Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ጆን ዶ የተሰኘው ኢትዮጵያዊ አማሪካዊና እና የኢትዮጵያ መንግስት በዲሲ ፍርድ ቤት

$
0
0

ቢላል አበጋዝ

ጁላይ 13፡2015

justiceዛሬ በዲትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ በዋለው ችሎት ጆን ዶ የተሰኘው ኢትዮጵያዊ አማሪካዊና እና የኢትዮጵያ መንግስት ጠበቆች ቀርበው ሁለቱም ወገኖች ዳኛው ፊት ቃላቸውን ሰጥተዋል።ጆን ዶ የተሰኘው ኢትዮጵያዊ አማሪካዊ የተሰጠው ስም (ጆን ዶ)  ይህ ስያሜ ስማቸው በግልጽ መገለጥ ለሌለባቸው ሰዎች በጅምላ የሚሰጥ ነው።ጆን ዶ ተብሎ መቅረቡ የክሱ መስራች የኢትዮጵያ መንግስት ወይም ወኪሎቹ ይህን ዜጋ ለይተው እንዳያጠቁት በሚል ወይም ስሜ ቢጠቀስ ጉዳት ያገኘኛል ከሚለው ስጋት ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት  ያቆማቸው ጠበቃ ግሪንበርግ ቱሪግ (Greenberg Traurig LLP)ለተባለ እዚህ ዋሽግቶን ዲሲ ለሚገኝ የጥብቅና ተቋም ሰራተኛ ናቸው።ኢትዮጵያዊ አማሪካዊውን ግለሰብ የወከሉት ኤሌክትሮኒ ፍሮንቲር ፋውዴሽ ከተሰኘ ድርጅት የቀረቡ ጠበቆች ነበሩ (Electronic Frontier Foundation) ዋና ድሬክተርዋ ሲንዲ ኮህን የተባሉ ሲሆኑ “ነጻነትና የሰው መብት ሲደፈር ፈጥነው የሚክላከሉ” በማለት ብሄራዊ የአማሪካ ጠበቆች መጻሄት( National Law Journal)ያደነቃቸው ናቸው።በእለቱ የኢትዮጵያዊ አማሪካዊውን ጉዳይ ያቀረበው ናታን ካርዶዞ የተባለው የዚሁ ድርጅት ጠበቃ ነበር።

ክሱ የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያዊ አማሪካዊው ላይ ያደረገው ህገወጥ ድርጊት የኮምፑተር ቫይረስ በመላክ ሰርስሮ በድብቅ ተኮምፑተር ገብቶ ቫይረሱ በኮምፑተሩ ይቀበርና ስለላን ለማካሄድ የሚያስችል የተንል መሳሪያ በተግባር ላይ ማዋል ነው።ይህን ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት የተለያዩ ኩባንያዎችን ተጠቅሟል። ወያኔ ዳቪድ ቪንቼንዜቲ በተባለ ጣሊያናዊ የሚመራ ሰርሳሪ ቡድን (The Hacking Team) የተባለ ኩባንያንም ተጠቅሟል።ኩባንያው ሚላኖ ኢጣሊያ የሚገኝ ነው።አገልግሎቱን ለሱዳን ሞሮኮ ግብጽ ከኢትዮጵያ ሌላ የሰጠ ሲሆን ስለ ኢትዮጵያ ሲጠየቅ ክዷል። ጋርዲያ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው።

በአማሪካን አገር ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የግለሰቡ መብት በመንግስት አካላት አይደፈርም። ያገሩ መንግስት ያልደፈረውን ህወሃት መሩ መንግስት ተዳፍሯል በማለት የከሳሽ ጠበቃ ሲናገር የተከሳሽ ጠበቃ ድርጊቱ እዚህ አማሪካ አልተፈጸመም የሚል ክርክር ዳጋግሞ አቅርቧል። ቀድሞ ባአማሪካ ዜጎች ላይ ተደርገው ነበር የሚላቸውን ክሶች አጣቅሷል። የከሳሽ ጠበቃ ህገ መንግስታዊ መርሆዎችን፡ስለላ የማካሄድን (መንግስት ከፍርድ ቤት አስፈቅዶ) ስለላው እዲደረግ ገፊ ምክንያቶችን ሁሉ የሚነካ ጉዳይ መሆኑን አስዘግቧል። ፍርድ ቤቱ የሚደርስበት ውሳኔ የህወሃት መሩ መንግስትን ተረቺ ካደረገ ይላል ጠበቃው የአሜሪካንን የስለላ ተቋማትን ሳያሳስብ አይቀርም። ለአጃዚራ እንደሰጠው ቃል።

እንደሚታወሰው ህወሃት መሩ መንግስት ይህኑ የስለላ ተግባር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ንዋይ አፍስሶ እነ እስክንድር ነጋ ላይ “መረጃ” አቀረብሁ ማለቱ ይታወሳል።መእራባውያን መንግስታት አይቶ እንዳላየ የሚሆኑት ዛሬ ህወሃት መሩ መንግስት በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ምእራቡን የሚያሳስበውን ሽብርተኝነት ለመዋጋት እንዳአጋር በመወሰዱ ነው።

ህወሃት መሩ መንግስት ልማት ሊያራምድ የሚችሉትን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በተግባር ለማዋል ቀርቶ ለስለላው መሽቀዳደሙ የመንግስቱ እኩይ ባህሪ ግፊት መሆኑን ከፍርድ ቤቱ መጥተው የታዘቡ ተናግረዋል።

በፍርድ ቤቱ የዲሲ ሜትሮ ነዋሪዎች፡የኢሳትና የቪኦኤ ጋዜጠኛች፡የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተገኝተው ነበር።


ፌደራል ፖሊስ ባራክ ኦባማ ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተዘጋጅተው ነበር ያላቸውን አሰረ * በክሱ ውስጥ ጋዜጠኛ ይገኛል

$
0
0

Habtamu

by Dawit Solomon
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት ሰርግና ምላሽ በኢትዮጵያ ከወዲሁ የተወሰኑ እስረኞችና በመፍታትና ብዛት ያላቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን በማሰር ወደ ቀኑ እየገሰገሰ ይገኛል፡፡የሰማያዊና የቀድሞው አንደነት አመራሮችና አባላት ኦባማ ወደ አገራችን ሲመጡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እያሴራችሁ እንደሆነ ደርሰንበታል በማለት ለእስር ተዳርገዋል፡፡

ባሳለፍነው ሐሙስ የሞያ አጋሮቹ መፈተታት የፈጠረበትን ደስታ አጣጥሞ ሳይጨርስ በቁጥጥር ስር የዋለው ጋዜጠኛ ሐብታሙ ምናለ ከአምስት ቀናት የእስር ቤት ቆይታ በኋላ ዝግ ችሎት ተሰይሞ በፖሊስ የ15 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተጠይቆበት ያቀረበው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎበት ወደ እስር ቤት እንዲመለስ መደረጉ አይዘነጋም፡፡


የአንድ ሳምንት የህትመት ብርሃን ካየች በኋላ በስርዓቱ ስልታዊ አፈና ዕድሜዋ እንዲቀጭ የተደረገችውን ‹‹ቀዳሚ ገጽ››ጋዜጣ በስራ አስኪያጅነት የመራት ሐብታሙ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ››ጋዜጣ ላይ በሪፖርተርነት ሰርቷል፡፡አስቂኙ የእስር ክስ እንደቀረበበት ከመደመጡ አስቀድሞም ‹‹ለጥያቄ እንፈልግሃለን››ባሉት ደህንነቶች ተይዞ ቃሉን እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ መለቀቁ ይታወሳል፡፡


የሞያ አጋራቸው ከታሰረበት ዕለት አንስቶ የእስሩን ምክንያት ለማወቅ ሲታትሩ የነበሩት ጋዜጠኞች ኤልያስ ገብሩና ኢዮኤል ፍስሐ ለማመን የከበዳቸውን የፈጠራ ክስ ከራሱ ከሐብታሙ አንደበት አዳምጠው ተመልሰዋል፡፡ሐብታሙ ‹‹የአልሻባብ የሽብር ቡድን አባል በመሆን የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ጥቃት ለመፈጸም ስትንቀሳቀስ ነበር››መባሉን ነግሯቸዋል፡፡


የፈጠራ ክስ በገዛ ዜጎቹ ላይ በማቅረብና በማስወንጀል የዳበረ ሪከርድ ያለው የፌደራሉ ፖሊስ ጋዜጠኛውን ለሽብር ድርጊቱ ተዘጋጅተው ያዝኳቸው ካላቸው 44 ተጠርጣሪዎች ጋር በአንድ መዝገብ ማቅረቡም ነገሩን አሳዛኝም አሳፋሪም ያደርገዋል፡፡ከተጠርጣሪዎቹም መካከልም የሶሪያና ሶማሌያዊ ዜግነት ያላቸው ስዊዲናዊያን እንደሚገኙበት ኦባማ ላይ ጥቃት ለማድረስ አሴረሃል የተባለው ሐብታሙ ተናግሯል፡፡

ሰቆቃ በማዕከላዊ

$
0
0

Nail

‹‹እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡››

አበበ ካሴ
እኔ አበበ ካሴ እባላለሁ፡፡ የሰሜን ጎንደር ተወላጅ ነኝ፡፡ በማዕከላዊ እስር ቤት ከ5 ወር በላይ ታስሬለሁ፡፡ ከዚህ መካከል 4 ወር ከ25 ቀናት በጨለማ ቤት ተቆልፎብኝ ቆይቻለሁ፡፡ ማዕከላዊ በነበርኩበት ወቅት የሁሉም እግርና እጆቼ ጥፍሮች ተነቅለዋል፡፡ አንዳንድ ቀን እጄ ላይ የሆነ ነገር ስለሚወጉኝ ጥፍሮቼ ሲነቀሉ አላውቅም፡፡ ስነቃ ነው መነቀላቸውን የማውቀው፡፡ ከዛም ቁስሉን እየነካኩ ያሰቃዩኛል፡፡ ማደንዛዣ ለምን እንደሚወጉኝ አላውቅም፡፡ ጥፍሮቼን ሲነቅሉኝ ብቻ ሳይሆን ሌላ ጊዜም ራሴን እንድስት ያደርጉኛል፡፡ እጅና እግሬን አስረው እንደ ፍሪጅ ያለ እቃ ውስጥ ያለ በረዶ ውስጥ ያስቆሙኛል፡፡ ለብዙ ሰዓት በጣም ቀዝቃዛ የሆነ ቦታ ላይ እስክደነዝዝ ቆሜ እውላለሁ፡፡ እስኪበቃቸው ከደበደቡ በኋላ እጅና እግሬን አስረው ከምርመራ ክፍሉ በታች በሚገኝ ምድር ቤት ክፍል ውስጥ ያለ ጉድጓድ ላይ ጥለውኝ ይሄዳሉ፡፡ ጉድጓዱ ጉንዳንን ጨምሮ ተባዮች ያሉት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እግሬንና እጄን አስረው ዘቅዝቀውኝ ይሄዳሉ፡፡ የመጣው ሁሉ ዝዋዥዌ እንደሚጫወት ህፃን ወዲያና ወዲህ ያደርገኛል፡፡ ገልብጠው አስረው ሲዘቀዝቁኝ በአብዛኛው ራሴን እስታለሁ፡፡ እግርና እጄን ከወንበር ጋር ያስሩኛል፡፡

ከወንዶች በተጨማሪ ሴቶችም ይመረምሩኛል፡፡ ሴቶቹ የሚመረምሩኝ ራቁቴን አርገው ነው፡፡ እነሱም ራቁታቸውን ሆነው ነው የሚመረምሩኝ፡፡ አሁን ለመናገር የማልደፈርው አፀያፊ ነገርም ፈፅመውብኛል፡፡ ይህን አፀያፊ ነገር የሚፈፅሙት አደንዛዥ እፅ እየተጠቀሙ ነው፡፡ ይህን ሲያደርጉ በአይኔ አይቻቸዋለሁ፡፡ መርማሪዎቹ ሰውነቴን በኤሌክትሪክ አቃጥለውኛል፡፡ ኤሌክትሪኩን የሚሰኩት ደረቴና የውስጥ እግሬ ላይ ነው፡፡ በዚህም የውስጥ እግሬ ተገልብጦ ሌላ ሰውነት አምጥቶ ነበር፡፡ እጄን ወደ ላይ አስረው ብልቴ ላይ ሀይላንድ አንጠልጥለውበታል፡፡ ሴቶቹ ሀይላንዱን የሚበቃቸውን ያህል ያወዛውዙታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ የዘር ፍሬየን ከጥቅም ውጭ አድርገው ዘሬን እንዳልተካ አድርገውኛል፡፡ ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም፡፡ ይህን ያህል አሰቃይተው ከጥቅም ውጭ ስሆን ቂሊንጦ አምጥተው ጣሉኝ፡፡ 11 ወር ያህል አልጋ ላይ ነበርኩ፡፡ በኤሌክትሪክ ግርፊያው ምክንያት ግራ ሰውነቴ ሽብ ሆኖ ነበር፡፡ ግራ እግሬ መንቀሳቀስ አይችልም ነበር፡፡ በምርኩዝ ነበር የምሄደው፡፡ አሁን እያነከስኩ ነው የምሄደው፡፡

በተለይ ማዕከላዊ ውስጥ ይህን ያህል የሚሰቃዩኝ አንደኛ የሚያግዛችሁ አገር ማን ነው በሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አማራ ክልል ውስጥ እንድትንቀሳቀሱ የሚተባበሯችሁን የብአዴን ባለስልጣናት ስም ተናገር እያሉ ነው፡፡ በሶስተኛ ደረጃ የሚያሰቃዩኝ የት የት ቦታ ነው የሰለጠንከው እያሉ ነው፡፡
እዚህ ቂሊንጦ ከመጣሁ በኋላም ያሰቃዩኛል፡፡ ወጣቶች እንዳይቀርቡኝ ያስፈራሩዋቸዋል፡፡ ማንም ጠርቶ እንዳይጠይቀኝ እየተደረገ ነው፡፡ ጨለማ ክፍል ወስደውም አስረውኝ ያውቃሉ፡፡ እነሱ ደብድበው ከጥቅም ውጭ ካደረጉኝ በኋላ የምደገፍበትን ምርኩዝም ቀምተውኛል፡፡ ‹‹ይህኮ የጦር መሳሪያ አይደለም፡፡ እንጨት ነው፡፡ ለምን ትቀሙኛላችሁ? ደግሞም እናንተ ናችሁ እንዲህ ያደረጋችሁኝ፡፡›› ብያቸው ነበር፡፡ የሚሰሙ ሰዎች አይደሉም፡፡ የታሰርኩበት ክፍል ውስጥ እንድተኛበት የተሰጠኝ ቦታ ሽንት ቤቱ አጠገብ ነው፡፡ ሽንት እየሸተተኝ ነው የምተኝው፡፡ ‹‹ወደ ሌላ ቦታ ቀይሩኝ!›› ስላቸው ‹‹ደግሞ ለአንተ ይህ አንሶህ ነው?›› ይሉኛል፡፡ ያ ሁሉ ድብደባ ደርሶብኝ አልጋ ላይ በነበርኩበት ወቅት ወጣቶቹ ህክምና እንዳገኝ ወደ ሀኪም ቤቱ ወሰዱኝ፡፡ እነሱ ግን ‹‹ለአንተ ህክምና ሳይሆን ጥይት ነበር የሚገባህ›› ብለው መለሱኝ፡፡ እንዲህ እያሉ ለምን እንደማይገድሉኝ ይገርመኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ልጆችዋ ለእልቂት፣ ለስደት፣ ለግድያ እየተዳረጉ ነው፡፡ በአካልም ሆነ በስነ ልቦና ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ዓለም ለሰው ልጅ ምቹ በሆነችት ከዓለም ውጭ ሆነናል፡፡ የመገናር፣ የመሰብሰብ፣ የመደራጀት በአጠቃላይ ሰው የሚያደርጉንን መብቶች ተነጥቀናል፡፡ ከሰው የማንቆጠርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ገዥዎቻችን ህዝብን እየገደሉና ከሰው በታች አድርገው እየገዙም ቢሆን ግን ዓለምን እያታለሉ ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ሁሉ የሚደረገው የአንድን ቡድን የበላይነት ለማስፈን መሆኑ ነው፡፡ እንዲጠፋ ሆን ተብሎ ጥቃት የሚደርስበት ህዝብም እንዳለ እያየን ነው፡፡ ግን ኢትዮጵያ የ95 ሚሊዮን ህዝን ሀገር ናት፡፡

አሁን ያለው ስርዓት የአንድ ቡድን ስርዓት ነው፡፡ ለእሱ መኖር ደግሞ ሌሎቹን ገድሎ፣ አሰቃይቶ፣ አሳድዶ መኖር ይፈልጋል፡፡ ለስሙ የብሄር ብሄረሰብ መብት እናከብራለን ቢባልም እውነቱ ግን ኢትዮጵያውያን የመናገር፣ የመፃፍ፣ የመደራጀትና ሌሎች መብቶችን ተነፍጎ ከሰውነት ወጥተው ይገኛሉ፡፡ በዓለም ደረጃ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ቋንቋና ዘርን አይለይም፡፡ ይህ የሚደረገው በህወሓት ስርዓት ብቻ ነው፡፡ እኔ በርካታ ሰቆቃ የደረሰብኝ ሰው ስለሆንኩ ስርዓቱ የሚፈፅመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመመስከር እችላለሁ፡፡ እኔን ሰቆቃ ያደረሱብኝ ሰዎች ማንነታቸው መታወቅ ስላለባቸው እንደሚከተለው ስማቸውን እዘረዝራለሁ:-

1. አቶ አሸነፍ ተስፋሁን ላቀው
2. አቶ አብርሃም አይሸሽም
3. ሙሉጌታ ወርቁ
4. አቶ ደረሱ አያናው
5. የአማራ ክልል ደህንነት ኃላፊ የሆነው አቶ ተሾመ
6. የሰ/ጎ/መ/የታክቲክ ኃላፊ አቶ ሙላ እንየው
7. የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ተክላይ
8. የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ጌትነት
9. አቶ አሰፋ አትንኩት (ምርመራበ ኃላፊ)
10. መቶ አለቃ ተስፋዬ (መርማሪ)
11. ሳጅን ፍሬ ህይወት (መርማሪ)
12. ሳጅን ፅጌ (መርማሪ)

ከላይ የጠቀስኳቸውን በስምና በአካል የማውቃቸው ሲሆኑ ከእነዚህ በተጨማሪ ከደህንነት መስሪያ ቤቱ እየመጡ የሚያሰቃዩን ስማቸውን የማላስታውሳቸውና በመልክም የማውቃቸው የህወሓት ደህንነቶች አሉ፡፡

እዚህ እኛን እንደዚህ ሲያሰቃዩ ሀገሪቱን ገንዘብ መዝብረው የታሰሩ ሰዎች ምንም አይሆኑም፡፡ ተመችቷቸው ነው የሚኖሩት፡፡ ቂሊንጦ ውስጥ ሰው እንዳይቀርበኝም ቢፈልጉም ሰው ግን በጣም ይወደኛል፡፡ አሁን ጥፍሮቼ በቅለዋል፣ መራመድ ችያለሁ፡፡ አንድ ሽህ አመት አይኖርም፡፡ በጣም ብዙ ወገኖቻችን ሞተዋል፡፡ እኔ አለሁ፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ባለስልጣናት እኔ ላይ የደረሰውን ጨምሮ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ በፈፀሙት ወንጀል መጠየቃቸው የማይቀር ነው፡፡
ይህ ሁሉ በደል ደረሰብኝ ስል ዝም ብዬ አይደለም፡፡ ማንኛውም ሰው መጥቶ የተሸማቀቀውን እግሬን፣ ቅጥ ባጣ ድብደባ የተጎዳው ሰውነቴን ማየት ይቻላል፡፡ ጥፍሮቼንም ለመስክርነት ይዤያቸዋለሁ፡፡ እነሱ ነቅለው ጥለው ሲሄዱ እኔ ስነቃ ሰብስቤ አስቀምጣቸዋለሁ፡፡ የተወሰኑትን ለመረጃነት አስቀምጫቸዋለሁ፡፡ ይህን ስል ግን እኔ ላይ የደረሰው ስቃይም የማይጠበቅ ሆኖ አይደለም፡፡ እነዚህ ሰዎች እንኳንስ ግለሰብ ሀገርም ገንጥለዋል፡፡ ከ40 አመት በፊት የነበረው የኢትዮጵያ ካርታ ተሸርፏል፡፡ እንኳን ሰው ሀገርም ለማጥፋት እየሰሩ ነው፡፡ ታሪካቸው፣ አመጣጣቸውም የሚያሳየው ይህን ነው፡፡ ይህን ሁሉ የምለውም መታወቅ ስላለበት ነው፡፡

የአንዷለም አራጌ ሁለተኛው መጽሐፍ ‹‹የሀገር ፍቅር ዕዳ›› እተነበበ ነው

$
0
0

Yehager Fikir Idaየቀድሞው አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የነበረውና አገዛዙ ጥርስ ውስጥ በመግባቱ ‹‹ሽብርተኛ›› በመባል የእድሜ ልክ እስራት የተበየነበት ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ሁለተኛ የሆነውን የፖለቲካ መፅሐፍ ቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ አበርክቷል፡፡ ቁርጠኛና የፅናት ተምሳሌት እንደሆነ የሚነገርለት አንዷለም ከዚህ በፊት ‹‹ያልተሄደበት መንገድ›› የሚል መፅሐፍ ከታጨቁባት እንድ ክፍል ውስጥ ሆኖ በማይመች ሁኔታ እስረኞች ሲተኙና በብርድ ልብስ ተሸፍኖ በመፃፍ ለሕትመት አብቅቶ ከፍተኛ አድናቆትን ማትረፉ ይታወሳል፡፡

የፖለቲከኛው ሁለተኛ ስራ የሆነው ‹‹የሀገር ፍቅር ዕዳ – ከቀሳ፣ ጎንደር እስከ ቃሊቲ እስርቤት›› መፅሀፍ ከአያሌ ውጣውረድ በኋላ በትናንትናው እለት ገበያ ላይ ውሎ እየተነበበ መሆኑን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡

መፅሐፉ 400 ገፅ ያለው ሲሆን በ32 ምዕራፎች የተከፋፈለ ነው፡፡ ዋጋውም 100 ብር እንደሆ ገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ አንዷለም በግፍ የታሰረለት ፓርቲ አንድነት ለተላላኪዎች ተላልፎ ከተሰጠ በኋላም ያለምንም የሞራል መንገራገጭ መፅሀፍ ማበርከቱ ታላቅነቱን በድጋሚ ያስመሰከረ ምርጥ ሰው ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

አንዷለም ከመፅሐፉ መግቢያ ላይ ካሰፈረው ተቀንጭቦ የተወሰደውን ቀጥሎ እናቀርባለን፡-

ለምን ይህንን ፃፍኩ?

ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በአንድ ወቅት የሚከተለውን ብለው ነበር፡- ‹‹አንድ አቋም ለመያዝ በምንነሳበት ጊዜ፣ ‹ፍርሃት› ይህ አቋም ምን አይነት አደጋ ያስከትልብኝ ይሆን? የሚል ጥያቄን ይመዛል፤ ‹አዋጭነት› በሌላ ወገን ይህን አቋም መያዝ ምን ያህል ብልጠት የተሞላ ነው? ሲል ይጠይቃል፤ ‹ከንቱነት› በበኩሉ ይህን አቋም መያዝ ምን ያህል ዝነኛ ያደርገኛል? ይላል፤ ህሊና ግን ከሁሉም የተለየ ጥያቄን ያነሳል፤ ይህ አቋም ምን ያህል ትክክለኛ አቋም ነው ሲል ይጠይቃል›› እንዲህ ዓይነት ምናባዊ ምልልሶች በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው ለውጥ ለማምጣት በሚተጉ ግለሰቦች አይምሮ ውስጥ ተደጋግመው የሚሰሙ ድምፆች ይመስሉኛል፡፡ በተለይም ኢትዮጵያን በሚመስል የአምባገነንነት መናኸሪያ ሀገር በሰላማዊ ትግል የአገዛዝ ስርዓትን ወደ ዴሞክራሲ ለመለወጥ የሚታገሉ ዜጎች እለት እለት በህይወታቸው የሚያጋጥሟቸው ጥያቄዎች መሆናቸውን በጥሞና እገነዘባለሁ፡፡

የእነዚህና ሌሎች ጥያቄዎች ድምጽ ከመታሰሬ በፊትም ሆነ በኋላ እየተመላለሱ እረፍት ይነሱኛል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ ትግል ለመታገል የሚነሳ ዜጋ ሀገር መውደዱ በቀይ መስመሮች መዥጎርጎሩን ለማስተዋል የሚያስፈልገው የቆመበትን መሬት ብቻ ጎንበስ ብሎ ማየት ነው፡፡ በኢትዮጵያችን የሰላማዊ ትግል ቀጠና የፈንጅ ወረዳ ነው፡፡ አገዛዙ ‹‹ህጋዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ›› የሚል ባነር የሰቀለበት ነገርግን በየእርምጃዎ ርቀት ፈንጅ የሰገሰገበት የፖሊቲካ መልክዓ ምድር ነው፡፡ በዚህ ቀጠና ውስጥ በተለይ ጎላ ያለ እንቅስቃሴ ሲደረግ ዶ/ር ኪንግ ያነሷቸው ጥያቄዎች መልስ ፍጥነት ይጨምራል፡፡

አቋምዎ ከእውነት ጋር በጽናት መቆም ከሆነ ቀጥለው የሚያስቡት፣ በህይወት ከቆዩ በሚያልፉበት የመከራ ሸለቆ ውስጥ ጉልበት የሚሰጥዎትንና ከግራ መጋባር የሚታደግዎትን ሀሳቦች ቀድመው ይዘጋጁባቸዋል፡፡ እኔም በትንሹ ከመታሰሬ ሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ከአገዛዙ ባህሪ አንፃር አሁን እያለፍኩበት ያለው ሁኔታ እንደሚፈጠር ለአፍታ ተጠራጥሬ አላውቅም፡፡ በተያዝኩባት ቅጽበት እንኳን ከጓደኛዬ በላይ ፈቃዱ ጋር እናወራ የነበረው ይኽንኑ ነው፡፡ ልክ በዚህ ጉዳይ ላይ እያወራን የመኪናው መስኮት ተንኳኳና ወደ ውጭ እንድወጣ ጠየቁኝ፡፡ የድንጋጤም ሆነ መገረም ስሜት አልመጣብኝም፡፡ የቀረኝ በማልፍበት የመከራ ሸለቆ ውስጥ ስለማነባቸው መፃህፍት፣ ስለምሰራው ስፖርትና ስለምፀልየው ፀሎት እያሰብኩ ወደ ግዞት ዓለም መነዳት ነበር፡፡

‹‹ምርጫ 97ን›› ተከትሎ ወህኒ ከወረደው የቅንጅት አመራር አንዱ ነበርኩ፡፡ ያን ጊዜ ወደ ወህኒ ስወርድ ትልቁ ህመም የሚሰማኝ ከእጮኛዬ በመለየቴ ነበር፡፡ አሁን ወደ ወህኒ ስወርድ የባለቤቴ ሃዘንና ግራና ቀኛቸውን የማይለዩት ልጆቼ ሁኔታም አብሮኝ ወህኒ ወረደ፡፡ የአምባገነንነት ኢሰብዓዊት ወደር የለውም፤ እነርሱም ኢትዮጵያን በተቀላቀሉ በጣም ጥቂት ጊዜ ውስጥ የአገዛዙ ሰለባ ሆኑ፡፡ በአባታቸው ማደግ የሚችሉ አባታቸው ከአገዛዙ የተለየ አቋም ካልያዘ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ከአገዛዙ የተለየ አቋም መያዝ አደጋው ከፍ ያለ ቢሆንም ነገር ግን ትክክል ነበር፤ ትክክልም ነው፡፡ ይኽን አቋም ስይዝ በተስፋቢስነት ሳይሆን በተስፋ ሙላት ነው፡፡ እኔና ጓደኞቼ ልጆቻችንና ሚስቶቻችን እንዲሁም ሌሎች ዜጎች የሚከፍሉት መስዋዕትነት በከንቱ እንደማይቀር በፅኑ አምናለሁ፡፡ ምንም ያህል የተዋረድን፣ የተናቅንና የተረገጥን ብንሆንም ዓላማችን እውነት፣ ፍቅርና የሁሉም ዜጎች ልዕልና መከበር በመሆኑ አንዳች ምድራዊ ኃይል እውን ከመሆን ሊያስቆመው አይችልም፡፡ ያ ቀን እስኪነጋ ድረስ ግን የሚከፈለውን ዋጋ በፀጋ ከመክፈል ውጭ ሌላ አማራጭ የለም፡፡

ከማዕከላዊ የሁለት ወራት ቆይታ በኋላ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ስገባ አንድም ቀድሞ የማውቀው ፖሊስም ሆነ የፖሊስ ኃላፊ አላጋጠመኝም፤ እግሬ የእስር ቤቱን ቅጥር እንደረገጠ ግን ከሌሎች እስረኞች ነጥለው ወደ ተለየ አቅጣጫ ወሰዱኝ፡፡ ቅጣት ቤት ነው፡፡ ገና ከማዕከላዊ መድረሴ ነው፡፡ ግን ወደ ቅጣት ቤት ተነዳሁ፤ (ስለዚች ቅጣት ቤት የአቶ መለስ ስንብት በምትለው ንዑስ ርዕስ ስር በጥቂቱ ዘርዘር አድርጌ ለአንባቢ ለማስረዳት ሞክሬአለሁ)፡፡ በዚች የጭንቅ ማማ ውስጥ ሆኜ ማንበብ፣ ስፖርት መስራት፣ መፀለይና መፃፍ በየዕለቱ አቅም በፈቀደ የምሞክራቸው ተግባሮቼ ናቸው፡፡ በጥፍሬ ቆሜም ቢሆን ‹‹ያልተሄደበት መንገድ›› የተሰኘችዋን መጽሐፌን ለማበርከት ሞክሬአለሁ፡፡ ግቢዋ ውስጥ የነበሩት እነ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ኦልባና ሌሊሳ፣ አቶ ቶሎሳ በቾና ኮማንደር ፈቃደ ረጋሳ ከቅጣት ቤቷ ወደ ተለያዩ ቦታዎች ተወሰዱ፡፡ እኔ እና አንድ ሌላ እስረኛ ስንቀር ቅጣት ቤቷ በአዲስ 16 እስረኞች ተጥለቀለቀች፡፡ በተለያየ ወንጀል የተከሰሱና የተለያየ የዕድሜ ደረጃ ላይ ያሉ በአመዛኙ ከ18-30 ዓመት የዕድሜ ክልል የሚገኙ ወጣቶች ናቸው፡፡

በግቢዋ ውስጥ ያሉት ሶስት ትንንሽ ክፍሎች ሃያ አራት ሰዓት በእስረኛ የተሞሉ ናቸው፡፡ ከቤት ወደ ውጭ ሲወጣም ግቢዋ ስፖርት በሚሰሩ እስረኞች ትጨናነቃለች፡፡ ምኗም ለምንም አይመችም፡፡ ፈንጠር ብሎ ቆሞ ለማሰብ እንኳን አትመችም፡፡ ቀኑ ቀጥ ብሎ ይቆማል፡፡ ያልተሄደበት መንገድ ለአንባቢ መድረሷን ሰምቼ ደስ ቢለኝም ቆሞ የሚውለውን የጊዜ ተራራ ለመውጣት ግን አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ አልኩ፡፡ የታሰርኩት ባነገብኩት ዓላማ ምክንያት ነው፡፡ የትም ቦታ በምንም ዓይነት ሁኔታም ሆኜ ለዓላማዬ መትጋት አለብኝ፡፡ ያልተፈጸመ ህልም ይዞ መተኛት ቢቻልስ እንዴት ይተኛል? ባልተሄደበት መንገድ አጎላድፌም ቢሆን አንድ የሚረባ መልዕክት እንኳን ለአንባቢ አድርሼ ከሆነ ትልቅ ነገር ነው፡፡ አሁንስ ሌላ አንድ ነገር ማለት ብችልስ? የሚል ጥያቄ ተመላለሰብኝ፡፡ ቀኑና ሃሳቤ አንድ ላይ ተዳምረው አዕምሮዬ ውስጥ ሌላ ተራራ ፈጠሩ፡፡ ቁጭ ብዬ የሀሳብ ውጥረትና የጊዜ መቆም እንዲገሉኝ ልፍቀድላቸው ወይንስ ጊዜንም ሃሳቤንም ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን በስራ ህይወት ልዝራባቸው? ጊዜም እንዲገድለኝ እኔም ጊዜን ልገድለው አያስፈልግም፤ እንደምንም ልጠቀምበት ወሰንኩ፡፡ ሌላ ዙር መጽሐፍ? ምኑን ከምን አድርጌ በምን ላይ እጽፋለሁ? ሌላ ጭንቅ፤ ለማን አማክረዋለሁ?

ካለሁበት ቅጣት ቤት ውስጥ ከባለቤቴና ከጥቂት የቤተሰብ አባላት ውጭ አብረውኝ ካሉ እስረኞች በተለየ እንዳልጠየቅ ተከልክያለሁ፡፡ ምክንያቱ ተቃዋሚነቴ ነው፡፡ ቅጣት ቤቷ ውስጥ የለመድኳቸው እስረኞች ቢሄዱም ከጥቂቶቹ ጋር መቀራረብ ጀመርኩ፡፡ ከመካከላቸው ፖለቲከኛ እኔ ብቻ ነኝ፡፡ አንዳንዶቹ በሚያስጨንቅ ሁኔታም ሆነው ስለ እኔ ይጨነቃሉ፤ ይበሳጫሉ፡፡ የመጠየቅ መብቴ በመገፈፉ ያዝናሉ፤ በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎችና የሚቸበቸቡ መፃህፍት እንዳይገቡልኝ ስከለከል ድግሞ ስሜታቸው ይገነፍልና ለምን አንድ ነገር አናደርግም ይላሉ፡፡

በእኔ በኩል ቀደም ሲል በቅንጅት ታስሬ በነበርኩበት ወቅት ከፖሊሶችና ከኃላፊዎች ጋር የነበረኝን ኃይል የተሞላበት ግንኙነት ትክክል አልነበረም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ፤ በመሆኑም ፖሊሶቹንም ሆነ ልጆቹን በትዕግስት የመገሰጽ ኃላፊነት በራሴ ላይ ጭኛለሁ፡፡ በፖሊሶችና በእስረኞች መካከል የተካረሩ ግጭቶች ሲፈጠሩ ሁሉንም እቆጣለሁ፡፡ በተለይ ልጆቹን በየተራ እመክራሉ፡፡ ችግሩ ሲፀና የበላይ ኃላፊዎች ሁሉ ከተጨማሪ የፖሊስ ኃይል ጋር ይደርሳሉ፡፡ ከዚያም ‹‹አንተነህ አይደል እያደራጀህ ይኽን የምትሰራው?›› ይላሉ፡፡ ሁልጊዜም ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ እኔ ነኝ፡፡ ነገም ሌላ ችግር ይፈጠራል፤ መሳሪያ ተቀባብሎ ይነጣጠርብናል፤ በዚያም መሃል ግን ሁለቱንም ለማረጋጋት እሞክራለሁ ነገርግን አሁንም እኔ ላይ ዛቻው ይቀጥላል፡፡ በመጨረሻ ላይ የእኔም ትዕግስት ያልቃል፤ ‹‹ልታስፈራሩኝ ከምትሞክሩ የምታስቡትን ብትፈጽሙ ይቀለኛል!›› እላለሁ፡፡ በኃይል በር በላያችን ላይ ተቆልፎ ስሜታችን እንደደፈረሰ በጉዳዩ ላይ እንወያያለን፡፡ መዳፍ በምታክለው ግቢ ውስጥ በየተራ ልጆቹን አናግራለሁ፡፡ አንዳንዶቹን አመሰግናለሁ፤ አንዳንዶቹን እገስጽና በዚህ ሁኔታም ስለምን ብጽፍ ይሻላል? የሚል ጥያቄ እራሴን እጠይቃለሁ፡፡………….

በዚህ ዘመንና ትውልድ ፊት ብቻ ሳይሆን ባልተወለዱ ልጆቻቸውና በሚመጣው ዘመን ሚዛን ተመዝኖ የማይወድቅ አቋም እንደያዝኩ የጸና እምነት አለኝ፡፡ የኢህአዴግን አረመኔነት ለመረዳት የሚያስችል መከራ በህይወቴ ያልደረሰ የሚመስለው አንባቢ ሲኖር ይገርማል፡፡ ስቃዩን እኔ ብቻ ሳልሆን ልጆቼም ያውቁታል፡፡ በእያንዳንዷ ቀን ሰዓትና ደቂቃ የማልፍበት የእስር ህይወት የአገዛዙን ባህሪ ከመረዳትም በላይ ብዙ የሚናገረው ነገር አለ፡፡ እኔ የአገዛዙ አፈና ገፈት ቀማሽ የሆንኩት ሰው ቀርቶ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ እንኳን በሚገባ ኢህአዴግን እንደሚረዳው እንድጠራጠር የሚያደርግ ምክንያት አይታየኝም፡፡ በሌላ በኩል ግን እራሳችን አምላካዊ ሌሎችን ደግሞ ሰይጣናዊ አድርጎ መውሰዱ ተገቢ ሆኖ አላገኘውም፡፡ መጽሐፉ ውስጥ እንደምናየው ይህ ባህሪ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ሁነኛ ባህሪ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት አቋም የያዙ ሰዎች ሁሉ ግን አብዮታዊ ዴሞክራሲ የተጠመቁ ናቸው ማለት አይደለም፡፡

ኢህአዴግንም ሆነ ሁላችንንም ያበቀለው የፖለቲካ ባህላችን ነው፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ከኋላ ጀምረን ለማየት ስንሞክር የአገዛዝ ባህላችን አሁንም ለምንገኝበት ዙሪያ መለስ መከራ ትልቅ ድርሻ እንዳለው እንረዳለን፡፡ የኢህአዴግን አይነት አምባገነን አዝሎ የሚንከራተት ነገር ግን ኢህአዴግን ከጫንቃው ለማውረድ እጅ ለእጅ መያያዝን የሞት ያህል የሚፈራ፤ ይልቅስ እርስ በእርሱ መነካከስና መጠላለፍን እንደ ትልቅ ስኬት የሚቆጥር ስንት ዜጋ እንዳለ ማን ማንን ሊያስረዳ ይችላል? ይኽስ ከኋላ ቀሩ የፖለቲካ ባህላችን የሚቀዳ መሆኑን ለመረዳት የሚቸገር ሊኖር ይችል ይሆን? አይመስለኝም፡፡ ሁልጊዜም በጣም ከባዱ ነገር ወደ ውስጥ ማየት እንጂ አሻግሮ ማየት አይደለም፡፡ ስለ ኢህአዴግ ምንነት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ አውርተናል፡፡ ነገር ግን ለምንድን ነው እስከአሁን ድረስ እላያችን ላይ እንደሰለጠነብን የቀጠለው? ከእኛ የጎደለውን ነገርም በድፍረት ማየት ተገቢ ነው፡፡

ኢህአዴግ ብሔራዊ እርቅን ተቀብሎ ሁላችንም ወደ አላስፈላጊ አዘቅት ተያይዘን እንዳንወርድ ቢሰራ የተሻለ መንገድ መሆኑን አምናለሁ፡፡ ይህን ማድረግ ካልፈለገ ግን ለህዝብ ፈቃድ መገዛት ግዴታው የሚሆንበት ሰዓት መድረሱ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ጊዜው እንደምናካሂደው ትግል ሊረዝምም ሊያጥርም ይችላል፡፡ በትጥቅ ትግል የሚያምኑ ሰዎች ስኬት የራቃቸው በሰላማዊ ትግል ምክንያት አድርገው ካሰቡ ስህተት ነው፡፡ በሰላማዊ ትግል የምናምን ሰዎችም በትጥቅ ትግል ምክንያት ሊሳካልን እንዳልቻልን ካሰብን ስህተት ነው፡፡

ለእኔ ከወሬ ባለፈ ሁለቱም ትግሎች ትርጉም ባለው መልኩ እየተካሄዱ ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ ስለዚህ ሰላማዊ ትግልን እንዳልባሌ ነገር የሚፈርጁ  ወገኖች መተቸት መብታቸው ቢሆንም ወደ ውስጣቸው ቢመለከቱ የተሻለ የሚያስከብር ተግባር ይመስለኛል፡፡

በግሌ አሁንም ግልጽ ለማድረግ የምወደው ነገር በሰላማዊ ትግል የሃይማት ያህል እንደማምን ነው፡፡ የኢትዮጵያን የመጠፋፋት የፖለቲካ ባህል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለወጥ የሚቻለው የጸና ሰላማዊ ትግል በማድረግ ነው፡፡ ሰላማዊ ትግልን በሚገባ ጥቅም ላይ ማዋል ስንችል ያጎበጠንን የአገዛዝ ቀንበት ከላያችን ላይ ማስወገድ ብቻ ሳይሆን የአገዛዝ ስርዓቶች መፍለቂያ የሆነውን የፖለቲካ ባህላችንን ማዘመን እንችላለን፡፡

በአጭሩ ኢህአዴግ የአብዮታዊ ዴሞክራሲን በቁጥጥር የተለከፈና ሁሉንም ተቃዋሚዎች አጥፍቶና ህዝቡን እረግጦ የመግዛት አባዜ የተጠናወተው ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያ የመጠፋፋት ባህልም ወራሽ ነው፡፡ …………………

እንደ ልብ እንዳላነብ መጽሀፍት እንዳይገቡልኝ ይከለከላል፡፡ በማመልከቻ ጽፌ እንዲሁም በአካል ስንገናኝ ‹‹የሮዴዥያ ነጮች ሮበርት ሙጋቤን በአሰሩበት ወቅት እንኳን ትምህትርት አልከለከሏቸውም፤ ከሶስት ያላነሱ ዲግሪዎችን ሰርተው ነው የወጡት፤ እናም እኔም ባልጠቅማችሁ እንኳን በመማሬ አልጎዳችሁምና በተልዕኮ እንድማር ፍቀዱልኝ›› የሚል ጥያቄ ደጋግሜ ባቀርብም ፈቃደኞች አልሆኑም፡፡ የሚፈልጉት የእኔን ባክኖና መክኖ መቅረት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በእኔ በኩል ይኽንን ሁኔታ ለመቋቋም ቀደም ሲል የጠቀስኳቸውን የእስር ቤት መርሃ-ግብሮቼን አጠናክሬ መቀጠል እንደ ሰው ያለመምከን ጥረት ብቻ ሳይሆን በስር ቤት ውስጥ ህልውናዬንም የማስቀጠያ ስልት ነው፡፡ ከእስር ቤት አጥር ውጭ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ለሀገሬ ይበጃል የምለውን ነገር አንስቼ የመወያየት ሰብዓዊ መብቴን ተግባራዊ የማድረግ ህልሜ አውን ሆኖ ለማየት እፈልጋለሁ፡፡ አካሌ ቢገደብም መንፈሴ እንዲገደብ አልፈልግም፡፡ በዚህ ሁኔታ ሆኜ ነው ይኽንን መፅሐፍ መከተብ የጀመርኩት፡፡

