፡

እነኝህ ሥጋቶች ጥርጣሬዎችና ስሞታዎች ተጨባጭና ትክክለኛ ስለመሆናቸው መፈተሽ ይኖርብናልና እንደ ቅደም ተከተላቸው እንፈትሻቸው፡-

  1. “ሸአቢያ ራሱ ስላልቻለ አቅም ስለሌለው በእኛ ተጠቅሞ ወያኔን ለመበቀል ለማስወገድ ነው እንጅ በፍጹም በፍጹም ሸአቢያ ለኢትዮጵያ በማሰብ ይሄንን ድጋፍ ሊያደርግ አይችልም፡፡ ሸአቢያ በዚህ ዓላማው ምክንያት በሚያደርግልን ድጋፍ ውጤት ቢመጣ እሱ እንጅ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ አትሆንም” የሚባለው ነገር ሸአቢያ እንዲህ ዓይነት ሐሳብ ሊኖረው ቢችልም እንኳን የእኛ ጠላት የሆነው ለሸአቢያም ጠላት መሆኑ ጥሩ ዕድል መፍጠሩን በመረዳት የጋራ ጠላትን አንድ ግንባር ፈጥሮ ወይም ተረዳድቶ ማጥቃቱ ማጥፋቱ ስልታዊ አኪያሔድ እንጅ ጉዳቱ ምኑ ላይ ነው? ይሄንን ሥጋት የሚያነሡ ወገኖች ይሄንን ያላቸውን ሥጋት በደፈናው ከመናገር በስተቀር ወያኔ በዚህ ጥምረትና መረዳዳት ቢጠፋ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ የማትሆንበትን ምክንያት በግልጽ እንዲህ እንዲህ ነው በማለት አያስረዱም፡፡ በደፈናው ከመጠራጠር በስተቀር የሚሉት ነገር የላቸውም፡፡ ስገምት ግን የእነሡ ሥጋት “ወያኔ ሲወድቅ በወያኔ ቦታ ሸአቢያ ይቀመጥና ውጤቱ ጉልቻ መለዋወጥ ነው የሚሆነው” የሚሉ ይመስላል፡፡ ይሄም ቢሆን ግን ሥጋቱ ተጨባጭ አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ ተገንጥላለች የተባለችው ባሕረ ምድር (ኤርትራ) ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንደ አንድ ሀገር አውቄሻለሁ ብሏታል ከተባለ በኋላ ሸአቢያ አዲስ አበባ ገብቶ ሥልጣን ሊይዝ የሚችልበት ምንም ዓይነት ሁኔታ አጋጣሚ አሠራር የሌለና ሊታሰብም የሚችል ባለመሆኑ ተደርጎ ቢገኝም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሕግ መሠረት “ወረራ” ተብሎ የሚወገዝና ወረራው በአባል ሀገራት የትብብር ጥቃት እንዲቀለበስ የሚደረግ በመሆኑ ሥጋቱ ተጨባጭ ያልሆነና ሊገመትም የሚገባ አይደለም፡፡
  2. “የወያኔና የሸአቢያ ፀብ የውሸት እንጅ እውነተኛ አይደለም እዛ ብንሔድ መልሶ ነው አሳልፎ ለወያኔ የሚሰጠን ወይም የሚፈጀን፣ ፀባቸው የእውነት ቢሆንም ወያኔና ሸአቢያ ቀደም ሲል ከነበራቸው ጥምረት ቁርኝትና ዝምድና አንጻር ለሸአቢያ ከወያኔ ይልቅ እኛ ቀርበነው ይሄንን ያህል ውለታ ሊውልልን አይችልም፣ ሊታመንልን አይችልም፣ ሸአቢያ ለኢትዮጵያ ከወያኔ የባሰ ሸረኛ ጠንቀኛ ጠላት ነው ብሎ ከመጠራጠር” ይሄ ደግሞ በጣም አስቂኝ ነው፡፡ ሰው አይጠርጥር አይጠንቀቅ አይባልም በተለይ በእኛ ሁኔታ መጠራጠርና መጠንቀቅ ተገቢና አስፈላጊም ነው፡፡ ነገር ግን የጠረጠርነውን ነገር ሊያስወግዱ ሊቀርፉ የሚችሉ ያሉና የሚታዩ ተጨባጭ ኩነቶች ባሉበት ሁኔታ አንድ ሰው በዚህ ደረጃ ተጠራጥሮ የማይመስል ነገርን ሲያስብ ብታገኙት ይሄ ሰው በጤነኛና ትክክለኛ የአእምሮ ጤና ውስጥ እንዳልሆነ እርግጠኛ ልትሆኑ ትችላላቹህ፡፡ ለእንደዚህ ዓይነት መስመር የሳተ አስተሳሰብ የሚዳረጉ ሰዎች እንዲህ ሊሆኑ የሚችሉበት ምክንያት ሲመረመር እንዲህ ብለው በሚጠረጥሯቸው በሚያስቧቸው አካላት ከባድ የሥነልቡና ጫና መታወክና መረበሽ የደረሰባቸው ሆነው ይገኛሉ፡፡ ከዚህም የተነሣ እነዚያን የሚጠረጥሯቸውን አካላት በተመለከተ ሊያደርጉትና ላያደርጉት ሊችሉትና ላይችሉት ሊሠሩትና ላይሠሩት ይችላሉ ብለው የሚያስቡት የሚገምቱት ሲመረመር ከሞላ ጎደል ትክክለኛ ሆኖ አይገኝም፡፡ ሥጋቶቻቸውና ጥርጣሬዎቻቸው ከታወከ ሥነልቡናቸው የሚመነጩና ከገሀዱ ዓለም ተጨባጭ እውነታዎች የራቁ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ያሉ ነገሮችንም በተጨባጭ ካሉ ከተፈጸሙ መሬት ላይ ከሚታዩ ነገሮች አንጻር መመዘን መለካት የሚፈልጉ አይደሉም፡፡

ይሁንና ምናልባት ያሉበትን ተጨባጭ ያልሆነ ምናባዊ አስተሳሰብ ማሰብ ማገናዘብ መረዳት ያስችላቸው እንደሆነ ከሚል እንዲህ ለሚሉ ሰዎች ላነሣቸው የምፈልጋቸው ጥያቄዎች አሉኝ፡- ሀ. የሸአቢያና የወያኔ ጸብ የውሸት ከሆነ የዚህ የውሸት ጸባቸው ምክንያት ዓላማና ግብ ምንድን ነው? ለ. ጸባቸው የውሸት ከሆነ ወያኔና ሸአቢያ ለ17 እና ለ30 ዓመታት ደርግን ሲታገሉ ከእያንዳንዳቸው ወገን ካለቀባቸው ሠራዊት በላይ በዚያች በአጭር ጊዜ ጦርነት ባደረጉት ጦርነት ብቻ ከእያንዳንዳቸው ወገን ሰባ ሰባ ሽህ የሚገመት ሠራዊት ላለቀበት አስከፊ ጦርነትስ እንዴት ሊዳረጉ ቻሉ? ሐ. ከዚያ አሰቃቂ ጦርነት በኋላስ ባሕረ ምድር (ኤርትራ) ከዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ተነጥላ በማዕቀብ ስር ሆና ሕዝቧም ለአስቸጋሪ የድህነት ኑሮ ተዳርጎ እስከ አሁንም ድረስ በከባድ ችግር ለማለፍ እንዴት ልትገደድ ቻለች? የሚሉ ጥያቄዎችን ለራሳቸው ለመመለስ ቢሞክሩ ጭንቅላታቸውን ወደ ትክክለኛውና ጤነኛው አስተሳሰብ ለመመለስ ይረዳቸው ይሆናል ብየ አስባለሁ፡፡ አንዱ እንዲህ ዓይነት ችግር ያለበት “ጋዜጠኛ” እማ ጭራሽ ምን አለ? “ጸባቸው የውሸት ነው” ካለ በኋላ “የውሸት መሆኑንም የሚያረጋግጠው ኢትዮጵያ ለኤርትራ በየዓመቱ 250 ሚሊዮን (አእላፋት) ዶላር ትረዳለች” በማለት ያለበትን የሥነልቡናና የሥነ አእምሮ የጤና መታወክ ደረጃ ቁልጭ አድርጎ ሊያሳየን ቻለ፡፡ ወይም ደግሞ የትጥቅ ጥግሉን ለማክሸፍ ለስውር ተልእኮ ወያኔ ከቀጠራቸው ቅጥረኞች አንዱ መሆኑን እንዲህ በል ተብሎ ሊሆንም ይችላል፡፡ ምክንያቱም ይህ ያለው ነገር የፈጠራ መሆኑን የሚያረጋግጠው አስቀድመን ከጠቀስናቸው የሸአቢያና የወያኔ ፀብ የውሸት አለመሆኑን ከሚያረጋግጡት ነጥቦች አኳያ የማይመስል ነገር መሆኑና ለወሬው መረጃውን ወይም ምንጩን መጥቀስ ያልቻለ መሆኑ ነው፡፡

ሌላው “ሸአቢያ ታማኝ አይደለም ሸአቢያ ለኢትዮጵያ ከወያኔ የባሰ ሴረኛ ሸረኛ ጠንቀኛ ጠላት ነው” ለሚለውን የዋሀን ወገኖቻችንም ይሄንን አጥብቀው ያነሣሉ፡፡ ለነገሩ እነሱን ጨምሮ የወያኔ ካድሬዎችም ጭምር ሸአቢያ ከወያኔ የባሰ ጠላት ለመሆኑ የሚጠቃቅሷቸው ነገሮች አሉ፡፡ በሸአቢያ በኩል ደግሞ እነኝህ የሚጠቀሱ ነገሮች ሐሜቶችና የወያኔ የፈጠራ ወሬዎች መሆናቸውንና እሱ ግን ከድሮ ጀምሮ ለኢትዮጵያ በማሰብ ቀና ቀና ነገሮችን ሲያደርግ እንደቆየ ቢናገርም እንዲያው አንዳችም የፈጸመብን ክፉ ተግባር የለም ማለት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ምንስ ቢሆን ሲዋጋ የኖረው ከእኛ ጋር መሆኑ ቀረ እንዴ! ጠላቱ አድርጎ የሚያስበንን ለመጉዳት ለማጥቃት ለማዳከም የማይመኘን የማይጥርብን ምን ያህል ታጋሽ አርቆ አሳቢ በሳል ይቅር ባይ ቢሆን ነው? እንኳንና የሚጠቀሱ ነገሮች እያሉ የቱንም ያህል ደግ አሳቢ ቅኖች የነበሩ ቢሆኑም እንኳ የዚህን ያህል ሊያመጻድቅ የሚችል ሥራ ሊኖራቸው እንደማይችል መገመት የሚቻል ይመስለኛል፡፡

