Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ያንዳርጋቸው ላፕ-ቶፕ ( ሄኖክ የሺጥላ )

$
0
0

ቻይናዊው ጠሐፊ ሱን ዙ << የጦርነት ጥበብ >> ( The Art of War ) በተባለው መጽሐፋቸው ፣ በምዕራፍ 4 ፣ ስልታዊ መሰናስኖች ወይም በፈረንጂኛው ( Tactical Dispositions ) በሚለው ዘውግ አርዕስት (Sub title ) ስር እንዲህ ይላሉ ፣ << To secure ourselves against defeat lies in our own hands, but the opportunity of defeating the enemy is provided by the enemy itself >>። ይህንን እንደወረደ ( በግርድፉ ) ወደ አማርኛ ብቀዳው << ራሳችንን ከተሸናፊነት ለመጠበቅ የሚያስችለው ነገር በራሳችን እጅ ላይ ያለ ሲሆን ፣ ጠላታችንን ለማሸነፍ የሚያስችለውን ዕድል ግን ራሱ ጠላታችን የሚያመቻቸው ነው >> ይላሉ ።
andargachew Tisge
ከምናየው ፣ ከደረሰብን እና ከምንረዳው ተነስተን እኛም አንድ ነገር መናገር እንችላለን ። ለቀጣዩ ትግል ራሳችንን ማዘጋጀት እና ወደ ትግሉ ጎራ መቀላቀል በኛ እጅ ያለ ሲሆን ፣ ራሳችንን የምንሰዋለት ትግል ፍሬያማነት ግን ከሞላ ጎደል እየተሳካ ያለው ፣ ወያኔ ( ህውሃት ) እያመቻቸልን ባለው እድል ነው ። የእድል ስም ዝርዝሮቹ በጥቂቱ የሚከተሉት ናቸው

1) የህዝቦች እኩልነትን ፣ እኩል ባለመሆን ሲያከብር
2) ምርጫ ዝንተ ዓለም ፣ ከስልጣን ዝንተ ዓለም ጋ ፣ ጋብቻ ፈጽመው ፣ እንከን በሌለው ሁናቴ ሕዝቡን በነጻነት ለመጨቆን የወሰኑ ለት
3) ሕዝብ ጉልበት የለውም የሚል ስርዓት ፣ የሕግና የሕገ መንግስት አርቃቂ እና ተርጏሚ ሲሆን
4) በማፈን ፣ በማሰር ፣ በመግደል እና በመዋሸት ሀገር ይመራል ብሎ በጽኑ የሚያምን ድርጅት ፣ የእድገት እና የለውጥ ሐዋርያ ስለመሆኑ ሲደሰኩር እና ሲደሰኮርለት
5) የእቃቃ ዘመኑን በጫካ አሳልፎ ፣ በአባወራ እድሜው እቃቃ የሚጫወት ጎልማሳ እና ሽማግሌ ባለስልጣን ፣ እሱ ከሌለ ሀገር እንደሚፈር እንድናምን ለማድረግ ሲሞክር
6) ነጻነት እንደ ቅንጦት በሚታይበት ሀገር ፣ ተመሳሳይ የሽብር ዘገባዎችን ፣ ጥናታዊ ፊልሞችን ፣ ክሶችን ፣ እና ውንጀላዎችን እያጠናቀረ ፣ ሕዝቡን የሚያምስ ስርዓት ፣ የፖለቲካ እስረኞች ፣ ጋዜጠኞች ፣ አረጋውያን እና ወዘተ ፣ በማረፊያ ቤት ቆይታቸው በቂ የህክምና አገልግሎት እንዳያገኙ ብቻ ሳይሆን በህክምና ፣ በምግብ ፣ እና በመሳሰሉት ነገሮች እጦት እንዲሰቃዩ በማድረግ የሚታወቅ ስርዓት ፣ ስለ እስረኛዎች እንክብካቤ ሲያወራ እና ሲተርክ

እነዚህ እና ሌሎች እልፍ ምክንያቶች ጠላታችንን ለማሸነፍ ፣ ጠላታችን ራሱ የሚያመቻቸው ነገሮች << the opportunity of defeating the enemy is provided by the enemy itself >> የተባለውን እንደሚወክል ነው ።

በነገራችን ላይ ፣ ታጋይ ቴዎድሮስ አድሃኖም ፣ አንዳርጋቸው ላፕ-ቶፕ እንደተሰጠው ፣ መጽሐፍም ጽፎ እንደጨረሰ ፣ አዳማንም አይቶ << ፑ ! አዳማ ! ያንቺን እድገት ሳላይ አስመራ በርሃ ላይ ባለመቅረቴ ፣ የመን ላይ ለያዙኝ የወያኔ ደህንነቶች ምስጋና ይግባቸው >>እንዳለ ነግረውናል ።

በነገራችን ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የጻፉት መጽሐፍ ለገበያ ሲቀርብ << በሀገሪቱ ፈጣን እድገት እንደተገረሙ ፣ በእስር ቤት ውስጥ ይህንን መጽሐፍ ጽፈው ለህትመት እስካበቁበት ድረስ እየተደረገላቸው ስላለው እንክብካቤ ፣ የወያኔ ባለስልጣናትን እንግዳ ተቀባይነት ፣ ድሮ ድሮ ስለ ህውሃት ቶርቸር የሰሙት እና እሳቸው የገጠማቸው ፍጹም የተለያየ እንደሆነ ፣ እንኳን ይቅርና ህዝቡ ፣ እሳቸው፣ ( ምንም እንኳ በአሸባሪነት ቢከሰሱም ) ፣ በቀን ሶስቴ እንደሚመገቡ ፣ ይህም አቶ መለስ ዜናዊ ሀገሪቷን የዛሬ ሃያ ዓመት በቀን ሶሥቴ የሚበላ ሕዝብ እንዲኖር አደርጋለሁ ያሉትን ቃላቸውን እንደጠበቁ ፣ ይህም ቃላቸው እስር ቤት << በወያኔኛ ታች ድረስ ወርዶ እየተተገበረ ያለ ስለመሆኑ >> ፣ ውጭ እያሉ የሰሙት እና እሳቸው ከማይታወቀው እስር ቤታቸው ውስጥ ሆነው ያዩት እጅግ እንደሚለያይ ፣ ያቺ አረንጏዴ ቱታቸውን እንኳ በእንክብካቤ ብዛት እንደወፈረች ፣ በቀን ሶሥቴ በላብ እንደምትታጠብ >> ይተርካል ተብሎ ይጠበቃል ። በነገራችን ላይ ግን አቶ መለስ ዜናዊ << ይህ ሕዝብ የዛሬ 20 ዓመት በቀን ሶሥቴ እንዲበላ እናደርጋለን >> ያሉት መከራውን ነው ንፍጡን ? ሀ ና ለ ያለው ማን ነበር ?

ለማንኛውም አንዳርጋቸው ላፕ- ቶፕ ተሰጥቷቸው ፣ ዘና ብለው ነው ያሉት ። ምንም ማሰብ አያስፈልግም !! እንደውም ፣ እንደውም ትንሽ ኮኔክሽን አስቸግሯቸው ስለነበር ፣ የተሻለ ኮኔክሽን ካለ ቼክ እንዲያረጉ፣ ወደ አዳማ ልከናቸዋል። በነገራችን ላይ የጻፉት መጽሐፍ አርስት << ኢትዮጵያ በልማት ጎዳና ስትጏዝ ፣ እኔና ግንቦት ሰባት ይህንን ለማፍረስ ኤርትራ ድረስ >> የሚል ነው አሉ ።

ለነገሩ እንግሊዝ ሀገር እኮ ላፕ- ቶፕ የለም ። በአሁኑ ጊዜ ፣ ይሄ ልማታዊ መንግስታችን ስለሆነ እንጂ ፣ ማን በነጻ ( ሊያውም እንደ አንዳርጋቸው ላለ ለአሸባሪ) ላፕ- ቶፕ ይሰጣል ? ደርግ ቢሆን ኖሮ እኮ ፣ ላፕ-ቶፕ ሳይሆን አፕ -ሳይድ ዳወን ዘቅዝቆ ተርቸር ነበር የሚያደርገው ። እንደ ወያኔ ያለ ቅዱስ ስርዓት ግን ያንን አይደርግም ። በነገራችን ላይ እኔ እስክንድርም ቢሆን << በቢክ እስክርቢቶ ስንጽፍ ነው ሃሳብ የሚመጣልን>> ስላሉ እንጂ ለነሱም ላፕ-ቶፕ ድርጅታችን ኢህአዲግ አዘጋጅቶ ነበር ።

በነገራችን ላይ እህታችን ርዮት አለሙ ለአራት ዓመት በጡት ህመም ስትሰቃይ ፣ ቢያንስ ቢያንስ የበሽታዋን መንስኤ ታውቅ ዘንድ ፣ ለምንድን ነው ላፕ- ቶፕ ያልተሰጣት ? አንዷለም አራጌ ፣ ተመስገን ደሳለኝ ፣ ውብሸት ታየ ፣ አቡበክር ( አቡኪ )ለምንድን ነው አዳማን እንዳያዩ የተደረገው ? <<በብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች >> እኩልነት የሚያምን ስርዓት ፣ በእስረኞች እኩልነት አያምንም ማለት ነው ? ለዚያውም እስረኞቹ ካንድ የክስ ብሔር የመጡ ሆነው ሳለም እንኳ? ማለጠ ፣ ቢያንስ ቢያንስ ፣ እስከምናውቀው << ከሰማነው >> እነዚህ ሰዎች በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ነው የታሰሩት ፣ ታዲያ የዚያ ብዙ የተወራለት ሽብር መስራች እና አናት ላፕ-ቶፕ ሲሰጠው ፣ ቢያንስ ቢያንስ ለነ እስክንድር አይ ፖድ ባለመሰጠቱ አዝነናል ። ደሞ ለሞላ ለተረፈ ኮምፕተር ። <<ቢለዩ ቢለዩ አመትም አይቆዩ>> የሚለው አባባል 24 ዓመት ህዝብና ሕዝብ በመለያየት ለኖረ ስርዓት ይሰራ ይሆን ?

ግን ለመሆኑ እንዴት ነው ለአቶ አንዳርጋቸው የሰጣችሁት ላፕ ቶፕ ባትሪው ከ << ሊትየም >> ይሆን የተሰራው ? ወይኔ ለኔ ቢሆን የሰጣችሁኝ ፣ ሲደብረኝ ባትሪውን ገምጬ አዝናናችሁ ነበር ። ምን ያረጋል !

ለማንኛውም ፣ በሚቀጥለው አቶ አንዳርጋቸውን ሰይፉ ፋንታሁን ሾው ላይ እንደምታሳዩን ተስፋ እናደርጋለን ። አዲስ ስለ ጻፉት መጽሐፍ ሲገልጹ ።

አዎ << To secure ourselves against defeat lies in our own hands, but the opportunity of defeating the enemy is provided by the enemy itself >>። << ራሳችንን ከተሸናፊነት ለመጠበቅ የሚያስችለው ነገር በራሳችን እጅ ላይ ያለ ሲሆን ፣ ጠላታችንን ለማሸነፍ የሚያስችለውን ዕድል ግን ራሱ ጠላታችን የሚያመቻቸው ነው >> የሚለው አባባል ፍጹም እውነት ነው ።


”አላሙዲን ሆይ…??”–ከኤርሚያስ ለገሰ

$
0
0

በዚህ አመት በሀገረ አሜሪካን በሚገኙ ታላላቅ ሚዲያዎች አነጋጋሪ የሆነውን የፒተር ሽዊዘር ” CLINTON CASH” የሚለውን መጵሀፍ እንደነበረ የሚታወቅ ነው። መጵሀፋን ከወዳጆቼ ተውሼ እያነበብኩ ገጵ 134 ስደርስ ከዛ በላይ መቀጠል አልቻልኩም። እንዲህ በማለት ራሴን ጠየኩ፣
” አላሙዲን ሆይ ከኢትዬጲያውያን የነጳነት ጫንቃ መቼ ነው የምትወርደው?፣
” አላሙዲን ሆይ እንደ ሰው ተቆጥረን የመኖር መብታችን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀህ የምትኖረው እስከመቼ ነው?”

እነዚህን ጥያቄዎች ለማንሳት ያስገደደኝ በፒተር መጵሀፍ ከገጵ 128 -134 የሰፈረውን ቁምነገር በማንበቤ ነው። ርግጥ አላሙዲን እና ከስሩ የኮለኮላቸው ኮልኮሌዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የፈጰሟቸውን ወንጀሎች ጠንቅቄ ስለማውቅ ፒተር በምርመራ አግኝቶ ከጳፈው በላይ መናገር እንደሚቻል አውቃለሁ። ጊዜውና ሰአቱ ሲደርስ። በነገራችን ላይ ከእኔ በላይ ስለ አላሙዲን እና ግብረአበሮቹ ብዙ የሚያውቁ ኢትዬጲያውያን በየቦታው አጋጥመውኛል። አንዳንዶቹም ለሼሁ እንደነገሩት እና ” ጆሮ ዳባ ልበስ!” እንዳለ አጫውተውኛል። እሁድ እለት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ላሊበላ ሆቴል ያገኘሁት የሆቴሉ ቋሚ ደንበኛ የሼሁ የቅርብ ጓደኛ እንደነበረ ብዙዎች ስለመሰከሩ፣ ጆሮዬን ከፍቼ አዳምጠው ነበር።
Shek AlAMUDI
ባለፋት 24 አመታት ሼህ መሀመድ አላሙዲን በኢትዬጲያውያን የእለት ተእለት ህይወት ውስጥ ተጵእኖ የሚያሳድር ሰው እንደሆነ ማንም አይክደውም። በዚህ ምክንያት የሼሁ ሁኔታ በኢትዬጲያውያን ዘንድ በበርካታ ወለፈንዲዎች የተሞላ ነው። ከኮልኮሌዎቹ አንጳር ሰውየው በተቃርኖ ውስጥ ባለ ቀጭን ገመድ ላይ ተዝናንቶ የቆመ ነው። በዝህች በተወጠረች ገመድ ስር በርካታ ሹል ምስማሮች ተሰክተው ይጠብቁታል። ቀን ሲጥለው እነዛን ሹል ምስማሮች ከማንም ቀድመው እየተስፈነጠሩ ይሰኩበታል። ምስማሮቹ ኮልኮሌዎቹ ናቸው። ከሌላው ኢትዬጲያዊ አንጳር የተቃርኖው ምንጭ ከሰው ሰው ይለያያል። በአንድ በኩል ሰውየው በሀገሪቱ ታይተው የማይታወቁ ኢንቨስትመንቶች አሉት፣ እጁን ፈታ አድርጐ ሊረዱ የሚገባቸው ታዋቂ ግለሰቦችን ይረዳል የሚል ነው። በሌላ በኩል የሀብት ምንጩ የሀገራችን ወርቅ፣ የተሰጡት የትየለሌ መሬቶች፣ በሞተ ዋጋ የገዛቸው መንግስታዊ ተቋማት ናቸው። የሚረዳውም በአካፋ ከወሰደው ውስጥ በቡና ማንኪያ ነው። አረዳዱም እንደ አለቆቹ በከፋፍለህ ግዛው መርሆ በመመራት ነው የሚሉ በርካታ ናቸው። እኔም የምስማማው በመጨረሻው ዘርፍ ካሉት ሰዎች ቢሆንም በዝች አጭር ማስታወሻ ከዚህ በላይ መሻገር አልፈልግም።

ለዛሬው ” አላሙዲን ሆይ… ?” የሚለውን ጥያቄ ከፒተር መጵሀፍ አንጳር ላንሳ። ፒተር በምእራፍ ስምንት ” WARLORD ECONOMICS” ብሎ በጠራው ክፍል ውስጥ በሼህ አላሙዲን፣ በመለስ ዜናዊ ( ነብሱን ይማረው!”) እና በክሊንተን መካከል የነበረውን ግንኙነት በዝርዝር ያብራራል። ሼህ መሀመድ እና ክሊንተን በእንግሊዝ ለንደን ተገናኝተው እንደነበረና እንደተወያዩ ይነግረናል። አፍታም ሳይቆይ እ• ኤ•አ ግንቦት 14 ቀን 2007 በተካሄደ አጭር ድግስ ሼሁ ለክሊንተን ፋውንዴሽን ሀያ ሚሊዬን ዶላር ለመስጠት ቃል ይገባል። የዛኑ እለት ሁለት ሚሊዬን ዶላር በቼክ ይከፍላል።

ፒተር ባደረገው ጥናት አላሙዲን የአማላይ ( lobbing firm) እንዳለው ያረጋግጣል። በዚህ አማላይ ተቋም ውስጥ በአባልነት ሶስት ትላልቅ ሰዎች በተከፋይ አማካሪነት እንደሚሰሩም ይናገራል። እንዲህ በማለት፣

“… His lobbying firm in washington included Senators George Mitchell, Lioyd Bentsen( who had been treasury secretary when Bill was president), and Bob Dole as paid advisers.”

ፒተር ከዚህ በኃላ የሚያመጣው መረጃ ለኢትዬጲያውያን በጣም አስደንጋጭ ነው። አላሙዲን ይህንን ቃል የገባው ኮንግረስ ማን ዶናልድ ፔይን የኢትዬጲያ ባለስልጣናትን የሚቀጣው H•R• 2003 ተብሎ የሚጠራው ህግ ባስተዋወቁ ወቅት እንደሆነ ይገልጳል። የህጉ ተኮላሽቶ መቅረት በዚህ ምክንያት እንደሆነ ያሳውቃል። በወቅቱ እነ አቶ በረከት ደረታቸውን ነፍተው ህጉ አይፀድቅም ያሉበት ዝርዝር ምክንያት በጣም ግልጵ ሆኖልኛል። ፒተር የጳፈው ከፊሉ እንደሚከተለው ይነበባል፣

” In may 2007, when he made his commitement to the clinton Foundation, the Ethiopian Democracy and Accountablity Act ( H•R• 2003) had just been introduced by congressman Donald Payen.”

ፒተር በዚህ ክፍል ሌላው የገለፀው በአላሙዲን እና በአቶ መለስ መካከል ስላለው ግንኙነት ነበር። አቶ መለስ በሞተ ሰአት አላሙዲን ቀኝ እጄ ተቆረጠ ብሎ እንደተናገረ አስታውሷል ( When Zenawi died with in 2012 of a mysterious stomach ailment, Amoudi would say, ” I lost my right hand”).

እንግዲህ በአጭሩ አላሙዲን የኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ጥሰትን የሚያበረታታው በዚህ መልኩ ነው። በኢትዬጲያ መንግስት ስም ገንዘብ እየለገሰ፣ ሴናተሮችን በአማላይነት እየቀጠረ እና በወሳኝ ወቅቶች ተጵእኖ እየፈጠረ። ያውም በራሳችን ገንዘብ!! … በነገራችን ላይ በህውሀት መራሹ መንግስት ላይ እንደዛ ውርጅብኝ እየወረደ የኦባማ ወደ ኢትዬጲያ መጓዝ ከላይ ከተጠቀሰው የሼሁ ተልእኮ አንጳር አይተነው ይሆን?…ታሪክ ያወጣዋል!… እስከዛው ግን ለራሴ ” ያልጠረጠረ ተመነጠረ!” የሚለውን የሀገሬ ብሂል ብል ምን ይለኛል?

Health: ቤትዎ ውስጥ ሆነው ሳልዎን የሚከላከሉባቸው 5 ዘዴዎች

$
0
0

ሳል በበርካታ መንገዶች ሊከሰት ቢችልም በዋናነት ግን በአየር ንብረት ለውጥ(በቅዝቃዜ እና ሙቀት)፣ በጉንፋን እና ተያያዥ ህመሞች፣ በአለርጂ፣ በማጨስ እንዲሁም በአስም በሽታ ታማሚዎች ላይ ሊከሰት የሚችል ነው።
couph
አንዳንዴም ለተለያዩ በሽታ የሚታዘዙ መድሃኒቶችን አዛብቶ መውሰድ ፣ አነቃቂ ንጥረ ነገሮችን መጠቀም የሳል መነሾ ሊሆኑ እንደሚችልም የጤና ባለሙያዎች ይገልፃሉ።

ሳል ሲከሰትብን የተለያዩ መድሃኒቶችን መጠቀማችንና ፈውስን መሻታችን ትክክል ቢሆንም ከዚህ በተሻለ ግን በቀላሉ በቤታችን በምናከናውናቸው ተግባራት ራሳችንን በመጠበቅ ሳልን ልንከላከል እንደምንችልም ነው እነዚህ ባለሙያዎች የሚናገሩት።

ለዚህም እነዚህን አምስት ተግባራት በየጊዜው በማከናወን ሳልን መከላከል እንችላለን ሲሉም ይመክራሉ።

1.በቂ ውሃ ማግኘት፣

በአብዛኛው ሳል የሚከሰተው እንደ ጉሮሮ ያለው የመተንፈሻ አካላችን ላይ የውሃ እጥረት ሲከሰትና ሲደርቅ በመሆኑ በየቀኑ በቂ ውሃ መጠጣት ይኖርብናል።

ፈሳሽ ነገሮችን በየጊዜው በበቂ መጠን መውሰዳችን የጎሮሮ ድርቀትን ብቻ ሳይሆን የመከርከር ስሜትንም ለማስቀረት ያግዛል።

2.ትኩስ መጠጦችን ማዘውተር፣

ትኩስ ነገሮችን በተለይም ሻይ በማር አልያም ሻይ በብርቱካን መጠጣት ጉሮሮን ለማፅዳት እና ምቾት እንዲሰማን ለማድረግ እጅግ ተመራጭ ነው።
በአማራጭነት ከማር የተሰራ ከረሜላ (ሎዘንጅስ)ን መጠቀምም ይቻላል።

ከዚህ በተጨማሪም እንደ ሻይ ፣ ወተት ፣ አጃ የመሳሰሉትን መጠጣታችን በጉሮሯችን ያሉ አላስፈላጊ ነገሮችን ለማስወገድ ጠቃሚ ያደርጋቸዋል።

tea1.jpg

3. ሙቅ ሻወር፣

ሙቅ ሻወር መውሰድ በሰውነታችን ላይ የተከማቹ ቆሻሻዎች በላብ መልክ እንዲወገዱ ብቻ ሳይሆን አፍንጫችንም በማፅዳት የአተነፋፈስ ስርዓታችን እንዲስተካከል ይረዳል ፤ ከዚያም በላይ ከሳልና ከተለያየ አለርጂ ለመጠበቅም እጅግ ጠቃሚ ነው።

ከዚህ በተጓዳኝ ስቲም መውሰድም ተመሳሳይ ጥቅሞችን ያስገኝልናል።

4.ጠንካራ ሽታ ያላቸውን ነገሮች ማራቅ፣

ምቾት የሚነሱና ጠንከር ያለ ሽታ ያላቸው ሽቶዎችን አለመጠቀም፣ በተመሳሳይ ጠንካራ ታ ያለው ኤር ፍሬሽነር( አየር መልካም ጠረን እንዲኖረው የመንጠቀመው ስፕሬይ)ን አለመጠቀም፤ እነዚህ ነገሮች ሳይነስ እና ሳልን ሊቀሰቅሱ ስለሚችሉ ጥምንቃቄ ያሻቸዋል ነው የሚሉት አለን ዌስ የተሰኙት የክሌቭላንድ ክሊኒክ የጤና ባለሙያ።

እጅግ የከፋው ሳል ቀስቃሽ ነገር ግን የሲጋራም ሆነ የማገዶ፣ የከሰል፣ የእንጨት ወይም ሌላ ጭስ ሲሆን፥ በተለይም የሲጋራ ጭስ ሳል በመቀስቀስ ረገድ ተወዳዳሪ እንደሌለው ነው የሚነገረው።

ደረጃው ቢለያየም ሁሉም አጫሽ ማለት ይቻላል ለሳል የተጋለጠ ነው፤ ከሳል ለመጠበቅ የተሻለው አማራጭ ሲጋራ ማጨስን ማቆም ብቻ ነው።

5.አቧራን ማስወገድ፣

አቧራ ሳልን ብቻ ሳይሆን እንደ አስም ፣ ሳይነስ የመሳሳሉ ህመሞችን ከሚቀሰቅሱ ነገሮች የሚመደብ ነው።

አካባቢያችን በቂ እርጥበት እንዲኖረው በማድረግ አቧራን መከላከል የምንችል ሲሆን፥ በየዕለቱ ቤታችን በቂ አየር እንዲያገኝ ለተወሰነ ሰዓት መስኮት በመክፈት ምቾት የሚነሳ ሽታን ማስወገድ እንችላለን።

አቧራማ ስፍራዎችን በአረንጓዴ ዕፅዋቶች ማለበስም ሌላው አባሯን የማራቂያ መንገድ ሊሆን ይችላል።

ምንጭ፦ http://www.webmd.com

ህዝብን ያማረሩ ባለስልጣናት እድገት እየተሰጣቸው መሆኑን ተገለፀ

$
0
0

Zehabesha News
• የየካ ክፍለ ከተማ ነጋዴዎች በግብር እየተማረሩ ነው

በየካ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ነጋዴዎች በ2006 ዓ.ም ይከፍሉት ከነበረው በ10ና 10 በመቶ ግብር ጭማሬ በ2007 ዓ.ም እንዲከፍሉ መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ነጋዴዎቹ ያማረሩ ባለስልጣናት እድገት እየተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ግብሩ የተጨመረባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2008 ዓ.ም ከ31 እስከ 38 ሚሊዮን ብር ለማሟላት በመታቀዱ ነው፡፡

በተለይ በየካ ክፍለ ከተማ የሚኖሩት ነጋዴዎች የክፍለ ከተማው የገቢዎች አወሳሰን ኃላፊ አቶ ወንድሙ አባቡቶ በሚወስኑባቸው ከአቅም በላይ በሆነ ግብር የተመረሩ ሲሆን ሰውዬው በዚሁ ህዝብን በማማረር ተግባራቸው ከቀበሌ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በሶስት አመት ውስጥ ወደ ክፍለ ከተማ ማደጋቸው ተግልጾአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አቶ ወንድሙ አባቡቶን ወደ ፌደራል ገቢዎች እድገት ለመስጠት ለሳምንት ሶስት ቀን በሲቪል ሰርቪስ የዲግሪ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ አቶ ወንድሙ በህዝብ ላይ በደል እየፈፀመ መሆኑን የበታች ሰራተኞች አቤቱታ ቢያቀርቡም ‹‹አርፋችሁ ስሩ እሱ ስራውን በሚገባ እየሰራ ነው፡፡›› የሚል የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡

ኦቦ በቀለ ገርባ አሜሪካ ገቡ

$
0
0

bekele gerba
Bekele Gerba 1
(ዘ-ሐበሻ) በ እስር ላይ ቆይተው ባለፈው ማርች 30, 2015 የተፈቱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር ኦቦ በቀለ ገርባ ዛሬ ጠዋት ዋሽንተን ዲሲ መግባታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታወቁ::

አቶ በቀለ ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ዱልስ ኤርፖርት ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በቀጣይም በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርጉ ተገልጿል:: በቅድሚያ ዋሽንግተን ዲሲ በሚደረገው በኦሳ (Oromo Studies Association/Waldaa Qorannoo Oromoo) ኮንፍረንስ ላይ የሚሳተፉት ኦቦ በቀለ በዚሁ ኦገስት 1 እና 2, 2015 በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ለ29ኛ ጊዜ በሚደረገው ኮንፍረንስ የክብር እንግዳና ተናጋሪ እንደሆኑ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል::

ኦቦ በቀለ በሚኒሶታ ኦገስት 8 ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርጉ ሲጠበቅ – ቦታውን እና ሰዓቱን እንደምናሳውቅ ከወዲሁ እንገልጻለን::

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ሶስተኛ ጉባዔ ተከናወነ

$
0
0

shengoከሰኔ ፳፮ እስከ ፰ ፪ ሺህ ፯ ዓ. ም  (July 3rd to July 5th 2015) በዋሺንግተን ዲሲ የተካሄደው የሸንጎው ሦስተኛ ጉባዔ  በጥሩ ሁኔታ ተካሂዷል። ጉባዔው ሸንጎ ባለፉት ሁለት ዓመታት ያካሄዳቸውን ዘርፈ ብዙ ስራዎችና የልዩ ልዩ የስራ ግብረ ኃይሎች ሪፖርት ገምግሞ በሚቀጥሉት ዓመታት ትኩረት ለሚያደርግባቸው ግቦች ስኬታማነት፤ የሰው፤ የገንዘብና ሌላ ቁሳቁስ፤ የመረጃ፤ የመገናኛና የሕዝብ ግንኙነት፤ የዲፕሎማሲ፤ የወጣቶችና ሴቶች ተሳፎ፤ በሃገር ቤትና በውጭ ከሚንቀሳቀሱ መሰል ድርጅቶች ጋር የግንኙነት አቅሙን ለማጠናከር… ወዘተ ከመቸውም የበለጠ ጥረት እንደሚያደርግ ወስኗል።