እንደ ሁልጊዜው ሁሉም ነገር የሚከናወነው ፍራሽ ላይ ነው፤ ወንበር አይፈቀድም፤ ለማንበብ፣ ለመመገብም ሆነ ለመፃፍ ያለችኝ ቦታ ዘጠና ሲንቲ ሜትር ፍራሽ ነች፡፡ በእርሷም ላይ የማዘዝ መብት የለኝም፡፡ ድንገት ፀብ ከተነሳ የግብግብ አውድማ ትሆንና ልብሴም ሁሉም ነገሬም ይረጋገጣል፤ ግልብጥብጧ ይወጣል፡፡ ፀቡ ሲበርድ ወደ ቀድሞው ንባብ እመለሳለሁ፡፡ ቴሌቪዥኗን እስከ መጨረሻ ድምፀዋን እንድትሰጥ በማድረግ ከጭንቀታቸው ያረፉ የሚመስላቸው ልጆች ደግሞ ዳንኪራውን ያቀልጡታል፡፡ ከማንበብ ውጭ ግን ሌላ አማራጭ የለኝምና እቀጥላለሁ፡፡ በየጊዜው በሚደረገው ፍተሻ ምክንያት አንዷ ክፍል ውስጥ ያለን እስረኞች ልብስና የተለያዩ ንብረቶችን ሁሉ እየፈተሹ አንድ ላይ ይቆለላሉ፡፡ ትቢያ ይለብሳሉ፣ ይረጋገጣሉ፡፡ ከፍተሻው በኋላ ለረጅም ሰዓት ንብረቶቻችንን የመለየት ስራ እንሰራለን፡፡ በጣም አድካሚ ነው፤ ግን አማራጭ የለንም፡፡ በየፌስታላችን ንብረቶቻችንን ቆጣጥረን እንደ ቀድሞው ወደ ህይወት መመለስ ያስቸግራል፡፡ ሰው መሆናችን ጨርሶ ተዘንግቷል፡፡ ኢሰብዓዊነት  እስር ቤት አውርዶኝም በዚያም ያሳድደኛል፡፡ ኢሰብዓዊነትን የማሸንፈው ግን ሰው በመሆን ነውና ሰብዓዊ ተግባሮቼን የሞት ሞቴን እቀጥላለሁ፡፡

በእንዲህ አይነት ሁኔታ እያለፍኩ አንዳንዴ ኃላፊዎች ይመጡና ‹‹ዋይ! እንዴት ነው ‹አንድ-ዓለም› ታረምክ?›› ይሉኛል፡፡ ነገሩ የሚያበሳጭና የሚያሳዝን ቢሆንም በአንክሮ ‹‹እኔ እኮ በተቀነባበረ ክስ የታሰርኩ የግፍ እስረኛ ነኝ፤ ከየትኛው ጥፋቴ ነው የምታረመው?›› እላቸዋለሁ፡፡ ‹‹ዋይ! አንተ ተው! ስንት ሰው አይዶለም እንዴ መንግስትን ተሳድቦ እቤቱ እያደረ ያለበት ሁኔታ ያለው! አንተን ነጥሎ መንግሥት ለምን ያስርሃል? በልዕ ዕስቲ ተናገራ!›› ይሉና ጥያቄዬን በጥያቄ ይመልሳሉ፡፡

በበኩሌም ‹‹ብዙሃንን ሰብስቦ ማሰር ሳይሆን ጥቂቶችን ነጥሎ በማሰር ህዝቡን ማስደንበርና ተሸማቆ እንዲኖር ማድረግ ነው – የአገዛዙ ስልት›› የሚል ምላሽ እሰጣቸዋለሁ፡፡ ‹‹ታዲያ አንተን ለምን መረጠ?›› የሚል ጥያቄ ያስከትላሉ፡፡ ‹‹ለምን እኔንና ጓደኞቼን እንደመረጠ በውል የሚያውቀው አገዛዙ ነው፡፡ ምናልባት ግን በጊዜው ፊት ለፊት ስለምንታይ የእኛን አንገት በመስበር ሌሎችን ‹እነርሱን የበላ እሳት እንዳይበላችሁ፤ እኔ እንደማዛችሁ ብቻ ተመላለሱ› ለማለት ነው፡፡›› የሚለው ምላሼ አያስደስታቸውም፡፡ ‹‹ዋዕይ! ላንተ ገና አልታረምክም!›› ይላሉ ‹‹ይልቅስ መታረም ያለበት የምታስተዳድሩት ተቋም ነው፤ የሁላችንም ተቋም ነው፤ ነገ የተሻለ ተቋም ሆኖ እንዲወጣ ከተፈለገ አሰራራችሁን አስተካክሉ፡፡ ሰውን እንደ ችቦ አንድ ላይ አስሮ በማንደድ ማጥፋት አይቻልም፡፡ የተለያዩ ስራዎችን በዝርዝር ነድፋችሁ ተግባራዊ ብታድጉ ይሻላችኋል›› የሚል ሃሳብ እሰነዝራለሁ፡፡………………

ከቤቴ ከወጣሁ ጀምሮ ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር ያለአንዳች ምክንያት ቅጣት ቤት ውስጥ መሬት ላይ እንደትል ስንከባለል ከቆየሁ በኋላ ድንገት ‹‹ፍራሽህን ይዘህ ውጣ!›› ተባልኩ፡፡ ድንገት ወጥቼ ‹‹ኋይት ሀውስ›› ወይንም ‹‹ዋይታ›› ወደምትባል ጠባብ ቦታ ተወሰድኩ፡፡ ወረቀቶቼ በር ላይ እየተመነጠሩ ሲለቀሙ እስክንድርም መጣ፡፡ ከረጅም ጊዜ በኋላ ተገናኘኝ፡፡ በእለቱም ከ50 ገጽ በላይ ወደ መጨረሻ ረቂቅ ለመጻፍ የተዘጋጁ ወረቀቶቼ ተወሰዱብኝ፡፡ እንደገና ማንበብ፣ እንደገና መፃፍ ቀጠልኩ፡፡ የልጆቼ ናፍቆት፣ የሰላማዊ ትግሉ መቀዛቀዝ፣ ወረቀቶቼን የመነጠቅ ስጋትና በዚህ ሁኔታም ሆኜ የጀመርኩት ገደል የመውጣት ትግል በስኬት እንዲጠናቀቅ መትጋት የአዕምሮዬን ጓዳ ከሞሉ ሀሳቦች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የፈጣሪ ፀጋ በዝቶልኝ ከብዙ አድካሚ ውጣ ውረድ በኋላ የሀገር ፍቅር ዕዳን በስኬት ለማጠናቀቅ ችያለሁ፡፡ ትንሽ ቅር ያለኝ ምዕራፍ አምስትን ሳዘጋጅ ጽሁፉ ከወጣ በኋላ የምዕራፉ 167 የግርጌ ማስታወሻ በፍተሻ ወቅት ስለተወሰደብኝ ሁኔታውን መለወጥ የምችልበትን ሁኔታ መፍጠር አልቻልኩም፡፡ ከዚህ ውጭ ያልተሄደበት መንገድ ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን በዚህኛው መጽሐፍ ላለመድገም ጥሬአለሁ፡፡ …………….

ትግሉ የዴሞክራሲና የነፃነት ትግል በመሆኑ የዜጎች ልዕልና የሚከበርበት፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በኢትዮጵያ እስኪገነባ ድረስ ትግሉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያሳስባል፡፡ ለዘመናት ያልነጋው ረጅሙ የአገዛዝ ሌሊት ሊነጋ የሚችለው የዴሞክራሲ ትግል ውጤት የሆነችው የዴሞክራሲ ጮራ በምድራችን ላይ ስትቀትር ነው፡፡

የዴሞክራሲ ትግሉ በተለይም በዚህ ሰዓት የተለየ ትርጉም ይሰጣል፡፡ አምስት፣ አምስት ዓመታትን እየቆጠረ አገዛዙ የሚተውነው አምስተኛው የምርጫ ተውኔት ተቃርቧል፡፡ የእኔ ፓርቲ አንድነት እንኳን የአገዛዙን አፈና ተቋቁሞ እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ በመግባት ህዝብን ነፃ ለመውጣት የሞት ሽረት ትግል ለማድረግ ሲታትር በስርዓቱ መንጋጋ ውስጥ ወድቋል፡፡ በተቃዋሚው ታግለን ለውጥ ማምጣት አንችልም ብለው የሚያምኑ ግለሰቦች ለውጥ የሚያመጡበትን ወንበር ይዘው መቀጠል ለምን እንደሚፈልጉ ለእኔ እንቆቅልሽ ነው፡፡ ዘመኑ ከችግሩ በላይ የሚገዝፉ መሪዎችን ይፈልጋል፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ ያለውን በባዶ ‹‹እኔባይነት›› አባዜ ካልተወገደ ተቃዋሚዎች የዴሞክራሲ ትግሉን ወደ ፊት የሚያራምድ አቋም ሊላበሱ አይችሉም፡፡

በህዝቡ በኩልም ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆሞ የሚያስብበት ጊዜ ነው፡፡ አሁን እያንዳንዱ ዜጋ እራሱን ነፃ ለማውጣት ምን እንዳደረገ እራሱን የሚጠይቅበት ወቅት ነው፡፡ ለሁሉም ነገር ምክንያት እየደረደርንና ሌሎችንም እየወቀስን ነገር ግን ከእኛ የሚጠበቅን አንዳች ሳንፈጽም የምንሸኘው ጊዜ ሊኖር አይገባም፡፡ በድፍረት ህዝቡ ሊወቀስ ይገባዋል፡፡ እያንዳንዱ ዜጋ ከዚህ በኋላ ስለእርሱ መጨቆን ማንንም ሊወቅስ አይችልም፡፡ ኢህአዴግን እንኳን ለመውቀስ መጀመሪያ ያመቻቸለትን ጀርባውን መከልከል ይገባዋል፡፡ ይኽንን ለማድረግ ደግሞ ጦር መምዘዝ ወይንም ዝናር ማንገብ አያስፈልገውም፡፡ ፍርሃትን ገድሎ በልበ ሙሉነት የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት ለመሆን መስራትና መታገል ነው፡፡ በፍርሃት መቃብር ላይ የፍትህ፣ የሉዓላዊነት፣ የዴሞክራሲና የወንችማማችነት ችግኞች ይንዘረፈፋሉ፡፡ አገዛዙ ይሄ እንዳይሆን መቁረጥ አለብኝ ያላቸውን እግሮች ሁሉ ቆርጧል፡፡ ቀሪው ትግል የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ እኔ ለዚህ ትግል ይረዳል ብዬ ያሰብኩትን ይኽንን መጽሐፍ ቀድሜ ተዘጋጅቼ አበርክቻለሁ፡፡

ፍፁም ለመኖር ሳይሆን ለማሰብ በሚከብድ ሁኔታ በአውራ ጣቴ ወደውቅያኖሱ እንዳልወድቅ በተራራው መሃል ላይ ትልቅ ጥረት በማድረግ ከፈጣሪ ጋር ቀጥ ያለውን ጋራ ተወጥቼዋለሁ፡፡ የታሰርኩለት ሰላማዊ የዴሞክራሲ ትግል ፎቀቅ ባለማለቱ ዘወትር ባዝንም ይህችን ትንሽ ነገር በምጥ ብዛት ሰርቼ በማጠናቀቄ የተወሰነ እፎይታ ተሰምቶኛል፡፡ ለጊዜው የገደሉ ጫፍ ላይ ቆሜ የወጣሁትን ገደል ርቀት እያየሁ ነው፡፡ ነገር ግን ብዕሬ ከጣቶቼ ሳይለይ ሌሎች ሊወጡ የሚገባቸው ገደሎች ተደርድረው ይታዩኛል፡፡ ዴሞክራሲ በሌለበት ሀገር ህይወታችን ሁሉ ጠመዝማዛ መንገድ የበዛበት ገደል ነው፡፡ ሸለቆው እስኪሞላ ገደሉም ሜዳ እስኪሆን ወገባችንንና መንፈሳችንን አጽንተን ለትግል እንነሳ፡፡ የሀገር ፍቅር ዕዳን እነሆ ብያለሁ፡፡

 

ፌደራል ፖሊስ ባራክ ኦባማ ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተዘጋጅተው ነበር ያላቸውን አሰረ * በክሱ ውስጥ ጋዜጠኛ ይገኛል

$
0
0

11168131_854803421272349_5137941628388784214_nየአሜሪካው ፕሬዘዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት ሰርግና ምላሽ በኢትዮጵያ ከወዲሁ የተወሰኑ እስረኞችና በመፍታትና ብዛት ያላቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን በማሰር ወደ ቀኑ እየገሰገሰ ይገኛል፡፡የሰማያዊና የቀድሞው አንደነት አመራሮችና አባላት ኦባማ ወደ አገራችን ሲመጡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እያሴራችሁ እንደሆነ ደርሰንበታል በማለት ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ባሳለፍነው ሐሙስ የሞያ አጋሮቹ መፈተታት የፈጠረበትን ደስታ አጣጥሞ ሳይጨርስ በቁጥጥር ስር የዋለው ጋዜጠኛ ሐብታሙ ምናለ ከአምስት ቀናት የእስር ቤት ቆይታ በኋላ ዝግ ችሎት ተሰይሞ በፖሊስ የ15 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተጠይቆበት ያቀረበው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎበት ወደ እስር ቤት እንዲመለስ መደረጉ አይዘነጋም፡፡

የአንድ ሳምንት የህትመት ብርሃን ካየች በኋላ በስርዓቱ ስልታዊ አፈና ዕድሜዋ እንዲቀጭ የተደረገችውን ‹‹ቀዳሚ ገጽ››ጋዜጣ በስራ አስኪያጅነት የመራት ሐብታሙ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ››ጋዜጣ ላይ በሪፖርተርነት ሰርቷል፡፡አስቂኙ የእስር ክስ እንደቀረበበት ከመደመጡ አስቀድሞም ‹‹ለጥያቄ እንፈልግሃለን››ባሉት ደህንነቶች ተይዞ ቃሉን እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ መለቀቁ ይታወሳል፡፡ የሞያ አጋራቸው ከታሰረበት ዕለት አንስቶ የእስሩን ምክንያት ለማወቅ ሲታትሩ የነበሩት ጋዜጠኞች ኤልያስ ገብሩና ኢዮኤል ፍስሐ ለማመን የከበዳቸውን የፈጠራ ክስ ከራሱ ከሐብታሙ አንደበት አዳምጠው ተመልሰዋል፡፡ሐብታሙ ‹‹የአልሻባብ የሽብር ቡድን አባል በመሆን የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ጥቃት ለመፈጸም ስትንቀሳቀስ ነበር››መባሉን ነግሯቸዋል፡፡ የፈጠራ ክስ በገዛ ዜጎቹ ላይ በማቅረብና በማስወንጀል የዳበረ ሪከርድ ያለው የፌደራሉ ፖሊስ ጋዜጠኛውን ለሽብር ድርጊቱ ተዘጋጅተው ያዝኳቸው ካላቸው 44 ተጠርጣሪዎች ጋር በአንድ መዝገብ ማቅረቡም ነገሩን አሳዛኝም አሳፋሪም ያደርገዋል፡፡ከተጠርጣሪዎቹም መካከልም የሶሪያና ሶማሌያዊ ዜግነት ያላቸው ስዊዲናዊያን እንደሚገኙበት ኦባማ ላይ ጥቃት ለማድረስ አሴረሃል የተባለው ሐብታሙ ተናግሯል፡፡

Elias Gebru Godana

ሰራዊቱ የትጥቅ ትግሉን እየተቀላቀለ እንደሆነ ተገለጸ

$
0
0

ESATበኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ተንሰራፍቶ ያለውን አፈናና የአንድ ብሄር የበላይነት በመሸሽ በርካታ ወታደሮች የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ላይ መሆናቸውን በሽግግር መንግስት ወቅት የኢትዮጵያ ዲፕሎማት የነበሩት አቶ መሀመድ ሀሰን ለኢሳት አስታወቁ።

ሰሞኑን ወደ ኤርትራ በመጓዝ በዚያ የሚገኘውን የትጥቅ ትግል መመልከት እንደቻሉ የተናገሩት የቀድሞው ዲፕሎማት፣ በቆይታቸው ከሰራዊቱ ጋር የተሰደዱ በርካታ ወታደሮችን እንዳነጋገሩ ገልጸዋል።

እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ 1994 አ.ም ስራቸውን በገዛ ፍቃዳችው እንዳቋረጡ የተናገሩት አቶ መሀመድ ሀሰን፣ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጦር የተባለ ሰራዊት እንዳሌላትና ሁኔታው የአፓርታይድ ጦር ሊያስብለው እንደሚችል አስረድተዋል።

በጦሩ ውስጥ ሀገራዊ ስሜት የለም ማለት ይቻላል የሚሉት አቶ መሀመድ የአንድ ብሔር ተወላጆች ብቻ በኦፊሰርነትና በተለያዩ ሀላፊነት ቦታዎች ተመድበው እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ነዋሪነታቸውን በቤልጂየም ያደረጉትና የቤልጂየም የሰራተኛው ፓርቲ አባልና አመራር የቀድሞው የኢትዮጵያ ዲፕሎማት መሀመድ ሀሰን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት በአሁኑ ወቅት በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን መረዳት እንደሚችሉ በቃለ ምልልሳቸው አመልክተዋል።

ሰሞኑን በአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነት ዴሞክራሲ ንቅናቄ የተጀመረው ጥቃትም በመንግስት ላይ አለመረጋጋትን ሊያመጣ እንደሚችልም ገልጸዋል።

በስልጣን ላይ ያለው ገዢው መንግስት የከፋፍለህ ግዛን ስርአት ዘርግቶ እንደሚገኝ ያስታወቁት መሀመድ ሐሰን በአማራ፤ ኦሮሚያ፤ ጋምቤላ፤ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና የተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ሲፈጸሙ ቆይተዋል ብለዋል።

Source:: Ethsat

Health: በአልኮል መጠጥ የተጎዳ ሰውነትን ለመጠገን የሚረዱ ምግቦች

$
0
0

Mediterranean food ethiopia
ለበርካታ አመታት ምናልባትም የአንድ ወጣት እድሜ እና ከዛ በላይ ለሆነ ጊዜ በብዛት የአልኮል መጠጦችንና ጠጥተው ወይም ሲጋራ አጭሰው ዛሬ ከእነዛ ደባል ሱሶች ተላቀዋል ።

በወጣትነት ተጀምሮ ለብዙ አመታት የቆየን ልምድ ወይም ሱስ በተለይም ደግሞ የአልኮል ሱሰኝነትን ማቆም እጅግ ከባዱ እና አስቸጋሪው ነገር ነው ። ይህን ተቋቁመው ከዚህ ሱስ ከወጡ እንኳን ደስ ያለዎት ።

ምክንያቱም በማቆምዎ እድሜ ልክዎን የሃኪም ደጅ እንዲጠኑ ከሚያደርግዎት ነገር በመጠኑም ተላቀዋልና ። የአልኮል መጠጦች ፤ የአዕምሮ ክፍልን ፣ ጉበትን ፣ ልብን ፣ የአንጀት ክፍልንና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ የማድረግ አቅም አላቸው ።

እንዳለመታደል ሆኖ ግን ብዙዎች ለማቆም ሞክረው የተወሰኑት ሲቀጥሉ አብዛኞቹ ግን ተመልሰው በመግባት እድሜ ልካቸውን የተበላሸ እና ምስቅልቅሉ የወጣ ህይዎት እንደሚመሩ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ ።

ከዚህ በታች ያሉት ደግሞ በከባድ ሁኔታ ለበርካታ አመታት በዚህ ሱስ ውስጥ አልፈው አሁን ከአልኮል መጠጦች የራቀ ህይዎት የሚመሩ ካሉ ትናንት ያበላሹትን ጤንነት ዛሬ እንዴት ማደስ እንደሚችሉ የሚያሳዩ ናቸው ።

ለተጎዳው ሰውነትዎ የተመረጠ አመጋገብ ስርአት ቢኖርዎት

በርካታ የአልኮል ሱሰኞች ለሰውነት አስፈላጊ በሆኑ የምግብ እጥረቶችና አልኮል በሚያመጣው ተፅዕኖ ሰውነታቸው እጅግ የተጎዳና የተጎሳቆለ ነው ።

ሰውነትዎ ካጣው የተመጣጠነ የምግብ እጥረትና በአልኮል ምክንያት ከተፈጠረበት ጉዳት እንዲያገግም ካልረዱት ደግሞ ውጤቱ የከፋ ይሆናል ።

አልኮልን አብዝቶ መጠጣት በደም ውስጥ የስኳር መብዛትን ያስከትላል ፣ የልብና የአተነፋፈስ ስርአትን ያዛባል ፣ እጅግ የተጎዳና የተጎሳቆለ ገጽታ ፣ ለስኳር በሽታ ፣ ለካንሰር ፣ ላልተፈለገ እና ጤነኛ ላልሆነ የስብ ክምችት ፣ የስርአተ ምግብ ሂደት መዛባት እና ከፍተኛ ለሆነ የመርሳት ወይም የአዕምሮ መቃወስ ያጋልጣል ።

በርካቶች ከዚህ ደባል ሱስ ሲላቀቁ እንደ መርሻ ወይም መተኪያ ብለው የሚወስዷቸው ጣፋጭ እና አንዳንድ አነቃቂ ፈሳሾችን ነው ፤ ይሁን እንጅ ይህ ልማድ ከቀደመው ሱስ ያልተናነስ አደገኛ እና የማይመከር ነው ይላሉ የአሪዞናው ዶክተር ጆን ኒውፖርት ።