ነገር ግን ይህ የሸአቢያ መልካም ሥራ እውነት መሆኑን ማጣቀሻዎችን እያነሡ የመሰከሩ የአንዳንድ ወገኖች ምስክርነትንም ሰምተናል፡፡ እንደኔ እንደኔ ሠራው የተባለው ክፋት እውነት ቢሆንም እንኳን ሊያስደንቀን የሚገባ አይደለም፡፡ በጠላትነት ተፈራርጀን ስንተላለቅ የኖርን ሰዎች ሆነን እያለ አንዳችም ክፉ ነገር እንዲያደርግብን መጠበቅ የኛን የዋህነት ሊያስይ ቢችል እንጅ ሊሆን የባይገባው ነገር መደረጉን የሚያሳይ አይመስለኝም፡፡ ምን ነካቹህ? በቀንደኛ ጠላትነት ተፈራርጀን ለ30 ዓመታት እኮ ነው ጦርነት ስናደርግ የኖርነው! እኛ እነሱን ልናጠፋ እነሱም እኛን ሊያጠፉ፡፡ ዛሬ ላይ ግን ያ ትግላቸው ለስኬት አብቅቷቸው የትግላቸውን ፍሬ እየለቀሙ ያሉበት ደረጃ ላይ በመሆናቸውና ትግላቸው “ያተረፉበት ወይስ የከሰሩበት? መሆን መደረግ የነበረበት ወይስ ያልነበረበት?” የሚል ጥያቄን ለራሳቸው እንዲያነሡ የተገደዱበት ወቅት ላይ ያሉ በመሆኑና ለትግል ያስወጣቸው ችግሮች የነበሩ ከሆነም እንኳን እነዚያን ችግሮች በሌላ መንገድ መፍታት ይቻል የነበረበትን አማራጭ መፈለግ የተሻለ እንደነበር የተረዱበት ወቅት ላይ ያሉ በመሆናቸው እድሜ የማያስተምረው የማያበስለውም የለምና ከዕድሜና ከተሞክሮም በመማራቸው ከዚህ አንጻር በዚያ ወቅት በኢትዮጵያ ላይ የሠሩት የፈጸሙት ሸር ሴራ ወንጀል ተንኮል ክፋት ቢኖርም እንኳን የሚጸጸቱበት እንጅ የሚኮሩበት ባለመሆኑ እንደቀድሟቸው ሁሉ አሁንም እንደዚያው ያደርጋሉ ያስባሉ በማለት ፍጹም አትጠራጠሩ ባልልም ድምዳሜ ላይ መድረሱ ግን የሚገባ ነው ብየ አላስብም፡፡

የወያኔ ካድሬዎች ተቀጣሪዎችና የዋሀን ወገኖች የፈለጉትን ሲያወሩ ለሸአቢያ የነበረን ሥዕል ከድሮው መጥፎ መሆኑ ስለ ሸአቢያ መጥፎነት ምንም ነገር ቢባል በቀላሉ እንድናምን እያደረገን ወደ እውነቱ እንዳንደርስ የተጫነን መስሎ ይሰማኛል፡፡ እኔ እንዲያውም አሁን አሁን እየተረዳሁት የመጣሁት ነገር ቢኖር በሸረኝነት በክፋተኝነት በጠንቀኝነት በሴረኝነት በጠላትነት ወያኔ ሸአቢያን እጥፍ አስከንድቶ የሚበልጠው መሆኑን እንጅ የሚያንሰው አለመሆኑን ነው፡፡ በግልጽ አማርኛ ከመጀመሪያውም ጀምሮ ከሸአቢያ ይልቅ ወያኔ እጅግ በጣም የከፋ ሸረኛ ሴረኛ ክፉ ጠላት ነው፡፡

ይሄንን ልታረጋግጡ የምትችሉበትን አንድ ሁለት ነገሮችን ላንሣላቹህ፡፡ ከ1990ዓ.ም. የወያኔ ሸአቢያ ጦርነት በኋላ እነ አቶ ኢሳይያስ ከዓለሙ ማኅበረሰብ የተነጠሉ መሆናቸውን ታውቃላቹህ፡፡ ለምዕራባዊያን ከኢትዮጵያ ይልቅ ባሕረ ምድር (ኤርትራ) ስልታዊ (strategic) ጠቀሜታ ያላት ነች፡፡ የወያኔ ሸረኝነት ሴረኝነትና ዋሽቶ የማሳመን ችሎታ ከሸአቢያ እጅግ የላቀ መሆኑ ባሕረ ምድር እንዲህ ዓይነት ስልታዊ ጠቀሜታ ያላት መሆኗ በቀላሉ ምዕራባዊያንን ከጎኗ ማሰለፍ የሚያስችላት ሆኖ ሳለ በጠቀስነው ችሎታ ወያኔን ስላልቻሉትና በዲፕሎማሲው (በአቅንኦተ ግንኙነቱ) ላይ የበላይነቱን በመያዙ ከጨዋታ ውጪ እንዳደረጋቸው ዓይተናል፡፡ ይሄው እስከዛሬም በአሳዛኝ ተሸናፊነት ተገልለው እንዲቀሩ አድርጓቸው ቀርቷል፡፡ ከሸአቢያ ያየነው ብቃት ቢኖር የዘመኑን የፖለቲካ ጨዋታ ባለመረዳት ከሁኔታዎች ጋር እንደወያኔ እየተጣጠፈ በብልጠት ጥቅሙን ማስከበር ሳይችል በግትርነት በድርቅና መጽናቱን ብቻ ነው፡፡

ይሄ ሽንፈት በድንበር ዳኝነቱ (ኮሚሽኑ) ውሳኔ ጊዜም ተደግሟል የዳኝነቱ ውሳኔ ትክክል ባይሆንም የድንበር ኮሚሽኑ (ዳኝነቱ) ይግባኝ በሌለው ውሳኔ ባድመን ለባሕረ ምድር የወሰነ ሆኖ እያለ ከሸአቢያ ችሎታ ማነስና ደካማነት ከወያኔ መሠሪነት ሸረኝነት የተነሣ ውሳኔው ተፈጻሚ መሆን እንዳይችል አድርጎታል፡፡ እንግዲህ ሸአቢያ ሊጠቀምባቸው መብቴ ነው የሚለውን ሊያስጠብቅበት የሚያስችለው ዕድሎችና አንዳንድ ነገሮች ቢኖሩትም ከደካማነቱ የተነሣ ጥቅሙን ማስጠበቅ ያልቻለ አካል ነው፡፡ ከእነዚህ ሁለት ሁኔታዎች የምንረዳው የወያኔንና የሸአቢያን በጣም የተራራቀና የማይመጣጠን የብቃትና የችሎታን አቅም ነው፡፡ እንደምናስበውና ከየዋሀን ወገኖቻችን ከወያኔ ቅጥረኞችና ካድሬዎች በሰፊው እንደሚወራልን ሸአቢያ ከወያኔ የላቀ የበለጠ መሠሪ ሸረኛ ብቃትና ችሎታ ያለው ቢሆን ኖሮ አይደለም ከወያኔ በበለጠ በተሸለ በምዕራባዊያኑ ተመራጭ ተፈላጊ ሊያደርገው የሚችሉ ነገሮች እያሉት ቀርቶ ባይኖረውም እንኳ የበላይነቱን ይዞ ልናየው በቻልን ነበር፡፡ የሆነው ግን የተገላቢጦሹ ነው ስልታዊ ጠቀሜታ እንደሌለውና በድንበር ኮሚሽኑ እንደተሸነፈ ሆኖ ከዓለም ዓቀፉም ኅብረተሰብ ተነጥሎ ተገልሎ ይሄ ሳያንሰው ማዕቀብ ተጥሎበት በማዕቀብ እየታሸ ለመኖር የተገደደ መሆኑ ነው፡፡

እዚህ ላይ አንዳንድ ሰዎች ምናልባት ሸአቢያ ምዕራባዊያኑን ከጎኑ ሊያሰልፍ የሚችልበት ጥቅም እያለው ምዕራባዊያኑ ከሸአቢያ ጎን ሊቆሙ ያልቻሉበትና ከወያኔ ጎን ሊቆሙ የቻሉበት ምክንያት “ወያኔ አልሸባብን አጥፍቶ ሱማሌን የተረጋጋችና መንግሥት ያላት ሀገር እንዲያደርግላቸው ስለሚፈልጉ እዚያ ላላቸው ጥቅም ወያኔን ስለሚፈልጉት ነው” የሚሉ ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እውነት እንነጋገር ከተባለ የምዕራባዊያኑ ፍላጎትና ጥቅም እውን ሶማሊያ የተረጋጋች ሀገር እንድትሆን ነው ወይ? እንዳልሆነ ሊቢያ ላይ ምን ብለው ምን አድርገዋቸው እንደቀሩ የታየውና የምናውቀው ነው፡፡ አፈራርሰዋት የአሸባሪዎች መፈንጫ አድርገዋት ቀሩ እንጅ ቃል የገቡትን የመልሶ ማቋቋሚያ ገንዘብ ሰጥተው መስፍነ ሕዝባዊ (ዲሞክራሲያዊ) መንግሥት እንዲመሠርቱ ሲረዷቸው ፈጽሞ አልታዩም፡፡ በመሆኑም የምእራባዊያኑ ጥቅምና ፍላጎት ሶማልያን ማረጋጋትና ባለመንግሥት ማድረግ ሆኖ ባሕረ ምድር ካላት ስልታዊ ጠቀሜታነት አንጻር ከሷ ሊያገኙት የሚችሉት ጥቅም ወያኔ ሱማሌ ላይ ከሚሰጣቸው ጥቅም በልጦባቸው አይደለም ከሸአቢያ ይልቅ ወያኔ በልጦባቸው ከወያኔ ጋር ሊቆሙ የቻሉት፡፡

እናም አትጠራጠሩ የከፋው የባሰው የላቀው መሠሪ ሸረኛና ሴረኛ ወያኔ እንጅ ሸአቢያ አይደለም፡፡ ሸአቢያ እንኳንና ፈጥሮ ፈልስፎ አሲሮ ጥቅሙን ሊያስጠብቅ ይቅርና በያዘው ጥቅሙን ሊያስጠብቅ የሚያስችሉትን ዕድሎች በመጠቀም ሌላው ቀርቶ ያንተ ነው የተባለለትን ውሳኔ ጥቅሙን ማስጠበቅ ያልቻለ ምስኪን ተሸናፊ ነው፡፡ ይህ ነገር ስለ ሸአቢያ መጥፎነት የመሠሪነት ብቃትና ችሎታ ሲወሩ ሲነገሩን የነበሩ ነገሮች ሁሉ እውነትነታቸውን እንደገና መለስ ብለን እንድናይ እንድንፈትሽ የሚያስገድደን ይመስለኛል ይገባልም፡፡ ቢያንስ የተባለው ሁሉ እውነት እንዳልሆነ የሚያረጋግጥ ይመስለኛል፡፡ ጥቂቱ እንኳ እውነት ሊሆን ቢችል አስቀድሜ እንደገለጽኩት ለምን እንዴት ብሎ መጠየቅ ድርጊቱንም ማውገዝ ተገቢ ቢሆንም ከነበሩ የጦርነት ነባራዊ ሁኔታዎች አንጻር በምንም ተአምር መፈጸም አልነበረበትም ማለቱና በዚህም ላይ ተመሥርቶ የመጨረሻ ድምዳሜ ላይ መድረሱ ግን እጅግ እጅግ የዋህነትና እጅግም አለመብሰል ነው፡፡ በቤተሰብ መሀከል በጥቅም ምክንያት ወንድም በወንድሙ እኅት በእኅቷ ወንድም በእኅቱ ልጆች በወላጆቻቸው ወላጅ በልጆቹ ክህደት እየፈጸመ በሚባላበት ዘመን ጠላት ተደራርገው አንዱ ሌላውን ለማጥፋት በሚታገል በታጠቀ ሠራዊት መሀከል አንዳንድ ነገሮች መፈጸማቸው አይቀርምና ይሄና ያ እንዴት ለምን ማለትና ምንም ነገር እንዲፈጸም አለመጠበቅ ያንን የተፈጸመውን ጉዳይም የነገሮች መጨረሻ አድርጎ መቁጠር አሁንም እላቹሀለሁ እጅግ የዋህነትና አለመብሰል ነው፡፡ ምን ነካቹህ እቃቃ ስናጫወት እኮ አይደለም የኖርነው በጦርነት እሳት ስንለባለብ እንጅ፡፡ በፖለቲካ ጨዋታ ውስጥ የሚታየው ዛሬ እንጅ ትላንት አይደለም በዓለማችን ትላንት ሲባሉ ሲቧጨቁ ሲጠፋፉ የነበሩ ዛሬ ላይ ግን እፍ ያለ ፍቅር ውስጥ የገቡ በርካታ ሀገራትንና ቡድኖችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