አንደሚታወቀው  ሸንጎ እንዲመሰረት ያስገደደው ዋና የፖለቲካ አደረጃጀትና የአመራር ክፍተት የተበታተነውና እርስ በእርሱ የሚጠላለፈው አገር ወዳድ ተቃዋሚ ኃይል ተባብሮ፤ ተመካክሮ፤ ተናቦ፤ ተደራጅቶ፤ ብቁነት ያለው አመራር መስርቶና የጋራ ሰነድ አዘጋጅቶ በተከታታይ ትውልድና ታሪክ ሊጠቀስ የሚችል አስተዋፆ ለማድረግ ሲችል ብቻ ነው የሚል እምነት ስላለው ነው።

አሁንም እንዳለፉት ሃያ አራት አመታት የሚታየው የፖለቲካ ሁኔታ ከህወሓት/ኢህአዴግ ጥንካሬ ይልቅ የተቃዋሚው ዘርፍ መፍረክረክ፤ መከፋፈል፤ መጋጨት፤ መነታረክ፤ አለመተማመን፤ መጠላለፍ፤ ራሱን ለሰርጎ ገቦች ማጋለጥ… ወዘተ ነው። በጉባዔው ትንተናና እምነት የተቃዋሚው ኃይል አብሮና ተባብሮ ለመስራት አለመወሰን ለአፋኙ፤ በዝባዡና፤ ጠባብ ጎሰኛው አምባገነን የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት በገንዘብ ሊገዛው የማይችል አስተዋፆ እያደረገለት ነው። በመግለጫውና ሃተታው እንደምናብራራው ተሳስቦና ተቻችሎ በአንድነት ከመስራት ውጭ ሌላ አማራጭ የለንም። ሰብሳቢ የሆኑ የአንድነት ኃይሎች በሙሉ የሚጋሯቸው፤ ለጋራ ሰነድ ዝግጅት ጠቃሚ ይሆናሉ ብለን የምንገምታቸው አስኳል ጉዳዮች አሉ።

ለዚህ ይጠቅማል ብለን የምንገምተው በሸንጎ ውስጥ የተጣመሩት የፖለቲካና የማህበረሰብ ድርጅቶችና የታወቁ አገር ወዳድ ግለሰቦች ተስማምተውና ተጋርተው የሚመሩባቸውን አምስት መርሆዎች መገምገም ነው። እነዚህም፤

አንድ፤ በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፤ በመላው ሕዝቧ የሥልጣን ባለቤትነትና ሉዑላዊነት ጽኑ ዕምነት ማስተጋባት፤

ሁለት፤ በሕግ ፊት የሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች እኩልነትንና የሰብአዊ መብቶች መከበር ወሳኝ መሆናቸውን መቀበል፤

ሶስት፤ ፍትኅ የሰፈነበትና የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ሥርዓት መመስረት አስፈላጊ መሆኑን ማመን፤

አራት፤ በድርጅቶች ውስጥና መሃከል ዴሞክራሲያዊነትን መመሪያ አድርጎ በስራ ላይ ማዋልና፤

አምስት፤ በስልጣን ላይ የሚገኘው የህወሓት/ኢህአደግ አገዛዝ ለዴሞክራሲ መስፈን፤ ለእርጋታ፤ ለሰላም፤ ለዘላቂና ፍትሃዊ እድገት እንቅፋት የሆነ ስርዓት በመሆኑ መወገድ እንዳለበት መቀበልና ያልተቆጠበ ጥረትና አስተዋፆ ማድረግ ናቸው።

ጉባዔው፤ እነዚህን ግቦች ስኬታማ ለማድረግ የመጀመሪያዎቹ ጊዜ የማይሰጡ ትኩረቶች ኢትዮጵያን ከመፈራረስ (አገር ለማዳን) እና ሕዝቧን ከእርስ በእርስ እልቂት ለማዳን በአንድነት መነሳት ነው የሚል ነው። ኢትዮጵያ ከጠፋች ሌላው ትግል ትርጉም የለውም ከሚል ስምምነት ላይ ደርሰናል።

ጉባዔው እነዚህ መርሆዎች አሁንም አግባብ እንዳላቸው ተቀብሎ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ በጥናቶች የተደገፈ ጥልቀትና ስፋት ያለው ሰፊ ውይይት አድርጓል። ከእነዚህ መካከል ትኩረት የሰጣቸው አስኳል ጉዳዮች የግንቦቱ የይስሙላ “ምርጫ” ትርጉመቢስነት፤ የገዢው ፓርቲና የተቃዋሚው ጎራ ጠንካራና ደካማ ጎኖች፤ አገር ቤትና ውጭ ከሚገኙ የአንድነት ዘርፍ የተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ተከታታይ ውይይት በማድረግ ሰፊና ጠንካራ የሆነ ግንባር መስርቶ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አግባብ ያለው አማራጭና የጋራ ሰነድ በማዘጋጀት፤ ወጣቶችና ሴቶች በሰፊው የሚሳተፉበትን ሁኔታ በማመቻቸት፤ በብሄር/ብሄረሰብና በየክልሉ ስም ተደራጅተውና ታጥቀው ትግል እናካሂዳለን የሚሉት ቡድኖች ከኢትዮጵያ አንድነት አንፃር እንዴት እንደሚታዩ በመዳሰስ፤ በአፍሪካ ቀንድና በሌሎች አካባቢዎች በተከሰቱት ሁኔታዎች፤ ለምሳሌ፤ የሃገራት መፈራረስ፤ የሽብርተኛነት መስፋፋትና የኃያላን መንግሥታት ሚና በኢትዮጵያ ላይ ያለው ጫና ምን አስከትሏል፤ ያስከትላል እና የወደፊቱ የትግል ስልታችን ምን መሆን አለበት… ወዘተ በሚሉት ላይ ነው።

የይስሙላውን “ምርጫ” በተመለከተ ሸንጎ ምርጫው ከመካሄዱ ከአንድ ዓመት በፊት የምርጫው ሂደት ነጻ፤ ፍትሃዊና አግባብ ያለው እንዲሆን ከተፈለገ ዘጠኝ ነጥቦችን ያቀፈ ቅድመ ሁኔታዎችና ዝግጅቶች መሟላትና መተግበር እንደነበረባቸው ገልጾ ነበር፡፤ ሆኖም አንዳቸውም ስራ ላይ እንዳልዋሉ አስታውሶ፤ ጉባዔው ህወሓት በበላይነት የሚያሽከረክረው ኢህአዴግ የመንግሥት ለውጥ በምርጫ እንዲካሄድ የማይፈቅድና በሕገ መንግሥቱ መመሪያ መሰረት የሚደረገው የሰላማዊ ትግል ጭላንጭል ሙሉ በሙሉ እንደተዘጋ ተስማምቶበታል። በሕገ መንግሥቱና በዓለም ህጎች መሰረት የመንግሥት ለውጥ በሰላም ሊደረግ አይችልም ብሎ ጭካኔውን፤ አፈናውን፤ ግድያውንና ማሳደዱን ከመቸውም በሚዘገንን ደረጃ የሚያካሂደው ህወሓት የሚያዘውና የሚቆጣጠረው ኢህአዴግ የሚያሳየው ባህርይና ድርጊት ካለፉት ስህተቶች ሊማር አለመቻሉን፤ የበላይ አለቆቹና ተተኪዎቹ ራሳቸው በፈጠሩት የጥላቻና የቂም በቀል ርእዮት ተበክለው በፍርሃት ዓለም ውስጥ የሚኖሩ መሆኑን፤ ይህ ፍርሃት መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የበከለው መሆኑን… ወዘተ ያሳያል።

የማህበረሰብ ሆነ የፖለቲካ፤ የኃይማኖት ሆነ የሰብአዊ መብቶች መከበር ጠበቃ የሆነ ግለሰብና ተቋም ድምፁን ሲያሰማ የሚደርስበት ተከታታይ ክስና የሃሰት መረጃ “ሽብርተኛ ነህ/ነሽ” የሚል ብቻ ነው። በጥላቻና በቂም በቀል የተበከሉት የህወሓት መስራቾችና ተተኪዎች በተደጋጋሚ ሊያስታውሱን የሚሞክሩት ሃቅ “እኛ በትጥቅ ትግል መስዋእት ከፍለን ያገኘነውን ስልጣን” ልትነጥቁን የምትችሉት እናንተም ተመሳሳይ ትግል አካሂዳችሁ ብቻ ነው የሚል እብሪተኛና ትምክህተኛ የሆነ ብሂል ነው። ይህ አብሪትና ትምክህተኛነት ሁለት የማያሻሙና መፈታት ያለባቸው ችግሮችን ያንፀባርቃሉ፤

አንድ፤ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ የመንግሥት አመራርና ስርዓት ለውጥ ወይንም ሽግግር በሰላም ሊተገበር አለማቻሉን፤ ይኼም ለዲሞክራሲ ምስረታ ማነቆ መሆኑን፤

ሁለት፤ በሃገር ውስጥ የእርስ በእርስ ጦርነትና በውጭ ወረራ ምክንያቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ በህይወቱና በኃብቱ ብዙ መስዋእት መክፈሉ፤ መራቆቱ፤ መድከሙ፤ መማረሩ፤ ክብሩን መገፈፉ፤ ሉዐላዊነቱና ትሥስሩ መውደሙ ናቸው።

ጉባዔው ይኼ ዑደት (Cycle) እና ሁከት (Cycle of Violence) ልክ እንደ ተራ ነገር የተለመደ መሆኑ ለሃገራችን ህልውና ዘላቂነትና ለስብጥር ሕዝቧ አብሮና ተቻችሎ ማደግና መኖር ፀር መሆኑንና አዲስ የፖለቲካ ምእራፍ መክፈት ብልህነት መሆኑን ተስማምቶበታል። አዲስ ፖለቲካ ስንል፤ ከጥላቻና ከቂም በቀል የፖለቲካ ባህል ወደ መቻቻል፤ መወያየት፤ መከባበር፤ መደማመጥ፤ አብሮ ችግሮችን ወደ መፍታት፤ መደጋገፍ… ወዘተ ባህል እንዙር ማለታችን ነው። የህወሓት/ኢህአዴግን የጥላቻ ባህል ይዘን ዲሞክራሳዊ ስርዓት ልንመሰርት አንችልም።

ህወሓት ይኼን የተያያዘ ጊዜ ያለፈበት የጥላቻና የቂም በቀል ፖለቲካ ባህል ይዞ መቀጠሉ ለተገንጣዮችና ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ ለሚመኙ የውጭ ኃይሎችና ለሽብርተኛነት በር ከፍቷል። የይስሙላው ምርጫ ያባባሰው ይኼን የማይካድ ሁከት ነው። ይኼን በተመለከተ፤ ኢትዮጵያን አፍኖ ለሚገዛው  ቡድን አሳፋሪ ሁኖ ያገኘነው ክስተት ገዢው ፓርቲ ከ547 የፓርላማ ወንበሮች “424 አሸንፊያለሁ” ብሎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማቅረቡ ብቻ ሳይሆን የቀሩትን ወንበሮች ራሱ ለፈጠራቸው፤ ታማኝና ታዛዥ ለሆኑ ተጠላፊ ፓርቲዎች መስጠቱ ነው። የዛሬ አምስት ዓመት “በ 99.6” አሸነፍኩ ያለውን የዓለም ሕዝብ ያልተቀበለውን ውጤት ከፍ አድርጎ “መቶ በመቶ አሸነፍኩ” ሲል ስርዓቱን በሕዝብ ድምፅና በሰላም ለመለወጥ አትችሉም የሚል የማያሻማ መልእክት አቅርቦልናል።

ስለሆነም፤ የጉባዔው ዘገባና ድምዳሜ አንድና፤ አንድ ብቻ ነው። ይኼውም፤ ሕግ መንግሥቱ የሚፈቅደው የምርጫ ሂደትና ለሃገሪቱ ሕዝብ አገልግሎት ይሰጣሉ ተብለው የተቋቋሙት ተቋሞች–የምርጫ ቦርድ፤ ፍርድ ቤቶች፤ የፌደራል ፖሊስ፤ መገናኛ፤ ደህንነት፤ መከላከያ…ወዘተ–ለገዢው ፓርቲ ማፈኛና መቆጣጠሪያ፤ መቆያና የኃብት ማካበቻ መሳሪያዎች ሁነዋል የሚል ነው። የምርጫ ቦርድ የፖለቲካ መሳሪያ መሆኑን በተደጋጋሚ አይተናል። በአለፉት አምስት ምርጫዎች ህወሓት/ኢህአዴግ ከዓለም የምርጫ መስፈርቶች ጋር የተጻረረ፤ እውነተኛ የሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያፈራረሰ፤ መሪዎችን ያሳደደ፤ ያሰረና፤ ምርጫውን ካሸነፈ በኋላም የገደለ፤ በመግደልና በማሳደድ ላይ ያለ፤ የሕዝብ እምቢተኛነት ሲከሰት ችግሩን ሁሉ በአፈናና በመሳሪያ ኃይል እፈታለሁ የሚል አምባገነናዊ አገዛዝ ሆኗል። በአጭሩ፤ ህወሓት በበላይነት የሚያሽከረክረው አገዛዝ ሃገሪቱን ለከፋ አደጋ ያጋለጠና የእርስ በእርስ ጥላቻና እልቂት እንዲካሄድ ያመቻቸ ሆኖ አግኝተነዋል።

በጉባዔው ዘገባ፤ ዲሞክራሳዊ ለውጥ ጊዜ የማይሰጥ አስቸኳይ ጉዳይ ሆኗል። ጉባዔው ለማጠናከር የፈልገው መልእክት፤ ህወሓት የሚያካሂደው “የከፋፍለህ ግዛው”፤ የብሄር/ብሄረሰብና የኃይማኖት ጥላቻና ጎሳዊ አድልዎ ለሃገራችን አንድነትና ሉዐላዊነት” እና ለመቶ ሚሊዮን ሕዝቦቿ ሰላም፤ ደህንነት፤ አብሮና ተሳስሮ መኖር ዋናው አደጋ ፈጣሪ ሆኗል። ለማጠናከር፤ ጉባዔው ከዚህ ዘገባና ድምዳሜ ለመድረስ ያመዛዘናቸውን አደገኛ ሁኔታዎች በአጭሩ እናቅርባለን።

ሌላውን ሁሉ መረጃ ወደ ጎን ትተን፤ ባውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት “የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ዓመታዊ” ሪፖርትን፤ ባለፈው ዓመት መጨረሻ (2014) የወጣውን  የ አሜሪካ ኢንተለጀንሰ መስሪያ ቤት ያዘጋጀውን ዘገባ( “U.S. National Intelligence Council Documentary on the TPLF”) እና መንግስታዊ ያልሁነው ፈንድ ፎር ፒሰ (The Fund for Peace, )  በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኙ መንግስታት (“Failed and Failing States”  ) በሚል ያቀርቧቸውን አስጊ ሁኔታዎች እንጠቅሳለን።

አንድ፤ የገንዘብና የተፈጥሮ ኃብት ዘረፋህወሓት እንደ ፓርቲ የሚቆጣጠራቸውና የፈጠራቸው የኢኮኖሚና የፋይናንስ ተቋሞች–ለምሳሌ ኤፈርት የተባለው ሞኖፖሊ፤ በበላይነት የሚቆጣጠረው መንግሥት፤ ጥቂት ምርጥ ግለሰቦች፤ የስለላ፤ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ የበላዮች አብዛኛውን ዘመናዊ ኢኮኖሚ ተቆጣጥረውታል። የጠባብ ጎሳ የበላይነትን ከኢኮኖሚና የተፈጥሮ ኃብት ባለቤትነትና የበላይነት ጋር አጣምረውታል። ገቢና ኃብት የሚገኝባቸውን ምንጮች ሙሉ በሙሉ የራሳቸው የግልና የቡድን አድርገውታል። ህወሓት የነጋዴዎች፤ የኪራይ ሰብሳቢዎች፤ የአትራፊዎችና የዘራፊዎች ስብስብ ቡድን ሆኗል። ሌላውን “አጥፊ ተቃዋሚ” እያለ በመወንጀል እራሱ ወንጀለኛ ከሆነ አመታት አልፈውታል።

ይኼን ነው፤ ዶኪውሜንተሪው “Ethnocracy combined with Plutocracy” ኢትዮጵያ በዓለም እርዳታ ከሚያገኙ ሃገሮች መካከል አራተኛውን ደረጃ፤ በአፍሪካ አንደኛውን ደረጃ ይዛ ሕዝቧን ለመመገብ አልቻለችም። ከሚለገሰው ግዙፍ እርዳታ ምን ያህሉ ድህነትን ለማጥፋት እንደሚውል አናውቅም። የምናውቀው የህወሓት የበላዮችና ጥቂት አጋሮቻቸው ታይቶ የማይታወቅ ድርጅታዊ ምዝበራ እያካሄዱ፤ ኃብት እንዳካበቱና በልጆቻቸውና በሌላ ዘዴ ብዙ ቢሊየን ዶላር ከሃገር እንዳሸሹ፤ የግል ኩባንያዎች እንዳቋቋሙ ተደርሶበታል። Global Financial Integrity, 2000-2009 ባወጣው ዘገባ $11.7 ቢሊዮን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተሰርቆ ወደ ውጭ ተልኳል፤ በዚህ ዓመት መጀመሪያ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት እምቤኪ የመራው ግብረ ኃይል ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ከኢትዮጵያ ተሰርቆ የሸሸው $10 ቢሊየን ነው። ህወሓት የማይክደ $21 ቢሊየን ዶላር ከሃገር ተሰርቆ ሸሽቷል። ስንት የስራ እድል ይፈጥር ነበር? ለዚህ ተጠያቂው ማን እንደሆነ አከራካሪ አይሆንም።

ሁለት፤ የዘር ፍጅት፤ ማጽዳት ዘመቻ (Genocide and ethnic cleansing) የህወሓት  መሪዎችና ተተኪዎች ሌሎች ጠባብ ጎሰኞችን አሳምነው በአማራው ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የተቀነባበረና ተከታታይ የዘር ፍጅት ዘመቻ አካሂደዋል፤ አሁንም እያካሄዱ ነው። የብሄር ጥላቻን እንደ ትግል ስልት ተጠቅመው ሌላውን በጥላቻ በክለውታል። ወጣቱ ትውልድ እንዲያምን የተገደደው ጥላቻን፤  የራስን ጥቅም የበላይነት…ወዘተ እንጅ አገራዊና ብሄራዊ ፍቅርንና ጥቅምን አይደለም።

ህወሓት ከጅምሩ፤ የትግራይን ሕዝብ “ያዳከመው፤ ያደኸየው፤ ያገለለውና ያጠቃው የአማራው ብሄርረሰብ ነው” በሚል ብሂል፤ የጥላቻ ጦርነት ሲያካሂድ ቆይቷል። ዘገባዎችና መረጃዎች የሚያሳዩት በጅጅጋ፤ በደቡብ ሸዋ፤ በጉራ ፈርዳ፤ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ፤ በጋምቤላ፤ በወልቃይት ጠገዴና ሌሎች ቦታዎች የሚዘገንንና በፍርድ የሚያስጠይቅ ፍጅት አካሂደዋል። የራሱ የገዢው ፓርቲ የሕዝብ ቆጠራ ያሳየው ቢያንስ ሁለት ሚሊየን አምስት መቶ ሽህ የአማራ ሕዝብ በጥቂት አመታት ውስጥ የት እንደደረሰ አይታወቅም፤ ሌሎች (ለምሳሌ ኢኮንሚስቱ ዶር ብርሃኑ አበጋዝ በምርምር የተደገፈ ማስረጃ) ይኼ ቁጥር ከአምስት ሚሊየን በላይ ሕዝብ መሆኑን ያሳያል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ይህ ሕዝብ የት ደረሰ፤ ተሰደደ፤ ተገደለ፤ ማንነቱን እንዲለውጥ ሆነ? ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂው ማነው? በኛ አመለካከት ህወሓትና አጋሮቹ መሆናቸው አያከራክርም።

በተጨማሪ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ችግሮችን በሰላምና በመደራደር በመፍታት ፋንታ በአኟክና (2003)፤ በኦጋዴን ኢትዮጵያዊ ሶማሌ ሕዝብ ላይ (በተደጋጋሚ)፤ የሚዘገንን፤ በቪዲዮ የተቀረጸ በፌደራል ፖሊስ የተመራ በዘር ፍጆት የሚመደብ ወንጀሎች ፈጽሟል። በተጨማሪ፤ በተራው የጋምቤላ፤ የኦሞ ሸለቆና ሌሎች ነዋሪዎች ላይ ሂውማን ራይትሰ ዋች፣ አምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ኢንተርናሽናል ሪቨርስ፣ ኦክላንድ ኢንስቲትዩት ፣ ጋርዲያን ጋዜጣና ሌሎቹም (Human Rights Watch, Genocide Watch, Amnesty International, International Rivers, Oakland Institute, the Guardian and others) የመዘገቡት የመሬት ነጠቃና ከዚህ ጋር የተያያዘው ነዋሪዎችን ከቀያቸው የማባረር ወንጀል በተደጋጋሚ ተፈጽሟል። ገዢው ፓርቲ እነዚህን የመሳሰሉ ወንጀሎች ሲፈፅም “በልማትና በፀጥታ አስፈላጊነት” ስም ነው። በተጨማሪ፤ እየለየ በድብቅ የሚገድላቸው፤ የሚያስራቸው፤ የሚደበድባቸው፤ ንበረታቸውን የሚገፋቸው፤ እንዲሰደዱ የሚያስገድዳቸው የሃገር ፍቅር ያላቸውን፤ ደፋሮቹን፤ መሪ ለመሆን ብቃት ያላቸውን፤ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የቆሙትን ነው። ምርጫውን “አሸነፍኩ” ካለ በኋላ የገደላቸው ደፋርና አገር ወዳድ መሪዎች ምን ወንጀል ሰሩ? ማን ገደላቸው፤ በማን ትእዛዝ? የገደሉት ለምን አልተያዙም? የተገደሉበት ዋና ምክንያት ለህወሓት ተወዳዳሪ የሆነ አገር ወዳድና በፍትህ የሚያምን ትውልድ እንዳይፈጠር መቀጣጫ ለማድረግ ነው።

ሶስት፤ የሰብዓዊ መብቶች፤ የኃይማኖትና የፕሬስ ነጻነት አፈና— ከላይ እንዳቀረብነው፤ ያለፈው ምርጫ የፖለቲካ ምህዳር መዘጋት ነፀብራቅ ነው። አምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂውማን ራይትስ ዋች፣ ፍሪደም ሀውስ፤ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪው ሲፒጄ ያሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፡ የአውሮፓ ማህበርና ሌሎችም የሚጋሩት የኢትዮጵያ አገዛዝ ለማህበራዊ (ለሰብአዊ) መብቶች ፀር መሆኑንና ይኼ ሁኔታ ከቀጠለ ለሃገሪቱ መፈራረስና ለእርስ በእርስ ጦርነት መዘዝ መሆኑን ነው። ሲፒጄ (CPJ) ባደረገው ጥናት መሰረት “ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማፈንና ከሃገር እንዲለቁ በማድረግ፤ ከዓለም አራተኛ፤ ከአፍሪካ ሁለተኛ” መሆኗን በተደጋጋሚ አስምሮበታል። ሽብርተኛ ተብለው ከታሰሩት መካከል እስክንድር ደስታ፤ ተመስገን ደሳለኝ፤ ውብሸት ታየ፤ አንዱ ዓለም አራጌ፤ ሃብታሙ አያሌው፤ አቡበከር አህመድ፤ አብርሃ ደስታ፤ የሸዋስ አሰፋ፤ ዳንኤል ሽበሽና ሌሎች ብዙ ሽዎች የፖለቲካ እስረኞች ይገኙበታል። ቢያንስ ሰባ ዘጠኝ ጋዜጠኞች ከሃገር ተሰደዋል፤ ይኼ “በዓለም የመጀመሪያውን ደረጃ” የያዘ ሃቅ ነው። ከላይ የጠቀስነው ዶኪሜንተሪ እንዳሳየው  የኢትዮጵያ መንግስት ከጋዳፊና ባለማችን ከታዩት ሌሎችም ጨካኝ አምባገነኖች የማይለይ መሆኑን ነው

ህወሓት ሁሉንም ተቋሞች ለመቆጣጠር በተከተለው ዘዴ መሰረት፤ ስልጣን በያዘ ማግስት የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኃይማኖትን አመራር በቁጥጥሩ ስር እንዲውል አድርጓል፤ አግባብ ያላቸውን ፓትሪያርክ አስወግዶ ለህወሓት ታዛዥና ታማኝ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ሹሟል። እንደ ዋልድባ ያሉ የማይተኩ ገዳሞችን ህልውና ለማሳጣት ሞክሯል፤ የዋልድባ አባቶችና እናቶች የሚተዳደሩበትን መሬት ለስኳር አገዳ ማምረቻ እንዲውል አድርጓል። ኃይማኖትን የፖለቲካ የበላይነት መሳሪያ ማድረግ ለሃገሪቱ አደጋ ፈጥሯል፤ ለውጭ ኃይሎች መግቢያ ቀዳዳ ሆኗል። በተመሳሳይ፤ የእስልምና ኃይማኖት አመራር ህወሓት በሚፈልገው መንገድ እንዲቋቋምና እንዲመራ አድርጓል፤ መሪዎችንና አባላትን አስሯል።

ገዢው ፓርቲ አስደናቂ እድገት እያሳየሁ ነው በሚላት የምግብ ጥገኛ ሃገር፤ ለወጣቱ ትውልድ የስራ እድል ለመፍጠር አልተቻለም። ዛሬ ሃገሪቱ ከምትታወቅባቸው አንዱ ወጣቱ ትውልድ በተከታታይ መሰደዱ ነው። በየዓመቱ፤ ብዙ ሽህ ወጣቶች በጅቡቲ፤ በሶማሊያ፤ በሰሜንና ደቡብ ሱዳን፤ በኬንያ ወይንም የመውጫ ፈቃድ አግኝተው በቦሌ ወደ ውጭ ይሰደዳሉ። ከወጡ በኋላ የህወሓት/ኢህአዴግ  አገዛዝ መብታቸውን አያስከብርም። የኢኮኖሚው አመራር በሕዝብ የበላይነት የሚመራ ካልሆነ፤ ሕዝብን የእድገት ማእከል ካላደረገና የእድገቱ ውጤት ለሕዝብ አገልግሎት ካልዋለ የኑሮው ቀውስና ስደቱ አያቆምም።

አራት፤ ከመንግሥት ባለቤትነት የመነጨ የመሬት ነጠቃ—አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚተዳደረው በእርሻና ተመሳሳይ ስራ ነው። በገጠር ሆነ በከተማ የመሬት ባለቤትነት የዜግነት መታወቂያና የኑሮ መመኪያ ነው። ህወሓት በበላይነት የሚመራው አገዛዝ የተፈጥሮ ኃብትን በሙሉ “የመንግሥት ነው” በሚል ዘዴ መሬትን ለንግድና ለግል ጥቅም አውሎታል። የመሬት ቅርምት (Land Grab) ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያውያንን አንጡራ የተፈጥሮ ኃብት ለውጭ አገር ኢንቬስተሮች ቸርችሮታል። ሳውዲ ስታር፤ የህንዱ ካሩቱሪ፤ ሩች ሶያ፤ የህንድ ድንች አምራቾች ተቋምና ሌሎች ጋምቤላን ሙሉ በሙሉ ተቀራምተውታል ለማለት ይቻላል። ብዙ ሚሊየን ሄክታር ለም መሬትና ወንዝ ለውጭና በሃገር ቤት ታማኝ ለሆኑ አትራፊዎች ተቸርችሯል። በጋምቤላ ብቻ የታወቀው ለውጭ ኢንቬስትሮች የተሰጠውና የግል የሆነው መሬት በዝቅተኛ 650,000 ሄካታር በከፍተኛ 2,000,000 ሄክታር ይደርሳል። የከተማና የገጠር መሬት ለግል ትርፍና ለሙስና ቁልፍ ሆኗል። በከተማ ቦታ ምደባ፤ ስደተኛውም ተጠቃሚ ሁኖ የከተማ መሬትን ዋጋ የማይቀመስ አድርጎታል። ይኼ በፖለቲካ የበላይነት የሚወሰን የመሬት አስተዳደር ሁኔታ እስካልተለወጠ ድረስ ፍትሃዊ የሆነ የመሬት አጠቃቀም ሊኖር አይችልም።

አምስት፤ የስለላ፤ የደህንነት፤ የመከላከያ፤ የፍርድና የፌደራል ፖሊስ ፍፁም የበላይነት —እነዚህና እንደ ጉምሩክ፤ መገናኛ ቁልፍ ሚና ያላቸው ተቋሞች የሚያገለግሉት ህወሓትን ነው። የፓርቲው ተቀጥላዎችና አገልጋዮች ከሆኑ ቆይተዋል። በ2009 የተገኘ መረጃ ያሳየው ከጠቅላላው የኢትዮጵያ የመከላከያ እዝ አስራ ሰባቱ ጀኔራሎችና አርባዎቹ ኮሎኔሎች የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ፤ አንድ የአገው ተወላጅና አንድ የአማራ ተወላጅ ጀኔራሎች ነበሩ። አንድም የኦሮሞ ጀኔራል የለም፤ በኮሎኔል ደረጃ ሌሎች ብሄረሰቦች አልተወከሉም። በፖለቲካው፤ በኢኮኖሚው፤ በባንኩና ፋይናንሱ፤ በመገናኛው፤ በአስተዳደሩ፤ በደህንነቱ፤ በመከላከያው፤ በፌደራል ፖሊሱ፤ በጉሙሩኩ ዘርፎች የፖሊሲና የውሳኔ ኃላፊዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው። እንደዚህ አይን ያወጣ አድልዎ የትም ሃገር አይታይም።