ከሰላሳ አመታት በላይ በተቋረጡ ሱሶች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሰሩት እና ምርምር ያደረጉት ዶክተሩ ፤ መሰል መተኪያ መንገዶች ወደ ቀደመው ሱስ እንዲመለሱ በማድረግ ለአደገኛ በሽታ እና ህልፈት ያጋልጣሉ ።

ከዛ ይልቅ የሜዲትራንያን የአመጋገብ ስርአትን መከተሉ አዋጭ ነው ።

የጥራጥሬ ውጤቶችን ፣ ፍራፍሬዎች ፣ አትክልትቶችና በጥሬ ሊዘጋጁ የሚችሉ ቅጠላ ቅጠሎች ፣ በፕሮቲን የበለጸጉ ስራስሮችና ቦሎቄ ፣ ቅባት ያልበዛባቸው እና ብዙ እሳት ያልመታቸው ምግቦች በአመጋገብ ስርአትዎ ውስጥ መካተት አለባቸው ይላሉ።

ከሜዲትራንያን የአመጋገብ ስርአት ጋር ተዋህዶ ገበታ ላይ የማይጠፋው ቀይ ወይን ግን በዚህ ሂደት ውስጥ አላስፈላጊ እንደሆነም ነው ዶክተር ኒውፖርት የሚናገሩት ፤ ስለዚህም በንጹህ ውሃ እና መሰል ፈሳሾች ምግብዎን ቢወስዱት መልካም ነው።

በንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ምግቦችን ለሰውነትዎ ቢመርጡ

ከነበሩበት ሁኔታ ተላቀው ወደ አዲስ ምዕራፍ ሲሸጋገሩ ለተጎዳው ሰውነትዎ የተመረጡና እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ምግቦችን መውሰዱ ዋስትና ይሰጥወታል ።

በዚህ በኩል እነዚህ ምግቦች ውጤታማ ናቸው ፤

ከስንዴ ዘር የሚገኙ ምግቦች ፤

እነዚህ የአሚኖ አሲድ አይነቶች ለሰውነትዎ ብርታትና ጥንካሬን ከመስጠታቸውም ባለፈ ፤ በሰውነትዎ ውስጥ አላስፈላጊ የሆነ የስኳር ፣ የአልኮል እና ሌሎች እጾችን ወይም መድሃኒቶችን ለማስወገድ ያግዙዎታል ።

ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ ፥ እነዚህ ደግሞ ከመጠን በላይ በወሰዱት የአልኮል መጠጥ የተጎዱ የሰውነት ክፍሎችዎን እንዲሁም በመጠጥ የተጎዳን የልብ ክፍልን እና የተዛባውን የስርአተ ምግብ መፈጨት ሂደትን እንዲስተካከል ያስችላሉ ።

ከዚህ ባለፈም ከመጠን በላይ በሆነ የአልኮል መጠጥ የተዛባውን እና የጠፋውን የማስታወስ ችግርን ለማስወገድ እና የአዕምሮ ክፍልዎ ያጣውን ነገር ለማስተካከልም ይረዳሉ ።

የአሳ ዘይት እና ዘቢብ ደግሞ በዚህ ይዘታቸው የበለጸጉ እና በቀላሉ ሊያገኟቸው የሚችሏቸው ምግቦች ናቸው ።

በቪታሚን ኤ የበለጸጉ ምግቦች ፥ በዚህ ይዘታቸው የበለጸጉ ምግቦች በጠጡት የአልኮል ብዛት በጉዳት የሳሳ እና ምናልባትም የተበላሸ አጥንትዎን እና ጥርስዎን የማገገሚያ ጊዜ ይሰጡታል ።

ከእህል በበለጠ አልኮልን ወስደው ላቋረጡ ጠጭዎች ቪታሚን ኤን መጠቀም ከካንሰርም ይጠብቃቸዋል።

ቪታሚን ቢ ፥ ይህ ደግሞ በመጠጥ ብዛት ደንዝዞ የነበረውን የሰውነትዎን የነርቭ ስርአት ለማስተካልና ንቁ ለማድረግ ያግዝዎታል ።

ከዚህ በተጨማሪም ሰውነትዎን ዘና በማድረግ እና ከድብርት በመከላከል ከአላስፈላጊ ጭንቀትና ወደ ነበሩበት ሱስ እንዳይመለሱም ያግዙዎታል ።

ቪታሚን ሲ ፥ በቀላሉ የሚያገኟቸው በቪታሚን ሲ የበለጸጉ ምግቦች ደግሞ አጠቃላይ የሰውነትዎን ሁኔታ ለማስተካል የሚረዱ ናቸው ፤ የተዛባውን የደም ዝውውር ስርአትዎንም ያስተካክላሉ ።

በአመታት የአልኮል ብዛት ከጥቅም ውጭ የሆነውን ጉበትም የተስተካከለ እና መደበኛ ስራውን እንዲሰራ ያስችሉታል ።

በቪታሚን ኢ የበለጸጉ ምግቦች ፥ እነዚህ ምግቦች በአልኮል ብዛት ለተዳከመውና ለተጎዳው ሰውነትዎ የተዛባውን የልብ ስርአት ለማስተካከልና የደከሙትን የሰውነትዎን የጡንቻ ክፍሎች በማበርታት የተስተካከለ ገጽታዎን ለመመለስ ያግዛሉ ።

አነቃቂ ነገሮችን አይጠቀሙ ፤

ምናልባት ጠዋት ሲነቁ አንድ ሁለት ሲኒ ቡና እና የሻይ መጠጦች መልካም ሊሆን ይችላል ። በካፌይን የበለጸጉ መጠጦች ሲበዙ ግን መዘዘኛ ናቸው እና እነሱን ባይጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ ዶክተር ኒውፖርት ።

አብዛኞቹ ከአልኮል ሱስ ያገገሙ ሰዎች በካፌይን የበለጸጉ መጠጦችን አብዝተው ሲወስዱ ይታያል ፥ ይህ ደግሞ በደም ውስጥ ያለውን ስኳር በማብዛት ጤናዎን አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ይከተዋል ።

ከፍተኛ ጭንቀት ፣ የእንቅልፍ እጦት ፣ መቅበዝበዝ ወይም ድንገተኛ እና ያልታሰበበት የሰውነት እንቅስቃሴ እና ያልተለመደ እና ጤነኛ ያልሆነ የሽንት ብዛት ደግሞ በዚህ መልኩ የተጠመዱ ሰዎች መገለጫዎች ናቸው ።

ለዚህ ደግሞ የበዛ የቡና ፣ የስፕሪስ ፣ ለስላሳ መጠጦች ( እንደ ኮካ ኮላ ያሉ ) እንዲሁም ጣፋጭ ቼኮሌቶችን ባይጠቀሙ መልካም መሆኑን ይናገራሉ ።
ለሚያገግመው ሰውነትዎ አነቃቂ ነገር ወይም ካፌይን የሌለበት አረንጓዴ ሻይ ፣ ንጹህ ውሃ ከቻሉ የታሸጉ እንዲሁም በውሃ ቀጠን ያለ የፍራፍሬ ጭማቂዎችን መውሰዱም ይመከራል ።

የሲጋራ ሱስ ካለብዎት ያቁሙ ፥

የሲጋራ ሱስ ካለብዎት ሳያመነቱ ቢያቆሙት ይመከራል ። የአልኮል መጠጥ ሱሰኛ የሆኑ ሰዎች ካልሆኑት ይልቅ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጋራ ያጨሳሉ ፤ እነዚህ ሰዎች ከአልኮል ነጻ ቢሆኑ እንኳን ከሲጋራ ሱስ ሲላቀቁ አይታይም ።

ሲጋራ ማጨስ አደገኛ ቢሆንም አልኮልን ለሚወስዱት ደግሞ ከመርዝም በላይ አደገኛነቱ ይጎላል ፤ ምክንያቱም በአልኮል ምክንያት በነርቭ ላይ አደጋ ከማስከተሉም ባለፈ የአዕምሮ የነርቭ ክፍሎችን ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጭ ማድረግ በመቻሉ ነው ።

ሲጋራን ከአልኮል ጋር ሲወስዱ በሂደት በጭንቅላትዎ ውስጥ ያሉ የደም ማስተላለፊያ ቱቦዎች ላይ ጉዳት በማድረስ በጭንቅላትዎ ውስጥ በቂ የደም ፍሰት እንዳይኖርና ከዛ ጋር ተያይዘው ለሚመጡ እጅግ አደገኛ ሁኔታዎች ያጋልጣል ።

የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ብዙዎቹ ከአልኮል ሱሰኝነታቸው ቢላቀቁም ሲጋራ ማጨሱ ላይ ግን ያመነታሉ ፤ ካጨሱ ደግሞ ወደ አልኮል መመለስዎ አይቀርምና ተዳብለው ከሚጎዱዎት ለጤናዎ የሚበጅዎን ቢመርጡ መልካም መሆኑን ባለሙያዎቹ ይመክራሉ ።

መጠጡን ለማቆም ያደረጉት ጥረት ለሲጋራውም ይረዳዎታልና ይጠቀሙበት ፤ የህክምና ክትትል እና የባለሙያ ምክርም ይረዳዎታልና እሱን በማድረግ አደገኛውን ልማድዎን ያስወግዱት ።

ምንጭ ፥ ቦተም ላይን ሄልዝ

አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጠ (የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ይዘናል)

$
0
0

andargachew new picture
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ወሰነ፡፡ የፌደራል አቃቤ ህግ ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር በአካል ተገናኝታችኋል›› የሚል ክስ የመሰረተባቸው ተከሳሾቹ ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታችኋል ከተባለ አቶ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ታስረው የሚገኙ በመሆናቸው መከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ ይታዘዝልን›› የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

የፌደራል አቃቤ ህግ በበኩሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ እና በእነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መዝገብ ላይ ክስ ቀርቦባቸው በእድሜ ልክና በሞት እንዲቀጡ ተወስኖባቸው የህዝባዊ መብታቸው የተሻረ በመሆኑ በምስክርነት ሊቀርቡ አይችሉም ብሎ ተቃውሟል፡፡ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ህዝባዊ መብት በመሻሩ ለፍርድ ስራ ልዩ አዋቂ ወይንም ነባሪ ሆነው መስራት አይችሉም ያለው የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በተጨማሪ ምስክርነት ቀርበው መመስከር አይገባቸውም ሲል የተከሳሾቹ ጥያቄ ውድቅ እንዲሆን ለፍርድ ቤቱ አመልክቶ ነበር፡፡

ሆኖም ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡላቸው የጠየቁት ለዋስት አሊያም ልዩ አዋቂ ምስክር ሆነው ሳይሆን ነበሩበት የተባለውን ጉዳይ ለመናገር ለምስክርነት በመሆኑ፣ ምስክርነትም ግዴታ እንጅ መብት በመሆኑ ሰኞ ሀምሌ 13/2007 ዓ.ም በእነ ዘመነ ካሴ መዝገብ ለተከሰሱት ተከሳሾች ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲመሰክሩ ወስኗል፡፡ ተከሳሾቹ አቶ አንዳርጋቸው የት እንደሚገኙና ማዘዢያው የት ተብሎ ሊፃፍላቸው እንደሚገባ ተጠይቀው ለቃሊቲ ማረሚያ ወይንም ለፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ሊጻፍላቸው እንደሚገባ፣ ካልቀረቡላቸውም ክሳቸው ከአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር የተገናኘ በመሆኑ አቶ አንዳርጋቸው በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ አቤቱታ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡

ተከሳሾቹ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡላቸው በጠየቁበት ወቅት በዳኞችና በአቃቤ ህጎች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ መፈጠሩንና ከአቶ አንዳርጋቸው ይልቅ ሌሎች መከላከያ ምስክሮችን ማቅረብ እንደሚችሉ፣ አቶ አንዳርጋቸውን በመከላከያ ምስክርነት ለማቅረብ መሞከር እንደሌለባቸው እንደገለፁላቸው ታውቋል፡፡ ዳኛው በድንጋጤ ‹‹እኛ እዚህ ጉዳይ ላይ የለንበትም›› ማለታቸውን ተከሳሾቹ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ውስጥ ላነጋገራቸው የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ገልጸውለታል፡፡
andargachew


የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 11 ወጣቶች አስመራ ወርደው ተቀላቀሉኝ አለ

$
0
0

TPDM
(የትህዴን ጋዜጣዊ መግለጫ) ከተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች፣ በርካታ ወጣቶች፣ ህወሃት ኢህአዴግን በመቃወም ወደ ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ መቀላቀላቸው፣ ከትህዴን ማሰልጠኛ ክፍል ወኪላችን አስታወቀ።

በህዝባችንና በሃገራችን ታሪክ ይቅር የማይለውን ግፍና በደል እየፈፀመ ያለውን ፀረ ህዝብ ስርዓት ማስወገድ የሚቻለው። በትጥቅ ትግል ብቻ ነው በማለት ወደ ትህዴን ማሰልጠኛ ከተቀላቀሉት ጥቂቶቹን ለመግለፅ።

1. ጠዓመ አማረ ተስፋይ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን፤ ጉለመኸዳ ወረዳ፤ ሸዊት ቀበሌ፤ ቦቑሎ አካባቢ፤
2. መብርሂት ረደሀኝ ገ/የሱስ፤ ከሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ክሳድ ገባ ወረዳ፤ ሕጻፅ ቀበሌ
3. ግርማይ ስእሉ ገ/ማርያም ከምስራቃዊ ዞን፤ ኢሮብ ወረዳ፤ እንዳልጌዳ ቀበሌ፤ መኸታ ቀበሌ፤
4. ጉዕሽ ተኽሊት ሊበን፤ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ፤ ዓዲ ፍታው ቀበሌ፤ ዓዲ ሓንገደ አካባቢ፤
5. ጋይም ወልደማርያም አብርሃ፤ ከምስራቃዊ ዞን፤ ኢሮብ ወረዳ፤ ዓሊቴና ቀበሌ፤ ዓይጋ አካባቢ፤
6. ፀጋይ ፍሻለ አብርሃለይ፤ ከምእራባዊ ዞን፤ ዓዲ ዳዕሮ ወረዳ፤ ዕጉብ ቀበሌ፤ ዓዲ ርእሶ አካባቢ፤
7. መለስ መሓሪ ሊባኖስ፤ ከሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ላዕላይ አድያቦ ወረዳ፤ ዓዲ ክልተ ቀበሌ፤ ገዛ ስቓ አካባቢ፤
8. ሓለፎም አረጋዊ ገብሩ፤ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ ዓዲ ፍታው ቀበሌ፤ ዓዲ ሓንገለ አካባቢ፤
9. አዳነ ታረቀ አበበ፤ ከአማራ ክልል፤ ሰቆጣ አበርጌለ ወረዳ፤ ቁጠብዋ ቀበሌ፤ አብደገን አካባቢ፤
10, ተኽሎም ብርሃነ ገ/ሚካኤል ከማእከላዊ ዞን፤ መረብ ለኸ ወረዳ፤ መዳሎ ቀበሌ፤ ዓዲ ፍታው አካባቢ፤

11, መኮነን ገብረገርግስ፤ አማናኤል ግደይና አረጋዊ ገብርሂወት፤ ከማእከላዊ ዞን፤ ዓዲ ዓሕፈሮም ወረዳ፤ ዝባን ጒላ ቀበሌ፤ ጎላጉል አካባቢ የሚገኙባቸው እጅግ በርካታ ወጣቶች እንደሆኑ ወኪላችን ከትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል በላከው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

እላይ ከተገለፁት ባርካታ ወጣቶች ውስጥ መብርሂት ረደኸኝ እንደገለፀችው። በወላጆቿ ሱቕ እየሰራች እንደነበረችና ባገራችን ያለው ቅጥ ያጣ የግብር አከፋፈል አስመልክታ በሰጠችው ሃሳብ ላይ የንግድ ማህበረሰቡ የንግድ ወጪውና ገቢው በተጣራ መንገድ ጥናት ተደርጎበት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ግብር እንዲከፍል ስለማይደረግ፣ አብዛኛውን ነጋዴ ለኪሳራ ተጋልጧል ስትል አስረድታለች።

ወጣትዋ ሃሳብዋን በማከል አንድ ነጋዴ ግብር ሰብሳቢዎችን አስቀድሞ ግቦ ካልሰጣቸውና በጥቅም ሊግባባቸው ካልቻለ፣ የተለያየ መሰናክሎች በመፍጠርና ከአቅሙ በላይ የሆነ ግብር እንዲከፍል በማስገደድ ከስራው ተማሮ ለማቋረጥ እንደሚያስገድዱት ገልጻለች።

በከብት እረኝነት ተሰማርቶ ይሰራ የነበረውን ፀጋይ ፍሻለ በበኩሉም በርካታ ከእርሻና ከእረኝነት ስራ የተያያዘ ሂወት እየመሩ የቆዩትን ዜጎቻችን ትጥቅና ስንቅ በማመላለስ ከትህዴን ጋር እየተባበራችሁ ነው በማለት እየታሰሩና የተለያየ ግፍ እየደረሰባቸው እንደሆኑ ገልጿል።

ግርማይ ስእሉና ጋይም ወለማርያም በበኩላቸው ዛሬ ባገራችን ውስጥ ትምህርት ጨርሰህ ስራ ማግኘት አይቻልም፤ ማንኛውም የመንግስት ስራም በግቦና በዘር አድልዎ ስለሚፈፀም አብዛኛው በሁኔታው ተማርሮ ወደ ስደት እያመራ ያለበት ሁኔታ እንደሆነ አስረድቷል።

በመጨረሻም ወጣቶቹ ወደ ስደት ማምራት የከፋ ችግር መፍጠር እንጂ ለችግራችን መፍትሄ ስለማይሆን መፍትሄው የትጥቅ ትግል ማካሄድ እንደሆነ አምነው ከትህዴን ጎን በመሰለፍ እንዲታገሉ መወሰናቸው አክለው አስረድቷል።

በወሊሶ ከተማ የገዢው መንግስት ወታደር ገበሬውን ለምን መሬቴን አላረስክም በሚል በጥይት አቆሰለው

$
0
0

weliso oromia ethiopia
የትህዴን ራድዮ እንደዘገበው በኦሮሚያ ክልል ወሊሶ ከተማና አካባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮች በኦሆዴድ ካድሬዎች “ለምን የኛ አገልጋዮች አትሆኑም?” እየተባሉ በላያቸው ላይ ግፍ እየተፈፀመባቸው እንደሚገኙ ተገለፀ።

ምንጮቻችን ከከተማዋ እንደገለፁት- በኦሮሚያ ክልል ወሊሶ ከተማ የሚገኙ አርሶ አደር ወገኖቻችን የካድሬዎች መሬት ተገደው እንዲያርሱት መደረጉን የገለጸው መረጃው አቶ ሲሳይ ከልካይ የተባለ የስርዓቱ የፖሊስ አባል ሰኔ 29/ 2007 ዓ/ም አቶ ጫላ ፈይሳ ለተባለ አርሶ አደር “መሬቴን ለምን አላረስክልኝም” በማለት ስለ አፋጠጠበት አርሶ አደሩም “በኔ ጉልበት ልትጠቀም; ልታስፈራራኝ አይገባህም” ስላለው ብቻ ፖሊሱ ጥይት ተኩሶ እጁን ስለአቆሰለው አቶ ጫላ ፈይሳ በከባድ ቆስሎ ወሊሶ ሆስፒታል ተኝቶ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው ይህ የስርአቱ ካድሬዎች የግፍ ተግባር በወሊሶ ከተማ ብቻ የታየ ሳይሆን በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች እየታየ ያለና የነበረ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል፤ ምእራብ ሸዋ ዞንና አካባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮች ማዳበርያ በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት አልቻልንም ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በማሰባቸው እየታሰሩ እንደሆኑ ተገለፀ።

በመረጃው መሰረት በኦሮሚያ ክልል፤ ምእራብ ሸዋ ዞን፤ ኖኖ ወረዳና አካባቢው የሚኖሩ አርሶ-አደሮች በያዝነው ዓመት ውስጥ መንግስትን ሁሉንም አርሶ-አደር በሚጠቀምበት መንገድ በተመጣጣኝ ዋጋ ማዳበርያ ልያቀርብልን አልቻለም በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በመጠየቃቸው ብቻ 15 የሚያህሉ አርሶ-አደሮች አነሳሾች ተብለው መታሰራቸውን ታወቀ።

ህጋዊ በሆነ መንገድ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቂያቸውን ስላቀረቡ ብቻ በስርዓቱ እንደ ጠለት ታይተው ከታሰሩት አርሶ-አደሮች መካከልም ክብረቴ ዳርጌ፤ ደብለው ቢተው፤ ፍቃዴ ደሳለኝና ሌሎችም እንደሚገኙባቸው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

ዕዉቁ ዲፕሎማትና የፕሮቶኮል ሹም፣ አምባሳደር ፍሰሐ ገዳ አረፉ

$
0
0
Fisha Geda

አምባሳደር ፍሰሐ ገዳ

ዕዉቁ ዲፕሎማት፣ የፕሮቶኮል ሹም፣ የህዝብ ግንኙነትና የማስታወቂያ ሹም፣ እንዲሁም የሠራዊቱ የኢንፎርሜሽን መኮንን የነበሩት አምባሳደር ሻለቃ ፍሰሐ ገዳ በተወለዱ በ76 ዓመታቸው አረፉ፡፡ በሰሜን ኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ የኢትዮጵያ ሆቴሎችና ቱሪዝም ኮሚሽነር፣ የርዕሰ ብሔሩ የፕሮቶኮል ዋና ሹም፣ የ3ኛ ሻለቃ ክፍለ ጦር ባልደረባና የሆለታ ጦር አካዳሚ ምሩቅ የነበሩት፣ ተወዳጁ መኮንን፣ አምባሰደር ፍሰሐ ገዳ ያረፉት ጁላይ 15 2015 በቨርጂኒያው መኖሪያ ቤታቸው ነው። የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ሰኞ ጁላይ 20/2015፣ በቨርጂኒያ 9902 Braddock Rd. Fairfax VA 22032, በሚገኘው Braddock Funeral Home and Cemetery ከጧቱ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚፈጸም ከቤተሰቡ የተገኘው ኢንፎርሜሽን ያስታውቃል።

ሻእቢያ ለምን ? ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ

$
0
0
ከቀደሙ ልምዶች መማር መጠየቅ ወይም መረዳት ተመሳሳይ ስህተቶች ተደጋግመው እንዳይፈፀሙ ይረዳል በተለያዩአጋጣሚዎች ባለፈው አሰርተ -አመት በጣት የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች ወደ አስመራ ተጉዘዋል ። ከነዚህም ውስጥ አንዱና ቀዳሚው እኔ ነኝ ብል ማጋነን አይሆንብኝም ። ደጋግሜም ወደ ኤርትራ ተጉዣለሁ ።
ከአርበኞቹ ጋር ሰላምታ ስለዋወጥ ። በተለይ ሰላምታ እየሰጠሁት ያለው አርበኛ ካሳሁን ሁንዴ ኢትዮጵያዊ የግንባሩ አመራር ይጠናከር በማለቱ በሻእቢያ ጉርጓድ ወስጥ ታስሮ ለወራት ሲሰቅይ ከቆየ በኋላ የተረሸነ ።
ወድ አንባቢዬ ሆይ!
 