የሆነ ሆኖ ይሄንን ሁሉ እንዳለ ተውትና ያልገባቸው ወገኖችም ሆኑ ወያኔ የገዛቸው ቅጥረኞች የሚናገሩት ክስ አንድም ሳይቀር ሁሉም እውነት እንደሆነ እንቁጠረውና ለወያኔ ከተገዙትና ከወያኔ ካድሬዎች በስተቀር የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወያኔ የተገዙና የወያኔ ካድሬዎች የሚያወሩትን ሳይሰማ ትግሉን ተቀላቅሎ ለድል የሚበቃበትን መንገድ ስናገር የሚከተለውን ይመስላል፡- የነጻነት ትግል ማለት ምንም ዓይነት መሰናክልና የፈተና ዓይነት እንቅፋት የሚያግደው የሚያደናቅፈው የሚገታው እንዲያግደው እንዲገታው እንዲያደናቅፈውም የማይፈቅድ ሁልጊዜም በተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ ሳይሆን ባልተመቻቸና እንቅፋት መሰናክሎች ፈተናዎች በበዙበት ሁኔታ የሚደረግ የማይመቹ ሁኔታዎች ስላሉ በፍጹም ከመደረግ የማይቆም የማይቀር፤ ያለው ዕድል ከጠጉር የቀጠነ ዕድልም እንኳ ቢሆን በከፍተኛ ጽናት ትዕግሥትና ብልጠት እሱን ተጠቅሞ ዓላማውን ለማሳካት ከፍተኛ ትግልና ትንቅንቅ የሚደረግበት ሌላው ቀርቶ ምንም ዓይነት ዕድልም እንኳ ባይኖር ራሱን ዕድሉን ፈጥሮ ግቡን ለማሳካት የሚደረግ መራራ ትግል እንጅ እንደ ሽርሽር ምቹ ሁኔታዎች የሚጠበቁበት የትግል ዓይነት አይደለም፡፡

እናም አኔ የምላቹህ የወያኔ ቅጥረኞችና ካድሬዎች እንደሚያወሩት ሸአቢያ ከወያኔ የከፋና የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ቢሆንም እንኳ ትግላችን የነጻነት ትግል በመሆኑና በምንም የሚመለስ ሊመለስም የሚገባ ባለመሆኑ እንኳንና ይሄንን ያህል ዕድል ተፈጥሮ ቀርቶ ምንም ዓይነት ዕድል ባይኖርም ራሱ ዋሽተን ወስልተን ቀጥፈን ሌሎች የብልጠት መንገዶችን ተጠቅመንም ቢሆን ዕድሉን ፈጥረን ግባችንን የማሳካት ግዴታ ያለብን በመሆኑ ሸአቢያ እንዳሉት ቢሆንም እንኳ ባለፈው ጊዜ እንዳልኳቹህ የልባችንን በልብ አድርገን መዋሸት ካለብን እየዋሸን “ቃል ግቡልኝ ፈርሙልኝ ማሉልኝ እንዲህ እንዲህ ታደርጉላኛላቹህ” ቢልም በፍጹም እንደማታደርጉት ልባቹህ እያወቀም አንኳ “እሽ ምን ችግር አለው! የፈለከውን እናደርጋለን! እኛ ሎሌህ ደጋፊዎችህ አጋሮችን ነን! ላንተ የማንሆነው የማናደርገው ነገር የለም!” እያልን ግጥም አድርገን በዐሥር ጣታችን በመፈረም እርኩስ ክፉ መሠሪ መሆኑን ብናውቅም “ደግ ቅንና ቅዱስ ነህ!” እያልን “ሸአቢያ ሽህ ዓመት ይንገሥ በሉ!” ቢል “ለምን ሽህ ዓመት ብቻ ለዘለዓለም ኑርልን!” እያልን ሥራችንን በመሥራት ይሄንን ክፉ ቀናችንን ዛሬን ተሻግረን ግባችንን አሳክተን ከነጻነቱ ቀን ነገ ላይ መድረስ ግድ ይለናል፡፡ ዕድል ባይኖርም ዕድል መፍጠር ይሉሀል ይሄ ነው፡፡ እንዲህ የምናደርገው ለምንድን ነው? እውነት ከሆነ ሸአቢያ የማይወደውን አቋም በመያዛችን በሸአቢያ እንዲጠፉ ተደርገዋል እንደተባሉት ወገኖች ከመጠቃት ለመዳን ነው፡፡ በዚህ የትግል ዘመን እውነት ብቻ ተናግረን ፈተናዎቻችንን ማለፍ መሻገር በፍጹም በፍጹም አንችልም፡፡ የልብን በልብ አድርገን ማስመሰልን መዋሸትን መቅጠፍን በሚገባ ልንካንበት ይገባናል ለምን ሲባል? ለዚህች ውድ ሀገራችንና ለውዱ ሕዝባችን ህልውናና ነጻነት ስንል፡፡ ተስፋ አደርጋለሁ አሁን ነገሩ የሚገባቹህ የሚገለጥላቹህ ይመስለኛል፡፡ በመሆኑም ወያኔ ወይም የወያኔ ቅጥረኛ ካልሆንን በስተቀር ሀገራችንን የምንወድ የሀገራችንንና የሕዝባችንን ነጻነት ፈላጊ ሆነን ከዚህ ሕዝባዊ ትግል ልንሸሽ ጭራሽም ትግሉት ልንቃወም የምንችልበት ምንም ዓይነት ምክንያት እንደሌለ በሚገባ በመረዳት እያንዳንዳችን እንደየችሎታችን ትግሉን በመደገፍ የትግሉ አካል መሆን አማራጭ የሌለው መሆኑን አውቀን መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡

  1. “የታጠቀ ኃይል የምንፈልገውን ዓይነት ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፣ በአፈሙዝ የሚገኝ ዲሞክራሲ (መስፍነ ሕዝብ) የለም፣ የታጠቀ ኃይል የራሱን እንጅ የሕዝብን ፍላጎት አያሟላም፡፡ ከሚል ዓለም አቀፋዊውን ነባራዊ ሁኔታ ካልተገነዘበ አስተሳሰብ” ይህ የሥጋት ሐሳብ ላይ ላዩን ሲያዩት እውነት ይመስላል፡፡ በተለይ ደግሞ ምሳሌ ይሉና ደርግንና ወያኔን ምሳሌ አድርገው ሲያቀርቡ እውነት ይመስላቹሀል፡፡ ትንሽ ልትጠረጥሩ የምትችሉት “ታዲያ ምን ይሻላል?” ብላቹህ ስትጠይቋቸው መልስ ሲያጡ ወይም የሚሰጡት መልስ አጥጋቢ ያልሆነና ወያኔን የሚጠቅም ሆኖ ስታገኙት ነው፡፡ ምናልባት እነኝህ ቅጥረኞች የሚያነሡትን ይሄንን የሥጋት ሐሳብ የሚያነሡ ሌሎች የዋሀን የሕዝብ ወገኖች ካሉ ለነሱ ላነሣው የምፈልገው ጥያቄ ቢኖር፡- ይሄንን የሚሉ ሰዎች ለሀገርና ለሕዝብ ታማኝ ከሆኑና ይሄንን ቅን ዓላማቸውን ይዘው የሚታገሉ ከሆነ ወያኔን አባራሪዎቹና እንደተመኙት ሁሉ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት የሚያደርጉት እነሱው አይደሉም ወይ? ሌላ ከማርስ የሚመጣ አብሯቸው የሚገባና አንባገነን ካልሆናቹህ ብሎ የሚያስገድዳቸው አካል አለ ወይ? ዋናው የዓላማ ጽናትና ታማኝነት ነው እንጅ መሣሪያው አይደለም፡፡ ታማኝ ያልሆነ ግለሰብ ወይም አካል ካለ ሲቪል (ሕዝባዊ) ሆኖም ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም በተጻራሪ በመቆም ሕዝብን የሚጨቁን የራሱን ወይም የቡድኑን ጥቅም የሚያስጠብቅ ለራሱና ለቡድኑ ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥ ከመሆን እንደማይድን የብዙ ሀገራት ተሞክሮ በሚገባ ያሳየናል፡፡

በዓለማችን በጦር ኃይል የተመሠረቱ መንግሥታት አንባገነን የሆኑ እንዳሉ ሁሉ የተደላደለ ሕዝባዊና ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) መንግሥት እንዲመሠረት እንዲፈጠር ያደረጉም አሉ፡፡ ዋናው የዓላማ ጽናትና ታማኝነቱ ነው፡፡ በዚህ ላይ አርበኞች ግንት 7 ዓላማው ምን እንደሆነ በግልጽ አስታውቋል “የምታገለው ሕዝብ የፈለገውን የወደደውን መሾም ያልፈለገውን ያልወደደውን መሻር የሚችልበት ሥልጣን እንዲኖረው የሥልጣን ባለቤት እንዲሆን ማድረግ ነው እንጅ ወያኔን አውርጀ ሥልጣን ለመያዝ አይደለም፡፡ ወያኔን ደምስሰን የኢትዮጵያ ሕዝብ የፈለገውን የወደደውን መርጦ መንግሥት ያቋቋመ የመሠተረ ጊዜ የኛ ትግል ይጠናቀቃል” በማለት፡፡ ስለሆነም እንግዲህ እውነተኛ የሕዝብ ልጅ ካለ ለግል ጥቅም ለሥልጣን ሳይሆን ለዚህች ሀገርና ለሕዝቧ ነጻነት ለፍትሕ ለእኩልነት እታገላለሁ የሚል ካለ ቦታው አርበኞች ግንቦት 7 ነው ሔደህ ግባ፡፡

እንዲያው ነገሩን አልን እንጅ እውነተኛና ትክክለኛ ለራሱ ቡድናዊና ግላዊ ጥቅምና ፍላጎት ሳይሆን ለሕዝብ የታመነ ኃይል ታግሎ መጥቶ ይሄንን ማድረግ ቢችልና ሕዝብ የወደድከውን የፈለከውን ምረጥ ተብሎ ሙሉ መብት ቢሰጠው ከባድ መሥዋዕትነት ከፍሎ ለዚህ ክብር ያበቃውን፣ ነጻነት ያቀዳጀውን፣ የሥልጣን ባለቤት ያደረገውን፣ ለሀገሩና ለወገኑ እስከ ሞት ድረስ ራሱን የሰጠለትን ትቶ እዚህ ከሞቀ ቤቱ ቁጭ ብሎ ሲያበግነው የኖረውን፣ እንቅፋት እንኳን እንዳይመታው እራሱን ሲጠብቅ የኖረውን፣ ከሕሕብና ከሀገር ይልቅ ራሱን የሚወደውን እራሱን የሚያስቀድመውን፣ ለሕዝብና ለሀገር ሲል ምንም ዓይነት ዋጋ ለመክፈል የማይፈቅደውን፣ ድፍረት ቁርጠኝነት ጽናት የሌለውን፣ ታማኝነቱን ሀገር ወዳድነቱን ከወሬ ባለፈ በተግባር መሥዋዕትነትን እስከመክፈል ድረስ ታምኖ ዋጋ ከፍሎ ማሳየት የማይችለውን፣ የጭርታ የሰላም ጊዜ አርበኛ ተሽታሻ ተሸታሻውን የሚመርጥ ይመስላቹሀል? በፍጹም!