ቢያንስ ዘጠና አምስት በመቶ የሚሆነው የደህንነቱን፤ የፌደራል፤ የልዩ ፖሊሱንና የመከላከያውን እዝ በበላይነት የሚመሩት ለህወሓት ታማኝ የሆኑ የትግራይ ብሄረሰብ አባላት ናቸው። ይኼ አይን ያወጣ  አድልኦ መሆኑ አያከራክርም።  ይኼ ለበላይነት የተዋቀረና እጅግ ጠባብ የሆነ  አመራር ለሃገሪቱ ደህንነትና ዘላቂነት፤ ለሕዝቧ ሉዐላዊነትና አንድነት፤ ለሕግ የበላይነትና ለዴሞክራሲ አደገኛ መሰናክል ፈጥሯል።  ህወሓት ይኼን የበላይነት ያጠናከረው ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተቋሞችን በማውደም፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በማጥፋት፤ የትምህርት ይዘቱን ክልላዊና ጎሳዊ በማድረግ፤ አገር ወዳድ የሆኑ መምህራንን በማባረር፤ የጥላቻ ባህል ጥልቀትና ስፋት ይዞ አዲሱ ትውልድ እርስ በእርሱ እንዳይተማመንና ብሎም እንዲጋጭ በማድረግ ነው። ዛሬ ልክ ዩጎስላቪያ እንደሆነው፤ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የሚያያይዙ ባህሎችና ልምዶች በህወሓት ወድመዋል ለማለት እንችላለን። ይኼ ሁኔታ ለእርስ በእርስ ግጭት፤ ለዘር ፍጅት፤ ለተገንጣይ ኃይሎችና ለውጭ ጠላቶች የጥቃት መግቢያ ሆኗል።

ስድስት፤ የውጭ መንግሥታት፤ በተለይ የአሜሪካ መንግሥት ሚና አሳሳቢነት–የምእራብ ሃገሮች፤ በተለይ የአሜሪካ መንግሥት ከሰብዓዊ መብቶች መከበር ይልቅ ለመረጋጋትና ለፀረ-ሽብርተኛነት ዘመቻ ቅድሚያ እየሰጠ አምባገነኑን የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ መደገፉ ለራሱ ጉዳት እንዳመጣ እናምናለን። የኢትዮጵያና የአሜሪካ ከመቶ አስር ዓመታት በላይ የቆየ ግንኙነት አስተማማኝ በሆነ ደረጃ ሊቀጥል የሚችለው አፋኙን አገዛዝ በማውገዝና የሚሰጠው የገንዘብና ሌላ እርዳታ እንዲቆም በማድረግ እንጅ ድጋፉን በመቀጠል አይደለም። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ቀውስ ውስጥ መግባት፤ መባባስ፤ የሰብአዊ መብቶች መረገጥ፤ የኃይማኖት ነጻነት መታፈን፤ በፀረ-ሽብርተኛነት ሽፋን የገዢው ፓርቲ ሕዝብ አሸባሪ መሆን፤ የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ መባከን፤ ከመቶ በላይ የሚገመቱ በጎሳ የተደራጁና የታጠቁ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሃገሪቱ ሁኔታ ተባብሶ የመገንጠል ዓላማቸውን ስኬታማ ለማድረግ መዘጋጀት፤ ለልማት መዋል የሚችል ግዙፍ የሆነ ኃብት ከሃገር እየሸሸ መውጣቱ…ወዘተ ለአሜሪካም ዘላቂ “ጥቅም” ጉዳት እንደሚያመጣ እንገምታለን። ለዚህ አግባብ ያለው፤ የማያሻማ መልእክት ለኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ መስጠት ነው።

ጉባዔው በቅርቡ ሸንጎ ለፕሬዝደንት ኦባማ የጻፈውን ግልፅ ደብዳቤ መሰረት አድርጎ፤ የአሜሪካ መንግሥት ለሚከተሉት መተክሎች (Principles) እና እሴቶች ትኩረት እንዲሰጥ የዲፕሎማቲክ ዘመቻ ማካሄድ ይኖርበታል በሚል ተስማምቷል።

አንድ፤ የፖለቲካ እስረኞች፤ ጋዜጠኞች፤ ብሎገሮችና የኃይማኖት መሪዎችና ተከታዮች በሙሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤ ጥቂቶቹን ለይስሙላ ፈትቶ ሌሎችን እያሰቃየ ነው፤

ሁለት፤ የመገናኛ ብዙሃን፤ የኃይማኖት፤ የመናገር፤ የመሰብሰብ፤ የመንቀሳቀስና የመደራጀት ነጻነት እንዲከበሩ፤ የማህበረሰብ ድርጅቶች እገባ እንዲቆም፤ የፀረ-ሽብርተኛው ሕግ እንዲነሳ፤

ሶስት፤ የፍርድ ቤት፤ የፌደራል ፖሊስ፤ የመከላከያና የምርጫ ቦርድ ተቋሞች ከገዢው ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ ሁነው መላውን ሕብረተሰብ እንዲያገለግሉ፤

አራት፤ ነዋሪዎችን ከመሬታቸው እንዲገለሉ የሚደረገው ዘመቻ እንዲቆም፤

አምስት፤ በዘር ፍጅት የሚታወቁ ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡና የዘር ፍጅት ዘመቻው በአስቸኳይ እንዲቆም።

ከላይ የቀረቡት መተክሎች አሜሪካ የምታምንባቸው እሴቶች እንደመሆናቸው መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደተግባር ካልተተረጎሙ የአሜሪካ መንግሥት ለህወሓት/ኢህአዴግ የሚሰጠውን እርዳታ በጥንቃቄ መመርመር ይገባዋል። ጉባዔው  ይኼን በሚመለከት የሸንጎ አመራር ለፕሬዝደንት ኦባማ ልዩ ደብዳቤ እንዲፅፍ አሳስቧል።

የትግል ስልት

ከላይ የቀረበውን ኃሳብና አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ጉባዔው ስለ ትግል ስልት ሰፊ ውይይት አድርጎ በሚከተለው ተስማምቷል። ህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካውንና የማህበረሰቡን ነጻነት ተስፋ፤ ምኞትና የመንቀሳቀስ ምህዳር ሙሉ በሙሉ በመዝጋቱ በሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መብት መሰረት በሰላም ለውጥ ለማምጣት የማይቻል መሆኑን አምኗል። ጉባዔው፤ ተቃዋሚዎች፤ የተለያዩ የትግል ስልቶች ቢከተሉም፤ ኢትዮጵያን እንታደግ፤ ለአገራዊና ብሄራዊ ስሜት እንታገል፤ መጠላለፍ እናቁም፤ እንደጋገፍና እንተባበር ከሚሉ አገር ወዳድ ከሆኑ የአንድነት ኃይሎች ጋር አብሮ ለመስራት ያደረገውን ጥሪ አሁንም ያድሳል።

ሸንጎ በመግቢያው የቀረቡትን መርሆዎች ስኬታማ ለማደረግ ከዚህ በፊት በተከታታይና በቆራጥነት ያልተሞከሩ የትግል መንገዶች ሁሉ መስተናገድ አለባቸው የሚል እምነት አለው። በተጨማሪ፤ ህወሓት/ኢህአዴግ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሲያስተጋባ ከቆየው የብሄር/ብሄረሰብና የኃይማኖት ከፋፋይነት፤ የጥላቻና የቂም በቀል የፖለቲካ ባህል ወደ ዴሞክራሲያዊ ባህል መሸጋገር ወሳኝ መሆኑን እናምናለን።

ምንም እንኳን የሃገሪቱ የተፈጥሮ ኃብትና እድገት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥቅም ይዋል፤ መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶች ይከበሩ፣ የሀገር አንድነት ይጠበቅ…ወዘተ የሚል እምነት ይዘው ገዢውን ፓርቲ  ሲታገሉ ብዙ ታጋዮች ቢገደሉም፤ ቢታሰሩም፤ ቢደበደቡም፤ ከሃገር ቢሰደዱም፤ አሁንም በሃገር ቤት ሁነው የሚታገሉ አገር ወዳድ፤ ደፋርና ለውጥ ፈላጊዎች ብዙዎች ናቸው። እነዚህን ደፋር፤ ቆራጥና አገር ወዳድ  ወገኖቻችንን በማንኛውም መንገድ መደገፍ አቅማቸውንም ለመገንባት በሚያደርጉት ጥረት ማገዝ  አስፈላጊ ነው።

በመርሆዎቻችን መሰረት ኢትዮጵያውያንን ያማከለና ያሳተፈ  የተጠናከረ ሰላማዊ ትግል እንዲካሄድና አፋኙ አገዛዝ በዴሞክራሲያዊ  አስተዳደር እንዲተካ ያልተቆጠበ ጥረት እናደርጋለን።  በሰላማዊ ትግል እናምናለን የሚሉ የፖለቲካ፤ የማህበረሰብ፤ የኃይማኖት፤ የሞያና ሌሎች ድርጅቶች፤ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎች የሚያካሂዱት ትግል ውጤታማ ሊሆን የሚችለው የዓላማ አንድነት ተከትለው (ተከትለን) በትግል ስልት የተለያዩትንም ሲያካትቱ (ስናካትት) ነው። ጉባዔው የተለያዩ የትግል ስልቶች መኖራቸውን ተቀብሎ የትግሉን ዘላቂነትና ውጤታማነት የሚወስነው ሕዝብን ማእከል፤ አጋርና አሳታፊ ማድረግ ከቻለ መሆኑን አስምሮበታል። ሕዝብን ያሳተፈ፤ ሕዝብ በባለቤትነት የያዘው ትግል በምንም ሊጠቃ አይችልም። ዴሞክራሲያዊ  አስተዳደር አስተማማኝ ሊሆን የሚችለው የሕዝብን አመኔታ ሲያገኝ ብቻ ነው የሚለውን ግብ ጉባዔው ተቀብሎታል። ትግሉ በከተማና በገጠር የተያያዘና የተቀነባበረ እንዲሆን ድርሻችን ከመወጣት ወደ ኋላ አንልም።

ለሰላማዊ ትግሉ ውጤታማነት  የሚጠቅመው የተሳሰረና የተቀነባበረ አመራር ያለው አገር አቀፍ እምቢተኛነት ነው የሚል እምነት አለን።  ለምሳሌ፤ ከተሜው፤ ገጠሬው፤ ወጣቱ፤ አዛውንቱ፤ ድሃው፤ ባለ ኃብቱ የተባበረበት የየካቲትን ወይንም የግንቦት ዘጠና ሰባትን የሚመስል የሕዝብ እምቢተኛነት ትግል፤ አንዱ ወገን ሲጠቃ ሌላው ድምፅ የማሰማት ትግል፤ የስራ ማቆም አድማ፤ ሰላማዊ ሰልፍ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ የግል የንግድ ተቋሞች እቀባ፤ በሃገር ቤትና በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች የዲፕሎማሲ ትብብር ገዢውን ፓርቲ የማጋለጥ ዘመቻ፤ የተጠናከረ የዘመናዊ መገናኛ ብዙሃን ተጠቅሞ ህወሓት/ኢህአዴግ ወጣቱን ትውልድ የሃገሩን ታሪክ፤ የጀግኖቿን ጀብዱ ስራ፤ የሕዝቡን ተቻችሎ መኖር ወዘተ የሃሰትና የሰው ሰራሽ ታሪክ መሰሪነት አውቆ ለሃገሩና ለወገኑ ተባብሮ የሚነሳበት ዘመቻ፤ በውጭ የሚገኘውን የህወሓት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ የማጋለጥና ሰላዮችን ለፍርድ የማቅረብ ዘመቻ፤ ከሃገር ተሰርቆ የሸሸውን ኃብት የማጋለጥና የማስመለስ ዘመቻ፤ በጥናትና ምርምር የተመሰረተ የእርቅና የሠላም ድርድር ዘመቻ፤ የአንድነት ኃይሎች መተባበርና ውጤት የሚያስገኝ ትግል ዘመቻ ወዘተ። እነዚህና ሌሎች በተከታታይነት ያልተሞከሩ የትግል ዘርፎች ናቸው። የህወሓት/ኢህአዴግን ፈቃደኛነት አይጠይቁም። ከላይ እንዳሳየነው፤ እብሪተኛው ገዢ ፓርቲ ለእርቅና ለሰላም የሚደረግ ጥሪን እንደማያስተናግድ እናምናለን። ሆኖም፤ ጥረቱ በጥላቻ፤ በቂም በቀልና በራስ ወዳድነት ለተበከለው የአዲስ ትውልድ ክፍል ትምህርታዊ ግብዓቶችን ያበረክታል፤ የዓለምን ሕብረተሰብ ልቦና ያንቀሳቅሳል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመንግሥት ለውጥ በመሳሪያ ብቻ እንጅ በመወያየትና በመደራደር አይታሰብምና ተቃዋሚዎች የሚፈልጉት ዲሞክራሲን ሳይሆን ስልጣንን ነው የሚለውን ከእውነቱ የራቀ  የህወሓት/ኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ የማይቀበሉ የአንድነት ኃይሎች እንዳሉ ያሳያል። እነዚህን ሁሉ ለማድረግ ቆራጥነትና ተባባሪነት ያስፈልጋል፤ በፅሁፍ መቅረባቸው ብቻ በቂ አይደለም።

 

በትጥቅ መንገድ እንታገላለን ከሚሉት ውስጥ ከዓላማችን ጋር የሚመሳሰል ዓላማ ካላቸው ጋር መተባበር እንዳለብን ጉባዔው ተወያይቶ ተስማምቷል። ሆኖም፤ ሁሉም በትጥቅ ትግል ህወሓት/ኢህአዴግን የሚፈታተኑት ለኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፤ ዘላቂነትና ጥቅም፤ ለመላው ሕዝቧ ሉዐላዊነት ትሥስርና እውነተኛ እኩልነት፤ ለፍትህና ለሕግ የበላይነትና ሁሉን የማህበረሰብ ክፍሎች ለሚወክል ዲሞክራሳዊ ስርዓት ይታገላሉ ማለት አይቻልም። በዚህ አኳያ ልናስብበት የሚገባን  ያለፈው የፖለቲካ ሂደት አንዱ ትምህርት አንድ አምባገነን አስወግዶ ሌላ አምባገነን መተካት እንዳይከተል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያሰፈልግ ነው። ህወሓት/ኢህአዴግን በመጥላት ከታጠቁ ተገንጣይ ኃይሎች የሚከሰተውን የኢትዮጵያን መፈራረስ፤ አደጋ የእርስ በእርስ ግጭትና የዘር ፍጅት ሴራዎች ሙሉ በሙሉ እንቃወማለን።

ኤርትራን በተመለከተ

ኤርትራ ከጥንቱ ጀምሮ የኢትዮጵያ ኣካል የሆነች ክፍለ-ሃገር ነች። ከ1890ቹ ጀምሮ ክፍለ-ሃገሪቱ የብዙ ፖለቲካ ምስቅልቅሎችና የትጥቅ ትግሎች ሰለባ ሆና እንደቆየች ኣይካድም። በዚህ ሂደት ህዝቡ የዴሞክራሲያዊ መብቱ ተከብሮ ስለመፃኢ ዕድሉ በነፃነት ሊወስንበት የቻለበት ሁኔታ ከተውንም አላገኘም። በ1993 (እ.አ.አ) በኢሳያስ ኣፈወርቂና በመለስ ዜናዊ ኣቀነባባሪነት ኤርትራ ተገንጥላ ‘ነፃ’ ሃገር እንድትባል መደረጉ የዚሁ ሂደት ኣካል ነው። ተካሄደ የተባለው ሬፈረንደም ተቃዋሚዎችን ያላሳተፈ፤ ህዝቡንም ምርጫ የሌለው ውሳኔ እንዲቀበል ያስገደደ፤ በጠብመንጃ ግፊት የተፈፀመ በመሆኑ ተቀባየነት የለውም። ስለዚህም ሸንጎው ኤርትራን እንደ ‘ነፃ’ ሃገር ሳይቀበል የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እስኪመሰረት ድረስ ትግሉን ይቀጥላል።

ብሄራዊ መግባባት እርቅና ሰላም

በህወሓት ላይ የሚደረገው ልዩ ልዩ ትግልና ጫና እንዳለ ሆኖ፤ ጉባዔው ሰፊ ምርምርና ጥናት አድርጎ፤ ከህወሓት/ኢህአዴግ የጥላቻና የጎሳ ፖለቲካ ወደ ነጻና ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ወደሚያሳትፍ ብሄራዊ መግባባት እርቅና ሰላም ውይይት መሸጋገር ለዴሞክራሲ ወሳኝ መሆኑን ተቀብሏል። ምንም እንኳን እብሪተኛው ህወሓት ለዚህ ዓይነቱ ድርድር ዝግጁና ፈቃደኛ አለመሆኑን ብናውቅም፤ የእርቅና ሰላም ጽንሰ ሃሳብ በሃገር ቤትና በውጭ ከፍተኛ ውይይት እንዲካሄድበት ጉባኤው አሳስቧል። ሸንጎ ለዚህ ለተቀደሰ አማራጭ ያልተቆጠበ ድጋፍና እርዳታ ያደርጋል።

በመጨረሻ ጉባዔው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያቀርበው አደራ፤ ለኢትዮጵያ ዘላቂነት፤ ለዴሞክራሲ፤ ለፍትህ፤ ለሕግ የበላይነት፤ ለመገናኛ ብዙሃን ነጻነት…ወዘተ ስኬታማነት እውን የሚሆነው በጋራ ዓላማ ላይ የተመሰረተ፤ የተቀነባበረ ሕዝባዊ ትግል ሲካሄድ ብቻ እንደሆነ ነው። ህወሓት ሊያፈራርሳቸው ቢሞክርም፤ አገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የአንድነት ዘርፍና አካል ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወሳኝ የሆነ ሚና ለመጫወት ስለሚችሉ ኢትዮጵያን ሆሉ የሞራልና የቁሳቁስ ድጋፋችሁን ለግሷቸው፤ እኛም የተቻለንን እናደርጋለን እንላለን።  በተመሳሳይ፤ ሸንጎ በሃገር ቤትና በውጭ ከሚታገሉ የአንድነት ስብስቦችና ግለሰቦች ጋር ተባብሮ ለመስራትና ለመታገል ዝግጁ መሆኑን በድጋሜ ቃል ይገባል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

 

 

የፈጣሪ ሥጦታ ንጡህ አዬርም ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ሹማምንት ፈቃድ ይጠዬቅበታል –በጨለማው ዘመን

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ  30.07.2015 /ሲዊዘርላንድ ዙሪክ/

ይድርስ ለፌስ ቡኩ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር  ለአቶ ቴውድርስ አድህኖም – አዲስ አባባ።

Commentአዎን! በሶሻሊስታዊ ፋሽስታዊ ጎጣዊ ሥርዓት ዬተለያችሁ ናችሁ። እናንተን የሚመሰል ዝብርቅ ሥርዓት ዓለም በ21ኛው ምዕተ ዓመት አለም አታስተናግድም እና። እንዲህ – ትቀልዳላችሁ፤ በተፈጥሮ – ትሳለቃላችሁ፤ በፈጠሪ ጥበብ – ታባጭላላችሁ፤ በፋሽስት ተግባራችሁም – ትንደላቀቃላቸሁ፤ በናዚያዊ ዬጭካኔ ድርጊታችሁ – ትዝናናላችሁ፤ በስው ልጆች ፈጣሪያዊ ጸጋ – ትራገጣላችሁ — ፈጣሪ በመረቀለን ሰብዕዊ ነፃነትም – ትንጠራራላችሁ፤ ተወጣጠራችሁ፤ ምን እናንተ የማትሆኑት አለና /// መሳቂያዎች! ጥብቆ – መንጠቆ።

አሁን – በአሁኑ ጊዜ ስለምን ዬአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን ሁኔታ መረጃ በለበጣ ለመስጠት አስፈለጋችሁ?! መቼም ስትፈጠሩ ሃፍረት የሚባል ነገር ሰርቶላችሁ አያውቅም፤ ዓይን አውጣ – ጉረኞች!

መቼም ኮረኮንች ናችሁና የደረደራችሁትን አሽዋማ – እኛም ውጪ ሆነን በኢንተርኔት እዬሳቅን ጎብኘት – እናደርገዋለን። የማላገጥ ጊዜ ሲያበቃ የመሸሸጊያ ትንሽ ቁጥቋጦ ካገኛችሁ …. ደባችሁን – ጠይቁት። የጭካኔ ሸራችሁ ይምልስላችኋል … አድራሻችሁ የት ሊሆን እንደሚችል አሳምሩ – ያረዳችኋል። ጥጋቡም ይተነፍሳል —-

ጠይቁን ብላችሁ አምልክታችሁ ዬሰጣችሁትን ቃለ ምልልስ – አዳምጠናል። የሰሞኑ መንደፋደፍ በትርምስ ተያይዛችሁታል። መጀመሪያ ድፍረት ይኑራችሁ፤ አርበኛችን ያሰራችሁበትን ቦታ ለመግለጽ። አርበኛችን የእኛ እንጂ የእናንተ ባልመሆኑ ሊዩት የናፈቁት ቆራጥ አርበኞች በመዲናች አሉ። መንፈሱ ሊቅ ነው። መንፈሱ የድል ሞገድ ነው። መንፈሱ የነገ ገድል ነው።

ለነገሩ እኮ ቆራጣ እፍረት ያለሰራላችሁ ስለመሆናችሁ እኮ፤ የ100 ዓመት ታሪኩ ተገልብጦ ባለታሪክ እናንተ – ሆናችሁ ዓይናችሁን በጥሬጨው ያጠባችሁ – ጉዶች፤ ለዛውም የሰው ልጆች ፍጥረት መገኛ የሆነችውን ድንቅነሽን ከዓለሙ መሪ ከክቡር ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በክህደታችሁ እዬተንዘፈዘፋችሁ አብራችሁ ቁማችሁ – እዬሳቅንባችሁ አዬናችሁ። ዋንጫውንም አብራችሁ አነሳችሁ – መሳቂያዎች¡ እንዲህ ናት ኢትዮጵያ ማለት ከእግር ሥር የምታንበረክክ –  የኃያሎች ኃያልፍጹም ልቅና ያላት የዓለም ሁለመና።

እናንተ ለሰው ልጆች መብት ተቆርቋሪዎች ሆናችሁ ደግሞ¡ – ወይ ማላገጥ፤ እንዲህ ትቀልዳላችሁ፤ እንዲህም ታፌዛላችሁ፤ ከመለሲዝም ናዚዝም ብጣቂ ነገር እንደማይገኝ ህቅ እሲካላችሁ ድረስ ስትጋቱት ሰንበታችኋል – እራሳችሁ በተሞሾራችሁበት፤ አታሞዋን ስታስነኩበት በሰነባባታችሁት መድረክ እንዳዬነው ደብቁቁኝ  – ደብቁኝ ብላችሁ ዬእንብርክክ ስትሄዱ፤ ዝናብ ያበሰበሰው ካፖርት ትመስሉ ነበር ደመመን ተጫጭኗቸሁ፤ ማፈሪያ! የዓለም መሳቂያ መሆናችሁን ማን – በነገራችሁ?! ምን አልባት የዛሬው ቃለ ምልልስ ተብዬው የደመር ውሎ ሊሆን ይችላል። የለቅሶ ሰሞናታችሁን በወል – የምታወራርዱበት። እፍረት የሚባል ነገር። ለነገሩ እናንተ አልሰራላችሁ – ዝክንትሎች። ዝልብልቦች፤

ትውልዱ አክ እንትፍ ብሎ አንቅሮ ከተዋችሁ እኮ ዓመታት – ተቆጠሩ። ደባውም፤ ሴራውም፤ ሽፋኑም፤ ግርዶሽም አልቆ፤ ውልቅልቅ ብላችሁ አውላላ ሜዳ ላይ ባዶአችሁን እንዲህ – ትንቀዋለላችሁ። ይልቅ እርስዎ ነጠል ብለው ወጥተው፤ ወደ ጥሩ የሥራ መስክ – ሽግግር አድርገዋል። ሥራ ስሌለዎት ዬፌስ ቡክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተርነቱን በዶክተሬትነት በመወስደዎት  – ዕድለኛ ነዎት¡ ከልጆቾዎት ጋራ እንዲህ ሰኞ – ማክሰኞ፣ እቃ – ዕቃ፣ ዝላይ፣ ሽግ – ሽጎሽ፣ አዬሁሽ አላዬሁሽ …. ጎሽ¡ መደበዎት ይህ ነው …. ጥሩ ምርጫ …. ልክዎትና –  ተረድተዋል፤

አርበኛችን የሚፈልገው የሸፍጥን ፎቅ – ድልዝ ተግባርን – አይደለም። የታላቋን ብርታንያ  – ያ በነፃነት እፎይ ያለውን፤ በሥልጣኔ መሠረትነት በዘላቂነት የተገነባውን አፓርትመንት፤ የሐገሪቱን ዬሥልጣኔ ሁለገብ – አውታራትን፤ የፍትህ ተቋማትን ሙሉ ነፃነት፤ የሰው ልጆችን የእኩልነት ተቋማት መንፈስን፤ እንዲሁም የሚወዳቸውን ቤተሰቦቹን ትቶ ነው የሀገሩን ነፃነት ፍለጋ መከራን አብዝቶ – የተቀበለው። በደረጃም – በጸጋም – በብልህነትም – በተግባር ሰውነትም – በማስተዋል ልቅናም – ይበልጠወታል!

የአርበኛችን ፍልስፍናው በመሳሪያ ኃይል፣ በጎጥ ዛር ፍዳ የምታይ፣ አሳር የከተመባት ሐገር ሳይሆን፤ እንደ የሰው ልጆች መፈጠሪያነቷ፤ እንደ ሥልጣኔ ቀደምትነቷ፤ እንደ ጥቁሮች ዬነፃነት ዓርማነቷ፤ እንደ ሁለገብ ብቁ – አብነቷ፤ እንደ ታሪክ – ማህደርነቷ፤ እንደ አፍሪካ ህብርትና የተባበሩት መንግሥታት – መሥራች አባልነቷ፤  በህዝብ ፈቃድና ውሳኔ በጸደቀ ህገ መንግሥት፤ በምልዕት ፍላጎት በሚመረጡ – ልጇቿ፤ በህግ እኩልነት የምትዳደር – ሐገርን ማዬት ነው የሚሻው።

አርበኛችን – በዕዳ የተዋጠች – በልማና እና በብድር ትንፋሿ ታፍኖ ጠግባ ሳታድር በራህብ እዬተቆላች ጉሮሯዋ ደርቆ፤ መንፈሷ ተሰንጎ መከራ ስንቋ የሆነች የዕንባ ሐገርን – አይደለም። የአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ራዕይ በራሷ አቅም፤ ባለት በቂ ቅምጥ የከርሰምድር ሃብታት – ጥሪትና ንብረት ዕውቅ ሳይንቲስቶቿ፤ ፈላስፋዎቿ፤ ሙሁር ልጆቿ ዘመኑ የፈቀደላቸውን ቡራኬ በአኩልነት ያገኙ ዘንድ በሙሉ ነፃነት ሙሉ ተሳትፎ የሚያደርጉበት አዲስ ብሄራዊ ሥርዓት በመፍጠር፤ ልዕልት ኢትዮጵያ – ቀለማም፣ ውብ፣ አስዳች፣ ተናፋቂ፣ ተጎብኝ ሀገር እንድተሆን ነው – ራዕዩ። ያ እሱ የናፈቀው ሥርዓት ሲዘረጋ ሁሉም ይሆናል …. በመዳፍ ያለ ነው። ኢትዮጵያዊነትን የዋጡ፤ እትዮጵያዊነትን ክብራችን ብለው የሆኑበትም ውድ ልጆች ንግሥት ኢትዮጵያ አላት። እሳት የሆኑ – ታታሪ – ትንታግ  – ባተሌ ለቃላቸው ያደሩ ልጆች አሏት እናት ኢትዮጵያ።

እንደ እርሶዎ በቧልተ ሊጥ ተቦክቶ ያልተጋገረ ስላልሆነ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ እሱ ምራቁን የወጠ የቁምነገር ፈላስፋ ነው። የሚገርመውና የሚደንቀው ደግሞ አሁንም እንዴት እንደምትፈሩትና የእሱ መንፈስ እንዴት በረድፍ በተጠንቀቅ በመደዴ እንዳሰለፋችሁ፤ እንደሚያንቀጠቅጣችሁም – ልባችሁ ያውቀዋል። የሰሞናቱ ስምሪት ይሄው ነው እሱ – በእሱ። ግን አሞራው በረረ ቅሉም ተሰበረ ነው …. ዕጣችሁ። የቀጠላችሁ ካርቦኖች።

ይህ ያደረጉት ከረባት፤ ይህ የለበሱት ሽክ ያለ ገበርዲን በደም የተጨማለቀ ነው፤ በምልዕቱ ዕንባ – የተዘፈዘፈ ነው። መጠን ሊወጣለት ባልቻለ ጽንስን በግፍ – በረገጠ የጨቀዬ ነው። ህሊና ቢኖራችሁ ለብሶ ለመታዬት በቀፈፋችሁ ነበረ። ግን አልሰራላችሁም ህሊና – የሚባል ነገር። መቃብር ነው የእናንተ የማስተዋል ደረጃ። አንድ ቀን አዎን አንድ ቀን እንዲህ መረን የለቀቀው የበዛ መቀናጣት የጨው ሐውልት እንደሚያደርጋችሁ –  እሰቡ። እናንተ ማሰብ – ይፈቀድላችኋል። ብዙኃኑ ግን ገና ልተሰብ ነው ተብሎ በግፍ ወደ እስር ይጋዛል – ይደበደባል። አውሬዎች!