እነዚህ ከአሁን ጀምሮ በተከታታይ የማቀርባቸውን የጉዞ ማስታወሻዎቼ እንዲያተኩሩ የምፈልገው በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ላይ ብቻ ነበር ። ሆኖም ግን ስለአርበኞች ግንባር መከታተል ስጀምር ህይወት በራሷ መንገድ ይዛኝ የነጎደችባቸው ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴዎች ነበሯትና እግረ መንገዴን ያየሁቸውና ያስተዋልኳቸው ብዙ ሁኔታዎች አጋጥመውኛል ።
 
 demisይህ ፅሁፌ የማንንም ወገን ወይም ቡድን የመጥቀምም ሆነ የመጉዳት አላማ የለውም ። ምናልባት ባቀራረቤ ከረር ወይም ለስለስ ያደረኩ ከመሰላችሁ ትኩረቴ እውነታው ላይ ብቻ ስለሆነ ፋክት መሆኑን ብቻ ተመልከቱልኝ ። ለወጣቱና በቦታው ላልነበርው የሃገሬ ዜጋ ሁሉ በጉዞዬ ላይ ያየሁትንና የሰማሁትን ማካፈል ግዴታየ ነው ። ሁሉም ሰው የሃገሩ ጉዳይ እኩል ይመለከተዋል ። አንድ ዜጋ ብሄራዊ ጥቅሙን ከማስጠበቅ አልፎ ለወደፊቷ የሃገሪቷ መፃኢ ትውልድ ሰላማዊት  ሃገር ማስተላለፍ ይችል ዘንድ ትክክለኛ መረጃ  ሊኖረው ይገባል ። በሰከነ መንፈስ ተረጋግቶ መርጃን የሚመዝን ሰው ፤ በቀላሉ ስህተት ውስጥ አይዘፈቅም ።
 
ወገኖቻችንና  ዜጎቻችን ከየትኛውም የአገራችን ክፍሎች ይምጡ፤ አምነውብውትም ይሁን ሳያምኑበት እየከፈሉት ያሉት መስዋእትነት አለ ።  መስዋእትነቱን ለመክፈል በፈቃደኝነት የሄዱት የጠበቃቸውና ያገኙት እንዳሰቡት ነበር ወይ ? ያለፈቃዳቸው በምርኮ የሄዱትስ ኑሯቸው እንዴት ነው ? ይህን ማንም ዜጋ ሊያጤነው ይገባል ብየ አስባለሁ ። በኤርትራው ተደጋጋሚ ጉዞዬ መልካምና ቅን የሆኑ ኤርትራውያን ተዋውቄአለሁ ።  በዚያው ልክ ደግሞ የሰው ልጅ ስቃይና መከራ ውስጣቸውን በሃሴት የሚያለመልምላቸው ቂመኛና ጥቅመኛ ኤርትራውያንም አጋጥመውኛል ። በኤርትራው ጉዞየ ላይ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ዘላለማዊ  ወንድሞችም አትርፌአለሁ ። ተኮራርፈን የቀረንም ወገኖች አለን ። ብንኮራረፍም ዛሬ ላይ ሆነን ሁላችንም የነበረውን ሁኔታ ስናጤነው ፤ የችግሮቻችን ምንጮች ምንና እነማን እንደነበሩም የተረዳን ይመስለኛል ። ያም ሆኖ አብዛኛዎቻችሁ  የሃገራችሁ ክብርና ፍቅር ልባችሁ ወስጥ እንደሚነድድ ተረድቻለሁ ። መንገዶቻችን የተለያዩ  ቢሆኑም በቅን ልቦና ለአርበኞቹ ትለፉ እንደነበር ግን ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለኝም ። ስለዚህም በዚህ አጋጣሚ ዘላለማዊ አክብሮቴን ልገልፅላችሁ እወዳለሁ ።         
 
ለምን ይህን ጊዜ መረጥክ የሚል ጥያቄ ልታነሱ የምትችሉ ወገኖች እንዳላችሁ አውቃለሁ ። እኔም ሆንኩ አብረውኝ የነበሩ ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ ሳንወተውት ያሳለፍንበት ጊዜ አልነበረም ። አንዳንዴ  ጊዜው ሌሎች ሁኔታዎች ላይ ያተኩርና የህዝቡን የማስተዋል አቅጣጫ ወደ ሌላ መስመር ይዞት ይነጉዳል  ። በሌላ ጊዜ ደግሞ ጊዜው ያመጣቸው የፖለቲካ ሾፌሮች የግል ፍላጎት ስለአርበኞች ግንባር መነጋገር ፤ የነሱን የፖለቲካ ስራ የሚያደናቅፍባቸው ወይም ጥላ የሚያጠላበት መስሎ ስለሚታያቸው እንዳይነገር እንዳይሰማ መሰናክል ይፈጥሩ ነበር ። ከዚህ ሌላ ደግሞ በነፃነት አስተያየትን መግለፅ ትክክል ነው ብለው የሚያምኑ በጣም ጥቂት ሚዲያዎች  እንዳሉ ሁሉ ፤   አብዛኛዎቹ ድጋፍ እናጣለን ከሚል ስጋት ማንም ሳያስገድዳቸው ራሳቸው ላይ ግለ-ሳንሱር (self censorship) ይጥላሉ  ።  እና መረጃዎች በትክክል እንዳይደርሱ ምክንያት  ይሆናሉ ።
አንድ ፀሃፊ በስሙ እስከፃፈ ድረስ የፅሁፉ ባለቤትነትና ሃላፊነት የራሱ ይሆናል ። የሚዲያዎቹ ሃላፊነት የመነጋገሪያ ፤ የመወያያና የመከራከሪያ መድረኩን ማዘጋጀት ብቻ መሆን ይኖርበታል ።    ስለዚህ በዚህና በመሳሰሉት ጉዳዮች ምክንያቶች  ሳላቀርባቸው ቆይቻለሁ ።ከብዙው በጥቂቱ ምክንያቶቼ እነዚህ ነበሩ ። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ዛሬ  አፍጥጦና ገጦ የወጣ ጉዳይ አለ ። የኢትዮጵያ ጉዳይ እየተመራ ያለው በኢትዮጵያውያን አይደለም ብዬ አምናለሁ ። የትእዛዝ ሰጪነትና ተቀባይነት ግንኙነት የሎሌነት ግንኙነት ነው ። ይህ ደግሞ አገራችንንና ህዝባችንን ከፍ ያለ ዋጋ ያስከፍላቸዋል ። ይህን መስል ግንኙነቶችም ወያኔና ህዝባችንን ያስከፈለው ዋጋ  የቅርብ ጊዜ ትዝታዎቻችን ናቸው ። አሁን ግን ጊዜው የደረሰ ስለመሰለኝ ፤ በተከታታይ አቀርበዋለሁ ።
 
  ስለ ኤርትራና  ስለኢትዮጵያ  ህዝቦች ባህላዊ ፤ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ግንኙነት እዚህ ላይ መጥቀሱ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም ። የዛሬው ጎልማሳ ትውልድ የአንድነቱንም ሆነ የልዩነቱን ዘመን በሚገባ ያውቀዋልና ።
 
በረራ ወደ አስመራ!
 
        የአስመራው በረራዬ  ከፍራንክፈርት ጀርመን የተነሳው አመሻሽ ላይ ነበር ። ወደ ደቡብ ምስራቃዊ አቅጣጫ አፍንጫውን የደገነው የተሳፈርኩበት አውሮፕላን የአውሮፓን ሰማይ እየሰነጠቀ ነጎደ ። በአውሮፕላኑ መስኮት አይን አስከሚደርስበት ድረስ የአውሮፓን ምድር ሳይ  አንዳንድ ቦታ ክምችት ክምችት ብለው ሌላ ቦታ ደግሞ ብትንትን ብለው የሚታዩት የኤሌክትሪክ ብርሃኖች ፤ ጥቁር ምንጣፍ ላይ የተበተኑ የአልማዝ ቁርጥራጮች ይመስላሉ ። የአልማዞቹ ምንጣፍ ወደኋላ እየቀረ የሜዲትራኒያን ባህር አየር ላይ መግባቱን የሉፍታንዛው አውሮፕላን የካርታ ማሳያ ጠቆመ ።
 
ሜዲትራኒያን ሲነሳ ሃሳቤ ከመፃህፍቱ አለም ካገኘኋቸው  የታሪክ እውቀቶች ጋር ለምዕተ- አመታት ወደኋላ ይዞኝ ነጎደ ። የዛሬዎቹ የመካከለኛው ምስራቅና የውሮፓው ቋንቋዎች ፊደላት ድምፀት በፊንቃውያን (Phoenicians)  የተጨለፈበት ባህር ነው ሜዲትራኒያን ።  የግርኮች ስልጣኔ ወርሶች የለመለሙትና ፍሬ ያፈሩት የዚህን ባህር ውሃ እየጠጡ ነው ። የካርታጎው አፍሪቃዊ የጦር ሰው ሃኒባል አውሮፓ ላይ በዝሆኖች በመዝመት ሮምን ያስጨነቀው ይህንኑ  ባህር በመሻገር ነበር ። ሮማውያን የሃኒባልን ጦር አሸንፈው ሰሜን አፍሪቃን በመቆጣጠር ቄሳራዊ ግዛታቸውን  የመሰረቱት በዚሁ ባህር ላይ  ።  ክሊዮፓትራና ግብፃዊ ህዝቧ በተለይ የማርክ አንቶኒና የክሊዎፓትራ ፍቅርና ትራጀዲ መድረክም ይኸው ባህር ነው ።  በሃዋርያዊ ጉዞ ለክርስትና መስፋፋት  ታላቁን ሚና በመጫወትም ይታወቃል ሚዲትራንያን ።  አረባውያኑ የነቢዩ ሞሃመድ ተከታዮችም መካከለኛው ምስራቅን አልፈው ሰሜን አፍሪቃን ተቆጣጥረው ስፔንንና ደቡባዊ ፈረንሳይ ድረስ የዘለቁት ይህንኑ ባህር ተሻግረው ነው ። ኦቶማን ቱርኮችም ፤ ተራቸውን እንዲሁ እየጠበቁ በአዕምሮየ ተመላለሱብኝ። በአለማችን ላይ ካሉት ባህሮች ሁሉ እንደሜዲትራንያን ባህር ሰፊ የሰው ልጆች ታሪካዊ ባህላዊና ሃይማኖታዊ በስተጋብሮችና ግንኙነቶችን ብሎም ጦርነቶች የተካሄዱበት ባህር የለም ማለት እችላለሁ ።  
 
 ምናቤን ከነዚህ የታሪክ ዘመናት አውጥቶ  ወደ ጉዞየ አቅጣጫ የመለሰው የፓይለቱ እወጃ ነበር ። በመጀመሪያ በጀርመንኛ ከዚያም በእንግሊዝኛ በአፍሪካ ሰማይ ላይ መሆናችንን አበሰረ ። ድሮ ድሮ አፍሪካ  “ጨለማው ክፍለ-አለም” ሲባል የትምህርት እጦት ጨለምተኝነት ብቻ ይመስለኝ ነበር ። የአፍሪካ ምድር ምሽት ድቅድቅ ጨለማ ነው ። የአፍሪካ የእውቀት ኋላ ቀርነት የብርሃንም  ጨለማ አድርጓታል ። ለምን እንደሆነ ባላውቅም ወደአስመራ የበረርኩባቸው ከአውሮፓ የተነሱ አውሮፕላኖች ሁሉ ወደ ኤርትራ ከመብረራቸው በፊት በጅዳ ሰማይ ላይ አንዣበው ነው የአስመራን አቅጣጫ የሚይዙት  ። ጅዳም ታዲያ ከአሮፓው ምድር ባልተናነሰ እንዲያውም በበለጠ ማለት እችላለሁ ብርሃን ለብሳለች ። የነቢዩ ሞሃመድ አገር መሆኗና የህዝቡ ሃይማኖቱን አክባሪነት ብሎም ፀሎተኝነት ፤ ጭው ባለው በረሃ ፤ ከከርሰ ምድሯ ጥቁር ወርቅ እንዲፈልቅላት እግዚአብሄር ፈቅዶ በብርሃን ተፍለቅልቃለች ።
 
ቀይ ባህርን ተሻገረ አውሮፕላናችን ። ብርሃን ግን የለም ።  አስመራ ስንደርስ ኤሌክትሪኩ ፏ ብሎ እንደሚጠብቀኝ ተስፋ አድረኩ ።  ቀድሞ የኢትዮጵያ አካል የነበረችውና ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ሁለተኛዋን ከተማ ትባል የነበረችውን አስመራ ለመጀመሪያ ጊዜ ላያት ነው ። በተለይ ወላጆቻቸው ከኤርትራ የነበሩ አብረውን ያደጉና የተማሩ አምቼዎች ስለአስመራ ሲያሞጋግሱና ትላልቆቹም ትውልደ-ኤርትራውያን እንዲሁ አፍሪቃዊቷ ሮም እያሉ ሲያንቆላጵሷት እየሰማሁ በአይምሮየ የቀረፅኳት አስመራ ለየት ያለች ነበረች ። ልቤ በሃይል መምታት ጀምሯል ። መንፈሴም ተነቃቅቷል ። አዲስ አበባ ውስጥ አንድ ቆንጆ ነገር ተደረገ ብለህ ስታወራ ፤ የኤርትራ ትውልድ ያላቸው ልጆች አስመራ ጣሊያን የሰራው እንዲህ እንዲህ የሚባል ቦታ ከዚህ የበለጠ አለ ።ድሮ ድሮ  ነው የተሰራው ብለው በደቦ እየተቀባበሉ የሚነግሩን ሁሉ ታወሰኝ ። “አደየ አስመራ ! አደየ ኤርትራ”
 
 አስመራንም አይቼ የአርበኞቹንም እንቅስቃሴ ተመልክቼ የምሰራው  ጋዜጣዊ ሪፖርት እየታየኝም ወስጤ በደስታ ሞልቷል ።በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፎች መምታት ይቻላል የሚባለው ለዚህ ይሆን?  አውሮፕላኑ ለመውረድ ማኮብኮብ ጀመረና ዝቅ እያልን ስንሄድ የመንደርደሪያው ማሳያ ሰልፈኛ ብርሃኖች ታዩኝ ። ከአገሬ ከወጣሁ ረዘም ያለ ጊዜ ስላለፈና የአገሬ አካል የነበረችውን የአስመራን መሬት የአውሮፕላኑ ጎማ ሲነካ የተደበላለቀ ስሜት ነበር የተሰማኝ ። ደስታ ይሁን ሃዘን ፤ ፍርሃት ይሁን ስጋት ወይም ጥንቃቄ ሁሉም በአንድነት ይተረማመሱብኛል፤ ምን ነካኝ? ስል ራሴን ጠየቅሁ ። ቀደም አድርጌ ደጋግሜ ያሰብኩበት ቢሆንም ፤ ያደረከው ውሳኔ ትክክል ነው ወይ ሲል ህሊናዬ እንደገና ራሴን ጠየቀኝ ። ትክክለኛም ሆነ አልሆነ አንዴ መጥተሃል  የመጥህበትን ጉዳዮች ፈፅም ሲልም መከረኝ ።
 
“…..አንታ ሃላፋይ መንገዲ እንተረኪብካያ ንመለይ፤
 ሰላም በልለይ።…..”
 
 ትርጉም                                  
“…..አንተ በመንገድ አላፊው ቆንጂትን ካገኘህልኝ ፡
 ሰላም በልልኝ።…… “ 
 
እያልኩ የአስመራን መሬት ረገጥኩ ።
 
   ከአውሮፕላን እንደወረድኩ እኔን ሊቀበሉ የመጡጥ ሰዎች አውሮፕላኑ ድረስ መጥተው ተቀበሉኝ ። ሁለት ነበሩ ። ሃላፊነታቸውንና የየትኛውመስሪያ ቤት ተወካይ እንደሆኑ ሳይነግሩኝ ስማቸውን  ብቻ በመግለፅ ተዋወቁኝ ። ሻእቢያዎች ናቸው በሚል ግምት እኔም ተዋወቅኳቸው ። ኤርፖርቱን በአይኔ ለመቃኘት ሞከርኩ ። ተርሚናሉ እዚህ አሜሪካን አገር አንድ መካከለኛ ገቢ ያለው ሰው ሊሰራው ከሚችለው ቤት አይበልጥም ። ከተርሚናሉ ትይዩ  በቆርቆሮ የተሰራ መኪና ቤት ውስጥ አንድ  የእሳት አደጋ መኪና ቆሟል ። ሊቀበሉኝ የመጡት ሰዎች ከሌሎቹ ተሳፋሪዎች ነጥለው ወደሌላ አቅጣጫ ወሰዱኝ ። በኔና በሌሎቹ ተሳፋሪዎች መካከልም የባላ ቅርፅ ያለው መንገድ ተፈጠረና እኔ ሌላ በር ሌሎቹን ተሳፋሪዎች ደግሞ ሌላ በር ዋጠን ። እኔ የገባሁበት በር ትላልቅ እንግዶች የሚገቡበት VIP በር ነበርና የክፍሉ ወለል ከዳር እስከዳር በቀይ ምንጣፍ ተሸፍኗል ። ሶፋዎቹም እንደዚሁ ቀያዮች ናቸው ። ይሁንና የወለሉ ምንጣፎች በጣም ያረጁ ናቸው ። ሶፋዎቹም እንደዚሁ ያረጁ ስለሆኑ  መዳፍ ፤ ክንድና ጭንቅላት የሚያርፍባቸው ቦታዎች  በሳሙናና በቡርሽ ከመታጠብ ብዛት የሶፋዎቹ ፀጉሮች አልቀው ድርና ማጋቸው ተጋልጦ ቀለማቸውን ለውጠዋል ። ከድዩቲ ፍሪ (Duty free) መግዛት የምትፈልገው እንዳለ ጠይቀውኝ ፤ ማየቱ አይከፋም በሚል በኮሪደሮች ውስጥ እያቆራረጥን ወደሱቁ ገባን ።  ኮሪደሮቹ  ወስጥ ከሶስት ኢንች ያልበለጠ ውፍረት ያላቸው የስፖንጅ ፍራሾች መሸፈኛ ጨርቆቻቸው የተቀዳደዱ ፤  በየቦታው ተበታትነው እንሱን እየዘለልንና እየተራመድን ነው ወደሱቁ የገባነው ። እነዚህን ፍራሾች ማንኛውም ወደ ኤርትራ ለስራም ሆነ ለጉብኝት ከሚመጣ ቱሪስት አይን የተሰወሩ አይደሉም ። እንግዶች እየጋበዝክ መግቢያህ ላይ ያለውን ቆሻሻ እንዳለማፅዳት ይቆጠራል ።  ከኤርፖርቱ  በአንዲት አሮጌ ቶዮታ ኮሮላ መኪና ከሁለቱ ተቀባዮቼ ጋር ወጣን ።  ከተማይቱ ምንም አይነት የመንገድ መብራትም ሆነ የቤቶች መብራቶች አይታዩባትም ፤ ጨለማ ውጧታል ። የኤርፖርቱ ኤሌክትሪክም በጀኔረተር እንደሚሰራ ተረዳሁ ።  ከኋላ ተቀምጬ የሚታየኝ የመኪናዋ መብራት  ማሳየት የሚችለውን ብቻ ነበር ። አቆራርጠን ተጣጥፈን  ከተማው መሃል ገባን  ። በኋላ ላይ እንዳረጋገጥኩት ከተማዋ መሃል ላይ በምትገኝ አንድ ተራ ካርቱም ሆቴል የምትባል  ውስጥ ነው መኝታው  የተያዘልኝ ። ወደክፍሌ ስገባ ኮሞው ላይ( White Horse) ውስኪ ተቀምጣል ። አማራ ውስኪና ጥሬ ስጋ ላይ ሲንደፋደፍ ፤ እኛ ኤርትራውያን ጥሬ ቆሎ እየበላን አሸንፈነው ነፃነታችንን ተቀዳጀን እያሉ ይፎክሩ የነበርው አባባላቸው ውስኪዋን ዘወር ብዬም እንዳያት አላደረገኝም  ። ክፍሉ ውስጥ ያሉ ሮቾች ግን ሰላም አልሰጡኝም ። ሲተረማመሱ  ስላይኋቸው እየቀፈፈኝም ቢሆን ተኛሁ ። ንጋት ላይ ከእንቅልፌ ተነስቼ መስኮቱን ከፈትኩ ። የውጪውን ቀዝቃዛ አየር ሳምባዬ እስከሚችለው ድረስ ሳብኩት ። ያደኩባት አገሬ አየር ሰውነቴን እስኪወጣጠር  ድረስ የሞላው መሰለኝ ።  ፀሃይ ገና አልወጣች ነበርና ደስታየን የተሟላ ያደርገው ዘንድ የወፎቹን የጠዋት ዝማሬ ማዳመጥ ተመኘሁ ። ምንም አይነት ዝማሬ የለም ። በቀጣዮቹ ማለዳዎችም የወፍ ዝማሬ የለም ። ወፎች አስመራ ውስጥ ለምን እንደሌሉ እስካሁን ሊገለፅልኝ  አልቻለም ። የወቅት ነው እንዳይባል በተለያዩ ወቅቶች ደጋግሜ ሄጃለሁ ፤ ወፎች የሉም ። አሽሟጠጠ አትበሉኝና  ለኤርትራ ወጣቶች የስደት መንገዱን (ስግረዶም) ያሳዩአቸው ወፎቹ ሳይሆኑ አይቀሩም ።  ዛሬ ወፎቹም የሉም ፤ ወጣቶችም የሉም ኦሮማይ! ። ስደቱ  ወደ ታዳጊዎችም እየተዛመተ ነው ። ሱዳን ሸገራብ ፤ ኢትዮጵያ እንዳባጉና የስደተኞች መቀበያ ማእከላትን በመመልከት የታዳጊዎቹን እድሜ ማወቅ ይቻላል ።  ሰሃራ ሳይናይና ሊቢያም ምስክሮች ናቸው ።
  