ወያኔ እኮ መሥዋዕትነትን እንደመክፈሉ እስከዛሬ ድረስ በተደረጉት 5 “ምርጫዎች” በኢትዮጵያ ሕዝብ ሊመረጥ ያልቻለው እኮ ወያኔ ካፈጣጠሩ ኢትዮጵያዊ ባለመሆኑ፣ ዓላማና አስተሳሰቡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሽዎች ዓመታት የገነባው የታሪኩ የአንድነቱ የማንነቱ የሥልጣኔው የእሴቶቹ ጠላት ሆኖ ከሚያውቀውና ከሚያምንበት በተጻራሪ ቆሞ ታሪኩን በማጉደፉ፣ ለማፈራረስ ጥረት በማድረጉ፣ በስንት ድካም የገነባውን አንድነቱን ጨርሶ ለማጥፋት በዘር በሃይማኖት እየከፋፈለ ለማባላት በመጣጣሩ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ተናቀ ተጠላ፤ ከትግሬና ከትግራይ ውጪ ኢትዮጵያን ለማየት ለማሰብ የሚችልበት አቅም አልባ በመሆኑ፣ አስተሳሰቡ ዓላማው ሩጫው ሁሉ ጎጠኛ በመሆኑ ኢትዮጵያ የምትባልን ሀገር ሥዕል በጭንቅላቱ የሌለች ከሌሎቻችን ልቦናም እንድትጠፋ የሚፈልግ በመሆኑ፣ ጭራሽም ሊያፈራርሳት ነገር የሚያሴር ክፋት የሚሸርብ በመሆኑ፣ ባጠቃላይ ለታሪኳ ለማንነቷ ለሥልጣኔዋ ለእሴቶቿ ሁሉ ጠላት በመሆኑ የሀገር ክህደት በመፈጸም ከመሬቷ ጀምሮ ሌሎች ብሔራዊ ጥቅሞቿን አሳልፎ የሚሰጥ የጠላት ቅጥረኛና ባንዳ በመሆኑ ለመንግሥትነት አይደለም ለዕድር አሥተዳዳሪነት እንኳን የሚበቃ አቅም ብቃት ችሎታ ቅንነት የኃላፊነት ታማኝነት ተጠያቂነት ግልጽነት ዕውቀት ተወዳጅነት የሌለው የወንበዴ ጥርቅም ስለሆነበት እንጅ መሥዋዕትነትን ለመክፈል ቆርጠው እንደመታገላቸውማ ቢሆን ማጭበርበር ማስገደድ ማስጨነቅ ማወናበድ ሳያስፈልጋቸው ዕድሜ ልኩን ያለ እነሱ የሚመርጠው ባልነበረ ነበር፡፡ ምክንያቱም ሕዝብ የሚወደውን እስከ ሞት ድረስ የሚታመንለትን ዋጋ የሚከፍልለትን የሚያከብረውን ይወዳልና፡፡ እሱም በተራው የመጨረሻውን ክብር ሰጥቶ ያከብራልና፡፡ የዛኑ ያሕል ደግሞ እስከ ሞት ድረስ መሥዋዕትነትን ለመክፈል የታመነ ቢሆንም እንኳ እንደወያኔ ሁሉ ለጥፋትና ለወረደ ለጠባብ የጥፋት ዓላማ መሥዋዕትነትን የከፈለ ሲያጋጥመው እጅግ ይንቃል ይጠላል ያወግዛል ይረግማል ያገላል ያዋርዳል ይጸየፋል ያንቋሽሻል ያበሻቅጣል እንደ መርገም ጨርቅ ይመለከታል፡፡

  1. “በዘመነ ደርግ ወያኔና ሸአቢያ ደርግን ሲታገሉ በነበረበት ወቅት የስንቅና ትጥቅ (logistics) ሌላም ድጋፍ ያደርጉላቸው እንደነበሩ ሀገራትና አንዳንድ አካላት በዚህ ዘመን ለእኛ ሊያደርግልን የሚችል ባለመኖሩ በቂ ስንቅና ትጥቅ ሊገኝ ስለማይችል ከንቱ ድካምና ከንቱ መሥዋዕትነት ነው” ለሚለው፡- እርግጥ ነው በዚያን ዘመን ወያኔና ሸአቢያ ሲያገኙት የነበረውን ዓይነት ድጋፍ ከእነኛው ሀገራት ማግኘት አንችል ይሆናል፡፡ ይሁንና በዚህ በኩል ያለውን ክፍተት ሸአቢያ ጦርነቱ የእኛ ብቻ ሳይሆን የራሱም መሆኑን በሚገባ ስለሚያውቅ ከምንም በላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከወያኔ ነጥለው አርቀው ብቻውን ማስቀረት የሚችሉና የኢትዮጵያን ሕዝብ ድጋፍ ማግኘት ከጎናቸው ማሰለፍ የሚችሉ እንዲህ ዓይነት አጋዥ ኃይል ማግኘቱን ቢሳልም የማያገኘው ወርቃማ ዕድል መሆኑን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በስንቅና ትጥቅ በኩል ያለውን ክፍተት ሸአቢያ ለእኛ ብሎ ሳይሆን ለራሱ ብሎ የሚያደርገው የሚያቀርበው በመሆኑ ይሄ የሚያሳስብ ጉዳይ አይደለም፡፡ እነ አቶ ኢሳይያስ በግልጽ እንዳስታወቁት “ላደረኩላቹህና ለማደርግላቹህ ድጋፍ ምንም ዓይነት ምላሽ አልፈልግም የተረጋጋች የበለጸገች እኩልነትና ፍትሕ የሰፈነባት ሰላማዊት ኢትዮጵያን ብሎብ የተረጋጋና ሰላማዊ የቀጠናው ሀገራት እንዲኖሩ ካለኝ ጽኑ ዓላማ ያደረኩትና የማደርገውም በመሆኑ” በማለት ያስታወቁና ለመካስም ካላቸው በጎና ቁርጠኛ አቋም በመነሣት የተዋሐደችና ጠንካራ ምሥራቅ አፍሪካን ለመፍጠር ካላቸው የተቀደሰና ታላቅ ርእይ አንጻር ይሄንን ለማሳካት ያስችል ዘንድ መሠራት ያለባቸውን ሥራዎች እየሠሩ እንደሆነ አምነው ታሪክ ሠርቶ ለማለፍ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ዓላማቸውን ከረጅም ጊዜና ከአጭር ጊዜ አቅድ አኳያ ግልጽ ያደረጉ በመሆኑ “እነ አቶ ኢሳይያስ ለዚህ ሁሉ ውለታ ምላሽ ሳይፈልጉ ይሄንን ሁሉ ነገር ሊያደርጉልን አይችሉም ላደረጉትና ለሚያደርጉት ምን ልንመልስ ምን ልንከፍል ነው?” የሚያስብልና የሚያሳስብ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሁላችንም መወጣት ያለብንን ግዴታና ኃላፊነት የሚጠበቅብንንና ማድረግ ያለብንን ሥራ ነው እየሠራን ያለነው፡፡

ይሁን እንጅ ለሀገራችንና ለሕዝባችን በማሰብ ታጋይ ወገኖቻችን የማይሆን ውለታ (commitment) ውስጥ እንዳይገቡ የምንሠጋና እንዲገቡም የማንፈልግ ከሆነ ለእኛ ነጻነትና ጥቅም ሲሉ ሁለንተናቸውን አሳልፈው የሰጡ እነሱ እንኳን እንዳሉ በማሰብ እያንዳንዳችን ከተረፈን ሳይሆን ምቾታችንን ቆጠብ በማድረግ “ለእኛ ይቅርብን! እኛን ይቸግረን!” ብለንም ቢሆን ትርጉም ያለው ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ በወሬና ከንፈር በመምጠጥ ወይም በማጨብጨብ ብቻ የሚገነባ የሚሠራ ምንም ነገር የለም፡፡ ተግባር ያስፈልጋል ሀገርን መውደድ በተግባር ከምናደርገው አንዳች ነገር ውጭ በምንም ሊገለጽ አይችልም፡፡ ይሄንን ማድረግ ሳይችል ወሬ ብቻ የሚያወራ ካለን ሊያመጣው የሚችለው ለውጥ ካለመኖሩም በላይ ለወያኔ ዕድሜ መርዘም የራሱን እገዛ በማበርከቱ በሀገር ላይ የሚደርሰው ጉዳትና ኪሳራ ከወያኔ በማይተናነስ መልኩ በታሪክ ተጠያቂ እንደሆንን ልንገነዘብ ይገባል፡፡

በተለይ በተለይ ሀገር ብዙ ወጪ አውጥታባቹህ ሳይማር አስተምሮ ተቸግሮ አሳድጎ ነገር ግን በተለያዩ ገፊ ምክንያቶች (push factors) ከሀገራቹህ ተሰዳቹህ እናንተ እዚህ እንድትደርሱ ሽራፊ ሳንቲም ያላወጣባቹህን የባዕድ ሕዝብና የባዕድ ሀገር በማገልገላቹህ ሀገራቹህን ሕዝባቹህን ባለማገልገላቹህ ውለታውን ለመክፈል ባለመቻላቹህ ቁጭት የሚያንገበግባቹህ የሚቆጫቹህ የሚከነክናቹህ ዕረፍት የነሳቹህ ወገኖች ካላቹህ በተለያየ ምክንያት በረሀ ወርዳቹህ ትግሉን በአካል መቀላቀን ባትችሉም ለዚህ ሕዝባዊ ትግል ትርጉም ያለው ድጋፍ በማድረግ ሀገርራቹህን ልታገለግሉ ባለመቻላቹህ የተሰማቹህን ቁጭት ጸጸት በዚህ መወጣትና ሀገር ወገናቹህን መካስ እንደምትችሉ እንዲሁም ደግሞ  ጉልበታቹህን ዕውቀታቹህን ችሎታቹህን በባዕድ ሀገራት በማፍሰስ ዕድሜያቹህን የፈጃቹህና በዕድሜ መግፋት ምክንያት ከዚህ በኋላ በዕውቀታቹህ በጉልበታቹህ በችሎታቹህ ሀገራቹህንና ሕዝባቹህን ማገልገል የማትችሉ ጡረተኛ ወገኖች ሁሉ ካፈራቹህት ካላቹህ ገንዘብና ንብረት ቁጭታቹህን ጸጸታቹህን ሊያስወግድላቹህ ሊያስወጣላቹህ የሚችል መጠን ያለውን ገንዘብ ለትግሉ በማበርከት መንፈሳዊ እርካታን እንድታገኙ ይንን አጋጣሚ እንድትጠቀሙበት ላመለክታቹህ እወዳለሁ፡፡