የወያኔ ሐርነት የጎጥ ሽማምንቶችና እንዲሁም ዬማንፌስቶ ውሸት ያልቃል – ቅጥፈቱም  ይቀበራል፤ – ሽዋዳውም – ይሞታል –  ዕብለቱም ይደረመሳል – ማባጭሉም – ይደቃል – መሳለቁም – ይተናል፤ ደባውም – ይቃጠላል፤ ግፉም – ያበቃል። መሬት ተከፍታ እንደትውጣችሁ ኤሉሄ አሌሄ የምትሉበት ጊዜ – ይመጣል። ዝምታ የጨዋውና የአስተዋዩ ህዝብ አመጻዊ ዬችሎት አደባባይ ነው። እወቁት –  ዕውነት በተባ ተግባር ያሸንፋል። ያ እንዳለፈው ሁሉ ይህም ዬጨለማ ዘመንም – ያልፋል። ይነጋል – በያነጋል!

የኔዎቹ መሸቢያ ጊዜ።

ምንጭ – http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45438

ክብር ለአርበኞቻችን!

አርቦኞቻችን መንገዶቻችን ናቸው።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ፤

 

የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የሚያስቅ እና የሚያሰቅቅ ጉብኝት –በኢትዮጵያ!

$
0
0

ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ- ጆርጂያ)

ይህ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ጉብኝት፤ ድንገት ትላንት የመጣ ሳይሆን – ቀደም ሲል ሲገነባ በቆየው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ነው። የትላንት ታሪካችንን ማየት የተሳናቸው የዘመኑ ገዥዎች ይህንን ላያውቁ ይችላሉ። ነገር ግን ታሪክ ሊፋቅ የማይቻል ሃቅ በመሆኑ፤ ደግመን ደጋግመን በእውነት በትር አናት አናታቸውን መቀወር ያስፈልጋል።
ADF6D103-B2F3-45BA-BEC7-4DA0AC962E4A_w640_r1_s
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በኦፊሴል ዲፕሎማቲክ ግንኙነት ከጀመሩ 112 አመታት ተቆጠሩ። በታህሳስ 1903 ከአጼ ምኒልክ ጋር የተነጋገሩት ከአሜሪካው ፕሬዘዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት የተላኩት፤ ሮበርት ስኪነር ነበሩ። ከአጼ ምኒልክ ጋር የተደረገው ስብሰባ ዘጠኝ ቀናትን የፈጀ ነበር። የሁለቱም አገር ህዝቦች በነጻነት እንዲዘዋወሩ፣ የንግድ ግንኙነት፣ እና አሜሪካ አባይን ለመገደብ እውቀቱ ያላቸውን ሰዎች እንድታበረክት ነበር። በኋላ ላይ ሃኪም ወርቅነህ እሸቴ (ዶ/ር ቻርልስ ማርቲን) በ1927 ወደ አሜሪካ መጥተው ሃርለምን ሲጎበኙ፤ የራስ ተፈሪን መልእክት አስተላለፉ። ወደአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመሄድም፤ በአጼ ምኒልክ ዘመን ስምምነት ላይ የተደረሰበትን የአባይን ግድብ ጉዳይ ተነጋገሩ። በእርግጥም አሜሪካውያን ጥናቱን ለማድረግ ብቻ ሳይሆን፤ ግድቡንም ለመስራት ስምምነት ላይ ተደረሶ ነበር። እነዚህን ነገሮች በደምሳሳው የምንጠቃቅሰው የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ግንኙነት ወይም የአባይ ግድብ ሃሳብ ጭምር ትላንት የተጀመረ አለመሆኑን ለመግለጽ ነው። አንድ አንቀጽ እንጨምርና ወደ ዋናው ጉዳይ እንሄዳለን።
እንዲህ እንዲህ እያልን… ጥቁሮች ዩኒቨርስቲ መግባት በማይችሉበት ወቅት እነመላኩ በያን ኦሃዮ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ያደረጉትን የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት ዋረን ሃርዲንግን ጭምር ማንሳት አስፈላጊ ነው። በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች ልባቸው ኢትዮጵያን ሲያስብ ኖሯል። በኢትዮጵያ እና ጣልያን ጦርነት ወቅት አለም ሁሉ ፊቱን ሲያዞርብን፤ የጣልያንን ወረራ ካልተቀበሉት አምስት አገሮች ውስጥ አሜሪካ አንዷ ነበረች። በኢትዮጵያ ውስጥ ግዙፉን አየር መንገድ እና የቀድሞውን አውራ ጎዳና መስሪያ ቤት የመሰረቱት አሜሪካኖች ናቸው። በ1963 ዓ.ም. ቀዳማዊ ኃይለስላሴ አሜሪካንን ሲጎበኙ፤ ፕሬዘዳንት ጆን.ኤፍ.ኬኔዲ ተቀብለው አስተናግደዋቸዋል። ኋይት ሃውስ በክብር የገቡትም የመጀመሪያው ጥቁር መሪ፤ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሆነዋል። አሜሪካኖች ከመልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታችን በተጨማሪ ተዋጊ መርከቦችን ጨምሮ፤ የሰጡን የጦር መሳሪያ እና የጦር ልምድ የትየለሌ ነው። ይህን ሁሉ ወደ ጎን ብንተው እንኳን፤ በ19ሰማንያዎቹ የድርቅ ዘመናት ከሌላው ህዝብ በላይ “We are the world” ብለው የታደጉንን ከቶ አንረሳውም። አለም በአውሮፕላን መቀራረብ ከጀመረች በኋላ የቀድሞዎቹ የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች ጂሚ ካርተር፣ ቢል ክሊንተን እና ጆርጅ ቡሽ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። አሁን ደግሞ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ጎበኙ። ከዚያስ? የሆነውን አብረን እንከታተል።

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በኦፊሴል ዲፕሎማቲክ ግንኙነት ከጀመሩ 112 አመታት ተቆጠሩ። በታህሳስ 1903 ከአጼ ምኒልክ ጋር የተነጋገሩት ከአሜሪካው ፕሬዘዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት የተላኩት፤ ሮበርት ስኪነር ነበሩ። ከአጼ ምኒልክ ጋር የተደረገው ስብሰባ ዘጠኝ ቀናትን የፈጀ ነበር። የሁለቱም አገር ህዝቦች በነጻነት እንዲዘዋወሩ፣ የንግድ ግንኙነት፣ እና አሜሪካ አባይን ለመገደብ እውቀቱ ያላቸውን ሰዎች እንድታበረክት ነበር። በኋላ ላይ ሃኪም ወርቅነህ እሸቴ (ዶ/ር ቻርልስ ማርቲን) በ1927 ወደ አሜሪካ መጥተው ሃርለምን ሲጎበኙ፤ የራስ ተፈሪን መልእክት አስተላለፉ። ወደአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመሄድም፤ በአጼ ምኒልክ ዘመን ስምምነት ላይ የተደረሰበትን የአባይን ግድብ ጉዳይ ተነጋገሩ። በእርግጥም አሜሪካውያን ጥናቱን ለማድረግ ብቻ ሳይሆን፤ ግድቡንም ለመስራት ስምምነት ላይ ተደረሶ ነበር። እነዚህን ነገሮች በደምሳሳው የምንጠቃቅሰው የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ግንኙነት ወይም የአባይ ግድብ ሃሳብ ጭምር ትላንት የተጀመረ አለመሆኑን ለመግለጽ ነው። አንድ አንቀጽ እንጨምርና ወደ ዋናው ጉዳይ እንሄዳለን።

obama
እንዲህ እንዲህ እያልን… ጥቁሮች ዩኒቨርስቲ መግባት በማይችሉበት ወቅት እነመላኩ በያን ኦሃዮ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ያደረጉትን የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት ዋረን ሃርዲንግን ጭምር ማንሳት አስፈላጊ ነው። በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች ልባቸው ኢትዮጵያን ሲያስብ ኖሯል። በኢትዮጵያ እና ጣልያን ጦርነት ወቅት አለም ሁሉ ፊቱን ሲያዞርብን፤ የጣልያንን ወረራ ካልተቀበሉት አምስት አገሮች ውስጥ አሜሪካ አንዷ ነበረች። በኢትዮጵያ ውስጥ ግዙፉን አየር መንገድ እና የቀድሞውን አውራ ጎዳና መስሪያ ቤት የመሰረቱት አሜሪካኖች ናቸው። በ1963 ዓ.ም. ቀዳማዊ ኃይለስላሴ አሜሪካንን ሲጎበኙ፤ ፕሬዘዳንት ጆን.ኤፍ.ኬኔዲ ተቀብለው አስተናግደዋቸዋል። ኋይት ሃውስ በክብር የገቡትም የመጀመሪያው ጥቁር መሪ፤ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሆነዋል። አሜሪካኖች ከመልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታችን በተጨማሪ ተዋጊ መርከቦችን ጨምሮ፤ የሰጡን የጦር መሳሪያ እና የጦር ልምድ የትየለሌ ነው። ይህን ሁሉ ወደ ጎን ብንተው እንኳን፤ በ19ሰማንያዎቹ የድርቅ ዘመናት ከሌላው ህዝብ በላይ “We are the world” ብለው የታደጉንን ከቶ አንረሳውም። አለም በአውሮፕላን መቀራረብ ከጀመረች በኋላ የቀድሞዎቹ የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች ጂሚ ካርተር፣ ቢል ክሊንተን እና ጆርጅ ቡሽ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። አሁን ደግሞ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ጎበኙ። ከዚያስ? የሆነውን አብረን እንከታተል።

ምን ያህል ሰው ልብ እንዳለው ማወቅ ያስቸግራል። የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን የእራት ምሽት ንግግር ልብ ይበሉ። በአማርኛ ቋንቋ “እንደምን ዋላቹህ?” ብለው ነው ንግግራቸውን የጀመሩት። “የኢትዮጵያ ታሪክ የ200 አመት ታሪክ ነው” ሲሉን ለነበሩ ሰዎች ነው – ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ መሆኗን እና ጥንታዊነቷን የመሰከሩት።
የአጼ ምኒልክን ወራሪነት ለሚሰብኩት ሰዎች ነው፤ “ኢትዮጵያ – ከጥቁር አሜሪካውያን በፊት ለነጻነቷ የተዋጋች አገር ናት” ብለው ያሞገሷት። ሌላው ቀርቶ የንጉሥ ሰለሞን እና የንግሥተ ሳባን ግንኙነት፤ “ተረት ተረት ነው” ሲሉን የነበሩ ሰዎች በብሄራዊ ሙዚየም፤ የንግሥተ ሳባን ስዕል እያዩ እና እያሳዩ ስናይ፤ የታሪክን አሸናፊነት ተገነዘብነ።
ሌላው ቀርቶ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የሉሲን አጽም በመገረም ሲመለከቱ፤ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ “የዚህ አጽም ብሄር ምን ይሆን?” ብለው… ሆዱን ቁርጠት ይዞት ፊቱን ቅጭም ያደረገ ህጻን ልጅ መስለው ነበር።
በአጠቃላይ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በዝርዝር ያቀረቧቸው የኢትዮጵያዊነት መገለጫዎች፤ በሰዎቹ የፖለቲካ መዝገበ ቃላት ውስጥ “የነፍጠኞች ታሪክ” ተብሎ የተመዘገበ ነው። ኢህአዴግ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ሰሞን፤ “በብሄራዊ ሙዚየሙ ውስጥ የሚገኙት የአጼ ምኒልክ እና የሌሎች ነገስታት አልባሳት መቃጠል አለባቸው” ሲሉ የነበሩትን ወገኖች በሙዚየሙ ጉብኝት ወቅትአላየናቸውም። ቢያንስ ተወካያቸው ግን በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያን ታሪክ የተማረ ይመስለናል። እናም “በፕሬዘዳንት ኦባማ ጉብኝት ወቅትት፤ ጎልቶ እና አሸንፎ ለወጣው የኢትዮጵያውያን ታሪክ ዘላለማዊ ክብር ይሁን!” አልነ።
በነገርዎ ላይ… የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በእራቱ ግብዣ የመጨረሻ ንግግራቸው ላይ፤ ለሁለቱ አገሮች ግንኙነት፣ ቀስተ-ደመና ለተወለደባት ለኢትዮጵያ እንዲሁም “ለጤናችን” ብለው ፅዋቸውን ለማንሳት ሲዘጋጁ፤ (የአስተናጋጁን ነውር አይታችኋል?) አተናጋጁ በግራ እጁ መለኪያውን ሰጥቶ ሂድት ይላል። የሱ ገርሞን ሳያበቃ… የኛው ሰውዬ ደግሞ በምላሹ፤ ከጽዋው ባይጎነጩም (ምናልባት በሃይማኖት ምክንያት ይሆናል)፤ “እኛም እጃችንን ዘርግተን እንቀበላችኋለን” ብለዋል። በቅሌት ላይ ቅሌት ሲደራረብብን፤ ከአንድ ቀን በፊት ቦሌ ላይ የነበራቸውን ሁኔታ አስታወሰን። ቦሌ ላይ እጅ ዘርግቶ መቀበል ብቻ ሳይሆን፤ ተንበርክከው መቀበል ቢኖርባቸው የሚያደርጉት ነው የሚመስለው። ለዚህ አባባል ምስክር እንዲሆነን፤ በፊልም ደንብ Flash back ሂደት ወደ ኋላ በማጠንጠን፤ ለፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ቦሌ ላይ የተደረገላቸው አቀባበል፤ “ኧረ የፕሮቶኮል ሹም ያለህ!” የሚያሰኝ ነውና – እስኪ ትንሽ እንጨዋወት።

ጁላይ 26 ቀን፣ 2015 የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ አዲስ አበባ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላቸው የብዙዎች ግምት ነበር። ሆኖም ምስቅልቅሉ በወጣ እና ፕሮቶኮሉን ባልጠበቀ፤ አሳፋሪ ግርግር የአቀባበሉ ስነ ስርአት ተበላሸ። እዚያ የተገኙት ጥቂት የኢህአዴግ ሹመኞችን ብንጠላቸውም እንኳን፤ እንደሰው መጠን አሳዝነውናል። ከሃዘናችን በላይ ግን ሰዎቹ ኢትዮጵያን ወክለው ሲቆሙ፤ ክብራችንን ዝቅ በሚያደርግ ደረጃ እንዲያዋርዱን መፍቀድ የለብንም። ለፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የተደረገውን አቀባበል የተመለከተ ማንም ሰው፤ በአገሪቱ የፕሮቶኮል ሹም ወይም የእንግዳ አቀባበል ስነ ስርት እንደሌለ ሊስማማ ይችላል።

እናም ቦሌ ላይ… “ኤርፎርስ አንድ” አውሮፕላን ካረፈ በኋላ፤ የመውረጃውን መሰላል የተሸከመው መኪና ግራ እንደተጋባ ያስታውቅ ነበር። መኪናው መሰላሉን ተሸክሞ ወደ ፓይለቱ መውረጃ ገሰገሰ። ሆኖም ቁመቱ አልደርስ ብሎት እየታገለ ሳለ፤ በአውሮፕላኑ ያልታሰበ ክፍል፤ ባራክ ኦባማ ከውስጥ በሩን ከፍተው ብቅ አሉ። መሰላሉ ግን በስፍራው የለም። ሰውየው ባራክ ኦባማ መሆናቸው በጀ እንጂ፤ ሌላ ቀልቃላ ፕሬዘዳንት ቢሆን ከአውሮፕላኑ ላይ ሊፈጠፈጥ እንደሚችል አትጠራጠሩ። እናም እንደአለም ዋንጫ ሂደቱን በቴሌቭዥን እያየን፤ “ኧረ ቆይ ክቡርነትዎ” እያልን ሰጋን። ሆኖም አትሙች ያላት ነፍስ ተመልሳ ወደ ውስጥ ገባች። ባራክ ኦባማ ከፍተው ሊፈጠፈጡበት የነበረው በር ተመልሶ ተዘጋ። ያ – የመውረጃ መሰላል የተሸከመውና በፓይለቱ መውጫ በኩል ለማስጠጋት ይጥር የነበረ ሹፌር… በፍጥነት አነዳድ ተከፍታ ወደተዘጋችው በር ሄደ። (ትዕይንት አንድ አበቃ)
ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ከአውሮፕላን ሲወርዱ ቀይ ምንጣፍ ተዘጋጅቶ አልጠበቃቸውም። ትንሽ ቆይተው ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ቀይ የቃልቻ የሚመስል ጃንጥላ ተይዞላቸው ወደ አውሮፕላኑ መጡ። ከሳቸው በፊት ቆመው የሚጠብቁትን ጥቂት ሚንስትሮቻቸውን ቀና ብለው እንኳን ሳያዩ ወደ አውሮፕላኑ ስር ተጣድፈው ደረሱ። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ከአውሮፕላኑ ወርደው ሳይጨርሱ፤ ህጻናቱ አበባ ለመስጠት አሰፈሰፉ። አንድ ሳይሆን ሁለት አበባ ይዘዋል። ሁለተኛው አበባ ለማን እንደሆነ አምላክ ይወቀው። (ትዕይንቱ ቀጥሏል)
አቀባበል ሊያደርጉ ከሄዱት ሚንስትሮች መካከል፤ ፌስ ቡክ ላይ ፎቶ በመለጠፍ የሚታወቁት የውጭው ጉዳይ ሚንስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ባራኪ ስልካቸውን ይዘው፤ ለፌስ ቡካቸው የሚሆን ፎቶ ለማንሳት ቢሞክሩም የአሜሪካው ሴኩሪቲ ኮስተር ብሎ ሲያያቸው፤ የሚገቡበት ጠፋቸው። ሌሎቹ ሚንስትሮች እንደምንም ተጋፍተው ወደ ባራክ ኦባማ ሲሄዱ ዶ/ር ቴድሮስ ከኋላ ተሸፍነው ቀሩ። ነገሩ ቅጥ አምባሩ ጠፋ። ፕሮቶኮል ትሁን ምን ያላወቅናት ሴትዮ፤ ከህጻናቱ ጋር አብራ ትጋፋለች። ተጋፍታ ሄዳ ፕሬዘዳንት ኦባማን ትጨብጣለች። የህወሃቱ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ጎንበስ ብሎ የሚሆነውን ሲመለከት፤ ሌሎቹም እሱን ተከትለው ሲያጎነብሱ – በሁኔታው ሃፍረት የተሰማቸው በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ ግርማ ብሩ፤ የብርሃነ ገብረክርስቶስን ጀርባ ደልቀው፤ ስነ ስርአት እንዲይዙ ለማድረግ ይሞክራሉ። ትርኢቱ እያሳቀ ያሳቅቃል።

ይሄ ሁሉ ሲሆን… ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ደግሞ፤ ስለህጻናቱም ስለሚንስትሮቻቸውም ግድ ሳይሰጣቸው፤ ከሁሉም በላይ ተንሰፍስፈው ወደ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ አመሩ። (እኛ በቲቪ እያየን “ኧረ አትንሰፍሰፉ” እንላለን) ጠ/ሚንስትሩ – ፕሬዘዳንቱን ጨብጠው ምን እንዳሏቸው ባናውቅም፤ አቶ ኃይለማርያም በደስታ የሚይዙት እና የሚጨብጡት ጠፍቷቸው ፍንድቅድቅ አሉ። እግር ኳስ ጨዋታ ሲጀመር፤ የቡድኑ ካፒቴን ግዜ ወስዶ – ሌሎቹን ተጫዋቾች የሚያስተዋውቀውን ያህል እንኳ አልተጨነቁም – አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ። ሚንስትሮቹን በስርአት ሳያስተዋውቁ፤ ወደ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ መኪና አብረው ሄዱ። ልክ ወደዛ እየሄዱ ሳለ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ቴዎድሮስ አድሃኖም፤ ለፌስቡክ የሚሆናቸውን ፎቶ ለማንሳት ስልካቸውን ይዘው ፎቶ ለማንሳት በድጋሚ ታዘብናቸው። ሆኖም በዚያች ቅጽበት ፕሬዘዳንት ኦባማ ወደመኪናቸው ገብተው፤ በፍጥነት ቦሌ አየር ማረፊያን ለቀው ሄዱ። እናም ለታላቁ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት የተደረገው አቀባበል እዚህ ላይ አበቃ። ለጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያምም፤ ለቃልቻ የሚያዘው ቀይ ባለ አዝራር ጃንጥላ ተይዞላቸው አየር መንገዱን ለቀው ወጡ።

እንደ እብድ ቡድን የተዘባረቀ ሱፍ የለበሱትን ሚንስትሮች ትተን አበባ እንዲሰጡ የተደረጉትን ልጆች እንቃኝ። ልጆቹ አበባውን ከሰጡ በኋላ ፕሬዘዳንቱን መኪናቸው ድረስ ተከትለው፤ የማናውቀውን ነገር ያወሯቸዋል። እነዚህ ልጆች እንደባህላችን ጸጉራቸውን ሽሩባ ተሰርተው… ደግሞም የአገር ባህል ለብሰው አልቀረቡም። ጭራሹን ከአራቱ አንዷ… ጸጉሯን ጨበርኛ ተሰርታ፣ ካኪ ኮት እና ጥቁር ሱሪ አድርጋ… ከታች ሸራ ጫማ ሸብ አድርጋ እንድትቀበል ነው የተደረገው። እንደዚህ አይነት አለባበስ ኢትዮጵያውያንን ሊወክል አይችልም። እንጨምር ከተባለ ሌላም ማለት ይቻላል።

በንጋታው ቡና ሲፈላ የነበረውን ሁኔታ እንመልከት። ቡና የሚያፈሉት ሴቶች ‘ለምን አሮጊቶች ሆኑ ብሎ መከራከር ወይም ለምን የትግሬ ሹሩባ ተሰሩ?’ ማለት አግባብ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ቡና ሲፈላ፤ በሙቀጫ የተወቀጠ የሚመስል – ጋቢ አይሉት ነጠላ አድርጎ ቡና ማስተናገድ ምን የሚሉት ባህል ነው? ባህል ለማሳየት ከሆነ ያስፈለገው እጣኑ በገል፣ ስኒው በረከቦት፣ ቄጤማው ተጎዝጉዞ፣ ፈንዲሻው ተበትኖ፣ ቁጢጥ ከሚሉም በርጩማ ላይ ቁጭ ብለው – አቦል ቶና በረካ ቢጠጡ ደስ ይል ነበር።
በዚያ ላይ ለዳንኪራ የተጠሩት ልጆች እንደድሮ የቀበሌ ኪነት፤ አራምባ እና ቆቦ ሲረግጡ አይተን… “የአገር ፍቅር ቴያትር ቤት ተወዛዋዦች ባይኖሩ፣ የማዘጋጃ እና የብሄራዊ ልጆች ወዴት ሄዱ?” ብለን አዝነናል። በዚያ ላይ ልጆቹ እስክስታቸውን ሲጨርሱ፤ አበባየሆሽ ለማለት እንደመጡ ህጻናት እየተገፈታተሩ ሲወጡ አይተን… “ምን እየተካሄደ ነው?” ማለታችን አልቀረም።
አቀባበሉን ከኬንያው ጋር ማነጻጸር አይቻልም። ኬንያዎቹ ሽር ጉድ ሳያበዙ ዘና ብለው ነው አቀባበል እና አሸኛኘት ያደረጉት። በሬድዮ እና በቴሌቭዥን ብዙ በጣም ብዙ ሲባል ነበር። በየመንገዱ ሳይቀር የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ፎቶ ተለጥፏል። ከፎቶውም ስር በትላልቁ፤ “Thank you for vesting Ethiopia!” ተብሎ ተጽፏል። የዚህ ቀጥታ ትርጉም “ኢትዮጵያን እንዳሻዎ ስለሚያደርጓት እናመሰግናለን” የሚል ነው። ይሄን እንዲጽፍ ሃላፊነት የተሰጠው ሰው visiting ለማለት ፈልጎ vesting ማለቱ እውነት ነው። “Thank you for visiting Ethiopia” ለማለት ነበር የተፈለገው። እንግዲህ ዲግሪ በገንዘብ በሚገዛበት አገር ይህ ነገር መፈጸሙ ሊገርመን አይገባም፤ ሆን ተብሎ ቢደረግም አይደንቀንም።

ወደ እንግዳው አቀባበል እንመለስ። በአገራችን ከአጼ ምኒልክ ዘመን ጀምሮ ትላልቅ እንግዶች ሲመጡ፤ ለክብራቸው 21 ግዜ መድፍ ይተኮሳል። እ.አ.አ በ1903 በአሜሪካው ፕሬዘዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የተላከው የመጀመሪያው ዲፕሎማት ሮበርት ስኪነር፤ አዲስ አበባ ገብቶ ከአጼ ምኒልክ ጋር ከተገናኘ በኋላ፤ ለክብራቸው 21 ግዜ መድፍ እንደተተኮሰ እና የንጉሠ ነገሥቱ የሙዚቃ ባንድ አጅቧቸው ወደ ራስ ወልደጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት ለማረፍ መሄዳቸውን ጽፏል። ከመቶ አመት በፊት አጼ ምኒልክ ለአሜሪካ ልዑካን ቡድን ያደረጉትን ያህል አቀባበል ማድረግ ሊያቅተን አይገባም ነበር። ይህችን አጋጣሚ በመጠቀም በወቅቱ የምኒልክን ፎቶ አንስቶ ነበር እዚህ ላይ ፎቶዋን አናካፍለናቹህ ወደ ጉዳያችን እንለፍ።

በኢትዮጵያ ታሪክ ለሰማይ እና ለምድር የከበዱ ሰዎች ሲመጡ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በዘመኑም ሆነ አሁን ጭምር በአለም ህዝብ ዘንድ ከፍ ብለው የሚታዩት የእንግሊዟ ንግሥት ኤልሳቤጥ ከአዲስ አበባ አልፈው ጢስ አባይን ጭምር ጎብኝተዋል። ከማርሻል ቲቶ ጀምሮ የብዙ አገር መሪዎች በክብር ተስተናግደዋል። የኩባውን ፕሬዘዳንት ፊደል ካስትሮን ጨምሮ በርካታ ፕሬዘዳንቶች ኢትዮጵያን ሲጎበኙ በጥሩንባ ጭምር፤ ህዝቡ በነቂስ እንዲወጣ ተደርጎ ነው አቀባበል ያደረገላቸው። ይሄን ማንሳታችን እንኳን፤ አንዳንድ ግዜ እራሳችንን እስከሚገርመን ድረስ፤ ከዚህ ዘመን በፊት አንድም ታዋቂ የአለም መሪ ኢትዮጵያ መጥቶ እንደማያውቅ ተደርጎ ስለተነገረን – በቁጭት አይነት ያነሳነው ጉዳይ ነው።

የደቡብ አፍሪቃው ኔልሰን ማንዴላ ለአፍሪካ አንድነት ስብሰባ አዲስ አበባ ሲገቡ፤ በሽግግር መንግስቱ ወቅት ፕሬዘዳንት የነበሩት መለስ ዜናዊ ጃኬት አድርገው ያደረጉት አቀባበል ገርሞን ሳያበቃ፤ የአሁኖቹ ደግሞ ሙሉ ሱፍ ልብስ አድርገው ይበልጥ አሳቀቁን። የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሬሳ ቦሌ ሲገባ የተደረገለትን ያህል አቀባበል፤ ለፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ማድረግ ተስኗቸው፤ እንደገመሬ ያለስርአት ሲግበሰበሱ አይተን ተገረምነ። እንደው… ‘ወደፊት ገና ብዙ የምንሸማቀቅበት ጉዳይ ይኖራል’ ብለን በማሰብ፤ ‘የባሰ አታምጣ’ ብለን በመጸለይ፤ ሃፍረታችንን ዋጥ አድርገን ትዕይንቱን ያለቁጥር መቁጠር ቀጠልን።

የሚገርመው ግን… ይሄን ሃፍረት የተመለከተ አምላክ አሳፍሮ አላሳፈረንም። ለአቀባበል በሚመስል መልኩ… በአዲስ አበባ ላይ ትልቅ ቀስተ ደመና ታየ። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ታላቅ አቀባበል ያደረገላቸውን ቀስተ ደመና ለማስታወስ ይመስላል። የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን፤ “Here is the land where the first harmony in the rainbow was born…” በማለት በእራት ግብዣ ንግግራቸው ላይ ታዳሚውን አስጨብጭበዋል።