 ከተማዋን ለማየት ከሆቴሉ ወጣሁ ።  ሆቴሌ የሚገኝበትን መንገድ ላይ ወደ ግራ ታጠፍኩና መቶ ሜትር ያህል እንደሄድኩ  ኮምፔሽታቶ ላይ “ሲኒማ ኢምፔሮ” ከሮማዊ ፅሁፉ ጋር ፊትለፊቴ አገኘሁት ይህ ሲኒማ ቤት በጣሊያኖቹ ዘመን  ለነጮቹ መዝናኛ ከተከፈቱት ሲኒማ ቤቶች አንዱ ነው ። ከሲኒማ ቤቱ በስተቀኝ የአስመራ ከተማ ምልክት የሆነችውን የሮማ ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ካቴድራልን ታገኛላችሁ ። ይህቺ ቤተ-ክርስቲያን በጣሊያኖች ቅኝ ግዛት ዘመን የኤርትራን የዘመኑ  ጌቶች ነጮችን  ከክርስቶስ ጋር የምታገናኝ ብቸኛ መንገድ ነበረች ። ስጋ-ወደሙም የሚቀበሉት የታላቂቱ ሮማ ዜጎች ብቻ ነበሩ ።  የአስመራ ከተማ መስራች የገበሬው የእንግዳ ቁቢ ልጅ አሉላ አባ ነጋ ይህን ሳያይ ቀድሞ መሞቱ ጠቀመው ። (ይህን የአስመራ ከተማ አመሰራረት ታሪክ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ) ።
  
  ከዚያ በተረፈ የከተማዋ ቤቶቹ የስሚንቶ ምርጎች በየቦታው ተቦዳድሰው  የቆመ የገበጣ  ገበታ ይመስላሉ ።  ቀለም የሚባል ነገር ካረፈባቸው ዘመናት ስለተቆጠሩ  የቀድሞ ቀለማቸውን አንኳ ማወቅ አይቻልም ። የአስፋልቶቹ እድሳቶች ያለእውቀት ወይም ለግብር ይውጣ አለያም በችኮላ የተሰሩ ሆነው ፤ አሮጌው ወይም ያረጀው ሬንጅ ሳይነሳ በላዩ ላይ አዲሱ ተመርጎበታል ።  በዚህም ምክንያት ሬንጁ እየቀለጠ ቀስ እያለ በመውረድ የውሃ መፋሰሻውን ደፍኖታል ። ጠዋት ነውና አስመራ እንደተኛች ነበረች ። በኋላ ላይ ስትነቃ ግን የሰዉ እንቅስቃሴ ይህን ሁሉ ትዕይንት ይጋርደዋል ።  
 
ከዚህ በኋላ አስፈላጊ ሆኖ ሳገኘው ወደ አስመራ ወጣ ገባ እያልኩ የማጫውታችሁ ይኖረኛል ።
 
አሁን ወደ አርበኞች ግንባር ።                
     
ኮለኔል ፍፁም ይስሃቅ በቅፅል ስሙ “ሌኒን’ የአርበኞች ግንባር ፤ የድምሕትና ፤ የግንቦት 7 ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጉዳይዋና አዛዥ ። በወታደራዊ ሰንሰለቱ “በስሪት አሃደ” በጀነራል ተክሌ ማንጁስ ስር መተዳደር የሚገባው ። ግን ከወታደራዊ ሰንሰለት ውጪ በቀጥታ ከፕሬዚደንቱ ፅ/ቤት ዋና ሹም ከኮለኔል ተስፋ ልደት ተ/ስላሴ ጋር የመገናኘት ስልጣን ያለው ።
ሻለቃ ሓድጎ የአርበኛችና የግንቦት ሰባት ተዋጊዎች ጋር አብሮ የሚኖር የእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸውን ተቆጣጣሪና በአርበኞቹ ላይ ያለገደብ ሙሉ ስልጣን የነበርው ።( ከኮለኔል ፍፁም ይስሃቅ ጋር ባለመግባባት ከስልጣኑ የተነሳ) ።
ሻለቃ ዳዊት የዲምህት TPDM ተዋጊዎች ጋር አብሮ የሚኖር የእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸውን ተቆጣጣሪና በተዋጊዎቹ ላይ ያለገደብ ሙሉ ስልጣን ያለው ። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ከሻለቃ ሓድጎ መባረር በኋላ የአርበኞች ግንቦት 7ና የድምህት ተዋጊዎች ላይ ሙሉ ስልጣን ያለው ።
ኮለኔል ተስፋ ልደት የፕሬዚደንቱ ፅ/ቤት ዋና ሹም ።
( እኔ በነበርኩበት ጊዜ) ኮለኔል ጣእመ አብርሃ ጎይቶም በቅፅል ስሙ “መቀለ” የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ወታደራዊናፖለቲካዊ ጉዳይ ዋና አዛዥ የነበረይህ ሰው ኮለኔል መንግስቱ ኅይለ ማርያምን ለመግደል በሻእቢያ ወደዚምባቡዌ ተልኮ ተነቅቶበት ተይዞ የተመለሰ ነው ።
እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው የሻእቢያ ወታደራዊ የጦር መኮንኖች ፤ቀጥታ ግንኙነት ከሌለው ከኮለኔል ተስፋልደት ተ/ስላሴ በስተቀር ሁሉም ፈላጭ ቆራጭ አዛዦች ናቸው ። በህይወት ላሉትም ሆነ ህይወታቸው ላለፈው ሰዎች ቀጥታ ተጠያቂዎች ናቸው
ከነዚህ ከላይ ከጠቀስኳቸው ሌላ የየድርጅቱን ሰራዊት ለውጊያ ወደ አገር ውስጥ ይዘው የሚገቡ መስመራዊ አዝማች የበታች ሹማምንት አሉ ።
በምንም መልኩ ጦርነት ከተነሳ አገራችን የምትወረረው በሻእቢያ ነው ። አዝማቾቹ ደግሞ እነዚሁ ከላይ የጠቀስኳቸው ወታደራዊ ሹማምንቶች ናቸው ። በሻእቢያ ቅኝት የሚራመዱት ደግሞ እንደ ባንዳ ወይም የሻእቢያ አጋሚዶ ሊቆጠሩ ይገባል ። እኔ እስከማውቀው ድረስ በሻእቢያ አመራር የሚዋጉ ፤ በራሳቸው ጦርነት የማንሳትም ሆነ የመዋጋት ወታደራዊ ብቃትም ችሎታም እንዲኖራቸው አይደረግም ፤ አይፈቀድምም ።
ይህ እየተሰማ ያለው  የጦርነት ነጋሪት ተጋግሎ ጦርንርት በሁለቱ አገሮች መካከል ቢነሳ አሁን ሻእቢያን አመራር የሚከተለው ሁሉ ሻእቢያን ደግፎ ሊሰለፍ ነው ማለት ነው? ተጨባጭ ማስረጃ እስካሁን ድረስ ባላገኝም ፤ በታሪካችን በሶማሊያ ጦርነት ጊዜ ሶማሊያን ደገፉ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ያንን እድፍ እስከዛሬ ድረስ አጥቦ ማፅዳት አልተሳካላችውም ። ዛሬም ሻእቢያን የሚደግፉ ወገኖች ቆም ብለው ሊያጤኑ ይገባቸዋል እላለሁ ።
አርበኞች ግንባር ቀድሞ ከነበረው ሃይል ሆን ተብሎ በየጊዜው እንዲመናመን ተደርጓል ። ምክንያቱም በውስጡ ያሉት ሰዎች በአብዛኛው አማሮች ናቸውና ። በሻእቢያ ህሳቤ አማራ ማለት የኢትዮጵያዊነት ቫይረስ ተሸካሚ ማለት ነው ። ሻእቢያ ደግሞ ኢትዮጵያ እስካልፈራረሰች ድረስ ኤርትራ ሙሉ ነፃነቷን ገና አላገኘችም ብሎ የሚያስብ ድርጅት ነው ። ስለዚህ የአማሮች መጠናከር አደጋ ያመጣል ብሎ ያስባል ። አማራ ያልሆኑ ሰዎችን ግን እንደፈለኩ አሽከረክራቸዋለሁ ብሎ ያምናል ።
ግንቦት 7 በሰው ሃይል አኳያ ከአንድ ሰው የእጅ ጣት በማይበልጥ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ነው መሰብሰብ ችሎ የነበረው ። እነዚህ ሰዎች ደግሞ ያለፍላጎታቸው ወደአውሮፓ ትሄዳላችሁ ። እዚያም የግንቦት ሰባትን አላማ ታስተምራላችሁ ። በመጀመሪያ ግን ኤርትራ ስልጠና ትወስዳላችሁ ተብለው ባዶ የውሸት ተስፋ ተሰጥቷቸው ከመጡ በኋላ እዚያው ሓሬና ማሰልጠኛ ጣቢያ ለሻእቢያ ባሪያ አስዳሪዎች መጫወቻ ሆነው የቀሩ ሰዎች ናቸው ። ስለዚህ አርበኞች ግንቦት 7 የተባለው ውህደት ትልቁን ቁጥር ልስጠውና ቢበዛ ከመቶ ሃምሳ  በላይ ተዋጊ የለውም ።። በነገራችን ላይ የግንቦት ሰባት ተዋጊዎች ናቸው ተብለው ፤ አይደለም ከፊት ለፊት ፤ ከኋላ እንኳን የተነሱትን ፎቶ ድርጅታቸው እስከዛሬ አሳይቶን አያውቅም ። የሌሎችን ድርጅቶች ፎቶዎችና ፊልሞች በገደምዳሜ የራሱ ለማድረግ ሲሞክርና ሲያሳይ ግን አውቃለሁ።
 ኦብነግ ( የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር) ከሌሎች የኢትዮጵያ ተዋጊ ሃይሎችና ድርጅቶች ለምሳሌ ከአርበኛችግንባር ድምሕት ወይም ከኦሮሞ ነፃ-አውጭ ርድጅት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይኖረው ተደርጎ ተነጥሎ ለብቻው ቀይ ባህር ላይ የተቀመጠና ልዩ ቁጥጥር የሚደረግበት ድርጅት ነው ።
 ያም ሆነ ይህ ኤርትራ ውስጥ ተዋሃደ የሚባለው አርበኞች ግንቦት 7 ፤ ብቻውን በራሱ ለውጊያ ብቃት አለው አልልም ።
የጦርነቱን ዜና እኛ አደረግነው እያለ አርበኞች ግንቦት 7 በራሱ ሚዲያ ቢወተውትም ፤ እየተዋጉ ነው ተብለው የምናያቸውና የምንሰማው ግን ድምህትቶ ናቸው ። የትግራዩ ድርጅትም ተዋህዷል እንዴ?

ተግባር አሸናፊ ነው! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 14.07.2015 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

ግን ዓይኔ የኔ ነበርክን? መንፈሴስ? በእርግጥም ከእኔ ጋር ነበራችሁን? „ የአንቺ – ነበርን“ – መልሱ።

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

አይደለም ዛሬ ቀድሞም ቢሆን ትግራይ – የበላይ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይን ለድል ያበቃው ጥንካሬው – አልነበረም። ጦርነትን ለማሸነፍ ሚስጢር በመዳፍ መሆንን – ይጠይቃል። አቅም ያለው፤ ቀልፉን የያዘ ሥጋና ደም ነበረው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ነበር ማለት – ይቻላል። ተገለን ተጨቁነን ነበር የሚለውን ቅጥፈት አመድ የሚያአደርገውም ይህ ቆሞ የሚሄድ – የታሪክ ሃቅ ነው። እነዛ የዘር ልክፍተኞች እንደ የተሰጣቸውን ሃላፊነት፤ የገቡትን ቃል ተላልፈው ታማኝነታቸውን አፈር አስግጠው ሚስጥርን እንደ ቄጠማ ባይነሰንሱት ኖሮ፤ በሁለት ቢላዋ ባይበሉ ኖሮ .. ኖሮ ኖሮ ወያኔና ኑሮው በጫካው የዕድሜ ልክ በሆነ ነበር። ክህደቱ ሀገርን እንዲህ አፈረሰ – ትውልድንም ቀጣ። ያን የመሰለ በ200 ዓመት ሊገነባ የማይችል ተቋማት፤ የመንፈስ ሃብታት ሁሉ – ፈራረሰ። በውስጥ አርበኛ – ባንዶች። ዛሬም የነፃነት ትግሉን ካባ ደርበው ውስጣችን እያረዱ የእኛ የሚመስሉ ግን የእኛ ያልሆኑ አሉ። ስለዚህ ቅኖች በቅንነት የሚያስተላልፉትን መልዕክት እንዳሻቸው በማደረግ፤ በመደለዝ ምኞታችን ህልማችን እንዲጎዳ ጥፈረ መጥምጦች አሉና ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፤ ጋርድ ተቁሞ ተውሎ የሚታደረውም – ለዚኽው ነው። የሳይበሩ ጦርነት ቅራኔው እዬከረረ በመጣ ቁጥር እጅግ የከፋ በመሆኑ ብዕሮች ትጥቃቸውን ጠበቅ አድርገው ሊጠብቁት ይገባል ነው – ዕድምታው። ህልም እንደፈቺው እንዳይሆንም፤ ብልህነት መልካም ስለሆነ ነበር የጻፍኩት። እንጂ ትራሴን ከፍ አድርጌ መተኛት – ይቻለኛል።

ጤና ይስጥልኝ የተከበሩ አቶ ይገረም አለሙ እንዴት ሰነበቱልኝ – በአያሌው። እጅግ አድርጌ – አመሰግነወታለሁ። ከሁሉም በላይ እንዲህ ቅርብ ያደረጉኝ መሆኑን በአሁኑ ጹሑፉዎት – ተገነዘብኩ። እንኳንም – ፃፍኩት። በውስጠዎት ሥርጉተ ያላትን የእህትነት ልዩ ቦታ መረዳት – ቻለች። እናም ሐሤትን አፈሰች – ቸረፈሰች። ከልቤ ነው ተረብ – እንዳይመስለዎት። እሺ!

ውድ ወንድሜ – ዛሬ የኔው ይባሉ፤ ወያኔ መጥላቱ ብቻ በቂ – አይደለም። ይህን ተግባር ላይ ስላሉ የሚውቁት – ይመስለኛል። ወያኔን ሃርነት ትግራይን የጠላንበትን መሠረታዊ ምክንያት ሥሙንም  ግብሩን ተንተርሶ ያወጣው ማንፌስቶውን ነው። ማንፌስቶ የተመሰረተበት ዓላማና ተልዕኮ – አለው። ተልዕኮውና ዓላማውን በመፈጸመና በማስፈጸም እረገድ ግዳጁን የተወጣ የጎጥ ድርጀት ነው። የቀረውም ቦታም ካለ እስከ ተኛን ድረስ – ይቀጥላል። ስለዚህ ዘንበል ወይንም ዘመም ብለው የሚቀርቡ ሃሳቦች ወደ ዬትኛው መንገድ ወይንም አቅጣጫ ወይንም ተፋሰስ እንደሚነጉዱ ወይንም ለዬትኛው ፍላጎት አቅም ሊሆኑ እንደሚችሉ ቆም ብለን በማስተዋል ሊቃኝ ይገባዋል ነበር የጹሑፌ – ዕድምታ። ያነበብኩት ከልብ ነበር ውስጤን ሰጥቼ –  ቢያቅለሸልሸኝም – ስለማከብረዎት። ፁሑፎዎት ዘሃበሻ ብቻም አይደለም ፖስት ያደረገው፤ ሌላ ቦታ ላይ – ተገናኝተናል። በጎሪጥ ሳላዬው ተዚኽም አለህ ለካ? ብዬ ከአቦል አስከ በራካው ቤት ያፈራውን የቡና ቁርሳችን እዬከሰከን – በቤተ – ኢትዮጵያ – ተንበሽብሸንበታል።

ወንድሜ – እኔ አይጋ ፎረም ገብቼ – አላውቅም። ምን እንደሚመስል መልኩንም ገፁንም – አላውቀውም። ወይንም በስልትና በጥበብ፣ በሚያምር የድምጽ ቅላጼ የመርዝ ሰለባ ለመሆን – አልፈቅድም። „ሲወዱም ሲጠሉም እስከ ንፍጥ ልጋጉ“ ይላሉ ጎንደሬዎች። ማለት የሸገር ራዲዮ ታዳሚ – አይደለሁም። ከሰማዬ ሰማይት በላይ ቅዝፈት በሚያሰኘው ጹዑም ድምጽ ዲዲት እሰኪበቃው ድረስ – ይረጫል፤ ዬኢትዮጵያዊነት ተቋማት ሁሉ – ያለርህራሄ ይደረመሳል – ዝግጅቱ። የተረሱ የቂም ኩትኩቶችን እዬቀራረፈ – ግመጡት ይላል – መሰናዶው፤ በፍቅር እብድ የሚሉ የተሰለቡ አሉ ማር ወላላ በሃሞት ጠቅልሎ  – ስለሚያዘንብላቸው፤ እኔ እህተዎ የተመሠረተበትን መሰረታዊ ፍላጎት ጠረኑን ከሩቁ – አውቀዋለሁ። „አማራጭ ራድዮ¡“ እንዴት ተቀለደ?!  ህም – ምን ልልዎት ነበር ለማለተርፍበት ጊዜ – አልከስርም። እምታደምባቸው ድህረ ገፆችም ቢሆኑ እጅግ ውስን – ናቸው። እኔን የሚመስሉኝን  – ብቻ። ውስጤን የሚፈውሱትን – ብቻ። ወይንም ዕንባን ሳይረገጡ ግን የተለዬ ሃሳብን የሚያስተናግዱትን – ብቻ፤ ወይንም ማጣቀሻ – ሲያስፈልገኝ፤ ወይንም ትንተናቸው ት/ቤቴ የሆኑትን ብቻ። ነገረ ጥፋትን ወያኔዊ ተፋሰሱንማ –  አድገን አረጀንበት እኮ፤ ጥዋት ማታ የሚፈሰው ዕንባ ይበቃል …. ዜናው እሱ ነው መሽቶ እስኪ ሲነጋ …. እሱም ይሰንብትልንም እዬተባለ ነው¡ – እያደመጥን፤ አይገርመዎትም መከራ ይቀጥል … ህም!