የሞቀ ቤታቸውን ቅንጡ ኑሯቸውን ከፍ ያለ ደረጃቸውን ሁለነገራቸውን ጥለው ለእኔና ለእናንተ ለሚወዷት ሀገራቸው ሲሉ ነፍሳቸውን እስከመስጠት ታምነውና ቆርጠው በረሀ የገቡ ፕሮፌሰር ዶክተር ኢንጂኒየር… ወገኖቻችን ግንባር በግንባር ተፋጠው ዕላያቸው ላይ የሚወርድባቸውን ዝናብና ፀሐይ ሳይማረሩ ከሞት ጋር ተፋጠው ለማሸለብ ፋታ አጥተው ያገኟትን ተቃምሰው በረሀብ እየተፈተኑ እነኝህንና ሌሎችንም ሁሉ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ መሆናቸውን እያወቃቹህ ከሞቀ ቤታቹህ ሆናቹህ ይህንን ማድረግ ይከብዳቹሀል ለማለት እጅግ ይከብደኛል፡፡

  1. “ሸአቢያ እኛን ይዞ ወያኔን ለማስፈራራትና ከወያኔ የሚፈልገውን ለማግኘት እንጅ የምናደርገው ትግል ፍሬ እንዲያፈራ ለስኬት እንዲበቃም በፍጹም አይፈልግም” ይሄንን የሚሉ ሰዎች ምን ይጠቅሳሉ ለምሳሌ ይሉና “የአርበኞች ግንባር ትግል ከጀመረ 16 ዓመታት ሆኖታል፡፡ ይሄንን ሁሉ ዓመታት ሲቆይ አንድም የሚጠቀስ ተግባር ለመፈጸም አልቻለም እንዲዋጋ አልተፈቀደለትም ዝም ብለው ነው እንዲቀመጡ ያደረጋቸው” ይላሉ፡፡ ይመስለኛል እንዲህ እንዲሉ ያደረጋቸው ስለትግል ስለጦርነት በቂ ግንዛቤ አለመያዛቸው ነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ባለው ሁኔታ ውጤት ያለው ጦርነትም ሆነ ሽምቅ ውጊያ በቂ ኃይል ሳይያዝ፣ በቅጡ ሳይደራጁ፣ ሕዝባዊ ዕውቅናና ድጋፍ በበቂ ደረጃ ሳይገኝ ማድረግ ታይቶ ለመጥፋት ካሆነ በስተቀር ዘለቄታ ያለው እንቅስቃሴ ለማድረግ አይቻልም፡፡ ይሄንን ቅሬታ እንደሚያነሡ ሰዎች አስተሳሰብ ቢሆን ኖሮ የአርበኞች ግንባር ባለው አነስተኛ ኃይል እንደተመሠረተ ተንቀሳቅሶ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ጠፍቶ ነበር፡፡ እንደሚመስለኝ ሸአቢያም ይሄንን እንዳያደርጉ የከለከለበት ምክንያት የተጠናከረ ኃይል እስኪኖራቸው እስኪይዙ መኖራቸው መደራጀታቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ በቂ ግንዛቤ እስኪያዝበት ድረስ መጠበቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡ በመሆኑም ይሄንን ቅሬታ የሚያቀርቡ የትግሉ አካል የነበሩ አሁን ላይ በዚህ ቅሬታቸው ምክንያት ከዓመታት በፊት ትግሉን ጥለው የወጡ ግለሰቦች በወቅቱ ሸአቢያ ይሄንን ባለመፍቀዱ ያነሡበት ቅሬታ ተገቢ አይመስለኝም፡፡ ሸአቢያን በጣም በጥርጣሬ ዓይን ስለምናይ ብቻ እያንዳንዷን ነገር በክፋት እየተረጎምን ለተሳሳተ ድምዳሜዎች እየተዳረግን እንደሆነ ልብ ብንል መልካም ነው፡፡ ይህ ችግር በሥራችን ላይ የራሱ የሆነ እንቅፋት ሊፈጥር ይችላልና በማስተዋል ብንራመድ መልካም ነው፡፡

አሳቢ የመሰሉ ወገኖች የሚሰጡትን ምክር ሐሳብና ተቃውሞ አሳቢ ሆነው ሳይሆን ወያኔ ገዝቷቸው ቅጥረኞች ስለሆኑ እንደሆነ በምን ልናውቅ እንችላለን?

ይሄን ለመለየት በተለይ በአሁኑ ጊዜ ብዙም የሚያስቸግር አይመስለኝም ለማንኛውም እነኝህ ነጥቦች ይጠቅማሉ ብየ አስባለሁ፡-

  1. የሚናገሩትና የሚጽፉት ነገር ከረጅም ጊዜና ከአጭር ጊዜ አኳያ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ሀገርንና ሕዝብን ሳይሆን ወያኔን የሚጠቅም ከሆነ፡፡
  2. የሚናገሩትና የሚጽፉት ነገር ትግሉን ወደኋላ ለመሳብ ለማሰናከል የሚያሴር ከሆነ፡፡
  3. አሳቢ መስለው እኩይ ሥራቸው የሚከውኑት ወሳኝና አንገብጋቢ ወቅትን (timing) እያዩ ከሆነ ማለትም ወያኔ ሥጋት በተጋረጠበት ሰዓትና አጋጣሚዎች ላይ ከሆነ፡፡ ለምሳሌ ባለፈው አርበኞችና ግንቦት ሰባት ውሕደት በፈጸሙ ወቅት፣ ሰሞኑን ማጥቃት በመጀመሩ ትግሉን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ወሳኝ ወሳኝ ምእራፎች በሚመዘገብበት ወቅቶች ላይ ማለት ነው እነኝህ ቅጥረኞችም ይሄንን እመርታ ሊቀለብስ የሚችል ሥራን በመሥራት እራሳቸውን ጠምደው ታይተዋል፡፡
  4. እነዚህ አሳቢ መስለው የቀርቡ ግለሰቦች ሕዝባችን ነጻ እንዲወጣ የሚያቀርቡት ተጨባጭና ጠቃሚ አማራጭ የሌለ መሆኑና “ዝም ብለን አርፈን በወያኔ መገዛት ነው የሚሻለን” የሚል ዓይነት ከሆነ፡፡

እነዚህ እነዚህ ነጥቦች ቅጥረኞችን ለመለየት ይጠቅማሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ እነዚህ ኅሊናቸውን ብቻ ሳይሆን ሁለንተናቸውን ለሆዳቸው የሸጡ ምንደኛ ግለሰቦች ለወያኔ ያደሩ ሳይመስሉ መርዘኛ ሐሳቦቻቸውን ሳይፈሩና ሳያፍሩ በነጻነት ለመናገር ለመጻፍ የሚጠቀሙበት አንድ ሽፋን አለ “ሐሳብን በነጻነት የመግለጽን መብት ከመጠቀምና ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ” በሚል ሽፋን ነው፡፡ እንዳሉትም በትክክል ሐሳብን በነጻነት ከመግለጽና ይሄንን ዲሞክራሲያዊ መብት ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ከሚል አንጻር ያደረጉት ከሆነ ሚዛናዊነትን ሲጠብቁ ከሁለቱም አቅጣጫዎች ጠንካራ ጠንካራ ሐሳቦችን ሲያስተናግዱ ታገኟቸዋላቹህ፡፡ ነገር ግን ከሁለቱም አቅጣጫዎች ያሉ ጠንካራ ጠንካራ የመከራከሪያ ሐሳቦችንና ተሟጋቾችን የማያስተናግዱና ሚዛናዊነትንም የማይጠብቁ ወያኔን ተጠቃሚ ወደሚያደርግ ወገን የማድላት ዝንባሌ የሚታይባቸው ከሆነ ይሄንን “ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ተግባራዊ ከማድረግ” የሚለውን መብት ሥውር ተልእኮዋቸውን ለማሳካት ለሽፋን እየተጠቀሙበት ነውና ቅጥረኞች መሆናቸውን ልታረጋግጡ ትችላላቹህ፡፡

ለምሳሌ የቪኦኤው “ጋዜጠኛ” ሔኖክ ሰማእግዜር አቶ ኃይለማርያም ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ ሊያገኙት ስለነበረውና በተቃውሞ ምክንያት እንዳያገኙ የተደረገውን ሽልማትና እውቅና ዘገባ በሠራበት ጊዜ ዘገባውን የሠራበት መንገድ ግልጽ በመሆኑ ማንነቱን ለመለየት አስቸጋሪ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ሆን ብሎ የጋዜጠኝነትን መርሖዎች ግልጽነትንና ሚዛናዊነትን ባለመጠበቅ ወያኔን ለመጥቀም በማሰብ ትክክለኛ መረጃወች እንዳይካተቱ በማድረግ ዕውነትን ያዛባ ዘገባ ሠርቷል፡፡

ይህ ሰው ይሄንን ዐይን ያወጣ ስሕተት ረዳት አብራሪ ኃይለመድኅን አበራ ቦይንግ 767 የመንገደኞች አውሮፕላንን (በረርትን) በመጥለፍ አውሮፓ ጥገኝነት የጠየቀበትን ዘገባም በተከታታይ በሠራበት ወቅት ወያኔ “አብራሪው ለረጅም ጊዜ የአእምሮ ጭንቀት ላይ ነበረ ይሄንን ያደረገው ሕመሙ ተባብሶበት ከዚህ ችግሩ የተነሣ ነው” ብሎ የደረሰበትን የፖለቲካ ኪሳራ ለመሸፋፈን ጥረት በማድረግ የሰጠውን ሐሰተኛ ስም አጥፊ መግለጫ እውነት ወይም ትክክለኛ ለማስመሰል በማሰብ አሁንም ሚዛናዊነትን ያልጠበቀና የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ የጣሩ ዝግጅቶችን አቅርቦ ነበር፡፡ እናም ማንም ጋዜጠኞችም ሆኑ የብዙኃን መገናኛዎች ግልጽ የሆኑ የሞያዊ አሠራር ግድፈቶችን ሲፈጽሙ ስታዩ ያ ሰው ወያም ያ አካል ለሚከላከልለት ሀቁን ለደበቀለት (ለወያኔ) ያደረ የተገዛ የሱን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚጥር እንደሆነ ልታረጋግጡ ትችላላቹህ፡፡ እንዲህ መሆኑ በግልጽ የታወቀ ሰው በዚያ የጥፋት ዲርጊቱ ቢገለልና ቢወገዝ ተወገዝኩ ተገለልኩ ጥቃት ደረሰብኝ ብሎ ሊከስ ሊያማርር ሊወቅስ አይችልም መብትም የለውም፡፡

ምክንያቱም ጉዳይ ከሞያዊ ግድፈት አልፎ ሞያውን በማርከስ ኃላፊነትና ግዴታውንም ለግል ዓላማውና ጉዳዩ በመተላለፍ ሞያው የጣለበትን ኃላፊነት አላግባብ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ በመጠቀም ማለትም ወያኔ ወይም የወያኔ አባል በመሆኑ ሆን ብሎ የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ በመሞከር ጉዳዩን ወደ የመደብ ትግል ፍትጊያ አሻግሮታልና ወይም እንዲለወጥ ያደረገ በመሆኑና የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ በወያኔ ላይ ተስፋ ቆርጦ ትጥቅ ያነሣበት ሁኔታ ላይ ያለ በመሆኑ ይህ ሰው ከመወገዝም አልፎ ቦታና ሁኔታዎች ቢፈቅዱና እርምጃ ቢወሰድበትም እንኳ ድርጊቱ ሕገ ወጥ ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ የለም፡፡ ምክንያቱም በጋዜጠኝነቱ ያለውን ከለላ በሠራው ወንጀል አጥቶታልና፤ እራሱን ከጋዜጠኝነት አውጥቶ እንደ አንድ የወያኔ ታጋይ ሁሉ የወያኔ ጥቅም አስከባሪ አድርጓልና፡፡