ከጭብጨባው ወጥተን ወደ ከተማው ከሄድን ደግሞ ብዙ ሹክሹክታ አለ። የቱን ይዘን የቱን እንደምንተው ግራ ይገባናል። “የብአዴን ሰዎች ለምን የሉም?” የሚሉ ሰዎች አሉ። በረከት ስምኦን ኦባማን እንደማይቀበል ሲያውቅ ወዲያው ነው የታመመው አሉ፡) “ግን እነአዲሱ ለገሰ? ተፈራ ዋልዋ? ከኦህዴድ የተጠራ ማንም የለም እንዴ? አባ ዱላ፣ ኩማ ደመቅሳ የታል? ከህወሃት ሰዎች እነአሞራ አልተጠሩም? የመለስ ሚስት የት ገባች? እነብሃት ነጋ? ስዩም መስፍን?” ይሄ ሁሉ ጥያቄ የውስጥ ለውስጥ ሹክሹክታ ነው። ከነዚህም ሰዎች አልፎ፤ በትክክለኛው ፕሮቶኮል መሰረት፤ “ፕሬዘዳንትን የሚቀበለው ፕሬዘዳንት ነው” ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ። ሃሳባቸውን ለአንድ ደቂቃ እንጋራና፤ “እውነት ግን… ለመሆኑ የኢትዮጵያው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የት ናቸው?” ማለታችን አይቀረም። (እንደ’እውነቱ ከሆነ… ብዙ ኢትዮጵያውያን ፕሬዘዳንቱን ቀርቶ፤ የፕሬዘዳንቱን ሙሉ ስም አያውቁም።)

በህገ መንግስቱ አንቀጽ 71 የፕሬዘዳንቱ ሚና ውሱን ቢሆንም፤ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ቢያንስ እንግዳ ለመቀበል የሚያንስ ትከሻ እንደሌላቸው ይታወቃል። እናም አንዳንዶች ‘ፕሬዘዳንቱ ቢያንስ ቦሌ ሄደው ባራክ ኦባማን ሊቀበሉ ይችላሉ’ ብለው አስበው ሊሆን ይችላል… ቦሌ ላይ ሲያጧቸው ደግሞ ‘ብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል ያደርጉላቸዋል’… ብለውም አስበዋል። ሁለቱም ግን አልሆነም። ህገ መንግስቱ እንደማይከበር ብናውቅም፤’ ፕሬዘዳንቱን በእድሜ እንኳን አክብረው ለዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ትንሽ ሚና ይሰጧቸው ይሆናል’ ብለን ብናስብም… ሰውየው የውሃ ሽታ ሆነው ቀሩ። ከዚያው ጋር ግን አንድ ቀልድ ሰማነ። ነገሩ እንዲህ ነው።

ፕሬዘዳንት ኦባማ አዲስ አበባ ከመግባታቸው በፊት የብሄራዊ ቤተ መንግስት በር ተንኳኳ። ፕሬዘዳንት ሙላቱ ተሾመ ጋቢያቸውን እንዳደረጉ፤ ‘ምን መጣ?’ ብለው በሩን ሲከፍቱ፤ ከአሜሪካ ኢምባሲ ከተላኩ ሰዎች ጋር ይፋጠጣሉ።
“ምን ልታዘዝ?” ፕሬዘዳንቱ ናቸው።
“ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ሲመጡ፤ ስለአቀባበላቸው ለመነጋገር ነበር።” አሜሪካኖች ይመልሳሉ።
“ታዲያ እኔ ምን አውቃለሁ? ሰዎቹን አናግሯቸው እንጂ።” ይላሉ ፕሬዘዳንት ተሾመ።
“እርስዎ በዚህ ጉዳይ መነጋገር አይችሉም?” አሜሪካኖቹ ገርሟቸው ጠየቁ።
“እኔ ቤት ጠብቅ ተብዬ ነው። አሁን ሰዎቹ የሉም።” ብለው በሩን ዘጉባቸው – አሉ።

የ’ነዚህ ሰዎች ነገር… አንዳንዱ ድርጊታቸው ቢያስቅም፤ ኢትዮጵያን ወክለው የሚያደርጉት ተግባር ግን እያሳቀቀን ነው።
የሆነው ሁሉ ሆኖ ግን በአንድ ነገር እንጽናናለን። ልብ በሉ። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ኢህአዴግ ለ17 አመታት አደረኩት ስላለው የጀብድ ትግል አላወሩም። ነገር ግን 130 አመታት ወደ ኋላ ተመልሰው፤ አጼ ምኒልክ አድዋ ላይ ያደረጉትን ድል አወደሱ። አጼ ምኒልክን የሚጠሉ ሰዎች አንገታቸውን ሊደፉ ይችሉ ይሆናል። ፕሬዘዳንቱ ግን… ደግመው ደጋግመው የኢትዮጵያውያንን ተጋድሎ ሲተርኩ፤ የምኒልክ ዘመን ሰዎችን ገድል ነው – የነገሩን። ሌላው ቀርቶ በአፍሪቃ ህብረት ንግግራቸው ላይ… በአፍሪቃ የሚገኙ አምስት ዲሞክራቲክ አገሮች ብለው፤ እነናይጄርያን፣ ጋና፣ ታንዛንያ የመሳሰሉትን አገሮች በምሳሌነት ሲጠቅሱ ኢትዮጵያ በዝርዝሩ ውስጥ የለችበትም። ይሄ ለነአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዱብ’ዳ መሆን አለበት።
እንዲህም ሆኖ ግን… ኢህአዴግ መራሽ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች አሁንም “ለፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።” ሲሉ ‘የት? መቼ?’ ማለታችን አይቀረም። የቦሌው ሲገርመን… በንጋታው በብሄራዊ ቤተ መንግስት ሲደርሱ፤ በጃንሆይ ግዜ አሎን ሲነጠፍ የምናውቀውን ምንጣፍ ውጪ አውጥተው ዘረጉት። ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፈውን ኢሳት እና ሌሎች ድረ ገጾች ለማፈን በቀን ብዙ ሚልዮን ዶላር የሚያባክን አምባገነን መንግስት በDust mite የነተበ ምንጣፍ ለባራክ ኦባማ ክብር ዘረጋላቸው። በጣም የሚያስቀውና የሚያሳቅቀው ደግሞ “Welcome” የምትል፤ ከWal Mart በ$3.99 ገዝተን ውጪ የምናቀምጣት አይነት፤ መናኛ እግር መጥረጊያ ተደረገላቸው። ከዚያም ለ20 ሰከንድ ያህል የቆየው የማርሽ ሙዚቃ አስደመመን። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማም… እንደ”አሳ በለው በለው” ዳንስ አራት መአዘን ሆኖ በተነጠፈ ምንጣፍ ላይ፤ ሲሽከረከሩ፤ ‘ነገሩ የህጻን ጨዋታ ነው እንዴ?’ አልነ። በዚያ ላይ ከዳይኖሰር አፍ የወደቁ ፓስታ የሚመስሉ ቀጫጭን ሰዎች ተሰልፈው ስናይ፤ የድሮ ት/ቤታችንን ባንድ አመሰገንን። ካልሲያቸውን ሱሪያቸው ላይ ገድግደው፤ ወይም ገምባሌያቸውን በሱሪያቸው ላይ ለብሰው ቆመው ስናይ፤ “የቤተ መንግስቱ የክብር ዘቦች እነዚህ ናቸው?” ብለን ተገረምን።
ሌላ ትዝብት እንጨምር። ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ከአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተሻለ እንግሊዘኛ ቢችሉም፤ አሜሪካም ሆነ የተባበሩት መንግስታት ፊት በአገራቸው ቋንቋ ነበር የሚያወሩት። ይቺን ጫፍ ይዘን ወደ ጋዜጣዊ መግለጫው እናምራ። “ፕሬዘዳንት ኦባማ – ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ።” ከዚያ በኋላ… አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንግሊዘኛውን እያነበቡ ሳለ፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ደግሞ ትርጉሙን ባማርኛ ያስነብበን ጀመር። የሚገርመው ታድያ አቶ ኃይለማርያም በእንግሊዘኛ የሚሉት እና ባማርኛ ተተርጉሞ የሚጻፈው አረፍተ ነገር ፈጽሞ የሚገናኝ አልነበረም። ይሄ ገርሞን ቀና ስንል ደግሞ፤ ኦባማ ማናገሪያ ላይ ኮከቧን ለጥፈዋታል። “ይሁን” ብለን ስናልፈው ደግሞ የማይታለፍ ነገር ገጠመን። ከሁለቱ ሰዎች ጀርባ አይናችንን የሚስብ ነገር አየነ። የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ባንዲራ በስቴፕለር ሽቦ አንድ ላይ ተሰፍተዋል። የኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ ሲንከረፈፍ አልታይ እያለ የሚያስቸግረውን፤ አምባሻ መሰል ሰማያዊ ኮከብ ለማሳየት ሲሉ፤ እንደሰፈር ልጆች… የኢትዮጵያን ባንዲራ በግድ ወደ ጎን ወጥረው ከአሜሪካ ባንዲራ ጋር ሰፍተውት ብንመለከት፤ መግለጫውን በደንብ ሳናጣጥመው አለቀ። በኋላ ላይ እንደሰማነው ግን፤ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ አንዳንድ ቁም ነገሮችን ተናግረዋል – አሉ። በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ አለመኖሩን በዘወርዋራ፤ በኤርትራ በኩል ዘልቀው የሚዋጉት አርበኞችም አሸባሪዎች አለመሆናቸውን በቀጥታ ማሳወቃቸውን ሰማነ።
ከዚያ በኋላ፤ “ፕሬዘዳንት ኦባማ ቡና ጠጡ። እስክስታ መቱ።” ይሄ ሁሉ እልል ሊያስብል ይችል ይሆናል።
እንግዲህ ሁሉም ነገር አበቃ። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ጽዋቸውን ሲያነሱ፤ ‘የኛ ሰውዬ’ ደግሞ እጃቸውን ዘረጉ። ከዚህ በኋላ ያለውን ታሪክ ለመጻፍ፤ የታሪክ መዝገቡ ክፍት ሆኖ እየጠበቀን ነው። እዚህ መዝገብ ላይ፤ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኘው ሃይል በአዲስ ምዕራፍ… የራሱን ታሪክ ጽፎ ማለፍ አለበት።

ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ያመኑበትን ጉብኝት አድርገዋል። ያላመኑበት ነገር ደግሞ አለ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ሰብአዊ መብት እንደማይከበር ገብቷቸዋል። የፕሬስ ነጻነት እንዲከበር አበክረው ገልጸዋል። ይህ አቋማቸው አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በመነባረቁ ነበር፤ ከሳቸው ጉብኝት በፊት የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች በከፊል እንዲፈቱ የተደረገው። በአፍሪቃ አንድነት አዳራሽ ውስጥ፤ “ምርጫ ማድረግ ማለት፤ ዲሞክራሲያዊ አያሰኝም።” ሲሉ በአዳራሹ ከላይ የተቀመጡት ሰዎች በጭብጨባ እና በሆታ ሃሳቡን ተቀበሉት። በነገራቹህ ላይ እነዚህ ሰዎች ብዙዎቹ፤ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ናቸው። ደሞዝ የሚከፍላቸውን መንግስት ቢወክሉም፤ የኢህአዴግ መንገድ ትክክል ስላልሆነ ነው – “ምርጫ ማድረግ ማለት፤ ዲሞክራሲያዊ አያሰኝም።” ሲባል፤ ሆ ብለው በደስታ የጮሁትም እነሱ ነበሩ። (አሸባሪ ተብሎ ከመከሰስ ያድናቹህ)

ፕሬዘዳንት ኦባማ በሌሎች አገሮች ጉብኝት ሲያደርጉ፤ ለመሪዎቹ የሚሰጡትን አክብሮት እርግፍ አድርገው በመተው፤ አምስት ካሏቸው ዲሞክራቲክ አገሮች ውጪ የኢትዮጵያን መሪዎች ጨምሮ ሙልጭ አድርገው ነው የነገሯቸው። መሪዎች በስልጣን ላይ የመቆየታቸውን በሽታ አስመልክቶ ትዝብታቸውን ከገለጹ በኋላ… ከአፍሪቃ ኔልሰን ማንዴላን፤ ከአሜሪካ አብርሃም ሊንከንን እንደጥሩ ምሳሌ አድርገው አቅርበዋል። ስልጣን ላይ የሚቆዩትን የአፍሪካ መሪዎች አምርረው ወቅሰዋል። የፕሬስ ነጻነትን ቀጫጫነት፣ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ኢትዮጵያ ውስጥ በበቂ መጠን እንዳልጎለበተ አምነዋል። የኤርትራን ድንበር አቋርጠው ለነጻነት የሚታገሉ አርበኞች አሸባሪዎች አለመሆናቸውን በቃላቸው መስክረዋል። ይህንን የበለጠ ማጉላት ያስፈልጋል።

ፕሬዘዳንት ኦባማ ከአፍሪቃ መልስ ኋይት ሃውስ ከገቡ በኋላ፤ “Shame on you” ከማለት ይልቅ (ብዙም ደስ የማይል ቃል ነው)፤ መልካም ጅምራቸውን አድንቆ፣ እውነቱን በመመስከራቸው አመስግኖ፤ ንግግራቸውን የሚያጠናክር ተጨባጭ መረጃ ማቀበል ያስፈልጋል። ያለበቂ ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎች እና የፖለቲካ እስረኞች ሊፈቱ፤ ንብረታቸውም ሊመለስላቸው እንደሚገባ፤ ደግመን ደጋግመን ለአሜሪካ መንግስት መግለጽ አስፈላጊ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ሚዲያ – የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት ጉብኝትን አመልክተው ብዙ ብለዋል። ብዙ የተባለው በሙሉ ግን፤ ለፖለቲካ ፍጆታ ያህል ጥቅም ላይ የዋለ ነው። የዚያኑ ያህል የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ቆይታ፤ በአሜሪካ ትላልቅ ሚዲያ ምንም አልተባለለትም – ማለት ይቻላል። ይህ ምን እንደሚያሳይ ግልጽ ነው። ከዚህ በመነሳት ወደ ቀጣዩ የታሪክ ምዕራፍ ራሳችንን ማሸጋገር ይኖርብናል።

በመጨረሻም ስንበት። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ በተደረገላቸው የእራት ግብዣ ላይ፤ የኢትዮጵያዊነት መአዛ ያለውን የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን አንቀፀ-ቃል ትንሽ አቃምሰው ነበር። ፕሬዘዳንቱ ሙሉውን አላሉትም። ሙሉው አንቀፀ-ቃል ከዚህ የሚከተለው ነው።

“Here is the land where the first harmony in the rainbow was born. We walk on the bed rock of our planet’s first continent. Here is the root of the Genesis of Life; the human family was first planted here by the evolutionary hand of Time….We walk on the footprints of the evolutionary ancestors of Man.” ፕሬዘዳንቱ ይህን ብለው ሲያበቁ፤ እኛም ጽዋችንን በቀኝ እጃችን አንስተን፤ “እነሆ በረከት” እንኳን ደህና ወጡ – ብለናቸዋል – ፕሬዘዳንታችንን።

የፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን የኢትዮጵያ ቆይታ በወፍ በረር ቃኝተናል። ጉብኝታቸውም ተጠንቆ ተሸኝተዋል። እኛንም ሸኙን። እነሆ ለስንብት “አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ” ብለን ጽዋችንን አንስተናል። በያላችሁበት አሜን በሉ።


ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር በአየር ባየር ንግድ እጅና ጓንት ሆኖ የሚሰራው ሃጎስ ወ/ገሪማ ተገደለ

$
0
0

Zehabesha News
የህወሓት ቀኝ እጅ የሆኑ ባለ ሃብቶች በስውር እተገደሉ መሆናቸው ታወቀ፡፡ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሕዝብ ግንኙነት ባሰራጨው ዜና የመለስ ዜናዊ የቅርብ ሰው የሆነ እና ከአዜብ መስፍን ጋር በአየር ባየር ንግድ እጅና ጓንት ሆኖ ይሰራ የነበረው ሀጎስ ወ/ገሪማ የተባለው የናጠጠ ቱጃር ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገድሏል፡፡

ሀጎስ ወ/ገሪማ የህወሓት ታጋይ የነበረ ህወሓት በዘመኑ ከፈጠራቸው የናጠጡ ቱጃሮች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን ሀምሌ 13 207 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡45 ላይ አ.አ ኮድ 2 ሰሌዳ ቁጥር 03220 የሆነች ውሃ ሰማያዊ ላንድ ክሩዘር መኪና በማሽከርከር ላይ እንዳለ አዲስ አበባ መስቀል ፍላወር አካባቢ ተገድሏል፡፡

ሀጎስ ወ/ገሪማ ከሳሞራ እና ከሌሎች የህወሓት ጀነራሎች ጋር ጥብቅ የሆነ ቁርኝት ያለው የንግድ ድርጅቶቻቸውን እንቅስቃሴ የሚያቀላጥፍ ነበር፡፡

በተጨማሪም ከትግራይ ወደ ሳንጃ በመሄድ በከፍተኛ ንግድና የእርሻ ልማት የተሰማራ አማረ የተባለ የህወሓት ባለ ሀብት በአካባቢው ሚሊሻዎች በጥይት ተደብድቦ ተገድሏል ሲል የአርበኞች ግንቦት 7 ዘገባ ያመለክታል::

ከ40 በላይ የሚሆኑ የአየር ኃይል አባላት ስርዓቱን ከድተው አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ

$
0
0
Photo File

Photo File

አርበኞች ግንቦት 7 እንደገለጸው በህወሓት አገዛዝ ስር የሚገኘው አየር ኃይል ከዚህቀደም የተንሰራፋው ዘረኝነት፣ ገደብ የሌለው ዘረፋ እና አስተዳደራዊ ግፍና በደል ያንገሸገሻቸው በርካታ አባላቱ ተዋጊ ጀቶችን እና ተዋጊ ሄሊኮፕተሮችን እየያዙ በተደጋጋሚ መክዳታቸው ይታወቃል፡፡ በአየር ኃይሉ ውስጥ የአባላት ኩብለላ ከምድር ኃይሉ በከፋ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ ከ40 በላይ የሚሆኑ ሞያተኛ አባላቱ ባንድ ጊዜ ከየምድቦቻቸው ተሰውረዋል፡፡

ስርዓቱን ከከዱት 40 ሞያተኛ የሆኑ የአየር ኃይሉ አባላት ውስጥ አብራሪዎች፣ ቴክኒሻኖች፣ የኮማንድ ፖስት እና የጠቅላይ መምሪያው ሰራተኞች ይገኙበታል፡፡ ቴክኒሻኖች ቁጥራቸው 15 ሲሆን ምድቦቻቸው ትራንስፖርት ሄሊኮፕተር ስኳድሮን፣ ሱ 27 ስኳድሮን እና አንቶኖቭ 12 ነበሩ፡፡

ከአየር ኃይል በየጊዜው ከሚከዱት ሞያተኞች ውስጥ የኤም.አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ስኳድሮን አዛዥ ሻለቃ አክሊሉ መዘነን ጨምሮ አብዛኞቹ ወደ በረሃ ወርደው አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቅለዋል፡፡

ወያኔዎች የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ለምን ያስጨንቃቸዋል?

$
0
0

ሽብሬ ደሳለኝ

ባለፉት 24 ዓመታት ወያኔዎች በሃገር ውስጥ (በሰላማዊ መንገድ) ለውጥ ለማምጣት የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካ ድርጅቶች እና ፖለቲከኞች ከማዳከም አልፈው በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት ተጽኖ መፍጠር እንዳይችሉ አድርገዋቸዋል።

andargachew

አብዛኛዎቹ ፖለቲከኞች የወያኔ አፈና ሲበረታ ከማምረር ይልቅ ፖለቲካውን እርግፍ አድርገው ይተውታል ወይንም ደግሞ ስደት ይወጡና ቀደም ሲል የተሰደደውን የኢትዮጵያ ስደተኛ ተቀላቅለው እንደ አብዛኛው ስደተኛ ቤተሰቦቻቸውን እና እራሳቸውን በኢኮኖሚ የማሻሻል ተግባር ላይ አተኩረው ይቀራሉ። ይህ እየተለመደ የመጣ አካሄድ ወያኔዎቹን ተመችቷቸው ኖረዋል፣ እነ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የጨዋታውን ህግ እስከቀየሩት ድረስ።

በርግጥም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ጓዶቹ ወደ ፖለቲካው ሜዳ ያመጡት አዲስ የጫወታ ህግ ሰርቷል!

ወያኔ አዲሱን የጨዋታ ህግ ከጅምሩ አልወደደውም፣ ከሚቆጣጠረው ግዛት ውጪ የሚደረጉ የለውጥ እንቅስቃሴዎች ኋይት ሃውስ ፊት ለፊት ሻማ ከማብራት ያለፉ እንዳይሆኑ ምኞቱ ነበር። ይህ አልሆነም።

አቶ አንዳርጋቸው እና ጓዶቹ ኢትዮጵያውያን የአሜሪካን ወይንም የእንግሊዝን መንግስት በመለመን ነጻነታቸውን እንደማይቀናጁ ይልቁንም ብረት አንስተው ወያኔን በሚገባው ቋንቋ የማነጋገር አስፈላጊነትን አስተማሩ፣ ወተወቱ፣ የመውጪያ መግቢያ ቀዳዳዎችንም አመላከቱ… ኤርትራ!
andargachew
ወያኔ በሃገር ውስጥ (በሰላማዊ መንገድ) የሚደረጉ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን ሲያዳፍን፣ ለውጥ ፈላጊው ትውልድ የሃይል አማራጮችን እንደሚያማትር አልጠፋውም፣ ወያኔዎች የለውጥ ፈላጊው ትውልድ የሃይል አማራጮችን በስራ ላይ ለማዋል ተባባሪ/ፈቃደኛ የጎረቤት ሃገሮች እንደሚያስፈልጉት ቀደም ብሎ መተንበዩ አልቀረም (ወያኔ ከደርግ መንግስት ጋር ባደረገው የሃይል ትግል ወቅት ሱዳን እና ሶማሊያ ዋንኞቹ መጠለያው ነበሩ)። ከሃገር ጥቅም ይልቅ ለመንበረ ስልጣኑ ቅድሚያ የሚሰጠው ወያኔ ለኢትዮጵያ አጎራባች ሃገሮች ሁሉ የሚጠይቁትን እየሰጠ (ለምሳሌ ሱዳን ከሃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ ይገባኛል የምትለውን የኢትዮጵያ መሬት ከወያኔ ተቀብላለች) በምላሹም ተቃዋሚዎቹን እንዳያስጠልሉ፣ አልፎ ተርፎም ተቃዋሚዎቹን እያደኑ እንዲያስተላልፉለት አግባባቸው። ይሁንና ይህ አካሄድ በጎረቤት ኤርትራ ሊሰራለት አልቻለም።

አንዳርጋቸው ጽጌ እና ጓዶቹ አውርተው አልቀሩም፣ ከኤርትራ መንግስት ጋር የተሳካ ግንኙነት ፈጠሩ፣ ጦርም ማደራጀት ቻሉ፣ ቀደም ሲል ጀምሮ በኤርትራ መሬት ይንቀሳቀሱ በነበሩት ሃይሎች መካከልም መልካም እና መተማመን የሰፈነበት ግንኙነት እንዲኖር አስቻሉ።

ወያኔ ከሚቆጣጠረው ግዛት ውጪ የሚደረገው የለውጥ እንቅስቃሴ እየበረታ መሄዱን በመገንዘብ እንቅስቃሴውን በእንጭጩ ለማስቀረት መንቀሳቀሱ አልቀረም፣ ይህንን ወያኔን እንቅልፍ የነሳ እንቅስቃሴ ወደ ተግባራዊነት እየቀየሩ ባሉት የግንቦት 7 አመራሮች ላይ አነጣጥሮ በተገዙና የተቃዋሚ ካባ በደረቡ ግለሰቦች አማካኝነት አመራሮቹን ከህዝብ ለመነጠል ከፍተኛ ሙከራ ቢያደርግም ውጤቱ አመርቂ አልሆነም። ወያኔ ከዚህ በኋላ ነበር አማተር ሰላዮቹን ወደ ኤርትራ በመላክ አርበኛውን አንዳርጋቸው ጽጌን ለመግደል ሙከራ ያደረገው ይህም አልተሳካም እንደውም ከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ደረሰበት (ብዙዎች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጠንቅቀው የማያውቁት ሳይቀሩ የአንዳርጋቸውን ማንነት ለመገንዘብ ቻሉ)።

ወያኔ በመጨረሻ ያደረገው ሙከራ ተሳክቶለት አቶ አንዳርጋቸውን ከየመን አፍኖ ወደ አዲስ አበባ መውሰድ ቻለ።

ለጊዜው ወያኔዎች ከፍተኛ የድል አድራጊነት ሰሜት ተሰምቷቸው ጮቤ ረገጡ ይሁንና ብዙም ሳይቆይ ደስታቸው እንደጉም በኖ እስካሁን በሚያቃዣቸው ስጋት ውስጥ እንዲዘፈቁ ሆነ። ጀግናቸው (አንዳርጋቸው ጽጌ) በወያኔ እጅ መውደቁን የሰሙ ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከጫፍ ተነቃነቁ፣ አንዳርጋቸው የጀመረውን የትግል ጉዞ ከግብ ለማድረስም ቁርጠኝነትቸውን አሳዩ፣ የአንዳርጋቸው ቤተሰቦች ሴት ከወንድ ሳይባል በአንዳርጋቸው ጽጌ እግር ተተክተው አንዳርጋቸው ያቀጣጠለውን ችቦ ተረከቡ።

የግንቦት 7 ንቅናቄ አመራሮችና የአንዳርጋቸው የትግል ጓዶች ዙሩን አከረሩት፣ በተደጋጋሚ ከወያኔ ጋር ባካሄዳቸው የሽምቅ ውጊያዎች ልምድ ካካበተውና የሰሜኑን የኢትዮጵያ ግዛቶች መግቢያ መውጫ ጠንቅቆ ከሚያውቀው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ጋር ውህደትን ፈጠሩ፣ በውጤቱም አርበኞች ግንቦት 7 ተወለደ።

በለስ ቀንቷቸው አቶ አንዳርጋቸውን በእጃቸው ያስገቡት ወያኔዎች ከሚቆጣጠሩት ግዛት ውጪ እየተካሄ ያለው እንቅስቃሴ በአንዳርጋቸው መያዝ ምክንያት መባባሱን ተረድተዋል። የእንቅስቃሴውን ፍጥነት ለመግታት በቁጥጥራቸው ስር ያለውን አንዳርጋቸው ጽጌን ለመጠቀም በማሰብ እየቆረጡ እና እየቀጠሉ የሚለቋቸው የአዳርጋቸው ጽጌ ቪዲዮዎች ምንም ውጤት አላመጡም፣ ይልቁንም በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ከፍተኛ ቁጭትን እየጫሩ አንዳርጋቸው ጽጌ የጀመረውን ትግል ከግብ ለማድረስ ቃላቸውን እንዲያድሱ አድርጓቸዋል።

ለዚህም ይመስላል አንዳርጋቸው ጽጌን የስፖርት ቱታ በማልበስ ሰው በሌለበት ጎዳና ላይ ፎቶ አንስተው “ተመልከቱ እባካችሁ አንዳርጋቸው ሰላም ነው” በማለት ኢትዮጵያውያኑን ለማረጋጋት የሞከሩት።

አርበኞች ግንቦት 7 ጥቃት መፈጸም ከጀመረና ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኤርትራ ገብቶ በአንዳርጋቸው እግር መተካቱ ከተሰማ በኋላ ደግሞ ወያኔዎች የአንዳርጋቸው ጉዳይ ፍም እሳት ሆኖባቸው የሚያደርጉትን አሳጥቷቸዋል፣ ለዚህም ምልክቱ ቴድሮስ አድሃኖም በቪኦኤ ላይ የተናገረው ነው “አንዳርጋቸው ላፕ ቶፕ ተሰጥቶት መጽሃፍ ጽፎ ጨርሷል፣ አንዳርጋቸው የሃገሪቱን ልማት ማየት ፈልጎ እያዟዟርን አሳይተነዋል ወዘተ…”

እውነታው ግን አንዳርጋቸው ጽጌን የት እንዳሰሩት አይናገሩም፣ አንዳርጋቸውን ቤተሰብም ሆነ ማንኛውም ሰው አይጎበኘውም። በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ወያኔዎች በአንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የሚያውቁትን የማሰቃያ መንገዶች ሁሉ በመጠቀም አንዳርጋቸው እነርሱ የሚፈልጉትን አይነት መልእት እንዲያስተላልፍ ለማድረግ እየሞከሩ ነው። ይሁንና ጀግናው አንዳርጋቸው ጽጌ እስካሁን የሚፈልጉትን አልሰጣቸውም (ይህንንም ለማረጋገጥ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ስቃይ እየፈጸሙ ቀርጸው የሚያሰራጯቸውን ቪዲዮዎችን መመልከት ይበቃል)።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአካል ተገኝቶ ትግሉን መምራት ባይችልም መንፈሱ ግን ትግሉን በማቀጣጠል ላይ ይገኛል። እንግዲህ ወያኔዎች የአንዳርጋቸው ጽጌን ለመቆጣጠር ነው ቁጭ ብድግ በመስራት ላይ ያሉት፣ ይሳካላቸው ይሆን? ወደፊት አብረን የምናየው ይሆናል።

“ዘፈኑን እየተውኩ ወደ ዝማሬው ዓለም እየገባሁ ነው”–ድምፃዊት(ዘማሪት) ዘሪቱ ጌታሁን [ቃለ-ምልልስ]

$
0
0

ዘሪቱ ከበደ ዘፈን አቁማለች ወይንስ አላቆመችም የሚሉ አናጋጋሪ ጉዳዮች በርካታ ጊዜያት ሲነሱ ቆይተዋል፡፡ ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ ከእርሷ አንደበት ይህ ነው የሚባል ቁርጥ ያለ ምላሽ ሳይሰጥበት በመቆየቱ በበርካቶች ዘንድ አከራካሪ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ዘሪቱ በየወሩ በአማርኛ ቋንቋ ታትሞ ለገበያ በሚበቃው ሪቪል (REVEAL)መፅሄት ባደረገችው ቃለ ምልልስ ከዘፈኑ አለም በመውጣት መንፈሳዊ ጉዞ ላይ መሆኗን አስታውቃለች፡፡ መፅሄቱ ከቀረበላት ጥያቄዎች መካከል ዋና ዋናዎች አለፍ አለፍ ብይ በመቃኘት ላስነብባችሁ፡፡
zeritu
☞ሪቪል፡ ከመንፈሳዊነት ጋር ተያይዞ መዝፈን አቁመሻል?
☞ዘሪቱ፡ መንፈሳዊነት ሁለገብና የሁለንተናችን ለውጥ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ደግሞ ከአለማዊነት ስንወጣ የማይነካ የህይወታችን ክፍል የለም፡፡ ሁሉም ነገር እኔ እንደምለውና ዓለም እንደምትሰብከው ሳይሆን እግዚአብሄር እንደሚለው የማድረግና የመሆን ሂደት ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ታዲያ እንደ ሁሉ ነገሬ የጥበብ ስራየም ሳይፈተሸ አያልፍም፡፡ ስለዚህ ሙዚቃም ይሁን ፊልም፤ ብቻ ምንም ነገር ልስራ የማደርገው ነገር እግዚአብሄር የሚፈልገውን መለዕክት ያደርሳል ወይ? ሰዎችን ይጠቅማል ወይ? ደሞስ እንደሱ ፍቃድና ልክ ሰዎችን ያሳዝናል? ያስደስታል ወይ ብዪ በመጠየቅና ይልቁንም ከሱ ከራሱ መለዕክትን በመቀበል ወደ መስራት መንፈሳዊነት እያደኩ ነው፡፡ መዝፈን ይሁን መዘመር አላውቅም፡፡ የማውቀው እግዚአብሄር እንደሚከብርበት ነው፡፡

☞ሪቪል፡ ብዙዎች ግን “ዘሪቱ ወይ ትዘምር ወይ ትዝፈን መቁረጥ አቅጧት እየወላወለች ነው” ይላሉ፡፡ በእርግጥ እየወላወልሽ ነው?