ሌላው ሃሳበዎትን በሃሳብ ሙግት እንዳልተመቸኝ የጻፍኩትም – ስላከበርኩዎት ነው። እርስዎ ሳላነብ እንደጻፍኩት አድርገው ነው – የገለጹት። አልከፋኝም። ሁሉንም ለማስመቸት ነው አደባባይ – የወጣሁት። ከዚህ በበለጠም ፈጨትም – ደቆስም ቢያደርጉኝም በመከራ የሰለጠነ ሰብዕና ስላለኝ አቀባበል ይደረግለታል –  ደስ ብሎኝ። ተደብቄ – አላውቅም።

አማርኛ ቋንቋ የፍልፍስና – ቋንቋ ነው። አማርኛ ቋንቋ የምርምር – ቋንቋ ነው። አንዱ ቃል፣ አንዱ ስንኝ፣ አንዱ ፊደል በዬሥርአቱ ሚስጢርን – ይቃኛል። ድምጽ ምቱ እራሱ ነጮች የቀረብን – ይሉታል። ቲያትርም – እጫወታለሁ። የቲያትር ቲሙ እኔን ከሚፈልግበት ዋንኛው አማርኛ ትረካዎቼንና ግጥሞቼን እጅግ ስለሚያፈቅሩት – ነው። ሙዚቃዊ ቃናው በነፋሻማ ምት እያዝናና፣ እዬጠገነ በልስሉስ መዳፉ – ይፈውሳል – ድህነትም ነው። አማርኛ ቋንቋ የአፍ መፍቻ ቋንቋዬ ነው። የጻፉት አሳምሮ – ገብቶኛል። እርግጥ – እርእሱ አልሰረሰረኝም። ወይንም እኔን ለመዝረፍ አቅም – አልነበረውም።

የማከብረዎት ጸሐፊ አቶ ይገርም እኔ የፖለቲካ መሪ – አይደለሁም። ወይም የፓርቲ አባል – አይደለሁም። ስለዚህ ውስጤን ግልጥልጥ አድርጌ ለማሳይበት የታሰርኩበት ፕሮግራምና የፓርቲ ደንብ – ገመድ የለም። ገፊ ኃይል የለኝም – ከዕንባ በስተቀር። ፖለቲካ መሪዎች ሆዳቸው የሚውቀውን ሃቅ ለበስ አድርገው በቅኔ – ይቃኙታል። ፖለቲካ ሥነ ጥበብ ነውና። ሥርጉቴ ግን ክንብንቡን ገለጥ አድርጋ ተክለ ቁመናውን ከውስጧ ጋር በሃዲድ – ታገናኘዋለች። የሆነ ሆኖ ህዝብ መስታውት ነው ዳኝነቱን ለብዙኃኑ ህሊና – አስጠዋለሁ። አንድ መስመርም ላይ ካለንም ደስታውን አልችለውም – ችርስ! በዚህ ባንመቻች በሌላው ይደምር ነው አይደል? በነገራችን ላይ የጹሑፎዎት ሊንክ በሙሉ – እይዛቸዋለሁ ዝምድና ስላላቸው – ከስሜቴ ጋር። ሳይመቸኝ ደግሞ እንዲህ ቅርቤ ስለሆኑ ወጥቼ አልተመቹኝም – እላለሁ። ሸጋ ነው አይደል?! እንደወደዱት መግቢያወት ፏ ብሎ አቀባበል – አድርጎልኛል። ለማንኛውም የወያኔ ሃርነት ትግራይን ማጣጣል ከፈለጉ ሥርዓተና ህግን በተሟላ ሁኔታ ያለው እጬጌው – ቅኔኛው አማርኛ ቋንቋ ህገ = ነጥብ አለው ስላቅ የሚባል ¡ እርስዎም ያውቁታል በዚህ ቢጠቀሙ ኖሮ በተወሰነ ደረጃ መግባባት እንችል – ነበር። ሌላው ስድስት ገፅ እንደሆነም – ነገርውኛል። የተሸከመው ዬዘሃበሻ ብራና ነው። ዘሃበሻ ስብሰባውን የሚመራበት ህገ ደንብ ሲኖረው በፍትሃብሄሩ ህግና ሥርዓት ክሱ – ይቀጣኛል ወይንም በወንጀለኛ መቅጫውና ሥርዓት። የተዳፈነ ወይንም የተከረቸመ ሙግት የለም። ያ ሙግት አይደለም። ተጠዬቅ ለማለት አቃቢ ህጉን፣ ዳኛውን፣ ጠበቃውን፣ ችሎቱን ሊይ የታደመውን ግራቀኙን መርታት መሠረት ያደረገውን መነሻውን ሳያስታምሙ ወይንም ሳያቆላምጡ መፋለም የተገባ ነበር።ከአያያዝ ይቀዳል ከአነጋገር ይፈረዳል“ እንዲሉ።  አማርኛ ቋንቋ እንደ ወድአራባ – ወዳከር ወይንም ደበር እንጀራ ሊጥ ሊሸበልል – አይችልምቦንዳም ወይንም ጣቃም – አይደለም። እራሱን መግለጽ እንዲችል ሆኖ የተፈጠረ ፀዲቅ ነው። እንደ ተፈለገ በክትና በዘወትር ቃናዎች ማዘናጠፍ – ይቻላል። ስለዚህ ሙግቴ ብትን ብሎ መብራራት – ስለነበረበት በፈቀድኩት መልክ – ተከውኗል። አንድ ተናጋሪ ለንግግር ከመሳናዳቱ በፊት ንግግሩን ሊያግዘው ፤ ለንግግሩ አጥንትና ሥጋ ሆኖ እንዲያቆመው መረጃዎችን በእውነት ላይ ተንተርሶ በአግባቡ እንደ ዕርዕሱ ፍላጎትና ዝንባሌ አቀናብሮ በዘርፍ ዘርፎ አደራጅቶ ማቅረብ – አለበት። በሚገባ ተሰናድቶ። ጸሐፊም እንደ ተናጋሪ ማለት ነው። ልዩነትም አንድነትም እንዳላቸው ለማጠዬቅ ነው „እንደን“ የተጠቀምኩት።

ሌላው አጫጭር ጹሑፎች ለራዲዮ፤ ለዜና፣ ለማስታወቂያ፤ ለባራሪ ጹሑፍና ለርዕሰ አንቀጽ የሚያገልግሉ ናቸው። ይህን በሚመለከት ከ5 ዓመት በፊት ድህረ ገጼ ላይ ያልሰረዝነው አለ። እንዲያውም የዛን ጊዜው እና የዛሬውን አቋሜንም ያሳዬወታል። በድምጽ ነው የተሠራ …. ለናሙና እንጂ ከጹሑፉ ጎል ጋር አደራጅቶ መምራቱም ቢሆን – ተኑሮበታል።

http://www.tsegaye.ethio.info/kana.html (www.tsegaye.ethio.info)

  • እስከ መቼ?
  • ክብር ከሚሸጥ …
  • ምን ምን ይሸትሃል?
  • ሞትና ሞት ሲፋጠጡ …
  • የራህቡ ነጋሪት ከአምስት ደቂቃ በላይ አልሄዱም ከሙዚቃ ጋር —-

ወንድሜ ሆይ! እርቅና ሰላም የሚወርደው በጥት ፍልስፍና – አይደለም፤ ነገን ለማሳደር ሃቅ ዓይነ እርግብ ተዘጋጅቶለትም – የማይሆን ነው። ቀጥ ባለ ግልጽነትና – ቀጥተኝነት እንጂ። ምንም እንኳን እርስዎን ባይመለከትም ጦር የተመዘዘበት የጋራ ሃብታችን አማርኛ ቋንቋ ከመሰረቱ ጠፍቶ በትግረኛ ቋንቋ እንዲተካ ተግቶ በታታሪነት እዬማሰነ ያለው የትግራይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንዴት ድቅቅ እንዳለ አንድ ጨዋታ – ላወጋዎት – ፈልግኩኝ። ያው ቋንቋውም የጥቃቱ ሰለባ – ስለሆነ። ዝምድናችንም – እንዲጠብቅልን በማሰብ፤ ቀኑን አላስታውስውም ሚዚያ ላይ በያዝነው ዓመት „አርተ“ የሚባል የኦስትሪያ የጀርመንና የሲዊዝ የጋራ የቴቪዥን ፕሮግራም አለ። „የትምህርት ሂደትና የትውልዱ እንክብካቤ“ የሚል በታላቋ ብርታንያ እና ኢትዮጵያ ያሉ ሁለት የ13 ዓመት ታዳጊዎችን በንጽጽር አቅርቦ ነበር። በዛ ፕሮግራም አፋር ነበር – የተመረጠው። የ13 ዓመት ታዳጊ ወጣቱ ሃመድ ት/ቤቱ ለመድረስ የሦስት ሰዓት የእግር ጉዞ – ያደርጋል። ደርሶ መልስ ስድስት ሰዓት፤ ቃጠሎ ነው ቋያ ነው። መንገዱ አሽዋ ነው። ውሃ ጥሙ ይህ ነው አይባልም ለዛ ለጋ – ቀንበጥ። ወደ ቤቱ ሲመለስ መንገድ ላይ ካለው ምንጭ መቅጃ ሳያስፈልገው አንገቱን ከጉድጓዱ ውስጥ እንዳለ አስገብቶ ተጎንብሶ – ይጠጣል። አይጠቅመውም – ተቃጥሏላ! ሃመድ ጎበዝ የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ነው። በሂሳብ አጅግ ጎበዝ ነው። ጋዜጠኛው „የትኛውን ትምህርት ትወዳለህ ብሎ ሲጠይቀው“ „አማርኛ ቋንቋን“ አለው። „ለምን?“ ሲለው „ስለምወደውና ከወገኖቼ ጋር መግባባት እንድችል“ አለው። በቃ የ40 ዓመት የተጋዳላይ ተልዕኮ አሽዋ ውስጥ ሲቀበር ቁጭ ብዬ – ተመለከትኩት። ተነስቼም ሻማ – አበራሁኝ። እንዲህ ነው ፈጣሪ ካሳ – የሚያዘጋጀው፤  ስለዚህ አማርኛ ለእኔ – ፀሐዬ ነው። በስስት ነው – እምወደው። አይቼም – አልጠግበውም። ማለት የፃፉት በመደዴ አልተሄደበትም – ገብቶኛል ለማለት ነው። ስለሆነም ለጻፍኩት መልስ ይቅርታ – አልጠይቅበትም። ትውልዱ አበጥሮና አንተርትሮ እንዲያውቅ በምፈልገው መልክ ተዛማጅ በደሎችን አክዬ – ኮልሜዋለሁ። ግቡን እንደሚመታም ተስፋዬ ዝልቅ ነው። „በቃኝን – እንዲያነጥር“ ሆኖ ተላከ። እርግጥ ነው ዕራእሱ ብቻውን ወንዳታ የሚሉለት  – ይኖራሉ። የእርስዎ ትንተና የሚመቻቸውም – ይኖራሉ። ክር ላይ የተንጠለጠሉ ዕሳቤዎች ጥገታቸው ስለሆነ። ኤንም ቢንም ሲንም ዲንም እንዳይከፋው መንደር ፍለጋ ሲማስኑ ውለው ለሚያድሩት ሊመች ይችል – ይሆናል። ለእኔ ግን ከእርእሱ ጀምሮ  – አልተመቸኝም ነበር። የአንድ ጹሑፍ እርእስ አኮ ጎል – ነው። ውስጥ ሳይገባ እርእሱ ራሱ በቂ  – ነበር።

ይህ ያነሱት ነጥብ በ90ዎቹ አጋማሽ እንደ ኢሮፓ አቆጣጠር አሽኮኮ የተበላለት ሃሳብ – ነበር። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከራሱ በበቀሉ ይጠፋል የሚል ዕድምታ የነበራቸው ወንድሞቼና እህቶቼ ብዙ – ደክመውበታል። እነዛ አድራጊ ፈጣሪ ሆነው የተከበከቡት ወገኖቻችን ግን ለቀለም ትምህርት ቅድሚያ በመስጠት ያን ተስፋ ጣል ጣል አድርገው እንጀራቸው ላይ በማተኮር ዛሬ እናቴ ቢጠሯቸውም – አይሰሙም። በቀለሙ ከመጨረሻው ደረጃ – ደርሰዋል። ያን ጊዜም ቢሆን „ትግራይ የሞተለትን ያህል አልተጠቀመም“ ነበር – ሙግታቸው፤ ወይ መዳህኒተአለም አባቴ እል ነበር ያን ጊዜ? ይገረም አሉ ሥመዎትን ይገረም ነው ነገርዬው፤ ዛሬም ቢሆን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከሥሩ ይነቀል ቢባሉ የሚስማሙ – አይመስለኝም። ክርና መርፌ የሚያደርጋቸው ማጣበቂያ መስመር አለና። የተከደነች ኪዳን አለች። ስለዚህ በዚህ ሃሳብ ዙሪያ ተደክሞበታል እነ አጅሬ ግን ወይ – ንቅንቅ!  እርግጥ ለዬት አድርገን ልናያቸው የሚገቡ ምርጥ ወገኖቼ እንዳሉ – አውቃለሁ። ዘውድ – የተከበሩ አቶ ገ/መድህን አርያ አይነት፤ በፐርሰንት ሲታይ ግን እጅግ ዝቅተኛ – ነው ዳታው።

ሌላው የተጎዳው አይደለም ቀልብ – የሚሰጠው። የአያያዝ ጥበቡም ቢሆን ተጠቃሚው ሲቆላመጥ ተዘውትሮ – ይታያል። ኑልን ተብሎ ሲለመን። ለእኔ ይህ የተንጋለለ – ነው። የተጎዳው ደግሞ እኩልነት ቀርቶበት ለሥነ – ልቦናው ራፊ ሲደረብለት – አይታይም። ብልጫው ቀርቶበት ማለቴ ነው። ማስታመሙ ይበቃ ነው – ጹሑፌ ያለው። ጊዜ ከመብላት አቅምን እንደ ዘር ከመበትን በስተቀር ትርፉ – ምንም ነው። አልጨመርነም። በ24 ዓመት ስንት አሉን?! ስንቶቹ ናቸው የእኛ – የሆኑት። እንዲያውም ከእኛ የተዘረፍነው የሚያል ይመስለኛል። አሁን እራሱ  ዬአርበኛውን እንቅስቃሴ በነቂስ እንደ ጦር ይፈሩታል ብዬ አስባለሁ። በነቂስ እንደ ጦር ይፈሩታል ብዬ አስባለሁ። ለዚህም ነው „ኤርትራ“  እነማን? ከእነሱ በላይ ላሳር – ያልንላቸው። ለዚህም ነው „ኤርትራ“ አጀንዳ የሆነችው። እናም ሁል ጊዜ ፍላጎታችን ቁልቅል ….

እንዲሁም – በፖለቲካ አስተሳሰብ ወተት ያደገውን እና ህሊናው ሊለማ የሚገባው ዕንቡጥ መንፈስ እኩል አይተረጉሙትምት – ጹሑፉዎትን። ለዚህ ነው በፈቃደኝነት በዘበኝነት የነፃነት ትግሉን እያገለገልኩ – ያለሁት። በትርጉም የሚቃናውን – በትርጉም፤ በሥርዓት መታረቅ ያለበትንም – በህግና በጭብጥ – እምፋለመው፤ የእኔ መርኽ ተከስክሰው ወይንም ተልከስክሰው ሊቀሩ የማይገባቸው የሃቅ ወርቆች በአታቸው መንበራቸው ላይ መሆን ይገባቸዋል ባይ – ነኝ። በመርህ ደራጃ በችግራችን አመንጪ ላይ መስማማት ካልተቻለ መፍትሄ አምንጭነቱም የጫጫ ነው የሚሆነው። ፍላጎታችን – ንፋስ በነፈሰ ቁጥር ሲፍረከረክ እንቦጭ ብሎ ሲወድቅ የሚታዬውም ለዚህ ነው።

የትም ቦታ ተሰክስከው ቀን አብረው ይተክላሉ፤ ሌት ሲነቅሉ – ያድራሉ። አቅም የማያድግበትም፤ አቅም የሚሳደድበትም ምክንያት ይሄው ነው። ቆዳ ለእኛ፤ ሥጋ – ለሥጋ። ይህን – አይተናል። ትናንት ኢትዮ ኤርትራዊውን የአጥፊው ማንፌስቱ መሥራች አዛውነቱን አቶ ሰዬ አብርሃምን ካልተቀበላችሁ፣ ዘውድ ካላደፋችሁ ይምራን ይግዛን ይንዳን ብለው ተራማጅነትን – አወጁ። ወይንም እስከ መገንጠል ብለው፤ አሻም ያልነውን ደግሞ በአጥር ጣሾች በተራማጅ ሃሳብ ሥር ይሾጎጡና እዬተገላበጡ እያደኑ አቅምን እንዴት እንዳወደሙት – ታዝበናል። ይገርመወታል ለጎሰኝነት ጥብቅና ቆመው አውራ የነበሩት ዛሬ ደግሞ በአንድ አፍ ሁለት ምላስ ሆነው – እያዬን ነው። ጃንጥላውን ሸንቁረውም ሸንጉረውም – ፈረሰ። ያ ጃንጥላ ግርዶሽ – ነበር። እንዲህ ዓይነት ሃሳቦች ድሎታቸው ነው።  አብዝተው ያደባሉ አቅም ብቅ ሲል ከተቀበሩበት ይወጡና ጦርነት – ያውጃሉ። ግን ምንግዜም አዝማቹ – ተግባር ነው። ተግባር – ያሸንፋል። አሸናፊው ተግባር ያስቀደመው ሃሳብ ደግሞ የብዙኃን ነው። አሁን አውላላ ሜዳ ላይ ያሉ – ይመስሉኛል። ትግሉ ዓላማን ማሳካት ሆኖ ሳለ ህዝበ ጠቀም በሆነ ፍላጎት ላይ ስንጥር ማባዛት። በቃ! ለነገሩ በሚመጥን ተግባር የሚመጥን ፍቅር ይዛቅበታል። በስተቀረ አይደለም መጠለያ – መቆናጠጫም አይኖርም። ስለዚህ ቀዳዳ የሚከፍቱ ነገሮች ሁሉ ጥንቃቄ ሊሰጣቸው ይገባል። አብሶ እርእስ በሚገባ በተደሞ ሊታይ ይገባዋል።

አዩ ወንድምአለም — ይህን የማነሳለዎት በምክንያት ነው። ተጠቃሚው በሥነ ልቦናው ላይ የደረሰበት ጉዳት – የለውም። ሥነ ልቦናው የበላይ ነው። በግራ በቀኝ ነው የሚደገፈው። የተጎዳው ግን ሥነ ልቦናው በግፍ – ተደርምሷል። መንፈሱ በልዟል – ወይቧል። ማዲያታማ ሆኗል። በተቀጠቀጠ ሥነ ልቦና አቅም መገንባት ፈፅሞ –  አይቻልም። ከምንግዜውም በላይ አቅምን ለማምጣት የተጎዳውን ሥነ ልቦና በጥሩ አቀራረብና አያዬአዝ የኃይል ምንጭ ማደረግን – አሁን ይጠይቃል። እሱዎ ያሉት ሃሳብ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩለዎት በ90ዎቹ አጋማሽ ብዙ – ተደክሞበታል፤ ግን – አልሠራም። እንዲህ በቀላሉ ለቅለቅ ተደርጎ ማጥራት – አይቻልም። የተጎዳና ያልተጎዳን፤ ተጠቃሚና – ተገፊን በእኩል አያያዝ በአንድ ማስኬድ በፍፁም – አይቻልም። እውነቱ ይሄ ነው። ከንፍሮ ጥሬ ካወጣቸው እጅግ እጅግ ጥቂቶች በስተቀር ጥቅሙን የሚጻረር ተጠቃሚ – የለም። ኑሮም – አያውቅም። በዬፌርማታው ነው – የሚንጠባጠበው። ንክኪ ያለው ሁሉ። ጥርት ላለ ድል ጥርት ያለ አቋም ወሳኝ ነው። በጥገና  – አይሆነም። በውሽልሽል ዕሳቢም ቀዳዳ በቀዳዳ ነው – የሚሆነው። የማይጠገነው – አይጠገነም። ሁለት ውሃ ዬያዘን ብርጭቆ አንድ ብርጭቆ አድርጎ ማዋህድ – አይቻልም። ቢሞከር ብርጭቆው ይሠበራል ውሃውም – ይፈሳል። ሃቁ ያለው ከበይ ተመልካቹ ሳይሆን – ከተጠቃሚው ነው። ተጠቃሚው አልተጠቀመም እዬተባለ አቅም መፍጠር – ፈጽሞ አይቻልም። በእኛ ውስጥ ለመኖር ጥቅምን በርግጫ ማለት – ያስፈልጋል። ስለማያውል – ስላማያሳድር። ስለማያሰነብትም። በመርኽ ድርድር – የለም። no አልተግባብቶም – yes ተግባብቶ። ይሄው ነው። ጨረስኩኝ። በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ይህ የመጨረሻዬ ነው። ሌላ ከኮለሙ ደግሞ ካልተመቸኝ መስመር ላይ እንገናኛለን .. ወይ ፌርማታው ላይ እንጠባበቃለን … ደህና ይሰንብቱልኝ። የእኔ ድንግልም – ትጠብቅልኝ።

የኔዎቹ እኔ ሰንበትን ተንተርሼ – አሰብኩኝ። ለዛውም አሁን ጥብብ ያለ ጊዜ ላይ – ነበርኩኝ። ታዲይንላችሁ በድንገት አቶ ይገርም ወደ ቤተ ሥርጉተ ጎራ አሉና ቡናና ሻይ፤ ሽሮዋንም ተከተክ አድርጌ በዘንጣፌ ቤት ለእንግዳ ስልላችሁ እግረ መንገዴን ናፍቆቴቼን ግኝት። መሸቢያ ሰሞናት! ዘሃበሻ ኑሩልኝ – ለምልሙልኝ።

„እንቅልፍ ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም!