ይህ እርምጃ ቢወሰድበት “ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ይከበር! እያሉ እነሱ ራሳቸው ይሄንን የሚያደርግን ሰው ያጠቃሉ” ተብሎ ሊገለጽ በፍጹም በፍጹም አይደባም፡፡ ይሄ ብየና አለመብሰልና አለማገናዘብም ነው፡፡ ምክንያቱም የሰውየው ሥራ ሆን ብሎ ከሞያዊ ሥነምግባሩ ውጭ በፈጸመው ስሕተት ምክንያት ሐሳብን በነጻ ከመግለጽ ጋራ ምንም የሚያገናኘው ነገር የሌለ በመሆኑና ይህ የፈጸመው ስሕተትም እራሱን እንደ አንድ የወያኔ ወታደር አድርጎ ስላቆመ ያለውን የጋዜጠኝነትም ሆነ የሌላ መብት ከለላውን ስለሚያሳጣው፡፡ ይህ ሰው ሚዛናዊነትንና ከሁለቱም ወገኖች ጠንካራ የሆኑትን ሐሳቦች ለማስተናገድ የፈቀደ ባለመሆኑ ይልቁንም ትክክለኛ መረጃዎችን ሆን ብሎ የሰወረ በመሆኑ ሐሳብን በነጻ የመግልጽ መብትን ለቅጥፈቱ ሽፋን ሊያደርግ ስለማይችል፡፡

ይሄ “ጋዜጠኛ” ሆነ ሌላ ማንነቱ የታወቀ ሰው ኢትዮጵያዊያን በሚያደርጉት ማንኛውም ኩነት ተገኝቶ ልዘግብ ቢልና ሕዝብ የሚያውቀው በወያኔነቱ በመሆኑ ከወያኔ ጋርም ልዩነታችንን በውይይትና በሌሎች ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) መንገዶች ልንፈታ የምንችልበት መንደግ ዕድል ተጠርቆሞ የተዘጋ በመሆኑና በቀረልን ብቸኛ አማራጭ በኃይል እርምጃ ለመፍታት መብታችንን ለማስከበር የተገደድንበት ሁኔታ ውስጥ ያለን በመሆኑ እንዲህ ዓይነቱን ሰው ሕዝቡ በራሱ ዝግጅቶች እንዳይገኝ የመከልከል የማስወገድ መብት አለው፡፡

“እነዚህ የሚከለከሉ (ከዚህ ዞር በሉልን አንያቹህ!) የተባሉ ጋዜጠኛም ሆኑ ሌሎች ግለሰቦች የወያኔ ደጋፊ ወይም ወያኔ እንኳን ቢሆኑ በመነጋገር ነው እንጅ ልዩነቱ መፈታት ያለበት ለምን በኃይል ይሆናል?” ከተባለ በመነጋገር ልዩነትን ለመፍታት 24 ዓመታት ለምነን ተማጽነን አይሆንም አይቻልም ተብለን መብታችንን ተነጥቀን ተነጋግሮ ልዩነትን የመፍቻው ዘመን አልፎ ሳንወድ በግድ ተገፍተን ወደ ሌላኛው የተተወልን ብቸኛ አማራጭ ማለትም በትጥቅ ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነትና መብት የማስከበር አማራጭ የገባንበት ወቅት ውስጥ በመሆናችን እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ካጠገባችን እንዳይደርሱ መከልከል ማራቅ እንችላለን መብታችንም ነው፡፡ ሌላ እርምጃ በእነሱ ላይ ለመውሰድ ያሉበት ሀገር ሕግና ሁኔታዎች አይፈቅዱም እንጅ እንደጠላትነታቸው ሁሉ ሁሉንም ዓይነት እርምጃ በእነሱ ላይ ለመውሰድ የያዝነውና የገባንበት ሕዝባዊ ትግል ያስገድደናል፡፡

ሌሎችም ድረ ገጾችና የብዙኃን መገናኛዎችም ቢሆኑ የመጻፍ፣ የመናገር፣ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ሲባል የሕዝብን የጋራ ጥቅም የሀገር ደኅንነትንና ህልውናን ለመጠበቅ ለመንከባከብ የተለየ ሐሳብ ካለ እሱን ለማስተናገድ የተሰጠ መብት እንጅ ሀገርንና ወገንን የሚጎዳ ወይም ሀገርንና ወገንን የሚጎዳን አካል ጥቅም ለመጠበቅ የሚነገር የሚጻፍ ሐሳብን ለማስተናገድ የተሰጠ መብት አይደለም፡፡ በግልጽ አማርኛ ወያኔ የዚህች ሀገርና የሕዝቧ ቀንደኛ ጠላት እንደመሆኑ ማንም ሰው የወያኔ ቅጥረኛ ሆኖ የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ ማለትም ከድሮ ጀምሮ የራሱን ቡድናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ሲል የሀገርን ሕልውናንና የሕዝብን ደኅንነትና ጥቅሞች ለመጉዳት ለማጥቃት ለአደጋ ለመዳረግ የሚያሴረውን የወያኔን ጥቅሞች ለማስጠበቅ የተሰጠ መብት አይደለምና በዚህ ሽፋን ይሄንን ሊያደርጉ እንደማይችሉ ጠንቅቀው ሊያውቁት ይገባል፡፡ የትም ሀገር ቢሆን ያለው አሠራር ይህ ነው፡፡ አሜሪካም ብትሆን ዜጋዋ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ ሥራ ሠርቶ “ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ነው” ቢል አትሰማውም “ብሔራዊ ጥቅሜን ለአደጋ ዳርጓል የሀገርንና የሕዝብት ደኅንነት ለአደጋ አጋልጧል ወይም ለጠላት ተቀጥሮ በመሥራት” ወንጂላ እንደ ስኖውደን ታሳድደዋለች እንጅ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ነው ብላ አትምረውም፡፡

እነኝህ አካላት ሞያዊ ሥነምግባራቸውን በመጣስ የሀገራችንን ጠላት የወያኔን ጥቅም ለማስጠበቅ ከወያኔ ጋር በማበር የወያኔ ቅጥረኛ በመሆን መረጃን በማዛባት እንደሚንቀሳቀሱ ባወቅን ጊዜ ይሄንን መብት አጥተዋልና ይሄንን መብት ለሽፋን መጠቀም አይችሉም፡፡ አሜሪካ ጥቅሟን የሚጎዳባትን ሰውና ዘገባ የሀገርና የሕዝብ ጠላት አድርጋ እንደፈረጀችና እንደምታሳድድ ሁሉ እኛ ኢትዮጵያዊያንም የሀገራችንንና የሕዝባችንን ብሔራዊ ጥቅሞች የሕልውናችንና የደኅንነታችን ጠላት የሆነው ወያኔን ያገለገለ ወይም የደገፈ ጋዜጠኛንም ሆነ ማንኛውንም ሌላ አካል ሁሉ የሀገራችንና የሕዝባችን ጠላት እንፈርጃለን እናሳድዳለንም፡፡ በግልጽ አማርኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ዕድሎች ተዘግተውበት መብቶቹን ለማስከበር ተገዶ የትጥቅ ትግል ውስጥ የገባበት ሁኔታ ውስጥ ያለ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ወዶና ፈቅዶ የወያኔ አባልና ደጋፊ የሆነ ካለ ይህ ሰው ሊሸሸግበትና ሊታደገው የሚችል ምንም ዓይነት ዋስትና እንደሌለው ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፡፡

ይመስለኛል በሌላም በኩል ወይ ድፍረት ቁርጠኝነት አጥተው ይሁን ወይ ደግሞ ቅድሚያ የሚሰጡት ቤተሰባዊም ሆነ ሌላ ጉዳይ ኖሮባቸው ብቻ በአንድም በሌላም ምክንያት በትጥቅ ትግሉ መሳተፍ የማይችሉ ከመሆናቸውና የትግሉ አካል ካለመሆናቸው የተነሣም “የሚመጣው ለውጥ በግል እኔን አያካትተኝም በተዋናይነት ቦታ ሰጥቶ አያሳትፈኝም” ከሚል ሥጋትና “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ከሚል ለራሳቸውም ለወለዷቸው ልጆችም ለሀገር ለወገንም ፈጽሞ የማይጠቅም የደነቆረና በሽተኛ የሆነ የራስወዳድነትና የምቀኝነት ጠንቀኛ አስተሳሰብ ወያኔ ወይም የወያኔ ደጋፊም ሳይሆኑ እየተደረገ ያለውን የትጥቅ ትግል የሚቃወሙ ወይም የማይደግፉ ያሉ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ የሚያስቡ ግለሰቦች የማሰብና የማገናዘብ ችሎታ በጣም የወረደ ነው፡፡ ከተቆጣጠራቸው ክፉ የምቀኝነት መንፈስ የተነሣ እንደ ዜጋ እራሳቸውን ጨምሮ ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው አስመስጋኝና አስከባሪ ሥራ በሌሎች ሲደረግ ሲያዩ ዐይናቸው ደም ይለብሳል፡፡ ዜጋ እንደመሆናቸው የዜግነት ግዴታ እንዳለባቸው ተረድተው እንደ ዜጋ ለሀገሬ ምን ማበርከት ይጠበቅብኛል? ሀገሬ ወገኔ ከኔ ምን ይጠብቃሉ? ብለው ራሳቸውን በመጠየቅ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት አስበው በቅንነት ተንቀሳቅሰው የሚያውቁ አይደሉም፡፡ ከተንቀሳቀሱም ለዝና ወይም ድብቅ የሆነ ሌላ የግል ጥቅማቸውን ለማስከበር ለማግኘት እንጅ ለሀገርና ለወገን በማሰብ አንዳች ነገር አድርገው አያውቁም፡፡

እነኝህ ግለሰቦች በሚቃወሙበት ጊዜ ለመቃወማቸው ምክንያት ሲጠየቁ ብዙ ጊዜ ሊያቀርቡት የሚችሉት ምንም ዐይነት ምክንያት የላቸውም፡፡ ካቀረቡም የረባ አይሆንም፡፡ ወይ እራሳቸው አይሠሩትም ወይ ደግሞ ሌላው እንዲሠራው አይፈልጉም አይፈቅዱም፡፡ ሌላው ሠርቶት ሲደነቅ ሲከበር ሲያዩ በሰይጣናዊ የቅናትና የምቀኝነት መንፈስ ቆሽታቸው ይደብናል፡፡ እንኳንና ለልጆቻቸው፣ ለሀገር፣ ለወገን ለራሳቸውም እንኳን ቢሆን ምን ቢሆን እንደሚበጅ በቅጡ የሚያውቁ ሰዎች አይደሉም፡፡ የሚገርመው ለምን እንዲህ እንደሚሆኑ ራሳቸውም እንኳን አያውቁትም፡፡ የሚያደርጉት ነገር ከግል ሕይዎታቸው ጀምሮ እስከ ሀገር ድረስ እንደሚጎዳ እንደማይጠቅም እንኳንና እራሳቸው ሊያስቡት ተነግሯቸውም እንኳ አይገባቸውም እንዲገባቸውም አይፈልጉም፡፡ በጣም የሚገርመው እንዲህ ዓይነት ክፉ የቅናትና የምቀኝነት መንፈስ ተማሩ በሚባሉት የሚብስ መሆኑ ነው፡፡ ችግሩ ግን የተማረ ከሚባለው ጀምሮ መሀይም እስከሚባለው ዜጋ ድረስ በየቦታው አለ፡፡ ሥራ እንዳይሠራ ብዙ ያውካሉ፡፡ በተለይ የተማሩ የተባሉቱ ተቃውሟቸውን የትም ሲያቀርቡ ተቃውሟቸው በቂና አሳማኝ ምክንያት ይኖረው ይሆናል በሚል ግምት ብዙ ጊዜ ሕዝብ ይሰናከልና ድጋፍ መስጠት ላለበት አካል ድጋፍ ይነፍጋል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ችግር ምክንያት የተቀደሰ ዓላማ ተይዞ ስንት ሊሠሩ የሚሞከሩ በርካታ ሥራዎች ከንቱ ሆነው ይቀራሉ፡፡ የእነዚህን ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ፈተና ተቋቁሞ ሥራ መሥራት የተቀደሰን ዓላማ ከግብ ማድረስ እንደ ዕድል አልፎ አልፎ የሚገኝ እንጅ በብዛት የሚታይ አይደለም፡፡ እናም ከዚህ ችግራቸው የተነሣ ሕዝባዊ ትግሉን የሚቃወሙ ወገኖች ሊኖሩ እንደሚችሉ እገምታለሁ፡፡ የሆነ ሆኖ የሚያቀርቡት ተቃውሞ ከወያኔነት አንጻር ባይሆንም ቅሉ በሕዝባዊ ትግሉ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከቅጥረኞች የማይተናነስ እንዲያውም የባሰ በመሆኑ እነሱንም እንደ ወያኔ ሁሉ የሀገርና የሕዝብ ጠላት አድርጎ መቁጠርና የሚፈጽሙትንም ጥቃት መከላከል ግዴታ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡

የተያያዝነው ትግል የሞት ሽረት ትግል ነው፡፡ ጨዋታ አይደለም የተያዘው ሀገርንና ሕዝብን ከጠባብ ጨካኝ ደንቆሮ አንባገነን አገዛዝ መዳፍ ፈልቅቀን ነጻ ለማውጣት ነው እየታገልን ያለነው፡፡ የግድ የሚወሰዱ ቆራጥ አቋሞች ይኖራሉ፡፡ የመረጥነውን የማውረድ መብቱ እያለን የመረጥነውን መንግሥት በኃይል ለማውረድ መሥዋዕትነት የምንከፍልበት ምንም ምክንያት የለንም መርጠን ያስቀመጥነውን መንግሥት ማንም በኃይል እንዲያስወግደው አንፈልግም አንፈቅድምም፡፡ አገዛዙ ያልመረጥነው በመሆኑና በኃይል የተጫነን ይህንን አገዛዝ በምርጫ ልናወርደው ልናስወግደው የሚያስችለን ሥርዓት በፍጹም የሌለ ስለሆነ እንጅ፡፡ ከተረባረብን በእርግጠኝነት ተሳክቶልን በቅርብ ጊዜ ሀገርንና ሕዝብን ነጻ እናወጣለን፡፡ ባለመብሰላችን እየሆነና ሊሆን ያለውን በማስተዋል አቅቶን አርቀንና ግራ ቀኝ መመልከት ተስኖን እያንዳንዳችን መወጣት ያለብንን ግዴታና ኃላፊነት መወጣት ቸግሮን መረባረብ መተባበር ካልቻልን ደግሞ ወያኔ እንደሚለው ለ60 ዓመታት ብቻ አይደለም ለዘለዓለሙ ባልመረጥከውና በኃይል ጫንቃህ ላይ ተጭኖ በነፍስ በሥጋህ እየተጫወተብህ ባለው አገዛዝ በወያኔ የጭቆና ቀንበር ስር ተጠፍንገህ ሰብዓዊ ክብርህን አተህ እየተዋረድክ የባርነት ኑሮህን እየኖርክ ይንንም የውርደት ኑሮ ለልጅህ እያወረስክ ፍዳህን ትቆጥራታለህ! በእርግጠኝነት ይህ እንዲሆን የሚወድና የሚደቅድ ኢትዮጵያዊ አይኖርምና ያለን ብቸኛ አማራጭ መረባረብ ነው እንረባረብ ወገን!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

 

በሳዑዲ አረቢያ በድምፃችን ይሰማ ደጋፊዎች ላይ የሕወሓት መንግስት እየሰራ ያለው ደባ ተጋለጠ

0
0

ኢንጅነር መሃመድ አባስ ሪያድ

የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረዓት ካድሬዎች መቀመጫቸውን ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ ካደረጉ ወዲህ የ ህዝበ ሙስሊም እንቅስቃሴ ለማፈን የተለያዩ ስልቶችን ነድፈው ከአካባቢው የመንግስት ሹማምንቶች ጋር ሲንቀሳቀሱ እንደ ነበር ይታወቃል። እነዚህ ምስለኔዎች ለመንግስት ባላቸው ታማኝነት ከጅዳ እስከ ሪያድ በዘለቀ የስለላ መረባቸው በሳውዲ« ድምጻችን ይሰማ የሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ » በሚያደርገው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚሳተፉ ሙስሊም ወገኖቻቸውን ስም ዝርዝር ለመንግስት በማቅረብ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ግፊት ሲያደርጉ የነበረ ከነፍሳቸው ይልቅ ለጥቅም ያደሩ መሆናቸውን አይሌ የእምነቱ ተከታዮች ይገልጻሉ፡፡ በተለይ እነዚህ ተላላኪዎች ባላቸው መጠነኛ ሃይማኖታዊ እውቀት ጥቂት የእማነቱን ተከታይ የሆኑ ወንድምና እህቶቻቸውን በማሳሳት ለዚሁ መንግስታዊ ሴራ ተልዕኮ ማስፈጸሚያ ግበአት አድረጓቸዎል ፡፡
news ethiopia 2
ከህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረዓት በሚወርድላቸው ባጀት ጡንቻቸው ከግዜ ወደ ግዜ እየፈረጠመ የመጣው መስለኔዎች የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት በመበታተን በሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ትግል አንድነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር መቻላቸው በጌቶቻቸው ዘንድ ምሳጋና ሲቸራቸው በአንጻሩ በህዝብ እይተተፉ የመምጣታቸው ሚስጠር የነዚህ ተላላኪዎች ማንነት እርቃኑን አስቀርቶጣል። በተለይ እነዚህ ወገኖች በኃይማኖት ሽፋን ዘረፋ ላይ መሰማራታቸውን የሚገልጹ ምንጮች ጅድና ሪያድ ጨምሮ በተለያዩ የሳውዲ ግዛቶች ውስጥ « ጽናት » ብለው ባደራጁት ስብስብ በመታገዝ የአባላት መዋጮ ፤ ልዩ መዋጮ ፤ለታሰሩ የትግል አጋሮቻችን ቤተሰብ ድጎማ …..…. ወዘተ በሚል ምክንያት እስከ 300.000 ሪያል ወይም ከ 1. 5 ሚልዮን በር በላይ ጥሬ ገንዘብ ያለደረሰኝ ከህዝበ ሙስሊሙ ኪስ በመሰብሰብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን ይናገራሉ፡፡ በተጨማሪም በግፈኞች ወህኒ እየማቀቁ የሚገኙ አስቷዝ ያሲን ኑር ዒሳ፤ አህመዲን ጀበል በቀርቡ ከወህኒ ቤት « ፈርዖን የአንባገነኖች ተምሳሌት ፤ ይወት ግብህን ቅረጽ » በሚል ርዕስ የጻፉትን ጽሁፍ በማሳተም ከመጽሀፉ ሽያጭ የተገኘውን በሚልዮን የሚቆጠር ጥሬ ገንዘብ ለግል ጥቅማቸውና ለዚሁ መንግስታዊ ድብቅ አጀንዳ ማስፈጸሚያ ማዋላቸው በአብዛኛው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ዘንድ ቁጣን አስነስቷል።

ከዚህ ባሻገር ይህ በኃይማኖት ሽፋን ዜጎቻችን ላይ የሚፈጸመው ምዝበራ በተለይ ሳውዲ በሚኖሩ ሙስሊም ሴት እህቶቻችን ላይ ያነጣጠር መሆኑን የሚናገሩ ምንጮች ለዚህ ተግባር ማስፈጸሚያ ጅዳ፤ ጣይፍ፤ እና መካ ከተሞች ውስጥ እስከ 150 የሚሆኑ የተለያዩ የዎትሳፕ « whatsApp » ጉሩፕ እንዳሏቸውና እያንዳንዱ ጉሩፕ ወረሃዊ መዋጮ የሚከፍሉ ከ 50 በላይ ሴት እህቶቻችንን በአባልነት ማቀፉን ያስረዳሉ።ይህ እራሱን «ጽናት» እያለ የሚጠራው የካድሬዎች ስብስብ ሪያድ ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ ከ 70 በላይ የዎትሳፕ « whatsApp » ጉሩፕ እንዳሉት ቢነገርም ሪያድ የሚገኙት «የጽናት» ኃላፊዎች ከእህቶቻችን ቦርሳ ህገወጥ በሆነ መንገድ ለወራት ሲሰበስቡ የከረሙትን ከ 80.000 ሺህ ሪያል አሊያም ከ ግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ጥሬ ገንዘብ ጅዳ ለሚገኙት የስረአቱ ታማኞች ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በተፈጠረ አለመግባባት በተከሰተ ግጨት እስካሁን ከሁለቱም ወገን የተጎዳ ባይኖረም የህወሃት /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት ሰውር ደባ መክሸፉን የሚናገሩ ምንጮች በሳውዲ አረቢያ «ድምጻችን ይሰማ» የነጻነት ትግል እንቅስቅሴ ላይ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖ መሰንበቱን አልሸሸጉም።

ይህን ተከትሎ በሙስሊሙ የትግል አንድነት ላይ የተቃጣውን ሰውር ደባ ህዝበ ሙስሊሙ አንድነቱን ጠብቆ መንግስት ላይ የጀመረውን ህገ-መንግስታዊ የመብት ጥያቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ «ድምጻችን ይሰማ » ሪያድ ከተማ ላይ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ማካሄዱን ፍትሕ ራዲዮ ካሰራጨው ዘገባ መረዳት ተችሏል። በዚህ ዙሪያ ጅዳ የሚገኘውን «የጽናት» ሃላፊ ሼክ መሃመድ ዘይን ዘህረዲን የዝግጀት ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ ለግዜው አልተሳካም ።

22 አመት እስራት ያስፈረደብን ኢስላማዊ መንግስት ወይስ ኢስላማዊ መጅሊስ እንዲቋቋም መጠየቃችን??