☞ዘሪቱ፡ እየሱስ ክርስቶስን ተከትያለሁ ብዪ በማምንባቸው ዓመታት ውስጥ በአካሄዴ ሁሉ እግዚአብሄርን ደስ አሰኝቻለሁ ብዪ አላስብም፡፡ ምንአልባትም በአንዳንድ የህይወቶቼ ክፍሎች እግዚአብሄርን አይፈሩም ተብለው ከሚታሰቡት ሰዎች እንኳን ብሼ አውቃለሁ፡፡ እንደእግዚአብሄር ምህረትና እንደ አባትነቱ ፍቅር ባይሆን ኖር ዛሬ ያለሁበት ቦታ አልገኝም ነበር፡፡ሰ አድርጌ የማላውቅ ግን መወላወል ነው፡፡ ፈርቼ አውቃለሁ፤ ግራ ገብቶኝም ያውቃል፤ ፈርሶ ሲሰራ እንደሰነበተ ሰው ደግሞ በሁሉም ነገር እርግጠኛ ሆኜ ሀሳቤን ሳለውጥ መጥቻለሁም ብዪ ለመናገርም አልደፍርም፡፡ ወላውዪ ግን አላውቅም፡፡

ዘሪቱ ሙዚቃ አቁማለች ብሎ ሚዲያ ጭምር ሲዘግብ ፤ እኔን ጠይቆና አነጋገግሮ አይደለም፡፡ መንፈሳዊ ከሆነች መቆሟ አይቀርም ብለው በራሳቸው በመደምደም ነው፡፡ እኔ ህይወቴን ስቀጥልና ከተነገሩት ዜናዎች በተቃራኒ የሙዚቃስራዎች ወደ አድማጭ ሲደርሱ የወላወልኩ የሚያስመስል መልክ ሊያሰጠኝ ችሏል፡፡
☞ሪቪል፡ ግን ዝናና ገንዘብን መስዋትነት ማድረግ የሚከብድ አይደለም?

☞ዘሪቱ፡ እኔ ለመተው የሚከብድ የገንዘብ ክምችት የለኝም፡፡ዝናንም በተመለከተ ዘማሪዎች ከዘፋኞች ባልተናነሰ ዝነኞች የሆኑበት ዘመን እንደሆነ ነው የማስበው፡፡ ከዝና ወደ ዝና ብሸጋገር አሁን ከምከፍለው ዋጋ የበለጠ እንደምከፍል አውቃለሁ፡፡

☞ሪቪል፡ ቤት መኪናና ሌሎች አያስፈልጉም ብለሽ ነው የምታምኚው?
☞ዘሪቱ፤ እኔ የማምነው ከሆነ ቦታ ተነስተህ የሆነ ቦታ ለመድረስ ትራንሰፖርት እንደሚያስፈልግ ነው፡፡ መኪናው ያንተ ከሆ ጥሩ፤ ካልሆነም መኖርህን ለማታውቅበት ለዛሬ ባለቤትነትህ ያለው ፋይዳ ውስን ነው፡፡ የቤትም አስፈላጊነት መጠለያነቱ፤ትርጉሙም አብረውህ በሚኖሩት ሰዎች እንጂ በባለቤተረነት ካርታው አይደለም፡፡ የባለቤተረነት ዋስትና ለእኔ ትርጉም የለሽ ነው፡፡እግዚአብሄር ወዶ ለሚጨምርልኝ ለእያንዳንዱ ቀን የሚያስፈልገኝን ሁሉ እንደሚያዘጋጅልኝ አምናለሁ፡፡
☞ሪቪል፤ እንደዚህ ያለ ህወት ግን ላገባችና በተለይም ልጆች እናት ለሆነች ሴት አይከብድም?

☞ዘሪቱ፤ እንደዚህ ያለ ህይወት ለማንም ቀላል አይደለም፡፡ በተለይም እንዳልከው፤ቤተሰብ ላለን ሰዎች ደግሞ የማይታሰብ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ በስጋዊ አቅማችን ስንሞክረው ነው፡፡ ሰው የመሆንን ትርጉም ለመረዳት በፈቀድን መጠን ግን ራሱ እግዚአብሄር በእና ውስጥ ይችለዋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ማለት፤ ሰው በሀጢያት ከመውደቁ በፊት ወደ ነበረው ማንነት የመመለስ ጉዞ ማለት ነው፡፡ ያ ማንነት ደግሞ ከእግዚአብሄር የመሆንና ማንነቱን የማንፀባረቅ ህይወት ነው፡፡ በመሬታዊ ገደብ እሱን ማንፀባረቅ አይቻልም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አሰልጣኝነት ከመሬታዊ ገደብ ወደ እሱ ማንነት የሚያሻግረን መመሪያ ሁሉ ደሞ በቅዱስ ቃሉ ወስጥ አለ፡፡ ኢየሱስ ለምን አይነት ክብር እንደጠራን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ከንግዳችን፣ ከቤተሰባችንና ከራሳችን ጭምር በላይ እሱን እንድናስቀድም ነው፡፡ ይህ ሲሆን ብቻ ደቀመዛሙርቶቹ ልንሆን እንምንችል በግልፅ አስቀምጦልናል፡፡ ስለዚህ እሱን በመከተል ውስጥ ምንም አይነት አቋራጭ አልፈልግም፡፡
☞ሪቪል፤ ባለቤትሽ በዚህ ደስተኛ ነው?

☞ዘሪቱ፤ በጣም ደስተኛ ነው እንጂ፡፡ የምተገዛ ሚስት አድረጎለታል፡፡ ከዚህ ህይወት ጋር በተዋወኩባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በእኔ ላይ ባስከተለው የማንነት መናጋት ተከትለው በመጡ ጥፋቶች ብዙ ዋጋ ከፍሏል፡፡ ሚስትህ ፈርሳ እስክተሰራ መታገስ ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ከመጀመሪያዋ የተሻለች ሚስት እንዳለችው እሱ ምስክር ነው፡፡
ጌታ ይባርክሽ ዘሪቱ!!
@የእውነት ቃል

በኢትዮጵያ እውነትና ፍትህ ከትቢያ የተሻለ ቦታ ቢኖራቸው ኖሮ….   አንዷለም አራጌ

$
0
0

የእስረኛው ማስታወሻ

ውድ ኢትዮጵያውን፡-

Free Andualem ሕዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት በሆነበት ሃገር ፍትህ ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ትቀመጣለች፡፡ እውነትም ምሰሶና ወጋግራ ሆና ፍትህን ዘወትር የመደገፍ እድሏን ትጎናጸፋለች፡፡ በኢትዮጵያ የፍትህና የእውነትን የክብር ቦታና ሚና አፈ-ሙዝ ወስዶታል፡፡ ፍትህና እውነት ደግሞ ትቢያ ላይ ተጥለዋል – ምንም እንኳ እንደወደቁ ባይኖሩም፡፡

በኢትዮጵያ ፍትህና እውነት ትቢያ ላይ ባይጣሉ ኖሮ ለዓመታት ይቅርና ለሰዓታት እንኳን በእስር ቤት ግርጌ መጣል ባላስፈለገንም ነበር፡፡ ፍትህና እውነት በኢትዮጵያ አድራሻ ቢኖራቸው ኖሮ ለዚህ ዓለም እንግዳ የሆኑት ልጆቼ ለዓመታት ሳይሆን ለሰዓታት እንኳን የአባታቸውን ፍቅር በግፍ ባልተነጠቁ ነበር፡፡ ፍትህና እውነት የሰፈኑባት ኢትዮጵያ እውን ብትሆን ኖሮ ለዓመታት ሳይሆን ለሰዓታት እንኳን ባለቤቴ ከእኔ ጋር የመኖር ሰብዓዊ መብቷን ተገፋ በወጣትነት እድሜዋ የመበለትነት ህይወት የመግፋት እዳ ባልወደቀባት ነበር፡፡ ፍትህና እውነት በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እንኳን መንሳፈፍ ቢችሉ ኖሮ በሃሰት ዶሴ ከታሰርኩ በኋላም ለዓመታት በእስር ቤት ውስጥ ተጨማሪ የግፍ ፅዋ እንድንጎነጭ ግድ ባልሆነብኝም ነበር፡፡ በኢትዮጵያ እውነትና ፍትህ ከትቢያ የተሻለ ቦታ ቢኖራቸው ኖሮ ረጅም ርቀት አቆራርጠው ሊተይቁኝ የሚመጡ ጠያቂዎቼ የመጠየቅ መብታቸውን ለዓመታት ሳይሆን ለሰዓታት እንኳን ባልተነፈጉም ነበር፡፡

በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊቷ ኢትዮጵያ እኔና ቤተሰቤ ፍፁም ኢሰብዓዊ ከሆኑ ነገሮች ጋር ተላምደን፤ በሞትና በህይወት መካከል ያለው ልዩነት እስኪጠፋን ድረስ በአባቶቻችን፣ በራሳችንና በልጆቻችን ሃገር፤ በህዝባችን ፊት በማናለብኝነት ጥቂት አፄዎች ጢባጢቢ እንዲጫወቱብን ተበይኖብናል፡፡ በውል የማውቀውን የራሴን ጉዳይ በዋናነት ባነሳም የእኔና የቤተሰቦቼ ህይወት የእነ እስክንድር ነጋንና ሌሎች አንባቢ ፈፅሞ የማይዘነጋቸው ኢትዮጵያውያንና ቤተሰቦቻቸውም ፅዋ መሆኑን ፈፅሞ ዘንግቼው አይደለም፡፡ በየትም ቢሆን አንድ ዜጋ የግፍ ፅዋ እንዲጎነጭ ሲገደድ የሚጠጣው የኢ-ፍትሃዊነት ስቃይ ጥልቅ ነው፡፡ በተለይ ግን በሚወደው ህዝቡ ፊትና የእኔ ብሎ በሚኮራበት ሃገሩ እንደርሱ ደምና ስጋ የለበሱ ጥቂቶች ያሻቸውን ሲፈፅሙበት የግፉ ስቃይ ከመቼውም በላይ ይከፋል፡፡ ይህንን ከመሰለው የኢፍትሃዊነት ስቃይ ለአፍታም ቢሆን የሚያሳርፋቸው ግን አንድ ነገር አለ፡፡ አንባቢ የማይዘነጋቸው ወይዘሮ ሮዛ ፓርክስ መቀመጫቸውን ለቀው የኋላ ወንበር ላይ እንዲቀመጡ አሊያም ከአውቶብስ እንዲወርዱ ሲጠየቁ በእግራቸው መሄድን መምረጣቸው ብቻ ሳይሆን ለምርጫቸው የሰጡት አመክንዮ ጥልቅ ትርጉም አለው፡፡ ‹‹በእግርሽ ይሄንን ያህል ማይል መጓዝ ይሻላልን?›› ለሚለው ጥያቄ ‹‹እግሮቼ ይደክማሉ ነፍሴ ግን ታርፋለች›!›› ብለው ነበር፡፡

እኔም በምወዳት ሃገሬ በህዝቤ ፊት ከእነቤተሰቤ የግፍ ሰለባ ብሆንም ህሊናዬን የሚጎረብጠኝ ነገር ባለመኖሩ የእኔም ነፍስ እረፍት አላጣችም፡፡ የሌሎች በግፍ የታሰሩ ጓደኞቼም ህሊናቸውው ፍፁም እረፍት የተጎናፀፈ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ትልቁ የህሊና እዳ በሃሰት ካሰሩኝ በኋላም በግፍ ተግባራቸው የሚመፃደቁት አሳሪዎቼ እንጂ የእኔ አይደለም፡፡ ያልተገባ ዋጋ እንዲከፍል የተገደደ እኔን የሚመስል ዜጋ ሞትንም እንኳን ቢሆን በክብርና በደስታ ለመጋፈት ይዘጋጃል እንጂ ህሊናውን ሰላም በሚያሳጣ ድር ተጠልፎ አይወድቅም፡፡

ውድ አንባቢ በእኔ ጫማ ውስጥ ቢቆሙ ከዚህ የተለየ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? በሃገርዎ፣ በህዝብዎ ከምንም በላይ በህልውናዎና በእጣዎ ላይ የግል አቋምዎን እንዳያራምዱ በሃሰት ዶሴ ተጠርቀው መቀመቅ ቢወርዱ ከዚህ የተለየ አቋም ሊኖርዎት ይችል ይሆን? በሚያምኑበት ጉዳይ ተሸብበው የሚነገርዎትን ብቻ እንዲፈፅሙ ቢነገርዎት ይስማማሉን? የመብቶቹ ባለቤት ላልሆነ ዜጋ ሰው መሆን ማለት ምን ትርጉም ይሰጣል? ይኸ ሁሉ አንሶ በእሾህ በታጠረ የፖለቲካ ሰርጥ ውስጥ በተቦዳደሰ እግርዎ እያነከሱ እንዳይንከላወሱ እንኳን ‹‹እግር በመቁረጥ›› ፈሊጥ የተካኑ ገዥዎች እግርዎን ቢቆርጡት ምን አይነት ስሜት ይፈጥርብዎታል? ጥቂት ዙፋን ላይ የተቀመጡ ባለጊዜዎች ምን ማሰብ እንዳለብዎ እንኳን ሳይቀር ሲወስኑልዎ እና ባጠቃላይ የርስዎ ህልውናና ተፈጥሮአዊ መብትዎችዎ በነሱ መዳፍ ስር ያሉ፤ ከፈለጉ ብቻ ቆንጥረው የሚሰትዎ ካላሻቸው የሚነፍጉት ሲሆን ምን አይነት ትርጉም ይሰጥዎት ይሆን?

አዎ ሀገር በጭቆና ቀንበር ስር ስትወድቅ ድጋፍ ብቻ እንጅ የተቃውሞ ድምጽ ማሰማት ስርየት የሌለው ሃጢያት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ለገዥዎች በታጠረው አጥር ውስጥ በድፍረት ለማቋረጥ ሲሞክሩ ‹‹ቀዩን መስመር አልፈዋል›› በሚል አይቀጡ ቅጣት ይቀጣሉ፡፡ በዜጎች ላይ የሚፈፀሙ ግፎች እንደነውር ወይም ግፍ ሳይሆን አገዛዙን ለማስቀጠል የሚያስፈልጉ፤ ከትልቅ አዕምሮ የተቀዱ ልዩ የፖለቲካ ቀመሮች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡

በአገዛዙና የግፍ ሰለባ በሆነ እኔን በመሰለ ዜጋ መካከል የሚደረገው ትግል ከወትሮው የተለየ ነው፡፡ አገዛዙ እስረኛውን ለማምከን ሲተጋ እኔን የሚመስል እስረኛ በግርግም ውስጥም ሆኖ ደግሞ ህይወት በከንቱ እንዳይባክን ይታገላል፡፡ ለዚህም ነው አገዛዙ እስር ቤት ውስጥ እንኳን ከሌሎች አያሌ እስረኞች በተለየ ግፍ የሚፈፀምብኝ፡፡ እኔም እኔን የመስበር ተልኳቸው ገብቶኛልና ግብግቡን ለማሸነፍ ፍፁም በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሆኘ ለሀገሬ ይበጃል ያልኩትን ሀሳብ በሁለት መፅሐፎች ለማድረስ ሞክሬያለሁ፡፡ ከነጉድለቱም ቢሆን ‹‹ያልተሄደበት መንገድ›› ከብዙ ፈተና በኋላ ለአንባቢ ሲደርስ የተሰማኝ ደስታ ወደር የለውም፡፡ አሁን ደግሞ የፈጣሪ ፀጋ በዝቶልኝ ታምር በሚመስል መልኩ ‹‹የሀገር ፍቅር ዕዳ›› የተሰኘውን ሁለተኛ መፅሐፌ ለአንባቢ በመድረሱ በጣም ተደስቻለሁ፡፡ በሀገር ፍቅር ዕዳ የግል ህይወቴን ጭምር ጨልፌ ለማካፈል ሞክሬያለሁ፡፡ የእኔ የዝቅታ ህይወት የሚሊዮኖችን ኢትዮጵያውያንን ህይወት እንደሚወክል በማመን፡፡ ምንም እንኳ የሚያስኮፍስ ያለፈ ታሪክ ባይኖረኝም ታሪክ የሚያኩራራው ብቻ አይደለምና ከተመላለስኩባቸው ውሃ አልባ ሸለቆዎች አንባቢዎች የሚቃርሟቸው ጥቂት ቁምነገሮች አይጠፉም፡፡ የህይወት ከፍታ ከሩቅ ስለሚታይ ነጋሪ አያሻውም፡፡ ዝቅታን ለማሳየት ግን ጉልበት ይጠይቃልና ለማሳየት በመሞከሬም እንዲሁ ደስታ ይሰማኛል፡፡

በሀገር ፍቅር ዕዳ የእኔን ከፍና ዝቅ ህይወት ብቻ ሳይሆን በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለኝን እይታ ያለምንም ማድበስበስ ለአንባቢ ለማካፈል ሞክሬያለሁ፡፡ ያልተሄደበት መንገድ ላይ በሩቁ የሰማኋቸውን አስተያየቶች በዚህኛው ለማረም ተፍገምግሜያለሁ፡፡ አንባቢ እንደሚረዳው መፅሐፌም እንደኔ ነፃነት የተነፈገ በመሆኑ እንደሌሎች መፅሐፍቶች  ከመታተሙ በፊት በተለያዩ ሰዎች ተገምግሞ እንደገና አርሜው የመውጣት እድሉን አላገኘም፡፡ ስለዚህ ግድፈቶች ካሉ አንዱ መንስኤ ይሄው ነው፡፡

ህይወቴ አንባቢን የሚስያተምሩ፣ ነገሮችን ከተለየ ማዕዘን ለማየት የሚረዱ፤ ከተቻለም ፈገግ የሚያሰኙ ነገሮች እንዲገኙበት ትልቅ ምኞት አለኝ፡፡ በህላዌ ዘመናችን ስንመላለስ የህይወትን ትርጉም ከሚሰጡ ምግባሮች መካከል አንዱን ለመከወን ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ ምን ያህል ተሳክቶልኝ ይሆን? ይህንን ለናንተ ልተወው፡፡

ለዘመናት ልባችን በናፍቆት ለዛለላት የዴሞክራሲና የነፃነት ጀምበር የምትወጣበት ታላቅ የንጋ ቀን ከመቼውም ጊዜ በላይ እየቀረበ መሆኑን በፍፁም በማመን፡፡

አንዷለም አራጌ (ቃሊቲ፤ የህሊና እስረኛ)

ኦባማ መጣ ኦባማ ሄደ ምን ፈየደ ? ህወሃት መሩ መንግስት ተጋለጠ::መጭው አኬል ዳማ ተበሰረ

$
0
0

ቢላል አበጋዝ ዋሽግቶን ዲ ሲ

ጁላይ 31፡2015

obama 45ህወሃት መሩ መንግስት ልዩ በዓል፤ልዩ ድምቀት፤ልዩ ምልክት፤ታሪዊ ንግርት ሌላም ጨመር አርጎ የፕሬዜዳንት ኦባማን ጉብኝት ቢያስወራውም አለቀ:: የተረፈ ምንም የለም። የተለወጠም ምንም የለም።ከታፈገው እስር ቤት በጣት የሚቆጠሩ ተፈተዋል። ህወሃት በዚህ አይመሰገንም።ህዝብም ዓለምም የታፈገውን እስር ነው የሚመለከተው። ይልቅስ የወያኔ መሃይም መንጋ ያደረገው የፕሮቶሎል ስተተት ሲያስቅ ሰነበተ።

ምን ደስ አለህ ብባል ፕሬዜዳንት ኦባማ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህንን አንስተው፤የሰው ልጅ መገኛ እያለ አክብሮት፤ ፍቅሩን እምቅ ስሜቱን ለናት አገሩ ስለገለጠላት ባለቅኔ መናገራቸው ነው።ጥቁር አማሪካውያን የባርነት ውርደትን አንቀበልም ሲሉ ኮከባቸው ኢትዮጵያ ነበረችና ገጣሚ ፖል ዱንባርን፡”ለኢትዮጵያ ከልብ” (Ode to Ethiopia) ብሎ የተቀኘውና ላግስተ ኁስ  ኢትዮጵያ በፋሽስ መንጋጋ ስትገባ “የኢትዮጵያ ጥሪ” ብሎ የገጠመውን ሌላ አኩሪ ገጣሚ ማንሳታቸው አልረሳም (Call of Ethiopia)። በተለይ በዘረኞች፤ በቂመኞች በከዳተኞ እጅ ባለችው አገር፡ይህ መሆኑ ይገርማል።ወይታሪክ? ያሰኛል።

ፕሬዜዳንት ኦባማ ወያኔን ሊያወድሱ ነው ወደ ኢትዮጵያ የተጔዙት የሚለው ጅሉ ቴድሮስ አዳኖም ነው።ፕሬዜዳንቱ ዓይናቸው ሽብርተኞች ላይ ነው።አልሸባብን ለመውጋት ከሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች ቢያገኙ ኖሮ ህወሃትን አይፈልጉም ነበር። ሰራዊቱን ለማቅረብ ሽርጉድ ደግሞ መለስ የጀመረው ነው። የተለወጠ ነገር የለም።የጥንቱ ኢትዮጵያ ጦር ድንበር አስከበረ።ጠበቀ።ይሄው ነበር።ለሰላም ጥበቃ ቢሰለፍ በተባበሩት መንግስታት ነበር።ሌላ አዛዥ አልነበረም።አዳኖም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ምንድነው ቢባል የህወሃት በስልጣን መቆየት ነው የሚል ነው።ለዚህ ደግሞ ማንስ ቢያዘው አይጨንቀውም።

ጅሉ ቴድሮስ አዳኖም ፕሬዜዳንት ኦባማ “መንግስታችን በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነው ብለውልናል” አለ ባደባባይ።ኦባማ ምን አገባቸው? አማሪካስ ? ባለቤቱ መስካሪው የኢትዮጵያ ህዝብ እያለ ? ፕሬዜዳንቱ ዛሬ ያለውን የመንግስታቸው አቌም ነው የሚንጸባርቁት።እንዴት የውጭ ጉዳይ ሆኖ ይህን አይረዳም? ጅሉ ቴድሮስ አዳኖም ይህ ሊገባው አይችልም። ባድር ባይነት ላገኘው ሹመት የሚበቃ አይደለምና።ሱዛን ራይስ ለምን ሳቅ አፈናት ? በዲሞክራሲያዊ መንገድ ነው ወይ የተመረጡት ስትባል? የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን አይከታተልም? እስቲ ይችን እመቤት ክሰሳት ? እስቲ ውቀሳት ?የት አባክ ትገባለህ? ቪኦኤ እድሉን ሰጥቶህ ነበር። ሱዚ አርባክንድ ምላስ ነው ያላት! ከፈለግህ አሁንም ሞክር።

ሌላው ነገር ፕሬዜዳንት ኦባማ አፍሪካ የሙስና ነቀርሳ አለባት ብለዋል።የሙስና ሙከራ ጣቢያ ሆና ቆይታ ዛሬ የሙስና ማዕከል የሆነችው አዲሳባ መጥተው ይህን ማለታቸው ለወያኔም ለሁሉም የአፍሪካ ሞሽላቆች ነው።የሚሰረቀው መጠን፤ የት እንደተደበቀ፤በማን? ሁሉን ከስለላ ድርጅታቸው ያገኙታል።ሟቹ ሞሽላቃው መለስ ዜናዊ የዘነጠላቸው ቢሊዮኖች ምስጢር አይደሉም። በነገራችን ላይ የናጄሪያ አዲሱ መሪ አገሬን ግጠው የበሏት ባለስልጣናት የዘረፉትን ለማስመለስ እርዱኝ ለማለት ነው ወደ አሜሪካ የመጡት፡የቦኮ ሃራምም ጉዳይ ቢቀድምም።ውጭ ጉዳይ የሚያናግሩህ ፋይልህን በጃቸው አርገው ነው።ዳሩ ምን ይገባሃል?