አርበኞቻችን መርሆቻችን መንገዶቻችን ናቸው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

መላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች፦ ዒድ ሙባረክ! –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0

ለ፴(ሰላሣ) ቀናት በፆም እና በፀሎት ተወስናችሁ፣ ፈጣሪያችንን ስትለማመኑ የከረማችሁ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ወገኖቻችን፦ ኢድ ሙባረክ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

moreshበመሠረቱ የረመዳን የፆም ወር በረከትን እና መተዛዘንን ይዞ እንደሚመጣ የሚታመንበት ወቅት ነው። ሙስሊሞች በዚህ ወቅት ራሣቸውን በፆም እና በፀሎት ወስነው፣ ፈጣሪያቸውን ከመለመን ባሻገር ለድሆች ሠደቃ (ምፅዋት) በመለገስ፣ ለሌሎች ሰዎች ውለታ በመዋል፣ ለተራቡ በማብላት፣ ለታረዙ በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ ሌሎችንም በጎ ተግባሮች በማከናወን ያሣልፉታል። ሆኖም ያለፉት ፳፬(ሃያ አራት) ዓመቶች ለኢትዮጵያውያን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ታላቅ የሠቆቃ እና የሽብር ዓመታት ሆነው ዘልቀዋል። ገና ከጥንስሱ «በከፋፍለህ ግዛው» መሠሪ የአገዛዝ ዘዴ ኢትዮጵያውያንን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሣው የትግሬ-ወያኔ፣ ኃይማኖትን ለኢትዮጵያውያን የመፋጃ አጀንዳ ለማድረግ ያልፈነቀለው ድንጋይ፣ ያልማሰው ጉድጓድ የለም። ጥረቱ እንዳሰበው ባይሣካለትም፣ አንዳንድ የታሪክ ጠባሣዎችን ትቶ ማለፉ አልቀረም። ይህ የትግሬ-ወያኔዎች የአገዛዝ አቅጣጫ የባንዳ ወላጆቻቸው ጌቶች ከነበሩት ከፋሽስት ጣሊያኖች የተቀዳ ዘዬ ነው።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የእስልምና ዕምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በጀመሩት «ድምፃችን ይሰማ» በተሰኘው ሰላማዊ የመብት ማስከበር ጥያቄ የተደናገጠው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ፣ አያሌ የዕምነቱን ተከታዮች ለእሥር ሲዳርግ ጥቂቶችንም በግፍ ገድሏል።  ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በኢትዮጵያውያን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ላይ በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የሚፈፀመውን የጅምላ እሥር እና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በከፍተኛ ሁኔታ ያወግዛል።

በዚህ አጋጣሚ በአስቸጋሪ ሁኔታ በእሥር ቤት ውስጥ ሆነው እንደዕምነታቸው ሥርዓት የኢድን በዓል ለማክበር ያልቻሉትን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ሁላችንም በያለንበት እንድናስባቸው አደራ እንላለን።

 

ኢድ ሙባረክ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

ታማኝ በየነ የኢሳት ቦርድ ሊቀመንበር ሆነ

$
0
0

Tamagn copy
(ዘ-ሐበሻ) አክቲቭስት እና አርቲስት ታማኝ በየነ የኢሳት ራድዮና ቴሌቭዥን የቦርድ ሊቀመንበር መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጹ::

ታማኝ በየነ የኢሳት ቦርድ ሊቀመንበርነቱን ቦታ የተረከበው ከነአምን ዘለቀ እንደሆነ የገለጹት እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከጁላይ መጀመሪያ ጀምሮም በቦታው እየሰራ እንደሚገኝ ታውቋል::

ከደቡብ አፍሪካ እስከ አውስትራሊያ ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ በተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር ለኢሳት ገቢ ማሰባሰብ ከፍተኛውን ሚና እየተጫወተ የሚገኘው ታማኝ የኢሳት ቦርድ ሊቀመንበር ከሆነ በኋላ ቴሌቭዥኑ በዚህ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ የሚያሰራጨውን የ24 ፕሮግራም መጀመሩን መግለጹ ይታወሳል::


አብዱ ኪያር አዲስ ነጠላ ዜማ –መልካም አመት በዓል (ዘፈኑን እና ግጥሙን ይዘናል)

$
0
0

መርካቶ ሠፈሬ በሚለው ታዋቂ ዘፈኑ ከሕዝብ ጋር የተዋወቀው አብዱ ኪያር አዲስ ነጥላ ዜማ ለቀቀ:: አዲሱ ነጠላ ዜማው “መልካም አመት በዓል” ሲሆን መል ዕክቱም ጠንካራ እንደሆነ ግጥሙን ያነበቡ ሰዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::

ዘፈኑን ይመልከቱ; ከዘፈኑ በታች ደግሞ ግጥሙን አስተናግደናል:-

መልካም አመት በዓል – አብዱ ኪያር

ተሰብስበን እንዳማረብን
በአውዳመቱ ፍቅር ያዝንብብን
ቤት ለሌሉት ለራቁት በአካል
በያሉበት መልካም አመት በዓል

አንቺ የኢትዮጵያ እናት ይለፍልሽ
ከአመት እስከ አመት ይሙላ ጓዳሽ
አንተ የኢትዮጵያ አባት እሺ ይበልህ
ከሰው እንዳታይ እንዳይጎድልህ

ጀግናዋ እህቴ የናቷ ልጅ
ከብረሽ ቆይልን ውለጅ ክበጅ
ወንድሜ አንበሳው ያባቱ ልጅ
ክፉ አያሳይህ ደጋጉን እንጂ

ከአገር ርቀው ለተሰደዱት
በህመም በስቃይ ካልጋ ለዋሉት
በህግ ተይዘው እስር ቤት ላሉት
ያድርግላቸው እንደሚመኙት

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን

ካለም ሚለየን ከማንም ዜጋ
የሚያሳምመን ልክ እንደ አለንጋ
ልብ ውስጥ ታትሞ የማይዘነጋ
ያገር ፍቅር ነው የነፍሶች ዋጋ
ያገር ፍቅር ነው የነፍሶች ዋጋ
ከእየሩሳሌም ደግሞም ከመካ
እኛን አክብሮ ከሩቅ ጃማይካ
ኢትዮጵያን ብሎ በኛ ሲመካ
ተቀብለናል ትመስክር አፍሪካ
ተቀብለናል ትመስክር አፍሪካ

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን

የወንጌሉ ሰው ላገሬ እስላሙ
ወገኑ አይደል ወይ ደራሽ ወንድሙ
የቁርአኑ ሰው ለክርስቲያኑ
ወንድሙ አይደል ወይ ደራሽ ወገኑ
ወንድሙ አይደል ወይ ደራሽ ወገኑ
ረመዳን ስፆም በርታ የሚል ጓዴ
አይዞህ የምለው ሲሆን ኩዳዴ
የኔና የሱን ታላቁን ፍቅር
ኢትዮጵያን ያየ ወጥቶ ይመስክር
ኢትዮጵያን ያየ ወጥቶ ይመስክር

እንዲሁ እንዳለን እንዳይለየን

ABDU_KIAR

ለሰላም ጥረት ሳይፈተሽ ጉልበት  –  ይገረም አለሙ

$
0
0

“ሰማይ ሲደማምን ይወረዛል ገደል ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል፣” የሀገሬ ሰው ብሶቱን በቀረርቶ የሚገልጽበት  ስንኝ ነው፡፡

peace-dove1አርበኞች ግንቦት 7 ፊሽካው ተነፍቷል ጦርነቱ ተጀምሯል ብሎ ባወጀ ማግሥት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ድምጻቸው የተሰማው የግንባሩ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ጦርነት  ያወጁት ኃይሎች  ወደውና ፈቅደው  ሳይሆን በወያኔ እብሪትና እምቢተኝት የገቡበት ጦርነት መሆኑን ገልጹ፡፡ከሁለቱም ወገን የሚጠፋው የወንድማማቾች ህይወት በመሆኑ ወደዚህ መንገድ በመግባታችን እናዝናለን፤ ገደልን ብለን የምንፎክርበት ሳይሆን በሚከተለው ጥፋት የምናዝንበት ነው ጦርነት ነው አሉ፡፡ አክለውም  ወደማንፈልገው ጦርነት የገፋን ወያኔ  ከእብሪቱ ወጥቶ ፈቃደኛ ከሆነ ጦርነቱን የጀመሩት ወገኖች አሁንም ቢሆን ኢትጵያን ለዴሞክራሲዊ ሥርዓት ለሚያበቃ ውይይትና ድርድር ዝግጁ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡ ጦርነት መጀመሩን ካወጀ ግንባር መሪ አንዲህ አይነት ቅዱስ የሆነ አነጋገር መስማት ያስደስታል፡ የወያኔ ተቀዋሚ የሆን ሁሉ እንደህ ብናስብ መልካም ይመስለኛል፡፡ አባረህ በለው እያሉ መፎከሩም ሆነ ኮረኔል ማራኪ እያሉ ስክስታ መውረዱ ሲበጅ አላየንም፡፡

በወያኔ በኩል የተደመጠው ግን ጥቂት ሻዕቢያ የላካቸው በሚል ንቀት ደምስሰናቸዋል የሚል ጉልበተኝነት ነው፡፡ ከህሊና የሚመነጭ ሳይሆን ከጡንጫ የሚወጣ ባሩድ ባሩድ የሚሸት አስተውሎት የጎደለው ከትናንት አለመማርን የሚያሳብቅ ቃል ነው የሰማነው፡፡

ደርግ ወያኔዎችን ተራ የመንደር ሽፍቶች እያለ ማናናቁም ሆነ ሳይቃጠል በቅጠል ብሎ  ለማጥፋት  የመረጠው ወታደራዊ ዘመቻ  ውጤት እንዳላስገኘ፣ መድፍ መትረየሱም ሆነታንክ አውሮፕላኑ በስልጣን እንዳላዘለቀው አይተናል፡፡እፍኝ የማይሞሉ ከሚል ማጥላላትና አወደምናቸው ደመሰስናቸው ከሚል ፕሮፓጋንዳ ወጥቶ፡ ጥያቄያቸው ምንድን ነው? ጠመንጃ አንስቶ ዱር ቤቴ ለማለት ያበቃቸው ብሶት ምንድን ነው? ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅመው መንገድ የቱ ነው ወዘተ ለማለት  ፈቃደኝነትም አስተውሎትም ያልነበራቸው ሰዎች በመጨረሻ ሰአት ጉልበት ሲከዳቸው ለድርድር እጃቸውን ቢሰጡም የሚፈይድ አልሆነምና በእብሪታቸው ራሳቸውን ለስደት ለእስራትና ለሞት ሀገሪቱን ለውድቀት ዳረጓት፡፡

ጠመንጃ አንግበው ዱር ቤቴ ያሉ ወገኖቸን አላማ በወታደራዊ ኃይል ማጥፋት እንደማይቻል ወያኔዎች ከራሳቸው በተማሩ ነበር፡፡ ነገር ግን  በሥልጣን ጥማት ታውረው እንኳን ከትናንት ከዛሬም የማይማሩ በመሆናቸው ዱር ቤት ከማለት አልፈው ፊሽካው ተነፍቷል ጦርነቱ ተጀምሯል ላሉ ወጎኖች የተለያየ ስም መስጠትና ጥቂቶች ናቸው ብሎ ማናንቅ፤ ደመስሰናቸዋል እያሉ መፎከር ገጠር ከተማ ሳይሉ ወጣቶችን የተለያየ ስም እየሰጡ ማሰርን ነው የተያያዙት፡፡

አሜሪካዊው ኤድመንድ በርክ የተናገሩት ተብሎ አንደሚጠቀሰሰው «መላው የሰው ልጅ ጥቅምና ደስታ ሁሉም መልካም ተግባር የተመሰረተው በፖለቲካ መቻቻልና አቅምን በማሸጋሸግ ድርጊት ነው»፡፡ስለሆነም  ዜጎችን ዱር ቤት ለማለት የሚያበቁ ምክንያቶችን በፖለቲካ መቻቻልና በብሄራዊ መግባባት ለማስቀረት መጣር ለራስም ለሀገርና ለህዝብም የሚጠቅም ውጤት ያስገኛል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ እኛም ዱር ውሎ ማደሩን፣ዝናር መታጠቅ ጠብ መንጃ ማንገብና ቃታ መሳቡን  እናውቅበታለን የሚል ደረጃ ከተደረሰ ደግሞ እያናናቁ፣ የተለያየ ስም እየሰጡና እየወነጀሉ ፕሮፓጋንዳ መስራት፣ወይም እንጨፍልቃቸዋልን እያሉ ጦር ማዝመት በሥልጣን ሊያሰነብት አለመቻሉን  ወያኔ ራሱ ከመጣበት ሂደት መረዳት በቻለ ነበር፡፡ ነገር ግን ሲረገጡና ሲረግጡ አእምሮ እኩል ስለማያስብ ወያኔ ከደረግ ሽንፈት መማር አልቻለም፡፡

ወያኔን በፋኖነቱም ሆነ በመንግስትነቱ እንዳወቅነው ለሥልጣኑ ሲል ሀገር ቢፈርስ ሕዝብ ቢጨራረስ  ደንታ የሌለው መሆኑ እንጂ  ለሀገርና ለሕዝብ  የሚያሰብ ቢሆን  ጦርነቱ ከመባባሱ በፊት የሰላም በሮችን በመክፈት ነገሮች ሁሉ በውይይት በፖለቲካ መቻቻልና አቋምን በማሸጋሸግ ዴሞክራሲያዊ አግባብ መስመር እንዲይዙ ቢያደርግ ለራሱም ይበጀው ነበር፡፡

ጦርነት ከተባባሰና የሰው እልቂትና የሀገር ሀብት ውድመት ከነገሰ በኋላ ለማደራደርም ሆነ እጅ ለመጠምዘዝ ላይ ታች የሚሉ መንግሥታትና ተቋማትም የተጀመረው ጦርነት  የሁለቱንም ወገን አቅም ወደሚፈትሽበት  ደረጃ ከመደረሱ በፊት ዛሬ አሁን  ቢያስቡበት ነው የተሻለ የሚሆነው፡፡ ነገሮች በገፉና በተካረሩ ቁጥር ዱር ቤቴ ያለው ወገን አቅሙን እየፈተሸ ጉልበቱን እያጠነከረ በራስ መተማመኑን እያዳበረ ስለሚመጣ በአንጻሩ ስልጣን ላይ ያለው ሀይል የሚወስዳው የጥፋት ርምጃዎች ይቅር ወደማይባል ደረጃ ስለሚደርስ ለድርድር መቀመጥ ቢቻል አንኳን ተዋጊው ኃይል የሚያቀርባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና የሚያነሳቸው ጥያቄዎች የደደሩ ይሆናሉ፡፡

ጦርነት ሰው አይመርጥም የፖለተካ አሰላለፍ የብሄረሰብ ማንነት የሀይማኖት ምንነት ሳይለይ ሁሉንም ነው ተጠቂ የሚያደርገው፡፡ ጦርነቱ በሚካሄድበት አካባቢ እየኖሩ የኢህአዴግ አባልና ደጋፊ በመሆን መዳን ተቀዋሚ በመሆን ማመለጥ የዳር ተመልካች በመሆን መትረፍ አይኖርም፡ስለሆነም በተለይ የጦርነቱ መቀጠል ወይንም መቆም መፍትሄ በእጁ የሆነው ወያኔ አባላት  የደርግና ወያኔን ጦርነት አጀማመርና እድገት ሂደትና ውጤት ቆም ብላችሁ አስቡና ለራሳችሁ ስትሉ መሪዎቻችሁ ከእብሪት መንገድ ወጥተው ወደ ሰላም መንገድ እንዲያመሩ  ጠይቁ፡፡

እዚህ በሀገር ቤት በሞቀ ጎጆአችሁ እየኖራችሁ ሌሎችም አውሮፓና አሜሪካ እየተንደላቀቃችሁ፤እስረው ግደለው ደምስሰው ወዘተ የምትሉ የወያኔ ደጋፊ ነን ባዮችም ለሀገርና ለሕዝብ ደንታ ባይኖራችሁም አድራጎታችሁ እንደግፈዋለን ለምትሉት ወያኔ እንደማይጠቅም በግዜ ብትገነዘቡ መልካም ነው፡፡

ዛሬ ትናንት አይደለም፤ በሕዝብ ላይ እልቂት በሀገር ላይ ውድመት አድርሶ ተደብቆ መኖር ከህግ አምልጦ ማደር አይቻልም፡፡ ነገር ግን ወያኔ እስከ ዛሬ ያደረሰው ጥፋት ከበቂ በላይ ቢሆንም፤ጥፋቱ እያባነነው የሕዝብ ደም እያቃዠው ዛሬም በጥፋት ላይ ጥፋት እየጨመረ ነው፡፡ አስተሳሰባቸው እንደ ጋሪ ፈረስ የተቀየደ ደጋፊዎቹም ሆታና ጫጫታ የቁልቁለቱን መንገድ እያፈጠነለት ነው፡፡ በዚህ ከቀጠለ ጠፍቶ እንዳያጠፋን ያሰጋል፡፡

ኢትዮጵያ በመላው አለም ተበትነው ለየሚኖሩበት ሀገር ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ያሉ እውቀትም ልምድም እድሜም የጠገቡ በረካታ አንቱ የተባሉ ልጆች አሏት፤እነዚህም ወገኖች በዚህ ወቅት የዳር ተመልካች ሊሆኑ አይገባም፡፡ ውድ ህይወታቸውን መስዋእት ለማድረግ በጦር ግንባር የተሰለፉ ልጆቿ ከሚያደርጉት የነጻነት ትል ጎን ለጎን ጥፋቱ ሳይበረታ ወያኔ ለድርድር አንዲንበረከክ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በያለበት በግል፤ በጋራና በተደራጀ ሁኔታ የሚችለውን ቢያደርግ ነው መልካም የሚሆነው፡፡ ዛሬ ምንም አንዳልያዩና እንዳልሰሙ ሆነው አድፍጠው የሚያዩትንና ኋላ እልቂት ሲባባስ ተደራደሩ ማእቀብ እንጥላለን፤አለም አቀፍ ፍርድ ቤት እናቀርባለን ወዘተ ለማለት የማይመለሱትን መንግሥታትና አለም አቀፍ ድርጅቶችም ማንቃት ማሳስብ ያስፈልጋል፡፡የወያኔ አባላትና ደጋፊዎችም ከጭፍን ሆይ ሆያታ ወጥታችሁ የድርጅታችሁ መሪዎች  ለድርድር ፈቃደኛ እንዲሆኑ ማሳሰብ መጠየቅ ብሎም ማስገደድ ብትችሉ ለድርጅታችሁም ለመሪዎቻችሁም ለእናንተም ይጠቅማል፡፡ ለሰላም የሚደረግ ጥረት ውጤት የሚያስገኘው አቅም ከመፈተሹ በፊት ሲሆን ነው፡፡ለማይቀር ውድቀት አወዳደቅን ማሳመር ብልሀትም እውቀትም ነው፡፡

የዲሲ ግብረሃይል ለዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የ15 ሺ ዶላር የሚያወጣ መድሃኒት እና 10 ሺ ዶላር ቼክ አስረከበ

$
0
0

dc force
(ዘ፡ሐበሻ) በዋሽንተን ዲሲ የሚገኙት ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ለ አርበኞች ግንቦት 7 የሚሆን 15 ሺ ዶላር የሚያወጣ መድሃኒት አና 10 ሺ ዶላር ቼክ ለዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አስረከቡ፡፡

በዲሲ በሚገኝ አንድ የኢትዮጵያውያን ሬስቶራንት ውስጥ ግብርሃይሉ ካበረከተ በሁዋላ በቀጣይም በትግል ላይ ያሉትን ወታደሮች ለማገዝ ከጎን አንደሚቆሙ ጠቁመዋል፡፡

ዶ/ር ብርሃኑ ለሰራዊቱ የተበረከተውን የመድሃኒት የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ ተቀብለው ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም ሁሉም በያለበት ትግሉን አንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአስቴር ቤተሰቦች ደብዳቤ:- ‹‹የእናት ጡት እየፈለገ በሚያለቅሰው ህጻን እማጸናችኋለሁ››

$
0
0

aster
by Dawit Solomon
ከጎንደር ተነስታ ስራ ፍለጋና ፓስፖርቷን ለማደስ ወደ አዲስ አበባ እንዳመራች በፌደራል ፖሊስ አባላት ተይዛ ማዕከላዊ ስቃይ ቤት መግባቷን የሚናገሩት የአስቴር(ቀለብ)ስዩም ቤተሰቦች ፍርድ ቤት ቀርባ በሽብርተኝነት መከሰሷን መስማታቸውን ይናገራሉ፡፡

በመንግስት መስሪያ ቤት ትሰራ የነበረችው አስቴር በምትኖርበት አካባቢም የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ውስጥ ትሰራ በነበረበት ወቅት ከሃላፊዎቿ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲቀርቡላት ቆይተው በመጨረሻም ለጥያቄያቸው ፈቃደኛ ሳትሆን በመቅረቷ ከስራ እንዳባረሯት ይገልጻሉ፡፡

በሞያዋ በአገሯ መስራት የተነፈገችው አስቴር በቤተሰቦቿ አገለለጽ በንዴትና በስሜት ተገፋፍታ አንድነት ፓርቲን ተቀላቀለች፡፡የስምንት ወር ልጅና በእድሜ የደረጁ እመዋ ያሏት በቤት ስሟ ቀለብ ወደ አዲስ አበባ ለስራ ፍለጋ እንዳመራች በቁጥጥር ስር እንድትውል ተደረገች፡፡

በደብዳቤው የተሳተፉት ወላጅ እናቷ እናቱን በግፍ የተነጠቀችውን ህጻን ልጃቸውን በስተርጅና ታቅፈው መቅረታቸው ሊሸከሙት የማይችሉት ሆኖባቸው
‹‹መንግስት እንዲፈታልኝ››ብለዋል፡፡የሚማጸኑት ደግሞ ‹‹የእናት ጡት እየፈለገ›› በሚያለቅሰው ህጻኑ ስም ነው፡፡ይሰሟቸው ይሆን ?

ይህ በእዲህ እያለ የአስር ወር ልጇ ጋር ነጥላችሁ መጫት ልጃችን ቀለብን ምንም በለለችበት አሸባሪ የሚል ስም ሰጥቶ ማሰሩ ተገቢ አለመሆኑንና ሃላፊነቱን እኛ ልንወስድ በኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሁም የእናት ጡት እያለ በሚያለቅሰው ልጅ ስም እንድትፈቱልን በአክብሮት እንጠይቃለን። እንለምናለን።

የዲሲ ግብረሃይል ለዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የ15 ሺ ዶላር የሚያወጣ መድሃኒት እና 10 ሺ ዶላር ቼክ አስረከበ

$
0
0

dc force
(ዘ፡ሐበሻ) በዋሽንተን ዲሲ የሚገኙት ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ለ አርበኞች ግንቦት 7 የሚሆን 15 ሺ ዶላር የሚያወጣ መድሃኒት አና 10 ሺ ዶላር ቼክ ለዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አስረከቡ፡፡

በዲሲ በሚገኝ አንድ የኢትዮጵያውያን ሬስቶራንት ውስጥ ግብርሃይሉ ካበረከተ በሁዋላ በቀጣይም በትግል ላይ ያሉትን ወታደሮች ለማገዝ ከጎን አንደሚቆሙ ጠቁመዋል፡፡

ዶ/ር ብርሃኑ ለሰራዊቱ የተበረከተውን የመድሃኒት የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ ተቀብለው ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም ሁሉም በያለበት ትግሉን አንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live