0
0

muslim addis
አቡ ዳውድ ኡስማን

የኢትዬጲያ ህዝበ ሙስሊም በኮሚቴዎቻችን አማካኝነት ለመንግስት ያቀረብነው ጥያቄ ኢስላማዊ መጅሊስ ይመስረት እንጂ ኢስላማዊ መንግስት ይቋቋምል የሚል ጥያቄ አልነበረም፡፡ ኮሚቴዎቻችንን እስከ 22 አመት የሚደርስ እስራት ያስቀጣቸው ወንጀል ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ህዝብን ለሽብር በማነሳሳት የሚል አሳፋሪ የሃሰት ክስ ነበር፡፡ አንዳንድ የሌላ እምነት ተከታዬች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ወይም የሚከፈላቸው ካድሬዎች ኮሚቴዎቻችን እንደተባለው ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት ሲንቀሳቀሱ መንግስት ያሰራቸው እንደሆነ አስመስለው ሲያቀርቡ እና አስተያየት ሲሰጡ ታዝቤያለው፡፡

እስቲ ለማንኛውም እዚህ ጋር ቆም እንበልናል ኢስላማዊ መጅሊስ ይመስረት ማለታችን ከቶውንስ በምን ስሌት ኢስላማዊ መንግስት ለመስረት መንቀሳቀስ በሚል ሊተረጎም እንደሚችል አብረን እንመልከተው

ቅድሚያ የመጅሊስ እና የመንግስትን ልዩነት ይህን ይመስላል

1. መጅሊስ የሙስሊሞች ተቋም ሲሆን መንግስት ግን የአንድን ሃገር ህዝብ በበላይነት በምርጫ ተመርጦ የሚያስተዳደር አካል ነው፡፡

2. መጅሊስ በሙስሊሞች በሚመረጡ የሃይማኖት አባቶች የሚመራ ሲሆን መንግስት ግን በሁሉም የሃገሪቱ ዜጎች ሃይማኖት፣ዘር፣ቀለም ሳይለያቸው በጋራ ያስተዳድረናል የሚሉትን በምርጫ ወስነው የሚሰርቱት አካል ነው፡፡

3. መጅሊስ በህዝበ ሙስሊሙ በየመስጂዱ በሚመረጡ የሃይማኖት አባቶች የሚመራ ሲሆን መንግስት ግን በቀበሌ ወይም በየምርጫ ጣብያ ተምርጦ በአብላጫ ድምፅ የፓርላማ ወንበር ባገኘ ፓርቲ የሚመራ አካል ነው፡፡

4. ኢስላማዊ መጅሊስ ማለት በኢትዬጲያ ውስጥ የሚገኙ ሙስሊሞችን ወኪል በመሆን ከየትኛውም የፖለቲካዊ አስተሳሰብ ፀድቶ በሃይማኖታዊ ጉዳዬች ላይ ሙስሊሙን ወከሎ የሚሰራ፣ ሃይማኖቱን ምዕመናን የሚማሩበትን እና የሚተገብሩበትን ሁኔታ የሚያመቻች፣ አማኙ ማህበረሰብ ከመንፈሳዊ ሂወቱ በተጨማሪም በሃገሪቱ ሰላም እና ልማት ላይ ተሳታፊ እንዲሆን የሚያግዝ ተቋም ማለት ነው፡፡ መንግስት ማለት ግን ከሃይማኖታዊ ጉዳዬች በጸዳ መልኩ በሁሉም የማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ እና ሌሎች ተግባራቶች ላይ ሀዝብን ተጠቃሚ እንዲሆን እና ዜጎች በሃገራችን በሰላም፣በአንድነት፣በነፃነት እና በሃገራቸው ፍትሃዊ በሆነ ልማት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ተግባር የሚያከናውን ግዙፍ አካል ነው፡፡

5. በተጨማሪም መጅሊስ እና መንግስት አንድ አለመሆናቸውን፣አንድ ሊሆኑም እንደማይችሉ በህገመንግስቱ አንቀፅ 11 ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡

ይህ የሰማይ እና የምድር ልዩነት እያለ ከቶውንስ እንዴት ኢስላማዊ መጅሊስ እና ኢስላማዊ መንግስትን ገዢው ፓርቲ መለየት ተሳነው??

በትግራይ ክልል የውቅሮ ከተማ ህዝበ ሙስሊም ወኪል የነበሩት ኡስታዝ ቡሽራ ያህያ ፍርድ ቤት መጅሊስን ተቃውማቹሃል በሚል በሽብር ወንጀል በተከሰሱበት ወቅት የመከላከያ ቃላቸውን ሲሰጡ እንዲህ ብለው ነበር

“እኛ እኮ መጅሊስ እና መንግስት የተለያዩ መስሎን ነበር፡፡ በህዝበ ሙስሊሙ ያልተመረጡ ህገ ወጥ አመራሮችን ህዝበ በመረጣቸው ይተኩ ብለን የመጅሊሱን አመራሮች መቃወማችን መንግስትን እየተቃወምን መሆኑን አላወቅንም ነበር ፡፡ መጅሊስ ማለት መንግስት መሆኑን አሁን ነው ያወቅነው” በማለት ቃላቸውን ሰጥተው ነበር፡፡

በትክክልም የሙስሊሞች ተቋም የሆነው ኢስላማዊ መጅሊስ ይቋቋም ብሎ መጠየቅ ኢስላማዊ መንግስት ይመስረት ብሎ ከመጠቅ ጋር አንድ ሊሆን የሚችለው መንግስት እና መጅሊሱ አንድ ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡

መንግስትም በሃምሌ 27 የፍርድ ውሳኔ በአደባባይ ያረጋገጠልን ነገር ቢኖር ይህንን ነው፡፡ የህዝበ ጥያቄ አንግበው መንግስት ጋር የቀረቡ ወኪሎችን እንዴት የመጅሊሱ አመራሮች ይቀየር ትሉኛላችሁ ? ምርጫው ቀበሌ ሳይሆን መስጂድ ውስጥ እንዴት ይካሄድ ትሉኛላቹ? ምርጫውንስ እንዴት ሙስሊሙ ነፃ ሆኖ እራሱ በሚያምንባቸው ህዝባዊ የምርጫ አስፈፃሚዎች ይካሄድ እንዴት ትላላችሁ?. መጅሊሱን መንካት እኔን መንካት ነው በመሆኑም ጥያቄያችሁ መጅሊሱን እንቀይር ማለታችሁ አንዱን የኔን ተቋም ኢስላማዊ ይሁን ማለታችሁ ነውና በማለት የ 22 አመት እስር ቅጣት በይኖባቸዋል፡፡

ሃገራችን ኢትዬጲያ ይህን ፍትህ የሚያሰፍን መሪ አልሰጣትም ፡፡ ጥቁሩን በነጭ ቀየረው.አሸባሪውን በንፁሃን መነዘረው፣ ህገ አክብሩ በሃይማኖት ጣልቃ አትግቡ ብሎ በአደባባይ ህገ መንግስቱን የሰበከውን ህገ መንግስቱን አፍራሽ ተብሎ በ22 አመት እስራት በግፍ እንዲቀጣ አደረገው፣ ሰላም የሰበከውን ሰላም አደፍራሽ አለው፣ ወዘተ…..

ሃይማኖት እና መንግስትን ለመደባለቅ የሚሞከር በፀረ ሽብር ክሱ 22 አመት እስራት የሚቀጣ ከሆነ ሐይማኖት እና መንግስት ይለያዩ፣ መንግስት በሃይማኖት ውስጥ እጁን ጣልቃ አያግባ ፣የህገ መንግስቱ አንቀፅ 11 ይከበር ያለ አካልስ ምን መሸለም ይኖርበታል?? ይህ ያደረጉት ወኪሎቻችንስ አሁን እጣ ፈንታቸው ምን ሆነ??

መጅሊሱን እና መንግስትን አንድ ተቋም ያደረጋቸው፣ የሃይማኖት ተቋሙን በፖለቲካ መሪ ካድሬዎች እንዲመሩ ያደረገ፣ የእምነት ቦታዎችን የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈፀሚያ ያደረገ ባጭሩ አብዬታዊ መጅሊስ የመሰረተው አካልስ በፀር ሽብር ህጉ በስንት አመት ይቀጣ???

‘አብዬታዊ መጅሊስ “በኢስላማዊ መጅሊስ ይተካ በማለታችን ነው ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት በማሴር በሚል የሃሰት ዲሪቶ ክስ የወከልናቸው ኮሚቴዎቻችን በግፍ እስራት የተበየነባቸው፡፡

አብዬታዊ መጅሊስን ወይም መንግስታዊ መጅሊስን መቃወም ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት መጣር መሆኑን ገዢዎቻችን እስቲ ከህገ መንግስቱም ሆነ ምናልባትም እነሱ ብቻ ከሚመሩበት ህግ ካላቸው በገባቸው ቋንቋ ያስረዱን??

muslim dim

በየትኛው የአለማችን ክፍል ይሆን የሃገሪቱ መተዳደሪያ ደንብ የሆነውን ህገ መንግስት ይከበር ብሎ የሚጠይቅ አሸባሪ ያለው??የትኛው አሸባሪ ይሆን ህግ መንግስቱን በእጁ ይዞ በአደባባይ ህጉን አክብሩ እያለ የሚሰብክ?? የትኛው አሸባሪ ይሆን ሲደበድቧችሁ፣ሲመቷቹህ፣ሲገድሏቹም በሰላማዊ መንገድ ችላቹህ ዝም በሉዋቸው የሚል አሸባሪ ያለው?? በየትኛው የአለማችን ክፍል ይሆን የሰው ሰራሽ ህግ የሆነውን ህገ መንግስት ይከበር እያለ ኢስላማዊ መንግስት ለመመስረት የሚንቀሳቀስ አሸባሪ ያለው?? የትኛው አሸባሪ ነው በአደባባይ የሌሎች እምነት ተከታዬችን አክብሩ፣በሰላም ተኗኗሩ እያለ የሚሰብከው??የትኛው አሸባሪ ነው በሚሊዬን የሚቆጠር ደጋፊ ኖሮት ህግ እና ስርአት አክብሮ እንዲከበር የሚንቀሳቀሰው??በየትኛው ሃገር ነው ለሃገሪቷ ልማት እና ሰላም ሁሌም የበኩሉን አስተዋፅኦ የሚወጣ አሸባሪ ያለው?? የትኛው አሸባሪ ነው ሰላምን፣ ፍቅርን፣መቻቻልን፣አንድነትን የሚሰብክ ?? የዚህ መሰሉ አሸባሪ ያለው እምዬ ሃገሬ ኢትዬጲያ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ይህን ተግባር በፈፀም የተወነጀሉት እነዚህ ብርቅዬ የሃገር ሃብት የሆኑ ኮሚቴዎቻችን ናቸው!!!

ውሸት ለጊዜው ፎቅ ገንብታ ብትቀመጠም በደሳሳ ጎጆ ያለችው እውነት አንድ ቀን ፈንቅላ መውጣቷ አይቀርም!

ውድ ወኪሎቻችን የሃቅ ፈራጁ ጌታ ነፃ ያወጣቹሃል ኢን ሻ አላህ

መስዋት እየሆኑ ለሚገኙት ኮሚቴዎቻን አላህ ብርታቱን፣ ቅዋውን፣ ሰብሩን፣ ኢስቲቃማውን፣ ደስታውን፣ ሰኪናውን ፣ ኢህላሱን ይወፍቃቸው!

አሚን

በቀለ ገርባ ሚኒሶታ ገቡ * የፊታችን ቅዳሜ ሕዝባዊ ስብሰባ አላቸው

0
0

bekele gerba 1

(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሞ ፌዴራሊስት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ኦቦ በቀለ ገርባ ሚኒሶታ ገብተዋል:: በሚኒያፖሊስ ሴንት ፖል ኤርፖርት ሞቅ ያለ አቀባበል የተደረገላቸው ኦቦ በቀለ የፊታችን ቅዳሜ ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳላቸው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል::

እንደደረሰን መረጃ ከሆነ የፊታችን ቅዳሜ ኦገስት 8, 2015 በኦሮሞ ኮምዩኒቲ ሴንተር ከ3 ሰዓት ጀምሮ ስብሰባው ይካሄዳል::

ስብሰባው የሚካሄድበት አድራሻ
465 Mackubin St, St Paul, MN 55103 ነው::

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live