ፕሬዜዳንት ኦባማ የደቡብ ሱዳንን፡የኬንያን ጸጥታ ጉዳይ አንስተዋል።ኢራቅ፤ሶሪያ፤አፍጋኒስታን ያለው ሁኔታ የበለጠ የሚሳስባቸው ይሆናል።ስለፓርቲያቸው የመጭው የምርጫ ውድድር ከማሰባቸው አንጻር የአፍሪካ ጉዳይ ቅድሚያ አይዝም ማለት ያስችላል።ንግዱም ከቻይናው አፈሰማይ ይተርፈኛል ማለት ያውም ይህን ያህል ጌዜ ተተኝቶ የሚያዋጣ አይደለም።በኔ አስተያየት ፕሬዜዳንት ኦባማ ለጉዞ ያነሳሳቸው እንዲው በስልጣን ዘመኔ ያባቴን አገርና ዘመዶቸን ልጠይቅ ማለት ነው ማለት ይቻላል።

ይህ የፕሬዜዳንት ኦባማ ጉብኝት ህወሃት መሩን መንግስት በጣም ያጋለጠ ነው።ከጉብኝቱ ትንሽ ቀደም ብሎ በአበኞች ግንቦት7 ተኩስ ቢከፈት መላው የወያኔ መንጋ ተርበተበተ።ወፋፍራሞቹ የህወሃት ድመቶች ግራ ተጋቡ።ጄኔራሎቹ መወቃቀስ ጀመሩ።ሚስጥር ይሾልክ ጀመር።ጨዋታው ባጭር ጊዜ መቀየሩ ግራ አጋባቸው።አጭበርባሪው መለስ እያለ በተማሪ እንቅስቃሴ ከተማራት ተንኮል መነጋገሪያ የምትሆን አንድ ነገር ጣል ያደርግ ነበር።የድል አጥቢያ አርበኛው ቴድሮስ አዳኖም፤የውሸት መዝገብ የሆነው በረከት፤ሰካራሙ ሽማግሌ፤ ሹላፉ አባይ ጸሃዬ አንዳቸው ብልሃት የላቸውም።በተለይ ቴድሮስ አዳኖም የት ?ምን ሲያደርግ ነበር ባለፉት ቅድም ወያኔ ዓመታት ? በሜዳው ትግል ምን ድርሻ ነበረው ? ያለው ዋና ሰርተፊኬት የመለስ ተላላኪነት ነው። በቪኦኤ ራዲዮም ያስረገጠው ይህንኑ ነው።ዛሬመ “ታላቁ መሪያችን ይላል” ይህ ሰው መሳቂያ ነው።

ልክ ጌታው ያሰለጠነው ውሻ አይነት ነበር የጅሉ ቴድሮስ አዳኖም ቃለመጠይቅ በቪኦኤ ራዲዮ። ያልተፈቱት ጋዜጠኞችስ ሲባል “የፍርድ ቤት ውሳኔ “ እያለ ቀላመደ።ልክ እንደ ጌታው እንደ መለስ።ስለ መቶ በመቶ ማቸነፍም ሲጠየቅ ራሱን ለትዝብት ዳረገ።ከዚህ ሰው ዲግሪ የቆስጤ በርሄ የተሻለ ነው ወይ ያሰኛል። ጌታው ያሰለጠነው ውሻ የሚያሰኘው አዳኖም ሲናገር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትግል ሜዳ መሄዱን አስመልክቶ ልክ እንደሟቹ ድውይ “መንገዱን ጨርቅ ያርግለት” ማለቱ ነው።ብርሃኑ ነጋ ወደ ኤረትራ አልሄደም። እደግመዋለሁ።ወደ ኤርትራ አልሄደም። ብርሃኑ ነጋ የሄደው የትግል እቶቹንና ወንድሞቹን ሊቀላቀል ወደ ትግል ሜዳ ነው የሄደው።በኤርትራ በኩል ? አዎን። በኤርትራ በኩል:: ደህና ካምፒንግ እንኳን ወጥቶ የማያቅ የወሬ ቋት ቴድሮስ አዳኖም : “ጨርቅ ያርግለት” ማለቱ አስቂኝ ነው። ራሳቸው ህውሃቶች(መኮንኖቹ)የሚስቁበት ይመስለኛል።

የጅሉ ቴድሮስ አዳኖም በዳያስፖራ ያለው ሁሉ የደርግ አባል የነበረ ይመስለዋል።እሱ እንጀራ በወጡን ሲዝቅ ደርግን ይታገል የነበረና ዛሬ በስደት ያለው ብዛቱ እንደሚያይል፤ህወሃትም አላስቀምጥ ብሎት የተሰደደ እጅግ ብዙ እንዳለ አያውቅም።አሁን እሱ ድፍን አፍሪካን አስሶ፤ የአፍሪካ አንድነት አርኪቴክት ከነበረው ክቡር አቶ ከተማ ይፍሩ ወንበር ላይ ይቀመጥ? አይ ኢትዮጵያ ? ቴድሮስ አዳኖም ታሪክ ይወቅስሃል የሚባል አይደለም።ትልቅ አፍ ያለው ትንሽ እንሰሳ በመሆኑ።ታሪክ ደግሞ እንዲህ ላለው አይጨነቅም።

ቴድሮስ አዳኖም “በዘዴ” በቪኦኤ ቃለ መጠይቁ ላይ አንዳርጋቸው ጽጌን አንስቷል።ይህ የሚያመለክተው ምንያህል ወያኔ ስለ አርበኞች ግንቦት 7 ሲጨነቅ እንደሚያድር ነው።አንዳርጋቸውን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ  ከመሰል የየመን ወሮበላ አረብ አብራችሁ ከያዛችሁ በኋላ ያሻችሁን አርጋችሁታል።ሁኔታውን የብሪጣኒያው አምባሳዶር ግልጥ አርጎታል።ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ከምትጠቀሙበት መጀመሪያ ከቤተሰቡ ታገናኙት ነበር። ከሰብእና ጎዳና ሳይሆን እናንተ ያላችሁት ከተንኮልና በቀል ጎዳና ነው።ውጭ ጉዳይ ቴድሮስ አዳኖም ለቀንደኛው ቂመኛ ለበረከት ስሞን ይህን ንገረው። የላከህም እሱ ነው። አንዳርጋቸው ጻፈ ያልክው መጽሃፍ ተነባቢነትም ታማኒነትም የሚያገኘው አቶ አንዳርጋቸው ተፈቶ፤ቤቱ ሎንዶን ተመልሶ ቢያሳትመው ብቻ ነው።ከዚህ የተረፈው ያው አኬልዳማችሁ ነው።መለስ ሲሞት መንደራችሁ ለጥቆ የጅል ሆነ።የሚታዘብ ያለ አይመስላችሁም።

ባጭሩ የፕሬዜዳንት ኦባማ ጉብኝት ለወያኔ የፈየደው ምንም የለም ከመጋለጥ፤መሳቂያ ከመሆን ሌላ።የእሳቸው ጉብኝት የምስራቅ አፍሪካን የሰላም ሁኔታ ያሻሽለዋል ማለት አይቻልም።በትንሹ የደቡብ ሱዳንን ሁኔታ ብቻ ቢያዩ የት ነበሩ ብሎ ያስጠይቃቸዋል። ግራ ቀኙ ፋይዳ ቢስ ነው።የህወሃት መሩ መንግስት ስንብት አዲስ ምእራፍ መክፈት መቻሉን “መንገዱን ጨርቅ ያርግላችሁ” የተባሉት እነ ብርሃኑ ነጋ ቀድመው አውቀውታል።መንገዱ ግን ጨርቅ አይደለም።ለወሬኛ ይመስለዋል እንጂ። እድሜ ይስጠን የኢትዮጵያ አምላክ።

 

ኢትዮጵያ በነጻነት በአንድነት ለዘላለም ትኑር!

ሽብርተኛ ድርሽ የማይልባት፡የተረጋጋች፡የበለጸገች አገር በህብረት እንገነባለን!

በግፍ የታሰሩ የስልምና ሀይማኖት ተከታይ ወንድሞቻችን ይፈቱ!

አርበኞች ግንቦት 7 ከሌሎች ታጋይ ሃይሎች ጎን ለጎን ወደፊት ይራመዳል!

በአገራችን ውስጥና በውጭ ያላችሁ አገር ወዳዶች ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ተባበሩ!

ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለምን በፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ በብዛት አይሳተፉም

$
0
0


semayawi-female1
የሴቶች በብዛት በፖለቲካ ጉዳይ ያለመሳተፋቸው በብዙ ሰዎች አዕምሮ ውስጥ ስለሚጉላላ የግል አመለለካከቴን ለአንባቢያን ለማካፈል የዚህ ርዕስ ጽንሰ ሃሳብ ነው፡፡

በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶች በፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ውስን ሆኖ መታየቱ ያስደንቃል፤ ብሎም በመንግስት ስራ ላይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ በቁጥር አናሣ ናቸው፡፡ መልሱ ግን ቀላል አይመስልም፤ይህ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዲሞክራሲና የእኩልነት መብት አለ በሚባልባቸው አገሮችም ውስጥ ቁጥራቸው የጎላ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያውያን ሴቶች እንኳን በአገር ቤት በውጭው አለም ወጥተው በሚኖሩባቸው አገሮች ባሉት የኮሚኒቲ ጽ/ቤቶች ውስጥ እንኳ በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ላይ ለመድረስ ሲጣጣሩ አይታዩም፡፡ ይህ ስርዓት መቼ ይቀየር ይሆን?

አንዳንዶች ወንድ/ሴት ይሁን ችሎታ ካለው ሁሉም ሰው በአገሩ ጉዳይ የመሳተፍ መብት አለው ሲሉ ሌላው ወገን ደግሞ የስራ መደቡ ሳይፈጠርላቸው የመሳተፍ መብት አላቸው ማለት ብቻ በቂ አይደለም ይላሉ፡፡ምክንያቱም በመጀመሪያ ደረጃ የፖለቲካ ስርአቱ እንቅፋት ሲሆንባቸው ተሳትፎአቸው ውስን ይሆናል፡፡ በመሆኑም ወንዶች በሚሳተፉበት ነገር ላይ የተሳትፎቸውን ራዕይ ለማሳካት የሚጥሩ ጥቂት ናቸው፡፡

ሴቶች ከፈለጉ በፈለጉበት ጉዳይ ውስጥ ለመሳተፍ ሙሉ ነጻነት አላቸው፡፡ነገር ግን ፍላጎት ቢኖራቸውም በጉዳዩ አይገፉበትም እየተባለ የሚነገረው ለይሰሙላ እንጂ ተግባራዊ ሲሆን አልታየም፡፡ምክንያቱም የቤተስብ ሃላፊነትና የግላቸው ችግር ስላለ ነው ይባላል፡፡ስለዚህ በመጀመሪያ የቤት ውስጥና የውጭ ችግራውን ለማቃለል ቅድመ-ፕላን ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ካለዚያ ተገለልን ወይም ዕድሉ አልተሰጠንም እያሉ ማማረራችውን ማቆም አለባቸው፡፡ ለምሳሌ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የሴት መሪ ለመሆን ዕድል ያገኙ በማላዊ፤ በላቤሪያና በጥቂት አገሮች ነው፡፡ ይሁን እንጂ በሚኒስቴርነት ደረጃ ላይ የደረሱ ብዙ አሉ፡፡በሥራቸውም አመርቂ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ በፖለቲካ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ ፍላጎቱ ቢኖራቸውም በትዳርና በቤተሰብ ሃላፊነት ስለሚጠመዱ ወደ ማህበራዊው ኑሮ ያደላሉ፡፡ በተጨማሪም የአገራቸው የፖለቲካ ስርዓት ግፊት ያደርጋል፤የማህበራዊና የኢኮኖሚ ችግሮቻቸው ወይም ሃላፊነታቸውም ይጫናቸዋል፡፡ ለማናቸውም የእኩልነት መብት የመሰጠቱ ጉዳይ መቅደም ይኖርበታል፡፡የማህበራዊ፣የፖለቲካዊና የኢኮኖሚ ምክንያቶች ካሉበት ክልል ወጥተው በትምህርት እንዲገፉ፤ በባህል አካባቢ ያለባቸው ተጽእኖ እንዲቃለልላቸው ተደርጎ በፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ እንዲችሉ መደረግ አለበት ብሎ አሳማኝ ማረጋገጫ የሚያቀርብ/የሚከራከር ግለሰብ ይኖር ይሆናል?

ሴቶች በፖለቲካ ውስጥ እንዳይሳተፉ የሚታወቅ እንቅፋት መኖሩ ከማይካድበት ሃቅ አንዱ ጠንካራ የገንዘብ መሰረት የሌላቸው ስለሆኑ፤ቢርቁት እንኳ የማይለቃቸው የቤተሰብ ሃላፊነት ስላለባቸውና የባህል ተጽእኖ ሌላው የማህበራዊ ኑሮ ችግራቸው ነው፡፡ሴቶችና ወንዶች የሚሰሩአቸው የሥራ ዓይነቶች ተለይተው በሃይማኖት እምነት ተጠቁመዋል፡፡

በከፍተኛ ደረጃ ሊማሩ የሚገባቸው የትምህርት አይነቶች ተለይተዋል፤ስለፖለቲካ ምንነት ለማወቅ እንዲጋለጡና ሌሎችም ተዛምዶ ላላቸው ነገሮች በልጅነታቸው ግንዛቤ እንዲያገኙ አልተደረጉም፤ በሚሉትና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ከማተኮሬ በፊት አንዳንድ ጉዳዮችን ግልጽ ማድረግ ያሰፈልጋል፡፡

በእርግጥ የተወሰኑ ሴቶች ስለአገራችን ፖለቲካ ሁኔታ እንዲያውቁ ተደርገው አስተዋጽኦ ያበረከቱ ቢኖሩም እነኝህ ሴቶች ብዙሃኑን አይወክሉም፡፡ሆኖም በአገር አቀፍ/በቀበሌ በፓርቲ ደረጃ እንዳይሳተፉ የሚያግዳቸው ነገር አለ፤ለምሳሌ በፖለቲካ ውስጥ ለመሳተፍ ጥረት ሲያደርጉ ሲታዩ፤መድረክ ላይ ወጥተው ንግግር ሲያደርጉ ድሮም ፖለቲካ ለሴት አይሆንም፤ሴቶች ለማድቤት ስራ እንጂ ለፖለቲካ ስራ አይመጥኑም እየተባለ ሲፌዝባቸውና ድምጻቸውን በማሳማት እንዳይታወቁ ጭቆናና ተጽዕኖ ሲለሚደረገባቸው በትምህርትም አይገፉም፡፡ ወደባልትናው ስራ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፤ በወንዶቸ በአጭሩ ይቀጫሉ፤ ጠቃሚ ነገር ሲሰሩም ላደረጉት አስተዋጽኦ እውቅና አይሰጣቸውም ወይም አይመሰገኑም፡፡

ለዚህ ጉዳይ አንድ በፍርድ ቤት ውስጥ የተሰማ ገጠመኜን ልጥቀስ፡፡ ባልና ሚሰት የሆኑ ግለሰቦች በጋራ የንግድ ድርጅት ከፍተው ሲያካሄዱ የሥራ ድርሻ ክፍፍል ያደርጋሉ፡፡ሚስት የዋጋ ተማኝ ስትሆን ባል ደግሞ እቃ አቅራቢ ሆነው ሲሰሩ ዕዳ ያለበትን አንድ ግለሰብ ከስሰው ፍርድ ቤት ቀርቡ፡፡ ዳኛውም የዕቃ ዋጋ የሚተምን ማነው? ተብለው ሲጠየቁ ሚስት እንደሆነች ተናገሩ፡፡ ለመሆኑ በባህል ሴት የቤት ስራ እንጂ በዋጋ ትመና ላይ ትሳተፋለች? በማለት ዳኛዋ ተገረመዋል፡፡

በትምህርታቸው አድገው አልፎ አልፎ ከከፍተኛ የስራ ደረጃ ላይ ቢደርሱም በፖለቲካው አለም ውስጥ እጅግም ስለማይታወቁ ከፍተኛ የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ በተወዳዳሪነት ቀርቶ በእጩነት ደረጃ እንኳ ቀርበው አያውቁም፤መርጫ ለማሽነፍ በህዝብ ታውቀው ለመወዳደር በፓርቲ ውስጥ መታቀፍ አለባቸው፡፡ይህ በማይሆንበት ጊዜ ለወንዶች እድል ይከፍታል፤ሴቶች ከተሳተፉ ለውጥ እንደሚያመጡ ስለሚታወቅ ይህ ለወንድ ፖለቲከኞች አይዋጥላቸውም፡፡ ህዝቡም በሴቶች ላይ እምነት አይጥልም፡፡ እነሱም/ሴቶችም ፍላጎት እንዳላቸው ስለማያሳውቁ በፖለቲካ አለመብሰላቸውን ያመላክታል፤ይህ የሚያሳየው የወንድ የበላይነትንና ፖለቲካና አገር ማስተዳደር ለወንዶች ብቻ ተወስኖ የተሰጠ የስራ ድርሻ አድርጎ የዓለም ህዘብ ያየዋል/ይቆጥረዋል፡፡

የማህበራዊ ኑሮ ባህላችንና የሀይማኖት እምነታችን ሴቶችን ጨቁኖ በመያዝ ሴቶች እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሆነው እንዲታዩ/ልጆችና ባሎቻቸውን ቀዳሚ ተንከባካቢ እንዲሆኑ፤ዶልተዋል፤ የቤት እመቤት ብቻ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ አድርገል ለማለት ያሰደፍራል፤ይህን ሁሉም ሰው ያምንበታል፤ሴቶች አስተያየታቸውና አመለካከታቸው ጠቃሚ እንዳልሆነ በባህል ስለታመነበት ድምጻቸውን እንዳያሰሙ ተደርገዋል፡፡

ይሁን እንጂ ስር ነቀል ለውጥ ማድረግ ጊዜው አሁን ነው፤አገራችን ከጥንት አንስቶ በወንድ ተገዝታ ለህዝቡና ለአገሪቱ የጎላ ለውጥ እንዳላሳየች ታሪክ ይመሰክራል፡፡ይህ የሚያመለክተው ወንዶች ህዝብ ረግጦ ለመግዛት እንጂ አገር ለማሻሻል/ለማሳደግና ሕዝብ ለማስተዳደር ያልታደሉ መሆኑን ነው፡፡ለለ ስለዚህ በሌሎች አገር ከወንዶች ይልቅ ሴቶች አገራቸውን የማሻሻል አቅጣጫ ለማሳየት የበቁበቻው አሉ፤ለየት ያለ መንገድ መሞከሩ አይጎዳምና አገር የመምራቱን እድል ለሴቶች ይሰጥና ይሞከሩ፡፡

ለምሳሌ ላቤሪያ ከብዙ አመታት ጦርነትና የምስልቅል የህዝብ ኑሮ በኋላ አገር የመምራት ፍንጭ የሌላቸውን የጦር መሬዎች አንስቶ በሴት ለመተካት በመቻሉ በብዙ የሰለጠኑ አገሮች ምስጋናን አትርፈዋል፡፡አፍሪካ መሪ አልተፈጠረባትም የሚለውን ለማስተባበል በአገራቸው አስችለዋል፡፡ ሰላም ለማስፈንና አገርን አንድ አድርገው ለመምራት በቅተዋል፡፡የእስያንና የአፍርካ አገሮች ለናሙና ያህል ተጠሩ እንጂ ባደጉ አገሮችም በከፍተኛ የፖለቲካ ስልጣን ላይ የወጡ አለም ያፈራቸው ከወንድ የሚበልጡ አገር የመምራት ችሎታ ያላቸው ጠንካራና ኃይለኛ ሴቶች አሉ፡፡ይህ የሚያሳየው ከወንዶች ይልቅ ሴቶች አገር የመምራት፤ የህዝብ ሰላምና መብት ጠብቀው የማስተዳደር ችሎታ እንዳላቸው ነው፡፡ የስቶች ችሎታ ያልታየና ያልተነካ፤አርቆ የማየት የተፈጥሮ ሞያ ያላቸው ለመሆናቸው በባለሙያዎች ተረጋግጧል፡፡

ለሴቶች የፖለቲካና አገር የማስተዳደር ችሎታቸው በአለም ዙሪያ ታውቆላቸው ሳለ በአፍሪካ አህጉራት ግን ሴቶች ከቤት እመቤትነት ሌላ ስራ አይፈልጉም፤ ፍላጎትም የላቸውም የሚባለውን አጉል አስተሳሰብ በሰለጠነው አገር በተግባር አሰመሰክረዋል፡፡

ስለዚህ ሴቶች የወንዶችን ያህል እንደሚሰሩ ስለታወቀ ሴቶች እህቶቻችን ስለሃገራቸውና ስለፖለቲካ ተሳትፏቸው ጉዳይ ሊያሰቡበት ይገባል፡፡ አፍሪካ የወንድ የበላይነት የነገሰባት አህጉር በመሆኗ ሴቶችን በባህል ተጽእኖ መያዟ መወገድ አለበት፡፡

ሴቶች በፖለቲካ ስራ ላይ እንዲሳተፉ አገር ወዳድና አርቆ አሰተዋይ ተባባሪ የወንዶች እገዛ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ በቀር ሴቶች የፖለቲካ ስልጣን ላይ አይወጡም፡፡የአዋቂዎችን አባባል ስናስታውስ “የእሳቱን ግለት ያልተቋቋመ ሰው ማእድ ቤቱን መልቀቅ አለበት” የሚባል አባባል አለ፡፡ ከወንድ ሌላ ስለፖለቲካ ጉዳይ የሚያውቅ የለም የሚለውን አስተሳሰብ የአፍሪካ ህዝብ ስለሚያምንበት በውዴታም ሆነ በግዴታ ስልጣኑን ይዞ ይቆያል እንጂ ከእሱ የተሻለ መሪ አስቀምጦ ውጤት መጠበቁ አይሆንልበትም፡፡ለምን ቢባል ብቅ የሚለውንና ለአገሩ የሚያስበውን ያርቁታል፤ይህንን ለመቋቋም በተለይ ወጣቱ ትውልድ በዘመናዊ ትምህርት የመታነጽ ዕድል ስላገኘ የወንድ ፖለቲከኞችን መታገል፤የወንድ የበላይነትን ጉዳይ ማመንመን ይኖርበታል፡፡

ሴቶችም ቢሆኑ ስልጣን ይዘው ካልተሳካላቸው ሴት ስለሆኑ ብቻ እንዳልሆነ ማወቅ አለባቸው እንጂ ሴት ስለሆንኩኝ ነው የሚለውን አስተሳሰብ ከአዕምሮአቸው ውስጥ ማስወገድ አለባቸው፤ወንዶች ምን ጊዜም የበላይ ናቸው በሚለው ኋላቀር አስተሳሰብ እንዳይታለሉ ፤ወንዶች የሚጫወቱትን የፖለቲካ ቁማር ለመጫወት ታጥቀው መቆም አለባቸው፡፡ ካላሸነፉ አብረው ጥሩ ስም የሚያስጠራ ስራ በመስራት ለመቆም፤ካለበለዚያ ማደግ የለምና የአስተሳሰብ ጠባብነትን ማስወገድ፤ ሴቶች ወንዶች የሚሰሩትን ማለትም ቆራጥንትን፤ብልጥነትን፤አርቆ አስተዋነት፤ ንቁነትን፤ ተባብሮ መኖርን፤ ወድቆ መነሳትን፤የወንዶች የበላይነትን አስተሳሰብን መቋቋም፤ አስተዋይነትንና አለመታለልን የአፍሪካ መሪዎች የሚጫወቱትን እሰጥ አገባ አብሮ መጨወትን፤ሆደባሻነትን፤ ሃዜኔታንና ማለቃቀስን ጠንቅቀው መረዳትና ማቆም አለባቸው፡፡

አሜሪካ ጯሂና የጾታ እኩልነት የሚያስከብር ህግ ቢኖራትም የአገር መሬነቱን ስልጣን ለሴቶች እስካሁን አላሰረከቡም፡፡ ወንዶችን ከመምረጥ ሴቶችን መምረጥ ያስፈልጋል የሚለው የጥንት አመለካከታቸው እሰከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ ስላልቀነሰ የመሪነቱን ወንበር ለመልቀቅ እስካሁን አልፈቀዱም፡፡ይህ በመሆኑ ኸለሪ ክሊነተን የአሜሪካ ፕሬዜዳንትነቱን ቦታ ለመያዝ እንደ አውሮፓ ቀን አቆጣጠር 2008 ዓ.ም ላይ ታግላ የውስጥ ጉዳይ በሆነ ነገር ባትመረጥም ጥሩ መሪ መሆን እንደምትችል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆና ችሎታዋን በተግባር ለዓለም ህዝብ አሳይታ ስለተረጋግጠላት አሁን የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ለመሆን ትግሏን ለሕዝብ እያሳየች ነው፡፡የእሷ ምሳሌነትም በብዙ አገሮች ውስጥ ሴቶች ሥልጣን ላይ ወጥተው ችሎታቸውን እንዲያረጋገጡ አድርጓል፡፡


አቶ አብርሃም ጌጡ በቤተሰብና በጠበቃ እንዳይጠየቅ ተከለከለ

$
0
0
11221585_747894495336211_7371459986177945389_n

አቶ አብርሃም ጌጡ

በአቶ ማሙሸት አማረ ካቢኔ የመኢአድ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበረው አቶ አብርሃም ጌጡ በቤተሰብና በጠበቃው እንዳይጠየቅ መደረጉን ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጹ፡፡ አቶ አብርሃም ጌጡ ሰኔ 12/2007 ዓ.ም ቤቱ በፖሊስ ተከቦ ከታሰረ በኋላ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ጉዳዩን በልደታ ፍርድ ቤት ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ ተደጋጋሚ ቀጠሮ ከሰጠው በኋላ ምርመራዬን አልጨረስኩም ላለው ፖሊስ ‹‹የመጨረሻ ቀጠሮ›› በሰጠበት ወቅት ፖሊስ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በማዛወር አራዳ ፍርድ ቤት ሲያቀርበው እንደቆየ ተገልጾአል፡፡

አቶ አብርሃም ጌጡ በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰበት የገለጹት ቤተሰቦቹ ሀምሌ 12/2007 ዓ.ም ወደ ማዕከላዊ ምርመራ መዛወሩን ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ወደ ማዕከላዊ ከተዛወረ በኋላ በቤተሰብና በጠበቃውም እንዳይጠየቅ በመከልከሉ ያለበትን ሁኔታም ለማወቅ መቸገራቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ወደ ማዕከላዊ እንደተዛወረ ብናውቅም በአሁኑ ወቅት የት እንዳደረሱት እርግጠኛ መሆን አልቻልንም›› ብለዋል፡፡

የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተመንግስት –ክፍል 2 “ሳሞራ የኑስ በበረሃ በርካታ የህወሓት ታጋይ ሴቶችን ድፍሯል”

$
0
0

TPLF leaders
መለስ ዜናዊ፣ ስብሀት ነጋ፣ ስዬ አብርሃ፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ገብሩ አስራት፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አውዓሎም ወልዱ፣ አረጋሽ አዳነ፣ አርከበ ዕቁባይ፣ ፃድቃን ገ/ተንሳይ፣ አበበ ተ/ኃይማኖት እና ክንፈ ገ/መደህን ለረጅም ጊዜ መቀሌ ላይ በመዶለት በኢትዮጵያና ህዝቦቿ ላይ አሲረው የበቀል፣ የዘረፋ፣ የመከፋፈል እና የረጅም ጊዜ የአፈና ስርዐት እቅድ ነድፈው ሰራዊታቸውን በባሌ ልከው እነሱ በቦሌ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

በአንድ ጃቸው መቀሌ ውስጥ ተጠፍጥፎ ተሰርቶ የተሳለ የበቀል ሰይፍ በሌላኛው እጃቸው የዘረኝነት ረጅም ዘንግ ጨብጠው አዲስ አበባ የገቡት የባንዳ ልጆች ስብስብ ሳይውሉ ሳያድሩ የጥፋት ተልዕኳአቸውን ዕቅድ አንድባንድ መተግበር ጀመሩ፡፡

የጥፋት ቡድኑ መሪ መለስ ዜናዊ “ከእናንተ ወርቅ ከሆናችሁት የትግራይ ህዝብ በመፈጠሬ እኳራለሁ፤ እንኳን ከእናንተ ተገኘን፤ እንኳን ይሄ ህዝብ የሌላ አልሆነ፤ እንኳን በሩቅ እያየን የምንቀናባችሁ አልሆናችሁ…” በማለት በአደባባይ ተናግሮ እሱም እንዳያቶቹ ኢትዮጵያዊነቱን ሽምጥጥ አድርጎ ካደ፡፡ሌላውን የኢትዮጵያ ህዝብ አቋንሸሸ፡፡ ታላቋ ኢትዮጵያ ከትግራይ እግር ስር ተንበርክካ ለዘላለም እንደምትኖርም አወጀ፡፡ ከክህደት የተገኘ የጣልያን ሶልዲ እየበላ ያደገው መለስ ዜናዊ ዕልፍ ዓዕላፍ አባቶቻችንና እናቶቻችን ደማቸውን ያፈሰሱበትን አጥንታቸውን የከሰከሱበትን ሰንደቅ ዓላማ ጨርቅ ነው ብሎ በማራከስ በኢትዮጵያ ምድር ላይ የኢጣሊያንና የፈረንሳይን ባንዲራ ተክለው እደአውለበለቡት አያቶቹ እሱም የወጣለት ባንዳ መሆኑን በሚገባ አስመሰከረ፡፡ “የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑነው” ሲልም “የ3 ሺህ ዓመታት ታሪክና ባህላችን መመኪያቸውና መፈክሪያቸው ሁኖ ይገኛል…” በማለት ገና በበርሃ እያሉ የፃፉትን እምነታቸውን በአንደበቱ አረጋገጠልን፡፡ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ገና የጥይት ድምፅ ሲሰማ ከጦር ሜዳ በመሸሽ 40 ኪሎ ሜትር የፈረጠጠው መለስ ዜናዊ፤ የድሀውን ገበሬ ልጆች አስጨርሶ ከሱ የሚሻሉትን ሰዎች እያሳሰረ፣ እያስገደለና እያሳደደ ስልጣን ለመያዝ የበቃው መለስ ዜናዊ፣ ድመቶችን በዙሪያው ሰብስቦ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነብር መስሎ ለመታየት የሞከረው አነሩ መለስ ዜናዊ ልክ እንደ አያቱ ኢትዮጵያን በገንዘብና በስልጣን ለውጧታል፡፡

ህወሓቶች “አማራው የትግራይን ነፃነት ገፎ ግልፅና ስውር በሆኑ ዘዴዎች /ሸዋዊ ዘይቤዎች/ የትግራይ ህዝብ በድንቁርና፣ በበሽታ፣ በርሀብ አዘቅት ውስጥ እንዲሰምጥ ያደረጉት በተለይም ትግሬነቱን በፍጥነት እንዲክድና ያለውድ በግድ አማራ ለማድረግ ያልሞከሩት ዘዴ ባይኖርም መሬቱ ተቋራርሶ ስለተወሰደበትና የተደራረበ ጭቆና ስለደረሰበት አገሩን ጥሎ ተሰደደ፡፡ ባጠቃላይ በሁኑ ጊዜ ትግራይ በአማራው ነፃነቷን የተገፈፈች መሬቷ ተቋራርሶ የተወሰደባትና የተወሳሰበ ችግር የደቆሰው ህዝብ ሚኖርባት ጭቁን ብሄር ናት፡፡” በማለት ገና በበረሃ እያሉ የፃፉትን የጥላቻ ታሪክ በመስበክ የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል ብዙ ለፍተው ደክመዋል፡፡

“ትግራይ ጭቁን ብሄር በመሆንዋ በመንግስት የተደገፈ ወይም በግል የተያዘ ፋብሪካ ሊኖራት አልቻለም ፋብሪካዎች የጨቋኝዋ ብሄር አማራ ዋና ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ ውስጥ ተከማችተው ይገኛሉ፡፡” ብለው ገና በበረሃ እያሉ ያምኑ የነበሩ ህወሓቶች ለአርባ አመታት ያለገደብ በዘረፉት የኢትዮጵያ ህዝብ ገንዘብ በትግራይ ህዝብ ስም ግዙፍ የንግድ ድርጅት በማቋቋም እና ፋብሪካዎችን በመክፈት ሌላው ኢትዮጵያዊ በትግራይ ህዝብ ላይ ጣቱን እንዲቀስር አድርገውታል፡፡ ይህም የትግራይ ህዝብ ከጎናቸው እንዲሰለፍ ከሸረቧቸው ታላላቅ ሴራዋች አንዱ ነው፡፡

ህወሓት በአንጠረኞቹ የፖሊት ቢሮ አባላቱ አማካኝነት ቀጥቅጦ የሰራውን የበቀል ሰይፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳረፈው ከአገራችን ክንድ ላይ ነው፡፡ ለዘመናት ተደክሞና ተለፍቶ በርካታ ሀብት ፈሶበት የተገነባውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አፈራርሶ በእሱ የበርሀ ድኩማኖች ሙሉ በሙሉ ተክቶታል፡፡

ህወሓት ከደደቢት በርሀ የቆረጠውን ረጅም የዘረኝነት ዘንግ ወደቀፎው ሰድዶ በመሸንቆር ኢትዮጵያን ንቦቿን በትኖ ህብረት እንዳይኖራቸው ለማድረግ ሞክሯል፡፡ በተለይም ደግሞ አፈራርሶ እንደገና ለመገንባት የሞከረው የመከላከያ ሰራዊት ክፉኛ የዘር ሰለባ ሆኖ ይገኛል፡፡

ህወሓት በሀገር መከላከያ ስም ያቋቋመው ሰራዊት አየር ኃይልም ሆነ ምድር ኀይል ከቁጥር ግዝፈት በዘለለ አገራችን ሊቃጣባት የሚችል የውጭ ጥቃት ቢኖር በአስተማማኝ ሁኔታ መክቶ ዳር ድንበሯን ማስከበር የሚሆንለት አይደለም፡፡ ሰራዊቱ ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ ለእለት ጉርሱ ሲልና ከጓድ መሪ እስከ ኤታማጆር ሹሙ በህወሓት ታጋዮች በግድ ተጠርንፎ ተይዞ መሽሎኪያ ቀዳዳ እያማተረ የሚገኝ ነው ፡፡

ህወሓት ከአገራችን ይገኙ ከነበሩት ወታደራዊ አካዳሚዎች አልፈው የምዕራባዊያንን የጦር ሳይንሥ ኮሌጆች ያዳረሱትንና የወርቁን ዋንጫ ያነሱትን ምርጥ ምርጥ መኮንኖች እያፈሰ በየወህኒው ካጎረ በኃላ በትኖ በማሰደድና ለማኝ በማድረግ በዘር ስሌት ብቻ የጀነራልነት ዳረጎት በቸራቸው የራሱ የበረሀ ድኩማኖች ብቻ ሞልቶታል፡፡ እነዚህ የጀነራልነት ማዕረግን በዕውቀት ሳይሆን በታማኝነት ያገኙ የጦር መሀይም የህወሓት ታጋዮች በሀገር መከላከያ ሰም በስራቸው የሚገኘውን የደሃ ልጅ አስገድደው በፀረ ህዝብነት በማሰለፍ ጦርነት ውስጥ እየማገዱ የስርአቱን እድሜ ለማራዘም ይተጋሉ፡፡በተጨማሪም የአገሪቱን ሀብት በመመዝበር ተግባር ላይም በሰፊው ተሰማርተው ይገኛሉ ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ዋነኛ ጠላቶች ከሆኑት የህወሓት ጀነራሎች የተደበቀ ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ- መንግስት የአንዳንዶቹን እነሆ፡፡
Samora (2)
1. ጀኔራል ሳሞራ የኑስ

ጀነራል ሳሞራ የኑስ ከሱዳናዊ አባቱ እና ኤርትራዊ እናቱ ኤርትራ ሳህል ከርከበት ተወልዶ ያደግና በአፍላ የጉርምስና ጊዜው በ1950 ዓ.ም ከወላጆቹ ጋር ወደ አክሱም በስደት የመጣ ነው፡፡

ለሰፌድ ስራ የሚያገለግል ዘንባባና አከት በመሽጥ በሚያገኙት እጀግ በጣም አንስተኛ የሆነች የቀን ገቢ ከለማኝ ኖሮ ባልተለየ ሁኔታ ህይወታቸውን ይገፉ የነበሩት የሳሞራ ወላጆች ሳሞራ ትምህርቱን ተምሮ ጨርሶ ለስራ በቅቶ እንደሚያሳልፍላችው በትንሹም ቢሆን ተስፋ ነበራቸው፡፡ ነገር ግን ሳሞራ በትምህርቱ እጅግ በጣም ሰነፍ በመሆኑ 11ኛ ክፍል ላይ በተከታታይ ሶስት ጊዜ በመውደቁ ከአክሱም አብረሃ ወአፅብሃ ትምህርት ቤት በ1968 ዓም ተባረረ፡፡

በዚያ ዘመን አክሱም በአብርሃ ወአፅብሃ ትምህርት ቤት ውስጥ ስመጥር ደደብና በወሮበላነቱ ስመገናና የነበረው ያኔው ብላቴና ሳሞራ የኑስ በድንቁርናው ምክኒያት እስከ መጨርሻው ከትምህርቱ ከተሰናበተ በኋላ የወላጆቹም የእሱም ተስፋ መክኖ ዘንባባና አከት ከመሸጥ በስተቀር ምንም አይነት የሕይወት አማራጭ በማጣቱ በነሀሴ ወር 1968 ዓ.ም ወደ ደደቢት በረሃ በመውረድ ህወሓትን ተቀላቀለ፡፡

በደካማ ጎኑ ዝና ለማፈስ የታደለው ሳሞራ የኑስ ህወሓትን በተቀላቀለ በአጭር ጊዜ ውስጥ በፈሪነቱ ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ሆነ፡፡ እንደ መለስ ዜናዊ እሱም በተደጋጋሚ ከጦር ሜዳ ሸሽቷል፡፡ የጥይት ድምፅ ሲሰማ የያዝውን መስሪያ አፍሙዝ አዙሮ የአፅፋ መልስ ከመስጠት ይልቅ ጠብመንጃውን ወርውሮ መሸሽጊያ ጥግ ፍለጋ እንደሚጣደፍና በፍርሃት እንደሚርበተበት በቅርብ የሚያውቁት የትግል ጓዶቹ ይናገራሉ፡፡

በድድብናው ከትምህርት ቤት የተባረረው ሳሞራ የኑስ በህወሓት ውስጥ በፍሪነቱ በጦር ሚዳ ባሳየው ነውረኛ ባህሪ ምንም አይነት እርምጃ አልተወሰደበትም፡፡ ይልቁንም የእሱ ቢጤ ፈሪ ለሆነው መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ጭምር ጆሮ ጠቢ ሆኖ በታማኝነት በማገልገሉ ባንድ ጊዜ ሀይል መሪ ለመሆን በቅቷል፡፡ ቀጥሎም ፀረ-መለስ ዜናዊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ብሎ በመፈረጅ በርካታ ታጋዮችን በማስረሽኑ የክፍለ ጦር አዛዠ ሆኖ ተሸሟል፡፡

ሆኖም ሳሞራ የኑስ የወታደራዊ አዛዠነቱን ቦታ ይያዝ እንጂ አንድም ጊዜ እራሱን ችሎ ያዋጋበት ጊዜ የለም፡፡ በሚመራው ስራዊት እጅግ በጣም የሚጠላ፣ ሁሉም የሚያዋርደው እና መሳቂያ መሳለቂያ የሚያደርገው ነበር፡፡

ሳሞራ የኑስ በቅርቡ በ1991 ዓ.ም ከኤርትራ ጋር በተደረገው ጦርነት ገና አንድ ጥይት ሲተኮስ ከዛላንበሳ ግንባር ፍርጥጦ አዲግራት በመግባቱ የሚመራውን ክፍለ ጦር ሙሉ በሙሉ አስደምስሶታል፡፡

ሳሞራ የኑስ አሁንም ቢሆን እስከ ጀነራልነት ማዕረግ ደርሶ የመከላከያ ኤታማጆር ሹም ለመሆን የበቃው ለመለስ ዜናዊ ባለው ታማኝነት ብቻና ብቻ ነው፡፡በመሆኑም መለስና ተከታዪቹ በእነሱ ግምት ለወደፊቱ የስልጣን ህልውናቸው ስጋት የሚደቅኑ አባላትን በማስረሸን ያስወገዷቸው በሳሞራ የኑስ አማካኝነት ነው፡፡ ሀየሎም አርአያን ጨምሮ፡፡
ሱዳናዊው ሳሞራ፤ ኤርትራ ሳህል ከርከበት የተወለደው ሳሞራ፤ ዘንባባና አከት ከጫካ እየለቀሙ የሚሸጡ እጅግ በጣም ችግረኛ ወላጆች ስለነበሩት አንድ ቀን ጠግቦ በልቶ የማያውቀው ሳሞራ፤ የአብረሃ ወአፀብሃ ዝነኛው ደድብ ተማሪና በህወሓት ውስጥ በፈሪነቱ ስሙ ገናና የሆነው ሳሞራ፤ የዛሬው የጦር ሳይንስ መሀይም የመጀመሪያው ጀነራል ሳሞራ የኑስ ከእግር ጥፍሩ እስከ ጭንቅላት ፀጉሩ ድረስ በወንጀል የጠለቀ ነው፡፡ ቂመኛ በመሆኑ ፈሪነቱን ሊያጋልጡ የሚሞክሩ በርካታ ታጋዮችን ጊዜ እየጠበቀ ሰበብ አስባብ በመፍጠር ረሽኗቸዋል፡፡

ሳሞራ የኑስ ሰነፍ፣ ፈሪና አድርባይ ብቻ ሳይሆን ሴሰኛም እንደሆነ ይነገራል፡፡ በበረሃ በርካታ የህወሓት ታጋይ የሆኑ ሴቶችን ድፍሯል፡፡ ይባስ ብሎ የተደፍሩት ሴቶች እንዳያጋልጡት ቀድሞ የፈጠራ ክስ በመመስረት ሐለዋ ወያኔ ወደተሰኝው አደገኛ እስር ቤት ይልካቸውና በዚያው ይረሸናሉ፡፡ ለአብነት ያክል በ1974 ዓ.ም ርግበ ሰለሞን እና ፀጌ ሰለሞን የተባሉትን ታላቅ እና ታናሽ እህትማማቾች በየተራ ካባለገ በኋላ ነውረኛ ተግባሩ ሊጋለጥበት ሲሆን “ሁለቱ ሴቶች አደገኛ ህንፍሽፍሾች ናቸው” በማለት ወደ ፃኢ ሀለዋ ወያኔ ልኳቸዋል፡፡ ከዚያም ጉዳዩ ወደስብሃት ነጋ ተላልፎ ስብሃት ነጋ ሁለቱን እህትማማች ሴቶች አንድ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ተጋድመው በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ አድርጓል፡፡

ሳሞራ የኑስ ዛሬም የመኪናውን የሰሌዳ ቁጥር በጥቁር ፕላስተር እየለጠፈ በየሴተኛ አዳሪዎች ቤት እንደሚልከሰከስ ብዙዎቹ ይመሰክራሉ፡፡

ይህ መረጃ የተገኘው ከአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ነው::

የማለዳ ወግ …የፍልስጥኤም ጥቃት ከጥይት ወደ እሳት! – (ነቢዩ ሲራክ)

$
0
0

palastine

* በእሳት የገደሉት የፍልስጥኤም ብላቴ … !
* የሰው ልጅን ክብር ከእንስሳ ያሳነሱት የመገናኛ ብዙሃን !

በሀገረ ፍልስጥኤም ሁለት አመት ያልሞላው ህጻን በጽንፈኛ የእስራኤል ሰፋሪዎች የግፍ ጥቃት በቤቱ ውስጥ ተቃጥሎ ሞቷል frown emoticon ትናንት አርብ ንጋት ላይ ነው ይህ የሆነው … በፍልስጥኤም ናብሎስ ዱማ መንደር አጠገብ በሚገኙ አንድ የቤተሰብ አባላት ሀገር ሰላም ብለው እንቅልፋቸውን በተኙበት ጽንፈኛ እስራኤላውያን የፍልስጥኤማውያኑን ቤት መስኮት በኃይል ሰብረው ወደ ውስጥ ተቀጣታይ ቦንብ ወረወሩ … መላው ቤተሰብ ከእሳቱ ለማምለጥ ጨርቅ ማቄን ሳይል ቤቱን ጥለው ሸሹ … መሮጥ መሸሸት ያልቻለውን የ 18 ወሩን ብላቴና የአሊ ሰአይ ደዋባሽ አባት ልጃቸው ሊያድኑ ቢታገሉም አልተቻላቸውም ፣ አባት ባሉበት ልጃቸው ማዳን ሳይችሉ ቀረና በእሳት ተቃጥሎ ብላቴና ልጃቸውን በሞተ ተነጠቁ … ህጻን ብላቴና ገዳይ ጽንፈኛ እስራኤላውያን አቃጥለው ሲሔዱ ለማጥቃታቸው ምክንያት ” በቀል ” መሆኑን ታብየው በፍልስጥኤማውያኑ መኖሪያ ግድግዳ ላይ ጽፈው የሄዱት መልዕክት ያስረዳል … !

ህዝቡ ከጫፍ እስከጫፍ ተቆጥቷል ፣ ፕሬዘደንት አባስም ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁም ጥቃቱን አወገዝነው እያሉን ነው! በድርጊቱ የተቆጡ ታጣቂዎች ለተዘነዘረው የግፍ ጥቃት በቀላቸው ሚሳኤል ወንጭፈው ቀጣዩን የደም መፋሰስ ገና ባይጀምሩትም ፍልስጥማውያን የጎዳና ላይ አመጹን ጀምረዋል …

ፍልስጥኤምና እስራኤላውያን ሰላም የላቸውም ። በሁሉም ሁከት የጥቃቱ ሰለባ ፍልስጥኤማውያን መሆናቸው አያከራክርም ። ሰበቡ የህዝቤን በቀል እመልሳለሁ ባዮች የፍልስጥኤም ሃማስና ሸማቂዎች ናቸው እየተባለ አምናም ፣ ካችማናም ብቻ በማይባል ለግማሽ ክፍለ ዘመን በተጠጋ በሁከት እየተፈጁ ውስጥ ነው እያለፉ ነው ያሉት ! የሚገርመው ትናንትም ዛሬም አለም ይህን መሰል ግፍ እያየ ከንፈር በመምጠጥ ዝም ብሎ እያለፈው ነው …

palstime

የሰው ልጅን ክብር ከእንስሳ ያሳነሱት የመገናኛ ብዙሃን ሚዛናዊነት ፣ ግልጽነትና ዲሞክራሲያዊ ነጻ የመጻፍ መናገርን መብይ የሚያቀነቅኑት የአለም ታዋቂ የመገናኛ ብዙሃንም ቢሆን በፍልስጥኤም ላይ የዝሆን ጀሮ ይስጠን ካሉ ቆይተዋል ። አልፎ አልፎ ብልጭ አድርገው ድርግም የሚያደርጉት መረጃ ባይጠፋም የሰውን ልጅ በግፍ የተሞላ ግድያ እንደ ሚዛናዊ ተቋም ሰፊ ቦታ ሰጥተውት አይስተዋልም ! በያዝነው ሳምንት አንድ ታዋቂ የአፍሪካ አንበሳ በአዳኝ ተገደለ የተባለውን ያህል የፍ ስጥኤሙን ብላቴና በእሳት ተቃጥሎ መገደል የግፍ ግፍያ እንደ አንበሳው አላራገቡትም ! እጅግ በጣም ያሳፍራል ፣ እጅግ በጣም ያማል … የሰው ልጅን ክብር ከእንስሳ ያሳነሱት የመገናኛ ብዙሃን ዛሬም የሚታመኑ የሚሰሩት ለጉልበተኞች መሆኑ ከምንም በላይ ገሀድ እያየነው ነው !

በፍልስጥኤማውያን ላይ በሁሉም አቅጣጫ እንዲህ ግፍ ይፈጸማል ! ፍልስጥኤማውያን ይህ መሰል ግፉ አስመርሯቸው ጠመንጃ አንስተው ሲዋጉ ፣ ቦምብ ታጥቀው ሲያፈነዱ ፣ ሚሳየል ሰርተው ሲያስወነጭፉ ደግሞ ቀድመን በማውገዝ የሚቀድመን የለም ! በአለም ፍትህ ጠፍቷል … የሞተውንና የሚሞቱትን ነፍስ ይማር frown emoticon ፍልስጥኤም እንደ አለም የቀረው ዜጋ የማይገፉባት ሀገርን ይዘው የማይበት ጊዜ ናፍቆኛል ! ፍትህ ፍትህ ለጎደለባቸው ለግፉዘን ሁሉ !
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ሀምሌ 25 ቀን 2007 ዓም

የሕወሓት መንግስት በርካታ ወጣቶችን ከአዲስ አበባ አፍሶ መውሰዱ ተዘገበ

$
0
0

afesa

afesa 2
(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን እና በደቡብ በተከፈተበት ወታደራዊ ጥቃት ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ የገባው የሕወሓት መንግስት ከትናንት ማማሻውን ጀምሮ በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ወጣቶችን ሲያፍስ መዋሉ ተዘገበ::

ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ከ4 ሺህ የማያንሱ የአዲስ አበባ ወጣቶች በትናንትናው እና በዛሬው ዕለት ታፍሰዋል:: አንዳንድ የዜና ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንደሚገልጹት ከሆነ የታፈሱት ወጣቶች በአብዛኛው ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ የተባሉት ናቸው:: በተለይም የአርበኞች ግንቦት 7ን ጥቃት ተከትሎ እነዚሁ ወጣቶች በአዲስ አበባ ከተማ ለለውጥ ሊነሱ ይችላሉ በሚል ስጋት ይህ አፈሳ እንደተካሄደ ይነገራል::

እነዚህ ወጣቶች መገናኛ አካባቢ የሚገኝ አንድ ትልቅ ስፍራ ውስጥ ታጉረው ከቆዩ በኋላ ወደ አልታወቀ ስፍራ በአውቶቡሶች ተጭነው መወሰዳቸውን የጠቆሙት የዜና ምንጮች ወደየት እንደተወሰዱ ለማረጋገጥ እንዳልቻሉ ገልጸዋል::

«ከመጥረቢያ ብረት የተሰራ ጦር ወደ አቡጀዲ ቢወረውሩት ወደ ጉቶ ይሄዳል» –ይገረም አለሙ

$
0
0

Commentይህ በርዕስነት የተጠቀምኩበት አባባል በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፋል ሸካ ዞን በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የሚነገር ነው፡፡አባባሉ በአካባቢው ቋንቋ ሲነገር ለጆሮ ይጥማል፣ቀልብ ይስባል፣እንዲህ ወደ አማርኛ ተመልሶም ቢሆን መልእክቱ ግልጽና በቀላሉ ለመረዳት የማያስቸግር ነው፡

ተፈጥሮው ሆኖበት እንጂ የሚቀለው አቡጀዲው ነበር፣ ጉቶው ግን ከባድ ነው፣ እንደውም የጦሩን ጫፍ ሊያጥፈው ሲብስም ሊሰብረው ይችላል፡ነገር ግን ጦሩ የተሰራው ከመጥረቢያ ብረት ሆነና መጥረቢያው ደግሞ ተፈጥሮውም ለጉቶ መፍለጥ፣ የኖረውም ከጉቶ ጋር ሲታገል በመሆኑ አቡጀዲውን አያውቀውምና ወደ ለመደው ግን ጠንካራና አስቸገሪ ወደ ሆነው ጉቶ መሄዱን ነው የሚመርጠው፡፡

የህውኃት መስራቾች ለሥልጣን ሲሉ ጫካ መግባታቸውን ብሶት የወለደን በሚል ማስመሰያ ጋርደው ዱር ገደሉን መኖሪያቸው አድርገው፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻቸውን ገድለው፣ በዛው መጠን የትግል ጓዶቻቸውን ካጠገባቸው አጥተው ለሥልጣን የበቁ በመሆኑ ሰላማዊ ትግል ብሎ ነገር አያውቁም፤ በልዩነት ተከባብሮ መኖርንም ሆነ የዓላማም ሆነ የአደረጃጅት ልዩነት ካላቸው ጋር ውይይት ብሎ ነገር አያስቡትም፤ከፖለቲካ አመለካከት ልዩነት በላይ የአንድ ሀገር ልጅነት ሚዛን የሚደፋ መሆኑ አይገባቸውም፡፡ ከመጥረቢያ ብረት የተሰራው ጦር ወደ ቀላሉ አቡጀዲ ሲወረወር ወደ ጠንካራው ጉቶ እንደሚሄደው ሁሉ ወያኔዎችም የህይወት ጥፋት፣ የሀገር ሀብት ውድመት፣ የትውልድ ተወቃሽነት፣ የህግና የታሪክ ተጠያቂነት በማያስከትለው የሰላማዊ ትግል መንገድ የሰለጠነ ፖለቲካ እናራምድ ሲባሉ እነርሱ የሚታያቸው ትናንት ለቤተ መንግሥት ዛሬ ለከበርቴነት ያበቃቸውና 24 ዓመት በሥልጣን የቆዩበት  የሀይሉ/የጡንቻው መንገድ ነው፡፡

ተፈጥሮአቸው ይህ በመሆኑም  ነው ስለ ሰላም የሚያዜሙትን፣ ሰላማዊ ትግል መርሀችን ብቻ ሳይሆን እምነታችን ነው ብለው ሁሉን ችለው የሚንፈራገጡትን፤ህገ መንግሥቱን መሰረት አድርገውና በቃል የሚነገረውን ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ተማምነው ብዕራቸውን ለዴሞክራሲ ምስረታ ዘብ ያቆሙትን ወዘተ  ጸረ ሰላም፣ አሸባሪ፤ወዘተ በማለት መወንጀልና ማሰርን ስራቸው ያደርጉት፡፡

ዝናር ታጥቀው፣ ጠብ-መንጅ አንግበው ከደደቢት በረሀ እስከ ምኒልክ ቤተ መንግሥት የደረሱት ነባር ታጋዮች መተካካት እያሉ እንዳንድ ጠብ-መንጃ ያልጨበጡ አዳዲሶችን ቢያሳዩንም የሚተኩት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ዶክትሪን ታንጸውና በህውኃት ጸበል ተጠምቀው በመሆኑ ራሳቸው ይለወጣሉ አንጂ ወያኔን አይለውጡትም፡፡ ስለሆነም የመጥረቢያው ብረት ወደ ጦር በመቀየሩ ተፈጥሮውን ሊተው እንዳልቻለው ሁሉ ከጫካ ሳይሆን ከከተማ የተገኙ አንዳንድ ሰዎች በወያኔ ውስጥ መታየት ወያኔ የተወለደበትንና ያደገበትን ማንነቱን ሊለውጠው አልቻልም፡፡

ተፈጥሮ በተመክሮም በተሞክሮም የሚለወጥ ባለመሆኑ ስለ ምርጫ እያወሩ ደም ገብረን ያገኘነውን ሥልጣን በስመ ዴሞክራሲ በምርጫ መንጠቅ ያምራችኋል ወይ ይላሉ፡፡ ስለ ዴሞክራሲ ሲነገር ስለአንባገነንት ያስባሉ፡፡ስለ መድብለ ፓርቲ እየደሰኮሩ ስለ አውራ ፓርቲ ይዘምራሉ፡፡ ስለ ሰላም እያወሩ ወንድ ከሆናችሁ እንደኛ ታግላችሁ ኑ በማለት ይሳለቃሉ፡፡ ይህም በመሆኑ ነው አምስት ሀገራዊ ምርጫዎች ተካሂደው ለውጥ ሊታይ ቀርቶ አንዳቸውም ምርጫዎች በተወዳዳሪ ፓርቲዎች ስምምነት፤ በህዝብ ዘንድ ተአማኒነት በአለም አቀፉ ማህበረሰብም ተቀባይነት ሊያገኙ ያልቻሉት፡፡

ስብሰባ፣ግምገማ፣ ወርክ ሾፕ፣ሥልጠና፣የአቅም ግንባታ ወዘተ የወያኔ የእለት ተእለት ሥራ ቢሆንም ተፈጥሮ በስር ነቀል ለውጥ እንጂ በእነዚህ የሚሻሻል ባለመሆኑ ነው ወያኔ የደደቢቱና ወያኔ የቤተ መንግሥቱ ምንም ልዩነት የሌላቸው ሆነው የሰላሙን መንገድ ሲያሳዩዋቸው የጦርነቱ መንገድ የሚታያቸው፡፡

ወደ አቡጀዲ ሲወረውሩት ወደ ጉቶ የሚምዘገዘገው ጦር ተምሳሌት የሚመለከተው ወያኔን ብቻ አይደለም፡፡ በተቃውሞው ጎራ ተሰልፈው፤ ተባበርን ባሉ ማግስት መለያታቸውን የሚያውጁ፣ ፍቅር ሲሉዋቸው ጸብ የሚያነፈንፉ፤ከመከባበር መናቆር የሚቀናቸው፤በተግባሩ ሳይሆን በመፎከሩ ቀዳሚ የሌላቸው ወዘተ እነርሱም ተፈጥሮአቸው ሆኖ ነው ጥሩውን ሲሉዋቸው መጥፎውን መምረጣቸው፡፡

ደግሞ አንዳንዶች አሉ ተፈጥሮአቸውም ሆነ እድገታቸው መቃወም ብቻ ሆኖ ለድጋፍ ሲያስቡዋቸው ለትብብር ሲጠሩዋቸው ምክር ሲጠይቋቸው ምላሻቸው ተቃውሞ፣ማጥላላት ማንኳሰስ ይሆነ፡፡ ጸባያቸው ታውቆ ሲተዉ ደግሞ እኛ የለለንበት በማለት ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉ፡፡ እንዲህም ሆነና ለውጥ እንደናፈቀን፣ዴሞክራሲ እንዳማረን ኖረን እኛ ወደማንወደው ለወያኔ ግን ተፈጥሮው ወደ ሆነው ጦርነት ማምራት ግድ ሆነ፡፡ ብእር ሊጨብጡ የሚገባቸው እጆች ጠመንጃ ለመያዝ ተገደዱ፡፡ ስንት የሰሩና ወደ ፊትም ብዙ ሊሰሩ የሚችሉ ሰዎች ያለ ተፈጥሮአቸው፤ያለ ልምድና ፍላጎታቸው ዱር ቤቴ ለማለት ተገደዱ፡፡

ፍላጎት ዓላማችን ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ማንሳት ብቻ ሳይሆን እየተረገዘ የሚጨነግፈው ዴሞክራሲ ለውልደትና ለእድገት እንዲበቃና ደራሲ አያልነህ ሙላቱ በአንድ ተውኔቱ እንደገለጸው በጋሜ የቀረችው ኢትዮጵያ ሹርባ ተሰርታ ማየት ከሆነ በሁሉም ዘንድ መሰረታዊ የሆነ ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ እስካሁን የመጣንበት መንገድ ወደ ድል ጎዳና አላመራንም፡፡በተፈጥሮም ይሁን በተሞክሮ ያዳበርነው አስተሳሰብ ለለውጥ አላበቃንም እናም ¾አሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት አብርሀም ሊንከን የተናገሩት ተብሎ የሚጠቀሰው ይህ ዘመን የማያደበዝዘው አባባል ምክር የሚሆን ይመስለኛል፡፡

«አንድ ትውልድ ያልፍና ሌላ ትወልድ ይተካል፣ ዓለም/መሬት ግን ለዘለአለም ትኖራለች፡፡ ጸጥ ረጭ ያለው ያለፈው ግዜ ፍልሰፍናዎች (ዶግማስ) አውሎ ነፋሳዊ ለሆነው ለዛሬው ችግር ለመፍትሄነት አይመጥኑም፡፡ ጊዜያችን ችግር ያዘለ ስለሆነ በአዲስ ሁኔታ ማሰብና በአዲስ ሁኔታም መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ራሳችንን ከሰቀልንበት ከፍታ ማውረድ ይገባል፡፡ ያን ግዜ አገራችንን ለማዳን እንችላለን፡፡ ታሪክን ልናመልጥ አንችልም፣ልንሸሸው አይሆንልንም፣ ክፉም ሰራን ደግ እንዘከራለን፣ (እንታወሳለን) ግለሰባዊ መታወቅ ወይም አለመታወቅ አንዳችንንም ሆነ ሁላችንን አያተርፈንም፣የምናልፍበት እሳታዊ ፈተና (ፍርድ) በክብር ወይንም በውርደት ማለፋችንን ይመሰክራል»

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live